id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
51964268
https://www.bbc.com/amharic/51964268
በአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ ምልክት ከታየባቸው አራቱ ነፃ ሆነው መገኘታቸው ተነገረ
በአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው ከነበሩ ስድስት ሰዎች መካከል አራቱ ነፃ መሆናቸው የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸው ከነበሩት መካከል የሁለቱ ውጤት እንደታወቀ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል። ይህ የተገለጸው በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ዛሬ በባሀርዳር በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለሶስተ መቶ የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መልካሙ አብቴ አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም አምስት የለይቶ ማቆያዎች ብቻ እንደነበሩ የገለጹት ኃፊው በሁሉም ዞኖች አንድ አንድ የለይቶ ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ መደረጉንም ገልጸዋል። በክልሉ በሚገኙ አራት አውሮፕላን ማረፊያዎች እና በመተማ ድንበር እስካሁን 1900 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሙቀት ምርመራ ማድረጉን ቢሮው አስታውቋል። በክልሉ በበሽታው የተያዘ ሰው አለመኖሩን እንደ መልካም ዕድል መጠቀም ዝግጅቶችን አጠናክሮ ማካሄድ እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማህተመ ኃይሌ ናቸው። ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው አካላት በመከታተል እና የግል ንጽህናውን አዘውትሮ በመጠበቅ የመከላከል ሥራውን ከእራስ መጀመር እንደሚገበባ አስረድተዋል። ከአውሮፕላን ማረፊያዎች እና ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር በተጨማሪ የክልሉ መግቢያ በሆኑት በደጀን፣ ደብረ ብርሃን እና ባቲ የሙቀት መለካት ሥራ ከሰኞ ጀምሮ ተግበራዊ ይደረጋል ብለዋል። የቫይረሱን ምርመራ በክልሉ ለመጀመር የሚመለከታቸውን አካላት እየጠየቁ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህ የሚሆን ግብዓት ከተገኘ ዝግጁ የሆነ ቤተ-ሙከራ መኖሩን ጠቁመዋል። ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ በክልሉ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን በምክትል ርዕሰ መስተዳደድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ሙሉነሽ አበበ ጠቁመው፤ ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል። የክልሉን ከፍተኛ ሥራ ኃፊዎች ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የሚመለከታቸው አካላት የተዋቀሩበት ግብረ-ኃይል ወደ ሥራ ገብቷል። የክልሉ መንግሥትም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለሚሠሩ ሥራዎች የሚውል 150 ሚሊዮን ብር መመደቡን ታውቋል።
news-41303692
https://www.bbc.com/amharic/news-41303692
ማሪያ የተባለው ከባድ አውሎ-ነፋስ ወደ ካረቢያን ደሴቶች እየተቃረበ ነው
ማሪያ ተብሎ የተሰየመው እጅግ አደገኛ አውሎ-ነፋስ ወደካረቢያን የሊዋርድ ደሴቶች እየተቃረበ ነው።
የአሜሪካው ብሔራዊ የአውሎ-ነፋስ ጣቢያ እንዳለው ይህ ምድብ አንድ ተብሎ የተመደበው አውሎ-ነፋስ በሚቀጥሉት 48 ስዓት ውስጥ ኃይሉን በማጠናከር ሰኞ አመሻሽ ላይ የሊዋርድ ደሴቶችን ይመታል ። ባሳለፍነው ወር ኢርማ ከባድ አውሎ-ነፋስ ይህን አካባቢ እንዳልነበር አድርጎት ነበር፣ አሁንም በተመሳሳይ አቅጣጫ ማሪያ እየመጣ ይገኛል። ጓዲሎፔ፣ ዶሚኒካ፣ ቅዱስ ኪትስና ኔቪስ፣ ሞናትሴራት እና ማርቲኒክ በተባሉ ደሴቶች የከባድ አውሎ-ነፋስ ማስጠንቀቂያ ተላልፎላቸዋል። ከነዚህ ደሴቶች መካከል አንዳንዶቹ በኢርማ ከደረሰባቸው ጉዳት ገና አላገገሙም። ይህ ምድብ 5 ተብሎ የነበረው አውሎ-ነፋስ የ37 ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት አውድሟል። የአሜሪካው ብሔራዊ የአውሎ-ነፋስ ጣቢያ እንዳለው አሁን ደግሞ ማሪያ በስዓት 137 ኪ.ሜ እየተጓዘ ይገኛል። ጣቢያው እንዳስጠነቀቀው ይህ አውሎ-ነፋስ አደገኛና ጠንካራ በሆነ ማዕበል የተጀበ ሲሆን የውሃን አካል ከ1.5-2.1 ሜትር ድርስ ከፍ ያደርጋል። በተለይም በማዕከላዊና በደቡባዊ ሊዋርድ እሰከ 20 ኢንች ሊደርስ የሚችል ዝናብ ሊኖር ይችላል። ይህም በደሴቶቹ ላይ አደገኛ ጎርፍና የመሬት መሸራተት ሊያስከትል እንደሚችል ትንበያ አስቀምጧል። ባለፈው ወር በተከሰተው በኢርማ አውሎ ነፋስ በብሪታንያዋ ቨርጅን ደሴቶች የነበሩ ቤቶች ሁሉ ወድመዋል። አካባቢውን የጎበኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሪስ ጆንሰን ጉዳቱን ከአንደኛው የአለም ጦርነት በኋላ ከተመለከቷቸው ምስሎች ጋር አመሳስለዋቸዋል። በአሜሪካም 11 ሰዎች ሲሞቱ ወደ 6.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ቤቶችም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል።
news-45911129
https://www.bbc.com/amharic/news-45911129
ኢትዮጵያዊያን በህጋዊ መንገድ ለሥራ ሚሄዱባቸው ሦስት አገሮች
ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች በውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት በህጋዊ መንገድ ተቀጥረው ለመስራት የሚችሉባቸው ሃገራት ሦስት ብቻ መሆናቸውንና እነሱም ከመንግሥት ስምምነት ያላቸው እንደሆነ ተገለፀ።
ቢቢሲ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳኡዲ አረብያ፣ ኳታርና ጆርዳን ጋር ብቻ የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረሙን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በፃፉት ደበዳቤ አሳውቀዋል። ከተጠቀሱት የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ውጪ በተለያዩ መንገዶች ለሥራ መጓዝ ህገውጥ እንደሆነና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ቁጥጥር እንደሚያደርጉና እርምጃ እንደሚወስዱም ተገልጿል። • ኩዌት ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞችን እንደምትፈልግ አሳወቀች • በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት ማለት የሌለብን 7 ነጥቦች ምክትትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፃፉት ደብዳቤ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ጠቅላይ ኣቃቤ ህግ፣ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደረጉ የሚያሳስብ ሲሆን፤ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ለሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርም ግልባጭ ሆኗል። መንግሥት የሁለትዮሽ ስምምነት ካልፈፀባቸው አገሮች ጋር ምንም ዓይነት የሥራ ስምሪት እንዳይደረግ የተጠቀሱት ተቋማት ቁጥጥር እንዲያደርጉ ኃላፊነት ተሰትቷቸዋል። አዲሱ የኢትዮጵያ የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት አዋጅ፤ ሰራተኛን በውጭ ሃገር ለሥራ ማሰማራት የሚቻለው በኢትዮጵያና በተቀባይ ሀገር መካከል የሁለትዮሽ ስምምነት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ይደነግጋል። በዚህም መሰረት፤ ወደ የመካከለኛ ምሥራቅ አረብ ሀገራት የሚደረግ የሥራ ስምሪት ክልከላ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም መነሳቱ ይታወሳል። የሁለትዮሽ ስምምነት ወደ አልተደረገባቸው ሃገሮች ማለትም ኩዌት፣ ባህሬይ፣ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬትስ፣ ሌባኖስና ዮርዳኖስ በዘመድ ጥየቃ፣ በጉብኝት፣ በንግድና በመሳሰሉ የቪዛ አይነቶች ከሃገር በመውጣት ሕገ ወጥ የሥራ ስምሪት እየተደረጉ መሆናቸውንና ተገልጿል። • ዛሚ ሬዲዮ ሊዘጋ ይሆን? • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ በዚህ በህገ ወጥ መንገድ በሚደርግ የሥራ ስምሪት ዜጎች ለመብት ጥሰት፣ ያለ ክፍያ ለመስራት፣ ለእንግልት፣ ለስቃይና ሲከፋም ለሞት እየተዳረጉ መሆናቸውን ደብዳቤው አመልክቷል። በመሆኑም በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ኤጀንሲዎች ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው አሳስበዋል። ከአራት ዓመታት በፊት የሳኡዲ መንግሥት ከ150 ሺህ በላይ ህጋዊ መኖርያና የሥራ ፈቃድ የላቸውም ያላቸውን ሰራተኞች ማባረሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ መካከለኛ ምሥራቅ የሚደረግ የሥራ ስምሪትን በህግ ከልክሎ መቆየቱ የሚታወስ ነው። በውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 መሰረት፤ ወደ ውጭ በመሄድ ለመስራት አንዳንድ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ተቀምጠዋል። በዚህም መሰረት ተቀጣሪዎች የትምህርት ደረጃቸው ቢያነስ ስምንተኛ ክፍልን ያጠናቀቁ፣ ለሚሰማሩበት ሥራ የሚያግዛቸው ከቴክኒክን ሙያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አስፈላጊውን ስልጣና መውሰዳቸው የሚገልፅ የብቃት መናረጋገጫ እንዲሁም በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የፀደቀ የሥራ ውል ሊኖር ይገባል። ከዚህ ውጪ የሚደረግ የሥራ ስምሪት ጉዞ ህገ ወጥ መሆኑን አዋጁ አስፍሯል።
news-53704726
https://www.bbc.com/amharic/news-53704726
በሕንዱ የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 18 ደረሰ
የኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በደቡባዊ ሕንድ ኬሬላ ግዛት በሚገኝ አየር ማረፊያ ባጋጠመው አደጋ ቢያንስ 18 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
190 ሰዎችን አሳፍሮ ከዱባይ የተነሳው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ላኪከት አየር ማረፊያ ሲደርስ በነበረው ዝናብ ምክንያት ከማኮብኮብያው አስፋልት ተንሸራቶ ወጥቶ ነው የተከሰከሰው። አውሮፕላኑ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ዱባይ ውስጥ ለወራት መንቀሳቀስ ያልቻሉ ሕንዳውያንን አሳፍሮ ነበር። ጠለቅይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በተፈጠረው አደጋ 'ሕመም' እንደተሰማቸው ገልፀዋል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን እንዲሁም የተረፉ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል ወስደዋል። 15 ሰዎች ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸው፤ በርካቶች ቀላል የሚባል አደጋ ነው ያጋጠማቸው ተብሏል። ኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የአውሮፕላኑ አብራሪዎች አንደሆኑ ይፋ አድርጓል። የበረራ ቁጥር አይኤክስ 1134፤ 10 ሕፃናትን ጨምሮ 184 መንገደኞችና 6 የአውሮፕላኑን ሠራተኞች አሳፍሮ ነበር። አውሮፕላኑ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 1፡40 ነው የተከሰከሰው። በወቅቱ በሥፍራው ከባድ ዝናብ እየጣለ ነበር ተብሏል። አብራሪዎቹ መጀመሪያ ለማረፍ ያደረጉት ሙከራ በዝናብ ምክንያት በማቋረጥ ለሁለተኛ ጊዜ ባደረጉት ሙከራ ነው አደጋው የተከሰተው። የሕንድ ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር ሃርዲፕ ሲንግ ፑሪ የአጋውን ኦፊሴላዊ ምክንያት በምርመራ ቡድን አባላት እንደሚጣራ አሳውቀዋል። ባለሥልጣናት፤ አውሮፕላኑ ለሁለት የተከፈለው ከመንደርደሪያው ውጭ ከነበረ አንድ ጎድጎድ ካለ ሥፍራ ጋር በመጋጨቱ ነው፤ በዚህም የአውሮፕላኑ ፊተኛው ክፍል በጣም መጎዳቱን አሳውቀዋል። ነገር ግን አውሮፕላኑ እሣት ባለማስነሳቱ ምክንያት በርካቶች ሊተርፉ እንደቻሉ ታውቋል። በሕንድ አሁን ወቅቱ ዝናባማ ነው። አውሮፕላኑ አደጋ ባጋጠመው አካባቢ ከቀናት በፊት በከባድ ዝናብ ምክንያት በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት ሰዎች እንደሞቱ ተዘግቦ ነበር። በፈረንጆቹ 2010፤ የኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ አውሮፕላን በተመሳሳይ ከመንደርደሪያ ወጥቶ በተፈጠረ አደጋ 158 ሰዎች መሞታቸው አይዘነጋም።
news-52965325
https://www.bbc.com/amharic/news-52965325
"አምባገነናዊ መንግሥት ሲመሰረት ተባባሪ ላለመሆን ኃላፊነቴን ለቅቄያለሁ" ወ/ሮ ኬሪያ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሒም ሕገ መንግሥት ከሚፈቅደው ውጪ አምባገነናዊ መንግሥት ሲመሰረት ተባባሪ ላለመሆን በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታወቁ።
የአፈጉባኤዋን ስልጣን መልቀቅ በተመለከተ ወ/ሮ ኬሪያ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት የአገሪቱን "ሕገ መንግሥት በየቀኑ ከሚጥስና አምባገነንነትን ከሚያራምድ ቡድን ጋር ለመስራት ፈቃደኛ ስላልሆንኩ ነው" ብለዋል። አፈጉባኤዋ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት በስልጣን ላይ ያለው ወገን "ሕገ መንግሥቱን በግላጭ ተጥሷል አምባገነናዊ መንግሥት ወደ መመስረት ገብቷል" ሲሉ ከሰዋል። ለዚህም እንደማሳያ ያስቀመጡት ስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ያለምርጫ በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲል በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያለ ክፍተትን በመፈለግ "አንዱን አንቀጽ ከሌላው ጋር በማጋጨት ክፍተት እንዲገኝና አማራጭ እንዲፈለግ" ጥረት ተደርጓል ብለዋል። በስልጣን ላይ ያለው አካል ካለሕዝብ ውሳኔ ባለበት ለመቆት መወሰኑንና ይህንንም ሕጋዊ ለማድረግ ክፍተት በመፈለግ ሕገ መንግሥታዊ ከሆነው መንገድ ውጪ "ባልተለመደ አካሄድ ሕገ መንግሥቱ እንዲተረጎም ግፊት እየተደረገ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ይህም አስቀድሞ የተወሰነ መሆኑን ጠቅሰው "ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነው" ብለዋል። ጨምረውም ይህ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔውን በማይቀበሉት ላይ "ማስፈራሪያና ዛቻ" እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህም ሳቢያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሲሆኑ "ሕገ መንግሥቱን የማክበር የማስከበር አደራ ስለተቀበልኩ፤ ሕገ መንግሥቱ ተጥሶ አምባገነናዊ መንግሥት ሲመሰረት ተባባሪ ላለመሆን" ሲሉ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን እንደለቀቁ ተናግረዋል። ጨምረውም "በሕገ መንግሥት ትርጉም ሽፋን የአምባገነናዊ ሥርዓት ሕግ የሚጥስ ድርጊትን ላለመተባበር ወስኛለሁ" ብለዋል ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም። ከሁለት ዓመት በላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ያገለገሉት ወ/ሮ ኬሪያ ስለውሳኔያቸው በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት ይህ እርምጃ የአገሪቱ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የስልጣን ባለቤትነትን የሚጥስ ነው ብለዋል። ቢቢሲ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ስለ አፈጉባኤዋ ሥራ መልቀቅ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ምክር ቤቱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገልጿል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ አቶ ገብሩ ገብረ ሥላሴ ለቢቢሲ የአፈ ጉባኤዋን ከሥራ መልቀቅ በተመለከተ የቀረበ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ቢሆንም ግን አፈ ጉባኤዋ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን በሚመለከት የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎችን መመልከታቸውን ገልጸው፤ በጽህፈት ቤቱ በኩል ግን የቀረበ ይህንን የሚያረጋግጥ ነገር የለም ብለዋል። የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ የሆነው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ በአፈ ጉባኤነት የሚመሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አነጋጋሪ በሆነው የሕገ መንግሥት ትርጉም ጉዳይ ላይ በቅርቡ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
news-46983372
https://www.bbc.com/amharic/news-46983372
ከአስር አመት በላይ ራሷን ሳታውቅ ኮማ ውስጥ ያለችን ታማሚ ያስረገዝው በቁጥጥር ስር ዋለ
አሜሪካ ውስጥ ከአስር ዓመት በላይ በህይወትና በሞት መካከል ሆና ራሷን የማታውቅ ታማሚ በህክምና ማዕከል ውስጥ ህጻን ልጅ መገላገሏ ከወደ አሪዞና መሰማቱ ብዙዎችን አስገርሞ ነበር።
ይህንን ተከትሎም የታማሚዎች መንከባከቢያን የሚያስተዳድረው ድርጅት ዋና ኃላፊ በገዛ ፈቃዳቸው ከስራቸው መልቀቃቸው ይታወሳል። ፖሊስ ዛሬ እንዳስታወቀው ደግሞ ታማሚዋ ላይ ጾታዊ ጥቃት አድርሷል ያለውን በማዕከሉ የሚሰራ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል። ተጠርጣሪው ናታን ሱዘርላንድ የተባለ የ36 ዓመት ነርስ ሲሆን በጤና ማዕከሉ ውስጥ ስሟ ያልተጠቀሰችውን ታማሚ ከሚንከባከቡት ነርሶች መካከል አንዱ ነበር ተብሏል። ታማሚዋ 'ሃሲዬንዳ' በተባለው የጤና ማዕከል ውስጥ ከአስር ዓመታት በላይ ህክምና ሲደረግላት የቆየ ሲሆን፤ ኮማ ውስጥ ስለሆነችም 24 ሰአት የዶክተሮች ህክምናና ክትትል ይደረግላታል ነበር። • በህክምና ስህተት የመከነው ህፃን • የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች በህክምና ማዕከሉ የሚሰራ አንድ ግለሰብ እንደተናገረው ታማሚዋ ከሌላው ጊዜ በተለየ የማቃሰትና ህመም ውስጥ እንደሆነች የሚያሳዩ ምልክቶችን አሳይታ ነበር ብሏል። አክሎም ታማሚዋ ልጇን እስክትገላገል ድረስ የትኛውም የማዕከሉ ሰራተኛ ነፍሰጡር እንደሆነች እንዳላወቀ ገልጿል። ፖሊስ በጉዳዩ በሰጠው መግለጫ በታማሚዋ ላይ ያለ ፍላጎቷና ከእውቅናዋ ውጪ ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞባታል ብሏል። በአሁኑ ሰዓት የተወለደው ህጻን ልጅ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝና የታማሚዋ ቤተሰቦች እየተንከባከቡት እንደሆነም ታውቋል። ጋሪ ኦማን የተባሉት የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ደግሞ በተፈጠረው አስነዋሪ ተግባር እጅግ ማፈራቸውን በመግለጽ ለሆነው ነገር ሁሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ አስታውቀው ነበር። ህጻኑ ከተወለደ በኋላ ፖሊስ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሁሉም የማዕከሉ ሰራተኞች የዘረመል ቅንጣት እንዲሰጡ ያደረገ ሲሆን በምርመራው ውጤት መሰረትም ተጠርጣሪው ናታን ሱዘርላንድ የልጁ አባት መሆኑ ተረጋግጧል። ተጠርጣሪው ረቡዕ ዕለት ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን 500 ሺ ዶላር አስይዞ ጉዳዩን ከውጪ ሆኖ እነዲከታተል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። • ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? በአሁኑ ሰዓት በማዕከሉ ከበድ ያሉ የደህንነት መጠበቂያ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ገልጸዋል። ማንኛውም ወንድ የማዕከሉ ሰራተኛ ወደ ሴት ታማሚዎች ክፍል ሲገባ አንድ ተጨማሪ ሴት ሰራተኛ አብራው እንድትገባ እያደረጉ እንደሆነም ምክትል ስራ አስኪያጁ አክለዋል።
news-54984434
https://www.bbc.com/amharic/news-54984434
ኮቪድ-19 የለዋወጠው የዓለም ውድ ከተሞች ዝርዝር
ኮሮናቫይረስ አጠቃላዩን የዓለም ሁኔታ በመቀየር የምድራችን ውድ ከተሞች ዝርዝር ላይም ለውጥ አምጥቷል።
አዲስ በወጣ ሪፖርት መሠረት የወቅቱ የዓለም ውድ ከተሞች ሆንግ ኮንግ፣ ዙሪክ እና ፓሪስ ሆነዋል። አምና ከሆንግ ኮንግ ጋር ተመሳሳይ ደረጃ ላይ የነበሩት ሲንጋፖር እና ኦሳካ ከዝርዝሩ ወርደዋል። 'ዘ ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት' የተባለው ተቋም ነው ይህንን ዓመታዊ የከተሞች የኑሮ ሁኔታ የደረጃ ሰንጠረዥ ያወጣው። የተቋሙ ኃላፊ ኡፓሳና ደት እንዳሉት፤ ለወትሮው በሰንጠረዡ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዙት የእስያ አገሮች በኮቪድ-19 ሳቢያ ወደ ታች ወርደዋል። በቻይና እና አሜሪካ መካከል ያለው ፍጥጫ መካረሩን ተከትሎ ብዙ የቻይና ከተሞች በዝርዝሩ ቀዳሚ ከሆኑት መካከል ተመዝግበዋል። የቻይና እና የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ተቋሞች ፉክክር የተለያዩ ቁሳቁሶች ዋጋ እንዲንር ምንክንያትም ሆኗል። ባንኮክ በዝርዝሩ 20 ደረጃ ዝቅ ብላ፤ 46ኛ ውድ ከተማ ሆናለች። የተቋሙ ጥናት ያተኮረው ወደተለያዩ አገሮች ተጉዘው በድጋሚ ወደ ትውልድ አገራቸው የተመለሱ ሰዎች ላይ ነው። ይህንን የጥናት ውጤት የጉዞ እቅድ የሚያወጡ ሰዎች ወይም ድርጅቶች ይጠቀሙበታል። በአሜሪካ፣ አፍሪካ እና ምሥራቅ አውሮፓ ከተሞች ኑሮ ከአምና ዘንድሮ ረክሷል። በተቃራኒው በምዕራብ አውሮፓ አገሮች ንረት አሳይቷል። ከአስሩ ውድ ከተሞች አራቱ ምዕራብ አውሮፓ ውስጥ ይገኛሉ። ዙሪክ እና ፓሪስ በመጀመሪያ ደረጃ ሲቀመጡ፤ ጄኔቫ እና ኮፐንሀገን ሰባተኛ እና ዘጠነኛ ሆነዋል። ይህ የአውሮፓ ገንዘብ በአንጻራዊንት ጠንካራ እንደሆነ ይጠቁማል። በከተሞች መካከል የኑሮ ውድነት ውድድር ሲካሄድ ማነጻጸሪያው ኒው ዮርክ ናት። በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ የታየው በኢራን መዲና ቴህራን ነው። ካለፈው ጊዜ 27 ደረጃ ከፍ ብላለች። የኑሮ ውድነት ያስከተለው አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ ነው። ተቋሙ ጥናቱን ሲሠራ መስከረም ላይ በ130 ከተሞች የነበረውን የ138 ቁሳቁሶችን ዋጋ አወዳድሯል። ጠቅለል ባለ ሁኔታ ሲታይ፤ ዋጋ የቀነሰ ቢሆንም እጅግ አስፈላጊ መገልገያዎች ተወደዋል። በወረርሽኙ ምክንያት በረራና ሌላም እንቅስቃሴ መገታቱ ለዋጋ ንረት ምክንያት ሆኗል። ዋጋቸው በጣም ከተወደደ ምርቶች መካከል ሲጋራ ይጠቀሳል። የኮምፒውተር ዋጋም ንሯል። በሌላ በኩል ልብስ ረክሷል።
news-51322281
https://www.bbc.com/amharic/news-51322281
የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስን የወቅቱ አሳሳቢ የምድራችን የጤና ስጋት መሆኑን አወጀ
የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ የወቅቱ አሳሳቢ የምድራችን የጤና ስጋት ነው ሲል አውጇል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክትር ዶክትር ቴድሮስ አድሃኖም ይፋ እንዳደረጉት ለዚህ ውሳኔ ዋነኛው ምክንያት "በቻይና የተከሰተው ነገር ሳይሆን በሌሎች አገሮች እየሆነ ያለው ነው" ብለዋል። የዓለም የጤና ድርጅት የበሽታ ወረርሽኝ ተከስቶ ከዚህ አይነት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ይህ ስድስተኛው ሲሆን ከዚህ ቀደም ኤችዋን ኤን ዋን የተባለው ኢንፍሉዌንዛ፣ ኢቦላ፣ ፖሊዮ፣ ዚካና በድጋሚ የተከሰተው ኢቦላ ምክንያት ነበሩ። • ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ተጠርጥረው የደም ናሙናቸው ለተጨማሪ የላብራቶሪ ምርመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኮ የነበሩት አራቱ ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ጉዳዩ ያሳስበኛል ያለው በተለይ ቫይረሱ ዝቅተኛ የጤና ሽፋን ባለቸው አገራት ቢከሰት ጉዳቱ ከባድ ይሆናል በማለት መሆኑን ገልጿል። አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ቻይና እንዳይሄዱ አስጠንቅቃለች። አሁን ባለው ሁኔታ ቻይና ውስጥ በበሽታው ቢያንስ 213 ሰዎች ሲሞቱ 10 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ከሆነ እስካሁን የሞተ ባይኖርም በሌሎች 18 አገራትም 98 የቫይረሱ ተጠቂዎች ተለይተዋል። • የአፍ ጭምብል ማጥለቅ ከቫይረስ ይታደገን ይሆን? አብዛኞቹ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቫይረሱ በተከሰተባት የቻይናዋ ዉሃን ከተማ የነበሩ ናቸው። ቢሆንም ግን በሰው ለሰው ንክኪ ምክንያት የተያዙ 8 ሰዎች በጀርመን፣ ጃፓንና ቬትናም መኖራቸው መረጋገጡን ድርጅቱ አስታውቋል። የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ቴድሮስ አድሃኖም "ታይቶ የማይታወቅ ወረርሽኝ" በማለት የገለጹት ይህን ቫይረስ "የተለየ ፈጣን ምላሽ ያስፈልገዋል" ብለዋል። የሌሎች አገራት ዝግጅት ምን ይመስላል? መቋቋም በማይችሉት አገራት ውስጥ ቫይረሱ ቢከሰት ምን ሊሆን ይችላል? ብዙዎቹ በማደግ ላይ ያሉ አገራት በሽታውን የመለያ መሳሪያ ያጥራቸዋል። ይህ በመሆኑም በሽታው በማይታወቅ ሁኔታ ወደ እነዚህ አገራት ገብቶ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ። ይህ በሽታ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለዚያውም ከፍተኛ ጥረት በምታደርገው ቻይና ውስጥ 10 ሺህ የሚጠጉ ግለሰቦችን አጥቅቷል። ይህ ቀላል ቁጥር እንዳልሆነ እየተነገረ ነው። • ኮሮናቫይረስ በመላዋ ቻይና መዛመቱ ተነገረ፤ የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ ነው በ2014 በምዕራብ አፍሪካ የተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ በታሪክ አስከፊው ወረርሽኝ ነበር። ይህ የሆነው ደግሞ ድሃ አገራት ለጉዳዩ የሚሰጡት ምላሽ ካላቸው አቅም ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ለእንደዚህ ዓይነት ችግር ድሃ አገራት በእጅጉ ተጋላጭ መሆናቸውን ያሳያል። አስቸጋሪው ኮሮናቫይረስም እንደዚህ አይነት አገራት ውስጥ ከተከሰተ ውጤቱ አስከፊ ሊሆን እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም። አሁን ሌሎች አገራት ቻይና ባለችበት ደረጃ አይደሉም። 99 በመቶ የሚሆነው የቫይረሱ ስርጭትና ተጠቂዎች ያሉት ቻይና ውስጥ ነው። ስለዚህ "ሌሎች አገራት ቻይና ወደገባችበት ችግር ውስጥ እንዳይገቡ ርብርብ ማድረግ ያለባቸው ቫይረሱ እዚያው ቻይና ውስጥ እንዲከስም በማድረግ ነው" በማለት የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። በተመሳሳይ የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱን በአሳሰቢ ደረጃ መፈረጁ ድሃ አገራት የቁጥጥር ስራቸውን እንዲያጠናክሩና ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ለማስቻል ነው ተብሏል። ለመሆኑ ይህ አዋጅ ያልተለመደ ነውን? የዓለም ጤና ድርጅት እንደዚህ ዓይነት አዋጅ የሚያውጀው "በጣም የተለየ ነገር ሲከሰትና በዓለም አቀፋዊ ስርጭት መጠን ለሌሎች አገራትም ከፍተኛ ስጋት ሲደቅን ነው።" ከአሁን በፊት አምስት አስቸኳይ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት አዋጅ በዓለም የጤና ድርጅት ታውጇል። ቻይና ወረርሽኙን እንዴት እየተቆጣጠረችው ነው? ቫይረሱ 'ቲቤት' ውስጥ ተገኘ ማለት በቻይና ሁሉም አካባቢዎች ተዳርሷል ማለት ነው። የአገሪቱ የጤና ሚንስቴር እንዳስታወቀው እስካሁን 9 ሺህ 6 መቶ 92 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ማዕከላዊዋ ግዛት ሁቤይ በሁሉም በኩል በሮቿ እንድትዘጋ የተደረገ ሲሆን ቫይረሱ ከዚችው ግዛት የተከሰተ በመሆኑም አብዛኛዎቹ ሟቾች የሁቤይ ነዋሪዎች ናቸው። 60 ሚሊዮን ዜጎች በግዛቷ ይኖራሉ። በዚያች ግዛት የሚኖሩ ሰዎችም መሻሻል እሰኪኖር ድረስ ቤታቸው ውስጥ ሆነው እንዲያሳልፉ ተነግሯቸው፤ ቤታቸውን ቆላልፈው ተቀምጠዋል። ወደ አገሪቱ የሚደረጉ ጉዞዎች በመሰረዛቸውና ከቻይና የሚመጡ ተጓዦች ላይም እገዳዎች እየተጣለ በመሆኑ የዓለማችን ሁለተኛዋ ግዙፍ የምጣኔ ሃብት ባለቤት ቻይና ላይ ቫይረሱ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። የዓለም ምላሽ ምን ይመስላል? የውጭ አገር ዜጎችን በፈቃደኝነት ላይ ከዉሃን ከተማ የማውጣቱ ሂደት እንደቀጠለ ነው። እንግሊዝ፣ አውስትራሊያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሲንጋፖርና ኒውዚላንድ ቢያንስ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ዜጎች ለ2 ሳምንታት ያህል በጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ እንዲሆኑና ሙሉ በሙሉ ነጻ እስኪሆኑ በመጠበቅ ስርጭቱን እየተከላከሉ ነው። አውስትራሊያ የተጠረጠሩ ዜጎቿን ከዋናው የአገሪቱ ክፍል ወደ 2 ሺህ ኪሎ ሜትር አርቃ በክሪስማስ ደሴት ለማቆየት ወስናለች። ሌሎች አገራትም ከምርመራ ጋር በተያያዘ የመጨረሻ ውጤት ያልተገኘላቸውን ዜጎቻቸውን ለብቻ እየለዩ ነው።
43241266
https://www.bbc.com/amharic/43241266
ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር. . .?
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቅ ጥያቄያቸውን በይፋ ካቀረቡ አንድ ወር አለፋቸው።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና በአንዳንድ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየተከሰቱ ካሉት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ጎን በበርካቶች ዘንድ በቀጣይ የኢህአዴግ ሊቀ-መንበርና የሃገሪቱ ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ይሆናል? የሚለው ጥያቄ አነጋጋሪ እንደሆነ ነው። በዚህ ዙሪያ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) በአመራሩ ውስጥ ያደረገው ሽግሽግ በበርካቶች ዘንድ ዶ/ር አብይን ለቀጣዩ ቦታ የማመቻቸት እርምጃ እንደሆነ ተገምቷል። የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄም (ብአዴን) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን አቶ ደመቀ መኮንን በድርጅቱ ሊቀ-መንበርነት እንዲቀጥሉ ወስኗል። ይህም ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ሊወዳደሩ ይችላሉ የሚል ግምት እንዲኖር አድርጓል። አቶ ኃይለማሪያም የመጡበት የኢህአዴግ አባል ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ቀሪውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ዘመን የመጨረስ ድርሻ አለው በሚል እጩ ሊያቀርብ ይችላል እየተባለም ነው። ደኢህዴን ባደረገው የአመራር ለውጥ በክልሉና በፌደራል መንግሥት ውስጥ የቆዩትን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በሊቀ-መንበርነት መምረጡን አሳውቋል። አቶ ሽፈራውም ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታው ከሚቀርቡት ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ ሲባል ይገመታል። ከሁሉ ቀድሞ የአመራር ለውጥ በማድረግ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ሊቀ-መንበሩ ያደረገው ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) በብዙዎች ዘንድ ለጠቅላይ ሚኒስትርነቱ መንበር ፍላጎት እንደሌለው በግምት ደረጃ ይነገራል። ነገር ግን እስካሁን ኢህአዴግ ማን ሊቀመንበሩና የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ አልሰጠም። አባል ብሔራዊ ድርጅቶችም እንዲሁ ሊቃነ-መናብርቶቻቸውን ከመሰየም ውጪ በይፋ የገለፁት ነገር የለም። የህወሓት/ኢህአዴግ የቀድሞ አባልና በትግራይና በድርጅቱ ውስጥ በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት እንደሚሉት ሊቀ-መንበር የመምረጡ ነገር የሚወሰነው በአራቱ ድርጅት ውሳኔ መሰረት ነው። አቶ ገብሩ እስካሁን ያለውን ዝንባሌ በመመልከት በዋናነት ሁለት እጩዎችን ''ከብአዴን አቶ ደመቀ መኮንንና ከኦህዴድ ዶ/ር አብይ አህመድ የቅርብ ተፎካካሪ ሆነው ይቀርባሉ'' ብለው ያስባሉ። ለዚህም ''አቶ ደመቀ በሰላ ተተችተው ደክመዋል እስካልተባሉ ድረስ ምክትል በመሆናቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ሊይዙ ይችላሉ'' በማለት ምክንያታቸውን ያስቀምጣሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ''በሃገሪቱ ውስጥ ባለው የፖለቲካ ሁኔታ ከኢህአዴግ አመራር ወጣ በማለት የኢትዮጵያንም ሆነ የሕዝቡን ጥያቄ እንመልሳለን ብሎ ከተነሳው ከኦህዴድ አመራር መካከል የሆኑት ዶ/ር አብይ ሌላኛው ተወዳዳሪ ይሆናሉ'' ብለው ያስባሉ አቶ ገብሩ። በኢህአዴግ አሰራር የፓርቲውን ሊቀ-መንበር የሚሰይመው ምክር ቤቱ ነው። ምክር ቤቱ ከእያንዳንዱ ብሔራዊ ድርጅት በእኩል 45 ድምፅ የተወከሉበት 180 አባላት ያለው ነው። ስለዚህም ሊቀ-መንበር ለመሆን አንድ እጩ ከሁለት አባል ድርጅቶች አባላት በላይ ድምፅ ማግኘት ይኖርበታል። እንደ አቶ ገብሩ ግምት ዶ/ር አብይና አቶ ደመቀ እጩ ሆነው ከቀረቡ ''በምርጫው ሂደት ተወዳዳሪዎቹ ከድርጅታቸው በተጨማሪ የህወሓትንና የደኢህዴን አባላት ድምፅን ማግኘት የግድ ይሆንባቸዋል።'' በዚህ የምርጫ ሂደት የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ምርጫ ወሳኝ ነው። የምክር ቤቱ አባላት ካሉበት ብሔራዊ ድርጅት እጩዎች ውጪ በእራሳቸው ውሳኔ የፈለጉትን እጩ የመምረጥ ዕድል ቢኖራቸውም ይህ ሊሆን ይችላል በሚለው ላይ አቶ ገብሩ ጥርጣሬ አላቸው። ''በግልፅ ድምፅ የሚሰጥ ከሆነ አባላት በዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አሰራር ስለሚያዙ ተመሳሳይ ምርጫ ሊያደርጉ ይችላሉ'' ሲሉ ያብራራሉ አቶ ገብሩ። ጨምረውም ነገር ግን ብዙ ጊዜ እንደሚሆነው የድምፅ አሰጣጡ ምስጢራዊ ስለሚሆን የምክር ቤቱ አባላት ከራሳቸው ፓርቲ እጩና ከድርጅታቸው ፍላጎት ውጪ የመምረጥ እድል እንዳላቸው አመልክተዋል። አቶ ገብሩ ለቀጣይ የኢህአዴግ ሊቀ-መንበርነትና ለሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርነት አቶ ደመቀ መኮንንና ዶ/ር አብይ አህመድ እጩ ሆነው እንደሚቀርቡ ያላቸውን ግምት ሲያስቀምጡ በሌሎቹ በኩል ያለውን ሁኔታም ገልፀዋል። የቀድሞ ድርጅታቸው ህወሓትን በተመለከተ ዶ/ር ደብረፅዮን የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው መሄዳቸው በውድድሩ ውስጥ እንዳይገቡ አድርጓቸው ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ደኢህዴንን በተመለከተም ድርጅቱ በአቶ ኃይለማሪያም በኩል እድሉን ማግኘቱንና ''እስከማውቀው ተገምግመው ብቃት የላቸውም ተብለው በመውረዳቸው እንዲሁም እራሳቸውም አልፈልግም ብለው በመልቀቃቸው ይህ ዕድል ለእነሱ ተመልሶ የሚሰጥ አይመስለኝም'' ሲሉ ግላዊ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ማዕከላዊ ስብሰባ ተጠናቆ ወደ ምክር ቤት ስብሰባ ተሻግሯል። 180 አባላት ያሉት ምክር ቤት ከሚወያይባቸው አበይት አጀንዳዎች አንዱ የፓርቲውን ሊቀ-መንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያምን የሚተካ መሪ መምረጥ ነው። ከሚቀጥሉት ቀናት በአንዱም ገዢውን ፓርቲና ሃገሪቱን የሚመራ ግለሰብ ሊታወቅ እንደሚችል ይጠበቃል።
news-53012386
https://www.bbc.com/amharic/news-53012386
ከቁማር ጋር በተያያዘ በፖሊስ ይዞታ የቆየችው አህያ ነጻ እንድትወጣ ተወሰነ
ከሕገ-ወጥ ቁማር ጋር በተያያዘ በፖሊስ ይዞታ ሥር የቆየችው አህያ እንድትለቀቅ የፓኪስታን ፍርድ ቤት ወሰነ።
በገጠራማ ፓኪስታን የአህያ ፍጥነትን መሰረት በማድረግ ሕገ-ወጥ ውርርድ ማድረግ የተለመደ ነው። ፖሊስ እንዳለው አህያዋ 600 ሜትር የሚሆን ርቀትን በ40 ሰከንድ ውስጥ ሮጣ ትጨርሳለች፤ አትጨርስም በሚል ውርርድ እያደረጉ የነበሩ 8 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ነበር። ከቀናት በኋላም አህያዋ ከፖሊስ ይዞታ ነጻ ስትሆን፤ ስምንቱ ሰዎችም በዋስ ከእስር ተለቀዋል ተብሏል። በፓኪስታን ይህ ዜና "አህያ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋለች" ተብሎ ከተዘገበ በኋላ የበርካቶችን ቀልብ ስቦ ነበር። ፖሊስ ግን ለቢቢሲ በሰጠው ቃል አህያዋን ላልተወሰ ጊዜ ለመያዝ ተገደድኩ እንጂ በቁጥጥር ሥር አላዋልኩም ብሏል። ፖሊስ ጨምሮ እንዳለው ስምንቱን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ባዋለበት ወቅት፤ መሬት ላይ ጨርቅ ተዘርግቶ የተሰበሰበ 121ሺህ ሩፒስ (740 ዶላር) የውርርድ ገንዘብ በኤግዚቢትነት መያዙን አስታውቋል። የአከባቢው ፖሊስ አዛዥ ፖሊስ በኤግዚቢት ከያዘው ገንዘብ ጋር አህያዋ ከፖሊስ ጣቢያው አቅራቢያ በሚገኝ ስፍራ ለአራት ቀናት ገደማ ታስራ ቆይታለች። የፓኪስታን ጋዜጠኖች አህያዋ ታስራ በቆችበት ፎቶግራፍ ሲያነሷት እና የፖሊስ አባላትን በጥያቄ ሲያጣድፉ ታይተዋል። አህያዋ ከፖሊስ ይዞታ ነጻ ከወጣች በኋላ ባለንብረቷ እንዲረከባት መደረጉ ተነግሯል።
news-51396100
https://www.bbc.com/amharic/news-51396100
አሜሪካዊቷ ጠፈርተኛ አዲስ የህዋ ላይ ቆይታ ክብረ ወሰን አስመዘገበች
የናሳዋ ጠፈርተኛ ክርስቲና ኮች እስካሁን ወደ ህዋ በተደረገ ጉዞ ከዚህ ቀደም በሌላ ሴት የተያዘን ረጅሙን የበረራ ቆይታ በማጠናቀቅ የመጀመሪያዋ ሆናለች።
ክርስቲና ኮች ጉዞዋን ያደረገችበት የሩሲያዋ የህዋ መንኮራኩር ጉዞዋን አጠናቃ ካዛኪስታን ውስጥ ያረፈችው ዛሬ ነው። ክርስቲና በዓለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ ውስጥ 328 ቀናት በማሳለፍ ቀደም ሲል በአገሯ ልጅ ፔጊ ዋይትሰን ተይዞ የነበረውን የቆይታ ክብረ ወሰን ሰብራለች። የክርስቲና ቆይታ እስካሁን በህዋ ጣቢያ ውስጥ በመቆየት ወደር አልተገኘለትም ከሚባለው ከወንዱ የስኮት ኬሊ ቆይታ በ12 ቀናት ብቻ ያነሰ እንደሆነ ተነግሯል። መንኮራኮሩ ምድር ላይ ካረፈ በኋላ ለጋዜጠኞች ስላሻሻለችው የህዋ ክብረ ወሰን ስትናገር "እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ ከማለት ውጪየምለው ነገር የለኝም" ብላለች። ክርስቲና ባለፈው ታህሳስ በዋይትሰን ተይዞ የነበረውን የ289 ቀናት የህዋ ቆይታን ለማሻሻል ችላለች። ይህም ክብረ ወሰን በቀጣይ በሚደረጉ የህዋ ጉዞዎች ሊሻሻል እንደሚችል አመልካች ነው ተብሏል። ነገር ግን ዋይትሰን በተለያዩ ጊዜያት ህዋ ላይ በተደረጉ ቆይታዎች ብዛት ክብረ ወሰኑን እንደያዘች ስትሆን፤ በሦስት የተለያዩ ጉዞዎች ለረጅም ጊዜ ቆይታለች። ክርስቲና ኮች በህዋ ላይ በነበራት ቆይታ 5,248 ጊዜ መሬትን የዞረች ሲሆን የ223 ሚሊዮን ኪሎ ሜትሮች ጉዞን አድርጋለች። ይህም ከመሬት ወደ ጨረቃ የሚደረግ የደርሶ መልስ ጉዞን ይሆናል።
news-52946965
https://www.bbc.com/amharic/news-52946965
በሰሜን አፍሪካ የአል-ቃይዳ መሪ መገደሉን ፈረንሳይ አስታወቀች
ማሊ ውስጥ በተካሄደ ዘመቻ በሰሜን አፍሪካ የአል-ቃይዳ መሪ የነበረው አብድልማሊክ ድሮክዴል መገደሉን ፈረንሳይ አስታወቀች።
የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስትር ፍሎረንስ ፓርሊ እንዳሉት ድሮክዴል እና የቅርብ አጋሮቹ በዕለተ ረቡዕ በሰሜናዊ ማሊ በተደረገ ዘመቻ ተገድለዋል። ሚኒስትሯ አክለውም በሌላ ዘመቻ የኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ቡድን አዛዥ የሆነ ሰው በፈረንጆቹ ወርሃ ግንቦት ላይ በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስታውቀዋል። "በኃያልነት የተወጣናቸው ዘመቻዎች ለአሸባሪ ቡድኖቹ ትልቅ ኪሳራ ናቸው" ሲሉ ሚኒስትሯ የዘመቻውን ውጤት ተናግረዋል። አክለውም "ጦራችን ከሳህል አጋሮቻችን ጋር በመሆን ቡድኖቹን የማደን ተግባሩን ይገፋበታል" ይላሉ። በእስልማዊ ማግሬብ የአል-ቃይዳ መሪ የሆነው አብድልማሊክ በሰሜናዊ አፍሪካ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች አስተባባሪ ነበር። አልፎም የአል-ቃይዳ አጋር የሆነው ጃማት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊም አዛዥም ነበር። የኢስላሚክ ስቴት ቡድን አለቃ የሆነውና በዘመቻው በቁጥጥር ስር የዋለው ሞሐመድ ምራባት ደግሞ በታላቁ ሰሃራ የኢስላሚክ ስቴት ከፍተኛ ሹም ነበር፤ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግንቦት 11 ቀን ነው ይላል ሚኒስትሯ ያወጡት መግለጫ። ወርሃ ግንቦት መጀመሪያ አካባቢ አይኤስ ታጣቂዎቹ ከአል-ቃይዳ ጋር ማሊና ቡርኪናፋሶ ውስጥ የለየለት ጦርነት ውስጥ እንደገቡ አስታውቆ ነበር። አይኤስ፤ ጃማት ኑስራት ግዛቴን ነቅንቋል፣ የነዳጅ መስመሬን አቋርጧል እንዲሁም ደጋፊዎቼን አስሯል ሲል ይወቅሳል። አብድልማሊክ ድሮክዴል ማነው? በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንዳለ የሚነግርለት አብድልማሊክ አፍጋኒስታን ውስጥ የሶቪዬት ወታደሮችን ተዋግቷል። ዓላማው እንደ ቀድሞው በኢራቅ የአል-ቃይዳ መሪ አቡ ሙሳብ አል-ዛርቃዊ መሆን እንደነበርም ይነገራል። በእስላማዊ ማግሬብ የአል-ቃይዳ መሪ ሆኖ ሳለ ከአራት ዓመታት በፊት በቡርኪናፋሶ ኦጋዱጉ በፈፀመው ጥቃት 30 ሰዎች ሞተው 150 መጎዳታቸው አይዘነጋም። ከስምንት ዓመታት በፊት አልጄሪያ ውስጥ በሌለበት የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል። የአሸባሪ ቡድን አባል ነው እንዲሁም ፈንጂ በመጠቀም ጥቃቶች ፈፅሟል የሚሉ ክሶች ነበር የቀረረቡበት። ከዚያ በኋላ አልጄሪያ ውስጥ በእሱ መሪነት በተፈፀሙ ጥቃቶች 22 ሰዎች ሲሞቱ 200 ያክል ሰዎች ቆስለዋል። አልጄሪያዊ ዜግነት ያለው አብድልማሊክ በሰሜናዊ አፍሪካና ሰሃራ ክልል እጅግ ስሙ የገነነ ነው ይባልለታል። አልጄሪያ ውስጥ ከአንድም ሁለት ሦስቴ ጥቃቶች ፈፅሟል። ማሊ ውስጥ የሰፈሩ የፈረንሳይና የሌሎች አገራት ወታደሮችም ላይ ጥቃት ሰንዝሯል። የተባበሩት መንግሥት የፀጥታው ምክር ቤት አብድልማሊክ ፈንጂዎችን በመስራት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን ገድሏል ይላል። ቱኒዚያ፣ ኒጀርና ማሊ ውስጥ የምዕራብ አገራት ዜጎችን በማፈንም ይፈለግ ነበር። ጂሃዲስት ቡድኖች በባሕሪያቸው መሪ ሲገደል ተተኪውን ወዲያውኑ ያሳውቃሉ። ነገር ግን በሰሜን አፍሪካ በአል-ቃይዳና በኢስላሚክ ስቴት መካከል ከበድ ያለ ውጥረት በመኖሩ የአብድልማሊክ ሞት ዜና እንዲሰማ አልተፈለገም። የማሊ ቅኝ ገዢ የነበረችው ፈረንሳይ ማሊ ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን አስፍራለች። ወታደሮቹ ታጣቂ ቡድኖችን ለመዋጋት በሚል ነው የሰፈሩት።
news-47451771
https://www.bbc.com/amharic/news-47451771
የድኅረ ዐብይ ሚዲያ ምን ያህል ነፃ ነው?
የቢቢሲ አማርኛ ባልደረቦች በተለያዩ ስፍራዎች ጉዞ በማድረግ ከተለያዩ የማህብረሰብ ክፍል አባላት ጋር በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች በማድረግ ላይ ናቸው።
ከነዚህም አንዱ ትናንት ሰኞ የካቲት 25 ረፋድ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር የውይይት መድረክ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተዘጋጅቶ ነበር። የውይይቱ ዋነኛ ጭብጥ የነበረውም ወደ ስልጣን ከመጣ አንድ ዓመት ለመድፈን የተቃረበው የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስተዳደር ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የወደፊት አቅጣጫውስ? የሚል ሲሆን ትኩረቱንም በመገናኛ ብዙሃን ላይ አድርጎ ነበር። • "የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቁ ስኬት ብዙ ሰው በተስፋ እንዲኖር ማድረጋቸው ነው" ዶ/ር ዮናስ አዳዬ በውይይቱ ላይ ቢሰጥ አያሌው (ዶ/ር) የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ ዳዊት አሞኝ (ዶ/ር) የሂውማኒቲስ ፋካሊቲ ኃላፊ እና አደም ጫኔ (ዶ/ር) የሂውማኒቲስ ፋካሊቲ ምክትል ኃላፊ በመወያያ ርዕሱ ላይ አስተያየታቸውን ያጋሩ ሲሆን፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን የውይይቱ ታዳሚዎች ነበሩ። ውይይቱ የተጀመረው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የታዩት በጎ ለውጦች ምንድናቸው በሚለው የመወያያ ጥያቄ ነበር። •ኢትዮጵያውያን ዛሬም ከአለት አብያተ-ክርስትያናትን ያንፃሉ ዶ/ር አደም በመገናኛ ብዙሃን ዙሪያ ታይተዋል ካሏቸው ለውጦች መካከል የሚዲያ ምህዳሩ መከፈት መጀመሩን በዋናነት ያነሳሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ወደ 20 የሚጠጉ አዲስ የህትመት እና የብሮድካስት ሚዲያዎች መፈጠራቸውን እና ከሃገር ውጪ የነበሩ መገናኛ ብዙሃን ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጋቸውን የሚዲያው ምህዳር እየሰፋ ስለመሆኑ ማሳያ መሆናቸውን ዶ/ር አደም ይናገራሉ። ''ከዚህ በተጨማሪ አይነኬ ይባሉ የነበሩ ጉዳዮች በመንግሥት ሚዲያዎች ሁሉ ሲቀርቡ እያየን ነው፤ በርካታ ድምጾችም እየተሰሙ ነው። ይህም የሚዲያው ምህዳር እየሰፋ ስለመሆኑ ያሳያል''ይላሉ። ዶ/ር ዳዊት በበኩላቸው ባለፉት 12 ወራት በመገናኛ ብዙሃን ከታዩት ለውጦች በተጨማሪ በማህበራዊ ሚደያዎች አጠቃቀም ላይ ለውጥ መምጣቱን ይናገራሉ። ዶ/ር ዳዊት ሃሳባቸውን ሲያስረዱ ሰዉ የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የተሰማዉን ስሜት በነጻነት እያጋራ ይገኛል ይላሉ። •ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት በውይይቱ ተሳታፊ ከሆኑት መካከል የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ተማሪ የሆነው ሙሉቀን አሰግደው ይገኝበታል። ሙሉቀን ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የታዩትን ለውጦች ከዚህ ቀደምም መንግሥታት ሲለወጡ እንመለከተ የነበረው አይነት ለውጥ ነው ይላል። ''ከዚህ ቀደም ከነበረን ታሪክ እንደምረዳው መንግሥታት ሲቀየሩ፤ አዲስ መንግሥት ሲመጣ ሚዲያውን የመክፈት ባህሪ አላቸው። ሚዲያዎች አዲስ የመጣውን መንግሥት ማጀገን፤ ያለፈውን ደግሞ ማሳጣት ሥራዬ ብለው ይያያዙታል። መንግሥትም ሚዲያዎቹ ፊታቸውን ወደእሱ እስኪያዞሩ ድረስ በይሁንታ ይዘልቃል'' ሲል ሃሳቡን ያስቀምጣል። ሙሉቀን ጨምሮም የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዳደርም ለሚዲያዎች ምን ያክል ክፍት መሆኑ የሚፈተነው ከአሁን በኋላ በሚኖሩ ሁነቶች ነው ይላል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደስልጣን ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ በመገናኛ ብዙሃን ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የሚለው ጥያቄ የውይይቱ ተሳታፊዎች የተነጋገሩበት ርዕሰ ጉዳይ ነበር። ዶ/ር አደም ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተያያዘ ተፈጥሯል ያሉትን የሚዲያ ምህዳሩ መስፋት ሊመጥን የሚችል የባለሙያ እጥረት አለ ይላሉ። ''በስነምግባሩ የታነጸ፣ ሙያውን የሚያከብር ብዙ ጋዜጠኛ አለን ወይ?''ሲሉ ይጠይቃሉ። •ያልተጠበቁ ክስተቶች የታዩበት ዓመት አክለውም ''የሚዲያ ፍልስፍና ስለመኖሩ ከመንግሥት በግልጽ አልተነገረንም'' የሚሉት ዶ/ር አደም፤ ''ከዚህ ቀደም የነበረው ኢህአዴግ ባህሪው ሚዲያ ጠል ነበረ። ይህም ከሚከተለው 'ፖለቲካዊ-ኢኮኖሚ ርዕዮተ አለም' ጋር አብሮ ይሄዳል። አሁን ለውጡ ስርዓታዊ መሆን ይኖርበታል።'' በማለት ይናገራሉ። ከሚዲያው በተጨማሪ ማህበረሰቡም የሚቀርቡለትን መረጃዎች በአስተዋይነት እና በጠያቂነት ባህሪ ሊያጤናቸው እንደሚገባ ዶ/ር አደም ምክር ይለግሳሉ። ዶ/ር አደም በሃገራችን መገናኛ ብዙሃን ዙሪያ ሌላው እንደ ችግር ብለው የሚያነሱት ጉዳይ ክልላዊ የሆኑ የሚዲያ ተቋማት ጽንፍ የያዙ ዘገባዎችን በስፋት እያስተናገዱ መምጣታቸውን ነው። ''ከዚህ ቀደም በኢሳት እና ኢቲቪ መካከል እንመለከት የነበረውን ዓይነት በክልል ሚዲያዎች እየታዘብን ነው'' ይላሉ። ፅንፈኝነት ማቆጥቆጥ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ ሚዲያ ተግዳሮት፤ የምርመራ ጋዜጠኝነት ትኩረት ማጣት እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያዎች በመገናኛ ብዙኃን ላይ እየፈጠሩት ያሉት ጫና ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ''አክቲቪስቶች ለሚዲያዎች ርዕሰ ጉዳይ ሲሰጡ እያስተዋልን ነው'' የሚሉት ዶ/ር ዳዊት መገናኛ ብዙሃን በማህበራዊ ሚዲያ እና በአክቲቪስቶች ተጽዕኖ ሥር የመውደቅ ምልክትን እንደ ትልቅ የሙያ ጉድለት ያነሱታል። ከጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል የመጣው ስንታየሁ በበኩሉ ''በሃገራችን ያሉት መገናኛ ብዙሃን ሳይሆኑ የህዝብ ግንኙነት ተቋሞች ናቸው'' ይላል። ለዚህም እንደ ማጣቀሻ የሚያነሳው የክልል ሚዲያዎች የሚወክሉት እና የሚያንጸባርቁት የክልል መንግሥቱን ፍላጎት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከፓርቲ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሚዲያዎችም ተመሳሳይ መንገድ እንደሚከተሉ ያስረዳል። "ሚዲያው ብዙኃኑን ከመከተልና የተመረጡ ጉዳዮችን ብቻ ከመሸፈን ድምጻቸው ላልተሰማ ትኩረቱን መስጠት ይኖርበታል።"ይላል። መዋቅራዊ የሆነ አሰራር ባለመኖሩና የግለሰቦችን አጀንዳ ሲያራግቡም እንደሚታዩ ስንታየሁ ይናገራል። ከዚህም ውስጥ እንደ ምሳሌ የሚያነሳው በአንድ ወቅት አንድ አቀንቃኝ (አክቲቪስት) ያለውን ጉዳይ ነው። •ቢቢሲ አማርኛ ወደ እናንተ መጥቷል ''አክቲቪስቱ በተደጋጋሚ በቴሌቪዥን ላይ ከመቅረቡ የተነሳ ጋዜጠኞችን ለምንድነው ሥራ የማትሠሩት ለምንድነው ስለ እኔ ብቻ የምታወሩት ሲል እስከመገስጽ ተደርሷል'' ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደስልጣን ከመምጣታቸው በፊት መገናኛ ብዙሃን በሁለት ጽንፍ ተለጥጠው የቆዩ ነበሩ የሚሉት ደግሞ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ ዘላለም ተስፋየ ናቸው። ''በመንግሥት እና በግል ሚዲያዎች ዘገባ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ልዩነት ነበር። ዘገባዎቹ ጽንፍ የያዙ ነበሩ። መካከል ላይ እውነታውን የሚያሳይ አልነበረም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደስልጣን ከመጡም በኋላ ይህ ባህሪ እንዳለ ነው። የተቀየረ ነገር የለም።'' ይላሉ። •በኢትዮጵያውያን ተሰርቶ የአውሮፓውያንን ድጋፍ የሻተው ላሊበላ ምንም እንኳን ችግሮች ቢኖሩም ከላይ የተጠቀሱት ስኬቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት ተስፋ ሊያስቆርጥ እንደማይገባ ዶ/ር አደም ይናገራሉ። ሚዲያውን አስረው የቆዩ ህጎችን መቀየር፣ ጠንካራ የሚዲያ ተቋማትን መገንባትና በራሳቸው እንዲቆሙ ማድረግ፣ ለጋዜጠኝነት ሙያ ትኩረት መስጠት እና ለጋዜጠኞች እና ለሚዲያ ተቋማት ተገቢውን የህግ ከለላ ማድረግ፣ የሚዲያ ካውንስል ማቋቋም ይደር የሚባሉ ጉዳዮች እንዳልሆኑ ተወያዮቹ በዝርዝር አስቀምጠዋል።
news-53089296
https://www.bbc.com/amharic/news-53089296
በኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞን ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ
በቅርቡ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በጽኑ ታምመው ለሚገኙ ሰዎች ተሰጥቶ ውጤት ማሳየቱ የተገለጸው ዴክሳሜታዞን የተባለው መድኃኒት በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲወል ተወሰነ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፌስቡካቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት እንዳስታወቁት በዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በዴክሳሜታዞን የተባለውን መድኃኒት ለኮቪድ-19 ህሙማን ለመጠቀም የተደረገውን ጥናትና ሪፖርቱን በዝርዝር መስሪያ ቤታቸው እንደተመለከተው ገልጸዋል። ጨምረውም የሚኒስቴሩ የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድንና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት ያቀረበውን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ ጥቅም ላይ እንዲውል መወሰኑን አመልክተዋል። በዚህም "ዴክሳሜታዞን ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን የህክምና ባለሙያዎች በሚያዙት መሰረት እንደ ድንገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል" ብለዋል። በተጨማሪም በዚህ መድኃኒት የሚሰጠውን ህክምና አስመልክቶ በባለሙያዎች የሚዘጋጅ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ እንደሚወጣ የጤና ሚኒስትሯ ገልጸዋል። በሙከራ ወቅት የኮሮናቫይረስ ጽኑ ህሙማን ላይ ባሳየው ውጤት መሰረት ይህን መድኃኒት የዓለም የጤና ድርጅት እንደተቀበለው ከቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል። በሙከራው ላይ ዴክሳሜታዞን በኮሮናቫይረስ በጽኑ ከታመሙ ሰዎች መካከል የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት ደግሞ በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት ማመልከቱ ተገልጿል። ዴክሳሜታዞን ከ1960ዎቹ (እአአ) ጀምሮ በተለያዩ ህመሞች ምክንያት የሚያጋጥሙ እብጠቶችን ለመቀነስና የተወሰኑ አይነት የካንስር ህመሞችን ለማከም ጥቅም ሲውል ቆይቷል። በርካሽ ዋጋና በስፋት የሚገኘው ዴክሳሜታዞን በኮቪድ-19 በጽኑ የታመሙ ሰዎች ሕይወት አድን መሆኑ መነጋገሪያ ሆኗል። ይህ መድኃኒት የኮሮናቫይረስን የመከላከልም ሆነ የመፈወስ የታወቀ ውጤት እንደሌለው ባለሙያዎች የገለጹ ሲሆን አስፈላጊነቱም በሐኪሞች ሲወሰን በጸና ለታመሙ ሰዎች ብቻ የሚሰጥ ነው። በጤና ሚኒስቴር የህክምና ግልጋሎት ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ያዕቆብ ሰማን ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአንዳንድ ሰዎች ተጋንኖ እንደሚነገረው ሳይሆን የመድኃኒቱ ፋይዳ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ በፅኑ ሕክምና ላይ የሚገኙ ህሙማንን የሞት መጠን መቀነስ እንደሆነ፣ ይህ አዎንታዊ ጠቀሜታውም በቁጥር ደረጃ ሲሰላ አነስተኛ ነው ብለዋል። ከበሽታው እራስን ከመጠበቅ አንጻርም "በማኅበረሰቡ ዘንድ መዘናጋትን እንዳይፈጠር አሁንም ዋነኛው መተኮር ያለበት መንገድ ባለሞያዎች የሚሰጡት የመከላከያ እርምጃዎች ተግባራዊ መድረግ ነው" ብለዋል አቶ ያዕቆብ ሰማን።
news-52881187
https://www.bbc.com/amharic/news-52881187
“ኮሮናቫይረስን ለሦስት ሳምንታት በሦስት ሆስፒታሎች ታገልኩት”
ሦስት ልጆች በዊልቸር ያለ አባታቸውን እየቦረቁ ሲቀበሉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ በሺህዎች ታይቷል።
ጃክ ማክሊሀህ ልጆቹ የጃክ ማክሊሀህ ናቸው። ቪድዮው የተቀረጸው በሦስት የተለያዩ ሆስፒታሎች ለሦስት ሳምንት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎለት ወደ ቤቱ ሲገባ ነው። ድሩሞር በተባለች ከተማ ይኖራል። የአይቲ ባለሙያ ነው። ህክምናውን ሲያጠናቅቅ፤ በክሪያጋቮን፣ በማተር ሆስፒታል እና በናይቲንጌል ሆስፒታል ኦፍ ቤልፋስት እንክብካቤ ያደረጉለትን የህክምና ባለሙያዎችን በአጠቃላይ አመስግኗል። ምስጋናውን በማኅበራዊ ሚዲያም አጋርቷል። ሆስፒታል የገባው በእናቶች ቀን ነበር። አገግሞ ከወጣ በኋላም ድካም እንደሚሰማው ይናገራል። “ትንሽ በእግሬ ስንቀሳቀስ ይደክመኛል፤ ሆስፒታል ሳለሁ ከስቻለሁ፤ ሰውነቴን ዳግመኛ መገንባት አለብኝ” ይላል። ህመሙ የጀመረው ሚያዝያ ላይ ነው። አስር ቀን ራሱን አግልሎ ቤቱ ባለው ቢሮ ተቀመጦ ነበር። ከሚስቱ፣ ከሦስት ልጆቹና ከአማቹ ጋር አይገናኝም ነበር። በሽታው ተባብሶ ለመተንፈስ ሲቸገር ሆስፒታል ተወሰደና በጽኑ ህሙማን ማቆያ ገባ። ወቅቱን እንዲህ ያስታውሳል. . . “ለባለቤቴ ደወልኩላትና ጠዋት ህሊናዬን ስቼ ልታገኚኝ ትችያለሽ አልኳት። ወደ ጽኑ ህሙማን ማቆያ ክፍል እየተወሰድኩ ነው፤ ቬንትሌተርም ተደርጎልኛል ብዬም ነገርኳት። ከዚያ ከሁለት ሳምንት በኋላ ራሴን ሌላ ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁት።” ከሆስፒታሉ የወጣው በሦስተኛ ሳምንቱ ቢሆንም የተፈጠረውን ነገር በቅጡ አያስታውስም። ባለቤቱ ያኔ የየዕለት ውሎ ማስታወሻ ትይዝ ነበር። የጤና ሁኔታውን፣ የጻፈችለትን ደብዳቤ፣ አስቸጋሪ የነበረውን ወቅት እና ተስፋ የጣለችበትን ጊዜም በጽሁፍ መዝግባለች። ለፋሲካ ቤቱ ቢመለስም ሙሉ በሙሉ አላገገመም ነበር። ዶ/ር ማይክል መኪያና እንደሚሉት፤ ለማገገም ጊዜ ይወስዳል። “በቫይረስ ሳቢያ የተከሰተ በሽታ የያዛቸው ሰዎች ቬንትሌተር የሚያስፈልጋቸው ለሁለት ወይም ቢበዛ ለአራት ቀን ነበር። አሁን ግን ከ14 እስከ 20 ቀን ሲያስፈልጋቸው እናያለን” ይላሉ። ጃክ በቤቱ መናፈሻ ከባለቤቱ ጋር የውሎ መዝገቧን ያገላብጣል። ወደ ቤት ከተመለሰ በኋላም ለማገገም ቀላል እንዳልነበረ ይናገራል። “እናቴ ከዓመታት በፊት ታማ የገዛሁላትን ዊልቸር ነው የተጠቀምኩት። መጸዳጃ ቤት፣ ማዕድ ቤትም ለመሄድ እሱን እጠቀም ነበር። ሁሉም ቅርብ ቢሆኑም የምንቀሳቀሰው በዊልቸር ድጋፍ ነበር” ሲል ጃክ ያለፈበትን ያስታውሳል። ዶክተሩ እንደሚሉት ከሆነ፤ የትኛው ሰው ከበሽታው በቶሎ እንደሚያገገም ማወቅ አዳጋች ነው። ጃክ የአሁኑን የበጋ ወቅት ያለፈውን ጊዜ በማስታወስ ማሳለፍ ይፈልጋል። ምን እንደገጠመው እና ገጠመኙ ሕይወቱን እንዴት እንደቀየረውም ያሰላስላል። “በጽኑ ህሙማን ማቆያ ሆኜ፤ ቤቴ መመለስ አለብኝ ብዬ ሳስብ አስታውሳለሁ” ይላል። ምኞቱ ሰምሮ ቤቱ በመመለሱ ደስተኛ ነው። “ከቤተሰቤና ከልጆቼ ጋር መሆን እጅግ አስደሳች ነው። ምንም እንኳን ከቤት ባንወጣም አብረን መሆናችን ያስደስታል። በሕይወት የሚያስፈልገው ነገር ምን እንደሆነም አሳይቶናል።”
news-54875546
https://www.bbc.com/amharic/news-54875546
ከተክሎች ጋር መኖርና እነሱን መንከባከብ ለጤናችን ምን ያክል ይጠቅማል?
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካቶች አነስተኛ ተክሎችን በቤታቸው ማሳደግና መንከባከብ ጀምረዋል። በተጨማሪም ሰፋ ያለና ምቹ ግቢ ያላቸውም ሰዎች በግቢያቸው ውስጥ ትልልቅ ዛፎችን መትከል እየተለመ መጥቷል።
ለመሆኑ ከተክሎች ጋር መኖርና እነሱን መንከባከብ ለጤናችን ምን ያክል ይጠቅመን ይሆን? ዛፎች ሕይወትዎን ማዳን ይችላሉ፣ ደስተኛ ያደርጋሉ እንዲሁም ጠንካራ ጭንቅላት እንዲኖርዎ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይጫወታሉ የሚል ዓለም አቀፍ ጥናት በቅርቡ ተሰርቶ ነበር። ምንም እንኳን ዛፎች ጎርፍን፣ ድርቅን እና የአፈር መሸርሸርን ለመካከል ጠቃሚ እንደሆኑ ለብዙ ዓመታት በበርካታ ባለሙያዎች የተጻፈ ቢሆንም ዛፎች ከሰው ልጆች አስተሳሰብና የጭንቅላት አሠራር ጋር ስላላቸው ቁርኝት ግን ብዙም አልተባለም። ብዙዎቻችን እንደምናስበው ንጹህ አየር እንድንተነፍስ ብቻ ሳይሆን ተክሎች በርካታ ጠቀሜታዎች አሏቸው። ዛፎችንና አረንጓዴ ተክሎችን ዝም ብሎ መመልከት በራሱ ማዕከላዊ የአዕምሮ ክፍላችንን እንደሚያረጋጋው የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ዛፎችን መመልከት በጭንቅላታችን ውስጥ የሚመረተውን ኮርቲሶል የሚባለውን ለጭንቀት እጢ የሚያጋልጥ ንጥረ ነገር መጠን ይቀንሳል፣ የልብ ምትን ዝግ ያደርጋል፣ የደም ግፊትንም ይቀንሳል። ሌላው ቀርቶ የዛፎችን ፎቶ መመልከት እንኳን በጭንቅላታችን ውስጥ ጥሩ ስሜት ይፈጥራል። በሌላ በኩል ደግሞ ዓለማችን ከመቼውም በላይ እየሞቀች ነው። እንደ የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ከሆነ፤ በዓለም ዙሪያ ኢንዱስትሪው ከመስፋፋቱ በፊት ከነበረው የአየር ጠባይ ጋር ሲነጻጸር በአሁኑ ሰዓት የዓለማችን ሙቀት በአንድ ዲግሪ ጨምሯል። በዚህ አካሄድ 2100 ላይ የዓለም ሙቀት ከ3-5 ዲግሪ ሰሊሺየስ የሚጨምር ይሆናል። ምንም እንኳን በኢንዱስትሪው ዘርፍ የበለጸጉት አገራት ወደ ከባቢ አየር የሚለቁትን በካይ ንጥረ ነገር መቀነስ ወሳኝ ቢሆንም ይህንን የዓለማችንን በከፍተኛ ሁኔታ መሞቅ ለመቀነስና ብሎም ለማስቀረት ተክሎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ምናልባት እያንዳንዱ ሰው በቤቱ ውስጥ የሚያስቀምጣቸው አነስተኛ ተክሎች አልያም በአቅራቢያው የሚተክላቸው ዛፎች ለውጥ የሚያመጡ ላይመስል ይችላል፤ ነገር ግን በቢሊየኖች የሚቆጠረው የዓለም ህዝብ ሲደመር ግን ትልቅ ለውጥ ይፈጠራል። ሌላው ቀርቶ በቤታችን የምናስቀምጣት ትንሿ ተክል በትንሹም ቢሆን ጥቅም አላት። ለአእምሯችን ከምትሰጠው ሰላምና እረፍት በተጨማሪ የምንተነፍሰውንም አየር ጭምር ትቆጣጠራለች። የዘርፉ ባለሙያዎች የቤት ውስጥ ተክሎች በቤት ውስጥ ያለውን አየር እንዲሻሻልና ሰዎች ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዲፈጠር እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም ብናኞች፣ አላስፈላጊ ጋዞች እንዲሁም መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ ይጠቅማሉ። ከእነዚህ ውስጥ እንደ በለስ፣ የመጥበሻ ቅጠል፣ ብርቱካን፣ ካላንኮ፣ ማሬል የመሳሰሉ እፅዋት ይገኙበታል። በሆስፒታል ተኝተው የሚገኙ ታማሚዎች በመስኮታቸው በኩል ዛፎችን ማየት ከቻሉ የመዳን ፍጥነታቸው ይጨምራል ይላሉ ባለሙያዎቹ። ዛፎች ያላቸው የማረጋጋት አቅም ጭንቀትንና ህመመን እስከመቀነስ ይደርሳል። ተፈጥሯዊ በሆኑ ዛፎች መካካል ሥራቸውን የሚያከናውኑ ሠራተኞችም ቢሆን ውጤታማነታቸው ከሌሎች ከፍ ያለ እንደሚሆን ጥናቶች ይጠቁማሉ። በአጠቃላይ አንድ የቤት እንስሳ እንደምናሳድገው ሁሉ አንድ ተክል በቤታችን ካለ የምናገኘው ደስታ ወደር የለውም። በተጫማሪም ተክሎቹን በመንከባከብ የምናሳልፈው ጊዜ የሚሰጠን የአእምሮ እርካታ ከፍተኛ ነው።
news-55478321
https://www.bbc.com/amharic/news-55478321
በክሮሺያ በደረሰ ርዕደ መሬት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ
በክሮሺያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ በርካቶች ጉዳት ሲደርስባቸው ሰባት ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገለፀ።
በማዕከላዊ ክሮሺያ የደረሰው ይህ ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 6.4 ተመዝግቧል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ርዕደ መሬቱ ከደረሰ በኋላ በጎበኟት ፐትሪንጃ ከተማ አንዲት የ12 ዓመት ታዳጊ መሟቷን አስታውቀዋል። አምስት ሌሎች ሰዎች ደግሞ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ግሊና ከተማ መሞታቸውን ምክትላቸው ተናግረዋል። ሰባተኛው ሟች የተገኙት ዛዚና ከተማ በርዕደመሬቱ ምክንያት በፈራረሰ ቤተ ክርስትያን ፍርስራሽ ስር መሆኑን የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የፐትሪንጃ ከንቲባ እንዳሉት የከተማዋ ግማሽ ክፍል ሙሉ በሙሉ ወደ ፍርስራሽነት የተቀየረ ሲሆን ሰዎች ከፍርስራሽ ውስጥ እየተፈለጉ እና እየተጎተቱ እየወጡ ነው። ርዕደ መሬቱ እስከ ክሮሺያ ዋና ከተማ ዛግሬብ ድረስ የተሰማ ሲሆን ጎረቤት አገራት ሰርቢያ እና ቦሲኒያ እንዲሁም በርቀት የምትገኘው ጣልያን ድረስ መሰማቱም ተዘግቧል። የክሮሺያ መገናኛ ብዙሃን በፐትሪንጃ ከተማ አንዲት ሴት ከፍርስራሽ ውስጥ ተጎትታ መውጣቷን ዘግበዋል። "ሰዎችን ከመኪናቸው ውስጥ ጎትተን ስናወጣ ነበር፤ እንሙት እንጎዳ አናውቅም ነበር" ሲሉ ለአካባቢው የዜና ወኪል የተናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ዳርኒኮ ዱምቦቪች ናቸው። ፐትሪንጃ 20,000 ነዋሪዎች ያሏት ሲሆን ከንቲባዋ በድጋሚ አነስተኛ መጠን ያለው ርዕደ መሬት ከተሰማ በኋላ ለመገናኛ ብዙሃን "ሁሉም ሰው ተረብሿል፤ ዘመድ ወዳጁን ለመፈለግ ከወዲያ ወዲህ ይሯሯጣል" ሲሉ አክለዋል። በቅርብ ርቀት በምትገኘው ሲሳክ ከተማም እንዲሁ ሰዎች በርዕደ መሬቱ የተነሳ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ማምራታቸው ተሰምቷል። የአካባቢው ሆስፒታሎች በርካታ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለማከም ሲታገሉ ማስተዋሉን የብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ ዘግቧል። ከርዕደ መሬቱ አደጋ በኋላ የክሮሺያ ጠቅላይ ሚኒስትር 20 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ያሏትን ፐትሪንጃ ከተማን የጎበኙ ሲሆን "ለመኖር ምቹ አይደለችም" ሲሉ ተናግረዋል። መንግሥት ከተማዋን ዳግም ለመገንባት ቃል የገባ ሲሆን ነዋሪዎቿ ጊዜያዊ መጠለያ ይፈለግላቸዋል ሲል ተናግሯል።
news-51110718
https://www.bbc.com/amharic/news-51110718
በብሩንዲ ከአራት ሺህ በላይ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ
የብሩንዲው የእውነትና እርቅ ኮሚሽን ሃገሪቱ በአውሮፓዊያን 1962 ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ከ4000 በላይ የጅምላ መቃብሮችን በምርመራው እንዳገኘ አስታወቀ።
በ2018 የተቋቋመው ኮሚሽኑ፤ ላለፉት አስርት ዓመታት በብሄር ግጭቶች ስትታመስ በቆየችው ብሩንዲ ባደረግኩት ምርመራ በዓመታቱ የተገደሉ 142 ሺ 505 ሰዎች ማንነትም ጭምር ደርሼበታለው ብሏል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁት በ 1965፣ 1969፣ 1972፣ 1988 እና 1993 የተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች ላይ የወቅቱ ፖለቲከኞችም ጭምር ተሳታፊ ነበሩ በሚል ክስ ይቀርብባቸዋል። • እግራቸው አሜሪካ ልባቸው አፍሪካ ያለ የሆሊውድ ተዋንያን • በ2019 አፍሪካ ያጣቻቸው ታላላቆች ፖለቲከኞቹ በሁቱ እና ቱትሲዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት እንዲቀሰቀስም ዋነኛ ተሳታፊዎች እንደነበሩ በርካቶች ገልጸዋል። የኮሚሽኑ ዋና ጸሀፊ ፒዬር ንዳዪካሪዬ ለሀገሪቱ ፓርላማ ግኝታቸውን ሲያቀርቡ እንደገለጹት ''ከዚህ በኋላ ገና በርካታ የጅምላ መቃብሮችን እንደምናገኝ እናስባለን፤ ምክንያቱም ስለመቃብሮቹ የሚያውቁት ሰዎች ስለጉዳዩ ለማውራት ይፈራሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ከድርጊቱ አሰቃቂነት የተነሳ ስለጉዳዩ ማስታወስ አይፈልጉም'' ብለዋል። በጅምላ መቃብሮቹ የተቀበሩት ሰዎች እንዴትና በማን እንደተገደሉ ማወቅ በጥቃት ፈጻሚዎቹና በተጎጂዎች ቤተሰብ መካከል ሰላማዊ የሆነ የእርቅና የመግባባት ሥራ ለመስራት መሳኝ መሆኑንም ጸሀፊው አክለዋል። ሰኞ ዕለት 270 አስክሬኖች የተቀበሩበት አንድ የጅምላ መቃብር በቡጁምቡራ ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ነበር። መቃብሩ በአውሮፓዊያኑ 1993 የሃገሪቱ የመጀመሪያው ሁቱ ፕሬዝደንት ሜልቾር ንዳዳዬ መገደላቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት የተገደሉ እንደሆነ በርካቶች ገልጸዋል። • ብሩንዲ መጠጥ ቤቶች በጊዜ እንዲዘጉ አዘዘች የፕሬዝዳንቱን መገደል በሁቱ አማጺያንና በቱትሲዎች በብዛት በተዋቀረው የሀገሪቱ መከላከያ ኃይል መካከል 'እጅግ አሰቃቂ' የሚባል ግጭት ተቀስቅሶ ነበር። 12 ዓመት በፈጀው ጦርነትም ከ300 ሺህ በላይ ዜጎች ሞተዋል። በቡጁምቡራ የጅምላ መቃብሩን የተመለከቱ አንዳንድ ሰዎች፤ የአስክሬኖቹን አልባሳት በመመልከት የሟቾችን ማንነት መለየት የቻሉ ሲሆን በተጨማሪነት ደግሞ ከአንዳንድ ሟቾች ጋር መታወቂያዎች መገኘታቸውም ታውቋል።
news-41411128
https://www.bbc.com/amharic/news-41411128
ሳዑዲ አረቢያ ሴቶች እንዳያሽከረክሩ ጥላ የነበረችውን እገዳ ልታነሳ ነው
የአገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው ንጉስ ሳልማን ይፋዊ መግለጫ በመስጠት ነበር ፍቃዱን ያወጁት። የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲም እንደዘገበው ከመጭው ሰኔ ጀምሮ ውሳኔው ተግባራዊ ይሆናል።
ሴቶች መኪና እንዳያሽከረክሩ በመከልከል ሳኡዲ አረቢያ በአለም ብቸኛዋ አገር ናት። በአገሪቷ ህግ ወንዶች ብቻ ነበሩ መንጃ ፍቃድ ማውጣት የሚችሉት። ሴቶች በአደባባይ ሲያሽከረክሩ ቢገኙ መታሰር ወይም የብር ቅጣት ይጠብቃቸው ነበር። በማያፈናፍነውም ህግ ምክንያት ብዙ ቤተሰቦች ሴቶችን ከቦታ ወደ ቦታ ለማንቀሳቀስ የግል አሽከርካሪም ይቀጥሩ ነበር። ለአመታት የመብት ተከራካሪዎች ሴቶች ማሽከርከር እንዲፈቀድላቸው ዘመቻዎችን ቢያካሂዱም ምላሹ ህጉን በመተላለፍ ምክንያት ለእስር መዳረግ ነበር። ከነዚህም አንዷ የመብት አቀንቃኝ የሆነችው ሉጃን አል ሐትሉል ባለፈው ዓመት ለ73 ቀናት በእስር ላይ የነበረች ሲሆን ይህንንም ውሳኔ ተከትሎ "ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን" የሚል መልእክቷን አስተላልፋለች። ሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ በኪንግ ፋህድ ስቴዲየም ገብተው ደስታቸውን እንዲገልፁ ተፈቅዶላቸዋል። ማናል አል-ሻሪፍ "ሴቶች ለማሽከርከር" (ውሜን ቱ ድራይቭ) የሚለውን ዘመቻ አስተባባሪ ስትሆን በዚህም እንቅስቃሴዋ ለእስር ተዳርጋ ነበር። ውሳኔውንም አስመልክቶ በትዊተር ገጿ እንዳሰፈረችው "ወደ ኋላ አንመለስም" ብላለች። ሌላኛዋ አቀንቃኝ ሳሐር ናሲፍ ጂዳ ላይ ሆና ለቢቢሲ እንደተናገረችው "በጣም ተደስቻለሁ፤ ከላይ ከታች እየዘለልኩና በመሳቅ ላይ ነኝ" ስትል ደስታዋን ገልፃለች። "አሁን የማልመውን ጣሪያው ተከፋች፤ ጥቁርና ቢጫ ቀለም መኪና ነው የምገዛው" ብላለች። በዚህ ውሳኔ ሁሉም አካል ደስተኛ አልነበረም በተለይም ወግ አጥባቂው አካል መንግሥትን የሸሪዓ ህግን አፍርሷል በማለትም ይወነጅላል። "እስከማውቀው ድረስ የሸሪዓ ምሁራን የሴቶችን ማሽከርከር የተከለከለ (ሀራም) እንደሆነ ተናግረዋል። እንዴት አሁን ተፈቀደ?" በማለት አንድ ግለሰብ ትችቱን በትዊተር ገፁ አስፍሯል።
news-47131238
https://www.bbc.com/amharic/news-47131238
ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን
የቻይና እጅ ሽሮ ሜዳ ድርሷል፤ እርግጥ ነው የቻይና እጅ ያልገባበት የለም። አዲስ አበባን ዞር ዞር ብሎ ለቃኘ ቻይናውያን ከዚህ በፊት ያልመድናቸውን ተግባራት ሲፈፅሙ ማየት አዲስ አይሆንበትም።
የባህል ልብስ ውበት ነው፤ የባህል ልብስ 'ባህል' ነው፤ በዓል ነው፤ መለያም ጭምር። እኒህ አልባሳት በባህላዊ መንገድ ተሠርተው ከአራቱም የሃገሪቱ ማዕዘናት ጉዟቸውን ወደ አዲስ አበባ፤ በተለይ ደግሞ ሽሮ ሜዳ ያደርጋሉ። • አክሱምና ላሊበላ ለስራዎቹ መስፈርት የሆኑት ዲዛይነር አሁን አሁን ግን አደጋ የተጋረጠባቸው ይመስላል። ቻይና ውስጥ ተሠርተው የሚመጡ ጨርቆች ገበያውን መቀላቀል ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። አቤል ብርሃኑ ሽሮ ሜዳ ግድም አንዲት የባህል አልባሳት መሸጫ ሱቅ አለችው። ገበያ ነውና ቱባውንም ይሁን የቻይና እጅ ያረፈባቸውን አልባሳትን ይሸጣል። የኑሮ ነገር «በሃገራችን እጅ የተሠራውን አንድም ሳልሸጥ የምውልበት ቀን በርካታ ነው፤ ነገር ግን ቻይና ሰራሹን በቀን እስከ 30 ድረስ ልሸጥ እችላለሁ» ሲል አቤል የገበያ ውሎውን ይናገራል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የዋጋ ልዩነቱ ነው፤ የቻይናው ከ400 ብር ጀምሮ ሲገኝ በሃገር ልጅ እጅ የተሠራው ከ2000 ብር አንስቶ እስከ አሰራዎቹ ድረስ ሊሸመት ይችላል። • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት ሌሎችም ሽሮ ሜዳ አካባቢ ያሉ መሰል አልባሳትን የሚሸጡ ነጋዴዎች የሚሉት ይህንን ነው። በሸማኔ ከሚሠራው የባህል ልብስ ይልቅ እየተቸበቸበ ያለው በማሽን ታትሞ በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርበው የቻይና እጅ ያረፈበት ልብስ ነው። የቱባውን ባህላዊ ልብስ ክብር የሚያውቅና አቅሙ ያለው ብቻ በሺህ ቤቶች አውጥቶ እንደሚገዛ አቤል ምስክርነቱን ይሰጣል። ወደ ኤግዚቢሽን ማዕከል. . . ዕለተ አርብ ነበር 10ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል የተዘከረው፤ በርካታ ባህላዊ ልብሶችን የሚሸጡ ነጋዴዎች በተገኙበት። ደርጉ ደሌ ሸማኔ ነው፤ ከባልደረባው ጋር በመሆን ትርዒቱ ላይ የሽመና ሥራን ለማስተዋወቅ ነበር ኤግዚብሽን ማዕከል የተገኘው። «በሸማኔ የሚሠሩ ባህላዊ ልብሶች ብዙ ውጣ ውረድ አልፈው ነው እዚህ የሚደርሱት። ከጥጥ ማምረት ጀምሮ፤ መፍተል እንዲሁም ከሳባ ወይም ከመነን ጨርቅ ጋር አስማምቶ መሸመን ትልቅ ጥበብ ነው፤ አድካሚም ነው» ይላል። የቻይኖቹ ነገርስ?. . .«በጣም ፈተና የሆነብን ነገር ነው» ይላል ደርጉ። «የቻይናዎቹ አቡጀዲ ጨርቅ ላይ እነሱ ያተሙት ጥለት መሰል ጨርቅ ይለጠፍበታል። ለመሥራት በጣም ቀላል ነው። ለዚያ ነው በርካሽ ዋጋ የሚሸጠው።» • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን አቤልም በዚህ ይስማማል። «ይሄ አሁን ለምሣሌ. . .» ይላል ከተንጠለጠሉት ቻይና ሠራሽ ልብሶች ወደ አንዱ በመጠቆም። «ይሄ አሁን ለምሳሌ 'ልጥፍ' ይባላል። አቡጀዲ ጨርቅ ነው። ከዚያ በቻይናዎች ማሽን የታተመ ጥለት መሳይ ነገር ይለጠፍበታል።» ፋና የባህል ልብስ መሸጫ ሱቅ አላት። ቱባ ምርቶቿን ማስተዋወቅ ያመቻት ዘንድ ነው ኤግዚቢሽኑ ላይ የተገኘችው። «እኔ የምሸጣቸውን ልብሶች የማሠራው በሸማኔ ነው» ትላለች። ነገር ግን የቻይና እጅ አርፎባቸው በረከሰ ዋጋ ገበያውን ያንበሸበሹት አልባሳት ጉዳይ ሳያስጨንቃት አልቀረም። «እኛ ትክክለኛውን እና ባህሉን የጠበቀውን ልብስ ወደ ገበያ ለማቅረብ ብዙ ነገር እናደርጋለን፤ ወጪውም ቀላል አይደለም። ነገር ግን አሁን አሁን ገበያ ላይ የሚታዩ የቻይና እጅ ያረፈባቸው ጨርቆች ጉዳይ እጅግ ሞራልን የሚነካ ነው።» • ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ? የሃገራችንን ባህላዊ ጥለት መስለው በማሽን የሚታተሙት ጨርቆች ግማሾቹ ከቻይና ተመርተው እንደሚመጡ፤ ኢትዮጵያ ውስጥም የሚመረቱ እንዳሉ የሽሮ ሜዳ ሰዎች ይናገራሉ። መርካቶ ውስጥ በጣቃ መልክ መጥተው በሜትር እንደሚሸጡም ነው ነጋዴዎቹ የሚያስረዱት። ቢቢሲ እንደታዘበውም አንዳድንድ ቦታ ጨርቆቹ በመጋረጃ መልክ ተሰቅለው ይታያሉ። የተቆጣጣሪ ያለህ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የቱሪዝም ቢሮ የባህል፣ እሴቶች እና ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አዳነች ካሳ ቢሯቸው «ሁኔታውን እየተከታተለው እንደሆነ» ይናገራሉ። ነጋዴዎች ግን ግብር ለማስከፈል በየወቅቱ ከሚጎበኟቸው የመንግሥት ሰዎች በዘለለ የቻይና እጅ መርዘምን ተመልክቶ በጀ ያላቸው ማንም ሰው እንደሌለ ያስረዳሉ። «እኔ እስከማውቀው ድረስ ማንም ሰው መጥቶ አላነጋገረንም፤ የሚመለከተው የሚባለው የመንግሥት አካል ቢመጣ እንኳ የቻይናውን ገዝቶ ይሄዳል እንጂ (ሳቅ) ነገሩ ሲገደው አላየሁም» ይላል አቤል። • የባለዳንቴሏ የክር ጫማዎች የሽማና ሙያተኛው ደርጉም ማንም ወደ ሽሮ ሜዳ ብቅ ብሎ 'የቻይናን ነገር ለእኔ ተዉት' ያለ የመንግሥትም ሆነ በግሉ የሚንቀሳቀስ ሰው እንዳላጋጠመው አውግቶናል። ወ/ሮ አዳነች ግን ዋናው የጉዳዩ ተባባሪ ሕብረተሠቡ እንደሆነ ያስረግጣሉ። «ይህ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ ብቻ አይደለም። በፌዴራል ደረጃም ሊታይ የሚገባው ነው። እኛ ከሚዲያውም ጋር ሆነ ከሚመለከታቸው ጋር ለመሥራት ዝግጁ ነን። ነገር ግን ዋናው ተዋናይ ሕብረተሰቡ ነው። ሕዝቡ አይሆንም ካለ፤ እኒህ የቻይና ጨርቆች ከገበያ የማይወጡበት ምክንያት የለም» ይላሉ። ያም ሆነ ይህ የቻይና እጅ ሽሮ ሜዳ መድረስ ግድ ሊለን የሚገባ ይመስላል። በጥንቃቄ ካልተያዘ ዘመናዊነት ይዞ የሚመጣው ለውጥ መልካም የባህል እሴትን ሊያጠፋ እንደሚችል የሁሉም ስጋት ነው። በሽመና ባለሙያዎች ጥበብ አምረው የሚሰሩት ባሕላዊ አልባሰት በቻይናዊያን ታትመው ከሚመጡት ጋር ተወዳድሮ ገበያ ውስጥ መዝለቁ እያነጋገረ ነው።
news-53195452
https://www.bbc.com/amharic/news-53195452
ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት ድርድራቸውን ለማጠናቀቅ ተስማሙ
ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲያደርጉት የነበረውን ድርድር ለማጠናቀቅ ሲስማሙ ኢትዮጵያም ከሁለት ሳምንት በኋላ የውሃ ሙሌት ለመጀመር እንዳቀደች አስታውቃለች።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ዛሬ ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይ ሦስቱ አገራት ድርድራቸውን በማጠናቀቅ ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ መወሰናቸውን አመልክቷል። ጨምሮም ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ ሙሌት በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ለመጀመር ዕቅድ የያዘች መሆኑን አመልክቶ በዚህ ጊዜም ቀሪ የግንባታ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ ገልጿል። በዚህ የሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥም ሦስቱ አገራት መቋጫ ባለገኙ ቀሪ ጉዳዮች ላይ ድርድራቸውን በማካሄድ ከስምምነት እንዲደረስ ትናንት በነበረው ውይይት ላይ እንደተስማሙ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ አመልክቷል። በውይይቱ ላይ አገራቱ ጉዳያቸው በአፍሪካ ሕብረት እንደተያዘ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት እንዲያሳቁና ሦስቱም አገራት አላስፈላጊ ከሆነ የመገናኛ ብዙሃን ውዝግብ እንዲቆጠቡ ተጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ [ዶ/ር] በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እንዳሉት በደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ መሪነት ትናንት ምሽት በሦስቱ አገራት መሪዎች መካከል በተደረገው ውይይት ላይ ከሁለት እስከ ሦስት ሳምንት አገራቱ ድርድራቸውን እንዲያጠናቅቁ ተስማምተዋል ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሮይተርስ፤ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በሚደረግ ድርድር ከስምምነት ላይ ሳይደረስ የህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት እንዳትጀምር ከስምምነት ላይ መደረሱን ዘግቧል። ሮይተርስ ከግብጽ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የወጣን መግለጫ ጠቅሶ፤ በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ በተናጠል ግድቡን በውሃ መሙላት እንደማትጀምር ገልጿል። ሮይተርስ ጨምሮም "ለሚደረገው ድርድር ስኬት አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ የተናጠል እርምጃ እንደማትወስድ" የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ እንደተናገሩ የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ብሏል። የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤኤፍፒም በጉዳዩ ላይ እንደዘገበው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን ግዙፍ ግድብ በውሃ የመሙላት ዕቅዷን እንደምታዘገየው የግብጽ ፕሬዝዳንትን ጠቅሷ ገልጿል። ኤኤፍፒ በተጨማሪም የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ "አገራቱ በድርድር ከስምምነት እስኪደርሱ ድረስ ግድቡን በውሃ የመሙላቱ ሥራ እንዲዘገይ ስምምነት ተደርሷ" ማለታቸውን ዘግቧል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳለው ኢትዮጵያ ባቀረበችው ሃሳብ መሰረት ከሦስቱም አገራት የተወጣጣ የቴክኒክ ኮሚቴ በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ አጠቃላይ የስምምነት ሃሳብ ለማቅረብ ይሞክራሉ። ቢቢሲ፤ ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እየወጡ ስላሉት መረጃዎች ለማጣራት ጥረት እያደረገ ነው። በኢትዮጵያ በኩል ግን የውሃ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት በአገራቱ መካከል ውይይት መደረጉንና በዚህም መሰረት በቀጣዮቹ ሦስት ሳምንታት ውስጥ ድርድራቸውን ለመቋጨት መስማማታቸውን እንጂ የግድቡን ውሃ ሙሌት መዘግየትን በተመለከተ ያሉት የለም። ኢትዮጵያ ግንባታውን እያጠናቀቀችው ያለው ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት ታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በሦስቱ አገራት መካከል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየው ድርድር ያለውጤት እስከ ዛሬ ደርሷል። ከሳምንት በፊት በኢንተርኔት አማካይነት ሲደረግ የነበረው ድርድር ግብጽ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግሥታት በመውሰዷ መቋረጡ ይታወሳል። ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ከማጠናቀቅ ጎን ለጎን የመጀመሪያ ደረጃ የውሃ ሙሌት ሥራ በመጪው ሐምሌ ወር ዕቅድ መያዟን ከወራት በፊት ያስታወቀች ሲሆን ከግብጽና ከሱዳን ተቃውሞዎች ተሰምተዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት 'አገሪቱ ከየትኛውም ወገን የሚሰጥን ይሁንታ ሳትጠብቅ በያዘችው ዕቅድ መሰረት ግድቡን በውሃ መሙላት እንደምትጀምር' አስታውቆ ነበር።
news-47357832
https://www.bbc.com/amharic/news-47357832
በረከት ስምኦን ስለራሱ ይናገራል
ኤርትራዊው በረከት ስምኦን ወላጆቹ ያወጡለት ስም በተለያየ ምክንያት በተለያዩ ፀሐፊያን ሲብጠለጠል እንደነበር የተረዳው ዘግይቶ ነው። ሰዎችን እንደገደለ፣ ከኢትዮጵያ አምልጦ ፈረንሳይ፣ ፓሪስ እንደሚኖር ተፅፏል። ይህ ሁሉ ሲሆን ጉዳዩን ከቁብ ቆጥሮ አልተከታተለውም።
በረከት ስምኦን በኋላ ላይ ግን የተፃፈው ነገር እሱን ብቻ ሳይሆን ሁለት እህቶቹንም አካተተ። ያኔም በርካቶች ይፈሩት፣ ይደነግጡ ጀመር፤ በዚህ ወቅት ስጋት ገባው። ከኤርትራዊያን የተወለደው በረከት ስምኦን ያደገው አዲስ አበባ ፖፖላሬ አካባቢ ሲሆን በልጅነቱ ክረምትን ያሳልፍ የነበረው ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ኤርትራ ውስጥ ነበር። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» ኑሮውን በፈረንሳይ ካደረገ 40 ዓመታትን ያስቆጠረው በረከት ስምኦን በስሙ ምክንያት ብዙ ችግሮች ገጥሞታል። ከኢትዮጵያ ከመውጣቱ በፊት ስለነበረው ሕይወት ብዙ ያጫወተን በረከት ለዘመቻ (ዕድገት በሕብረት) ወደ ወለጋ ተልኮ ከነበረበት ጥሎ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሰና ኢህአፓን በአዲስ አበባ ውስጥ ወረቀት በመበተን መቀላቀሉን ያስታውሳል። በረከት በወቅቱ የኢህአፓን የፕሮፓጋንዳ ጽሑፎች ቤት ለቤት ይበትን ነበር። ከዚያም አልፎ በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች 'መንግሥትን ክደዋል' ተብሎ ስም ዝርዝራቸው የተያዘ ግለሰቦችን ሰነድ ሰርቆ ያጠፋ እንደነበርም ያስታውሳል። አንዳንዴ የጦር መሣሪያዎችን እንዲደብቅ ወይም እንዲያቀብል ይጠየቅና ይከውን እንደነበርም አልሸሸገም። በረከት እንደሚያስታውሰው በዙሪያው ከነበሩት ሰዎች መካከል የጠፉ፣ ሀገር ጥለው የወጡ፣ የታሰሩና የተገደሉ አሉ። • በደብረማርቆስ 'ባለስልጣኑ አርፈውበታል' የተባለው ሆቴል ጥቃት ደረሰበት በረከት ከዕድገት በሕብረት ዘመቻ በመመለሱ አቋርጦት የነበረውን ትምህርቱን የመቀጠል ብርቱ ፍላጎት ነበረው። በዚህ ወቅት ነው ስሙ 'ኮብልሏል' ከሚል ዝርዝር ውስጥ መካተቱን ያወቀው። ይኼኔ ይላል በረከት "ወረቀት የመስረቅ ልምድ ስለነበረኝ አራት ኪሎ ከሚገኝ መሥሪያ ቤት ገብቼ ስሜ የነበረበትን ደብዳቤ፤ አጣጥፌ በኪሴ ደብቄ ወጣሁ።" ይህን በማድረጉ ከመንግሥት ትኩረት ለጊዜውም ቢሆን መሰወር ስለቻለ ወደ ሊሴ ገብረማሪያም ተመልሶ ትምህርቱን አጠናቀቀ። ከሊሴ ገብረማሪያም ከተመረቀ በኋላም ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝቶ ወደ ፈረንሳይ ማቅናቱን ይናገራል። "ወረቀቱን ከሠረቅኩበት መሥሪያ ቤት ሄጄ ከሃገር ለመውጣት እንድችል የሚያሰፈልገኝን ወረቀት እንዲፈርሙልኝ ጠየኳቸው... እነሱም ፈረሙልኝና ወጣሁ።" የበረከት ስምኦን መታወቂያ በረከት ስምኦን ማን ነው? በረከት ስምኦንን፤ የቀድሞውን የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትርና በአሁኑ ወቅት በባህር ዳር በማረሚያ ቤት የሚገኙት ሞክሼው ጋር ይተዋወቁ እንደሆን ስንጠይቀው "ማን እንደሆነ አላውቅም። አግኝቼውም አላውቅም። እኔ ግን በረከት ስምኦን እባላለሁ" ሲል መልሶልናል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስትር የነበረው በረከት ስምኦን ስሙን የወረሰው ከእኔ እንደሆነ የሚገልጽ ጽሑፍ ወጥቶ እንደነበር ሰምቻለሁ የሚለው በረከት፣ በዚህም የተነሳ ሰዎች ከእሱ ጋር እንደሚያመሳስሉት ይናገራል። "መጀመሪያ ምንም አልሰማሁም ነበር። በረከት ስምኦን ትክክለኛ ስሙም ይመስለኝ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት እህቶቼ አሥመራ እያሉ 'ወንድማችሁ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየሠራ ነው' ብለዋቸው ትኩረቴ ተሳበ። ምን እንደሆነ ለማየት ብቻ አሥመራ ሄድኩኝ። ሲያዩኝ ሌላ ሰው እንደሆንኩኝ ሲገነዘቡ ምንም አላሉኝም።" • "...ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ ከዚያ ቀጥሎ ግን በበይነ መረብ ብዙ ነገሮች ማንበብ እንደጀመረ ይናገራል። ከስም መመሳሰል ውጪ እርሱን ከበረከት ስምኦን ጋር ማገናኘታቸው ግራ እንደሚያጋባው ገልጾ "ታሪኩ ከእኔ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም" ይላል። "ጸሐፊው እንዴት አድርጎ እኔ ላይ እንዳተኮረ ሊገባኝ አልቻለም" የሚለው አቶ በረከት "በተለይ ሁለቱንም እህቶቼን ጠቅሶ የጻፈ በመሆኑ ነው ቀጥታ ከእኔ ጋር ሊያያዝ የቻለው። እኔ ግን [የኮሙኑኬሽን ሚኒስትሩ] አልነበርኩም።" "በአንድ ወቅት ቀልድም መስሎኝ ነበር" የሚለው በረከት ነገሩ እየተደጋገመ ሲመጣ ግን እያስጨነቀው መጣ። "አብረውኝ የተማሩት ጓደኞቼን በስልክ ሳገኛቸው... ያነበቧቸውን ነገሮች በሙሉ እኔ እንደሆንኩ አርገው ነበር ያመኑት" በማለት ያስረዳል። የአቶ በረከት ስምኦን የልደት ምሥክር ወረቀት ኤርትራዊው በረከትና የተሳከረው ማንነት በረከት ስምኦን ኢትዮጵያ በየተወሰነ ጊዜ ይመላለሳል። በአንድ ወቅት ከባለቤቱ ጋር ላሊበላ ባለ አንድ ሆቴል ቆይታ ለማድረግ ፈልገው ለእንግዳ ተቀባዩ ማንነታቸውን የሚገልፅ መረጃ እየሰጡ ሳለ የእሱን ስም ሲመዘግቡ መደናገጣቸው በፊታቸው ይነበብ ነበር ይላል። በረከት ስምኦን እሱን እና እህቶቹን የጠቀሰው ጽሑፍ ስለማንነቱ የተወሰኑ መረጃዎችን በማስፈሩ ብዙ ሰዎች እንዲፈሩት፣ እንዲጠራጠሩት እንዳደረገ ይናገራል። • 'በእኔ በኩል ሒሳቤን ዘግቻለሁ ' አቶ ታምራት ላይኔ "ሰዎችን ገድሏል፣ ከኢትዮጵያ አምልጦ ፓሪስ ነው ያለው ተብሎ ነበር የተጻፈው። ጸሐፊው ከየት አምጥቶ ይህን ሁሉ እንደጻፈ አልገባኝም። እኔ የወጣሁት በሕጋዊ መንገድ ነው። ደግሞም ፓሪስ ኖሬ አላውቅም። ቤተሰባችን ውስጥ 10 ነን፤ ነገር ግን ሁለቱን እህቶቼን ብቻ መርጦ ለምን እንደጠቀሰ ግራ ገብቶኝ ነበር" ካለ በኋላ "እኔ እንደሚመስለኝ ሁለቱ እህቶቼ ታጋይ እንደነበሩ፣ በረከት ስምኦን የሚባልም [ወንድም] እንዳላቸውና... ፈረንሳይ መሆኔን ካወቀ በኋላ ነገሮቹን አገጣጥሞ ታሪክ የሠራ ይመስለኛል።" አሥመራ የነበሩት እህቶቹ በዚህ ጽሑፍ ምክንያት 'ወንድማችሁ ከሃዲ ነው'፣ 'ወንድማችሁ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየሠራ ነው' እና ሌላም ወቀሳ ይደርስባቸው እንደነበር ያስረዳል። በረከት ምን ይሠራል? "ምናልባት ሌላ በረከት ስምኦን ሊኖር ይችላል። እኔ ግን 'በረከት እያሱ' እንጂ ሌላ በረከት ስምኦን የሚባል ገጥሞኝ አያውቅም" የሚለው በረከት፣ በስሙ የተነሳ ከበርካታ ሰዎች ጋር የነበረው ግንኙነት እንደተበላሸ ይመሰክራል። ይህንንም ሲያስረዳ "አንድ ጓደኛዬ ሰው ሞቶበት ላጽናናው ደውዬለት ጭራሽ እንደማያውቀኝ ሆነብኝ። እኔም ግራ ገባኝ። ከዚያ ሲያስረዳኝ ትክክለኛው በረከት ስምኦን መስዬው እንደሆነ አስረዳኝ። ከብዙ ጓደኞቼ ጋር ግን አቆራርጦኛል።" • "በረከትና ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ ሰው ገድሏል በመባሉ የሸሹትን ሰዎች ሲያስብ "ያናድዳል" ይላል። አሁን ነገሩ እየከበደ ሊመጣ ይችላል እያለ የሚሰጋው በረከት "ክስ ልመሠርት ሁሉ አስባለሁ" ይላል። በረከት በአሁኑ ወቅት በፈረንሳይ ናንት በምትባል ከተማ ውስጥ ኑሮውን ያደረገ ሲሆን የሦስት ልጆች አባትም ነው። የእንስሳት ሐኪም የሆነውና የራሱን ክሊኒክ ከፍቶ እየሰራ የሚገኘው የ60 ዓመቱ በረከት "ጡረታ ልወጣ ትንሽ ነው የቀረኝ" በማለት ልጆቹ ለዩኒቨርሲቲ እንደደረሱለት አጫውቶናል።
news-55631984
https://www.bbc.com/amharic/news-55631984
አሜሪካ ፡ የፕሬዝደናት ዶናልድ ትራምፕን መከሰስ የፓርቲያቸው አባላት ጭምር እየደገፉ ነው
ዲሞክራቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕን ጥቂት ቀናት ከቀረው ሥልጣናቸው ለማባረር የሚያደርጉት ጥረት ከሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተነገረ።
የፓርቲያቸው አባል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሥልጣን እንዲባረሩ የሚጠይቀው ክስ እንዲመሰረትባቸው ድጋፋቸውን ከገለጹት መካከል በተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛዋ የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴ ሊዝ ቼኒ፤ ባለፈው ሳምንት ዋሺንግተን ውስጥ ከነበረው ግርግር ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንቱ እንዲከሰሱ ድምጽ እንደሚሰጡ በይፋ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ለሳምንት ያህል ድምጻቸውን አጥፍተው ከቆዩ በኋላ ማከስኞ ምሽት በሰጡት ቃል ደጋፊዎቻቸው በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ለፈጸሙት ጥቃት ኃላፊነቱን እንደማይወስዱ ገልፀዋል። የዛሬ ሳምንት በአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት የሚተኩት ዶናልድ ትራምፕን ከቀሯቸው የሥልጣን ቀናት በውርደት እንዲባረሩ ዲሞክራቶች ግፊት እያደረጉ ነው። የአገሪቱ ምክር ቤት በፕሬዝዳንቱ ላይ አመጽ በማነሳሳት በሚቀርብባቸው ክስ ላይ ዛሬ ረቡዕ ድምጽ የሚሰጥ ሲሆን፤ በዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በስልጣን ዘመናቸው ሁለት ጊዜ የተከሰሱ መሪ ይሆናሉ። የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ ሴት ልጅ የሆኑት ሊዝ ቼኒ በማለት የአንድ ፓርቲ መሪ የእራሳቸውን አባል ለመክሰስ መስማማታቸው በርካቶችን አስደንቋል። ባወጡት መግለጫ ላይ ትራምፕ "በሕገ መንግሥቱና በገቡት ቃል ላይ ክህደት ፈጽመዋል" ብለዋል። የዋዮሚንግ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሊዝ ጨምረውም ፕሬዝዳንቱን "አመጸኞቹን ጠርተው በማሰባሰብ የጥቃቱን እሳት ለኩሰዋል" ሲሉ ከሰዋቸዋል። ሁለት ተጨማሪ የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባላትም በትራምፕ ላይ የሚከፈተውን ክስ በመደገፍ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል። በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑትና የትራምፕ ወዳጅ ኬቭን ማካርቲ ክሱን እንደሚቃወሙት የገለጹ ሲሆን፤ ነገር ግን የፓርቲያቸው አባላት በሙሉ በምክር ቤቱ ውስጥ የተቃውሞ ድምጽ እንዲሰጡ ጥሪ እንደማያደርጉ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ለቅርብ ሰዎቻቸው ተናገሩት ብሎ እንደዘገበው፤ ፕሬዝደንቱን በዲሞክራቶች መከሰሳቸው ትራምፕን ከፓርቲው ለማስወገድ ይረዳል ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል። ማኮኔል ለተባባሪዎቻቸው ጨምረው እንደተናገሩት ፕሬዝደንት ትራምፕ ሊያስከስስ የሚችል ጥፋት ፈጽመዋል ብለው እንደሚያምኑ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።
news-53338930
https://www.bbc.com/amharic/news-53338930
በአፍሪካ ኮሮናቫይረስ እየተሰራጨ የሚገኘው በምን ያህል ፍጥነት ነው?
በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከተቀረው ዓለም ጋር ሲነጻጸር ያነሰ ቢሆንም፤ በአንዳንድ አገሮች የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ አሳሳቢ ሆኗል።
በአህጉሪቱ 100,000 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙት በመቶ ቀን ነበር። ነገር ግን በቀጣዮቹ 18 ቀናት ቁጥሩ በእጥፍ ሲጨምር፣ በ20 ቀን ውስጥ ደግሞ 400,000 ደርሷል። ቁጥሩ እየጨመረበት ያለው መንገድ በበሽታው ክፉኛ ከተጠቁ የዓለም ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለውም፤ ወረርሽኙ በማኅበረሰቡ ውስጥ ተሰራጭቷል። ይህ ማለት ደግሞ ኮቪድ-19 ከያዘው ሰው ጋር ቀጥታ ንክኪ የሌለውም ሰው ለበሽታው ሊጋለጥ ይችላል ማለት ነው። ይህም የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ከባድ ያደርገዋል። በአፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡት የትኞቹ አገሮች ናቸው? በግብፅ እና በደቡብ አፍሪካ በሽታው በስፋት ተሰራጭቷል። ግብፅ በቫይረሱ ሳቢያ በርካታ ሰዎች በማጣት ከአፍሪካ ቀዳሚ ናት። ደቡብ አፍሪካ እጅግ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ከጣሉ አገሮች አንዷ ስትሆን፤ ግንቦት ላይ ገደቡ ሲላላ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ናይጄሪያም አስጊ ሁኔታ ውስጥ ካሉ አገሮች አንዷ ናት። የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው ከሆነ በኮቪድ-19 ሳቢያ በሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአህጉሪቱ ሁለተኛ ነች። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ሞሪታንያ ውስጥ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። በሌላ በኩል የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች በአንጻራዊነት ጥቂት ህሙማን ነው ያስመዘገቡት። በአፍሪካ ምን ያህል ሰዎች እየሞቱ ነው? የአህጉሪቱ የጤና መዋቅር ደካማ ቢሆንም፤ የተመዘገበው የሞት መጠን ከሌሎች የዓለም ክፍሎች አንጻር ያነሰ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፤ ለዚህ ምክንያቱ አፍሪካ ውስጥ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት ወጣቶች መሆናቸው ነው። ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከ25 ዓመት በታች ሲሆኑ፤ ኮቪድ-19 በዋነኛነት የሚያጠቃው በእድሜ የገፉ ሰዎችን ነው። ሌላው የሞት መጠን መለኪያ በበሽታው ከተያዙት መካከል ምን ያህሉ ሕይወታቸውን አጡ? የሚለው ነው። በዚህ መሠረት ከፍተኛ መጠን ያላቸው አምስት አገሮች ቻድ (8.5%)፣ አልጄሪያ (6.6%)፣ ኒጀር (6.2%)፣ ቡርኪና ፋሶ (5.5%) እና ማሊ (5.3%)ናቸው። • በኢትዮጵያ ክረምቱ የኮቪድ-19 ስርጭትን ሊያባብስ ይችላል? በጤናው ዘርፍ የተሰማራው አምሬፍ ኸልዝ አፍሪካ የተባለው የተራድኦ ድርጅት ኃላፊ የሆኑት ጊትሂንጂ ጊትሃይ እንደሚናገሩት፤ ከፍተኛ የሞት መጠን የሚያሳየው፤ ከተመዘገበውም በላይ ሰዎች በበሽታው እየተያዙ መሆኑን ነው። በተጨማሪም ምርመራ በስፋት እየተከናወነ አለመሆኑን ይጠቁማል። አነስተኛ ሰው ከተመረመረ በበሽታው መያዛቸው የሚረጋገጠውም ጥቂት ሰዎች ይሆናሉ። የሞት መጠን ግን ይጨምራል። በአፍሪካ ምን ያህል ምርመራ እየተከናወነ ነው? አስር አገሮች በአህጉሪቱ ከተደረገው ምርመራ 80 በመቶውን ይሸፍናሉ። እነዚህም ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ጋና፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሞሪሸስ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ እና ሩዋንዳ ናቸው። ሐምሌ ላይ ደቡብ አፍሪካ ከ1,000 ሰዎች 30 ስትመረምር፤ ዩናይትድ ኪንግደም 72፣ አሜሪካ ደግሞ 105 ሰዎች ነው የመረመሩት። ናይጄሪያ በ1,000 ሰዎች የምርመራ መጠኗ 0.7 ሲሆን ጋና 10፣ ኬንያ ደግሞ ሦስት ሰዎች መርምረዋል። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ጉዳዮች መምህር የሆኑት ቺልዶ ንዋንክዋር እንደተናገሩት፤ ቁጥሩ አጠቃላይ ወካይ እንደሆነ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ይላሉ። • አሳሳቢው ምልክት የማያሳዩ ግን በሽታውን የሚያዛምቱ ሰዎች ነገር የታንዛንያው ጆን ማጉፉሊ፤ የመመርመሪያ መሣሪያዎች ውጤት አስተማማኝ ስላልሆነ ከሚመዘገበው ውጤት ከፊሉን ብቻ ለሕዝብ እያስታወቁ ነበር። በኢኳቶሪያን ጊኒ የዓለም ጤና ድርጅት ወኪል በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ቁጥር እያጋነኑ ነው ብላ ቁጥሩን ለተወሰነ ጊዜ ይፋ አለማድረጓ ይታወሳል። በናይጄሪያዋ ካኖ ግዛት ሰኔ ላይ 1,000 ሰዎች ሞተው ነበር። ሆኖም ግን መንግሥት ምን ያህሉ በኮቪድ-19 እንደሞቱ አልገለጸም።
news-48419804
https://www.bbc.com/amharic/news-48419804
አይስላንድ አንድ ተማሪ ብቻ የቀረውን ትምህርት ቤት ልትዘጋ ነው
በሃገረ አይስላንድ ግሪምሲይ በምትሰኝ ከተማ የሚገኝ ትምህርት ቤት አንድ ተማሪ ብቻ ስለቀረው ሊዘጋ ስለመሆኑ ተነገረ።
በአነስተኛ የደሴት ከተማ ላይ የሚገኘው ትምህርት ቤቱ፤ እአአ 2001 ላይ 14 ተማሪዎች ነበሩት። ይሁን እንጂ ከአንድ ዓመት በፊት የትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ቁጥር ወደ 4 ዝቅ ብሎ ነበር። የአንድ ቤተሰብ አባላት ደሴቷን ለቀው ወደ ሌላ ሥፍራ ለመዘዋወር መወሰናቸው በትምህርት ቤቱ አንድ ተማሪ ብቻ እንዲቀር ምክንያት ሆኗል። • ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ የቀረው አንድ ተማሪ በቀጣዩ የትምህርት ዓመት ወደ ዘጠነኛ ክፍል ይዘዋወር ነበር። ነገረ ግን ላልተወሰነ ጊዜ ትምህርት ቤቱ ዝግ ሆኖ ይቆያል ተብሏል። ''ትምህርት ቤቱ ከተገነባ ከ40 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። ለአካባቢው ማኅብረሰብም ዘረፈ ብዙ አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቆይቷል። የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የህጻናት መዋያ፣ የሃኪሞች ቢሮ ሆኖ አገልግሏል። ትምህርት ቤቱ ተዘግቶ ይቀራል ብዬ አላስብም።'' በማለት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ካረን ኖት ቪኩዳጉር ለተሰኝ ለአካባቢው ጋዜጣ ተናግረዋል። • በዋግ ኸምራ አስተዳደር 7 የዳስ ት/ቤቶች አሉ ግሪምሲይ ለተሰኘችው ይህች የደሴት ከተማ ዋነኛ የገቢ ምንጭ የአሳ ምርት የነበረ ሲሆን በአካባቢው የነበሩ አሳ አምራቾች ንግድ አልሳካ ቢላቸው አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። ጎብኚዎችም ቢሆኑ ይህችን በረዷማ አካባቢ የሚጎበኙት በሞቃታማ ወራት ብቻ ነው። ምንም እንኳ የአይስላንድ መንግሥት ተደራሽ ወዳልሆኑት ግሪምሲይ እና ሌሎች ሥፍራዎች በድጎማ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ቢያቀርብም ይህ ነው የሚባል ፋይዳ ለአካባቢው እንዳላመጣ ይታመናል።
54690649
https://www.bbc.com/amharic/54690649
ነገ በሚቀጥለው ድርድር የትራምፕ አስተያየት አሉታዊ ተጽዕኖ አይኖረውም ተባለ
የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ተቋርጦ የነበረው የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ከነገ ጀምሮ ቀጥሎ እንደሚካሄድ አስታወቁ።
በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የሬዲዮ ኦፕሬተር በመሆን የምታገለግል ሠራተኛ ለሰባት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው ድርድር ከነገ ጀምሮ መካሄድ እንደሚጀምር ይፋ የተደረገው በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር ሲሪል ራማፎሳ ትዊተር ገጽ ላይ ነው። ፕሬዝደንት ራማፎሳ ከሶስቱ አገራት መሪዎች ጋር ማለትም ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱ ፋታህ አል-ሲሲ፣ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር ጥልቅ ምክክር ከተካሄደ በኋላ የሶስትዮሽ ድርድሩ ነገ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። ይህ ድርድር የሚቀጥለው ፕሬዝደንት ትራምፕ የሕዳሴ ግድብን ግብጽ "ልታፈነዳው ትችላለች" የሚል አስተያየት ከሰጡ በኋላ ነው። ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው አርብ ምሽት በዋይት ሃውስ ጋዜጠኞች በተሰበሰቡበት፤ ኢትዮጵያ ወደ ስምምነቱ መመለስ አለባት፤ ግብጽ ብትበሳጭ ልትኮነን አይገባም፤ "ያን ግድብ ልታፈነዳው ትችላለች" ሲሉ ተደምጠዋል። ኢትዮጵያ፤ የፕሬዝደንት ትራምፕን አስተያየት በተመለከተ በግድቡ ዙሪያ የሚሰጡ ማስፈራሪያዎች ከመረጃ ክፍተት የሚነሱ፣ ውጤታማ ያልሆኑ እና የዓለም አቀፍ ሕግን የጣሱ ናቸው ማለቷ ይታወሳል። የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለቢቢሲ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተያየት ነገ ቀጥሎ በሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ አሉታዊ ጫና አያሳድርም ብለዋል። "ድርድሩ ራሱን የቻለ ነው፤ ሦስቱ አገራት በአፍሪካ ሕብረት አማካይነት እየተደራደሩ ያሉበት ጉዳይ ነው። ፕሬዚደንቱን አይመለከትም። የሚመለከታቸው ነገር ካለ እንድንስማማ መገፋፋት፣ መደገፍ፣ እኛ የተስማማንበትን ነገር መቀበል ብቻ ነው እንጂ ከዚህ ውጭ ይሄ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ እየተደረገ ያለ ጉዳይ ስለሆነ የሌላ የማንም ሰው ጉዳይ ሊሆን አይችልም" ብለዋል አምባሳደር ዲና። ፕሬዝደንት ራማፎሳ ሶስቱ አገራት ወደ ትብብር እና በቅን መንፈስ ተቀባይነት ወዳለው ድርድር ለመመለስ መወሰናቸውን በበጎ እንደሚቀበሉት ገልጸዋል። የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ሶስቱ አገራት በሕግ እና ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ከስምምነት እንደሚደርሱ ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። በአሜሪካ ዋሽንግትን ዲሲ ሲካሄድ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ በሚደረገው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንደማትካፈል ማስታወቋ ይታወሳል። የካቲት 2012 ዓ. ም. ላይ ኢትዮጵያ በዋሽንግተን የመጨረሻ ቀጠሮ ተይዞለት በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጣይ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ ለአሜሪካ አስታውቃ ነበር። በአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ አደራዳሪነት በአዲስ አበባ፣ ካይሮ፣ ካርቱም እና ዋሽንግተን ዲሲ ሲደረጉ የነበሩት ውይይቶች ያለ ውጤት እንዲበተኑ የሆነው የግብጽ መከራከሪያ ነጥቦች መለዋወጥ መሆኑ ተጠቁሟል። ቢቢሲ ለውይይቱ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች እንደተረዳው ምንም እንኳን የሚካሄደው ውይይት በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ እንዲሆን ኢትዮጵያ ጥረት እያደረገች ቢሆንም ግብጽ ድርድሩ የውሃ ድርሻ ላይ እንዲያተኩር ግፊት እያደረገች ነው።
news-54841979
https://www.bbc.com/amharic/news-54841979
"ወታደራዊው ተልዕኮ ውስን ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የፌደራል መንግሥቱ ትግራይ ክልል ላይ የሚያደርገው ወታደራዊ ዘመቻ "ግልፅ፣ ውስንና ተጨባጭ ውጤቶችን ማግኘት" ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል።
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በበኩላቸው ከዚህ ቀደም የፌደራል አስተዳደሩ ክልሉን ለመውረር እያሴረ ነው በማለት ሲወነጅሉ ተሰምተዋል። በፌደራል መንግሥቱና በክልሉ ያለው ወታደራዊ ግጭት ወደ እርስ በርስ ጦርነትም እንዳያመራም ስጋቶች አሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአስቸኳይ ጦርነቱን እንዲያረግቡትም ጥሪ አድርጓል። ግጭቱ በምን ሁኔታ ነው ያለው? የፌደራል መከላከያ ሰራዊት ወደ ትግራይ ክልል ተጨማሪ ወታደሮችን እንደሚልክና በአገሪቷም የሚገኙ የሰራዊቱ አባላትንም እየተሰበሰሰቡ መሆኑንም የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ሐላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከሰሞኑ አስታውቀዋል። ጄኔራል ብርሃኑ እንዳሉት የሰራዊት አባላቱ በክልሉ ለሚገኘው የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ድጋፍ ለመስጠት እንደሆነ ገልፀዋል። የሰሜን እዝ በክልሉ አስተዳዳሪ ህወሃት ቁጥጥር ስር እንዳለ ክልሉ ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በትግራይ ላይ የሚደረገው የጦር ተልዕኮ "ውስን" እንደሆነና "የፌደራል መንግሥት ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለወራት ያህል በትእግስት ተሞክሮ ባለመሳካቱ ጦርነቱም የመጨረሻ አማራጭ ሆኗል" በማለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት ደብረፅዮን በበኩላቸው የትግራይ ኃይል በክልሉ የሚገኙትን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ጦር መሳሪያም ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል። ቀውሱ እየተቀጣጠለና ምንም አይነት የመቀዛቀዝ ሁኔታም እንደሌለም እየተነገረ ነው። በውጊያው ስለተገደሉም ሆነ ስለተጎዱ ሰዎች ምንም አይነት መረጃ ባለመገኘቱ ግጭቱ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማወቁን ፈታኝ አድርጎታል። ይህም በተወሰነ መንገድ ግጭቱን ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በትግራይ ክልል ከመቋረጡ ጋር ተያያይዞ ነው። በክልሉ ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ተመልሷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ስለ ግጭቱ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን በምትኩ የጦርነት ተልዕኮው ሲጠናቀቅ መረጃዎች ይፋ እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል። በአሁኑ ሰዓት የምናውቀው ነገር ቢኖር የጦርነት ወሬዎች ከሁለቱም አካላት በተደጋጋሚ መነገራቸውን ነው። ደብረፅዮን በበኩላቸው ክልሉን ለመከላከል ዝግጁ እንደሆኑ ገልፀው ትግራይ "ለወራሪዎች መቀበሪያ ትሆናለች" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ህወሃት በተደጋጋሚ ግጭት በማነሳሳት የወነጀሉት ሲሆን "ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል።" ብለዋል። ጄኔራል ብርሃኑ በበኩላቸው ለህወሃት ታማኝ የሆኑ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎችንም በአገር ክህደት ወንጅለዋቸዋል። የፌደራል መንግሥቱንና ክልሉን ምላሽ የተመለከቱ ታዛቢዎች የእርስ በርስ ጦርነት ጅማሮ ነው በማለት ቢሰጉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ይህንን ፍራቻ ቀለል አድርገውታል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የወጣው መግለጫ እንደሚያመላክተው የትግራይ ክልል ለመጪዎቹ ስድስር ወራት በወታደራዊ ዕዝ (ኮማንድ ፖስት) ትተዳደራለች። በጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የሚመራም ግብረ ኃይል ተቋቁሟል። ግብረ ኃይሉ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጀምሮ የክልሉ አስተዳዳሪ ህወሃትና የፌደራል መንግሥት ግንኙነት ከጊዜ ወደጊዜ እየሻከረ መጥቶ የማይታረቅ የቅራኔ ደረጃም ላይ ደርሰዋል። ለሁለት አስርት አመታት የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ መስራችና አውራ የነበረው ህወሃት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ተፅእኖው ቀንሷል። በባለፈው አመትም በብሄር የተደራጁትን የግንባሩን ፓርቲዎች በማዋሃድ ብሄራዊ የሆነ ብልፅግና ፓርቲን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢመሰርቱም ህወሃት አልቀላቀልም በማለት በእምቢተኝነት ፀንቷል። በዛሬው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በወጣው መግለጫው የተወሰኑ የህወሃት አባላት "ከፍትህ ሸሽተው" እንደተደበቁና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ ላይ ያደረጉትን ማሻሻያ የሚቃወሙ ናቸው ብለዋል። በተለይም የፌደራልና የትግራይ ክልል መንግሥት ግንኙነት የማይታረቅ ደረጃ የደረሰው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሆነ ፓርላማው ምርጫው በሕገ መንግሥት ትርጓሜ እንዲራዘም ያፀደቀ ቢሆንም የትግራይ ክልል ምርጫ ማድረጉ የበለጠ ነገሩን አክርሮታል። የፌደራል መንግሥት ክልሉ ያደረገውን ምርጫ ህገወጥና ተፈፃሚነት የሌለው ነው ብሏል። በፌደራል መንግሥቱ ተቀባይነት ሳይኖረው ክልሉ ያደረገው ምርጫ ጥያቄን የፈጠረ ሲሆን ክልሏ ራሷን የቻለ አስተዳደር 'ዲፋክቶ ስቴት' እንዲኖራት የሞከረ ነው በማለት አስተያየታቸውን የሰጡ አሉ። ህወሃት በበኩሉ ክልሉ የኢትዮጵያ አካል እንደሆነና" የራስን በራስ መተዳዳርና የመወሰን መብትን" አሳልፎ እንደማይሰጥና ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ጠንካራ አሃዳዊ ስርአት" ለመገንባት እየሞከሩ ነው በማለት ተቃውሟል። የፌደራል መንግሥት በትግራይ ላይ ለስድስት ወራት የሚቆይ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያሳለፈ ሲሆን በክልሉ በረራዎችን ማድረግም ተከልክሏል። ዲፕሎማቶች ምን እያሉ ነው? የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል የተፈጠረው ግጭት "እጅግ አሳሳቢ" እንደሆነ ገልፀው ውጊያውን እንዲያረግቡት ጥሪ አድርገዋል። በዚሁ ሳምንት በአሜሪካ ምርጫ ተሰቅዘው ያሉት የውጭ ጉዳይ ኃላፊው ማይክ ፖምፔዮም ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አድርገዋል። "በዚህ ሁኔታ ህይወት መታጣቱ አሳዝኖራል። ሰላም እንዲመለስና ግጭቶች እንዲረግቡ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ እናደርጋለን። የሰላማዊ ዜጎች ደህንነትና ጥበቃ አስፈላጊ ነው" ብለዋል በመግለጫቸው በአዲስ አበባ ተቀማጭነቱን ያደረገው የአፍሪካ ህብረትም በበኩሉ ውይይት እንዲካሄዱ ግፊት ቢያደርግም መንግሥት ለድርድር ፈቃደኛ እንዳልሆነ ሮይተርስ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
news-45352037
https://www.bbc.com/amharic/news-45352037
ጀርመን በናሚቢያ በፈመጸችው የዘር ማጥፋት ወቅት የወሰደቻቸውን የራስ ቅሎችን መለሰች
ከ100 ዓመታት በፊት ናሚቢያ የጀርመን ቅኝ ግዛት በነበረችበት ወቅት በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የተወሰዱ የናሚቢያውያን ቅሪተ አካላት ተመልሰዋል።
የናሚቢያ መንግስት የወከላቸው የልዑካን ቡድን አባላት በጀርመኗ ዋና ከተማ በርሊን በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተገኝተው የራስ ቅሎቹን ተረክበዋል። የራስ ቅሎቹና ሌሎች የአካል ክፍሎቹ ወደ ጀርመን የመጡት የአውሮፓውያንን የአእምሮ ልህቀት ለማረጋገጥ ይካሄድ ለነበር ምርምር እንዲረዳ ነበር። ቀኝ ገዢዎቻቸውን የተቃወሙ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የሄሬሮ እና ናማ ብሄረሰብ ናሚቢያውያን ተገድለዋል። የልጅ ልጆቻቸው እስካሁንም ይፋዊ ይቅርታ ከጀርመን መንግስት እየጠበቁ ነው። እ.አ.አ በ1904 የሄሬሮ እና ናማ ተወላጆች በግድ የተወሰደባቸውን መሬት ለማስመለስ ጥረት ማድረግ ሲጀምሩ ነበር የዘር ማጥፋቱ ትዕዛዝ የተላለፈው። ቁጥሩን በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም የሟቾች ቁጥር እስከ 100 ሺ ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል። • ያለመከሰስ ለማን? እስከምን ድረስ? • ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አድማ ጀርባ በመጨረሻም በህይወት የተረፉት የአካባቢው ተወላጆች ለኑሮ ወደማይመች የሃገሪቱ በረሃማ ክፍል እንዲሄዱ የተገደዱ ሲሆን፤ ወደ ድሮ መሬታቸው ለመመለስ የሞከሩት ደግሞ ይገደሉ አልያም የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ይታሰሩ ነበር። የዘር ማጥፋቱ ሲፈጸም ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት የሄሬሮ እና ናማ ተወላጆች ተገድለዋል። በጀርመን በመቶዎች የሚቆጠሩ የናሚቢያውያን የራስ ቅሎች ቢኖሩም አሁን የተመለሱት ግን ሃያ አምስቱ ብቻ ናቸው። የናሚቢያውያን ብቻ ሳይሆን እንደ ካሜሩን፤ ታንዛኒያ፤ ሩዋንዳ እና ቶጎ ባሉ የጀርመን ቅን ግዛት የነበሩ ሃገራትም ጭመር የራስ ቅሎች ይገኛሉ። ጀርመን ከ100 ዓመታት በፊት ለፈጸመችው የዘር ማጽፋት ወንጀል ይቅርታ ለመጠየቅ እንዳሰበች እ.አ.አ በ2016 ብትገልጽም፤ በይቅርታ ሂደቱ ላይ ከናሚቢያ መንግስት ጋር እስካሁን እተደራደረች ነው። አንዳንድ ናሚቢያውያን ጉዳዩን ኒውዮርክ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት ወስደውታል። ጀርመን በበኩልዋ እስካሁን ድረስ የናሚቢያ ዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በእርዳታ መልክ መስጠቷን ትናገራለች። • ተጭበርብራ የተሞሸረችው ሴት አፋቱኝ እያለች ነው ዕሮብ ዕለት በተከናወነው የራስ ቅሎቹን የመመለስ ስነ-ስርዓት ለሶስተኛ ጊዜ የተከናወነ ነው። የተጎጂዎቹ የልጅ ልጆች አሁንም እየተሰራ ባለው ነገር ደስተኛ አይደሉም። የጀርመን መንግስት ይፋዊ ይቅርታ አለመጠየቁና እነሱ የድርድሩ አካል አለመሆናቸው ትክክል አይደለም እያሉ ነው። የተመለሱት የራስ ቅሎች ወደ ናሚቢያ ተወስደው የት እንደሚቀበሩ እስከሚወሰን ድረስ በሃገሪቱ ብሄራዊ ሙዚየም እንደሚቀመጡ ተገልጿል።
47952555
https://www.bbc.com/amharic/47952555
ከ40 በላይ ኢትዮጵያውያን ባህር ላይ መሞታቸው ተሰማ
በያዝነው ወር ከጅቡቲ ወደ የመን ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰጥማ ከ40 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ።
ከሟቾቹ መካከል አብዛኛዎቹ ትግራይ ክልል ውስጥ ከምትገኘው አጽቢ ወንበርታ ወረዳ ጉዞ የጀመሩ መሆናቸውም ታውቋል። የወረዳዋ ነዋሪዎች የሆኑ ወደ አርባ የሚጠጉ የሟች ቤተሰቦችም ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ መርዶ ተረድተዋል። ከእነዚህም መካከል ወንድሙን ያጣው ካልአዩ ገብረዮሃንስ አንዱ ነው። ወንድሙ ንጉስ ገብረዮሃንስ በጉዞው ወቅት የት እንደደረሰ በስልክ ይነግራቸው እንደነበር የሚገልፀው ካልአዩ፤ ነገር ግን ከአንድ ሳምንት በኋላ ምንም ዓይነት ግንኙነት ማድረግ እንዳቆመ ይናገራል። እሱ እንደሚለው ከዚህ በፊት ወንድሙ በሕገወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተጉዞ ስምንት ወራት ቆይቶ ነበር። በሳዑዲ የመኖሪያም ሆነ የሥራ ፍቃድ ስላልነበረው በሳዑዲ ባለሥልጣናት ተይዞ ወደ ሃገር ቤት እንዲመለስ ተደርጎ ነበር። • ‘ቤቴን ከ28 ስደተኞች ጋር እጋራለሁ’ • የኢትዮጵያዊያንና የኤርትራዊያን ሰቆቃ በየመን ከሳዑዲ ከተመለስ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ የቆየው ለሦስት ቀናት ብቻ ሲሆን ተመልሶም ባለፈው መጋቢት 20 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመመለስ ጉዞ መጀመሩን ወንድሙ ያስረዳል። ከትግራይ ክልል አጽቢ ወንበርታ ኮሚኬሽን ቢሮ ባልደረቦች የተገኘው መረጋ እንሚያመላክተው ወደ 60 የሚጠጉ ወጣቶች ከሳምንታት በፊት በእግራቸው በአፍራ ክልል አድርገው ወደ ጅቡቲ የተጓዙ ሲሆን ሳዑዲ አረቢያ ለመግባትም በየመን በኩል ለማቋረጥ ሞክረዋል። አቶ ብርሃኔ ትኩ የአጽቢ ወንበርታ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ፤ መጋቢት 28/2011 ዓ.ም. ላይ ወጣቶቹ ሲጓዙበት የነበረው ጀልባ ችግር ስላጋጠመው ባህር ውስጥ መስጠሙን ተናግረዋል። አቶ ትኩ አደጋው መድረሱን ወላጆች ከአደጋው ከተረፉ እና ከአንድ ደላላ መስማታቸውን ያስረዳሉ። የትግራይ ክልላዊ መንግሥትም በደረሰው አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልጿል። ክልሉ በሃዘን መግለጫው 40 የሚሆኑ ወጣቶች በአደጋው ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ጠቅሷል። • የቤት ሰራተኞችን ለመላክ ከኩዌት ጋር ድርድር እንደሚያስፈልግ ኢትዮጵያ አስታወቀች • ኢትዮጵያዊያን በህጋዊ መንገድ ለሥራ መሄድ የሚችሉባቸው ሃገራት የትኞቹ ናቸው? ከአፍሪካ ቀንድ ተነስተው ወደ የመን የሚሄዱ ጀልባዎች በተደጋጋሚ አደጋ የሚያጋጥማቸው ሲሆን ባለፈው የካቲት ወር ላይም ከጅቡቲ የተነሳ ጀልባ በመገልበጡ 47 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። በወርሃ ሰኔ ባጋጠመ ሌላ አደጋም ከሶማሊያ ባህር ዳርቻ ተነስቶ በመሄድ ላይ የነበረ ጀልባ ተገልብጦ 46 ኢትዮጵያውያን አልቀዋል። የተባበሩት መንግሥታት በቅርቡ እንዳስታወቀው በየወሩ 7000 ስደተኞች በዚሁ ተመሳሳይ መንገድ ባህር ለማቋረጥ ይሞክራሉ።
news-53544123
https://www.bbc.com/amharic/news-53544123
የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ 'የመተላለፍ ዕድሉ ዝቅተኛ ነው'
የኮሮናቫይረስ ላለባቸው እናቶች አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ከተደረገ በወሊድ ጊዜ ወደ ህጻናቱ የመተላለፍ እድሉ ዝቅተኛ ሊሆን እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።
አሜሪካ ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ሆስፒታሎች ኮሮናቫይረስ ካለባቸው እናቶች ከተወለዱ 120 ህጻናት ውስጥ አንዳቸውም በበሽታው አለመያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ውጤት የተገኘው ህጻናቱ ከተወለዱ በኋላ ባለው ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከተወለዱ ከሁለት ሳምንታት በኋላ አንዳንዶቹ የእናታቸውን ጡት የመጥባት እድል ካገኙና በአንድ ክፍል ውስጥ አብረው ከቆዩ በኋላም ጭምር ነው። ጥናቱን ያደረጉት ባለሙያዎች እንደሚሉት የተገኘው ውጤት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም ተጨማሪ ሰፋ ያለ ሙከራዎች ማድረግ ያስፈልጋል። በእርግዝናና በጡት ማጥባት ወቅት የበሽታውን ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታን በተመለከተ ያለው መረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ የሚሰጠው ምክርም የተለያየ እንዲሆን አድርጎታል። የዩናይትድ ኪንግደም ሐኪሞች እናቶች ጡት ማጥባት የሚፈልጉ ከሆነ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ ተደርጎላቸው ልጆቻቸውን ጡት ማጥባትም ሆነ አንድ ክፍል ውስጥ መሆን ይችላሉ ብለዋል። ባለሙያዎቹም ሆነ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚሉት በኮሮናቫይረስ የመያዝ ስጋት የበለጠ ጡት ማጥባት ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል የቫይረሱን ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ዕድልን ለመቀነስ አዲስ የተወለዱ ህጻናት ለተወሰነ ጊዜ ከእናታቸው ተለይተው እንዲቆዩ የማድረግ ሃሳብን ተግባራዊ ለማድረግ እያሰበ ነው። ኮሮናቫይረስ ያለባት እናት ከወለደችው ልጅ ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንድትቆይ የሚደረግና ጡት እንድታጠባ የሚፈቀድላት ከሆነ፤ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንድትጠቀምና በተደጋጋሚ እጇን መታጠብ እንደሚኖርባት በጥናቱ ተመልክቷል። ጥናቱን የመሩት ዶክተር ክርስቲን ሳልቫቶሬ እንዳሉት "ጥናታችን ወረርሽኙ ያለባቸው እመጫት እናቶች ቫይረሱን ወደ ልጃቸው የማስተላለፍ ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ነገር ግን ሁኔታውን የበለጠ ለመረዳት አሁንም ሰፋ ያለ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል" ብለዋል። በጉዳዩ ላይ በዩናይትድ ኪንግደም የተደረገ ቅኝትን የመሩት ፕሮፌሰር ማሪያን ናይት እንደገለጹት ጥናቱ በአገሪቱ ያለውን መመሪያ የሚደግፍና የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። ጨምረውም "በዩናይትድ ኪንግደም ከአንድ ሺህ በላይ ኮቪድ-19 ያለባቸው እናቶች የወለዱ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ከ1 እስከ 2 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት ላይ ብቻ ነው ቫይረሱ የተገኘው። በሽታውም በህጻናቱ ላይ የከፋ ህመምን አላስከተለም።" በአሜሪካ የተደረገው አነስ ያለ ጥናትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምበል መጠቀመን የመሰሉ ቀላል የጥንቃቄ እርምጃ በመውሰድ የኮሮናቫይረስ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ሁኔታ እንዳይከሰት ማድረግ መቻሉን ፕሮፌሰሯ ጠቅሰዋል። የጥናቱ ውጤት የህጻናትና የአዋቂዎች ጤና ጉዳይ ላይ በሚያተኩረው የላንሴት የህክምና ሙያዊ መጽሔት ላይ ታትሟል።
news-52703740
https://www.bbc.com/amharic/news-52703740
ትራምፕ አሜሪካ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ መሆኗ 'ክብር' ነው አሉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በተረጋገጡ ሰዎች ብዛት ከዓለም ቀዳሚ መሆኗ "ክብር" ሊያሰጣት እንደሚገባ ተናገሩ።
ዋይት ሐውስ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ላይ "ይህንን ነገር በተለየ መልኩ ነው የምመለከተው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ "የተገኘው ውጤት እንደ ጥሩ ነገር ነው የማየው። ምክንያቱም ይህ የምናደርገው ምርመራ ከሁሉም የተሻለ መሆኑን ያሳይል" ብለዋል። የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ በሚያወጣው መረጃ መሰረት በአሜሪካ በአሁኑ ጊዜ 1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 92 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ህይወታቸውን አጥተዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሜሪካ ከተከሰተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኞ ዕለት ባካሄዱት የካቢኔ ስብሰባቸውን ያካሄዱት ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት አገራቸው በበሽታው በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ የሆነችው ከየትኛውም አገር በበለጠ ምርመራ በማድረጓ መሆኑን አመልክተዋል። ጨምረውም "በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ሲኖረን በአንድ መልኩ እንደ መጥፎ ነገር አላየውም ምክንያቱም ምርመራችን የተሻለ መሆኑን ስለሚያመለክት" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጨምረውም የተገኘው ውጤትን "እኔ እንደ ክብር ምልክት ነው የማየው። በአውነትም የከብር ምልክት ነው። የተገኘው ውጤት በመመርመር እና በተለያዩ የህክምና መስኮች ላይ የተሰማሩት ባለሙያዎች ላከናወኑት ሥራ የተገኘ ውጤት ነው" ብለዋል። የተቀናቃኛቸው ዲሞክራቲክ ፓርቲ ብሔራዊ ኮሚቴ ግን ከሪፐብሊካን ፓርቲ የመጡትን ፕሬዝዳንት በዚህ ንግግራቸው ተችቷቸዋል። ፓርቲው በፕዊትር ገጹ ላይ እንዳሰፈረው በአሜሪካ 1.5 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ህሙማን መገኘታቸው የሚያስከብር ሳይሆን "የአመራሩን ፍጹም ውድቀት" የሚያመለክት ነው ብሏል። የአሜሪካ መንግሥት የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ባወጣው መረጃ መሰረት በመላው አገሪቱ በ12.6 ሚሊዮን ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጓል።
news-52383761
https://www.bbc.com/amharic/news-52383761
በአማራ ክልል አምስት ዞኖች የአንበጣ መንጋ ጉዳት እንደያደርስ ተሰግቷል
በአማራ ክልል በሚገኙ 36 ወረዳዎች ላይ የተከሰተው የአምበጣ መንጋ በመስኖና በአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ተሰግቷል።
የአንበጣ መንጋው በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ በሰሜን ጎንደር እና በዋግኽምራ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ መከሰቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ለቢቢሲ ገልጿል። የቢሮው ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ጎባው እንደገለጹት የአንበጣ መንጋው በተለያዩ በአምስት ዞኖችና በ36 ወረዳዎች ውስጥ ተከስቷል። መንጋውን የመከላከል ሥራው በጠቅላላ በባህላዊ ዘዴ እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ "በጥሩምባ፣ በሰዎች ድምጽ፣ በመኪና፣ በጅራፍ እና በሌሎች መንገዶች" የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ጥረት እያደረጉ ነው። የበረሃ አምበጣው አሁን ወቅቱ በጋ በመሆኑ መስክ ላይ ሰብል እንደሌለ ያመለከቱት አቶ አምሳሉ፤ ነገር ግን መንጋው "የመስኖ እና አረንጓዴ ልማታችችን እንዳያወድም" ስጋት መኖሩንና ይህንንም ለመከላከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም የአሁኑ የበረሃ አንበጣው የዕድገት ደረጃውን የጨረሰ በመሆኑ አጥፊ አለመሆኑን ጠቁመው፤ አንበጣው የሚያሰጋው ወደፊት መሆኑን ተናግረዋል። የአንበጣ መንጋው "በዚህ ወቅት እንቁላል በመጣል ሊራባና ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል ስጋት ስላለ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው" ብለዋል። በዚሁ ምክንያት አውሮፕላን ርጭት ለጊዜው አስፈላጊ አይደልም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ኬሚካል ግን በጣም በተወሰኑ ቦታዎች ላይ መጠቀማቸውን ተናግረዋል። የበረሃ አንበጣው የደቀነውን ትልቅ ስጋት ከግምት በማስገባት ግብርና ቢሮው ከግብርና ሚንስቴር ጋር ከመረጃ ልውውጥ ጀምሮ እየሠራ ይገኛል። መንጋው ከተከሰተባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው በሰሜን ሸዋ ዞን የበረሃ አምበጣው በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑን የዞኑ የግብርና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሠረት ኃይሌ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በአካባቢው መጋቢት 19 ከተከሰተ በኋላ በድጋሚ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ በዞኑ አራት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 16 ቀበሌዎች ላይ ተከስቷል። ኃላፊዋ መንጋው ወደፊት "አስጊ" ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል ያሉ ሲሆን፤ የበረሃ አምበጣውን ለመከላከል ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መረጃ መሰረት በአንበጣ መንጋ ክፉኛ ይጠቃሉ ተብለው ከተሰጋላቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን 22,550 ሔክታር ስፋት ያለው መሬቷ ለጉዳት ተጋላጭ እንደሚሆን ተነግሯል። የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት-ፋኦ እንዳለው የአንበጣ መንጋው ክፉኛ ከሚያሰጋቸው አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ሰፊ ቦታን የሚሸፍን አካባቢ በአንበጣው የውድመት ክልል ውስጥ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በአፋጣኝ እርዳታው ተገኝቶ መከላከል ካልተቻለ ከባድ ቀውስን ሊያስከትል ይችላል ተብሏል። የተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት ለቢቢሲ እንደገለጸው በአንበጣ መንጋው ክፉኛ በተጠቁት በኢትዮጵያ፣ በኬንያና በሶማሊያ በእያንዳንዱ አገር ውስጥ ቢያንስ 100 ሺህ ሔክታር ስፋት ያለው መሬት የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጨት ያስፈልጋል።
news-44856188
https://www.bbc.com/amharic/news-44856188
አሜሪካ ሩሲያዊቷን በሰላይነት ከሰሰች
የአሜሪካ መንግሥት የ29 ዓመቷን ሩሲያዊቷን የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ውስጥ ሰርጎ ለመግባት በማሴር ከሷታል።
የተለያዩ የአሜሪካ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ማሪያ ከሪፐብሊካን ፓርቲ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያላት ሲሆን የጦር መሳሪያዎችን መያዝ ታበረታታ ነበር ብለዋል። ሩሲያ 60 የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አባረረች ይህ ክስ ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የአሜሪካ ምርጫ ላይ ሩሲያን ጣልቃ ገብታለች በማለት ስትወነጅል ከነበረው ጋር ተያይዞ ሳይሆን በቀጥታ ከክሬምሊን በተሰጣት ትዕዛዝ ስትሰራ ነበር ተብሏል። የማሪያ ቡቲና ጠበቃ ሮበርት ድሪስኮል በበኩላቸው ሰኞ በሰጡት መግለጫ "ደንበኛየ ሰላይ አይደለችም፤ የዓለም ዓቀፍ ተማሪ ናት፤ ይህንንም ትምህርቷንም በቢዝነሱ ዓለም ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ዕቅድ ላይ ነበረች"ብለዋል። ሩሲያ ከ2018ቱ የክረምት ኦሎምፒክ ታገደች ክሱ በጣም የተጋነነ ነው ያሉት ጠበቃው የአሜሪካን ፖሊሲ በየትኛውም ተፅእኖ ውስጥ ለማሳረፍም ሆነ ለማጣጣል ያደረገቸው ሙከራ የለም ብለዋል። ጠበቃው ጨምረውም ውንጀላውንም ተከትሎ ደንበኛቸው ከተለያዩ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ላይ እየተባበረች መሆኗን ገልፀዋል። "እንግሊዝ በእሳት እየተጫወተች ነው"ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች በዋሽንግተን ነዋሪነቷን ያደረገችው ማሪያ ቡቲና እሁድ የተያዘች ሲሆን ረቡዕ ዕለትም ለፍርድ እንደምትቀርብ የፍትህ ዲፓርትመንት በመግለጫው አትቷል። የመታሰሯ ዜና የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ አቻቸውን ቭላድሚር ፑቲንን ጋር ተገናኝተው ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የአሜሪካ ምርጫ የሩሲያ ጣልቃ ገብነትን ካስተባበሉ ከሰዓታት በኋላ ነው። ዩናይትድ ኪንግደም 23 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከሀገር እንዲወጡ አዘዘች "ሩስያ በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ የምትገባበት ምንም ምክንያት የላትም" ብለዋል ትራምፕ። ከጥቂት ቀናት በፊትም የአሜሪካ የፍትህ ዲፓርትመንት ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የአሜሪካ ምርጫ መረጃን በመጥለፍ 12 ሩሲያዊ የደህንነት ኃላፊዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
news-56023791
https://www.bbc.com/amharic/news-56023791
በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንደሚሰጥ ተነገረ
የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች እንደሚወስዱ ገለጹ።
በአካባቢው የትምህርት መሠረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናውን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚወስዱ አስረድተዋል። በሚቀጥሉት ሳምንታት ተፈታኞች በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚጓጓዙና ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማ መቀለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ የኒቨርስቲዎች እንደሆኑ ተገልጿል። በኦንላይን (በበይነ መረብ) ይሰጣል ተብሎ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከየካቲት 29፣ 2013 ዓ. ም ጀምሮ በወረቀት እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫል ብሏል። ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በበይነ መረብ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ መግለፃቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ፈተናው በወረቀት እንዲሰጥ ውሳኔ ላይ የተደረሰው ታብሌቶች ወደ ሀገር ውስጥ ባለመግባታቸው ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር በፈተና አሰጣጡ ላይ ለተፈጠረው መዘግየት ይቅርታ ጠይቋል። ከየካቲት 21 እስከ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱ ተገልጿል። በዚህም መሰረት የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል። ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ እና 12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ መሆናችውን መናገራቸው ይታወሳል። በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናም እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ መያዙን ገልጸው ነበር። ባለፈው ዓመት በመላው ዓለም የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የትምህርት ተቋማት መዘጋታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ግን በተለያዩ ደረጃዎች የመማር ማስተማሩ ሂደት ይጀምራል ተብሎ ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በትግራይ ውስጥ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።
news-52870104
https://www.bbc.com/amharic/news-52870104
"ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ የገደለው ፖሊስ 'አስቦና አቅዶ' ነው"
በምድር አሜሪካ እንደ ሰደድ እሳት የተዛመተ ተቃውሞን ያስነሳው የጆርጅ ፍሎይድ ጉዳይ ዛሬም አልበረደም።
በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ምሽቱን ዘረፋና ንብረት ማውደም፣ መኪናዎችን ማቃጠል እንዲሁም ሰላማዊ ተቃውሞዎች እየተፈራረቁ ሲደረጉ ነበር። በዚህ ተቃውሞ መሀል የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ ጠበቃ ግድያውን በተመለከተ አዲስ መረጃን ይፋ አድርጓል። ነጩ ፖሊስ በጆርጅ ፍሎይድ አንገት ላይ እጅ በኪስ አድርጎ በጉልበቱ ሲቆምበት ፍሎይድ ትንፋሽ አጥሮት እየሞተ እንደነበር አሳምሮ የተገነዘበ ሲሆን፤ ነፍሱ እስክትወጣ ድረስ በዚያው ሁኔታ ተጭኖት መቆየቱን የሚያሳዩ ተጨማሪ የተንቀሳቃሽ ምሥል መረጃዎችን ማግኘቱን ተናግሯል። በዚህም ምክንያት ክሱ የ3ኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል ሳይሆን መሆን ያለበት የ1ኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል ሊሆን ይገባል ሲል ጠበቃው አስታውቋል። የሜኒያፖሊስ የፖሊስ መኮንን የሆነው ተከሳሽ ዴሪክ ቾቪን ክስ የተመሰረተበት 3ኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል በሚል ነው። የሟች ቤተሰብ ጠበቃ ቤንጃሚን ክራምፕ ለሲቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገረው ክሱ አሁኑኑ መሻሻል ይኖርበታል። "እኛ እንደምናስበው ክሱ 1ኛ ደረጃ ግድያ ነው መሆን ያለበት፤ ምክንያቱም ለ9 ደቂቃ አንገቱን ሲጫነው ትንፋሹ ጨርሶውኑ እንዲጠፋ አስቦና አቅዶ ነበር። በዚያ ላይ 'ትንፋሽ አጥሮኛል' እያለ እየለመነው ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ነው የጭካኔ ድርጊቱን የገፋበት" ብሏል ጠበቃው። የሟች ቤተሰብ ጠበቃ ለሲቢኤስ ቴሌቪዥን ጨምሮ እንዳስረዳው የፖሊስ መኮንኑ፤ ሟች ፍሎይድ ትንፋሽ አጥሮት መንፈራገጥ ማቆሙን አስተውሎ እንኳ ከአንገቱ ሊነሳለት ፍቃደኛ አልነበረም። ይህም የሚያሳየው ድርጊቱን የፈጸመው ሆን ብሎ አስቦበትና አቅዶ መሆኑን ነው። ዴሪክ ቾቪን ጠበቃው ሌላ ያነሳው መከራከርያ ከፖሊስ አገኘሁት ባሉት ሌላ ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ የተመሰረተ ነው። ይኸውም በወቅቱ ከነበሩት ፖሊስ መኮንኖቹ አንዱ "አሁን የልብ ምቱ ቆሟል በጀርባው እናዙረው" በሚልበት ጊዜ ተጠርጣሪው ፖሊስ ዴሪክ ቾቪን "ተወው ባክህ በዚሁ ሁኔታ (ቆልፈን) እናቆየዋለን" ሲል ይደመጣል። ይህም ግድያውን ሆን ብሎ አስቦ መፈጸሙን የሚያስረዳ ማስረጃ ነው ሲል ተከራክሯል። ጠበቃው ሌላ ያነሱት አዲስ መረጃ ደግሞ ገዳይና ሟች ከዚህ ክስተት በፊት ይተዋወቁ እንደነበረ ነው። ትውውቃቸው በምን ደረጃ እንደነበር ግን አላብራሩም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ምሽቱን በፊላደልፊያ የተካሄደን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ከፍተኛ ዝርፍያ ነበር ተብሏል። በፊላደልፊያ የፖሊስ መኪናዎች ከመቃጠላቸውም በላይ የልብስ ቤቶች፣ መድኃኒት ቤቶችና ሌሎች ሱቆች ተዘርፈዋል። ፕሬዝዳትን ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ የፊላደልፊያ ተቃዋሚዎች አደብ እንዲገዙ ካልሆነ ግን ልዩ ኃይል እንደሚያዘምቱባቸው አስጠንቅቀዋል። የፍሎይድ ግድያ ጉዳይ የፈርጉሰኑን ማይክል ብራውንና የኒውዮርኩን ኤሪክ ጋርነርን ግድያዎች ተከትሎ በአሜሪካ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነ ዘረኝነት የተጸናወተው ተግባር ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ድርጊት "ብላክ ላይቭስ ማተር" የሚለው የጥቁሮች የመብት እንቅስቃሴ ዳግም እንዲፋፋም ያደረገ ሆኗል። ይህን የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ ከአሜሪካ ውጪ በበርካታ የአውሮፓ ከተሞችም ተቃውሞዎች የተካሄዱ ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም መዲና ለንደን በርካቶች አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን አሰምተዋል።
news-47249328
https://www.bbc.com/amharic/news-47249328
ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው?
የጥንታዊው የሰው የዛፍ ፍሬ ለቅሞ እና እንስሳት አድኖ ህይወትን አስቀጥሎ ከዚህ ደርሷል።
በጊዜ ሂደት እና በቴክኖሎጂ እድገትም የአኗኗር ዘያችን በፍጥነት እየተቀየረ መጥቷል። ለዚህም ማሳያ የሚሆነን ደግሞ 'ዲጂታል ገንዘቦችን' ለምርት እና አገልግሎት መገበያያነት ማዋል መቻላቸው ሊጠቀስ ይችላል። 21ኛው ክፍለዘመን ካስተዋወቀን የቴክኖሎጂ ምጡቅ ቃላት መካከል ብዙ እየተባለለት ያለው 'ክሪይፕቶከረንሲ' አንዱ ነው። ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት 'ክሪይፕቶከረንሲን' እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደህንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ። • «በቋንቋው ሳያስተምር ያደገ ሃገር እኔ አላውቅም» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ አይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ። በስፋት ከሚታወቁት መካከል ቢትኮይን፣ ኤቴሪያም፣ ሪፕል እና ቢትኮይን ካሽ የሚባሉት ከበርካታ ክሪፕቶካረንሲዎች መካከል ሊጠቀሱ ይችላሉ። በቅድሚያ የ'ዲጂታል ከረንሲውን' ተቀላቅሏል ሚባልለት እና በስፋት በሚታወቀው ቢትኮይን ላይ ትኩረታችንን እናድርግ። ቢትኮይን ምንድነው? ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል+ገንዘብ+መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ/ቡድን በዓለም ላይ 21 ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጠ/ጡ ይታመናል። የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን 17 ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል። የቢትኮይን ዋጋ መዋዠቅ? ከአንድ ዓመት በፊት እአአ የካቲት 15/2018 የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 10,031 የአሜሪካ ዶላር ነበር። ከአንድ ዓመት በኋላ ማለትም የካቲት 15/2019 የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ወደ 3,561 የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ብሏል። ቢትኮይን ከተፈጠረ 10 ዓመታት ተቆጠረዋል። ባለፉት አስር ዓመታትም የቢትኮይን ዋጋ እጅጉን እየጨመረ መጥቷል። የካቲት 2010 ዓ.ም የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከ10ሺህ ዶላር በላይ ደርሶ ነበር። ከሁለት ዓመት ከነበረው ዋጋ ጋር ሲነጻጸርም ከ27 እጥፍ በላይ ጨምሯል። አሁን ላይ ደግሞ ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ዋጋ ጋር ሲነጻጸር ወደ 3 እጥፍ በሚጠጋ ዋጋ ቀንሷል። • ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ? ከሁለት ዓመታት በፊት ዋጋ በፍጥነት ሲጨምር ለዋጋው መጨመር ምክንያቱ በትክክል ይህ ነው ማለት አልተቻለም። አንዳንድ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ግን ኢንቨስተሮች ''እድሉን እንዳያልፋቸው'' ከሚገባው በላይ ፈሰስ እያደረጉበት ነው የሚል ምክንያት ያቀርባሉ። ሌሎች ደግሞ የቢትኮይን ተቀባይነት እየጨመረ በመምጣቱ ዋጋው እንደጨመረ ያስቀምጣሉ። በቢትኮይን ግብይት መፈጸም ይቻላል? አዎ። ለሚያቀርቡት ምርት እና አገልግሎት ቢትኮይንን በክፍያ መልክ የሚቀበሉ በርካቶች ድርጅቶች አሉ። ማይክሮሶፍት፣ የፈጣን ምግብ አቅራቢዎቹ ኬኤፍሲ እና ሰብዌይ፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ። በቢትኮይን አማካኝነት ክፍያ ሲፈጸም የገዢውን ማንነት ይፋ አለማድረግ ያስችላል። ይህም በርካቶች በኢንተርኔት አማካኝነት ማንነታቸውን ሳይገልጡ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ስለሚያስችላቸው በቢትኮይን አማካኝነት የሚደረጉ የንግድ ልውውጦች ቁጥር እጅጉን ጨምሯል። ቢትኮይን እንደስጋት? አሸረትስ በተባለ የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ኩባንያ ውስጥ ባለሙያ የሆኑት ብራደሊይ ራይስ በቢትኮይን ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር እንደማይደረግበት ያስታውሳሉ። ቢትኮይንን በመጠቀም የገዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ በየትኛውም ሰዓት እና በየትኛውም ስፍራ የቢትኮይን ዝውውር ማድረግ ይቻላል። የግዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት መፈጸም ይቻላል። • ወላጆች ለልጆቻቸው የሚመኟቸው ኢትዮጵያዊ መምህር በዚህም ሕገ-ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ በርካቶች ናቸው። በሌላ በኩል በርካታ የፋይናንስ ባለሙያዎች ቢትኮይን ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር አለመደረጉ ተፈላጊነቱን እንደጨመረው ያወሳሉ። በቢትኮይን የሃገራት ምልከታ እአአ 2009 ላይ ከበርካቶች ጋር የተዋወቀው ቢትኮይን፤ ሕጋዊ ነው? ወይስ አይደለም? በሚሉ ጥያቄዎች ታጅቦ ቆይቷል። 'ሕጋዊ ነው? ወይስ አይደለም?' ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የምናገኘው ግን የት የሚለው ሲካተትበት ብቻ ነው። አሜሪካ፣ ካናዳ፣ የአውሮፓ ህብረት እና አውስትራሊያን የመሳሰሉ የዓለማችን ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ለቢትኮይን አዎንታዊ ምልከታ አላቸው። ከላይ በተጠቀሱት ስጋቶች ምክንያት ቬትናም፣ ቦሊቪያ፣ ኮሎምቢያ እና ኢኳዶር በቢትኮይን መገበያየትን ከከለከሉ ሃገራት መካከል ይገኙበታል። ቢትኮይን 10 ዓመታት ቢያስቆጥርም አሁንም ቢሆን በርካታ የዓለማችን ሃገራት ክሪፕቶከረንሲዎችን በተመለከተ ግልጽ ሕግ የላቸውም። ክሪይፕቶከረንሲዎችን መቆጣጠር የማይቻል በመሆኑም ለመንግሥታት ፈተና ሆኖ ቆይቷል።
news-53803446
https://www.bbc.com/amharic/news-53803446
ትራምፕ ምርጫው ይጭበረበራል ብለው የፈሩት ለምንድነው?
ትራምፕ የኅዳሩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኮሮጆው ይገለበጣል የሚሉት ለምንድነው? በመጪው ኅዳር አሜሪካዊያን ዶናልድ ትራምፕን ያሰናብቷቸዋል ወይም ያጸኗቸዋል፡፡
ይህን ለማድረግ ድምጽ መስጠት አለባቸው። ድምጽ የሚሰጡት ደግሞ አንድም በድምጽ መስጫ ጣቢያ በመገኘት ሲሆን ሌላው ደግሞ ድምጻቸውን በፖስታ ቤት በመላክ ነው። ሁለተኛው ዘዴ ‹‹ሜይል ኢን ባሎት›› እያሉ ይጠሩታል፣ የአገሬው ሰዎች። አሁን አሜሪካ በወረርሽኝ ውስጥ ናት። 5 ሚሊዮን ተኩል ሕዝቧ ታሞባታል። 170ሺህ ሞቶባታል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ መራጩን ሕዝብ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየሄድክ ተሰልፈህ ድምጽ ስጥ ማለት ብዙም ስሜት የሚሰጥ ጉዳይ አልሆነም። ይህም በሁለት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ አንዱ በምርጫ ጣቢያዎች የሚፈጠረውን መተፋፈግ፣ የድምጽ መስጫ ቁስ ንክኪና ማኅበራዊ ርቀትን አለመጠበቅ በርካታ ሰዎችን ለጤና ችግር ሊዳርግ ይችላል። ሁለተኛ ምርጫው እንደተለመደው በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ የሚሰጥበት ከሆነ በርካታ ዜጎች መምረጥ እየፈለጉ ነገር ግን ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ የጤና ቀውስ ያስከትልብናል ብለው በመስጋት ብቻ ይህንኑ ላያደርጉ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የምርጫውን ውጤት እንዳልተጠበቀው ሊያደርገው ይችላል። ፖለቲካ አዋቂዎች የሚሉት ታዲያ ትራምፕ የፖስታ ድምጽ አሰጣጥ እንዳይኖር የፈለጉት የርሳቸው ደጋፊዎች ስለ ወረርሽኙ ደንታም ስለሌላቸው ድምጽ መስጫ ጣቢያ ለመውጣት አይሰጉም። በፖስታ ድምጽ መስጠት አዲስ ነገር ነው? ይህ የፖስታ ድምጽ አሰጣጥ በአሜሪካ ምርጫ ሥርዓት ውስጥ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ሲሰራበት የኖረ ነው፡፡ ብዙ ግዛቶች ይህን ይፈቅዳሉ፡፡ አብሰንቲ ባሎት ይሉታል፡፡ ‹‹አብሰንቲ ባሎት›› የሚባለው አንድ ሰው በጤና፣ በሥራ ወይም በሌላ በማንኛውም ምክንያት ምርጫ ጣቢያ ሄዶ ድምጽ መስጠት እንደማይችል ሲገነዘብ፣ ‹‹ምርጫ ጣቢያ ሄጄ ድምጽ መስጠት ስለማልችል በአድራሻዬ ቅጽ መጥቶልኝ ቅጹን ሞልቼ በፖስታ ቤት በኩል ድምጼን ልላክ›› ብሎ የሚጠይቅበት አሰራር ነው፡፡ ይህ አሰራር በማረሚያ ቤት ሆነው ድምጽ የመስጠት መብት ያላቸው፣ በሰላም አስከባሪ ጦር ውስጥ በተልእኮ ሌላ ቦታ የሚገኙ የሰራዊት አባላት፣ በትምህርት ምክንያት ከመኖርያ አድራሻቸው የራቁ አሜሪካዊያን ወይም በሌላ ምክንያት በምርጫው ዕለት ምርጫ ለመስጠት በተመዘገቡበት አድራሻ መገኘት ያልቻሉ አሜሪካዊያን ‹‹አብሰንቲ ባሎት›› የምርጫ ደምጽ መስጫ አማራጭን በመጠቀም ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ በአጭሩ አብሰንቲ-ባሎት የሚባለው መራጩ በአንዳች ምክንያት የምርጫ ጣቢያ ሄዶ ድምጽ መስጠት እንደማይችል በመገንዘብ በፖስታ ቤት ድምጽን ሲሰጥ ነው፡፡‹‹ሜይል-ኢን-ባሎት›› የሚባለው አብሰንቲ ባሎትንም ሆነ እንዲሁ ግዛቱ ያን አሰራር ስለሚጠቀም ሊሆን ይችላል በማንኛውም ምክንያት ብቻ ድምጽ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ሳይሆን በፖስታ ቤት በኩል የሚሰጥበት አሰራር ጥቅል የወል ስም ነው፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ለምን የፖስታ ቤት ምርጫን ጠሉት? ትራምፕ በፖስታ ቤት ድምጽ ከተሰጠ ምርጫው ይጭበረበርብኛል ነው የሚሉት፡፡ የአሜሪካ ፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚሉት ግን ዶናልድ ትራምፕ ሰዎች ወደ ድምጽ መስጫ ጣቢያ እየሄዱ እንዲመርጡ የሚፈልጉበት ምክንያት በርካታ አሜሪካዊያን በፖስታ ቤት በኩል ድምጻቸውን ከላኩ የዲሞክራት እጩዎች በርከት ያለ ድምጽ ያገኛሉ ብለው ስለሰጉ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም የፖስታ ምርጫን ማጥላላት ይዘዋል፡፡ ‹‹የፖስታ ምርጫ በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የምርጫ መጭበርበር ያስከትላል፡፡ እኔ ተናግሪያለሁ ኋላ›› እያሉ ነው ትራምፕ፡፡ ሆኖም ጥናቶች የሚያሳዩት ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ በፖስታ ቤት በኩል የሚደረጉ ድምጽ አሰጣጦች ለመጭበርበር ያላቸው ዕድል በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ በ2016 በነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ (ዶናልድ ትራምፕን ነጩ ቤተ መንግሥት ባስገባው ምርጫ ማለት ነው) ከመራጩ አንድ አራተኛ የሚሆነው ድምጹን የሰጠው በዚሁ መንገድ ነው፡፡ የትኞቹ ግዛቶች የትኞቹን አሰራሮች ይመርጣሉ? ግዛቶች ሁሉም የራሳቸው የምርጫ አሰራር ድምብና ሥርዓት አላቸው፡፡ ይህን ተከትለው ባለው ነባራዊ ሁኔታ ዜጎች በፖስታ ቤት በኩል ድምጻቸውን እንዲሰጡ የሚያመቻቹ ግዛቶች እንደሚበረክቱ ይጠበቃል፡፡ አሁን ባለው አሰራር ምርጫ ሙሉ በሙሉ በፖስታ ድምጽ የሚሰጥባቸው አምስት ትልልቅ ግዛቶች አሉ፡፡ ካሊፎርኒያን ጨምሮ፡፡ በፖስታ ድምጽ ለመስጠት ምንም ምክንያት የማይጠየቅበትና የዜጎች ፍላጎት ብቻ እንደሆነ ያወጁ ደግሞ 28 የአሜሪካ ግዛቶች አሉ፡፡ ሌሎች 15 ግዛቶች ግን ዜጎች በፖስታ ድምጽ እንስጥ ካሉ ምክንያት እንዲሰጡ ይጠይቃሉ፡፡ አሁን ባለው አሰራር 6 ግዛቶች የኅዳሩን ምርጫ ሙሉ በሙሉ በፖስታ ቤት በኩል እንዲሆን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ዩታ፣ ሃዋይ፣ ኮሎራዶ፣ ኦሪገንና ዋሺንግተን እንዲሁም ሰፊው ካሊፎርኒያ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በነዚህ ስድስት ግዛቶች በአካል ድምጽ መስጫ ጣቢያ የለም ባይባልም በጣም ውስን ነው፡፡ እነዚህ ግዛቶች አስቀድመው ለመራጮች ቅጽ በአድራሻ በመላክ የምርጫው ቀን መራጩ ድምጹን በፖስታ ቤት በኩል እንዲልክ ያመቻቹ ናቸው፡፡ ከአሜሪካ ግዛቶች ግማሾቹ ማንኛውም ዜጋ ድምጼን በፖስታ ነው መላክ የምፈልገው ካለ ይህንኑ ወዲያውኑ፣ ማስረጃ ሳይጠይቁ ይፈቅዳሉ፡፡ የተቀሩት ግዛቶች ግን አንድ ሰው በፖስታ ቤት በኩል ድምጼን ልስጥ ካለ አሳማኝ ምክንያት እንዲያቀርብ የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ዕድሜው ከ65 በላይ መሆን፣ ወይም የጤና እክል ወይም ምርጫ ለመስጠት በተመዘገቡበት አድራሸ በሥራ ምክንያት አለመኖር ወይም ሌላ፡፡ የሚገርመው ምርጫው በፖስታ ቤት ከሆነ ይጭበረበራል የሚሉት ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸው የፍሎሪዳን የፕራይመሪ ምርጫ ድምጽ የሰጡት በፖስታ ቤት በኩል መሆኑ ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሥልጣኑ የላቸውም እንጂ ምርጫ ይራዘም የሚል ሐሳብም አቅርበው ነበር፡፡ አዲስ የተሾሙት የአሜሪካ የፖስታ ቤት አለቃ ሉዊስ ዲ ጆይ (ጥብቅ የትራምፕ ደጋፊ እንደሆኑ ይነገራል) ምርጫ በፖስታ ቤት በኩል ከሆነ ሚሊዮን ድምጾች በወቅቱ ላይደርሱ ይችላሉ ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡ ይህም ዶናልድ ትራምፕን ለመደገፍ ያደረጉት እንደሆነ በመታሰቡ የታችኛውም ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲ ፖስታ ቤቱን እናድን የሚል ጥሪ ለምክር ቤት አባላት አስተላልፈዋል፡፡
news-54114420
https://www.bbc.com/amharic/news-54114420
ጃፓን ፡ ደብዛዎን ማጥፋት ፈልገዋል? ለምን ጃፓን አይሄዱም? የደብዛ ማጥፋት አገልግሎት ያገኛሉ
አንዳንድ ጊዜ "ጥፉ ጥፉ" አይላችሁም? በቃ መትነን አያምራችሁም? እንደ ጭስ።
ያን ጊዜ ነበር ጃፓን መሄድ። በጃፓን ይህንን የሚያመቻቹ ሰዎች አሉ። ለዚያውም ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው። የመረራቸው ሰዎች እምጥ ይግቡ ስምጥ እንዳይታወቅ አድርገው፣ ዱካቸውን ሳይተዉ እንዲሰወሩ ያግዛሉ። ተግተው ይሰራል። ማስታወቂያቸው ራሱ "ሰዎችን እንሰውራለን፣ ስንል እንሰውራለን፤ አንቀልድም" የሚል አይነት ነው። የእነዚህ ሰዎች ስም ጆሐትሱ (jouhatsu) ይባላል። ይህ ቃል በጃፓን ቋንቋ ትነት (evaporation) ማለት መሆኑ ራሱ ስለ አገልግሎታቸው ብዙ የሚነግረን ነገር አለ። በቃ፣ ሰዎችን ያስተንናሉ። እንደ ጭስ ተነው እንዲቀሩ ያግዝዎታል። "ለመሆኑ ሥራ ከየት ያገኛሉ?" እንዳይሉ። ደንበኛ በሽ በሽ ነው። እንዲያውም ወረፋ አለው። በየዓመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እልም ብለው መጥፋት ይፈልጋሉ። አብዛኞቹ ትዳር ያቃጠላቸው ናቸው። ሌሎች ደግሞ ሥራ ያታከታቸው፣ የቤተሰብ ጫና ናላቸውን ያዞራቸው፣ በዕዳ የተነከሩ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በቃ ሕይወት ራሷ የሰለቸቻቸው፤ እነሱም የሰለቿት። አንዳንዶች ደግሞ አገራቸው የሰለቻቸው። የገዛ አገርም ይሰለቻል አንዳንዴ። የገዛ ሕይወትም ይሰለቻል አንዳንዴ። ደንበኞቻችን በብዛት ከአሜሪካ ከጀርመንና ከዩናይትድ ኪንግደም ናቸው ይላሉ፤ አትናኞቹ። ደንበኞቻቸው መጥፋት ሲፈልጉ ታዲያ ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደርሰው ነው። የማያወላዳ ውሳኔ። እንደው ለጨዋታ እንዳይመስላችሁ እንጥፋ የሚሉት። ምክንያቱም አንዳንዶቹ ወደ ሕይወታቸው የሚመለሱት የወለዷት ልጅ አግብታ ወልዳ ከብዳ ነው። አንዳንዶቹ ወደ ቀድሞ ሕይወታቸው የሚመለሱት ከአስርታት በኋላ ነው። ታዲያ ወዴት እንደሚሄዱ ለማንም ትንፍሽ አይሉም። ወደዚህ ሄጃለሁ አይባልም። አሊያማ ምኑን ደብዛቸው ጠፋ፤ ምኑን ተነኑት። "ከሰው ጋር ማውጋት እጅ እጅ አለኝና ጠፋሁ" "የሰው ልጅ ሁሉ ሰለቸኝ። እጅ እጅ አለኝ። አንድ ሳምሶናይት ብቻ ይዤ ወጣሁ፤ አልተመለስኩም" ይላሉ የ42 ዓመቱ ሱጊሞቶ። ሱጊሞቶ የእውነተኛ ስማቸው አይደለም። "በቃ እጅ እጅ ከሚለው ሰው አመለጥኩ።" ሱጊሞቶ ተወልደው ባደጉበት ሰፈር ሁሉም ሰው ያውቃቸዋል። ምክንያቱም ከትልቅ ቤተሰብ ነው የተገኙት። ይህ በራሱ መፈናፈኛ አሳጣቸው። በቃ ከዕለታት አንድ ቀን እዚህ ሄጃለሁ ሳይሉ ጠፉ፣ ጠፉ። ብዙዎቹን ፍቅር አልባ ትዳር ያስጠፋቸዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ የዕዳ ክምር። ሌሎች ደግ ልክ እንደ ሱጊሞቶ ሳይቸግራቸው፣ በመታወቅ ውስጥ ለሕይወት ጣዕም ማጣት ያስጠፋቸዋል። እነዚህ ኩባንያዎችን "የሕይወት ኮንትሮባንዲስቶች" ብለው የሚጠሯቸው አሉ። በሌሊት ነው ደንበኞቻቸውን ይዘው የሚሾልኩት፤ ወደ ሆነ ደሴት ሊሆን ይችላል። አዲስ ማንነት ሰጥተው። አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ከፍተው። ሾ ሐቶሪ በዚህ የሥራ ዘርፍ ጥርሱን ነቅሎበታል። ኩባንያውን የከፈተው ድሮ በ1990ዎቹ ነው። እሱ ራሱ በፊት ይመስለው የነበረው ሰዎች በኢኮኖሚ ሲፈተኑ ብቻ ነበር የሚጠፉ የሚመስለው። ነገሩ የተገላቢጦሽ መሆኑ በኋላ ነው የገባው። "ሰዎች ገንዘብ ብቻ አይደለም የሚያስጠፋቸው፤ የገንዘብ መብዛት፣ መታወቅ፣ ብቸኝነት፣ የህሊና ሰላም ማጣት፣ ዝርዝሩ ብዙ ነው።" "በአጭሩ የእኛ ሥራ ለደንበኞቻችን ሁለተኛ ሕይወት መስጠት ነው፤ ምዕራፍ ሁለት ሕይወት" ይላል ሾ ሆቶሪ። "ትዳሬ ጎመዘዘ፤ ጥፊ ጥፊ አለኝ" የማኅበረሰብ ሳይንስ ባለሙያው ኂሮኪ ናካሞሪ ስለነዚህ ጆሐትሱዎች ብዙ ጥናትና ምርምር አሳትመዋል። በጥናታቸው እንደደረሱበት ከሆነ ጆሐትሱ መጀመርያ ቃሉ አገልግሎት ላይ የዋለው በ60ዎቹ ነበር። በ60ዎቹ ሰዎች በፖለቲካ ምክንያት ድንገት ይሰወሩ ነበር። ያን ጊዜ እከሌ የት ሄደ ሲባል 'ተነነ' ይባል ነበር። በኋላ ላይ ደግሞ በትዳራቸው ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ጀመሩ። በጃፓን የፍቺ አሐዝ በጣም ዝቅተኛ ነው። ምክንያቱ ግን ሰዎች በትዳራቸው ደስተኛ ሆነው አይደለም፤ ፍቺ ከባድ ሂደት ስለሚጠይቅ እንጂ። ስለዚህ ቀላሉ መንገድ እዚህ ነኝ ሳይሉ ወጥቶ መቅረት ሆነ። ለዚህ ደግሞ ጆሐትሱዎች አሉ። በጃፓን ፖሊስ እከሌ ጠፋብኝ ስለተባለ ብቻ ፍለጋ አይወጣም። ፍለጋ ለመጀመር አንዳች ወንጀል ወይም አንድ አደጋ ስለመኖሩ ከቤተሰብ ማረጋገጫ ማግኘት አለበት፤ አደን ዝምብሎ አይጀመርም። ስለዚህ ለሚሰወረው ሰው ሁለተኛ ሕይወቱን ቀላል ያደርግለታል። ምክንያቱም ፖሊስ እያደነው እንዳልሆነ ያውቃልና። "የተሰወረ አባል ያለው ቤተሰብ ማድረግ የሚችለው ከፍተኛ ገንዘብ ከፍሎ የግል መርማሪ መቅጠር ብቻ ነው። ሌላው አማራጭ መጠበቅ ብቻ ነው" ይላሉ ሶሲዮሎጂስቱ ኂሮኪ ናካሞሪ። "ትዳሬ ጎመዘዘ፣ እንደወጣሁ ቀረሁ" የሚሉት የበዙትም ለዚሁ ነው። "ክው ብዬ ቀረሁ" እናት ናቸው። የ22 ዓመት ልጃቸው ከዕለታት አንድ ቀን ጠፋ። ቢጠብቁ የለም። ለፖሊስ "አቤት!" አሉ። ፖሊስ ግን ሊረዳቸው አልቻለም። ልጃቸው ሁለት ጊዜ ከሥራ ተባሮ ነበር። "ምናልባት ያ መጥፎ ስሜት ፈጥሮበት ይሆናል" ይላሉ እናት። "ይኖርበት ወደ ነበረበት ቤት አካባቢ እየሄድኩ ተደብቄ መኪና ውስጥ ቁጭ ብዬ ከደጅ እጠብቃለሁ። ድንገት ብቅ ካለ በሚል። ይኸው ስንት ዓመቴ።" እናት ከፖሊስ እርዳታ አለማግኘታቸው አብግኗቸዋል። "ይገባኛል፣ የልጄ መረጃ ለሌላ ዓላማ ሊውል ይችላል። ነገር ግን እኔ ወንጀለኛ ወይም ሰው አሳዳጅ አይደለሁም፤ እናት ነኝ። እናት እንዴት ስለልጇ መረጃ ትነፈጋለች? ይሄ ተገቢ አይደለም።" የጃፓን ሕግ የሰዎችን ገለል የማለት ምርጫ እጅጉኑ ያከብራል። እናት አንዲህ አሉ፣ በመጨረሻ፡- "ሕጉ እስኪለወጥ ደረስ ያለኝ አማራጭ የወጣት ሬሳ ባየሁ ቁጥር ልጄ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ብቻ ነው።" "የጠፋሁት ባሌ አንገብግቦ ሊገድለኝ ሲል ነው" ጆሐትሱዎች ራሳቸው ብዙዎቹ ከቤተሰባቸው የጠፉ ሰዎች ናቸው። ሌላውም እንዲጠፋ የሚያግዙት ወደው አይደለም። አንድም ቢዝነሳቸው ነው፤ አንድም ሕይወታቸው። ድሮ የጠፋው ሱጊሞቶ ለቢቢሲ ሲናገር፣ "ሁልጊዜ ሕሊናዬን ይቆረቁረኛል፣ ለምን መሰለሽ፤ ልጄን ካየኋት ስንትና ስንት ዓመት ሆነኝ መሰለሽ። መጣሁ ብያት ጠፋሁባት፤ ፀፀት ይቦረቡረኛል።" ሲጊሞቶ ከቶኪዮ ወጣ ብላ በምትገኝ ደበቅ ያለች ሰፈር ውስጥ ነው የሚኖረው። በዚህ ታሪክ ስሙን ስለቀየረ ቤተሰቦቹ ይህን አንብበው ሊደርሱበት አይችሉም። የሚኖርበት ቤት ያከራየችው ሴትዮ ሳይታ ትባላለች። እሷም ስሟን ቀይራለች። እሷ ራሱ ድሮ ጠፍታ ነው ወደዚህ የመጣችው። አሁን እሷ ራሱ ጆሐትሱ ሆናለች። ቤቷን ይህንን ሥራ ለሚሰሩ ምስጢራዊ ኩባንያዎች ታከራያለች። "ባሌ ይደበድበኝ ነበር። የሆነ ቀን መረረኝ። እዚህ ነኝ ሳልል ከቤት ወጣሁ። ይኸው እንደቀልድ 17 ዓመት አለፈኝ።" ሳይታ ሰው ላይ መፍረድ አትወድም። ያለ ምክንያት አይደለም። "አሁን ብዙ ደንበኞች አሉኝ። ለመጥፋት ያበቃቸው ነገር ይለያያል። ታሪካቸውን ሲያጫውቱኝ 'ምን ካቸው? አሁን ይሄ ምክንያት ይሆናል?' አልልም። ተራ ጉዳይ ነው ያስጠፋችሁ አልላቸውም። ለምን መሰለሽ? ምክንያቱም ከታማሚው በላይ ህመሙን የሚያውቅ ሰው ቡዳ ነው።"
news-55489740
https://www.bbc.com/amharic/news-55489740
የተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 ምርጥ ፊልሞች የትኞቹ ናቸው?
የቢቢሲ የፊልም ሀያሲዎች ኒኮላስ ባርበር እና ክሬይን ጄምስ በተጠናቀቀው 2020 ጎልተው ወጥተዋል ያሏቸውን ምርጥ ፊልሞች ይፋ አድርገዋል። ለመሆኑ እነዚህ ፊልሞች የትኞቹ ናቸው? ማንግሩቭ (Mangrove)
የዚህ ፊልም ዳይክተር ስቲቭ ማክዊን በርካታ ጥቁር እንግሊዛያውያን እና የካረቢያን ማህበረሰቦች ከ1960ዎቹ እስከ 1980ዎቹ ባሉት ጊዜያት ውስጥ ያሳለፏቸውን መከራዎች በማሳየት ይታወቃል። ማንግሩቭ ደግሞ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲሆን በ1960ዎቹ አካባቢ አንድ የምግብ ቤት ባለቤት ላይ ፖሊስ ስለሚያደርሰው መከራ ያሳያል። ዋናውን ገጸ ባህሪ ወክላ የምትጫወት ሌቲሺያ ራይት በወቅቱ የነበረውን የጥቁሮች እንቅስቃሴ ትመራለች። በፊልሙ ላይ ፖሊስ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ የሚወስደው እርምጃ በወቅቱ ምን ያክል ጭካኔ የተለመደ እንደነበር ማሳያ ነው ይላሉ ኒኮላስ ባርበር እና ክሬይን ጄምስ። ዎልፍዎከርስ (Wolfwalkers) ይህ የአኒሜሽን ፊልም በርካቶችን ማስደነቅ ችሏል። የዋና ገጸ ባህሪ ሮቢን ድምጽ በሻን ቤን የተሰራ ሲሆን በ1600 አካባቢ በአየርላንድ ውስጥ የነበረች አዳኝ ሴት ልጅ ላይ ያተኮረ ነው። የሮቢን አባት ከጫካ ውስጥ ተኩላዎችን ሲያጠፋ በፊልሙ ላይ ሮቢን አንድ ተኩላ ወደ ሰውነት መቀየር እንደሚችል ታስተውላለች። አባቷ ለማጥፋት የሚተጋውን ተኩላ ለማዳንና ጫካውን ባለበት ለማቆየት የምታደርገው ፍልሚያ አስገርሞናል ብለዋል ባለሙያዎቹ። አም ቲንኪንግ ኦፍ ኤንዲንግ ቲንግስ (I’m Thinking of Ending Things) ይህ የቻርሊ ኮፍማን አስፈሪ ድራማ በዓመቱ ካየናቸው ፊልሞች ሁሉ ይለያል። ዋናውን ገጸ ባህሪ ወክላ የምትጫወተው ጄሲ ባክሊ በፊልሙ ላይ የፍቅር ጓደኛዋን ቤተሰቦች ለመተዋወቅ በበረዶ የተሞላ አካባቢ በመኪና ትሄዳለች። ቤተሰቦቹ ጋር ከተዋወቀች በኋላ ለመረዳት የሚከብዱ ነገሮችን ማስተዋል ትጀምራለች። ቤተሰቦቹ ልብሳቸው አይቀየርም፣ እድሜያቸው ደግሞ ቶሎ ቶሎ ይቀያየራል። እሷም ብትሆን ስሟን ማስታወስ ያቅታታል። ይህ ፊልም በጣም ግራ የሚያጋባ፣ የሚያስፈራና በሌላ በኩል ደግሞ የሚያጓጓ ነው። አኖማይት (Ammonite) ታዋቂዋ ተዋናይ ኬት ዊንሰልት በዚህ ፊልም ላይ እጅግ ድንቅ የተባለ የትወና ችሎታዋን ማሳየት የቻለችበት ነው። በፊልሙ ላይ ኬት ዊንስሌት በ19ኛው ክፍለ ዘመን የፓሊዮንቶሎጂ ዘርፍን የቀየረ የቅሪተ አካል ያገኘችው ሜሪ አኒንግን ወክላ ነው የምትጫወተው። የፊልሙ ጸሀፊና ዳይሬክተር ፍራንሲስ ሊ ሜሪ በእድሜዋ አጋማሽ አካባቢ ስላጋጠማት የፍቅር ሕይወት፣ ስራ እና የጾታ ተጽዕኖ ለማሳየት ሞክሯል። ሮክስ (Rocks) የዚህ ፊልም ዳይሬክተር ሳራህ ጋቨርን ናት፤ ጸሀፊ ደግሞ ቴሬሳ ኢኮኮ እና ክሌር ዊልሰን። አንዲት ታዳጊ እና ታናሽ ወንድሟ እናታቸው በድንገት ከቤት ከጠፋች በኋላ ስለሚያሳልፉት ሕይወት ይተርካል። ታዳጊዋን ሆና የምትተውነው በኪ ባክሬይ በፊልሙ ላይ በርካታ ስህተቶችን ብትሰራም ጥሩ ጓደኞች ግን አሏት። ልብን በሀሴት የሚሞላና ተስፋ የሚሰጥ ፊልም ነው ብለውታል ኒኮላስ ባርበር እና ክሬይን ጄምስ። ማ ሬይኒስ ብላክ ቦተም (Ma Rainey's Black Bottom) በቅርቡ በሞት የተለየን ታዋቂው የብላክ ፓንተር ተዋናይ ቻድዊክ ቦዝማን የሚተውንበት ይህ ፊልም በ1924 በቆዳ ቀለሙ ምክንያት በሚደርስበት ጥቃት የተጎዳ ሙዚቀኛ ሆኖ ነው የሚተውነው። ገጸ ባህሪው ሊቪ የሚሰኝ ሲሆን በልጅነቱ በደረሰበት የዘር ጥቃት የአዋቂነት ሕይወቱ ሲቃወስ ያሳያል። አምቆት የቆየው ቁጣው የሆነ ሰአት ላይ ሲፈነዳም ይታያል። ሊቪ ተጫዋች፣ ዳንስ የሚወድ፣ ሳቂታ ወጣት ነው። ቻድዊክ ደግሞ ገጸ ባህሪውን በደንብ ተላብሶ ተጫውቶታል። ዳ 5 ብለድስ (Da 5 Bloods) ስፓይክ ሊ ከሰራቸው ፊልሞች መካከል ይሄኛው በጣም ምርጥ ከሚባሉት ነው ብለዋል ኒኮላስ ባርበር እና ክሬይን ጄምስ። አራት ጥቁር አሜሪካውያን በወጣትነታቸው ለጦርነት ወደሄዱባት ቬትናም ይመለሳሉ። ዋናው አላማቸው ደግሞ በጦርነቱ ሕይወቱን ያጣውን ጓደኛቸውን አስክሬን ይዞ ለመመለስና የደበቁትን ወርቅ ለማምጣት ነው። በዚህ ፊልም ላይ የአራቱን ጓደኛማቾች አስገራሚ የሕይወት ጉዞ እና በአሜሪካ ያለውን ዘረኝነት ይታያል። ዘ ሃንት (The Hunt) ይህ ፊልም ገና ለተመልካች ይፋ ሳይደረግ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር። በፊልሙ ላይ ሀብታም አሜሪካውያን ግራ ዘመም ደሀ አሜሪካውያንን አግተው ወስደው እንደ እንስሳ እያሳደዱ ሲያድኗቸው ይታያል። በአሜሪካ ባጋጠሙ ሁለት ጥቃቶች ምክንያት ፊልሙ ሁለት ጊዜ የሚለቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ተገድዷል። በመጨረሻ ፊልሙ ይፋ ሲደረግ በርካቶችን ያስደሰተ ፊልም መሆን ችሏል። ፊልሙን እየተመለከቱ ማን ቀጥሎ ይሞት ይሆን፣ማን ከማን ጋር አብሯል፣ መጨረሻው ምን ይሆን የሚሉ ጥያቄዎችን አለመጠየቅ በጣም ከባድ ነው።
44723897
https://www.bbc.com/amharic/44723897
መከላከያ የኢህአዴግ የመጨረሻ ምሽግ?
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመከላከያና የደህንነት አደረጃጀት ህገመንግስቱ ላይ እንደተቀመጠው ባለፉት ሁለት አሰርታት ህዝብን ከማገልገል ይልቅ የወገንተኝነት ፖለቲካ ውስጥ እንደነበሩ ባለፈው ለፓርላማ ንግግር ሲያደርጉ አመላክተው ነበር።
ቀጥሎም የእነዚህ ተቋማት አሰላለፍ ከመንግስትና ከስርዓት ጋር የሚቀያየር ሳይሆን ወገንተኝነታቸው ለህዝብና ለሃገር ይሆን ዘንድ ማሻሻያ እንደሚደረግባቸውም ተገልጿል። ይህን ተከትሎም የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ጀነራል ሳሞራ የኑስ በጀኔራል ሳአረ መኮንን፤እንደሁም የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ በጀነራል አደም ሞሃመድ መተካት ሊደረግ የታሰበው ማሻሻያ ጅማሮ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። ማሻሻያ ይደረግ ሲባል ከሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች መካከል ላለፉት ሁለት አሰርታት ከወገንተኝነት ፖለቲካ የፀዱ አልነበሩም የተባሉት የመከላከያና ደህንነት ተቋማትን ከዚህ መስመር ማውጣት የሚቻለው በምን አይነት ማሻሻያ ነው? የሚለው ቀዳሚው ነው። "መከላከያ የኢህአዴግ የመጨረሻ ምሽግ" የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበሩት ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ መከላከያ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው የሚያትት ደብዳቤ ፅፈው ነበር።የኢህአዴግ የመጨረሻ መደበቂያ ነው የሚሉት መከላከያም ሆነ ደህንነቱ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዛሬም ጥርጥር የላቸውም። "መከላከያ የመጨረሻው የኢህአዴግ ምሽግ ነው።ፀረ ህገመንግስት የሆነ መመሪያም ነበራቸው"በማለት አንዳንድ የመከላከያ ባለስልጣናትም ፖለቲካ ውስጥ መግባታቸውንም ይጠቅላሉ። ማሻሻያው መጀመር ያለበት ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረውና ምንም እንኳ ጥሩ ነገሮች ቢኖሩትም በርካታ ችግሮች ያሉበት የአገሪቱ የውጭ ግንኙነትና ደህንነት ፖሊሲን ከማሻሻል መጀመር እንዳለበት ያስረዳሉ። በማንኛውም ዘርፍ የሚደረግ ማሻሻያ ቀላልል እንዳልሆነ ይበልጥ ደግሞ እንደ መከላከያና ደህንነት ያሉ ተቋማት ማሻሻያ ከባድ እንደሚሆን አመልክተዋል። ሁሌም የለውጥ ሂደት ላይ ለውጥ ደጋፊና ተቃዋሚ እንደሚኖር ሁሉ መከላከያና ደህንነትን በማሻሻል ሂደት ውስም በጥላቻና በዘረኝነት ፀረ ለውጥ ሃይሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገምታሉ። ለዚህ መፍትሄ የሚሉት ለለውጥ ሂደቱ የሚወጡ መመሪያዎችም ይሁኑ ሌሎች አቅጣጫዎች ህገ መንግስቱንና ህገመንግስቱን ብቻ የሚከተሉ መሆናቸውን ማረጋገጥን ነው። ከሁሉም በላይ አጠቃላይ የማሻሻል ሂደቱ በባለሙያ በቂ ጥናት ተደርጎበት የሚገባበት ለውጥንና የአገሪቱን ወቅታዊ እውነታ ያገናዘበ እርምጃ መሆን እንዳለበትም ያሳስባሉ። እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ባለ ታዳጊ አገር ባደጉ አገራትም የመከላከያና የደህንነት ተቋማት ሁሌም ወደ አንድ ወገን የማዘንበል ነገር የሚታይባቸው በመሆኑ የትኛውም አይነት ሪፎርም ቢደረግ እነዚህን ተቋማት ሙሉ በሙሉ ከወገንተኝነት እንደማያፀዳቸው ያስረዳሉ። ቢሆንም ግን በአገሪቱ የህግ የበላይነትን አረጋግጦ በተቻለ መጠን የተቋማቱ ወገንተኝነት ለህዝብ እንዲሆን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያስረግጣሉ። "ለውጥ አልተጀመረም አልተሞከረምም" በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተወንጅለው በእስር የነበሩትና በቅርቡ በይቅርታ የተለቀቁት እንዲሁም ማእረጋቸው እንዲመለስ የተወሰነው ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ መከላከያን ስለማሻሻል ሲታሰብ ዋናው ችግር በወረቀት ላይ የሰፈረው ነገር ሳይሆን በተግባር የሚታየው ነው ይላሉ። ለእሳቸው ይበልጡን ተቋማቱን የሚዘውሩት እነማን ናቸው? የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ነው። እሳቸው እንደሚሉት በወሳኝ ወታደራዊ ተቋማት መዋቅር ላይ የሚቀመጡት ሰዎች በቅርፅ ደረጃ ህገመንግስቱን መሰረት አድርጎ የህዝብና የሃገሪቱን ጥቅም ታሳቢ ያደረጉ ቢመስልም የመጡበት የፖለቲካ መስመር ተፅእኖ ግን በተጨባጭ የሚታይ እንደሆነ ይገልፃሉ። በደህንነት ተቋማት በኩል ያለው ነገርም ከዚህ ይለያል ብለው አያምኑም። "የማሻሻያው ጅምር ተደርገው በሚታዩት የቅርብ ጊዜ ሹመቶችም የነበረው ችግር መንፀባረቁን ቀጥሏል" ይላሉ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው። ከዚህና ከተመሳሳይ ሃሳቦች በመነሳት መከላከያውንና ደህንነቱን የማሻሻል እርምጃ እንዳልተጀመረ ጨርሶም እንዳልተሞከረ ይናገራሉ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው። በሌሎች አገራት በመከላከያም ይሁን በደህንነት ሰዎች ሲሾሙ ከብቃትና ለስርአት ታማኝ ከመሆን የበለጡ መስፈርቶች እንደሌሉና በኢትዮጵያ ግን ድጋፍ ሰጭው ሃይል ሳይቀር መዋቅሮች ከአንድ ፓርቲ ከህወሃት በወጡ ሰዎች መሞላታቸውን ይጠቁማሉ። የአየር ሃይል አዛዥ የነበሩትና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ጀነራል አደም መሃመድን ሹመት እንደማሳያ በመውሰድ ቀጣዩን ብለዋል። "እሳቸው ተሾሙ ማለት ተቋሙን ከታች እስከ ላይ ይመሩታል ማለት አይደለም።በየደረጃው ያለው መዋቅር የተሞላው በሌላ ሃይልና ፍላጎት ነው።"ይላሉ። ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው እንደሚሉት አማራ ወይም ኦሮሞ ብሎ ሾሞ ከሌላ ብሄር የወጣ መሆኑን ለህዝብ ለማሳየት መሞከር መሬት ላይ ያለውን እውነታ የመሸፈን ተፅእኖ ስላለው እርምጃው አደገኛ ነው። ከላይ እስከ ታች ብቃትን መሰረት አድርጎ ከሁሉም ህዝቦች የተውጣጣ እኩል ውክልናና ስልጣንን የሚሰጥ አካሄድን መከተል ባለው የአገሪቱ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ እሳቸው አዋጭ የሚሉት አካሄድ ነው። በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የሰላምና ደህንት ባለሞያ ሆኑት ዶክተር ጌታቸው ዘሩ " አሁን እተደረገ ያለው ለውጥ የዛሬ ሳይሆን የቆየ ሂደት ነው " ይላሉ። ይሁን እንጂ አሁን ለውጡ ካለፈው ጠንከር ያለ ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። እሳቸው እንደሚሉት በፀጥታና ደህንነት ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች ከሉዓላዊነትም ይሁን ከአገር ውስጥ ፖለቲካ አንፃርም በጥንቃቄ መታይት አለባቸው።በተለይ ደግሞ አካሄዱ አራቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የተነጋገሩበትና የተስማሙበት መሆን ይኖርበታል። የሚሾሙ ሰዎችም ተቋማቱን የመምራት ብቃት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።ካልሆነ ግን ውስጣዊ ሽኩቻዎች ተቋማቱ ላይ ተፅእኖ ማድረጋቸው አይቀሬ እንደሚሆን ያስረዳሉ። ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም "መንግስት የመሰረቱት እነዚህ ድርጅቶች እስከሆኑ ድረስ ስምምነታቸው ወሳኝ ነው" ይላሉ።
news-49123855
https://www.bbc.com/amharic/news-49123855
አሜሪካ ከ16 ዓመት በኋላ የሞት ቅጣት ልትጀምር በመሆኑ ትችት ቀረበባት
አሜሪካ የሞት ቅጣትን ከ16 ዓመት በኋላ ልትጀምር መሆኑ ከዲሞክራቶችና ከመብት ተሟጋቾች ተቃውሞ ገጥሞታል።
በርካታ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ ዲሞክራቶች የሞት ቅጣት እንዲቀር ጥሪ አቅርበዋል። ሐሙስ እለት ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ዊሊያም ባር፣ አምስት እስረኞች የሞት ቅጣት እንደሚፈፀምባቸው ተናግረው ነበር። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ የሞት ቅጣቱ የሚፈፀምባቸው ሰዎች በግድያ ወይንም ሕጻናትና እና አዛውንቶችን በመድፈር ተከስሰው የተፈረደባቸው እንደሆኑ ጨምረው ገልጸዋል። • ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ለሳዑዲ የጦር መሳሪያ ሊሸጡ ነው • ደኢሕዴን የሐዋሳና የሲዳማ ዞን አመራሮችን አገደ • ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው ቅጣቱ የሚፈፀመው በመጪው ሕዳርና ታሕሳስ ወር እንደሆነም ቀን ተቆርጦለታል። አቃቤ ሕጉ በመግለጫቸው "በሁለቱም ፓርቲዎች አስተዳደር የፍትህ ቢሮው በከባድ ወንጀል ተይዘው የተፈረደባቸው ግለሰቦች ላይ የሞት ቅጣት እንዲፈፀም ይፈልግ ነበር " በማለት "የፍትህ ቢሮው የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የተበዳዮችና ቤተሰቦቻቸው ኃላፊነት ስላለበት፣ በፍትህ ሥርአታችን ውስጥ የተቀመጠው ይህ ቅጣት ተፈፃሚ እንዲሆን እንጠይቃለን" ብለዋል። የአቃቤ ሕጉ መግለጫ ይፋዊ ባልሆነ መልኩ እንዲቆም ተደርጎ የነበረው የሞት ቅጣት እንደገና ሊጀመር መሆኑን ያረጋገጠ ነው። አሜሪካ ለመጨረሻ ጊዜ በሞት የቀጣችው ወንጀለኛ የ53 ዓመቱን ሉዊስ ጆንሰን ሲሆን፤ ግለሰቡ የገልፍ ጦርነት ወታደር አባል ነበር። ሉዊስ ጆንሰን የ19 ዓመቱን ወታደር ትራሲ ጆይ ማክብራይድን በመግደሉ ነበር የሞት ቅጣት የተበየነበት። ይህ የሞት ቅጣት የተፈፀመው በ2003 ቀጥታ ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት ውሳኔ መሆኑ ይታወሳል። በአሜሪካ 29 ግዛቶች የሞት ቅጣት ሕጋዊ ነው። እኤአ ከ1976 ጀምሮ በሞት በመቅጣት ከፍተኛውን ቁጥር የያዘችው ግዛት ቴክሳስ ስትሆን 561 ወንጀለኞችን በሞት ቀጥታለች። ቨርጂኒያ 113 ወንጀለኞችን፣ ኦክሎሀማ ደግሞ 112 በመቅጣት ይከተላሉ። በአሜሪካ በአሁኑ ሰዓት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ቀናቸውን የሚጠባበቁ 2673 እስረኞች ይገኛሉ። ካሊፎርኒያ 733 የሞት ፍርደኞች ሲኖሯት፤ ከ1976 ጀምሮ 13 የሞት ቅጣቶችን ብቻ አስፈፅማለች።
news-53816679
https://www.bbc.com/amharic/news-53816679
ጣልያን፣ ቱኒዝያ ስደተኞችን እንድታስቆምላት 13 ሚሊዮን ዶላር ልትሰጥ ነው
የጣልያን መንግሥት የሜድትራንያን ባህር አቋርጠው የሚገቡ ስደተኞችን እንድታስቆምላት 13 ሚሊዮን ዶላር ለቱኒዝያ ለመስጠት መወሰኑ ተገልጿል።
በርካታ ስደተኞች በትናንሸ ጀልባዎች ሜድትራንያን ባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን እንደሚያቀኑ የተገለፀ ሲሆን ይህ የገንዘብ ልገሳም ቱኒዝያ የባህር ድንበሯን ለማጠናከርና ስደተኞቹንም ለማስቆም ያለመ ነው። የጣልያን መንግሥት በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለማስቆምም የባህር ላይ ድንበሮችን ጥበቃ ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ለቱኒዝያ መንግሥት መልእክት አስተላልፏል። ይህንን የተናገሩት በቱኒዝ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉይጂ ዲ ማሪያ ናቸው። ሚኒስትሩ በአገራቸው ውስጥ "በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ተሻግረው ለሚገቡ ስደተኞች" ቦታ የለም ብለዋል። ስደተኞችን በየትኛውም መንገድ ለማስቆም እየሰራ ያለው የጣልያን መንግሥት የቱኒዝያን የባህርና ፀጥታ ኃይሎች ለማሰልጠንም ጠይቋል። እነዚህም ሰልጣኞች ስራቸው ስደተኞች በባህር ሊሻገሩ ሲሉ አድኖ መያዝና በቁጥጥር ስር ማዋል ይሆናል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በየቀኑ የሚገቡባት ጣልያን ባለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቀውስ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ችግር ፈጥሮብኛል እያለችም ትገኛለች።
50510793
https://www.bbc.com/amharic/50510793
ዛፎችና የአእምሮ ጤና ምን ያገናኛቸዋል?
ዛፎች ሕይወትዎን ማዳን ይችላሉ፣ ደስተኛ ያደርጋሉ እንዲሁም ጠንካራ ጭንቅላት እንዲኖርዎ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይጫወታሉ ይላሉ በቅርቡ ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎች የሠሩት ጥናት።
የጀርመኑ ፈላስፋና ገጣሚ ሀርማን ሂስ እንደሚለው፤ ዛፎች የነፍስ መጠለያዎች ናቸው። ዛፎች በብዛት ያሉበት አካባቢ ድብርት ቦታ ሊኖረው አይችልም ይላል። የዓለማችን ትልልቅ የሚባሉ ጸሀፍትም ቢሆኑ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ስለዛፎችና ጥቅማቸው ብዙ ነገር መጻፍ እያዘወተሩ ይመስላል። • ወደ ጫካነት የተቀየረው ስታዲየም • የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ህይወት እየቀየረ ያለው የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራ ዛፎች ጎርፍን ለመከላከል፣ ድርቅን ለመከላከልና የአፈር መሸርሸርን ለመካከል ጠቃሚ እንደሆኑ ለብዙ ዓመታት በብዙ ባለሙያዎች የተጻፈ ቢሆንም ዛፎች ከሰው ልጆች አስተሳሰብና የጭንቅላት አሠራር ጋር ስላላቸው ቁርኝት ብዙም አልተባለም። ብዙዎቻችን እንደምናስበው ንጹህ አየር እንድንተነፍስ ብቻ ሳይሆን ዛፎች በርካታ ጠቀሜታዎች አሏቸው። ዛፎችንና አረንጓዴ ተክሎችን ዝም ብሎ መመልከት በራሱ ማዕከላዊ የአዕምሮ ክፍላችንን እንደሚያረጋጋው የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ዛፎችን መመልከት በጭንቅላታችን ውስጥ የሚመረተውን ኮርቲሶል የሚባለውን ለጭንቀት የሚያጋልጥ ንጥረ ነገር መጠን ይቀንሳል፣ የልብ ምትን ዝግ ያደርጋል፣ የደም ግፊትንም ይቀንሳል። ሌላው ቀርቶ የዛፎችን ፎቶ መመልከት እንኳን በጭንቅላታችን ውስጥ ጥሩ ስሜት ይፈጥራል። በሆስፒታል ተኝተው የሚገኙ ታማሚዎች በመስኮታቸው በኩል ዛፎችን ማየት ከቻሉ የመዳን ፍጥነታቸው ይጨምራል። ዛፎች ያላቸው የማረጋጋት አቅም ጭንቀትንና ህመመን እስከመቀነስ ይደርሳል። ተፈጥሯዊ በሆኑ ዛፎች መካካል ሥራቸውን የሚያከናውኑ ሠራተኞችም ቢሆን ውጤታማነታቸው ከሌሎች ከፍ ያለ እንደሚሆን ጥናቶች ይጠቁማሉ። እድሜያቸው ከ 12 እስከ 18 የሚሆኑ 9 ሺ በጎ ፈቃደኞችን ባሳተፈ አንድ ጥናት መሰረት፤ ተፈጥሯዊ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩት የድብርትና የጭንቀት መጠናቸው በእጅጉ የቀነሰ ነው። በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል 11.5 በመቶ የሚሆኑት የድብርት ምልክት ታይቶባቸው ነበር። የእነዚህን ተሳታፊዎች መኖሪያ መንደር ያጠናው ቡድን ልጆቹ በተጨናነቁ ህንጻዎችና ምንም አይነት ዛፎች በሌሉባቸው አካባቢዎች እንደሚኖሩ ደርሶበታል። እንግሊዝ ውስጥ የአካላዊ፣ አዕምሯዊና መንፈሳዊ መረጋጋትን ለመፍጠር በሚል የተቋቋመ አንድ 'ዉድላንድ ትረስት' የሚባል ድርጅት አለ። ድርጅቱ እንደሚለው፤ የድሮ ሰዎች ጭንቀትና ፍርሀት ያለባቸውን ሰዎች ጫካ ውስጥ ጥቂት ቀናት እንዲያሳልፉ ያደርጓቸው ነበር። በጫካው ውስጥ ምግባቸውን ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረትና ለኑሯቸው ምቹ የሆኑ ቦታዎችን ለመምረት በሚያደርጓቸው ውሳኔዎች መካከል ችግራቸውንና ጭንቀታቸውን ይረሱታል። • ከምድረ-ገጽ የመጥፋት ሥጋት በሰውነት መጠን ይወሰናል • ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ለምንስ ግድ ይሰጠናል? ምናልባት ምግባቸውን ካገኙና መጠለያቸውን ከሠሩ በኋላ የድሮው ጭንቀታቸው ቢመለስ እንኳን ዛፎቹን ነፋስ ሲያንቀሳቅሳቸው ሲመለከቱና የወፎችን ዝማሬ ሲሰሙ የመታደስ እንዲሁም የደህንነት ስሜት እንደሚሰማቸው ያምኑ ነበር። በአንዳንድ ባህሎች ደግሞ የድብርትና የጭንቀት ጠባዮች የሚታዩባቸው ሰዎች ዛፎችን ረዘም ላለ ሰዓት እንዲያቅፉ ይደረጉ ነበር። ምናልባት ዛፍ ያቀፈ አንድ ሰው ብንመለከት ግራ ሊገባን ይችላል። ምንም ጥቅም የለውም ልንልም እንችላለን። ጉዳዩ ግን ወዲህ ነው ይላሉ ባለሙያዎቹ። አንድ በድብርት የሚሰቃይ ሰው ሰውነቱ አንድ ዛፍን ሄዶ ስላቀፈ ችግሩ ሁሉ ጥሎት ሊሄድ እንደማይችል ይታወቃል። ነገር ግን ዛፉን በሚያቅፍበት ጊዜ በጥሞና ውስጥ ሆኖ የነፋስ ሽውታን መስማት እና የዛፉ ቅርንጫፎች ነፋስ ሲያንቀሳቅሳቸው መመልከት ከፍተኛ የሆነ የህሊና እርካታ ይሰጠዋል።
news-54490417
https://www.bbc.com/amharic/news-54490417
ኮሮናቫይረስ ፡ ማይክሮሶፍት ሠራተኞቹ ከኮቪድ-19 በኋላም ከቤታቸው እንዲሰሩ ፈቀደ
ግዙፉ ማይክሮሶፍት ለሠራተኞቹ ትልቅ የብሥራት ዜና ይዞ መጥቷል፡፡
ኮሮናቫይረስ ከቤት መሥራት አስገዳጅ አድርጓል፡፡ ኮሮናቫይረስ ሲጠፋም ግን ከቤት ሆናችሁ መሥራት መብታችሁ ነው ብሏቸዋል፡፡ ይህም ወደ ፊት ለሥራ ወደ ቢሮ መምጣት የግድ እንደማይሆን ያመላከተ ውሳኔ ሆኗል፡፡ የማይክሮሶፍት ሠራተኞች በቋሚነት ከቤት፣ ከካፌ ወይም ከፈለጉበት ሆነው ሥራቸውን መከወን እንዲችሉ በቅድምያ የሥራ አስኪያጃቸውን ይሁንታ ብቻ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከማይክሮሶፍት በፊት ሌሎቹ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ተመሳሳይ ሐሳብ አንስተው ነበር፡፡ በተለይም የፌስቡክና የትዊተር ሠራተኞች ወደፊት ከቤት ሆነው ሥራቸውን ማሳለጥ እንደሚችሉ ተስፋ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በርካታ ግዙፍ የዓለማችን ኩባንያዎች ይህንን የቤት አሠራር ከግምት በማስገባት ላይ ናቸው፡፡ ነገሩን በጥሞና እያሰቡበት እንደሆነ አመላካች የሆነው የቢሮ ይዞታቸውን ለመቀነስ እየሰሩ መሆኑ ነው፡፡ ማይክሮሶፍት እንደሚለው አንዳንድ የሥራ መደቦች በባህሪያቸው ቢሮ መገኘትን የግድ የሚሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሠራተኞቹ የግድ ቢሮ መምጣት የለባቸውም፡፡ ከፈለጉበት ሆነው ሥራቸውን እስከሰሩ ድረስ ኩባንያው ደስተኛ ይሆናል ብለዋል፡፡ የማይክሮሶፍት ቃል አቀባይ ‹የኛ ህልም ከጊዜ ጋር መራመድ፣ ጊዜው የሚፈልገውን ማቅረብና ለሠራተኞቻችን ምቹ መሆኑ ነው፡፡ ከቤት የመሥራቱ ሐሳብም የዚህ አካል ነው›› ብለዋል፡፡ በርካታ ሠራተኞች ኮሮናቫይረስን ተከትሎ ከቤት መሥራት ውጤታማና ምርታማ አድርጎናል ሲሉ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ጊዜው በሄደ ቁጥር ይህ ሐሳባቸው እየተቀየረ መምጣቱ ነው የተነገረው፡፡ የማይክሮሶፈት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ትውልደ ህንዳዊው ሳቲያ ናዴላ ሰሞኑን በነበረ አንድ ስብሰባ ላይ እንዳሉት፤ በግል ሕይወታችንና በሥራችን መሀል መስመር ስናጣ ሥራ ላይ እያንቀላፋን እንዳለን ያህል ነው የሚሰማን ብለዋል፡፡ ብዙ ኩባንያዎች ከኮሮናቫይረስ በኋላ የሥራ አካሄድ ምን ሊመስል ይችላል በሚል ውይይት ጀምረዋል፡፡ የአብዛኛዎቹ ምርጫ ግን በሳምንት ቢያንስ ሁለት ቀናት ሠራተኞች ከቤት ሆነው መሥራት እንዲችሉ ማመቻቸት ነው፡፡ የተቀሩት ቀናት ግን ሠራተኞች ከአለቆቻቸው ጋር በአካል እየተገናኙ ቢወያዩ የሥራ መንፈስን ማጎልበት ይቻላል፣ ለመሥርያ ቤቱ ታማኝ መሆንን ያረጋግጣል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለአእምሮ ጤናም መልካም ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ሙሉ በሙሉ ከቤት መሥራት በረዥም ጊዜ ሂደት ለጤና እክልና ለመሰላቸት ሊዳርግ ይችላል የሚል ስጋት አለ፡፡ በአንጻሩ ግዙፍ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ከቤት እንዲሰሩ ሲፈቅዱ በከተሞች አካባቢ የቢሮ ኪራይ ፍላጎት እየቀነሰ እንዳይመጣ ተሰግቷል፡፡ በዋና ከተሞች አካባቢ ቤት ኪራይ የመወደዱ አንዱ ሚስጢርም ለቤት ቅርብ ሆኖ ከመስራት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በኒውዮርክና ሳንፍራንሲስኮ ይህ ከወዲሁ እየታየ ነው፡፡ በሁለቱ ከተሞች የቢሮና የቤት ዋጋ ኪራይ መጠነኛ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡
news-55235537
https://www.bbc.com/amharic/news-55235537
የኮቪድ-19 መረጃን የሚያጠናቅሩት አሜሪካዊቷ ተመራማሪ ቤታቸው በፖሊስ ተፈተሸ
በአሜሪካዋ ፍሎሪዳ ግዛት የኮቪድ-19 መረጃዎችን የማጠናቀር ኃላፊነት የነበራቸው ተመራማሪ ሬቤካ ጆንስ መኖሪያ ቤት በፖሊስ መፈተሹ ተሰምቷል።
ተመራማሪዋ በአሜሪካ የጤና ዲፓርትመንት በቀረበባቸው ክስ መሰረት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ ተጥሎ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለማላላት በማሰብ ስለቫይረሱ የተሰበሰቡ መረጃዎችን ሆን ብለው አስተካክለዋል። ኃላፊዋ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስቀመጧቸው ተከታታይ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች ቤታቸውን ሲፈትሹ ታይቷል። በተጨማሪም ፖሊስ የኃላፊዋን ላፕቶፕና ተንቀሳቃሽ ስልቅ በቁጥጥር ስር አውለዋል። ፖሊስ እንደሚለው ፍተሻውን ለማድረግ የተገደደው የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስርአት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ እንደሆነ ቢገልጽም ኃላፊዋ ግን ምንም የማውቀው ነገር የለም ብለዋል። ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ሬቤካ ጆንስ ይሰሩበት የነበረው የአሜሪካ ጤና ዲፓርትመንት ላይ ክስ በማቅረባቸው ምክንያት ከስራቸው ተባረው የነበረ ሲሆን ኃላፊዋ ከዚህ በኋላ በግላቸው የራሳቸውን መረጃ መሰብሰብና ማጠናቀር ጀምረው ነበር። ፖሊስ እንደሚለው በያዝነው ሕዳር ወር ላይ ለድንገተኛ ምላሽ ክፍል ሰራተኞች ፍቃድ ያላገኘ መልዕክት የተላከ ሲሆን መልዕክቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመሞታቸው በፊት ሀሳባቸውን እንዲገልጹ የሚጠይቅ ነበር። የፍሎሪዳ የሕግ ማስከበር ዲፓርትመንት ባወጣው መግለጫ ላይ በመረጃ ስርአቱ ላይ የተፈጸመው ጥቃት መነሻው ከኃላፊዋ መኖሪያ ቤት አድራሻ እንደሆነ የገለጸ ሲሆን ይህንን መሰረት በማድረግም የፍተሻ ፈቃድ እንደተገኘ አስታውቋል። የዲፓርትመንቱ ኮሚሽነር ሪክ ስዌሪንገን እንዳሉት ኃላፊዋና ልጆቻቸው መሳሪያ ተደግኖባቸው ፍተሻ ተካሂዷል ማለታቸውን በተመለከተ ሐሰት ነው ብለዋል። ''መርማሪዎቹ በተለመደው ሕጋዊ አሰራር መሰረት ፍተሻውን አካሂደዋል፤ በዚሁም ለምርመራው የሚጠቅሙ በርካታ መሳሪያዎችን አግኝተዋል'' ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። ''በየትኛውም ሁኔታ ምንም አይነት መሳሪያ ማንም ላይ አልተደገነም''.ኃላፊዋ ቤታቸው ከተበረበረ በኋላ ለአንዳንድ ወጪዎች እንዲረዳን በማለት ባዘጋጁት የገቢ ማሰባሰቢያ ደግሞ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ሰአታት ብቻ 65 ሺ ዶላር ማግኘታቸው ተገልጿል።
news-45544685
https://www.bbc.com/amharic/news-45544685
የኦሮሞ ነፃነት ግንባሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ማናቸው?
የ66 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ፤ ዳውድ ኢብሳ ትውልዳቸው ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ውስጥ ነው። በቀደመ ስማቸው ፍሬው ኢብሳ ይታወቃሉ።
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚያው ወለጋ የተማሩት ዳውድ ኢብሳ የሁለተኛ ደረጃ ትምህረታቸውን ለመከታተል ወደ አዲስ አበባ አምረተዋል። አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ጀነራል ዊንጌት ትምህርት ቤትን ተቀላቀሉ። ከጀነራል ዊንጌት በኋላ የቀድሞውን ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የስታትስቲክስ ትምህርት መከታተል ጀመሩ። • ከ2000 በላይ ሰልጣኝ ፖሊሶች የጤና እክል ገጥሟቸው ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ • በአዲስ አበባ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ባጋጠመ ግጭት 5 ሰዎች ተገደሉ • የቡራዩ ተፈናቃዮች በምስል በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው በንጉሡ የአስተዳደር ዘመን በነበረው የተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ተሳታፊ ነበሩ። በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ ሱዳን በመሰደድ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባርን የተቀላቀሉት ዳውድ፤ በስደት ላይ ሳሉ የአንድ ዓመት ወታደራዊ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ወደ ሃገር ቤት በመመለስ በወለጋ አካባቢ ይንቀሳቀስ የነበረውን የኦነግ ጦር መምራት ጀመሩ። ብዙም ሳይቆዩ በደርግ ባለስልጣናት ዕይታ ውስጥ ገቡ። ዳውድ ኢብሳ እሳቸውን ጨምሮ 9 የቅርብ ጓደኞቻቸው በደርግ አማካኝነት መመረዛቸወን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የተቀሩት ጓደኞቻቸው ህይወታቸው ሲያልፍ የእሳቸው ነፍስ ብቻ መትፏን ይናገራሉ። የዳውድ ኢብሳ አብሮ አደግ ጓደኛ የሆኑት ዶ/ር ደገፋ አብዲሳ፤ ዳውድ ኢብሳ በባህሪያቸው ብዙ ምግብ ስለማይመገቡ ነው ህይወታቸው የተረፈው ሲሉ ተናግረዋል። ኋላ ላይ ዳውድ 1970ዎቹ አጋማሽ በደርግ ቁጥጥር ሥር ዋሉ። ለአራት ዓመታትም በእስር ቆይተዋል። በእስር ላይ ሳሉ ከፍተኛ የጤና መታወክ ይገጥማቸው እነደነበርም ያሰታውሳሉ። ለህክምና ወደ ጤና ተቋም በሚመላለሱበት ወቅት በሃኪሞች አማካኝነት ከእስር ማምለጥ ችለዋል። ከደርግ እስር ካመለጡ በኋላ ወደ ኤርትራ በማቅናት በድጋሚ ኦነግን ተቀላቀሉ። በወቅቱም የኦነግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ። በሽግግር መንግሥቱ ወቅት ከኢህዴግ ጋር ሳይስማሙ በመቀረታቸው ወደ ኤርትራ ተመልሰው ለረዥም ዓመታት በዚያው ቆይተዋል። ስለ አቶ ዳውድ ኢብሳ እውነታዎች በስድሳዎቹ መጀመሪያ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ንቅናቄ ተሳታፊ ነበሩ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከተመሰረተ ጀምሮ የግንባሩ ደጋፊ ነበሩ። የእድገት በህብረት ዘመቻ ተሳታፊም ነበሩ። ከዘመቻ መልስ የኦነግ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ። ከእስር እንደተለቀቁ በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸው ቢመለሱም ወዲያው አቋርጠው ወደ ሱዳን በመሄድ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው የኦነግን ትግል ተቀላቀሉ። በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ተቋቁሞ በነበረበት ወቅት የግንባሩ ወታደራዊ ክፍል አዛዥ የነበሩ ሲሆን በኋላም እንደገና ወደ ኤርትራ በመሄድ መቀመጫቸውን በዚያ በማድረግ ትግል ቀጥለዋል።
news-50806053
https://www.bbc.com/amharic/news-50806053
ለጃኮብ የተሰራለት ተንቀሳቃሽ ሰው ሰራሽ እጅ ወንድሙን ማቀፍ አስችሎታል
ጃኮብ መወለድ ካለበት ሁለት ወራት ቀደም ብሎ ሲወለድ የግራ እጁ አብዛኛው ክፍል በቦታው አልነበረም።
ጃኮብ እጁ ከተገጠመለት በኋላ ወንድሙን በደስታ አቅፎ ታይቷል ወላጆቹም ለልጃቸው የሚንቀሳቀስ ሰው ሰራሽ እጅ እንዲሰራለት በኢንተርኔት ላይ 16 ሺህ ፓውንድ ማሰባሰብ ችለዋል። ብሔራዊው የጤና አገልግሎትና ብዙ ኩባንያዎች የሚሰራ ሰው ሰራሽ እጅ ጃኮብ ባለው ቀሪ የእጅ ክፍል ላይ ብዙም አገልግሎት አይሰጥም ሲሉ ቆይተዋል። • እሷ ማናት?፡ ማየትና መስማት የተሳናት የመብት ተሟጋችና የሕግ ባለሞያዋ ሃበን ግርማ • ኢትዮጵያዊው የ100 ሜትር ክብረወሰን ባለቤት በዚህ ጊዜ ነበር ቤን ሪያን ለአምስት ዓመቱ ጃኮብ ሰው ሰራሽ እጅ ለመስራት ዲዛይን ማድረግ የጀመረው። ሪያን ቀደም ሲል የአስር ዓመት ልጁ በአደጋ እጁን በመቆረጡ ምክንያት ተንቀሳቃሽ ሰው ሰራሽ አካል አዘጋጅቶ ነበር። ከዚህም በኋላ ሪያን የሥነ ልቦና መምህርነቱን በመተው 'አምቢዮኒክ' የተባለውን ድርጅትን ካቋቋመ ሁለት ዓመታት አልፈውታል። ድርጅቱም 'ግሌዝ' ከተባለው የፖላንድ ሰው ሰራሽ አካል አምራች ኩባንያ ጋር በዚህ ዓመት ተዋህዷል። ሁለቱ ኩባንያዎችን ጥምረት ተከትሎ ምርታቸውን ከተጠቀሙት የመጀመሪያ ተገልጋዮች መካከል ታዳጊው ጃኮብ አንዱ ነው። ጃኮብ ከእናቱ ከጌማ ጋር ሪያን ለጃኮብ የተሰራው ተንቀሳቃሽ እጅ የተዋጣለት እንዲሆን የሰው ሰራሽ አካል ባለሙያ ከሆነ ግለሰብና ከጃኮብ ቤተሰቦች ጋር በመሆን ሲሰራ ቆይቷል። ቤተሰቡ በተለያዩ አቅጣጫዎች መንቀሳቀስ የሚችል፣ ለመጨበጥ የሚያስችልና ከተፈጥሯዊው እጅ ጋር ተቀራራቢ አገልግሎት የሚሰጥ እጅ ልጃቸው እንዲያገኝ ፈልገው ነበር። ጃኮብ የሰው ሰራሽ እጁን አድርጎ ጃኮብ በሚንቀሳቀሰው ሰው ሰራሽ እጁ ነገሮችን መያዝ ይችላል ለጃኮብ የተሰራው ሰው ሰራሽ እጅ የተለያዩ ተግባራትን አመቺ በሆነ ሁኔታ እንዲከውን የተዘጋጀ ሲሆን ብሪያን ዲዛይኑን አዘጋጅቶ ፖላንድ ውስጥ ያሉት አጋሮቹ ደግሞ እንዳመረቱት ተነግሯል። ሰው ሰራሹ እጅ ተለቅ ያለና አረንጓዴ ቀለም ያለው ሲሆን "ይህም የጃኮብን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ትልቅ እጅ ሲሆን ከልጁ ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም ተደርጎ የተሰራ ነው" ሲል ብሪያን ተናግሯል። ተንቀሳቃሹ ሰው ሰራሽ እጅ ለጃኮብ በተሰጠበት ጊዜ ብሪያን እንዳለው "አሁን ጃኮብ ወንድሙን ማቀፍና እጁን መያዝ ይችላል።" ጃኮብ ሲወለድ ጀምሮ አብዛኛው የግራ እጅ ክፍል አልነበረውም ሰው ሰራሹ እጅ ለልጇ ከተገጠመለት በኋላ የፖሊስ መኮንን የሆነችው እናቱ ጌማ ልጇ የተሰራለትን እጅ አድርጎ ማየት "እጅግ ደስ ያሰኛል" በማለት "በጣም ወድጄዋለሁ፤ እሱም አድርጎታል" ስትል ተናግራለች። እናትየው ጨምራም ጃኮብ የማይንቀሳቀስ ሰው ሰራሽ እጅ እንዲደረግለት ፍላጎት እንዳልነበረው ስትጠቅስ "እንደ ሌሎች ሰዎች እጅ ያለው ሆኖ መታየትን አይፈልግም ነበር" ብላለች። የተሰራለት ተንቀሳቃሽ ሰው ሰራሽ እጅ ጃኮብ የሰውነት ሚዛኑን እንዲጠብቅ እንደገዘው እናቱ ተናግራለች። • "የሚያክሙን ሙዚቃዎች እንዳሉ ሁሉ የሚያውኩንም አሉ" ዶ/ር መልካሙ ለጃኮብ ይህንን እጅ ለማሰራት ከተለያዩ ሰዎች የገንዘብ ድጋፍ የተሰበሰበ ሲሆን አንዲት በጎ አድራጊም 5 ሺህ የእንግሊዝ ፓውንድ አበርክታለች። እናቱም የገንዘብ እርዳታ መጠየቅ "ደስ የማይል ስሜትን የሚፈጥር ቢሆንም ማድረግ ያለብንን አድርገናል" ብላለች። ሰው ሰራሽ እጅ ከላይኛው የእጅ ክፍል የሚጀምር ከሆነ የማይሳካ እንደሆነ ለረጅም ጊዜ ቢታሰብም ብሪያን ዲዛይን ያደረገው የጃኮብ እጅ ግን ይህንን የቆየ እውነታ የለወጠ ነው ተብሏል። የአምስት ዓመቱ ጃኮብም የተሰራለት ተንቀሳቃሽ እጅ ከሌሎች ተግባራት በተጨማሪ ወንድሙን ለማቀፍ እንዲሁም እጁን ለመያዝ ስለሚያስችለው ተጨማሪ ደስታን ይፈጥርለታል ተብሏል።
51131485
https://www.bbc.com/amharic/51131485
ለ18 ሰዓታት በረዶ ውስጥ ተቀብራ የቆየችው የ12 ዓመት ታዳጊ በህይወት ተገኘች
በፓኪስታን ካሽሚር ግዛት ውስጥ ለ18 ሰዓታት በረዶ ውስጥ ተቀበራ የቆየችው ታዳጊ በህይወት ተገኘች።
በአካባቢው በድንገት የተከሰተ የበረዶ ናዳ ውስጥ ለ18 ሰዓታት ተቀብራ የቆየችው የ12 ዓመቷ ሳሚና ቢቢ በህይወት መገኘት አነጋጋሪ ሆኗል። ታዳጊዋ ሳሚና ቢቢ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ሳለች ነበር ደንገተኛ የበረዶ ናዳ መኖሪያ ቤቱን የዋጠው። ምንም እንኳ የታዳጊዋ ህይወት ቢተርፍም በርካታ የሳሚና የቤተሰብ አባላት በድንገተኛ አደጋው ህይወታቸው አልፏል። ይህ ያልጠበቀችው አደጋ ሲያጋጥማት "እዚያው እሞታለሁ" ብላ ሰግታ እንደነበርለሬውተርስ ተናግራለች። በአካባቢው የተከሰተው የበረዶ ናዳ እና የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 74 ሰዎችን ገድሏል። በሕንድ የምትተዳደረው ካሽሚርና አፍጋኒስታን ተመሳሳይ ችግር እያስተናገዱ ነው። ካሽሚር 'የሆነው ሁሉ በቅጽበት ውስጥ ነበር' ከአደጋው የተረፉት የሳሚና እናት እንደሚሉት ከሆነ ድንገተኛው የበረዶ ናዳ ሲከሰት የቤተሰቡ አባላት አንድ ላይ ተሰባስቦ እሳት እየሞቀ ነበር። "ምንም ድምጽ አልሰማንም ነበር። ሁሉም ነገር በቅጽበት ውስጥ ነበር የተከሰተው" ይላሉ የሳሚና እናት። ልጃቸው በሕይወት አገኛለሁ የሚለው ተስፋቸው ተመናምኖ እንደነበረ ለሬውተርስ ተናግረዋል። የፓኪስታን የአደጋ መከላከል ባለስልጣን እንደገለጸው በመላው አገሪቱ በበረዶ በተመቱ አካባቢዎች ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በሕንድ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ አደጋ 8 ሰዎች ሞተዋል። ካሽሚር 138 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የምትሸፍን ሲሆን ሃይቆቿ፤ ሜዳዎቿና በበረዶ የተሸፈኑ ተራራዎቿ የውበቷ ምንጮች ሲሆኑ በቀሪው ዓለም ዘንድም እውቅና አሰጥተዋታል። ሕንድና ፓኪስታን እአአ 1947 ላይ ነጻነታቸውን ከተቀዳጁ በኋላ አካባቢው ለሁለት ተከፍሎ የውዝግብ ምንጭ ሆኗል።
54526621
https://www.bbc.com/amharic/54526621
በአሜሪካ ሲካሄድ የነበረ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ተቋረጠ
ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ሲያካሂድ የነበረውን ምርምር አንድ በጎ ፍቃደኛ መታመሙን ተከትሎ ማቋረጡን አስታወቀ።
ኩባንያው እንዳለው በክትባት ሙከራው ላይ እየተሳተፈ የነበረው በጎ ፍቃደኛ የጤና እክል የገጠመው ክትባት ለማግኘት ከሚደረገው ምርምር ጋር ተያይዞ ስለመሆኑ ይጣራል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፍቃደኞች በሚሳተፉበት ምርምር ላይ በጎ ፍቃደኞች የጤና እክል ሊገጥማቸው እንደሚችል ኩባንያው አስታውሶ፤ ለጥንቃቄ ሲባል ሶስተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው የሙከራ ምርምሩ እንቋዲረጥ ተደርጓል ብሏል። የበጎ ፍቃደኛውን ግላዊ መብት ለመጠበቅ ሲባል የተሳታፊው ማንነት እና ያጋጠመው ህመም እንደማይገለጽ ተጠቁሟል። የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እንዲቋረጥ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በዩናይትድ ኪንግደም በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ ጥምረት ሲካሄድ የነበረው ምርምር ላይ አንድ በጎ ፍቃደኛ ላይ የጤና መቃወስ ማጋጠሙን ተከትሎ ሙከራው ከተቋረጠ በኋላ ምርምሩ እንደገና መጀመሩ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ከ180 በላይ የኮሮናቫይረስ ክትባት ምርምሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ አንዳቸውም የክሊኒካል ሙከራቸውን ማጠናቀቅ አልቻሉም። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ኩባንያ እያካሄደ ያለው የኮሮናቫይረስ ምርምር ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና አስትራ ዜኔካ የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ የቻለ ነበር። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ሲያካሂድ በነበረው የምርምር ስራ ላይ በጎ ፍቃደኞችን መመልመል የጀመረው መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። ሙከራው 60ሺህ ተሳታፊዎችን በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ያሳትፋል ተብሎ ነበር።
news-54729317
https://www.bbc.com/amharic/news-54729317
ኮሮናቫይረስ፡ ማክሮን በፈረንሳይ ሁለተኛ ዙር ብሔራዊ የእንቀስቃሴ ገደብ አወጁ
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቢያንስ እስከ ህዳር መጨረሻ የሚዘልቅ ብሔራዊ ገደብ ለሁለተኛ ጊዜ ማወጃቸውን አስታውቀዋል ፡፡
በአዲሶቹ እርምጃዎች መሠረት ከአርብ ጀምሮ ሰዎች ለአስፈላጊ ሥራ ወይም ለህክምና ብቻ ከቤት እንዲወጡ ይፈቀዳል ፡፡ በገደቡ መሠረት እንደምግብ ቤቶች እና ቡና ቤቶች ያሉ እና ወሳኝ ያልሆኑ ንግዶች ሲዘጉ ትምህርት ቤቶች እና ፋብሪካዎች ክፍት ሆነው ይቆያሉ። በቫይረሱ ምክንያት በፈረንሣይ በየቀኑ የሚከሰተው ሞት ከሚያዝያ ወዲህ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ማክሰኞ 33 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፡፡ አገሪቱ "ከመጀመሪያው የሚበልጥ አደጋ እንደተደቀነባት" ማክሮን ገልጸዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ጀርመን መለስተኛ የተባለ እና ምግብ ቤቶች፣ ጂሞች እና ቲያትሮች መዝጋትን ያካተተ የአስቸኳይ ጊዜ ገደብ ወስዳለች ፡፡ ቫይረሱ በመላው አውሮፓ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን እንግሊዝን ረቡዕ ዕለት 310 አዲስ ሞት እና 24,701 በቫይረሱ የተያዙ አዲስ ሰዎችን መዝግባለች። 46 ሚሊዮን ፈረንሳዊያንን ጨምሮ የሌሊት እንቅስቃሴዎች በብዙ ሃገራት ታግዷል። በአውሮፓ ታላላቅ ኢኮኖሚ ባለቤቶች የተገበሩት አዳዲስ ገደቦች የፋይናንስ ገበያው ላይም ከፍተኛ ውድቀት አስከትሏል ፡፡ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን "በሁለተኛው ዙር ውስጥ ነን፡፡ የዘንድሮው የገና በዓል የተለየ ይሆናል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል፡፡ ማክሮን በቴሌቪዥን ብቅ ብለው "በወረርሽኙ መፋጠን ምክንያት እንዳንዋጥ ጨከን ብለን ገደቦችን ተግባራዊ ማድረግ አለብን" ብለዋል ፡፡ "ከታሰበው በከፋ መልኩ ቫይረሱ ባልገመትነው ፍጥነት እየተሰራጨ ነው" ብለዋል ማክሮን። እንደመጀመሪያው እገዳ ሁሉ በአዲሱ ህጎች መሠረት ሰዎች ቤታቸውን ለቅቀው ለመውጣት ቅጽ መሙላት ይኖርባቸዋል ፡፡ ማህበራዊ ስብሰባዎችም ታግደዋል ፡፡ የህዝብ አገልግሎት ሰጪዎች እና ፋብሪካዎች ክፍት ሆነው እንደሚቀጥሉ በመግለጽ ኢኮኖሚው "መቆምም ሆነ መፍረስ የለበትም" ብለዋል ፡፡ የጀርመን መራሂተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል አገራቸው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመዋጋት እርምጃ መወሰድ አለበት በሚል ጥሪ አቅርበዋል። ጀርመን ከሌሎች በርካታ የአውሮፓ ክፍሎች አንጻር አነስተኛ ስርጭት መጠን ቢኖራትም ባለፉት ሳምንታት ቫይረሱ የተስፋፋበት ፍጥነት በርሊንን አስጨንቋታል፡ "የጤና ስርዓታችን ለዛሬ ይህንን ፈታኝ ሁኔታ መቋቋም ይችላል። በዚህ የስርጭት ፍጥነት በሳምንታት ውስጥ የአቅም ገደቡ ጫፍ ላይ ይደርሳል" ብለዋል ሜርክል፡፡ የጀርመን መንግሥት ለገና ቤተሰቦች እና ጓደኞች እንዲገናኙ ለማስቻል ከፍተኛ ፍላጎት አለው ቢባልም በየዕለቱ የሚመዘገበው ቁትር ወደ 14 ሺህ 964 ከፍ ሲል በ24 ሰዓታት ውስጥም 85 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል ፡፡
48854510
https://www.bbc.com/amharic/48854510
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ600ሺህ ተማሪዎች የደንብ ልብስ ሊያሰፋ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የደንብ ልብስ በነፃ ለማቅረብ በያዘው ዕቅድ መሠረት ተስማሚ የደንብ ልብስ ለማቅረብ ፋሽን ዲዛይነሮች አንዲሳተፉበት አድርጓል።
በዚህም መሰረት በባለሞያዎቹ በቀረቡ የደንብ ልብስ ዲዛይኖችን ለተማሪዎች፣ ለመምህራን፣ ለወላጆች፣ ለሥነ ልቦና ባለሞያዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ ሃሳብ እንዲሰጥበት መደረጉን ከከንቲባው ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከመጪው ዓመት ጀምሮ ወደ 600 ሺ የሚጠጉ ከ400 በላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች የደንብ ልብስ፣ ደብተርና ሌሎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ወጪ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን ተገልጿል። ''የትምህርት ሥርዓቱን ለማገዝ፣ ለነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ ለመገንባትና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በማሰብ ነው ይህንን እቅድ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ያስጀመሩት''ብለዋል የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ፌቨን ተሾመ። ከዚህ በመነሳት በተለይ በመንግሥት ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች ቤተሰቦችን ሸክም ለመቀነስና ችግራቸውን ለመጋራት የከተማ አስተዳደሩ መወሰኑም ተገልጿል። • አራት ህጻናትን በአንዴ ያገኘው ቤተሰብ ተጨንቋል በዚህም መሰረት በከተማዋ ያሉት ትምህርት ቤቶች ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ አራት አይነት የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) የሚኖራቸው ሲሆን የአፀደ ህጻናት፣ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል፣ ከአምስት እስከ ከስምንት እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሚል ተከፋፍሏል። "ሙሉ ወጪውን የከተማ አስተዳደሩ የሚሸፍነው ከሆነ ወጥ የደንብ ልብሶች መዘጋጀታቸው ሥራውን እንደሚያቀለውና በከተማዋ የሚስተዋለውን የተዘበራረቀ የትምህርት ቤቶች የደንብ ልብስ ለማስተካከል ይረዳል" ብለዋል ፕሬስ ሴክሬታሪዋ። በሌሎች ሃገራት የሚገኙ ከተሞች ተሞክሮም ከግምት ውስጥ መግባቱንም አክለዋል። የደንብ ልብሶቹን ተማሪዎች የሚወድዋቸውና ደስ ብሏቸው የሚለብሷቸው እንዲሆኑ ከኢትዮጵያ ፋሽን ዲዛይነሮች ማህበር ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል። • መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች ''የዲዛይንና የቀለም ምርጫው ባለሙያዎቹ እንዲወስኑት ያደረግነው ከዘመኑ ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል እንዲሆን ነው'' በማለት ፌቨን ትናገራለች። ለአንድ ተማሪ በአማካይ ምን ያህል ብር ያስፈልጋል የሚለው ገና ዲዛይኖቹ ተጠናቀው ሲቀርቡ የሚታወቅ ሲሆን በከተማዋ ላሉት ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎች የደንብ ልብስ ለማሰፋት ትክክለኛ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን እስካሁን ባይታወቅም በግምት እስከ 300 ሚሊዮን ብር ድረስ ሊያስወጣ እንደሚችል ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ይናገራሉ። ተማሪዎችና ወላጆች የደንብ ልብስ ምርጫቸው የተለያየ የመሆኑ ጉዳይ ከግምት ውስጥ ገብቷል ወይ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ሲመልሱ የእነዚህን ሁሉ ሰዎች ሃሳብ ሊያስታርቅ የሚችል ነገር ይዘው መቅረብ የሚችሉት የዘርፉ ባለሙያ የሆኑት ዲዛይነሮች ስለሆኑ ከባለሙያዎቹ ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። "ሃላፊነቱን ለእነሱ የሰጠነው ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው" ብለዋል። ለብዙ ዓመታት ማገልገል የሚችል፣ ተማሪዎች የሚወዱትና ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል አይነት ደንብ ልብስ እንደሚሆን የከተማ አስተዳደሩ ተስፋ ያደረገ ሲሆን በመጪዎቹ ሳምንታት የዲዛይን ሥራው ተጠናቆ ለእይታ ይቀርባል። የከተማዋ የትምህርት ቢሮም ከወላጆች ጋር ውይይት እያደረገ ሲሆን ዲዛይንና ቀለሙ ላይ አስተያየት በመሰብሰብ አብዛኛውን ተማሪና ወላጅ ፍላጎት የሚያሟላ የደንብ ልብስ ይመረጣል። • የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው ''ከዚህ በመቀጠል የሚሆነው የተመረጠውን የደንብ ልብስ በብዛት የማስመረትና ለተማሪዎች የማከፋፈል ሥራ ነው። ይህንን ሥራ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቀን ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጁ ለማድረግ እየሰራን ነው'' ብለዋል። ''በቀን በመቶ ሺዎች ማምረት የሚችሉ ትልልቅ ፋብሪካዎች ስላሉ ዲዛይኑ ተጠናቆ ተቀባይነት ሲያገኝ ወዲያው አምርቶ መጨረስ ይቻላል'' ብለዋል። ምንም እንኳን ሃሳቡን ያመጡት ምክትል ከንቲባው ቢሆኑም ሥራው ቀጣይነት እንዲኖረውና በሚቀጥሉት ዓመታት ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል በማሰብ ተቋማዊ መዋቅር ለመዘርጋት እየተሰራበት መሆኑን ፕሬስ ሴክረተሪዋ ገልጸዋል። በዚህም መሰረት በከተማ አስተዳደሩ የበጎ ፈቃደኞች ማስተባበሪያ ቢሮ የተቋቀመ ሲሆን ገንዘብ ማሰባሰብና የግሉን ዘርፍ በዚህ አይነት ሥራዎች ውስጥ እንዲሳተፍ የማድረግ ሥራውን ቢሮው በበላይነት የሚመራው ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ በከተማዋ ለሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የደብተር ወጪ ለመሸፈን የከተማ አስተዳደሩ ባቀደው መሰረት ከሰባት ሚሊየን በላይ ደብተሮች የሚያስፈልጉ ሲሆን በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በጎፈቃደኞች፣ ባለሃብቶችና ድርጅቶችን በማስተባበር 3.5 ሚሊየን ደብተሮች ማሰባሰብ ተችሏል። በቀጣይ ሳምንታት ደግሞ ቀሪዎቹን ደብተሮች በማሰባሰብ ለተማሪዎች የማዳረስ ሥራ እንደሚጀመር ገልጸዋል ፕሬስ ሴክሬታሪዋ። • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ ደስ ብሏቸው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና እንዲነሳሱ በማሰብ ትምህርት ቤቶቹን እንዲታደሱ እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ በመንግሥት የሚተዳደር አዳሪ ትምሀርት ቤት ስለሌላት የቀድሞው እቴጌ መነን ትምህርት ቤት አሁን የካቲት 12 ተብሎ የሚጠራውን ተመልሶ የአዳሪ ትምሀርት ቤት የሚሆን ሲሆን ለሴት ተማሪዎች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል። አቃቂ የሚገኘው ኢትዮ ጃፓን ትምሀርት ቤት ደግሞ እድሳት ከተደረገለት በኋላ በተመሳሳይ ወንድ ተማሪዎችን ብቻ የሚያስተናግድ አዳሪ ትምህርት ቤት ይሆናል ተብሏል። በሁለቱም አዳሪ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ምርጥ 500 ሴትና 500 ወንድ ተማሪዎች የሚማሩባቸው እንደሆነም ታውቋል።
news-51569236
https://www.bbc.com/amharic/news-51569236
ዘረኛ የተባለውን የፋሽን ትዕይንት ያዘጋጀው ይቅርታ ጠየቀ
መቀመጫውን በአሜሪካዋ ኒው ዮርክ ያደረገ አንድ የፋሽን ትምህርት ቤት ያዘጋጀው የፋሽን ትዕይንት ዘረኝነትን አስተጋብቷል መባሉን ተከትሎ ይቅርጣ ጠየቀ።
በፋሽን ትዕይንቱ የተሳተፉ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ትልልቅ ጆሮዎችና ከንፈሮች እንዲሁም ጥቅጥቅ ያለ አርቲፊሻል ሽፋሽፍት እንዲለብሱ የተደረገ ሲሆን ዝንጀሮዎችን እንዲመስሉ ተደርገዋል በሚል ነው ወቀሳ የደረሰባቸው። የፋሽን ትዕይንቱን በመጀመሪያ የተቃወመችው አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት ሞዴል ናት። ''በግልጽ ዘረኝነት ነው የተፈጸመው'' ብላለች። 'ዘ ፋሽን ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ' በመባል የሚታወቀው ትምህርት ቤት ጉዳዩን እየመረመርኩት ነው ብሏል። ''በአሁኑ ሰዓት ባለን መረጃ ለፋሽን ትዕይንቱ ጥቅም ላይ የዋሉት ተጨማሪ አርቲፊሻል አካላት ለየት ባለ መልኩ አልባሳቱን ለማቅረብ የተዘጋጁ እንጂ ከዘረኝነት ጋር የተያያዘ ምንም ነገር አላገኘንም'' ብለዋል ትምህርት ቤቱ ፕሬዝዳንት ጆይስ ኤፍ ብራውን። አክለው ግን ''እኛ ማስተላለፍ የፈለግነው መልዕክት በሌላ መልኩ መተርጎሙን አስተውለናል። ለዚህም ለሰራነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን ። በዝግጅቱ ለተሳተፉ ሞዴሎች፣ ተማሪዎች እና በሁኔታው ለተበሳጩ ሰዎች በሙሉ ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን'' ብለዋል። 'ዘረኛ' የተባለው የፋሽን ትዕይንት ወደ መገናኛ ብዙኃን ጆሮ የደረሰው በዝግጅቱ አልሳተፍም ብላ ተቃውሞዋን በይፋ በገለጸች ጥቁር ሞዴል አማካኝነት እንደሆነ ታውቋል። ጥቁር አሜሪካዊቷ ሞዴል ኤሚ ሌፍር ለኒውዮርክ ፖስት እንደገለጸችው ለፋሽን ትዕይንቱ አዘጋጆች በውሳኔያቸው ደስተኛ እንዳልሆነችና ሌላ መልዕክት ሊያስተላልፍ እንደሚችል ነግሬያቸው ነበር ብላለች። • ዘረኝነት ሽሽት - ከአሜሪካ ወደ ጋና ''ልብሶቹን ለመልበስ አልፈልግም፤ ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ስላቸው 'ለ 45 ሰኮንዶች ብቻ ነው፤ ጥሩ ስሜት ባይሰማሽም ችግር የለውም' አሉኝ'' ብላለች።
news-47499776
https://www.bbc.com/amharic/news-47499776
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ዶ/ር አምባቸው መኮንን ማን ነበሩ?
ሰኔ 15/2011 ዓ.ም በተካሄደው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተገደሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት ከአራት ወራት በፊት ነበር።
በወቅቱም በክልሉ ምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ሲፈፅሙ የተጣለባቸው ኃላፊነት "ከባድ፣የሚያስጨንቅና በውስብስብ ፈተናዎች የተሞላ..." ሲሉ ነበር የገለጹት። • መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች •የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መልቀቂያ አቀረቡ ደቡብ ጎንደር ጋይንት ያደጉት ዶ/ር አምባቸው መኮነን ሲሳይ የ48 ዓመት ጎልማሳ ነበሩ። በልጅነታቸው የፊዚክስና የሒሳብ ትምህርቶችን አብልጠው ይወዱ እንደነበር የሚነገርላቸው ዶ/ር አምባቸው ሕልማቸው መምህር መሆን ነበር። የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወቅቱ በነበረው ጦርነት ምክንያት ለማቋረጥ ተገደዋል። ከዚያም ትግሉን ከተቀላቀሉ ከ5 ዓመታት በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት በርቀት አጠናቀዋል። የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ነው። የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን ደግሞ ደቡብ ኮሪያ በሚገኘው ኬዲአይ የፐብሊክ ፖሊሲና አስተዳደር ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። •የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ንቅናቄ ትናንት እና ዛሬ በቅድመ ምረቃም ሆነ በድኅረ ምረቃ ያጠኑት የትምህርት ዘርፍ ምጣኔ ሐብትን ነው። ከኮሪያ ተመልሰው ለ11 ዓመታት በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ካገለገሉ በኋላ ለሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት ወደ እንግሊዝ አቅንተዋል። ሦስተኛ ዲግሪያቸውንም እንዲሁ በምጣኔ ሐብት ዙርያ ከእንግሊዙ ኬንት ዩኒቨርስቲ ነው ያገኙት። በበጀት እጥረት ምክንያት ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ለማቋረጥ ጫና እንደነበረባቸው፤ ደኞቻቸው ገንዘብ በማዋጣት ጭምር ያግዟቸው እንደነበር ከዚህ ቀደም ካፒታል ለተሰኘው ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። • ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የአማራ ክልል ገለፀ ዶ/ር አምባቸው ከትጥቅት ግሉ በኋላ ከወረዳ ጀምሮ አስተዳደራዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። ዋናነት ከሚጠቀሱት መሀል በአማራ ክልል የሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር፣ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ለአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር፣የአማራ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊነቶች ይገኙባቸዋል። በፌዴራል ደረጃ ደግሞ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ኾነው ለአንድ ዓመት ያህል አገልግለዋል።ከዚያ በኋላም የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር በመሆን ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ጊዜ ሰርተዋል። ከግንቦት 2010 ዓ.ም ጀምሮ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሲሆን፣ ከሕዳር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ይህንን የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የመሠረተ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ኾነው አገልግለዋል። ዶ/ር አምባቸው ከለውጡ በኋላ ለርዕሰ ብሔርነት ታጭተው እንደነበርና ሕዝቡም ሆነ ፓርቲያቸው በፖለቲካው ተሳትፏቸው እንዲቀጥሉ በመፈለጋቸው ሐሳባቸውን መቀየራቸው ሲነገር ነበር።
news-45267605
https://www.bbc.com/amharic/news-45267605
ፌስቡክና ትዊተር ከሩሲያና ኢራን ዘመቻ ጋር የተገናኙ አካውንቶች ሊያግድ ነው
ፌስቡክና ትዊተር ከኢራንና ከሩሲያ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉና ሃሰተኛ መረጃን የሚያሰራጩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አካውንቶችን አግጃለሁ ሲሉ አስታውቀዋል።
ፌስቡክ ከወራቶች ጥናት በኋላ ኢራንና ሩሲያ ከሚያካሄዱት ዘመቻ ጋር ተያይዞ ሃሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ በርካታ አካውንቶችን ለይቻለሁ ሲል አስታውቆ ነበር። በዚህም መሰረት እስካሁን ከ650 የሚበልጡ የፌስቡክ ገፆች አሳሳች ሆነው ተገኝተዋል ሲሉ የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ አስታውቀዋል። • 'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት? • ፌስቡክ በመረጃ ፍሰት ላይ ማሻሻያ ሊያደርግ ነው • ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ ኩባንያው በመግለጫው ላይ እንዳለውም " እንደዚህ አይነት የቅጥፈት ባህሪ የሚታይባቸውን አካውንቶች ለማገድ ተገደናል። ምክንያቱም ሰዎች በሚያደርጉት የማህበራዊ ሚዲያ ግንኙነት እንዲተማመኑ ስለምንፈልግ ነው" ብሏል። ትዊተር በበኩሉ ለጊዜው 284 አካውንቶች ከኢራን ጋር ግንኙነት ኖሯቸው በማግኘቱ ከመጠቀም አግዷቸዋል። ይህ የሆነው ማይክሮሶፍት ኩባንያ ሩሲያ በአሜሪካ ወግ አጥባቂ ቡድኖች ላይ የምታደርገውን የመረጃ ምንተፋ አሰናክለዋል ካለ በኋላ ነው። ምንም እንኳን ምርመራው አሁንም በሂደት ላይ ያለ ቢሆንም ዘመቻው በመካከለኛው ምስራቅ፣ ላቲን አሜሪካ፣ እንግሊዝና አሜሪካ የሚገኙና የተለያዩ በይነ መረብ አገልግሎት የሚጠቀሙ ሰዎች ላይም ተግባራዊ ይሆናል" ሲል የማህበራዊ ሚዲያ ኔትወርክ ጨምሮ ተናግሯል። አካውንቶቹ ቁጥጥር የሚደረግባቸው እንዴት ነው? የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች የመረጃ መረብ ደህነትን ጠንቅቀው ከሚያውቁና እሳት የላሰ ዓይን ካላቸው ድርጅቶች ጋር በጋራ ይሰራል። ከድርጅቱ ጋር ባደረገው ስምምነትም የኢራንን ፕሮፖጋንዳ የሚያዛምቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው አካውንቶችን ለማወቅ ተችሏል። ከአውሮፓውያኑ 2011 አንስቶ የነበሩት የተወሰኑት ዘመቻዎች ይዘታቸው በአብዛኛው ከመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ጋር ግንኙነት የነበረው ነው ፤ ከዚህም ባሻገር በእንግሊዝና በአሜሪካ ያለውንም ፖለቲካ የተመለከተ ነበር። ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ በበኩሉ ከመረጃ ብርበራው ጀርባ መረጃ መንታፊዎች እንዳሉበት ተናግሯል። ማይክሮ ሶፍት ወደ እርምጃ የገባው አሜሪካ 12 ሩሲያዊ የመረጃ በርባሪ ሊቆችን ሒላሪ ክሊንተንንና የዲሞክራቲክ ፓርቲ የሚጠቀሙበትን የኮምፒዩተር መረጃ እንዲመነትፉ መደራደሯን ተከትሎ ነው።
news-54869784
https://www.bbc.com/amharic/news-54869784
ትግራይ፡ ዶ/ር ደብረጺዮን ጦርነት ቆሞ ድርድር እንዲካሄድ መጠየቃቸው ተሰማ
የፌደራል መንግሥት ከአማራ ክልል ጋር በመሆን ከትግራይ ክልል ኃይሎች ጋር ወደ ግልጽ ጦርነት ከገቡት ስድስት ቀናት አልፈዋል።
ባለፉት ሁለት ቀናት አዳዲስ ነገሮች ተሰምተዋል። ከእነዚህም መካከል የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጸዮን (ዶ/ር) ድርድር እንዲካሄድ መጠየቃቸው አንዱ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ቢያንስ በ8 ቦታዎች ጦርነቶች እየተካሄዱ ይገኛል ብሏል። የድርድር ጥያቄ የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲካሄድ መጠየቃቸው ተሰምቷል። ደብረጺዮን (ዶ/ር) የአፍሪካ ሕብረት በፌደራል እና ትግራይ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ጦርነቱን እንዲያስቆም እና ከእርስ በእርስ ጦርነት አገሪቷን እንዲታደግ ጠይቀዋል። የክልሉ ፕሬዝደንት ለወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት በጻፉት ደብዳቤ ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት እንዲካሄድ ጠይቀዋል። ደብረጺዮን (ዶ/ር) በደብዳቤያቸው "ፖለቲካዊ ችግሮች በወታደራዊ አማራጮች እንደማይፈቱ ጽኑ እምነት አለኝ" ብለዋል። በተመሳሳይ ሮይተርስ የዜና ወኪል ደብረጺዮን (ዶ/ር) ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲደረግ መጠየቃቸውን ትናንት ምሽት አስነብቧል። ይህ ይሁን እንጂ በፌደራል መንግሥቱ በኩል ለድርድር ፍላጎት ያለ አይመስልም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ትናንት ለውጪ ማህብረሰቡ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር መንግሥት የጀመረውን እርምጃ ያጠናቅቃል ብለዋል። ከሁለት ቀናት በፊትም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በትዊተር ገጻቸው ላይም "ወንጀለኛ አካላት ዕርቅ እና ድርድር ፈላጊ በመምሰል ከሕግ የበላይነት ሊያመልጡ አይችሉም። የሚከናወነው ኦፕሬሽን ዓላማው፣ የሚገባቸውን ቅጣት ሳያገኙ ከገደብ አልፈው የቆዩትን አጥፊ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሀገራችን ሕግጋት መሠረት ተጠያቂ ማድረግ ነው" ብለው ነበር። የተመድ መግለጫ የተባበሩት መንግሥት ድርጅት በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ቢያንስ በ8 ቦታዎች ጦርነቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ ብሏል። ተመድ ከዚህ ጦርነት ጋር በተያያዘ እስከ 9 ሚሊዮን ሕዝብ ሊፈናቀል ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። የተባበሩት መንግሥት ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች በሙሉ ዝግ መሆናቸውን እንዲሁም የኮሚኒኬሽን አገልግሎት በመቋረጣቸው የእርዳታ ቁሳ ቁሶች የሚደርሱበት አማራጭ የለም ብሏል። ድርጅቱ በጦርነቱ በርካቶች መገደላቸውን እና በርካታ የአየር ጥቃቶች ስለመፈጸማቸው ሪፖርት ደርሶናል ብሏል። መከላከያ ድል አደረኩ ስለማለቱ የአገር መከላከያ ኢንዶክትሬኔሽን እና የሕዝብ ግነኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ ለአገር መገናኛ ብዙሃን ባለፉት ቀናት በምዕራብ ትግራይ በኩል በተደረገው ጦርነት መከላከያ ሠራዊት ድል እያደረገ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሜ/ጀነራል መሐመድ ትናንት በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙትን እንደ ማይዳሉ፣ ዳንሻ፣ ባአካር፣ ሉግዲ በቁጥጥር ሥር አውለናል ብለዋል። ሜ/ጀነራሉ ጨምረውም፤ ቅራቅር እና ጸገዴ ወረዳን እንዲሁም ዳንሻ አከባቢ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ ተቆጣጥረናል ብለዋል። በትግራይ የሚገኙ ባንኮች መዘጋት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ "ሕወሓት በትግራይ ክልል የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች ላይ ዘረፋ እየፈፀመ ነው" በሚል በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የባንክ ቅርጫፎች እንዲዘጉ ወስኗል። ብሔራዊ ባንክ በተለያዩ ባንኮች ውስጥ ያለው ገንዘብ ደህንነቱ አደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኛል ያለ ሲሆን በትግራይ ክልል 616 የባንክ ቅርንጫፎች አሁን ባለው ሁኔታ በክልሉ የሚገኙ ባንኮች አገልግሎት መስጠት ስለማይችሉ ተዘግተው እንዲቆዩ ተወስኗል ብሏል። 'ተዋጊ ጄት መትተን ጥለናል' የሕውሃት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ በድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን ቀርበው በምዕራብ ትግራይ ከባድ ጦርነት እየተካሄደ ነው ብለዋል። አቶ ጌታቸው በአፋር ክልል እና በራያ በኩል የፌደራል መንግሥቱ ተጨማሪ ኃይል በማሰማራት ጦርነት ለመክፈት በዝግጅት ላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በምዕራብ ትግራይ በኩል መከላከያ ሠራዊት ድል አደረኩ ማለቱ እውነት አይደለም ሲሉም ተደምጠዋል። አቶ ጌታቸው የፌደራሉ መንግሥት ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረው፤ ትናንት እሁድ አንድ ተዋጊ ጄት ተመትቶ ወድቋል ብለዋል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ግን ይህ ሃሰት ነው ሲሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል። ሜጀር ጄኔራል መሐመድ አየር ኃይሉ አሁንም ቢሆን የተመረጡ ቦታዎችን ማጥቃቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።
48237007
https://www.bbc.com/amharic/48237007
የሆንግ ኮንግ የሕዝብ እንደራሴዎች ተቧቀሱ
በሆንግ ኮንግ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በወንጀል የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ለቻይና ተላልፈው እንዲሰጡ የሚፈቅደውን ሕግ ለመቀየር በሚደረግ ክርክር ላይ በተፈጠረ አለመግባባት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የቡጢ ሜዳ ሆኗል።
በርካታ የምክር ቤቱ አባላት የተጎዱ ሲሆን አንድ ፖለቲከኛ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ውጥረቱ የተባባሰው ፖለቲከኞች መሳደብና ከጠረጴዛ ጠረጴዛ መዝለል ሲጀምሩ እንደሆነ ተገልጿል። • "ምርጫው እንዲራዘም እንፈልጋለን" አቶ አንዷለም አራጌ ሆንግ ኮንግ 'ዋን ካንትሪ ቱ ሲስተም' (አንድ ሀገር ሁለት ስርአት እንደማለት) በሚለው ፖሊሲ መሰረት ከቻይና የተለየ ሕግ ያላት ግዛት ነች። ቤይጂንግ ከቅኝ ገዢ እንግሊዝ ሆንግ ኮንግን የተረከበችው እ.ኤ.አ በ1997 ሲሆን፤ በወቅቱም ግዛቲቱ ከውጭ ግንኙነትና ከመከላከያ በስተቀር ራሷን የቻለች ግዛት ሆና ለ50 ዓመት እንድትቀጥል ተስማምታ ነበር። ነገር ግን የቤይጂንግ መንግሥት አፍቃሪ ናቸው የሚባሉት ኬሪ ላም፤ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወንጀል የሰሩ ግለሰቦች እንደየጉዳያቸው አይነት ወደታይዋን፣ ቻይና እና ማካኡ ተላልፈው እንዲሰጡ የሚፈቅደውን ሕግ አቀርበዋል። • ስጋን የተካው "ስጋ" ፖለቲከኛው ለዚህ ሕግ መነሻ የሆናቸው የ19 ዓመት ሆንግ ኮንጓዊ ከነፍሰ ጡር ፍቅረኛው ጋር በታይዋን እየተዝናኑ ሳሉ ፍቅረኛውን በመግደሉ ነው። በወቅቱ ታይዋን ተጠርጣሪውን አሳልፋ መስጠት ብትፈልግም፤ የሆንግ ኮንግ ባለስልጣናት ግን በሁለቱ ሀገራት መካከል ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት አለመኖሩን በመጥቀስ አሻፈረኝ አሉ። የሕጉ ተቺዎች እንደሚሉት፤ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ የሚሰጠውን ሕግ መቀየር የሆንግ ኮንግን ነፃነትን ይጋፋል። • ''እያሉ'' በሌሉበት የተከሰሱት አቶ ጌታቸው አሰፋ ይህንን ረቂቅ ሕግ በመቃወምም በሆንግ ኮንግ ትልቅ የሕዝባዊ ሰልፍ ተደርጎም ነበር። ባለስልጣናት እንደሚሉት፤ ለውጡን ማድረግ ያስፈለጋቸው በነፍስ ማጥፋት የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ወደታይዋን ለመውሰድ እንዲያስችላቸው ነው። አንድ የቤይጂንግ ደጋፊ የሆኑ ፓለቲከኛ "ለሆንግ ኮንግ የሐዘን ቀን ነው"ሲሉ ተደምጠዋል።
news-55305980
https://www.bbc.com/amharic/news-55305980
ትግራይ ፡ ከ40 ቀናት በኋላ በመቀለ የስልክና የመብራት አገልግሎት መጀመሩ የፈጠረው ስሜት
በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል የጸጥታ ኃይሎችና በፌደራል መንግሥቱ መካከል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ላለፉት 40 ቀናት በክልሉ የኤሌትሪክ፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተቋርጠው ቆይተዋል።
በእነዚህ ጊዜያት በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የስልክ፣ መብራት፣ ኢንተርኔት ባንክና የመሳሰሉት ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ወሳኝ የሆኑ አገልግለቶች ተዘግተው ከርመዋል። ይህም ቢቢሲ በተለያየ ወቅት ያናገራቸው በክልሉ ውስጥ እንዲሁም በሌላ የአገሪቱ አካባቢና ከአገር ውጪ በሚኖሩ ላይ ሰዎች ላይ ጭንቀትና ከባድ ጫና ማስከተሉን ገልፀው ነበር። ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም፣ የግንኙነት መስመሮች እንዲከፈቱና የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ የአቅርቦት መስመሮች አለገደብ ክፍት እንዲሆን ሲጠይቁ ቆይተዋል። ኢትዮ-ቴሌኮም ከትናንት በስተያ ቅዳሜ የስልክ አገልግሎት በትግራይ ዋና ከተማ መቀለ ላይ እንደጀመረ ቢገልጽም፣ የመብራት አገልግሎት በወቅቱ ባለመጀመሩ ጥቂቶች ብቻ በአገልግሎቱ ለመጠቀም ችለው ነበር። ይሁን እንጂ፣ ከትናንት አመሻሽ 11 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ መብራት አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙና ከትግራይ ክልል ውጪ ካሉ ዘመድ ወዳጆቻቸው ጋር መገናኘት ችለዋል። በውጭ አገራት የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች በበኩላቸው፣ የቤተሰባቸው አባላትና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ችለዋል። በማኅበራዊ ሚድያ ላይ፣ በርካቶች ቤተሰቦቻቸውን ማነጋገራቸው በመግለጽ የተሰማቸውን ደስታ ሲገልጹ፣ አንዳንዶች ደግሞ በጦርነቱ ወቅት አልያም ከዚያ በኋላ የተጎዱ አልያም በተለያየ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ የቤተሰብ አባላቶቻቸውንና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን መርዶ እንደሰሙ ጽፈው ታይቷል። "ጨላማ ውስጥ ነበርን" አንድ ለደኅንነቱ ሲባል ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የመቀለ ከተማ ነዋሪ "ከአንድ ወር በላይ የስልክና የመብራት አገልግሎት መቋረጡ ኑሯችንን አክብዶታል። በቀላሉ ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ሆነ ሥራ ለመሥራት የማንችልበት ጨለማ ውስጥ ነው የቆየነው" ብሏል። በአጋጣሚ ቀደም ብሎ ቀለብ የሸመተ ሰው ካልሆነ በስተቀር፣ እጁ ላይ ምንም ዓይነት ነገር ያልነበረው ግለሰብ እህል መሸመት ስለማይችል ከባድ ችግር ላይ ወድቆ እንደነበረም ጨምሮ ተናግሯል። በተለይ የባንክ አገልግሎት ፈጥኖ ካልተጀመረ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የሚሰጉ በርካቶች መሆናቸውን ቢቢሲ መረዳት ችሏል። ቢቢሲ ያነጋገረው ይህ ወጣት ከተማዋ ስላለችበት ሁኔታም ሲያስረዳ "12 ሰዓት ላይ ወደ ቤት ለመግባት ተገደን ነበር። ከዚያ በኋላ ስለሚሆነው ነገር የምንሰማበት ሁኔታ አልነበረም። እሱን ለመስማት የግድ እስከ ጠዋት ድረስ መጠበቅ ይኖርብናል። ቴሌቪዥንና ሬድዮም በመብራት መጥፋት ምክንያት ስለማይሰሩ ምን እየተፈጸመ እንደሆነ ማወቅ አንችልም ነበር" በማለት ይገልጻል። ቢቢሲ መቀለ ከተማ ስላለው ሁኔታ ለመጠየቅ የደወለለት ሌላ ግለሰብ "አንተ ሰው ከሰላምታ ውጪ ሌላ ነገር እንዳታናግረኝ፤ እንዳትጠይቀኝ" በሚል ለደኅንነቱ እንደሚሰጋ ገልጿል። በዚህም የተነሳ መቀሌ በህወሓት ስር በነበረችበት ጊዜም ሆነ ከዚያ በኋላ ስላለው፣ ስለ ሰማውና ስለተመለከተው ነገር ለቢቢሲ ለመናገር አልደፈረም። ከመቀለ ውጪ- ስጋትና ጭንቅ በርካቶች በከተማዋ የስልክና የመብራት አገልግሎት በመጀመሩ ደስተኞች ቢሆኑም፣ ከከተማዋ ውጪ በክልሉ ያሉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ ባለመቻላቸው መጨነቃቸውን ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት ጀምሮ በምዕራብ ትግራይ ሑመራ፣ ዳንሻና በመሳሰሉት እንዲሁም በደቡብ ትግራይ በአላማጣ ከተሞች አካባቢ የስልክ አገልግሎቱን መስጠት መጀመሩ መገለጹ ይታወሳል። በተቀሩት የትግራይ ክልል ከተሞች ግን እስከአሁን የግንኙነት መንገድ ዝግ በመሆኑ የተነሳ ሕዝቡ ያለበት ሁኔታ እንደሚያስጨንቃቸው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰቦች ገልፀዋል። በተለይ ደግሞ ከባድ ጦርነት በተካሄደባቸውና "እየተካሄደባቸው ነው በሚባሉ ከተሞች" የቤተሰባቸው ሁኔታ እንደሚያስጨንቃቸው ተናግረዋል። ቢቢሲ ካነጋገራቸው ግለሰቦች መረዳት እንደቻለው በክልሉ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ያልተጀመረ ሲሆን፣ በአብዛኛው ከከተማ ወደ ከተማ ተንቀሳቅሰው ወዳጅ ዘመዶቻቸው ያሉበትን ሁኔታ መጠየቅ ሆነ ማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። አንዳንዶቹ ግን በተለያዩ አቅራቢያ ከተሞች ስላሉ ቤተሰባቸው ሁኔታ ለማወቅ እንደቻሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። የስልክና የኢንትርኔት አገልግሎቶች ለሳምንታት ተቋርጠው በመቆየታቸው የተነሳ በፌደራል መንግሥትና በህወሓት መካከል ወታደራዊ ግጭቱ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ፣ በክልሉ በትክክል ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ አልተቻለም። ቢቢሲም ከየትኛውም ወገኖች ሲሰጡ የነበሩ መረጃዎችን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም። በኢትዮጵያ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጠው ብቸኛው ተቋም ኢትዮ ቴሌኮም በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆውን አገልግሎቱን በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳለው የክልሉ ታጣቂ ኃይሎች በሽረ እና በመቀለ የሚገኙትን ማዕከላት የኃይል አቅርቦት ሆን ብለው በመቋረጣቸው መሆኑ ተገልጿል። ጨምሮም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ባሉ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በመፈጸሙ እነዚህን በመጠገን በቅርብ ቀናት ውስጥ አጠቃላይ ክልሉ አገልግሎቱ እንደሚጀመር ተነግሯል። ሌሎች እንቅስቃሴዎች በፌዴራል መንግሥት የተሰየመው በሙሉ ነጋ (ዶ/ር) የሚመራው የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ሰሞኑን ሥራ መጀመሩን ያሳወቀ ሲሆን በተለይ በሽረ ከተማ አዲስ ከንቲባ መሾሙን አሳውቋል። ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ ተቋርጦ የቆየው የመንግሥት መደበኛ ሥራ እንዲጀመርና የመንግሥት ሰራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ አሳውቋል። የጤና ማዕከላት በከተማዋ ሆነ በክልሉ መሠረታዊ የህክምና አገልግሎት በማይሰጡበት ደርጃ ወርደው እንደነበር ሲገለጽ የቆየ ቢሆንም ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማኅበር በበኩሉ ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መድኃኒት ማጓጓዙን ተገልጿል። የፌዴራል መንግሥት በበኩሉ ሰሞኑን በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች ላይ እርዳት ማድረሱን ገልጿል።
news-52742939
https://www.bbc.com/amharic/news-52742939
ስፔን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማደረግን የሚያስገድደውን ሕጓን አጠበቀች
በስፔን አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በማይቻልበት ሁኔታ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብልን (ማስክ) በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ማድረግን ግዴታ አደረገች።
በዚህ ሐሙስ ተግባራዊ መደረግ በሚጀምረው አዲሱ ሕግ የማይካተቱት ከስድስት ዓመት በታች ያሉ ሕጻናትና የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ብቻ ናቸው። ምንም እንኳን በርካታ የአውሮፓ አገራት በሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎቶች ላይ ማስክ ማድረግን አስገዳጅ ቢያደርጉም፤ የስፔን ግን ጠበቅ ያለ ሆኗል። ስፔን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክፉኛ ከተጠቁት የአውሮፓ አገራት አንዷ ስትሆን፤ አሁን ላይ ከቤት ያለመውጣት ገደቡን እያላላች ነው። ቀደም ብላም በሕዝብ ማጓጓዣዎች ላይ ማስክ ማድረግን ብትጠይቅም፤ አሁን ላይ ሕጉን በአጠቃላይ በሕዝቡ ላይ ጠበቅ እያደረገች ነው። በስፔን ከፈረንጆቹ መጋቢት ጀምሮ 28 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸውን ሲያጡ 232 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይሁን እንጂ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በመሆኑም ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ህጻናትን ለ6 ሳምንታት ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ማድረግን ጨምሮ በምድራችን ካሉ አገራት በጣም ጥብቅ የሆኑ እርምጃዎችን ወስዳለች። ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያራዝምላቸው ጠይቀዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ አባላቶች ግን የጠቅላይ ሚንስትሩን ጥያቄ ተቃውመውታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አዋጁን ማራዘም ሕዝቡን ከወረርሽኙ ለመታደግ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል። ሕጉ ምን ይላል? ሕጉ አካላዊ ርቀትን ቢያንስ በሁለት ሜትር መጠበቅ በማይቻልባቸው ጎዳናዎች ላይ፣ በመናፈሻ ቦታዎች እንዲሁም ሕዝብ በሚገለገልባቸው ቤቶች፣ በገበያ ማዕከላትና በመሳሰሉት ውስጥ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ )ማድረግ ግዴታ መሆኑን ያትታል። ሆኖም ከስድስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ይህንን እንዲተገብሩ አይገደዱም። ነገር ግን ከሦስት እስከ 5 ዓመት ያሉ ህጻናት ማስክ እንዲያደርጉ ይመከራል። የመተንፈሻ አካል ህመም እና ሌላ የጤና እክል ያለባቸው እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለማድረግ የማያስችል አካል ጉዳት ያለባቸው ሕጉን እንዲተገብሩ አይገደዱም። ሌሎች አገራት የሚያደርጉት ምንድን ነው? በአውሮፓ አገራት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን ወስደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ጤናማ ሰዎች ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ማስክ ማድረግ ይኑርባቸው አይኑርባቸው የሚለውን ለመወሰን በቂ መረጃ እንደሌለው ተናግሯል።
news-56817110
https://www.bbc.com/amharic/news-56817110
ሱዳን በሕዳሴ ግድብ ላይ ያላት ተቃውሞ ለምን ጠነከረ?
ሱዳን ለአስርት ዓመታት ያህል በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል የማያባራ ውዝግብ በቀጠለበት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መሃል አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች።
የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌቱን የሚያሳይ የሳተላይት ምስል ለዓመታት ያህል የታላቁ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የሱዳን እይታ (አቀራረብ) የነበረው ሁኔታውን ሰፋ አድርጎ በማየት የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተጠራጣሪነትና የጠብ አጫሪነት ሚናን መጫወት ጀምራለች። ይሄ ለውጥ በብዙ መልኩ ለረዥም ዓመታት ሱዳንን የገዟትን ኦማር አል-በሽር ከስልጣን መገርሰስን ተከትሎ ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲያሻግራት በጊዜያዊነት የመጣው የሽግግር መንግሥት ላይ ወታደራዊው ሥርዓት ከፍተኛ ጫና ነፀብራቅ ነው። በተለይም ያለ ሦስትዮሽ ስምምነት ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት በመጪው ክረምት እጀምራለሁ ማለቷ ጋር ተያይዞ ዲፕሎማሲያዊው ግፊት ከፍ ብሏል። ሁለቱ አገራት ግብጽና ኢትዮጵያ ስለ ሕዳሴ ግድብ ሲያነሱ የህልውናቸው መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ብርሃን ለተነፈገው 60 በመቶ ሕዝቧ ብርሃን ያመጣል እንዲሁም ለልማቴ ቁልፍ ነው ትላለች። ግብጽ በበኩሏ ግድቡ አገሪቷ የምታገኘውን የውሃ መጠን እንደሚቀንስና የሕዝቧን ህይወት መሰረት ያናጋዋል ትላለች። ሁለቱን አገራት በሚያገናኘው ወንዝ መካከል የምትገኘው ሱዳን በበኩሏ ቆፍጠን ያለ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፍ ጀምራለች። የሚመነጨው ኃይል ሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ያስችላል የግንባታ ወጪከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ግንባታው የተጀመረው2003 ዓ.ም. የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት የበላይ የሆኑት የሌተናል ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን አማካሪ የውሃ ጦርነት እንደሚነሳ ገልፀዋል፤ "ከሚታሰበው በላይ የከፋ ይሆናል" በማለት አስጠንቅቀው "ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ጣልቃ ገብቶ መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ ጦርነት አይቀሬ ነው" ብለዋል። ግድቡ በመጀመሪያ ተቀባይነት ነበረው ወደ ኋላ አስራ አራት ወራትን መለስ ብለን ብናጤን ከመዲናዋ ካርቱም በግድቡ ጉዳይ የተለያዩ ድምፆች ይሰሙ ነበር። በአውሮፓውያኑ የካቲት 2020 የውሃ ሚኒስትሩ ያሲር አባስ ግድቡ ምን ያህል ለሱዳን ጠቃሚ እንደሆነ አብራርተው ነበር። ምናልባት መስተካከል ካለባችው አንዳንድ ጥቃቅን ጉዳዮች በስተቀር የሕዳሴ ግድብ የናይልን ፍሰት በተመጠነ መልኩ እንደሚያደርገውና ሦስተኛ የእርሻ ወቅትን በአገሪቷ ሊያስጀምር ይችላል ሲሉ ተደምጠው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በቀን ውስጥ 12 ሰዓታት ያህል የኤሌክትሪክ አገልግሎት በሚቋረጥባት ሱዳን በአስተማማኝና በረከሰ ዋጋ አቅርቦት ማግኘት ነው ተባለ። ነገር ግን በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ይካሄድ በነበረው የሦስቱ አገራት የኪንሻሳው ድርድር ፍሬ አልባ መሆኑን ተከትሎ የውሃ ሚኒስትሩ ያሲር አባስ ኢትዮጵያ አገራቱ የሚያወዛግቧቸው ጉዳዮች ሳይፈቱ በውሃ ሙሌቱ የምትቀጥል ከሆነ የአገሪቱን ብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ላይ ይጥላል በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ሱዳን ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌቱን በምን ያህል ጊዜ እንደምታከናውን እንዲሁም ግድቡ የሚቋጥረው የውሃ መጠንን በተመለከተ መመሪያ ሳይሆን አሳሪ የሆነ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ትፈልጋለች። ከዚህም በተጨማሪ ለወደፊቱ አለመግባባቶች ቢፈጠሩ እንዴት ሊፈቱ ይችላሉ የሚለውም ላይ ግልፅ ያለ ሁኔታ መኖር አለበት ትላለች። ያሲር አባስ በቅርቡ ለቢቢሲ ኢትዮጵያ ውሃውን ለእርሻ መጠቀም እፈልጋለሁ ብላለች በማለት ገልፀው ይህም ሁኔታ እስካሁን የነበሩ ድርድሮችን የበለጠ እንደሚያወሳስባቸው ተናግረዋል። "ያለ ምንም ስምምነት የሕዳሴ ግድብ ለታችኛው ተፋሰስ አገራት ሕዝቦች ከባቢ ሁኔታም ሆነ ለሕዝቡ አኗኗር አደጋ ነው" በማለት አክለዋል። የሕዳሴ ግድብ ሙሌቱ የአባይ ወንዝን ፍሰት መጠን የሚቀንሰው ከሆነ ከግብጽ በላይ የምትጎዳው ሱዳን ናት የሚሉት ሚኒስትሩ፤ ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት ግብጽ በአስዋን ግድብ ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ተቀማጭ ውሃ እንዳለት በመግለፅ ነው። እነዚህ ሱዳን እንደ ምክንያትነት የምታቀርባቸው መረጃዎች ለረዥም ዘመናት የሚታወቁ ጉዳዮች ነበሩ። ነገር ግን የተቀየረ ጉዳይ ቢኖር የአልበሽርን መውደቅ ተከትሎ የመጣው በሲቪልና በወታደራዊው አመራር መካከል የትኛው የበለጠ የኃይል ሚዛን አለው የሚለው ነው። በተጨማሪም በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር መካከል በአልፋሽጋ የተነሳው የግዛት ይገባኛል ውዝግብ ሱዳን ለኢትዮጵያ እንዳትወግን ካደረጓት ምክንያቶች መካከል ተጠቃሹ ሊሆን ይችላል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ድንበር በትክክል ባይሰመርም፤ የቅኝ ግዛት ውሎች አልፋሽጋ የሱዳን ግዛት መሆኑን ያሳያሉ። ይሁን እንጂ በስፍራው ኢትዮጵያውያ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ግብርም ይገብሩ የነበሩት ለኢትዮጵያ መንግሥት ነበር። በአውሮፓውያኑ 2008 ኢትዮጵያ ግዛቱ የሱዳን እንደሆነ ዕውቅና ብትሰጥም ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን ቀጥለዋል። ከቅርብ ወራት በፊት ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተነሳው ግጭት ፊቷን ባዞረችበት ወቅት ሱዳን ይህንን ክፍተት በመጠቀም ወታደሮቿን ወደ አልፋሽጋ እንዲሰማሩና እንዲቆጣጠሩ አድርጋለች። የሱዳን ወደ ግብጽ መጠጋት የሱዳን መንግሥት በድንበር አካባቢው የሚደረገው ወታደራዊ እርምጃ ሕዝቡ እንዲደግፍ ከፍተኛ የሆነ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል። የዚህም ዘመቻ አካል የሆነው በአገሪቷ ተፅእኖ ፈጣሪ የሚባሉ ግለሰቦችን ወደ ድንበር አካባቢ መውሰድ እንዲሁም ስመጥር ዘፋኞች በወታደራዊ መለዮ በካርቱም እንዲዘፍኑ ማድረግ ይገኝበታል። በሰሜናዊ ሱዳንም የአገሪቱ አየር ኃይል ከግብጽ ጋር በጋራ ስልጠና በማድረግ ላይ ይገኛሉ። "ኢትዮጵያን ለመሸንቆጥ የሚያደርጉት ሙከራ በደንብ ግልፅ ነው" በማለት የቀድሞ ብርጋዲየር ማህሙድ ጋሌንደር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በተደጋጋሚ የሕዳሴ ግድብ በሱዳን ላይ ምንም አይነት ጉዳት አያስከትልም በማለት ሱዳን ስጋት እንዳያድርባት ለማድረግ ሞክራለች። በባለፈው ሳምንት እሁድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እንዲሁ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ "በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ጉዳት የማስከተል ምንም አይነት አላማ የላትም" በማለት በትዊተር ገፃቸው አስፍረው እንዲያውም በባለፈው ዓመት የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ምክንያት "ጎረቤት አገር ሱዳንን ሊያጥለቀልቃት ከነበረው ክፉኛ ጎርፍ ታድጓታል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ከመጪው የክረምት ወር ከሚደረገው ሙሌት በፊት መረጃ መለዋወጥን በተመለከተ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የቀጣይ ድርድሮች አስፈላጊነት በጠነከሩበት በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልዕክት ሱዳንም ሆነ ግብጽ ከማስፈራራታቸው ቆጠብ የሚያደርጋቸው አልሆነም። እንዲያውም ከሰሞኑ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ በሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ሕጋዊ መፍትሄ ለማግኘትና ለዚህም አጋሮች ለማግኘት በአህጉሪቷ እየዞሩ ነው። "የግድቡ አሰራርና የውሃ ሙሌቱ የሦስቱን አገራት ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ" እንዲሆን ለማድረግ በሚልም ነው የሚኒስትሩን ጉብኝት በተመለከተ የግብጽ መንግሥት ያወጣው መግለጫ ያተተው። የሱዳኑ ጄኔራል ቡርሃን በበኩላቸው በባለፈው ሳምንት ከአንድ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዲሁ ተመሳሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል። ይህ ይሁን እንጂ የዲፕሎማሲያዊ ጫና ቢጠነክርም፣ ውሳኔ ላይ ተደረሰም አልተደረሰም በመጪው ክረምት በሚዘንበው ዝናብ የግድቡ ሙሌቱ መከናወኑ የሚቀር አይመስልም።
news-50997659
https://www.bbc.com/amharic/news-50997659
በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ሮናልዶና ሜሲን ማን ይተካቸው ይሆን?
ክሪስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲ ከአውሮፓውያኑ 2010 እስከ 2020 ባሉት ዓመታት የዓለምን እግር ኳስ ተቆጣጥረውና የኳስ አፍቃሪውን ይሄኛው ይበልጣል ያኛው በሚል ክርክር ውስጥ ከትተው ቆይተዋል።
ነገር ግን ለጁቬንቱስ የሚጫወተው የ34 ዓመቱ ሮናልዶና የባርሴሎናው የ32 ዓመት አጥቂ ሜሲ ለዘለዓለም ሊቆዩ አይችሉም። ለመሆኑ የእነሱን ቦታ ማን ሊተካው ይችል ይሆን? • ጋና የብሔራዊ ቡድኗን አሠልጣኞች በጠቅላላ አባረረች • "የዘረኝነት ጥቃቱ ከዚህም በላይ ሊከፋ ይችላል" ንጎሎ ካንቴ የቢቢሲ ስፖርት ክፍል ተከታዮቹን ተጫዋቾች ተተኪ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ መርጧቸዋል። ኪሊየን ምባፔ (ፒኤስጂ እና ፈረንሳይ) የውልደት ቀን: ታህሳስ 20/1998 (በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር) የሚጫወትበት ቦታ: አጥቂ ምባፔ ገና በ21 ዓመቱ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጋር 2018 የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችሏል። ማንሳት ብቻ ሳይሆን ለቡድኑ ዋንጫ ማንሳት የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል ማለት ይቻላል። እጅግ አስገራሚ ፍጥነትና ተፈጥሮአዊ ግብ የማስቆጠር ችሎታው በዓለማችን እጅግ ተፈላጊውና ውዱ ተጫዋች አድርጎታል። በሚቀጥሉት አስር ዓመታትም የዓለማችንን እግር ኳስ አፍቃሪ ቀልብ ይዞ እንደሚቆይ ጥርጥር የለውም። የሮናልዶና ሜሲ ተተኪ ለመሆን የሚገዳደረው ያለ አይመስልም። በአሁኑ ሰአት ለፈረንሳዩ ፒኤስጂ የሚጫወተው ምፓቤ በሚቀጥለው የክረምት የዝውውር መስኮት በዓለማችን ከፍተኛው በሆነ ዋጋ የስፔኑ ታላቅ ክለብ ሪያል ማድሪድን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል። ምናልባት ሜሲ እና ሮናልዶ እስከሚቀጥለው ዓመት ድረስ የዓለም ምርጥነት ቦታውን ሊፎካከሩት ይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን ከዚያ ቀጥሎ ባሉት ዓመታት አብዛኛውን የዓለም ምርጥነት ሽልማቶች መሰብሰቡ የጊዜ ጉዳይ ይመስላል። ጃዎ ፌሊክስ (አትሌቲኮ ማድሪድና ፈረንሳይ) የውልደት ቀን : ሕዳር 10/1999(በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር) የሚጫወትበት ቦታ: አጥቂ የ20 ዓመቱ ፌሊክስን ባለፈው የዝውውር መስኮት ነበር አትሌቲኮ ማድሪድ 113 ሚሊየን ዩሮ በሆነ ዋጋ ከቤኔፊካ የገዛው። በወቅቱ ሶስተኛ ከፍተኛው የዝውውር ወጪ ነበር። • የጣልያኑ ሴሪ ኤ ለጸረ ዘረኝነት ዘመቻው የዝንጀሮ ምስል መጠቀሙ ቁጣን ቀሰቀሰ በፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ውስጥም ቢሆን የክርስቲያኖ ሮናልዶ ተፈጥሯዊ ተተኪ እንደሚሆን በማሰብ ከአሁኑ ብዙ ሀላፊነቶች እየተሰጡት ይገኛሉ። ባለፈው ዓመትም የዓለማችን ምርጡ ታዳጊ ተጫዋች ተብሎ ዱባይ ላይ ተሸልሟል። ጆርዳን ሳንቾ (ቦርሺያ ዶርትመንድ እና እንግሊዝ) የውልደት ቀን : መጋቢት 25/2000(በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር) የሚጫወትበት ቦታ: የክንፍ መስመር አጥቂ ይህ ተጫዋች በዶርትመንድ እጅግ አስገራሚ ብቃቱን በማሳየት ላይ ይገኛል። ለግብ የሚሆኑ በርካታ ኳሶችን ከሳምንት ሳምንት ለቡድን አጋሮቹ ከማቀበል ባለፈ ምርጥ ምርጥ ግቦችንም በስሙ ያስመዘግባል። በራስ መተማመኑም ቢሆን በሜዳ ውስጥ በደንብ ይታያል። አንሱ ፋቲ (ባርሴሎና እና ስፔን) የውልደት ቀን : 31 ጥቅምት 2002(በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር) የሚጫወትበት ቦታ : የክንፍ መስመር አጥቂ እጀግ አስገራሚ ፍጥነትና ኳስ የመግፋት ችሎታ የታደለው አንሱ ፋቲ አስቸጋሪ ኳሶችን እንኳን ወደ ግብነት የመቀየር አቅሙ ከፍተኛ ነው። ነገሮችን ይበልጥ ተስፋ ሰጪ የሚያደርጋቸው ደግሞ ታዳጊው ለባርሴሎና መጫወቱ ነው። ከአጠገቡ ሊዮኔል ሜሲና ሌሎች ከዋክብት መኖራቸው ያለውን አቅም ይበልጥ አሟጥጦ እንዲጠቀም ሊረዳው ይችላል ተብሎ ይታሰባል። የ17 ዓመቱ አንሱ ፋቲ በባርሴሎና ታሪክ በእድሜ ትንሹ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን በሻምፒዮንስ ሊግም ግብ በማስቆጠርና ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ በማቀበል የባርሴሎናን ታሪክ መቀየር ችሏል። ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ (ሊቨርፑልና እንግሊዝ) የውልደት ቀን: ጥቅምት7/1998(በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር) የሚጫወትበት ቦታ: ቀን ተመላላሽ 21 ዓመቱ የሊቨርፑል ተጫዋች ባለፈው ዓመት ከቡድኑ ጋር ቻምፒየንስ ሊግን ማሸነፍ ችሏል። ከባርሴሎና ጋር በነበራቸው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የነበረውን አስተዋጽኦ ማንም አይረሳውም። • "በአንድ ጨዋታ ሰባት ግቦችን በማስቆጠር ታሪክ መስራቴ አስደስቶኛል" ሎዛ አበራ በመካከሉ ድንቅ ከመሆን ባለፈ ወደ ግብ የሚልካቸው ኳሶች የቡድን አጋሮቹን በትክክል ነው የሚደርሱት። በዚህ አጨዋወቱ የሚቀጥል ከሆነ ይህ ተጫዋች ምንም እንኳን ዋና ሃላፊነቱ መከላከል ላይ ያተኮረ ቢሆንም ወደፊት በመሄድ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎቹ ተስፈኛ መሆኑን ያመላክታሉ። ካይ ሃቨርትዝ (ባየር ሊቨርኩሰን እና ጀርመን) የውልደት ቀን: ሰኔ 11/ 1999(በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር) የሚጫወትበት ቦታ: አማካይ ጀርመኖች በእግር ኳሳቸው አስደሳች ተጫዋቾችን ማየት ባቆሙበት ወቅት ይህ ወጣት ብቅ ማለቱ ተስፋን እንዲሰንቁ አድርጓቸዋል። ከፍተኛ የሆነ የኳስ እውቀት አለው የሚባለው ሃቨርትዝ ገና በ 20 ዓመቱ በጀርመን ቡንደስሊጋ ከ100 በላይ ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል። ፊል ፎደን (ማንቸስተር ሲቲ እና እንግሊዝ) የውልደት ቀን : ግንቦት 28/2000(በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር) የሚጫወትበት ቦታ: አማካይ በእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ የአሰለጣጠን ስልቱና ተጫዋቾችን የማብቃት ክህሎቱ ከፍተኛነት በሚነገርለት የማንቸስተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዮላ ስር መሆኑ ለዚህ ታዳጊ ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ብዙዎች እየተናገሩ ነው። • ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ በተጨማሪነት ደግሞ እንደ ኬቨን ደብራይነ፣ ዳቪድ ሲልቫና በርናርዶ ሲልቫን የመሳሰሉ ድንቅ ተጫዋቾችን እያየ መጫወቱ ለወደፊቱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ እንደሚችል አመላካች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የሪያል ማድሪዱ ሮድሪጎና የማንቸስተር ዩናይትዱ ሜሰን ግሪንዎድም በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የዓለምን እግር ኳስ ተቆጣጠር እንደሚቆዩ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።
news-57067390
https://www.bbc.com/amharic/news-57067390
በቻይና ባለመስታወት ድልደይ ላይ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ ካጋጠመው አደጋ ተንጠልጥሎ ተረፈ
በቻይና ባለመስታወት ድልደይ ላይ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ ካጋጠመው አደጋ ተንጠልጥሎ ተረፈ
የመስታወት መርግጫ ያለውና በቻይና የሚገኘው ድልድይ ላይ እየተጓዘ ነበረ - ግለሰቡ። ሆኖም በጉዞው መካከል በተፈጠረ ሀይለኛ ንፍስ መስታወቶቹ መርገፍ ጀመሩ። ይሄኔ መርገጫ ያጣው ግለሰቡ የድልድዩን ሌላ አካል የሙጥኝ ብሎ በመንጠልጠል ነው የተረፈው። 100 ሜትር ከፍታ ባለውና በቻይና ሰሜን ምስራቅ የሚገኘውን ፒያን ተራራን መሰረት አድርጎ የተገነባው የመስታወት ድልድይ ላይ የተፈጠረው ክስተት የገጠመው ባለፈው አርብ ነበር። ታዲያ በተከሰተው ንፋስ የድልድዩ ልዩ መገለጫ የሆኑትን የመስታወት ወለሎች በሰዓት 150 ኪሎ ሜትር በሚገመት ፍጥነት በታትኗቸዋል። ቻይና 2300 የሚጠጉ የመስታወት ወለሎች ያሏቸው ድልድዮች እንዳሏት ይታመናል። ድልድዮቹ በቻይና እያደገ የመጣውን የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ይበልጥ ለማስፋፋት ያለሙ ናቸው። በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት የተጋራ አንድ ምስል አንድ ጎብኚ ወለሉ የረገፈ በባለመስታወት ድልድይ ላይ ትንጠልጥሎ ይታያል። የአደጋ መከላከል ሰራተኞች ድልደዩ ላይ የነበረውን ቱሪስት ለማዳን ደርሰው እያየረዱት ራሱን መትረፉ መቻሉን ተገልጾል። ሰውዬው ለማንኛውም በሚል ወደ ሆስፒታል የተወሰድ ሲሆን አሁን "አካሉም ስነልቦናውም ተረጋግቷል" ተብሏል። አደጋ የደረሰበት አካባቢ ዝግ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተሰምቷል። በቻይና እንዲህ አይነት አደጋ ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 ሄቢ የተሰኘችው የቻይና ግዛት የድህንነት ፍተሻዎችን በማድረግ መረማመጃዎችን ጨምሮ ከመስታወት የተሰሩ የቱሪስት መስህቦችን ዘግታ ነበር። በሌላ የሀገሪቱ ክፍል በ2019 በመስታወት በተሰራ የቱሪስት መስህብ ላይ የተፈጠረው አደጋ አንድ ሰው ሲሞት ስድስት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በ2019 በመስታወት ድልድይ ላይ በደረሰ አደጋ አንድ ቱሪስት ተጎድቷል።
news-48782365
https://www.bbc.com/amharic/news-48782365
ቦይንግ 737 ማክስ የተሰኘው አውሮፕላን ሌላ ችግር ገጥሞታል
የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳዳሪ [ኤፍኤኤ] ቦይንግ 737 ማክስ የተሰኘው አውሮፕላን እክል እንዳጋጠመውና የሙከራ በረራ ማድረግ እንዳማይችል አስታውቋል።
በቦይንግ አውሮፕላን ማምረቻ ታሪክ ከፍተኛ ሽያጭ አስገኝቶ የነበረው ማክስ 737 ሞዴል አውሮፕላን በተከታታይ ከደረሰበት አደጋ በኋላ ሽያጩ ቀንሷል። አውሮፕላኑን የገዙ አየር መንገዶች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የደብረ-ዘይቱ አደጋ በኋላ 737 ማክስ አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርገዋል። • ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ ከኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ አየር መንገዶች አደጋ በኋላ ቦይንግ ማክስ 737 ተብሎ የሚጠራውን ሥሪት 'ሶፍትዌር' [ውስጣዊ አሠራር] ለማደስ ደፋ ቀና ማለት ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል። እድሳቱ ተጠናቆ የመኩራ በረራ ያደርጋል ተብሎ የተጠበቀው ቦይንግ 737 ግን አሁንም ችግር እንዳልተለየው ነው የተሰማው። የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳዳሪ ችግሩ ምን እንደሆነ በውል ባያስቀምጥም '737 ማክስ መብረር አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል ቦይንግ አሁንም ችግሩን ቢያጤነው' ሲል ተደምጧል። ባለፈው ወር ተቆጣጣሪው አካል [ኤፍኤኤ] ቦይንግ እድሳቱን ካጠናቀቀ ወርሃ ሐምሌ ላይ የሙከራ በረራ ማድረግ ይችላል ብሎ ነበር። • ቦይንግ "ችግሩ ተፈቷል" እያለ ነው የአውሮፕላኑ ዋነኛ ችግር አፍንጫውን ወደፊት አድርጎ ወደታች እንዳይምዘገዘግ የሚያደርገው ሶፍትዌር እንደሆነ የሚናገሩት ባሉሙያዎች ቦይንግ ይህንን ችግር ሊቀርፍ ይገባል ሲሉ ይከራከራሉ። ከባለሙያዎች የተለያዩ መላምቶች እየተሰነዘሩ ቢሆንም ቅሉ አሁን ማክስ 737 የገጠመው ችግር በውል የሚታወቅ አይደለም። ኤፍኤኤ የተሰኘው ተቆጣጣሪ አካል እድሳቱ በቂ አይደለም ብሎ ካሰበ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ሰማይ ላይ የምናይበት ጊዜ ሩቅ ይሆናል ማለት ነው። • ቦይንግ የ737 ማክስ ሶፍትዌርን አሻሽያለሁ አለ
52335999
https://www.bbc.com/amharic/52335999
ኮሮናቫይረስ፡ "መደብር ሄጄ የውጪ አገር ሰው አንቀበልም አሉኝ" ኢትዮጵያዊቷ በቻይና
ቻይና የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶች ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንዲሁም ከሆቴል እንዲወጡ መገደዳቸው ከተሰማ ቀናት ተቆጥረዋል።
ጉዋንዡ የሚኖሩ አፍሪካውያን ከመኖሪያቸው ተባረዋል ለዚህም እንደምክንያት እየቀረበ ያለው የኮሮናቫይረስ ፍራቻ ነው። አፍሪካውያኑ የዘር መድልዎ እየደረሰባቸው እንደሆነም ተናግረዋል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ ያሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ጥቁሮች ፓስፖርት ሲነጠቁ፣ መገበያያ መደበር አትገቡም ሲባሉና ወደ መኖሪያቸው እንዳይገቡ ሲከለከሉም ያሳያሉ። "መደብር ሄጄ የውጪ አገር ሰው አንቀበልም አሉኝ" ስሟ እንዲጠቀስ የማትፈልግ ቻይና የምትኖር ኢትዮጵያዊት ለቢቢሲ እንደተናገረችው፤ እሷም ከምትኖርበት ቦታ ፓስፓርቷ ተስዶ ነበር። "ፓስፓርቴን ሲወስዱብኝ ለምን እንደሆነ አላስረዱኝም ነበር፤ እዚያ ላለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቄ በሦስት ቀን ተመለሰልኝ" ትላለች። ቤቷ ድረስ ሄደው ፓስፓርቷን ሲወስዱ 'ነገ ወይም ከነገ ወዲያ እንመልስልሻለን' ከማለት ውጪ ምክንያቱን እንዳላሳወቋት ትናገራለች። በምትኖርበት አካባቢ የዘር መድልዎ እየደረሰባቸው ስለመሆኑም ኢትዮጵያዊቷ ትገልጻለች። አንድ ጓደኛዋ በታክሲ ለመሄድ ስትሞክር አሽከርካሪው ለኃላፊዎች ደውሎ፤ ወደ ለይቶ ማቆያ እንድትገባ መደረጓን እንደማሳያ ትጠቅሳለች። "አንዳንድ ነገር ልገዛ ወደ ሱፐር ማርኬት ሄጄ 'ይቅርታ የውጪ አገር ሰው አንቀበልም' ብለው ከልክለውኛል" ስትልም የደረሰባትን ታስረዳለች። በቻይና፣ በማክዶናልድስ 'ጥቁሮችን አናስተናግድም' የሚል መልዕክት በመጻፉ ማክዶናልድስ ይቅርታ ጠይቋል እሷና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ጓደኞቿ የእንቅስቃሴ ገደቡ እስኪነሳ ድረስ ባሉበት ሆነው ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው ተናግራ፤ "ገደቡ ከተነሳ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ አላሰብኩም፤ ትምህርቴን መቀጠል አለብኝ" ትላለች። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድጋፍ ሊያደርግላቸው እየሞከረ እንዳልሆነም አያይዛ ታነሳለች። "እይደለም በዚህ ጊዜ በሌላውም ጊዜ ችግር አለ" ስትልም በኤምባሲው በኩል ያለውን ክፍተት ታስረዳለች። አሁን የሚገኙበት ሁኔታ ስለ ቻይና ያላቸውን አመለካከት እንደቀየረውና እምነት እንዳጡ ትናገራለች። ሆኖም ግን "ይሄም ያልፋል ብዬ ማሰብ እፈልጋለሁ" ስትል ተስፋዋን ገልጻልናለች። "ለይቶ ማቆያ እንድንገባ አስገድደውናል" ስሙን የማንጠቅሰው ናይጄሪያዊ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ጉዋንዡ መኖር የጀመረው ከአምስት ወር በፊት ነበር። የቀጣዩ የትምህርትዘመን ክፍያ ካጠናቀቀ በኋላ የተከራየበት ቤት ባለቤት፤ ቤቱን ለቆ እንዲወጣ ነገሩት። ፖሊሶች እሱና ጓደኞቹን ከቤቱ ውጪ እየጠበቋቸው ስለነበር ያለውን እቃ ለመሰብሰብ ይጣደፍ ጀመረ። እቃውን ጓደኛው ቤት ለማስቀመጥ ሲሄድ መግባት አትችልም በመባሉ፤ ለቀናት ጎዳና ላይ አድሯል። "አያችሁ እንዴት ቤታችንን ለቀን እንድንወጣ እንዳስገደዱን? ለይቶ ማቆያ እንድንገባም አስገድደውናል" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ተማሪው ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ ቢነገረውም ከለይቶ ማቆያ እንዲወጣ አልተፈቀደለትም። የሚገኘውም ሆቴል ውስጥ ነው። ጉዋንዡ ውስጥ አብዛኞቹ አፍሪካውያን ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ እንደተገደዱና ጎዳና ላይ የወጡ እንዳሉም ተገልጿል። አንድ የአፍሪካውያን ነዋሪዎች ወኪል "የተደበቁም አሉ" ሲል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስታውቋል። አፍሪካውያን የሚኖሩበትና የሚነግዱበት አካባቢ ተዘግቷል ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሁለት ናይጄሪያውያን ማምለጣቸውን ተከትሎ፤ አፍሪካውያን የሚኖሩበትና የሚነግዱበት አካባቢ እንደተዘጋ ጭምጭምታ የተሰማው በዚህ ወር መባቻ ነበር። የቻይና መገናኛ ብዙሀን ናይጄሪያዊ ታማሚ ቻይናዊ ነርስ ላይ ጥቃት ማድረሱን ዘግቧል። ጤና ጥበቃም አፍሪካውያንን በስፋት መመርመር ጀምሯል። በከተማዋ ከሚኖሩ 4,500 አፍሪካውያን 111ዱ ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተገልጿል። ናይጄሪያዊው ተማሪ እንደሚለው፤ 'የቻይና መንግሥት ትዕዛዝ ነው' ብለው ጤና ባለሙያዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ወስደዋቸዋል። አንድ የጉዋንዡ ነዋሪ "ከቫይረሱ ምርመራ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ነገር አለመግባባት ይመስለኛል። የዘር መድልዎ አይደለም። የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲህ ያለ ነገር አያውቁም" ብለዋል። ጉዋንዡ ውስጥ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪካውያን ይኖራሉ። በከተማዋ ከሚኖሩት ብዙዎቹ ከቻይና ሸቀጥ ገዝተው ወደ አገራቸው ለመላክ በአጭር ጊዜ ቪዛ የገቡ ናቸው። የቻይና መንግሥት የቀረበበትን የዘረኝነት ክሶች አጣጥሎ፤ ቻይና እና አፍሪካ ወዳጆች፣ አጋሮች፣ ወንድማማቾች ናቸው ብሏል። ዘረኝነትን እንደማይታገስም አስታውቋል። በተቃራኒው ቢቢሲ ያነጋገራቸው አፍሪካውያን ዘረኛ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ይናገራሉ። የአፍሪካውያን ነዋሪዎች ወኪሉ፤ "98 በመቶ የሚሆኑት አፍሪካውያን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ናቸው" ይላል። "እቅዳቸው እኛን መስዋዕት አድርጎ ሌሎችን ማዳን ነበር" በመላው ቻይና የሚኖሩ አፍሪካውያን እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ይናገራሉ። ዉሃን ውስጥ ዩኒቨርስቲዎች ቢዘጉም አፍሪካውያን ተማሪዎች ግን አልወጡም። "እኛን ትተውን ሄደዋል" ይላል ጋናዊው ተማሪ ማይክል አዴኔይ ለሁለት ወር ያህል የጋና መንግሥት ወደ አገራቸው እንዲመልሳቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ ሲያደርግ ነበር። ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በነበረበት ወቅት 5,000 አፍሪካዊ ተማሪዎች ከዉሃን መውጣት አልቻሉም ነበር። የየአገራቸው መንግሥታትም ዜጎቻቸውን አላወጡም። "የመስዋዕት በግ እንደሆንን ይሰማናል፤ እቅዳቸው እኛን መስዋዕት አድርጎ ሌሎችን ማዳን ነበር" ሲል አንድ ተማሪ ገልጿል። የአፍሪካ አገራት መንግሥታት ዉሃን ያሉ ዜጎቻቸውን ከቫይረሱ ለመጠበቅ ምንም አለማድረጋቸውንም ይናገራል። በውሃን እንቅስቃሴ ላይ የተጣለው ገደብ ተነስቷል ዉሃን ከሳምንት በፊት እንቅስቃሴ ላይ ጥላ የነበረውን ግድብ አንስታለች። በግዛቲቱ ሕይወት የቀደመ ገጽታውን እየተላበሰም ይመስላል። በሌላ በኩል በዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ አፍሪካውያን ተማሪዎች እስካሁን ካሉበት አልወጡም። መቼ እንደሚወጡም የሚያውቁት ነገር የለም። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በጉዋንዡ የሚኖሩ አፍሪካውያን መረጃ እየተለዋወጡ ነው። በመላው አገሪቱ ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎችና ተማሪዎች በየትኞቹ ሆስፒታሎች እና ሆቴሎች እንደሚገኙ የሚያሳዩ ፎቶዎችም ይለቃሉ። አንዳንዶች ከኮሮናቫይረስ ነፃ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ፣ ሌሎች ደግሞ ከአቅማቸው በላይ ተጠየቁትን የህክምናና የሆቴል ቆይታ ክፍያ በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋራሉ። መድልዎ ለደረሰባቸው ሰዎች አገልግሎት የሚሰጥ የስልክ መስመር ቢከፈትም፤ አሁንም ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ አፍሪካውያን ስጋት እንደሸበባቸው ነው። 'ትንሿ አፍሪካ በቻይና' በመባል የሚታወቀው ዢዎ ቤይ ሉ ጎዳና ለወትሮው በአፍሪካውያን ነጋዴዎች ይሞላ ነበር። አሁን ግን ፀጥ ረጭ ብሎ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያ ተሰራጭተዋል።
news-52916929
https://www.bbc.com/amharic/news-52916929
የደቡብ ኮሪያ እና የሰሜን ኮሪያ የብሽሽቅ ፊኛዎች ውዝግብ
ከሰሜን ኮሪያ ሸሽተው ወደ ደቡብ ኮሪያ የሚሻገሩ ሰዎች በየዓመቱ በሺህ የሚቆጠሩ ፊኛዎችን ወደ አገራቸው ሰሜን ኮሪያ ይልካሉ። ይህንን የሚያደርጉትም ከደቡብ ኮሪያ የድንበር ከተማ ሆነው ነው።
የደቡብ ኮሪያ አክቲቪስቶች ጸረ ሰሜን ኮሪያ መንግሥት መልዕክቶችን ከያዙ ፊኛዎች ጋር ሰሜን ኮሪያን የሸሹት ብቻም ሳይሆን የደቡብ ኮርያ መብት ተሟጋቾች ጭምር በርካታ መልዕክት የያዙ ረዣዥም ፊኛዎችን ወደ ጎረቤታቸው ይልካሉ። በፊኛዎቹ ውስጥ የሚጠቀለሉት መልዕክቶች በአመዛኙ ሰሜን ኮሪያ ዜጎቿን በጭቆና አረንቋ ማኖሯን እንድትተው የሚወተውቱ ናቸው። አንዳንዶቹ መልዕክቶች ደግሞ የብሽሽቅ ይዘት ያላቸው ናቸው። "እኔ ደቡብ ኮሪያዊ ነኝ፤ የኪም ቤተሰብ አይደለሁም፤ ለኪም ባሪያ አይደለሁም፤ ነጻ ዜጋ ሆኛለሁ" የሚሉ መልዕክቶች ይገኙበታል። ይህ በፊኛ የብሽሽቅ መልዕክት ጠቅልሎ ወደ ጎረቤት አገር በንፋስ ኃይል የማሻገሩ ነገር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰሜን ኮሪያን እያስቆጣት መጥቷል። በእርግጥ ድርጊቱ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም ሰሜን ኮሪያ ግን እንደ አሁኑ ተበሳጭታ አታውቅም። በእነዚህ ፊኛዎች ውስጥ ብሽሽቅ ይኑርባቸው እንጂ የፍቅር ደብዳቤዎችን ጨምሮ ቼኮሌቶችና አንዳንድ ጊዜም ዶላሮች በፊኛው ውስጥ ተደርገው ወደ ሰሜን ኮሪያ እንዲበሩ ይደረጋሉ። በተለይም መብት ላይ የሚሰሩ ደቡብ ኮሪያዊያን በየዓመቱ ይህንን ማድረግ ባሕልና አንድ የትግል መሣሪያ አድርገውት ቆይተዋል። በ2014 እንዲያውም የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች እነዚህን ፊኛዎች በመሳሪያ ተኩሰው ለመጣል በመሞከራቸው በድንበር አካባቢ መጠነኛ የተኩስ ልውውጥ እንዲፈጠር አድርጓል። አሁን ግን የሰሜን ኮሪያ ቁጣ እየገነፈለ በመምጣቱ ደቡብ ኮሪያ ነገሩን ለማጤን ተገዳለች። ሰሜን ኮሪያም በበኩሏ ጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ይሄን "ጅላጅል ድርጊት" እንድታቆም የሚጠይቅ የመልስ ፊኛ ልካ ታውቃለች። የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት እህት ኪም ኦን ጁንግ ባለፈው ሐሙስ ከሰሜን የሚበሩ ፊኛዎች አስቆጥተዋት ረዥም መግለጫ ማውጣቷ ተሰምቷል። ይህም በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ተነቧል። ፊኛዎች የፖለቲካ መልዕክት ብቻ ሳይሆን የፍቅር ደብዳቤዎችን፣ ቼኮሌቶችንና ዶላሮችንም ይዛሉ የሴትዮዋ ቁጣ የመነጨው ከአገሯ የከዱ ዜጎች ከደቡብ ኮሪያ ድንበር ሆነው በፊኛ የላኳቸው ፖስት ካርዶችና በራሪ ወረቀቶች ናቸው። ኪም ኦን ጁንግ "እነዚህ የሰው አይጠመጎጦች" ስትል ነው የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለማንኳሰስ የሞከረችው። በሰሜን ኮሪያ ፓርቲ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ሥልጣን አላት የምትባለው ኪም ኦን ጁንግ "እነዚህን የሰው አይጠ መጎጦች የለቀቀብን ኃይል ደግሞ ሊጠይቅ ይገባል" ብላለች። ይህም ደቡብ ኮሪያ መንግሥትን የሚመለከት ተደርጎ ተተርጉሟል። ይሄ ፊኛ የመላኩን ነገር ደቡብ ኮሪያዊያን ካላቆሙት የጋራ ድንበር የሰላም ስምምነቱን ጨምሮ በጋራ የተፈጠረው የካሶንግ ኢንደስትሪ ፓርክ ስምምነትን ልታፈርስ እንደምትችል ዝታለች። የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ይህ የሰሜን ኮሪያ ዛቻ ያስፈራው ይመስላል። ፊኛ የመላኩንደ ድርጊት በሕግ ለማስቆም እያሰበ ይገኛል። ሆኖም በዛቻው ተደናግጦ ለዚህ ውሳኔ እንደበቃ አላመነም። "ለነገሩ እነዚህ ፊኛዎችና የሚይዙት መልዕክት አንዳንድ ጊዜ በእኛ መሬት ላይ ስለሚቀር አካባቢን እየበከለብን ነው። እሱን ማስወገድ በራሱ ትልቅ ሥራ ነው የሆነብን" ሲል ነገሩን ለማቆም እንደሚገደድ ጠቁሟል። ፊኛ ላኪዎቹ ግን በደቡብ ኮሪያ መንግሥት የአቋም ለውጥ ያፈሩ ይመስላል። "የፈለገ ነገር ቢመጣ ይህንን ነገር በፍጹም አናቆምም። እንዲያውም አንድ ሚሊዮን ፖስት ካርዶችና በራሪ ወረቀቶችን አዘጋጅተናል። ፊኛዎቹን ወደ ሰሜን ኮሪያ መላኩን አጠናክረን እንቀጥልበታለን" ብለዋል። ከሰሜን ኮሪያ ነጻ የወጡ አርበኞች ግንባር ኃላፊ ፓርክ ሳንግ ባለፈው ዓመት ብቻ ማኅበራቸው 11 ጊዜ በሺህ የሚቆጠሩ ፊኛዎችን ወደ ሰሜን ኮሪያ መላኩን ተናግሯል። "ይህ ሰሜን ኮሪያ አይደለም። ይህ ደቡብ ኮሪያ ነው፤ በደቡብ ኮሪያ ዜጎች ሦስት መብቶች አሏቸው። ከእነዚህ አንዱ የመናገር ነጻነት ነው" ሲል የአርበኞቹ ግንባር በድርጊቱ እንደሚገፉበት ዝቷል። ኃላፊው "ፊኛዎችን ወደ ሰሜን ኮሪያ መላክ ከተከለከልን ቀጥሎ የምንልከው ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ይሆናል" ሲል ዝቷል። ፓርክ የሚመራው በደቡብ ኮሪያ የሰሜን ኮሪያ አርበኞች ግንባር 40 ሺህ ከሰሜን ኮሪያ የኮበለሉ አባላትን ይዟል። ሰሜን ኮሪያ ለምን ኑክሊዬርን መረጠች?
53104051
https://www.bbc.com/amharic/53104051
በኒውዚላንድ ከ11 ዓመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፖሊስ ተገደለ
እጅግ ሰላማዊ በምትባለው ኒው ዚላንድ አንድ ፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ‹‹ጉድ!›› እየተባለ ነው፡፡ ፖሊስ መደበኛ አሰሳ እያደረገ ሳለ ነበር አንድን ግለሰብ መኪናውን ሊያስቆም ሲሞክር ተተኩሶበት የሞተው፡፡
ሌላ ባልደረባው የሆነ የትራፊክ ፖሊስም ክፉኛ ቆስሏል ተብሏል፡፡ የአንድ ፖሊስ መገደል በዚያች አገር አነጋጋሪ ዜና የሆነው እንዲህ አይነት ድርጊት ከጎርጎሳውያኑ 2009 ጀምሮ ተሰምቶ ስለማያውቅ ነው፡፡ የኒውዚላንድ ፖሊስ የተለየ ሁኔታ ከሌለ በስተቀር መሣሪያ አይታጠቅም፡፡ ፖሊስ በሥራ ላይ ሳለ ተገደለ ሲባልም ከ11 ዓመታት በኋላ የትናንቱ የመጀመርያ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ከ11 ዓመታት ወዲህ በግንቦት 2009 የተገደለው ሌላኛው የኒውዚላንድ ፖሊስም እንዲሁ ቤት ለቤት መደበኛ አሰሳ ሲያደርግ ነበር አደጋው የደረሰበት፡፡ ‹‹ሟቹን ባልደረባችንን በጸሎታችን እናስበዋለን፤ እጅግ አዝነናል›› ብለዋል የፖሊስ አዛዡ አንድሩ ኮስተር፡፡ አንድሩ ለሚዲያ እንደተናገሩት ሟቹ ፖሊስ በተሸከርካሪዎች ላይ አሰሳ በሚያደርግበት ወቅት ምንም ዓይነት መሣሪያ አልታጠቀም ነበር፡፡ በዚህ ዓመት በኒውዚላንድ ለ6 ወራት ብቻ ለልምምድ ያህል ‹‹የታጠቁ ፖሊሶች ቡድን›› ተሰማርቶ ነበር፡፡ የፖሊሶች አዛዥ አንድሩ ኮስተር ይህ ስልጠና አሁን እንዳበቃና ኒው ዚላንድ የፖሊስ ኃይሏ መሣሪያ አንጋች እንደማይሆን አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹እኛ የሕዝባችን አገልጋዮች ነን፤ ሕዝባችን ስለኛ የሚሰማው ስሜት መልካም ሆኖ እንዲቆይ እንፈልጋለን፡፡ ስለዚህ በኒውዚላንድ እኛ ፖሊሶች መቼም ቢሆን ጠመንጃ አናነግትም›› ብለዋል አቶ ኮስተር
news-46362809
https://www.bbc.com/amharic/news-46362809
''የአንድ ቤተሰብ አባላት ግድያ'' በቤኒሻንጉል ክልሏ ያሶ ከተማ
ባለፈው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ከተማ በፈፀመ ጥቃት ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ህዳር 11 ቀን 2011 ማታ ከሶስት ሰዓት በኋላ ታጣቂዎች የቤተሰብ አባላቱን በጥይት ገድለው ቤታቸውንም እንዳቃጠሉ በጥቃቱ ባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድሞች ያጡት የስምንት ልጆች እናት ወ/ሮ ልኪቱ ተፈራ ይናገራሉ። "መጀመሪያ ተኩስ ከከፈቱብን በኋላ ቤት ውስጥ ጭድ ጨምረው እሳት ለኮሱብን። እኔና ልጆቼ በጓሮ በር በኩል አመለጥን። ሌሎቹ ግን እዚያው ተቃጠሉ" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ። • "ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ • የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ ልጃቸው አቶ ወጋሪ ፈይሳ በመኖሪያ ቤታቸው በወቅቱ ሃያ አንድ የቤተሰብ አባላት እንደነበሩና ቤታቸውም ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በመሆኑ ደህንነት ተሰምቷቸው እንደነበር ይናገራል። ነገር ግን ያልጠበቁት ነገር መከሰቱንና በተፈጠረው ነገርም ህፃናት ልጆች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉም ይገልፃሉ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ከተማው ውስጥ ግድያ ስለ መከሰቱ መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ገልፀዋል። ከጥቃቱ የተረፉ የቤተሰቡ አባላት ሸሽተው የተጠለሉበት አዋሳኝ የምሥራቅ ወለጋ ሃሮ ሊሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋሮማ ቶሎሳ ግድያው ስለመፈፀሙ ማረጋገጫ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አባቴ ፈይሳ ዲሳሳ፣ ወንድሙ ዲንሳ ዲሳሳን ጨምሮ ስምንት የአጎቶቼ ልጆችን አጥተናል። ግድያው በጣም አሰቃቂ ነበር" ይላሉ አቶ ዋጋሪ። • በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ • "የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ በተመሳሳይ እለት የቤተሰብ አባላቱን ግድያ ጨምሮ በያሶ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት አርባ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ኗሪዎችና የአዋሳኝ ወረዳ አስተዳዳሪው ቢናገሩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙሳ ግን አስር ሰው ብቻ ስለመገደሉ መረጃ እንዳላቸው ይገልፃሉ። ሆኖም ግን ጉዳዩን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው "መንገድ በመዘጋቱ ነገሮችን በቅርበት ማጣራት አልቻልንም" በማለት ተናግረዋል። አቶ ሙሳ እንደሚሉት የረቡዕ ጥቃት ከመፈፀሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ሁለት የመንግሥት ሰራተኞች ተገድለዋል። አርብ እለትም ደግሞ በካማሼ ሌሎች ሦስት ሰዎች መሞታቸውንም ገልፀዋል። በያሶ ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች ከመሆናቸው በዘለለ ስለታጣቂዎቹ እስካሁን ምንም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለ አቶ ሙሳ ይናገራሉ። 'ያፈነገጡ የኦነግ ታጣቂዎች' ለአካባቢው ስጋት እየሆኑ እንደሆነ አቶ ሙሳ ቢናገሩም ያነጋገርናቸው ኗሪዎች እና የአዋሳኝ ወረዳ ሃላፊዎች ግን በአካባቢው የኦነግ ታጣቂ እንደሌለ ገልፀዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አራት የካማሺ ዞን ሃላፊዎች አሶሳ ከተማ ስብሰባ ቆይተው ወደ ካማሺ በመመለስ ላይ ሳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ብዙዎች መገደላቸውንና ወደ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት ግን ነገሮችን ለመቆጣጠር በያሶ ከተማ ፌደራል ፖሊስ፤ በካማሽ ደግሞ መከላከያ ሠራዊት እንደገባ አቶ ሙሳ ገልፀዋል።
news-56797639
https://www.bbc.com/amharic/news-56797639
ሩስያ 20 የቼክ ሪፐብሊክ ዲፕሎማቶችን አባረረች
ቼክ ሪፐብሊክ ባለፈው ቅዳሜ 18 የሩስያ ዲፕሎማቶችን ማባረሯን ተከትሎ ሩሲያ በአጸፋው 20 የቼክ ሪፓብሊክ ዲፕሎማቶችን አባረርች።
የቼክ ደህንነት ሰዎች እንደሚሉት የተባረሩት ሩስያዊያን ዲፕሎማቶች በድብቅ የስለላ ሥራ የሚሠሩ ናቸው። ቼክ ሪፐብሊክ ሰዎቹን ያባረረቻቸው በፈረንጆቹ 2014 በአንድ የጦር መሣሪያ ማከማቻ ዴፖ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ላይ እጃቸው አለበት በሚል ነው። የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሰኞ ዕለት ስለ ጉዳዩ እንደሚመክሩ ተነግሯል። ሩስያ የቼክ ሪብሊክ ዲፕሎማቶች በአንድ ቀን ሞስኮን ጥለው እንዲወጡ ያዘዘች ሲሆን ቼክ ሪፐብሊክ ደግሞ 72 ሰዓታት ሰጥታለች። የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቼክን ውሳኔ "ያልተጠበቀ" እንዲሁም "ጠብ አጫሪ" ብሎታል። "በቅርቡ ሩስያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስን ለማስደሰት ካላቸው ፍላጎት አንፃር ነው የቼክ ባለሥልጣናት ይህን ድርጊት የፈፀሙት" ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ በለቀቀው መግለጫ። የተከሰተው ምንድነው? የቼክ ባለሥልጣናት እንደሚሉት የሩስያ ዲፕሎማቶች የደህንነት ሰዎች ናቸው። ሩስያ ደግሞ ይህ ክስ መሠረት አልባና ግራ አጋቢ ነው ትላለች። በፈረንጆቹ ጥቅምት 2014 ቼክ ሪፐብሊክ ውስጥ ካለ አንድ የጦር መሣሪያ ማከማቻ ላይ የደረሰው ፍንዳታ ማከማቻውን ከጥቅም ውጭ አድርጎት ነበር። ቭርቢቲች ጫካ ውስጥ የነበረው ማከማቻ ላይ የደረሰው ፍንዳታ በአቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎችን መኖሪያ መስኮት መስታወት ሰባብሮ ነበር። ማከማቻው ውስጥ ይሠሩ የነበሩ አንድ የ56 ዓመት ግለሰብና ሌላ የ69 ዓመት ሰው ሬሣ ከአንድ ወር በኋላ በሥፍራው መገኘቱ ይታወሳል። በወቅቱ ፍንዳታው ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሳይሆን አደጋ ነው ተብሎ ነበር። ነገር ግን የቼክ ሪፐብሊክ ባለሥልጣናት ምርመራ ካደረጉ በኋላ ጣታቸውን ሩስያ ላይ ጠቁመዋል። የቼክ ፖሊስ አሌክሳንደር ሚሽኪን እና አናቶሊ ቼፒጎቭ የተባሉት ሁለት ሩስያዊያንን በፍንዳታው እጃቸው አለበት በሚል ማንነታቸውን ይፋ አድርጎ ነበር። ፖሊስ ይህን ያለው ማከማቻውን ያስተዳድር ከነበረው አይሜክ ግሩፕ ኢሜይል ውስጥ የሁለቱ ሰዎች የፓስፖርት ፎቶ በመገኘቱ ነው። በኢሜይል መልዕክቱ ውስጥ የሁለቱ ሰዎች የፓስፖርት ፎቶ ተገኝቷል። ኢሜይሉ ሁለቱ ሰዎች ፈቃድ እንዲሰጣቸውና በማከማቻው ተገኝተው ምርመራ እንዲያደርጉ ይጠይቃል። ሰዎቹ በዚህ ኢሜይል ላይ ስማቸውና ዜግነታቸው ተቀይሮ ነው የቀረበው። ሁለቱ ግለሰቦቹ እንግሊዝ ውስጥ አንድ የቀድሞ የሩስያ ሰላይን በመመረዝ ተጠርጥረው ነበር። ቼክ ሪፐብሊክ ክሳቸውን ለአውሮፓ ሕብረትና ለኔቶ ለማቅረብ ተሰናድተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቼክ ሪብሊክ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል። አሜሪካ በቅርቡ ሩስያ ላይ ማዕቀብ መጣሏና 10 ሩስያዊያን ዲፕሎማቶች ሃገሯን ጥለው እንዲወጡ ማዘዟ አይዘነጋም።
56656818
https://www.bbc.com/amharic/56656818
"በቲክቶክ የገቢ ምንጭን ጨምሮ ሦስት ዕድሎች አግኝቸበታለሁ" የትናየት ታዬ
ዶይን በሚል መጠሪያ በቻይና የሚታወቀው መተግበሪያ ቲክቶክ በሚል ስያሜ ለቀረው ዓለም የተዋወቀው በፈረንጆቹ በ2018 ነው።
አጭር ዕድሜ ያለው ቲክ ቶክ በስኬት ግን 'ታላላቆቹን' ቀድሟል። ቲክ ቶክ በዓለም ዙሪያ ከ800 ሚሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎች አሉት። በኢትዮጵያም ተወዳጅነትን እያገኘ ነው። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት የተመረቀችው የትናየት ታዬ: ቲክቶክ ላይ ከ208 ሺህ በላይ ተከታዮች አሏት። ለየትናየትና ለሌሎች 'እንጀራ' እየሆነ ያለው ቲክቶክ የግለሰቦችን መረጃ እየመነተፈ ለቻይና መንግስት ይሰጣል የሚል ሀሜት ይቀርብበታል። በዚህም ምክንያት ህንድ አግዳዋለች። የትናየት በዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘርፍ 'ዝነኛ' ከመሆን በላይ ሦስት ዕድሎችን አግኝቸበታለሁ ትላለች::
news-57067383
https://www.bbc.com/amharic/news-57067383
ግብፃዊው መነኩሴ ጳጳስ በመግደላቸው በሞት ተቀጡ
በግብፅ የሚገኝ አንድ ገዳም አበምኔትና ጳጳስ ገድለዋል የተባሉት አንድ መነኩሴ በስቅላት ሞት ተቀጡ።
ጳጳስ ኤፒፋፊኒየስ የተገደሉት ከሶስት አመታት በፊት ቅዱስ ማካርየስ በሚባል ገዳም ሲሆን በከፍተኛ ድብደባ እንደሆነም ተገልጿል። በግድያው እጃቸው አለበት የተባሉ ሌላ መነኩሴ እንዲሁ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። የጳጳሱ ግድያ የግብፅን የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ምዕመናንን በከፍተኛ ሁኔታ ያስደነገጠ ሆኗል። የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ምዕመናን በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ የክርስትና እምነት ቁጥር ይይዛል። ዋኤል አል ሳድ ታዋድሮስና ሬሞን ራስሚ ማንሱር የተባሉት መነኮሳት የገዳሙን አበምኔትና ጳጳስ በሰሜን ምዕራብ ካይሮ በሚገኝ ዋዲ አል ናቱርን በተባለ ስፍራ እንደገደሏቸው ተዘግቧል። ለግድያው ምክንያትም የተባለው በነበራቸው ልዩነት ሲሆን ይህ ልዩነት ምን እንደሆነ አልተጠቀሰም። አቃቤ ህግ እንዳለው መነኩሴው ዋኤል አል ሳድ ታዋድሮስ ጳጳሱን በብረት ዘንግ ደብድበው እንደገደሏቸው የተናዘዙ ሲሆን ሌላኛው መነኩሴ ሬሞን ራስሚ ማንሱር ሰው እንዳይመጣ ሲጠብቁ ነበር ተብሏል። የመነኩሴው የስቅላት ሞት ቅጣት እሁድ እለት ተፈፅሟል። ሬሞን ራስሚ ማንሱር በመጀመሪያ የፍርድ ቤቱ ብያኔ የሞት ፍርድ ፈርዶባቸው የነበረ ቢሆንም በኋላ ይግባኝ ማለታቸውን ተከትሎ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተቀይሮላቸዋል። የጳጳሱን ግድያም ተከትሎ የኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን ለአዳዲስ መነኮሳት ማዕረግ ከመስጠት ለአመት ያህል ተቆጥባ ነበር። የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በግብፅ ዋነኛ የክርስትና እምነት ተከታዮች ቁጥር የያዙ ሲሆን ምንም እንኳን አብዛኛው በግብፅ ቢኖሩም ከአገሪቷ ውጭም አንድ ሚሊዮን አማኞች ይኖራሉ ተብሏል። የኮፕቲክ እምነት ተከታዮች ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ50 አመተ ምህረት እንደተጀመረ የሚያምኑ ሲሆን ይህም ሃዋርያው ማርቆስ ግብፅን መጎብኘቱን ተከትሎ እንደሆነ ይነገራል።
news-48803468
https://www.bbc.com/amharic/news-48803468
"ብ/ጄነራል አሳምነው በባጃጅ ለማምለጥ ሲሞክሩ ነው የተገደሉት''
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጠው የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ሰሞኑን በአማራ ክልል የተፈጸመው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሃገሪቱ የተያያዘችውን ሽግግር አያደናቅፍም ብሏል።
በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር የተፈጸሙ ግድያዎችን የማጣራት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ያስታወሱት የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም፤ በአሁኑ ወቅት የፌደራል እና የአማራ ክልል በቅርበት አብረው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። • “የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” • "ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል. . . ግን እናሸንፋለን" • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት አራት ቁልፍ ቦታዎች ላይ ያተኮረ እንደነበረ ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ተናግረዋል። በወቅቱ በባህር ዳር የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዱ ''በቅድሚያ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ በክልሉ ፕሬዝዳንት ቢሮ በመገኘት የተፈጸመውን ግድያ ትዕዛዝ ሲሰጡ ነበር'' ብለዋል። ብ/ጄነራል አሳመነው የስብሰባ አደራሽ ውሰጥ አይግቡ እንጂ በግቢ ውሰጥ ሆነው ትዕዛዝ ሲሰጡ ነበር ያሉት ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ይህም የክልሉ ፕሬዝደንት ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና በሌሎች ላይ ጥቃት የተሰነዘረበት ቦታ መሆኑን አስታውሰዋል። ብ/ጄነራል አሳምነው ከክልሉ ፕሬዝዳንት ቢሮ ወደ የክልሉ ባለስልጣናት መኖሪያ ወደሆነው ስፍራ (ገስት ሃውስ) ማቅናታቸውን ቢልለኔ ስዩም ይናገራሉ። ''በዚህም ስፍራ (የባለስልጣናት መኖሪያ ስፍራ) ሌሎች ባለስልጣናትን ከማፈን በተጨማሪ ወደ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር በመደወል ኦፕሬሽኖች መወሰዳቸውን እና ቀጣይ እርምጃን በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጥ ለህዝብ እንዲያሳውቅ ትዕዛዝ አስተላልፈው ነበር።'' ''ሶስትኛው ስፍራ የክልሉ ፖሊስ ከፖሚሽን ቢሮ ነው።'' ያሉት ብልለኔ፤ በዚሁ ስፍራ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን እና የክልሉን ልዩ ኃይል አዛዥ ለስበሰባ በመጥራት ታፍነው እንዲያዙ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት ሁለቱ የጸጥታ ኃይል ሃላፊዎች እየተካሄደ የነበረውን የመፈንቅለ መንግሥት ማክሸፍ ሥራን ማገዝ እንዳልቻሉ ጠቁመዋል። አራተኛው ስፍራ ደግሞ የክልሉ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር መኖሪያ ቤት እንደሆነ እና እሳቸውም ሊገደሉ በእቅድ ከተያዙ ሰዎች መካክለ እንደሚገኙበት ፕሬስ ሴክሩታሪዋ ተናግረዋል። የክልሉ እና የፌደራል ጸጥታ ኃይል አባላት እርምጃ ሲበረታ ብ/ጄነራል አሳምነው ጉዳት እንደደረሰባቸው እና በቪ 8 መኪና ታጅበው ማምለጣቸውን ተነግሯል። ከሁለት ቀናት በኋላም በባለ ሶስት እግር መኪና ወይም ባጃጅ ወደ ጎንደር ሊያመልጡ ሲሉ ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በክልሉ ልዩ ኃይል መገደላቸውን ቢልለኔ ስዩም አስታውቀዋል።
news-47249323
https://www.bbc.com/amharic/news-47249323
ትራምፕ ለግንቡ ገንዘብ ለማግኘት 'ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ' ሊያውጁ ነው
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራም አሜሪካ ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ለመገንባት ላሰቡት ግንብ ገንዘብ ለማግኘት በማሰብ 'ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ' ሊውጁ እንደሆነ ዋይት ሃውስ አስታወቀ።
በአሜሪካ ዜጎች ላይ የተደቀኑ የጤና እና የደህንነት ስጋቶችን በመደበኛ ሕጎች መግታት ሳይቻል ሲቀር ፕሬዚዳንቱ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ወይም 'ናሽናል ኢሜርጀንሲ' የማወጅ ስልጣን አላቸው። በዚህም መሰረት የአሜሪካ ጦር በጀትን ለግንቡ መስሪያ ሊጠቀሙት እንደሚችሉ የዋይት ሃውስ መግለጫ አስታውቋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይህን የሚወስኑት ከዲሞክራቶች ፍላጎት እና ውሳኔ በተጸረረ መልኩ ነው። • የትራምፕ አማካሪ፡ የግንቡ ውጥን ውድቅ ከተደረገ ሰነባብቷል በርካታ ዲሞክራቶች ትራምፕ ''ስልጣንን ያለ አግባብ እየተጠቀሙ ነው'' ሲሉ አምርረው እየወቀሷቸው ነው። ፕሬዚደንት ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ግንቡን መገንባት ዋነኛ እቅዳቸው እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው ሲቀሰቅሱ ነበር። ይሁን እንጂ እስካሁን ግንቡን የሚያገነቡበት በጀት ማግኘት ቀላል አልሆነላቸውም። ትናንት ኮንግረሱ ትራምፕ ለግንቡ ግንባታ የጠየቁትን ገንዘብ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ አሳልፏል። ይሁን እንጂ ይህ ረቂቅ አዋጅ ሕግ ሆኖ የሚጸድቀው የትራምፕ ፊርማ ሲኖርበት ብቻ ነው። ''ፕሬዝዳንቱ አሁንም ቢሆን ግንቡን ለመገንባት ቃላቸውን እየጠበቁ ነው፤ አዋሳኝ ድንበሩ ይጠበቃል፤ ትልቋ ሀገራችን ደህንነቷ የተጠበቀ ይሆናል'' ብለዋል የዋይት ሃውስ ፕሬስ ሴክረተሪ ሳራ ሳንድረስ። • ትራምፕ ስለስደተኞች በተናገሩት ወቀሳ ደረሰባቸው ሳራ ሳንድረስ ጨምረውም ፕሬዝዳንቱ በድንበሩ አማካኝነት የሚከሰተውን ብሄራዊ የደህንነት ስጋት እና ሰብአዊ ቀውስ ለማስቆም የተለያዩ እርምጃዎችን ይወስዳሉ፤ ከእነዚህም መካከል ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ይገኝበታል ብለዋል። ኮንግረሱ ትናንት ለድንበር ደህንነት ያጸደቀው ገንዘብ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፤ ትራምፕ ለግንቡ ግንባታ 5.7 ቢሊዮን ዶላር ጠይቀዋል። በአሜሪካ እና ሜክሲኮ ድንበር ላይ ይገነባል ተብሎ የነበረው የኮንክሪት ግንብ መነጋገሪያ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። • ትራምፕ ዲቪን ማስቀረት ይችላሉ? በቅርቡ ከሥራቸው የተሰናበቱት የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ጆን ኬሊይ የኮንክሪት ግንብ ሃሳብ ውድቅ የተደረገው በትራምፕ የመጀመሪያዎቹ የፕሬዚዳንትነት ወራቶች ነው ሲሉ ተናግረው ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ግን ''Wall'' ወይም ግንብ የሚለውን ቃል በትዊተር ገጻቸው ላይ በርካታ ጊዜያት ተጠቅመውታል።
news-48868371
https://www.bbc.com/amharic/news-48868371
ለኢትዮጵያና ለኢንዶኔዢያ የአውሮፕላን አደጋ ተጎጂ ቤተሰቦች በቦይንግ የቀረበው ካሳ ቁጣን ቀሰቀሰ
በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ለተከሰከሱት ሁለት የ737 ማክስ 8 አውሮፕላን ተጎጂ ቤተሰቦች የአውሮፕላኑ አምራች ቦይንግ አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ካሳ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ይህ ገንዘብ በሁለቱ አውሮፕላኖች አደጋ ለሞቱ በድምሩ ለ346 ተጎጂ ቤተሰቦች የሚከፋፈል ሲሆን ገንዘቡ የሟች ቤተሰቦችን የትምህርትና የኑሮ ወጪን የሚሸፍነው ነው ብሏል ቦይንግ። ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሲከሰከስ የአቶ እያሱ ተሾመ ባለቤት ከተሳፋሪዎቹ መካከል አንዷ ነበሩ። በአደጋውም ህይወታቸው አልፏል። • የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች • ቦይንግ ለተጎጂ ቤተሰቦች 100ሚ. ዶላር ሊሰጥ ነው ከቦይንግ ውሳኔ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ለቢቢሲ የሰጡት አቶ እያሱ ''ለእኔ 100 ሚሊየን አይደለም 100 ቢሊየን እንኳን ሚስቴን አይመልስልኝም'' ብለዋል። ''አንድ ድርጀት ችግር ያለበት ምርት ወደገበያ አስገብቶ ቤተሰቦቻችንን ነው ያሳጣን። ይሄ በገንዘብ የሚተካ ወይም የሚተመን አይደለም።'' አቶ እያሱ ጨምረውም "አውሮፕላኑ ችግር እንዳለበት ይታወቃል፤ ከመጀመሪያው አደጋ በኋላ ማስቆም ይችሉ ነበር። እነሱ ግን ትርፋቸውን በማሰብ በሰው ልጅ ህይወት ፈርደዋል።" የሰው ህይወት በገንዘብ አይለወጥም የሚሉት አቶ እያሱ፤ ገንዘቡን ሳይሆን ከሁሉ በፊት ፍትህን አንደሚፈልጉ በምሬት ይናገራሉ። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? • "እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ኖሚ ሁሴን በአሜሪካ ቴክሳስ የሚገኙ የህግ ባለሙያ ሲሆኑ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ያጡ አንዳንድ ቤተሰቦችን በመወከል ጥብቅና ቆመዋል። እሳቸው እንደሚሉት ቦይንግ ያቀረበው ሃሳብ የተጎጂ ቤተሰቦች ያጡትን ነገር ከግምት ውስጥ ያለስገባና ካሳ ለመባል እራሱ ቅርብ እንዳልሆነ አመልክተዋል። ጠበቃው ለቢበሲ እንደገለጹት አንዳንዶቹ ደንበኞቻቸው በገንዘብ ካሳው ብዙም ደስተኛ አይደሉም ''ቦይንግ በጥሩ ሁኔታ ሲሸጥ የነበረውን አውሮፕላኑን ለመከላከል በማሰብ በሰው ህይወት ቁማር ተጫውቷል፤ እነሱ ያስቀደሙት ትርፋቸውን ነው'' ብለዋል። ጠበቃ ሁሴን በሰጡት መረጃ መሰረት እስካሁን ሰባት የተጎጂ ቤተሰቦችን ወክለው ፍርድ ቤት እየተከራከሩ ሲሆን አንዳንዶቹ ደንበኞቻቸው እስከ 276 ሚሊየን ዶላር የሚደርስ ካሳ ጠይቀዋል። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? •"ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም ሌላኛው በአደጋው ባለቤታቸውንና ሦስት ልጆቻቸው ያጡት ኬንያዊው ጆን ኩዊንዶስ በበኩላቸው የተጎጂ ቤተሰቦችን የዋትስአፕ ቡድን ፈጥረው እንደሚገናኙና ምንም አይነት የካሳ ገንዘብ ላለመቀበል መስማማታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ቦይንግ እስካሁን በግላቸው እንዳላነጋገራቸውና ስለካሳው በዜና መስማታቸውንም አክለዋል። የቦይንግ ሊቀ መንበርና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ሙይልንበርግ "ቦይንግ በሁለቱም አደጋዎች ለተቀጠፈው የሰዎች ሕይወት በከፍተኛ ሁኔታ አዝኗል። የጠፋው ሕይወት በሚቀጥሉት ዓመታትም የሚረሳ አይሆንም" ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ገንዘብ የሟች ቤተሰቦች በፍርድ ቤት ላቀረቡት ክስ የተሰጠ ሳይሆን ድርጅቱ ከፍርድ ሂደቱ ውጭ ያደረገው ክፍያ ነው።
48646100
https://www.bbc.com/amharic/48646100
ትራምፕ በነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ለተፈፀሙት ጥቃቶች ኢራንን ከሰሱ
ኢራን በዖማን ባሕረ-ሰላጤ ውስጥ በሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ በተፈፀመው ጥቃት ውስጥ እጄ የለበትም ማለቷን የአሜሪካው ፕሬዝደንት አጣጣሉት።
ፕሬዝደንት ትራምፕ በትንሽዬ ጀልባ ላይ የሚታዩ የኢራን ኃይሎች ያልፈነዳ ፈንጂ ከአንደኛው መርከብ አካል ላይ ሲያነሱ የሚያሳይ የቪዲዮ ማስረጃን በመጥቀስ ነው ኢራንን ተጠያቂ ያደረጉት። ጉዳዩ ያሳሰባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ "እውነታው ጥርት ባለሁኔታ መታወቅ አለበት" ብለዋል። ሩሲያ በበኩሏ ሁሉም በጥድፊያ ከሚሰጥ ድምዳሜ እንዲቆጠብ አስጠንቅቃለች። • ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ስታቋርጥ በየቀኑ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች • የደም ሻጮችና ለጋሾች ሠልፍ የአሁኑ የፈንጂ ጥቃት የተፈፀመው ከወር በፊት ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ አራት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላ ነው። አሜሪካም በወቅቱ ለጥቃቶቹ ኢራንን ተጠያቂ አድርጋ ብትከስም ምንም ዓይነት ማስረጃ ግን አላቀረበችም ነበር፤ ኢራንም ክሱን አስተባብላው ቆይታለች። ፕሬዝደንት ትራምፕ ከተመረጡ በኋላ በአሜሪካና በኢራን መካከል የነበረው ፍጥጫ በከፍተኛ ደረጃ ተካሯል። ትራምፕ አሜሪካ በፕሬዝደንት ኦባማ የአስተዳደር ዘመን ከኢራን ጋር ደርሰው የነበረውን የኑክሊዬር ስምምነትን ከሰረዙ በኋላ በሃገሪቱ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አጥብቀውታል። ትራምፕ ምን አሉ? ፕሬዝዳንቱ ለፎክስ ኒውስ እንደተናገሩት "ኢራን ጥቃቱን ፈፅማዋለች" ብለዋል። "እንደምገምተው ካጠመዷቸው ፈንጂዎች መካከል እንዱ አልፈነዳም ነበር፤ በላዩ ላይም የኢራን ስም ሳይኖርበት አይቅርም፤ በዛ በጨለማ ከመርከቡ ላይ ያልፈነዳውን ፈንጂ ሲያነሱ ተጋልጠዋል" ሲሉ ኢራንን ከሰዋል። ፕሬዝደንቱ ጨምረውም በባሕር ላይ ክሚጓጓዘው የዓለም የነዳጅ ፍጆታ አንድ ሦስተኛው የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ሰርጥን ኢራን ልትዘጋው ትችላለች ብለው እንደማያስቡም ገልፀዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ኢራንን የወነጀሉት የሃገራቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ጥቃቱን በተመለከተ ፈንጂዎችን፤ የሠለጠኑ ጥቃት ፈፃሚዎችንና በቅርብ በኢራን አማካይነት ተፈጽመዋል የተባሉ ተመሳሳይ ጥቃቶችን በማነጻጸር ኢራን ከጥቃቶቹ ጀርባ እንዳለች ከከሰሱ በኋላ ነው። • ኤርትራ በቤተ ክርስቲያን ስር ያሉ የጤና ተቋማትን ወሰደች የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ፓትሪክ ሻናሃንም "በዚህ ዓለም አቀፍ ችግር ላይ ዓለም አቀፍ መግባባት ለመፍጠር" አሜሪካ ያላትን የደህንነት መረጃ እያጋራች ነው በማለት ጣታቸውን ወደ ኢራን ጠቁመዋል። የኢራን ምላሽ ምንድን ነው? የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሩሃኒ አርብ ዕለት "አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ መረጋጋት ላይ አሳሳቢ ስጋት እየደቀነች ነው" ሲሉ በዖማን ባሕረ-ሰላጤ ላይ የተፈፀሙትን ጥቃቶች በቀጥታ ሳይጠቅሱ ከስሰዋል። አክለውም የትራምፕ አስተዳደር በተናጠል እራሱን ያገለለበትን የ2015 የኑክልዬር ስምምነት እንዲከበር ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዛሪፍ በትዊተር ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ አሜሪካ "ቅንጣት ታክል ተጨባጭም ሆነ አመላካች ማስረጃ ሳይኖራት ዲፕሎማሲያዊ አሻጥር ለመፈፀም እየሞከረች ነው" ሲሉ ከሰዋል።
news-49432458
https://www.bbc.com/amharic/news-49432458
በስፔን ከ550 በላይ የሚሆኑ ሴቶችን የተጋለጠ አካል የሚያሳይ ቪዲዮ የቀረፀው ተከሰሰ
በስፔን ማድሪድ ከ550 በላይ የሚሆኑ ሴቶችን የተጋለጠ አካል የሚያሳይ ቪዲዮ ያለፈቃዳቸው በመቅረፅ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ግለሰቡ ሴቶቹን ቪዲዮ ከቀረፃቸው በኋላ አብዛኛውን በድረገፆች ላይ አሰራጭቶታል ተብሏል።
አብዛኛዎቹ ሴቶች ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በማድሪድ ሜትሮ ነው • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና የ53 ዓመቱ ኮሎምቢያዊ ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ምስሉን የቀረፀው በጀርባው ባዘለው ቦርሳው ውስጥ በደበቀው ተንቀሳቃሽ ስልኩ ነው። ፖሊስ እንዳስታወቀው 283 የሚሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የወሲብ ፊልሞች በሚተላለፉባቸው ድረ ገፆች ላይ የጫነው ሲሆን በሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ተመልክተውታል። ጥቃቱ ከተፈፀመባቸው 555 ሴቶች መካከል ህፃናትም ይገኙበታል። • 'የተሳመው ከንፈር' ጥቃት ደረሰበት ግለሰቡ የቀረበበት ክስ እንደሚያስረዳው ተንቀሳቃሽ ምስሎቹን በድረገፆች ማሰራጨት ከጀመረበት ባለፈው ዓመት አንስቶ ድርጊቱን የዕለት ተዕለት ሥራው አድርጎት ነበር። ከዚህም ባሻገር ድርጊቱን በገበያ ማዕከላት አንዳንዴም ደግሞ ጥራት ያለው ምስል ለማግኘት እንዲያስችለው ቆም ብሎ ራሱን በማስተዋወቅ ይቀርፅ እንደነበር ተነግሯል። በሜትሮ አንዲት ሴትን በመቅረፅ ላይ ሳለ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው ተጠርጣሪ ምርመራ እየተካሄደበት ነው። የአገሪቷ ፖሊስም በትዊተር ገፅ ላይ በተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ሥር ተጠርጣሪውን " የሴቶችን ግላዊ መብት የጣሰ ቀንደኛ ወንጀለኛ" ሲሉ ገልፀውታል። ፖሊስ የግለሰቡን ቤት ፍተሻ ባደረገበት ወቅት ላፕቶፖችንና የፋይል ማስቀመጫ [ሃርድ ድራይቭ] ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቪዲዮዎችን አግኝቷል። በግለሰቡ ስም የተከፈተው ድረ ገፅም 3 ሺህ 519 ተከታዮች አሉት። በስፔን የሴቶች አካል ያለፈቃዳቸው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ፎቶ ማንሳት እንደ ወሲባዊ ጥቃት የሚቆጠር ሲሆን በእስራት ያስቀጣል። በእንግሊዝና ዌልስም በደራሲ ጊና ማሪን ከተካሄደ ዘመቻ በኋላ የሴቶችን አካል ያለፈቃዳቸው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስልም ሆነ ፎቶ ማንሳት ወንጀል ሆኖ ተደንግጓል።
news-52267349
https://www.bbc.com/amharic/news-52267349
ኮሮናቫይረስ፡ በድብቅ በተዘጋጀ ድግስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 6 ሰዎች ቆሰሉ
የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ባዘዘችው የአሜሪካዋ ግዛት ካሊፎርኒያ ውስጥ በድብቅ በተዘጋጀ ድግስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ስደስት ሰዎች በጥይት መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
ተኩሱ የተከሰተው ባለፈው አርብ ሌሊት ላይ ቤከረስፊልድ ተብሎ በሚታወቅ የመኖሪያ ህንጻዎች ጊቢ ውስጥ እንደሆነ የአካባቢው ፖሊስ ገልጿል። በጥቃቱ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው አራት ሴቶች፣ አንድ ወንድና አንዲት ታዳጊ ሲሆኑ፤ የህክምና እርዳታ ማግኘታቸውና ጉዳቱም ህይወታቸውን ለክፉ የሚሰጥ እንዳልሆነ ተነግሯል። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሰው ባይኖርም፤ በመኪና ከአካባቢው ሲሸሹ የታዩ አራት ሰዎች ጥቃቱን ፈጽመዋል ተብለው ተጠርጥረዋል። ፖሊስ እንዳለው በተፈጸመው ጥቃት ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው። በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ሁሉን አቀፍ የእንቅስቃሴ ዕገዳ ከባለፈው መጋቢት ወር አንስቶ ተግባራዊ ሆኖ ይገኛል። ግዛቲቱ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተመቱት የአሜሪካ ግዛቶች አንዷ ስትሆን አስካሁንም ከ21 ሺህ 800 በላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን 651 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በዚህም ሳቢያ የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሰም ባወጡት ትዕዛዝ ነዋሪዎች ምግብና መድኃኒት እንዲሁም ስፖርት ለመስራት ካልሆነ በስተቀር ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለዋል። በግዛቲቱ ውስጥ የሚገኙ አስፈላጊ ያለሆኑ መደብሮች እንዲዘጉ የተገደዱ ሲሆን የምግብ መደብሮች፣ መድኃኒት ቤቶችና የነዳጅ ማደያዎች ብቻ ክፍት እንዲሆኑ ተደርጓል።
54279608
https://www.bbc.com/amharic/54279608
ሰብዓዊ መብት ፡ "የሕግ የበላይነት መሰረቱ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ማክበር ነው" ኢሰመኮ
በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊመብቶች ኮሚሽን የፍርድ ቤት የዋስትና መብት የተፈቀደላቸው በሙሉ በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድም ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ መግለጫ አውጥቷል።
የኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሰብዓዊ መብቶች መከበር ዋና ዋስትናው የፍርድ ቤት ውሳኔ መከበር መሆኑን በመግለጫው ላይ አመልክተዋል። አክለውም አቶ ልደቱን ጨምሮ በፍርድ ቤት ዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጠላቸው ታሳሪዎች "በሙሉ በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊፈቱ ይገባል" ማለታቸው በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። ቢቢሲ ይህንንና ተያያዥ ጉዳዮችን በማንሳት የኮሚሽኑ ከፍተኛ አማካሪ ከሆኑት ከአቶ ምስጋናው ሙሉጌታ ጋር ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፡ የፍርድ ቤት ውሳኔ ካለመፈጸም ጋር በተያያዘ መግለጫ ለማውጣት አልዘገያችሁም? አቶ ምስጋናው፡ መዘግየቱን በሚመለከት ከዚህ ቀደምም ስንከታተል ነበር። በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን ሁኔታ ኮሚሽኑ ይከታተላል። ሁሉንም የክትትላችንን ውጤት ለሕዝብ ይፋ እናደርጋለን ማለት አይደለም። ይህንን ችግር [የአቶ ልደቱ ዋስትና መብት አለመከበር] መነሻ ተደርጎ ነው እንጂ፣ የተወሰኑ የተደጋጋሙ ነገሮችም አሉ። እንደዚህ በስም ታዋቂ ያልሆኑ የዋስትና መብት የተፈቀደላቸው ነገር ግን በፖሊስ እስር ስላሉ ሰዎች የደረሱን ጥቆማዎች አሉ። ስለዚህ ይህ በአጠቃላይ አሁን የአቶ ልደቱ ታዋቂም ስለሆኑ፣ ብዙ ሰው ጉዳያቸውንም ስለሚከታተል ጥሩ ማሳያ ይሆናል በሚል ነው እንጂ፤ አሁንም እየተከሰተ ያለ ነገር ስለሆነ ዘግይቷል ብዬ አላስብም። ምን ያህል ውጤታማ ይሆናል የሚለው ግን በእኛ እምነት ሰብዓዊ መብትን ማክበርና ማስከበር በዋነኛነት የመንግሥት ኃላፊነት ነው። የመንግሥት አካላትም እኛ ያወጣነውን መግለጫ መሰረት በማድረግ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳሉ። የሕግ የበላይነት የሚባለው መሰረቱ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን አክብሮ መንቀሳቀስ ስለሆነ ነው። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የተመለከቱ መግለጫዎችን ታወጣላችሁ። እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ከመንግሥት አካላት ጋር ትነጋገራላችሁ? አቶ ምስጋናው፡ አዎ እንነጋገራለን። እንዲህ አይነት መግለጫ ማውጣት አንደኛው ፋይዳ የመንግሥት አካላትም ነገሩን እንዲገነዘቡ፣ ሕብረተሰቡም ይህንን እንዲረዳውና ግፊት እንዲያደርግ እድል እፈጥራል ብለን እናስባለን። እንነጋገራለን። መግለጫዎች ከማውጣታችን በፊት ችግሮች ሲደርሱ፣ ከደረሱ በኋላ ምርመራ አድርገን የማስተካካያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት እናደርጋለን። አንዳንዶቹ ይፈታሉ፤ አንዳንዶቹ ጊዜ የሚወስዱ ናቸው ተብሎ ቃል ይገባልናል። እነርሱንም ግን መተግበራቸውን እንከታተላለን። መግለጫዎቹ በመንግሥት ላይም ሆነ ይህንን ውሳኔ በሚወስኑ አካላት ላይ ጫና ይፈጥራሉ ብለን እናስባለን እና በዚያ መልኩ ነው እየሄድንበት ያለነው። ግን ይህ የሚቆም ነገር ሳይሆን ከአሁን በኋላም የምንቀጥልበት ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፈርጀ ብዙ ናቸው። በተለያዩ ስፍራዎች የተለያዩ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይሰማሉ። በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉት ጥሰቶች ስፋትና ጥልቀት የእናንተ ሪፖርት ምን ያህል ሁሉንም ይሸፍናል? አቶ ምስጋናው፡ በሚፈለገው መጠን ሁሉም ቦታ ላንደርስ እንችላለን። ሰብዓዊ መብቶች እንደምታውቀው ለሁሉም ነው ተግባራዊ የሚሆኑት። አይበላለጡም፤ የማይነጣጠሉ ናቸው። አንድ ሰብዓዊ መብት ከአንድ መብት አያንስም። አንድ አካባቢ የሚደርስ ነገር ከአንድ ቦታ አይበልጥም። ይህ በመርህ ደረጃ በደንብ መሰመር ያለበት ነው። ኮሚሽኑ ሪፎርም ላይ ነው፤ የአቅም ውሱንነት አለበት። ስለዚህ ሁሉም ቦታ ለመድረስ ላይችል ይችላል። ግን በተቻለ መጠን ዋና ዋና የሚባሉትን ለመመርመር ለመከታተል እየሞከርን ነው። ለምሳሌ በወላይታ ምርመራ አድርገናል። በቅርቡም ኦሮሚያ ውስጥ የተከሰቱ ጥሰቶችን ለመመርመር ባለሙያዎች ልከን ምርመራ አድርገናል። የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲደረጉ በየደረጃው ከሚገኙ የመንግሥት አካላትን እየወተወትን እንገኛለን። እና ከችግሩ ስፋት አንጻር በአቅም ውሱንነት ምክንያት ያላየናቸው ይሆናሉ እንጂ የቁርጠኝነት ችግር የለም። በቅርቡም የሚወጡ ሪፖርቶች ይኖራሉ።በዚህም የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱና ወደፊት እንዳይደገሙ ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን ማለት ነው። እንደሚሉኝ በእናንተ በኩል ተነሳሽነቱ ካለ ዋነኛ ችግሮቻችሁ ምንድን ናቸው? አቶ ምስጋናው፡ አንደኛው የአቅም ነው። ኢትዮጵያ በጣም ሰፊ አገር ናት። የሰብአዊ መብት ጉዳዮች እዚህም እዚያም በተደጋጋሚ ይነሳሉ። በተለይ ከግጭት ጋር የተያያዘ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሰፊ ናቸው። ስለዚህ ኮሚሽኑ የባለሙያዎች ብዛትና የሀብት ክፍተቶች አሉ። ሁለተኛ በተቻለ መጠን ሰፊ የሆነ ተደራሽነት እንዲኖር ለማድረግ እየተሞከረ ነው። ነገር ግን በተለይ አሁን ያለንበት ሁኔታ ነገሮች በጣም በፍጥነት እየተከሰቱና ሰፊ ቦታ እየሸፈኑ ነው። እንደዚያም ሆኖ በእኛ እምነት ዋና ዋና የሚባሉትን በደንብ እየተከታተልን ነው። የምንከታተለውን በሙሉ ለሕዝብ ይፋ ላናደርግ እንችላለን። ግን ባለን አቅም ያለምንም ማበላለጥ ጉዳዮቹን ለመከታተል ጥረት እያደረግን ነው። አቅማችን ደግሞ ሲጠነክር በሚታይ መልኩ ተደራሽነታችንን እናሰፋለን ብለን እናምናለን። ከየትኛው የመንግሥት አካል ጋር ነው በደንብ በቅርበት እየሰራችሁ ያላችሁት? አቶ ምስጋናው፡ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ነጻና ገለልተኛ ተቋም ነው። ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ጋር እንደ አስፈላጊነቱ ግንኙነት እናደርጋለን። ለምሳሌ ለፓርላማው ነው ተጠሪነታችን በዋነኝነት። የእኛም ሥራ እንደ ቁጥጥር ሥራ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል። እና እኛ እንደ አግባብነቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር የምናገኛቸውን ግኝቶች እናነሳለን። መፍትሄ እንዲሰጣቸው እናደርጋለን። እና በዚያ ረገድ ነው መታየት ያለበት። በዋነኛነት የሰብዓዊ መብት ማክበር ማስከበር የመንግሥት ኃላፊነት ነው። ስለዚህ ይህንን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣታቸውን እንከታተላለን። እንዲወጡ እንወተውታለን። ጥሰቶችም ሲገኙ ያው ምርመራ አድርገን በተቻለ መጠን ተጠያቂነት እንዲኖር እና ወደፊት እንዳይደገም የማድረግ ነገር ነው ያለን።
news-45319113
https://www.bbc.com/amharic/news-45319113
ለህገወጥ አዳኞች ፈተና የሆኑት ውሾች
ፈር ቀዳጅ የተባለለት አዲስ መንገድ የሰው ልጅ ታማኝ ጓደኛን የህገወጥ አዳኞች ከባድ ፈተና ለማድረግ የታሰበ ነው።
በባህርና በተለያዩ የሟጓጓዣ መንገዶች የሚዘዋወሩ የዝሆን ጥርስ፤ የአውራሪስ ቀንድ እና ሌሎች ነገሮችን የሰለጠኑት ውሾች አነፍንፈው ማግኘት ይችላሉ። ይህ አዲስ የመከላከል ስርአት እየተሞከረ ያለው በአለማችን ብዙ ሀገወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶች ይዘዋወሩበታል በሚባልለት የኬንያው ሞምባሳ ወደብ ነው። በቅርቡ የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በዚሁ በሞመባሳ ወደብ ብቻ እ.አ.አ ከ2009 እስከ 2014 ባሉት ዓመታት ውስጥ ከአስራ ስምንት ሺ ኪሎ ግራም በላይ ህገ-ወጥ የዝሆን ጥርስ መዘዋሩን ያሳያል። ይህን ያህል ቁጥር ያለው የዝሆን ጥርስ ለማግኘት ከ2400 በላይ ዝሆኖች መገደላቸውንና በፍተሻ ወቅት ያልተያዘው ሲደመር ደግሞ ቁጥሩ እጅጉን ከፍ ሊል እንደሚችል ጥናቱ ያሳያል። • ታይዋናዊ ቱሪስት ፎቶ ሊያነሳው በነበረው ጉማሬ ተነክሶ ሞተ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሙያው ድሪው ማክቬይ ግን ከዚህ በኋላ ቁጥሩ ሊቀንስ እንደሚችል ተስፈኛ ነው። ''ይህ መንገድ ብዙ ነገር ይቀይራል፤ በህገወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ ሃገራት በተለይ ወደ እስያ ገበያዎች የሚዘዋወሩ የዝሆን ጥርስና ለሎች የዱር እንስሳት የሰውነት ክፍሎች በቀላሉ ለመቆጣጠር ይረዳል'' ብሏል። ''ውሻዎች ያላቸው የላቀ የማሽተት ችሎታ ላይ ተገቢው ስልጠና ሲጨመርበት ከአስራ ሁለት ሜትር በላይ ከፍታ ያለው የእቃ መጫኛ ውስጥ የተደበቁ ነገሮችን አነፍንፈው ማግኘት ይችላሉ።'' • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ እጅግ የተወሳሰቡና በየጊዜው የሚቀያየሩ የማዘዋወሪያ መንገዶችን ስለሚጠቀሙ፤ የውሾቹ ወደ ስራ መግባት በከፍተኛ ሁኔታ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ድሪው ማክቬይ ያስባል። ፍተሻ በሚደረግባቸው ጣቢያዎች ላይ ከእቃ መጫኛዎቹ ውስጥ የአየር ናሙና ይወሰድና ውሻዎቹ እንዲያሸቱት ይደረጋል። ተፈጥሮአዊ የማነፍነፍ ችሎታቸውንና ያገኙትን ስልጠና ተጠቅመው ውሻዎቹ ምልክት ይሰጣሉ። አሁን በሙከራ ላይ ያለው አዲሱ የቁጥጥር መንገድ በሞምባሳ ወደብ የሚያልፉ እስከ 20 ሺ የመርከብ ላይ እቃ መጫኛዎችን በአንድ ቀን መፈተሽ አስችሏል። ከዚህ በፊት ግን የቁጥጥር ባለሙያዎቹ አንድ በአንድ እቃ መጫኛዎቹ ውስጥ በመግባት ነበር ፍተሻ የሚያካሂዱት። • አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው? እስካሁን በተደረጉ ፍተሻዎችም ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ህገወጥ የዱር እንስሳት አካላትን ጭነው የነበሩ 26 እቃ መጫኛዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተገኘው መረጃም በአለማቀፍ አዘዋዋሪዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሰራውን ወንጀል ባህሪ ለመረዳት እንዳስቻላቸው የሃገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል። አለማቀፉ የዱር እንስሳት ጥበቃ ድርጅት እንደሚለው በአሁኑ ሰአት 25 ሺ የሚሆኑ ጥቁርና ነጭ አውራሪሶች የቀሩ ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ብቻ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑት ባለፈው አመት በህገወት አዳኞች ተገድለዋል። በየቀኑ 55 የአፍሪካ ዝሆኖች እንደሚገደሉም ድርጅቱ ገልጿል።
news-57222404
https://www.bbc.com/amharic/news-57222404
አንድ ጋዜጠኛን ለመያዝ በረራ ላይ የነበረ አውሮፕላን እንዲያርፍ ተገደደ
ከግሪክ ወደ ሊቱዋንያ እየተጓዘ የነበረ የራየንኤር አውሮፕላን ቤላሩስ አርፎ ለሰዓታት እንዲቆይ መገደዱ ተነገረ።
የመብት ተሟጋቾች እንዳሉት አውሮፕላኑ ማረፊያውን እንዲለውጥ የተደረገው በአውሮፕላኑ ተሳፍሮ የነበረ ጋዜጠኛን ለመያዝ ነው። የአውሮፓ አገራት ድርጊቱ አስቆጥቷቸዋል። ቤላሩስን "መንግሥት የሚደግፈው ሽብር" እያራመደች ነው በሚልም ኮንነዋታል። አውሮፕላኑ ወደ ሊቱዋንያ እንዲጓዝ የተፈቀደው ኔክስታ ግሩፕ የተባለ መገናኛ ብዙሃን የቀድሞ አርታኢ የነበረው ሮማን ፕሮቶቪች ከተያዘ በኋላ ነው። የቤላሩስ መገናኛ ብዙሃን እንዳሉት፤ አውሮፕላኑ ውስጥ ቦንብ ሊኖር ይችላል በሚል ስጋት አውሮፕላኑ ወደ ሚንስክ ቢወሰድም ምንም ነገር አልተገኘም። አውሮፕላኑ ሉቲዋንያ ያረፈው ሰባት ሰዓታት ዘግይቶ ነበር። አውሮፕላኑ ለምን ወደ ሚንስክ እንደተወሰደ እንዳልተነገራቸው ተሳፋሪዎች ገልጸዋል። አንድ ተሳፋሪ ደግሞ ጋዜጠኛው ሮማን ፕሮቶቪች አውሮፕላኑ መንገድ ሲለውጥ ፈርቶ እንደነበር ተናግረዋል። "ፍርሀት ይታይበት ነበር። አይኑን ስመለከተው ያሳዝንም ነበር" ብለዋል። ሞኒካ ሲምኪኔ የተባለች ተሳፋሪ ለኤኤፍፒ "ፊቱን ወደተሳፋሪዎቹ አዙሮ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተናግሯል" ብላለች። የአውሮፓ ሕብረት እና የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን አገራት ጣልቃ እንዲገቡ ተጠይቀዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ዶምኒክ ራብ "ይህ ያልተገባ ድርጊት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይወስዳል" ብለዋል። የቤላሩስ የተቃዋሚ መሪ ስቪትና ቲካንቫክያ ጋዜጠኛው እንዲለቀቅ ከጠየቁት መካከል ናቸው። የጋዜጠኛው ደጋፊዎች ይጓዝበት በነበረው ከተማ ሲጠብቁት ስለተፈጠረው ነገር ምን ተባለ? ከግሪክ የተነሳው አውሮፕላን ወደ መዳረሻው ሲቃረብ ነበር መስመር ለውጦ ወደ ሚንስክ እንዲሄድ የተደረገው። 171 ተሳፋሪዎች ጭኖ ነበር። ራየንኤር እንዳለው፤ የአውሮፕላኑ ሠራተኞች በደኅንነት ስጋት ሳቢያ አውሮፐፕላኑ እንዲያርፍ መደረጉ ተነግሯቸዋል። ሚንስክ ውስጥ ፍተሻ ከተደረገ በኋላ ምንም አጠራጣሪ ነገር ባለመገኘቱ ወደ መዳረሻው እንዲሄድ ተወስኗል ተብሏል። የጋዜጠኛውን መታሰር ይፋ ያደረገው 'ኔክስታ' የተባለው መገናኛ ብዙሃን ነው። ድርጊቱ ብዙዎችን አስቆጥቷል። በቤላሩስ የአሜሪካ አምባሳደር ጁሊ ፊሸር፤ አውሮፕላኑ ውስጥ ቦንም ተገኝቷል በሚል ውሸት ጋዜጠኛው እንዲታሰር መደረጉን ኮንነዋል። የአውሮፓ ምክርት ቤት ኃላፊ ቻርልስ ሚሼል እንዳሉት የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ጉዳዩ ላይ ይወያያሉ። አንዳች እርምጃ እንደሚወስዱም ይጠበቃል። የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን አገራት ዋና ጸሐፊ የንስ ስቶትልበርግ "የተፈጠረው ነገር አደገኛ እና አሳሳቢ ነው" ብለዋል። ላቲቪያ እና ሉቲዋኒያ በቤላሩስ በኩል ማለፍ አስጊ መሆኑ ተገልጾ ዓለም አቀፍ በረራ እንዲታገድ ጠይቀዋል። የፓላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ማቲዮዝ ሞራዊኬይ "አውሮላን መጥለፍ በመንግሥት የተደረገ ሽብርተኝነት ነው። ሊቀጡ ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል። በአውሮፓ ታዋቂ የሆኑ የፓለቲካ ሰዎች የቤላሩስ መንግሥት ማዕቀብ እንዲጣልበት እየጠየቁ ነው። ጋዜጠኛው ማነው? የ26 ዓመቱ ጋዜጠኛ ከቤላሩስ የወጣው እአአ በ2019 ነው። ኔክስታ ለተባለው መገናኛ ብዙሃን የቤላሩስም የ2020 ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ዘግቧል። ኔክስታ በዋነኛነት በቴሌግራም የሚሠራጭ መገናኛ ብዙሃን ሲሆን፤ በትዊተር እና በዩቲዩብ ላይም ይገኛል። በምርጫው ወቅትና ከምርጫው በኋላም የቤላሩስን የተቃውሞ ድምጽ በማሰማት ከፍተኛ ሚና አለው። ጋዜኛው ከምርጫ ዘገባው በኋላ ቤላሩስ ከሳዋለች። ቤላሩስ ውስጥ በሽብርተኝነት ስለተፈረጀ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተቃዋሚዋ ስቪትና ቲካንቫክያ ተናግረዋል። ተቃዋሚዋ በምርጫው ማሸነፋቸውን ይናገራሉ። ሆኖም ግን ከቤላሩስ መንግሥት ሸሽተው ሊቱዋንያ ለመሸሸግ ተገደዋል።
news-56616316
https://www.bbc.com/amharic/news-56616316
ተፈጸመ ስለተባለው ግድያ የኢትዮጵያ መንግሥት ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ
ትግራይ ውስጥ ማኅበረ ዴጎ በተባለ ስፍራ ተፈጽሟል የተባለውን ግድያን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት ምርመራ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
ይህ የተነገረው ትግራይ ውስጥ በኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ሰዎች መገደላቸውን በተመለከተ ለወጣው ዘገባ በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምላሽ በሰጠበት መግለጫ ነው። ኤምባሲው ላለፉት ሳምንታት በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ሲዘዋወር የቆየውንና አሁን የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ርዕስ ስለሆነው ትግራይ ማኅበረ ዴጎ በሚባል ቦታላይ ተፈጽሟል የተባለውን ጭፍጨፋ የሚያሳየውን የሚረብሽ ቪዲዮ እንደተመለከተው ገልጿል። የቢቢሲ 'አፍሪካ አይ' ፕሮግራምም በዚሁ ቪዲዮ ላይ ባደረገው ምርመራ ግድያው በኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት መፈጸሙን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች ማግኘቱንና በዚህም ቢያንስ 15 ሰዎች የተገደሉበትን ትክክለኛው ቦታ ለመለየት መቻሉን ዘግቦ ነበር። ኤምባሲው በመግለጫው ላይ በንጹሃን ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸምን ጥቃትም ሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልጿል። በኢትዮጵያ ውስጥ በተልዕኮ ላይ ያሉ ወታደሮችን ጨምሮ ማንም ሰው ከሕግ በላይ አለመሆኑን ያመለከተው የኤምባሲው መግለጫ፤ መንግሥት የተፈጸሙ በደሎችን በጥልቀት ለመመርመር ቁርጠኛ መሆኑንና ማስታወቁን አስታውሷል። ከዚህም አኳያ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የተባሉትን የወንጀል ድርጊቶችን የፈጸሙትን ተጠያቂ ለማድረግ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና ከፌደራል ፖሊስ የተወጣጣ ልዩ ግብረ ኃይል ባለፉት ሳምንታት ጉዳዩን ከስፍራው ሆኖ ለማጣራት ወደ ትግራይ መሰማራቱን ገልጿል። ኤምባሲው አክሎም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በመሆን በትግራይ ተፈጽመዋል የተባሉ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ምርመራ እንደሚያደርግና ውጤቱንም ይፋ ይደረጋል ብሏል። የእነዚህ ምርመራዎች ውጤትም የጥፋቱን ፈጻሚዎች ለሕግ ለማቅረብና ትግራይ ውስጥ ተፈጸሙ ለተባሉት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ወንጀሎች ምላሽ ለመስጠት መንግሥትን እንደሚያስችል አመልክቷል። ኤምባሲው ለማየት የሚረብሸውን ቪዲዮ በተመለከተም ተፈጽሟል ስለተባሉት ወንጀሎች ምርመራ እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት መገናኛ ብዙሃንና ሕዝቡ ግምት ላይ የተመሰረት ሃሳብ ከመሰንዘር እንዲቆጠቡ ጠይቋል። የታጠቁና የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ያልታጠቁ ወንዶችን ከአንድ የገደል አፋፍ ላይ በመውሰድ አንዳንዶቹን ላይ በቅርብ ርቀት በመተኮስ አስከሬኖችን ወደ ገደል ገፍተው ሲጨምሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታይቶ ነበር። ቢቢሲ ይህ ድርጊት የተፈጸመው የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት ኃይሎችን እየተዋጋ ባለበት ትግራይ ክልል ውስጥ ማኅበረ ዴጎ ከተባለች ከተማ አቅራቢያ መሆኑን አረጋግጧል። ቀደም ሲል ቢቢሲ ያገኛቸውን ማስረጃዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት በማቅረብ ምላሽ የጠይቆ የነበረ ሲሆን መንግሥት "በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ነገሮችና ክሶች እንደ ማስረጃ ሊወሰዱ አይችሉም" በማለት "ገለልተኛ ምርመራዎችን ለማካሄድ የትግራይ ክልል ክፍት ነው" ሲል ምላሽ ሰጥቶ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው እንደተናገሩት፣ ትግራይ ውስጥ በኢትዮጵያ ሠራዊት ተፈጸሙ ስለተባሉት ጥፋቶች አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች በሕግ እንደሚጠየቁ መናገራቸው ይታወሳል። ትግራይ ውስጥ ግጭቱ የተቀሰቀሰው የህወሓት ኃይሎች በመንግሥት ጦር ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ ነበር። ህወሓትም የጠቅላይ ሚኒስትሩን እርምጃ በመቃወም "ትግሉን እንደሚቀጥል" ገልጾ ነበር። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው ግጭቱ አስካሁን ድረስ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ እንዲፈናቀሉ ያደረገ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ እንዲጠብቁ አድርጓቸዋል። ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ወቅት በተለያዩ የግጭቱ ተሳታፊዎች ከባድ የመብት ጥሰቶችና ጥቃቶች እንደተፈጸሙ ዓለም አቀፍ ተቋማትና የሰብአዊ መብት ተቋማት ሪፖርት ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ይህንንም ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተና ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ተፈጸሙ ስለተባሉት የመብት ጥሰቶች ምርመራ ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሠራዊት ግድያ መፈጸሙን ማስረጃዎች አመለከቱ
54956303
https://www.bbc.com/amharic/54956303
ኮሮናቫይረስ ፡ በዩናይትድ ኪንግደም የኮቪድ-19 ተስፋ ሰጪ የክትባት ሙከራ ተጀመረ
ውጤታማ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሰዎችን ከኮቪድ-19 የሚከላከል የክትባት ሙከራ በዩናይትድ ኪንግደም ተጀመረ።
መሰል ሙከራዎች ሲካሄዱ ይህ ሦስተኛው ነው። ክትባቱ የተዘጋጀው በአንድ የቤልጂየም ተቋም ሲሆን፤ የተሠራው ዘረ መሉ ከተሻሻለ የጉንፋን ቫይረስ ነው። ክትባቱ በሽታን የመከላከል አቅምን እንደሚያዳብርም ተነግሯል። ከሳምንት በፊት ከበሽታው 90 በመቶ የሚከላከል ክትባት መገኘቱ ተሰምቷል። ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ የተባሉት ተቋሞች ያስተዋወቁት ክትባት ለዓለም ሕዝብ ተስፋን ሰጥቷል። ሆኖም ግን ወረርሽኙን ለመግታት በርካታ የተለያዩ ክትባቶች ያስፈልጋሉ። ፋይዘር እና ባዩኤንቴክ ያገኙት ክትባት ገና ፍቃድ አልተሰጠውም። በሽታው የመከላከል አቅሙ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እና አረጋውያን ላይ ያለው ውጤታማነት እስካሁን አልታወቀም። በዩናይትድ ኪንግደም የሚካሄደውን ሙከራ የሚመሩት ፕሮፌሰር ሳውል ፋውስት "ከተለያዩ አምራቾች የተለያዩ ክትባቶችን መሞከር አለብን" ብለዋል። እያንዳንዱ ክትባት ምን አይነት ውጤት እንደሚያሳይ እንደማይታወቅና በአንድ ድርጅት የሚመረት ክትባት ብቻ ለሁም ተደራሽ እንደማይሆን ተናግረዋል። ከዩናይትድ ኪንግደም 6000 ሰዎች በሙከራው ላይ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ከሌሎች የተለያዩ አገራትም አስከ 30,000 የሚደርሱ ሰዎች ተሳታፊ እንደሚኖሩ ይጠበቃል። ከሙከራው ተሳታፊዎች ግማሹ በሁለት ወር ልዩነት ሁለት ጊዜ ክትባቱባቱን ያገኛሉ ተብሏል። ከዚህ ቀደም በአንድ ጠብታ ሙከራ ተሠርቷል። ሁለት ጠብታ በመስጠት የክትባቱ በሽታ የመከላለከል አቅም ምን ያህል እንደሆነ ይፈተሻል። ውጤቱ ሊታወቅ የሚችለው በስድስት እስከ ዘጠኝ ወር ባለ ጊዜ ውስጥ ነው። ይህ ክትባት ከፋይዘር ክትባት በተለየ መልኩ የጉንፋን ቫይረስን በማሻሻል የተሠራ ሲሆን፤ ጉዳት እንዳያስከትል እና ኮሮናቫይረስን እንዲመስል ተደርጎ ነው የተቀመመው። ይህም ሰውነት ቫይረሱን እንዲያውቀውና እንዲዋጋው ይረዳል። ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እና አስትራዜንካ የሚሠሩት ክትባትም ተመሳሳይ መንገድ ይከተላል። በሌላ በኩል ይህኛው ክትባት የሚሞከረው በሰው ላይ ሲሆን፤ የኦክስፎርዱ ግን ዝንጀሮዎች ላይ ሙከራ እየተሠራበት ነው። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን 25 ሺህ ዜጎች በተለያዩ የክትባት ሙከራዎች ተሳታፊ ሆነዋል። የአገሪቱ መንግሥት እስካሁን ስድስት ክትባቶችን ለመግዛት ተስማምቷል። ከእነዚህ መካከል አዲሱን ክትባት 30 ሚሊዮን ጠብታ እንደሚገዛ አስታውቋል።
sport-45088836
https://www.bbc.com/amharic/sport-45088836
ክለባቸውን ሊለቁ የሚችሉ ዘጠኝ የፕሪምየር ሊጉ ተጫዋቾች
የዘንድሮው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የፊታችን ሃሙስ በይፋ ይዘጋል። ብዙ የእንግሊዝ ክለቦች የመጨረሻው ቀን ከመድረሱ በፊት ይጠቅሙኛል ያሏቸውን ተጨዋቾችን ለማስፈረም እየተሯሯጡ ነው።
ቶተንሃም በመጨረሻም ተጫዋች ያስፈርም ይሆን? የማንቸስተሩ አንቶኒ ማርሻል ወደ ሌላ ክለብ ይዘዋወር ይሆን? በዚህኛው የዝውውር መስኮት ክለቦቻቸውን ሊለቁ የሚችሉ ዘጠኝ የፕሪምየር ሊጉ ተጫዋቾችን እንመልከት። ቶቢ አልደርዌረልድ (ቶተንሃም) ቤልጂየማዊው ተከላካይ ባለፈው ዓመት ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በቶተንሃም የቋሚ አሰላለፍ ቦታ ለማግኘት ተቸግሮ ነበር። ኮንትራቱ በዚህ ዓመት የሚጠናቀቀው አልደርዌረልድ፤ ስሙ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እየተያያዘ ነው። ለተጫዋቹ የቀረበው የመግዣ ዋጋ ደግሞ 75 ሚሊዮን ፓውንድ ነው። • ጅማ አባጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆነ • ኢትዮጵያዊው ጀማል ይመር በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ ጃክ ግሬሊሽ (አስቶን ቪላ) የ21 ዓመቱ እንግሊዛዊ ግሬሊሽ በቻምፒዮንሺፑ አስቶን ቪላ ላደረገው ግስጋሴ ከፍተኛ አስተዋጸኦ አድርጓል። ክለቡ በአሁኑ ሰአት የገንዘብ እጥረት ያጋጠመው ሲሆን፤ በተለይ ደግሞ ቶተንሃሞች ተጫዋቹን የግላቸው ለማድረግ እስከ 20 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ተዘጋጅተዋል። አስቶን ቪላ ግን ቶተንሃሞች ያቀረቡትን ዋጋ እጥፍ እየጠየቁ ነው። ዳኒ ኢንግስ (ሊቨርፑል) በአንድ ወቅት እንግሊዝ ካፈራቻቸው ምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ ተብሎ ሲወደስ ነበረው ዳኒ ኢንግስ ሊቨርፑል ባሳለፋቸው ሶስት ዓመታት እጅግ አስቸጋሪ ጊዜ አሳልፏል። በባለፈው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግም አንድ ጊዜ ብቻ ነው ግብ ማስቆጠር የቻለው። ሊቨርፑሎችም ለተጫዋቹ የ20 ሚሊዮን ፓውንድ መሸጫ ዋጋ ለጥፈውበታል። ተጫዋቹን በጥብቅ ከሚፈልጉት ክለቦች መካከል ደግሞ ክሪስታል ፓላስ የመጀመሪያውን ስፍራ ይዟል። ሃሪ መጓየር (ሌስተር ሲቲ) በተለይ በአለም ዋንጫው ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ያሳየው ወጥና አስገራሚ አቋም በአሁኑ ሰአት ይህን ተከላካይ ተፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል። የሃሪ መጓየር ዋነኛ ፈላጊ ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሆሴ ሞሪንሆ ናቸው። ለተጫዋቹም እስከ 56 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የተጫዋቹ ባለቤት ሌስተር ሲቲ ደግሞ ለተከላካዮች ሪከርድ የሆነ 80 ሚሊዮን ፓውንድ ጠይቀዋል። አንቶኒ ማርሻል (ማንቸስተር ዩናይትድ) ከአሌክሲስ ሳንቼዝ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ መምጣት በኋላ አንቶኒ ማርሻል የቋሚ አሰላፍ ቦታ ለማግነት ተቸግሮ የቆየ ሲሆን፤ ለአለም ዋንጫው በብሄራዊ ቡድኑ አለመካተቱ ደግሞ ክለቡን እንዲለቅ ምክንያት ሊሆነው እንደሚችል ተገልጿል። በሌላ በኩል ተጫዋቹ ሁለተኛ ልጅ ሲወለድለት የቅድመ ውድድር ጨዋታውን ጥሎ ወደ ፈረንሳይ መመለሱ የማንቸስተሩ አሰልጣን ሆዜ ሞሪንሆን ያስደሰታቸው አይመስልም። መሸጫ ዋጋውም እስከ 80 ሚሊዮን ፓውንድ ይደርሳል ተብሏል። ሲሞን ሚኞሌ (ሊቨርፑል) ቤልጂየማዊው ግብ ጠባቂ በሊቨርፑል ቤት የቋሚ አሰላለፍ ቦታውን በካሪየስ ተነጥቆ ነው የቆየው። አሁን ደግሞ ብራዚላዊውን ግብ ጠባቂ አሊሰን ከሮማ ማስፈረማቸው ደግሞ የተጠባባቂውን ቦታ እንኳን እንዳያገኝ ሊያደርገው ይችላል። በአስገራሚ ሁኔታ የላሊጋው አሸናፊ ባርሴሎናዎች በግብ ጠባቂው ላይ ፍላጎት አሳይተዋል። አሮን ራምሴ (አርሰናል) ዌልሳዊው አማካይ ራምሴ በአርሰናል ቤት 10 ዓመት የቆየ ሲሆን፤ 300 ጨዋታዎችን ደግሞ ለክለቡ አድርጓል። አዲሱ የአርሰናል አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ራምሴን ጠቃሚ ተጫዋች ነው ብለው ቢገልጹትም፤ ከቼልሲ የቀረበላቸው የ35 ሚሊዮን ፓውንድ መገዣ ዋጋ እና የሊቨርፑል ፍላጎት ሃሳባቸውን ሊያስቀይራቸው እንደሚችል ይገመታል። ዊሊያን (ቼልሲ) ይህ የማይደክመው የሚባልለት የክንፍ ተጫዋች በአለም ዋንጫው ለሃገሩ ብራዚል በአምስቱም ጨዋታዎች በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ መግባት ችሏል። ባለፈው ዓመት ቼልሲ በኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ከማንቸስተር ይናይትድ ጋር ሲጫወቱ በቀድሞው አሰላጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ተጠባባቂ ቦታ ላይ መቀመጡ ደግሞ ልቡን እንዳስሸፈተው ይገመታል። የተጫዋቹ ዋነኛ ፈላጊ ሆነው እየተፎካከሩ ያሉት ደግሞ ሪያል ማድሪድ፤ ባርሴሎና እና ማንቸስተር ዩናይትድ ሲሆኑ፤ 65 ሚሊዮን እንዲፍሉ ተጠይቀዋል። ዊልፍሬድ ዛሃ (ክሪስታል ፓላስ) ምንም እንኳን የባለፈው ዓመት የውድድር ዘመን የመጀመሪያዎቹን ስድስት ጨዋታዎች ለቡድኑ መሰለፍ ባይችልም፤ ከዚያ በኋላ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ግን ዘጠኝ ግቦችን አስቆጥሮ ሶስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አቀብሏል። አሰልጣኝ ሮይ ሆድሰን ኮትዲቯራዊውን ተጫዋች በቡድናቸው ለማስቀረት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፤ ከተለያዩ ክለቦች እየቀረበላቸው ያለው ከፍተኛ ገንዘብ ሃሳባቸውን ሊያስቀይራቸው እንደሚችል ይገመታል።
news-51367708
https://www.bbc.com/amharic/news-51367708
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ አረፉ
ከኬንያ ነጻነት በኋላ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት ሆነው ከሃያ ዓመታት በላይ በብቸኝነት አገሪቱን የመሩት ዳልኤል አራፕ ሞይ በ95 ዓመታችው አረፉ።
ፕሬዝዳንት አራፕ ሞይ የምሥራቅ አፍሪካዋን አገር ኬንያን በበላይነት ለ24 ዓመታት የመሩ ሲሆን፤ አገሪቱ ከእንግሊዝ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ስልጣን የያዙ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። በሥልጣን ላይ በነበሩበትም ወቅት ሃገሪቷን በጠንካራ ክንዳቸው ገዝተዋል የሚባሉት ዳንኤል አራፕሞይ፤ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚተቿቸው አሉ። • ኬንያ የነዳጅ ድፍድፍ ወደ ውጭ መላክ ጀመረች • አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ኬንያ ውስጥ ተገኘ ሞይ ኬንያን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በብቸኝነት ሲመሩ ቆይተው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት ነበር እንደ ጎርጎሳውያኑ 1992 ሌሎች ፓርቲዎች ወደ ምርጫው መድረክ እንዲመጡ የፈቀዱት። በስልጣን ዘመናቸው ሙስና፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ግርፋትን ሰቆቃን በመፈጸም ቢወቀሱም በርካታ የሃገሬው ሰው ደግሞ በፍቅር ማሸነፍ ችለዋል ይባልላቸዋል። ሞይ ስልጣንን በማን አለብኝነት ይዞ በመቆየትና በጨቋኝነት ስማቸው ቢነሳም በዙሪያቸው በሚገኙ የጎረቤት ሃገራት አንዣቦ የነበረውን ጦርነት ወደ ሰላም በመቀየር ግን የተሻለ ሥራ መስራታቸው ይነገርላቸዋል። የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዝዳንት ጀሞ ኬንያታ መሞታቸውን ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጡት አራፕ ሞይ በመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዘመናቸውም 'ፈለግ' የሚለውን ቃል በሚተካው ስዋሂሊ "ንያዮ" መፈክር በርካታ ተከታዮችን አፍርተዋል። አገሪቱንም አሁን ወዳለችበት የዕድገት ደረጃ እንድትገባ መንገድ ማስጀመር እንደቻሉ ይነገራል። ነገር ግን በጎርጎሳውያኑ 1982 የተደረገባቸው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በአንድ ጊዜ ወደ አምባገነንነት ቀይሯቸዋል። በዚህም ሳቢያ በርካቶች ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ ሆነዋል። በተጨማሪም የጎሳ ግጭት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ግድያዎች ተፈጸሙ። • ኬንያ በአንድ ቢሊዮን ዶላር የሰራችውን የባቡር መንገድ ልትመርቅ ነው 'ፈለግ' የሚለው መፈክር ለሀገር ፍቅር ጥሪ ተደርጎ ቢቀነቀንም በኋላ ግን ግርፋት፣ የንጹሃን መታሰር፣ የመንግሥት ተቃዋሚዎችን መግደልና ያለፍርድ ማሰር የስልጣን ዘመናቸው መገለጫዎች ወደመሆን ተቀየረ። በ1990 ሞይ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ነበር። በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተደረገባቸው ማዕቀብ፣ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲን እንዲያሰፍኑና የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸውን እንዲገድቡ ጫናዎች ተደርገውባዋል።
52320882
https://www.bbc.com/amharic/52320882
ኮሮናቫይረስ፡ ትራምፕ ግዛቶችን ዳግም ወደ ስራ ለመመለስ የሚረዳ እቅድ አስተዋወቁ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአሜሪካ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለተለያዩ ግዛት አስተዳዳሪዎች በሚቀጥሉት ወራት ግዛቶቻቸውን ወደ ሥራ መመለስ የሚያስችል መመሪያ ሰጡ።
መመሪያው "አሜሪካን ዳግም ወደ ስራ መመለስ" የሚል ሲሆን ባለ ሦስት ምዕራፍ ነው ተብሏል። ይህም ግዛቶች ቀስ በቀስ ቤት ውስጥ የመቀመጥ ትዕዛዛቸውን እንዲያላሉ ያስችላቸዋል። • "የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም" ዶ/ር ፅዮን ፍሬው • የኮሮናቫይረስ ፅኑ ህሙማን እንዴት ያገግማሉ? ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለግዛቶቹ አስተዳዳሪዎቹ ከተሞቻቸውን ለእንቅስቃሴ የመክፈቱን ሂደቱን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በጋራ በመሆን ራሳቸው እንደሚያከናውኑት ቃል ገብተዋል። አሜሪካ እስካሁን ድረስ 654,301 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 32,186 መሞታቸው ታውቋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ አንዳንድ ከተሞች በዚህ ወር እንዲከፈቱ ሃሳብ አቅርበዋል። ትራምፕ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት ምን አሉ? ትራምፕ ትናንት ምሽት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "በጦርነታችን ላይ ቀጣዩ ምዕራፍ አሜሪካን ዳግም ወደ ስራ መመለስ ነው" ብለው ነበር። "አሜሪካና አሜሪካውያን ዳግም ወደ ስራ መመለስ ይፈልጋሉ" በማለትም " አጠቃላይ አገሪቱን ከእንቅስቃሴ ውጪ ማድረግ የረዥም ጊዜ መፍትሄና አዋጭ አይደለም" ብለዋል። አክለውም ለረዥም ጊዜ ሰዎች በቤት እንዲቀመጡ ማድረግ አደገኛ የሆነ የማህበረሰብ ጤና ቀውስ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚዎች፣ የጠጪዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ፣ የልብ እና የ" አካላዊና የአእምሮ" ጤና ችግሮችም ይስተዋላሉ ብለዋል። ትራምፕ ጤናማ ዜጎች "ሁኔታዎች ከፈቀዱ" ወደ ስራ መመለስ ይፈልጋሉ ያሉ ሲሆን፣ በተጨማሪም አሜሪካውያን አካላዊ ርቀታቸውን እንዲጠብቁ፣ ጤንነት ካልተሰማቸው ደግሞ ቤታቸው እንዲቀመጡ ይመከራል ብለዋል። • ቻይናውያን ሀኪሞች ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ነው ተባለ የአሜሪካን ኢኮኖሚ ዳግም ወደ ስራ ለመመለስ "ጥንቃቄ የተሞላበት አንድ እርምጃ በአንድ ጊዜ" ይወሰዳል ካሉ በኋላ የግዛቶቹን አስተዳዳሪዎች ግን "ማድረግ የሚፈልጉትን በጣም በጣም በፍጥነት" እንዲያከናውኑ ጠይቀዋል። የዲሞክራቶች መሪ የሆኑት ናንሲ ፒሎሲ ግን እቅዱን " አሻሚና ወጥነት የሌለው" ሲሉ አጣጥለውት ነበር። የትራምፕ እቅድ ምንድን ነው? ትራምፕ በዚህ በባለ 18 ገጽ ሰነድ ግዛቶች ዳግም እንዴት ወደ እንቅስቃሴ እንደሚመለሱ አስቀምጠዋል። በዚህ እቅድ መሰረት እያንዳንዱ ምዕራፍ በትንሹ 14 ቀናት ተሰፍረውለታል። በእያንዳንዱ ምዕራፍ ጥሩ የንጽህና አጠባበቅ እና ቀጣሪዎች በሰራተኞቻቸው መካከል አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚያስችል ፖሊሲ መፈፀሙን እንዲያረጋጡ፣ ምርመራ እና ንክኪዎችን መለየትን መከናወኑን እንዲያረጋገጡ ይጠይቃል። በመጀመሪያው ምዕራፍ አሁን ባለው የእንቅስቃሴ ገደብ አላስፈላጊ የተባሉ ጉዞዎች፣ በቡድን መሰባሰብ እንደተከለከሉ ናቸው። ነገር ግን ምግብ ቤቶች፣ የአምልኮ ስፍራዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች "ጥብቅ የሆነ የአካላዊ ርቀትን መጠበቅ ተግባራዊ ተደርጎ መስራት ይችላሉ" ተብሏል። በዚህ ወቅት የኮሮናቫይረስ መዛመት የማይታይ ከሆነ ወደ ምዕራፍ ሁለት የሚገባ ሲሆን በዚህም ወቅት አላስፈላጊ የተባሉ ጉዞዎች ተፈቅደዋል። በዚህ ወቅት ትምህርት ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ተከፍተው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ። ይህ ግን የሚሆነው የሚይዙት ሰው ቁጥር ተቀንሶ መሆኑ ተቀምጧል። በሶስተኛው ምዕራፍ ዝቅተኛ የሆነ የቫይረሱ ስርጭት የሚታይባቸው ግዛቶች "የህዝብ ቅርርብን" ሊፈቅዱ ይችላሉ። • ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት ድርጅት ሥራው በትክክል ምንድነው? አገሮችንስ የማዘዝ ሥልጣን አለው? ይህ ግን የሚሆነው አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንዳለ ሆኖ ነው ተብሏል። በዚህ ወቅት ሆስፒታልና የአዛውንቶች መንከባከቢያ ስፍራን መጎብኘት ይፈቀዳል፤ መጠጥ ቤቶችም የሚያስተናግዷቸውን ሰዎች ቁጥር ከፍ ያደርጋሉ። በዚህ ምዕራፍ አንዳንድ ግዛቶች ወደመደበኛ ህይወታቸው ተጠቃለው ሊገቡ እንደሚችሉ ተገልጿል። ይህ ሁሉ ግን በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ባሉባቸውና ቫይረሱ ዳግም በሚያገረሽባቸው ግዛቶች ረዘም ያለ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል በእቅዱ ላይ ተቀምጧል። ይህ ሦስተኛው ምዕራፍ "አዲሱ የህይወት ዘዬ" ነው የተባለ ሲሆን፣ ነገር ግን ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ህዝብ ከሚሰበሰበበ ስፍራዎች መራቅ አለባቸው ተብሏል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ግዛቶች ወደ ቀደመው ህይወታቸው እንዲመለሱና ኢኮኖሚው መንቀሳቀስ እንዲጀምር ይወትውቱ እንጂ የኒው ዮርኩ ገዢ አንድሪው ኩሞ ለቀጣዮቹ አንድ ወር ኒው ዮርካውያን ከቤት ሳይወጡ ይቆያሉ ሲሉ ተናግረዋል። በኒው ዮርክ በዚህ ሳምንት የቫይረሱ ስርጭት መረጋጋት ያሳያል የተባለ ሲሆን አሁንም ግን የሟቾቹ ቁጥር እየጨመረ ነው። የሚቺጋን፣ የኦሃዮ፣ የዊስኮንሲን፣ የሚኒሶታ፣ የኢሊኖይስ፣ የኢንዲያና እና የኬንታኪ አስተዳዳሪዎች ክልሎቻቸውን ወደ ስራ ለማስገባት በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል። እነዚህ አስተዳዳሪዎች ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ባይኖርም የተለያዩ የምጣኔ ሃነብት ዘርፎችም በምዕራፍ ምዕራፍ ከፋፍሎ ለማስጀመር ማቀዳቸው ታውቋል። በሚችጋን 1,700 ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሲሆን አስተዳዳሪው ግሪቸን ዊትሜር በወሰዱት የቤት መቀመጥ እርምጃ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነበር።
news-54245287
https://www.bbc.com/amharic/news-54245287
ትራምፕ፡ ለዋይት ሀውስ መርዝ የላከችው ግለሰብ በአሜሪካና በካናዳ ድንበር ላይ በቁጥጥር ስር ዋለች
ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሪሲን የተሰኘውን መርዝ የያዘ ጥቅል ልካለች በሚል የተጠረጠረች ሴት በቁጥጥር ስር መዋሏን የአሜሪካው የስደተኞች ቢሮ አስታውቋል።
ማንነቷ ያልተገለፀው ይህች ሴት በኒውዮርክ፣ ቡፋሎ ድንበር አቋርጣ ወደ ካናዳ ልትገባ ስትል መያዟ የተገለፀ ሲሆን የጦር መሳርያ ይዛ እንደነበርም ተዘግቧል። ገዳይ የሆነውን መርዝ የያዘው ደብዳቤ ከካናዳ እንደተነሳ እንደሚታመን በስፍራው የሚገኙ መርማሪዎቹ ተናግረዋል። ደብዳቤው የተገኘው ዋይት ሃውስ ከመድረሱ በፊት ባለፈው ሳምንት ነበር። ሪሲን በተፈጥሮ የጉሎ (ካስተር) ፍሬ ውስጥ የሚገኝ መርዝ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋይት ሃውስ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚያስቡ ሰዎች ሲጠቀሙት ተስተውሏል። የትራምፕ አስተዳደር እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ አስተያየት አልሰጠም። የፌደራሉ ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) እና የደህንነት ቢሮው ጥቅሉን መመርመር የጀመሩት በአንድ በማቀነባበሪያ ድርጅት ውስጥ ወደ ዋይት ሃውስ ሊላክ እየተዘጋጀ ሳለ ነው። ኤፍቢአይ "በዚህ ወቅት የታወቀ የሕብረተሰብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነገር የለም" ማለቱን ሲኤንኤን ዘግቧል። ተጠርጣሪዋ በቴክሳስ ለሚገኙ አምስት የተለያዩ አድራሻዎች የሪሲን መርዝን የያዘ ጥቅል መላኳ የተጠረጠረ ሲሆን ከተላከላቸው መካከልም የማረሚያ እና የፖሊስ ቢሮዎች ይገኙበታል ተብሏል። እንደ ባለስልጣናቶቹ መግለጫ ከሆነ በጥቅሎቹ ላይ ሪሲን የተሰኘው መርዝ መኖሩ የፋ የተደረገው ኤፍቢአይ በተደጋጋሚ ፍተሻ ካደረገ በኋላ ነው። የካናዳ ፖሊስ ቅዳሜ እለት "ወደ ዋይት ሃውስ ከተላከ አጠራጣሪ ደብዳቤ ጋር በተያያዘ" ከኤፍ ቢአይ ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑን ተናግሮ ነበር። ተጠርጣሪዋ ማክሰኞ እለት ቡፋሎ ውስጥ ፍርድ ቤት ትቀርባለች። ሪሲን ገዳይ መርዝ ሲሆን ከተዋጠ፣ ወደ ውስጥ በትንፋሽ ከተሳበ፣ ወይንም በመርፌ ከተወጉት ማስመለስ፣ ማቅለሽለሽ ሊከሰት እንዲሁም የውስጥ አካል ሊደማ እና ስራ ሊያቆም ይችላል። እስካሁን ድረስ ሪሲንን ለመፈወስ የሚያገለግል መድሃኒት መኖሩ አይታወቅም። ለመርዙ የተጋለጠ አንድ ሰው እንደ ወሰደው መጠን ከ36 ሰዓታት እስከ 72 ሰዓታት ባለው ጊዜ ውስጥ ይሞታል። የአሜሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጣር እንዳስታወቀው መርዙ፣ ለተለያዩ የሽብር ተግባራት እየዋለ የሚገኘው ይህ መርዝ፣ በዱቄት፣ በጤዛ እንዲሁም በእንክብል መልክ ሊዘጋጅ ይችላል። ዋይት ሃውስ እንዲሁም ሌሎች የፌደራል መስሪያ ቤቶች ከዚህ ቀደምም ሪሲን የያዘ ጥቅል ተልኮላቸው ያውቃል። በ2014 በሚሲሲፒ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ለባራክ ኦባማ እና ሌሎች ባለስልጣናት የሪሲን ብናኝ የተነከረ ደብዳቤ በመላኩ 25 ዓመት እስር ተፈርዶበት ወህኒ ተወርውሯል። ከአራት ዓመት በኋላ ደግሞ የቀድሞ ወታደር ለፔንታጎንና ለዋይት ሀውስ መርዝ የያዘ ደብዳቤ በመላኩ ክስ ተመስርቶበታል።
news-56333482
https://www.bbc.com/amharic/news-56333482
የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ ኢትዮጵያ ያደረገቻቸው አምስት ምርጫዎች በጨረፍታ ሲቃኙ
ኢትዮጵያ ስድስተኛ አገር አቀፍ ምርጫን ለማካሄድ ቀን ቆርጣ በዝግጅት ላይ ናት። በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ምርጫ ቦርድ በያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን የማስመዝገቢያ ጊዜ ተጠናቋል።
በ673 የምርጫ ክልሎች ላይ ለሚከናወነው ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ የቀረው ጊዜ 12 ሳምንታት ገደማ ነው። ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቷን የመራው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በ1984 የብሔራዊ፣ ክልላዊ፣ የዞን እና የወረዳ ምክር ቤት ምርጫ ተካሂዷል። ይህም በሽግግር መንግሥቱ ለነበረው የተወካዮች ምክር ቤት አባልነት መንግሥት ምስረታ ሲሆን በወቅቱ የነበረው የብሔራዊ፣ ክልላዊና የወረዳ ምክር ቤት አባላት ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅም ምርጫውን አስተባብሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕገ መንግሥቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አገሪቷ በአጠቃላይ አምስት ጠቅላላ ምርጫዎችን አካሂዳለች። ከዚህም በተጨማሪ የማሟያና የአካባቢ ምርጫዎችን ጨምሮ ስድስት ሕዝበ ውሳኔዎች በአጠቃላይ 14 ምርጫዎች ተካሂደዋል። ወደ ኋላ መለስ ብለን አገሪቱ ባደረገቻቸው አምስት ጠቅላላ ምርጫዎች ምን ያህል ሕዝብ መርጧል፣ የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ብዛት፣ በምርጫዎቹስ ማን አሸነፈ የሚለውን ታሪካዊ ዳራ እንቃኛለን። ምርጫ 2007 ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ለማካሄድ እየተዘጋጀችበት ካለው ምርጫ በፊት ያደረገችው የመጨረሻ ምርጫ ነው። ምርጫ 2002 ታሪካዊ የሚባለውን ምርጫ 1997ን አልፎ የተደረገው የ2002 አራተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ የተከናወነው ግንቦት 15/2002 ነበር። ምርጫው በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተከናውኗል። ምርጫ 1997 በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የ1997 ዓ.ም ምርጫ እንደ ትልቅ ምዕራፍ የሚታይ ነበር። የፖለቲካ ምሀዳሩ ከሌላው ጊዜ በተለየ ከፈት ማለቱና በተለያዩ የፖሊሲ አማራጮች ዙሪያ የተካሄዱት የጦፉ ክርክሮች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣምረው ጥምረቶችን ፈጥረው መምጣትና የምርጫ ቅስቀሳዎች ሂደቱን አጓጊ አድርገውት ነበር። ምርጫ 1992 ምርጫ 1987 ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
news-54063387
https://www.bbc.com/amharic/news-54063387
ጃዋር መሐመድ ፡ ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ ጃዋርን የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ አደረገ
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በእነ አቶ ጃዋር የቅድመ ምርመራ መዝገብ ላይ የቀረበውን የዋስትና መብት ውድቅ አደረገ።
አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ ሃምዛ ቦረና አቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰምቶ በመጨረሱ ፍርድ ቤቱ ክስ የሚመስርትበትን ጊዜ ለመስጠትና ተጠርጣሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ትዕዛዝና ውሳኔ ለማስተላለፍ ነበር ለዛሬ ቀጠሮ የያዘው። ፍርድ ቤቱ በነሐሴ 29/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት አቃቤ ሕግ ክስ ለመመስረት፣ የቅድመ ምርመራ ግልባጭ ከደረሰው በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንደሚመሰርት ያመለከተ ሲሆን፣ ጠበቆች በበኩላቸው የቅድመ ምርመራ ከተጠናቀቀበበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ክስ ይመስርት በማለት ተከራክረዋል። በዛሬው ችሎት አቃቤ ሕግ ከ1 እስከ 10 ባሉ ተጥረጣሪዎች ማለትም በአቶ ጀዋር መሐመድ፣ በአቶ በቀለ ገርባ፣ በአቶ ያለምወርቅ አሰፋ፣ በአቶ ጌቱ ተረፈ፣ በአቶ ታምራት ሁሴን፣ በአቶ በሽር ሁሴን፣ በአቶ ሰቦቃ ኦልቀባ፣ በአቶ ኬኔ ዱሜቻ፣ በአቶ ዳውድ አብደታ እና በአቶ ቦጋለ ድሪሳ ላይ እስከ መስከረም 8/ 2013 ዓ.ም ድረስ ክስ እንዲመሰርት ወስኗል። የቅድመ ምርመራ ግልባጭም ለዐቃቤ ሕግና ጠበቆች ከጳጉሜን 2/2012 እስከ ጳጉሜን 5/2012 ዓ.ም ድረስ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱ አዟል። በሌላ በኩልበእነ አቶ ጃዋር ቅድመ ምርመራ መዝገብ ከ11-14 ባሉት ተጠርጣሪዎች፤ በአቶ ሐምዛ አዳነ፣ በአቶ ሸምሰዲን ጣሃ፣ በአቶ ቦና ቲብሌና በአቶ መለሰ ድሪብሳ ላይ ዐቃቤ ሕግ ማስረጃ አቅርቦ ስላላሰማ ክስ የሚኖረው ከሆነ በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል። የዋስ መብት ፍርድ ቤቱ በነሐሴ 29/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተጠርጣሪዎችና ጠበቆቻቸው የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ችሎቱን ጠይቀው ነበር። በተለይ ጠበቆች "ወንጀል እንደፈፀሙ የሚያሳይ ነገር እስከሌለ ድረስ ተጠርጣሪዎች እስር ቤት መመላለስ የለባቸውም። የዋስ መብት ሊጠበቅላቸው ይገባል" በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋል። በሌላ በኩል ዐቃቤ ሕግ ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል ከ15 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚያስችል በመሆኑ የዋስ መብታቸው ሊጠበቅላቸው አይገባም በማለት ተከራክሯል። ፍርድ ቤቱም በዚሁ ችሎት የተጠርጣሪዎችና ጠበቆቻቸው ያቀረቡትን የዋስ መብት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ እስከ መስከም 8/2013 ዓ.ም እስር ቤት እንዲቆዩ አዟል። የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልተተገበረም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በነሐሴ 29/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ለየብቻቸው መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አመልክተው፤ ማረሚያ ቤቱ ለየብቻቸው መታሰራቸው ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ አንድ ለይ እንዲሆኑ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁንና ይህ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዳልሆነ ተጠርጣሪዎችና ጠበቆቻው ተናግረዋል። አቶ ጃዋር መሐመድ "ፖሊሶች ሊተባበሩን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ከላይ ባለባቸው ጫና ምክንያት ትዕዛዙን ተግባራዊ ማድረግ አልቻሉም። ፖሊስ ትዕዛዙን ለመፈፀም የፍርድ ቤት ድጋፍ ያስፈልጋገዋል" በማለት ተናግረዋል። በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የተጠርጣሪዎች ቆይታ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር የኔነሽ ገ/እግዚአብሔር፣ "ትዕዛዙን የበላይ ዳይሬክተር ነው የተቀበለው። ለምን እንዳልተፈፀመ ግን ምክንያቱን አላውቀውም" በማለት በችሎቱ ላይ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱም የፌደራል ፖሊስ ማረሚያ ቤቶች አስተደደርና ጉዳዩ የሚመለከተው ክፍል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ትዕዛዙን እንዲፈጽሙ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም አፈጻጸሙን ረፖርት እንዲያርግ አዟል። በችሎት ላይ ምን ተባለ? በዛሬው ችሎት ላይ አቶ ጃዋር ምስጋና ማቅረብ እንደሚፈልጉና ለመንግሥትም መልዕክት እንዳላቸው የተናገሩ ሲሆን፣ ለዳኞችና ለፖሊስ ምስጋና አቅርበዋል። የመናገር መብታቸው እንደተጠበቀላቸውና ፖሊሶችም ጥሩ እንክብካቤ እያደረጉላቸው እንደሆነ ጨምረው ተናግረዋል። " ይኹን እንጂ ይህ እንክብካቤ ለታዋቂ ሰዎች ብቻ ሳይሆን፤ ለሁሉም ሰዎች መሆን እንዳለበት በማንሳት በሌሎች ስፍራዎች ደንብ ልብስ የለበሱት ፖሊሶች "ሰዎችን እየገደሉ ነው" በማለት ተናግረዋል። አክለውም " እኛ የፖለቲካ ታሳሪዎች ነን፤ ገድለን፣ ሰርቀን ወይንም ዘርፈን አይደለም እዚህ የተገኘነው፤ የታሰርነው ለኦሮሞ ሕዝብ ስለታገልን ነው" ያሉት አቶ ጃዋር፣ የፍትህ አካላትም፣ ፍትህ ከፖለቲካ ሥልጣንና ከፖለቲካ ድርጅት በላይ እንዲሆን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል አቶ በቀለ ገርባ "በእስካሁኑ ቆይታ ለፍርድ ቤቱ፣ ለአቃቢያነ ሕግ እና ለፖሊሶች ክብር አለን" ብለዋል። " የፖለቲካ ሰዎች ተመርጠው የዋስ መብት የማያሰጥ አንቀጽ እየተፈለገባቸው እየተከሰሱ ነው" ያሉት አቶ በቀለ መንግሥት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መወያየት እንዳለበት ተናግረዋል።
news-49493107
https://www.bbc.com/amharic/news-49493107
የዝሆን ግልገሎች ለዓለም ንግድ እንዳይቀርቡ ታገደ
በስዊዘርላንድ ጀኔቫ በተካሄደው ጉባዔ ከአፍሪካ የዝሆን ግልገሎችን በማደን ለእንስሳት ማቆያ እንዳይሸጡ የሚከለክለው ሕግ ፀድቋል።
አደጋ ላይ በሚገኙ የእንስሳት ዝርያዎች ዓለም አቀፍ ንግድ ላይ የሚያተኩረው ጉባዔ ተሳታፊዎች በጉዳዩ ላይ ለቀናት ከተከራከሩበት በኋላ ሕጉን ለማጥበቅ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታውቋል። •የባቢሌ ዝሆኖች ህልውና አደጋ ላይ ነው እግዱ በ87 አብላጫ ድምፅ ድጋፍ እና በ29 ተቃውሞ ካገኘ በኋላ እንዲፀድቅ ተወስኗል። ይሁን እንጂ ዝሆኖችን ወደ ውጭ በመላክ የምትታወቀው አፍሪካዊት ሃገር ዚምባብዌ ልክ እንደ አሜሪካ ሁሉ እግዱን ተቃውማለች። ዚምባብዌ እንቅስቃሴውን አጥበቃ በዘመቻ ስትቃወም የነበረ ሲሆን የአውሮፓ ሕብረትም በዓለም ላይ ያለውን የእንስሳት ዝርያ ስብጥር እንዳይኖረው ያደርጋል ሲሉ መጀመሪያ አካባቢ ተቃውመውት ነበር። ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ዝሆን በብዛት የሚገኝባቸው ዚምባብዌና ቦትስዋና 'ተቀባይነት ላላቸውና ትክክለኛ ለሆኑ' ተቀባይ ሃገራት ዝሆኖችን ወደ ውጭ ለመላክ ይፈቅዱ ነበር። በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ዝሆኖች የሚገኙባት ቦትስዋና በዚህ በያዝነው ዓመት ዝሆኖችን ማደን የሚከለክለው ሕግ፣ ገበሬዎችንና ከዚህ በፊት በማደን ገቢ ያገኙ የነበሩ ግለሰቦችን እየጎዳ ነው በሚል መፍቀዷ ይታወሳል። • ቦትስዋና ዝሆን ማደን ፈቀደች ዚምባብዌ ከጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2012 ጀምሮ ከ100 በላይ የሚሆኑ የዝሆን ግልገሎችን በመያዝ ለቻይና የእንስሳት ማቆያ መላካቸውን ሁዩማን ሶሳይቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። በመሆኑም ትናንት የተላለፈው ውሳኔ የዝሆን ንግድን ቁጥጥር እንዲጠብቅ ያደርጋል ተብሏል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ዝሆኖች ከዱር ተይዘው በእንክብካቤ በሚቆዩበት በየትኛውም የዓለማችን አካባቢ መቆየት የሚችሉ ሲሆን ይህ ግን የሚቻለው በከተማዋ የኮሚቴ አባላት ሲፀድቅ ይሆናል። • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። ይሁን እንጅ የአውሮፓ ህብረት በልዩ ሁኔታ መላክ እንደሚቻልና በእንስሳት ማቆያ ያሉ ዝሆኖችን ማዛወር እንደሚቻል ሕጉ የተወሰነ መሻሻል ከተደረገበት በኋላ ሃሳቡን ቀይሯል። "ይህ ማለት አንድም ዝሆን ከዱር ተይዞ በውጭ አገር ለእንስሳት ምቹ በሆኑ ማቆያዎች አይገቡም ማለት አይደለም" ሲሉ የቦርን ፍሪ ፋውንዴሽን ፕሬዚደንት ዊል ትሬቨርስ ተናግረዋል። አክለውም እግዱ በተለይ በወደ ሩቅ ምስራቅ በጅምላ ያለ አግባብ የሚላኩ ዝሆኖችን ለመቆጣጠር ሕጉን ማጥበቅ አስፈላጊ እንደሆነም ገልፀዋል።
news-56170892
https://www.bbc.com/amharic/news-56170892
አደንዛዥ እፅ፡ በ'ቢሊዮኖች ዩሮ' የተገመተ ኮኬይን በጀርመንና ቤልጂየም ወደብ ተያዘ
የጀርመንና የቤልጂየም ጉምሩክ ባለሥልጣናት ከ23 ቶን በላይ የኮኬይን እፅ መያዛቸው ተገለፀ።
በጀርመን የተገኘው ኮኬይን ከ1 ሺህ በላይ ጣሳዎች ውስጥ ተደብቆ ነበር በመጠኑ ከዚህ በፊት አጋጥሞ የማያውቅ ነው የተባለው ኮኬይን፤ መዳረሻው ኔዘርላንድስ እንደነበር ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የጀርመን ባለሥልጣናት ከፓራጓይ በአምስት የማጓጓዣ ኮንቴይነር የተጫነ 16 ቶን ኮኬይን በሃምበርግ ወደብ ላይ በቁጥጥር ሥር አውለዋል። የኔዘርላንድስ ፖሊስ በደረሰው ጥቆማም በአንትወርፕ የቤልጂየም ወደብ ተጨማሪ 7.2 ቶን ኮኬይን ተይዟል። የጀርመን ባለሥልጣናት የኮኬይን እፁ በ'ቢሊየኖች ዩሮ' ዋጋ እንደሚገመት ተናግረዋል። እፁን በማዘዋወር የተጠረጠረው የ28 ዓመት ወጣት በኔዘርላንድስ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የደች ፖሊስ ረቡዕ እለት አስታውቋል። የጉምሩክ ባለሥልጣናት እንዳሉት የተያዘው ኮኬይን በመንገድ ላይ ዋጋ በቢሊየኖች ዩሮ ይገመታል። የጉምሩክ በላሥልጣናት እንዳሉት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተካሄዱ ሁለት ፍተሻዎች 'እጅግ ብዙ መጠን' ያለው የኮኬይን እፅ ለመያዝ ምክንያት ሆኗል። እፁ በቤልጂየም አንትወርፕ ወደብ የተያዘው ከፓናማ እንጨት በተሰራ ሳጥን ተሞልቶ በኮንቴኔር ውስጥ ተደብቆ ነው። ከዚህ ቀደም ከፓራጓይ ወደ አውሮፓ ገብቶ የነበረውና በሰሜናዊ የጀርመን ከተማ ሃምበርግ የተያዘው ኮኬይን ደግሞ በቆርቆሮ ጣሳ ተሞልቶ ነበር የተገኘው። የጉምሩክ ባለሥልጣናቱ ከፓራጓይ የገባውን ኮንቴነር በጥብቅ ለመፈተሽ የወሰኑትም በጭነቱ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ነገሮችን ካስተዋሉ በኋላ ነበር። "በኮኬይኑ የተሞሉት የቆርቆሮ ጣሳዎች ከኮንቴነሩ በር ጀርባ ከተጫኑ ሌሎች እቃዎች መሃል ተሰግስገው ነበር" ብለዋል ባለሥልጣናቱ። መርማሪዎች ኮንቴኔሮቹ ላይ ባደረጉት ፍተሻም ከ1ሺህ 700 በላይ ጣሳዎች ውስጥ የታሸገ የኮኬይን እፅ ማግኘት ችለው ነበር። የጀርመን ጉምሩክ እንዳለው ይህ እስካሁን በአውሮፓ ከተያዘው እፅ በጣም ከፍተኛው ሲሆን በዓለም ደረጃም በአንድ ጊዜ የተያዘ ከፍተኛ መጠን ያለው እፅ ነው። የሀምበርግ ጉምሩክ ባለሥልጣን ሬኔ ማትሽክ ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት 16 ቶን የሚመዝነው እፅ ከ1.5 ቢሊየን እስከ 3.5 ቢሊየን ዩሮ ይገመታል። ሃምበርግ ወደብ በትልቅነቱ ከአውሮፓ ሦስተኛው ሲሆን በጀርመን ደግሞ በጣም ትልቁ ነው። ፓራጓይ ለዓመታት ቁልፍ የእፅ ማሸጋገሪያ አገር ሆናለች። ከጎረቤት አገር ብራዚል አደገኛ እፅ አዘዋዋሪ ቡድኖች ወደ ፓራጓይ በመሻገር በርካታ የእፅ ዝውውር ተግባራትን ያከናውናሉ። እፁም በአብዛኛው ከፓራጓይ በኮንቴነር ተጭኖ ወደ አውሮፓ የወደብ ከተሞች ይወሰዳል። ጥቅምት ወር ላይ ከደቡብ አሜሪካ የመጣ 11 ቶን ኮኬይን በአንትወርፕ ወደብ ተይዟል። ከሁለት ዓመታት በፊት ነሐሴ ወር ላይ ደግሞ፤ በሃምበርግ ወደብ ቦሎቄ ነው በሚል ወደ አውሮፓ ሊገባ የነበረ 4.5 ቶን ኮኬይን በጉምሩክ ባለሥልጣናት በቁጥጥር ሥር ውሏል። በወቅቱ ይህ ኮኬይን ከፍተኛ ጥራት ያለው በመሆኑ 1 ቢሊየን ዩሮ ዋጋ እንደሚያወጣ ተገልጾ ነበር። ከፍተኛ ጥራት ያለው ኮኬይን ዋጋን ለመጨመር፤ እፁን በመቆራረጥና ከሌላ እፅ ጋር በመደባለቅ በመንገድ ላይ ይሸጣል። ባለፈው ዓመትም 102 ቶን ኮኬይን ወደ አውሮፓ ሊገባ ሲል መያዙ ይታወሳል።
news-47052866
https://www.bbc.com/amharic/news-47052866
የቬንዙዌላ ፍርድ ቤት በተቃዋሚ መሪው ላይ የጉዞ እገዳ ጣለ
የቬንዙዌላ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቃዋሚ መሪ ጁአን ጉአኢዶ ከሃገር እንዳይወጡ የጉዞ እገዳ እና የባንክ ሂሳብ እንዳያንቀሳቅሱ ገደብ ጣለ።
እራሳቸውን ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ብለው የሰየሙት ጁአን ጉአኢዶ የተቃዋሚ መሪው ጁአን ጉአኢዶ ባለፈው ሳምንት እራሳቸውን የቬንዙዌላ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አድርገው መሾማቸው ይታወሳል። የተቃዋሚ መሪው የአሜሪካ እና የካናዳ መንግሥትን ጨምሮ የበርካታ ሃገራት እውቅናን አግኝተዋል። ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ደግሞ የሩሲያ እና የቻይና ድጋፍ እንዳልተለያቸው ይናገራሉ። አሜሪካ በዲፕሎማቶቿ እና በተቃዋሚ መሪው ጁአን ጉአኢዶ ላይ የሚደርሱ ማናቸውም አይነት ማስፈራሪያዎች ላይ ''የማያዳግም እርምጃ ያስወስዳሉ'' ስትል የቬንዙዌላ መንግሥትን አስጠንቅቃ ነበር። • አሜሪካ የቬንዙዌላ መንግሥትን አሰጠነቀቀች • ቬኔዙዌላ ምናባዊ ገንዘብ ይፋ አደረገች ቬንዙዌላ ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን እያስተናገደች ትገኛለች። እጅግ የተጋነነ የዋጋ ግሽበት፣ መድሃኒት እና ምግብን ጨምሮ የመሰረታዊ ቁሶች እጥረት በርካቶች ሃገሪቱን ለቀው እንዲሰደዱ ምክንያት እየሆኑ ነው። ኒኮላስ ማዱሮ በቅርቡ በሃገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ አሸንፊያለሁ በማለት ከ20 ቀናት በፊት ነበር ሁለተኛ ዙር የስልጣን ዘመናቸውን የጀመሩት። ማዱሮ አሸነፍኩ ባሉበት ምርጫ በርካታ ተቃዋሚዎች በምርጫው እንዳይሳተፉ ተደርገው ነበር። ለፕሬዚዳንት ማዱሮ ታማኝ ነው የሚባለው የሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተቃዋሚ መሪው ጁአን ጉአኢዶ ''በሪፐሊኩ ሰላም እንዲደፈርስ በማድረጋቸው'' ቅድመ ምርመራዎች እስኪጠናቀቁ ''ሃገር ለቀው እንዳይወጡ ተከልክለዋል'' ሲል ውሳኔውን አስተላልፏል። የተቃዋሚ መሪው በጉዳዩ ላይ ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሲሰጡ ''ይህ አዲስ አይደለም'' ያሉ ሲሆን ጨምረውም ''ስጋት አለኝ፤ ይሁን እንጂ ማድረግ ያለብንን እያደረግን ነው'' ብለዋል። • ካናዳ የቬንዝዌላን አምባሳደር አባረረች የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪው ጆን ቦልተን ማስፈራራት የሕግ ጥሰት ነው ሲሉ የቬንዙዌላን መንግሥት አስጠንቅቀው ነበር። በተጨማሪ ''ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው'' በማለት የኃይል እርምጃ ከአማራጮቹ መካከል አንዱ እንደሆነ ጠቁመው አልፈዋል። እራሳቸውን ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ብለው የሰየሙት ጁአን ለረቡዕ እና ቅዳሜ ለተቃውሞ ሰልፍ ደጋፊዎቻቸውን አደባባይ ጥርተዋል። ስፔን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሃገራት በቬንዙዌላ በስምንት ቀናት ውስጥ ምርጫ ካልተጠራ ለተቃዋሚው የፕሬዚዳንትነት እውቅና እንሰጣለን ብለዋል። ፕሬዚዳንት ማዱሮ ግን የአውሮፓውያኑን ሃገራት ማስጠንቀቂያ አጣጥለውታል።
news-53601771
https://www.bbc.com/amharic/news-53601771
ምርጫ፡ በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ አምስት ፓርቲዎች ተመዘገቡ
በትግራይ ክልል ይካሄዳል በተባለው ክልላዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ አምስት የፖለቲካ ድርጅቶችና 11 የግል እጩዎች መመዝገባቸው የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ኮሚሽኑ በምርጫው መሳተፍ የሚፈልጉ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ከሐምሌ 21/2012 እስከ ሐምሌ 23/2012 እንዲመዘገቡ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ግለሰቦችና የፖለቲካ ፓርቲዎች መመዝገባቸው ተገልጿል። በዚህም መሰረት በምርጫው ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው የተመዘገቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ህወሓት፣ ባየቶና፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ የትግራይ ነጻነት ድርጅትና አሲምባ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ናቸው። በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች መካል አንዱ የሆነው ባይቶና ከተለያዩ አቅጣጫዎች ተግዳሮቶች እንዳሉ በመግለጽ፤ ይህ ግን በክልሉ ከሚካሄደው ምርጫ ውጪ እንደማያደርገው ገልጿል። ድርጅቱ እንዳለው "ከፌደራል መንግሥት የሚመጣ ጫናን እንዲሁም በትግራይ ክልል መንግሥት አማካይነት እየተደረገ ያለውን አፈና ተቋቁመን ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ወስነናል" ሲል መግለጫ ሰጥቶ ነበር። ከዚህ ባሻገር በትግራይ ክልል ላይ ትኩረት አድርገው የሚንቀሳቀሱት አረና ትግራይ እና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ድርጀት በበኩላቸው ክልሉ ሊያካሂድ ያቀደው ምርጫ ሕገወጥ እንደሆነ በመግለጽ እንደማይሳተፉ ቀደም ብለው ማስታወቃቸው ይታወሳል። በቅርቡ የተቋቋመው የክልሉን የምርጫ ኮሚሽን የሚመሩት ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም በሰጡት መግለጫ፤ የመራጮች ምዝገባ እና ምርጫ የሚደረግበት ዕለት የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም ከዛሬ ጀምሮ ለምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎች የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶላቸው በፖሊሲያቸው ላይ ክርክር ያደርጋሉ ሲለ ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፤ ከምርጫው በተያያዘ ኮሚሽኑ በርካታ የሚጠበቁበትን ሥራዎች ለማከናወን መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል። የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ስድስተኛው ዙር ምርጫን እንዲያስፈጽምለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ከተደረገ በኋላ የተናጠል ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ወስኗል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሰኔ ወር ባካሄደው ስብሰባ፤ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። የትግራይ ክልል ምክር ቤት ግን ሰኔ 5/2012 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ምርጫ እንዲካሄድ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አሳልፎ በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ የክልሉን የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሚያ፣ የምርጫ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጆችን አጽድቋል። ይህንን ተከትሎም ሐምሌ 9/2012 ዓ.ም የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የሚካሄደውን ክልላዊ ምርጫ የሚያስፈጽመውን ኮሚሽን የሚመሩ አምስት ሰዎችን መሾሙ ይታወሳል።
56151142
https://www.bbc.com/amharic/56151142
ዩናይትድ አየር መንገድ ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ አገደ
የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ 24 ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ አገደ።
አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን ከበረራ ያገደው ባሳለፍነው ቅዳሜ ከአውሮፕላኖቹ አንዱ ሞተሩ ላይ አደጋ ካጋጠመው በኋላ ነው። አውሮፕላኑ 231 መንገደኞችንና አስር የበረራ አስተናጋጆችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን በዴንቨር አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል። እስካሁን በአደጋው የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። የአውሮፕላኑ ስብርባሪዎችም በአቅራቢያው ባሉ የመኖሪያ ቦታዎች ወዳድቀው ተገኝተዋል። ይህንንም ተከትሎ ጃፓን ተመሳሳይ ፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞተር የተገጠመላቸውን ቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን የሚጠቀሙ ሁሉም አየር መንገዶች አየር ክልሏ እንዳይገቡ ጠይቃለች። ወደ ሃዋይ ሆኖሉሉ ከተማ ለመብረር የተነሳው ዩናይትድ 328 አውሮፕላን በቀኝ በኩል ባለው ሞተሩ ላይ አደጋ እንደገጠመው የፌደራል አቪየሽን አስተዳደር ገልጿል። አደጋውን ተከትሎም አስተዳደሩ የፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞተር የተገጠመላቸው ቦይንግ 777 አውሮፕኣኖች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ አዟል። "አደጋው ካጋጠመ በኋላ ሁሉንም የደህንነት መረጃዎች ተመልክተናል" ሲሉ የፌደራል አቪየሽን አስተዳዳሪ ስቴቭ ዲክሰን በመግለጫቸው ተናግረዋል። በመጀመሪያ ደረጃ በተገኘው መረጃ መሠረትም፤ ምርመራው በቦይንግ 777 አውሮፕላኖች ላይ ብቻ ለሚገጠመው ለዚህ የሞተር ሞድል የተለየ የሆነው ወደ ሞተሩ ንፋስ ማስገቢያ [ፋን] ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ድምዳሜ ላይ ደርሰናል ብለዋል። የፌደራል አቪየሽን አስተዳደርም ከሞተር አምራቹ ድርጅት እና ከቦይንግ ተወካዮች ጋር እየተነጋገረ ነው። የአገሪቷ የመጓጓዣ ደህንነት ቦርድ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ እንደሚያመላክተው አውሮፕላኑ አደጋ ያጋጠመው በቀኝ ሞተሩ ላይ ሲሆን፤ በሌሎች ሁለት ንፋስ ማስገቢያ [ፋን] ተሰነጣጥቀዋል። ሌሎቹም እንዲሁ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጂ የአውሮፕላኑ ዋነኛ አካል ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል መሆኑን ቦርዱ ገልጿል። "በኃይል ሲርገፈገፍ ነበር" ይህ አደጋ ባጋጠመው አውሮፕላን ላይ ተሳፍራው የነበሩት መንገደኞች ለበረራ እንደተነሱ ወዲያውኑ ከፍተኛ ፍንዳታ እንደሰሙ ተናግረዋል። ከመንገደኞቹ አንዱ የሆኑት ዴቪድ ዴሉሲያ "አውሮፕላኑ በኃይል ሲነቃነቅ ነበር። ከዚያም ከፍ ብሎ መብረር ስላልቻለ ወደ ታች መውረድ ጀመረ" ብለዋል። አክለውም እርሳቸውና ባለቤታቸው ምንአልባት አደጋ ካጋጠመን በሚል የኪስ ቦርሳቸውን ኪሳቸው ውስጥ እንደከተቱት ተናግረዋል። የብሩምፊልድ ከተማ ፖሊስ የአውሮፕላኑ የሞተሩ ሽፋን ስባሪ በአንድ መኖሪያ ቤት አትክልት ቦታ ላይ መውደቁን የሚያሳይ ምስል አጋርቷል። ሌሎቹ ስብርባሪዎችም በከተማዋ አንድ የእግር ኳስ ሜዳ ላይ ወድቀው ታይተዋል። ከአውሮፕላኑ ላይ በወደቀው ስብርባሪ ግን የተጎዳ አለመኖሩ ተገልጿል። በጃፓን የፕራት እና ዊትኒ 4000 ሞደል ሞተር የተገጠመላቸው ሁሉም 777 አውሮፕላኖች ተጨማሪ ማስታወቂያ እስኪነገር ድረስ አየር ክልሏ መግባት ያቆማሉ። ይህም ለበረራ መነሳትን፣ ማረፍን እና በአገሪቷ የአየር ክልል ላይ መብረርን ያካትታል። ባለፈው ታህሳስ ወር የጃፓን አየር መንገድ አውሮፕላን በግራ በኩል ያለው ሞተሩ መስራት ባለመቻሉ ወደ ናሃ አየርማረፊያ እንዲመለስ ተገዶ ነበር። አውሮፕላኑ ባለፈው ቅዳሜ አደጋ ካጋጠመው የዩኒይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር በተመሳሳይ የ26 ዓመት እድሜ ያለው ነው። በ2018፤ አንድ የዩናይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን በሆኖሉሉ ከማረፉ በፊት የቀኝ ሞተሩ ተሰብሮ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በተካሄደው ምርመራ የአገሪቷ የመጓጓዣ ደህንነት ቦርድ አደጋው የአውሮፕላኑ ሙሉው የንፋስ ማስገቢያ [ፋን] በመሰንጠቁ ምክንያት ያጋጠመ እንደሆነ አስታውቆ ነበር።
47218261
https://www.bbc.com/amharic/47218261
ኦሮምኛ ዘፋኙ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን አጣ
ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ሙዚቃዎችን በመጫወት የሚታወቀውና በዘፈኖቹ በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጎ የነበረው የኦሮምኛ ዘፋኝ ዳዲ ገላን ሰኞ እለት ሙዚቃዎቹን ባቀረበበት መድረክ በጥይት ተመትቶ ሞቷል።
የኦሮምኛ ዘፋኙ ዳዲ ገላ በምስራቅ ሸዋ በቢሾፍቱ አቅራቢያ በምትገኘው የሊበን ዝቋላ ወረዳዋ ትንሿ የገጠር ከተማ አሹፌ ካለፈው ቅዳሜ እስከ ሰኞ ምሽት ደስታና ጭፈራ ነበር። ይጨፈር የነበረው ለአንድ ሆቴል ምርቃት ነበር። ደስታና ጭፈራው ግን አልዘለቀም። •ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ? •ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን የምርቃቱ ታዳሚዎች በደስታ ጥይት ወደላይ ይተኩሱ ነበር። የመድረኩ ፈርጥ የነበረው ታዋቂው ኦሮምኛ ዘፋኝ ዳዲ ገላን ድንገት በጥይት ተመትቶ እንደወደቀ የሆቴል ምርቃቱ የሙዚቃ ድግስ መድረክ አስተባባሪ የነበረው ጓደኛው አቶ ቱፋ ወዳጆ ይናገራል። "ለቅሶም ላይም ይተኮሳል። ልጅም፣ አባትም ክላሽ መታጠቅ ባህል ነው። በወቅቱ እየተተኮሰ እያለ ማን እንደሆነ አይታወቅም ከመሀል ልቡን መትቶት ወደቀ" በማለት ይገልፃል። በህግ የተከለከለ ቢሆንም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ለሰርግ፣ለሃዘን ፣ለልደትና ለሌሎችም መሰል አጋጣሚዎች ጥይት መተኮስ የተለመደ ነው ማለት ይቻላል። በሃይማኖት አባቶችና በገዳዎች ምክር ጭምር ጥይት መተኮስ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ አዲስ እንደተጀመረ ዘፋኙ ህይወቱን ያጣበት የሊበን ጩቃላ ወረዳ ፖሊስ ፅፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ግርማ ሚደቅሳ ለቢቢሲ ገልፀዋል። •የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን ከ2009 ዓ.ም የለውጡን እንቅስቃሴ ተከትሎ በተለያዩ በዓላትና አከባበሮች ላይ ደስታንም ሆነ ኃዘንን ለመግለፅ መተኮስ እንደተጀመረ ኢንስፔክተር ግርማ በተጨማሪ ገልፀዋል። ባለፈው አመትም አቅራቢያው በሚገኝ ሌላ አካባቢ አንድ ወጣት የደስደስ ጥይት ሲተኩስ ጓደኛውን በመግደሉ መልሶ ራሱን እንዳጠፋ ኢንስፔክተር ግርማ ያስታውሳሉ። ኦሮምኛ ሙዚቃዎችን የሚጫወተው ዳዲ አስከሬን ለምርመራ ተልኮ ከነበረበት ጳውሎስ ሆስፒታል ዛሬ ከሰዓት በኋላ የትውልድ ቀዬው አሹፌ መድረሱን ኢንስፔክተሩ ገልፀውልናል።
news-42814528
https://www.bbc.com/amharic/news-42814528
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፖለቲካ ጥያቄ እንዴት ይመለስ?
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ 22 ምሁራን አመልክተው እንደነበር ይታወሳል። ከእነዚህ 13ቱ ተለይተው ስትራቴጂያቸውን እንዲያቀርቡና እንዲያብራሩ ተደርጎ ስምንቱ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ አልፈው ነበር።
የዶ/ር ጀይሉ ዑመር ሁሴንና ፕ/ር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ እነዚህ ደግሞ ጥር 4 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በተገኙበትና የምርጫ ኮሚቴው ባስተባበረው የቃለ-መጠይቅ ፓናል መርሀ-ግብር ቀርበው ባገኙት ነጥብ መሰረት አምስቱ ተመርጠው ስማቸው ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ መተላለፉን የዩኒቨርሲቲው ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል። ቦርዱም ከቀረቡለት አምስት ተወዳዳሪዎች ሦስቱን በመምረጥ ለመጨረሻ ውሳኔ ለትምህርት ሚኒስቴር አስተላልፏል። በቅርቡም ውጤቱ እንደሚታወቅ ይጠበቃል። በአገሩቱ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ላለፉት ወራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በግጭት ሲታመሱ ነበር። በዚህም የተማሪዎች ህይወት አልፏል፤ የአካል ጉዳትም ደርሷል። የመማር ማስተማር ሂደትም ተስተጓጉሏል። የውድድሩ መጨረሻ ላይ ለደረሱት ሶስቱ ተወዳዳሪዎች ለፕ/ር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ፣ ዶ/ር ጀይሉ ዑመር ሁሴንና ፕ/ር ጣሰው ወልደሀና ካህሳይ ቢቢሲ አንድ ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ለእጩዎቹ ያቀረብነው ጥያቄ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለሚፈጠሩ ግጭቶችና የተማሪዎች የፖለቲካ ጥያቄን ተከትለው ለሚነሱ ተቃውሞዎች መፍትሄ የምትሉት ምንድነው? የውድድሩ አሸናፊ ብትሆኑ እናንተ በምትመሩት ዩኒቨርሲቲ እንዲህ አይነት ነገር ቢፈጠር ምን ታደርጋላችሁ? የሚል ነበር። ፕ/ር ጣሰው ምላሽ ያልሰጡ ሲሆን የሁለቱን እጩዎች ምላሽ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ዶ/ር ጀይሉ ዑመር ሁሴን ላለፉት ስድስትና ሰባት አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የደህንነት ችግር አልነበረበትም ። በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ግን ችግሮች ነበሩ። ችግሩ በሁለት መንገድ ይፈታል ብዬ አምናለው። የዩኒቨርሲቲዎች አለመረጋጋት በተቋማቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሊነሳ ይችላል። አስተዳደራዊ ወይም አካዳምያዊ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል ከውጭ በሚመጣ ግፊት በዩኒቨርሲቲዎች አለመረጋጋት ሊፈጠር ይችላል። ተማሪዎች የህብረተሰቡ አካል ስለሆኑ የህብረተሰቡን ጥያቄ ይዘው ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ሊመጡ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ጥያቄው ምንድን ነው? ችግሩስ? በዩኒቨርሲቲው አቅም ሊፈታ የሚችለው የቱ ነው? የሚለው ላይ መወያየት ያስፈልጋል። ከዩኒቨርሲቲው አቅም ውጭ ለሆኑት ጉዳዮች ደግሞ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመለከታቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችና የመንግሥት አካላትን አገናኝቶ የማወያየት ሚና ሊኖረው ይገባል። ሦስተኛው ነገር ዩኒቨርሲቲ ለመንግሥትም ሆነ ለህዝብ ትልቁ የእውቀትና የምርምር ተቋም እንደመሆኑ በፖለቲካው የሚታዩ ችግሮችን በሚመለከት ማወያየት፣ የተለያዩ ሃሳቦች በነፃነት መንፀባረቅ የሚችሉባቸውን መድረኮች ማመቻቸት፣ የመፍትሄ አቅጣጫም የመጠቆም ሥራ መስራት ይኖርበታል ብዬ አስባለው። ተማሪዎች የህብረተሰቡን ጥያቄ ወደ ዩኒቨርሲቲ በማምጣታቸው ''ለምን?' የሚያስብል ነገር አይኖርም። በእርግጥ የፖለቲካና ፖለቲካ ነክ ጥያቄዎች በዩኒቨርሲቲ አቅም የሚፈቱ አይመስለኝም። ነገር ግን ዩኒቨርሲቲ ተሰሚነቱ ከፍ ያለ ስለሆነ የሚመለከታቸውን ክፍሎች ከተማሪዎች ጋር ሊያወያይ ይችላል። ሌላው ተማሪዎች ጥያቄ እስኪያነሱም ሳይጠበቅ ምርምር አድርጎ የፖሊሲ ለውጥ እንዲመጣ ተፅኖ ማምጣት ይገባዋል። ዩኒቨርሲቲ በህዝብና በመንግሥት መካከል ድልድይ መሆን ይገባዋል። ፕ/ር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ ተማሪዎች የህብረተሰብ ጥያቄ፣ የፖለቲካ ጥያቄ አያንሱ ሥራቸው መማር ብቻ ነው ማለት አይቻልም። ተማሪ የህብረተሰብ አካል ነው። የተማሪ ንቅናቄም ከበፊት ያለ ነው። ልዩነቱ ድሮ ተማሪዎች አንድ ላይ ሆነው ሥርዓትን ነበር የሚታገሉት። አሁን ግን ተማሪዎች በብሄር ስለሚከፋፈሉ አንድነት አለ ማለት አይቻልም። ባለፉት ዓመታት ስለ ማንነት ፖለቲካ ብዙ ተነግሮ በርካቶች እሱን ያንፀባርቃሉ። እነዚህ ተማሪዎች ያንን የማንነት ፖለቲካ የተረዱበት መንገድ ለዛሬው ችግር አስተዋፅኦ ያለው ይመስለኛል። ተማሪዎች ማንነታቸው እንዳለ ሆኖ ስለ አገራቸው፣ ስለሰው ክብር፣ ሰብአዊነት፣ እኩልነትና የመሳሰሉ እሴቶች ሊኖሯቸው ይገባል። በዚህ ረገድ ተማሪዎቹ ያለፉበት ትምህርት አንድ ነገር ብቻ በማጉላት ተጠያቂ ይመስለኛል። መስራት የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው። የትግላቸው ስልት መሆን ያለበት ምንድን ነው? ጉልበትን ማካተት አለበት? እርስ በርስስ በብሄር መከፋፈል ይገባል? ወይስ አንድነታቸውን አጠንክረው ስለፍትህ ስለዴሞክራሲ ማሰብ ይገባቸዋል? በአገሪቱ የመቻቻልና የመደማመጥ ባህል አለ ግን እየተሸረሸረ ሄዷል። እዚያ ላይ መስራት ያስፈልጋል። የመደማመጥ፣ የመወያየትና የሰላም መንፈስን በተማሪዎች መካከል ማስረፅ ያስፈልጋል። ጥያቄያቸውን ማሰማታቸው ልክ ቢሆንም መንገዳቸውን ማስተካከል ያስፈልጋል። ዩኒቨርሲቲ ብቻውን የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። ያለው የፖለቲካ፣ የማህበራዊ ሁኔታ መንግሥት ህዝቡን የሚያዳምጥበትና ለህዝቡ ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ ነው ወሳኙ። በዚህ ውስጥ ግን ዩኒቨርሲቲ የራሱ ሚና ይኖረዋል። ወቅታዊውን ነገር ብናይ በመንግሥት በኩል ጥፋት አለ መዘግየትም አለ። ይህ ነገሮችን አባብሷል። ዩኒቨርሲቲ በመንግሥትና በማህበረሰብ፣ በተማሪም መካከል ግንኙነት ፈጣሪ መሆን ይኖርበታል። ተማሪዎች በተለይም የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ከሚባለው ትምህርት የሚያገኙት እሴት ምንድን ነው? የሚለው ሊታይ ይገባል። ይህ ለዘላቂ መፍትሄ ሊሰራበት የሚገባ አቅጣጫ ነው። ዩኒቨርሲቲ ሰውንና የሰው ህይወትን የሚያከብር ዜጋ ነው ማፍራት ያለበት። ተማሪዎች ከጉልበት ይልቅ የመነጋገርና ችግሮችን የመለየት ልምድ እንዲያዳብር ማድረግ የረዥም ጊዜ መፍትሄ መሆን አለበት። ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት እጩ ሆነው ከቀረቡት ሦስት ምሁራን መካከል ሁለቱ አሳሳቢ በሚባለው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አመለካከትና መፍትሄ ያሉትን ሃሳብ ነበር ከላይ ያቀረብነው።
news-48741853
https://www.bbc.com/amharic/news-48741853
ስለ 'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች
ቅዳሜ ዕለት አመሻሽ ላይ ባህር ዳር ከተማ በአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ውስጥ እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ በአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ቤት ውስጥ የተፈጸሙት ጥቃቶች ስላስከተሉት ጉዳት በስፋት ተነግሯል።
የባህር ዳሩ ጥቃት የክልሉን ርዕሰ መስተዳደርንና የአማካሪያቸውን ሕይወት መቅጠፉ በይፋ ቢነገርም የተጨማሪ ሰዎች ሕይወት እንደጠፋበት ለክልሉ አስተዳደር ቅርብ የሆኑ ሰዎች ይናገራሉ። • በቅዳሜው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ምግባሩ ከበደ አረፉ በአዲስ አበባው ጥቃት ደግሞ በሥራ ላይ የነበሩና በጡረታ የተገለሉ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገድለዋል። ባህር ዳር ከተማ በቀዳሚነት በክልሉ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የጀመረው ተኩስ ቁልፍ ከሚባሉት የክልሉ አመራር ክፍሎች መካከል በሚመደቡት የጸጥታ ጽህፈት ቤት፣ የፖሊስ ኮሚሽን እና የክልሉ ገዢ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ላይም ጥቃት እንደተፈጸመ ተነግሯል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ በቴሌቪዥን ቀርበው ባህር ዳር ውስጥ ያጋጠመው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደሆነ ይፋ ሲያደርጉ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ አጭሮ ነበር። አሁንም ድረስ ድርጊቱ በባለስልጣናት ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው? ወይስ እንደተባለው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ? የሚለው ዝርዝር ምላሽ ያላገኘ ዋነኛ ጉዳት እንደሆነ አለ። • ታስሯል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ራሱን ማጥፋቱ ተገለፀ ከዚህ በተጨማሪ ባህር ዳርና አዲስ አበባ ውስጥ ካጋጠመው ክስተት ጋር ተያይዞ በርካታ እያነጋገሩ ያሉና አሁንም ድረስ ግልጽ መልስ ያላገኙ ነገሮች አሉ። ከቅዳሜው ጥቃት ጋር በተያያዘ ያላወቅናቸው ነገሮች የትኞቹ ናቸው? • በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው? ወይስ የመንግሥት ግልበጣ? የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደሆነ የተገለጸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቃባይ በኩል ሲሆን፤ በርካቶች ክስተቱን የመንግሥት ግልበጣ ብሎ ለመጥራት የሚያበቁ ሁኔታዎች የሉም በሚል ይከራከራሉ። የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሊያስብሉ የሚችሉ ቁልፍ ጉዳዮች በሌሉበትና በሉአላዊ አገር ስር በሚገኝ ግዛት ውስጥ መሆኑ ጥያቄን እያስነሳ ነው። • በጥቃት ፈጻሚዎቹና በክልሉ ባለስልጣናት መካከል እስከ ግድያ የሚያደርስ ቀደም ያለ አለመግባባት ነበር? ቅዳሜ ዕለት ከነበረው ክስተት ቀደም ብሎ የጥቃቱ መሪ እንደሆኑ የተነገረላቸው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ምንም እንኳን በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚያደርጉት ንግግር ከሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት በተለየ አነጋጋሪ ጉዳዮችን አንደሚያነሱ የታወቀ ቢሆንም አለመግባባት እንዳለ በግልጽ የሚያሳዩ ነገሮች አልታዩም ነበር። • ጥቃቱ/የመንግሥት ግልበጣው ምን ውጤት ለማምጣት ያለመ ነበር? ጥቃቱ ወይም የመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራው ቢሳካ ምን ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ግልጽ ያለ ነገር የለም። ቢሳካ የፌደራል መንግሥቱ በቦታው እያለ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ክልሉን ተቆጣጥረው አላማቸውን የማሳካት ዕድላቸው በጣም ጠባብ ነው። • የሥራ ኃላፊነታቸውን "ከባድና የሚያስጨንቅ... ነው" ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ? • በርዕሰ መስተዳደሩ ጽህፈት ቤት ውስጥ በጥቃቱ ወቅት ምን ተከሰተ? ጥቃቱ የተፈጸመው የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ በሚያደርጉበት ጊዜ እንደሆነ ተገልጿል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ ስብሰባ ላይ በነበሩት የክልሉ አመራሮች ላይ ተኩስ ስለመክፈታቸውና ለግድያ ስለመምጣታቸው ከመነገሩ ወጪ የነበሩ ሁኔታዎችና ስለ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም። • በባህር ዳርና በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጸሙት ጥቃቶች አላቸው የተባለው ግንኙነትት ግልጽ ያለመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በጄነራሎቹ ላይ የተፈጸመው ግድያ ባህር ዳር ውስጥ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር የሚያገናኘው ነገር እንዳለ በተደጋጋሚ የተገለጸ ቢሆንም በውጤት ረገድ የሁለቱ ክስተቶች ትስስርን በተመለከተ በግልጽ የተቀመጠ ማስረጃ አልተገኘም። • የተገደሉ ባለስልጣናትና ጄኔራሎችን ለመዘከር የሃዘን ቀን ታወጀ •ከከፍተኛ ባለስልጣናትና ጄነራሎች ባሻገር ሌሎች የሞቱ ሰዎች ይኖሩ ይሆን? የተለያዩ ምንጮች በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች አምስት ብቻ ሳይሆኑ ቁጥሩ ከዚያ ከፍ እንደሚል እየተናገሩ ቢሆንም ይፋዊ የክልልና የማዕከላዊ መንግሥት ምንጮች ግን ያሉት ነገር የለም። • ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ስለተያዙ ሰዎች ጥቃቱ ተፈጽሞ የመከላከያ ሠራዊት በባህር ዳርና በዙያዋ ከተሰማራ በኋላ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነው ጥቃት ጋር በተያያዘ በክልሉ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች የነበሩ ሰዎችና ሌሎችም እንደታሰሩ ይነገራል። ነገር ግን እስካሁን እነማንና ምን ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ በይፋ የታወቀ ነገር የለም። • የጥቃቱ መሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጉዳይ? የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ብርጋዴረ ጄነራል አሳምነው ፅጌ "የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው" መሪ እንደሆኑ ጥቃቱ ከተፈጸመ ከሰዓታት በኋላ ተነግሯል። ነገር ግን ጄነራሉ ይህንን ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉት ከነማን ጋር እንደሁነ፣ ክስተቱ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ እንዴት እንዳመመለጡ፣ የት እንደሚገኙና አሁን ስላሉበት ሁኔታ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። ሰኞ ከሰዓት በኋላ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ባህር ዳር አቅራቢያ በጸጥታ ኃይሎች ተመትተው መገደላቸው ታውቋል።
news-42686404
https://www.bbc.com/amharic/news-42686404
528 እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ከሁለት ቀናት የተሃድሶ ስልጠና በኋላ ይፈታሉ
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ 528 እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ይለቀቃሉ ብለዋል። ጠቅላይ አቃቢ ህጉ ክሳቸው የሚቋረጠው እና ይቅርታ የሚደረግለቸው በጸረ-ሽብር ህጉ የተከሰሱትንም ይጨምራል ብለዋል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ በኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተሰጠው መመሪያ ለማስፍጸም ግብረ ኃይል መቋቋሙን ገልጸው፤ ይህ ግብረ ኃይል የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅዶችን አውጥቷል። በዚህም መሰረት በአጭር ጊዜ እቅዱ የተፈረደባቸውን እስረኞችን በምህረት መልቀቅ እና ክስ የተመሰረተባቸውን ደግሞ ክሳቸውን ውድቅ ማስደረግ ተቀዳሚ ተግባሩ መሆኑን ተናግረው ከዚህ በተጨማሪ እሰረኞች/ተጠርጣሪዎች በማረሚያ ቤቶች እና በፖሊስ ጣቢያዎች የሚያዙበትን አያያዝ ማሻሻል ነው ብለዋል። ጠቅላይ አቃቢ ህጉ የሚፈቱት እሰረኞች የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ ናቸው ብለዋል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያሟሉ እስረኞች ከሁለት ቀናት የተሃድሶ ስልጠና በኋላ ይፈታሉ ተብሏል። ከሚፈቱት እስረኞች መካከል 115 በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሥር የሚገኙ ሲሆን በክልል ደረጃ የሚገኙትን ደግሞ ክልሉ በሚወስነው መሰረት ተግባራዊ ይሆናል። እሰካሁን ድረስም የደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል ብቻ 413 የሚሆኑ የእስረኞችን ስም ዝርዝር አቅርቦ ክሳቸውን ለማቋረጥ ወስኗል ብለዋል። ክሳቸው ተቋርጦ ከሚፈቱ እሰረኞች መካከል የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች የሚገኙበት አንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፤ ''በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ስም ዝርዝራቸው ይፋ ሲደረግ የምንመለከተው ይሆናል'' ያሉ ሲሆን፤ አቶ ጌታቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው በተለመዶ ማዕከላዊ ተብሎ የሚጠራውን የምርመራ ማዕከል ዘግቶ ወደ ሙዝየምንት የመቀየሩን ሥራ የሚሰራው ሌላ ግብረ ኃይል ነው ብለዋል።
news-50357374
https://www.bbc.com/amharic/news-50357374
ኬኤፍሲ ምግብ ቤት ውስጥ ቀለበት አስረው የደቡብ አፍሪካዊያንን ቀልብ የሳቡት ጥንዶች
ደቡብ አፍሪካ የሚገኝ ኬኤፍሲ ምግብ ቤት (ከዶሮ የሚዘጋጁ ምግቦችን የሚያቀርብ) ውስጥ ቀለበት ያሰሩት ጥንዶች የበርካቶችን ቀልብ ስበዋል።
ጥንዶቹ ዶሮ እየተመገቡ ሳለ፤ ወንዱ ተንበርክኮ "ታገቢኛለሽ ወይ?" ሲል ሴት ጓደኛውን ጠየቀ። "እዎ!" ብላም ቀለበት አሰሩ። ኬኤፍሲም፤ "እኒህን ጥንዶች አፋልጉን" ሲል ጥንዶቹ ቀለበት ሲያስሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ የመገናኛ መድረክ ላይ ለቀቀ። • ትዳር ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ተንቀሳቃሽ ምስሉን 17ሺህ ሰዎች ከተጋሩት በኋላ፤ ጥንዶቹ በኸት ሄክተር እና ኖናሀላና እንደሆኑ ታወቀ። ተንቀሳቃሽ ምስሉን ያዩ ደቡብ አፍሪካዊያንም፤ ጥንዶቹ የተመኙት አይነት ሠርግ እንዲደግሱ ገንዘብ ማሰባሰብ ጀመሩ። ዛካስ ባንቲዊኒ የተባለ ድምጻዊ ሠርጋቸው ላይ በነጻ ለመዝፈን ተስማምቷል። የጫጉላ ሽርሽር ወደሚያደርጉበት ሥፍራ በነጻ ለማድረስ ፍቃደኝነት ያሳዩም አልጠፉም። ድራም የተባለ መጽሔት፤ የጥንዶቹን የፍቅር ታሪክ እንደሚዘግብ አሳውቋል። መጠጥና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ቃል የገቡም አሉ። • 'ሰልፊ' ለመነሳት ሲሞክሩ የሰመጡት ሙሽሮች ጥንዶቹ ቀለበት ሲያስሩ ቪድዮ የቀረጻቸው ካታካ ማሎቦላ የተባለ ግለሰብ ነው። ፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ ምስሉን ከለቀቀ በኋላ በርካቶች ተጋርተውታል። ጥንዶቹም ሊደግፏቸው የፈቀዱ ሰዎችን ባጠቃላይ አመስግነዋል። ጥንዶቹ ከስምንት ዓመት በፊት ጋብቻ መስርተው ነበር። ነገር ግን ሙሽራው በወቅቱ በገዛው ቀለበት ደስተኛ አልነበረም። ስለዚህም ለባለቤቱ ሌላ ቀለበት ለመግዛት ወሰነ። • ቢዮንሴ በህንድ ለቱጃር ልጅ ሰርግ ዘፈነች "ሥራ ስለሌለኝ ኖናሀላና የሚገባተን አይነት ቀለበት መግዛት አልቻልኩም" ሲል ተናግሯል። በኸት ሄክተር መላው ደቡብ አፍሪካዊያንን አመስግኖም፤ "የፍቅር ታሪካችን በዚህ መጠን የብዙዎችን ልብ ይነካል ብለን አላሰብንም ነበር" ብሏል።
news-50178501
https://www.bbc.com/amharic/news-50178501
የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አመራሮች ጋር ተወያዩ
የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር ዛሬ እንደተወያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ህዝብ ግነኙነት መላከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሠይፈ ለቢቢሲ ተነገሩ።
የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ዛሬ ዓርብ ከሰዓት በኋላ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ከመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ፣ ከሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል እና ከፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሸነር ጋር ተወያይተዋል። መላከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ፤ በውይይቱ ላይ የቤተክርስቲያኗ ተወካዮች በቤተክርስቲያን ላይ የሚቃጣው ጥቃት እንዲቆም እና መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን እንዲያከናውን ጠይቀዋል። ትናንት የተጀመረውን የቤተ ክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተከትሎ የእምነቱ ተከታዮችና ቤተ ክርስቲያኗ በተለያዩ ስፍራዎች እየገጠሟቸው ናቸው ባሏቸው ጥቃቶችና ችግሮች ዙሪያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲያናግሯቸው የቤተክርስቲያኗ አባቶች በጠየቁት መሰረት ነው ውይይቱ የተካሄደው። • ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ • የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ አወጀ ረቡዕና ሐሙስ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች በነበሩት የተቃውሞ ሠልፎች ላይ ክርስትያኖችና አብያተ ክርስቲያናት ጥቃት ደርሶባቸዋል ያሉት መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ፤ "ተቃውሞው የፌደራል መንግሥቱ ላይ ይምሰል እንጂ ጥቃት የደረሰው በአካባቢው የሚኖሩ ክርስቲያኖችና ቤተ ክርስቲያናት ላይ ነው" ሲሉ ይናገራሉ። የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬ ዳዋ ከተሞች፤ አምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቢ፣ አዳማ፣ ሞጆ እንዲሁም በድሬዳዋ እና ሀረር፣ የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ዛሬ የመከላከያ ሚኒስትር ገልጿል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ህዝብ ግነኙነት መላከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሠይፈ ለቢቢሲ፤ "'ሕግ የማስከበር ሥራን እንስራለን፣ እናንተም እርዱን በጸሎት አግዙን' ብለውናል" ሲሉ ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ስለነበራቸው ውይይት ተናግረዋል። • የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬ ዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት መሰማራቱ ተገለፀ በአዲስ አበባ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር የተሰባሰቡ ከ60 በላይ ሊቃነ ጳጰሳት ለስብሰባ ተቀምጠው የነበሩ ሲሆን በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ አካባቢ፣ ዶዶላ፣ አርሲ ነገሌ፣ ኮፈሌ አካባቢ በክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን እንደሰሙ ተደናግጠው ከሰዓት በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ሲወያዩ መቆየታቸውን ተናገግረዋል። ሊቃነ ጳጳሳቱ በሁኔታው እጅግ ከማዘናቸው የተነሳ "ስብሰባውን በትነን ወደ ሚመለከተው አካል ሄደን ከልጆቻችን ጋር ሰማዕትነትን እንቀበላለን" እስከማለት መድረሳቸውን ይናገራሉ። ትናንት ከሰዓት በኋላ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገራቸውንና ግጭቶቹ በተነሱባቸው አካባቢዎች መከላከያ ሠራዊት መላኩ እንደተነገራቸው መላከ ሕይወት ያስረዳሉ። ግጭቶች በተነሱባቸው አካባቢዎች ሕዝበ ክርስቲያኑ ጥቃቱን በመሸሽ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ መጠለላቸውን የተናገሩት መላከ ሕይወት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በተለየ መልኩ በተለያዩ አካባቢዎች ጥቃት እየደረሰባት መሆኑን አስታውሰው ከመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ ከዚህ ቀደም መወያየታቸውን አስታውሰዋል። በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤ ትናንት ከተጀመረ በኋላ በመሃል በአገሪቱ እያጋጠመ ያለውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ ለቤተክርስቲያኗ ምዕመናንና ለመላው ህዝብ የሰላም ጥሪ በማቅረብ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የጸሎትና የምሕላ ዐዋጅ ማወጁ ይታወሳል። • በሁለቱ ቀናት ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 27 ደረሰ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በተለያዩ ቦታዎች ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ መደበኛ ጉባኤውን በማቋረጥ በምዕመናንና በአብያተ ክርስትያናት ላይ ደረሱ በተባሉ "ጉዳቶችና ባሉ ስጋቶች" ላይ በመወያየት መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ሲመክር ማምሸቱ ተነግሯል። ሲኖዶሱ ያቀረበው የሰላም ጥሪ በዋናነት "መስመር እየለቀቀ የመጣውን በምዕመናንና በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን የማያባራ ጥፋት ማስቆምን" የሚመለከት መሆኑን አመልክቷል። ትናንት የወጣው መግለጫ አክሎም "እስከ አሁን ድረስ በግጭቶች እየደረሱ ካሉት የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ልንማር ባለመቻላችን ችግሩ ቀጥሎ በዚህ ሳምንትም በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያና በሌሎችም ክልሎች እየተከሰተ ያለው ግጭት እጅግ አሳሳቢ ነው" ሲል ገልጿል ሲኖዶሱ። ችግሩ ጊዜ የማይሰጥና ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በሕብረት ችግሩን ካልቀረፍነው መጠነ ሰፊ ጉዳትን የሚያስከትል በመሆኑም ከሌሎች የመወያያ አጀንዳዎች በማስቀደም በጉዳዩ ላይ በስፋት መወያየቱንም አመልክቷል።
51922333
https://www.bbc.com/amharic/51922333
አሜሪካ በበጎ ፈቃደኞች ላይ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ጀመረች
አሜሪካ ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ላይ ሞከረች።
አራት በኮሮናቫይረስ የተያዙ አሜሪካውያን ሲያትል በሚገኝ የምርምር ማዕከል ክትባቱን ወስደዋል። ክትባቱ ኮቪድ-19 ከሚያሲዘው ቫይረስ ጎጂ ያልሆነ የጄኔቲክ ኮድ ኮፒ ተደርጎ የተወሰደ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ይገልጻሉ። ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ክትባቱ መስራት አለመስራቱን ለማወቅ በርካታ ወራት ይጠይቃል። • አምቡላንስ ሰብሮ ያመለጠው ከቫይረሱ ነጻ ሆኖ ተገኘ • የአሊባባ ባለቤት ቻይናዊው ባለጸጋ ጃክ ማ አሜሪካንን ረዳ • በኮሮናቫይረስ ጥርጣሬ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እራሳቸውን ለይተው ተቀመጡ የመጀመሪያዋ በጎ ፈቃደኛ ጄኔፈር ሀለር፣ የሁለት ልጆች እናት የሆነች የ43 ዓመት ሴት ስትሆን በትናንትናው ዕለት ክትባቱን ስትወስድ " አንድ ነገር በመቻሌ ለኔ ይህ ትልቅ እድል ነው " ስትል ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ተናግራለች። በዓለማችን ላይ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ተመራማሪዎች የቫይረሱን መከላከያ ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ነው። እናም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ላይ የተደረገው ሙከራ ከዚህ በፊት ክትባቱ የመከላከል አቅምን ያዳብር እንደሆን በእንስሳት ላይ የሚደረገውን ሙከራ ወደ ጎን ያለ ነው ተብሏል። ነገር ግን ከዚህ ምርምር ጀርባ ያለው የባዮቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ሞደርና ቴራፒዩቲክስ፣ ክትባቱ አስፈላጊውን የሙከራና የፍተሻ ሂደቶችን ያለፈ ነው ሲል ማረጋገጫ ሰጥቷል። ዶ/ር ጆን ትሬጎኒንግ በኢምፒሪያል ኮሌጅ ለንደን የተላላፊ በሽታዎች ተመራማሪ ሲሆኑ " ክትባቱ ቀድሞ የነበረን ቴክኖሎጂ ይጠቀማል" ብለዋል። አክለውም " ክትቱ የተሰራው በከፍተኛ ሁኔታ ደረጃቸውን በጠበቁ፣ ሰው ላይ ለመጠቀም ደህንነታቸው በተረጋገጠ ነው። ሙከራው ላይ የሚሳተፉም የቅርብ ክትትል ይደረግላቸዋል" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። በመቀጠልም "አዎ በርግጥ ይህ ሙከራ ፈጥኗል። ነገር ግን እሽቅድምድም የያዝነው ተመራማሪዎች እርስ በርሳችን ሳይሆን ከቫይረሱ ጋር ነው። የሚሰራውም ለሰው ልጅ ትርፍ ተብሎ ነው" ብለዋል። የኮቪድ 19 ክትባት ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆኑት ሕሙማን ላይ የተለያየ መጠን ያለው ክትባት ነው የተሰጣቸው። ግለሰቦቹ በ28 ቀናት ልዩነት ክንዳቸው ላይ ሁለት ክትባት የሚወጉ ይሆናል። ይህ ሙከራ እንኳ የሚሳካ ቢሆን ለአጠቃላይ ማህበረሰቡ ዝግጁ ለማድረግ 18 ወራት እንደሚፈጅ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ።
51189811
https://www.bbc.com/amharic/51189811
"ማማውን ከ10 ዓመት በላይ ሰርቼዋለሁ"፡ ጎንደር ላይ አደጋ ያጋጠመውን ማማ የሰራው አናጺ
የጥምቀት በዓል በጎንደር ሲከበር በተለይ እንግዶች ባሕረ-ጥምቀቱን የተሻለ ቦታ ሆነው እንዲያዩ በማሰብ ለዓመታት የእንጨት ማማ እየተሰራ እዚያ ላይ እንዲቀመጡ ይደረጋል።
ጎንደር በባሕረ ጥምቀቱ የደረሰው አደጋ በተመሳሳይ ዘንድሮም የእንግዳው ቁጥር ሊጨምር ይችላል በሚል እሳቤ ከአሁን በፊት ከነበረችው አንዲት ማማ በተጨማሪ ሦስት ማማዎች መሰራታቸውን የጎንደር ከተማ ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ አስቻለው ወርቁ ተናግረዋል። ማማው የተሰራው ከአሁን በፊት ሲሰራው በነበረው አናጺ መሆኑን የተናገሩት አቶ አስቻለው የተሰራውም ከዚህ በፊት በተሰራበት የእንጨት መጠን ነው ይላሉ። "ከዚህ በፊትም እንግዶችን ለማስቀመጥ ሲባል ተመሳሳይ ማማ በመሥራት እንደግዶችን እናስተናግድ ነበር፤ ዘንድሮ አደጋ ያጋጠመው ማማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ማማው ላይ ስለወጣበት ነው" ይላሉ። ሰዉ ማማው ላይ በፊት ለፊት በኩል ለመውጣት ሲሞክር በጥበቃዎች በመከልከሉ ከኋላ በኩል ብዙ ሰው ተንጠላጥሎ ስለወጣበት ሚዛኑን ስቶ መውደቁን ያብራራሉ። ማማውን የሰራው አናጺ አቶ ወንድም በቀለ ይባላል። እርሱ እንደሚለው በዚሁ በአጼ ፋሲል የመዋኛ ገንዳ ለጥምቀት በዓል ማድመቂያ እየተባለ ላለፉት አስር ዓመታት ማማውን ሲሰራ ቆይቷል። በሥራውም ተመሳሳይ ዲዛይን እንደሚጠቀም የተናገረው አናጺው "የዘንድሮውን ማማ የሠራሁት አምና በሰራሁበት እንጨት ልክ ነው" ብሏል። በአብዛኛው ከአሁን በፊት ዘንድሮ የተሰራውን ማማ ለሚቀጥለው ዓመት የተጎዳውን እንጨት በመቀየር ሲሰራ እንደቆየም ተናግሯል። ዘንድሮ ከተጨመሩት ሦስት ማማዎች መካከል አንዷን የሰራት ወንድም ነው። ባለፈው ዓመት ተሰርታ ዘንድሮም ጥቅም ላይ የዋለችውን ማማም የሰራው ወንድም ነው። ወንድም እንደሚለው እርሱ አምና የሰራት እና ሌሎች ጓደኞቹ ዘንድሮ የሰሯቸው ሁለት ማማዎች በድምሩ ሦስት ማማዎች ለእንግዶች የተዘጋጁ ስለነበሩ በልካቸው ብቻ ሰው እንዲይዙ ተደርገው ምንም ጉዳት አላደረሱም። ነገር ግን አንዷ እርሱ ዘንድሮ የሰራት ማማ ለሕዝቡ የተሰራች ስለነበረችና ሕዝቡም ያለገደብ ስለተሰቀለባት አደጋውን ለማስተናገድ ተገድዳለች ይላል። "በፊት ለፊት በኩል ያለውን መከላከያ እየጠበቀው ስለነበር በአብዛኛው ከኋላ የመጡ ሰዎች ናቸው መጥተው የሰፈሩበት። እዚያ ላይ የቆሙት የጥበቃ ሰዎች ማስቆም ነበረባቸው። ምክንያቱም የሌሎቹ መቀመጫዎች ይበቃል ተብሎ በልካቸው ብቻ ሰው ስለተቀመጠ ምንም የደረሰባቸው ነገር የለም። ነገር ግን ይሄኛው ከኋላ የመጣ ሰው ስለወጣበት ውረዱ ሲባሉም የሚሰማ በመጥፋቱ ሚዛኑን ስቶ ተደርምሷል" "እስካሁን ከሰራሁት በተለየ መልኩ ዘንድሮ የተሻለ አድርጌ ነው የሰራሁት፣ በተደጋጋሚ አረጋግጨዋለሁ" በማለት የሰራው ማማ ጥራቱን የጠበቀ እንደነበር አናጺው ይናገራል። የጎንደር ከተማ የሰላም ግንባታና የሕዝብ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን በበኩላቸው የአደጋው ምክንያት የጥራት ማነስ ይሁን አይሁን ወደፊት በባለሙያ ተጣርቶ የሚገለጽ እንጂ አሁን ባለበት ሁኔታ እንዲህ ነው ለማለት አልችልም ብለዋል። በአደጋው የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የሟቾችን ቁጥር በተለያየ አሃዝ ገልጸውታል። አቶ ተስፋ በአደጋው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 10 መሆናቸውን እና ከእነዚህም መካከል 3ቱ ሴቶች መሆናቸውን ተረጋግጠዋል። እንደ አቶ ተስፋ ገለጻ በአደጋው 147 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተልከዋል። ከነዚህ መካከል 67 የሚሆኑት ወዲያውኑ ታክመው ወደቤታቸው ተመልሰዋል። 80 የሚሆኑት ደግሞ እስካሁን ሆስፒታል ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው ነው። ከነዚህ መካከል 2 ተጎጅዎች በጣም የከፋ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ተስፋ የተወሰኑ የውጭ ዜጎችም ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
news-43482151
https://www.bbc.com/amharic/news-43482151
ፌስቡክ ግላዊ መረጃን አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ
የአሜሪካው ፌዴራል የንግድ ኮሚሽን ፌስቡክ የ50 ሚሊየን ተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ ለፖለቲካ አማካሪ ድርጅት አሳልፎ ሰጥቷል በሚል ምርመራ እያከናወነበት ይገኛል።
የሰዎችን ግላዊ መረጃ ያለይሁንታቸው በመበርበር የተወነጀለው ፌስቡክ ከሰኞ ጀምሮ ባሉት ቀናት በገበያ ላያ ያለው ድርሻም እየወረደ እንደመጣ እየተዘገበ ነው። የእንግሊዝና ሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ፓርላማዎች የፌስቡክ አለቃ የሆነው ማርክ ዙከርበርግ ሁኔታውን እንዲያስረዳ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ። ወቀሳው ከተሰማ በኋላ በነበረው የፌስቡክ ሠራተኞች ስበሰባ ላይ ዙከርበርግ እንዳልተገኘና ስብባው በኩባንያው ምክትል ጠቅላይ አማካሪ እንደተመራ ለማወቅም ተችሏል። በሰሜን አሜሪካ የቢቢሲ ቴክኖሎጂ ነክ ዜናዎች ዘጋቢ የሆነው ዴቭ ሊ እንደሚለው ፌስቡክና ዙከርበርግ ላይ ጫናው እጅግ በርትቷል። ኩባንያው በ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ በትራምፕ ቅስቀሳ ቡድን የተቀጠረ 'ካምብሪጅ አናሊቲካ' በተሰኘ ተቋም 'መታለሉን' ነው የፌስቡክ ቃል-አቀባይ የሆኑ ሴት ለመገናኛ ብዙሃን ያስታወቁት። ዜናው ከተሰማ ወዲህ ቢያንስ 60 ቢሊየን ዶላር የሚሆን የገበያ ድርሻ ያጣው ኩባንያ ፌስቡክ አለቃ ዙከርበርግ ዛሬ በሚሰበሰበው የአሜሪካ ኮንግረስ ፊት በመቅረብ ስለሁኔታው ያስረዳል ተብሎ ይጠበቃል። በሌላ በኩል ፌስቡክ አታሎኛል ሲል የወቀሰው 'ካምብሪጅ አናሊቲካ' የተሰኘ ተቋም ኃላፊ አሌክሳንደር ኒክስ በቦርድ አባላት ትዕዛዝ ከስራቸው ለግዜው መታገዳቸውም ታውቋል። መቀመጫውን ለንደን ከተማ ያደረገው እና የአሜሪካን የምርጫ ህግጋት ተላልፏል በሚል ክስ የቀረበበት ይህ ተቋም መሰል ውንጀላዎችን አስተባብሏል። የፌስቡክ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑ ሮብ ሼርማን የተሰኙ ግለሰብ "የሰዎችን ግላዊ መረጃ ለመጠበቅ የማንፈነቅለው ድንጋይ የለም፤ እንደውም ምርመራው ይህን እንዳሳይ አጋጣሚ ይሆነናል" ሲሉ ተደምጠዋል። የወደቀ ዛፍ እንዲሉ ወቀሳ የበዛበት ፌስቡክ ለተጠቃሚዎች ግላዊ መረጃ ያለው ቦታ እንዲታወቅ በሚል ከተፈበረከ ጀምሮ ያሉ የሁለት አስርት ዓመታት መረጃዎቹም እንዲጣሩ የንግድ ኮሚሽኑ ትዕዛዝ አስተላልፏል።