id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-47382341
https://www.bbc.com/amharic/news-47382341
ቀብር አስፈጻሚዎች ከሞት አስነሳሁ ያለውን ፓስተር ሊከሱ ነው
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የቀብር አስፈጻሚዎች የሞተን ሰው አስነሳሁ ያለን አንድ እራሱን ነብይ ብሎ የሚጠራን ግለሰብ ፍርድ ቤት እናቆማለን እያሉ ነው።
ፓስተር አልፋ ሉካው ከሞት አስነሳሁት ካለው ግለሰብ ጋር ቀብር አስፈጻሚዎቹ እንደሚሉት ፓስተር አልፋ ሉካው ከሞት ማስነሳት እንደሚችል ለምዕመናኖቹ ለማሳየት ባቀናበራው ሀሰተኛ ድርጊት ውስጥ ሳያውቁ እንዲሳተፉ ስላደረጋቸው ነው ጉዳዩን ወደ ሕግ ለመውሰድ የወሰኑት። በበርካታ ሰዎች እየታየ ባለው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ፓስተር አልፋ ሉካው ከፊቱ ከተቀመጣ የሬሳ ሳጥን ውስጥ ያለን አስከሬን "ተነስ" በማለት ከፍ ባለ ድምጽ ሲያዝ፣ ሳጥን ውስጥ ያለው ግለሰብ ሲነሳና ምዕመኑም በደስታ ሲጮሁ ይታያል። • በምሥራቅ ወለጋ የአራት ቀን ሬሳ አስነሳለሁ ብሎ መቃብር ያስቆፈረው 'ነብይ' በቁጥጥር ሥር ዋለ የቀብር አስፈጻሚዎቹ ክስም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው። ምክንያታቸውንም ሲያስቀምጡ በዚህ የተቀነባበረ ድርጊት ውስጥ ተሳታፊ እንድንሆን ተደርገናል ነው የሚሉት። በዚህ ድርጊትም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጆሃንስበርግ አቅራቢያ የሚገኘው የፓስትር ሉካው ቤተክርስቲያን ከበርካቶች ውግዘት የገጠመው ሲሆን መሳለቂያም ሆኗል። "እንዲህ አይነት ተአምር የለም" ሲል የደቡብ አፍሪካ የባህል፣ ሃይማኖትና የቋንቋ ማሰፋፋትና ጥበቃ ኮሚሽን ለሃገሪቱ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጿል። ጨምሮም "እንዲህ አይነት ነገሮች ተስፋ መቁረጥ ከገጠመው ሕዝብ ላይ ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚፈጥሩት ነው" ብሏል። • በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው በአዞ ተገደሉ ሦስት የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ሳያውቁ በዚህ ድርጊት ውስጥ እንዲሳተፉ በመደረጋቸው በመልካም ስማችን ላይ ጉዳት ደርሷል በሚል ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ሦስቱ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅቶች ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የቤተክርስቲያኑ ተወካዮች በተለያየ መንገድ አታለው በድርጊቱ ውስጥ እንድንሳተፍ አድርገውናል ብለዋል። "የሟች ቤተሰብ ነኝ" የሚል ግለሰብ ወደ አንደኛው የቀብር አስፈጻሚ ድርጅት ቀርቦ ከሌላ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅት ጋር አለመግባባት ውስጥ እንደገቡ መናገሩን፤ በተጨማሪም በግል መኪናቸው ላይ የሌላኛውን የቀብር አስፈጻሚ ስም በመለጠፍ እውነተኛ ለመምሰል መሞክራቸው ተገልጿል። • ዚምባብዌ ኤች አይ ቪ እፈዉሳለሁ ያለዉን ፓስተር ቀጣች ለዚህ ድርጊት ጥቅም ላይ የዋለው የሬሳ ሳጥንም ከሌላ የቀብር አስፈጻሚ ድርጅት መምጣቱም ተነግሯል። 'ሃሌሉያ ሚኒስትሪስ ኢንተርናሽናል' በመባል የሚታወቀው የፓስተር ሉካው ቤተክርስቲያን በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ በቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ይህ ነገር ይፋ ከወጣ በኋላም በፓስተሩ አማካይነት ከሞት ተነስቷል ስለተባለው ሰው ዜና ቤተክርስቲያኑ ማስተባበያ እየሰጠ ነው። ሞተ የተባለው ግለሰብ ወደ ስፍራው ሲመጣ በህይወት እንደነበረም እየተነገረ ነው። • ሰባኪው አውሮፕላን ግዙልኝ አለ በዚሁ ዙሪያም 'ሃሌሉያ ሚኒስትሪስ ኢንተርናሽናል' ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገረው "በእግዚአብሔር የተጀመረውን ግለሰቡን ከሞት የማስነሳት ተአምር ፓስተር ሉካው አጠናቆታል" ሲል ምላሽ ሰጥቷል። ይህ የአንድን ግለሰብ ከሞት መነሳትን የሚያሳየው ቪዲዮ በስፋት መሰራጨትን ተከትሎ በሃሰተኛ ፓስተሮች ዙሪያ ሃገር አቀፍ ክርክር እየተደረገ ሲሆን ድርጊቱም ከቀደምት የዕምነት ተቋማት በኩል ውግዘትን አስከትሏል።
55438467
https://www.bbc.com/amharic/55438467
የኮሮናቫይረስ ታማሚው ሆስፒታል ውስጥ ሌላ ታማሚን ገደለ
አሜሪካ፣ ካሊፎርንያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ተይዞ ሆስፒታል የነበረ ግለሰብ ሌላ ቫይረሱ ያለበትን ታማሚ ገደለ።
የ37 ዓመቱ ግለሰብ ባለፈው ሳምንት ታማሚውን የገደለው በኦክስጅን መያዣ ታንክ ደብድቦት ነው። ግለሰቡ በግድያ እና በጥላቻ ወንጀል ተከሷል። ጀሲ ማርቲኔዝ የተባለው ግለሰብ የ82 ዓመት አዛውንት በኮሮናቫይረስ ተይዘው እሱ የሚገኝበት የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ከገቡ በኋላ ነው ግድያውን የፈጸመው። ለሎስ አንጀለስ ፖሊስ በሰጠው ቃል መሠረት አዛውንቱ የሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ እየጸለዩ ስለነበረ ተበሳጭቶባቸዋል። አዛውንቱ በኦክስጅን ታንክ ከተመቱ በኋላ በቀጣዩ ቀን ሕይወታቸው አልፏል። ፓሊስ እንዳለው፤ ሁለቱ ግለሰቦች በተመሳሳይ የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ሕክምና ሲደረግላቸው ነበር። ከዚያ በፊትም አይተዋወቁም። አንቲሎፕ ቫሊ በተባለውና በደቡብ ካሊፎርንያ በሚገኝ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግለት የነበረው ጀሲ "አዛውንቱ ሲጸልዩ ተበሳጨና በኦክስጅን ታንክ ገደላቸው" ሲል ፖሊስ መግለጫ አውጥቷል። ከግድያ በተጨማሪ የጥላቻ ወንጀል እና አረጋውያንን የማሰቃየት ክስም ተመስርቶበታል። ካሊፎርንያ ውስጥ በስድስት ሳምንት ብቻ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ሆስፒታሎች ህሙማንን ለማስተናገድ እየተጣጣሩም ነው። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በግዛቲቱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎች እጥረት ስለገጠማቸው ከአውስትራሊያ እና ታይዋን 3000 ባለሙያዎች ለመውሰድ አቅደዋል። የካሊፎርንያ የጤና ቢሮ ጸሐፊ ዶ/ር ማርክ ጋሊ በዚህ ወር መጨረሻ ለህሙማን አልጋ ላይኖር እንደሚችል ተናግረዋል። አገረ ገዢው ጋቪን ኒውሰም ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ አዘዋል። እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ አገልግሎቶች ውጪ ያሉ ተቋሞችም ተዘግተዋል።
news-52758353
https://www.bbc.com/amharic/news-52758353
በደቡብ አፍሪካ አራስ ልጅ በኮሮናቫይረስ ምከንያት መሞቱ ተሰማ
በደቡብ አፍሪካ ከተወለደ ሁለት ቀን የሆነው አራስ በኮሮና ምክንያት መሞቱ ተሰማ። ይህም በደቡብ አፍሪካመበቫይረሱ ከሞቱ ግለሰቦች ሁሉ በእድሜ ትንሹ መሆኑን የአገሪቱ ጤና ሚንስትር ገልፀዋል።
ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ይገኛሉ። የጨቅላው እናት ኮሮናቫይረስ እንዳለባት በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ሕጻኑ ከጊዜው ቀድሞ በመወለዱ ምክንያት የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ያስፈልገው ነበር ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚንስትር ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ በኮቪድ-19 ተይዘው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 339 የደረሰ ሲሆን ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ ደግሞ 18 003 ደርሷል። በደቡብ አፍሪካ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ብቻ እስከ 40 ሺህ ሰዎች ድረስ ሊሞቱ እንደሚችሉ ተተንብይዋል። • የህንድ ሆስፒታል ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው እናቶች ከ100 በላይ ህጻናትን አዋለደ • 12 የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ጉጂ ውስጥ በታጣቂዎች ተገደሉ የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚንስትር ዶ/ር ዝዌሊ ማክሄዚ "በአሳዛኝ ሁኔታ በኮቪድ-19 ምክንያት ጨቅላ ሕፃን ሞቶብናል። ጨቅላው ከተወለደ ሁለት ቀን የሆነው ሲሆን መወለድ ካለበት ጊዜ ቀድሞ የተወለደ ነበር" ብለዋል። እንዲሁም " ጨቅላው ሳንባው ላይ ችግር ስለነበረበት እንደተወለደ መተንፈሻ ተገጥሞለት ነበር" በማለት የሕጻኑን ህይወት ለማትረፍ ለተረባረቡ የጤና ባለሙያዎችና ለእናትየው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልፀዋል። ቢቢሲ የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግን በአፍሪካ ውስጥ በኮቪድ-19 ከሞቱ ሰዎች መካከል ይህ አራስ ህፃን በእድሜ ትንሹ መሆን አለመሆኑን ባጣራው መረጃ" እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት በአፍሪካ ይህ ጨቅላ በኮሮና ምክንያት የሞተ በእድሜ ትንሹ ሕፃን ነው" የሚል ምላሽ አግኝቷል። በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከሞቱ ሌሎች ታዳጊዎች መካከል በዩናይትድ ኪንግደም የሞተው የሶስት ቀን ጨቅላ ሲገኝበት በሚወለድበት ወቅት እናትም ሆኑ ጨቅላ ሕፃኑ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተግለጿል። ሕፃኑ ሲወለድ የልብ ምቱ በጣም ደካማ የነበረ ሲሆን ወደ ጭንቅላቱ በቂ ደምና ኦክስጅን አይሄድም ነበር ተብሏል። በዚህም ምክንያት የተነሳ ኮቪድ-19 ለጨቅላው ሞት ሁለተኛ መሆኑ በሕክምና ባለሙያዎቹ ገልፀዋል። የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስትር በተጨማሪም እንደገለፁት በአገሪቱ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተመዘገቡ 27 ሞቶች መካከል የሁለት ዓመት ሕፃን ይገኝበታል። ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚገኙባት ስትሆን ግብጽና አልጄሪያ ደግሞ በኮሮና ምክንያት በሞቱ ሰዎች ቁጥር 680 እና 568 በማስመዝገብ ይበልጣሉ። .
news-55601343
https://www.bbc.com/amharic/news-55601343
አሜሪካ ፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ክስ እንዲከፈት ግፊት እየተደረገ ነው
ዲሞክራቶች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ረቡዕ ዕለት ካፒቶል ሒል እንዲወረር በነበራቸው ሚና ምክንያት እንዲከሰሱ የሚያደርግ አንቀፅ ለማስተዋወቅ አቅደዋል።
ዶናልድ ትራምፕ፡ ዴሞክራቶች ፕሬዝዳንቱን ለመክሰስ የሚረዳቸው አንቀፅ ለማስተዋወቅ አቅደዋል አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልጣናቸውን በፍጥነት ካልለቀቁ በጉዳዩ እንደሚገፉ ገልጸዋል። በፕሬዝዳንቱ ላይ "የአመጽ ማነሳሳት" ክስ ዴሞክራቶች ሰኞ ዕለት ይከፈታልም ተብሎ ይጠበቃል። በኮንግረሱ ውስጥ አምስት ሰዎች የሞቱበትን አመፅ በማበረታታት ትራምፕን እጃቸው አለበት በሚል ይከሳሉ። የተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትራምፕን ከስልጣን የማነሳቱ ጉዳይ የኮንግረስ ውሳኔ እንደሆነ ቢናገሩም "ለረዥም ጊዜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሥራውን ለመያዝ ብቁ አይደሉም" ብለው ሲያስቡ እንደነበር ተናግረዋል። ዋይት ሐውስ በበኩሉ ክሱን "ታላቋን አገራችንን የበለጠ ለመለያየት ብቻ የሚያገለግል፤ በፖለቲካዊ ፍላጎት የተሞላ" እርምጃ ነው ሲል አጣጥሎታል። ወደ 160 የሚጠጉ የምክር ቤቱ ዴሞክራቶች ረቂቁን የፈረሙ ሲሆን፣ የካሊፎርኒያው ቴድ ሊዩ እና የሮድ አይላንዱ ዴቪድ ሲሲሊ ረቂቁን ማዘጋጀት ጀምረዋል። ሂደቱ ከቀጠለ ምክር ቤቱ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ የከስልጣን የማንሳት ክስን ሲያቀርብ ለሁለተኛ ጊዜው ይሆናል። ባለፈው ዓመት በታችኛው ምክር ቤት ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀማቸው እና የኮንግረሱን ሥራ በማደናቀፍ ክስ ትራምፕን ከስልጣን ለማንሳት ክስ ቀርቦባቸው ነበረ። ነገር ግን ሴኔቱ በየካቲት 2020 በሁለቱም ክሶች ነጻ እንዳደረጋቸው ይታወሳል። ከዚህ በፊት አንድም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሁለት ጊዜ ክስ ከሥልጣን የሚያስነሳ አልተመሰረተበትም። በሴኔት ውስጥ የትራምፕ ፓርቲ የሆነው ሪፐብሊካን ሰፊ ድጋፍ ስላለው ጉዳዩ የሚሳካ አይመስልም። የሪፐብሊካን ሴናተር የሆኑት የአላስካዋ ሊዛ ሙርኮቭስኪ አርብ ለአንኮራጅ ዴይሊ ኒውስ እንደተናገሩት ትራምፕ "ስልጣን መልቅቅ አለባቸው" ብለዋል። ትራምፕን በመተቸት የሚታወቁት የኔብራስካው የሪፐብሊካኑ ሴናተር ቤን ሳሴ በበኩላቸው ክሱን ሊደግፉት እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል። ነገር ግን የፕሬዚዳንቱ ፓርቲ አባላት ትራምፕን ለመክሰስ ስለመስማማታቸው እስካሁን ድረስ ፍንጭ የለም። ይህም የምክር ቤቱ ክስ ትራምፕን ለኮንግረሱ ወረራ ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቅም እርምጃ ብቻ ሊሆን ይችላል። አንድ የሴኔት ማስታወሻ እንደሚገልጸው ምክር ቤቱ ማንኛውንም ክስ ሊቀበል የሚችለው ትራምፕ የስልጣን ዘመናቸው ከማለቁ ከአንድ ቀን በፊት እንደሚሆን ሲገልጽ ይህም የፍርድ ሂደቱ ሊጀመር የሚችለው ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ብቻ እንደሆነ ያስታውቃል። የሕገ-መንግሥት ባለሙያዎች በዚህ ክስተት ውስጥም ቢሆን ክሱ ወደ ሴኔት መሻገር መቻሉ ላይ ተከፋፍለዋል። ትራምፕ ጥፋተኛ ከተባሉ ለቀድሞ ፕሬዚዳንቶች የሚሰጣቸውን ጥቅማ ጥቅምን የሚያጡ ሲሆን፤ ሴናተሮች በቋሚነት ከመንግሥት የኃላፊነት ቦታዎች እንዲታገምዱ ድምጽ መስጠት ይችላሉ። የካፒቶል ሒል ወረራ ከፍተኛ ፖለቲከኞችን በእጅጉ ያሳሰባቸው ሲሆን፣ አፈ-ጉባኤ ፔሎሲም ትራምፕ የኒውክሌር ኮዶችን እንዳያገኙ ለመከላከል ስለሚቻልባቸው መንገዶች ከአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር እንዲነጋገሩ አስገድዷቸዋል። ረቂቁ ምን ይላል? የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ያገኘው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ "አመጽ ማነሳሳት" የሚል ሃሳብ የያዘ ነው። ረቂቁ "ዶናልድ ጆን ትራምፕ ሆን ብለው በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ላይ ሁከትን በማነሳሳት በከፍተኛ ወንጀልና በደል ላይ ተሰማርተዋል" ይላል። ፕሬዚዳንቱ "በካፒቶል ሒል ላይ ሕገወጥ እርምጃን የሚያበረታቱ መግለጫዎችን በመናገራቸውም" ይከሳሉ። ረቂቁ በተጨማሪም ይህ ድርጊታቸው በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተመረጡት ባይደን ያሸነፉበትን የምስክር ወረቀት "ለማደብዘዝ እና ለማደናቀፍ ከቀድሞ ጥረቶቹ ጋር የሚጣጣም ነበር" ብለዋል። "በአሜሪካ ሕዝብ ላይ በግልጽ የሚታይ ጉዳት አድርሷል" ተብሏል። ባይደን በምርጫው የውክልና ድምጽ ባገኙት ውጤት አሸናፊነታቸው በኮንግረስ በተረጋገጠበት ቀን ፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎቻቸው ወደ ካፒቶል ሒል እንዲሄዱና አበረታተዋል ተብለው እተወቀሱ ነው። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ትክክለኛነትን ጥርጣሬ ውስጥ የከተተ የድጋፍ ሰልፍ ከማካሄድ ባለፈ ያለማስረጃም "ምርጫው የተጭበረበረ" መሆኑን ጠቅሰዋል። "ወደ ካፒቶል አቅንተን ደፋር ሴናተሮቻችንን እና የኮንግሬስ አባላቶቻችንን እናበረታታለን" ሲሉ የተናገሩት ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን "እንዲታገሉ" አሳስበዋል። ዴሞክራቶች እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች እነዚህ ቃላት ከማነሳሳት ጋር የተቆራኙ ናቸው ሲሉ ተከራክረዋል። በአሜሪካ መንግሥት ሕጎችን አርቅቆ ሚያወጣው ኮንግረስ ፕሬዚዳንቶችን ለፍርድ ለማቅረብ ይችላል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፕሬዚዳንቱ ላይ ክሶች ማቅረብ ይችላሉ። ምክር ቤቱ ክሱን ለማሳለፍ ድምጽ ከሰጠ ፕሬዝዳንቱ ጥፋተኛ መሆን አለመሆናቸውን ወደ የሚወስነው ወደ ሴኔት ይመራል። ይህም ከወንጀል ይልቅ ያልተለመደ ክስተት እና የፖለቲካ ሂደት ነው። ትራምፕ ተመሳሳይ ክስ ሲቀርብባቸው ሦስተኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ናቸው። ሁለቱ በጎርጎሮሳዊያኑ 1999 ቢል ክሊንተን እና አንድሪው ጆንሰን ደግሞ በ1868 ናቸው። ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን ከመከሰሳቸው በፊት ስልጣናቸውን ለቀዋል። እንዴት እዚህ ደረስን? ሲቢኤስ ኒውስ እንደዘገበው ዲሞክራቶች ጥረቱን በከፍተኛ ደረጃ ይደግፉ የነበረ ሲሆን የኦሪገኑ ተወካይ ከርት ሽራደር ብቻ እንዲህ ዓይነቱ እርምጃ አገሪቱን ይበልጥ የሚከፋፍል ነው ሲሉ ተከራክረዋል። ፔሎሲ የመረጡት ሃሳብ ትራምፕ በ 25ኛው አሜንድመነት መሠረት በአእምሮ ወይም በአካላዊ ህመም ሳቢያ ተግባራቸውን ማከናወን ካልቻሉ ምክትል ፕሬዚዳንቱ እንዲተኩ የሚያደርገው ሕግ እንዲተገበር እየጠየቁ ነው። ይህ ካልሆነ ግን ፕሬዝዳንቱን በመክሰስ ከስልጣን ማወረድ ሌላኛው ሃሳብ ነው። ሆኖም እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ በጣም የማይታሰብ ነው ተብሏል። ምክትል ፕሬዝዳንት ፔንስም አሜንድመንቱን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን የሚያሳይ ምልክት የለም። ፔሎሲ አርብ ዕለት ኮንግረሱ ትራምፕ በስልጣን ላይ እያሉ አሜሪካውያንን ለመጠበቅ የተቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
news-52634068
https://www.bbc.com/amharic/news-52634068
ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን ሃሳብ አልቀበልም ማለቷ ተሰማ
ሱዳን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላልን በተመለከተ ከኢትዮጵያ የቀረበላትን ሃሳብ አልቀበልም ማለቷ ተሰማ።
በአባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያ እየገነባቸው ባለው አወዛጋቢ ግዙፍ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የስምምነት ሃሳብ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልተቀበሉት ተገልጿል። በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል ሲካሄድ የቆየው ድርድር መቋረጡን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ግብጽ ኢትዮጵያ እየገነባቸው ባከለው ግድብ ዙሪያ አቤቱታዋን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቅርባ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ሃሳብ ውድቅ ያደረጉት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለው ግድብን በተመለከተ ያለተፈቱ ቴክኒካዊና ሕጋዊ ጉዳዮች አሉ በማለት ነው። ግብጽና ሱዳን በምዕራብ ኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድበን ከወንዙ የምናገኘውን የውሃ መጠን በከፍተኛ መጠን ይቀንስብናል የሚል ስጋት አላቸው። በቢሊዮኖች ዶላር አውጥታ ግድቡን እየገነባችው ያለችው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችላትን ውሃ በመጪው ሐምሌ ወር ውሃ መሙላት እንደምትጀምር አስታውቃለች። ሦስቱ አገራት ከወራት በፊት በአሜሪካና በዓለም ባንክ አማካይነት ዋሽንግተን ውስጥ በከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው አማካይነት ተከታታይ ድርድሮች ቢያደርጉም ከመቋጫ ላይ መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል። በተለይ ኢትዮጵያ በመጨረሻ ላይ የቀረበው የስምምነት ሰነድ ጥቅሟን የሚነካና ለግብጽ ያደላ ነው በሚል እራሷን ከፊርማው መራቋ ይታወሳል። ለዘመናት ከፍተኛውን የወንዙን ውሃ በመጠቀም የምትታወቀው ግብጽ የግድቡ ግንባታና ውሃ አሞላልን በተመለከተ ከፍያለ ስጋት ስላደረባት አሜሪካንን ጨምሮ የአረብ አገራትን ድጋፍ ለማሰባሰብ ባለፉት ወራት ጥረት አድርጋለች። የአረብ ሊግ አገራትም የግብጽን ፍላጎት የሚያስከብር የአቋም መግለጫ ባወጡበት ጊዜ ሱዳን መግለጫውን ተቃውማ እራሷን አግልላ ነበር። ሱዳን ቀደም ባሉት ጊዜያት በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የኢትዮጵያን ሃሳብ የሚደግፉ አቋሞችን ስታንጸባርቅ ከመቆየቷ ባሻገር ከአረብ ሊግ ውሳኔ እራሷን በማግለሏ ከኢትዮጵያ ምስጋናን ከግብጽ በኩል ደግሞ ወቀሳ ቀርቦባት ነበር። ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ ሙሌትና ሥራን በተመለከተ የእራሷን የስምምነት ሃሳብ ማቅረቧም ተነግሯል።
news-53778972
https://www.bbc.com/amharic/news-53778972
ቤላሩስ፡እንግልት፣ ግርፋትና ስቃይ ያስከተለው የቤላሩስ ምርጫ
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በቤላሩስ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ እያሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ ኃይል እየተወሰደ እንደሆነ እየገለጹ ነው።
በተጨማሪም ታሳሪዎቹ ግርፋትና ማሰቃየት እደረሰባቸው እንደሆነም ይናገራሉ። እስካሁን 6 ሺህ 700 የሚሆኑ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ሰዎች የተለቀቁ ሲሆን በነበራቸው ቆይታ በርካታ የመብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙባቸው እየገለጹ ይገኛሉ። አምነስቲ ኢንተርናሽናልም በበኩሉ ሰዎችን ማሰቃየት በስፋት እየታየ ነው ብሏል። በቤላሩስ እየተካሄደ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ አምስተኛ ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን የሰልፈኞች ዋነኛ ጥያቄ ደግሞ የምርጫ ውጤት ተጭበርብሯል የሚል ነው። ባሳለፍነው እሁድ በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝደንት ሉካሼንኮ አሸናፊ መሆናቸው በምርጫ ኃላፊዎች ተገልጿል። ነገር ግን የተቃዋሚ ተፎካካሪዋ ስቬትላና ቲካኖቭስካያ ደጋፊዎች አሸናፊዋ እሷ ናት በማለት ተቃውሟቸውን እየገለጹ ያሉት። የካቢኔው ቃል አቀባይ ናታላያ ኮቻኖቫ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት ፕሬዝዳንቱ በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ይፋዊ ምርመራ እንዲደረግ ማዘዛቸውንና ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ መፈታታቸውን ገልጸዋል። ከእስር የተፈቱት ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እያጋሯቸው በሚገኙ ምስሎች ላይ በርካቶች ድብደባና ማሰቃየት ደርሶባቸው እንደነበር እያሳዩ ነው። አንዳንዶቹ ያበጠና የቆሰለ የሰውነታቸውን ክፍል ፎቶ በማንሳት ይፋ አድርገዋል። ጉዳቱን ያደረሰብንም ፖሊስ ነው ገልጸዋል። '' ሰዎችን በጭካኔ ይገርፋሉ፤ ያለምንም ክስ ሁሉንም ሰው በቁጥጥር ስር እያዋሉ ነው። በአንድ ክፍል ውስጥ ሌሊቱን በሙሉ ቆመን እንድናሳልፍ ተደርገናል። ሴቶች እየተገረፉ የድረሱልን ድምፅ ሲያሰሙም ሰምተናል። እንዲህ አይነት ጭካኔ ምንም አይገባኝም'' ሲል አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግሯል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከታሳሪዎች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ሰዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ ተደርገው ተገርዋል፤ እንዲሁም የመድፈር ማስፈራራት ደርሶባቸዋል። '' በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ሰዎች እንደነገሩን ማቆያ ማዕከላቱ ወደ ማሰቃያ ማዕከልነት ተቀይረዋል። ለተቃውሞ የወጡት ዜጎች ቆሻሻ አፈር ላይ እንዲተኙ በማድረግ ፖሊስ ይደበድባቸውና ያስፈራራቸው ነበር'' ብላለች በድርጅቱ የምስራቅ አውሮፓ እና ማዕከላዊ እስያ ዳይሬክተር ማሪ ስትሩተርስ። አንድ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ባገኘው የድምጽ ማስረጃ ላይ ደግሞ በዋና ከተማዋ ሚንስክ በሚኘውና ኦክሬስቲና በሚባለው ማዕከል ውስጥ ሰዎች ሲጮሁ ይሰማል። የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዩሪ ካራዬቭ በተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ለተወሰደው እርምጃ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ በመግለጽ በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ደግሞ ይቅርታ ጠይቀዋል። ታዛቢዎች እንደገለጹት መንግሥት በደረሰበት ዓለማቀፋዊ ጫና ምክንያት ቢሆንም በርካታ ሰዎችን እየለቀቀ ይገኛል። የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችም ቢሆኑ ቤላሩስ ላይ ማዕቀብ ለመጣል እየተዘጋጁ ነበር ተብሏል። ባለስልጣናት እንደገለጹት ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋትና ግጭት ምክንያት ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። አንደኛው ግለሰብ በተቃውሞ ቦታው ላይ ሰኞ ዕለት የተገደለ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ነው ሕይወቱ ያለፈችው። በቤላሩስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ላይ ደረስ የተበለው የመብት ጥሰትና አካላዊ ጉዳት መጠን ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሰዎች መካከል ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞችና በመንገድ ላይ ሲያልፉ የነበሩ ሰዎች ይገኙበታል። በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ጋዜጠኛ ኒኪታ ቴሊዜንኮ በአንድ ቀን ውሎው ያጋጠመውን እና ያስተዋለውን ሁኔታ ዘርዝሮ ጽፏል። ሁኔታውን ሲገልጽም ''ሰዎች አንድ በአንዱ ላይ ተደራርቦ መሬት ላይ ይተኙ ነበር፤ አንዳንዶቹም በደምና በሰገራ ተበክለው ይታያሉ። መጸዳጃ ቤት እንዲጠቀሙ አይፈቀድላቸውም ነበር። ሌላው ቀርቶ ጀርባን ለማሳረፍ መገላበጥ እንኳን ክልክል ነበር'' ብሏል። አክሎም በርካታ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን እንደተመለከተ ገልጿል። ''እግራቸው የተሰበረና አካላቸው ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው በርካቶች ነበሩ። ህክምና እንዳያገኙ መደረጋቸው አልበቃ ብሎ ጠባቂዎቹ እንደገና ይደበድቧቸው ነበር'' በማህበራዊ ሚዲያ በተለቀቀ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ደግሞ የተቃዋሚ መሪዋ ማሪያ ዋና ከተማዋ ሚንስክ ውስጥ አበባ በመያዝ ሴት ሰልፈኞችን ሲቀላቀሉ ታይተዋል። የተቃዋሚ መሪዋ ባለቤታቸው በቁጥጥር ስር ውሎ የመምረጥ መብቱን እስከሚነጠቅ ድረስ በቤት ልጆቻቸውን በመንከባከብ የሚያሳልፉ የቤት እመቤት ነበሩ። በአሁኑ ሰአት ግን የፕሬዝዳንቱ ዋነኛ ተፎካካሪ በመሆን በርካቶችን ከጎናቸው ማሰለፍ ችለዋል።
news-55120405
https://www.bbc.com/amharic/news-55120405
በናይጄሪያ በደረሰ አሰቃቂ ጥቃት በርካታ አርሶ አደሮች ተገደሉ
በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ በደረሰ አሰቃቂ ጥቃት ቢያንስ 43 አርሶ አደሮች ተገድለዋል።
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት "ዘግናኝ" ባሉት በዚህ ጥቃት በሩዝ እርሻ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች በስለት ታርደው የተገደሉት በትናንትናው (ቅዳሜ) እለት ነው። ጥቃት አድራሾቹ አርሶ አደሮቹን በቦርኖ ግዛት ማይዱጉሪ በምትባል አካባቢ አስረውም ነው ያረዷቸው ተብሏል። ቦኮ ሃራምና የምዕራብ አፍሪካው አይ ኤስ ቡድን በከፍተኛ ሁኔታ ይንቀሳቀሱበታል በሚባለው በዚህ አካባቢም በቅርብ ወራት ውስጥ የደረሰ አስከፊ ጥቃትም እንደሆነ ተገልጿል። እስካሁን ድረስም ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም። "በቦርኖ ግዛት ቀን ተሌት ሳይሉ ኑሯቸውን በሚገፉ አርሶ አደሮች ላይ በአሸባሪዎች የተፈፀመውን ግድያ አወግዛለሁ። እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ግድያም መላ ህዝቡን አሳዝኗል። በዚህ ጥቃት ቤተሰቦቻቸውን ላጡት መፅናናትን እየተመኘሁ የሟቾችንም ነፍስ በሰላም ያሳርፍ" በማለት ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ተናግረዋል። "እስካሁን ባለው የ43 ሰዎችን አስከሬን አግኝተናል። ሁሉም ታርደው ነው የተገደሉት። ከዚህም በተጨማሪ ስድስት ሰዎችም ክፉኛ ቆስለዋል" በማለት አርሶ አደሮቹን በማስመለጥ እርዳታ ያደረገ የአካባቢ ታጣቂ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግሯል። ከዚህም በተጨማሪ ቢያንስ ስድስት አርሶ አደሮች ታፍነው ተወስደዋል ተብሏል። ጥቃት የደረሰባቸው አብዘኛዎቹ የመጡት ሶኮቶ ከሚባል፣ 1 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ካለው አካባቢ ሲሆን ቦርኖ ግዛትም ለስራ እንደመጡ ኤኤፍፒ ሌላ የአካባቢውን ታጣቂ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። አርሶ አደሮቹ "ጥቃት የደረሰባቸው ሲያሰቃያቸው የነበረን የቦኮ ሃራም ታጣቂ በቁጥጥር ስር በማዋልና ትጥቁንም በማስፈታታቸው ነው" በማለት የአካባቢው የፓርላማ አባል አህመድ ሳቶሚ ፕሪምየም ታይምስ ለተሰኘ ጋዜጣ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደምም ለሰራዊቱ መረጃን ያስተላልፋሉ በሚል ጥርጣሬ አርሶ አደሮቹ በቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ጥቃት ይደርስባቸው እንደነበር ተዘግቧል። በባለፈው ወር በመስኖ ስራ የተሰማሩ 22 አርሶ አደሮች በቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ተገድለዋል። በዛሬው ዕለትም በቦርኖ ግዛት ስድስት ወታደሮች በአድፍጦ ታጣቂዎች መገደላቸውን የቢቢሲው ክሪስ ኤዎኮር ከአቡጃ ዘግቧል። ወታደሮቹ በግጭት በተፈናቀሉ አካባቢዎች የምግብ ስርጭት ጣቢያን ደህንነት ለመቆጣጠር የተሰማሩ እንደሆነም ተገልጿል።
51166802
https://www.bbc.com/amharic/51166802
ልዑል ሃሪና ሜጋን ያለባቸውን ዕዳ ሠርተው እንደሚከፍሉ አስታውቀዋል
የእንግሊዙ ልዑል ሃሪና ባለቤቱ ሜጋን ማርክል ከዚህ በኋላ የቤተ-መንግሥት መጠሪያቸውን እንደማይጠቀሙ አሳውቀዋል። ባልና ሚስቱ ከዚህ ባለፈ የቤተ-መንግሥት ገንዘብ እንደማይጠቀሙም ጠቁመዋል።
መግለጫውን ያወጣው የእንግሊዝ ንጉሳዊያን መቀመጫ የሆነው የባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ነው። አልፎም ጥንዶቹ ከዚህ በኋላ ንግሥቷን እንደማይወክሉ ተሰምቷል። ጥንዶቹ እንግሊዝ ሲመጡ የሚያርፉበት ፍሮግሞር ጎጆ ለተሰኘው ቤት የወጣውን 2.4 ሚሊዮን ፓውንድ ሠርተን እንከፍላለንም ብለዋል። 'የሰሴክስ ዱክ እና ዱቸስ' የሚል መጠሪያ ያላቸው ሃሪና ሜጋን የቤተ-መንግሥት ሥልጣንና ኃላፊነት በቃኝ ካሉ ወዲህ መነጋገሪያነታቸው ይልቁኑ ጨምሯል። ጥንዶቹ በወደፊት ዕጣ-ፈንታቸው ዙሪያ ከንግሥቲቱ ጋር ከመከሩ በኋላ ነው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ተብሏል። ንግሥቲቱ በለቀቁት መግለጫ ላይ 'ከወራት ውይይት በኋላ ለልጅ ልጄ እና ቤተሰቡ የሚበጅ ውሳኔ ላይ በመድረሳችን ደስተኛ ነኝ' ሲሉ ተደምጠዋል። 'ሃሪ፣ ሜጋንና ልጃቸው አርቺ ሁሌም ተወዳጅ የቤተሰቡ አባላት ሆነው ይቀጥላሉ' ይላል መግለጫው። መግለጫው ላይ እንደሚመለከተው የእንግሊዟ ንግሥት ሃሪና ሜጋንን አመሰግነዋል። በተለይ ደግሞ 'ሜጋን ከቤተሰቡ ጋር ለመቀላቀል ጊዜም አልወሰደባት' ብለዋል። ቤተ-መንግሥቱ ባወጣው ሌላ መግለጫ ጥንዶቹ የልዕልና ማዕረጋቸውን ከዚህ በኋላ መጠቀም እንደማይችሉ አሳውቋል። ነገር ግን ይህ ብዙዎችን ግራ ያጋባ ሆኗል። ምክንያቱ ደግሞ ጥንዶቹ የቤተ-መንግሥት ኃላፊነት በቃን እንጂ የቤተሰብ አባልነታችን ይገፈፍ አላሉምና ነው። የጥንዶቹ መፃኢ ዘመን ምን ሊመስል ይችላል የሚለው አሁንም ማነጋገሩን ቀጥሏል። ገንዘብ ከየት ያገኛሉ? የግል ጠባቂ ማን ይመድብላቸዋል? እና የመሳሰሉት። ቤተ-መንግሥቱ በመሰል ጉዳዮች ላይ አስተያየት መስጠት እንደማይችል አሳውቋል። ሃሪና ሜጋን ከጋብቻ በፊትም ሆነ ከጋብቻ በኋላ በእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ እጅግ እየተፈተኑ እንደሆነ ሲጠቅሱ ነበር። የልዕልት ዲያና ልጅ የሆነው ልዑል ሃሪ 'ሚስቴ እንደ እናቴ ዓይነት ዕጣ ፈንታ እንዳይገጥማት እሰጋለሁ' ሲልም ተደምጦ ነበር። የሜጋንና ልዑል ሃሪ ሠርግ ይህን ይመስል ነበር
46616106
https://www.bbc.com/amharic/46616106
ቴክኖሎጂ የመጥፋት አደጋ የጋረጠባቸው ሙያዎች
«ማንኛውም ዓይነት ሥራ፤ በተለይ ደግሞ ብዙ ሊከብድ የማይችል ተብሎ የማይታሰብ፤ ከአምስት እና አሥር ዓመት በኋላ በሂሳብ ቀመር ሊሠራ ይችላል።»
'ሮቦቶቹ እየመጡ ነው' በሚለው አነጋጋሪ መፅሐፉ የሚታወቀው ጆን ፑሊያኖ መፃዒውን ሲተንብይ ነው እንዲህ ሲል ያስቀመጠው። ፑሊያኖ፤ ከቢቢሲ ጋር ወግ ሲጠርቅ ነው ወደፊት በሰዎች የሚሠሩ ሙያዎች፤ በተለይ ደግሞ የፋብሪካ ሥራዎች በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎች ይወረሳሉ ሲል የተደመጠው። • አምስቱ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጎዳናዎች በ2018 ይህ ዜና ለሰሚ ጆሮ አዲስ አይደለም፤ አዲሱ ነገር ቴክኖሎጂ ብዙ አይነካቸውም ተብለው የሚታሰቡ መስኮችም አደጋ ላይ መሆናቸው ነው። «ዶክተሮች አሊያም የሕግ ባለሙያዎች ሥራቸውን በቴክኖሎጂ ላይነጠቁ ይችላሉ፤ ነገር ግን ተያያዥ ሥራዎቻቸው አደጋ ላይ ነው።» ተስፋ ያላቸው ያልተጠበቁ ችግሮችን መፍታት የሚችሉ ሰዎች ቴክኖሎጂ ሊያከናውን የሚችለውን ነገር የሚሠሩ ከሆነ 'አበቃላቸው' ባይ ነው ፑሊያኖ። ፑሊያኖ፤ የኮምፒውተር ደህንነት ባለሙያዎች በሚመጣው ዘመን ተፈላጊነታቸው እጅግ የላቀ ነው፤ በተለይ የሳይበር ጥቃትን ቀድመው መገመት እና መከላከል የሚችሉቱ ሲል ያምናል። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ «ግን እንዲህ ስላችሁ ሌላው ሙያ አፈር በላ ማለቴ አይደለም» ይላል ፀሐፊው፤ የሳይኮሎጂ (ስነ-ልቡና) ባለሙያዎች፤ የአእምሮ ጤንነት አማካሪዎች እና ተያያዥ ሙያዎችም ተፈላጊነታቸው እየላቀ ይመጣል። ቢያንስ ባደጉት ሃገራት ከታች የምንጠቅሳቸው ሰባት የተከበሩ ሙያዎች በቴክኖሎጂ ምክንያት አደጋ የተጋረጠባቸው ናቸው፤ በፀሐፊው ቀመር መሠረት። ሕክምና ይህ ሃሳብ የሚዋጥ ባይሆንም ግን ሃቅ ነው ሲል ፑሊያኖ ያትታል። ባደጉ ሃገራት የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ወደፊት ጤና የሚጠበቀው በቴክኖሎጂ እገዛ ስለሚሆን ሙያቸው አደጋ ላይ ነው። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች እና የቀዶ ጥገና ባለሙያዎች ግን ከዚህ አደጋ የተረፉ ናቸው። የሕግ ባለሙያዎች ተሽከርካሪ ወንበራቸው ላይ እየተንፈላሰሱ ከጠረጴዛ ጋር የተገናኘ ሥራ የሚሰሩ የሕግ ባለሙያዎች ወዮላቸው፤ ፑሊያኖ እንደሚለው። ፀሐፊው፤ በአንድ የተለየ የሕግ ሃሳብ ላይ የረቀቀ እውቀት የሌላቸው የሕግ ሰዎች፤ እመኑኝ አደጋ ላይ ናቸው ሲል ማስጠንቀቂያ ቢጤ ጣል ያደርጋል። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? የሥነ-ሕንፃ ባለሙያዎች 'ምጡቅ' ተማሪዎች ብቻ ተመርጠው የሚገቡበት የሥነ-ሕንፃ ትምህርት ክፍል ሰዎች ይህን ቢሰሙ ይኼ ሰውዬ አበዛው ማለታቸው አይቀርም። ፑሊያኖ ግን ነገሩ ወዲህ ነው ይላል። የህንፃ ዲዛይኖች በቀላሉ የኢንተርኔት አውታር ላይ በሚገኙበት ዓለም ላይ እንዴት ሆኖ ነው 'አርክቴክቶች' በጣም ተፈላጊ ናቸው የምንለው የሚል መከራከሪያ በማቅረብ። ተስፋ ቢጤ ግን ጣል ሳያደርግ አላለፈም። እጅግ የተለየ ጥበባዊ ሥራ የሚሠሩ 'አርክቴክቶች' የማይደገም ዲዛይን ሊሠሩ ስለሚችሉ ተስፋ አላቸው ይላል ፑሊያኖ። አካውንታንቶች [የሒሳብ ሰራተኞች] በጣም ውስብስ የሆኑ ፈተናዎችን መመፍታት የሚችሉ አካውንታንቶች እንኳ ችግር የለባቸውም፤ ነገር ግን የተለመዱ ሥራዎችን የሚሠሩ የአካውንቲንግ ባለሙያዎች በገበያው የመፈለጋቸው ነገር አስጊ ነው። የጦር አውሮፕላን አብራሪዎች አሁንም እያየነው እንዳለነው ሃገራት ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን በመጠቀም ላይ ናቸው። ይህ ደግሞ ወደፊትም የሚቀጥል እንጂ የሚቆም አይደለም። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ፖሊስ እና መርማሪ እኚህ ሙያዎችም መቼም አይጠፉም፤ ነገር ግን አስፈላጊነታቸው እየመነመነ እንጂ እየጨመረ አይመጣም። በምትኩ በተለይ ያደጉ የሚባሉ ሃገራት እጅግ የረቀቁ መሣሪያዎችን በመጠቀም ወንጀልን መከላከል ይመርጣሉ። • የወባ በሽታን በትንፋሽ ማወቅ ተቻለ ድለላ ድለላ መቼም የማይነጥፍ ሥራ ሊመስለን ይችላል፤ ቢሆንም የምንፈልጋቸውን ዕቃዎች እና አገልግሎቶችን ይዘው በኮምፒውተር መስኮቶቻችን ብቅ የሚሉ ድረ-ገፆች ተበራክተዋል። እርግጥ በይነ-መረብን ተጠቅመው የሚደልሉ ላይጠፉ ይችላሉ፤ እንደቀደመው ጊዜ ግን በእግር መንከራተቱ የሚያበቃለት ይመስለኛል ሲል ይተነብያል። ፑሊያኖ ከላይ የጠቀሳቸው መስኮች አደጉ በሚባሉ ሃገራት የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ናቸው ይባሉ እንጂ በጊዜ ሂደት በማደግ ላይ ወዳሉ ሃገራት መምጣታቸውን መገመት ግን የሚከብድ አይመስልም፤ ዘመኑ የቴክኖሎጂም አይደል!
news-47479373
https://www.bbc.com/amharic/news-47479373
ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞን ቀሰቀሱ
የ20/80ና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ይፋ መሆን ጋር ተያይዞ ቦታው የኦሮሚያ ነው በሚል በ10 ኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የተገነቡባቸው አካባቢዎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሆነው የአዲስ አበባ መስተዳድር ውሳኔ የሚያሳልፈው እንዴት ነው፤ ለተፈናቃዮቹ አርሶ አደሮች የተሰጠው ካሳ እዚህ ግባ የማይባል ነው፤ የተቀናጀው ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ሀሳቦችን ተቃዋሚዎቹ አንስተዋል። •«ማስተር ፕላኑ ተመልሶ ይመጣል» አቶ ኩማ ደመቅሳ በምስራቅ ኦሮሚያ ጪሮ ከተማ ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ ሰልፈኛ " በዚህ ተቃውሞ ላይ ዋነኛ መልዕክታችን በአዲስ አበባ አካባቢ ያሉት መሬቶች ለኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ሊመለስ ይገባል" የሚል ነው። ተቃዋሚው ጨምሮም ለብዙዎች ሞት ምክንያት የሆነው አወዛጋቢው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሊመለስ አይገባም ብሏል። ተቃውሞዎቹ በሻሸመኔ፣ ጪሮ፣ ጂማ፣ አሰላ፣ አዳማና ሂርና ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተስፋፉ ሲሆን በሻሸመኔ አካባቢ የሚገኙ ሰልፈኞች "ኦዲፒ ያልነውን ረስታችሁታል፤ መሬታችን የደም ስራችን ነው" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ነበር። •የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ በትናንትናው ዕለት 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል የዕጣ ማውጫ ስነ ስርአት ለተጠቃሚዎች የተላለፈ ሲሆን፤ ከአካካቢው ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ያለ እጣ እንዲሰጣቸው በከተማው አስተዳደር ካቢኔና በቤቶች አስተዳደር ውሳኔ መሰረት እንዲተላለፍ መወሰኑን ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በትናንትናው ዕለት ገልፀዋል። የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ሲገነቡ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ያልደበቁት ምክትል ከንቲባው "በተለይም የእርሻ መሬታቸውን ለነዚህ ተግባራት ሲሉ የለቀቁና ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ የአርሶ አደር ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ህመማችሁ የእኛ መሆኑን እንድታውቁ" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። ምክትል ከንቲባው ይህንን ቢሉም ኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ትችቶችም እየተሰሙ ነው። ምንም እንኳን የተቀናጀው ማስተር ፕላን ከፍተኛ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ውድቅ ቢደረግም የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባና ኦህዴድ ሊቀ መንበር አቶ ኩማ ደመቅሳ ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ "ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል" ብለው ለቢቢሲ መናገራቸው የሚታወስ ነው። •ልማትና የአርሶ አደሮች መፈናቀል በአዲስ አበባ ምንም እንኳን ከመንግሥት በኩል ምንም አይነት መግለጫ ባይሰጥም በቅርቡ ከውጭ ሀገር የተመለሰው የተባበሩት ኦነግ በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ያለውን ድንበር መወሰን ያለበት የኦሮሚያ ክልል ነው የሚል ነው። በ13ኛው ዙር የ20/80 ቤቶች 32ሺ 653 ቤቶችና በ2ኛ ዙር የ40/60 ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 1ሺ 248 ስቱዲዮ፣ 18ሺ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7ሺ 127 ባለሁለት መኝታ እና 5ሺ455 ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ መሆናቸው ተገልጿል። በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱትም በ1997 ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ደንበኞች መሆኑ ተገልጿል።
news-53987821
https://www.bbc.com/amharic/news-53987821
ካንሰር፡ የንብ ሰንኮፍ የያዘው መርዝ "የተወሰኑ የጡት ካንሰር ሴሎችን ይገድላል"
አውስትራሊያውያን ተመራማሪዎች የንብ ሰንኮፍ አደገኛ የሆነ የጡት ካንሰር ሴልን እንደሚያጠፋ በላብራቶሪ ሙከራ ወቅት ማረጋገጣቸውን ገልፀዋል።
በንብ ሰንኮፍ ውስጥ ያለው መርዝ ሜልቲን የተባለ ውህድ የያዘ ሲሆን ይህም ሁለት ለማከም አስቸጋሪ የሆኑ የካንሰር ዓይነቶች ለማከም ምርምር ተደርጓል። እነዚህ የካንሰር አይነቶች ትሪፕል ኔጋቲቭ እና HER2 የተባሉ ናቸው። የምርምር ውጤቱ በሳይንቲስቶቹ "አስደናቂ" በሚል የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን ተጨማሪ ምርመር መደረግ እንዳለበት ተገልጿል። በዓለማችን ላይ ሴቶችን ከሚያጠቁት የካንሰር አይነቶች መካከል የጡት ካንሰር አንዱ ነው። በቤተ ሙከራ ውስጥ የካንሰር ሴሎችን ለመዋጋት በሺዎች የሚቆጠሩ ኬሚካሎች ቢኖሩም ለሰው ልጅ ህክምና ጥቅም ላይ የሚውሉት ግን ጥቂቶቹ ናቸው። ከዚህ ቀደም የንብ ሰንኮፍ የያዘው መርዝ ሜላኖማ ለሚሰኝ የካንሰር ዓይነት ፀረ ካንሰር የሆነ ንጥረ ነገር መያዙ ይታወቅ ነበር። ጥናቱ እየተሰራ ያለው በምእራብ አውስትራሊያ በሚገኘው በሃሪ ፐርኪንስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ሜዲካል ሪሰርች ሲሆን፣ የጥናቱ ውጤት የታተመው ደግሞ በዘርፉ ባለሙያዎች አርትኦትና ግምገማ በሚሰራለት ኔቸር ፕሪሲሽን ኦንኮሎጂ መጽሔት ላይ ነው። በጥናቱ የተገኘው ምንድን ነው? ከ300 ከሚበልጡ እና ከሁለት አይነት የንብ ዝርያዎች የተወሰደው መርዝ ላይ ሙከራ ተደርጓል። የንቦቹ አይነት የማር ንብ እና 'በምብል ቢ' የሚባሉት ናቸው። ከማር ንብ የተወሰደው መርዝ "በጣም ኃይለኛ" መሆኑን ለሶስተኛ ዲግሪዋ ምርምሯን እየሰራች የምትገኘው እና ጥናቱን የምትመራው የ25 ዓመቷ ሲያራ ዱፊ ተናግራለች። በንቦቹ ሰንኮፍ ውስጥ ያለው መርዝ ሌሎች ሴሎች ላይ አነስተኛ ጉዳት በማድርስ፣ የካንሰር ሴሎችን በአንድ ሰዓት ውስጥ ይገላል ስትል የጥናቷን ግኝት ታስረዳለች። ተመራማሪዎቹ ጨምረው ያገኙት ነገር ሜሊቲን የተሰኘው ውህድ በራሱ የካንሰር ሴል እድገትን በማስተጓጎል አልያም "በማቋረጥ" ረገድ ውጤታማ መሆኑን ነው። ሜሊቲን በማር ንብ ሰንኮፍ መርዝ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በፋብሪካም ሊመረት ይችላል። ከጡት ካንሰሮች ሁሉ አደገኛ የሆነው ትሪፕል ኔጋቲቭ በቀዶ ህክምና፣ ራዲዮቴራፒ እና ኬሞቴራፒ ነበር የሚታከመው። በዚህ የካንሰር ዓይነት የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር ከአጠቃላይ የጡት ካንሰር ታማሚዎች ከ10 እስከ 15 በመቶ ያህል ያለውን ይይዛሉ። ወደ ፊት ልንገለገልበት እንችላለን? ረብዑ እለት፣ የምዕራብ አውስትራሊያ ተመራማሪዎች ኃላፊ ውጤቱን "እጅጉን አስደናቂ" ሲሉ ገልፀውታል። "በተጨባጭ ሜሊቲን እንዴት የጡት ካንሰር ሴሎችን እድገትና መራባት እንደሚያቋርጥ አሳይቷል" ያሉት ፕሮፌሰር ፒተር ክሊንከን ናቸው። "ይሀ የተፈጥሮ ውህዶች የሰውን ልጅ በሽታ ለማከም እንዴት እንደሚውሉ የሚያሳይ ሌላ ድንቅ ምሳሌ ነው" ነገር ግን ተመራማሪዎቹ የንብ ሰንኮፍ የያዘው መርዝ መድሃኒቶች ካንሰርን በሚዋጉበት ልክ መዋጋት ይችላል የሚለው ላይ ሌላ ምርመር እንደሚቀረው አስጠንቅቀዋል። ከሲድኒ በጋርቫና ኢንስቲትዩት ኦፍ ሜሪካል ሪሰርች የሚሰሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር አሌክስ ስዋርብሪክ በበኩላቸው የንብ ሰንኮፍ የያዘው መርዝ የካንሰር መድሃኒት ነው ብሎ ለመደምደም " ጊዜው ገና ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጡት ካንሰር 12 ምልክቶች
news-53297255
https://www.bbc.com/amharic/news-53297255
በጃፓን የእንክብካቤ ማዕከል በጎርፍ ተጥለቅልቆ 14 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ
በጃፓን ደቡባዊ ደሴት ክዩሹ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ በተፈጠረ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ 16 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የደረሱበት አለመታወቁ ተገለፀ።
ከሟቾቹ 14ቱ የተገኙት በጎርፍ በተጥለቀለቀ አንድ የእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ነው። የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል። ኩማሞቶ እና ካጎሺማ በአደጋው ክፉኛ የተጠቁ ግዛቶች ናቸው። የኩማሞቶ ገዢ ኢኮ ካባሺማ በእንክብካቤ ማዕከላት የነበሩት ተጎጂዎች ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ መሞታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ የጤና ባለሙያዎች የሞት ምስክር ወረቀት አለመስጠታቸውም ተገልጿል። አደጋውን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፤ ቤቶችና መኪኖች በጎርፍ ተውጠው ከሚያሳይ ፎቶ ጋር በኩማ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ በጎርፍ ሲወሰድ ያሳያሉ። ባለሥልጣናትም ከ200 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ያዘዙ ሲሆን፤ የነፍስ አድን ሰራተኞችን ለማገዝም 10 ሺህ ወታደሮችን ወደ ሥፍራው ልከዋል። ይሄው እየጣለ ያለው ዝናብ ዛሬም እንደሚቀጥል ትንበያ ተቀምጧል። ጠቅላይ ሚኒስተር ሽንዞ አቤ በበኩላቸው ሰዎች በተጠንቀቅ እንዲጠባበቁ አሳስበዋል። የጃፓን የሚትዮሮሎጂ ኤጀንሲ በአካባቢው እንደዚህ ዓይነት ዝናብ ከዚህ በፊት አጋጥሞ እንደማያውቅ ተናግረዋል። በተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ የሚገኙ አንድ ሴት ዝናብ ይህን ያህል ኃይለኛ ሊሆን ይችላል ብለው በእውናቸውም በህልማቸውም አስበው እንደማያውቁ ተናግረዋል። ሌላኛዋም በበኩላቸው በአቅራቢ ያለው ወንዝ እየነጎደ ሲወርድ ምን ያህል አደገኛ እንደነበር መረዳታቸውን ገልፀዋል። የጃፓን ብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን (ኤንኤችኬ) ታኪኖ አካባቢ ስምንት ቤቶች በጎርፍ እንደተወሰዱ የሚያስረዱ ዘገባዎች መኖራቸውን ገልጿል።
news-56898071
https://www.bbc.com/amharic/news-56898071
የጣልያን ፖሊስ 30 ተጠርጣሪ የናይጄሪያ 'ወሮበላ' ቡድን አባላትን ያዘ
የጣልያን ፖሊስ በመላው አገሪቱ አሰሳ ካካሄደ በኋላ የናይጄሪያ 'ብላክ አክስ' የማፊያ ብድን አባላት እንደሆኑ የተጠረጠሩ 30 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ።
ተጠርጣሪዎቹ በሰዎችና በዕፅ ዝውውር፣ በወሲብ ንግድና በኢንተርኔት የሚደረግ ውንብድና ላይ በመሳተፍ የሚሉትን ጨምሮ ከ100 በላይ ክስ እንደሚጠብቃቸው ፖሊስ ገልጿል። የወንበዴ ቡድኑ 'ዳርክ ዌብ' በተሰኘ ድብቅ የኢንተርኔት መረብ ውስጥ በዲጂታል ገንዘብ ወይም ቢትኮይን በመገበያየትም ተጠርጥሯል። እንደ አውሮፓውያኑ በ970ዎቹ በናይጄሪያ ብቅ ያለው 'ብላክ አክስ' በመድፈር፣ በአካል ማጉደልና በመግደል ይታወቃል። ቡድኑ ቀስ በቀስ ጠንካራ የግንኙነት መረቡን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ማሳደግ ችሏል። በጣልያን የሚገኘው ቡድን ናይጄሪያ ካለው በአርማ፣ በቃላት አጠቃቀምና ተግባሮቻቸውን በማየት ቀጥታ ግንኙነት እንዳላቸው ፖሊስ ገልጿል። በጣልያን በሚገኙ 14 አውራጃዎች በተደረገ አሰሳ ነው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል በጣሊያን 'የብላክ አክስ' መሪ ነው የተባለ የ35 ዓመት ግለሰብም ይገኝበታል። "ይህ የፖሊስና የፍትሕ አካላት ተግባር ወንጀላቸውን ማስፋፋት ለሚፈልጉ አዳዲስና የቀድሞ የወንበዴ ቡድኖችን ለማደን ያለውን አቅም የሚረጋግጥ ነው" ሲሉ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሉቺያና ለሞራጋሴ ባወጡት መግለጫ አስረድተዋል። 'ብላክ አክስ' ማነው? በናይጄሪያ የተመሠረተው ቡድኑ በዓለም ላይ ዝነኛ ስም ያለው በድብቅ የሚንቀሳቀስ የወንበዴዎች ስብስብ ነው። 'ብላክ አክስ' ከ50 ዓመታት በፊት የተመሠረተና ቀድሞ 'ኒዎ ብላክ ሙቭመንት' በሚል የሚታወቅ ሲሆን፤ ዓላማዬ የሚለው ደግሞ ጥቁር ዘርን "ነፃ ማውጣት" የሚል ነበር። ሆኖም ቡድኑ ዓላማዬ ብሎ ከያዘው በተቃራኒ ሰዎችን መግደልና መድፈር መታወቂያው ሆነ። ከሚሊሻ ጋር የሚመሳሰል የዕዝ ሰንሰለት ያለውም ነው። ይህ የ'ወሮበላ' ቡድን በናይጄሪያ በመቶች የሚቆጠሩ አባላቱ ቢታሰሩበትም አሁንም አዳዲስ አባላትን በተለይም ከዩኒቨርስቲ እንደሚመለምል ተዘግቧል።
news-49850088
https://www.bbc.com/amharic/news-49850088
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ስለአባይ አጠቃቀም ምላሽ ሰጡ
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር የአባይ ወንዝ ለተፋሰሱ ሃገራት የጋራ ሃብት እንጂ የፍጥጫ ምንጭ ሊሆን እንደማይገባ አሳሰቡ።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዝዳንቷ በ74ኛው የድርጅቱ ጉባኤ ላይ በአማርኛ ባደረጉት ንግግር ላይ ኢትዮጵያን በተመለከተ የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን በማጠቃለያቸው ላይ የግብጹ ፕሬዝዳንት ከእርሳቸው ቀደም ብለው አባይን በተመለከ ለገለጹት ስጋት ምላሽ ሰጥተዋል። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባለፈው ረቡዕ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለችውን ግድብ በተመለከተ የሚደረገው ድርድር ውጤት ላይ አለመድረሱ በአካባቢው ላይ አለመረጋጋትን ሊያስከትል እንደሚችል መናገራቸው ይታወሳል። • ክፍል 1 ፡በፅኑ የታመመው የዓባይ ወንዝ • አል ሲሲ ግብፅ በአባይ ላይ ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ ቃል ገቡ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ለዚህ የግብጹ ፕሬዝዳንት ንግግር ምላሽ በሚመስል ሁኔታ "የአባይ ወንዝ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ሃብት እንጂ የጥርጣሬና የውድድር ምንጭ ሊሆን አይገባም" በማለት ሃገራቱ የወንዙን ውሃ በጋራ መጠቀም እንዳለባቸው አመልክተዋል። ፕሬዝዳንቷ አክለውም የተፋሰሱ ሃገራት "የአባይን ወንዝ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ለመጠቀምም በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ" በንግግራቸው ላይ አንስተዋል።። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያ ከሰባት ዓመት በፊት በአባይ ወንዝ ላይ መገንባት የጀመረችውን ግዙፉን የህዳሴ ግድብ በተመለከተ ቅሬታና ተቃውሞ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። • ክፍል 2 ፡የህዝብ ብዛት መጨመርና የአካባቢ ብክለት ሌሎቹ የዓባይ ስጋቶች • ክፍል 3 ፡የዓለማችን ረጅሙ ወንዝ መፃኢ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? አሁንም የዓለም ሃጋራት መሪዎች ስለሃገራቸውና በተለይ እንዲሁም ስለዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ንግግር በሚያደርጉበት ዓመታዊው የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ የግድቡን ጉዳት አንስተውታል። በዚህ ንግግራቸውም ፕሬዝዳንቱ በሚገነባው ግድብ ዙሪያ ለዓመታት እየተካሄደ ያለው ውይይትና ድርድር ውጤት አለማስገኘቱ እንዳሳሰባቸው አመልክተዋል። አክለውም ከግድቡ ግንባታ ባሻገር ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚጀመረውን የውሃ አሞላልና አያያዝን በተመለከተ ለዓመታት የተደረጉትን ውይይቶች አንስተው እንደተፈለገው ውጤታማ ሊሆኑ እንዳልቻሉ ለጉባኤው ታዳሚዎች ተናግረው ነበር። ይህም በዚህ ከቀጠለ በሃገራቸው መረጋጋትና ልማት ላይ እንዲሁም በአካባቢው ሃገራት ላይ ከፍ ያለ ተጽእኖን እንደሚያስከትል አሳስበዋል። ፕሬዝዳንት ሲሲ በንግግራቸው እንዳሉት ኢትዮጵያ ግድቡን ያለ በቂ ጥናት ለመገንባት መነሳቷን አመልክተው በዚህም ሃገራቸው ቅሬታ እንዳልነበራት ቢገልጹም በወቅቱ በስልጣን ላይ ከነበሩት የግብጽ ፖለቲከኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቶ እንደነበር አይዘነጋል። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ፣ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት ካይሮ ላይ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ በተከታታይ የሚያደርጉት የሦስትዮሽ ውይይት ካይሮ ላይ የተካሄደ ቢሆንም ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በ74ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከዚህ ከአባይ ጉዳይ ባሻገር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ንግግር አድርገዋል። የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር በመቅረፅ አበረታች ስራ መስራቷን ገልፀዋል። አፍሪካ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ቋሚ መቀመጫ አንዲኖራትም ጠይቀዋል።
news-48687915
https://www.bbc.com/amharic/news-48687915
የአለም ተፈናቃዮች ቁጥር ከ70 ሚሊዮን በላይ ደርሷል
በባለፈው የፈረንጆች ዓመት በዓለም ዙሪያ አዲስ ከተፈናቀሉ ሰዎች መካከል ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው መረጃ አመለከተ።
የተፈናቃዮቹ ቁጥር 1.5 ሚሊዮን ሲሆን ከእነዚህም መካከል 98 በመቶዎቹ እዚያው ሃገር ውስጥ የተፈናቀሉ ናቸው። ይህ አሃዝ ቀደም ሲል ከነበረው ከእጥፍ በሚበልጥ ቁጥር የጨመረ ሲሆን ከዚያም በኋላ ቁጥሩ ጨምሯል። • የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ • የጌዲዮ ተፈናቃዮች የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ለዚህ መጠኑ ከፍተኛ ለሆነው የሃገር ውስጥ መፈናቀል ተጎራብተው በሚኖሩ የተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል ባለፈው ዓመት ባጋጠሙ ግጭቶች ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስር የስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው አካል በዓለም ዙሪያ በግጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በታሪክ ካጋጠመው ከፍተኛ ቁጥር ላይ መድረሱንም አስታወቋል። ድርጅቱ በየዓመቱ በሚያወጣው የስደተኞች ሁኔታ ሪፖርቱ ላይ እንዳመለከተው በአሁኑ ወቅት የተፈናቃዮቹ ቁጥር ከ70 ሚሊዮን በላይ ደርሷል። በጦርነቶችና ጥቃቶችን በመሸሽ ከቀያቸውና ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ መጠጊያና መፍትሄ ለመስጠት አዳጋች እንደሆነ ድርጅቱ አመልክቷል። • አምስት ነጥቦች ስለጌዲዮ ተፈናቃዮች • የጌዲዮ ተፈናቃዮች ሁኔታ በፎቶ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች የወጡባት ሃገር ቬንዙዌላ ናት። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ፊሊፖ ግራንዴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የተከሰተውን አሳሳቢ የስደተኞች ጫና ተሸክመው የሚገኙት ደሃ ሃገራት ሲሆኑ ባለጸጋዎቹ ሃገራት እገዛ ለማድረግ የበለጠ መስራት አለባቸው። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ መሰረት በዓለም ዙሪያ ካሉ ስደተኞች መካከል ከሁለት ሦስተኛው የሚበልጡት የመጡት ከአምስት ሃገራት ነው። እነሱም ሶሪያ (6.7 ሚሊዮን)፣ አፍጋኒስታን (2.7 ሚሊዮን)፣ ደቡብ ሱዳን (2.3 ሚሊዮን) ማይናማር (1.1 ሚሊዮን) እና ሶማሊያ (900 ሺህ) ናቸው።
news-52430499
https://www.bbc.com/amharic/news-52430499
ኮሮናቫይረስ : ስለቫይረሱ ከሚናፈሱት በጥቂቱ፣ የአሪቲ መድኃኒትነት፣ የአለምን ህዝብ መቆጣጠሪያ መንገድ
የቢቢሲ ጋዜጠኞች ቡድን ከሰሞኑ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ማህበራዊ ሚዲያውን ያጥለቀለቁትንና ሃሰተኛ ወይም መሰረት የሌላቸውን መረጃዎች ሰብስቧል። የ ተዋናዩ ዘሮክ የገንዘብ ስጦታ
አሜሪካዊው ተዋናይ ድዋይን ጆንሰን ወይም ዘሮክ በኮሮናቫይረስ ወረርሸኝ ምክንያት ለተቸገሩ ሰዎች ገንዘብ ይሰጣል የሚል መረጃ በሺዎች በሚቆጠሩ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተጋርቷል። ከፍተኛ ገንዘብ እንደሆነም የተገለፀ ሲሆን በበርካታ ቋንቋዎችም ተተርጉሟል። አንዳንዶቹ ቪዲዮዎችም ሆነ ፎቶዎች እንደገና በማስመሰል ጥበብ ወይም በፎቶ ሾፕ የተሰሩ ናቸው። •በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበር መስራች አቶ መንግሥቴ አስረሴ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት ይህንንም ገንዘብ ለማሸነፍ ውድድር ተዘጋጅቷል የሚል መረጃም አብሮ የወጣ ሲሆን፤ ተሳታፊዎች ከሽልማቱ ዝርዝር ውስጥ ከስማቸው የመጀመሪያ ፊደል ጋር የሚመሳሰል መምረጥ ይኖርባቸዋል። አንዳንዶች በአስገራሚ ሁኔታ የባንክ መረጃዎቻቸውን በፌስቡክ አስተያየት መስጫ ያሰፈሩ ሲሆን፤ ለእርዳታም የተማፀኑም አልታጡም። ሽልማቶቻችሁን ኑ ውሰዱ በሚል የቀጠለ ሲሆን አንደኛው ቪዲዮ ላይ አንድ ግለሰብ ከፍተኛ ገንዘብ ሲቀበል ያሳያል። ይህንንም ቪዲዮ አራት ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል። ነገር ግን ቢቢሲ ማረጋገጥ እንደቻለው ቪዲዮው የሮክ አይደለም፤ የገንዘብ ሽልማቱም ማጭበርበር ነው። በፕሬዚዳንቱ ኮሮናቫይረስን ይፈውሳል የተባለው መድኃኒት የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት የኮሮናቫይረስን የሚከላከል ወይም የሚያድን መድኃኒት የለም ቢልም የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት ግን ኮሮናቫይረስን የሚከላከል መፈወሻ አግኝቻለሁ ብለዋል። ከዕፅዋት ተገኘ የተባለው መድኃኒት ከአርቲሜዥያ ወይም በኢትዮጵያውያን ዘንድ አርቲ ከሚባለው ተክል ነው። ይህ እፅ የወባ በሽታን የሚፈውሱ ንጥረ ነገሮችንም በውስጡ አካቷል። ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊና ታዲያ ይህንን የአርቲ ተክል ከሌሎች እፅዋት ጋር በመቀላቀል መድኃኒት እንደተሰራና፣ ሙከራም ተካሂዶ ፈዋሽነቱ ተረጋግጧል ብለዋል። ሁለት በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችንም ማዳኑንም ይፋ አድርገዋል። መድኃኒቱ ስለ ፈዋሽነቱ ምንም አይነት ማስረጃ ያልቀረበ ሲሆን የምርምር ተቋማትም ማረጋገጥ አልቻሉም። ፕሬዚዳንቱ ግን አልሰማም ብለዋል፤ ሃገሪቱ ጥላው የነበረውንም አስገዳጅ የቤት መቀመጥ ውሳኔም በከፊል አንስተዋል። •በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? •ከሚስታቸውና ከልጃቸው ጋር ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የአዳማ ነዋሪ ወደ ቤታቸው ተመለሱ የሃገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው ከአንድ ሺህ በላይ ወታደሮች በመዲናዋ አንታናናሪቮ ተሰማርተው መድኃኒቱን እያከፋፈሉ ነው። ህዝቡም ለመቀበል የተሰለፈበት ቪዲዮም ወጥቷል። አቅማቸው ለማይፈቅደው ማህበረሰብ በነፃ የሚከፋፈል ሲሆን ለሌላው ግን በትልልቅ መደብሮች መሸመት ይችላሉ። የጀርመኑ ማክስ ፕላንክ ተቋም በአርቴሚዥያ (አርቲ) ኮሮናን ለመፈወስ ያስችላል ወይ በማለት ምርመራ የጀመረ ሲሆን ውጤቱ አልታወቀም። ኮንጎም በአትክልቱ ላይ የምርምር ስራዎችን ጀምራለች። የብርቱካን ልጣጭ ፈዋሽነት ከሰሞኑ ሙቅ ውሃ፣ የብርቱካን ልጣጭ፣ ቪክስ ተብሎ የሚጠራው ቅባትን በመቀላቀል መጠጣት ቫይረስንም ሆነ ባክቴሪያን ይገላል፣ ሁሉንም ፀረ ተህዋሲያንንም ከሰውነት ያስወግዳል የሚለው ቪዲዮ በከፍተኛ ሁኔታ መነጋገሪያ ሆኗል። ወደ 1.6 ሚሊዮንም ሰዎች በቲክቶክ ተመልክተውታል። ቲክቶክ ቪዲዮውን ከገፁ ላይ ካወረደው በኋላም ቪዲዮው በኢንስታግራም ላይ ወጥቶ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል። ኢንስታግራምም ቪዲዮውን ከገፁ አጥፍቶታል። ሙቅ ውሃም ሆነ ሲትሪክ አሲድ ያለባቸውን ፍራፍሬዎች መመገብ የኮሮናቫይረስን ለማዳናቸው ምንም መረጃ የለም። በቪዲዮ ተጠቃሚዎች ዘንድ ዝነኛ በሆነው ቲክቶክ የተለያዩ ውዝግብን የሚያጭሩ ቪዲዮዎችም ወጥተዋል። ለምሳሌም ያህል የኮሮናቫይረስን እያዛመተ ያለው 5ጊጋ ባይት ኢንተርኔት ነው በሚል ከሴራ ጋር የተገናኙ መረጃዎች ተለቀዋል። በወጡትም ቪዲዮዎች ላይ በቴሌኮም ዘርፉ የሚሰሩ ሰራተኞችን ጥቃት እንዲደርስባቸው የሚያበራቱ መልእክቶችም ተላልፈዋል። ቪዲዮዎቹ ከቲክቶክ ገፅ ላይ የጠፉ ሲሆን ካሁን በኋላ በሴራ ላይ የሚያጠነጥኑ ቪዲዮዎችን እንደማይቀበሉም ለቢቢሲ ገልፀዋል። •የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ የግድ አስፈላጊ ሊሆን ነው? የኤድስ ምርምር ለቫይረሱ መንስኤ አይደለም ከሰሞኑ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሳይንቲስት ጋር በተደረገ ቃለ መጠይቅ የኮሮናቫይረስ በላብራቶሪ ነው የተፈጠረው የሚለው አስተያየት ከፍተኛ ውዝግብን ፈጥሯል። ሉክ ሞንታግኒየር የኤች አይቪ ቫይረስን ካገኙት ሳይንቲስቶች አንዱ ሲሆኑ በፈረንሳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበውም ቫይረሱ በድንገት ከውሃን ላብራቶሪ እንዳመለጠ ገልፀዋል። ሳይንቲስቱ እንደሚሉት የኤድስ በሽታ ላይ የሚደረግ ክትባትም ምርምር ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። ሳይንቲስቱ ይህንን ማለታቸውን ተከትሎ በርካታ መላምቶች ቢሰሙም ኮሮናቫይረስ ድንገት ከላብራቶሪ ለመውጣቱ ምንም አይነት መረጃ እንደሌለ የቢቢሲው የሳይንስ አዘጋጅ ፖውል ሪንከን ይናገራል። እስካሁን በቫይረሱ ላይ የተደረጉ ምርምሮች እንደሚያሳዩት ቫይረሱ ከእንስሳት እንደመጣ ነው። የሳይንቲስቱ አስተያየት የሰፈረበት ቪዲዮ ከፍተኛ ተመልካች አይቶታል፣ ለበርካታ መላምቶችም በር ከፍቷል። የአለምን ህዝብ የመቆጣጠሪያ መንገድ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዘው የሚሰጡ አስተያየቶች ማብቂያ የላቸውም። ኮሮናቫይረስን የፈጠሩት በአለም ታላላቅ የሚባሉ ኃይሎች ሲሆኑ ይህም የአለምን ህዝብ ለመቀነስ የወጠኑት ሴራ እንደሆነ የቀድሞው የሩሲያ ወታደራዊ ደህንነት ኃላፊ ቭላድሚር ካቭችኮቭ በዩቲዩብ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል። የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ በሰው ወይም በላብራቶሪ ስለመሰራቱ ሳይንሳዊ መረጃዎች ቢኖሩም በርካታ ሳይንቲስቶች ግን ከእንስሳት ነው የመጣው በማለት አጣጥለውታል ብለዋል። በባለፈው ወር የወጣው ይህንን ቃለ መጠይቅ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎች የተመለከቱት ሲሆን በርካቶችም በፌስቡክ እያጋሩት ነው፤ በተለያዩ ቋንቋዎችም ተተርጉሟል። •በኒውዮርክ የመድኃኒት መደብሮች የኮሮና ምርመራ ሊጀመር ነው
news-55895202
https://www.bbc.com/amharic/news-55895202
ትግራይ፡ ተመድ እና ኤንአርሲ በትግራይ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው አሉ
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር እና የኖርዌጂያን ሪፊዉጂ ካውንስል ዋና ጸሐፊ በትግራይ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው አሉ።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በትግራይ ያደረጉትን ጉብኝነት ሲያጠናቅቁ በክልሉ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል። በተመሳሳይ የኖርዌጂያን ሪፊውጂ ካውንስል (ኤንአርሲ) ዋና ጸሓፊ ጃን ኢግላንድ በትግራይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች በበቂ ሁኔታ ድጋፍ እያገኙ አይደለም ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መንግሥት በበኩሉ ለተፈናቃዮች የሚያስፈልገውን እርዳታ ለማቅረብ አቅሙ እና ዝግጁነቱ አንዳለው ከዚህ ቀደም አስታውቋል። ጃን ኢግላንድ "ባለፉት ሦስት ወራት ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ዘላቂነት ያለው እርዳታ መስጠት አልቻሉም። ወደ 2 ሚሊዮን ሰዎች ገደማ አፋጣኝ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ብዙ የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች ገብተዋል የሚባለው እውነት አይደለም። በተለይ በምዕራብና ማዕከላዊ ትግራይ ሰዎችን መድረስ አልቻልንም። እርዳታ መስጠት የተቻለው በመቀሌ ዋና ጎዳና ለሚገኙ እና በፌደራል መንግሥት ቁጥጥር ሥር ባሉ አካባቢዎች ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግራል። ከወራት በፊት በሕወሓት ኃይሎች እና በፌደራሉ መንግሥት መካከል በተከሰተው ግጭት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማስታወቁ ይታወሳል። የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ትናንት በሰጡት መግለጫ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሳይሆኑ የሰብዓዊ እርዳታ ሊደርሳቸው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው ጉብኝት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕምድን ጨምሮ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸውን ገልጸዋል። የሰላም ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከኮሚሽነሩ ጋር ወደ ትግራይ መጓዛቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፈረዋል። ወ/ሮ ሙፈሪያት ተፈናቃይ ዜጎችን ከፊሊፖ ግራንዲ ጋር መጎብኘታቸውን ገልጸው “መሻሻል ያለባቸው የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ . . . ከተወካዮች ጋር ተወያይተናል። አገልግሎታችንን የበለጠ ለማሻሻል እንድንችል ከባለጉዳዮቹ ያሉ አዎንታዊ አፈፃፀሞችና ጉድለቶችን ለመረዳት እድሉን አግኝቻለሁ” ብለዋል። ፊሊፖ ግራንዲኒ በበኩላቸው በጎበኟቸው በስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ያገኟቸው ስደተኞች ጾታዊ ጥቃቶች እንደደረሱባቸው ሪፖርት እንዳደረጉላቸው ተናግረው በአሁኑ ወቅት ጾታን መሠረት ያደረጉት ሪፖርቶችን በአሃዝ ማስቀመጥ እንደማይቻል ገልጸዋል። ግራንዲ፤ መንግሥት ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰተኞችን በገለልተኝነት አጣርቶ ጥፋተኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ እና የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ምንም አይነት ክልከላዎች እንዳይኖሩ ጠይቀዋል። በሌላ በኩል የሰላም ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት፤ “ከሚመለከታቸው ጋር ሆነን መልካም ተሞክሮዎቻችንና አቃፊ እሴቶቻችንን ይበልጥ እያጠናከርን ወገኖቻችን ያሉባቸውን ችግሮች ለማቃለል እንደሁልጊዜውም ሌት ተቀንእንተጋለን” ብለዋል። “ሰዎችን መድረስ አልቻልንም” የኖርዌጂያን ሬፊውጂ ካውንስል ዋና ጸሐፊ ጃን ኢግላንድ ትናንት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን ለመድረስ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም እርዳታ የሚሹ ሰዎችን መድረስ አለመቻላቸውን ተናግረዋል። “ሰዎችን መድረስ እንድንችል በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበናል። አንዳንዴ በፌደራል አንዳንዴ በክልል ደረጃ ፍቃድ ያላገኘንባቸው ወቅቶች አሉ። እርዳታ የሚፈልጉት ሰዎች ከሁለት ሚሊዮን በላይም ሊሆኑ ይችላሉ። አናውቅም። ድህነት የተንሰራፋበትና እርዳታ የሚፈልግ አካባቢ ነው” ሲሉ ተናግራል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር 2.5 ሚሊዮን መሆኑን እና ለእነዚህምዜጎች አስፈላጊ የሆነ እርዳታ ለማድረስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ሲያስታውቅ ነበር። የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራአመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ፤ "በትግራይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውሰዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን ሳይሆን 2.5 ሚሊዮን ነው" ብለዋል። ኮሚሽነሩ፤ 2.5 ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት መንግሥት በቂ ዝግጅት አድርጓልም ብለዋል። ጃን ኢግላንድ ግን “ጥቂት የጭነት መኪናዎችና እርዳታ ሰጪዎች እንዳሉ እንገነዘባለን። ያ ግን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች በቂ ተደራሽ አይሆንም” ይላሉ። “ሰብአዊ አርዳታ ሰጪዎችና መንግስት በጋራ ባደረጉት ግምገማ ወደ ምስራቅና ደቡባዊ ትግራይ ተጉዘዋል። ብዙ እርዳታ የሚፈልጉ እንዳሉ ታይቷል። የኖርዌጅያን ሬፊዩጂ ካውንስልን ጨምሮ ሌሎችም ድርጅቶች እርዳታ መስጠትይሻሉ። ከግጭቱ በፊት በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች እርዳታ ሰጥተናል። አሁን ደግሞ ከዚህም በላይ ለማድረግዝግጁ ነን።” ጃን ኢግላንድ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አራት ኤርትራውያን ከሚገኙባቸው መጠለያ ጣቢያዎች በሁለቱ እርዳታ ቁሶችን ማቅረባቸውን ይሁን እንጂ የተቀሩት ሁለት መጠለያ ጣቢያዎች መድረስ አለመቻላቸው እንዳሳሰባቸው ለቢቢሲተናግረዋል። “ሁለት ካምፖች ውስጥ ለኤርትራውያን መጠነኛ እርዳታ ማድረግ ተችሏል። በኤርትራውያኑ ዘንድ የእርዳታ ፍላጎቱ ከፍተኛ ነው። ሁለት ካምፖችን ግን መድረስ አለመቻሉ እጅግ ያሳስባል። የሰብዓዊ መብትና ግጭትን የተመለከቱ ዓለም አቀፍ ሕግጋት ጥሰት እንዳሉ ሪፖርቶች ደርሰውናል። ስደተኞች ጥቃት እንደደረሰባቸው ሰምተናል። ወደ ኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ሄጄ በርካታ ስደተኞች አግኝቻለሁ። አሰቃቂ ታሪኮች ነው የነገሩኝ።"
news-52297720
https://www.bbc.com/amharic/news-52297720
የመጀመሪያውን ኮሮናቫይረስ ስላገኘችው ሴት ያውቃሉ?
የመጀመሪያውን ኮሮናቫይረስ ያገኘችው የስኮትላንዳዊ አውቶብስ ሾፌር ልጅ ናት።
ጁን አልሜዳ ትባላለች። ትምህርት ያቋረጠችው በ16 ዓመቷ ነበር። ዶ/ር ጁን በቫይረስ ምርምር ፈር ቀዳጅ ከሚባሉት አንዷ ናት። የኮሮናቫይረስ ወረርሽን ተከትሎም ከዓመታት በፊት የሠራቸው ሥራ ዳግም መነጋገሪያ ሆኗል። ኮቪድ-19 አዲስ ቫይረስ ቢሆንም ከኮሮናቫይረስ አይነቶች አንዱ ነው። የመጀመሪያውን ኮሮናቫይረስ ዶ/ር ጁን ያገኘችው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1964፣ በለንደኑ ሴንት ቶማስ ሆስፒታል ውስጥ በሚገኝ ቤተ ሙከራዋ ነበር። በ1930 የተወለደችው ጁን፤ መደበኛ ትምህርት እምብዛም ሳታገኝ ነበር ከትምህርት ቤት የወጣችው። ነገር ግን ግላስጎው ውስጥ የቤተ ሙከራ ቴክኒሻንነት ሥራ አገኘች። 1954 ላይ ወደ ለንደን አቅንታ ኤንሪኬ አልሜዳ ከሚባል ቬንዝዊላዊ አርቲስት ጋር ትዳር መሰረተች። የጉንፋን ምርምር ጥንዶቹ ልጃቸውን ይዘው ወደ ቶሮንቶ ካናዳ ሄዱ። ዶ/ር ጁን ማይክሮስኮፕ የመጠቀም ችሎታዋን ያዳበረችው በኦንትርዮ ካንሰር ተቋም እንደሆነ የህክምና ጉዳዮች ጸሐፊው ጆርጅ ዊንተር ይናገራል። ቫይረሶችን በተሻለ ሁኔታ ማየት የሚቻልበትን መንገድ በመቀየስ ፈር ቀዳጅ የሆነችው፤ ዶክተሯ በ1964 ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ተመልሳ በሴንት ቶማስ ሆስፒታል ትሠራ ጀመር። (ይህ ሆስፒታል የዩኬው ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ የታከሙበት ነው።) ዶ/ር ጁን በወቅቱ በጉንፋን ላይ ይመራመር ከነበረው ዶ/ር ዴቪድ ታይሮል ጋር ተጣመረች። ዶ/ር ዴቪድ ከፍቃደኛ ሰዎች የአፍንጫ ፈሳሽ ናሙና በመውሰድ ከጉንፋን ጋር የተያያዙ ጥቂት ቫይረሶችን ለማግኘት ችሎ ነበር። ሁሉንም የቫይረስ አይነቶች ግን አላገኘም ነበር። ከናሙናዎቹ አንዱ በ1960 ከነበረ አዳሪ ትምህርት ቤት የተወሰደ፤ B814 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ነበር። ዶ/ር ዴቪድ ይህ ናሙና በኤሌክትሮን ማይክሮስኮፕ ይታይ እንደሆነ ዶ/ር ጁንን ጠየቀ። ዶክተሯም የቫይረሱን ቅንጣቶች አይታ እንደ ኢንፍሉዌንዛን ቢመስልም ኢንፍሉዌንዛ ያልሆነ ቫይረስ መሆኑን ገለጸች። ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የሰው ኮሮናቫይረስ ነው። ኮሮናቫይረስ የህክምና ጉዳዮች ጸሐፊው ጆርጅ እንደሚለው፤ ዶ/ር ጁን የአይጦች ሄፒታይተስ እና ዶሮዎችን የሚያጠቃ ብሮንካይትስ ላይ ስትመራመር ተመሳሳይ የቫይረስ ቅንጣቶች አግኝታለች። ሆኖም ጥናቷ በሙያ አጋሮቿ መጽሔት ላይ ለመውጣት ተቀባይነት አላገኘም ነበር። የመፍሔቱ ዳኞች፤ ተመራማሪዋ የተጠቀመቻቸው የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ቅንጣቾች ምስሎች መጥፎ ናቸው ብለው ነበር ጥናቱን ውድቅ ያደረጉት። በ1965 ግን ጥናቱ በ ‘ብሪትሽ ሜዲካል ጆርናል’ ታተመ። ዶ/ር ጁን የተጠቀመችው ምስል ደግሞ ከሁለት ዓመት በኋላ ‘ጆርናል ኦፍ ጄነራል ቫይሮሎጂ’ በተባለ መጽሔት ታትሟል። ኮሮናቫይረስ የሚለውን ስያሜ ያወጡት ዶ/ር ጁን፣ ዶ/ር ዴቪድ እና የወቅቱ የሴንት ቶማስ ኃላፊ ፕሮፌሰር ቶኒ ዋተርሰን ናቸው። የቫይረሱን ምስል ሲመለከቱ፤ እንደ ጨረር ያለ ነገር እንደከበበው ስላዩ ኮሮናቫይረስ ብለውታል። ጁን፤ ዶክትሬቷን ያገኘችው ለንደን ውስጥ ነበር። በመጨረሻም ‘ዌልካም ኢንስቲትዩት’ ውስጥ ስትሠራ የተለያዩ ቫይረሶችን በመለየት አስመዝግባለች። ከዚህ ተቋም ከለቀቀች በኋላ፤ ዩጋ መምህርት ሆና ነበር። በ1980ዎቹ ግን ወደ ህክምናው ዘርፍ ተመልሳ፤ የኤችአይቪ ቫይረስ ምስሎችን በማንሳት አማካሪ ሆናለች። ዶክተሯ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው በ2007፣ በ77 ዓመቷ ነው። ሕይወቷ ባለፈ በ13 ዓመቱ ለሥራዋ ተገቢውን እውቅና እያገኘች ነው። ዛሬ ላይ የመላው ዓለም ራስ ምታት የሆነውን ቫይረስ ለመገንዘብ የዶ/ር ጁን ምርምር አስፈላጊ ነበር።
51004414
https://www.bbc.com/amharic/51004414
ኢራን ከዚህ በኋላ ለአሜሪካና አጋሮቿ ማዕቀብ እንደማትገዛ አስታወቀች
ኢራን ከዚህ በኋላ ለ2015 [በግሪጎሪ ኦቆጣጠር] የኒውክሌር ስምምነት እንደማትገዛ አስታውቃለች።
ኢራን ባወጣችው የአቋም ሃተታ በስምምነቱ መሠረት የተጣሉባት ማዕቀቦች ከዚህ በኋላ እንደማይገዟትና እንዳሻት እንደምትንቀሳቀስ አስታወቃለች። የኢራን ካቢኔ ዋና ከተማዋ ቴህራን ላይ ከመከረ በኋላ ነው አቋሙ የወጣው። ኢራናዊው ኃያሉ የጦር ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒ በትራምፕ ትዕዛዝ ባግዳድ ውስጥ መገደላቸውን ተከትሎ አሜሪካና ኢራን ውጥረት ውስጥ ናቸው። • ቴህራን ጥቃት ከፈፀመች በሚል አሜሪካ 52 የኢራን ተቋማት ላይ መሳሪያዋን አነጣጥራለች • "ትውስታዎቼ መራር ናቸው"- ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዕሁድ አመሻሹን ጥቃት እንደተሰነዘረበትም ተሰምቷል። የቢቢሲ ምንጮች እንደሚሉት አራት ጊዜ ኤምባሲውን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶች ተሠንዝረዋል። የደረሰ አደጋ ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢራናውያን ለጄኔራል ሶሌይማኒ የጀግና አሸኛኘት ለማድረግ ጎዳናዎችን ሞልተው ታይተዋል። የጄኔራሉ ቀብር ማክሰኞ ዕለት ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል። አሜሪካ ኢራቅ ውስጥ 5000 የጦር ሠራዊት አላት። ወታደሮቹ አይኤስ የተሰኘውን ታጣቂ ቡድን ለመዋጋት በሥፍራው የከተሙ ናቸው። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፏቸው በርካታ መልዕክቶች ኢራን የአሜሪካንን የጦር ሠፈሮች ልታጠቃ ብትሞክር ምላሹ የከፋ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። • ኢራቃዊያን የጀነራሉን አስክሬን ሲሸኙ ''ሞት ለአሜሪካ'' ሲሉ ተደምጠዋል 2015 ላይ ዩናይትድ ኪንገደም፣ ፈረንሳይ፣ ሩስያ፣ ቻይና፣ ጀርመን እና የአውሮጳ ሕብረት እንዲሁም አሜሪካ ሆነው የደረሱት ስምምነት ኢራን ኒውክሌር ማብላላቷን እንድትገታ ያስስባል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ስምምነቱ ከምርጫ ቅስቀሳቸው ጀምሮ ሲያጣጥሉት ከርመው ሥልጣን ከጨቡ በኋላ ከስምምነቱ ሃገራቸውን ማግለላቸው አይዘነጋም። ኢራን ለስምምነቱ የማትገዛ ከሆነ ኒውክሌር ማብላላቱን በነፃነት ትገፋበታለች የሚል ስጋት ከሌሎቹ የስምምነት ፊርማ ካኖሩ ሃገራት ይደመጣል። በሃገሪቱ ቴሌቪዠን ጣቢያ የተደመጠው የኢራን አቋም መግለጫ 'ኢራን ኒውክሌር ማብላላቷን ያለምንም ገደብ ትገፋበታለች' ሲል ተሰምቷል። ኢራን ኒውክሌር የማብላላው ለሰላማዊ ተልዕኮ ነው የሚል የቀደመ አቋም አላት።
news-53033059
https://www.bbc.com/amharic/news-53033059
የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች መለያ በስማቸው ምትክ የጥቁሮች ፍትህ ጥያቄ ሊሰፍርበት ነው
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች ቀሪዎቹን 12 ጨዋታዎች ሲያደርጉ ከመለያቸው ጀርባ ላይ በስማቸው ፈንታ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' [የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አለው] የሚለውን ጽሁፍ እንደሚያሰፍሩ ተገለጸ።
በተጫዋቾቹ ስም ምትክ የጥቁሮች የመብት ጥያቄ ይሰፍራል ተብሏል ከዚህ በተጨማሪም ፕሪምየር ሊጉ ከጨዋታ በፊትም ሆነ በኋላ የጥቁሮች የፍትህ ጥያቄ መለያ በሆነው ተንበርክኮ ድጋፋቸውን ለመግለጽና መልዕክት ማስተላለፍ የሚፈልጉ ተጫዋቾች አይከለከሉም ብሏል። ቀድሞ በተጀመረው የጀርመን ቡንደስሊጋ የሚጫወቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ነበሩ የጆርጅ ፍሎይድን ሞት አስመልከቶ ሜዳ ውስጥ ቀድመው መልዕክት ያስተላለፉት። የፕሪምየር ሊጉ 20 ቡድኖች ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ "እኛ እንደ እግር ኳስ ተጫዋች በህብረት በመቆም የዘር መድሎን ለማስወገድ አብረን እንቆማለን" ብለዋል። አክለውም ሁሉንም ያካተተ፣ መከባበር ያለበትና በቀልም እንዲሁም በጾታ ሳይለይ ሁሉም እኩል እድል የሚያገኝበት ዓለም አቀፋዊ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ የሚለውን መልዕክት የዘንድሮው የውድድር ዓመት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ተጫዋቾች በጀርባቸው ላይ የሚያደርጉ ሲሆን በተጨማሪም በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን የሚያመሰግን መልዕክትም ያስተላልፋሉ። በርካታ የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች በስልጠና ሜዳዎች ላይ በመንበርከክ ዘረኝነትን ያወገዙበትን ምስል ቀደም ሲል በማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ አጋርተዋል። ባለፈው ወር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሳል ህይወቱ ባለፈቸው የ46 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ምክንያት ዘረኝነት ይቁም በማለት ሜዳ ውስጥ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ አራት የጀርመን ቡንደስሊጋ ተጫዋቾች በእግር ኳስ ማኅበሩ ምርመራ ተደርጎባቸው ነበር። በመጨረሻ ግን የትኛውም ተጫዋች ቅጣት እንዳልተጣለበትና ተጫዋቾች በሚቀጥሉት ሳምንታት ዘረኝነትን በመቃወም መልዕክታቸውን ማስተላለፍ እንደሚችሉ የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር አስታውቋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከሦስት ወራት በኋላ በዝግ ስታዲየሞች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ የሚጀመር ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በርካታ ጥንቃቄዎች ይደረጋሉ ተብሏል። የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንና የኒውካስል እንዲሁም የቶተንሀም አማካይ ጀርሜይን ጄናስ ለቀሪዎቹ 12 ጨዋታዎች የሚተላለፈው መልዕክት በዘላቂነት ቢታሰብበት ጥሩ ነው ብሏል። "ሁሉም ክለቦችና ተጫዋቾች በዚህ ጉዳይ ላይ ተስማምተው ዘረኝነትን ለመዋጋት ማሰባቸው በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው። ቀላል ለማይባሉ ሰዎች መልዕክቱ እንደሚደርስም እርግጠኛ ነኝ። ፕሪምየር ሊጉ በመላው ዓለም በርካታ ተከታታዯች ያሉት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ጠንከር ያሉ መልዕክቶች ለወደፊቱም ቢቀጥሉ ጥሩ ነው" ብሏል ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ። አክሎም "በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጥቁር አሰልጣኞች እንደሌሉ በስፋት ይነገራል፤ አሰልጣኞችና ሌሎች አባላት ሲመለመሉ ብዝሃነትን ባማከለ መልኩ መደረግ ያለባቸው ይመስለኛል’’ ብሏል።
news-53763226
https://www.bbc.com/amharic/news-53763226
ስፖርት፡ እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥቁር ስፖርተኛ ሐውልት ያቆመችው መቼ እንደሆነ ያውቃሉ?
ጃክ ሌዝሊ፤ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን ማልያ አጥልቆ ታሪክ ከሠራ 100 ዓመታት ሊሞላው ቢሆን እንኳ በቅጡ የሚያስታውሰው ሰው አልነበረም። ይህ የሆነው በቆዳው ቀለም ብቻ ነው።
ጊዜው 1925 ነበር። እንግሊዝ ከአየርላንድ ጋር ለነበራት የወዳጅነት ጨዋታ መልማዮች ተጫወቾችን እየመለመሉ ነበር። በወቅቱ ሌዝሊ የፕላይማውዝ ተጫዋች ነበር። መልማዮቹ የሚጫወትበት ሜዳ መጥተው ሲመለከቱ ሌዝሊን ጥቁር ሆኖ ያገኙታል። በዚህም ምክንያት ሌዝሊ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የተሰለፈ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ታሪክ የሚሠራበትን አጋጣሚ መና ያደርጉበታል። ይኸው ሌዝሊ አሁን ገንዘብ ተዋጥቶለት ሃውልት ሊሰራለት እየታቀደ ነው። እስካሁን ቢያንስ 135 ሺህ ፓውንድ ተዋጥቶለታል። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 240 ስፖርተኞችን የሚዘክሩ ሃውልቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል 10 ብቻ ናቸው ለጥቁርና አናሳ ቁጥር ላላቸው እንግሊዛውያን ክብር የቆሙት። ከአስሩ መካከል አምስት ለእግርኳስ ተጫዋቾች የቆሙ ሲሆን ጎልፍና ክሪኬት የመሳሰሉ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ምንም ዓይነት የጥቁር ግለሰብ ሐውልት የላቸውም። ለምን? ሼፊልድ ዩኒቨርሲቲ የሠራው አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው የጥቁር ስፖርተኞች ሐውልቶች ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩት ባለፉት 10 ዓመታት ነው። አብዛኛዎቹ ሐውልቶች በተለይ ደግሞ የእግር ኳስ ተጫዎቾች መታሰቢያዎች ተጫዎቾቹ ጫማ ከሰቀሉ ከ20ና 30 ዓመታት በኋላ ነው የሚሠሩት። አብዛኛዎቹ የጥቁር እግር ኳስ ተጫዋቾች ሐውልቶች ለምን ባለፉት 10 ዓመታት ተሰሩ የሚለውን ጥያቄ የሚመልሱት ዶ/ር ክሪስ ስትራይድ፤ በእንግሊዝ እግር ኳስ መድረክ ከ1980ዎቹ [በአውሮፓውያኑ] በፊት በጣም ጥቂት ተጫዋቾች ነበሩ ይላሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ካላት 240 ሐውልት መካከል 10 ሃውልቶች ለጥቁሮች መድባለች። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ የተገነቡት ባለፉት 10 ዓመታት ነው። ይህ ደግሞ የ1980ዎቹ ተጫዎቾች መታሰብ የጀመሩት አሁን መሆኑን ማሳያ ነው ይላሉ ምሁሩ። እንግሊዝ ውስጥ ከቆሙ የጥቁር ተጫዋቾች ሐውልቶች መካከል ጎልቶ የሚወጣው በአውሮፓውያኑ 2019 የተገነባው የሶስቱ የዌስት ብሮሚች አልቢዮን ተጫዎቾች ሃውልት ነው። ሎሪ ካኒንግሃም፣ ሲሪል ሬጂስና ብንዶን ባስቶን ዌስትብሮም በ1970ዎቹ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታዋቂው ቡድን እንዲሆን የጎላ ሚና ተጫውተዋል። እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጥቁር ስፖርተኛ ሃውልት ያቆመችው በአውሮፓውያኑ 2001 ነው። ይሄም የታዋቂው ቦክሰኛ ራንዲ ቱርፒን ነው። ከዚያ በመቀጠል ሐውልት የቆመለት ጥቁር ተጫዋች የአርሰናሉ ፈረንሳዊ አጥቂ ቲየሪ ሄንሪ ነው። ሴቶች? ዩናይትድ ኪንግደም በዓለማችን በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሃውልቶች ያሏት ሃገር ናት። በጠቅላላው በዓለማችን 700 የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሐውልት እንደቆመላቸው አንድ ጥናት ይጠቁማል። ነገር ግን ከእነዚህ ሐውልቶች መካከል ለሴት ስፖርተኞች መታሰቢያ የሆኑ ዘንድ የቆሙ ሐውልቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ሊሊ ፓር እንግሊዝ ውስጥ ሐውልት የተሰራላት የመጀመሪያዋ ሴት ስፖርተኛ ናት። በ1920ዎቹና 30ዎቹ ዲክ ለተሰኘው የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የተጫወተችው ሊሊ ሃማንቸስተር ውስጥ ሐውልት የተሰራላት ባለፈው ዓመት [2019] ነው። ከሊሊ በተጨማሪ ሃውልት የቆመላቸው እንግሊዛውያን ስፖርተኞች 3 ናቸው። እነዚህም ቴኒስ ተጫዋቿ ዶሮቲ ራውንድ፣ የኦሊምፒክ ሻምፒዮናዎቹ ሜሪ ፒተርስና ኬሊ ሆልምስ ናቸው። ከ1980ዎቹ በኋላ ያለው የእንግሊዝ እግር ኳስ በጥቁር ተጫዎቾች የደመቀ ነው። ያለፈው አስር ዓመትም ጥቁር የእግር ኳስ ፈርጦችን አፍርቷል። የእነዚህን ተጫዎቾች ሐውልት መች እናይ ይሆን? የበርካቶች ጥያዌ ነው።
news-45662601
https://www.bbc.com/amharic/news-45662601
ጉግል ስለእርስዎ ብዙ ያውቃል፤ እርስዎስ ስለ ጉግል ምን ያውቃሉ? እነሆ 10 ነጥቦች
ጉግል 20ኛ ዓመት የልደቱን በዓሉን ሊያከብር ሽር ጉድ እያለ ነው። ይህን ተንነተርሰን ስለ ጉግል ምናልባት የማያውቋቸው 10 ነጥቦች ይዘን ብቅ ብለናል።
ጉግል ለሁለት ተማሪዎች የተሰጠ 'የቤት ሥራ' ነበር ቢባል ማን ያምናል? ከጉግል በፊት ሕይወት ምን ትመስል ነበር? አንድ መረጃ በፍጥነት ሲፈልጉ ምን ያደርጉ እንደነበር ያስታውሱታል? ምንም ይፈልጉ ምን፤ የአንድን ቃል ትርጓሜ እና አፃፃፍም ይሁን የቦታ ጥቆማ፤ ብቻ የሆነ ነገር ሲፈልጉ ወደ ጉግል መሮጥ የተለመደ ሆኗል። 'ዕድሜ ይስጠውና' ጉግል ፊት ነስቶን አያውቅም፤ 'ጎግለው' እንዲል የሃገሬ ሰው። • የደመራ በዓል ዝግጅትና አከባበር በምስል • «አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7 በየሰከንዱ ይላል ፎርብስ የተሰኘው መፅሄት መረጃ. . .በየሰከንዱ 40 ሺህ ሰዎች 'ይጎግላሉ'፤ በቀን 3.5 ቢሊዮን እንደማለት ነው። ጉግል ሁሉ ነገር ሆኗል፤ ማስታወቂያ በሉት፣ የቢዝነስ ዕቅድ እንዲሁም ግላዊ መረጃ መሰብሰቢያ ነው። እንግዲህ እውነታውን ልናፈራርጠውም አይደል፤ እናማ ስለጉግል አንድ ሚስጢር እንንገርዎት። መረጃ ፍለጋ ወደ ጉግል በሮጡ ቁጥር ጉግል ስለእርስዎ የተወሰነ መረጃ ይሰበስባል። «ግን ምን ያህል መረጃ?» አሉን?፤ መልካም! እነሆ የጠየቁንን ጨምሮ ስለጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች። ፩. ስያሜው ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው። በእንግሊዝኛው 'googol' ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው። እና ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ። • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ ፪. የጀርባ ማሻ የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው 'Backrub' ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር። ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ። ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ። ፫. የተንጋደደ አያስቦ፤ እይታዎ ሳይሆን ምስሉ ነው የተንጋደደው ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ። እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት። ውጤቱ አዩት? ፬. ፍየሎች ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው። አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ። ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና። ፭. እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ' ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም ወይ ቴሌግራም ይጠቀማሉ? የማን ንበረት እንደሆኑስ ያውቃሉ? ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል። ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው። ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው። ፮. ዱድል የጉግል የተማሪዎች ውድድር ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው። ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል። አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል። • ከደሴ - አሰብ የሞላ? ፯. ለሌሎች ያመለጠ ዕድል በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ። ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም። አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው። ፰. መሪ ቃላት 'ከይሲ አይሁኑ' ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር። 'ምን አገባው' የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል። ፱. ምግብማ ግድ ነው ከጉግል ዋና መሥሪያ ቤት የማይጠፋ ነገር ቢኖር ምግብ ነው ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ። የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል። ፲. የጉግል ባልንጀራ የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል። ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል። አጀብ ነው! • «አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7
news-56398435
https://www.bbc.com/amharic/news-56398435
አሜሪካ በጦር መሳሪያ ንግድ ቀዳሚነቷን ስታስጠብቅ ሽያጯም ከፍ ብሏል
ባለፉት አምስት ዓመታት አሜሪካ ለሌሎች አገራት የምታቀርበው የጦር መሳሪያ መጠን በ37 በመቶ መጨመሩን አንድ በስዊዲን የሚገኝ የምርምር ተቋም አስታወቀ።
ከአሜሪካ በተጨማሪ ፈረንሳይና ጀርመን ለሌሎች አገራት በሽያጭ የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ መጠን መጨመር በሩሲያና በቻይና አቅርቦት ምክንያት የተፈጠረውን ክፈተት የሚሞላ ነው ተብሏል። በአሁኑ ጊዜ የአገራት የጦር መሳሪያ ግዢና ሽያጭ መጠን ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ከፍተኛ ከሚባለው ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፤ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተብሎ ይገመታል። በዓለም ላይ ከታየው የጦር መሳሪያ ግዢ ውስጥ ከፍተኛው የተመዘገበው በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ነው ተብሏል። የጦር መሳሪያዎች ግዢና ሽያጭን በተመለከተ ምርምሩን የሰራው የስቶክሆልም የሠላም ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፒተር ዊዝማን "ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የታየው ፈጣን የጦር መሳሪያ ግብይት አብቅቷል ለማለት ጊዜው ገና ነው" ብለዋል። ባለሙያው ጨምረውም የኮሮናቫይረስ የሚያስከትለው የምጣኔ ሀብት ተጽዕኖ አገራት በቀጣይ ዓመታት ውስጥ የሚገዙትን የጦር መሳሪያ መጠን መለስ ብለው እንዲቃኙ ሳያደርጋቸው አይቀርም። "ወረርሽኙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባለፈው ዓመት እንኳን፣ በርካታ አገራት ወሳኝ የሚባሉ ጦር መሳሪያዎችን ለመግዛት ከፍተኛ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።" የጥናት ተቋሙ እንዳመለከተው ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ቀደም ሲል ከነበረው ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ጋር ሲነጻጸር በነበረበት የመርጋት ሁኔታ አሳይቶ ነበር። አሜሪካ ወደ ውጭ ከምትልከው የጦር መሳሪያ ወደ ግማሽ የሚጠጋው፣ ማለትም 47 በመቶው፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የቀረበ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥም ሳዑዲ አረቢያ ብቻዋን ከአጠቃላዩ የአሜሪካ የመሳሪያ ሽያጭ 24 በመቶውን ትወስዳለች። ባለፉት አምስት ዓመታት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ድርሻ በጨመረበት ጊዜ 96 አገራት ደንበኞቿ ሆነዋል። ከአሜሪካ በመከተል የፈረንሳይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ በ44 በመቶ ሲጨምር የጀርመን ደግሞ በ21 በመቶ ከፍ ብሏል። ከእነዚህ በተጨማሪም እስራኤልና ደቡብ ኮሪያ ምንም እንኳን ከዋነኞቹ ጋር ሲነጻጸር የሚያቀርቡት የጦር መሳሪያ መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም በዚህ ወቅት ሽያጫቸው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። ግጭትና ውጥረት በማይለየው መካከለኛው ምሥራቅ የጦር መሳሪያ ግዢ ፍላጎት በፍጥነት እያደገ ይገኛል። በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ወደዚህ አካባቢ የተሸጠው የጦር መሳሪያ መጠን ቀደም ሲል ከነበሩት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በ25 በመቶ ከፍ ብሏል። ከፍተኛው የጦር መሳሪያ ግዢ የተከናወነውም በሳዑዲ አረቢያ ሲሆን በዚህም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከተላከው 61 በመቶውን ገዝታለች። በተከታይነት ግብጽና ኳታር ይጠቀሳሉ። የእስያና የኢዢያ አገራት ቀደም ሲል 42 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ መጠን ያለውን ዋነኛ የጦር መሳሪያዎችን በመሸመት ቀዳሚ ነበሩ። በአካባቢው ሕንድ፣ አውስትራሊያ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያና ፓኪስታን ዋነኞቹ የጦር መሳሪያ ሸማች አገራት ነበሩ። ምንም እንኳን አሁንም ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገራት ዋነኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች ቢሆኑም፤ ቀደም ሲል ከዋነኞቹ የጦር መሳሪያ ላኪዎች መካከል የነበሩት ሩሲያና ቻይና ሽያጫቸው ቀንሷል። በዚህም ሳቢያ ሩሲያ ወደ ውጭ አገራት የምትልከው መሳሪያ በ22 በመቶ የቀነሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ ሕንድ የምትልከው 53 በመቶ የሚሆነው ነበር። የዓለም ትልቋ አምስተኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢ የሆነችው ቻይና ሽያጯ በ7.8 በመቶ ቀንሷል። ፓኪስታን፣ ባንግላዲሽና አልጄሪያ ዋነኞቹ የቻይና ጦር መሳሪያ ገዢዎች ነበሩ።
44610952
https://www.bbc.com/amharic/44610952
በሰኔ 16 ቅዳሜ ሰልፍ ላይ የታየው ክፍተት ምን ነበር?
ቅዳሜ ሰኔ 16 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ሚሊየኖች ተገኙ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተገኙበት በዚህ ሰልፍ ላይም የቦንብ ፍንዳታ ደረሰ።
ትናንት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል በቅዳሜው ሰልፍ ላይ የታየው የደህንነት ክፍተት ሆን ተብሎ በፖሊስ ቸልተኝነት የተፈጠረ መሆን አለመሆኑም ይጣራል፤ በእለቱ በመድረኩና በህዝቡ መካከል ያለው ርቀት መስፋት ሲገባው መቀራረቡም እንደ ክፍተት ተወስዶ ተገምግሟል ብለዋል።። ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎ የተፈጸመውን ጥቃት ማክሸፍ አለመቻሉ በእለቱ የተስተዋለ ክፍተት ነው ብለዋል። የአሜሪካው ኤፍ ቢ አይ በቦምብ ፍንዳታው ምርምራ ላይ መሰማራቱ ተገለፀ የሆነው ምን ነበር? ኢቲቪ እያስተላለፈ በነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፍ ቀጥታ ስርጭቱ ላይ እንደታየው ጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ነው የፍንዳታ ድምጽ የተሰማው። ቀጥሎም መድረኩ አካባቢ የነበሩ ግለሰቦች ሲሯሯጡ ተስተውሏል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአደጋው በኋላ ''ኢትዮጵያውያን በፍቅር ተደምረው ፍቅር እንዲዘንብ ያደረጉበት ዕለት ቢሆንም የአገራችንን ሰላም የማይፈልጉ አካላት በተጠና እና በታቀደ መልኩ ሙያቸውን ታግዘው ይህን ደማቅ ስነ-ስርዓት ለማደፍረስ የሰው ህይወት ለመቅጠፍ እና ደም ለማፍሰስ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል" ብለዋል። የድጋፍ ሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጉደታ ገላልቻ በበኩላቸው " ከፌደራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ፖሊስ ጋር በመሆን በቅንጅት ስንሰራ ነበር አሁን የተፈጠረው ግን ከደህንነት አካላት በኩል ክፍተት መኖሩን አሳይቶናል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አደጋው ከደረሰ ከጥቂት ሰአት በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ለኢቲቪ በሰጡት መግለጫ " የጸጥታ ሃይሎች ብዙ ተግባር አከናውነናል ይሁን እንጂ ጥቃት አድራሾቹ ከፍተኛ ዝግጅት አድርገው ስለነበር ጥቃቱ ሊፈፀም ችሏል" ብለዋል። ከዚህ ቃለምልልስ በኋላ ግን እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎች ዘጠኝ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፌደራል ፖሊስ አባላት ከስራቸው መባረራቸውን እንዲሁም በስራቸው ላይ ክፍተት በማሳየታቸው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተዘግቧል። በዛኑ ዕለትም ፖሊስ 6 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልፆ ነበር፡፡ ከትናንት ጀምሮ የምረመራው ሂደት በውጭ አገር መርማሪዎች ሊደገፍ እንደሆነ ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ለቢቢሲ እንዳስታወቁትም ፖሊስ ከአደጋው ጀርባ ያሉ ግለሰቦችን ለመለየት የሚያደረገው ክትትል ቀጥሏል። ከኤፍቢአይ ጋርም በጥምረት መስራት ጀምሯል፤ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ቁጥርም 28 ደረሷል ብለዋል፡፡ አቶ ቢተው በላይ የቀድሞ ታጋይና የኢህአዴግ ምክር ቤት አባል ናቸው። በደቡብ ክልልም ከፀጥታና ደህንነት ጋር በተያያዘ ሲሰሩ ነበር። እርሳቸው ቅዳሜ እለት ስለተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ዝግጅት ከአንዳንድ ሰዎች ጠይቀዋል። ከንግግራቸው እንደተረዱትም "አዘጋጆቹ ከፀጥታ አካላት ጋር በሚጠበቀው መንገድ ተቀናጅተው የገቡበት አይመስልም።" አቶ ቢተው ስለዝግጅቱ ከመንግስት አካላት ጠይቆ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረው አንዳንድ ቦታዎች የፍተሻ መላላት እንደነበር ቀድመው በስፍራው ገብተው ያደሩም እንደነበሩ መነገሩ ሌላው የፀጥታው ጉዳይ መላላቱን ማሳያ ነው። ይህንን ሃሳባቸውን ሲያጠናክሩም ከውጭ ሆኖ ለሚመለከተው ግለሰብ የተቀናጀ ነገር እንዳልነበር ያሳያል ይላሉ። እንዲህ አይነት ትልቅ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሲዘጋጁ በየደረጃው ካሉ የፀጥታ አካላት ጋር ከመነሻው ጀምሮ በጋራ በመሆን ማቀድ ያስፈልግ እንደነበር ያስታውሳሉ። "እንዲህ አይነት በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ህዝባዊ ሰልፍ ሲደረግ ፍላጎት የሌላቸው ደግሞ በዓሉን ለማደናቀፍ የሚያደርጉትን ነገር ለመከላከል ዝግጅት ወሳኝ ነው" ይላሉ። ምንም እንኳ ከመንግስት ውጭ የተዘጋጀ ሰልፍ ቢሆንም ከመንግስት አካል ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ችግር ቢከሰት እንኳ እንዴት መፍታት እንደሚቻል መታቀድ ነበረበት ይላሉ አቶ ቢተው። በአቶ ቢተው ሃሳብ እነዚህ አካላት ከመነሻው ጀምሮ አለመገናኘታቸው ክፍተቱን ፈጥሮ ሊሆን እንደሚችል ይችላል። ለአቶ ቢተው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚደረገው ጥበቃ ምን ይመስል እንደነበር ለመናገር በስፍራው የነበረ ሰው የሚታዘበው እና አስተያየት ቢሰጥበት የተሻለ እንደሚሆን ገልፀው ነገር ግን ጥበቃው በስፍራው ላይ ቀድሞ በመገኘት መጠናከር ይኖርበት እንደነበር ይገባኛል በማለት አስተያየታቸውን ያጠናቅቃሉ። በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ላይ የሚካሄደው ምርመራ ተጀምሯል በማለት ለቢቢሲ የተናገሩት።የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል የምርመራውን ሂደት አስመልክቶ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በምርመራ ሂደቱ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የተውጣጡና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆኑን አስረድተዋል። ምርመራው የድርጊቱን ፈጻሚ? የድርጊቱን ኢላማ? በድርጊቱ ውስጥ የፖሊስ ተሳትፎ መኖር አለመኖሩን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ያለመ መሆኑንም ነው የተናገሩት። ከዚህ በተጨማሪ ኮሚሽነሩ በጥቃቱ ላይ የፖሊስ ተሳትፎ ስለመኖሩ የሚጣራ ነው የሚሆነው ብለዋል። ድርጊቱ ከመድረኩ ባልራቀ ቦታ ላይ መፈጸሙም በእለቱ እንደ ክፍተት የታየ ጉዳይ መሆኑንም ጠቁመዋል። በተጨማሪም ቦምብን ያክል መሳሪያ ብዙ ህዝብ በተሳተፈበት ሁኔታ መገኘቱ በፌደራል ፖሊስ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ መሆኑን ገልጸዋል። የአሜሪካው ኤፍ ቢ አይ በቦምብ ፍንዳታው ምርምራ ላይ መሰማራቱ ተገለፀ
news-55729095
https://www.bbc.com/amharic/news-55729095
ትራምፕ በመጨረሻው ቀናቸው ለቀድሞው ረዳታቸው ስቲቭ ባነን ምህረት አደረጉ
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሥልጣናቸው የመጨረሻ ቀን በማጭበርበር ወንጀል ተከስሰው ለነበሩት የቀድሞ ረዳታቸው ስቲቭ ባነን ምህረት አደረጉ።
ስቲቭ ባነን የሜክሲኮን ግንብ ለመገንባት የተሰበሰበን ገንዘብ በማጭበርበር ነበር የተወነጀለው ይህ የዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ የተሰማው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው በፊት ነው። ትራምፕ በመጨረሻው የስልጣን ዘመናቸው ከ140 በላይ ለሚሆኑ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጋቸው ተገልጿል። ምህረት ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል ራፐር ሊል ዋይኔ እና ኮዳክ ብላክ ሲገኙበት የዲትሮይት ከንቲባ ለነበሩት ክዋሜ ኪልፓትሪክ ደግሞ ቅጣታቸው ተቀንሶላቸዋል። 73 ታራሚዎች ይቅርታ ሲደረግላቸው 70 ያህሉ ደግሞ ፍርዳቸው እነዲቀነስላቸው እንደተደረገ ከዋይት ሐውስ የወጣው መግለጫ ያስረዳል። ስቲቭ ባነን፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ2016 በነበራቸው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ቁልፍ ስትራቴጂስት እና አማካሪ የነበሩ ሲሆን ባለፈው ዓመት በነሐሴ ወር ላይ በአሜሪካ እና በሜክሲኮ መካከል ለሚገነባው አጥር የተሰበሰበን ገንዘብ በማጭበርበር ተከስሰው ነበር። ዐቃቢያነ ሕጎች እንዳሉት ባነን እና ሌሎች ሦስት ሰዎች በሜክሲኮ ድንበር ላይ አጥር ለመገንባት ከለጋሾች የተሰጠን በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ አጭበርብረዋል። "እንገነባዋለን" በተሰኘው በዚህ ዘመቻ 25 ሚሊዮን ዶላር ያህል ተሰብስቧል። ባነን ከ1ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀብለዋል የተባለ ሲሆን የተወሰነውን ለግል ወጪያቸው አውለውታል ተብሏል። እርሳቸው ግን ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ጉዳያቸው ገና እየታየ ነበር። ዋይት ሐውስ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ባነን "በጣም ቁልፍ ሰው" በማለት ፖለቲካዊ ብቃታቸውንም አድንቋል። ራፐሮቹ ሊል ዋይኔ እና ኮዳክ ብላክ ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሲሆን ክዋሜ ኪልፓትሪክ ደግሞ በሙስና ወንጀል ተከስሰው 28 ዓመት ተፈርዶባቸው ነበር። የሥልጣን ዘመናቸውን አጠናቅቀው ዋይት ሐውስን የሚለቅቁ ፕሬዝዳንቶች ለተከሳሾቹና ፍርደኞች ምህረት ማድረጋቸው የተለመደ ነው። ይቅርታ የሚደረግለት ታራሚ ክሱ ውድቅ የሚደረግለት ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ የእስር ጊዜው እንዲያጥር ወይንም እንዲያበቃ ሊደረግ ይችላል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከወንጀል ጋር በተያያዘ በፌደራል ችሎት ውስጥ ምህረት ለማድረግ ያልተገደበ ስልጣን አለው። ከቅርብ ወራት ወዲህ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለበርካቶች ምህረት አድርገዋል። ይቅርታ ከተደረገላቸው መካከል በርከት የሚሉት ረዳቶቻቸው አልያም የቅርብ አጋሮቻቸው የነበሩ ሰዎች ናቸው።
news-56795572
https://www.bbc.com/amharic/news-56795572
አዲስ አበባ ውስጥ የእጅ ቦምብ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባልታወቀ ሁኔታ የፈነዳ የእጅ ቦምብ የሁለት ሰዎች ህይወት መቅጠፉን እና አንድ ሰው ደግሞ መቁሰሉን ፖሊስ አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘውና ሜትሮሎጂ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በፈነዳው የእጅ ቦምብ የሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉንና አንድ ሌላ ሰው ደግሞ ክፉኛ መቁሰሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ ፍንዳታውን ተከትሎ አደጋው ባጋጠመበት ስፍራ ላይ ከአንደኛው ሟች ኪስ ውስጥ ተጨማሪ ያልፈነዳ የእጅ ቦንብ ማግኘቱን አስታውቋል። ለሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው ፍንዳታ ያጋጠመው እሁድ ሚያዝያ 10/2013 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ፣ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተባለው ስፍራ ለልማት በተዘጋጀ ቦታ ላይ እንደሆነ ፖሊስ አመልክቷል። የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ረዳት ኢንስፔክተር ዳንኤል ታፈሰ ስለተከሰተው ፍንዳታ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን፣ አንድ ግለሰብ ሁለት ሴቶች ጋር ለልማት ወደታጠረው ስፍራ ከገባ በኋላ ፍንዳታ መከሰቱን ገልጸዋል። ለሁለት ሰዎች ሞትና ለአንድ ሰው መቁሰል ምክንያት የሆነው አደጋን ተከትሎ የአዲስ አበባና የፌደራል ፖሊስ የቴክኒክና የፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች በአደጋው ስፍራ ተገኝተው ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አካባቢውን ከእንቅስቃሴ ነጻ በማድረግ ምርመራ ማድረጋቸው ተገልጿል። ፖሊስ ስለተከሰተው የቦምብ ፍንዳታና ምክንያቱ እንዲሁም በክስተቱ ህይወታቸው ስላለፈው ሰዎች ማንነት ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል።
news-53646927
https://www.bbc.com/amharic/news-53646927
የትግራይ ክልል የፌዴሬሸን ምክር ቤቱ ምርጫ አታካሂዱ የማለት ስልጣን እንደሌለው ጠቅሶ ምላሽ ሰጠ
የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ፣ በፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በ21/11/2012 ለተጻፈው ደብዳቤ ትናንት ሰኞ እለት ምላሽ ሰጥተዋል።
በዚህ ምላሻቸውን በያዘው ደብዳቤ ላይም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ለክልሉ ምርጫ አታካሂዱ ብለው የመጻፍ ሥልጣን እንደሌላቸው አሳስበዋል። አፈ ጉባኤው የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ደብዳቤ ሕገመንግሥታዊ መሰረት የሌለው በማለት የገለፁት ሲሆን፣ "የሕገ መንግሥት መርሆዎችን የሚጥስ፣ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነትን የሚጻረር" በመሆኑ የትግራይ ክልል መንግሥትና ህዝብ እንደሚቃወሙት ገልፀዋል። የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ በፃፉት ደብዳቤ ላይ ምክር ቤቱ ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ እንዲራዘምና የምክር ቤቶችንና የፌደራል አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና የስራ ዘመን ለማራዘም የወሰነውን ውሳኔ አለመቀበሉን በመጥቀስ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትን የሚጎዳ አካሄድ መሆኑን ገልጿል። አክለውም የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምርጫ ስነምግባር ህግ ማውጣቱ፣ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙና የምርጫ ሂደት መጀመሩ "ኢ ህገመንግስታዊ ነው" ካለ በኋላ፣ ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ጣልቃ እንደሚገባ ገልጧል። የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አፈጉባኤ በበኩላቸው ደብዳቤው የተጻፈው የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ በሌለበት እና ክልሉ ምርጫ ይራዘምልኝ ብሎ ባልጠየቀበት ሁኔታ እንደሆነም በደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰዋል። ክልሉ የምርጫ ሕግ የማውጣት፣ ምርጫ ኮሚሽን የማቋቋም እና ምርጫ የማካሄድ ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን እንዳለው የጠቀሱት አፈ ጉባኤው፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ፌደራል መንግሥት በክልሉ ሕገ መንግሥታዊ መብት ጣልቃ እየገቡ እንደሆነ እና በዚሁ ጣልቃ ገብነት ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂዎቹ እነሱው ናቸው በማለት አስጠንቅቀዋል። "የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚያካሄደው ምርጫ ኃላፊነትን መወጣት እንጂ ከፍላጎት የሚመነጭ አይደለም" ያሉት አፈ ጉባኤው፣ ውሳኔውም የክልሉ መንግሥት ውሳኔ በክልሉ ህገመንግሥት መሰረት የተመሰረተ ነው ብለዋል። ህገ መንግሥቱ በየአምስት አመቱ ምርጫ እንዲደረግ ያስገድዳል በማለትም ምርጫ ማካሄድ ለህገመንግሥታዊ ስርዓቱ ዋስትና መስጠትና ኃላፊነትን መወጣት ያመለክታል እንጂ ለህገመንግሥቱ አደጋ ሊሆን አይችልም በማለት ደብዳቤው አስፍሯል። ከዚህም በተጨማሪ ደብዳቤው ህገመንግሥቱን የሚጥስና ህጋዊ ውጤትም ሊያስከትል አይችልም በማለት በአስቸኳይ ሊታረም ይገባል ብሏል። የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምርጫ እንዲደረግ በምክር ቤት መወሰኑ፣ የምርጫ ስነምግባር ህግ ማውጣቱ፣ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሙንና የምርጫ ሂደት መጀመሩ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 13፣ 39 እና 52 መሰረት ለህገመንግሥቱ ስርአት ያለውን ታማኝነትና ተገዢነት ያሳያል ይላል ደብዳቤው። ፌዴሬሽኑ በህገመንግሥት ትርጓሜ ሰበብ ምርጫ ለማራዘም ያሳለፈውን ውሳኔ ኢህገመንግሥታዊ በማለትም፣ የክልሉ ምክር ቤት ምርጫ ለማራዘም ምንም አይነት ህገመንግሥታዊ ሥልጣን የለውም በማለት ክልሉም የጣሰው ነገር የለም ሲል አስተባብሏል። አፈጉባኤው አክለውም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትም ሆነ ሌሎች ክልሎች ምርጫ ይራዘምልኝ ብለው ያቀረቡት ጥያቄ እንደሌለ በመጥቀስ ፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ባልቀረበለት ጥያቄ "ውሳኔ መስጠትና ማስፈፀም አይችልም" ሲሉ ገልፀዋል። አፈ ጉባኤው የአገሪቱ ሕገመንግሥት አንቀጽ 9(3)ን በመጥቀስ መንግሥት የሚመሰረተው በምርጫ መሆኑን ካስረዱ በኋላ፣ ይህ አንቀጽ በክልሉ ህገመንግስትም "ገዢ አስገዳጅና የማይጣስ" መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም በህገመንግሥቱ አንቀጽ 56 እና 73 አንድ ፓርቲ ስልጣን መያዝ ያለበት በምርጫ አብላጫ ድምጽ ካገኘ መሆኑን በመጥቀስ ከዚህ ህገመንግስት አንቀጽ ውጪ ስልጣን መያዝ ህገወጥ መሆኑን በማስቀመጥ፣ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በምርጫ የራሱን መንግሥት ለማቋቋም መወሰኑ ህገመንግስታዊ ነው ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ህገመንግሥታዊ ክፍተትን በህገመንግሥት ትርጉም ለመሙላት፣ ያሉት ምክር ቤቶችና የአስፈጻሚው አካል ስልጣንና 6ኛው አገራዊ ምርጫ እንዲራዘም ትርጉም መስጠቱ፣ "በሂደቱም በውጤቱም ህገ መንግሥቱን የሚጥስ" በመሆኑ የትግራይ ክልል እንደማይቀበለው በጊዜው መወሰኑን አስታውሰዋል። ይህ የምክር ቤቱ ውሳኔ በአንቀጽ 8 (2) (3)፣ 9(3)፣ 38፣ 56፣ 73 መሰረት ኢ ህገመንግሥታዊ ነው በማለት፣ በክልል መንግሥትና በፌደራል መንግሥት ደረጃ ያለውን ዜጎች አስተዳደራቸውን የማደራጀት፣ የማስተዳደር ስልጣን አሳጥቷል ሲሉ ገልፀውታል። አክለውም ህገ መንግሥታዊ ቀውስ ፈጥሯል ብለዋል። የመንግሥትንም ስልጣን ኢ ህገመንግሥታዊ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል።
news-55715932
https://www.bbc.com/amharic/news-55715932
ቻይና "ትራምፕ እንኳን ተወገዱ" አለች
የቻይና ባለስልጣናት አስተያየት የሚንፀባረቅባቸው የመንግሥት ሚዲያዎች በተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና ደጋፊዎቻቸው ከስልጣን መወገድ የተሰማቸውን ስሜት ለአለም ከመንገር ወደኋላ አላሉም።
የቻይናው ዜና ምንጭ ዢኑዋ ደግሞ ግልፅ ባለ ቋንቋ "ዶናልድ ትራምፕ እንኳን ተወገዱ!" የሚል መልዕክት በትዊተር ገፁ አስፍሯል። ብሄራዊው ግሎባል ታይምስ ጋዜጣም እንዲሁ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በተመለከተ ባወጣው ዘለግ ባለ ፅሁፍ "ቻይና ከትራምፕ የስልጣን ዘመን የተማረችው ነገር ቢኖር ሁለቱ አገራት ግንኙነትን በተመለከተ ምንም መጠበቅ እንደሌለባት ነው። የቻይናና አሜሪካን ግንኙነት በተመለከተ እውነታውን የማያንፀባርቅ ተስፋ የለንም፤ ምንም አንጠብቅም" በሚል አስፍሯል። በተለይም በትራምፕ አስተዳደር ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ላይ ባለስልጣናቱ ስድብ ቀረሽ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚያደርገው የተለመደው መግለጫም ቃለ አቀባይዋ ሁዋ ቹንይንግ "በማይክ ፖምፔዮ በኩል ሲነዛ የነበረው መርዛማ ውሸት በሙሉ ይጠራል። ልኩ እሱም ተጠርጎ እንደወጣው ውሸቱም በታሪክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ይጣላል" ብለዋል። ነገር ግን ቃለ አቀባይዋ ማይክ ፖምፔዮን ይናፍቋቸዋል ወይ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸው "በደንብ! በርካታ መዝናኛ የሚሆኑ ነገሮችን እኮ ያመጣልን ነው። በየቀኑ ድራማ እየተከታተልን ነበር" በማለት ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ አወዛጋቢ ጉዳዮችን በመፃፍ የሚታወቁትን ትራምፕ ግሎባል ታይምስ "ውደዱትም፣ ጥሉትም። ማህበራዊ ሚዲያው ያለ ዶናልድ ትራምፕ ተመሳሳይ አይሆንም። ለብዙዎች አሳዛኝ ነው ብሏል" ጋዜጣው መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ እንደፃፈው " በዊቡ ማህበራዊ ሚዲያ ዶናልድ ትራምፕ በመፈለግ የቁንጮነት ቦታን ይዘዋል። በ2020ም በከፍተኛ ሁኔታ ስማቸው በመነሳትና በዊቡ አንደኛ ስፍራን በመያዝ 589 ጊዜ 'ትሬንድ' አድርገዋል። ይኼም የወረርሽኙን ዜና፣ ታዋቂ ሰዎችንና እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን በመብለጥ ነው" በማለትም አስፍሯል።
news-55458662
https://www.bbc.com/amharic/news-55458662
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አራት የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት በመተከል ዞን ከተፈጸመው የበርካታ ሰዎች ግድያ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አራት የምክር ቤቱ አባላትን ያለመከሰስ መብት አነሳ።
የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበባቸው አቶ አድጎ አምሳያ፣ አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፣ አቶ ግርማ መኒ እና አቶ አረጋ ባልቢድ ናቸው። አቶ አድጎ አምሳያ ቀደም ሲል የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበርና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩ ሲሆን፣ አቶ ሽፈራው ጨሊቦ የክልሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር በመሆን በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ናቸው። በተጨማሪም አቶ አረጋ ባልቢድ የመተከል ዞን አመራር የነበሩና አቶ ግርማ መኒ የክልሉ ምክር ቤት አባል ሲሆኑ አራቱ ሰዎች በክልሉ የመተከል ዞን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ምክር ቤቱ በአባልነታቸው ያላቸውን ያመከሰስ መብት እንዲነሳ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። የአራቱ የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት በተነሳበት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታደለ ተረፈ በመተከል ዞን የተፈጸመው ጥቃት አሳዛኝና ሊደገም የማይገባው መሆኑን መናገራቸውን የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ገልጿል። አራቱ ግለሰቦች ባለፈው ሳምንት ከተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት በኋላ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የክልሉ ምክር ቤት አባል በመሆናቸው የሚኖራቸው ያለመከሰስ መብት በቀዳሚነት መነሳት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ምክር ቤቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው። ቀደም ሲል ከዚሁ መተከል ዞን ውስጥ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ሰዎች መካከል በክልሉና በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩ ይገኙበታል። በዚህም የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት አቶ ቶማስ ኩዊ አንዱ ናቸው። በተጨማሪም አቶ ባንዲንግ ማራ የመተከል ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ ገመቹ አመንቲ የክልሉ የግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ አድማሱ መልካ የገጠር መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ይገኙበታል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለወራት የዘለቀ ተከታታይ ጥቃት በነዋሪዎች ላይ ሲፈጸምበት በቆየው የመተከል ዞን ውስጥ በሚገኘው ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሳስ 13/2013 ዓ. ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት አሰሳ ከአርባ በላይ ታጣቂዎች መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን በጭፍጨፋው ውስጥ በተለያየ መልኩ እጃቸው አለበት የተባሉ የመንግሥት ባለሰልጣናትም በቁጥጥር ሰር ውለዋል። ከጥቃቱ በኋላ የአካባቢውን ጸጥታ የሚቆጣጠር ግብረ ኃይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተቋቋመ ሲሆን ግብረ ኃይሉም ሥራውን በዚህ ሳምንት መጀመሩ ተገልጿል። ይህ ግብረ ኃይል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሰልጣናትና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችን ያቀፈ ሲሆን በመተከል ዞን የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንደተሰጠው ተነግሯ። ግብረ ኃይሉ በሌፍተናንት ጄኔራል አስራት ዴኔሮ የሚመራና በዞኑ በንፁሃን ላይ ጥቃት በመፈጸም ህይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን በማደን ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር አውሎ በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
news-56884827
https://www.bbc.com/amharic/news-56884827
ለአንድ የውሻ ዘር ብሔራዊ በዓል ያወጀችው አገር
ቱክሜኒስታን ትባላለች። የቀድሞ የሶቭየት ኅብረት አካል ነበረች። በመካከለኛዋ እሲያ የምትገኝ በተፈጥሮ ጋዝ የታደለች አገር ናት። ቱክሜኒስታን አሁን አዲስ የብሔራዊ በዓል አውጃለችው። በዓሉ ለአንድ ውሻ ዝርያ ክብር የታወጀ ነው።
አላባይ በተርከመኒስታን ለብዙ ዓመታት ብርቅዬ ዝርያ ተደርጎ የሚወደድ ነው በዲሞክራሲ መብቶች አፈናና በሙስና ስሟ ተደጋግሞ ይነሳል። ቱክሜኒስታን አሁን አዲስ የብሔራዊ በዓል አውጃለችው። በዓሉ ለአንድ ውሻ ዝርያ ክብር የታወጀ ነው። የውሻ ዝርያው ስም አላባይ ይባላል። የሼፔርድ ውሻ ዓይነት ሲሆን በዚያች አገር ለብዙ ዓመታት ብርቅዬ ዝርያ ተደርጎ የሚወደድ ነው። ትናንት እሁድ ልዩ የእውቅና በዓል ተደርጎለታል። ሽልማትም ተበርክቶለታል። ፕሬዝዳንት ጉባንጉሊ በርዲሙካሜዶቭ የዚህን አላባይ ውሻ በብሔራዊ ደረጃ መወደስ አስፈላጊነትን ያንቆለጳጰሱ ሲሆን ውሻው ብሔራዊ ኩራታችን ነው ብለዋል። በቱክሜኒስታን ይህ አላባይ ውሻ ብቻ ሳይሆን አሃል ቴክ ፈረስ ዝርያም የብሔራዊ ኩራት መገለጫ ነው። ትናንት እሁድ ለአላባይ ውሻ ዝርያ ልዩ ክብረ በዓል ተሰናድቶ ነበር። የአላባይ ውሾች የቁንጅና ውድድርም ተደርጓል። የአላባይ ውሾች ቁንጅና ውድድርን ተከትሎ ደግሞ ብልህና ቀልጣፋ ውሾች ውድድርና የእውቅና የመስጠት ሥነ ሥርዓት ተካሄዷል። የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር በርዴሙካመዶቭ በድንበር አካባቢ በጥበቃ ታማኝና ጀብዱ ለፈጸመ ውሻ የአገሪቱን ትልቅ ሜዳሊያ ሸልመውታል። ይህን ሜዳሊያ ለርዕሰ ብሔሩ ያቀበሉት ደግሞ የፕሬዝዳንቱ ወንድ ልጅና የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ሰርዳር በርዲሞካመዶቭ ናቸው። በውቧ የቱክሜኒስታን ዋና ከተማ አሽጋባት የተገነባው የዚህ ውሻ ዝርያ ማራቢያ ማዕከልም በፕሬዝዳንቱ ተመርቋል። አላባይ ውሾች በቱርከሜኒስታን እጅግ ተወዳጅና በእረኞች ዘንድ የሚዘወተሩ ሲሆኑ በዓለም ውሾች ዝርያም ግዙፎቹ ናቸው። አንድ የአላባይ ውሻ በአማካይ እስከ 80 ኪሎ ይመዝናል። ባለፈው ዓመት የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር በርዲሙካመዶቭ 6 ሜትር ቁመት ያለው ከወርቅ የተሠራ የውሻ ሐውልት በዋና ከተማዋ አደባባይ መርቀዋል። ዋና ከተማዋ አሽጋባት በርካታ የውሻና የፈረስ ሐውልቶች አሏት። አምባገነን ናቸው፣ ተቀናቃኝ የላቸውም የሚባሉት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚስተር በርዴ ሙካመዶቭ የየትኛውንም አገር መሪ ሲጎበኙ የውሻ ወይም የፈረስ ስጦታን ይዘው ነው የሚሄዱት። በጎርጎሳዊያኑ 2017 ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን አላባይ ውሻን በስጦታ ባበረከቱበት ወቅት ድንክየውን ውሻ በማጅራቱ በኩል አንጠልጥለው በእንዝላልነትና ርህራሄ በጎደለው አኳኋን ለፑቲን ማስረከባቸው እጅግ ሲያስተቻቸው ነበር። ቅጽበቱም በቪዲዮ በመላው ዓለም ተዛምቶ ሚሊዮኖች ከፍ ዝቅ አድርገዋቸው የዓለም መሳቂያ ሆነው ነበር። ስጦታውን የተቀበሉት ቪላድሚር ፑቲን ግን አላባይ ድንክ ውሻውን በፍቅር አቅፈው መቀበላቸው በአንጻሩ ውዳሴን አስገኝቶላቸው ነበር።
45794453
https://www.bbc.com/amharic/45794453
በሜክሲኮ ሲቲ የሴቶችን ገላ እየቆራረጡ ሲሸጡ የነበሩ ባልና ሚስት በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ባልና ሚስት በቤታቸው የሰው "ስፔርፓርት" ነበራቸው ነው ያለው ፖሊስ። ከሜክሲኮ ወጣ ብላ በምትገኘው ኤካቴፔክ በምትባል ትንሽ መንደር የሚኖሩት ባልና ሚስት የሰው ልጅን አካል እየከታተፉ ለማን ይሸጡ እንደነበር ገና አልተደረሰበትም።
ናንሲ ሂትሮን ከሕጻን ልጇን ጋር ድንገት ከተሰወረች ወራት ተቆጥረው ነበር። ኾኖም ባልየው ለፍርድ ቤት እንዳመነው ባለፉት ጊዜያት ብቻ 20 ሴቶችን ገድሏል። ሰውነታቸውንም ለገበያ አቅርቧል። ፖሊስ ባልና ሚስቱ ከሚኖሩበት አፓርትመንት በቅርብ ርቀት በሚገኝ ቤት ያስቀመጧቸውን ገና ያልተሸጡ፣ ነገር ግን የሟቾቹ አካላት እንደሆኑ የተገመቱ የሰውነት ክፍሎችን በብዛት አግኝቷል። ባልና ሚስቱ እያደኑ ይገድሉ የነበረው ሴቶችን ብቻ እንደነበረም ተመልክቷል። ይህ ሴቶችን ብቻ የመግደል ድርጊት ሜክሲኮ ገጠራማ ቦታዎች ላይ የተለመደ እንደሆነ ዘገባዎች ያስረዳሉ። ጎረቤቶቻቸው እንደመሰከሩት ባልና ሚስትን ሁልጊዜም የሚያይዋቸው የሕጻን ማዘያ ጋሪን እየገፉ ነው። ይህም ምናልባት የሟቾችን ገላ የሚሸጡበት ዘዴ እንደሆነ ፖሊስ ጥርጣሬውን ገልጿል። ጁዋን ካርሎስ በሚል ስም የተጠቀሰው ተጠርጣሪ ሴቶቹን ከመግደሉ በፊት ጾታዊ ጥቃት እንደሚፈጽምባቸው አምኗል። ከዚያ በኋላ ጌጣጌጦቻቸውንና የሰውነታቸውን ክፍል በውል ላልተለዩ ደንበኞች ሲሸጥ እንደነበር ለፖሊስ ቃል ሰጥቷል። ባልና ሚስቱ በሚኖሩበት አካባቢ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቢያንስ ሦስት አግብተው የፈቱ ሴቶች ከነልጆቻቸው መሰወራቸው ሪፖርት ተደርጎ ነበር። ምናልባትም እነዚህ ሴቶች በነዚህ ባልና ሚስት ተቀጥፈው እንደሆነ ጥርጣሬ አለ። ሕጻናቱን ግን ሳይገድሉ በሽያጭ እንደሚተላለፉ ተጠርጣሪዎቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ሜክሲኮ ስቴት ወትሮም ሴቶች ድንገት የሚሰወሩባት ከተማ ናት። በተለይም የመንግሥት ወታደሮች ለመሄድ በሚሰጉባቸውና ወንጀለኞች በሚበዙባቸው ሰፈሮች ሴቶች እንደወጡ ይቀራሉ። ከጥር እስከ ሚያዚያ ብቻ 395 ሰዎች የት እንደገቡ አልታወቀም። ከነዚህ ውስጥ 207ቱ ሴቶች ናቸው።
news-50217516
https://www.bbc.com/amharic/news-50217516
ኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ሁከት 359 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል አጋጥሞ ከነበረው ግጭትና ጥቃት ጋር በተያያዘ 359 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ከፍያለው ተፈራ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ያለው ሁኔታ እየተረጋጋ መምጣቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ተፈራ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ኮሚሽነር ጀነራሉ እሁድ ዕለት የሟቾች ቁጥር 67 እንደሆነ መናገራቸውን አስታውሰው፤ ከዚያ ወዲህ በግጭት ሳቢያ የሞቱ ሰዎች አለመኖራቸውን ገልጸዋል። • ስለባለፈው ሳምንት ግጭቶችና ጥቃቶች አስካሁን የምናውቃቸው ነገሮች በአብያተ ክርስቲያኖቿና በምዕመኖቿ ላይ ጥቃት እንደተፈጸመ የገለጸችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግነኙት ኃላፊ የሆኑት መልዓከህይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ በበኩላቸው 60 የሚደርሱ የእምነቱ ተከታዮች ባለፈው ሳምንት ባጋጠመው ሁከት መገደላቸውን ተናግረዋል። አክለውም "ከእሁድ ወዲህ በሞጆ ከተማ 1 ሰው በባሌ ሮቤ ደግሞ 2 ሰዎች ተገድለው ተገኝተዋል። የሰዎቹ ግድያ ከግጭቱ ጋር የተያያዘ ይሁን በሌላ ምክንያት ይሁን አስካሁን አልታወቀም። የማጣራት ሥራዎች እየተሰሩ ነው" ሲሉ አመልክተዋል። ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች 80 በመቶ (54 ሰዎች) የሞቱት በእርስ በእርስ ግጭት እንደሆነ እና የተቀሩት ደግሞ ከጸጥታ አስከባሪ ጋር በነበረው ግጭት ህይወታቸውን ያጡ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ከተቃውሞ ሰልፍ ወደ ሃይማኖታዊ መልክ ወደላው ግጭት በተቀየረው ሁከት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት 'ይሄኛው አካል ነው ወይም ያኛው ነው' ማለት አይቻልም ብለዋል ኮሚሽነሩ። • በግጭት ለተፈናቀሉት የተሰበሰበው አስቸኳይ እርዳታ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ "ሁከቱ ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት ከተቀየረ በኋላ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የዚኛው ሃይማኖት ተከታይ ነው ማለት አይቻልም። የተቃውሞ ሰልፉ ወደ ግጭት ከተቀየረ በኋላ በሁለቱም ጎራ ባሉት ሃይማኖት ተከታዮች በኩል ህይወት ጠፍቷል" ብለዋል። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሞቱብኝ ምዕመኖች ቁጥር 60 ነው ማለቷን ተከትሎ ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው በሰጡት ምላሽ "እኛ እንዲህ አይነት መረጃ የለንም። በክልሉ ውስጥ የሚፈጠረውን የምንቆጣጠረው እኛ ነን። እነሱ ይህን መሰል መረጃ ከየት እንዳመጡ አናውቅም" ብለዋል። የፖሊስ ኮሚሽነሩ ጨምረው እንደተናገሩት ሰሞኑነ በነበረው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው ሦስት የዕምነት ቤቶች ብቻ መሆናቸውን ጠቁመዋል። "በአዳማ ከተማ አንድ መስጅድ እንዲቃጠል ተደርጓል። ከአዳማ ወጣ ብለው በሚገኙ ገጠራማ ስፍራዎች ደግሞ አንድ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን እና ሌላ አንድ ግንባታው ገና እየተጀመረ ያለ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተቃጥሏል" ብለዋል። • ቅዱስ ሲኖዶሱ ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ከመከላከያ ሚንስትሩ ጋር ተወያየ ከሰሞኑ የተከሰተውን ግጭት ኦሮሚያ ፖሊስ ፈጥኖ መቆጣጠር ላይ ድክመት አሰይቷል በሚባለው ትችት ላይ ምላሻቸውን ሲሰጡ "የኦሮሚያ ፖሊስ ግጭቱን ለመቆጣጠር ህይወት እስከመክፈል ድረስ መስዋትነት እየከፈለ ነው" ነው በማለት የክልሉ ፖሊስ ጥረት ማድረጉን አመልክተዋል። በሁሉም ስፍራዎች የወጡት የተቃውሞ ሰልፎች ከአቅም በላይ የሆኑ እንደነበሩ የጠቀሱት የፖሊስ ኮሚሽነሩ፤ ከሌሎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ግጭቱ አሁን ወደ ደረሰበት ደረጃ እንዲወርድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተው የኦሮሚያ ፖሊስ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ተፈራ በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በተተኮሰ ጥይት ሰዎች መገደላቸውንም አምነዋል። "በአምቦ ከተማ ይህን መሰል ክስተት አጋጥሟል። ይህን ድርጊት የፈጸሙትም በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር ውለው የምረመራ እየተከናወነባቸው ነው። የወሰዱት እርምጃ ተመጣጣኝ ነው ወይ? ይህን እርምጃ እንዲወስዱ ያስገደዳቸው ሁኔታ ምን ነበር? የሚሉት ጉዳዮች ከተመረመሩ በኋላ መጠየቅ ያለበት ሰው ተጠያቂ ይደረጋሉ" ብለዋል። 'ኦሮሚያ ፖሊስ ለአንድ አካል ወግኗል' ኦሮሚያ ፖሊስ ለአንድ አካል ወግኗል የሚለውን ክስ ኮሚሽነር ጀነራሉ አይቀበሉትም። "ይህ አይነት ባህሪም በአባላቶቻችን ዘንድ አልተስተዋለም" ብለዋል። "ፖሊሶቻን ሁሉንም ህዝብን ይታደጋሉ። በሁከቱ ወቅት በሁለቱም ጎራ የነበረውን ከግንዛቤ በማስገባት የሕግ ማስከበር ሥራውን ሲያከናውን ነበር። ለአንድ ወገን አድልቶ ሌላውን ሲጎዳ ነበር የሚለው ፍጹም ውሸት ነው" ብለዋል ኮሚሽነር ጀነራሉ። ባለፈው ሳምንት ካጋጠመው አለመረጋጋት ጋር ግነኙነት አላቸው ተብለው በመጠርጠር በቁጥጥር ስር ከዋሉት 359 ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ሰዎችንም በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየተረሰራ መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽንር ከፍያለው፤ አሁን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ችግሩ ተፈጥሮባቸው የነበሩት ከተሞች ወደ ቀደመ ሰላማቸው ተመልሰዋል ብለዋል። • በተለያዩ ሥፍራዎች ባጋጠሙ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር 67 ደርሷል ኮሚሽነሩ ጨምረውም "አሁን ላይ የተዘጉ መንገዶች የሉም፣ ሰው ወደ ዕለት ሥራው ተሰማርቶ በሰላም እየመሰል ነው፣ በሁከቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ቤቶች መልሰው እየተገነቡ ነው፣ በተለየዩ ከተሞችም ከህዝብ ጋር ውይይቶች እየተካሄዱ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ባለፈው ረቡዕ በኦሮሚያ፣ በድሬዳዋና ሐረር ውስጥ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ባጋጠሙ ግጭቶችና ጥቃቶች ሳቢያ ከ65 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንዳጋጠመ ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም የእምነት ቤቶች፣ የንግድ መደብሮች፣ መኖሪያ ቤቶችና ተሽከርካሪዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች በእሳት ቃጠሎ የመውደምና ከጥቅም ውጪ የመሆን ጉዳት ደርሶባቸዋል።
news-53317140
https://www.bbc.com/amharic/news-53317140
የትግራይ ቴሌቪዥንና የድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን ስርጭት ተቋረጠ
በትናንትናው ዕለት የትግራይ ቴሌቪዝንና ድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ጣብያዎች የሳተላይት ስርጭት መቋረጡ ታውቋል።
የሁለቱ መገናኛ ብዙሃን ጣብያዎች ሥራ አስኪያጆች ጉዳዩን ለቢቢሲ ያረጋገጡ ሲሆን የትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተሻለ በቀለ የቴሌቪዥኑ ጣብያ የሳተላይት ስርጭት እንዲቋረጥ የተደረገው በኢትዮጵያ መንግሥት ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "መንግሥት የሳተላይት ስርጭቱ እንዲቋረጥ አድርጓል። ስለተፈጠረው ነገር ለማወቅ ሳተላይቱን ወደ አከራየን ድርጅት ስንደውል የኢትዮጵያ መንግሥትና የፈረንሳይ መንግሥት ተነጋግረው በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት አቋርጠነዋል የሚል ምላሽ ነው የሰጡን፤ ምክንያቱን ስንጠይቅም የፈረንሳይ መንግሥት ያለውን መፈፀም አለብን ነው ያሉት።" በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን አንዷለም ለቢቢሲ በሰጡት ቃል "እስካሁን ባለኝ መረጃ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ሚዲያዎችን የመዝጋት እርምጃ አልወሰደም "ብለዋል። የትግራይ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅ ስርጭታቸው እስከ መቼ ድረስ ተቋርጦ እንደሚቀጥል ያውቁ እንደሆን ተጠይቀው ይህንን ጥያቄ ስርጭቱን ላቋረጠው ድርጅት ማቅረባቸውን ይገልፃሉ። እነርሱም እስከመቼ ድረስ እንደተቋረጠ እንደማያውቁ እና "ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተነጋገሩ" ማለታቸውን ገልፀዋል። ሥራ አስኪያጁ አቶ ተሻለ አክለውም ወደ ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን መደወላቸውንና ስልካቸውን የሚመልስላቸው አለማግኘታቸውን ተናግረዋል። አቶ ተሻለ ለቢቢሲ ጨምረው እንደተናገሩት መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ ከድርጅቱ አለመጻፉን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በትግራይ ክልል የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር የሁለቱ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት እየተላለፈ አለመሆኑን አረጋግጧል። አቶ አበበ አስገዶም፣ የድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ጣብያ ሥራ አስኪያጅ ለሪፖርተራችን እንዳረጋገጡት፣ በበኩላቸው ስርጭታቸው እንደተቋረጠ ፈረንሳይ አገር ወደ ሚገኘው የሳተላይት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት መደወላቸውንና የቴክኒክ ክፍል ኃላፊው የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲቋረጥ ማድረጉን እንደነገራቸው ገልፀዋል። ባለፈው ሳምንት ድምፂ ወያነ በአዲስ አበባ የሚገኘው ቢሮው አቃቤ ሕግ በሚያደርግበት ምርመራ የተነሳ ፍተሻ እንደተደረገለት መዘገቡ ይታወሳል። የብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን እነዚህ ሁለት ድርጅቶች የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መጻፋቸውን አስታውሰዋል። ቢሆንም ግን የጣቢያዎቹ ስርጭት እንዲቋረጥ ባለስልጣኑ የወሰደው ምንም አይነት እርምጃ እንደሌለ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-56659421
https://www.bbc.com/amharic/news-56659421
በኖርዌይ ከሞቱ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ በቤታቸው የተገኙት ግለሰብ አስከሬን ጥያቄ አስነሳ
በኖርዌይ ከሞቱ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው አስከሬናቸው የተገኘው ግለሰብ ጉዳይ ፖሊስ ጥያቄ እንዳጫረበት ከሰሞኑ አስታውቋል።
በ60ዎቹ እድሜ ላይ የሚገኙት ግለሰብ ከሞቱ ዘጠኝ ዓመታትን ቢያስቆጥሩም መሞታቸው ሳይታወቅ እስካሁን ቆይቷል ተብሏል። ፖሊስ ለኖርዌይ ሚዲያ ኤንአርኬ እንደተናገረው ግለሰቡ ጠፍተዋል ወይም ለዚህን ያህል ዓመታት አልታዩም ብሎ ሪፖርት ያደረገ አካል እንደሌለ ነው። ፖሊስ የግለሰቡን አስከሬን ያገኘው በዋናዋ መዲና ኦስሎ በሚገኝ የጋራ መኖሪያ ቤት በባለፈው ዓመት ታኅሣሥ ወር ውስጥ ነው። እንደ ኤንአርኬ ዘገባ ከሆነ የግለሰቡ አስከሬን የተገኘው ህንፃውን የሚቆጣጠረው ግለሰብ አንዳንድ ጥገናዎች ለመስራት ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመግባቱ ነው። ፖሊስ በስፍራው ላይ የተገኙ የወተት ካርቶኖችን፣ ደብዳቤዎችንና ሌሎች መረጃዎችን በማጣቀስ ግለሰቡ የሞቱት በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 2011 መሆኑን ነው። የኦስሎ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ግሬት ሊየን ሜትሊድ ለኤንአርኬ እንደተናገሩት "ለዓመታት በተለያዩ ሞቶች ላይ የሰራነው እኔም ሆነ የሥራ ባልደረቦቼ በጣም ነው ያሳሰበን" የሚሉት ኃላፊው "ይሄ ለየት ያለ ጉዳይ ነው፤ እንዴት ለዚህን አመታት ያህል መሞታቸው ሳይታወቅ ቆየ የሚለው በርካታ ጥያቄዎችን የሚያጭር ነው" በማለት ያክላሉ። አስከሬኑ ላይ በተደረገ ምርመራ ግለሰቡ በተፈጥሯዊ ምክንያቶች መሞታቸውን ጠቁሟል። የኖርዌይ የሥራና ደኅንነት አስተዳደር የጡረታ ገንዘባቸውን መላክ ያቆመው ከሦስት ዓመታት በፊት ነው። መስሪያ ቤቱ ግለሰቡን ማግኘት ስላልቻለ ክፍያውን ማቆሙን ሪፖርቶች ያሳያሉ። ስለ ግለሰቡ ማንነት ጠለቅ ያለ መረጃ ባይገኝም ኤንአርኬ እንደዘገበው ለበርካታ ጊዜያት አግብተው እንደነበርና ልጆችም እንዳፈሩ ነው። "በቤታቸው ካገኘናቸው ፎቶ በመነሳት ከሌሎች ጋር ብዙም ግንኙነት መፍጠር እንደማይፈልጉ ተረድተናል" በማለት ኃላፊው ይናገራሉ። ፖሊስ ከአንድ ጎረቤት አገኘሁት ባለው መረጃ ከሰዎች ጋር ማውራት እንደማይወዱ ነው። የግለሰቡ አሟሟት ጉዳይ ፈጥኖ አለመታወቅ አገሪቷ በቴክኖሎጂ የደረሰችበትን የላቀ ደረጃና ማህበረሰቡ እንዴት እየተቀየረ እንዳለ ማሳያ ነው ተብሏል።
news-44572627
https://www.bbc.com/amharic/news-44572627
የደቡብ ሱዳኑ ማቻር ሃገር ሊቀይሩ ነው
በቁም እሥር ደቡብ አፍሪቃ የሰነበቱት የደቡብ ሱዳን አማፂ ቡድን መሪ ሪዬክ ማቻር ወደ ሶስተኛ ገለልተኛ ሃገር ሊዛወሩ እንደሆነ ተነግሯል።
ይህ የሆነው ሃገሪቱን ወደ አንፃራዊ ሰላም ሊመራ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበት በነበረው የአዲስ አበባው ድርድር ወቅት ነው። ምንም እንኳ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር እና ተቃዋሚው ሪዬክ ማቻር ከሁለት ዓመታት በኋላ ዓይን ለዓይን ቢተያዩም ስምምነት ላይ ሊደርሱ አልቻሉም። ድርድሩን የመሩት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚስትር አብይ አሕመድ ሁለቱን መሪዎች ለማስማማት ብዙ ቢጥሩም 'አመድ አፋሽ' ሆነዋል። ለሁለት ዓመታት ያህል በቁም እሥር ላይ የነበሩት ማቻር ግን ስሟ ወዳልተጠቀሰ ሶስተኛ ሃገር ተዛውረው በነፃነት እንዲኖሩ ስምምነት ተደርሷል። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ከቀድሞ ምክትላቸው ጋር በሽግግር መንግሥት ተጣምረው እንዲሰሩ የቀረበላቸውን ጥሪ 'አንገቴን ለካራ' በማለት ፉርሽ አድገውታል። ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ የተካሄደው ስብሰባ በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች ላለችው ደቡብ ሱዳን ሰላም ያመጣል ተብሎ ቢጠበቅም ውጤት አልባ ሆኗል። በቀጣይ በካርቱም እና ናይሮቢ ሊካሄድ የታቀደው ስብሰባ በጦርነቱ ምክንያት ለደቀቀው የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት መፍትሄ ያበጃል ተብሎ ይጠቃል። በተፈጥሮ ሃብት በተለይም ነዳጅ የካበተችው የዓለማችን በዕድሜ ትንሿ ሃገር ደቡብ ሱዳን ሰላም ከራቃት ዓመታት ተቆጥረዋል። የአዲስ አበባውን ድርድር የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ "ሰላም የማይስማማችሁ ከሆነ አማራጮችን ከመጠቀም ወደኋላ አንልም" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ በሃገሪቱ በተከሰተው ግጭት ምክንያት አስር ሺዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።
52831057
https://www.bbc.com/amharic/52831057
በሩሲያ 380ሺ ሰዎች በኮሮና ተይዘው ሟቾች እንዴት 4ሺ ብቻ ሆኑ?
ሩሲያ ከዓለም 3ኛ ናት፤ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ብዛት፡፡ ከላይ ያሉት አሜሪካና ብራዚል ናቸው፡፡
አሜሪካ 1ሚሊዮን 7መቶ ሺህ ተይዞባት ትናንት የሞቱባት ዜጎች ቁጥር 100 ሺ ማለፉን ተናግራለች፡፡ ብራዚል 440ሺ ተይዞባት 27ሺ ዜጎች ሞተውባታል፡፡ ሩሲያ 380ሺህ ዜጎች ተይዘውባት እንዴት የሟቾች ቁጥር 4ሺ ብቻ ሆነ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ ተቺዎች ሩሲያ የምታወጣው ቁጥር ተአማኒ አይደለም ሲሉ ሩሲያ በበኩሏ በተህዋሱ የሚያዙ ሰዎችን ቶሎ መርምሬ ስለምደርስባቸው ነው የሟቾች ቁጥር ትንሽ የሆነው ትላለች፡፡ ዛሬ የሞስኮ ባለሥልጣናት የቁጥር ማሻሻያ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡ በሚያዚያ ወር በሞስኮ ከተማ በኮቪድ-19 የሞቱት ሰዎች ቁጥር 639 ብቻ ነው ያልነው ትክክል ስላልሆነ 1ሺህ 561 በሚል ይስተካከል ብለዋል፡፡ እነዚሁ የሞስኮ ባለሥልጣናት የሟቾችን ቁጥር አሳንሳችኋል በሚል ከነጻው ሚዲያ ሲተቹ የነበሩ ናቸው፡፡ ያን ጊዜ የመለሱት ‹‹ሚዲያው ሐሳዊ ነው፤ መቅጠፍ ልማዱ ነው›› የሚል ነበር፡፡ ዛሬ ተነስተው ለምን የቁጥር ማሻሻያ ለማድረግ እንደተገደዱ ግልጽ አይደለም፡፡ አሁን በስፋት እየተነሳ ያለው ጥያቄ በሞስኮ ብቻ ሳይሆን በመላው ሩሲያ የሟቾች ቁጥር 4ሺ 142 ብቻ እንዴት ሊሆን ይችላል የሚለው ነው፡፡ መንግሥት አሁንም ይህን ጥያቄ የሚያነሱ መገናኛ ብዙኃንን መርዶ ናፋቂዎች እያለ ይተቻል፡፡ ‹‹ዜጎቼ የማይሞቱት በስፋት የኮቪድ ምርመራን ተደራሽ ስላደረኩ ነው›› ትላለች ሩሲያ፡፡ ሞስኮ የኮቪድ ወረርሽኝን አስታካ በርካታ ጋዜጠኞችን በሰበብ አስባቡ እያሰረች ትገኛለች፡፡ ይህም ከምዕራቡ ውግዘትን እያስከተለባት ይገኛል፡፡ ሞስኮ የሟች ቁጥር ማስተካከያ ለምን አደረገች? ባለሥልጣናቱ ለዚህ የሰጡት ምላሽ በኮቪድ እንደሞቱ ያላወቅናቸው ሰዎች ዘግይተን ምርመራ ስናደርግ በበሽታው መያዛቸውን ስለደረስንበት ነው ብለዋል፡፡ በሬሳዎች ላይ ያደረጉት ምርመራ ተጨማሪ ዜጎች በኮቪድ ስለመያዛቸው እንዲያውቁ እንዳደረጋቸው ነው የሚናገሩት፡፡ 169 ሰዎች ኮቪድ የለባቸውም ተብለው ከሞቱ በኋላ በሬሳቸው ላይ የተደረገ ምርመራ ፖዘቲቭ ሆነው ተገኝተዋል፤ እንደ ባለሥልጣናቱ መረጃ፡፡ በተጨማሪም በሚያዚያ በሌሎች በሽታዎች ሞተዋል የተባሉ 756 ሰዎች ሲጣራ በኮቪድ መሞታቸው ተደርሶበታል፡፡ • አንዳንዶች በኮሮናቫይረስ ሌሎች ደግሞ በሐሳዊ ዜና ወረርሽኝ እየሞቱ ነው የቢቢሲዋ ባልደረባችን ሳራ ሬይንስፎርድ እንደምትገምተው ይህ በሞስኮ ከተማ በሬሳዎች ላይ የተደረገ ምርመራ ቁጥሩን በዚህ ደረጃ የሚቀያይረው ከሆነ በመላው ሩሲያ የሟቾች ቁጥር ከተገለጸው በብዙ እጥፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ባለሥልጣናቱ በበኩላቸው የግንቦት ወር የሟቾች ቁጥር በዚህ መረጃ እንዳልተካተተ ተናግረዋል፡፡
news-48116658
https://www.bbc.com/amharic/news-48116658
አሜሪካ የግብፁ ሙስሊም ብራዘርሁድን በአሸባሪነት ልትፈርጅ ነው
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የግብፁን ሙስሊም ብራዘርሁድ አሸባሪ ድርጅት ብሎ ለመፈረጅ በዝግጅት ላይ መሆኑን ዋይት ሀውስ ትናንት በመግለጫው አስታውቋል።
በመካከለኛው ምስራቅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት ይህ ድርጅት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ በድርጅቱና በአባላቱ ላይ የጉዞና የኢኮኖሚ ማእቀቦች የሚጣሉ ይሆናል። አሜሪካ ሙዝሊም ብራዘርሁድን በአሸባሪነት ለመፈረጅ የወሰነችው ከሶስት ሳምንታት በፊት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አሜሪካን መጎብኘታቸውን ተከትሎ ነው። መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ዶናልድ ትራምፕ ይህን እንዲያደርጉ አል ሲሲ ጠይቀዋቸዋል። ትራምፕና አል ሲሲ መገናኘታቸውን ተከትሎ ትራምፕ ወዲያው ሙስሊም ብራዘርሁድ ላይ የኢኮኖሚ ማእቀብ መጣል የሚቻልበትን መንገድ እንዲፈልጉ የደህንነትና የዲፕሎማሲ አማካሪዎቻቸውን አዘውም ነበር። ትናንት የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሳራ ሳንደርስ የትራምፕ አስተዳደር በውሳኔው እየገፋበት እንደሆነ አስታውቀዋል። • ተስፋዬ ገብረአብ ስለ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምን ይላል? • በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተሞሸሩት ጥንዶች "ፕሬዝዳንቱ ከደህንነት አማካሪዎቻቸው እንዲሁም ከአካባቢው መሪዎች ጋር በጉዳዩ ላይ መክረዋል። እናም ይህ ውሳኔ በዚያ መሰረት እየተኬደበት ያለ ነገር ነው" ብለዋል ሳንደርስ በመግለጫቸው። በ2013 የጦር ሃይል አዛዥ የነበሩት አል ሲሲ የሙስሊም ብራዘርሁዱን ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ሙርሲን ከስልጣን አስወገዱ እንደ አውሮፓውያኑ በ2013 የግብፅ ጦር አዛዥ የነበሩት አል ሲሲ በወቅቱ ፕሬዝዳንት የነበሩትን የሙስሊም ብራዘርሁዱ ሞሃመድ ሙርሲን በመፈንቅለ መንግሥት ከስልጣን ማውረዳቸው የሚታወስ ነው። ሙርሲ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ የሙስሊም ብራዘርሁድ አባላት መታሰራቸውም ይታወቃል። የአሁኑ የአሜሪካ ፍረጃ ይፋ ከተደረገ ከሙስሊም ብራዘርሁድ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦችና ኩባንያዎች ላይ የኢኮኖሚና የጉዞ ማእቀቦች ተግባራዊ ይሆኑባቸዋል። ሙስሊም ብራዘርሁድ ዋይት ሃውስ ምንም ይበል ምን በእንቅስቃሴው ፀንቶ እንደሚቀጥል በድረ ገፁ ላይ ማስፈሩን ሮይተርስ ዘግቧል። በሌላ በኩል የኒዮርክ ታይምስ ዘገባ እንደሚያመለክተው ደግሞ ውሳኔው በዋይት ሃውስ ባለስልጣናትና በፔንታጎን ሃላፊዎች መካከል አለመግባባት ፈጥሯል። • «አቶ ገዱም ሆነ ደመቀ እኛም ብንፈተሽ ግድፈት አለብን ማለታቸውን አስታውሳለሁ» የአቶ ታደሰ (ጥንቅሹ) ባለቤት
47354024
https://www.bbc.com/amharic/47354024
ሳዑዲ ልዕልቷን የአሜሪካ አምባሳደር አደረገች
ሳዑዲ አረቢያ፤ ልዕልት ሪማ ቢንት ባንዳር አል-ሳዑድን በአሜሪካ የሳዑዲ አምባሳደር አድርጋ ሾመች። ልዕልቷ መሰል ሥልጣን የተሰጣት የመጀመሪያ ሴት ናት።
ልዕልት ሪማ ቢንት ባንዳር አል-ሳዑድ ልዕልቷ ከልጅነት ህይወቷ ከፊሉን ያሳለፈችው በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ሲሆን፤ ለአምባሳደርነት መመረጧ ይፋ የሆነው ቅዳሜ እለት ነበር። የጋዜጠኛው ጀማል ኻሾግጂን ግድያ ተከትሎ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሳዑዲ ላይ ጣቱን በቀሰረበት ወቅት በአምባሳደርነት መሾም የልዕልቲቷን የሥራ ኃላፊነት ከባድ ያደርገዋል እየተባለ ነው። • ኢትዮጵያውያን እስረኞች ከሳዑዲ ወደ ኢትዮጵያ እየተመለሱ ነው ሳዑዲ በኻሾግጂ ግድያ ዙሪያ እርስ በእርስ የሚጣረስ መረጃ ስታወጣ መቆየቷ ይታወሳል። ሳዑዲ፤ በኻሾግጂ ግድያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን እጃቸው የለበትም ብትልም የአሜሪካ የስለላ ተቋም ነገሩ አልተዋጠለትም። የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ኋይት ሀውስ ነገሩን እንዲያጣራ ጫና ለማሳደር ሞክረዋል። የኮንግረሱ አባላት የኒውክሌርና የየመን ጦርነት ገዳይን ጨምሮ በአሜሪካና በሳዑዲ መካካል ያለውን ግንኙነት መርምረዋል። ልዕልቷ ሥልጣኑን የምትረከበው ከልዑል አልጋ ወራሹ ታናሽ ወንድም ልዑል ካሊድ ቢን ሳልማን ነው። • ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች የልዕልቷ አባት ባንዳር ቢን ሱልጣን አል-ሳዑድ እንደ አውሮፓውያኑ ከ1983 እስከ 2005 ድረስ በአሜሪካ የሳዑዲ አምባሳድር ነበሩ። በአባቷ ስልጣን ምክንያት አሜሪካ ያደገችው ልዕልቷ፤ ከዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ በሙዝየም ጥናት የመጀመሪያ ዲግሪዋን አግኝታለች። ልዕልት ሪማ ቢንት ባንዳር አል-ሳዑድን በ2005 ከአሜሪካ ወደ ሪያድ ተመልሳ በመንግሥትና በግል ተቋሞች ውስጥም አገልግላለች። በበርካታ የቢዝነስ ተቋሞችን በሀላፊነት የምትሠራው ልዕልቷ፤ ለሴቶች እኩልነት በመከራከር ትታወቃለች። ሳዑዲ ሴቶችን በመጨቆን ከሚተቹ ሀገሮች አንዷ መሆኗ ይታወቃል። • ከቤተሰቦቿ አምልጣ ካናዳ የገባችው የሳዑዲዋ ወጣት፡ 'ምንም የሚጎልብኝ የለም' ልዕልቲቷ በቅርቡ የሳዑዲ የስፖርት ባለሥልጣን ነበረች። ሥራዋ በዋነኛነት ሴቶች በስፖርት ዘርፍ ያላቸውን እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያለመ ነው። ልዕልቷ ስለ ጡት ካንሰር ግንዛቤ ለመፍጠር ንቅናቄ በማድረግም ትታወቃለች።
51886207
https://www.bbc.com/amharic/51886207
ቢልጌትስ ከማይክሮሶፍት የቦርድ አመራርነቱ ወረደ
ማይክሮሶፍትን ከመሰረቱት አንዱ የሆነው ቢልጌትስ ከኩባንያው የቦርድ አባልነቱ በበጎ አድራጎት ስራዎቹ ላይ ሰፊ ጊዜ ለማሳለፍ በሚል መልቀቁ ተነገረ።
ቢልጌትስ በጤና፣ የልማት ስራዎች፣ ትምህርትና የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት የሚሰሩ ስራዎች ላይ ማተኮር እንደሚፈልግ ተናግሯል። ጌትስ ከማይክሮሶፍት የዕለት ተዕለት ስራውን የለቀቀው እአአ በ2008 ነበር። • የዓለማችን ሃብታም ሴቶች • የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ተረጋገጠ • ራስዎን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል እጅዎን ታጥበዋል? ስልክዎንስ? ጌትስ ይህንን ውሳኔውን ሲያሳውቅ ኩባንያው" ሁሌም የሕይወቴ ወሳኝ አካል ሆኖ ይቀጥላል" በማለት በአመራሩ ላይ ያለውን ተሳትፎ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ነገር ግን በማለት" ቀጣዮን መስክ ደግሞ ወዳጅነትንና አጋርነትን ለመፍጠር፤ እጅግ ለምኮራባቸው ሁለት ኩባንያዎች የማበረክተውን ለመቀጠል፣ እንዲሁም የዓለም ትልልቅ ተግዳሮቶች የሆኑትን በአግባቡ ቅደም ተከተል አስይዤ ለመስራት እንደ ወሳኝ ነጥብ አየዋለሁ" ብሏል። ቢል ጌትስ በፎርብስ ከአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ ቀጥሎ ሀብታም ሲሆን፣ አጠቃላይ ሀብቱ 103.6 ቢሊየን ዶላር ተተምኖ የዓለማችን ሁለተኛው ከበርቴ ሆኗል ። ሀብቱን ያካበተው ለግል መጠቀሚያነት የሚያገለግሉ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በማምረት ነው። ቢል ጌትስ ማይክሮሶፍትን ከልጅነት ጓደኛው ፖል አለን ጋር በመሆን የመሰረተ ሲሆን በወቅቱ የየኒቨርስቲ ትምህርቱን በሟቋረጥ ነበር ወደዚህ ስራ የተሰማራው።
news-54903833
https://www.bbc.com/amharic/news-54903833
የሴት ልጅ ጥቃት፡ መደፈርን የምትቃወመው ሊቢያዊቷ ተሟጋች በሽጉጥ ተገደለች
በሊቢያ ውስጥ የመደፈር ጥቃትን በመቃወም የምትታወቀው ተሟጋቿ ሃናን አል ባራሲ በሽጉጥ መገደል ቁጣን ቀስቅሷል።
ሃናን አል ባራሲ በአገሪቷ ምስራቃዊ ክፍል በምትገኘው ቤንጋዚ ግዛትም ነው የተገደለችው ተብሏል። በቤንጋዚ ዋና ጎዳና ላይ በመኪናዋም ውስጥ እያለች እንደተተኮሰባትም ተገልጿል። በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በፅኑ የምትታወቀው ሃናን አል ባራሲ በሙያዋ ጠበቃም ናት። በቅርቡም በከተማዋ ላይ ደረሰ የተባለ የመደፈር ጥቃትና ትንኮሳን አጋልጣለች። የመደፈር ጥቃቱም ሆነ ትንኮሳዎቹ የደረሱት ጄነራል ካሊፋ ሃፍታር ከተባሉትና የአገሪቷን የተወሰነ ክፍል ከተቆጣጠሩት ኮማንደር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተዋጊዎች እንደሆነም ይፋ አድርጋ ነበር። ይህንን ማጋለጧን ተከትሎ በሷም ላይ ሆነ በሴት ልጇ ላይ የሞት ማስፈራሪያዎች ሲደርሳቸው እንደነበር የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ አስታውቋል። የተሟጋቿ ሞት በሊቢያ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን በርካቶችም ፍትህን እየጠየቁ ይገኛሉ። ለበርካታ አመታት ሊቢያን የገዟት መሪዋ ሙዓመር ጋዳፊን ሞት ተከትሎ አገሪቷ እርስ በርስ ጦርነት እየተናጠች ትገኛለች። በቅርቡም የአገሪቷን የወደፊት አቅጣጫ አስመልክቶ በጎረቤቷ ቱኒዝያ ውይይት በመደረግ ላይ ይገኛል።
news-54084793
https://www.bbc.com/amharic/news-54084793
የትግራይ ምርጫ ለፌዴራሊዝሙ ጥንካሬ እንጂ ስጋት አይሆንም፡ ጌታቸው ረዳ
በትግራይ የሚካሄደው ምርጫ ለአገሪቱ ፌዴራሊዝም ጥንካሬ እንጂ ስጋት እንደማይሆን የህወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጌታቸው ለቢቢሲው ኒውስዴይ ተናገሩ።
አቶ ጌታቸው እንዳሉት ክልሎች ምርጫ ማድረግ ያለባቸው "መብታችን ስለሆነ ነው። እኛ በዚህ ላይ አንደራደርም። ዋጋ ከፍለንበታል። ምርጫ እናድርግ ስንል አይቻልም የሚባል ምላሽን ከአራት ኪሎ አንቀበልም" ብለዋል። እንደ እሳቸው አባባል ምርጫን የማራዘሙ ነገር በሁሉም ክልሎች ታምኖበት በቂ ምክንያት ኖሮ ቢሆን ኖሮ ነገሩን ለማጤን ድርጅታቸው እንደሚገደድ ተናግረው "ነገር ግን ይህ ውሳኔ በማዕከላዊ መንግሥት የተወሰደ የተናጥል እርምጃ ነው። ፍላጎቱን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ለመጫን የተደረገ ነው" በማለት እንደተቃወሙት አመልክተዋል። ኒውስዴይ በትግራይ ፌዴራል መንግሥትን ውሳኔ ቸል ተብሎ የሚካሄደው ምርጫ ምን ፋይዳ እንደሚኖረው አቶ ጌታቸውን ጠይቆ በሰጡት ምላሽ "በጤናማ ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆን መጠየቅ የነበረበት ጥያቄ ለምን ምርጫ አታካሄዱም ነበር። ነጻ ገለልተኛና ተዓማኒ ምርጫዎች የትም መሆን ያለባቸው ነገሮች ናቸው" በማለት ማዕከላዊው መንግሥት የሥልጣን ዘመኑን በግድ እያራዘመ መሆኑን ተናግረዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ በሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ምርጫው እንደማይካሄድ የታወቀ ሲሆን ትግራይ ለምን ተለይታ ከማዕከላዊ መንግሥቱ ጋር ቅራኔ ውስጥ እንደገቡ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው "እኛ ብቸኞቹ ከሆንን መብታችንን ስለተነጠቅን ነው እምቢ ያልነው። ውድ ዋጋ የከፈልንበት መብት ነው። ሌሎች ክልሎች ውድ ዋጋ አልከፈሉም ማለቴ ግን አይደለም" ብለዋል። ጨምረውም ሌሎች ክልሎች ምርጫው የመራዘሙን ነገር ሙሉ በሙሉ ተቀብለውታል ማለት እንዳልሆነ ጠቅሰው "ኦሮሚያ በአፈና ውስጥ ነው ያለው። ሰዎች እዚህና እዚያ እየተገደሉ ነው። በኦሮሚያም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ማለቴ ነው። መንግሥት ሕዝቡን መስማት አይፈልግም" ብለዋል። ኒውስዴይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ምሽት ለብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ክልሉን ለማስተዳደር ሙሉ መብት እንዳላቸው መግለጻቸው ውጥረቱን ያረግበው እንደሆነ አቶ ጌታቸውን ጠይቆ "ችግሩ ዐብይ የሚናገውን የሚያደርግ ሰው አለመሆኑ ነው። ከመጣ ጀምሮ ሲያደርጋቸው የነበሩ አብዛኛዎቹ ነገሮች በሙሉ ችግር ፈጣሪ ነበሩ" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ማክሰኞ ምሽት ከብሔራዊው ቴሌቪዥን ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ላይ ምርጫው ሕጋዊ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። "ሕጋዊ አይደለም፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ምርጫ ማከናወን የሚችለው የምርጫ ቦርድ ብቻ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "አሁን በዚህ ሰዓት የሚደረጉ የእቁብ ስብስቦች ወይም ጉባኤዎች የእኛ ትልቅ እራስ ምታት መሆን የለባቸውም" በማለት ምርጫው መንግሥታቸውን እንደማያሳስብ ተናግረዋል። ጨምረውም በዚህ ሳቢያ መንግሥታቸው ግጭት እንደማይገባ አረጋግጠዋል "በእኔ በኩል ለኢትዮጵያ ውጊያ ያስፈልጋል ብዬ አላምንም። እኔ በፍጹም ውጊያ ከሚደግፉ ሰዎች ጎን መመደብ አልፈልግም። እኔ የምፈልገው ለትግራይ አንድ ጥይት መላክ ሳይሆን፣ ለኮሮና መከላከሉ አንድ የአፍ መሸፈኛ ነው መላክ የምፈልገው" ሲሉ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ ከአገሪቱ ሕገ መንግሥት ጋር የሚቃረን በመሆኑ "እንዳልተደረገ የሚቆጠር፣ የማይጸናና ተፈጻሚነት የሌለው ነው" ሲል በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ይታወሳል።
news-54145141
https://www.bbc.com/amharic/news-54145141
በአሜሪካ 99 ሺህ ዶላር የተያዘበት ኢትዮጵያዊ ገንዘቡ ሊወረስ ይችላል ተባለ
ባለፈው ሳምንት ለጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ሳያሳውቅ ወደ 99 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከአሜሪካ ሊያስወጣ ሲል የተያዘበት ኢትዮጵያዊ ገንዘቡ ሊወረስ እንደሚችል ተገለጸ።
ግለሰቡ ገንዘቡን በሻንጣው፣ በጫማና በጂንስ ሱሪ ኪሶች ውስጥ ደብቆት ነበር ተብሏል ቢቢሲ በአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅንነት መስሪያ ቤት ስር ከሚገኘው የጉምሩክና የድንበር መቆጣጠሪያ ክፍል ባገኘው መረጃ መሰረት ከኢትዮጵያዊው ላይ የተያዘው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በመንግሥት ሊወረስ ይችላል ተብሏል። የዛሬ ሳምንት ረቡዕ ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ ከነበረው መንገደኛ ላይ ዋሽንግተን በሚገኘው ደለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ተቆጣጣሪዎች የተያዘው ገንዘብ 99 ሺህ ዶላር የሚጠጋ እንደሆነ ተነግሯል። ቢቢሲ እንዳረጋገጠው ከግለሰቡ ላይ የተያዘው የገንዘብ መጠን 98,762 ዶላር ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ከ3.6 ሚሊዮን ብር በላይ ይሆናል። የጉምሩክ መስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሠራተኛ ስቲቭ ሳፕ ለቢቢሲ በሰጡት የጽሁፍ ምላሽ ላይ እንዳመለከቱት፣ ግለሰቡ ይዞት የነበረው ዶላር የተያዘበት ተጓዦች የያዙትን የገንዘብ መጠን እንዲያሳውቁ የሚጠይቀውን የአገሪቱን ሕግ በመተለላፍ ነው። በተጨማሪም ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ግለሰቡ በዚሁ ሳቢያ ያልታሰረ ሲሆን የወንጀል ክስ ስላልተመሰረተበትም ማንነቱ እንደማይገለጽ ለማወቅ ተችሏል። እንዲህ አይነት የሕግ ጥሰቶች ሲያጋጥሙ ክስ መመስረትን በተመለከተ የአሜሪካ ዐቃቤ ሕግ ውሳኔ እንደሚሰጥ ያመለከቱት ስቲቭ ሳፕ፤ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዐቃቤ ሕጉ የወንጀል ክስ ላለመመስረት በመወሰኑ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት እንዳልሄደ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነገር ግን ግለሰቡ የአገሪቱን የገንዘብ ዝውውርና መጠን የማሳወቅ ግዴታን ባለመፈጸሙ 98,762 ዶላር ተይዞበታል። ስቲቭ ሳፕ እንዳሉት ተጓዦች በተለያየ መንገድና በተደጋጋሚ የያዙትን የገንዘብ መጠን በትክክል እንዲያሳውቁ እንደሚጠየቁና በመጨረሻም ይህን በጽሁፍና በቃል ለጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች ማሳውቅ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ሳይሆን ከተገኘ የያዙት ገንዘብ እንደሚያዝ ተናግረዋል። ባለስልጣናት እንዳሉት ኢትዮጵያዊው ግለሰብ በአሜሪካ ሕጋዊ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ሲሆን ወደ አዲስ አበባ በሚያደርገው ጉዞ ላይ ነበር ገንዘቡ ሊያዝ የቻለው። በወቅቱ ግለሰቡ የያዘውን የጥሬ ገንዘብ መጠን በቃልና በጽሁፍ እንዲያሳውቅ መጠየቁንና 14,000 ሺህ ዶላር እንደያዘ ቢገልፅም ይዞት በነበረው ቦርሳ ውስጥ 19,112 ዶላር ተገኝቷል። ይህንን ተከትሎ በጉምሩክና በድንበር ተቆጣጣሪዎች ተፈትሾ አልፎ በነበረው ሌላ ሻንጣ ላይ በተደረገ ብርበራ ተጨማሪ 79,650 ዶላር በጫማና በጂንስ ሱሪ ኪሶች ውስጥ አግኝተዋል። በአጠቃላይም የተገኘው የዶላር መጠን 98,762 ሆኗል። ስቲቭ ሳፕ ጨምረውም ግለሰቡ ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንደያዘና ለምን አገልግሎት ሊያውለው እንደነበር ያልገለጸ ሲሆን፤ የገንዘቡ ምንጭ ከየት እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም። በምድር፣ በአየርና በባሕር የአሜሪካ ድንበርን የሚያቋርጡ ሰዎች በሚይዙት የገንዘብ መጠን ላይ በሕግ የተጣለ ገደብ ባይኖርም መንገደኞች ከ10 ሺህ ዶላር በላይ የሆነ ገንዘብ ወይም ሌላ የገንዘብ መገልገያዎችን ወደ አገሪቱ ሲያስገቡም ሆነ ሲያስወጡ ለጉምሩክ ሠራተኞች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። ይህንን ሕግ ተላልፈው የያዙትን ገንዘብ በትክክል ሳያሳውቁ የተገኙ ተጓዦች ከተያዘባቸው ገንዘብ አብዛኛውን ወይም ሁሉም የሚወረስ ሲሆን በተጨማሪም የወንጀል ክስ ሊመሰረትባቸው ይችላል። ገንዘቡ የተያዘበት ግለሰብ እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት ያለው ቢሆንም የተወረሰው ገንዘብ ምንጭና ሊውል የታሰበበት አላማ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል። መንገደኞች ወደ አሜሪካ ሲገቡም ሆነ ሲወጡ በእጃቸው ላይ ያለን የትኛውንም አይነት ገንዘብ መጠኑን ማሳወቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህንንም የአሜሪካ የጉምሩክና የድንበር ቁጥጥር መስሪያ ቤት ያስፈጽማል። መስሪያ ቤቱ በተጨማሪም የአገሪቱን የምድር፣ የአየርና የባሕር ድንበሮችን ከመጠበቅ ባሻገር ሕጋዊ የንግድና የጉዞ እንቅስቃሴ እንዲሁም ገንዘብ ልውውጥ እንዲኖር የተለያዩ ሕጎችን ያስፈጽማል።
news-49548015
https://www.bbc.com/amharic/news-49548015
እራስን ለማጥፋት ከማሰብ ወደ ሚሊየነርነት
ኤንዲ ፐዶኮምብ እንደማንኛውም እንግሊዛዊ ኑሮውን ይገፋ ነበር። ነገር ግን በድንገት ባጋጠሙት አሳዛኝ ሁነቶች ሕይወቱ አስቦት ወደማያውቀው አቅጣጫ ተጉዛለች።
ሪቻርድ ፒርሰን እና ኤንዲ ፐዶኮምብ በ1212 የራሳቸውን ድርጀት መስርተዋል የ22 ዓመት ወጣት እያለ በአንድ ምሽት ከጓደኞቹ ጋር ለመዝናናት በመዲናዋ ለንደን ወደሚገኝ ግሮሰሪ ጎራ ይላሉ። ከግሮሰሪው ወጥተው በር ላይ ቆመው ሳለ አንድ ያልጠበቁት አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ። ጠጥቶ ሲያሽከረክር የነበረ አንድ ግለሰብ በፍጥነት መጥቶ ገጫቸው። በአደጋው ኤንዲ ሁለት የሚወዳቸውን ጓደኞቹን አጣ። ከጥቂት ወራት በኋላ ደግሞ እህቱ በሳይክል አደጋ ሕይወቷ አለፈ። • የጥሩ አባትነት ሚስጥሮች ምንድናቸው? • ጥሩ ሰው ምን አይነት ነው? ሃዘኑ በዚህ አላበቃም ነበር። የቀድሞ የፍቅር ጓደኛው ሆስፒታል ውስጥ ቀዶ ጥገና እየተደረገላት በድንገት ሞተች። በወቅቱ ኤንዲ በስፖርት ሳይንስ ዲግሪውን ለመያዝ እየተማረ ነበር። ነገር ግን በድንገት ባጋጠሙት አሳዛኝ ሁነቶች ትምህርቱን ለማቋረጥ ተገደደ። በተደጋጋሚም እራሱን ለማጥፋት ይፈልግ ነበር። በመጨረሻ ግን ወደ ሂማልያ ተራራ ለመጓዝና የቡድሃ መነኩሴ ለመሆን ወሰነ። ሙሉ የእስያ አህጉርን በመዞር ለ10 ዓመታት በጥሞናና በተመስጦ አሳለፈ። በቀን ለ16 ሰአታትም ያለምንም እንቅስቃሴ በጥሞና ያሳልፍ ነበር። በዚህ ምክንያት በሕይወቱ ለነበሩት ብዙ ጥያቄዎችም ምላሽ ማግኘቱን ኤንዲ ይናገራል። ''አስተሳሰቤ በሙሉ ተቀይሯል- ስለራሴ እያሰብኩ የማሳልፈውን ጊዜ እንድቀንስ እና ስለሌሎች ሰዎች ደስታ እንዳስብ አድርጎኛል'' ይላል የአሁኑ የ46 ዓመት ጎልማሳ። ኤንዲ ፐዶኮምብ ጓደኞቹና የቅርብ ቤተሰቦቹ በመጀመሪያ አካባቢ በሁኔታው ተደናግጠው ነበር። ''እንዴት የተደላደለ ሕይወቱን ትቶ ተራራ ላይ ሄዶ መነኩሴ ይሆናል? '' እያሉ ያስቡ ነበር ይላል ኤንዲ። እ.አ.አ. በ2005 ኤንዲ ወደ ትውልድ አገሩ እንግሊዝ በመመለስ ጥሞናን ለአገሩ ሰዎች ለማስተዋወቅ ሞክሮ ነበር። ነገር ግን እምብዛም ተቀባይነት አላገኘም። ለንደን ውስጥ የራሱን የጥሞና ማስተማሪያ በመክፈት የብዙ ሰዎችን ሕይወት ቀስ በቀስ መቀየር መቻሉን ይናገራል። ዛሬ ላይ ኤንዲ እና ባልደረባው ሪቻርድ ፒርሰን በጥምረት የሰሩት የጥሞና መተግበሪያ በጣም ተወዳጅ ሆኖ 16 ሚሊየን ሰዎች በተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸው ላይ ጭነውታል። በዓመት እስከ 100 ሚሊየን ዶላር ትርፍም ያገኙበታል። ባልደረባው ሪቻርድ በ2005 ከኤንዲ ጋር ሲተዋወቅ በሥራውና በሕይወቱ ደስተኛ አልነበረም። ጥሞናን ከተማረ በኋላ ግን ብዙ ነገሮች ባላሰበው ፍጥነት መቀየር መጀመራቸውን ያስታውሳል። • ስለ አልጋዎ ማወቅ ያለብዎት 13 ነጥቦች • ምግብ ወሲብን የተሻለ ያደርጋል? ''ይሄን የመሰለ ሕይወት የሚቀይር እውቀት ይዞ በአንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ጊዜውን ሲያሳልፍ ማየት ከባድ ነበር። ለዛም ነው ትምህርቶቹን ከፍ ወዳለ ደረጃ ማሳደግ የሚችልበትን መንገዶች ማውራት የጀመርነው። እሱ ጥሞናን አስተማረኝ እኔ ደግሞ ብዙ ሰዎችን መድረስ የሚችልትን መንገድ አሳየሁት።'' ቀስ በቀስ የኤንዲ እና ሪቻርድ ተቀባይነት እጨመረ መጥቶ በእንግሊዝ ስማቸውን የማያውቅ ሰው ጠፋ። ብዙዎችም በኤንዲ ትምህርቶች ሕይወታቸውን ማስተካካል ስለመቻላቸው ምስክረነቶችን ሰጥተዋል። ከአምስት ዓመታት በኋላ በ2010 ሙሉ እንግሊዝን በመዞር ብዙ ትምህርቶችን ሰጥተዋል። በ2013 ደግሞ መቀመጫቸውን ከለንደን ወደ አሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ከተማ አዞሩት። በአሁኑ ሰአት ድርጅታቸው 300 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን ከጥሞና ባለፈ በተለያዩ ጤና ነክ ሥራዎች ላይም ብዙ ሚሊየን ዶላሮችን ፈሰስ በማድረግ ይሠራል። ከዚህ ባለፈም እንደ ጉግል፣ ሊንክድኢን፣ ጀነራል ኤልክትሪክና ዩኒሊቨር ከተባሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር ይሠራል። ለድርጅቶቹ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ዕለታዊ የጥሞና ትምህርቶችን ይሰጣል። በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመዘዋወርም ስለ ጥሞና ጥቅሞች ያስተምራሉ።
news-55158928
https://www.bbc.com/amharic/news-55158928
ምግብ ፡ ሲንጋፖር በቤተ ሙከራ ለተፈጠረ የዶሮ ሥጋ ፍቃድ ሰጠች
የሲንጋፖር የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን በቤተ ሙከራ "ምጥ" ተወልዶ ያደገውንና በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ሰው ሰራሽ ዶሮ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቀደ።
ይህ የዶሮ ሥጋ ልዩ የሚያደርገው ከታረደ ዶሮ የተገኘ ሳይሆን በሳይንስ ከቤተሙከራ የተፈጠረ መሆኑ ነው። ይህ ውሳኔ መቀመጫውን ሳንፍራንሲስኮ ላደረገው "ኢት ጀስት" ለተሰኘው አዲስ ኩባንያ በሲንጋፖር ገበያ ይከፍትለታል ተብሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከጤናና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ ሥጋና የሥጋ ተዋጽኦ ውጤቶች የገበያ ድርሻቸው እያነሰ መጥቷል። ከጤና፣ ከአካባቢ ጥበቃና ከአየር ንብረት ለውጥ ሰንሰለቶች ጋር ተያይዞ ሰዎች ማንኛውም ዓይነት ሥጋ መብላታቸው የሚደገፍ አልሆነም። የዓለም ሕዝብ ወደ አትክልት መመገብ ሙሉ ለሙሉ ፊቱን እንዲያዞር ማድረግ ደግሞ ቀላል አልሆነም። ችግሩን ለመቅረፍ አንድ አማራጭ ተደርጎ ይታሰብ የነበረው ሥጋን ከከብቶች ሳይሆን ከቤተ ሙከራ በመፍጠር የሕዝቦችን አመጋገብ ሥርዓት መቀየር ነበር። ይህን ተከትሎ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዳዲስ ሐሳቦች ብቅ ብቅ እያሉ ነው። አንዱ ሳይንሳዊ ምርምር ያተኮረው ከእንሰሳቱ የመቅኔ ህዋስ ወስዶ ያንን ወደ ቤተ ሙከራ በማስገባት ጣፋጭና በቂ ፕሮቲን የሚሰጥ ሥጋን በመፈብረክ የእንሰሳት እርድን ማስቀረት ነው። በዚህ ዘዴ የከብት ማርባት፣ ማሳደግና ማረድ እንዲሁም የቄራ ሂደቶችን ማስቀረት ይቻላል የሚል ትልም ነው የተሰነቀው። የቤተሙከራ ሥጋ እውን ሲሆን አንዳችም የከብት እርድ ሳይፈጸም መፈሰክ፣ በርገር መግመጥ፣ ሥጋ ወጥ መሥራት ይቻላል። ከዶሮ፣ ከበግ፣ ከፍየልና ከበሬ በተወሰደ የመቅኔ ህዋስ ብቻ በቤተ ሙከራ የተፈለገውን ያህል ሥጋ መቅረብ እንዲቻል በዓለም ላይ በብዙ አገሮች ምርምሮች እየተካሄዱ ናቸው። ብዙዎቹም ውጤት አስገኝተዋል። ኢት ጀስትና መምፊስ ሚትስ ኩባንያዎች በዚህ ረገድ ከፊት ይሰለፋሉ። ከመቅኔ ህዋሲ ወስዶ ሥጋ ለመሥራት ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት ይወስዳል ተብሏል። በቤተ ሙከራ የሚፈበረክ ሥጋ ጣዕሙን በተፈለገው መልኩ መቀያየር ይቻላል ይላሉ ሳይንቲስቶች። ከሰሞኑ ማክዶናልድን ጨምሮ በአትክልት ውጤቶች ፈጣን ምግብ ቤቶች ዘንድ እንደ አማራጭ መቅረብ ጀምረዋል። ከተለያዩ አትክልትና ከአተር የሚቀመሙት ምግቦች ሥጋ ባይሆኑም የሥጋ ጣዕም እንዲኖራቸው ተደርገው የተሰነጉ ናቸው። ቢዮንድ ሚስ እና ኢምፖሲብል ፉድ ደግሞ በሱፐርማርኬቶች የአትክልት አማራጮችን ይዘው መቅረብ ችለዋል። የአሜሪካው ኢት ጀስት ይዞት የቀረበው ሐሳብ ግን ከዚህ ሁሉ የተለየ ነው። የአትክል አማራጭን ሳይሆን ከእንሰሳት መቅኔ ህዋስ የተወሰደና በቤተ ሙከራ የበለጸገ የዶሮ ሥጋን መሰረት በማድረግ ነው ወደ ገበያ እየመጣ ያለው። በመቅኔ ህዋስ ውስጥ በቤተሙከራ አሚኖአሲድና ካርቦሀይድሬት በመጨመር ሥጋው እንዲደረጅ ይደረጋል። ኢት ጀስት ኩባንያ ሲንጋፖር የሰው ሰራሽ ዶሮ ሥጋ መፍቀዷ የዓለምን የአመጋገብ ሥርዓት ከነአካቴው የሚቀይር ትልቅ ተስፋን የጫረ ነው ሲል አሞካሽቶታል። በርካታ አገራትም ይህንኑ ይከተላሉ ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግም ገልጧል። ባለፉት ሁለት አሥርታት በርካታ አዳዲስ ኩባንያዎች ከእርድ ያልተገኙ የሥጋ ውጤቶችን በምርምር ለማምጣትና ወደ ገበያ ለማቅረብ ሞክረው አልተሳካላቸውም። ሁለት የእስራኤል የምግብ ቴክኖሎጂ ምርምር ተቋማት የሆኑት ፊውቸር ሚት ቴክኖሎጂስ እና በቢል ጌትስ የሚደገፈው ሜምፊስ ሚትስ በቤተ ሙከራ የተገኙ ሥጋዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ገበያ ለማቅረብ ሞክረዋል። በርካቶች ይህንን የሳይንስ ግኝት የምግብ ዋጋን በማውረድ፣ የአካባቢ ብክለትን በመከላከል ትልቅ አስተዋጽ ይኖረዋል ቢሉም ሌሎች ሳይንቲስቶች ደግሞ እንዲያውም ቤተ ሙከራ ውስጥ የተመረተ ሥጋ የዓለም ገበያን ሲቆጣጠር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ብለው ይሰጋሉ። የከብት ርቢ ለአካባቢ ጥበቃ አደጋ ነው የሚባለው ከብቶችን ለማርባት በሚደረገው ሂደት ተረፈ ምርትና ከከብት ርቢ የሚወጣው ዝቃጭ ወንዞችንና ምንጮችን ስለሚበክል ነው። የሲንጋፖር ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የቤተ ሙከራ ግኝቱ ሥጋ ከጤና አንጻር ምንም አይነት ጉዳት ስላላገኘሁበት ለጊዜው በዶሮ ቅልጥም ጥብስ መልኩ ለገበያ መቅረብ ይችላል ሲል ፈቃድ ሰጥቷል። ሥጋ ጠል- ቅጠል በል ሰዎች በዚህ የሳይንስት ግኝት ላይ ልዩነት አሳይተዋል። ግማሾቹ ጭካኔ የተሞላበትን የእርድ ሂደት ስለሚያስቀር ከዚህ በኋላ ሥጋ መብላት ችግር የለውም ሲሉ፤ ሌሎች በተቃራኒው ዞሮ ዞሮ ሰው ሰራሽ ሥጋው የተሰራበት ህዋስ የእንሰሳት ስለሆነ ይህን ሥጋ መመገብ ትክክል አይደለም ይላሉ።
news-42009899
https://www.bbc.com/amharic/news-42009899
በዚምባብዌ የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ አራቱ ቁልፍ ግለሰቦች
የዚምባብዌ ጦር ሃገሪቱን የተቆጣጠርኩት በሙጋቤ ዙሪያ ያሉትን የጦር ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው ማለቱ ይታወሳል።
በዚምባብዌ ፖለቲካዊ ቀውስ መስተዋል የጀመረው ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው የነበሩትን ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከስልጣን በማንሳት በምትካቸው ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤን ሊተኩ ካቀዱ በኋላ ነው። የሃገሪቱ የጦር አዛዥ ጀነራል ኮስታንቲኖ ቺዌንጋ ባሳለፍነው ሰኞ በዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ውስጥ መከፋፈል ካልቆመ ጦሩ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል አስጠንቅቀውም ነበር። • የዚምባብዌ ጦር "ጣልቃ እንደሚገባ" አስጠነቀቀ የፖለቲካ ተንታኞች አሁን ላይ የዓለም ሕዝብ ቀልብን መሳብ በቻለው የዚምባብዌ ፖለቲካ ኡደት ውስጥ አራት ቁልፍ ሰዎች አሉ ይላሉ። 1. ሮበርት ሙጋቤ ዚምባብዌ በአውሮፓውያኑ 1980 ነጻነቷን ከቅኝ ገዢዋ እንግሊዝ ከተቀዳጀች በኋላ በተደረገ ምርጫ ነበር አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡት። ሙጋቤ በስልጣን ዘመናቸው ከከወኗቸው ተግባራት በ1990ዎቹ መባቻ ላይ ያከናወኑት ሁሌም ይወሳል። በወቅቱ ሙጋቤ በጥቂት ነጮች ተይዞ የነበረውን ሰፊ መሬት በመንጠቅ ለጥቁር ዚምባብዌውያን አከፋፈሉ። ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በሥልጣን የቆዩት የ93 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ ሙጋቤ ስልጣን ለመልቀቅ ምንም አይነት ፍላጎት ባያሳዩም ጤናቸው ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ መምጣቱን ተከትሎ የሚተካቸው ማነው የሚለው ጥያቄ በበርካቶች ዘንድ ነበር። በተለይም ደግሞ በቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤና በቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት በኤመርሰን ምናንጋግዋ መካከል ውጠረት ተፈጥሮ ቆይቷል። 2. ግሬስ ሙጋቤ የሮበርት ሙጋቤ ሁለተኛ ሚስት የሆኑትና ከሙጋቤ በ40 ዓመት የሚያንሱት ግሬስ ሙጋቤ ከፕሬዝዳንቱ የቢሮ ፀሐፊነት በመነሳት በሃገራቸው ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴት ለመሆን በቅተዋል። ወዳጅና ደጋፊዎቻቸው "የድሆች እናት" እያሉ የሚጠሯቸው ግሬስ በነቃፊዎቻቸው ዘንድ ደግሞ ለሥልጣንና ሃብት እንደሚስገበገቡ ተደርገው ሲሳሉ ይስተዋላል። የሃገሪቱ ቀዳማዊ እምቤት መሆናቸውን ተከትሎ የአውሮፓ ሕብረትና አሜሪካ ሙጋቤ ላይ የጣሉት የጉዞና ሃብት ማንቀሳቀስ እገዳ ለእርሳቸውም አልቀረላቸውም። ግሬስ ሃይለኛ ተናጋሪ እንደሆኑም ይነገራል፤ ሙጋቤ ምክትላቸውን ባባረሩበት ወቅት ምናንናግዋ "እባብ ስለሆነ ጭንቅላቱ መመታት አለበት" ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም። 3. ኤመርሰን ምናንናግዋ ግሬስ ሙጋቤ ብቅ ብቅ ከማለታቸው በፊት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የሙጋቤ 'ትክክለኛ' ምትክ ተደርገው ነበር የሚቆጠሩት። ከምክትል ፕሬዝደንትነታቸው ከተባረሩ በኋላ ለህይወቴ ያሰጋኛል በማለት ሃገር ጥለው ሸሽተው ነበር። የልተረጋገጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግን ጦሩ ሃገሪቱ ከተቆጣጠረ በኋላ ኤመርሰን ምናንጋግዋ ወደ ዚምባብዌ ተመልሰዋል። በግብፅና በቻይና ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱት ኤመርሰን ላይቤሪያን ከቅኝ ግዛት ለማስወጣት በነበረው ትግል የራሳቸውን ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረጉ ይነገራል። ከነፃነት በኋላ በነበሩት ዓመታት በተከሰተ ግጭት በርካቶች እንደሞቱ ሲነገር በዚያን ጊዜ የደህንነት ሚኒስቴር የነበሩት ኤመርሰን በደረሰው ጥፋት ውስጥ ምንም ዓይነት ድርሻ የለኝም ብለውም ነበር። በዚምባቡዌያን ዘንድ 'አዞ' እየተባሉ የሚጠሩት ኤመርሰን የደህንነት ሚኒስቴር ሆነው ከመሥራታቸው አንፃር የሃገሪቱን ጦር ኃይልና የደህንነት ኤጀንሲውን በደንብ እንደሚያውቁት ይነገራል። 4. ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ የምናንጋግዋ ቅርብ ወዳጅ ናቸው የሚባሉት የ61 ዓመቱ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ የዚምባብዌን ጦር ኃይል ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ መርተዋል። በ2002 የአውሮፓ ሕብረት፣ አሜሪካና ኒውዚላንድ የጉዞና የንብረት ማንቀሳቃስ እገዳ ከጣሉባቸው የዚምባብዌ ባለሥልጣናት አንዱ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ነበሩ። ዕለተ ሰኞ የዚምባብዌ ጦር ኃይል በፖለቲካ ኡደቱ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ግልፅ የሆነ መልእክት ሲያስተላልፉ ብዙዎች እጅግ ተገርመው ነበር። እርሳቸው ይህን ባሉ በሁለተኛው ቀን የዚምባብዌ ጦር ሃገሪቱን የተቆጣጠሩ ሲሆን መፈንቅለ-መንግሥት አለመሆኑን በቴሌቪዠን ቀርበው ተናግረዋል። አሁን ላይ ሙጋቤ በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ምን ሊሆን እንደሚችል በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።
news-49354647
https://www.bbc.com/amharic/news-49354647
ካስተር ሰሜኒያ፡ «ሴት ስፖርተኞች ደግፈውኝ አያውቁም»
የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊዋ ደቡብ አፍሪቃዊቷ ካስተር ሰሜኒያ 'ሴት ስፖርተኞች ከጎኔ ቆመው አያውቁም' ስትል ቅሬታዋን አሰምታለች።
የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ አሸናፊዋ ደቡብ አፍሪቃዊት ካስተር ሰሜኒያ በ800 ሜትር ለሃገሯ ደቡብ አፍሪቃ ሶስት ጊዜ ወርቅ ያመጣችው ሰሜኒያ ወርሃ መስከረም ዶሃ ላይ በሚካሄደው ውድድር ላይ እንደማትሳተፍ ታውቋል። ምክንያቱ ደግሞ ለሴት አትሌቶች ከሚፈቀደው በላይ የቴስቴስትሮን ሆርሞን ውስጥ አለ በመባሉ ነው። «ዒለማ የሆንኩት ልሸንፍላቸው ስላልቻልኩ ነው» ስትል የ28 ዓመቷ የ800 ሜትር ሯጭ ሃሳቧን ሰጥታለች። «የስፖርቱን ዓለም ከተቀላቀልኩ ወዲህ ድጋፍ አግኝቻለሁ ብዬ አላስብም፤ በተለይ ደግሞ በሴት የሙያ አጋሮቼ።» ጆሃንስበርግ ውስጥ በተካሄደ የሴቶች ውይይት ላይ ተሳታፊ የነበረችው ሰሜኒያ «በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተቀናቃኞቼ ይህንን ምክንያት ይዘው ሲመጡ ሳይ፤ ምን ብዬ ልጥራው. . .ብቻ አስደሳች ያልሆነ ምክንያት ነው።» የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማሕበር [አይኤኤፍ] እርሷንና ሌሎቹ አትሌቶች በውስጣቸው ያለው የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን በሕክምና እንዲቀነስ ተደርጎ እንዲወዳደሩ ወይም ወደ ሌላ ርቀት እንዲቀይሩ የሚያዘውን ህግ በመቃወም ስትሟገት ቆይታለች። ሰሜኒያ፤ በቀጣዩ ክረምት ቶክዮ ላይ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር መሳተፍ እና ማሸነፍ ከቻለች በሶስት ተከታታይ ኦሎምፒኮች ወርቅ በማምጣት ታሪክ ትሠራለች። ነገር ግን ውሳኔው በፍርድ ቤት እጅ ነው የሚገኘው። አይኤኤፍ ሁለት ጊዜ ሆርሞኗን በመድሃኒት ካልቀነሽ አትወዳደሪም በሚል ከውድድር ውጭ ያረጋት ሲሆን ለዚህም ውሳኔ ይግባኝ ጠይቃለች። «በመስኩ በጣም ምርጧ ነኝ። የዓለም ምርጥ ሆነሽ ስትገኝ ሰዎች የምታደርጊውን ነገር ሁሉ መከታተል ይጀምራሉ።» «እኔ ችግር የሆንኩት በጣም ስኬታማ ስለሆንኩ ነው። ሰዎች ደግሞ ሊያስወግዱኝ ይፈልጋሉ።» «እኔን ማስቆም የሚፈልግ ሰው ከመሮጪያ መስመሩ ላይ ጎትቶ ሊያስወጣኝ ይችላል። ሌላ የምለው ነገር የለኝም። የምነግራችሁ ነገር ቢኖር እኔ የመጨዋቸው ሜዳ ላይ መሆኔን ነው።»
news-50342658
https://www.bbc.com/amharic/news-50342658
በቦሊቪያ ተቃዋሚዎች የከንቲባዋን ጸጉር አስገድደው ላጩ
ቦሊቪያ ውስጥ የምትገኘው ቪንቶ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ፓትሪሽያ አስር፤ በተቃዋሚዎቻቸው መሬት ላይ በባዶ እግራቸው ተጎትተው፣ ቀይ ቀለም ተደፍቶባቸው፣ ጸጉራቸው በግድ መቆረጡ ተሰማ።
ከንቲባዋ፤ በተቃዋሚዎቻቸው መሬት ላይ በባዶ እግራቸው ተጎትተው፣ ቀይ ቀለም ተደፍቶባቸው፣ ጸጉራቸው በግድ ተቆርቷል የገዢ ፓርቲው 'ማስ ፓርቲ' አባል የሆኑት ከንቲባዋ፤ ከሰዓታት በኋላ ለፖሊስ ተላልፈው ተሰጥተዋል። ባለፈው ወር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያካሄደችው ቦሊቪያ፤ በመንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ግጭት እየተናጠች ሲሆን፤ እስካሁን ሦስት ሰዎች ሞተዋል። • ከቼጉቬራ ልጅ ጋር ሞተር ሳይክል መንዳት • የደቡብ ኮርያ ፖለቲከኞች ለምን ጸጉራቸውን በአደባባይ ይላጫሉ? ተቃዋሚዎች ቪንቶ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ድልድይ ዘግተው ሳለ፤ በከተማዋ አቅራቢያ ሁለት ተቃዋሚዎች በመንግሥት ደጋፊዎች እንደተጎዱ ወሬ ተናፍሶ ነበር። ይህን ተከትሎም ተቃዋሚዎቹ ከንቲባዋን ተጠያቂ ያደርጉ ጀመር። ከንቲባዋን፤ ፕሬዘዳንት ኤቮ ሞራሌስን ደግፈዋል ብለው የኮነኑት ተቃዋሚዎች፤ "ገዳዮች፣ ነፍስ አጥፊዎች" እያሉ ይጮሁ ነበር። በዚህ መሀል ጭንብል ያጠለቁ ወንዶች ከንቲባዋን በባዶ እግር ወደ ድልድዩ ወስደዋል። ከንቲባዋን አንበርክከው፣ ቀይ ቀለም ቀብተው፣ ጸጉሯቸው ከቆረጡ በኋላ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ እንዲፈርሙም አስገድደዋቸዋል። ከሰዓታት በኋላ ለፖሊስ ተላልፈው የተሰጡት ከንቲባዋ፤ በፖሊሶች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። • ፈቲያ መሐመድ፡ ከዐረብ ሃገር ኑሮ ወደ ሚሊየነርነት • ቻይና ጌም በሚያዘወትሩ ታዳጊዎች ላይ ሰዓት እላፊ ጣለች ምርጫ በተካሄደበት ዕለት፤ የድምጽ ቆጠራው ለ24 ሰዓት መቋረጡን ተከትሎ፤ ቦሊቪያ ውጥረት ውስጥ ናት። የተቃዋሚው ካርሎስ ሜሳ ደጋፊዎች፤ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2006 ጀምሮ አገሪቱን የመሩት ፕሬዘዳንት ኤቮ ሞራሌስ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ለማስቻል ምርጫው ይጭበረበራል ብለው ይሰጋሉ። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት በምርጫው የመጀመሪያው ዙር ከተቃዋሚው አስር በመቶ የሚበልጥ ድምጽ እንዳገኙ ተነግሯል። ሆኖም 'ኦርጋናይዜሽን ኦፍ አሜሪካን ስቴትስ' የተባለው የታዛቢ ቡድን ውጤቱን እየመረመረ ነው። ተቃዋሚው ካርሎስ ሜሳ፤ ምርመራው ፖርቲያቸውን ያገለለ መሆኑን በመግለጽ ተቃውሞ አሰምተዋል። ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው ተቃዋሚያቸውን መፈንቅለ መንግሥት ሞክረዋል ብለው ይከሳሉ። የሁለቱም ወገኖች ደጋፊዎች በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ እየገቡም ይገኛሉ።
news-50093607
https://www.bbc.com/amharic/news-50093607
"ውስኪ ጠጪ ኢህአዴጎች እባካችሁ ውሃ የናፈቀው ሕዝብ እንዳለ አትርሱ" ጠ/ሚ ዐብይ
ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ በነበረው 'መደመር' የተሰኘው መጽሐፋቸው ምርቃ ሥነ ሥርዓት ማብቂያ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ለተቺዎቻቸው ጠንከር ባሉ ቃላት ምላሽ ሰጥተዋል።
"የፓርቲ ውህደት ጉዳይ አላለቀም" በማለት "የመደመር ፍልስፍናን የምናምን ሰዎች በውይይት ስለምናምን ምንም እንኳን ሰነዱ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ሙሉ ተጠንቶ ያለቀ ቢሆንም ላለመበተን ስንለማመን፣ ስንወያይ ከርመናል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "አሁንም ውይይቱ አልተቋጨም" በማለት አንዳንዶች "ይህ የፓርቲ ውህደት መጨፍለቅ ነው፤ ኢትዮጵያን ከፌደራል ሥርዓት ወደ አሃዳዊ ሥርዓት የሚወስድ ነው በማለት የሚሰጡት መግለጫ በእኛ ውስጥ ታስቦና ታልሞ የማያውቀውን መርዶ አረዱን" ብለዋል። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "መደመር" መጽሐፍ ተመረቀ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ውህደትን በተመለከተ ሲናገሩ "እኛ ኢህአዴጎች ለ30 ዓመታት አንድ መሆን ተስኖን እንዴት ነው ኢትዮጵያን አንድ ማድረግ የምንችለው?" ሲሉ በድርጅታቸው ውህደት ላይ ትችትን የሚሰነዝሩ ወገኖችን ጠይቀዋል። "ኢህአዴግ ባለፉት ዓመታት ሕገ መንግሥቱን በብዙ መንገድ ሲጥሰው ቆይቷል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ከዚያ ውስጥ አንዱ ሕገ መንግሥቱ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ መፍጠፈር ቢልም እንኳን፤ ፓርቲው ኢትዮጵያን አንድ ሊያደርግ ቀርቶ ራሱ አንድ መሆን ተስኖት ቆይቷል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መደመር ፍልስፍና ከሆነና ፓርቲውን ወደ ውህደት ካመራ ወደ እልቂት እናመራለን የሚለውን ሀሳብም በማንሳት "እልቂትን ምን አመጣው?" በማለት ጥያቄ ሰንዝረዋል። "አንድ ፓርቲ መሆንና መደመር የማያዋጣ ከሆነ ጀግና ሰው ውስኪውን አስቀምጦ 'መባዛት' የሚል አማራጭ ሃሳብ ይዞ ይመጣል" በማለት "ያኔ መደመርና መባዛት የሚለውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ለጎን በማስቀመጥ 'መደመር አያስፈልገንም' ይላል እንጂ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ምን ያገዳድለናል?" ሲሉም ተናግረዋል። • የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ከየት ወደ የት? እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚቀጥለው አማራጭ መገዳደል ነው የሚለው አሮጌ አስተሳሰብ ነው በማለት ካጣጣሉ በኋላ፤ " እኛ ውስኪ ጠጪ ኢህአዴጎች፤ እባካችሁ ውሃ የናፈቀው ሕዝብ እንዳለ አትርሱ ይላል መደመር" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። "መደመር ሌብነትን ቀይ መስመር ነው ያለበት ምክንያት" በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከሀገር ውጪም ቤት ደርድሮ ለህዝብ አስባለሁ ማለት ስላቅ ነው ብለዋል። አስከትለውም ሆቴል ተቀምጦ ዳቦ የራበውን ሕዝብ ለአንተ ቆሜልሃለሁ ማለት ተረት ተረት ነው ካሉ በኋላ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣቶች "የምንቀልድባችሁን ቀላጅ ፖለቲከኞች ወደጎን አራግፋችሁ አገራችሁን ጠብቁ" ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተጨማሪ "በተሰጠው እድል መጠቀም ሳይችል፤ እድል ሲነጠቅ በትውልድ እድል መቀለድ አይቻልም" ሲሉም በጠንካራ ድምጸት ተናግረዋል። ኢህአዴግ እንዴት ይዋሃዳል? ምን ስምና ግብር እኖረዋል የሚለውን እኔ አልወስንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "እኔ ዲሞክራት መሪ ስለሆንኩ ለውይይት ሃሳቤን አቀርባለሁ" ብለዋል። • ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ብቻ ነው መማር የሚችሉት- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሻለ እና የኢህአዴግ ብዙኀን አባል ድርጅቶች ሃሳብ የሆነውን ግን በቅርቡ ለሕዝባችን እንገልፃለን። 'መደመር' እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ተስፋ የሚያደርግባት ሀገር ትኑር ይላል በማለትም እያንዳንዱ ዜጋ ሀገሬን ልመራ እችላለሁ ብሎ የሚዘጋጅባት ለሁሉም እኩል የሆነች ኢትዮጵያን መፍጠር ያስባል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተም ሲናገሩ "ምርጫው የምናላግጥበት ሳይሆን ሀሳብ ይዘን ቀርበን፤ በሃሳብ ተወያይተን አብዛኛው ወጣት የሚያድግበት አማራጭ ተሰንዶ የምንወዳደርበት ብቻ ይሆናል" ብለዋል። "ኢትዮጵያዊያን በፍፁም መገዳደል የለብንም ሀሳብ ብቻ ነው ማፍለቅ ያለብን በሀሳብ ብቻ ነው መሟገት ያለብን" ሲሉም ተናግረዋል። 'መደመር' የተሻለ ሀሳብ ለመምረጥና ለመቀበል የኢትዮጵያዊያን ጭንቅላት ያንሳል ብሎ በፍፁም አይምንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ይህችን ታላቅ ሀገር መልሰን ታላቅ ብቻ ሳይሆን፤ የበለጸገች እናድርጋት ብሎ ያምናል ደግሞም ያደርጋል።" ኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋ እንዳላት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብዙዎች የብልፅግና ጉዞው የሚደናቀፍና የሚቆም ይመስላቸዋል በማለት "ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች... ካለችበት ሁኔታ ከፍ ትላለች ኢትዮጵያ እንዳትበለጽግ የሚፈልጉ ይጠፋሉ አንጂ የኢትዮጵያ ብልፅግና አይጠፋም" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርቡ ያገኙትን የኖቤል ሽልማት አስመልክቶ ሲናገሩም "እኔ ከበሻሻ የወጣሁ፣ ጥሩ የምስክር ወረቀት እንኳ ያላየሁ ነኝ፤ ይህ የእናንተ ውጤት ነው" በማለት ልትጠብቁት ይገባል ካሉ በኋላ "አሁን በሌሎች ዘርፎችስ እንዴት ነው ኖቤሎችን የምናመጣው የሚለውን ማሰብ አለብን" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
news-47156018
https://www.bbc.com/amharic/news-47156018
ከ300 በላይ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፤ ሚዛን ካምፓስ ተማሪዎች መታመማቸው ተሰማ
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ሚዛን ካምፓስ 330 ተማሪዎች ታመው ህክምና ማግኘታቸው ተሰማ።
ህመሙ በዩኒቨርስቲው መከሰቱን የሰሙት ማክሰኞ ዕለት ጥር 28/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ጀምሮ እንደሆነ የተናገሩት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ ወርቁ መጀመሪያ ላይ 15 ተማሪዎች ወደ ሆስፒታላቸው መምጣታቸውን ገልፀዋል። • የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ስጋት ነግሶበታል ዶክተሩ እንደተናገሩት በዩኒቨርስቲው ክሊኒክ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ተማሪዎቹ የህመም ምልክት ማሳየት የጀመሩት ባለፈው ሳምንት አርብ ጥር 24 /2011 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ነው። "እንዲህ አይነት ወረርሽኝ ሲከሰት ኮሌራ ተከስቶ ይሆን የሚለው አስግቶን የነበረን ቢሆንም ምርመራው ተደርጎ አለመሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል።" በምርመራው የተገኘው ኢኮላይ የተሰኘ ባክቴሪያ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል። ዶ/ሩ እንደተናገሩት የታመሙ ተማሪዎቹ ቁጥር ከፍተኛ ሲሆን በግቢው ክሊኒክ ውስጥ ጊዚያዊ የህክምና መስጫ አቋቁመው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ከተማሪዎቹ ከተወሰደው ናሙና የተገኘው ጥገኛ ተዋህስ ከሰው ልጅ ጋር ተስማምቶ የሚኖር ባክቴሪያ ቢሆንም በተለያየ ምክንያት ግን ጠቃሚ የነበረው ጎጂ ሊሆን ይችላል ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ይሁን እንጂ በሽታው በአንድ ጊዜ ተማሪዎቹ ለተመሳሳይ ነገር ተጋልጠው የመጣ ሊሆን እንደሚችልም ይጠረጥራሉ። ህመሙ በውሃ ወይም በምግብ አማካይነት ሊከሰት ስለሚችል መንስኤውን ለማወቅ ከፌደራልም ሆነ ከክልል የሚመጡ ባለሙያዎች ምርመራ እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ነገሮች ማመቻቸታቸውን አስረድተዋል። • በአሜሪካ ሀሰተኛ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች መታሰር በሕንድ ቁጣን ቀሰቀሰ በአሁኑ ሰዓት በጊዜያዊ ማቆያውም ሆነ በሆስፒታሉ ተኝተው እየታከሙ ያሉት ተማሪዎች ቁጥር ከ20 እንደማይበልጥ የሚናገሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ በሽታው በአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ በቴፒ ካምፓስ ስለመለከሰቱ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ቴሊል የጤና ችግሩ በምን ምክንያት እንደተከሰተ እስካሁን እንዳልተረጋገጠ የተናገሩ ሲሆን ማክሰኞ ዕለት ግን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ተማሪዎች የጤና መታወኩ እንዳጋጠማቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ሕክምና ያገኙት ተማሪዎች ቁጥር 330 ሲሆኑ አብዛኞቹ በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ክሊኒክ የታከሙ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ማስተማሪያ ሆስፒታል ሕክምና አግኝተዋል። አብዛኞቹም ከህመማቸው በማገገማቸው በህክምና ላይ የነበሩት ተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀነሰ አስረድተዋል። ዩኒቨርሲቲው አንገብጋቢ የውሃ ችግር ያለበት መሆኑንና ግቢ ውስጥ የሚጠቀሙት የጉድጓድ ውሃ በቂ ባለመሆኑም ከከተማ እያስመጡ እንደሚጠቀሙ የሚናገሩት ፕሬዚዳንቱ የጤና መታወኩ ከመከሰቱ አስቀድሞ ለተከታታይ 3 ቀናት በግቢው ውስጥ ውሃ ጠፍቶ እንደነበር አስታውሰዋል።
47770243
https://www.bbc.com/amharic/47770243
በወሲብ ፊልሞች ሱሰኛ የሆኑ ወጣት ሴቶች
ኔላም ቴለር የወሲብ ፊልሞችን ማየት የጀመረችው በ12 ዓመቷ ነበር። ገና አንድ ፍሬ ልጅ በምትባልበት ጊዜ። በመኝታ ክፍሏ ተደብቃ አጠር ያለ የአስር ደቂቃ የወሲብ ፊልም ማየት የጀመረችው በለጋ እድሜዋ ነው።
ኋላ ላይ እስከ አንድ ሰዓት ርዝማኔ ያላቸው ምስሎችን ማየት ጀመረች። በጊዜው ከቤተሰቦቿ ተደብቃ ታይ እንደነበር የምትናገረው ኔላም ለመጀመሪያ ጊዜ የወሲብ ፊልም ስታይ "የፍቅር ፊልሞች ወሲብን የተቀደሰና በፍቅር የተሞላ አድርገው ነበር አዕምሮዬ ላይ የሳሉት፤ ልክ በወንዶች ሃያልነት የተሞላና አካላዊ ተራክቦው የጎላበትን ምስል ማየት በጣም ነው ያስደነገጠኝ" ትላለች። የወሲብ ምስሎችን ማየት የጀመረችበትን ሰበብ ስታስታውስ ጉዳዩን ለማወቅ ከነበራት ፍላጎት ወይም ለአቅመ-ሔዋን እየደረሰች ስለነበረ የአፍላ ጉርምስና ግፊት ይሆናል በማለት ትናገራለች። ከጊዜ በኋላም የተለያዩ የወሲብ ምስሎችን ከማየቷ የተነሳ የራሷ ምርጫዎች እያዳበረች መጣች። • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት • የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ? "ወጣት ሴቶች በዕድሜ ገፋ ካሉ ወንዶች ጋር ሆነው ለሚሰሩ የወሲብ ምስሎች ልዩ ስሜት አደረብኝ። ሴቶቹ ታዛዥ ሆነው ወንዶቹ የበላይ የሆኑባቸውን ምስሎች በ13 ዓመቴ መፈለግ ጀመርኩ" የምትለው ኔላም ይህ ፍላጎቷ ብዙ የወሲብ ምስል ከማየቷ የተነሳ ይሁን ወይም ተፈጥሯዊ የሆነ ስሜት መለየት ይከብዳታል። የ25 ዓመቷ ሳራም ከኔላ የተለየ ልምድ የላትም። የወሲብ ምስሎችን ማየት የጀመረችው በ13 ዓመቷ ነበር፤ ለዚያውም በሳምንት ሁለት ጊዜ። "10 ወንዶችና 1 ሴት፤ በውስጡም ብዙ የወንዱን የበላይነት የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎች የተካተቱበትን ምስሎች ያየሁት የሩካቤስጋ መፈፀም ከመጀመሬ በፊት ነው " የምትለው ሳራ አሁን በ25 አመቷ ወደ ወሲብ ስሜት ለመግባት በጣም እንደሚከብዳት ትናገራለች። እስካሁን የወሲብ ምስል ሱስ በወንዶች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ በደንብ የተጠና ሲሆን፤ በሴቶች ላይ ያለው ጫና ግን በውል አልተጠናም። ብዙ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ሴቶች የወሲብ ምስልን እንደሱስ እንደማይጠቀሙትና በእነርሱ ላይ ብዙም ተፅዕኖ እንደሌለው ይናገራሉ። በዚህ የሕይወት መንገድ ላይ ያለፉ ሴቶች ግን ተመሳሳይ መልስ አይሰጡም። ዶ/ር ለይላ ፈሮድሻ የፅንስና የማህፀን አማካሪ ስትሆን በ20 ዓመት የስራ ልምዷ "አንድም የማያቸው የወሲብ ምስሎች ችግር እየፈጠሩብኝ ነው" ብላ የመጣች ሴት አጋጥማት እንደማታውቅ ትናገራለች። በጉዳዩም በደንብ ጥናት እንዳልተደረገበት የምትናገረው ለይላ "ሴቶች አካላዊና ስለ ልቦናዊ ጥቃት እየደረሰባቸው ነገርግን የሐኪም እርዳታ እየጠየቁ ስላልሆነ ነው? ወይስ ስለደረሰባቸው ችግር ለመናገር አፍረው? ወይስ ምንም ችግር እየፈጠረባቸው አይደለም?" በማለት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ታቀርባለች። ኔላም 16 ዓመቷ ሲሆን የወሲብ ምስሎችን ማየት አቆመች፤ ለዚህ ደግሞ ሰበብ የሆናትን ስትጠቅስ ምስሎቹ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ስለሚከቱ ነው ትላለች። ከእውነታው እያራቀች እንደነበር የምትገልፀው ኔላም "የወሲብ ምስል አይቼ የማገኘው የስሜት እርካታና ከጓደኛዬ ጋር ከወሲብ በኋላ ያለኝ ስሜት ያላቸው ልዩነት ያስፈራኝ ነበር።" አሜሪካዊቷ ፀሃፊ ኤሪካ ጋርዛ የወሲብ ምስል ማየት የጀመረችው በ12 ዓመቷ እንደሆነ ስትናገር "ትምህርት ቤት ያላግጡብኛል፤ ብዙ ጊዜም ብቸኛ ነበርኩ። ስለዚህም የወሲብ ምስሎችን ችግሬን የምረሳበትና እራሴን የማስደስትበት ነገር ነበር" ትላለች። ኤሪካ የወሲብ ምስሎችን ማየቷ በጣም ጫና እንዳደረሰባትና ለአንዳንድ የተለዩ የወሲብ መንገዶች የተለየ ስሜት እንዲኖራት እንዳደረገ ትናገራለች። በወሲብ ጊዜ ወንዱ ጉልበተኛና እኔን እንደፈለገ ማድረግ እንደሚችል ዓይነት ስሜቶችን እንድቀበል አድርጎኛል የምትለው ኤሪካ "ወንዶቹ ከሴቶቹ በዕድሜ ትልቅ የሆኑባቸውን ምስሎች ማየቴም ወንዶች በወሲብ ጊዜ ጉልበተኛ እንዲሆኑ እንድፈልግ አድርጎኛል" ስትል ታስረዳለች። ኔላምም በተመሳሳይ መልኩ የወሲብ ምስሎችን በለጋ ዕድሜዎ ማየቷ ወሲብን የምታይበትን መንገድ እንደቀየረው ትናገራለች። " 17 ወይም 19 እድሜዬ ላይ ስደርስ ታላቆቼ ከሆኑ ጋር ግንኙነት መፍጠር ጀመርኩ። ይህ ሁኔታዬ የተፈጥሮ ባህሪዬ ይሁን የወሲብ ምስል ማየቴ የፈጠረው ለማወቅ አልችልም" ትላለች። እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገ የ300 የወሲብ ምስሎች ግምገማ 88 በመቶ የሚሆኑት አንዱ ፆታ በወሲብ ላይ ያለውን የበላይነትን የሚያመላክቱ ሲሆን ብዙዎቹም የወንዶች የበላይነት ናቸው። በምስሎቹም ሴቶቹ በወንዶቹ ባህሪ በደስታ ወይም ከስሜት ነፃ በሆነ መልኩ እንደሚመልሱ ያሳያሉ።
news-48768339
https://www.bbc.com/amharic/news-48768339
የጦር እና ሲቪል መሪዎቹ ግድያ፡ ከቅዳሜ እሰከ ዛሬ ምን ተከሰተ?
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሥልጣን መያዝ በኋላ በርካታ ሰበር ዜናዎችን ሰምተናል፤ ገሚሱ አስደሳች ገሚሱ ደግሞ አሳዛኝ። የሰሞኑ ግድያ እና መዘዙን የመሠለ ግን ያለ አይመስልም።
አሁንም በርካቶች ከብረት የከበደ ጥያቄ ውስጣቸው እንዳዘለ አሉ። ምንድነው እየተከሰተ ያለው? እኛ ምላሽ ባይኖረንም ክስተቶቹን በጊዜ ከፋፍለን ለማየት ሞክረናል። • ስለ'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች ቅዳሜ ቅዳሜ ሰኔ 15/2011፤ ከሰዓት 10፡00 ላይ ሰባቱ የአማራ ክልል ባለሥልጣናት ለስብሰባ ተቀመጡ። እነሱም የአማራ ክልል አስተዳዳሪ አቶ አምባቸው መኮንን [ዶ/ር] እና ምክትላቸው አቶ ላቀ አያሌው፣ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ፣ የአስተዳዳሪው አማካሪ አቶ እዘዝ ዋሴ፣ አቶ ዮሃንስ ቧያለው፣ አቶ መላኩ አለበል እና አቶ አብራሃም አለኸኝ ናቸው። 11 ሰዓት ገደማ [ስብሰባው አንድ ሰዓት ያክል ከሄደ በኋላ] ወታደሮች የስብሰባ አዳራሹን ከበቡት። ከግድያው ከተረፉት አራት ባለሥልጣናት ሶስቱ ኋላ ላይ በቴሌቪዥን ቀርበው እንደተናገሩት ከሆነ፤ ወታደሮቹ የስብሰባ አዳራሹን በር ጥሰው ለመግባት ሙከራ ማድረግ ያዙ። ነገር ግን አቶ እዘዝ ዋሴ በሩን እንዳይከፈት አድርገው በመያዛቸው የተቀሩቱ ባለሥልጣናት ሌላ መውጫ ፈልገው ሲወጡ ታጣቂዎቹ አገኟቸው፤ ገደሏቸውም። ምሽት 1 ሰዓት ከሩብ ገደማ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ ቀርበው 'በአማራ ክልል መንግሥት ላይ መፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ተድርጓል' ሲሉ ዜናውን ሰበሩ። ቅዳሜ ምሽት በግምት 3፡00 ገደማ የኢትዮጵያ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን በገዛ ጠባቂያቸው መኖሪያ ቤታቸው ሳሉ በጥይት መመታታቸው ተነገረ። ጄነራሉ በገዛ ጠባቂያቸው በጥይት ሲመቱ አብረዋቸው የነበሩት ጄነራል ገዛዒ አበራም ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነገረ። ዕኩለ ለሊት ገደማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ ቀርበው ቀኑን ሲነገር የቆየው የባህር ዳሩ ግርግርና የአዲስ አበባው ክስተት እውነት መሆኑን ተናግረው የቆሰሉ እና የሞቱ ሊኖሩ እንደሚችሉ አሳወቁ፤ ስም ግን አልጠቀሱም። የባህር ዳሩና የአዲስ አበባው ጥቃት ግንኙነት እንዳላቸውም ጠቆሙ። ሰንበት እሁድ ጠዋት 2፡45 አካባቢ ከሁሉ በፊት ድምፅ ወያኔ በቴሌቪዥን ጣቢያው ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ወዳጃቸው ጄነራል ገዛዒ አበራ መገደላቸውን ሰበረ። ለጥቆ ደግሞ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው የአማራ ክልል አስተዳዳሪ አቶ አምባቸው መኮንን እና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ በደረሰባቸው ጥቃት መሞታቸውን በሰበር ዜና አሰማ። ይህ የሆነው ታድያ 3፡10 ላይ ነው። ረፋዱ ላይ መግለጫ የሰጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት የተከሰተውና የተዘገበው ሁሉ 'እውነት ነው' ካለ በኋላ፤ የባህርዳሩ ጥቃት መሪ ብራጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ናቸው፤ የአዲስ አበባው ጥቃት ደግሞ በጄነራል ሰዓረ የግል ጠባቂ መፈፀሙን ተናገሩ። መግለጫው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ይያዙ አይያዙ ባይጠቅስም የጄነራሉ የግል ጠባቂ ግን ቢቆስልም በቁጥጥር ሥር እንዳለ ነበር የሚያትተው። ሰኞ ሰኞ ከተሰሙ ዜናዎች ቀዳሚው የነበረው በቅዳሜ ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩት የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደ ማለፍ ነበር። ይህ ዜና የተሰማው ረፋድ 4፡00 ገደማ ነበር። እኩለ ቀን ላይ ደግሞ ቅዳሜ በተፈፀመው የባህር ዳሩ ግድያ 'ተጠርጣሪ' ናቸው የተባሉት ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ በፀጥታ ኃይሎች ተመትተው መገደላቸውን የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅሰው ሃገር ቤት ያሉ መገናኝ ብዙሃን ዘገቡ። • ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ ብርጋዴሩ የተገደሉት ከባህርዳር ወደ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ላይ ከምትገኘው ዘንዘልማ የተሰኘች ሥፍራ መሆኑም ተነገረ። ከሰዓቱን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ብቅ ያሉት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ጄነራሎቹን ገድሏል የተባለው ጠባቂ ራሱን ማጥፋቱን ተናገሩ። ሰኞ ምሽቱን ደግሞ ፌደራል ፖሊስ በብሔራዊው ቴሌቪዥን (ኢቢሲ) ቀደም ሲል ራሱ የሰጠውን መግለጫ አስተባብሎ ጠባቂው በሕይወት እንደሚገኝ አስታውቀ። • ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ ማክሰኞ ማክሰኞ የነበረው ዓብይ ጉዳይ የጄነራሎቹ አስከሬን ሽኝት ነበር። ሚሊኒየም አዳራሽ በነበረው የአስከሬን አሸኛኘት ሥነ-ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድንና ፕሬዝደንት ሳህለ-ወርቅ ዘውዴ እና ሌሎች በርካት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል። 'የመፈንቅለ መንግሥቱ' ሴራ ጠንሳሽ ናቸው የተባሉት የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ አስክሬንም ወደትውልድ ሥፍራቸው ላሊበላ የተላከውም ትናንት ማክሰኞ ከሰዓት ነበር። የአከባቢው ባለስልጣናት የብ/ጄነራል አሳምነው አስክሬን ወደ ትውልድ ቀያቸው የተላከው ከቤተሰቦቻቸው በቀረበው ጥያቄ መሰረት መሆኑ ተገልጿል። • የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው አስክሬን ላሊበላ ገባ በቅዳሜው ጥቃት ሕይወታቸው ያለፈው የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና በአዲስ አበባ የተገደሉት የጦር ጄነራሎች እንዲሁም የሴራው ጠንሳሽ ናቸው የተባሉት የብ/ጄነራል አሳምነው ጽጌ የቀብር ስነ-ሥርዓት በባህር ዳር፣ መቀለ እና ላሊበላ ዛሬ ተፈጽሟል። • የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ
news-52734563
https://www.bbc.com/amharic/news-52734563
ሁለት ጊዜ በጥይት ተመታ በህይወት የተረፈችው አራስ
ከአንድ ሳምንት በፊት ታጣቂዎች አፍጋኒስታን ካቡል በሚገኘ አንድ ሆስፒታል ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ይታወሳል።
በወላዶች ክፍል ላይ በተሰነዘረው በዚህ ጥቃት እናቶች፣ ጨቅላ ህጻናት እና ነርሶችን ጨምሮ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 24 የደረሰ ሲሆን በርካቶች መቁሰላቸውን የአገሪቱ ጤና ሚንስትር ተናግረዋው ነበር። ከዚህ ጥቃት ቀጥሎ በነበረው ቀንም፤ አንድ የቀብር ሥነ ሥርዓትን ታድመው በነበሩ ሰዎች ላይ አንድ አጥፍቶ ጠፊ እራሱን በቦምብ አጋይቶ ለሌሎች 34 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። በፖሊስ አዛዡ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ለተፈጸመው ጥቃት አይኤስ ኃላፊነቱን እውስዳለሁ ብሏል። እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ አካል ባልተገኘለት የሆስፒታሉ ጥቃት ከሞቱት በርካታ ሰዎች ባሻገር በርካቶች ሲቆስሉ አንዲት አራስ በሁለት ጥይት ተመትታ ተርፋለች። እናቶችን ኢላማ ባደረገው በዚህ የካቡል ሆስፒታል ጥቃት 16 ወላዶች ተገድለዋል። ከሟቾቹ መካከል የጨቅላዋ አሚና እናት ትገኝበታለች። ጨቅላዋ አሚና ግን ሁለት ጊዜ በጥይት ብትመታም በህይወት መትረፍ ችላለች። የአሚና አባት የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውሱ፤ ታጣቂዎች ሆስፒታሉ ላይ ጥቃት መሰንዘር ሲጀምሩ አሚና ገና መወለዷ ነበር። ታጣቂዎቹ ወደ ሆስፒታሉ ዘልቀው በመግባት እናቶችን ዒላማ አድርገው ሲገድሉ፤ አሚናም ሁለት ጊዜ እግሯ ላይ በጥይት ተመታለች። ዶክተሮች የአሚናን በህይወት መትረፍ "ታዓምራዊ ነገር ነው'' ሲሉ ይገልጹታል። "የተኩስ ድምጽ እየተሰማ እያለ ባለቤቴ 'አጥፍቶ ጠፊ ነው?' ስትል ጠየቀችኝ። እንዳትጨነቅ በማሰብ 'አጥፍቶ ጠፊ አይደለም' አልኳትንና እንድትደበቅ ነገሪያት አንዱን ታጣቂ ተከትዬ ወጣሁ። "ስመለስ አሚናን እንደታቀፈች ተገድላ አገኘኋት" በማለት የጨቅላዋ አባት ራፊኡላ ይናገራል። ባለቤቱ ልቧ ላይ እና አግሯን በጥይት እንደተመታች የሚናገረው ራፊኡላ፤ አዲስ የተወለደችውን ሴት ልጁን ለማዳን በፍጥነት ህክምና እንድታገኝ ለማድረግ መጣሩን ይናገራል። "ባለቤቴን እየቀበርኩ እያለሁ ዶክተሮች ደውለው 'የአሚና እግር መቆረጥ አለበት' አሉኝ እኔም 'እባካችሁ እግሯን አትቁረጡ። እናት የሌላት ጨቅላ ናት። የወደፊት ህይቷን አታክብዱባት' አልኳቸው" ይላል። የተቻላቸውን ለማድረግ ቃል የገቡለት ሃኪሞች ያካሄዱት የቀዶ ህክምና ተሳክቶ የአሚና እግር ሳይቆረጥ ቀርቷል። በተደረገላት ሁለት ተከታታይ የቀዶ ህክምና አሁን ላይ ሃኪሞች አሚና ከፍ ስትል መራመድ እንደምትችል ተስፋ አድርገዋል።
news-54251609
https://www.bbc.com/amharic/news-54251609
ደጋፊዎችን የወሩ መጨረሻ ላይ ወደ ስታዲየም የመመለሱ እቅድ ውድቅ ሆነ
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች ላይ ደጋፊዎችን ከመስከረም 21 ጀምሮ ወደ ስታዲየም የማስገባቱ እቅድ ወድቅ መደረጉ ተገለጸ።
ይህ የሆነበት ምክንያት በዩናይድ ኪንግደም እና በተቀሩበት የአውሮፓ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኔ አባል የሆኑት ማይክል ጎብ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው እቅድ እስከ 1ሺህ የሚደርሱ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ገብተው ክለባቸውን እንዲደግፉ መፍቀድ ነበር። በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሼፊልድ ዩናይትድ መስከረም 23 በሚያደርጉት ጨዋታ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየሞች ይገባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ካለፈው መጋቢት ወር ወዲህ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ውድድሮች በዝግ ስታዲየም ሲካሄዱ ቆይተዋል። በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ስፓርታዊ ውድድሮች በዝግ ስታዲየም እንዲደረጉ መወሰኑ በክለቦች ላይ ከፍተኛ የፋይንስ ቀውስ አስክትሏል። የባህል፣ ሚዲያ እና ስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ጁሊያን ናይት “ታዳሚዎች ወደ ስታዲየሞች የሚመለሱበትን ብልህ የሆኑ አሰራሮች ካልዘረጋን የስፖርት እና ባህላዊ መሠረተ ልማቶቻችን ተንኮታኩተው ይቀራሉ” ብለዋል። ከ100 በላይ የስፖርታዊ ውድድሮች አመራሮች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ካጋጠማቸው ኪሳራ ለማገገም ለጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል። ስፖርት ኢንግላንድ የተሰኘው የመንግሥት አካል 200 ሚሊዮን ፓውንድ ለአስቸኳይ ወጪ መሸፈኛ በሚል ለስፖርት ክለቦች ድጋፍ አቅርቧል። ይሁን እንጂ ይህ ገንዘብ ክለቦች ያጋጠማቸውን ኪሳራ ለመሸፈን በቂ አይደለም ተብሏል።
news-52278684
https://www.bbc.com/amharic/news-52278684
ኮሮናቫይረስ፡ ትራምፕ የእንቅስቃሴ ገደቡን የማስነሳት ሙሉ ስልጣን አለኝ አሉ
ፕሬዝደንት ትራምፕ ከአሜሪካ ግዛቶች አስተዳዳሪዎች እና የሕግ ባለሙያዎች አረዳድ በተጻረረ መልኩ በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ተጥሎ የሚገኘው የእንቅስቃሴ ገደብ የማንሳት ሙሉ ስልጣን አለኝ አሉ።
"ውሳኔውን የሚሰጠው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ነው" ሲሉ ተናግረዋል፤ ፕሬዝደንት ትራምፕ ትናንት በሰጡት ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ። የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ግን በግዛቶች ውስጥ ሕግ እና ሥርዓት መከበሩን የሚያረጋግጡት ግዛቶቹ እራሳቸው ናቸው ይላል። በምሥራቅ እና በምዕራብ አሜሪካ የሚገኙ 10 ግዛቶች ጥብቅ የሆነውን ከቤት ያለመውጣት ትዕዛዝን ለማንሳት እያሰቡ ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊዮን ለመድፈን ተቃርቧል። ከእነዚህም መካከል 1/3ኛው የሚገኙት በአሜሪካ ነው። ትራምፕ ያሉት ምንድነው? ሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንት ትራምፕ በኮሮናቫይረስ ላይ ትናንት በተሰጠው ዕለታዊ መግለጫ ላይ፤ አስተዳደራቸው የአሜሪካንን ምጣኔ ሃብት መልሶ ለመክፈት የሚያስችል ዕቅድ እያጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል። ትራምፕ ጨምረውም የፈረንጆቹ ሜይ 1 (ሚያዚያ 23) የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ታልመው ተፈጻሚ ሲደረጉ የነበሩት ጥብቅ መመሪያዎችን ማላላት የሚጀምሩበት ዕለት እንደሚሆን ተናግረዋል። አሜሪካውያን ወደ ምግብ ቤቶች አትሂዱ፣ እጅግ አስፈላጊ ካልሆኑ በስተቀር ከጉዞዎች እራሳችሁን ቆጥቡ እንዲሁም ከ10 ሰዎች በላይ በአንድ ቦታ አትሰባሰቡ የሚሉት ጥብቅ መመሪያዎች የሚያበቁት ሚያዚያ 22 ነው። ግዛቶች ያስተላለፏቸው መመሪያዎችን ትራምፕ ማንሳት ስለመቻላቸው ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፤ "አንድ ሰው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሲሆን' ስልጣኑ የተሟላ ነው" ብለዋል። ትራምፕ ጨምረውም "ሙሉ ነው [ስልጣናቸው]። ገዢዎቹም ያውቁታል" ብለዋል። ይሁን አንጂ የሕግ ባለሙያዎች ፕሬዝደንቱ የሕዝብን ጤና ለመጠበቅ ሲባል በግዛቶች እና በታችኛው የአስተዳደር ክፍል የተላለፉ መመሪያዎችን ማንሳት አይችሉም ይላሉ። ትራምፕ አሜሪካውያን ማኅበራዊ ርቀታቸውን መጠበቃቸው የቫይረሱን ስርጭት እንዲቀንስ አድርጓል ብለዋል። በዕለታዊ መግለጫው ላይ ዋይት ሐውስ ፕሬዝደንት ትራምፕ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት እየወሰዱት ስላለው አመርቂ እርምጃዎች እና የግዛቶች አስተዳዳሪዎች ለፕሬዝደንቱ ያላቸው አድናቆት የሚያሳይ ቪዲዮ አጫውቷል። ይሁን እንጂ ዕለታዊ መግለጫውን በቀጥታ ሲያስተላልፉ የነበሩ በርካታ መገናኛ ብዙሃን ዋይት ሐውስ ቪዲዮን ማሳየት ሲጀምር የቀጥታ ስርጭታቸውን አቋርጠዋል።
news-46518069
https://www.bbc.com/amharic/news-46518069
ደቡብ አፍሪካ ሚኒስትሯ ሊንድዌ ሲሱሉ ሴተኛ አዳሪ ተብላ በሩዋንዳ ጋዜጣ መሰደቧን ተቃወመች
በሩዋንዳ የሚገኝ አንድ የመንግሥት ደጋፊ ጋዜጣ አንዲት ሴት የደቡብ አፍሪካ ሚኒስትርን "ሴተኛ አዳሪ" ብሎ በመጥራቱ በምላሹ ደቡብ አፍሪካ በፕሪቶሪያ የሚገኘውን የሩዋንዳ ልዩ መልዕከተኛ አስጠርታለች።
ይህንን ዘለፋ ያስተናገዱት የውጭ ኃገራት ሚኒስትር የሆኑት ሊንድዌ ሲሱሉ ሲሆኑ፤ ከፍተኛ ኃላፊነት ያላቸው የሩዋንዳ ባለስልጣንም በትዊተር ገፃቸው ተችተዋቸዋል። የሚኒስትሯ ቃል አቀባይ ዘለፋው ተቀባይነት እንደሌለውና ሊቆም እንደሚገባ ተናግረዋል። •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ •ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች •የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? ሊንድዌ ሲሱሉ በቅርቡ በግዞት ላይ ካሉት ሩዋንዳዊ ፖለቲከኛ ጋር መገናኘታቸው በሁለቱ ኃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ጥላሸት እንደቀባው ተዘግቧል። በባለፈው ወር በነበረውም ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሩዋንዳን የቀድሞ የጦር ጄነራል ፋውስቲን ካዩምባ ንያምዋሳ በጆሐንስበርግ ማግኘታቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ የተቃዋሚ ፓርቲ የመሰረቱት ንያምዋሳ ከሩዋንዳ መንግሥት ጋር ድርድር ለመጀመር ማሰባቸው "እንዳስደነቃቸውም" ተናግረዋል። ፋውስቲን ካዩምባ ንያምዋሳ ከፕሬዚዳንት ፓውል ካጋሜ ጋር ከተጣሉ በኋላ ከአውሮፓውያኑ 2010 ዓ.ም ጀምሮ በግዞት መኖር መጀመራቸው ተዘግቧል። ከጋዜጣው ዘለፋ በተጨማሪ የሩዋንዳ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቨር ንዱንጊርሔ በትዊተር ገፃቸው ደቡብ አፍሪካን ተችተዋል። በፅሁፋቸውም እንዳተቱትም "ማንኛውም ደቡብ አፍሪካዊ ኃገርን ለመበጥበጥ ከሚሞክርና ከተከሰሰ ወንጀለኛ ጋር ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ ነገር ግን በሂደቱ ውስጥ ሩዋንዳን ማሳተፍ አይችሉም።" ብለዋል። የሩዋንዳ መንግሥት ደጋፊ ጋዜጣም ሚኒስትሯን የፋውስቲን ካዩምባ ንያምዋሳ "ሴተኛ አዳሪ" በሚል ርዕስ መሳደቡን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ምንጭ በጆሀንስበርግ ለቢቢሲ ዘጋቢው ሚልተን ንኮሲ ተናግረዋል። ምንም እንኳን ፅሁፉ ከጋዜጣው ቢወገድም አደጋው ማድረሱን ግን ጋዜጠኛው ጨምሮ ዘግቧል። የሚኒስትሯ ቃል አቀባይ ንድሁዎ ማባያ በበኩላቸው ፕሪቶሪያ ለሚገኘው የሩዋንዳ መንግሥት መልዕክተኛ የጋዜጣው ዘለፋ በምንም መንገድ ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋል። ከአራት አመታት በፊት ጆሐንስበርግ በሚገኘው ቤታቸው ላይ ጥቃት የደረሰባቸው ፋውስቲን ካዩምባ ንያምዋሳ ጋር በተያያዘ ሶስት ዲፕሎማቶችን ደቡብ አፍሪካ አባራ ነበር። በምላሹም ሩዋንዳ ስድስት የደቡብ አፍሪካ ዲፕሎማቶችን አባረረች። ፖለቲከኛው በዚሁ ግዞት ላይ ባሉበት ወቅት ብቻ ከሁለት የግድያ ሙከራዎች ተርፈዋል። በአንደኛው ጥቃትም አራት የታጠቁ ሰዎች ፖለቲከኛው ሆድ ላይ በጥይት በማቁሰል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። በሁለቱ ኃገራት መካከል ያለው ግንኙነት የሻከረው የቀድሞው የሩዋንዳ የደህንነት ኃላፊ ኮሎኔል ፓትሪክ ካሬጋያ ከአራት ዓመታት በፊት በሆቴል ውስጥ ተገድለው በመገኘታቸው ነው። ከተገደሉ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ፕሬዚዳንት ካጋሜ " ሩዋንዳን ከድቶ ተመጣጣኝ ቅጣት አለመቀበል አይቻልም። ሌሎችም በህይወት ያሉት የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የዘሩትን ይለቅማሉ" ብለዋል።
news-55693948
https://www.bbc.com/amharic/news-55693948
ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ 10 አዳዲስ የኮቪድ-19 ክትባት መስጫ ማዕከላት ሊከፈቱ ነው
እንግሊዝ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ አዳዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መስጫ ማዕከላትን ልትከፍት እንደሆነ አስታውቃለች።
ይህ የሆነው መንግሥት ከአንድ ወር በኋላ በዩናይትድ ኪንግደም 15 ሚሊዮን ሕዝብ ለመከተብ ያቀደውን ግብ ለማሳካት ነው። ብላክበርን ካቴድራል እና ቅዱስ ሄለንስ ራግቢ ግራውንድ (ሜዳ) አሁን አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን ሰባት ማዕከላት ይቀላቀላሉ። የእንግሊዝ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት [ኤንኤችኤስ] ማዕከላቱ በሳምንት በሺዎች የሚቆጠሩ ክትባቶችን እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በብሔራዊ የክትባት ዘመቻው የተሳተፉትን አመስግነዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት 3.3 ሚሊዮን ሰዎች ቁጥር በላይ ማለትም 3.5 ሚሊዮን ሰዎች ክትባቱን ወስደዋል። ሆኖም ከተመዘገበው ቁጥር በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እንደሚኖሩ ይታመናል። መንግሥት ቁጥራቸው 15 ሚሊዮን ለሚሆኑ፤ ከ70 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ፣ ለበሽታው ተጋላጭ ለሆኑ የሕክምና ባለሙያዎች እና የእንክብካቤ ማዕከላት ሰራተኞችን በሙሉ በየካቲት ወር አጋማሽ ክትባቱን ለመስጠት ቃል ገብቷል። በእንግሊዝ ታሪክ ሰፊው በሆነው በዚህ የክትባት መርሃ ግብር ሕዝቡ አረጋዊያንን በመርዳትና በቀጠሯቸው እንዲገኙ በማገዝ ድርሻውን እንዲወጣ መንግሥት አሳስቧል።
news-41614280
https://www.bbc.com/amharic/news-41614280
ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ይፈታል ተብሎ ቢጠበቅም አልተፈታም
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ የእስር ጊዜውን ቢያጠናቅቅም ባላወቅነው ምክንያት የዝዋይ ማረሚያ ቤት አስተዳደር አልፈታውም ብሏል ሲል የተመስገን ወንድም ለቢቢሲ ተናግሯል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የ3 ዓመት የፍርድ ጊዜውን ዓርብ (ጥቅምት 3) ቢያጠናቅቅም የዝዋይ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ግን ያለምንም ምክንያት ተመስገንን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ስላልሆነ ወደ መጣንበት አዲስ አባባ እየተመለስን ነው ሲል ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በስልክ ገልጾልናል። ''ትናንት ሃሙስ የእስረኞች አስተዳደር ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ግለሰብ ተመስገን የሚፈታበትን ቀን ጠይቄው መዝገብ አገላብጦ ዛሬ እንደሚፈታ አረጋግጦልኝ ነበር። የእስር ጊዜውም ስለሚጠናቀቅ እንደሚፈታም እርግጠኛ ነበርኩ'' ይላል ታሪኩ። ተመስገን፤ ታሪኩ እና ጓደኞቹን በማረሚያ ቤት ውስጥ ሊያናግራቸው ሲመጣ ባልተለመደ መልኩ በስምንት ወታደሮች ታጅቦ እንደነበር ወንድሙ ይናገራል። በነበራቸውም ቆይታ ''መፈታት ነበረብኝ ነገር ግን እንደማይፈቱኝ ነግረውኛል፤ ለምን እንደሆነ አላውቅም'' ሲል ተመስገን ነግሯቸዋል። የተመስገን እናት፣ የቤተሰብ አባላት እና ጓደኞቹ የእርሱን መፈታት ተስፋ አድርገው በጉጉት እየጠበቁ ነበር። ይፈታል በሚል ተስፋ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ውስጥ እና ከዚህ ቀደም የፃፋቸውን የተለያዩ ፅሑፎች ስብስብ ''ጊዜ ለኩሉ'' በሚል ርዕስ በመፅሃፍ ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል።
news-42278634
https://www.bbc.com/amharic/news-42278634
ጥያቄን ያዘለው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን
በአፋር ክልል መዲና ሰመራ "በሕገ-መንግስታችን የደመቀ ሕብረ ብሔራዊነታችን ለህዳሴያችን" በሚል ርዕስ ለአስራ ሁለተኛ ጊዜ በመከበር ላይ የሚገኘው 'የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች' ቀን በዓል ከወትሮውም በበለጠ ለበርካታ ጥያቄዎች መጫር ምክንያት ሆኗል።
ጥያቄዎቹ በክብረ በዓሉ ፋይዳ ላይ ሳይወሰኑ ዕለቱ ይዘክራቸዋል ተብለው እስከሚታመኑት ሕግ-መንግሥት እንዲሁም ብሔርን መሰረት ያደረገ ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይም የሚያጠነጥኑ እንደሆኑ ይስተዋላል። ባለፉት ወራት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች የተቀሰቀሱ ብሔር ተኮር ግጭቶች እና ማንነት ላይ ባነጣጠሩ ጥቃቶች ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ለህልፈት ተዳርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው እና ንብረቶቻቸው መውደሙ፤ የዘንድሮውን ክብረ በዓል በተለየ ሁኔታ ትርጉም አልባ ያደርገዋል ሲሉ የሚከራከሩ ወገኖች አሉ። "የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ" በኢንዲኮት ኮሌጅ የዓለም አቀፍ ሕግ እና የሰብዓዊ መብቶች መምህር የሆኑት ዶክተር ሰማኸኝ ጋሹ የአመለካከት፣ የፍላጎት እና የፖለቲካ አቋም ልዩነቶች በገነኑባቸው አገራት የብሔር ብሔረሰብ ቀንን የመሳሰሉ በዓላት የሰላም እና የእርቅ ዓላማን ለማራመድ ብሎም አገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ሊያገለግሉ እንደሚችሉ ያወሱና፤ በእኛ አገር እየሆነ ያለው ግን ከዚህ የተለየ ነው ሲሉ ይናገራሉ። "ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን እንዲሁ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እና የሥርዓቱን ተቀባይነት የማጠናከር ዓላማን የሰነቀ ነው" ሲሉ ዶክተር ሰማኸኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዓሉ የሚወክለው ሥርዓት መሠረታዊ ችግሮች የሚስተዋሉበት ከመሆኑም ባሻገር፤ የዲሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብት መርሆች ሊከበሩ ባለመቻላቸው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ምህዳር ከድጥ ወደማጥ በመቆርቆዝ እንደሚገኝ ዶክተር ሰማኸኝ ጨምረው ይገልፃሉ። የሰመራ ከተማ በዓሉን ለማክበር ከየሥፍራው የመጡ እንግዶቿን ስታስተናገድ በሥራ ተጠምዳ ሰነባብታለች። ለዚህም ዝግጅት በመቶ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ እንደዋለ ይገመታል። ከሁለት ዓመት በፊት በጋምቤላ ከተማ ላይ የተስተናገደው ክብረ በዓል ከ340 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት መዘገቡ ይታወሳል። በአንድ በኩል በአሁኑ ሰዓት ከመኖሪያ ቀያቸውን የተፈናቀሉ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለማቋቋም ከፍተኛ ገንዘብ ያስፈልጋል። ለጥቂት ቀናት የሚካሄዱ የአደባባይ ትርዒቶች እና ዓውደ ጥናቶች በተለያዩ ብሔሮች መካከል መከባበርን ለማምጣት፣ የፖለቲካ እኩል ተሳታፊነትን እንዲሁም የምጣኔ ኃብት እኩል ተጠቃሚነት ለማስገኘትም የሚያበረክቱት እዚህ ግባ የሚባል ፋይዳ እንደሌለ በማውሳት በበዓሉ ከመገኘት እንዲቆጠቡ በተለይ የኦሮሚያ መብት ተሟጋቾች ሲወተወቱ ቆይተዋል። "ብዝኃነት አደጋ ላይ ወድቋል" በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም መምህር የሆኑት አቶ ናሁሰናይ በላይ አገሪቷ ያለችበት ፖለቲካዊ ነባራዊ እውነታ ዕለቱ የሚወክለውን ሥርዓት ከመቼው ጊዜ በበለጠ ማክበር የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ መደረሱን የሚጠቁም ነው ይላሉ። "በዕለቱ የምናከብረው ሕገ-መንግሥት ላይ ያለ መርኅ ነው። ይህ መርኅ የፖለቲካ ከባቢው መጥፎ ሲሆን ወይንም አንዳች ዓይነት ኹከት በተፈጠረ ቁጥር የምናከብረው ወይም ደግሞ የምንተወው መሆን የለበትም" በማለት አቶ ናሁሰናይ ለቢቢሲ ገልፀዋል። "የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ስንል ብዝኃነትን መቀበል ማለት ነው። በብዝኃነት ውስጥ የሚፈጠር አንድነትን መዘከር ማለት ነው። ስለዚህ ከዚህ ሰዓት በላይ መቼ እናክብር? በአሁኑ ወቀቅት ተግዳሮቶችና መፈራቀቅ የበዙበት ጊዜ ነው። ብዝኃነት ፈተና ላይ የወደቀበት ሰዓት ነው" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። እንደዚያም ሆኖ ግን በየስፍራው የተነሱ የመብት ጥያቄዎች፣ ተቃውሞዎች፣ ግጭቶች እና ጥቃቶች በየዓመቱ ህዳር 29 ከሚዘከረው ሕገ-መንግሥትና ካለው የፌዴራሊዝም ሥርዓት ጋር አይገናኙም በማለት አቶ ናሁሰናይ ይከራከራሉ። "ዜጎች ያነሷቸው የተለያዩ የዲሞክራሲ እና የምጣኔ ኃብት ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ናቸው። መብት ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ የዲሞክራሲ ጥያቄ ነው። ፌዴራሊዝም የሰጠኝ መብት ስለበዛ ይቀነስልኝ ብሎ የመጣ አካል ግን የለም። በራሴ ሰዎች መተዳደር አስጠልቶኛልና በራሴ ቋንቋ መናገር አልፈልግም ያለ ሕዝብ መኖሩን አላውቅም። እነዚህን ጥያቄዎች ሲነሱ ነው ፌዴራሊዝሙ ጥያቄ ውስጥ ወደቀ የምንለው። ያሉትን ጥያቄዎች በሙሉ ወደ ሥርዓቱ መውሰድ ስህተት ነው" ይላሉ። "ሕገ መንግሥቱ አካታች አይደለም" መፍትሄ ካልተሰጠ ሊደርስ በሚችለው አደጋ መጠን ላይ መግባባት፤ እየመጣ ያለውን ማዕበል ለማስቀረት የመጀመሪያው እርምጃ ነው የሚሉት አቶ ናሁሰናይ የችግሮቹን መሠረታዊ መንስዔ የአገሪቱ የፖለቲካ አመራር አካላት ፌዴራሊዝምን እና ብዝኃነትን ለመቀበል አቅምና ትከሻ ካለመደንደን ጋር ያያይዙታል። ፖለቲካው ሕገ-መንግሥቱን እንዲመስል ማስቻል ዓይነተኛው መዋቅራዊ መፍትሄ እንደሆነ አቶ ናሁሰናይ ይገልፃሉ። "እገሌን በእገሌ የመተካት ጉዳይ አይደለም። የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚረጋገጥባቸው የምርጫ እና የውክልና ሥርዓቶች በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ይሁኑ። የዜጎች ኢትዮጵያዊነት ትርጉም የሚኖረው በሕገ መንግሥቱ መሠረት መብቶቻቸው ሲጠብቁላቸው ብቻ ነው።" እንግሊዝ አገር በሚገኘው በኪል ዩኒቨርስቲ ሕግን የሚያስተምሩት ዶክተር አወል አሎ ከአሃዳዊ ሥርዓት በበለጠ ፌዴራላዊ ሥርዓት በብሔርም ሆነ በስነ ምድራዊ አካባቢ ቢዋቀር በጥቅሉ ግጭት እንደማያጣው ይናገራሉ። "ማንነትን ማዕከል ያደረገ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሲዋቀር ደግሞ በተለይም ፖለቲካዊ በደል፣ ምጣኔ ሃብታዊ መገለል እና ባሕላዊ ጭቆና መገለጫዋ በሆነች አገር ውስጥ ሲሆን ግጭቶች የመከሰት ዕድላቸው ከፍ ይላል" በማለት ዶክተር አወል ለቢቢሲ ያስረዳሉ ። ዶክተር አወል እንደሚሉት ሆኖም አሁን ያለው በሕገ-መንግሥት ፀንቶ የተቀመጠ ብሔርን መሰረት ያደረገው ፌዴራላዊ ሥርዓት አገሪቷ ውስጥ ለሚታዩ ነውጦች መነሻ ሆኗል ለማለት የሚያበቃ ማስረጃ የለም። "ምክንያቱም ሕገ-መንግሥቱ በአግባቡ ሥራ ላይ አልዋለም" ይላሉ። እንደዚያም ቢሆን ግን ሕገ መንግሥታዊ የፌዴራል ሥርዓት ግጭቶችን ጨርሶ ለማስቀረቱ ምንም መተማመኛ እንደሌለ ዶክተር አወል ያምናሉ። የሕገ-መንግሥቱ በትክክል አለመተግበር ዋነኛው የጥያቄዎች ምንጭ መሆኑ ሲደመጥ የመጀመሪያው ባይሆንም ችግሩ እርሱ ብቻ ያለመሆኑን የሚከራከሩም ጥቂት አይደሉም። ዶክተር ሰማኸኝ ከእነዚህ ወገን ናቸው፤ እርሳቸው እንደሚሉት ሕገ-መንግሥቱ በራሱ መርኁ ከፋፋይና ልዩነትን አግናኝ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሕገ-መንግሥቱ የተረቀቀበት ሂደት ተቀባይነት አጠያያቂ ነው። በተለይም በሽግግሩ መንግሥት እና ሕገ-መንግሥትን በመፃፉ ሒደት ውስጥ የተፈለጉ ፓርቲዎች ብቻ ተነቅሰው መሳተፋቸው ሂደቱ አካታች እንዳልነበር የሚያሳይ እንደሆነ ዶክተር ሰማኸኝ ይናገራሉ። "በርካታ ኅብረ-ብሔራዊ ፓርቲዎች እና የአማራ ልኂቃን ሕገ-መንግሥቱን ከማርቀቅ ሂደቱ ተገልለዋል። ይህም በሁለቱ ወገኖች ዘንድ በሕገ-መንግሥቱ ላይም ሆነ ሕገ-መንግሥቱን በሚዘክሩ ክብረ በዓላት ላይ ጥርጣሬ እንዲኖር በር ከፋች ነው" የሚሉት ዶክተር ሰማኸኝ "ችግሮቹ የመዋቅርም የአፈፃፀምም ናቸው" ይላሉ።
news-50825247
https://www.bbc.com/amharic/news-50825247
ታላቁ የህዳሴ ግድብ፡ አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ጦርነት መፍትሄ አይሆንም አሉ
የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታ አል-ሲሲ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ላለው ግድብ አለመግባባት ጦርነት መፍትሄ አይሆንም አሉ።
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ አል-ሲሲ በግብጿ የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው ሻርመ ኤል ሼህ ከተማ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ በግድቡ ዙሪያ በቀጣይ ወር የአሜሪካ ተወካዮች በሚገኙበት በዋሽንግተኑ ስብሰባ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ነው ትኩረት መሰጠት ያለበት ብለዋል። "ያሉን ውስን ሃብቶች በጦርነት እና በግጭት መባከን የለባቸውም። ህዝቡን እና ሃገራችንን ለማልማት ልንጠቀምበት ይገባል" ጦርነት መልስ አይሆንም የሚለው የአል-ሲሲ ንግግር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ፓርላማ ላይ ለተደረገው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ንግግር ምላሽ የሰጡ ይመስላል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥቅምት 11፣ 2012 ዓ. ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ "የማንንም ፍላጎት ለመጉዳት የጀመርነው ፕሮጀክት አይደለም" ያሉ ሲሆን፤ "ቁጭ ብለን እናወራለን፤ ማንም ይህንን ግንባታ ማስቆም አይችልም። ይህ ሊሰመርበት ይገባል" ብለው ነበር። በወቅቱ ከግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚሰነዘሩ የጦርነት እንከፍታለን መልዕክቶችን አስመልክተው ሲናገሩ፤ "ማንንም አይጠቅምም [ጦርነት] ብለን እናምናለን . . . ጦርነትም ከሆነ ኢትዮጵያ ብዙ ሕዝብ አላት፤ በሚሊዮን ማሰለፍ እንችላለን" ማለታቸው ይታወሳል። ዛሬ በሻርም ኤል ሼክ ጋዜጠኞችን ያነጋገሩት አል-ሲሲ ዋናው ነገር በመጪው ወር በአሜሪካ ዋሽንግተን በሚደረገው ንግግር ዘላቂ መፍትሄ ላይ መድረስ ነው ብለዋል። "ስለ ራሳችን ኃያልነት ብዙ ማለት አንፈልግም። ግን ሚሊዮኖችን ትመለምላለህ ወይስ ግድብ ትገነባለህ?" ሲሉ ጠይቀዋል። "ሚሊዮኖችን በሚቀጥፍ ግጭትና ጦርነት ሃብታችን ሊፈስ አይገባውም። ይልቁንም ያን ገንዘብ ለህዝብና ለአገር ልማት እናውላለን" ሲሉ አል-ሲሲ ተደምጠዋል። ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታንና የውሃ አሞላል ሂደትን በተመለከተ ለዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ውይይቶች ውጤት አልባ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል። በዚህም የአሜሪካ እና የዓለም ባንክ ተወካዮች የተገኙባቸው የውይይት መድረኮች እየተካሄዱ ይገኛሉ።
news-45987994
https://www.bbc.com/amharic/news-45987994
ቻይናና ሩስያ የትራምፕን የግል ስልክ ጠልፈው ሲሰልሉ ነበር፡ ኒውዮርክ ታይምስ
ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የዶናልድ ትራምፕ የግል ስልክ ሳይጠለፍ አይቀርም የሚል ዘገባ ይዞ መውጣቱን ተከትሎ ጉዳዩ በስፋት መነጋገሪያ ሆኗል።
ዶናልድ ትራምፕ የግል ስልካቸው በቻይናና ራሺያ ተጠልፏል የሚለው ስጋት አይሏል ጋዜጣው እንደሚለው ከሆነ ቻይናና ሩስያ የዶናልድ ትራምፕን አስተሳሰብ ለመረዳት እንዲያስችላቸው የፕሬዚዳንቱን የግል ተንቀሳቃሽ ስልክ ሳይጠልፉት አልቀረም። ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ይህ ዘገባ ትንሽ ያበሳጫቸው ይመስላል። ትናንት በትዊተር ገጻቸው ላይ በለጠፉት የመልስ ምት "ተንቀሳቃሽ ስልኬን የምጠቀመው ከስንት አንዴ ነው። እናንተ እንደሁ የውሸት ዜና ጠፍጥፋችሁ መጋገርን ታውቁበታላችሁ" ሲሉ ብስጭታቸውን ገልጸዋል። ይህንን ዜና የሰማችው ቻይና በበኩሏ ቀልድ ቢጤ ጣል አድርጋለች፤ "ክቡር ፕሬዝዳንት፣ ስለምን አይፎንዎን ጥለው የኛ ምርት የሆነውን ሁዋዌን አይጠቀሙም?" ስትል። ዘገባው እንደሚለው የትራምፕ ረዳቶች ፕሬዝዳንቱ የግል ስልካቸውን እንዳይጠቀሙ በተደጋጋሚ መክረዋቸዋል፤ አሻፈረኝ ቢሉም። የቻይናው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት አለቃ ሁዌ ቺኒዪንግ ሐሙስ ዕለት እንዲህ ሲሉ ቀለዱ፤ "ዛሬ ስለ ትራምፕ ስልክ የተባለውን ስሰማ ኦስካርን ለማሸነፍ ጥሩ የፊልም ስክሪፕት መጻፍ የሚችሉ ትጉሃን እንዳሉ ነው የተረዳሁት።'' ወይዘሮዋ ጨምረው እንደቀለዱት "ይህን ያህል ነገሩ ካስጨነቃቸው ፕሬዝዳንቱ አፕል ስልክን መጠቀም ማቆም ይኖርባቸዋል፤ ህዋዌ አለላቸው" ብለዋል። ወይዘሮዋ በዚህም አላበቁም፤ " ወይ ደግሞ ህዋዌንም መጠቀም ካሰጋቸው፣ ለምን ስልክ የሚባል ነገር አይቀርባቸውም? እስከናካቴው ከተቀረው ዓለም ጋር መገናኘት ቢያቆሙስ?" ብለዋል። ሩስያም የፕሬዝዳንቱን ስልክ ጠልፈሻል መባሏን አስተባብላለች። • ለእነ ባራክ ኦባማ የተላከው ጥቅል ቦምብ የፕሬዝዳንት ፑቲን ቃል አቀባይ ሲናገሩ "እኛኮ እንዲህ ዓይነት ዘገባዎችን ከመጤፍም አንቆጥራቸው፤ እንደ ፌዝ ነው የምንመለከታቸው" ብለዋል። ኒውዯርክ ታይምስ በዚህ ዘገባው አረጋገጥኩ እንደሚለው ከሆነ ቻይናም ሩስያም የዶናልድ ትራምፕን የግል የስልክ ንግግሮች ጠልፈው ያዳምጣሉ። ይህም ፕሬዝዳንቱ በቁልፍ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግላዊ አስተያየት እንዲረዱ አግዟቸዋል። ይህ ደግሞ በድርድር ጊዜ የፕሬዝዳንቱን አስተሳሰባን በቀላሉ ለመግራት ይረዳቸዋል። ሁለቱ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች የሆኑት ቻይናና አሜሪካ በቅርቡ በከፈቱት የንግድ ጦርነት የዓለምን ምጣኔ ሐብት እያመሱት ይገኛሉ። የቻይናው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች የሆኑት ህዋዌና ዜድቲኢ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ለአሜሪካ ደኅንነት ስጋት ናቸው በሚል ሲብጠለጠሉ ቆይተዋል። በ2012፤ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ፤ የአሜሪካ ኮንግረስ ፓናል ሁለቱ የቻይና ኩባንያዎች ለአገሪቱ ስጋት ስለሆኑ አሜሪካ ውስጥ ከማንኛውም ውጤታማ የንብረት ቁጥጥር እንዲገለሉ ሐሳብ ማቅረቡ ይታወሳል። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ
news-55389284
https://www.bbc.com/amharic/news-55389284
ኢትዮጵያ የወሰደችው ቆራጥ እርምጃ ነው - ሙሳ ፋኪ መሐማት
የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱን አንድነትና መረጋጋት ለማረጋገጥ የወሰደው እርምጃ ቆራጥነት የተሞላበት መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ተናገሩ።
ሙሳ ፋኪ ማሐማት ይህንን የተናገሩት ትናንት እሁድ ጂቡቲ ውስጥ በተካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) 38ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ነው። የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ጨምረውም የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት የወሰደው እርምጃ "የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለማስከበር" መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ሁሉም አገራት የሚጠበቅባቸው ሕጋዊ ኃላፊነት መሆኑንም አመልክተዋል። ሙሳ ፋኪ እንዳሉት በዚህ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው መፈናቀል መከሰቱን ገልጸው፤ በዚህ ረገድ ኢጋድ ለስደተኞችና ለተፈናቀሉ ሰዎች የተለየ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ ከምታደርገው የሰብአዊ ድጋፍ ጥረት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ኮሚሽነሩ ፋኪ ማሐማት ከዚህ በፊት፣ የፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልል ወደ ድርድር እንዲመጡና ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። ለአንድ ቀን በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የኢጋድ አባል አገራት ከአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር በተጨማሪ ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፋቸውን መግለጻቸው ተነግሯል። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ የአገራቱ መሪዎች "የሕግ ማስከበር እርምጃዎቻችንን ሕጋዊነት በመረዳታቸውና እውቅና በመስጠታቸው እንዲሁም ኢትዮጵያን ለመደገፍ ቁርጠኝነታቸውን በመግለጻቸው" ምስጋና አቅርበዋል። በጥቅምት ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ከኢትዮጵያ አልፎ በአካባቢው አገራት ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ሲነገር የነበረ ሲሆን፤ የኢጋድ አባላት ጉዳዩን አንስተው መወያየታቸው ተነግሯል። ለሳምንታት የዘለቀው ወታደራዊ ግጭት የኢትዮጵያ ፌደራል ሠራዊት የትግራይ ክልል ዋና ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ መንግሥት "ሕግ የማስከበር ዘመቻ" ያለው መጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል። በወታደራዊ ግጭቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ሳይጠፋ እንዳልቀረ የተገመተ ሲሆን፤ በአገር ውስጥ እንደተፈናቀሉ ከሚገመቱ ሰዎች ባሻገር ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ግጭቱን ሸሽተው ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን የረድኤት ድርጅቶች ይናገራሉ። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በዚህ ባካሄደው አስቸኳይ ልዩ ስብሰባው ላይ በአባል አገራቱ ውስጥና በአገራት መካከል ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር አፋጣኝ እርምጃ በሚያስፈልጋቸው ላይ ውሳኔዎችን ሰጥቷል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ አግኝተዋቸው ከነበሩት ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ፣ ከኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ከሶማሊያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ ፋርማጆ፣ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት እንዲሁም ጅቡቲው ፕሬዝደንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር ተወያይተዋል። መሪዎቹ በአባል አገራት ውስጥ እንዲሁም በአንዳንድ አገራት መካከል ስላሉ ጉዳዮች አንስተው መወያየታቸው ተገልጿል። መቀመጫውን በጂቡቲ ያደረገው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ኤርትራን፣ ሱዳንን፣ ኢትዮጵያን፣ ጂቡቲን፣ ደቡብ ሱዳንን፣ ኬንያን፣ ሶማሊያንና ኡጋንዳን በአባልነት የያዘ ቀጠናዊ ተቋም ነው።
56211120
https://www.bbc.com/amharic/56211120
ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በካርቱም ተደራራቢ ችግር ውስጥ ነን አሉ
በሱዳን ካርቱም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በራሳቸው ገንዘብ ነዳጅ እና ዳቦ እንኳ ለመግዛት በመከልከላቸው መቸገራቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው በካርቱም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንዳስረዱት በአለም ዓቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የስደተኛ እውቅና አግኝተው ለረዥም ዓመታት በከተማው የኖሩ ቢሆኑም የአገሪቱ ፖሊስ እንግልት እያደረሰባቸው መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል። እነዚህ ስደተኞች እንደሚናገሩት ከሆነ በተለይም ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር ይገባኛል የተነሳ ውዝግብ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደግሞ በብዙ ፍራቻና ስጋት ውስጥ እንደሚኖሩ ይናገራሉ። ስደተኞቹ ከኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት የወጡና ለአመታትም ሱዳንን መኖሪያቸው ያደረጉ ናቸው። በአገሪቱ ፖሊስ የሚደርስባቸውን እንግልት በመጥቀስ ለጥያቄያችን መልስ አልተሰጠንም ያሉት ስደተኞቹ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሥደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን /ዩኤንኤችሲአር/ ግቢ ውስጥ ለሶስት ወራት ከኖሩ በኋላ በመኪና ተወስደው የካርቱም የከተማው ቆሻሻ የሚደፋበት ስፍራ ላይ እንዲቆዩ መደረጋቸውንም ይናገራሉ። ስደተኞቹ አክለውም አሁን እንዲኖሩበት የተደረገው ይህ ስፍራ ከካርቱም ውጪ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርስቲ በስተጀርባ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በስፍራው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ብቻ ከ700 በላይ አባወራዎች እንደሚገኙ ገልፀው የኮንጎ፣ ብሩንዲ፣ ኤርትራ እና ሌሎች አፍሪካ አገራት ስደተኞች ይገኛሉ ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው በሱዳን ካርቱም የሚኖሩት ስደተኞች እያጋጠማቸው ባለው ችግር ሴቶችና ሕጻናት የበለጠ ተጎጂ መሆናቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ስደተኞች የተሟላ የስደተኛ ሰነድ ያላቸው ቢሆንም ችግር እየደረሰባቸው መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። በጎዳና ላይ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የአገሪቱ ፖሊስ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚያደርስባቸውም ይገልጻሉ። ቢቢሲ ካነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከልጆቻቸው ጋር እየተቸገሩ መሆኑን የገለፁት የአራት ልጆች እናት የሆኑት ኩለኒ በየነ ላለፉት 28 ዓመታት በሱዳን ካርቱም ኖረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ስር ተመዝግበው የስደተኛ እውቅና ቢሰጣቸውም አሁን ግን የከፋ ችግር ውስጥ እንዳሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወ/ሮ ኩለኒ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የድንበር ይገባኛል ውዝግብ ከተነሳ ወዲህ የሚደርስባቸው እንግልት መጨመሩን ያስረዳሉ። ሌላዋ ቢቢሲ ያነጋገራቸውና የሰባት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ የሺ ከበደ ደግሞ "ልጆችን ይዤ መንገድ ላይ እየተቸገርኩ ነኝ፤ ባለቤቴ ብቻ ነው እየሰራ ያለው፤ ልጆቻችንን የምናሳድግበት አጥተን እየተቸገርን ነው" ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ዮሐንስ ሳሙዔል በምስራቅ ሱዳን ከሰላ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞች ካምፕ ለስድስት ዓመታት ከቆዩ በኋላ ካርቱም ገብቶ ሁሉንም የስደተኝነት መስፈርት በማሟላቱ ረዥም ዓመታት ቢኖሩም በአሁኑ ሰዓት ግን መብታቸው እየተገፈፈ መሆኑን ይናገራሉ። "በምሽት ፖሊሶች መጥተው በብዙ መኪና ጭነውን ከከተማ አውጥተውን ካርቱም ከተማ ቆሻሻ የሚጣልበት ስፍራ ጥለውን ተመለሱ። . . . የምንጠለልበት የለም፤ የሚሰጠን ድጋፍም የለም፤ አሁን የግል ኮንቴይነር አግኝተን በጋራ እየኖርን ነው" ብለዋል አቶ ዮሐንስ። ኢትዮጵያን ጨምሮ ከስድስት አገራት የመጡ ስደተኞች በዚህ ስፍራ እንደሚገኙም አቶ ዮሐንስ ጨምረው አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ አንዳንድ ዜጎች የሚደርስባቸውን ሲናገሩም "ዳቦ ለመግዛት በምንሰለፍበት ከሰልፉ ያባርሩናል፤ ነዳጅ ለእኛ አይሸጡም። የድንበር ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ደግሞ ከመኪና ውስጥም ያስወርዱናል" ብለዋል። በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስደተኞች ያላቸውን ስጋት እንደሚያውቅ ገልፆ፣ በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ በተለየ በአገሪቷ መንግሥት እውቅና የደረሰ ችግር ባይኖርም "ውስጥ ውስጡን ጉዳት እየደረሰ መሆኑን እናውቃለን" ብሏል። ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራዎች ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሚካኤል ጦብያስ በከተማ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰውን ችግር ለአገሪቷ መንግሥት አሳውቀው መፍትሄ እንዲያገኝ እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል። አቶ ሚካኤል በካርቱም ከተማ ውስጥ በተለያየ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ችግሮች እንደሚገጥማቸው እንደሚያውቁ ለቢቢሲ አስረድተዋል። የሱዳን ፖሊስም በእነዚህ ስደተኞች ላይ የመብት ጥሰትን እየፈፀመ እንደሚገኝ በመናገር 'በድፍረት እንዳንጠይቅ ወይንም እንዳንከራከር ብዙዎቹ ከሕግ ውጪ ወደ አገሪቷ መግባታቸውን' እንዳገዳቸው ይገልጻሉ። የአገሪቷ የሰብዓዊ መብቶች እና የፍትህ አሰጣጥ ሂደት ደካማ ስለሆነ ፖሊስ በሰጠው ማስረጃ እና ቃል ብቻ ፍርድ ቤቱም ፍርድ ሲሰጥ እንደቆየ ጨምረው አስረድተዋል። በዚሁ አካሄድ ብዙ ሰዎች ከአገር እንዲወጡ ተደርጓል ሲሉ አቶ ሚካኤል ተናግረዋል። "ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥብቻ በዚህ መንገድ 220 የሚሆኑ ሰዎች ተይዘው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል፤ ሌሎች ሰዎችን ደግሞ ያለፈቃድ ሰርታችኋል በማለት ፖሊስ ሲቀጣቸው ቆይቷል።" አቶ ሚካኤል እንደሚሉት የኢትዮጵያ ስደተኞችም ሆነ ሌሎች በቁጥጥር ስር በሚውሉበት ጊዜ በእስር የሚቆዩበት ሁኔታ የጤናና ምግብ አገልግሎት ችግር እንዳለበት ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩልም በሕገወጥ ወደ አገሯ የገቡን የተወሰኑትን እያሩሌሎቹ ደግሞ እየመለሰች መሆኑን ተስተውሏል። የኢትዮጵያ ስደተኞች ስጋት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የመጣው በሁለት ምክንያት መሆኑን የዲያስፖራ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ሚካኤል ያብራራሉ። የመጀመሪያው የአገሪቷ ምጣኔ ኃብት መዳከም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ያጋጠመ ሲሆን የሚቀርበው ዳቦ እና ነዳጅ ከፍተኛ እጥረት ማጋጠሙን ገልፀዋል። ከዚህም የተነሳ የአገሪቷ ዜጎች ስደተኞች ናቸው ስራ እየቀሙን በማለት እንደሚቃወሙ ይናገራሉ። ሌላኛው ምክንያት ብለው የሚጠቅሱት በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳ ሲሆን 'ድንበር ላይ ሰዎቻችንን ትገድላላችሁ፤ እዚህ ደግሞ ዳቦችንን እየተሻማችሁ ትበላላችሁ' በማለት ጫና አያደረጉ መሆናቸውን መስማታቸውን ተናግረዋል። በሳምንት ቢያንስ ወደ አስር የሚሆን አውቶብስ ስደተኞች በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አቶ ሚካኤል ጨምረው አስረድተዋል። በዩኤን ኤችሲአር ስር ተመዝግበው ያሉ ስደተኞች ወደ ኤምባሲ ስለማይመጡ መርዳት እንደማይችሉም አሳስበዋል። "ቢሆንም ግን ዜጎቻችን ስለሆኑ መብቶቻቸው እንዲከበሩ የአገሪቷን መንግሥት ስናሳስብ ቆይተናል" ብለዋል። በእነዚህ ስደተኞች የቀረበውን ቅሬታ ይዘን የዩኤን ኤች ሲአር ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።
news-55301771
https://www.bbc.com/amharic/news-55301771
ሱዳን ለሽብር ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት ዝርዝር ውስጥ ወጣች
አሜሪካ በይፋ ሱዳንን ለሽብር ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት ዝርዝር ውስጥ አስወጣቻት።
አል-ቃይዳ በታንዛኒያ እና ኬንያ በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት የቡድኑ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን መቀመጫው ሱዳን ነበር። ሱዳን ለሸብርተኞች እና ለሽብር ቡድኖች ድጋፍ ታደርጋለች በሚል በአሜሪካው ጥቁር መዝገብ ላይ ስሟ ሰፍሮ ለዓመታት ቆይታለች። ሱዳን ከዚህ መዝገብ ለመውጣት 335 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል መስማማቷን ተከትሎ ፕሬዝደንት ትራምፕ ሱዳንን ከዝርዝሩ እንደሚያስወጡ አስታውቀው ነበር። ሱዳን ለመክፈል የተስማማችው ገንዘብ አል-ቃይዳ በታንዛኒያ እና ኬንያ በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ባደረሰው የሽብር ጥቃት ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች የሚከፈል ካሳን ይጨምራል። በኤምባሲዎቹ ላይ ጥቃቶቹ ሲሰነዘሩ የአል-ቃኢዳ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን በሱዳን ይኖር ነበር። አሜሪካ እአአ 1993 ላይ አል-ቃኢዳ መቀመጫውን ሱዳን አድርጓል በሚል ሱዳንን በዚህ ዝርዝር ውስጥ አካታ ቆይታለች። ይህንንም ተከትሎ ማዕቀብ ተጥሎባት የቆየ ሲሆን በቀጠጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ጫና በማሳደሩ የሱዳን ምጣኔ ሃብትን ሲጎዳው ቆይቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሱዳን በአሜሪካ አሸማጋይነት በቅርቡ ከእስራኤል ጋር ግንኙነቷን ለማሻሻል መስማማቷ ይታወሳል። ከሱዳን በፊት የትራምፕ አስተዳደር ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ፣ ባህሬን እና በቅርቡ ደግሞ ሞሮኮ ለእስራኤል እውቅና እንዲሰጡ ማደራደሩ ይታወሳል። የሱዳኑ የቀድሞ መሪ ፕሬዝደንት ኦማር አል-በሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ የአሜሪካ እና ሱዳን ግንኙነት መሻሻል አሳይቷል። አል-በሸር ሕዝባዊ ተቃውሞ ከበረታባቸው በኋላ በአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት ተፈጽሞባቸው ነው ከሥልጣን ወርደው ለእስር ተዳርገው የሚገኙት። እንደ አውሮፓዊያኑ በ1989 አልበሽር መፈንቅለ መንግሥት አድርገው ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ነበር ካርቱምን የጽንፈኞች መናኽሪያ ያደረጓት ይላሉ የአካባቢው ተንታኞች። በዚህም ጂሐዲስቶች ነጻ አገር አገኙ። በአሜካና በምዕራቡ ላይ ለመዝመት እንቅስቃሴያቸውን ከዚያ ማድረግ እንደጀመሩ ይነገራል። በአሜሪካ፣ በሳዑዲ አረቢያ፣ በግብጽ፣ በኢትዮጵያ፣ በዩጋንዳና በኬንያና በታንዛኒያ እንዲሁም በየመን ለተፈጸሙ ጥቃቶች ግንኙነት ሲካሄድ የነበረው ከሱዳን እንደነበር የደኅንነት መረጃዎች ያመለክታሉ።
51016651
https://www.bbc.com/amharic/51016651
136 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የፈፀመው በዕድሜ ይፍታህ ተቀጣ
159 ወሲባዊ ጥቃቶችን በማድረስ የተከሰሰው ግለሰብ በዕድሜ ይፍታህ ተቀጥቷል፤ ዳኛውም የመፍታት ተስፋው የመነመነ ሲሉ ገልፀውታል።
ሬይናርድ ሲናጋ የተሰኘው ግለሰብ የእንግሊዟ የማንችስተር ከተማ ነዋሪ 48 ወንዶችን በመድኃኒት በማደንዘዝ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመውሰድ ወሲባዊ ጥቃት አድርሷል፤ ድርጊቱን በካሜራም ቀርጿል። ፖሊስ የ36 ዓመቱ ሲናጋ ቢያንስ 190 ሰዎችን ዒላማ እንዳደረገ ማስረጃ አለኝ ብሏል። የዕድሜ ይፍታህ ፍርድ የበየኑበት ዳኛ ግለሰቡ ቢያንስ ለ30 ዓመታት ከርቸሌ እንዲከርም ይሁን ብለዋል። ግለሰቤ እስኪረድበት ድረስ ማንነቱ በመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንዳይሆን ተብሎ የነበረ ቢሆንም ዳኛው ፍርዱን ካስተላለፉ በኋላ ማንነቱ ይፋ እንዲሆን ተደርጓል። የድህረ-ምረቃ ተማሪው ግለሰብ አሁን ከተበየነበት ፍርድ ቀድሞ በሌሎች ሁለት ጥፋቶች 20 ዓመታት ተፈርዶበት እሥር ቤት ውስጥ ይገኛል። ከኢንዶኔዥያ የመጣው ግለሰቡ በአንድ ጊዜ አራት ክሶችን ይከታተል ነበር። ፍርደኛው 48 ተጠቂዎች ላይ 136 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች፣ 8 የአስገድዶ መድፈር ሙከራዎች፣ 14 ወሲባዊ ፈጽሟል በሚል ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። መርማሪዎች ሌሎች 70 ተጠቂዎች ወደ ፖሊስ ባለመቅረባቸው ምክንያት ክስ መመሥረት አልቻልንም እንጂ ግለሰቡ ተጨማሪ የሚጠረጥርባቸው ወንጀሎች አሉ ይላሉ። በግለሰቡ ጥቃት ደርሶብናል ያሉ ለፖሊስ አቤት እንዲሉም ጥሩ አቅርበዋል። ዳኛ ሱዛን ጎዳርድ 'ይህ ሠይጣናዊነት የተጠናወተው ወሲባዊ ጥቃት አድራሽ በርካታ ወጣት ወንዶች ላይ ወንጀል ፈፅሟል' ሲሉ ተደምጠዋል። ግለሰቡ ጥቃት የሚያደርስባቸው ወንዶች ከምሽት ክለቦች ሲወጡ ይጠብቅና ከመረዛቸው በኋላ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመውሰድ ራሳቸውን በሳቱበት ወሲባዊ ጥቃት ያደርስባቸዋል ይላል የፖሊስ መዝገብ። ብዙዎች ጥቃት የደረሰባቸው ወንዶች ከነቁ በኋላ ምን እንደተፈጠረ እንደማያስታውሱ አስረድተዋል። ምንም ዓይነት ወንጀል አልፈፀምኩም የሚለው ግለሰብ ወሲብ የፈፀምኩት በግለሰበቹ ፍቃድ ነው፤ ቀረፃውንም ቢሆን እንደዚሁ ሲል ተከራክሯል። ፍርድ ቤት ግን ማስተባበያውን ውድቅ አድርጎታል። ሊድስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የዶክትሬት ድግሪውን ይከታተል የነበረው ሲናጋ ለመጀረመሪያ ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው ሰኔ 2017 ነበር። ከሳሾቹ ደግሞ ወሲባዊ ጥቃት እያደረሰባቸው የነቁ ግለሰቦች ናቸው። ግሰለቡ በእንግሊዝ ሕግ መዝገብ በጣም አሰቃቂ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመ ተብሏል።
45431405
https://www.bbc.com/amharic/45431405
ኬንያ ቻይናዊውን በዘረኛ ንግግሩ ምክንያት ልታባርር ነው
የኬንያዊያንን የሚያንቋሽሽ ቃላትን ሲጠቀም በቪዲዮ የተቀረፀው ቻይናዊ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሃገሪቱ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ገለፁ።
መስሪያ ቤቱ ጨምሮ እንዳሳወቀው የግለሰቡ የሥራ ፈቃድ የተሰረዘ ሲሆን ከኬንያ እንደሚባረርም አመልክተዋል። ሊዩ ጂያኪ የተባለው ቻይናዊ "ሁሉም ኬንያዊያን ፕሬዝዳንቱን ኡሁሩ ኬንያታን ጨምሮ ዝንጀሮዎች ናቸው" ሲል የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ በኬንያዊያን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል። የኬንያ ፖሊስም ቪዲዮው በርካታ ሰዎች እጅ ከገባ ከሰዓታት በኋላ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎታል። • ጉግል ኢንተርኔትን በላስቲክ ከረጢት ይዞ ኬንያ ገብቷል • በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ተቃጠሉ በሞተር ሳይክል ንግድ ላይ የተሰማራው ቻይናዊ ይህንን ለማለት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግልፅ ባይሆንም ንግግሩ የተቀረፀው ከሥራ ሊያባርረው ከነበረ ሰራተኛ ጋር በነበረው ምልልስ ወቅት ነበር። ሰራተኛውም በጊዜው ለቻይናዊው ግለሰብ "የምታደርገው ነገር ስህተት ነው" እያለ ሲሞግተውና እሱም "ግድ አይሰጠኝም" በማለት ሲመልስለት በቪዲዮው ላይ ይታያል። ቻይናዊው ጨምሮም ጥቁሮችን የሚያንቋሽሽና ከዝንጀሮ ጋር የሚያመሳስሉ ነገሮችን በማንሳት ከእነሱ ጋርም መነጋገር እንደማይፈልግ የመጣውም ገንዘብ ፍለጋ መሆኑን ከሰራተኛው ጋር ሲመላለስ ይሰማል። ይህንን ንግግር በተመለከተ እራሱም ሆነ በሚወክለው የሕግ ባለሙያ በኩል ምንም አይነት አስተያየት አልተሰጠም። ከሦስት ዓመታት በፊት ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ አንድ የቻይናዊያን ምግብ ቤት ከአመሻሽ 11 ሠዓት ጀምሮ አፍሪካዊያንን አናስተናግድም የሚል አሰራር እንደነበር ይፋ ወጥቶ ነበር። ይህንንም ተከትሎ የኬኒያ መንግሥት ምግብ ቤቱን ለአጭር ጊዜ ዘግቶ ባለቤቱን በማሰር ክስ መስርቶበት እንደነበር ይታወሳል።
news-50754153
https://www.bbc.com/amharic/news-50754153
የጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ተወሰነ
የጥምቀት ክብረ በዓል በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ መወሰኑን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አስታወቀ።
ድርጅቱ በኮሎምቢያ-ቦጎታ በቅርስ ጥበቃ ዙሪያ እያካሄደ ባለው ስብሰባ ነው የጥምቀት ክብረ በዓል አከባበር በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ (Representative List of Intangible Cultural Heritage of Humanity)ሆኖ እንዲመዘገብ ውሳኔ ያስተላለፈው። በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ የጥምቀት ክብረ በዓል አከባበርን፣ በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ የትምህርትና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ)በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት የተጀመረው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። • እሷ ማናት?: ለነፃነትም ለጥበብም ያልታከቱ እጆች • የቀድሞው የፀረ ሽብር አዋጅ ታሳሪዎች ያልተመለሱ ጥያቄዎች • 14ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በፎቶ ኢትዮጵያ እስካሁን ሦስት የማይዳሰሱ ቅርሶቿን የመስቀል በዓል፣ ፊቼ ጫምባላላና የገዳ ሥርዓት በዩኔስኮ አስመዝግባለች፡፡ የገዳ ሥርዓት በ2009 ዓ.ም. አዲስ አበባ በተደረገው የዩኔስኮ ጉባኤ መመዝገቡ ይታወሳል፡፡ ከዚህ በፊት ከኢትዮጵያ ውጪ የማይዳሰስ ቅርሳቸውን ካስመዘገቡ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ማላዊ፣ ኒስማ በሚባለው ባህላዊ ምግቧ፤ ሞሪሸስ ሙዚቃ፣ ዳንኪራና ዝማሬን ባካተተው ‹‹ሰጋ ታምቡር›› በሚባለው ባህላዊ ሙዚቃዋ፤ አይቮሪኮስት ዛዑሊ በሚባለው የጉሮ ማኅበረሰብ ባህላዊ ሙዚቃና ዳንኪራ ይገኙበታል። ጥምቀት በወርኃ ጥር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአደባባዮች በድምቀት ተከብሮ የሚውል ኃይማኖታዊ በዓል ነው። የጥምቀት በዓል ከዋዜማው ጥር 11 ተጀምሮ በማግስቱ ጥር 12 ቃና ዘገሊላም በድምቀት ይከበራል። ጥምቀት በኢትዮጵያ ውስጥ በድምቀት ከሚከበርባቸው የኢትዮጵያ ከተሞች መካከል አዲስ አበባና ጎንደር ይገኙበታል።
41746655
https://www.bbc.com/amharic/41746655
ፈር ቀዳጅ የታይፎይድ ክትባት ተገኘ
ከአስር አይነት የታይፎይድ በሽታዎች ዘጠኙን መከላከል የሚያስችል አዲስ ክትባት በዓለም የጤና ድርጅት ቀርቧል።
የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት በየዓመቱ ለ220 ሺህ ሰዎችን ሞት እንዲሁም ለ22 ሚሊዮን ሰዎች መታመም ምክንያት ለሆነው ለዚህ በሽታ መፍትሄ ይሆናል ብለዋል። በዋናነት በበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠቁት ህፃናት ሲሆኑ፤ ይህ ክትባት ከሌሎች በተለየ ሁኔታም ህፃናት ላይ ውጤታማ ነው። ክትባቱ በቀላሉ የሚዛመተውን የታይፎይድ በሽታን ለማጥፋት ይጠቅማልም ተብሎ ተስፋ ተደርጓል። የታይፎይድ በሽታ የሚከሰተው ሳልሞኔላ ታይፊ በሚባል ባክቴሪያ ሲሆን ምልክቶቹም፡ በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት የሚተላለፈው ይህ በሽታ ከፍተኛ የመተላለፍና የመሰራጨትም ባህርይ አለው። የንፅህና ችግርና የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግር ያለባቸው አካባቢዎች በከፍተኛ ደረጃ ለበሽታው ተጋላጭ ሲሆን፤ የታይፎይድ በሽታ በደቡብ እስያ እንዲሁም ከሰሀራ በታች ባሉ ሃገራት በስፋት ይከሰታል። በአሁኑ ጊዜ ይህን በሽታ ለመከላከል ሁለት የታይፎይድ ክትባቶች የፀደቁ ሲሆን፤ እስካሁን ከሁለት ዓመት በታች ላሉ ህፃናት ፍቃድ ያለው ክትባት አልነበረም። በአለም አቀፍ ጤና ድርጅት የክትባቱን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተለው ቡድን መሪ ፕሮፌሰር አሌሃንድሮ ክራቪዮቶ "ለመጀመሪያ ጊዜ ውጤታማ የሆነ ክትባት አግኝተናል" ብለዋል። ቡድኑም ክትባቱ ስድስት ወር ለሆናቸው ህፃናት ጭምር እንደሚሰጥ ገልጿል። ፕሮፌሰር አሌሃንድሮ እንዳሉት በዓለማችን በተሰራጩት በርካታ አይነት ፀረ-ተህዋሲያን መድሃኒቶች ምክንያት የታእፎይድ ባክቴሪያ መድሃኒቶቹን እየተላመደ በመምጣቱ ምክንያት የዚህ ክትባት መገኘት ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል። ክትባቱ ላይ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በተደረገ የክሊኒክ ሙከራ የተገኙ መረጃዎች በላንሴት የሜዲካል ጆርናል ላይ ታትሟል። በጥናቱ 112 ሰዎችን ታይፎይድን በሚያስከትለው ባክቴሪያ እንዲያዙ ተደርጎ የክትባቱ ውጤታማነት የተሞከረ ሲሆን 87 በመቶ ተፈላጊውን ውጤት አስገኝቷል። ሙከራውን ያደረጉት ፕሮፌሰር ፖላርድ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግኝቱን "ፈር ቀዳጅም ነው" ብለዋል።
news-55561319
https://www.bbc.com/amharic/news-55561319
ሰሜን ኮርያ፡ ፕሬዝዳንት ኪም የአገራቸው ምጣኔ ሀብት እቅድ አለመሳካቱን ተናገሩ
የሰሜን ኮርያ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የአገራቸው የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት እቅድ "በሁሉም ዘርፎች ሊባል በሚችለ ሁኔታ" የተቀመጠለትን ግብ አለማሳካቱን ተናገሩ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን የያሉት በፓርቲያቸው ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው። የሰሜን ኮርያ የሠራተኞች ፓርቲ ስብሰባ ሲያደርግ ይህ ስምንተኛው ብቻ ነው ተብሏል። ሰሜን ኮርያ ካለፈው ዓመት ታኅሣስ ወር ጀምሮ ምንም እንኳ አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው የለም ብትልም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚል ድንበሯን ዘግታለች። ይህም ከጎረቤቷና አጋሯ ቻይና ጋር ተቆራርጣ እንድትቀር አድርጓታል። በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 80 በመቶ መውደቁ ተገልጿል። በሰሜን ኮርያ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ቤቶችን ያወደመ ሲሆን በኒውክለር ፕሮግራሟ የተነሳም ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥብቅ የሆነ ማዕቀብ ተጥሎባታል። ፕሬዝዳንት ኪም የሚሰሯቸውን ስህተቶች ሲያምኑ የመጀመሪያቸው አይደለም። በቴሌቪዥን በተላለፈው የፓርቲው ጉባኤ ላይ አዳራሹ በተሰብሳቢዎች ሞልቶ የታየ ሲሆን አንዳቸውም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አላደረጉም። ፕሬዝዳንቱ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ሲገቡ ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነስተው በጭብጨባ ተቀብለዋቸዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በ2016 ያስተዋወቁት የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት ስትራቴጂ "በሁሉም ዘርፍ ሊባል በሚችል ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅተኛ አፈጻጸም አስመዝግቧል "ስህተቶችን ደግሞ በይፋ መቀበል ያስፈልጋል" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የፓርቲያቸው አባላትን የኮሮናቫይረስን በመከላከል ረገድ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል። ሰሜን ኮርያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መጠርጠራቸውን ለዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ሪፖርት ብታደርግም አንድም ሰው በቫይረሱ ተይዟል ብላ ሪፖርት አላደረገችም። ፕሬዝዳንት ኪም ለምክር ቤቱ አባላት አዲስ የአምስት ዓመት የምጣኔ ሀብት እቅድ ያስተዋውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
49724311
https://www.bbc.com/amharic/49724311
"በሳዑዲ የደረሰው ጥቃት ውጥረቱን እንዳያባብሰው እንሰጋለን" የኔቶ ኃላፊ
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን አገራት (ኔቶ) ወታደራዊ ጥምረት የበላይ ኃላፊ፤ የሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ላይ ጥቃት ከደረሰ በኋላ የውጥረቱ መጋጋል እጅጉን እንደሚያሳስባቸው ተናገሩ።
ጄንስ ስቶልትነበርግ ኢራን "ቀጠናውን እያመሰችው ነው" ሲሉ ከሰዋል። ሰኞ ዕለት አሜሪካ የለቀቀችው የሳተላይት ምስሎች፤ እሁድ ኢራን አደረሰችው ተብሎ ጣት የተቀሰረባት "ያልተጠበቀ" ጥቃት ያስከተለውን የጉዳት መጠን አሳይቷል። ኢራን በፕሬዝዳንቷ ሐሰን ሮሃኒ በኩል የለሁበትም ያለች ሲሆን፤ "በየመን ሕዝቦች የተወሰደ አፀፋዊ እርምጃ" ሲሉ ገልፀውታል። • የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃ • በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም፡ ግብጽ • ራማፎሳ በሌሎች አፍሪካውያን ላይ በደረሰው ጥቃት ማፈራቸውን ገለፁ ከኢራን ጋር አብረዋል ተብሎ የሚነገርላቸው የየመን ሁቲ አማፂያን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስደዋል። ነገር ግን አማፂያኑ ያለ ማንም ድጋፍ ይህንን ያህል ጥቃት፣ በዚህ ያህል ትክክለኛነት ያከናውናሉ መባሉ ለአሜሪካ አልተዋጠላትም። በሳዑዲ የሚመራውና በየመን ከሁቲ አማፂያን ጋር እየተዋጋ የሚገኘው ወታደራዊ ጥምረት ኢራን መሣሪያውን እንደሰጠች ያምናል። ጄንስ ስቶልትነበርግ "እንዲህ አይነት ለቀጠናው በአጠቃላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው ጥቃት ዳግመኛ እንዳይደርስ እንድንከላከል ጥሪ እናቀርባለን፤ ውጥረቱ እንዳይባባስም ከፍተኛ ስጋት አለብን" ሲሉ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል በሰጡት ቃለመጠይቅ ወቅት ተናግረዋል። ሁቲዎች ከዚህ ቀደም በሳዑዲ ምድር የነዳጅ ማምረቻና ማቀነባበሪያ ላይ ጥቃት አድርሰው ያውቃሉ። ነገር ግን ይህ ጥቃት በመጠኑ የገዘፈ እና በዓለማችን ከፍተኛ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ስፍራና ሌላ የነዳጅ ማውጫ ቦታ ላይ የተፈጸመ ነው። ከዚህ ጥቃት በኋላ የዓለማችን የነዳጅ አቅርቦት 5 በመቶ የቀነሰ ሲሆን ዋጋውም መጨመር አሳይቷል። የዘርፉ ባለሙያዎች እንዳሉት፤ ስፍራው ከደረሰበት ጉዳት ተጠግኖ ዳግመኛ ወደ ሥራ እስኪመለስ ሳምንታትን ይጠይቃል። አሜሪካ ሳዑዲ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኢራንን ተጠያቂ ለማድረግ ጊዜ አልወሰደባትም። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ፤ ቅዳሜ ዕለት የሳዑዲ ነዳጅ ማውጫ ተቋማት ላይ ለተሰነዘረው የድሮን ጥቃት ኢራንን ተጠያቂ አድርገዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ በበኩላቸው "ለጥፋቱ ማን ተጠያቂ እንደሆነ ስለምናውቅ አቀባብለን የሳዑዲ መንግሥት ምክረ ሃሰብ ምን እንደሆነ እየጠበቅን ነው" በማለት ወታደራዊ አማራጭ ከግምት ውስጥ እንደገባ አመላክተዋል። በስም ያልተጠቀሱት የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን ሲናገሩ፤ ዒላማ የተደረጉት 19 ቦታዎች እንደነበሩ እና ጥቃቱ የተሰነዘረው ከምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ መሆኑን ጠቁመው፤ ጥቃቶቹ የተነሱባቸው ስፍራዎች በየመን የሁቲ አማጺያን የሚቆጣጠሯቸው ቦታዎች አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ባለስልጣኑ ጨምረው እንደተናገሩት፤ የተገኘው መረጃ ጥቃቱ የተሰነዘረው ከኢራን ወይም ኢራቅ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማል ብለዋል። አሜሪካ ይፋ ያደረገቻቸው የሳተላይት ምስሎች በነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማቱ ላይ የደረሰውን ከፍተኛ ጉዳትም አመላክተዋል። በሳዑዲ ላይ የተሰነዘሩት የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች መሆናቸውን እና ሁሉም ዒላማቸውን መምታት አለመቻላቸውን የአሜሪካ የደህንነት ቢሮ መረጃ ጠቁሟል። 'ኤቢሲ' ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣኑን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ፕሬዝደንት ትራምፕ ለጥቃቱ ተጠያቂዋ ኢራን መሆኗን አምነዋል። የሳዑዲ ባለስልጣናት ጥቃቱ በሰው ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም በማለት የድሮን ጥቃቱ ስላደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ ቀርተዋል። ነገር ግን ጥቃቱ የሳዑዲ አረቢያ የድፍድፍ ነዳጅ የማምረት አቅምን በግማሽ መቀነሱ ተረጋግጧል። ሳዑዲ አረቢያ የዓለማችን ቁጥር አንድ ነዳጅ አምራች ስትሆን በየቀኑ ወደ 7 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ወደ ውጪ አገራት ትልካለች።
news-45057711
https://www.bbc.com/amharic/news-45057711
ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ
"ናይሮቢ ውስጥ የህግ ሥራ በመስራት ጥሩ ገቢ እያገኘሁ ዘናጭ መርሴዲስ ቤንዝ እያሽከረከርኩ መኖር ለእኔ ቀላል አማራጭ ነበር። እኔ ግን ወደ ትውልድ ስፍራዬ መመለስ ነበር የፈለግሁት።"
ፋጡማ አብዱልቃድር አዳን እግር ኳስን እንደ የሴት ልጅ ግርዛት በመሳሰሉ ነውር ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ዝምታውን ለመስበር እየተጠቀመችበት ነው፡፡ የፋጡማ አብዱልቃድር ህይወት ይህን ሊመስል ይችል ነበር። እሷ ግን እግር ኳስን መጫወት ለልጃገረዶች ነውር በሆነበት አካባቢ ይህንን ስፖርት መረጠች። "አካላዊ ድብደባ ደርሶብኛል። መሬት ላይም ተጥያለሁ" ትላለች ያኔ የዛሬ አስር ዓመት በሰሜን ኬንያ ማርሳቤት ግዛት የሴቶችን ቡድን ማቋቋም ስትጀምር የነበረውን ትግል ስትገልጽ። ፋጡማ የአፍሪካ ቀንድ የልማት ተቋም ወይም በ2003 በሚጠራበት ስሙ ሆዲ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም መስርታለች። እግር ኳስ ሰዎችን በአንድ እንዲያሰባስብ እና በባህላዊ አመለካከት ዙሪያ ለውጥ እንዲያመጣ ትፈል ነበር። እግር ኳስን በ2005 በጎሳዎች መካከል ከተፈጠረውና 100 ሰዎችን ከገደለው እልቂት በኋላ የማህበረሰቡን ወጣት ወንዶች ልብ ለማሸነፍ ተጠቅማበታለች። "ኤኬ-47 ጠመንጃ የእግር ኳስ ቡድኑን ቦታ ተክቶ ነበር።" ወዲያውኑ ወጣት ወንዶቹ መሳሪያቸውን መጣል ብቻ ሳይሆን ሊጣሏቸው ይገባ ከነበሩት የጎሳ አባላት ልጆች ጋር መጫዎት ጀመሩ። ከመጀመሪያዎቹ የእግር ኳስ ውድድሮች አንደኛው ግጭት በነበረባቸው ማህበረሰቦች መካከል ይቅርታን ለማውረድ ያለመ ነበር ባህላዊ አመለካከትን መጋፈጥ ፋጡማ ፊቷን ወደ ልጃገረዶች ባዞረች ጊዜ ያለእድሜ ጋብቻን እና የሴት ልጅ ግርዛትን ጨምሮ ችግራቸውን ማሰወገድ ፈልጋ ነበር። ዝምታውን መስበር የተሰኘው ዘዴዋ በአስር ዓመት ውስጥ ከ152 የኬንያ ማርሳቤት ክልል መንደሮች 1645 ልጃገረዶችን እግር ኳስ እንዲጫወቱ አስችሏል። በተለይ ባህላዊ የቤተሰብ እና የጎሳ መዋቅር ማለት ህጻናት እና ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ ድምጽ አልባ ማድረግ በሚሆንበት አካባቢ ልጆች ለራሳቸው ዘብ እንዲቆሙ አቅማቸውን ማጎልበት የተልዕኮዋ ዋነኛው ክፍል ነው። • የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች • አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው? "በቀደመው ጊዜ የ13 ወይም የ12 ዓመት ልጃገረድን መዳር ምን ችግር አልነበረውም" በማለት የምተገልጸው ፋጡማ "ዛሬ የ13 ዓመት ልጅ ብታገባ አብረዋት በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ሴቶች ይቃወማሉ። ወንዶች ልጆችም እንዲሁ" ይላል። ምንም እንኳ የሴት ልጅ ግርዛትም ሆነ ያለ እድሜ ጋብቻ በኬንያ ህገ-ወጥ ቢሆኑም የአካባቢው ባህል ጠንካራና በቀላሉ የማይቀየሩ ናቸው። ፋጡማም እነዚህን ድርጊቶች ተቃርና ለመከራከርም ሆነ አብራቸው ለመስራት መጠንከር ነበረባት። የተገበረችው አካባቢያዊ ዘዴም ለዚህ ጠቅሟታል። እግር ኳስ መጫወት ለሚፈልጉ ልጃገረዶች የሚሆን በቂ የስፖርት ትጥቅ እንዴት ማሰፋት እንዳለባት ኢማሞች ካማከረች በኋላ፤ አሁን ሆዲ የእስልምና ትምህርት ቤት ውስጥ የልጃገረዶች ቡድን አቋቁሟል። "በህይወት ኖሬ ይህ ሲሆን ማየቴን እስካሁን ማመን አልቻልኩም" ትላለች። ውድድሩ በ2008 ሲጀመር ለልጃገረዶች እግር ኳስ መጫወት በራሱ በሰሜን ኬንያ ነውር ነበር አንድ ልጃገረድ በአንድ ጊዜ የፋጡማ ሥራ በእያንዳንዳቸው ተሳታፊ ሴቶች ህይወት ላይ እየተጫወተው ያለውን አውንታዊ ውጤት መመልከት የተከተለችውን ፈጠራ የተሞላበት ዘዴ ስኬታማነትን ያሳያል። የ14 ዓመቷ ፋጡማ ጉፉ የትምህርት ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ናት። ድሃ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ ብቸኛ ሴት ልጅ ሆና በእናቷ እጅ ያደገችው ፋጡማ እንደምትለው "እግር ኳስ ህይወቷን ቀይሮታል።" "በመጀመሪያ በጣም ዓይን አፋር ነበርኩ" ትላለች። "ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እግር ኳስ ቀየረኝ። ለበርካታ ዓመታት ወላጆች ልጃገረዶች እግር ኳስ እንዲጫወቱ አይደግፉም ነበር። ወደፊት ግን እኔ እናት ስሆን ልጃገረዶች እግርኳስ እንዲጫወቱ መደገፍ እፈልጋለሁ።" የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ወ/ሮ ካሜ ኮቶ እንደሚሉት እሷ በክፍል ውስጥ በአብዛኛው ለአንደበተ ርቱዕ ወንዶች ከሚተወው ከምርጥ አምስቶች ውስጥም ናት። "በእግር ኳስ መሳተፍ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በትምህርቷም ሆነ በአመራር በኩል ያላትን ክህሎት ማሳየት ችላለች'' ይላሉ። "ይሄ ሁሉ የተቻለው በእግር ኳስ ነው" የምትለው ፋጡማ፤ "ልጃገረዶች ግፊት ማድረግ እና በክፍል ውስጥም ሆነ በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ።" የ14 ዓመቷ ፋጡማ ጉፍራ እንደምትናገረው እግር ኳስ የህይወት ግቧን ለመለወጥ በራስ መተማመን አጎናጽፏታል
46121117
https://www.bbc.com/amharic/46121117
15 ሕፃናትን በማቀዝቀዣ ውስጥ ጭኖ ወደ እንግሊዝ ለመግባት የሞከረ መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ
21 ሰዎች ማቀዥቀዣ ባለው መኪና ውስጥ ተደብቀው ወደ እንግሊዝ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ዕድሜያቸው 12 ዓመት የሚሆናቸው ታዳጊዎች ይገኙበታል።
መኪናው የተያዘው በኒው ሔቨን ወደብ አካባቢ ነው። ወደ እንግሊዝ ሊገቡ ሲሉ የተያዙት እነዚህ ስደተኞች ቬትናማዊያን እንደሆኑ ተገምቷል። ስደተኞቹን የጫነው ባለማቀዝቀዣ መኪና የታሸገ ውሃ የጫነ ሲሆን ስደተኞቹም ከታሽገው ውሃ መካከል መገኘታቸው ነው የተዘገበው። የድንበር ጠባቂዎች ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም ምርመራ ግን መጀመሩ ታውቋል። • ትላልቅ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች "አዋጭ አይደሉም" • በኢትዮጵያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ 10 ሰዎችን ገደለ መኪናውን ያሽከረክር የነበረ ሮማኒያዊ ያለ ህጋዊ ፈቃድ ሰዎችን ወደ እንግሊዝ ለማስገባት በመሞከር ተብሎ በቁጥጥር ስር ውሏል። የታሸገ ውሃ የጫነው መኪና ከፈረንሳይ የመጣ ሲሆን ሁሉም ስደተኞች ቬይትናማዊ ነን ያሉ 15 ህፃናትና 6 አዋቂ ሰዎችን አሳፍሯል። ህፃናቱ ማህበራዊ ድጋፍ ወደ ሚያገኙበት ስፍራ ሲወሰዱ 18 አመት የሆነው ወጣትና 27 ዓመት የሚሆናት ሴት ከእንግሊዝ እንዲለቀቁ ተደርጓል። 4 አዋቂ ሰዎች ግን በስደተኞች ማቆያ ጣቢያ ሆነው ጉዳያቸው እየታየ ይገኛል።
52312481
https://www.bbc.com/amharic/52312481
የኮሮናን ህግ ተላልፈዋል የተባሉት ህንዳዊው የእስልምና እምነት ምሁርና ሰባኪ "በግድያ" ወንጀል ተከሰሱ
ህንዳዊው የእስልምና እምነት ምሁርና ሰባኪ መሃመድ ሳድ ካንዳቪ አገሪቷ ያሳለፈችውን አስገዳጅ ቤት የመቀመጥ ውሳኔ በመተላለፋቸው "በግድያ "ወንጀል ተከሰዋል።
ሰባኪው የወረርሽኙ ማዕከል በሆነችው ደልሂ ስብሰባ አካሂደዋል በሚል ነው የተከሰሱት። ፖሊስ እንዳሳወቀው ኒዛሙዲን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው መስጊድ የተጀመረው ስብሰባ ባለፈው ወር ህንድ ቤት የመቀመጥ ውሳኔን ከማወጇ በፊት የተጀመረ ቢሆንም፤ ውሳኔውም ተግባራዊ ከሆነ በኋላም ህጉን ተላልፈው በስብሰባው ቀጥለዋል ብሏል። አራት ሚሊዮን ሩዋንዳውያንን ስለኮሮና ለማስተማር የወጠነው የሬዲዮ ድራማ የኮሮናቫይረስ ፅኑ ህሙማን እንዴት ያገግማሉ? ስብሰባው በአስራ ሰባት ግዛቶች ውሰጥ ከተጠቁት 1023 የኮሮና ቫይረስ ህሙማን ጋር ቀጥታ ግንኙነት አለው የተባለ ሲሆን፣ ከሌላ አገር በመጡ በስብሰባው ተሳታፊዎች ነው ቫይረሱ የተዛመተው ተብሏል። ሰባኪውም ሆነ ድርጅታቸው ምንም ስህተት አልፈፀምንም በማለት የፖሊስን ውንጀላ አጣጥለውታል። የዴልሂ ፖሊስ በበኩሉ መሃመድ ሳድ የሰዎችን ህይወት አደጋ በመጣልና፣ ለሞት በመዳረግ እንደተከሰሱና የዋስ መብታቸው እንደማይከበር አስታውቋል። ሰባኪው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ በሌሉበትም ክሳቸው ቀርቧል። ቤት ጥቃት ሲበዛ ወደየት ይሸሻል? ቻይና ከኮሮናቫይረስ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በቅርብ የታዘበው ኢትዮጵያዊ ዶክተር ፖሊስ አክሎም ሁለት ጊዜ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ውስጥ የነበረውን ስብሰባ ቀጥለውበታል በማለት ተናግሯል። ድርጅታቸው ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ አስገዳጅ የቤት መቀመጥ መመሪያ ሲሰማ ስብሰባው እንደተቋረጠና ተሳታፊዎችም ወደየቤታቸው እንዲሄዱ መወሰኑን አሳውቀዋል። ምንም እንኳን ብዙዎች ወደመጡበት ቢመለሱም፣ ከተሞች ድንበሮቻቸውን መዝጋታቸውን ተከትሎ አንዳንዶች ወደ አካባቢያቸው መመለስ አልቻሉም። ህንድ በከተሞች ያሉ ድንበሮችን ከመዝጋት በተጨማሪ የአውቶብስና ባቡሮች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ጥላለች። በዚህም የተነሳ በመስጊዱ ውስጥ ባሉ ማደሪያዎች ተሳታፊዎቹ ሊቆዩ ተገደዋል። ማደሪያዎቹ በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰዎችንም ማስተናገድ ይችላሉ ተብሏል። አዘጋጆቹ ጨምረውም በአካባቢው ለሚገኙ ፖሊሶች እንዳሳወቁና የጤና ባለሙያዎችም በግቢው በመገኘት ተሳታፊዎቹን ሲመርመሩም ሆነ ሁኔታውን ሲቆጣጠሩ እንደተባበሩ አስረድተዋል።
news-54201400
https://www.bbc.com/amharic/news-54201400
ኮሮናቫይረስ፡ በዓለማችን ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል
በጆንስ ሆፕኪንስ አሐዝ መሠረት በዓለም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሚሊዮን አልፏል። 940,000 ሰዎች ሞተዋል።
ከየትኛውም የዓለማችን አገራት በበለጠ በሕንድ ቫይረሱ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው በወረርሽኙ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሜሪካ፣ ሕንድና ብራዚል ናቸው። አውሮፓ ውስጥ ደግሞ ቫይረሱ እያገረሸ ነው። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ቫይረሱ በሁለተኛ ዙር የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ተጨማሪ የጥንቃቄ እርምጃዎች ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። እስራኤል ለሁለተኛ ጊዜ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ መጣሏ ይታወሳል። አፍሪካ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። እየተካሄደ ያለው ምርመራ ቢጨምር ከዚህም በላይ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል መላ ምት አለ። ክፉኛ የተጎዱ አገራት በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳችው አሜሪካ ናት። 6.6 ሚሊዮን ሰው በበሽታው ሲያዝ 197,000 ሰዎች ሞተዋል። አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከሐምሌ አንጻር እየቀነሰ ነው። በሕንድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአምስት ሚሊዮን አልፏል። ይህም በዓለም ሁለተኛው ከፍተኛ የህሙማን ቁጥር ነው። በየቀኑ 90,000 ገደማ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ይገኛሉ። የጽኑ ህሙማን አልጋና ኦክስጅን ውስን ሲሆን፤ 80,000 ሰዎች ሞተዋል። በብራዚል 4.4 ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። 34,000 ሰዎች ሞተዋል። ከአሜሪካ ቀጥሎ በርካታ ሰዎች የሞቱት በብራዚል ነው። ፕሬዘዳንት ዣቪር ቦልሶናሮ ቫይረሱ የሚያስከትለውን ጉዳት በማቃለላቸው ተተችተዋል። ቫይረሱን ‘ትንሽዬ ጉንፋን’ ብለው የጠሩት ፕሬዘዳንቱ ሐምሌ ላይ በበሽታው ተይዘው እንደነበር አይዘነጋም። ላቲን አሜሪካ ውስጥ አርጀንቲና እና ሜክሲኮም በበሽታው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአርጀንቲና ከ600,000 በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በሜክሲኮ ደግሞ ቁጥሩ 680,000 ደርሷል። የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው አውሮፓ ውስጥ ቫይረሱ ማገርሸቱ እንደ ማንቂያ ደውል መታየት አለበት። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን የድርጅቱ የአውሮፓ ኃላፊ ሀንስ ክሉግ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት ብቻ በአውሮፓ 300,000 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ይህም የወረርሽኙ ስርጭት ከጀመረበት ወቅት በላይ ነው። እስካሁን አምስት ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙና ከ228,000 በላይ እንደሞቱ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ተስፋ አለ? ውጤታማና አስተማማኝ ክትባት ለማድረግ በርካታ አገሮችና ተቋሞች እየተረባረቡ ይገኛሉ። ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ ምርጫ በፊት ክትባት ይገኛል ብለው ነበር። የጤና ባለሙያዎች ግን የትራምፕ ንግግር ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል። ሩስያ ነሐሴ ላይ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቅዳለች። ይህም የመጀመሪያዋ አገር ያደርጋታል። የሩስያ ሳይንቲስቶች ክትባቱ በሽታ የመከላከል አቅም በማዳበር ረገድ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማሳየቱን ተናግረዋል። የሙከራ ሂደቱ የተገባደደ ክትባት የለም። ክትባት ለማግኘት የሚደረገው ጥረት ከሰዎች ጤና ይልቅ የፖለቲካ ጫና ያደረበት መሆኑ የሚያሰጋቸው ባለሙያዎች አሉ። አሁን ወደ 150 ክትባቶች ላይ ምርምር እየተካሄደ ሲሆን፤ ክትባት የማግኘት ሩጫውን ሀብታም አገሮች ያሸንፋሉ ብለው የሚፈሩም አሉ።
news-56294154
https://www.bbc.com/amharic/news-56294154
የጣልያኑ መዝገበ ቃላት ሴት ለሚለው የሰጠውን 'አፀያፊ' ትርጉም እንዲቀይር ተጠየቀ
100 የሚሆኑ ስመ- ጥር ጣልያናውያን ትሪካኒ የተባለው የጣልያን መዝገበ ቃላት ሴት በሚል ያስቀመጠውን ትርጓሜ እንዲቀይር ፊርማ አሰባስበዋል።
ዘመቻውን የሚያራምዱ ሰዎች መዝገበ ቃላቱ ሴት የሚለውን አፀያፊ በሆነ ሁኔታ ተርጉሞታል ይላሉ። በመዝገበ ቃላቱ ሴት ለሚለው ቃል ተመሳሳይ ተብሎ የሰፈረው ፑታና (ሸርሙጣ ወይም የወሲብ ንግድ ተዳዳሪ ) በሚል ሲሆን ፤ለሴት ተመሳሳይ ትርጉም ነው ተብሎ ከሰፈረው ዘርፍ ሊወገድ ይገባል ብለዋል። እንደዚህ አይነት ትርጉሞች"አፀያፊ፣ ፆተኛ፣ ሴቶችን በወሲብ አይን ብቻ የሚመለከቱና የበታችነት ቦታ የሰጡ ናቸው" ብሏል። በበይነ መረብ መዝገበ ቃላቶችን በማተም የቁንጮነትን ስፍራ የተቆናጠጠው ትሪካኒ በበኩሉ ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጠ ሲሆን ከዚህ ቀደም ግን ደግፎ ተከራክሮ ነበር። ደብዳቤውን ከፈረሙት መካከል የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን መብት የሚከራከሩት ፖለቲከኛ ኢማ ባታግሊያ፣ ፖለቲከኛ ላውራ ቦልድሪኒና የጣልያን ባንክ ዋና ዳይሬክተር አሌሳንድላ ፔራዛሊና ይገኙበታል። የዘመቻው ፅሁፍ የተፃፈው በሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ማሪያ ቢትሪስ ጂዮቫናርዲ ሲሆን ከዚህ ቀደምም የኦክስፎርዱ እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ለሴት ተመሳሳይ ተብለው የሰፈሩት ቃላት ወፍና ሌሎች ቃላቶችን እንዲያስወግዱ ዘመቻ ከከፈቱት መከካል አንዷ ናቸው። ተመሳሳይ የተቃውሞ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈረማቸውን ተከትሎ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ትርጉሙን ለማሻሻል ተገዷል። በተጨማሪ በትሪካኒ መዝገበ ቃላት የወሲብ ንግድ ተዳዳሪዎችን ትርጓሜ በተመለከተ 30 ቃላትን የተጠቀመ ሲሆን ይህም ከኦክስፎርዱ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት የከፋ እንደሆነ ቢትሪስ ጂዮቫናርዲ ለሮይተርስ ተናግረዋል። ነገር ግን ወንድ ለሚለው ቃል የተሰጠው ትርጓሜ አዎንታዊ ሲሆን ለምሳሌም የንግድ ሰው የሚል ነው። "ቋንቋዎች የምንኖርበት አለም ላይ ተፅእኖ ያሳርፋሉ። ሴቶች በምን መንገድ ሊታዩ እንደሚችሉም ጠቋሚ ናቸው" በማለትም በደብዳቤው ላይ አስፍረዋል። "መዝገበ ቃላት፣ ኢንሳይክሎፒዲያና ሌሎች ከቋንቋዎች ጋር የተገናኙ መፃህፍት ለበርካታ ተማሪዎች እንደ ተጨማሪ መማሪያ የሚያገለግሉ የትምህርት መሳሪያዎች ናቸው። የትሪካኒን መዝገበ ቃላት በትምህርት ቤቶች፣ ቤተ መፃህፍትና በቤቶቻችን የምንጠቀምባቸው ናቸው" ይላሉ። "የመዝገበ ቃላቱ ትርጉም መቀየር በየቀኑ የሚደርሰውን ፆተኛነት አያስቀረውም። ነገር ግን ሴቶች በማህበረሰቡ ላይ ያላቸውን ትክክለኛ ሚና እንዲሁም አሁን ባለንበት ማህበረሰብ ሊኖራቸው የሚችለውን ራዕይ ሊያንፀባርቅ ይችላል" ብለዋል። በህዳር ወር ላይ ትሪካኒ ባወጣው ፅሁፍ መዝገበ "የቃላቱ ትርጉም በሞራል ፍርድ ወይም በጭፍንነት ተሞልቶ አይደለም"፤ ነገር ግን "ማህበረሰቡና ባህሉ አንዳንድ ቃላትን በአሉታዊ መልኩ ይገልፃቸዋል። መዝገበ ቃላትም ይህንን አገላለፅ አልመዘግብም አይልም" ብሏል መግለጫው
41497362
https://www.bbc.com/amharic/41497362
እነሆ የቤተሰብ ፎቶ
ሲያን ዴቪስ የተባለው እንግሊዛዊ ተጓዥ ጋዜጠኛ ቤተሠብ ፈርጀ ብዙ የሕብረተሰብ አካል እንደሆነ የሚመስክሩ ፎቶዎችን እየዞረ ሲያነሳ ከርሟል። ምስሎቹን በካሜራው ዓይን ያነሳቸው ሰዎቹ ለማዕድ በተቀመጡበት ወቅት ነው። ተናጋሪ ያላቸውን ፎቶዎች እነሆ!
በመግቢያው ላይ ሩ እና ፒተር ከተባሉ ሁለት ልጆቹ ጋር የምትመለከቱት ቶም በቤት-መሰል መኪናው ውስጥ ምግብ ሲያበስል የተነሳው ፎቶ ነው። ትውልደ ዚምባብዌያዊው ቺሻሚሶ ኩንዲ የልጅነት ጊዜውን በእርሻ ውስጥ ነበር ያሳለፈው። ምህንድስና ያጠናው ቺሻሚሶ ከትዳሩ ሦስት ልጆች አፍርቷል። "አባል የነበርኩበት ፓርቲን ሙጋቤ ማሳዳድ ሲጀምሩ ለደህንነቴ በመስጋት ወደ እንግሊዝ ሃገር ተሰደድኩ። ነገሮች ሲመቻቹልኝ ቤተሰቦቼን አመጣለሁ የሚል ተስፋ ነበረኝ። እንዲህ እያልኩ እነሆ 16 ዓመታት ተቆጠሩ" ይላል ቺሻሚሶ። "የመጣሁ ሰሞን ሳውዝሃምፕተን ውስጥ መንገድ ላይ ነበር ማድረው። ብዙ ጊዜ ዝናብ ደብድቦኛል።" የቺሻሚሶ ቤተሰቦች አሁንም ዚምባብዌ ውስጥ ይኖራሉ። "በ18 ዓመቴ ነበር ሆሊን የወልደኳት" ትላለች ሬቤካ። "አቅጄው ስላልነበር በዛ ዕድሜዬ ልጅ ማሳደግ ከብዶኝ ነበር።" ሬቤካ እና ሆሊ ከሬቤካ እናትና አባት አቅራቢያ ይኖራሉ። "ፍቅራችን ለየት ያለ ነው" ትላለች ሬቤካ። ጂም ከጆይስ ጋር ለ63 ዓመታት ዘልቋል። ነገር ግን ከሦስት ዓመታት በፊት ጆይስ አለፈች፤ ጂምም በብችኝነት ኑሮውን መግፋት ያዘ። ጂም የመጃጀት በሽታ ተጠቂ ሲሆን፤ ሁሌም በሳምንቱ መጨረሻ ልጁ ሪቻርድ ሊጎበኘው ራቅ ወዳለው ስፍራ ይመጣል። የቤተሰቡ አባላትም ከያሉበት ይሰባሰባሉ። ሪቻርድ ስለአባቱ ሲናገር "ለሁሉም ሰው ምላሹ ፈገግታ ነው። የእርሱ ፈገግታ ለእኛ ሁሉ ነገራችን ነው።" ከልጅነታቸው ጀምሮ የሚተዋወቁት ኬት እና አያን ሞሪሰን አሁን ላይ ሁለት ልጆች አፍርተው ይኖራሉ። ኬት ስትናገር "ልጆቻችን ኒያል እና አሜሊያ ለቀጣይ ሕይዋታቸው የሚሆን ስንቅ እንዲኖራቸው እኔና ባሌ ሁሌም እንተጋለን" ትላለች። "እኛ ቤት ነገሮችን ለማድረግ ጊዜ ወይም ወቅት አንጠብቅም፤ ሲሆን ይሆናል ነው" ትላለች ዴኒስ። አራት ልጆቿን ለብቻዋ የምታሳድገው ዴኒስ በርሚንግሃም ውስጥ የልዩ ፍላጎት አስተማሪ በመሆን ትሠራለች። ልጆቿን ግልጽ፣ ታማኝ እና እርስ በርስ እንዲደጋገፉ አድርጋ አሳድጋለች። ልጆቿ የየራሳቸው ተሰጥኦ ያላቸው ሲሆኑ ትንሹ ልጇ ሬማር በሌይስተር ሲቲ እግር ኳስ ቡድን ውስጥ ችሎታውን እያሳደገ ይገኛል። ቶም እና አና በጓደኞቻቸው አማካይነት ነው የተዋወቁት። "እርስ በርስ ጥሩ ስሜት ነበረን። በመጨረሻ አንድ እንደምንሆን አናውቅ ነበር" ይላል ቶም። ከስምንት ዓመት በፊት የተወለደው ቢሊ የአካል እና የአእምሮ ዕድገት በሽታ ተጠቂ ነው። በጨቅላ ዕድሜው ብዙ መከራዎችን አልፏል። አና "ፈገግታው ከብዙ ነገሮች ይታደገዋል" ስትል ትናገራለች። ክርስቲና ሴባስትያንን የተገላገለችው በ26 ዓመቷ ነው። አባቱ በውትድርና ዘርፍ ስላለ ብዙ ጊዜ ቤት አይገኝም። ቀን ቀን በካሸርነት ማታ ማታ ደግሞ በአንድ ሆቴል ውስጥ በሼፍነት ታገለግላለች። እሷ ሥራ ላይ በምትሆን ጊዜ ሴባስትያንን እናቷ ጋር ታስቀምጠዋለች። "ቁርስ ላይ ብቻ ነው ብዙ ጊዜ የምንገናኘው። አንድ ላይ ስንሆን እንዴት ደስ እንደሚል" ባይ ናት ክርስቲና።
53681745
https://www.bbc.com/amharic/53681745
የተቋረጠው የህዳሴ ግድብ ድርድር በመጪው ሳምንት ሊቀጥል እንደሚችል ተገለፀ
በአፍሪካ ህብረት ታዛቢነት እየተደረገ ያለው የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሶስትዮሽ የበይነ መረብ ድርድር የተቋረጠ ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንትም ይቀጥላል ብላ ኢትዮጵያ እንደምትጠብቅ በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ አርብ ማለዳ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ በአሁኑ ወቅት ግብፅ እና ሱዳን ተቃውሞ ያነሱባቸው ኃሳቦች አዲስ እንዳልሆኑና ኢትዮጵያ የግድቡ ሙሌት ያለ ስምምነት አሁን ተፈፅሞ ተራዛሚ ጉዳዮች በሌላ ስምምነት መከናወናቸው እንዲቀጥል ትፈልጋለች ብለዋል። ግብጽ ከምታነሳቸው ቅሬታዎች መካከል ኢትዮጵያ ግድቡን ሙሉ አቅም እየተጠቀመች ድርቅ ቢያጋጥም ችግሩ የሦስቱም አገራት ጉዳይ ነው የሚል አቋም ላይ መድረሷን ነው። ወደፊት ድርቅ ቢያጋጥም ኢትዮጵያዊያንን ግምት ውስጥ ያስገባ የውሃ አጠቃቀም ማድረጓ አይቀርም የሚል ኃሳብን የሰነዘሩት አምባሳደሩ፣ ነገር ግን ከአሁኑ ሊኖረው የሚችለውን የውሃ መጠን ለመወሰን ትቸገራለች ሲሉ አክለዋል። ከግድቡ ድርድር ታዛቢዎች መካከል አንደኛዋ ከሆነችው አሜሪካ ጋር ኢትዮጵያ ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲያብብ እንደምትፈልግ የተናገሩት ዲና ሆኖም ጫና የማሳደር ሙከራዎችም አንቀበልም ሲሉ ተናግረዋል። "ከአሜሪካ ጋር ያለን ግንኙነት ታሪካዊ ነው፤ ረጅምም ግንኙነት ነው፤ በርካታ ነገሮችን አብረን ሰርተናል" ያሉት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት "እንንከባከበዋለን፤ እንዲያድግ ነው የምንፈልገው፤ እንዲበላሽ አንፈልግም።" ኢትዮጵያ ዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረውንም ድርድር ያቋረጠችበት ምክንያት በግብጽ ፍላጎት ታዛቢ እንዲሆኑ የገቡት አሜሪካና የዓለም ባንክ ለግብጽ ከመወገን አልፈው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ላይ ጫና ለማሳደር ሞክረዋል በማለት ኢትዮጵያ መውቀሷ የሚታወስ ነው። አሜሪካ፣ የዓለም ባንክ ከግብጽ ጎን ቆመው ነበር በተባለው በዚህ ድርድር ላይ ከመጀመሪያው ሙሌት በኋላ ኢትዮጵያ ለምትጠቀመው ውሃ ለግብጽ የተጠራቀመ የውሃ ጉድለት ማካካሻ እንድትሰጥ የሚያስገድድ እንደሆነም ተገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ የግብጽ ሃሳብ በአባይ ወንዝ ላይ ተፈጥሯዊ መብት እንዳይኖራት ወይም ምንም ዓይነት የውሃ ልማት ያልተገነባበት ፍሰት እንዲኖር የሚጠብቅ ነው በማለትም ተችታለች ። በድርድሩ ላይ ግብፅ እና ሱዳን በተደጋጋሚ እየወጡ እየገቡ "ቢያሰለችም፣ [ድርድር] ተስፋ የሚቆረጥበት ጉዳይ አይደለም" ያሉት አምባሳደሩ በሚቀጥለው የሁለቱ አገራት ተደራዳሪዎች በጠየቁት መሰረት በጊዜያዊነት የተቋረጠው ድርድር ኢትዮጵያ ባቀረበችው የውኃ ሙሌት ደንብ ላይ ውይይት አድርገን እንመለስ በሚል ባሉት መሰረት ሰኞ እንደሚቀጥል እንጠብቃለን ሲሉ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በውሃ ሙሌቱ ላይ ያላትን ኃሳብ ብታቀርብም በተዛላቂ የውሃ ድርሻ እና አጠቃቀም ላይ ግን ሌላ ራሱን የቻለ ውይይት መደረግ ይገባዋል ብላ እንደምታምን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ግብፅ በኢትዮጵያ ዙርያ በሚገኙ አገራት ወታደራዊ የጦር መንደሮች ለማቋቋም እየጣረች ነው የሚሉ ዘገባዎች መሰራጨታቸውን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው አምባሳደር ዲና "ግብፅ እንደሉዐላዊ አገር ከፈለገችው አገር ጋር ግንኙነት መፍጠር ትችላለች፤ ከሶማሊላንድም፣ ከሶማሊያም፣ ከሱዳንም ጋር። እነርሱ የሚፈጠሩት ግንኙነት ግን በኢትዮጵያ ኪሳራ መሆን የለበትም። በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ፣ በኢትዮጵያ ነፃነት ላይ፣በኢትዮጵያ ደህንነት ላይ ያነጣጠረ መሆን የለበትም" ሲሉ መልሰዋል። "ይህንን ለሶማሊላንድም አስረግጠን ነው የምንነግራቸው፤ ለደቡብ ሱዳንም ለተቀሩትም አገራት።" ሲሉ አጠቃልለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በሊባኖሷ መዲና ቤይሩት በደረሰው ፍንዳታ የአንድ ኢትዮጵያዊ ሕይወት ሲያልፍ ሌሎች ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ እንደሚገኙ አምባሰደር ዲና ሙፍቲ አረጋግጠዋል። በትናንትናው ዕለትም ቢቢሲ በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመርንም ባናገረበት ከህይወት ማለፉ በተጨማሪ ህክምና እየተከታተለች የነበረች ኢትዮጵያዊት በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ እንደምትገኝም ገልጸዋል። በቤይሩት ውስጥ የሚኖሩ እና ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ህልውናቸው ላይ ስጋት የተጋረጠባቸው ኢትዮጵያዊያንን ለመታደግ የቆንስላ ፅህፈት ቤቱ ስራ እየሰራ መሆኑን ጨምረው የተናገሩት ዲና፣ በአሰሪዎች ደመወዝ ከመከልከል አንስቶ ጎዳና ላይ እስከመውጣት ድረስ ፈተናን እየተጋፈጡ ያሉ ስደተኞች መኖራቸውን ተናግረዋል። በፍንዳታው በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የሟቾችም ቁጥር መቶን የተሻገረ ነው።
41230028
https://www.bbc.com/amharic/41230028
በህንድ ጥቅም ላይ የዋሉ የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች ለምን ተፈለጉ?
የወር አበባ በህንድ ሀገር በተለይ በገጠራማ አካባቢዎች እንደ ነውር የሚቆጠር ነገር ነው። ስለ ወር አበባ መናገርም እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ተደርጎ ይቆጠራል። እንዲህ ባለ ሁኔታ ከህንድ ሴቶች ጥቅም ላይ የዋሉ የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች ን መሰብሰብ ምን ያህል ሊከብድ እንደሚችል አስቡት።
ነገር ግን በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት የተሰማሩ ተመራማሪዎች ይህንን ከመፈፀም ያገዳቸው ነገር አልነበረም። ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት ደግሞ የሚሰበስቡት ጥቅም ላይ የዋለ የንፅህና መጠበቂያ ጨርቅ የማህፀን በር ካንሰርን ለመመርመር እንዲያስችላቸው ነበር። በዓለማችን ካሉ የማህፀን በር ካንሰር ታማሚዎች ሩብ ያህሉ የሚገኙት በህንድ ሃገር ነው። እንዲያም ሆኖ በተለያዩ ምክንያቶች በርካታ ቁጥር ያላቸው ህንዳውያን ሴቶች አሁንም የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ አያደርጉም። የጤና ማዕከላት በአስፈላጊው መጠን አለመኖር እና ህክምናውን ለማግኘት የሚጠየቀው ከበድ ያለ ወጪ ሰዎች ምርመራውን እንዳያደርጉ ከሚያግዱ ምክንያቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑ በገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ህንዳውያን ሴቶች ከዘመናዊዎቹ የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች በተቃራኒ ቤት አፈራሽ ጨርቅን በወር አበባ ጊዜ ለንፅህና መጠበቂያነት ይጠቀማሉ። ተመራማሪዎች እንደደረሱበት ከሆነ እነዚህን ጥቅም ላይ የዋሉ የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች በመጠቀም የማህፀን በር ካንሰር አምጪ ቫይረስ መኖር አለመኖሩን ማረጋገጥ ይቻላል። ''በጣም ቀላል እና አመቺ መንገድ ነው" ይላሉ የምርምር ቡድኑ መሪ ዶክተር አቱል ባዱክ። ጨምረው ሲናገሩም "ምርምራችንን በድንብ እንዳናካሂድ ያገደን ነገር ቢኖር የሴቶች ፈቃደኛ አለመሆን ነው።'' ተመራማሪዎቹ እንደሚናገሩት የህንድ ሴቶች የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ የሚደርግላቸው በሌላ የጤና እክል ምክንያት ወደ ጤና ተቋም ሲመጡ ነው። ቀዘቃዛ ዘረ-መል ሁለት ዓመት ለሚፈጀው ምርምር ዕድሜያቸው ከ30-50 ዓመት የሆነ እና የካንሰር በሽታ የሌለባቸው 500 የሚሆኑ ሴቶች ተመርጠዋል። ተሳታፊዎቹ ሴቶች የወር አበባ ማየት በጀመሩ የመጀመሪያ ቀን የተጠቀሙበትን የንፅህና መጠበቂያ ጨርቅ በተሰጣቸው ባለዚፕ ቦርሳ ውስጥ እንዲያስቀምጡ እና በአካባቢው ላሉ የጤና ጥበቃ ሰራተኞች እንዲያቀብሉ ተነገራቸው። የተሰበሰቡት የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች ከ20 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ባነሰ ሙቀት ውስጥ እንዲቀመጡ ተደርጎ ወደ ምርምር ማዕከሉ ተላኩ። ዘረመሎቹ ከደረቁት የንፅህና መጠበቂያ ጨርቆች ላይ ከተወሰዱ በኋላ ምርመራው ተደረገ። በተገኘው ውጤትም ሃያ አራት ሴቶች የማህፀን በር ካንሰር አምጪ ቫይረስ እንዳለባቸው ታውቆ ለተጨማሪ የሕክምና እርዳታም ወደተሻለ የጤና ማዕከል ተላኩ። የመራቢያ አካላት ንፅህና የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው የመራቢያ አካላትን ንፅህና አለመጠበቅ ለማህፀን በር ካንሰር አምጪ ቫይረሶች መፈጠር እና መራባት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል። በ2011 የተደረገው የህንድ ህዝብ ቆጠራ እንደሚያሳየው 41 በመቶ የሚሆኑ ቤቶች መፀዳጃ ቤት የሌላቸው ሲሆን መፀዳጃ ቤት ካላቸው 16 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ጣራ የሌላቸው መፀዳጃ ቤቶች ናቸው። ዶክተር ባዱክ እንደሚያምኑት "በገጠር አካባቢዎች የመፀዳጃ ቤቶች እጥረት ስላለ ሴቶች የመራቢያ አካላቸውን ለማፅዳት ምቹ ቦታ የላቸውም።" ከዛም በላይ ጥቅም ላይ የዋሉ ጨርቆችን መልሶ መጠቀም ቫይረሱን እንደሚያባብሰው ዶክተር ባዱክ ያሳስባሉ። ከወር አበባ ጋር በተያያዘ ህንድ ውስጥ ያሉት ባህል እና እምነቶች ለተመራማሪዎቹ ሥራቸውን እጅግ ከባድ እንዲሆን አድርጎታል። የወር አበባ የሚያዩ ሴቶች ማዕድቤት ውስጥ እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም። ከዛም አልፎ በፀሎት ሥፍራዎች ላይ እንዳይኙና ሀይማኖታዊ ስርዓቶችን እንዳይካፈሉ ይደረጋሉ። ወደ መፍትሄው የማህፀን በር ካንሰርን መከላከያ መንገዶችን የሚያሳዩ የጤና ትምህርቶች በተለይ ደግሞ ለጎሳ መሪዎች፣ ከማህበረሰቡ ጋር በቅርበት ለሚሰሩ ሰራቶኞች እንዲሁም ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ማስተማር ሴቶች ከማህፀን በር ካንሰር ራሳቸውን እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል። ላቅ ሲልም የወር አበባን የተመለከቱ በጎ ያልሆኑ አመለካከቶችን ማስወገድ መቻል ለበሽታው አለመከሰት የራሱን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ጥናቱ ጠቁሟል። የጥናቱ አንድ ክፍተት ሆኖ የተመዘገበው የወር አበባ ማየት ያቆሙ እና ማየት ያልጀመሩ ሴቶችን አለማካተቱ ነበር። ዶክተር ባዱክ እንደሚጠቁሙት ግን ቢያንስ የወር አበባ የሚያዩ ሴቶችን በዚህ መንገድ የማህፀን በር ካንሰር እንዳለባቸው ከመለየት አልፎ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ማድረግ ተችሏል። እንደ አዲስ የማህፀን በር ካንሰር መመርመሪያ መሳሪያ ልትቆጥሩት ትችላላችሁ ይላሉ ዶክተሩ ሲያጠቃልሉ።
news-41847668
https://www.bbc.com/amharic/news-41847668
ሄግ ፍርድ ቤት የቀረበው የቀይ ሽብር ተከሳሽ ምስክሮችን እንዲያድኑት ተማፀነ
ኢትዮጵያ ውስጥ ከ40 ዓመት በፊት በተፈፀመው ''ቀይ ሽብር'' ወቅት ተሳታፊ ነበር ተብሎ ኔዘርላንድስ ውስጥ በጦር ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ የድርጊቱ ሰለባዎች ከክሱ ነፃ እንዲያወጡት ተማፀነ።
ኢትዮጵያን ለ17 ዓመታት የመራው እጅግ የሚፈራው ወታደራዊ ቡድን ደርግ አባል እንደነበረ ያመነው እሸቱ አለሙ፤ በፍርድ ቤቱ ውስጥ ከኋላው ተቀምጠው ወደነበሩት የቀይ ሽብር ሰለባዎች በመዞር ''እባካችሁ ከዚህ ነገር አድኑኝ። አዎ ድርጊቱ ተከስቷል፤ ቢሆንም ግን እኔ የለሁበትም። በቦታው አልነበርኩም'' ሲል ተማፅኗቸዋል። "ወንጀለኛ አይደለሁም። ከዚህ በኋላ መኖርም አልፈለግም" ሲልም ለሄግ ዳኞች ተናግሯል እሸቱ። ትናንት በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ አምስት ሰዎች ዘመዶቻቸውን ማጣታቸውን ለችሎቱ ተናግረዋል። ከእነዚህም መካከል አንዲት ሴት "በጣም ውብና ቅን ወንድሜ የት እንደገባ ሳላውቅ አጥቼዋለሁ" ስትል ምስክርነቷን ሰጥታለች። የሴትየዋ ጠበቃ ሁለት ያረጁ ፎቶዎችን በምስክረነት ለዳኞች አስረክቧል። እጅግ በሃዘን እንደተጎዳች የገለፀችው ምስክር "በስተመጨረሻም ፍርድ ሲሰጥ ለማየት በመብቃቴ ዕድለኛ ነኝ" ስትል ተደምጣለች። ሌላ የድርጊቱ ሰለባ ''በጨለማ ክፍል'' ውስጥ እንደታሰሩ እማኝነታቸውን ሰጥተው፤ 82 ሰዎች ሲገደሉ ማየታቸውን እና አስከሬናቸውም በአንድ የጅምላ መቃብር እንደተቀበረ ተናግረዋል። በቀጣይ ቀንም አሳሪዎቹ የተገደሉትን ሰዎች የጋብቻ ቀለበትና ልብሶቻቸውን ለብሰው እንዳዩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። እሸቱ አለሙ በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ተገደሉ በተባሉ 75 ሰዎች፣ ሰቆቃ በመፈፀም፣ በጅምላ እስር እና ከህግ ውጪ ሰዎችን በማሰርን የቀረቡበትን አራት የጦር ወንጀሎችን አልፈፀምኩም ብሏል። የፍርድ ሂደቱ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
news-55103339
https://www.bbc.com/amharic/news-55103339
የኩባ ፖሊስ የረሃብ አድማ አድራጊዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ
በኩባ አንድ የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ መታሰሩን በመቃወም የረሃብ አድማ ሲያደርጉ የነበሩ ሰዎችን ፖሊስ መክበቡ ተሰማ።
የረሃብ አድማውን የሚመራው ቡድን ቢሮን በመዲናዋ ሃቫና ፖሊስ ከከበበ በኋላ በአድማው የተሳተፉ የተባሉ አባላትን በቁጥጥር ስር አውሏል። ሳን ኢሲድሮ የተባለው እንቅስቃሴ ቡድን አራማጆችም እንደተናገሩት የተወሰኑት አባላሎቻቸው በፖሊስ እንደተደበደቡና መከበባቸውም ይፋ እንዳይሆን የማኅበራዊ ሚዲያቸውም እንደተዘጋ ገልፀዋል። ራፐር ዴኒስ ሶሊስ ከፖሊስ ጋር በገባው እሰጣገባ ምክንያት ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። የኩባ ባለስልጣናት ከበባው የተደረገው ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የተሰጠውን የጤና መመሪያን በመጣሳቸው ነው ብለዋል። የሳን ኢስድሮ እንቅስቃሴ በቅርቡ ዓለም አቀፍ እውቅናን ማትረፍ ችሏል። ከሁለት ዓመታት በፊት የተቋቋመው ይህ እንቅስቃሴ የአርቲስቶች፣ የሙዚቀኞች፣ የጋዜጠኞችና የምሁራን ስብስብን የያዘ ሲሆን የኩባ ኮሚዩኒስት መንግሥት ያደርሰዋል የሚሉትንም ጭቆናን ለመቃወም ነው። የቡድኑ አባላት ለቢቢሲ ሙንዶ እንደተናገሩት በመዲናዋ ሃቫና የሚገኘው ቢሯቸው በትናንትናው ዕለት በፖሊስ እንደተከበበ ነው። ሌሊትም ላይ በቁጥጥር ስር ከዋሉት 14 አባላቱ መካከል ሦስቱ ያሉበት እንደማይታወቅ ነው። የእንቅስቃሴው ስድስቱ አባላት ረሃብ አድማ ላይ ነበሩ። ቡድኑ ከፖሊስ ጋር በነበረው የቃላት እሰጣገባ ምክንያት ስምንት ወር እስር የተፈረደበት ራፐር እንዲለቀቅ እየጠየቀ ነው። የኩባ ባለስልጣናት ባወጡት መግለጫ ሳን ኢስድሮን ቢሮ የከበቡት ካርሎስ ማኑኤል አልቫሬዝ የተባለ ጋዜጠኛ የኮሮናቫይረስ መመሪያን በመጣስ በህንፃው ውስጥ በተቃውሞ በመሳተፉ ነው። "እርምጃው የተወሰደው በሕጉ መሰረት ነው። የማንኛውንም ዜጋም ሆነ ተሳታፊዎችን መብት አልጣስንም" ይላል መግለጫው። ሳን ኢስድሮ በበኩሉ በሰጠው ምላሽ "የማይረባ ሽፋን" ብሎታል። ሳን ኢስድሮ ጥበብና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን በማጣመር ውዝግብንም መፍጠር የቻለ ቡድን ነው። ማይክል ካስቲሎ የተባለው የቡድናቸው አባል ፖሊስ ለጥያቄ ሲፈልገው ተቃውሞውን ለማሳየት "አፉን ሰፍቶ" ነበር። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ሆኑ የአሜሪካ መንግሥት ዴኒስ ሶሊስ እንዲፈታና መንግሥት ከሳን ኢስድሮ እንቅስቃሴ አራማጆች ጋር ውይይት እንዲያደርግም ጠይቀዋል። የኩባ መንግሥት በበኩሉ ሳን ኢስድሮ መንግሥትን ለመገልበጥ ከአሜሪካ ተልዕኮን ያነገበና በገንዘብ የሚደገፍ ነው ይላል። ሳን ኢሲድሮ በበኩሉ ይህንን ውንጀላ አይቀበለውም።
52397464
https://www.bbc.com/amharic/52397464
ኮሮናቫይረስ፡ የእስራኤል ፖሊስ በዜጎች እንቅስቃሴ ላይ በስልክ የሚያደርገውን ክትትል አቋረጠ
የእስራኤል ፖሊስ ዜጎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋትን ለመከላከል የተቀመጠውን የእንቅስቃሴ ገደብ በትክክል መተግበር አለመተግበራቸውን ለመከታተል ስልካቸው ላይ የሚገኙበትን አቅጣጫ ጠቋሚ እንዳይጠቀም ታገደ።
እገዳው የመጣው ከግል ደህንንት ጋር በተያያዘ መሆኑ ተሰምቷል። የእስራኤል መንግሥት እንዲህ አይነት ክትትል እንዲያደረግ የተፈቀደው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው የተባለ ሲሆን ይህም ራሳቸውን ነጥለው እንዲቀመጡ የሚጠበቅባቸው ዜጎች በትክክል መተግበራቸውን ለመከታተል ነበር ተብሏል። • "በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ የዜጎች ሰብዓዊ መብት መጣስ የለበትም" ኢሰመኮ • ኮሮናቫይረስን የሚፈውስ መድኃኒት መቼ ይገኛል? • ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ለረሃብ ከተጋለጡ 5 አገራት መካከል ናት ተባለ አሁን ግን የእስራኤል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን ክትትል ለማራዘም የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ አግዶታል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አባል የሆኑ አንድ ግለሰብ ከጥቅሙ ይልቅ የግል ደህንነት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት አመዝኖ አግኝተነዋል ብለዋል። ፖሊስ የእንቅስቀቃሴ ገደቡን ጥሰው የተገኙ 203 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የገለፀ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የተወሰኑት በስልካቸው በተደረገ ክትትል መያዛቸውን ተናግሯል። ነገር ግን በምክር ቤቱ የውጪ ጉዳይና የመከላከያ ኮሚቴ አባል የሆኑት አይለት ሻኬድ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ፣ "ቤታቸው እንዲቀመጡ የተነገራቸውን ዞረን ተመልክተናል ብዙዎቹ እየተገበሩት ነው" ብለዋል። የእንቅስቃሴ ገደቡን የሚከታተለውን ኮሚቴን የሚመሩት ጋቡ አሻክናዚ እንዳሉት መንግሥት ከተነሱት ነጥቦች አንጻር ህጉ ላይ የተቀመጡ አገላለጾችን የሚከልስ ሲሆን ለአሁን ግን ህጉ ተነስቷል ብለዋል። በእስራኤል ንክኪን ለመለየት የሚያገለግለው ፕሮግራም ግን አሁንም በስራ ላይ መሆኑ እየተገለፀ ነው። ይህ የኮቪድ-19 ካለባቸው ሰዎች ጋር ያሉ ንክኪዎችን ለመለየት የሚያገለግለው ፕሮግራም፣ ሺን ቤት፤ የእስራኤል ደህንንት አገልግሎቱ ይሳተፍበታል ተብሏል። ባለፈው ወር ስሎቫኪያ የስልክ አቅጣጫ ጠቋሚ በለይቶ ማቆያ ያሉ ሰዎችን ለመከታተል አንዲውል የሚፈቅድ ሕግ አጽድቃለች። የአውሮፓ የግለሰብ ደህንነትና የአጠቃላይ መረጃ አያያዝ ደንብ ለማህበረሰብ ጤና ሲባል በስልክ የሚደረግን ክትትል አይከለክልም። ነገር ግን ባለስልጣናት ከአንድ ሰው ጋር ያለውን ንክኪ ለመለየት የሚወሰዱ እርምጃዎች የግለሰቡን ደህንናትና መብቶች ማክበር አለባቸው ይላሉ። በርካታ አገራት ሰዎችን በስልካቸው ለመከታተል ብሉቱዝ ለመጠቀም እያሰቡ ነው። አፕልና ጉግልም በጋራ ሶፍትዌር እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
56659416
https://www.bbc.com/amharic/56659416
ኡጋንዳና ግብጽ የወታደራዊ ደኅንነት መረጃ ልውውጥ ስምምነት ተፈራረሙ
ኡጋንዳና ግብጽ ወታደራዊ የደኅንነት መረጃዎችን ለመለዋወጥ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተዘገበ።
ስምምነቱ የተፈረመው በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ለዓመታት የዘለቀው ድርድር አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ወቅት ነው። የኡጋንዳ ሕዝብ መከላከያ ኃይል ባወጣው መግለጫ ስምምነቱ የተፈፀመው በሁለቱ አገራት ወታደራዊ ደህኅነት ከፍተኛ ባለስልጣናት አማካኝነት በያዝነው ሳምንት ረቡዕ ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ነው። "እውነታው ኡጋንዳና ግብጽ የናይልን ወንዝ የሚጋሩ አገራት ናቸው። በሁለቱ አገራት መካከል ያለ ትብብር ሊቀር የሚችል አይደለም። ኡጋንዳ ላይ ተፅእኖ የሚያደርስ ጉዳይ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ግብጽ ላይ ተመሳሳይ ሁኔታ መፍጠሩ አይቀርም" በማለት ወደ ኡጋንዳ አቅንቶ የነበረው የግብፍ ደኅንነት ኃላፊውን ጄኔራል ሳሜህ ሳበር ኤል ደግዊን ዋቢ አድርጎ በመግለጫው አትቷል። የህዳሴ ግድብ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ለአመታት ያህል ከፍተኛ ውጥረት መንስኤ ሆኗል። በባለፈው አመት ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አወዛጋቢ የተባለውን ግብፅ የህዳሴ ግድብን ልታፈነዳው ትችላለች በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል። ኢትዮጵያ ይህንን የሃይድሮኤሌክትሪክ ግድብ ቁልፍ የሆነ የኃይል ምንጭ እንደሆነና አገሪቷ ለምታደርገው ኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረቴ ነው ትላለች። የታችኛው ተፋሰስ አገራት ግብፅና ሱዳን በበኩላቸው አራት ቢሊዮን ዶላር የወጣበት ይህ ግድብ ወደ አገራቱ የሚፈሰውን ውሃ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሰዋል በማለት ይሰጋሉ። የአባይ ወንዝ ከሁለት አገራት የሚነሳ ሲሆን አንደኛውና ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ጥቁር አባይ መነሻና ገባሪ ኢትዮጵያ ስትሆን የነጭ አባይ ምንጭ ደግሞ ኡጋንዳ ናት። ለዓመታት ሲደረግ የነበረው የሦስትዮሽ የሕዳሴ ግድብ ድርድር ከሰሞኑም ያለምንም ፍሬ ተቋጭቷል። በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስርና በዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ትሽሴኬዲ አሸማጋይነት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ባለመግባባት የተቋጨው በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ነበር። ግብጽ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ የተለያዩ አገራት ከጎኗ እንዲቆሙ በተለያየ መልኩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ከዚህ ቀደም በግድቡ ዙሪያ እምብዛም ተቃውሞ አሰምታ የማታውቀው ሱዳን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከግብጽ ጋር የሚቀራረብ ሀሳብ ስታንጸባርቅ እንደነበር ተነግሯል። ከቅርብ ወራት ወዲህም ከሱዳን ጋር የወታደራዊ ትብብር ስምምነት የተፈራረመችው ግብጽ ከተለያዩ የተፋሰሱ አገራት ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር እጣረች ትገኛለች። ከኡጋንዳ ጋር የደረሰችው ስምምነትም የዚሁ ጥረቷ አንድ አካል እንደሆነ ይታመናል።
news-54068173
https://www.bbc.com/amharic/news-54068173
ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መጨመር እንዳሳሰባት ገለፀች
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ደቡብ ሱዳን እንዳሳሰባት ገልፃለች።
መጋቢት ወር ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጀምሮ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመጣባት ኢትዮጵያ በባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳኗ መዲና ጁባ በየቀኑ ከአዲስ አበባ በረራ የሚያደርግ ሲሆን ይሄም ሁኔታ አስጊ ነው በማለት የጤና ባለስልጣናቱ ተናግረዋል። "በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በእርግጥ ሊያሳስበን ይገባል፤ ስለዚህ የመከላከያ መንገዶቻችንንም ልናጠናክር ይገባል" በማለት የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ዶክተር ቶው ሎይ ሲንጎት በጁባ ለሚገኙ ሪፖርተሮች ተናግረዋል። ሆኖም ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ በየቀኑ የሚደረጉት በረራዎችም እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ቃለ አቀባይ ሁሉም አገራት ለዜጎቹ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደረገው ከፍተኛ ጥንቃቄን ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል። "ከአዲስ አበባ የሚደረጉ የየቀኑ በረራዎች የሚቀጥሉ ይሆናል። አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ አይቆምም" ብለዋል ዶክተር ቶው ሎይ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ደርሷል፤ ከነዚህም ውስጥ 21 ሺህ 789 ያገገሙ ሲሆን 933 ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው ዕለት የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጋራ መግለጫ አስፍሯል።
news-56877326
https://www.bbc.com/amharic/news-56877326
የእንግሊዝ እግር ኳስ ክለቦች ማሕበራዊ ሚድያን ጥለው ሊወጡ ነው
የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ፣ እንግሊሽ ፉትቦል ሊግ እና የሴቶች ሱፐር ሊግ ክለቦች ለአራት ቀናት ከማሕበራዊ ድር አምባዎች ራሳቸውን ሊያገሉ ነው።
ክለቦች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ የሚታዩ ብዘበዛዎችና ማግለሎችን በመቃወም ነው። አድማው የሚጀምረው ከአምስት ቀናት በኋላ ሚያዚያ 22 ነው። የእግር ኳስ ማሕበር፣ እንዲሁም ሌሎች ይመለከተናል የሚሉ መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ ኪክ ኢት ኦፍ የተባለው ፀረ-ማግለል ድርጅት በዚህ አድማ ላይ ይሳተፋሉ። የኪክ ኢት ኦፍ ሊቀመንበር ሳንጃይ ባንዳሪ "ይህ አድማ ምን ያክል እንደመረረን የሚያሳይ ነው" ይላሉ። "ማሕበራዊ ድር አምባ አሁን አሁን በጣም መርዛማ ለሆኑ ብዝበዛዎች የተጋለጠ ሆኗል ።" እኛ አንድ ላይ ሆነን ይህን አድማ የምንመታው ሥልጣኑ ላላቸው መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። እርምጃ እንድትወስዱ እንፈልጋለን። ለውጥ እንድታመጡ እንሻለን።" ሊቀ መንበሩ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ፊታቸውን ደብቀው ለሚበዘብዙ ሳይሆን ለእግር ኳሱ ቤተሰቡ ነው የተመቸ ሊሆን የሚገባው ሲሉ ይሞግታሉ። ባለፈው ዓመት የቆዳ ቀለሙን አስመልክቶ ብዝበዛ የደረሰበት የሼፊልድ ዩናይትዱ ዴቪድ ማክጎልድሪክ "ጊዜው አሁን ነው" ይላል። "በእኔ ላይ የደረሰው በሌሎች በርካታ ተጫዋቾች ላይ ደርሷል። የሆነ ነገር ሊፈጠር ይገባዋል። የቆዳ ቀለምን መሠረት አድርጎ ጥቃት ማድረስ ለብዙዎች ቀላል ነው።" ጎልድሪክ ትላንት [ቅዳሜ] ምሽት ከብራይተን ጋር በነበረው ጨዋታ አንድ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑ እንዲያሸንፍ አስችሏል። ተጫዋቹ ከግጥሚያው በኋላ በሰጠው አስተያየት "ሱፐር ሊግን በ48 ሰዓታት አስወገድን። ዘረኝነት መርታት ያቃተን ለምንድነው?" ሲል ጠይቋል። የብራይተኑ ፈረንሳዊ አጥቂ ኒል ሞፔም በተመሳሳይ ማሕበራዊ ድር አምባው ላይ ጥቃት ደርሶበታል። ተጫዋቹ ለስካይ ስፖርት በሰጠው ድምፅ "አድማው ትክክለኛ ነው" ሲል ተደምጧል። "ተጫዋቾች በይነ መረብ ላይ ብዙ ጥቃት ይደርስባቸዋል። ይህን መዋጋት አለብን። አሁን አንድ ላይ መሆናችን መልካም ነገር ነው።" ክለቦችን ጨምሮ አስተዳዳሪ አካላት እንዲሁም የእግር ኳስ ዳኞች ማሕበር ከትዊተር፣ ፌስቡክና ኢንስታግራም ራሳቸውን ለአምስት ቀናት ለማግለል ተስማምተዋል። ከሳምንታት በፊት ስዋንሲ ሲቲ የተሰኘው ቡድን ተጫዋቾቹ ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የአንድ ሳምንት አድማ አድርጎ ነበር። ሌላኛው የቻምፒዮንሺፕ ቡድን በርሚንግሃም ሲቲና የስኮትላንዱ ሬንጀርስም ማሕበራ ድር አምባው ላይ አድማ መትተው ነበር። የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ፈረንሳዊው ቲዬሪ ሄንሪ በዘረኝነትና በሌሎች ጥቃቶች ሳቢያ ከማሕበራዊ ድር አምባዎች ራሱን ሙለ በሙሉ ማግለሉን ማስታወቁ አይዘነጋም። ከቢቢሲ ጋር ቆይታ የነበረው የ43 ዓመቱ ሄንሪ "በቃ ማለት በቃ ነው" ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። ሊቨርፑል ሶስቱ ጥቁር ተጫዋቾቹ አሌክሳንደር-አርኖልድ፣ ናቢ ኬታና ሳዲዮ ማኔ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ቁጣውን መግለፁ ይታወሳል። አድማ መቺዎች ዓላማቸው ማሕበራዊ ድር-አምባዎች ጥላቻን እንዲያስወግዱና ትምህርትም እንዲሰጡ መሆኑን በመግለጫቸው አትተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ትላልቅ የማሕበራዊ ድር አምባ ኩባንያዎች ችግሩን መቅረፍ ካልቻሉ ቅጣት እንደሚጥል ዝቶ ነበር። ፌስቡክ የካቲት ላይ ከበድ ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንዳሰበ አስታውቆ ነበር። በፌስቡክ የሚተዳደረው ኢንስታግራም ደግሞ ባለፈው ሳምንት ተጠቃሚዎች ጓደኞቻቸው ያልሆኑ ሰዎች መልዕክት እንዳይልኩላቸው የሚያስችል መንገድ አምጥቻለሁ ብሏል።
news-53695034
https://www.bbc.com/amharic/news-53695034
የፌስቡክ ዛከርበርግ ሃብት 100 ቢሊዮን ዶላር ገባ
የፌስቡክ ፈጣሪ ማርክ ዛከርበርግ ሃብት 100 ቢሊዮን ዶላር ገባ።
ማርክ ዛከርበርግ የዛከርበርግ ሃብት ጣሪያ የነካው አዲስ የተንቀሳቃሽ ምስሎች መጋሪያ ገፅ ያለው ቴክኖሎጂ ኢንስታግራም ላይ ተግባራዊ ካደረገ በኋላ ነው ተብሏል። አዲሱ ቴክኖሎጂ አነጋጋሪውን የቻይና አፕ ቲክ ቶክን ለመቀናቀን የመጣ ነው ተብሏል። ረቡዕ ዕለት ፌስቡክ፤ 'ኢንስታግራም ሪልስ' የተሰኘውን አዲስ ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል። በቀጣዩ ቀን ሐሙስ የፌስቡክ የገበያ ድርሻ በ6 በመቶ ማደጉ ተሰምቷል። ዛከርበርግ የፌስቡክን 13 በመቶ የገበያ ድርሻ ይቆጣጠራል። ማርክ ዛከርበርግ፣ የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ እና የማይክሮሶፍት ፈጣሪ የሆነው ቢል ጌትስን በመከተል 'ሴንቲቢሊየነር ክለብ' [ሃብታቸው ከመቶ ቢሊዮን በላይ የሆነ] የተሰኘውን ቡድን ተቀላቅሏል። የቴክኖለሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እያካበቱ ባሉት ሃብት ስማቸው የመገናኛ ብዙሃን አፍ ማሟሻ ሆኗል። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ትርፋማነታቸው ከጨመረ ድርጅቶች መካከል ፌስቡክ፣ አማዞን፣ አፕልና ጉግል ይጠቀሳሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት በርካቶች ቤታቸው በመቀመጣቸው ግብይትም ሆነ የሚፈልጓቸውን ነገሮች በበይነ መረብ አማካይነት በማድረጋቸው ነው። የዛከርበርግ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ22 ቢሊዮን ዶላር ጨምሯል። የአማዞን ፈጣሪ የሆነው ጄፍ ቤዞስ ደግሞ 75 ቢሊዮን ዶላር አፍሷል ሲል ብሉምበርግ አስነብቧል። ሪልስ የተሰኘው የፌስቡክ አዲስ ቴክኖሎጂ በቻይናውያን ከሚተዳደረው ቲክ ቶክ ጋር ለመቀናቀን የመጣ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ቴክኖሎጂው የፌስቡክ ንብረት በሆነው ኢንስታግራም ላይ የተካተተ አዲስ ገፅ ነው። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቲክ ቶክን አግዳለሁ እያሉ በሚዝቱበት ወቅት ይህ ቴክኖሎጂ ይፋ መሆኑ ዛከርበርግ ትርፋም እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል። ቢሆንም ዛከርበርግና ሌሎች ጉምቱ ቢሊየነሮች ኃይላቸው ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው ተብለው በአሜሪካና በአውሮፓ ሕብረት መንግሥታት ይተቻሉ። አምስቱ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ማለትም አፕል፣ አማዞን፣ አልፋቤት፣ ፌስቡክና ማይክሮሶፍት ያላቸው የገበያ ድርሻ የአሜሪካን ጠቅላላ ምርት 30 በመቶ መሸፈን የሚችል ነው። የአሜሪካው ሴናተር በርኒ ሳንደርስ ለምርጫ በሚወዳደሩበት ወቅት ፕሬዝደንተ ከሆነ እኒህን ትላልቅ ኩባንያዎች በደንብ እቀርጣለሁ ማለታቸው አይዘነጋም። ሳንደርስ ከቢሊየነሮቹ የሚቀረጠው ገንዘብ መከፍል ለማይችሉ አሜሪካውያን የሕክምና ወጭ ይሆናል ብለው ነበር። ዛከርበርግ በአንድ ወቅት ከፌስቡክ ድርሻ 99 በመቶውን ለተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች እሰጣለሁ ብሎ ነበር።
news-56867425
https://www.bbc.com/amharic/news-56867425
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከሩብ ሚሊዮን አለፈ
በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ከተረጋገጠ በኋላ ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጠባቸው ሰዎች ቁጥር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሆነ።
ወረርሽኙ ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ መገኘቱ የተረጋገጠው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የነበረ ሲሆን እነሆ ከአንድ ዓመት ከአንድ ወር በኋላ የኮቪድ-19 ቫይረስ የተገኘባቸው አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ250 ሺህ ማለፉ ታውቋል። የጤና ሚኒስቴርና የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት በየዕለቱ ስለበሽታው አጠቃላይ ሁኔታ የሚያወጡት ሪፖርት ቅዳሜ ሚያዝያ 16/2013 ዓ.ም ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ በሽታው የተገኘባቸው አጠቃላይ ሰዎችን አሃዝ 250,955 ደርሷል። በኢትዮ በወረርሽኙ የተያዘ የመጀመሪያው ሰው መገኘቱ ይፋ የተደረገው መጋቢት 04/2012 ዓ.ም ሲሆን ከዚያ በኋላ በነበሩት ቀናት ውስጥ በተደረጉ ምርመራዎች የተለያዩ ቁጥሮች ያላቸው ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ሲገኙ ቆይቶ እነሆ ከዓመት በኋላ አሃዙ ከ250 ሺህ ተሻግሯል። በዚህ መሠረት ከመጋቢት 04/2012 ዓ.ም አስከ ሚያዝያ 16/2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት 408 ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ቀን በአማካይ ከ615 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ይህ ቁጥር አሁን ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሆኗል። ይህ ቫይረሱ ያለባቸው አጠቃላይ ሰዎች አሃዝ የተገኘው በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 2 ሚሊዮን 544 ሺህ 095 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ካደረጉት ላይ ነው። ከእነዚህ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የኮቪድ-19 ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች 57 ሺህ 409 ሲሆኑ አብዛኞቹ ወይም 190 ሺህ 013 የሚሆኑት ከበሽታው ማገገማቸውን የአገሪቱ ጤና ጉዳዮች ተቋማት ያወጡት መረጃ አመለክቷል። ከዚህ ውጪ በወረርሽኙ በአሁኑ ጊዜ በጽኑ ታመው ህክምና እየተደረገላቸው ያሉ ሰዎች ቁጥር 987 ሲሆን አስከ ሚያዝያ 16/2013 ዓ.ም ድረስ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ 531 ደርሷል። ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ኮቪድ-19 የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከሩብ ሚሊዮን ማለፉ በአፍሪካ ወረርሽኙ የተገኘባቸው በርካታ ሰዎች ካሉባቸው አገራት ከቀዳሚዎቹ ውስጥ እንድትገኝ አድርጓታል። የአፍሪካ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል መረጃ እንደሚያመለክተው ከደቡብ አፍሪካ፣ ከሞሮኮ፣ ከቱኒዚያ ቀጥሎ ኢትዮጵያ በርካታ ቫይረሱ የተገኘባት አራተኛ አገር ሆናለች። በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በአጠቃላይ 4 ሚሊዮን 488 ሺህ 320 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የተመዘገበ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 4 ሚሊዮን 29 ሺህ 494 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአህጉሪቱ ውስጥ በሽታው ከተከሰተ በኋላ 119,645 የሚሆኑ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ለሞት መዳረጋቸውን የማዕከሉ መረጃ ያመለክታል። አስካሁን በዓለም ዙሪያ 146 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት በወረርሽኙ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ያመለክታል።
48470898
https://www.bbc.com/amharic/48470898
ቤተሰብና ጓደኛ የሚያከራየው ድርጅት
ጃፓናዊው ዩሺ ኢሺ 38 ዓመቱ ነው። በልጅ ብዛት ከእድሜ እኩዮቹ መካከል የሚወዳደረው የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ዩሺ ኢሺ 25 ቤተሰቦችና 35 ልጆች አሉት። እንዴት? ማለት ጥሩ. . . • አራት ህጻናትን በአንዴ ያገኘው ቤተሰብ ተጨንቋል ዩሺ፤ ከአስር ዓመት በፊት የመሰረተው 'ፋሚሊ ሮማንስ' የተባለ ድርጅት ያልተለመደ አገልግሎት ይሰጣል- ቤተሰብና ጓደኛ የማከራየት። ድርጅቱ 2,200 ተቀጣሪዎች አሉት። ሥራቸው ደግሞ እንደ አባት፣ እናት፣ አጎት፣ አክስት ወይም አያት ሆኖ መተወን ነው። እነዚህ ሠራተኞችና ዩሺ 'ቤተሰቦች' እና 'ልጆች' ያፈሩትም በቅጥር ነው። የኪራይ ቤተሰብና ጓደኛ ከዩሺ ጓደኞች አንዷ ልጇን መዋለ ህፃናት ለማስገባት ስትሞክር፤ ትምህርት ቤቱ ለልጇና ለባለቤቷ ቃለ መጠይቅ ማድረግ እንደሚፈልግ ተነገራት። የትዳር ጓደኛ ስላልነበራት ዩሺን 'ባሌ ነው' ብላ ለቃለ መጠይቅ ወሰደችው። ዩሺና ልጁ አንዳችም ትስስር ስለሌላቸው እንደአባትና ልጅ መተወን አልቻሉም። ዩሺ፤ ብዙ ሰዎች ቤተሰብ ወይም ጓደኛ በማጣት እንደሚቸገሩ የተገነዘበበት ወቅት ነበር። 'ፋሚሊ ሮማንስ' የተባለውን የቤተሰብና ጓደኛ አከራይ ድርጅት የወጠነውም በዚህ አጋጣሚ ነበር። "የውሸት ቢሆንም ለጥቂት ሰዓታት ጓደኛችሁ ወይም ቤተሰባችሁ መሆን እችላለሁ" ይላል። • ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ለአራት ሰዓት ለመከራየት ወደ 5ሺህ ብር ይከፈላል ዩሺ በየአይነቱ ደንበኞች አሉት። ብዙዎች የኪራይ እናትና አባት ወይም ጓደኛ ይሻሉ። የኪራይ ቤተሰብ ሲቀጠር፤ የግለሰቡ ገጽታና ተክለ ሰውነት ከግምት ውስጥ ይገባል። 'ልጄ ነው' ከሚሉት ሰው ጋር መመሳሰል አለባቸውና። • ሶሻል ሚድያ በተጠቃሚዎች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ? ጓደኛ ከሌለዎት ከማን ጋር ላውራ? ከማንስ ጋር ልንሸራሸር? ብለው መጨነቅ የለብዎትም። በዩሺ ድርጅት የሚከራዩት 'ጓደኛ' አብሮዎት ይበላል፣ ይጠጣል። ማውራት፣ ሸመታ መውጣትና መንሸራሸርም ይቻላል። ልጅ ወይም የልጅ ልጅ የሚከራዩ የእድሜ ባለጸጋዎችም አሉ። ከልጆቻቸው ጋር ያሳለፉትን ውብ ጊዜ ለማስታወስ አልያም የሌላቸውን 'ልጅ' ለመተካት። ለልጆቻቸው አባት የሚከራዮ እናቶችም አሉ "የ 'አባት' ተከራዮች ቁጥር ጨምሯል" ዩሺ እንደሚለው፤ በእጅጉ ከሚፈለጉ ሚናዎች አንዱ 'አባትነት' ነው። ጃፓን ውስጥ በየዓመቱ 200 ሺህ ሰዎች ስለሚፋቱ ብዙዎች ልጆቻቸውን ለብቻቸው ለማሳደግ ይገደዳሉ። ማኅበረሰቡ የተፋቱ ሰዎችን ያጥላላል። ልጅ ለብቻ ማሳደግም እምብዛም አይደገፍም። ታዲያ ዩሺ፤ በማኅበረሰቡ ለተገለሉ ሰዎች "ከለላ እንሰጣለን" ይላል። • ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች ደንበኞቹ የተለያየ አይነት ባህሪ ያለው 'አባት' ይፈልጋሉ። ቁጡ፣ ለስላሳ. . . እንደየምርጫቸው 'አባት' ይሰናዳላቸዋል። አንዳንዴ 'አባት' የሚቀጠርላቸው ህፃናት ነገሩ ትወና መሆኑን ለመገንዘብ እድሜያቸው ስለማይፈቅድ፤ ግለሰቡ የእውነትም ወላጅ አባታቸው እንደሆነ ያምናሉ። ተቀጣሪው ሥራውን ጨርሶ ሲሰናበታቸውም ለመለየት ይከብዳቸዋል። የ 'ፋሚሊ ሮማንስ' ተቀጣሪዎች 'ቤተሰብ' መሆን የሚችሉት ለአምስት ቤተሰብ ብቻ ነው። ዩሺ እስካሁን ለ25 ቤተሰቦች 'ቤተሰብ' ሆኖ ተውኗል፤ 35 ልጆች 'አባታችን ነው' ብለው ያምናሉ፤ 69 ሰዎች ደግሞ 'ዩሺ የቅርብ ጓደኛዬ' ነው ይላሉ። "አንዳንዴ የደንበኞቼን ቅጽል ስም ስለምረሳው ማስታወሻ እይዛለሁ" ይላል። • እናት አልባዎቹ መንደሮች 'ልጆቹን' ትምህርት ቤት ያደርሳል፤ የቤተሰብ ውይይት ይካፈላል. . . ሌሎችም የሚጠበቁበት ተግባራትን ያከናውናል። ሥራው እንደሌሎች ሙያዎች ባሻው ጊዜ እረፍት የሚወጣበት አይደለም። በቀን ከሦስት ሰዓት በላይ ማረፍ አይችልም። "ከእኩለ ለሊት አንስቶ ለሦስት ሰዓት አርፋለሁ። ፊልም አያለሁ፤ እስላለሁ።" ደንበኞቹ በገሀዱ ዓለምና በትወና መካከል ያለውን ልዩነት እንዳይዘነጉ ያስጠነቅቃል የእውነትና ውሸት መስመር የቱ ጋር ነው? ዩሺ አላገባም፤ አልወለደም፤ ትዳር መመስረትና ልጅ ማፍራትም አይፈልግም። አዲስ ቤተሰብ ቢመሰርት አሁን ካሉት 25 የውሸት ቤተሰቦች ጋር የሚጋጭ ይመስለዋል። "የእውነት ባገባ ደንበኞቼ ምን ይሰማቸዋል? ልጆች ብወልድም ከሀሰተኛ ልጆቼ ጋር የሚምታቱብኝ ይመስለኛል።" ዩሺ የሚነግደው ውሸት ነው። የእንጀራ ገመዱ የተዘረጋውም ማስመሰል ላይ ነው። ታዲያ ይህ የውሸት ዓለም ከገሀዱ ዓለም ጋር እንዳይጋጭ ከደንበኞቹ ጋር የሚስማሙባቸው መርሆች አውጥቷል። • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች የድርጅቱ ሠራተኞች የሚመሩባቸው ሕግጋት አሉ። ለምሳሌ ከደንበኞች ጋር መሳሳምና ወሲብ መፈጸም ክልክል ነው። እጅ ለእጅ መያያዝ ግን ይፈቀዳል። ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ለአራት ሰዓት ለመከራየት 180 ዶላር (ወደ 5ሺህ ብር ደገማ) ይከፈላል። ተከራዩ የሠራተኛውን የምግብና መጓጓዣ ወጪ መሸፈንም ይጠበቅበታል። ድርጅቱ "ከእውነት ደስታ ይበልጣል" በሚል መሪ ቃል ይተዳደራል። ሆኖም 'እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል' እንዲሉ እውነት አንድ ቀን መገለጧ አይቀሬ ነው። ዩሺ እንደሚለው፤ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን እስከወዲያኛው መዋሸት አይገባቸውም። የሰዎች ግንኙነት በላላበትና በጋራ መኖር ፈታኝ በሆነበት ማኅበረሰብ ውስጥ እንደ 'ፋሚሊ ሮማንስ' ያለ ድርጅት እንደሚያስፈልግ ያምናል። በተለይም ጃፓናዊያን፤ ሰዎች ስለነሱ ያላቸው አስተያየት ስለሚያስጨንቃቸው በድርጅቱ ከመገልገል ወደኋላ አይሉም። "የምንፈልገውን መሆን ይከብዳል። ራሳችንን ባሻን መንገድ መግለጽም ቀላል አይደለም። ማኅበሰረሱ የኛን አገልግሎት የማይሻበት ዓለም ቢፈጠር መልካም ነበር። ሆኖም እውነታው ከዚህ የራቀ ነው።"
47534783
https://www.bbc.com/amharic/47534783
ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓውያኑ በ1945 ሥራ የጀመረው በአሜሪካ ሠራሽ አውሮፕላኖች ነበር። በጊዜው አየር መንገዱን ከከፈቱት ዐፄ ኃይለሥላሴ ጋር በተደረገ ስምምነት አየር መንገዱ ያቋቋመው ዛሬ ላይ ገበያ ላይ የሌለው የአሜሪካኑ TWA (Trans World Aviation) ነበር።
ከ15 ዓመታት በላይ ስለ አቬየሽን ኢንዱስትሪ የዘገበው የሪፖርተር ጋዜጠኛ ቃለየሱስ በቀለ ኢትዮጵያ አየር መንገድና ቦይንግ ከ60 ዓመት በላይ የዘለቀ የንግድ ግንኙነት እንዳላቸው ይናገራል። "ለምሳሌ እንደ አውሮፓውያኑ በ1960ዎቹ D720 የመጀመሪያው ጀት ኤንጅን ያለው አውሮፕላንን መጀመሪያ ወደ አፍሪካ ያመጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው።ከዚያም ቦይን 707፣ 727፣737፣ 757፣ 767ን አስመጥቷል።" ሲል ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ 747 ውጭ ሁሉንም የቦይንግ አውሮፕላኖች እንደተጠቀመ ይገናገራል። የጦር ኃይሎችን አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ ለመንደርደሪያ በቂ ስላልነበር የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መገንባትም ከቦይንግ ጋር የሚያስተሳስረው የታሪክ ቅንጣት እንዳለው ይጠቅሳል። • ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው ቃለ እየሱስ እንደሚለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 ፣ ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላኖችን ወደ አፍሪካ በማምጣት የመጀመሪያው ነው። ወደ አፍሪካም ብቻ ሳይሆን ከሁለቱ የጃፓን አየር መንገዶች ቀጥሎ ከአሜሪካ አየር መንገዶች በፊት ቦይንግ 787ን ዓለም ላይ የተጠቀመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደሆነም ያስረዳል። ለምሳሌ እንደ ቦይንግ 707 እና 727 ያሉ የኩባንያው ሥሪት አሮጌ አውሮፕላኖች አሁን ከገበያ መውጣታቸውን በመጥቀስ ቃለየሱስ አውሮፕላን አምራቾች በየጊዜው የሚሻሻሉ አውሮፕላኖችን ከብዙ ጥናትና ምርምር በኋላ እንደሚያወጡ ይናገራል። አውሮፕላኖቹ ሲሻሻሉ ደግሞ በዋናነት የነዳጅ አጠቃቀምና የመንገደኛ ምቾት ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች ናቸው። "የአንድ አየር መንገድ ትልቁ ወጪ ማለትም ከ40 በመቶ በላይ ነዳጅ ስለሆነ አዳዲስ አውሮፕላኖች በተለይ ነዳጅ የሚቆጥብ እንዲሆኑ ይፈለጋል።" ከትናንት ወዲያ የተከሰከሰው ቦይንግ 737-8 ማክስ በዚህ ረገድ ከ10-12 ከመቶ ነዳጅ ቆጣቢ እንደሆነ ይነገርለታል። ይህ አውሮፕላን ሥሪት በቦይንግ ታሪክ ብዙ ገበያን ያገኘና በ737 ሞዴሎች ዝርዝር ውስጥ የመጨረሻውና እጅግ ዘመናዊው ነው። የንግድ አውሮፕላን ኾኖ ወደ ገበያ የገባውም እንደ ፈረንጆቹ በ2016 ነበር። በእነዚህ ሁለት የአገልግሎት ዓመታት ውስጥ ታዲያ አውሮፕላኑ ሁለት ጊዜ አደጋ አጋጥሞታል። ከአምስት ወራት በፊት በኢንዶኔዥያ ጃካርታ ያጋጠመው አደጋ የመጀመርያው ሲሆን የእሑዱ ሁለተኛው መሆኑ ነው። አውሮፕላኖቹ በተነሱ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መከስከሳቸው ሁለቱን አደጋ እንደሚያመሳስለው ይገልፃል። የአደጋው መንስኤ ምርመራ ተደርጎ በሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን እስኪገለፅ እንዲህ ነው፣ እንዲያ ነው ብሎ መገመትን ዓለም አቀፉ የሲቪል አቬሽን ድርጅት ስለሚከለክል የመቆጠብ ነገር ቢኖርም "በኢንዶኔዥያውና በአሁኑ የኢትዮጵያ አደጋ ከበረራ መቆጣጠሪያ ጋር የተያያዘ ችግር ያለ ይመስላል" ሲል ቃለየሱስ የሩቅ ግምቱን ያስቀምጣል። ዓለም ዓቀፍ የአቬሽን ኤክስፐርቶችም በስፋት እየገለጹ ያሉት የአውሮፕላኑ የበረራ መቆጣጠሪያ ስሪቱ አንዳች ችግር ሳይኖረው አይቀርምና እሱ ላይ ትኩረት ተደርጎ ምርመራ መደረግ አለበት እያሉ እንደሆነ በመጥቀስ ግምቱን ያጠናክራል። በአሁኑ ሰዓት በርካታ ግዙፍ አየር መንገዶችም ይህንኑ ሥሪት ለጊዜው ከአገልግሎት ውጭ ለማድረግ መወሰናቸውም የሚነግረን ይህንኑ ነው። • ቻይና በቦይንግ 737 ማክስ 8 የሚደረጉ በረራዎችን አገደች "አዲስ አውሮፕላን አዲስ እንደተወለደ ልጅ ነው" ቃለየሱስ እንደሚለው አዲስ አውሮፕላን ሲመረት ብዙ ጊዜ ከችግር ጋር ነው የሚመጣው። እርግጥ ነው አዲስ ቴክኖሎጂ ስለሆነ ብዙ ሙከራ አድርገው ነው የሚያወጡት። ብዙ ፍተሻም ይደረግባቸዋል። "ይሄን ሁሉ ፍተሻ አልፎ ሲወጣ ግን አውሮፕላን ላይ አንድ ችግር አይጠፋም" የሚለው ቃለየሱስ ድሪምላይነር 787 ከባትሪ ጋር የተያያዘ ችግር እንደነበረበት በዚህም ዓለም ላይ ያለ ድሪምላይነር 787 ሁሉ ለወራት እንዳይበር ተደርጎ እንደነበር ያስታውሳል። የዚህ ዓይነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድሪምላይነር አውሮፕላን 2013 ላይ በለንደኑ ሄዝሮው አውሮፕላን ማረፊያ በቆመበት እሳት ተነስቶ እንደነበርም፣ ጃፓን አየር መንገድም በዚሁ አውሮፕላን ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት እንደነበር ቃለየሱስ ያስታውሳል። "የባትሪው ችግር ከተፈታ በኋላ ዛሬ ግን ድሪምላይነር 787 በጣም ጥሩ አውሮፕላን ነው።" "የአቬሽን ኢንዱስትሪ ኤክስፐርቶች አዲስ የተሠራ አውሮፕላንን አዲስ ከተወለደና ጥርስ ሲያወጣ ከሚያስቀምጠውና ጉንፋን ቶሎ ቶሎ ከሚይዘው ህፃን ጋር ያመሳስሉታል" ሲል ነገሩን በቀላሉ ለማስረዳት ይሞክራል። አዲስ አውሮፕላን ሲመጣ አስፈላጊውን ስልጠና በሙሉ አብራሪዎች እንዲወስዱ ማድረግ ወጪው ቀላል ስላልሆነ አየር መንገዶች በዚህ ጉዳይ ላይ ደከም ሊሉ እንደሚችሉ ይነገራል ።እዚህ ጉዳይ ላይ ቃለየሱስን አስተያየቱን ጠይቀነው ነበር። "ኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ ብቻ ሳይሆን አሁን የኤርባስም ባለቤት ሆኗል። አዲስ አውሮፕላን ሲወጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓይለቶች አምራቹ ጋር ሄደው ስልጠና ይወስዳሉ። ይህን ኤርባስ ሄጄ ተመልክቻለሁ" የሚል መልስ የሰጠው ቃለየሱስ ይህ ተለመደ አሰራር እንደሆነ ያስረግጣል። • በአዲስ አበባ ህዝባዊ ውይይት የታሰሩ ተለቀቁ ከአውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ምን ዓይነት መረጃ ይገኛል? የአውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን አንደኛው አውሮፕላኑ ጋቢና ውስጥ አብራሪዎቹ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ጋር ያደረጉትን ንግግር ሲቀዳ ሌላኛው ደግሞ አውሮፕላኑ በምን ያህል ፍጥነት፣ አንግልና ከፍታ ሲበር እንደነበር የሚሉና ተያያዥ የበረራ መረጃዎችን የሚመዘግብ ነው። ጥቁሩ ሰንዱቅ የመጀመሪያው ፓይለቶቹ አውሮፕላኑ ውስጥ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የተነጋገሩትን የግል ወሬ ሳይቀር ይቀዳል ማለት ነው" ሲል ያስረዳል ቃለየሱስ። ለመሆኑ ይህን የመረጃ ሳጥን የመመርመር ሥልጣን ያለው ማን ነው? ጥቁሩ የመረጃ ሰንዱቅ እጅግ ረቂቅ በመሆኑ ምርመራ የሚደረገው ወደ ውጭ ተልኮ ነው። የምርመራ ውጤቱ ከውስብስብ የአቪየሽን ፖለቲካ ነጻ ለማድረግም ከፍተኛ ጥንቃቄን ይፈልጋል። ይህም የሚሆነው አውሮፕላን አምራቾችን ጨምሮ አየር መንገዶች በውጤቱ ላይ እጃቸው ረዥም ስለሚሆን ነው። በዓለም አቀፉ የሲቪል አቬሽን ድርጅት አሠራር መሠረት የአደጋውን ምርመራ የመምራትና ምርመራ የማድረግ ሥልጣን አደጋው የደረሰበት አገር ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ይሆናል። ቤሩት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ሲደርስበት የምርመራውን ሂደት የመራው የሊባኖስ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን እንደነበርና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሊባኖስ አቪየሽን ከኢትዯጵያ በርካታ መረጃዎችን ቢወስድም በምላሹ ለኢትዯጵያ መረጃዎችን በመስጠት ረገድ በሚፈለገው ደረጃ ተባባሪ እንዳልነበር ያወሳል።
news-54382778
https://www.bbc.com/amharic/news-54382778
ኮሮናቫይረስ፡ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ ተያዙ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ቀደም ብሎ የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ረዳት በኮሮናቫይረሱ መያዟን ተከትሎ እርሳቸው እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርገው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ አሳውቀው ነበር። ለሁለተኛ ዙር የምርጫ ዘመን ፉክክር እተዘጋጁ ያሉት የ74ቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ በሆነው የዕድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ፤ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከታወቀ በኋላ "በጋራ እናልፈዋለን" ሲሉ ትዊተር ላይ አስፍረዋል። የምርመራውን ውጤቱን ተከትሎ እርሳቸው እና ባለቤታቸው በኮቪድ-19 መያዛቸውን ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይፋ አድርገዋል። በኮሮናቫይስ መያዟ የተነገረው የትራምፕ የቅርብ ረዳት የ31 ዓመቷ ሆፕ ሂክስ ናት። ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ "እኔ እና ቀዳማዊት እመቤት በቫይረሱ ተይዘናል። እራሳችንን ለይቶ የማቆየት እና ወደማገገም ሂደት በፍጥነት እናመራለን" ብለዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ትራምፕ የምርጫ ክርክር ለማድረግ ወደ ኦሃዮ ባቀኑበት ወቅት ሆፕ ሂክስ አብራቸው በኤር ፎርስ ዋን የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን ተጉዛለች። ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ ማሪን ዋን በተሰኘው የፕሬዝደንቱ ሄሊኮፕተር ውስጥ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በቅርበት ሆና መጓዟ ተገልጿል። የትራምፕ ሐኪም ሾን ኮንሌይ ባወጡት መግለጫ፤ ፕሬዝዳንቱም ሆኑ ቀዳማዊቷ ዕመቤት በአሁኑ ጊዜ "ሁለቱም ለማገገም ዋይት ሐውስ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያቸው የህክምና ክትትል እተደረገላቸው ለመቆት አቅደዋል" ሲሉ አመልክተዋል። "ፕሬዝዳንቱ ከበሽታው ለማገገም የሚያስፈልገውን እያደረጉ የሚተበቅባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ እንደሚቀጥሉ ላረጋግጥላቸሁ እወዳለሁ" ያሉት ሐኪሙ በቀጣይ የትራምፕን ጤና በተመለከተ የሚኖሩ ለውጦችን በሂደት እንደሚያሳውቁም ገልጸዋል። የትራምፕ በቫይረሱ መያዝ ሁለተኛውን ፕሬዝደንታዊ ክርክር እንዴት ሊያውክ እንደሚችል ግልጽ አይደለም። ሁለተኛው የፊት ለፊት ክርክር በፍሎሪዳ ማያሚ ውስጥ ጥቅምት 15 ለማካሄድ ቀን ተቆርጦለታል። ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ "ሆፕ ሁልጊዜም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ታደርግ ነበር። ውጤቷ ግን ፖዘቲቭ ሆኗል” ብለዋል። በሽታው ከ7.2 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያንን ያጠቃ ሲሆን ከ200 ሺህ በላይ ለሚሆኑት የአገሪቱ ዜጎች ሞት ደግሞ ምክንያት ሆኗል። ሆፕ ሂክስ ዋይት ሐሃውስ ለሁሉም የፕሬዝደንቱ አማካሪዎች እና ከፕሬዝደንቱ ጋር በየዕለቱ ለሚገናኙ ሰዎች በሙሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ብዙ ጊዜ የአፍ እና አፍንጫ ጭምብል ማድረግን የሚያጣጥሉት ፕሬዝደንት ትራምፕ ከአማካሪዎቻቸው ጋር ሲገናኙ ርቀታቸውን ሲጠብቁ አይታዩም። ብሉምበርግ እንደዘገበው ከሆነ በኮቪድ-19 መያዟ የተረጋገጠው የትራምፕ አማካሪ የበሽታውን ምልክት አሳይታለች። ግንቦት ወር ላይ የምክትል ፕሬዝደንቱ አማካሪ ኬቲ ሚለር በቫይረሱ ተይዘው ማገገማቸው ይታወሳል። ሆፕ ሂክስ የትራምፕን ቡድን የተቀላቀለችው እአአ 2014 ላይ ነበር። በወቅቱ የፖለቲካ ልምድ ያልነበራት ሆፕ ከአንድ ዓመት በኋላ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ አካል እንድትሆን ተደርጓል። ትራምፕ "ሆፕስተር" እያሉ የሚጠሯት ሆፕ ሂክስ ትራምፕ ከሚያምኗቸው አማካሪዎች መካከል አንዷ ስትሆን፤ የፕሬዝደንቱን አመለካከት ማስቀየር ከሚችሉ ጥቂት አማካሪዎች መካከል ሆፕ አንዷ ነች ይባላል።
news-53719599
https://www.bbc.com/amharic/news-53719599
ሊባኖስ፡ በቤይሩቱ ፍንዳታ 2 ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ200 በላይ ሆነ
በቤይሩቱ ፍንዳታ ምክንያት የሞቱ ሰዎች አሃዝ ከሁለት መቶ በላይ ሲደርስ የሁለት ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸው እንዳለፈ በከተማዋ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ገለጸ።
ባለፈው ማክሰኞ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ ያጋጠመውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለሞት ሲዳረጉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በፍንዳታው ሰበብ ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች ውስጥ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ኢትዮጵያዊያን ዜጎች እንደሚገኙበት በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመር ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተጨማሪም ከፍንዳታው ጋር ተያይዞ የመቁሰል ጉዳት እንደደርሰባቸው የተረጋገጡ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ከሐኪም ቤት መውጣታቸውን የቆንስላው ኃላፊ ተናግረዋል። አደጋው ከተከሰተ በኋላ የሊባኖስ መንግሥት ባወጣው የሟቾች ዝርዝር ውስጥ ስማቸውና ዜግነታቸው ያልተጠቀሱ ሰዎች በመኖራቸው የተለያዩ አገራት መንግሥታት ያልታወቁትን ሟቾች ለመለየት የማጣራት ሥራ እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል። ይህንን በተመለከተ ቆንስላ ጄነራሉ አቶ ተመስገን ኡመር ለቢቢሲ፤ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች አስከሬኖቹ ወደ ተቀመጡባቸው ስምንት ሆስፒታሎች በመሄድ ፍለጋ ማድረጋቸውንና ከሟቾቹ መካከል ኢትዮጵያዊ እንዳላገኙ አመልክተዋል። ቆንስላው በቤይሩት ውስጥ ያሉትን ኢትዮጵያዊያን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑንና ከፍንዳታው ጋር ተያይዞ የሚያስፈልጉ ነገሮችን እያከናወነ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል። የቤይሩት ከተማ ዋና አስተዳዳሪ በማክሰኞው አውዳሚ ፍንዳታ ከ200 በላይ ሰዎች ሞተዋል ተብሎ እንደሚታመን አመልክተዋል። ባለስልጣኑ ማርዋን አቡድ ጨምረው እንደተናገሩት አብዛኞቹ ከውጭ አገራት የመጡ ሠራተኞች እንደሆኑ የሚታመኑ በርካታ ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። የሊባኖስ ሠራዊት የፍንዳታው ዋነኛ ማዕከል በሆነው የወደብ አካባቢ ሲያካሂድ የነበረውን የነፍስ ማዳን ፍለጋ ሥራን ተልዕኮውን የመጀመሪያ ምዕራፍ አጠናቋል። ባለፉት ቀናት የአገሪቱ መንግሥት ለደረሰው የፍንዳታ አደጋ በሰጠው ምላሽ ላይ ቁጣቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች ከፖሊሶች ጋር ተጋጭተዋል። የፍንዳታ አደጋውን ተከትሎ አንድ ሚኒስትርና በርካታ የፓርላማ አባላት ከኃላፊነታቸው ቢለቁም በሕዝቡ ዘንድ የተቀሰቀሰው ቁጣ አልበረደም። በዋና ከተማዋ ለደረሰው ከባድ ፍንዳታ ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ ለስድስት ዓመታት ተከማችቶ በነበረ አሞኒየም ናይትሬት አማካይነት መሆኑን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
news-45019063
https://www.bbc.com/amharic/news-45019063
ማንነታቸው ያልታወቀ 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ
ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ።
ምንጮች ለቢቢሲ እንደገለፁት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት የታጠቁ ወታደሮች ተልዕኮና ማንነታቸው ባይታወቅም ኢትዮጵያዊያን እንደሆኑ አመልክተዋል። • ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መቼ አገር ቤት ይገባሉ? • ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ ከሁለት ቀናት በፊት ከሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ የተጠረጠረው አንቶኖቭ አውሮፕላንና አሳፍሯቸው የነበሩት 40 የታጠቁ ወታደሮች በመቀሌው የአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ መያዛቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የክልሉ ባለስልጣን በአካባቢው ለሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ገልፀዋል። ምንጮቹ ጨምረው ወታደሮቹ አንቶኖቭ ተብሎ በሚታወቀው ግዙፍ አውሮፕላን በአሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ በድንገት ያረፉት በስህተት መሆኑን ገልፀው፤ የክልሉ ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመረው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
news-46263190
https://www.bbc.com/amharic/news-46263190
የነጻነት ቅርጫት: ሊፕስቲክ
በቅርቡ በሃገር አሜሪካ የተካሄደ ጥናት እንደጠቆመው ወደ ስራ ቦታ ከማቅናታቸው በፊት ሊፕስቲክ የሚቀቡ ሴቶች ከማይቀቡት የተሻለ ይከፈላቸዋል።
የውበት መጠበቂያ ምርት ኢንዱስትሪ በዓመት $500 ቢሊዮን ያንቀሳቅሳል። ተቺዎች የውበት መጠበቂያ ምርት ማስታወቂያዎች ከእውነታው የራቀ ውበት እንደሚያጎናጽፉ ተደርገው ይቀርባሉ ይላሉ። በአንዳንድ የእስያ ሃገራት ቆዳን የሚያነጡ ምርቶችም ለገበያ ይውላሉ። ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ። መዋቢያ ቁሳቁስ "ወንዶች ፊታቸውን ሳያስውቡ ቢወጡ ምንም ነገር አይባሉም" ምቾች የሌለው ፋሽን "ሰዎች ለምን እንደሚያደርጓቸው አይገባኝም። ያማሉ፣ አይመቹም ደግሞም ቋሚ የሰውነት በሽታ ያስከትላሉ" ቤት ውስጥ የተዘጋጀ ምግብ "ሴት ልጅ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ብቻ ነው መሆን ያለባት የሚለው ሃሳብ ሰልችቶኛል" - ኤማ የቤት ውስጥ ሥራዎች "እኩልነት ከቤት ስለሚጀምር ወንዶች ተነስታችሁ ቤት አፅዱ።" ጡት መያዣ "መዋብ ግዴታዬ አይደለም። ያለእሱ ቆንጆም አዋቂም ነኝ̃።" - ሊዛ ዝነኛ ሰዎችን የማድነቅ ባህል "ሁሉም የቁንጅና ሞዴሎች ሰውነት አንድ ዓይነት ነው፤ ደግሞም ደስተኛ አይመስሉም። ይሰለቻል።"- ዌንዲ ጋብቻ "እንደኔ እንደኔ የቃልኪዳን ቀለበቶች በሴት መብት ተሟጋቾች ዘንድ የስድብ ያህል ናቸው። ምክንያቱም ቀለበት ያደረገች ሴት የሌላ ሰው ንብረት መሆኗን ስለሚያመለክት።" ማቲልድ ማህበራዊ ድረ ገፆች "ለታዳጊ ወጣቶች አዕምሮ ሰላም በጣም አደገኛ ነው። በተለይ ለሴቶች። ምክንያቱም ከእውነታ የራቁና አደገኛ በሆኑ አመለካከቶች ተከበዋል።" - ሮሻን በፆታ የተለዩ መጫወቻዎች "በፆታ የተከፋፈሉ መጫወቻዎች በሙሉ ወንዶችንም ሴቶችንም ልጆች የተወሰኑላቸውን ነገሮችን ብቻ እንዲወዱ ያደርጋሉ።" - አና ተጨማሪ ዕቃ የጭቆና መሣሪያዎች ምንድን ናቸው? 'የፀረ-ነፃነት ቆሻሻ መጣያ' የተሰኘውን አመላከከት ምን እነዳስጀመረው ለማየት የራስዎን መሣሪያ ያጋሩን። በተጨማሪም ማስታወቂያዎቹ ላይ የሚስተዋሉት የሞዴሎች መልክ በብዙ መልኩ ተቀናብሮ የሚቀርብ ሲሆን፤ ሴቶች እራሳቸውን ከሞዴሎቹ ጋር እንዲያነጻጽሩ ይደረጋሉ ይላሉ። የመጀመሪያዎቹ የሊፕስቲክ ተጠቀሚዎች ለፖለቲካ ተሳትፎ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ አሜሪካውያኖች እንደሆኑ ይገመታል። ዛሬ ላይ ሴቶች ምንም አይነት የመዋብያ ምርት ሳይጠቀሙ እራሳቸውን ፎቶግራፍ (ሰልፊ) በማንሳት የማሕብረሰቡን አስተሳሰብ እየተጋፈጡ ይገኛሉ።
news-54913704
https://www.bbc.com/amharic/news-54913704
ትግራይ፡ ወደ ሱዳን የሚሸሹ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው ተባለ
በፌደራል መንግሥት እና ትግራይ ኃይሎች መካከል የሚደረገውን ጦርነት በመሸሽ ወደ ሱዳን እየገቡ ያሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሱዳን የስደተኞች ኮሚሽን አስታወቀ።
የተባበሩት መንግሥታት በበኩሉ በግጭት ቀጠናው የቴሌኮም አገልግሎቶች መቋረጣቸው እና መንገዶች ዝግ መሆናቸው የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ለሚያደርገው ጥረት እንቅፋት ሆኖብኛል ብሏል። በአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ለወራት በውዝግብ ውስጥ የቆዩት የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል አስተዳደር ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወደ ግልጽ ጦርነት መግባታቸው ይታወሳል። የሱዳን የስደተኞች ኮሚሽነር አልሲር ካሊድ ለቢቢሲ በአዋሳኝ የድንበር አቅራቢያ በምትገኘው የሱዳኗ ካሳላ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እስከ ትናንትናው እለት ድረስ ብቻ ከ5ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ ተናግረዋል። አልሲር ካሊድ እንደሚሉት እነዚህ ከ5ሺህ በላይ ስደተኞችን ወደ ሱዳን የገቡት በአንድ በኩል ብቻ ነው። ኮሚሽነሩ ሉቅዲ ተብላ በምትጠራ ቦታም ትናንት እና ዛሬ 1100 በላይ ስደተኞች መድረሳቸውን ተናግረዋል። "የስደተኞች ቁጥር ከዚህ በላይ ይሆናል። በአንድ ሳምንት እስከ 20ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች ይመጣሉ ብለን እንጠብቃለን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ ምንም እንኳ የስደተኞች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም ለስደተኞቹ በቂ ምግብ እና መጠለያ ማቅረብ አለመቻሉን ገልፀዋል። "በቂ ምግብ እና መጠለያ የለም። መጠለያው እጅግ ትንሽ ነው። 300 ሰዎችን ብቻ ማስተናገድ የሚችል ነው። ያሉት ስደተኞች ግን ከ5ሺህ በላይ ናቸው" በማለት በከሰላ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ያለውን ሁኔታ ይገልጻሉ። በአካባቢው ከሚሰሩም ሆነ ከሌሎች መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ተቋማት አጥጋቢ ምላሽ እያገኙ እንዳልሆነ የስደተኞች ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ስደተኞቹ በጣም ተደናግጠው ነው የመጡት። ሦስት እና አራት ቀናት በእግራቸው ተጉዘው ነው እዚህ የሚደርሱት። የጦር አባላት አሉበት፤ በሽተኞችም አሉ" ሲሉ ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ጦርነቱን ሸሽተው ወደ ሱዳን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብሏል። የተመድ የኢትዮጵያ ተወካይ እና የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ካትሪን ሶርዚ (ዶ/ር) ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ በግጭት ቀጠና የቴሌኮም አገልግሎቶች መቋረጣቸው እና መንገዶች ዝግ መሆናቸው የሰብዓዊ እርዳታ ለማደረግ በሚያደርገው ጥረት ላይ እንቅፋት እንደሆነበት ገልፀዋል። ካትሪን (ዶ/ር) በትግራይ ከ800 በላይ የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚሰሩ ሰዎች እንዳሉ ተናግረው፤ "የቴሌኮም አገልግሎቶች ተቋርጠው ይገኛሉ። ይህም በሥራችን ላይ ጫና አሳድሯል። የሰዎች እንቅስቃሴንም መከታተል ከባድ አድርጎታል። የሚያስፈልግ እርዳታ ምን እንደሆነ መለየትም አልተቻለም" ብለዋል። "ይሁን እንጂ መሠረታዊ የሆኑ እንደ የምግብ እህል ዱቄት እና ነዳጅ እጥረት እንዳለ ሪፖርት ተደርጎልናል። የኤሌክትሪክ አገልግሎትም በተደጋጋሚ ይቋረጣል። ባንኮች ዝግ በመሆናቸው በነዋሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በእኛ ሥራ ላይም እንቅፋት ሆኖብናል" ይላሉ። የሁመራ፣ ሽሬ እና ሽራሮ ነዋሪዎች በትግራይ ወደሚገኙ ሌሎች ስፋራዎች ስለመፈናቀላቸው ሪፖርት እንደደረሳቸው ተናግረዋል። የሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ከ7ሺህ በላይ ነዋሪዎች ጦርነቱን በመሸሽ ወደ ሱዳን መሸሻቸውን ሪፖርት አድርጓል ሲሉ ካትሪን (ዶ/ር) ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ቀድሞውንም ቢሆን በትግራይ ከ600ሺህ በላይ የሚሆኑ በቋሚነት የምግብ እርዳታ የሚሹ ሰዎች ይገኙ ነበር" ያሉት ካትሪን (ዶ/ር)፤ በአራት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከ96ሺህ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች መኖራቸውን ጠቀሰው የሰብዓዊ እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል። ለስደተኞቹ የዕርዳታ ድጋፍ የሚሰጠው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል ያለው የመሠረታዊ ፍጆታዎች ክምችት በቅርቡ ሊሟጠጥ እንደሚችል አስጠንቅቋል። ለስደተኞች ቁጥር መጨመር ምክንያት የሆነው ፍጥጫ አሁን ወደ ጦርነት የተሸጋገረው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መስተዳደር በኩል የነበረው ቅራኔ እየተባባሰ የመጣው ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደማይካሄድ ከታወቀ በኋላ በትግራይ የተናጠል ምርጫ በመደረጉ ሳቢያ ነው። ይህንንም ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫውን ሕገወጥና ተፈጻሚነት የሌለው እንደሆነ መወሰኑን ተከትሎ ማዕከላዊው መንግሥት ከክልሉ መስተዳደር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያካሂድና የበጀት ድጋፍ እንዳይሰጥ ከወሰነ በኋላ ነገሮች እየተካረሩ መሄዳቸው ይታወሳል።
news-46370331
https://www.bbc.com/amharic/news-46370331
ኤች አይ ቪ ለምን በምራቅ እንደማይተላለፍ እና ሌሎች የተሳሳቱ አመለካከቶች
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ከሆነ ኤች አይ ቪ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ የጤና ጉዳይ ከመሆን ባለፈ እስከ አሁን ድረስ ከ35 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ቀጥፏል።
ባለፈው ዓመት ብቻ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከኤች አይ ቪ ጋር በተተያዙ መንስኤዎችን ህይወታቸው አልፏል። 37 ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች ቫይረሱ ያለባቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት አፍሪካ ውስጥ ናቸው። በአውሮፓዊያኑ 2017 ደግሞ 1.8 ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው ተጠቅተዋል። በኤች አይ ቪ ቫይረስ መጋለጥ በኤድስ መያዝን ማወቅያ ብቸኛ መንገድ ነው። • ኤች አይ ቪን የሚከላከለው መድሃኒት ተስፋ ሰጪ ነው ተባለ • ምግብ ማብሰልና ማጽዳት የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመቀነስ • 'ምን ለብሳ ነበር?' ለመጀመሪያ ጊዜ በሽታው በ1980ዎቹ ከተስፋፋ በኋላ የኤች አይ ቪ ቫይረስ እንዴት እንደሚተላለፍ እና ከኤች አይ ቪ ጋር መኖር ምን እንደሚመስል እጅግ በጣም ብዙ የተሳሳቱ አመለካከቶች፤ ጭፍን ጥላቻ እና መገለልን ፈጥረዋል። ዓለም አቀፍ የኤድስ ቀን በሚከበርበት ዕለት በጣም በተለመዱት አንዳንድ ግንዛቤዎች ላይ እናነጣጥራለን። የተሳሳተ አመለካከት: ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭ ከሆኑ ጋር በመሆኔ በኤች አይ ቪ እያዛለሁ ይህ የተሳሳተ ግንዛቤ ለረዥም ጊዜ በኤች አይ ቪ በሚኖሩ ሰዎች ላይ መድልዎ አስከትሏል። ከፍተኛ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች ተካሂደውም በአውሮፓዊያኑ 2016 እንግሊዝ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ኤች አይ ቪ በቆዳ ንክኪ ወይም በምራቅ እንደሚተላለፍ ያምኑ ነበር። ይሁን እንጂ በንክኪ፣ በእንባ፣ በላብ፣ በምራቅ ወይም በሽንት አይተላለፍም። በእነዚህ ምክንያቶችም በኤች አይ ቪ አይያዙም:- በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ኤች አይ ቪ የሚተላለፈው እንደ ደም፣ የዘር ፍሬ፣ የሴት ብልት ፈሳሽ እና የጡት ወተት በመሳሰሉ የፈሳሽ ልውውጥ ነው። የተሳሳተ አመለካከት: መድኃኒቶች ኤች አይ ቪን ሊፈውሱ ይችላሉ በጭራሽ እውነት አይደለም። ተለዋጭ መድሃኒት፤ ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ መታጠብ ወይም ከድንግል ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም ከኤች አይ ቪ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም። በሕንድ፣ በታይላንድ እና ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት ከድንግል ጋር ወሲብ መፈጸም ከኤች አይ ቪ ያድናል የሚለው የተሳሳተ አደገኛ አመለካከት አለ። ይህ አስተሳሰብ ወጣት ልጃገረዶችን አስገድዶ ከመድፈር በተጨማሪ አንዳንዴም ሕፃናት ጭምር እንዲደፈሩ እና በኤች አይ ቪ እንዲያዙ በር ከፍቷል። ሰዎች ቂጥኝ እና ጨብጥ መያዛቸውን ተከትሎ ይህ ሐሳብ በ16 ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓ ውስጥ ስር ሰዶ ነበር፤ ይህ ግን ለእነዚህ በሽታዎችም አይሠራም። ጸሎት እና ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እንዲቋቋሙ ሊረዱ ቢችሉም በቫይረሱ ​​ላይ ምንም ዓይነት ህክምናዊ ተጽዕኖ የላቸውም። የተሳሳተ አመለካከት: ትንኞች ኤች አይ ቪን ሊያሰራጩ ይችላሉ ምንም እንኳን ቫይረሱ በደም ቢተላለፍም፤ በሚነክሱ ወይንም ደም በሚመጡ ትንኞች ምክንያት ቫይረሱ አይተላለፍም። ለዚህ ደግሞ ሁለት ምክንያቶች አሉ፡ 1) ከዚያ በፊት የነከሱትን ሰው ደም በሚነክሱበት ወቅት አለማውጣታቸው እና 2) ኤች አይ ቪ በውስጣቸው ለአጭር ጊዜ ብቻ መቆየቱ ነው ስለዚህ እርስዎ ብዙ ትንኞች እና ከፍተኛ የኤች አይ ቪ ተጋላጭነት ባለባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ቢሆንም ሁለቱ ነገሮች ተዛማጅ አይደሉም። የተሳሳተ አመለካከት: በአፍ በኩል በሚፈጸም ወሲብ ኤችአይ ቪ አልያዝም በአፍ የሚፈጸም ወሲብ ከሌሎች የወሲብ ዓይነቶች ይልቅ ለአደጋ የማጋለጥ ዕድሉ አነስተኛ መሆኑ እውነት ነው። ከ10,000 ጊዜ የቫይረሱ መተላለፍ ዕድል ከአራት ያነሰ ነው። ነገር ግን ኤች አይ ቪ ኤድስ ካለባቸው ሰዎች ጋር በአፍ የሚፈጸም የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ቫይረሱ ሊከሰት ይችላል። ለዚህ ነው ዶክተሮች በአፍ በኩል ለሚደረግ ግብረ ስጋ ግንኙነትም ቢሆን ኮንዶም መጠቀምን የሚመክሩት። የተሳሳተ አመለካከት: ኮንዶም ከተጠቀምኩበኤች አይ ቪ አልያዝም በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ኮንዶም ቢቀደድ፣ ቢንሸራትት ወይም ፈሳሽ ካስተላለፈ ለኤች አይ ቪ ተጋላጭነትን ሊከላከሉ አይችሉም። ለዚህም ነው ስኬታማ የኤድስ ዘመቻዎች ኮንዶም በመጠቀም ላይ ብቻ ሳይሆን የኤች አይ ቪ ምርመራ በማድረግ እና ካለባቸውም ህክምናውን ወዲያውኑ በማግኘት ላይ ማተኮርን የሚመክሩት። የተሳሳተ አመለካከት: ምንም የሕመም የለምማለት ኤች አይ ቪ የለም ማለት ነው አንድ ግለሰብ ምንም ምልክት ሳይታይበት ከኤች አይ ቪ ጋር አሥር ወይም አሥራ አምስት ዓመት ሊኖር ይችላል። በበሽታው ከተያዙ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት እንደኢንፍሉዌንዛ በሽታ ምልክት የሚመስል ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ማሳከክ ወይም የጉሮሮ ህመም የመሳሰሉ ምልክቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ሌሎች ምልክቶች የበሽታ መከላከያ ስርዓቱ ሲዳከም በጊዜ ሂደት የሚመጡ ናቸው። እነዚህም የክብደት መቀነስ፣ ትኩሳት፣ ተቅማጥ እና ሳል ናቸው። ሕክምና ካላገኙ ሳንባ ነቀርሳ፣ ክሪፕቶኮካል ማጅራት ገትር፣ በከባድ የባክቴሪያ በሽታ እና እንደሊምፎማስ እና ካፖሲስ ያሉ ካንሰሮችን የመሳሰሉ ከባድ ሕመሞች ሊከሰቱ ይችላሉ። የተሳሳተ አመለካከት: ኤች አይ ቪ ያላቸው ሰዎች በለጋ ዕድሜያቸው ይሞታሉ ኤች ቨይ ቪ እንዳለባቸው የሚያውቁና ህክምናውን በትክክል የሚከታተሉ ሰዎች ጤናማ ኑሮ እየመሩ ነው። እንደ ዩኤንኤድስ ከሆነ ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች 47 በመቶ በሚሆኑት ቫይረሱ እጅግ የተጨፈለቀ ከመሆኑ የተነሳ በደም ውስጥ ያለው የኤች አይ ቪ መጠን በምርመራ "ሊታወቅ" አይችልም። የተጨፈለቀው ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው ሰዎች ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት ቢያደርጉ እንኳን ​​ሊያስተላልፉ አይችሉም። ይሁን እንጂ ህክምናውን ካቆሙ መጠኑ ከፍ በማለት በሚታወቁበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው በኤች አይ ቪ የተያዙ 21.7 ሚሊዮን ሰዎች በአውሮፓዊያኑ 2017 መድኃኒት እየወሰዱ ሲሆን ይህም በ2010 ከነበረው በስምንት ሚሊዮን የሚበልጥ ነው። ይህ ማለት ቫይረሱ እንዳለባቸው ካወቁ ሰዎች 78 መቶ የሚደርሱት መድኃኒት እያገኙ ነው። የተሳሳተ አመለካከት: ኤች አይ ቪ ያለባቸው እናቶች ልጆች ሁልጊዜ ተጋላጭ ናቸው በፍጹም ትክክል አይደለም። ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ያደረጉ እናቶች ቫይረሱን ሳያስተላልፉ ልጅ ሊወልዱ ይችላሉ።
news-46431521
https://www.bbc.com/amharic/news-46431521
ቻይና ቅጥ ያጡ ሰርጎችን ልትቆጣጠር ነው
የቻይና ባለስልጣናት እጅግ የተጋነነ ወጪ የሚደረግባቸውና አንዳንዴም አላስፈላጊ ተግባራት የሚፈጹሙባቸው ሰርጎችን ለማስቀረት ጥረት እያደረጉ ነው ተብሏል።
ቻይናውያን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ጠርተው ቅንጡ ሰርጎችን መደገስ ባህል እያደረጉት መጥተዋል እንደ ባለስልጣናቱ ከሆነ ዘመነኛ የሚባሉት ሰርጎች ከቻይናውያን ባህል ከማፈንገጣቸው በተጨማሪ አላስፈላጊ ወጪም ይወጣባቸዋል። በባለስልጣነቱ እንደ መፍትሄ የቀረበው ሀሳብ ደግሞ ለሰርጎች የሚሆን የመመሪያ ሰነድ ማዘጋጀትና ስነስርአቶቹ ባህላዊውን የቻይና ስርአት የተከተሉ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። አሁን አሁን በመላው ዓለም እየተስተዋለ እንዳለው፤ ቻይናውያንም በሰርግ ድግሶቻቸው ወቅት ከቤተሰብ፣ ጎረቤት እንዲሁም ከጓደኞቻቸው የተሻሉ መሆናቸውን ለማሳየት ከፍተኛ ወጪ ለድግስ ከማውጣት እስከ ዓለምን መዞር የደረሱ ተግባራትን ይፈጽማሉ። • ተጭበርብራ የተሞሸረችው ሴት አፋቱኝ እያለች ነው • ትዳር ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ይሄ ደግሞ በሚሊዮን ዶላሮች ከፍሎ ድግሱን ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ማዘጋጀት፣ ከቻይና ውጪ ተጉዞ የሰርግ ፎቶዎችን መነሳት እንዲሁም አውሮፕላን መከራየትን ያካትታል። የሰርጉ ታዳሚዎችም ቢሆኑ ውድ ውድ ስጦታዎችን የማምጣት ግዴታ አለባቸው። እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተካተውበት የሚደገሰው የሰርግ ስነ-ስርዓት ደግሞ ሌላ አሳሳቢ ባህልም ተጨምሮበታል። ሙሽሮቹን በሰርጋቸው ዕለት ዘና እንዲሉ ለማድረግ በማሰብ ቤተሰቦችና የቅርብ ጓደኞች ሙሽሮቹን ማስደንገጥን የመሳሰሉ የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማሉ። ታዲያ እነዚህ ተግባራት ከማስደንገጥ አልፈው እስከ ማዋረድና አደጋ እስከ ማደረስ ደርሰዋል። ባለፈው ሳምንት እንኳ በተደረገ የሰርግ ስነ-ስርዓት ጓደኞቹ ከወንበር ጋር አስረው ሲገርፉት የነበረ ሙሽራ ለማምለጥ ሲሞክር በመኪና ተገጭቶ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። በሌላ አጋጣሚ ደግሞ የወንድ ሙሽራ ሚዜዎች ሙሽሪት ያረፈችበትን ክፍል መስኮት በመጥረቢያ ሰብረው ለመግባት ሲሞክሩ የመስታወት ስባሪ ያገኛቸው ሚዜዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ሄደው ነበር። አንዳንዴም ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ይሆኑና ሴት ሚዜዎች ጾታዊ ትንኮሳ ይደርስባቸዋል። ጉዳዩ ያሳሰበው የቻይናው የሲቪል ጉዳዮች ሚኒስትር መስሪያ ቤት ደግሞ ያለአግባብ የሚወጡ ወጪዎችን ለመቀነስና የሃገሪቱን ባህል ለመታደግ በማሰብ አዲስ መመሪያ አዘጋጅቷል። ''የሰርግ ስነ-ስርዓቶች የቻይናን ሶሻሊስት አስተሳሰብና የቀድሞ ባህል ባስጠበቀ መልኩ ለማካሄድና ዘመን አመጣሽ የቅንጦት አስተሳሰቦችን ለመዋጋት አዲሱ መመሪያ ይረዳል'' ብሏል መስሪያ ቤቱ። በቅርቡም ለሰርግ ስነ-ስርዓቶች የሚወጣውን ገንዘብ መጠን የሚወስንና የሰርጉን አጠቃላይ አካሄድ የሚቆጣጠረው መመሪያ ተግባራዊ ያደረጋል ተብሏል። • ከቀይ ሽብር ሰሞን ሰርግ እስከ ኢትዮጵያዊነት ዕምባ
news-53394394
https://www.bbc.com/amharic/news-53394394
የሳተላይት ምስሎች የህዳሴ ግድብ የውሃ መጠን መጨመሩን አመለከቱ
በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ አካባቢ የተገኙ የሳተላይት ምስሎች በግድቡ ውስጥ ያለው የውሃ መጠን እየጨመረ መሆኑን አመለከቱ።
ይህ 5 ቢሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግበት የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል ድርድር እየተደረገበት ነበር። አዲሱ የሳተላይት ምስል የተወሰደው ሰኔ 20/2012 እና ሐምሌ 5/2012 ሲሆን ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን በተከታታይ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል። ቢቢሲ በአካባቢው ካሉ የግብርና ባለሙያዎች በማጣራት እንደተረዳው ግድቡ በሚገኝበት በምዕራብ ኢትዮጵያ ጉባ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የክረምት ዝናብ በመጣል ላይ ነው። ጋዜጠኛ ቤንጃሚን ስትሪክ የሳተላይት ምስሎቹን በመከታተል እንደገለፀው ምናልባት ግድቡ ከፍተኛ ውሃ መያዝ የጀመረው በአካባቢው በሚጥለው ዝናብ ምከንያት ይሆናል። የግብጹ አል አህራም ጋዜጣም በአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ የተነሱ ሳተላይት ምስሎችን መሰረት አድርጎ ግድቡ ውሃ መያዝ የጀመረ መሆኑን አመልክቶ፤ ይህ ግን በአካባቢው በሚጥለው ከባድ ዝናድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የክራይስስ ግሩብ ተንታኝ ዊሊያም ዳቪሰንን ጠቅሶ ዘግቧል። Interactive A large reservoir is beginning to form behind the dam 12 July 2020 26 June 2020 የኢትዮጵያ መንግሥት በሐምሌ ወር ግድቡን በውሃ መሙላት እንደሚጀምር በተደጋጋሚ የገለፀ ሲሆን ግብጽ በበኩሏ ድርድሩ ሳይጠናቀቅ ሙሌቱ እንዳይካሄድ ፍላጎት አላት። በአፍሪካ ሕብረት አሸማጋይነት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በትዊተር ገፃቸው የያሰፈሩት ዛሬ ማለዳ ነበር። እስካሁን በተካሄደው ድርድር መሻሻሎች ቢኖሩም በአጠቃላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ የገለፁት ሚኒስትሩ፣ በዛሬው ዕለትም አገራቱ የደረሱባቸውን ጉዳዮች ለመሪዎቹ እንዲሁም ሲያሸማግል ለነበረው አፍሪካ ሕብረትም በሪፖርት መልክ ያቀርባሉ ብለዋል። የሦስቱ አገራት ድርድር ሦስቱ አገራት ሲያደርጉት የነበረው ለዓመታት የዘለቀው ድርድር ያለምንም ውጤት ሲንከባለል መጥቶ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሙሌትን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እጀምራለሁ ማለቷን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ግብጽ መጠየቋ የሚታወስ ነው። ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት ሸምጋይነት ለኢትዮጵያ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት የተባለ ሲሆን፤ የግድቡ ውሃ አሞላልና አለቃቅ፣ የድርቅ የውሃ ስሌት፣ የግድቡ አስተዳደርና ቁጥጥር፣ የግድቡ ደኅንነት ጉዳዮችን በተመለከተም የአገራቱ ቴክኒክና ሕግ ባለሙያዎች እየተወያዩ ነበር ተብሏል። በአስረኛው ቀንም የሦስቱ አገራት የውሃና መስኖ ሚኒስትር የቴክኒካልና ህጋዊ ኮሚቴ ውይይቶችን መገምገማቸውንም የግብጽ የውሃና መስኖ ሚኒስቴርን ጠቅሶ 'ኢጅፕት ቱደይ' ዘግቧል። በተለይም በባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ስምምነት ያልተደረሳባቸው ጉዳዮች ለሌላ ጊዜ ይተላለፉ ማለታቸው ከግብጽ በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱንም ዘገባው አስነብቧል። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ከሰሞኑ ለአገሪቱ ሚዲያዎች በሰጠው መግለጫ ድርድሩ ፍሬ አልባ እንደነበር ገልጿል። አረብ ኒውስ በበኩሉ ኢትዮጵያ ለአወዛጋቢዎቹ የሕግ እና ቴክኒካዊ ጉዳዮች አማራጭ ሃሳቦችን ብታቀርብም በግብጽ ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘ ዘግቧል። ኢትዮጵያ የአማራጭ ሃሳቧን በስምንተኛው የድርድር ቀን ማቅረቧን የገለፀው ዘገባው ስምምነት ያልተደረሰባቸውን ጉዳዮችንና ስምምነቶቹ ተግባራዊ መሆናቸውንም ለማየት አንድ የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደዚያ እንዲያመራ ማሰቧን ዘግቧል። ግብጽ በበኩሏ ድርቅና የድርቅ ውሃ ስሌትን በተመለከተ አማራጭ ሃሳብ ማቅረቧን የውሃና መስኖ ሚኒስትሩን ጠቅሶ ዘግቧል። ቴክኒካል ጉዳዮችንም በተመለከተ አንዳንድ መሻሻሎች መኖራቸውንም የሱዳን የውሃና መስኖ ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ዘገባው አስነብቧል።
news-51513393
https://www.bbc.com/amharic/news-51513393
በጠምባሮ ወረዳ ከሰማይ ወረደ የተባለው እሳት ወይስ ሚትዮራይትስ?
ባለፈው ሳምንት አርብ ለሊት 6 ሰዓት አካባቢ ከሰማይ ወረደ የተባለ እሳት በከምባታ ጠምባሮ ዞን፣ ጠምባሮ ወረዳ በአራት ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ 30 የሳር ቤቶችን ማቃጠሉን የጠምባሮ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደጀኔ ለመንቾ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
ኃላፊው እንደሚሉት ስለአደጋው ሰምተው ጉዳት ወደደረሰባቸው አካባቢዎች በሄዱበት ወቅት ነዋሪዎች እንደነገሯቸው፤ እሳቱ የወረደው ከሰማይ እንደሆነና ከሚቃጠሉት ቤቶቹን ውስጥ እቃ ለማውጣት እንዳልተቸገሩ መናገራቸውን ያስታውሳሉ። "ቤቱ እየተቃጠለ ሰው እቃውን ለማውጣት ሲሞክር እንደማያቃጥል፤ ነገር ግን በውሃም ሆነ በእርጥብ ነገር ለማጥፋት በሚሞከርበት ጊዜ ግን የበለጠ እየተባባሰ እንደሚሄድ ነግረውናል" ብለዋል። "ከዚህ በተቃራኒው ግን" ይላሉ ኃላፊው አቶ ደጀኔ "ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት ወደ ፈጣሪ ፀሎትና ልመና በሚያደርግበት ወቅት እሳቱ ይቀንሳል" በማለት መናገራቸውን ጨምረው አስረድተዋል። የአካባቢው ገበሬዎች እሳት የተነሳበት ቤት አጠገብ የሚገኙ የቆርቆሮ ቤቶች ሳይቃጠሉ አልፎ አልፎ ያሉ የሳር ቤቶች ብቻ በእሳት መያያዛቸውን በመመልከትና የእሳቱን ባህሪ በማስተዋል ይህ "የፈጣሪ ቁጣ እንጂ፤ የሰው ሥራ ወይንም የተፈጥሮ አደጋ ነው ብለው ለማመን መቸገራቸውን" ጨምረው ገልጸዋል። አተቶ ደጀኔ እንዳሉት እሳቱ ከሰማይ ወረደ የተባለባቸው ዱርጊ ፥ ሲገዞ ቀበሌዎች ኩታ ገጠም ሲሆኑ፣ ዘንባራ እና ሆዶ ደግሞ የተራራቁ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከቤቶቹ በተጨማሪ 6 የዳልጋ ከብቶች እና የጤፍ ክምርም የጉዳቱ ሰለባ መሆናቸውን ተገልጿል። በአራቱም ቀበሌዎች በተመሳሳይ ሰዓት ተነሳ በተባለ በዚህ የእሳት ቃጠሎ መንስዔውን ፖሊስ ለማጣራት ሙከራ እያደረገ መሆኑን በወቅቱ ተዘግቦ ነበር። አቶ ደጀኔ እንደሚሉት ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም አካባቢ፣ በወረዳው አጎራባች ቀበሌዎች እንዲሁ ከሰማይ ወረደ በተባለ እሳት 80 ቤቶች መውደማቸውን አስታውሰው፤ በ2009 ዓ.ም ደግሞ 8 ቤቶች በሌላ አካባቢ እንዲሁ መቃጠላቸው ክስተቶቹን አደጋ ነው ብሎ ለማመን እንደተቸገሩ ይናገራሉ። ከሰማይ የወረደ እሳት ወይስ ሳይንሳዊ ክስተት? አቶ ነብዩ ሱሌይማን በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ውስጥ የሚሰሩ ሲሆን አስትሮኖሚና አስትሮ ፊዚክስን በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ አጥንተዋል። ቢቢሲ በጠምባሮ ወረዳ የተከሰተውን በማንሳት ምን ሊሆን ይችላል በማለት የጠየቃቸው ሲሆን እርሳቸውም ሚትዮራይቶች [ከህዋ የሚወርዱ የአለት ስብርባሪዎች] ከደቃቅ አሸዋ እስከ ትላልቅ ድንጋዮች ድረስ እንደሚያክሉ በመግለጽ፣ አብዛኛዎቹ ወደ ምድር ሲመጡ ተቃጥለው እንደሚያልቁ ያስረዳሉ። እነዚህ ከአሸዋ ቅንጣት እስከ ትልልቅ አለት ድረስ የሚያክሉት ሚትዮራይቶች በምንኖርበት ከባቢ አየር ላይ ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ቢያልቁም ተቃጥለው ያላለቁ ትንንሽ ስብርባሪዎች መሬት ሊደርሱ ይችላሉ በማለት ያብራራሉ። እነዚህ አካላት ሰው በተለምዶ ተወርዋሪ ኮከብ ብሎ ይጠራቸዋል የሚሉት አቶ ነብዩ "ማህበረሰቡ ኮከብ ቢላቸውም፤ ኮከብ አይደሉም" በማለት የሚቃጠል አለት በእኛ ከባቢ ላይ ሲያልፍ የምናይ በመሆኑ ኮከብ የሚለውን ስያሜ መሰጠቱን ያስረዳሉ። እነዚህ ሚትዮራይቶች አንዳንዶች ትልልቅ ሲሆኑ ግዝፈታቸው ከአንድ መኪና በላይ እንደሚሆንም ገልፀዋል። አክለውም ሩሲያ ውስጥ እኤአ 2012 አካባቢ ከእኛ አገሩ በተለየ በርከት ያሉ ስፍራዎችን የሚሸፍን ስብርባሪ ወድቆ ከፍ ያለ አደጋ ማድረሱን እንደሚያስታውሱ ያስረዳሉ። እንዲህ አይነት አካል ሲመጣ የመሬት ከባቢ አየር አቃጥሎ ስለሚያስቀረው እንጂ ጨረቃ በቴሌስኮፕ ብትታይ ገጽታዋ የተደበደበ እንደሚመስል በመጥቀስ እነዚህ ሜቶራይትስ ተቃጥለው ሳያልቁ አካሏ ላይ በማረፋቸው ያ መከሰቱን ያብራራሉ። ሜቶራይትስ የሚባሉት ድንጋያማ አለቶች የኮሜትና አስትሮይዶች ቅሪቶች ናቸው። ኮሜትም አስትሮይድም ግዙፍ አለቶች መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ነብዩ፤ አስትሮይዶች ከጁፒተርና ከማርስ መካከል የሚገኙ አካላት መሆናቸውን ይገልጻሉ። ብዙዎቹ ግዙፍ ናቸው በማለትም እነዚህ አካላት ወደ መሬት ወይም ወደ ሌላ አካል ቀረብ ሲሉ እየተሰባበሩ፣ እየተሰባበሩ ይመጡና፤ መሬት በፀሐይ ዙሪያ ስትሽከረከር እነርሱን ስለምትስብ፣ ወደመሬት እየመጡ ብዙዎቹ ተቃጥለው ያልቃሉ በማለት ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። እነዚህ ተቃጥለው ያላለቁ አካላት ወደመሬት በከፍተኛ ፍጥነት የሚመጡ ሲሆን እንደ ጎጆ ቤት አይነት ቤት ላይ ካረፉ ቀስ እያሉ እየተፈረካከሱ ተቃጥለው እንደሚያልቁ ይናገራሉ። "ቅሪቱ ግዙፍ የሚያክል ቢሆን እንኳ ወደ መሬት ሲመጣ እየተቃጠለ፣ እየተቃጠለ ይመጣል። ፍጥነቱም ቢሆን ከጥይት ፍጥነት 20 እና 30 እጥፍ ሊበልጥ ይችላል። ወደመሬት እየቀረበ ሲመጣና ፍጥነቱ እየጨመረ ሲመጣ ይፈረካከሳል" ይላሉ አቶ ነብዩ። አክለውም "አንድ አካል የነበረው ወደ ብዙ አካላት ሲፈረካከስ አንዱ ፍርካሽ አንድ ቀበሌ ላይ ሲያርፍ ሌላኛው ደግሞ ሌላ ቀበሌ ላይ ሊያርፍ ይችላል" በማለትም በጠምባሮ ወረዳ አራት ቀበሌዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት እሳት ወረደ የተባለው ለዚያ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። እሳቱን በእርጥብ ነገርና በውሃ ለማጥፋት አይቻልም? ተብለው የተጠየቁት አቶ ነብዩ "እነዚህ አለቶች ተቀጣጣይ ነገር ይዘው አይወርዱም" በማለት ነገር ግን ፍጥነት ስላላቸው ነገሮች እንዲቃጠሉ ያደርጋሉ በማለት ያስረዳሉ። "እሳቱ ቤቱ ላይ ሲያርፍ ሰዎቹን ያላቃጠለው ተቀጣጣይ ነገር ስላልሆነ ሰዎቹን ሊጎዳ አይችልም" በማለትም እነርሱ ስለማይታያቸው እንጂ መሬትንም አልፈው ሊገቡ ይችላሉ በማለት ሙያዊ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። ከጎጆ ቤቶቹ ጎን ያሉት ቆርቆሮ ቤቶች ያልተቃጠሉበት ምክንያት ሊሆን የሚችለውም ይኸው ነው ያሉት ባለሙያው፣ አለቶቹ ወደ መሬት ሲምዘገዘጉ ተቀጣጣይ ነገር ይዘው ባለመምጣታቸው መሆኑንም ያክላሉ። ስለፕላኔቶች አፈጣጠር የምናውቀውን ይቀይራል የተባለው አዲስ ግኝት ሜቲዮሮይዶች፣ የተለያየ ዓይነት ስሪት አላቸው በማለትም በሚቃጠሉበት ወቅት የተለያየ ዓይነት ቀለም እንደሚያወጡ ያስረዳሉ። "አንዳንዶቹ በካሊሺየም የበለፀጉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በአይረን፣ አንዳንዶቹ በፖታሺየም የበለፀጉ ስለሚሆኑ ሰማይ ላይ በሚቃጠሉበት ወቅት የተለያየ ቀለም ያሳያሉ።" ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በወረዳውና አካባቢው ላይ እንዲሁ ከሰማይ ወረደ የተባለ እሳት ቤቶች ማቃጠሉን በመጥቀስ እነዚህ ሜትዮራይትስ የት እንደሚወድቁ ማወቅ ይቻል እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ነብዩ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ አመልክተዋል። ሩሲያ ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ አጋጥሟት ያውቃል በማለት የቅርብ ጊዜ ክስተትን ያስታወሱት አቶ ነብዩ ይህ ሊሆን የቻለው ሩሲያ ግዙፍ በመሆኗ እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም በማለት ያብራራሉ። አክለውም "መሬት በራስዋ ዛቢያ ላይና በፀሐይ ዙሪያ ስትሽከረከር በአጋጣሚ ሆኖ ሜትዮራያቶች ወደኛ ምህዋር ይመጣሉ። እናም የት እንደሚያርፉ ብዙ ጊዜ አይታወቁም። እነዚህ ነገሮች የሚገመቱም አይደሉም። አካባቢ አይመርጡም" ብለዋል። ከዚህ ቀደም በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን በጉራዋ ወረዳ፣ ሙደና ጅሩ በሊና በምትባል የገጠር ቀበሌ ውስጥ ከሰማይ ወረደ በተባለ እሳት ከ40 በላይ የሳር ቤቶች መቃጠላቸው እንደተነገረ ይታወሳል።
44079204
https://www.bbc.com/amharic/44079204
"ወደ ቀድሞ ቀያቸው ተመልሰው ህይወታቸውን መምራት ይችላሉ"
ባለፈው ጥቅምት ወር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሼ ዞን ተወላጆች እና ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ስፍራው በማቅናት ኑሯቸውን በመሰረቱ አርሶ አደሮች መካከል ግጭት ተቀስቅሶ ሞት፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀልን አስከትሏል።
በግጭቱ ምክንያት ከተፈናቀሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች መካከል ከአምስት መቶ የሚልቁ አባወራዎች በባህር ዳር ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ። ህዝቡን የማረጋጋት ሥራ እየተሰራና ለተጎዱ ቤተሰቦች እርዳታ እየተደረገ ሲሆን አደጋ ያደረሱ 65 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው በክስ ሂደት ላይ እንደሚገኙ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ለቢቢሲ ገልፀዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ከዚህ ቀደምም ተከታታይ ግጭቶች እንደተፈጠሩና ባለፈው ጥቅምት ላይ በተከሰተው ግጭት አመራሮችን ጨምሮ 65 ሰዎች ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ገልፀዋል። "አሁንም በብሔሮች መካከል ግጭቶችን የሚፈጥሩ፣ ግለሰቦችን እየለዩ ጥቃት የሚያደርሱና ሌሎች ያለአግባብ እንቅስቃሴዎችን የሚያደረጉ ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ክልሉ ተግቶ ይሰራል" ብለዋል። በቅርቡ በተከሰተው ግጭትም እጃቸው አለበት የተባሉ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በክስ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የተፈናቀሉትም "ወደ ቀድሞ ቀያቸው ተመልሰው ህይወታቸውን መምራት ይችላሉ" በማለት አቶ አሻድሊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከተፈናቃዮቹ መካከል ወደ ቀድሞ ቀያቸው የተመለሱም እንዳሉ ገልፀው ቀሪዎቹም ቢመለሱ በሰላም ከህብረተሰቡ ጋር መኖር የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በባህርዳር ከተማ በቤተ-ክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙት ተፈናቃዮች የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁንና ሌሎች ሃላፊዎች እንዲመለሱ ቢያነጋግሯቸውም አሁንም ስጋት ስላላቸው መመለስ እንደማይፈልጉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-53261077
https://www.bbc.com/amharic/news-53261077
የለንደን ፖሊስ የአጼ ኃይለ ሥላሴ ሐውልትን ያፈረሱትን እየተከታተለ መሆኑን አስታወቀ
በደቡብ ምዕራብ ለንደን ዊምብሌደን በሚገኝ ፓርክ የነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት በተወሰኑ ሰዎች መፍረሱ ይታወቃል፡፡
ፖሊስም ማክሰኞ ዕለት ምሽት በካኒዛሮ ፓርክ የተፈጠረውን ይህንን ወንጀል እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ሐውልቱ ያፈረሱት 100 የሚጠጉ ሰዎች አንድ ላይ በመሰባሰብ እንደሆነ የዐይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ የዊምብልደን ነዋሪ የሆኑት አንድሪው ሞሪስ፤ ከውሻቸው ጋር የእግር ጉዞ እያደረጉ ሳለ በፓርኩ ውስጥ የተሰባሰቡ ሰዎች መመልከታቸውንና ግለሰቦቹ መፈክሮችን እና በራሪ ወረቀቶችን ይዘው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ አንድሪው አክለውም ሐውልቱ ሲፈርስ ድምጽ መስማታቸውን ጠቅሰው ምን እንደተፈጠረ ግን በዐይናቸው አለማየታቸውን አስረድተዋል፡፡ የከተማዋ ፖሊስ መረጃ የማሰባሰብና የምርመራ ሂደቱ እንደቀጠለ መሆኑንና እስካሁን ግን በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው እንደሌለ ገልጿል፡፡ ድርጊቱ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ ከተፈጠረ ተቃውሞ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ የድምጻዊውን መገደል ተከትሎም በሐረር የሚገኘው የአጼ ኃይለ ሥላሴ አባት ልዑል ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ሐውልትም ለታቃውሞ በወጡ ቡድኖች ፈርሷል፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴ በጎርጎሮሳዊያኑ 1936 የጣሊያንን ወረራ ተከትሎ ለስደት እንግሊዝ ባመሩበት ወቅት የቆዩት እንግሊዝ ውስጥ ነበር፡፡ በዚያም ከእውቋ እንግሊዛዊት ቀራጺና ደራሲ ቤተሰቦች ጋር ይኖሩ በነበረበት ወቅት ሐውልታቸው በቀራጺዋ የተሰራ ሲሆን በኋላ ላይም በካኒዛሮ ፓርክ እንዲቆም ተደርጓል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በድምጻዊው ሞት የተቆጡና ብረትና ተቀጣጣይ ነገር ያዙ ወጣቶች በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራና የሚዲያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ያለው ከበደ ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ወጣቶቹ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማን በማውረድ ለማቃጠል መሞከራቸውን በምትኩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሰንደቅ አላማ መስቀላቸውንና በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ጨምረው አስረድተዋል። በኤምባሲው የቆንስላ ክፍል ውክልና ለመስጠት መጥቶ የነበረ አንድ ተገልጋይን ሲወጣ በማግኘት መደብደባቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። የወጣቶቹ ዋና አላማ ኤምባሲው በመግባት ጉዳት ማድረስ እንደነበር ያመላከቱት አቶ ያለው ተቀጣጣይ ነገርና ብረት ይዘው እንደነበር ለቢቢሲ አስረድተዋል፡፡
news-47812021
https://www.bbc.com/amharic/news-47812021
የበረራ አስተናጋጆች ከአደጋው በኋላ በነበራቸው በረራ ምን ተሰማቸው?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢት 302 መጋቢት 1/2011 ዓ.ም ጠዋት 2፡38 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለሚያደርገው በረራ ጉዞ በጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ተከስክሷል። በአደጋው የበረራ ሠራተኞችን ጨምሮ 157 ግለሰቦች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
አደጋው በመላው ዓለም ድንጋጤን የፈጠረና ያሳዘነ ነበር። ታዲያ በረራ የዘወትር ሥራቸው ለሆነው የበረራ አስተናጋጆች ከአደጋው በኋላ በነበራቸው በረራ ምን ተሰምቷቸው ነበር? ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች የበረራ አስተናጋጅ ስለአደጋው የሰማችው ቤት ውስጥ ከቤተሰብ ጋር ተሰብስበው እየተጫወቱ እንደነበር ታስታውሳለች። ከዚያም ድንገት ስልኳ አቃጨለ "ተርፈሻል?" ለማለት ከጓደኛዋ የተደወለ ስልክ ነበር። የሰማችውም ያኔ ነው። " በፍፁም ላምን አልቻልኩም ነበር " ትላለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሀዘን መግለጫ ሲያወጡ የሚወራው ሁሉ እርግጠኛ መሆኑን እንዳረጋገጠች ትናገራለች። • "እናቱ ስታየኝ 'ልጄ ያሬድ ይመጣል' እያለች ታለቅስ ነበር"- በናይሮቢ የካፒቴኑ ጸጉር አስተካካይ ከዚያም በየተራ ሰው መደወል ጀመረ... ያኔ " እኔም ልሆን እችል ነበር ... ብዙ ጊዜ በማክስ አውሮፕላን እበራለሁ፤ በ20 ሰዓት ልዩነት ስለምንመደብም ልመደብ እችል ነበር" ስትል በሃዘኔታ አጋጣሚውን ታስታውሰዋለች። "አደጋው ሁላችንንም ያስለቀሰ ነበር፤ እሞታለሁ ብለንም ስለማንወጣ በጣም ነበር ያዘንኩት፤ ለተሰጠን ሥራ 'እንደ ወታደር' እሽ ብለን ነው የምንሄደው" ስትል ታክላለች። ያው የሥራ ጉዳይ ነውና ይህች የበረራ አስተናጋጅ አደጋው በተፈጠረ ዕለት ማታ ወደ ታይላንድ፣ ባንኮክ በረራ ነበራት። ይሁን እንጂ ቤተሰቦቿ እንዳትሄድ አጥብቀው ተማፅነዋት እንደነበር ታስታውሳለች። "እናቴም፣ አያቴም፣ ሁሉም ዛሬ ከቤት አትወጭም! እንደዚህ ሆኖ ይወጣል? ሰው ሞቱን ነው ወይ የሚፈልገው?" ሲሉ ከልክለዋት ነበር። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? በጊዜው እርሷም ፍርሃትና ጭንቀት ገብቷት እንደነበር አልደበቀችም "ከበረራ በፊት ውይይት ስናደርግ ሕይወታቸው ያለፉት አስተናጋጆች ትዝ ይሉን ነበር፤ ድባቡ ያስጠላ ነበር፤ ከባድ ነበር ...እንቅልፍ ሁሉ ነስቶኝ ነበር" ትላለች። "አደጋው ያጋጠመው አውሮፕላኑ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ስለነበር፤ እኛም ልክ አውሮፕላኑ ገና ሲነሳ ሁሉም እያለቀሰ ነበር፤ አገልግሎት መስጠት ተስኖን ነበር" ስትል ታስታውሰዋለች። "ከበፊት ጀምሮ ከቤት ስወጣ ለእግዚያብሔር አደራ ሰጥቼ ነበር የምወጣው፤ አሁንም ይህንኑ ማድረግ የዘወትር ተግባሬ ነው" ትላለች። ይህች የህግ ምሩቅ የሆነችው አስተናጋጅ ቤተሰቦች በአደጋው ምክንያት በስጋት መኖራቸው አልቀረም "አባቴ በተመረቅኩበት ትምህርት እንድሰራ ማስታወቂያዎችን እያየ 'ሞክሪ!... እስከመቼ ተሳቀን እንኖራለን' " ሲሉ ይወተውቷት ነበር። እርሷ ግን ሥራዋን አብዝታ ስለምትወደው የእነርሱን ውትዎታ ከቁብም አልቆጠረችው። ሌላኛዋ ያነጋገርናት የበረራ አስተናጋጅ ለምለም ያደሳም የተለየ ሃሳብ የላትም። የአደጋው ዕለት በርካታ የስልክ ጥሪዎችን አስተናግዳለች። አንዳንዶቹ ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው እያሉ ሲያበረታቷት ቤተሰብ ግን "ሥራውን ተይው" እስከማለት ደርሰው ነበር። ይሁን እንጂ በማንኛውም ሥራ ላይ ሊያጋጥም የሚችል በመሆኑና ለሥራው ፍቅር ስላላት ለንግግራቸው ጆሮዋን አልሰጠችም። • "በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት ከአደጋው ማግስት በረራ የነበራት ወደ ደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ነበር። ቤተሰቦቿ ሲሸኟትም የውስጧን በውስጧ አድርጋ "አይዟችሁ ምንም አልሆንም፤ አታስቡ" የሚል መፅናኛ ቃል እንደሰጠቻቸው ታስታውሳለች። "መጀመሪያ ስገባ በጣም ፈርቼ ነበር፤ እንዲህ ዓይነት አደጋ ይፈጠራል ብለን አስበን ስለማናውቅ በጣም ተጨንቄ ነበር" የምትለው ለምለም ከዚያ በኋላ ጥንቃቄ ላይ ትኩረት እንድትሰጥ ምክንያት እንደሆናት ትናገራለች። "ብዙ ዓይነት አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብኝ ከወትሮው በተለየ በትኩረትና በንቃት መከተታል ጀምሬያለሁ" ስትልም አክላለች። የበረራ አስተናጋጇ ለምለም "ኢትዮጵያ አየር መንገድን ከመግባቴም በፊት እወደዋለሁ፤ አሁንም ከዚህ የተለየ ስሜት የለኝም፤ ሥራዬን እወደዋለሁ፤ እንዲህ ዓይነት አደጋ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ሊያጋጥም ስለሚችል ሥራዬን ወድጄው፤ በአግባቡም እየሰራሁ ነው" ስትል ለቢቢሲ ስሜቷን አጋርታለች።
news-53931095
https://www.bbc.com/amharic/news-53931095
የትግራይ ምርጫ፡ '2.6 ሚሊዮን መራጭ ተመዝግቧል'
የትግራይ ክልል ምርጫ በመጪው ጳጉሜ አራት በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ እተደረገ ባለው የመራጮች ምዝገባ 2̂ ሚሊዮን ሕዝብ እንደተመዘገበ የምርጫው አስተባባሪ አካል አስታወቀ።
ከክልሉ ምክር ቤት ይሁንታ አግኝቶ በቅርቡ የተቋቋመው የምርጫ ኮሚሽን የመራጮች ምዝገባ ማከናወን የጀመረው ባለፈው ሳምንት ነበር። መደበኛው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ የሚጠናቀቅ ቢሆንም በተለያየ ምክንያት መመዝገብ ያልቻሉ ሰዎች ቅዳሜና እሁድ መመዝገብ እንዲችሉ ዕድል መመቻቹትን ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ለቢቢሲ ተናግረዋል። እስከዛሬ [ነሃሴ 21/2012] ባለው ጊዜ 2.6 ሚሊዮን መራጮች መመዝግባቸውን ኮሚሽነሩ ይናገራሉ። ይህም በትግራይ ክልል ታሪክ ትልቁ የመራጮች ቁጥር ነው ይላሉ። በአዲሱ ዓመት ዋዜማ የሚከናወን የትግራይ ክልል ምርጫን እንዲታዘቡ በሚል ኮሚሽኑ ለሃገር ውስጥና ለሃገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። መቀሌ የሚገኘው የቢቢሲ ባልደረባ የምርጫ ምዝገባው ባለፈው አርብ ሲጀመር በአሸንዳ በዓል ምክንያት ብዙም ሰው ሲመዘገብ ባይስተዋልም በዚህ ሳምንት ግን በርካቶች ወደ መምዘገቢያ ጣቢያዎች ሲተሙ ተመልክቷል። የምርጫ መመዝገቢያ ጣብያዎች ድምፅ ሰጪዎች ለመመዝገብ ሲመጡ የአፍና አፍንጫ ጭምብል እንዲያጠልቁና ወደ ውስጥ ሲዘልቁ እጃቸውን በሳኒታይዘር እንዲያፀዱ እንደሚመክሩ ባልደረባችን ታዝቧል። ባለፈው ሳምንት መግለጫ የሰጡት የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መረሳ ፀሐዬ 3 ሚሊዮን መራጭ ሊመዘገብ ይችላል ብለው እንደሚገምቱ ተናግረው ነበር። በክልሉ ለድምፅ መስጫ የሚሆኑ 2 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች ተሰናድተዋል። ምርጫውን ለመታዘብ ከ60 በላይ የተለያዩ አካላት መመዝገባቸው የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ሕዝብ ግነኙነት ኃላፊ አቶ አቤል ግኡሽ ለቢቢሲ ገለጸው፤ በርካታ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫውን እንዲታዘቡ ጥሪ ማድረጋቸው አመልክተዋል። በክልሉ ውስጥ ያሉ ሲቪክ ማኅበራትም ምርጫውን ለመታዘብ እየተመዘገቡ ሲሆን እስካሁን ከ60 በላይ ታዛቢዎችን ማመልከቻ መቀበላቸውን ገልፀዋል። እነዚህ መካከል ሲቪክ ማኅበራት፣ በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኅበር፣ ሌሎች የማኅበረሰብ ድርጅቶችና በትግራይ ያሉ የሐይማኖት ተቋማት ጥምረት እንደሚገኙበትና ቁጥራቸው ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል አቶ አቤል ገልጸዋል። ገዥው ፓርቲ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይን ጨምሮ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከቀናት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፓርቲዎቹ የመጀመሪያውን የምርጫ ክርክር በመገናኛ ብዙሃን በተላለፈ የቀጥታ ሥርጭት አከናውነዋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ገዥው ፓርቲ ሕወሓት ላለፉት 27 ዓመታት መሰዋዕትነት የተከፈለበትን የትግራይ ጥቅም አላስጠበቀም፤ እንዲሁም የክልሉን ሕዝብ ረስቶት ነበር ሲሉ ወቅሰዋል። በክርክሩ ላይ የተሳተፉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለትግራይ ነፃነት አሊያም በኮንፌዴሬሽን ከሌሎች ክልሎች ጋር አብሮ ለመኖር እንደሚታገሉ ይፋ አድርገዋል። ነገር ግን አሲምባ የተሰኘው ፓርቲና ገዥው ሕወሓት ከሦስቱ ፓርቲዎች [ባይቶና፣ ሳልሳይ ወያነ፣ ውናት] በተፃራሪ እንደ ሃገር አብሮ መቀጠል የሚለውን ሐሳብ ሲያንፀባርቁ ተስተውለዋል። በምርጫው ለመወዳደር ከተመዘገቡ 11 የግል ተወዳዳሪዎች መካከል ስድስት ግለሰቦች በተለያዩ ምክንያቶች ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸው ከቀናት በፊት ተዘግቧል። የኢትዮጵያ አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ቢራዘም ምርጫውን ለማካሄደው የወሰነው የትግራይ ክልል ጳጉሜ 4/2012 ምርጫውን ያከናውናል።