id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
54328500
https://www.bbc.com/amharic/54328500
ቤተሰብ፡ ልጆቻችን ስልክና ፊልም ላይ ተጥደው መዋላቸው ምን አደጋ አለው?
የዘመኑ ልጆች የስክሪን ትውልድ ናቸው፡፡ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡
እንግዳ ሲመጣ ሰውየውን ሳይሆን ስልኩን ይናፍቃሉ፡፡ ዐይናቸው ይቁለጨለጫል፡፡ ስልክ የሚሰጣቸው ዘመድ ምርጡ የቤተሰብ አባል ነው፡፡ ሐፍረት የሚባል አልፈጠረባቸውም፡፡ ስልክ ጎልጉለው ጌም የሚከፍቱበት ፍጥነት አስደናቂ ነው፡፡ የተቆለፈ ስልክ ሰብረው ሲገቡ በብርሃን ፍጥነት ነው፡፡ የዛሬ ልጆች ማህጸን ውስጥ አጭር የኮምፒውተር ስልጠና ወስደው ወደዚህ ምድር የመጡ ነው የሚመስሉት፡፡ ይህ እንደ ወላጅ እኛን ሊያሳስበን ይገባል? መልሱ 'አዎ'ም 'አይ'ም ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ አሰናጅ ስለ ልጇ ባህርይ በመተረክ ትጀምራለች፡፡ "…ልጄ ከሰው ጋር መነጋገር ከመጀመሯ በፊት ከስልኬ ጋር ነው የተነጋገረችው፡፡ ሰዎችን ከመለየቷ በፊት ስልኬን ነው የለየችው፡፡ የኔን ስልክ አባቷ ሲነካ ታለቅሳለች፡፡ የአባቷን ስልክ እኔ ከነካሁት ይከፋታል፡፡ የአባቷና የኔ ስልክ ሁለቱም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እንዴት እንደምትለየው ከፈጣሪ በስተቀር ማንም አያውቅም፡፡ እኛ ራሱ ለመለየት የምንቸገረውን እሷ እንዴት አትቸገርም? ስልኬ ላይ የሚገኝን ፎቶ ለሰው ለማሳየት እንኳ ስሞክር ልጄ ይከፋታል፡፡ ያ ስልክ የኔ ብቻ መሆኑን ነው የምታውቀው፤ ከኔ ቀጥሎ ደግሞ የሷ ነው፡፡ የሌላ የማንም አይደለም፡፡" የዚች ልጅ ባህሪ የብዙ ልጆችን ባህሪ ይወክላል፡፡ አደገኛ የስክሪን ትውልድ ነው እየመጣ ያለው፡፡ የዛሬ ልጆችን ምንም ነገር እንደ ፊልም ቀልባቸውን አይሰርቅም፡፡ ምንም ነገር እንደ ጌም አይገዛቸውም፡፡ ጠዋት ማታ ታብሌትና ላፕቶፕ ላይ ነው የሚጣዱት፡፡ ብርድ ልብሳቸው ከስክሪን ቢሰራላቸው ደስታቸውን አይችሉትም፡፡ እንቅልፍን የሚጠሉት ከስክሪን ስለሚለያቸው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህ ታዲያ እንዴት አያስጨንቅም? እንደ ወላጅ ያስጨንቃል፡፡ ለነገሩ ልጆችን በስክሪን ሱስ እንከሳለን እንጂ እኛ ብንሆን? አንብስም? ‹እኔ ለምሳሌ የስክሪን ጊዜ ለመቀነስ ብዙ ጥሬ አልተሳካልኝም› ትላለች የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ፡፡ "…እጄ ተምዘግዝጎ ቦርሳዬ ውስጥ ገብቶ ስልኬን መዞ ያወጣዋል፡፡ በስልክ ጉዳይ እጄን አእምሮዬ አያዘውም፡፡ የራሱ ጭንቅላት አለው፡፡ ስልኬን ይነካካል፡፡ ከጀመረ ማቆም ያቅተዋል፡፡ ምሽቴ በቴሌቪዥን የተሞላ ነው፡፡ መሥሪያ ቤት ላፕቶፕ ላይ ተጥጄ ነው የምውለው፡፡… በስልኬ ማኅበራዊ ሚዲያን እቃኛለሁ፣ ከዲጂታል ጉሊት አስቤዛ እገዛበታለሁ፣ መኪና ስነዳ አቅጣጫ ይመራኛል፣ ከዚህም ሁሉ አልፎ መጻሕፍትን ማንበብ ስፈልግ የድምጽ ንባብ አደርግበታለሁ፡፡ ታዲያ እኔ ማን ነኝ?" ጸሐፊዋ ትቀጥላለች… ሕይወቴ መቼ ከስክሪን ተላቆ አያውቅም፡፡ አሁን ደግሞ ይህ አባዜ ወደ ልጄ ተዛምቷል፡፡ ከኔ ይልቅ የልጄ በስክሪን ሱስ መጠመድ ያሳስበኛል፡፡ ሳይንስ ስለዚህ ነገር ምን ይል ይሆን? የስክሪን ጥሩና መጥፎዎች ሳይንስ ስክሪን ለልጆች መጥፎ እንደሆነ ይናገራል፡፡ በድፍኑ! ነገር ግን ሊያሳስበን አይገባም ይላል፡፡ ምክንያቱም በአግባቡ ከሆነ ብዙ ትሩፋቶችም አሉት፡፡ አዲስ ቴክኖሎጂዎች በየዘመኑ ሲመጡ ኅብረተሰብ ላይ ሽብር ይነዛል፡፡ ሬዲዮ ሲፈጠር እንዲያ ነበር፡፡ ቴሌቪዥን ሲፈጠር ጉድ ፈላ ተብሏል፡፡ ፈላስፋው ፕላቶ ሳይቀር ግጥምና ድራማ በተፈጠረበት በዚያ ዘመን ወጣቶች አእምሯቸው ሊበከል ይችላል ሲል ስጋት ገብቶት ነበር፡፡ በተለይ ቴሌቪዥን ቤት ውስጥ በገባበት ዘመን የቤተሰብ ሕይወት አበቃለት ተብሎ ነበር፡፡ ‹‹ይሄ አራት መአዘን ሳጥን የማያሳየው ጉድ የለም፣ ኅብረተሰብ ተበከለ፣ ባሕል ተቀየጠ፣ እሴት ተናደ›› ተብሎ ብዙ እዬዬ ተብሏል፣ በዚያ ዘመን፡፡ ምናልባት ለዚህ ይሆን ‹‹ቻርሊ ኤንድ ዘ ቼኮሌት ፋክተሪ›› በተሰኘው ዝነኛ መጽሐፉ የሚታወቀው ደራሲ ሮልድ ዳህል ድሮ በ1964 እንዲህ ሲል የገጠመው፡- "So please, oh please, we beg, we pray, "Go throw your TV set away, "And in its place you can install "A lovely bookshelf on the wall." የግጥሙን መንፈስ ብንተረጉመው ይህን ሊመስል ይችላል፡- እረ እናንተ ሰዎች ተው ተለመኑ፣ ሰው የሚላችሁን ስሙ ይሄን ቴሌቪዥን አውጥታችሁ ጣሉ፣ ልጃችሁን ሳሙ ይልቅ በዚያ ስፍራ ስቀሉ ሳጥን መጽሐፍ ደርድሩበት በዕውቀት የሚያጥን፡፡ ምንም እንኳ መጻሕፍት ለልጆች ዕውቀትን ለመመገብ እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም ይህ ማለት ግን ልጆች ቴክኖሎጂ አመጣሽ ከሆኑ ነገሮች ምንም አያተርፉም ማለት አይደለም፡፡ ልጆች እያደጉ ያሉት በስክሪን ተከብበው ነው፡፡ ወደፊት የሚጠብቃቸው ዓለም ከስክሪን የራቀ አይደለም፡፡ ስለዚህ በተመጠነ መልኩ ከስክሪን ጋር ዕውቂያ ቢኖራቸው ልንሰጋ በፍጹም አይገባም፡፡ በዚህ ዓረፍተ ነገር ሊሰመርበት የሚገባው ‹የተመጠነ› የሚለው ቃል ነው፡፡ እርግጥ ነው የልጆች የስክሪን ሱስ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈሪ ስለመሆኑ አሐዞች ያሳብቃሉ፡፡ ገና 2 ዓመት ያልሞላቸው ሕጻናት በቀን በአማካይ 3 ሰዓት በስክሪን አፍጥጠው ይቆያሉ፣ በአሜሪካ፡፡ ይህ አሐዝ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በእጥፍ ጨምሯል፡፡ ይህ ጥሩ ዜና አይደለም፡፡ ይልቅ የልጆቻችን የስክሪን ቆይታ በበዛ ቁጥር ልንደነግጥ ይገባል፡፡ ለምን? ምክንያቱም የስክሪን ቆይታቸው ስለልጆቻችን ብዙ የሚነግረን ነገር ስላለ ነው፡፡ አንደኛ ልጆች ስክሪን ላይ አፈጠጡ ማለት እንቅስቃሴያቸው ተገደበ ማለት ነው፡፡ ወደ ደጅ ወጥተው መጫወት እያስጠላቸው ይመጣል ማለት ነው፡፡ ከሰው ጋር ማውራት ቶሎ ይሰለቻቸዋል ማለት ነው፡፡ ለእራት ወደ ጠረጴዛ ለመቅረብ እንኳን ይሰንፋሉ፡፡ ከሶፋው ጋር የተሰፉ ነው የሚመስሉት፡፡ ልጆችዎ ስክሪን ላይ ተጣብቀው ዋሉ ማለት ሌላም ትርጉም አለው፡፡ ይህ ማለት ልጅዎ ለአላስፈላጊ ውፍረት ተጋለጠ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት የበሽታዎች ማደሪያና መዋያ ለመሆን በዝግጅት ላይ ነው ማለት ነው፡፡ ልጆች ከእኩዮቻቸው ጋር ደጅ ወጥተው ቢጫወቱ እጅግ ጤናማ መሆኑን ሳይንስ ደጋግሞ ደርሶበታል፡፡ የስክሪን ሰዓታቸው ሲጨምር ሌላም አደጋ አለው፡፡ እንቅልፍ እምቢኝ ይላቸዋል ማለት ነው፡፡ ኢንሶምኒያ ይይዛቸዋል፤ የእንቅልፍ እጦት በሽታ፡፡ ቦዲ-ማስ-ኢንዴክስ (BMI) የክብደትና ቁመት ምጣኔ ማሳያ ነው፡፡ ሰውነት ብዙ ስብ እንዲያከማች የሚገደደው እዚያው በልተን እዚያ ተዘፍዝፈው በሚውሉ ልጆች ላይ ነው፡፡ ልጆች ደግሞ ወዲያ ወዲህ እያሉ ካልተንቀሳቀሱ አደጋ ነው፡፡ በልጅነታቸው ሰውነታቸው ለበሽታ የተመቸ ሜዳ ይሆናል፡፡ አንድ ጥናት በመኝታ ክፍላቸው ቲቪ የገባላቸው ልጆች፣ ቲቪ በመኝታቸው ከሌለ ልጆች ይልቅ በአማካይ ግማሽ ሰዓት ያነሰ እንቅልፍ እንደሚተኙ ያስረዳል፡፡ ይህ ጥሩ ዜና አይደለም፡፡ ቲቪውን ከክፍላቸው ያውጡት፡፡ የስክሪን ትሩፋቶች እስካሁን የነዛነው መረጃ ሽብርና ፍርሃት ውስጥ የሚከት ነው፡፡ ነገር ግን የጤና አዋቂዎች ወላጆችን ያን ያህልም ስጋት አይግባችሁ ሲሉ ይመክራሉ፡፡ ሁሉም ልጆች በስክሪን በኩል የሚያዩት ነገር መቅሰፍት ይዞ አይመጣም፡፡ እንዲያውም ካወቅንበት ልጆችን ከስክሪን ተጠቃሚ ልናደርጋቸው እንችላለን፡፡ በቅድሚያ ለስክሪን መጋለጥ ያለባቸው ልጆች ቢያንስ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑት ብቻ ነው፡፡ ከ2 ዓመት በታች ላሉ ልጆች ግን ስክሪን አደጋ ነው፡፡ ልጆች የስክሪን ሰዓታቸውን ከገደብነው ቀጥሎ ሊያሳስበን የሚገባው የሚያዩት ነገር ይዘት ነው፡፡ ብዙ ወላጆች በዚህ ረገድ ነገሩ ግድም አይሰጣቸው፡፡ የልጆች ሥነ ልቡና አዋቂዎች ግን ይዘት ወሳኝ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ ልጆች ማየት ያለባቸው በባለሙያዎች የተፈቀዱ ይዘቶችን ብቻ ነው፡፡ በተለይም ከ3-5 ዓመት ያሉ ልጆች ለእድሜያቸው የተመጠነ ይዘት ያላቸውና የአእምሮ ልቀት (Cognitive skills) ላይ ያተኮሩ የቲቪ ትእይንቶችን ብቻ ቢመለከቱ ይመረጣል፡፡ ‹‹ትምህርታዊ ይዘት ያላቸው የቲቪ ትእይንቶች ለልጆች ጎጂ አይደሉም፡፡ በተለይ ብዙ የልጆች ግብአት ለማያገኙ ልጆች እንዲያውም ጥሩ እድል ነው፡፡›› ይላሉ ካቲ ሂርሽ፤ ካቲ በቴምፕል ዩኒቨርስቲ፣ ፊላደልፊያ፣ የልጆች ቋንቋ ጥናት ተመራማሪ ናቸው፡፡ ‹‹ነገር ግን ማታ የዓለም ዜና ቤተሰቡ ሲመለከት (አልጃዚራ፣ ቢቢሲ፣ ሲኤንሴን…) ልጆች አብረውን የሚመለከቱ ከሆነ እየጎዳናቸው እንጂ እየጠቀምናቸው አይደለም፡፡›› ለልጆች ያልተገቡ በይዘታቸው ነውጥ የሚበዛባቸው ጌሞች፣ ፊልሞችና አንዳንድ ጊዜም የዜና ዘገባዎች ለአዳጊዎች ጭንቅላት በፍጹም አይመከሩም፡፡ ያቀዣብሯቸዋል፡፡ በይዘታቸው አሳታፊ የሆኑ የስክሪን ቆይታዎች ይበልጥ ለልጆች ተመራጭ ናቸው ይላሉ ባለሞያዎች፡፡ ለምሳሌ በጥያቄ ቀስፎ የሚይዛቸው የጌም ዓይነት፣ ጠያቂና ሞጋች፣ አዝናኝና አስተማሪ የቲቪ ትእይንት እንዲሁም ታሪክን የሚነግር፣ ከሌላው ዓለም ካሉ ልጆች ጋር የሚያስተሳስር ማኅበራዊ ሚዲያ መጥፎ አይደለም፡፡ ልጆችን ከዘመድ አዝማድ፣ ከአክስት ልጆችና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር እንዲያወሩ ስክሪንን አንድ የመገናኛ መንገድ ማድረግም የሚበረታታ ነው፡፡ ከሁሉም አደጋ ተብሎ የሚታሰበው ልጆች ከስክሪን የሚመጣውን ነገር ተቀባይ ብቻ ሲሆኑ ነው፡፡ ይሄ ይጎዳቸዋል፡፡ አሳታፊ ይዘት ግን ይጠቅማቸዋል፡፡ አንድ ጥናት እንዳሳየው ልጆች አዲስ ቃላትን በመዝሙር ወይም ጠያቂና አሳታፊ በሆኑ ቪዲዮዎች የተሻለ መማር ይችላሉ፡፡ ያንን አዲስ ቃል በድግግሞሽ ከሚማሩት ይልቅ በተሳትፎ ቢማሩት የተሻለ ነው፡፡ ወላጆች በሥራ ይጠመዳሉ፡፡ ልጆች ሌላ ጣጣ እንዳይሆኑባቸው ይሰጋሉ፡፡ ስለዚህ አንድ ፊልም ከፍተው ታብሌት/ስልክ/ላፕቶፕ ያስታቅፏቸውና ይገላገሏቸዋል፡፡ ልጆቹ ዝም ማለታቸው እንጂ የሚያዩት ነገር በልጆች አእምሮ ስለሚፈጥረው አሉታዊ ጎን ብዙም አይጨንቃቸውም፡፡ ይህ መጥፎ ነው፡፡ ስክሪን ልጆቹን ተቀባይ እንጂ ተሳታፊ አያደርጋቸውም፡፡ የስክሪን ሱሰኛ ሆነው እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል፡፡ ልጆች በስክሪን የሚያዩትን ነገር ከወላጆቻቸው ጋር ወይም ከእኩዮቻቸው ጋር እያወሩበት ቢመለከቱት በእጅጉ የተሻለ እንደሆነ ይመከራል፡፡ ይህ የሚመከረው የልጆች አእምሮ ዕድገት ገና ያልተጠናቀቀ ወሳኝ ሂደት ላይ በመሆኑና ለዕድገቱ ደግሞ ወሳኙ ነገር መቀበል ሳይሆን መሳተፍ በመሆኑ ነው፡፡ መቀበልና መሳተፍ ቁልፍ ቃላት እንደሆኑ ልብ ይበሉ፡፡ ለምሳሌ የ15 ወር ሕጻን ከስክሪን አዲስ ቃል ሊማር ይችላል፡፡ ትልቅ ልጅ እስኪሆን ግን ያንን ቃል ለመተግበር ሊቸገር ይችላል፡፡ አሳታፊ ስክሪኖች ግን ይህን ችግር ይቀርፉታል፡፡ ልጆቹ ቃሉን እንዲደግሙት፣ ከጓደኞቻቸው ጋር እንዲያወሩበት ያበረታታቸዋል፡፡ ሌላ አንድ ሰፋ ያለ ጥናት ስክሪን ላይ አድፍጠው የሚቀመጡ ልጆች የፈጠራና ምናባዊ ምሥሎችን የመፍጠር አቅማቸው እየተዳከመ እንደመጣ አሳይቷል፡፡ ምናባዊ ምሥል ማለት የሰውን፣ የቦታንና የጽንሰ ሐሳብን ሁኔታ በምሥለ አእምሮ ቅልብጫ አድርጎ መመልከትና ያንን ለሌሎች መግለጽ መቻል ማለት ነው፡፡ ልጆች ይህን ክህሎት እንዲያዳብሩ ከእውናዊው ዓለም ጋር መስተጋብር እንዲፈጥሩ ማድረግ የተሻለ ነው፡፡ በተለይ መጻሕፍት እያነበቡ ቢያድጉ የተሻለ ጽንሰ ሐሳብን የመረዳት፣ ምሥለ አእምሯቸውም በፍጥነት የመዳበር ዕድል ይኖረዋል ይላል ሳይንስ፡፡ ስክሪን የምሥለ አእምሮ ሥራን ያራክሳል፣ ስክሪን ዓይንና ጆሮን እንጂ ሌሎች የስሜት ህዋሳቶችን አያሳትፍም፡፡ ይህ በራሱ ለልጆች ሁለንተናዊ እድገት ደንቃራ ነው፡፡ አንድ ጥናት ተካሄደ፡፡ ጥናቱ ዕድሜያቸው 3-9 የሚደርሱ 266 ልጆችን ቀኑን ሙሉ የሚከታተል ነበር፡፡ በ10 ወራት ውስጥ የምሥለ አእምሮ ወይም ምናባዊ መረዳት (imagery) የሚለካ ፈተና ቀረበላቸው፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳሳየው በስክሪን ብቻ ዓለማቸው የተገደቡ ልጆች ስለነገሮች ምናባዊ መረዳታቸው አንሶ ተገኘ፡፡ ይህም ልጆች ይበልጥ መማር የሚችሉት ነገሮችን እያደረጉ፣ እየነኩ፣ እየኖሩ መሆኑን አሳየ፡፡ ልጆች በስክሪን አንድ ነገር ስላዩ ብቻ ተማሩት ማለት አይደለም፡፡ የሚሰጣቸው ትርጉም ውስብስብ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም አእምሯቸው አልጎለበተም፡፡ ስክሪን ቀጥተኛ ተሳትፎ (Active participation)ን ሳይሆን የተዘዋዋሪ ተሳትፎን (Passive participation) የሚያበረታታ መሣሪያ ስለሆነ ነው እምብዛምም ለልጆች የአእምሮ ልቀት የማይመከረው፡፡ ይህን ቀለል ባለ ቋንቋ ለማስቀመጥ እንሞክር፡- አንዲት ሕጻን ልጅ በስክሪን ሳምንቱን ሙሉ ዳክዬ አሻንጉሊቶች ሲዋኙ የሚያሳይ ፊልም እየተመለከተች ቆየች እንበል፡፡ ይቺ ልጅ ይህንን የዋና ስሜት መረዳት፣ በምናብ ማቆየትና በአእምሮዋ ማደርጀት ይሳናታል፡፡ ለምን? ምክንያቱም ሁሉም የስሜት ሕዋሳቶቿ ተሳትፎ አላደረጉም፡፡ ነገር ግን በሳምንት ሁለት ጊዜ ዋና ቦታ እናቱ ይዛው የምትሄድ ሌላ ሕጻን፣ ስለ ውሀው፣ ስለ ዋና ቦታ መስተጋብር፣ ስለ መቅዘፍ፣ መንሳፈፍና ተያያዥ ስሜቶች በስክሪን መቶ ጊዜ ከተመለከተች ልጅ የላቀ ግንዛቤን ያዳብራል፡፡ ይህ ለምን የሚሆን ይመስላችኋል? ምክንያቱም ስክሪን ለሕጻናቱ ያደርግላቸዋል እንጂ አያሳትፋቸውም፡፡ እንዳደረጉት እንዲሰማቸው ስለሚያደርግ ሰነፍ ወይም ስልቹ የመሆን ዕድላቸው የሰፋ ነው፡፡ ሁሉም ነገር እንዲደረግላቸው ብቻ ፈላጊ ይሆናሉ፡፡ ተሳትፎን ይጠላሉ፡፡ እራት ብሉ ሲባሉ ይነጫነጫሉ፡፡ እራቱን ራሱ በስክሪን በኩል ቢመጣላቸው ይመርጣሉ፡፡ ተመራማሪዋ ሂርሽ ፓስክ ደምዳሚያቸው ይህ ነው፡- በዚህ ዘመን ከስክሪን መላቀቀ የሚቻል አይደለም፡፡ የስክሪን ጊዜን መገደብ፣ የስክሪን ይዘትን መምረጥ፣ አሳታፊ የሆኑ የስክሪን ይዘቶችን ማበረታት መልካም ግን ይቻላል፡፡ ከዚሁ ሁሉ በላጩ ግን ልጆች ደጅ ወጥተው ሁሉንም ነገር እያደረጉት ቢማሩ ነው፡፡
news-55844430
https://www.bbc.com/amharic/news-55844430
በባሌ ዞን በቁጥጥር ስር የዋለው 'ኢስላሚክ ስቴት ሴንተር' ታጣቂ ቡድን ማን ነው?
በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ዳሎ መና ወረዳ ከአልሸባብና አይኤስ ቡድኖች ጋር ትስስር አለው የተባለ እና ራሱን 'ኢስላሚክ ስቴት ሴንተር' ብሎ የሚጠራ ቡድን በቁጥጥር ሥር መዋሉን ቢቢሲ ያነጋገራቸው በኦሮሚያ የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጂብሪል አህመድ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ይህ ቡድን መርሆውና አስተምህሮው ከአይኤስ ጋር አንድ መሆኑን የሚናገሩት ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወረዳው መጅሊስ ኃላፊ ሼህ ሁሴን አሊ በአካባቢው ለረዥም ጊዜ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ቡድኑ አንድ እስላማዊ መንግሥት በአንድ ኢምር ስር ሆኖ መግዛት አለበት በሚል ዓላማ እንደሚንቀሳቀስም አቶ ጂብሪል አክለው ገልፀዋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ግለሰቦች መካከልም ወጣቶችና ሴቶች ይገኙበታል ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ቡድን ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም ከሶማሊያ ክልል የተመለመሉ አባላት እንደሚገኙበትም ቢቢሲ ያነጋገራቸው እኚህ ኃላፊ አረጋግጠዋል። መንግሥትን በኃይል ለመጣል እየተንቀሳቀሰ ነበር የተባለው ይህ ቡድን በአስተምህሮ ለመንግሥት ግብር መክፈል እንደማይገባ ሲያስተምር መቆየቱም ተገልጿል። አቶ ጂብሪል እንዳሉት፤ ይህ ቡድን ሰዎችን በመመልመል፣ ገሚሱን ሥልጠና አስገብቶ ሌሎቹን ደግሞ ለሥልጠና እያዘጋጀ በነበረበት ወቅት በፀጥታ አካላት ክትትል ቁጥጥር ሥር ውሏል። በደሎ መና ነዋሪ የሆኑት አቶ ሡልጣን ቡድኑ "ካዋሪያ በማለት ራሱን ይጠራል" ሲሉ ይገልጹታል። ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደር ጊዜ አንስቶ በአካባቢው እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበርም ይናገራሉ። የካዋሪያ ቡድን ማን ነው? የደሎ መና ነዋሪ የሆኑት አቶ ሡልጣን ይህ ቡድን በወረዳቸው ውስጥ ለረዥም ጊዜ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሌሎች የእስልምና እምነት ተከታዮች ራሱን በመለየት "የአክራሪነት አመለካከት" ይዞ ሲንቀሳቀስ ነበር ይላሉ። የቡድኑ አባላት ግማሾቹ ከሶማሌ፣ ከሐረር፣ ከወለጋ እና ከሌሎች ቦታዎች መምጣታቸውንም ለቢቢሲ አስረድተዋል። "ከዚህም ብዙ ሰዎች እንደተቀላቀሏቸው አውቃለሁ። እያስተማሩ ወደ ራሳቸው ይጨምሩ ነበር። ከሙስሊሞች ጋራ አይዋደዱም። ይህ ቡድን ለረዥም ዓመት የእኛን እምነት ያጠፋ ነው። መንግሥትም ይቆጣጠርልን በማለት ሕዝቡ አቤቱታውን ሲያሰማ ነበር የቆየው።" እንደ አቶ ሡልጣን ይህ ራሱን ካዋሪያ ብሎ የሚጠራው ቡድን በደሎ መና ወረዳ አዮዳ እና ሸዌ የሚባሉ ስፍራዎች ሠፍሮ ነበር። "አሁን ደግሞ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወደ ደጋው ገቡ። እዚያም ተጋጭተው አንድ ታጣቂ እንደሞተ አውቃለሁ፤ ሴቶችም በመካከላቸው ይገኛሉ። ከፀጥታ አካላት ጋር ተታኩሰው ገሚሶቹ ሲሸሹ ቀሪዎቹ ደግሞ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አውቃለሁ" ብለዋል። ሼህ ሁሴን አሊ በደሎ መና ወረዳ ነዋሪና የወረዳው መጅሊስ ኃላፊ ሲሆኑ ስለዚህ ቡድን ሲናገሩ "በፊት ካዋሪያ በመባል ይታወቃሉ፤ አሁን ደግሞ እስላማዊ መንግሥት እናቋቁማለን ነው የሚሉት፤ ይህ ደግሞ ትክክለኛው እስልምና አይደለም። ከውጪ አካላት እንደ ዳዒሽ ካሉ ጋራ ግንኙነት እንዳለው እየሰማን ነው። ከመለስ ዜናዊ አስተዳደር ጀምሮ ነው ስለ እነዚህ ሰዎች አቤቱታ ስናሰማ የነበረው። ይኹን እንጂ በቁጥጥር ሥር ካዋሏቸው በኋላ ለቀቋቸው" ብለዋል። "ግብር መክፈል ሃራም ነው" ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወረዳው ነዋሪ አቶ ሡልጣን እንደሚሉት ቡድኑ "በካፊር መንግሥት አንተዳደርም። ቢቆይም ሥልጣን እንይዛለን ብለው ያምናሉ፤ አቋማቸውንም ሕዝቡ ያውቃል" ይላሉ። "ለዚህ መንግሥት ግብር መክፈልን አይፈልጉም። ግብር ለፈጣሪ ብቻ ነው የሚከፈለው። የሚከፈል ግብር ሃራም ነው የሚሉ አካላት ናቸው። ከራሳቸው ተከታዮች ውጪ ሌሎች ሴቶች እንኳ አያገቡም" በማለት አቶ ሡልጣን ያብራራሉ። ራሱን ካዋሪያ በማለት የሚጠራው ይህ ቡድን እስላማዊ መንግሥት እናቋቁማለን ከሚሉ ጋር ተመሳሳይ አቋም እንዳለው የደሎ መና መጅሊስ ኃላፊ ሼህ ሁሴን አሊ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። "በእኛ መስጂድ አይሰግዱም" ሼህ ሁሴን የዚህ ቡድን ተከታዮች ሌሎች ሙስሊሞች በሚሰግዱበት መስጂድ ውስጥ እንደማይሰግዱ ይናገራሉ። ሶላታቸውም የተለየ ነው ብለዋል። "ዋናው ዓላማቸው ሙስሊምም ሆነ ክርስቲያን ሃሳባቸውን የሚቃወም ከሆነ ገድሎ ማጥፋት ነው። ከምሽት ከ4 ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ ተሰብስበው ከተወያዩ በኋላ ሳይነጋ እንደሚበተኑ ስንሰማ ቆይተናል። በኋላ ላይ ደግሞ የራሳቸው የሆነ እስላማዊ መንግሥት እናቋቁማለን፤ ለመንግሥት ቀረጥ አንከፍልም፤ አሁን ያሉት መስጂዶች እና ቤተ ክርስትያናት መቃጠል አለባቸው በማለት ሲንቀሳቀሱ ነበሩ" ይላሉ የመጅሊሱ ኃላፊ ሼህ ሁሴን። የቡድኑ አባላት ናቸው የተባሉት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው በተዘገበበት ወቅት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣብያው አህመድ ረሻድ የሚባሉ ግለሰብ የዚህ ቡድን አስተምህሮች ከአይኤስ ጋር ተመሰሳይነት ሊኖረው እንደሚችል ሲናገሩ ተደምጧል። ሼህ ሁሴን በበኩላቸው እንደ ሙስሊም ማህበረሰብ ስለዘህ ቡድን ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መሰራቱን ይናገራሉ። "የእነርሱ አስተምህሮ ትልቅ ስህተት ይፈጥራል። ቅዱስ ቁርዓንን አዛብተው ነው የሚናገሩት። ስለዚህ በትክክል ቁርዓንን የማያውቁ ሰዎችን ሊያሳስቱ ይችላሉ" ብለዋል ሼህ ሁሴን። የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ሡልጣን እንደሚሉት፤ ቡድኑ ሼህ እንዳለውና፣ ገርባ ሃሬ በሚባል ስፍራ ላይ እንደሚያስተምሯቸው ይናገራሉ። መንግሥት ምን አለ? የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጂብሪል አሕመድ "ይህ ቡድን ራሱን ለሽብር ሲያዘጋጅ ነበር። በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ሰዎችን በማሰባሰብ አዲስ ኃይል ለማሰልጠን የሥልጠና ስፍራ አስገብቷል። ሥልጠናውም የትጥቅ ስልጠና ነው። እንዲሁም ሌሎቹ በዝግጅት ላይ ነበሩ። ቡድኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሰላም በማወክ ወደ አፍሪካ ቀንድ ለመሸጋገር ያለመ ይመስላል" ብለዋል። አቶ ጂብሪል፤ ይህ ቡድን ዓላማዬ እስላማዊ መንግሥት መመስረት ነው ቢልም በሱማሊያ ከሚንቀሳቀሰው አልሸባብ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የአገሪቱን ሰላም ማወክና የሽብር ተግባር መፈፀም አጀንዳው ነበር ሲሉ አክለዋል። መንግሥት ይህን ይበል እንጂ ቢቢሲ ከተባለው ቡድን በዚህ ጉዳይ ላይ ያረጋገጠው ነገር የለም። "የአል ሸባብን ተልዕኮ በመቀበል በአገሪቱ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው። በፀጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍተው ነበር። በፀጥታ አካላትም ከዚህ ቡድን አባላት ሰዎች ተገድለዋል" ብለዋል አቶ ጂብሪል። በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች የውትድርና ሥልጠና መውሰዳቸውን ሲገልፁ፣ በተጨማሪም ለሥልጠና ተዘጋጅቶ የነበረው ሥፍራ ላይ በመድረስ ማፍረሳቸውን ተናግረዋል። አሁንም የፀጥታ አካላት ቡድኑ ሲንቀሳቀስበት በነበረው ሥፍራ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አቶ ጂብሪል አክለው ተናግረዋል። ይኹን እንጂ ይህ ቡድን በማን እንደሚመራ እና ታጥቀው ጫካ ውስጥ ይገኛሉ ከተባሉት በቁጥጥር ስር የዋሉት ምን ያህል እንደሆኑ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።
news-47702784
https://www.bbc.com/amharic/news-47702784
ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት
ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉትን የጌዲዮ ጉብኝትን ትከትሎ ተፈናቃዮች በመንግሥት ላይ ተስፋቸው ከፍ ያለ ይመስላል። የቢቢሲ ዘጋቢዎች በስፍራው ተገኝተው ያዩትን፣ የችግሩን ስፋትና አሳሳቢነት እንዲህ ይተርካሉ።
እቴነሽ አበበ ልጇን የተገላገለችው መንገድ ላይ በሽሽት ላይ ሳለች ነበር የዓይናለም ከፍያለው ምጥ በሃያዎቹ መጀመሪያ የምትገኘው ዓይናለም ከፍያለው አራተኛ ልጇን የተገላገለችው በጌዲዮ ዞን፥ ገደብ ወረዳ ጎቲቲ ቀበሌ ከሚገኙ ስድስት የተፈናቃይ መጠለያዎች በአንደኛው ውስጥ ነው። ተያይዘው ከተደረደሩ ጠባብ የድንኳን መጠለያዎች በአንደኛው ውስጥ፥ የረባ ምንጣፍ እንኳ ባልለበሰ አቧራማ መሬት ላይ የሦስት ቀን ዕድሜ ያለው ጨቅላ ልጇን አቅፋ ተቀምጣለች። "ምጥ ሲይዘኝ አጠገቤ ማንም አልነበረም፤ እዚሁ መሬት ላይ ነው የወለድኩት" ትላለች ድካም በበረታበት ድምፅ። በወርሃ ታኅሣሥ መጀመሪያ ትኖርበት የነበረውን የምዕራብ ጉጂ ዞን የኋሊት ጥላ፥ ይደርስብኛል ብላ የሰጋችውን ጥቃት ሽሽት ወደጌዲዮ ዞን ስታቀና ጉዞ የዋዛ እንዳልነበር ለቢቢሲ ታስታውሳለች። "ብዙ ሩጫ ነበር። እኔ ደግሞ እርጉዝ ነበርኩ። እና ስወድቅ ስነሳ ነው እዚህ የደረስኩት። ስወድቅ ጉዳት ደርሶብኛል። አሁን ብታዩት ሦስት አራት ቦታ ታስሯል ወገቤ። ሩጫ ላይ ስለወደቅኩ።" በቀድሞ መኖሪያዋ በቡና እና እንሰት እርሻ ትተዳደር እንደነበር ለቢቢሲ ዘጋቢ የገለፀችው ዓይናለም፥ "እዚያ እያለን፥ ቆጮ በጎመን፥ ቆጮ በሥጋ እየበላን ጠግበን ነበር የምናድረው። ምንም የምግብ ችግር አልነበረም። ኑሯችን ጥሩ ነበር። እዚህ ከመጣን በኋላ ግን ኑሮው ምንም ሊመሳሰል አልቻለም። ሌት ተቀን እየራበን ሲመጣ የምግብ ፍላጎቱም እየቀነሰ መጣ" ስትል ትናገራለች። ከወሊድ በኋላ ምግብ ለመመገብ የተቸገረች በመሆኑ ጨቅላ ልጇንም ጡት ማጥባት አልቻለችም። "በመጥፎ የጤና ሁኔታ ውስጥ ነው ያለሁት። ያገኘሁት ምንም ዓይነት ሕክምና የለም" ትላለች:: ዓይናለም በጎቲቲ ቀበሌ ከሠፈሩ በዐሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች መካከል አንደኛዋ ናት። ተፈናቃዮቹ በአብያተ ክርስትያናት ውስጥ እና በአካባቢው በሚገኙ አንድ አንድ ቦታዎች ላይ በድንኳን፣ ሌሎች ቦታዎች ላይ ደግሞ በጭራሮ እና ቅጠላ ቅጠሎች እንደነገሩ በተሸፋፈኑ ጠባብ ማደሪያዎች ውለው ያድራሉ። ለወራት ያህል ማንም ዞር ብሎ አላየንም ሲሉ በምሬት የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ለውጥ መኖሩን ይመሰክራሉ። የተለያዩ የዜና ዘገባዎች እና የማኅበራዊ ሚዲያ ዘገባዎች የችግሩን ጥልቀት ካመላከቱ በኋላ በግለሰብም ይሁን በተቋም ደረጃ እርዳታ የማሰባሰብ እንዲሁም ወደ ስፍራው የማድረስ ጥረቶች ተጠናክረው ተስተውለዋል። ምግብ እና አልባሳትን ይዘው ወደመጠለያዎቹ የሚያቀኑ አካላትም ከወራት በፊት ከነበረው ተሽሎ ታይቷል። ይሁንና የሚቀርበው እርዳታ፥ ለተረጂዎቹ ከሚያስፈልገው ጋር ሊመጣጠን ቀርቶ ሊቀራረብ እንኳ እንዳልቻለ የቢቢሲ ዘጋቢዎች በስፍራው ያነጋገሯቸው በጎ ፈቃደኞች እና የምግባረ ሰናይ ድርጅት ሠራተኞች ይገልፃሉ። በመጠለያ ጣብያዎቹ ከምግብ እጥረት እና ከንፅህና ጉድለት ጋር በተገናኘ የተለያዩ በሽታዎች መስፋፋታቸው ከእስካሁኑም የከፋ መዘዝ እንዳያመጣ ስጋታቸውን የገለፁልን ባለሞያዎችም አሉ። የእቴነሽ አበበ ስቃይ የሠላሳ ሁለት ዓመቷ እቴነሽ አበበ ስምንት ልጆች አሏት። ያቀፈችውን የመጨረሻ ልጇን የወለደችው ከሁለት ወራት በፊት ከምዕራብ ጉጂ ዞን በምትሸሽበት ወቅት መንገድ ላይ ነው። "ስወልድ ከፍተኛ ችግር ነበር። አንደኛ ከኋላ እያባረሩን ነው። ከፍተኛ ደም እየፈሰሰኝ ነበር። ባሌ አብሮኝ ነበር። ሁለት ጉርድ ልብስ ነበር፤ በእርሱ እያሰርን፥ እያስታገስን ነው ወደዚህ የመጣነው" ትላለች ሁኔታውን ስታስታውስ። በጎቲቲ ቀበሌ ግንባታ ላይ ባለው ቃለእየሱስ ቤተክርስትያን ውስጥ በሚገኘው ጊዜያዊ የመጠለያ ጣብያ ከገባች በኋላ ተገቢውን የጤና እንክብካቤ ማግኘት ቀርቶ የሚላስ የሚቀመስ እንኳ ብርቅ ሆኖባታል። እንዲያም ቢሆን "ከሁሉም ነገር ሕይወት ስለምትበልጥ እስካሁን ሕይወቴ አለች" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ለትምህርት የደረሱት ልጆቿ ከመደበኛ ትምህርት ተለያይተዋል፤ በዕድሜ ከፍ ያሉት አምስቱ በተለያዩ ቤቶች ውስጥ ሥራ በመቀጠራቸው ርቀዋታል። ሦስቱ ግን አብረዋት በመጠለያ ጣብያው ውስጥ አሉ። ታዲያ ከምንም በላይ የሚያሳስባት የሁለት ወር ጨቅላ ልጇ የጤና እክል ነው፤ "ያስመልሳታል፥ ትኩሳት አላት፥ ያስቀምጣታል።" ካለፈው ሰኞ መጋቢት ዘጠኝ አንስቶ አነስተኛ የሕክምና ባለሞያዎች ቡድን በመጠለያ ጣብያው ውስጥ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። "በአጭር ጊዜ ውስጥ ማከም የምንችለውን በሽታ ለማከም ነው የመጣነው" ይላሉ ቡድኑን የሚያስተባብሩት እና በቋሚነት በዲላ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የሚሠሩት ዶክተር መላኩ ጌታሁን። የቆዳ ላይ እከክ (ስኬቢስ) እና ከፍተኛ የምግብ እጥረት በተለይ እስከ አምስት ዓመት ባሉ ሕፃናት ላይ የሚስተዋሉ የጤና እክሎች ሲሆኑ፤ ሁሉም ሕፃናት ሊባል በሚችል ደረጃ የዓይን በሽታ (ኮንጃክቲቫይተስ) ተጠቂዎች መሆናቸውን ዶክተር መላኩ ያስረዳሉ። እርሳቸው በነበሩበት የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አንድ ሕፃን ከምግብ እጥረት ጋር በሚያያዙ የጤና ችግሮች ምክንያት ሕይወቱ ማለፉንም ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? የዓለሙ ዋቆ ተስፋ በመጠለያ ጣብያዎቹ ውስጥ በርካታ ነብሰ ጡሮች በመኖራቸው፥ የተቻለውን ያህል አይረን እና ፎሊክ አሲድ ለማቅረብ እየሞከሩ፥ የቲቢ በሽተኞችንም ለመለየት ሥራ መጀመራቸውን የሚናገሩት ሐኪሙ፤ የችግሩ መጠን እና የቡድኑ አቅም ያለመመጣጠን፥ ከቡድኑ ጊዚያዊነት ጋር ተደማምሮ ለከፋ የጤና ችግር መፈልፈል ምክንያት እንዳይሆን ስጋት አላቸው። በመጠለያ ጣብያው ውስጥ ወራትን ያሳለፉት ተፈናቃዮች በበሽታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ጥቂት የማይባል እንደሆነ ይናገራሉ። በጎ አድራጊዎች የድጋፍ እጃቸውን ባይዘረጉለት ኖሮ የሁለት ዓመት ተኩል ልጁን በሞት ይነጠቅ እንደነበር የሚናገረው ዓለሙ ዋቆ ነው። የአርባ አምስት ዓመቱ ዓለሙ በሽሽት መሀል ከሚስቱ ጋር ከተጠፋፋ በኋላ ሕይወቷ ማለፉን ሰምቷል። "የፀጥታ ችግር ሲነሳ ሁላችንም ሕይወታችንን ለማትረፍ እየሮጥን ነበር። እርሷም በዚያውም መልክ ሸሽታ ነበር። ምሥራቅ ጉጂ ውስጥ ነው የሞተችው። በምን እንደሞተች፥ ማን እንደገደላት ግን አላውቅም።" ስምንት ልጆቹን ይዞ በጎቲቲ ጊዜያዊ መጠለያ ጣብያ በሚኖርበት ጊዜ ነው የመጨረሻ ልጁ የሰናይት ጤና ይታወክ የያዘው። • የክልል እንሁን ጥያቄ እዚህም እዚያም? • አምስት ነጥቦች ስለጌዲዮ ተፈናቃዮች "ያስመልሳታል፥ ቆዳዋን ያሳክካታል፥ ያስቀምጣታል" ይላል በይርጋ ጨፌ ከተማ ላገኛቸው የቢቢሲ ዘጋቢዎች። አካሏ ክፉኛ ተጎሳቁሎ፥ ሰውነቷ ተመናምኖ እጅጉን መጠውለጓን ያዩ በይርጋ ጨፌ ከተማ አንድ ክሊንክ ያላቸው የሕክምና ባለሞያ ልጁን ይዞ እንዲመጣ ካደረጉ እና የጤና ክብካቤ በነፃ ማቅረብ በጀመሩበት ጊዜ ሰናይት ከሞት አፋፍ ላይ እንደነበረች ይገልፃል። በጎቲቲ ካሉ የመጠለያ ጣብያዎች በአንደኛው የምትገኛው ሌላኛው ሴት ልጁ በላይነሽ በተመሳሳይ የጤና ችግር ክፉኛ መያዟን ዓለሙ ይናገራል። ቀድሞ የሚኖርበትን ስፍራ ለቅቆ ከሸሸ በኋላ መተዳደሪያውን ግብርናን መተውን የሚያስረዳው ዓለሙ "በድጋፍ የምናገኘውን እንበላለን እንጅ ከዚህ ሌላ ምንም ገቢ የለንም" ይላል። "መንግሥት የሚያደርገውን ነገር ተስፋ አድርጌ እየጠበኩኝ ነው። ሌላ ምንም ተስፋ የለኝም።"
47512844
https://www.bbc.com/amharic/47512844
የቱኒዚያው ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በ11 ህፃናት ሞት ምክንያት ስልጣን ለቀቁ
ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አብደራሁፍ ቸሪፍ ስልጣናቸውን የለቀቁት በአገሪቱ መዲና ቱኒዝ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ባለቀው ሳምንት በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 11 ህፃናት ከኢንፌክሽን ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ነው።
የቱኒዚያ ህክምና አገልግሎት በሰሜን አፍሪካ አድናቆት የተቸረው ነበር የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ከተሾሙ ገና አራት ወራቸው ነበር። ሁኔታውን ተከትሎ የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሱፍ ቻሂድ በአገሪቱ አጠቃላይ የመንግስት ጤና ተቋማት፣ የመድሃኒትና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ተቋማት ሰፊ ምርመራ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። የቱኒዚያ የህፃናት ሃኪሞች ማህበር በፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው ለ11ዱ ህፃናት ህልፈት ምክንያት የሆነው ኢንፌክሽን ደረጃውን ባልጠበቀ መድሃኒት የተከሰተ ሊሆን ይችላል። • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች • በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም የተቀሰቀሰው ውዝግብ ማህበሩ በአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጡ ያለበት ሁኔታም አደገኛ መሆኑን ጠቁሟል። ቀደም ባሉት ዓመታት የቱኒዚያ የህክምና አገልግሎት የተደነቀና በህክምና ቱሪዝምም ለአገሪቱ ጥሩ ገቢ ያስገኘ ነበር። ነገር ግን እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 የፕሬዝዳንት ዜን ቢን አሊ ከስልጣ መውረድን ተከትሎ የአገሪቱ ጤና ዘርፍ በአመራር ጉድለትና በገንዘብ እጥረት ከባድ ችግር ውስጥ ወድቋል።
53628661
https://www.bbc.com/amharic/53628661
ጾታዊ ጥቃት፡ በስድስት ወንዶች የተደፈረችው ታዳጊ ሰቆቃ
ዝናቡ ሳይበግራቸው በጠዋት ነበር የህክምና ባለሙያዎች የጎዳና ተዳዳሪ ሴት ህጻናት መከላከያ ተሃድሶና መቋቋሚያ ግቢ የደረሱት።
በድርጅቱ ከ20 በላይ በተለያየ ዕድሜ የሚገኙ ህጻናት እና ሴቶች ይገኛሉ። (ስለተወሰኑት ህጻናት በቅርቡ እንመለስባቸዋለን።) የህክምና ባለሙያዎቹ የወቅቱን ትኩሳት ኮቪድ-19 ለመመርመር ነው የተገኙት። መጀመሪያ ህክምና የተደረገላት 10 ዓመት የሚሆናት ልጅ ናት። ቀጥሎ ደግሞ የዛሬዋ ባለታሪክ። ምርመራዋን አጠናቅቃ ከደቂቃዎች በኋላ መጣች። 17 ዓመቷ እንደሆነ ነው የተነገረን። የአፍና በአፍንጫ ጭንብል እድርጋ ነው የመጣችው። ቁመናዋን ስንመለከት ግን 17 ዓመትም የሞላት አትመስልም። ማህሌት አበበ (ለዚህ ታሪክ ሲባል ስሟ የተቀየረ) እንደምትባል እና ዕድሜዋ በትክልልም 17 እንደሆነ ገለጸችልን። ውልደቷም ዕድገቷም ምዕራብ ጎጃም ነው። ትምህርቷንም ዕድሜዋ እስከሚፈቅድላት ድረስ ገፍታለች። (ሁሉንም መረጃዎች የጠየቅናት ቢሆንም እንዳንዶቹን ማንነቷ በቀላሉ እንዳይለይ ለማድረግ አስቀርተናል።) ትምህርቷን ለመቀጠል ነበር ወደ ባህር ዳር ያቀናችው። ይህ ጉዞዋ ከቤተሰብ አባላት 'ይሁን' ተብሎ የተፈቀደ ነበር። በተለያየ ምክንያት ትምህርት የመቀጠል ህልሟ ሊሳካ አልቻለም። ሌላ ውሳኔ። ሌላ እርምጃ። ሌላ አማራጭ። ፊቷን ወደ ሥራ አዞረች። "የተገኘውን እሠራ ነበር። ፑል ማጫወትም ጀምሬ ነበር። ቀጥሎ ግሮሰሪ ላይ ማስተናገድ ጀመርኩኝ" ስትል ያለ እድሜዋ ብዙ ሥራዎችን መሥራቷን ትናገራለች። ሥራውን ለማግኘት ብዙም አልከበዳትም። በሚያውቋት እና አሠሪዎቿን በሚያውቁ ሰዎች ነው ሥራዎቹን ያገኘችው። መጨረሻ ላይ የሠራችው በአንድ አነስተኛ ግሮሰሪ ነበር። ረቡዕ ሰኔ 10/2012። የተለመደው ቀን ነበር። ስለ ዕለቱ ስታወራ ትንሽ ዝም ከማለት ውጭ ከጀመረች በኋላ ያለማቋረጥ ታሪኳን ታጫውተን ጀመር። በኮሮና ምክንያት ሥራ አቁመን ስለነበር ዝም ብዬ ቤት ነበርኩ። 10 ሰዓት ሲሆን እንደተለመደው አየር ለመቀበል 'ዎክ' ለማድረግ ወጣሁ። ጉዞ ደግሞ ወደ ጣና ሆነ። ወጣሁኝ። ሰፈር ጓደኛዬ ነበር። ትንሽ ዎክ አድርገን ነፋስ ተቀብለን ሳይመሽ ወደ ቤት እንመጣለን ተባብለን ወጣን። አብሯት ያለው የፍቅር ጓደኛዬ አይደለም። ሰፈር ውስጥ የማውቀው ጓደኛዬ ነው። 10፡30 አካባቢ ይሆናል። ሰፈር ውስጥ በዓይን ብቻ የማውቀውን ልጅ ሠላም አልኩት። ከልጁ ጋር ምንም አይነት ቅርርብም የለንም። ከእሱ በተጨማሪ ሁለት ጓደኞቹም አብረውት ነበሩ። ሁለቱ ጓደኛዬን ሳብ አደረጉትና አስቀሩት። እሱ [ጓደኛዬ] የዚህ ሃገር [ባህር ዳር] ልጅ ስለሆነ የሚያውቁት ነው የመሰለኝ። ስሙን ጠርተው ወደ ኋላ ሳቡት። እሱን ለካ አባረውታል እኔን ይዘውኝ ሄዱ። በዓይን የምታውቀው ልጅ እያወራ አብሯት ሲሄድ 'ጓደኛዬ አይመጣም ወይ?' እያልኩ ዞር ብዬ አይ ነበር። [በዓይን ብቻ የማውቀው ልጅ] ቁጭ ብሎ በሠላም ሲያዋራኝ ቆየ። 'የምን ሃገር ልጅ ነሽ? ምንድነው የምትማሪው? ሥራ እንዴት ነው? እያለ ሲጠይቀኝ ቆየ። እሱ በሥራ ልብስ ነበር። የጋራዥ ልብስ ለብሶ ነበር። በኋላ 'ልሄድ ነው' አልኩት። 'ልሄድ ነው' ስለው 'አይ የትም አትሄጂም' አለኝ። 'ለምን?' ስለው 'ከእኔ ጋር የሆነ ቦታ ትሄጃለሽ' አለ።" እኔ 'የትም አልሄድም' ስለው አስፈራቶ ጩቤ ምናመን አውጥቶ የሆነ ቦታ ወሰደኝ። [ባህር ዳር] ቀበሌ 3 ማለት ነው። ጩቤ ይዞ እያስፈራራኝ ነበር። ሁለቱ ጓደኞቹ መጡ። ጓደኛዬ ግን የለም። ጩቤ ጎኔ ላይ ይዞ ነው የወሰደኝ። መጮህም አልቻልኩም ብትነፍሺ ወየውልሽ እያለ ያስፈራራኝ ነበር። አንድ ቤት ይዞኝ ሄደ። ትልቅ ግቢ ነው የቆርቆሮ አጥር አለው። ቤቱ ፍርስርስ ያለ የጭቃ ቤት ነበር። ሰው አይኖርበትም። እዚያ ወሰደኝ። ስንገባ ደግሞ 3 ልጆች አገኘን። ከእነሱ ጋር ሠላም ተባባለ። እኔን 'ሂጂ ተቀመጪ' ሲለኝ 'አልቀመጥም' ስለው 'አንቺ ተቀመጪ ቀበጥሽ' ብለው አስፈራሩኝ። በጥፊ ሁሉ መቱኝ። ሰፈር ውስጥ የማውቀው ልጅ ሌሎቹን ከግቢው ውስጥ አስወጣቸው። ግቢው በጣም ትልቅ ነው። እኔ እያለቀስኩ ነበር። 'ነይ' አለኝ 'ምንድነው?' ስለው። 'ሁሉም ጓደኞቼ ያሰቡት እየመጡ ካንቺ ጋር ግንኙነት ሊያደርጉ ነው። እኔ ደግሞ ያ እንዲሆን አልፈልግም ምክንያቱም በሰፈር ስለማውቅሽ እንደዚህ እንዲሆን አልፈልግምና እነሱ እንዳይመጡ መጀመሪያ ከእኔ ጋር ግንኙነት ማድረግ አለብሽ' አለኝ። በአይን እንጂ አላውቀውም። ስሙንም ያወቅኩት ሲጠሩት ነው። 'ከእኔ ጋር ግንኙነት አድርገሽ ላስወጣሽ' አለኝ። 'አልፈልግም' አልኩት። 'እነሱም ማድረግ ፈልገዋል' አለኝ። 'እረ በእናትህ ብዬ' ብዙ ለመንኩት። 'ምን አይነት ነሽ? በሁሉም መደፈር ፈልገሽ ነው?' ብሎ ሰደበኝ። 'እኔ እንደዛ ፈልጌ አይደለም። ግን አልፈልግም' ብዬ ያላቀረብኩት ምክንያት የለም። ከዚያ 'አላውቅልሽም' ብሎ በጥፊ መታኝ። ቤቱ ጋደም ያለ ነው። መሬቱ አፈር ነው። በጭቃ ነው የተሰራው። ፍርስርስ ያለ ነው በጣም። ምንም የተነጠፈ ነገር የለም። 'ተኚ' አለኝ። 'ተኚ ልብስሽን አውልቂ' ሲለኝ 'እምቢ' አልኩት። የቅድሙን ጩቤ አወጣና 'በዚህ ነው የምዘለዝልሽ' አለኝ። 'እምቢ' ስለው በጣም ብዙ ታገለኝ። ቱታ ነበር የለበስኩት። ሰፊ ቱታ ነበር። እሱን በ 'እንደዚህ ነው ራቁትሽን የምልክሽ' ብሎ በጩቤ ቀዳደደው። እየወጋጋ ብጥርቅ ብጥርቅ እያደረገ ብዙ ቀዳደደው። አለቀስኩ። እንደምንም እየታገለኝ እየመታኝ በእግሩ እየረጋገጠ [ወሲብ ፈጽሞ] ከጨረሰ በኋላ 'ነይ ላስወጣሽ' ብሎ እጄን ያዘኝ። 'በሠላም ቢሆን ኖሮ እንደዚህም አትጎጂም። ልብስሽም አይቀደድም' አለኝ። 'በሠላም ከእኔ ጋር ብታደርጊ ኖሮ እንደዚህ አታለቅሺም' አለኝ። ፊቴ አብጦ ነበር። 'እስኪ ተጎዳሽ?' እያለ ሲያይልኝ 'አትንካኝ' እያለኩ እያለቀስኩ እጄን ጎትቶ ወሰደኝ። መቶኝ ስለነበር ነው [ፊቴ] ያበጠው። ሆዴንም ረግጦኛል። እምቢ እያልኩት ነበር [የደፈረኝ።] ታግዬዋለሁ። ተኝቼም ብዙ ይመታኝ ነበር። ከዚያ እጄን ጎትቶ ወደ ግቢው አስወጣኝ። ግቢው መሃል ላይ 'ቁሚ እዚህ' አለኝ። 'ለምን?' ስለው 'ላስወጣሽ አይደል? እነሱ [ግቢ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ጓደኞቹ] መኖራቸውን ልይ' አለኝ። ፈርቼ ከኋላው ከኋላው ተከተልኩት። ለካ ጓደኞቹ ውጭ ነበሩ። አውቆ ነበር እንደዚያ ያለኝ። በሩን ከፍቶ 'ቻው' ብሎ ስቆብኝ አለ አይደል አላግጦ 'ቻው' ብሎ ወጥቶ ሄደ። ከዚያ አምስቱ ተከታትለው ገቡ። ከዚያ 'እረ በማርያም ብዬ ኡኡ' ብዬ ጮኽኩኝ። [ከአምስቱ] 3ኛው ልጅ 'አንቺ ቀበጥሽ' ብሎ እንትን ነገር ቆረጠ። ግቢው በጣም ሰፊ ነው፤ ዛፍ ምናምን አለው። ሽመል ነገር ቆርጦ 'አልቀበጥሽም?' ብሎ መታኝ። አንደኛው እጄን ይዞኝ '[የመጀመሪያውን ልጅ ስም ጠቅሶ] ስለኔ አላወራሽም' አለኝ? 'እረ ምንም አላወራኝም' አልኩት። 'ነይ ግቢ' ብሎ ሁሉም ካደረጉ [ወሲብ አብረውኝ ከፈጸሙ] በኋላ ወጥተው ሄዱ መጨረሻ ላይ። በወቅቱ [ሲደፍሩኝ] በጣም ያመኝ ነበር። መሃል ላይ ራሴን ስቼ ነበር። የሚያደርጉትን ግን አውቃለሁ። ከሦስተኛው በኋላ መታገል አቃተኝ። ራሴን መታኝ። አንዱ ደረቴን ሲመታኝ ጸጥ አልኩኝ። ውሃ ሁላ ደፍተውብኛል። ውሃ ደፍተውብኝ ሲቆነጥጡኝ ሁላ አልሰማም። አያቸዋለሁ ግን አልሰማም ነበር። ሲቆነጥጡኝ አላመመኝም። በጥፊ ሁላ ይመቱኛል። ግን ምንም አያመኝም ነበር። ምን እንደሚያደርጉ አያቸው ነበር። ሰውነቴ ዛለ። ሰውነቴን መቆጣጠር አልችልም ነበር። ውሃ ከደፉብኝ በኋላ ነቃሁ። በጣም ታምሜ ነበር በሰዓቱ በጣም። ስድስት መሆናቸውን አውቃለሁ ምክንያቱም ራሴን ስቼ ሰውነቴን ባልቆጣጠርም ልጆቹ ምን እንደሚያደርጉ አይ ነበር። ስልኬ ዝግ ነበር። እነሱ ነበሩ ስልኬን የያዙት። ቀምተውኝ ስልኩን ዘግተውታል። መጨረሻ ላይ አበሩት እና 'በይ ሂጂ። የሆነ ነገር ብተነፍሺ አታመልጪንም' ብለው አውጥተው ወረወሩኝ። ጸጉሬንም አራገፉልኝ። እንደአጋጣሚ ስልኬ ሲበራ ጓደኛዬ ደወለ። እኔም አነሳሁትና 'ናልኝ' አልኩት። እየሮጠ መጣ። አንድ የማውቀውን ልጅ ከሴት ጓደኛው ጋር አገኘሁት። አንደኛው ልጅ [ከደፈሩኝ አንዱ] እየተከተለኝ ነበር እና ያዝልኝ አልኩት። ሆኖም በጨለማው ገብቶ አመለጠ። የማውቀው ልጅ እያለቀስኩ ስለነበር የተመታሁ ብቻ ነው የመሰለው። 'ወደ ህክምና ልውሰድሽ' ሲለኝ 'አልፈልግም ወደ ጣቢያ ውሰደኝ' አልኩት። ጣቢያ ወሰደኝ። ህክምና ተደረገልኝ ቃሌንም ተቀበሉኝ። ጣቢያ አደርኩ። ከዚያ ወደዚህ [ድርጅት] መጣሁ በነጋታው። እንቅልፍ አልተኛሁም። ሲያመኝ፣ ሳቃስት ነበር። 'ሽንት ቤት ልሂድ ብዬ አምልጬ ራሴን ላጥፋ' ብዬ የዛን ቀን ምሽት ላይ በጣም ብዙ ሳስብ ነበር። ራሴን ማጥፋት አለብኝ ብዬ ብዙ አስቤያለሁ። ከዚያ በኋላ ሽንቴን መሽናት አልችልም ነበር። ለስድስት ቀን ሽንቴን መሽናት አልቻልኩም ነበር። ማሕጸኔ ላይ በጣም ያመኝ ነበር። እዚህ ከመጣሁ በኋላ ህክምና ተደረገልኝ። ቱቦ ተተክሎልኝ በዚያ ነበር የምሸናው። ለሦስት ቀን ተበሎ ነበር ቱቦው የገባልኝ። ሆኖም በሁለተኛው ቀን በጣም አመመኝ። በጣም ሲያምኝና ደምም ሲፈሰኝ ቱቦው በሁለተኛው ቀን ተነቀለልኝ። ስሽና የህመም ስሜት ነበር። አሁን ደህና ነኝ። ከዚህ ከመጣሁ በኋላ በጣም አመመኝ። ሽንቴ እምቢ አለ። ጨነቀኝ። በጣም ያመኝ ነበር ማህጸኔ ላይ። ሽንቴን መሽናት ሲያቅተኝ ስታመም ሐኪም ቤት ሄድኩኝ። ከዚህ ከመጣሁ በኋላ ብዙ ህመም ነበርኝ። ከዚያ ተሻለኝ። ወደዚህ ድርጅት አንዲት የፖሊስ ባልደረባ ናት የላከችኝ። 'ሁሉም ነገር እስኪጠናቀቅ በማዕከሉ ሁኚ' ብላ። ፖሊሶቹ [የወሊድ] መቆጣጠሪያ ወዲያው ሰጡኝ ሌላውን ምርመራ ሁሉንም ነገር አድርጌያለሁ። የኤችአይቪ ምርመራ ከሦስት ወር በኋላ አሉኝ። አምስቱ ተይዘዋል። አንዱ አምልጧል። እኔም ፍርድ ቤት ሄጄ ቃሌን ሰጥቻለሁ። አምስቱም ቀርበው ነበር። ወደ ማዕከሉ ሰኔ 11 ነው የመጣሁት። ወደ ማዕከሉ ከመጣሁ አንድ ወር ሆነኝ። ብዙ እንክብካቤ ከልጆቹ የተለየ ህክምና ተደርጎልኛል። ሽንቴን መሽናት ሲያቅተኝ የግል ሃኪም ዘንድ ወሰዱኝ። መድሃኒቴን ሰዓት እየጠበቁ ይሰጡኝ ነበር። በጣም ተንከባክውኛል። አሁን ወንድ ልጅ ራሱ ሳይ በጣም ነው የሚያስጠላኝ። ማርያምን። አዕምሮዬ በጣም ነው የተነካው። አሁን ሰውነቴ ጋር ምንም ችግር የለብኝም። እጄ በጣም በልዞ ነበር። ፊቴ አብጦ ነበር። በድርጅቱ እገዛ በጣም ተሽሎኛል። አሁን ደህና ነኝ። በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት። ወደፊት ቤተሰብ ጋር ሄጄ ትምህርቴን መማር እፈልጋለሁ ቢስተካከልኝ። ሴቶችን ማለት የምፈልገው እንጠንቀቅ ለእንደዚህ አይነት ነገር እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ። ወንዶችን ደግሞ ቢያንስ ከሴት ነው የተፈጠርነው እናት እህት ሊኖረን ይችላል እንደዚህ ዓይነት ጉዳት ባይደርስ እላለሁ። ለህግ አካላት ደግሞ ተገቢውን ፍርድ እንዲሰጡ እላለሁ። ቤተሰቦቼ አልሰሙም። እንዲሰሙም አልፈልግም። እነሱ እንዲጨነቁ ስለማልፈልግ እንዲሰሙ አልፈግልም። አንድ ዘመዴን በፊት የደፋሪዎቹ ቤተሰቦች እንደራደር እያሉ ያስቸግሯት ነበር። ቢቢሲ፡ በምንድነው እንደራደር የሚሉት? ማህሌት፡ በገንዘብ። በፊት ላይ ማለት ነው ገንዘብ እንስጥሽ እና ክሱን አቁሚ ይሉ ነበር። ቢቢሲ፡ እና ለምን አልደራደርም አልሽ? ማህሌት፡ በገንዘብ መደራደር አልፈልግም፤ ምንክያቱም እኔ ይሄን ነገር በገንዘብ ተደራድሬ ባልፍ ነገ ደግሞ እህቶቼ አሉ እንደዚህ የሚደረፈሩ። ያ እንዲሆን አልፈልግም በእኔ የደረሰው ጉዳት በሌሎች እንዲደርስ አልፈልግም። የጎዳና ተዳዳሪ ሴት ህጻናት መከላከያ ተሃድሶና መቋቋሚያ ድርጅት በተለያየ ምክንያት ጥቃት የሚደርስባቸውን ህጻናት ይረዳል። ከ2000 ዓ.ም ጀምሮም የህጻናቱን መሠረታዊ ፍላጎት ከማሟሏት ባለፈ የስነልቦና ድጋፍ ያደርጋል። ህገ ወጥ የህጻናት ዝውውር፣ ያለዕድሜ ጋብቻ እና ወሲባዊ ትንኮሳ የደረሰባቸው ሴቶች በብዛት ወደ ድርጅቱ ይሄዳሉ። ድርጅቱ ከሴቶቹ ባለፈ ቤተቦቻቸውን በማማከር የተሻለ ህይወት እንዲመሩ ያግዛል። ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ለሚታይም ከለላ በመስጠት ውሳኔ እንዲያገኙ ያግዛል። ጥቃት የደረሰባቸው ህጻናት እና ሴቶች ወደ ድርጅቱ የሚመጡት በፖሊሶች አማካይነት ነው። ማህሌትንም ወደ ድርጅቱ ያመጧት የባህር ዳር ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አባላት ናቸው። ዋና ሳጅን ቢራራ ሞላ የባህር ዳር ከተማ የስድስተኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ ናቸው። "በ17 ዓመቷ ማህሌት ላይ በቀን 10/10/2012 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ ነው ወንጀሉ የተፈጸመባት" ሲሉ ጉዳዩን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ወንጀሉ ከተፈጸመባት በኋላ ጉዳዩ ወደ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ግለሰቧ ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ሄዳ በቂ ህክምና ተደርጎላት ወደ ጣቢያ መመለሷን ገልፀው፣ ምርመራው በነጋታው መቀጠሉን አስታውቀዋል። ሰኔ 11 ጀምሮ በተደረገ የምርመራ ሥራ የተጠርጣሪዎች ስም ማወቅ በመቻሉ "ሁሉም የፖሊስ ሰራዊት በመረባረብ አምስቱ ሲያዙ፣ አንዱ ሳይያዝ ቀርቷል" ብለዋል። "በአምስቱ ላይ ምርመራው ቀጥሎ የህክምና ማስረጃውንም አምጥቶ ዕድሜያቸውንም በማስመርመር፣ ሁሉም ከ17 ዓመት በላይ የሆኑና ወንጀሉን ስለመፈጸማቸው በከፊል አምነዋል፣ በከፊል የካዱ ቢሆንም የህግ ማስረጃዎች ግን በወቅቱ የተፈጸመውን ነገር በሚገባ አስረድተው ስለነበር ተከሳሾችን በቁጥጥር ስር አውለን መዝገባችንን አጠናቀን ለባህር ዳር ከተማ ፍትህ ቢሮ ልከን መዝገቡ ተከፍቷል" ብለዋል። "የሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ አንገብጋቢ ስለሆነ" በዚህ ውስጥ የባህር ዳር ፍትህ ቢሮ ፍርድ ቤትን ጨምሮ በቂ እገዛ እንዳደረጉላቸው አስታውቀዋል። መዝገቡ ተከፍቶ ከተመሠከረ በኋላ ለመከላከያ ሲባል ተከሳሾች ወደ ማረሚያ ቤት እንዲሄዱ ፖሊስ ጠይቋል። በተጠየቅነው መሠረትም ፍርድ ቤት ጉዳዩ አሳማኝ ነው ብሎ ስላመነ ተጠርጣሪዎች ወደ ባህር ዳር ከተማ ማረሚያ ቤት እንዲገቡ ተደርጓል። ስድስተኛውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል እና "ሁሉም ተቋማት በመተባበር እና በመረባረብ በመዝገቡ ላይ በመሳተፍ ውሳኔ እየጠበቅን ነው" ብለዋል።
news-46683800
https://www.bbc.com/amharic/news-46683800
አርበኞች ግንቦት 7 ለሰላምና ለህግ የበላይነት እሰራለሁ አለ
የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬ ረቡዕ አዲስ አበባ በሚገኘው ፅሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ መሳሪያ ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩ አባላቱ ወደ ካምፕ እንዲገቡ ትዕዛዝ ከሰጠበት ጊዜ አንስቶ ከምንም ዓይነት ግጭት ጋር በተገናኘ ስሜ ተነስቶ አያውቅም ብሏል።
የንቅናቄው ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አርበኞች ግንቦት ሰባት ኤርትራ ውስጥ የነበሩት 300 ያህል ታጣቂዎች ሙሉ ትጥቃቸውን ፈትተው ጎንደርና ወረታ አካባቢ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ በመንግሥት ድጋፍ እንደገቡ ገልፀው፤ የተወሰኑት ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውን አክለው ተናግረዋል። •አርበኞች ግንቦት ሰባት ፈርሶ አዲስ ፓርቲ ሊመሰረት ነው ንቅናቄው ኤርትራ ውስጥ ከነበሩት ታጣቂዎች በዘለለ አገር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 550 ያህል አባላቱን ወደ ካምፕ ለማስገባት ጥረት ላይ መሆናቸውንም አቶ አንዳርጋቸው ተናግረዋል። ንቅናቄያቸው ተገፍቶ ወደትጥቅ ትግል ገብቶ እንደነበር አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው በአመፅ ላይ የተመሰረቱ ትግሎች ዘላቂ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ለውጦች ያስገኙባቸው አጋጣሚዎች በዓለም ላይ በጣም ጥቂት መሆናቸው ሲያሳስበን ቆይቷል ብለዋል። •"ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ተገንጥሎ የሚወጣ አካል የለም"-ኤፍሬም ማዴቦ የፖለቲካ ቡድኖች ሰላማዊ እና ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲቀንሳቀሱ ስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሁኔታዎችን በተወሰነ ደረጃ ቢያመቻችም ሂደቱ ባለመጠናቀቁ ታጋሽነትን እንዲያሳዩ አቶ አንዳርጋቸው አሳስበዋል። የፖለቲካ ቡድን አመራሮች በግልፅ እና በማያሻማ ቋንቋ አባሎቻቸው ከአመፅ እንዲርቁ ማሳሰብ አለባቸውም ሲሉ ተናግረዋል። ጨምረውም "አመፅን እያጣቀሱ መሄድን የማይፈቅድ ስስ ሁኔታ ላይ እንገኛለን" ብለዋል ዋና ጸሐፊው። በሻሸመኔ አካባቢ ተፈፀመ ተብሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ የሚገኘውን እና ወጣቶች የዕድሜ ባለፀጋዎችን ሲያጠቁ የሚያሳየውን ቪዲዮ በተመለከተ ለቀረበ ጥያቄ ሌላኛው የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ ቸኮል በሰጡት ምላሽ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ግለሰቦች የንቅናቄው አባላት መሆን ያለመሆናቸውን በማጣራትና ጉዳዩንም በመከታተል ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። •"ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው'' አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ንቅናቄው እየገጠመው ያለ ችግር መኖር ያለመኖሩን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ አንዳርጋቸው፤ በየትኛውም አካባቢ ተንቀሳቅሶ የመስራት መብታቸውን ለማስከበር እንደሚታገሉ ተናግረዋል። "ሰላም ማስከበር የመንግሥት ኃላፊነት ቢሆንም፤ የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ ግን አይደለም። የፖለቲካ ቡድኖች የመንግሥትን ሰላም የማስከበር ኃላፊነት የሚያዳክም ሥራ ከመስራት በመቆጠብ ለውጡን የጀመሩትን የመንግሥት አካላት መደገፍ ያሻል" ሲሉ ገልፀዋል አቶ አንዳርጋቸው። አክለውም "ህገ መንግሥቱ የግለሰብ መብትን ሳያስቀድም የብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሕዝቦችን መብት ያሰከብራል ብለን ባናምንም የመደራጀት እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማከናወን መብትን የሚነፍግ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ ችግር አይፍጥርብንም" ብለዋል። በተጨማሪም የፍትህ ሥርዓቱንና ሌሎች ተቋማትን በአንድ ጀምበር ፍፁም ማድረግ ባይቻልም ተስፋ ሰጭ እርምጃዎች መስተዋላቸው ግን እሙን ነው እንደአቶ አንዳርጋቸው ገለፃ። የፌዴራል መንግሥትን የሚቆጣጠሩት አካላት ልዩ ልዩ ተቋማትን ነፃ እና ገለልተኛ ለማድረግ ሥራ እየከወኑ ቢሆንም ወደ ክልል እና ክልሎች ወደሚያስተዳድሯቸው ወረዳዎች ሲወረድ ግን ወገንተኛነት እና ብሔርተኝነት ገንኖ ይታያል ብለዋል። ክልሎቹ ወገንተኝነት የሚታይባቸው እና በዚያው አካባቢ የተቋቋሙ ሚሊሺያዎች፣ ልዩ ኃይሎች፣ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃይሎች ያሏቸው መሆኑ ለምርጫ መተግበር የሚያስፈልገውን ነፃ ሜዳ በመፍጠር ረገድ ደንቃራ ሊፈጠር እንደሚችል አቶ አንዳርጋቸው ጠቁመዋል።
news-56530283
https://www.bbc.com/amharic/news-56530283
ፕሮፌሰር ሂሩት ለአፍሪካ ሕብረት የኮሚሽነርነት ቦታ ለምን ሳይመረጡ ቀሩ?
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትነት እስከ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴርነት ድረስ ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማሪያም በአፍሪካ ሕብረት የትምህርት እና የሳይንስ ጉዳዮችን ለመሚመለከተው ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ሳይመረጡ ቀርተዋል።
ለዚህም እንደ ምክንያት ከተቀመጡት ጉዳዮች መካከል በያዝነው ዓመት መተግበር የጀመረው እና በየሩዋንዳው ፕሬዘዳንት ፖል ካጋሜ መሪነት ሲዘጋጅ የነበረው የኮሚሽኑ አዲስ መዋቅር መፅደቁ ነው። ካጋሜ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር ሆነው ባገለገሉበት አንድ ዓመት ማለትም ከፈረንጆቹ 2018 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት ሕብረቱ ውጤታማ አልነበረም በሚል አዳዲስ የለውጥ ሃሳቦችን አቅርበው ነበር። ይህንን ተከትሎም ባዋቀሩት ኮሚቴ በኩል ሕብረቱን ሙሉ ለሙሉ ኦዲት ያስረደረጉ ሲሆን የሥራ ድግግሞሽን ማስቀረት ብሎም የፋይናንስ ጥገኝነትን ማስቀረት የዚሁ ለውጥ ዋና አላማዎች ነበሩ። በፖል ካጋሜ የተመራው ይህ የለውጥ ሃሳብ ካነገባቸው አራት አላማዎች አንዱ የነበረው የሕብረቱን መዋቅር በሰብሰብ እና ውጤታማነቱን መጨመር ይገኝበታል። በዚህ መሰረትም ሲጠና የቆየው አዲሱ መዋቅር ከዚህ ቀደም ስምንት የነበረውን የኮሚሽነሮች ቁጥር ወደ ስድስት ቀንሷል። በ34ኛው መደበኛ የመሪዎች ጉባኤው ላይም በመጀመሪያው ቀን ምርጫ ዋና ኮሚሽነር፣ ምክትል ኮሚሽነር እና ስድስት የዘርፍ ኮሚሽነሮችን ለመምረጥ ነበር እቅድ የተያዘው። በሕብረቱ ታሪክ የመጀመሪያ በተባለለት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪን ለሁለተኛ ግዜ የመረጠው ጉባኤው ከሩዋንዳ የመጡትን የ ዶ/ር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ ደግሞ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ኮሚሽነር አድርጎ መርጧል። የሩዋንዳዋ ተወካይ የመጀመሪያዋ የኮሚሽኑ ሴት ምክትል ኮሚሽነር ሆነው የተመረጡ ሲሆን ይህም ፕሮፌሰር ሂሩትን በተዘዋዋሪ ከውድድር ውጪ አደርጓቸዋል። ከፕሮ. ሂሩት ጋር እነማን ተወዳደሩ በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው ይህ የኮሚሸነሮች ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በተያዘው ዓመት ሊስተጓጎል ይችላል የሚሉ ስጋቶች ቢኖሩም ከስድስቱ ኮሚሽነሮች አራቱን በመምረጥ ተገባዷል። ዓመቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዕጩ የቀረበበትም ነበር። የኮሚሽነሮች ምርጫ በአህጉሩ ካሉ አምስት ቀጠናዎች ተመጣጥኖ እንዲመረጥ ይደረጋል። ስለዚህም ተመራጭ ኮሚሽነሮቹ ካላቸው ብቃት በሻገር የቀጠና ምጣኔም ዋና ግብአት ነው። የሕብረቱ አምስቱ ቀጠናዎች የምሥራቅ፣ የምዕራብ፣ የደቡብ፣ የሰሜን እና የማዕከላዊ ናቸው። ፕሮፌሰር ሂሩትን ጨምሮ አምስት ተፎካካሪዎ የቀረቡበት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት ዘርፍ ከፍተኛ ዕጩ የቀረበበት ነበር። ከምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ብቻ ሦስት ተፎካካሪዎችን ይዞ የመጣ ሲሆን ከኡጋንዳ እና ሞሪሺየስም ተወዳዳሪዎች የነበሩበት ነው። ሪታ ታግዊራ ሞርሺየስን ወክለው የቀረቡ ሲሆን ጆን ፓትሪክ ካባዮ ደግሞ ከኡጋንዳ ከፕሮ. ሂሩት ጋር ተፎካካረዋል። በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ እና ዚምቧብዌ ተፎካካሪዎችን አቅርበዋል። ከአፍሪካ ሕብረት ጋር የተገናኘ ሰፊ የሥራ ልምድ ያላቸው አንድ የቢቢሲ ምንጭ እንደሚገልጹት አንድ ቀጠና ሦስት ሰው ማቅረቡ በራሱ በአገራቱ መካከል ያለውን ከፍተኛ ያለመናበብ የሚያሳይ ነው ይላሉ። የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና የሩዋንዳዋ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጥ ከውድድር ውጪ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ፍርሃት እንዳላቸው ፕሮ. ሂሩት ከኢትዮጵያ ቴሌቪሽን ጋር ጥር 22/2013 ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልፀው ነበር። "ስለቀጣዩ የምርጫ ደረጃ የሰማሁት ነገር ትንሽ ግራ አጋቢ ነው ነው። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ወይም ምክትል ከምሥራቅ አፍሪካ የሚመጣ ከሆነ ሌላ ኮሚሸነር ከቀጠናው እንደማይቀበሉ ነው። ይህ ከእኛ ቁጥጥር ውጪ ነው። ግን ያው በተስፋ እጠብቃለሁ" ሲሉ ሂሩት ገልፀው ነበር። የዶክተር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው "ሳይታለም የተፈታ" እንደነበረ የምርጫ ሂደቱን በቅርበት የተከታተሉት ምንጫችን ያስረዳሉ። ይህም ሞኒክ የሩዋንዳ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት በተለይም የአገሪቷን የንግድ አመቺነት ደረጃ ከፍ ማድረግ መቻላቸውን ጨምሮ በርካታ ስኬት ያስመዘገቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው መሆኑ ነው። የአፍሪካ ሕብረት እያካሄደ ካለው ራሱን በፋይናንስ የመቻል እቅድ ጋር ተያያዞ የሞኒክ መመረጥ የሚጠበቅ ነው ሲሉ የቢቢሲ ምንጭ ያስረዳሉ። እንዲሁም ከሃርቫርድ ኬኔዲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤትን ጨምሮ ከተለያዩ በዓለም ላይ ታዋቂ በሆኑ የኢኮሚክስ ትምርት ቤቶች መማራቸው ከተፎካካሪዎቻቸው ጋር ሲነፃፀሩ ከፍተኛ ብልጫ እንዳላቸው የሚያሳይ መሆኑንም ጨምረው ይገልፃሉ። ሞኒክ የተወዳደሩበት ዘርፍም ቢሆን ሙሉ በሙሉ የምሥራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪዎች የቀረቡበት ነበር። የሩዋንዳ፣ የሶማሊያ እና የኡጋንዳ ተወዳዳሪዎችን በመብለጥ ነው የተመረጡት። ኢትዮጵያን ጨምሮ የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን የያዘው ይህ ቀጠና ባለመናበብ እና እርስ በእርስ መግባባት ያለመቻሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይቷል ሲሉ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሦስት ለሕብረቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ያስረዳሉ። ይህ በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በጂቡቲ እና በኬንያ መካከል የነበረው ፍጥጫም ማሳያ እንደነበረ ይናገራሉ። ሌሎች አገራት ወደ ምርጫው ከመግባታቸው በፊት በሚያካሂዱት ድርድር ቀጣናቸውን የሚወክል ሰው ለተለያዩ ምርጫዎች የሚያቀርቡ ሲሆን በተለይም የደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና በዚህ የሚታወቅ ነው ይላሉ ባለሞያዎቹ። ፕሮ. ሂሩት የተወዳደሩበትን ዘርፍ ጨምሮ ቀሪ ሁለት የኮሚሽነሮች ምርጫ በመጪው ክረምት በሚካሄደው ጉባኤ ላይ እንደሚመረጡ ይጠበቃል። የሁለቱ ኮሚሽነሮች ምርጫ በድጋሚ በሚካሄድበት ጊዜም ሂሩትን ጨምሮ የምሥራቅ አፍሪካ ኮታ በመሙላቱ በድጋሚ መወዳደር አይችሉም። ስለ ፕሮፌሰር ሂሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "በካቢኔዬ ውስጥ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር የነበሩትና አሁን ደግሞ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሆኑት ፕሮፌ. ሂሩት ለቦታው ተገቢ ዕጩ ናቸው" ሲሉ የፕሮፌሰር ሂሩትን ዕጩነት ደግፈው በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈው ነበር። በተጨማሪም "እንደ ምሁር፣ ሳይንቲስት፣ የለውጥ መሪ እና የዲፕሎሲ ቡድን መሪነት የተለያየ ልምድ ያላቸው ሂሩት ለዚህ ቦታ ተገቢው ሰው ያደርጋቸዋል" ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲመረጡ ቀስቅሰውላቸዋል። "በአካዳሚው ዘርፍ ከፍተኛውን ማዕረግ ያገኙት ሂሩት በሦስት የተለያዩ የሚኒስትርነት ኃላፊነት ሾመናቸው አገልግለዋል" ሲሉም ስለፖለቲካዊ ተሳትፏቸው አቶ ደመቀ ገልጸው ነበር። ፓን አፍሪካኒዝምን በአፍሪካ የትምህር ሥርዓት ውስጥ ማካተት፣ ጠንካራ የፓን አፍሪካ የትምህርት ዕድል ፕሮግራሞች መክፈት፣ በአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የተጣጣመ እና እንደ አውሮፓው ኤራስ መስሙንደስ ያለ የእውቅና ሥርዓት መጣጣም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ መሪ የሆኑ የልህቀት ማዕከላትን ማቋቋም ዋና አላማዎቼ ናቸው ሲሉ ሂሩት ለመመረጥ ሃሳብ አቅርበው ነበር። ሂሩት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መስራች ሚኒስቴር ናቸው። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን በሚመሩበት ወቅትም በተለይም ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታግተው እስካሁን ያሉበት የማይታወቁ ተማሪዎች ጉዳይን በተመለከተ ትችት የሰነዘርባቸው ነበር። ቢቢሲ ለሳምንታት ከፕሮፌሰር ሂሩት አስተያየታቸውን ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ጉዳዩን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሆነ በመግለፅ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ሂሩት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በመሆን እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲን በመወከል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።
news-47209249
https://www.bbc.com/amharic/news-47209249
መምህር ሥዩም ቦጋለ፡ የተማሪዎቻቸውን ገላና ልብስ የሚያጥቡት መምህር
ስድስት የውሃ መቅጃ ጀሪካንና ሁለት ሳፋ (ጥሽት) አላቸው። እስካሁን በግምት ከ650 በላይ ህጻናት ተማሪዎችን ገላ አጥበዋል። በአማካይ አንድን ተማሪ ለማጠብ 30 ደቂቃ ይፈጅባቸዋል።
በሳምንት ሁለት ቀናት ማለትም ረቡዕና አርብ የ60 ተማሪዎችን ልብስ ያጥባሉ። የተማሪዎቻቸው ንፅህና ተጠብቆና በትምህርታቸው ልቀው ማየት ህልማቸው ነው። ካላቸው አነስተኛ ደመወዝ አንድ ሦስተኛውን ለዚህ በጎ ስራቸው ለማዋል በጅተውታል። • ሀሁ አስቆጣሪው ጃማይካዊ • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት • የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም የአገሬው ሰው "ምን ሀጢያት ቢሰራ ነው፤ እንዲህ ያለ እዳው ጎንበስ ቀና የሚለው?" እያሉ ያጉመተምቱ ነበር- ነገሩ እስከሚገባቸው ነው ታዲያ። ከገባቸው በኋላማ "አንተ 'እንትፍ ...እንትፍ' ብለህ ከመረቅካቸውም ይበቃል" ሲሉ ያሞግሷቸዋል። የሚያውቋቸው "ጋሸ" እያሉ ነው የሚጠሯቸው። ሲበዛ ያከብሯቸዋል። "የእርሳቸውን ነገር ለማውራትም ይከብዳል" ይላሉ። እንዲያው በአጭሩ "ለትውልድ ነው የተፈጠሩት" ሲሉ ይገልጿቸዋል። ተማሪዎቻቸው ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል ቢሸጋገሩም እርሳቸው የሚያስተምሩበትን አንደኛ ክፍል ላለመልቀቅ ሲሉ " ምነው እንደ ሊቁ ያሬድ ሰባት ጊዜ በወደቅኩ" ብለው ይመኛሉ አሉ። እኝህ ሰው ማን ናቸው? መምህር ሥዩም ቦጋለ የእንግሊዘኛ መምህር ሲሆኑ በ1998 ዓ.ም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከበፊት ጀምሮም በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን የማየትና ለዚያም መፍትሔ የማፈላለግ ፍላጎት እንደነበራቸው ይናገራሉ። በእርግጥ የእርሳቸው አስተዳደግም የተንደላቀቀ ባለመሆኑ ለችግር ብዙም ሩቅ አይደሉም። እንዲህ ዓይነት የበጎ ሥራን ማከናወን የጀመሩት አባታቸው በ13 ዓመት እድሜያቸው በሞት ከተለዩ በኋላ ከእርሳቸው በታች ያሉ እህትና ወንድማቸውን የማስተማር ኃላፊነት ከተረከቡበት ጊዜ አንስቶ ነው። "እነርሱን በሚፈለገው እውቀትና የሥነ ምግባር ደረጃ ለማብቃት የራሴን ሕይወት ከፍያለሁ፤ የልፋቴን ዋጋም በእነርሱ ማየት ችያለሁ"ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት ደካማ እናታቸውን እየረዱ ይኖራሉ። የቤት ውስጥ የሚባል ማንኛውንም ሥራ ያከናውናሉ። ምንም የሚቀራቸው የለም። ይሄው ልማድም ጎልብቶ ወደ ሙያቸው እንደመጣ ያስረዳሉ- መምህር ሥዩም። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ በሚያስተምሩበት አካባቢ ወላጆች እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ለመቀስቀስ ጋራና ሸንተረሩን ያቋርጣሉ። ሰለቸኝ ደከመኝ አይሉም። ሠርግ፣ ለቅሶ፣ እድር ላይ የአገሬውን ሰው መስለው ይሳተፋሉ። የአገሬው ሰው ቢሆኑም ቀለም ቀምሻለሁ ብለው ግን እራሳቸውን አያመፃድቁም። ከዚያም የማትለያቸውን ማስታወሻ ደብተር አውጥተው የሚሰሟቸውን ቤተሰባዊ ችግሮች እየጠየቁ ይመዘግባሉ። "ሁሉም ሰው ችግራችንን ይጠይቀናል፤ ግን ከንፈር ከመምጠጥ ባለፈ መፍትሔ የሰጠን የለም" የሚል ተደጋጋሚ መልስ ነው የሚያገኙት። አንድ ቀን አንዲት ተማሪ "ልብሴ ቀዳዳ በመሆኑ፤ የተቀደደ ልብስ ለብሼ ትምህርት ቤት መምጣት አልፈልግም" ስትል ትምህርት ቤት ላለመግባቷ መልስ የሰጠቻቸውን ያስታውሳሉ። በወቅቱ የሰሙት ነገር ከእንቅልፋቸው ያባንናቸው ነበር። ይህን ስሜታቸውን ለማስታገስ ቢያንስ ሁለት ተማሪ መርዳት እንዳለባቸው ከራሳቸው ጋር ተነጋግረው ወሰኑ። ልብስ አሰፍተው፣ የትምህርት ቁሳቁስ በሚችሉት አሟሉላት። እርሷም አላሳፈረቻቸውም። ከክፍሏ ቀዳሚ በመሆን ትምህርቷን እንዳጠናቀቀችና እርሳቸው እንደሚሉት ይህች ልጅ በምህንድስና ተመርቃ ሥራ ላይ ትገኛለች። የእርሷ ለስኬት መብቃት "ትውልድ እየቀጨጨና እየጠፋ ያለው በእኛ ምክንያት ነው" ሲሉ ጣታቸውን ወደ የቀለም አባቶች እንዲቀስሩ ምክንያት ሆናቸው። ችግሩ ያለው ከትውልዱ ሳይሆን ከቀራፂው መሆኑን አመኑ። ለዚሁ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ረዳት የሌላቸውንና የአቅመ ደካማ ልጆችን ንፅህና መጠበቅ እንዲሁም የትምህርት ጥራት የበጎ ሥራቸው ዋና ማጠንጠኛቸው ሆነ። ይህ ብቻም አይደለም። ቀደም ብሎ የ7ኛ እና የ8 ኛ ክፍል የእንግሊዘኛ አስተማሪ በነበሩበት ጊዜ ተማሪዎቹ 'G' እና 'J' የእንግሊዝኛ ፊደል መለየት ሲያዳግታቸው ያዩት መምህር ሥዩም እነዚህ ተማሪዎች እዚህ የደረሱት በየት ተንሳፈው ቢመጡ ነው? ምን ዓይነት መምህር ቢያስተምራቸው ነው? የሚለው የዘወትር ጥያቄያቸው ነበር። ስለሆነም እንዲህ ዓይነት ትውልድ እንዴት እናፈራለን? ሲሉ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ፋግታ ለኮማ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት አቤት አሉ። ለዚህም መፍትሔ ይሆን ዘንድ ከደረጃቸው ዝቅ ብለው አንደኛ ክፍል ማስተማር እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቀረቡ። ይሁን እንጂ እንዳሰቡት ቀላል አልሆነላቸውም። "አንደኛ ክፍልን ለማስተማር መሰልጠን ያለብዎትን ሥልጠና አላገኙም" የሚል ጥያቄ ሞገታቸው። የሚያበቃኝን ሥልጠና ስጡኝ ሲሉ በአቋማቸው ጸኑ፡፡ የኋላ ኋላ ተሳክቶላቸው አንደኛ ክፍልን ብቻ ማስተማር ጀመሩ። የእርሳቸው ሥራ ከታች ተማሪዎችን አብቅቶ ለቀጣዩ መምህር ማቀበል ብቻ ሆነ። በሥራ ተወጥሮ ለሚውል አርሶ አደር፣ ውሃ በቀላሉ በማይገኝበት የገጠር አካባቢ፤ ምን አልባትም ውሃ ለመቅዳት በእግር ብዙ ርቀት መጓዝን በሚጠይቅ የኑሮ ሁኔታ አልያም ምርኩዝ ይዞም ቢሆን ውሃ ከወንዝ መቅዳት ለማይሆንለት ቤተሰብ፤ የራስንም ሆነ የልጆችን ንጽህና መጠበቅ ዘበት ሊሆን ይችላል። ይህ ሌላኛው የሚያሳስባቸው ጉዳይ ነው- ለመምህሩ። ከዚህ በኋላ ነበር ሳሙናዎችንና የማጠቢያ ሳፋ (ጥሽት) በመግዛት የተማሪዎችን ንፅህና ለመጠበቅ ሲሉ ልብሳቸውንና ገላቸውን ማጠብ የጀመሩት። መምህር ሥዩም በዘንድሮው ዓመት በሁለት ፈረቃ 130 ተማሪዎችን ያስተምራሉ። ማስተማር ብቻ ሳይሆን ንፅህናቸውን መጠበቅ፣ ዐይናቸው በትራኮማ በሽታ እንዳይጠቃ ፊታቸውን ማጠብ፣ በሳምንት ሁለት ጊዜ ልብሳቸውን ማጠብና ገላቸውን ማጠብ ለራሳቸው የሰጡት ኃላፊነት ነው። ዘወትር ሀሙስ ጠዋት ሁሉንም ተማሪዎቻቸውን ተቀያሪ ልብስ በመያዝ ከትምህርት ሰዓታቸው ቀደም ብለው እንዲመጡ ይጠሯቸዋል። ምንም እንኳን በትምህርት ቤቱ በእጅ እየተወዘወዘ የሚፈስ ቧንቧ ቢኖርም ብዙ ስለሚያለፋቸው ከእርሱ ጋር መታገል አይፈልጉም። ከትምህርት ቤቱ 200 ሜትር ርቀት ላይ ኩልል እያለች የምትፈስ ንፁህ የመስኖ ውሃን መጠቀምን ይመርጣሉ። ከዚያም ባሏቸው ጀሪካኖች ውሃ በመቅዳት ለዚሁ አገልግሎት ብለው በገዙት ማጠቢያ ሳፋ ለሴት ተማሪዎቹ ቅድሚያ በመስጠት ገላቸውን በየተራ ያጥቧቸዋል። ለዚህ ተግባራቸው የአሸዋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት አቶ ያረጋል ካሳሁን ምስክር ናቸው። ርዕሰ መምህር አቶ ያረጋል በትምህርት ቤቱ መስራት ከጀመሩ አራት ዓመታትን አስቆጥረዋል። ምንም እንኳን መምህር ሥዩም ይህንን ድርጊታቸውን ቀደም ብለው የጀመሩት ቢሆንም በቆዩባቸው አራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሥራቸውን በቅርብ ሆነው እንደሚከታተሉ ይናገራሉ። "ከትምህርት ቤቱ ድጋፍ እንዳናደርግላቸው አቅም ባለመኖሩ፤ በዚህ ዓመት ለሳሙና መግዣ እንኳን ቢውል ብለን 1500 ብር ብቻ ድጋፍ አድርገንላቸዋል" ይላሉ። • የ29 ዓመቷ የህክምና ዶክተርና ኢንጅነር ዕልልታ ጉዞ አቶ ያረጋል እንደሚሉት የመምህር ሥዩም ድርጊት በሌሎች መምህራን ላይም መነሳሳትን ፈጥሯል። በዚህም ምክንያት ትምህርት ቤቱ በትምህርት አሰጣጥ በወረዳው ካሉ የተሻለ ሆኖ መገኘት ችሏል። በወረዳው በተካሄዱ የተለያዩ የትምህርት ቤቶች የቀለም ውድድርም ማሸነፍ ለመቻላቸው የእርሳቸውን አስተዋፅኦ ያነሳሉ። "በእርሳቸው ክፍል የሚያቋርጥ ተማሪ የለም፤ ሁሉም የዓመቱን ትምህርት ያጠናቅቃሉ፤ ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የመላክ ፍላጎት አላቸው" ሲሉ ያክላሉ። ከተማሪዎቹ ወላጆች የሚያገኙት ግብረ መልስ ምን እንደሆነ የጠየቅናቸው ርዕሰ መምህሩ አስተያየቱ አዎንታዊ እንደሆነና 'እንደ አባት' ሙሉ እምነት እንደጣሉባቸው ያስረዳሉ። መምህር ሥዩም ይህን በጎ ተግባር ከጀመሩ ከ10 ዓመታት በላይ እንደሚሆናቸው የሚናገሩት አቶ ያረጋል ሁሉም የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በእርሳቸው የእንክብካቤ እጅ ስለሚያልፉ ከሁለተኛ ክፍል በላይ ያሉ ተማሪዎችም ሌላ ቅናት አያድርባቸውም። "እንዲያውም መስከረም ሲመጣ ወደ 2ኛ ክፍል ያለፉ ተማሪዎች እርሳቸውን ጥለው ለመሄድ ይቸገራሉ፤ ህፃናትም ስለሆኑ ሁልጊዜ አንደኛ ክፍል ቢማሩ ደስታቸው ነው- ለእርሳቸው ሲሉ" በማለት የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ለእርሳቸው ያላቸውን አክብሮት ይገልፃሉ። በተለይ ተማሪዎችን በትምህርት ለማብቃት የሚከተሉትን ሥነ ዘዴ ለማየት ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ጎብኝዎችም እንደሚመጡ ያስረዳሉ። ፈቃዱ እጅጉ አዲስ አበባ በመንግሥት ሥራ ላይ የሚገኝ ሲሆን እርሳቸውን በቅርበት ያውቃቸዋል። ለእርሱ ባይደርሱም ታናናሾቹን ያስተማሯቸው መምህር ሥዩም ናቸው። "ሙያውን ያከብራሉ፤ ደግነታቸው የበዛ ነው" ይላል። በአካባቢው ተወዳጅ የሆኑ ሰው እንደሆኑ ይመሰክራል። የተቸገረን በመርዳት እንደሚታወቁ ይናገራል። "አንድ ተማሪ ቸገረን ሲል ለምን ስዩምን አትጠይቁም" ይባል እንደነበር ያስታውሳል። መምህር ሥዩም በዚህ በጎ ሥራቸው የተለያዩ ሽልማቶች የተበረከተላቸው ሲሆን በ2010 ዓ.ም በተካሄደው 6ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በመምህርነት ዘርፍ እጩ ሆነው ተመርጠዋል። የዋንጫና የገንዘብ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል። በወረዳና በፌዴራል ደረጃ ሜዳሊያና የተለያዩ የምስክር ወረቀቶችን አግኝተዋል።
news-44366061
https://www.bbc.com/amharic/news-44366061
"ሰልፊ" ፎቶ እና የሞራል መላሸቅ
አፍቅሮተ-ራስ ጣሪያ የነካበት ዘመን ላይ ሳንሆን አንቀርም።
ሰዎች የሌሎችን ትኩረት ለማግኘት ብዙ ርቀት ይጓዛሉ። በሞት አፋፍ ላይ ያለን ሰው ከመርዳት ይልቅ የራሳቸውን ምስል ለማስቀረት የሚሟሟቱ ምን ተብለው ይጠራሉ? ጣሊያን ውስጥ አንድ ወጣት በዚህ ድርጊቱ ቁጣን ቀስቅሷል። በባቡር ተገጭታ በሞት አፋፍ ላይ ትገኝ ከነበረች ካናዳዊት ጎን በመቆም የራሱን ምስል ሲቀርጽ ድርጊቱ በሌላ ፎቶግራፈር እጅ ከፍንጅ ተይዟል። በራስ ምስል አፍቅሮት የሰከረው ይህ ወጣት የሞራል ልዕልናችን መላሸቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ይኸው ጎረምሳ በባቡር ተገጭታ ክፉኛ ከተጎዳች ሴት ጎን ፎቶ ሲነሳ ፎቶ ያነሳው አንድ የዜና ወኪል ባልደረባ ሲሆን "ሥነ ምግባር እያጣን ነው" ሲል በክስተቱ ማፈሩን ተናግሯል። ፖሊስ የራስ ምስል ወሳጁን ወጣት በቁጥጥር ሥር አውሎ ፎቶዎቹን ከስልኩ እንዲሰርዛቸው አስገድዶታል። ይህ ብቻም ሳይሆን ምርመራም ጀምሮበት ነበር። ነገሩ የሞራል እንጂ የሕግ ጉዳይ ባለመሆኑ ግን ምርመራው ተቋርጧል። ካናዳዊቷ ሴት ከአደጋው በኋላ ወደ ሆስፒታል ብትወሰድም አንድ እግሯን አጥታለች። ምናልባት በአግባቡ ካልተዘጋ የባቡር በር አፈትልካ ወጥታ አደጋ እንደደረሰባት ተገምቷል። ፓይሴንዛ በተባለ ባቡር ጣቢያ የመሳፈሪያ ወለል ላይ ሆኖ የራሱን ምስል እየወሰደ የነበረው ይህ ወጣት ድርጊቱን ሲፈጽም የሚያሳየው ምስል በጣሊያን ሚዲያ በመበተኑና ድርጊቱም በመገናኛ ብዙኃን መናኘቱ በሞራል ጉዳይ አዲስ የውይይት በር ከፍቷል። የሚደንቀው ግለሰቡ ከተጎጂዋ በቅርብ ርቀት ሆኖ የራሱን ምስል ሲወስድ የእናሸንፋለን ምልክት ወይም "V" በማሳየትና በቅንጦት ኾኖ ነበር። ላ ስታምፓ የተባለው የጣሊያን ዕለታዊ ጋዜጣ በአስተያየት ገጹ ስለጉዳዩ በታተመ አንድ ጽሑፍ ግለሰቡን ክፉኛ ወርፎታል። "ይህ ወጣት መጥፎ ሰው አይደለም፤ ምክንያቱም የልቡን ባልቦላ አጥፍቶታል፤ የኢንተርኔት ባሪያ ነው። አትፍረዱበት" ሲል አንድ አምደኛ በጋዜጣው ላይ ጽፏል። ኒኮላ ሳቪኖ የተባለ የሬዲዮ አሰናጅ በበኩሉ "ሰብአዊነት በፍጥነት አየተሸረሸረ ስለሆነ የሰው ዘር መጥፊያ የደረሰ ይመስለኛል።" ብሏል። ሌላ የትዊተር ተጠቃሚ በገጹ ላይ "ከእንግዲህ ምንም ነገር እየረገመኝ አይደለም" ሲል በሰው ልጅ ላይ እየታየ ያለው የሞራል ዝቅጠት እንዳሳሰበው በተመጠነ ቋንቋ ስሜቱን አንጸባርቋል።
46629551
https://www.bbc.com/amharic/46629551
ኦነግ የመንግሥት ሠራዊት በተለያዩ ቦታዎች በመሰማራቱ ላይ ጥያቄ አለው
ከሰሞኑ በኦሮሚያ አካባቢ በተፈጠሩ ግጭቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም የፖለቲካና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ጋሹ ለሜሳ ጋር ቆይታ አድርገናል። ጥያቄ፡ አስመራ ላይ ከመንግሥት ጋር ባደረጋችሁት ስምምነት መሠረት ነገሮች እየሄዱ እንዳልሆነ ታነሳላችሁ፤ መንግሥት ማድረግ ሲኖርበት ያላደረገው ነገር ምንድነው?
አቶ ጋሹ፡ አስመራ ላይ በተደረገው ስምምነት አገር ቤት እንደገባን ብዙ ነገሮች ነበሩ፤ ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር የሚሟሉ ማለት ነው። አንድ በሰላማዊ መንገድ ለአገሪቱ የሚስማማውን የፖለቲካ ሂደት ማካሄድ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በ1992 (እአአ) ከአገር ስንወጣ የተዘረፉ የኦነግ ንብረቶች፣ ቢሮዎች ብዙ ነገሮቸ አሉ። እነዚህ ነገሮች ባግባቡ እንዲመለሱ፤ የ"ኦሮሞ ሪሊፍ አሶሴሽን" የሚባል ሰብአዊ ድርጅት ነው፣ እሱም ተመዝግቦ በሥራ ላይ እንዲውል ነበር የተስማማነው። [እነዚህ] ሁኔታዎች እስካሁን ድረስ እምብዛም አልተሟሉም። አንድ ጉለሌ ያለ ቢሮ ብቻ ከፊሉ ተመልሷል፤ ሌላው ትልቁ አልተመለሰም። እና ይሄ ይሄ ነው ያለው። • "ለውጡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ውጤት ነው" ዳዉድ ኢብሳ በሰላማዊ መንገድ ትጥቅ እንፍታ ነው የተባለው ከዚያ በኋላ መንግሥትም ተመልሶ አላስፈላጊ ጦርነት የመቀስቀስ ሁኔታ ይታያል ፤ በድንበር አካባቢ። እና ሕዝቡንም ደግሞ በየከተማው በየገጠሩ በጦር ማስፈራራት ጦር ማስፈር ይታያል። እነዚህ ችግሮቸ ናቸው ያሉት፤ እነዚህ ደግሞ እንደገና በንግግር በመመካከር የአገር ሽማግሌዎችን በመላክ እንፈታለን ብለን በዚያ ሂደት ላይ ነው ያለነው። ጥያቄ፡ ምዕራብ ኦሮሚያ ላይ ያለ የኦነግ ጦር ወደ ካምፕ አልገባም። ለምን? አቶ ጋሹ፡ አዎ ይሄ በሂደት ላይ ነው ያለው። እኛም እየተመካከርን ነው ። ይሄ በሂደት ላይ እያለ በመንግሥት ጦር በዚያ አካባቢያ ጦርነት ተከፈተ። ጦርነቶች ተቀሰቀሱ። ተገቢ ያልሆ ፕሮፓጋንዳ፣ የትጥቅ እናስፈታለን የሚል ዛቻና አነጋገር፣ በየማኅበራዊ ሚዲያው ሲሰራጭ ነበር። ይሄ ሁሉ በሕዝቡ ዘንድ አጠያያቂ ሆነ። የመንግሥት የጦርም ደግሞ በየከተማውና በአካባቢው በስፋት በመስፈሩ ይሄ ሁሉ አጠያያቂ ጉዳይ ሆኖ እስካሁን ሳይሳካ በዚህ ሂደት ላይ ነው ያለው። ለወደፊቱ ግን ልክ እንደተስማማነው በሰላማዊ መንገድ እንፈታለን ብለን ነው ያቀድነው። • «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) ጥያቄ፡ ማክሰኞ ምዕራብ ሸዋ ላይ ምንድነው የተፈጠረው? በኦነግ ታጣቂዎችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጦች ነበሩ? አቶ ጋሹ፡ እኛም እንደዛው ነው የሰማነው፤ ያው ከሚዲያ ነው የሰማነው እንጂ በእኛ በኩል ተኩስ ልውውጡ የተደረገበት ቦታ ያለ አይመስለኝም። የእኛ ሠረዊትም ደግሞ አላግባብ የተኩስ ልውውጥ የሚያደርግበት ቦታም አይደለም ያለው። ነገር ግን አሁንም ምዕራብ ኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የኦነግ ሠራዊት አለው፤ እየተንቀሳቀሰ ያለ። የታጠቀ የኦነግ ኃይል ምዕራብ ኦሮሚያ ላይ ይንቀሳቀሳል። ጥያቄ፡ በምን አግባብ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው? አቶ ጋሹ፡ ምዕራብ ኦሮሚያ ላይ በጣም ትኩረት ተደረገበት እንጂ የሚንቀሳቀስ የታጠቀ የኦነግ ሠራዊት ምዕራብ ኦሮሚያ ብቻ አይደለም ያለው። በደቡብም አለ፣ በመሐልም አለ፣ በምሥራቅም አለ። በሰፊው የኦሮሚያ ቦታዎች እየተንቀሳቀሰ ነው ያለው። ግን ዋንኛው ትኩረትና የፖለቲካ ጫወታ ያለው በምዕራቡ ላይ ነው። • በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ እና ሠራዊቱ አሁንም ልክ እንደ 'ጎሪላ' ነው ያለው። ግን ያላግባብ ጦርነቶችን ውጊያና ግጭቶችን እየቀሰቀሰ አይደለም። ነጻ ባወጣቸው መሬት ላይ ሰፍሮ ነው ያለው። ግን ደግሞ ቀደም ሲል እንዳልኩት አስመራ ላይ በተስማማነው ውል የሠራዊቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዴት እንደሚሆን በሂደት ላይ ነው ያለው። ሰራዊቱ ግን እንዳለ ነው ያለው። ጥያቄ፡ የኦነግ ሠራዊት ነጻ ባወጣቸው መሬቶች ላይ ሰፍሮ ነው ያለው ብለውኛል። መሬቶቹን ከማን ነው ነጻ ያወጣቸው? አቶ ጋሹ፡ ከወራሪ መንግሥት ወይም ከወራሪ ሠራዊት ነው ነጻ ያወጣው። እኛ ወራሪ ብለን ወይም ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ብለን ከምንፈርጃቸው ከወያኔ ወራሪዎች ነጻ አውጥቶ ነው በአካባቢው አሁን ሰፍሮበት ያለው። ጥያቄ፡ መንግሥት በየአካባቢው ያሰማራቸው ወታደሮች ችግር እየፈጠሩ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ? አቶ ጋሹ፡ አዎ እኛ ችግር ይፈጥራሉ ነው የምንለው። ጠላት በሌለበት ቦታ ጠላት ብሎ ሕዝቡ ላይ ማስፈር ችግር ይፈጥራል። ሕዝቡና መንግሥት እንዲጋጭ ያደርጋል። የሕዝቡን ሰላም ያውካል። ሕዝቡ ባለፈው ሥርዓት በጣም በጣም ነው በሥነ ልቦናው የተጎዳው። • ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት የሃገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው [ያኔ] ሰራዊቱ በየከተማው እየሄደ የሕዝቡን ቤት ይፈትሻል፣ ሕዝቡን ይዘርፋል፣ ያላግባብ ተማሪዎችን ያስራል፣ ይገድላል፣ ይደበድባል፣ ወደ ፍርድ ቤት ይወስዳል፤ ያ ሁሉ ሰቆቃ በሕዝባችን ላይ አለ ማለት። አሁንም ደግሞ ሠራዊቱ በየከተማው ከባድ መሳሪያ በየመኪናው ላይ ደግነው ሲሄዱ ሕዝቡ ይሰጋል። ይሄ ደግሞ መንግሥትና ሕዝቡን ያጋጫል ማለት ነው። ሕዝቡ አመኔታ ያጣል። ይሄ አግባብ አይደለም፤ ሰራዊት ከከተማ ምን ያደርጋል? ገጠርም ቢሄድ ደግሞ አርሶ አደሩን ሕዝብ እንደዛው ሰፍሮበት ያላግባብ መደብደብ ማሰር ይሄ ሁሉ ራሱ ትክክል አይደለም። ሠራዊት ካምፕ ውስጥ ነው የሚኖረው። መንግሥት በሲቪሉ ላይ የሚያሰፍርበት ሁኔታ ተገቢ አይደለም። ስለዚህ ይሄ ችገር ይፈጥራል። እንደገና ደግሞ በሰላማዊ መንገድ እንፈታለን ብለን፣ የአገር ሽማግሌዎችም ገብተውበት፣ በሁለቱም በኩል የተመረጡ አካሎች ሰላም ለመፍጠር በሚጥሩበት ጊዜ ሄዶ ያላግባብ ግጭት ከኦነግ ሠራዊት ጋር መፍጠር በራሱ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ አያመጣም። ነገሮችን በውጊያ ከሚፈታ በውይይት መፍታት ነው ተገቢ። ጦርነት ያብቃ ብለን ነው እኛ የምናምነው። ይሄ የኦነግ አመለካከት ነው ማለት ነው። ጥያቄ፡ ከንግግርዎ የምረዳው መንግሥት ኦሮሚያ ላይ የጸጥታ ኃይል ማስፈሩ ስህተት ነው እያሉኝ ይመስላል? አቶ ጋሹ፡ ያልኩት የመንግሥት ጸጥታ ኃይል ጸጥታ ባልሰፈነበት ቦታ ሰፍሮ ጸጥታን ማምጣት ነው እንጂ ጸጥታ ባለበት በሲቪሉ ሕዝብ መሐል ማስፈር ትክክል አይደለም ነው። ወታደሮችን ሁከት በሌለበት ቦታ፤ ሕዝቡ በሰላም በሚኖርበት ቦታ ሂዶ አስፍሮ ሕዝቡን ማወክ ተገቢ አይደለም። [እርግጥ ነው] የጸጥታ አስከባሪ ጸጥታ በሌለበት ቦታ መስፈር አለበት። ለምሳሌ በየድንበሩ ከኦሮሚያ ሕዝብና ከሌሎች ጎሳዎች ጋር ግጭት ነበር። ያንን ግጭት ማስቆም አለበት። ሠራዊት እዚያ ቦታ ነው የሚያስፈልገው። ከተማ ውስጥ ደግሞ ሁከት ከተፈጠረ፣ ሕዝቡ ጸጥታ ከሌለው ፖሊሶች አሉ። ኦሮሚያ ፖሊስ አለ፤ የሌላም ፖሊስ አለ፤ በየክልሉ። ፖሊሶች ጸጥታ ማስከበር ያወከውንም በአግባቡ ለሕግ ማቅረብ አለባቸው። • ከምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው? ጥያቄ፡ አሁን ከኦነግ ታጣቂዎች ጋር ግጭቶች አሉ? አቶ ጋሹ፡ አንዳንድ ቦታዎች አሉ። ይሄ እንዲቆም ደግሞ ከመንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው። ጦርነት አያስፈልግም። ችግር ካለ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ተነጋግሮ መፍታት ነው። እና አላግባብ ግጭቶች በየቦታው ይታያሉ። ጥያቄ፡ የጸጥታ ችግር በሌለበት ቦታ ሠራዊት ማስፈር አይገባም እያሉኝ ነው። ከዚህ አንጻር አሁን ኦሮሚያ ላይ ሠራዊቱ ባላስፈላጊ ሁኔታ ሰፍሮባቸዋል የሚሉት የትኞቹ ቦታዎች ላይ ነው? አቶ ጋሹ፡ በምዕራብ ወለጋ በብዙ ቦታዎች ተሰማርቷል። በመሐከለኛ ቦታዎች ብዙ ቦታ ተሰማርቷል። ነቀምት፣ ጊምቢ፣ ቤጊ እና ደንቢዶሎ በመሳሰሉ የምዕራብ ከተማዎች ውስጥ ሰራዊት ይሰማራል። በዚህ አባይ መንገድ ጊዳ፣ ኡኬ-ቀርሳ የሚባሉ፣ በምዕራብ ሸዋ በኩል እስከ ባኮ ብዙ ቦታዎችን መጥቀስ እንችላለን። ሠራዊቱ ተጭኖ በከተማ ሲያልፍ ይታያል። ይሄ ሁሉ ለሕዝቡ ስጋት ነው። ካለፈውም ሥርዓት ያ ሁሉ ሰቆቃ አለበት። አሁንም ደግሞ ምን መጣብን እያለ ነው ሕዝቡ። ሕዝቡ የጸጥታ ችግር እንዳለበት ለኦነግም እየነገረ ነው፤ ይሄ ሁሉ ነው ያለው። እና ሠራዊት መኖር ያለበት በካምፑ፤ ኃይለኛ ችግር ከተፈጠረና በድንበር ላይ ችግር ካለ ደግሞ እዚያ ሰላም ማስፈን የሠራዊቱ ፋንታ ነው ማለት ነው። • ''በደኖ የሚባል ቦታን ረግጨው አላውቅም'' አቶ ሌንጮ ለታ ጥያቄ፡ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ግጭቶች አሉ። ለነዚያ ግጭቶች የመንግሥት ሰራዊት መሰማራቱ ችግር ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? አቶ ጋሹ፡ ግጭቶችን ለማብረድ የመንግሥት ሠራዊት መሰማራቱ ግዴታ ነው፤ አለበትም። በየድንበሩ ባለው ግጭት ሰበብ አድርጎ ወደ ከተማ መጥቶ ሕዝቡን ማወክ ነው ችግር። ግጭቱን ሳያበርዱ በዚያ ሰበብ በየከተማው ሰራዊቱን ማጓጓዝ፣ ማስፈር ተገቢ አይደለም ነው የምንለው። ግጭት መብረድ አለበት። ያ ግጭት ከሳምንት እስከ ወር፣ ከወር እስከ ዓመት መቆየት የለበትም። ግጭቶች እየተፋፋሙ ነው ዛሬም ድረስ፤ ሰው እየተፈናቀለ ነው፣ እየተገደለ ነው፣ ከቦታ ቦታ ተፈናቅሎ ብዙ ፍዳ እያየ ነው። ያ ሁሉ ዕዳ ደግሞ መልሶ ሕዝቡ ላይ ነው የሚወድቀው። ሠራዊቱ ያንን ማብረድ ነው እንጂ ወደ ከተማ ተመልሶ ሕዝቡን ማወክ የለበትም። ጥያቄ፡ ለግጭቶች የኦነግ ሠራዊት እየተወነጀለ ነው እኮ። እጁ አለበት ይባላል። አቶ ጋሹ፡ መረጃ ካለ በዚህ ቦታ እንደዚህ አድርጓል፤ በዚህ ቀበሌ እንዲህ አይነት ግጭት ፈጥሯል ይባል። በዚህ ሰዓት፣ በዚህ ቀን፣ በዚህ ደቂቃ የእገሌን ንብረት ዘርፏል የሚል ተጨባጭ የሆነ መረጃ ያየነው የለም እኛ፤ ተጨባጭ መረጃ ኖሯቸው በዚህ ቀን በዚህ ሰዓት በዚህ ቦታ እከሌ እንዲህ ተደረገ የሚል የለም። ግን ደግሞ እንደዚህ እንሰማለን በየሚዲያው፤ ይሄ ለ27 ዓመት ሲጠቀሙበት የነበረ ነው። ሁላችንም የምናውቀው በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው፤ የኦነግ ስም ከሌለበት ፖለቲካ አይጥምም [ልክ በቃ ጨው እንዳጣ ምግብ ማለት ነው]። ስለዚህ ለወንጀልም፣ ለሁካታም፣ ለድክመትም፣ ለሽንፈትም ማን መጠራት አለበት? ኦነግ ነው! ይህን ሕዝቡ በደንብ ያውቃል፤ ዓለምም ያወቀው ነገር ነው። ባለፈው የወያኔ ሥርዓትም በየፓርላማው በየምኑ ኦነግን ካልወነጀሉ ለድርጊታቸው ለጥፋታቸው ሰበብ አልነበራቸውም። ጥያቄ፡ ስለዚህ አሁን ኢህአዴግ ኦነግን እየወነጀለው ነው እያሉኝ ነው? አቶ ጋሹ፡ በብዙ ቦታ ኦነግ ያላደረገውን አደረገ ማለት ያለ ነው፤ ለሆነው ነገር ሁሉ ኦነግ ነው ማለት ያለ ነው። እናንተ ጋዜጠኞችም የመንግሥት አካልም ሆነ የሚወነጅለውን አካል ተጨባጭ በሆነ ነገር ላይ አትጠይቁም፤ የት? መቼ? እንዴት? የሚል ጥያቄ አትጠይቁም። በቃ ይሄን ነገር [አሁንማ] ለምደነው አይሰማንም፤ ኦነግን ያላግባብ መወንጀል ስህተት እንደሆነ ሕዝባችን በደንብ ተረድቷል። ኦነግ አያጠፋም ማለት ግን አይደለም፤ [እንደዛ ማለት] አንችልምም። [ነገር ግን] ኦነግ ባጠፋው ቦታ እኛ ከስህተታችን በደንብ ነው የምንታረመው። ጥያቄ፡ አቶ ለማ መገርሳና አቶ ዳውድ ኢብሳ በጋራ ለመሥራት ስምምነት አድርገው ነበር። በጋራ እንሠራለን ትላላችሁ። ፍቃደኝነትም ታሳያላችሁ። ደግሞም ትወነጃጀላላችሁ። ስምምነታችሁ ፍሬ ማፍራት ያልቻለው ለምንድነው? አቶ ጋሹ፡ የምትይው ይገባኛል። ግን ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጋር ስምምነት ላይ ነው ያለነው። በኦሮሞ ችግሮች ሁሉ አንድ ላይ ለመሥራት ስምምነት ላይ ነው ያለነው። አንዳንድ ሰዎች የሚያጋንኑት ከስምምነታችን ይልቅ ልዩነታችን ላይ ትኩረት ስለሚያደርጉ ነው። ብዙ የተነጋገርንባቸው፣ የተሰምማንባቸው፣ በመሬት ላይም እየሠራንባቸው ያሉ ነገሮች አሉ፤ ለወደፊቱም ደግሞ በመልካም እንጨርሳለን ማለት ነው። ትናንሽ ነገሮች ካሉ፤ አለመስማማቶች ካሉ ይሄንን በሰላማዊ መነግድ እንጨርሳልን። ጥሩ ጥሩ የሆኑ ሽማግሌዎች አሉ፤ አባገዳዎች አሉ፤ ልዩነታችን በቀላሉ የምነፈታበት ሁኔታ አለ። እኛም ደግሞ እንደ ድሮ አይደለም፤ የኦሮሚያ መንግሥት ፕሬዝዳንትም ሆነ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ካለፉት ጊዜያት የተማርናቸው ነገሮች አሉ። እኛም እርስ በራሳችን እየተነጋገርን በቀላሉ እንጨርሳለን፤ ልዩነት ግን መፈታት አለበት። ጥያቄ፡ ኦነግ ምርጫ ቦርድ ተመዘገበ? አቶ ጋሹ፡ አልተመዘገብንም፤ ግን በሂደት ላይ ነው ያለነው፤ እንመዘገባለን ብለን ነው እየጠበቅን ያለነው። ጥያቄ፡ ምንድነው ያጋጠመው ችግር? አቶ ጋሹ፡ በሂደት ላይ ነው ያለው፤ ይሄ ነው ተብሎ አሁን ለሚዲያ የሚነገር ነገር የለም።
news-45352040
https://www.bbc.com/amharic/news-45352040
ወንዶች አዞ ለመምሰል ቆዳቸውን የሚበሱባት ሃገር
በአለማችን ሁለተኛዋ ትልቅ ደሴት በሆነችው ፓፓ ኒው ጊኒ፤ 80 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች መኖሪያቸው ገጠራማ በሆኑት አካባቢዎች ነው። አብዛኛዎቹ ለሰለጠነው አለም ብዙም ቅርበት የላቸውም። በዚህ ዘመን ይኖራሉ ተብለው የማይታሰቡ ባህላዊ ስነ ስርአቶች አሁንም ድረስ በዚህች ደሴት ላይ ይስተዋላሉ።
በፓፓ ኒው ጊኒ ''የመንፈስ ቤቶች'' ተብለው የሚጠሩት የአምልኮ ቦታዎች በአብዛኛው ነዋሪ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ናቸው። በዚህ ቦታ የተለያዩ ሰዎች ነፍሳቸውን በተለያዩ የእንሰሳት መንፈስ የሚመሰሉላቸው ሲሆን፤ የአዞ መንፈስን የሚስተካከለው የለም። እነዚህ የአምልኮ ቦታዎች በብዙ የእንስሳት ቅሪቶች የተሞሉ ሲሆን፤ ከአሳማ እስከ ፈረስ፤ ከእባብ እስከ ንስር አሞራ ቅሪቶች በግድግዳዎቹ ላይ ይሰቀላሉ። ነገር ግን ለዚህ አካባቢ ሰዎች እንደ አዞ ሃይል እና ብልሃትን ያጣመረ እንስሳ የለም። • ሻደይ፦ለሴቶች፣ በሴቶች ፌስቲቫል • የባለዳንቴሏ የክር ጫማዎች ታዳጊ ወንዶች በእድሜ መብሰላቸውን ለማረጋገጥ ወደ እነዚህ የመንፈስ ቤቶች በመሄድ ጀርባቸው፣ ትከሻቸውና ደረታቸው ላይ ስለት ባላቸው ነገሮች ይበሳሉ። ምንም እንኳን ስነ ስርአቱ ከባድ ህመም ያለው ቢሆንም፤ ባህል ነውና ሁሉም የፓፓ ኒው ጊኒ ታዳጊዎች በጉጉትና በደስታ ያደርጉታል። ለእነሱ አዞን መምሰል የጥንካሬያቸውና በእድሜ የመብሰላቸው ማሳያ ነው። ታዳጊዎቹ ወደ መንፈስ ቤቶቹ የሚወሰዱት በአጎቶቻቸው ሲሆን፤ ቆዳቸውን የመብሳቱ ሂደት ከአንድ እስከ ሁለት ሰአት ሊፈጅ ይችላል። እንደውም ከዘመናዊ ፈጠራዎች መምጣት ጋር ተያይዞ የሚጠቀሟቸው ስለቶች እተሻሻሉ መጡ እንጂ፤ በድሮ ጊዜ የሚጠቀሙት ስል ቀርከሃ እንደነበር የአካባቢው ምክትል ተወካይ አሮን ማሊነጊ ይናገራሉ። ታዳጊዎች ከህመሙ ብዛት አንዳንድ ጊዜ ራሳቸውን ስተው እንደሚወቀድቁም ተወካዩ ይናገራሉ። ቁስሉ ቶሎ እንዲድንና ሌላ ችግር እንዳይፈጥር በአካባቢው በብዛት ካለ ዛፍ የሚገኝ ዘይት ይደረግበታል። ስነ ስርአቱ ያስፈለገው የታዳጊዎቹ እናቶች እነሱን ሲወልዱ ያፈሰሱትን ደም ለማስታወስና ከዚህ በኋላ የራሳቸውን ደም በማፍሰስ ትልቅ ሰው መሆናቸውን ለማሳየት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ታዳጊዎች ስነ ስርአቱን ከጨረሱ በኋላ በመንፈስ ቤቶች ውስጥ ለወራት በመቀመጥ ከታላላቆቻቸው የህይወት መንገዶችንና እንደ አሳ ማጥመድ ያሉ ሌሎች አስፈላጊ እውቀቶችን ይማራሉ። • "ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው" • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት ሃገሪቱን ቅኝ የገዛችው ጀርመን በ1885 አካባቢ ክርስትናን በፓፓ ኒው ጊኒ ካስተዋወቀች በኋላ ይህ ባህላዊ ስነ ስርአት ህልውናው ጥያቄ ውስጥ እየወደቀ መጥቷል። ነገር ግን የፓፓ ኒው ጊኒ ተወላጆች ባህላቸውን ለማስቀጠል እየተጣጣሩ ነው።
49123868
https://www.bbc.com/amharic/49123868
የኦሳ 33ኛ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀመረ
ኦሮሞ ስተዲስ አሶስዬሽን(ኦሳ) [የኦሮሞ ጥናት ማህበር] 33ኛውን ጉባኤ በአዲስ አበባ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ማካሄድ ጀምሯል። በዋነኛነት የኦሮሞን ታሪክ፣ ቋንቋ እና ባህል ለማጥናት የተቋቋመው ኦሳ፤ ላለፊት 32 ዓመታት ጉባኤውን ከኢትዮጵያ ውጪ ሲያካሄድ ነበር።
ዛሬ በተጀመረውና ለሦስት ቀን በሚቆየው ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ፕሬዘዳንት ኩለኒ ጃለታ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ ስለ ኦሮሞ ታሪክ ያለውን የተዛባ ትርክት ለማስተካከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። • በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን • "እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ • "ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ከኦሮሞ ቋንቋ እና ባህል ውጪ ስለሌሎች ብሔረሰቦች ታሪክ በማጥናት ጽሁፎች ያዘጋጃል። በዚህም የተቀረው ዓለም ስለነዚህ ማህበረሰቦች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው ይረዳል ሲሉ ፕሬዘዳንቷ ተናግረዋል። በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ እስካሁን የጥናት ተቋሙ ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል። በፖለቲካ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ ተገዶ የነበረው የጥናት ተቋምና ደጋፊዎቹ "አሸንፈዋል" ብለዋል። "ለመላው የኦሮሞ ሕዝብ ልጆቻችሁ እንኳን ተመለሱላችሁ" ብለዋል አቶ ሽመልስ በንግግራቸው። አሁን ያለው ትውልድ የገዳ ሥርዓት እንዲጠነክር እየተካሄደ ያለው ጥናትና ምርምር እንዲቀጥልበት ምክትል ፕሬዘዳንቱ ጥሪ አስተላልፈዋል። "ተሳታፊዎች በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል የጀመረው 'የዜግነት አገልግሎት' ሥራ ላይ እንደውል ሊደግፉ ይገባል" ብለዋል። የኦሳ ፕሬዘዳንት፤ የጥናት ተቋሙ የጥናት ማዕከል ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ ፍኖተ ካርታ ማሳየት አለበት ብለዋል። በጉባኤው ላይ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሠን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ምሁራን ይታደማሉ።
42999951
https://www.bbc.com/amharic/42999951
“ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ
በዓስር ዓመታት ውስጥ 11 መፅሐፎችን የፃፈው ደራሲና ኃያሲ አለማየሁ ገላጋይ በጠንካራ ማሕበራዊ ሕይወቱ፣ በኃያሲነቱ እና አዳዲስ ነገሮችን ሞካሪ መሆኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ።
"ከጎረቤቶቼ ከጓደኞቼ ጋር ካልሆንኩ፣ ካላሳለፍኩ፣ ዘግቼ የምቀመጥ ከሆነ እንዴት መፃፍ እችላለሁ?" ሲል የሚጠይቀው አለማየሁ "ብቸኝነት በራሱ የምታስባቸውን ነገሮች ይወስናል ፤ ለአንድ ደራሲ ዘጠና በመቶ መፃፍ ስራው ነው ብዬ አላስብም" ይላል። አንድ ደራሲ ቲያትር መመልከት እንዲሁም ሲኒማ ማየት አለበት የሚለው አለማየሁ ሰውን ሳይለዩ ከማንኛውም ሰው ጋር ማሳለፍ በተለየ ለደራሲ አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራል። በተለይ ልብወለድ የሚፅፍ ሰው እንደ ሳይንቲስት ወይም የሒሳብ ሊቅ በአንድ ነገር ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም የሚለው አለማየሁ ዙሪያ ገቡን የሚያውቅ የተሟላ አለም መፍጠር እንዲችል አለም የያዘቻቸውን በሙሉ ቀምሶ የሚያጣጥም መሆን ስላለበት ከሰዎች ጋር በማሳለፍ የሕይወት ልምዱን ማስፋት እንዳለበትም ይናገራል። "እናም እኔ ከወዳጆቼ እና ጎረቤቶቼ ጋር ሳሳልፍ ለስራው እንደሚከፈል መስዋእትነት ነው" ሲል ያክላል። አለማየሁ በቀን ውሎው ከወዳጆቹ ጋር አሳልፎ ለሊት ከ ዘጠኝ ሰአት በኋላ በመነሳት የማንበብ ፣ የመፃፍ አልያም ደግሞ በጥሞና የመመሰጥ ልምድ እንዳለው ይናገራል። "ብዙ ጊዜ የምፅፈው ሁለት አመትም ሆነ አንድ አመት ያብሰለሰልኳቸውን ነው። እነዚህን በወረቀት ላይ ለማስፈር አንድ ወር፣ ሐያ ስምንት ቀን፣ ምናልባት 25 ቀን ቢፈጅብኝ ነው። ስለዚህ ቀሪውን ጊዜ ለወዳጅ ዘመድ አተርፋለሁ ስለዚህ አልቸገርም" ይላል። የትኛውን ስራውን የበለጠ ይወዳል አለማየሁ ከስራዎቹ ሁሉ ጥሩ የሚለው ቀጥሎ የሚፅፈውን ነው። "የፃፍኳቸውን ልብ ወለዶች መለስ ብዬ ማየት አልችልም ፤ እንዳውም አልወዳቸውም ማለት ይቻላል" ይላል። ለውይይት እንኳ ሲቀርቡ በስራዎቹ ላይ አንተርሰው የሚነግሩኝ ነገር እንጂ ስለስራዎቹ የሚነግሩኝን አልወድም ይላል። ፅፎ ከጨረሰም በኋላም የአርትኦት ስራ የሚሰሩለት ሌሎች መሆናቸውን የሚናገረው አለማየሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመታተሙ በፊት ሁለቴ ያነበበው 'በፍቅር ስም' የሚለውን መፅሐፉን ብቻ ነው። "ያኔም ግፊት ስለነበር ነው፣ ከአሁን በኋላም ሁለቴ ከማንበብ ፈጣሪ ይጠብቀኝ" ሲል ያክላል። የዛሬ ሁለት ወር የሚወጣ አዲስ መፅሐፍ ፅፎ መጨረሱን የሚናገረው አለማየሁ "ይህ መፅሐፍ አሁን ስለሚወጣ እወደዋለሁ ማለት አይደለም ከሱ የሚቀጥለውን ለመፃፍ እየተዘጋጀሁ ስለሆነ ይህንን የሚያነቡ ምን ይሉኛል ስል ነው የምጨነቀው"ሲል ያስረዳል። "ወደ ኋላ የምንመለከት ከሆነ ወደፊት ለመጓዝ ያስቸግራል" የሚለው አለማየሁ ስራዎቹ የሌሎች ሰዎች ሆነው ምናለ ደጋግሜ ባነበብኳቸው የሚል ምኞት አለው። አለማየሁ ሥነጽሑፍን ያስተማሩት ሰዎች አንድ ሰው መፃፍ ያለበት እድሜው አርባ አመት ሲሞላው በሕይወት ልምድ ሲካብት ነው እንዳሉት ያስታውሳል። "በርግጥ እነርሱም ይህንን ከአርስቶትል ነው የወሰዱት። እኔም ጅል ስለሆንኩ የእነርሱን ምክር ተከትዬ የመጀመሪያ ስራዬ የሆነውን አጥቢያን ያሳተምኩት ልክ አርባ አመት ሲሞላኝ የዛሬ አስር አመት ነበር።" ሲል ያስታውሳል። በዚህ 10 አመት ውስጥ 11 መፅሐፎችን የፃፈውም አባከንኳቸው የሚላቸውን ጊዜዎች ለማካካስ እንደሆነ ይናገራል። "በዚህ ፌስ ቡኩ፣ በዚህ ኢንተርኔቱ ቀልብ ያሳጣል በዚህ ፈጣን ዘመን ቶሎ ቶሎ ካልፃፍኩ ምን ሊውጠኝ ነው።" ይላል አንድ ደራሲ ለአንድ ሐገር ሲሰጥ በረከት ነው ብሎ እንደሚያምን የሚናገረው አለማየሁ "አለመፃፌ መክሊትን እንደመቅበር ነው። እንደመቅሰፍት አየዋለሁ" ይላል። ለሚቀጥለው ትውልድ የነበረበትን ዘመን አንፀባርቆ ማለፍ አለብኝ ብሎ እንደሚያስብም ይናገራል። የቋንቋው ከባድነት በድርሰቶቹ ውስጥ የቋንቋው ውበት እና ምጥቀት በድርሰቱ ውስጥ የሚነሱ ሀሳቦቹን እንዳይረዱ እንቅፋት ነው የሚሉ አስተያየቶች ከአንባቢዎች የሚመጡ ሲሆን ይህንንም በተመለከተ "ቋንቋዬ ይከብዳል አልልም። እንዳውም ወደ ፊት የሚመጣው ይከብዳል ነው የምለው" ይላል። "መጉደል ይታየኛል ጊዜና ሁኔታዎች ቢገጣጠሙልኝ ጎንደር ጎጃም ወሎ እየሄድኩ የጎደለኝን ሞልቼ ብመለስ ስል አስባለሁ" ይላል። የተወሰነ ጊዜ የተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች በመቀመጥ የሀገሩን ባህል እንዲሁም የቋንቋውን ውበት ቀስሞ በስራዎቹ ውስጥ ለመጠቀም ዘወትር እንደሚያስብ ይናገራል። "አንድ ደራሲ ቋንቋውን ላክብድ ወይም ላቅልል ብሎ ማክበድም ማቅለል አይችልም" የሚለው አለማየሁ "ያ ከሆነ ተፈጥሮአዊ አይሆንም"ይላል። ጎስቋላ ገፀባሕርያት በስራዎቹ ውስጥ ጎስቋላ ገፀባህሪያት መኖራቸው የህይወቱ ነፀብራቅ እንደሆነ አለማየሁ ያስረዳል። "የኖርኩት ቁርስ ተበልቶ ምሳ የማይበላበት ምሳ ከተበላ እራት የማይደገምበት አካባቢ ነው። በስራዎቼ ያንን ሕይወት ማሳየት ካልቻልኩ አስቸጋሪ ነው" ይላል። የሐብትን ኑሮ አላውቀውም የሚለው አለማየሁ "የኖርኩበት እየመረጥኩም የምኖረው ሕይወት ይህንኑ ስለሆነ ፤ የማውቀውን ነው የምፅፈው" ሲል ይናገራል። በመፅሐፎቹ ውስጥ በገፀባሕሪነት የተሳሉ አብዛኞቹም ከህይወቱ የተጨለፉ እንደሆነ የሚናገረው አለማየሁ "አብሬ የኖርኳቸው የዘመን አሻራ የሆኑ እድሜዬን የተሳተፉ ናቸው።" አንዳንዴ በስራዎቹ ውስጥ በአንድ ገፀባሕሪ ውስጥ ተዳብለው የሚመጡ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ በእውኑ አለም ካለ ሰው ላይ ተጎርደው ይመጣሉ ሲል ያብራራል። የኖረበትን አካባቢ ገፀባህሪያት በአንድ ላይ ፅፎ አስቀምጦ እሱ እንኳ ባይችል ሌሎች ቢፅፏቸው ደስ እንደሚለውም አለማየሁ ይናገራል። "ነባር መንደሮች ሕይወታቸው ተመሳሳይ ስለሆነ ሌላ አካባቢ ያለው ኑሮ በድርሰቴ ውስጥ ከተሳለው ጋር ተመሳስሎባቸው ይሀኛው ገፀባህሪ እኛ ሰፈር ያለውን ሰው ይመስላል የሚሉ አንባቢያን እንደገጠሙት ይናገራል። እናቶቻችን ተመሳሳይ ናቸው፤ የአባቶቻችን ግድየለሽነት ተመሳሳይ ነው ስለዚህ አንባቢ ሲያነብ የኔን መንደር ብቻ ሳይሆን የእርሱን አካባቢ ሰው የሚመስሉ ቢያገኝ የፃፍኩት ዘመኑን ስለሆነ ነው" ይላል። አንዳንዴ ልብወለዶች ወደታሪክነት ይቀየራሉ የሚለው አለማየሁ በፈጣን ለውጥ ውስጥ የሚፈርሱትን መንደሮች ሕይወት ተፅፎ ለታሪክነት መቅረት እንዳለበትም ያምናል። "መንደሮች ሲፈርሱ እኮ የሰው ልጅ ነው አብሮ የሚፈርሰው። ሳይሞት ወደ መቃብር እንደወረደ ሰው እየው። ይህንን ነው ፅፎ ቢቻል ታሪክ አድርጎ ማስቀረት። ይህ የዘመን እዳ ነው፤ የኔ ዘመን እዳ፤ እንዴት ይህን እዳዬን ሳልከፍል ሳልፅፍ እቀራለሁ?" ሲል ይቆጫል። ድርሰትና ሒስ ከማህበረሰቡ ጋር ደራሲዎች ሲኖሩ የሚታዩትንና የሚሰሙትን ቅሬታዎች መግለፅ እንዳለበትም ያምናል። "ይህ እዳ መክፈያም ጭምር ነው" ይላል። ራሱንም እንደ ህዝብ ወገንተኛ እንደሚያይም ይናገራል። ''የምኖርበትን አካባቢ ሳየው ከሚፈርስባቸው ወገን ስለሆንኩ ለብዙሃን ይጠቅማል የምለውን ሳልፈራ እሰነዝራለሁ፤ ፖለቲካ ባትሔድ ይመጣብሃል ሸሽተህ የትም አትደርስም" ይላል። በደርግ ወቅት የሶሻሊዝም ርዕዮተ-ዓለምን የሚደግፉ እንደነ በአሉ ግርማ የመሳሰሉ ፀሀፊዎች ይፅፉ ነበር የሚለው አለማየሁ በዚህም ስርዓት ከሱ ተቃራኒ ስርዓቱን ደግፎ የሚፅፍ ሰው ቢያገኝ ሌላኛውን እይታ ማንፀባረቅ ይቻላልም ብሎ ያምናል። ተስፋ መቁረጥ አለማየሁ በደራሲነቱ ተስፋ የቆረጠበት ወቅቶች እንደነበሩ ይናገራል። "የደራሲነት አንዱ ግዴታ እስኪመስል ድረስ መፅሐፍ ሻጮች ገንዘቤን እንዲሰጡኝ ለምኜ አውቃለሁ" ይላል። የመፅሀፍ ሻጮች ማጉላላት እንደሚያሳምመው የሚናገረው አለማየሁ ለአሳታሚ እና ለአከፋፋይ ለመደወል ብዙ ጊዜ ይሳቀቅም ነበር። ጭቅጭቁም አሰላችቶት አላሳትምም ብሎ ተስፋ የቆረጠበትም ጊዜ እንደነበር ይገልፃል። ከበፍቅር ስም በኋላም ራሱ ማሳተም በመጀመሩ ብዙ ለውጥ እንዳየም ይናገራል። የገቢውም ሁኔታ እንደተሻሻለ ይገልፃል። በጎ ተፅዕኖ በወዲያኛው ዘመን ከነበሩ ደራሲያን ያመለጠኝ በአሉ ግርማ ብቻ ነው የሚለው አለማየሁ ከበርካታ ትልልቅ የሀገሪቷ ደራሲያን ጋር አብሮ በማሳለፉ ከነሱም ብዙ እንደተማረም ይናገራል። ከስብሐት ገብረእግዚአብሔር የመጨረሻ የሕይወት ዘመኖቹም አብሮ ከማሳለፉ በተጨማሪ እነ አበራ ለማ፣ አስፋው ዳምጤ፣ አብደላ እዝራ፣ የሺጥላ መኮንን፣ ደበበ ሰይፉ ስልጠና ስለሰጡት በሱ ህይወት ላይ ተፅእኖ መፍጠር ችለዋል። "ከእነርሱ በተጨማሪ ስራዎቻቸውን ማንበቤ እና በደንብ መመርመሬ አብጠርጥሬ ለመተቸት መቻሌ እንዲሁም መፅሐፍ መፃፌ ረድቶኛል" ይላል። "እኔ ሁሌም የምፎካከረው ከወደቀው ደራሲ ጋር አይደለም የሚለው አለማየሁ ፉክክሬ ከነሀዲስ አለማየሁ እና ከነበአሉ ግርማ ጋር ነው" ሲል ሃሳቡን ይቋጫል።
news-56417944
https://www.bbc.com/amharic/news-56417944
ክሪፕቶአርት: ዲጂታል ሥዕል በመሸጥ ሚሊየነር እየሆኑ ያሉ የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች
ክሪፕቶአርት ይባላል። አሁን አሁን ይህ የዲጂታል ሥዕል ግብይት ዘዴ እጅጉን የገነነ ነው። ለዘመናት በድህነት የጎበጡ የሥነ ጥበብ ሰዎች ክሪፕቶአርት ሠርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል።
አላና ኤዲንግተን ይህን አዲስ ጥበብ በዚህ አዲስ ዘመን ላይ በመምጣቱ ሕይወታቸውን እየለወጡ የሚገኙ የምዕራቡ ዓለም አርቲስቶች ቁጥር ቀላል አይደለም። አርቲስት ቢፕል ከሰሞኑ አንድ ዲጂታል ሥዕል 69 ሚሊዮን ዶላር በመሸጥ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል። ሥዕሉ የተሸጠው በብሎክቼይን የዲጂታል ግብይት ዘዴ ነው። በዚህ መንገድ ሥዕሉን የሸጠው አርቲስት እንደሚለው ይህ የክሪፕቶአርት ሽያጭ በዓለም ላይ ትልቅ ተሰሚነት ካላቸው 3 አርቲስቶች መሀል አንዱ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አላና ኤዲንግተን ሌላዋ አርቲስት ናት። በእዳ ቁልል ኑሮዋን ስትገፋ ነው የኖረችው። ይህ የዲጂታል ሥዕል ገበያ ግን ሚሊየነር አድርጓታል። በምህጻሩ ኤንኤፍቲ (NFT) በሚሉ ቃላት የሚወከለው ይህ አዲስ ዘዴ Non-Refundable Token የሚል ሐረግን የሚወክል ነው። ነገሩ አርቲስቶች ሥራዎቻቸውን በዲጂታል መንገድ የሚሸጡበት አዲስ አሰራር ነው። በሌላ አነጋገር ኤንኤፍቲ የዲጂታል ጉሊት ሲሆን አርቲስቶችና አጫራቾች እንዲሁም ሸማቾች የሚገናኙበት ዲጂታል ሥፍራ አድርገን ልናየው እንችላለን። ገዢው የሚገዛው የአርቲስቱን ቱባ ሥራ ዲጂታል የባለቤትነት ካርታ ነው። እንደ ቢትኮይን ያለ የዲጂታል ገንዘብ አንድ ቅጥያ የሆነው ኤንኤፍቲ ዓለምንና የገንዘብ ልውውጥን ከሥር መሠረቱ ይለውጣል ተብሎ የሚጠበቀው የክሪፕቶከረንሲ አካል ነው። በዚህ ዘዴ የሚሸጠው የዲጂታል ሥዕል በምንም መንገድ እንዳይቀዳ፣ እንዳይባዛ፣ እንዳይጋራ ስለሚደረግ ዘላለሙን ቱባነቱን ይዞ ይቆያል። አንድ ሰው ይህን ዓይነት ሥራ ሲገዛ የሥዕል ሥራው ወደሚገኝበትን ፋይል ለመግባት የሚያስችል ቁልፍ ወይም ዲጂታል ካርታ አገኘ ማለት ነው። ልክ ሰዎች ለመሬታቸው ካርታ እንደሚሰጣቸው ሥዕሉን የሚገዛው ሰው ዲጂታል የባለቤትነት ካርታን ያገኛል። ገንዘቡን በሥዕል ሥራው ላይ የሚከሰክሰውም ይህንኑ ለማግኘት ነው። ይህም ካርታ በምንም መልኩ የማይደመሰስና በሌላ ሰው የማይቀዳ ዘላለማዊ የሥዕል ሥራ በእጅ የማስገባት መብትን ያስገኛል። ይህ ሥዕል በድጋሚ በተሸጠ ቁጥር ፈጣሪው በመቶኛ ትርፍ ስለሚያገኝ ሁልጊዜም ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርገዋል። ሰዎች ቢትኮይንን በቢትኮይን ሊቀይሩ ይችሉ ይሆናል። ይህ የዲጂታል ካርታ ግን በምንም መልኩ ሊጋሩት ወይም ሊለዋወጡት የሚችሉት አይደለም። አንድ ቢትኮይን በሌላ ቢትኮይን ቢቀየር በተመሳሳይ ጊዜ ከሆነ አንድ ብርን በአንድ ብር መቀየር እንደማለት ነው። የይህንን ዲጂታል ካርታ ከሌላ ሰው ጋር ለመጋራት መሞከር ግን አንድን የኮንሰርት ትኬት ግማሹን ቆርጦ ለሰው የመስጠት ያህል ትርጉም አልባ ነው። ይህ ቱባነቱ ነው ሰዎች በዲጂታል ገበያ እንዲወዳደሩና ገንዘባቸውን ከስክሰው ዲጂታል የሥዕል ባለቤትነት ካርታን እንዲገዙ የሚያደርጋቸው። አላና ኤዲንግተን ከልጆቿ ሚሊየነርነት እንደዋዛ አርቲስት አላና ጎበዝ ሠዓሊ ብትሆንም ራሷን "መሸጥ" የምትችል ሴት አልነበረችም። ዓይነ አፋር ናት፤ ሥራዎቿን ጋለሪ ለመውሰድ እንኳ ትፈራለች። ስለዚህ በትርፍ ጊዜዋ ሥዕል እየሰራች 3 ልጆቿን በማሳደግ ተጠምዳ ነው የኖረችው። ኑሮዬን ከደጎመልኝ በሚል በዲግሪ የአበባ እርሻ ሳይንስ ስታጠና ቆየች። እንደ ብዙ የዓለም ሕዝብ ሁሉ ሁልጊዜም ሐሳቧ ከዞረ ድምር የዕዳ እሽክርክሪት መቼ እንደምትወጣ ስትጨነቅ ነው የኖረችው። ኑሮ ሞልቶላት አያውቅም። ሸራ ላይ በዘይት ቀለም የሠራችውን ሥዕሏን የሆነ ቀን ድንገት ወደ ድረ-ገጽ ገብታ በ500 ዶላር ስትሸጠው ለራሷ ደነገጠች። በሌላ ቀን ወደ ድረ-ገጽ የሥዕል ጨረታ በገባችበት ጊዜ 16 ሥዕሎቿን በመቶ ሺህ የካናዳ ዶላር የሚገዛ ሰው አገኘች። ይህ ከአእምሮ በላይ ሆነባት። ማመን ተሳናት። የ35 ዓመቷ አርቲስት አላና "ሰዎች ለእኔ ሥዕል ይህን ያህል ዋጋ ይከፍላሉ ብዬ ለማመን ተቸግሬያለሁ" ስትል ተናግራለች። ይህ ስኬቷ የአርቲስቷን ሕይወት ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገረው። መጀመርያ የኮሌጅ ትምህርት ክፍያዋን ከፈለች፣ ጣሪያ የነኩ የእዳ ክምሮቿን አቃለለች፣ ቤተሰቧን ወደ ሌላ ከተማ ወስዳ ማኖርም ጀመረች። በአእምሮ እድገት ውስንነት ይሰቃይ የነበረውን አንድ ልጇን ጥሩ ሕክምና እንዲያገኝም አደረገች። "ይህ የዲጂታል ሥዕል ግብይት በተለይ ለሴት አርቲስቶች አዲስ በር የከፈተ ነው" ትላለች አርቲስት አላና። 22 ሺህ የካናዳ ዶላር የተሸጠው የአላና ዲጂታል ሥዕል ኤንኤፍቲ ምንድን ነው? ኤንኤፍቲ (NFT)ዲጂታል ሰርተፍኬት ወይም የሥዕል ባለቤትነት ካርታ እንደማለት ነው። የአንድን የፈጠራ ሥራ ባለቤትነት የሚመሰክር ዲጂታል ካርታ። በክሪፕቶአርት ዓለም አንድን የፈጠራ ሥራ አንድ ሰው ብቻ በባለቤትነት ይዞት ይቆያል። ቱባውን የሥዕል ሥራ ማባዛትም፣ መቅዳትም፣ መለወጥም አይችልም። ይህ ዲጂታል ሰርተፍኬት በብሎክቼይን ውስጥ ነው የሚገኘው። ብሎክቼይን ቴክኖሎጂ የዲጂታል ገንዘብ ልውውጥና ግብይት የሆነውን ክሪፕቶከረንሲን የሚያስተዳድር ሲሆን ቢትኮይን የመሰሉ ዲጂታል ገንዘቦች በስሩ ይገኛሉ። ይህም ኤንኤፍቲ የዚህ አካል ነው። ስለዚህ አንድ የሥዕል ሥራን ሁሉም ሰው ኦንላይን ገብቶ ቅጂውን ሊያየው ቢችልም ኤንኤፍቲ ግን ባለቤትነቱን ለገዛው ሰው ብቻ ስለሚሰጥ የሥዕሉ ባለቤት ያ ሰው ብቻ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ ሥዕሉን ሁልጊዜም በአስተማማኝ ጥበቃ ስር እንዲቆይ ያደርገዋል። ልክ የቤት ካርታ እንደመያዝ ሁሉ የኤንኤፍቲ ካርታ መያዝ የባለቤትነት ሰርተፍኬት ያስገኛል። አንድ የመሬት ባለቤት መሬቱን ሲሸጥ ካርታ እንደሚሸጠው ይህ ኤንኤፍቲ የፈጠራ ባለቤትነት መብት ለሌላ ሁለተኛ ሰው ለማስተላለፍም ተመሳሳይ ሂደትን ይከተላል። ሰዎች ሥዕሉን በገዙበት ጊዜ ሁሉ ግን የፈጠራ ባለቤትነቱ የአርቲስቱ ሆኖ ይቆያል። ከሽያጩም በመቶኛ ክፍያን ያገኛል። ዳሪየስ ፑያ "ሙልጭ ያልኩ ድሀ ነበርኩ፤ድንገት በአንድ ጊዜ የ250ሺህ ዶላር ጌታ ሆንኩ" የሳይንስ ልቦለድና የ3ዲ አርቲስት ዳሪየስ ፑያ ሕይወቱን የቀየረውን አጋጣሚ ሲያስብ ይገረማል። መጀመርያ ጓደኞቹ በድረ ገጽ ሥራዎቻቸውን መሸጣቸውን ሲነግሩት አላመነም ነበር። እስኪ ልሞክረው ብሎ ፈራ ተባ እያለ ገባበት። ብዙም ተስፋ አድርጌ አልነበረም ዲጂታል ገበያውን የተቀላቀልኩት ይላል። ዳሪየስ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሳንቲሞችን ማግኘት ጀመረ። አክሮፎቢያ የተሰኘው ዲጂታል ሥዕል ሥራው በአንድ ጊዜ 12 ሺህ ዶላር ተሸጠለት። ማመን አልቻለም። "ፍቅረኛዬን ወዲያውኑ ደውዬ፣ ምን እየሆነ እንደሆነ ልትነግሪኝ ትችያለሽ? ይህ የማየው ነገር እውነት ነውን?" ስል ጠየቅኳት ይላል። ከዚህ ስኬት በኋላ አርቲስት ዳሪየስን የሚያቆመው ሰው ጠፋ። "ከ20 ቀናት በፊት ሳንቲም ቸግሮኝ ግራ የገባኝ ሰው ነበርኩ። በ20 ቀን ውስጥ የ250 ሺህ ዶላር ጌታ ሆንኩ፤ ይህም ማን ያምናል?" ይላል። ከ35 ሺህ ዶላር በላይ የተሸጠው የዳሪየስ ዲጂታል ሥዕል ዲጂታል ሥዕሎችን የሚገዛው ማን ነው? ራጋቫንዴራ ራዉ በኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ የገንዘብና ተያያዥ ጉዳዮች ፕሮፌሰር ናቸው። ይህ የዲጂታል ግብይት ዘላቂ ይሆናል ብለው እምብዛም አያምኑም። "ብዙ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ወደ ውጭ ስለማይወጡ ለዚያ ማካካሻ ገንዘባቸውን በዚህ መንገድ ወጪ እያደረጉት ነው የሚመስለው" ሲሉ ለቢቢሲ ሐሳባቸውን አጋርተዋል። ፕሮፌሰሩ እንደሚተነብዩት ዲጂታል ግብይቱ ቢቀጥል እንኳ በዚህ ዘዴ ወደፊት ሁሉም አርቲስት ይሸጣል ማለት አይደለም። ምናልባት ገናናዎቹ ብቻ በዚህ የዲጂታል ግብይት ተፈላጊነታቸው ሊቀጥል ይችል ይሆናል። "ገዢዎች ለጊዜው ብዙ ገንዘብ ሊያገኙ ይችላሉ፤ ብዙ ገንዘብም ሊያጡ ይችላሉ። እንዲህ ዓይነት ነገሮች አስተማማኝ አይደሉም፤ ጊዜያዊ ናቸው" ይላሉ። በኤንኤፍቲ ገበያ ላይ ተሳታፊው ኔልሰን ሮህርባች በበኩሉ የክሪፕቶ አርት መነቃቃትና መጎልበት የአመጽ ያህል ነው ይላል። ለዓመታት አርቲስቶች ሲበዘበዙና ሥራቸውም ዋጋ እያጣ ቆይቷል። አሁን ያን ለመቀየር የተደረገ ተቃውሞ ነው። እሱ እስካሁን 20 ሺህ ዶላር በማውጣት የተወሰኑ ሥዕሎችን መግዛት ችሏል። ያን ማድረጉ ትልቅ ኢንቨስትመንት እንደሆነ እንጂ ብክነት አድርጎ አያስበውም። ወደፊት ግብይት የሚደረገው በዚህ መንገድ መሆኑ አይቀርም ይላል። "አርቲስቶችን ማገዝ እፈልጋለሁ። አርቲስቶች ለሥራዎቻቸው ዋጋ ሲያገኙ ማየት ነው ህልሜ። ገንዘቤን በዚህ መንገድ ዲጂታል ሥዕል በመግዛት ማውጣቴ አደጋ አለው፤ ነገር ግን የሚመጣውን ለመቀበል ፍቃደኛ ነኝ" ብሏል።
news-53831245
https://www.bbc.com/amharic/news-53831245
"ባለብኝ ህመም የተነሳ ከሁለት ዓመት በላይ ምግብ በአፌ አልዞረም"
ምንም ነገር በአፍዎ ሳይዞር ቢውሉ ምን ይፈጠራል? ቢያድሩስ?"
ፈርናንዳ ማርቲኔዝ በየዕለቱ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ገጿ ብቅ ባለች ቁጥር የሚቀርብላት ጥያቄ ነው። ፈርናንዳ ለሚቀርቡላት ጥያቄዎች ሁሉ ቅሬታ ሳታሳይ፣ ባለባትን በዘር ምክንያት የሚተላለፍ በሽታ የተነሳ ላለፉት ሁለት ዓመታት ተመግባ እንደማታውቅ ታስረዳለች። የ22 ዓመቷ ብራዚላዊት ኢህለርስ-ዳንሎስ ሲንድሮምስ (Ehlers-Danlos syndromes) እየተሰቃየች እንደምትገኝ ትናገራለች። ይህ ሕመም በጥቂት ሰዎች ላይ ብቻ የሚከሰት ሲሆን፣ በሰውነት ውስጥ የምግብ መፈጨትን የሚያስተጓጉል ተገቢ ያልሆነ ኮላኝ (ፕሮቲን) እንዲፈጠር ያደርጋል። እንደ ኢህለርስ ዳንሎስ ሲንድሮምስ ማህበር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በሽታው 13 ዓይነት የያለው ሲሆን በዓለም ላይም 5 ሺህ ያህል ሰዎች በዚህ በሽታ እንደተጠቁ ይገመታል። ፈርናንድም በኢዲኤስ የተነሳ ሰውነቷ ምግብ መፍጨት ስለማይችል እአአ ከ2018 ጀምሮ የመመገብያ ቱቦ ተሰክቶላት ነው ምትኖረው። ይህ ብቻ ሳይሆን ፈርናንድ በዘሯ ውስጥ ያለ እና በእርሷም ላይ የተከሰተ የታይሮይድ ካንሰር ታማሚ ናት። ፈርናንዳ ዓለም ስለጤንነት ሁኔታዋ እንዲያውቅ እና ሌሎች እንዲማሩ በማሰብ በየጊዜው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስላለችበት የጤና ሁኔታ ትጽፋለች። የፈርናንዳ ዋነኛ ችግር በአጭር ቋንቋ ሲገለፅ መብላትም መጠጣትም አለመቻል ነው። የምትበላቸውን ምግቦች ሰውነቷ እንዲቀበል በምግብ መስጫ ቱቦ በኩል መደገፍ አለባት። የሚሰጣትም ምግብ ቢሆን ሰውነቷ መፍጨት ስለማይችል ከየአይነቱ ተቀምሞና ተመጥኖ በጠብታ መልኩ ነው እንድትወስድ የሚደረገው። ፈርናንዳ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቿ ስላለችበት ሁኔታ ለመግለጽ አትታክትም፤ ይህ ደግሞ በግል ሰሌዳዋ ላይ ብቻ ሳይሆን በእንዲህ አይነት ባልተለመደ ህመም በሚጠቁ ህሙማን ገጽ ላይ በመገኘትም የምታደርገው ገለጻ የየእለት ተግባሯ ነው። ገለፃዎቿ ተወዳጅ ናቸው። ተስፋ ሰጪ ንግግሮቿ አበረታች ናቸው፤ በቲክ ቶክ የማህበራዊ ሚዲያ ዓለም ላይ የምትለጥፋቸው መልእክቶች ተመልካቾች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ደርሷል። ፈርናንዳ በቲክቶክ ላይ የምትለጥፋቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች 1 ሚሊዮን ድረስ ተመልካች ያገኛሉ ፈርናንዳን የገጠማት ችግር ምንድን ነው? "ሕጻን ሳለሁ፣ የሆነ ችግር እንዳለብኝ ምልክት ይታይ ነበር" ትላለች። ሕጻን እያለች እግርና እጇ ላይ ከፍተኛ ሕመም ነበረባት፣ አንድ ጆሮዋ መስማት አይችልም ነበር፤ እናም በከፍተኛ ሁኔታ ያስመልሳታል። መገጣተሚያዎቿንም ቢሆን ከተለመደው ርቀት በላይ ማወዛወዝና ማጣጠፍ ትችላለች፤ ይህ ደግሞ ለውልቃትና ቦታ መሳት ያጋልጣል። "እነዚህ ምልክቶች እያደግኩኝ ስሄድ እየተባባሱ መጡ. . .ሁሉም ሰው የሆነ ችግር እንዳለብኝ ያውቃል፣ ነገር ግን ምን እንደሆነ ማወቅ አልቻሉም ነበር" ማህበራዊ ሚዲያ ነው የፈርናንዳን ችግር እንድታውቅ የረዳት፣ አንድ ፌስቡክ ቡድን ስለ ኢህለርስ ዳንሎስ ሲንድሮምስ ይወያይ ነበር ትላለች ሁኔታውን ስታስታውስ። ከዚያም "ጄኔቲክስ ወደሚያጠኑ ባለሙያዎች ዘንድ ሄጄ ሁሉንም ምርመራ አደረገችልኝ እና በሽታው እንዳለብኝ ተረጋገጠ" ትላለች የ22 ዓመቷ ወጣት። ፈርናንዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመርምራ ሕመሙ እንዳለባት ሲረጋግጥ 17 ዓመቷ ነበር። አሁን ግን በሽታው ከፍተኛ የሚባል ደረጃ ደርሷል። መገጣጠሚያዎቿን ያማታል፤ ልቧንና አንጀቷን የሚቆጣጠረው የነርቭ ስርዓትም በአግባበቡ ስለማይሰራ ዳይሳውቶኒሚያ ለሚባል ሕመም ተጋልጣለች። " የሆድ ሕመም፣ ማስመለስ እና ተቅማጥ ያስቸግረኛል" ስትል ታስታውሳለች። "ቢያንስ ግን ለሚሆነው ነገር ሁሉ ስም አለው። አሁን ስለ ሕመሜ ማብራራትና ለዶክተሮችና ለሌሎች ማስረዳት እችላለሁ" ኤህለርስ ዳንሎስ የኮሎኝን ምርት ነው የሚያስተጓጉለው፤ ኮሎኝ ደግሞ ፕሮቲን ሲሆን ሰውነት አጥንት፣ ቆዳ፣ ጅማቶችንና የመሳሰሉት ቅርጽና መልክ እንዲያሲዝ በማድረግ ውስጥ ትልቅ ድርሻ አለው። "መገጣጠሚያዎቼ እና ሌሎች አካል ክፍሎቼ በቀላሉ ለጉዳት ይጋለጣሉ እንዲሁም የደም ስሮቼ በቀላሉ ይበጠሳሉ" ትላለች ፈርናንዳ። ይርባት ይሆን? "ምንም ነገር አልበላም አልጠጣም" ትላለች። "ባለብኝ ሕመም የተነሳ የውስጥ አካሎቼ እና ጡንቻዎቼ ደካማ ሆነዋል። የምግብ መፈጨትን የሚያቀላጥፈው፣ የነርቭ ስርኣቴም ቢሆን ተጎድቷል" "ነገር ግን ለረዥም ጊዜ ርቦኝ አያውቅም፣ ምከንያቱ ደግሞ ረሃብ የሚመሰረተው በሆድ ውስጥ ባለ እንቅስቃሴ የተነሳ ነው እና የእኔ ፈጽሞ አይንቀሳቀስም" ፈርናንዳ እንደምትለው አንዳንድ ጊዜ የመብላት ፍላጎት እንደሚያስቸግራት እና ግን ስነ ልቡናዊ ብቻ መሆኑን ታስረዳለች። ይህ ዓይነት ስሜት ሲሰማት ምግብ አኝካ ሳትውጥ ትተፋዋለች። " ግን አሁን አሁን እናቴ ምሳዋን ስትመገብ ብቻዋን እንዳትሆን አብሬያት እቀመጥና የተለመደውን አኝኮ የመትፋት ተግባሬን አከናውናለሁ" ስትል ታክላለች። ፈርናንዳ መብላት እያቃታት የመጣው በ2016 የነበረ ሲሆን ወዲያውኑ በምግብ ዕጥረት ተጎዳች። " በጣም ትንሽ ትንሽ ነበር የምመገበው፤ አመጋገቤንና የምግብ ዓይነቶቼን ለመቀየር እየሞከርኩ" በ2018 ግንቦት ወር ላይ የምትመገብበት ቱቦ ተሰካላት። ይኼኔ ችግሯ የተቃለለ መሰለ። ነገር ግን ከአንድ ዓመት ከግማሽ በኋላ ሰውነቷ በቱቦው የሚሰጣትን ምግብ ሁሉ መቀበል አቆመ። የሆድ እቃዋ የትኛውንም ዓይነት የተመጣጠነ ምግብ መቀበል አልቻለም። በ2019 መጨረሻ ላይ በምግብ እጥረት በመጎዳቷ የተነሳ ሆስፒታል የገባች ሲሆን ዶክተሮች ከተለያዩ የምግብ ዓይነቶች የተመጠኑና በቀጥታ ከደሟ ጋር መዋሃድ የሚችሉ ምግቦችን ይሰጧት ጀመር። እንዴት ነው ገላዋን የምትታጠበው? ፈርናንዳ ውሃ ሲነካት ገላዋ ይቆጣል፤ የውሃ አለርጂ አለባት፤ ዶክተሮች ይህንን አኩዋጄኒክ አርቲሳሪኣ (aquagenic urticaria) ይሉታል። " በተቻለኝ መጠን ውሃ እንዳይነካኝ እጠነቀቃለሁ። እንዳይርበኝ እጠነቀቃለሁ፣ ዝናብ እንኳ እንዳይነካኝ እጠነቀቃለሁ" ትላለች። ወደ ባህር ዳርቻም ሆነ መዋኛ ገንዳ ጋርም አትቀርብም። ይህ ሁሉ ይሁን እንጂ በሳምንት ሁለቴ ገላዋን ትታጠባለች። ነገር ግን አስቀድማ ፀረ አለርጂክ መድሃኒት መውሰድ አለባት። ይህ ሆኖ እንኳ ጦስ አያጣትም። "ገላዬን ያሳክከኛል፤ በአጠቃላይ ቀይ ቀይ ነጠብጣብ አውጥቷል" ትላለች። አለርጂ እንኳ ባይኖርባት ለፈርናንዳ ገላ መታጠብ በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ምግቧን የምትወስድበት ቱቦ መርጠብ ስለሌለበት ነው። ኤህለርስ ዳንሎስ ሲንድረም ይድን ይሆን? እስካሁን ድረስ ለኢዲኤስ የታወቀ መድሃኒት የለም። 'የመገጣጠሚያዬ ችግር በፊዚዮቴራፒ የሚታከም ነው፣ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስ" ስትል ታስረዳለች። ነገር ግን ሐኪሞች ለፈርናንዳ የጨጓራዋ ጉዳይ ይስተካከላል ብለው እንደማይጠብቁ ነግረዋታል፤ እናም ቀሪውን እድሜዋን በሙሉ የምግብ እርዳታ የምትቀበልበት ቱቦ አብሯት ይዘልቃል ማለት ነው። ይሁን እንጂ ፈርናንዳ ሕይወትን እንደተለመደው ለመኖር ትጥራለች። ኦንላየን ጌሞችን መጫወት የምትወደው ፈርናንዳ " በሁኔታዬ አልበሳጭም፤ ይልቁንስ ካለብኝ ችግር ለመማር እጥራለሁ" ትላለች። በተደጋጋሚ ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ተቋም መመላለሷ ለሕክምና ሳይንስ ፍቅር እንዲያድርባት ያደረገ ሲሆን፤ የጤና ሳይንስ ብታጠናም ደስተኛ ናት። እስከዚያው ድረስ ግን በብዛት የማይከሰቱ ህመሞችን መሰነድ ትፈልጋለች። በምትሰንደው መረጃ አንድ ሰው እንኳ መርዳት ከቻለች ደስተኛ እንደምትሆን ጨምራ አስረድታለች።
news-54417245
https://www.bbc.com/amharic/news-54417245
ትግራይ፡ ህወሓት በመንግሥት ሹመት ላይ ያሉ አባላቱ ቦታቸውን እንዲለቁ ማዘዙን ገለጸ
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታ ላይ የነበሩ አባላቱን፣ የክልሉ ተወካይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ኃላፊነታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን አቶ ጌታቸው ረዳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
አቶ ጌታቸው ረዳ የፓርላማው የስልጣን ዘመን በትናንትናው ዕለት ማክተሙን በመግለጽ፣ ከፓርላማው በተጨማሪ ፓርላማው ያቋቋመው መንግሥም፣ ካቢኔም የተመረጡት ለአምስት ዓመት መሆኑን ጠቅሰው የሰልጣን ዘመናቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልፀዋል። ስለዚህ ዛሬ በሚካሄደው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ትግራይ ክልል ተወካዮቹን እንደማይሳተፉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። "ትግራይ ክልል ተወካዮች ከምክር ቤቱ እንዲወጡ ተነግሯቸዋል። በፓርላማ ብቻ ሳይሆን በካቢኔ ውስጥ፣ በሌሎች የመንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታዎች ላይ የነበሩ የህወሓት ተወካዮች እንደዚሁ እንዲወጡ ተደርገዋል" ሲሉ ተናግረዋል። አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አምስተኛ የፓርላማ ዘመን ስድስተኛ ዓመት የሥራ ጊዜ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሰኞ መስከረም 25/2013 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ይካሄዳል። ጉባኤው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚገኘው የስብስባ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያው ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሚያደርጉት ንግግር የሁለቱ ምክር ቤቶችን የጋራ ስብሰባ ይከፈታል። አቶ ጌታቸው "በአሁኑ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ካቢኔያቸው፣ እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ምንም አይነት ሕጋዊ ስልጣን የላቸውም በማለት፤ ከዛሬ ጀምሮ ከእነዚህ አካላት ጋር ምንም አይነት ሕጋዊ ግንኙነት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም" ብለዋል። የትግራይ ክልል የምርጫ ጊዜያቸው አልቋል በሚል ግንኙነቱን ከእነዚህ አካላት ጋር ቢያቋርጥም እንደ አቶ ጌታቸው ረዳ ከሆነ ከፍትህ ተቋማት፣ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከዲፕሎማቲክ ሚሽን ከሚሰጡ ተቋማት እና በተለያየ ደረጃ የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎት ከሚሰጡ አካላት ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል። "መንግሥት በትክክለኛው መንገድ ለመመስረት የሚያስችል እድል እስኪገኝ ድረስ ግንኙነታችን ከእነዚህ ጋር ብቻ ይሆናል" በማለት "ፈርሰዋል" ካሏቸው ጋር ያላቸው ግንኙት መቋረጡን አስታውቀዋል። የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በተፈጠረው የኅብረተሰብ ጤና ስጋት ሳቢያ ባለፈው ዓመት መካሄድ የነበረበት ምርጫ መካሄድ ሳይችል በመቅረቱ ሁለቱ የፌደራል ምክር ቤቶችና በሁሉም ክልሎች ውስጥ ያሉት ምክር ቤቶች ምርጫው እስኪካሄድ በሥራ ላይ እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን በማቋቋም በተናጠል ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ በመወሰኑ ከፌደራል መንግሥቱ በተለይም ደግሞ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫው መካሄድ እንደሌለበት ድርጊቱም ሕገወጥና ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ተገልጾ ነበር። በዚህም ሳቢያ በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ሄዶ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከመስከረም 25 በኋላ ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚያበቃ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ ከቀናት በፊት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይህንኑ በተመለከተ እንደተናገሩት "በእስካሁኑ እንቅስቃሴ ክልሉ ሕገ-መንግሥቱን አደጋ ላይ ጥሏል" ለዚህም እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ መሰረት መኖሩን አመልክተዋል። ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል የክልሉን ሕግ አውጪና ሕግ አስፈጻሚውን ማገድ የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ አካሄድ አንዱ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋምና የፌደራል የፀጥታ አካላት በማሰማራት ሕገ መንግሥቱን አደጋ ላይ የጣለውን ድርጊት መቆጣጠር ሌላኛው መሆኑን አፈጉባኤው ገልጸዋል።
news-55474308
https://www.bbc.com/amharic/news-55474308
ሴቶች፡ በ13 ዓመት ዕድሜ እርግዝና እና ትምህርት
የታንዛኒያ መንግስት ባለፉት ወራት ያረገዙ ሴት ተማሪዎችና በልጅነታቸው የወለዱ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ መከልከሉን ተከትሎ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት ነበር። እንዲህ አይነት መሰል ሕግ በመተግበር ታንዛኒያ በዓለማችን ላይ ካሉ ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ናት።
ፋቱ የ13 ዓመት ታዳጊ ስትሆን በደረሰባት ጾታዊ ጥቃት የተነሳ የአራት ወር ነብሰ ጡር ናት የዛሬ ዓመት አካባቢ ደግሞ የሴራሊዮን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንግሥት በተመሳሳይ ያወጣውን ሕግ እንዲተወው ወስኗል። ለመሆኑ በዚህች ምዕራብ አፍሪካዊት አገር ከሕጉ መሻር በኋላ ምን ተቀይሮ ይሆን? ፋቱ (ትክክለኛ ስሟ አይደለም) የ13 ዓመት ታዳጊ ስትሆን የአራት ወር ነብሰ ጡር ናት። ያረገዘችውም በደረሰባት ጾታዊ ጥቃት ነው። እስከያዝነው ዓመት ድረስ ፋቱ ባለችበት ሁኔታ ትምህርቷን ማቋረጥ ግድ ይላት የነበረ ሲሆን፣ በግድ ትዳር እንድትመሰረትም ትደረግ ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ሰአት ትምህርቷን በመከታተል ላይ ትገኛለች። ወደፊትም ነርስ የመሆን ህልም አላት። በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነበር ሴራሊዮን ነብሰ ጡር ታዳጊዎች ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ የሚከለክለውን ሕግ ውድቅ ያደረገችው። የምዕራብ አፍሪካ አገራት ማህበር የሆነው ኢኮዋስ ፍርድ ቤት ሕጉ አግላይና ትምህርትን የማያበረታታ መሆኑን መግለጹን ተከትሎ ነው ሕጉ እንዲቀር የተደረገው። ሴራሊዮን ለረጅም ዓመታት ታዳጊ ሴቶች ቶሎ ቶሎ የሚያረግዙባት አገር ስትሆን በአውሮፓውያኑ 2013 በተሰራ ዳሰሳ መሰረት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ከሆኑት ዜጎቿ መካከል 35 በመቶ የሚሆኑት የልጅ እናቶች ናቸው። በአገሪቱ የኢቦላ ወረርሽኝ ተከስቶ በነበረበት ወቅት ደግሞ ቁጥሩ ወደ 65 በመቶ አድጎ ነበር። 2014 ላይ ወረርሽኙን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ስለነበር በርካታ ታዳጊዎች አርግዘዋል። ይህንን ተከትሎም ነው የሴራሊዮን መንግሥት ትምህርት ቤት የሚማሩ ታዳጊዎች ካረገዙ ትምህርታቸውን መቀጠል እንደማይችሉ ያስታወቀው። በወቅቱ መንግሥት ይህ ውሳኔ ታዳጊዎች መሰል ነገር ከመፈጸማቸው በፊት ቆም ብለው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል ብሎ ነበር። ሴራሊዮን ለረጅም ዓመታት ታዳጊ ሴቶች ቶሎ ቶሎ የሚያረግዙባት አገር ስትሆን በአውሮፓውያኑ 2013 በተሰራ ዳሰሳ መሰረት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ከሆኑት ዜጎቿ መካከል 35 በመቶ የሚሆኑት የልጅ እናቶች ናቸው 2015 ላይ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት በዚሁ ሕግ ምክንያት 3 ሺ የሚጠጉ የሴራሊዮን ታዳጊ ሴቶች ከትምህርታቸው እንዲሰናከሉ ተደርገዋል። እንደውም ቁጥሩ ከዚህ ከፍ ያለ እንደሆነ የሚከራከሩም አልጠፉም። ምንም እንኳን እርጉዝ ተማሪዎችና ወላድ እናቶች ከትምህርት ተቆራርጠው እንዳይቀሩ በሚል ተመሳሳይ የትምህርት ማዕከላት የተቋቋሙ ቢሆንም በሳምንት ሶስት ቀን ብቻ ነው ትምህርት የሚሰጥባቸው። በተጨማሪም የሚሰጡት የትምህርት አይነቶች አራት ብቻ ናቸው። ይህንን ተከትሎም ነው ኢኮዋስ 2019 ላይ ሕጉ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ማግለልን የሚያበረታታና የትምህርት ዕድልን የሚነጥቅ እንደሆነ የገለጸው። ሴራሊዮንም ሕጉን በቶሎ እንድትሽረው አዝዟል። በሴራሊዮን ሕጉ ተግባራዊ በተደረገበት ወቅት በርካታ ሴት ተማሪዎች ወደ ሁለተኛ ደረጃ እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለመግባት የሚሰጠውን ብሔራዊ ፈተና መውሰድ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል። ፈተናውን ላለፈ ሰው ትምህርቱን ባይቀጥል እንኳን ስራ ማግኘት ቀላል ነው። ''ታዳጊ ሴቶችን እምነት ገደል ከትተነዋል'' ይላሉ በሴራሊዮን በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ላይ የሚሰራው ድርጅት ውስጥ የሚሰሩት ፋትማታ ያምባሱ። ይሄው ድርጅት ከሌሎች ጋር በመተባባር ነው መንግሥትን ፍርድ ቤት የከሰሰው። ''በወቅቱ ሁሉም ሰው ኢቦላን ማጥፋትና መከላከል ላይ ነበር ትኩረቱ። በታዳጊ ሴቶች ላይ ይፈጸም የነበረውን ጥቃት ማንም ዞር ብሎ አላየውም። ነገር ግን አሁን ትምሀርት አግኝተናል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት እነዚህን ታዳጊዎች ግን ብቻቸውን አንደማንተዋቸው ቃል ገብተንላቸዋል'' በአሁኑ ሰአት በአገሪቱ ነገሮች የተለወጡ ይመስላሉ። መንግስትም ችግሩን በመረዳት የመፍትሄ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ባሳለፍነው ዓመት አስገድዶ መድፈር ብሔራው አስቸኳይ ጉዳይ መሆኑን እስከማወጅ ደርሰዋል። ፈጣን እርምጃም እንደሚወሰድ ቃል ገብተዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዴቪድ ሞይኒና ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ የሕጉን መሻር ሲያበስሩ ''ሁሉም ህጻናት ህልማቸውን የማሳካትና ዓለማቀፍ መብት የሆነው የመማር መብታቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መፈቀዱን አስታውቃለሁ'' ብለው ነበር። የዓለም ባንክ ታንዛኒያ ውስጥ በየዓመቱ ትምሀርታቸው ከሚያቋርጡ 60 ሺ ተማሪዎች መካከል ከአምስት ሺ በላይ የሚሆኑት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡት በእርግዝና ምክንያት ነው ብሏል ከዚህ ሕግ መሻር በኋላም 1 ሺ ሴት ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ፈተናውን ለመውሰድ ተቀምጠዋል። ነገር ግን ፋትማታ ያምባሱ እና ሌሎችም በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ ሰዎች እንደሚሉት ምንም እንኳን መንግሥት በጉዳዩ ላይ ማሻሻያዎችን እያደረገ ቢሆንም ዋናው መቀየር ያለበት ግን የማህበረሰቡ አስተሳሰብ ነው። አሁንም ድረስ ሴራሊዮን ውስጥ ያረገዙ ሴቶችን ከትምህርት ቤት ማባረር የተለመደ ነገር ነው። ሕጉ እንዲሻር ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ እንኳን በርካታ ቤተሰቦች እንዴት ልጆቻችንን ካረገዙ ታዳጊዎች ጋር አብረው እንዲማሩ እናደርጋለን? በማለት ተቃውመውት ነበር። 'ለልጆቻችን ጥሩ መልዕክት አያስተላልፍም' ነው የሚሉት ቤተሰቦች። የፋቱ ቤተሰቦች ልጃቸው ተመልሳ ትምህርት ቤት መግባት መቻሏ በጣም ያስደሰታቸው ሲሆን የመንግሥት ውሳኔ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አመለካከት እንዲቀይሩ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። ቤተሰቦቿ እንደሚሉት በጉዳዩ ላይ ማህበረሰቡ ውስጥ የተቀላቀለ አመለካከት ነው ያለው። ''አንዳንዶች ልጃችን ላይ የደረሰውን ጥቃት ለፖሊስ በማሳወቃችን እና ጉዳዩን ይፋ በማድረጋችን ደስተኞች ናቸው። ነገር ግን አንዳንዶቹ ልጃችሁን እንዴት ወደ ትምሀርት ቤት ትልካላችሁ? ይሉናል'' ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ፋቱ ደግሞ ትምሀርት ቤት መሄዷ ቢያስደስታትም ነገሮች ግን ቀላል እንዳልሆነ ትገልጻለች። ''ትምህርት ቤት ሄጄ የሚመች አቀማመጥ ማግኘት ከባድ ነው። ለረጅም ሰአት አንድ ቦታ ላይ መቀመጥም ቢሆን አልችልም። ስለዚህ ትምህርቴን በአግባቡ መከታተል አልችልም'' ትላለች። ''በተጨማሪም የትምህርት ቤት ጓደኞቼ አብረውኝ ለመጫወትም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ለማድረግ ፈቃደኞች አይደሉም። ምሳ እንኳን አብሮኝ የሚበላ ልጅ የለም'።' ነገር ግን ምንም ቢፈጠር ትምህርቷን ማቋረጥ እንደማትፈልግና እንደማታቋርጥ ለቢቢሲ ተናግራለች። ''አንድ ቀን ትምህርቴን ጨርሼ ነርስ መሆን እፈልጋለሁ። ትልቅ ሰው ስሆን ለሌሎች ሴቶች አርዓያ መሆን እፈልጋለሁ'' ፋቱ የምትማርበት ትምህርት ቤትም ቢሆን ነገሮች ቀላል እንዳልሆኑ ገልጿል። አንዳንድ ተማሪዎች ፋቱን እንዳገለሏትና አብረዋት መጫወት እንደማይፈልጉ አንድ አስተማሪ ገልጾ ነበር። በተጨማሪም አንዳንድ መምህራን ፋቱን በተለየ መልኩ ያይዋት ነበር። ከሶስት ዓመት በፊት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ያረገዙ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት መባረር አለባቸው ብለው ከተናገሩ በኋላ በአገሪቱ እየተበራከተ የመጣው የታዳጊዎች እርግዝና ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የውዝግብ ርዕስ ሆኖ ነበር። ፕሬዝዳንቱ አንድ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው "ካረገዛችሁ፤ አለቀላችሁ" በማለት ተማሪ ልጃገረዶችን ካስጠነቀቁ በኋላ ከፍተኛ ወቀሳና ትችት ቀርቦባቸው ነበር። በወቅቱ ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት፣ ያለውን የአገሪቱን ሕግ ጠቅሰው ነበር። እንደ አውሮፓዊያኑ በ2002 የጸደቀው ሕግ ተማሪ ልጃገረዶች አርግዘው ከተገኙ ከትምህርት ቤት ማባረርን ይፈቅዳል። የተባበሩት መንግስታት ባወጣው መረጃ መሰረት ታንዛኒያ ውስጥ በአውሮፓውያኑ 2016 እድሜያቸው ከ15 እስከ 19 ከሆኑ ታዳጊ ሴቶች መካከል ከአራቱ አንዷ አርግዛለች አልያም ልጅ ወልዳለች። በሌላ የመንግሥት መረጃ መሰረት ደግሞ በዚያው ዓመት በአገሪቱ ትዳር ከመሰረቱ ሴቶች መካከል 36 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነበር። የዓለም ባንክ ደግሞ ታንዛኒያ ውስጥ በየዓመቱ ትምሀርታቸው ከሚያቋርጡ 60 ሺ ተማሪዎች መካከል ከአምስት ሺ በላይ የሚሆኑት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡት በእርግዝና ምክንያት ነው መሆኑን ገልጿል።
news-48833050
https://www.bbc.com/amharic/news-48833050
ጄኔራል አብረሃ ወልደ ማርያም (ኳርተር) ማን ነበሩ?
መታመማቸው እምብዛምም ሳይሰማ ነው ሞታቸው የተሰማው፤ ከወደ ባንኮክ።
ምናልባትም አገሪቱ ሁለት ውድ ጄኔራሎቿን በአሰቃቂ መልኩ ያጣችበት ማግስት መሆኑ የጄኔራሉን የሞት ዜና ጎልቶ እንዳይወጣ አድርጎት ይሆን? እንጂማ የጄኔራል አብረሃ የትግል ታሪክ ደማቅም ዘለግ ያለም ነበር። የትግል ጓዶቻቸው እነ ጄ/ል ታደሰ ወረደና ጀኔራል ቢተው በላይ ለቢቢሲ የመሰከሩትም ይህንኑ ነው። ለመሆኑ ጄ/ል አብረሃ ለምን ኳርተር ተባሉ? •በሃየሎም ይምሉ የነበሩት ጄነራል ሰዓረ መኮንን ማን ናቸው? ጄኔራሉን የሚያውቁት ሰዎች የቅጽል ስማቸውን አመጣጥ እንዲህ ይተርካሉ። በአንድ ወቅት ደቡብ ትግራይ ዋጅራት አካባቢ 12 የሚሆኑ የሕወሓት ወታደሮች እጅግ ተራቡ። የሚላስ የሚቀመስ ጠፋ። ታጋይ አብረሃ ተረኛ የሌሊት ጠባቂ ነበር። ተጨነቀ። ሌሊቱ ከመጋመሱ በፊት ከየትም ተሯሩጠው ሦስት እንጀራ ከአንዲት እናት አገኘና ለታጋይ ጓዶች «ዛሬ እንጀራ ኳርተር ኳርተር ነው የሚደርሰን» አለ። ሩብ እንጀራዋን ለ12 ጓዶቹ አከፋፈለ። ለዚያች የረሀብ ምሽት መታሰቢያ ጓዶቹ «ኳርተር» አሉት። አንድ አራተኛ እንደማለት። ቅጽል ስሙ የትግል ስሙ ሆነና በዚያው ጸና። እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ድረስ ከዋና ስሙ በላይ ኳርተር የሚለው ስሙ ገነነ። •ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ በትግራይ ማዕከላዊ ዞን በእንዳባፃህማ ወረዳ እንዲጪዋ ቀበሌ ነሐሴ በ1953 ዓ.ም የተወለዱት ጀኔራል አብርሃም ይቺን ምድር ሲለዩ ዕድሜያቸው 58 ደርሶ ነበር። ከተራ ወታደርነት የጀመረው የትጥቅ ትግል ታሪካቸው እስከ ጦር አዛዥነት በኋላም እስከ የዘመቻ መምሪያ ኃላፊነት አድርሷቸዋል። ከደርግ ሥርዓት መወገድ በኋላ በመካከለኛና ከፍተኛ ኃላፊነቶች በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ያገለገሉት ጄኔራል አብረሃ በርዋንዳ የሰላም ማስከበር ተልእኮ የመጀመርያው የጉና ሻለቃን በምክትል አዛዥነት የመሩትም እርሳቸው ነበሩ። ጡረታ እስከሚወጡበት ቀን ድረስ በተለይም በቀደምው ጠቅላይ ሚኒስትር የመጨረሻ ወራት የኳርተር ስም በክፉም በበጎም ሲነሳ ቆይቷል። ጄኔራሉ በደቡብ ምሥራቅ እዝ ዋና አዛዥ በነበሩበት ወቅት ተፈጸሙ በሚባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እጃቸው ነበረበት ብለው የሚከሷቸው ጥቂት አይደሉም። የሂውማን ራይትስ ዎች የኢትዮ-ኤርትራ ተመራማሪ ፌሊክስ ሆርን ለቢቢሲ በሰጡት አጭር የድምጽ ማስታወሻ ስለ ጄኔራሉ ይህንን ብለዋል። «ጄ/ሉ በምሥራቅ እዝ አዛዥ ሳለ ሠራዊቱ በኦጋዴን ነጻ አውጪ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል። በዚያን ጊዜ በሠራዊቱ የጦር ወንጀሎች የሰብአዊ መብት ጅምላ ጥሰቶች ተፈጽመዋል። የጅምላ ግድያዎች ከመፈጸማቸውም በላይ ሴቶች ተደፍረዋል። በ2007/8 እና 9 ጄ/ሉ የሚመሩት ሠራዊቱ በዚህ ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ ካደረገ በኋላ በክልሉ ልዩ ኃይል ወደ ማደራጀት ነው የተገባው። አብዲ ኢሌ የክልሉ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ ልዩ ፖሊስም የተለያዩ ተመሳሳይ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጽም ነው የነበረው። ሂውማን ራይትስ ዎች በዚህ ረገድ በርካታ ሰነዶችን ሰንዷል። •ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ እኔም በቅርቡ አካባቢው በነበርኩ ጊዜ እዚያ የተፈጸሙ ወንጀሎችን በተመለከተ ተጠያቂነት እንዲኖር ሕዝቡ ጥያቄ ሲያነሳ ነበር። ጄ/ል አብረሃ በሚመሩት ሠራዊት ስለተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎች እንዴት ተጠያቂነት አይኖርም? እንዴትስ ምርመራ አይደረግም ሲሉ ነበር። ቢያንስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደረጃ ወንጀል ስለመፈጸሙ እንዴት አይገለጽም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ይህን ጉዳይ በስፋት አንስተውልኛል።" ባልደረባችን ግርማይ ገብሩ ያነጋገራቸው በጄኔራሉ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተገኝቶ ያነጋገራቸው ነባር ታጋይ ጄኔራል ታደሰ ወረደ በበኩላቸው ኳርተር በክልሉ ሰላምንና መረጋጋትን ያመጣ ቆፍጣና ወታደር ነበር ይላሉ። «ጄኔራል አብረሃ የተሰጠውን ኃላፊነት ቆንጥጦ የሚሰራ፣ በእልህ የሚፈጽም ሰው ነበር። እሱ ግዳጅ ተሰጥቶት ያልፈጸመው ነገር የለም። የምሥራቅ እዝ አዛዥ ሳለ መደበኛ ያልሆኑ ዊጊያዎች ነበር የሚደረጉት ኦብነግንና አልሸባብ ጋር ነበር የሚታገለው። በተለይም በጸረ ሽምቅ ዉጊያዎች ክልሉን በማጽዳት ልማትንና መረጋጋትን ለማምጣት በኩል ትልቅ ሥራ ሠርቷል። አካባቢውን በጥሩ ሁኔታ ያረጋጋ እንደነበር ነው የማውቀው። ኳርተር ንቁ፣ ጥንቁቅና ተጠራጣሪ ሰው ነበር።» ትምህርታቸውን ገታ አድርገው ወደ ትግል የገቡት ጄኔራል አብረሃ ከድል በኋላ ያቋረጡትን ትምህርት ቀጥለውበታል። በአዲስ አበባ ግንቦት 20 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማሩ በኋላ በአስተዳደር የመጀመርያ ዲግሪ በአመራር ሳይንስ ደግሞ ከግሪንዊች ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዲግሪን አግኝተዋል። አብረሃ ወ/ማርያም ኳርተር የሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ ያገኙት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጊዜ ሲሆን በጡረታ የተሰናበቱት ደግሞ የጠ/ሚ ዐብይ አህመድን መምጣት ተከትሎ ነው። •ጄኔራል አደም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ ጄኔራል አብረሃ ለሁለት ሳምንት በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ተኝተው ታከሙ፤ አልተሻላቸውም። ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ታይላንድ አቀኑ። ሰኔ 21፣ 2011 የሞታቸው ዜና ተሰማ። የጄኔራሉ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመቀሌ ካቴድራል ቅዱስ ገብርኤል ከጄራናል ሰዓረ መኮንንና ጄኔራል ገዛኢ አበራ ጎን ተቀብረዋል። ጄኔራል አብረሃ የሁለት ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ። ዛሬ ለክብራቸው 15 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።
56841527
https://www.bbc.com/amharic/56841527
ምርጫ 2013፡ የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን መክሰሱን አስታወቀ
ከሐረሪ ክልል ውጭ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጅ አባላት በሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አባላት ምርጫ ላይ መሳተፍ አይችሉም የሚለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱን የሐረሪ ክልል አስታወቀ።
የሐረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊና የፖለቲካና የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልሃኪም ኡመር ለቢቢሲ እንደገለፁት ቦርዱ "ሕጋዊ አግባብን አልተከተለም፤ የሕግ ጥሰት ፈፅሟል" በማለት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት መክሰሳቸውን አስታውቀዋል። የሐረሪ ክልል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ከመውሰዱ በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ለምርጫ ቦርድ የላካችሁት ሰነድ ማህተም የሌለውና ፍትሃዊ ባለመሆኑ ውድቅ ተደርጓል" በሚል አቤቱታ ማቅረባቸውን ይናገራሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰነዶቹን ማህተም አድርጎ ለምርጫ ቦርድ ቢልክም ውሳኔው ባለመቀልበሱ ወደ ፍርድ ቤት ማምራታቸውን ይናገራሉ። የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት፣ የሐረሪ ሕዝባዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትና የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የሐረሪ ሕዝብ የክልሉ ምክር ቤት አካል ለሆነው ለሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ እንዲመርጡ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄያቸውን አቅርበው ነበር። ጥያቄው መነሻውን ያደረገው መጋቢት 6/1987 የሽግግር መንግሥቱ የተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀውን ውሳኔ ተንተርሶ መሆኑንም ከምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ከዚህም በተጨማሪ የሐረሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 50 ቁጥር 2 እንደሚያትተው የክልሉ ምክር ቤት አባላት የሆኑትና 14 አባላት ያሉት "የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አባላት በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎችና ከተሞች ከሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ አባላት ይመረጣል" የሚለውን መሰረት ያደረገ እንደሆነ አቶ አብዱልሃኪም ያስረዳሉ። ምርጫ ቦርድም ክልሉ ያቀረባቸውንና በ1987 የሽግግር መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት የወሰናቸውን ውሳኔዎችና ሰነዶቹን ከሕገ መንግሥት አንፃር እንደመረመረ አስታውቆ፤ ከክልሉ ውጭ ያሉ የሐረሪ ተወላጆች በመጪው ምርጫ የመሳተፋቸውን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉን ሚያዝያ 1/2013 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ቦርዱ ለዚህም ሕገ መንግሥቱን የጠቀሰ ሲሆን "ቦርዱ በሕገ መንግሥቱ መሰረት በአንድ ክልል የመንግሥት መዋቀር ውስጥ የሚገኙ የምክር ቤት አባላት መመረጥ የሚኖርባቸው በክልሉ ድምፅ መስጠት በሚችሉ ነዋሪዎች ነው" በማለት ገልጿል። ጨምሮም "ከዚህ ውጭ ሕገ መንግሥቱ አንድ ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ ብሔረሰብ ለክልል ምክር ቤቶች ሲያስመርጥ ከክልሉ ውጭ ያሉ የብሔረሰብ አባላት እንዲመርጡ የደነገገው እንዲሁም ለዚህ ብሔረሰብ አባላት ለብቻው የተለየ አሰራር መተግበር የሚያስችል በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለ ድንጋጌ በምርመራው ቦርዱ ያገኘው ነገር የለም" ብሏል። የሐረሪ ክልል ብሔራዊ ጉባኤ ሚያዝያ 3/2013 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ እንደማይቀበል አስታውቆ ነበር። "ምርጫ ቦርድ ይህንን የመወሰን ስልጣን የለውም" የሚሉት አቶ አብዱልሃኪም እንደ ምክንያትነት የሚያቀርቡትም የሽግግር መንግሥቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወሰነውን ውሳኔና የክልሉን ሕገ መንግሥት በመጥቀስ ሲሆን "በሕግ የተደነገገ ነው" ይላሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1987 ውሳኔ ባልተሻረበት ሁኔታ የክልሉ ሕገ መንግሥት በግልፅ ባስቀመጠበት ሁኔታ "እነዚህን ሕጎች መፃረሩ ከአንድ ትልቅ ተቋም የሚጠበቅ አይደለም" ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫ ቦርዱ የሽግግር መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ከክልሉ ውጭ ነዋሪ በሆኑ የብሔረሰቡ አባላት ይመረጣል የሚለውን ውሳኔ የሚደግፍ ሕገ መንግሥታዊ አንቀፅ አለመጠቀሱን ምርጫ ቦርድ ገልጿል። ይህንን በተመለከተም አቶ አብዱልሃኪም እንደሚሉት ምርጫ ቦርድ የአገሪቱንና የክልሎችን ሕገ መንግሥት መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚሰራ ጠቅሰው፤ አንዳንድ የፌደራል ሕገ መንግሥት ላይ ያልተጠቀሱ ጉዳዮች በክልል ሕገ መንግሥቶች ላይ በዝርዝር ሊቀመጡም እንደሚችሉ ይናገራሉ። እንደ ምሳሌነትም የደቡብ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤትን ይጠቅሳሉ። የብሔረሰቦች ምክር ቤት በፌደራል ሕገ መንግሥት ባይቀመጥም በክልሉ ሕገ መንግሥት የተቀመጠና ምርጫ ቦርድም ይህንኑ መነሻ አድርጎ ነው ምርጫውን እያስፈፀመ ነው ያለው ይላሉ። ቦርዱ የክልሎችን ሕገ መንግሥቶች ባከበረ መልኩ ነው ሲሰራ የነበረው። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛውም የአገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ክልሎችን (ጣቢያዎችን) ሲያቋቁም መነሻው የፌደራል እንዲሁም የክልሉ ሕገ መንግሥት እንደሆነ ያወሳሉ። ምርጫ ቦርድ ከዚህም በተጨማሪ መጋቢት 6/1987 የሽግግር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 102ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ የምክር ቤቱ ማህተም ያረፈበት ስላልሆነ ውሳኔው አግባብ አለመሆኑ አመልካች ነው፤ እንዲሁም የሰነዱን ተቀባይነት ችግር ላይ ጥሎታል ብሏል። ሰነዱ ማህተም የለውም ወይ? የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ የቀረበላቸው አቶ አብዱልሃኪም በበኩላቸው ለምርጫ ቦርድ ስለቀረቡ ሰነዶች ምላሽ አላቸው። ስድስት ገፆች ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር የተያያዘ ሲሆን መሸኛ ደብዳቤው ላይ ቀን፣ ቁጥርና ማህተም አለው። ከዚህም በተጨማሪ በጊዜው የነበረው ኮሚቴ ያቀረበው ሪፖርት 17 ገጽም ተያይዟል። የተያያዙት ሰነዶች ላይ ምንም አይነት ማህተም እንደሌለው የሚናገሩት አቶ አብዱልሃኪም "በዚህኛው ውሳኔ ብቻ የተፈጠረ ነው? ወይስ ከዚህም በፊት የነበሩ ውሳኔዎች ተመሳሳይ ሂደት ነው ያላቸው? አሰራሩን መፈተሽ ያለበት ምርጫ ቦርድ ነው" ይላሉ። እንደ አቶ አብዱልሃኪም ምርጫ ቦርድ ሰነዶቹ ማህተም የላቸውም ከተባለ ውሳኔውን ከማሳለፉ በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት አቅርቦ ጠይቆ፣ ፈትሾና መርምሮ በዚያ መሰረት መወሰን ይገባው ነበር ይላሉ። "በዚያ መነሻነት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ መሆን አለመሆኑን ሲያረጋግጥላቸው ምላሹን ከሰሙ በኋላ ውሳኔ መወሰን በተገባቸው ነበር። ተቋማዊ አሰራር ያልተከተለ ነው" ይላሉ። የሐረሪ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰነዶቹ ተቀባይነት እንደሌላቸው ጠቅሶ አቤቱታ ማስገባቱን ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በበኩሉ የ1987 ሰነዶችን መነሻ በማድረግ የራሱንም ውሳኔ ጨምሮ ክልሉ ያቀረበለትን ደብዳቤ ጨምሮ ወደ 39 ገጽ በራሱ ማህተም ለምርጫ ቦርድ መላኩንም ይናገራሉ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ "የወሰንነውን ውሳኔ መልሰን የምናይበት አግባብ ስለማይኖር ሌላ ውሳኔ የሚሰጥ አካል ውሳኔ የሚሰጥበት መንፈስ ያለው አይነት ምላሽ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ልኳል" ይላሉ። በሕዝብ ተወካዮች በኩል ያለው ጉዳይ በራሱ እየሄደ ቢሆንም በፍርድ ቤትም በኩል እንዲወሰን በመሻት ክልሉ መክሰሱን ይናገራሉ። በሌላ በኩል አቶ አብዱልሃኪም ምርጫ ቦርድ ባለፉት አምስት ብሔራዊ ምርጫዎች ይጠቀምበት የነበረውን መመሪያ "በዚህ ውሳኔ እውቅናን ነፍጓል" ቢሉም ቦርዱ በበኩሉ መመሪያውን ከጽህፈት ቤቱ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል። ዝርዝር መመሪያው የ1987ቱን የተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት ያደረገና የባለፉትንም አምስት ምርጫዎች በዚሁ መልኩ ሲያስፈጽም የነበረ መሆኑ ተጠቅሷል። አቶ አብዱልሃኪም በዚህ አባባል አይስማሙም "ሥራ ላይ ያሉት መመሪያዎች የእኔ አይደሉም፤ አላውቃቸውም ማለቱ ትክክል አይደለም" ይላሉ። ነገር ግን ቦርዱ በፃፈው ደብዳቤ እንደጠቀሰው ምንም እንኳን ለሐረሪ ጉባኤ የሚመረጡ ተወካዮች ከክልሉ ውጭ ባሉ የብሔረሰብ አባላት ምርጫ ቦርድ ሲያስመርጥ ቆይቶም ከሆነ ሕገ መንግሥታዊና የምርጫ ሕጉ መሰረት የሌላቸውን አሰራሮች እንደማይከተል አስታውቋል። ቦርዱም በምርጫ ማሻሻያው እንዲህ አይነት ልምዶች እንዲቀሩ እየሰራ ነው ብሏል። ምንም እንኳን ላለፉት አስርት ዓመታት የተተገበረ ጉዳይ ነው ብሎ ቦርዱ ቢወስን "ሌሎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ብሔረሰቦች ከክልላቸው ውጭ ያሉ አባሎቻቸው በምርጫው እንዲሳተፉ ቢጠይቁ ቦርዱ ልፈፅም አልችልም ቢል የቦርዱን በፍትሐዊነት እና በገለልተኛነት ምርጫን የማስተዳደሩ ጉዳይ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል" ይላል። አቶ አብዱልሃኪም በበኩላቸው "ባለው ነገር ላይ መጨመር ነው እንጂ ሌሎች አናሳ ብሔሮችም እንዲህ አይነት የመብት ጥያቄ ቢጠይቁኝ መመለስ ስለማልችል የናንተንም በዚህ ወቅት ማስተናገድ አልችልም የሚለው ትክክል አይደለም" ይላሉ። ኢትዮጵያም ውስጥ የመከላከያ ሰራዊት፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየአካባቢያቸው የሚመርጡበት አሰራር እንዳለና በሌሎች አገራትም እንዲሁ በየኤምባሲዎቻቸው የሚመርጡበት ሁኔታ ልምድ መኖሩን ጠቅሰው የ "ሃረር የተለየ እንዳዳልሆነ" ይናገራሉ። "አገራችን ላይ ሕጉ አለ፤ ይሄንንም በተመለከተ ምርጫ ቦርድ መመሪያ ያወጣል የሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ አለ፤ የምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅም ላይ አለ" ይላሉ አቶ አብዱልሃኪም። "ያንን ከመተግበር አንፃር የኢኮኖሚ አቅማችንና የእድገታችን ደረጃ ገና ስለሆነ ይሄ የመተግበርና ያለ መተግበር ጉዳይ ነው" ሲሉ ያክላሉ። የሐረሪ ሕዝብ ክልል ምክር ቤት ከሁለት ጉባኤዎች የተዋቀረ ሲሆን እነዚህም የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤና የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ናቸው። የሕዝብ ተወካዮች ጉባኤ 22 አባላት ሲኖሩት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ደግሞ 14 የሐረሪ ብሔረሰብ አባላትን የያዘ ነው። ምርጫ ቦርዱ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ የሐረሪ ተወላጆች በጉባኤው ምርጫ መሳተፍ አይችልም የሚል ውሳኔን ቢያስተላልፍም የሐረሪ ጉባኤ 14 መቀመጫ በሐረሪ ብሔረሰብ አባላት የመያዙን ሁኔታ አይቀይረውም። ጉባኤው ከሐረሪዎች ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ በተያያዘ ማንነትና ህልውናቸው እንዲቀጥል ከማድረግ ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን የሚያስተላልፍና በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው የሚኖሩ የሐረሪ ተወላጆችን የሚያስተሳስር እንደሆነ አቶ አብዱልሃኪም ይናገራሉ።
news-42266025
https://www.bbc.com/amharic/news-42266025
ኦዶ ሻኪሶ-ወርቅ 'መርዝ' የሆነባት ምድር
ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል።
ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት አድርጎባቸዋል። የእሳቸውን እና የልጆቻቸውን ጤንነት ይከታተሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእሳቸው አጥንት ህመምም ሆነ የልጃቸው እግር አጥንት መልፈስፈስ ምክንያቱ ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወ/ሮ ሑቴ የሚኖሩበት ዲባ በቴ ቀበሌ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ የሚገኝበት ነው። "ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ። ጭንቅላታቸው መጠኑ በጣም ያነሰ ነው። እጅና አይናቸውም ተጎድቶ ይወለዳሉ። ሰው ታሞ ወደ ሐኪም ቤት ሲሄድ ከ 'ነርቭ' ጋር የተያያዘ ችግር ነው ይባላል።" በማለት የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ ዱቤ ጋሸራ ሚጁ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚሁ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት እኚህ አዛውንት "ድሮ ይህንን የሚመስል ችግር አልነበረም"ይላሉ። "መንግሥት የወጣቱን ቅሬታ ከመስማት ውጭ ምንም የለወጠው ነገር የለም።" ዓይናቸው ከማምረቻው ውስጥ በሚወጣ ኬሚካል መጎዳቱን እንዲሁም በአግባቡ ቆመው መሄድ እንደሚያቅታቸው ነግረውናል። በተጨማሪም ከዚሁ ችግር የተነሳ በከብቶች እና በዱር እንስሳት እየደረሰ ያለው እልቂት ለትልቅ ችግር አጋልጦናል ይላሉ። 'ሳናይድ' እና የአካል ጉዳተኝነት የሚድሮክ ለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ ወርቅና ነሐስ በሚያመርትበት ወቅት ወርቁን ለማፅዳት የሚጠቀምበት ኬሚካል 'ሳናይድ' ይባላል። ይህ ኬሚካል ራስ ምታት፣የልብ፣ የአእምሮ እና የነርቭ ህመሞች እንደሚያስከትል የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጦና ዋሬ ነግረውናል። ከዚህም ባሻገር የሰው አጥንት ለማጠንከር የሚረዱ እንደ ብረት(አይረን) ያሉ ንጥረ ነገሮች ከሰው እና ከእንስሳት አካል ውስጥ መጠኑን ይቀንሳል። ይህም ለአጥንት መሳሳት እና መሰባበር እንደሚያጋልጥ አቶ ጦና ዋሬ ያስረዳሉ። የወርቅ ማምረቻው የሚገኝበት ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥም የአካል ጉዳተኝነት ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው። የቢቢሲ ሪፖርተር በአካል በቀበሌው ተገኝቶ አንድ ኪሎ ሜትር ባልሞላ መንደር ውስጥ ሶስት የአካል ጉዳት ያለባቸው ህፃናትን አይቷል። በህፃናት ላይ የሚደርሰው የአካል ጉዳት በቀበሌው ውስጥ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ነዋሪዎች ወልደው ለመሳም እየተሳቀቁ እንደሆነ ይናገራሉ። ወ/ሮ ደምበሊ ሔጦ የአካል ጉዳት ያለባት ህፃን አላቸው፤ "ልጆቼ በታመሙ ቁጥር ስጋት ያድርብኛል። ሌላ ተጨማሪ ልጅ ለመውለድ እንደዚሁ ልጅ ይሆንብኝ ይሆን ስል እሰጋለሁ" ይላሉ። በተጨማሪም ነፍሰጡር ሴቶች ልጃቸውን ወልደው ከአካል ጉዳት ነፃ መሆኑን እስኪያረጋግጡ ድረስ ማርገዛቸውን እንደሚደብቁ፣ የአካል ጉዳት ያለበትን ህፃን የወለዱ እናቶችም ከሰው አይን ከልለው በቤት ውስጥ ደብቀው እንደሚያሳድጓቸውም የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። በተጨማሪም የሳይናይድ ኬሚካል የተቀላቀለበት ወራጅ ውሃ የሚጠጡ እንስሳት ወዲያውኑ እንደሚሞቱ፣ የተበከለ አየር ውስጥ የሚቆዩት ደግሞ ከወደቁ በኋላ መነሳት እንደማይችሉ፣ አጥንታቸውም በቀላሉ እንደሚሰበር የአካባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ። "ድጋሚ ተመሳሳይ ችግር ይደርስብኝ ይሆን ብዬ እሰጋለሁ።" የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የፋብሪካው የጥበቃ ሰራተኞች በህብረተሰቡ ላይ ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደሚያደርሱ ቅሬታዎች ይሰማሉ። ይህንን ቅሬታ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የወረዳው አስተዳደር ሰራተኞችም ይጋሩታል። ለፋብሪካው ከሚደረገው ከፍተኛ ጥበቃ የተነሳ መንግስት በሰጣቸው ኃላፊነት ተጠቅመው በፋብሪካው ውስጥ ገብተው የቁጥጥር እና ክትትል ስራ ማድረግ እንዳልቻሉ የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ቦሬ ጦና ይናገራሉ። ሰራተኞችንም በሚቀጥሩበት ወቅት ህጉ በሚያዘው መሰረት እንደማያሳትፏቸወው ከድርጅቱ የሚያገኙት ምላሽም "እኛ በእናንተ ሳእሆን በፌደራል መንግስት ነው የምንመራው" የሚል እንደሆነም ይናገራሉ። የስራ እድል ማግኘትን ጨምሮ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ የማእድን አምራች ድርጅቶች ጥቅም እያገኘን አይደለም፤ ከዚህም አልፎ ችግር እየደረሰብን ነው በማለት የወረዳው ነዋሪዎች በተለያየ ጊዜ ሰልፍ ወጥተዋል። ምላሽ የአካባቢውን ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ቅሬታ መልስ ለማግኘት ወደ ማእድን ማምረቻው በሄድንበት ወቅት የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት መልስ የሚሰጡን የስራ ኃላፊዎች እንደሌሉ ነግረውናል። ነገር ግን ይህ ፅሁፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣ በኋላ ሚድሮክ ለቢቢሲ በፃፈው ደብዳቤ ጉዳቱን አላደረስኩም ብሏል። የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር የለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ሳናይድ የተባለው ኬሚካል በሕዝብና በአካባቢ ላይ ጉዳት አለማድረሱን በደብዳቤው ገልጿል። በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን አዶ ሻኪሶ ወርቅ በማምረት የተሰማራው ይህ ኩባንያ አካባቢውን በጠበቀና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እየሰሩ መሆኑንም ጭምር ገልፀዋል። "በአካባቢ ላይም ሆነ በሰዎች ላይ ከኬሚካል ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ችግር የለም" ብሏል። ሚድሮክ በአካባቢው የተባሉት ችግሮች ተከስተው ቢሆን ኖሮ የሚያውቅበትም ዕድል እንደነበር ገልፆ የአካባቢን ጉዳዮች ለመከታተል ራሱን የቻለ ክፍል እንዳቋቋሙ ጠቁሟል። ከዚህም በተጨማሪ በአዶ ሻኪሶ አካባቢ በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ የተሰማራው ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ኩባንያዎች በአካባቢው በመኖራቸው ከኬሚካል ጋር ተያይዞ ደረሰ የተባለው ጉዳት በእርግጥ ከሚድሮክ ጋር ብቻ የተያያዘ ስለመሆኑ ማረጋጋጫ የለም ብለዋል። ሚድሮክ በአካባቢው ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ገልጾ፤ ትምህርትቤቶች፣የጤና ኬላዎች፣ የመንገድ ግንባታ ላይ በመሳተፍ ለብዙ ሰዎችም የስራ ዕድል እንደፈጠሩ አስታውቋል። በማእድን ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የአካባቢ እና የማህበረሰብ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት ወ/ሮ እናት ፋንታ ግን "እስከ መጋቢት 2009 ዓ.ም ባደረግነው ክትትልና ቁጥጥር መሰረት በኬሚካል የደረሰ ጉዳት አላየንም፤ ከማህበረሰቡም ሆነ ከመንግስት አካል የደረሰንም ቅሬታ የለም" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የማዕድን፣ነዳጅ እና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ግን በሚድሮክ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችችን ለመፍታት ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር መስራት አለበት። ኬሚካል እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ እየደረሰ ያለው ጉዳትም በ አስቸኳይ በገለልተኛ አካል መጣራት አለበት እንዳሉ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል። ይሁን እንጂ ጥያቄው የወርቅ ምርቱ ተጠቃሚነት ሳይሆን በህይወት የመቆየት ስጋት የሆነባቸው የዲባ ባቴ ነዋሪዎች "ከመንግስት በኩል መፍትሄ እንፈልጋለን" እያሉ ነው። የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር በ1989 ዓ.ም የለገደንቢን የወርቅ ማእድን ከመንግስት እጅ በ172 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለ20 ዓመታት በሊዝ ነበር የተረከበው። ድርጅቱ በ2014 እኤአ በአለም ባንክ በተዘጋጀው ፎረም ላይ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የሚድሮክ ለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ እኤአ ከ 1997-2014 ድረስ ባሉት 16 አመታት 52 0444.71 ኪሎ ግራም ወርቅ እንዲሁም 14 670.6 የብር ማእድን አምርቶ 17.24 ቢሊዮን ብር እንደሸጠ ያሳያል። ድርጅቱ ለ20 ዓመታት የተፈራረመው ውል አሁን በያዝነው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ የሚጠናቀቅ ሲሆን ስምምነቱ እንዲታደስለት አመልክቷል።
50709583
https://www.bbc.com/amharic/50709583
ስድስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በጣና እምቦጭ ዙሪያ
ስለእምቦጭ አረምና ጣና ሐይቅ ከሚሰጡ ምላሾች ይልቅ የሚነሱት ጥያቄዎች ይበልጣሉ። አረሙን ለመከላከል እስካሁን የተደረጉ ጥረቶች የሚጠበቀውን ውጤት እያስገኙ አይደለም። ከጥረቱ በተቃራኒ አረሙ በከፍተኛ ፍጥነት ጣና ሐይቅን ብቻ ሳይሆን አባይንም እያጠቃ ነው። ይህንን ከግምት በማስገባት የአማራ ክልል የጣና እና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃ እና ልማት ኤጀንሲን በቅርቡ አቋቁሟል። በጉዳዩ ላይ ዋና ዋና የሚባሉ ጉዳዮች እንደሚከተለው ተዳስሰዋል።
"አንድም በዓይን የሚታይ አረም ወደ ሚቀጥለው ዓመት እንዳይተላለፍ እናደርጋለን" ዶ/ር አያሌው ወንዴ ምን ያህል ጉዳት አደረሰ? ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ በብዙሃን መገናኛ እና ማህበራዊ ድር አምባው መወያያ ርዕስ ሆነው ከዘለቁት ጉዳዮች መካከል አንዱ በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተው እምቦጭ ነው። ኑሯቸውን በሐይቁ ላይ የመሠረቱት ግን ነጋ ጠባ የሚያስቡት ስለሐይቁ እና ስለ ሐይቁ ብቻ ነው። አረሙ ጣና ሐይቅ ላይ ከመታየቱ በፊት በ2004 ዓ.ም መገጭ በሚባል ወንዝ ላይ ቀድሞ መከሰቱን የሚናገሩት ዶ/ር አያሌው ወንዴ የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው። እንዴት እንደተከሰተ "ግምት" ከማስቀመጥ ውጭ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ የለም ይላሉ። "ሐይቁ በዓሳ፣ በሩዝ እና በመኖ ምርታማ የሚባለው አካባቢ ነው በአረሙ ተያዘው" ይላሉ። • የጣና ዕጣ ፈንታ ለገዳማቱ መነኮሳት አሳሳቢ ሆኗል • የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል • ጣና ሐይቅ የተጋረጡበት ፈተናዎች አረሙ ከመስፋፋቱም ጋር ተያይዞ ጀልባዎች እንዳይንቀሳቀሱ እንቅፋት ከመሆን ባለፈ የዓሳ ምርቱም በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ምክንያት ሆኗል። ከዚህ የከፋው ግን በአካባቢው አርሶ አደሮች እና ብዝሃ-ህይወቱ ላይ የሚያደርሰው ችግር ነው። ለእርሻ ይውል የነበረውን ቦታ ከመሸፈን ጀምሮ፤ እንስሳት ሲበሉት ጤናቸው ከመታወኩም በላይ ወተት እና ስጋቸው ያለውን ጣዕም ያጣል ሲሉ የአካባቢው አርሶ አደሮች ይገልጻሉ። ከ20 በላይ ገዳማትን የያዘው ጣና ሐይቅ ከሐይማኖታዊ ሃብቱ በተጨማሪ የቱሪስቶች መዳረሻም ጭምር ነው። ከሁለት ዓመት በፊት የቢቢሲ ባልደረቦች ከገዳማቱ አንዱ በሆነው እንጦስ ኢየሱስ ገዳም በተገኙበት ወቅት እማሆይ ወለተማርያምን አግኝተው አናግረው ነበር። "ጣና የገዳሙ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱም ሃብት ነው" የሚሉት እማሆይ ወለተማርያም አረሙ ገዳሙ አካባቢ አለ መባሉ ጭንቀት ፈጥሮባቸዋል። "አረሙ ሐይቁን ሊያደርቅብን ይችላል የሚል ስጋት አድሮብናል" ይላሉ። በሐይቁ ዙሪያ ያለው የቆሻሻ አወጋገድ እንዲሁም የሌሎች መጤ አረሞች መስፋፋትም ችግሩን አባብሰውታል። እምቦጭ ምን ያህል እየተስፋፋ ነው? ከሁለት ሺህ እስከ 50 ሺህ ሔክታር ድረስ የሚሆነው የሐይቁ ክፍል በእምቦጭ ተይዟል የሚሉ መረጃዎች በተለያየ ጊዜ ይወጣሉ። ሐይቁ ላይ ካለፉት ዓመታት ጀምሮ የእምቦጭ አረም በፍጥነት እየተሰራጨ ይገኛል። ከ60 በላይ ቀበሌዎች በሐይቁ ላይ ተመርኩዘው ህይወታቸውን ይመራሉ። እንደ ዶ/ር አያሌው ከሆነ "እምቦጭ 27 ቀበሌዎችን አዳርሷል -ገልዳ ወንዝ ከሚባለው ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ እስከ ደልጊ ድረስ።" • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . "ጉዳቱ እየደረሰበት ያለው በዳርቻው አካባቢ ነው። የሐይቁ አጠቃላይ ዙሪያ ብንወስድ 385 ኪሎ ሜትር ነው። ከዚህ ውስጥ በየጊዜው በመስፋፋት እምቦጩ 27 ቀበሌ ደርሷል። ይህም ወደ 190 ኪሎ ሜትር የሐይቁ ዳርቻ ማለት ነው። ይኼውም በብዛት በመካካለኛ እና በአነስተኛ ሁኔታ የተያዘ ነው።" "በሳይንሱ የሐይቅ ዳርቻ ተጎዳ ማለት ዋናው ትንፋሹ ተጎዳ ማለት ነው። ውሃ ብቻ ነው ያለው ማለት ነው። ውሃ ደግሞ ነገ ይደርቃል" ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ከሁለት ሺህ እስከ 50 ሺህ ሔክታር ድረስ የሚሆነው የሐይቁ ክፍል በእምቦጭ ተይዟል የአየር ንብረት ለውጥ እና በእምቦጭ አረም ላይ ያለው ዕውቀት አነስተኛ መሆኑ ከእምቦጭ በተጨማሪ ሌሎች አረሞች እንዲስፋፉ በር ከፍቷል። እምቦጭ ብቻ ነው ጣናን የሚያሰጋው? የእምቦጭ ጉዳይ መፍትሔ ሳይሰጠው ሌሎች መጤ አረሞችም ጣና ሐይቅ ላይ ስጋት ደቅነዋል። ዶ/ር አያሌው ብዙም ያልተወራላቸው እንደአዞላ እና ኢፖማ ዓይነት አረሞች መከሰታቸው ሌላ የስጋት ምንጭ ሆኖባቸዋል። "እምቦጭ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አረሞችም ስጋት ፈጥረዋል። ለምሳሌ ለአፈር እና ለውሃ ጥበቃ ተብሎ የተተከሉ መጤ ዝርያዎች አሉ። የሁሉም የወንዞች መግቢያ በእነሱ ተሸፍኗል። ጣና ላይ ዋናው አረም እምቦጭ ቢሆንም ሌሎች በርካታ ችግሮች አሉ። • መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ "የአረም ብቻ ሳይሆን የብክለት ችግርም አለ። የባህር ዳር እና የጎንደር ከተማ ቆሻሻ ወደ ሐይቁ ይገባል። ይሄን ተሸክሞ አረሞቹን መዋጋት ተረት ይሆናል" ይላሉ። ሐይቁ የደለል ስጋትም ተጋርጦበታል። በዚህ ምክንያት ሐይቁ ጥልቀት ከፍተኛ ፍጥነት መቀነሱ ይገለጻል። የችግሮቹ መደራረብ እና አረሙ የጋረጠው ስጋት ለጣና ሐይቅ መፍትሔ ማበጀት ጊዜ የሚሰጠው እንዳይሆን አድርጎታል። "በጥንዚዛዎች እምቦጭን ማጥፋት የብዙ ሃገር ተሞክሮ ነው" ምን አማራጭ ማጥፊያ ዘዴዎች አሉ? ችግሩን ለመቅረፍ የሠው ወይም የማሽን ጉልበት፣ ኬሚካል ወይንም ደግሞ እምቦጭን ሊያጠፉ የሚችሉ ሌሎች እጽዋትን መጠቀም የተለመዱ ዘዴዎች ናቸው። የተለያዩ ሃገራት ዘዴዎቹን ለየብቻ ወይንም በጋራ እንደችግሩ ሁኔታ ይጠቀሙባቸዋል። ዘዴዎቹን በመጠቀም ለመከላከል በተለያዩ ግለሰቦች እና በተቋማት ደረጃ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው በነበሩ በጢንዚዛዎች እምቦጭን ማጥፋት የብዙ ሃገር ተሞክሮ ነው ይላሉ። "ጢንዚዛዎቹ እምቦጭን ብቻ ነው የሚመገቡት። ሥራ የጀመርነው ከሶስት ዓመት በፊት ጀምሮ ነው። ቪክቶሪያ ሃይቅ ላይ ውጤታማ ሆኗል። ሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች ላይ ውጤታማ ናቸው። ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የማያደርሱ ምንም አይነት ወጪም የማይጠይቁ ናቸው" ይላሉ። • ባህር ዳር፡ ዘመቻ 90 ደቂቃ • "ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው ቀን አስገድዶ ደፈረኝ" አቶ ሙላት ባሳዝነው የሙላት ኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ ድርጅታቸው ማጨድ እና አረሙን ማጓጓዝ የሚችል ማሽን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሠርቷል። "እምቦጭ መጣ ሲባል ያለንን ለማዋጣት ተነስተን የራሳችንን ሞዴል ሠርተናል። እምቦጩን የማስወገድ አቅሙ ካቀድነው በላይ ነው። ከውጭ ከመጣው የተሻለ ውጤታማ ማሽን ሠርተናል" ሲሉ ስለማሽናቸው ይገልጻሉ። "በምርምር እምቦጭን በ24 ሰዓት የሚያደርቅ" ፈሳሽ ማዘጋጀታቸውን የሚናገሩት መሪ ጌታ በላይ አዳሙ የመድሃኒት እና ሽቶ ዕጽዋት ላይ ተማራማሪ ናቸው። "የኔ ምርምር ፈሳሽ ነው። እምቦጩ ላይ ይረጫል። አረሙ በ24 ሰዓት ይደርቃል። ተፈጥሮአዊ በመሆኑ በሃይቁ ብዝሃ ህይወት ላይ ጉዳት አያመጣም" ይላሉ። ሌሎችም እምቦጭን ለማጥፋት የሚረዳ ዘዴ እንዳላቸው ወይንም እምቦጭን ተጠቅመው ጠቃሚ ምርት ለመሥራት የሚያስችል ብቃት እንዳላቸው ይገልጻሉ። ይህ ሁሉ ሆኖም ግን አረሙን ማጥፋት አልተቻለም። አረሙን ለምን ማጥፋት አልተቻለም? ህብረተሰቡ በጉልበት እና በገንዘብ የሚያደርገው ድጋፍ ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ አረሙን በጉልበትም ሆነ በማሽኖች እንዲጠፋ እገዛ አድርጓል። "አርሶ አደሮች ባለፉት ዓመታት ቢሠሩም፤ ስልታችን የተጠና አለመሆኑ የልፋታቸውን ዋጋ አላገኙም" ይላሉ ዶር አያሌው። አረሙ በንፋስ አማካይነት መንቀሳቀሱ እና በከፍተኛ ፍጥነት መዛመቱ፤ ከውጭ የመጡት ማሽኖች በየጊዜው መበላሸት እና ሐይቁ ጥልቀት በሌለው ቦታ አለመሥራታቸው ሥራውን ከባድ አድርጎታል። [አብዛኛው የእምቦጭ አረም ሐይቁ ጥልቀት በሌለው ቦታ ላይ ነው ያለው።] ጢንዚዛዎቹን ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅት ቢጠናቀቅም የሚያስፈልገው የውሃ ገንዳ በፍጥነት አለመገንባቱ ሥራውን አጓቶታል። ፈሳሹን መከላከያን ወደ ሥራ ለማስገባት ያለው የጎንዮሽ ጉዳት አለመጠናቱ እና በሃገር ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ፈሶበት የተሠራውን ማሽን የአካባቢ ባለስልጣን ተረክቦ ሥራ አለማስጀመሩ መፍትሔውን አርቀውታል። • ከአሥመራ መጥቶ ባሕር ዳርን ያስዋበው ዘምባባ "በማሽን ብቻ ለማጥፋት የመሬት አቀማመጡ አስቸጋሪ ነው። የውጭ ማሽኖች ለመሥራት አንድ ሜትር [ጥልቀት ያለው] አካባቢ ይፈልጋሉ። የእኛ ለመሥራት 30 ሴንቲሜትር ጥልቀት ያለው ውሃ ይፈልጋል። ሆኖም አረሙ አነስተኛ ጥልቀት ያለው ቦታ ላይ በመሆኑ የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል" ይላሉ አቶ ሙላት። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት ዶ/ር አያሌው "አጥንተን ለተለያዩ ዘዴዎች የሚስማሙትን ቦታዎች መርጠናል። በማሽን እና በሰው መታረም በማይችል ቦታ ላይ ባዮሎጂካል [እምቦጭን የሚያጠፉ ተፈጥሮአዊ መንገዶች] ዘዴ መፍትሔ ነው። አንድ የሚባል መፍትሔ የለም። በጢንዚዛ ብቻ አጠፋን የሚባል የውጭ ተሞክሮ የለም። የተለያዩ ዘዴዎችን በጋራ መጠቀም አለብን" ብለዋል። ምን ቢሠራ በቁጥጥር ስር ይውላል? ትኩረቱን እምቦጭ እና ሌሎች መጤ አረሞች ላይ ያደረገው የጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ በቅርቡ ተቋቁሞ የ5 ዓመት የሥራ ዕቅድ ተነድፎ ተግበራዊ ሆኗል። የመጀመሪያው ሥራው በዓይን ሊታይ የሚችለውን አረም ማስወገድ ነው። "በሰው ሃይልም ሆነ በተለያየ መንገድ በዓይን ሊታይ የሚችለውን አረሙን ማስወገድ ነው" ብለዋል ዶ/ር አያሌው። በዕቅዱ መሠረት ሙሉ በሙሉ በዓይን የሚታይ አረም እንዳይኖር ይደረጋል። ይህ ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2012 የሚሠራ ይሆናል። "የኔ ምርምር ፈሳሽ ነው። እምቦጩ ላይ ይረጫል። አረሙ በ24 ሰዓት ይደርቃል። ተፈጥሯዊ በመሆኑ በሃይቁ ብዝሃ ህይወት ላይ ጉዳት አያመጣም" ይህንን ለማከናወን ደግሞ ሁሉንም የመከላከያ ዘዴዎች ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል። ከውጭ ከመጡት አንጻር የተሻለ ማሽን መሥራታቸውን የሚናገሩት አቶ ሙላት፤ ከወጪ ውጤታማነት እና ፍጥነት አንጻር የሠሯቸው ማሽኖች ወደ ሥራ እንዲገቡ ፍላጎት አላቸው። በተመሳሳይ "ዛሬ ለጢንዚዛዎቹ የሚያስፈልገው ገንዳ ከተሠራ ዛሬውኑ ወደ ሥራ እንገባለን" ሲሉ ዝግጁ መሆናቸውን ዶ/ር ጌታቸው ያስረዳሉ። "ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን። ቅንጅታዊ ሆኖ በቅደም ተከተል እንሠራለን። በቀዳሚነት በማሽንና በሰው ሃይል ይከናወናል" ብለዋል ዶ/ር አያሌው። ለዚህ ደግሞ ባለፉት ዓመታት አረሙን ለማጥፋት ከህብረተሰቡ የተሰበሰበ ገንዘብን በመጠቀም ማሽኖች እና የሰው ጉልበትን በማቀናጀት ይከናወናል። "በኤጀንሲው አስተባባሪነት አረሙ በተከሰተባቸው 4 ዞኖች 8 ወረዳዎች ከህዳር 1/2012 'እኔ ለጣና' በሚል መሪ መልዕክት ለ45 ቀናት ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ሥነ ህይወታዊ እና ኬሚካላዊ አረሙን የማጥፊያ ዘዴዎች በጥናት ላይ ናቸው። አሁን በሰው ጉልበት እና በአራት ማሽኖች ነው የሚሠራው" ያሉት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው ናቸው። "50 ሚሊዮን ብር [ከህብረተሰቡ ተሰብስቦ ሥራ ላይ ከዋለው የቀረ እና በጣና ሃይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ የሚገኝ የገንዘብ መጠን] አውጥተን በዓይን የሚታይ ምንም አረም እስከማይኖር ድረስ እናስወግዳለን፤ የማገገም ሥራ እንሠራለን።" "ፍሬው 20 ዓመት ሊቆይ ሲችል ጣና ግን የተመቸ ስለሆነ በፍጥነት ሊበቅል ይችላል። አንድም በዓይን የሚታይ አረም ወደ ሚቀጥለው ዓመት እንዳይተላለፍ እናደርጋለን" የሚሉት ዶ/ር አያሌው ሃሳባቸውን የሚያጠናቅቁት "ውሃ እና ወንዞች ላይ ተደብቆ የሚከርም [አረም] መኖር የለበትም። 100 በመቶ ካልተወገደ ባይሠራ ይሻላል" በማለት ነው።
news-55301531
https://www.bbc.com/amharic/news-55301531
መቋጫ ያላገኘው በመተከል ዞን የሚፈጸመው ጥቃትና የነዋሪዎች ስጋት
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀ ተከታታይ ጥቃት የበርካታ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ደግሞ ለጉዳት መዳረጋቸ በተለያዩ ጊዜያት ተዘግቧል።
በዚህም ሳቢያ የሚፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለማስቆም የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስን ያካተተ ኮማንድ ፖስት በስፍራው ከተቋቋመ ወራት ተቆጥረዋል። ነገር ግን በአካባቢው ባሉ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ከአንድ ወር በፊት ከቡለን ወረዳ ወደ ቻግኒ ይጓዝ በነበረ የሕዝብ ትራንስፖርት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው። በወቅቱ ከግድያው ካመለጡት ውስን ሰዎች መካከል የቡለን ወረዳ ነዋሪ የሆነው ወጣት በጥቃቱ ቆስሎ በሕይወት መትረፍ መቻሉን ለቢቢሲ ተናግሯል። ወጣቱ ተኩሱ ሲከፈት ቆስሎ ሲወድቅ ሌሎች ሰዎች ተመትተው እላዩ ላይ በመውደቃቸው ገዳዮቹ እንደሞተ አስበው ሲሄዱ ከጥቃቱ ከተረፉ ሌሎች ሰዎች ጋር ወደ ጫካ በመግባት እንዳመለጠ ይገልጻል። ከቡለን ወደ ቻግኒ ይጓዝ የነበረው ይህ ተሽከርካሪ፣ ዕለቱ የገበያ ቀን ስለነበር በርካታ ሰዎችን ጭኖ እንደነበር የሚያስታውሰው ወጣቱ፣ ቂዶ የምትባል ሰፈር ሲደርሱ ጫካ ውስጥ ተደብቀው በነበሩ ታጣቂዎች ጥቃቱ ተፈጸመባቸው። "ተኩስ ከፈቱብን፣ ከዚያም ሹፌሩ መኪናውን አቆመው። ሁሉም መጥተው ብዙዎቹን ተሳፋሪዎች ገደሏቸው። እኔ ላይ አስከሬን ተጭኖኝ ስለነበር ቆስዬ ለመትረፍ ቻልኩ" በማለት የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳል። እነዚህ ጩቤ፣ ክላሽንኮቭ እና ቀስት ይዘው ነበር ያላቸው ከ20 እስከ 30 የሚሆኑት ጥቃት አድራⶄች አካባቢውን ለቀው መሄዳቸውን በመግለጽ "ብዙም ጉዳት ያልደረሰብን ሰዎች እንደምንም ብለን ከአካባቢው አመለጥን" ብሏል። የክልሉ ባለስልጣናት ይህን አይነቱን ተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ አካላትን "አማጺያን፣ የህወሓት ተላላኪ እና ከኦነግ-ሸኔ ጋር ያበሩ" የሚሉ ጥቅል ስሞችን ይሰጧቸዋል። ነገር ግን እስካሁን ለእነዚህ ጥቃቶች በይፋ ወጥቶ ኃላፊነት የወሰደም ሆነ አላማውን የገለጸ አካል የለም። ተደጋጋሚ ጥቃት በሚያጋጥመው በመተከል ዞን በቡለን ወረዳ ተወልዶ ያደገው አሁንም እዚያው የሚኖረው አቶ አበበ (ለደኅንነቱ ሲባል ስሙ የተቀየረ) በአካባቢው ከሌላ ቦታ መጥቶ ጥቃቱን የሚፈጽም "አማጺ የሚባል ቡድን የለም" ይላል። ጨምሮም "አብረውን የሚኖሩ ፖሊሶች፣ ታጣቂዎችና የጥበቃ ሠራተኞች ናቸው ይህንን ጉዳት የሚያደርሱት" የሚለው አቶ አበበ በቅርቡ አንዝባ ጉና በሚበላው ቀበሌ ውስጥ የተፈጸመውን ጥቃት እንደማሳያ ያነሳዋል። "በወቅቱ ጥቃቱን አድርሰው ከተያዙት ሰዎች መካከል አንዱ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ ሆኖ ተገኝቷል። ራሱም አምስት ሰዎች መግደሉንም አምኗል" በማለት የአካባቢው አመራር የግጭቱ ተሳታፊ መሆኑን ያስረዳል። ባለፈው ሳምንት የአካባቢውን ጸጥታ ለመጠበቅ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ያለፉት አራት ወራት ሥራውን በገመገመበት ጊዜ በመተከል ዞን ለተከሰተው ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ 284 ታጣቂዎች መደምሰሳቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በአካባቢው በተከታታይ ከተፈጸሙት ጥቃቶች ጋር በተያያዘ ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ 66 በተለያየ አመራር ደረጃ ላይ በነበሩ ኃላፊዎች ላይ ፖለቲካዊ እርምጃ መወሰዱ ተነግሯል። አማጺ ቡድን የሚባል የለም የሚለው አቶ አበበ ግን "ኮማንድ ፖስቱ ራሱ የችግሩ አካል ነው" ይላል። በማስረጃነት የሚያቀርበው ደግሞ ጉብላክ ከተባለው ቦታ ላይ የተከሰተውን ጥቃት ነው። መንገዱ ሽፍቶች እንዳሉና አስተማማኝ ስላልሆነ ወደዚያ እንደማይሄድ አሽከርካሪው ፈቃደኛ እንዳልነበረና የኮማንድ ፖስቱ አባላት በአጀብ እንደሚሸኟቸውና የተወሰነ መንገድ አብረዋቸው እንደተጓዙ አበበ ይናገራል። "ነገር ግን በፓትሮል ሸኝተዋቸው የሆነ ቦታ ተመለሱ፤ እነሱ ከተመለሱበት ቦታ 300 ሜትር አለፍ ብሎ ደግሞ መኪናው በሽፍቶች እንዲቆም ተደርጎ በተሳፋሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል" ይላል። ባለፈው ወደ ቻግኒ ሲጓዝ ጥቃት የደረሰበት ተሽከርካሪም ሹፌሩ አልሄድም ቢልም "አንተ ራስህ ችግር ፈጣሪ ነህ ተብሎ በወረዳው ፖሊስ ተገዶ ነው የሄደው" በማለትም ያክላል። የአካባቢው አመራር ውስጥ ያሉና ሌሎች ሰዎች በነዋሪው መካከል ጥርጣሬና ስጋት የሚፈጥሩ ወሬዎችን በሚያሰራጩበት ወቅት ጥቃቶች እንደሚፈጸሙና እንደሚባባሱ አቶ አበበ ከዚህ በፊት ያጋጠሙ ክስተቶችን በማስታወስ ይናገራሉ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለይ በመተከል ዞን እየተፈጸሙ ካሉ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ በአካባቢው ያሉ የመስዳደር አካላት ላይ ከነዋሪዎች የተሰነዘረውን ክስ በተመለከተ ቢቢሲ ምላሽ ለማግኘት አቶ መለሰ በየነ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊን ጠይቆ ነበር። ኃላፊው በሰጡት ምላሽ "ማንኛውም አመራር በዚህ ቀውስ ውስጥ ተሳትፎ ካለው ጥያቄ የሚያነሱት ነዋሪዎች መረጃ ሰጥተውን እርምጃ እንወስዳለን። እስካሁንም እየወሰድን ነው" በማለት፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአመራርና በጸጥታ አካላት ላይ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት ፖለቲካዊ ርምጃና ለሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን ገልጸዋል። በአንጻሩ ኮማንድ ፖስቱ ችግሩ ሲፈጠር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያላቸውን 67 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ የፖሊስ አባላትን መያዙን አስታውቋል። በአካባቢው በሚፈጸሙ ጥቃቶች በሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ከመድረሱ ባሻገር በሺዎች የሚቆጠሩት ለመፈናቀል ተዳርገዋል። በዚህም በመተከል ዞን ቢያንስ 22 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የኮማንድ ፖስቱ ባለፈው ሳምንት ባደረገው ግምገማ ላይ ተገልጿል። የኮምዩኒኬሽን ኃላፊው አቶ መለሰ በየነ እንዳረረጋገጡት በርካታ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፤ "እነዚህን ተፈናቃዮች በክልሉ አደጋ መከላከልና በሰላም ሚንስትር አማካኝነት ሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው" በማለት በቀጣይም ወደቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳን ጠቅሶ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው በመተከል ዞን "ከጥፋት ቡድኑ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በተሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ማለታቸውን ተዘግቧል። አቶ ጌታሁን ጨምረውም በዞኑ በተደጋጋሚ ከሚከሰቱ ጥቃቶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት አላቸው በተባሉ አመራሮች፣ የጸጥታ አካላትና የተለያዩ ግለሰቦች ላይ ፓለቲካዊና ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን መናገራቸውን ገልጿል። ይህ ክስተት ያሳሰበው የቤኒሻንጉል ክልልን ብቻ ሳይሆን በተፈጸሙ ጥቃቶች ኢላማ ተደርገዋል ባላቸው የክልሉ ተወላጆች ሳቢያ የአማራ ክልልም የፌደራል መንግሥቱም ሆነ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጥቃቶቹን ለማስቆምና የዜጎችን ደኅንንት እንዲያስጠብቁ ሲጠይቅ ቆይቷል። በቅርቡ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ባወጧቸው መግለጫዎች ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል። በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው የመተከል ዞን ውስጥ በታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ወራትን አስቆጥሮ፤ አሁንም ድረስ በተለያዩ ጊዜያት በሚፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል። ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰነውና በሰባት ወረዳዎች በተዋቀረው የመተከል ዞን የተለያዩ ብሔረሰቦች ይኖራሉ። በዋናነት የጉሙዝ፣ የሽናሻ፣ የአማራ፣ የአገው፣ የኦሮሞና የበርታ ብሔሮች ይገኙበታል። በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጸሙ ጥቃቶች ማንነትን የለየና በተወሰኑት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ቢቢሲ ያናጋረቸው ነዋሪዎችና ከዚህ በፊት የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
news-48687256
https://www.bbc.com/amharic/news-48687256
የ27 ፈጠራዎች ባለቤት የሆነው የ17 ዓመቱ ታዳጊ ኢትዮጵያዊ፡ ኢዘዲን ካሚል
በፀሐይ ኃይል ያለ ፔዳል እንደ ሞተር የሚንቀሳቀስ ብስክሌት? ...
ኢዘዲን ካሚል ለፈጠራ ሥራዎቹ ከጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ሰርቲፊኬት ሲቀበል ... በተራመዱ ቁጥር ስልክዎን ቻርጅ ለማድረግ የሚበቃ ኃይል ከፀሐይ የሚያመነጭ ጫማ፣ የዘይት ጄሪካን ላይ ስልክ ተገጥሞለት የእሳት አደጋ ሲከሰት ጥሪ የሚያደርግ መሣሪያ፣ ድንገት ቁርስ ሠርተው ከረፈደብዎ ምድጃ ማጥፋት ረስተው ወደ ሥራ ቢሄዱ ከስልክዎ የሚያጠፉት ማብሰያና ከሌሎች 23 የፈጠራ ሥራዎች በስተጀርባ አንድ ታዳጊ አለ ኢዘዲን ካሚል። • የብስክሌት ጀልባ የሠራው ወጣት • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ ኢዘዲን ካሚል የ17 ዓመት ኢትዮጵያዊ ወጣት ሲሆን እስካሁን በአጠቃላይ 27 የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ የፈጠራ ሥራዎችን ከ14 ዓመቱ ጀምሮ ሲሠራ ቆይቷል። ሃሳቦቹን ከየት አመጣቸው? ለፈጠራስ እንዴት ተገፋፋ? ወደፊትስ ምን የማድረግ ሕልም አለው? ኢዘዲን ካሚል ኢዘዲን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሲሆን ያደገው የወልቂጤ ክፍለ ከተማ በሆነችው ጉብሬ ውስጥ ነው። ወደ ቴክኖሎጂ ፊቱን ሲያዞር ገና የ14 ዓመት ታዳጊ የነበረ ቢሆንም ለፈጠራዎቹ ከተለያዩ ተቋማት ከሥራዎቹ በቁጥር የማይተናነሱ ሰርቲፊኬቶች ተሰጥተውታል። ያደገበት ከተማ ለቴክኖሎጂ ያላት ቅርበት እንደ አዲስ አበባ ስላልሆነ ለፈጠራ ሥራው የሚያስፈልጉት እንደ ላፕቶፕ፣ ኢንተርኔትና ሌሎች ቁሳቁሶችን እንደልብ አለማግኘቱ ኢዘድንን ተስፋ አላስቆረጠውም። ለዚህም በአካባቢው ከሚያገኛቸውም ሆነ አንዳንድ ጊዜ አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ አገልግለው የተወገዱ ወይም የወዳደቁ ዕቃዎችን ከመርካቶ በትንሽ ዋጋ በመግዛት ያሰባቸውን አዳዲስ ፈጠራዎች እውን እንደሚያደርግ ይናገራል። •ኢትዮጵያ ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር እንዴት ትውጣ? ከፀሐይ ኃይል ማመንጨትንና ባደጉ ሃገራት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ አጠቃላይ የቤት ውስጥ መገልገያ ቴክኖሎጂዎችን አስቦና አስተውሎ መሥራት ያልተሳነው ይህ ወጣት "ማንም ሰው ምንም ነገር ለመፍጠር ሲያስብ ከችግር ተነስቶ ነው ሊፈጥር የሚችለው" በማለት የሥራዎቹን መነሻ ምክንያት ይናገራል። በጫማዎ ስልክዎን ቻርጅ ማድረግ አስበው ያውቃሉ? የኢዘዲን የፈጠራ ሥራዎች ብዙውን ጊዜ በቀን ሩጫ የተጠመደ ሰው ማለዳ ስልኩን ሙሉ በሙሉ ቻርጅ አድርጎ ቢወጣም አንዳንድ ጊዜ በቀኑ መጨረሻ ግን የስልኩ ባትሪ ሊያልቅ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች አይጠፉም። አንዳንዴ ለአካባቢ ብክለት ታስቦም ይሁን ብዙ ገንዘብ የማያስወጣና የማያደክም የትራንስፖርት አማራጮችን የሚፈልጉም ሰዎች ከመካከላችን ላይጠፉ ይችላሉ። አልፎ አልፎ በችኮላ መካከል ጠዋት ተጥዶ የነበረውን ሻይም ሆነ መጥበሻ እዚያው ከማብሰያው ላይ ተረስቶ የሚወጡባቸውም ቀናት ሊያጋጥሙ ይችላሉ ወይንም የተረሳ ሻማ ቃጠሎ የሚፈጥርበት ጊዜስ ብለን ብናስብ. . . ? ለእንደዚህ ዓይነት የዕለት ተዕለት ችግሮችና ከባድም ሆነ ቀላል ጉዳትን ሊያስከትሉ ለሚችሉ አደጋዎች መፍትሄ የሚሆኑ ዘዴዎችን ኢዘዲን ሠርቷል። የፀሐይን ኃይል በመጠቀም የእጅ ስልክ ቻርጅ የሚያደርግ ጫማ፣ ተቀምጠው ብቻ የፀሐይን ብርሃን በመጠቀም እንደ ሞተርሳይክል ያለ ፔዳል በእራሱ የሚሄድ ብስክሌት፣ ያልጠፉ የቤት መገልገያ ዕቃዎችን የሚያጠፋ እና የእሳት አደጋን የሚጠቁም መሣሪዎች ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው። •ጄኔራል አደም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ የኢዘዲን የፈጠራ ሥራዎቹ በአጠቃላይ 27 ሲሆኑ ከአስደናቂዎቹ ናሙናዎች (ፕሮቶታይፖች) መካከል የተወሰኑት ከዚህ በታች ባለው ምስል ይታያሉ። ሌባ ያደገበትን ቤት ሲያንኳኳ ... ሰው ችግሩን ለመቅረፍ በማሰብ ነው ወደ ፈጠራ የሚሰማራው የሚለው ኢዘዲን አንድ ቀን የእጅ ስልኩን ቻርጅ እንዲያደርግ ቤቱ ትቶት ወደ ሌላ ቦታ ሄዶ ሲመለስ የጠበቀው ክስተት በጄሪካን ለሠራው ፈጠራ ጅማሬ መሆኑን ያስታውሳል። "ስመለስ የጎረቤታችን ቤት በእሳት ጋይቶ ጠበቀኝ። መጀመሪያ ላይ ድንጋጤው እንድነቃነቅ አላደረገኝም ነበር። ከዚያ ግን ሰው ሁሉ ሲሯሯጥ እኔም እሳቱን ለማጥፋት ለማገዝ ሞከርኩ" የሚለው ኢዘዲን ቻርጀር ላይ ተሰክቶ የነበረው ስልኩን አስታውሶ ለእሳት አደጋው ደራሽ ቢሆን የሚል ሃሳብ እንደሆነው ይነግረናል። ሃሳቡን ወደ ተግባር በመለወጥ ቤት ውስጥ የሚፈጠርን ጭስ በመለየት የእሳት አደጋ ምልክትን በአቅራቢያ ላሉ ሰዎች በድምፅ ይሰጣል። በዚህም በቅርብ ያሉ ሰዎች እርምጃ ካልወሰዱ በመሣሪያው ላይ በተገጠመ ስልክ አማካይነት መዝግቦ ለያዛቸው ሁለት ቁጥሮች ለምሳሌ ለቤቱ ባለቤት እና ለእሳት አደጋ መከላከያ በመደወል የእሳት አደጋ ጥሪ ያስተላልፋል። 'ኤክስ ፋየር' ብሎ የሰየመው ይህ ፈጠራው "የእሳት አደጋ ሲከሰት ሦስት የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናል። መጀመሪያ ላይ በአቅራቢያ ለሚገኙ ሰዎችና ጎረቤቶች የድረሱልኝ ጥሪ ያሰማል፣ ቀጥሎ ደግሞ የእሳት አደጋ መነሳቱን ለቤቱ ባለቤትና ለእሳት አደጋ ተከላካዮች በመደወል ያሳውቃል፤ ይህንን እያደርገ ካርቦን ዳይዮክሳይድ በመርጨት እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ያደርጋል" ሲል የሚናገረው ኢዘደኒን ለዚህ ፈጠራው አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እውቅና እንደሰጠው ይጠቅሳል። • 600 ዓመታትን ያስቆጠረው የሣር ድልድይ እንደዚህ ዓይነት የቤትን ደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች በውድ ዋጋ የሚቀርቡ በመሆናቸው የቅንጦት መሣሪያዎች ሊመስሉ ይችላሉ የሚለው ኢዘደን፣ በእሳት የተቃጠለውን የጎረቤቶቹን ቤት በማሰብ እንደዚህ ዓይነት መሣሪያዎች በሰው ላይ የሚደርስ ጉዳትንና የንብረት ውድመትን ሊያስቀሩ እንደሚችሉ ይናገራል። ከዚህ በተጨማሪም በአንድ ወቅት ሌባ ወደቤታቸው መግባቱን የሚያስታውሰው ኢዘዲን ሌባ ወደ ቤት ለመግባት ሲሞክር በድምጽ ምልክት የሚሰጥ መሣሪያም እንዳለው ይናገራል። "ሌባው ጓንት ቢያደርግ መሣሪያው ለይቶ ሊያውቀው አይችልም፤ ይህ መሣሪያ ምልክት የሚሰጠው ሌባው በእጁ ከነካው ብቻ ነው" የሚለው ኢዘዲን ይህ ፈጠራው የሚቀረው ነገር እንዳለና ሌሎች የሚያሰባቸው ብዙ ዓይነት የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት ለቢቢሲ ገልጿል። (ከላይ በግራ) ኢዘዲን ከአንደኛው ጣልያን ስፖንሰር ጋር (ከላይ በቀኝ) ኢዘዲንና አባቱ (ሌላው) ለኢዘዲን ከተሰጡት ሰርቲፊኬቶች መካከል የተወሰኑት ኢዘዲን ካሚል ዛሬ እና ነገ ኢዘዲን እስካሁን ለሠራቸው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎቹ ብዙ የሚያመሰግናቸው ሰዎች ቢኖሩም፤ በቀዳሚነት የሚማርበትን ዩኒቨርሲቲ ጠቅሶ እንደልቡ የሚመራመርበትን ክፍል ከማዘጋጀት ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት ለፈጠራ ሥራዎቹ ያስፈልጉኛል ብሎ የሚጠይቃቸውን መሣሪያዎች እና ቁሳቁሶች እንዲገዙለት ማድረጋቸውን ይጠቅሳል። በተጨማሪም ከካቶሊክ ሚሽን ጋር የተያያዙ ድርጅቶችና ሁለት ጣልያናዊ ሙዚቀኞች ለሦስት ተከታታይ ዓመታት እንደረዱት እንዲሁም 34 ሺህ ብር፣ አርድዊኖ የተባለ ሶፍትዌር እና 2 ላፕቶፕ ኮምፕዩተሮችን አበርክተውለታል። የተለያዩ ውድድሮች ላይ ከመሳተፍ ወደ ኋላ የማይለው ኢዘዲን በቅርቡ በተሳተፈበት ውድድር ላይ የ300 ሺህ ብር ተሸላሚ መሆኑንና 6 የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን ሠርቶ እንዲያቀርብ መጠየቁን ገልጿል። በዚህም "በጣም ደስ ብሎኛል አሁን ስድስት ሥራዎቼን በትክክለኛ ዕቃዎች ሠርቼ ማቅረብ እችላለሁ" ይላል። ከተለያዩ ድርጅቶች፣ ማዕከላትና ተቋማት ሰርትፍኬትና ሽልማት ያገኘው ኢዘዲን ከሁሉም በላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እውቅና ተስጥቶት መሸለሙ ወደፊት ለሃገሩ ብቻ ሳይሆን አህጉሪቱንም ተሻግሮ ለዓለም ብዙ ነገሮችን ሊያበረክት እንደሚችል ተስፋ እንዳለው ነግሮናል። ከሁሉም በላይ የወጣትነት ሕልሙ ምን እንደሆነ ሲጠየቅ "አሁን የውጪ ትምህርት ዕድል አግኝቼ ብዙ ነገሮችን ደግሞ ወደፊት መሥራት ብችል ደስታዬን አልችለውም" በማለት ያለውን የወደፊት ዓላማ ለቢቢሲ ተናግሯል።
news-41159243
https://www.bbc.com/amharic/news-41159243
"ሁሉም ሴቶች ከጥቃት ውጭ አይደሉም! "
"ምናለበት እንደ ህፃን ልጅ ቢያየኝ ኖሮ? የመማርና የማወቅ ህልሜን ባያጨልመዉ? መጪዉን ህይወቴን ነዉ የነጠቀኝ።" በማለት የምትናገረዉ ዘቢባ እንድሪስ* እድሜዋ 16 ሲሆን በእህቷ ባል ከአንድ ዓመት በፊት አሰቃቂ የሆነ የወሲብ ጥቃት ደርሶባታል።
የተደፈረች ህፃን የልጇን እጅ ይዛ በደረሰባት ጉዳት ፈገግታዋን፣ የልጅነት ነፃነቷን የተነጠቀችዉ ዘቢባ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በህፃንነቷ የልጅ እናት ሆናለች። ይህንንም ሁኔታ መረር ባለ ቃል እንዲህ ትገልፀዋለች "ልጅ ፀጋ ነዉ ሲሉ እሰማለሁ፤ ልጅ በልጅነት ሸክም ነዉ እንጂ እንዴት ፀጋ ይሆናል? " የተወለደችበትን መንደር ብትናገር በቤተሰቦቿ ላይ ሃፍረት አመጣለሁ ብላ የምታምነዉ ዘቢባ ከደቡብ አካባቢ እንደመጣች ትናገራለች። አጥቂዉን ሳይሆን ተጠቂዎችን ማሳፈርና ማውገዝ በተለመደባት ቦታ፤ ዘቢባ ብቻ ሳትሆን ጥቃት የደረሰባቸዉ ህፃናትም ይሁኑ አዋቂ ሴቶች በሚደፈሩበት ወቅት ክብራቸዉን እንዳዋረዱ ይሰማቸዋል። የዘቢባም ስሜት ከዚህ የተለየ አይደለም። ሀገሯ በነበረችበት ወቅት የሰባተኛ ክፍል ተማሪ የነበረችዉ ዘቢባ ድንገተኛ የሆነ የማያቋርጥ መንቀጥቀጥ እና የጀርባ ህመም ስለተሰማት ትምህርቷን ለማቋረጥ ተገደደች። ለህክምናም እንዲሁም ትምህርቷን ለመቀጠል ትችል ዘንድ ታላቅ እህቷ ወደምትኖርበት አዲስአበባ መጣች። እህቷ የተለያዩ ግለሰቦች ቤት እየተዘዋወረች ልብስ በማጠብ እና ድንች ጠብሳ በመሸጥ የምተዳደር ሲሆን ወደቤትም የምትመጣዉ መሸትሸት አድርጋ ነዉ። ዘቢባ ቀኑን የእህቷን ልጅ በመጠበቅ እንዲሁም የቤት ሥራዎችን በመስራት ታሳልፋለች። ሲያማት ተኝታ ብታሳልፍም መፅሀፎቿን ማየትና ማንበብ አላቋረጠችም። ዘቢባ ጀርባዋ እስኪጎብጥ ድረስ እበት እየዛቀች ያሳደጋቻትን የእናቷን ህይወት ለመቀየር ዋነኛ ህልሟ የህክምና ዶክተር መሆን ነበር። ያንን ህልሟን የሚያጨልም ጉዳይ የተከሰተዉ አንድ ቀን ተኝታ በነበረችበት ወቅት ነዉ። ከእህቷ ጋር በመጋረጃ በተከፈለ አንድ ጠባብ ቤት ዉስጥ በጋራ የሚኖሩ ሲሆን፤ ባልና ሚስቱ አልጋ ላይ ሲተኙ እሷ ደግሞ ፍራሿን አንጥፋ ትተኛለች። የእህቷ ባል ቀድሞ ከሥራ የሚገባ ሲሆን ብዙ ጊዜ ከትንሽ ቃላት ውጭ ምንም ተባብለዉ እንደማያዉቁ ዘቢባ ታስታውሳለች። በአንደኛዋ ቀን ግን አንድ ሰዓት አመሻሹ ላይ ጀርባዋን ከፍተኛ ህመም ተሰምቷት ጋደም ባለችበት ወቅት በቢላ አስፈራርቶ እንደደፈራት ትናገራለች። ለሌላ ሰው ትንፍሽ ብትል እንደሚገድላትም ጭምር ነበር የነገራት። "እሱ ስላስፈራራኝ ብቻ ሳይሆን የእህቴን ህይወትም መበጥበጥም ስለማልፈልግ ለማንም መንገር አልፈለኩም" ትላለች። ከዚያ ትንንሽ እጆቿን እያፋተገችና እንባዋ በጉንጮቿ ላይ እየወረደና ሳግ እየተናነቃት "ብዙ ደም እየፈሰሰኝ ነበር። ደሜን ጠራርጌ ወደየት እንደምሄድ ሳላዉቅ ወደ መንገድ እያለቀስኩ ወጣሁ" መንገድ ላይ አይዞሽ ያላትም ሰው አልነበረም። ለምን ያህል ሰዓት መንገድ ላይ እንደቆየችም አላወቀችም ደንዝዛ ቆማ ባለችበት ጊዜ እህቷ ከሥራ ስትመለስ ተገናኙ። ብዙ የተደፈሩ ህፃናት ለእርግዝና ይዳረጋሉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ መንገድ ላይ ምን እየሰራች እንደሆነ ስትጠይቃት "አይ ትንሽ አሞኝ ነዉ" በማለት መለሰችላት እህቷም ምንም አልጠረጠረችም፤ ህይወትም በዛው ቀጠለ። አንድ ቀን ውሀ በቤት ውስጥ ስላልነበር ቀድታ ስትመለስ ወድቃ የጎን አጥንቷ ስለተጎዳ እህቷ ወደ ሆስፒታል ወሰደቻት። ከዚህ ጉዳቷ በተጨማሪ የሰባት ወር እርጉዝ መሆኗን በምርመራ ወቅት በመታወቁ የዶክተሩ የመጀመሪያ ጥርጣሬ የቤት ዉስጥ ሰራተኛ መስላዉ ነበር። ዶክተሩም እህቷን አስጠርቶ እርጉዝ መሆኗን በተናገረበት ጊዜ ነበር ምን እንደደረሰባት ለመንገር የተገደደችዉ። ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተመራ፤ ህይወት ሙሉ በሙሉ የጨለመባት በመሰላት ወቅት ለተደፈሩ ሴቶች መጠለያ ወደሆነዉ የሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር በሰዎች ትብብር የመጣችዉ። የደፈራት ግለሰብ ምን ያህል ዓመት እንደተፈረደበት ባትሰማም እንደታሰረ አውቃለች።ከእስሩ በላይ ያስደሰታት ነገር ቢኖር እህቷ ለእሷ የሰጠቻት ድጋፍ ነወ። "ከጎኔ መሆን ብቻ ሳይሆን የእኔ ደፋሪ ከሆነ ሰዉ ጋር፤ ልጅነቴን ከቀማኝ ሰዉ ጋር ትዳር ብላ አለመቀጠሏ ሁሉ ነገር ጨለማ አለመሆኑን ያሳየኝ ጉዳይ ነው" ትላለች ዘቢባ። ሰዎችን ቀና ብላ ለማየት ብዙም የማትደፍረው ዘቢባ መጠለያው ዉስጥ ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ ህይወቷ እንደተቀየረ ትናገራለች። "እርጉዝ በነበርኩበት ወቅት ራሴን ከሰዎች በታች ነበር የማየዉ ማድረግ የምችለው ማልቀስ ብቻ ነበር" በማለት ዘቢባ እያለቀሰች ትናገራለች። የተደፈረች ህፃን ልጅ በፖሊስ እርዳታ ወደ መጠለያው ስትወሰድ ያንሰራራ ተስፋ በመጠለያው ቆይታቸው በምግብ ሥራ፣ በልብስ ስፌት፣ በፀጉር ሥራ፣ በቀርከሃና በጣዉላ ሥራዎች የተለያዩ ስልጠናዎች መዉሰድ የሚችሉ ሲሆን ዘቢባም የፀጉር ሥራ ስልጠናን እየወሰደች ነው። "ይሄንን ቤት ፈጣሪ እንዳዘጋጀልኝ ነው የምቆጥረው" ትላለች ዘቢባ። አሁን ያለችበት ቦታ ለመድረስ ግን በማዕከሉ ውስጥ በተለያዩ የምክር አገልግሎት ማለፍ ነበረባት። የማዕከሉ የስነልቦና አማካሪዎች በደረሰባት ጥቃት ደፋሪዋ የእሷን ክብር ሳይሆን ራሱ እንደተዋረደ፤ ከልጇም ጋር ባላት ግንኙነት ዙሪያና የወደፊት ህይወቷንም በተስፋ እንድታየው አግዘዋታል። "ምንም እንኳን በወራት ውስጥ ማልቀሴ እየቀነሰና ጓዋደኞችም ስላፈራሁ መሻሻል ባሳይም አሁንም ብቸኝነቱና ተስፋ መቁረጡ አለ" ትላለች። በዚህ መጠለያ ከሚገኙት ውስጥ ዘቢባ ብቸኛዋ አይደለችም። የጭካኔ በትር የ13 ዓመት እድሜ ያላት ማስተዋልም ከመጣች ስምንት ወሯ ሲሆን፤ የተደፈረችዉ ጎረቤት ከብት ለማገድና ለአንዳንድ ሥራዎች በተቀጠረ ግለሰብ ነው። እንጨት ለመልቀም በምትሄድበት ወቅት በለበሰችው የአንገት ልብስ አፍኖ እንደደፈራት ፈራ ተባ በማለት ትናገራለች። ይሄንን የሚሰቀጥጥ ሁኔታ የዘጠኝ ዓመት እህቷ ተመልክታለች። "ለሰዓታት ራሴን ስቼ ነበር። በኋላ እህቴ ነች ያነቃችኝ" ትላለች ማስተዋል። ማስተዋልም ለአሳዳጊ አያቶቿ የገጠማትን ትንፍሽ ማለት አልፈለገችም። "በደም የተበላሸውን ልብስ እንዳያዩት ደበቅኩት፤ ምክንያቱም የኔ ጥፋትና አውቄ እንዳደረኩት ነው የሚያስቡት። እናም በህይወት መኖር አልፈለኩም። ለታናሽ እህቴ ስል ነው በህይወት የቆየሁት" በማለት ፊቷን በእጇ ሸፍና በማልቀስ ትናገራለች። ነገሩ የታወቀው የማያስቆም የማያስቀምጥ ህመም ማህፀኗ አካባቢ ሲሰማት ታናሽ እህቷ ለአያቷ ተናግራ ጉዳዩንም ህግ እንዲይዘው ተደረገ። የማስተዋል የአካል ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም ጥቃት አድራሹ ከትንሽ ጊዜ እስር በኋላ ተለቀቀ። ይሄ ጉዳይ ለማስተዋል ግልፅ አልሆነላትም። "ፍርድ ቤት የሚረዱ መስሎኝ ነበር እነሱ ግን ምንም አልመሰላቸውም" በማለት ተስፋ የቀረጠችበትን ሁኔታ ትገልጻለች። ጉዳዩ በሰፈሯ ከተሰማም በኋላ የሰፈሩ ህፃናት መሳቂያ መሳለቂያ አደረጉዋት። የደፈራትም ሰው መተናኮሉን ቀጥሎ አያቶቿንም መሳደብ እንዲሁም እንደመታት ትናገራለች። ትምህርቷን ለመቀጠል ከብዷት በነበረበት ጊዜ ነበር አክስቷ ወደዚህ መጠለያ ያመጣቻት። እዚህ ከመጣች በኋላ ለወደፊቱ የምታልመው ፖሊስ የመሆን ተስፋዋ ቢያንሰራራም አሁንም የታናሽ እህቷን ጉዳይ ስታስብ ጭንቅ ይላታል። "እስከዛሬ የሚያስቀምጧትም አይመስለኝም" ትላለች እንባ እየተናነቃት። ለማመን በሚከብድ ሁኔታ በጭካኔ ቆሳስለው፤ አንዳንዶቹም ፊታቸው በእሳት ተጠብሶ ነው ወደዚህ መጠለያ የሚመጡት። የተደፈሩ ሴቶች ስልጠና ሲወስዱ ብሩህ ተስፋ በዚህ መጠለያ ውስጥ መስማት የሚከብዱና ተስፋ የሚያስቆርጡ ብዙ ታሪኮች ቢኖሩም በስቃይ ውስጥ አልፈው ነገን ለመኖር በተስፋ ሲያልሙ ማየት የሚገርም ነው። ቤተሰቦቿ ገና በስድስት ዓመቷ ሞተውባት በሰው ቤት ስትንከራተት የአሰሪዋ ልጅ በጩቤ አስፈራርቶ የደፈራት የ14 ዓመት እድሜ ያላት መሰረት፤ የምታስበው ህፃናት እንዴት እንዳይደፈሩ ማድረግ ይቻላል የሚለው መፍትሄ ላይ ነው። "ሁሉም ሴቶች ከጥቃት ውጭ አይደሉም" የሚል እምነት ያላት መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህንን የሚያረጋግጥ ነገር አይታለች። ይህ መጠለያ ከ14 ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በተወጣጡ አምስት ሴቶች እንደተጀመረ የሚናገረው የድርጅቱ የፕሮግራም አስተባባሪ ግሩም አለማየሁ፤ ፆታዊ ጥቃት ተከላካይ ማህበር ተብሎ እንደተመሰረተ ይናገራል። የዚህ ሀሳብ መነሻ የሆነው የተደፈሩ ህፃናትና ሴቶች ወደ ክስ ካመሩ በኋላ በተደጋጋሚ ጥቃት በመድረሱ፤ እንዲሁም በቤተሰብ የሚደፈሩ ህፃናት ጉዳዩ ወደ ክስ ከሄደ በኋላ ቤታቸው ተመልሰው መሄድ ስለማይችሉ ይሄ መጠለያ ማረፍያ እንዲሆን ታስቦ ተሰራ። መጠለያው ምግብ ማደሪያ የምክር አገልግሎት የተለያዩ ስልጠናዎችን ይሰጣል። ከዚህም በተጨማሪ በሁለት የተከፈለ የትምህርት ፕሮግራምም አለ። የመጀመሪያው አጠቃላይ ትምህርት የሚሰጥበት ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በቤተሰብ የተደፈሩና ትምህርታቸውን ቤታቸው ሆነው መከታተል ለማይችሉ ሴቶች ዩኒቨርስቲ እስኪጨርሱ ድረስ ድጋፍ የሚሰጥበት ነው። ከአዲስ አበባው መጠለያ በተጨማሪ በአዳማ ከተማ እንዲሁም በሃዋሳ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ የማረፍያ አገልግሎት ይሰጣቸዋል። በአጠቃላይም ከ1500 በላይ ለሆኑ ሴቶችም መጠለያ ነው። አቶ ግሩም እንደሚገልፁት መቀበል ከሚችሉት በላይ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ስለሚመጡ ከአልጋ በተጨማሪ ፍራሽ በማንጠፍ ይቀበሏቸዋል። ምንም እንኳን አንዲት ሴት በአማካኝ ለሶስት ወራት ትቆያለች ብለው ቢያስቡም፤ አቶ ግሩም እንደሚሉት ብዙዎቹ ወልደው ስለሚመጡ ታርሰው እንዲሁም ልጆቻቸውን እስኪጠነክሩ ድረስ እስከ ሁለት ዓመት የሚቆዩበት ጊዜ አለ። ቆይታቸውን ከጨረሱ በኋላ የሶስት ወር የቤት ኪራይና በቀጣዩ ለሚሰሩት ሥራ መነሻ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። በዓመታትም ውስጥ ብዙ ሴቶች ተስፋቸው አንሰራርቶ ከወጡ በኋላ ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ ያለው ውጣ ውረድ ትንሽ ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ የሚናገረው አቶ ግሩም ይህ መጠለያ አዲስ ህይወት እንደሚሰጣቸው ግን አይጠራጠርም። *የጥቃት ሰለባዎቹ ስም ለደህንነታቸው ሲባል ተቀይሯል።
news-55141539
https://www.bbc.com/amharic/news-55141539
የፖሊስን ጭካኔ ተቃውሞ የሚመሩት ናይጄሪያውያን ሴቶች
ሪኑ ኦዱዋላ ገና የ22 አመት ወጣት፣ ደፋርና፣ ሃሳቧን ያለምንም ፍራቻ የምትገልፅ ናት።
ሪኑ ኦዱዋላ ባህርይዋ ለናይጄሪያ መንግሥት ፍራቻ ፈጥሮበትም የባንክ አካውንቷ እንዲታገድ ትዕዛዝ ተላልፏል። ሪኑ ናይጄሪያውያን የፖሊስ ጭካኔን በመቃወም መንግሥት ለውጥ እንዲያመጣ አላፈናፍን በማለት ተቃውሟቸውን በመግለፅ ታሪክ ከሰሩ በአስር ሺህ ከሚቆጠሩ ወጣቶች መካከል አንዷ ናት። ዘረፋን ለማስቆም የተቋቋመውን ልዩ የፖሊስ ክፍል ወይም ሳርስ ተብሎ የሚታወቀው ቡድን አንድን ሰው ሲገድል የሚያሳይ ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎ ተቃውሟዋን ለመግለፅ ሪኑ ጎዳና ላይ ወጣች። ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ሰዎችን ማሰር፣ ማሰቃየትና ግድያም ይፈፅማል በሚልም ቡድኑ እንዲበተን ጠየቁ። ሪኑም ከሌጎስ አስተዳዳሪ ቢሮ ውጭም ተቃውሟቸውን ለማሰማትም መጠለያ በመስራትም በርካቶችም ለተቃውሞ ሰፈሩ። የመገናና ብዙሃን ባለሙያ መሆኗም በማኅበራዊ ሚዲያ ሰልፈኞችን በመጥራት፣ ውጪ ለሚያድሩ ተቃዋሚዎችም ብርድ ልብስ የማሰባሰብ ሥራዎችን ለመስራት ጠቅሟታል። በርካታዎችም በመንግሥት ቢሮዎች ህንፃ ውጪ ለ72 ሰዓታት ተቃውሟቸውን እየገለፁም ውለው አድረዋል። በኋላም ፖሊስ ጥቃት በማድረሱ ተበትነዋል። ከ172 ሺህ በላይ የትዊተር ተከታዮች ያሏት ሪኑ በባለፉት ስድስት ሳምንታት የናይጄሪያን መንግሥት መሰረት ካብረከረከው በርካታ የሴት ተቃዋሚዎች መካከል አንዷ ናት። ሳርስ መቆም አለበት በሚለው የትዊተር እንቅስቃሴዋም ትዊተር በሰማያዊ ይፋ መለዮ እውቅና ሰጥቷታል። በአሁኑ ወቅት በሌጎስ የፖሊስን ጥቃትና ትንኮሳን የሚከታተል የፍትህ አጣሪ ኮሚቴ ስብስብ አባል ናት። የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ሳርስ መበተናቸውን ተከትሎም ነው ይህ የፍትህ አጣሪ ኮሚቴ እንዲመሰረት ከፍተኛ ጥያቄ ቀርቦ የነበረው። ሆኖም እሷም ሆነ 20 የተቃውሞው አስተባባሪዎች ደኅንነት አደጋ ላይ ወድቋል። የሪኑም ሆነ የሌሎቹ አስተባባሪዎች የባንክ አካውንት እንዲታገድ ትዕዛዝ ከማዕከላዊ ባንክ ከተላለፈ ሁለት ሳምንታትን አስቆጥሯል። "የፖሊስን ጭካኔ ለማስወገድ የተነሳንበት ጥሩ አላማ እንደ ሽብርተኛ እንደሚያሳየን ማወቁ በጣም ልብ የሚሰብር ነው" በማለት ለቢቢሲ ተናግራለች። ማዕከላዊ ባንክ በበኩሉ የእነዚህን ግለሰቦች የገንዘብ ምንጭን ለማጣራት በሚል ለሦስት ወራት ያህል የባንክ አካውንታቸው እንዲታገድ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተላልፏል ብሏል። ጠበቃዋም ትዕዛዙን በመቃወምም እየሞገቱ ነው። "ይሄ የመጀመሪያው ነው" ሌላኛዋ ሳርስ እንዲበተን ስትሟገት የነበረችው ጠበቃ ሙዱፔ ኦዴሌም ባለፈው ወር ፓስፖርቷን ተነጥቃለች። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ለእስር የተዳረጉ ግለሰቦችን ወክላም ሙያዊ እርዳታዋን ስትለግስ ነበር። ባለፈው ሳምንትም በፌሚኒስቶች ጥምረት የተቋቋመ ድረ ገፅ ተዘግቷል። በአስር ሴቶች የተቋቋመው ይህ ድረ ገፅ የተዛባ የሥርዓተ- ፆታን መዋቅር ለማቃናት የተቋቋመ ሲሆን በተቃውሞውም ላይ ከፍተኛ ሚና ነበረው። ድረ-ገፁን የዘጋው አካልም ሆነ ለምን ተዘጋ የሚለው ጉዳይ ግልፅ አይደለም። የታዋቂው አፍሮ ቢት ሙዚቀኛ ፌላ ኩቲ እናት ፉንሚላዮ ራንሶም ኩቲ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች 385 ሺህ ዶላር ማሰባሰብ ችለዋል። የተወሰነውንም ገንዘብ በተቃውሞው ለታሰሩት የሕግ ባለሙያ ምክር እንዲያገኙ ለማስቻል፣ ለቆሰሉት የህክምና ወጪ፣ በተቃውሞውም ላይ የግል ጥበቃን ለመቅጠርና በየዕለቱም ለሻይና አንዳንድ ወጪዎችም ውሏል። ቀሪው የተሰባሰበውም ገንዘብ በፖሊስ ጭካኔ ጥቃት ለደረሰባቸውና በፖሊስ ለተገደሉ የጥቃት ሰለባ ቤተሰብ አባላትና እንዲሁም ለአዕምሮ ጤና ማማከር አገልግሎት ይውላል ተብሏል። በፖሊስ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎችም ማስታወሻ የሚሆኑ ተግባራትንም ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ይዟል። "ይህ በናይጄሪያ ወጣቶች የመንቃት ሁኔታ ጅማሮ ነው። አገሪቷ ያለችበትን ሁኔታ ለማሻሻል ብዙ እንሰራለን" በማለት የፌሚኒስት ጥምረት መስራች ከሆኑት መካከል ፋክሪያህ ሃሺም ለቢቢሲ ተናግራለች። "ይህንን ትግላችን እንቀጥላለን በተለይም በሴቶች ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት" ብላለች። ናይጄሪያ ስር የሰደደ የሴት ጭቆና ያለበት አባዊ (ፓትርያርካል) ማኅበረሰብ የሰፈነባት አገር ብትሆንም ሴቶች ለውጥን በመሻት ከፍተኛ ድምፅ በማሰማት ይታወቃሉ፤ በተለይም በቅኝ ግዛት ትግል ወቅት። ከዚህም ጋር ተያይዞ ሳርስ መበተን አለበት በማለት ተቃውሞውን የሚመሩት ሴቶች መሆናቸውን ባለስልጣናቱን ማስደነቅም ሆነ ማስደንገጥ አልነበረበትም። በጎሮጎሳውያኑ 1929 የአባ ሴቶች አመፅ ወይም (የሴቶች ጦር) መነሻው በደቡባዊ ናይጄሪያ የሚገኙ የገበያ ሴቶች ላይ ግብር መጣሉን ተከትሎ ነው። ለሁለት ወራትም ያህል በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ተቃውሟቸውን በቅኝ ገዥዎች ባለቤትነት ስር ያሉ ሱቆች፣ ባንኮችና ፍርድ ቤቶች በማቃጠል ገለፁ። በመጨረሻም የቅኝ ገዢዎቹ አስተዳዳሪዎች እቅዳቸውን መከለስ ነበረባቸው። ከአባ ሴቶች አመፅ 18 ዓመታት በኋላ የታዋቂው አፍሮ ቢት ሙዚቀኛ ፌላ ኩቲ እናት ፉንሚላዮ ራንሶም ኩቲ በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦች ላይ የተጣለውን ግብር በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን አደራጅታለች። 'የሊሳቢ አንበሲት' የሚል ቅጥያ ስም የተሰጣት ፉንሚላዮ ለነፃነት በተደረገው ትግል እንዲሁም የሴቶችን ጥያቄም በማጉላት ከፍተኛ አስተዋፅኦን በማበርከት ታሪክ ያስታውሳታል። አቤኩታ ተብሎ የሚጠራውም የሴቶች ማኅበራቸውም 20 ሺህ ሴቶች አባላትን የያዘ ሲሆን በፅናታቸውም ይታወቃሉ። "በናይጄሪያ ታሪክ ውስጥ ለመብታቸው የታገሉ በርካታ ሴቶች አሉ፤ ጠመንጃም ያነሱ በርካቶች ናቸው። ሴቶች የታገሉባቸው የጦር አውድማዎች ወይ ተዘንግተዋል ወይም ከታሪክ ተፍቀዋል" ትላለች የሴቶች መብት ተሟጋችና ሳርስ ይበተን ስትል የተቃወመችው ንዲ ካቶ። የሳርስ ይበተን የጀርባ አጥንት በቺቦክ ግዛት በፅንፈኛው ታጣቂ ቡድን ቦኮ ሃራም ታግተው የተወሰዱ ታዳጊ ሴት ተማሪዎችን ለማስመለስ ባለፉት ስድስት ዓመታት ስትሰራ የነበረችውና የ'ብሪንግ ባክ አወር ገርልስ' እንቅስቃሴ አንደኛዋ መስራች አይሻ የሱፉ በዚህም ተቃውሞ ውስጥ አንደኛዋ ተሳታፊ ነበረች። በመዲናዋ አቡጃ ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ በመርጨት ተቃዋሚዎችን ለመበተን ሲሞክር አይሻ ፍንክች አለማለቷ ብዙዎችን አስደንቋል። በፅናት ፖሊሶችን መጋተሯም የሚያሳየው ፎቶ የሳርስን መበተን ለሚቃወሙ ሰልፈኞችም ምልክትና አርአያ ሆናለች። ሴቶች የፖሊስ ጭካኔን የሚቃወመው ሰልፍ የጀርባ አጥንት መሆናቸው ለአይሻ አስገራሚ አይደለም። "ሴቶች ሁሉን ነገር በማከናወን ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ። በአገሪቱ ላይ ለውጥ ያመጡ የተቃውሞ ሰልፎችንም ብናይ የተመራው በሴቶች ነው" ትላለች። "የሳርስ መበተን ተቃውሞም እንዲህ የተሳካው ሴቶች በተጫወቱት ከፍተኛ ሚና ነው። በተለይም የፌሚኒስቶች ጥምረት ተግባርና ትብብር በጣም አስደናቂ ነው። እነዚህ ሴቶች አስገራሚ ናቸው" ብላለች። አይበገሬዎቹ ንዲ ካቶ ትግሉ ገና እንደተጀመረ ትናገራለች "ወጣቶች ተመልሰው ድምፃችን የሚሰማበትን የተለያዩ መንገዶች ለመንደፍ እየሞከርን ነው። ተቃውሞውን አላቆምንም።" ሳርስን ለመበተን በተደረገው ትግል ሴቶች በማኅበራዊ ሚዲያም ሆነ መሬት ላይ ድምፃቸው እንዲሰማ የሄዱበትን መንገድም ለሴቶች እኩልነት በሚያደርጉት ትግልም መጠቀም እንዳለባቸው አይሻ ትናገራለች። "ከፌሚኒዝም ባሻገር ሴቶች በኃይል አሰላለፉ ላይ መምጣት አለባቸው። ቦታ እንዲሰጠን መጠየቅ የለብንም እኛ ነን መፍጠር ያለብን" ትላለች። "በፖለቲካው መሳተፍ ለምትፈልግ ማንኛዋም ሴት ጊዜው አሁን ነው። ራሳችንን መጠራጠር የለብንም። የሚገባንን ድርሻ እንጠይቅ ለዚያ ደግሞ ምንም አይነት ምክንያት አያስፈልገውም" በማለትም ታስረዳለች። ሙዱፔ ኦዴሌም ትግሉ ይቀጥላል ትላለች። "መጪው ጊዜ ለሴቶች ብሩህ ነው። ምን ማከናወን እንደምንችል ተረድተናል። ሴቶች ለማኅበረሳባቸውም ሆነ ለራሳቸው የሚፈልጉትን ማከናወን ከወሰኑ ማንም የሚያስቆማቸው የለም" በማለትም አፅንኦት ሰጥታለች።
news-51217774
https://www.bbc.com/amharic/news-51217774
በትራምፕ የድጋፍ ደብዳቤ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት
በአዲግራት ከተማ ተወልዳ ያደገችው አጸደ ንጉሥ 2ኛ ደረጃ ትምርቷን በያለም ብርሃን፤ የመሰናዶ ትምህርቷን ደግሞ በአግአዚ ትምህርት ቤት ተከታትላለች።
አልገፋችበትም እንጂ ለከፍተኛ ትምህርት የሚያበቃትን ነጥብ አምጥታ ሐዋሳ ዩኒቨርስቲም የዲግሪ ትምህርቷን መከታተል ጀምራ ነበር። ይሁን እንጅ ከሁለት ዓመት በፊት በገዛ ባለቤቷ የተፈጸመባት አሰቃቂ ጥቃት የሕይወቷን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ለውጦታል። "እናቴ ብቻዋን ነው ያሳደገችኝ፤ አባቴ ታጋይ ነበር፤ ወደ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ የወሰደኝ ኑሮን ለማሸነፍ በሚል ነበር። በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ በሚሠራ አንድ ሕንጻ ውስጥ ሥራ አገኘሁ።" ትላለች። • የደረሰባቸውን ጥቃት በመንገድ ላይ የሚጽፉት የኬንያ ሴቶች • የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት አጸደ በዚያ ጊዜ ነበር ሕይወቷን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያመራ ያደረገውን ባለቤቷን የተዋወቀችው። "እሱ የፌዴራል ፖሊስ ባልደረባ ነበር። በዚያ ወቅት ደግሞ በጅግጅጋ ፖሊስ የፈለገውን ነበር የሚያደርገው፤ ስለዚህ በጣም እፈራው ነበር" ትላለች ጊዜውን ስታስታውስ። የትዳር ጥያቄውን የተቀበለችው ወዳና ፈቅዳ ሳይሆን በፍርሃት እንደነበረ ታስረዳለች። የተወሰነ ጊዜ ጅግጅጋ ከቆዩ በኋላ ወደ ጋምቤላ እንደሚሄዱ ነገራት። በጋምቤላ ከተማ እሱ ባጃጅ እየሠራ እሷ ደሞ ጅግጅጋ ትሠራ እንደነበረው ዓይነት ተመሳሳይ የኮንስትራክሽን ሥራ ውስጥ እየሠራች መኖር ጀመሩ። በዚያው ዓመት፤ በ2004 ዓ.ም መሆኑ ነው፤ ወንድ ልጅ ተገላገለች። አጸደ እየቆየች ስትሄድ ግን "ትዳር ማለት የሕይወትን ሸክም ተካፍሎ ማቅለል ነው" የሚለው ትርጉም እውነት ሆኖ አላገኘችውም። "ባለቤቴ ሞገደኛ ነው፤ በሚረባውም በማይረባውም፤ በትንሹም በትልቁም ይመታኛል፤ ያከራዩኝ ሰዎች ሁኔታችንን ሲያዩ እግዚኦ ይላሉ።" ትላለች የነበረችበትን ሕይወት ወደ ኋላ መለስ ብላ ስታስታውስ። ምንም እንኳን ድብደባው ቢበረታባትም፤ አጸደ እሷ ያደገችበትን ሁኔታ ስለምታውቅ ልጇን ያለ አባት ልታስቀረው አልፈቀደችም። "ልጅ ከወለድኩ በኋላ እኛ አባታችን ስላልነበረ፤ እናታችን እንዴት ተቸግራ እንዳሳደገችን ስለማውቅ ሁሉን ችዬ እኖር ነበር። እንደዚያ ሲደበድበኝ አንድ ቀን እንኳን ለእናቴም ሆነ ለእህቴ ነግሬያቸው አላውቅም፤ አንድም ቀን" ስትል እምባ እየተናነቃት ለቢቢሲ ተናግራለች። ከልጇ ጋር ሁሉን ችላ መኖሯ ግን የኋላ ኋላ መዘዝ ይዞባት መጣ። "የነበርኩበትን ሁኔታ የሚያውቁ ዘመድ አዝማዶች እናነጋግረው ሲሉኝ 'ተው እንጂ! ምንም ቢሆን እኮ የልጄ አባት ነው' እያልኩ ኑሮዬን ቀጠልኩ" ትላለች። ነገሮች በዚህ ሁኔታ ቀጠሉ። በ2007 ዓ.ም ልጇን አዲግራት የምትኖረው እናቷ ጋር እንድትወስደው እሷ ደግሞ ከነበረችበት ሥራ ወጥታ በራሷ ሥራ እንድትጀምር ሐሳብ አቀረበላት። የሰጣት ገንዘብ ግን አልነበረም። ልጇን ትታ መኖሩ እንዳሰበችው ቀላል አልነበረም። ስለ ልጇ ትብሰለሰል ያዘች። ቀኑ ነግቶ አልመሽ አላት። አንድ ቀን "ወይ ከሥራዬ ወይ ከልጄ አልሆንኩ ምን ተሻለ?" ብላ ትጠይቀዋለች። እርሱ ግን ሀሳቧን እና ጭንቀቷን ከመጤፍ ሳይቆጥር ገንዘብ የሚባል የለኝም፤ የማውቀው ነገር የለም ሲል እንደመለሰላት ትናገራለች። በዚህ አንድ ሁለት ሲባባሉ በተነሳ ግጭት በቡጢ ስለመታት ፊቷ አብጦ ነበር። • አሲድን እንደ መሳሪያ • መአዛን በስለት ወግቶ ከፖሊስ ያመለጠው አሁንም አልተያዘም ጋምቤላ ያሉ ዘመዶች እሷና ባሏ ተስማምተው መኖር እንደማይችሉ በመረዳታቸው ተለያይተው እንዲሞክሩት በማሰብ እሷ ወደ አገሯ ሄዳ ሥራ እንደትሰራ ይመክራሉ። በዚህም ተስማምተው 10 ሺህ ብር ሰጥተው አለያዩኝ ትላለች። ወደ አዲግራት እንደተመለሰች አረብ አገር የምትኖር እህቷና እናቷ አግዘዋት ትንሽዬ የውበት መጠበቂያ ምርቶች [ኮስሞቲክስ] መሸጫ ሱቅ ከፈተች። ጥሩ መንቀሳቀስ ጀምራም ነበር። ባለቤቷ ግን ድንገት ወደ አዲግራት ጠቅልሎ በመምጣት በቤተሰብ ግፊት በድጋሚ አብረው መኖር ጀመሩ። ይሁንና አሁንም ሊስማሙ አልቻሉም። ይባስ ብሎ ሱቋ ውስጥ "ማን ገባ? ማን ወጣ?" እያለ መጨቃጨቅ ጀመረ። ከዕለታት አንድ ቀን ባለቤቷ ብድግ ብሎ ወደ አረብ አገር ሄደ፤ ሳይነግራት። ከጂቡቲ ድንበር ደውሎ 8 ሺህ ብር ለደላላዎች ላኪልኝ አላት። በሁኔታው የተደናገጠችው አጸደ ከዚያም ከዚህም ብላ ላከችለት። ከየመን ወደ ሳዑዲ ከተሻገረ በኋላ ደግሞ አረብ አገር ከምትኖረው እህቷ የሒሳብ ደብተር 15 ሺህ ብር እንድታስልክ አደረገ። ሳዑዲ ከገባና ሥራ ከጀመረ በኋላ ግን ጭራሽ መደወል ትቶ እንደተራራቁ ትናገራለች። ሄድኩ ሳይል እንደወጣው፤ ከእለታት አንድ ቀን ደግሞ መጣሁ ሳይላት መጣ- አዲግራት። "አሲድ አይቼ አላውቅም" ቅዳሜ ሐምሌ 8 ቀን 2009 ዓ.ም። አጸደ እዚያች ኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቋ ውስጥ ምሽት ላይ ከጓደኛዋ ጋር እራት በልተው ይጫወቱ ነበር። በጨዋታቸው መካከልም አንድ አፍታ ባለቤቷ ውልብ ሲል አየችው። በዚያ አካባቢ እሱን ማየቷ ደስ ስላላት ጓደኛዋን ትታ ወደ ቤቷ ጉዞ መጀመሯን ታስታውሳለች። ጉዞዋ ቤታቸው በር እስክትደርስ ሰላማዊ ነበር። "ቤታችን ግቢው በር አካባቢ ዝግባና ጥድ አለ። እዚያ ተደብቆ ቆይቶ ድንገት ደፋብኝ። ይሄ ቢጫው ሐያት የሚባለው የዘይት መያዣ ጄሪካን አለ አይደል? በሱ አሲድ ይዞ ነበር፤ ከዚያም ደፋብኝ" ትላለች። በወቅቱ በመላ አካሏ ምን እንደፈሰሰባት የምታውቀው ነገር አልነበረም። "የተደፋብኝ ነገር ጋዝ ነበር የመሰለኝ፤ በእሳት ሊያቃጥለኝ ፈልጎ መስሎኝ ነበር" ትላለች። "ትንሽ ቆይቶ ግን ሰውነቴ መንደድ ጀመረ። ኡኡ እያልኩ ድረሱልኝ ስል ጮህኩ፤ እሱ ግን ባጃጅ አዘጋጅቶ ስለነበር አመለጠ። እናቴም እህቴም ባጃጁን ቢከተሉትም ሊደርሱበት አልቻሉም።" አሁን ከራስ ቅሏ መላ አካላቷ የፈሰሰው አሲድ መላ አካላቷን ቀይሮታል። የዐይን ብርሃኗን አሳጥቷታል። በጠዋት በሙሉ አካሏ ትታው የወጣችበት ቤት ማታ ተመርታ ገባች። አጸደ በሕይወቷ አሲድ አይታ አታውቅም። "ቃሉንም የማስታውሰው ኬሚስትሪ ስንማር ነው። በጭራሽ አይቼ አላውቅም። ሐኪሙም ግራ ገብቶት ነበር፤ ስለዚህ እርዳታ በቶሎ ማግኘት አልቻልኩም" ትላለች። በመጀመሪያ አካባቢ ዐይኗ አካባቢ በተደረገላት ሕክምና የተወሰነ ማየት ጀምራ ነበር። ነገር ግን ዕይታዋ ከአንድ ሳምንት አላለፈም። በዚህ የአሲድ ጥቃት ከዕይታዋ በተጨማሪ አንድ እግሯ፣ ሁለቱም እጆቿ፣ ሙሉ የፊት ገጽታዋ እስከ ደረቷ ድረስ፤ ጸጉሯ፣ የራስ ቅሏ እንዲሁም ጆሮዎቿ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። • ፆታዊ ትንኮሳን ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት ለአርባ ቀናት የተመላለሰችበት የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ብዙም እንዳልረዳት ትናገራለች። ለተሻለ ሕክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ከተላከች በኋላም 40 ቀን የቆየ የአሲድ ጥቃት እንዴት አድርገን እንቀበል ብለው እምብዛምም ሊረዷት እንደማይችሉ እንደነገሯት ታስታውሳለች። ሆኖም በመጨረሻ እኔ ኃላፊቱነት እወስዳለሁ ያለች አንዲት ሐኪም በማግኘቷ እርዳታ ማግኘት እንደቻለች እምባ እየተናነቃት ትናገራለች። "ዐይንሽ መውጣት አለበት" አጸደ በ2010 ዓ/ም መጀመሪያ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ታይላንድ ሄዳ ነበር። ለሁለት ወራት በዘለቀው ሕክምና ከ3 መቶ ሺህ በላይ ብር አስፈልጓት ነበር። ይህንን ወጪ ለመሸፈን አቅሙ ስላልነበራት በተለያዩ አገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና የሌሎች አገር ዜጎች ጭምር ድጋፍ አድርገውላት ሕክምናውን መከታተል ጀመረች። ሆኖም ሕክምናው እንዳሰበችው አልሆነላትም። ከሁሉም በላይ ይመልሱልኛል ብላ ተስፋ ያደረገችበት እና በጉጉት ትጠብቀው የነበረው የዐይን ብርሃኗ መርዶ ይዞ መጣ። አብራት የነበረችው ታላቅ እህቷ አንድ እሁድ ጠዋት በግሏ ይዛው ቆይታ የነበረውን ትልቅ ምሥጢር ነገረቻት። "ኢንፌክሽን እየፈጠረብሽ ስለሆነ መውጣት አለበት ተብሏል አለችኝ" ስትል ዕለቱን በጠለቀ ሐዘን ታስታውሳለች። እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን እሄድ ነበር፤ "ዐይኔን በሰንበት እንዲያወጡት አልፈልግም፤ አገሬ ውሰጅኝ አልኳት" ለእህቴ ትላለች። ሕክምናዋን አቋርጣ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰቸው አጸደ፤ በሴቶች ማኅበር አዲስ አበባ በተቋቋመ ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ማገገሚያ ማዕከል ለስምንት ወር እንድትቆይ ተደረገች። "አንድ ሰው በረዳህ ቁጥር፤ ያንተ ቁስል እየሻረ ይሄዳል" ወ/ሮ መንበረ አክሊሉ በዚህ ማገገሚያ ማዕከል ሳለች በአርቲስት አዜብ ወርቁ በኩል አንዲት እገዛ ልታደርግላት የምትችል ሴት አገኘች፤ ይቺ በጎ አድራጊ ሴት ወ/ሮ መንበረ አክሊሉ ናት። በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የምትኖረው መንበረ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን በማገዝ ስሟ የሚጠራ በጎ አድራጊ ናት። በወንዶች የሚፈጸም ጥቃትን ጊዜ ሳትሰጥ የምታግዝበት ምክንያት እርሷም ኢትዮጵያ ሳለች ያለ ፈቃዷ በልጅነቷ ያገባቸው ሰው ያደረሰባት ግፍና መከራን በማስታወስ እንደሆነ ትገልጻለች። "ሲጋራውን ካጨሰ በኋላ፤ ፊቴ ላይ ይተረኩሰው ነበር፤ አፍንጫዬን እስከመስበር የደረሰ ጥቃት ያደርስብኝ ነበር፤ ሦስት አራት ጊዜ ሊገድለኝ በመሞከሩ በመጨረሻ ቤቴን ለቅቄ እንድጠፋ ሆንኩ። በዚህ ምክንያት ጎዳና ለማደር ሁሉ በቅቼ ነበር በአንድ ወቅት" ትላለች ወ/ሮ መንበረ። አሁን ያ ጊዜ አልፎ መልካም ትዳርና ጥሩ ሕይወት እየመራች እንደሆነ ትናገራለች። በአጸደ የደረሰውን የአሲድ ጥቃት በማህበራዊ ሚዲያ በኩል መስማቷን የምትናገረው መንበረ፤ ከባለቤቷ ጋር በመመካከር እሷን ለመርዳት እንደወሰኑ ለቢቢሲ ገልጻለች። "እሷ ላይ የደረሰውን ስመለከት እንደ ማንኛውም ዜጋ ሐዘን ተሰማኝ። በተለይ ልጅ እንዳላት ስሰማ አዘንኩ። እኔም እናት ስለሆንኩ ራሴን በእሷ ቦታ አስቀመጥኩት፤ በዚህ ልቤ እጅግ ተነካ፤ ከዚህም በተጨማሪ እኔም ያለፍኩበት መንገድ ስለሆነ እሷን ማገዝ አለብኝ ብዬ ተነሳሁ።" መንበረ በአሲድ የተጠቃችን ዜጋ ስታግዝ አጸደ የመጀመሪያዋ አይደለችም። በፈረንጆቹ በ2017 ዓ.ም አንዲት መሠረት የምትባል በፍቅረኛዋ አሲድ የተደፋባት ሴት ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ በመውሰድ ሕክምና እንድታገኝ አድርጋለች። መሠረት አሁን በመልካም ጤንነትና በጥሩ መንፈስ አሜሪካ ራሷን ችላ እየኖረች ትገኛለች። አጸደን ወደ አሜሪካ ለመውሰድም ለመንበረ መንገዱ አልጋ በአልጋ አልነበረም። ሦስት ጊዜ ያህልም በአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳዩ ተቀባይነት አላገኘም ነበር። በመጨረሻም ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ደብዳቤ ጽፋ፤ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትዕዛዝ ነበር የተሳካው ትላለች። የአጸደ ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ የምትናገረው መንበረ "አሁን አጸደ ዐይነ ስውር ናት። ሆኖም በቅርቡ ማየት እንደምትችል እርግጠኛ ነኝ" ስትል ሙሉ ተስፋዋን ትገልጸላች። "ራሴን ስለምወደው ነው እሷን ለማገዝ የወሰንኩት። ምክንያቱም አንድ ሰው ባገዝክ ቁጥር ያንተ ቁስል እየሻረ ይሄዳል። ምናልባትም እኔ ያደረኩት ነገር አይተው ሌሎች ሰዎችም ሌሎችን ማገዝ ይጀምሩ ይሆናል።" ትላለች መንበረ። አጸደ አሁን ከመንበረ ጋር እየኖረች ትገኛለች። መንበረ የአጸደን የሕክምና ሁኔታ እና በሕይወቷ ስላሳደረችባት አዎንታዊ ተጽእኖ በማህበራዊ ሚዲያ ጽፋ ነበር። አጸደ በበኩሏ ስለሷ የምትናገርበት ቃላት እንደሌላት ትናገራለች። ስላደረገችላት ነገር መናገር ስትጀምር ከቃላት ቀድመው እምባዎቿ ዱብ ዱብ ይላሉ። "ዓለም የሁላችንም ናት" አጸደ በአሜሪካ ያካሄደችውን ሕክምና እንደወደደችው ትገልጸላች። በተደረገላት የመጀመሪያ ቀዶ ጥገና የዐይን ክዳን እንደተሰራላት ትገልጻለች። አሁን ዐይኗን መክደንና መግለጥ ትችላለች፤ የአሲድ ጥቃቱ የዐይን ብርሃኗን ብቻም ሳይሆን የዕይን ሽፋኗን ሙሉ በሙሉ አጥፍቶት ነበር። በቅርቡ ደግሞ እዚያው አሜሪካ ለመኖር የሚያስችላትን ፍቃድ አግኝታለች። ይህ ደግሞ ከእሷ ተለይቶ ኢትዮጵያ የሚገኘው ልጇን ወደ አሜሪካ ለመውሰድ የሚያስችላት ነው። አጸደ ስለ ሕይወት ያላት ትርጉም የሚደንቅ ነው። "መልኬን አይቼው አላውቅም። እኔ ከ2 ዓመት በፊት የነበረችው አጸደን እንጂ አሁን ያለችውን አጸደን አይቻት አላውቅም" ትላለች። የደረሰባት አካላዊ ጥቃት ሕይወቷን እንድትጠላ እንዳላደረጋት ግን አስረግጣ ትናገራለች። በተቃራኒው እንዲያውም ለሕይወት መልካም አተያይን አዳብራለች። "ሕይወት የሁላችንም ናት፤ በዚህ ዓለም ብዙ ጨካኝ አለ፤ ብዙ መልካም ሰዎች ደግሞ አሉ። በተለይ አንዳንድ ጊዜ ፈጣሪ እንዲህ ዓይነት ፈተና የሚያመጣብን ዓለም መልካም ሰዎች እንዳሏት እንድናስተውል ይሆን?" ትላለች። አጸደ ከሕክምናዋ ጎን ለጎን ትምህርት ትማራለች። ማየት የማይችሉ ሰዎች የሚጠቀሙበትን የብሬል ትምህርት ተምራ አጠናቃለች። አሁን ደግሞ ኮምፒውተር እየተማረች ነው። "ተምሬ ትልቅ ደረጃ እንደምደርስ እርግጠኛ ነኝ። አላማዬም እሱ ነው። ወደ ኋላ ተመልሼ የምጸጸትበት ነገር አይኖርም።" "እሷ እናቴ አይደለችም፤ የኔ እናት ቆንጆ ናት" የአጸደ ልጅ ሃኒ ነው ስሙ። ትናንት የደረሰባትን በደል፤ ደም ግባቷንና ዕይታዋን አስረስቷታል። አሁን ብርሃኗ ልጇ ነው። ሀኒ ዕድሜው ገና 7 ነው። እኔ በሕይወት የምኖርበት አንዱ ምክንያቴ እሱ ነው ትላለች። ይህ አደጋ አጸደ ላይ ሲደርስ እሱ ገና 5 ዓመቱ ነበር። በአሲዱ ምክንያት የደረሰባትን የገጽታ ለውጥ ሲመለከት ታዲያ በልጅነት አዕምሮው እናቱን ሊለያት አልቻለም። "መጀመርያ ላይ በጣም ፈርቶ ነበር። እናትህ አጸደ እኮ እሷ ናት ሲሉት፤ ኖ ኖ እሷ እናቴ አይደለችም፤ የኔ እናት ቆንጆ ናት" እንዳለ ታስታውሳለች። "አሁን ግን ሁኔታዎችን ስለተረዳ አይዞሽ ይለኛል። እሱ ስላለልኝ ደግሞ እኔ ጠንክሬ በሁለት እግሬ ለመቆም ቻልኩ ትላለች።" አሁን ልጇ በአባቱ ቂም ቋጥሮ ጥላቻ እንዲያሳድር እንደማትፈልግ ትናገራለች። "ልጄ ይቅርታ አድራጊ ሰው እንዲሆን ነው የምፈልገው። እኔም ይቅርታ አድራጊ ሰው እንድሆን እንጂ እንዲህ አድርጎኝ የምል ሰው መሆን አልፈልግም።" ትላለች። "እኔን ሳይሆን የገዛ ልጁን ነው የበደለው" በማለት ልጇ በለጋ እድሜው መሸከም ከሚችለው በላይ ጫና መሸከሙን ትናገራለች። የዘገየ ፍትሕ የአጸደ ጥቃት አድራሽ ዛሬም ድረስ በፍትሕ አደባባይ አልቆመም። በወቅቱ የሚመለከተውን ክፍል ያሳወቀች ቢሆንም ይገኝበታል የሚባልባቸው ቦታዎችን ፈልጎ ለሕግ ለማቅረብ የሚመለከታቸው አካላት ግዴታቸውን እንዳልተወጡ ትናገራለች። በደል የሚፈጽሙ አካላት በወቅቱ ሊጠየቁና የሚገባቸውን ቅጣት እንዲያገኙ የሚያስችል ሕግ እንደሌለ ጨምራ ታስረዳለች። መንበረ በበኩሏ ሕብረተሰብን ከማስተማር ጎን ለጎን በአጥፊዎች ላይ ተገቢውን ቅጣት መጣል እንዲህ አይነት ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ ያግዛል ትላለች። ምክንያቱም ትላለች መንበረ፤ ይህ የአሲድ ጥቃት አጸደን ብቻ አይደለም የጎዳት፤ ልጇን፣ እናቷን፣ እህቷን እንዲሁም መላ ቤተሰቧንም ጭምር ነው። ይህንን በተመለከተ የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋን አነጋግረናቸው ነበር። ይህንን ወንጀል የፈጸመው ሰው ጠፍቶ ከአገር መውጣቱን የገለጹት አቶ አማኑኤል፤ ፖሊስ ከመጀመሪያው ይህንን ጥቃት ስለፈጸመው ሰው የተሟላ መረጃ አለማግኘቱን፤ በኋላም ወደ መሀል አገር ሄዷል በተባለ ጊዜ ደግሞ በአገሪቱ በነበረው ፖለቲካ፤ መሀል አገር ላለው አካል አመልክተው ሊተባበሯቸው እንዳልቻሉ ይገልጻሉ። በአቃቢ ሕግ በኩል ደግሞ መጀመሪያ ችግሩ የነበረው በሕይወት ትቆያለች ወይ የሚለውን ለመገመት አስቸጋሪ ስለነበረ አቃቢ ሕግ በምን አግባብ ይክሰስ የሚለው አልተወሰነም ነበር ይላሉ። "በአካል ማጉደል ከስሶ፤ በኋላ ደግሞ አንድ ጊዜ ከተፈረደበት በኋላ መልሶ በሰው መግደል ልታስፈርድበት ስለማይቻል አስቸጋሪ ነበር" ብለዋል ኃላፊው። በኋላ ግን ሁኔታዎች በሕክምና ከተረጋገጡ በኋላ ግለሰቡ በከባድ የመግደል ሙከራ ተከሷል። አሜሪካ ሆና በ'ስካይፕ' ቃሏን እንድትሰጥ ተደርጎ ምርመራ ተካሄዶ አሁን ተከሶ እድሜ ልክ እንደተወሰነበት አቶ አማኑኤል ይገልጻሉ። ወንጀለኛው በኢንተርፖል ወይም በሌላ መልኩ ወደ አገሩ ሲገባ ይህ ቅጣት ተፈጻሚ ይሆናል። "ምን በድዬህ ነው?" ከዚያች መጥፎ ዕለት ጀምራ አጸደ ባለቤቷን አይታው አታውቅም፤ ስለሱ ሰምታም አታውቅም። በአካል ድጋሚ ብታገኘው ግን አንድ ጥያቄ ልትጠይቀው አንደምትፈልግ ለቢቢሲ ተናግራለች። "ምንድን ነው የበደልኩህ?" የሚል
news-55570797
https://www.bbc.com/amharic/news-55570797
የአሜሪካ ምክር ቤት፡ የጆ ባይደንን የምርጫ ውጤት አረጋገጠ
የአሜሪካ ምክር ቤቶች የጆባይደንን የምርጫ ውጤት አረጋገጡ።
የሁለቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች የተሰጡትን የውክልና ድምጾች (ኤሌክቶራል ቮት) በመቁጠር ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን አረጋግጧል። ኮንግረስ ጆባይደን እና ምክትላቸው ካምላ ሀሪስን ቀጣዮቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ ያገኙትን ድምጽ አጽድቋል። የተሰጡት የውክልና ድምጾች የጸደቁት የሁለቱ ምክር ቤት ተወካዮች በፔንሰልቫንያ እና አሪዞና ግዛቶች የቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው። የአገሪቱ ሕዝብ እንደራሴዎች ተሰብስበው ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የምርጫ ውጤት ዙሪያ በመነጋገር ላይ ሳሉ በድንገት በሺህ የሚቆጠሩ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ምክር ቤቱን ሰብረው ገብተዋል። በዚህም የተነሳ ተቋርጦ የነበረው የምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ቀጥሏል። ዋሺንግተን ውስጥ የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ፍጥጫ አራት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል። በተቀሰቀሰው ግርግር ሳቢያ የዋሺንግተን ከንቲባ በከተማዋ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል። የካፒቶል ሂል አካባቢም ሙሉ በሙሉ ዝግ እንዲሆን ተደርጓል። ከጥቃቱ በኋላ ጆ ባይደን በቴሌቪዥን ቀርበው በቀጥታ ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር"በአሜሪካ ዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል" ብለዋል። ተቀናቃኛቸው ትራምፕም በአስቸኳይ ወጥተው ውንብድና ላይ ያሉ ደጋፊዎቻቸውን አደብ እንዲያሲዙ ጠይቀዋል። ካፒቶል ሒል በነውጥ ላይ እያለ ከዋሺንግተን ዲሲ በሚጎራበቱ ግዛቶች የአሜሪካ ወታደሮች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ሆነዋል። የካፒቶል ሒል ፖሊሶችን ለመደገፍም ኤፍቢአይ ወደ ስፍራው ተሰማርቷል። ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማን ናቸው? ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት በመሆን ተመርጠዋል። ባይደን የባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። ደጋፊዎቻቸው ባይደን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ አዋቂ ናቸው ይሏቸዋል። በእርጋታቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛ በግል ሕይወታቸው አሳዛኝ ክስተቶችን አሳልፈዋል። ባይደን የፖለቲካ ሕይወታቸው የጀመረው ከ47 ዓመታት በፊት ነበር። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ጥረት ማድረግ የጀመሩት ደግሞ ከ33 ዓመታት በፊት እአአ 1987 ላይ። ባይደን በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት አላቸው። የቀረቡባቸው ክሶች ከአንድ ዓመት በፊት 8 ሴቶች ባይደን ጾታዊ ትንኮሳ አድርሰውብናል በማለት አደባባይ ወጥተው ነበር። እነዚህ ሴቶች ባይደን ባልተገባ መልኩ ነካክቶናል፣ አቅፎናል አልያም ስሞናል የሚሉ ክሶችን ይዘው ነው የቀረቡት። ይህንን ተከትሎ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ባይደን ከዚህ ቀደም በይፋዊ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ሴቶችን በጣም ተጠግተው ሰላምታ ሲሰጡ የሚያሳዩ ምስሎችን አውጥተው ነበር። በአንዳንድ ምስሎች ላይ ደግሞ ባይደን ሴቶችን በጣም ተጠግተው ጸጉር የሚያሸቱ የሚመስሉ ምስሎችን አሳይተዋል። ከወራት በፊትም ረዳታቸው የነበረች ታራ ሬዲ የተባለች ሴት ባይደን ከ30 ዓመታት በፊት ከግደግዳ አጣብቀው ወሲባዊ ትንኮሳ ፈጽመውብኛል ብላ ነበር። ባይደን በበኩላቸው "ይህ በፍጹም አልተከሰተም" በሚል አስተባብለዋል። ስህተቶችን ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ባይደን በዋሽንግተን ፖለቲካ ውስጥ ረዥም ልምድ አላቸው። 8 ዓመታትን በተወካዮች ምክር ቤት፣ 8 ዓመት ሴናተር በመሆን፣ 8 ዓመት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን አገልግለዋል። ይህ ግን ፕሬዝደንታዊ ምርጫን ለማሸነፍ ሁሌም በቂ አይሆንም። 28 ዓመታትን በሴኔት ውስጥ ያሳለፉት ጆና ኬሪ እንዲሁም 8 ዓመታትን በሴኔት እንዲሁም 8 ዓመታት ቀዳማዊት እመቤት ሆነው ያገለገሉት ሂላሪ ክሊንተር ከነሱ ያነሰ የፖለቲካ ልምድ ባላቸው እጩዎች ተሸንፈዋል። የባይደን ደጋፊዎች ግን ባይደን ይህ እጣ እንደማይገጥማቸው ተስፋ አድርገዋል። ረዥም ታሪክ ባይደን ባለፉት አስርት ዓመታት በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ በተላለፉ ቁልፍ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ውስጥ ተሳትፎ አላቸው ወይም ተሳትፎ እንዳላቸው ይነገራል። ይህ ታዲያ አሜሪካ አሁን ባለችበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ በጥሩ መልኩ የሚታይ አይደለም። ለምሳሌ እአአ በ1970ዎቹ በአሜሪካ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጥቁር እና ነጭ ተማሪዎችን ለማሰባጠር ተማሪዎች ከሚኖሩባቸው ቦታዎች በአውቶብስ በሟጓጓዝ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመመደብ የተደረገውን ጥረት ተቃውመው ነበር። በዚህም ዘንድሮ ባካሄዱት የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሲተቹ ቆይተዋል። እአአ 1991 ላይ የባህረ ሰላጤውን ጦርነት ተቃውመው እአአ 2003 ላይ አሜሪካ ኢራቅን እንደትወር ደግፈዋል። መልሰው ደግሞ ባይደን አሜሪካ ወደ ኢራቅ መሄዷ ትክክል አልነበረም በማለት ትችት ሲሰነዝሩ ተሰምተዋል። ባይደን ባለቤታቸውን እና ሴት ልጃቸውን በመኪና አደጋ ምክንያት በሞት ተነጥቀዋል። ባይደን የመጀመሪያ የሴኔት ድላቸውን ተከትሎ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ባለቤታቸው የመኪና አደጋ አጋጥሟቸው ነበር። ባለቤታቸው እና ሴት ልጃቸው ሕይወታቸው ሲልፍ ሃንተር እና ቤኡ የተባሉት ሁለት ወንድ ልጆቻቸው ላይ ጉዳት ደርሷል። ቤኡ እአአ 2015 ላይ በአእምሮ ኢጢ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። በሕይወት ያለው ቀሪው ልጃቸው ሃንተር ጠበቃ ሆነ። ገንዘብ ግን ሕይወቱን ከቁጥጥር ውጪ አደረገበት። ከዚያም ሃንተር ከባለቤቱ ጋር ተፋታ። በፍቺው ወረቀት ላይ የሃንተር የቀድሞ ባለቤት ሃንተር አልኮል እና አደንዛዥ እጽ እንደሚጠቀም እንዲሁም የምሽት መዝናኛ ክበቦችን እንደሚያዘወተር ገልጻለች። ሃንተር በተደረገለት ምርመራ ኮኬይን በሰውነቱ ውስጥ በመገኘቱ ከአሜሪካ ጦር ባህር ኃይል ተጠባባቂነት ተሰርዟል። ከዛም ሃንተር ባለፈው ዓመት አንድ ሳምንት ብቻ ካወቃት ሴት ጋር ትዳር መስርቷል። ይህም የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ካምላ ሃሪስ ማን ናቸው? ካምላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ታሪክ ሰርተዋል። ይህም ብቻ የመጀመሪያዋ ጥቁር እና እስያ አሜሪካዊ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን በታሪክ መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ። ካማላ ሕንዳዊ ከሆኑት እናታቸው እና ጃማይካዊ ከሆኑት አባታቸው በካሊፎርኒያ ነበር የተወለዱት። የ55 ዓመቷ የካሊፎርኒያ ሴናተር በዚህ ወሳኝ ወቅት ከተመራጩ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋር በመሆን አሜሪካንን ለቀጣይ አራት ዓመታት ይመራሉ። ካማላ ገና በልጅነታቸው ወላጆቿ መፋታታቸውን ተከትሎ እናታቸው ነበሩ ያሳደገቿው። የካማላ እናት እውቅ የካንስር ሕመም ተመራማሪ እና የመብት ተሟጋች ነበሩ። ካማላ አስተዳደጋቸው የህንድ ባህል የተከተለ ነበር። ከወላጅ እናታቸው ጋር በተደጋጋሚ ለጉብኝት ወደ ህንድ ይጓዙ ነበር። ይሁን እንጂ ካማላ ወደ ፖለቲካው ከገቡ በኋላ ወላጅ እናታቸው ያሳደጓቸው የጥቁር አሜሪካውያንን ባህል እና አኗኗርን በተከተለ መልኩ ነበር። "እናቴ ሁለት ጥቁር አሜሪካውያንን እያሳደገች እንደሆነ ነው የምትረዳው። ያደግነበት ማህብረስብ እኔን እና እህቴን እንደ ጥቁር ሴቶች አድርጎ እንደሚቀበለን ተረድታ ነበር" በማለት ካማላ የሕይወት ታሪካቸውን በያዘው መጽሐፍ ላይ አስፍረዋል። ካማላ በልጅነት እድሜያቸው በካናዳ ኖረዋል። ወላጅ እናታቸው ካናዳ በሚገኘው ማክጊል ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ። በካናዳዋ ሞንትሪያል ለአምስት ዓመታት ኖረዋል። የኮሌጅ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ደግሞ በአሜሪካዋ ሆዋርድ ዩኒቨርሲቲ ነው። ከአራት ዓመታት የትምህርት ቆይታ በኋላ ካማላ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ለመስራት ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያን ተቀላቅለዋል። ካማላ ዐቃቤ ሕግ በመሆን ረዘም ላለ ዓመታት አገልግለዋል። እአአ 2003 ላይ ካማላ የመጀመሪያዋ የካሊፎርኒያ ጥቁር ሴት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በመሆን ተመርጠዋል። እአአ 2014 ላይ የሕግ ባለሙያ ከሆኑት ዶግ ኤምሆፍ ጋር ትዳር መስረተዋል።
news-48250897
https://www.bbc.com/amharic/news-48250897
የሥራ ቃለመጠይቅ ማድረግ ያስፈራዎታል? መፍትሄዎቹን እነሆ
ዓመታትን ተምረው ሲመረቁ፣ በሰለጠኑበት ሙያ ሥራ ማግኘት ፈታኝ ሲሆን፣ በዛ ላይ ደግሞ አሠሪዎች ምን እንደሚፈልጉ ሳያውቁ ሲቀር በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል። ሠራተኞችን የመቅጠሪያ ዘዴ በየጊዜው የሚለዋወጥ ቢሆንም አካላዊ ቃለ-መጠይቅ ግን እስካሁን ያልተቀየረ የምልመላ ወሳኝ አካል ነው።
ቃለመጠይቅ አሁንም ሠራተኞችን ለመመልመል ወሳኝ ዘዴ ነው "ቃለ-መጠይቅ እስካሁን ለማንኛውም የሥራ ምልመላ በጣም አስፈላጊው ሠራተኞችን የመለያ መንገድ ነው" የምትለው ጄን ቲፕን በሎይድ ባንኪንግ ግሩፕ የሰው ኃይል ባለሙያ ናት። ከሰው ፊት ሃሳብን መግለፅና ጥያቄዎችን መመለስ መቻል የሰዎችን ሥራ የማግኘት እድል ይወስናል ትላለች። • "ሊወልዱ እያማጡም የእናታቸውን ስም ነው የሚጠሩት" ሚዲዋይፍ በቃለመጠይቅ ጊዜ የሚረዱ ጥቂት ነጥቦች እነሆ፡ 1.ስለመሥሪያ ቤቱ ጥናት ያድርጉ ቃለመጠይቁ ምን ዓይነት ሊመስል እንደሚችል ጥናት ያድርጉ በመጨረሻ የሚፈልጉትን ስራ አግኝተው ለቃለመጠይቅ ከደረሱ ከቃለመጠይቁ በፊት ስለ ድርጅቱ በቂ ጥናት ማድረግዎን እንዳይዘነጉ። ጥናትዎ ድርጅቱ ምን አይነት ሥራ ላይ ነው የተሰማራው? አመታዊ ገቢው ምን ያህል ነው? አለቃው ማን ነው? የሚሉትን ጥያቄዎችና የድርጅቱን ቀንደኛ ተፎካካሪዎች ለማወቅ ይሞክሩ። ስለድርጅቱ ለማጥናት ሲፈልጉም ከድረ-ገፅ መጀመር ስራን ያቀላል። ድርጅቱ ላይ ካደረጉት ጥናት ባለፈ ቃለ መጠይቅ የሚያደርግልዎትን ኃላፊ ለማወቅ ይሞክሩ። ቃለመጠይቁም ካለቀ በኋላ የሚጠይቁት ጥያቄ ማዘጋጀት ስለድርጅቱ ያለዎትን እውቀትና ፍላጎት ስለሚያሳይ የተመራጭነት እድልዎትን ያሰፋል። 2.ሊጠየቁ የሚችሏቸውን ጥያቄዎች ይለማመዱ ጓደኞችዎን ደርድረው ቃለመጠይቅ ማድረግ ይለማመዱ ቃለመጠይቅ ከመግባትዎ በፊት ሊጠየቁ ይችላሉ ብለው የሚያስቧቸውን ጥያቄዎች መርጠው በመመለስ ይለማመዱ። ጥያቄዎቹ ከከበድዎት የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዴት ባለ መልኩ መመለስ እንዳለብን የሚያስረዱ ድረ-ገፆችን መመልከት ይችላሉ። • ያለ እናት የመጀመሪያው የእናቶች ቀን መልስዎትን ሲያዘጋጁ ብዙ ጊዜ ካሳለፏቸው የሥራ ልምዶች ምሳሌዎችን እየወሰዱ ቢሆን ይመረጣል። ምሳሌዎትንም መቼ፣ የትና እንዴት እንዳደረጉት በመግለፅ ጥልቀት ይስጡት። የሚሰጧቸው መልሶች ከባለፈው የሥራ ልምድዎ ተነስተው በአዲሱ የሥራ ዘርፍ ላይ የሚፈጥሩትን መልካም እሴት ቢያስረዱ መልካም ነው። 3.ቀልብን የሚገዛ አለባበስ ይልበሱ ራስዎን ከተጠራጠሩ በደንብ በመልበስ የራስ መተማመንዎን ይጨምሩ የመጀመሪያ እይታ አሁንም ወሳኝ ነው። አንዳንድ ቀጣሪዎች ውሳኔያቸውን የሚያደርጉት በ30 ሰከንድ ውስጥ ነው። አንዴ የአሰሪዎን ቀልብ ካልገዙ አስገራሚ መልሶችን ቢመልሱም ስራውን የማግኘት እድሎ ይጠባል። ድርጅቱ የአለባበስ ምርጫ ባይኖረውም በቃለመጠይቅዎ ጊዜ ግን በጅንስ እንዲመጡ አይጠብቁም። ሥራ ቀጣሪዎች ሠራተኞች ለቃለመጠይቅ ሲመጡ ለሥራው የሚመጥነውን "ፕሮፌሽናል" ልብስ እንዲለብሱ ይጠበቃሉ። ለወንዶች ሱፍ በከረባት የተመረጠ እንደሆነ የቀጣሪዎች ሃሳብ ነው። • በብሔር ግጭት የተነሳ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ ቀለል ያለ ቃለመጠይቅ ከሆነ ደግሞ ንፁህና የተተኮሰ ልብስ ቢለብሱ መልካም ይሆናል። 4.አጨባበጥዎን ያስተካክሉ ከቃለመጠይቅዎ በፊት የሚያደርጉት አጨባበጥ ሚና አለው ብዙ ጊዜ ችላ የምንለው ነገር ቢሆንም ሥራ ቀጣሪዎ በእጅ አጨባበጥዎ ሊገምትዎት ይችላል። ትክክለኛ ጠንከር ያለ ሰላምታ ደፋር፣ የሥራ ሰውና ስለራስዎ ያለዎትን በጎ ግንዛቤ ይናገራል። ነገር ግን ከመጠን ያለፈ ጠንካራ ሰላምታ የሚሰጡ ከሆነ የበላይነት ባህሪ እንዳለዎት ሊናገር ይችላል። በሌላ መልኩ እጅዎ ላላ ያለ ከሆነ የማፈርና የመፍራት ባህሪ እንዳለዎት ያሳብቃል። ይሄንንም ለማሻሻል ጓደኞችዎን ሰላም በማለት ተለማምደው እጆትን ማላላት ወይም ማጥበቅ እንዳለብዎት ይለዩ። • ስጋን የተካው "ስጋ" የቃለመጠይቁ ቀን ሰላምታ ሲሰጡ ዓይን ለዓይን መተያየትን አይዘንጉ። ከሰላምታ በፊትም የእጆትን ላብ መጥረጊያ መሃረብ መያዝ እንዳይረሱ ማንም ሰው በላብ የተጠመቀ መዳፍ መጨበጥ አይፈልግም። 5.ፈገግታ እዚህ በመገኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ! ተጨንቀውና በሃሳብ ተውጠው ባሉበት ጊዜ ሌላው ቀርቶ ስሞትንም ሊረሱት ይችላሉ። ፈገግታ በቀላሉ ሰላምታ ማስተላለፍ ሲችል "እዚ ስለተገኘው ደስ ብሎኛል፤ ደስተኛ ሰው ነኝ" ይላል። ስለዚህ በሩን ከፍተው ከገቡበት ቅፅበት ጀምሮ ፊቶን ፈገግታ ባይለየው እድሎትን ያሰፋሎታል። አካላዊ አቀማመጥን በተመለከተ ደግሞ ቀጥ ብሎ መቀመጥ ከፈገግታ ጋር ተጨምሮ መልካም አካላዊ ገፅታ ይሰጥዎታል። 6.ጭንቀት እድልዎን እንዲያሳጣዎት አይፍቀዱለት ከቃለመጠይቅ በፊት ራሶትን ያረጋጉ፤ ትንፋሽ መውሰድ አንዱ መንገድ ነው አድሬናሊን በጣም አስገራሚ ነገሮችን እንድናካሂድ ወይም ደግሞ በጣም የወረደ ስራ እንድንሰራ ሊያደርገን ይችላል። ቃለመጠይቁን ስንደርስ ያጠናናቸውና ለመመለስ የተዘጋጀናቸው መልሶች በሙሉ በነው ሊጠፉ ይችላሉ። ከዚህም አልፈው በአካላዊ ገፅታችን እጃችን ሲንቀጠቀጥ፣ ሲያልበን ወይም ስንደናበር ለሰዎች ሊታይ ይችላል። • ቴምር በረመዳን ለምን ይዘወተራል? እርስዎ እንደዚህ ያለ ጭንቀት የሚያስቸግርዎት ከሆነ ከቃለመጠይቁ በፊት ራስዎን ለማረጋጋት የሚረዱ እንደ ትንፋሽ መውሰድ የመሳሰሉ ልምዶችን ሊያዳብሩ ይችላሉ። መልካሙ ነገር አድሬናሊን የተለየና በጣም አሪፍ ቃለመጠይቅ እንድናደርግ ሊረዳን ስለሚችል ነው። 7.እርስዎን ምን ልዩ እንደሚያደርጎት ይናገሩ በቃለመጠይቅ ላይ እርስዎን ልዩ የሚያደርጎትን ነገሮች ይግለፁ የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት የሆኑት ዴርሞት ሮኒ "ፊት ለፊት የሚደረግ ቃለመጠይቅ ሰዎች ስለራሳቸው ልዩ ተሰጥኦ፣ ፍላጎትና ባህሪ እንዲናገሩ እድል ይሰጣቸዋል" ይላሉ። በቃለመጠየቁ ጊዜ ራስዎን በጥልቀት ማስተዋወቅ መቻል አለብዎት። ከዚህም በተጨማሪ ምን ያህል ሥራውን ለማግኘት ጉጉት እንዳለዎት፣ ድርጅቱን ምን ያህል እንደሚወዱትና መሥራት እንደሚፈልጉ መግለፅ መልካም ነው። 8.ተስፋ አይቁረጡ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የሚችሉትን ጥረት ማድረግ ይቀጥሉ! ቃለመጠይቁ በጠበቁት መንገድ እየተሳካልዎት ባይሆንም እርስዎ ግን እንደማያገኙት ወስነው ከመሞከር መሸሽ የለብዎትም። ቃለመጠይቅ አድራጊዎቹም እንዳልወደድዎት ሊሰማዎት ይችላል፤ ነገር ግን ውሳኔያቸውን ሳይሰሙ አይወስኑ። • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት የሥራ ቀጣሪው የሚፈልገው የእርስዎን ቀጣይ መልስ ሊሆን ስለሚችል ለሁሉም ጥያቄዎች የሚችሉትንና አሪፍ የሚሉትን ይመልሱ።
news-48361902
https://www.bbc.com/amharic/news-48361902
ኢትዮጵያ፡ በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ ምን አለ?
አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ-ሕንፃና የቅርስ ጥበቃ መምህር ሲሆኑ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ከሚደረገው እድሳት ጋር ተያይዞ በበጎ ፈቃደኝነት ያስጎበኛሉ።
እርሳቸው እንደነገሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ መንግሥቱ ከመጎብኘቱ አስቀድሞ 'እንግዶች ስለሚመጡ ባለሙያዎች ቢያስጎበኟቸው ይሻላል' በሚል ከቅርስ ጥበቃ፣ ከኪነ ሕንፃ ባለሙያዎች፣ የታሪክ አዋቂዎች የተውጣጡ ሰባት ባለሙያዎች በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ የተጋበዙ ሲሆን እርሳቸው አንዱ ነበሩ። • ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ምን ይላሉ? በወቅቱም የሚያሰማሙ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው የጋራ ነጥቦች ያዘጋጁ ሲሆን፤ ለጎብኝዎች ገለፃ ሲያደርጉ ነበር፤ በተለያየ ጊዜም ቤተ መንግሥቱን የመጎብኘት ዕድል ገጥሟቸዋል፤ በመጭው መስከረም ወር ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል በተባለው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ? ስንል ጠይቀናቸዋል። ቤተ መንግሥቱ በ40 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በውስጡ የተለያዩ ታሪካዊ ቅርሶች ይገኙበታል። ከስፋቱ የተነሳ ቦታውን ለማስጎብኘት በቤተ መንግሥት ውስጥ ያሉትን ቦታዎች በ5 ይከፍሉታል። አንደኛው በፊት ተትቶ የነበረ የቤተ መንግሥቱ ጓሮ ሲሆን በዚህ ሥፍራ የወዳደቁ ቆርቆሮዎች፣ የወታደሮች መኖሪያ፣ የተበላሹ የጦር መኪኖች የሚቆሙበት ቦታ ሲሆን አሁን እድሳት ተደርጎለት ጥሩ የመናፈሻ ሥፍራ ሆኗል። ሁለተኛው አጤ ሚኒሊክና አጤ ኃይለ ሥላሴ ያሰሯቸው የቤተ መንግሥትና የጽ/ቤት ሕንፃዎች ይገኛሉ። ሦስተኛው የኮሪያ መንግሥት ያሰራቸው ቢሮዎች ሲሆኑ አሁን አገልግሎት እሰጡ ይገኛሉ፤ ይሁን እንጂ ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት አይሆኑም። አራተኛው በተለያየ ምክንያት የማይጎበኝ ሲሆን ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ካገር በወጡበት ጊዜ ቢሯቸው ይሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች እርሳቸውን ለማስደሰት የሰሩላቸው እዚያው ግቢ ውስጥ ነጠል ብሎ የተሰራ ቤት ነው። • ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ ይህም ብቻውን የተሰራና ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ መኖሪያ ጀርባ ይገኛል። ለመጎብኘትም በመኖሪያቸው ማለፍን ስለሚጠይቅ ለጉብኝት ክፍት አይሆንም። የዚህ ቢሮ የተወሰነ ክፍሉ እንደፈረሰም ይነገራል። አምስተኛው በሸራተን ሆቴል በኩል ሲታለፍ የሚታየውና በፊት ገደላማና ጫካ ሆኖ የሚታየው አዲስ የሚሰራው የእንስሳት ማቆያና አኳሪየም (የውሃ አካል) ሲሆን ግንባታ እየተካሄደበት ነው። አሁን ሙሉ ቤተ መንግሥቱን ልንጎበኝ ነው፤ አርክቴክት ዮሐንስ አንድ ሰው ቤተ መንግሥቱን ለመጎብኘት ሲገባ ከሚያገኘው ይጀምራሉ። 1ኛ. የመኪና ማቆሚያና ሞል ይህ ቦታ ከሒልተን ሆቴል ወደ ላይ አቅጣጫ ስንጓዝ ቤተ መንግሥቱ ከመድረሳችን በፊት በስተቀኝ ይገኛል። ታጥሮ የቆየ ባዶ ቦታ የነበረ ሲሆን አሁን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የአካባቢው ወጣቶች ተደራጅተው የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ይሰሩበታል። በቅርቡ ግንባታው የሚጀመር ሲሆን ለጎብኝዎች የመኪና ማቆሚያ ሆኖም ያገለግላል። ይሁን እንጂ ግንባታው ስላልተጠናቀቀ ሰው የሚገባው በታች ባለው የደቡብ አቅጣጫ በር ነው፤ እዚያ ሲደርሱ የትኬት ቢሮ፣ ሻይ ቤት፣ መታጠቢያ ክፍሎች፣ የእንግዶች ማረፊያና መረጃ የሚሰጥባቸው ቦርዶችና ዲጂታል ማሳያዎችን ያገኛሉ። ይህ የትኬት ቢሮ ከዚህ ቀደም ያልነበረ ሲሆን ከመሬት ጋር ተመሳስሎና ተስተካክሎ የተሰራ በመሆኑ ከላይ ሲታይ ቤት መሆኑ በጭራሽ አያስታውቅም። 2ኛ. የመረጃ መስጫ ቦታ ይህን ሥፍራ ከትኬት ቢሮው ወደ ላይ ሲጓዙ ያገኙታል። በዚህ ቦታ ለጉብኝት ክፍት የሆኑ ቦታዎች በዲጅታልና በህትመት ገለፃ ይደረግበታል። ከጥላ ጋር የተዘጋጀ ማረፊያ ወንበሮች ያሉት ሲሆን ተሰርቶ ተጠናቋል። እሱን አለፍ እንዳልን ልጆች የሚቆዩበት የመጫዎቻ ቦታ እናገኛለን፤ በጣም የተጋነነ ባይሆንም መጠነኛ ተደርጎ ለልጆች መጫዎቻ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ተሟልቶ የተዘጋጀ ነው። • ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት አረንጓዴ ሥፍራ ተብሎ የተሰየመውን ጠመዝማዛ መንገድ ደግሞ የልጆች መጫወቻውን እንዳለፍን እናገኘዋለን። ቦታው ወደ ቤተ መንግሥቱ የሚኬድበት ዳገታማ መንገድ አለው፤ ይህም ለአካል ጉዳተኞች እንዲመች ተደርጎ በእግረኛ መረማመጃ ንጣፍ የተሠራ ነው። ወደፊት በግራና በቀኝ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የጥበብ ሥራዎች አሊያም ታሪካዊ ሁነቶች ማሳያዎች ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፤ አሁን ዛፎችና ሳሮች የተተከሉ ሲሆን መንገዱም ዝግጁ ሆኗል። 3ኛ. የልዑላን ማረፊያ ቦታ ልጅ እያሱ፣ ንግሥት ዘውዲቱ፣ አጤ ኃይለ ሥላሴ ንጉስ ሆነው ከመሾማቸው በፊት በዚህ ቤት ኖረውበታል። ቤቱ በእንጨትና በድንጋይ የተሠራ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ነው። ፊቱን ወደ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ያዞረው ህንፃው በአጤ ሚኒሊክ የተሠራ ሲሆን አዲስ አበባን ቁልቁል ለማየት የሚያስችል ነው። የኪነ ህንፃ ባለሙያዎች 'የአዲስ አበባ መልክ አለው የሚባል የሕንፃ ዓይነት ነው' ይሉታል- ኢትዮጵያዊ ጥበብ ያረፈበት መሆኑን ለመግለፅ። ከፊት ለፊቱ አዲስ የተሠራና ብዙ ሰዎች ሰብሰብ ብለው ፎቶ የሚነሱበት ሥፍራ አለው። በቅርቡ በተደረገው የእራት ግብዣ በነበረው ጉብኝት ቤቱ እንዳይጎዳ በሚል ውስጥ ሳይገባ ከውጭ ነበር የተጎበኘው። 4ኛ. የዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ጽ/ቤትና መኖሪያ ቤት (ኮምፕሌክስ) በዚህ ሥፍራ መጀመሪያ የምናገኘው የፊት አውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴን (አባ መላ) መኖሪያ ነው። አባ መላ የአጤ ሚኒሊክ የጦር ሚንስትር የነበሩ ሲሆን ይኖሩበት የነበረ ትንሽ የእንጨት ቤት ከአጤ ምኒሊክ መኖሪያ ቤት ጎን ላይ ይገኛል። አጤ ሚኒሊክ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላም እንደ መኖሪያና ቢሮ አድርገው ሲጠቀሙበት ነበር። ቤቱ ፈርሶ የነበረ ሲሆን አሁን ሙሉ በሙሉ ታድሷል። ወደ አጤ ሚኒሊክ ባለ አንድ ፎቅ መኖሪያና ጽ/ቤት በሮች በእንጨት የተሠሩ ሲሆን በሚያምር መልኩ የአበባና የሐረግ ጌጥ የተፈለፈለበት ነው። ይህ ቤት ከሁለት ሌሎች ቦታዎች ጋር በድልድይ ይገናኛል። አንደኛው በሰሜናዊ አቅጣጫ የአጤ ምኒሊክ የፀሎት ቤትና የሥዕል ቤት ሲሆን እንቁላል ቤት በመባል ይጠራል። አንዳንዴም እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበት ነበር። የአጤ ሚኒሊክ የግብር አዳራሽ በቀደመው ጊዜ የፀሎት ቤቱና የሥዕል ቤቱ ባለ ሁለት ፎቅ ነው። ሁለተኛው ፎቅ ላይ ከፍ ብላ የተሠራች በመስታወት የተሸፈነች ቤት አለች፤ ይህች ቤት 'ቴሌስኮፕ' ያላት ሲሆን አዲስ አበባን በሁሉም አቅጣጫ ማየት ታስችላለች። በዚች እንቁላል ቤት መገናኛው ድልድይ ጋ የመጀመሪያው ስልክ የገባበት ቤት ይገኛል። ቤቱ ከድንጋይና ከእንጨት የተገነባ ነው። አርክቴክት ዮሐንስ የኪነ ህንፃውን ጥበብ ሲገምቱ ከአርመኖችና ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ሕንዶች ሳይሳተፉበት እንደማይቀሩ ይገምታሉ። ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የውይይት ክበብ በመሆን አገልግሏል። • አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ሌላኛው ከአጤ ሚኒሊክ ቤት ጋር በድልድይ የሚገናኘው የእቴጌ ጣይቱ ቤት ነው። ይህ ቤት ከቤተ መንግሥቱ በምሥራቃዊ አቅጣጫ የሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ነው። በምድር ቤት የዙፋን ግብር ቤት ይገኛል። የነገሥታቱ መመገቢያ አዳራሽ ሲሆን ንጉሣዊ ቤተሰቦች ምግብ የሚመገቡበት ክፍል ነበር፤ ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የደርግ ምክር ቤት መሰብሰቢያ በመሆን አገልግሏል። 5ኛ. ሦስት አብያተ ክርስቲያናት አብያተ ክርስቲያናቱ ከግብር ቤቱ አዳራሽ በስተ ምሥራቅ በኩል ይገኛሉ። የኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን (የአጤ ሚኒሊክ ሥዕል ቤት)፡ በአጤ ሚኒሊክ ጊዜ ለብቻ በአጥር ያስከለሏት ሲሆን አሁን ሕዝብ ይገለገልባታል። ይሁን እንጂ አጤ ሚኒሊክ ከመኖሪያቸው ተነስተው የሚሄዱባት መንገድና በር አሁንም ድረስ ይገኛል። የባዕታ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን (በንግሥት ዘውዲቱ የተሰራ ሲሆን የአፄ ሚኒሊክም አፅም ያረፈው እዚሁ ነው) አሁን ከቤተ መንግሥቱ ውጭ ሲሆኑ ጥበቃ ይደረግለታል። ጎብኚዎችም ሲመጡ እዚያ ያሉት ካህናት ምድር ቤት ያለውን መቃብራቸውን ከፍተው ያሳያሉ። በበርካታ ሰው የሚጎበኝም ከሆነ ለቤተ መንግሥቱ ቀድሞ እንዲታወቅ ይደረጋል። ሦስተኛው ከዚህ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ የሚገኘውም የገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ነው። 6ኛ. ታችኛው የዙፋን ችሎት ይህ ችሎት በአጤ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የተሠራ ሲሆን በታችኛው መዋቅር ያልተፈታ አገራዊ ጉዳይን የሚያዩበት የ'ሰበር ሰሚ ችሎት' ቦታ ነው። ይህ ባለ አንድ ፎቅ ቤት የንጉሡ ጽ/ቤትም በመሆን አገልግሏል። በውስጡ ጽ/ቤታቸውን ጨምሮ መዝገብ ቤትና ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችም አሉት። አጤ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ የደርግ ወታደሮች ቤቱን ተቆጣጥረውት ነበር። የኮሎኔል መንግሥቱ አስተዳደርም ቢሮ አድርጎ ይጠቀምበት ነበር። ንጉሡ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላም ችሎታቸውና ቢሯቸው ከነበረው ቦታ ምድር ቤት እንደተቀበሩና በኋላም አፅማቸው ወጥቶ እንደተወሰደ ይነገራል። የደርግ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ቢሮ፣ የመንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ረዳት የመንግሥቱ ገመቹ ቢሮ፣ እንዲሁም ታስረው የነበሩ ደርግ ወታደሮች የታሰሩበት ቦታም ነው። • በመፈንቅለ መንግሥቱ ዙሪያ ያልተመለሱት አምስቱ ጥያቄዎች በአንድ ወቅት በመንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ላይ የመግደል ሙከራ በተደረገበት ጊዜ ያመለጡበት ቦታም ይሄው ሕንፃ እንደሆነ ይነገራል። ኢህአዴግ አገሪቱን ሲቆጣጠርም የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ይህንን ሕንፃ መኖሪያ አድርገውት ነበር። አቶ መለስ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላም አስክሬናቸው የወጣው ከዚሁ ቤት ነው። በአቶ መለስ ዜናዊ ጊዜ ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን በቤተ መንግሥቱ ውስጥ መኖሪያ ቤት ማሠራት ጀምረው ነበር። ከዚያም በኋላ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መኖሪያ አድርገውት የነበረ ቢሆንም አራት ዓመታትን ከቆዩ በኋላ አዲስ ወደ ተሠራው ቤት ተዘዋውረዋል። ይህም ለጉብኝት ክፍት እንደማይደረግ መረጃ እንዳላቸው አርክቴክት ዮሐንስ ነግረውናል። 7ኛ. የመንግሥቱ ኃይለማሪያም ቤት መንግሥቱ ኃይለማሪያም ባንድ ወቅት ረዘም ላሉ ቀናት ወደ አውሮፓ አቅንተው ነበር። በዚህ ጊዜ ወዳጆቻቸው እርሳቸው ሲመለሱ ለማስደሰት ለመንግሥቱ አዲስ ቤት ለመሥራት ተነጋገረው በጣም በአፋጣኝ ቤት ሠርተውላቸው ነበር። ቤቱ መዋኛ እንደነበረው የሚነገር ሲሆን ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው አርክቴክት ዮሃንስ ገልፀውልናል። 8ኛ. የአንበሶችና ሌሎች እንስሳት ማቆያ ይህ ሥፍራ በቤተ መንግሥቱ ደቡባዊ አቅጣጫ ይገኛል። በብረት ፍርግርግ የተሠራ ትንሽ የእንስሳት ማቆያ ሲሆን በአሁን ወቅት ምንም ዓይነት እንስሳት አይኖሩበትም። ቀደም ሲል የነበሩት እንስሳት ወደ ሌላ ሥፍራ ተዛውረዋል የሚል መረጃ አለ። 9ኛ. በአጤ ሚኒሊክ ጊዜ የተሠራው የጽህፈት ቤት በዚህ ቤተ መዛግብት የተለያዩ መረጃዎች ተሰንደው ይገኛሉ። ዘመናዊ በሆነ መልኩ የተደራጀ ሲሆን ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ የነበሩ ታሪካዊ ሰነዶች ይገኙበታል። ከትምህርት ሚኒስቴር በስተቀር ሌሎች የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በሙሉ ሰነዶቻቸውን ያስቀምጡበት እንደነበር ይነገራል። የደብዳቤ ልውውጦች፣ የብራና ጽሁፎችና ሌሎች የአገር ውስጥ ጉዳዮች የተሰነዱበት ሲሆን አሁን እድሳት ያልተደረገበትና ጎብኝዎችም ወደዚያ መጠጋትም ሆነ ማየት አይችሉም። 10ኛ. የታችኛው ዙፋን ችሎት የዙፋን ችሎቱ በቤተ መንግሥቱ ደቡባዊ አቅጣጫ ፊቱን ወደ ሸራተን ሆቴል አቅጣጫ አዙሮ የቆመ ትልቅ ሕንፃ ሲሆን በአጤ ሚኒሊክ ጊዜ የተሠራ ነው። ከሕንፃው ፊት ለፊት ሰንደቅ ዓላማ መስቀያ ይገኛል። በፊት ለፊቱም ነጋሪት እየተጎሰ፤ እምቢልታ እየተነፋ ትልልቅ የጦርነት አዋጆች የታወጁት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሃገራዊ ጉዳይ የሚነገርበትና የሚታወጅበት አደባባይ አለው። ሕንፃው ምድር ቤት ያለው ሲሆን ከላይ ያጌጠ አዳራሽ አለው፤ አዳራሹ ውስጥ የዘውድ ምልክት ያለው በሃር ከፋይ የተሠራ ዙፋኑን የሚያጅብ መቀመጫ አለ። መሰብሰቢያ አዳራሽ እና በግራና በቀኝ ሰፋፊ ክፍሎች አሉት። በደርግ አስተዳዳር ጊዜ የደርግ ምክር ቤት ሆኖ ለረጂም ጊዜ አገልግሏል። የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሹማምንትም በዚሁ ምድር ቤት ታስረው ነበር። የምክር ቤቱ አባላት ከላይኛው ፎቅ ሆነው 'ይገደሉ አይገደሉ' የሚል ክርክሮች ይካሄዱበት ነበር- በምድር ቤቱ ደግሞ ሞታቸውን አሊያም ሽረታቸውን የሚጠባበቁ እስረኞች ይህን እየሰሙ ይሳቀቁ እንደነበር ይነገራል። ምድር ቤቱ ውስጥ አራት ክፍሎች አሉት። በእነዚህ ቤቶች ወፍራም የብረት ዘንጎች ያሉ ሲሆን ሰዎች ተሰቅለው ይገረፉበት ነበር ይባላል። አሁን በሙዚየሙ እድሳት እንደ አዳራሽ እንዲጎበኝ ሦስት ነገሮች ታስበዋል። • ከኢትዯጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት ሊመለሱ ነው የደርግ ችሎት የነበረው ኢትዮጵያ ተቀብላቸው የነበሩ ትልልቅ ሰዎች እንደ የዩጎዝላቪያው ቲቶ፣ የፈረንሳዩ ቻርለስ ደጎል፣ የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥና የሌሎችም ፎቶ ለዕይታ ተዘጋጅተዋል። በአጤ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ እነዚህ ሰዎች በዚህ አዳራሽ አቀባበል ተደርጎላቸው ስለነበር እነርሱን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ይታዩበታል። ሌላኛው በደቡባዊ አቅጣጫ የመንግሥታት ታሪኮች ለዕይታ ይቀርብበታል፤ አሁን ላይ ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ እስከ አቶ ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ ድረስ ያሉ የኢትዮጵያ መሪዎች ፎቶና በእነሱ ዘመን የተሠሩ ሥራዎች ለዕይታ ይቀርባሉ። በምሥራቃዊው ክፍል አገር የተመሠረተችበት ንግርት (አፈ ታሪክ) አንድ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ ሥነ ልቦና የተዋቀረበት ንግርት ይቀርብብታል። በዚህ አዳራሽ ሰሜናዊ ክፍል ከውጭ የተቀበልናቸውና ሀገር ውስጥ የዳበሩ ኃይማኖቶች ይቀርቡበታል፤ ዋቄ ፈታ ፣ ቤተ እስራኤላዊያን ይከተሉት የነበረው የአይሁድ እምነት፣ ከዚያም እስልምና፣ ክርስትና፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት እንዲሁም ሌሎች የክርስትና እምነቶች በተወጠረ ሸራ ላይ በዲጂታል እንዲታዩ ይደረጋል። ከሕንፃው ወጥተን በደቡባዊ አቅጣጫ ግድግዳው ላይ የብረት ቀለበቶች ይታያሉ፤ እነዚህ ቀለበቶች በዳግማዊ ሚኒሊክ ጊዜ መኳንንቶቻቸው በቅሎዎቻቸውን የሚያስሩበት ቦታ ነበር። በደርግ ጊዜ ደግሞ ኋላ ላይ የተረሸኑት የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሹማምንት እስረኞች ፀሐይ የሚሞቁበት ቦታ ሆኖም አገልግሏል። በ1981 በነበረው መፈንቅለ መንግሥት የተሳተፉት 12ቱ ጀኔራሎችም የታሰሩበት ቦታ ነው። 11ኛ. አዲስ እየተሠራ ያለው አኳሪየም እና የእንስሳት ማቆያ ቦታው ከቤተ መንግሥቱ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን በአፄ ሚኒሊክና በአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ የተጀመረውን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በተሻለ መንገድ ለመተግበር አዲስ እየተሠራ ያለ ሥፍራ ነው። 12ኛ. የአጤ ሚኒሊክ የግብር አዳራሽ ይህ አዳራሽ በጣም ትልቅ አዳራሽ ሲሆን ኪነ ሕንፃው የኢትዮጵያዊያን፣ የአርመናዊያንና የሕንዶች እጅ ያለበት እንደሆነ ይገምታሉ። የግብር አዳራሹ በግምት 8 ሺህ ሰዎችን ያስተናግዳል ተብሎ ይገመታል፤ በዘመኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ያሏቸው በሮች ያሉት ሲሆን በቅርቡም እድሳት ተደርጎለታል።'ገበታ ለሸገር' የእራት ግብዣ የተካሄደውም በዚሁ አዳራሽ ነው። 13ኛ. ትንሿ ኢትዮጵያ ይህ ቦታ ቀድሞ ያልነበረና የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ሃሳብ ነው። ከአዳራሹ በስተ ደቡብ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች የአኗኗር ዘይቤን የሚያሳዩ የሃገረሰብ ኪነ ሕንፃ የሚታይበት ሥፍራ ነው። በአሁኑ ሰዓት ብዙ የተሠራ ነገር ባይኖረውም ሥራው ተጀምሯል። በመጨረሻም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ የሚታደሱትና የሚጠገኑትን ቅርሶች በተመለከተ ቅሬታ ያላቸው ሰዎች መኖራቸውን ያነሳንላቸው አርክቴክት ዮሐንስ "የተሠራው የእድሳት ሥራ የሚያስወቅስ ነው ለማለት እቸገራለሁ፤ ይሁን እንጂ የባለሙያ ተሳትፎና ድጋፍ ቢኖራቸው ከዚህ የተሻለ ማድረግ ይቻል ነበር የሚል እምነት አለኝ፤ ይህንንም በፅሁፍ ለሚመለከተው አቅርቤያለሁ" ብለዋል። ፕሮጀክቱ የተደገፈው በአረብ ኢሜሪትስ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት የወጣ ውጪ አለመኖሩን መረጃው እንዳላቸው ገልፀውልናል።
49631096
https://www.bbc.com/amharic/49631096
2011፡ በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት
የ2011 ዓ.ምን ስንብት አስታክከን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ መልክዐ ምድር የኋሊት ስንገመግም ዓመቱ የስክነትም የውዥንብርም ነበር ማለት እንችላለን።
የቀዳሚውን 2010 ዓ.ም ገሚስ ስልጣን ላይ ያሳለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና መንግሥታቸው ወራቱን ትንፋሽ ለመሰብሰብ እንኳን ፋታ ይሰጥ በማይመስል እንቅስቃሴ፤ በርካታ ስር ነቀል እርምጃዎችን አከታትለው ሲከውኑ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ተችሯቸው ነበር። ሞቅታው ሊረግብ ግን ጊዜ አልፈጀበትም። • የንግድ ሽርክና ከኤርትራ ጋር? • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት • "ለዋጋ ግሽበት የውጪ ምንዛሪ ማሻሻያው ምክንያት ነው" ተከትሎ የመጣው እና አሁን ሊጠናቀቅ ጫፍ ላይ የደረሰው ዓመት ግን ገና በማለዳው ፈንጠዝያው ሰከን ብሎ መረር ያለ እውነታ የተተካበት ሆኗል። በአዲስ አበባ ዳርቻዎች እና በአጎራባች ቡራዩ አካባቢዎች በዓመቱ መባቻ የተከሰቱት የብሔር መልክ ያላቸው ግጭቶች እና ጥቃቶች፣ የዜጎች መፈናቀል፤ ወራት እየተተካኩ ሲሄዱ በበርካታ የአገሪቱ ስፍራዎች ተደጋግመው የዓመቱ አይነተኛ ምልክት ሆነዋል። በርካቶች ተገድለዋል፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፤ ታዳጊዎች ከትምህርታቸው ተነጥለዋል። መንግሥት ለነዚህ ችግሮች የሰጠው ምላሽ የቁጥር ሙግት ውስጥ ከመግባት አንስቶ፤ በተለይ በሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች እርቅን እስከማከናዎን በኋላም ተፈናቃዮችን ወደ መነሻ ቀየዎቻቸው እስከመመለስ የሚደርስ ነው። በክረምት መባቻ የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ከሚል መንግሥታቸው ሁሉንም ተፈናቃዮች የመመለስ ዕቅድ እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል። ከዚህም በዘለለ ለሞት እና መፈናቀል ምክንያት ሆነዋል የተባሉ አካላትን ለፍርድ ማቅረብ መንግሥት አድርጌዋለሁ የሚለው ሌላኛው እርምጃ ነው። ፍርድ ቤቶች እንደቀደሙት ዓመታት ሁሉ በዚህም ዓመት የትኩረት ማዕከል ነበሩ። • ጥቁር ገበያውን ማሸግ መፍትሄ ይሆን? • አየር መንገድንና ቴሌን ለሽያጭ ለማቅረብ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው? ከአንድ ዓመት በፊት በመስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ላይ በተፈፀመና የሁለት ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ከተከሰሱ ሰዎች አንስቶ፤ የሃገርን ሐብት በመመዝበርና ያላግባብ በስልጣን በመባለግ ችሎት እስከተገተሩ ሰዎች ድረስ፤ በኋላም በባህር ዳር እና በአዲስ አበባ በተፈፀሙ የከፍተኛ ባለስልጣናት እና ወታደራዊ መኮንኖች ግድያዎች ጋር በተገናኘ የታሰሩ ተጠርጣሪዎች የችሎት ሒደቶች አትኩሮትን ይዘው ነበር። አንዳንድ ክሶችን የተደበቀ ፖለቲካዊ ዓላማ አላቸው ሲሉ ትችት የሚያሰሙ የመኖራቸውን ያህል የችሎት መጓተት እና የቀጠሮዎች መደጋገምን የቅድመ-ዐብይ ጊዜያትን ያስታውሳል ብለው የሚነቅፉም አሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩን አስተዳደር ክፉኛ ከፈተኑ ጉዳዮች መካከል የአስተዳደራዊ አሃድ ጥያቄዎች ናቸው። ገንነው የተስተዋሉት ክልል የመሆን ጥያቄዎች ሲሆን የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ የበርካቶችን ሞትና ጉዳት አስከትሏል። በወርሃ መጋቢት አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው 'የአዲስ ወግ' መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዋናው ቁምነገር ዋልታ የረገጡ አመለካከቶችን ወደ መካከል ማምጣት እንደሆነ ተናግረው ነበር። ያለፈው ዓመት ግን ተቃርኖዎች እምብዛም ሲለዝቡ አልተስተዋሉበትም። እርሳቸው በሚመሩት እና አገሪቷን እያስተዳደረ ባለው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ውስጥ ያለ ተቃርኖ ገሃድ የወጣበትም ዓመት ነው። በተለይም በግንባሩ ሁለቱ ቀዳሚ አባል ፓርቲዎች ህወሃት እና አዴፓ መካከል ያለው ግልጽ የሆነ የቃላት ጦርነት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚያነሱት የፓርቲ ውህደት የሚጣጣሙ አይመስሉም። ፍትጊያው የጎንዮሽ በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ብቻ አልነበረም፤ ኢሕአዴግ ሙሉ በሚያስተዳድረው ፌደራል መንግሥት እና የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በሚያስተዳድሯቸው የክልል መንግስታት ጭምርም እንጅ። ይህም ፌደራላዊው መንግሥት የአስፈፃሚነት አቅም አንሶታል ለሚሉ ትችቶች ተዳርጓል። 2011 የሰልፍ ዓመትም ጭምር ነበር። ሐኪሞች፣ መምህራን እንዲሁም ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎቻችን አልተመለሱም ያሉ በርካታ ዜጎች አደባባይ ወጥተዋል። በምጣኔ ኃብት ረገድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት ጋር ተያይዞ ገዥው ፓርቲ ከዚህ ቀደም እከተለዋለሁ ይለው ከነበረው መንግሥታዊ ተሳትፎን የሚያበረታታ ፖሊሲ ማፈንገጥ መጀመሩ በተንታኞች ይወሳል። የተገባደደው ዓመት ይህን የፖሊሲ ለውጥ የሚያመላክቱ እርምጃዎች ሲወስዱ የተስተዋለበት ሆኖ አልፏል። በአንድ በኩል መንግሥት ለወትሮው አይነኬ መሆናቸውን ይናገርላቸው ከነበሩ የልማት ድርጅቶች እና ዘርፎች መካከል አንዳንዶቹን ለግል ባለሃብቶች ክፍት እንደሚያደርግ ካሳወቀ በኋላ በተሰናባቹ ዓመት የክንውን ዕቅዱን በተመለከተ በአንፃራዊነት የተሻለ መረጃ ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ለምሳሌ የግል ባለሃብቶች ከግዙፉ ኢትዮቴሌኮም ድርሻ መገብየት እንደሚቻላቸው ይህም ተቋም በከፊልም ቢሆን ወደግል በመዛወር በቅድሚያ ከሚሰጣቸው መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል። ትርፋማው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለግል ባለሃብቶች ክፍት ይሆናል መባሉ ግን ከተለያዩ ተችዎች ነቀፌታን አስተናግዷል። በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የንግድ ክንውን ለማሳለጥ ያግዛሉ የተባሉ የሕግ እና የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ ብሎም ወደስራ ለመግባት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የተደረጉ ውይይቶችን ለሕዝብ ሲያሳውቅ ቆይቷል። ይሁንና እነዚህን መሰል ለግሉ ዘርፍ ይሰጥ የነበረውን አትኩሮት የሚጨምሩ፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ጨምሮ ዘርፉን የሚጋብዙ የፖሊሲ መስመሮች፣ በተለይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ይተገብሩትና ተተኪያቸው ሃይለማርያም ደሳለኝ አስቀጥለውት ነበር ከሚባለው ድሃ ተኮር የምጣኔ ኃብት ፖሊሲ ትሩፋቶች ላይ ውሃ የሚቸልስ ነው ሲሉ የሚተቹት አልታጡም። የመንግሥት የምጣኔ ኃብት ባለሟሎች በበኩላቸው ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የምጣኔ ሃብት ቁመና የነበረውን ጎዳና ይዞ መቀጠል የማይቻል በመሆኑ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል ይላሉ። 2011 ዓ.ም እንደሌሎች የቅርብ ዓመታት ሁሉ የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ኢትዮጵያን ሰንጎ የሸሸበትም ነበር። የዕጥረቱ ዳፋ በተለይ ከውጭ የሚመጡ ጥሬ ዕቃዎችን ለሚጠቀሙ አምራቾች እንዲሁም ቁሳቁሶችን ከውጭ በማስመጣት ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎችና የንግድ ድርጅቶች ፈተና አብዝቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በውጭ አገራት የሚገኙና ብዛታቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያ የዘር ግንድ ያላቸው የውጭ አገር ዜጎችን የምጣኔ ኃብቱን በማነቃቃት ረገድ ሚና እንዲጫወቱ ፍላጎት እንዳላቸው መገንዘብ አያዳግትም። ሆኖም ያሳለፍነው ዓመት በዚህ ረገድ ምን ያህል ስኬትን አስጨብጧቸዋል የሚለው ብዙም ግልፅ አይደለም። ለምሳሌ በወርሃ ግንቦት የግብርና ዘርፍን ከማዘመን ጋር በተያያዘ በተዘጋጀ አንድ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ በውጭ አገራት ካሉ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ የዘር ግንድ ካላቸው የሌሎች አገራት ዜጎች በ'ኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ' በኩል ለመሰብሰብ የታሰበውን ያህል ገንዘብ ማግኘት እንዳልተቻለ አምነዋል። ተሰናባቹ ዓመት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ምርቃት ቢያስተናግድም፣ እንደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ መንግሥታዊ ፕሮጀክቶች እምብዛም ከነበሩበት ፈቀቅ ሲሉ አልታዩም። ከዚያ ይልቅ በተለይ መዲናዋን አዲስ አበባን ማዕከል ያደረጉ ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይፋ ተደርገዋል።
news-47382344
https://www.bbc.com/amharic/news-47382344
የጉግል አጠቃቀምዎን የሚቀይሩ ሰባት እውነታዎች
በቀን ውስጥ ጉግልን ምን ያህል ጊዜ ይጠቀማሉ?
ምንም እንኳ ጉግልን አዘውትረው የሚጠቀሙ ቢሆኑም የመፈለጊያ ሳጥኑ ውስጥ የማናውቃቸው ሚስጥራዊ መገልገያዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል ላታውቋቸው ትችላላችሁ ያልናቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው አሰቀምጠናቸዋል፤ ይሞክሯቸው። 1. የዕድል ጨዋታ ሎተሪ መጫዎት ወይም ደግሞ ድንገቴ ውሳኔዎችን መወሰን ያስደስተዎታል? ለዚህ ፍላጎትዎ ጉግል ምላሽ አለው። በተለይ የቁጥር ዕጣ ለማውጣት "random number generator" ብለው ይጻፉና ቁጥሮችን የት ማስቀመጥ እንዳለብዎ ይመለከታሉ። "Generate" የሚለው ላይ ከተጫኑ የቁጥር ሥርዓቱ የሚፈልጉትን ያህል ድንገቴ ቁጥሮችን ያወጣል። • የሲሊከን ቫሊ ልጆች ትልቁን ኢትዮጵያዊ የመረጃ ቋት የመፍጠር ህልምን ሰንቀዋል ልብ አንጠልጣይ በሆነ መልኩ አዝናኝ ማድረግ ከፈለጉ ደግሞ "spinner" ብለዉ ይጻፉና በቀኝ በኩል የሚታየውን "Number"ን ይምረጡ። ከዚያ እስከ 20 ቁጥሮችን የሚያስቀምጡበት ቦታ ይመጣል። "Spin"ን ተጭነው ውጤቱን ይመልከቱ። ጉግል የዕድለኛ ቁጥሮችን ያወጣልዎታል። በመቀጠል "Face or cross" ብለው ጽፈው ይመልከቱ፤ ጉግል ያሉትን ዕድሎች ለማሳየት ሳንቲሞች ሲወረውር ይመለከታሉ። 2. ከባድ የሂሳብ ስሌቶችን መፍታት የመፈለጊያ ሳጥኑ ላይ "calculator" ብለው ከጻፉ መሰረታዊውን ካልኩሌተር ሊያገኙ ይችላሉ። ነገር ግን መስራት የሚፈልጉት የተወሳሰበ የሂሳብ ስሌት ከሆነ ትክክለኛ ቀመሩን (formula) በትክክል ያስቀምጡ። ውጤቱን ማምጣት የጉግል ፋንታ ይሆናል ማለት ነዉ። ለምሳሌ የሚከተለውን ስሌት ብናስቀምጥ ወዲያውኑ እንዴት ግራፍ ስሎ ሊያሰቀምጥ እንደሚችል እናያለን። cos (12x) + sin (8x) 3. መለኪያዎችንና የመገበያያ ገንዘቦችን ለመቀየር "Conversion of measures" ብለው ይጻፉ። ከዚያ በኋላ መቀየር የሚፈልጉትን ርቀት፣ ስፋት፣ የሙቀት መጠን፣ ይዘት እና የተለያዩ መጠኖችን የሚያወዳደሩበትን ካልኩሌተር ያገኛሉ። • ስለጉግል የማያውቋቸው 10 እውነታዎች "Currency converter" ብለው ከጻፉ ደግሞ የተለያዩ ሀገራትን የመገበያያ ገንዘብ ንጽጽር በቀላሉ ማወደደር ይችላሉ። 4. በዘፈኖች ምት መካከል ምልክት ለማስቀመጥ ሙዚቀኛ ከሆኑ ይህ መተግበሪያ የሜሎዲ ጊዜን ለመለየት እጅግ ጠቃሚ ነው። "Metronome" ብለው ይጻፉና የሚመጣውን ምልክት በማየት እያዳመጡ ምቶችን በየደቂቃዉ እንዴት መጨመርና መቀነስ እንደሚቻል መማር ይችላሉ። 5. የሚመችዎትን የሙዚቃና ዘፋኝ ለማግኘት የአንድን ሙዚቀኛ ስምና የአንድ ዘፈኑን ርዕስ ይጻፉ። ውጤት ማሳያ ሳጥኑ ላይ "Other versions of this song" የሚል ምርጫ ያግኛሉ። • 'ጉግል ያርጉት' ዓለምን የቀየረው የሁለቱ ተማሪዎች ፕሮጀክት! እዚሁ ላይ ሲጫኑ ታደያ ይህን ዘፈን የዘፈኑትን አርቲስቶች ዝርዝር የሚያሳይ የዩቲብ ዝርዝር ያገኛሉ። የሚመችዎትን ሙዚቃና ዘፋኝ በቀላሉ በዚህ መልኩ ማግኘት ይችላሉ። ለምሳሌ ይህን ይጻፉና ይሞክሩ "John Lennon Imagine" 6. እረፍት ለመውሰድ ብስጭት ወይም ጭንቀት ተሰምቶዎታል? እንግዲያውንስ "breathing excercise" ብለው ጉግል ላይ ይጻፉ ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሚያዝናናዎት እና ቀለል ያለ ስሜት እንዲሰማዎ የሚያደርግ ሰማያዊ ሳጥን ይመጣልዎታል። • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ 7. በቪዲዮ ጨዋታዎች ለመዝናናት ቀላል የቪዲዮ ጨዋታዎችን መጫዎት የሚፈልጉ ከሆነ "Google Pacman" ብለው ጉግል ላይ ይጻፉ። ምርጫዎ ሌላ ጨዋታ ከሆነ ደግሞ "Atari Breakout" ብለዉ ይፈልጉ። በተጨማሪም "Snake" ብለዉ ከጻፉ በዝነኛውን "Snake" ጨዋታ መዝናናት ይችላሉ።
news-48960645
https://www.bbc.com/amharic/news-48960645
ኢህአዴግ ከአባል ፓርቲዎቹ መግለጫ በኋላ ወዴት ያመራል?
የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ በበርካቶች ዘንድ የተለያዩ ጉዳዮችን በማስነሳት እያነጋገረ ይገኛል። ከእነዚህ መካከል ዶ/ር አደም ካሴ አበበ፣ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ገቢሳ፣ እንዲሁም አቶ ልደቱ አያሌው በመግለጫውና በገዢው ፓርቲ ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል። የ ኢህአዴግ ዕጣ
ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ገቢሳ እንደ ጥምረት ፓርቲዎቹ አንድ ሃሳብ እንዲኖራቸው የሚጠበቅ አይደለም ይላሉ። ለፕሮፌሰሩጥምር ፓርቲ ውስጥ ያሉ ቡድኖች ካልተግባቡ የመፍረስ እድል ይኖራል፤ ይህም አዲስ ነገር አይደለም። ዋናው ነገር የኢህአዴግ ፓርቲዎች ጥምረት ከሌለ ሃገሪቱ እንዴት እንደምትተዳደር ነው የሚሉት ፕሮፌሰሩ "ገዢው ፓርቲ ችግር ውስጥ ከገባ ሰንብቷል" ሲሉ አስተያየታቸውን ይቀጥላሉ። ኢህአዴግን በአንድነት አዋህዶ ይዞት የነበረው ህወሐት እንደነበር የሚናገሩት ፕሮፌሰር ህዝቅኤል አሁን ህወሐት ያንን ለማድረግ በሚችልበት ደረጃ ላይ ስላልሆነ እያንዳንዱ የጥምረቱ አባል የሆነ ፓርቲ በተለያየ አቅጣጫ መሄድ ከጀመረ ቆይቷል ባይ ናቸው። ወደፊት ልዩነቶቻቸውን አቻችለው አብረው ሊቀጥሉ ይችላሉ ወይም ደግሞ ሊታረቅ ወደማይችል ቅራኔ ውስጥ ገብተው ፓርቲው ሊፈረካከስ ይችላል ሲሉም ያላቸውን ግምት ያስቀምጣሉ፤ ነገር ግን በማለት "አሁን ካለው ሁኔታ ተነስተን ይሄ ሌሆን ይችላል ለማለት አስቸጋሪ ቢሆንም ከሁለቱ ግን አንዱ ይሆናል"ብለዋል። • የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሙሉ መግለጫ ምን ይላል? • ኢህአዴግ እዋሃዳለሁ ሲል የምሩን ነው? የኢህአዴግ ጥምር ፓርቲዎች ውስጥ እየታዩ ካሉት ነገሮች በመነሳት በጥምረቱ ውስጥ በአንድነት የመቆየት እድላቸው የመነመነ ይመስላል የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ ቢሆንም ግን ሃገሪቱ ወደ ምርጫ እየሄደች በመሆኗ ያሉባቸውን ችግሮች አቻችለው ለዚያ ሲሉ አብረው ሊቆዩ ይችላሉ ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። አቶ ልደቱ በበኩላቸው ህወሐት አሁን ሀገሪቱ የገባችበት ችግር እውነት ያሳስበው ከሆነ በመውቀስ በመክሰስ ሳይሆን፣ ለዚህ ችግር አገሪቷንና ሕዝቡን የዳረጉት መሰረታዊ ነገሮች ምንድን ናቸው? የሚለው ገምግሞ፣ የእርሱ ተጠያቂነት ከፍተኛ እንደነበር አምኖ በመቀበል ነው መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው" ይላሉ አቶ ልደቱ። ህወሐት "ባለፉት 27 ዓመታት የተሰራው ሁሉ መልካም እንደሆነና፣ ሀገሪቱ አሁን ያለችበት ችግር እርሱ ከስልጣን ከተነሳ በኋላ የተፈጠረ አድርጎ የማቅረብ ሙከራው ካለፈው ውድቀቱ አለመማሩን ነው የሚያሳው" ይላሉ። አቶ ልደቱ አክለውም "ህወሐት የችግሩ አካል ነው፤ የመፍትሄውም አካል መሆን አለበት፤ መፍትሄው አካል ሲሆን ደግሞ በሙሉ የሀላፊነት ስሜት መሆን አለበት" ሲሉ ይመክራሉ። ኢህአዴግ በድሮ ግርማ ሞገሱ አለን? ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አለ፤ በድሮው በጥንካሬው በድሮው አስተሳሰብና ሞገስ ግን የለም ያሉት ደግሞ አቶ ልደቱ አያሌው ናቸው። "ተወደደም ተጠላም ግን ኢህአዴግ አለ፤ አሁን ሀገሪቱን እየመራት ያለው እርሱ ነው" በማለትም አሁን ለውጡን እየመሩት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትርም የተመረጡትም በኢህአዴግ ነው ሲሉ ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ። ኢህአዴግ እርሳቸውን ሲመርጣቸው የህወሐት አባላትም እዚያው ቁጭ ብለው እጃቸውን አውጥተው ነው የመረጧቸው ያሉት አቶ ልደቱ ይህንን ሀገርና ህዝብ ወደዚህ አይነት ከፍተኛ ችግር የከተተው እንደ ድርጅት ራሱ ኢህአዴግ የሚባለው ድርጅት ስለሆነ ከዚህ ችግር ለማውጣትም መስራት ከፍተኛ ሚና መጫወት ያለበት ራሱ ኢህአዴግ ነው ብለው ያምናሉ። "ኢህአዴግ ስንል ደግሞ ህወሐትንም ይጨምራል። ስለዚህ ከመነጣጠል ይልቅ በአብሮነት በመስራት ለለውጡ መትጋት አለበት።" በማለትም የፕሮፌሰሩን ሀሳብ ይሞግታሉ። የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ዶ/ር አደም ካሴ በበኩላቸው ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ የድሮው ኢህአዴግ ነው ለማለት ይከብዳል ይላሉ፤ ከመሪዎቹ አንፃርም አብረው ሊታዩ ቢችሉም አብረው እየሰሩ ነው ለማለት ይከብዳል። ከዚያ አንፃር የኢህአዴግ የድሮው ጥንካሬና ሞገስ አለ ብሎ ማሰብ አይቻልም በማለት ህወሐት መግለጫ ላይ ከዚያ አንፃር ያዩት አዲስ ነገር እንደሌለ ጠቅሰው "አዲሱ ነገር ግልፅ ማድረጋቸው ነው" ብለዋል። ህወሐት ከአዴፓ ጋር ለመስራት እንደሚቸገር ከገለጸበት ይልቅ ከአዳዲስ ኃይሎች ጋር ለመስራት ያለውን ፍላጎት አንድ ላይ ሲታይ የሚያሳየው ነጥብ ከኢህአዴግ መልቀቅን እንደ አንድ አማራጭ እያቀረቡ መሆኑን ነው ያሉት ዶ/ር አደም "ይህ ለኢህአዴግ ከግንባርነት ወደ ወጥ ፓርቲነት እሸጋገራለሁ እያለ ባለበት ጊዜ ላይ መከሰቱ የኢህአዴግ ዕጣ ፈንታ ላይ ጥያቄዎች እንድናነሳ ይጋብዘናል" ሲሉ የፈጠረባቸውን ጥያቄ ያነሳሉ። • አምነስቲ በቅርቡ የታሰሩ ጋዜጠኞች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥትን ነቀፈ ፕሮፌሰር ህዝቄል በበኩላቸው ከሁሉ ግልጽ እየሆነ የመጣው በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች በግንባሩ ዉስጥ የፈጠሩትን ጥምረት በማስቀረት ወደ አንድ ወጥ ውሁድ ፓርቲነት እንሸጋገራለን ያሉት ዕቅድ ፈጽሞ ሞቶ የተቀበረ ጉዳይ መሆኑን በመግለፅ የግንባሩ ውህደት የማይሆን እንደሆነ ይናገራሉ። ዶ/ር አደም አክለውም ከዚህ በፊትም ህወሐት 'ኢህአዴግ ይዋሃዳል' ሲባል ጥያቄ ማንሳቱን አስታውሰው "ከዚያ አንፃር የምንጠረጥረውን ነገር እውነተኛነት የሚያረጋግጥና ኢህአዴግ በአንድ ግንባርነት መቀጠል እየተሳነው መሆኑን የሚያመለክት ነው" በማለት ከፕሮፌሰር ህዝቄል ጋር የሚመሳሰል ሀሳብ ያነሳሉ። እንደ ግንባር የአባል ድርጅቶቹ ድክመትና ጥንካሬ የግንባሩ ድክመትና ጥንካሬ ነው የሚሉት ዶ/ር አደም አሁን ግን ሁሉም ፓርቲዎች በራሳቸው የተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ናቸው ሲሉ ያክላሉ። በተለይ ሦስቱ አዴፓ፣ ኦዴፓና ደኢህዴን በየክልላቸው የራሳቸው ፈተናዎች አለባቸው ያሉት ዶ/ር አደም፤ እስካሁን በክልሉ ውስጥ ጠንካራ ሆኖ የሚታየው ህወሐት ብቻ ነው በማለት ግንባሩ ኣለበትን ፈተና ለማሳየት ይሞክራሉ። ስለዚህ እነዚህ ድርጅቶች እንደፓርቲ ከችግሮቻቸው ተላቀው ጠንካራ ካልሆኑ በስተቀር ግንባሩ ጠንካራ ሆኖ እንደበፊቱ ሊቆም ይችላል የሚለው አስቸጋሪ ነው ያሉት ዶ/ር አደም፣ ፓርቲዎቹ ራሳቸውን ማጠናከር ላይ መስራት ካልቻሉ የግንባሩ ህልውናን ማስቀጠል ፈታኝ እንደሆነ ይናገራሉ። ፓርቲዎቹ ራሳቸውን አጠንክረው መቆም ካልቻሉ ለራሳቸው ህልውናም ሆነ ለኢህአዴግ አንድ ሆኖ መቆም ፈታኝ ነው የሚሆነው ሲሉም ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ክልሎች ግጭት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ? "እንደዚያ የሚያስቡ ወይንም ሙከራ የሚያደርጉ ኃይሎች ሊኖሩ ይችላሉ" ኣሉት አቶ ልደቱ ናቸው። ነገር ግን የትግራይም ሆነ የአማራም ህዝብ በአሁኑ ወቅት አሁን ከገባበት ችግር መውጣት ነው እንጂ ወደሌላ አሳሳቢ ውጥረትና ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት አለው ብዬ አላምንም በማለት በሕዝቡ ላይ ያላቸውን ጠንካራ እምነት ይገልፃሉ። "ህዝቡ የዚያ አይነት እምነት እስካለው ድረስ እንደዚያ አይነት የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች የሚፈልጉትን ነገር ያደርጋሉ ብዬ አላምንም።" ዶ/ር አደም በበኩላቸው ህዝቡ መንግሥታችን ጠንካራ ነው ካለ መረጋጋቱ ሰላሙ ይኖራል። ካልሆነ ግን ደካማ መንግሥት ነው ያለው ብሎ በሚያስብ ማህበረሰብ ውስጥ ሰላምና መረጋጋትን ማሰብ አስቸጋሪ መሆኑን ይጠቅሳሉ። አክለውም መንግሥት የተለያዩ የሕግ ጥሰቶች ላይ መለሳለስ ሲያደርግ መታየቱን በማንሳት ግጭቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ያላቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። "እነዚህ ግጭቶች በተለያዩ ብሔሮች መካከል ሊከሰቱ ይችላሉ። በአንድ ብሔር ውስጥም፣ እርስ በእርስ ሊሆን ይችላል። ሌላው ደግሞ በክልሎች መካከል ሊከሰት ይችላል።" ለኢትዮጵያ የወደፊት ችግር የሚሆነው የኢህአዴግ የወደፊት ሁኔታ ነው የሚሉት ዶ/ር አደም፣ የአባል ድርጅቶች አቋም መለያየት፣ ምርጫ ላይ ያለው ሁኔታና የሲዳማ ጉዳይ ከሚኖሩ ችግሮች መካከል መሆናቸውን ይጠቅሳሉ። እነዚህ ጉዳዮች በብስለትና በትዕግስት ካልታዩ ግጭት አይኖርም ማለት እንደሚከብድ ዶ/ር አደም አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አብሮ መስራት አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከራስ ቡድን ፍላጎትና ጥቅም በላይ የሀገር ጥቅም የሚያሳስባቸው ከሆነ አማራጩ እርስ በእርስ መካሰስ፣ የፖለቲካ ሽኩቻው ወስጥ መግባት ሳይሆን አንድ ላይ መቆም ነው የሚሉት አቶ ልደቱ አያሌው ናቸው። • "ብ/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ ህወሐት 27 ዓመት ሙሉ የበደለውን ህዝብ ለመካስ የሚፈልግ ከሆነ መፍትሔው ጥሎ መውጣት አይደለም የሚሉት አቶ ልደቱ፤ ግንባሩ ውስጥ ሀቀኛ የሆነ ትግል አድርጎ ችግሩን በጋራ እንዲፈታ መጣር እንዳለበት ይመክራሉ። "ኢህአዴግ እንደ አንድ ድርጅት መቆም የሚጠበቅበት ጊዜ ዛሬ ነው።" በዚህ ሰዓት አኩርፎ መውጣት የኢትዮጵያን ችግር የበለጠ ያወሳስበዋል እንጂ መፍትሄ የሚሰጥ አይሆንም በማለትም ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ። ከሌላ ድርጅት ጋር በጋራ ስለመስራት ይህ ሀሳብ ከፋፋይ ነው፤ አሁን ኢትዮጵያዊያኖች በአጀንዳ በተለያየ መልኩ ተከፋፍለን እርስ በእርስ የምንታገልበት ወቅት መሆን የለበትም። አንድ ላይ ሆነን ይህንን ችግር ተወጥተን ህዝቡ ወደ ሚፈልገው አቅጣጫ፣ ይህችን ሀገር ለማሻገር ነው መጣር ያለብን የሚሉት አቶ ልደቱ ናቸው። ስለዚህ ህወሐት "ከልጅነት ጀምሮ የተጠናወተው የመከፋፈል ባህሪ" አሁንም እንዳልለቀቀው ያወጣው መግለጫ በደንብ ያሳያል ይላሉ አቶ ልደቱ። ስለዚህ ከዚህም አንፃር የያዘው መንገድ ትክክል አይደለም። አሁን የሚጠበቀው አንድ ላይ ቁጭ ብሎ መስራት ነው እንጂ መነጠል እንዳልሆነ ይመክራሉ። በሀሳብ ደረጃ ካየነው በሚያራምዱት ሀሳብ፤ የህወሐት አይነት የብሔረተኝነት አስተሳሰብ ከሆነው፣ ጠንካራ ብሔርተኝነት ካለባቸው ጋር እንደሆነ የሚጠቁሙት ዶ/ር አደም፤ "ስለዚህ ወደፊት ከሚመሰረተው ክልል ከሲዳማ ጋር፣ ጠለቅ ብለህ ካሰብከው ደግሞ በመርህ ደረጃ ከአማራ ክልሉ አብን ጋር፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ካለው ከኦነግ ጋርም የሚመሳሰል ነገር ነው ያለው" በማለት ህወሀት ከኢህአዴግ ጋር አልቀትልም ቢል ከነማን ጋር እሰራል ለሚለው ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ነገር ግን ህወሐት ከአማራና ከኦሮሚያ ክልል ውጪ ካሉ ቡድኖች ጋር አብሮ ሊሰራ ይችላል በማለት ቢሆንም ግን ውጤታማ ትልቅ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመሆን እንደሚከብደው አመልክተዋል። ህወሐት እንደ ፓርቲ ትልቅ ለመሆንና አሁን ያለውን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ለማስቀጠል ከትልልቅ ክልሎች ከወጡ ፓርቲዎች ጋር መስራት ይጠበቅበታል ይላሉ ዶ/ር አደም። • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) ድርጅቱ በግልፅ ከእነዚህ ከእነዚህ ጋር እሰራለሁ ባላለበት በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት ይቸግረኛል የሚሉት አቶ ልደቱ "ነገር ግን ፖለቲከኛ ስለሆንኩ በተዘዋዋሪ ምን ለማለት እንደፈለገ ይገባኛል" በማለት "ይህ አካሄድ አፍራሽ ነው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኃይል አሰላለፍ በከፍተኛ ደረጃ የሚያናውጥ ሀገሪቱን ወደበለጠ ውስብስብ ችግር የሚከት ነው።" ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። በዚህ መግለጫ ትኩረት የተደረገው አዴፓ ላይ ነው። እርሱን እንደጠላት በመፈረጅ ከእርሱ አመለካከት ጋር የሚሄዱ ሌሎች ድርጅቶችን ምናልባትም ከኢህአዴግ ውጪ ካሉ ድርጅቶች መካከል ከህወሓት አመለካከትና አደረጃጀትጋር አብረው ከሚሄዱ ኃይሎች ጋር ለመስራት የመፈለግ ነገር እንደሚያዩ ይናገራሉ አቶ ልደቱ። ኢህአዴግ ምን ያድርግ? ገዢው ፓርቲ፤ ኢህአዴግ የሀገሪቱን ዕጣ ፈንታ በብቸኝነት ተቆጣጥሮ እያለ በሀላፊነት ስሜት መስራት አቅቶት የሚበታተን ከሆነ እርሱ ውስጥ የሚፈጠረው መበታተን ለሀገርም ሊተርፍ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው አቶ ልደቱ። ስለዚህ ትልቅ ሀገርና የሕዝብ ሀላፊነት ያለባቸው መሆናቸውን አውቀው ከመቼውም በላይ ከግል እንዲሁም ከቡድን ስሜትና ፍላጎት፣ ከፖለቲካ ሽኩቻ በፀዳ መልኩ አብረው መስራት አለባቸው ሲሉም ይመክራሉ። "አዴፓም አሁን ባለበት ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ሊረዳ የሚገባው ነው" ያሉት አቶ ልደቱ ከፍተኛ አመራሮቹ ተገድለውበት ተዳክሟል፤ ይህንን ድርጅት በዚህ ወቅት ለማጥቃት መሞከርም ተገቢ አይደለም ሲሉም ይወቅሳሉ። • "አገሪቷ አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት ህወሐት ተጠያቂ ነው" አዴፓ • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሀገር እንደሚመራ ትልቅ ፓርቲ ኢህአዴግ ያለበት ሀላፊነት ትልቅ ነው ያሉት ዶ/ር አደም፤ በእርግጥ በገዢው ፓርቲ አባላት መካከል ልዩነቶች አሉ። ይህ ደግሞ በፓርቲዎቹ መካከል ብቻ ሳይሆን በአንድ ፓርቲ ውስጥም ሊያጋጥም ይችላል ብለዋል። "ነገር ግን መሰረታዊ በሆኑት ጉዳዮች ላይ መስማማት ያስፈልጋል።" በማለትም ሰላምን መጠበቅ፣ በሕዝቦች መካከል መከባበር እና ትግስት እንዲኖር ማድረግ፣ ያንን ለማድረግ ግን እንደፓርቲ እየተነጋገሩ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን ይጠቅሳሉ። "ሀገርን የሚመለከት ጉዳይን በጋራ ማሳካት ካልቻሉ ግን ሀገርን እንደሚመራ ፓርቲ የእነሱ ችግር ሀገሪቱን ችግር ውስጥ ሊጥላት ይችላል" በማለት ያላቸውን ስጋት ያስቀምጣሉ። አክለውም እነዚህ ግን ኢህአዴግ ብቻውን የሚፈታቸው ችግሮች አይደሉም በማለት አንዳንዶቹ ችግሮች ላይ ሌሎች ፓርቲዎችም ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ይጠቅሳሉ። "ዋናው ነገር ልዩነት ተፈጥሯዊ እንደሆነ ተማምኖ በተፈጠረው ነገር ሳይደናገጡ የጀመሩትን የዲሞክራሲ መንገድ ማስቀጠል ነው" በማለት ዶ/ር አደም ሀሳባቸውን ያጠናቅቃሉ።
news-46902017
https://www.bbc.com/amharic/news-46902017
እንዴት የእንቁላል ምስል ኢንስታግራም ላይ 46 ሚሊዮን 'ላይክ' አገኘ ?
እንደው የኢንተርኔት ነገር ድንቅ አይሎትም?
እንቁላሉና ኬሊ ጄነር ከ46 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ኢንስታግራም ላይ የተለጠፈ የእንቁላል ምስልን ወደውታል ወይም 'ላይክ' አድርገውታል። የዚህ እንቁላል ባለቤት ማን እንደሆነ፣ ፎቶው መቼ እንደተነሳ፣ እንቁላሉ ጫጩት ይሁን ወይም ተጠብሶ አሊያም ተቀቅሎ ይበላ የሚቃወቅ ነገር የለም። የሚታወቀው ከ46 ሚሊዮን በላይ ሰዎች 'ላይክ' እንዳደረጉት ብቻ ነው። • ከሽብር ጥቃቱ በኋላ ምን ተከሰተ? • "በብሔር ግጭት ወደ 900 ሰዎች ገደማ ተገድለዋል" • ኮማንድ ፖስቱ በምዕራብ ኢትዮጵያ 835 ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ የእንቁላሉ ፎቶ ከመለጠፉ በፊት፤ የቴሌቪዥን መሰናዶ አዘጋጇ ኬሊ ጄነር አምና የተወለደ ልጇን ያስተዋወቀችበት ዜና 18 ሚሊዮን 'ላይክ' በመሰብሰብ ሪከርዱን ይዞ የነበረው። ከቀናት በፊት ማለትም ታህሳስ 26፤ ማንነቱ ያልተወቀ የኢንስታግራም ተጠቃሚ፤ ዎርልድ_ሪኮርድ_ኤግ ("world_record_egg") የሚል የኢንስታግራም ገጽ በመፍጠር የእንቁላሉን ፎቶ በመለጠፍ 46.8 ሚሊዮን 'ላይክ' ማግኘት ችሏል። ከእንቁላሉ ጋር አብሮ የተለጠፈው ጽሁፍ ''በኢንስታግራም ገጽ ላይ ብዙ 'ላይክ' በማስገኘት የዓለም ሪኮርድን አብረን እናስመዝግብ'' ይላል። እንደተባለውም ሆነ። ከሁለት ቀናት በፊት ሪኮርዱ ተሰብሯል። የኢንስታግራም ገጹን ማን እንደሚያስተዳድረው አይታወቅም ሪኮርዱን የተቀማችው ኬሊ ጄነር፤ እንቁላል ስትሰብር የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ''ይህን ደቃቃ እንቁላል አንሳው/ሺው'' ከሚል ጽሁፍ ጋር በኢንስታግራም ገጿ ላይ ለቃለች። ኬሊ ጄነር በኢንስታግራም ገጿ ላይ በስፖንሰር ለምትለጥፈው አንድ ማስታወቂያ አንድ ሚሊዮን ዶላር ታስከፍላለች።
50461401
https://www.bbc.com/amharic/50461401
በግጭት አዙሪት ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሃሙስ ምሽት ካፌ ውስጥ እራት ላይ ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር ፤ እስካሁን እየተጣራ ቢሆንም አርብ ጠዋት ደግሞ የአንድ ተማሪ ከፎቅ ወድቆ ወይም ተወርውሮ መሞትን ተከትሎ ተማሪው በአጥር እየዘለለ ግቢውን ጥሎ መውጣቱን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት የሴቶች ፕሬዝዳንት የአብስራ አስፋው ትናገራለች።
ከእሷና አንድ ስሙ እንዲገለፅ ካለፈለገ ሌላ ተማሪ እንደሰማነው ተማሪዎች በአጥር እየዘለሉ ለመውጣት የተገደዱት የዩኒቨርሲቲው በር ተማሪዎች እንዳይወጡ ዝግ በመደረጉ ነው። •ኢትዮጵያውያንን እየቀጠፈ ያለው የሞት ወጥመድ •"እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ የተቋረጠው ትምህርትም ዛሬ ሊጀመር ታስቦ የነበረ ቢሆንም አብዛኛው ተማሪ በአጥር ዘሎ በመሄዱ ግቢው ውስጥ በቀረው ጥቂት ተማሪ ይህን ማድረግ እንዳልተቻለ ተማሪዎቹ ገልፀውልናል። ከተማሪዎቹ መረዳት እንደቻልነው ምንም እንኳ ከሃሙስ ምሽቱ ወዲህ ጉልህ የሚባል አለመረጋጋት በዩኒቨርሲቲው ባይኖርም ተማሪዎች ግን ከፍተኛ ስጋት ስላደረባቸው ግቢውን እየለቀቁ ነው። ሴት ተማሪዎች ተደፈሩ የሚል መረጃ እየወጣ ስለመሆኑ ጥያቄ ያቀረብንላት የአብስራ በተማሪው ዘንድ ሴቶች ተደፍረዋል የሚል ወሬ እየተወራ ቢሆንም ለተማሪዎች ህብረት ለስርዓተ ፆታ ቢሮም የቀረበ ሪፖርት እንደሌለ ትገልፃለች። "ዶርም ለዶርም እየሄድን ጠይቀናል ፤ሆስፒታልም ሄድን ለማጣራት ሞክረናል"የምትለው የአብስራ በሃሙስ እለቱ የካፌ ግርግር ወገባቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሴት ተማሪዎች ሆስፒታል ሄደው እንዳገኙ ታስረዳለች። ዩኒቨርሲቲው እየተጠበቀ ያለው በፌደራል እና በመከላከያ አባላት እንደሆነ ማወቅ ተችሏል። •የ31 ዓመቱ ኢሕአዴግ ማን ነው? ዛሬ ደግሞ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ከኦሮሚያ ክልል የሄዱ በርካታ ተማሪዎች 'ወደ መጣንበት እንመለስ" በማለት የተቃውሞ ድምፅ ማሰማታቸውን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ገልፀውልናል። ባለፈው ሳምንት ከፌደራልም፣ ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል የሚመለከታቸው ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው ወደ ቀያቸው መመለስ እንደሌለባቸው፤ ይልቁንም ትምህርታቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ተገልፆላቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ነው ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ተማሪዎች የሚናገሩት። ተማሪዎቹ እንደሚሉት ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ አንድ አዳራሽ ውስጥ ተሰባስበው ለማደር ተገደዋል። እንቅስቃሴያቸው በመገደቡም ለተለያዩ አገልግሎቶች ችግር ተጋልጠዋል። አንድ አዳራሽ ውስጥ ተሰብስቦ ማደር፣ በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ውስጥ መንቀሳቀስ አለመቻል በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ዩኒቨርሲቲዎች ታይቷል። ባለፈው ሳምንት በደምቢደሎ ዩኒቨርሲቲ ከአማራ ክልል የሆነ ተማሪ በስለት ተወግቶ መሞቱን ተከትሎ ተማሪዎች ፍርሃት ውስጥ ገብተው በተመሳሳይ ነገር ውስጥ ለማለፍ ተገድደዋል። ጥቂት በማይባሉ የኦሮሚያና አማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በግጭት እየተገደሉ እና እየቆሰሉ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው። •በአክሱም ዩኒቨርስቲ ግጭት የተጠረጠሩ ተያዙ ዛሬ ነገሮች ረገቡ ትምህርት ተጀመረ ወይም ሊጀመር ነው ሲባል ግጭቶች እያገረሹ ጥቂት በማይባሉ የመማር ማስተማር ሂደት እንደተቋረጠ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ተማሪዎችን ከዩኒቨርሲቲዎች ቅጥር እንዳይወጡ መከልከልም ብዙ ጥያቄዎች እያስነሳና ችግር እያስከተለ እንዳለም አስተያየት እየተሰጠ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፍ ሳምንት ማብቂያ ከሚመለከታቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲሁም ከደህንነት ሃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ በመከሩበት ወቅት ዩኒቨርሲቲዎች የማይረጋጉ ከሆነ መንግሥት እስከ መዝጋት እርምጃ እንደሚወስድ ገልፀዋል። ሆን ብለው ረብሻ የሚቀሰቅሱ ተማሪዎችን ህግ ፊት የማቅረብ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመዋል። አሁንም ግን የዩኒቨርሲቲዎች ቀውስ በዘላቂነት የሚፈታው እንዴት ነው? የሚለው በቀላሉ የሚመለስ የማይመስል ጥያቄ ነው።
news-54532377
https://www.bbc.com/amharic/news-54532377
45 ዓመታትን በሰማይ ላይ
ለ45 ዓመታት ያበረሩት ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ፓይለት፤ ካፒቴን ተስፋይ አምባዬ።
ካፒቴን ተስፋይ አየር መንገድ የበረራ መምሪያ ኃላፊ በመሆን ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል። ካፒቴን ተስፋይ ወላጅ አባታቸው በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በጁሩንድ (ገንዘብ ሚኒስቴር) ውስጥ የአገር ውስጥ ገቢ ሹም ስለነበሩ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር ነበር። ማይጨው ከተማ ውስጥ የተወለዱት ካፒቴን ተስፋይ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በተንቤንና መቀለ ተከታትለዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአፄ ዮሐንስ ትምህርት ቤት ተምረዋል። የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ጥሩ ውጤት በማምጣታቸው በ1966 ዓ. ም. ወደ አዲስ አበባ አምርተው ነበር። ወቅቱ ንጉሡ ከሥልጣናቸው ወርደው ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የተተካበት እና ሁኔታው ያልተረጋጋ ስለነበር ከወንድማቸው ውስ ጋር ቤትጥ ቁጭ ብለው ይውሉ እንደነበር ያስታውሳሉ። አንድ ቀን አንድ የጎረቤት ልጅ፣ ‘ፓይለት ለመሆን ስልጠና መወስድ የምትፈልጉ ተመዝገቡ’ የሚል ማስታወቂያ መለጠፉን ነገራቸው። የያኔው ተማሪ ተስፋይ ግን ብዙም ደስተኛ አልነበሩም። ቢሆንም ግን ቁጭ ብሎ ከመዋል ለምን አልሞክርም በሚል ለመወዳደር ማመልከታቸውን ያስታውሳሉ። በወቅቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአብራሪነት ስልጠና ወስዶ ለመቀጠር ካመለከቱት 600 ያህል ወጣቶች በፈተና ተጣርተው መጨረሻ ላይ 8 ልጆች አለፉ። ከእነዚህም መካከል አንዱ ተስፋይ ነበሩ። በዚሁ መልኩ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራቸውን አሀዱ ብለው ጀመሩ። ካፒቴን ተስፋይ ሥራ ሲጀምሩ ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት የተረፉትን ‘ዲሲ ስሪ’ (ዳኮታ) አውሮፕላን ማብረር መጀመራቸውን ያስታውሳሉ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቀጠረ ጀማሪ አብራሪ ለአንድ ዓመት ረዳት አብራሪ በመሆን መሥራት ስለሚጠበቅበት ረዳት አብራሪ ሆነው አገልግለዋል። ካፒቴን ተስፋይ፤ በአሁኑ ሰዓት ‘ትሪፕል ሰቨን’ (ቦይንግ 777) የሚያበሩ የድርጅቱ አንጋፋ ፓይለት ናቸው። አውሮፕላን አየር ላይ እንዴት 'መንሳፈፍ' ቻለ? አውሮፕላን ሰው ጭኖ እንደምን በአየር ላይ መንሳፈፍ ቻለ? በሚል ታዳጊ ልጆች መንደር ውስጥ ይከራከራሉ። አንዱ በክንፍ ታግዞ ነው የሚበረው ይላል። ሌላኛው ደግሞ በሞተር ምክንያት ነው የሚበረው ብሎ ይከራከራል። ቀጥለው ለምን ዘበኛውን አንጠይቅም? በማለት አጠገባቸው የነበሩትን አዛውንት ጠየቁ። የተከራከሩበትን ርዕስና የየራሳቸውን ግምት በማቅረብ፤ አዛውንቱ ማንኛቸው ትክክል እንደሆኑ ፍርድ እንዲሰጧቸው በጽሞና ጠበቁ። አጋጣሚ ሆኖ ዘበኛው ‘ሁሉንም ነገር አውቃለሁ’ ባይ ስለነበሩ፤ ሁላችሁም ተሳስታችኋል በማለት የሚከተለውን መልስ ሰጡ። ሁለት አጋንንቶች አሉ። አንዱ የመሬት ሁለተኛው ደግሞ የሰማይ በመባል ይከፈላሉ። መሬት ላይ ያለው ጋኔን አውሮፕላንዋን አንደርድሮ ከመሬት ያስነሳትና ‘ያዝ እንግዲህ ተቀበል’ ብሎ ሰማይ ላይ ላለው ጋኔን ያስረክበዋል። ሰማይ ላይ የቆየው ጋኔን ደግሞ አውሮፕላንዋን ይዞ ይበርና ልታርፍ ስትል አንተ ደግሞ በፊናህ ተቀበል ብሎ መሬት ላይ ላለው መልሶ ይሰጠዋል። አዛውምቱ “መልሱ ይህ ነው። በማታውቁት ነገር ጥልቅ አትበሉ” አሏቸው። ካፒቴን ተስፋይ ይህንን ገጠመኝ አብዱል ከሚባል ጓደኛቸው የሰሙ ዕለት ፈገግ ማለታቸውን ይናገራሉ። ዋናው የአውሮፕላኑ በአየር ላይ ያለ ችግር መንሳፈፍ ምስጢሩ ሞተርና ክንፍ ላይ የሚገኘው ‘ኤሮ ዳይናሚክ’ ነው ሲሉ ለቢቢሲ በአጭሩ መልሰዋል። 45 ዓመታት በሰማይ ላይ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንብ መሠረት አንድ ካፒቴን 60 ዓመት ሲሞላው ጡረታ ይወጣል። አሁን ላይ ወደ 65 ዓመት ከፍ እንዲል መደረጉን ካፒቴን ተስፋይ ይገልጻሉ። በዚህ መሠረት ካፒቴኑ በያዝነው ጥቅምት ወር ውስጥ ጡረታ ይወጣሉ። ለ45 ዓመታት ያለማቋረጥ ማብረራቸውን የሚናገሩት ካፒቴኑ፣ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ 27 ሺህ ሰዓታት በመብረር ከአንድ መቶ በላይ አገራትን አዳርሰዋል። “ከዕድሜዬ በላይ ነው እየኖርኩ ያለሁት፤ የሌላ ሰው ዕድሜ እየኖርኩ ያለሁ ያህል ይሰማኛል። ምክንያቱም አንድ ሰው ባለው ዕድሜ ውስጥ የተወሰኑ ነገሮችን ብቻ ነው ማድረግ የሚችለው። እኔ ግን ከተወሰኑ ነገሮች በላይ በማየቴ፣ ከተፈቀደልኝ ዕድሜ በላይ የኖርኩ ሰው ነኝ ብዬ ነው የማስበው” ይላሉ ካፒቴን ተስፋይ። አንዳንድ ጊዜ ኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በኋላ የምትደርስበትን የዕድገት ደረጃ በሌሎች አገራት ስላዩት፤ “አገራችን ውስጥ ያሉ ሰዎች ከማየታቸው አስቀድሞ እኔ አይቼዋለሁ” የሚል ስሜት እንደሚሰማቸው ይገልጻሉ። ካፕቴን ተስፋይ በ45 የበረራ ዓመታት ውስጥ በጣም ብዙ ችግሮች ቢያጋጥማቸውም፤ ይህ ነው የሚባል የከፋ አደጋ አልደረሰባቸውም። እንዲያውም ከዕድለኞቹ አንዱ ነኝ ብለው እንደሚያስቡ ይናገራሉ። የአውሮፕላኑ አንድ ሞተር መጥፋት የተለመደ ነው ከዕለታት አንድ ቀን ካፒቴን ተስፋይ አውሮፕላን አስነስተው ይበራሉ። ከሰባት ደቂቃዎች በኋላ በሞተር ዘይት ውስጥ በተፈጠረ ሙቀት ምክንያት ዘይት ይጎድላል። ይህን የታዘቡት ረዳት አብራሪ ለካፒቴኑ ሪፖርት ያደርጋሉ። ከዚያ በኋላ የማስጠንቀቂያ ቀይ ምልክት ከመብራቱ በፊት ሞተሩን አጠፉት። ከሁለቱ ሞተሮች አንዱ ከጠፋ ደግሞ በረራውን ማስቀጠል አይቻልም። ወድያውኑ አውሮፕላኑ ተመልሶ እንዲያርፍ በማድረግ የብዙዎች ሕይወት እንዲድን አድርገዋል። “በረራ ላይ እያለህ ሞተር ከጠፋ ነገሩ ቀላል ነው። አውሮፕላኑ በማኮብኮብ ላይ ለመነሳት በሚያደርገው ቅፅበት ሞተር ከጠፋ ግን ከባድ ነው። አውሮፕላኑ አኮብኩቦ ከመነሳቱ በፊት ባለው ‘የመነሳትና የመቆየት’ ቅፅበት፣ ሞተሩ ቢጠፋም ማቆም ብሎ ነገር ከቶውኑ አይታሰብም። አውሮፕላኑ የግድ መነሳት አለበት። ከተነሳ በኋላ ግን አይቀጥልም። ዞሮ በፍጥነት ተመልሶ ማረፍ ይኖርበታል። እንደዚህ አይነቱ አጋጣሚ ግን አልፎ አልፎ የሚታይ ክስተት ነው” ሲሉ ያስረዳሉ። በአሁኑ ጊዜ መኪና ከመንዳት በበለጠ አውሮፕላን ማብረር አተማማኝ ነው። አውሮፕላን ውስጥ ከመኪና በተሻለ “ደህንነትህ የተጠበቀ ይሆናል” ይላሉ ካፒቴን ተስፋይ። 'ብላክ ቦክስ' አውሮፕላን የመከስከሱ ዜና ሲሰማ 'ብላክ ቦክሱ' ተገኝቷል ወይ የሚል ጥያቄ ቀድሞ አብሮ የሚነሳ ጉዳይ ነው። ካፒቴን ተስፋይ "ሰው ከመሞቱ በፊት በኑዛዜ ወቅት ምን ብሎ ተናዞ ይሆን ብለን እንደምንጠይቅ አድርጎ ማሰብ ይቻላል። በተለይ ደግሞ ከመሞቱ ከ30 ደቂቃዎች በፊት ምን ብሎ ተናግሮ ነበር የሚለውን መረጃ የሚሰጠን ይሆናል።" 'ብላክ ቦክስ' ወይም ጥቁሩ ሳጥን እንደሱሙ ቀለሙ ጥቁር ሳይሆን ብርቱኳናማ ነው። ብላክ ቦክስ በየሰላሳ ደቂቃው እየደመሰሰ እና እየቀዳ መረጃዎችን ይቀመጣል። አንድ አውሮፓላን ላይ አደጋ ቢያጋጥም ከአደጋው በፊት የነበሩ የመጨረሻዎቹን 30 ደቂቃ መዝግቦ ይይዛል ማለት ነው። የብላክ ቦክሱ በድምጽ ቅጂ መያዣ ክፍሉ አብራሪዎቹ አደጋው ከመድረሱ በፊት የተነጋገሩትን ድምጽ ቀርጾ ያስቀምጣል። ካፒቴን ተስፋይ እንደሚሉት ብላክ ቦክሱ በጣም አስፈላጊ መሳርያ ስለሆነ በአደጋ ወቅት በቀላሉ ጉዳት እንዳይደርሰበት ታስቦ በአውሮፕላኑ ጭራ አከባቢ ነው የሚቀመጠው። ምክንያቱ የአውሮፕላን የኋላ ጫፍ ክፍል ከአደጋው የመትረፍ ዕድሉ ትልቅ ስለሆነ ነው። የባለሞያዎቹ ቡድን ብላክ ቦክሱ የያዘውን መረጃ በመተንተን ለአውሮፕላኑ መከስከስ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ይለያሉ። አውሮፕላን አብራሪ ሥነ ምግባር መጠበቅ አለበት። ከማንኛውም አይነት ሱስ የጸዳ፣ የአመጋገብ ሥርዓቱን ያስተካከለ፣ በቂ እንቅልፍ የሚተኛ እና አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርግ መሆን ይገባዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደግሞ “በሥነ ምግባር መርህ ላይ አይደራደርም” ይላሉ ካፒቴን ተስፋይ። ጥሩ የሠራ የሚበረታታበትና የሚያድግበት፣ ያጠፋ ደግሞ ያለ ምንም ማቅማማት የሚቀጣበት ተቋም መሆኑን ከካፒቴን ተስፋይ ንግግር መረዳት ይቻላል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብዙ አደጋዎች የማያጋጥሙትና ብዙዎች ከደህንነት አንጻር የሚመርጡት መሆኑ ይነገርለታል። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የአየር መንገዱ ሠራተኞች መልካም ሥነ ምግባር መሆኑን ካፒቴን ተስፋይ ይናገራሉ። ካፒቴን ተስፋይ ደስተኛ ጊዜያትን እንዳሳለፉ ሁሉ በጣም ያዘኑበት ወቅትም አለ። በተለይም በአጋቾች ምክንያት ኮሞሮስ ደሴት ላይ የተከሰከሰውን አውሮፕላን እንዲሁም ከሌባኖስ ቤይሩት ከተነሳ በኋላ አደጋ የደረሰበትን አውሮፕላን ይጠቅሳሉ። ከሁሉም በላይ ግን በቅርቡ ቢሾፍቱ ላይ የተከሰከሰው አውሮፕላን ያስታውሳሉ። በተለይ ደግሞ አብራሪዎቹ ምንም ማድረግ የማይችሉበት ሁኔታ በመከሰቱ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል። አደጋው በደረሰበት አውሮፕላን የነበረው ዋና ፓይለት አብሮዋቸው ረዳት ሆኖ ይሠራ እንደነበር አስታውሰው፤ “በጣም ጎበዝና ትልቅ ተስፋ የነበረው ወጣት ነበር” ሲሉ ይገልጹታል። ‘ቆይ ቦምቤ እንድረስና እንተያያለን” ካፒቴን ተስፋይ አውሮፕላን አስነስተው ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ወደ ቦምቤ ሕንድ እያመሩ ነው። አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች የምዕራብ አፍሪካ ሰዎች ናቸው። አንድ ናይጄርያዊ እና ሕንዳዊ ተጣልተው አውሮፕላኑ ተበጠበጠ። ካፒቴኑ መንገደኞቹን ማረጋጋት ያዙ። ‘አንተም ተው አንተም ተው’ ግልግል ገቡ። አረጋጉት። ናይጄርያዊው “ቆይ ቦምቤ እንድረስና እንተያያለን” ብሎ ዝቶ ወደ ወንበሩ ተመልሶ ጉዟቸውን መቀጠላቸውን ያስታውሳሉ። ጠጥቶ አውሮፕላን መሳፈር የተከለከለ ነው። ቢሆንም ሰክሮ መጨፈር የሚዳዳው አይታጣም። ጉዞ መሀል ላይ ብድግ ብሎ “አወርዱኝ” የሚልም ሞልቷል። ካፒቴኑ እንደነገሩን፤ ትንሽ ብልሽት ስላጋጠመን አስተካክለን ጉዟችንን እንቀጥላለን ሲባል፤ “ድሮም አልጣመኝም። አውርዱኝ!” ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚልም በብዛት ያጋጥማል።
49699381
https://www.bbc.com/amharic/49699381
"ፋና የሚፈልገን አይመስለንም" የምን ልታዘዝ ደራሲ
"ምን ልታዘዝ" ተከታታይ ድራማ በፋና ቴሌቪዥን ላይ ዳግመኛ እንደማይታይ የድራማው ደራሲና ፕሮዲውሰር አቶ በኃይሉ ዋሴ ለቢቢሲ ቢያረጋግጡም፤ የፋና ቴሌቪዥን የመዝናኛ ክፍል ከፍተኛ አዘጋጅ አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ በበኩላቸው "ድራማው የተቋረጠው ለምዕራፍ እረፍት ነው፤ በእርግጠኛነት ይቀጥላል" ብለዋል።
"ምን ልታዘዝ" ተከታታይ ድራማ፤ በፋና ቴሌቪዥን ላይ ከ2010 ዓ. ም. ጀምሮ በሦስት ምዕራፍ ለ38 ክፍል ሲተላለፍ የቆየ ድራማ ነበር። ይህ ፖለቲካዊ ስላቅ የሚቀርብበት ተከታታይ ድራማ፤ ዘወትር እሁድ ከሰዓት ከሚተላለፍበት ፋና ቴሌቪዥን ለእረፍት ተብሎ እንደተቋረጠና ዳግመኛ በጣቢያው ለእይታ እንደማይበቃ የተሰማው በመገናኛ ብዙኀን ነበር። የድራማው ፀሀፊ እና ፕሮዲውሰር አቶ በኃይሉ ዋሴ፤ ድራማውን በፋና ቴሌቪዥን ለማስተላለፍ ፍላጎት እንደሌላቸው ለቢቢሲ አረጋግጧል። • "ስተዳደር የቆየሁት በዋናነት ለመለስ በሚሰጠው የጡረታ ገቢ ብቻ ነው" ወ/ሮ አዜብ መስፍን • "ፍቅር እስከ መቃብርን አልረሳውም" ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም አቶ በኃይሉ እንደሚለው፤ ከፋና ጋር መሥራት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ሁኔታዎች አልጋ በአልጋ አልነበሩም። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ "ምን ልታዘዝ" በሚተላለፍበት ሰዓት ላይ ይዘቱ ከድራማው ጋር አንድ ዓይነት የሆነ ሌላ ድራማ እየተላለፈ መሆኑ "የሚነግረን ነገር አለ" በማለት፤ ጣቢያው እንደገፋቸው ያስረዳል። የድራማው አዘጋጆች ለሦስት ወር እረፍት (ሲዝን ብሬክ) ጠይቀው ድራማው መተላለፍ ማቋረጡን የሚናገረው በኃይሉ፤ በዚህ መካከል ፋና ብሮድካስቲንግ ሌላ ድራማ በነሱ ሰዓት ላይ ማስተላለፍ መጀመሩን አለመንገሩ፤ "ፋና የሚፈልገን አይመስለንም" እንዳስባላቸው ይገልጻል። የፋና ብሮድካስቲንግ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ዋና አዘጋጁ አቶ ዘካሪያስ በበኩላቸው፤ የእሁዱ የአየር ሰዓት ላይ ሌላ ድራማ እየተላለፈ መሆኑን አረጋግጠው፤ ይህ ግን "ምን ልታዘዝ" ከእረፍት እስኪመለስ ድረስ እንደሆነ ይገልጻሉ። አቶ ዘካሪያስ አክለውም፤ በእርግጥ እየተላለፈ ያለው ድራማ 'ሲትኮም' ቢሆንም በይዘት ግን ከ"ምን ልታዘዝ" ጋር አይገናኝም ብለዋል። በተጨማሪም የዚህ ድራማ ክፍሎች በቅድሚያ ማክሰኞ ምሽት ከታዩ በኋላ እሁድ እንደሚደገሙ ገልጸዋል። "የ "ምን ልታዘዝ" የምዕራፍ እረፍቱ ረዝሟል። እኛ ቶሎ እንዲመለሱ ብንፈልግም፤ እነርሱ የሦስት ወር የእረፍትና የዝግጅት ጊዜ በጠየቁት መሰረት አሁን ያሉት እረፍት ላይ ነው። የምናውቀው መስከረም ላይ እንደሚጀምሩ ነው" ይላሉ አቶ ዘካሪያስ። አክለውም የእሁዱ ሰዓት አሁንም ቢሆን የ"ምን ልታዘዝ" ነው ሲሉ አረጋግጠዋል። የድራማው ደራሲና ፕሮዲውሰር ከፋና ጋር የነበረን ግንኙነት አልጋ በአልጋ አልነበረም ሲሉ ላቀረቡት ቅሬታ አቶ ዘካሪያስ ሲመልሱም፤ "ከሁሉም ተባባሪ አዘጋጆች ጋር እንደምንነጋገረው ከእነርሱ ጋርም እንነጋገራለን። ሥራዎችን እንገመግማለን። እንጂ ከዚህ ውጪ የተፈጠረ ነገር የለም" ብለዋል። የ "ምን ልታዘዝ" ስፖንስር የነበሩ ሁለት ድርጅቶች ምክንያቱን በማያውቁት ሁኔታ ድጋፋቸውን እንዳቋረጡ አቶ በሀይሉ ይገልጻል። አክሎም ሌሎች ድርጅቶች የእነርሱን ድራማ ስፖንሰር ለማድረግ ይፈራሉ ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል። አቶ ዘካሪያስ ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም። ስፖንሰር ማድረግ አቋረጡ የተባሉት ድርጅቶች "እውነት ነው አቋርጠዋል" ካሉ በኋላ፤ ነገር ግን ይህ የተለመደ አሠራር ነው ይላሉ። እንዲያውም በድርጅቱ አሠራር በፕሮግራሞች ላይ ማስታወቂያዎች ቢተላለፉ፤ ለፋና እንዲሁም ለፕሮግራሞቹ አዘጋጆች አትራፊ መሆኑን ያብራራሉ። "ከዚህ አንፃር ካየነው፤ በፋና ቴሌቪዥን ካሉ ከ25 በላይ ተባባሪ አዘጋጆች እስካሁን ድረስ በገቢ ደረጃ አንደኛ "ምን ልታዘዝ" ነው" ብለዋል። የስፖንሰር መኖር ወይም አለመኖር ፋናንም ሆነ "ምን ልታዘዝ"ን በገቢ አይጎዳውም የሚሉት አቶ ዘካሪያስ፤ በርካታ ማስታወቂያዎች በድራማው ላይ እንደሚተላለፉ በመጥቀስ አቶ በኃይሉ ያቀረቡትን ምክንያት ያጣጥላሉ። በዚህ ሀሳብ የማይስማማው አቶ በኃይሉ፤ "የምንጠቀመው ስፖንሰር ቢኖረን ነው" ሲል ያስረግጣል። • የኢትዮጵያ ሙዚቃ- ከመስከረም እስከ መስከረም • በፈረንጅ "ናይት ክለብ" ጉራግኛ ሲደለቅ አቶ በኃይሉ ድራማውን በሌላ መንገድ ለመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ገልጾም "በድረ ገፅ ልናስተላልፈው እንችላለን" ሲል ፍንጭ ሰጥቷል። አቶ ዘካሪያስ ግን "ድራማው ተቋረጠ" መባሉን ከማኅበራዊ ሚዲያዎች ነው የሰማነው ይላሉ። "እስካሁን ቀርቦ ያነጋገረን አካል [ከድራማው አዘጋጆች ወይም ፕሮዲውሰሮች] የለም" ካሉ በኋላ፤ "የእረፍት ጊዜያቸው ስላለቀ ከድራማው አዘጋጆች ጋር ቁጭ ብለን እንነጋገራለን" ብለዋል።
46733684
https://www.bbc.com/amharic/46733684
አቶ ጌታቸው አሰፋ በየትኛው የሕግ አግባብ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ?
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በሰብዓዊ መብት ጥሰት የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸውን አቶ ጌታቸው አሰፋን አሳልፎ ለመስጠት ትብብር አላደረገም ብሏል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ይህን ያሉት፤ የመስሪያ ቤታቸውን የአምስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሰሞኑን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነበር። ከምክር ቤቱ አባላት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ ለምን ተይዘው ሕግ ፊት አልቀረቡም የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፤ ግለሰቡን በተመለከተ ለሚገኙበት ክልል ጥያቄ መቅረቡን ተናግረዋል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የት ናቸው? የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል? አክለውም አቶ ጌታቸው የክልል ምክር ቤትም ሆነ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አለመሆናቸውን ገልጸው፤ "አቶ ጌታቸው በትግራያ ክልል ተሸሽገው እንደሚገኙ መረጃው አለን። እሳቸውን አሳልፎ እንዲሰጠን ክልሉን ብንጠይቅም ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል" ብለዋል። ''እሳቸውን ለመያዝ ሌላ ሰው መግደል የለብንም'' ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በሰዎች ላይ የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሊያሳዝነን እና ሊያሳምመን ይገባል እንጂ ለግለሰቦች ከለላ መስጠት የለብንም ብለዋል። አቶ ጌታቸው አሰፋ በየትኛው የሕግ አግባብ ተላልፈው ሊሰጡ ይችላሉ? የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን ለመወሰን በወጣው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1996 አንቀጽ 4.3 መሠረት የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሰው ልጆች መብት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች የዳኝነት ሥልጣን እንዳላቸው ይደነግጋል። የሕግ ባለሙያው አቶ አዲ ደቀቦ፤ በወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ ማንም ይሁን ማን፤ ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረበት ወንጀል በፌደራል መንግሥት ስልጣን ስር የሚወድቅ እስከሆነ ድረስ፤ የፌደራል መንግሥቱ የማንንም ፍቃድ ሳይጠይቅ ወደ የትኛውም ክልል ሄዶ በወንጀል የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር የማዋል ስልጣን አለው ይላሉ። የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ከሚኖረው የወንጀል እይነቶች መካከል፤ በሰው ልጆች መብት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በውጪ ሃገራት መንግሥታት ላይ የሚፈጽሙ ወንጀሎች፣ የበረራ ደህንነትን የሚመለከቱ ወንጀሎች እና የመሳሰሉት በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚታዩ የወንጀል አይነቶች ናቸው። አቶ አዲ አንደሚሉት አንድ ግለሰብ የፌደራል መንግሥት ሰራተኛ ሳለ ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረበት ወንጀል ካለ፤ የፌደራል መንግሥት የየትኛውንም ክልል ፍቃድም ይሁን ይሁንታ ሳያስፈልገው ተጠርጣሪዉን በቁጥጥር ሥር አውሎ የመመርመር ስልጣን አለው ይላሉ። • ሜጀር ጄኔራል ክንፈ: ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም፤ ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’ በተመሳሳይ መልኩ ሌላው የሕግ ባለሙያ ሆኑት አቶ ኤፍሬም ታምራት አንድ የክልል መንግሥት በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠረን እና በፌደራል አቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተበትን ግለሰብ አሳልፌ አልሰጥም ቢል፤ ሕገ-ምንግሥቱን፣ የፌደራል የወንጀል ሕጉን፣ የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን ለመወሰን የወጣውን የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅን፣ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉን እና የፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅን ይተላለፋል ይላሉ። አቶ ኤፍሬም ሃሳባቸውን ሲዘረዝሩ፤ በሕገ-መንግሥቱ ሦስተኛው ምዕራፍ ላይ በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌዴራል መንግሥትና የክልል ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካሎች የመብቶችና የነፃነቶች ድንጋጌዎችን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለባቸው ተጠቅሷል። ''የማክበር ግዴታ ማለት እራሱ የመንግሥት አካል ወንጀል እንዳይፈጽም መከላከል ሲሆን የማስከበር ማለት ደግሞ ወንጀል የፈጸመውን ግለሰብ የመመርመር እና ሕግ ፊት የማቅረብ ኃላፊነት ማለት ነው'' ይላሉ። አቶ ኤፍሬም የክልሉ ውሳኔ የፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እንዴት እንደሚጻረር ሲያስረዱ፤ አንቀጽ 6 ሥር የተቀመጠውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን ሥልጣን እና ተግባርን በመዘርዘር ያስረዳሉ። አቶ ኤፍሬም እንደሚሉት ከኮሚሽኑ ሥልጣን እና ተግባራት መካከል በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሥልጣን ክልል ስር የሚወድቁ ወንጀሎችን ይከላከላል፤ ይመረምራል። የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን ለመወሰን የወጣውን የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1996 የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የተፈጸሙ የወንጀል ተግባራትን ማየት የሚችለው የፌደራል ፍርድ ቤት መሆኑን በመጥቀስ ለፌደራል መንግሥት የተሰጠ ስልጣን ክልሎች እንደማይኖራቸው የሕግ ባለሙያው ያስረዳሉ። የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉም ማንኛውም ዜጋ በተግባሩ ጉዳት እስካልደረሰበት ድረስ፤ በወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ አሳልፎ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት እንደሚያትት የሚናገሩት የሕግ ባለሙያው የክልል መንግሥታትም ቢሆኑ ይህን የሕግ ኃላፊነት ከመወጣት ወደኋላ ማለት አይችሉም ይላሉ። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ተገለፀ በወንጀል የሚፈለግን ግለሰብ አሳልፌ አልሰጥም ማለት በራሱ ፍትህን የማስተጓጎል ወንጀል ነው የሚሉት አቶ ኤፍሬም፤ ዛሬ ላይ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠረን ግለሰብ አሳልፌ አልሰጥም የሚል የሕግ አስፈጻሚ አካል፤ ነገ ሰልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም በሚል በወንጀል ሊጠየቅ ይችላል ይላሉ። ይህን ተግባራዊ ሊያደርግ የሚችለው የየትኛው የፌደራል አካል ነው? የሕግ ባለሙያው አቶ አዲ ይህ ከወንጀል ምርመራ ጋር የተያያዘ ሰለሆነ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር የማዋል ስልጣኑ የፌደራል ፖሊስ ነው ይላሉ። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመጣመር ሥራውን ሊያከናውን እንደሚችልም ይጠቁማሉ። የፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 መሠረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት ሲዘረዝር፤ ከክልሎች አቅም በላይ በሆኑ ጉዳዮች ኮሚሽኑ በመንግሥት ውሳኔ መሠረት በክልሎች ውስጥ ጣልቃ ገብቶ በሚሠራበት ወቅት የሚመለከታቸው የክልል ፖሊስ ኮሚሽን ትብብር ማድረግ አለባቸው ይላል። አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ የተመሰረቱት ክሶች ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ጋር በተያያዘ ለአምስት ወራት አከናወንኩ ያለውን የምርመራ ውጤት ሕዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም ይፋ አድርጎ ነበር። በወቅቱ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታን በተመለከተ በዋናነት ወንጀሉን የመሩትና በገንዘብ የደገፉት የብሔራዊ ደህንነት እና መረጃ ኤጀንሲ የቀድሞው ኃላፊ ናቸው ብለው ነበር። • የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተነሱ በተጨማሪም ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በሽብር ተጠርጥረው የሚያዙ ግለሰቦች በብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አመራሮች እና አባላት አማካኝነት የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይፈጸምባቸው እንደነበረ ዘርዝረዋል። የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ምላሽ ሰሞኑን የጠቅላይ አቃቤ ሕጉ የተናገሩትን ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግሥት ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጠ ሲሆን፤ ቢቢሲም ከክልሉ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። ነገር ግን ቀደም ብሎ ከሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እስር ጋር በተያያዘ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳደር የሆኑት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ክስ እና እስሩን በመኮነን ጠንከር ያለ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። የቀረቡት ክሶች በአንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ መሆኑን አንስተው ''የኛ ሰው ለምን ታሰረ? አንልም።. . . ሁሉም መጠየቅ አለበት" በማለት እርምጃው ፖለቲካዊ አላማን የያዘ መሆኑን ተናገረዋል። ጨምረውም ክሱ የተለየ ዘመቻ መሆኑንና ማንነታቸውውን በግልጽ ያላስቀመጧቸው ወገኖች እጅ እንዳለበት "ትግራይን ለማዳከም የውጪ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እየታየ ነው፣ በትግራይ ህዝብ ላይ አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል'' በማለት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በማለት ክስ እና እስሩን ተቃውመውት ነበር።
news-49232053
https://www.bbc.com/amharic/news-49232053
"የክልሎች ልዩ ኃይልን በተመለከተ ውይይት ያስፈልጋል" የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝደንት
ከ16 ወራት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ መንበረ ስልጣኑን ተረክበው ሃገሪቱን መምራት ሲጀምሩ፤ ለአስተዳደራቸው ከፍተኛ ፈተና ይሆናል ተብሎ ተገምቶ የነበረው የሶማሌ ክልል ሁኔታ ነበር።
ይሁን እንጂ የሶማሌ ክልል እንደተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ምናልባትም ከተቀረው የአገሪቱ ክፍል በተሻለ መልኩ አንጻራዊ ሰላም የሚታይበት ክልል ሆኗል በማለት የሚመሰክሩ በርካቶች ናቸው። የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ ሙሐመድ በክልሉ ለተመዘገበው አዎንታዊ ውጤት ምክንያት ናቸው ያሏቸውን ነጥቦች ለቢቢሲ ተናግረዋል። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ በርካቶች ክልሉ ወደ መረጋጋት በቀላሉ አይመለስም ብለው እንዲያስቡ ያደረጓቸው ሦስት ነጥቦች አሉ ይላሉ። • መንግሥትና ኦብነግ የጀመሩት ጉዞ የት ያደርሳል? የመጀመሪያው "አቅሙ ይብዛም ይነስ በክልሉ የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል ነበር። ሁለተኛው ደግሞ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አጎራባቸው ቀበሌዎች የተከሰቱት ግጭቶች ሲሆኑ ሦስተኛው ደግሞ ሐምሌ 8 በጅግጅጋ ትውልደ ሶማሌ ያልሆኑ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ከግምት በማስገባት ነው" ይላሉ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በሃገር አቀር አቀፍ ደረጃ እንደታየው፤ በርካታ ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ወደ ሃገር ተመልሰዋል። ታጥቆ የፖለቲካ ትግል ሲያደርግ የነበረው ኃይልም ወደ ክልላችን በሰላማዊ ትግል ለማድረግ መወሰኑ ለክልላችን ሰላም የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል ይላሉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ። "በኦሮሚያ እና ሶማሌ ደንበር አቅራቢያ ችግሮችን ይፈጥር የነበረው አመራሩ ነበር። አመራሩ ከተቀየረ በኋላ ህዝቡ በሰላም መኖር ጀመረ። ከዚያ ችግሩ ተቀርፏል።" ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት በጅግጅጋ ተከስቶ የነበረው ሁከት አሁን ተረጋግቶ ህዝቡ የተመለደውን ህይወት እየመራ እንደሆነ እና ክልሉ ላስመዘገበው ውጤት ይህ ወሳኙ ጉዳይ መሆኑን ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ ይናገራሉ። የድንበር ይገባኛል ግጭቶች ባለፉት ሦስት ዓመታት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች አዋሳን ስፍራዎች ላይ ለሚከሰቱ ግጭቶች እንደምክንያት ተደርገው ሲቀርቡ ከነበሩት መካከል የግጦሽ መሬት እና የድንበር ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው። ከድንበር ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት አስተዳደራቸው ምን እየሰራ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ ሲመልሱ "በመጀመሪያ ደረጃ ባለፉት ዓመታት ለተከሰቱት ግጭቶች ምክንያቱ የግጦሽ መሬት ወይም የድንበር ጉዳዮች አልነበሩም። የመንግሥት መዋቅር ያለበት አሻጥር ነው ህዝቡን ከፍተኛ ችግር ውስጥ የከተተው እና ያፈናቀለው።" • አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ ምክትል ፕሬዝድንት ሙሰጠፌ እንደሚሉት ከሆነ በሁለቱ ክልሎች አጎራባች ድንበር ላይ ለተከሰተው ግጭት የድንበር ወሰን ማበጀት መፍትሄ አይሆንም። "የህዝቡ ችግር በዘላቂነት የሚፈታው በማካለል [ድንበር] አይደልም። ህዝቡ አብሮ እንዲኖር የአመለካከት ለውጥ በማምጣት እና ሁሉንም ከልማት ተጠቃሚ በማድረግ ነው።" ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ እንደሚሉት አሁን ሃገሪቱ ያለችበት ሁኔታ የድንበር ማካለል ሥራ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አለመሆኑን እና ወደፊት መንግሥት በሚያስቀምጠው መርሃ ግብር ሊከናወን እንደሚችል ጠቁመዋል። የሞያሌ ከተማ እጣ-ፈንታ ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የምታዋስነው የሞያሌ ከተማ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ይካሄድባታል። የኬንያ እና የኢትዮጵያን መንግሥትን ጨምሮ በብዙ ሃገራት የተያዘው የላሙ ወደብ ፕሮጀክት ሞያሌን የደረቅ ወደብ መናኸሪያ ያደርጋታል ተብሎም ይጠበቃል። ሞያሌ በርካታ የኦሮሞ እና የሶማሌ ተወላጆች በስፋት ይኖሩባታል። ታዲያ ይህች የንግድ ከተማ ትገባኛለች በሚል በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደጋጋሚ ግጭቶች ተከስተዋል ጉዳትም ደርሷል። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ለዚህ ችግር መፍትሄ ለማበጀት የፌደራል እና የሁለቱ ክልል መንግሥታት ምን እየሰሩ ነው? ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ ሲመልሱ፤ "ቅድሚያ የምንሰጠው ለሰላም ነው። ስላም ለማስፈን እየሰራን ነው። በአሁኑ ወቅት ግጭቶች የሉም። በሞያሌ ከተማ ዙሪያ ከአከባቢው ነዋሪዎች፣ ኦሮሚያ እና ከፌደራል መንግሥት ጋር በመወያየት መፍትሄ እንሰጣለን እንጂ፤ አሁን ላይ መፍትሄው ይህ ነው ብዬ ለመናገር ይከብደኛል" ብለዋል። ፍትህ እና ነጻነት ከአንድ ዓመት በፊት በጅግጅጋ የሶማሌ ተወላጅ ባልሆኑ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሞ ነበር። በወቅቱ መንግሥት ለጥቃቱ ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን ኃይሎች ለፍርድ እንደሚያቀርብ የገለጸ ሲሆን፤ ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌም አስተዳደራቸው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ተናግረዋል። "የጥቃቱ ዋና አቀነባባሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ሌሎች ተሳታፊ የሆኑት ደግሞ አሁንም ድረስ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው፤ ተይዘው እየቀረቡ ነው። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸውንም በተቻለን አቅም እየደገፍን ነው።" • የቀድሞው የሶማሌ ክልል ሰንደቅ አላማ እንዲመለሰ ተደረገ ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ፤ "ዋናው ትኩረታችን መሰል ጥቃቶች በክልላችን ዳግም እንዳይከሰቱ ማደረግ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት ምንም አይነት ችግር አልገጠማቸውም። ማንም ሰው የየትኛውም እምነት ተከታይ ሆኖ መኖር ይችላል። ለዚህም የክልሉ መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል" ሲሉ ተናግረዋል። ይህን የፕሬዝዳንቱን ቃል የበለጠ የሚያጠናክረው ደግሞ ባለፈው ዓመት በተፈጸመ ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው አብያተ ክርስቲያናትን ጥገና ለማድረግ የክልሉ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በይፋ የሰጠችው እውቅና የሚጠቀስ ነው። የሙሰጠፌ አስተዳደር ፈተናዎች ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ ትልቁ የአስተዳደራቸው ፈተና ከፍተኛ ቁጥር ላለው ሥራ አጥ ወጣት ሥራ መስጠት መሆኑን ይናገራሉ። ሥራ አጥ የሆነው ወጣት ቁጥር በጨመረ መጠን የክልሉ ሰላም የመደፍረስ እና የልማት እንቅስቃሴዎች የመስተጓጎል አጋጣሚዎች ከፍ እንደሚሉ ያስረዳሉ። "ሥራ አጥ የሆነን ወጣት የትኛውም ኃይል ሊጠቀምበት ይችላል" የሚሉት ምክት ፕሬዝደንቱ ለወጣቶች ሥራ የሚያስገኙ የልማት ሥራዎች ላይትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ይናገራሉ። ልዩ ፖሊስ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በተደጋጋሚ የመብት ጥሰት እንደሚፈጽም ክስ ይቀርብበት የነበረው የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ፤ የአደረጃጀት ለውጦች እንደተካሄዱበት ምክትል ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል። ጥፋተኛ የተባሉት ከልዩ ኃይሉ እንዲገለሉ ከተደረገ በኋላ በሰብዓዊ መብት አያያዝ እና የሕገ መንግሥት ስልጠናዎች እንዲወስዱ እንደተደረጉ ምክትል ፕሬዝደንቱ ተናግርዋል። "ከፍተኛ መሻሻል እንዳለ ህዝቡ ይመሰክራል። ልዩ ኃይል አሁን ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አይፈጽምም" ብለዋል። • መንግሥት ልዩ ፖሊስን እንዲበትን አምነስቲ ጠየቀ በክልሎች ደረጃ የልዩ ኃይል አስፈላጊነትን የተጠየቁት ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ፤ "አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ልዩ ኃይል የሚያከናውናቸው ቀልጣፋ ሥራዎች አሉ። ልዩ ኃይል በእኛ ክልል ይቀጥላል። በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያለው" ያሉ ሲሆን "ወደፊት የክልል ልዩ ኃይሎች ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር ስለሚኖራቸው ቁርኝት ወይይቶች ሊያስፈልጉ ይችላሉ" ብለዋል። ኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) በቅርቡ የትጥቅ ትግሉን አቁሞ ወደ ሃገር መመለሱ ይታወሳል። ምክትል ፕሬዝደንት ሙሰጠፌ እንደሚሉት ታጥቆ ልዩ ኃይልን የተቀላቀለ የኦብነግ ኃይል የለም። "የኦብነግ ታጣቂዎች አስፈላጊው ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ነው የተደረጉት" ብለዋል።
49644837
https://www.bbc.com/amharic/49644837
"ከልጅነቱ ጀምሮ የተረጋጋ ነበር" እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ
ከጥቂት ወራት በፊት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ. ም. ኢትዮጵያ በታሪኳ በብዙዎች ዘንድ የማይሽር የታሪክ ጠባሳን ጥሎ ያለፈ ክስተት አጋጠማት።
የብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ እናት እማሆይ የውብሰፈር አሳዬ የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን፣ ሜጄር ጄኔራል ገዛኢ አበራ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴንና የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደን በጥቂት ቀናት ውስጥ አጥታለች። ይህንን የከሸፈውን "መፈንቅለ መንግሥት" አቀነባብረዋል የተባሉት በወቅቱ የአማራ ክልል የደኅንነትና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ከክስተቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውም ተነገረ። ባህርዳር ዙሪያ በሚገኝ ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በባጃጅ ለማምለጥ ሲሞክሩ እንደሞቱ ተዘግቧል። የብርጋዲየር ጄኔራሉ ቀብር በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በቤተ ጊዮርጊስ ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ. ም. ተፈፅሟል። በቅርቡ ላሊበላ የነበረው የቢቢሲ ባልደረባ የቀድሞው የደኅንነትና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ እንዴት እንደሚታወሱ ከእናታቸው እማሆይ የውብሰፈር አሳዬ፣ ከእህታቸው ደስታ ፅጌና ጓደኛቸው ፀጋዬ ማሞ ጋር ቆይታ አድርጓል። እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ- እናት ቢቢሲ፡ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ሲወለዱ የተለየ የሚያስታውሱት ነገር አለ? እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ ሁለተኛ ልጄ ነው፤ እኔ ወራቱን አላውቀውም። የጥምቀት ታቦቱ ሲወርድ ነው የተወለደው። አውደ ዓመት ስለነበር እንግዳም አዝማሪም ሞልቷል። የዓመት አውደ ዓመት አለ፣ የታህሳስ ተክለሃይማኖት ይባላል በአገራችን። ቤተሰብ በተሰባሰበበት ታላቅ ወንድሙ ስምሪት ቆይቶ ይመጣል። እዚያ ቆይቶ ሲመጣ አዝማሪውም እንግዳውም ሆይ ሆይ እያለ፣ ትልቅ አዳራሽ ነው፤ ከዚያ ከሞላው እንደመጣ ገብቶ ወጋግራውን ያዘ። ና ሲሉት ወጋግራውን ይዞ ዝም አለ። "ተዉት እስቲ ያስተውልና ወደሚፈልገው ይቅረብ" ሲል አባትየው፤ ዝም ብሎ ቆይቶ ታላቅ ወንድሙ "ጌታሸት" ሲል "አቤት አለ" አባትየው "የሚወለደው ወንድ ነው ስሙን አሳምነው በለው" አለው። ወዲያው አባትየው "ሊቀመኳስ" ብሎ "አቤት" ይለዋል "አዳምጠኝ" ይለዋል፤ "እሺ" ሲለው "አይቆረጠምም የተልባ ቆሎ አሳምነው ጽጌ በትንቢት ያለ" ብሎ እዚያው ገጠመ። እንደዛሬው ራዲዮ የለም፤ ቴሌቪዥን የለም፤ አዝማሪ ነው ቤተሰብ የሚያሟሙቅ፣ በዚያው ሆኖ ቀረ ስሙ። ጎበዝ ተማሪ ነበሩ? እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ ላሊበላ ነው ትምህርት ቤት የጀመረው። አስኳላ ነው የጀመረው። አዎ ድንቅ ነው። የሙያ ሕይወታቸውን በመምህርነት ነው የጀመሩት፤ እንዴት ወደ ትግሉ ገቡ? እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ መጀመሪያ መምህር ነው የነበረው ሌላ ቦታ። እኒህ ህወሓቶች ሲመጡ ወደ መቄት ሲሻገሩ ልጄን ይገሉብኛል ብሎ አባትየው በበቅሎ ይዞት መጣ። ይዞት መጥቶ ና ተቀመጥ አለው። እነሱም እዛው ነበሩ። እነሱ ጋር እየገባ እየወጣ፣ እየገባ እየወጣ ወሰዱት፤ ኋላ "አገር ጎብኝተን ልንመጣ ነው" አለኝ። "መቼ ትመጣላችሁ" ስል "አይታወቅም" አለኝ። ከማንጋር ነው ስለው "እገሌ ጋር" አለኝ። ባልንጀራው ጋር እንደሱ መምህር ነበር። ታዲያ ቶሎ ትመጣላችሁ ስለው "አይታወቅም" አለኝ። እሽ ብዬ ዝም አልኩኝ።በ ኋላ በአራተኛ ቀን ይሆናል እኛ ያለንበት ስብሰባ አድርገው ለአገራችን፣ ለድርጅታችን ያሉት ወንድሞቻችን እነአሳምነው ጽጌ እና ደጉ አስናቀ ይኼው ትግል ሄደዋል ተብሎ ተነገረ። ያን ጊዜ ከስብሰባው ወጥቼ እሪ አልኩኝ ጎረቤትም ተሰብስቦ አፅናናኝ፤ ልጁ ደግሞ ወደ ደጅ ወጥቶ አያውቅም ከተማሪ ወጥቶ አስተማሪ ነው የሆነው። • የብ/ጄነራል አሳምነው ፅጌ ሚስት መታሰራቸውን ልጃቸው ገለጸች • የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ • "ብ/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ከአስተማሪነት ወጥቶ ነው ትግል የገባው። ያው ሲያገኙት ሆይ ሆይ ብለው አስገቡት። በዚያው ሄዶ፤ ደህና ሳይቆስል፣ ምን ሳይል መጣ። በሠላም መጣ። እኔም መጣልኝ ብዬ ደስ ብሎኝ ሳለ ደግሞ እዚሁ ድርጅት ገባ። ከዚያ ወዲህ እንዲህ ነው ያለው። አንዴ ውጭ አገር ሂድ ሲሉት፣ አንድ ጊዜ ታሰር ሲሉት፤ ብሎ ብሎ መጨረሻው ይኼ ሆነ። ምን አይነት ልጅ ነበሩ? እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ ባህሪው ጥሩ ነው፣ የተለየ ባህሪ የለውም፣ የታወቀ ነው። እንደሰው አሁን ቁጥት፣ አሁን ሳቅ አይልም። ጠባዩ አንድ ነው። ቅብጥብጥ ያለ ነገር የለውም። እንደልጅ ጨዋታ፣ ፍቅርም ጠብም የለውም። የተረጋጋ ነው ከልጅነቱ ጀምሮ። መቼም ድንቅ ነው እንደ ልጅ ቅብጥብጥ ያለ ድርስ ምልስ ያለ ነገር የለውም። ድንቅ ልጅ፣ ቀና፣ ለኔ አሳቢ ነበር፤ ለሁሉም ነገር። እስር ቤት ሳሉ የነበሩበት ሁኔታስ? እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ እኛ እየሄድን ማየት ነው እንጂ ሁኔታውን ማን ያውቃል። አዲስ አበባ ቃሊቲ አሰሯቸው፤ ከዚያ ደግሞ ዝዋይ ወሰዷቸው። እዚያ በዓመት ሁለት ጊዜ እየሄድኩ እጠይቀዋለሁ። ምን ይለኛል "መንገድ መሃል ገብተሽ አትሂጂ፤ ልብሽ ብዙ ያስባልና ሃሳብ ላይ ስላለሽ መኪና ይመታሻል የፊትሽን ስታዪ በኋላ ይገጭሻል"። "የኋላ መጣ ስትዪ፤ የፊትሽ ይገጭሻል፤ ወይ ከዚህ ሆነሽ ወይ ከዚያ ሆነሽ ጸልዪ መንገድ አትግቢ" ይህንን ይለኛል። ሊፈቱ ነው ተባለ። እኛም እነሱን ለማምጣት ሄድን። ተፈቱልን ይዘን መጣን። ከዚያ አገርም ጎብኝተው፣ ከዚህም አርፈው ወደ አዲስ አበባ ሄዱ። ዓመት በዓልንስ እንዴት ነው የሚያሳልፉት እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ ያርዳል፣ እኛ እንጠምቃለን እንጋግራለን። ጎረቤት፣ ቤተሰብ ጋር አብረን በልተን ጠጥተን፣ ስቀን፣ ተጫውተን አመት በዓል እናሳልፋለን እንደዚህ ነው አዋዋሉ። ከዚያ መለስም ወረቀት ያነባል። በዓመት በዓልም፣ በሌላውም ጊዜ ይረዳኛል። ሁልጊዜም ጠያቅዬ ነው። ቤተሰብ አፍርተዋል? ከሞቱ በኋላስ ይጠያየቃሉ? እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ አዎ አግብቷል ወልዷል። ከመጀመሪያ ሚስቱ አንድ ልጅ ወልዷል። ከእሷ ጋር ሲለያዩ ደግሞ ሦስት ልጅ ወልዷል። አይ የሞተ እለት መጥው ነበር። የ40ው ዕለትም መጥተው ነበር፤ እንጂ ምን አቅም አግኝቼ? እያኸኝ። ያው እሱ ታስሮ ሳለ ወደ እሱ ነበር እሄድ የነበረው። ፊት እነሱንም እጠይቅ ነበር፤ ኋላ ግን እየደከመኝ አልሆን አለኝ። ለመጨረሻ ጊዜ መች ነው ያዩዋቸው? እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት "ለትንሳኤ ነይ ብሎ ነው። አምና ካንቺ ውለናል ዘንድሮ ነይ ከእኛ" ብሎ ሚስቱን ላካት። እኔ እንኳን አልሄድም ስል፤ ከዚህ ነው የምንውለው ብሎ ላከብኝ። ሄድኩኝ ለትንሳኤ አየሁት። ታርዶ፣ ተጠምቆ ነበር። ከሰዎች ጋር መጥቶ ለአውደ ዓመት ቀምሶ ሄደ እንጂ ደግሞ አልመጣም። ከዚያ ወዲህ አልመጣም። አሁን የጠፋው ወንድሙ ሌላ ስፍራ ነበር። ከእሱ ሄደን ስንጫወት ውለን በዚያችው እንደተለያየን ቀረን። ቀኑን ለይቼው አላውቅም፤ ሆዴ እየተጨነቀ እምቢ ሲለኝ ደውሉልኝ አልኩ። ደሞ ወደማታ አሁን መጥቶ ይሆናል ደውሉለት ስል፤ ኧረ ደክሞት ይተኛል፤ ደሞ ይረፍበት የሚያሳርፈው የለም አሉኝ። ከሥራው ደግሞ ይደውሉለትና በዚህ ና ይሉታል፣ ውክቢያ ነው የሱ ኑሮ ተይው ጥቂት ይረፍ ይሉኛል። ድንቅ እላለሁ፣ በዚያው ድምጹን ሳልሰማ ቀረሁ፣ በዚያው ቀረሁ። ሰኞ መጀመሪያ ባህርዳር ረብሻ ተነስቶ ተኩስ ተሰምቷል መባሉን ስሰማ፤ እንዴት ሆኖ ይሆን? ይኼ ልጅ እንዴት ነው ነገሩ? ስል እሱማ ያሰለጠናቸውን ወታደሮች ይዞ ጎንደር ገብቷል ያንቺው ልጅ ይሉኛል። ጎንደር ከገባልኝማ ልጄ አይሞትም። እንኳን በዓይን አይተውት በዝና ታስሮ እያለ፤ ጀነራል ተፈራ ማሞ፤ ጀነራል አሳምነው ጽጌን ፍቱልን እያሉ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ሲጠይቁ ነበር ሲባል ሰምቻለሁ። ጎንደር ከገባማ ልጄ አይሞትም እያልኩን ተስፋ አደረኩኝ በእጄ የያዝኩት መስዬ። በኋላ ደግሞ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲህ ተብሎ ተወርቶ፤ ሰኞ እንዲህ ሆነ እያሉ መጡ። እንደው የማይረሳዎት ትዝታ አለ? እማሆይ የውብ ሰፈር አሳዬ፡ ምን አስታውሳለሁ። ይጦረኛል ይቀብረኛል ነው እንጂ ምን አስታውሳለሁ። አሁንማ ተፈቶልኝ ደስ ብሎኝ ነበር። ይሄንን ነው የማስታውሰው እንጂ ሌላ ምን አስታውሳለሁ። ደስታ ጽጌ- እህት አሳምነው ሦስተኛ ታላቄ ነው። እኔ ህጻን እያለሁ፣ እሱ አስተማሪ ነበር። እየመጣ ይጠይቀን ነበር፤ ተማሪ ይለኝ ነበር። ርህሩህ አንጀት ነው ያለው፤ ያለውን ነገር ይዞ ከቤተሰቦቹ ጋር ሰብሰብ አድርጎ፣ አውደ ዓመትም ይሁን ከቆዬበት ሲመጣ ተሰባስበን፣ ያለውን ነገር አብረን ተካፍለን ተጫውተን እንድንለያይ ነው የሚፈልገው። የወንድ ልጅ ሳይሆን የእናት አንጀት ነው ያለው እላለሁ። የእስር ቆይታቸው ምን ያህል ለቤተሰቡ ከባድ ነበር? ደስታ ጽጌ፡ እስር ቤቱ በጣም ከባድ ነበር፤ ያውም ዘጠኝ ዓመት። መጀመሪያ ማዕከላዊ ነበር። ስንቅ ዝም ብለው ይቀበሉናል። እኛ ተስፋችን ስንቅ ሲቀበሉን ነው፤ መኖር አለመኖሩን የምናውቀው ማለት ነው፤ ሰሃኑን ከተቀበሉን ደስ ብሎን እንመለሳለን። ዛሬ አንቀበልም ብለው ምግቡን ይዘን ከተመለስን፤ ነገ ነግቶ ደግሞ ምን እንደሚፈጠር እየጠበቅን እያለቀስን ነው የምንውለው። እነሱን ወደ ማረሚያ ሲልኩ አሁን ተሰወረ የተባለው ወንድሜ እሱ ተለቀቀ። ሦስት ወር አይደል ጨለማ ቤት የነበሩት። ከዚያ እነሱ ወደ ቃሊቲ የእድሜ ልክ እስራት፤ እሱ ነጻ ተብሎ ተለቀቀ። ቃሊቲ ስንቅ እያመላለስን እያለ በኋላ ደግሞ ወደ ዝዋይ አራቁት። እስር ቤት በነበረበት ወቅት፤ እሱን ብዬ፣ ሁሉን ነገር ትቼ አዲስ አበባ ነበርኩ። ቤት ተከራይቼ የማላውቀውን ሥራ ሁሉ ሰርቻለሁ ለእሱ ስል። እኛ ለሁሉም ነገር አቅሙ የለንም። ኃይል የእግዜር ነው። ያንን ሁሉ አልፎ ነበር። ብርዱ፣ ታክሲው አልፏል። እየተገፋን፣ ዘንቢል ይዘን ወድቀን ነበር። እግዜር ለቅሶአችንን ሰምቶት ሰጥቶን ነበረ። አሁን ደግሞ መጨረሻ አንድ ዓመት ያልሞላ ደስታ። ብቻ ከባድ ነው። ሰው ሆኖ መቆማችን ራሱ ህልም ይመስለኛል። ወንድሜ ሳይሆን እናቴ ነው ማለት እችላለሁ። በምን ታስታውሻቸዋለሽ? ደስታ ጽጌ፡ እኔ እስከማውቀው ርህሩህ መሆኑን፣ ሰው አፍቃሪነቱን፣ ቤተሰብ የሆነ ያልሆነ አለማለቱን ነው። ማዕድ ተዘርግቶ፤ ይሄኛው አይበቃኝም፣ ይሄኛው ይሂድ የሚል ሰው አለ። እሱ አምጡ አቅርቡ ነው። ለምን ትመልሳለችሁ? ግባ በሉት? ነው የሚለው። ይሄንን ማንም መጠየቅ ትችላለሁ። በዓል አያከብርም፤ ለእኛ ግን ያከብርልናል። እመጣለሁ ይላል እናዘጋጃለን። ለቤተሰብ ደስታ ሲል ደርሶ ተመልሶ ይሄዳል። ለሰው የሚኖር እና የተፈጠረ ነው፤ እኛን አስደስቶ ይሄዳል። ልጆቹን በጣም ይወዳል። ጸጋዬ ማሞ - ጓደኛ ትውውቃችሁ እንዴት ነው? ጸጋዬ ማሞ፡ ከ1984 ጀምሮ አውቀዋለሁ። የላሊበላ አስተዳዳሪ ሆኖ፤ በትጥቅ ትግል ወቅት እኔም እሱም ታግለናል። ትውልድ አካባቢያችን ተመሳሳይ ነበር። በኋላም በትውልድ አካባቢያችን ተመደብን፤ እሱ የቡግና ወረዳ አስተዳዳሪ ሆኖ። እኔ ደግሞ በጤና ሙያ እየሠራሁ ነው የምንተዋወቀው። ብርጋዴር ጄነራል አሳምነውን እንዴት ይገልጿቸዋል? ጸጋዬ ማሞ፡ አሳምነው ፍጹም ዴሞክራት፣ ጥሩ፣ ሰው አክባሪ ስብዕና ያለ፣ ፍጹም ሜካናይዝድ ሰው ነው። ሰውን ዕኩል የሚያይ፣ ተገልጋይ ቢሮ ሲሄድ ከመቀመጫው ተነስቶ ችግር የሚፈታ አይነ ግቡ ትልቅ ሰው ነው። ተጫዋች፣ በሥራ የሚያምን፣ ትሁት ነው። ለቅሶ ይሄዳል፤ በማኅበራዊ ሕይወቱ ደግሞ ትልቅ ቦታ ነበረው። ህብረተሰቡ ከድህነት ወጥቶ፣ ልማት፣ ትምህርትና ጤና እንዲደራስ ሳያሰልስ ሰርቷል። ብዙም አሳክቷል። ህብረተሰቡ ተለውጦ ስኬታማ እንዲሆን ነበር ምኞቱ። አሳምነው በጣም የእምነት ሰው ነው። አባቱም አገልጋይ ነበሩ። ኪዳነምህረት ሁሌም ይዘክራል። ጎረቤት እየጠራ ይዘክራል። እንደጓደኛ እኔም እሳተፍ ነበር። በዓልን እንደ ሕዝበ ክርስቲያኑ ያከብር ነበር። ሕዝቡን እኩል የሚያይ ነበር። ሁሌም ሲመጣ ስለ ክልሉ፣ ስለ ልማት እና ስለአማራ ሕዝብ አንስቶ ይብሰለሰላል፤ መጥቶም ለተተኩት አስተያት ይሰጣል። ሲመጣም ስለሕዝቡ ነው ብሶቱ፤ በግልም የሚነግረኝ ስለቤተሰቡና ስለ ግል ሕይወቱ ሳይሆን፣ ስለህብረተሰቡ ሲያወራ ነው የማውቀው።
news-55677504
https://www.bbc.com/amharic/news-55677504
ማኅበራዊ ሚዲያ፡ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ወደ ቴሌግራም ለምንድን ነው እየፈለሱ ያሉት?
ለመልዕክት ደኅንነት አስተማማኝ እንደሆነ ሲነገርለት የቆየው ዋትስአፕ የተሰኘው መተግሪያ በአጠቃቀም ደንብና መመሪያው ላይ ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ በርካታ ተጠቃሚዎች ወደ ሌሎች አማራጭ መተግበሪያዎች እያማተሩ ነው።
ዋትስአፕ በዓለም ዙሪያ ሁለት ቢሊዮን ያህል ተጠቃሚዎች እንዳሉት የሚነገር ሲሆን ተጠቃሚዎች የሚለዋወጧቸው መልዕክቶች ምስጢራዊነታቸው ከየትኛውም ወገን የተጠበቀና አስተማማኝ እንደሆነ ስለሚታመን በርካታ ተጠቃሚን ማፍራት ችሎ ነበር። ነገር ግን በቅርቡ ዋትስአፕ የተጠቃሚዎቹን ግላዊ መረጃዎች ለሚያስተዳድረው ፌስቡክ እንደሚያጋራ በመጥቀስ የአጠቃቀም ደንቡና መመሪያውን እንዳሻሻለ አሳውቆ፤ በዚህ የሚስማማ አብሮት እንዲቀጥል ካልሆነም መተግበሪያውን መተቀም እንዲያቆም አስከ የካቲት መጀመሪያ ሳምንት ድረስ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ነበር። ይህ ውሳኔ ከብዙዎች ዘንድ ተቃውሞና ትችትን ያስከተለበት ዋትስአፕ ውሳኔው እንደማይለወጥ በመግለጽ ነገር ግን የተቀመጠው የጊዜ ገደብ እስከ ግንቦት አጋማሽ ድረስ እንሚቆይ ገልጿል። ግላዊ መረጃቸውና የሚለዋወጡት መልዕክት ደኅንነት ያሰጋቸው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አማራጭ መተግበሪያዎችን በመፈለግ ወደዚያው እያቀኑ ነው፤ በተለይ ሲግናልና ቴሌግራም የተባሉት የመልዕክት መለዋወጫዎች የተጠቃሚያቸው ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው ተብሏል። ይህ መሆኑ ለምን ያሳስበናል? የግል መረጃዎቻችንን ደኅንነትስ እንዴት መጠበቅ አለብን? የዘርፉ ባለሙያ ከሆነችው ብርሃን ታዬ ጋር ቆይታ አድርገናል። ብርሃን ታዬ 'አክሰስ ናው' በሚባል ሲቪክ ማኅበራት ውስጥ የአፍሪካ ፖሊሲ ማናጀር ናት። ድርጅቱ ሰዎች ከኢንተርኔት ውጭ መብት እንዳላቸው ሁሉ ኢንተርኔት ሲጠቀሙም መብቶቻቸው [ዲጂታል ራይትስ] እንዲከበር ይሰራል። ብርሃን ያጠናችው ፖለቲካ ሳይንስና ሰብዓዊ መብት ትምህርት ነው። ከዚህ በተጨማሪም ናይሮቢ በሚገኘው ስትራትሞር ዩኒቨርሲቲ ተጋባዥ አጥኝ ናት። ቢቢሲ፡ ዋና ዋና የሚባሉት የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች የትኞቹ ናቸው? ብርሃን፡ በዓለም ላይ ዋና ዋና የሚባሉት የማኅበራዊ ድረ ገፆች ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም ሲሆኑ ሦስቱም በፌስቡክ ድርጅት ስር የሚተዳደሩ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ትዊተርና ዩቲዩብ ወደ ቻይና ስንሄድ ደግሞ የራሳቸው የሆነው ዊቻትንና ቲክቶክን መጥቀስ ይቻላል። ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ሰው የሚጠቀመው ፌስቡክን ነው። ፌስቡክ በኢትዮጵያ ከ6 እስከ 8 ሚሊዮን ተጠቃሚ አለው ተብሎ ይገመታል። የትዊተር ተጠቃሚዎች ግን ከ200 ሺህ እንደማይበልጡ ይነገራል። ኢትዮጵያ ውስጥ አዲሱ መንግሥት ከመጣ በኋላ የመንግሥት ባለሥልጣናት ትዊተር መጠቀም ሲጀምሩ ተጠቃሚው ወደ ትዊተር እየሄደ ነው። በርካታ የአፍሪካ አገራት ዋትስ አፕን ሲጠቀሙ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ብዙ ሰው የሚጠቀመው ቴሌግራምን ነው። ይሁን እንጂ የዋትስአፕ ተጠቃሚም እያደገ ነው። ሌላ አንድ 'ሲግናል' የሚባል የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያም አለ። ይህ መተግበሪያ ከሌሎቹ የሚለየው መተግበሪያው የሚተዳደረው በበጎ አድራጎት ድርጅት አሊያም ለትርፍ በማይሰራ ድርጅት መሆኑ ነው። ቢቢሲ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰው የቴሌግራም ተጠቃሚ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? ብርሃን፡ምክንያቱ ይሄ ነው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው። ገበያው መጠናት አለበት። እንደማስበው ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ቡድኖች አሉ። ቡድኑ ለማንም ክፍት ነው። በመሆኑም ብዙ ሰው ቴሌግራም የሚጠቀመው መተግበሪያው ብዙ ፊቸሮች [የምንፈልገውን ማድረግ የሚያስችሉን ነገሮች] ስላሉት እና ለሰው ደስ ስለሚለው ይመስለኛል። ለምሳሌ በዋትስ አፕ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አንድ ቡድን ውስጥ መኖር የሚችለው የሰው ቁጥር እስከ 250 ሰው ብቻ ነው። ቴሌግራም ግን እስከ 100 ሺህ ሰው ድረስ አንድ ቡድን ውስጥ ማካተት ይችላል። በዚህ ምክንያት ተመራጭ የሆነ ይመስለኛል። ቢቢሲ፡ በመላው ዓለም 2.2 ሚለዮን አካባቢ የዋትስአፕ አዲስ ተጠቃሚዎች ወደ ሌሎች መተግበሪያዎች ፈልሰዋል ተብሏል። በትክክል ምንድን ነው የተፈጠረው? ብርሃን፡ በፈረንጆች ጥር ስድስት ላይ ዋትስአፕ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ደኅንነት እንዴት እንደሚጠብቁ አዲስ ደንብ አውጥቷል። ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራምና ፌስቡክ የሚመሩት በአንድ ድርጅት ማለትም በፌስቡክ ነው። ታዲያ በዚህ ፖሊሲ ላይ ሰዎች በ'ፋየር ፎክስ'፣ 'ኢንተርኔት ኤክስፕሎለር'፣ ጉግል ክሮም ላይ የመረጃ አሰሳ [ሰርች] ታሪክ መረጃ፤ ዋትስአፕ የምንጠቀምበት ቋንቋ፣ ያለንበትን አገር ሰዓት፣ የኢንተርኔት አድራሻ [የአይፒ አድራሻ]፣ የምንጠቀመው የሞባይል ኔትወርክ ፣ ኢንተርኔት አገልግሎቱን ከየት እንዳገኘን እና ሌሎች መረጃዎችን ለኢንስታግራምና ለፌስቡክ አጋራለሁ በማለቱ ነው ይህ የሆነው። ለምሳሌ፡ የፌስቡክ አካውንት ከፍተን ስንጠቀም ለቤት ውስጥ ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የኢንተርኔት ቁጥርን [አይፒ አድሬስ ]ይሰጣል። በመሆኑም በዚህ ኢንተርኔት ዋትስአፕ የምንጠቀም ከሆነ ፌስቡክና ዋትስአፕ መረጃዎች ሲቀባበሉ፤ እኛ እንደሆንን ያውቁናል። በዚህም ፌስቡክ ላይ ሼር የሚደረገው መረጃ ዋትስአፕ፤ ዋትስአፕ ላይ የሚጋራውን መረጃ ፌስቡክ ያውቀዋል ማለት ነው። በመሆኑም ሰው ለቆ እየወጣ ያለው ለዚህ ነው። ድርጅቱም ከመጪው የካቲት ስምንት ጀምሮ መረጃዎችን እናጋራለን፤ የማትፈልጉ ከሆነ የእኛን መተግበሪያ ለቅቃችሁ መውጣት ትችላላችሁ ብሏል። ቢቢሲ፡ ይህ መሆኑ ለምን ያሳስበናል? መረጃዎቻችንን ቢጋሩት ለምን እንፈራለን? ብርሃን፡በምድር ላይ 53 በመቶው ሕዝብ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው። ብዙዎቻችን ለትምህርትም ሆነ ለሥራ ጊዜያችንን የምናጠፋው ኢንተርኔት ላይ ነው። ሕይወታችን ወደ ዲጂታል እየተቀየረ ነው። ስለዚህ አንድ የግል የሆነ፣ ለትርፍ የሚሰራ ድርጅት ይህን ሁሉ ግላዊ መረጃ ያውቃል። የእኛን ግላዊ የሆነና ለሁሉም ሰው የማናጋራውን መረጃ ስንልክ፤ ያን በመሰብሰብ ከዚያ ጋር የሚገናኝ ማስታወቂያ ይላካል። የእኛን ሃሳብ የሚያስቀይር ማስታወቂያ ይላካል። በተዘዋዋሪ ይህ መረጃ ተሰብስቦ ይሸጣል ማለት ነው። ፌስቡክ ገንዘብ የሚያገኘው ወይም በነጻ አገልግሎት ሰጠን የምንለው ምርቱ እኛ ስለሆንን ነው። ለምሳሌ፡ ጫማ መግዛት እንደምንፈልግ ለጓደኛችን ጽፈን ከሆነ ይህን የግል መረጃ በመያዝና እኛን በመከታተል የጫማ ማስታወቂያዎችና ከዚህ ጋር የተያያዙ መረጃዎች ይላካሉ። ዕድሜያቸው ከ25-30 የሆኑ ከዚህ በፊት አዲስ ጫማ የገዙ እነማን ናቸው? በሚል ተፈልገን ሳንፈልግ ማስታወቂያዎች በገጻችን በኩል ይላካሉ። የዚህ ውጤት በማስታወቂያ ብቻ ሳይሆን በምርጫ ላይ ተፅዕኖ ሲያሳድርም ታይቷል። አንድ የግልና ትርፋማ ድርጅት የእኛን መረጃ ነው እየሰበሰበ የሚሸጠው። ቢቢሲ፡ እነዚህ መተግበሪያዎች ስንጠቀም አንከፍልም። ለምንድን ነው ውለታ የሚውሉልን? ብርሃን፡ ደግ ሆነው ሳይሆን እኛ ደግ ሆነን ነው። ፌስቡክ በቢሊየን ዶላር እያወጣ አፍሪካዊያን በኢንተርኔት አገልግሎት እንድንተሳሰር ይሰራል። ሌሎችም እንዲሁ። ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ወደውን ወይም አፍቅረውን አይደለም። ከእኛ የሚያገኙት መረጃ ስለሚሸጥ ነው። ስለዚህ በነፃ የሚሰጡን ይመስለናል እንጂ የሚሸጠው የእኛው መረጃ ነው። ፌስቡክ የሚሰራው ማስታወቂያ በመሸጥ ነው። ዓለም ላይ ያሉ ድርጅቶች በፌስቡክ ምርቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ። ስለዚህ ፌስቡክ ገንዘቡን የሚያገኘው እኛ ቁጭ ብለን ስለምናይለት ነው። ከሌሎች ማስታወቂያዎች ለየት የሚያደርገውም ፌስቡክ ላይ የሚሰራው ማስታወቂያ ለእያንዳንዱ ሰው ተብሎ ተቀርጾ መሰራቱ ነው። ለምሳሌ የሆነ ጊዜ መኪና ስለመግዛት ከጓደኛችን ጋር ተጻጽፈን ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ይህን መረጃ በመያዝ በግል ገጻችን ላይ የምናየው ማስታወቂያ ስለ መኪና ይሆናል። ልክ እንደሌሎቹ ማስታወቂያዎች ለጠቅላላው ሕዝብ የተሰሩ አይደሉም። ቢቢሲ፡ ከእነዚህ መተግበሪያዎች ውጪ ኢንተርኔት ላይ ሌሎች መረጃዎችን ስንፈልግም፤ ከፈለግነው መረጃ ጋር ተያያዥ የሆኑ ሌሎች መረጃዎች ይመጣሉ። ለምንድን ነው? ብርሃን፡መረጃውን ለመፈለግ የገባንበት ድረ ገጽ ላይ ኩኪዎች የሚባሉ አሉ። ልክ ጫማችን አቧራ ነክቶ ቤት ውስጥ ስንገባ የጫማ ዱካችን ቤቱ ወለል ላይ ይቀራል። ቤቱን ለቀን ብንሄድም ዱካው ያስታውቃል። በመሆኑም ሌላ መተግበሪያዎችን ስንከፍት ዱካችንን [ከዚህ በፊት ያሰስነውን] ይፈልጋሉ። ከዚህ በፊት ከፍተን ያየነውን ነገር ድረ ገጾቹ እርስ በርስ ይነጋገራሉ። "ከዚህ በፊት የፈለጉት ይህ ነበር። የሚያሳስባቸው ጉዳይ ይህ ነው" በማለት መረጃ ይለዋወጣሉ። ስለዚህ የሚመጣው በየቦታው ዱካ እየጣልን የሄድነው ነው። ቢቢሲ፡ የመብት ተሟጋቾች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች መንግሥት ክትትል የሚያደርግባቸው አካላት ይህ ጉዳይ ያስጨንቃቸዋል። የመረጃ መለዋወጫ መንገዶቻቸውንም ይመርጣሉ። እንደ ማኅበረሰብ መረጃዎቻችንን ቀላል ዋጋ እየሰጠን እንዳናጋራ የትኛውን መተግበሪያ መጠቀም አለብን? ሌሎች ማድረግ ያሉብን መሰረታዊ ጥንቃቄዎችስ? ብርሃን፡የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞች ሲሆኑ እነሱ ጋር ያለው አደጋ ከሌላው ኅብረተሰብ የተለየ ነው። እነሱ የተለየ መፍትሔ ነው መፈለግ ያለባቸው። ነገር ግን ሁላችንም እንደዜጋ ማሰብ ያለብን ብዙዎቻችን ስልካችንና ኮምፒዩተራችን ላይ መሆናችንን ነው። ስለዚህ የምንተወው መረጃ በጣም አሳሳቢ ነው። መንግሥት ከፈለገ የአንድን ሰው የቀን ውሎ ማወቅ ይችላል። መተግበሪያዎቹ እኛ የማናስታውሰውን መረጃ እንኳን ይዘው ነው የሚቀመጡት። ለምን ያህል ጊዜ ይዞ እንደሚቆይ አናውቅም። ስለዚህ የምናጋራው መረጃ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚህም ባሻገር በየትኛውም ዘመናዊ ስልክ የደኅነንት መጠበቂያዎች አሉ። ለምሳሌ አንድን መተግበሪያ ወደ ስልካችን ስናወርድ እኛ ያለንበትን ቦታ መረጃ እንድናጋራ ይጠይቃል። ስለዚህ ስናወርድ ግድ ሲሆን ብቻ ነው ይህን የማደርገው የሚለውን መምረጥ አለብን። ሌላኛው የሰውን የግል መረጃ የሚጠብቅና የሚከላከለው 'ሲግናል አፕ' መረጃ ለመለዋወጥ ጥሩ አማራጭ ነው። የሚያስተዳድረው ድርጅት ለትርፍ ያልተቋቋመ በመሆኑ የእኛን መረጃ አይፈልግም። በተጨማሪም የኢሜይል እና የሌሎች መተግበሪያዎችን የይለፍ ቃል [ፓስወርድ] ተመሳሳይ አለማድረግም ይመከራል።
news-50307434
https://www.bbc.com/amharic/news-50307434
የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ደፍሮ የገደለን ተጠርጣሪ ስም ይፋ እንዲደረግ ወሰነ
የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ19 አመቷን ኡይኔኔ ምርዌትያናን ደፍሮ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ላይ ስሙ ይፋ እንዳይሆን ጥሎት የነበረውን ገደብ አንስቷል።
የቀድሞ የፖስታ ቤት ሰራተኛው ሉያንዳ ቦታ የሚባል ሲሆን ነሐሴ ወር ላይ ነው ተጠርጥሮ የታሰረው፤ እስካሁንም ጥፋተኛነቱን አላመነም። በወቅቱ የኬፕታውን ዩኒቨርስቲ ተማሪዋ እቃ ለመውሰድ ፖስታ ቤት አቅንታ በነረበት ወቅት ደፍሮ በብረት ዘንግ እስክትሞት ድረስ እንደቀጠቀጣት ተገልጿል። •የተነጠቀ ልጅነት •አሲድን እንደ መሳሪያ ጥቁር ሹራቡም በደም እንደተለወሰ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው። የተማሪዋ መሞት በኃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፤ ብሔራዊ የተቃውሞ ሰልፍም ተደርጓል። •ወሲባዊ ትንኮሳን ሪፖርት በማድረጓ ተቃጥላ የተገደለችው ከዚህም በተጨማሪ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቀጣይዋ እኔ ነኝ በሚል ሃሽታግም በኃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አጋልጧል። ይህንንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጥቃት በሚያደርሱት ላይ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል።
news-53304141
https://www.bbc.com/amharic/news-53304141
ከሃጫሉ ሁንዴሳ መገደል በኋላ በአርሲ ዞን የተከሰተው ምንድን ነው?
ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም ምሽት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉ ከተሰማ በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞችና በአዲስ አበባ ውስጥ ግጭቶች ተስተውለዋል።
በእነዚህ ግጭቶች የሰው ህይወት መጥፋትና ንብረት ውድመት መድረሱን የመንግሥት ባለስልጣናት ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል አርሲ ዞን በደረሰ ጥቃት 23 ሰዎች ህይወት ማለፉንና በርካታ ንብረት መውደሙን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አልዩ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የአርሲ ዞን 28 ወረዳ እንዳሉት የሚናገሩት አስተዳዳሪው ችግሩ የተስተዋለው በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች ሳይሆን በአምስቱ ብቻ መሆኑን ይገልጻሉ። ከሞቱት ሰዎች መካከል አንድ የፓሊስ እና አንድ የሚሊሻ አባል እንደሚገኙበት ገልፀው፣ ግጭቱ የተከሰተባቸውን ቦታዎችን በስም ሲጠቅሱ ዶዶታ፣ ዝዋይ ዱግዳ፣ ጢዮ፣ መልካና ጀጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የዞኑ አስተዳዳሪ ግጭቶች የተከሰቱት በሰዎች መካከል በነበረ ጠብ እንጂ የብሔርም ሆነ የሃይማኖትም መልክ አልነበረውም ብለው ለቢቢሲ ቢናገሩም ጥቃቱ የደረሰባቸው ሰዎች ግን በሐይማኖታቸውና በማንነታቸው ምክንያት በደል እንደተፈፀመባቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ቢቢሲ ችግሩ ባጋጠመባቸው የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ቢያናግርም አንዳንዶቹ ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሲሆን፤ ሌሎች ግን በሪፖርቱ ውስጥ ስማቸው እንዲጠቀስ ፈቃደኛ ቢሆኑም ቢቢሲ ያሉበትን ሁኔታ ከግምት በማስገባት ዘገባውን ያለስማቸው አውጥቷል። ቀርሳ ሦስት የቤተሰቦቻቸውን አባላት ደረሰባቸው ባሉት ጥቃት አጥተዋል። "የአክስቴን ልጅ፣ ልጁንና አማቹ ተገድለዋል" ሲሉ ለቢቢሲ በሃዘን ይናገራሉ። የከፋ ችግር የነበረው በአርሲ ዞን በቀርሳ ሙኔሳ ወረዳ ነበር ያሉት ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰብ የደረሰውን ሲገልፁም፤ ሙኔሳ ዳሞት ቅምቢባ የሚባል ገበሬ ማኅበር የጥቃቱ እምብርት ነው ይላሉ። በአካባቢው የሚገኝ ወደ 40 ገበሬ ማኅበር ላይ ጥቃቱ እንደደረሰ መረጃ አለን የሚሉት እኚህ ግለሰብ ግድያና ዘረፋ የተካሄደው ዳሞት ቅምቢባ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ ነው ብለዋል። ጥቃቱ የደረሰው ድምጻዊ ሃጫሉ መገደሉ በተሰማበት ሰኞ ሌሊት መሆኑን የሚገልፁት እኚህ ግለሰብ ጥቃት አድራሾቹ የታጠቁ እንደነበሩ ይናገራሉ። "ፊታቸውን ሸፍነው ነበር፤ የሚፈልጉትን ሰው በስም እየጠሩ በሩን እያንኳኩ ነበር የሚያስወጡት" በማለትም ገጀራ፣ ስለት ያላቸው ነገሮችና ጦር መሳሪያ መያዛቸውን ያስረዳሉ። በዚህ አካባቢ ሦባት ሰዎች በገጀራና በጥይት መገደላቸውን በመግለጽ ሁለት ሰዎች ከባድ መቁሰል ጉዳት ደርሶባቸው በአሰላ ሆስፒታል እንደሚገኙ ነግረውናል። "ሁለት ሰዎች (ስማቸውን ጠቅሰዋል) ሞተዋል ብለው ጥለዋቸው ሄደው ነው በህይወት የተገኙት" በማለት በአሁኑ ሰአት በአሰላ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እያገኙ መሆኑን ገልፀዋል። በማግስቱ ማክሰኞ ረፋድ ላይ ፖሊስ መምጣቱንና የሞቱና የቆሰሉትን ሰብስቦና ማኅበረሰቡን አረጋግቶ መሄዱን ያስታውሳሉ። ነገር ግን በስፍራው የፖሊስ ኃይል አለመኖሩን በመገንዘባቸው ጥቃት አድራሾቹ በድጋሚ መምጣታቸውን የሚናገሩት እኚህ ግለሰቡ የአካባቢው ሰው ሸሽቶ ሙኔሳ ገብርኤል ወደሚባል አካባቢ ሄዶ ማደሩን ገልፀዋል። በዚህ ዕለትም ንብረቶች መዘረፋቸውን ቤቶች መቃጠላቸውን የሚናገሩት ግለሰቡ በማግስቱ ረቡዕም፣ የሞቱት ሰባት ሰዎች ቀብር መከናወኑን ይገልፃሉ። ፖሊሶች በወቅቱ መጥተው የነበረ ቢሆንም ሁኔታዎች የተረጋጉ ሲመስሉ "ዳግም አይመጡም" ብለዋቸው መሄዳቸውን ያስታውሳሉ። • የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያና ያለፈው ሳምንት ክስተት ነገር ግን ለሦስተኛ ጊዜ ጥቃት አድራሾቹ በመምጣታቸው ለለቅሶ ተሰባስቦ የነበረው ሰው ነፍሱን ለማትረፍ በየጫካው ማደሩን ይገልፃሉ። ከቅዳሜ ጀምሮ ፖሊስ በአካባቢው በቋሚነት ተመድቦ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ ቤት ንብረታቸውን ጥለው የሸሹ ሰዎችን በግዴታ የአካባቢው አስተዳደርና ፖሊስ እያስመለሳቸው እንደሆነ ይናገራሉ። በአካባቢው እንዲህ አይነት ነገር ሲደርስ የመጀመሪያው ነው የሚሉት ግለሰቡ፤ ከዚህ በፊት የተለያዩ አለመረጋጋቶች በአገሪቱ ውስጥ ሲከሰቱ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት የሚከሰት ቢሆንም እንደ አሁኑ ግን በሐይማኖት ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት አይተው እንደማያውቁ ገልፀዋል። በአካባቢው የደረሰው የብሔር ግጭት አይደለም የሚሉበትንም ምክንያት ሲያስረዱ ቤታቸው የወደመባቸው፣ የሞቱ የተዘረፉ ሰዎች በአካባቢው የሚኖሩ የተለያዩ ብሔር ሰዎች ነገር ግን የአንድ እምነት ተከታዮች መሆናቸውን በመጥቀስ ነው። ዴራ በአርሲ ዴራ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና ልጃቸውን ያጡት ግለሰብ ልጃቸው ከአዳማ ሊጠይቃቸው የመጣው ሰኞ ዕለት ማታ እንደሆነ ይናገራሉ። ሰኞ ለማክሰኞ አጥብያ የሃጫሉን ሞት ተከትሎ በአካባቢያቸው ረብሻ መከሰቱን ተናግረዋል። ልጃቸው በአጥር ዘሎ ወደ ጎረቤት ጊቢ ሲያመልጥ ከዚያ ጎትተው በማውጣት መንገድ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን ለቢቢሲ ተናግረዋል። 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤታቸው፣ እስከነ ሰርቪሱ፣ ሱቃቸው እስከነ ሙሉ እቃው መዘረፍ መቃጠሉን እንዲሁም ከብቶቻቸውን መንዳታቸውን ይናገራሉ። ሌላኛው ልጃቸው መፈንከትና ስብራት እንደደረሰበት ገልጸዋል። ግለሰቡ የሚሉት በከተማዋ ላይ በደረሰው የቤት ቃጠሎ ወደ 300 የሚደርሱ ቤቶች መውደማቸውን ገልፀው። በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ይናገራሉ። በከተማዋ የጸጥታ ኃይል ቢኖርም፣ ከአሰተዳደሩ ምንም ዓይነት መፍትሄ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ። በአካባቢው በሚገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት ከ50 በላይ ሰዎች እንደሚገኙ የሚናገሩት ቢቢሲ ያናገራቸው ግለሰቦች፣ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በሚገኝ አዳራሽና በየመቃብር ቤት በረንዳ ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ በመግለጽ ማንም የሚመለከተን አካል አልመጣም ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል። በአካባቢው የደረሰው ጥቃት የሐይማኖት መልክ እንደነበረውም በመግለጽ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን በሐይማኖታቸው ምክንያት ጥቃት እንደደረሰባቸው ይናገራሉ። ምግብ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ሆቴል፣ ሥጋ ቤት፣ የዱቄት ፋብሪካ፣ መጋዘን፣ እንጨት ቤቶች መቃጠላቸውን ያነጋገርናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። በየጥሻው ውስጥ ተደብቀን ነው የተረፍነው የሚሉት ግለሰቦቹ፤ ጥቃቱ አድራሾቹ ስለት ያላቸው መሳሪያዎች፣ ጦር መሳሪያዎች ይዘው እንደነበር ተናግረዋል። ልጆቻቸውን በየዘመዱ የበተኑ፣ አልባሳት እና ምግብ የሌላቸው ሰዎች በቤተክርስቲያኒቱና በአካባቢው ሕዝብ እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ይናገራሉ። በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከተጠለሉ ስድስተኛ ቀናቸው እንደሆነ የሚናገሩት ግለሰቦቹ ከአካባቢው አስተዳደር ብቅ ብሎ እንኳን የጠየቀን የለም ሲሉ ለቢቢሲ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። አዳማ ውስጥ የመንግሥት ሠራተኛ የነበረውን ሊጠይቃቸው የመጣ ልጃቸው በአጥቂዎቹ የተገደለባቸው አባት ሐዘን የሚቀመጡበት ቦታ አጥተው በሐዘን ክፉኛ መጠቃታቸውን ለመግለጽ "ምነው ልጄ እኔን ብሎ ባለመጣ" በማለት እራሳቸውን በጥፋተኝነት ስሜት እየወቀሱ ነው። አርሲ ነገሌ ቢቢሲ ያነጋገራት በአርሲ ነገሌ የንግድና የመኖሪያ ቤት ያላት የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ግለሰብ ሌላው ማክሰኞ ዕለት በከተማዋ በተፈጸመው ጥቃት ባለቤቷንና ንብረቷን አጥታለች። እርሷ እንደምትለው የሃጫሉ ሞት ከተሰማ በኋላ ለሊቱን ከርቀት ጩኸት ይሰማቸው ነበር። በቅድሚያ የሞተ ሰው ያለ መስሎን ወጥተን አየን ስትል ሁኔታውን ታስታውሳለች። መኖሪያቸው የሚገኘው አርሲ ነገሌ ባለ ቀበሌ ውስጥ መሆኑን ትናገራለች። በዚህ አካባቢ አስር ክፍል መኝታ ቤት (ቤርጎ) ያለው ግሮሰሪ እንደነበራት እንዲሁም ቤታቸው ከግሮሰሪው ጀርባ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጻለች። "ግለሰቧ በፊትም ይዝቱ የነበሩ ሰዎች አሉ" ትላለች። ስለዚህ በከተማዋ ውስጥ ጥቃቱ ሲፈጸም እርሷም ሆነች ባለቤቷ ቤታቸውን ዘግተው ከተቀመጡ አደጋው ወደ እነርሱ እንደማይመጣ አስበው ነበር። "ባለቤቴ 'ቤት ውስጥ ከተቀመጥን የሚነካን የለም' ሲለን ዘግተን ተቀመጥን፤ እነርሱ ግን ሆ ብለው በሩን ሰባብረው ገቡ" ትላለች። በጥቃቱ በንግድ ቤታቸው ውስጥ የሚሰሩ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን እንዲሁም በራቸው ላይ ደግሞ 'ለምን ይህንን ታደርጋላችሁ?' ያለ ጎረቤት መገደሉን ታስታውሳለች። እርሷ፣ ልጆቿንና ሠራተኞቿ ጎረቤት ያስጥለናል ብለው በአጥር ሾልከው ቢሸሸጉም ጥቃት አድራሾቹ እዚያም ተከታትለው መጥተው እንደወሰዷት ትናገራለች። በዚህ ወቅትም ይፈልጉ የነበሩት ባለቤቷን እንደነበር በመናገር እየጎተቱ እንደወሰዷት እንደምታስታውስ ለቢቢሲ ተናግራለች። ህይወቷ የተረፈው በቀበሌው አስተዳደር አካባቢ የሚገኙ የፀጥታ አካላት አማካኝነት መሆኑን በመግለጽ፣ የጸጥታ አባላቱም ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዷት ገልጻለች። የባለቤቷን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደል የሰማችው በወሬ መሆኑን የምትናገረው ይህች ግለሰብ በአሁኑ ሰዓት በሰው ቤት ተጠልላ በስጋት እንደምትኖር ትናገራለች። የባለቤቷ አስከሬንም ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ አድሮ በነጋታው መቀበሩንም ለቢቢሲ አረጋግጣለች። "አሁንም ዛቻ አለ" የምትለው ይህች እናት "ሲያስፈራሩን ሰው ቤት ህጻናት ይዤ በፍርሃት ነው ያለሁት" በማለት ቤት ንብረቷ እንዲሁም የልጆቿ አባትን አጥታ መሄጃው እንደጠፋት ለቢቢሲ ገልጻለች። በከተማዋ አምስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የምትናገረዋ ሌላዋ የከተማዋ ነዋሪ ጥቃቱ የሐይማኖት ብቻ ሳይሆን የብሔር መልክም ነበረው ትላለች። በከተማዋ ተዉ ስላሉ የተገደሉ፣ የተወጉ፣ የተደበደቡ ሰዎች አሉ የምትለው ግለሰቧ ከዚህ የባሰ የደረሰም አለ በማለት የሰማችውን ለቢቢሲ አካፍላለች። ግለሰቧ አክላም "ሕጻናት ባዩት ነገር አእምሯቸው ተረብሿል፤ የ11 ዓመት ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለውን ግለሰብ በማየቱ ራሱን አጥፍቷል" ስትል ለቢቢሲ ያለውን መረበሽና ጭንቀት ታስረዳለች። ህጻናቱ በፍርሃት ነው ያሉት በማለትም፣ ወደ ከተማዋ የጸጥታ ኃይል ማክሰኞ ከሰዓት ገብቶ ቢያድርም ጥቃት አድራሾቹ በነጋታው ወደ ገጠር ቀበሌዎች በመሄድ ጥቃት ማድረሳቸውን ተናግራለች።። የአርሲ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጀማል የደረሰውን የንብረት ውድመት ለማጣራት በአካባቢው ፖሊስ መምሪያ የሚመራ ኮሚቴ መዋቀሩን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አጠቃላይ ጉዳት የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነት ግርማ ገላን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ውስጥም በተፈጠረው አለመረጋጋት 11 የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ የ156 ሰዎች ህይወት አልፏል። ከዚህ በተጨማሪ በተፈጸሙት ጥቃቶች ሳቢያ 167 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ምክትል የፖሊስ ኮሚሽነሩ ጨምረውም የተፈጸሙትን ጥቃቶች "ዘግናኝና አሳፋሪ የግድያ ወንጀሎች" መሆናቸውን አመልክተው የዚህ ድርጊት አላማ በማኅበረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ታስቦ የተፈጸመ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በተለያዩ ስፍራዎች በተፈጸመው ጥቃቶች ከደረሰው ጉዳትና የንብረት ውድመት ጋር በተያያዘም ፖሊስ ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን ግለሰቦች መያዙን አስታውቋል። 1084 ሰዎችን መያዙን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሲያስታውቀ፣ በአዲስ አበባና በድሬዳዋም በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
news-47565673
https://www.bbc.com/amharic/news-47565673
ትጥቅ የፈቱ የኦነግ ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ ናቸው
በአባ ገዳዎች ማግባባት ትጥቅ ፈትተው ወደተዘጋጀላቸው መጠለያ የገቡና አንድ ሺህ የሚሆኑ የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ገለፁ።
በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኙት እነዚህ የቀድሞ የኦነግ ወታደሮች በካምፑ ለአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ መጋለጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንድ የቀድሞ የኦነግ ወታደር "የተያዝንበት ሁኔታ በጣም አስከፊ ነው። ብዙ ጓደኞቻችን በምግብ እጥረትና በንፅህና መጠበቂያ አገልግሎት ችግር ታመዋል" ሲል ሁኔታውን ለቢቢሲ ገልጿል። • ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል ከዚህም በተጨማሪ በቀጣይ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ይመለሱ ዘንድ ይሰጣችኋል የተባለው ስልጠናም ሆነ ሌሎች የተገቡላቸው ቃሎች አለመፈፀማቸውን ገልፀዋል። የኦነግ ወታደሮች ትጥቅ ፈትተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ ኦነግን እና መንግስትን ሲያሸማግል የነበረው ኮሚቴ አባል የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አቶ በቀለ ገርባ ወታደሮቹ ችግሮች እንዳሉባቸው የሰሙ ቢሆንም በካምፑ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት የክልሉን መንግሥት ፍቃድ እየጠበቁ እንደሆነ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን የክልሉ ሃላፊዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
45430404
https://www.bbc.com/amharic/45430404
የቢቢሲ አማርኛ በአንድ ዓመት ውስጥ ያቀረባቸው ተነባቢ ዘገባዎች
ቢቢሲ አማርኛ ዜናና ትንታኔዎችን ማቅረብ ከጀመረ እነሆ አንድ ዓመት ሆነ። በዚህ ወቅትም በሃገሪቱ በርካታ ጉልህ ክስተቶች ተመዝግበዋል። በተለያዩ ስፍራዎች ተቃውሞ የተከሰተበት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተላልፎ የተነሳበት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን የለቀቁበት፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት፣ እስረኞች የተፈቱበት፣ ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሰላም የመጡበት ዓመት ነበር።
የቢቢሲ አማርኛ በአንድ ውስጥ ያቀረባቸው ተነባቢ ዘገባዎች በዚህ በርካታ ክስተቶች በተከናወኑበትና የለውጥ ዓመት በነበረው 2010 ዓ.ም የቢቢሲ አማርኛ አስር ተነባቢ የነበሩ ፅሁፎች የሚከተሉት ነበሩ። 1. አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ - በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል። አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ተነግሯል። 2. 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ- ማንነታቸው ያልታወቀ 40 የታጠቁ ወታደሮችን ይዞ ትግራይ ክልል የገባ አንቶኖቭ አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ። 3. መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ- ኮ/ል መንግሥቱ ደርግን ኮትኩተው አሳድገውት ይሆናል። ነገር ግን አልወለዱትም። የደርግ እናትም አባትም ኮ/ል አጥናፉ ናቸው። ሆኖም ደርግ ፈጣሪውን መልሶ ለመብላት የወሰደበት ጊዜ ከ5 ዓመት ያነሰ ነበር፡፡ ኅዳር 3/ 1970 በዕለተ ቅዳሜ አጥናፉ ተገደሉ። "አብዮት ልጆቿን በላች" ተባለ። 4.ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? - የታላቁ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ከተገኘ በኋላ እሰካሁን ያገኘናቸው አስር የተረጋገጡ መረጃዎች። 5.አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ - የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር መዋላቸው፣ ከስልጣን ከመውረዳቸው በፊት ከአቶ አብዲ መግለጫ ውስጥ የበርካቶችን ትኩረት የሳበው የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋን በሚመለከት የሰጡት አስተያየትና ከስልጣን መውረዳቸው ተነባቢነትን አግኝቷል። 6. ጀዋር መሐመድ ከ"ቲም ለማ" ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት ነበረው? - አሁን ካሉት አመራሮች ጋር በትግሉ ወቅት የቀደመ ትውውቅና ግንኙነት ስለመኖሩ የተጠየቀው ጀዋር ቀጥተኛ ምላሽ ለመስጠት ባይፈቅድም አሁን ያለው አመራር ወደፊት ገፍቶ እንዲመጣ ውስጥ ውስጡን ላለፉት ዐሥርታት በደኅንነትም በወታደራዊ ክንፍ በርካታ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ለቢቢሲ ተናግሯል። 7. ብሔርን ከመታወቂያ ላይ ማስፋቅ. . . - ብሔር መታወቂያ ላይ መካተቱን ከሚቃወሙት አንዱ የፊልም ባለሙያ የሆነው ያሬድ ሹመቴ ይህንን ለማስቀየር ብዙ እርቀት ተጉዟል። "ብሔር ለሚለው ሀሳብ ለኔ ኢትዮጵያ የምትለው ትበቃኛለች" በማለትም ይናገራል። 8.አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ - የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር የሆኑት አቶ አብዲ ሞሃመድ ከክልላቸው የመገናኘ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሯቸው ነገሮች አነጋጋሪ ሆኗል። • የታተመበት ቀን ሐምሌ 5/2010 9.ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? - በ1997 የኢትዮጵያ ምርጫ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጎሜዝ ዲፕሎማቶች የተፈጠሩት እንዲዋሹ አይመስለኝም። ዝም አልልም፤ ለምን ዝም እላለሁ ይላሉ። 10."አቶ በረከት ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ - የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ በከፍተኛ ሙስና ክስ ተመስርቶባቸው ለአምስት ዓመታት የታሰሩ ሲሆን ከእስር የተለቀቁት ከጥቂት ወራት በፊት ነው። በቀድሞ ፓርቲያቸው ብአዴን ውስጥ እየተወሰደ ስላለው እርምጃና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
news-54270103
https://www.bbc.com/amharic/news-54270103
ቱሪዝም፡ በኮሮናቫይረስ ምክንያት እግራቸውን የሰበሰቡ ጎብኚዎች የሚመለሱት መቼ ይሆን?
በኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት ማሻሻያ ከተካተቱት ቁልፍ ዘርፎች መካከል ቱሪዝም አንዱ ነው። ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ አከባበርን ተከትሎ በርካታ ጎብኚዎች ወደ አገር መጥተው ነበር።
ከሐምሌ 2011 እስከ ታኅሳስ 2012 ባሉት ወራት ከግማሽ ሚሊየን በላይ ጎብኚዎች ወደ አገር ውስጥ ገብተው እንደነበር ይናገራሉ። ተስፋ አይቶ የነበረው የቱሪዝም ዘርፍ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከእንቅስቃሴ ውጪ ሆኗል ከሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህንንም በተመለከተ ቢቢሲ በዘርፉ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆነው ሥራና ኑሯቸው ከተስተጓጎለባቸው ሰዎች መካከል የተወሰኑት አናግሯል። "ፈረንጅ ካየን 7 ወር አለፈን" በቅሎዎችን ለጎብኚዎች በማከራየት የሚተዳደሩት ቀሲስ አሰፋ ለጋስ ነዋሪነታቸው በጥንታዊቷ የላሊበላ ከተማ ሲሆን የላሊበላ የበቅሎ አከራዮች ማኅበርንም 30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በሊቀመንበርነት መርተዋል። አሁንም በማኅበሩ የስምሪት ክፍል ውስጥ እያገለገሉ ሁለት በቅሎዎችን በማከራየት ኑሯቸውን ይደጉማሉ። በዚሁ ሥራ ታግዘው የስድስት ልጆቻቸውን የትምህርት ደረጃ ከ8ኛ ክፍል እስከ መጀመሪያ ዲግሪ አድርሰዋል። በዚህም የቱሪዝም እንቅስቃሴው በሚደራበት ወቅት በቅሎዎቹን ከላሊበላ ወደ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ገነተ ማርያም፣ አሽተን እና አቡነ ዮሴፍ ተራራዎች ለሚሄዱ ጎብኚዎች በማከራየት በአማካይ በወር እስከ 3 ሺህ ብር ያገኙ እንደነበር ቀሲስ አሰፋ ያስታውሳሉ። ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ ከሰባት ወር በፊት ግን ይህንን እንቅስቃሴ ማስቀጠል አልተቻለም። ቀሲስ አሰፋ እድሜ ልካቸውን በዚሁ ሥራ ሲሰማሩ አልፎ አልፎ የሚስተዋለው የጎብኚዎች ቁጥር ከፍና ዝቅ ማለት ካልሆነ በስተቀር ሥራውን አደጋ ላይ የጣለ ክስተት ገጥሟቸው አያውቅም። "ማኅበሩን ከአባቶቻችን ነው የተረከብነው" የሚሉት ቀሲስ አሰፋ፤ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ የመኪና መንገድ ባልተሰራበት ወቅት እንግዶችን ከአውሮፕላን ማረፊያ በመቀበል ወደ ላሊበላ በመውሰድም የበቅሎ ማኅበሩ የማይረሳ እንዳለው ይናገራሉ። የኮሮናቫይረስ መከሰት ግን በዚህ የዕድሜ ጠገብ የሥራ ዘርፍ ላይ በእርሳቸውም በአባቶቻቸውም ዘመን አይተውት የማያውቁትን ጫና አሳድሯል። "ከተማችን ከፍተኛውን ገቢ የምታገኘው ከጎብኚዎች ነው፤ አሁን ግን ፈረንጅ ካየን ሰባት ወር አለፈን" በማለት ሥራው ሙሉ በሙሉ ቀሟል ይላሉ። ወትሮውንም አንዳንድ የአስተዳደር ችግሮችና የጥቅም ተጋሪዎች በየአቅጣጫው ብቅ ብቅ ማለት ለማኅበሩ ስጋት የነበረ ቢሆኑም በመላው ዓለም የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ግን ችግሩን አባብሶታል። ወደ ላሊበላ ለሚመጡ ጎብኚዎች በቅሎዎቹን በማከራየት የምትመራ ህይወት ከሰባት ወራት ወዲህ ፈተና ገጥሟታል። አሁን በቅሎዎቹን አከራይቶ ከሚገኘው ገቢ ይልቅ ለበቅሎዎቹ የሚሆን መኖ ለመግዛት የሚወጣው ወጪ አይሏል። ይህም በኪሳራ እንደመኖር ማለት ነው ይላሉ። እናም የማኅበሩ አባላት መፍትሔ ያሉትን ርምጃ መውሰድ ጀምረዋል፤ በቅሎዎቻቸውን ሸጠው ህይወታቸውን መምራት። እንደ ቀሲስ አሰፋ ገለጻ በማኅበሩ ውስጥ የነበሩት የበቅሎዎች ብዛት 600 ደርሶ ነበር። አሁን ግን አብዛኛው የማኅበሩ አባላት በቅሎዎቻቸውን በመሸጣቸው ቁጥሩ ወደ 106 አሽቆልቁሏል። ችግሩ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ አሁን የያሉት በቅሎዎችም ተሸጠው ማኅበሩ ሊፈርስ ይችላል ብለው አሰፋ ይሰጋሉ። ጎንደርና ቱሪዝም አዝማሪ ወረታው ማለደ የእርሱን እና የቤተሰቡን ሕይወት የሚመራባት ብቸኛ መሳሪያው ማሲንቆው ነች። ሙሽሮችን ሠርጋቸውን ያደምቅላቸዋል፣ እንግዶችን በማሲንቆው ይቀበላል፣ በባሕላዊ ምሽት ቤቶች በመዘዋወር አዝናኝ ጨዋታውን ያቀርባል፣ ጎብኚዎችን በማሲንቆው ያስደምማቸዋል። ይህ ለበርካታ ዓመታት የኖረበት የሥራ ዘርፉ ነው። ከሞያ አጋሩ ጋር በትዳር ተሳስረው ያፈሯቸውን አራት ልጆች የሚያሳድጉትም ከዚሁ ሥራ ከሚያገኙት ገቢ ነው። ነገ ሙያዬን አሳድጌ የተሻለ ደረጃ እገኛለሁ እንጂ የተለመደውን ሥራዬን ማንም ይነጥቀኛል ብሎ አያስብም። "ባሕላችንን በመሸጥ የምንተዳደር በመሆናችን የባሕል አምባሳደሮች ነን" የሚለው ወረታው፤ "ቋሚ ደመወዝ ባይኖረንም ጎብኚዎችንና ሌሎች የሙዚቃ መድረኮችን በመጠቀም ብቻ ህይወታችንን ያለ ችግር እንመራ ነበር" ይላል። በዚህም ሥራ እንደየወቅቱ ሁኔታ በወር በአማካይ እስከ 10 ሺህ ብር ያገኙ እንደነበር ያስታውሳል። ጎብኚዎችን በማስተናገድ፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ከጎርጎራ እስከ ባሕር ዳር በመርከብ ወይም በጀልባ ሲሄዱ በማጀብ "ዳጎስ ያለ ገንዘብ እናገኝ ነበር" የሚለው ወረታው፤ ከጎንደር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ቤተ እስራኤላዊያን ሲመጡ ምርጫቸው አዝማሪ በመሆኑ እነሱን በማዝናነት ጥሩ ሥራ ይስሩ እንደነበርም ይናገራል። በተለይ ከቤተ እስራኤላዊያን ጋር የተለየ ቁርኝት እንደነበረው እና እነርሱ ሲመጡ እንደ አዝማሪ ብቻም ሳይሆን እንደ አስጎብኚም በመሆን ገቢ ያገኝ እንደነበር ይገልጻል። ከዕለት ደራሽ ሥራዎች ባሻገርም ከባለቤቱና በተመሳሳይ ሙያ ከሚገኙ ሌሎች 11 አዝማሪዎች ጋር በመሆን "ኮራሁ በባህሌ" የሚል የምሽት መዝናኛ ቤት ከፍተው እየሰሩ በነበረበት ጊዜ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ ቤታቸውን ቆላልፈው ያለ ምንም ሥራ እንዲቀመጡ አድርጓቸዋል። "ያለፉት ሰባት ወራት ምንም ያላገኘንባቸውና በህይወታችን ገጥሞን የማያውቅ አደጋ ላይ የወደቅንበት ነው" በማለት የችግሩን ክብደት ይገልጻል። "መንግሥት በሚያሰናዳቸው ፕሮግራሞች እንዳንሳተፍም በወረርሽኙ ምክንያት መንግሥት ሰው የሚሰባሰብባቸውን ዝግጅቶች ሰርዟል። የራሳችንን ቤት እንዳንከፍትም የሚመጣ ሰው ስለማይኖር ከጥቅሙ ጉዳቱ አመዘነብን፤ እንዲሁ ተጨንቀናል" ይላል። ወረታው እንደሚለው ይህን ክስተት አንዳንዴ ለማመን ሁሉ እንደሚቸገር ሲናገር "ይህ በተለይ በእኛ ሥራ ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ ስለሆነ ለ7 እና ለ8 ወራት ያለሥራ መቆየታችን በጣም አሳሳቢ ነው።" አክሱም፣ መቀለ፣ አድዋና ገረዓልታ ይዞር የነበረው ጉዕሽ ወጣት ጉዕሽ ከልጅነቱ ጀምሮ ተወልዶ ወደ አደገባት አክሱም ከተማ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎች እያየ ሲያድግ 'ምን ፈልገው ነው?' የሚል ጥያቄ ይመላለስበት እንደነበር ይናገራል። ቀስ በቀስ በታሪክ ዙርያ ያለውን ግንዛቤና እውቀት አሳድጎ በዚያው ወደ አስጎብኚነት ገባ። ጉዕሽ፣ ከአክሱም እስከ መቀለ፣ አድዋና ገረዓልታ ጎብኚዎችን ይዞ ይዞር ነበር። ኑሮውንም የመሰረተው ከዚሁ ሥራ በሚያገኘው ገቢ ነው። ባለፈው ዓመት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ግን ወደ አካባቢው የሚመጡ የጎብኚዎች ቁጥር እንደቀነሰና ለዓይኑ እንኳ የውጭ አገር ዜጋ ካየ መከራረሙን ለቢቢሲ ተናግሯል። "በዚህ ምክንያት አሁን ምንም ገቢ የለኝም። ኮቪድ-19 በህይወታችን ላይ ያሳደረው ተጽእኖ ቀላል አይደለም" ይላል። የሚያገኘው ገቢ እየቀነሰ በመምጣቱ ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ያቋቋመው ማኅበር አቅሙ እየተዳከመ፣ አባላቱም ተስፋ በመቁረጥ ወደ አለመግባባት መድረሳቸውን ይገልጻል። ያጠራቀምኩትን ስለጨረስኩ ሥራ ለመቀየር ተገድጃለሁ የዲንሾ ከተማ ነዋሪ የሆነው አወል ሱልጣን በአስጎብኚነት ለስምንት ዓመት ያህል ሰርቷል። በእነዚህ ዓመታት በሐረር፣ ቦረና አብጃታ፣ ሻላ፣ ላንጋኖና ሌሎች የቱሪስት መስህቦችን በማስጎብኘት ኑሮውን ይመራ እንደነበር ለቢቢሲ ይናገራል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ግን እርሱም ሆነ ሌሎች የሥራ አጋሮቹ እጅጉን መጎዳታቸውን ይመሰክራል። "ህይወታቸው ከቱሪዝም በሚያገኝ ገቢ ላይ የተመሰረተ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ባጠራቀሙት ገንዘብ ነው እየኖሩ ያሉት። አንዳንዶች ያጠራቀሙትን ገንዘብ ጨርሰው ለችግር ተጋልጠዋል። ለምሳሌ እኔ በእጄ የነበረ ገንዘብ በመሟጠጡ ሥራ ለመቀየር ተገድጃለሁ።" በሆቴል፣ ባህላዊ እቃዎችን ሰርተው የሚሸጡ፣ በማኅበር በመደራጀት ፈረስ የሚያከራዩ፣ እና ሌሎችም ሥራ ፈትተው ለችግር መጋለጣቸውን አወል ያስረዳል። ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ታጥቷል በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከውጭ አገራት የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን የአገር ውስጥ ቱሪዝሙም ተጎድቶ ቆይቷል ያሉት የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ ናቸው። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የብሔራዊ ሙዚየም፣ የአንድነት ፓርክን የመሳሰሉ ስፍራዎች ተዘግተው በመቆየታቸው የተነሳ ለትምህርታዊም ሆነ ለመዝናናት የሚመጡ ጎብኚዎች በዚሁ ምከንያት መቅረታቸውን ያስታውሳሉ። አሁንም ቢሆን እንቅሳቃሴው ክፍት ሲሆን በፍጥነት ይሻሻላል ብለን የምንጠብቀው የውጭ አገር ጎብኚዎችን ሳይሆን የአገር ውስጦቹን ነው ሲሉ አቶ ስለሺ ተስፋቸውን ይናገራሉ። ኃላፊው እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ ስጋት ቀንሶ፣ የቱሪዝም እንቅስቃሴው ሲፋጠን ይሻሻላል ብለው የሚጠብቁት የአፍሪካ ቱሪዝም ነው። ለአፍሪካ ቱሪስቶች የእንጦጦ፣ የሸገር እና የአንድነት ፓርክን የመሳሰሉት አዳዲስ መዳረሻዎች ከዚህ ቀደም ከነበሩት ጋር ተደምረው በርካታ ጎብኚዎችን እንደሚያመጡ ተስፋ አድርገዋል። በቱሪዝም ዘርፍ በርካታ የሥራ እድሎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ጫና ደርሶባቸዋል ያሉት አቶ ስለሺ፤ በቱሪዝም ዘርፉ ተፈጥረው የነበሩ የሥራ እድሎች ሆቴሎች፣ የባህል ምግብ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች፣ በየቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ያሉ የአስጎብኚ አገልግሎቶች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች በሙሉ መጎዳታቸውን ይጠቅሳሉ። የኮቪድ-19 ከቱሪዝም ይገኝ የነበረውን ጥቅም ማሳጣቱን ሲገልፁም ድርጅታቸው በግሉ ያጣውን በማሳየት ይጀምራሉ። ቱሪዝም ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ቀርጾት የነበረው "የኩነት ቱሪዝም ብራንድ"ን፣ በጀርመን ፍራንክፈርት ለማስተዋወቅ ይዞት የነበረውን እቅድ መሰረዙን ይገልፃሉ። እንዲሁም ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶችን ለማካሄድ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ይዘውት የነበረው በየክልሉ በቱሪዝሙ ዘርፍ የሚሰጧቸው ስልጠናዎች መቋረጣቸውንም ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም ጋር ስትወዳደር የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ካስቻሏት ነገሮች መካከል አንዱ የባህል፣ የታሪክና የተፈጥሮ ሀብት መስህቦቿ፤ ሌላኛው ርካሽ የዋጋ ተመን፣ ሦስተኛው ደግሞ የደኅንነት ጉዳይ አስተማማኝ ስለነበር እንደሆነ አቶ ስለሺ ያነሳሉ። ስለዚህ ቱሪዝምና ሰላም ያላቸውን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታነት በማንሳት፤ ይህንን ጠብቆ ማቆየት ለመዝናናት፣ ለእረፍት እንዲሁም ለቤተሰብ ጥየቃ በመምጣት የተለያዩ መስህቦችን በመዲናዋም ሆነ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችን የሚጎበኙ ሰዎችን ማበረታታት ተገቢ መሆኑን ያሰምሩበታል።
news-47851139
https://www.bbc.com/amharic/news-47851139
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የመደመር እሳቤ ከአንድ ዓመት በኋላ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት አንደኛ ዓመት ከመከበሩ ቀደም ብሎ በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሲዘዋወር የነበረና አፈትልኮ ወጣ የተባለው ቪዲዮ እንደሚለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊትም 'መደመር' የሚለው ቃል ከአንደበታቸው የማይይለይ እንደነበር ያሳያል።
ብዙዎቹ "ለመተቸትም ለመደገፍም ጽንሰ ሃሳቡ ግልጽ ተደርጎ ተተንትኖ አልወጣም" የሚል ጥያቄ የሚያነሱ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን መንበረ ስልጣኑ ከተቆጣጠሩ ጊዜ ጀምሮ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይህንን ቃል ደጋግመው ሲጠቀሙበት ይስተዋላል። በስልጣን ላይ አንድ ዓመታቸውን የደፈኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፤ ከአንዳንድ ወገኖች አድናቆትን ከሌሎች ደግሞ ነቀፌታን እያስተናገዱ ይገኛሉ። የኢህአዴግ ሊቀ መንበር ሆነው በርካታ እርምጃዎች የወሰዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቆየው የግንባሩ አመራር የተለየ የሚመስል አቋም ሲያራምዱ ይስተዋላሉ። • በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከቆየው የኢህአዴግ አስተዳደር ከሚለዩባቸው መካከል የሚጠቀሙባቸው ቃላቶችና አገላለጾች አንዱ ነው። ዶ/ር አብይ ግን ከእነዚህ በብዙዎቹ 'የተሰለቹ' ከሚባሉ ቃላት ርቀው 'መደመር' የሚለው ቃል ዘወትር ከንግግራቸው መካከል የማይጠፋ ሆኗል። ለመሆኑ ይሄ ጽንሰ ሃሳብ በውል ሙሉ ትርጉም አግኝቷል ማለት ይቻላልን? የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችስ እንዴት ይረዱታል? መደመር. . . መደመር. . . አቶ አንዱአለም አራጌ በርከት ላሉ ዓመታት በእስር ቆይተው ባለፈው ዓመት መፈታታቸው የሚታወስ ነው። በቅርቡ በዜግነት ፖለቲካ የተሰባሰቡ ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰብሳቢ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መደመር ሲሉ 'በምንድነው' የሚገለጸው የሚለውን ግልጽ ማድረግ እንደነበረባቸው ይናገራል። "እንደተቃዋሚ የምንደመረው በምንድነው? የማንደመረውስ በምንድን ነው? የሚለው ግልጽ አይደለም" በማለት ሙሉ ለሙሉ ሊደመሩ ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ይናገራሉ። "አገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሰባሰብ እና ኢትዮጵያን ከጭቆና ዘመን ነጻ የማውጣት እንቅስቃሴ ካለ እንደምንተባበር ይታወቃል።" ብዙዎችን ከእስር መፍታት፣ በውጭ የነበሩ ተቃዋሚዎችን ወደ አገር ቤት ገብተው እንዲታገሉ መፍቀድና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝቅ ብሎ ከዜጎች ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆንና ለመሳሰሉት እርምጃችዎቻቸው ከፍተኛ ዋጋ ይሰጡታል። ከእነዚህ ውጪ ግን ይላሉ " እሳቸው መደመር መደመር ቢሉም መሬት ላይ የሚታው ነገር ግን ሌላ ነው" ይላሉ። "ሰው በማንነቱ እና በሚናገርበት ቋንቋ ተፈርጆ የሚገደልበት፣ የሚገለልበትና የሚፈናቀልበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። ህዝቡ የመደመር ጽንሰ ሃሳብ በትክክል የተረዳው አይመስለኝም። እንደፍላጎታቸው መጠን መሬት ላይ ወርዷል ብየ አልወስድም" ሲሉ ይናገራሉ። "እንደ ህመም ማስታገሻ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት የአገሪቱ ፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብቶ የነበረበት ዘመን ነው። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተለያዩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች የነበሩ ሲሆን ኢህአዴግም እንደ ድርጅት የመፍረስ አደጋ አጥልቶበት ነበር። የሕግ ባለሙያዋ ህሊና ብርሃኑ ጠቅላይ ሚንሰትሩ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ይህንን የመደመር ሃሳብ ይዘው መምጣታቸው ሁኔታዎችን ለመቀዝቀዝና ነገሮችን ለማብረድ ረድቷል የሚል እምነት አላት። "ለግዜው የመደመር ሃሳብ አስፈላጊ ነበር" የምትለው ህሊና ሃሳቡ "ለግዜው እንደ ህመም ማስታገሻ" ትገነዘበዋለች። ''በወቅቱ በጣም ብዙ ችግሮቻችን ጫፍ ደርሰው የነበረበት በመሆኑ፤ እንደ አገር ወዴት እየሄድን ነው የሚለው ጉዳይ በጣም አጠያያቂ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር" ትላለች። • የጠቅላይ ሚንስትሩን የአንድ ዓመት የስልጣን ዘመን እንዴት ይመዝኑታል? "ጉዳዩ የፖለቲካ ውስብስብነት የሌለበት፣ ለማንኛውም ማህበረሰብ በቀላሉ በሚገባ መልኩ እንደ ማስታገሻ ወስደነዋል።" ይሁን እንጂ ጽንሰ ሃሳቡ ከማስታገሻነት አልፎ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ሊያሻግረን አልቻለም የሚል አቋም አላት። "ከጊዜያዊ ማስታገሻነት ግልጽ ወደሆነ በየቀኑ ሊገባን ወደሚችለው መልስ መምጣት ነበረበት። ወደ መሬት ሊወርድ ይገነባ ነበር።" ህሊና ሃሳቡ ግልጽነት ይጎለዋል ትላለች። "ማንም መጥቶ መደመር ማለት ይሄነው እያለ ለራሱ በሚጠቅም መልኩ ጠምዝዞ እንዳይጠቀምበት ግልጽ ሆኖ መቀመጥ ነበረበት'' ትላለች። መደመር-ለኤርትራውያን ? የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር ሃሳብ በውጭ ግንኙነት እንቅስቃስያቸው ዙርያም ተደጋግሞ ይነሳል። እስከ የዳቮሱ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም በዓለም ዐቀፍ መድረኮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተውታል። የተለያዩ ጥያቄዎች የሚነሱበትና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ስኬቶች እንደ አንዱ የሚወሰደው የኢትዮ ኤርትራ ዕርቅ ላይም ይኸው ሃሳብ በተደጋጋሚ ተነስቷል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስም "ይሄ ህዝብ ሁለት ህዝብ ነው ብሎ የሚያምን ታሪክን ያልተረዳ ብቻ ነው" ማለታቸው አይዘነጋም። ይሁን እንጂ አንዳንድ ምሁራን እንደሚሉት ጽንሰ ሃሳቡ በግልጽ ካለመቀመጡ የተነሳ በኤርትራውያን ዘንድም ጥርጣሬን እንደፈጠረ አንዳንዶች ይናገራሉ። የተቃውሞ ደብዳቤም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የጻፉ ኤርትራዊያንም አልጠፉም። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ምዕራፍ በስዊድን ነዋሪ የሆነው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ካሊድ አብዱ "መደመር ለእኛ ለኤርትራዊያን ትልቅ ስጋት ነው" ብሏል ለቢቢሲ። "መደመር የሚለው ሃሳብ ኢሳያስ ኤርትራን አሳልፎ እየሰጣት ነው። ከኢትዮጵያ ጋር አንድ ሊያደርጋት ነው" የሚል ስሜት እንደፈጠረ ይናገራል። "የኤርትራ ህዝብ ስለ መደመር ያሰማው ድምጽ የለም። አንድ ግለሰብ ብቻ እየወሰነ ነው።የኤርትራ ህዝብ የሚቀበለው ጉዳይ ግን አይደለም" ይላል። መደመር-ትናንትና ዛሬ መደመር የሚለው ሃሳብ ሲጀመር ችግር ያለው እንዳልሆነ ፋሲል ተስፋዬ ይናገራል። በወቅቱ የገባቸውም ያልገባቸውም እንደተደመሩበት ይገልጻል። ለእሱ መደመር "አንድ መሆን" ነው። ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ከአንድ ዓመት በኋላ የተለየ አቋም ሲያንጸባርቁ ከታዩት መካከል አንዱ ነው። የዛሬ ዓመት ለውጡ ሲጀመር የነበረው ስሜት 'ዛሬ በውስጤ የለም' ይላል። 'መደመር' የሚለው ቃልም ከጨመረው ይልቅ ያጎደለው ጎልቶ እንደሚታየው ይናገራል። ጽንሰ ሃሳቡ- የተወሰነ ወገን ጠቅሞ ከሆነ እንጂ ሁሉም ህብረተሰብ ሲጓጓና ሲጠብቅ የነበረው ሁኔታ ያሰገኘ ነው የሚል እምነት እንደሌለው ያምናል። "ከዚያ ይልቅ ጥርጣሬ፣ የእርስ በርስ አለመተማመንና ወደር የሌለው ስግብግብነት ነግሷል" የሚል ግምገማ ነው ያለው። "ሰዉ ነገን በስጋት እንዲመለከት አድርጎታል" ይላል። "ችግሩ ግን መደመሩ ላይ አይደለም፤ እሳቤውም አይደለም። ወይም ደግሞ ህዝቡ በዚያ መንፈስ መቀላቀሉ አይደለም። ይህንን አስተሳሰብ ወደፊት አምጥተው ህዝቡ በዚህ ዙርያ እንዲሰበሰብ ያደረጉ ኃይሎች፤ በትክክል እንድንጠቀምበት አልቀረጹልንም። አስተሳሰቡን ተግባራዊ አድርገው እየመሩንም አይደለም" በማለት ይነቅፋል። አዲስ ሃሳብ ነውን? አቶ አንዱአለም አራጌ ቀደሞ ሲል በአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አመራር አባል ሆነው ሲታገሉ ነበር። እሳቸው እንደሚሉት መደመር የሚለው ጽንሰ ሃሰብ ድርጅታቸው ስለአንድነትና አብሮነት ሲያቀነቅንና በአቋም ደረጃም የኢትዮጵያ አንድነትን የማስቀደም አዝማሚያ እንደነበረው ይናገራሉ። ለብዙ ዘመናት የአንድነት የዜግነት ፖለቲካ ማራመዳቸውን ጠቅሰው መደመር የሚለው ለእነሱ አዲስ ሃሳብ እንዳልሆነ ይጠቁማሉ። በአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ ናሁሰናይ በላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መምህራንን ሰብስበው ሲያነጋግሩ "መደመር ምን ማለት ነው?" የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው፤ "እሱ የምሁራን ሥራ ነው፤ እናንተ ተመራመሩበት" ማለታቸውን ያስታውሳሉ። "ሃሳቡን የመተርጎምና የማርቀቅ ተግባር የጉዳዩ አምጪ ሥራ ነው" ይላሉ። •"እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የሥነ አዕምሮ ሃኪምና በአነቃቂ ንግግራቸው የሚታወቁ ዶክተር ምህረት ደበበ "መደመር አዲስ ሃሳብ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን አዲስ አቅጣጫ (ፓራዳይም) ነው" በማለት ይገልጹታል። በኢትዮጵያ ባለፈው 50 ዓመት በመከፋፈልና በዘር እይታ በዙ ልዩነት ተፈጥሮ የእርስ በርስ ጦርነት መካሄዱ አስታውሰው፤ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተግባር ላይ ከዋለ አዲስ የአመለካከት ጽንሰ ሃሳብ እንደሆነ ይናገራሉ። "በተፈጥሮም ውስጥ አብሮ ያለ ነገር ነው አዲስ ልንለው አንችልም" ይላሉ። የተደመረና ያልተደመረ አቶ ናሁሰናይ መደመርና አለመደመር ጠላትና ወዳጅ ለመለያ፤ ተደመረ ያልተደመረ እየተባለ ለማጥቃት ጥቅም ላይ ውሏል ይላሉ። "ምን ማለት እንደሆነ አይታወቅም። ተደመርክ ማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሚሉት ማጨብጨብ ነው፤ አለመደመር ማለት ደግሞ ተጠራጠርክ ወይም ተቃዋሚ ሆንክ ማለት ነው" በማለት በተግባር ሲገመገም ይህ ነው የሚባል ጽንሰ ሃሳብ አይደለም ይላሉ። ዶክተር ምህረት ግን ከዚህ የተለየ ሃሳብ አለቸው። በተለይ በማህበራዊ ሚድያ ቃሉ ላልተገባ ጥቅም እየዋለ እንደሆነ ጠቅሰው፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍላጎትም ይህ አንዳልሆነ ይናገራሉ። "በተለያዩ አካባቢዎች ማህበረሰቡን ተደመረ አልተደመረ እያለ መለየትና ሰው ላይ ጥላሸት በመቀባት ጽንሰ ሃሳቡን ያልተረዳ አለ" የሚሉት ዶክተር ምህረት ሃሳቡ በቀና መንገድ ወደ ህብረተሰቡ እንዲገባ መሰራት አለበትም ይላሉ። "መደመር፤ ላለመደመርም ነጻነት የማይሰጥ ከሆነ ከራሱ ከቃሉ ጋርም ይቃረናል" በማለት ሃሳቡ ነጻነትን የሚሰጥ መሆን እንዳለበት ያመለክታሉ። ዐብይ አህመድ፡ ያለፉት 100 ቀናት በቁጥር ለመሆኑ መደመር ምንድን ነው? ከሃሳቡ ጋር የቆየ ቁርኝት እንዳለቸው የሚናገሩት ዶክተር ምህረት ደበበ፤ ሰዎች ተግባብተው አንዱ የሌለውን ነገር ከሌላው እንዲያገኝ፤ እያንዳንዱ አንድ ነገር ለብቻ ከሚሰራ በጋራ ቢሰራ ስኬታማ እንደሚሆን የሚያመላክት አስተሳሰብ እንደሆነና ቀላል የሂሳብ ቀመር ሳይሆን ረቂቅ ግንኙነት እንዳለበት ይናገራሉ። መደመርን በተመለከተ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በተግባር ለመፈተሽ አጭር ጊዜ እንደሆነ የሚገልጹት ዶ/ር ምህረት፤ ይሄ ጽንሰ ሃሳብ በምሁራን ተተችቶና ጥናት ተደርጎበት በግልጽ የተፈተሸ ነገር እንዳልሆነ አመልክተው ይሁን እንጂ ለክርክር ክፍት መሆን እንዳለበት ያምናሉ።
news-49470306
https://www.bbc.com/amharic/news-49470306
አማርኛ የሚኮላተፉ፣ ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች....-ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም
አንድ የማይታወቅ መንደር- እዚህ እዛ ተፈራርቀው በተመሰረቱ የሳር ጎጆዎችና በድንጋይ በተሰሩት ህድሞዎች መካከል የጥይት ድምፅ ያንባርቃል። አቧራ በለበሰው መንገድ በፒክ አፕ መኪና የተጫኑና ኤኬ 47 ጠመንጃ ያቀባበሉ ወታደሮች መንገዱን እየሰነጠቁ ይጓዛሉ።
የቆሸሸ ነጭ ጉርድ ቲሸርት የለበሰና ጡንቻው ፈርጠም ያለ ወታደር፣ ባንዳና ጭንቅላታቸው ላይ ያሰሩ፣ ጥቁር መነፅር ሻጥ ያደረጉ ወታደሮች በቤቶቹ ላይ ጥይት ማዝነብ ጀመሩ፤ ቦምብ በመወርወርም ቤቶቹን እንዳልነበር አወደሟቸው። በሚጋዩ ቤቶችና በሚጮሁ ድምፆች መሃል ላይም የአንድ ግለሰብ ድምፅ ይሰማል 'ማይ ካንትሪ ኢዝ ብሮክን፤ ዴዝ ኢዝ ስፕሬዲንግ፤ ዘ ኒው ገቨርንመንት ኢዝ ዌጂንግ ዋር ኤጌይንስት ዘ ሬብልስ' (ሃገሬ ፍርስርሷ ወጥቷል፤ ሞት በዝቷል። አዲሱ መንግሥት በአማፂያን ላይ ጦርነትን አውጇል) በማለት እየሆነ ያለውን ይተርካል። •ሞሳድ ቤተ-እስራኤላዊያንን ለመታደግ የፈጠረው ሐሳዊ ሪዞርት ለአባቶቻቸው ቃል የተገባላቸውን ትንቢት ለማስፈፀም ለ2700 አመታት ያህል የጠበቋትን የቅድስቲቷና የተስፋይቷ ምድር ጉዞም እንደጀመሩ ይኸው ድምፅ ያበስራል። ይህ በቅርቡ ኔትፍሊክስ ላይ ለእይታ ከበቃው 'ዘ ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት' መግቢያ የተቀነጨበ ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው ይህ ፊልም በ1970ዎቹ ሞሳድ ቤተ እስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ለመውሰድ የነበረውን አደገኛና መስዋእት የተሞላበት ተልዕኮ የሚያሳይ ነው። ኦፐሬሽን ብራዘርስ (ትዕይንተ ብራዘርስ) በሚል የሚጠራው በዚህ ሚስጥራዊ ተልእኮ ሞሳድ ሃሳዊውን 'አሮስ' ሪዞርት ከሱዳን መንግሥት በሊዝ ይገዛል። ሪዞርቱን ለስለላ ስራው እንደ ሽፋን በመጠቀም ቤተ እስራኤላውያንን በመርከብ ነዳጅ አስመስሎ በማውጣት በሲናይ በረሃ በኩል በጀልባ ለማስገባት የተደረገ ተልእኮ ነው። •በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ በእስራኤላዊው ጌዴዮን ራፍ ተደርሶ ዳይሬክት የተደረገው ይህ ፊልም ላይ የቤተ እስራኤላውያንን እንቅስቃሴ ሲያስተባብር የነበረው ፈረደ አክሎም በአፍሪካዊ አሜሪካዊው ሚካኤል ኬኔዝ ዊልያምስ ከበደ ቢምሮ በሚል ገፀ ባህርይ ተወክሏል። በዚህ ፊልም ሌላኛው አፍሪካ አሜሪካዊ ክሪስ ቾክ ቤተ እስራኤላውያንን ወክለው ተውነዋል። ኢትዮጵያን አስመስሎ ናሚቢያ በተቀረፀው በዚህ ፊልምና በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች (ቤተ እስራኤላውያኖችን) ለመውሰድ በተደረገው ትግል የኢትዮጵያውያን ቁጥር ከእጅ ጣቶች አይበልጥም። "ደም የጠማቸው፣ ነፍሰ ገዳይ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች" ፊልሙ ሲጀምር ኢትዮጵያ የሚል ፅሁፍ በመኖሩ ብቻ እንጂ ይህቺ የጦር አውድማ የምትመስለው መንደር አካባቢ የት እንደሆነም ለመገመት ይከብዳል። አማፂያን ተብለው እርስ በርስ የሚዋጉትም ሆነ ወታደሮቹ እነማን እንደሆኑ ምንም አይነት ፍንጭ ስለማይሰጥ ፊልሙን ለተመለከቱት ኢትዮጵያውያን ግራ አጋብቷል። በተለይም ፊልሙ ሲጀምር አካባቢ ደም የጠማቸው አውሬዎች ተደርገው የተሳሉት ወታደሮች ከአለባበሳቸው ጀምሮ ፤ የሚጠቀሙት አማርኛ ኮልታፋ ከመሆኑ አንፃር ኢትዮጵያ በወቅቱ የነበሯት ወታደሮች ምን አይነት ናቸው? የሚል ጥያቄንና ትችቶችንም በማስተናገድ ላይ ነው። ፊልሙ ላይ የርስ በርስ ጦርነት እንደነበር ዋነኛው ገፀ ባህርይ ከሚተርከው ውጭ ምንም የሚያሳይ ነገር የሌለ ሲሆን ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወታደሮች ለማምለጥ የነበረውን ሞት ቀረሽ ትንቅንቅና በየቦታው ወታደሮች ባዩዋቸው ቁጥር አፈሙዝ መደገናቸው ሲታይ፤ በጊዜው የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት በቤተ እስራኤላውያን ላይ ጦርነት አውጆ ነበር ወይ የሚል ጥያቄም አጭሯል። በተለይም አንድ አስር አመት የማይሞላውን ህፃን የሚያሳድዱበት ቦታ ስራቸው መግደል ብቻ እንደነበር አሳይ ነው የሚሉም አልታጡም። በሰብሎች መሃል ሲጫወት የነበረው ህፃን ልጅ ተኩሱን ሲሰማ እግሬ አውጭኝ ብሎ መንገዱን ሰንጥቆ ይሮጣል። የወታደሮቹም መኪኖች ሰብሉን እየጨፈላለቁ ተከተሉት። እሱ ልቡ እስክትሰነጠቅ ቢሮጥም ከሚከተሉት መኪኖች ማምለጥ አልቻለም። ወታደሮቹ ህፃኑን ሲያዩት ነፍሱ ከስጋው ልትላቀቅ በሚመስል ሁኔታ ደንግጦ ያያቸዋል። ባንዳና ጭንቅላቱ ላይ አስሮ መነፅር ያደረገው ወታደር 'የማሽን' ጠመንጃውን ያንደቀድቀው ጀመር። ፊልሙ ላይ ዋነኛ ገፃባህርይ ሆኖ የሚጫወተው ታዋቂው የሆሊውድ ተዋናይ ክሪስ ኤቫንስ በርካታ ነፍስ ያለው በሚመስል ሁኔታ ከሞት መንጋጋ ፈልቅቆ ልጁን አፈፍ አድርጎ ሮጠ። በመኪና ከሚከተሉት ወታደሮች በተጨማሪ ቆንጨራ ያነገቡና የእንስሳት ቀንድ አንገታቸው ላይ ያሰሩት ወታደሮች ደም እንደጠማት ውሻ እያበዱና እየተኮሱ ቢከተሏቸውም አልደረሱባቸውም። ወታደሮቹንም ካመለጡ በኋላም ነጮቹ የሞሳድ ሰራተኞች እንደ 'ሙሴ' እየመሯቸው ሱዳን የሚገኘው ጌዳሬፍ መጠለያ ሲደርሱ ይታያሉ። ከዚያ በኋላም ቤተ እስራኤላውያኖቹ ብዙ የማይታዩ ሲሆን፤ 2፡05 ርዝማኔ ባለው ፊልም ላይ የሞሳድ ጀብደኝነትና፣ የሲአይኤ ሚናን በከፍተኛ ሁኔታ በማጉላት ፊልሙ ይጠናቀቃል። በፊልሙ ላይ ቤተ እስራኤላውያን ተብለው የተሳሉት ስደተኞች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የሚናገሩት ቃላቶች የተመጠኑ፤ አካባቢውን ቢያውቁትም የሚመሩት በነጮቹ እንዲሁም ባህላቸው፣ አለባበሳቸው፣ ፍቅራቸው ምንም አይነት መስተጋብራቸው አይታይም። ቤተ እስራኤላውያኖቹ ወደዚህ ኑ ሲባሉ ከመምጣት፣ ተኙ፣ ብሉ፣ ጠጡ ሲባሉ ትእዛአዝ ከመቀበል በስተቀር ምንም አይነት አስተዋፅኦ እንዳልነበራቸው ፊልሙ ያሳያል። በተለያዬ አጋጣሚም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አደጋ ተጋርጦባቸው አንድ ነጭ ሲያድናቸው ማዬት ተአማኒነቱ ላይ ጥያቄን የፈጠረባቸው ጥቂቶች አይደሉም። በድርጊት የተሞላውን ፊልም ለተመለከቱት አብዛኛው ኢትዮጵያዊያውያን ሊዋጥላቸው አልቻለም፤ 'ኢትዮጵያን የጦር አውድማ አድርጎ ከመሳል ጀምሮ፣ የኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላውያን ታሪክ ከመሆኑ አንፃር ኢትዮጵያውያንን አለማሳተፉ፣ አማርኛ በትክክል መናገር የማይችሉና አማርኛ እየተኮላተፉ የሚያወሩበት ገፀ ባህርያን መሞላቱ፣ የታሪክ ግድፈት እንዲሁም በነጭ አዳኝነት (ዋይት ሴቪየር)ና የኢትዮጵያንም ሆነ የአፍሪካን የተለመደውን ጨለምተኛ ታሪክ አነጋገር ዘዬ የተከተለ በሚል ትችቶች አየቀረቡበት ነው። ፊልሙን ከተመለከቱት አንደኛው ሰሚር አሊ በተደጋጋሚ ሆሊውዶች ራሳቸውን የሚክቡበትና፤ ታሪኩንና እውነታውን የካደ ነው በማለት ፊልሙን ይተቸዋል። የአምስት አመት ልጅ ይመስል አማርኛን በቅጡ የሚናገሩ ተዋንያን መሳተፍ ለሰሚር የሚዋጥ አይደለም። የማህበረሰቡ አኗኗር፣ ታሪክ ላይ ምንም አይነት ጥናት ባለማድረጉም ቤተ እስራኤላውያን 'ሆቴል ሩዋንዳ' ከሚመስል ጭፍጨፋ እንደወጡ ተደርጎ ነው የተሳለው ይላል። "ጀብደኛና ግድየለሽ" ብሎ በጠራው ፊልም ላይ በተለይ ኢትዮጵያውያን የተወከሉበት መንገድንም ይጠይቃል። "ያው ለነሱ አፍሪካ ሲባል አንድ አይነትና እንደ አንድ አገር ነው የሚቆጥሩት፤ የተለያዬ ባህል፣ የፊት ገፅታ፣ቋንቋ፣ እምነት ያለ አይመስላቸውም። ሁሉንም ሃገራት በአህጉሯ አፍሪካ ነው እንጂ በዚህም አጋጣሚ የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ አይሰማም። ዋነኛ ባለታሪኮቹን የሉም ማለት ይቻላል። ዝም ብለው እንዳልባሌ ነገር ነው የተቆጠሩት፤ እንደ እቃ አውጥተው አንጠልጥለው ያወጧቸው ነው የሚመስለው"በማለት ወቀሳውን ያቀርባል። ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ? በእውነቱ ቤተ እስራኤላውያን በጉዟቸው ላይ አስተዋፅኦ አልነበራቸውም? የብዙዎች ጥያቄ ነው። "በባቢሎን ተራራዎች ስር ተቀምጠን ፅዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን፤ ፅዮን ሆይ ቀኜ ትርሳሽ ምላሴም ከትናጋዬ ጋር ይጣበቅ እየሩሳሌምን ከፍ ከፍ ባላደርጋት።" ለ2700 አመታት ያሀል ቅዲስቲቷንና የተስፋይቱን ምድር እውን መሆን ሲጠብቁ የነበሩት የቤተ እስራኤላውያን በልባቸው የተታተመ ቃል ነው። በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1948 የእስራኤል መንግሥት መመስረትን ተከትሎ የተለያዬ ሃገራት ነዋሪ የነበሩ እስራኤላውያንን ተሳባሰቡ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ቤተ እስራኤላውያንም በልባቸው ወደሰነቋት እየሩሳሌም ለመሄድ የቆረጡት። አቶ አዳነ ታደሰ በ1976 ዓ.ም ከጎንደር ፀዳ የምትባል አካባቢ ተነስተው መሬቷን ትተው ፊታቸውን ሳያዞሩ ጉዟቸውን ሌት ተቀን ወደሚያልሟት እስራኤል አደረጉ። በወቅቱ 16 አመታቸው የነበሩት አቶ አዳነ 'ተነቅለው' በሚባል ሁኔታ ወላጆቻቸው፣ ወንድሞችና እህቶቻቸው፣ አጎታቸውና አክስቶቻው ሆነው ከሌሎች ቤተ እስራኤላውያን ጋር ሆነው ጓዜን ፣ማቄን ሳይሉ ረዥሙን ጉዟቸውን ወደ ሱዳን ያደረጉት። "ኢትዮጵያ ውስጥ የጊዜው ነዋሪ ነው የነበርነው፤ ቋሚ ነዋሪ ሆነን አናውቅም፤ አንድ ቀን ኢየሩሳሌም እንደርሳለን በሚል ተስፋ ነው ስንኖር የነበረው" ይላሉ በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግሥት ከሃገር ሊወጣ ሲል የተያዘ ሰው እስር ሲብስም "ቀይ ሽብር" ይፋፋምብን በሚልም መገደልም ነበር። የተደበደቡ፣ ለእስር የተዳረጉ፣ እና የተገደሉም እንዳሉ በሃዘኔታ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዳያዩዋቸው ጉዟቸውን ሲያደርጉ የነበረው ማታን ጠብቀው ሲሆን በተለይም አርማጭሆ እስኪደርሱ ያለው በጣም አሰቃቂ ገደል ከመሆኑ ጋርም ተያይዞ እግራቸውን የተሰበሩ እንዲሁም ተንከባለው ወድቀው ጉዳት የደረሰባቸው አሉ። "ልጆችም ጫማ የሌላቸው በመሆኑ ይሄ አቃቅማ እሾሁ እግራቸውን ብጥስጥስ አደረገው፤ ውሃ በጭራሽ አይገኝም፤ ከተገኘም የቆሸሸ እንዲሁም የሞቀና መጠጣት የማይችል ነው፤ በረሃብና በውሃ ጥም ብዙዎች አልቀዋል" ይላሉ። ፊልሙ ላይ የሞሳድ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ወታደሮች መንጋጋ ፈልቅቀው ቤተ እስራኤላውያንን እንዳዳኗቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው ተልዕኮ አካሂደዋል የሚል ቢሆንም በወቅቱ እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ምንም አይነት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስላልነበራት እንደ ፊልሙ ሳይሆን ራሳቸውን አስተባብረው ሱዳን እንደደረሱም በወቅቱ የነበሩት አቶ አዳነ ይናገራሉ። "የሞሳድ ሰራተኞች ኢትዮጵያ ላይ በአካል አልደረሱም" ይላሉ "ከነበርንበት ከአካባቢያችን ከደምቢያ፣ ላስታ፣ሽሬ፣ አክሱም፣ ወልቃይት፣ ጎንደር፣ ደምቢያ እንዲሁም ወገራ የነበሩትን ነጭ አይደለም ከዚያ አውጥቶ ከባዱን ድካም ሱዳን እስከምንደርስ ያሻገረን፤ እነዚህን ያደረጉትን እኔ ራሴ የማውቃቸው የቤተ እስራኤላውያን ማህበር አስተባባሪዎች ናቸው" ይላሉ በፊልሙ ላይ ከበደ ቢምሮ ተብሎ የተወከለውና በእውነተኛው ከትግራይ አካባቢ የመጣው ፈረደ አክሎም ቤተ እስራኤላውያንን አስተባብሮ ሱዳን ያደረሳቸው አንደኛው መሪ እንደሆነ አቶ አዳነ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ። ከአቶ አዳነ በተጨማሪ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ምርምር አድርጎ "Red Sea spies: The true story of Mossad's fake holiday Resort" በሚል ርዕስ መፅሀፍ የፃፈው የቢቢሲው ጋዜጠኛ ራፊ በርግም ፈረደ አክሎም ቤተ እስራኤላውያንን በማስተባበር ደረጃ ከፍተኛ የጀግንነት ታሪክ እንዳለው ነግሮናል። ፈረደ አክሎም በህይወት ባይኖርም በህይወት ያሉና ጉዞውን ያስተባበሩት አቶ ተገኘ የሚባሉ የደምቢያ ተወላጅ እንደነበሩ የሚናገሩት አቶ አዳነ በመንገድ ላይ ሊያጋጥማቸው ስለሚችሉ ችግሮች እንዲሁም ህዝቡን በማስተባበር፣ ከሞሳድ ጋርም በመቀናጀት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ፊልሙ እንደሚያሳየው ሞሳድ ከኢትዮጵያም ይሁን ከሱዳን እንዳወጣቸውና ቤተ እስራኤላውያን ምንም ሚና እንዳልነበራቸው ቢያሳይም ራፊ እንደሚለው ይህ ከእውነት የራቀ ነው። በኦፐሬሽን ብራዘርስ ላይ 7ሺ የሚሆኑ ቤተ እስራኤላውያን ከመንደራቸው በእግራቸው አቆራርጠው ሱዳን እንደደረሱና ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን በሚያደርጉት ጉዞም ሞሳድ ምንም ሚና እንዳልነበረው ይናገራል። ሱዳንም በመድረሳቸው ምክንያትም ነው የሞሳድ ሰራተኞች ወደ እስራኤል ሊወስዷቸው የቻሉት ይላል "የማዳን ስራ ሳይሆን የማድረስ ስራ ነው የተሰራው። ቤተ እስራኤላውያኑ ሱዳንም ከደረሱ በኋላ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው የሞሳድ ሰላዮችም ሆነው ያገለገሉም ነበሩ" ይላል። አቶ አዳነ በሱዳን መጠለያ የደረሱት ከአንድ ወር የእግር ጉዞ እልህ አስጨራሽና ፈታኝ ጉዞ በኋላ ሲሆን ለአስራ ሶስት ወራትም የሱዳን ቆይታቸው ሰቆቃ የተሞላበት እንደነበር ያስታውሳሉ።"ተዳክመናል፣ ተጎሳቁለናል፤ ለአስራ ሶስት ወራትም በጭብጥ ሽምብራ ውለን አድረናል" በማለት ፈታኙን ጊዜ ያስታውሱታል። ረሃቡ፣ ጥማቱ ይባስ ብሎ ህፃናትን የሚገድል አንከል የሚባል በሽታ ገብቶ ፈጃቸው። በቀን ውስጥ አምስት፣ ስድስት ሰዎች የሚሞቱበት በአንድ ቀንም እስከ ሃያ አምስት ሰዎች የቀበሩበት ጊዜም እንደነበር ያወሳሉ። አራት ሺ የሚሆኑ ስደተኞችም እንደ ቅጠል ረግፈዋል። እሳቸውም ጊዜው ቢረዝምና ሶስት አስርት አመታት ቢያልፍም ታናናሽ እህቶቻቸውንና ወንድማቸውን የነጠቃቸውን የሱዳን የስደት ጊዜ ትናንት የተፈጠረ በሚመስል ሁኔታና ሃዘናቸውን በሚያሳብቅ ሁኔታ በቁጭት ያወሩታል። የሁለት አመቷ እናትዬ፣ የአራት አመቱ ታምራት፣የስምንት አመቷ ተጓዳ፣ የህፃን አንጀታቸው አልችል ብሎ፤ ያለውን ፈታኝ ሁኔታ ሊቋቋሙ ባለመቻላቸው ጨቅላ ሰውነታቸው ይህችን አለም ተሰናብታ ሄዳለች። ሱዳን በገቡ በአራት ወራቸውም ነው ላይመለሱ ያንቀላፉት። የተስፋይቱን ምድር ለማየት ጓጉተው ተንከራተው ህይወታቸውን ያጡትንም በአመት አንድ ቀን ቤተ እስራኤላውያን በፀሎት እየሩሳሌም ላይ ይዘክሯቸዋል። የኦፐሬሽን ብራዘርሰ በጀልባ ወደ እስራኤል መውሰድ እንዳቆመ በጥቂት ሳምንታት ወደ ሱዳን የገቡት አቶ አዳነ ኦፐሬሽን ሞሼ (ትዕይንተ ሙሴ) አካል ሲሆኑ ወደ እስራኤልም የተወሰዱት በአውሮፕላን ነው። እህት ወንድም ፣ ቀብሮ በተለይም ለወላጆቻቸው በጣም ፈታኝ የነበረ ቢሆንም "የተስፋይቱ ምድር ሲደርሱ" በርከክ ብለው መሬቷን ስመዋል። የፊልሙ ባለታሪክ አካል ከመሆናቸው አንፃር እንዴት አዩት? ምንም እንኳን የሞሳድን አስተዋፅኦ ባይዘነጉም የቤተ እስራኤላውያን ልፋት፣ እንግልት፣ ስቃይ፣ ታሪክና ማንነት በፊልሙ ላይ ምንም ትኩረት አልተሰጠውም ይላሉ። "አለም ማወቅ የነበረበት የኛን ልፋት ነበር፤ ህፃን፣ አዛውንት ርቀቱ ሳይበግራቸው 600 ኪ.ሜትር አቆራርጠው፤ አንድ ቀንም ቢሆን በአካል ያላይዋትን ሃገር በእምነታቸው እየሩሳሌም፤ የተቀደሰች ስፍራ፤ የተስፋይቱ ምድር በሚል፤ ምግቡም ውሃውም እንደሚያልቅ ገብቶናል፤ የሞተው ሞቶ የዳነው ድኖ እንደርሳለን የሚል ተልእኮ ነበር የያዝነው። ይህንን ፊልሚ አይናገርም" ይላሉ አብዛኛው ቤተ እስራኤላውያን የገጠር ሰዎች እንደመሆናቸው መጠን የአለም ካርታ አይተው አያውቁም፤ እስራኤል በካርታ ላይ የት እንደምትገኝ በወቅቱ የነበሩት ፅንሰ ሃሳቡ ባይኖራቸውም "እየሩሳሌም ሁልጊዜ ከልባችን የተቀመጠች ናት" ይላሉ "ፅኑ እምነታችንን ቀርቶ፤ አራት ሺ ሰዎች ህይወታቸውን ሰውተዋል፤ እኔ ራሱ ሁለት እህቶቼን አንድ ወንድሜ መንገድ ላይ ቀርተዋል፤ የእኔን ድካም፣ ማንነቴን፣ ባህሌን፣ እኔ ምን አይነት ችግር እንዳጋጠመኝ፣ ምን አይነት አስተዋፅኦ እንዳደረኩ ፊልሙ አይናገርም" ይላሉ። በግራ ያለው ፈረደ አክሎም ሲሆን በቀኝ ያለው ደግሞ ባሩች ተገኘ ነው የታሪክ ግድፈቶች ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ከማለቱ አንፃር ሙሉ በሙሉ እውነት መሆን ባይጠበቅበትም ታሪክን እንደገና መፃፍም ሆነ ሙሉ በሙሉ ግን መካድ አይችልም ይላሉ የሙያው ተንታኞች ። ፊልሙ ላይ ለምሳሌ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሌላት ይናገራል፤ ወቅቱ ግን የደርግ ጊዜ ከመሆኑ አንፃር ኢትዮጵያ የአሰብንና የምፅዋ ወደቦችን ትጠቀም የነበረና ባህር በር የነበራት ወቅት ነው። ራፊም አንዳንድ ጉዳዮች ለፊልሙ ማሳመሪያ ተብለው የገቡና እውነትነት የሌላቸው ሁኔታዎችንም ጠቅሶልናል። የሱዳን ወታደሮች በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን ስደተኞችን እንደጨፈጨፉ ቢያሳይም ይህ አልተፈጠረም። ሃሳዊ ሪዞርቱ ላይ ቤተ እስራኤላውያን እንደቆዩ የሚያሳየውም እንዲሁ፤ ከዚህም በተጨማሪ ሲአይኤ የዚህ ተልእኮ ላይ ከፍተኛ ሚና እንደነበረውና ቤተ እስራኤላውያንንም በአውሮፕላን እንደወሰዷቸውም ፊልሙ ቢያሳይም ሲአይኤም ሆነ አሜሪካ እንኳን ቤተ እስራኤላውያንን ልትወስድ ስለ ተልእኮው ምንም መረጃ እንዳልነበራት ራፊ ያስረዳል። ራፊ ፊልሙ ጥቁር እስራኤላውያን (ቤተ እስራኤላውያን) መኖራቸውን በማሳየት ሚና እንደተጫወተ ቢገልፅም ፊልሙ ቤተ እስራኤላውያን የነበራቸውን ሚናም ሆነ ታሪክ አጉልቶ ባለማውጣቱ ያጣው ነገር እንዳለ ይናገራል። የሁለት ሰዓት ፊልም እንደመሆኑ መጠን ሁሉንም የታሪክ ትዕይንቶች ማስገባት ባይቻልም እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ1981-1984 ድረስ ባለው አስራ አምስት ሚስጥራዊ የሆኑ ተልእኮዎች በመሬት፣ በአየር እንዲሁም በጀልባ ተከናውኗል ይላል። የነጭ አዳኝነት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ፊልሞች ጥቁርም ሆኑ ግሎባል ሳውዝ (ከነጩ አለም ውጭ) ታሪክን እንነግራለን የሚሉ ፊልም ሰሪዎችም ዋነኛ ፈተናቸው በተለይም ከበጀት ጋር ተያይዞ፤ የታሪኩን ማእከል ወይም ዋነኛ ገፀ ባህርዩን ነጮችን (የነጮችን አዳኝነት ታሪክ እንዲያስገቡ መገደዳቸው እንደሆነ ይናገራሉ። በዚህም ኃይሌ ገሪማ አድዋን ለመስራት ከፍተኛ በጀት ጠይቀው በነበረበትም ወቅት የሚኒልክ አማካሪ ነጭ ሰው እንዲያደርግ መጠዬቁን እንደ ምሳሌ የሚነሳ ነው። "የኔ እናት ወይም አያት በፊልሞች ላይ እንድትኖር ለማድረግ አንድ ነጭ ሰው ሊኖር ይገባል"በማለትም በአንድ ወቅት ተናግረዋል። በአፍሪካ ላይ የሚያጠነጥኑ አንዳንድ ፊልሞችን ወደኋላ ሄደት ብለን ብናይ ለምሳሌ "queen of the jungle" ብናነሳ ትንቢት የተነገረላትና ወርቃማ ፀጉር ያላት አንዲት ነጭ አፍሪካን ስታድን የሚያሳይ ነው። የምዕራቡ አለም ከአንድ ቢሊዮን በላይ ህዝቦች በላይ የሚኖሩባትን አህጉር በተለይም በፀሃፍያን ዘንድ የምትመሰልበትን መንገድ ሽሙጣዊ በሆነ መልኩ በፃፈበት "ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ (ስለ አፍሪካ እንዴት መፃፍ እንችላለን) በሚለው ፅሁፉ ቢንያቫንጋ ዋይናይና "የመፅሃፋችሁን ሽፋን በየቀኑ የምናገኛቸውን አፍሪካውያንን ፎቶ ሳይሆን ኤኬ 47 ጠመንጃን የተሸከመ፤ የሽምቅ ውጊያ፣ የተራቆቱ ጡቶች፤ የገጠጡ አጥንቶችን አድርጉ" በማለት ምዕራባውያን ስለ አፍሪካ ሲፅፉ በተደጋጋሚ የሚያወጧቸውን ፎቶዎች በማየት በነገር ሸንቆጥ አድርጓቸዋል። ረሃብ፣ ችግር፣ ጦርነት፣ እርስ በርስ መጨፋጨፍ ብቻ በተሞላችባት በሆሊውዷ አፍሪካ ላይ ይህንን ሲቀርፉ የሚታዩትና ሲያድኑ የሚታዩትም ነጭ ሰዎች ናቸው። ከነዚህም ውስጥ ብዙዎች የሚጠቅሷቸው "ብለድ ዳይመንድ" ዘረኛ ነጭን ወክሎ የሚጫወተው ቅጥረኛው ነፍሰ ገዳይ ሊዮናርድ ዲካፕሪዮ ጥቁሩን ሴራሊዮናዊና ልጁን ሲያድን ከጥቁር ነፍሰ ገዳዮች ሲያድንም ይታያል። የፊልም ልሂቃን ቆጥረው ከማይዘልቋቸው መካከል አምስቴድ፣ ቲርስ ኦፍ ዘ ሰን፣ ክራይ ፍሪደምና በኢትዮጵያ ረሃብ ላይ የሚያጠነጥነው ቢዮንድ ቦርደርስና ሌሎችም ይገኙበታል። የባርነትን ታሪክ እንደገና ከመፃፍ ጀምሮ፣ ኔቲቭ አሜሪካውያንን ሰው በላ አድርጎ መሳል፣ አፍሪካውያንን ነፃ በማውጣትና በመርዳት ነጮችን የአዳኝነት ታሪክ ስፍራ ሆሊውድ እንደፈጠራላቸው ተችዎች ይተነትናሉ። በዚህም ፊልም ላይ ኢትዮጵያውያንን ማዳን ብቻ ሳይሆን ሱዳን ውስጥ ያለን አንድ ብሔር የሰው ስጋ እንደሚበሉ የሚነገርበት፤ የፀጥታ ኃይሉ ምንም ርህራሄ የሌለውና (ያልተፈጠረ ታሪክ በመጨመር) ሱዳናውያን ኢትዮጵያውያን ሲጨፈጭፉ የሚያሳየው ዝም ብሎ የሚወሰድ ሳይሆን ለዘመናት የላቁበት የታሪክ አነጋገር ዘያቸው እንደሆነ ተችዎች ፅፈዋል። በብዙ ፊልሞች ዘንድ የተሳተፈው ያሬድ ሹመቴም ሆሊውድ ወይም የነጩ አለም ነጭ ጀግኖችን በመፍጠር የነጩን አለም ልዕልናንና የሞራል ከፍታን የማሳየት ተልእኮ ለዘመናት የመጣ ከመሆኑ አንፃር በዚህ ፊልም ላይ እንዳልደነቀው ይናገራል። ከዚህ በላይ ግን ከፍተኛ ጥያቄን የፈጠረበት ፊልሙ ታሪክ እንደሚያይ ምንም አይነት እውቅና ያልተሰጠውና ሆሊውድ ፊልም ሲሰራ ተመልካቾቼ ከሚላቸው ዝርዝው ውስጥ ኢትዮጵያውያን እንዴለሉበት ኣሳይ ነው ይላል። በቋንቋም፣ በመልክአ ምድርም፣ በታሪክ አካሄድም "ኢትዮጵያውያን ውሸት እንዴት ለምን ይነግሩናል ቢሉ ግድ እንደማይሰጣቸው የሚያሳይ ነው። ይላል በተለይም ፊልሙን እንደ ኢትዮጵያዊ ሲያየው በጣም የሚጎረብጥ ሆኖ ነው ያገኘው። የሱ ክርክር ይህ የታሪካችን ክፍል ለምን ታዬ ሳይሆን የውክልና ጥያቄ ነው። የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል አኗኗር፣ የቋንቋ ዘዬና መልክአ ምድር ጠንቅቆ የማያውቅ ፊልም ነው የሚለው ያሬድ "ኢትዮጵያ የሌለችበት ስለ ኢትዮጵያ የተሰራ ፊልም ነው።" ብሏል። የተዘበራረቀ መልክዓ ምድር ቤተ እስራኤላውያን የሰፈሩት ሽረ፣ አደጋሮም፣ ወልቃይትና ተከዜን ፣ወገራ፣ ዳባት አባጊዮርጊስ፣ ደምቢያ፣ ፀዳ፣ ማክሰኚት፣ ወደ ሰሜን ደግሞ ደጎማ፣ የመሳሰሉትን ቦታዎች ላይ እንደሆነ አቶ አዳነ ይናገራሉ። ፊልሙ የተሰራው ናሚቢያ ሲሆን ታሪኩ የተፈፀመበት ቦታ ተብሎ የተወሰደውና የቤተ እስራኤላውያን መኖሪያ ደግሞ ከአባይ ወንዝ ዳርቻ ላይ ያለ ቦታ ይመስላል። የመልክአ ምድር አቀማመጡና የቤተ እስራኤላውያንን አሰፋፈር ግምት ውስጥ የከተተ አይደለም በማለትም ያሬድ ይከራከራል። ቤተ እስራኤላውያኑ በስደትም ላይ ትንሽ ተጉዘው ውሃ ውስጥ ይገባሉ። አካባቢውን በደንብ ለሚያውቀው ያሬድ ከጎንደር ተነስቶ የአርማጭሆ በረሃን አቋርጦ፤ የሱዳንን ድንበር ለመሻገር ወደ ጎጃም በመተከል አድርገው ካልሄዱ በቀር፤ በኢትዮጵያ መልክአ ምድር ውስጥ አባይን ሊያቋርጡ፤ ውሃውን ሊያቋርጡ የሚችሉበት ምንም አይነት የመልክአ ምድር ግጥጥሞሽ እንደሌለም አበክሮ ይናገራል። "ፊልሙ ላይ ሆን ተብሎ አንዲት ኢትዮጵያዊ ባህር ውስጥ ስትሰጥም አጉልቶ ለማሳየት በሚል ለማየት የተፈጠረ ይመስለኛል። ይህ አሁን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በከፍተኛ ሁኔታ ይረብሻል።" ይላል ከመልክአ ምድር መዘበራረቅ በተጨማሪ በጣም ያሳዘነው ኢትዮጵያዊ ውስጥ የኖሩ ቤተ እስራኤላውያን ከመሆናቸው አንፃር አለባበሳቸው፣ ቋንቋቸው ኢትዮጵያዊ መሆን ሲገባው አማርኛ መናገር የማይችሉና የሚኮላተፉ ገፀባህርያት መጠቀማቸው ነው። "ይህ በጣም ለኔ ጎርብጦኛል፣ አናዶኛል። የተናደድኩት ለምንድን ነው እንደዚህ የምሆነው ለምንድን ነው ብዬ ስል ለታሪኩ ሳይሆን መታመን የፈለጉት እኛ በጭራሽ፤ እንደ ፊልም ተመልካች አልተቆጠርንም" ይላል ፊልሙን ለምን ኢትዮጵያ አልሰሩትም የሚለው ዋነኛው ጥያቄው የሆነው ያሬድ በ70ዎቹ ላይ የነበረ ታሪክን እንስራ ቢሉ እንደማይከለከሉ ያምናል። ኢትዮጵያ የታየችው እንደ ታሪክ ማሳያ ወይም ማሟሻ ተደርጋ ከመሆኑ አንፃር ጉግል አድርገው በቀላሉ መመለስ የሚችሏቸውን ታሪኮች ስተዋል ይላል። "ስለ መኪና ጎማ ፊልም ብትሰሪ የመኪና ጎማ ስታሳየኝ አጣመምከኝ አይልም፤ ምክንያቱም አንደበት የለውም። እኛም አንደበት እንዳለው አስተያየቱን እንደሚሰጥ አካል አልታየንም።" ይላል። እስራኤላውያን በጀርመን የነበረውን እልቂት የሰሩት ታሪኩን አበላሽተው ሳይሆን እንደ ታሪኩ ባለቤት እውቅና ሰጥተው ሲሆን ይህም ሆሊውድ ላይ አብዛኞቹ ትልልቅ ስቱዲዮዎች ባለቤት ስለሆኑ ተፅእኖን መፍጠር ችለዋል ይላል። የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ላይ ያጠነጠነው ዘ ኢንተርቪው ፊልም ፕሬዚዳንቱ ክብሩን ዝቅ የሚያደርግ ነው በሚል የሶኒ ፊልም ላይ ሳይበር አታክ አድርሰዋል። "ኢትዮጵያን የሚያዋርድ ነገር ተሰርቶ ኢትዮጵያም ምንም አትልም።ይህ የሚያሳየው የመናቅ ደረጃችንን ነው" ይላል ኢትዮጵያን አይወክልም ብሎ የሚሞግቱ ሰዎችና ኢኮኖሚያቸው፣ ደህንነታቸውና ገበያቸው ላይ ችግር የሚያመጣ ስለሌለ ቸልተኝነት እንደፈጠረ ይገልፃል። ስለ ቻይና ቢሰሩ ቻይና የሚመስሉ ሰዎች እንደማያመጡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለታሪኩ ታማኝ አልሆኑም በማለትም ያስረዳል። የመፃፍ ነፃነት እስከምን ድረስ ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ከማለቱ አንፃር ያልነበሩ የታሪክ ሁነቶችን ማስገባት ይቻል ይሆን? የፀሐፊው ነፃነትስ እስከምን ድረስ ነው የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ። መነሻውን ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ቤተ እስራኤላውያን ነበሩ በማለት ልብወለድና ፀሐፊው በምናቡ የሚመላለሱ ታሪኮችን ማካተት እንደሚቻል ያሬድ ያስረዳል። እንዲህ አይነት ነፃነት ካለ ስህተቱ ታዲያ ምን ላይ ነው? ያሬድ ምላሽ አለው። "በዚህ ፊልም ላይ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲል የትኛው ነው እውነተኛ ታሪክ የሚለው ነው ጥያቄ ውስጥ የሚገባው፤ የትኞቹ ናቸው እውነተኛ ታሪክ ብሎ የሚከራከራቸው፤" ብሎም ይጠይቃል። ሰዎቹ ኢትዮጵያዊ ካልሆኑ፣ ባህላቸው፣ ቋንቋቸው ከሌለ፤ ሃገሪቷ ኢትዮጵያ ካልሆነች፤ የታሪክ ግድፈት ካለበት ስለየትኞቼ ህዝብ ነው የሚያወሩት "እንደሰውም አልተቆጠርንም፤ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የሚያዋርድ ፊልም ነው፣ እንደ አፍሪካዊም የሚያሳፍር ነው፣ እንደ አንድ ፊልም ሰሪ የቤት ስራቸውን ያልጨረሱ ፊልም ሰሪዎች እንደ ተመልካች 'ማይኖሪቲ' ብለው ለሚያስቡት ታማኝ ያልሆኑበት ነው።" ይላል ቤተ እስራኤላውያን በትዕይንተ ሰለሞን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ሲወሰዱ ቤተ እስራኤላውያን በኢትዮጵያ ስለ ቤተ እስራኤላውያን አመጣጥ ሁለት ማብራሪያዎች ይሰጣሉ ። አንደኛው ንግሥት ሳባ የእየሩሳሌምን ንጉስ ሰለሞን ልትጠይቅ ሄዳ ምኒልክ ተወለደ የሚል ሲሆን ይህ ግን ከአፈ ታሪክ ያልዘለለ እንደሆነ ኢትዮጵያ ላሉ ቤተ እስራኤላውያን የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ኃላፊ አቶ ንጉሴ ዘመነ አለሙ ይናገራሉ። ቤተ እስራኤላውያን የሚያምኑትና መፅሀፍ ላይ የሰፈረው በሰባኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው ቤተመቅደስ በፈረሰበት ሰዓት ይሁዳውያኖች መሰደድ ጋር ተያይዞ የመጣውን ነው። ከ አስራ ሁለቱ ነገዶችም መካከል ዳን ተብሎ የሚጠራው ነገድ ወደ ግብፅ ተሰደደ፤ ከግብፅም የናይል ወንዝን በመከተል ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሰፍረዋል። በኢትዮጵያ በሚኖሩበት ወቅት ፈላሻ ወይም ካይላ የሚል ስያሜ ተሰጥቷዋል። አቶ ንጉሱ እንደሚናገሩት ፈላሻ የሚለው ቃል 'ሊፍሎሽ' ከሚለው የእብራይስጥ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ሲሆን ከቦታ ቦታ የሚዞር ቋሚ ቦታ የሌለው ማለት ነው። ካይላም እንዲሁ 'ክሂላ' የሚለው ከእብራይስጥ የተወሰደ ሲሆን አንድ ላይ የሚሆን በማህበር የሚሄድ ማለት ቢሆንም ለዘመናት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ስድብ አገልግሏል። ቀጥቃጭ፣ አንጥረኛ፣ ቡዳ በሚልም ለዘመናት ሲገለሉ ሲዋረዱም ኖረዋል። የእስራኤል መንግሥትን ምስረታ ተከትሎ ቤተ እስራኤላውያን ወደ እስራኤል የሚያደርጉትን ጉዞ የተጀመረ ቢሆንም በ1906 ዓ.ም ፕሮፌሰር ታይታሎቪች በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በመምጣት ጥናት አድርጎ ይሁዲዎች ኢትዮጵያ እንዳሉ ከዚያ 50 የሚሆኑ ወጣቶችን ወደ አውሮፓ እንደወሰደ አቶ ንጉሱ ይናገራል። ኦፐሬሽን ሞሰስ፤ በጎርጎሳውያኑ 1980፣ 1981 ላይ የነበረ ሲሆን የሞሳድ ድርጅት ትብብር በማድረግ ከ7ሺ በላይ ይሁዲዎችን በሱዳን ምድር ይዞ የሄደበት ኦፐሬሽን ሲሆን ከዚያ በኋላ ደግሞ የቀሩት ይሁዲዎች ወደ አዲስአበባ በመሄድ በአዲስ አበባ የተደረገው ጉዞ ነው። የመግሥት ለውጥ ከተደረገ በኋላ ኦፐሬሽን ሰለሞን (ትዕይንተ ሰለሞን) በጎርጎሳውያኑ 1991 ከ14ሺ600 በላይ ቤተ እስራኤላውያን በ36 ሰአታት ውስጥ ተወስደዋል። ከዚያ በኋላም ትንንሽ ጉዞዎች የነበሩ ሲሆን ክንፈ ዮና፣ ሸአሪት ይሁዲ ኢትዮጵያ (የቀሩ ይሁዲዎችን መውሰድ) የሚሉም ተካሂደዋል። በአዲስአበባና በጎንደር ያሉ የተመዘገቡ 8 ሺ 200 የሚጠባበቁ ቤተ እስራኤለውያን ያሉ ሲሆን፤ እስራኤል ሃገር ያለው የ2017 የእስራኤል ስታትስቲክስ መሰረት 150ሺ ቤተ እስራኤላውያን አሉ።
54956575
https://www.bbc.com/amharic/54956575
ትግራይ [ምልከታ] ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው ችግር ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ነው?
ኢትዮጵያ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እያመራች ይመስላል።
በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የተከፈተው ጦርነት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። አገሪቱን ሊከፋፍላት እንደሚችልም ተሰግቷል። ጦርነቱ የመሣሪያ ብቻ አይደለም። የቃላትም ጭምር እንጂ። ሁለቱም ወገኖች ዜጎችን ከጎናቸው ለማሰለፍና ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማሳመንም እየሞከሩ ነው። የፌደራል መንግሥትና ህወሓት አንዳቸው ሌላውን ግጭቱን በማጫር ይወነጅላሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የመከላከያ አባላት በጭካኔ ተገድለዋል ይላሉ። የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ደግሞ መከላከያ ሠራዊቱ ከኤርትራ ኃይል ጋር ሆኖ ጥቃት እንደሰነዘረ ይናገራሉ። መረጃዎቹ በገለልተኛ ወገን እስከሚጣሩ ድረስ አሁን ላይ ማስረጃ የሌላቸው ክሶች ናቸው። 'የጨለማ ዓመታት' ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያን ታሪክ የሚመለከቱት በተለያየ መነጽር ነው። አብዮቱን ተከትሎ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከሥልጣን ሲወገዱ ወታደራዊው የደርግ አገዛዝ ተተካ። ይህ ወቅት በቀይ ሽብር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች የተገደሉበት ነው። በመላው አገሪቱ ይንቀሳቀሱ ከነበሩ አማጽያን ጋር ረዥም ጊዜ የወሰደ የእርስ በእርስ ጦርነትም ተካሄዷል። ለትግራይ ተወላጆች እነዚህ ዓመታት ጨለማ ነበሩ። በተደጋጋሚ የአየር ድብደባ ይካሄድ ስለነበር ሰዎች በሌሊት ለመንቀሳቀስ ተገደው ነበረ። ከሁሉም የከፋው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ የ1988ቱ የሀውዜን የአየር ድብደባ ነው። ወደ 2500 ሰዎች ተገድለዋል። የአየር ድብደባውን ተከትሎ ከተማዋ በጭስና አቧራ ሳቢያ በቀን በጨለማ ተውጣ ነበር። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሚመራው የኢሕአዴግ ጥምረት ደርግን አሸንፎ ሥልጣን ከያዘ በኋላ፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ "ቀዳሚ ግባችን ኢትዮጵያውያን በቀን ሦስቴ እንዲበሉ ማስቻል ነው" ማለታቸው ይታወሳል። በ27ቱ ዓመታት የኢሕአዴግ ዘመን የህጻናት ሞት መቀነሱ ይገለጻል። ቀድሞ ከአምስት ልጆች አንድ ይሞት የነበረ ሲሆን፤ ቁጥሩ ከ20 ህጻናት ወደ አንድ ህልፈት ቀንሷል። ረሀብ ጠፍቷል። መጠነ ሰፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ተወግዷል። ሆኖም ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ብርሃን አላየችም። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እና ደጋፊዎቻቸው ይህን ወቅት "27 የጨለማ ዓመታት" ይሉታል። ወጣቱ ትውልድ ድምጹ እንደታፈነ እና ከፖለቲካው እንደታገደ ይሰማዋል። ባለፈው ሳምንት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አዲስ አበባ ውስጥ ለሠራዊቱ ደም ለግሰዋል የትግራይ ተወላጆች ፖለቲካውን፣ ምጣኔ ሀብቱን እና ወታደራዊ ኃይሉን ተቆጣጥረው ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት የሚከራከሩ አሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡት በዋነኛነት ኦሮሚያ ውስጥ በተቀሰቀሰ ሕዝባዊ ተቃውሞ አማካይነት ነው። ሥልጣን ከያዙ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩን በአንጻራዊነት አሰፉ። ኢሕአዴግን አክስመውም የብልፅግና ፓርቲን መሠረቱ። እርምጃዎቻቸው እውቅና አተረፉላቸው። ተቺዎቻቸው ግን "ማፍረስ መገንባት አይደለም" ሲሉ ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኤርትራ ጋር እርቀ ሰላም በማውረዳቸው የኖቤል የሰላም ሽልማት አግኝተዋል። የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለዓመታት የኢትዮጵያን ወታደራዊ ኃይልና አገሪቷንም የማፍረስ አቋም ቢያንጸባርቁም፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የቅርብ ወዳጃቸው አድርገዋቸዋል። የፕሮቴስታንት ሐይማኖት ተከታዩ ጠቅላይ ሚንስትር በፈጣሪ የተመረጡ መሪ እንደሆኑ የሚጠቁም ንግግር ሲያደርጉ ይደመጣል። የሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያቸውን ጨምሮ አብዛኞቹ ጽሁፎቻቸው ራስ አገዝ የንግድ ትምህርት ቤት ማስተማሪያ ይመስላሉ። በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳላቸው አያጠያይቅም። እሳቸውም ይሁን ፓርቲያቸው በብሔራዊ ምርጫ ቀርበው ምን ያህል ድጋፍ እንዳላቸው ግን ገና አልተፈተሹም። የሕገ መንግሥቱ ጉዳይ በፌደራል መንግሥትና በህወሓት መካከል የነበረው መካረር ጫፍ የደረሰው በትግራይ የተናጠል ክልላዊ ምርጫ ሲካሄድ ነው። ምርጫው ሕገ ወጥ ነው ሲል የፈደራል መንግሥቱ ውድቅ አድጓል። በኮቪድ-19 ምክንያት ብሔራዊ ምርጫ ሲራዘም፤ ትግራይ ክልል ለብቻው ምርጫ ካካሄደ በኋላ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዳደር የሥልጣን ጊዜው ስላለፈበት ሕገ ወጥ እንደሆነ ሲገልጽ ነበር። ሁለቱም አካላት ለመከራከሪያቸው የሚያጣቅሱት ሕገ መንግሥቱን ነው። ሕገ መንግሥቱ የሰጠው የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን ተግባራዊ የማድረግ ጥያቄ ከሚነሳባቸው ክልሎች መካከል ትግራይ እና ኦሮሚያን መጥቀስ ይቻላል። በእርግጥ ህወሓት ጥያቄውን በግልጽ ባያቀርብም አሁን ላይ ያለው ጦርነት ወደ መገንጠል ሊያመራ ይችላል። ህወሓት ለ27 ዓመታት የፖለቲካ ምህዳሩን መቆጣጠሩ በኦሮሞና ሌሎችም ብሔሮች ዘንድ ተቃውሞ ማስነሳቱ አይዘነጋም። 'አዲሱ ተቃውሞ' ባለፉት ጥቂት ወራት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ያመጣቸው የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ላይ ፊታቸውን አዙረዋል። በተለይም ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ በኋላ በተነሳው ተቃውሞ ከ150 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ታዋቂ ፖለቲከኞቹ አቶ አጀዋር መሐመድና አቶ ልደቱ አያሌውን ጨምሮ ወደ 10 የሚደርሱ ሰዎች ታስረዋል። አቶ ጀዋር በሽብር ሲከሰሱ፤ አቶ ልደቱ ደግሞ ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ተከሰዋል። በሌላ በኩል ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ተገንጥሎ እንደወጣ የሚነገርለት ኦነግ-ሸኔ በቅርቡ በወለጋ ከ50 በላይ የአማራ ተወላጆችን ገድሏል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ለግድያው በዘወርዋራ አገላለጽ "አገሪቱን መምራት ወይም ማበላሸት" የሚፈልጉ ያሏቸውን "የኢትዮጵያ ጠላቶች" የሚሏቸውን ህወሓቶችን ተጠያቂ አድርገዋል። የፌደራል ሥርዓቱ ተገርስሶ አሃዳዊ አስተዳደር እንዲፈጠር የሚሹ የአማራ የፖለቲካ ልሂቃን ለጠቅላይ ሚንስትሩ ድጋፍ አላቸው። በእርግጥ ብሔርን መሠረት ያደረገ የፌደራሊዝም ሥርዓት በተለያየ ምክንያት ይተቻል። ሆኖም የተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያለ ፈቃዳቸው ሊመሩ እንደማይችሉ በግልጽ አሳይተዋል። ከጦርነት ቀጠናው የወጣ ሪፖረት ንጹሃን የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን ይጠቁማል። ከአዲስ አበባና ከሌሎችም ከተሞች የተገኙ መረጃዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ የጅምላ እገዳ እንደተጣለባቸው እያመለከቱ ነው። በትግራይ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ከመቋረጡ ባሻገር ማንኛውም መጓጓዣ ወደ ክልሉ ስለማይገባ ሰብዓዊ እርዳታ ማድረስም አልተቻለም። ህወሓት ትግራይ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ የነበሩ የኤርትራ ወታደሮችን መማረኩን አስታውቋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ትግራይ ከፌደራል መንግሥቱ በተመደበ መዋቅር እንድትመራ ይሻሉ። የኢትዮጵያን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉ አካላት ይህ ሊሆን እንደማይችል ያምናሉ። በትግራዩ ጦርነት እጃቸው እንዳለበት የሚነገረው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ እስካሁን ምንም አላሉም። 14 ቀኑን የያዘው ጦርነት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል። በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉም ይገመታል። ይህን ጽሑፍ የተጻፈው በአሜሪካው ተፍት ዩኒቨርስቲ፣ በፍሌቸር የሕግና የዲፕሎማሲ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኘው የወርልድ ፒስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሆነው በአሌክስ ደ ዋል ነው።
news-41605761
https://www.bbc.com/amharic/news-41605761
ኢትዮ-ቴሌኮምና በኢንተርኔት ዋጋ እና ፍጥነት የተማረሩ ደንበኞቹ
በስራ ጉዳይ ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚጓጓዘው ወንድሜነህ እንግዳ በርካታ የአፍሪካ ሃገራትን የመጎብኘት አጋጣሚ አግኝቷል። በቅርቡም ወደ ኬንያ ለሳምንት ያህል አምርቶ ነበር። በእነዚህ አጋጣሚዎችም ሃገሩ ኢትዮጵያ አልፎም መኖሪያው አዲስ አበባ ከመሰል ከተሞች ጋር ያላትን ልዩነትና ምስስል መታዘብ ችሏል።
"ከሁሉም ከሁሉም በበርካታ ሃገራት የማስተውለው የኢንተርኔት ፍጥነት እና አቅርቦት ጉዳይ ያስደንቀኛል" ይላል ወንድሜነህ። "የእነዚህ ሃገራት መንግስታት ኢንተርኔት ለአንድ ሃገር ዕድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የተረዱት ይመስላል" ሲል ትዝብቱን ያስቀምጣል። "አንድ ቀን ኢትዮጵያም እንደጎረቤት ሃገራት ፈጣንና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ኢንተርኔት ታቀርብ ይሆናል። ማንያውቃል. . . " ይላል ወንድሜነህ። የቴሌኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ዕድገት አብይ ማሳያ የሆነው የኢንተርኔት አገልግሎት አሁን አሁን አስፈላጊነቱ ከምንም ጊዜ በላይ እየጨመረ እንደመጣ አያጠራጥርም። ዓለማችን በሉላዊነት አንድ እንድትሆን ትልቅ ሚና ከተጫወቱ ቴክኖሎጂዎች መካከልም ቁንጮ ሆኖ ይቀመጣል። የዓለም አቀፉ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ማሕበር በአውሮፓውያኑ 2016 ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በቴሌኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ከዓለም 169ኛ ደረጃ ከአፍሪካ ደግሞ 33ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ሞሪሺየስ የምትመራው የአህጉራችን የቴሌ ዘርፍ ጎረቤት ሃገር ኬንያን 9ኛ ላይ ሲያስቀምጥ፤ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ በተከታታይ 20ኛ 22ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ታላቅ ቅናሽ 60 ሚሊዮን ደንበኞች እንዳሉት የሚናገረው ኢትዮ ቴሌኮም ከእነዚህ ውስጥ 17 ሚሊዮን ያክሉ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የኢንተርኔት አግልግሎት ተጠቃሚ ናቸው። የኢትዮ ቴሌኮም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ እንደሚናገሩት የ3ጂ ኢንተርኔት በአሁኑ ሰዓት በመላ ሃገሪቱ የተስፋፋ ሲሆን ተጠቃሚዎችም አገልግሎቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እያገኙ ይገኛሉ። ኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔት በተለይም ደግሞ በተንቀሳቃሽ ስልክ የሚቀርበውን አገልግሎት በዝቅተኛ ታሪፍ ለደንበኞቹ ያቀርባል ሲሉ ይናገራሉ አቶ አብዱራሂም። "አይሲቲ አፍሪካ የተባለ ድርጅት በሚያወጣው ደረጃ መሠረት ኢትዮጵያ በተንቀሳቃሽ ስልክ ኢንተርኔት ዋጋ በዝቅተኛው ደረጃ ላይ ትገኛለች። ይህም ማለት 0.03 ዶላር በአንድ ደቂቃ ዋጋ ላይ ትገኛለች። በተነፃፃሪ ደግሞ ኬንያ በ0.07 ዶላር የአንድ ደቂቃ ኢንተርኔት ትሸጣለች" በማለት አቶ አብዱራሂም ያስቀምጡታል። ወንድሜነህ ግን በዚህ ሃሳብ የሚስማማ አይመስልም። "እኔ በሄድኩባቸው እንደ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ የመሳሰሉ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የተንቀሳቃሽ ስልክ ኢንተርኔት አግልግሎት በተነፃፃሪ እጅጉን ርካሽ እና ፈጣን ሆኖ ነው ያገኘሁት" ሲል ያስረግጣል። የቴሌኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆነው ተክሊት ሃይሌም ሃሳቡ ተመሳሳይ ነው። "በቅርቡ ግብፅ ሄጄ የኢንተርኔት አግልግሎቱን በርካሽ ዋጋ መጠቀም ችያለሁ። ያውም እጅግ ፈጣን የሆነ አገልግሎት" ሲል ይናገራል። ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የሚያቀርበውን የኢንተርኔት አግልግሎት ዋጋ ከኬንያው ሳፋሪኮም ጋር ለማነፃፀር እንደሞከርነው የኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔት አቅርቦት መጠን ባደገ ቁጥር ዋጋው እጅግ ከፍ እያለ ይመጣል። ሳፋሪኮም ዝቅተኛውን የ5 ሜጋ ባይት ኢንተርኔት በ5 ሽልንግ ወይም አሁን ባለው የምንዛሪ ዋጋ 1ብር ከ30 ሳንቲም አካባቢ ያቀርባል። ኢትዮ ቴሌኮም ደግሞ የ25 ሜጋ ባይት ኢንተርኔት በ5 ብር ያቀርባል። በዚህ ረገድ ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ሲሆን የኢንተርኔት መጠኑ ከፍ ሲል ግን ሳፋሪኮም እጅግ በተሻለ ዋጋ ኢንተርኔትን ለደንበኞቹ ያቀርባል። ለምሳሌ ኢትዮ ቴሌኮም 1ጂቢ በ165 ብር ሲሸጥ በተነፃፃሪ ሳፋሪኮም 1ጂቢ በ500 ሽልንግ ወይም አሁን ባለው የምንዛሪ ዋጋ በ130 ብር አካባቢ ይሸጣል። መረጃዎቹ ከኢትዮ ቴሌኮምና ሳፋሪኮም ድረ-ገፆች የተገኙ ናቸው ወጥ-አልባነት ወንድሜነህም ሆነ ተክሊት በአንድ ተጨማሪ ነገር ይስማማሉ። በኢትዮ-ቴሌኮም የኢንተርኔት አቅርቦት ወጥ-አልባነት። "የዋጋው ነገር እንዳለ ሆኖ" ይላል ወንድሜነህ "አንዳንድ ወቅት ዘለግ ላለ ጊዜ የምትጠቀምበት ኢንተርኔት በሌላ ወቅት በደቂቃዎች ውስጥ ያልቅብሃል። በምን ዓይነት መስፈርት እንደሚሰራ ግልጽ አይደለም" ይላል። በመንግስት ሥራ የምትዳደረው መክሊት የ2ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ነች። "2ጂም ሆነ 3ጂ ልዩነቱ አይታየኝም። እንደውም አንዳንዴ 3ጂ ከሚጠቀሙ ጓደኞቼ የኔ ኢንተርኔት ፈጥኖ ይገኛል" ትላለች። "አንዳንድ ጊዜ በ5 ብር የገዛሁትን ጥቅል አገልግሎት ረዘም ላለ ጊዜ እጠቀማለሁ ሌላ ጊዜ ወዲያው ያልቅብኛል" ስትል ትናገራለች። ሞኖፖሊ የኢትዮጵያን ቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ በበላይነት የሚቆጣጠረው ኢትዮ ቴሌኮም ሌላ ምርጫ የሌላቸውን ደንበኞቹን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ እያሳደገ ቢመጣም የኢንተርኔት ነገር ለብዙዎች አሁንም አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ተክሊት ለዚህ ችግር መፍትሄው አማራጭን ማስፋት ነው ይላል። "እኔ ቴሌኮም ለውጭ ድርጅት ይሸጥ ወይም አክሲዮን ይሰጥ የሚል እምነት የለኝም። ነገር ግን ለሃገር ውስጥ ድርጅቶች ዘርፉን ክፍት ማድረግ ቢቻል በሚቀጥሉት ዓመታት ቴሌኮም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሁሉም ማቅረብ እንደሚቻል አምናለሁ" ሲል ይናገራል። "ኬንያ የሄድኩ ጊዜ ሳፋሪኮም፣ ኤይርቴል እና ቴልኮም የተባሉ አበይት አማራጮች ስላሉ ሰው እንደፍላጎቱ አማርጦ ሲጠቀም ተመልክቻለሁ። እኛ ሃገር ስትመጣ ግን ያለህ አማራጭ አንድ እና አንድ ነው። እሱም አሰራሩ ወጥ ነው ብዬ አላምንም" ሲል ወንድሜነህ በሌሎች ሃገራት የታዘበውንና የሃገሩን ሁኔታ ይተርካል። ጨምሮም "እንደኬንያ በመሳሰሉ ሃገራት ረከስ ባለ ዋጋ ተገዝቶ ከግለሰቦች ቤት አልፎ በሕዝብ ማመላለሻ ባሶች ውስጥ ሳይቀር የሚገጠመው 'ዋይፋይ' ኢትዮጵያ ውስጥ ከብቸኛው አቅራቢ ኢትዮ-ቴሌኮም በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የማይታሰብ ነው" ይላል። ኢትዮ-ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎትን ከማስፋት ባለፈ ጥራት እና ፍጥነት ላይ እየሰራ እንደሆነ አቶ አብዱራሂም ይናገራሉ። "ታሪፍን በተመለከተ በተከታታይ እያየን ማሻሻያ የምናደርግበት ጉዳይ ነው። የሚቆም ጉዳይ" አይደለም ይላሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም ከኬንያው ሳፋሪኮም ጋር በትብብር ሊሠራ ነው ተብሎ በተለያዩ ዜና ምንጮች የተነገረው መሠረተ ቢስ መሆኑን አቶ አብዱራሂም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሆኖም መክሊት እና ወንድሜነህን የመሳሰሉ ደንበኞች አሁንም ጥያቄ ያነሳሉ። "መች ይሆን ኢንተርኔት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሁም በአስተማማኝ ፍጥነት የምናገኘው?" በማለት. . .
news-54054560
https://www.bbc.com/amharic/news-54054560
ሃጫሉ ሁንዴሳ፡ ለብዙሃኑ ድምጻዊ ለሌሎች ደግሞ 'ዐይን' የነበረው ሃጫሉ
የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ዓመቱ ሊጠናቀቅ ሁለት ወራት ሲቀሩ የተከሰተ ቢሆንም ከቤተሰቦቹ ጀምሮ በሌሎች በርካታ ግለሰቦች ህይወት ላይ ካስከተለው ከባድ ሐዘን በተጨማሪ በአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ የፈጠረው ተጽዕኖ ጉልህ የሚባል ነው።
ከዚህ አንጻር የሃጫሉ መገደልና እሱን ተከትሎ የተከሰተው አለመረጋጋት የብዙዎችን ሕይወት አናግቶ በሽግግር ላይ የሚገኘውን የአገሪቱ ፖለቲካንም ወደ ቀውስ መርቶታል። በዚህም በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገው ዓመቱ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል። ቢቢሲም ይህንን ጉልህ የዓመቱ አስደንጋጭ ክስተትን ሲዘክር ስለወጣቱ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ብዙም ያልተነገሩ ጥቂት ነገሮችን ለመቃኘት ሞክሯል። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም. ምሽት 3፡30 ገዳማ በጥይት ተመትቶ ተገደለ። የሃጫሉ ግድያ በርካቶችን ያስደነገጠ፣ ያሳዘነ እና ያስቆጣ ነበረ። የድምጻዊውን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ንብረት ወድሟል። በሺዎች የሚቆጠሩም ለእስርና መፈናቀል ተዳርገዋል። የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በ2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ከተፈጠሩ አነጋጋሪ ጉዳዮች መካከል አንዱ በመሆን አልፏል። በዚህ ዘገባ ውስጥም ስለ ድምጻዊ ሃጫሉ የሙዚቃ እና ህይወት ያልተሰሙ እውነታዎችን እንደሚከተለው ለመቃኘት ወደድን። ከልጅነቴ ጀምሮ አፌ እረፍት የለውም ነበር . . . 1976 ዓ.ም. የተወለደው አርቲስት ሃጫሉ፤ ትውልድ እና እድገቱ ምዕራብ ሸዋ አምቦ ከተማ ነው። ዘጠኝ ወንድም እና እህት ያለው ሃጫሉ፤ ከአብሮ አደግ ጓደኞቹ ጋር ከብት በመጠበቅ ነው ያደገው። በሙዚቃ ፍቅር ገና በልጅነቱ እንደወደቀ የሚናገረው ሃጫሉ፤ "እዘፍናለሁ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ አፌ እረፍት የለውም ነበር" ብሎ በአንድ ወቅት ተናግሯል። በትምህርት ቤት የሙዚቃ ክበብ አባል በመሆን ይዘፍን ነበር። ወላጅ አባቱ አቶ ሁንዴሳ ግን በዚህ ደስተኛ አልነበሩም። "አባቴ ዶክተር ወይም ፕሮፌሰር እንድሆን ነበር የሚፈልገው። 'ዘፋኝ ትዳር አይመሰርትም' ይላል" ሲል ሃጫሉ በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። እስር በልጅነት ሃጫሉ ገና የ17 ዓመት ታዳጊ ሳለ ያጋጠመው ነገር ህይወቱን የቀየረ አጋጣሚ ሆኗል። በ1995 ዓ.ም. ላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የነበረው ሃጫሉ ክስ ሳይመሰረትበት፣ ጥፋተኛ ሳይባል አምስት ዓመታት በአምቦ 'ከርቸሌ' በእስር አሳልፏል። እርሱ እና ጓደኞቹ ከአምስት ዓመታት እስር በኋላ "ነጻ" ተብለው መሰናበታቸውን ሃጫሉ ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ ተናግሯል። እስር ቤት ሳለ ግን የሙዚቃ ክህሎቱን እንዲያሳድግ መልካም አጋጣሚ ሆኖ እንዳለፈ በተደጋጋሚ ሲናገር ተደምጧል። "ከዚያ ቀደም መዝፈን እንጂ ግጥም እና ዜማ ለመጻፍ ሞክሬ አላውቅም ነበር" ያለው ሃጫሉ፤ ግጥም እና ዜማ መጻፍ የጀመረው የአምቦ ከርቸሌ ታሳሪ ሳለ ነበር። የሃጫሉ የሙዚቃ ሕይወት ሃጫሉ "ሰኚ ሞቲ" እና "ዋኤ ኬኛ" የተሰኙ ሁለት የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጭ ጆሮ አብቅቷል። ከአልበሞቹ በተጨማሪ ግን የለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎች እጅግ ተወዳጅ ሥራዎቹ ሆነዋል። ከአምስት ዓመታት በፊት 'ማለን ጅራ?' [ምኑን አለሁት?] በሚል ለሕዝብ ያበቃው ነጠላ ዜማ የኦሮምኛ ቋንቋን በማይችሉት ዘንድ ሁሉ ተወዳጅ ሆኖለታል። ሃጫሉ ይህን ሙዚቃ የሰራው በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለው የመሬት ወረራ እጅጉን ስላሳሰበው መሆኑን ለቢቢሲ እንዲሁም ለሌሎች መገናኛ ብዙሃን ተናግሮ ነበር። 'ማለን ጅራ' የሚለው ነጠላ ዜማ ለህዝብ ጆሮ ከበቃ ከሁለት ዓመታት በኋላ፤ 'ጅራ ጅራ . . .' [አለን አለን . . . ] የተሰኘውን ሌላ ተወዳጅ ሥራውን ለአድናቂዎቹ አቅርቧል። በቀደመ የነጠላ ዜማ ሥራው 'ምኑን አለሁት' ያለው ሃጫሉ 'ጅራ ጅራ . . .' በሚለው የነጠላ ዜማው ደግሞ በአገሩ ያለውን ተስፋ ያንጸባረቀበት ነበር። ሃጫሉ ከመገደሉ በፊት በኦኤምኤን ቴሌቪዥን ላይ ባደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ ለሕዝብ ጆሮ ያልደረሱ የተለያዩ ሥራዎች እንዳሉት ተናግሮ ነበር። በአሁኑ ወቅት ከ7 ያላነሱ የሙዚቃ ሥራዎች በተለያዩ ስቱዲዮች ውስጥ እንደሚገኙ፤ እንዲሁም የቤተሰብ አባላትና ጓደኞቹ ከሚመለከታቸው ጋር ተወያየተው በአልበም መልክ ለአድናቂዎቹ ለማቅረብ ሃሳብ እንዳላቸውም ቢቢሲ መረዳት ችሏል። ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን እና ሃጫሉ ሃጫሉ ከገጣሚ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ጋር የቅርብ የሥጋ ዝምድና እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ተናግሯል። "ኦሮሞነትን እና ኢትዮጵያዊነትን አጣጥሞ መሄድ እንደሚቻል ከሎሬት ጸጋዬ ተምሬያለሁ" በማለት ሃጫሉ በተደጋጋሚ ሲናገርም ተደምጧል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን የባህል ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሳሙኤል ለይኩን ሃጫሉ እና ሎሬት ጸጋዬ "ለሞት ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው" ይላሉ። በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን አስተሳሰብ ላይ መሠረት ያደረጉ የሃጫሉ ሥራዎች መኖራቸውንም የማዕከሉ ዳይሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር ሳሙኤል ይናገራሉ። ለማሳያም የሎሬት ጸጋዬን 'የት አባቱ ሞትም ይሙት' የሚለውን ግጥም ያስታውሳሉ። እባካችሁ ዘመዶቼ ስሞት ሞትም አብሮኝ ይሙት በሳቅ በደስታ ግደሉት በሃሴት በእልልታ ወግሩት ካጥንቴ በታች ቅበሩት እባካችሁ ዘመዶቼ ለሞት የልብ ልብ አትስጡት ይላል የሎሬቱ ግጥም። ሃጫሉም በሙዚቃ ሥራዎቹ 'ከእኔ በኋላ ትውልድ አለ'፣ 'የሞት ፍርሃት አምቦ ከርቸሌ ተቀብሯል' የሚሉ ይዘት ያላቸው የሙዚቃ ሥራዎች እንዳሉት ያመለክታሉ። ሃጫሉ በፖለቲካ አቋሙ እና በሙዚቃ ሥራዎቹ ምክንያት፣ ከተለያዩ አካላት ማስፈራሪያዎች እና የግድያ ዛቻዎች ይደርሱበት እንደነበረ በተደጋጋሚ ተናግሯል። በዚህም ከአገር እንዲወጣ በተለይ ወላጅ እናቱ በተደጋጋሚ ሲጠይቁት፤ "ምነው የእኔን ሞት ምን የተለየ ያደርገዋል? ቆሜ እቀራለሁ እንዴ?" እያለ ይመልስላቸው እንደነበረ ወላጅ እናቱ ይናገራሉ። "ውለታሽ በዛብኝ" ሃጫሉ ትዳር የመሰረተው እና ሦስት ልጆችን የወለደው የልጅነት ፍቅረኛውን አግብቶ ነበር። ሃጫሉ ለውድ ባለቤቱ ፋንቱ ደምሴ፤ "ውለታሽ በዛብኝ" ሲልም ተቀኝቶላታል። ሃጫሉ እና ፋንቱ ፍቅር የጀመሩት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳሉ ነበር። ብዙም ሳይቆይ ሃጫሉ ለእስር ተዳረገ። ፋንቱ ለእስር የተዳረገ እጮኛዋን ከቤተሰብ ተደብቃ፣ ስንቅ በመቋጠር በየዕለቱ ትጎበኘው እንደነበረ የሃጫሉ ጓደኞች ይናገራሉ። ሃጫሉም በሙዚቃው "ችግር እና መከራን አብረሽኝ ላየሽው . . . ውለታሽን ለመመለስ አቅም የለኝም። ህይወቴ አልፎ ከመድረ ገጽ ብጠፋም መቼም አልረሳሽም" ሲል ለፋንቱ ተቀኝቷል። ሃጫሉ በሚያደርጋቸው ቃለ መጠይቆቹ ሁሉ ስለ ሚስቱ ተናግሮ አይጠግብም፤ "በእርሷ ሁሉም ይሳካልኛል። በጣም ነው የምወዳት" ሲል ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። ሃጫሉ የቤተሰብ ዐይን ነበር ሃጫሉ ለብዙሃኑ ድምጻዊ ነበር። ለአንዳንዶች የነጻነት ታጋይ ለቤተሰቡ ግን "ዐይን" ነበር። አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ልጃቸውን ሲያስታውሱ "ልጄ ጀግና ነው። ለእውነት ይሞታል" ይላሉ። "ሃጫሉ ከልጅነቱ ጀምሮ ጀግና እና ደፋር ነበረ። ውሸት አይወድም። እውነት ነው የሚወደው፤ የሚሞተውም ለእውነት ነው" የሚሉት የሃጫሉ ወላጅ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ፤ ሃጫሉ ለሞት የተዳረገው ለወገኑ በመቆርቆሩ እና "ያገባኛል" በማለቱ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሃጫሉ እናት ወ/ሮ ጉደቱ ደግሞ "ልጄ ገና ከልጅነቱ አስተዋይ ነበር" ይላሉ። "ልጄ በእኔ ነበር የሚምለው" የሚሉት ወ/ሮ ጉደቱ ለሃጫሉ ልዩ ፍቅር እንዳላቸው ይናገራሉ። የሃጫሉ ታላቅ ወንድም የሆነው ሃብታሙ ሁንዴሳ በበኩሉ፤ ሃጫሉ ለሰው ፍቅር ያለው እና በሌሎች ዘንድ ተወዳጅ እንደበረ በማስታወስ፤ "ሃጫሉ ለቤተሰቡ ዐይን ነበር" በማለት ይናገራል። "ልጄ የሞተው ለእውነት ነው" የሃጫሉ የመገደል ዜና ሰኔ 22 ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጥይት ተመትቶ መገደሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ከእኩለ ለሊት በኋላ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ሰኔ 25/2012 ዓ.ም. የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት በአምቦ ከተማ በሚገኘው የገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተፈጽሟል። የሃጫሉ ግድያ በቤተሰቦቹና በአድናቂዎቹ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ድንጋጤን ፈጥሯል። አስካሁንም ይኽው ስሜት ከአገሪቱ አየር ላይ ቀለል ሳይል ዓመቱ ሊጠናቀቅ ነው። የሃጫሉ መገደልን ተከትሎ በአገሪቱ የተከሰተው አለመረጋጋት የበርካቶችን ህይወት ከመቅጠፉ በተጨማሪ የአካል ጉዳትንና የንብረት ውድመትን አስከትሏል። ግድያው በአገሪቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ላይም በዓመቱ ከተከሰቱት ሁሉ ትልቅ ተጽእኖ የነበረው ክስተት ሆኖ አልፏል።
44639407
https://www.bbc.com/amharic/44639407
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ሰልፉን ዘግቡ ብሎ ማስገደድ ይችላል?
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የተደረገውን የድጋፍ ሰልፍ ተከትሎ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለኢኤንኤን እንዲሁም ለትግራይ ክልል ቴሌቭዥን ጣቢያዎች ከሰልፉ ሽፋን ጋር በተያያዘ ደብዳቤ መፃፉ ላለፉት ሁለት ቀናት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።
አንዳንዶች እንደገመቱት ባለሥልጣኑ ለተቋማቱ ደብዳቤ የፃፈው "ለምን ቀጥታ አላስተላለፋችሁም?" በሚል ሳይሆን በጊዜው ስለ ሰልፉ ምንም ባለማለታቸው እንደሆነ የባለሥልጣኑ ሕዝብ ግንኙነት አቶ ፍቃዱ ውበቴ ለቢቢሲ ገልፀዋል፤ "ይህን ለማድረግም ተቋሙ ሥልጣን አለው" ይላሉ። ባለሥልጣኑ ለሕዝብ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅም አስተዋፅኦ የሚያደርጉ መገናኛ ብዙኃን እንዲበራከቱ የሚሠራ መሆኑን በማስታወስ የመገናኛ ብዙኃንም በሃገሪቱ ውስጥ የሚከናወኑ ማናቸውም ማኅበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እየተከታተሉ ለሕዝቡ የማስተላለፍ ግዴታ እንዳለባቸው ባለሙያው ይናገራሉ። ለመገናኛ ብዙኃኑ ፍቃድ ሲሰጥም እነዚህ ነገሮች ከግምት ገብተው እንደሆነም ያመለክታሉ።ከዚህ በመነሳት እንዲሁም ጉዳዩ ካለው ሕዝባዊ ጠቀሜታ አንፃር ተቋማቸው ለቴሌቭዥን ጣቢያዎቹ ደብዳቤ እንደፃፈና ይህን ለማድረግም ተቋሙ ሥልጣን እንዳለው ገልፀዋል። የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አብዱ አሊ ሂጅራ ግን ባለሥልጣኑ ለሚዲያዎቹ ለምን የድጋፍ ሰልፉን አላስተላለፋችሁም ብሎ ማብራሪያ የመጠየቅ ሥልጣን እንደሌለው ያስረዳሉ። እሳቸው እንደሚሉት ይልቁንም የድጋፍ ሰልፉ ሰው የአገር ጉዳይ ነው ብሎ የሚሰማውና መገናኛ ብዙኃንም ፈጥነው ሊዘግቡ የሚረባረቡበት ዓይነት ነው። "ባለማድረጋቸው ነውር ነው ሊባል ይችል ይሆናል።ነገር ግን ይህ የሕግ ግዴታ ያለበት ነገር አይደለም" ይላሉ። የትግራይ ቴሌቭዥን ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አባዲ በሕግ ባለሞያው አቶ አብዱ ሃሳብ ይስማማሉ። "የሚተላለፉት ፕሮግራሞችን በሚመለከት ሕገ መንግሥቱን የሚጻረሩ፣ ሕዝብ ለሕዝብ የሚያጋጩና ሃይማኖት፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የሚጣረሱ ዝግጅቶች ከተላለፉ ባለሥልጣኑ የመጠየቅ ኃላፊነት አለው። ዝግጅቶች ከመተላለፋቸዉ በፊት ግን የትኛውን ፕሮግራም ነው የምታስተላልፈው፣ የትኛውን ነው ያላስተላለፍከው ብሎ ለመጠየቅ የሚፈቅድለት አዋጅ የለም" በማለት ለቢቢሲ ገልፀዋል። በተለይም ባለሥልጣኑ እንደ ኢኤንኤን ላለ የግል ሚዲያ በዚህ መልኩ ደብዳቤ መፃፍ አይችልም ሲሉ የሚያስረግጡት አቶ አብዱ ምናልባት ትግራይ ክልል ቴሌቭዥን የሕዝብ ነው ከሚል መነሻ ደብዳቤው ተፃፈ ቢባል እንኳ ይህም ራሱ አከራካሪ ነው ይላሉ። የትግራይ ክልል ቴሌቭዥን እንደ ሕዝብ መገናኛ ብዙኃን ከሕዝብ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ግዴታ አለበት ቢባል እንኳ ይህ የሕዝብ አገልግሎት ነው አይደለም የሚል መከራከሪያ ሊኖር እንደሚችል አቶ አብዱ ያስረዳሉ። "በሌላ በኩል ደግሞ ብሔራዊ ቴሌቭዥኑ ሰልፉን በቀጥታ ስላስተላለፈው የትግራይ ክልል ቴሌቭዥን ባለማስተላለፉ ምን አጎደለ?" የሚል ነገርም ጥያቄ እንደሚነሳም ይጠቁማሉ። ብሮድካስት ባለሥልጣን ለዓመታት ይህን አስተላልፋችኋል፤ ያን አላስተላለፋችሁም በማለት ባልተገባ መልኩ መገናኛ ብዙሃንን ሲጠይቅ መቆየቱን ያስታውሳሉ። በመጨረሻም አቶ አብዱ "የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ኢትዮጵያን የሚመለከት ነገር ሳይዘግብ ሲቀር መቼ ነው የጠሩት።ኢትዮጵያ ቴሌቭዥንና ኢትዮጵያ ሬድዮ ለዓመታት ሲቀልዱ ብሮድካስት ባለሥልጣን የት ነበር?" በማለት ይጠይቃሉ።
news-48571966
https://www.bbc.com/amharic/news-48571966
በዓመታት ውስጥ ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ ያሳየው የኢትዮጵያ በጀት
በትናንትናው ዕለት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 71ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2012 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ ሥራዎችና አገልግሎቶች የፌደራል መንግሥት በጀት ረቂቅ ላይ ተወያይቶ፤ 386 ቢሊዮን 954 ሚሊዮን 965 ሺህ 289 ብር እንዲሆን ውሳኔ በማሳለፍ እንዲፀድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቶታል።
ከዚህም ውስጥ ለመደበኛ ወጪዎች 109 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪዎች 130 ቢሊዮን፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ 140 ቢሊዮን እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ ድጋፍ መመደደቡን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ይህ ለቀጣይ ዓመት የተያዘው ሃገራዊ በጀት ላለንበት 2011 ዓ.ም ከተያዘው ጋር ሲነጻጸር በ11.5 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፤ ከባለፈው 2010 ዓ.ም ጋር ደግሞ በ20.6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። •‹‹እነ ቴሌን ለግል ባለሀብት?›› ታሪካዊ ስህተት ወይንስ መልካም አጋጣሚ ? •ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ? ይህም በመጠናቀቅ ላይ ባለው ከ2011 ዓ.ም በጀት ጋር ሲወዳደር ከአርባ ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ አሳይቷል። በዚህ በጀት ዓመት 346 ቢሊዮን 915 ሚሊዮን 451 ሺ 948 ተመድቦ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው። ለመደበኛ ወጪ 91 ቢሊዮን 67 ሚሊዮን 160 ሺ 588 ብር እንዲሁም ለካፒታል ወጪ 113 ቢሊዮን 635 ሚሊዮን 559 ሺ 980 ተመድቦ ነበር። ይህ በጀት በ2010 ዓ.ም ከፀደቀው አንፃር የ3.6 በመቶ ጭማሪ እንደነበረውም ተገልጿል። በ2010 የነበረው በጀት 320.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን፤ ከ60 በመቶ የሚበልጠው ለትምህርት፣ ለግብርናና ለመሰረተ ልማትና ለጤና ማስፋፊያ እንዲሆን ተብሎ የተበጀተ ገንዘብ ነበር። •የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? ከ300 ቢሊዮን ብር በታች የነበረው የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት በ2009 ዓ.ም ላይ 274.3 ቢሊዮን በጀት ተመድቦ ነበር። የፌደራል የመንግሥት በጀት በአራት ዓመታት ውስጥም ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ አሳይቷል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀጣይ ዓመት የሃገሪቱ በጀትን በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ ለሆነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቅ ይኖርበታል። ከዚህ በፊት ከነበረው ልምድ በመነሳት የቀረበው በጀት ያለችግር እንደሚጸድቅ ሲሆን ምክር ቤቱም የዓመቱን የሥራ ጊዜውን ከማጠናቀቁ በፊት የጨረሻው ውሳኔ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
news-53988785
https://www.bbc.com/amharic/news-53988785
ኮሪያ ፡ “የአባቴን አፅም በሻንጣ ይዤ እትብቱ ለተቀበረበት ስፍራ አበቃሁት"
የሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት የተጠናቀቀው በጎርጎሳውያኑ በ1953 ነበር። ጦርነቱ ቢጠናቀቅም 50 ሺህ የሚሆኑ የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች ከቤታቸው እንደወጡ ቀርተዋል።
በሰሜን ኮሪያም በጦር እስረኝነት ህይወታቸውን ለመግፋት ተገደዋል። በርካታዎቹ በአስገዳጅ ግዞት ጉልበታቸው ተበዝብዟል፤ የተገደሉትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። በአሁኑ ወቅትም የአነዚህ ወታደሮች ልጆች እንደወጡ የቀሩ ወላጆቻቸው እውቅና እንዲሰጣቸው እየጠየቁ እንደሆነ በኮሪያ የቢቢሲ ዘጋቢ ሰቢን ኪም ፅፏል። ምንም ጭንቅላቷን ብታስጨንቀው፣ ብትለፋም ሊ አባቷና ወንድሟ ላይ ሦስት ጥይት ከተተኮሰባቸው በኋላ ስለነበረው ነገር ምንም አታስታውስም። ወቅቱ ከሦስት አሰርት ዓመታት በፊት ነበር፤ እድሜዋም በሰላሳዎቹ ውስጥ ነበር የሚገኘው። ወንድሟና አባቷ ከመገደላቸው በፊት ስለነበረው ግን ትናንት የነበረ ያህል ታስታውሳለች። የፀጥታ ኃይሎች እየጎተቱ በሰሜን ኮሪያ ገጠራማ ቦታ ወደሚገኝ ስታዲየም ወሰዷት። ከእንጨት ድልድይ ስር በሚገኝ ስፍራም በማታውቀው ምክንያት እንድትቀመጥ አስገደዷት። ሕዝቡም ተሰበሰ፤ አንድ የጭነት መኪና ቆመ። ሁለት ሰዎችም ከጭነት መኪናው እንዲወርዱ ተደረጉ። አባቷና ወንድሟ ነበሩ። "ከቆመ እንጨት ጋር አብረው አሰሯቸው። አገራቸውን የከዱ ባንዳዎች፣ ሰላዮች ፀረ-ሕዝብ እያሉ ይሰድቧቸው ነበር" በማለት የምትናገረው ሊ፤ ከዚያ በኋላ ስለሆነው ነገር ብዙ አታስታውስም "እየጮሁኩ የነበረ ይመስለኛል።" "መንጋጋዬ ተላቀቀ፤ ጎረቤቴም ወደቤቴ ይዞኝ ሄደ።" ትላለች የተረሱት እስረኞች የሊ አባት የሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ በሰሜን ኮሪያ ከቀሩት አምሳ ሺህ የጦር እስረኞች መካከል አንዱ ነበሩ። ከእነዚህም መካከል በግዳጅ የግንባታ ሥራዎች ላይና በማዕድን ቁፋሮ የተሰማሩ እንዲሁም የሰሜን ኮሪያን ጦር እንዲቀላቀሉም ከፍቃዳቸው ውጭ የተወሰነባቸው ነበሩ። የጦርነቱን ማብቂያ ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት የጦር እስረኞችን እንዲቀያየሩ ያለመ ከመሆኑ አንፃር፤ ደቡብ ኮሪያውያንም የጦር እስረኞች ወደ አገራቸው እንሄዳለን የሚል ተስፋን ሰንቀው ነበር። ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊትም የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሲንግማን ሪ በአገራቸው በቁጥጥር ስር የነበሩ 25 ሺህ የሚጠጉ ሰሜን ኮሪያውያን የጦር እስረኞችን ወደ አገራቸው ላኩ። በዚህም የተኩስ አቁሙንም በማወጅ በጦርነቱ መቀጠል እንደማይፈልጉ አሳዩ። ፕሬዚዳንቱ ዋነኛ አላማቸውም የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ሁለቱን ኮሪያዎች በደቡብ ኮሪያ ስር በማድረግ አንድ አገር ያደርጋቸዋል የሚልም ተስፋ ነበራቸው። ሆኖም እሳቸው እንዳሰቡት ሳይሆን ደቡብ ኮሪያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጦር እስረኞችን መልቀቋ በሰሜን ኮሪያ የሚገኙ የጦር እስረኞችን ሁኔታ አወሳሰበው። ሰሜን ኮሪያ በምላሹ የለቀቀቻቸው በጣም ጥቂት የሚባሉ የጦር እስረኞችን ነበር። ደቡብ ኮሪያም የጦር እስረኞቹን እርግፍ አድርጋ ተወቻቸው። በዓመታት ውስጥ ሦስት የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንቶች ከሰሜን ኮሪያ መሪዎች ጋር ቢገናኙም የጦር እስረኞቹ ሁኔታ እንደ አጀንዳ ተነስቶ አያውቅም። የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሲንግማን ሪ የሊ ቤተሰቦች በሰሜን ኮሪያውያን ዘንድ እንደ ባንዳ ነበር የሚታዩት። የሊ አባት በደቡባ ኮሪያ የተወለዱ ሲሆን በኮሪያ ጦርነትም ከተባበሩት መንግሥታት ጥምር ኃይል ጎን በመቆምም ከሰሜን ኮሪያ በተቃራኒ ተሰልፈው ተዋግተዋል። ይህም ሁኔታ በሰሜን ኮሪያ ዘንድ ጥቁር ነጥብ እንዲጣል አደረገባቸው። የቤተሰቡ በአቅም ዝቅተኛ መሆን በኑሯቸው ከፍተኛ ልፋትን እንዲጋፈጡ ሕይወታቸው መራራ እንዲሆን አድርጎታል። የሊ አባትም ሆነ ወንድም በከሰል ማውጫ ስፍራ ይሰሩ የነበረ ሲሆን፤ ቦታው ፈታኝ በመሆኑም በርካታ አደጋዎችም ያጋጥማል። የሊ አባት ሁለቱ አገራት አንድ ሲሆኑ ወደ ቤታቸው የመሄድ ህልምንም ሰንቀው ነበር። ከሥራ በኋላም ሁልጊዜም ልጆቻቸውን ሰብስበው የልጅነት ሕይወታቸውን ይነግሯቸው ነበር። በደስታ የተሞላ፣ ለምለሟና ወተትና ማር ይፈስባታል ስለሚሏቸው ደቡብ ኮሪያ ይተርኩላቸው ነበር። ከቻሉም ወደ ደቡብ ኮሪያ እንዲያመልጡም ይመክራቸው ነበር "ሜዳልያ ይጠብቀኛል እናንተም የጀግና ልጅ ተብላችሁ፣ ትከብራላችሁ" ይለን ነበር ትላለች። እናም የሊ ወንድም አንድ ቀን እየጠጣ እያለ ለጓደኞቹ ይህንን እቅድና አባቱ የሚያወራውን ነገር አሾለከ። አንደኛ ጓደኛው ይህን ወሬ ለሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት አስታወቀ። በወራትም ውስጥ የሊ አባትና ወንድሞቿ ተገደሉ። በጎርጎሳውያኑ 2004 ሊ አምልጣ ወደ ደቡብ ኮሪያ ለመግባት ቻለች። አባቷ በደቡብ ኮሪያ እንደ ጀግና እታያለሁ ብሎ እንዳሰቡት ሳይሆን ማንም ያስታወሳቸውም ሆነ ከቁብ የቆጠራቸው ሰው አልነበረም። የጦር እስረኞቹን ለመመለስ ጥረትም አልተደረገም። ወታደሮቹ በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ኑሯቸው ስቃይ፣ ሲኦልም ነው ማለት ይቻላል። የአገሪቱ ጠላት ተደርገው ይታዩ ነበር። በሰሜን ኮሪያ ማኅበረሰብ ውስጥ ባለው የኑሪ መደብ ደረጃ ውስጥ "ሶንግበን" በሚል ስያሜ ዝቅተኛና የመጨረሻ ስፍራም ነው የተሰጣቸው። ይህ ሁኔታ ለጦር እስረኞቹ ብቻ ሳይሆን መከራውና ጦሱ ለልጆቻቸውም ተረፈ። የከፍተኛ ትምህርት ደረጃን መከታተልም አይችሉም ሥራም በፈለጉበት ዘርፍ ተሰማርተውም የመስራት ዕድል አይሰጣቸውም። ቾይ በትምህርቷ ጎበዝና ኮከብ የምትባልም ተማሪ ነበረች። ሆኖም በአባቷ ምክንያት ዩኒቨርስቲ የመማር ህልሟ ተጨናገፈ። በአንድ ወቅትም አባቷን ከፍ ዝቅ አድርጋ ስለገጠማት ነገር በቁጣ "አድሃሪ ቆሻሻ ነህ። ለምን ወደ አገርህ አትመለስም?" በማለት ዘለፈቻቸው። አባቷም ጮክ ብለው አልተናገሯትም፤ በምላሹ አገራቸው እነሱን ለማስመለስ ደካማ ናት አሉ። ከስምንት ዓመት በፊት ቾይ ቤተሰቦቿን ትታ ወደ ደቡብ ኮሪያ ሸሸች። "አባቴ ወደ ደቡብ ኮሪያ መምጣት ይፈልግ ነበር። በሕይወቴ የምወደውና የማደንቀው ሰው መምጣት ቢፈልግም መምጣት አልቻለም። ለዚያም ነው ልጆቼንና ባለቤቴን ትቼ የመጣሁት" ትላለች። የቾይ አባት ከጥቂት ዓመታት በኋላ ቢሞቱም በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ይፋዊ መረጃ እንደሚያሳየው በጦርነቱ ወቅት እንደሞቱ እንጂ በጦር እስረኝነት በግዞተኝነት እንደሞቱ አይደለም የሚያሳየው። ሰን የአባቷን አፅም በሻንጣ ወደ ደቡብ ኮሪያ ወስዳ ልትቀብር ችላለች የአባቴን አፅም ይዤ ተመለስኩ ሰን ምዮንግ ህዋ አባት ሲሞቱ የመጨረሻ ኑዛዜያቸው "ወደ ደቡብ ኮሪያ ከሄድሽ አፅሜን ይዘሽ ሄደሽ የተወለድኩበት ስፍራ ቅበሪኝ" ብለው ተናዘዙ። የሰንም አባት በምርኮ ሰሜን ኮሪያ የቀሩ የደቡብ ኮሪያ ወታደር ነበሩ። የጦር ምርኮኛም ሆነው በከሰል ማውጫ ስፍራና ደን መቁረጫ ስፍራም ለአስርት ዓመታት አገልግለዋል። በዓመታት ውስጥ ወደ ቤት እንዲሄዱ የተፈቀደላቸው ለአስር ቀናት ያህል ነበር። መጨረሻም በካንሰር ሞቱ። ለልጃቸውም "ወላጆቼን በአካል ሳላይ መሞት እንዴት መራር እንደሆነ። እትብቴ የተቀበረበት ስፍራ ወስደሽ ቅበሪኝ" አሏት። ሰንም ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ሸሽታ ወደ ደቡብ ኮሪያ ገባች። ሆኖም የአባቷን አፅም ወደ ደቡብ ኮሪያ ለመውሰድ ስምንት ዓመት ፈጅቶባታል። እህቶቿና ወንድሞቿን የአባቷን አፅም ቆፍረው በማውጣት ደብቀው ቻይና ወደሚገኝ ደላላ እንዲልኩ ጠየቀቻቸው። ሦስት ሻንጣዎችም ተዘጋጁ። ሁለት ጓደኞቿና እራሷም ጭምር የአባቷን አፅም ይዘው ሄዱ። ሰን ለጦር ጀግናው አባቷ እውቅና ይሰጠው ስትልም ለአመት ያህልም ተቃውሞ አድርጋለች ሰን ለጦር ጀግናው አባቷ እውቅና ይሰጠው ስትልም ለዓመት ያህልም ተቃውሞ አድርጋለች። ከአምስት ዓመታት በፊትም የአባቷን አፅም እንደ መጨረሻ ኑዛዜቻቸው በብሔራዊ መካነ መቃብር ተካሄደ። "የልጅ ግዴታዬን፣ ኃላፊነቴን እንደተወጣሁ ተሰማኝ፤ ሆኖም አባቴ የመጨረሻ እስትንፋሱ የወጣችው ሰሜን ኮሪያ መሆኑ ልቤን ሰበረው" ትላለች። ሰን የአባቷ አፅም ደቡብ ኮሪያ እንዲቀበር ቤተሰቦቿ ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈሉ የተረዳችው በኋላ ነው። በሰሜን ኮሪያ የሚገኙት እህቶቿና ወንድሞቿ እስር ቤት ወረዱ። ሰን በአሁኑ ወቅት የኮሪያ ጦር ምርኮኞች ቤተሰብ ማኅበርን እየመራች ትገኛለች። ማኅበሩ በሰሜን ኮሪያ ምርኮኛ ሆነው የቀሩ ደቡብ ኮሪያውያን ወታደር ቤተሰቦች የተሻለ ሕይወትን እንዲመሩ የሚሟገት ነው። ሰን አባቷ የቀድሞ ወታደር መሆናቸውን ለማረጋገጥ የዲኤንኤ ምርመራ ማድረግ ግዴታዋ ነበር። በዚህም መሰረት ደቡብ ኮሪያ ለቀድሞው ወታደር ያልከፈለቻቸውን ደመወዝም መቀበል ችላለች። ምንም እንኳን በርካታ የጦር ምርኮኛ ልጆች አምልጠው ደቡብ ኮሪያ ቢገቡም ዕውቅና አልተሰጣቸውም። ሰሜን ኮሪያ በምርኮ የቀሩ ወታደሮች ሁኔታም ሞተዋል ወይም ጠፍተዋል ተብሎ ይታሰባል። የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሙን ጄ የቀድሞ ወታደሮችን የሞቱበትን 70ኛው ክብረ በዓል ሲዘክሩ በጣም ጥቂት የሚባሉ የቀድሞ ደቡብ ኮሪያ ወታደር ልጆች ናቸው ከሰሜን ኮሪያ አምልጠው ወደ ደቡብ ኮሪያ መግባት የቻሉት። እነዚህ ብቻ ናቸው ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ የተከፈላቸው። ሰሜን ኮሪያ የቀሩት ወታደሮች ምንም አይነት ካሳም አልተከፈላቸውም። በዚህም ዓመት ሰንና ጠበቆቿ፤ ደቡብ ኮሪያ የጦር እስረኞቹንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን ዘንግታቸዋለች፤ ይህም ኢፍትሃዊ ነው በማለት ስለጉዳዩ በሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት ክስ መስርተዋል። "ከጦር እስረኞች መወለዳችን ኑሯችንን ጨለማ አድርጎት ነበር። ደቡብ ኮሪያም አምልጠን ከመጣን በኋላ የተቀበሉን መንገድ በጣም አሳዛኝ ነው" ብላለች።
news-49027549
https://www.bbc.com/amharic/news-49027549
ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ?
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከጅማሮው በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩት የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ አንድ ዓመት አስቆጠሩ።
ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው በድንገት አልፎ ከተገኘ በኋላ፤ በወቅቱ የፌደራል ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ኢንጅነሩ ራሳቸውን እንዳጠፉ በምርመራው እንደደረሰበት ማሳወቁ ይታወሳል። መኪናቸው ውስጥ የተገኘውም ሽጉጥ የኢንጂነሩ እንደነበር በምርመራው አረጋግጫለሁ ብሏል። •ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? •ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ የግድቡ ምልክት ተደርገው የሚወሰዱት ኢንጅነር ስመኘው ሞት፣ በርካቶችን ያስደነገጠ እና ኃገሪቱ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የፈሰሰበት የህዳሴ ግድብ ከየት ይደርሳል? የሚል ስጋትን የፈጠረም ነበር። በኢንጅነር ስመኘው ቦታ የተተኩት የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፤ ''አንድ ሰው በግሉ የሚቻለውን ያክል ነው አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችለው እንጂ የጀመረውን ሁሉ ይጨርሳል ማለት አይደለም'' በማለት የቀድሞውን የፕሮጀክቱን መሪ ያስታውሳሉ። አክለውም ''ህዳሴ ግድብ የህዝብ ነው። እኔም አሻራዬን ትቼ ላልፍ እችላለሁ የኢንጅነር ስመኘውን አስተዋጽኦንም እንዲሁ ነው የምመለከተው'' ይላሉ። የቀድሞው የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሪ ከሞቱ በኋላ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የህዳሴ ግድብ አፈጻጸም እንዴት ነው? ምን ተለወጠ? ምን ችግር አጋጠመው? ከኢንጅነር ክፍሌ ጋር ቆይታ አድርገናል። • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፕሮጀክቱ ለምን ዘገየ? ኢንጅነር ክፍሌ ፕሮጀክቱ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ባይሄድም በአሁኑም ወቅት ህዝብ እና መንግሥት ለአባይ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዳላቋረጡ ይናገራሉ። በዋናነት ከፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ሁለት ፈተናዎች አሉ የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ የመጀመሪያው ከስነ-ምድር (Geology) ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገልጻሉ። የአባይ ወንዝ የሚሄድበት መሬት ሥሩ ጠንካራ ነው ተብሎ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው፤ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ ግን መሬቱ እንደተጠበቀው ሳይሆን እንደቀረና መሬቱን ቆፍሮ በኮንክሪት የመሙላቱ ሥራ ብዙ ጊዜ መውሰዱን ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ለህዳሴ ግድብ መዘግየት እንደ ሁለተኛ ምክንያትነት የሚጠቅሱት ደግሞ ከብረታብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር የተያያዘ ነው። እንደ ኢንጅነር ክፍሌ ከሆነ መንግሥት የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ግንባታው ሲገባ በተቻለ መጠን በግድቡ ላይ ሃገር በቀል ተቋማት አስተዋጽኦዋቸውን እንዲያበረክቱ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ነበር። በዚሁ መንፈስ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሥራውን እንዲያከናውን በንዑስ ተቋራጭነት እንዲሰራ መወሰኑን ያስረዳሉ። ተቋሙ የኤክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን የመገንባት አቅምም ሆነ ልምድ ስለሌለው የግንባታ ስራውን ወደፊት ማስኬድ አልቻለም ብለዋል። "ፕሮጀክቱ ላይ ብዙ ቢሊየን ብር ቢፈስም፤ መልክ አልያዘም" ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የሲቪል ሥራው ወደ 84 በመቶ በላይ ቢጠናቀቅም፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው 28 በመቶ የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ወደ ስልሳ ስምንት በመቶ መድረሱን ተናግረዋል። መጋቢት 10፣ 2011ዓ.ም በነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክርቤት ጽሕፈት ቤት፣ ከሚዲያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በነበረው የውይይት መድረክ የግድቡ የግንባታ ቡድን ተወካይ አቶ ኤርሚያስ ውብሸት የግድቡ የሲቪል ሥራ 85 በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ 25በመቶ እና የብረታ ብረት ስራ 13 መድረሱንና በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ 66.24 በመቶ ደርሷል ብለዋል። መንግሥት ለሜቴክ ተሰጥቶ የነበረውን ውል ካቋረጠ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እና ልምድ ላላቸው ለአዳዲስ ተቋራጮች በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ ተግባርም ተከናውኗል ። በግንባታ ስራው ተሰማርተው የሚገኙት ስድስትተቋራጮች እንደሆነ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ከእነዚህም መካከል የፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቻይና ኩባንያዎች ይገኙበታል ይላሉ። በውይይት መድረኩ ላይም እንደተጠቀሰው ከተቋራጮቹም መካከል ሲጂጂሲ፣ ሳይኖ ሃይድሮ፣ ቮይት፣ ጂኦ ሃይድሮ ፍራንስና ኤክሲዲ ይገኙበታል በማለት በስም ይዘረዝራሉ። •ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? እንደ ተርባይን ያሉ ከውሃ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግንባታዎች ከፍተኛ ልምድ የሚጠይቁ ሥራዎች መሆናቸውን ኢንጅነር ክፍሌ ገልፀው አዳዲሶቹ ተቋራጮች የግንባታ ሥራውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየሠሩ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የሳሊኒ ቅሬታ እና የፕሮጀክቱ ክንውን የሲቪል ሥራውን ለማከናወን ኮንትራት ወስዶ ሲሰራ የቆየው የጣሊያኑ ሳሊኒ ከግንባታ ክፍያ መዘግየት ጋር ተያይዞ ቅሬታዎችን ሲያሰማ ነበር። ኢንጅነር ክፍሌ እንደሚሉት ሳሊኒ ያነሳቸው ቅሬታዎች አግባብነት ከተጠና በኋላ መንግሥት እና ሳሊኒ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል ይላሉ። "ሳሊኒ ሲያነሳው የነበረው ቅሬታ 'ፕሮጀክቱ የዘገየው እኔ በፈጠርኩት ችግር አይደለም። ሜቴክ የሚጠበቅበትን የተርባይን እና ሌሎች ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ብረቶችን በወቅቱ ማቅረብ ቢችል ኖሮ ሥራውን በሰዓቱ ማጠናቀቅ እችል ነበር። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ለኪሳራ ተጋልጫለሁ' የሚል ነበር" በማለት ኢንጅነር ክፍሌ ያስረዳሉ። ሳሊኒ በዚህ ምክንያት ለደረሰበት ኪሳራ መንግሥት ካሳ እንዲከፍለው ጥያቄ አቅርቦ ነበር። •ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ " ከሳሊኒ ጋር ያለው ጉዳይ አልተፈታም። በመንግሥት የተወሰደው እርምጃ በዚህ የመዘግየት ምክንያት ኪሳራ ደርሶበት አስጊ የሆነ የገንዘብ ደረጃ ላይ በመድረሱ፤ ሳሊኒ ይገባኛል የሚለው ጥያቄ እልባት እስኪያገኝ ድረስ በታሳቢነት 124 ሚሊዮን ብር እንዲከፈለው ተወስኗል። ይህ የተወሰነው ስራውን ከማስቀጠል አንፃር ነው። የሳሊኒ ያቀረበው የኪሳራ ይገባኛል ካሳ ሙሉ በሙሉ መቀበል ማለት አይደለም። እየታየ እንዲሁም እየተጠና ነው። እውነት ይህ ሁሉ ኪሳራ ይደርስበታል ለሚለውም በዝርዝር እየታየ ነው"ይላሉ ኢንጅነር ክፍሌ። ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ሳሊኒ ብቻ ሳይሆን ጉዳቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጭምር ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "እውነት ለመናገር ህዝቡ በግንባታው ሞራሉ ተነክቷል። ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ በማስመልከት ለህዝብ የሚሰጠው መረጃ የተሳሳተ ነበር። እውነቱ ተደብቆ ቆይቶ በአንዴ እውነቱ ሲገለጥ ህዝቡ ማዘኑ አልቀረም" ይላሉ። መቼ ይጠናቀቃል? ፕሮጀክቱ በተጀመረበት ወቅት በአራት ዓመት ውስጥ በሁለት ተርባይኖች አማካኝነት ኃይል ማመንጨት ይጀምራል መባሉን እና በሰባት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደነበረ ኢንጅነር ክፍሌ ያስታውሳሉ። ይህን መሰል ግዙፍ ፕሮጀክት በሰባት ዓመታት ውሰጥ መጨረስ ይቻላል ተብሎ መጀመሩ በራሱ ስህተት ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ሜቴክ "የሚጠበቅበትን በወቅቱ ማድረግ ቢችል ኖሮ ቢያንስ በ2009 ላይ ኃይል ማመንጨት መጀመር ይቻል ነበር" ይላሉ። ከሁለት አመታት በኋላ ኃይል የማመንጨት ጅማሮ እቅድ እንዳለ የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ በአራት ዓመታት ውስጥ ደግሞ ግንባታው ሙሉ በሙሉ የማጠናቀቅ እቅድም እንደተያዘ ይናገራሉ። ነገር ግን ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉም አልደበቁም። በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ ሁሉም ተርባይኖች ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ማለት ሳይሆን በመጀመሪያ ግድቡ ውሃ የሚሞላበት ሁኔታ ላይ የታችኛው የተፋሰስ ሃገራትን ማወያየት ዋናው ስራ እንደሆነ ይናገራሉ። "ተርባይኖቹ በሙሉ አቅም ኃይል የሚያመነጩት በግድቡ ውሃ መሙላት ላይ ተሞርኩዞ ነው። የተርባይኖቹ ስራ ግን ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ ታቅዷል" ይላሉ። የፕሮጀክቱ ተጨማሪ ወጪ ሃሳብ ሆኗል? የዚህ ፕሮጀክት ወጪ ከህዝብ ከሚሰበሰበው እና መንግሥት ከሚመድበው በጀት ሲሆን፤ መንግሥት ተጨማሪ በጀት እየመደበ የግንባታ ሥራው እንዲቀጥል እያደረገ መሆኑንም ይናገራሉ። ህዝቡም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በማዋጣት ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቅሰዋል። የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና ከግንባታው መጓተት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ወጪ ፕሮጀክቱን እንደጎዳው የሚናገሩት ኢንጅነር ክፍሌ "ህዝብ እና መንግሥት አሁንም ፕሮጀክቱን ከግብ ማድረስ ያለስለሰ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ" ተናግረዋል።
news-56795577
https://www.bbc.com/amharic/news-56795577
የ15 ዓመት ታዳጊ እያሉ ታስረው በ83 ዓመታቸው የተፈቱት አዛውንት
የ15 ዓመት ታዳጊ እያሉ በፈጸሙት ወንጀል ለ68 ዓመታት ታስረው በመጨረሻ የእድሜ ዘመናቸው የተፈቱት ጀ ሊጎን አሁን 83 ዓመታቸው ነው።
ጆ ሊጎን ለሰባት አስርት ዓመታት ያህል የእድሜያቸውን ከሦሰት አራተኛ በላይ በእስር ቤት ያሳለፉት አዛውን ተለቀው ወደማያውቁት ዓለም ተቀላቅለዋል። በአስር ቤት "ብቻዬን ሆኜ ባላውቅም ብቸኛ ነኝ። ብቻዬን መሆንን እመርጣለሁ።" "ከታሰርኩበት ጊዜ ጀምሮ እስከምለቀቅ ድረስ አንድ ክፍል ውስጥ ነበር የቆየሁት።" በአንድ ክፍል መታሰር "እንደ እኔ ብቸኝነትን ለሚፈልጉ" የተሻለው አማራጭ ነው ይላል ጆ ሊጎን። ታሠረ ታሠረ። በሩ ከተከረቸመበት በኋላ "ውጭ የሚከናወነው ሁሉ አላይም አልሰማም።" ብቸኝነቱን ያስቀሩለት ሬዲዮና ቴሌቪዥኑ ሲፈቀድላቸው ነበር። የእስር ቤት ሕይወት ለጆ ሊጎን የተስማማው ይመስላል። የ68 ዓመቱ እስር አንገቱን ደፍቶ፣ አፉን ዘግቶ እና ከችግሮች እንዲላቀቅ አስተምሮታል። ብቸኛ መሆኑን የተሻለ አማራጭ እንደሆነ ስለሚያምን ዕድሜ ልክ በአንድ ክፍል ተቆልፎበት መቆየቱ አላሳሰበውም። ከእስር ቤትም ውጭም ጓደኛ አልነበረውም። "ያገኘኋቸውን ብዙ ሰዎች… እንደ ጓደኛ እንዳደረኳቸው ነበር የሚቆጥሩት። አሪፍ ነገር ነበረን። ጥሩ ግንንኙነትም ነበረን" ይላል። "ቃሉ ከፍ ያለ ትርጉም ስላለው ጓደኛ የሚለውን ቃል ግን አልጠቀምም። ብዙ ሰዎች [ጓደኛ ካበዛችሁ] ትልቅ ስህተት ልትሠሩ ትችላላችሁ ይላሉ" ሲል ያስረዳል። ሊጎን ብቸኛ የሚባል ዓይነት ሰው ነበር። በአላባማ በበርሚንግሃም ቅድመ አያቶቹ ዘንድ ነው ያደገው። ብዙ ጓደኛ አልነበረውም። በቤተሰቦቹ ዘንድ አስደሳች ጊዜያትን ማሳለፉን ያስታውሳል። ከእነዚህ አስደሳች ጊዜያት መካከል እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን ውስጥ አያቱ ሲሰብኩ መመልከቱ ነው። በኋላም አካባቢውን ቀየረ። ከነርስ እናቱ፣ ከመካኒክ አባቱ፣ ከታናናሽ ወንድም እና እህቱ ጋር ለመኖር ወደ ፊላዴልፊያ አቀና። ያኔ 13 ዓመቱ ነበር። ከትምህርት ጋር አይንና ናጫ ነበረ። ማንበብም ሆነ መፃፍ አይችልም። ስፖርትም አያስደስተውም። ጓደኞቼ የሚላቸውም በባህሪ የሚግባቡት አልነበሩም። "ብዙ አልዝናናም። አንድ ወይም ሁለት ጓደኞች ያሉኝ ዓይነት ሰው ነበርኩ። ብዙ ሰው ወደተሰበሰበበት አልሄድም" ይላል። ሊጎን መቼም የጎርጎሮሳዊያኑን 1953 አንድ ዓርብ ምሽትን አይረሳትም። "ችግር ውስጥ የከተተችው" ነበረች። በዕለቱ አብረውት የነበሩትን በትክክል አያውቃቸውም። በአጋጣሚ ከሚያውቃቸው ሁለት ሰዎች ጋር ሰፈራቸው ውስጥ ዞር ዞር ሲሉ ነበር ከሚጠጡ ሰዎች ጋር ተገናኙ። ተቀላቅለው "ተጨማሪ ወይን ለመግዛት ሰዎችን ጥቂት ገንዘብ መጠየቅ ጀመርን . . . እናም አንዱ ነገር ወደ ሌላው አመራ…" መጨረሻው ያላማረ ምሽት። አለመግባባት ተፈጠረ- ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ስድስቱ ቆሰሉ። እሱም በግጭቱ ተሳታፊ ነበር። ሊጎን ነበር መጀመሪያ ዘብጥያ የተወረወረው። ጆ ሊጎን 68ቱን እስር ዓመታት በስድስት አስር ቤቶች አሳልፈዋል ፖሊስ ጣቢያው ማን አብሮት እንደነበረ እውነቱን መናገር እንደማይችል ለፖሊስ ይናገራል። "ሁለቱ የማውቃቸውን እንኳን ትክክለኛ ስማቸውን አላውቀውም። በቅጽል ስማቸው ነበር የምጠራቸው" ይላል። ሊጎን በሮድመን ጎዳና ከሚገኘው ቤታቸው ርቆ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ነበር የተወሰደው። ለአምስት ቀናትም የሕግ ድጋፍ አላገኘም። ወላጆቹ ሊጠይቁት ሲሞክሩም መከልከላቸው ለረዥም ጊዜ አስቆጥቶት እንደነበር ይናገራል። በዚያው ሳምንት የ15 ዓመቱ ታዳጊ በግድያ ወንጀል ተከሰሰ። እሱ ክሱን አልፈጸምኩም አለ። በኋላም ሁለት ሰዎችን በስለት መውጋቱን ከአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ፒቢኤስ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ገለጸ። ሁለቱም በሕይወት መትረፋቸውንና መጸጸቱንም አስረዳ። "[ፖሊሶቹ] እንድንፈርም ጽሑፎች ሰጡን። ጽሑፉ እኔ በግድያው መሳተፌን ይገልጻል። እኔ ግን ማንንም አልገደልኩም።" ፔንሲልቬንያ በዕድሜ ልክ እስራት ላይ አመክሮ ከሌላቸው ስድስት የአሜሪካ ግዛቶች አንዷ ናት። ሊጎንን ጉዳዩን ሲያምን ዳኛውም በአንደኛ ደረጃ ግድያ ሁለት ክሶች ጥፋተኛ ይሉታል። ታዳጊው ያለአመክሮ ዕድሜ ይገፍታህ ተረደበት። ፍርድ ቤት ሆኖ ግን ውሳኔውን አልሰማም። ቅጣቱ ከጊዜው አንጻር የተለመደ የሚባል ነው። ቅጣቱን በውል ሳያውቀው ወደ እስር ቤት ወረደ። ማንንም የመጠየቅ ዕድልም አላገኘም። "ምን መጠየቅ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም ነበር። ለማመን ከባድ ቢሆንም እውነታው ያ ነበር። ህይወቴን በሙሉ እስር ቤት እንደምሆን አላውቅም ነበር። 'አመክሮ ያለው ዕድሜ ልክ' የሚሉ ቃላትን ሰምቼም አላውቅም" ይላል ሊጎን። "ልጅነቴ ምን ያህል የተበላሸ እንደነበር መናገር እፈልጋለሁ። ማንበብም ሆነ መጻፍ አልችልም። ስሜን እንኳን መፃፍ አልችልም ነበር። ስሜ ጆ መሆኑን አውቅ ነበር። እኔ እስከ ማስታወሰው ድረስ በጆ ነበር የምጠራው።" ከመፍራት ይልቅ ግራ ተጋብቶ ወደ ማረሚያ ቤቱ እንደገባ ሊጎን ይናገራል። በአዕምሮው የሚመላለሰው ነገር ቤተሰቡ ነበር። "ከእነሱ ርቆ በአንድ ክፍል ታጥሮ መቀመጥ። ይህ ነበር የማስበው ጉዳይ" ይላል። ጆ ሊጎን አባቱ ሜካኒክ እናቱ ደግሞ ነርስ ነበሩ ከ68 ዓመታት በላይ በስድስት እስር ቤቶች አሳልፏል። ሁሌም ከማረሚያ ቤቱ ህይወት ጋር ራሱን ያለማምዳል። "ጠዋት 12 ሰዓት በጥሩምባ እንቀሰቀሳለን። አሊያም በድምጽ 'ሁሉም ሰው ለመቆጠር ይነሳ፣ የመቁጠሪያ ሰዓት ነው' እንባላለን። አንድ ሰዓት የምግብ ሰዓት ነው፣ 2 ሰዓት ደግሞ የሥራ ሰዓት።" ሊጎን አልፎ አልፎ በምግብ አብሳይነትና ልብስ ማጠቢያ ክፍል ውስጥ ቢሠራም በአብዛኛው የሠራው በጽዳት ሠራተኝነት ነበር። ከምሳ በኋላ በድጋሚ ወደ ሥራው ይመልሳል። እንደገና ምሽት ላይ በእራት ሰዓት በድጋሚ ጥሪ የተደርጎ የአንድ ቀን ከክፍሉ ውጭ ያለው ውሎው ማብቂያ ይሆናል። የእስር ቤት ሕይወቱ በአብዛኛው ተመሳሳይ ቢሆንም የውጭው ዓለም በአስርተ ዓመታት ውስጥ የማይቀየር ለውጥ እያስመዘገበ ነው። "አደንዛዥ ዕፅ አልተጠቀምኩም፣ አልጠጣም፣ ሰዎች እንዲገደሉ ምክንያት አልሆንኩም፣ ለማምለጥ አልሞከርኩም እንዲሁም ለማንም መጥፎ አልሆንኩም" በማለት ቆይታውን ያስታውሳል። "በተቻለኝ መጠን በትህትና አሳለፍኩኝ። ማረሚያ ቤቱ ያስተማረኝ ስለራስ ማሰብን፣ ሁል ጊዜም ትክክለኛውን ለማድረግ መሞከርን እና ከመጥፎ ድርጊት መራቅን ነው" ብሏል። በዚህ ሁኔታ 53 ዓመታት አለፉ። በኋላ አንድ ጠበቃ ሊያየው እንደሚፈልግ ተነገረው። ግለሰቡ ብራድሌይ ኤስ ብሪጅ ይባላል። የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአውሮፓውያኑ 2005 ታዳጊዎች በግድያ ሊቀጡ አይገባም በሚል ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ፤ ብራድሌይ ኤስ ብሪጅ ያለ አመክሮ ዕድሜ ይፍታህ ስለተፈረደባቸው ታዳጊዎች መመርመር የጀመረ ባለሙያ ነው። ጆ ሊጎን እና ጠበቃው ብሪጅ በወቅቱ ፔንሲልቬንያ በተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩ 525 እስረኞች ነበሯት። እንደ ብሪጅ ከሆነ ቁጥሩ በአሜሪካ ከፍተኛው ነው። ፊላዴልፊያ 325 ሲኖራት ሊጎን ደግሞ ረዥም ዓመት የታሰረው ፍርደኛ ነው። ለዚህም ነው ረዳት ጠበቃው ሊያገኘው ቀጠሮ የያዘው። ከፊላዴልፊያ ተከላካይ ጠበቆች ማኅበር የመጣው ብሪጅ "ስለ ፍርዱ በትክክል አያውቅም ነበር" ሲል ስለ ሊጎን ይገልጻል። "እስካገኘው ድረስ ምንም አያውቅም ነበር። ተስፋ አለመቁረጡ አስደሳች ነገር ነው። ሙሉ በሙሉ ተስፋ ነበረው። ከመጀመሪያው ጀምሮ አንድ ነገር እንደሚፈጠር ይጠብቅ ነበር" ብሏል። "እንዴት እንደማስረዳው ግን ግልፅ አልነበረም። ተስፋ ነበረው። ሊስተካከል ስለሚችል ቁጭ ብሎ ለመጠበቅ ፍጹም ታጋሽ ነበር" ይላል። ውይይቱ ለሊጎን ዓይን ከፋች ነበር። ብሪጅ ሁኔታውን የሚቃወምበትን የይግባኝ ቅጅ ሲያሳየው ነበር ሊጎን የእስሩን ዝርዝር መረጃ ለመጀመሪያ ያወቀው። "ከተያዝኩበት ጊዜ አንስቶ በደል እየተፈፀመብኝ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ። ለወጣት ጥፋተኞች ያለአመክሮ መታሰር ሕገመንግሥታዊነትን የተፃረረ መሆኑን ተረዳሁ" ይላል። ምንም እንኳን ሊጎን አንድ ቀን ከእስር ቤት መውጣት ስለመቻሉ የተስፋ ጭላንጭል ቢያይም ለ15 ዓመታት ለመረዳት የሚከብዱ ውሳኔዎችን ሲያደርግ ነበር። ጆ ሊጎን ከአስር እንደወጡ የውጪውን ዓለም ፈፍሞ እንደማያውቁት ይናገራሉ "የዕድሜ ልክ መዘዝ" ያለው ነው ባለው ምክንያት የመፈታት ዕድል ገጥሞት ውድቅ አድርጎታል። "የአመክሮ ቦርዱ ሁለት ጊዜ ጎብኝቶኝ ነበር። ከዓመታት በፊት የአመክሮ ምህረትን መቀበል አቋራጭ መንገድ ነበር። "[ነገር ግን] ምህረቱ በቀሪው ህይወቴ በምሠራው ሥራ ላይ የተመረኮዘ ሲሆን የእኔ ጉዳይ ግን የዕድሜ ልክ አመክሮን አይጠይቅም ነበር። የእኔ ጉዳይ ያንን ቢጠይቅ ምንም ችግር አልነበረውም። ለዚያም ነው ያልተቀበልኩት" ሲል ያስረዳል። እአአ በ2016 የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁሉም ወጣት ጥፋተኞች በድጋሚ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ይወስናል። ሊጎን በቀጣዩ ዓመት 35 ዓመታት ተፈረደበት። በእስር ባሳለፈው ጊዜ ምክንያት የአመክሮ ጥያቄ የማቅረብ ዕድል ከፈተለት። ብሪጅ ጥያቄውን እንዲያቀርብ ቢገፋፋውም እምቢታ ሆነ መልሱ። "ከባልደረባዎቼ፣ ከአስተዳደር ሠራተኞች እና ከእስረኞች በጣም መጥፎ ምላሽ ነበር ያገኘሁት… 'ለምን አመክሮ አይጠይቅም? [ሁሉም ይሉ ነበር]" በማለት ሊጎን ያስታውሳል። "እኔም 'የማድረግ የምችለውን ነገር አልቀበልም' እላለሁ። መጥፎ ለመሆን ወይም ክፉ ለመሆን [አላደረግሁትም] አሁንም ቢሆን አመክሮ የምቀበል ከሆነ እየተበደልኩ ነበር።" "ሁሌም እነዚህን ቃላት ብቻ ነበር የምጠቀመው 'ነፃ ወጥተሃል መባልን እፈልጋለሁ'" ይላል። ብሪጅ የ2017ቱን ውሳኔ መቃወም ነበረበት። ጉዳዩን ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤት ወስደው። በ2020 እአአ ዳኛው ብሪጅን ደግፎ ውሳኔውን አስተላለፈ። የካቲት 11 ቀን ሊጎንን ለመውሰድ ብሪጅ ወደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ በሄደ ጊዜ የቀድሞው እስረኛ በአስደናቂ ሁኔታ የተረጋግቶ አገኘው። "'ኦህ አምላኬ ጠንከር ያለ ምላሽ ጠብቄ ነበር። ግን ምንም ስሜት አልነበረውም። አንዳች ድራማ የለም - ምንም" ብሏል። ሊጎን ምናልባትም ለአስርተ ዓመታት ያከናወነውን እያደረገ ነበር - ሃሳቦቹን በራሱ አምቆ መያዝ። ከእስር ከተለቀቀ ከአንድ ወር በኋላ ግን ከፊኒክስ ማረሚያ ቤት የወጣበትን ቀን በሚያስደንቅ ሁኔታ ይገልጻል። "እንደገና እንደመወለድ ነበር። ምክንያቱም ሁሉም ነገር ለእኔ አዲስ ነበር። ሁሉም ነገር [ተለውጧል]። ሁሉም ነገሮች አሁንም ለእኔ አዲስ እንደሆኑ ናቸው።" "ከእነዚህ አዳዲስ መኪኖች መካከል የተወሰኑትን እመለከታለሁ። እነዚህ መኪኖች በፊት ከማውቃቸው መኪኖች ጋር ተመሳሳይ ንድፍ የላቸውም። እነዚህን ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች እመለከታለሁ ... አሁን እንደማያቸው ዓይነት ሕንፃዎች በፊት አልነበሩም።" በክፍሉ ውስጥ እጆቹን እያወዛወዘ "ይህ ሁሉ አዲስ ነው" ይላል። "እለምደዋለሁ። እወደዋለሁ። ይህ ለእኔ አስደሳች ነው። ይህ በእውነት የሚያስደስት ነው" ይላል። ሊጎን ያለፉትን 68 ዓመታት ዋጋ ከፍሎባቸዋል። ያለ አመክሮ ለመለቀቅ ሲል ዓመታትን በእስር ማሳለፉን ያውቀዋል። ይህም ከቤተሰቦቹ ጋር ሊያሳልፍ የሚችለውን ጊዜ ከማሳጣት ባለፈ በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ የቤተሰቦቹ አባላት ህይወት አልፏል። "የእህቴ ልጅ ቫለሪ እስር ቤት በነበርኩበት ጊዜ ተወለደች። ታላቅ እህቷ እና ታናሿ እዚያው እያለሁ ተወለዱ። ሁሉም የቅርብ ቤተሰቦቼ አልፈዋል። አሁንም በሕይወት ያሉነው እኔ፣ [ቫለሪ] እና የቫለሪ እናት ብቻ ነን" ሲል ይገልጻል። የ83 ዓመት አዛውንት ለረጅም ጊዜ ከጠበቀው ህይወት ጋር ራሱን እያዋሃደ ጥቂት ዕቅዶችንም እያወጣ ነው። ለዚህም በደንብ የሚያውቀው ሥራ መሥራት ይፈልጋል። "በሕይወቴ ዘመኔ በሙሉ የሠራሁትን ለመሥራት ዝግጁ ነኝ። የጽዳት ሠራተኛ በመሆኔ የጽዳት ሥራ ስጡኝ" ሲል ያጠናቅቃል።
news-45944294
https://www.bbc.com/amharic/news-45944294
በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል አማጺ ቡድን የሆነው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ስምምነት ላይ ደረሰ
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ የሶማሌ ክልል የራስን ዕድል በእራሱ እንዲወስን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥረቱን እንደሚቀጥል አስታወቀ።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁም እሁድ ጥቅምት 11/2011 ዓ.ም የኦብነግን ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀውን የትጥቅ ትግል የሚያበቃ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል። በተደረሰው ስምምነት መሰረት ሁለቱም ወገኖች ግጭቶችን እንደሚያቆሙና፤ ኦብነግም የሶማሌ ክልልን በተመለከተ የሚያካሂደውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በሰላማዊ መንገድ እንደሚያደርግ ተስማምቷል። የኦብነግ የውጪ ግንኙነት ፀሐፊ የሆኑት አህመድ ያሲን ለቢቢሲ ሶማሊኛ እንደተናገሩት ሁለቱ ወገኖች ኦብነግ የፖለቲካ ተሳትፎውን "በሰላማዊና በነፃነት" እንደሚያካሂድ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። • በዝምታ የምትጠማ ከተማ -ሐረር • ፖሊስ: አብዲ ሞሐመድ ዑመር ከእስር ቤት ለማምለጥ ሞክረዋል "ስምምነት ላይ ከደረስንባቸው ነገሮች መካከል የሶማሌ ክልል ሕዝብ ጉዳዩን ያለጣልቃገብነት በነፃነት እንዲያከናውንና ኦብነግም የራስን ዕድል በእራስ የመወሰን ጥያቄውን ጨምሮ ፖለቲካዊ ፍላጎቱን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲያካሂድ ማድረግን ይጨምራል" ሲሉ አቶ ያሲን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፀሐፊው ጨምረውም ከውይይቱ በኋላ የኦብነግ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጥያቄን በሚመለከት የሚወያይ የጋራ ኮሚሽን ይቋቋማል ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መንግሥት ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ያካሄደው ለውጥ አካል በሆነ ውሳኔ ኦብነግ ከሽብተኛ ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ እንዲወጣ በሃገሪቱ ፓርላማ ሲወሰን ነሐሴ ወር ላይ ተኩስ አቁም አውጇል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ኦብነግ ለበርካታ ዓመታት የቡድኑ መቀመጫ በነበረችው አሥመራ ውስጥ በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ተገናኝተው ነበር ውይይታቸውን የጀመሩት። *ማረሚያ ጥቅምት 14/2011 ዓ.ም፡ ቀደም ሲል በወጣው ዘገባ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ጋር ካደረገው ተከታታይ ውይይት በኋላ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ተስማምቷል ተብሎ የተፃፈው ስህተት ነው። ለበርካታ ዓመታት በምሥራቃዊው የሃገሪቱ አካባቢ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ወደ ሃገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ ትግል ውስጥ ለመሳተፍ መወሰኑ ለሃገሪቱ ሰላም በአጠቃላይ በተለይ ደግሞ ለሶማሌ ክልል ሰላም ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ኦብነግ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ትግል ያደርጉ ከነበሩ አማፂ ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ1984 ነበር የተመሰረተው። ቡድኑ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ተብለው ከተሰየሙ ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ሦስት የፖለቲካ ቡድኖች ከሽብር ቡድን ዝርዝር ውስጥ በፓርላማው ውሳኔ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ በውጪ የሚገኙ የታጠቁ ተቃዋሚዎች ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው ይታወቃል። አማፂው አብነግ የኦጋዴን ሕዝብ ብሎ የሚጠራውን በምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚገኘው የሶማሌ ሕዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለማስከበር በፖለቲካዊና ወታደራዊ መስኮች ትግል ሲያደርግ ቆይቷል። ኦብነግ ከምስረታው አስራ አራት ዓመታት በኋላ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ሊግ ጋር በመዋሃድ የሶማሊ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን መስርተው ነበር። • ኦብነግ የተኩስ አቁም አወጀ • መንግሥትና ኦብነግ የጀመሩት ጉዞ የት ያደርሳል? ምን መቼ ሆነ? ሚያዚያ 1996 ዓ.ም፡ የተቃዋሚ የሆነው ሬዲዮ ነፃነት ኦብነግ በኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች ላይ በፈፀመው ጥቃት በርካታ ወታደሮችን መግደሉን ዘገበ። መጋቢት 1998 ዓ.ም ፡ የኦብነግ መሪዎች ከዴንማርክ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ ያሉ ሶማሌዎች ላይ በመንግሥት ይፈፀማል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ አስረድተዋል። የዴንምርክ ባለስልጣናትም ያለው አስተዳደር ዴሞክራሲን የማይተገብር በመሆኑ ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን እርዳታ አቋርጠዋል። ጥር 2001 ዓ.ም ፡ ኦብነግ ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አልዎ መልዕክት አስተላለፈ። ጥቅምት 2002 ዓ.ም ፡ የኦብነግ ኮምኒኬሽን ሃላፊ ሁሴን ኑር የፑንትላንድና ሶማሊላንድ አስተዳደሮች ከኢትዮጵያ ሸሽተው የሄዱ ሶማሌዎችን አሳልፈው ለኢትዯጵያ መንግሥት ይሰጣሉ ሲል ከሰሰ። ነሐሴ 2002 ዓ.ም ፡ ኦብነግ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርቧል የሚለውን ዘገባ አስተባበለ። ጥር 2003 ዓ.ም ፡ ከ400 የሚበልጡ የግንባሩ አመራሮችና አባላት ከእስር ተለቀቁ። ሰኔ 2003 ዓ.ም ፡ ኦብነግ ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ በኢትዮጵያ መንግሥት ተፈረጀ። ጥር 2004 ዓ.ም ፡ ግንባሩ እንግሊዝ ውስጥ ባወጣው መግለጫ መንግሥት አጠቃላይ የሆነና በሦስተኛ ወገን አደራዳሪነት በገለልተኛ ስፍራ ላይ ለመደራደር ፈቃደኛ ከሆነ ኦብነግ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ። ጥቅምት 2005 ዓ.ም ፡ ኦብነግ መስከረም ላይ በኬንያው የመከላከያ ሚኒስትር ሞሃመድ ዩሱፍ ሃጂ አደራዳሪነት ናይሮቢ ውስጥ ከመንግሥት ጋር ሲያደርገው የነበረው የሰላም ድርድር ተቋረጠ። ጥር 2008 ዓ.ም ፡ ኦብነግ በሶማሌ ክልል በሚካሄደው የነዳጅ ዘይት ፍለጋ የክልሉን ህዝብ ያላሳተፈ በመሆኑ የህዝቡን ጥቅም የሚያስከብር እርምጃ እንደሚወስድ በፍለጋው ላይ የተሰማሩን የውጪ ኩባንያዎችን አስጠነቀቀ። ግንቦት 2009 ዓ.ም ፡ ኦብነግ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር በጋራ ለመስራት መስማማቱን ቡድኖቹ ባወጡት መግለጫ አሳወቁ። ሁለቱ ቡድኖች ጀርመን ፍራንክፈርት ውስጥ ለሦስት ቀናት ያካሄዱትን ስብሰባ ተከትሎ ነው ውሳኔያቸውን ያሳወቁት። ነሐሴ 2009 ዓ.ም ፡ የሶማሊያ መንግሥት የኦብነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አብዲካሪም ሼክ ሙሴን (ቀልቢ ደጋ) በሰሜን ሶማሊያዋ ከተማ አዳዶ ውስጥ ይዞ ለኢትዮጵያ መንግሥት መስጠቱን አረጋገጠ። ሰኔ 2010 ዓ.ም ፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ባለስልጣናት ውይይት መጀመራቸውን ተከትሎ የኦብነግ ምክትል ሊቀመንበርና ቃል አቀባይ ሙሃመድ ኦስማን አዳኒ ግንባራቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ንግግር ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን ተናገሩ። ሰኔ 2010 ዓ.ም ፡ በአወዛጋቢ እርምጃ በፕሬዝዳንት ፎርማጆ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተላልፎ የተሰጠው የኦብነግ የጦር አዛዥ አብዲካሪም ሙሴ (ቀልቢ ደጋ) ተለቀቀ። ሰኔ 2010 ዓ.ም ፡ የኢትዮጵያ ካቢኔ አርበኞች ግንቦት 7ን እና ኦነግን ጨምሮ ኦብነግን የሃገሪቱ ፓርላማ ከሽብርተኝነት መዝገብ እንዲያስወጣ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ። ነሐሴ 2010 ዓ.ም ፡ ኦብነግ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ግንባሩን የሽብር ቡድን ነው የሚለውን ውሳኔውን ውድቅ እንዲያደርግና ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ስለሰጠው የጦር አዛዡ በይፋ ይቅርታ እንዲጠየቅ ሃሳብ አቀረበ። ነሐሴ 2010 ዓ.ም ፡ ኦብነግ ጅግጅጋ ውስጥ የተከሰተውን ግጭት አውግዞ ሁሉም ወገኖች ከኃይል ድርጊት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ነሐሴ 2010 ዓ.ም ፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን የሰላም ጥሪን ተከትሎ ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚሆን የተናጠል ተኩስ አቁም አወጀ። ነሐሴ 2010 ዓ.ም ፡ አስር የሚደርሱ የኦብነግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በማዕከላዊ ሶማሊያ ጋልሙዱግ በሚባለው ስፍራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ነሐሴ 2010 ዓ.ም ፡ ኦብነግ ሙስጠፋ ኦማር የሶማሌ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀበለው ገልጾ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በክልሉ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ አስጠንቅቋል። ነሐሴ 2010 ዓ.ም ፡ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ሞሃመድ ኦማር በቁጥጥር ስር መዋል እንደሚደግፍና ይህም ፍትህን ለማስፈን የተጀመረ ትክክለኛ እርምጃ ሲል ገልጾታል። የኦብነግ መሪዎች ሊቀመንበር፡ ኡትማን አድም ሙሃመድ ኡማር (ከጥቅምት 2002 ጀምሮ) ምክትል ሊቀመናብርት፡ አዳኒ ሙሃማድ ኦስማን፣ ኦማር ሙሃመድ ኢስማኤል የኮምኒኬሽን ኃላፊ፡ ኑር ሁሴን
55160212
https://www.bbc.com/amharic/55160212
ትግራይ ፡ በተወሰኑ የትግራይ ክልል አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩ ተገለፀ
በፌደራሉ መንግሥት እና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት በተወሰኑ አካባቢዎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ለሳምንት አገልግሎቱ ተቋርጦባቸው ከነበሩት አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው በአላማጣ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩንና የተወሰኑ ቀናትም መቆጠሩንም ኃላፊዋ ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪ በምዕራብ በኩል በዳንሻ፣ በተርካን፣ ሁመራ፣ ሽራሮ፣ ማይካድራና ማይፀብሪም አገልግሎቱ በከፊል ተጀምሯል ብለዋል። በእነዚህ አካባቢዎች በከፊል አገልግሎት መስጠት የተጀመረበትንም ምክንያትም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ሲያስረዱ በአካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ባለመኖሩ መሆኑን አመልክተው፤ ለዚህም እንደመፍትሄ አማራጭ ኃይል ብለው የጠቀሷቸውን ጄኔሬተርና ሶላር የኃይል ማመንጫዎችን በመጠቀማቸው እንደሆነ ገልፀዋል። በአጠቃላይ በክልሉ የተቋረጠውን የቴሌኮም አገልግሎት ለመመለስ ኢትዮ-ቴሌኮም የጥገና ሥራ እያካሄደ መሆኑን የገለፁት ፍሬሕይወት ለዚህም የኃይል አቅርቦት ችግሩን ለመቅረፍ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በጥምረት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። ከሦሰት ሳምንታት በላይ ወታደራዊ ግጭት በተካሄደባት ትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ በመቆየቱ ግንኙነት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።
news-50065727
https://www.bbc.com/amharic/news-50065727
"50 ዓመታት በትዳር የኖርነው ጥፋት ሳይኖር ቀርቶ አይደለም" ኢትዮጵያዊያኑ ጥንዶች
ወ/ሮ አበባ ገብረ ሥላሴ ከባለቤታቸው ከአቶ ገብረ ክርስቶስ ጋር በትዳር 50 ዓመታትን ማሳለፋቸውን ይናገራሉ። በቅርቡም ከዘጠኝ ልጆቻቸውና ከ17 የልጅ ልጆቻቸው ጋር በመሆን የ50ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን አክብረዋል።
ከትዳር አጋራቸው ጋር ይህን ያህል ዓመት ሊኖሩ የቻሉት "መቻቻል በመካከላችን ስለነበር" ነው ይላሉ። የትዳር አጋራቸው "ጥፋት ሳያጠፋ ቀርቶ አይደለም" የሚሉት ወ/ሮ አበባ፤ ነገር ግን ተረጋግተው ሰከን በማለት ነገሮችን ለመፍታት መሞከራቸው ደስተኛ የትዳር ህይወት ለማጣጣም እንደረዳቸው ይናገራሉ። እንደ ባልና ሚስት ቁጭ ብሎ ለመነጋገር የከበዳቸው ጥንዶች፣ ልጅ ስለወለዱ ብቻ አብረው የሚኖሩ ባልና ሚስት፣ እርስ በርስ ጣት በመቀሳሰር የሚወነጃጀሉ አጋሮች ማየት ግን የተለመደ ነው። ይህ አለመግባባት አድጎ ሰማኒያቸውን የቀደዱ፣ የመሰረቱትን ቤተሰብ የበተኑም ቀላል አይደሉም። ለመሆኑ የኢትዮጵያዊያንን የትዳር አከርካሪ ምን ይሆን እየሰበረ ያለው ስንል ከ10 ዓመት በላይ በጋብቻና ቤተሰብ ማማከር ላይ የቆዩትን ትዕግስት ዋልተንጉስና እንዳልክ አሠፋን ጠይቀን። ትዕግስትና እንዳልክ ባለፉት 10 ዓመታት በትዳር ምክክር ላይ የሰሩ ሲሆን የእርቅ ማዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መስርተው የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ናቸው። የትዳርና የፍቅር ግንኙነትን ፈተና ላይ ከሚጥሉ ነገሮች መካከል ይላል እንዳልክ፣ ጥንዶች ስለ ትዳርና የፍቅር ግንኙነት ያላቸው እውቀት ማነስ አንዱ ነው። ትዕግስት በበኩሏ "ትዳር እኮ የሚጀምረው ከራስ ነው" በማለት የትዳር አጋርን ከመመልከት በፊት ራስን መመልከት እንደሚገባ ትገልፃለች። ሰዎች ስለትዳርና ስለፍቅር ያላቸው እውቀት የተዛባ መሆን፣ የኢኮኖሚ አቅም መዳከም፣ የባሕል ልዩነት፣ አስተሳሰብ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የትዳርና የፍቅር ግንኙነትን አጣብቂኝ ውስጥ ከሚጥሉ መካከል ይጠቀሳል ያለው እንዳልክ በይበልጥ ግን በሁለቱ የትዳር አጋሮች መካከል ያለ የተግባቦት ክህሎት ማነስ የችግሮች ሁሉ መንስኤ ሆኖ እንዳገኘው ይጠቅሳል። ወ/ሮ አበባ በበኩላቸው አማቴንም ሆነ ምራቴን እንደቤተሰቤ መቀበሌ እና ደስተኛ መሆኔ ትዳሬ እንዲሰምር ረድቶኛል ይላሉ። "እኔና ባለቤቴ ተጣልተን እናውቃለን፤ ግን መቻቻል እስከዛሬ አኑሮናል" በማለት ከፍቺ ይልቅ ፍቅርን አስቀድመው እዚህ መድረሳቸውን ይመሰክራሉ። ከትዳር በፊት ራስን ማየት ትዕግስት ባለፉት ዓመታት የትዳር አጋሮችንና ቤተሰቦችን በምክክር ስታገለግል ያስተዋለችው ዋናው ነገር ትዳርን በመሪነት የሚሾፍረው ሁለቱ ጥንዶች ለራሳቸው ያላቸው ግምት መሆኑን ነው። ይህንኑ ሃሳቧን ስታፍታታም ትዳር እንደተጀመረ ወንዱም ሆነ ሴቷ 'መልአካዊ' ባህሪ ያሳያሉ በማለት ነው። ችግሮች መከሰት የሚጀምሩት እያደር ነው። "ቀን ቀንን ወልዶ በትዳር የዕለት ተዕለት አዙሪት ውስጥ የፍቅር ማዕበሉ ፀጥ ሲል የጥንዶቹን የግል ማንነት የሚመራው ለራሳቸው ያላቸው አመለካከት መገለጥ ይጀምራል" ስትልም ሃሳቧን ታብራራለች። አክላም ትዳር የሚመሰርቱ ጥንዶች በቅድሚያ ኪሳቸውን ወይንም የባንክ አካውንታቸውን እንደሚያዩት ሁሉ፤ ለራሳቸው ያላቸውን እምነትና አመለካከትም ማየት እንደሚያስፈልጋቸው ትጠቅሳለች - ትዕግስት። ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ትዳር ከመመስረታቸው በፊት በቅድሚያ ከራሳቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን ይመስላል የሚለውን መፈተሽ፣ የጎደለንን ነገር መመልከት፣ የሚፈሩትን ነገር ሳይደብቁ ይፋ አውጥተው መነጋገር ወሳኝ መሆኑንም ትመክራለች። እንዳልክና ትዕግስት በትዳርና በፍቅር ግንኙነት ውስጥ በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ ነገሮች አማካሪ አለመኖር እንደችግር ያነሳሉ። ወ/ሮ አበባም ሁሌም ምነው አማካሪ በኖረ ብለው እንደሚያስቡ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ በነበራቸው ወቅት ተናግረዋል። ጥንዶቹ ወደ ጋብቻ ከመሄዳቸው በፊት ሊመሰርቱ ስለሚያስቡት ቤተሰብ፣ ቤተሰቡ ስለሚኖረው ግብ፣ ዕሴትና ሌሎች ነገሮች ቁጭ ብሎ የሚያማክር ወገን አለመኖር ወደ ትዳር ዘለው የሚገቡ ጥንዶች የሚገጥማቸውን ተግዳሮት በራሳቸው ብቻ እንዲወጡ ያደርጋቸዋል ይላሉ ባለሙያዎቹ። እንዳልክ ይህንን ሀሳብ ለማጠናከርም "ትዳር በእውቀት ነው የሚመራው" በማለት ትዳር ምንድን ነው? እንዴት ይመራል? የሚሉና የወንድና የሴት ተፈጥሮን ማዕከል ያደረጉ መሠረታዊ እውቀቶች እንደሚያስፈልጉ ይናገራል። እውቀቱ ከየት ይገኛል? ትዳርን በሁለት እግሩ አቁሞ ጠንካራ የቤተሰብ መሰረት ለማድረግ ተቋማት ያስፈልጋሉ ይላሉ ሁለቱም ባለሙያዎቹ። ወ/ሮ አበባም የቀደሙ ሰዎች ትዳራቸወን እንዴት እንደመሩ በመጠየቅ ትምህርት ለማግኘት ይጥሩ እንደነበር ነግረውናል። የማህበራዊ ተቋማት፣ ባህላዊ መስተጋብር ያለውን እውቀት መጠቀም፣ የመንፈሳዊ እናቶችና አባቶችን እንዲሁም ተቋማቱን መጠቀም፣ በተጨማሪም በሙያው የሰለጠኑ የጋብቻ የምክክር አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን መጎብኘት ስለ ትዳርና ግንኙነት እውቀት የምናገኝባቸው ስፍራዎች መሆናቸውን እንዳልክ ይናገራል። ጎጆ መቀለስ ወይንም ሦስት ጉልቻ መመስረት ወልዶ ከመሳም፣ አንድ ጣሪያ ሥር ከመኖር የዘለለ መሆኑን የሚያማክር ወገን መኖር እንዳለበት ትዕግስትም ትናገራለች። ሰዎች ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት ስለ ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ማወቅ ተገቢ ነው የሚለው እንዳልክ፤ የሴት ተፈጥሯዊ ባህሪ ምንድን ነው? የወንዱስ? ባልነት የሚጠይቀው ኃላፊነት ምንድን ነው? እናትነትና አባትነት ውስጥ ያሉ ኃላፊነቶች ምንድን ናቸው? የሚለውን ማወቅ ጥንዶቹ በጋብቻቸው ውስጥ በመረዳዳትና በአግባቡ ለመተዋወቅ እንደሚረዳቸው ይናገራል። የወንድ ልጅ ደመነፍሳዊ ባህሪ መጠበቅ፣ መከላከል፣ መሆኑን ማወቅ፤ ሴቷ ደግሞ ነገሮችን ዘርዝሮ የመረዳት፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ተፈጥሯዊ ክህሎቶችና እውቀቶች እንዳሏት መረዳት ትዳርን በእውቀት ለመምራት የሚረዱ መግቢያዎች ናቸው ይላል። ወንድ ችግሮች ሲገጥሙት ወደ ራሱ ተፈጥሯዊ ዋሻ ገብቶ መፍትሄ እንደሚፈልግ መረዳት፣ ሴቶች ችግር ሲገጥማቸው ደግሞ ተነጋግሮ የሚፈቱበት መንገድን ተፈጥሮ እንዳደለቻቸው ማስተዋል፤ ችግር በሚገጥምበት ወቅት መፍታት የሚችሉባቸውን መንገዶች እንዲያውቁ ይረዳቸዋል ይላል እንዳልክ። ሁለቱም ጾታዎች አንዳቸው የሌላኛቸውን ተፈጥሯዊ ባህሪ መረዳት ሲችሉ፤ ችግር በገጠማቸው ወቅት እንዴት እንደሚፈቱትና እንዴት በጋራ እንደሚወጡት ይረዳዳሉ። ካልሆነ ግን ላለመግባባት፣ ኩርፊያና ቅያሜ ያጋልጣል ይላል። እነዚህን እውቀቶች ከንባብ፣ ከባለሙያ አልያም ከበይነ መረብ ማግኘት እንደሚቻልም ይጠቅሳል። ትዕግስት በበኩሏ ከመጻህፍትም ሆነ ከበይነ መረብ የምናገኘውን እውቀት ለመውሰድ በቅድሚያ በራሳችን ያለብንን ክፍተት መረዳትና ያንንም ለማስተካከል ዝግጁነት ሊኖረን እንደሚገባ ትናገራለች። ጎጆ ከመቀለስ፣ ከሦስት ጉልቻ በፊት ራስን መሥራት ቢቀድም መልካም መሆኑን ትናገራለች። አንድን ትዳር የሚመራው የሁለቱ ሰዎች መዋደድ፣ ሁለቱ ሰዎች ያላቸው ገንዘብ እና ፍቅር ብቻ ሳይሆን ለራሳቸው ያላቸው ግምት ጭምር ነው ስትልም ሃሳቧን ታጠናክራለች። የሦስት ጉልቻ ፈተናዎች ትዕግስትና እንዳልክ በአስር ዓመት የማማከር ልምዳቸው ኢትዮጵያዊን ጥንዶችን ወገቤን እንዲሉ ያደረጓቸውን ጉዳዮች ታዝበዋል። ችግር ውስጥ የገቡ ባለትዳርና ቤተሰቦች ውስጥ የሚታዩት መሠረታዊ ችግሮች አለመተማመን፣ አለመስማማት፣ የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት፣ ለራስ ያለ ግምት መውረድ፣ ወሲብና መግባባት አለመቻል መሆናቸውን የምትዘረዝረው ትዕግስት ናት። ነገር ግን የዚህ ሁሉ ችግር ምንጭ ከሥሩ ይመንገል ተብሎ ሲቆፈር ጥንዶቹ ለራሳቸው የሚሠጡት ስፍራ ገኖ እንደሚታይ ትጠቅሳለች። ያለመግባባት ምክንያት ሆነው በጥንዶች መካከል የሚነሱት ነገሮች በአጠቃላይ ከላይ የሚታዩ የበሽታው ምልክቶች እንጂ ራሱ በሽታው አይደለም ስትል ታጠናክራለች። በትዳር ውስጥ አንዳንዱ ለራሱ ያለው ግምት 'እኔ ብቁ ነኝ' በሚል ማንነት የተለበጠ ሲሆን ሌላው ደግሞ 'ብቁ አይደለሁም' በሚል የራስ መተማመን ማጣት የተናጋ ነው የምትለው ትዕግስት "'ብቁ አይደለሁም፣ ተወዳጅ አይደለሁም' የሚል አጋር፤ ሌላኛው አጋሩን አይሰማም" በማለት ያለመግባባቱን ስር ማየት እንደሚያስፈልግት ትመክራለች። በሥራዋ አጋጣሚ እኔ ያልኩት ይሁን ብቻ የሚሉ ጥንዶች ገጥመዋት ማየቷን በማስታወስ 'ተቀባይነት የለኝም፣ ተወዳጅ አይደለሁም' የሚለው ሀሳብ በተለይ ከትዳር አጋር የሚመጣን ሃሳብ ውድቅ ማድረግ ከሆነ ደግሞ እንደ ጥቃት የመቁጠር ዝንባሌ አዳብረው ማስተዋሏን ትናገራለች። ስለዚህ ጥንዶች ስለራሳቸው የሚሰማቸው ነገር ምን እንደሆነ ማጤንና መፈተሽ ቀዳሚው ነገር ቢሆን የሚል ሀሳብ ታነሳለች። ለራሳቸው ዝቅተኛ ግምት የሚሠጡ ሰዎች በትዳራቸው ላይ ቁጡ፣ ጯሂ፣ ለማንኛውም ነገር ቀድመው መልስ የሚሠጡ፣ ሁሉን ነገር አውቃለሁ የሚሉ ስለሚሆኑ ለትዳር አጋራቸው ፈታኝ ይሆናሉ ስትልም ሃሳቧን ታጠናክራለች። "የትዳር ስንክሳሮች ብዙ ቢሆኑም" የሚለው እንዳልክ "ችግሮች ሁሌም መፍትሔ እንዳላቸው መረዳት ለጥንዶቹ ቀዳሚ ነጥብ መሆን አለበት" ይላል። ሌላው እንዳልክ የሚያነሳው ነጥብ ከመፋታት ይልቅ ችግርን መፍታት አስፈላጊ በመሆኑ ተረጋግቶ፣ የጥሞና ጊዜ ወስዶ ለችግሮቻቸው መፍትሄ መስጠትን ይመክራል። ችግሮቻቸውን ራሳቸው መፍታት ካልቻሉም ለሌላ ወገን እድል ሊሰጡ ይገባል የሚለው እንዳልክ የጋብቻ ምክክር ባለሙያዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ በእድሜ በሰል ያሉ ሰዎች ለዚህ መፍትሄ ናቸው ይላል። ትዳር ከተመሰረተ በኋላ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ግጭት ተከስቶ፣ የነበረው እንዳልነበር ሲሆን፣ አፍ ቁልምጫን ረስቶ ዘለፋ ሲቀድም፣ የሚያሳየን "የትዳር የፍቅር ባንክ ውስጥ ያለው ሂሳብ ማለቁን ነው" ይላል እንዳልክ። ከዚህ አንጻር ሁለቱም ባለሙያዎች በአንድ ድምፅ የሚስማሙት በትዳር ውስጥ የሚኖር ፍቅር በክፉ ጊዜ እንደሚቀመጥ ገንዘብ ነው በማለት ነው። ማንኛውም ባለትዳር በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ የትኞቹንም ግጭቶች ችሎ የሚኖረው፣ ጥንዶቹ በደህና ጊዜ ያጠራቀሙት ፍቅር በመኖሩ መሆኑን ይጠቅሳሉ። "የፍቅር ካዝናችሁ ባዶ ከሆነ መልሶ በስሜት በመተካከም፣ ፍቅርን በመገላለጥና አንዳችሁ ለአንዳቸሁ ያላችሁን ስሜት በመገላለጥ የተራቆተውን ትዳር ዳግም ማሞቅ" እንደሚያስፈልግ ትዕግስት ትናገራለች። ትዳር ውስጥ ግጭት ተከስቶ ሽምግልና የሚቀመጡ ሰዎች በቅድሚያ የሚሰሙት ግጭቱ የጀመረው ትናንት አለመሆኑን እንደሆነ የምትናገረው ትዕግስት፤ ከዓመታት በፊት የጀመረ የጠብ እርሾ ተብላልቶ ወደ አደባባይ እስኪወጣ ያኖራቸው የተጠራቀመው "የፍቅር የቁጠባ ሂሳብ" እንደሆነ ትገልፃለች። ባለቤቷ ወይንም ባለቤቱ በፍቅር ወቅት የቆጠቡት "የፍቅር ሂሳብ" ካለቀ እንደ አዲስ የሚያዋጡት "የፍቅር ሂሳብ" መኖር አለበት ሲል እንዳልክ ይመክራል። በትዳር ውስጥ አንድ ባልና ሚስት በአካል ቢራቆቱ እንደማይተፋፈሩ ሁሉ፤ በስሜትም ራቁት መሆን እንደሚያስፈልጋቸው የምትናገረዋ ትዕግስት ደግሞ በመካከላቸው ሚስጥር መኖሩና መደባበቅ መፈጠሩ ለግጭት እርሾ ትቶ እንደሚያልፍ ታስረዳለች። ነገር ግን ይህ ግልፅ መሆን በአንድ ጊዜ የሚመጣ ሳይሆን በሂደት መሆኑንም ታሰምርበታለች። ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ የሚኖራቸው ቅርበት የበለጠ እየጠነከረ የሚሄደው፤ ባልም እናት አባቱን ትቶ ሚስትም ቤተሰቦቿን ርግፍ አድርጋ ከትዳር አጋሯ ጋር የምትጣበቀው በሂደት መሆኑንም ታሰምርበታለች። ጥንዶች ለቤተሰቦቻቸው ያላቸው ስሜትና ቅርበት የግጭትና የፍቺ ምክንያት ሆኖ እንደሚታይ በማስታወስም፤ ከትዳር ተጣማጅ ጋር የሚኖር ቅርበት ሂደት መሆኑን ማስታወስ ለሁለቱም ጠቃሚ መሆኑን ትናገራለች። ሚስጥርንም ሆነ ሌሎች ጉዳዮችን ግልፅልፅ አድርጎ ለመናገርና "በስሜት ራቁት ለመሄድ" ጊዜ እንደሚያስፈልግ ትዕግስት ትናገራለች። ስለትዳር መቼ ነው ምክር የምንጠይቀው? የትዳር የመጀመሪያ ወራቶች ሁሉም ነገር ጥዑም መዓዛ ያለው፣ መስኩ አበባ፣ እዳው ገለባ የሆነበት ጊዜ መሆኑን በማስታወስ፣ አዲስ ተጋቢዎችን በቅድሚያ ራሳችሁን ፈልጋችሁ አግኙ ብሎ መመካከር 'አይደለም ራሴን የትዳር አጋሬን ፈልጌ አግኝቻለሁ' ወደ ሚል ምላሽ ሊያመራ ይችላል የምትለው ትዕግስት ናት። ቅድመ ጋብቻ ትምህርት የሚሰጠው ሁሉን ነገር ጨርሶ ለመጣ ሰው ሲሆን እንደሚያስቸግር በመጥቀስ ታዳጊዎች ስለራስ ማወቅ በእድሜያቸው ለጋነት ቢማሩ ጤናማ ትዳር ለመመስረትና ጤናማ ቤተሰብ ለመምራት ይረዳቸዋል ይላሉ ባለሙያዎቹ። "ከቅድመ ጋብቻ ትምህርት በፊት ቀድመው የሚሰሩ ነገሮች ቢኖሩ መልካም ነው" በማለትም አፍላ ወጣትነት ላይ እያሉ ስለ ራስን ፈልጎ ማግኘት፣ እሴትን ማስቀመጥ፣ ስለ ፍቅር ግንኙነትና የትዳር አጋር የሚያማክራቸው ቢኖር መልካም ነበር ትላለች። እንዳልክ በበኩሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ውስጥ ሆነ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርቱ ቢኖር ጤናማ ቤተሰብ ለመመስረት እንደሚረዳ ይናገራል። ከመጋባታቸው በፊት ልጅ ወልደው ቤት ውስጥ ሆነው ለማሳደግ የተስማሙ ሚስቶች፣ ወይንም ልጆቹን እናታቸው ሥራ ፈትታ እንድታሳድግ በሚፈልግ ባል መካከል አለመግባባት የሚነሳው በቅድሚያ የሕይወት እሴታቸውን ሲበይኑ በግልፅ ባለማስቀመጣቸው መሆኑን ትዕግስት ታብራራለች። 'ትምህርት መማር እፈልጋለሁ'፣ 'ከልጅ ጋር ቤት ውስጥ ታስሮ መዋል ጨነቀኝ'፣ 'መማር የልጅነት ህልሜ ነበር' የሚሉ ነገሮች የሚመጡት በቅድሚያ በግልፅ የተበየነ የሕይወት ዕሴት ባለመኖሩ መሆኑን ትገልፃለች። ይህ ንግግር የተጀመረው ትዳር ከተጀመረ በኋላ ከሆነ ደግሞ የትዳር አጋሩ ከጊዜ በኋላ የመጣ ባህሪ እንደሆነ እንዲሰማውና ለጠብ መንስኤ እንዲሆን እንደሚያደርግ ታስረዳለች። የፍቅር ጓደኛ አልያም የትዳር አጋር ከመምረጣችን በፊት ስለግንኙነቱ በደንብ ራሳችንን በዕውቀት ማነፅ እንደሚያስፈልግ የምትመክረው ትዕግስት፤ አንድ ጊዜ ምርጫ ካደረጉ በኋላ ስለራስ አመለካከት፣ ለራስ ስለሚኖር ክብር፣ ከራስ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት፣ ፍላጎትን ስለ መለየት፣ ዕሴትን ስለማስቀመጥ ማወቅና ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ትናገራለች። የትዳር አጋሮች ሲጋቡ መደራደር የማይችሉት፣ የማይቀይሩት፣ ካላቸው ዕሴት ውጪ ቢኖሩ ደስተኛ የማይሆኑባቸው ጉዳዮች ይኖራሉ የምትለው ትዕግስት፤ ይህንን አስቀድመው ለይተው ያላወቁ ተጋቢዎች ትዳር ውስጥ ገብተው የማያስደስታቸውን ነገር እያደረጉ መኖር ሲጀምሩ ከሌላኛው ወገን ጥያቄ መነሳት እንደሚጀመር ትጠቅሳለች። "ዕሴትን ከትዳር አጋር ጋር መነጋገርና ማስረዳት አለመቻል ራስን አለማወቅ ነው" በማለትም ራሳችንን በሚገባ ፈልገን ሳናውቅ ሌላ ሰው ሕይወታችን ውስጥ በማምጣት ትዳር ከመሰረትን በኋላ፣ የአጋራችንን ፍላጎት ለመረዳት፣ ህልሙንና እሴቱን ለመኖር ጥረት ስናደርግ ጠብ ይከሰታል ትላለች። የትዳር አጋሮች የጋራ ራዕይ ጥንዶች 'ዓለምሽ ዛሬ ነው' ተብሎ ተዘፍኖ፣ ትከሻ እስኪነቀል ተጨፍሮ ከተዳሩ በኋላ ልጅ ሲመጣ፣ ቤት ሲሰሩ ከዚያም ሌሎች በህይወታቸው ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሲያሟሉ "እርስ በእርስ ፍቅር መገላለጡን ይረሱታል የምትለው" ትዕግስት ለዚህ መፍትሔው የጋራ ራዕይ ማኖር ነው ትላለች። አንድ ሰው በግሉ ዓላማ እንዳለው ሁሉ ትዳር ውስጥ ደግሞ ሲገባ የጋራ ሕልም፣ ግብና ራዕይ ማኖር አስፈላጊ መሆኑን ታሰምርበታለች። "የጋራ ህልማቸው ቤት መሥራት ከሆነ ቤት ብቻ ይሰራሉ። ስሜታቸው ላይ ግን አይሰሩም። የጋራ ግቡ መኪና መግዛት ከሆነ መኪና ይገዛሉ ቤተሰባቸው ላይ ግን አይሰሩም" ትላለች ትዕግስት። አክላም የመሰረቱት ቤተሰብ ከአምስት ዓመት በኋላ በስሜት፣ በኢኮኖሚና ከሚኖሩበት ማህበረሰብ ጋር እንዴት አድርገው አጣጥመው እንደሚሄዱ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚኖር ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት ካላቀዱ ለቤተሰቡ ኪሳራ መሆኑን ታስረዳለች። ይህንን የጋራ እቅድ ሲያወጡ ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ እንደሚችሉ፣ እርስ በእርስ እንዴት እንደሚተናነፁ ካላወሩ የቁስ ግንባታ ብቻ ትዳርን በሁለት እግሩ እንደማያቆመው ትናገራለች። በትዳር ያሉ ጥንዶች ልጅ ወልደው ስመው፣ ቤት ሰርተው፣ መኪና ገዝተው፣ በቂ ገንዘብ ኖሯቸው በትዳራቸው ደስተኛ ሳይሆኑ አስተውላ እንደምታውቅ የምትናገረው ትዕግስት፤ ያኔ የጥንዶቹ የፍቅር የሂሳብ መዝገብ መጉደሉን አልያም ማለቁን እንደሚነግራት ትጠቅሳለች።
54270105
https://www.bbc.com/amharic/54270105
ብልጽግና፡ "የታሰሩ ስላሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተጎድቷል የሚለውን አንቀበልም" ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
በዚህ ሳምንት ማክሰኞ እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ወስኗል።
አንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ግን ከወረርሽኙ በላይ፤ በአገሪቷ የሚታየው የፀጥታ ችግር ሳይፈታ ምርጫ ማካሄድ የማይሆን ነው ሲሉ ይናገራሉ። በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳን፤ በእርግጥ የንጹሃን ሰዎች መገደል፣ መፈናቀል፣ ንብረት መውደም እየተሰማበት ባለበት በዚህ ሰዓት ምርጫ ማካሄድ ይቻላል? ስንል ጠይቀናቸው ነበር። ዶ/ር ቢቂላ፡ በኢትዮጵያ ምርጫ ማድረግና የኢትዮጵያን ከባቢያዊ ሁኔታ ማሻሻል፣ ማዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ረዥም ታሪክ የተጓዘ፣ አንገብጋቢ አገራዊ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊ ሁኔታ በአግባቡ መፈተሽና ዘመናዊ እንዲሆን በተለይ ደግሞ አመኔታን ያተረፈ ምርጫን በማካሄድ ተቀባይነትና አመኔታን ያገኘ መንግሥት መመስረት አስፈላጊ ነው የሚለው ጉዳይ የሁሉም ማኅበረሰቡ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዛሬ ሁለት ዓመት በበዓለ ሲመታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን የፖለቲካ ከባቢያዊ ሁኔታን በእጅጉ በማሻሻል ነጻ፣ ዲሞክራሲያዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ በማካሄድ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ሥርዓት እንገነባለን ብለው ነበር። ይንን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተደረጉ ድርጊቶችና የተወሰኑ ውሳኔዎች እጅግ በጣም ወሳኝ ናቸው ብለን ነው የምናምነው። አንደኛ ለዘመናት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ መብረር እንኳ የማይችሉ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ በፖለቲካ ምክንያት ብቻ እስር ቤት የነበሩ ሰዎች እንዲለቀቁ ተደርገዋል። በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከውጪ አገር ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል። እኔ እስከማስታውሰው ድረስ በውጪ አገር የቀረ የፖለቲካ ፓርቲ የለም። የሚዲያ ከባቢው እንዲሰፋ፣ ተዘግተው የነበሩ ድረገጾች እንዲከፈቱ እንዲሁም ደግሞ የአገር ውስጥ ሚዲያዎች በነጻነት እንዲሰሩ የሲቪል ሶሳይቲ ሕጉም እንዲሻሻልና . . . ቢቢሲ፡ [በማቋረጥ] እነዚህ ነገሮች በተደጋጋሚ ሲገለፁ ነው የቆዩት። ጥያቄው አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ምርጫ ለማድረግ ያስችላል ወይ? ነው። ዶ/ር ቢቂላ፡ የእኛ አቋም፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተወሰኑ ውሳኔዎችና የተሄደባቸው ሁኔታዎች የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ ወይም ከባቢን አሻሽለውታል ብለን ነው የምናስበው። ለውጥ በሚመጣበት ወቅት ለውጡ ወደፊት እንዲሄድ የሚፈልግ አካል አለ። ይህ የለውጥ ባህሪ ነው። ለውጡ እንዲሳካና የተፈለገውን አላማ እንዲመታ የሚፈልግ አካል አለ። የዚያኑ ያህል ደግሞ ለውጡ እንዳይሳካና የተፈለገለትን አላማ እንዳይመታ የሚያደርግ አካልም አለ። ከዚህ ጋር ተያይዞ በአገራችን አሁን የምንመለከተው የግጭት፣ የሰዎች መፈናቀል በየቦታው የጉልበተኝነት ባህሪ እና በተደራጀ ሁኔታ ይህ ለውጥ እንዲቀለበስ የሚያደርግ ኃይል እንቅስቃሴ ነው ብለን ነው የምናምነው። በመሆኑም በየቦታው የታዩ የሰላም እጦቶች እንዲሁም ደግሞ በሰው ልጆች ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮች፤ ለውጡን የመቀልበስ አላማ አድርገን ስለምንመለከት እርሱን ቦታ ማስያዝ፣ በዚሁ ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ማዋልና በሕግ ብቻ እንዲመሩ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህንን የመቆጣጠር ሁኔታ በተለይ ደግሞ ሕግና ሕግን ብቻ የተከተለ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ሥራ እንዲሰራ ማድረግ በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ስለዚህም እዚህም እዚያም የሚታይ ችግር አገራችን እንድትቆምና ምርጫ እንዳታካሂድ፣ የመሻገር ሥራ እንዳትሰራ፣ የኢትዮጵያ የምርጫ ፖለቲካ ከባቢ መሻሻል እንዳያሳይ፤ ስለዚህም በየቦታው የሚከሰቱ ግጭቶችን ብቻ ቆመን እያየን እንድንቆዝም ለማድረግ የታሰቡ ናቸው። ነገር ግን እኛ ከዚህ ባሻገር ለግጭቱ ምክንያት የሆኑ አካላት፣ ይህንን ከጀርባ ሆነው የሚያስተባብሩ፣ የሚያቀናጁ፣ የሚያቅዱና ስፖንሰር የሚያደርጉ አካላትን ሕግ ፊት እንዲቀርቡና የሕግ የበላይነት እንዲከበር በማድረግ በየቦታው ለዚህ አስተዋጽኦ ያደረጉ፤ የብልጽግና አመራርንም ጭምር ካሉ በሕግ እንዲጠየቁ እያደረገ ነው። በዚህም የሕግ የበላይነት እንዲከበር በማድረግ የአገሪቱ ፖለቲካ በማዘመን ሥራ በማከናወን በሕዝብ ተቀባይነት ያለው መንግሥት እንዲመሰረትና ምርጫ ሕግና ሥርዓቱን ተከትሎ እንዲካሄድ የማድረጉን ተግባር ግን መቀጠል አለብን ብለን ነው የምናስበው። ስለዚህ እያከናወንን ያለው ሁለት ሥራ ነው ማለት ነው። አንደኛው የሕዝብን ደኅንነትን መጠበቅ፣ ፀጥታን ማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበር እዚህም እዚያም የሚታዩ የደኅንነት ችግሮችን ፈር ማስያዝ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን ነው የምናስበው። ቢቢሲ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በእስር ላይ የነበሩ ፖለቲከኞች ከእስር ተለቅቀዋል፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ወደ አገር እንዲገቡ ተደርገዋል። አሁን ላይ ግን ጠንካራ ተፎካካሪ የሚባሉ ፓርቲዎች አመራሮች እስር ላይ ይገኛሉ። አንዳንዶቹ እንደውም እስራቸው ፖለቲካዊ እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ ባለበት ሁኔታስ ምን አይነት ምርጫ ነው ማካሄድ የሚቻለው? ዶ/ር ቢቂላ፡ ቀደም ሲል እንዳልኩት የሁለት ነገሮችን ሚዛን ማስጠበቅ ያስፈልጋል። ይህ በጣም በአቋም የምንናገረው ነገር ነው። አንደኛ በአንድ አገር ውስጥ የፍትህና ሕግ ሥርአቱ መስራት መቻል አለበት። ይህ ማለት ምን ማለት ነው፤ በአንድ አገር ውስጥ ከወንጀል ጋር የተያያዙ፣ ከፍትህ ጋር የተያያዙ፣ ከሕግ የበላይነት ጋር ተያያዙ ነገሮችን የአገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት ለፍትህ ሥርዓቱ መተው ጥሩ ነው። ስለዚህ በእያንዳንዷ ነገር የፖለቲካንና የፍትህን፣ የሕግን ጉዳይ እየቀላቀልን አንድ አድርጎ በአንድ ኮሮጆ ከትተን የምንመለከት ከሆነ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። ከዚህ አንጻር ስንመለከተው፤ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ከባቢያዊ ሁኔታ እንዲሻሻል መንግሥት ቁርጠኝነት ነው፤ ገዢው ፓርቲም ቁርጠኛ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በምንም አይነት መንገድ ለሕዝብ የተገባው ቃል አይቀለበስም። ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። እዚህ ጉዳይ ውስጥ ግን በሕግ ጉዳያቸው የተያዘ፤ የአገሪቱ የፍትህ ሥርዓት የምጠረጥረው ነገር አለና በፍርድ ቤት አቅርቤ፣ መረጃ አስቀርቤ፣ የተሰራ ወንጀል አለ ያ ወንጀል የሕግ የበላይነት መከበር ስላለበት በሕግ መጠየቅ አለብን ብሎ የፍትህ ሥርዓቱ ሲጠይቅ ይህንን ለፍትህ ሥርዓቱ መተው ያስፈልጋል። ነገር ግን በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ለሕዝብ የተገባው በአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመገንባቱ ነገር እንዴት ይቀጥል የሚለውን ሚዛኑን አስጠብቆ መሄድ ያስፈልጋል። ከዚህ ውጪ በእያንዳንዷ ነገር የታሰሩ ሰዎች ስላሉ ብለን፤ ምርጫ አይካሄድም ወይንም ቢካሄድም ሕጋዊ አይሆንም ብሎ መናገር በጣም በጣም የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሥርዓት ይጎዳዋል። በዚህ መንገድ መሄድ የለበትም። ስለዚህ እኛ የፍትህን ጉዳይ ለሕግ ሰዎች፣ ለፍርድ ቤት፣ ለዐቃቤ ሕግ፣ ለፖሊስ ትተን፤ ፊት ለፊታችን ያለውን የሕዝብ ጥያቄ፣ የአገሪቱን ፖለቲካ የማዘመን ጥያቄ፣ ነጻ ፍትሃዊ ምርጫ የማድረግ ጥያቄ እንዴት አድርገን ሚዛኑን አስጠብቀን እናስኪድ የሚለውን መመልከት ይገባል። ስለዚህ የታሰሩ ሰዎች ስላሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተጎድቷል የሚል በፍፁም እንደ ፓርቲ አንቀበልም፤ እኔም በግሌ አልቀበልም። ቢቢሲ፡ አገራዊ ምርጫውን ለማካሄድ መንግሥት ምን ያህል ዝግጁ ነው። አገሪቱስ ምን ያህል ዝግጁ ናት? ዶ/ር ቢቂላ፡ በአጠቃላይ መንግሥት የመንግሥትነት ድርሻ ነው የሚወጣው። . . . የመንግሥትነት ድርሻ ማለት ከፀጥታ ጋር፣ ከሕዝብ ደኅንነት ጋር የተገናኙ የሕዝቡን ሰላም ማስጠበቅ፣ ምርጫ ለማካሄድ የሚሆን የፀጥታና የመረጋጋት ተግባርን ማከናወን የመንግሥት ሥራ ነው። ከዚህ ጋር በተገናኘ ምርጫን ለማካሄድ የሚሆን ተቋም እንዲቋቋም፣ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ በማድረግ ሂደት ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ለዚህ የሚያስፈልገውን ድጋፍ እንዲያደርጉ የማድረግ እንዲሁም ደግሞ ተቋማቱ ነጻና ፍትሃዊ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ፣ ሙያዊ ሥራቸውን እንዲሰሩ የማድረግ ሥራ ከመንግሥት ይጠበቃል ብለን ነው የምናምነው። ስለዚህም መንግሥት ከሌሎች ፓርቲዎች በተለየ ሁኔታ በእጅጉ ትልቅ ኃላፊነት አለበት ብዬ አስባለሁ፤ በዚያም አምናለሁ። ነገር ግን መንግሥት ብቻውን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሥርዓት ያሻሽላል ብዬ አላስብም። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ እጅግ ብዙ ተዋናዮች ናቸው ያሉት። እነዚህ ተዋናዮች ሁሉ የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ይሻሻላል ብዬ አምናለሁ። የኢትየዮጵያ ሰማይም ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ነጻነትና ልማት የነፈሰበት ይሆናል ብዬ አምናለሁ።
news-52560731
https://www.bbc.com/amharic/news-52560731
በእግር ኳስ በፌዴሬሽኑ ውሳኔ ላይ የክለብ አመራሮች ምን ይላሉ?
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የ2012 ዓ.ም ሁሉም የሊግ ውድድሮች መሰረዙን ትላንት አስታውቋል። ውድድሩ በመሰረዙም አሸናፊ እና ወራጅ ቡድን አለመኖሩን አስታውቆ፤ ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የኮንፌደሬሽን ካፕ ላይ እንደማትሳተፍ ገልጿል።
የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን በተከናወነበት ሊግ ቀሪ 13 መርሃ ግብሮች መካሄድ ይጠበቅባቸው ነበር። ይህም 45 በመቶ የሚሆነውን ውድድር ይሸፍናል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኘን ምክንያት በማድረግ የተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ የሊጉ ክለቦች ምን ይላሉ? የባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ፍቃዱ፤ የፌደሬሽኑን ውሳኔ የሰሙት ከመገናኛ ብዙሃን መሆኑን ጠቅሰው "የተወሰደው እርምጃ ጥሩ እና ወቅታዊ ነው" ሲሉ ይገልጻሉ። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት የፋሲል ከነማ ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዮት ብርሃኑ ናቸው። እንደ አቶ አብዮት ከሆነ "ከየትኛውም ነገር በላይ የሰው ልጅ ህይወት ስለሚበልጥ" ውድድሩ በመቋረጡ ላይ ቅሬታ የላቸውም። የመቀሌ 70 አንድርታ ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ተክለሃይማኖት ግን "የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ውሳኔ ወቅታዊ ነው። ቢሆንም እንደግለሰብ የውሳኔው ሂደት ላይ ቅሬታ አለኝ። አሰልጣኞችን በማነጋገር ብቻ ነው ጥናት ያደረጉት። የክለብ ኃላፊዎችን አላነጋገሩም። ከባለቤቱ መረጃ ማግኘት ነበረባቸው። ውሳኔው ላይ ቁንጽል መረጃ ነው የወሰዱት" ይላሉ። የባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ ልዑልም በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ። "ክለቦች የራሳቸውን ሃሳብ ያቀረቡበት ነገር ያለ አይመስለኝም፤ እንደክለብ ምንም አስተያት አላችሁ በሚል የቀረበ ነገር የለም። እንዲህ ቢሆን? ያለው ነገር የለም" ብለዋል። "የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ተነጋግረዋል" የሚሉት የፌደሬሽኑ ጊዜያዊ ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቶ ባህሩ ጥላሁን ናቸው። "የሊጉ አብይ ኮሚቴ ወይም ሼር ካምፓኒ ከሚመለከታቸው ክለቦች እና ከውድድርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ጋር እንዲወያይ አቅጣጫ ተሰጥቶት ነበር" ይላሉ። "እነዚህን ሂደቶች ተከትለናል። ሼር ካምፓኒው ከአብይ ኮሚቴ እና ከውድድርና ስነ-ርዓት ኮሚቴ ጋር በመሆን ምክረ ሃሳብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አቀረበ። ፌደሬሽኑ ደግሞ ከመንግስትም የተቀመጠውን አቅጣጫ በመመልከት ውሳኔ አስተላለፈ" ባይ ናቸው። "ከሊጉ ጋር የተያያዘውን ሼር ካምፓኒው ኃላፊነት እንዲወስድ የተደረገ ሲሆን አብይ ኮሚቴው ደግሞ ከክልቦች የተወጣጡ ስለሆኑ ተሳትፈዋል" ብለዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ክለቦቹን የሚወክለውን ሼር ካምፓኒ አናግሬያለሁ ቢልም ክለቦቹ ግን በዚህ ተቃራኒ ቆመዋል። "ሼር ካምፓኒ ተቋቁሟል እኛም አባል ነን። ካምፓኒው እና ፌደሬሽኑ ተነጋግረው ሊሆን ይችላል። ካምፓኒው ግን ክለቦቹን አላናገረም" ያሉት አቶ ልዑል ናቸው። አቶ ሽፈራውም ተመሳሳይ አቋም አላቸው። "ለግብር ይውጣ ሼር ካምፓኒ ቢያናግሩም እኛን ካማፓኒው ማናገሩን ማወቅ ነበረባቸው። ዓለም አቀፉ የእግርኳስ አስተዳዳሪ /ፊፋ/ ፍኖተ ካርታ ክለቦችን አናግራችሁ ለሃገር ተስማሚ የሆነ ውሳኔ ላይ እንድትደርሱ ብሏል። እኛ አስተዳዳሪ አካላችን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ነው። አወዳዳሪ አካላችን ደግሞ ሼር ካምፓኒው ነው። በቴክኖሎጂም ቢሆን ሃሰባችንን ማድመጥ ነበረበት" ብለዋል። ሌላው የውሳኔው ወቅታዊነት ላይ የሚቀርብ ጥያቄ ነው። የስፖርት ጋዜጠኛው መኳንንነት በርሄ እንደሚለው ያነጋገራቸው አብዛኛዎቹ ክለቦች በጉዳዩ ላይ ውይይት እንዳላደረጉ እንደገለጹለት አስታውቋል። ለዚህም "ክለቦችን ያላማከለ የሊግ ካምፓኒውንም የፈጠነ ይመስለኛል። አንዳንድ ክለቦችን ሳነጋግር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ሆነ ሊግ ካምፓኒው አላነጋገረንም የሚል ሃሳብ አንስተዋል። ክለቦች ሊግ መስርተዋል። ሊጉ ያለ ክለቦች ምንም ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ውሳኔው ትንሽ የፈጠነ ይመስለኛል።" የፌደሬሽኑ ጊዜያዊ ዋና ጸሐፊ አቶ ባህሩ "ካፍ እስከ ሜይ 5 [ሚያዚያ 27] ባለው የኢትዮጵያን የሊግ ሁኔታ አሳውቁን ብሎ ነበር" በማለት ያስረዳሉ። በሃገሪቱ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአምስት ወራት የሚቆይ መሆኑ እና በሽታው መቼ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚቻል አለመታወቁም ሌላው ጉዳይ ነው። አቶ ሽፈራው "የሚጠበቁ የተወሰኑ ውሳኔዎች ተካተዋል። የሊጉ ጨዋታዎች መሰረዝ ካለው ሃገራዊ ችግር አንጻር እሱ ላይ ብዙም አልተከፋሁም" ይላሉ። እንደ አቶ ሽፈራው፤ "ሰኔ ላይ ወረርሽኙ አለቀ ተብሎ ጨዋታዎች ይቀጥሉ ቢባል እንኳን ብዙ ፈተናዎች ሊጉን ይፈትኑታል። ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ እና የሃገሪቱ የመጫወቻ ሜዳዎች ለክረምት የሚሆኑ አለመሆናቸው፤ የብዙ እግር ኳስ ተጫዋቾች ውል ሰኔ 30 መጠናቀቁ፤ ጨዋታዎች ወደ መስከረም እና ጥቅምት እንዲተላለፉ ከተደረገ ደግሞ ብዙዎች በበጀት ምክንያት የሚሳካላቸው አይመስልም። "ጨዋታ መሰረዝ አንዱ አማራጭ ነው። በውድድሩ እስካሁን የማይናቅ ገንዘብ ቢወጣበትም። ወራጅም ወጪም የለም። በተለይ ወደ ላይ ለሚወጡት ክለቦች ብዙ በጀት አፍስሰው ተስፋ ቢያደርጉም መሰረዙን አልቃወምም። እስከዚህ ድረስ እስማማለሁ" ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልፃሉ። በውሳኔው ላይ ያላቸው ልዩነት ከዚህ ይጀምራል። "ሃገራችን የካፍ መስራች ሆና በአፍሪካ መድረክ አትሳተፍም ማለት ግን ስህተት ነው። 16 ክለቦች ማን ቢወክል ይሻላል በሚል በጥልቀት መወያየት ነው እንጂ ኢትዮጵያ አትሳተፈም ማለት ክለቦች የላትም የሚል ስለሆነ እሱ ላይ ተቃውሞ አለኝ" ብለዋል። በውድድሩ እነማን መሳተፍ አለባቸው በሚለው ላይ "ህጋዊ መንገዶችን ትቼ በቀላሉ ጠንከር ያለ ኢኮኖሚ ያላቸውን መላክ፣ በስምምነት የባለፈው ዓመት ውጤት ይዞ እነሱን ማሳተፍ ወይም እስካሁን ባለው ደረጃ ወይም ደግሞ በዕጣ መስጠት ይቻላል። ብዙ አማራጮች አሉ። በዕጣ በማድረግ ኢትዮጵያን ማዳን ይችሉ ነበር" ሲሉ ያስረዳሉ። ለስፖርት ጋዜጠኛው መኳንንት በርኼ ደግሞ የሌሎች ሃገራትን ተሞክሮ መመልክት አንዱ አማራጭ ነው። "ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ቡርኪና ፋሶ 1ኛ እና 2ኛ ሆነው የጨረሱትን ነው በሻምፒዮንስ ሊግ እና በኮንፈደሬሽን ካፕ እንዲሰለፉ ያደረጉት። ቡርኪናፋሶ አምና የተሳተፉትን ነው ያሳለፈችው። ክለቦቹ አቅም አለን እንጫወታለን ካሉ ተጫወቱ መባል ነው የነበረበት። ገዳቢ ይመስለኛል ውሳኔው" ይላል። የባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ፍቃዱ ግን የተለየ ሃሳብ ያነሳሉ። "በትክክል አፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ሆነ የኮንፈደሬሽን ካፕ ውድድሮች ይካሄዳሉ?" የሚል። ካልተካሄደ ውሳኔው ማስቀጠል ካልሆነ ግን ክለቦችን ባሳተፈ መልኩ የሌሎችን ሃገራት ልምድ ወስዶ መተግበርን ይመርጣሉ። እስካሁን ባለው የሊጉ ውድድር በ17 ጨዋታ ፋሲል ከነማ በ30 ነጥብ ሊጉን ይመራል። ሥራ አስኪያጁ አቶ አብዮት ውሳኔውን "እስካሁን ለደረስንበት ተገቢው እውቅና ካለመስጠቱ በተጨማሪ በአፍሪካ መድረክ ተወዳዳሪ የለም በሚል ፋሲልን ከውድድር ውጭ ማድረጉ ተገቢ አይደለም። ውድድሩ መቋረጡ ላይ ልዩነት ባይኖረንም በአፍሪካ መድረክ ጉዳይ ላይ ቅሬታ አለን" ይላሉ። በመጀመሪያ ሃገሪቱን ተሳትፎ በማቀጨጭ የተጫዋቾችንም እድገት የሚጎዳ ነው ብለውታል። "እንደ ካፍ መስራች እንደኬንያ እና ቡርኪና ፋሶ ካሉ ሃገራት የተለየ ውሳኔ መሰጠቱን የተሳሳተ መሆኑን ያሳያል። ሊጉን የሚመራው ፋሲል በዚህ ይጎዳል" ብለዋል። የፋይናነስ ቀውስ የሊግ ውድድሮች መሰረዙ ሌላው ያስከተለው ችግር የፋይናነስ ቀውስ ነው። በተለይ ደግሞ ከፍተኛ የስታዲየም ገቢ የነበራቸው ለዚህ ይጠቀሳሉ። እንደ አቶ ባህሩ ከሆነ ፌደሬሽኑ ፋይናንስን በተመለከተ መንግስት ለክለቦች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርቧል። "ኮቪድ በሊጉ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ላይ ፊፋ ጥናት አካሂዷል። ፊፋ ቀደም ሲል የለቀቀው የ500 ሺህ ዶላር ፈንድ ለሥራ ማስኬጃ ነው። የኢመርጀንሲ ፈንድ ለተወሰኑ ሃገራት ሊለቅ ይችላል። እኛም የዚህ አካል ልንሆን እንችላለን በሚል እየጠበቅን ነው። እንደዛ ከሆነ ለክለቦች ድጋፍ እናደርጋለን" ብለዋል። ስለቀጣይ ውድድር ዓመትም ተጠይቀው "በሚቀጥለው ዓመት የወረርሽኙ ጉዳይ መጨረሻው ካልታወቀ የ2013 ውድድርም ላይጀምር ይችላል" ያሉት አቶ ባህሩ "ስለዚህ ውሳኔው የኮቪድ-19 በቁጥጠር ስር መዋል እና አለመዋል ጋር የተያያያዘ ነው" ሲሉ ያስረግጣሉ።
news-50937543
https://www.bbc.com/amharic/news-50937543
በ2019 አፍሪካ ያጣቻቸው ታላላቆች
ሊገባደድ ጥቂት ቀናት በቀሩትየጎርጎሳውያኑ 2019 አፍሪካ ያጣቻቸውን ታላላቆች ቢቢሲ ዘክሯል።
ጥር ኦሊቨር ምቱኩድዚ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1970ዎቹ የዚምባብዌን የነጭ ጨቋኝ አገዛዝ በመቃወም የአብዮቱ ድምፅ የሆነው ኦሊቨር ምቱኩድዚ የዚምባብዌ ምሰሶ ተደርጎ ይታያል። በቅፅል ስሙ "ቱኩ" የሚታወቀው ስመ ጥሩው ዘፋኝ ከፖለቲካው በተጨማሪ ኤችአይቪ ኤድስ እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ ቀውሶችን በግጥሙ ውስጥ የሚያነሳ ሁለ ገብ አርቲስት ነበር። ሁዋሪ ማናር የአልጀሪያን የሃገረሰብ የባህል ሙዚቃ ወደፊት ማምጣት የቻለ፤ እንዲሁም አነጋጋሪ ጉዳዮችንም በሙዚቃው በመድፈሩም አልጀሪያውያን ያወሱታል። ህይወቱ ያለፈው የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና እያደረገ በነበረበት ወቅት ነው። ተችዎች በግጥሙ የሚያነሳቸው የማህበሩ ስስ ጉዳዮች መካከል የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ መካተቱን ያወግዙታል። አህመድ ሁሴን ሱዋሌ በጋናዋ መዲና አክራ በሚገኘው የወላጆቹ ቤት በተተኮሰበት ጥይት የተገደለው ታይገር አይ (የነብር አይን) የሚል መጠሪያ ያለው የምርምር ጋዜጠኞች ቡድን አባል ነበር። በጋና በእግር ኳስ ሊጎች ላይ የተንሰራፋውን ሙስና ያጋለጠም የምርምር ዘገባም ሰርተዋል። ፖሊስ ከስራው ጋር በተያያዘ እንደተገደለ እምነት አለው። የካቲት ቢሲ ሲልቫ ኮንቴምፖራሪ ተብሎ በሚጠራው የአፍሪካ ጥበብ ትልቅ ስፍራ ያላት ቢሲ ሲልቫ በሌጎስ 'ኮንቴምፖራሪ አርት ኢን ሌጎስ' የሚባል ማዕከል እንዲሁም አሲኮ የተባለ ለመላው አፍሪካዊ ስነ ጥበብን የሚያስተምር የትምህርት ስርአት መስራች ናት። በመላው አለም የአፍሪካን ስነጥበብ ስራዎች የሚያንፀባርቁ አውደ ርዕዮችን አሰናድታለች። በጎርጎሳውያኑ 2014 ጄዲ ኦክሃይ ኦጄኬሬ የተባለው ፎቶግራፍ ስራዎችን የመሰነድን ጠቃሚነት አስመልክቶ ቢቢሲ ባናገራት ወቅት እየሞቱ ያሉ ባህሎችና ልምዶችን ልንጠብቃቸው ይገባል ብላለች። ፍራንስ አልበርት ሬኔ ሲሸልስ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣቷን ተከትሎ በጎርጎሳውያኑ 1977 በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን ያዙ፤ ፍራንስ አልበርት ሬኔ ሲሸልስንም ለ27 አመታት ገዝተዋል። ደጋፊዎቻቸው በሶሻሊስት ርእዮተ አለም የተቃኘ ልማት አምጥተዋል ቢሏቸውም ተችዎቻቸው ግን ጨቋኝ ነበሩ ይሏቸዋል። ዶሮቲ ማሱካ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1950ዎቹ በደቡብ አፍሪካ ዝቅተኛው ማህበረሰብ ውስጥ በሙዚቃው አለም እንደ ጀግኒት የምትታይ ነበረች። የፖለቲካ ግጥሞቿም በአፓርታይድ አገዛዝ ዘንድ አልተወደደም፤ ብዙ ነገርም አስከፍሏታል። ዳንኤል ማላን ስለተባለው የአፓርታይድ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የኮንጎ መሪ የነበሩት ፓትሪስ ሉምምባ አገዳደል ጋር የተያያዙ ሴራዎችን በግጥሟ ውስጥ ማካተቷም ለሰላሳ አመት ግዞት ዳርጓታል። ካሮሊን ምዋታ ፖሊስ የሚያከናውናቸውን ግድያዎች አፈንፍኖ በመሰነድ የምትታወቀው ካሮሊን ምዋታ ለአምስት ቀናት ከጠፋች በኋላ አስከሬኗ በሌላ ሰው ስም ተመዝግቦ ተገኝቷል። ባለስልጣናቱም ህጋዊ ካልሆነ ፅንስ ማቋረጥ ጋር ሞቷን አያይዘውታል። አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቲ አምነስቲ ሞቷ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ነው ብሎታል። አለም አቀፍ ዝናን ያተረፉት ስመ ጥር ፀሃፊ ቻርለስ ሙንጎሺ ታላላቅ ሽልማቶችን ማሸነፍ የቻሉ ናቸው። 'ካሚንግ ኦፍ ዘ ድራይ ሲዝን' የተሰኘው የአጫጭር ታሪኮች ስብብ የሆነው መፅሃፋቸው እንደ ጎርጎሳውያኑ 1972 ዚምባብዌን ያስተዳድር በነበረው ቅኝ ገዥም ታግዶ ነበር። ክሪስ ካንታይ ካታንዳ በሚል ቅፅል ስሙ የሚታወቀው ራፐር በዘርፉ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት ሙዚቀኞች አንዱ ነው። በግጥሞቹና በአዘፋፈኑም ስታይል በጎርጎሳውያኑ 2000ዎቹ መግነን ችሎ ነበር። የካቲት የአፍሪካ ሲኒማ መስራች የሚባሉት ሜድ ሆንዶ በጎርጎሳውያኑ 1967 የሰሩት' ሶሌሊ' የሚል ርዕስ የተሰጠው ፊልምም በዘርፉ አድናቆትን ማትረፍ ችሏል። ታሪኩም አንድ ወጣት ስደተኛ በፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ የሚያጋጥመውን ዘረኝነት የሚተርክ ነው። ኦኬይ አፍሪካ እንደዘገበውም ለኤዲ መርፊና ሞርጋን ፍሪማንን የመሳሰሉ ታላላቅ ተዋናዮችን ጨምሮ በሆሊውድ ለሚሰሩ ፊልሞች የፈረንሳይኛ ድምፆችን ወክለውም ሰርተዋል። ኦክዊይ ኤንዌዞር ኦክዊይ ኤንዌዞር የአፍሪካ ጥበብ በአለም አቀፉ መድረክ ዘንድ እንደ ጥበብ በቁም ነገር ይወሰድ ዘንድ አስችሏል። በናጄሪያዋ ግዘት ካላባር የተወለደው ኦክዊይ ኤንዌዞር ትምህርቱን የተከታተለው በኒውዮርክ ነው። በኮንቴምፖራሪ የአፍሪካ ጥበብ ላይ የሚያጠነጥንም ኢንካ የተባለ መፅሄትንም የመሰረተው ከአስርታት አመት በፊት ነው። በ2015 የቬኒስ አውደ ርዕይን በ120 አመት ታሪክ ውስጥ በማሰናዳት (ኪውሬት በማድረግ) የመጀመሪያው አፍሪካዊ በመሆን ታሪክ ሰርቷል። በርናርድ ዳዲዬ በምፀታዊ ስራዎቻቸው የሚታወቁት በርናንድ ዳዲዬ በቅኝ ግዛት ወቅት የነበረውን ዕውነታ በስራዎቻቸው ማሳዬት ችለዋል። 'ድራይ ዩር ቲርስ' (እንባችሁን ጥረጉ) የሚለውም ግጥማቸውም ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ የቻለ ስራ ሆኗል ። በእንግሊዝኛ ቋንቋ በመፃፍ በአፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያው ከሆኑት አንዱ ጋብርዬል ኦካራ በተለይም በ1964 የፃፉት ዘ ቮይስ የሚለው ስራቸውም ብዙዎች አንብበውታል። ሲማሮ ሉቱምባ ለስስድስት አስርት አመታት ያህል የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሙዚቃ ዋልታና ማገር የነበሩት ሲማሮ የሙዚቃ ፀሃፊ፣ መሳሪያ ተጫዋች እንዲሁም አቀናባሪ ነበሩ። መሞታቸውም የዘመን ማብቂያ ነው ተብሎለታል። በካናዳ የሚገኘው የካርልተን ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ጥናት ማእከል ዳይሬክተር የነበረው ምሁሩ ህይወቱ ያለፈው ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በተነሳ በደቂቃ ውስጥ አደጋ በደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። ሚያዝያ ሪቻርድ ሙዞኮ በዲሞከራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቡቴምቦ ግዛት የኢቦላ ህመምተኞችን እያከመ በነበረበት ወቅት በተተኮሰበት ጥይት ነው ዶክተር ሪቻርድ ሙዞኮ ህይወቱ ያለፈው። አልፍሬድ ታባን ካርቱም ሞኒተር የተባለው የመጀመሪያው ነፃ የእንግሊዝኛ ጋዜጠኛ መስራችና ዋና አዘጋጅ ነበር፤ ደቡብ ሱዳን ነፃነቷንም ማግኘቷንም ተከሎ ጋዜጣው ጁባ ሞኒተር የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ጋዜጠኛው አልፍሬድ ታባን በሙያውም ምክንያት በተደጋጋሚ ዘብጥያ የመውረድ ገፈት ቀማሽ ሆኗል። ፓፒ ፋቲ ለረዥም ጊዜ በልብ ህመም እየተሰቃዬ የነበረው ፓፒ ፋቲ በስዋዚላንዷ ከተማ እስዋቲኒ እየተካሄደ በነበረው ጨዋታ ራሱን ስቶ ከወደቀ በኋላ ህይወቱ አልፏል። ግንቦት ቢንያቫንጋ ዋይናይና በአፍሪካ ስነ-ፅሁፍ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ የነበረው ቢንያቫንጋ በቋንቋው ውበት፣ በጠንካራ አቋሙ፣ በድፍረቱና አፍሪካንና ህዝቦቿን ማእከል ባደረገ ፅሁፎቹ ይታወቃል። ከነዚህም ፅሁፎቹ መካከል 'ዋን ደይ አይ ዊል ራይት አባውት ዚስ ፕሌስ'፣ 'ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ' ይገኙበታል። የምዕራቡ አለም ከአንድ ቢሊዮን በላይ ህዝቦች በላይ የሚኖሩባትን አህጉር በተለይም በፀሃፍያን ዘንድ የምትመሰልበትን መንገድ ሽሙጣዊ በሆነ መልኩ በፃፈበት "ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ (ስለ አፍሪካ እንዴት መፃፍ እንችላለን) በሚለው ፅሁፉ ቢንያቫንጋ ዋይናይና "የመፅሃፋችሁን ሽፋን በየቀኑ የምናገኛቸውን አፍሪካውያንን ፎቶ ሳይሆን ኤኬ 47 ጠመንጃን የተሸከመ፤ የሽምቅ ውጊያ የተራቆቱ ጡቶች፤ የገጠጡ አጥንቶችን አድርጉ" በማለት ምዕራባውያን ስለ አፍሪካ ሲፅፉ በተደጋጋሚ የሚያወጧቸውን ፎቶዎች በማየት በነገር ሸንቆጥ አድርጓቸዋል። በአርባ ስምንት አመቱ ህይወቱ ያለፈው ቢንያንጋ ተቃውሞን የማይሸሽ፤ ብቻውን መቆም የማይፈራ ግለሰብ ነበር። ፖለቲካውን በግል ህይወቱ እስከ መጨረሻው ድረስ የኖረ፤ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወንጀል በሆነባት ኬንያ፣ ስለ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የፃፈ፤ እንዲሁም በተደጋጋሚ ድፍረት የተሞላባቸውን ንግግሮች ያደርግ የነበረ ነው። ሬጂናልድ ሜንጊ በርካታ ቁጥር ያላቸው ጋዜጦችና የቴሌቪዝን ባለቤት የነበሩት ሬጂናልድ ሜንጊ በፎርብስ ግምት መሰረት ወደ 560 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት አከማችተዋል። ሰኔ ሞሃመድ ሙርሲ የቀድሞው የግብጽ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሙርሲ ፍርድ ቤት ውስጥ በድንገት ተዝለፍልፈው ከወደቁ በኋላ መሞታቸው የተዘገበው በዚህ አመት ነው። ሙርሲ እንደ አውሮፓዊያኑ በ2013 ነበር በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን የተነጠቁት። በግብጽ ታሪክ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይሁንታን ያገኙ የመጀመርያው ርዕሰ ብሔር ነበሩ። ያም ሆኖ አገሪቱን መምራት የቻሉት ለአንድ ዓመት ብቻ ነበር። የሕዝብ ተቃውሞን ተከትሎ በአልሲሲ የተመራ ወታደራዊ ኃይል ሥልጣናቸውን ነጥቋቸዋል። ሰዓረ መኮንን ሰኔ 15፣ 2011 ዓ. ም. የደረሰው ጥቃት፤ ከተሾሙ አንድ ዓመት ከጥቂት ቀናት ብቻ የሆናቸውን የአገሪቱን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን ሕይወት ቀጥፏል። ከሳቸው በተጨማሪ በጡረታ የተገለሉትና በወቅቱ በጄኔራል ሰዓረ ቤት የነበሩት ሜጄር ጄኔራል ገዛዒ ከጠባቂያቸው በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የሚመለከታቸው አካላት አስታውቀዋል። ጥቃቱ በደረሰባቸው ሰዓት አማራ ክልል የ"መፈንቅለ መንግሥት" ሙከራን ለማክሸፍ ሲሠሩ እንደነበርም ተገልጿል። ዴቪድ ኮሌን በጨቋኙ አፓርታይድ ግዛትም ሆነ ከዚያ በኋላ ለጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን መድረክ ያመቻቹ አርቲስት ነበሩ። ፀሃፊ፣ ሰዓሊና መምህር የነበሩት ዴቪድ ኮሌን የጆሃንስበርግ ዝቅተኛ ህይወትንም በስራዎቻቸው አንፀባርቀዋል። ሐምሌ ቦብ ኮሊሞር በምሥራቅ አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ስኬታማው ሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነበሩ ቦብ ኮሊሞር፤ ህይወታቸውም ያለፈው በካንሰር ምክንያት ነው። ቦብ ካሊሞር የካሪብያኗ ጉያና ሃገር ተወላጅ ሲሆኑ በዜግነት ደግሞ እንግሊዛዊ ነበሩ። ቦብ ኮሊሞር የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ሲሆን፤ በቆይታቸውም በሞባይል ስልክ ክፍያን መፈጸምን ጨምሮ ድርጅቱ በአካባቢው ሃገሮች ውስጥ ያለውን የመሪነት ደረጃ ጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ አስችለውታል። ኖምህሌ ኢንኮዬኔ በ1960ዎቹ ውስጥ አፓርታይድን በመቃወም ከታገሉት የጥበብ ባለሙያዎች አንዷ ስትሆን በኬፕ ፐርፎርሚንግ አርትስ ቲያትርም በመተወን የመጀመሪያዋ ጥቁር ናት። ማንድላ ማሴኮ ጠፈርተኛ በሚል ቅፅል ስሙ የሚታወቀው ማንድላ ማሴኮ በጠፈር ላይ በመውጣት የመጀመሪያው ጥቁር ሲሆን፤ ህይወቱ ያለፈው በሞተር ሳይክል አደጋ ነው። ሆዳን ናላያህ አብዛኛዎቹ መገናኛ ብዙኃን ሶማሊያን የጦርነት ቀጠና፣ ድርቅ እና ረሃብ የማይለያት፣ የእርዛትና ጥማት ተመሳሌት፣ እንዲሁም የእርስ በርስ እልቂት ምሳሌ አድርገው ነው የሚስሏት። አንዲት ሴት ግን ይህን ለመቀልበስ ተነሳች። ይህቺ ሴት ሆዳን ናላያህ ትባላለች። ትውለደ ሶማሊያዊ የሆነችው ሆዳን ከ6 ዓመቷ ጀምሮ ካናዳ ነው ያደገችው። ይሁን እንጂ ልቧ ሁሌም ሶማሊያ ነው ያለው። የሶማሊያን ውበት፣ መልካም ገጽታና የሕዝቧን ትስስር ለተቀረው ዓለም ለማሳየት ቆርጣ የተነሳች ሴት በመሆኗ ከዓመት በፊት ከካናዳ ወደ ሶማሊያ ተመለሰች። ዓላማ ያደረገችው በዓለም ላይ እንደ አሸዋ የተበተኑ ሕዝቦቿን በተለይም ውጭ አገር ያደጉ የሶማሊያ ወጣቶችን ማነቃቃትና አገራችን እንዲወዱ ማድረግ ነበር። የሞተችውም በደቡባዊ ሶማሊያ በአንድ ሆቴል ላይ በደረሰ ጥቃት ነው። ቤጂ ካይድ ኤሴቢሲ በአለም ትልቁ ፕሬዚዳንት በመሆን ቱኒዝያን ለዘመናት መርተዋል። ነሐሴ ካካማን ካካማን በሚል ስም የሚታወቀው የስድስት አመቱ ህፃን ዳርሲይ ኢራኮዜ በኢንተርኔትና በቲያትር ቤቶች በሚያቀርባቸው ኮሜዲ ሥራዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፤ ህይወቱ ያለፈው በወባ በሽታ ነው። ዳርሲይ ከታዋቂው ብሩንዲያዊው ኮሜዲያን ኪጊንጊ ጋር ባለፈው ነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ተውኗል። ከጊኪንጊ ጋር በድጋሜ የኮሜዲ ሥራዎችን ለማቅረብም እቅድ ይዞ እንደነበር ተገልጿል። ኡይኔኔ ምርዌትያና በወቅቱ የኬፕታውን ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበረችው ኡይኔኔ ምርዌትያና እቃ ለመውሰድ ፖስታ ቤት አቅንታ በነረበት ወቅት የቀድሞ የፖስታ ቤት ሰራተኛ ደፍሮ በብረት ዘንግ ገድሏታል። የተማሪዋ መሞት በኃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፤ ብሔራዊ የተቃውሞ ሰልፍም ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቀጣይዋ እኔ ነኝ በሚል ሃሽታግም በኃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አጋልጧል። ጆን ደ ማቲው የኩኩዩ ሙዚቃ ንጉስ መጠሪያ ያገኘው ጆን ደ ማቲው የሞተው በመኪና አደጋ ነው። የ33 አመቱ ዲጄ አረፋት ወይም አንጂ ዲዲየር የሞተው በሞተር አደጋ ነው። ፈረንሳይኛ በሚናገሩ ሃገራት ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈው ዲጄ አረፋት የአይቮሪኮስት የዳንስ ሙዚቃ ተብሎ በሚጠራው ኩፔ ዴካልም ንጉስ የሚል ስያሜም ማትረፍ ችሏል። በዘናጭነቱ የሚታወቀው ሙዚቀኛው ፈጣን የሆነ የከበሮ ምት፣ ሂፕሆፕ ቅላፄ ባለው ዘፈኖቹ ብዙ አድናቂዎችን ማትረፍ ችሏል። ዳውዳ ጃዋራ ጋምቢያን ለሶስት አስርርት አመታት አንቀጥቅጠው የገዙ መሪ ነበሩ። መስከረም ሮበርት ሙጋቤ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1924 የተወለዱት ሮበርት ሙጋቤ የእንጨት ሠሪ ልጅ ናቸው። የተማሩት በሮማን ካቶሊክ ሚሽነሪ ትምህርት ቤት ነበር። ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ፎርት ሀሬ ዩኒቨርስቲ ነፃ የትምህርት እድል አግኝተው ከተማሩ በኋላ፤ ጋና ውስጥ መምህር ነበሩ። በህመም ሳቢያ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሙጋቤ ዚምባብዌ ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የመጀመሪያው መሪ ናቸው። ሙጋቤ አገራቸው ዴሞክራሲ የሰፈነባት እንደምትሆን ቃል ገብተው ነበር። ያሉት ግን አልሆነም። ዚምባብዌ በግጭት የምትናጥ፣ በሙስና የተጨመላለቀች፣ ኢኮኖሚዋ የተናጋ አገር ሆነች። ቼስተር ዊልያምስ ከሁለት አስርት አመታት በፊት ብቸኛው ጥቁር ራግቢ ተጫዋች ነበር። ዛይን ኢል አባዳን ቢን አሊ ቱኒዚያን ለሁለት አስርታት በኃያል ክንዳቸው የገዟት ዛይን ኢል አባዳን ቢን አሊ በ83 ዓመታቸው ያረፉት በዚህ አመት ነው። ቢን አሊ ህልፈታቸው የተሰማው በጥገኝነት ከኖሩባት ሳኡዲ አረቢያ ነው። ፕሬዚዳንቱ ቱኒዝያን ለ23 አመታት ያህል የገዙ ሲሆን መረጋጋትና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማምጣት ይወደሳሉ። ነገር ግን ፖለቲካዊ ነፃነትን በማፈንና ሙስና በተንሰራፋ ስርአታቸውም በከፍተኛ ሁኔታ ይተቻሉ። በጎርጎሳውያኑ 2011 የህዝቡን አመፅ ተከትሎም ከስልጣን ተገርስሰዋል። ጥቅምት አይዛክ ፕሮሚስ የናይጄሪያ ብሄራዊ ቡድን ሱፐር ኤግልስ አምበል ነበር። አንዲሌ ጉምቤ ሲምባን በቲያትር ቤቶች ለአስር አመታት ተጫውቷል። በርናርድ ሙና በሩዋንዳ በደረሰው ዘር ጭፍጨፋ የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ምክትል አቃቤ ነበሩ። ህዳር ቦጋለች ገብሬ በልጅነታቸው በግርዛት ምክንያት ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል። ሦስት ጊዜ ያህል ከተደረገባቸው የጠለፋ ሙከራ አምልጠዋል። ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቱ በእርሳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በእህቶቻቸውም ላይ ደርሶ ሁለቱን እህቶቻቸውን በግርዛት ምክንያት በሞት አጥተዋል። በእስራኤል አገር በሂብሪው ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የትምህርት ዕድል አግኝተው 'ማይክሮ ባዮሎጂ' እና 'ፊዚዮሎጂ' አጥንተዋል። ከዚያም በአሜሪካ አገር በማሳቹሴትስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲም በ'ኢፒዲሚዎሎጂ' ሦስተኛ ድግሪያቸውን አግኝተዋል። በ1989 ዓ.ም ወደ አገራቸው በመመለስ በእርሳቸው ላይ ሲደርስ የነበረው በደል በሌሎች ላይ እንዳይደርስ ለመሞገት ከምባታ ጠንባሮ ዞን የተጀመረውን እና 'ከምባቲ ሜንቲ ጌዝማ' [ኬ ኤም ጂ] ወይንም የከምባታ ሴቶች ራስ አገዝ በመባል የሚታወቀውን አገር በቀል ድርጅት መስርተዋል። ድርጅቱ በአካባቢው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን ከግርዛት እንደታደገ ይነገራል። "ያልተገረዘች ሴት ባል አታገኝም" የሚለውን የአካባቢውን የቆየ ልማድ ታግሎ፤ የነበረውን የግርዛት ሽፋን 3 በመቶ እንዲወርድ ያደረገ ታላቅ ተግባር ማከናዎናቸውን ብዙዎች ይናገሩታል። ፆላኒ ግዋላ ጋዜጠኛው ከካንሰር ጋር የሚያደርገውን ትግል በመናገሩ ብዙዎች የሚያደንቁት ግለሰብ ነበር። ኢማስ ኤልማን በሞቃዲሾ በበራሪ ጥይት የሞተችው ኢማስ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነበረች።
news-54507780
https://www.bbc.com/amharic/news-54507780
ኢትዮጵያ፡ አካል ጉዳተኛው የቴኳንዶ ስፖርት አሰልጣኝ
ከማል ቃሲም የተወለደው ጎንደር ከተማ ነው። በህጻንነቱ ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ወደ ወረታ አመሩ።
የቴክዋንዶ ሦስተኛ ዳንን በአንድ እግር ማግኘት የቻለው ከማል ቃሲም "ተጫዋችና ደስተኛ" ነበርኩ የሚለው ከማል በአምስት ዓመቱ የገጠመው አደጋ ህይወቱን እስከወዲያኛው ቀይሮታል። "ጉዳት የደረሰብኝ በ1985 ዓ.ም ነበር። ወረታ ውስጥ ከእኩዮቼ ጋር ስጫወት በመንግሥት ሽግግር ወቅት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ በተተወ ታንክ ነው ጉዳት የደረሰብኝ።" በወቅቱ የአምስት ዓመት ታዳጊ የነበረው ከማል ታንኩ ላይ እየተጫወተ ሳለ "አፈሙዙን በሚያሽከረክረው ክፍተት መሐል አንድ እግሬ ሆኖ ለመሻገር ስሞክር አንደኛው እግሬ አፈሙዝ ስር ገባ። በዚያው ቅጽበት አፈሙዙ በሚዞርበት ጊዜ እግሬ ላይ አደጋው ደረሰ" ሲል ያስታውሳል። ከወረታ ወደ ባሕር ዳር ለህክምና ተወስዶ ለወራት እዚያው ከቆየ በኋላ ወደቀየው ተመለሰ። በድንገተኛው አደጋ ጉዳት የደረሰበት ታዳጊው ከማል ከህክምናው ሲመለስ ቀኝ እግሩ ጉልበቱ ላይ ተቆርጦ በሁለት ምርኩዞች ተደግፎ ነበር። "ህይወት እንደ አዲስ ተጀመረ። ያኛው ሌላ አሁን ደግሞ ሌላ ህይወት" የሚለው ከማል "በአካባቢያችን ሌላ አካል ጉዳተኛ አልነበረም። እንኳን በዚያ ወቅት አሁን እንኳን ማኅረሰቡ ውስጥ ስለአካል ጉዳተኝነት ያለው አመለካከት ፈታኝ ነበር። መውጣት መግባት መጫወት አልችልም ነበር" ይላል። በታዳጊነቱ በደረሰበት አደጋ አካል ጉዳተኛ የሆነው ከማል ተደራራቢ ችግሮችን መጋፈጥ ጀመረ። ሌላ ችግር ቤተሰቡ ውስጥ ተከሰተ፤ አባት እና እናቱ ተለያይተው በተለያየ ቦታ በየፊናቸው ህይወታቸውን ለመምራት ሲወስኑ፤ እሱም ከእናቱ ተለይቶ ከአባቱ ጋር መኖር ጀመረ። አደጋው ከደረሰበት በኋላ ከማል ሰባት ዓመት ሲሆነው ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ጀመረ። ነገር ግን "ሙሉ ለሙሉ ህይወቴ ስለተቀየረ ትምህርት ቤት እረብሽ፣ እነጫነጭ ነበር" ሲል በጸባዩ ላይ ለውጥ መከሰቱን ያስታውሳል። ለአካል ጉዳተኞች የሚመች መሠረት ልማት አለመኖር እና ህብረተሰቡ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው አስተሳሰብም ህይወቱን ከባድ አድርጎት ነበር። "ከባድ ነው። ትምህርት ቤት ነጻ ሆኜ መጫወት አልችልም። ትልልቆቹም ባለፍኩ ባገደምኩ ቁጥር ከንፈር መምጠጥ፤ በዚህ እድሜው እንደዚህ ሆኖ እያሉ ሲናገሩ መስማት ተስፋ ያስቆርጣሉ" ይላል። በሁለት ክራንች መንቀሳቀስም መጫወትም አልመችህ ሲለው አንዱን ክራንች በመተው እንደልቡ ለመሆን ሞከረ። በዚህም ለመንቀሳቀስ በሚያደርገው ሙከራ በተደጋጋሚ በመውደቅ እግሩ መጎዳት እና መድማት ይገጥመው ጀመር። በዚህ መልኩ እስከ ስድስተኛ ክፍል ወረታ ውስጥ ተማረ። በወቅቱ "ጸባዬ አስቸጋሪ እረባሽና አልቃሻ ሆኜ። ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፍኩት። ከልጆች ጋር ጋር መግባባት እየተቸገርኩ እጣላ ነበር። አንዳንድ ጊዜም በክራንች እስከመማታት እደርስ ነበር" የሚለው ከማል 6ኛ ክፍል ሲደርስ ወደ እናቱ ተመልሶ ጎንደር መኖር ጀመረ። ጎንደር ሌሎች የአካል ጉዳተኞችን ተዋወቀ ስለዚህም ከወረታ ብቸኝነቱ በተወሰነ ደረጃ ተላቀቀ። ነገር ግን እናቱ ሥራ ስላልነበራቸው የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚያገኙት አንድ አካል ጉዳተኞችን ከሚረዳ ድርጅት ነበር። "ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን ስንዴ እና ዘይት በችግር ላይ ለነበረችው እናቴ አመጣላት ነበር። እዚያ ሌሎች አካል ጉዳተኞችን ባገኝም ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ነበር። የዝቅትኝነት ስሜት ይሰማኝ ጀመር" የሚለው ከማል 'ረጂ እንጂ ተረጂ አልሆንም' ብሎ እርዳታውን መቀበል አቆመ። ስምንተኛ ክፍል ደርሶ ለማለፍ የሚያስችለውን ውጤት ባለማምጣቱ ለመድገም ተገደደ። በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሠው ሠራሽ እግር ለማሠራት ወደ ደሴ አምርቶ ለወራት እዚያው በመቆየቱ ስምንተኛ ክፍልን በማታው ክፍለ ጊዜ መማር ጀመረ። የማታ ተማሪ መሆኑ እንዲሁም ቀን ላይ የሚሰራው ነገር ስላልነበረው አጋጣሚው ከቴኳንዶ ስፖርት ጋር እንዲተዋወቅ ዕድል ፈጠረለት። ከጓደኛው ጋር ቴኳንዶ የሚሰራበት ቦታ በመሄድ ስፖርቱን የተመለከተው ከማል፤ ለሰዓታት ከተመለከተ በኋላ አንዳች ነገር ውስጡ ተፈጠረ። ከማልን የተመለከተው የቴኳንዶ አሰልጣኙ ስሜቱን ጠይቆት ፍላጎት ካለው በነጻ እንዲማር ስለፈቀደለት በቴኳንዶ ፍቅር ወደቀ። "እየወደቅኩ እየተነሳሁ ከምንም በላይ በአስተማሪዬ ድጋፍ እና በጓደኞቼ አይዞህ ባይነት ቴኳንዶውን መለማመድ ቀጠልኩ" ነገር ግን በዙሪያው ካሉ ሰዎችና ከቤተሰቡ ጭምር 'ምን ያደረግልሃል?' ይሉት ነበር። ሆኖም እንዳሰበው ቀላል አልነበረም። ከወላጆቹ በስተቀር ሁሉም 'ምን ሊያደርግልህ?' የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ተስፋ አስቆራጭ አስተያት ሰጥተውታል። "በአንድ እግር ቴኳንዶ ከባድ ነው። ወድቄ እሰበራለሁ። እጄን ተሰብሬያለሁ። የቀረችውን አንድ እግሬን ተሰብሬ 2 ወር በተኛሁበት ጊዜ የነቀፉኝ ሰዎች ደስ አላቸው። እኔ ግን እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ስፖርቱን ከመሥራት ማንም እንደማያግደኝ አወቅኩኝ።" ከማል ቴኳንዶ መጀመሩ ብዙ ነገሮችን እንዲለውጥ ምክንያት ሆኖታል። አንደኛው ደግሞ ክራንቹን የሚጠቀምበትን ዘዴ መቀየሩ እና በሚመቸው መንገድ እንዲያስተካክለው ማድረጉ ነው። "ክራንቹ መጀመሪያ ላይ ብረት ብቻ ነው። ቴኳንዶ ይህንን ምቹ እንዳደርግ ረድቶኛል። ይኸውም እንደጫማ ምቹ አድርጌ እንድሠራ አድርጎኛል። እንደጀመርኩ እግሬን ሳነሳ ክራንቹ ተሰብሮ ወድቄያለሁ። ሳስተምርም ወደቄ አውቃለሁ። የውሃ ቱቦ ነው በየጊዜው ቼክ አደርገዋለሁ። በየጊዜው እቀይረዋለሁ አሁን በምቾት እሠራለሁ።" ቴኳንዶ በተለያዩ የቀበቶ ቀለሞች የሚሰጡ ደጃዎች አሉት። ጀማሪዎች በነጭ ቀበቶ ይጀምራሉ። ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ቀይ እና ጥቁር። እነዚህን ቀበቶዎች አንድ ሰልጣኝ የተለያዩ የስልጠናዎችን ካጠናቀቀ በኋላ ከአሰልጣኙ የሚያገኘው ይሆናል። ከዚያ በኋላ ደግሞ በዲግሪ የሚገለጹና ዳን የሚባሉ ዘጠኝ ደረጃዎች አሉ። ዳን የሚሰጠው በአሰልጣኝ ሳይሆን በቴኳንዶ ማኅበራት የተግባርና የጽሁፍ ፈተና ሲታለፍ ከኮሪያ የሚሰጥ ነው። "ወደ ሦስተኛ ዳን ዲግሪ ደርሻለሁ። የሚሻሻሉ ዲግሪዎች ናቸው። አሁን 3ኛ ዳን አለኝ። በዚህ ዓመት አራተኛውን ላገኝ እችላለሁ። ጊዜው ደርሷል" ይላል ከማል በቴኳንዶ የደረሰበትን ደረጃ ሲገልጽ። "ለእኔ ሲባል ምንም የተለየ የሚደረግልኝ ነገር የለም" የሚለው ከማል በዚህ ሂደት ውስጥ ሁሉ የተለያዩ ጉዳቶች ቢገጥሙትም ወደኋላ አላለም። ሦስተኛ ዳን የፈተኑት የውጭ አገር ሰዎች እንደነበሩ የሚኣስታውሰው ከማል፤ የሚተበቅበትን ካከናወነ በኋላ ፈታኞቹ ቆመው እንዳጨበጨቡለት ይናገራል። "የተፈተንነው 15 ነበርን፤ ስድስቱ ወደቁ። ዘጠኛችን አለፍን። የእኔ ውቴት ጥሩ ነበር። ቴኳንዶ የሚጠይቀውን የሥራ የፓተርን ሙሉ ሠርቼ ነው ያገኘሁት" ነው በማለት ተወዳድሮ ፈተና በማለፍ አሁን ላለበት መብቃቱን ይጠቅሳል። ከማል ቴኳንዶን ለሌሎች ማስተማር በሚያስብበት ጊዜ አካል ጉዳተኛ የቴኳንዶ አስተማሪ ስለሌለ 'ይሳካልኝ ይሆን?' እያለ ጥርጣሬ ቢገባውም የጓደኞቹና የአስተማሪው ማበረታቻ ድጋፍ ሆኖት በ2002 ዓ.ም ወረታ ውስጥ የማስተማሪያ ማዕከል ከፍቶ ማስተማር ጀመረ። ሆኖም እንዳሰበው ቀላል አልነበበረም። ለማስተማር የሚረዳውን ፈቃድ አላገኘም። መንቀሳቀሻ የሚሆን በቂ ገንዘብ እጁ ላይ አልነበረውም። ለመንቀሳቀሻ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘትም ፎቶውን አስር አስር ብር ሸጦ ወደ ሁለት ሺህ ብር ገደማ ሲያገኝ ሥራውን ጀመረ። "ማስታወቂያ ስለጥፍ ግራ ገባቸው። 'ማነው የሚያስተመረው አሉኝ?' ሰዉ ለመማር ፈቃደኛ አልሆነም። የማውቃቸውን ጠርቼ በነጻ ማሠራት ጀመርኩኝ። አዳራሽም ዘመድ ፈቀደልኝ። አራት ወይም አምስት ሰው ይዤ ስሠራ ሌላው ሰው አዳራሽ ሞልቶ ያይ ነበር" ይላል። ከዚያም ሰልጣኞች መምጣት ሲጀምሩ ፈቃድ ማውጣት ስለነበረበት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ በመፈተን በተግባርና በጽሑፍም አንደኛ በመውጣት ፈቃድ ማግኘቱን ይናገራል። ከስድስት ወር የቴኳንዶ ስልጠና በኋላ 40 ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ። የተለያዩ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች የገጠሙት ከማል ቃሲም ከወራታ ፓዌ ከዚያም ወደ ባሕር ዳር በመሄድ ስልጠና ሰጥቷል። በ2007 ዓ.ም ላይ አዲስ አበባ በተዋወቀው አንድ የውጭ አገር ዜጋ አማካይነት ባገኘው ድጋፍ ወደ ጀርመን በመሄድ ሰው ሠራሽ እግር ሲሰራለት በዚያውም የአንድ ወር ስልጠና አግኝቷል። ከማል ለዓመታት በዘለቀው የቴኳንዶ ስፖርት ህይወቱ የተለየ ደስታ የፈጠረለትን አጋጣሚ "የመጀመሪያዋውን ጥቁር ቀበቶ ስቀበል ነው" ሲል ያስረዳል። ባለትዳር እና የልጅ አባት የሆነው ከማል በቀጣይ ለቤተሰቡ "ጥሩ ነገር መስጠት" እንዲሁም የቴኳንዶ ስልጠና ሥራውን የበለጠ የማጠናከር አላማ አለው። ከዚህ በተጨማሪም በግል ህይወቱ ዙሪያ መጽሐፍና ዘጋቢ ፊልም ማዘጋጀት ይፈልጋል። አሁንም ብዙዎች ቴኳንዶ መሥራቱን እንደሚጠራጠሩ የሚናገረው ከማል "ለሰዎች ፎቶዬን ሳሳያቸው በፎቶ ጥበብ የተዘጋጀ ነው ይሉኛል። እኔም ወስጄ በተግባር እሰራሁ አሳያቸዋልሁ።" በቴኳንዶ ስፖርት ከ15 ዓመት በላይ የቆየው ከማል በወረታ፣ በፓዌ እና በባሕር ዳር በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰልጥኗል። በተጨማሪም በዘርፉ ውድድር ባይኖርም የተለያዩ መድረኮች ላይ ትዕንቶችን በማቅረብ ሽልማቶችን አግኝቷል። በመላው ኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች በሚሳተፉበት የፓራሎምፒክ ውድድር ላይ ደግሞ የአማራ ክልልን በመወከል በጦርና አሎሎ ውርወራ፤ በተሽከርካሪ ወንበር እንዲሁም ክብደት ማንሳት ተሳትፎ ከሃያ በላይ ሜዳሊያዎችን አጥልቋል። በቅርቡ በተመሠረተው የተሸከርካሪ ወንበር የቅርጫት ኳስ ውድድርም ተሳታፊ በመሆን ላይ ይገኛል። ከስፖርቱ ጎን ለጎን ከማል ቃሲም የተሽከርካሪ ወንበር ተጠቃሚዎችና የእግር አካል ጉዳተኞች ማኅበር ሊቀ መንበር በመሆን ያለውን ልምድ በማካፈል ላይ ይገኛል።
news-44852682
https://www.bbc.com/amharic/news-44852682
ተዘግቶ ለ20 ዓመታት በቆየው የኤርትራ ኤምባሲ ውስጥ ምን ተገኘ?
በ1990 የድንበር ጦርነቱ ሲቀሰቀስ አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት አስርታት ተዘግቶ ከቆየው የኤርትራ ኤምባሲ በሮች በኤርትራ ባለስልጣናት ሲከፈት ክፍሎች ውስጥ በአቧራ የተሸፈኑ መኪኖች፣ የቤት ውስጥ እቃዎች እና የተለያዩ መጠጦች ባሉበት ተገኝተዋል።
ቢራ፣ ወይንና የወይራ ዘይት የያዙ ጠርሙሶችም ተገኝተዋል ጦርነቱ በ1992 ቢያበቃም ግንኙነታቸው ሻክሮ እስካሁን ድረስ ቆይቶ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ኤርትራ መጓዛቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ነው ኤምባሲው መልሶ የተከፈተው። እነዚህ ፎቶግራፎች የኤርትራ ኤምባሲ ዛሬ ሲከፈት በቢቢሲ የተነሱ ናቸው። እነዚህ መኪኖች በኤምባሲው ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ ባሉበት ቆይተዋል በእነዚህ ወንበሮች የመጨረሻው የኤርትራ አምባሳደር ይገለገሉበት ነበር በኤምባሲው ክፍሎች ውስጥ ከተገኙ የቤት መገልገያዎች ውስጥ ይህ አልጋ ይገኝበታል። የኤምባሲው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የታደሙ የማርሽ ሙዚቃ ቡድን አባላት ፕሬዝዳንት ኢሳያስና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኤምባሲውን የውስጥ ክፍል ሲመለከቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተገኙበት የኤርትራን ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ከ20 ዓመታት በኋላ ኤምባሲውን ከፍተዋል የፎቶግራፎቹ ባለቤትነት መብት በሕግ የተጠበቀ ነው
news-41029285
https://www.bbc.com/amharic/news-41029285
ጉንዳኖች የሚረጩትን ንጥረ-ነገር በመጠቀም የሚንቀሳቀሰው አዉቶብስ
የተወሰኑ ተማሪዎች ከተለዋጭ ታዳሽ ነዳጆች ይልቅ ተግባራዊና የበለጠ ተግባራዊ እና ዘላቂነት ያለው ኃይል ለማከማቸት የሚያስችል መፍትሔ ኣግኝተዋል ።
የቲም ፋስት አባላት ለኣብነት የሠሩት አውቶብስ ብልሆቹ ወጣቶች ዓለምን በኣንድ አዉቶብስ በመጀመር ቀስ በቀስ ዓለምን የመለወጥ ፍላጎት እንዳላቸዉ ገልጸዋል ። ከኤይንድሆቨን የቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር የተቆራኘ "ቲም ፋስት" ከተሰኘ ኩባንያ የመጣዉ ሉካስ ቫን ካፕሊለን ፈጠራቸዉን እንዲህ በማለት ገልጿል " የሃይድሮጂን ዓይነት ግልጋሎት ያለዉ፤ ነገር ግን እጅግ በጣም ርካሽ መፍትሄ ሆኖ የሚያገለግለውን የዓለምን አውቶቡስ ሠርተናል" በመቀጠልም "የራሳችንን የወደፊት ሕይወት እየገነባን ነው" ብሏል። አብረዉት የሚማሩትም 40 የሚሆኑት ተማሪዎች በከባቢ አየር ላይ የሚከሰተውን ዓለም አቀፋዊ ትግል ለማገዝ የሚረዳውን የነጻ ኃይል ማጓጓዣ አማራጮችን ለማልማት ጥረት እያደረጉ ነው። እነሱም ወደፊት የራሳቸውን ሥራ የመሥራት ፍላጎት ስላላቸዉ በዚህ ዘርፍ ባለሙያ ለመሆን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ፎርሚክ አሲድ በመባል የሚታወቀዉ አሲድ በተፈጥሮ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እሱም በጉንዳኖች እና በሌሎች ነፍሳት መንደፊያ በኩል የሚተላለፍ ሲሆን የጉንዳን የላቲን ቃሉ ደግሞ "ፎርሚካ" በመባል ይታወቃል። በተጨማሪም ይህ ቀላል የካርቦክሲሊክ አሲድ (በኬሚካላዊ አወቃቀሩ ኤች ሲ ኦ ኦ ኤች የተሰኘዉ) በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳ ምርት ማቀነባበሪያ ድርጅቶች፣ የከብቶች ምግብ ከመበላሸት እንዲከላከልና ኣንዳንድ ግዜም ደግሞ የቤት ቧንቧ ሻጋታ ማስወገጃዎች ውስጥም ይገኛል። በኃይድሮዛይን የተሞላዉ ተጎታች በአውቶብሱ የጀርባ ኣካል ላይ ይያያዛል የቲም ፋስት ቡድን አሲዱ በቀላሉና በጥሩ ሁኔታ ለሃይድሮጂን የነዳጅ ሴሎች የሚስፈልጓቸዉን ነገሮችና የኤሌክትሪክ መኪናዎች የሚጠቀሙበትን ኃይል ማጓጓዝ የሚቻልበትን መንገድ አግኝተዉታል። ይህም ነዳጅ ቡድኑ እንደሰየመዉ ኃድሮዛይን የነዳጅ ፈሳሽ ሲሆን ከተለመደዉ ነዳጅ ጋር ሲነጻጸር በቀላሉ ማጓጓዝና ተሽከርካሪዎችን ለመሙላት ጊዜ የማይፈጅ ነዉ። በዋነኝነት ይህንን ነዳጅ ልዩ የሚያደርገዉ ደግሞ በጣም ንፁህ መሆኑ ነው። ቫን ካፕሊን እንደገለፀው "የጭስ ማዉጫዉ ካርቦን ዳይኦክይሳድና ውሃ ብቻ ብቻ ነዉ የሚያስወግደዉ" በመቀጠልም "እንደ ናይትሪክ ኦክሳይድ፣ጥላሸት ወይም ሰልፈሪክ ኦክሳይድ የመሳሰሉ ሌሎች ጎጂ ጋዞችን ኣያስወግድም" ይህንን ጽንሰ ሃሳብ ኣዋጪነት ለማረጋገጥ በኔዘርላንድ አንድ የኤሌክትሪክ አውቶብስ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ በተለመዱት የአውቶብስ መስመሮች፣ በንግድ ሥራዎችና በኢንዱስትሪ ኤግዚብሽን ማዕከል ለእይታ ይቀርባል። ቪዲኤል በመባል የሚታወቀዉ የአውቶቡስ ኣምራች የዚህን አውቶብስ የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያዉን የሠራ ሲሆን አውቶብሱ ተጨማሪ ኃይል ከኋላዉ በሚገኘዉ ተጎታች ፎርሚክ አሲድ በማግኘት ይጓዛል። "300 ሊትር የመያዝ ኣቅም ስላለዉ የአውቶቡሱን መስመሮችን በ 200 ኪ.ሜ (180 ማይል) እናራዝማለን ፤ ሆኖም የታንኩን የመያዝ ኣቅም በቀላሉ መጨመርም እንችላለን" በማለት ቫን ካፕሊን ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል። ኤሌክትሪከ መኪና ወይስ አውቶብስ ? በአሁኑ ወቅት የአውቶቡሶች የሃይድሮጂን ነዳጅ ሴሎች እስከ 400 ኪ.ሜ መንገድ የመሄድ ኣቅም አላቸው ። ይሁን እንጂ መኪና ከመሆን ይልቅ አውቶቡስ መነደፍ ያለበት ለምንድን ነው? "መኪና ከሠራን ከኤሌክትሪክ መኪና ከሚሠሩ ድርጅቶች ጋር ልንወዳደር ነዉ ነገር ግን በባትሪ ኃይል የሚሄዱ መኪኖች ለብዙ ሰዎች ጥሩ መፍትሄ እንደሆኑ እናምናለን" በማለት ቫን ካፕሊን ሓሳቡን አካፍሏል። "ይሁን እንጂ የአውቶቡስ ኩባንያዎችን ፍላጎት የሚያሟላ አውቶቡስ እስከ 400 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችልና በፍጥነት ነዳጅ የሚሞላ አዉቶቡስ ማቅረብ እንደምንችል ብናሳይ ግን የሃይድሮዛይንን አቅምና ዘላቂነት ውድድር በሌለበት አሳየን ማለት ነዉ" በማለትም ጨምረው ተናግረዋል። ሃይድሮዛይን የሚፈጠረዉ በውሃ (ኤችቱኦ) እና በካርቦን ዳይኦክሳይድ (ሲኦቱ) በሚደረገዉ የኬሚካል ልዉውጥ ነው ። "በሃይል ማመንጫው ውስጥ ውሃና ካርቦን ዳይኦክሳይድ የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም ይጣበቃል፤ይህ ቀጥተኛና ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኬሚካላዊ ሂደት ነው" በማለት ቫን ካፕለን ያስረዳል ። ሃይድሮዛይኑ በሌላ ኃይል ወደ ሃይድሮጅን እና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ተከፋፍሎ በመቀየር እሱም ቲም ፋስት የፈጠራ ፈቃድ ለማግኘት እየሞከሩለት ባለዉ ሪፎርመር ብለዉ በሰየሙት መቀበያ ዕቃ ዉስጥ ይገባል ። ይህ አዲስ ሪፎረመር ከዚህ በፊት ከተለመዱት ሪፎርመሮች ለየት የሚያደርገዉ በአንድ አስረኛ የሚያንስ ሆኖ በዚህም ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ተግባራዊ መሆን ችሏል። ከዚያም ሃይድሮጂኑ ወደ ነዳጅ ክፍል ዉስጥ ተጨምሮ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ከኦክሲጂን ጋር እንዲዋሃድ ይደረጋል እሱም ለመኪናዉ ሞተር ኃይል ማመንጨት ይጀምራል ። አየር በማይበክል ነዳጅ የሚሽከረከሩ አውቶብሶች በከተማው መንገዶች እየበዙ ነዉ የቪዲኤል ኢኔብሊንግ ትራንስፖርት ሶሉሽንስ ሥራ ኣስኪያጅ የሆኑት ሜኖ ክሌይንጌልድ ድግሞ "አየር የማይበክሉ ኣዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ ለማስፋፋት ያለማሳለስ እየፈለግን ነዉ" ብለዋል ። ቀጥሎም "የፎርሚክ አሲድ ወደ ሃይድሮጅን መከፋፈል ከተስፋ ሰጪዎቹ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መሃል አንዱ ነው" በማለትም ገልጸዋል ። ጥያቄው ይህ ቴክኖሎጂ ግን በርግጥ ይሳካል ማለት ነዉ? "በዓለም ከሚገኙት የተለመዱትን የነዳጅ ማደያዎች ወደ የሃይድሮዛይን ማደያዎች ለመቀየር ወደ 35,000 ዩሮ (1 ሚልየን የኢትዮጵያ ብር ገደማ) የሚፈጅ ሲሆን ይህም ደግሞ ቧንቧዎቹን መተካትና ታንከሮቹን መከላከያ ቀለም መቀባትን ያካትታል " ይላል ቫን ካፕለን። "በአሁኑ ጊዜ ኔዘርላድ ዉስጥ ሃይድሮዛይን ከቤንዚን ነዳጅ ቢረክስም ከናፍጣ ግን ይወደዳል፤ ወደፊት ደግሞ ዋጋዉ እየቀነሰ ይመጣል ብለን እናስባለን" ብሏል። ምንም እንኳን ይህ አውቶቡስ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ቢያመነጭም ቲም ፋስት ግን ከኣየር ወይም ከጭስ ማዉጫ እንደመሳሰሉት ካሉ ምንጮች ሃይድሮዛይን ለመሥራት ስለሚጠቀሙበት ተጨማሪ ካርቦን ዳይኦክሳይድ እንደማያመነጩ በማሳወቅ የገጠመ የካርቦን ዑደት እንደሆነ ገልጸዋል ። ኣንዳንድ የጉንዳን ዘሮች ኣራሳቸዉን ለመከላከል ፎርሚክ ኣሲድ ያመነጫሉ አንዳንድ ባለሙያዎች ቴክኖሎጂው ተስፋ እንዳለዉ ያምናሉ ። የደች ኢንስትትዩት የኃይል ምርምር ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ቫን ዲ ሳንደን "ቲም ፋስት ጥሩ ሥራ ነዉ የሠሩት" ብለዋል ። "እጅግ በጣም አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ላይ ነዉ የሚሠራው፤ እሱም ታዳሽ ኃይልን ተጓጓዥ በሆነ መልኩና መጠቀም በሚቻልበት መንገድ መሠራቱ ነዉ" በማለትም ተናግረዋል ። በርካታ ኩባንያዎችም ፕሮጀክቱን ደግፈዋል። የተማሪዎቹ ቁርጠኝነት እጅግ አስደናቂ የሚያስደንቅ ነዉ ከ 40ዎቹ መካከል 15ቱ ሙሉ ጊዜያቸዉን ሰዉተዉ እዚህ ፕሮጄክት ላይ እየሠሩ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በሳምንት ከ 20 እስከ 325 ሰዓታት ይሠራሉ ። ለዚህ ፕሮጄክት ከዩኒቨርስቲዉ ምንም ዐይነት ነጥብ እንደማያገኙበት በተለይም ደግሞ የተሟላ እዉቀት ከዩኒቨርሲቲ ብቻ እንደማይገኝና ተግባራዊ ሥልጠናዎች ኣስፈላጊ እነደሆኑም ቫን ካፕለን ይናገራል። " የራሳችን የወደፊት ሕይወታችንን እየገነባን ነዉ " በማለትም ያጠቃልላል ።
news-51396025
https://www.bbc.com/amharic/news-51396025
ኮሮናቫይረስ፡ "ጭንቀት ላይ ነን" ኢትዮጵያዊቷ ከቻይና ውሃን
በቻይናዋ የዉሃን ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ዘርፍ ትምህርቷን አጠናቃ፣ ለአንድ ሴሚስተር ማንዳሪን ቋንቋ ለመማር በሚል ቆይታዋን ያስረዘመችው ሶልያና አረጋዊ፤ ወደ አገሯ የመመለሻ ቀኗን የቆረጠችው በዚሁ ወር ነበር።
ለአራት ዓመታት ያህል በታሪካዊዋ በጎርጎሳውያኑ 1893 የኪንግ ስርወ መንግሥትን ይመራ በነበረው ዛንግ ዚዶንግ የተመሰረተችው፣ ጥንታዊቷ የቻይና ዚኪያንግ ተቋም የአሁኗ ዉሃን ዩኒቨርስቲ ውስጥ የማይረሳ ጊዜም ነበራት። የመጨረሻ ሳምንታቶቿን አንዳንድ የቀሯትን ነገሮች በማጠናቀቅ ላይ እያለች ነው አዲስ አይነት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያጠቃው፣ ከአራት መቶ ሰዎች በላይ ህይወትን በነጠቀው ኮሮናቫይረስ ምክንያት ካለችበት ከተማ መውጣት እንደማትችል ያወቀችው። •የኮሮናቫይረስ ስጋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ •በኮሮናቫይረስ ከተጠረጠሩ አራት አዲስ ሰዎች አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ ተገለፀ ከሳምንታት በፊት ትኩሳት (ፊቨር) እንደተከሰተና ጥንቃቄ አድርጉ፣ ጭምብል አጥልቁ የሚባሉ መልዕክቶች መተላለፍ ጀምረው የነበረ ቢሆንም እንደዚህ የከፋ ደረጃ ደርሶ ከአገር መውጣትና መግባት ይከለከላል ብላ ሶልያና አላሰበችም። አስራ አንድ ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት፣ ስምንተኛዋ ትልቋ የቻይና ከተማና የንግድ መናኸሪያዋ ዉሃን ፀጥ ረጭ ብላለች። በያንግትዜና ሃን ወንዞች የተከፋፈለችው፣ የብዙ ሐይቆችና ፓርኮች የጥንታዊት ቻይና ስልጣኔ መገለጫ የሆነችው ዉሃን በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተወረረች ከተማ መስላለች። በቱሪስቶች የሚሞሉት ሙዚየሞች፣ በቡድሂስት አማኞች ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ጉያን ቴምፕል (ምኩራብ)፣ በነዋሪዎቿ ዘንድ ልብን የሚሰርቀው የዉሃን ያንግትዜ ድልድይ፣ እነ ሰመር ሃውስ ፒዛ ባር፣ ዳሚያኖ የጣልያን ሬስቶራንት፣ አሎሃ፣ አቶሚየም ጭር ብለዋል። ከዉሃን ዩኒቨርስቲ በሃያ ደቂቃ የምትገኘውና በማንታቀላፋው በሶልያና 'ዳውን ታውን' ሰፈርም እንቅስቃሴ ከጠፋ ሰነባበተ፤ ሶልያናም እየለመደችው ይመስላል። "ድሮ ማታ ላይ ተኝቼ ራሱ መኪና ማለፍ አያቆምም፤ ውይ መተኛት ከባድ ነበር። ሁልጊዜም ሲያልፉ እንደቀሰቀሱኝ ነው። አሁን መኪናም የለም። ያስፈራል፤ የሞተች ከተማ መስላለች። እንዴ ዉሃን እንደዚህ ነበረች ወይ እንላለን?" ትላለች። የሶልያና ሰፈር ብቻ አይደለም። ከተለያዩ አገራት በመጡ ቢያንስ ሦስት ሺህ ተማሪዎች የምትጨናነቀው ዉሃን ዩኒቨርስቲ እንቅስቃሴ አይታይባትም፤ ተማሪዎች ዶርማቸውን ከርችመዋል። ኑሮ፤ መንቀሳቀስ በማይቻልባት ዉሃን ቤት ውስጥ ቁጭ ማለት የማትወደው ሶልያና ያሁኑን አያድርገውና ዉሃንን ከጫፍ ጫፍ አዳርሳታለች። ብዙ ጓደኞችንም አፍርታባታለች። የተለያዩ ዝግጅቶችም ሲኖሩም ሶልያና አትቀርም። በአሁኑ ሰዓት ግን ድንገተኛ ካልሆነ መኪናም ሆነ ሞተር መንዳት በከተማዋ ውስጥ ክልክል ነው። ከተማው ውስጥ የተመደቡት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት ጥቂት ናቸው። ከቤት መውጣትና መንቀሳቀስ ከተማዋ ውስጥ ባይመከርም ክልክል አይደለም፤ "ግን ወጥቼስ የት እሄዳለሁ ትላለች ሶልያና?" ሁሉ ነገር ዝግ ነው በሰዓት ወስነው ከሚከፍቱት እነ ዋልማርትን ከመሳሰሉ ትልልቅ መደብሮች በስተቀር፤ ሆነም ቀረም ጭምብል ሳያጠልቁ እንቅስቃሴ ብሎ ነገር የለም። ሶልያናም ሙሉ በሙሉ የሚያስፈልጓትን ግብይቶችን የምትፈፅመው የተለያዩ ድረገፆችን በመጠቀም ነው። •ኬንያ ተማሪዎቿን ከቻይና ዉሃን ከተማ ልታስወጣ ነው •ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን በስምንት ቀናት ሆስፒታል ገነባች ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ ባለባት ዉሃን መንቀሳቀስ ከተከለከለ ሁለት ሳምንት ሊደፍኑ ነው፤ ቀኑስ ለሶልያና እንዴት ያልፋል፣ ይመሻል፣ ይነጋልስ? ከእንቅልፏ የምትነሳው አርፍዳ ነው፤ በሱም የተወሰነውን ቀን ትገፋዋለች። 'ዳያሪዋ' ላይ ትፅፋለች፣ ማንበብ የምትፈልጋቸውን መፃህፍትና ጊዜ በማጣት የተወቻቸውን እያነበበች እንደሆነም በሳቅ በተሞላ ንግግሯ ገልፃለች። ፊልም ማየት፣ ጓደኟቿ ጋር ማውራት፣ ቤተሰብ ጋር በመደወል መመለሻዋን በመናፈቅ ቀናቱን እያሳለፈች ነው። "ወይ ቁጭ ብለሽ ታነቢያለሽ፤ ስልክ ታወሪያለሽ፤ መውጣት ብትፈልጊም ስለማትችይ ያው ቢሰለችም ምን ማድረግ ይቻላል" ትላለች። ሶልያና ምንም እንኳን ከቤተሰቦቿ ጋር በቀን ሁለት ጊዜ የምታወራበት ጊዜ ቢኖርም ያለችበትን ሁኔታ አያምኑም። "ቀን በቀን ነው የሚደውሉት፤ እናም ምን አዲስ ነገር አለ ትባያለሽ? ያው ምንም የለም፤ አትጨነቁ ደህና ነኝ፤ ሁሉ ነገር አለኝ እላቸዋለሁ" የምትለው ሶልያና ከውጭ ሆኖ ለሚያየው ሁኔታው ቢያስፈራም "እኔ እዚህ ስላለሁ ሁሌም አልደነግጥም። ይለመዳል" ትላለች ቀለል አድርጋ። በመጀመሪያ ስለቫይረሱ ለቤተሰቦቿ አልነገረቻቸውም ነበር፤ ምክንያቱም በአንድ ሳምንት ውስጥ ተዘግቶ ሁሉ ነገር ይሻሻላል በሚል ግምት፤ ዜና ላይ ሲሰሙ ደወሉላት ብታስረዳቸውም ጭንቀቱ አልለቀቃቸውም። ለእናቷ በተለይ ልጃቸውን ማረጋጋትም ሆነ እሷ ጋር መደወል በቂ አልነበረም፤ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሄዳቸውን በፈገግታ ሶልያና ትገልፃለች። " እዚህ አስፈላጊ የሚባሉ መረጃዎች መምህሮቻችንም ሆነ ዩኒቨርስቲው ስለሚሰጡን፤ አትሂጂ እያልኳት ነው የሄደችው" እናቷም አሻፈረኝ ብለው ጥያቄዎቻቸውን ጠይቀው፤ ስልክም ተቀብለው መጥተዋል ። "ያው እንደ ወላጅ ያስጨንቃል፤ ምክንያቱም ምንም ማድረግ የማትችይበት ሁኔታ ሲሆን ትንሽ ያሳስባል" ትላለች። የተማሪዎች ስጋትና መልሱን ጥያቄ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሺህ በላይ መሆን በተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። ምንም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ኢትዮጵያውያን ባይኖሩም፤ ወደ አገራችን መልሱን በሚሉ በሺዎች በሚቆጠሩ አፍሪካውያን ተማሪዎች ተሞልታለች። ድምፃቸውን በዩኒቨርስቲው ግቢ እየተንቀሳቀሱ አይደለም እያሰሙ ያሉት፤ ሰውን በመፍራት፣ ቫይረሱን በመፍራት ኢንተርኔትን መርጠዋል። ከሰው ጋር ንክኪ የሚያስፈራበት ዘመን፤ የኢትዮጵያውን ተማሪዎችም በዚሁ ግራ መጋባት ውስጥ ናቸው። በዉሃን ዩኒቨርስቲ ከሦስት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ያሉ ሲሆን፤ በሁቤይ ግዛት ውስጥ በሚገኙ ከተሞችም ያሉ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ400 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች አሉ። በዉሃንም ሆነ በአካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች እንቅስቃሴ የተገደበ ስለሆነ ብቸኛው የመገናኛ መንገዳቸውም በኢንተርኔት መልዕክት በመላላክ ነው። ሶልያና ከተማሪዎች ማደሪያ ውጭ ተከራይታ በራሷ ስለምትኖር ሁኔታዎችን ቀለል ቢያደርግላትም በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚያድሩ ተማሪዎች ምግብ፣ ውሃም ሆነ ሌሎች ቁሳቁሶች ቢቀርብላቸውም አንዳንዶች ቸልተኝነት እንዳለባቸው ከኢትዮጵያውያኑ ሰምታለች። ተማሪዎቹ የቡድን (ግሩፕ) ቻት ስላላቸው ያሉበትን ሁኔታ፣ ስጋታቸውን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ይቀያየራሉ። "አንዳንድ ተማሪዎች ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳልሆኑ ይናገራሉ። ትምህርት ቤቱ ቸልተኝነት በማሳየቱ ወይም የሚገባቸውንና የሚያስፈልጋቸውን ባለመስጠቱ ይሆናል" ትላለች። የምግብ እጥረት፣ የህክምና ቁሳቁሶች ለምሳሌ የጭምብል እጥረት በተደጋጋሚ የሚነሱ ጉዳዮች ነበሩ። በሆዋጆንግ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ቴክኖሎጂ በሲቪል ኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት የዶክትሬት ተማሪ የሆነችውና በቻይና ዉሃን ውስጥ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ዘሃራ አብዱልሃጅ በበኩሏ እነዚህ እጥረቶች የአንድ ሰሞን ችግር እንደነበሩ ነው። አንድ ሰሞን የጭምብል እጥረት አጋጠመ በተባለበት ወቅት ህብረቱ ሪፖርት አድርጎ ፋርማሲ ሄደው መግዛት እንዲችሉ መመቻቸቱንና፤ የምግብ አቅርቦት ችግር አለ ከተባለም እንዲሁ ህብረቱ በሚያሳውቅበት ወቅት የቻይና መንግሥት ምላሽ ፈጣን መሆኑን ነው። •ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? •ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? ምንም እንኳን በሁቤይ ግዛት ሁሉም ሰው እንቅስቃሴውን እንዲያቋርጥና፣ በቤቱ እንዲገደብ ቢወሰንም የቻይና መንግሥትም ማንኛውንም እርዳታ ለመለገስ መዋቅር ተዘርግቷል። ቫይረሱን ለመግታት ከፍተኛ ዘመቻ ላይ እንደሆኑ ሶልያናም ሆነ ዘሃራ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ሲሆን በእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የውጭ አገር ተማሪዎችን የሚንከባከቡበትን ሁኔታም አድናቆቷን ዘሃራ ችራለች። የቻይና መንግሥት በእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ ነፃ ምግብ ከማቅረብ በተጨማሪ የተማሪዎቹን ጉዳይ ለመቆጣጠር ፕሮፌሰሮች ተመድበዋል። ከዚህም በተጨማሪ ያሉበትን የጤና ሁኔታ እንዲሁም ያለባቸውን ችግር ሌሎችንም ጉዳዮችን ለመከታተል ዓለም አቀፍ ቢሮዎች አሉ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ደግሞ ችግር በሚፈጠርበት ወቅት የሚወያዩበት እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን የሚያንሸራሽሩበት የቻት [የውይይት] ቡድን አላቸው። አንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ችግር በሚፈጠርበት ወቅት ህብረቱ ለቆንስላው ሪፖርት ያደርጋሉ፣ ያ ፅህፈት ቤት ደግሞ ለዉሃን ባለስልጣናት ያሳውቃል፤ እነሱም የተዘረጋውን የራሳቸውን መዋቅር በመጠቀም ዩኒቨርስቲው ጋር ግንኙነት ይፈጥራሉ። የሚያስፈልጓቸውን የምግብ አቅርቦት የጤና ቁሳቁሶችን በሟማላት ላይ የነበሩ ቢሆንም ነገር ግን በየዕለቱ ከሚሰሙ ዜናዎች ሁኔታዎች እየከፉ በመሄዳቸው ተማሪውን እንዲረበሽ አድርጎታል። ተማሪዎቹ እስከመቼ በዚህ ሁኔታ እንቀጥላለን? ወደ አገራችን ብንሄድ? የሚሉ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ መነሳቱን ተከትሎ ህብረቱ ተማሪዎቹን እንዲያስወጣ ጥያቄያቸውን ለኤምባሲ አስገብተዋል። "የተማሪው እንቅስቃሴው ስለተገደበ በራሱ የሚያስጨንቅ ነገር አለው። ግፊትም ስለበዛብን ኤምባሲው እንዲያስወጣን ጥያቄውን አቅርበናል" ትላለች ዘሃራ። በተለይም አሜሪካና ፈረንሳይን የመሳሰሉ አገራት ዜጎቻቸውን ማውጣታቸውን ተከትሎ ሌሎች የእስያ አገራት ተማሪዎቻቸውን ወስደዋል። ያ ሁኔታ በራሱ ግፊት እንደፈጠረ ዘሃራ ታምናለች። ሶልያናም ሆነ ዘህራ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር መጨመር እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ያሉበት ጭንቀት ተማሪዎቹ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ነው የሚጠቅሱት። "ተማሪው ከቤተሰቡ ጋር ሲያወራ፤ ቤተሰብ ይጨነቃል የሚሰማው ነገር በጣም ከባድ ነው፤ ስለዚህ እስከመቼ ነው እንደዚህ የምንቆየው 'ኳረንታይን' መደረግ ካለብን እንደረግ ከቤተሰቦቻችን መቀላቀል ይሻለናል" በማለት በተደጋጋሚ እንደሚናገሩ ዘሃራ ትናገራለች። ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ መልስ ይሰጠን እያሉ እየጠየቁ ሲሆን ማህበሩም "ታገሱን ዝግጀት ይፈልጋል። ኤምባሲውም የራሱ የሆነ ሂደት አለው፤ የውጭ ጉዳይም እንዲሁ፤ ይህንን ሂደት እየተጠባበቅን ነው ያለነው" የሚል ምላሽም በመስጠት ላይ ናቸው። ሆነም ቀረም "ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች በጣም አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን እያሰቡ እንዲጨነቁ አልፈልግም፤ ከራሳቸው ዜጋ ባልተናነሰ መልኩ ክትትል እየተደረገልን ነው" በማለት ቤተሰቦች መረጋጋት አለባቸው ትላለች። ሁሉም ሰው በጭንቀት ላይ እንደሆነ የምትናገረው ሶልያና "ምክንያቱም መልስ እየጠበቅን ነው፤ ለምንም ነገር መዘጋጀት አለብን፤ እሱ ላይ ትንሽ ግራ ስለተጋባን፤ አብዛኞቻችን መወዛገብ ሁኔታ ላይ ነን" ትላለች። በተለይም ህብረቱ ደብዳቤ ካቀረበ በኋላ ኤምባሲው ምላሽ አለመስጠቱ ለሶልያናም ሆነ ለተማሪዎቹ አሳሳቢ በመሆኑ ሶልያና ጉዳዩን ወደ ትዊተር በመውሰድ ለሚመለከታቸው አካላት "እባካችሁ መልስ ስጡን" በማለትም ጠይቃለች፤ ተማፀናለች። በትዊተርም ምላሽ ስጡን ብላ ትዊት ካደረገች በኋላም ብዙዎች በጎ ምላሽ ቢሰጧትም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፀጥታ አስጨንቋታል። ከአራት መቶ በላይ ተማሪ ማስተናገድ ቀላል እንዳልሆነና ጫናውንም ብትረዳም "ዝም ከማለት ምንም አይነት ምላሽ ይሻላል" ትላለች። በአብዛኛው እየቀረበ ያለው ጥያቄ ከዉሃን ታስወጡናላችሁ ወይ? ከሆነስ እንዴት ነው የሚሆነው የሚል ነው? ተማሪዎቹን ከዉሃን ማስወጣት ከተቻለ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዝግጅት ምን ይመስላል? ምክንያቱም ሙቀት መለካት ብቻ ሳይሆን በሽታው ሳይገለጥ 14 ቀናት ሊቆይ ስለሚችል፤ የክትትሉ ሁኔታ ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። ሌሎች አገራት በለይቶ ማቆያ ለአስራ አራት ቀን እንደሚያስቀምጡ ኢትዮጵያስ ያንን ትከተላለች ወይ የሚሉት ጥያቄዎችም የተማሪዎቹ መወያያ ሆኗል። የምርመራ ሁኔታው ምን ይመስላል? ተመርምረው ቫይረሱ ከተገኘ ኢትዮጵያ በቂ ህክምና የማድረግ ዝግጅቱም ሆነ ብቃቱ አላት ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች በተማሪዎች ዘንድ እየተንሸራሸሩ ነው። ይህ የተማሪዎቹ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አፍሪካ የተረጋገጠ የኮሮናቫይረስ በሽታ ቢያጋጥማት ያላት ዝግጅት ላይ ስጋት እንዳለው ገልጿል። "ተማሪዎችን ካወጣሽ እነዚህን ሁሉ ተሟልተው መሆን አለበት፤ ይህ ባልተሟላበት ሁኔታ ማውጣት ችግር ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ቫይረሱ ይኑርብሽ አይኑርብሽ ላታውቂ ትችያለሽ፤ እዚህ ተጋላጭ ነን" የምትለው ሶልያና ነገር ግን ተማሪዎቹን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለማቆየት ዝግጅት ካለ መውጣቱን ትመርጣለች። "ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል የመቆየቱ ሁኔታ ተማሪዎቹን የበለጠ እያጋለጣቸው እንጂ የሚጨምረው ነገር የለም" በማለትም ተማሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ታስረዳለች። ምላሽ ቢሰጣቸው ነገሮችን ያቀላል የምትለው ሶልያና "እናስወጣችኋለን ከተባለ ዝግጅት ታደርጊያለሽ፤ አይሆንም ከተባለም ምግብ እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ወደ ማከማቸት ትሄጃለሽ" ትላለች። ቀድሞም ለመዘጋጀት፣ ቲኬትም ለመግዛት፣ የቤት ኪራይ ልክፈል አልክፈል የሚሉ ጥያቄዎችም እንዲሁ መነጋገሪያ ጉዳዮቻቸው ከሆኑ ከራረሙ። የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቻይና ምክትል ሚሽን መሪ የሆኑት አቶ ገነት ተሾመ የተማሪዎቹ ጥያቄ በማህበሩ በኩል እንደቀረበና፤ አጠቃላይ ሁኔታውንም እየገመገሙት እንዳሉና የቻይና መንግሥትም ሁኔታውን ለመቆጣጠር አበክሮ እየሰራ ከመሆኑ አንፃር ተማሪዎቹ ከቤት እንዳይወጡ ምክር እየሰጧቸው ነው። "በእኛም አገር በኩል ይሄ ዝግጅትም፣ ውሳኔም ይጠይቃል፤ ዝም ብለን ከዚህ ማውጣት አይቻልም ፤ መጀመሪያ መውጣታቸው መታመን አለበት፤ በቂ ኳረንታይን ያስፈልጋል የሚያስፈልጋቸውን መሰረታዊ ፍጆታዎች ምግብና መገልገያዎች ለተማሪዎቹ በነፃ እየቀረበ ነው" ብለዋል። የተማሪዎቹን የመውጣት ፍላጎት ጉጉት ቢገባቸውም፤ ከተማው በኳረንታይን የሚቆየው እስከ ጥር ሰላሳ ከመሆኑ አንፃር መንቀሳቀስ ሲፈቀድ ነገሮች እንደሚስተካከሉ አቶ ገነት ተስፋ ያደርጋሉ። ሁሉንም ነገር አጠናቃ በዚህ ወር ወደ አገሯ ለመጓዝ ቲኬቷን ቆርጣ የነበረችው ሶልያና እስካሁን በቫይረሱ የተያዘ ሰው ባታውቅም፤ ጉንፋንም ሆነ ሙቀት ሰው ሲሰማቸው ያለው ድንጋጤ ከፍተኛ ነው። ያለው የአየር ፀባይ ብርድ ከመሆኑም አንፃር ጉንፋን ሰው በሚታመምበት ወቅት እንዲሁም ምልክቶቹም ስለሚመሳሰሉ በድንጋጤ በተደጋጋሚ ድንገተኛ ቁጥሮችን ይደውላሉ ትላለች። "የሆነ ቀን ሳስነጥስ ደንግጨ ነበር፤ የሌለ ጥርጣሬ ነው የሚፈጥረው።" •አባቱ በኮሮናቫይረስ የተጠረጠረው አካል ጉዳተኛ ታዳጊ ሞተ የጤና ተቋማት የኮሮናቫይረስን በማከም በከፍተኛ ሥራም ስለተጠመዱ እንዳው ማንኛውም ስሜት ሰው ስለተሰማው ተዘሎ አይኬድም፤ ድንገተኛ ተደውሎና ምልክቶቹን እርግጠኛ ካልሆኑ ዝም ብሎ መሄድም አይመከርም። ቻይና ኮሮናቫይረስን ለማከም ከአቅሟ በላይ መሆኑ እየተነገረ ሲሆን በብቸኝነትም በሽታውን ማከም የሚችሉ ሆስፒታሎችን ገንብታለች። በተለይ ሶልያና ትምህርቷን ከማጠናቀቋ አንፃር እንዲሁም ለመመለስ በዝግጅትም ላይ ስለነበረች መቼ ነው ሊሻሻል የሚችለው? የሚለውን እርግጠኛ አለመሆን፣ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር እንዲሁም ሌሎች አገሮችም ላይ እየተከሰተ መሆኑ የሚያሳስቧት ጉዳዮች ናቸው። "ትጨነቂያለሽ ራስሽን ደግሞ ያንን ያህል አታስጨንቂውም፤ ያው ያለሽበት ሁኔታ ስለሆነ ችለሽ ትቀጥያለሽ። ያው መቆጣጠራቸው አይቀርም፤ ግን ጊዜ ይፈጅባቸዋል ብዬ አስባለሁ።"
news-49814330
https://www.bbc.com/amharic/news-49814330
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሃላፊ ተዘረፉ
ዜጎችን ከዘራፊዎችና ከነጣቂዎች መታደግ የፖሊስ ቀዳሚ ሃላፊነት ቢሆንም ፖሊሶችም እንኳን ለሌላ ለራሳቸው መሆን አቅቷቸው የቀማኛ ሲሳይ የሚሆኑበት አጋጣሚም አልፎ አልፎ አይጠፋም።
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አዛዥ ጀነራል ኬህላ ሲቶልም ያጋጠማቸው ይህው ነው። ሌቦች ከፖሊስ አዛዡ መኖሪያ ቤት በመግባት ሁለት ቴሌቪዥኖችን ይዘው ጠፍተዋል። ምፑማላንጋ በተኘ ግዛት ውስጥ በግንባታ ላይ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲዘረፍ የፖሊስ አዛዡ ኬፕታወን ውስጥ ነበሩ ተብሏል። የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት መኖሪያ ቤታቸው ሲዘረፍ የፖሊስ አዛዡ እየተበራከተ ያለውን ወንጀል ለመከላከል በሚሰራ ስራ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ነበሩ። • በደቡብ አፍሪካ በየቀኑ 57 ሰዎች ይገደላሉ • በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ
news-50191992
https://www.bbc.com/amharic/news-50191992
በዶዶላ ቤተክርስቲያናት ተጠልለው የሚገኙ ምዕመናን ስጋት ላይ መሆናቸውን ገለፁ
ባሳለፍነው ረቡዕ በተለያዩ ቦታዎች የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በምዕራብ አርሲ፤ ዶዶላ ከተማ በተፈጠረ ግጭት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የተላኩ ሁለት ግለሰቦችን ጨምሮ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ከነዋሪዎችና ከሆስፒታል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
• ዶዶላ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት የ4 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በሌሎች ከተሞችም ተቃውሞው ቀጥሏል • ወደ ኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለፀ የዶዶላ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ እየበሩ ዓለሙ ላለፉት አራት ቀናትም በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በከተማዋ በሚገኙ ቤተክርስቲያናት ተጠልለው እንደሚገኙ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በዚህም ጨቅላ ሕፃናት፣ እናቶች፣ ነፍሰጡር ሴቶች፣ አረጋዊያን እና ሕሙማን የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸውን ይናገራሉ። የቤተ ክህነቱ ፀሐፊ ዲያቆን ደለለኝ ማሞ በበኩላቸው ባነጋገርናቸው ወቅት በሚገኙበት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁለት እናቶች ያለ ህክምና እርዳታ መውለዳቸውን ነግረውናል። "ጭንቀት ውስጥ ነን ያለነው" በዶዶላ ከተማ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው ከሚገኙት መካከል ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀችን የሦስት ቀን አራስ ትገኛለች። ይህች እናት ረቡዕ ዕለት ወጣቶች ከፊት ለፊታቸው የነበሩ ቤቶችን ሲያቃጥሉ አይተው እግሬ አውጭኝ ብለው እንደሸሹና ሕይወታቸውንም ለማቆየት ቤተክርስቲያኗ ውስጥ እንደተጠለሉ ታስረዳለች። "ወደኛ በኩል ድንጋይ ሲወረውሩ፤ በጓሮ በኩል አጥር ቀደን ወጣን፤ ምንም ሳንይዝ እያለቀስን ነው የወጣነው፤ በሰው ግቢ በኩል እየተረማመድን ወደ ቤተክርስቲያኗ መጣን" ትላለች። የነበረው ሁኔታ በጣም አስፈሪ ነበር የምትለው አራሷ የተገላገለችውም ቤተክርስቲያኗ ውስጥ ነው። "በልምድ የሚያዋልዱ ሰዎች ረድተውኝ በሰላም ተገላግያለሁ፤ ጡቴ ወተት እምቢ ብሎ፤ ውሃ በጡጦ እያጠባሁ ነው ያለሁት" ትላለች። እርሷ እንደምትለው ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር በመኖሩም ችግሩን አባብሶታል። ከሐዋሳ እናቷ ጋር ለመታረስ ብትመጣም በነበረው ብጥብጥ እናቷን ጨምሮ የሰባት ወር ህፃን የያዘች የአክስቷ ልጅ፤ በአጠቃላይ ሦስት ህፃናትና አራት አዋቂዎች ሆነው እንዳመለጡ ታስረዳለች። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በከፍተኛ የምግብ እጥረት እየተሰቃዩ እንደሆነ የምትናገረው እናት ቢቢሲ ከቀኑ 7፡35 አካባቢ ባናገራት ወቅት ምግብ እንዳልቀመሰችና ሻይ ብቻ እንደጠጣች ተናግራለች። ወደቤት ሄደውም ሆነ ውጭ ወጥተው ለመመገብ ለደህንነታቸው ስለሰጉ ችግር ላይ መሆናቸውን ታስረዳለች። • በተለያዩ ሥፍራዎች ባጋጠሙ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር 67 ደርሷል • ቅዱስ ሲኖዶሱ ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ከመከላከያ ሚንስትሩ ጋር ተወያየ ረቡዕና ሐሙስ ዕለት የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሠረት የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱንና ሁኔታዎች እንደተረጋጉ ቢገለፅም አራሷ በዚህ ሃሳብ አትስማማም። "ተረጋግቷል የሚባለው መንቀሳቀስ ሲቻል ነው። ያሉት ወታደሮች ቤተ ክርስቲያኗን በመጠበቅ ላይ ናቸው" ትላለች። አክላም "ያለነው በመከራ፣ በስቃይ ነው፤ ከፍተኛ ብርድ አለ፤ አራስ ሆነን ውጭ እያደርን ነው፤ የታመሙ ህፃናት አሉ፤ አንዲት የአምስት አመት ልጅ ቶንሲል ታማ ስታለቅስ ነበር ግን ምን ማድረግ ትችላለች" ስትል መንግሥት እንዲደርስላቸው ተማፅናለች። ዲያቆን ደለለኝም በኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ከሁለት መቶ በላይ አባወራዎችም ልጆቻቸውንና ቤተሰባቸውን ይዘው በመቃብር ቤቶች እንዲሁም ድንኳን ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የሦስት ቀጠና ማህበረሰብ፤ ቀጠና 4፣ 5 እና 7 በዚችው ቤተክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙና ሌሎች ደግሞ በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ይገኛሉ ብለዋል። በዛሬው ዕለት በአንፃሩ ከተማው እንደተረጋጋና ከቤተክርስቲያኗም በቅርብ ርቀት የሚገኙ ሰዎች ከቃጠሎ የተረፈ ንብረትም በመሰብሰብ ላይ የሚገኙ እንዳሉም ገልፀዋል። በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ አንድ ፓትሮል፣ አስራ አምስት የማይሞሉ የመከላከያ ኃይል በአካባቢው እንዳለ ጠቅሰዋል። ይሁን እንጅ ተጠልለው የሚገኙት ምዕመናንም በምግብና ውሃ እጥረት እየተሰቃዩም እንደሆነ ለቢቢሲ ገልፀዋል። "አንዳንድ ግለሰቦች ከውጭ ምግብ እያመጡ በሚረዱት ነው እየተዳደርን ያለነው። በጣም የተቸገርነው ደግሞ ውሃ መቅዳት ባለመቻሉ ነው።"ይላሉ። ወደ ቤተ ክርስቲያኗ የሚመጣው የውሃ መስመር በመቋረጡ እንዲሁም ወንዝ ሄደው እንዳይቀዱ ለደህንነታቸው በመስጋታቸው በውሃ ጥም እንዲሰቃዩ ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። ቤተክርስቲያኗን ለቀው ቢወጡ አካባቢውን የሚጠብቀው ኃይል ለደህንነታቸው ዋስትና ስላልሰጣቸው አሁንም ስጋት እንዳደረባቸውና በጭንቀትም ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል። "ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት ነው" የሚሉት ዲያቆን ደለለኝ ከሰባት ቤት በላይ ተቃጥሏል፣ የተዘረፈና የወደመ ንብረት አለ ይላሉ። ረቡዕ ዕለት በቤተክርስቲያኗ አባቶች ላይ ድብደባ እንደደረሰም ይናገራሉ። እስካሁን ባለው ስድስት ሰዎች እንደተቀበሩና በዛሬው ዕለትም ከሃዋሳ የመጣች የአንዲት ሴት ሥርዓተ ቀብር መፈፀሙን ይገልፃሉ። "በሞትና በሕይወት ስላለው ሰው በቁጥር ልናገር አልችልም፤ ሦስት ሰዎች በሞትና በሕይወት መካከል ሆነው አሁንም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ነው ያሉት" ሲሉም ጉዳት ያጋጠማቸው በርካታ ሰዎች መኖራቸውን ያስረዳሉ። በከተማዋ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደሚገኙ የገለፁልን የዶዶላ ወረዳ ቤተክህነት ኃላፊ ሊቀ ልሳናት ቀሲስ እየበሩም በበኩላቸው እንደ ኃይማኖት መሪ በግምት ለመናገር ቢቸገሩም በዚች ቤተክርስቲያን ብቻ 2ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀውልናል። ከረቡዕ ዕለት አንስቶ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ህፃናት ፣ ሴቶች፣ አረጋዊያን ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀው፤ የተጎዳ ሰው ለመጠየቅ ትናንት ወደ ሆስፒታል በማምራት ላይ ሳለች ድብደባ የተፈፀመባት አንዲት ሴትም ሕይወቷ በማለፉ ዛሬ የቀብር ሥነ ሥርዓቷ እንደተፈፀመ ነግረውናል። በርካታ ሰዎች ላይ 'ዘግናኝ ጥቃት' እንደተፈፀመ የተናገሩት ቀሲስ እየበሩ፤ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ንብረቶች መውደማቸውን ያክላሉ። "ዛሬ ጠዋት ላይ መንገድ ተከፍቷል በሚል ከተለያየ ቦታ ለለቅሶና ለሌላ ጉዳይ የመጡ ነበሩ፤ እነርሱም ላይ የማዋከብና የማሰር ድርጊት እየተፈፀመ ነው" ብለዋል። እስካሁን ድረስ በሥፍራው ተገኝተቶ የጎበኛቸው የመንግሥት ባለሥልጣናትም እንደሌሉ ይናገራሉ። "በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው የተፈፀመው፤ ሰው መረጋጋት አልቻለም። እናቶችና ሕፃናት እየተራቡ ናቸው፤ ውሃ ወጥቶ መቅዳት አልቻልንም። ወደ ፈጣሪ ከመጮህ ውጭ ሌላ የምናደርገው ነገር የለም" ይላሉ። "በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አንድ መፀዳጃ ቤት ነው ያለው፤ ውሃ የለም ፤ ምግብ የለም" ሲሉም በዚሁ ከቀጠለ ለበሽታ ሊዳረጉ እንደሚችሉ ስጋት አላቸው። ግጭቱም ከብሔር ጋር የተገናኘ ቢሆንም መልኩን ቀይሮ ወደ ሃይማኖት እንደዞረ በማስረዳትም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ስብጥር ያለውና በአብዛኛው የኦርቶዶክስ አማኞች መሆናቸውን ያስረግጣሉ። ዛሬ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ሀዋሳ ሆስፒታል ተልከው የነበሩትን ሁለት ሰዎች ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 8 መድረሱን ነግረውናል። የተጎዱትን ለማስታመም ወደ ሆስፒታል ያመሩ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሟል ስለመባሉ ያነሳንላቸው ዶክተር ቶላ፤ ዝርዝር መረጃ ባይኖራቸውም ሀሙስ እለት ግን ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥም ግጭቶች እንደነበሩ ገልፀውልናል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዶዶላ ተወላጆች፣ የሟቾች ቤተሰቦች በመሰባሰብ ለሚዲያዎች ፣ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት አቤት ለማለት እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ የዶዶላ ተወላጅ እና በአዲስ አበባ በሥራ ላይ የሚገኘው አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ደምሴ ገልፆልናል። ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው እንዲገቡም መንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቋል። "ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት በርሃብ ሊያልቁ ነው፤ ሕፃናት፣ የሚያጠቡ እናቶች አሉ፤ ትናንትና እና ከትናንት ወዲያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ንፍሮ ቀቅለው ነው የበሉት" ይላል። ግጭት በተፈፀመባቸው አካባቢዎች መከላከያ እንደተሠማራ መንግሥት ቢገልፅም አሁንም ድረስ በከተማዋ ጥቃት እየተፈፀመ እንደሆነም ለቢቢሲ ገልጿል። በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንደውልም ጥረታችን ሳይሳካ ቀርቷል። የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሠረት በአምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቤ፣ አዳማ፣ ሞጆ እንዲሁም በድሬዳዋ እና ሐረር የመከላከያ ሠራዊት እንደተሠማራ መገለፁ ይታወሳል።
57184360
https://www.bbc.com/amharic/57184360
ኢትዮጵያ ቴሌኮም፡ ጨረታ ያሸነፈው የቴሌኮም ተቋም ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል?
ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሳተፍ ፈቃድ የሰጠችው ተቋም ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ነዋይ ወደ አገሪቱ እንደሚያስገባና በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተነገረ።
የቴሌኮም ዘርፉን ለውጪ ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ ክፍት ያደረገችው ኢትዮጵያ የበርካታ ተቋማት ስብስብ ለሆነው ኩባንያ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ መስጠቷን አስታውቃለች። በዚህም መሠረት ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለውና የስድስት ኩባንያዎች ጥምረት የሆነው ተቋም አገሪቱ ለጨረታ አቅርባቸው ከነበሩት ሁለት የቴሌኮም ፈቃዶች ውስጥ አንዱን በማሸነፍ በዘርፉ እንዲሰማራ መመረጡን የገንዘብ ሚኒስቴርና የኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን ይፋ አድርገዋል። የኬንያው ሳፋሪኮም፣ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎን እና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካ ቮዳኮም፣ የጃፓኑ ሱሚቶሞ እንዲሁም ዲኤፍሲ ናቸው በአገሪቱ በኢትዮ ቴሌኮም ከ120 ዓመታት በላይ በብቸኝነት ተይዞ ወደነበረው ዘርፍ ለመግባት ፈቃድ ያገኙት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው የተሰጠውን ፈቃድ "ታሪካዊ ውሳኔ" ብለውታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመረጠው ተቋም ከፍተኛ የፈቃድ ክፍያ ዋጋ እና አስተማማኝ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ዕቅድ እንዳቀረበ ጠቅሰው ይህም "እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ከተደረጉት የውጪ ቀጥተኛ የዋዕለ ነዋይ ፍሰቶች ብልጫ እንዳለው" በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ተሳታፊዎቹ እነማን ነበሩ? ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት እንደምታደርግ ካሳወቀች በኋላ ሁለት ፈቃዶችን ለዘርፉ ተሳታፊዎች በጨረታ አቅርባ ነበር። ኅዳር 18/2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን በአገሪቱ የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ለመሰማራት ፍላጎቱ ላላቸው ኩባንያዎች ይፋዊ የጨረታ ጥሪ አቅርቦ ሚያዝያ 16/2013 ዓ.ም ሁለት ተቋማት በጨረታው ተሳታፊ መሆናቸውን ማሳወቁ ይታወሳል። በዚህም መሠረት የተለያዩ ኩባንያዎች ጥምረት የሆነው ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው ተቋም ከፍተኛውን 850 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ በጨረታው ተመራጭ ሲሆን ሁለተኛው ፈቃድ ሳይሰጥ ቀርቷል። ጨረታው ከወጣ በኋላ በርካታ የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ለመሳተፍ ፍለጎት እንዳላቸው የገለጹ ቢሆንም የፈረንሳዩን ኦሬንጅ እንዲሁም የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ኢቲሳላትን ጨምሮ ሌሎችም በጨረታው ላይ ሳይሳተፉ መቅረታቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል። ሁለተኛ ተጫራች የነበሩት የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን እና አጋሩ የቻይና መንግሥት ኢንቨስትመንት አካል የሆነው ሲልክ ሮድ ፈንድ 600 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታው ያቀረበ ቢሆንም ሳይመረጥ ቀርቷል። በዚህም ሳቢያ ሁለተኛው የቴሌኮም ዘርፍ አዲስ ፈቃድ ሳይሰጥ ቢቀርም በቀጣይ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ለጨረታ እንደሚቀርብ የገንዘብ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ብሩክ ለብሉምበርግ ገልጸዋል። ምን ይዘው ይመጣሉ? በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ካላቸው ቀዳሚ አገራት መካከል የምትመደበው ኢትዮጵያ፤ የቴሌኮም ዘርፍ በአንድ አገልግሎት ሰጪ ያለተፎካካሪ በብቸኝነት ተይዞ በመቆየቱ ተጠቃሚዎች በዋጋም ሆነ በአገልግሎት ጥራት አማራጭ ሳይኖራቸው ቆይቷል። እነዚህም አዳዲስ ቴክሎኖሎጂዎች፣ ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ነዋይ፣ በርካታ የሥራ ዕድሎች እንዲሁም የተለያዩ የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ግንባታዎች ናቸው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያውና ፌርፋክስ አፍሪካ ግሎባል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የቴሌኮም ዘርፉ ለውድድር ክፍት መሆኑ ጥራት ያለው አገልግሎት በርካሽ ዋጋን ከማስገኘቱ ባሻገር "ለሥራ ፈጠራና ለውድድር በር ይከፍታል" ይላሉ። የጨረታው ውጤት ይፋ በተደረገበት መግለጫ ላይ የአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እንዳሉት ውሳኔው አገሪቱ በምታካሂደው የምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ ሂደት ውስጥ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰው "ይህም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥራት ያው አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ያስችላል" ብለዋል። በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው የተለያዩ ታዋቂ የቴሌኮም ኩባንያዎች ስብስብ የሆነው ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ውስጥ ከ750 በላይ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ይነገራል። የኩባንያዎቹ ዘርፈ ብዙ ልምድ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ውስጥ ጉልህ ለውጥ ለማምጣት እንደሚያስችላቸው የሚጠበቅ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ቴሌኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኢንጂኒየር ባልቻ ሬባ እንዳሉት "የተሰጠው ፈቃድ ሚሊዮኖች ጥራት ያው አስተማማኝ አገልግሎትን እንዲያገኙ በማስቻል በአገሪቱ የቴሌኮም ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል" ብለዋል። በኢትዮጵያ እንዲሰራ ፈቃድ ያገኘው አዲሱ የቴሌኮም ተቋም ከ110 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባላት አገር ውስጥ ሰፊ የገበያ ዕድል ያለው ሲሆን ዘመኑ ያፈራቸውን የቴሌኮም ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተለያዩ አገልግሎቶችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር አማካሪ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት በጨረታው የተመረጠው ተቋም የ4ጂ እና የ5ጂ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ያቀርባል። በተጨማሪም ሳተላይት በመጠቀም ከሁለት ዓመት በኋላ መላው አገሪቱ የ4ጂ የኢንተርኔት ሽፋን እንዲያገኝ ያደርጋል ብለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የመጀመሪያውን ፈቃድ ያገኘው የውጭ ተቋም በርካታ ጥቅሞችን ለአገሪቱና ለሕዝቧ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል። በተለይ በየጊዜው እያደገ ከመጣው የሥራ ፈላጊ ወጣት ቁጥር አንጻር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የተነገረ ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያለው የሥራ ዕድልን ይፈጥራል ተብሏል። ዶ/ር ብሩክ እንዳሉት ተቋሙ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ እስከ 1.5 ሚሊዮን የሚደርሱ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር ሲሆን 8.5 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ መዋዕለ ነዋይን ወደ አገሪቱ ያስገባል። በውጭ ኩባንያዎች ከሚያዙት ሁለቱ የቴሌኮም ፈቃዶች በተጨማሪ ዋነኛው የአገሪቱ አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ ቴሌኮምም በሩን ለባለሃብቶች ይከፍታል። በዚህም በመንግሥት ብቸኛ ባለቤትነት ሥር የቇየው ተቋሙ በቅርቡ 40 በመቶን ድርሻ ለውጪ ባለሃብቶች፣ 5 በመቶን ለኢትዮጵያውያን እና 55 በመቶውን መንግሥት እንደሚይዘው ይጠበቃል። የኢትዮጵያን የቴሌኮም ገበያ በብቸኝነት እያገለገለ ያለው መንግሥታዊው ኢትዮ ቴሌኮም ሲሆን፤ በአህጉሪቱ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ የሆነችው አገር የቴሌኮም ዘርፍ ለውጭ ኩባንያዎች አጓጊ ገበያ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል። በዚህም ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለሚሳተፉ ኩባንያዎች ሁለት ፈቃዶችን ከማዘጋጀቷ በተጨማሪ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኘውን የኢትዮቴሌኮም የተወሰነ ድርሻ ለመሸጥም እቅዷን አሳውቃለች። በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የቴሌኮም አገልግሎትን በብቸኝነት እየሰጠ የሚገኘው ኢትዮቴሌኮም በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር የሞባይል ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ ካላቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው። ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ተቋማት ክፍት እንደምታደርግ ያስታወቀችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች ነው። በአፍሪካ በርካታ ሕዝብ ይዛ አንድ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ያላት አገር ኢትዮጵያ አሁን ለዘርፉ በሯን ከፍታለች። በዚህም መሠረት የተለያዩ ኩባንያውያዎች ጥምረት የሆነው ተቋም ቀዳሚው የውጭ አገልግሎት ሰጪ ለመሆን ተመርጦ ፈቃድ ተሰጥቶታል። ለመሆኑ የስድስት ኩባንያዎች የጋራ ጥምረት የሆነው ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው ተቋም በውስጡ የያዛቸው ኩባንያዎች እነ ማን ናቸው? በዘርፉ ያላቸውስ ልምድ? ሳፋሪኮም ዋና መሥሪያ ቤቱ ናይሮቢ የሚገኘው ሳፋሪኮም የኬንያ የቴሌኮም ድርጅት ሲሆን፤ ኬንያ ውስጥ ትልቁ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢና በምሥራቅ እና በመካከለኛው አፍሪካ ትርፋማ ከሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። ሳፋሪኮም የተንቀሳቃሽ ስልክ መስመር፣ የኢንተርኔት፣ የስልክ ግብይት እንዲሁም ሌሎችም አገልግሎቶች ይሰጣል። እአአ በ1997 ገደማ የተቋቋመው ሳፋሪኮም፤ በተለይም ኤምፔሳ በተባለው የሞባይል ገንዘብ ማዘዋወሪያ አገልግሎቱ በስፋት ይታወቃል። ሳፋሪኮም በሌሎች አገራት ከሚሠሩ የቴሌኮም ድርጅቶች ጋር በመጣመር አገልግሎቱን እያስፋፋ ነው። ከእነዚህ መካከል ታንዛንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሕንድ ይጠቀሳሉ። የሳፋሪኮም ድረ ገጽ እንደሚያሳየው፤ ከኬንያ የቴሌኮም ገበያ 64.5 በመቶ ድርሻን ይወስዳል። ወደ 35.6 ሚሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎችም አሉት። የዩናይትድ ኪንግደሙ ቮዳፎን ኩባንያ ከሳፋሪኮም 40 በመቶ ድርሻን ገዝቷል። ቮዳኮም በአፍሪካ ውስጥ ሰፊ የቴሌኮም አገልግሎት ከሚሰጡት ኩባንያዎች መካከል ቮዳኮም ይጠቀሳል። የኢንተርኔት፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥሪ እንዲሁም ከገንዘብ ዝውውወር ጋር የተያያዙ ዘርፎችም አሉት። መነሻውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው ቮዳኮም፤ በታንዛንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሞዛምቢክ፣ ሌሶቶ እና ኬንያ ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል። የሞባይል ኔትወርክ ዝርጋታው ከ296 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ እንዳደረገ የድርጅቱ ድረ ገጽ ይጠቁማል። ቮዳኮም ቢዝነስ አፍሪካ በሚል በ29 አገራት ንግድ ነክ አገልግሎቶች ይሰጣል። ከቮዳኮም 60.5 በመቶ የሚሆነው የባለቤትነት ድርሻ የብሪታኒያው ቮዳፎን ነው። የ3ጂ እና 4ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጠው ቮዳኮም፤ በአፍሪካ በግንባር ቀደምነት የቀጥታ 5ጂ ኔትወርክ እንደዘረጋ ይነገርለታል። ቮዳፎን የብሪታኒያው ቮዳፎን አገልግሎት የሚሰጠው በአውሮፓ፣ በእስያ እና በአፍሪካ ሲሆን፤ በ21 አገራት ውስጥ ኔትወርክ ዘርግቷል። አውሮፓ ውስጥ በኔትወርክ ዝርጋታ የአንበሳውን ድርሻ እንደያዘ የሚነገርለት ቮዳፎን፤ አፍሪካ ውስጥ ከ42 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሞባይል ገንዘብ መለዋወጫ አገልግሎትን እንዲጠቀሙ እንዳስቻለ በድረ ገጹ የሰፈረው መረጃ ይጠቁማል። ቮዳፎን የተንቀሳቃሽ ስልክ ጥሪ፣ ኢንተርኔትና ሌሎችም ተያያዥ አገልግሎቶች ይሰጣል። በኢንተርኔት አማካይነት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ነክ መገልገያዎችን በማስተሳሰር የሚታወቀውና 'ኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስ' የሚባለውን አገልግሎት በተለይም ለንግድ ተቋማት ያቀርባል። እንደ አውሮፓውያኑ ከ1980ዎቹ ወዲህ የተስፋፋው ቮዳፎን የስልክ ጥሪ፣ የጽሁፍ መልዕክትና ኢንተርኔት የሚያቀርብ ሲሆን፤ አውሮፓ ውስጥ የ5ጂ ዝርጋታ ላይ በስፋት ይሠራል። በአፍሪካ በጋና፣ በሊቢያና በካሜሩን፤ በመካከለኛው ምሥራቅ ደግሞ በኳታር፣ በባህሬንና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፤ በእስያ ደግሞ በጃፓን እና በሕንድ አገልግሎት ይሰጣል። ኤምቲኤን ግሩፕ ኤምቲኤን ግሩፕ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገ የቴሌኮም ተቋም ነው። በተለያዩ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እንዲሁም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት አገልግሎት ይሰጣል። ዋና መሥሪያ ቤቱን ደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ያደረገው ተቋም ወደ 273 ሚሊዮን የሚጠጉ ተገልጋዮች እንዳሉት በድረ ገጹ ያሰፈረው መግለጫ ይጠቁማል። በ20 አገሮች የሚሠራው ኤምቲኤን ግሩፕ ከፍተኛውን ገቢ የሚያገኘው ከናይጄሪያ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ1994 ገደማ ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት በተገኘ ድጋፍ ነበር የተቋቋመው። ሱሙቲሞ ኮርፖሬሽን ሱሙቲሞ ኮርፖሬሽን የጃፓን ተቋም ሲሆን ቴሌኮምን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማራ ነው። በብረት ምርት፣ በትራንስፖርትና ምህንድስና፣ በማዕድን፣ በሪልስቴት እና ሌሎችም ዘርፎች ለረዥም ዓመታት ሠርቷል። ከእነዚህ በተጨማሪ በመገናኛ ብዙሃን እና በቴሌኮምዩኒኬሽን ዘርፍ የሚሰጠው አገልግሎት የኬብል ቴሌቭዥን እና 5ጂ የሞባይል ኢንተርኔትን ያካትታል። ቲ-ጋያ የሚባል የሞባይል አከፋፋይ ያለው ሱሙቲሞ ኮርፖሬሽን አጠቃላይ አገልግሎቶቹን በ66 አገራት እንደሚሰጥ ከድረ ገጹ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። ከተሰማራባቸው ዘርፎች መካከል የመገናኛ ብዙሃን እና ቴሌኮምዩኒኬሽን ቅርንጫፉ 11.9 በመቶ ድርሻ ይይዛል። እንደ አውሮፓውያኑ በ1919 ኦሳካ ኖርዝ ሀርበር በሚል ስያሜ ከተቋቋመ በኋላ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማራው ድርጅቱ፤ በምሥራቅ እስያ፣ በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና ሌሎችም የዓለም ክፍሎች ውስጥ ይንቀሳቀሳል። ሲዲሲ ግሩፕ የብሪታንያው ሲዲሲ ግሩፕ እንደ አውሮፓውያኑ በ1948 ከተመሠረተ ወዲህ ላለፉት 70 ዓመታት በፋይናንስ ዘርፍ ሲሠራ ቆይቷል። በተመሠረተበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በዛምቢያ የሲሚንቶ ዘርፍ፣ በቦትስዋና የከብር እርባታ ዘርፍና በሌሎችም የአፍሪካ እና እስያ አገሮች ውስጥ ሠርቷል። በ1998 ላይ ሴልቴል በተባለ የአፍሪካ የሞባይል ስልክ ድርጅት ኢንቨስት ማድረጉ ከቴሌኮም ዘርፍ እንቅስቃሴው አንዱ ነው። በድረ ገጹ ላይ በሚገኘው መረጃ መሠረት፤ በተለያዩ አገሮች በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ፣ በጤና እና ሌሎችም ዘርፎች ኢንቨስት ማድረግ ይቻላል። ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የተደረገባቸው አገራት ሕንድ፣ ናይጄሪያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኮትዲቯር ናቸው።
50218915
https://www.bbc.com/amharic/50218915
አሳሳቢው የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር በኢትዮጵያ
በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የባህል ቅርስ ባለሙያ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ቢራራ የዛሬ ስድስት ዓመት በጉለሌ አካባቢ የሕገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር ምን እንደሚመስል ጥናት አካሂደው ነበር።
ጥናታቸው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከእንጦጦ ጫካ ጋር ተያይዘው ባሉ አካባቢዎች እንደነበር ያስታውሳሉ። በወቅቱ ከነበረው ሁኔታ እንደተረዱት ሕገወጥ መሳሪያ ዝውውሩ ይደረግ የነበረው ሌሊት ነው። ይህንንም ማወቅ የተቻለው በጫካውና በተለይ በቀጨኔ መድኃኒያለም የቀብር ቦታዎች አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ይሰማባቸው የነበሩ ጊዜያት መመዝገባቸው ነው። • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? በጫካውና በቀብር ስፍራዎቹ አካባቢ ይሰማ የነበረው ጦር መሳሪያ ተኩስ በመሳሪያ ሽያጭ ልውውጡ ወቅት የሚደረግ ፍተሻ እንደነበር ያስታውሳሉ። በወቅቱ በጥናታቸው ውስጥ እንደ ችግር ያነሱት የመሳሪያ ፈቃድ አሰጣጡ የላላ መሆንን ነው። ፈቃድ ሰጪው አካል የመሳሪያው ምንጭ ከየት እንደሆነ፣ ለምን እንደተፈለገ፣ መሳሪያውም ምን እነደሆነ ሳይታወቅ ፈቃድ እንዲሰጠው የሚፈልግ ሰው የመሳሪያውን ፎቶ ብቻ ይዞ በመሄድ ብቻ ያገኝ እንደነበር ያስታውሳሉ። ይህ ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ የትጥቅ ማስፈታት ሳምንት ሆኖ ሲከበር ቆይቷል። በኢትዮጵያም በተለያየ ወቅት በክልሎችም ሆነ በመዲናዋ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲዘዋወር ተያዘ የሚል መረጃ በተደጋጋሚ ይሰማል። ይህ የሕገ ወጥ ጦር መሳሪያ ዝውውር በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በተደጋጋሚ እንደሚስተዋል የሚናገሩ ባለሙያዎች ይህ ሁኔታ ወደ ከፋ ጉዳት እንዳያመራ ያላቸውን ስጋት ያስቀምጣሉ። በአንድ ወቅትም ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖለቲካ የደህንት ጉዳዮች ተንታኙ አቶ ዳደ ደስታ፤ በግለሰቦች ወይም በአነስተኛ ቡድኖች ሊያዙ የሚችሉ ሕገ ወጥ መሳሪያዎች መሰራጨታቸው ኃይል መጠቀም የመንግሥት ብቻ የሆነ ስልጣን ሆኖ ሳለ በሌሎች ሰዎች፣ ቡድኖችና ድርጅቶች እጅም እየገባ መሆኑን እንደሚያሳይ ገልፀው ነበር። • በግጭት ለተፈናቀሉት የተሰበሰበው አስቸኳይ እርዳታ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ አቶ ዳደ 'አደገኛ ነው' የሚሉትን የሕገ ወጥ መሳሪያ ዝውውር፤ በክልሎች ከሚነሱ ግጭቶች፣ ከፕሮፓጋንዳ መሳሪያነቱ እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡ ድርጅቶች ጋርም ያያይዙታል። አክለውም የጦር መሳሪያዎች ዝውውሩ ወጥቶ መግባትንም አስጊ እንደሚያደርገው ይናገራሉ። ኅብረተሰቡ መንግሥት ላይ አመኔታ ሲያጣ ቤተሰቡን ለመጠበቅ ወደ ጦር መሳሪያ ሸመታ ሊያመራ መቻሉ ደግሞ ስጋታቸውን ያከብደዋል። በጉምሩክና በመከላከያ በኮንትሮባንድ የተያዙ የጦር መሳሪያዎች ብዛት ጉምሩክ በመላው ሀገሪቱ 12 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ያሉት ሲሆን በ2011 እና በ2012 ዓ.ም ውስጥ በዘጠኙ የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች የተለያዩ አይነት ሕገ ወጥ መሳሪያዎችና ጥይቶች መያዛቸውን ለማወቅ ተችሏል። በ2011 ዓ.ም ብቻ በጉሙሩክና መከላከያ የተያዙ መሳሪያዎች ብዛት 2020 ሽጉጥ፣ 62 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 4 መትረየስ መሆኑን ከገቢዎችና ጉሙሩክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በዚሁ ዓመት 917 የመትረየስ ጥይት፣ 2ሺህ 983 የብሬን ጥይት፣ 15 ሺህ 717 የብሬን ጥይት፣ 80 ሺህ 764 የሽጉጥ ጥይት መያዛቸውን ተቀምጧል። ባለንበት ዓመትም 1 መትረየስ፣ 113 ክላሽንኮቭ፣ 382 ሽጉጦች መያዛቸው ተመዝግቧል። • በአፋር ክልል በተፈፀመ ጥቃት 17 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል በዚሁ ዓመት 111 የመትረየስ ጥይት፣ 3 ሺህ 581 የብሬን ጥይት፣ 5 ሺህ 231 የክላሽንኮቭ ጥይት 4 ሺህ 910 የሽጉጥ ጥይትና 122 የክላሽ ካዝና መያዛቸውን የጉሙሩክ መረጃ ያሳያል። ከዘጠኙ የጉሙሩክ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕገ ወጥ መሳሪያና ጥይት የተያዘው በቃሊቲና ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆን ዝቅተኛ መሳሪያ የተያዘው ደግሞ በመቀሌው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በኩል መሆኑን መረጃው ያሳያል። በመስሪያ ቤቱ የኢንተለጀንስና ኮንትሮባንድ ክትትል የሥራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ ዘላለም እንደሚናገሩት በ2011 ዓ.ም በልዩ ሁኔታ በቦሌ አየር መንገድ ሴኪዩሪቲ መጋዘን በተደረገው ፍተሻ 3 ስናይፐር፣ 3 የአደን ጠመንጃ፣ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን የጦር መሳሪያ መለዋወጫ እንደተገኘም ተናግረዋል። መሳሪያዎቹ መቼ እንደገቡና በማን እንደገቡ አይታወቅም የሚሉት ኃላፊው፣ መጋዘኖቹ ውስጥ አጠቃላይ ፍተሻ ሲደረግ መገኘታቸውን ያስረዳሉ። በመንገደኞች ጓዝ በኩል ከጀርመን ሲገባ የተያዘ 1 ሽጉጥ በዚሁ መጋዘንም እንደተገኘ ከጉሙሩክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አንድ ዓለም አቀፍ ድርጅትም ፈቃድ ሳያገኝ ለጥበቃ ሰራተኞቹ ሊያስገባ የነበረው 59 ሽጉጥና 122 ሺህ ጥይት በጉሙሩክና በድርጅቱ ቁልፍ ተቆልፎ እንደሚገኝም ጨምረው አስረድተዋል። እነዚህን መሳሪያዎች ውሳኔ ባለማግኘታቸው አሁንም እንደተቆለፈባቸው መሆናቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ከወራት በፊት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋለ የተባሉ የጦር መሳሪያዎች በክልሎች በኩል ያለው ገጽታ በትግራይ የጸጥታና ደህንነት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሃፍታይ መለስ በክልሉ በተለያየ አጋጣሚና አካባቢ የሚዘዋወር ህገወጥ የጦር መሳርያ አለ ይላሉ። ባለፈው ዓመት 155 ሽጉጥ፣ 16 ክላሽ፣ 22 ቦንብ፣ 10 ሺህ 922 የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስታውሳሉ። እነዚህ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ትግራይን ከአማራ ክልልና ከሱዳን በሚያዋስኑ አካባቢዎች ሲገቡ የተያዙ መሆናቸውንም ጨምረው ያስረዳሉ። ሌሎች በትግራይ ውስጥ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውንም ለቢቢሲ ጨምረው አስረድተዋል። • ". . . ጦርነት ታውጆብን ነበር" ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እነዚህ የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሮች በአቋራጭ ጥቅም ለማግኘትና ለመበልጸግ በመፈለግ የሚደረግ ተግባር መኖሩን እንደሚያመለክት ገልፀዋል። ሕገ ወጥ መሳሪያውን ሲያዘዋውሩ የተያዙ አካላት ጉዳያቸው በሕግ እየታየ መሆኑን አስረድተው ፍርድ የተሰጣቸው መኖራችውንም ያስረዳሉ። ከኦሮሚያ፣ ከአማራ ክልልና ከፌደራል ፖሊስ የሕገወጥ መሳሪያዎችን በሚመለከት መረጃ ለማግኘት ደጋግመን ብንሞክርም ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ሊሳካልነን አልቻለም። የተወሰዱ ርምጃዎች በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ እንዲህ በስፋት የሚዘዋወርባቸውን ምክንያት ሲያስረዱ አሁን ያለው የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ እንዳይቀጥል ለማድረግ እንደሆነ በቀዳሚነት ይጠቅሳሉ። በተለይ ደግሞ ይህ የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር የሕዝብን አንድነትና ሰላም በማይፈልጉ አካላት መሆኑን በመጥቀስ፤ የገንዘብ አቅማቸውን ለማደለብ የሚሰሩ የተደራጁ ቡድኖችም በዚህ ድርጊት ውስጥ እጃቸው እንዳለበት ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ በሚፈጠር ስጋት ጋር ተያይዞ የጦር መሳሪያ ለመግዛት ያለ ፍላጎት እየጨመረ ያለበት ሁኔታ እንደሚታይም ይናገራሉ። በተደጋጋሚ ወደ ሀገር ውስጥ ሕገወጥ መሳሪያ ለማስገባት የሚሞክሩ አካላትን የጸጥታ መዋቅሩ እየተከታተለ በቁጥጥር ስር እንደሚያውል የሚናገሩት አቶ ዝናቡ፤ ሕገወጥ መሳሪያ ዝውውሩ እየጨመረ መምጣቱንም የሚያመላክቱ ነገሮች መኖራቸውን አልሸሸጉም። • የአይ ኤስ መሪ አቡ ባካር አል ባግዳዲ ማነው? በዚህ ጉዳይ ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱን ተናግረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን፤ በተጨማሪም መሳሪያዎቹ ሲጓጓዙባቸው የነበሩ መኪኖችም በቁጥጥር ስር ውለው በሕግ ውሳኔ መሰረትም የተወረሱ እንዳሉ ገልፀዋል። መሳሪያዎቹ ድንበርን አቋርጠው አንደሚመጡ የሚናገሩት አቶ ዝናቡ፤ ከድንበር አልፈው ንግድ እንቅስቀሴ በስፋት በሚካሄድባቸው በሰሜን በኩል ከሱዳን ጋር ኢትዮጵያ በምትዋሰንባቸው፣ በምሥራቅ በሶማሌ ድንበር በኩል፣ በደቡብ ደግሞ በሞያሌ ኬኒያ በኩል እንደሚገቡና ንግድ እንደሚካሄድ አስረድተዋል። ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ለመቆጠጠር አዲስ ሕግ የመሳሪያ አያያዝ አጠቃቀምና ፈቃድ አሰጣጥን ሂደትን ትኩረት ሰጥቶ የህግ ማሻሻያ ቢደረግ በማለት የጦር መሳሪያ መያዝ ያለበት ማን ለምን አንደሆነ ቁርጥ ያለ አቅጣጫ ተቀምጦ ማስተካከያ ቢደረግ ሲሉ በጥናታቸው መጠቆማቸውን አቶ ደሳለኝ ቢራራ ያስታውሳሉ። ከዚህ አንጻርም ሕገ ወጥ መሳሪያውን ለመቆጣጠር በድርጊቱ የተሳተፉ አካላት ተገቢ የሆነ ቅጣት እንዲያገኙ ጠንከር ያለ የሕግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ለቢቢሲ ጠቁመዋል። በሥራ ላይ ያሉ ሕጎች ያልሸፈኗቸው ጉዳዮች በመኖራቸውም ይህንን ህግ ማርቀቅና ወጥነት ያለው ሥርዓትን መዘርጋት አስፈልጓል የሚሉት አቶ ዝናቡ፤ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች በባህል የተነሳ መሳሪያ መታጠቃቸውን በማስታወስ በምን ዓይነት ሁኔታ መተዳደር ይቻላል የሚለውንም መወሰን ያስፈልገናል ሲሉ ተናግረዋል። አሁን ያለው ሕግ የተያዙ ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች እንዲወረሱ ቢያዝም አዘዋዋሪዎቹ ላይ ጠንከር ያለ ቅጣት እንደማይጣል ገልጸው ያለው ሕግ አስተማሪ አልሆነም ይላሉ። እየተዘጋጀ ያለው ረቂቅ ሕግ ከባለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ እየተረቀቀ መሆኑን አስታውሰው በውስጡ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም፣ የተከለከሉ ተግባራት፣ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለባቸው ስፍራዎች፣ ጦር መሳሪያ ፈቃድ የማይሰጥባቸው ተቋማት፣ የጦር መሳሪያ ፍቃድንም ማስተዳደርን የተመለከቱ ጉዳዮች በረቂቁ ውስጥ መካተታቸውን ተናግረዋል። • ቅዱስ ሲኖዶሱ ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ከመከላከያ ሚንስትሩ ጋር ተወያየ በተጨማሪም አዲሱ ረቂቅ ሕግ እነማን ምን አይነት መሳሪያ ይታጠቃሉ፣ በተቋማት ደረጃ ምን አይነት መሳሪያ መታጠቅ ይቻላል የሚሉ ጉዳዮችም ተካተዋል ብለዋል። በረቂቅ ሕጉ ላይ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ተቀምጧል በማለትም "የጦር መሳሪያ የያዘ፣ ያከማቸ፣ ያዘዋወረ፣ ያደሰ/የጠገነ፣ እየተዘዋወረ አይቶ ዝም ያለ ላይ ሁሉ ቅጣት ይጣላል" ይላሉ። በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቀመጠው ቅጣት ከ10 ዓመት ጀምሮ ሲሆን የገንዘብ ቅጣትም አንደሚኖረው ተናግረዋል። መሳሪያዎቹ በድንበር አካባቢዎች መግባታቸውን በማስታወስም ይህንኑ ለማስቀረትም ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ እየተሰራ መሆኑን ያስረዳሉ። ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በ2012 ዓ.ም በመጀመሪያው ሩብ አመት ከወንጀል ጋር ተያያዥነት ያላቸውን በርካታ ንብረቶች በፍርድ ቤትና ከፍርድ ቤት ውጭ (በጉምሩክ ባለሰልጣን መ/ቤት) ለመንግሥት ገቢ መደረጋቸውን የገለጹት አቶ ዝናቡ ከእነዚህም ውስጥ የጦር መሳሪያዎች ይገኙባቸዋል። እነሱም 4 ከባድ መትረየስ፣ 42 ክላሽ፣ 1 ማካሮቭ፣ 20‚996 የተለያዩ አይነት ጥይቶች፣ 27 ካዝና፣ እንዲሁም 10‚676 የክላሽና የሽጉጥ ጥይት፣ 1 ባለሰደፍ ክላሽ ፣ 6 ሽጉጥ፣ በአቃቤ ህግ ውሳኔና በጉምሩክ አዋጅ እንዲወረሱ ለፖሊስ ትዕዛዝ መተላለፉን ያስረዳሉ። ከዚሁ ጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቀረቡ 8 ክሶች መነሻ የሁሉም ተከሳሾች የዋስትና መብት ታግዶ ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን አብራርተዋል። አቶ ዝናቡ አክለውም ሦስት አይሱዙ መኪኖች እንዲሁም ሌላ ተሽከርካሪ የጦር መሳሪያ ሲያጓጉዝ በመያዛቸው እንዲወረሱ መወሰኑን ተናግረው፤ አይሱዙ የጭነት መኪናው በሀሰተኛ ሰነድ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ በመያዙ መወረሱንም ገልጸዋል። ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ዳደ የሕገ ወጥ መሳሪያዎቹ በዘራፊዎች ወይም ሕገ ወጥ የፖለቲካ አላማ ባላቸው ሰዎች እጅ ሊገቡ የሚችሉበት እድል መኖሩን በመግለጽ፤ መንግሥትን ኃይል ከማሳጣቱ ባሻገር ህብረተሰቡን አደጋ ላይ የሚጥልም እንደሆነ ይገልፃሉ። አቶ ዳደ ዝውውሩ ወጥቶ መግባትንም አስጊ እንደሚያደርገው ይናገራሉ። ኅብረተሰቡ መንግሥት ላይ አመኔታ ሲያጣ ቤተሰቡን ለመጠበቅ ወደ ጦር መሳሪያ ሸመታ ሊያመራ መቻሉ ደግሞ ስጋታቸውን ከፍ ያደርገዋል። • የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ • የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው? አቶ ዳደ ሕግና ሥርዓት ማስጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት መሆኑን አስረግጠው፤ "መንግሥት ሳይዘገይ አስፈላጊ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ አለበት። አስፈላጊውን ንቅናቄ ማድረግም አለበት" በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። "ተራው ዜጋ በድብቅ መሳሪያ ከታጠቀ ብቸኛ ምክንያቱ ሊሆን የሚችለው ፖለቲካዊ ነው" ብለው፤ ይህ ደግሞ አገርን አደጋ ላይ እንደሚጥል ያስረዳሉ። በተለይም የጦር መሳሪያ ስርጭቱ በተደራጀ ኃይል ቁጥጥር ስር የሚውል ከሆነ ወደ እልቂት ማምራቱ አይቀርም ብለዋል።
53915682
https://www.bbc.com/amharic/53915682
ኮሮናቫይረስ፡ ከኮሮናቫይረስ የዳነው ሰው ዳግም በወረርሽኙ ተያዘ
የሆንግ ኮንግ ሳይንቲስቶች መጥፎ ዜና ይዘዋል፡፡
ዕድሜው በ30ዎቹ የሚገመት አንድ ሰው በኮሮና ተይዞ ሙሉ በሙሉ ከዳነ በኋላ በድጋሚ መያዙን ደርሰውበታል፡፡ በተለምዶ ይታመን የነበረው አንድ የተያዘ ሰው ማገገም ከቻለ ሰውነቱ ከዚያ በኋላ ተህዋሲውን የሚቋቋም መከላከያ ስለሚያመርት በተመሳሳይ ተህዋሲ በድጋሚ አይወድቅም የሚል ነበር፡፡ ይህ ሆንግ ኮንግ በድጋሚ ተይዞ የተገኘው ሰው መጀርመያ ኮቪድ-19 ተህዋሲ የነካው ከአራት ወር ተኩል በፊት ነበር፡፡ ከዚህ ዘለግ ያለ ጊዜ በኋላ ነው በድጋሚ መያዙን የሆንግ ኮንግ ሳይንቲስቶች የደረሱበት፡፡ የሆንግ ኮንግ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት የሰውየው ዘረመል ጥልፍልፍ (genome sequencing) ያሳያቸው ነገር ቢኖር ሰውየው መጀመርያ የተያዘበት የቫይረሱ ዓይነት ከአራት ወራት በኋላ ከያዘው ጋር ፍጹም የሚለይ ቅርጽ አለው፡፡ በመሆኑም ግለሰቡ በዓለም የመጀመርያው በቫይረሱ በድጋሚ መያዙ የተረጋገጠ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህ ክስተት ላለፉት ዘለግ ያሉ ወራት በጤና ባለሞያዎች ዘንድ ሲያከራክር ለነበረው ጉዳይ ምላሽ የሰጠ ነው፡፡ አንድ ሰው በቫይረሱ ከተያዘ በኋላ ከዳነ መልሶ ሊያዝ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብም ውሀ ቸልሶበታል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ በአንድ ሰው የጤና ሁኔታ ላይ ተመስርቶ ድምዳሜ ላይ መድረስ አያሻም ይላል፡፡ በድጋሚ መያዝ በአንዳንድ ሰዎች ብቻ አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ነገር ሊሆን ይችላል ይላል፤ ደብሊው ኤች ኦ፡፡ አሁን በመላው ዓለም 23 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በተህዋሲው ተነክተዋል፡፡ ተህዋሲው ሰውነታቸው የገባባቸው ሰዎች ከዳኑ በኋላ ያ ተህዋሲ በድጋሚ እንዳይዛቸው የሚያስችል በቂ ትጥቅ ነጭ የደም ሴላቸው አዘጋጅቷል ተብሎ ነው የሚገመተው፡፡ በተህዋሲው በጣም የታመሙ ሰዎች ሰውነታቸው በጣም ጠንካራ የመከላከያ መሰናዶ ስለሚያደርግ በድጋሚ የመያዝ እድላቸው ጠባብ ነው ይላሉ፣ ተመራማሪዎች፡፡ ነገር ግን አሁንም ድረስ ያልታወቀው ነገር ይህ ሰውነት የሚያሰናዳወው የመከላከል ትጥቅና ስንቅ ምን ያህል ጠንካራ ነው፣ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል የሚለው ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በዚህ ጉዳይ ላይ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ በበርታካ የቫይረሱ ታማሚዎች ላይ ጥናት መደረግ አለበት ይላል፡፡ ኮቪድ-19 ተህዋሲ መልኩን የሚለዋውጥ ከሆነና ብዙ የቫይረስ ዝርያ ካለው ሰዎችን በተደጋጋሚ እየመጣ ሊጎበኝ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ ክትባቱንም ዋጋ ቢስ እንዳያደርገው ይፈራል፡፡
news-50198593
https://www.bbc.com/amharic/news-50198593
የአይ ኤስ መሪ አቡ ባካር አል ባግዳዲ ማነው?
የአሜሪካ ጦር ሠራዊት የአስላማዊ መንግሥት ተብሎ የሚጠራው ቡድን መሪ አቡ ባካር አል ባግዳዲ በሚገኝበት አካባቢ ላይ ያካሄደውን ጥቃት ተከትሎ እራሱን ማጥፋቱን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ።
ፕሬዝዳንቱ የአል ባግዳዲን ሞት ይፋ ከማድረጋቸው ከሰዓታት ቀደም ብለው ያለተጨማሪ ማብራሪያ በትዊተር ገጻቸው ላይ "አንድ ትልቅ ነገር ተከስቷል!" በማለት ግልጽ ያልሆነ መልዕክት አስፍረው ነበር። ከዚያም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቤተ መንግሥታቸው በቀጥታ በቴሌቪዥን መስኮት ላይ ቀርበው ይፋ እንደደረጉት የአይኤስ መሪ የሆነው አቡባካር አልባግዳዲ በአሜሪካ ልዩ ኃይል የተደረገበትን ከበባ ተከትሎ ታጥቆት የነበረውን ቦንብ እራሱ ላይ አፈንድቶ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል። • በዶዶላ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ምዕመናን ስጋት ላይ ነን አሉ • በተለያዩ ሥፍራዎች ባጋጠሙ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር 67 ደርሷል ከዚህ በፊት የአይኤስ መሪ የሆነው ባግዳዲ ስለመገደሉ በተደጋጋሚ የተሳሳቱ መረጃዎች መውጣታቸው ይታወሳል። ኒውስዊክ የተባለው መጽሄት ስማቸው ያልተጠቀሱ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው "እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል" መረጃ በመገኘቱ የአሜሪካ የልዩ ዘመቻ ኃይሎች ጥቃት መፈጸማቸውን ዘግቧል። መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የሶሪያ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ተከታታይ ቡድን እንዳለው "ከእስላማዊ መንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች" ባሉበት የሶሪያዋ ኢድሊብ ግዛት ውስጥ ባለ አንድ መንደር አቅራቢያ በሄሊኮፕተር በተፈጸመ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን አመልክቷል። ከጥቂት ሳምንት በፊት የአሜሪካ ሠራዊት ከሰሜናዊ ሶሪያ እንዲወጣ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከባድ ትችት ሲሰነዘርባቸው ለሰነበቱት ፕሬዝዳነት ትራምፕ የባግዳዲ ሞት ትልቅ ድል እንደሆነ እየተነገረ ነው። አል ባግዳዲ ማነው? አቡ ባካር አል ባግዳዲ ተብሎ የሚታወቀው ኢብራሂም አዋድ አል ባዳሪ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ከሚገኙ የሱኒ እስልምና ከሚከተሉ ቤተሰቦች እኤአ በ1971 ኢራቅ ውስጥ ሳማራ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ነበር የተወለደው። ቤተሰቦቹ ከነብዩ ሙሐመድ የዘር ግንድ እንደመጡ የሚናገሩ ሲሆን እምነታቸውን አጥብቀው በመከተል የሚታወቁ ናቸው። አል ባግዳዲ ወጣት እያለ የቁርአን ጥቅሶች በቃሉ ሸምድዶ ያለስህተት የሚደግም የነበረ ሲሆን ኃይማኖታዊ ህግጋትን አንድ በአንድ ተግባራዊ በማድረግም ይታወቃል። • አይ ኤስን ተቀላቅላ የነበረችው እንግሊዛዊት ዜግነቷን ልትነጠቅ ነው • ሴቶች ስለምን የአሸባሪ ቡድኖች አባል ይሆናሉ? ከዘመዶቹ መካከል ጥብቅ የሆኑትን ሃይማኖታዊ ህግጋትን በማያከብሩትን ላይ ባለው ጠንካራ አቋም የተነሳ ቤተሰቦቹ "አማኙ" የሚል ቅጽል ስም ሰጥተውታል። አል ባግዳዲ በሃይማኖት ላይ የነበረው ፍላጎት ወደ ከፍተኛ ተቋማት አድጎ የመጀመሪያ ዲግሪውን በእስላማዊ ጥናት ከባግዳድ ዩኒቨርስቲ ከዚያም ሁለተኛና የዶክትሬት ዲግሪውን ደግሞ በቁርአን ጥናት ከኢራቅ የሳዳም ዩኒቨርስቲ ወስዷል። ባግዳዲ ከሁለት ሚስቶቹና ከስድስት ልጆቹ ጋር በሚኖርበት አቅራቢያ ባለ መስጊድ ውስጥ ያሉ ልጆችን ቁርአን ከማስተማሩ ባሻገር በእግር ኳስ ጨዋታ የአካባቢው ኮከብ ነበር። ዩኒቨርስቲ ውስጥ በነበረበት ጊዜ አጎቱ የሙስሊም ወንድማማችነት ቡድን አባል አግባባውና ቡድኑን ተቀላቀለ። ብዙም ሳይቆይ ቡድኑ ውስጥ ከሚታወቁት ጥቂት ወግ አጥባቂ አክራሪ አባላት መካከል አንዱ ሆኖ ታወቀ። ከዚያም የሳላፊስት ጂሃዳዊ እንቅስቃሴን ተቀብሎ መንቀሳቀስ ጀመረ። አቡ በከር አልባግዳዲ በቅርቡ ለደጋፊዎቹ በኦን ላየን በተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ታይቶ ነበር ከእስር ወደ አማጺነት ከ15 ዓመት በፊት በአሜሪካ የተመራው የኢራቅ ወረራ በተጀመረ በጥቂት ወራት ውስጥ ጃይሽ አህል አል ሱናህ የተባለ የደፈጣ ተዋጊዎች ቡድን በመመስረት ተሳታፊ ነበር። እኤአ የካቲት ወር 2004 ላይ የአሜሪካ ኃይሎች አል ባግዳዲን ፋሉጃ ውስጥ በቁጥጥር ስር አውለው ባቆዩበት ጊዜ ውስጥ ትኩረቱን በሃይማኖታዊ ተግባራት ላይ በማድረግ፣ የአርብ ጸሎትን በመምራትና አብረውት ላሉት ታሳሪዎች ሃይማኖታዊ ትምህርት በመስጠት ጊዜውን ያሳልፍ ነበር። አብረውት ታስረው የነበሩ ሰዎች እንደሚሉት ባግዳዲ እስር ቤት ውስጥ በነበረው እንቅስቃሴ ቁጥብ የነበረና በእስር ላይ ከነበሩት የሳዳም ታማኞችና የጂሃድ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች መካከል በመሆን ተሰሚነትን ለማግኘት ችሎ ነበር። ባግዳዲ በእስር ቤት ቆይታ ከአብዛኞቹ ታሳሪዎች ጋር ትብብርን ለመፍጠር ከመቻሉ በተጨማሪ ከእስር ከተለቀቀም በኋላ ግንኙነቱ ሳይቋረጥ ቀጥሏል። • የብሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት በመካኖች ላይ የሚደርስን ጥቃት በመቃወም አቀነቀኑ ባግዳዲ ከእስር ከተፈታ በኋላ በኢራቅ ውስጥ ያለውን የአልቃኢዳ አንድ ክንፍን የሚመራው ዮርዳኖሳዊው የአቡ ሙሳብ አል ዛርቃዊ ቃል አቀባይን መገናኘቱ ይነገራል። በ2006 ላይ ዛርቃዊ በአሜሪካ በተፈጸመበት የአየር ጥቃት ሲገደል ግብጻዊው አቡ አዩብ አል ማስሪ የመሪነቱን ቦታ ተረከበ። ወዲያውኑም ግብጻዊው በኢራቅ ያለውን የአልቃኢዳ ክንፍ አፍርሶ የኢራቅ እስላማዊ መንግሥት (አይኤስአይ) የተባለውን ቡድን መሰረተ። ነገር ግን ቡድኑ ለአልቃኢዳ ያለውን ታማኝነት እንደማያቋርጥ አሳወቀ። ወደ አመራር ማደግ ባግዳዲ በነበረው ሃይማኖታዊ ዕውቀትና አዲስ በተመሰረተው ቡድን የሌላ ሃገር ዜግነት ባላቸውና በኢራቃዊያን አባላቱ መካከል ያለውን ክፍፍል ለማጥበብ በነበረው ብቃት ምክንያት በፍጥነት ወደ አመራር ስፍራ ለማደግ ቻለ። በ2010 ላይ የኢራቅ እስላማዊ መንግሥት (አይኤስአይ) መሪ በሞት ሲለይ የቡድኑ ከፍተኛ ምክር ቤት አቡ ባከር አል ባግዳዲን በመሪነት ቦታው ላይ እንዲቀመጥ አደረገ። ባግዳዲ መሪነቱን እንደያዘ በአሜሪካ ልዩ የዘመቻ ኃይል በተፈጸመበት ጥቃት ተዳክሞ የነበረውን የቡድኑን እንቅስቃሴ መልሶ የማጠናከር ሥራን ጀመረ። በሶሪያ ውስጥ የተቀሰቀሰውን የእርስ በርስ ጦርነት ተከትሎም ለቡድኑ የተፈጠረውን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም በእርሱ ዕዝ የነበረ የሶሪያ ዜጋ የአል ኑስራ ግንባር የተባለ ምስጢራዊ ቅርንጫፍ ሶሪያ ውስጥ እንዲያቋቁም አደረገ። የአይሲስ መፈጠር ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ከአል ኑስራ ግንባር መሪ ጋር አብረው ለመስራት ስላልተግባቡ ተለያዩ። ባግዳዲም የተጽእኖ ክልሉን ሶሪያ ውስጥ ለማስፋት የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። በ2013 ላይ አል ኑስራ የኢራቅ እስላማዊ መንግሥት (አይኤስአይ) አንድ አካል እንደነበረና ቡድኑን በማጠቃለል "በኢራቅና አል ሻም/ሌቫንት እስላማዊ መንግሥት" (አይኤስአይኤስ/አይኤስአይኤል) በሚል ስያሜ ቡድኑን እንደገና አዋቀረው። ነገር ግን አልቃኢዳ በዚህ እርምጃ ባለመደሰቱ የቡድኑ መሪ አይማን አል ዛዋሂሪ አል ባግዳዲ የአል ኑስራን ነጻነት እንዲያከብር ቢጠይቀውም ሳይቀበለው ቀረ። ይህንንም ተከትሎ ዛዋሂሪ አይኤስአይኤስን ከአል ቃኢዳ እንዲባረር አደረገ። • የአይ ኤስ መሪ ባግዳዲ ድምፁ ተሰማ ባግዳዲም ለዚህ ውሳኔ ምላሽ ያደረገው አል ኑስራን በመዋጋት ቡድኑ በምሥራቃዊ ሶሪያ ጥብቅ ሃይማኖታዊ ህጎችን ተግባራዊ በማድረግ ያለውን ይዞታውን ማጠናከር ቀጠለ። እስላማዊ መንግሥት ከአምስት ዓመት በፊት ሰኔ ወር ላይ አይሲስ የኢራቋን ሁለተኛ ትልቅ ከተማን ሞሱልን መቆጣጠሩን ተከትሎ ቡድኑ ስሙን "እስላማዊ መንግሥት" በሚል አሳጥሮ በቃል አቀባዩ በኩል ጥንታዊው እስላማዊ መንግሥት መመስረቱን አሳወቀ። ከቀናት በኋላም ባግዳዲ ሞሱል ውስጥ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ አርብ ዕለት በነበረ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር የእስላማዊው መንግሥት መሪ (ከሊፋ) መሆኑን ተናገረ። ከዚህ በኋላም የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን አል ባግዳዲ እንደተገደለ የሚያመለክቱ በርካታ የተሳሳቱ ዘገባዎችን ሲያርቡ ቆይተዋል። ባግዳዲ ባለው ለየት ያለ እውቀትና የአመራር ብቃት ቡድኑን ሲመራ ቆይቷል። ቡድኑ እርሱን ካጣ ከባድ ፈተና እንደሚገጥመው ይታመናል።
50443852
https://www.bbc.com/amharic/50443852
ኢሕአዴግ እዋሀዳለሁ ማለቱን የፖለቲካ ተንታኞች እንዴት ያዩታል?
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ተሰምቷል።
ኮሚቴው ዛሬ በሚያካሂደው ስብሰባ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ መክሮ የወደፊት አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል። የውህደት ጉዳይ አጀንዳ እንደሚሆንም ሲወራ ሰንብቷል። ኢሕአዴግ ከግንባርነት ወደ ውህድ ፓርቲነት የሚያደርገው ጉዞ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ቢነሳም እውን ሆኖ አልታየም። የብሔር ድርጅቶች ግንባር የሆነው ኢሕአዴግ እውን ይዋሀዳል? የሚል ጥያቄ እየተነሳ ሲሆን፤ በቅርቡ ግንባሩ ከሕወሓት ውጪ ሊዋሀድ ይችል ይሆናል የሚል ጭምጭምታም ተነስቷል። በጉዳዩ ላይ የፖለቲካ ተንታኙ አደም ካሴ (ዶ/ር) እና የቀድሞው የሕወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ገብሩ አስራትን አነጋግረናል። "የኢሕአዴግ መዋሃድ ጫፍ የደረሰ ይመስላል" አደም ካሴ (ዶ/ር) የኢሕአዴግ መዋሃድ ጫፍ የደረሰ ይመስላል የሚሉት የፖለቲካ ተንታኙ አደም ካሴ (ዶ/ር)፤ የኢሕአዴግ አባል የሆኑት ሦስቱ ፓርቲዎች አጽድቀውታል ተብሎ መወራቱ የሚያሳየው ውህደቱ የቀጠለ መሆኑን ነው ይላሉ። እንደ ፖለቲካ ተንታኙ፤ ውህደቱን ሕወሓት ሲቃወመው ቢቆይም የሚቀር አይመስልም። ዶ/ር አደም፤ አንዳንድ ዝርዝር ጉዳዮችን አሁንም የማናውቅ መሆኑን በማንሳት፤ አዲሱን ውህድ ፓርቲ ጠለቅ ብሎ ለማየት ፈታኝ መሆኑን ያነሳሉ። ኢሕአዴግ ውህደቱን ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ ያለው እንደ ፓርቲ በመሆኑ ሁሉንም ነገር በግልጽ ማወቅ አለብን ማለት አንችልም የሚሉት ዶ/ር አደም፤ የጋራ የሆነ ፕሮግራሙ ምን እንደሚመስል፣ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ፓርቲዎቹ ምን እንደተስማሙ አለማወቃችንን በመጥቀስ ስለ አዲሱ ውህድ ፓርቲ የሚኖረን ምስል ጎዶሎ መሆኑን ያስቀምጣሉ። በተለይ ለኦዲፒም ሆነ ለአዴፓ መሠረታዊ የሚባሉና በግልጽ የሚታወቁ ጉዳዮች ላይ (እንደ አዲስ አበባ ያሉ) የወሰዷቸውን ውሳኔዎችን አልሰማንም ይላሉ። • የ31 ዓመቱ ኢሕአዴግ ማን ነው? • ኢህአዴግ እዋሃዳለሁ ሲል የምሩን ነው? እንዲህ አይነት ሁለቱን ፓርቲዎች የሚያፋጥጡ ነገሮች ዘግይተው ሲሰሙ፤ በታችኛው አባላት ዘንድ ግርታና መከፋፈልን ሊፈጥር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ውህደቱ ቢሳካ እና ኢሕአዴግ ከሕወሓት ውጪ ቢዋሀድ፤ አዲሱ ፓርቲ ከቁጥር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዮች አንጻር የሶማሊያና ሌሎች አጋር ተብለው የቆዮ ፓርቲዎች ስለሚቀላቀሉት ሊያካክሰው ይችላል ይላሉ። ዶ/ር አደም፤ ከባድ ሊሆን የሚችለው፤ ሕወሓት በውህደቱ ውስጥ ካልተካተተ ከእርሱ ጋር የሚሠሩ ሌሎች ፓርቲዎችን መፈለግ ስለሚኖርበት ነው በማለት፤ ሕወሓት በሃሳብ ወይንም በርዕዮተ ዓለም የሚመስሉትን የሚፈልግ ከሆነ፤ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጎልተው የሚታዮትና በብሔር ፖለቲካ አስተሳሰብ አቋማቸው ከእርሱ ጋር የሚመስሉትን ኦነግ፣ አብንና ምናልባትም ኦፌኮ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ። እነዚህ ፓርቲዎች የብሔር ፖለቲካን መሰረት አድርገው የተደራጁ መሆናቸውና ጠንካራ ተገዳዳሪ መሆን ከሚችሉ ክልሎች መገኘታቸውን በመጥቀስ፤ ከእነዚህ አካላት ጋር ለመሥራት ፍላጎት ሊኖር እንደሚችል ያላቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። ሆኖም ግን በኦሮሚያም በአማራ ክልልም ከሕወሓት ጋር በሃሳብ የሚጣጣሙ ፓርቲዎች ቢኖሩም፤ ሁለቱም ክልሎች ላይ ያሉት ገዢ ፓርቲዎች ከክልላቸው ተቃዋሚዎች ጋር አብሮ ለመሥራት የመሰባሰብ አዝማሚያ ማሳየታቸው፤ ሕወሓት ግንባር የሚሆነው ፓርቲን እያሳነሰበት እንደሚሄድ ዶ/ር አደም ይጠቅሳሉ። ሕወሓት በሚቀጥሉት አምስት አስር ዓመታት በክልሉ ውስጥ ጠንክሮ ሊሄድ እንደሚችል የሚገልጹት ዶ/ር አደም፤ በሌላ ክልል ካሉ ፓርቲዎች ጋር በግንባር ለመሥራት ያለው ሁኔታ እንደሚታሰበው ቀላል አይሆንለትም ሲሉ ይገልጻሉ። "ሕወሓት ብቻውን የመሆን እድሉ ሰፊ ነው" በማለትም፤ ከኢሕአዴግ ጋር ድርድር አድርጎ ለመቀጠል ወይም ከሌሎች ጋር በጋራ ለመሥራት ያለው እድል ፈታኝ ዳገት መሆኑን ያነሳሉ። ሕወሓት በአገር ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ለመቀጠል ትልልቅ ፓርቲዎች ውስጥ መግባት እንደሚጠበቅበት በማስታወስ፤ ያንን ከየትኛው ወገን፣ ግንባር፣ ጥምረት ጋር ሆኖ እንደሚያደርገው በሂደት ይታያል ይላሉ። "ሕወሓት በመግለጫ እንገነጠላለን ብሎ አያውቅም" የሚሉት ዶ/ር አደም፤ ካለው ሥርዓት አንጻር በክልል ደረጃ ያለውን ሥልጣን መጠየቁ መጥፎ አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ። በዚህ መካከል ግጭትና አለመግባባት ቢነሳ፤ አሁን ባለው የፌደራል ሥርዓት ውስጥ ግጭቶችን መፍቻ መንገድ የለም የሚሉት ዶ/ር አደም፤ ሁሉም በየክልሉ 'ይኼ የኔ ነው፤ ይኼ የኔ ነው' በሚልበት በአሁኑ ወቅት ግጭቶች እንደሚጠበቁ በማንሳት፤ በአሁኑ ሰዓት እንደ ቀድሞው ግጭቶቹን በፓርቲው በኩል የሚፈታ ሥርዓት አለመኖሩን በመጥቀስ ያላቸውን ስጋት ያስቀምጣሉ። ከፓርቲው ውጪ ግጭቶችን መፍታት የሚያስችል የሕግ ሥርዓትን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ያነሳሉ። ዛሬ ሕወሓት አለኝ የሚለውን ቅሬታ ነገ ሌላ ክልል ሊያነሳው ስለሚችል፤ ዲሞክራሲያዊ አገር ለመገንባት ግጭቶችን መፍቻ መንገድ ማበጀት እንደሚገባም ይመክራሉ። አሁን ያለችው ኢትዮጵያ፤ ሁሉ ነገሯ በብሔር የተዋቀረ መሆኑን በማንሳት፤ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖረውን የኢሕአዴግ የውህደት አጀንዳ ለማስፈፀም ላይ ታች ሲሉ የከረሙት በብሔር የተዋቀረውን ክልል መቀየር ባይችሉ እንኳን፤ የፓርቲ ሥርዓቱን አንድ በማድረግ ማለዘብ አስፈላጊ መሆኑን በማመናቸው ነው" ይላሉ። • ኢህአዴግ ከአባል ፓርቲዎቹ መግለጫ በኋላ ወዴት ያመራል? • "ለውጡን ለማደናቀፍ ከተቻለም ለመቀልበስ የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ" ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ ከበርካታ ወገኖች ቅሬታ የሚቀርብበት ቢሆንም፤ በጥሩ መልኩ ከሄደ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋግመው እንደገለፁት ትንንሽ ፓርቲዎች ተውጠው፣ በሃሳብ ዙሪያ የሚደራጁ ትልልቅ ፓርቲዎች መፈጠራቸው አይቀርም ሲሉ ያላቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። "በኦሮሚያ ውስጥ ያለው ብሔርተኝነት ለዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እርምጃ ትልቁ ፈተና ነው" የሚሉት ዶ/ር አደም፤ በቀጣይ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ላይ መቆየታቸውን ለማረጋገጥ፤ በክልላቸው ድጋፍ የማግኘት እድላቸው አጠራጣሪ በመሆኑ፤ ኢሕአዴግ ሲዋሃድ ከሌሎች አካባቢዎች በሚያገኙት ድምጽ እድላቸው እንደሚሰፋም ይናገራሉ። ዶ/ር አደም፤ "ውህደቱ ከዐብይ የሚያልፍ፣ በሀሳብ ላይ የተመሰረተ መሆን አለመሆኑ ላይ ጥያቄ አለን" በማለት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያየ ምክንያት በሥልጣን ባይቀጥሉ ውህደቱ ይቀጥላል ወይ? የሚለውን ለማየት፤ የአዲሱን ውህድ ፓርቲ ፕሮግራም ማየት አስፈላጊ መሆኑን ይመክራሉ። "ፓርቲ ሊበተን ይችላል፤ ይሄ የአገርን እጣ ፈንታ መወሰን ግን የለበትም" አቶ ገብሩ አስራት የቀድሞው የሕወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ ገብሩ አስራት፤ ስለ ውህደት ሲነሳ፤ የፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት በሌለበት ሁኔታ ከሆነ በገዢ ፓርቲው ዘንድ ቀውስ እንዳለ ያመለክታል ይላሉ። በእርግጥ በየትኛውም አገር የፓርቲ ግንባር ሊፈርስ፣ አዲስ ቅንጅት ሊፈጠር እንደሚችልም ቢጠቅሱም፤ ይህ ሂደት ወደ ኢትዮጵያ አውድ ሲመጣ ምን ሊያስከትል እንደሚችል እንዲህ ያብራራሉ። "ኢትዮጵያ ውስጥ ገዢ ፓርቲ የመንግሥት መዋቅርን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረ፣ ሕዝቡንም ለመቆጣጠር የሚሞክር ስለሆነ አንድ ፓርቲ ሲላላና ሲዳከም የሚፈጠሩ ችግሮች አሉ። ከአራቱ መስራች ድርጅቶች አንዱ ሕወሓት ከወጣ፣ [ውህደቱ] የተቀሩት ተወያይተው የተስማሙበት ካልሆነም ችግሩ ለሕዘብ የሚተርፍ ይሆናል።" በኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ ኢሕአዴግን ጨምሮ ፓርቲዎች የሚፎካከሩ ሳይሆኑ በጥቅም የተሳሰሩ እንዲሁም አንዱ ሌላውን እየጠለፈ የሚሄድ መሆኑን በማጣቀስ፤ "እስካሁንም ገዢ ፓርቲው አለመስማማቱ፣ አንድ አለመሆኑ ኢትዮጵያን ብዙ ዋጋ እያስከፈላት ነው" ይላሉ። ኦቶ ገብሩ በመርህ ደረጃ ውህደትን እንደማይቃሙና እንዲያውም ኢሕአዴግ ለውህደት ዘግይቷል ብለው እንደሚያስቡ ይናገራሉ። ሆኖም ግን በችኮላ፣ ለፓለቲካ ጨዋታ ሲባልና ስምምነት ሳይፈጠር መዋሀድ ዘላቂነት ይኖረዋል? ሲሉ ይጠይቃሉ። ኢሕአዴግ መዋሀድ ካለበት፤ የጋራ ፕሮግራም እና የጋራ ሕገ ደንብ መኖርን እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጣሉ። ሕወሓት በውህደቱ አልሳተፍም ካለም መብቱ እንደሆነና ችግር እንደማይፈጠርም ያክላሉ። ሆኖም ግን ጉዳዩ ችግር ሊያስከትል የሚችልባቸውን ሁለት አካሄዶች እንዲህ ያስቀምጣሉ። "አንደኛ፤ ቀሪዎቹ ሦስት ድርጅቶች እኔ ያልኩትን ብቻ፣ የኔን ርዕዮተ ዓለም ብቻ ተቀብለው ካልሆነ በስተቀር አልዋሀድም ከተባለ ስህተት ነው። ሁለተኛ፤ እኔ በዚህ ውህደት ከሌለሁ ትግራይም ትገነጠላለች የሚለው አካሄድም ስህተት ይመስለኛል።" አቶ ገብሩ፤ የፓርቲውን አለመስማማትና የሥልጣን ሽኩቻ ወደ ሕዝብ ወስዶ፤ እኔ እዚህ ሥልጣን መሀል ካልቆምኩ፤ ሕዝብም ይገነጠላል የሚለው አስተያየት የተሳሳተ እንደሆነ ይገልጻሉ። ይህ ከምጣኔ ሀብት፣ ከደህንነት እንዲሁም ከዲፕሎማሲ አንጻርም ለትግራይ ሕዝብም ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር እንዲሁም ሕዝቡ ብዙ ታግሎ ያገኛቸውን ነገሮች የሚያሳጣ እንደሆነም ያክላሉ። "ሕወሓት ርዕዮተ ዓለሙን የማራመድ፣ ከመሰሉት ድርጅቶች ጋር የመጣመርም መብት አለው። ፓርቲ ሊበተን ይችላል፤ ይሄ ግን የአገርን እጣ ፈንታ መወሰን የለበትም። አገር ሊበተን ይችላል ማለትም አደገኛ ነው" ሲሉም አቋማቸውን ይገልጻሉ። ሕወሓት እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ ሊቀጥል ይችላል ወይ? በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ፤ ውይይትና ድርድር የማይሆን ሲሆን ከፓርቲ ወጥቶ አቋምን ማራመድ በፖለቲካ ያለ ቢሆንም፤ አሁን ላይ ሕወሓት እጅግ የተዳከመበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለ በመግለጽ "የሚከተለውን ርዕዮተ ዓለም ይዞ ሕዝብን ያሰባስበል የሚል አመለካከት የለኝም" ይላሉ። መሀል ቦታ የነበረው ድርጅት ለምን በአጭር ጊዜ ተበታተነ? የሚለው መታሰብ አለበት የሚሉት አቶ ገብሩ፤ ችግሩ ቆም ተብሎ ከታየ፤ መልሶ ፓርቲ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ • የምክር ቤቱ ስብሰባ ኢህአዴግን ወዴት ይመራው ይሆን? • ህወሓት፡ ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች ከሳምንት በፊት የሕወሓት ልሳን በሆነው 'ወይን' መጽሔት ላይ አገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ በማካሄድ 'ዲ ፋክቶ ስቴት' ይሆናል መባሉ ይታወሳል። አቶ ገብሩ "የተባለው እውን የሚሆን አይመስለኝም "ይላሉ። አሁን ላይ የትግራይ ተወላጆች ከተለያየ ቦታ እየተፈናቀሉ መሆናቸውን፣ የሕወሓት አጋሮች በትግራይ ሕዝብና በሕወሓት ላይ እየዛቱ መሆኑንም ጠቅሰው "በሁሉም በኩል ጽንፈኛ አካሄድ አለ" ይላሉ። "ሕወሓት ብቻ ሳይሆን አዴፓ፣ ኦዲፒም ጽንፈኛ ፖለቲካ እያራመዱ ነው። የራሳችን መንግሥት እንመሰርታለን የሚለው ጽንፍ ጊዜያዊ ሁኔታው የፈጠረው ነው። ነገር ግን ጊዜያዊ ሁኔታ የፈጠረውን ችግር እንደ ዘላቂ ስትራቴጂ መውሰድ ችግር አለበት" ሲሉም ያብራራሉ። አንድ ፓርቲ ስለተሸነፈ፣ የፓርቲ አመራር ከሥልጣን ስለተወገደ የትግራይ ሕዝብ እድል በዛ መወሰን የለበትም የሚሉት አቶ ገብሩ፤ "መሰረቱ ሕዝብ ለሕዝብ አይጣላም፣ ሕዝብ ለሕዝብ አይዋጋም፣ ሕዝብ ለሕዝብ አይራራቅም" ሲሉም ያክላሉ።
news-53118423
https://www.bbc.com/amharic/news-53118423
የማይመጣውን አባታቸውን የሚጠብቁት የዶክተር አምባቸው ልጆች
ቅዳሜ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም። አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ።
ባህር ዳር ዕለቱን እንደተለመደው ደመቅመቅ ብላ ጀመረች። ከሰዓት በኋላ ላይ ግን ተኩስ በየአቅጣጫው ይሰማባት ጀመር። ከዚያ በኋላ የተፈጠረው ክስተት፤ ቅዳሜ ሰኔ 15 በባህር ዳር ታሪክ ፀሊሟ ቀን የሚል ስያሜ ቢያሰጣት አያስገርምም። አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) እና ወይዘሮ የሹሜ ደምሳሽ በትዳር ለ29 ዓመታት አብረው ኖረዋል። አምስት ልጆችም አፍርተዋል- አራት ሴት አንድ ወንድ። አምባቸው (ዶ/ር) እንደ አማራ ክልል ፕሬዝዳንትነታቸው የሥራ ቦታቸው ባህር ዳር ነው። ቤተቦቻቸው ደግሞ አዲስ አበባ ነው የከተሙት። አምባቸው (ዶ/ር) ከባህር ዳር ለሥራ ሲመጡ መሄጃቸውንም ሆነ መመለሻቸውንም አይናገሩም። እንደ ወይዘሮ የሹሜ "በቃ ሲመጣ ምጥት ሲሄድም መሄድ ነው። እንደዚህ ነው የእሱ ጸባይ።" "አንድንድ ነገር እንኳን አዘጋጅቼ እንድጠብቅህ" በሚል፤ መሄጃ እና መመለሻህን ንገረንም ተብለው ተጠይቀው ያውቃሉ። "እኔ ከእናንተ የተለየ ነገር አልፈልግም ይለኛል" ምላሻቸው ነው። አዲስ አበባ የሚገኘው የአምባቸውን (ዶ/ር) ቤት እንግዳ አያጣውም። ቅዳሜ ሰኔ 15/2012 ዓ.ም ጥየቃ የመጡ ቤተ ዘመዶች ቤቱን ሞልተውታል። ቤቱ በጨዋታ ደምቋል። የቤቱ እማወራ የወይዘሮ የሹሜ የአክስት ልጅ ስልክ እስኪደውል ድረስ ጨዋታው ቀጥሏል። "ደውሎ 'ባህር ዳር ተኩስ አለ' አለኝ። . . . ለአምባቸው ደወልኩኝ። ስልኩ አይሠራም" ይላሉ ወይዘሮ የሹም። መረጃ ለማግኘት የተለያዩ ሰዎች ዘንድ ደወሉ። ምላሽ የለም። የት እንደሚደውሉና ምን እንደተከሰተ ለማወቅ ቢያወጡ ቢያወርዱ አማራጭ ጠፋ። "እንደ ብርድም፤ እንደ ህመምም፤ እንደ መንቀጥቀጥም [አደረገኝ]። ምንም መቋቋም አልቻልኩም። ሰውነቴ ደረቀ" ይላሉ። አንዳች ነገር እንደተከሰተ ደመነፍሳቸው የነገራቸው ወ/ሮ የሹም ትንሽ ቆየት ብለው አምባቸው (ዶ/ር) እግራቸውን በጥይት ተመትቶ ለህክምና ወደ አዲስ አባባ ሊመጡ መሆኑን ይሰማሉ። "'ተጎድቶም ይትረፍልኝ። ተጎድቶም ለልጆቼ ይኑርልኝ' አልኩኝ። አዳር አይባልም እንዲሁ ሳለቅስም፣ ስነሳም ስወድቅም ምንም ስል በከፋ ስቃይ ውስጥ ሌሊቱ አለፈ" ሲሉ የመከራውን ሌሊት ያስታውሳሉ። አይነጋ የለም ሌሊቱ ነጋ። እሑድ ሰኔ 16/2011 ዓ.ም ። ፀሐይ ወጥታ ባለቤታቸው ካሉበት ደርሰው ከጎናቸው ለመቆም ወደየት መሄድ እንዳለባቸው የሚነግሯቸውን ሰዎች ሲጠብቁ የነበሩት ወይዘሮ የሹሜ በማለዳ የአምባቸውን (ዶ/ር) ሞት ከቤተሰብ እና ዘመድ አዝማድ ተረዱ። ቀሪው ታሪክ ነው። "ትልቅ ሐዘን በጣም፤ ልብ የሚሰብር ሐዘን ደርሶብናል። እንኳን ቤተሰቡን የሌላውንም ልብ ሰብሯል። የአባት ሞት የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ ይሰብራል። በጣም መራር የሆነ ሃዘን ነው የወደቀብን።" "በቃ ቤተሰቡ በአምባቸው ሞት ክፉኛ ነው የተሰበረው። ተጎዳን። . . . የአምባቸውን ሞት እኔ እራሴ እስካሁን መቀበል አልቻልኩም" ሲሉ የሐዘናቸውን ጥልቀት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተለይ ለሥራ ወጥቶ ስለቀረው አባታቸው ለልጆች መንገርና እንዲቀበሉት ማድረግ ካበድ ነው የሆነባቸው። "ከፍ ከፍ ያሉት ልጆች ጉዳዩን ይረዱታል። ከባዱ ነገር ዘወትር የአባታቸውን መምጣት በር በር እያዩ ለሚጠብቁት ለትንንሾቹ ማስረዳት ነው" ይላሉ። የቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ አራት ዓመቷ ነው። ሁሌም ትጠይቃለች። "አባቴ አይመጣም ወይ" እያለች። "'ሥራ ሂዷል አይመጣም' ስትባል ጸሎት ቤት ትገባና 'አባን አምጣልኝ ብዬ ለመንኩት' ትለኛለች አሁንም ድረስ። 'አይመጣም እኮ' ብዬ ነግሬሻለሁ ስላት ምንም አትረዳም። በቃ ምንጊዜም ቢሆን አዲስ ናት። እሷ አሁንም ይመጣል ነው የምትለው። ". . . ወንዱ ልጅ 13 ዓመቱ ነው። እሱ ብዙ ነገር ስለሚያውቅ አይናገርም። በጣም የተጎዳው እሱ ነው። አይናገርም ዝም ነው የሚለው። ነገር ግን ከፊቱ ላይ ጥበቃውንና ሐዘኑን እረዳለሁ። "እሱም እኛን ያያል የሆንነውን ይረዳል። የሁሉንም ሰው ዓይን ዓይን እያየ የሚረዳው ነገር አለ" ሲሉ የአባታቸው ከቤተሰቡ መጉደል በተለይ በልጆቻቸው ላይ የፈጠረውን ስሜትና እርማቸውን እንዲያወጡ ለማስረዳት እንዴት እንደከበዳቸው በሐዘን ተሞልተው ይናገራሉ። እንደ አካላቸው ክፋይ የሕይወት አጋራቸው እሳቸውም "እንኳን አሁን ተለይቶች በህይወት እያለ አምባቸውን ሳላስበው ውዬ አድሬም አላውቅም" የሚሉት ወ/ሮ የሹሜ አምባቸውም (ዶ/ር) ለእርሳቸው ያለቸውን መሳሳትና ትዝታቸው አሁን ድረስ ትኩስ ነው ይላሉ። የቤተሰብ ሰው የነበሩት አምባቸው (ዶ/ር) ቀልድ እና ጨዋታ አዋቂ እንደነበሩ የሚናገሩት ባለቤታቸው "ማታ እቤት የሚሰራውን ነገር እንኳን ይዞ ቢመጣ ሰዓቱን አጣቦም ቢሆን ቁጭ ብለን የምንጫወተውን ምንጊዜም አስታውሰዋለሁ። ከቁም ነገርኝነቱ ባሻገር ቀልድም ጨዋታም በጣም ይችላል" ሲሉ ብዙ ነገር ቤተሰቡ እንዳጣ ይጠቅሳሉ። አምባቸው (ዶ/ር) ከመሞታቸው ከጥቂት ቀናት በፊት የተጨዋወቱተን ፈጽሞ አይረሱትም። "በጨዋታ መሃል ድንገት 'አንቺ እኮ ጎበዝ ነሽ፤ ልጆችሽን ታሳድጊያለሽ' አለኝ ሊሞት አንድ ሳምንት ሲቀረው። 'እኔ እንዲህ ዓይነት ቀልድ አይመቸኝም። ሁለተኛ እንዲህ ዓይነት ነገር እንዳታወራ' አልኩት። "እኔም 'ምን አስቦ ይሆን? ምን ተሰምቶት ይሆን?' አልኩኝ። ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርም ምንም አላለኝም። ይሄንን ነው ያለኝ። ስቆጣ በቀልድ ቀየረው። ረሳነው። ወዲያው ተውነው። ምን እንዳሰበ እና ለምን እንደተሰማው ባላውቅም ይሄንን ብሎኛል" በማለት ጥያቄያቸውን ይዘው በሃሳብ ወደዚያች ቀን ተመለሱ። በአማራ ክልልና በፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሰሩት አምባቸው (ዶ/ር) ካላቸው ኃላፊነት አንጻር ከፍተኛ የሥራ ጫናና ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ነበረባቸው። ቢሆንም ግን ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ከቤተሰባቸው ጋር ጊዜያቸውን ማሳለፍን ይመርጡ እንደነበር ባለቤኣተቸው ይናገራሉ። ለልጆቻቸው እንደ አባት ፍቅር ለመስጠት፣ ለማስተማርና ለመምከር አንድ ቀንም ወደኋላ የማይሉት አምባቸው (ዶ/ር) ልጆቻቸው ጠንካራና በእራሳቸው የሚተማመኑ እንዲሆኑ አዘውትረው ይመክሩ ነበር። በተለይ ልጆች በምቾት እንዳይዘናጉ "'አስለምደዋለሁ እግሬን ካለጫማ፤ ምንግዜም ደህና ቀን አይገኝምና እያለ አባቴ ይነግረኝ ነበር። እናንተም እንደዚህ ብላችሁ ማደግ አለባችሁ። እኔ ቋሚ አይደለሁም'" ይሏቸው እንደነበር ወ/ሮ የሹሜ ያስታውሳሉ። አሁን የቤተሰቡ ኃላፊነት በወይዘሮ የሹሜ ትከሻ ላይ ሙሉ ለሙሉ ወድቋል። ቢሆንም ግን ልጆቹም ከአባታቸው ፍቅር ሌላ የሚጎድልባቸው የለም ይላሉ። "እነሱ የአባትነትን ፍቅር ማጣቱ፣ እሱን ካጠገባቸው ማጣታቸውና የእሱን መምጣት በመጠበቅ ከሚፈጠርባቸው ጫና ውጪ በሌላው ጉዳይ ልጆቹ ያለምንም ችግር ያድጋሉ" ይላሉ። በዕለቱ ባህር ዳር ውስጥ ስለተፈጸመው ነገር የተለየ ነገር የሚያውቁትም የሰሙትም ነገር የሌለው ወ/ሮ ሹሜ እሳቸውም "እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ ነው እየሰማሁ ያለሁት" ይላሉ። "ጀነራሉ ገደለ። እሱም ተገደለ ተባለ። አለቀ። ከዚያ ውጪ ፍትህ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው የምጠብቀው። እኔ ፍትህ አግኝቻለሁ አልልም። ከእሱ ጀርባ ያለው አሁንም አልጸዳም። እሱ ብቻውን አያደርገውም፤ እሱ ብቻውን አልገደለውም። ከኋላ ቆስቋሹ ማነው? የሚለውን ያወቅኩት ነገር የለኝም" በማለት ጉዳዩ እንዳልተቋጨ ይናገራሉ። ቢቢሲ፡ ለመጨረሻ ጊዜ ከዶ/ር አምባቸው ጋር ስለምን አወራችሁ? ወይዘሮ የሹሜ፡ ብዙም አላስታውሰውም ግን እኔ ነጋ፣ ጠባ ይገድሉሃል እላለሁ። ይገድሉሃል ስል ነበር። ቢቢሲ፡ ለምን ነበር እንዲዚያ የሚሉት? ወይዘሮ የሹሜ፡ አንድ ሰው ደውሎ ነገረኝ። ቢቢሲ፡ ምን ብሎ ነገርዎት? ወይዘሮ የሹሜ፡ ለአምባቸው የምትነግሪልኝ መልዕክት ብሎ እንደሚገደል ነገረኝ። ከዚያ ደነገጥኩና አንተ ማን ነህ? ስለው 'ማንነቴ ምን ያደርግልሻል። እሱን ሰውዬ ግን ተጠንቀቅ በይው' አለኝ። ከዚያም ነገሩ ስላሳሰበኝ እንዲጠነቀቅ ነገርኩት። ስነግረው 'የሹሜ እንደዚህ እያልሽ አዕምሮሽን እያስጨነቅሽ በሽተኛ እንዳትሆኚ። እኔ ምን አድርጌ ነው የሚገድሉኝ? ምን አጥፍቼ ነው የሚገድሉኝ?' አለኝ። ይሄንን አስታውሳለሁ . . . እና በጣም ያሳዝናል። የእሱ ሞት ለእኔ አንጀት የሚያሳርር ምንግዜም አዲስ ነው። እኔ እስከምሞት ድረስ በቃ እንዲሁ ስቃጠል ነው የምኖረው። አሟሟቱ በጣም ነው የሚያሳዝነው። አገሬን ላለ ሰው፣ ለዚያውም ቢሮ ውስጥ ወረቀትና ስክሪብቶ ብቻ ይዞ መገደል፤ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በጣም ነው የማዝነው። የሰኔ 15/2011 ዓ.ም በባህር ዳርና በአዲስ አበባ ውስጥ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትና የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች የተገደሉበት ክስተት ፈጽሞ ከኢትዮጵያም አልፎ ዓለምን ያነጋገረ ነበር። ክስተቱ በአማራ ክልልም ሆነ በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ትልቅ ጠባሳን የጣለ እንደነበር የሚያምኑት ወ/ሮ የሹሜ ባለቤታቸው ባላቸው አቅም ሁሉ ለዘመድ ወገን ደራሽ ሌብነትን የሚጸየፉ እንደነበሩ ይናገራሉ። "ምንም ምንም የሌለን እንዲህ አድርጉልን እያልን በልመና ነው የምንኖረው። አምባቸው የመንግሥትን ሰባራ ሳንቲም የማይመኝና የማይነካ ንጹህ ህሊናና ንጹህ እጅ የነበረው ንጹህ ደሃ ነበር፤ ንጹህ። በዚህም ደረቴን ነፍቼ አንገቴን ቀና አድርጌ እንድሄድ አድርጎኛል" በማለት በባለቤታቸው ሥራ እንደሚኮሩ ይገልጻሉ።''አባቴ የቼልሲ ደጋፊ ነበር'' የሜጄር ጄኔራል ገዛዒ አበራ ልጅ "የዶክተር አምባቸው ባለቤት ስባል የሌባ ሚስት እንደማልባል አውቃለሁ" የሚሉት ወ/ሮ የሹሜ፤ በአምባቸው (ዶ/ር) ሞት ከቤተሰቡ በተጨማሪ የአማራ ክልል በአጠቃላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ጉዳት ደርሶበታል ብለው ያምናሉ። አምባቸው (ዶ/ር) በኃላፊነት በቆዩበት ጊዜ በተለይ አንድ ጉዳይ የበለጠ ያስጨንቃቸውና ይቆጫቸው ነበር የሚሉት ባለቤታቸው የሰዎች መፈናቀል ዋነኛው ነገር ነበር። "'በኃላፊነት ላይ ሆኜ ሕዝቡ ከቀየው ተፈናቅሎ እረፍት የለኝም' ይል ነበር። ይህንንም ለማስተካከል "ችግር ባለባቸው ቦታዎች መረጋጋትን ማምጣት ዋነኛው ትኩረቱ ነበር። የቀን ጭንቀቱ የሌሊት ህልሙ ይህ ነገር ነበረ" ይላሉ። ከዚህ በተጨማሪም "ፋታ አጥቶ ነበር" ነበር የሚሉት ወ/ሮ የሹሜ በጎን ደግሞ "የእሱን አመራርነት ያለውደዱ ሰዎች በዚያም ተኩስ በዚያም ማፈንዳት በዚያም ማቃጠል ሥራቸው ነበር። ይሄ በጣም ያስጨንቀዋል" በማለት የክልሉ ነገር በፌደራል ኃላፊነት ላይ ሆነው ጭምር ያሳስባቸው እንደነበር ይመሰክራሉ። ለሕዝቡ ሠላምና መረጋጋትረ ማምጣትና ከድህነት እንዲወጣ ለማድረግ ሌት ከቀን ከመጨነቅ ውጪ በሌላው ነገር ግን "በራስ መተማመንና የንጹህ ህሊና ባለቤት ነበረ። ፍርሃትን የማያውቅ ሙልት ያለ ልበ ሙሉ ጀግና ነበር። ሌላ የሚያስጨንቀው ነገር የለውም።" ወይዘሮ የሹሜ ከአንድ ዓመት በፊት የተለዩአቸው ባለቤታቸው ስላላቸው መልካምነት ለማወቅ አብረውት ከዋሉና ከሰሩ ሰዎች መካከል ከትንሽ እስከ ትልቁ የሚመሰክሩላቸው ሰው አክበሪነታቸውን እንደሆነ ይናገራሉ። ይህንንም "አምባቸው የበላዩን የማይፈራ የበታቹን የሚያከብር" ሲሉ ይገልጿቸዋል። ሠላምተኛ፣ ትሁትና ሰው ወዳጅ ነበሩ የሚሏቸው የባለቤታቸው መልካም ባህሪያት መለያቸው እንደነበሩ ይመሰክራሉ። ባለቤታቸው እንደሚሉት አምባቸው (ዶ/ር) ዘመድ ወዳድም ናቸው። "የእኛ ቤት የባለስልጣን ቤት አይመስልም። ዘመድ ጎረቤት የሚያዘወትረው ነው። እሱም ከሥራ ለምሳ ሲመለስ እንግዳ ይዞ ነው የሚመጣው። ጊዜ ሲያገኝ ከጓደኞቹ ከዘምድ ጋር መሆንን የሚመርጥ ሰው ወዳድ ነበር" ይላሉ። ከሁለት ዓመት በፊት በመጣው ለውጥ ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ተብለው ከሚጠቀሱት ሰዎች መካከል አንዱ እንደሆኑ የሚጠቀሱት አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ከተደሰቱባቸው ነገሮች መካከል በለውጡ የተገኘው ውጤት ነው። በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መሾም ትልቅ ደስታን ፈጥሮላቸው እንደነበር ባለቤታቸው ይጠቅሳሉ። "የዚያን ቀን በህይወቱ በጣም ከተደሰተባቸው ቀናት መካከል አንዱ ነበር። ወደ ቤት ሲመጣ እጅግ ተደስቶ 'ከየትኛውም ጊዜ በላይ በህይወቴ በጣም የተደሰትኩበት ቀን' ብሎ ነው ያመሸው።" ወይዘሮ የሹሜ ከነቤተሰባቸው የሚኖሩት አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን የመንግሥት ሠራተኛ ናቸው። ከባለቤታቸው ሞት በኋላ በሚያገኙት ጡረታ ልጆቻቸውን እያስተዳደሩ ነው። አዲስ አበባ አሁን ያሉበት ቤት የመንግሥት የኪራይ ቤት ነው። በፊትም ባለቤታቸው በሚያገኙት የመንግሥት ደሞዝ ላይ የተወሰነ ገቢን ይመሩ ስለነበረ ቤተሰባቸው የተቀማጠለ ሕይወት አለመልመዱን የሚናገሩት ወ/ሮ የሹሜ "እኔ ተንቀባርሬ እንደፈለኩ እያወጣሁ ስላልኖርኩ በተለመደው ህይወት ቀጥያለሁ" ይላሉ። ዋነው ግባቸው ልጆቻቸውን ሳይቸገሩ ማሳደግ እንደሆነ የሚገልጹት ከመንግሥትና ከፓርቲው ድጋፍ እንደተደረገላቸው ጠቅሰው አሁንም ቤተሰቡን ለመደገፍ የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉና በአምባቸው (ዶ/ር) ስም ፋውንዴሽን ለማቋቋም ሐሳብ እንዳለ ገልጸዋል። "የጎደለብን ነገር የለም እግዚአብሔር ይመስገን። በዚያ ላይ መንግሥትም መሪ ድርጅቱም ገንዘብ ሰጥተውናልናል። አሁንም መንግሥትን ሕዝብንም ሁሉንም ነው የምንጠይቀው። ለፋውንዴሽኑን የሚደረግ ትብብር እንጂ ለቤታችንና ለኑሯችን ችግር የለብንም።" ቤተሰባቸውና ወዳጆቻቸው በአምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ስም የሚቋቋመው ፋውንዴሽን በትምህርት እና በበጎ አድራጎት ላይ ያተኩራል ተብሏል። "አምባቸው የፊዚክስና የሒሳብ ትምህርቶችን የሚወድ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበር። በእነዚህ የትምህርት ዘርፎች ላይ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎችን ለመደገፍና ለእሱም ማስታወሻ ለማቆም ነው በፋውንዴሽኑ የታሰበው። ዘወትር መልካም ነገሮችን ለሰዎች ስለሚያስብ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በስሙ እንሠራለን ብዬ እናስባለሁ" ብለዋል። የአምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ህልፈት በቤተሰቡ ላይ የማይጠገን ክፍትት ከመፍጠሩ ባሻገር ለእናታቸውም ሞት ምክንያት ነው ብለው ባለቤታቸው ያምናሉ። እሳቸው እንደሚሉት ለቤተሰባቸው የመጀመሪያ ልጅ የነበሩት አምባቸው የእናታቸው ተንከባካቢና የዘወተር ተስፋ ነበሩ "የእሱን ሞት ሲሰሙ መኖር አልቻሉም። በሕይወት መቆየትም አዳጋች ሆነባቸው። በዚህም አልበላም አልጠጣም በማለት ራሳቸውን ጉድተዋል" ሲሉ የልጃቸው ሞት የነበረውን ተጽእኖ ይናገራሉ። ወ/ሮ የሹሜ አምባቸው (ዶ/ር) ሞት በቤተሰቡ ላይ ካሳረፈው ከባድ ጉዳት ሁሉ ትንንሹቹ ልጆቻቸው የአባታቸውን ፍቅር ሳያጣጥሙ መቅረታቸው ነው። "ከባዱ ጉዳት ልጆች በእሱ ፍቅር በእሱ አዕምሮ ተቀርጸው ማደግ ነበረባቸው። እነዚህ ትንንሽ ልጆች ልክ እንደትልልቆቹ ማሳደግ ነበረበት። በአንድ እናት ብቻ ከባድ ነው። በጣም ነው ያሳዘነኝ። ለሃገር ለህዝብ ሲል ለልጆቹም ሳይሆን የእሱን ፍቅር እና የእሱን ስነምግባር ሁሉንም ነገር ሳያውቁ ሲያድጉ መሞቱ በጣም ያሳዝነኛል" ሲሉ ሳግ በሸፈነው ድምጽ ቁጭታቸውን ገልጸዋል። ባህር ዳር ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት አምባቸው መኮንን (ዶ/ር)፣ አቶ ምግባሩ ከበደ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደረጃ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እና አቶ እዘዝ ዋሲ የርዕሰ መስተዳድሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ በክልሉ ምክር ቤት ውስጥ በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። አዲስ አባባ ላይ ደግሞ የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ጓደኛቸው ጡረታ ላይ የነበሩት ሜጀር ጀመነራል ገዛኢ አበራ ኤታማዦር ሹሙ ቤት ውስጥ ሳሉ አመሻሽ ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል።
news-45505863
https://www.bbc.com/amharic/news-45505863
ታምራት ላይኔ፡ የአቶ በረከትና የመሰሎቻቸው ሐሳቦች የሙታን ሐሳቦች ናቸው
በሸኘነው ዓመት ማገባደጃ በሚዲያ ጎልተው ከወጡ ሰዎች መሐል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ አንዱ ናቸው። በጥቂት ፖለቲካዊና በርከት ባሉ ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙርያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ጥያቄ፦ 2010 እንዴት ነበር? አቶ ታምራት: አንደኛው ለረዥም ዓመት የነበረው የፖለቲካ አስተሳሰብ አዲስ ነገር እንደሚፈልግ፤ ያለፈው ሁኔታ መሞት እንዳለበት ሕዝቡ ራሱ በተለያዩ መንገዶች ያሳየበት ዓመት ነበር። አሮጌ አስተሳሰቦች፣ አሮጌ አስተደደራዊ ዘይቤዎች ማለፍ፣ መሞትና መቅረት አንዳለባቸው የተበሰረበት ነበር። ሁለተኛ መልካም ጅማሮች የታዩበትና ተስፈ የፈነጠቀበት ዓመት ነበር። ይህን የምለው ሕዝብ አስተያየቱን ያለምንም መደናቀፍ በነጻነት የሚገልጽበት ሁኔታ የተፈጠረበት በመሆኑ ነው። ይሄ ነው አዲሱ ፋና። ገና ጅማሮ ነው። ግን ጥሩ ጅማሮ ነው። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» • "...ባለሐብቶችን ለቅመህ እሰር ብሎኝ ነበር" አቶ መላኩ ፈንታ • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" ጥያቄ፦ ከሰጧቸው ቃለምልልሶች በመነሳት የቀድሞው ባልደረቦችዎ ለምሳሌ እንደነ አቶ በረከት ስምኦን እርሶ ላይ የተአማኒነት ጥያቄን አንስተዋል። አቶ ታምራት: በእኔ በኩልና ቤተሰቤ የነበርንበትን ሁኔታ ለረዥም ጊዜ ኢህአዴግና ባለሥልጣናቱ፣ በተለይ አቶ በረከትን ጨምሮ፣ ሕዝቡን ሲዋሹና ሲያጭበረብሩ የነበረበትን ሁኔታ እውነቱ ይሄ ነው ብለን ተናግረናል። እሱ ብቻ ሳይሆን እኔ በበኩሌ በሥልጣን በነበርኩባቸው ዓመታት አጠፋሁ ያልኳቸውን 'አጠፋሁ' ብዬ፣ ሕዝቡንም በሆነው ነገር ሁሉ ይቅርታ ጠይቄ፣ በኔ በኩል ሒሳቤን ዘግቻለሁ። ከዚህ በኋላ እንደገና እሰጣገባ ውስጥ የምገባበት ምክንያት የለኝም። ሕዝቡ የትኛው እውነት የትኛው ውሸት እንደሆነ ያውቃል ብዬ አምናለሁ። አቶ በረከት መግለጫ ሰጡ ከተባለ በኋላ የሕዝቡን ምላሽ እያየሁ ነው። ሕዝቡ ያውቃል። ማን ውሸታም እንደሆነ ያውቃል። አብረዋቸው ለረጅም ጊዜ የሠሩ ሰዎች ሳይቀር እየወጡ ምን ያህል ዋሾ እንደሆኑ እሳቸውና ሌሎችም ጓደኞቻቸው ምን ያህል በቀለኛ ፣ ምን ያህል ቂመኛ እንደሆኑ እኔ ሳልሆን ሌሎቹ እየተናገሩ ናቸው። እኔ እንኳ እነኚህን ሁሉ ነገሮች ባውቅም ጉዳዩ የመበቀል ሳይሆን አዲሱን ትውልድ የማስተማር ጉዳይ ስለሆነ ዝርዝር ውስጥ አልገባሁም ነበር። ሁለተኛው [እዚህ ጉዳይ ውስጥ መመለስ]የማልፈልግበት ምክንያት ይሄ የአቶ በረከትና የመሰሎቻቸው ሐሳቦች የሙታን ሐሳቦች ናቸው፤ ከዚህ በኋላ፥ የሕያዋን ሐሳቦች አይደሉም። እኔ ደግሞ የሕያዋን የሆነ ሐሳብ ይዤ፣ አዲስ ከሚመጣው አስተሳሰብና ኢትዮጵያዊያን ወደ ፊት ሊያራምዳት ይችላል ብዬ ከማስበው ጋር ወደፊት የማስብ እንጂ ወደ ኋላ የማስብ ሰው አይደለሁም። ጥያቄ፦ በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች የሞቱ ሰዎችን ወቅሰዋል። ለምሳሌ አቶ መለስ እና አቶ ክንፈን። በሕይወት ያሉ ባለሥልጣናትን ስም ግን ከመጥቀስ ይቆጠባሉ። እውነትን ለትውልድ ማስተላለፍ ከፈለጉ ለምን ግማሽ እውነት መናገር መረጡ? አቶ ታምራት፦ እንደኔ አመለካከት የሰዎችን ስም አለመናገር ግማሽ እውነት ሊባል አይችልም። ስም ያላነሳሁበት ምክንያት ቃለ ምልልሴ በዋናነት እውነቱን ለመናገርና ሁኔታውን ለትምህርት ለመተው ነው እንጂ ሰዎችን እያነሱ ለማብልጠል አይደለም። አቶ በረከት ምስጋና ይግባቸውና በኔም በቤተሰቤም ላይ ሲያሴሩ የኖሩትን ሰዎች እነማን እንደሆኑ እኔ ሳልናገር ራሳቸው ተናግረውልኛል። እነማ እነማ እንደሆኑ፣ እነ እገሌ እነ እገሌ ብለው ራሳቸው ጠቅሰዋቸዋል። አንድ ጊዜ እኔን አንድ ጊዜ አቶ ታደሰን፥ አንድ ጊዜ አቶ ህላዌን አንድ ጊዜ አቶ አዲሱን እያሉ ጠቅሰዋል ሰዎቹ። የሰዎችን ስም መናገር ለእኔ በጣም ቀላል ነገር ነው። ወደፊትም ደግሞ በዚህ ብቻ የሚቆም አይደለም። አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ በመጽሐፍ መልክም ይሁን በሌላ ስሞችን መግለጽና ማውጣት ይቻላል። እናንተም ቢሆን ስም ላይ ባተተኩሩ ጥሩ ነው። ዋናው እውነቱ ፤ የተደረገው ነገር ነው። እኔ ይሄን ያደረኩት የሚመጣው መንግሥት እንዲህ ዓይነት ሥራዎችን እንዳይሠራ ነው እንጂ ወደኋላ ተመልሶ ለመቆዘም አይደለም። በነገራችን ላይ በዚያ ቃለ መጠይቅ ውስጥ ክስና በቀል እንዳይመስል ብዬ ያላነሳኋቸው ብዙ ሌሎች ጉዳዮች አሉ። አዳዲስና ያልተሰሙ ጉዳዮች። ወደፊት እንደ የሁኔታው በመጽሐፍ ወይም በሌሎች መንገዶች ላነሳቸው የምችል። ጥያቄ፦ መጽሐፍ እየጻፉ ነው ማለት ነው? አቶ ታምራት: የመጽሐፍ ሐሳብ አለኝ። በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በእኔም በቤተሰቤም ሕይወት ላይ ያተኮረ እንደ ማስታወሻ ዓይነት ነገሮች የመጻፍ ሐሳብ አለኝ። ደግሞ እንዳልኩት ዋናው ዓላማ ለመበቀል ለመክሰስ ሳይሆን ትምህርቱ ለሚቀጥለው ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ነው። ተስፋ አደርጋለሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሆናል። ጥያቄ፦ ትዊተር ወይ ፌስቡክ ገጽ አለዎት? አቶ ታምራት: ትዊተር የለኝም። የፌስቡክ ገጾች ነበሩኝ በተለያየ ጊዜ የኔን የፌስቡክ ገጾች ሌሎች እየወሰዱ እቸገራለሁ። የኔ ያልሆነ መልዕክት እየተላለፈ ተቸግሬያለሁ። አንደኛው ችግርም የኢህአዴግ መሪዎች ናቸው፤ ስልካችንንም እየጠለፉ፣ ፌስቡካችንንም 'ሀክ' እያደረጉ ይጠቀሙ የነበሩት እነርሱ ናቸው። ባለፉት 10 ዓመታት ከተፈታሁም በኋላ እስከዚህ ደረጃ ድረስ የወረደ ክትትል ነበረ፤ አሁንም ፌስቡክ አለኝ፤ ነገር ግን የኔ ያልሆኑ መልእክቶች እየተላለፉ ስላየሁ አልጠቀምበትም። ጥያቄ፦ የት አገር ነው የሚኖሩት? ለመሆኑ የግል መኖርያ ቤት አለዎት? አቶ ታምራት: ብዙ አሉባልታዎች ተብለው ያውቃሉ። ንግድ ውስጥ ተሰማርቷል። አሜሪካ ውስጥ ነዳጅ ማደያ አለው። ኮካ ኮላ ኩባንያ ውስጥ ሼር አለው። ትላልቅ ሕንጻዎች አሉት። ያልተባለ ነገር የለም። የኢህአዴግ መሪዎች ናቸው ሲዋሹ የኖሩት። እግዚአብሔር ፈቃዱ ከሆነ [እኔና ቤተሰቤ] አገራችን ተመልሰን መኖር እንፈልጋለን። እንደማንኛውም ሰው ቤት እንዲኖረን እፈልጋለሁ። አሁን የምኖረው መንግሥት በሰጠኝ የኪራይ ቤት ነው። ጥያቄ፦ ኪራይ ቤቱን እንዴት አገኙ? [ከእስር እንደተፈታሁ] ኪራይ ቤት እፈልጋለሁ፤ ቤት የለኝም አልኩ። እንደሌለኝ ያውቁም ስለነበር ኪራይ ቤት አገኘሁ። ጥያቄ፦ ሼክ ሙሐመድን አግኝተዋቸው ያውቃሉ? አቶ ታምራት: አግኝቻቸው አላውቅም ጥያቄ፦ቢያገኘቸው ሊነግሯቸው የሚፈልጉት ነገር ይኖር ይሆን? አቶ ታምራት: ምንም የምላቸው ነገር የለም። እግዚአብሔር ይርዳቸው፤ በማንኛውም ነገር። እጸልይላቸዋለሁ፤ እንደማንኛውም ሰው። ድሮ እንደማውቃቸው፣ ልክ ለኢህአዴግ መሪዎች እንደምጸልየው እጸልይላቸዋለሁ። እግዚያአብሔር በኑሯቸውም በሕይወታቸውም እንዲረዳቸው እጸልያለሁ። ጥያቄ፦ ዶ/ር ዐብይ የእርስዎ እርዳታ ቢያስፈልጋቸው በምን መንገድ ሊያግዟቸው ይችላሉ? አቶ ታምራት: አሁን ያለው ለውጥ ግንባር ቀደሞች የሆኑት ዶ/ር ዐብይን ጨምሮ እገዛ ያስፈልገኛል በሚሉበትና በሚያምኑበት ሁሉ ለማገዝ እኔ በበኩሌ ዝግጁ ነኝ። በዚህ በዚህ ብዬ አልመርጥም። ዓላማዬ ሁለት ነው። እንደኛ አሁን የተጀመረው ተስፋ በምንም መንገድ መቀልበስ አለበት ብዬ አላምንም። ሁላችንም እንደዛ እንዲሆን መፍቀድ የለብንም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን መፍቀድ የለበትም። ሁለተኛ ለኢትዯጵያ ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ ነጻነትና ፍትህ የሚሰፍንበት ሁኔታ እንዳይ ነው የምመኘው። እነዚህን ጉዳዮች እስካገዘ ድረስ በዚያ ቦታ በዚህ ቦታ፣ በዚህ ሁኔታ በዚያ ሁኔታ ሳልል ምርጫ ሳይኖረኝ ለማገዝ ዝግጁ ነኝ። ጥያቄ፦ ከመንፈሳዊ ሕይወት ውጭ ባሉ ሁኔታዎች ምን ያዝናናዎታል? አቶ ታምራት: አንደኛው በጣም የምወደው ነገር ኳስ ነው። ከልጅነቴም እወድ ስለነበር አሁንም ጊዜ ሲኖረኝ እከታተላለሁ። ሌላው በጣም የሚያዝናናኝ መጽሐፍ ነው። በድካምም ቢሆን በብስጭትም በጉዞም ላይ ቢሆን መጸሕፍት አነባለሁ። ሌላው እኔም ባለቤቴም በጣም የምንወደው ተፈጥሮን ወደ ምናደንቅበት ቦታ መሄድ ነው። ኮሎራዶ ነው የምንኖረው፤ በጣም ደስ የሚል ተራራማ ቦታ ነው። ወደ ተራሮች እንሄዳለን። አሜሪካዊያን ብዙ ጓደኞች አሉን። ከነርሱ ጋር እናሳልፋለን። አዘውትሬም ባይሆን አንዳንድ ጊዜ የማደርጋቸው ነገሮች ደግሞ አሉ፤ ከጓደኞቻችን ጋር ቴኒስ መጫወትና ማየት፥ አሳ ማጥመድ ወዘተ። ጥያቄ፦ ከክለብ የማን ደጋፊ ኖት? የባርሴሎና ደጋፊ ነኝ። ጫዋታቸው ደስ ስለሚለኝ ነው። [እኔ አንድ ቡድንን] የምደግፈው በሃይማኖተኝነት ወይም በአምልኮ መልክ አይደለም። ጥሩ የሚጫወት አርቲስቲክ የሆነ ቡድንን እደግፋለሁ። በዚህም አሁን የምደግፈው ባርሴሎናን ነው። ድሮ ብራዚልን እደግፍ ነበር። ጥያቄ፦ከተጫዋዎቾችስ በስም የሚጠቅሷቸው አሉ? አቶ ታምራት: ሜሲን ነው የምወደው። በጣም እወደዋለሁ፤ አደንቀዋለሁ። ባርሴሎና አጨዋወታቸው ጥበብ የተሞላበት ነው። ራሳቸውን አዝናንተው ሌሎችንም የሚያዝናኑ ስለሆኑ ነው። ኔይማርንም በዚሁ መለኪያ አደንቃለሁ። በእርግጥ ገና በደንብ ማየት አለብኝ እሱን። ሮናልዲንሆንም አደንቃለሁ። እነዚህ ተጫዋቾች ለራሳቸው ብቻ የሚጫወቱ ሳይሆኑ ሌላውንም የሚያጫውቱ [በተለይ ሜሲ] ያለቀላቸውን ኳሶች በመስጠት ከግለኝነት ውጭ የሆነ ጨዋታን የሚጫወት ነው። በነዚህ መመዘኛዎች ባርሳ እወዳለሁ። ጥያቄ፦ ከአገር ውስጥ የየትኛው ቡድን ደጋፊ ነዎት? አቶ ታምራት: ከአገር ውሰጥ አላውቃቸውም። ከኢትዮጵያ ርቄ ስለነበር አላውቃቸውም። የማውቃቸው ቡድኖች የሉም። እከሌ እከሌ ለማለት እቸገራለሁ። ጥያቄ፦ ቡናን ጊዮርጊስን አያውቁም፤ አቶ ታምራት? የድሮው ጊዮርጊስን አውቀዋለሁ። ግን ደጋፊ አልነበርኩም። ልጅ ሆኜም ተማሪ ሆኜም አንድ መቻል የሚባል ቡድን ነበር። የመቻል ደጋፊ ነበርኩ። ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የአየር መንገድ ደጋፊ ነበርኩ። በአንድ ወቅትም የአየር መንገድ ቡድን ለተወሰነ ጊዜ እጫወት ነበር። ጥያቄ፦ ጎበዝ ነበሩ ማለት ነው ኳስ ላይ? የት ቦታ ነበር የሚጫወቱት? አጥቂ? ተከላካይ? አቶ ታምራት: ተማሪ ቤት እያለሁ አማካይ ነበር የምጫወተው። ያን ያህል የምደነቅ ተጫዋች አልነበርኩም። ጥያቄ፦አውዳመት እንዴት ነው ሊያከብሩ ያሰቡት? አቶ ታምራት: ከ22 ዓመት በኋላ አዲስ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ከቤተብ ጋር ሆኜ አሁን ለመጀመርያ ጊዜ ላከብር ነው (ቃለ ምልልሱ ከአዲስ ዓመት ቀደም ብሎ የተደረገ ነው)። 12 ዓመት በእስር ቤት ስለነበርኩ አክብርው አላውቅም። ብቻዬን ስላሠሩኝ ሻማ አበራለሁ፣ እንደዚህ እንደዚህ አደርጋለሁ እንጂ ከቤተበስ አክብሬ አላውቅም። ከተፈታሁ 10 ዓመት አድርጊያለሁ። 10 ዓመት አሜሪካን አገር በአሉን እያሰብን እንውላለን እንደ ኢትዯጵያ ባይሀንም። ኢትዯጵያ ውስጥ ግን አክብሬ አላውቅም። አሁን ከባለቤቴ ጋር አብረን ሆነን፣ እናት አለችኝ፣ ከናቴ ጋር አብረን ሆነን፣ ሌሎችም ዘመዶች አሉኝ ከነርሱ ጋር ሆነን ለመጀመርያ ጊዜ ከ22 ዓመት በኋላ ላከብር ነው። ብዙ ጓደኞቼ 'እኛ ቤት ነው የምትመጡት፣ እኛ ቤት ነው የምትመጡት' ብለው ቀኖቹን በየተራ አንድ ሳምንት ያህል ከጓደኞቻችን ጋራ ስናሳልፍ ነው የምንቆየው። በተስፋና በአዲስ መንፈስ ጥያቄ፦ የሚናፍቁት ሰፈር አለ ከአዲስ አበባ? አቶ ታምራት: በጣም የምወደው ሰፈር ቦሌ አካባቢን ነው፤ ተወልጄ ያደኩትም እዚያው ስለሆነ። ከመስቀል አደባባይ ጀምረህ ስታዲየም አካባቢ እነ መሿለኪያ፣ እነ ኦሎምፒያ፣ ወሎ ሰፈር፣ ኡራኤል እነዚህ ያደኩከባቸው ሰፈሮች ናቸው። በኳስ በትምህርት ቤት፥ በጓደኝነት ወዘተ። ከእነዚህ ሰፈሮች ጋር ልዩ ስሜት አለኝ። ጥያቄ፦ የት ሰፈር ነው የተወለዱት? አቶ ታምራት: የተወለድኩት ኦሎምፒያ አካባቢ ነው። ያደኩትም እዚያው አካባቢ ነው። ሌለሎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የምወዳቸው ሰፈሮች አሉ። የፊት በር አካባቢ፣ ከዚያም በላይ ግን የንፋስ ስልክ ሳሪስ አካባቢን በጣም እወደዋለሁ። ከምወዳቸው ጓደኞች ጋር ብዙ ያሳለፍንብት ሰፈር ነው። ጉለሌ አካባቢ ላይ ከኢህአፓ ጋር በተያያዘ ብዙ ሠርቼበታለሁ እና እወደዋለሁ። አሁን ሰፈሮች ተለዋውጠዋል። መግቢያ መውጫቸው ተለዋውጧል። ብሄድ ልጠፋም እችላለሁ። ጥያቄ፦ ባለሥልጣን እያሉ የት ነው የኖሩት? አቶ ታምራት: ቦሌ አካባቢ አብዛኛው ባለሥልጣናት የሚኖርበት ሰፈር ነው የኖርኩት። ጥያቄ፦ አሁን መንገድ ላይ ሰዎች ሲያገኝዎት ምን ይልዎታል? አቶ ታምራት: ሰው መንገድ ላይ ሲያየኝ ሰላምታ ይሰጠኛል፤ ያቅፉኛል በተለይ ወጣቶች። ካፌ ሬስቶራንት እገባለሁ፤ ተከፍሏል ይሉኛል። በጣም በጎ መንፈስ ነው ያለው። ጥያቄ፦ የምግብ ምርጫዎ ምንድነው? አቶ ታምራት: የምግብ ምርጫ የለኝም። ያገኘሁትን እበላለሁ። በጣም ጤነኛ ስለሆንኩ የፈለኩትን እበላለሁ። በጤና ምክንያትም የምመርጠው የለኝም። የኢትዮጰያ ምግብ በአጠቃላይ ይስማማኛል። ጥያቄ፦ ይህ ነገር ቁርጥን ይጨምራል? አቶ ታምራት: ቁርጥ እንኳን በልቼም አላውቅም። አንድ ጊዜ መብላቴን አስታውሳለሁ፤ አንድ ዘመድ አምጥቶልኝ በልቻለሁ። ቦታው ላይ ሄጄ ሳይሆን ቤት አምጥቶልኝ በልቻለሁ። ቁርጥ ብዙም አልበላም። አልወድም ማለቴ ሳይሆን አላዘወትርም ማለቴ ነው። ጥያቄ፦ በ12 ዓመታት የእስር ጊዜ ምን አነበቡ? ከመንፈሳዊ መጻሕፍት ውጭ የትኞቹን ወደዷቸው? አቶ ታምራት: ዘውዴ ረታን በጣም አደንቃቸዋለሁ። የበዓሉ ግርማን ብዙዎቹን ሜዳ እያለሁ ያነበብኳቸው ቢሆንም በድጋሚ አንብቤአቸዋለሁ። የነ ገብረክርስቶስና የነጸጋዬን ግጥሞችም እንደገና አንብቢያቸዋለሁ። ጥያቄ፦ ዛሬም ኢህአዴግ ውስጥ በሥልጣን ያለ፣ የኔ የሚሉት ጓደኛ አለዎት? አቶ ታምራት: አብረን ከነበርናቸው እና ከቆዩት መሐከል ጓደኛዬ የምለው የምቀርበውም የለኝም። ለሁሉም ግን እጸልያለሁ። ለሁሉም መልካምን እመኛለሁ። ምንም ዓይነት ቂም በቀል የለኝም።
news-56065423
https://www.bbc.com/amharic/news-56065423
የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ ተጠባቂ የሚያደርጉ አምስት ነጥቦች
በ2007 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ኢሕአዴግ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መቀመጫዎችን ሙሉ በሙሉ አሸንፌያለሁ ባለ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ፀረ መንግሥት አመፆች ተቀሰቀሱ።
ይህም ከግዜ ወደ ግዜ እየተጋጋለ ግንባሩ ከውጪም ከውስጥም ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንዲወድቅ እና ሊቀመንበሩ እና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ ምክንያት ሆነ። የሕዝባዊ አመፁን፤ ብሎም በገዢው ፓርቲ ውስጥ የተፈጠረውን የመከፋፈል ምዕራፍ ይዘጋል ተብሎ በተጠበቀው ለውጥ፣ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መጋቢት 18/ 2010 የፓርቲው ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፣ በበዓለ ሲመታቸው አስተዳደራቸው ሊያከናውናቸው ያሰባቸውን ዋና ዋና ተግባራት ያካተተውን ንግግራቸውን አሰሙ። ታዲያ በንግግራቸው ላይ፤ መንግሥት 'ከተፎካካሪ' የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የነበረውን ግንኙነት ማሻሻል እንዲሁም ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን የተጠቀሰ ጉዳይ ነበር። በምርጫ ዙሪያ አስተዳደራቸው ያለውን ቁርጠኝነት በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብበራሪያ በሰጡበት ሌላኛው የምክር ቤት ንግግራቸው ላይም ‹‹ላለፉት ሶስት አመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጫፍ ጫፍ አካሄዳችን መቀየር አለበት፣ ሰላም እና ዴሞክራሲ ናፍቆናል ብሎ ከውጪም ከውስጥም ባደረገው ጥረት ለኢትዮጵያ የህልውና ጥያቄ የሆነውን እውነተኛ ዴሞክራሲ ለመገንባት የሚቀጥለው ምርጫ እንደ አንድ ዋና መመዘኛ ተወስዷል›› ሲሉም ተደመጡ። ታዲያ ከዚህ ለውጥ ማግስት የሚካሄደው ምርጫ ምን የተለየ ያደረገዋል? ብርቱካን ሚደቅሳ ‹‹መንግሥት ለራሱ ቅርበት ያላቸውን ሰዎች በምርጫ፣ ለቦርድ አመራርነት ያስመርጣል የሚውን ክስ ከግምት ውስጥ ያስገባ›› በማለት የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ስማቸው የሚታወቀውን ብርቱካን ሚደቅሳን እጩ ማድረጋቸውን አስረዱ። የቀድሞዋ ዳኛ፣ ፖለቲከኛ እና ምርጫ ቦርድ ፍትሃዊ አልሆነም ሲሉ ከስ የመሰረቱት፤ ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ምርጫውን ለማስፈጸም በዝግጅት ላይ መሆናቸው መጪውን ምርጫ በጉጉት እንዲጠበቅ ከሚያደርጉ ጉዳዮች አንዱ ነው። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ሹመትን ተከትሎ ነበር ብርቱካን ሚደቅሳ በስደት ከሚኖሩበት ሰሜን አሜሪካ ለኃላፊነት ወደ ኢትዮጵያ ጠቅልለው የመጡት። ቦርዱ ከእርሳቸው በፊት ሶስት ሰብሳቢዎች ኖረውት ያውቃል። ሕገ መንግስቱ ከፀደቀ በኋላ የመጀመሪያው የቦርዱ ሰብሳቢ የነበሩት ከማል በድሪ ከ1986-1997 ዓ.ም ድረስ አገልግለዋል። ቀጥሎም መርጋ በቃና ከ1999-2009 ዓ.ም እንዲሁም ሳሚያ ዘካሪያ ከ2010-2011 ቦርዱን መርተዋል። ብርቱካን ከሌሎቹ በምን ይለያሉ? ብርቱካን በ1997 ዓ.ም. በተካሄደው ሶስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ቅንጅትን ወክለው ተወዳደረዋል። ምርጫውን ተከትሎም መንግሥት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን እና አመራሮችን የማሰር እርምጃ ሲወስድ የዚህ ገፈት ቀማሽ ነበሩ። በፖለቲካ ተሳትፏቸው ዓመታትን በእስር ያሳለፉት ብርቱካን በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ከተመራጭነት ይልቅ ምርጫውን የሚያስፈጽመውን ተቋም ይመራሉ። ‹‹ዛሬ የማቀርባቸው እጩ ለመንግሥትም ቢሆን በተሳሳተ መንገድ እጅ የማይሰጡ፣ ለሕግ እና ስርዓት ጽኑ እምነት ያላቸው፣ እምነት ብቻ ሳይሆን፤ ለዚያ ዋጋ ለመክፈልም ዝግጁ መሆናቸውን በተግባር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስመሰከሩ ናቸው›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምክር ቤት ስለ ሰብሳቢዋ ተናግረዋል። አዲሷ ሰብሳቢ ከመጡ ቦርዱ የተቋሙን ሕጋዊ እና ተቋማዊ ቅርፅ በተለያ መልኩ ቀይሯል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም ዘጠኝ አባላት የነበሩት ሲሆን፤ በአዲሱ የምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት ወደ አምስት ዝቅ ተደርጓል። ኢትዮጵያ ምርጫን የምታስተዳድርባቸው ሶስት ሕጎች ወደ አንድ ተጨምቀው እና የተለያዩ ማሻሻያዎች ተደርገውበት ሥራ ላይ ውሏል። ቦርዱ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችን በመቀየር አዳዲስ ቁሳቁሶችን ማስተዋወቅ ከጀመረም ሰነባብቷል። ብርቱካን በ1996 ዳኛ ከነበሩበት ግዜ ጀምሮ በሚይዙት ጠንካራ አቋም ስማቸው ይነሳል። በስደት በቆዩበት አሜሪካም ተጨማሪ ትምህርት፤ በተለይም ከዴሞክራሲ ጋር የተያያዙ ልምዶችን ማግኘታቸው ተደምሮ መጪውን ምርጫ የሚያስፈጽመውን ቦርድ መምራታቸው፣ የምርጫው ተዓማኒነት የራሱ ሚና ይኖረዋል የሚሉ አስተያየቶች ተደጋግመው ተሰምተዋል። በሕገ-መንግሥት እና ምርጫ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችን ያደረጉት የሕግ ባለሞያው አደም ካሴ፤ የቦርዱ ሰብሳቢ ጥንካሬ የቦርዱ ጥንካሬ ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዳለው ቢስማሙም፤ ከግለሰብም በላይ ሌሎች የቦርዱ አባላት ገለልተኛነት ብሎም የተቋሙ ጥንካሬ ይወስናል ሲሉ ያስረዳሉ። ነፃ ምርጫ ለማካሄድ ምርጫ ቦርድ ጠንካራ ዳኛ መሆኑ ወሳኝ ቢሆንም ይህ ያለ መንግሥት ትብብር ውጤታማ ምርጫ ለማካሄድ ያስችላል ማለት እንዳልሆነም አደም ይገልፃሉ። የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ ገዢው ፓርቲ የመንግሥት መዋቅርን ተጠቅሞ ከሚያደርስብን በደል አልተከላከለንም ሲሉ በተደጋጋሚ ገልፀዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲዎች በቀጣዩ ምርጫ የመሳተፍ አቋም ላይ አንገኝም ሲሉ ቆይተዋል። ኦፌኮ እና ኦነግ አባላቶቻችን ሲታሰሩ እና ጽህፈት ቤቶቻችን ሲዘጉ ምርጫ ቦርድ በዝምታ አልፎናል ሲሉም በተደጋጋሚ ተደምጠዋል። ‹‹ምርጫ ቦርድ እንደተቋም ራሱን በማጠንከር ስራዎች ላይ ተጠምዶ መቆየቱ በተለይም የተወዳዳሪ ቡድኖችን መብቶች መጠበቅ ላይ ክፍተቶች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን ይሄም ለቦርዱ በቀረበው በማስረጃ ላይ የተመሰረተ አቤቱታ ላይ ይመሰረታል›› ሲሉ አደም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ለዚህም ቦርዱ በቅርቡ ገዢው ፓርቲ በሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ስም አጥፍቷል ተብሎ ለቀረበለት አቤቱታ የሰጠውን ማስጠንቀቂያ እንደማስረጃነት ይጠቅሳሉ። ነገር ግን ምርጫው እየተቃረበ ሲሄድ እና የፖለቲካ ግለቱ ሲጨምር እንዲህ ያሉ ወቀሳዎች ይጨምራሉ፤ ቦርዱም እየተፈተነ ይሄዳል ሲሉ ያስረዳሉ። "አሸባሪ" ተብለው ተፈርጀው የነበሩ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት መሆኑ መጪውን አገራዊ ምርጫ ልዩ ከሚያደርጉት ጉዳዮች ሌላኛው፤ ነፍጥ አንግበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፓርቲዎች በዘንድሮ ምርጫ ስልጣን ለመያዝ መወዳደራቸው ነው። በአንድ ወቅት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 'አሸባሪ' ተብለው ተፈርጀው የነበሩት፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር እና አርበኞች ግንቦት 7 (ከስሞ ኢዜማ ሆኖ) ወደ አገር ቤት ተመልሰው በምርጫው ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ ናቸው። በመጀመሪያው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ከመሳተፍም ባሻገር የክልሉን ምርጫ አሸንፎ የነበረው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በመጪው ምርጫ ላይ ለመወዳደር እጩዎቹን እያዘጋጀ ይገኛል። ግንባሩ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ውድድር ሜዳ የገባው፣ የካቲት 01/2011 ዓ.ም 1740 ታጣቂዎቹን ትጥቅ በማስፈታት በሶማሌ ክልል በሚገኙ የሲቪል እና የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ለመመለስ ከክልሉ መንግሥት ጋር ተስማምቶ ነበር። ምንም እንኳን የፓርቲው መሪዎች እርስ በእርስ ብሎም ከክልሉ መንግሥት ጋር የተለያዩ ፖለቲካዊ ያለመግባባቶች ውስጥ ገብተው የነበረ ቢሆንም አንድም የግንባሩ አባል ወደ ትጥቅ ትግል አለመመለሱን ፓርቲው ለቢቢሲ ገልጿል። የፓርቲው ሊቀ መንበር አብዲራሂም መሃዲ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የተገባላቸው አብዛኛው ቃል ባይፈፀምም ፓርቲያቸው በሰላማዊ ትግል ተስፋ እንዳልቆረጠ እና በክልሉ ያለውን ሰላም እንደ ስኬት እንደሚቆጥረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ‹‹ሕዝባችን ከዚህ በኋላ ወደ ጦርት እንዲገባ አንፈልግም፣ ለዚህም ነው ልዩነት ወደ ግጭት እንዳያመራ የራሳቸንን ድርሻ እየተወጣን ያለነው። መጪው ምርጫም ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ምርጫ ቦርድ እና የፌደራል መንግሥት ምን እንደሚያደርጉ ባናውቅም የክልሉ መንግሥት ግን ወደ አገር ከገባንበት ቀን ጀምሮ የሚያደርስብን ጫና አሳሳቢ ነው›› ሲሉም አብዲራሂም ገልፀዋል። መሠረቱን በኦሮሚያ ክልል ያደረገውን እና የጠቅላይ ሚንሰትሩን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ወደ አገር የተመለሰው ኦነግ፤ በአገሪቱ ሕግ መሠረት ዓላማዬን 'በሠላማዊ ለማሳካት እየተንቀሳቀስኩ እገኛለሁ' ይላል። ከ400 በላይ የምርጫ ወረዳ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቶ ለቀጣዩ ምርጫ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ኢዜማ፣ 6 ፓርቲዎች ከስመው የመሰረቱት ነው። ከእነዚህ ውስጥ ነፍጥ አንግቦ ሲታገል የነበረው አርበኞች ግንቦት 7 ተጠቃሽ ነው። ኢዜማ "ዜግነትን መሠረት ያደረገ" ፖለቲካን በማራመድ፤ በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህን ማረጋገጥ ቀዳሚ ግቤ ብሎ ለምርጫው ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። የሕገ-መንግሥት እና ምርጫ ጉዳዮች ባለሙያው አደም ካሴ፤ ከዚህ ቀደም በነበረው አፈና ምክንያት የተቃውሞ ፖለቲካ መሰረቱ በአብዛኛው በውጪ አገራት ነበር ይላሉ። አደም የእነዚህ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት መመለስ ከፍተኛ ተስፋ እንዲሁም ጫና እና ጭንቀት ይዞ የመጣ ነው ብለዋል። ‹‹አንዳንዶቹ እንግልት አለብን፣ ቢሮ ከፍተን መንቀሳቀስ አልቻልንም እያሉ ነው፤ ሌሎቹ ደግሞ በእስር ላይ ናቸው። በተለይ ከፍተኛ ፉክክር የሚያደርጉት ፓርቲዎች ከዚህ አንጻር ያኔ ሲመጡ የነበረውን የሚያክል ተስፋ አሁን ባይኖርም፤ ተስፋው ሙሉ በሙሉ ተሟጥጧል የሚል ግምት የለኝም፣ ይህም በቀጣይ ወራት የሚኖረው መሻሻል ላይ ይመሰረታል›› ሲሉ ባለሙያው ያስረዳሉ። በርካታ ፖለቲከኞች እስር ላይ ሆነው መካሄዱ በኢትዮጵያ በተለይም ከሶስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በኋላ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላቶች በእስር ላይ ሆነው ምርጫ ማካሄድ እንግዳ ነገር አይደለም። በየትኛውም መለኪያ ቢሆን ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በተለይም በ2002 እና 2007 ከተካሄዱት ምርጫዎች የተሻለ ሆኖ ይካሄዳል የሚሉት አደም፤ ከሁለቱ ምርጫዎች የማይሻል ምርጫ ማካሄድ አይቻልም ሲሉ ያነፃፅራሉ። ነገር ግን መለኪያው መሆን ያለበት ሕገ መንግሥታዊ ስርአቱ እና ሕጎች የሚጠይቁት መመዘኛዎች መሟላታቸው ነው፤ ከዚህ አንፃር ዘርፈ ብዙ ጎዶሎች አሉ ይላሉ። በአሁኑ ወቅት የኦነግ፣ የኦፌኮ እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በአዲስ አበባ ያለውን ዋና ጽህፈት ቤቱን ጨምሮ 103 ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋታቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል። በዲስትሪክት ደረጃ 989 አባላቶቼ ታስረው ይገኛሉ ያለው ኦነግ 145 መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም 32 ከፍተኛ አመራሮቼ በእስር ላይ ናቸው ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። የኦፌኮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እስር ላይ መሆናቸውን በማስታወስ "አሁን በምርጫ አንሳተፍም አንልም። ይሁን እንጂ ምርጫ መሳተፍ የማያስችል ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው" ይላሉ። በተመሳሳይ ግንቦት 28 ለሚካሄደው ምርጫ፤ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ፤ "የምንሄደው ምርጫ ውስጥ እንገባም የሚል እምነት የለንም። ነገር ግን እንደ አገር የምንገባበት ምርጫ አሁን ያለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ያሳስበናል" ሲሉ ለቢቢሲ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ተናግረዋል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የቀድሞ ሊቀ መንበር ደሳለኝ ጫኔ ፓርቲው የታሰረበት አባል ወይም አመራር ባይኖርም፣ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ወደ 20 የሚቆጠሩ ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ደሳለኝ እንደሚሉት በኦሮሚያ ክልል ፓርቲያቸው እጩዎቹን ያስመዘግባል፤ ነገር ግን ቅስቀሳን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን እንዴት ያካሂዳል የሚለው ያሳስበናል ብለዋል። አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች መደበኛ ስብሰባ እንኳን እንደልባቸው ለማካሄድ የማይፈቀድላቸው ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የሚጠቅሱት አደም፤ ገዢው ፓርቲ ግን የኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር የወጡ ደንቦችን እንኳን የማያከብሩ ሰልፎችን ሲያካሂድ መመልከት በራሱ አሁንም ለገዢው ፓርቲ የሚያደላ ስርአት እንዳለ ያሳያል ሲሉ ያብራራሉ። ‹‹መንግሥት አሁንም የፖለቲካ ችግሮችን እንደ ፀጥታ ችግር አድርጎ የማየት አባዜው ስላለ በተለይም ምርጫው እየቀረበ ሲሄድ እና ሙቀቱም ከፍ እያለ ሲመጣ በተቃዋሚዎች ላይ ጫና ሊጨምር ይችላል›› ሲሉ ባለሞያው ያስረዳሉ። በዚህ የሚቀጥል ከሆነም ውድድር የማይፈቀድበት ምርጫ ሊሆን ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። ህወሃትን የማያሳትፈው ምርጫ ሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ከፍተኛ ተፅእኖ ፈጣሪ በነበረባቸው ያለፉት አምስት አገር አቀፍ ምርጫዎች የተለያዩ ወቀሳዎችን ሲያስተናግድ ቆይቶ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫን በተመለከተ ግን ከማዕከላዊ መንግሥት ሙሉ በሙሉ የተገለለው ፓርቲው ወቀሳዎችን ሲያቀርብ ነበር። በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ምርጫ እንዲራዘም ሲወሰንም ህወሃት በክልሉ ምርጫ ማካሄዱ ብሎም ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ፓርቲው ከጥቂት ወራት በኋላ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር ውስጥ የተሰረዘ ሲሆን፣ የፓርቲው አመራሮች በክልሉ ከተቀሰቀሰው ጦርነት ጋር ተያይዞ የተወሰኑት ህይወታቸው አልፏል፣ ሌሎቹ በትጥቅ ትግል በበረሃ የሚገኙ ሲሆን የተወሰኑት በሕግ ጥላ ስር ይገኛሉ። እናም ህወሃት ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀ ጀምሮ እንደ ፓርቲ ተሰርዞ የሚካሄድ የመጀመሪያው አገር አቀፍ ምርጫ ይሆናል። በክልሉ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ ከሌላው የአገሪቱ ክፍል ዘግይቶ እንደሚደረግ ምርጫ ቦርድ ገልጿል። አደም እደሚያስረዱት ህወሃት በትግራይ ክልል ብቻ የሚወዳደር ፓርቲ እንደመሆኑ የፓርቲው ያለመኖር በቀጥታ ከቀጣዩ ምርጫ ጋር ግንኙነት ባይኖረውም በሂደት የሚታዩ ውጤቶች ግን መኖራቸው አይቀሬ ነው ይላሉ። እንደ አደም ገለፃ ፓርቲው እንደ አንድ ነባር ፓርቲ ያካበተው የራሱ ልምድ፣ አቅም እና ሃብቶች የነበሩት መሆኑ እና አሁን ያ ሙሉ ለሙሉ መጥፋቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የራሱ ጉድለት ይኖረዋል። በህወሃት የሚደገፉ ፓርቲዎች ከዚህ በኋላ ያንን ያለማግኘታቸው የፓርቲው መጥፋት ከክልሉ ያለፈ ሚና ይኖረዋል ሲሉም ያስረዳሉ። ምርጫው ኢትዮጵያ ለገባችባቸው ችግሮች መፍትሄ ያመጣ ይሆን? በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰፍቶ በመተከል ዞን ላይ ተተግብሯል። ኢትዮጵያ እና ሱዳንም አንዴ ሞቅ አንዴ ቀዝቀዝ በሚል ግጭት ውስጥ ገብተዋል። በአገሪቱ የተለያዩ የፖለቲካ ልዩነቶች ተካረው እንዲሁም ልሂቃኑ በሚመሩት የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ መገኘቷን ብዙዎች ደጋግመው ያነሳሉ። በአገር ውስጥ በተነሱ ግጭቶች አያሌ ዜጎች ህይወታቸውን ያጡበት እና እስከ አሁንም ድረስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከቀዬአቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ። ብሔርን፣ ሃይማኖትን ብሎም ሌሎች ማንነቶችን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መስማትም የተለመደ እየሆነ መጥቷል። የአብን የቀድሞ ሊቀ መንበር ደሳለኝ ጫኔ መጪው ምርጫ ኢትዮጵያ ከገባችበት ቀውስ ማውጣቱ ወይም መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ለአዲስ ቀውስ ይጋብዛል ብለው ይሰጋሉ። ፓርቲያቸው ከምርጫ በፊት አገራዊ ንግግር ያስፈልግ ነበር ብሎ ቢጎተጉትም ተቀባይነት አላገኘም ሲሉ ያስረዳሉ። ምርጫውን ተከትለው የሚኖሩ ውጤቶች ወደ ሌላ ቀውስ ሊያስገቡ ይችላሉ ብለው ቢያምኑም፣ ምርጫው መደረጉ ስላልቀረ ግን ጠንክረው ለመወዳደር ተዘጋጅተዋል። በደሳለኝ ሃሳብ የሚስማሙት አደም ምርጫ እንኳን እንዲህ በተለያዩ ቀውሶች ውስጥ በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥም ብዙ ግዜ ውጥረት ይፈጥራል ይላሉ። የምርጫ ውጤት ለአምስት አመት ስለሚዘልቅ የተሸነፈው ቡድን ገዢው ፓርቲም ይሁን ተፎካካሪዎቹ በቀላሉ በፀጋ አይቀበሉትም። ‹‹ መሰረታዊ የፖለቲካ ልዩነቶች እያሉ ያለንግግር በሚደረግ ምርጫ ብቻ ካለው ችግር መውጣት አይቻልም። ተቃዋሚዎች የሕዝብ ቅቡልነት እንዳላቸው እና የሚወክሉት እና የሚደግፋቸው የሕዝብ ክፍል እንዳለ አምኖ ለንግግር መቀመጥ ያስፈልጋል›› የሚሉት አደም ‹‹ያለ ንግግር ምርጫን ማካሄድ እንደ ህመም ማስታገሻ ለተወሰነ ግዜ ቅቡልነት ያመጣ ይሆን እንጂ ዘላቂ ውጤት አያመጣም›› ብለዋል። ኢትዮጵያ ከ 2007 ምርጫ መማር ያለባትም ይህንኑ እንደሆነ የገለፁት የሕግ ባለሞያው ከምርጫው በኋላ ለጥቂት ወራት ሰላም ቢሆንም ችግሮቹ ከመሰረታቸው ካልተፈቱ ለውጥ አይመጣም ይላሉ። ይህም በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነት የፖለሲ ሳይሆን በመሰረቱ በአገረ መንግስቱ ላይ ገና መስማማት ሳይደርስ የተመረጠው ፓርቲ ቅቡልት አለኝ ብሎ መሰረታዊ የፖለቲካ ለውጦችን፣ ካስፈለገም ሕገ መንግስቱን እቀይራለሁ የሚል ከሆነ ወደ ባሰ ቀውስ ሊከት ይችላል ሲሉ ይከራከራሉ። ነገር ግን መንግስት ከምርጫው በኋላ በሚመረጡ እና ቅቡል በሚሆኑ ፓርቲዎች አማካኝነት ንግግሩ ይካሄደል ያለውን የሚተገብር ከሆነ ምርጫው ምን አልባት አገሪቷ ካጋጠሟች ችግሮች የሚያወጡ መፍትሄዎችን ሊያመጣ ይችላል ሲሉም ተስፋቸውን ያስቀምጣሉ።
news-41975123
https://www.bbc.com/amharic/news-41975123
ሐረርና ጀጎልን በምስል
የጀጎሏ ሐረር በአነስተኛ የመሬት ስፋት በርካታ ጎብኚዎችን ከሚያስተናግዱ ጥቂት የዓለማችን ከተሞች አንዷ ናት፤ ከ1000 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የከተማዋ ታሪክ ቅርሶቿም እንዲበዙ እድል ፈጥሮላታል። የጀጎል ግንብና አምስቱ በሮች፣ የወርቅ ሳንቲሞች፣ ረጅም እድሜን ያስቆጠሩ መስጊዶች ፣ የስነ-ሕንፃ፣ የታሪክን አሻራ የሚያንፀባርቁ የቤት ውስጥ ዕቃዎች ቱሪስትን ከሚስቡት ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።
በፈረንሳዊው ጸሃፊ አርተር ራምቦ የተሰየመው ሙዚየም አንዱ ነው። በሙዚየሙ ከረጅም ዓመታት በፊት የተነሱ የሐረር ከተማ ፎቶዎችና በከተማዋ ላይ ያተኮሩ ምርምሮችን ያካተቱ ክፍሎች ኣሉበት። አርተር ራምቦ 1880 ወደሃረር ከተማ በመሄድ በ11 ዓመት ቆይታው ለ120 ዓመታት መቆየት የቻሉ ፎቶዎችን አንስቷል። የዚህ ሙዚየም ግንባታ ጂዋጅ በሚባል ህንዳዊ እንደታነጸ መረጃዎች ያመለክታሉ። አፍላላ ዉፋ ከሸክላ የሚሰሩ የባህላዊ እቃዎች ሲሆኑ በቁጥርም አራት ናቸው፤ በሐረሪ ብሄረሰብ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በቅደም ተከተል ይቀመጣሉ። እያንዳንዳቸውም የየራሳቸው አገልግሎት አላቸው። የመጀመሪያው የእናት ባንክ ሲሰኝ ባል ለቤት ወጪ የሚሆነውን ገንዘብ የሚያስቀምጥበት ፤ሁለተኛው ባህላዊ መድኃኒቶችን ማስቀመጫ፤ ሶስተኛው የመድኃኒቶችና የእህል ዘሮች ይቀመጥበታል። አራተኛው ደግሞ የግብርና የተለያዩ ክፍያዎች ደረሰኞችን የሚይዝ ነው። ቆሪ ሃዳ- በሠርግ ወቅት እናት የምትድራት ልጇን ወደ አማቶቿ ቤት ሂዳ በመልሱ እስክትመጣ ድረስ የሚጠቅሟትን ዝሁቅ፣ አቅሌል፣ መቅሊ እና ሌሎች ምግቦችን ስንቅ የምትቋጥርበት ነው። እስከ 25 ኪሎግራም የሚመዝን ምግብ የመያዝ አቅም ሲኖረው፤ እነዚህንም የባህል ምግቦች ይዘው የሚሄዱት ሰዎች የሐረርን ባህል በደንብ የሚያወቁ ሰዎች መሆን አለባቸው።ይህ ከዋንዛና ከሌሎች የዛፍ አይነቶች የሚሰራው ቆሪ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ወደልጅቱ ቤተሰቦች የተለያዩ ስጦታዎች ተደርገውበት ይመለሳል። በሐረሪ ባህል ቤቶች ውስጥ የመደብ መቀመጫ ትልቅ ቦታ አለው። በአንድ ቤት ውስጥ አምስት መደቦች የሚሰሩ ሲሆን ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ የሚያመለክቱ ናቸው። እውቀት፣ ጾታና እድሜን መሰረት ያደርጋሉ። ከፍተኛ የኃይማኖት እውቀት ያላቸው ምሁራን ከፍ ያለው መደብ ላይ ሲቀመጡ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችም በሚዘጋጅላቸው መደብ ላይ ይቀመጣሉ። አምስቱ መደቦች ስያሜያቸው በሃደሬ ቋንቋ ''አሚር ነደብ'' ''ግድር ነደብ'' ''ጥት ነደብ'' ''ጉት ነደብ'' እና ''ገብትሄር ነደብ'' ይባላሉ። እንዳሁኑ ጫማ በዘመናዊ መልኩ መሰራት ከመጀመሩ በፊት የሐረሪ ህዝብ ከእንጨትና ከቆዳ የሚሰሩ ጫማዎችን ይጫማ ነበር። ከእንጨት የሚሰራው ጫማ ቤት ውስጥ ለመንቀሳቀስ የሚያገለግል ሲሆን ከቆዳ የሚሰራው ደግሞ ለረጅም ጉዞ ያገለግላል። የጀጎል ግንብ በ1551/52 በንጉስ/አሚር ኑር ቢን ሙጃሂድ እንደተገነባ የታሪክ መዛግብት ያመላክታሉ። ይህ ግንብ ከምድር 4 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን ወርዱ ደግሞ ከ50-75 ሴንቲሜትር ይሰፋል። ግንቡ አምስት በሮች ያሉት ሲሆን ውሃ ያለበትን አቅጣጫም ለማመልከት የተሰሩ ናቸው። ከአምስቱ በሮች እንዱ ከረ ፈልአና ሲሆን ስያሜውን ያገኘው በዚህ ስም ወደምትጠራ መንደር ስለሚወስድ ነው ይባላል። ሐረሪዎች ደግሞ ይህንኑ በር ከረ አሱሚ ብለው ይጠሩታል፤አሱሚ በሃደሪኛ በርበሬ ማለት ሲሆን ፊት ለፊት ከሚገኘው ቀይ ቀለም ያለው ወንዝ የተወሰደ ነው ይላሉ።
news-57251125
https://www.bbc.com/amharic/news-57251125
ምርጫ 2013፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በምርጫው ላይ ጫና ይዞ ይመጣ ይሆን?
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ግንቦት 13 በሕግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎች በምርጫ የመወዳደር መብት አላቸው ወይስ የላቸውም በሚል ለወራት የዘለቀውን ክርክር በባለ ስምንት ገፅ ውሳኔ ዘግቶታል።
በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመልካችነት የቀረበውን አቤቱታም "በዕጩነት እንዳይመዘገቡ የሚከለከሉበት ሕጋዊ ምክንያት የለም" ሲልም ችሎቱ በይኗል። የፓርቲው መስራች እና ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ እና የፓርቲው አባላት የሆኑት ስንታየሁ ቸኮል እና ቀለብ ስዩም ከአንድ ዓመት በፊት የታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተፈጠው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። ግለሰቦቹ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በተለያዩ የምርጫ ክልሎች ፓርቲያቸውን በመወከል ለስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በዕጩነት ለመመዝገብ ጥያቄያቸውን አቅርበው ነበር። በሕግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎች በዕጩነት ይመዝገቡልን የሚለው ጥያቄ ምንም እንኳን እንደ ባልደራስ ወደ ፍርድ ቤት አያምራ እንጂ ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሲነሳ ቆይቷል። በተለይም በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በርካታ ለዕጩነት የሚቀርቡ አባሎቻቸው መታሰራቸውን አንስተዋል። ኦነግ ከዕጩዎች የምዝገባ ጊዜ በኋላ አባሎቼ ይፈቱ እንደሆነ በሚል 'በእስር ላይ እያሉ ተመዝግበው ይቆዩልኝ' የሚል ጥያቄ ለምርጫ ቦርድ አቅርቦ ነበር። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳም በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን በዕጩነት ለመመዝገብ የአገሪቱ ሕግ እንደማይፈቅድ መልስ ሰጥተዋል። "እሱን በር ከከፈትነው የኦነግ አባላት ብቻ ሳይሆኑ በነፍስ ግድያ የተከሰሱትም ባይፈረድባቸውም በዕጩነት እንቅረብ ሊሉ ነው" ሲሉ ዋና ሰብሳቢዋ መልሰዋል። "አንዳንድ አገራት ባልተለመደ መልኩ ይህንን ይፈቅዳሉ፣ የእኛ ሕግ ግን ያንን የሚፈቅድ አይደለም፤ ለምን ያንን አልፈቀደም ወደ 'ሚለው መሄድ አልችልም፤ ግን ያንን የሚፈቅድ ስላልሆነ እስር ላይ ያሉ የፓርቲ አባላት በዕጩነት አይቀርቡም" ሲሉ ለኦነግ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ገልጸዋል። በሌላው ዓለም የታሰሩ ሰዎች ዕጩ መሆን ይችላሉ? አደም ካሴ (ዶ/ር) በምርጫ ሕጎች ላይ ጥናቶችን ያደረጉ እና ኔዘርላንድስ ውስጥ መሰረቱን ባደረገው የዴሞክራሲ እና የምርጫ ድጋፍ ላይ አተኩሮ የሚሰራ ተቋም ባልደረባ ናቸው። በዓለም ላይ የታሰሩ ሰዎች ለምርጫ ዕጩ መሆን ከአገር አገር ቢለያይም፤ በሕግ ጥላ ስር ሆነው ክስ ያልተመሰረተባቸው ሰዎች ግን በዕጩነት መመዝገብ መቻላቸው አጠያያቂ አይደለም ይላሉ። "እንደ ሕንድ ያሉ አንዳንድ አገራት ተከሰው ያልተፈረደባቸው ሰዎች በምርጫ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ሕግ አላቸው። የተፈረደበት ሰው ግን ወጥቶ ሕዝብን ማገልገል ስለማይችል ይህ ቢከለከል ተገቢ ነው ብዬ አስባለሁ" ይላሉ። በክስ ላይ ያሉ ሰዎችን በተመለከተ በሕግ ግልጽ ሆኖ መቀመጥ ነበረበት የሚሉት አደም፤ ይህ አለመሆኑ ምርጫ ቦርድንም ፈተና ውስጥ የሚከት ነው ይላሉ። አሁን ላይ ሕጉ በዚህ ረገድ ቢሻሻል ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም ሲሉም ያስረዳሉ። የፍርድ ሂደቱ ምን ይመስላል? የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሦስት አባሎቼ በዕጩነት ይመዝገቡልኝ ሲል ለየምርጫ ክልሎቹ አስፈፃሚዎች ጥያቄ አቅርቦ ነበር። በየክፍለ ከተማው ያሉ የቦርዱ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች በሕግ ጥላ ስር ሆኖ ለዕጩነት መመዝገብ አይችሉም በሚል ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋል። ፓርቲው ውሳኔውን ለአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ ያለ ሲሆን ተመሳሳይ ውሳኔ ተሰጥቶበታል። ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም "በእስር ላይ የሚገኝ ሰው የመንቀሳቀስ መብቱ ወይም ነፃነቱ የተገደበ ሰው የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይችልም፣ ቢመረጥም ሕዝቡን ሊያገለግል አይችልም" በሚል ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ "በሕግ የመምረጥ ወይም የመመረጥ መብቱ ያልተገፈፈ" የሚለው ሐረግ የዋስትና መብታቸው ተገፎ በማረሚያ ያሉ ሰዎችን ይጨምራል ወይስ አይጨምርም የሚለውን ተርጉሟል። "ማረሚያ ቤት ውስጥ ያለ ሰው እንኳንስ ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ፣ ከፈጣሪ የተሰጡ ሰብአዊ መብቶቹ፣ በተለይም የነፃነት መብቶቹ ተገድበው ያለ ዜጋ ነው" ይላል የችሎቱ ውሳኔ። "በሕግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎች በውጪ ካሉ ሰዎች ያነሰ መብቶች አሏቸው፣ ሕገ መንግሥቱ ስለተከሰሱም ሆነ ስለተፈረደባቸው ሰዎች በሚያስረዳበት ክፍሉ የመመረጥ መብት የሚያስረዳ አንዳች ነገር የለም" ሲል ውሳኔው ያትታል። አክሎም በምርጫ ሕጉ ላይ የተቀመጠው ክልከላ የሚያስረዳው የዋስትና መብት ተከልክለው በእስር ላይ ስላሉ እጩዎች የመወዳደር መብት ሳይሆን ከሕግ ከለላ ውጪ ስላሉ ሰዎች ነው ይላል። ነፃ ሆኖ መገመት ማለት በወንጀል ክስ ወቅት ድርጊቱን የማስረዳት ሸክም ተከሳሽ ላይ እንደማይወድቅ ለማስረዳት እንጂ ተከሳሽ ዴሞክራሲያዊ መብቶቹን እንዲተገብር የሚፈቅድ አይደለም ሲልም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ አስቀምጧል። የልዩነት ሃሳብ አለኝ ያሉት ዳኛ ሙሉሰው ድረስ የተሰኙት በከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተሰየሙት ዳኞች በሁለተኛ ላይ የተቀመጡት ዳኛ በውሳኔው ባለመስማማታቸው በዚህ ጉዳይ ላይ የልዩነት ሃሳብ ይዘዋል። "ሕግ ግልፅ በሆነ ግዜ ትርጉም አያስፈልገውም" የሚለውን ወርቃማ የሕግ አተረጓጎም መርኅን መሰረት አድርገው ልዩነታቸውን አስፍረዋል። የምርጫ ሕጉ አንቀፅ 31 ለዕጩነት የሚያበቁ መመዘኛዎችን ያስቀምጣል ያሉት ዳኛው ከእነዚህም ውስጥም በሕግ ወይም በፍርድ የመመረጥ መብት መከልከል ተጠቅሷል ብለዋል። ዳኛ ሙሉሰው እንዳሉት ቦርዱ የሕግ ወይም የፍርድ ቤት ክልከላን አላቀረበም፣ ሕጉም በሕግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎች በዕጩነት መመዝገብ አይችሉም የሚል ክልከላ አላስቀመጠም ሲሉ ሞግተዋል። ምርጫ ቦርድ በሕግ ወይም በፍርድ ቤት የግለሰቦቹ የመመረጥ መብት መገፈፉን የሚያስረዳ ማስረጃ አላቀረበም የሚለው ለልዩነታቸው ዋነኛ ምክንያት ነው። የሰበር ውሳኔ ምን ይላል? የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ማለት በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 80 መሰረት ከሕገ መንግሥት ውጪ ያሉ ሕጎች ላይ የመጨረሻ ትርጉም የመስጠት ስልጣን ያለው ችሎት ነው። ችሎቱ ቢያንስ አምስት ዳኞች ይሰየሙበታል። በሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጡ ውሳኔዎች ይግባኝ የማይባልባቸው ብሎም ገዢ ናቸው። ውሳኔዎቹም ከተሰጡበት ቀን ጀምሮ በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ ባሉ ፍርድ ቤቶች እንደሚተገበሩ በአዋጅ ተደንግጓል። ሰበር አስገዳጅ የሕግ ውሳኔ ሲሰጥም ታትሞ ይሰራጫል። ታዲያ በባልደራስ እና በምርጫ ቦርድ ክርክር ላይም ይሄው ችሎት የመጨረሻ፣ ይግባኝ የማይባልበትን እና ገዢ ውሳኔ ሰጥቷል። በባልደራስ አመልካችነት አቤቱታውን የተመለከተው የሰበር ሰሚ ችሎቱ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ የሕግ ስህተት አለበት ሲል ሽሮታል። ለሰበር የቀረበው አቤቱታም በሕግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎችን በዕጩነት ከመመዝገብ የሚከለክል ሕጋዊ ክልከላ የለም፣ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሕጋዊ መሰረት የለውም እና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተከሰሱ ሰዎች በሕግ ንፁህ ሆኖ የመገመት መብትን ይፃረራል የሚሉ ናቸው። ችሎቱ በቅድሚያ የተመለከተው ምርጫ ቦርድ የሰበር ሰሚ ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን የለውም ሲል ያቀረበው መከራከሪያ ላይ ነው። ሕጎችን በማጣቀስ ማንኛውም የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ጥሰት ካለ የመመልከት ስልጣን አለኝ ሲል ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ችሎቱ አንድ ሰው የመምረጥ እና የመመረጥን ጨምሮ ሕዝባዊ መብቶቹ በፍርድ ቤት ለተወሰነ ጊዜም ይሁን ለዘወትር ሊከለከሉ እንደሚችሉ ውሳኔው ያትታል። የወንጀል ሕጉን ድንጋጌዎች በመጥቀስ ከሞት ፍርድ እና የፅኑ እስራት ቅጣት ውጪ ከሕዝባዊ መብት መሻር እንደ ተጨማሪ ቅጣት የሚወሰድ፤ ፍርድ ቤቱ የጥፋቱን ክብደት እና የጥፋተኛውን ባህርይ በማየት የሚወስነው መሆኑን ያብራራል። ከፍርድ በፊት ነጻ ሆኖ መገመት ማለት ተከሳሹ በሕግ በግልጽ ያልተከለከሉ መብቶቹ እንዳይነኩበት አላማ የያዘ ነውም ይላል። "ዕጩው የመንቀሳቀስ መብቱ ተገድቦ ሳለ የምርጫ ቅስቀሳን ጨምሮ ሌሎች ተግባራትን ማካሄድ ስለማያስችለው" በሚል ከቦርዱ ለመጣው አቤቱታ ችሎቱ መልስ ሰጥቷል። "ዕጩው የቀረቡት በፓርቲው በመሆኑ የምርጫ ቅስቀሳው በዋናነት የሚሰራው በፓርቲው በኩል መሆኑን መገንዘብ አስቸጋሪ ካለመሆኑ ባሻገር፤ በዚህ ረገድ የቀረበ አቤቱታ በሌለበት የስር ፍርድ ቤቱ ለውሳኔው መሰረት ማድረጉ አግባብ አይደለም" ሲል መከራከሪያውን ውድቅ ያደርጋል። ሰበር ሰሚው የምርጫ ሕጉን በመጥቀስ የመምረጥ መብታቸው ያልተከለከለ እና በሕግ ጥላ ስር ያሉ ሰዎች የመምረጥ መብታቸው እንዲጠበቅ ልዩ ሥርዓት ተዘርግቷል ሲል ያስረዳል። "ይህም ለዜጎች የፖለቲካ ተሳትፎ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን እና የሚበረታታ መሆኑን ያሳያል ነው" ሲል ችሎቱ ያክላል። የሰበር ሰሚ ችሎቱ የስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፣ ሊታረም ይገባል ሲል ውሳኔውን ሰጥቷል። በቀጣይ ወዴት ያመራል? ከዚህ ቀደም በእስር ላይ ያሉ አባላቶቻቸውን በተመለከተ በስብሰባዎች ላይ ጥያቄ ሲያቀርቡ ከነበሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ፓርቲያቸው በዚህ ውሳኔ መሰረት የሚያቀርበው ጥያቄ እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አጠቃላይ የፖለቲካ ምኅዳሩ ስለተበላሸ ለእኛ ይሄ ብዙ ጥቅም የለውም። ከ200 በላይ ቢሮዎቻችን ተዘግተውብናል። ያለፈው ዓመት ሚሊዮኖችን የምንሰበስብበት ጊዜ ነበር" ብለዋል። "እኛ አጠቃላይ ምርጫው ምርጫ መሆን ስለማይችል ነው የወጣነው" ሲሉም አክለዋለ። "የኔ ስጋት የፍርድ ቤት ነፃነት እንዳለ ለማስመሰል እንዳይሆን ነው፤ ከልደቱ ውጪ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሲከበር አላየንም" ያሉት መረራ "ለልጆቹ [ለባልደራስ አባላት] ግን ሞራል ይሰጣል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ የሚለዩት አደም ይህ ውሳኔ በፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን እምነት የሚጨምር ነው ይላሉ። ነገር ግን እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች በፍጥነት አለመስተናገድ የሚያመጣውን ጫናንም ያሳያል ብለዋል። አደም በኦሮሚያ ክልል የሚወዳደሩት ሁለቱ ፓርቲዎች በምርጫው ላይ የሕጋዊነት ጥያቄ እንዲያነሱ እድል የሚሰጥ ውሳኔ መሆኑንም ያብራራሉ። "እነዚህ ፓርቲዎች በዕጩዎቻቸው መታሰር በምርጫው ፍትሃዊነት እና ተአማኒነት ላይ ሲያነሱ የነበረውን ጥያቄ ወደ ሕጋዊነት ጥያቄ ይወስደዋል። 'እኛ ያቀረብናቸው ሰዎች ያላግባብ ከመወዳደር ስለተከለከሉ ሕጋዊነት የለውም' ብሎ ከምርጫው በኋላ ክርክር ማንሳት የሚያስችላቸው ውሳኔ ነው" ሲሉ አደም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቦርዱ ሁለት ሕጋዊ አማራጮችን ሊከተል እንደሚችል የሚናገሩት አደም የሕገ መንግሥት ትርጉም ይሰጥልኝ ብሎ ለአጣሪ ጉባኤው ማመልከት አንዱ ነው። ይህ በተለይ ከምርጫው በፊት ባለው ቀሪ ጊዜ ውስጥ የሚሆን እንደማይመስላቸው ያብራራሉ። "ቦርዱ ይህንን ውሳኔ መቀበል፣ ካልሆነ ደግሞ ዕጩዎቹ በውሳኔው መሰረት መብት እንዳላቸው ገልፆ፤ ነገር ግን ይህንን ለመፈጸም የማይችልበትን ምክንያት አስረድቶ በዚህ ምርጫ ላይ ተፈጻሚ እንዳይሆን ውሳኔ (declaratory judgment) መጠየቅ ይችላል" ሲሉ የሕግ ባለሞያው ያስረዳሉ። ምርጫ ቦርድ በፍርድ ቤት የታዘዘውን በሌላ በምንም ምክንያት አልፈጽምም ማለት እንደማይችል የሚያብራሩት አደም ይሄ መንግሥት በተደጋጋሚ እየተወቀሰበት ካለው የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ያለማክበር ጋር ተመሳሳይ እና አጠያያቂ ያደርገዋል ይላሉ። እንደ መውጫ ይህ ውሳኔ የሚተገበር ከሆነ በቦርዱ ሎጂስቲክ አቅርቦት ላይ ጫና ያመጣል የሚሉት አደም ይህም የዕጩዎች ዝርዝር የያዙ ሰነዶችን ማረም ይጠይቀዋል ይላሉ። "በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሉ፣ በተለይም በአሮሚያ ያሉ ፓርቲዎች ክስ የሌለባቸው ይሁን ያለባቸው 'ዕጩዎቻችን ይመዝገቡልን' ብለው ሲጠየቁ እንደማይችሉ ምላሽ ተሰጥቷቸው ነበር" ሲሉ አደም ያስታውሳሉ። አደም ይህ ውሳኔ ከሕጋዊ አንድምታው ሌላ የፖለቲካ አንድምታ እንደሚኖረው ያብራራሉ። ፓርቲዎቹ አሁን ዕጩዎቻቸውን ባያስመዘግቡ እና ለውጥ ባያመጡም የምርጫው ሕጋዊነት ላይ የሚያነሱትን ወቀሳ እንደሚያጠናክረው ይናገራሉ። "በአጠቃላይ ተቀባይነት ይኑረውም አይኑረው ይህ ውሳኔ የምርጫው ቅቡልነት እና ፍትሃዊነት ላይ ብቻ ሳይሆን ሕጋዊነቱ ላይ ጭምርም ጥያቄ ሊያስከትል ይችላል" እንደ ባለሞያው መደምደሚያ። አደም የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በተቋማት መካከል እርስ በእርስ በሕግ የመፈታተን እንዲሁም ራሳቸውን የቻሉ ተቋማት መጠንከር እና ጠንክሮ መቆምን የሚያሳይ እንደሆነም ያክላሉ።
49192266
https://www.bbc.com/amharic/49192266
ለዓመታት የተጠፋፉት የወላይታ ሶዶዋ እናትና የኖርዝ ኬሮላይናዋ ልጃቸው
አማረች ከበደ እባላለሁ። 20 ዓመቴ ነው። አሁን የምኖረው ኖርዝ ኬሮላይና፤ የተወለድኩት ደግሞ ወላይታ ሶዶ።
አማረች ከዓመታት በኋላ ከእናቷ ጋር ስትገናኝ ስለ ልጅነት ሕይወቴ ልንገርሽ. . . ሁለት ታላላቅ ወንድም እና አንድ ታናሽ እህት አለኝ። እህቴ አስቴር ትባላለች። ወላጅ አባታችን ብዙም በሕይወታችን ስላልነበረ አቅመ ደካማ እናቴ ብቻዋን አራት ልጆች ለማሳደግ ትንገታገት ነበር። እናቴ ቤተሰባችንን ለማስተዳደር ብዙ ውጣ ውረድ አይታለች። ከእኛ ከልጆቿ ውጪ አንዳችም አጋዥ አልነበራትም። ገበያ ወጥቼ አትክልት እገዛና አትርፈን እንሸጠዋለን። ያገኘሁትን ብር ለቃቅሜ ወደ ቤተሰቦቼ እሮጣለሁ። • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" ያኔ እንደ ሌሎች የሰፈራችን ህጻናት አልጫወትም። [እቃቃ. . . ሱዚ. . . ቃጤ. . . የሚባል ነገር የለም]። በልጅ ጫንቃዬ ቤተሰብ የመደገፍ ኃላፊነት ወደቀብኝ። ታናሽ እህቴን የምንከባከበው እኔ ነበርኩ። እናቴ ስትሠራ እኔ አስቴርን ስለምይዝ ትምህርት ቤት መሄድ አልቻልኩም። በዚህ በኩል እህቴን መንከባከብ በሌላው እናቴን መርዳት. . . አሁን ሳስበው ይህ ሁሉ ለልጅ በጣም ይከብዳል። ከታላቅ ወንድሞቼ አንዱ አይነ ስውር ነው። ከሁላችንም በበለጠ የእሷን ትኩረት ይፈልግ ነበር። ልዩ እንክብካቤና ድጋፍ ስለሚያሻው አብዛኛውን ጊዜዋን ትሰጠዋለች። የሚያስፈልገውን ሁሉ ማሟላት ነበረባትና እናቴ ጫናው በረታባት። ልክ 11 ዓመት ሲሆነኝ ነገሮች እየተባባሱ መጡ። ያኔ አስቴር አምስት ዓመት ሞልቷት ነበር። በቃ! እናቴ እኛን ማሳደግ በጣም ከበዳት. . . እሷ ልትሰጠን ያልቻለችውን ነገር ሁላ እያገኘን እንድናድግ ትፈልግ ነበር። እኔና አስቴር የተሻለ ሕይወት እንዲኖረን ተመኘች። እዚያው ወላይታ ሶዶ የሚገኝ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ አስገባችን። እኔና እህቴ ከእናታችንና ከወንድሞቻችን ተለያየን! ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ ያለ ፍቅር ስለኖርኩበት ጊዜ ላጫውትሽ. . . በወላይታ ሶዶ የህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ ከቆየን በኋላ አዲስ አበባ ወደሚገኝ ሌላ ማሳደጊያ ተወሰድን፤ ሦሰት ወር ቆይተናል። በህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ መኖር የመተው ስሜት እንዲሰማሽ ያደርገል። እዚያ ፍቅር የለም። ሁላችንም ድርጅቱ ውስጥ የተገኘነው በማደጎ ለመወሰድ ነው። ሞግዚቶቹም ሆኑ ሠራተኞቹ አይወዱንም። ፍቅር የሚሰጥሽ ሰው የሌለበት ቦታ መኖርን አስቢው. . . እኔና እህቴ ከአንድ ዓመት በላይ ማሳደጊያው ውስጥ ኖርን። • ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ 2010 [በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር] ላይ የሪችመንድ ቤተሰብ የጉዲፈቻ ልጅ ፍለጋ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ አቀኑ። ያኔ ወደ ድርጅቱ ሲመጡ ወደ አሜሪካ ሊወስዱን እንዳሰቡ አላወኩም። አዲስ አበባ ውስጥ የቆዩት ለአምስት ቀናት ነበር። ወደ አሜሪካ ለመብረር አንድ ቀን ሲቀረን የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ ሆነን ወዴት እንደምንሄድ፣ ለምን እንደምንሄድ ገባኝ። ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም፤ ማልቀስ ጀመርኩ። ቤተሰቤን፣ አገሬን፣ የማውቀውን ነገር በሙሉ ጥዬ ልሄድ እንደሆነ የታወቀኝ በመጨረሻው ቀን ነበር። ያን ቀን በጣም ስሜታዊ ሆኜ ነበር። የእኔ ከሚሉት ነገር ተለይቶ፤ ወደማይታወቅ ዓለም መጓዝ እንዴት አያሳዝን፣ እንዴት አያስፈራ? አማረች፣ አስቴር እና የጉዲፈቻ ቤተሰቦቻቸው አሜሪካ ገባን. . . የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ሦስት ልጆች አሏቸው። ሁለት ወንድና አንድ ሴት። እኔና አስቴር አዲሱን ቤተሰባችንን ተቀላቀልን ማለት ነው። በመጀመሪያዎቹ ወራት እኔና እህቴ ስላየናቸው አዳዲስ ነገሮች እናወራ ነበር። ለሁለታችንም ትልቅ ለውጥ ነበር። እንዲያውም ለተወሰነ ጊዜ የጫጉላ ሽርሽር ላይ እንዳሉ ሰዎች ሆንን። አሜሪካን ወደድናት። ከተወሰኑ ወራት በኋላ ግን ሁሉም ነገር አስጠላኝ። ወደ አገሬ፣ ወደ ቤቴ መመለስ ፈለግኩ። ደፍሬ ባልናገረውም አዕምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው የቤተሰቦቼ ጉዳይ ነበር። እናቴ ናፈቀችኝ፤ ወንድሞቼ ናፈቁኝ፤ አገሬ ናፈቀኝ። የማውቀውን ሕይወት፣ የማውቀውን ሰው፣ የለመድኩትን ምግብ መልሶ ማግኘት ብቻ ነበር የምፈልገው። ኑሮ አልገፋ አለኝ፤ መላመድ አቃተኝ። አስቴር ትንሽ ልጅ ስለነበረች እንደእኔ አልተቸገረችም፤ በቀላሉ ከአሜሪካዊ አኗኗር ጋር ተላመደች። ኢትዮጵያ ስላሉት ቤተሰቦቻችን ብዙ ትውስታ ስላልነበራት አዲሱን ሕይወት ማጣጣም ጀመረች። እኔ ግን ተረበሽኩ። • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ትምህርት ቤት ስገባም ጓደኛ ማፍራት አልቻልኩም። ክፍል ውስጥ የነበሩት ልጆች እርስ በእርስ ይተዋወቃሉ። ባይተዋርነት ተሰማኝ። በዚያ ላይ እንግሊዘኛ አልችልም። እንዴት ከልጆቹ ጋር ልግባባ? እንደ ልጅ ሳልጫወት ማደጌን ነግሬሽ የለ? እናም እነሱ በእረፍት ሰዓት ሲጫወቱ ግራ ገባኝ። ኢትዮጵያ ሳድግ ከቤት ወጥቼ የምጫወትበት ጊዜ አልነበረኝም። ከእድሜዬ በላይ ብዙ ኃላፊነቶች ነበሩብኝ። ታዲያ አሜሪካ ስመጣ እንዴት ልጅ መሆን እንዳለብኝ ማወቅ አልቻልኩም። ጨዋታ መልመድ፣ ልጅነትን መማር ነበረብኝ። አማረች እና እህቷ የጉዲፈቻ ልጆችን ጓደኛ አደረኩ ወደሚናፍቀኝ ሕይወት መቼ እንደምመለስ አለማወቄ ይረብሸኝ ነበር። አሜሪካ ያለው ነገር ሊማርከኝ አልቻለም። ምኑም ምኑም! ሕይወትን በመጠኑ ያቀለለልኝ እንደኔው በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ የመጡ ጓደኞች ማፍራቴ ነው። እነዚህ ልጆች ኢትዮጵያ ሳለሁ ህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ አብረውኝ ኖረዋል። እናም ጓደኞቼ አሜሪካ እንዳሉና ላገኛቸው እንደምፈልግ ለጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ነገርኳቸው። እኔና እህቴን ወደ አሜሪካ ያመጣን ኤጀንሲ ስልክ ቁጥራቸውን እና የኢሜል አድራሻቸውን ሰጠን። • ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻን ማገድ አዋጭ ነው? ከሦስቱ ጓደኞቼ ጋር ዘወትር በስልክ እናወራ፣ እንገናኝም ነበር። ሁላችንንም በተመሳሳይ ነገር ውስጥ እያለፍን ስለነበረ እንግባባለን። አንዳችን ከሌላችን ምን መስማት እንደምንፈልግ እናውቃለን። ዝም ብለን እናወራለን. . . እናወራለን. . . እናወራለን. . . ስቃዩን በወሬ አስተነፈስነው። ወሬያችን እንዴት እንደረዳኝ ልነግርሽ አልችልም። የአሜሪካን ሕይወት ለመላመድ ድፍን አራት ዓመት ወስዶብኛል። ታናሽ እህቴ አብራኝ ባትሆን ኖሮ ምን እንደማደርግ አላውቅም። እዚ ያለችኝ ብቸኛ የሥጋ ዘመዴ ናት። አብሬያት ማደጌን እወደዋለሁ። ታናሼ ስታድግ፣ ስትመነደግ በቅርብ ማየት ደስ ይለኛል። ምን ይናፍቀኝ እንደነበረ ልንገርሽ. . . ከወንድሞቼ ጋር ብዙ አሳልፈናል። ታሪካችንን መልሶ መላልሶ ማሰብ ያስደስተኛል። ትውስ የሚለኝን ለእህቴ አወራላታለሁ። ትዝታዬን ለእሷ ማካፈል ታሪኬን መዝግቤ የማቆይበት መንገድ ነበር። ከምንም በላይ ምን ይናፍቀኝ እንደነበረ ታውቂያለሽ? ከእናቴ ጋር የነበረን ግንኙነት። በጣም እንቀራረብ ነበር። ሁሉንም ነገር አብረን እናደርጋለን። እንደሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበርን. . . እናቴን ሳላይ መኖር በጣም ከበደኝ። አማረች ከወንድሞቿ እና ከእናቷ ጋር ስትገናኝ በወንድሞቼ ሕይወት ውስጥ ቁልፍ የሚባሉ ክንውኖች እያመለጡኝ መሆኑ ውስጤን አደማው። ወንድሜ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ሲጨርስ. . . ታላቄ ከኮሌጅ ሲመረቅ እኔ አልነበርኩም። አሜሪካ ሆኜ ብዙ ውብ ቅጽበቶች እያለፉኝ መሆኑ እረፍት ነሳኝ። አብሬያቸው መሆን ባለብኝ ቁልፍ ወቅት ተለየኋቸው! በጄ አላልኳቸውም እንጂ፤ የጉዲፈቻ ወንድሞቼና እህቴ ሊቀርቡኝ ይሞክሩ ነበር። ልቀርባቸው፣ ልቀበላቸው ዝግጁ አልነበርኩም። አፍቃሪ እና ተግባቢ ነበሩ። ፍቅራቸውን በፍቅር መመለስ ግን አልቻልኩም። ፍቅሬን ኢትዮጵያ ላለው ቤተሰቤ መቆጠብ እንዳለብኝ ይሰማኝ ነበር። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ያኔ ላቀርባቸው ያልቻልኩት የመተው ስሜት ይሰማኝ ስለነበረ ይመስለኛል። ማንም እንዲጠጋኝ አልፈልግም። ስሜቱ በህጻናት ማሳደጊያ ከዓመት በላይ ከመቆየት የመነጨ ይመስለኛል። የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ይወዱኛል። እኔ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቼን እወዳቸዋለሁ። እናቴና ወንድሞቼን ትቻቸው አሜሪካ ስለሄድኩ ሌላ አዲስ ፍቅር አልፈለኩም። ለአዲስ ፍቅር ቦታ አልነበረኝም። ቤተሰቤን መፈለግ ጀመርኩ. . . እኔ እና እህቴ ወደ አሜሪካ የተወሰድነው በ 'ክሎዝድ አዶፕሽን' ነበር። [ይህ ማለት በጉዲፈቻ የሚወሰዱ ልጆችና የጉዲፈቻ ቤተሰቦቻቸው ስለ ልጆቹ ወላጆች መረጃ አይሰጣቸውም።] ከኢትዮጵያ ከወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ቤተሰቦቼ ምንም መረጃ ማግኘት አልቻልኩም። 2011 ላይ እናቴ አንድ ሪፖርት ደርሷታል። ሪፖርቱ ከጉዲፈቻ በኋላ ለወላጆች የሚሰጥ ነው። እና በሪፖርቱ የእኔ እና የእህቴ ፎቶ ለእናቴ ተሰጥቷታል። 2012 ላይ እኔ እና እህቴን ከጉዲፈቻ ቤተሰቦቻችን ጋር ያገናኘን ኤጀንሲ ተዘጋ። ስለ ቤተሰቦቼ ማንን ልጠይቅ? ስለእነሱ ምንም ሳልሰማ ስድስት ዓመታት ተቆጠሩ። ብቸኛ አማራጬ ፌስቡክ ላይ መፈለግ ሆነ። ግን ምንም ላገኝ አልቻልኩም። • ኮሎኔል መንግሥቱ ለህፃናት አምባ ልጆች ደብዳቤ ላኩ በሕይወት መኖራቸውን፣ ደህና መሆናቸውን ማወቅ አለመቻሌ ያስጨንቀኝ ነበር። አለቅስ ነበር። ስለቤተሰቦቼ ማሰብ ማቆም ስላልቻልኩ ፍለጋዬ ፍሬ ባያፈራም ገፋሁበት። እንደው አንድ ቀን ኢንተርኔት ላይ አገኛቸዋለሁ የሚል ህልም ነበረኝ። በስተመጨሻ ግን ተስፋ መቁረጥ ጀመርኩ. . . ቤተሰቦቼን ማግኘት እንደምፈልግ ለጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ነገርኳቸው። ቤተሰቤን ሳላገኝ መኖር አልችልም አልኳቸው። የጉዲፈቻ አባቴ 18 ዓመት ሲሞላኝ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚወስደኝና ቤተሰቦቼን እንደምንፈልጋቸው ቃል ገባልኝ። ግን ከ18ኛ ዓመት ልደቴ በፊት ሕይወቴን የለወጠ ዜና ደረሰኝ። ለካ እናቴም እኔ እና እህቴን እየፈለገችን ነበር አንድ ቀን 'መላው ቤተሰብ ይሰብሰብ' ተባለ። የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼ ሁላችንንም አንድ ላይ አድርገው 'አስደሳች ዜና አለን' አሉ። እናቴ እኔና አስቴርን እያፈላለገችን እንደሆነ ነገሩን። እናቴ የጉደፈቻ ሪፖርቱ ሲቋረጥባት እኛን መፈለግ ጀምራ ነበር። ወላይታ ሶዶ ውስጥ ለምትገኝ አንዲት ማኅበራዊ ሠራተኛ ስለእኛ ነገረቻት። ፎቷችንን ሰጠቻት። ቅጽል ስሜ አያኔ መሆኑን፣ ጀርባዬ ላይ 'ማርያም የሳመችኝ' ምልክቱ እንዳለ ሳይቀር አውርታላታለች. . . ያላትን መረጃ ባጠቃላይ ዘረገፈችላት ብልሽ ይቀለኛል. . . ማኅበራዊ ሠራተኛዋ 'ቤተሰብ ፍለጋ' በሚባል ድርጀት በኩል የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼን አገኘቻቸው። ይሄ ሀሉ ሲነገረኝ የደስታ ሲቃ ተናነቀኝ። በጣም ደንግጬም ነበር። እኔ ለዓመታት ስፈልጋቸው ነበር። ታዲያ እንዴት እኔ ሳላገኛቸው ቀድመው አገኙኝ? ያልጠበቅኩት ነገር ነበር። አማረች፣ እናቷ እና ታላቅ ወንድሟ ቀጥሎ ምን እናድርግ? ደብዳቤ እንጻፍ? ጥያቄዬን ማከታተሉን ተያያዝኩት. . . እህቴም ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ተጋብታ ነበር። ዝም ብላ እኔን ትከተል ጀመር። ከዚያም ደብዳቤ ጽፈን ለቤተሰቦቼ ላክልናቸው። ከሁለት ሳምንት በኋላ ፎቶና ቪድዮ ላኩልን። በዚያ ቅጽበት ሕይወቴ እስከወዲያኛው ተቀየረ። ከቤተሰቦቼ ጋር ከተገናኘሁ ስምንት ዓመት ተቆጥሮ ነበር። እናቴ እና ታላላቅ ወንድሞቼን ስፈልጋቸው እነሱም እየፈለጉኝ ነበር። እኔንም አስቴርንም። አድራሻቸውን ካገኘሁ በኋላ ያለማቋረጥ ማውራት ጀመርን። ወደ ሶዶ ተመለስኩ. . . ባለፈው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ለመብረር ትኬት ቆረጥኩ። እህቴ 'ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ዝግጁ አይደለሁም' ስላለቺኝ የሄድኩት ብቻዬን ነበር። ልክ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ስደርስ በጣም ተጨነቅኩ። ታላቅ ወንድሜ መጥቶ እጄን ቢይዘኝ ተመኘሁ. . . አይገርምም መጀመሪያ ያገኘሁት እሱን ነበር። አቅፎኝ ሊለቀኝ መሰለሽ? አዲስ አበባ ውስጥ በቆየንባቸው ቀናት እጄን ይዞ ነበር የሚንቀሳቀሰው፤ አለቀቀኝም። እንደ ልጅነታችን ዳግመኛ ተሳሰርን። ከዚያ ወደ ሶዶ ሄድን። እናቴን ሳያት ዝም ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ፤ እሷም አለቀሰች። የደስታ እንባ አነባን። ከአምስት ደቂቃ በላይ ሳንላቀቅ ተቃቅፈናል። እናቴ ስማኝ ልትጠግብ አልቻለችም። እውነት እውነት አልመስልሽ አለኝ. . . ሁሉም ነገር እንደ ድሮው ተመለሰ። የማውቃቸውን ቤተሰቦቼን አገኘሁ። ሶዶ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ስልም እንግዳ የሆንኩ አልመሰለኝም። ሦስት ሳምንትን አሳለፍኩ። በጉዲፈቻ ባልሰጥ ኖሮ ሕይወቴ ምን ሊመስል እንደሚችል ከእናቴ ጋር አወራን። እኔ እና እህቴን ለጉዲፈቻ መስጠቷ እንደማይጸጽታት ነግራኛለች። እውነት ነው በሕይወቷ ካደረገቻቸው ነገሮች ከባዱ እኛን ለማደጎ መስጠት ነበር። ቢሆንም 'ለጉዲፈቻ የሰጠኋችሁ ያለ ምክንያት አይደለም፤ እንደዚህ በችግር እንድትኖሩ አልፈልግም' አለችኝ። በእርግጥ ኤጀንሲው ተዘግቶ እኛን ለማግኘት ስትቸገር ለጉዲፈቻ በመስጠቷ ተጸጽታ ነበር። ልጆቿ እንዴት እየኖሩ እንደሆነ ማወቅ ባለመቻሏ ለሳምንታት እንዳለቀሰች፣ በጣም እንደተጎዳችም ጓደኛዋ ነገረችኝ። እናቴ እንደእኔው እየተሰቃየች እንደነበር ማወቄ ልቤን ሰብሮታል። ለእኔ አሜሪካ መኖር ጥሩ ነው። ቁሳዊ ነገር አላጣሁም። ቤተሰብን ግን አይተካም። የሆነ ነገር እንደጎደለኝ ይሰማኝ ነበር። ለካ እናቴም እንደኔው ነበረች. . . አሁንማ ሕይወቴ ውብ ነው አሁን የመጀመሪያ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ነኝ። ቢዝነስ እያጠናሁ ነው። የጉዲፈቻ ቤተሰቦቼን በጣም እወዳቸዋለሁ። እውነቱን ለመናገር ከእነሱ ጋር ለመላመድ ጊዜ ወስዶብኛል። የማያውቁትን ሰው እማዬ፣ አባዬ፣ እህት ዓለም ወንድም ዓለም ማለት ከባድ መሆኑን አልክድም። ግንኙነታችንን ለመገንባት ጊዜ ቢወስድብንም አሁን ቤተሰብ ነን። • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች እናቴ እኔን እና እህቴን ለማደጎ መስጠቷ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብዬ አስባለሁ። ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ሕይወት ቢከብደኝም. . . እናቴን ተረድቻታለሁ። በጉዲፈቻ ባትሰጠኝ ኖሮ ብዙ መከራ ይጠብቀኝ ነበር። ከጉዲፈቻ ወንድሞቼ እና ከእህቴ ጋር እንቀራረባለን። ኢትዮጵያ ካሉት ወንድሞቼ ጋርም እንዲሁ። ወንድሞቼን ሳዋራቸው የሆነ ጉልበት አገኛለሁ። ምንም ነገር ላሳካ እንደምችል ይሰማኛል። ያበረቱኛል። ያጠነክሩኛል። ምን እንደማስብ ታውቂያለሽ? ምናልባትም የጉዲፈቻ ልጅ ያልሆነ ሰው ይሄ አይገባው ይሆንል. . . የጉዲፈቻ ልጆች ስለ ወላጆቻቸው ማወቅ አለባቸው። 'ማንን ነው የምመስለው?' 'ከየት መጣሁ?' እያሉ ሕይወትን መግፋት የለባቸውም። በጥያቄ መሞላት፣ በናፍቆት መማቀቅ የለባቸውም። ቤተሰቦቼን ካገኘኋቸው በኋላ ሕይወቴ ተቀይሯል። ደስተኛ ሰው ሆኛለሁ። አሁን የማስበው ዲግሪዬን አግኝቼ ጥሩ ሥራ ስለመያዝ ነው። ያለፈ ሕይወቴ ጥያቄዎች ስለተመለሱ ስለ ወደፊቴ ማሰብ እችላለሁ።
news-47465734
https://www.bbc.com/amharic/news-47465734
አረጋውያንን በነጻ የሚያሳፍረው ባለታክሲ
ማርቆስ ዘሪሁን ብዙ በረከት ከተቸረው ባለታክሲዎች አንዱ ሳይሆን አይቀርም። በአዲስ አበባ ከተማ የላዳ ታክሲ አገልግሎት በመስጠት ነው የሚተዳደረው። ታዲያ በላዳው የጀርባ መስታወት ላይ ዕድሜያቸው ለገፉና ለአቅመ ደካሞች የነጻ አገልግሎት እሰጣለሁ የሚል ጽሑፍ ከስልክ ቁጥር ጋር አስቀምጧል።
አቅመ ደካሞችን በመንገድ ላይ እያዩ ማለፍ ይከብደኛል የሚለው ማርቆስ በተለይ ነፍሰጡሮችን ዝም ብሎ ለማለፍ ልቡ ስለማያስችለው ገንዘብ ሳይጠይቅ በነፃ ወደሚፈልጉበት ቦታ ይወስዳቸዋል። ይህ ተግባሩ በብዙ ሰዎች ዘንድ እውቅና ያሰጠው ማርቆስ በአካባቢው ባይኖር ብዙ ሰዎች በስልክ ደውለው ይጠሩታል። እሱም የተለመደ መተባበሩን ያከናውናል። ''ሥራ ላይ ካልሆንኩኝ በፍጥነት ሄጄ እተባበራቸዋለሁ። '' ይላል • አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ ''ታክሲው ባዶ ሆኖ መሄድም ቢሆም አልወድም። '' እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን የመተባበር ሥራ ላይ ስታተኩር ዋናው ሥራህ ጋር አይጋጭብህም ወይ? ስንል ለማርቆስ ጥያቄ አቅርበንለት ነበር። ''ሲጀመር እኔ ምንም አላስበውም፤ ከሥራዬም ጋር እስካሁን የተጋጨብኝ ነገር የለም። እንደውም መጀመሪያ ያንን ሥራ አስቀድሜ ከጀመርኩ ቀኔ ደስ የሚል ሆኖ ነው የሚውለው'' በማለት ይመልሳል። በጠዋት ከቤት ሲወጣ ለትራንስፖርት አገልግሎት የተሰለፉ ዕድሜያቸው የገፋ ሰዎችን ሲመለከት ሁለትም ይሁን ሦስት ፌርማታ ድረስ የሚፈልጉበት ቦታ ያደርሳቸዋል። አንዳንዴ አምስትም ስድስትም ሊወስድ እንደሚችል ይናገራል። አንዳንድ ጊዜም ደንበኛ ጭኖ እየሄደ እንኳን አቅመ ደካሞችን ሲመለከት አስፈቅዶ ሰዎቹን እንደሚጭናቸው ይናገራል። ደንበኞችህ፣ ጓደኞችህና ሌሎች በአቅራቢያህ ያሉ ሰዎች ምን ይሉሃል? ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ፣ ''ደንበኞች በጣም ደስ ይላቸዋል። አንዳንዶቹ እኔ በምሄድበት መንገድ ከሆነ ምንም ችግር የለውም ይላሉ። ሌሎቹ ደግሞ የሚሄዱበት መንገድ ካልሆነ ደስተኞች አይሆኑም'' ብሏል። ''ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ሊኖረው አይችልም። ጓደኞቼ ደግሞ ''በርታ፣ ጠንክር እኛ ያላሰብነውን ነገር ነው እያደረግክ ነው ያለኸው ይሉኛል።'' የላዳ ታክሲ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሁለት ዓመት የሆነው ማርቆስ፤ በሹፌርነት ተቀጥሮ በሚሠራበት ወቅትም ይህንኑ ተግባር ያከናውን እንደነበር ይናገራል። ''ታክሲው ባዶ ሆኖ መሄድም ቢሆም አልወድም። '' ''ወደ ተለያዩ ቦታዎች ስላክ ብዙ ጊዜ ብቻዬን ስለሆነ የምሄደው በመንገዴ ያገኘኋቸውን ሁሉ እየጫንኩ አልፍ ነበር። ተቀጣሪ እንደመሆኔ የመኪናው ባለቤቶች ደስተኞች አይሆኑም። እኔ ግን ዝም ብዬ የተቸገሩ ሰዎችን ሳገኝ እተባበር ነበር።'' '' እንደውም የራሴ መኪና ቢኖረኝ እኮ እንደልቤ እሠራ ነበር እያልኩ እመኝ ነበር፤ አሁን ይኸው የተመኘሁትን ነገር እያደረግኩ ነው።'' ማርቆስ ይህንን በጎ ተግባር ሲፈጽም ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እንዳልሆነ ይናገራል። • ለ10 ዓመታት እጆቹን ያልታጠበው የቴሌቪዥን አቅራቢ • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን አንዳንድ ሰዎች ተቸግረናል እዚህ ቦታ ቶሎ ድረስልን ብለው ደውለውለት እሱ በቦታው ደርሶ ሲደውልላቸው አውቀን ነው፤ እውነተኛ መሆንህን ለማረጋገጥ ፈልገን ነው የሚል ምላሽ እንደሚሰጡት ይናገራል። ''ረጅም መንገድ ተጉዤና ያንን ሁሉ ጊዜዬን አባክኜ እንዲሁም ነዳጄን ጨርሼ በቦታው ስደርስ 'ታማኝነትህን ለማረጋገጥ ነው' የሚሉ ሰዎች ናቸው ትንሽ ያስቸገሩኝ።'' ከዚህ በተረፈ ግን እስካሁን ምንም ችግር እንዳላጋጠመው የሚናገረው ማርቆስ ወደፊትም ቢሆን ይህንን በጎ ተግባሩን እንደሚቀጥልበት ጽኑ እምነቱ ነው።
news-52662950
https://www.bbc.com/amharic/news-52662950
ኮሮናቫይረስ ያወጣቸው የቤተልሔም አበበ ገፀ ባህሪያት
ቤትልሔም አበበ 'ማኒ ሃይስት' በመባል በሚታወቀው የኔትፍሊክስ ተከታታይ ፊልም ላይ ተዋናዮቹ የሚለብሱትን፣ የስፓኒሽ አርቲስቱን የሳለቫዶር ዳሊን ማስክ በመሆን፣ ሲያምራት የ'ፓይረትስ ኦፍ ዘ ካሪቢየን' ዋና ገፀ ባህሪ ካፕቴን ጃክ ስፓሮውን፣ ሲያሰኛት ደግሞ 'ዘ ማስክ' የተባለውን በፈርንጆቹ በ1994 የወጣው ፊልም ላይ ያለውን ገፀ ባህሪ በመምሰል ራሷን ትቀያይራለች።
ግራ: ቤትልሔም አበበ ቀኝ: (ቤትልሔም አበበ) ሳለቫዶር ዳሊ 'ማኒ ሃይስት' ይህ ብቻ ግን አይደለም፤ ሌሎች ብዙ ገፀ ባህሪያትን በመሆን ዘመድ ጓደኞቿን ታዝናናለች። ከቤቢ ዮዳ (ስታር ዎርስ ፊልም እ.አ.አ 2019)፣ ከማሌፊሸንት (ማሌፊሸንት 1 እና 2 ፊልም እ.አ.አ 2014ና 2019 ) እና ከካፕቴን ስፖክ (ስታር ትሬክ ፊልም እ.አ.አ 1966) ገፀ ባህሪያት በስተጀርባ ያለችው ቤተልሔም አበበ ማን ናት? ዘ ማስክ ቤተልሔም ከአዲስ አበባ ሕንፃ ኮሌጅ የዛሬ ሦስት ዓመት ተመረቃለች። "ሁሌም ለጥበብ ታደላ ነበረ" የምትለው ልቧም፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከማቅናቷ በፊት አልማው እንደነበረው ወደ ጥበብ ጎዳና መራት። የሥነ-ሕንፃ ምሩቅ የሆነችው ቤተልሔም በሁለቱ ሥራዎች መካከል ብዙም ልዩነት የለውም እያለች ቀስ በቀስ ወደ ሜካፕ [የገጽ የቅብ ባለሙያ] ሥራ ተሰማራች። ሆኖም ግን እሷ የምትሠራው በውበት ሳሎን ወይም ለሠርግ እንደሚሞሽሩት፣ በሃገራችን የተለመደው ሜካፕ [የገጽ ቅብ] አልነበረም። የቤቲ ሜካፕ ሥራ አንዳንዴ ሊያስፈራ የሚችል፣ አንዳንዱን ግር የሚያስብል ወይንም አልፎ አልፎ የሚያዝናና እና 'ወይ ጉድ' ሊያስብል የሚችል ነው። • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች "በእርግጥም የጀመርኩት ብዙዎቻችን በምናውቀው በኮስሜቲክ ወይም ማስዋብያ ሜካፕ ነው" የምትለው ቤትልሔም፣ ገና ሳትመረቅ የሚወዷት አክስቷ ከውጪ አገር ለሠርግ መጥተው ለሜካፕ ሥራ ያላትን ተሰጥዖ ልብ አሉ። ወደ ኑሮዋቸው ሲመለሱ "ቢያስፈልግሽ" ብለው የተሟላ የሜካፕ ዕቃ ይልኩላታል። ከዚያም በተላከላት ስጦታ የገጽ ቅቡን ሥራ ተያያዘችው። ቤቲ ግን ትፈልግ የነበረው ፊልም ላይ የምታያቸውን ከሰው አንስቶ አውሬ እስከሚምስሉ ያሉትን ገፀ ባህሪያት አስመስሎ መሥራት ነበር። ቤቢ ዮዳ ከተመረቀችም በኋላ የፕሮዳክሽን ድርጅት ተቀላቅላ የመጀመሪያዋን ሥራ፣ አርት ዳይሬክተር ሆና የፊልም አልባሳትና የቀረፃ መድረኮችን ዲዛይን በማድረግ ጀመረች። ቤትልሔም የሚታዩ ጥበባትን እንደምትወድ በመግለፅ "ፊልም ላይ ሴት ወይም ኢንቫይሮንመንት ዲዛይን በጣም እወዳለሁ። ገፀ ባህሪያቱ ምን ይምሰሉ፣ ምን ይልበሱ፣ የት ይሁኑ እና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች ልዩ የሆኑ 'ክሪዬቲቭ' መፍትሔዎችን ማግኘት ያስደስተኛል" ትላለች። ከልጅነቷ የሚያስታውሷት ጓደኞቿ መቀባባት፣ መለባብስ እንደምትወድ ያስታውሳሉ የምትለው ቤቲ "ለቀልድ እንጂ" ሥራ ብላ እንዳልያዘቸው ታስረዳለች። የሚወዷት አክስቷ ግን በየጊዜው የጨረሰቻቸውን የሜካፕ ዕቃዎችና ሌላም ሌላም ጨመር ጨመር እያደረጉ መላካቸውን አላቆሙም። • በሊባኖስ ያሉ ኢትዮጵያዊን ለአንድ ጉዞ ከፍተኛ ገንዘብ ተጠየቅን አሉ ሁሉም ነገር የጀመረው በምዕራቡ ዓለም የሙታን ቀን ተብሎ በሚከበርበት ዕለት (ኦክቶበር 31፡ 2019)ነው። 'ለኮስትዩም ፓርቲ' የተጠራችው ቤቲ ራሷን ቀያይራ 'ባትማን' በተሰኘው ፊልማ ላይ ክፉ ገፀ ባህሪ የሆነውን 'ዘ ጆከር'ን ሆና ተገኘች። በዚያ ዝግጅት ላይ ያዩዋት በሙሉ በሥራዋ በጣም መደነቃቸውን ይገልፁላታል። የሰዎችን አድናቆትና አበርታች ስሜቶችን ልብ ያለችው ቤተልሔም ተሰጥዖ እንዳላት ተረዳች። ማሌፊሸንት "ጆከርን ከሠራሁ በኋላ ብዙ ልሠራቸው የምችላቸውን ገፀ ባህሪያት ዘረዘርኩኝ። ልሠራቸውም አቀድኩኝ። እንደውም የራሴን ስቱድዮ ከፍቼ ሁሉ እውን ላደርጋችው ተመኘሁኝ" የምትለው ቤተልሔም ፍላጎቷ እያደር እያደገ ቢመጣም እንኳ በዕለት ተዕለት ሩጫ መካከል እምብዛም ጊዜ አለማግኝቷን ትናገራለች። • በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተደናቀፈው ጣናን ከእምቦጭ የማጽዳት ሥራ ከወራት በኋላ ግን የኮሮናቫይረስ ወረርሺኝ ዓለምን ሲያንቀጠቅጥና ሁሉም ከቤት ሆኖ እንዲሠራ ሲታዘዝ ተመኝታ የነበረውን ጊዜ ማግኘቷን ትናገራለች። ከዚያም ከዚህ ቀደም የተዘረዘሩትንና ማይክል ጃክሰን ድሮና ዝንድሮ፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ከእነ ባለቤታቸው ዝናሽ ታያቸው፣ ጃንሆይንና ሌሎችንም ትሠራ ጀመር። ከሥነ-ሕንፃ ትምህርት ተነስታ ወደ የገጽ ቅብ፣ ለዚያውም ወዳልተለመደው፣ ማቅናቷን ሲሰሙ ቤተስቦቿ ምን እንዳሉ ጠየቅናት። በስተግራ: (ሊድያ አበበ) ማይክል ጃክሰን ድሮ በስተቀኝ: (ቤተልሔም አበበ) ማይክል ጃክሰን ዘንድሮ "ወላጆቼ በጣም ደስተኛ ናቸው። በጣም ያበረታቱኛል። መጀመሪያ በግዳጅ ሳይሆን የወላጅ ሃሳባቸውን፣ ሕክምና እንዳጠና ይፈልጉ ነበር። እኔ ግን አርት እወድ ስለነበር ሥነ-ሕንፃን መረጥኩኝ። ምክንያቱም 'አርኪቴክቸር' ዲዛይንም አርትም ጥበብም ነው" ትላለች። አክላም "ሥነ-ሕንፃ ስገባም ሆነ ከዚያም ወደ ሜካፑ ስሰማራ በጣም 'ሰፖርት' ያደርጉኝ ነበር። ዕድለኛ ነኝ" በማለት ለቤተሰቦቿ ያላትን አድናቆት ትገልፃለች። በኮሮናቫይረስ ምክንያት በጅማ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ ዓመት ተማሪ የሆነችው ታናሽ እህቷም ቤት በመሆኗ አልፎ አልፎ እንደምታግዛት አጫውተናለች። "ታናሽ እህቴ እንደውም እኔን ለማገዝ ስትል ሌሊት እንኳን ትነሳልኛለች" የምትለው ቤቲ ፀጥታው ለሥራ ስለሚመቻት ሌሊቱን ቀን፣ ራቷን ቁርስ አድርጋ ሠርታ አድራ ሲነጋጋ እንደምትተኛ ትናገራለች። "ጠዋት ያለው የተፈጥሮ ብርሃን ለፎቶ በጣም ይመቻል። ስለዚህ ሌሊት የሠራሁትን ፎቶ እንድታነሳኝ እህቴን ብዙ ጊዜ እቀሰቅሳታልሁ። እርሷም ትታዘዘኛለች። አንዳንዴ እንደውም እሷ ከእኔ ጠየም ስለምትል ወደ አንዳንድ ገፀ ባህሪያት እሷንም ጭምር እቀይራታለሁ" በማለት የሥራ ሂድቷን ታስረዳለች። ቤትልሔም ስፖክን ሆና ከወላጆቿ ጋር "አንዳንዴ ክፉ ነገር ሲገጥመን ጥሩ ጎኑን ፈልገን ራሳችንን ወደሚጠቅመን ነገር መቀየር ሃሪፍ ነው" በማለት ምንም ነገር ወይም ማንም ሰው እንዳሰበው ነገሮች እንደማይሳኩ ትናገራለች። የፈለገቻቸውን ገፀ ባህሪያት ለመሥራት በአሁን ሰዓት ከበድ እንደሚል የምትናገረው ቤትልሔም ያሰበቻቸውን 35 ገፀ ባህሪያት ለመሥራት የሚያሰፈልጋት ዕቃ እጇ ላይ አለመኖሩን ትናገራለች። ሆኖም ግን እስከዛሬ አክስቷ የላኩላትን የኮስሞቲክስ ሜካፕ በመጠቀም፣ ከ35ቱ አሥሩን ገፀ ባህሪያት ባለፉት 4 ሳምንታት ብቻ መሥራቷን ትናገራለች። • የቀድሞ ነፃ ትግል ተፋላሚና ተዋናይ ልጁን ከመስጠም አድኖ ህይወቱ አለፈ "እንደ ልቤ ወጥቼ የምፈልገውን ዕቃ ባሁን ሰዓት ማሟላት አልችልም። ቢሆንም ግን መሥራት የምፈልጋቸውን ሳይሆን ባሉኝ ዕቃዎች መሠረት መሥራት የምችላቸውን ነው እየሠራሁ ያለሁት። ለምሳሌ ጃክ ስፓሮውን ለመሥራት ፊልሙን ደግሜ ማየት ሁሉ ነበረብኝ፤ ምክንያቱም ሁሉን ነገር ማመሳሰል የምችልበትን ዕቃ ማሰብ ነበረብኝ። ማንኛውንም ገፀ ባህሪ ከመሥራቴ በፊት ቅድመ ጥናት አደርጋለሁ" የምትለን ቤቲ እንደ ገፀ ባህሪያቱ መልበስና መምሰል ብቻ ሳይሆን ገፀ ባህሪውን መላበስ አስፈላጊ መሆኑን ትገልፃለች።
news-48741581
https://www.bbc.com/amharic/news-48741581
ኢትዮጵያ የተገደሉ ባለስልጣናትና ጄኔራሎችን ለመዘከር የሃዘን ቀን አወጀች
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ተሞከረ በተባለው መፈንቅለ መንግሥትና ግድያ ህይወታቸውን ላጡት የክልሉ ባለስልጣናትና የመከላከያ ሠራዊት ጄኔራሎችን ለመዘከር በመላው አገሪቱ ዛሬ ሰኔ 17 የሃዘን ቀን ሆኖ እንዲውል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንትናው እለት አውጇል።
የአማራ ክልል መንግሥትም ለተገደሉት ሁለት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ሁለቱ ጄኔራሎች ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የሃዘን ጊዜ ማወጁ ተሰምቷል። በአማራ ክልል የተሞከረውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እንዲሁም የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ጡረታ ላይ የነበሩት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ጄኔራል ገዛኢ አበራ መገደላቸው ይታወሳል። •ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ •ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው •በሃየሎም ይምሉ የነበሩት ጄነራል ሰዓረ መኮንን ማን ናቸው? በመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ የተገደሉ ባለስልጣናትና ጄኔራሎችን ሥርዓተ ቀብር የሚያስፈፅም ኮሚቴ መዋቀሩን ትላንትና የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
news-55365774
https://www.bbc.com/amharic/news-55365774
ኮቪድ-19፡ የቡሩንዲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ
የቡሩንዲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፒየር ቡዮያ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን የአጎታቸው ልጅና የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
የ71 አመቱ የቀድሞ መሪ በፓሪስም ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል። በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚዳንት ቡሩንዲን ለ13 አመታትም ያህል መርተዋል። በዚህም አመትም ጥቅምት የቡሩንዲ ፍርድ ቤት የመፈንቅለ መንግሥቱ ጉዳይ ላይ በተመሰረተ ክስ በሌሉበት የእድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸው ነበር። ፍርድ ቤቱ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በጎሮጎሳውያኑ 1993 የተመረጡትን ፕሬዚዳንት ሜልቾይር ናዳየን ገድለዋቸዋልም በሚል ነው ብያኔውን ያስተላለፈው። በወቅቱም 300 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግን ምንም አይነት ስህተት አልፈፀምኩም በማለት ክደዋል። በአፍሪካ ህብረት የሳህልን ቀጠና ወክለው ልዩ መልዕክተኛ የነበሩ ሲሆን ባለፈውም ወር ነው ከዚሁ ኃላፊነታቸው የለቀቁት፤ ንፁህነታቸውንም ለማስመስከር እስከ መጨረሻ ድረስ እታገላለሁም በማለት ፀንተው ነበር።
49950187
https://www.bbc.com/amharic/49950187
ግብፅ በህዳሴ ግድብ ላይ አለም አቀፍ አደራዳሪዎች ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበች
የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ ለሁለት ቀናት ያህል መስከረም 23፣ 24 2012 ዓ.ም በህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ያደረጉትን የሦስትዮሽ ምክክር ተከትሎ ግብፅ አለም አቀፍ አደራዳሪዎች እንዲገቡ ጥሪ አቅርባለች።
ግብፅ የሦስትዮሽ ስምምነቶቹ ምንም ዓይነት ውጤት ባለማምጣታቸው አለም አቀፍ አደራዳሪ እንዲገባ ጥሪ ማድረጓን ተከትሎ ኢትዮጵያ በበኩሏ የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል ገልፃለች። • በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም፡ ግብጽ • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሱዳን መዲና ካርቱም የተደረገውን የሦስትዮሽ ውይይት ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ የግብፅ የሦስተኛ ወገን ጥሪ እስካሁን በሦስቱ አገራት ላይ የተደረሱ አበረታች ስምምነቶችን የሚያፈርስ ከመሆኑ በተጫማሪ ሦስቱ አገራት በመጋቢት 2017 የፈረሟቸውን የመግለጫ ስምምነቶችም ይጥሳል ይላል። መግለጫው አክሎም የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ሳይሆን በሱዳን በኩል ተቀባይነት የሌለውና በአገራቱ መካከል ያለውን ዘላቂ ትብብር የሚጎዳ፣ በአገራቱ መካከል የነበሩ ቴክኒካዊ ውይይቶችን ዕድል ቦታ ያልሰጠ እንዲሁም የነበረውን የውይይት መንፈስ የሚያጠለሽ ነው ብሏል። የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው ግብፅ ያቀረበችውን አደራዳሪ ኃሳብ እንደማይቀበሉት የገለፁ ሲሆን "ለምንድን ነው አዲስ አጋሮች የሚያስፈልገን? ስምምነቱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ይፈለጋል ማለት ነው?" በማለት ለሪፖርተሮች መናገራቸው ተዘግቧል። • ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? ግብፅ ማን አደራዳሪ ይሁን በሚለው ላይ ምንም ባትልም የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ፤ አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ላይ ያላት ሚና ከፍ ያለ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ የመሙላት ሂደትና አጠቃቀም ላይ ትብብር፣ ዘላቂነትና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን በተመለከተ እየተደረገ ያለውን ድርድር እንደምትደግፈው አሜሪካ ከውይይቱ በፊት መግለጫ አውጥታ ነበር። ይህ የተገለጸው ከኋይት ሃውስ የፕሬስ ጽህፈት ቤት በወጣና ዝርዝር ጉዳዮችን በማይጠቅሰው አጭር መግለጫ ላይ ሲሆን፤ መግለጫው የወጣበት ምክንያትም አልተገለጸም። በዚህ አጭር መግለጫ ላይ "ሁሉም የአባይ ተፋሰስ አገራት በምጣኔ ሃብት የመልማትና የመበልጸግ መብት አላቸው" ይልና ሲቀጥል "አስተዳደሩ [የአሜሪካ] ሁሉም አገራት እነዚህን መብቶች ሊያስከብር የሚችልና የእያንዳንዳቸውን የውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያስከብር በጎ ፈቃደኝነትን የተላበሰ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ ያቀርባል" ይላል። ከውይይቱም በኋላ የግብፅ ፕሬዚዳንት ግብፅ በናይል ላይ ያላትን መብት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት እንዳላት ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቱ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት " ግብፅ በናይል ላይ ያላትን መብት ለማስጠበቅ በፖለቲካዊ ምክክር እንደምትቀጥልና በአለም አቀፉ ሕግጋት ማዕቀፍ ሥር አስፈላጊውን እርምጃ ትወስዳለች" ብለዋል። •ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ስለአባይ አጠቃቀም ምላሽ ሰጡ የህዳሴ ግድቡን የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ጉዳይ ከግብፅ በኩል ለፖለቲካ ምክክር እንዲቀርብ ኃሳብ መቅረቡ የጉዳዩን መፍትሔ ያላገናዘበ፤ የሦስቱ አገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉዳዩን ለመፍታት ቴክኒካዊ ምክክር አስፈላጊነቱን በተመለከተ የሰጡትን መምሪያ የጣሰና መፍትሔም እንደማያመጣ ኢትዮጵያ በምላሹ ገልፃለች። ውይይቱን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ በትዊተርና ፌስቡክ ገፁ እንዳሰፈረው በህዳሴ ግድብ ሙሌትና መለቀቅ ላይ የሚደረጉ ስምምነቶችን ለማስቀጠል እንደሚፈልግና ከሁለቱም አገራት ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። አስራ አንዱ የናይል ተፋሰስ አገራት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ያለምንም ጉዳት የሚጠቀሙበትና ኢትዮጵያም ከውሃ ኃብቷ በመጠቀም ሕዝቦቿ የሚጠቀሙበትን መንገድ ለመቀየስ እንደምተሠራ ተገልጿል። •አሜሪካ የአባይ ወንዝ አጠቃቀምን በተመለከተ መግለጫ አወጣች ኢትዮጵያ የትኛውንም ዓይነት ያለመስማማቶችም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች በሦስትዮሽ ውይይቶች ለመፍታት እንደምትሠራ ብትናገርም ከግብፅ በኩል የሚሰሙት ውይይቶቹ ፍሬ አልባና ወደየትም የማያስኬዱ ናቸው የሚሉ ናቸው። ባለፈው መስከረም 3 እና 4/2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ፣ የግብጽና የሱዳን ባለሥልጣናት ካይሮ ላይ የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ ባደረጉት የሦስትዮሽ ውይይት፤ ግብፅ የህዳሴ ግድቡ የውኃ አሞላልን በተመለከተ በተናጠል ያቀረበችው ሃሳብ በኢትዮጵያ ውድቅ መደረጉ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከካይሮው ድርድር በኋላ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ግብጽ በግድቡ ውሃ አሞላል ላይ አዲስ ሃሳብ እንዳቀረበችና ኢትዮጵያ ሃሳቡን ውድቅ እንዳደረገች ተናግረዋል። ግብፅ በተናጠል ያቀረበችው የውሃ ሙሌቱን አለቃቅ ሰነድ ከአገራቱ ማዕቀፍ ትብብር ያፈነገጠና እየተካሄዱ ያሉ ስምምነቶችን የሚቃረን ነው ተብሏል። እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፤ ግብጽ ያቀረበችው ሃሳብ የግድቡ የውሃ የሚሞላው በሰባት ዓመት እንዲሆን፣ ኢትዮጵያ በዓመት 40 ቢሊየን ሜትር ኪዮብ ውሃ እንድትለቅና የአስዋን ግድብ የውሃ መጠኑ ከምድር ወለል በላይ 165 ሜትር ላይ ሲደርስ ግድቡ በዋናነት ውሃ እንዲለቅ የሚጠይቅ ነው። ኢትዮጵያም ይህ የግብጽ ሃሳብ ቀደም ሲል በሦስቱ ዋነኛ የተፋሰሱ አገራት መካከል የተፈረመውን የአባይ ወንዝ ውሃን አጠቃቀም የተመለከተውን "የመርህ ስምምነት የጣሰና ጎጂ ግዴታን የሚያስቀምጥ ነው" በማለት እንደማትቀበለው አሳውቃለች። ሚኒስትሩ በተጨማሪም ይህ የቀረበው ሃሳብ "ግብጽ የወንዙ ዓመታዊ የውሃ ፍሰት 40 ቢልየን ሜትር ኪዩብ እንዲሆን ያቀረበችው ጥያቄ፤ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ የአባይ ውሃን እንዳትጠቀም የሚከለክል በመሆኑ አልተቀበለችውም" ብለዋል። •"የሰለጠነና በሙሉ አቅም የሚዋጋ ኃይል ነው ችግሩን የሚፈጥረው" የማዕከላዊ ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ግድቦቹን ለመሙላት የሚያስፈልገው 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ ከአራት እስከ ሰባት ዓመታት ብታስቀምጥም ግብፅ በበኩሏ የውሃ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል በሚል ረዘም ያለ ጊዜ እንዲሰጥ ጠይቃለች። ግብፅ የህዳሴ ግድብ መገንባት በየአመቱ የምታገኘውን 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሊቀንሰው እንደሚችል ስጋቷን በተደጋጋሚ እየገለፀች ነው። የሦስቱ አገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት ከመካሄዱ በፊት በግድቡ የውሃ አሞላልና የመልቀቅ ሂደት ዙሪያ ሁኔታዎች እንዲያጠና የተቋቋመው የአገራቱ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን ከመስከረም 19 እስከ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በካርቱም አምስተኛ ዙር ስብሰባውን አካሂዶ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሙሌት እና የውሃ አለቃቀቅ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስብሰባውን አካሂዷል። የሦስቱ አገራት የውኃ ሚኒስትሮች በካይሮ ስብሰባቸው ላይ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌቱንና አለቃቀቋን ዕቅድንና ግብፅና ሱዳን የሚያቀርቡትን ሰነድ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ትንታኔና ምክረ ሃሳብ እንዲያቀርብ ታዞ ነበር። በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ሳይንሳዊ ቡድኑ ለአራት ቀናት ያህል በካይሮ ባደረገው ስብሰባ የኢትዮጵያን የግድብ ሙሌት እና የውሃ አለቃቀቅ እቅድ፤ ግብፅ እና ሱዳን ያቀረቡትን የሙሌትና እና የውሃ አለቃቀቅ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በማዳመጥ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከመስማማት ቢደረስም አንዳንድ ሃሳቦች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም። ኢትዮጵያ እና ሱዳን ማናቸውም ቴክኒካዊ ጉዳዮች ለሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ቀርበው ትንተና እንዲደረግባቸው የውይይት አካሄድ ቢከተሉም ግብፅ የሳይንስ ጥናት ቡድኑ ትንተናን አሻፈረኝ በማለት ያቀረብኳቸው ሃሳቦች በሙሉ ተቀባይነት ካላገኙ ውይይቱ ሊቀጥል አይችልም በማለቷ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ሥራውን በተሟላ አኳኋን ማከናወን ሳይችል እንደቀረ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው አትቷል። •በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ ግብፅ አሻፈረኝ ማለቷ አዲስ አካሄድ ሳይሆንም ከዚህ ቀደምም በግድቡ ላይ ሦስቱ አገራት ሊያከናውኑት የነበረውን የውሃ፣ የአካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ጥናት በግብጽ ወገን እንዲስተጓጎል በተደረገ ጊዜ የታየ የሳይንስ እና የምክክር የመፍትሔ አማራጭን የማፍረስ ዘዴ እንደሆነ ነው በማለት ኢትዮጵያ ትተቻለች። በሁለቱ ቀናት ውይይትም ቡድኑ የደረሰበትን ተመልክተው ቀጣዩ ሂደትን ለማስቀመጥ ጥረት ቢደረግም ከግብፅ በኩል በነበረው እምቢተኝነት የጥናት ቡድኑ በቀጣይ ስለሚሠራቸው ጉዳዮች መመሪያ ሳይተላለፍ እንደቀረ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመግለጫው አክሎ ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ የናይል ውሃን አስመልክቶ ለተደረጉት እና በኢትዮጵያ ላይ ምንም ዓይነት ተፈጻሚነት የሌላቸውን ስምምነቶች እውቅና እንደማይሰይጥም በመግለጫው ተካትቷል።
48104027
https://www.bbc.com/amharic/48104027
ተስፋዬ፣ ሌንጮና ገብሩ ስለ ዶ/ር ነጋሶ
የተወለዱት በምዕራብ ኦሮሚያ ደምቢዶሎ ከተማ ነው ። የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በያኔው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ከሠሩ ጥቂት ዓመታት በኋላ ወደ ጀርመን አቀኑ። ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የህይወት ዘመን ተሳትፎ አድርገዋል ሊባል ይችላል።
ለበርካታ ዓመታት ከኖሩባት ጀርመን ሲመለሱ የአሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድን ተቀላቀሉ። የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ህልፈት ባለፈው ቅዳሜ ነበር ለዓመታት ከኖሩበት ከወደ ጀርመን የተሰማው። ዶ/ር ነጋሶን አንዳንዶች በእጅጉ በመርህ እንደሚያምን ፖለቲካኛ ሌሎች ደግሞ ለፖለቲከኛ የሚሆን ስብእና የሌላቸው አድርገው ይስሏቸዋል። • አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጋዜጠኞች ተስፋ • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ዶ/ር ነጋሶ -የጋጤኛው ማስታወሻ "የታሰረ አንበሳ" ብዙዎች በአፃፃፍ ችሎታው በተደነቁበት የጋዜኛው ማስታወሻ መፅሃፉ ተስፋዬ ገብረአብ ዶ/ር ነጋሶን ቤተ መንግስት ውስጥ እንደታሰረ አንበሳ ገልጿቸዋል። ኋላ ግን ኢህአዴግን ተለይተው የተቃውሞ ፖለቲካውን በመቀላቀላቸው እሳቸውን የሚያይበት መንገድ መቀየሩን ተስፋዬ ይናገራል። የታሰረ አንበሳ ያላቸው ምንም እንኳ አቅም ቢኖራቸው ህወሃትን ያገለግሉ ስለነበር እንደሆነ "የጋዜጠኛው ማስታወሻ የታሰረው አንበሳና በኋላ በህዝብ ጉዳይ ላይ በሰፊው የተሳተፉት ዶ/ር ነጋሶ የተለያዩ ናቸው" በማለት ያስረዳል። ኋላ ላይም ዶ/ር ነጋሶና ተስፋዬ ይገናኙ እንደነበር ተስፋዬ ይናገራል። የሚገናኙት በኢሜልና በስልክ የነበረ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በአንድ ፎረም ላይ ዶ/ር ነጋሶ ሊያቀርቡት በነበረ ፅሁፍ ምክንያት እንደነበር ያስታውሳል። ዶ/ር ነጋሶ የማስታወቂያ ሚኒስትር ሳሉ በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት መምሪያ ሃላፊ ለነበረው የተስፋዬ አለቃው ነበሩ። እሱና ሌሎች ባልደረቦች ያናግሯቸው የነበረው እንደ ጓደኛ እንደነበር፣ ራሳቸውን ከፍ የማያደርጉ ፣ አክብሩኝም የማይሉ ሰው እንደነበሩ ይናገራል። "ሚኒስትር እያሉ ከመኪና ወርደው ሱቅ ላይ ሲጋራ ገዝተው የሚሄዱ ሰው ናቸው" ሲልም ያክላል። በጋዜጠኛው ማስታወሻ 'የታሰረ አንበሳ' ያላቸው እንደ እሳቸው ያለ ጥሩ የታሪክ ምሁር፣ ቅን እና ጥሩ ስብእና ያለው ሰው እንዴት ከዚያ "ሰው በላ" ስርዓት ጋር አብሮ ይሰራል በማለት እንደሆነም ይገልፃል። ህገመንግሥቱ መከበር አለበት የሚል አቋም እንደነበራቸው ይህ ብቻም ሳይሆን ሊከበር ይችላል ብለው ያስቡም እንደነበር የሚናገረው ተስፋዬ "ይህ ቅንነታቸውን ያሳያል ።ይህ ቅንነታቸው ደግሞ ከፖለቲካ ሰው የማይጠበቅ ነበር " ይላል። 'ኢህአዴጉ' ዶ/ር ነጋሶ እና 'ኦነጉ' ሌንጮ አቶ ሌንጮ ለታና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አንድ ላይ ነው። አብሮ አደጎች ነበሩ ማለት ይቻላል። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳሉ ብዙ አፍሪካ ሃገራት ከቅኝ ገዢዎቻቸው ነጻነታቸውን የተቀዳጁበት ወቅት ስለነበር የራስን መብት በራስ ስለመወሰን ብዙ ጊዜ ያወሩ እንደነበር አቶ ሌንጮ ያስታውሳሉ። አቶ ሌንጮ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ ሲያቀኑ ዶ/ር ነጋሶ ደግሞ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲን ተቀላቀሉ። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ዶ/ር ነጋሶ የተማሪዎች ንቅናቄ ተሳታፊ እንደነበሩ አቶ ሌንጮ ያስታውሳሉ። እኛ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ስንመሰርት እሱ ለትምህርት ጀርመን ነበር። በወቅቱ የታሪክ ትምህርት ለማጥናት ነበር የሄደው። "አንተ ውጪ ሃገር ሄደህ ታሪክ ተማር እኛ ታሪክ ሰርተን እንጠብቅሃለን ብዬው እንደነበር ከብዙ ጊዜ በኋላ አስታውሶኛል። እኔ ግን ረስቼው ነበር።"ይላሉ አቶ ሌንጮ። እንደ አቶ ሌንጮ አገላለፅ ዶ/ር ነጋሶ በጣም እልኀኛና በአንድ ጉዳይ ላይ አቋም ከያዙ ወደኋላ የማይሉም ናቸው። ምን ይደርስብኛል ብለውም አያስቡም።"ለዚህም ይመስለኛል ከኢህአዴግ ጋር የተለያየው።"ይላሉ። "ፕሬዝዳንት በነበረበት ወቅት ለስራ ወደ ውጪ ሃገራት ሲሄድ ብዙ ጊዜ ተገናኝተን እናወራ ነበር። ያው እኔ ኦነግ እሱ ደግሞ ኢህአዴግ። ነገር ግን በሃሳብ ብቻ ነበር እርስ በርሳችን የምንታገለው።" "በኢህአዴግ ክፍፍል የወሰደው አቋም ታሪካዊ ነው" በወቅቱ ትግል ላይ የነበረው ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ህወሃት ነጋሶን ጀርመን ሃገር ሳሉ እንዴት እንደቀረበና እንዳነጋገራቸው የቀድሞ የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የአረና ፓርቲ መስራች አቶ ገብሩ አስራት ያስታውሳሉ። • በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት • በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች ዶ/ር ነጋሶ ኦህዴድ ፤ አቶ ገብሩ ደግሞ ህወሃት ሆነው ብዙ ጊዜ በማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ይገናኙ ነበር። ሁለቱም ኢህአዴግን ለቅቀው በመውጣት እንደገና በተቃዋሚ መስመር ሰልፍ ላይም ተገናኝተዋል። እናም አቶ ገብሩ ዶ/ር ነጋሶን በእነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ አይተዋቸዋል። ዶ/ር ነጋሶ ከኢህአዴግ ከተለዩ በኋላ ደምቢደሎ ላይ ተወዳድረዋል የአንድነት ፓርቲ ሊቀ መንበር ሆነውም አገልግለው ነበር። "አቋም ያለው ቅን ሰው ነው። ብቻውንም ቢሆን ላመነበት ነገር እንደሚቆም ያረጋገጠ ሰው ነው" በማለት ይገልጿቸዋል አቶ ገብሩ ዶ/ር ነጋሶን። በተለይም በኢትዮጵያና በኤርትራ ጦርነት፣ ኢህአዴግ ውስጥ መከፋፈል ተፈጥሮ በነበረበት ወቅት የያዙትን አቋም ከዚያም ኢህአዴግ አምባገነን ሆኗል ብለው ድርጅቱን የለቀቁበትን ሁኔታ አቶ ገብሩ ያስታውሳሉ። በጥቅሉ "ላመነበት ነገር ቆሞ ያለፈ ሰው ነው" በማለት ነው የሚገልጿቸው። ኢህአዴግ ከባድ መከፋፈል ውስጥ በነበረበት በዚያ ወቅት ድርጅቱ አምባገነን እየሆነ አደገኛ መንገድ ላይ መሆኑን ብዙዎች ሊሞግቷቸው ይቅርና ሊያናግሯቸው በሚፈሯቸው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ፊት በግልፅ መናገር ዶ/ር ነጋሶን በፖለቲከኞች በህዝብ ዘንድም ከፍተኛ ነጥብ ያሰጠ እርምጃ ነበር። "እኔ እንኳን ስብሳባው ላይ አልነበርኩም ግን ጓደኛዬ አምባሳደር አዋሎም ነግሮኛል። መለስ መንግስቱ የጦር መኮንኖችን አሸንፎ የተናገረውን የሚመስል ነገር ሲናገር ልክ መንግስቱን መሰልከኝ ብሎ በድፍረት ተናግሮታል" ይላሉ። በርግጥም ይህ የዶ/ር ነጋሶ ህይወትና የፖለቲካ እርምጃ ላይ በተፃፈውና "ዳንዲ" በተሰኘው መፅሃፋቸው ላይ የሚገኝ ሲሆን በተባለው ስብሰባ ላይ ተገኝተው የነበሩት አምባሳደር ገነት ዘውዴ 'እንዴት መለስን ከመንግስቱ ጋር ታመሳስለዋለህ' ብለው ስለማልቀሳቸውም ተፅፏል። አቶ ገብሩ ያ ጊዜ አቶ መለስ ዜናዊ በዶ/ር ነጋሶ ላይ ቂም በመያዝ እስከ መጨረሻው ሊያጠቋቸው የወሰኑበት እንደሆነ ያምናሉ። ከዚያ በኋላ በዶ/ር ነጋሶ ላይ የሆነውም የዚህ ማረጋገጫ ነው ይላሉ። በተቃራኒው ዶ/ር ነጋሶ ብዙ በደል ባደረሱባቸው የኢህአዴግ ሰዎች ላይ ቂም እንዳልነበራቸው አቶ ገብሩ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ። አቶ ገብሩ ራሳቸውም ብዙ በደሎች ቢደርሱባቸውም ገለልተኛ ካልሆነ የፍትህ ስርዓት ፍትህ አገኛለው ብለው ባለማመን ወደ ህግ አልሄዱም። "እሱ ግን ፍርድ ቤት እየሄደ ይሟገት ነበር" በማለት እንደ ቀድሞ ፕሬዝዳንትነት የሚገባቸውን መብት በሚመለከት በሁለት ፍርድ ቤቶች አሸንፈው እንደነበር ይናገራሉ። "ነገሩ ኋላ የፖለቲካ ውሳኔ ነው የሆነው። የተፃፈለትን ደብዳቤ አሳይቶኝ ነበር አሁንም እጄ ላይ አለ" ይላሉ። ብዙዎች 'ዳንዲ፡ የነጋሶ መንገድን" ካነበቡ በኋላ የዶ/ር ነጋሶ ስብእና የፖለቲከኛ ዓይነት አይደለም የሚል አየስተያየት ሰንዝረው ነበር። አቶ ገብሩ በዚህ አስተያየት በተወሰነ መልኩ ይስማማሉ። ነገር ግን ለሳቸው ችግሩ የዶ/ር ነጋሶ ስብእና ሳይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ አካሄድ ብልጣብልጥነትና አድርባይነት መሆኑ ነው። "የመርህና የዓላማ ፖለቲካ የሚያራምድ ሰው በአገራችን ፖለቲካ ቦታ የለውም ይላሉ። እሱ ደግሞ ግልፅ፣ የዋህና ቀጥ ብሎ የሚሄድ ነው" ይላሉ። • 360 ብር ለአንድ ሕጻን "ዶ/ር ነጋሶ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተንኮል መጠን መሳያ" የ 'ዳንዲ' ፀሃፊ አቶ ዳንኤል ተረፈ ለመፅሃፉ ከዶ/ር ነጋሶ ጋር ለሶስት ወራት ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቁሳዊ ነገር ላይ ብዙ ጉጉት የላቸውም የሚላቸው ዶ/ር ነጋሶ የኢትዮጵያ የተንኮልና የሴራ ፖለቲካ ልክ ማሳያ ናቸው ሲልም ይደመድማል። ኑሯቸው እንደ ቀድሞ ፕሬዘዳንት ሳይሆን እንደ ተራ ግለሰብ እንደነበር የአደባባይ ምስጢር ነው። ህልፈታቸውን ተከትሎ ብዙዎች እንዴት በተለያየ አጋጣሚ እንዳገኟቸው ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ ፅፈዋል። አንድ ሰው ታክሲ ላይ እንዳገኛቸውና መኪናቸው ጋራጅ ገብቶ እንደሆነ ጠይቋቸው እሳቸውም መኪና የለኝም ብለው በቀጥታ እንደመለሱለትና እሱም ምን ያህል እንደሚያከብራቸው እንደገለፀላቸው በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል። አቶ ዳንኤል እንደሚለው ደግሞ ላመኑበት ነገር እንደ ተራ ሰው ከመኖር በላይ ሁሉ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነበሩ ይላል። ይኖሩ ከነበረበት የሚያፈስ ቤት እንዲለቁ ደብዳቤ ተፅፎላቸው እንደነበር በማስታወስ " የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጎዳና ተዳዳሪ ሊሆኑ ነው የሚል ፅሁፍ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ሲወጣ ነው መልሰው ነገሩን የተውት" ይላል። እሱ እንደሚለው ውሳኔአቸው የሚያስከፍላቸውን ዋጋ ሁሉ ለመክፈል የስነ ልቦና ዝግጅት ነበራቸው ዶ/ር ነጋሶ። እንደ አቶ ገብሩ ሁሉ ገዳይ ጀግና በሚባልበት ፣ ተንኮለኛና ሴረኛ አሸናፊ ሆኖ በሚወጣበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የዶ/ር ነጋሶ እንደ ገራገር መታየታቸው የሚገርም አይደለም ይላል ዳንኤል። በኢህአዴግ ሂስህን አውርደህ መቀጠል ፣ ተራ አባል ሆኖ መቀጠል ፣ መሄድ የሚሉ ሶስት ምርጫዎች ሲቀርቡላቸው በመህር ላይ ቆመው ከድርጅቱ ለመልቀቅ የወሰኑ ፖለቲካኛ መሆናቸውን የሚናገረው ዳንኤል "ጥንቁቅ ፖለቲካኛና የሚያምኑበትን ለማድረግ ወደ ኋላ የማይሉ ናችው" ይላል። የዶ/ር ነጋሶ ሁለተኛ መፅሃፍ በመጠናቀቅ ላይ እንደነበር ዳንኤል ይናገራል። ስነዳ ላይ እጅግ ጎበዝ ናቸው የሚላቸው ዶ/ር ነጋሶ ለቤተ መፃሀፍት የሚሆኑ መፅሃፍት፣ ጋዜጦችና በርካታ ፅሁፎች እንዳሏቸውም ይናገራል። "ኢህአፓ የበተነው ወረቀት፣ መኢሶን የፃፈው ፅሁፍና አንድ ጊዜ ብቻ የታትማ የቀረች መፅሄት እንዲሁም የአሁኑ መፅሄትና ጋዜጦች እያንዳንዱ እትም የሚገኘው ዶ/ር ነጋሶ ቤት ነው" ይላል።
50245030
https://www.bbc.com/amharic/50245030
በመካከለኛው ምስራቅ አዲስ የአረብ አብዮት ሊቀሰቀስ ይሆን?
የመካከለኛው ምስራቅ ወደ አዲስ የአረብ አብዮት እየተሸጋገረ ይመስላል።
በመካከለኛው ምስራቅ፣ ኢራቅን ጨምሮ፣ መንግሥትን የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው በኢራቅ የተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ሞተዋል፣ በሊባኖስ የተቃውሞ ድምጻቸውን የሚያሰሙ ሰዎች ሀገሪቷን ቀጥ አድርገዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ሳድ አል ሃሪሪ እንዲወርዱ ሲጠይቁ ተደምጠዋል። ባለፉት ሳምንታት ደግሞ የግብፅ ደህንነት ኃይል በፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ላይ የተቃውሞ ድምጻቸውን ያሰሙ ሰልፈኞችን በትኗል። • ኢትዮጵያና ግብፅ በአሜሪካ ለውይይት እንጂ ለድርድር አይገናኙም ተባለ ኢራቅ፣ ሊባኖስ እና ግብፅ በርካታ ልዩነት ቢኖራቸውም የተቃዋሚዎች የቁጣ ምክንያት ተመሰሳይ ነው። ይህ ቁጣ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ አረብ ሀገራት ያሉ ሚሊየኖች፣ በተለይ ደግሞ በወጣቶች ዘንድ ከፍ ያለ የቁጣ ስሜት ነው። በዚህ ቀጠና ባሉ ሀገራት ካሉ ህዝቦች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች እንደሆነ ይገመታል። ወጣቶች ለአንድ ሀገር ወሳኝ ኃይሎች ናቸው። ይህ ግን የሚሆነው ምጣኔ ኃብቱ፣ የትምህርት ስርዓቱ እና የሀገሪቱ የተለያዩ ተቋማት የወጣቶቹን ፍላጎት ለማስጠበቅ በአግባቡ ሲሰሩ ነው። በእነዚህ የአረብ ሀገራት ግን ይህ እየሆነ አይመስልም። በሊባኖስ፣ ኢራቅ እና በቀጠናው ባሉ ሌሎች ሀገራት ወጣቱ ስራ አጥ በመሆኑ ስር የሰደደውን ሙስና ሲመለከት በቀላሉ ይቆጣል። ሙስና በእነዚህ ሀገራት ከተነሱ ቁጣዎች ሁለቱ ሙስናና ስራአጥነት የቀሰቀሳቸው ናቸው። እንደ ዓለም ዓቀፉ ሙስናን አመላካች ተቋም ከሆነ በዓለማችን ሙሰኛ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት የምትገኘው ኢራቅ ናት። ሊባኖስ ከኢራቅ የምትሻለው በትንሹ ነው። የቢቢሲ መካከለኛው ምስራቅ ኤዲተር ሙስና የተጠቂዎቹን ተስፋና ምኞችት እምሽክ አድርጎ የሚበላ ካንሰር ነው ይላል። • "በመንግሥት መዋቅር ሥር ሆነውም ግጭቶችን የሚያባብሱ እንዳሉ እናውቃለን" ኢዜማ እሱ እንደሚያስቀምጠው በሙስና በተዘፈቀ ስርዓት ውስጥ ያሉ እና የሚከስሩ ግለሰቦች፣ ተምረው ስራ ሲያጡና ወደ ኪሳቸውም ወደ አፋቸውም የሚያደርሱት ቁራሽና ሰባራ ሳንቲም ሲያጡ በጣም በፍጥነት ይቆጣሉ። በተለይ ደግሞ የመንግሥት መዋቅሩ፣ የሕግ አስከባሪና የጸጥታ አካላት በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ሲገኙ የስርዓቱ መውደቅ ማሳያዎች ናቸው። በሊባኖስም ሆነ በኢራቅ ሰልፈኞች መንግሥት ስልጣኑን እንዲለቅ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የመንግሥት መዋቅሩ እንዲለወጥና በሌላ እንዲተካ ይፈልጋሉ። ሠልፈኞች ላይ መተኮስ በኢራቅ ሰልፈኞቹ ስራ አጥነትና ሙስናን እያነሱ መንግሥት ላይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የጸጥታ አካላት ጥይት በመተኮስ በትነዋቸዋል። በኢራቅ በአሁኑ ሰዓት ያለው ሰልፍ መሪ አልባ ይመስላል። ነገር ግን መንግሥት ሰልፉ በተጠናከረ ቁጥር የራሱን መሪ ይወልዳል የሚል ስጋት አለው። • የአይ ኤስ መሪ አቡ ባካር አል ባግዳዲ ማነው? ሠልፈኞቹ በባግዳድ ታዋቂ ሰዎች፣ ባለስልጣናት፣ ኢምባሲዎች የሚኖሩበትንና ትልልቅ የመንግሥት ቢሮዎች የሚገኙበትን አካባቢ ለተቃውሟቸው ማዕከል አድርገዋል። በባግዳድ የተጀመረውን ሰልፍን ተከትሎ ወዲያውኑ ማታ ቅዱስ ከተማችን ወደ ሚሏት ካራባላ ተዛምቷል። የተቃውሞ ሰልፉ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ ከጸጥታ አካላት በሚተኮሱ ጥይቶች የሚሞቱና የሚቆስሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። እስካሁን ድረስ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ ባይነገርም የሞቱ እንዳሉ ግን ማወቅ ተችሏል። ከኢራቅ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት አንዳንድ ወታደሮች የኢራቅን ሰንደቅ ዓላማ ትከሻቸው ላይ ለብሰው ታይተዋል። ይህም በወታደሩ ዘንድ ሰልፈኞቹን የመደገፍ አዝማሚያ መኖሩን ያሳያል ይላል የቢቢሲ የመካከለኛው መስራቅ ከፍተኛ አዘጋጅ። ያልተጠናቀቀ የቤት ሥራ በሊባኖስ የተቃውሞ ሰልፉ የተጀመረው በወርሃ ጥቅምት አጋማሽ ላይ መንግሥት ትምቧሆ፣ የዋትስ አፕ ጥሪዎችና ነዳጅ ላይ ታክስ ለመጨመር ማሰቡን ሲናገር ነበር። መጀመሪያ ሰልፉ በሰላም እየተካሄደ የነበረ ቢሆንም በኋላ ግን ግጭቶች መከሰት ጀመሩ። እኤአ በ2011 የተጀመረው የአረብ አብዮት ያላለቀ የቤት ሥራ ይሆን? ሲል የሚጠይቀው የቢቢሲ የመካከለኛው መስራቅ ከፍተኛ አዘጋጅ፣ በ2011 የተካሄደው የአረብ አብዮት የሚፈለገውን ነፃነት አላመጣም ይላል። ዜጎች አንደሚፈልጉት ከጨቋኝ መንግሥታቶቻቸው አልተላቀቁም ሲልም ሀሳቡን ያጠናክራል። • አሳሳቢው የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር በኢትዮጵያ ይሁን እንጂ በእነዚህ ሀገራት አሁንም የአብዮቱ ትኩሳት ይሰማል። ሶሪያ፣ የመን እንዲሁም ሊቢያ በጦርነት ይታመሳሉ። ግብጽ ውስጥ ጠንካራ የደህንነት ቁጥጥር ይታያል። አሁንም ግን የ2011 አብዮት የቀሰቀሰው ብሶት በአንዳንድ ሀገራት እንደውም በባሰ ሁኔታ ባለበት አለ። በሙስና የተበላሸ የመንግሥት አስተዳደር ከፍተኛ ስራ አጥ ባለባቸው ሀገራት ለሚገኙ ወጣቶች የስራ እድል የመፍጠር አቅሙ በመዳከሙ ወጣቶቹን እንደ እሳት ከሚንቀለቀለው ቁጣቸው እና ከሚያሰሙት ተቃውሞ ሊያቆማቸው አልተቻለውም።
news-56471330
https://www.bbc.com/amharic/news-56471330
ብሔራዊ ቡድኑን ወደ የአፍሪካ መድረክ ለመመለስ የሚመኘው ሽመልስ በቀለ
ትውልድ እና እድገቱ አዋሳ ከተማ ኮረም ሰፈር ነው።
እንደ አብዛኛው የኢትዮጵያ ልጆች ኳስ እና ሽመልስ በቀለን ያስተዋዋቃቸው ትምህርት ቤት ነው። በእረፍት ጊዜ ባለችው ትንሽ ክፍተት ኳስን መጫወት የጀመረው ሽመልስ ወደ ሰፈሩ ሲመለስም ከሰፈር ጓደኞቹ ጋር ከማታ ጥናት በፊት ያለችውን የ አንድ ሰዓት ክፍተት ኳስ በመጫወት ያሳልፋ ነበር። ዛሬ ላይ በግብጽ ፕሪሚየር ሊግ ተወዳዳሪ ለሆነው ሚሰረ ሌል ማካሳ እየተጫወተ ይገኛል። ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለማለፍ ከማደጋስካር አቻዋ ለምታደርገው ጨዋታ ቁልፍ ሚና ከሚኖራቸው መካከል አንዱ የሆነው እግር ኳሰኛው ሽመልስ በቀለ ስለ 'ፕሮፌሽናል' የእግር ኳስ ሕይወቱ ለቢቢሲ የሚከተለውን አጋርቷል። በግብፅ ሊግ የመጫወት እድል ግብፅ ሄጄ የመጫወት እድል የተፈጠረልኝ፤ በቅድሚያ ሊቢያ እና ሱዳን ሄጄ የነበረኝ አጭር ቆይታ ብሎም በኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩኝ እንቅስቃሴዎች ናቸው። በሱዳን ለስድስት ወር ያክል ተጫውቼ ነበር። ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ለ ሁለት ወር ያክል ዝግጅት ላይ እያለሁ አሁን ያለው ወኪሌ ቪዲዮዎችን እንድልክለት ይጠይቀኝ ነበር። እኔም በውጪ የነበረኝን እና በአገር ውስጥ የነበሩኝን ቆይታ የሚያሳዩ ምስሎች ላኩለት። በተጨማሪም አጭር ግዜ ቢሆንም ወጥቼ የመጫወት ሪከርድ ስላለኝ አሱ ያገዘኝ ይመስለኛል። ፔትሮጅክት የሚባል ክለብ ቪዲዮዎቹን ተመልክቶ ነበር። አሰልጣኞቹ ደስተኛ ነበሩ። በተለይ ምክትል አሰልጣኙ የበለጠ በእኔ ደስተኛ ነበር። ከቪዲዮ በተሸለ በአካል መጥተው ለማየት ተነጋገሩ እኔም ደስተኛ ነበርኩ። አዲስ አበባ ላይ ከአልጄሪያ ጋር በነበረን ጨዋታ መጥተው ተመለከቱኝ፤ ምንም እንኳን ሁለት ለአንድ ብንሸነፍም በእንቅስቃሴዬ ደስተኛ ስለነበሩ ለክለቡ ለመፈረም እድሉን አገኘሁ ማለት ነው። በፕሮፌሽናል የኳስ ህይወትህ ወርቃማ የምትለው ጊዜ የቱ ነው? በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቴ ወርቃማ ብዬ የማስበው ከሁለት አመታት በፊት ፔትሮጄት የነበርኩበት ነው። ይህም በእግር ኳስ ህይወቴ አምበል ሆኜ ቡድን መርቼ አላውቅም ነበር። በወቅቱ አምበል ሁኜ ነበር። ይህ ከአገር ወጥቼ ለመጀመሪያ ክለቤ ፔትሮጄት መሪ መሆኔ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። የብሔራዊ ቡድኑን አቋም እንዴት አገኘኸው? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አቋም ከዓመት ዓመት ልዩነት አለው። እኔ በሄድኩበት ግዜ በተለይ በመጨረሻው ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ 18 ጠንካራ ክለቦች ነበሩ። በዚህ ዓመት እንደሚታወቀው 13 ክለቦች ነው ያሉት። ይሄ በራሱ በብሔራዊ ቡድኑ አቋም ላይ የራሱ ጫና አለው። ነገር ግን አሁን ላይ ሊጋችን በቀጥታ ለዓለም መታየቱ [በዲኤስቲቪ አማካኝነት] ደግሞ የራሱ የሆነ በጎ ነገር ያመጣል ብዬ አስባለሁ። እግር ኳስና የኮሮናቫይረስ እንዴት እየሄዱ ነው? ኮሮናቫይረስ ከመጣ በኋላ ፊፋ ባወጣው ሕግ መሰረት ሁል ጊዜ ጨዋታ ሲኖረን ከሁለት ቀን በፊት ምርመራ እናደርጋለን። ኮሮናቫይረስ ያለበት ሰው አይጫወትም። ይሄ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ነው። ለአፍሪካ ዋንጫ እየተዘጋጃችሁ ነው። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋንጫ ካለፈች ዘጠኝ ዓመት አለፈ። አሁን ያለው ቡድን የሚያልፍ ይመስልሃል? አዎ ለአፍሪካ ዋንጫ እናልፋለን ብዬ አምናለሁ። ባፈው ሳምንት ከማላዊ ጋር ያካሄድነው የወዳጅነት ጨዋታ በብቃት ነው የተወጣነው። ጎበዝ ተጫዋቾች ከተለያዩ ክለቦች ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ተጠርተዋል። ሁሉም ተጫዋች ጥሩ አቋም ላይ ነው ያለው። ያለፈውን ሳምንት ጨዋታ በብቃት እንደጨረስነው ሁሉ ከማዳጋስካር ጋር የምናደርገውን ጨዋታም በድል እንወጣዋለን። ለዚህም ምክንያቱ አሪፍ ተጫዋቾች እና አሪፍ አሰልጣኞች ስላሉን ነው። ስለዚህ እነዚህን በድል ከቋጨን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማናልፍበት ምን ምክንያት አለ? እአአ 2013 ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከናይጄሪያ አቻው ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም በነበረው ጨዋታ ወቅት የናይጄሪያው ግብ ጠባቂ ቪንሰንት ኢኒያም እና ሽመልስ በቀለ ያኔ አንተ የነበርክበት ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ በአገሪቱ የነበረው ስሜት እንዴት ታስታውሰዋለህ? ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ምንም የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፎ አላደረግንም። ይሄ በጣም ረጅም ጊዜ ነው። አሁን ግን ወደ 10ኛ ዓመት ከመግባታችን በፊት እኛ ቡድኑን አሳልፈን ያኔ እኛ የነበረንን ስሜት ድጋሚ ለሁለተኛ እንዲሰማን እፈልጋለሁ። የዚያን ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ካለፈው ቡድን ውስጥ አሁን ያለነው ሦስት ተጫዋቾች ብቻ ነን። እኛ ያለፍንበትን ስሜት አሁን ያሉት አዳዲስ ልጆች እንዲሰማቸው እንፈልጋለን። እሱ ጊዜ ሲነሳ በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ተፈጥሮ ያለፈው ከፍተኛ መነቃቃት እና ደስታ ይታወሰኛል። ያ ስሜት እንዲደገም እፈልጋለሁ። ሕዝቡ ጋር የነበረው ስሜት ከባድ ነበር። ብዙ ነገሩን ትቶ ያኔ ኳስ ለመመለከት እና ለአገሩም የነበረው ትልቅ ስሜት ያንጸባርቅ ነበር። ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋችን የፈጠረው ደስታ በጣም ትልቅ ነበር። አገራችን አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ያ ስሜት እንደገና እንዲመጣ እንፈልጋለን። ከእግዚአብሔር ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ የምናልፍ ከሆነ ሁሉንም ነገር የምናስረሳበት ጊዜ ይመጣል ብዬ አስባለሁ። በፖለቲካ ምክንያት ሁሉም ቦታ ጭንቀት ነው የሚሰማው፤ ምንም ሰላም የለም። ሕዝቡ ሰላሙን እንዲያገኝ እና ያኔ የነበረው የደስታ ስሜት እንዲመጣ እፈልጋለሁ። በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አዲስ እየመጡ ካሉ ጎበዝ ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ አቡበከር ናስር ተደጋግሞ ስሙ ይነሳል። ከእሱ ጋር ተጣምሮ መጫወትን እንዴት አገኘኸው? አቡበከር ናስር እና እኔ አሁን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ አብረን የመጫወት እድል አግኝተናል። በእኔ አይን ባጭሩ ምርጡ ተጫዋች ነው። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም። ጎበዝ ተጫዋች ነው። ልጁ ገና 21 ዓመቱ ነው፤ ትልቅ ደረጃ መድረስ የሚችል ነው። ከዚህ በኋላ ራሱን አጠንክሮ እና ታግሶ የሚሰራ ከሆነ የሚያሳየው ብቃት ተስፋ ያሳድራል። ራሱን ወደ ላይ ሳያደርግ የሚጫወት ልጅ ነው። እያደርም እኔ ካለሁበት ደረጃ የበለጠ ትልቅ ቦታ ላይ መድረስ የሚችል ልጅ ነው። የኳስ ተንታኞች የኢትዮጵያ ተጫዋቾች እድል አጥተው እንጂ የቴክኒክ ብቃት አላቸው ይላሉ። አንተ ከአገር ወጥተህ ስትጫወት ምን ታዘብክ? አዎ በቴክኒክ በኩል ጥሩ ተጫዋቾች አሉን ከኳስ ጋር የተያያዙ ብዙ እድሎች ግን የሉም። ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ብዙ ተሰጥኦ ያላቸው አግር ኳስ የሚችሉ ምርጥ ልጆች አሉ። ያሰልጣኝ ችግር፣ የቁሳቁስ ችግር እና የመሳሰሉት ነው ጎልተው እንዳይወጡ ያደረጋቸው። እነዚህ እድል ቢሰጣቸው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በጣም ስኬታማ መሆን እና ወደ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ መምጣት ይችላሉ። ሰባት ዓመት በግብጽ ስትኖር ሕዝቡን እንዴት አገኘኸው? ብዙ ግብጻዊያን ጓደኞች አሉኝ። ከክለብ አጋሮቼ ባሻገርም በምኖርበትም አከባቢ ግብጻዊያን ጓደኞች አሉኝ። በደንብ እንነጋገራለን ጥሩ ጓደኝነት አለን። በኳስ ህይወቴ ላይም ምንም ያደረሰብኝ ጫናም የለም። ፖለቲካዊ ጉዳዮችን አንስተን ብዙም ተነጋግረን አናውቅም፤ ያው ግን ሁሉም ለአገሩ አይደለ፤ በተረፈ ግን አሪፍ ባህሪ አላቸው። እአአ 2013 በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቡርኪና ፋሶ አቻው ጋር በተገናኘበት ወቅት። በታዳጊነት እድሜህ ላይ ብትሆን እና አሁን ባለው እውቀትህ ላይ ሆነህ የእግር ኳስ አካዳሚ ብትገባ የትኛው ክህሎትህን ታሻሽል ነበር? ያለኝን የኳስ ክህሎት ላይ በደንብ ብሰራ ደስ ይለኛል። ነገር ግን ዋናው የአካል ብቃት ጥንካሬ ላይ በጣም አተኩሬ የምሰራ ይመስለኛል። ምክኒያቱም አንድ ሰው ምንም ያህል የቴክኒክ ብቃት ቢኖረው ጥንካሬው ዝቅተኛ ከሆነ መቋቋም ይከብዳል። ምን አልባት ተመልሼ በልጅነት አካዳሚ ብገባ የአካል ጥንካሬዬ ላይ በጣም የምሰራ ይመስለኛል። ብዙ ግዜ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ከአገር ሲወጡ ሳይሳካላቸው በቶሎ ይመለሳሉ። ምክንያቱ ምድነው? የሥነ ልቦና ጉዳይ በእግር ኳስ ህይወት ላይ ከባድ ችግር ነው። ሌላው ከአገር ቤት ይዘን የምንሄደው ብቃትን እዚያ ሄደን ከፍ ማድረግ ያስፈለጋል። እንደዛ ካልሆነ ብቃት ይወርዳል፤ ያኔ ተፈላጊነት ይቀንሳል። ብዙ ትንንሽ የሚመስሉ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥሩ ፈተናዎች አሉ። ለምሳሌ ተጫዋች ቤቱ ነው መመገብ ያለበት። እኔ ደግሞ ማብሰል አልችልም ነበር። ከፍተኛ ፈተና ሆኖብኝ ነበር። አገርም ይናፍቃል። እና እመለሳለሁ እያለ የሚጫወት ሰው ደግሞ ወዲያው ተመልሷል። ለሥራ እስከወጣን ድረስ ዋናው የሥነ ልቦና መጠንከር እና ትዕግስተኛ መሆን ለስኬት ቁልፍ ነው። በጣም ብዙ ችግሮች አሉ እነዚያን መቋቋም እና ዲሲፕሊንም ይጠይቃል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በቴሌቪዝን መታየቱ የሚጨምረው ፋይዳ አለ? አሁን ያለው ፕሪሚያር ሊግ በቀጥታ በቴሊቪዥን መቅረቡ ከፍተኛ የመታየት እድል መፍጠሩ አይቀርም። ቅድም እንዳልኩት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ የኳስ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች አሉ። ክለቦች ተጫዋቾቻው ወጥተው እንዲጫወቱ ማበረታታት አለባችው። ክለብ ብቻ ሳይሆን ፌዴሬሽኑ የራሱ ኃላፊነት አለበት። ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ ትልቅ ነገር መስራት ይጠበቅበታል። ለምሳሌ ሌሎች አገራት ለተጫዋቾቻቸው ነፃ ቪዛ ስለሚያመቻቹ ሄደው ይሞክራሉ። ብዙ ግንኙነት ማድረግ እና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር መነጋገር አለበት። ባለሞያዎች እንደሚሉት አንድ ቡድን ከተገነባ ከ 4 እስከ 10 ዓመት ዋና ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይቀያየሩ በተመሳሳይ ብቃት መቀጠል ይችላል ይላሉ። ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈው ቡድን ወዲያውኑ ለምን ደከመ? ወይስ ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፋችሁት በአጋጣሚ ነበር? ጠንካራ ክለብ ያለመኖሩ ነው ብሔራዊ ቡድኑን ያደከመው። ቡና እና ጊዮርጊስን ጨምሮ ብዙ ጠንካራ የክልል ክለቦች ነበሩ። አሪፍ ብሔራዊ ቡድን የተሰራው በዕድል ሳይሆን በጥንካሬ ነው። ተጫዋቾችም በትንሽ ነገር እንሸወዳለን። ትንሽ ድል ያታልለናል። በዚያ ውስጥ እንጠፋለን። ተጫዋቾች ትንሽ ድል ስናገኝ ብዙ ነገር የሰራን ይመስለናል። የዓለም ዋንጫን ደጋግመው የወሰዱት እንደ ጀርመን እና ብራዚል እንኳን በዚያው ነው ጠንክረው የሚቀጥሉት።
news-48716650
https://www.bbc.com/amharic/news-48716650
ለብቻ ልጆችን ማሳደግ፡ የኢትዮጵያውያን ላጤ እናቶች ምርጫና ተግዳሮት
ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ ላጤ እናት (Single Mother) ይሆናሉ። ከአጋራቸው ጋር በሞት አሊያም በፍቺ ሲለያዩ፣ በተፈፀመባቸው ጥቃት ሳቢያ የልጅ እናት ለመሆን ሲገደዱ፤ እንዲሁም የጀመሩት ግንኙነት እንዳሰቡት አልሰምር ሲላቸው ልጃቸውን (ልጆቻቸውን) ብቻቸውን የማሳደግ ውሳኔ ላይ ከሚደርሱባቸው ምክንያቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
ነገር ግን ፈልገውና አቅደው፤ ልጅ ብቻ እንዲኖራቸው በማለም ላጤ እናት (Single Mother) የሚሆኑ ሴቶችም አሉ። • ያለ እናት የመጀመሪያው የእናቶች ቀን • እናት አልባዎቹ መንደሮች በተለያዩ አገራት የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በተለያየ ምክንያት ልጃቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። በአፍሪካ በተለይ በኬንያና በደቡብ አፍሪካ ላጤ እናት የመሆኑ ልማድ እንግዳ አይደለም። ምንም እንኳን የተሰሩ ጥናቶች ባለመኖራቸው ቁጥራቸውና የጉዳዩ ስፋት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም በኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች አካባቢ ላጤ እናትነት አንዱ የሕይወት ዘይቤ መሆኑ ይነገራል። ሴቶች አስበውና አቅደው ለምን ላጤ እናት ይሆናሉ? "በሕይወቴ ያሰመርኩት ቀይ መስመር ነበር፤ እርሱን ማለፍ ስለማልችል ላጤ እናት ሆኛለሁ" የምትለው የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። ስሟን ያልጠቀስናት የይህች እናት ለትዳር ግን ክብር እንዳላት አልሸሸገችም። በሕይወቷ የምታስበውና የምታልመው ስላልሆነ የግድ በትዳር መታሰር የለብኝም የሚል አቋም ላይ እንደደረሰች ትናገራለች። ይሁን እንጂ ላጤ እናት መሆን በርካታ ተግዳሮቶች እንዳሉበት ታነሳለች። እያንዳንዷ ሴት በሰውነቷ ላይ እንዲሁም በምትመሰርተው ቤተሰብ ላይ ውሳኔዎችን ትወስናለች፤ ውሳኔዋም እንደምትኖረው ሕይወት የተለያየ ነው የሚሆነው" የምትለው ደግሞ የሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል ሰለሞን ናት። ይሁን እንጂ ሴቶች ፈልገውና አቅደው ላጤ እናት የሚሆኑባቸውን ምክንያቶችንም ትጠቅሳለች። በማህበረሰቡ የሴት ልጅ ሕይወት በጊዜ የተገደበ እንደሆነና እስከተወሰነ ዕድሜያቸው ድረስ ማግባትና መውለድ ካልቻሉ ሕይወታቸው እንደተመሳቀለ ተደርጎ መወሰዱ ለእንዲህ ዓይነት ውሳኔ ከሚገፏቸው ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ትናገራለች ። አክሊል እንደምትለው በቀደመው ጊዜ አንዲት ሴት ሳታገባ ብትወልድ ለልጁ 'ዲቃላ' የሚል ስያሜ በመስጠት እናትየዋ ትወገዝ ነበር። አሁን ላይ ግን ይህ ልማድ በትንሹም ቢሆን እየቀረ በመሆኑ ሴቶች እንዲህ ዓይነት ውሳኔ እንዲያሳልፉ አደፋፍሯቸዋል። "ከዚህ ቀደም ሴቶች ሥራ በማይሰሩበትና የኢኮኖሚ ጥገኛ በሆኑበት ጊዜ ልጅ ወልደው ለብቻቸው ማሳደግ የማይታሰብ ነበር" የምትለው አክሊል የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም ማደግም ሌላኛው የላጤ እናትነት ምክንያት ነው ትላለች። እንደ የመብት ተሟጋቿ ከሆነ አንዲት ሴት በሕይወት ያየችው የትዳር ሕይወት እኩልነት የሌለበት፣ ሴቷ ጥገኛ የሆነችበት፣ ጥቃት የሚፈፀምበት፣ የኃይል ሚዛኑ እኩል ያልሆነበት፣ ሁኔታዎች በሙሉ ለሴት የማይመቹ ከነበሩ፤ ይህን ባለመፈለግ ላጤ እናት ልትሆን ትችላለች። ቢሆንም ግን እኩልነትን እያዩ ያደጉትም ሌሎች ምክንያቶች ወደ ውሳኔው ሊያንደረድሯቸው ይችላል። በተለያየ መልኩ የሴቶች አቅም እየጎለበተ ቢመጣም ሴቶች አቅማቸውንና የትዳር ሕይወታቸውን ማጣጣም ተስኗቸዋል የሚሉ እንዳሉ ያነሳንላት አክሊል "የሴቶች አቅም እየጎለበተ በመጣ ቁጥር ኃላፊነት እየተደራረበባቸው ነው የመጣው፤ የቤቱን ሳንቀንስ ነው የውጪውን የጨመርንባቸው" ስትል ትሞግታለች። ማጣጣም ተስኗቸዋል፤ አልተሳናቸውም ለማለት መጀመሪያ ያለባቸው ጫና ሊቀርላቸው ይገባል ትላለች። በተጨማሪም ላጤ እናት መሆንም ይህንን ጫና አያስቀረውም ብላለች። • የልጃቸውን ደፋሪ የገደሉት እናት ነጻ ወጡ • ልጁን ጡት ያጠባው አባት በአሃ የሥነ ልቦና አገልግሎት አማካሪ የሆኑት አቶ ሞገስ ገ/ማሪያም በበኩላቸው "ይህ ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ የሚታይ ልማድ ሆኗል" ይላሉ። የምክር አገልግሎት ፈልገው ወደ እርሳቸው የሚመጡ ላጤ እናቶች መኖራቸውንም ይገልፃሉ። ባለሙያው እንደሚሉት ጉዳዩ ከሥልጣኔ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። የኢኮኖሚና በራስ የመተማመን አቅም ሲያድግ የባልና የሚስት ግንኙነት ወደ ጎን ተትቶ ግንኙነቱ ኢኮኖሚ ላይ ብቻ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል። በዚህም ምክንያት ሌሎች ማህበራዊ፣ አካላዊ፣ መንፈሳዊ እሴት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንደማያስፈልግ አሊያም እንደ ሁለተኛ ደረጃ ተወስዶ ሴቶች ላጤ እናትነትን በፍላጎት ይመርጣሉ። ለንግግራቸው "እኔ በኢኮኖሚ ጥሩ ደረጃ ስለደረስኩኝ፤ ከመጀመሪያውም ጀምሮ የወሰንኩት ሳላገባ ልጅ ለመውለድ ነው" ያለቻቸውን ደንበኛቸውን በምሳሌነት ያጣቅሳሉ። እንዲህ ዓይነት ሃሳቦች የባልን (የትዳር አጋርን) ሚናና ትርጉም ከማዛባት ጋር የተያያዘም ነው ይላሉ- አቶ ሞገስ። ባለሙያው እንደሚያስረዱት ላጤ እናትነትን ከኢኮኖሚ ጋር ብቻ ማያያዝ አይቻልም። ጉዳዩ ከራስ ስሜትና አስተሳሰብ ጋር እንዲሁም ካለፈ ታሪክ ጋር የሚያያዝም ነው። በመሆኑም ተፅዕኖውን ውስጣዊና ውጫዊ በማለት ይለዩታል። ውስጣዊ ተፅዕኖ ለአንድ ውሳኔ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የውስጥ ሁኔታ ነው ይላሉ- የሥነ ልቦና ባለሙያው አቶ ሞገስ። ይህ የውስጥ ሁኔታ የውጫዊ ተፅዕኖ ነፀብራቅም ይሆናል። ለምሳሌ የውስጥ ፍላጎት፣ አመለካከት፣ ቤተሰብ፣ ጎረቤት ወይም አካባባቢ የሚያሳድረው ተፅዕኖ የውስጥ ውሳኔ ላይ ያደርሳል። "ለራሳችን ያለን የጠነከረ አስተሳሰብና (Ego) ለራስ የምንሰጠው ግምት ከመጠን ያለፈ ሲሆን (Super Ego) ነገሮችን ሁሉ እኔ ማድረግ እችላለሁ፤ እኔ ማድረግ የምችል ከሆነ ሌላ አያስፈልገኝም የሚል ስሜት ይመጣል። በመሆኑም ይህንን ሚዛናዊ ማድረግ ካልተቻለ እዚህ ውሳኔ ላይ በቀላሉ ይደረሳል" ይላሉ። ውጫዊ ተፅዕኖ እንደ አቶ ሞገስ ከሆነ ፆታን መሠረት ያደረጉ የህብረተሰብ አመለካከትም ለላጤ እናትነት ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ የሚደርስባቸው ጫና፣ ሚዛናዊ ያልሆነ ሚና፣ የወንዶች የበላይነትን በመጥላትና በመፍራት፣ አካባቢያችን ያሉ ወይም በሚዲያ የምንሰማቸውና የምናያቸው አርአያዎች በሚፈጥሩት ተፅዕኖ ሴቶች እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ያደርጋቸዋል። በሌላ በኩል ማህበረሰቡ በጉዳዩ ላይ ያለው አቋም ጠንካራ ካልሆነ ሴቶች ውስጣቸው የሚጠይቃቸውን ለማድረግ ዕድሉን ያገኛሉ። የራስ ማንነት እያሸነፈ ሲመጣ፤ አይሆንም የምንላቸው ነገሮች እየበዙ ይመጣሉ። ፍላጎታችንን ማስቀደም ይቀናናል። ስለዚህም ላጤ እናትነት የማህበረሰቡ እሴት እንደተሸረሸረ አንዱ ማሳያ ሊሆን እንደሚችልም ያክላሉ። በላጤ እናቶች ላይ የሚደርስ ጫና ያነጋገርናት እናት እንደምትለው ልጆችን ለብቻ ማሳደግ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚና የሃሳብ ጫና አለው። ከማህበረሰቡ፣ ከቅርብ ቤተሰብ እንዲሁም ከልጆች የሚደርሰው ጫናም ቀላል አይደለም። "ልጆቸ ራስ ምታት እንኳን ሲያማቸው የማካፍለው ሰው አለመኖሩ በጣም ከባድ እንደሆነ ተመልክቸዋለሁ፤ ግን የራሴ መርህ ስላለና እርሱን መታገስና እንደ እናቶቻችን መቻል ስለማልችል ውሳኔውን ወስኛለሁ" ትላለች። ይህች እናት አዘውትረው ከሚጠቀሱት ጫናዎች በዘለለ የወሲብ ሕይወትን ማጣትም ላጤ እናትነትን ይፈትናል ትላለች። ምንም እንኳን እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ወሲባዊ ሕይወት ቢኖረውም እርሷ ግን ከሕይወት አጋር ውጪ ወሲብ መፈፀም እንደማትፈልግ ትናገራለች። የመብት ተሟጋቿ አክሊል እንደምትለው ውሳኔው የሚያሳፍር ድርጊት ነው ተብሎ በሚቆጠርበት ማህበረሰብ ውስጥ በፍላጎት ላጤ እናት መሆን ማህበራዊ ጫናው ከፍተኛ ነው። እነዚህን እናቶች የሚያግዝ አሠራር ከሌለ በስተቀር ሁሉም ነገር በአንድ ሰው ትከሻ ላይ ብቻ ስለሚወድቅ ኃላፊነቱ ከባድ ይሆናል። በመሆኑም የኢኮኖሚ ጫናውም ቀላል አይሆንም፤ ይህንን ለማስተካከል ሥራ መስራትና ጊዜን ሥራ ላይ ማጥፋት ይጠይቃል። "የልጆች ኃላፊነት መደረብም ሁኔታውን ከባድ ያደርገዋል" የምትለው አክሊል በዚህ ሂደት ውስጥ እናትየዋ ለእረፍት ማጣት ስለምትጋለጥ በተለያየ መልኩ ልትጎዳ እንደምትችል ታስረዳለች። ይህንን የተመለከቱ ጥናቶች በአፍሪካ ብዙም የሉም የሚሉት የሥነ ልቦና ባለሙያው ጉዳቱ ከፍ ያለ ነው ይላሉ። ጫናው ከአካላዊ፣ ማህበራዊ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት (wellbeing) ይጀምራል። በመሆኑም ላጤ እናቶች ካገቡት ይልቅ ለተለያዩ ቀውሶች ሊዳረጉ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል፡ • ኢኮኖሚያዊ ጫና ይበረታባቸዋል • አካላዊ ጤንነታቸው፤ ከጭንቀትን መቋቋምና ከበሽታ መከላከል አንፃር ይዳከማል • የስሜት ጥንካሬና መረጋጋት አይኖራቸውም • ማህበራዊና መንፈሳዊ ድጋፋቸውም የላላ ይሆናል ከሥነ ልቦና አንፃር ብቸኝነት፣ ድባቴ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ዋጋ የለኝም ማለት፣ በራስ መተማመን ማጣትና ለማንነት ችግር እንደሚጋለጡም ባለሙያው በዝርዝር ያስረዳሉ። የልጆቹ አባቶችም ከሴቶቹ ባልተለየ መልኩ የችግሮቹ ተጋሪ ይሆናሉ። የስሜት ጫና፣ ድባቴ፣ ማህበራዊ ጫና ፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ምቾት ማጣት፣ የፀፀት ስሜት (ልጄን በሚገባው መልኩ ድጋፍና ክትትል እያደረኩለት አይደለም) የሚሉ ሥነ ልቦናዊ ስሜቶች ይታያሉ። • የሴቶችና ወንዶች የኢኮኖሚ እኩልነት እንዴት ይስፈን? ወንዶች፤ ልጆቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ከአጠገባቸው ማጣት ብቻም ሳይሆን በሥነ ልቦና አገልግሎት ውስጥ ገና ለገና እንፋታለን ብለው ሲያስቡ ሚዛናቸውን መሳትና ከፍ ወዳለ የሥነ ልቦና ቀውስ ውስጥ እንደሚገቡም ባለሙያው ያክላሉ። በልጆች ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራል? "በተለይ ልጆች እድሜያቸው ከፍ እያለ ሲሄድ ለብቻ ማስተዳደር ፈታኝ ነው" የምትለው ይህች እናት በቤት ውስጥ ኃላፊነትን በማከፋፈል በሕይወታቸው ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው በማድረግ ፈተናውን መቋቋም ችላለች። "ቤታችን ፓርላማ ይመስላል፤ ልጆቼ ተነጋግረው ወስነው እኔ ጋር የሚመጡት ለማፅደቅ ነው፤ በሁሉም ነገር ተሳታፊ ናቸው" ትላለች። ይህም እነርሱን እንደውም ይበልጥ ጠንካራ እንዳደረጋቸውና ሴት ብቻዋን ልጆች ማሳደግ ትችላለች፤ በማለት እርሷን እንደ አርአያ ማየት እንደጀመሩ ታስረዳለች። በተለይ ወንድ ልጇ በእርሷ መኩራት እንደሚሰማው ትናገራላች። የምታስማማበት ጉዳይ በትዳር ውስጥ ሆኖ ልጆችን በተገቢው መንገድ ማሳደግ መተኪያ እንደሌለው ነው፤ ነገር ግን ትዳር ለመያዝ ተብሎ አሊያም ያልሆነ ትዳር ይዞ ሕይወትን መግፋት ደግሞ የማታምንበት ጉዳይ። የሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል ቤተሰብ የሚባለው ትርጓሜ ከድሮው በተሻለ ተቀይሯል ትላለች። በመሆኑም ልጆች የአባትና የእናትን ሚና ካለማግኘት በበለጠ ማህበረሰቡ የሚያደርስባቸው ጉዳት ያይላል ትላለች። በተቃራኒው አቶ ሞገስ ልጆች የአባታቸውንና የእናታቸውን ሚና እያዩ ባለማደጋቸው ለተለያዩ የሥነ ልቦና ችግሮች ይዳረጋሉ ይላሉ። በመሆኑም ክሊኒካል (ድብርትና ጭንቀት) እና ባህሪያዊ የሥነ ልቦና ችግሮች ይታዩባቸዋል ይላሉ። እንደ ባለሙያው ገለፃ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በብዛት ለእንዲህ ዓይነት የሥነ ልቦና ችግር የሚዳረጉ ሲሆን የሚያጋጥማቸውም 'ክሊኒካል' የሚባለው የሥነ ልቦና ችግር ነው። ወንዶች ደግሞ ባህሪያዊ ችግር ያጋጥማቸዋል፤ ከሁኔታዎች ጋር ተስማምቶ መኖር ይቸግራቸዋል። ችግሮቹ እንደ እናቶቹ ባህሪ የሚወሰን ቢሆንም በትምህርት፣ በሥራና በማህበራዊ ስኬቶቻቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድርባቸዋል ብለዋል። አቶ ሞገስ ላጤ እናቶች ሁለት ባህሪ አላቸው ይላሉ። አንደኛው ልጆቻቸው ሕይወት ውስጥ ጥሩ ድርሻ ያላቸው፣ ፍቅርና እንክብካቤ በጥሩ ሁኔታ የሚሰጡ (Involved) ሲሆኑ ሌላኛው ደግሞ ልጆቻቸውን ችላ የሚሉና በልጆቻቸው ሕይወት ውስጥ የማይገቡ (Rejecting) ናቸው። ይሁን እንጂ በሁለቱ የተለያየ ባህሪ የሚያድጉ ልጆች ለተለያዩ ሥነ ልቦና ችግሮች መዳረጋቸው አይቀርም። ጥሩ ድርሻ ያላቸው እናቶች እንክብካቤና ፍቅራቸው ከልክ ያለፈ ስለሚሆን ልጆች ለጥገኝነት መንፈስ ይጋለጣሉ። በሌላ በኩል ግድ የለሽ በሆኑት እናቶች የሚያድጉት ደግሞ ማግኘት ያለባቸውን የስሜት ደህንነት ስለማያገኙ ቀደም ብለው ለተጠቀሱት የሥነ ልቦና ችግሮች ይዳረጋሉ። ለምክር አገልግሎት ወደ እርሳቸው ቢሮ ጎራ ከሚሉት ላጤ እናቶች አብዛኞቹ ስሜታቸው ተመሳሳይ መሆኑንና ልጆቻቸው ላይም የድብርት ስሜት ማየት እንደቻሉም ባለሙያው አካፍለውናል። የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች እንዴት ይፍቱት? በተለያየ ምክንያት ልጆቻቸውን ብቻቸውን የሚያሳድጉ እናቶች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች እንዴት ሊቋቋሟቸው እንደሚችሉ የሥነ ልቦና ባለሙያው ይመክራሉ። • ጤናማ ስሜትና ጤናማ አካል እንዳላቸው ማረጋጋጥ፣ • ከውስጥ ግጭት ነፃ መሆን፤ ፍርሃት ካላቸው ለልጆቻቸው እንዳያስተላልፉ መጠንቀቅ • ከልጆች ጋር ደረጃ በደረጃ፤ እንደ ዕድሜያቸው ሁኔታ ያለውን ሁኔታ በግልፅ ማሳየት እና • ልጆች ከአባታቸው ጋር ግንኙነት ሊያስፈልግ እንደሚችል በማመን ከአባታቸው ጋር እንዲገናኙ እድል ማመቻቸት የእነርሱንም ሆነ የልጆቻቸውን ሕይወት በተወሰነ መልኩም ቢሆን ቀላል ያደርገዋል። በመጨረሻም... ብዙ ጊዜ ላጤ እናቶች በኢኮኖሚ፣ በአስተሳሰብ፣ በትምህርት የተሻሉ ናቸው ይባላል። ይህንንኑ ጥያቄ ለሴቶች መብት ተሟጋቿ አክሊል አንስተን ነበር። "ለብቃት (Empowerment) ሰፊ ትርጓሜ በመኖሩ እነዚህ ሴቶች ብቁ ናቸው አይደሉም ማለት አልችልም" ትላለች። ይሁን እንጂ ሰዎች የሚወስኑበት መንገድ ቢለያይም 'ልጅ ካልወለድኩ ሴት አይደለሁም፤ ስለዚህ ጊዜዬ ሳያልፍ ልጅ መውለድ አለብኝ' የምትል ሴት ብቁ (Empowered) እንደሆነች አላምንም፤ ምርጫ ግን ነው" ስትልም ታብራራለች። ምንም እንኳን ውሳኔው ላይ በምን ምክንያት ተደረሰ የሚለው ወሳኝ ቢሆንም የአንድ ሰው ዋጋው የሚለካው በልጅ መኖርና አለመኖር አይደለም። በመሆኑም ሴትነቷ የሚለካው ልጅ በመውለድ አቅምና ላጤ እናት በመሆን አለመሆኑን በመግለፅ የግል አስተያየቷን ሰጥታለች።
news-48264661
https://www.bbc.com/amharic/news-48264661
''ኢትዮጵያን ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል ሌላ መሪ የለም'' የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝዳንት
ቢቢሲ በየወሩ የሚያዘገጀውና 'ቢቢሲ ወርልድ ኩዌስችንስ' የተባለው አለማቀፍ የክርክር መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ተካሂዶ ነበር። ከ200 በላይ ታዳሚያን በተገኙበት ዝግጅት ፖለቲከኞች፣ ተንታኞችና የማህበረሰብ አቀንቃኞች ተሳታፊዎች ነበሩ።
የክርክር መድረኩ ዋነኛ ማጠንጠኛ ሃሳብ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ባለፉት 12 ወራት ይዘውት የመጡት ለውጥና እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች ላይ ነበር። ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ እስካሁንም ለምን መረጋጋት ተሳናት ሲል የመድረኩ አዘጋጅ የነበረው ጆናታን ዲሞቢልቢ ጠይቋል። በመድረኩ ከተገኙት መካከል ደግሞ የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር፣ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና፣ የአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጸዳለ ለማ እንዲሁም እስክንድር ነጋ ይጠቀሳሉ። • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? • ተስፋዬ ገብረአብ ስለ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ምን ይላል? ከተሳታፊዎች የመጣው የመጀመሪያ ጥያቄ ደግሞ እውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያን የበለጸገች፣ ሰላማዊና የተረጋጋች ሃገር ማድረግ ይችላሉ ወይ? ነበር። ለዚህ ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የጀመሩት የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር ነበሩ። '' በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ተረድቶ ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል መሪ ከአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተሻለ ሰው ሃገሪቱ ታገኛለች ብዬ አላምንም'' ብለዋል። በጥላቻና መጠራጠር ተሸብቦ የነበረን ህዝብ ወደ ፍቅርና አንድነት ማምጣት እጅግ ከባድ ፈተና ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የማይቻል አይመስለኝም በማለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሃገሪቱን ወደተሻለ ከፍታ ለመውሰድ ከባዱ ፈተና የሚሆንባቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ራሳቸው የሚመሩት ኢህአዴግ ነው ብለዋል። ''ብዙዎቹ የፓርቲው አባላት ለለውጥ የተዘጋጁ አይደሉም፤ ጠቅላዩ ከሚያመጧቸው የለውጥ ሃሳቦች ጋርም አብረው መጓዝ አይችሉም። አሁንም ቢሆን ፈጣን ለውጥ ማምጣት የማይችሉ ከሆነ ህዝቡ መጠየቅ ይጀምራል።'' ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን እየተከተሉት ባለው አካሄድ ሃገሪቱን ወደ ብልጽግና ይመሯታል ብዬ አላስብም በማለት ተከራክሯል። ''ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥ ለማምጣት የመረጡት መንገድ የተሳሳተና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚመራ ነው'' ብሏል። ጋዜጠኛ ጸዳለ ለማ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈተናዎች ከሁለት አቅጣጫዎች እንደሚመነጩ ታስረዳለች። ''ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥና ብልጽግና ሊመጣ የሚችለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የሚመሩት ፓርቲ ራሱን ፈትሾ ለለውጥ ሲዘጋጅና በብሄር ፖለቲካ ሲገዳደል የነበረው ህዝብ ይቅር ለመባባል ሲዘጋጅ ነው'' ብላለች። ሌላኛው ተሳታፊዎቹን ያከራከረ ሃሳብ በብሄር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ ያስፈልጋታል ወይስ አያስፈልጋትም የሚለው ጥያቄ ነበር። በዘር የተከፋፈለውና መስማማት የማይችለው የተማረው ሃይል ራሱን ለመቀየርና ልዩነቶቹን አጥብቦ አብሮ ለመስራት እስካልተዘጋጀ ድረስ ምንም አይነት ለውጥ ሊመጣ አይችልም የሚሉት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በደንብ ከታሰበበት ፌደራሊዝሙ በራሱ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ብለው ያምናሉ። እስክንድር ነጋ በበኩሉ ከሶስት ሚሊየን በላይ ሰዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት የሆነው ፌደራሊዝሙ ነው፤ አሁንም ቢሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ዙሪያ አልተሳካላቸውም ብሎ የተከራከረ ሲሆን የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ኦማር ግን ተቃራኒ ሃሳብ አላቸው። ''ከዚህ በፊትም ቢሆን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ይፈናቀሉ ነበር። ነገር ግን ይህን ያክል ሰዎች ተፈናቅለዋል ብሎ እንኳን ማውራት አይቻልም ነበር። አሁን ግን ሌላው ቢቀር በነጻነት ስለተፈናቃዮቹ ማውራት ጀምረናል'' ብለዋል። አክለውም ''በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሳው ግጭት ሙሉ በሙሉ ሃገሪቱ አልተረጋጋችም ለማለት በቂ አይደለም። ህዝቡ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት ፍራቻ አለመሳየቱ በራሱ የሚያሳየው ነገር አለ። ሁሌም ቢሆን ለውጥ ሊመጣ ሲል መንገራገጭ ያለ ነው።'' ''መረሳት የሌለበት ሌላኛው ነገር በሃገር ውስጥ የሚፈናቀሉት እንዳሉ ሆነው ለውጡን ለመደገፍና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ወደሃገር ቤት የተመለሱትስ? '' በማለት አቶ ሙሰጠፋ ሃሳባቸውን አጠናክረዋል። • የክልል እንሁን ጥያቄ እዚህም እዚያም? የለውጡ ጎዳና እስከየት? የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅም በመድረኩ ብዙ ሃሳቦችን ያንሸራሸረ ጉዳይ ነበር። ረቂቅ አዋጁ የጥላቻ ንግግር ትርጉም ብሎ ሲያስቀምጥ "ሆን ብሎ የሌላ ግለሰብን፣ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሔርን፣ ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ፆታን አካል ጉዳኝነትን ዜግነትን፣ ስደተኝነትን፣ ቋንቋን፣ ውጫዊ ገፅታን መሰረት በማድረግ ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል የሚያንኳስስ፣ የሚያስፈራራ፣ መድልዎ ወይም ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል መልዕክቶችን በመናገር፣ ፅሁፍ በመፃፍ፤ በኪነ ጥበብ እና እደ ጥበብ፣ የድምፅ ቅጂ ወይም ቪዲዮ፣ መልእክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨትን" እንደሚመለከት ይገልጻል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንደሚለው ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ህግ ያስፈልጋታል። ነገር ግን አተረጓጎሙ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬና ስጋት አለኝ ብሏል። ''ልክ የጸረ ሽብር ህጉ የመናገር ነጻነትን እንደገደበው ሁሉ ይሄኛውም ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።'' ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ደግሞ የጥላቻ ንግግር ህጉ አሳሳቢ ነው በማለት ጀምረዋል። ''ምክንያቱም ህግ ተርጓሚው አካል በነጻነትና ሙሉ መረጃዎችን ይዞ መስራት የማይችል ከሆነ አሁንም ቢሆን ህጉ በተሳሳተ መልኩ ሊተረጎም ይችላል።'' ጋዜጠኛ ጸዳለ ለማ ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ በመንግስት መፍረድ ከባድ ነው ብላለች ''በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉ አጋጣሚዎች በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጩ የተሳሳቱና ግጭት በሚያስነሱ መልእክቶች ብቻ ለብዙ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል።'' ነገር ግን የህጉ አተገባበር ላይ አሁንም ቢሆን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ትስማማለች። የክርክር መድረኩ ከላይ ከተጠቀሱት ሃሳቦች በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተለያዩ የመንግስት ድርጅቶችና ፋብሪካዎችን ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደግል ባለሃብቶች ለማዘዋወር ያቀረቡት ሃሳብ እንዲሁም በቀጣይ ሊደረግ ስለታሰበው ምርጫ ውይይት ተደርጓል።
56094153
https://www.bbc.com/amharic/56094153
"አቶ በቀለ በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ጦር ኃይሎች መወሰዳቸው ከህግ አግባብ ውጭ ነው" ጠበቃቸው
የተቃዋሚ ፓርቲ ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበርና በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙት አቶ በቀለ ገርባ በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ መንግሥታዊው የጤና ማዕከል ጦር ሃይሎች ሆስፒታል መወሰዳቸውን ቢቢሲ ከጠበቃቸውና ከሃኪማቸው መረዳት ችሏል።
ከአቶ በቀለ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሃመድ ጅማ፤ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመተላለፍ አቶ በቀለ ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል በኃይል መወሰዳቸው "ከህግ አግባብ ውጭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና በሕገ-መንግስት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ችሎት ሰኞ እለት የካቲት 8፣ 2013 ዓ.ም እነ አቶ በቀለ ገርባን በግል የጤና ተቋም በሆነውና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዲታከሙ ውሳኔ አስተላልፏል። ይህንን የፍርድ ቤት ውሳኔ በዚያኑ ዕለት፣ ሰኞ ጠበቆቻቸው ለቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዳስገቡና ደብዳቤውንም እንደተቀበሏቸው አቶ መሃመድ አስረድተዋል። ከጥር 19፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ውሃ ምንም የማይቀምሱትና የረሃብ አድማ ላይ ናቸው የተባሉት አቶ በቀለ የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታም በማሽቆልቆሉ ሃኪሞቻቸው ተኝተው እንዲታከሙ ውሳኔ ላይ መደረሱን ዶክተር ኢሊሊ ይናገራሉ። በትናንትናውም ዕለት የካቲት 9፣ 2013 ዓ.ም ዶክተር ኢሊሊ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ በቀለ ገርባን ለመውሰድ ጥዋት 4፡00 አካባቢ እንደደረሱ ገልፀዋል። ማረሚያ ቤቱ የሚያከናውናቸውን ስራዎችን ጨርሶ ወደ ምሳ ሰዓት አካባቢ ላንድ ማርክ ሆስፒታል ለመውሰድ ጉዞ ጀመሩ። ሃኪማቸው ዶክተር ኢሊሊ፣ ጠበቆቻቸው፣ ቤተሰባቸው፣ አቶ በቀለና ማረሚያ ቤቱም የሚያውቁት ወደ ላንድ ማርክ ሆስፒታል እንደሚሄዱ ነው። በአምቡላንስ ተጭነው ወደ ላንድ ማርክ እየሄዱ በነበረበት ወቅት አፍሪካ ህብረት አካባቢ አንድ ነጭ ፒክ አፕ መኪና መንገድ እንደዘጋባቸውና አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር በቦታው የነበሩት ዶክተር ኢሊሊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ከላይ በመጣ ትዕዛዝ መሰረት ወደ ላንድ ማርክ ሆስፒታል ሳይሆን ወደ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል መወሰድ እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል። ይኼንን ለአቶ በቀለ በሚነግሯቸው ወቅት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት "መልሱኝ" በማለት ጥያቄ ማቅረባቸውንም ዶክተር ኢሊሊ ያስረዳሉ። ከአቶ በቀለ በተጨማሪ ዶክተር ኢሊሊም እንዲሁ ወደ ላንድ ማርክ መውሰድ የማይቻል ከሆነ ወደ ቃሊቲ እንዲመልሱዋቸው መጠየቃቸውን ይናገራሉ። በምላሹ ግን "በኃይል" ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንደወሰዷቸው ይናገራሉ። "ወደ ላንድ ማርክ መውሰድ ካልቻላችሁ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውሰዱን እያልን እየጠየቅን እያለ እምቢ ብለው፣ ያለኛ ፈቃድ በግድ ወደ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ይዘውን ሄዱ" ይላሉ። ጦር ሐይሎች ሆስፒታል ከደረሱም በኋላ አቶ በቀለ አልታከምም እንዳሉና የማረሚያ ቤት ሰዎችም መመለስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለአራት ሰዓታት ያህል በሆስፒታሉ እንደቆዩ ዶክተሯ ይናገራሉ። "አቶ በቀለ 'እኔ በፍፁም ፍርድ ቤት የፈቀደልኝ ቦታ ነው የምታከመው። ከፍርድ ቤት በላይ ሆናችሁ ያንንም ከወሰናችሁ መብታችሁ ነው ቢያንስ ወደማርፍበት ክፍል ውሰዱኝ ብለው ለመኑ'" በማለት ዶክተሯ የሆነውን ያስረዳሉ። በወቅቱም የማረሚያ ቤቶቹ ሰዎች ለማግባባት እንደሞከሩና እንዲሁም ከላይ ተፃፈ የተባለው የትዕዛዝ ደብዳቤ በጠቅላይ አቃቤ ህግ ጌዴዎን ጤሞቴዎስ የተፈረመ ደብዳቤ እንዳሳዩዋቸውም ይናገራሉ። ደብዳቤው የተፃፈው ለማረሚያ ቤቱ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲቀየር ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ መጠየቁንና ይህ እስኪሆን በመንግሥት ተቋማት ነው መታከም የሚችሉት የሚል ይዞታ ያለው ደብዳቤ እንዳዩ ይናገራሉ። የአቶ በቀለ ጠበቃ አቶ መሃመድም በዛሬው ዕለት የማረሚያ ቤቶቹን ኃላፊዎች ባናገሯቸው ወቅት የጠቅላይ አቃቤ ህግ የዶክተር ጌዴዎን ደብዳቤ በቴሌግራም ደብዳቤ እንደደረሳቸውና "ትዕዛዙን ለማስቀየር ፍርድ ቤት ማመልከቻ አስገብተናልና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከምናወጣ ድረስ የግል ሆስፒታል እንዳይሄዱና ወደ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል እንዲወሰዱ የሚል ነው"። ምንም እንኳን ማረሚያ ቤቱ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሆንም ነገሩን የተረዱት መንገድ ላይ እንደሆነም አቶ መሃመድ ከማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ተረድተዋል። አቶ መሃመድ እንደሚሉት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ደብዳቤ ለማረሚያ ቤቱ ቀደም ብሎ መፃፍ ሲችል "መንገድ የተዘጋበትን ሁኔታ" አለመረዳታቸውን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ደንበኛቸው አቶ በቀለ "በሃይል መወሰዳቸው ከህግ አግባብ ውጭ መሆኑ" እንዲሁም "በፀጥታ ኃይሎች መንገድ በመዝጋት" የተሰራው አሰራር ትክክል እንዳልሆነ ይናገራሉ። "ጠቅላይ አቃቤ ህግ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ማገድ አይችልም እንዲሁም ሁለቱም የመንግሥት አካል ሆነው ሌላኛው አካል መንገድ በመዝጋት በኃይል ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር" ትክክል እንዳልሆነም ጠቁመዋል። ቢቢሲ የጠቅላይ አቃቤ ህግ አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ፍርድ ቤቱም በዛሬው ዕለት የጠቅላይ አቃቤ ህግን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ በግል ሃኪም ቤት እንዲታከሙ መወሰኑን አቶ መሃመድ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤቱ በግል ሃኪም ቤት እንዲታከሙ የወሰነላቸው ሲሆን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ የፀጥታና ደህንንነት በተመለከተ ያለውን ሁኔታ አቅርቦ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የካቲት 2፣ 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲወሰዱ ወስኖ ነበር። በወቅቱ ማረሚያ ቤቱ ታሳሪዎቹ የረሃብ አድማ ላይ በመሆናቸው "ታመው ከወደቁ ዝም ብለን ማየት ስለማንችል፤ ቀደም ብለው ስለማይነግሩንና በዛ አጭር ሰዓት ውስጥ እነሱ የፈለጉት ሆስፒታል ላይ ሃይል አሰባስበን ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስለምንቸገር፤ ድንገት ከወደቁ ግን ጦር ሃይሎች ሆስፒታል እንድናሳክም ይፈቀድልን" ብለው በማመልከታቸው ለጊዜው ፍርድ ቤቱ ይኼንን ፈቅዶላቸው እንደነበር አቶ ጅማ ያስረዳሉ። ጠበቆቻቸው በበኩላቸው ሆስፒታሉን ከስምንት ሰዓት በፊት እንደጠየቁና ደንበኞቻቸው በመረጡት ሆስፒታል እንዲታከሙ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲያስተላልፍና ከዚህ ቀደም የነበረውን ውሳኔ እንዲያፀና ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም ውሳኔውን በመቀልበስ እነ አቶ በቀለ በላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዲታከሙ ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህም ውሳኔ መሰረት ነው በዶክተር ኢሊሊ አጃቢነት አቶ በቀለ ገርባ ወደ ላንድ ማርክ ሆስፒታል የተወሰዱት ። ከዚህ ቀደምም ለሳምንታት ያህል ህክምና አሻፈረኝ ብለው የነበሩት አቶ በቀለን በማግባባትና ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጋር ወደ ግል ሆስፒታል ለመውሰድ ተስማምተው ነበር። የካቲት 5 የህክምና ቡድኑ ቃሊቲ የፌደራል ማረሚያ ቤት ከደረሱ በኋላ ግን መንግሥት ሆስፒታል ነው መወሰድ የሚችሉት ተብሎ ተነግሯቸዋል። የጤና ሁኔታቸው እያሽቆለቆለ የሚገኙት አቶ በቀለን ወደ ግል ሆስፒታል ለመውሰድ በሚሞክሩበት ወቅት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደሩ ማስቆሙን ተከትሎ ዶክተር ኢሊሊ ስራ ማቆማቸውን ተናግረው ነበር። ጠበቃቸው መሃመድም እንዲሁ አርብ በ5፣ 2013 ዓ.ም ሆስፒታል ባለመግባታቸው ያንን ቅሬታ ገልፀው በያዝነው ሰኞ ፍርድ ቤት ማመልከቻ ማስገባታቸውን ይናገራሉ። "እኛ ማከሙን አቁመናል ስለተገደድን፤ ለማከም ሆስፒታል መውሰድ አልቻልንም። በዚህ ወቅትም መቻላችንንነ አናውቅም። ተመልሰን መጀመሩ ራሱ ያስፈራናል" በማለትም ሰኞ እለት ለዋለው ችሎት ዶክተር ኢሊሊ አስረድተዋል። በምላሹም ዶኞቹ ውሳኔው እንዲፀናና በግል ሃኪም ቤት እንዲታከሙና የህክምና ባለሙያዎቹም ተመልሰው ስራቸውን እንዲጀምሩና እንዲከታተሏቸው መጠየቃቸውን ዶክተሯ ይናገራሉ። በትናንትናው ዕለት አቶ በቀለ ምንም ዐይነት ህክምና ሳያገኙ "ተንገላተው ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመመለሳቸው" የጤና ሁኔታቸውን አሳሳቢ እንዳደረገው ዶክተሯ አልደበቁም። "ትናንት የተፈጠረው ነገር ይበልጥ እንድንፈራና እንድንጠራጠር አድርጎናል። አሁን ባለው ሁኔታ እኛ መልሰን ጤናቸውን የመከታተል ሃሳቡም የለንም። ለራሳችን እየፈራን ነው" ይላሉ ዶክተር ኢሊሊ እነ አቶ በቀለ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነ ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። እነ አቶ ጃዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፣ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሣሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ ሲሆኑ በወቅቱ ውሳኔ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ መሆናቸውም የሚታወስ ነው።
54394721
https://www.bbc.com/amharic/54394721
ሥነ-ጽሑፍ፡"ሴቶች የታሪክ አካል ተደርገው አይቆጠሩም፤ በታሪክነትም አንመዘግባቸውም" መዓዛ መንግሥቴ
ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ሴት የነፃነት ታጋዮችን በሚዘክረው 'ዘ ሻዶው ኪንግ' መፅሃፏ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ ለቡከር ሽልማት ከታጩት መካከል አንዷ ሆናለች።
ለነፃነት በተደረገው ትግል ላይ የጥቂት ወንዶች ሚና በጎላበት ሁኔታ ሴት ነፃነት ታጋዮች ከታሪክ መዝገብ መፋቃቸውንና ግዙፍ ሚናቸው ምን ይመስል ነበር በማለት አስርት አመታትን ወደ ኋላ ተጉዛም መዓዛ በ'ዘ ሻዶው ኪንግ' ታስቃኛለች። መዓዛ መንግሥቴ ከቢቢሲ ጋር ስለ አዲሱ መፅሃፏ፣ በጦርነቱ ወቅት ኢትዮጵያውያን ሴቶች በጣልያን ወታደሮች የደረሰባቸውን መደፈርና ጥቃት፣ ለአገር ነፃነትና በሰውነታቸውም ለመከበር ያደረጉትን ትግል በተመለከተም ቆይታ ካደረገችባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል። ቢቢሲ፡ ለቡከር ሽልማት በመታጨትሽ ምን ተሰማሽ? መዓዛ፦ታቂያለሽ የማይታመን ነው። ምንም ያልጠበቅኩት ጉዳይ ነው። ለኔ ዋነኛውና ትልቁ ነገር መፅሃፉን መጨረስ ነበር። ከሚባለው በላይም መፅሃፉን ለመጨረስ ረዥም ጊዜ ነው የወሰደብኝ። ለበርካታ አመታትም መፅሃፉን እጨርሰዋለሁ፤ አቅሙ የለኝም ብየም የማስብበት ጊዜ ነበር። በዚህም ትግል መፅሃፉን ጨርሼ፣ ማሳተሜ እንዲሁም ሰዎች ማንበባቸው ለኔ በጣም አስደናቂ ነው። ሆኖም ከዚህ ባለፈ በሽልማቱ ውስጥ መካተቴን በተደወለልኝ ወቅት የተሰማኝን ስሜት እንዲህ በቃላት ልገልፀው አልችልም። የሆነ የምኖርበት አለሜ ግልብጥብጡ የወጣ ነው የመሰለኝ፤ ለካ ይቻላል! በጣም መልካም ነው። ሌላ ምን እላለሁ። ቢቢሲ፡ የመጀመሪያ መፅሃፍሽ 'ቢኒዝ ዘ ላየን ጌዝ' ከወጣ ከአስር አመታት በኋላ ነው 'ዘ ሻዶው ኪንግ የተፃፈው። ዘ ሻዶው ኪንግ እንዴት እንደተፃፈ ልትነግሪን ትችያለሽ? መፅሃፉ በዋነኝነት የሚያጠነጥንባቸው የሴቶች አርበኞች ታሪክ፣ ታሪክን በነሱ መነፅር ማየትና መፃፍስ ምን ይመስላል? መዓዛ፦መፅሃፉን ስጀምረው ዋነኛ ፍላጎቴ የጣልያን ወረራን በተመለከተ መፃፍ ነበር። የጣልያን ጦር ከአፍ እስከ ገደፉ በመሳሪያ ቢታጠቅም ለነፃነት ሲባል ስለታገሉና ስለተዋደቁ ኢትዮጵያውያንና ከአምስት አመት የመራራ ትግል በኋላ ማሸነፍ ስለቻሉት ኢትዮጵያውያንን ነበር መዘከር የፈለግኩት። ታሪኩን መፃፍ ስጀምርም የተገነዘብኩት ነገር ቢኖርና የበለጠ የሳበኝ ነገር ቢኖር የግል ታሪኮች፣ የቀን ተቀን ኑሮ፣ ግንኙነት ነበር። ጦርነቱ እንደዚያ በተፋፋመበትና በተጋጋመበት ወቅት በወቅቱ የነበሩ ኢትዮጵያውን የቀን ተቀን ህይወትና፣ የርስ በርስ ግንኙነት የበለጠ ሳበኝ። በዚህ ሁሉ ቀውስ መካከል ኑሮ ምን ይመስላል የሚለውን ማውጠንጠን ጀመርኩ። የጦርነት ገድሎችን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጌም በዚህ ውስጥ ጋብቻዎች እንዴት ይሆናሉ? የፍቅር ግንኙነቶች በጦርነት ውስጥ ምን ይመስላሉ? እርስ በርስስ ያሉ ግንኙነቶች፣ በሴቶች፣ በወንዶች መካከል ጦርነቱ ምን አይነት ተፅእኖን ያሳርፋል የሚሉትንም ማጥናት ጀመርኩ። በዚያውም በአለም ላይ ተንሰራፍቶ የነበረው የቅኝ ግዛት ኢንተርፕራይዝ ታሪኮችን (አፈ ታሪኮችን)፣ እምነትን፣ ሃሰትን፣ እና ፎቶዎችን በመጠቀም እንዴት ሚሊዮኖችን ለመጨቆንና ተቀባይነት ያለው ለማስመሰል እንዴት እንደጣሩም ማየት ጀመርኩ። እናም ታሪኩ ከጣልያንና ኢትዮጵያ ጦርነት በላይ ሆነ። ከዚያም ባለፈ እኛ እና እነሱ አብረን እንዴት እንደምንኖር መመርመርና ማጥናቴን ቀጠልኩ። ቢቢሲ፡ የምርመራው ጊዜ ምን ያህል ጊዜ ወሰደብሽ? መዓዛ፦ ሳቅ የአምላክ ያለህ፣ ታቂያለሽ! መፅሃፉን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ለመጨረስ አስር አመታት ያህል ወስዶብኛል። ለሁለት ወይም ለሶስት አመታት ያህል አትኩሮቴ ምርምሩ ላይ ነበር። በመሃልም ለመፃፍ እሞክራለሁ። ምርመራውንም ለማድረግ ጣልያንኛ ቋንቋ መማር ነበረብኝ። በርካታ የተከማቹ መዛግብትን ለመፈተሽም በአስተርጓሚ መስራት አልፈለግኩም። ከዚያም ባለፈ ስለ ጦርነቱ የነበረኝ ስሜት እና በአፍሪካውያን ላይ ጦርነት ስላወጁት አውሮፓውያን የነበረኝ ስሜት አሉታዊ ወይም ጨለምተኛ ነበር። የጣልያንን መሬትም ስረግጥ ከፍተኛ የሆነ ንዴት ነው የተሰማኝ። መዛግብታቸውን ሳገላብጥና የምርምሩን ስራ ስጀምር የትኛውም ጣልያናዊ ምንም እንዲለኝ አልፈለግኩም። ከዚያም አሰብኩበትና በከፍተኛ ንዴት ሆኖ መፅሃፍ መፃፍ አይቻልም አልኩኝ። እንዴትስ የተፈጠረውን ነገር ሙሉ በሙሉስ መረዳት ይቻላል? ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ። እናም ከዚያ በኋላ ነው ጣልያኖቹን በተለይም ኢትዮጵያን የወጉትን ወታደሮች ልጅ፣ ልጆች ለማናገር እናም በምን መንገድ እንደሚረዱት ለማወቅም ነው ጣልያንኛ የተማርኩት። ይሄም በራሱ የተወሰነ ጊዜ ወስዷል። ታሪኩም ሙሉ በሙሉ ተከፈተልኝ ማለት እችላለሁ። ታሪኩም የግለሰቦች ታሪክ ሆነ። ቢቢሲ፡ የግለሰቦች ታሪክ ነው ብለሽ ስትናገሪ አንድ ነገር አስታወሰኝ። በአንድ ወቅት ሴት አያትሽ በጦርነቱም ዘምታ እንደነበር ተናግረሻል። ከመፅሃፉ ታሪክ ጋር ምን ያህል ቁርኝት አለሽ። ከአንቺስ የግል ታሪክ ጋር ምን ያህል የተገናኘ ነው? መዓዛ፦ጦርነቱ ቤተሰባችን ጋር ይገናኛል። በአባቴ በኩል ወንዱ አያቴም ሆነ የአባቴ ወንድሞች (አጎቶቼም ) በጦርነቱ ዘምተዋል። የአባቴ የአጎት ልጆችም በጦርነቱ ተሰውተዋል። የቀድሞ ፎቶዎችንም ከቤተሰብ ጋር ሰብሰብ ብለን በምናይበት ወቅት በጦርነቱ የተገደሉ ሰዎችን እየጠቆሙ እነዚህን አጥተናል ይላሉ። በጦርነቱ ላይ የሴቶች ዘማቾችን ታሪክ ሰምቻለሁ። ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን የሚተረክበት መንገድ ወንዶቹን እንዴት ተከትለው እንደሄዱ ነው። የሞቱትን በመቅበር፣ የቆሰሉትን በመንከባከብ፣ ውሃ በመቅዳትና በመሳሰሉት፤ መፅሃፉን ጨርሼ ለመጨረሻ ጊዜ ምርምር ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ፣ በመፅሃፌ ውስጥ የተካተቱትና ጦርነት የተካሄደባቸውን ቦታዎች ለመጎብኘትም ከእናቴ ጋር አብረን ሄድን። ጉዞውም አስር ቀናትን ያህል የፈጀ ነው። ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለ መፅሃፉ እያወራን እንዲሁም በጦርነቱ ላይ የተሳተፉ ሴቶች ፎቶግራፍ ማግኘቴን እየነገርኳትም ነበር። ምንም እንኳን ታሪኩን ባለውቀውም ሌሎች ሴቶች አርበኞች ሊኖሩ ይችሉ ይሆን እያልኳት እያለ እናቴም ዝም ብላ እንደ ቀልድ ቅድመ አያትሽስ አለችኝ? ለቡከር ሽልማት የታጨችው ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ እንደዛ ስትለኝ በማይገባኝ ቋንቋ እያወራች ሁሉ ነው የመሰለኝ። እና ምን አልሺኝ ብዬ ጠየቅኳት። በእነዚህ አመታት ሁሉ ምርምር ሳደርግ ታውቃለች። ስለ ሁሉም ነገር ታውቃለች። ከነዚህ ሁሉ አመታት በኋላ በዚህ ወቅት ነው ለመናገር የመረጠችው እናም ለምን ከዚህ ቀደም አልነገርሽኝም? ብዬ ጠየቅኳት። እሷም በምላሹ ጠይቀሽኝ አታውቂም አለችኝ። በጣም ነው ያስደነቀኝ። ምክንያቱም የዚህ ጦርነት ታሪክ ምንድን ነው ስንል ሴቶች እርስ በርስ የሚነጋገሩት ታሪክ አይካተትም፤ በቤታቸው፣ በማዕድ ቤት። በእህቶች መካከል የሚነገረው ታሪክ፣ በእናትና በልጅ መካከል የሚነገረው እንደ ታሪክ አይነገርም። ወንዶቹን ነው የምናየው። በቤተሰቤ የወንዶቹን ታሪክ አውቀዋለሁ ነገር ግን ይህንን ሰምቼ አላውቅም። ይሄ መፅሃፍ ከወጣ በኋላም ለብዙዎች የምናገረው በቤተሰቦቻችሁ ሴቶቹን ጠይቁ።በጦርነቱም ሆነ ነፃ በማውጣት ስለተሳተፉት በመላው አፍሪካ፣ በደቡቡ አለም፤ ምክንያቱም ሴቶች በእነዚህ ጦርነቶችም ሆነ ነፃ በማውጣቱ ተሳትፈዋል። የናይጄሪያ ሴቶች ታሪክ መንፈሴን አነቃቅተውታል፣ የደቡብ አፍሪካ ሴቶች ለነፃነት ያደረጉትን ትግል መጥቀስ ይቻላል፤ ይሄ አዲስ ታሪክ አይደለም።ነገር ግን አናወሳቸውም፤ ስለነሱም አናወራም። የታሪክ አካል ተደርገውም አይቆጠሩም። ታሪክ ናቸው ተብለውም አይነገርላቸውም። በመማሪያ መፅሃፎች ውስጥ አልተካተቱም። በአለም ታሪክ መዛግብት ውስጥም አልተካተቱም። በአለም ላይ ባለው ስርአት የአፍሪካ ታሪክ የአፍሪካ ነው። የአውሮፓ ታሪክ ደግሞ የአለም ታሪክ ተደርጎ ነው የሚታየው። እሱንም የአተራረክ መንገድ ነው መስበር የፈለግኩት። ጥቁር ሴቶች የአለም ታሪክ አካል ናቸው። ከመጀመሪያው ጀምሮ ታሪክ ሰርተዋል የሚለውንም ማስተላለፍ ነው የፈለግኩት ቢቢሲ፡ እስቲ በመፃህፍሽ ላይ ስላሉት ሴቶች እናውራ፤ ዋነኛ ገፀ- ባህርያቱ ሴቶች ናቸው ለምሳሌ ሂሩት። ከዚህም በተጨማሪ የሴቶች ወታደሮች (አርበኞች) አስተዋፅኦ ጎልቶ እንዲወጣ አድርገሻል። ይሄ መፅሃፍሽ ላይ መካተቱ በጣም የሚያስደስት ነው። በዳሆሜ(ከ16ኛው- 18ኛው ክፍለ ዘመን በአሁኗ ቤኒን አካባቢ የነበሩ የሴት ጦረኞች) ስለነበሩት የሴት ወታደሮች ሰምተናል። መፅሃፍሽ ላይ የተጠቁሰት የሴት ጦረኞች በቅርብ ጊዜ በአፍሪካ የነበረ መሆኑን ማወቅም፣ ማንበብም በጣም ያስደስታል። መፅሃፍሽን መፃፍ ስትጀምሪ የነዚህ አርበኛ ሴቶች ታሪክ ዋነኛ የታሪኩ አካል ይሆናል ብለሽ አስበሽ ነበር? መዓዛ፡ በጭራሽ! መጀመሪያ ስፅፍ የነበረው ሳድግ የሰማኋቸውን የጦርነት ታሪኮች አይነት ተመሳሳይ መጽሐፍ እፅፋለሁ ብዬ ነበር የተነሳሁት። ስለ ሴት አርበኞች ታሪክ የማውቀው አልነበረም። ምናልባት አንድ የሰማሁት ታሪክ ሴቶቹ ከጣልያን እንደሚወልዱ ሰምቻለሁ። ወይም ደግሞ አክስትሽ ግማሽ ጣልያን የሆነ ሰው አገባች የሚሉ ታሪኮችን እሰማለሁ። ምን ተፈጠረ ስል? ምላሹ ስለዚህ ጉዳይ አናወራም የሚል ነበር። እናም በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት እንደደረሰባቸውና እንደተደፈሩ አወቅኩኝ። ጥቃቱ፣መደፈሩ፤ ማስፈራራቱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሰውነታቸው ላይ የታወጀባቸው ሌላኛው አይነት ጦርነት ነበር። የደረሰባቸውን ጥቃት፣ መደፈር ማሳያው ግን በግልፅ እየታየ ነበር። እሱን ማሳየት ፈልጌ ነበር፤ ነገር ግን ስለ ጦርነቱ የወንዶች ታሪክ ነበር እየፃፍኩ የነበረው እሱንም ነው በደንብ የማውቀው፤ ዚህ አጋጣሚ አስደሳች የምለውና በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ህዳር 19፣ 1935 የወጣ አንድ ፅሁፍ አየሁ። ይህም ኢትዮጵያዊት ሴት በጦርነቱ አውድማ ላይ በጦርነቱ የወደቀውን የባለቤቷን ጠመንጃ አንስታ እሱ ሲመራው የነበረውን ሁለት ሺህ ወታደሮች (ዘማቾች) በመምራት ጦርነቱን ቀጥላለች። ፅሁፉን ሳነብ፣ መፅሀፌን፣ ታሪኩን በአዲስ መልክ ነው የቀያየረው። ጠመንጃውን አንስታ ወንዶቹን ለመምራት በጦርነቱ ውስጥ ስትዋጋ ነበር ማለት ነው። ወንዶቹም እንዲከተሏት ያስቻላቸው በሆነ የጦር አመራር ቦታ ነበረች ማለት ነው። ለጦሩ አዲስ አልነበረችም። ይህም ማለት በጦሩ ውስጥ በርካታ ሴቶች ነበሩ። ጭንቅላቴንም ሆነ መፅሃፉን በአዲስ መልኩ ነው የከፈተው ቢቢሲ፡ መፅሃፉ ምን ያህሉ ነው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው? መዓዛ፡ ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ እውነተኛ ታሪክ ነው። እንደ ሂሩት አይነት ሰው አውቃለሁ? ስለ ሂሩት ስፅፍ ታዳጊ ልጅ ሆና የአባቷን ጠመንጃ ለማግኘት ስለምትታገል ልጅ አላውቅም ነበር። ቅድመ አያቴ የአባቷን ጠመንጃ ለማግኘት መታገሏንና መፋለሟን አላውቅም ነበር። እንዲህ አይነት ታሪኮች በእውነተኛው መፈጠራቸውን እናቴ እስከምትነግረኝ ድረስ አላወቅኩም ነበር። ይህንንም የነገረችኝ መፅሃፌን እየቋጨሁ በነበረበት ወቅት ነው። ነገር ግን መፅሃፌ ላይ እንዳሉት ገፀ ባህርያት ሂሩት፣ አስቴር፣ በታሪክ እንደነበሩ አውቃለሁ። ከልብወለድ መፅሃፎች ጋር በተያያዘ ሁሌም የሚነሳው አንዱ ይህ ነው። በታሪክ ውስጥ የተፈጠረውን ክፍተት አግኝቸዋለሁ። ነገር ግን እነዚህ ሴቶች ነበሩ፣ ምንም እንኳን ስማቸው አስቴር፣ ወይም ሂሩት ባይሆንም። መፅሃፉ ላይ ያለችው ምግብ አብሳይዋ ስሟን መናገር አትፈልግም፣ እንደ ምግብ አብሳይዋ ሴት በባርነት የተገዙ ሴቶች አውቃለሁ፤ ሆኖም የሰብዓዊነት ክብራቸውን በሆነ መልክ ያስጠበቁና ያስከበሩ ሴቶችን አውቃለሁ። የመኖር መብታቸውንም በቻሉት መንገድ ያስከበሩ ሴቶችን አይቻለሁ። ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እንዲሁም ከሌሎች አገራት የሚመጡና በተለምዶም ደካማ ተብለው የሚጠሩ ሴቶችን፤ ወይም ተጨቆኑ የሚባሉ ሴቶችን፤ እኔ ደካማ ሴት አጋጥማኝ አታውቅም። ዝም ያሉ ወይም ዝምታን የመረጡ ሴቶች አጋጥመውኛል፤ አውቃለሁ። ዝምታ ግን ደካማነት አይደለም። ያንንም ነው በመፅሃፌ ላይ ማሳየት ፈለግኩኝ። ቢቢሲ፡ በቤተሰብሽ ውስጥ ስለ ጦርነቱ የሚያውቁ ግን ምንም ማለት ያልመረጡ እንዳሉ እየተናገርሽ ነበር። የሌላ ትውልድ አካል መሆንሽና በጦርነቱ ውስጥ አለመሳተፍሽ ታሪኩን በልብወለድ መልኩ እንድትናገሪ ቀለል አድርጎልኛል ብለሽ ታስቢያለሽ? መዓዛ፡ በሆነ መንገድ ቀለል አድርጎልኛል። ከጦርነቱም ሆነ ካስከተለው ጉዳት ጋር ቀጥታ የሆነ ግንኙነት የለኝም። ጦርነቱ ያስከተለውን ውርድት፣ ጣልያኖች በሰው ልጅ ላይ የፈፀሙትን ውርደት፣ ለመዝናናት ሲሉ ያስከተሉትን ኢሰብዓዊ ድርጊትና ስቃይ አላውቀውም። ቅኝ ግዛት ይህንን ነው የፈፀመው። ጭካኔንና ኃይልን በሰዎች ላይ ስለሚችሉ ብቻ ጭነዋል። ያ ሁኔታ እኔ ላይ አልተፈፀመብኝም። ነገር ግን በዚህ ፅሁፍ ሂደት ላይ የተፈጠሩትን ታሪካዊ እውነቶች እንደገና ለማሰብ በምሞክርበት ወቅት፣ ጣልያኖችን የፈፀሙትን ግፍ ለማሰብ በምሞክርበት ወቅትም በከፍተኛ ሁኔታ ሸክም እንደተጫነብኝ ያህል እየከበደኝ መጣ። ታሪኩ ከአስርት አመታት በፊት የተፈጠረ ሳይሆን አሁን እየተከናወነ ያህል ይሰማኝ ነበር።በተቻለኝ መጠን ለማድረግም የሞከርኩት አንባቢው ያንን ወቅት እንዲያልፍበት ነገር ግን እንዲቋቋመው ማድረግ ነው። እሱን ማመጣጠን ትግል አለ። ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ ስለ ወሲባዊ ጥቃትም ፅፌያለሁ፣ አባዊ ስርአት (ፓትሪያርኪ) ሴቶች በየትኛውም የጦርነት ወገን ቢሆኑም ያስከተለውን ጭቆናና ጥቃትም ተመልክቻለሁ። በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆናና ግፍ እስካሁን ድረስ የቀጠለውና የትኛውም የአለማችን ክፍል የሚፈጠረውን የሴቶች ጭቆናም ጋር የተያያዘ ነው። ይህንንም ስናየው ታሪኩ ያለፈ፣ የአሁንና የቀጠለ ይሆናል። ከአሁኑ የአለማችን እውነታም ጋር ይገናኛል። ይህንን ስፅፍ አሁን አለምን ካጥለቀለቀው 'ሚቱ' እንቅስቃሴ በፊት እንዲሁም በዚያኑ ወቅት ነው። ከሂሩት ታሪክ ባሻገር፣ የሴቶችና የታዳጊዎችን ታሪክ መስማት ልብ የሚሰብር ጉዳይ ነው። መፅሃፉ ላይ ያሉት ሂሩት፣ አስቴርና በአሁኑ ሰዓት የምሰማቸው የሴቶችና ታዳጊዎች የትግል ታሪክ ይመሳሰላል። በቻሉትም መጠን በህይወት ለመኖር ይታገላሉ፤ ትግላቸውም እንደቀጠለ ነው። ሴት አርበኞቹም ነበሩ፤ በአሁኑ ሰዓትም አሉ። በየመንገዱም፣ በየጎዳናው ፖሊስን፣ ሙስናን ሲጋፈጡ እናያቸዋለን። ፖሊሲዎችን ተቃውመው ድምፃቸውን ሲያሰሙም እናያለን። ጨቋኝ የትዳር አጋሮቻቸውን ሲታገሉም እያየን ነው። ይሄ ለኔ ተስፋ ይሰጠኛል። ስፅፈውም ተስፋን የሰጠኝ ጉዳይ ነው። ቢቢሲ፡ መፅሃፉ ከታተመ በኋላ ምን አይነት አስተያየቶችን እያገኘሽ ነው? መዓዛ፡ በጣም የሚያስደስት ነው። ከአንባቢዎች ኢ-ሜይል፣ ደብዳቤ ማግኘት ደስ ያሰኛል። ከመላው አለም ነው መልእክት እየደረሰኝ ያለው። መፅሃፉ ጥሩ ተቀባይነትን አግኝቷል። ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ታሪኩ ጋር መገናኘት በቻሉ አንባቢዎች ሁሉ በደንብ ተቀብለውታል። የስልጣን፣ ኃይል፣ ጥቃት፣ ቅኝ ግዛትን ታሪክ የተረዱ ሁሉ መፅሃፉ ከፍተኛ ትስስር አለው፤ ትርጉምም ሆነ ተስፋ ሰጥቷቸዋል። ይህም ሁኔታ በቃላት መግለፅ ከምችለው በላይ ያስደስታል። ከአንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት አንድ ኢሜይል አገኘሁ። "ምናልባት በአያትሽ እድሜ ላይ ልሆን እችላለሁ። መፅሃፍሽ ወደ ልጅነቴ መለሰኝ። ያስታወሰኝም በ60ዎቹ የነበረውን አብዮት ነው። ያንን ጊዜ ለተወጡት ሴቶች በሙሉ ዘውድ ባጠልቅላቸው ምኞቴ ነው" አለችኝ። ሁኔታው በጣም ነው የነካኝ። እንደዚህ ስሜት የሚነኩ የተለያዩ መልዕክቶችን አገኛለሁ፤ የሚያስደስት ነው። ለዚህም አንባቢው በዚህ መንገድ ትስስር መፍጠሩ ክብር ይሰማኛል። ቢቢሲ፡ እንደ ፀሃፊ ተፅእኖ ያሳረፉብሽ እነማን ናቸው? መዓዛ፡ ለኔ ዋነኛ ተፅእኖ አሳረፍብኝ የምላት የጋናዋ ፀሃፊ አማ አታ አዱ 'አወር ሲስተር ኪል ጆይ' የሚለው መፅሃፍ ነው። ይህንን መፅሃፍ ሳነብ ገና ጀማሪ አንባቢ ነበርኩኝ። ኮሌጅ ትምህርቴን የጀመርኩበት ወቅት ነው። ትምህርቴን የተማርኩት በአሜሪካ ነው፣ መምህራኖቻችን እንድናነብ ይሰጡን የነበሩት መፃህፍት የኔን ታሪክ ያላካተተ ነው። የኔ ታሪክ እንደ ስደተኛ፣ አፍሪካዊ፣ እንደ ጥቁር ሴት አይንፀባረቅበትም። በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ራሴን እንደ እንግዳ የማይበትና መቼም ቢሆን መገናኘት ያልቻልኩት ማህበረሰብ ውስጥ ነው። እናም በዚህ ወቅት ይህንን መፅሃፍ ሳነብ ብርሃን የተገለጠልኝ ነው የመሰለኝ። ራሴንም በተወሰነ መልኩ አገኘሁበት። የሆነ ሰው ዕውቅና የሰጠኝ መሰለኝ፣ ራሴን አየሁበት።እዛ መፅሃፍ ላይ የምመለስበትም ምክንያት በመሰረታዊ ደረጃ ፀሓፊዋ ያደረገችው ነገር ረቂቅ ነው። ግሩም በሆነ መልኩ የተፃፈ ነው። ለዚያም ነው ይህ መፅሃፍ መሰረቴ ነው የምለው። ከዚያ በተጨማሪ ከግሪክ ፀሃፊዎች መካከል የሆመርን ፅሁፎች ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ትርጉም ይሰጡኝ ነበር። ታሪኮቹን በጣም ነበር የምወዳቸው እናም የሚስቁብኝና የሚያፌዙብኝ ነበሩ። አንዲት አፍሪካዊት፣ ጥቁር የግሪክ ታሪኮችን ለምን ታነባለች? መምህራኖቼም ከግሪክ ፀሃፊዎች ጋር በፍፁም ትስስርም ሆነ ግንኙነት እንደሌለኝ አድርገው ነው ያሰቡኝ። እናም በመፅሃፎቹ ላይ ኢትዮጵያ የሚለውንም ሳገኝ ይህ አፍሪካዊ ነው ማለት ጀመርኩ። ሮም መንደር እያለች እኛ ሃገር መስርተናል፤ እናንተ ጭራሽ አገር የሚለውንም ፅንሰ ሃሳብ አታውቁትም ነበር እላለሁ። እኛ ግን በጥንታዊ ግሪክ ውስጥ ተጠቅሰናል፤ አለን። ሆመር እውቅና ሰጥቶናል ለምንድን ነው የኔ ታሪክ የማይሆነው፤ ከኔ ጋር ትስስር የማይኖረው ለምንድን ነው? የሆመርን ታሪኮች በማይበትም ወቅት፣ አፍሪካውያን ለምን ያህል ሺ አመታት ነው ታሪክ ነጋሪዎች የነበሩን። የማሊ ግሪዮትስን (ታሪክ ነጋሪዎችን) መጥቀስ ይቻላል። የምዕራቡ አለም በጭራሽ ያልነበረው ነው። ሆመር አዲስ ነገር አልፈጠረም። በአፍሪካ ከጥንት ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የነበረ ነው። ታሪኮቻችንን ከትውልድ ወደ ትውልድ አሻግረናል፤ ትዝታዎቻችንን፣ የዘር ግንድና አመጣጥ በዘፈኖቻችን በታሪኮቻችን አሻግረናል። የሆመርን ግጥሞች መግቢያ ሳነብ ለኔ አዝማሪዎችን ያስታውሰኛል። በዚህ ባህል ነው ያደግኩት፣ አቀዋለሁ። ቢቢሲ፡ ታሪኮቻችንን በቃል መንገር ብቻ ሳይሆን በመፅሃፍ መልክ መፃፉ ጥቅሙ ምንድን ነው ብለሽ ታስቢያለሽ? መዓዛ፡ ይሄንን ሳስብ የቅድመ አያቴ ታሪክን አስታውሳለሁ። ከመሞቷ በፊት አግኝቻታለሁ። ነገር ግን የጦርነቱ አርበኛ እንደነበረች አላውቅም። ስለዚህ ታሪክ ምንም አላውቅም። ከሰዎች ሰዎች ሲነገር የማቀውን ነው የሰማሁት። እናቴ ባትነግረኝ ኖሮ ይሄ ታሪክም ሳይታወቅ፣ ከታሪክ መዛግብት ተፍቆ ይቀር ነበር። ለዛም ነው ታሪክ መፃፍ ያለበት፣ መመዝገብ ያለበት፣ በበርካታ የእስያና አፍሪካ አገራት አገር በቀል ቋንቋዎች እየጠፉ ነው፣ እየሞቱ ነው። በርካታዎቹም የራሳቸው ፊደል የላቸውም። እናም የምናጣው ታሪክ ስጋት ፈጥሮብኛል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂን በመጠቀም መቅረፅ (ሬኮርድ) ማድረግ እንችላለን። ታሪኮቹን፣ ቋንቋዎቹን መቅዳትና ማስቀመጥ የምንችልበት ዘመን ላይ ነን። ቤተሰቦቻችሁ ጋር ሄዳችሁ ታሪካቸውን ጠይቁ፣ በስልካችሁ ቅዷቸው። ምን እንደሚያመጣ አታውቁም። እነዚህን ታሪኮች እየሰበሰቡ ያሉ ሰዎች እንዳሉም ተስፋ አደርጋለሁ። ማግኘትም እፈልጋለሁ። ሆኖም በመላው አፍሪካ ይህንን ማድረግ አለብን። የምዕራቡም አለም በሚፅፈው ታሪክ ነው የበላይነቱን ማሳየት የሚፈልገው ፤ ታሪክ አለን፣ የተፃፈ መሆን የለበትም። በማንኛውም መንገድ ሊሆን ይችላል፣ ማስቀጠል አለብን።
news-55000107
https://www.bbc.com/amharic/news-55000107
ኮንሶ ውስጥ ባጋጠመ ግጭት በአስር ሺህዎች ሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው ተነገረ።
በኮንሶ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በተከሰቱ ግጭቶች ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙ የዞኑ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሀሰን ወላሎ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ አካባቢ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ዳግም ባገረሸ ግጭት ምክንያት የሰዎች ህይወት ማለፉን፣ የቆሰሉ እና በሰገን ሆስፒታል ገብተው ሕክምና ያገኙ ሰዎች መኖራቸውን፣ ቤቶች ላይ ቃጠሎ መድረሱንም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ከተማ ገለቦ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በዞኑ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ነዋሪዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ። ከዚህ ቀደም በአካባቢው 290 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን በአደጋ ስጋት ሥራ አመራር መለየቱን የሚገልፁት አቶ ከተማ፤ በአሁኑ ግጭት ምን ያህል ቤት እንደተቃጠለ ለማወቅ አልተቻለም ብለዋል። በሰገን ወረዳ የሚገኙ እና ተደጋጋሚ ጥቃት እና የቤት ማቃተል የሚደርስባቸው ቀበሌዎች በማለትም ገርጬ፣ አዲስ ገበሬ፣ ሃይሎታ ዱካቱና መለጌ ዱጋያ ጠቅሰው በአሁኑ ሰዓትም ከሰገን ከተማ በተጨማሪ በእነዚህ ቀበሌዎች ላይ ጥቃት መድረሱን ይናገራሉ። የኮንሶ ዞን ከሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞን ወጥቶ ለብቻው ከተደራጀ በኋላ የመዋቅርና አስተዳደር ጥያቄ አለን የሚሉ ወገኖች ጥቃቱን በመፈፀም እንደሚጠረጠሩም ጨምረው ይናገራሉ። አቶ ዴርሻ ኦለታ የኮንሶ ዞን ኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ሲሆኑ ወደ ሰገን ከተማ ለድጋፍና ክትትል ሥራ ከባልደረቦቻቸው ጋር ያመሩት ባለፈው ሳምንት እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል። በአሁኑ ሰዓት በሰገን ከተማ አስተዳደር ቅጽር ግቢ ውስጥ ወደ 400 የሚሆኑ ሰዎች መንገድ ተዘግቶባቸው ታግተው እንደሚገኙም ያስረዳሉ። ረቡዕ ዕለት ከአካባቢው ለመውጣት ሙከራ ማድረጋቸውን ያስታወሱት ኃላፊው፤ ነገር ግን የፀጥታ ኃይሎች መኪና ተመትቶ አንድ የፖሊስ አባል በመሞቱ ምክንያት መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን ይገልፃሉ። እነዚህ 400 ሰዎች የሰገን ከተማ አስተዳደር ሠራተኞች፣ ተፈናቅለው ወደ አስተዳደሩ መጥተው የተጠለሉና አራት የዞኑ አስተዳደር ሠራተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል። የተፈናቀሉት ሰዎች ከሰገን ከተማ አዲስ ገበሬ እንዲሁም ሰገን ገነት ከሚባል መንደሮች ያለውን ግጭት ሸሽተው የመጡ መሆናቸውን ይገልጻሉ። እነዚህ የተፈናቀሉ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት በልዩ ኃይል ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኙም ይገልፃሉ። ውሎና አዳራችን ቢሯችን ውስጥ ነው የሰገን ከተማ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ከተማ ገለቦም እርሳቸውም ሆኑ ሌሎች የወረዳው አስተዳዳሪዎች በደኅንነት ስጋት ምክንያት ከቢሯቸው ርቀው መሄድ እንደማይችሉ ይናገራሉ። የኮንሶ ዞን ከሰገን አካባቢ ሕዝቦች ወጥቶ ከተደራጀ እና በአካባቢው የሰገን ወረዳን ካደራጀ በኋላ እስከ አሁን ድረስ ባለሙያዎችና አመራሮች ውሎና አዳራቸው በቢሯቸው ውስጥ መሆኑን ይናገራሉ። "ከቢሮ 50 ሜትር ርቀው መሄድ አይችሉም" በማለት "ያለው ነገር ፈር የለቀቀ ይመስለኛል" ሲሉ ሁኔታውን ይገልጹታል። እርሳቸውም ቢሆኑ ውሎ እና አዳራችን ቢሯቸ ውስጥ መሆኑን የተናገሩት አስተዳዳሪው "ቀን ቀን የተኛሁበትን ፍራሸ ከምቀመጥበት ወንበር ጀርባ በማቆም ነው ባለጉዳዮችን የማስተናግደው" በማለት የፀጥታ ስጋቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና የትም ርቀው መሄድ እንደማይችሉ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ግጭቱ በድጋሚ ሲያገረሽ የአካባቢ ሽማግሌዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሞ ሰዎች መሞታቸውንም ይናገራሉ። በአካባቢው የክልሉ ልዩ ኃይል፣ የፌደራል ፖሊሰ እንዲሁም የዞኑ ፖሊስ አባላት ቢኖሩም ጥቃቱ በቀጥታ እነሱም ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ መቆጣጠር ማስቸገሩን ገልፀዋል። ነዋሪዎች ምን ይላሉ? በግጭቱ አባታቸውን ያጡት አቶ ኡርማሌ ኡጋንዴ "አባቴን እንኳ አፈር ማልበስ አልቻልኩም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በግጭቱ ቅዳሜ ዕለት ዘጠኝ ሰዓት ላይ የሰገን ከተማ ላይ ነዋሪ የነበሩት የ58 ዓመት ጎልማሳ እና የ11 ልጆች አባት የሆኑት አቶ ኡጋንዴ አንጋሬ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው እንዳለፈ ልጃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ኡርማሌ እንደሚሉት አባታቸው የቤተ ክርስትያን አገልጋይና የአገር ሽማግሌ የነበሩ ሲሆን በአካባቢው "ሰላምን የማይፈልጉ ኃይሎች እና 'የጉማይዴ ልዩ ወረዳ አስመላሽ' ነን የሚሉ ታጣቂዎ" አባታቸው ላይ ትኩረት አድርገው ጥቃቱን መፈፀማቸውን ገልፀዋል። እነዚህ ታጣቂዎች አባታቸው ላይ ትኩረት ማድረግ የጀመሩት በመንግሥት አስታራቂ ሽማግሌ ተብለው ከተመረጡ በኋላ መሆኑንም ያስታውሳሉ። አቶ ኡጋንዴ አንጋሬ በተገደሉበት ወቅት በቤታቸው እንደነበሩ የተናገሩት አቶ ኡርማሌ፣ ቤታቸው በጥይት ተደብድቦ፣ አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች መካከል አንድ ልጃቸው እግሯን በጥይት ተመትታ በሰገን ሆስፒታል መታከሟን ነግረውናል። እናታቸው እና ሌሎች በቤት ውስጥ የነበሩ ሴቶች ግን በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን እና ያሉበትን ቦታ እስካሁን እንደማያውቁ ገልፀዋል። "ከዚህ በፊት እነዚህ ታጣቂዎች ሌሊት ሌሊት ተደብቀው በመምጣት ጥቃት ይፈፅሙ ነበር" የሚሉት ነዋሪዎቹ አሁን ግን በቀን ጥቃት መሰንዘር መጀመራቸውን ያስረዳሉ። አቶ ኡርማሌ አባታቸው በሰላሙ ጊዜ ቢሆን መቀበር የነበረባቸው በአቅራቢያቸው በሚገኘው የመካነ ኢየሱስ ቅጽር ግቢ ውስጥ መሆኑን አስታውሰው፤ አሁን ግን በሰላም እጦት ምክንያት ካረፉ ከሦስት ቀናት በኋላ በአካባቢው አስተዳደር ግቢ ውስጥ መቀበራቸውን ገልፀዋል። እርሳቸውም መንገድ ዝግ በመሆኑ ወደስፍራው ሄደው "አባታቸውን አፈር ማልበስ" አለመቻላቸውን ይናገራሉ። በሃይሎታ ዱጋቱ የመገርሳ መንደር ነዋሪ የሆኑ እና ስማቸው ለደኅንነታቸው ሲባል እንዳይገለጽ የየጠየቁ ግለሰብ በበኩላቸው ከአካባቢያቸው ሴቶችና ህጻናት ሸሽተው ወደ ሌላ ስፍራ መሄዳቸውን ነግረውናል። እርሳቸውም ማሳላይ የነበረ ጤፍ እና አንድ ቤታቸው ተቃጥሎ ከሌሎች የአካባቢው ወንዶች ጋር በመንደራቸው ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈፀም ለመከላከል መቅረታቸውን ይናገራሉ። "የቻሉ ወደ ካራት ቀበሌ ያልቻሉ ደግሞ ሰላም ወደ ሆኑ ቀበሌዎች ሸሽተዋል" የሚሉት ግለሰቡ እንዲህ አይነት ጥቃት ኮንሶ ዞን ከተመሰረተ ለሦስተኛ ጊዜ እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። "ከዚህ በፊት 2011 ዓ.ም ሚያዚያ ወር ላይ፣ 2012 ዓ.ም ነሐሴ ወር ላይ አሁን ደግሞ 2013 ኅዳር ወር ላጥ ጥቃት ደርሶብናል" በማለት የመንደራቸው ሊቀመንበርን ጨምሮ በርካቶች በታጣቂዎች መገደላቸውን ያስታውሳሉ። የኮንሶ ዞን ኃላፊዎች ምን ይላሉ? የኮንሶ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳና ቀበሌዎች ላይ ታጣቂዎች የሚያደርሱት ጥቃት "ወረራ የሚመስል ነው" ሲሉ ይናገራሉ። በርካታ መንደሮች በእሳት መጋየታቸውን፣ በመሳሪያ የታገዘ ጥቃት እንደሚደርስ እና የፀጥታ ኃይልን እየከበቡ ማጥቃት እንደሚፈጽሙ ይናገራሉ። በዚህም የሰው ህይወት ማለፉን አካል ጉዳት መድረሱንና ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት መውደሙን ይናገራሉ። በዞኑ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የዞኑ፣ የፌደራልና የክልሉ ልዩ ኃይል ቢኖሩም ታጣቂዎቹ እነዚህን ፀጥታ አካላት በቀጥታ ኢላማ በማድረግ እንደሚያጠቁ ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ከሆነ በዞኑ በተፈፀመ ጥቃትም ከ70 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። በአሁኑ ጊዜ የኮንሶ ዋና ከተማ በሆነችው ካራት ከተማ ጭምር የሚኖሩ ሰዎች ስጋት ላይ እንደሚገኙ በመናገር ያለውን ሁኔታ ለክልሉ ማሳወቃቸውን ገልፀዋል። በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ አካባቢ በተደጋጋሚ ስለሚከሰተው ግጭት እንዲሁም ስለደረሰው የጉዳት መጠን ለማወቅ ለዞኑ ዋና እና ምክትል አስተዳዳሪዎች፣ ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለሰላምና ፀጥታ እንዲሁም የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊዎች በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም። የሰገን ሕዝቦች አስተዳደር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ለረጅም ጊዜ የቆየ የወሰንና የአስተዳደር መዋቅር ጥያቄዎች ሲነሱ የነበረ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ በተደጋጋሚ በአካባቢው ባሉ ማኅበረሰቦች ዘንድ ግጭት ሲከሰት ቆይቷል። በእነዚህ ግጭቶች ውስጥ የተደራጁና የታጠቁ ቡድኖች በሚፈጽሟቸው ጥቃቶችም በተለያዩ ጊዜያት በአከባቢው ባሉ ነዋሪዎች ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል። ሰሞኑን የተከሰተው ጥቃትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ እንደሆነ የአካባቢው አስተዳዳሪዎችና ነዋሪዎች ይናገራሉ።
48935081
https://www.bbc.com/amharic/48935081
"ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ
ከ35 ዓመት በፊት ወደ ሱዳን ከተሰደዱ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያዊያን መካከል አራት ልጆች ያሏቸው ጥንዶች ይገኙበት ነበር። ሱዳን ውስጥ ወደሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ለመድረስ ለሳምንታት በእግር ተጉዘዋል። መጠለያው ውስጥ በቂ ምግብና መድሀኒት አልነበረም።
ውጣ ውረዱ የብዙዎችን ሕይወት እንደዋዛ ቀጥፏል። ጥንዶቹም በስደት ላይ ሳሉ ከልጆቻቸው ሁለቱን በሞት ተነጥቀዋል። ኢትዮጵያዊያኑ መጠለያ ውስጥ ለወራት ከቆዩ በኋላ "ኦፕሬሽን ሞሰስ" [ዘመቻ ሙሴ] በተባለ ዘመቻ ወደ እስራኤል ተወሰዱ። ይህም ኢትዮጵያዊያን አይሁዶች ወደ እስራኤል ከተወሰዱባቸው ዘመቻዎች አንዱ ነበር። • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" ጥንዶቹ ይመኟት የነበረውን የእስራኤል ምድር ከረገጡ በኋላ ሕይወትን 'ሀ' ብለው ጀመሩ። ናዝሬት ከተማ ውስጥ። እስራኤል በደረሱ በአራተኛው ዓመት አቨቫ የተባለች ልጅ ተወለደች። አቨቫ ደሴ። "በፀጉሬ ይስቁብኝ ነበር" አቨቫ ያደገችው ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሚኖሩበት መንደር ነው፤ ጓደኞቿም ኢትዮጵያዊያን ነበሩ። እስራኤል ለኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ለሌሎች ጥቁሮችም ምቹ አገር አለመሆኗን የተገነዘበችው ትምህርት ቤት ስትገባ ነበር። የምትማርበት ክፍል ውስጥ የነበሩት ተማሪዎች ነጮች ብቻ ነበሩ። በቆዳ ቀለሟ ይጠቋቆሙ፣ በባህሏ ይሳለቁ፣ በፀጉሯም ይስቁ ነበር። በእስራኤላዊያን ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቷ ኢትዮጵያዊ ማንነቷን ጠላችው። እስራኤላዊያንን ለመምሰል ትጣጣርም ጀመር። "አሁን ስናገረው ያሳፍረኛል፤ ግን ልጅ ሳለሁ በቤተሰቦቼ አፍር ነበር፤ የቤተሰቤን ጉዞና ታሪክ ረስቼ ነበር" ትላለች። አቨቫ እንጀራ አትበላም ነበር። ጓደኞቿ በኢትዮጵያዊነቷ የሚሳለቁባት ስለሚመስላት ወደ ቤቷ ልትጋብዛቸው አትፈልግም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች ከነበሯት መምህራን አንዷን እንዲህ ታስታውሳታለች። • የኤርትራ ዘፈኖች በኢትዮጵያዊ አቀናባሪ "ከነጭ ጓደኞቼ ጋር ስሆን መምህርቷ በጣም በትህትና ሰላም ትለናለች። ከኢትዮጵያዊያን ጓደኞቼ ጋር ስታየኝ ግን እንደ ነጮቹ በትህትና አታዋራንም፤ ትጮህብን ነበር።" "ወደ ማንነቴ የተመለስኩት በሙዚቃ ነው" አቨቫ ሙዚቃ ነፍሷ ነው። ከአራት ታላላቅ እህቶቿ አንዷ የአርኤንድቢ እና ሶል ሙዚቃ ቪድዮ ካሴቶች ታሳያት ነበር። ቤት ውስጥ ታንጎራጉራለች፤ ትደንሳለች። አይን አፋር ስለነበረች ከቤት ውጪ ባታደርገውም። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች ሙዚቃ መጻፍ ጀመረች፤ ነገር ግን ለማንም አታሳይም ነበር። የእስራኤል ወጣቶች ወታደራዊ ግዴታ መወጣት ይጠበቅባቸዋልና አቨቫም ድንበር አካባቢ ተመደበች። "የተሳሳተ ቦታ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር። አገሪቱን ከወታደራዊ አገልግሎት በሌላ መንገድ ማገልገል እንደምችል አምናለሁ። በእርግጥ በወቅቱ ስለ ራሴ ተምሬያለሁ።" ያኔ ሙዚቃ እንዲሁ የሚያስደስታት ነገር እንጂ፤ ከዚያ በዘለለ የሕይወቷ ጥሪ እንደሆነ አታስብም ነበር። እንዲያውም ሥነ ልቦና ማጥናት ነበር ምኞቷ። ሆኖም አንድ ክፉ አጋጣሚ ሕይወቷን እስከወዲያኛው ቀየረው። ከባድ የመኪና አደጋ! ከአደጋው ለማገገም ወደ ሁለት ዓመት ገደማ ወስዶባታል። በእነዚያ ዓመታት ስለ ሕይወት ስታሰላስል "መኖር ያለብኝ የምወደውን ነገር እየሠራሁ ነው" ከሚል ውሳኔ ላይ ደረሰች። • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" "ዘ ቮይስ" የተባለው ታዋቂ የሙዚቃ ውድድር እስራኤል ውስጥ ሲጀመር ተቀላቀለች። ውድድሩ ላይ የአንድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ኃላፊ ተዋውቃ ነበር። ትምህርት ቤቱ ገብታም የጊታርና የድምፅ ትምህርት መውሰድ ጀመረች። በሙዚቃ ትምህርት ቤቱም ስለ "አፍሮ ፖፕ" ስልት ስትማር ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃም ሰማች። ችላ ካለችው ኢትዮጵያዊ ማንነት ጋር በሙዚቃ ታረቀች። "ወደ ማንነቴ ያደረኩት ጉዞ የተጀመረው በሙዚቃ ነው። ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ መማር ጀመርኩ። ስለ ኢትዮጵያ ባህል ማጥናትና አማርኛ መለማመዱንም ተያያዝኩት። ጊዜ ቢወስድብኝም ቤቴ የምለው አገር እንዳለኝ ተገነዘብኩ። የወላጆቼን ሙዚቃ ወደድኩት።" አቨቫ አሁን 31 ዓመቷ ነው። ሦስት አልበሞች አሳትማለች። "ኢን ማይ ቶውትስ" [በሀሳቤ]፣ "ሁ አም አይ" [ማነኝ?]፣ "አይ አም አቨቫ" [አቨቫ እባላለሁ] የተሰኙ። ሙዚቃዎቿ ዘረኝነትን የሚያወግዙ፤ ፍቅርና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው። • "የሚያክሙን ሙዚቃዎች እንዳሉ ሁሉ የሚያውኩንም አሉ" ዶ/ር መልካሙ ከኢትዮጵያ ሙዚቃና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከሆነ ነገር ጋር በፍቅር ወድቄያለሁ የምትለው አቨቫ፤ በሙዚቃዋ የአማርኛ ስንኞች ታካትታለች፤ ዘፈኖቿን በመሰንቆና ክራር ታጅባለች። ቪድዮ ክሊፕ ስትሠራ የአገር ባህል ልብስ ለብሳ፣ ሹሩባ ተሠርታም ነው። ባለፉት ሦስት ዓመታት በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝታለች። ሸራተን አዲስ በነበረ የሙዚቃ ትርዒትም ተሳትፋለች። የጥላሁን ገሠሠ፣ የመሀሙድ አህመድ፣ የጂጂ (እጅጋየሁ ሽባባው) እና የቴዲ አፍሮ (ቴዎድሮስ ካሳሁን) ሙዚቃዎችን ታቀነቅናለች። በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ሳለች የጂጂን ዘፈን ዳግመኛ ሠርታ እንጦጦ ተራራ ላይ ቪድዮ ክሊፕ ሠርታለች። "ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴን እንዴት ብዬ ልተው. . . " አቨቫ ራሷን በጊታር አጅባ የምታዜመው ዘፈን ነው። ሶል፣ አርኤንድቢና የኢትዮጵያ ሙዚቃ ሦስት የምትወዳቸው ስልቶች ናቸው። ሶል እና አርኤንድቢ ውስጥ መሰንቆና ክራር ብዙም አለመለመዱ ሥራዎቿን ተወዳጅ እንዳደረጋቸው ታምናለች። "ጥቁር ስለሆንሽ እልወድሽም" ዘረኛነት በተንሰራፋበት ማህበረሰብ ውስጥ መኖር፣ የራስን ማንነት ጥያቄ ውስጥ ማስገባትና በስተመጨረሻም ከራስ ጋር መታረቅ ለአቨቫ ሙዚቃ ግብዓት የሆኑ የሕይወት ተሞክሮዎች ናቸው። ከተሞክሮዎቿ አንዱን እንዲህ ታወሳለች። "ከጥቂት ዓመታት በፊት መዋዕለ ህጻናት ውስጥ ሠርቼ ነበር። ሁሉም ህጻናት ነጭ ነበሩ። ልጆቹን ባጠቃላይ ወድጃቸው ነበር። አንድ ቀን አንድ አስተማሪ ልጆቹ ወደ ክፍል እንዲገቡ እንድጠይቃቸው ነገረኝ። ተማሪዎቹን ስጠራቸው አንድ ልጅ ወደ ውስጥ መግባት አልፈለገም ነበር። ከዚያ አናገርኩት. . . 'እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል?' ስለው 'እኔ ግን አልወድሽም' አለኝ? 'ለምን?' ስለው 'ጥቁር ስለሆንሽ' አለኝ። ልጁ አምስት ዓመቱ ነበር፤ ብዙ ኢትዮጵያዊያንን አልተዋወቀም። ግን ጥላቻን ተምሮ ነበር። ከጥቂት ወራት በኋላ ከልጁ ጋር ወዳጆች ሆንን። የተናገረውን ነገር ትርጉሙን ተረድቶና ሆነ ብሎ እንዳላላው አውቃለሁ።" ይህ ማህበረሰቡ እንዴት እንደሚያስብ ካየችባቸው አጋጣሚዎች አንዱ ነበር። ከማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግሮች አንዱን እንደ መነሻ አድርጋ "ብላክ" [ጥቁር] የተሰኘ ሙዚቃ የጻፈችውም በዚህ ምክንያት ነበር። • "ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" አሊ ቢራ በሙዚቃዎቿ ስለ ቤተሰቦቿ ሕይወትም ታወሳለች። ልጅ ሳለች እናቷ ይነግሯት ከነበረው ታሪክ ተነስታ ስለ ቤተሰቦቿ የትውልድ ቀዬ እንፍራዝ ዘፍናለች። "ሙዚቃ ሕክምና ነው" ሀሳቧን፣ ቢሆን ብላ የምትመኘውንም በሙዚቃዎቿ ታስተላልፋለች። "ውስጤ የሚንቀለቀሉና ማውጣት እንዳለብኝ የሚሰሙኝ ስሜቶችን በሙዚቃ እገልጻቸዋለሁ። ሙዚቃ መጻፍ ሕክምና ነው። ብዙዎቹ ዘፈኖቼ ስለ ውጣ ውረድ ይናገራሉ። መልስ ለማግኘት ያለሙም ናቸው።" "አይ ዋነ ጎ" [መሄድ እፈልጋለሁ] እናቷን አጥታ ግራ ስለተጋባች ትንሽ ልጅ ይተርካል። በፍቅር ከፍታ ውስጥ ሳለሁ የጻፍኩት የምትለው "ማይ ኸርት" [ልቤ] የተሠራው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ምት፣ እስክስታ ተጨምሮበት ነው። አቨቫ ማየት የምትፈልገውን እኩልነት የሰፈነበት ዓለም በሙዚቃዎቿ ታስተጋባለች። "ሰውን በአካል ማጥቃት ብቻ ሳይሆን ዘረኛ ንግግርም ያማል። 'ኢትዮጵያዊያን ባጠቃላይ ጥሩ ናችሁ' ይባላል። ነገር ግን እኛ አንድ ሰው አይደለንም። የተለያየ ባህሪ አለን። በሙዚቃዬ ማሳየት የምፈልገውም ይህንን ነው።" "ከለር" [ቀለም] የተባለ ዘፈኗ ሁለት የተለያዩ ሰዎች፤ አንዳቸው ሌላቸውን ለመቀየር ሳይሞክሩ በመቻቻል ስለሚኖሩበት ዓለም ይተርካል። የእስራኤል ማህበረሰብ ኢትዮጵያዊያንን እንዳሉት ባለመቀበሉ ራሷን ለመቀየር መሞከሯን ታስታውሳለች። "እስራኤላዊ ከመሆንና ኢትዮጵያዊ ከመሆን መካከል መምረጥ እንዳለብኝ ይሰማኝ ነበር። ሁለቱንም መሆን እንደምችል፣ መደበቅ ሳይሆን መኩራት እንዳለብኝ ለመረዳት ዓመታት ወስዶብኛል። እስራኤል የብዙ ባህሎች አገር ናት። ይህም ውብ ነው። ሰዎችን ለመቀየር መሞከሩን ትተን በመከባበርና በመፈቃቀር መኖር አለብን።" "መንግሥት ለእኛ ቅድሚያ አይሰጥም" ኢትዮጵያዊያን በእስራኤል ፖሊሶች የሚደርስባቸውን ጥቃት በመቃወም በርካታ ሰልፎች ተደርገዋል። በትምህርትና በሥራው ዘርፍ ያለውን መድልዎ በመቃወምም በርካቶች ድምጻቸውን አሰምተዋል። ሆኖም ይህ ነው የሚባል ለውጥ የመጣ አይመስልም። ከሳምንታት በፊት ሰለሞን ተካ የተባለ ቤተ እስራኤላዊ ሥራ ላይ ባልነበረ ፖሊስ መገደሉ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም ከታዩ የተቃውሞ ሰልፎች በተለየ ጠንካራ ተቃውሞ ተካሂዶ ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች ተዘግተውም ነበር። "የተቃውሞ ሰልፍ ሲካሄድ 'ወደ ኢትዮጵያ መልሷቸው የሚሉ አሳዛኝ መልዕክቶች አያለሁ። በጣም የከፋ ደረጃ ላይ እንደደረስን ይሰማኛል። ህመሙና ተስፋ መቁረጡን እረዳለሁ። በፖሊስ ጭካኔ ምክንያት በተለይ ኢትዮጵያዊያን ወንዶች መንገድ ላይ ለመሄድ እንኳን ይፈራሉ። ለሕይወታቸው እየታገሉ ነው። ለብዙ ጊዜ የታመቀ ቁጣ ነው የገነፈለው" ትላለች ሙዚቀኛዋ። መዋዕለ ህጻናት ኢትዮጵያዊያን ህጻናትን መቀበል አይፈልጉም። በሥራ ቦታም ኢትዮጵያዊያን እንደሚገለሉ ትናገራለች። ሁሌም የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ መንግሥት 'ለውጥ ይመጣል' ብሎ ቃል ቢገባም አንዳችም መሻሻል እንዳላዩ ትገልጻለች። መንግሥት ለጥያቄዎቻቸው መልስ የማይሰጠው ለኢትዮጵያዊያኑ ጉዳይ ቅድሚያ ስለማይሰጥ እንደሆነም ታክላለች። "ቤተሰቦቼ እስራኤል ከመጡ ጀምሮ ስለዚህ ነገር ይወራል። ያኔም ተቃውሞ ነበር፤ አሁንም አለ። የተለወጠ ነገር ግን የለም።" ሆኖም ተስፋ አልቆረጠችም። ነገሮች የተሻሉ እንደሚሆኑም ትጠብቃለች። "ሙዚቃዬ ሩስያ መድረሱን አላወኩም ነበር" እስራኤል ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞች መበራከታቸው ማህበረሰቡ ስለ ቤተ እስራኤላዊያን ባህል እንዲረዳ እንደሚያግዝ ታምናለች። ሙዚቃቸው አሁን ካለበት በላይ እንደሚያድግም ተስፋ ታደርጋለች። ከኢትዮጵያዊያንና ከእስራኤላዊያን አድማጮቿም ጥሩ ምላሽ እያገኘች እንደሆነ ትናገራለች። • "ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" አሊ ቢራ "ማኅበራዊ ጉዳዮችን ስዳስስ ድምፅ እየሆንኳቸው እንደሆነ አምናለሁ። ቤተሰቦች 'ለልጆቻችን አርዓያ ነሽ' ሲሉኝ በጣም እኮራለሁ። ምክንያቱም በኔ ትውልድ ብዙም ስኬታማ ጥቁር ሴት አርዓያ የለንም።" አቨቫ በሙዚቃ ሕይወቷ እጅግ ከኮራችባቸው ቅጽበቶች አንዱ የገጠማት ሩስያ ሳለች ነው። አንድ ፌስቲቫል ላይ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ነበሩ። የድምፅ ሙከራ ስታደርግ ሰዎች አብረዋት ይዘፍኑ ነበር. . . "ምን?!. . . በጣም ነው የገረመኝ. . . ሙዚቃዬ ሩስያ መድረሱን አላወኩም ነበር". . . ሙዚቃ ስትጀምር ቤተሰቦቿ እምብዛም አይደግፏትም ነበር። ዛሬ ግን ከትርዒቶቿ አይቀሩም። ልጅ ሳለች እናቷ ያንጎራጉሩላት እንደነበር ታስታውሳለች። አንድ ቀን ከእናቷ ጋር በጥምረት የመሥራት ምኞትም አላት። በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊነት ትርጉም የማይሰጣት አቨቫ ዛሬ ትልቁ ህልሟ ኢትዮጵያ ውስጥ ሙዚቃዎቿን ማቅረብ ነው። እናቷ የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው ከአንድም ሁለት ሥራ እየሠሩ እንዳሳደጓቸው ታስታውሳለች። በአንድ ወቅት ይህንን ባትገነዘብም አሁን ላይ ተቀይራለች። "አሁን ትልቅ ሴት ሆኜ ሳየው ቤተሰቦቼ ጀግኖቼ ናቸው። እናቴ ጀግናዬ ናት። በጣም እኮራባታለሁ።" እስራኤል ውስጥ ያለውን መደልዎ በመቃወም ሰልፍ ሲካሄድ እናቷን ተመሳሳይ ጥያቄ ትጠይቃለች። "እዚህ በመምጣታችሁ ደስተኛ ናችሁ?" እናቷ ሁሌም የሚሰጧት መልስ ተመሳሳይ ነው። "ቦታዬ እዚህ ነው፤ ሌላ ቦታ መኖር አልፈልግም፤ ብዙ ውጣ ውረድ ቢኖርብንም እዚህ በመኖሬ እኮራለሁ።"
news-56045020
https://www.bbc.com/amharic/news-56045020
ትግራይ፡ ፀረ መንግሥት ተቃውሞች በትግራይ የሰዎች ሕይወት መቅጠፋቸው ተነገረ
በትግራይ ክልል በዚህ ሳምንት በተነሳው ተቃውሞ ቢያንስ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ።
የመቀለ ከተማ ከተቃውሞው በፊት ከአዲስ አበባ የተላኩ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎችን ወደ መቀለ መምጣትን በመቃወምም ሰልፈኞች በጎዳናዎች ላይ ጎማ ሲያቃጥሉ እንዲሁም በርካቶች ቤት ውስጥ በመቀመጥ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። ልዑካኑ ከክልሉ የተለያዩ የማህበረሰብ አባላት ጋር የሰላም ውይይት ለማድረግ ነው የመጡት ተብሏል። እንግዶቹ በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ምሽት፣ የካቲት 1/2013 ዓ. ም ላይ ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ተከትሎ ነዋሪው ላይ ቁጣ ማስከተሉን የአይን እማኞች ይናገራሉ። በርካታ ተጋሩዎች የልዑካኑን ቡድን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተወሰደውን ወታደራዊ እርምጃ በመደገፍ ከመንግሥት ጎን ቆመዋል በማለት ይወነጅሏቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የክልሉን ህዝብ ጥሪ ችላ ብለዋልም ይሏቸዋል። "መቀለ አሁንም ቢሆን ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ የሌለባት ከተማ ናት። የተወሰነ በሚባል መልኩ ወይም ደግሞ ምንም አይነት የሰዎች እንቅስቃሴ የለም። ሱቆችም ሆኑ የግል ተቋማት ተዘግተዋል። በከተማዋ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት የለም" በማለት አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ በዚህ ሳምንት ረቡዕ ዕለት ተናግረዋል። ከመቀለ በተጨማሪ በሽረ፣ አዲግራት እንዲሁም ከመቀለ 45 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ውቅሮ በተከሰተ ተቃውሞ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የውቅሮ ነዋሪ የሆነና ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የህክምና ባለሙያ ተናግረዋል። የመቀለ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጠዓመ በበኩላቸው ተቃውሞውን አውግዘው "ለዘረፋ ለስርቆት እንዲመቻቸው ተራ ዱርየዎች ያወጁት ነው" ማለታቸውን የአካባቢው ሬድዮ በዘገባው አሰምቷል። የፌደራል መንግሥቱ የክልሉን መዲና መቀለን ህዳር 19፣ 2013 ዓ. ም መቆጣጠሩን ተከትሎ ውጊያው ማቆሙን ገልጿል። ይህ ሁኔታ በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት በሚመራው የትግራይ ኃይሎች በጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም የተነሳው ግጭት መቋጫ ተደርጎም ታይቷል። ምንም እንኳን መንግሥት ወታደራዊ እርምጃው ተጠናቋል ይበል እንጂ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ ሌሎች የረድዔት ድርጅቶች በአንዳንድ የትግራይ ክፍሎች ውጊያው እንደቀጠለ ይናገራሉ። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። ህዝቡን ያስቆጣው ምንድን ነው? የሰሞኑ ተቃውሞ የፌደራል መንግሥቱ መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ የተነሳ የመጀመሪያ ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው። በህዝባዊ ስብሰባው ላይ የአካቢቢውን የሃይማኖት አባቶች ወክለው እንዲሳተፉ ተጠርተው የነበሩ ግለሰብ እንደሚናገሩት የሰላም ውይይት የሚለው ጉዳይ የህዝቡን "ቁጣ እንዳገነፈለው" ነው። "እነዚህ የሃይማኖት አባቶች ህዝቡ አንድ ላይ እንዲመጣ ይፈልጋሉ። በችግራችን ወቅት የት ናችሁ? ብለው አልጠየቁንም። በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ታጅበው በትግራይ ሰላም ሰፍኗል የሚል ገፅታን ለመፍጠር እየሞከሩ ነው ይህ ደግሞ ሀሰት ነው" ብለዋል። ግለሰቡ ራሳቸው ህዝባዊ ጉባኤው ሊጀመር 20 ደቂቃ ሲቀረው ለጉባኤው እንዲሳተፉ እንደተጠሩና ግብዣውንም ውድቅ ማድረጋቸውን ይናገራሉ። "ትግራይ በጦርነት ላይ ናት። ህዝብ በየቀኑ እየሞተ ነው። እንደ ሃይማኖት አባት እንዲህ አይነት ግብዣን አልቀበልም። የደረሰውን ግፍ ሳያወግዙ የሰላም ድርድር ምን ማለት ነው? በርካታ ካህናት ሲገደሉ፣ አብያተ ክርስቲያናትና የእምነት ተቋማት ሲቃጠሉና ሲወድሙ እነዚህ የእምነት ተቋማት አንዲት ቃል ትንፍሽ አላለሉም" ይላሉ። መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ለወሰደው ወታደራዊ እርምጃ በርካታ የእምነት ተቋማት ድጋፋቸውን ያሰሙ ሲሆን ይህም በርካታ ተጋሩዎችን አስቆጥቷል። የትግራይ ክልል የህዝብ ግንኙነት እቴነሽ ንጌሴ በበኩላቸው "ነዋሪው ከቤት እንዳይወጣና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም ሃሰተኛ መረጃ ተሰራጭቷል" ብለዋል። አክለውም " ህዝባዊ ጉባኤው የተካሄደው በሃይማኖት አባቶቹና በአካባቢው ተወካዮች መካከል ነው። ከተማዋን ለመጎብኘት ሲመጡ እነዚህ ልዑካን የመጀመሪያዎቹ አይደሉም። በዚህ ወቅት የመጡት በትግራይ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ለመመልከትና ቁልፍ የሚባሉ ጉዳዮችም ላይ ለመወያየት ነው" በማለት ይናገራሉ። በፌደራል መንግሥት የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ነዋሪዎች ከአስተዳደሩ ጋር እንዲሰራ ይፋዊ መግለጫ መሰጠቱን ያወሳሉ። "ችግሮች ካሉ ቢነግሩን እናሻሽላለን። ያለበለዚያ እንዲህ አይነት ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ሰላሙን የሚያጠለሹና ወደኋላም የሚጎትቱን ናቸው" በማለት ይናገራሉ። በተቃውሞው ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ምን ያህል ነው ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሟቾችም ሆነ የቁስለኞች ቁጥርን በተመለከተ መረጃ እንደሌላቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። ማክሰኞ የተፈጠረው ምንድን ነው? ተቃውሞውን ማን እንዳስተባበረው ግልጽ አይደለም። አብዛኛው ነዋሪ ከቤት አልወጣም ነበር። መደብሮችና ሌሎችም የግል ድርጅቶች ዝግ ነበሩ። አንድ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአይን እማኝ "ትራንስፓርት አልነበረም" ሲሉ በስልክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጸጥታ ኃይሎች ነዋሪዎች ሱቃቸውን እንዲከፍቱ ሲያስገድዱ እንደነበር የገለጹት የአይን እማኙ "በፕላኔት ሆቴል የተካሄደውን ጉባኤ ሰዎች እንዲሳተፉ ሲገደዱ ነበር። ይህም በአብዛኛው የከተማው አካባቢዎች ወጣቶች በድንጋይ መንገድ እንዲዘጉና ጎማ እንዲያቃጥሉ ምክንያት ሆኗል" ብለዋል። አንዳንዶቹ ወጣቶች የጸጥታ ኃይሎች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ፤ የጸጥታ ኃይሎቹ በምላሹ ተቃዋሚዎቹ ላይ ጥይት እንደተኮሱም የአይን እማኙ ለቢቢሲ ይናገራሉ። በመቀለ በሚገኝ ሆስፒታል የሚሠሩ ባለሙያ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ስምንት ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ሆስፒታል ሄደዋል። አዲሀዋሲ ሰፈር የሚኖሩ አንድ ግለሰብ እንዳሉት በተለያዩ ቦታዎች ፍተሻ እየተካሄደ ነበር። በከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ ጥበቃ ሲደርግና የጸጥታ ኃይሎች እየተዘዋወሩ ሲቆጣጠሩም ነበር ሲሉም አክለዋል። አይደር አካባቢ የሚኖሩ ሌላ ግለሰብ ረቡዕ ምሽት የተኩስ ድምጽ እንደሰሙና የጸጥታ ኃይሎች ከመንገድ ዘወር እንዲባል ማድረጋቸውን አስረድተዋል። የመቀለ ከተማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነዋሪዎች ሱቃቸውን እንዲከፍቱና አለበለዚያ ግን የከተማ መስተዳድሩ በሕግ እንደሚጠይቃቸው ማስጠንቀቃቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በተቃውሞው ተሳትፈዋል የተባሉ 12 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት "ብዙ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉና እየተደበደቡም "ነው። በሌሎች ከተሞች የተነሱ ተቃውሞዎች ተቃውሞ ከተነሳባቸው ከተሞች አንዷ ውቅሮ ናት። ተቃውሞው የተቀሰቀሰው ረቡዕ ጠዋት፣ የካቲት 3/2013 ዓ.ም ነበር። አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደገለጹት የሃይማኖት መሪዎች ወደ ውቅሮ ሄደው ከነዋሪዎች ጋር የሰላም ውይይት እንደሚያደርጉ እየተወራ ነበር። ይህንን ተከትሎም ሁሉም መደብሮችና መንገድም እንደተዘጋ እንዲሁም አንዳንድ ተቃዋሚዎች ጎማ እንዳቃጠሉ ነዋሪው ገልጸዋል። ረቡዕ እለት ስልክ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት ተቋርጦ ነበር። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሕክምና ባለሙያ "መንገድ ላይ ነበርኩ። ከዚያም የተኩስ ድምጽ ሰማን። ሁላችንም ወደየቤታችን መሮጥ ጀመርን። ኢላማ የተደረጉት መንገድ ላይ ቀርተው የነበሩ ሰዎች ናቸው" ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለሙያውን ስናናግራቸው ከጎረቤቶታቸው ሁለት ሰዎች እንደተገደሉ ገልጸውልናል። ሟቾቹ ጋሪ በመንዳት ይተዳደሩ ነበር።፣ በርካቶች ጉዳት ሲደርስባቸው፤ ስምንት ሰዎች ደግሞ እንደሞቱ ተገልጿል። ከሞቱት ሰዎች መካከል አንድ የቀበሌ 16 ነዋሪ፣ ሁለት በቅሳነት ትምህርት ቤት እቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ እና አንድ ሌላ በመቀለ ጫፍ የሚኖሩ ሰው እንደሚገኙበትም ለቢቢሲ ገልፀዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት፤ ከተገደሉት ሰዎች መካከል እርዳታ ለመውሰድ ከገጠር ከተሞች የሄዱ ይገኙበታል። ሐሙስ ዕለት የሁለት ሰዎች ሥርዓተ ቀብር፣ ረቡዕ ዕለት ደግሞ የሦስት ሰዎች ሥርዓተ ቀብር በእንዳ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። ሌሎች ሁለት ግለሰቦች በእንዳ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ተቀብረዋል። በጉዳዩ ላይ የፌደራል መንግሥት እስካሁን አስተያየት አልሰጠም። ቢቢሲ የክልሉን ቃል አቀባይ ጨምሮ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ምላሽ ለማግኘት እየሞከረ ነው። ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ሐሙስ እለት ነገሮች መሻሻል አሳይተዋል። ጥቂት ሰዎች ከቤት መውጣትም ጀምረዋል። ግጭቱ ከተጀመረ 100 ቀናት ያለፉ ሲሆን፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ትግራይ ውስጥ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በተጨማሪም ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ሱዳን ተሰደዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአውሮፓ ሕብረት በክልሉ የተከሰው ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያሰጋቸው ገልጸው፤ እርዳታ ሰጪዎች ያለ ምንም ገደብና ክልከላ ወደ ክልሉ እንዲገቡ ጠይቀዋል። መደፈር፣ ብሔርን መሠረት ያደረገ ግድያ፣ መታፈን እና ዘረፋ ሪፓርት መደረጋቸውን በተመለከተ በገለልተኛ አካል እንዲጣራም አሳስበዋል። ባለፈው ሳምንት የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች ምግብ ማድረስ ለመጀመር ስምምነት አድርገዋል።
sport-45245940
https://www.bbc.com/amharic/sport-45245940
በሁለተኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች የትኞቹ ተጫዋቾች ልቀው ታይተዋል?
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዋች የአምና አሸናፊዎቹ ማንቸስተር ሲቲዎች ሃደርስፊልድ ላይ 6 ግብ ያስቆጠሩበት፤ ብራይተኖች በድጋሚ አስገራሚ ድል ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ የተቀዳጁበትና ቼልሲ የለንደን ተቀናቃኛቸው አርሰናልን 3 ለ 2 ያሸነፉበት ሆኖ አልፏል።
በሌሎች ጨዋታዎች በነሃሴ ወር ምንም ግብ ማስቆጠር ያልቻለው የቶተንሃሙ ሃሪ ኬን አንድ ግብ ሲያስቆጥር፤ የኤቨርተኑ አዲስ ፈራሚ ሪቻርልሰን አሁንም ግብ ማስቆጠር ችሏል። ነገር ግን በሳምንቱ መጨረሻ ድንቅ ብቃታቸውን ካሳዩ ተጫዋቾች መካከል የትኞቹ በጋሬት ክሩክ ምርጥ 11 ውስጥ ገቡ? ግብ ጠባቂ- ጆርዳን ፒክፎርድ የሳውዝሃምፕተኑ አዲስ አጥቂ ዳኒ ኢንግስ ወደ ግብ የሰደዳትን ኳስ ያዳነበት መንገድ እጅግ አስገራሚ ነበር። የኤቨርተኑ ግብ ጠባቂ በሌላ አጋጣሚ ስህተት ሰርቶ የነበረ ቢሆንም፤ ወዲያውኑ ስህተቱን አስተካክሎ ኳሱን ግብ ከመሆን አድኖታል። • አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ • ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን? • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ ተከላካዮች- ሼን ዳፊ፥ ስቲቭ ኩክ፤ ቤንጃሚን ሜንዲ ሼን ዳፊ: ባለፈው ሳምንት የብራይተኑ አሰልጣኝ ቡድኑ በዋትፎርድ ሲሸነፍ ተጫዋቾቹን በእጅጉ የኮነነ ቢሆንም፤ በዚህ ሳምንት ማንቸስተርን ባሸነፉበት ጨዋታ ግን አስራ አንዱም ተጫዋቾች ድንቅ ብቃታቸውን አሳይተዋል ብሏል። ብዙ ሙገሳ ካገኙት ተጫዋቾች መካከል ደግሞ ተከላካዩ ሼን ዳፊ አንዱ ነበር። ሼን የማንቸስተር የፊት መስመር ተጫዋቾችን ፋታ ነስቷቸው ነበር። ስቲቭ ኩክ: የበርንማውዙ የመሃል ተከላካይ ስቲቭ ቡድኑ ገና ወደ ፕሪምር ሊጉ ሳይቀላቀል ጀምሮ በታማኝነት ሲያገለግል የነበረ ተጫዋች ነው። ከዌስትሃም ጋር በነበራቸውም ጨዋታ ወጥ የሆነ አቋሙን ማሳየት ችሏል። ቤንጃሚን ሜንዲ: የቤንጃሚን ሜንዲ በሲቲ ቤት ወደ ቋሚ አሰላለፍ መመለስ ከማንም በላይ የጠቀመው ለአጥቂው ሰርጂዮ አጉዌሮ ነው። ምክንያቱም ሜንዲ ጉልበቱንና ፍጥነቱን ተጠቅሞ ወደፊት በመውጣት የሚያሻማቸው ኳሶች ለአጉዌሮ ብዙ የግብ እድሎችን እየፈጠሩለት ነው። ሃደርስፊልድ ላይ 6 ግብ ባስቆጠሩበት ጨዋታም ይህንኑ ነው ማድረግ የቻለው። አማካዮች- ጊልፊ ሲጉድሰን፤ ዳቪድ ሲልቫ፤ ጄምስ ማዲሰን፤ ማርኮስ አሎንሶ ጊልፊ ሲጉድሰን: ይህ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ባለፈው የውድድር ዘመን ብዙ ገንዘብ ወጥቶተበት ወደ ኤቨርተን ቢዘዋወርም፤ አስደሳች ጊዜ አላሳለፈም ነበር። በዚህ ዓመት ግን በአዲሱ አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ስር ሆኖ ድንቅ ብቃቱን የሚያሳየን ይመስላል። አይስላንዳዊው ሲጉድሰን ከሳውዝሃምፕተን በነበራቸው ጨዋታ አስገራሚ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሎ ነበር። ዳቪድ ሲልቫ: ሲቲዎች ሃደርስፊልድን ስድስት ለምንም በረመረሙበት ጨዋታ ዳቪድ ሲልቫ የቡድኑን ጨዋታ ሲያቀጣጥልና የመሃሉን ስፍራ በተገቢ ሁኔታ ሲመራ ነበር። ማንቸስተር ዩናይትዶች በብራይተን ከተሸነፉ በኋላ ሲቲዎች ሊያቆሟቸው የሚችሉት ሊቨርፑሎች ብቻ ይመስላሉ። • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት • የእግር ኳስ ማልያዎች ለምን ውድ ሆኑ? • የጀግና አቀባበል ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጄምስ ማዲሰን: ብራይተኖች በቻምፒዮንሺፑ በነበሩባቸው ጨዋታዎች ብዙም ብቃቱን ማሳየት ያልቻለው ማዲሰን ማንቸስተር ዩናይትድን ባሸነፉበት ጨዋታ ግን አስገራሚ ነበር። ይህ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ባለፈው ሳምንት ዎልቭስ ላይ ግብ ያስቆጠረ ሲሆን፤ አመቱ ጥሩ የሚሆንለት ይመስላል። ማርኮስ አሎንሶ: የቼልሲው አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ከአንቶኒዮ ኮንቴ ለየት ያለ አዲስ አይነት ቡድን ይዘው የመጡ ይመስላል። ይህ አጨዋወት ከተስማማቸው ተጫዋቾች መካከል ደግሞ አሎንሶ አንዱ ነው። በነጻነት እተጫወተ ነው። የማሸነፊያዋን ሶስተኛ ግብም ማስቆጠር ችሏል። አጥቂዎች- ካሉም ዊለሰን፤ ሰርጂዮ አጉዌሮ፤ ሃሪ ኬን ካሉም ዊለሰን: የቦርንማውዙ ዊልሰን ቡድኑ ከዌስትሃም ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች እስካሁን አምስት ጊዜ ግብ አስቆጥሯል። በቅዳሜው ጨዋታም ሶስት የዌስትሃም ተጫዋቾችን አልፎ ያስቆጠራት ግብ ብቃቱን የምታሳይ ነች። ሰርጂዮ አጉዌሮ: አርጀንቲናዊው አጥቂ ወደ አስፈሪ አቋሙ የተመለሰ ይመስላል። ሃደርስፊልድን ስድስት ለአንድ ሲያሸንፉ፤ ሶስት ግቦችን አስቆጥሮ ሃትሪክ መስራት ችሏል። ከአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ጋርም ቢሆን ግንኙነታቸው የሰመረ ይመስላል። ተቀይሮ ሲወጣም አሰልጣኙ ደስታውን በመሳም ገልጾለታል። ሃሪ ኬን: ሃሪ ኬን በመጨረሻም በነሃሴ ወር ያጋጠመውን የጎል ድርቅ መስበር ችሏል። እንደውም ያባከናቸው ሌሎች ግብ ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎች ተጠቅሞ ቢሆን ኖሮ ሃትሪክ መስራት ይችል ነበር።
news-48754366
https://www.bbc.com/amharic/news-48754366
"ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል" ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ
ቅዳሜ ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ የተገደሉትን ሁለት ጄነራሎች ለመሸኘት በሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ በተደረገው ሥነ ሥርዓት ላይ የሃገሪቱን ፕሬዝዳንታና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከባለስልጣኖቻቸው ጋር ከፊት መስመር ላይ ተቀምጠው እያለቀሱ በሃዘን ውስጥ ሆነው በተደጋጋሚ በቴሌቪዥን መስኮት ላይ ቢታዩም በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር አላደረጉም። • ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሟቾቹ ጄነራሎች ልጆች እንዲሁም የጄነራል ሰዓረ ምክትል የሆኑት ጄነራል ብርሃኑ ጁላና የቅርብ ጓደኛቸው ጄነራል አበባው ታደሰ በእንባና በሃዘን የታጀበ ጠንካራ ንግርር አድርገዋል። "ሠራዊታችንን ለመገንባት ሞዴል የሆኑን የጦር መሪ ናቸው።" ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ፤ የጄነራል ሰዓረ በ17 ዓመት የነበራቸው አጠቃላይ የትግል እንቅስቃሴ፣ ሠራዊታችንን ለመገንባት እንደ ሞዴል የተጠቀምንበት ታሪክ ነው ብለዋል። በሠራዊት ግንባታ፣ በውጊያ ዝግጅት፣ በውጊያ አመራር፣ በጀግንነት፣ ችግሮችን ጥሶ በማለፍ፣ ፅናት የተላበሰ የሠራዊት ጄነራል ናቸው ሲሉ ገልፀዋቸዋል። • በሃየሎም ይምሉ የነበሩት ጄነራል ሰዓረ መኮንን ማን ናቸው? "እንደ እሳቸው ዓይነት ወታደራዊ አመራሮች የሚያንፀባርቁት፣ የሚያሳዩትና የሚውሉበት ውሎ ትውልድን የሚቀርፅ ነው" ያሉት ምክትል ኤታማዦር ሹሙ፤ ጄነራል ሰዓረን የመሰሉ ሌሎች ጀግኖች እንደ ሞዴል እየወሰድን ሠራዊታችንን ሀገሩን መከላከል የሚችልና ለሌሎች የሚተርፍ ጀግና ሠራዊት ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዋነኛ ምሳሌ እንደነበሩ ተናግረዋል። ጄነራል ገዛኢንም አንስተው ለዚህች ሀገር የለፉ ሰው ናቸው በማለት ከሕገ-መንግሥት ምስረታ በኋላ የመከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ትልልቅ ሥራ ሰርተዋል ሲሉ መስክረዋል። ጄነራል ገዛኢ የመከላከያን ሎጀስቲክ ያደራጁና ባህሉን የገነቡ ናቸው ያሉት ጄነራል ብርሀኑ "የሎጀስቲክ መሀንዲስ ብለን ነው የምናውቃቸው" ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። "ፈጥኖ መዘጋጀት የሚችል ከፍተኛ ኃይል በአንድ ጊዜ ማንቀሳቀስ የሚችል ለሎጀስቲክ የተፈጠረ በሳል መሪ ነበሩረው" ሲሉም አወድሰዋቸዋል። • የሥራ ኃላፊነታቸውን "ከባድና የሚያስጨንቅ... ነው" ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ? ከጄነራል ሰዓረ ጋር በቅርብ አልሰራሁም ያሉት ምክትል ኢታማዦር ሹሙ እርሳቸው ማዕከላዊ ዕዝ ሆነው ጄነራል ሰዓረ በሌሎች ዕዞች ውስጥ ሆነው እንደሚተዋወቁ ጠቁመው፤ "ጄነራሉ በግል ባህሪያቸው የተረጋጉ፣ ሌላውንም የሚያረጋጉ፣ ሰው አክባሪ ናቸው" በማለትም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። እንደዚህ በ30 እና በ40 ዓመት የሚፈጠሩ ጄነራሎችም ይሁን የሀገር መሪዎችን ማጣት ያማል ያሉት ጄነራል ብርሀኑ አሟሟታቸውን በማንሳት ቁጭታቸውን ከእንባቸው ጋር እየታገሉ ገልፀዋል። "ለሀገር እየሰራ፣ ሁሉንም እያቻቻለ፣ ሁሉንም እያገለገለ፣ ሁሉንም እየሰማ፣ ሁሉንም እያስተናገደ ባለበት ወቅት፤ ምን በድሎ ነው የሚገደለው የሚል ጥያቄ ሳነሳ እንደ ግለሰብ ያመኛል" ብለዋል። ጄነራል ሰዓረ የሥልጣን ጥምና ሩጫ የላቸውም ያሉት ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ሰው እንዳይሞት፣ የተፈናቀለ እንዲመለስ ነው እየሰሩ የነበረው ሲሉ ገልፀዋቸዋል። "እኛ ይኼ ነገር በጣም ቆጭቶናል፤ በጣም አናዶናል፤ ግን ጄነራል ሰዓረ ሲሰራቸው የነበሩ ዓላማዎችን በማሳካት የጄነራሉን ገዳዮች በማሳፈር የእነርሱ ፍላጎት እንዳይሳካ ለማድረግ ቆርጠን እንታገላለን" ብለዋል። • መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች ሠራዊታችን አንድነቱን ጠብቆ የጄነራል ሰዓረን አርማና ፅናትን ይዞ ኢትዮጵያ ሀገሩን ለመጠበቅ በፅናት እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል። በጄነራሎቹ ላይ የተፈጸመው ግድያ አላማው "እኛን መበተን ነው" ያሉት ጄነራል ብርሃኑ "በዘር ተከፋፍለን እንድንባላ፣ መንግሥት እንዳይረጋጋና እንዲፈርስ ነው። ሳይረጋጋ ሲቀር በሽግግር ስም ወደ ስልጣን ለመምጣት የሚደረግ ሩጫ ነው" በማለት ይህ እንደማይሳካና እንደሚታገሉት ገልፀዋል። "በኦሮምኛ አንድ ተረት አለ የማይረባ ሰው ጀግናን ያበላሻል ይባላል። እንደዛ አይነት ነገር ነው ያጋጠመን። ስለሆነም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል። የክልል አመራር ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የሚረሽኑ የስልጣን ጥመኞች ችግር ፈጥረውብናል፤ እንቁ መሪዎቻችንን አጥተናል፤ ከፍተኛ የሀዘን ድባብ ውስጥ እንገኛለን ግን እናሸንፋለን" ሲሉ ሳግ እየተናነቃቸው ተናግረዋል። የኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን ልጅ መዓሾ ሰዓረ "አባቴ በአንድነት፣ በመቻቻል፣ አብሮ በመስራት የሚያምን፣ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ነበር። ጄኔራል ሰዓረ ስለሞተ አገር ይፈርሳል ማለት አይደለም እኛ ጠንክረን ከቆምን ኢትዮጵያን አንድ እናደርጋታለን" ሲል በአባቱ ሞት የተሰማውን ሃዘን የገለፀ ሲሆን ጄኔራል ገዛኢም ይህ እንዳማይገባቸው ከእንባው ጋር እየታገለ ተናግሯል። • የጄነራል ሰዓረ ቀብር አዲስ አበባ ሳይሆን መቀሌ ይፈጸማል በዚሁ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኘው የጄኔራል ገዛኢ አበራ ልጅም ክብሮም ገዛኢ "ገዛኢ ፍቅሩ፣ ዘመን ተሻጋሪ ምክሮቹ፣ በቃላት ተነግሮ የማይገለፅ አባት ሲሆን ለውድ ባለቤቱ ፍፁም የልብና የፍቅር ሰው ነበር። ስብዕናውም ሩህሩህ፣ ሰውን አክባሪ፣ ሰውን በሰውነት ብቻ የሚያከብር፣ ቁጥብ፣ ታጋሽ፣ ብልህ፣ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢ ነበር" ሲል አባቱ ጄኔራል ገዛኢ የነበራቸውን ምግባር በሃዘን ገልጿል። ጀኔራል ገዛዒ ጡረታ ከወጡ በኋላም ለአገራቸውና ለህዝባቸው ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በሃገርና በህዝብ ጉዳይ የተጠመዱ አባት እንደነበሩም ክብሮም አክሏል። "ከሰውም በላይ፤ ከሰውም በታች እንዳትሆኑ" እያሉም ይመክሯቸው እንደነበር ክብሮም አስታውሷል። "ጀግኖች ናቸው ፤ ጀግኖች ህያው ናቸው፤ ይሄ ደማቸውም ፈሶ አይቀርም፤ ቃላቸውን እንጠብቃለን" በማለት ተናግሯል። በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የጄነራል ሰዓረ የቅርብ ጓደኛ የሆኑት ጀኔራል አበባው ታደሰ በበኩላቸው "ጀኔራል ሰዓረ በአላማው ፅኑ የሆነ፣ ለህዝብ ጥቅም ራሱን አሳልፎ የሰጠ ፣ ከህዝብ በላይ ራሱን የማያይ፣ ከልጅነቱ ጀምሮ አንድ ቀን ሳይንቀባረር ሕይወቱን ሙሉ ለህዝብ የሰጠ ጀኔራል ነበር" ሲሉ ጀኔራል ሰዓረን አስታውሰዋል። ጀኔራል ሰዓረ ጀግና ማፍራት የሚችሉ፣ ለችግር መፍትሄ የሚያበጁ ከመሆን አልፈው የሚኳቸውን በርካቶች ማፍራታቸውን ጠቅሰዋል። "በሥራው ምስጉን፣ ጦርነትን በሚገባ የሚያውቅ፣ ጦርነትን በሚገባ የሚያዘጋጅ፣ ብልህ፣ ጠንቃቃ፣ የጀግና የጀግና ምሳሌ ነበር" ብለዋል። አክለውም ጄኔራል ሰዓረ ኃይማኖት፣ ዘርና ብሔር የማይለዩ፤ በኢትዮጵያዊነታቸው የማይደራደሩ ፍፁም ኢትዮጵያዊ መሆናቸውንም ጀኔራል አበባው መስክረዋል። • ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ ጀኔራል አበባው በንግግራቸው ማሃል "አንድ ነገር ልንገራችሁ... ከፈለገም ይፈንዳ ... " በማለት ለውጡ ከመጣ በኋላ ሰዓረ በጥቂት ቡድኖች እንደ ከሃዲ መቆጠራቸውን ተናግረዋል። ጄኔራል ሰዓረ ኢትዮጵያዊነቱን አሳልፎ እንዲሰጥም ከፍተኛ ተፅዕኖ ይደርስበት እንደነበርና 'ቤተሰቤ ይበተናል እንጂ፤ ኢትዮጵያዊነቴን አሳልፌ አልሰጥም' ሲሉ ይነግሯቸው እንደነበር አስታውሰዋል። "ማንም ይምጣ ማን አስከምሞት ድረስ በኢትዮጵያዊነቴ ሳልደራደር እሰራለሁ" ማለታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ አንድን ጦርነት ከሚያሸንፉና ወሳኝ ተብለው ከሚጠሩ ወሳኝ ሥራዎች ከኋላ የሚሰራ የሎጂስቲክ ሥራ መሆኑን ያነሱት ጀኔራል አበባው "ጀኔራል ገዛኢን የሚያክል ሎጂስቲክስ አለ ብዬ አላምንም" ብለዋል። "ሃሳብ ያመነጫል፣ አስተዋይ ነው፣ አርቆ ያስባል፤ አሁን ላለው ሰላም መሰረት የጣለ ብልህ መሪ ነበር" ሲሉ መስክረዋል። በጀኔራሎቹ ሞት የተሰማቸውን መሪር ሃዘን ገለፁት ጄኔራሉ ይበልጥ ሃዘኑን ያበረታባቸው ሕይወታቸው በማለፉ ሳይሆን የሞቱበት አግባብ ሁለተኛ ሞት በመሆኑ ነው ብለዋል። በመጨረሻም ጀኔራሉ "ከዚህ በኋላ ቆም ብለን ብናስብ፤ ጣት ባንጠቋቆም፤ በሃሳብ መማር ካልቻልን በደም አንማርም" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
47355925
https://www.bbc.com/amharic/47355925
ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል
ሐሙስ ሰኔ ሰባት ቀን 2010 ዓ.ም የሀዋሳ ከተማ ከዚያ ቀደም ብዙም የማታውቀው ዓይነት የብሄር መልክ ያለው ግጭት ካስተናገደች ስምንት ወራት አለፉ፤ ሆኖም ከተማዋ ጠበሳዋ የደረቀላት፣ የወትሮ ድምቀቷን መልሳ የተላበሰች አትመስልም።
በግጭቱ ሰዎች ተደብድበዋል፤ ተገደለዋል፤ የመኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ተቋማት ተዘረፈዋል፤ ለህልውናቸው ዋስትና እንዳጡ የተሰማቸው ዜጎች ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ሸሽተዋል። በወቅቱ መንግሥት አስራ አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልፆ የነበረ ሲሆን የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ቁጥሩ ከዚህም ይልቃል ይላሉ። የግጭቱን መርገብ ተከትሎ እርቅ ተካሂዷል፤ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች ተከናውነዋል፤ ባለስልጣናት ከመንበራቸው ገሸሽ ተደርገዋል፤ ለፍርድ የቀረቡና የሚፈለጉም አሉ። እነዚህ ሁሉ እርምጃዎች የራቃቸውን የደህንነት ስሜት መልሰው እንዳላስገኙላቸው በከተማዋ ለተገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ያጫወቱት ወደ ስድሳ ዓመታቸው እየተጠጉ ያሉት ጴጥሮስ አብርሃም (የተቀየረ ስም) ናቸው። • ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ ከሦስት አስርት ዓመት በላይ በከተማዋ የኖሩት ጴጥሮስ በቆይታቸው ሁሉ ባለፈው ክረምት መባቻ ያጋጠመውንና እርሳቸው "ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት" የሚሉትን መሰል ክስተት አይተው እንደማያውቅ ያስረዳሉ። በከተማዋ ዳርቻ የገነቡት መኖሪያ ቤታቸው በድንጋይ ውርጅብኝ መሰባበሩን በሳግ በታፈነ ድምፅ የሚገልፁት ጴጥሮስ ቤታቸውን ተመልሰው ሊኖሩበት ቀርቶ ሄደው ለማሳደስ እንኳ እንዳልቻሉና 'ዳግመኛ ጥቃት ይደርስብኝ ይሆን' የሚል ስጋት እንደጥላ እንደሚከተላቸው ይናገራሉ። ለአዛውንቱ ጴጥሮስ ባለፉት ወራት በከተማዋ የሰፈነው ሰላም ከስክነት የተፋታ፥ ውስጥ ውስጡን ውጥረት የሚርመሰመስበት ነው፤ ጥቃት አድራሾች ነበሩ የሚሏቸው ግለሰቦች ለፍርድ ሲቀርቡ አላየሁምም ይላሉ። "ምንም ደህንነት አይሰማኝም። ምክንያቱም እስካሁንም ድረስ የህግ የበላይነት አልተጠበቀም። አሁንም እየተፈራራን ነው ያለነው። እንጅ እንደበፊቱ እንኖራለን የሚል ተስፋ የለኝም" ብለዋል። ወደ ትውልድ ቀያቸው ወላይታ እንዳይመለሱ ህይወታቸውን የገነቡት በሀዋሳ የመሆኑ እውነታ አግዷቸዋል። ጴጥሮስ ከወርሃ ሰኔ አንስቶ ቤተሰባቸውን ይዘው በከተማዋ እምብርት በኪራይ ይኖራሉ፤ የሦስት ወራት የቤት ኪራይ እና የአንድ ወር ቀለብ መሸፈኛ ነው የተባለ ክፍያ ከመንግሥት ቢወስዱም የተደረገላቸው ድጋፍ በቂ ነው ብለው አያምኑም። ተሰማ ኤልያስ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ቤት ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። የካቲት 13 ቀን የሲዳማ ብሔር ክልላዊ አስተዳደር የመሆን ጥያቄ በአፋጣኝ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድበት የሚጠይቅ ሰልፍ ሲካሄድ ከአስተባባሪዎቹ መካከልም አንዱ ነበሩ። በሰልፉ ዋዜማ በከተማዋ ውጥረት የነበረ ፣ በዕለቱም በርካታ የንግድ ተቋማት በሮቻቸውን በፍራቻ ጠረቃቅመው የነበረ ቢሆንም ሒደቱ ያለአንዳች ኮሽታ መጠናቀቁን የሚገልፁት በኩራት ነው። የወርሃ ሰኔውን ግጭት ተከተሎ ከተማዋን የሰነጉትን ፖለቲካዊ ሕመሞች "አርቴፊሻል" እና "በተለይ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት ግጭት ገጥሟቸው የማያውቁ የወላይታ እና የሲዳማ ብሄርን በማላተም" ፖለቲካዊ ጥቅም ለማካበት የሚጥሩ ወገኖች ስሪት ናቸው ይላሉ አቶ ተሰማ። የወቀሳ ጣታቸውም "ለሃያ ሰባት ዓመት ያህል ሕዝቦችን በመጋጨት ስልጣኑን ሲያደላድል ነበር" የሚሉት ገዥው ፓርቲ እና "በብሄር ፖለቲካ የማያምኑ፥ የከተማ ፖለቲካ የሚያራምዱ የአንድነት ኃይሎች" የሚሏቸው አካላት ላይ ያነጣጥራሉ። ቢቢሲ በከተማዋ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች የሰኔ ሰባቱ ግጭት ከመፈንዳቱ አስቀድሞ እውነታ ላይ ያልተመሠረቱ ነገር ግን ስሜትን የሚኮረኩሩ፣ የተጠቂነት መንፈስ የሚኮተኩቱ ወሬዎች በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች እና በአካልም ሲነዙ እንደነበር ይመሰክራሉ። መሰል ወሬዎች አሁንም አልፎ አልፎ በማኅበራዊ ሚዲያም በአካልም ሲሰራጩ የሚስተዋል መሆኑ ተመሳሳይ ግጭት ዳግመኛ ላለመከሰቱ መተማመኛ እንዳይኖራቸው እንዳደረገ የተናገሩም አሉ። • ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው የታሪክ ዕዳ የሲዳማ ክልል መመሥረትን የሚመለከት ሕዝበ ውሳኔ እንዲከናወን የሚጠይቀው ሰልፍ ጅማሮውን ያደረገው ከሀዋሳ ወጣ ብላ ከምትገኘው ሎቄ ነው። ከአስራ ሰባት ዓመት በፊት በርካቶች ሕይወታቸውን ያጡባት ቦታ ናት ሎቄ። የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዎች በወቅቱ እንዳጠናቀረው ዘገባ የመንግስት ኃይሎች ቅዋሜ ለማሰማት በተሰባሰቡ የአካባቢው አርሶ አደሮች ላይ በከባድ መሳርያዎች በከፈቱት ተኩስ ሃያ አምስት ሰዎች ተገድለው፣ ሃያ ስድስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። መንግስት በበኩሉ የሟቾቹን ቁጥር ወደ አስራ አምስት ዝቅ አድርጎ ያሰማራቸው የፀጥታ አስከባሪ አባላትም መገደላቸውን ገልጿል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የራስ አስተዳደርን ጥያቄ በሚያነሱ የሲዳማ ተወላጆች ሎቄ የመሰባሰቢያ ነጥብ ሆናለች ሲሉ የአካባቢውን ፖለቲካ የሚከታተሉ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ምሁር ለቢቢሲ አስረድተዋል። በተለይ በወቅቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት ኃይለማርያም ደሳለኝ እስከጠቅላይ ሚኒስትርነት ለደረሰ ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት ስልጣን መመረጣቸው ፣ ድርጊቱን የፈፀሙ ታጣቂዎች እና ያዘዙ ባለስልጣናት ተገቢ ፍርድ አላገኙም ሲሉ ለሚብሰከሰኩ ተወላጆች የእግር እሳት ሆኖ መቆየቱን ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉት ምሁር ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ስልጣን ለቅቀው አብይ አህመድ ከተተኩ በኋላ ታዲያ ታፍኖ የቆዩ ጥያቄዎች እና ስሜቶች ገንፍለው ወጥተዋል እንደእርሳቸው አገላለፅ። በደምሳሳው ኤጄቶ እየተባሉ የሚታወቁ ወጣቶች እና የፖለቲካ ተሟጋቾች በቅርብ ጊዜ የአደባባይ እንቅስቃሴዎች የሎቄን ግድያ በአልባሳት ህትመቶች ማሰባቸው፣ ክስተቱ በሕዝባዊ የትውስታ ማህደር ያለመደብዘዙን የሚያመላክት ይመስላል። ኤጄቶ ማን ነው? ከሲዳማ ብሔር ፖለቲካ ጋር በተያያዘ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰርክ ስሙ የሚነሳ ቡድን ነው ኤጄቶ። በከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናት ሳይቀር አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋለውን ለውጥ በማምጣት ረገድ ላቅ ያለ ሚና ተጫውተዋል እየተባሉ የሚሞካሹትን ኢመደበኛ ቡድኖች ፈለግ ተከትሎ በአካባቢው ለፖለቲካዊ ለውጥ የሚሠራ ይመስላል። ኤጄቶ ለሲዳማ መብት መከበር በእውነት ላይ የተመሠረት ትግል ለሚያደርጉ የብሔሩ ጎበዛዝት የሚሰጥ የማዕረግ ስም ነው ሲሉ የብሔሩ ተወላጆች ለቢቢሲ አስረድተዋል። የሲዳማ ብሔር በተለያዩ መንግስታት ውስጥም ራሱን የማስተዳደር መብቱን ለማስከበር ሲታገል፣ ብዙዎች የሞቱለትን ዓላማ ግብ ለማድረስ ስያሜውን ተላብሰው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶችን የያዘ ቡድን ነው ይላሉ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲው ተሰማ ኤልያስ። "ኤጄቶ በአንዳንድ ሰዎች እና ሚዲያዎች እንደሚባለው የመንጋ ፖለቲካ አራማጅ አይደለም። በእውነት ላይ ተመሥርቶ ለሕዝብ ድምፅ የሆነ ቡድን ነው።" ተሰማ፣ ኤጄቶ ወጣቶችን በብዛት ይሰብሰብ እንጅ፣ በዕድሜያቸው ገፋ ያሉም፣ በመደበኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚሳተፉም ሆኑ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ለሲዳማ መብት መከበር በሃቀኝነት እስከታገሉ ድረስ ስያሜው ይገልፃቸዋል ሲሉም ያክላሉ። ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት ይሁንና ቡድኑን በበጎ የማያነሱት አልጠፉም። የሀዋሳ ከተማ ከልዩ ልዩ ብሔሮች የተውጣጡ ብዙሃንን አቅፋ እንደመያዟ፣ በዋናነት ለሲዳማ የራስ ማስተዳደር መብት ይታገላል የሚባለውን ቡድን በጥርጣሬ የሚገረምሙት አሉ። በሰኔ ሰባቱ ግጭት ጥቃት የደረሰባቸው ግለሰቦችን የማማከር ሥራ ስሠራ ቆይቻለሁ የሚሉ የሲዳማ ብሔር ተወላጅ ያልሆኑ የከተማዋ ነዋሪ ኢጄቶ የመንግስት መዋቅሮችን ተጠቅሞ የዳበረ ቡድን ነው ይላሉ። "ፖለቲከኞች ፖለቲከኛ በመሆናቸው ብቻ በግልፅ ማድረግ የማይችሏቸውን ድርጊቶች በጀርባ የሚያስፈፅሙበት ቡድን ነው። ፖለቲከኞቹ የሚፈልጓቸውን ግቦች ለማሳካት እንደመደራደሪያም እንደማስፈራሪያም ይጠቀሙበታል። "ስማቸውን ብንገልፅ ለደህንነታቸው ስጋት እንደሚገባቸው የነገሩን እኚሁ የከተማዋ ነዋሪ በርካታ ሥራ የሌላቸው ወጣቶች በኤጄቶ ጥላ ሥር መሰባሰባቸውን እና ቡድኑ መደበኛ ባለመሆኑ በስሙ ለሚፈፀሙ ጥፋቶች ተጠያቂ እንዳይሆን ነፃነት ሰጥቶታል ይላሉ። የከተማዋን ሁኔታ "አሳዛኝ" ሲሉ የገለፁልን እኚሁ ነዋሪ የውስጥ ለውስጥ ውጥረቱ መርገብ ያለመቻሉ ማሳያ ዜጎች የሚኖሩባቸውን ሠፈሮች ከመምረጥ አንስቶ ያለመተማመን መኖሩ ፣ የእምነት ቦታዎቻቸውን እስከመለየት መድረሳቸው ነው። ቢቢሲ ባለፉት አስር ወራት በሌሎች የኢትዮጵያ መሰል ከተሞች የማይስተዋል ዓይነት በተለይ ስሱ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ ኃሳብን በነፃነት የመግለፅ ፍርሃት፣ በሃዋሳ እንዳለ አስተውሏል። በቅርብ ዓመታት ትልልቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን የሚያስተናግድ ስቴድየም፥ ከአገሪቱ መዲና ጋር በአፋጣኝ የሚያገናኝ የአውሮፕላን መስመር እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት መኩራሪያ የሆነ የኢንዱስትሪ ፓርክ ያገኘችው ሀዋሳ ክፉኛ ካናወጣት ህመም ሙሉ በሙሉ ያገገመች አትመስልም።
42985388
https://www.bbc.com/amharic/42985388
እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጌ በይቅርታ ሊፈቱ ነው ተባለ
ታዋቂው ጋዜጠኛ እና አምደኛ እስክንድር ነጋና የቀድሞው የአንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አንዷለም አራጌ በይቅርታ እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው ወደሦስት መቶ የሚጠጉ የፌዴራል ታራሚዎች መካከል እንደሚገኙ ለመንግስት የሚቀርብ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጠቅላይ አቃቤ ሕግን ጠቅሶ ዘግቧል።
አቶ እንዷለም ከአንድነት ለፍትህ እና ዲሞክራሲ ፓርቲ መስራቾች መካከል አንደኛው ሲሆኑ መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም ከታሰሩ በኋላ ለሽብር ጋር በተያያዘ በተመሰረተባቸው ክስ የዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው ይታወቃል። እስክንድር በእስር ላይ ሳለ እ.ኤ.አ የ2012ን የፔን/ባርባራ ጎልድስሚዝ የፅሁፍ ነፃነት እና እ.ኤ.አ የ2017 የዓለም አቀፍ የፕሬስ ተቋምን የዓለም የፕሬስ ነፃነት የጀግንነት ሽልማትን ተቀዳጅቷል። ሁለቱም የተከሰሱባቸውን ወንጀሎች የሚያስተባብሉ ሲሆን የተለያዩ የዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች እስራታቸውን በፖለቲካ የተነሳሳ ነው በማለት ሲያጣጥሉት ቆይተዋል። የፋና ዘገባ እንደሚለው ከሆነ ከፌዴራል እስር ቤቶች በይቅርታ ከሚወጡ ታራሚዎች በተጨማሪ ከአማራ ክልል እሴ ቤቶች ለሚገኙ 119 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል። ዘገባው ጨምሮ ታሳሪዎቹ የሚፈቱት በይቅርታ ቦርድ ለፕሬዚዳንቱ ከቀረበ፣ የተሃድሶ ስልጠናም ከወሰደ በኋላ ብሏል። የጥፋተኝነት ፍርድ ከተላለፈባቸው እና የእስር ቅጣታቸውን በመፈፀም ላይ ከሚገኙት ውጭ ክሳቸው በመታየት ላይ ያለ 329 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ ይደረጋልም ተብሏል።
48961636
https://www.bbc.com/amharic/48961636
ኢህአዴግን ያጣበቀው ሙጫ እየለቀቀ ይሆን?
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ. ም አጠናቆ መግለጫ አውጥቷል።
መግለጫው በርካቶችን ያስደነገጠ ሲሆን በተለይ አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) መረር ያለ ምላሽ እንዲሰጥ አድርጎታል። ይህ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ባልተለመደ መልኩ መነቋቆርና በመግለጫ እስከመመላለስ መድረስ ምን ያሳየናል ስንል ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን እና የኢዜማ ምክትል መሪ አቶ አንዷለም አራጌን ጠይቀናቸዋል። ፓርቲዎቹ ለስም አብረው አሉ ቢባልም እንደተለያዩ የሚያምኑት ዶ/ር ዳኛቸው "ምንም እንኳን ከፌደራል መንግሥቱ የሚያገኙትን ነገር ሳያቅማሙ እየተቀበሉ ቢሆንም ትግራይ ሪፐብሊኳን ይዛ ለብቻዋ ነው ያለችው። ህወሓቶች ማዕከላዊውን መንግሥትም የተቀበሉት አይመስልም" ይላሉ። በዚህ ሰዓት ከምክንያት ይልቅ ስሜት የሚሞቅበትና የሚገንበት ነው የሚሉት አቶ አንዷለም አራጌ በበኩላቸው ሁለቱም ፓርቲዎች ነገሩን የያዙበት መንገድ ተገቢ እንዳልሆነ ያስቀምጣሉ። • የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሙሉ መግለጫ ምን ይላል? ህወሓቶች በጉልበትም ቢሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፊት ሆነን እንመራለን የሚሉ ስለሆኑ ይህንን ሃሳብ የሚመጥን መስከን፣ ስልጣኔና አርቆ አሳቢነት ከእነርሱ ይጠበቃል ይላሉ አቶ አንዷለም። ልዩነቶችም ሲኖሩ ልዩነቶችን በሰከነ ሁኔታ በፊት እንደሚያደርጉት ከመጋረጃ ጀርባ ከዚህም በበለጠ ደግሞ በብልሀትና በሆደ ሰፊነት ነገሮችን መያዝ ያስፈልግ ነበር ሲሉ ያስረዳሉ። አዴፓ ህወሓት ካወጣው መግለጫ አንጻር የሰጠው መግለጫ ተገቢ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ዳኛቸው የህወሓት መግለጫ በፓርቲው ውስጥ እየታየ የነበረውን ልዩነት የበለጠ እያሰፋው መሆኑንና ከፌደራል መንግሥቱ የተለየ አካል እየሆነ መምጣቱን ያመለክታል ብለዋል። አዴፓ በግድያ አመራሮቹን ሲያጣ "ይህ ነገር በመከሰቱ እናዝናለን ከማለት ይልቅ ከእናንተ ጋር ለመስራት እንቸገራለን የሚል መግለጫ ማውጣት ስህተት ነው፤ የሚያበሳጭ ነገር ነው ለዚህም አጸፋ ከአዴፓ ተገቢውን ምላሽ ያገኙ ይመስለኛል" ይላሉ ዶ/ር ዳኛቸው። ልዩነቶቻቸውን ተገማግመውና ተሞራርደው በአግባቡ መያዝ ሲገባቸው ህወሓት እንዲህ አይነት መግለጫ ቀድሞ ማውጣቱ ከብልህነት አንፃር ተገቢ ያልሆነ፤ ነገር ግን አጭር እይታ ላይ የተመሰረተ እና ምናልባትም አድብቶ ነገሮችን የማድረግ ይመስላል ያሉት ደግሞ አቶ አንዷለም ናቸው። • ኢህአዴግ ከአባል ፓርቲዎቹ መግለጫ በኋላ ወዴት ያመራል? በሌላ በኩል ደግሞ በአዴፓ በኩል የማየው በጣም የበዛ መቆሳሰል እንዲሁም የበዛ ለተመልካች፣ ለሰሚ፣ ለሀገሩ ብዙም የተጨነቀ የማይመስል እልህ የመወጣት የሚመስል ውዝግብ ነው በማለት በአጠቃላይ የኢህአዴግን ስብስብ የብቃትና የአርቆ አሳቢነት ደረጃን የሚያሳብቅ ነው ሲሉ ይተቻሉ። ኢህአዴግ በግንባርነት የመቆያ ጊዜው እያበቃ እሆን? ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከዚህ በፊትም "ይህንን ለውጥ ለማሳካት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፈተና የሚሆነው የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎችን በአግባቡ ማስተዳደር ነው" ማለታቸውን አስታውሰው፤ ይህ አለመስማማት ከዚህ በፊትም በመካከላቸው የነበረ ነው በማለት መነሻው የጋራ ግብ አለመኖሩ ነው ይላሉ። "ለውጡን እንዴት ማስኬድ አለብን? እስከ የትስ እናስኬደዋለን? ብለው ከመስማማታቸው በፊት የገቡበት ይመስለኛል" የሚሉት ፕሮፌሰሩ ኢህአዴግ ይህንን ለውጥ ብቻውን ለማስኬድ መምረጡ እንዳይስማሙ እንዳደረጋቸው በመግለፅ በዚህ መልኩ ከቀጠሉ አንዱ ሌላውን ሊያፈርስ ይችላል ይላሉ። የህወሓት መግለጫና አቋም አዴፓን ብቻ የሚያብጠለጥል ሳይሆን የፌደራል መንግሥቱንም ጭምር የሚመለከት እንደሆነ የሚጠቅሱት ዶ/ር ዳኛቸው በበኩላቸው "ከአዴፓ ጋር አንሰራም ሲሉ አንሰራም እያሉ ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋርም ነው" ይላሉ። አንዷለም አራጌ በበኩሉ የኢህአዴግ ጊዜ እያበቃ ሊሆን ይችላል ይላል። "ከዚህ በፊት የከረረ ጉዳይ ሲኖራቸው ለቀናት ወይም ለሳምንታት በውስጣቸው ይዘው በመነጋገር ለመገናኛ ብዙሀን እንኳ የማይገልጡበት ሁኔታ ነበር። አሁን ግን ኢህአዴግን ያጣበቀው ሙጫ እየደረቀ፣ እየተፈረቀቀ ይመስለኛል" በማለት ያክላል። • "አገሪቷ አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት ህወሓት ተጠያቂ ነው" አዴፓ አሁን እየታየ ያለው በእራሱ በኢህአዴግ ውስጥ በተለይ ደግሞ ህወሓት "ለውጡ ለእኔ ሳይሆን በእኔ ላይ ነው የመጣው" በማለት ከመጀመሪያው ያቄመ ይመስለኛል የሚሉት አቶ አንዷለም ለውጡን ለማደናቀፍ እየሰራ ይሆን የሚል ጠንካራ ጥርጣሬ አለኝ ይላሉ። "አሁንም እነዶክተር ዐብይ ብቻቸውን ህዝብን ሊያሸጋግሩ አይችሉም" የሚሉት አቶ አንዷለም "ሀገርን ህዝብን ሊያሸጋግር የሚችለው የብዙኀን ተሳትፎ ነው" ሲሉ አስረግጠው ይናገራሉ። "የመሪነቱን ኃላፊነት እነርሱ ቢወስዱም ህዝቡን በብዛት ማሳተፍ አለባቸው። እያንዳንዱ ጡብ ማቀበል አለበት እንጂ ሀገርን ወደ ዲሞክራሲ የማሸጋገር ሥራ ጥቂቶች ጀምረው የሚጨርሱት አይደለም።" "ሀገር ለለውጥ በምትዳክርበት እና ብዙ አርቆ አሳቢ በሚያስፈልግበት በዚህ ወቅት የአጭር ጊዜ ህልምን ለማሳካትና የግል ቁርሾህን ለመወጣት ግብግብ የምትገጥምበት አይመስለኝም" ይላሉ አቶ አንዷለም። በተጨማሪም በሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎችም ሆኑ ሌሎች አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ከፍ ያለ ማስተዋልን፣ ሰፊ ልብና የመንፈስ ልዕልናን የሚጠይቅ መሰባሰብ፣ መወያየት ከአቋራጭና ጊዜያዊ ድሎች፣ ተራ ብሽሽቆች እንዲሁም ዘለፋዎች እርቀን ሀገራችንን ወደተሻለ የፖለቲካ ሥርዓትና ዘመን የምናሸጋግርበት፤ አርቆ አሳቢነትና ብልህነት የሚጠይቅ ዘመን ላይ እንገኛለን ሲሉም ይመክራሉ። • ኢህአዴግ እዋሃዳለሁ ሲል የምሩን ነው? በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኩል ያለው ቀና ሀሳብ በካድሬዎቻቸው ዘንድ እንኳ ተቀባይነት እንዲኖረው ለለውጥ የተመቸ ሁኔታ መፍጠሩ ላይ በጣም ይቀራል የሚሉት አቶ አንዷለም ኢህአዴግ ራሱ ችግሩን ቢፈታ ለለውጡ አንዱ እገዛ ይመስለኛል ይላሉ። በአመራር በኩል የሚደረግ ለውጥ የተወጠረውን ሊያላላና የተፈጠረውን መቋሰል ሊያሽር እንደሚችል ሃሳብ የሚሰነዝሩት ዶ/ር ዳኛቸው ህወሓትን የሚመሩት ሰዎች ለረጅም ዘመናት የቆዩ መሆናቸውን በሚተቹት ወጣቶችን ወደ አመራር የሚያመጡ ከሆነ ብዙ ነገሮች የሚለወጡና የሚሰክኑ ይሆናሉ ብለው ያምናሉ። የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች አብረው ባይቀጥሉ ምን ይሆናል? በኢህአዴግ ታሪክ "በዚህ መልኩ ወደ አደባባይ ወጥቶ አንዱ ሌላውን መተቸት የመጀመሪያ ነው። ይህ ደግሞ ምን ያህል ስር የሰደደ ችግር በመካከላቸው እንዳለና የሃገሪቷ እጣ ፈንታ አደጋ ላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው" ይላሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና። አቶ አንዷለም ደግሞ አሁን ባለው አሰላለፍ ህወሓት ከግንባሩ ቢወጣ እንኳ ሌሎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አብረው ይቀጥላሉ የሚል ሀሳብ አላቸው። ስለዚህም በቅርብ ርቀት "ሌሎቹን አባል ፓርቲዎች ያጣበቀው ሙጫ ይላቀቃል" ብሎ እንደማያስብ ይናገራሉ። "ያ ሙጫ የስልጣን፣ የዓላማ ወይንም ሌላ ሊሆን ይችላል" የሚለው አንዷለም የተወሰነ ጊዜም ቢሆን አብረው እንዲጓዙ እንደሚረዳቸው ያሰምርበታል። በአንድ ጊዜ በአንድ ሃገር ውስጥ ሁለት መንግሥት ሊኖር አይችልም የሚሉት ዶ/ር ዳኛቸው "መጥራት ያለበት ነገር ይጠራል" በማለት "ህወሐት ሁሉን ነገር ተቆጣጥሮ ስለያዘው የምንሰማው የእነሱን እንጂ የትግራይን ህዝብ ድምጽ አይደለም የህዝቡ ድምጽ ታፍኗል" ይላሉ። ስለዚህ ህዝቡ እዚህ ውስጥ ስለሌለበት ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚወስደን ነገር እንደሌለም ያምናሉ። • "እስሩ አብንን ለማዳከም ያለመ ነው" ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) የትግራይ ህዝብ ደግሞ ከኢትዮጵያዊነት ያፈነግጣል የሚል ቅንጣት ጥርጣሬ የለኝም ጉዳዩ ፓርቲው ጋር ነው ያለው" በማለት ይናገራሉ። "የትግራይ ህዝብ ፍትህን ያውቃል ከምንም በላይ ኢትዮጵያዊነትን ይወዳል ስለዚህ የህወሓት የበላይነት እንዲቀጥልለት ወደ ጦርነት ይገባል ብዬ አላስብም" በማለትም በህዝቡ ላይ ያላቸውን ተስፋ ይገልፃሉ። ህወሓት እያለመ ያለው የሚመስለኝ በሽግግሩ ላይና በሽግግሩ ሂደት ብቻ ሳይሆን ከሽግግሩ በኋላ ሊኖረው የሚችለውን ነገር ጭምር ይመስላል የሚለው አንዷለም "ሌላ አይነት የፖለቲካ ቀመር ለማምጣትና ይመቹኛል የሚላቸውን አጋሮች እየፈለገ" ይመስለኛል ይላል። "ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች፤ ሕዝቧም ትልቅ ነው" የሚለው አንዷለም "ያለንበት ችግር የተወሳሰበ ቢሆንም የማይለያይ የተቆራኘ ማንነት አለን ብዬ አምናለሁ" በማለት የኢትዮጵያ ሁኔታ ችግር አይገጥመውም ባይባልም ችግሩን የማለፍ አቅም አለው ብሎ እንደሚያምን ያስረዳል።
news-55230523
https://www.bbc.com/amharic/news-55230523
"አል-ሸባብ እና ኦነግ-ሸኔን ከቀጠናው ብናስወግድ ሕብረታችን ይጠነክራል" ጠ/ሚ ዐብይ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ኬንያ እና ኢትዮጵያ የአል-ሸባብ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር- ሸኔ ታጣቂዎችን ከቀጠናው ቢያስወግዱ የሁለቱ አገራት ሕብረት እንደሚጠናከር ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት በሞያሌ የተገነባውን የድንበር መተላለፊያ ከፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው። "አል-ሸባብ እና ኦነግን ከቀጠናው ብናስወግድ ሕብረታችን ይጠነክራል" ብለው ተናገሩ ሲሆን ኦነግ ሲሉ ኦነግ-ሸኔ የተባለውን ታጣቂ ቡድን እንደሆነ የጠቅላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ስዩም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ከኦነግ ተገንጥሎ በመውጣት በምዕራብ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት ደቡባዊ ክፍል የትጥቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ ይነገራል። ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማምጣት የአካባቢው ደህንነት ማረጋገጥ ግድ መሆኑን ተናግረዋል። "የደኅንነት ችግር እያለብን ኢኮኖሚያዊ ድል ማስመዝገብ አይቻለንም" ያሉት ፕሬዝደንት ኡሁሩ፤ "እንደ ሁለት ጎረቤት አገራት በውስጣችን እየኖሩ የኢትዮጵያንም የኬንያንም ሰላም የሚያውኩት ላይ መስራት ይኖርብናል" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ "መሰረተ ልማቶች ላይ በጋራ እንደምንሰራው ሁሉ የአከባቢውን ደህንነት ለማረጋገጥ እንድንሰራ" ለፕሬዝደንት ኡሁሩ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከዛሬ ረቡዕ ጀምሮ የሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መግባታቸው ይታወሳል። ይህ ጉብኝት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገሪቱ ሠራዊት በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን ይፋ ካደረጉ በኋላ የሚደረግ የመጀመሪያው የውጪ አገር ጉብኝታቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀዳሚነት ያቀኑት ሁለቱን አገራት ወደምታዋስነው የድንበር ከተማ ሞያሌ ነበር። እዚያም የኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል። በዚህ ጉብኝት ሁለቱ መሪዎች አገሮቻቸውን ያስተሳስራሉ ከተባሉት ታላላቅ ፕሮጀክቶች መካከል የተጠናቀቁትን የሚመርቁ ሲሆን በግንባታ ላይ ያሉትን ደግሞ ይጎበኛሉ። ይህም በድንበራቸው ሞያሌ ላይ ያለውን የድንበር መተላለፊያ እና አዲሱን የላሙን ወደብ ይጨምራል። በተለይ 'ላፕሴት' በመባል በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል የሚጠራው በውስጡ በርካታ ዕቅዶችን ያቀፈው የላሙ ወደብ ፕሮጀክት በጉብኝቱ ሰፊውን ቦታ ይይዛል። ይህ የላሙ ወደብ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን ኬንያን ብቻ የሚያስተሳስር ሳይሆን ደቡብ ሱዳንንም ያካተተ ግዙፍ ፕሮጀክት እንደሆነ ይነገራል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ኢትዮጵያ ወቅታዊውን ሁኔታ ለማስረዳት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት በተጓዙበት ወቅት ወደ ናይሮቢ በመምጣት ከፕሬዝዳንቱ ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል። ሁለቱ አገራት ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን መሪዎቹም በተደጋጋሚ ሲገናኙ ቆይተዋል፤ የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ከዚሁ ጋር የሚገናኝ ሲሆን ከወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ወሳኝ ጊዜ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለቱን አገራት በሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎች በሚኖሩ ማኅበረሰቦች መካከል በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶች የሚያጋጥሙ እንደሆነ ይታወቃል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት በድንበር አካባቢ ካሉ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ አካሂዶ እንደነበር ይታወሳል። በዚህም ሠራዊቱ ወደ ኬንያ ድንበር ዘልቆ በመግባት ቢያንስ 10 ኬንያዉያንን ይዘው መውሰዳቸው ተነግሯል። ሁለቱ መሪዎች በሚያደርጉት ውይይት በድንበር አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን በተመለከተ ከሚመካከሩባቸው ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ይሆናል ተብሏል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለመድረግ ረቡዕ ወደ ኬንያ እንደሚገቡ የተገለጸ ሲሆን፤ በጉብኝታቸውም ኢትዮጵያ እና ኬንያን የሚወሰኑበትን የሞያሌና የላሙ ወደብን ይጎበኛሉ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በጉበኝታቸው ከኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን የሞያሌን የድንበር መተላለፊያ በርን መርቀው የከፍቱ ሲሆን፤ በተጨማሪም የሁለቱ አገራት መሪዎች በላሙ ግዛት ግዙፉን 'ላፕሴት' ፕሮጄክትን ይጎበኛሉ። 'ላፕሴት' ፕሮጀክት ምንድነው? ላፕሴት (LAPSSET) የተባለው ፕሮጀክት የሚለው ምህጻረ ቃል የላሙ ወደብ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ የትራንስፖርት መተላለፊን ሚወክል ነው። የላፕሴት ፕሮጀክት ይፋዊ ድረ-ገጽ እንደሚያመለክተው ግዙፉ ፕሮጀክት የኬንያ፣ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ፕሮጀክት ነው። ፕሮጅክቱ ሦስቱን አገራት እርስ በእርስ የሚያስተሳስር ሲሆን ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ጋርም የሚያገናኛቸው ነው። ግዙፉ ላፕሴት ፕሮጀክት በውስጡ 7 ፕሮጀክቶችን አቅፏል። እነዚህም የወደብ ግንባታ፣ የመንገድ ግንባታ፣ የባቡር መስመር ዝርጋታ፣ ሁለት የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ዝርጋታ ፕሮጀክቶች፣ የአየር ማረፊያ ግንባታ እና የሪዞርት ከተሞች ግንባታን ያቀፈ ነው። 1. የአውራ ጎዳናዎች ግንባታ ይህ ፕሮጀክት የኬንያ የወደብ ከተማ ላሙን ከወደብ አልባዎቹ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኢትዮጵያን እና ደቡብ ሱዳን ጋር የሚያገናኝ ነው። በፕሮጀክቱ የሚገነባው መንገድ ከኬንያዋ ላሙ ወደብ ተነስቶ-ኢሲኦሎ የሚደርስ ሲሆን፤ ኢሲኦሎ (ኬንያ) - አዲስ አበባ እንዲሁም ከኢሲኡሎ - ጁባ (ደቡብ ሱዳን) የሚያገናኝ ፕሮጀክት ነው። በዚህ ፕሮጀክት ውስጥ የሚገነቡት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፤ ላሙ ወደብ - ዊቱ ጋሪሰን መንገድ ግንባታ 60 በመቶ ተጠናቋል። ኢሲኦሎ - ሞያሌ - ሐዋሳ መንገድ ግንባታ ተጠናቋል። ከላሙ ወደብ - ጋሪሳ - ኢሲኦሎ የሚወስደው መንገድ ዲዛይን በአፍሪካ ልማት ባንክ ወጪ የተጠናቀቀ ሲሆን ኢሲኦሎ - ሎኪቻር - ናዳፓለ - ቶሪት - ጁባ መንገድ ደግሞ የኬንያ እና ደቡብ ሱዳን መንግሥታት ከዓለም ባንክ ጋር በመሆን በቅርቡ የአዋጭነት ጥናት አካሂደዋል። ሎኪቻር - ናዳፓለ ያለውን መንገድ ለመገንባታ የዓለም ባንክ 500 ሚሊዮን ዶላር ፈቅዷል። የባቡር መስመር [ፎቶ ፋይል] 2. የባቡር መስመር ዝርጋታ ይህ የባቡር መስመር ዝርጋት የሦስቱን አገራት መዲናዎችን የሚያገናኝ ነው። የባቡር መስመሩ ከላሙ ወደብ ኢሲኦሎ፣ ከኢሲኦሎ አዲስ አበባ፣ ከኢሲኦሎ ጁባ እንዲሁም ከኢሲኦሎ ናይሮቢ ይዘረጋል። የባቡር ዝርጋታው ወጪም ከ7 ቢሊየን ዶላር በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል የሚዘረጋው የባቡር መስመር ቅዳሚ ዲዛይን ተጠናቋል። የሁለቱ አገራት መንግሥታትም በላፕሴት ፕሮጀክት ውስጥ የተካተተውን ይህን ፕሮጀክት በጋራ ለማልማት ከሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝመውን አዲስ አበባ - ጅቡቲ የባቡር መስመር የዘረጋው የቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሸን (ሲሲሲሲ) በላፕሴት ፕሮጅከት ውስጥ በኬንያ በኩል ያለውን የባቡር ዝርጋ የአዋጭነት ጥናት እና ዝርዝር የዲዛይን ሥራ እንደሚያከናውን ተጠቅሷል። 3. የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ዝርጋታ ሁለት አይነት የነዳጅ ማስተላለፉያ ቱቦዎች ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል። እነዚህም የድፍድፍ ነዳጅ እና የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ናቸው። ድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ያልተጣራውን ነዳጅ ወደ ማጣሪያ የሚወስድ ሲሆን የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ደግሞ ምርት ወደ ገበያ የሚያስተላልፍ ነው። የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ከሎኪቻር - ወደ ላሙ ወደብ (ኬንያ) የሚዘረጋ ነው። በሌላ በኩል የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ በላፕሴት ከታቀፉ 7 ፕሮጀክቶች ውስጥ ከታተካተቱት ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ነው። ይህ ፕሮጀክት ከላሙ ወደብ - ኢሲኦሎ - ሞያሌ - ሐዋሳ - አዲስ አበባ የሚዘልቅ ነው። 790 ኪሎ ሜትር ያህልም ይረዝማል። ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በደቡብ ኢትዮጵያ ያለውን የነዳጅ ምርት ፍላጎት ለማሟላት የሚሰራ ይሆናል። ከላሙ ወደብ - ኢሲኦሎ-ሞያሌ - ሐዋሳ - አዲስ አበባ የሚዘረጋው የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ፕሮጀክት ዝርጋታ የጸደቀው በኬንያ መንግሥት እአአ 2016 ላይ ነበር። ከዚያም ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ድርድሮች ከተካሄዱ በኋላ በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈርሟል። የላሙ ወደብ 4. ላሙ ወደብ ይህ ወደብ የሚገነባው በኬንያዋ ላሙ ግዛት ውስጥ ሲሆን 32 መርከቦች በተመሳሳይ ሰዓት መልህቃቸውን እንዲጥሉ የሚያስችል ነው። የዚህ ወደብ ግንባታ አጠቃላይ ወጪ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። የመጀመሪያዎቹ ሦስት መርከብ ማረፊያዎች ግንባታ ወጪ በኬንያ መንግሥት የሚሸፍን ይሆናል ተብሏል። የመጀመሪያው መርከብ ማቆሚያ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ሁለተኛው እና ሦስተኛዎቹ የመርከብ ማቆሚያዎች ግንባታ ደግሞ በቀጣይ ወራት ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይገመታል። ይህንንም ተከትሎ የላሙ ወደብን ወደ ሥራ ለማስገባ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። 5. የአየር ማረፊያዎች ግንባታ በላፕሴት ፕሮጄክት ውስጥ ከተያዙት ፕሮጄክቶች መካከል የሦስት አየር ማረፊያዎች ግንባታ ይገኝበታል። ሦስቱም አየር ማረፊያዎች በኬንያ ላሙ እና ቱርካና ግዛት እንዲሁም በኢሲኦሎ ከተማ የሚገነቡ ናቸው። የእነዚህ አየር ማረፊያዎች ግንባታም እያንዳንዳቸው ከ143 እስከ 188 ሚሊዮን ዶላር የሚያስወጡ ይሆናሉ። 6. ሪዞርት ከተሞች ግንባታ የላፕሴት ፕሮጄክት ሌላው አካል የሦስት መዝናኛ ከተሞች ግንባታ ነው። የሪዞርት ከተሞቹ በኬንያዎቹ ላሙ፣ ኢሲኦሎ እና ቱርካና ሐይቅ ላይ የሚገነቡ ናቸው። ወጪያቸውም እንደ የቅድመ ተከተላቸው 970፣ 200 እና 42 ሚሊዮን ዶላር ወጪን ይጠይቃል ተብሏል። የኬንያ መንግሥት ከተሞቹ በሚገነቡባቸው ስፍራዎች የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን ካጠናቀቀ በኋላ፤ የከተሞቹ ግንባታ የሚከናወነው በግል ኢንቨስተሮች ይሆናል። በአሁኑ ሰዓት የላሙ ሪዞርት ከተማ ማስተር ፕላን ዝግጅት እየተካሄደ ይገኛል።
54989207
https://www.bbc.com/amharic/54989207
"የባይደን መምጣት ትራምፕ ግድቡን በተመለከተ ይሰጡት የነበረውን ባዶ ተስፋ ይቀንሳል"
ከሳምንታት በፊት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አወዛጋቢ የተባለውን ግብፅ "ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች" ብለው መናገራቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ፤ አዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ማብራሪያ ጠይቃለች።
በዩናይትድ ኪንግደም፣ ለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ንግግሩን በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል፤ በበርካታ ኢትዮጵያውያንም ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል። ከሳምንት በፊት በተካሄደው የአሜሪካ ምርጫ የዴሞክራት እጩው ጆ ባይደን ማሸነፋቸው ይፋ ተደርጓል። የጆ ባይደን ማሸነፍ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲሁም የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሦስትዮሽ ውይይት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ይኖር ይሆን? የምሥራቅ ናይል ቴክኒካዊ አህጉራዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ከሆኑት አቶ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ ጋር ቆይታ አድርገናል። ቢቢሲ፡ የጆ ባይደን ማሸነፍ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲሁም የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሦስትዮሽ ውይይት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ አለ? አቶ ፈቅአሕመድ፡ የአገር ፖሊሲ ስለሆነ የፖሊሲ ለውጥ አይኖርም። አሜሪካ ከግብፅም ከኢትዮጵያ ጋርም አጋርነት ስላላት ማስቀየም አትፈልገም። ማስቀየም ካለባት ግን ግብፅን ማስቀየም አትፈልግም። ትራምፕ እንደሚሉት ግድቡን ማፍረስ ወይም ማውደም በተበላሸ ዲዛይን የተገነባ ሪልስቴት እንደማፍረስ ነው። ግድቡን ማፍረስ ተከትሎ የሚመጣውን ብጥብጥ፣ ረብሻ እና እልቂትን አላሰቡም። ባይደን ሲመጡ ይህንን ንግግር ተከትሎ የሚመጣው ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ይወገዳል። ባይደን ከ40 ዓመት በላይ በፖለቲካው ቆይተዋል። ከኦባማ ጋር ሰርተዋል። አፍሪካን መረዳታቸውና ከግል ባህሪያቸው አንጻር ንግግሩ የሚያመጣው ተጽዕኖ ይቀረፋል። በአገራቶቹ መካከል ያለውን ልዩነት ስንመለከት በተለይ የአሜሪካ መሪዎች ግድቡን በተመለከ መፍትሔ ያመጡልናል የሚል እምነት ስላለ። በተለይ [ግብፆች] ፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ ትልቅ እምነት ነበራቸው። ስለዚህ ወደ ስምምነት የመቅረብ ፍላጎት አያሳዩም ነበር። ባይደን መምጣታቸው ትራምፕ ይሰጣቸው የነበሩ ባዶ ተስፋና ድጋፍን ይቀንሳል። ስለዚህም አገራቱ በተሻለ ሁኔታ የመነጋገርና ፍላጎቱ ካላቸው ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲመጡ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ። ቢቢሲ፡ የትራምፕ ንግግር ግብፅ ግድቡ ላይ ጥቃት እንድትሰነዝር በማደፋፈር፣ በድርድሩ ያላትን አቋም በመቀየር ወይም በሌላ መንገድ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል? አቶ ፈቅአሕመድ፡ የግብፅ መሪዎች ግድቡን በተመለከተ መፍትሔ እናገኛለን ብለው የሚያስቡት ከምዕራባውያን አገራትና መሪዎች ነው። በተለይ ትራምፕ መፍትሔ ይሰጣል የሚል እምነት አላቸው። የትራምፕ ንግግር ግብፆችን ልባቸውን ከማሞቅ ድርድሩ ላይ በፊት የነበራቸውን ያለመስማማት ፍላጎት ከማጠናከር ውጪ የሚያመጣው ነገር የለም። ያው ግብፆች ግን ንግግሩን በመስማት አሜሪካ ከጎናችን ነች በማለት በፊት ከነበራቸው አቋም ትንሽ ጠንከር ያለ አቋም ይዞ የመምጣት ሁኔታ ይኖራል ብዬ እገምታለሁ። በፊት ከጠየቁት የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝላቸው አቋም ይዘው የመምጣት ሁኔታ ይኖራል። የትራምፕ አለመኖር እነሱ እንደ ድጋፍ የሚወስዱትን ባዶ ተስፋ ያስቀራል የሚል እምነት አለኝ። ከዛ ውጪ በግድቡም ሆነ በድርድሩ ሂደት ላይ ምንም ተጽዕኖ አይኖረውም። ቢቢሲ፡ አሜሪካ እንዲሁም የዓለም ባንክ በሦስትዮሽ ድርድሩ ጣልቃ መግባታቸው ላይ ጥያቄ የሚያነሱ አሉ። እርስዎ ደግሞ የባይደን መኖር አገራቱ ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲመጡ ሁኔታዎች ሊያመቻች ይችላል ያሉትን ነጥብ ያብራሩልን። አቶ ፈቅአሕመድ፡ በወሰን ተሻጋሪ ውሃ (በተለይ በናይል ውስጥ) የሦስተኛ አካል ተሳትፎ አይደገፍም። ሦስተኛ አካል ወደ ድርድሩ ሲመጣ የራሱን ጥቅም ለማስከበር ነው። የራሱ ፍላጎት አለው። ያ የሱ ፍላጎት ደግሞ ከአገራቱ ፍላጎት ጋር እንደማይጣጣም የታወቀ ነው። አገራቱ ልዩነት ቢኖራቸውም ልዩነታቸውን አጥብበው መስማማት ይችላሉ። ምክንያቱም የራሳቸው ፍላጎት፣ ስጋትና ፍርሀት አላቸው። በወንዙ ተሳስረዋል። ተለያይተው መኖር አይችሉም። ስለዚህ ልዩነታቸውን መፍታት አለባቸው። ሦስተኛው አካል ግን ፍላጎቱ በፍጹም ከነዚህ አገራት ጋር አይጣጣምም። የሶስተኛውን ፍላጎት ለመሳካት በሚያደርገው ጥረት በአገራቱ መካከል አንዳንዴ አላስፈላጊ ግጭት መፍጠር ይችላል። ስለዚህ ሦስተኛ አካል ባይገባና አገራቱ ራሳቸው ልዩነታቸውን አጥብበው ወደ ስምምነት ቢመጡ ይመረጣል። የባይደን መመረጥ በአገራቶቹ መካከል መስማማት ሊያፋጥን ይችላል ያልኩት በሂደቱ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ሳይሆን ጣልቃ ባለመግባት ነው። ባይደን ጣልቃ አይገቡም የሚል እምነት አለኝ። ጣልቃ ቢገቡም ትራምፕ እንዳደረጉት ገፍተው ሄደው፣ የአንድን አገር ሉዓላዊ መብት ጨፍልቀው ወይም በአገራቱ መካከል መጨረሻ የሌለው ግጭት እንዲነሳ የሚያበረታታ ንግግር አያደርጉም። አንድን አገር ለይተው ድጋፍ ካልሰጡ አገራቱ የሚደራደሩት በተስተካከለ ሜዳ ላይ፣ ሁሉም ተመሳሳይ አቋም ይዘው ይሆናል። ስለዚህም በቀላሉ ልዩነታቸውን ሊፈቱ ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ። ባይደን በዚ ሁደት ቢሳተፉ የአገሪቷ ፖሊሲ ስላለ ማድላታቸው ስለማይቀር ያው ተመልሶ ልዩነቱ እየሰፋ ነው የሚሄደው። ስለዚህ እሳቸው ስምምነቱን የሚያፋጥኑት ጣልቃ ባለመግባት ነው። ቢቢሲ፡ አሜሪካ በቅርቡ ይፋ እንዳደረገችው ሱዳንን ሽብርተኝነትን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር የማውጣት እቅድ አለ። ይህ ደግሞ በምጣኔ ሀብቷ ላይ ልዩነት ሊፈጥር ይችላል። ባለፈው ትራምፕ ከተናገሩት በመሳት ደግሞ በአሜሪካ በኩል፤ ሱዳን ኢትዮጵያ ላይ ጫና እንድታሳድር የመግፋት ነገር ሊኖር እንደሚችል መረዳት ይቻላል። ይህ አዝማሚያ በባይደን አስተዳደርም የሚቀጥል ነው? አቶ ፈቅአሕመድ፡ አሜሪካ ሱዳንን ሽብርተኛን የምትደግፍ በሚል ማዕቀብ በመጣል የአገሪቷን ኢኮኖሚ ስታሽመደምድ እና አገሪቷንም ከፍተኛ ብጥብጥ ውስጥ ስትከት ነበር። ያ እንደ አገር የሚከተሉት ፖሊሲ ነው። ይሁን እንጂ በአሁን ወቅት ሱዳንን ከዚህ ዝርዝር ውስጥ እናወጣሻለን፣ ማዕቀቡንም እናነሳለን፣ የኢኮኖሚ ግንኙነትም እናጠናክራለን፤ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ፍጠሪ የሚለው ግን ፕሬዘዳንት ትራምፕ የጨመሩበት አቅጣጫ ነው። የአገር ፖሊሲ አይደለም። ስለዚህ በጣም ዝርዝር ጉዳይ ስለሆነ የፖሊሲ ጉዳይም አይሆንም። ትራምፕና መንግሥታቸው ግብፅን ለመጥቀም አልፎም በሱዳን እና እስራኤል መካከል ስምምነት ለመፍጠር በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ያለ ነው። በተለይም ትራምፕ በእስራኤል እና በፍልስጥኤም መካከል ሰላም ለማውረድ ያዘጋጁት ስምምነት ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያደርጉት ጥረትም አካል ነው። አሁን በሱዳን ላይ እያሳደሩ ያሉት ጫና ግብፅን ለመጥቀም ሲባል ፕሬዘዳንት ትራምፕና መንግሥታቸው የተከተሉት አቅጣጫ ነው እንጂ የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ ነው የሚል እምነት የለኝም። ቢቢሲ፡ ግብፅ ከምትተችባቸው ነገሮች አንዱ የኢትዮጵያን ውስጣዊ ፖለቲካ የግድቡ ግንባታ ወይም ድርድሩ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር መጠቀሟ ነው። አሁን ደግሞ የፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልል ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በግድቡ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል? አቶ ፈቅአሕመድ፡ ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በናይል ተፋሰስ አገራት ላይ ከምትከተላቸው በርካታ ስልቶች ውስጥ አንደኛው የተፋሰሱን አገራት ደካማ፣ ተጋላጭና ያልተረጋጉ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በተለይ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ አንድም አገራቶቹ ልማት ላይ ያላቸውን ትኩረት ይቀንሳሉ፤ የጀመሩትን ያቆማሉ የሚል እምነት አላቸው። ስለዚህ ያንን አለመረጋጋት ለማበረታታት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ስለዚህ በዚያ በኩል የራሳቸውን እንቅስቃሴ ያደርጋሉ የሚል እምነት ነው ያለኝ። ይሁን እንጂ በግድቡ ግንባታ ላይ የሚመጣ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አይኖርም። ምክንያቱም የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተለየ ሁኔታ የሚታይ ስለሆነ። ከዚያ ውጭ ድርድሩ ይቀጥላል። ከድርድሩ ጋር ይህም ቢሆን ቀጥተኛ ግንኙነት የለውም። በእነሱ እምነት ይህ ሁኔታ ለነሱ ትልቅ ዕድል እንደሚሰጣቸው አድርገው ነው የሚወስዱት። መሬት ላይ ስንወርድ ግን እምብዛም ተፅዕኖ ያለው አይመስለኝም። ቢቢሲ፡ ድርድሩ ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ በድጋሚ መጀመሩ ይታወሳል። አሁን ድርድሩ ምን ላይ ይገኛል? አቶ ፈቅአሕመድ፡ ባለኝ መረጃ አሁን እየተናገጋገሩ ያሉት አደራዳሪ ወይንም አሸማጋይ በሆነው የአፍሪካ ሕብረት ሚና ላይ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ሚና ምን ይሁን? የሚለው ላይ ሦስቱ አገራት ተነጋግረው መስማማት አልቻሉም። በተለይ ኢትዮጵያና ሱዳን በድርድሩ ውስጥ ሕብረቱ የተሻለ ሚና እንዲኖረው ይፈልጋሉ። ግብፅ ግን የአፍሪካ ሕብረት የተሻለ ሚና ይቅርና አደራዳሪ እንዲሆንም አትፈልግም። ምክንያቱም የአፍሪካ ሕብረት እንደ አሜሪካ መንግሥት ወይም እንደ ትራምፕ መንግሥት ለነሱ አድልቶ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚነካ፣ የወደፊት በውሃው የመጠቀም ተስፋ የሚያጨልም ስምምነት እንድትፈርም ያስገድዳታል የሚል እምነት የላቸውም። ስለዚህ ግብፆች የአፍሪካ ሕብረት ባይሳተፍ ይመርጣሉ። አልተስማሙም እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ ነው እየተነጋገሩ ያሉት።