id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-53021260
https://www.bbc.com/amharic/news-53021260
ቀጣዩ 8.5 በመቶ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት በባለሙያዎች ዕይታ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደሚያደርገው በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት አዳራሽ ሐሙስ ሰኔ አራት ቀን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ 476.1 ቢሊዮን ብር ገደማ ይሆናል በተባለው በቀጣዩ የበጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቷል።
ከዚሁ ውስጥ በመንግሥት ረቂቅ በጀት መሰረት 176 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚሆነው ለክልሎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የፌዴራል መንግሥት ደግሞ ለመደበኛ ወጪዎቹ 133 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎቹ 160 ቢሊዮን ብር ይደርሰዋል መባሉን የአገር ውስጥ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች ዘግበዋል። ረቂቅ በጀቱን በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት የፌዴራል መንግሥቱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ቀጣዩ የበጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት እንደሚመዘገብ ለሕዝብ እንደራሴዎቹ ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ 9 በመቶ የምጣኔ ሃብት ዕድገትን እጠብቃለሁ ብላ ነበር። ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት ምጣኔ ሃብት ላይ ከባድ የሚባል ጫናን እየፈጠረ ባለበትና የዚህ በሽታ ተጽዕኖ ለዓመታት ባይሆን ለቀጣይ ረዥም ወራት እንሚቀጥል እየተነገረ ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዚህ መጠን ሊያድግ የሚችልበት ዕድል መኖሩ እያነጋገረ ነው። የቀጣዩን የበጀት ዓመት የአገሪቱን በጀትና ተጠባቂ ዕድገትን በተመለከተ ቢቢሲ የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎቹን አለማየሁ ገዳን (ዶ/ር) እና አቶ ዋሲሁን በላይ ያላቸውን ዕይታ ጠይቋል። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ አቶ ዋሲሁን በላይ ባለፈው የበጀት ዓመት ቀርቦ ከነበረው 386.9 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ የቀረበው በጀት ከፍ ያለ ብልጫ ያለው ቢመስልም፤ በመገባደድ ላይ ያለው የበጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት መንግሥት 28 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ በጀት ማስፀደቁን ጨምረው በማስታወስ አሁንም ጭማሪው የሚታይ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ነገር ግን የቀጣይ ዓመት የአገሪቱ በጀት ከመጨመሩ ጎን ለጎን ይመዘገባል ተብሎ በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበው የተጠባቂ ዕድገት ቁጥር ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ላይ ባለሞያዎቹ ጥያቄዎችን ያነሳሉ። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ዙርያ ምጣኔ ሃብቶችን በሚገዳደርበት እና "በርካታ አገራት ዕድገታቸው የቁልቁል እንደሚሆን በተነበዩበት ወቅት፤ ከስምንት በመቶ የሚሻገር ዕድገትን መጠበቅ አስቸጋሪ ነው" ይላሉ አለማየሁ (ዶ/ር)። "ምናልባት በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበው የተጠባቂ ዕድገት መጠን በወረርሽኙ የሚደርሰውን ምጣኔ ሃብታዊ ጡጫ ያላካተተ ይሆን?" ሲሉም ይጠይቃሉ። ወረርሽኙ በ2013 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት (ከቀጣዩ ሐምሌ እስከ መስከረም) ድረስ የኢትዮጵያን ምጣኔ ሃብት ክፉኛ ይደቁሳል፤ ከዚያ ወዲያ ግን ተግ ይላል ብለን ብናስብ እንኳ ይላሉ ባለሞያው አለማየሁ "በእኔ ግምት ምጣኔ ሃብቱ በ5.6 በመቶ ይቀነሳል" ሲሉ የእራሳቸውን እይታ ያስቀምጣሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ግምታቸውን ባደረጉት ጥናት ላይ መሠረት እንዳደረጉ ይገልፁና "ይህ ማለት የ8.5 በመቶ ዕድገት ላይ ለመድረስ ወረርሽኑ ከሚያደርሰው ጉዳት ጋር የሚደመር አጠቃላይ የ14 በመቶ ገደማ ይጠበቃል እንደማለት ነው" ይላሉ። ይህን መሰል ዕድገት ማስመዝገብ ደግሞ የመሆን ዕድሉ የጠበበ ነው ባይ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትሩ የተጠባቂ ዕድገት መግለጫ የወረርሽኙን ጉዳት ያላካተተ ከሆነ ግን ከጉዳቱ ጋር ተወራርዶ የሚኖረው ዕድገት 3 በመቶን የሚጠጋ ይሆናል እንደማለት ነው እንደእርሳቸው ግምት። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን እንደሚሉት ምንም እንኳ የወረርሽኙ ዳፋ ለኢትዮጵያ ባይቀርላትም፤ ቢያንስ እስካሁን እጅጉን የተጋነነ ስርጭትን ባለማስተዋሏ ወደሌሎች አገራት የምትልካቸው ቡናን የመሳሰሉ ምርቶች ፍላጎትም ሲቀንስ ባለመታየቱ መልካም ነገር ነው ይላሉ። የኮሮናቫይረስ ጣጣ ለረጅም ጊዜ ሊዘልቅ እንደሚችል የሚሰጉት አለማየሁ (ዶ/ር) እንደሚሉት የወረርሽኙ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ላይ ብቻ ይቀጥላል ማለት "ይህ ጥሩ የሚባለው፥ ከቀናን (ቤስት ኬዝ ሲናርዮ) የሚባለው ግምት ነው" ይላሉ። ወደ እውነታ የሚጠጋው ግምት ግን የወረርሽኙ ምጣኔ ሃብታዊ ጫና "አነሰ ቢባል ለስድስት ወራት ያህል፤ ያ ማለት እስከ ታኅሳስ ወር ድረስ" ይዘልቃል የሚለው ነው እንደ አለማየሁ (ዶ/ር)። ለሁለት ሩብ የበጀት ዓመታት ያ ማለት እስከወርሃ ታህሳስ ድረስ የኮቪድ-19 መዘዝንና ቡጢውን ምጣኔ ሃብቱ ላይ ማሳረፉን ከቀጠለ ደግሞ ባለሙያው እንደሚገምቱት ምጣኔ ሃብቱ በአስራ አንድ በመቶ እንደሚቀንስ ነው። "በታዳጊ አገራት ከፍ ያለ ዕድገትን ማስመዝገብ አስገራሚ ነገር አይደለም" የሚሉት አቶ ዋሲሁን፤ ከዚሁም አንፃር በአዲሱ የበጀት ዓመት 8.5 በመቶ ዕድገት ይመዘገባል መባሉ የሚደንቅ ሊሆን አይገባም ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ከፍተኛ በጀት በጅተህ መሠረተ ልማት ላይ ማፍሰስ ብቻውን እኮ የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን (ጂዲፒውን) እንዲያድግ ያደርገዋል" ሲሉ የእድገት ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉት ነገሮች መካከል ይጠቅሳሉ፤ አቶ ዋሲሁን። አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ ምጣኔ ሃብቱን ለማረጋጋት ብሎም ለማነቃቃት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ያደንቃሉ፤ የበለጠ እንዲያደርግም ይመክራሉ። በአንድ በኩል መንግሥት እንደሌሎች በርካታ አገራት ምጣኔ ሃብቱን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት በኢትዮጵያ አውድ እንደማያዋጣ አውቆ እርሱን ያለማድረጉ እና ከዚያ ይልቅ ሥራዎች ከሞላ ጎደል እየተሰሩ ጥንቃቄዎች እንዲወሰዱ ማድረግን ዓይነተኛ አቅጣጫ አድርጎ መንቀሳቀሱ ተገቢ ነበር ይላሉ። "ሰዎች የጤናቸው ሁኔታ ባሉበት መስሪያ ቤት አካባቢ እየተጠበቀ፤ ምጣኔ ሃብቱ እንዲንቀሳቀስ ማድረጉ ቆንጆ ነገር ነው።" በሌላ ወገን ወረርሽኙ ለሚጎዱ ዘርፎች የማነቃቂያ ድጋፍ ማዘጋጀቱና ይህንን ለማቅረብ መስራቱም መልካም ነው ባይ ናቸው። ሆኖም "የግል ክፍለ-ኢኮኖሚውን በተለይ ኢንደስትሪው አገልግሎት ላይ ያሉትን ሰዎች እንዴት እንደሚደግፍ ኮስተር ያለ ዕቅድ አውጥቶ መከታተል ያለበት ይመስለኛል። [የእስካሁኑን እንቅስቃሴ] ሳየው ወጥ የሆነ አሰራር አይመስልም" ይላሉ። "በደንብ ታስቦበት፣ በአጭር ጊዜ እንደዚህ [ይሆናል] በረጅም ጊዜ እንደዚህ [ይሆናል] ተብሎ እየተሄደበት አይመስለኝም።" ከዚህም በዘለለ ቁጥራቸው ከሦስት ሚሊዮን ይሻገራል ያሏቸውን ራሳቸውን በራሳቸው (አንዳንዶቹ) ቤተሰባቸውን ጨምሮ የሚያስተዳድሩ ሰዎች "የመንግሥታዊ ድጋፍ ጠበል አልደረሳቸውም" ይላሉ። የእነዚህ ሰዎች ዋነኛ ወጪ የመስሪያ ቦታ ኪራይ ክፍያ በመሆኑ እርሱን በተመለከተ በአከራዮች በጎ ፈቃድ ላይ የማይመሰረት የክፍያ ቅነሳ እርምጃ ያስፈልጋል ባይ ናቸው። መንግሥት የኪራይ ወጪያቸውን በተወሰነ ድርሻ እንዲከፍል ማድረግም ሌላ የማነቃቂያ እርምጃ ሊሆን ይችላል ሲሉ አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚችለውን ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ትንበያን በተመለከተ አቶ ዋሲሁን ግምታቸውን ሲያስቀምጡ "የተለጠጠ ታቅድና በጥረት የምትደርስበት ያህል ነው የምትሰራው። መንግሥት ይሄን ሲያስቀምጥ የጥረቱን ያስቀመጠ ይመስለኛል።" "ምክንያቱም ምን ያህል በሽተኛ ይዘህ ነው 8.5 በመቶ አድጋለሁ የምትለው? ሰላሳ አርባ ሺህ ነው ወይንስ አሁን እየሆነ እንዳለው በየቀኑ መቶ መቶ እየጨመርን? የሚለውም መታየት አለበት" ሲሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቀጣይ ወራት ሊፈጥር የሚችለው እንቅፋት ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለበት ይጠቅሳሉ።
52534319
https://www.bbc.com/amharic/52534319
ኮሮናቫይረስ፡ በስልጤ ዞን ኮቪድ-19 ያለባቸው ሴት እንዴት ሊገኙ ቻሉ?
የጤና ጥበቃ ሚንስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በየዕለቱ በሚያወጡት የ24 ሰዓታት የኮሮናቫይረስ ሪፖርት እሁድ፣ ሚያዚያ 25 2012 ዓ.ም ለ1560 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ሁለት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።
የመጀመሪያው ታማሚ የ49 ዓመት ኢትዮጵያዊ በአዲስ አበባ ህክምና በመከታተል ላይ ያሉ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊት እና በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ነዋሪ ናቸው። አብዱልዋሪስ ጀማል የስልጤ ዞን የጤና መምሪያ ኃላፊ ሲሆኑ በዞኑ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የተደራጀው ቡድን የተለያዩ ሥራዎችን ሲያከናውን ነበር ብለዋል። • በኮሮናቫይረስ እንዳንያዝ የተፈጥሮ በሽታን የመከላከያ ሥርዓታችን መገንባት • "ያስጨነቀኝ ከእኔ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ጤንነት ነበር" የኮሮናቫይረስ ታማሚዋ ከባህር ዳር "የቤት ለቤት አሰሳ እና ጉብኝት እንሠራ ነበር። በተዘጋጀው ማኑዋል መሠረት የጤና ባለሙያዎች፣ በጎ ፈቃደኞች እና ሌሎችን በማስልጠን ባለፉት 2 ሳምንታት ከ93 ሺህ ቤተሰቦች ወይም ከ324 ሺህ በላይ ግለሰቦችን በቤታቸው በማስተማር ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተሰርቷል። ጎን ለጎንም ቫይረሱ ያለባቸውን የመለየት ሥራ ተከናውኗል።" በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ45 ዓመት ሴት በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ነዋሪ ናቸው። ግለሰቧ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው በተመሳሳይ ቤት ለቤት በተደረገ አሰሳ ነው። አቶ ካሚል ጃቢር በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሲሆኑ በወረዳው ኮሚቴ በማዋቀር፣ ግብዓት በማሟላት እና በጀት በማጽደቅ በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውቀዋል። "500 ሺህ ብር ወጪ ተደርጎ የመከላከል ሥራ ተሠርቷል። . . . በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወጡ ክልከላዎችን በማስተግበር እና ግንዛቤ በመፍጠር ዙሪያ ተሰርቷል" ይላሉ። "አካሄድ ቀየረን" የሚሉት አቶ ካሚል "እስከ ሚያዝያ 24 ድረስ 7800 አባወራዎችን ተደራሽ አድርገናል። ይህም 32 ሺህ 590 አካባቢ ሰዎችን ደርሰናል ማለት ነው። ምልክቶች መለየትና ለወረዳ ሪፖርት ማድረግ በተጨማሪነት ይሠራል። ከዚያም ለዞን ሪፖርት ይደረጋል" ሲሉ ያስረዳሉ። • ኮሮናቫይረስ ሁለቴ ሊይዘን ይችላል? የ45 ዓመቷ በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ነዋሪ ሆኑት ግለሰብም በዚሁ መሠረት ነው ሊለዩ የቻሉት። አንዲት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ በቀበሌ ውስጥ በምታስተምርበት ወቅት ሳል ያለባቸው 4 ሰዎችን በመለየት ለወረዳው መረጃ ትሰጣለች። "የወረዳው ፈጣን ምላሽ ሰጪ ኮሚቴ ሄዶ ካጣራ በኋላ በዞን ደረጃ ላለው ኮሚቴ ሐሙስ ሪፖርት አድርጓል። አርብ ለአራቱ ሰዎች እና በሌሎች ሆስፒታሎች ያሉ ተጠርጣሪዎችን ናሙና ሰብበስበን ወደ ሃዋሳ ልከናል። እሁድ ውጤቱን ሰምተናል" ሲሉ አቶ አብዱላዋሪስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ በኋላ ከግለሰቧ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ሥራ ማከናወን ተሰርቷል። "ከእሷ ጋር ንክኪ ያላቸውን ቤተሰቦች እና ቅርብ ንክኪ ያላቸውን ሌሎች 16 ሰዎች ወደ ማቆያ አስገብተናል። እሷ ወደ ወራቤ ሆስፒታል አምርታለች" ብለዋል አቶ ካሚል። እንደ አቶ ካሚል ገለጻ ከሆነ ባለቤቷ ቀደም ሲል ናሙና ከተወሰደላቸው አራት ሰዎች አንዱ ሆኖ ነጻ መሆኑ ቢረጋገጠም ናሙናው ከተወሰደ በኋላ ከባለቤቱ ጋር በድጋሚ ንክኪ ስለነበረው ወደማቆያ እንዲገባ ተደርጓል። የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል ትኩረቱን ቫይረሱን በመከላከል ላይ አድረጎ እየሰራ ይገኛል። ኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰቱ ከተገለጸ ጀምሮ ማህበራዊ ርቀትን፣ የግል ንጽህናን ስለመጠበቅ እና ሰለቫይረሱ የሚረዱ ሌሎች መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ሲያደርስ ቆይቷል። ጎን ለጎን ደግሞ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቢመጡ በሚል ዞኑ ያለውን ሃብት በጠቀም ለይቶ ማቆያ እና ህክምና መስጫ ሲያዘጋጁ መቆየታቸውን የሆስፒታሉ ባልደረባ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፈድሉ ጀንፋ ገልጸውልናል። "ግለሰቧ የ45 ዓመት እናት ናቸው። ከገጠር ወረዳ ቀበሌ የመጡ ናቸው። ከውጭ ጉዞም ሆነ ከሚጠረጠር ሰው ወይም ከሚታወቅ ሰው ጋር ግንኙነት ስላላቸው ሳይሆን የምትጠረጥሯቸውን እና ሳልና ትኩሳት ያለባቸውን ሰዎች ናሙና መላክ ትችላላችሁ በመባሉ ነው የተገኙት። እኚህ እናት ለሁለት ሳምንት ገደማ ሳል ስለነበራቸው ናሙናቸው ተላከ። አሁን 'ስቴብል' ናቸው። ለሳምንታት የነበራቸው ደረቅ ሳል አሁን ትንሽ ሲሆን እሱም እየጠፋ ነው። ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ምንም ምልክት ወደሌለው እየተቀየሩ ነው" ሲሉ ስለጤንነታቸው ሁኔታ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሁኔታ መልሰዋል። • የኪነጥበብ ባለሙያዎች መልዕክት ስለ ኮሮናቫይረስ • ኦፕራህ ዊንፍሬይ ኮሮናቫይረስ በጥቁሮች መጨከኑ እየረበሻት እንደሆነ ተናገረች የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እና ከተተረጠረም ሆነ ቫይረሱ እንዳለበት ከታወቀ ግለሰብ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖራቸው በቫይረሱ መያዛቸው ስጋት አይፈጥርም ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ስጋት ይፈጥራል። በጣም ይፈጥራል። ቫይረሱ እንዴት እሳቸው ጋር እንደደረሰ ለማወቅ እየተሠራ ነው። እሳቸው ባያምኑበትም ከውጭ ከመጣ ሰው ጋር ንክኪ ነበራቸው የሚል መረጃ እየደረሰን ነው። በህብረተሰቡ ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት እንደሌለ ስለሚታወቅ ስጋት ይፈጥራል" ብለዋል። ሁሉም እስካሁን ያሉት [በቫይረሱ የተያዙት] ከውጭ የመጡ ወይም ንኪኪ ያላቸው እንጂ ወደ በህብረተሰብ ውስጥ ስርጭት ስለመኖሩ አልታወቀም የሚል እሳቤ ነው ያለው። ሴትየዋ የቤት እመቤት ናቸው። ገበያ ይሄዳሉ። ሳሉ ከጀመራቸውም በኋላ ገበያ ሄደዋል። ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ተብሎ 35 ሰዎች ተለይተው ለ14 ቀን ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል። "ስጋት አለ" ይላሉ ዶ/ር ፈድሉ። በህብረተብ ደረጃ ስርጭት ወደምንለው ደረጃ መሸጋገሩን የሚያሳይም ሊሆን ይችላል ብለዋል ለቢቢሲ ጉዳዩን ሲያስረዱ። "አሁን ባለው መረጃ ማለት ንክኪ የላትም ብለን መናገር የምንችልበት ደረጃ ላይ አልደረስንም " ብለዋል። ናሙና ሲወሰድ የሚሞላ ፎርም አለው። የጉዞ ታሪክ፣ ከበሽታው ከተጠረጠረ ወይም ከታየበት ጋር ንክኪ ስለመኖሩ ጥያቄ ይቀርባል። "በዚህ በኩል በደንብ ለማጣራት ሞክረናል። በአካባቢው ወደሚገኙ ገበያዎች ይንቀሳቀሳሉ። ከውጭ ከመጡ፣ ከአዲስ አበበባ ከመጡ ሰዎች ጋር ንክኪ ካለ ለማጣራት በጣም ጥረት አድርገናል። እስካሁን ግን ያላገኘንበት ሁኔታ ነው ያለው። በአካካቢው የተጠናከረ ስራ እየሰራን ነው። ግንኙነት ያላቸውን ናሙና ወስደን ዛሬ ልከናል። ሁኔታው በጣም አስደንጋጭ ነው። ግለሰቧ የገጠር ነዋሪ ናቸው። አሁን የተጠናከረ ስራ እየሠራን ነው።" ያሉት ደግሞ አቶ አብዱላዋሪስ ናቸው። በዞኑ የቫይረሱን ስርጨት ለመቆጣጠር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የወጡ ደንቦች ተግባራዊ እንዲሆን በመስራት ላይ መሆናቸው ኃላፊዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደወረዳቸው ስጋቶች መኖራቸውን ያጫወቱን አቶ ካሚል በተሽከርካሪዎች ትርፍ መጫን፣ በገበያ ቦታዎች ርቀትን አለመጠበቅ ይታያል ብለዋል። ባለፉት ቀናት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ መሆን መዘናጋት መፍጠሩን አስረድተዋል። በቤተ እምነቶች አካባቢ ደንቦች እየተከበሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን ግን በወረዳው "ባለ ሶስት እግር ተስከርካሪዎች አንድ ሰው ብቻ እንዲጭኑ፣ ጋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ፣ ሞተር ሳይክሎች እንዳይንቀሳቀሱ (የመንግስት ሞተር ሳይክሎች ሰው እንዳይጭኑ)፣ በከተሞች እና ሰዎች በሚበዛባቸው ከጉልት ያለፈ ትልቅ ገበያ ተከልክሏል" ብለዋል። • የመጀመሪያውን ኮሮናቫይረስ ስላገኘችው ሴት ያውቃሉ? እንደ አቶ ካሚልም ከሆነ ከተማው ላይ ጫት መሸጥም ተከለከለ ሲሆን፣ የሚሸጡ ሲገኙም እየታሸገባቸው ነው። የጀበና ቡና ሽያጭ የተከለከለ ሲሆን "ሁኔታዎችን እያየን ተጨማሪ እርምጃዎችን እንወስዳለን" ብለዋል። እንደ አቶ አብዱላዋሪስ ጀማል ከሆነ ስልጤ ዞን ለቫይረሱ "ተጋላጭ ዞን" ነው። "በርካታ የአካባቢው ሰዎች በሥራ ምክንያት ወደተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተሰራጭተዋል። ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት በኮሮና ምክንያት እየተመለሱ ነው" ሲሉ ምክንያታቸውን ያስቀምጣሉ። • ኮሮናቫይረስ ቤተሰብን ያቀራርብ ወይስ ያራርቅ ይሆን? "ቀደም ሲል 305 ሰዎችን በወራቤ ዩኒኒቨርሲቲ ማቆያ ለ14 ቀናት አቆይተናል። እነዚህ ከአዲስ አበባ እና አዳማ የመጡ ሲሆን ምንም ምልክት ስላላሳዩ ክትትል በማድረግ ወደ ቤተሰብ መልሰናቸዋል። ዞኑ ተጋላጭ በመሆኑ እና ከህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ እስካሁን ትንሽ ነው የተመመረረው" ብለዋል። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማሽን ለማስገባት በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸውልናል።
43484631
https://www.bbc.com/amharic/43484631
ለጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ዓይኖች በእነዚህ ሰዎች ላይ ናቸው
ያሳለፍናቸው ሁለት ወራት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታን ይዘው አልፈዋል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ጠንካራ የሚባል የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ ተከናወነ። በቀጣዮቹ ቀናት በሽብር ወንጀል የተከሰሱና ተፈርዶባቸው የነበሩ ፖለቲከኞች እንዲሁም ጋዜጠኞችም ተፈቱ፤ ለጥቆም ጠቅላይ ሚንስትሩ የስልጣን ልልቀቅ ጥያቄያቸውን አቀረቡ፤ ተከትሎም አነጋጋሪ የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ተሰናባቹን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ማን ይተካቸዋል የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው። በርካቶችም በማህበራዊ የትስስር ዘፌዎች እና መገናኛ ብዙሃን ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩን ሊተኳቸው ይችላሉ የሚሏቸውን ሰዎች ሲጠቅሱ ቆይተዋል። ማዕከላዊ ስብሰባውን አጠናቆ ወደ ምክር ቤት ስብሰባ የዘለቀው ኢህአዴግ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ከባድ የሚባሉ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። 180 አባላት ያሉት ይህ ምክር ቤት ከሚወያይባቸው አበይት አጀንዳዎች አንዱ የፓርቲውን ሊቀ-መንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያምን የሚተካ መሪ መምረጥ ነው። የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 73 ንዑስ አንቀጽ 1 ስለ ጠቅላይ ሚንስትሩ አሰያየም በግልጽ እንደሚያትተው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ይመረጣል። ሊመረጥ የታሰበው ግለሰብ ግን የምክር ቤቱ አባል ካልሆነ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ቦርድ ሟሟያ ምርጫ እንዲያካሂድ ከጠየቀ በኋላ፤ ዕጩውን ግለሰብ በሟሟያ ምርጫው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኖ መመረጥ አለበት። ተሻሽሎ በወጣው የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም መሰረት የሟሟያ ምርጫ የሚካሄደው፤ በየደረጃው ያሉ የምክር ቤቶች በተለያየ ምክንያት የተጓደሉባቸውን አባላት እንዲሟሉላቸው ለምርጫ ቦርዱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም በሕጉ መሰረት የቀረበ የይውረድልን ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው። ቦርዱም ጥያቄው በደረሰው በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ የሟሟያ ምርጫ ያካሂዳል። ማሟያ ምርጫ ማለት በይውረድልን ወይም በማንኛውም ምክንያት በየደረጃው የሚገኙ የተጓደሉ የምክር ቤት አባላት መቀመጫዎችን ለማሟላት የሚካሄድ ምርጫ ማለት ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩን ለመተካት የሚታጨው ግለሰብ ግን የምክር ቤት አባል ከሆነ በተለመደው የኢህአዴግ አሰራር መሰረት፤ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዶ ሊቀመንበሩን ከመረጠ በኋላ፤ ሊቀመንበሩን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ በጠቅላይ ሚንስትርነት እንዲሰየም ይደረጋል። ሰሞኑን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ በተደጋጋሚ ስማቸው እየተጠቀሰ የሚገኙት ሰዎች የሚከተሉት ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች እነማን ናቸው? አጭር የሕይወት ታሪካቸውን እንደሚከተለው ቀርቧል። ስማቸው የተዘረዘረው በእንግሊዝኛ የፊደላት ቅደም ተከተል መሰረት ነው። ዶክተር አብይ አህመድ ዶክተር አብይ አህመድ በአጋሮ ከተማ የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ሰርተዋል። በግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ እና በሊደርሺፕ ተቋም ደግሞ የሥራ አመራር ሳይንስ አጥንተዋል። እንዲሁም አሽላንድ ዩኒቨርሲቲ በንግድ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እና ደህንነት ጥናት ፒኤችዲ አላቸው። በመጀመሪያ 40ዎቹ የሚገኙት ዶክተር አብይ ኦህዴድን የተቀላቀሉት በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው። ከፖለቲካ ተሳትፏቸው በተጨማሪ በወታደራዊ ጉዳዮች ሰፊ ተሳትፎ የነበራቸው ሲሆን የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ አላቸው። በተባበሩት መንግሥታት የስላም ማስከበር ተልዕኮን ለማስፈጸም ሩዋንዳ ዘምተዋል። ከ2000 እሰከ 2003 የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መስራች እና ዳይሬክተር በመሆነ አገልግለዋል። ከዚያም የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር በመሆን ሰርተዋል። ከ2002 ጀምሮ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ሲሆን፤ ከ2007 ጀምሮ ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ ላለፉት ሦስት ዓመታት የኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። የኦህዴድ ሊቀ-መንበር ሆነው በቅርቡ የተመረጡት ዶክተር አብይ በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው። ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በትግራይ ሽረ ወረዳ ነው የተወለዱት። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከተቀላቀሉ በኋላ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ትጥቅ ትግል ገብተዋል። በትጥቅ ትግል ወቅት ወደ ጣልያን አገር በመሄድ በመገናኛ ቴክኖሎጂ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፤ በ1972 ዓ.ም የህወሓት ሬድዮ ጣብያ ድምፂ ወያነን አቋቁመዋል። ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ሲወጣ የደህንነት መ/ቤቱን ይመሩ የነበሩት የአቶ ክንፈ ገብረ መድህን ምክትል ሆነውም አገልግለዋል። ቀደም ሲል ያቋረጡትን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ተከታትለው የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተቀብለዋል። እንዲሁም ደግሞ የዶክትሬት ድግሪያቸውን ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ለንደን አግኝተዋል። ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽንና ኮምዩኒኬሽን ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪ ሆነውም ሰርተዋል። በአሁን ሰዓት የህወሓት ሊቀመንበር፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደርነት የትግራይ ክልልን እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ሚንስትር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። ዶክተር ደብረፅዮን በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው። ደመቀ መኮንን በ1980 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በባዮሎጂ ትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። ከዚያም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በግጭት አፈታት አጠናቀዋል። በ1980ዎቹ መጀመሪያ ኢህአዴግን የተቀላቀሉት አቶ ደመቀ፤ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተመራጭ ሆነው ነበር። በ1997 የአማራ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው የተመረጡ ሲሆን፤ በቀጣዩም ዓመት የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል። አቶ ደመቀ መኮንን የብአዴን ሊቀመንበር ሲሆኑ በኀዳር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክትል ሊቀምንበር ሆነው ከተመረጡበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት እያገለገሉ ይገኛሉ። የቀድሞው መምህር ወደዚህ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት የትምህርት ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል። አቶ ደመቀ መኮንን በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው። አቶ ለማ መገርሳ አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል፤ አሁን ደግሞ ምክትል ሊቀ-መንበር እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ናቸው። በአርባዎቹ መጨረሻ ላይ እንደሚገኙ የሚነገርላቸው አቶ ለማ፤ ትውልድ እና እድገታቸው ምስራቅ ወለጋ ነው። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም ከዚያው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት በኦሮሚያ ህዝባዊ ተቃውሞ በበረታበት ወቅት ነበር የኦህዴድ ሊቀመንበር እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው የተመረጡት። አቶ ለማ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ኦህዴድን የተቀላቀሉ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ከመሆናቸው በፊት የክልሉ ምክር ቤት - የጨፌ አፈጉባኤ ነበሩ። አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት-ጨፌ አባል ሲሆኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ግን አይደሉም። ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን እስከ ቅርብ ጊዜ አገልግለዋል። የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስትርም ናቸው። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በፖለቲካል ሳይንስ እና በውጪ ግንኙነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አጠናቀዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ በፖሊስ ሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪን አግኝተዋል። 1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ የተወለዱት ዶክተር ወርቅነህ ለረጅም ዓመታት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሸነር በመሆን አገልግለዋል። ከ2004 ጀምሮ የትራንስፖርት ሚንስትር በመሆን ለአራት ዓመታት ሰርተዋል። ከ1980ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ የኦህዴድ አባል የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ፤ ከ2004 ጀምሮ የኦህዴድ እና የኢህዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸው። ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት አባል እንጂ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አይደሉም። ተጨማሪ ምንጮች፡ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ፣ Historical Archives
news-53447240
https://www.bbc.com/amharic/news-53447240
"የሌሎችን ንብረት ከውድመት ለመከላከል በሄድኩበት፤ ሌሎች ደግሞ የእኔን ቤት አትርፈውታል"
ከሦስት ሳምንታት በፊት የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ የአንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች የተከሰውን ነገር ድንገተኛ ዱብዳ እንደሆነ ነው አሁን ድረስ የሚሰማቸው።
የሃጫሉ ግድያ ዜና በተሰማ በሰዓታት ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ከተሞችና መንደሮች በጥቃት ፈጻሚዎች መወረራቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በዚህም የበርካታ ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል፤ ግለሰቦች በዘመናት ጥረት ያቆሟቸው መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት ከነሙሉ ንብረታቸው የእሳት እራት ሆነዋል። ጎራ ለይተው በድንገት ለጥፋት የተሰማሩት ጥቃት ፈጻሚዎች ምንም እንኳን ያደረሱት ጉዳት ያልታሰበና ከባድ ቢሆንም በየአካባቢዎቹ ያሉ ቀና ሰዎች ጥረት ባይታከልበት ኖሮ ከዚህ የባሰ ውድመትና የሰው ህይወት መጥፋት ሊከሰት እንደሚችል ቤት ንብረታቸው ወድሞ በህይወት የተረፉ ሰዎች ለቢቢሲ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ግን እንዲህ ያሉ ቀናና ሰብዓዊነት የተላበሱ አስተዋይ አባቶችና እናቶች ባሉበት ከተማና አካባቢ ያንን ሁሉ ጥፋት የግፍ ግድያ የፈጸሙ ጥቃት ፈጻሚዎች ከወዴት እንደመጡ የበርካቶች ጥያቄ ነው። ታዲያ በተለያዩ ስፍራዎች ጥቃቱ የተፈፀመባቸውና ንብረታቸው እንደወደመባቸው የሚናገሩ ሰዎች በህይወት ለመትረፋቸው ምክንያት የሆኗቸው ለዘመናት አብረው በጉርብትና የኖሯቸው ሰዎች ድፍረት የተሞላበት ጣልቃ ገብነት እንደሆነ ሲናገሩ ይሰማል። የጥቃቱ ኢላማ የነበሩ ሰዎችን ከአጥቂዎች በመታደግ በኩል ቢቢሲ ካነጋገራቸው የጥቃቱ ሰለባዎች መካከል ስማቸው በበጎ እየተደጋገመ ከሚነሱት በጎ ሰዎች መካከል የባቱ ከተማ ነዋሪው አቶ ተስፋዬ ኤዳኦ ሴሮ ይጠቀሳሉ። አቶ ተስፋዬ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ናቸው። የመንግሥት ሠራተኛ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን የሚተዳደሩት በግል ሥራ ነው። በአካባቢያቸው ባለ ቤተ ክርስቲያን እና ልጆችን በሚደግፍ ፕሮጀክት ላይም ለማኅበረሰባቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማደረግ በነዋሪው ዘንድ ይታወቃሉ። በከተማዋ ምን ተከሰተ? "ክስተቱ ከመፈፀሙ በፊት የሰማነው ምንም ነገር የለም፤ ነገር ግን አገር ሰላም ብለን በተኛንበት ሌሊት ላይ ጩኸት ሰማን" ይላሉ አቶ ተስፋዬ፤ ጩኸቱ ከሰፈራቸው ራቅ ብሎ ነበር የሚሰማቸው። ጩኸቱን ለማጣራት ሲወጡም በአካባቢው የማይታወቁ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን ተመለከቱ። ከዚያም ጨለማው እየገፈፈ ሲመጣ ወደ እርሳቸው ሰፈርም በመምጣት የሰው ቤት መደብደብ ጀመሩ። የአካባቢው ሽማግሌዎችና ሌሎች ወጣቶች በጋራ ሆነው "ይህ ለምን ይሆናል?" በማለት "ባለን አቅም ድርጊቱን ለማስቆም መሞከር ጀመርን" በማለት ሁኔታውን ያስታውሱታል። አቶ ተስፋዬና ጎረቤቶቻቸው ጣልቃ ገብተው ጥቃት ፈጻሚዎቹ "ተዉ" ባይሉ ኖሮ በአካባቢው ከደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት በላይ የከፋ ይደርስ እንደነበር ነዋሪዎች ይመሰክራሉ። በጥቃቱ ዕለት ጎረቤታቸው የሆነና ሆቴሉ የተቃጠለበት አንድ ግለሰብ ሆቴሉ በእሳት እንድወድም መደረጉንና እንዲደርሱለት ሲጠራቸው ፈጥነው የደረሱት አቶ ተስፋዬ፤ ጥቃት ፈጻሚዎቹ መኖሪያ ቤቱን ለማውደም በመሄዳቸው 'አይ ቤት ሂድና ልጆቼን ከቤት አድንልኝ' ተብለው እንደተላኩ ይናገራሉ። ስለሁኔታ እውነታነት የሚናገሩት አቶ ተስፋዬ "ልጆቹንና ቤተሰቡን ወደ እኛ ቤት ወስደን ካስገባን በኋላ፤ መኪናውን በማውጣት፤ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመተጋገዝ ቤቱ ደጅ ላይ ለሰዓት ያህል ቆመን ተከላክለን አትርፈንላቸዋል" ሲሉ ይህንን ለወገንና ለጎረቤት በጥቃት ጊዜ የመድረስ ተግባራቸውን ለሌሎችም በመፈጸም አረጋግጠዋል። እንደ አባት እንደ አካባቢ ሽማግሌ ከጎረቤቶቸቻው ጋር ቆመው ድርጊቱን ለማስቆም የጣሩት አቶ ተስፋዬ "ማፍረስ፣ ማቃጠል አትችሉም። ቤት ማቃጠል ነውር ነው፣ መዝረፍ ነውር ነው፤ ይህ ባህላችን አይደለም" እያሉ ፊት ለፊት በመጋፈጥና በሰዎች በር ላይ በመቆም እንደተከላከሉ ያስረዳሉ። አቶ ተስፋዬ ጥቃት ፈጻሚ ወጣቶቹ ከመጮህ እና 'ዞር በሉ እናጥፋ!' ከማለት ውጪ፤ ለምን ድርጊቱን እንደሚፈፅሙ ትርጉም ያለው ነገር ሲናገሩ አለመስማታቸውን ይናገራሉ። በዚህም ነዋሪው ጣልቃ ሲገባና ድርጊቱን ሲያወግዝ ያሰቡትን መፈጸም እንደማይችሉ ሲያውቁ "በወቅቱም ሰዎች ሲተባበሩና መከላከሉ ሲጠናከር አልፈው ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳሉ" ብለዋል። እነዚህ ጥቃት አድራሾች የማይታወቁና ቁጥራቸው በርካታ መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ፤ አንዱ ለአንዱ እንኳን እንዳይደርስ ተከፋፍለው በተመሳሳይ ሰዓትና ሁሉም ቦታ መሰማራታቸውን ይገልፃሉ። አቶ ተስፋዬ እንደሚናገሩት በጥቃቱ የተለያዩ ብሔሮች ላይ ጉዳት መድረሱን በመጥቀስ፤ ጥቃት ፈጻሚዎቹ እንዲሁ በዘፈቀደ ዝም ብለው መደዳውን ደህና ቤት ሲያዩ ጥቃት ለማድረስ ከመሮጥ በዘለለ፤ በከተማቸው ውስጥ እየመረጡ ነው ጥቃት ያደረሱት የሚል እምነት እንደሌላቸው ያስረዳሉ። "ሁሉም ወጣት አንድ አይደለም፤ ከኅብረተሰቡ ጋር የሚተባበሩ ወጣቶች አሉ" የሚሉት አቶ ተስፋዬ፤ እርሳቸው የሌላውን ቤት ከጥቃት ለመከላከል በወጡበት ሰዓት፤ የእርሳቸውን ቤት ከቃጠሎ ያተረፉት ሌሎች ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ይናገራሉ። ምክንያቱ ምንድን ነው? አቶ ተስፋዬ ከዚህ በፊት በግለሰብ ደረጃ ከሚፈጠሩ ግጭቶች ውጪ እንደዚህ ዓይነት ወረራ በዘመናቸው አይተው እንደማያውቁ ይናገራሉ። "እኛ ይህ ለምን እንደሆነ አናውቅም፤ ፈጣሪ ይወቅ፤ ከየትና እንዴት እንደመጣ አናውቅም፤ እንደ ቤተክርስቲያን ሰው ፈጣሪ ይወቅ፤ የመጣውን እግዚአብሄር ይመልስ ነው የምንለው" ይላሉ። የአካባቢው ማኅበረሰብም እንደ ኢትዮጵያዊነቱ፤ በሠርግም በለቅሶም፤ ክፉውንም ደጉንም አብሮ ማሳለፍ እንጂ በብሔር መነጣጠል አለመኖሩን በማውሳት በከተማቸው ውስጥ ያጋጠመው ጥቃትና ውድመት መነሻው ምን እንደሆነ ለመረዳት ተቸግረዋል። "በማኅበረሰባችን ውስጥ የአብሮነት ስሜት እንጂ መነጣጠል በባህላችንም የለም፤ ይህ አዲስ ክስተት ነው፤ የምናውቀው ነገር የለም" ሲሉ የጥቃት ፈፃሚዎቹ ድርጊት የአንድ ወገን መገለጫ አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ። ሁሉንም የጎዳ ጥቃት የባቱ ከተማ ነዋሪው አቶ ተስፋዬ፤ በደረሰው ውድመት የንብረት ባለቤቶቹ ብቻ ሳይሆኑ የከተማው ነዋሪዎችና አልፎ ሂያጅ መንገደኞችም ጭምር ነው የተጎዱት ይላሉ። "የተጎዱት ሰዎች ወንድሞቻችን ናቸው፤ ከእነርሱ ጋር ብዙ መስተጋብር አለን። የእነርሱ አዕምሮ ሲጎዳ፤ እኔም ነኝ የተጎዳሁት" ብለዋል። የወደሙት ሱቆች፣ ሆቴሎችና ሌሎች ተቋማት አገልግሎት ባለመስጠታቸው ተገልጋዩ መቸገሩንም በመግለጽ፤ እነዚህ ድርጅቶች ግብር ከፋይ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ተስፋየ፤ "በውድመቱ ከተማዋ፤ ከፍ ሲልም አገር ተጎድቷል፤ በዚህም አዝነናል" ሲሉ ስሜታቸውን ገልጸዋል። "ባህላችንን መልሰን ማደስ አለብን" አቶ ተስፋየ እንደ አገር ሽማግሌነታቸው በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለውን መሰል ድርጊት ለማስቆም ይበጃል የሚሉት ሃሳብ አላቸው። ይህም "ባህላችንን መልሰን ማደስ አለብን፤ ባህልን የሚጥሰውን አዲሱን ትውልድ ባህላችንን ማስተማር አለብን" ይላሉ። ጨምረውም ተቻችሎ፣ ተከባብሮና ተደጋግፎ የመኖር ባህልን እየጣሰ የሚሄደውን ትውልድ በቤተ እምነትና በባህል መግራት እንደሚያስፈልግም ይመክራሉ። የቤተ እምነት መሪዎች ወጣቶቹን በእምነታቸው እንዲጓዙ ማድረግና ማረም እንዳለባቸው የሚጠቅሱት አቶ ተስፋዬ " ሽማግሌዎች መምከር አለብን፣ በእምነት ቤት ያሉ ሰዎች ደግሞ ማስተማር፣ የባህል ሰዎችም ባህሉንም እንዲያውቁ ማድረግ፣ አባ ገዳዎችም ኅብረተሰቡ አንድ እንደሆነና በአንድነት መራመድ እንዲችል ማስተማር አለባቸው" ብለዋል። "ሰው ፈጣሪን ካልፈራ፤ በራሱ መንገድ ይሄዳል፤ በመሆኑም ልጆች ፈጣሪን እንዲፈሩ ማስተማር ያስፈልጋል፤ ሰው መንግሥትን የሚሰማው እምነት ሲኖረው ነው" ያሉት አቶ ተስፋዬ፤ በከተማቸው የተከሰተው ነገር በተመለከተ አንድ ነገር ለማድረግ እየጣሩ ነው። በዚህም ከተፈጠረው ጥቃትና ውድመት በመማር ዳግም እንዳይከሰት ጊዜ ሳይወስዱ መደረግ ስላለባቸው ነገሮች ከተለያዩ ቤተ እምነቶች ጋር በጋራ እየተወያዩ እንደሆነና በዚህ መልኩ ትውልዱን ለመቅረፅ መሰራት የሚገባቸውን ለማከናወን እየሞከሩ እንደሆነ ገልፀዋል።
news-52254850
https://www.bbc.com/amharic/news-52254850
በኮቪድ - 19 የሞተ ሰው የቀብር ሥነ- ሥርዓት እንዴት መፈጸም አለበት?
የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሦስት ወራት በፊት ተቀስቅሶ መላውን ዓለም ባዳረሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ የተጠጋ ሲሆን፤ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ100 ሺህ በላይ ደርሷል፡፡ አሃዙም በፍጥነት እየጨረ ነው።
በጣልያን በኮሮናቫይረስ የሞተ ሰው ሥርዓተ ቀብር ለመሆኑ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች መቀበር ያለባቸው እንዴት ነው? ምን አይነት ጥንቃቄዎችስ መደረግ አለበት? በኮሮናቫይረስ የሞተ ሰው አስክሬንስ ቫይረሱን ያስተላልፋል? እነዚህን ጥያቄዎች በስዊድን አገር በሚገኘው ማላርዳሌንስ ዩኒቨርሲቲ ‘የግሎባል ኸልዝ’ መምህር እና የማሕበረሰብ ጤና ባለሙያ ለሆኑት አቶ በንቲ ገለታ አንስተንላቸው ነበር፡፡ አቶ በንቲ ጥናቶችን ጠቅሰው እንደሚሉት፤ አንድ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ከሞተ/ች በኋላ በሽታውን አያስተላልፍም/አታስተላልፍም፤ ነገር ግን ግለሰቡ/ቧ ከሞተ/ች በኋላ የሞቱበት አካባቢ እንዲሁም የተጠቀሙባቸውና የነካኳቸው ዕቃዎች በቫይረሱ ሊበከሉ ይችላሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ከተለያዩ የሰውነት ቀዳዳዎች ፈሳሾች ሊወጡ ይችላሉ፡፡ በእነዚህና ሌሎች ተመሳሳይ መንገዶች አማካኝነት ቫይረሱ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው በኮቪድ-19 ሕይወቱ ካለፈ በኋላ ግብዓተ መሬቱ በጥንቃቄ ሊፈጸም ይገባል ሲሉ ይመክራሉ፡፡ ባለሙያው እንደሚሉት አንድ ሰው በኮቪደ-19 ሲሞት አሸኛኘቱ ሦስት ደረጃዎች አሉት፡፡ 1. አዘገጃጀት በአገራችን በሁለት ዓይነት ሁኔታ አስክሬን ሊዘጋጅ እንደሚችል ባለሙያው ያስረዳሉ፡፡ በህክምና ተቋማት እና ከህክምና ተቋም ውጭ የሚከናወን ነው፡፡ “አንድ ሰው በህክምና ተቋማት ሲሞት አስክሬኑ እንዴት መዘጋጀት እንዳለበት የህክምና ባለሙያዎች በቂ ሥልጠና ስለሚኖራቸው፤ እዚያ ላይ ትኩረት ማድረግ አልፈልግም” የሚሉት ባለሙያው በቤት አሊያም ከህክምና ተቋም ውጭ የሞተን ሰውን እንዴት መዘጋጀት እንዳለበት ይገልጻሉ፡፡ በቅድሚያ ግለሰቡ ሕይወቱ እንዳለፈ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ደውሎ ማሳወቅና የጤና ተቋሙ በዚህ ያሰለጠናቸውን ሰዎች መላክ ይጠበቅበታል ይላሉ፡፡ ባለሙያው በዚህ ረገድ የሰለጠኑ ሰዎች በየቀበሌው መኖር አለባቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም በኮቪድ-19 የሞተ ሰው በሌላ በሽታ እንደሞተ ሰው ሳይሆን አስክሬኑ በጥንቃቄ መዘጋጀት አለበት፡፡ በመሆኑም አስክሬኑን የሚያዘጋጀው ሰው የእጅ ጓንቶች፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) እንዲሁም ገዋን ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ አካባቢውንም በጸረ ተህዋስ ኬሚካል መርጨት ያስፈልጋል፡፡ ግለሰቡ የተጠቀመባቸው ቁሳቁሶች፣ የለበሳቸው አልባሳቶች በበረኪና ወይም ኬሚካል ማጠብና መገልገል ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ዕቃዎቹ ወይም ቁሳቁሶቹ በዚህ መልክ ከጸዱ ማቃጠል ላያስፈልግ ይችላል፡፡ 2. አሸኛኘት በኮቪድ -19 የሞተን ሰው አስክሬን ከማዘጋጀት በተጨማሪ አስክሬን አሸኛኘት ዋናው ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ አቶ በንቲ እንደሚሉት በተለይ በእኛ አገር ባህል መሠረት ሰው በብዛት ወጥቶ አስክሬን መሸኘት የተለመደ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሳታወቅ የሟች አስክሬን በሰዎች ሊነኩ ይችላሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር ከእርስ በርስ በሽታው ሊተላለፍ ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት አስክሬን የሚሸኙ ሰዎች ቁጥር እጅግ ማነስ እንዳለበት ይመክራሉ፡፡ በሽኝቱ ላይም በተቻለ መጠን ቤተሰብና የቅርብ ወዳጆች ብቻ ቢገኙ፤ እነርሱ ቢሆኑ አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው በርቀት ቢሸኙ ይመረጣል፡፡ 3. ግብዓተ መሬት አፈጻጸም አንድ በኮቪድ -19 የሞተ ሰው አስክሬን ከተዘጋጀና ከተሸኘ በኋላ ግብዓተ መሬት ይፈጸማል፡፡ በዚህ ሂደት ቀብር የሚፈጽሙ ሰዎች ቢያንስ ጓንት ማድረግ አለባቸው፡፡ በሃይማኖትም ሆነ በሌላ ምክንያት አስክሬኑ በሳጥን የማይቀበር ከሆነ በአስክሬን ሻንጣ (በላስቲክ ተጠቅልሎ )መቀበር አለበት፡፡ ከሟቹ የሚረጩ አንዳንድ ፈሳሾች አለ ብለው የሚገምቱ ከሆነም ተደራቢ ጋዎን እና ማስክና ማድረግ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡
news-48914948
https://www.bbc.com/amharic/news-48914948
"ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?"
ለመሆኑ ኢስላማዊ ባንክ እስከናካቴው ቢቀርብን ምን ይቀርብናል? የብሔር ዘመም ባንኮች አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ ሃይማኖታዊ ባንክ መምጣቱ አደጋ የለውም? ደግሞስ እንዴት ነው ባንክ ያለ ወለድ አትራፊ የሚሆነው? ላለፉት ለ11 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋከልቲ ያስተማሩትንና የዓለም አቀፉ የቢዝነስ ጥናት ኩባንያ ዴሎይት የኢትዮጵያ ቢሮ የሂውማን ካፒታል ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ሙከሚል በድሩን አነጋግረናቸዋል። 'ክርስቲያን ባንክ' ብለን አናውቅም 'ኢስላሚክ ባንክ' ለምን እንላለን? በሃይማኖት ስም ባንክ መክፈት ስጋት አያሳድርም?
ላለፉት ለ11 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋከልቲ ያስተማሩትንና የዓለም አቀፉ የቢዝነስ ጥናት ኩባንያ ዴሎይት የኢትዮጵያ ቢሮ የሂውማን ካፒታል ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ሙከሚል በድሩ። ተገቢ ስጋት ሊሆን ይችላል። የስጋቱን ምንጭ መረዳት ነው ቁምነገሩ። አንዱ አሁን የዓለም ስጋት የሆነው ሽብርተኝነት ነው። ይህ ስጋት ከኢስላሙ ዓለም ጋ አብሮ ስለሚነሳና ከገንዘብ ጋ ንክኪ ሲያደርግ ስጋት ቢፈጠር የሚገርም አይሆንም። • ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አሥመራ ካቀኑ እነሆ አንድ ዓመት፤ ምን ተለወጠ? ሌላው ደግሞ ሰዎች ካላቸው የግንዛቤ ማነስ የሚመነጭ ነው። "ኢስላሚክ" የሚለውን ስም ሲሰሙ ቢዝነስ ሳይሆን ወደ አእምሯቸው የሚመጣው መስጊድ ወይም መጅሊስ ነው። [መታወቅ ያለበት ግን] የማንኛውም ንግድ የአሠራር ሂደቱንና አተገባበሩ ከየትኛውም ፍልስፍናና እምነት ሊመነጭ ይችላል። በተመሳሳይ ይህ የባንክ አሠራር ከሸሪዓ የወሰዳቸው ደንቦች አሉት። መርሆቹን ከሸሪዓ መውሰዱ ግን የእምነት ተቋም አያሰኘውም። ወለድ አልባ ባንክ በአጭሩ ቢዝነስ እንጂ ሌላ አይደለም። ለአንድ ባንክ ሁለቱንም አገልግሎት መሳ ለመሳ መስጠት ምንድነው ችግሩ? በወለድም ያለ ወለድም ማለቴ ነው በእምነት ምክንያት ወይም በግል የሕይወት መርህና ፍልስፍና ወለድን የማይጠቀሙ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ። ልክ አራጣን እንደሚጸየፉ የተለያየ እምነት ተከታዮች ሁሉ፤ ወለድን የማይፈቅዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሉ። እነኚህን ለማካተት የፋይናንስ አማራጭ ማቅረብ አለብን። ለዚያም ነው ወለድ አልባ ባንክ 'ኢንክሉሲቭ ባንክ' የሚባለው። 'አካታች ባንክ' እንደማለት። በአገር ደረጃ ብዙ ቁጥር ነው ይሄ። እነዚህን [የኅብረተሰብ ክፍሎች] ወደ ፋይናንስ ተቋም ካላመጣናቸው ምጣኔ ሀብቱ የተቀነጨረ የተወሰነ የኅብረተሰብ ክፍል እየፈጠርን ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ዞሮ ዞሮ አገርን ይጎዳል። ራሱን የቻለ 'ኢስላሚክ' ባንክ ማቋቋም ለምን አስፈለገ ነው የኔ ጥያቄ? ወለድ ነጻ የሚፈልግ ተገልጋዮች የባንክ መስኮቶች አሉላቸው አይደለም እንዴ? ለዚያውም 10 ባንኮች... በብዙ ደረጃ [የተንሸዋረረ] አስተሳሰብን ያዘለ ጥያቄ ነው የጠየቅከኝ። አንደኛ ባንክ ማቋቋም መብት ነው። በቂ ሱቆች አሉና ንግድ ፍቃድ አታውጡ ይባላል እንዴ? በቢዝነስ መርህ የሚያስኬድም አይደለም። አዋሽ ባንክ እያለ ለምን ዳሽን ተከፈተ እንደማለት ነው። በአመክንዮም ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም። አገልግሎቱን አስፍቼ ብከፍት ያዋጣኛል ያለን ነጋዴ/ባለሀብት ግዴለም ጠባብ መስኮት ይበቃሃልና ይቅርብህ አይባልም። • በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች ሁለተኛ የዛሬ 10 ዓመት ገደማ ነው ብሔራዊ ባንክ ለወለድ ነጻ አገልግሎት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት አለ የሚል ጥናት ያወጣው። በመስኮት ደረጃ ያሉ ባንኮች የሚሰጡት አገልግሎት ደግሞ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። [የወለድ ባንክ ሊያቀርባቸው የሚችሉ] አገልግሎቶቹ ተሟልተው እየተሰጡ አይደለም። አገልገሎቱ በደንብ እየተሰጠ ነው የሚባለው ምናልባት 'ሙራባሃ' የሚባለው ሰርቪስ ብቻ ነው። ይቺ ግን አንድ አገልግሎት ብቻ ናት። በአሁኑ ሰዓት በመስኮት የማይሰጡ በጣም ብዙ የወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎቶች አሉ። መስኮቱ ጠባብ ነው። ይሄን ያዩ ሰዎች መስኮቱን ባንክ እናድርገው ቢሉ ምንድነው ችግሩ? ሦስተኛ ከወለድ ጋ [በሩቁም ቢሆን] አልነካካም ብሎ ከፋይናንስ ዘርፉ ገለል ያለ በርካታ ሕዝብ አለ። ይህንን የምልህ ባንክ ተጠቃሚን ብቻ አይደለም። ባንክ ላይ ባለቤት መሆን የሚፈልግም ጭምር ነው የምልህ። አሁን [ለምን ራሱን የቻለ] የወለድ ነጻ ባንክ ትከፍታለህ ስትለው በሌላ ቋንቋ ምን እያልከው ነው...ግዴለም ከኔ ሱቅ ስኳርም ሳሙናም ግዛኝ። አንተ ግን ሱቅ እንዳትከፍት እያልከው ነው። በወለድ የሚሠሩ ባንኮች ከወለድ ነጻ አገልግሎት እየሰጡም ከነሱ ጋ መሥራት የማይፈልግ ሰዎች አሉ እያሉኝ ነው? [ትክክል] ለዚህ ሌላ ማሳያ የሚሆን ነገር ልንገርህ። በወለድ ምክንያት ከባንኮች ጋ ላለመነካካት በርካታ ሰዎች ኮንዶሚንየም ዕድልን አሳልፈዋል። ብዙ ጥናቶች ዜጎች በወለድ ከሚሠሩ ባንኮች ጋ ላለመነካካት ገንዘባቸውን ወደ ባንክ ይዘው እንደማይመጡ አሳይተዋል። ዜጋን በሚከተለው መርህና እምነቱ ከፋይናንስ ተጠቃሚነት ማግለል ደግሞ ኢፍትሃዊነት ነው። • ባለ አምስት ኮከቡ የኖርዌይ እስር ቤት ይህን በምሳሌ ላስረዳህ። በ2017/18 የግል ባንኮቻችን ወደ 20 ቢሊዮን ጥቅል ትርፍ አትርፈዋል። ከዚያ ውስጥ ግማሹ የንግድ ባንክ ነው። ወለድ ነክ ባንክ ጋር መሥራት የማይፈልጉ ዜጎች አሉ። በእምነታቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል ይሄ፣ በሌላ ምክንያት ሊሆንም ይችላል። እነዚህን በመስኮት ብቻ ይወሰኑ ስትል ከዚህ 20 ቢሊዮን ትርፍ እያገለልካቸው ነው። ምን ማለቴ ነው... የባንክ ባለድርሻ መሆን የሚፈልጉ አሉ። 'እኔ [በተዘዋዋሪም ቢሆን] ከወለድ አልነካካም ስላሉ ብቻ በእጅ አዙር ከዚህ ግዙፍ ትርፍ ለምን ታገላቸዋለህ? ለምንድነው ከወለድ ነጻ አገልግሎት ከሚሰጥ ባንክ ጋርም ቢሆን መሥራት የማይፈልጉት? በእምነትም ሆነ በሌላ የግል ምርጫቸው ይሄን የማይፈልጉ አሉ። ይህን የባንክ ዘርፍ ልዩ የሚያደርገው በባንኩ የሚንቀሳቀሰው ገንዘብ በሁሉም መልኩ ንጹህ መሆን አለበት ብሎ መነሳቱ ነው። ለምሳሌ ቢራ ፋብሪካ በዚህ ባንክ መስተናገድ አይችልም። ኅብረተሰብን ይጎዳሉ፤ የሞራል ዝቅጠት ያደርሳሉ የሚባሉ ዘርፎች በሙሉ ወለድ ነጻ ባንክ በሩቁም ቢሆን አይነካካም። መጠጥ፣ ዝሙት፣ ቁማርና ሌሎች ለኅብረተሰብ ጠንቅ ናቸው በሚባሉ ቢዝነሶች/ኢንዱስትሪዎች ንክኪ የለውም። ማስታወቂያ አይሰጥም፣ አያበድርም፣ ተቀማጭም አያደርግም...ወዘተ። ኢስላሚክ ባንክ ቢቀር ምን ይጎድልብናል? ቢኖርስ ምን ይፈይዳል? አንዱ በእምነቱ ምክንያት ከዘርፉ የራቀን ሰፊ ማኅበረሰብ ፋይናንሱን ይዞ መጥቶ ወደ ኢኮኖሚው እንዲያስገባው ማስቻሉ ነው። በትንሹ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ወለድ አይፈልግም ብንል [ሌላውን ትተን ማለቴ ነው] እንደው በትንሹ 30 ምናምን ፐርሰንት ኢትዮጵያዊ ከፋይናንስ ተገለለ ማለት ነው። የሱ ጉዳት ደግሞ የአገር ጉዳት ነው። ሁለተኛ እንደ አገር ከገንዘብ ንክኪ የራቀ ማኅበረሰብ መፍጠር ይፈለጋል። ይህ የብዙ አገር ግብ ነው። ከባንክ የተገለለ ማኅብረሰብ ማለት ብሩን እንሥራ ውስጥ ያስቀመጠ ማኅበረሰብ ማለት ነው። [ ከወለድ ነጻ አገልግሎት ይቅርብ ስንል] ኢኮኖሚው ውስጥ ሊዘዋወር ይችል የነበረን ግዙፍ ገንዘብ እንሥራው ውስጥ እንደተቀመጠ ይቅር ማለት ነው። • የጥላቻ ንግግርን የሚያሠራጩ ዳያስፖራዎች እንዴት በሕግ ሊጠየቁ ይችላሉ? አሁን እንኳ በወለድ አልባ መስኮቶች 30 ቢሊዮን ብር ይንቀሳቀሳል። ይህ የሚያሳየን ሰፊ ፍላጎት እንዳለ ነው። ከዚህ ሌላ በመደበኛ ባንክ የሌለ በዚህኛው ባንክ ሊመጣ የሚችል ተጨማሪ ነገር አለ? መጠነኛ የሥራ ዕድል ከመከፈት ባሻገር ማለቴ ነው። ማኅበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ልንመለከተው እንችላለን። ከወለድ ነጻ ባንክ አንዱ ግዴታ ድህነት ቅነሳ ላይ መሳተፍ ነው። በዚህ ረገድ እነዚህ ባንኮች መደበኛው ባንክ ከሚያወጣው በብዙ እጥፍ ያወጣሉ። ይህም ከባለሐብት ገንዘብ ተቀብሎ ለድሀ ማከፋፈል ነው። ለምሳሌ በመደበኛ ባንክ አሠራር በየወሩ ደንበኛው መክፈል ሲኖርበት ሳይከፍል ሲቀር ወለድ ይከመርበታል። በዚህኛው ግን ወለድ ስለሌለ ቅጣት የሚጣልበት ሁኔታ አለ። ከዚህ የቅጣት ገንዘብ የተወሰነች ፐርሰንት ወደ ማኅበረሰብ ችሮታ የምትሄድ ናት። ይህ ለድህነት ቅነሳ ከፈተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ለምሳሌ 2017 በዚህ መንገድ በተቀረው ዓለም 518 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል። • ወሲባዊ ትንኮሳ ያደረሰባት አለቃዋን በማጋለጧ የታሠረችው ሴት የፋይናንስ መረጋጋትን ከመፍጠር አንጻርም ከወለድ ነጻ ባንኮች ይጠቀሳሉ። የዓለም የገንዘብ ቀውስን ታስታውሳለህ። በደፈናው ችግሩን የፈጠረው በትንቢት ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ አሠራር ነበር። በወለድ ነጻ ባንክ አሠራር ግን ስቶክ ገዘተህ ይጨምራል ይቀንሳል እያልክ መቆመር አትችልም። ይህ አይፈቀድም። ሁሉም ነገር የሚመሠረተው ከንብረትና ከምርታማነት ጋር በተያያዘና በሚጨበጥ ነገር ላይ ነው። ለዚህ ነው ያ ሁሉ የፋይናንስ ተቋም ሲንኮታኮት ወለድ አልባ ባንኮች ያን አስቸጋሪ ጊዜ ያለፉት። በአገራችን ሁኔታም ተያያዥ ነገር ማንሳት ይቻላል። ልማት ባንክን ውሰድ። በጋምቤላና ሌሎች ቦታዎች ለሰፋፊ እርሻዎች ከፍተኛ ገንዘብ ለቀቀ። ባለሃብቶቹ [እርሻውን] ለይስሙላ ነካኩትና ገንዘቡን ከተማ መጥተው ፎቅ ሠሩበት። ባንኩ አሁን ችግር ውስጥ ገብቷል። የተበላሸ የብድር መጠኑ 40 ከመቶ አልፏል። ይሄ ዓይነቱ አጋጣሚ በወለድ ነጻ ባንክ አሠራር ሊከሰት የሚችልበት ዕድል ጠባብ ነው። ለምን ካልከኝ የሚከተለው የቢዝነስ ፍልስፍና [ንብረት መር] ወይም 'አሴት-ባክድ' ስለሆነ ነው። • አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ አፍሪካን ያጥለቀልቅ ይሆን? በዚህ ወለድ አልባ ባንኪንግ አሠራር ንብረቱን እንጂ ገንዘቡን አትከተልም። ምን ማለት ነው ባንኩ ገንዘቡን አይሰጥህም። ገንዘብ ሰጥቶህ ትርፉን በወለድ አይጠብቅም። ይልቅስ ሄዶ አብሮህ ነው የሚሠራው። ትርፍና ኪሳራን ነው የሚጋራው። ትራክተር ግዛ ብሎ ብር አይሰጥህም። ራሱ ነው የሚገዛው፤ ሥራ ማስኬጃ ብሎ ጥሬ ገንዘብ አይሰጥም። አብሮህ ነው የሚያመርተው። ስለዚህ ተመሳሳይ ውድቀቶች የመከሰት ዕድላቸው ዝቅተኛ ይሆናል። ከወለድ አልነካካም የሚለው ሕዝብ ቁጥሩ ይታወቃል? ይሄ በብሔራዊ ደረጃ መረጃ ማሰባሰብ ይጠይቃል። ቀላል ቁጥር እንዳልሆነ ግን ደግሜ መናገር እችላለሁ። የተወሰኑ ለ2ኛ ዲግሪ ማሟ የተሰሩ የጥናት ወረቀቶችን ይህንን ያመላክታሉ። ሰዎች ወደ ባንክ ለምን አይሄዱም ተብለው ለሚነሱ ጥናቶች አብዛኛው ድምዳሜ ከእምነቴና አስተሳሰቤ ጋር አይጣጣምልኝም የሚለው ብዙ ቁጥር ይይዛል። ከአካባቢዬ ደግሞ ልነሳልህ። እጅግ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሰው ኮንዶሚንየም ዕድልን አሳልፏል። በእምነቱ የተነሳ። የወለድ ሲስተም ውስጥ ላለመግባት። እንዲሁ በየትኛውም ምክንያት ወደ [ማንኛውም ዓይነት] ባንክ ተደራሽ ያልሆነ ሕዝብ ቁጥር ከ50 በመቶ አያንስም። የእኔን ግምት ከጠየቅከኝ ከዚህ ውስጥ ብዙውን ቁጥር ከእምነት ጋር ሊያያዝ የሚችል እንደሆነ መገመት ይቻላል። ከሙስሊም አገራት ውጭ ይህ የባንክ ዘርፍ ምን ያህል ይሠራበታል? በኛ አገርስ ባንኩ ለእስልምና ተከታዮች ብቻ ነው የሚከፈተው? አንዱ የግንዛቤ እጥረት ይሄ ነው። አንደኛ ይሄን ባንክ ሊጠቀም የሚችለው ብቻ ሳይሆን ሊመሠርት የሚችለውም ከአንድ እምነት የሚመጣ ነው አይደለም። ይሄ ቢዝነስ እንጂ ሃይማኖት አይደለም። ትርፍ ያመጣልኛል ያለ ማንም መሥራች ሊሆን ይችላል። ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ ኢስላሚክ ባንክ የሙስሊም ባንክ ሆኖ ይታየናል እንጂ ማንኛውም ዜጋ የባንኩ ባለቤትም ሆነ ተጠቃሚ መሆን ይችላል። በብዙ አገራት የሚሠራበት ነው። ነገሩ እንደ ተጨማሪ አማራጭ ነው መታየት ያለበት። አንድ የሰፈርህ ሱቅ እኔ ቢራ አልሸጥም፤ ለስላሳ መጠጥ ነው የምሸጠው ሊል ይችላል። የሱቁ ባለቤት የትኛውንም ሃይማኖት ሊከተል ይችላል። ደንበኞቹም እንዲሁ። ከሙስሊም አገራት ውጭ... አዎ...እንዳልኩህ በርካታ አገራት የሚሠራበት ነው። ከአረቡ ዓለም ውጭ በዚህ ባንክ ብዙ ልምድ ያላት እንግሊዝ ናት። አል-ረያን የሚባለው ከወለድ ነጻ ባንክ ግዙፉ የሪቴይለር [ችርቻሮ] ባንክ ነው በእንግሊዝ። ከ8 ዓመት በፊት ባንኩ ከነበሩት ደንበኞች ከአስሩ አንዱ ብቻ ነበር ሙስሊም ያልሆነው። በ2018 ምን ሆነ...ከሦስቱ የባንኩ ደንበኞቹ አንዱ ብቻ ነው ሙስሊም ያልሆነው። • በደቡብ ወሎ እውን የህፃናት ስርቆት አለ? ኋላ ላይ ጥናት ተሠራ። ለምን ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ አደገ የሚል። ግንዛቤ ሲጨምር ነው ሁኔታዎች የሚለወጡት። ወልድ አልባ ባንኮች በሆንግ ኮንግ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ በኬንያም ከፍተኛ ገበያ አላቸው። አሁን ባሉ 16 ባንኮች የሌለ ምን ምን ትሩፋት ሊኖር ይችላል? ከተጠቃሚ አንጻር... 16ቱ ባንኮች ያላቸው አገልግሎት ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው። 160 ቢሊየን ብር ወደ ገበያ በብድር መልክ አስገብተዋል 16 ባንኮች በድምሩ። ይህ ገንዘብ የመጣው በዋናነት ከአስቀማጩ ከሚሰበስቡት ገንዘብ ነው። ከሰበሰቡት ገንዘብ ለብድር የሚያውሉት በጣም ትንሽ መጠን ነው። ትርፋቸውን በዲቪደንድ ይከፋፈሉታል። ሌላው ለካፒታል ኢንቨስትመንት ያውሉታል። ለብድር የሚያውሉት የሰበሰቡትን ነው። ይህ ደግሞ አንጻራዊ መልኩ በጣም ትንሽ መጠን ነው። ወለድ አልባው ባንክ ግን ገንዘቡን አብዛኛውን አብሮ ለመሥራት ነው የሚያውለው... ሌላው ወለድ አልባ ባንኮች ሲመጡ ደግሞ አዲስ አማራጭ ይዘው ይመጣሉ። ለምሳሌ ለሥራ ፈጠራ ያላቸውን አማራጭ ማንሳት ይቻላል። • ጥሩ ሰው ምን አይነት ነው? በርካታ ወጣቶች ሐሳብ ይዘው ፋይናንስ አጥተው ተቀምጠዋል። ወለድ አልባው ባንክ አሠራሩ ትርፍና ኪሳራን የመጋራት ዘዴ ነው። ስለዚህ ሐሳብ አለኝ ካልክና አዋጪነቱ ከታመነበት ባንኩ ካሽ ላይሰጥህ ይችላል። ሲያምንበት ግን አብሮህ ይሠራል። ይሄ [እንደኛ የሥራ አጥ ቁጥር ለበረከተበት አገር] መልካም ዜና ይመስለኛል። አሁን ባሉት 16 ባንኮች ግን ይሄ የለም። ባንክ በራሱ ኢንቨስትመንት ውስጥ አይገባም። ሊያደርግ የሚችለው ምንድነው በከፍተኛ ወለድ ገንዘብ ቢያበድርህ ነው። እሱም መያዣ ትጠየቃለህ። ሙሻረካና ሙዳረባ አገልግሎት ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው የሚሰሩት። ነገሩን ካነሱት አይቀር...ምንድነው ሙሻረካ-ሙዳረባ? እንዴትስ ነው ያለ ወለድ ባንክ አትራፊ የሚሆነው? ለምንስ ሰው ወለድ የማያስገኝ ከሆነ ብሩን ወደ ባንክ ይዞ ይመጣል? እስኪ በቀላል ምሳሌ ያስረዱን... እንደምታውቀው በመደበኛው ባንክ ተቀማጭና ተንቀሳቃሽ ሒሳብ የሚባል አለ። ደንበኛው ባስቀመጠው ገንዘብ ከ7 እስከ 9 በመቶ ወለድ ያገኝበታል። በወለድ አልባ ያለው ግን ሙዳረባና ሙሻረካ የሚባል የሒሳብ ዓይነት ነው፤ በዋናነት። መሠረታዊው ልዩነት በወለድ አልባ አስቀማጩ ገንዘቡን የሚያስቀምጠው ባንኩ በተቀመጠው ገንዘብ ሠርቶ ከሚያገኘው ትርፍና ኪሳራ ለመጋራት ወስኖ ነው። ስለዚህ ገንዘቡን ያለ ወለድ ቢያስቀምጥም ምንም ጥቅም አያገኝም ማለት አይደለም። • «ሙሉ ቤተሰቤን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ» በመደበኛ ባንክ ልክ ገንዘብ ስታስቀምጥ በእርግጠኝነት ወለድህን ታገኛለህ፤ የተተመነውን። በወለድ አልባው ግን አስቀማጩ ወይም ባንኩ በመረጠው መንገድ ተነግዶበት ከሚያመጣው ትርፍ ላይ ተካፋይ ለመሆን ነው ገንዘቡን የሚያስቀምጠው። ስለዚህ ብር ስታስቀምጥ ትርፍ አታገኝም ማለትም አይደለም፤ ታገኛለህ ማለትም አይደለም። በአጭሩ አንድ አስቀማጭ ሲመጣ ባንኩ ካተረፈ ልጋራ፣ ከከሰረም ልከስር ብሎ ነው የሚገባው። ከወለድ ነጻ በመስኮት ብቻ እኔና አንተ በምናወራበት ሰዓት 30 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል። ይሄ ገንዘብ ግዴለም ወለድ አይሰጠኝ ያለ ሰው ያስቀመጠው ገንዘብ ነው። ስለዚህ እነዚህ ባንኮች ሲከፈቱ እንዲህ የሚሰበሰው ብር አስቀማጩ ጋ በሚደረግ ስምምነት ቢዝነስ ይሠራበታል ማለት ነው። ቢዝነሱ ሲሳካ አስቀማጩ ያተርፋል፤ ሲከስር ይከስራል። ዋና ዋና የሚባሉት አገልግሎቶቹን በቀላሉ በምሳሌ ቢያስረዱን ብዬ ነበር... ብዙ ናቸው። ሦስቱን ብቻ እናንሳ... አንዱ ሙራባሃ ይባላል። 10 የሚሆኑት ወለድ አልባ መስኮቶች ይህን አገልግሎት ይሰጣሉ። እንበልና መኪና መግዛት ፈለክ። ባንኩን በሙራባሃ መኪና መግዛት እፈልጋለሁ ስትለው መኪናውን ባንተ ፍላጎት ተመሥርቶ ራሱ ይገዛዋል። መኪናውን ገዝቼልህ ላንተ ስሸጥልህ ማትረፍ የምፈልገው 40ሺህ ብር ነው ሊለው ይችላል። ይደራደራሉ። ገንዘቤን መቼ ትሰጠኛለህ ሲለው ከ2 ዓመት በኋላ ሊለው ይችላል፤ ደንበኛው። ዝርዝሩ ብዙ ነው ብቻ ባንኩ ይገዛና ለደንበኛው አትርፎ ይሸጥለታል። ክፍያውን የሚቀበለው ግን በቁርጥ ዋጋ ለመክፈል በተስማማበት ጊዜ ነው። መኪናውን ግን በስሙ ነው የሚገዛው ባንኩ። ሪስኩን የሚያካክሰው በስሙ በመግዛት ነው። ልክ እንደ ነጋዴ ገዝቶ አትርፎ ነው የሚሸጥልህ፤ ትርፉም ባንኩ ያተርፈኛል በሚለው በድርድር የሚወሰን ነው። ባንኩ ነጋዴ ይሆናል ማለት ነው። ከመደበኛው ባንክ የሚለየው ደንበኛው በውሉ መሠረት መጨረሻ ላይ መኪና ተገዝቶ ስለተሰጠው የሚከፍለው ገንዘብ የተቆረጠ መሆኑ ነው። ከፍና ዝቅ ማድረግ አይቻልም። ከባንኩ ጋ በሽርክና መሥራት ብለውኝ ነበር ቅድም... ልመጣልህ ነው...ሁለተኛው አገልግሎት ሙዳረባ ይባላል። ለምሳሌ ካፌ መክፈት ብፈልግ ባንኩን አነጋግረዋለሁ። በሙዳረባ አካውንት ብቻ የሚያስቀምጡ ደንበኞች ይኖሩታል ባንኩ። አስቀማጮቹ ምን ይላሉ 'ባንኩ እኔን ወክሎ፣ ቢዝነስ ሐሳብ ያለውን ሰው ተቀብሎ፣ ገምግሞ አዋጪ ነው በሚለው ዘርፍ እኔን ወክሎ ይነግድልኝ' ሊሉ ይችላሉ። ስለዚህ ክህሎትና ሐሳብ ያለው ሰው፣ ነገር ግን ብር የሌለው ሰው ሲመጣ ባንኩ ደግሞ ብሩን ይዞ ይገባል። ንግድ ይነግዳሉ ትርፍንም ኪሳራንም ይጋራሉ ማለት ነው። ይሄ በተለይ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች በጣም ጠቃሚ ነው። ሦስተኛው ሙሻረካ ይባላል። ይህ እንደ ሙዳረባ ሆኖ ነገር ግን የቢዝነስ ሐሳብ አመንጪው በገንዘብም ይሳተፋል። በአጭሩ የሽርክና ቢዝነስ ማለት ነው። ሲያተርፉም ሲከስሩም አብረው ነው። ዲሚኒሺንግ ሙሻረካ የሚበልም ዘርፍ አለ። እዚሁ ላይ፤ ምን ማለት መሰለህ እየቀነሰ የሚሄድ ሽርክና ማለት ነው። ባንኩ ለምሳሌ እኔ ንብረቱን አልፈልግም ስለዚህ እየቀነሰ በሚመጣ ሽርክና እንግባ ካለ ሽርክናውን በጋራ ይጀምሩና ባንኩ ቀስ እያለ ከሽርክናው ይወጣል። ባለቤትነቱም በተወሰነ ዓመታት የግለሰቡ ይሆናል። ለምሳሌ አንድ ግለሰብ ይመጣና ሪልስቴት ልገዛ ፈልጌ ነው ይለዋል። አንድ ሚሊዯን ብር ቢሆን ቤቱ ደንበኛው 4 መቶ ሺህ አለኝ ቢል ባንኩ 600 ሺህ ይከፍልና ቤቱ የሁለቱም ይሆናል። ልብ ማለት ያለብህ ቤቱ የደንበኛው ብቻ አለመሆኑን ነው። ቤቱ የባንኩም ጭምር ነው። ቤቱ እየተከራየ ነው ብንል ግለሰቡ የኪራይ ብሩን በስምምነታቸው መሠረት ለባንኩ እየከፈለ ይቀንሳል። ባንኩ ከቤቱ የስምምነቱን አትርፎ ግለሰቡን ሙሉ የቤት ባለቤት ያደርገዋል። ይሄ ሲሆን ቫሊዊሸን የንብረት ዋጋ ግምት እንዳለ ሆኖ ለባንኩ የኪራይ ዋጋ ለገዛበት ዋጋ እየከፈለ በሆነ ዓመት ቤቱን ለደንበኛው ለቆለት ይወጣል። • “በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ ለምሳሌ ቤቱ 10ሺ ቢከራይ ባንኩ በየወሩ የኪራይ ብር 9ሺህ ሲያገኝ ለሱ ትርፉ ያ ነው። 90 በመቶ ለከፈለለት ደግሞ ገዢው በየዓመቱ 10 ፐርሰንት እያስለቀቀ ይመጣል። ሌላውና ሦስተኛው ኢጃራህ የሚባል ነው። ይሄ ከሊዝ ፋይናንሲንግ ጋ የሚመሳሰል ነው። ባንኩ የሆነ ማሽን ይገዛና ላንተ በኪራይ ያከራይሃል። ስምምነታችሁ የ10 ዓመት ቢሆን ማሽኑን ለ10 ዓመት ያከራይሃል። ሳልቬጅ [ሲያረጅ] ትገዛኛለህ አይልህም። በ11ኛው ዓመት የግዴታ ማሽኑን ትገዛለህ ተብለህ አትገደድም። ስለዚህ ቅድም ባንኩ ነጋዴ ሆኖ ነበር አሁን ደግሞ ባንኩ አከራይ ሆነ ማለት ነው። አሁን በመስኮት ደረጃ የሚሠሩት ባንኮች ብዙ ብር ሰብስበዋል። ወለድ አልባ ባንኮች ሲከፈቱ ፍልሰት አይገጥማቸውም? ሕልውናቸው አያሰጋም? አሁን በመስኮት የሚሰሩት ዝም ብለው ይወድቃሉ ማለት አደለም። በጣም ጠንካራ ልምዱ ያላቸው እነሱ ናቸው። ቁጭ ብለው አያዩም። ውድድር ነው። ብዙ ተወዳዳሪ የሚሆኑ ይመስለኛል። ገና ለገና ባንኮቹ ውድድር ሊገጥማቸው ይችላል ተብሎ ግን ወለድ አልባ ባንክ አይከለከልም። አዲስ የሚመጣው ባንከጅ ተጨማሪ አማራጭ ይሆናል እንጂ አሁን ያሉትን ያንኮታኩታል ማለት አይደለም። በርካታ ኢስላሚክ ባንኮች ምሥረታ ላይ እንደሆኑ ይሰማል። አሁን እንኳ በሥራ ላይ ያሉት ባንኮች ለመጣመር እየሞከሩ አዲስ የሚመጡት ተፈረካክሰው ነው። ለምን?ለመሆኑ የውጭ ባንክ መምጣት ኢስላሚክ ባንክን አያሰጋውም? [ያው እኔ ኢስላሚክ ባንክ ከሚለው ይልቅ ወለድ ነጻ ባንክ የሚለው አጠራር ነው የሚመቸኝ፤ እንደሱ እያልኩ ልቀጥልልህ] የውጭ ባንክ ሲመጣ ወለድ አልባ ባንክን በደንብ ያሰጋዋል። በቅርብ ካሉት እንኳ ብናይ እነ ኬሲቢ [የኬንያው] በደንብ ነው ልምድ ያላቸው፤ የደቡብ አፍሪካውም እንዲሁ። ካፒታል አቅማቸውም ግዙፍ ነው። አንዱ አዲስ ለሚመሠረቱ ባንኮች ያላቸው ዕድል የችርቻሮ ባንኪንግ ዕድል ነው። በየገጠሩ እየገቡ በመሥራት ጫነውን መቋቋም ይችላሉ። ተበታትነው ለምን ይመሠረታሉ ላልከው... እኔ አሁን የታየውን ነገር ታፍኖ እንደተለቀቀ ሙቀት ነው የማየው...ማኅብረሰቡ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮ ነበር፤ [ለዓመታት ዘርፉ ባለመፈቀዱ]። ልክ ሲፈቀድ ሰው ተፈጥሯዊ ምላሽ ነው የሰጠው፤ ሲፈቀድ ሩጫ ጨመረ፤ ይሄ ለምን ሆነ አይባልም። [እየመጡ ያሉት] ብዙ ሊመስልህ ይችላል እንጂ በቅርቡ አውቀዋለሁ...አሁን ላይ ያለኝ መረጃ ብሔራዊ ባንክ ሄደው የተመዘገቡት 3 ብቻ ናቸው። ከ3ቱ ሁለቱ አንድ ለመሆን ድርድር ላይ ናቸው። ስለዚህ ምናልባት ቢበዛ ሁለት ወይ ሦስት ባንኮች ቢወጡ ነው። ሰዎች ባንክ በዛ ይላሉ። ማርኬት በጣም ሰፊ እንደሆነ አይረዱም። 40 ሚሊዮን ሕዝብ ኖሯቸው 70 ባንክ ላላቸው አገራት እያሉ ለኛ ሦስትና አራት ባንክ ብዙ ነው ብዬ አላምንም። የነዚህ ባንኮች ፈተና ምንድነው ይላሉ? ከሰው ኃይልና ከመሠረተ ልማት አንጻር ፈተና ይኖራል። ወለድ አልባ ፋይናንስኢንግ የሚያሰለጥን ከፍተኛ ተቋም የለንም። ሌላው ፈተና በተለይም ከሬጉሌሽን አንጻር ብዙ ሥራ ይጠበቃል። ሜዳውን ምቹ የማድረግ ሥራ ከብሔራዊ ባንክ ያስፈልጋል። ብሔራዊ ባንክ በዚህ ረገድ ያለው ዝግጁነት አመርቂ የሚባል አይደለም። የመጨረሻ ጥያቄ ላንሳ፡ አንድ ቢራ ፋብሪካ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ይዞ ከወለድ ነጻ ባንኮች ሂሳብ ልክፈት ቢል ይፈቀድለታል? አይችልም። አመሰግናለሁ!
news-53568976
https://www.bbc.com/amharic/news-53568976
የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ፡ ከሰኞ ሰኔ 22/2012 እስከ ዛሬ ድረስ
በበርካታ አድናቂዎቹ ዘንድ የሚወደደው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ ለመጨረሻ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቦ ቃለ ምልልስ ያደረገው ሰኔ 15/2012 ኦኤምኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ነበር።
ከሳምንት በኋላም ሰኔ 22/2012 ምሽት የሞቱ ዜና ተሰማ። ሰኔ 24/ 2012 ዓ.ም ደግሞ ግብዓተ መሬቱ በተወለደባት አምቦ ከተማ ተፈጽሟል። የሃጫሉ ህልፈት ሚሊዮኖችን አስደንግጧል፤ በርካቶችን አስቆጥቷል። አሳዝኗል። ግድያውን ተከትሎም በተነሳ አለመረጋጋት ከ167 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቤት ንብረታቸው ዶግ አመድ ሆኗል። ከ7000 በላይ ሰዎችም ከተከሰተው ሁከት ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን የመንግሥት ባለስልጣናት ከሰጡት መግለጫ መረዳት ይቻላል። የኦኤምኤን ቃለ መጠይቅ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ ከአንድ ሳምንት በፊት ከኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ አየር ላይ ውሎ ነበር። ሃጫሉ ለመጨረሻ ጊዜ ለሕዝብ የታየውም በዚያ ቃለ መጠይቅ ላይ ነው። ሃጫሉ ከኦኤምኤን ጋር በነበረው ቆይታ በሰጣቸው አስተያየቶች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ሃጫሉ ከተገደለ በኋላ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከሰጣቸው መግለጫዎች በአንዱ፤ በኦኤምኤን ላይ የተደረገው ቃለ መጠይቅ፣ ድምጻዊው ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር እንዲጋጭ የሚያደርጉ ሌሎች አመለካከቶቹን እንዲያጸባርቅ በጠያቂው በኩል ተደርጓል ሲሉ በጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ጸጋ ተናግረዋል። ሰኔ 23 ረፋዱ ላይም በአዲስ አበባ የሚገኘው የኦኤምኤን ቢሮ በፌደራል ፖሊስ ብርበራ ተካሂዶበት እንዲዘጋ ተደርጓል። ሃጫሉ ሁኔዴሳን ያነጋገረው ጋዜጠኛም ቆየት ብሎ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ሃጫሉ ለመጨረሻ ጊዜ ለህዝብ የታየውም በኦኤምኤን ቃለ መጠይቅ ላይ ነበር የመገደሉ ዜና ሰኔ 22 ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጥይት ተመትቶ መገደሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ከእኩለ ለሊት በኋላ ይፋ አደረገ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በብሔራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው በተናገሩበት ወቅት በግድያው ወንጀል የተጠረጠሩ የተወሰኑ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል። የሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ተመቶ የመገደል ዜና ከፖሊስ መግለጫ በፊት በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መዘዋወር የጀመረው ከምሽቱ 5፡30 አካባቢ ጀምሮ ነው። ሌሊቱን በፌስቡክ አማካኝነት ሲሰራጩ በነበሩ የቀጥታ ስርጭቶች፤ በርካቶች መንገድ ላይ በመውጣት ሲያለቅሱ ታይተዋል። ሃጫሉ በጥይት ከተመታ በኋላ ወደ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ተወስዶ ነበር። ከዚያም የሃጫሉ አስክሬን ለምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ተላከ። ቁጣ፣ አለመረጋጋት እና ጥቃት የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቁጣ ተሰምቷል፣ አለመረጋጋት ተከስቷል፤ በንጹሃን ዜጎች ህይወት እና ንብረት ላይም ጥቃቶች ተፈጽሟል። ንጋት ላይ እንደ አዳማ፣ ጅማ እና ጭሮ ባሉ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ። በምሥራቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ ከተሞች ደግሞ መንገዶች ዝግ ተደረጉ። በሌሎች አከባቢዎች ደግሞ ማክሰኞ አጥቢያ ላይ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በተለይ በባሌ እና አርሲ አካባቢዎች ብሔር እና ሐይማኖትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በንጹሃን ዜጎች ላይ ተፈጽመዋል። በዚህም በርካቶች ተገድለዋል። የንብረት ውድመትም አጋጥሟል። የተለያዩ ሰዎች የሃዘን መልዕክት የሃጫሉን ሞት ተከትሎ ከማክሰኞ ሰኔ 23 ጀምሮ የተለያዩ ሰዎች ሃዘናቸውን መግለጽ ጀመሩ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በድምጻዊው ሞት የተሰማቸውን ሀዘን "ውድ ህይወት አጥተናል" ካሉ በኋላ "የዚህ ድንቅና አንፀባራቂ ወጣት አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህይወት መቀጠፍ ከተሰማ ጀምሮ በከባድ ሃዘን ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁም" በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድምጻዊው ግድያ ከባድ ሐዘን እንደተሰማቸው ገልጸው "ሃጫሉን የገደለው ማንም ይሁን ማን ከህግ ማምለጥ አይችልም" ሲሉ ተናግረው ነበር። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናትም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል። የአስክሬን ሽኝት የአርቲስቱን አስክሬን ለማጀብና ለመሸኘት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአዲስ አበባ ዙሪያ ወደ መዲናዋ መትመም የጀመሩት ከሰኔ 23 ንጋት በፊት ነበር። ብዙም ሳይቆይ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስክሬን ግብዓተ መሬት መፈጸም ባለበት ስፍራ ላይ አለመግባባቶች ተፈጠሩ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ እና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ የመንግሥት ባለስልጣናት የአርቲስቱ ቤተሰቦች ቀብሩ እንዲፈጸም የሚፈልጉት በአምቦ ነው ብለው ነበር። የሃጫሉ ወንድም ሃብታሙ ሁንዴሳ፤ "ቤተሰብ ሃጫሉ እንዲቀበር የሚፈልገው በአምቦ ከተማ ውስጥ ነው" ሲል በወቅቱ ለቢቢሲ ተናግሯል። የአርቲስት ሃጫሉ አስክሬን ከጰውሎስ ሆስፒታል ወደ አምቦ እያመራ ቡራዩ ከደረሰ በኋላ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በአዲስ አበባ ነው መፈጸም ያለበት በሚል ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ተደርጎ ለተወሰኑ ሰዓታት በኦሮሞ ባህል ማዕከል ውስጥ ቆይቶ ነበር። ከዚያም አስክሬኑ አዲስ አበባ ስታዲም አቅራቢያ ከሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማዕከል በሄሊኮፕተር ተጭኖ ከአምቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ወደ ሚገኘው ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ተወሰደ። የእነ ጃዋር መሐመድ እስርና የኢንተርኔት መቋረጥ ማክሰኞ ሰኔ 23 ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 35 ሰዎች በቁጥጥር እንዲውሉ መደረጉን የፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሸን በጋራ በሰጡት መግለጫ ይፋ አደረጉ። በወቅቱ እነ ጃዋር ላይ ከቀረበው ክስ መካከል "በጃዋር መሐመድ የሚመራው ቡድን የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ አድርጓል" የሚለው ይገኘበታል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ በበኩላቸው "በጃዋር መሐመድ የሚመራው ቡድን አስክሬኑ በቤተሰቡ ጥያቄ መሰረት ከጳውሎስ ሆስፒታል ወጥቶ ወደ አምቦ እየተሸኘ ሳለ፤ ከቤተሰቡ ፍቃድ ውጪ ቡራዩ ሲደርስ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ አደርጓል" ብለው ነበር። የኢትንተርኔት አገልገሎት በመላው አገሪቱ ለሦስት ሳምንታት ያህል የተቋረጠው በአርቲስቱ ግድያ ማግስት ማክሰኞ ሰኔ 23 ጀምሮ ነበር። በቅድሚያ የሞባይል ዳታ ከዚያም ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን በወቅቱ ተጠቃሚዎች ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ሌላ ግድያ በአምቦ ሰኔ 24 የሃጫሉ አስክሬን አምቦ በደረሰበት ዕለት የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከሚፈጸምበት ቦታ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ ግጭቶች የሃጫሉን አጎት ጨምሮ 5 ሰዎች ተገደሉ። ከሃጫሉ አጎት በተጨማሪ ሦስት የቤተሰብ አባላት በጥይት ተመትተው የተለያየ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሃጫሉ ወንድም ሃብታሙ ሁንዴሳ ለቢቢሲ ተናግሯል። የሃጫሉ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኔ 25 የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት በአምቦ ከተማ በሚገኘው የገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተፈጸመ። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው የሽኝት ፕሮግራምም ሆነ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በተፈጸመበት ቤተ-ክርስቲያን በደኅንነት ስጋት ምክንያት የተገኘው ሰው ቁጥር ዝቅተኛ ነበር። የአርቲስት ሃጫሉ የቅርብ ጓደኞች እና የቤተሰብ አባላት ሳይቀሩ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ መገኘት ባለመቻላቸው ሥርዓቱን በኦቢኤን ቴሌቪዥን ለመከታተል ተገደለዋል። ለቀብር ከአምቦ ዙሪያ የሚመጡ ሰዎች ወደ ከተማው እንዳይገቡም ተከልክለው ነበር። የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ሃዘንተኞች ወደ ከተማው እንዳይገቡ እና ወደ መጡበት እንዲመለሱ ለማድረግ አስለቃሽ ጭስ ሲተኩስ ነበር ሲሉ አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች በወቅቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሃጫሉ ግድያ የተጠረጠሩ ሐምሌ 3 ላይ ጠቅላይ አቃቤ ዐቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ቀጥተኛ ተሳታፊ ናቸው ብለው በስም የጠቀሷቸው ሦስት ግለሰቦችን ይፋ አደረጉ። እነዚህ ግለሰቦች ጥላሁን ያሚ፣ አብዲ አለማየሁና ከበደ ገመቹ የሚባሉ ሲሆኑ በወቅቱ እንደተገለፀው፤ ሃጫሉ ሁንዴሳን በጥይት ተኩሶ በመግደል የተጠረጠረው ጥላሁን ያሚ የተባለው ግለሰብ ነው። ጨምረውም ሦስቱ ግለሰቦች የግድያውን ተልዕኮ ኦነግ-ሸኔ ከተባለው ቡድን ተቀብለው ማስፈጸማቸውን በመግለጽ፤ ቡድኑ ከግድያው ጀርባ እጁ እንዳለበት ዐቃቤ ሕጓ ተናግረዋል። ሐምሌ 1 በአሜሪካው ሴንት ፖል ሚኒሶታ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በዲያስፖራው መካከል ልዩነት መፈጠር የአርቲስት ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፎች የታዩት በአገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን፤ በአሜሪካ፣ አውሮፓ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ እና አውስትራሊያም ጭምር ነበር። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መንግሥትን የሚቃወም እና ለአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ፍትህ የሚጠይቁ ሰልፎች ተካሂደዋል። በሌላ በኩል ለጠቅላይ ሚንሰትሩ ድጋፋቸውን የሚገልጹ እና የሃጫሉን ግድያና ተከትለው የተፈጸሙ ጥቃቶችን የሚያወግዙ ሰልፈኞችም በተለያዩ የውጪ አገራት ከተሞች ታይተዋል። አርቲስት ሃጫሉ ለህዝብ ጆሮ ያልደረሱ ከ7 ያላነሱ የሙዚቃ ስራዎች አሉት "ልጄ ጀግና ነው። ለእውነት ይሞታል" አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ልጃቸውን ሲያስታውሱ "ልጄ ጀግና ነው። ለእውነት ይሞታል" ይላሉ። "ሃጫሉ ከልጅነቱ ጀምሮ ጀግና እና ደፋር ነበረ። ውሸት አይወድም። እውነት ነው የሚወደው፤ የሚሞተውም ለእውነት ነው" የሚሉት የሃጫሉ ወላጅ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ፤ ሃጫሉ ለሞት የተዳረገው ለወገኑ በመቆርቆሩ እና "ያገባኛል" በማለቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል። "እኔ የሚያበሳጨኝ ነገር ሃጫሉ እንደእሱ ጀግና በሆነ ሰው ሳይሆን በገንዘብ በተገዙ ፈሪዎች መንገድ ላይ መቅረቱ ነው" ሲሉም ያክላሉ። የሃጫሉ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ሃጫሉ ማን ነበር? ሃጫሉ ሁንዴሳ ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ አንድ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምተገኘው አምቦ ከተማ ውስጥ ነው። እናቱ ወይዘሮ ጉደቱ ሆራ፣ ሃጫሉ ከልጅነቱ ታሪክን መስማትና የመንገርና ዝንባሌውንና ችሎታውን ጠንቅቀው ተረድተውት ስለነበር ከመጀመሪያው አንስቶ ያበረታቱት እንደነበር በተደጋጋሚ ሃጫሉ ያስታውሳል። አባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ደግሞ ልጃቸው ሃጫሉ በትምህርቱ ዓለም ገፍቶ ዶክተር ወይም የዩኒቨርሲቲ መምህር እንዲሆንላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው። ሃጫሉ ግን ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በፍቅሯ ለወደቀላት ሙዚቃ ነበር መላው ትኩረቱ። ሃጫሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ በ1995 ዓ.ም የ17 ዓመት ታዳጊ እንዳለ ታስሮ ለአምስት ዓመታት በተለምዶ "ከርቸሌ" ተብሎ በሚጠራው አምቦ በሚገኘው እስር ቤት አሳልፏል። ሃጫሉ እና ፋንቱ በትዳር ከመጣመራቸው በፊት ለበርካታ ዓመታት በፍቅር ጓደኝነት አብረው ቆይተዋል መታሰሩ በይበልጥ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና ጭቆና እንዲገባው ማድረጉን በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር። የሙዚቃ ግጥሞችን ዜማዎችን መጻፍ የጀመረውም በእስር ላይ እያለ ነበር። ከአምስት ዓመታት በኋላ ሲለቀቅ የደረሰበትን በደል ለመቃወምና ለሚሊየኖች ድምጽ ለመሆን ወስኖ እንደወጣ ይናገራል፤ ሃጫሉ። በአጭር ጊዜም በኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመላዋ አገሪቱ ተወዳጅ የሆነለትን 'ሳኚ ሞቲ' የተሰኘውን አልበሙን አቀረበ። የዚህ የሙዚቃ ስብስብ አብዛኛዎቹ ግጥሞችና ዜማዎች ሃጫሉ በእስር ላይ እያለ የሰራቸው እንደነበሩ ይነገራል። የ36 ዓመቱ ሃጫሉ የሦስት ልጆች አባት ነበር። የሃጫሉ ለሕዝብ ጆሮ ያልደረሱ የሙዚቃ ሥራዎች አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ለሕዝብ ጆሮ ያልደረሱ ከ7 ያላነሱ የሙዚቃ ሥራዎች በተለያዩ ስቱዲዮች ውስጥ እንደሚገኙ ከቅርብ ጓደኞቹ ሰምተናል። የቤተሰብ አባላት እና ጓደኞቹ ከሚመለከታቸው ጋር ተወያየተው በአልበም መልክ ለአድናቂዎቹ ለማቅረብ ሃሳብ እንዳላቸውም ቢቢሲ መረዳት ችሏል።
news-55079314
https://www.bbc.com/amharic/news-55079314
ትግራይ፡ ኤርትራ በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል ግጭት እጇን አስገብታለች?
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ የመጣው የፌደራል መንግሥትና የትግራይ ክልል ግንኙነት የማይታረቅ ደረጃ ደርሶ ወደ ወታደራዊ ውጊያ ከተሸጋገረ ከሦስት ሳምንታት በላይ ሆኖታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች በትግራይ የሚገኘውን ትልቁንና በትጥቅ የተደራጀውን የመከላከያ ሠሜን ዕዝ ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልፀው ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወሳል። ውጥረቱ ወደ ወታደራዊ ግጭት ከማምራቱ በፊት በፌደራል መንግሥትና የትግራይን ከልል በሚመራው ህወሓት መካከል የነበረው መቃቃር የተባባሰው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሆነ ፓርላማው በአገሪቱ ታቅዶ ነበረው ምርጫ እንዲራዘም የሰጡትን ውሳኔ ባለመቀበል የትግራይ ክልል የተናጠል ምርጫ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የፌደራል መንግሥቱ "ኢ-ሕገ መንግሥታዊና ተቀባይነት የሌለው" ባለው በዚህ ምርጫ ህወሓት በማሸነፉ "ሕጋዊ አስተዳደር መስርቻለሁ" ብሏል። ለሳምንታት በዘለቀው ግጭት የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ዋና የምትባለውን የሽሬን፣ አድዋን፣ አክሱምንና አዲግራትን ጨምሮ ምዕራባዊ ትግራይ ግዛቶችን ተቆጣጥሯል፤ እንዲሁም በደቡብ በኩልም ራያን በቁጥጥሩ ስር አድርጓል። በግጭቱ የሞቱና የቆሰሉ አካላት እንዳሉ ከሁለቱም ወገን ቢጠቀስም ቁጥሩ አልተገለፀም። ከዚህም በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ያስታወቀው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ ዩኤንኤችሲአር ቁጥሩን ከ40 ሺህ በላይ መድረሱን አስታውቋል። በትግራይ ክልል የሚደረገው የአየር ጥቃት መቀጠሉ ተገልጿል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጦርነቱ ውስንና በተወሰኑ የህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረና ሕገ መንግሥትን ለማስከበር እየተወሰደ ያለ እርምጃ መሆኑን ገልፀው በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ መግለፃቸው ይታወሳል። የትግራይ ክልል በበኩሉ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጦርነት እንደተከፈተበትና ሕዝቡም ላይ ያነጣጠረ ነው ይላል። በሁለቱ ኃይሎች መካከል ያለው የውጊያው ሌላ ገፅታ ደግሞ የአገር ውስጥ ግጭት ቢሆንም ጎረቤት አገር ኤርትራ በግጭቱ ውስጥ እጇን አስገብታለች መባሏና ያላት ሚና ጥያቄ ሆኗል። በግጭቱ ላይ የኤርትራ ሚና ምንድን ነው? ኤርትራ ሠራዊቷን በድንበር በኩል በሽራሮ እንዲሁም በአላማጣ በኩል ከፌዴራል መከላከያ ሠራዊት ጋር እንዳሰለፈች የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናግረዋል። የኤርትራ መንግሥት በቀጥታ ተሳታፊ መሆኑን ህዳር 1/2013 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት ርዕሰ መስተዳድሩ የኤርትራ ሠራዊት አባላት በምዕራብ ትግራይ በኩል ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመዋል ሲሉ ከሰዋል። የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከፌደራል መንግሥት ጋር በመወገን በሁመራ በኩል በካባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት እንደፈፀሙና ድንበር ጥሰው በባድመ በኩል በመግባት ጦርነት ከፍተዋል ብለዋል በወቅቱ በሰጡት መግለጫ። ይህንንም ተከትሎ ከትግራይ ክልል የተነሱ ተወንጫፊ ሮኬቶች በኤርትራ መዲና አሥመራ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ኢላማ አድርገዋል። አየር ማረፊያው የኤርትራ አየር ኃይልም የሚገኝበት ነው። ከክልሉ የተነሱ ሦስት ሚሳይሎች ወደ ኤርትራ የተወነጨፉ ሲሆን አንደኛው አየር ማረፊያው አካባቢ ሲወድቅ ሁለቱ ደግሞ መኖሪያ ሰፈሮች መውደቃቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ኤርትራንና ኢትዮጵያን በሚያዋስነው ድንበር በኩል በተለያዩ ግንባሮች ከባድ የጦር መሳሪያዎች የተሳተፉበት ውጊያ መደረጉንም ቢቢሲ ከምንጮቹ ሰምቷል። ግጭቶቹም በአሊቴና፣ ዛላምበሳ፣ ፆረናና መረብ በኩል መከሰቱም ሪፖርት ተደርጓል፤ እነዚህ ቦታዎች በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት(1990-1992) ወቅት የግጭቱ ገፈት ቀማሽ ነበሩ። የኤርትራ ምላሽ ምንድን ነው? የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትን ክስ ማጣጣላቸውን ሮይተርስ ህዳር 1/ 2013 ዓ.ም ባወጣው ዘገባ አመልክቷል። "ይህ ውስጣዊ ግጭት ነው። እኛ የግጭቱ አካል አይደለንም" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በስልክ እንደገለጹለት ሮይተርስ ዘግቧል። በለንደን የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲም በበኩሉ የዩናይትድ ኪንግደም ኢንተር ፓርቲ የፓርላማ ቡድን የትግራይ ክልል ከኤርትራ አደጋ ተጋርጦበታል ብሎ የሰጠውን መግለጫ አጣጥሏል። በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር እስጢፋኖስ ሐብተማርያም ለኮመን ዌልዝ የውጭ ጉዳይ ቢሮ በፃፉት ደብዳቤ "የትግራይ ክልል ከኤርትራ መንግሥት በኩል አደጋ ተጋርጦበታል በሚል ያወጣውን የፓርላማ ቡድን ሪፖርት አይቀበልም" ብለዋል። በፀረ-ህወሓት ትዊታቸው የሚታወቁት አምባሳደሩ አሥመራ ላይ የተወነጨፉትንም ሚሳይሎች በተመለከተ ምላሽ ሰጥተዋል። "ህወሓት ሕገወጥ የሆነና የሃሞተ ቢስ ተግባር ህዳር 4/ 2013 አከናውኗል" ያሉት አምባሳደር እስጢፋኖስ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትንም በመጀመር ህወሓን ወንጅለዋል። አምባሳደሩ ይህንን ይበሉ እንጂ ከ100 ሺህ ሰዎች በላይ በነጠቀውን ጦርነት የጀመረችው ኤርትራ መሆኗን የግልግል ዳኝነት ኮሚሽን ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ከዚህ ምላሽ ውጪ ኤርትራ ዝምታን መርጣለች። የኤርትራ መንግሥት ሚዲያም ስለ ግጭቱ የጠቀሰው ነገር የለም። ነገር ግን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በበኩላቸው የህወሓትን ድርጊት "ማጉላት" አያስፈልግም በማለት ህዳር 9/ 2013 ዓ.ም በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። "በአስራ አንደኛው ሰዓት የሚጠበቅና ትርጉም በሌለው ድርጊት ማጉላትም ሆነ ምላሽ መስጠት አያስፈልግም" ብለው ያሰፈሩ ሲሆን፤ የትኛውን ድርጊት እንደሆነ በግልፅ አልጠቀሱም። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ሆኑ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ጄኔራሎች የተወሰነው ሠራዊት ከኤርትራ ድንበር በኩል የህወሓትን ኃይል እንደተፋጠጡ አመላክተዋል። የትግራይ ኃይል የሰሜን ዕዝን ማጥቃቱን ተከትሎ የተወሰነው የሠራዊቱ አካል ሁለቱን አገራት የሚያዋስናቸውን ድንበር አቋርጠው ወደ ኤርትራ ገብተዋል ተብሏል። በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥሪ ተደርጎላቸው ወደ ውትድርና ኃላፊነት የተመለሱት ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌም ከትግራይ ኃይል ጥቃት የተረፉ የሠራዊቱ አባላትን በዛላምበሳ፣ ራማና ሽራሮ መጎብኘታቸውን አስታውቀዋል። ለሌተናል ጄኔራሉም ሆነ የጠቀሷቸው የሠራዊቱ አባላት የሚገኙባቸው ቦታዎች የኤርትራ ግዛቶችን ተገን ሳያደርጉ መዋጋቱ የማይቻል ነው። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ወታደሮች በበርካታ የኤርትራ ከተሞች የታዩ ሲሆን ቁስለኛ የሠራዊቱ አባላትም በአገሪቱ በሚገኙ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ቢቢሲ ትግርኛ ከነዋሪዎችና ከምንጮች ሰምቷል። ከዚህም በተጨማሪ በኤርትራ ደቡባዊቷ ከተማ ሰንአፈ በሚገኝ የመንግሥት ሆስፒታል የሠራዊቱ አባላት ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ቢቢሲ ከታማኝ ምንጭ ያገኘው መረጃ ያስረዳል። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በህወሓትና በኤርትራ አመራር በኩል ያለው ቁርሾ የቀደመ ቢሆንም የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ግንኙነታቸውን የቋጨ ሆኗል። በተለይም በድንበር ግጭቱ ሦስተኛው ዙርና በግንቦት ወር 1992 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሠራዊት የኤርትራን መከላከያ አሸንፎ የደቡብ ምዕራብ በርካታ ግዛቶችን ተቆጣጥሮ ነበር። ሽንፈቱ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አሳፋሪ የነበረ ሲሆን በኤርትራውያንም ዘንድ የድንበር ጦርነቱን እያካሄዱ ያሉበት መንገድ ትችትን እንዲያስተናግዱ ምክንያት ሆኗል። ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግሥት ኤርትራን ከዓለም አቀፉ ዲፕሎማሲ እንድትነጠል የተሳካ ሥራን ሰርቷል። ለረዥም ጊዜያትም ኤርትራ የተገለለች ሆና ቆይታለች። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምንም እንኳን ዓለም አቀፉ የድንበር ኮሚሽን ግዛቶቹን ለኤርትራ ቢወስንም፤ የምዕራባውያን መንግሥታት በድንበር ግጭቱ ላይ ከህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወግነዋል በማለት ሲወነጅሉም ነበር። የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና የምዕራባውያን አጋሮቻቸው እሳቸውንም ከስልጣን ለመገልበጥ "ያሴሩብኛልም" ብለዋል ፕሬዚዳንት ኢሳያስ። በምላሹም ኤርትራ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ታጣቂ ኃይሎች የሆኑትን ግንቦት ሰባት፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣ የኦጋዴ ነፃነት ግንባር፣ደምሂት መቀመጫ ሆና ነበር። ኢትዮጵያም የኤርትራ ተቃዋሚዎችን ትደግፍ ነበር። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቀጠናው ላይ አለመረጋጋት በመፍጠርና በሶማሊያ እስላማዊ ታጣቂዎችን ይደግፋሉ በሚልም የተባበሩት መንግሥታት ማዕቀብ ቢጣልባትም ኤርትራ በዚህ ውንጀላ በፍፁም አትስማማም። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አገራቸው ጦርነት ላይ ናት በማለትም ለዲሞክራሲያዊ ለውጦች እምቢተኝነት፣ ተቺዎቻቸውን ለማሰር፣ ነፃ ሚዲያዎችን ለማገድ፣ አስገዳጅ ብሔራዊ አገልግሎትንም በሕዝባቸው ላይ ለመጫን ተጠቅመውበታል። በተለይም አስገዳጁ ብሔራዊ አገልግሎትንም ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን ከአገራቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል። የ2010 የሰላም ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ካከናወኗቸው ዋነኛ ተግባራት መካከል በሁለቱ አገራት መካከል እርቅ ማውረድ ነው። ግንቦት 28/2010 ዓ.ም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበልም ወሰነ። ይህ ውሳኔ አጨቃጫቂ የተባለችውን የባድመ ግዛት ለኤርትራ የሰጠ ነበር። ለረዥም ዘመናትም ኤርትራ የኮሚሽኑን ውሳኔ ኢትዮጵያ ያለ ቅድመ ሁኔታ ካልተቀበለች ውይይት አይኖርም ስትል ቆይታለች። የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔውን ካሳለፈ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ሰኔ 13/ 2010 ዓ.ም ለሁለቱም አገራት ሕዝብ አስደናቂ ነገር ተፈጠረ። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ "ያለውን ሁኔታ በጥልቀት ለመረዳትና የወደፊቱንም አቅጣጫ ለመቀየስ" በሚል ልዑካን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልኩ አስታወቁ። በዚሁም ንግግራቸው ላይ ጠላት ለሚሉት ህወሓት "ጨዋታው አብቅቷ" አሉ። በወቅቱ ያደረጉት ንግግር አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ልታድሰው ባሰበችው ግንኙነት ጠላታቸው ብለው የሚያስቡትና በወቅቱም የኢህአዴግ አካል የነበረው ህወሓትን አለማካተቱ አመላካች ነበር። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከሁለት አስርት ዓመታት ቆይታ በኋላ አዲስ አበባን በጎበኙበት ወቅት ከህወሓት መሪ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው ነበር። ሁለቱ መሪዎች ዛላምበሳ በመስከረም ወር 2011 ዓ.ም በነበረው የዛላምበሳና የሁመራ-ኦምሃጄር ድንበር መከፈትም በነበረው ዝግጅትም እጅ ተጨባብጠዋል። ከዚያ በፊት ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሐምሌ 1/ 2010 ዓ.ም ወደ አሥመራ መጓዛቸው ዓለምን ያስደመመ ነበር። ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም እንዲፈጠር በርካታ ጊዜ ቢሸመገሉም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በእምቢተነኝታቸው ፀንተው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በኤርትራ መዲና አሥመራም በተቀላጠፈ ትግርኛቸው የሰላም፣ የምጣኔ ሀብት ትብብር መጠንሰሱን በተናገሩበት ወቅት የበርካታ ኤርትራውያንም ልብ ማሸነፍ ችለዋል። "ባፈረስነው ድልድይና በገነባነው የጥላቻ ግንብ ልጆቻችን እንዲገነቡት ሸክም አንጣልባቸው" ብለዋል። "ውድ የኤርትራ ሕዝብ ጦርነትም ሆነ የጦርነት ድምፅ ይበቃችኋል። ሰላም ይገባችኋል" በማለትም ተናግረዋል። ባልተጠበቀ ሁኔታ ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩ አገራትን ወደ ሰላም ማምጣታቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸነፉ። ህወሓትና ህግደፍ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የኤርትራ ነፃ አውጭ ግንባር በኋላም ህግደፍ (ህዝባዊ ግንባር ንደሞክራስን ፍትሕን) ደርግን ከማሸነፋቸው በፊት ግንኙነታቸው የተመሳቀለ ነበር። በአውሮፓውያኑ 1975 ቁልፍ የሚባሉ የህወሓት መስራቾች በቀድሞው የኤርትራ ነፃ አውጭ ግንባር አማካኝነት ኤርትራ ውስጥ ሰልጥነዋል። በወቅቱ ከነበረው የመንግሥቱ ኃይለማርያም አመራርም ጋር ወሳኝ በሚባሉ ውጊያዎችም በተለይ በአውሮፓውያኑ 1985 በአንድ ላይ ተሰልፈው ተዋግተዋል። ሆኖም በርዕዮተ ዓለም ልዩነት ምክንያት ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ ያቋረጡባቸውም ጊዜያት ነበሩ። ነገር ግን ከ1988 ጀምሮ ሁለቱም አካላት መረዳዳት ጀመሩ፤ በተለይም ህወሓት/ኢህአዴግ አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት በ1983 ዓ.ም የኤርትራ ተዋጊዎችና ኮማንዶዎች አብረው ነበሩ። የደርግ ሥርዓትም ከተገረሰሰ በኋላ ለሰባት ዓመታት ያህል ሰላማዊ የሚባል ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ጠንካራ የኢኮኖሚ ትብብርም መስርተው ነበር። ወጣቶቹ መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወዳጅነታቸው የጠነከረ ቢሆንም እየቆየ ግን መሸርሸር ጀመረ። ይሄም ቁርሾ ወደ ጦርነት አድጎ በሁለቱ አገራት መካከል ለተከሰተው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ሆነ። ለዚህም ነው ህወሓት ወደ ኤርትራ ጣቷን ብትጠቁም የማያስገርም የሚሆነው።
news-56327362
https://www.bbc.com/amharic/news-56327362
መስፍን ሽመላሽ ፡ ከቀን ሰራተኝነት ተነስቶ የሕክምና ዶክተር የሆነው ወጣት
በሕይወት ዳገት የማይፈተን የለም። ይህን ፈተና ተቋቁመው በፅናት የሚወጡት ግን ጥቂቶች ናቸው። ዶ/ር መስፍን ሽመላሽ ከእነዚህ ብርቱዎች አንዱ ነው።
መስፍን ለቤተሰቡ አምስተኛ ልጅ ነው። ቤተሰቡ እርሱን ጨምሮ ስምንት ልጆች አሏቸው። ሁለቱ ከአንድ እናት ቀሪዎቹ ደግሞ ከሌላ እናት የተወለዱ ናቸው። ቤተሰቡ የሚተዳደረው በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ወታደር የነበሩት አባታቸው በሚያመጡት ገቢ ነበር። አቶ ሽመላሽ በደቡብ ካምፕ ውስጥ በነበሩ ጊዜ በተማሩት የልብስ ስፌት ሙያ ነበር የተሰማሩት። ልባሽ ጨርቆችን በመሸጥም ቤታቸውን ይደጉሙ ነበር። በዚህ መሃል ግን ታመሙ። ያኔ መስፍን የ4ኛ ክፍል ተማሪ ነበር። አቶ ሽመላሽ ህመማቸው ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ስለነበር ሥራቸውን መቀጠል አልቻሉም። እርሳቸውን ለማዳን ለስድስት ወራት ያህል መላው ቤተሰብ ተረባረበ። በሕክምና፣ በሃይማኖት፣ በባህልም ተሞከረ፤ አልሆነም። ቤተሰቡ ችግር ላይ ወደቀ። ሁሉም በየፊናቸው የዘመመ ጎጇቸውን ለማቃናት መታተር ጀመሩ። ከባለቤታቸው ጋር ተፋትተው ገጠር ይኖሩ የነበሩት የእነ መስፍን እናት ሳይቀሩ ልጆቻቸውን ለማስተማር በቤት ሰራተኝነት ተቀጠሩ። ሌሎቹ በሚያውቁት የእጅ ሙያ ተሰማሩ። ታላቅ ወንድሙ ቡታጋዝና ፌርሜሎ [የከሰል ማንደጃ] እየጠጋገነ መሸጥ ጀመረ። አሳዳጊ እናታቸውም አባታቸው የተዉትን የልባሽ ጨርቅ ሥራ ጀመሩ። ግን ከሙያው ጋር እምብዛም ቅርበት አልነበራቸውምና አላዋጣቸውም፤ ከሰሩ። በዚህ ጊዜ ታላቅ ወንድሞቹ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ። የመጀመሪያው ልጅ ልባሽ ጨርቆችን መነገድ ጀመረ። ሌላኛው ደግሞ ብረታ ብረት ቤት ገባ። መስፍንም እንደ ቤተሰብ አባላቱ ሥራ አላማረጠም። የአራተኛ ክፍል ተማሪ ሳለ ባልጠና ጉልበቱ የብረታ ብረት ሥራ ጀመረ። በዚህ ሁኔታ ወንድሙ ትምህርቱን መቀጠል ባይችልም መስፍን ግን ግማሽ ቀን ጋራዥ እየሰራ፤ ግማሽ ቀኑን ለትምህርቱ ሰጠ። በእርግጥ እርሱም ቢሆን የሚማረው የማቋረጥ ያህል ነበር። አንድ ወር ቢማር አንድ ወር አይሄድም። ይህን ገጽ ይዞ ሕይወት ቀጠለ። ወንድሙ ማታ ማታ ሰርቶ የማይጨርሳቸውን አሮጌ የከሰል ማንደጃዎች እና ቡታጋዝ ፤ መስፍን በጠዋት ተነስቶ አጠናቅቆ፤ ሸጦ ገንዘቡን ለወንድሙ ሰጥቶ በዚያው ትምህርት ቤት ይሄዳል። መስፍን በአካባቢው ሰው ቀልጣፋና ጎበዝ እንደሆነ ይታወቃል። በርካቶች ስለእርሱ ወደፊት እምነት ነበራቸው። መስፍን "ጋሽ መሃመድ" እያለ የሚጠራቸው ግለሰብ እጅግ ያበረቱት እንደነበር ያስታውሳል። "በጋ ላይ የሰራሁትን ወስጄ ስሸጥላቸው ይቆጡኝ ነበር፤ 'መስራት ያለብህ ክረምት ነው' እያሉ ትንሽም ቢሆን ገንዘብ ሸጎጥ ያደርጉልኝ ነበር" ይላል። "አንተ ዶክተር ነው የምትሆነው" ይሉት ነበር። ምንም እንኳን አብረውት ከሚሰሩት ጓደኞቹ በትምህርት አብረውት የገፉ ባይኖሩም፤ እርሱን ግን በአቅማቸው ይደግፉት ነበር። ወላጅ እናቱም ሰው ቤት ተቀጥረው በሚያገኙት ገንዘብ ደብተርና የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ አያሳጡትም። "እናቴ እንደ ህጻን ልጅ "ነይ!" እየተባለች ስትላላክ ማየት ያመኝ ነበር" መስፍን ተወልዶ ያደገው በደሴ ከተማ እምብርት አራዳ በተባለ አካባቢ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በመንበረ ፀሐይ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በንጉስ ሚካኤል እንዲሁም የመሰናዶ ትምህርቱን ሆጤ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። ተምሮ የቤተሰብ ችግሩን መፍታት ምኞቱ ነበር። በሕይወቱ የገጠመውን ፈተና መለወጥ ይፈልግ ነበር። አባቱ ባጋጠማቸው የአዕምሮ ጤና ችግር ምክንያት፤ ሰዎች "አባቱ እብድ ነው" የሚሉትን ንግግር መቀየር ይፈልግ ነበር። እናቱንም ለመጠየቅ ሲሄድ ፤ የወለዱት እናቱ እንደ ልጅ "ነይ!" እየተባሉ ሲላላኩ ማየትም ህመም ነበር ለእርሱ። ይህን ለመለወጥ ያለው ብቸኛው አማራጭ ደግሞ ትምህርት ብቻ ነበር። የሩቅ ህልሙን ለማሳካት ወገቡን አጠበቀ። የአዕምሮ ስንቅም ያዘ። አባቱ ሌሊት ለፀሎት ሲነሱ ለጥናት ይቀሰቅሱታል። አንብቦ ሲጨርስ፤ አባቱን ፀበል አስጠምቋቸው ወደ አራዳ ይሄድና የሚሸጡ እቃዎችን ዘርግቶላቸው ወደ ትምህርት ቤት ይሄዳል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ አልፎ በስምንተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና 99 ነጥብ በማስመዝገብ ወደሚቀጥለው ክፍል ተሸጋገረ። 9ኛ እና10ኛ ክፍልም ቢሆን ከሁሉም ክፍሎች አንደኛ ነበር የሚወጣው። መበለጥን አይወድም። እርሱ እንደሚለው አስረኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናም ለተማረበት ንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች 'ኤ' ያስመዘገበው የመጀመሪያው ተማሪ እርሱ ነበር። ይሁን እንጂ 11ኛ ክፍል በመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ላይ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ አካሄዱ ወዳለመው የሕክምና ትምህርት ላያስገባኝ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አደረበት። 12ኛ ክፍል ላይ አቋርጦ፤ ራሱን በሚገባ አዘጋጅቶ ተፈተነ። በጊዜው ከፍተኛ የተባለውን 546 ውጤት በማስመዝገብ የሕክምና ትምህርት ለመከታተል ጎንደር ዩንቨርሲቲ ገባ። ሕይወት በዩንቨርሲቲ፡ "የእናቴ አሰሪ ልጅ አብሮኝ ይማር ነበር" የሕክምና ትምህርቱ እረፍት የለውም። በርካታ ወጪዎችም አሉት። ይህን ለማሟላት እረፍት ሲኖረው ወደ ቤተሰብ ሄዶ ወደ አሮጌ ቡታጋዝና የከሰል ማንደጃ ጥገና ሥራው ይመለሳል። ከዚያም ሰርቶ ባጠራቀመው ገንዘብ ለትምህርቱ የሚያስፈልጉትን ያሟላል። በእርግጥ በዚህ ጊዜ ቤተሰቡ ትንሽም ቢሆን ያግዙት ነበር፤ ነገር ግን ራሱን መርዳት ስለነበረበት ከመስራት ወደ ኋላ አይልም። ሦስተኛ ዓመት እያለ ግቢ ውስጥ በብረት ብየዳ ሙያ የቀን ሥራ ሰርቷል። በእርግጥ ፈተናው የኢኮኖሚ ብቻ አልነበረም። የሞራልም እንጂ። ዩንቨርሲቲ በሁሉም የኢኮኖሚ ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች አንድ ላይ የሚማሩበት ተቋም ነው። አንዳንዱ የቀን ሥራ ሰርቶ ይማራል። በሌላ ጥግ ደግሞ በዘመናዊ ሆቴል እየተመገቡና እየኖሩ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ አሉ። ይህ በችግር ውስጥ ሆነው ለሚማሩት ሥነ ልቦናዊና ሞራላዊ ተፅዕኖው ቀላል አይደለም። ይህንንም ለመቋቋም ሌላ የመንፈስ ብርታትን ይጠይቃል። መስፍን "እናቴ አዲስ አበባ ተቀጥራ የምትሰራባቸው አሰሪዎች ልጅ ከእኔ ጋር ሕክምና ይማር ነበር" ይላል። ከአዲስ አበባ ሲመጣም ደረቅ ምግቦችን ይዞለት ይመጣ ነበር። "ይሰማዋል እያለ ነው መሰል፤ ብዙም አንገናኝም፤ እቃ ሲላክ ሰጥቶኝ ብቻ ነበር የሚሄደው" ይላል። ዶ/ር መስፍን የሕክምና ትምህርቱን 3.34 በማስመዝገብ በማዕረግ ነው የተመረቀው። "የተመረቅኩ እለት አባቴ ሲያለቅስ ነው የዋለው፤ ያንን ነገር ሁሉ በማለፌ ደስተኛ ናቸው" ይላል። የዶ/ር መስፍን ቀጣይ ህልም ዶ/ር መስፍን በማህፀንና ፅንስ ዘርፍ ሙያውን ማሳደግ ይፈልጋል። በእርግጥ ከአባቱ የአዕምሮ ጤና ጋር ተያይዞ የአዕምሮ ሕክምና ማጥናት ይፈልግ ነበር። ይህ ሃሳቡ የተቀየረው ለሥራ ልምምድ ከወጣ በኋላ ነው። ለዚህም ሁለት ምክንያቶችን ያነሳል። "ከደም ጋር የተያያዘ ሙያ ነው። ውጤቱ ግን እርካታን ይሰጣል። በልምምድ አንድ ዓመት በሰራሁበት ጊዜ ደስ እያለኝ እሰራ ነበር " ይላል ዶ/ር መስፍን። ሌላኛው ምክንያቱ ደግሞ በተለይ እንደ ከሚሴ እና አፋር ካሉ አካባቢዎች ወደ ደሴ ከተማ ለሕክምና የሚመጡ እናቶች ስቃይ ነው። በእነዚህ አካባቢዎች እናቶች በሴት ልጅ ግርዛት የተጠቁ በመሆናቸው በወሊድ ወቅት ይሰቃያሉ። በመሆኑም በሙያው የእነርሱን ስቃይ ለማቅለል በማለም ነው። "በሽተኛ ሐኪም እየፈለገ፤ ሐኪም ደግሞ ሥራ እየፈለገ መተላለፍ" ዶ/ር መስፍን ከተመረቀ ወራት ተቆጥረዋል። ውጣ ውረዱን ካለፈለት ሙያው ጋር ግን አልተገናኘም። ሥራ ፍለጋ ላይ ነው። "ከዚህ ቀደም ጤና ሚኒስቴር ጠቅላላ ሐኪም ይመድብ ነበር። አሁን ግን 'በጀት የለንም' ብለው ምደባ አቁመዋል" ይላል ዶ/ር መስፍን። በእርግጥ በግልም ሥራ ለማግኘት ሞክሯል። ኮምቦልቻ ቤተሰብ መምሪያ ነጻ አገልግሎት ይሰጣል። ከወንድሞቹ ጋር በመሆን ቤት ለቤት የጤና እንክብካቤ ለመስጠት የሚያስችል ሥራ ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ ነው። ይሁን እንጅ ፍቃድ ለማውጣት ቢያንስ ሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያስፈልጋል መባሉን ይናገራል። "እኛም በተማርንበት ዩኒቨርሲቲ ያ ሁሉ ሐኪም ኖሮ በቀን 30 ታማሚ እናይ ነበር፤ ይህ ሁሉ ታማሚ እያለ፤ ሐኪምን በበጀት ምክንያት መቅጠር አንችልም ማለት ይከብዳል። ያን ሁሉ መከራ አሳልፎም ሥራ ማግኘት አለመቻልም ያማል" ይላል። ዶ/ር መስፍን ሽመላሽ ከወላጆቹ ጋር በምርቃት ዝግጅት ላይ "ወደ ጎረቤት አገር ሄዶ መስራት ይቻላል፤ ግን አሁን ባለው ሥርዓት ይህም የማይቻል ነው።" በማለትም አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ይገልጻል። ዶ/ር መስፍን እንደሚለው ጊዜዎች በረዘሙ ቁጥር ሙያውንም መርሳት ይመጣል። ራስን በአዳዲስ እውቀቶች ማበልፀግ የሚቻለውም በሥራ ላይ 'ኬዝ' ሲገጥም ነው። "የቤተሰብ ጉጉት ሲደበዝዝ ማየት፣ ያንን ያህል ዓመት ተለፍቶ፣ የአገር ሐብት ፈስሶ፤ በሽተኛ ሐኪም እየፈለገ፤ ሐኪም ደግሞ ሥራ እየፈለገ መተላለፍ ከባድ ነው" ብሏል።
news-54317323
https://www.bbc.com/amharic/news-54317323
ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶቿን መልሳ ለመክፈት ምን አይነት ዝግጅቶችን አድርጋለች?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት ትምህርት ቤቶችን ዘግታ የነበረችው ኢትዮጵያ በያዘችው አዲሱ አመት እንዲከፈቱ ወስናለች።
የመማር ማስተማሩም ሂደቱ የትምህርት ቤት ማህበረሰቡን ደህንነትና ጤንነት ባስጠበቀ መልኩም እንዲሆን የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችንም ትምህርት ሚኒስቴርና የሚመለከታቸው አካላትም እያካሄዱ ነው። ከነዚህም መካከል በመላ አገሪቱ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስን ማቅረብም አንዱ እንደሆነም የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሚዩኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሐረግ ማሞ ለቢቢሲ እንደገለፁት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ ሙቀት መለኪያ፣ እና የንጽህና መጠበቂያ በአገሪቱ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሙሉ የሚያገኙበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው። ተማሪዎች፣ መምህራንና በአጠቃላይ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ አገሪቱ ተቀብላ ተግባራዊ ስታደርጋቸው የነበሩ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችንም በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ እንደ ግዴታ መቀመጡንም ዳይሬክቶሬቷ አፅንኦት የሰጡበት ጉዳይ ነው። የመማር ማስተማሩን በአዲስ መልኩ ከመመለስ ጋር ተያይዞም ሲነሳ የነበረው የ8ኛ ክፍልና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች የሚሰጡበት ቀንና በምን መንገድ የሚሉትም ጥያቄዎች ባለፈው ሳምንት ምላሽ አግኝቷል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ መሰረት የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ. ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ መሆናቸውን አስታውቋል። በተመሳሳይ ደግሞ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁ እና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ጠቁሟል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ሚኒስቴሩ በኦንላይን (በበይነ መረብ) እንደሚሰጥም ገልጿል። በአገሪቷ ካለው የኢንተርኔት ስርጭት ማነስና የአቅርቦቱ መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ጥያቄ ቢነሳም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መመረጣቸውን ኃላፊዋ ገልፀዋል። ከኢንተርኔት መቆራረጥ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ችግሮችንም ለመቅረፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አስረድተዋል። በቴክኖሎጂ በኩል የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት ችግር ያጋጥመናል ብለው እንደማያስቡ የሚናገሩት ሐረግ ከኢንተርኔት አቅርቦት ጋር በተያያዘ በርካታ ስራዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሰራ ነው ብለዋል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንገዶች እገዛ ያገኙ የነበሩ ተማሪዎች ነበሩ። ከዚህም ጋር ተያይዞ ምዘናው እንዴት ሁሉንም የአገሪቱን ተማሪዎች በእኩል ያማከለ መሆን ይችላል? ተብሎም ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኃላፊዋ የፈተና አወጣጥ ስርዓቱ ሁሉን ባማከለ መልኩ እንደሚሆንና "በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ያሉትን ተማሪዎች ባማከለ መልኩ እንዲሆን ነው ያደረግነው" ሲሉ መልሰዋል። ተማሪዎቹ ለፈተናው እንዲዘጋጁ 45 ቀናት የሚሰጣቸው ሲሆን ቀዳሚው ስራ ተማሪዎቹን በስነልቦና ከትምህርት ቤቱ ጋር የማገናኘት ስራ እንደሚሆንም ያስረዳሉ። ጎን ለጎን ደግሞ ያልተሸፈኑ የትምህርት ክፍሎች፣ ክለሳዎች፣ የማካካሻ ስራዎች እንደሚሰሩ ይናገራሉ። ብሔራዊ ፈተና ከሚወስዱት በተጨማሪ አገሪቷ በአጠቃላይ ትምህርት ቤቶችን ከሶስት ሳምንት በኋላ እንደምትከፍት አስታውቃለች። ትምህርት ቤቶቹንም በሶስት ዙር ለመክፈትም ምክረ ኃሳብ ቀርቧል። በዚህም መስረት በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መጀመሪያ በተባለው ዙር ጥቅምት 9/2013 ዓ.ም፣ በሁሉም ዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በ2ኛው ዙር ጥቅምት 16/2013 እንዲጀምሩ ሃሳብ ቀርቧል። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን የሚገኙት ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴር በሦስተኛ ዙር ብሎ ባስቀመጠው ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም ይጀምሩ የሚል ምክረ ሐሳብ መቅረቡ ተገልጿል። ትምህርት ቤቶቹን በተለያየ ጊዜ በሶስት ዙር ለመክፈት የተወሰነውም ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘም እንደሆነ ኃላፊዋ ይናገራሉ። የቫይረሱ ስርጭት ሰፋ ብሎ የሚታይባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶቹ የሚከፈቱት በሶስተኛው ዙር መሆኑንም ያስረዳሉ። በተለያዩ ጊዜና ዙር ትምህርት ቤቶቹን ለመክፈትም ትምህርት ሚኒስቴር ከጤና ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃም በማጠናቀርም እንደሆነ ኃላፊዋ ያስረዳሉ። ኃላፊዋ እንደሚገልፁት ትምህርት ቤቶችን መክፈትና መደረግ ያለባቸው ምክረ ኃሳቦች ከመቅረባቸው በፊትም ትምህርት ሚኒስቴሩ ያቋቋመው ግብረ ኃይል የመማሪያ ክፍሎች ጥበትና እጥረት ያለባቸው አካባቢዎች ገምግሟል። ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ክልሎች ከሰጡት መረጃ በመነሳት በአንድ ክፍል የተማሪ ጥግግት ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ትምህርት በፈረቃ እንዲሆን መወሰኑን ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ምን ያህል ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ሊማሩ ይገባል ብሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባጤነው መሰረትም ከ20-25 ተማሪዎች እንዲሆኑም መስሪያ ቤቱ ወስኗል። ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ውሳኔ ሲያሳልፍም በትምህርት ቤት አቅራቢያ የሚገኙ አንዳንድ ተቋማትን ታሳቢ ተደርገዋልም ይላሉ። ተቋማት በሌሉበት ሁኔታም ደግሞ ጊዜያዊ መጠለያ በመገንባት በነዚያ ውስጥ ለማስተማርም ትምህርት ሚኒስቴር እቅድ ይዟል። በአጠቃላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአንድ ጊዜ በትምህርት ቤት የሚገኙ የተማሪዎችን ቁጥርም ለመቀነስ የተለያዩ አማራጮችን የሚጠቀም ሲሆን ከነዚህም መካከል በሶስት ፈረቃ መክፈልና የትምህርት አሰጣጡን በቀናት መከፋፈልም ይገኙበታል። ትምህርት በሚከፈትበት ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ የኮሮናቫይረስ ስጋቶችን ለመቀነስ ዝግጅት አድርጌያለሁ ያለው ሚኒስቴሩ የመምህራን እጥረትም ካጋጠመ አማራጭ እቅዶችን አቅርቧል። በአካባቢው ያሉ በጎ ፈቃደኞችንና በጡረታ የተገለሉ ነገር ግን እድሜያቸው ያልገፉ መምህራን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግም ታስቧል። ሆኖም በአገሪቷ ውስጥ ያሉትን የመምህራንን ቁጥር በተመለከተ ተጨማሪ መምህራን ሳያስፈልጉ ባሉት ብቻ መሸፈን የሚቻልባቸው ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንም የመስሪያ ቤታቸውን መረጃ ዋቢ አድርገው ኃላፊዋ ያስረዳሉ። በአገሪቱ ውስጥ ያሉ መምምህራን ከተቀመጠላቸው የክፍለ ጊዜ መጠን በላይ እንደማይይዙና ይህንንም መደረግ በማይቻልባቸው ትምህርት ቤቶች ለበጎ ፈቃደኞች ጥሪ እንደሚደረግ እንዲሁም መመረቂያ ጊዜያቸው የደረሱ መምህራን በፍጥነት ተመርቀው ወሰደስራ እንደሚገቡ አስረድተዋል። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ በተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ተማሪዎች ለሰባት ወር ያህል ከትምህርት ገበታ ርቀው ቆይተዋል። ከ12 እና ከስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች በስተቀር ተማሪዎች በግማሽ ዓመቱ በነበራቸው ውጤት መሰረት ወደ ቀጣዩ ክፍል እንዲዘዋወሩም ተደርጓል። ትምህርት ቤቶች ዝግ በነበሩባቸው በእነዚህ ወራት ልጆች ለተለያዩ የጉልበት ብዝበዛ ተዳርገዋል፣ በርካታ ህፃናት ያለ ዕድሜ ጋብቻ ተጋልጠዋል እንዲሁም ፆታዊ ጥቃቶችም ደርሶባቸዋል። በዚህም የተነሳ ለስነልቦና ጫና ተጋልጠው መቆየታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር እንደሚረዳ ኃላፊዋ አብራርተዋል። እነዚህን ክፍተቶችና ችግሮችም በመረዳት በዘንድሮው የትምህርት ዓመት እነዚህ ልጆች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ ክልሎች ከዚህ ቀደም የነበራቸውን አደረጃጀት ተጠቅመው ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲመጡ እንዲያደርጉ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር መግባባት ላይ መደረሱን ጠቅሰዋል። እነዚህ ሁሉ ዝግጅቶች ተጠናቅቀው የኮሮናይረስ ምልክቶች የሚታይባቸው መምህራን እና ተማሪዎች ቢኖሩ ከዚህ ቀደም ይደረጉ የነበሩ መካላከሎችና መመሪያዎችም ተግባራዊ ይሆናሉ ብለዋል።
54485207
https://www.bbc.com/amharic/54485207
ኮሮናቫይረስ ፡ "ኮቪድ-19 የሚያስከትለው የአእምሮ ጤና ችግር ለብዙ አስርት ዓመታት ሊቀጥል ይችላል"- ፕ/ር መስፍን አርዓያ
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ከኮሮናቫይረሰ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ በአፍሪካ የአእምሮ ጤና መታወክ እየተከሰተ መጥቷል።
ድርጅቱ ባለፈው ሐሙስ እለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተባለው፤ በአፍሪካ የአእምሮ ጤና መታወክ ከኮቪድ-19 በኋላ መጨመር አሳይቷል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሕክምና አገልግሎቶችን በማስተጓጎሉ ሁኔታውን የበለጠ ፈታኝ አድርጎታል። በዛምቢያ የአእምሮ ጤና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሪም ዳላል እንዳሉት፤ በአህጉሪቱ ከወረርሽኙ በኋላ የአእምሮ ጤና ችግሮች ስለመባባሳቸው መረጃዎች አሉ። በዚህ ሳምንት በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1.5 ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን ቢያንስ ከ36,787 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በኢትዮጵያም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 82,662 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,271 ደርሷል። ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል መምህር እና ሐኪም ናቸው። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ የአእምሮ ህመሞች በጣም ሰፊ መሆናቸውን ይናገራሉ። ወረርሽኙ በራሴ፣ በቤተሰቤና በአካባቢዬ ላይ ይከሰታል የሚለው ስሜት ከፍተኛ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ድብርት እንዲያም ከፍተኛ ወደ ሆነ የአእምሮ መረበሽ ሊያደርስ ይችላል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኮቪድ-19 በአካል ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ምክንያት በአካባቢያችንና በቤተሰባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከዚህም ጋር በተያያዘ የሚከሰተው ሰርቶ ያለማደርና ቤት ውስጥ ተዘግቶ መዋል ከፍተኛ ጭንቀትና ድብርት እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ሕጻናት እና የአእምሮ ጤና ሕጻናትና ሴቶች በቤት ውስጥ ወይንም በአንድ አካባቢ ብቻ መዋላቸው ከሚያደርስባቸው የአእምሮ ጤና ችግር በላይ በተቃራኒ ጾታ የሚደርስባቸው ጥቃት መስተዋሉን ፕሮፌሰሩ ያነሳሉ። ላለፉት ሰባት ወራት ከመዋዕለ ሕጻናት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድረስ ከትምህርት ገበታ ርቀው በቤት ውስጥ መቆየታቸውን በማስታወስም፤ ይህ የአእምሮ ጤና ላይ ጫና እንዳለው ያብራራሉ። ልጆች እየተሯሯጡ፣ ከእኩዩቻቸው ጋር ሲጫወቱ አካላቸው ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ መስተጋብራቸውም እያደገ እንደሚመጣ የሚያስረዱት ፕሮፌሰሩ፤ እነዚህ ሕጻናት በጋራ ሲጫወቱ አንዳቸው ከሌላኛቸው የሚማሩት እውቀትና ክህሎት ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት፤ ለረዥም ወራት በአንድ አነስተኛ ግቢ ወይንም ቤት ውስጥ ተገድቦ መቀመጥ ለሕጻናቱ ከፍተኛ ጫና መሆኑን ያነሳሉ። ከዚህም የተነሳ ሕጻናቱ በከፍተኛ ሁኔታ ሊሰላቹ፣ ሊጨናነቁ፣ ሊወጣጠሩ ይችላሉ ብለዋል። ሕጻናቱ እንደ አዋቂዎች የሚሰማቸውን መናገር አለመቻላቸው ሌላው ችግር በመሆኑ ለተለያዩ የሕጻናት የአእምሮ ጤና ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በተለይ በከተማ የሚኖሩ እና የተማሩ የሚባሉት ወላጆች ልጆችን ከኤሌክትሮኒክስ ጋር ስለሚያጋፍጧቸው ለኮምፒውተር ጌም ሱስ እንደሚያጋልጧቸው ይገልፃሉ። በዚህም የተነሳ ትምህርት በሚከፈትበት ወቅት ከእኩዮቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ እንደሚችል ጨምረው አብራርተዋል። ወረርሽኞች የአእምሮ ጤና ችግር ያስከትላሉ? "የሚገድሉ ሕመሞች በጣም ያስጨንቃሉ" የሚሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ተላላፊ በሽታዎች ግለሰቦች ላይ ባይደርስ እንኳን ገና ለገና 'ይመጣብኛል' የሚለው ስጋት እንደሚያሳቅቅ ይናገራሉ። እንደ ኮሌራና ኢቦላ ያሉ ወረርሽኞች ተመሳሳይ ተጽዕኖ እንዳላቸው የሚገልፁት ፕሮፌሰሩ፤ የኮሮናቫይረስ ባህሪ በየጊዜው ይበልጥ በታወቀ ቁጥር የሚፈጥረው ስጋትና ጭንቀት እየጨመረ እንደሚመጣ ገልፀዋል። መጀመሪያ ላይ በእድሜ የገፉ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው መረጃ ከተሰማ በኋላ፣ ወጣቶችና ሕጻናትም ተጋላጭ መሆናቸው መታወቁ፣ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው መረጃ ከተሰራጨ በኋላ፣ የሌለባቸውም ተጋላጭ መሆናቸው መታየቱ፤ "ጭንቀት በሰው ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንዲመጣ" ማድረጉን ይናገራሉ። ገና ለገና በሽታው ይመጣብኛል የሚለው አስጨናቂ መሆኑን ተናግረው፤ ጭንቀትን የሚያባብሰው ከራስ አልፎ ለቅርብ ቤተሰብ የሚኖረው ስጋት ነው ይላሉ። ቤተሰቦቼ ይያዙ ይሆን? ምልክት ሳላሳይ ቫይረሱን ይዤ እየዞርኩ ይሆን? በእድሜ የገፉ ወላጆቼን፣ ታማሚ ቤተሰቦቼን፣ ልጆቼን አስይዝ ይሆን? የሚሉት የበለጠ ያስጨንቃሉ። ከዚህ በሽታ ጋር ተያይዞ መጀመሪያ የሚከሰተው የጤና ችግር ጭንቀት የሚባለው መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ይናገራሉ። ይህ ከቀላል ጭንቀት ጀምሮ እስከ ከፍተኛው እንደሚደርስ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው በቤተሰብ ውስጥ ሲገኝ ደግሞ ሕመሙ በመከሰቱ ለበለጠ ጭንቀት መጋለጥ እንደሚኖር እንዲሁም ሊባባስ እንደሚችልም ያብራራሉ። በቫይረሱ የተያዘ የቤተሰብ አባል በሞት ሲታጣ ደግሞ ወደ ተራዘመ ሐዘንና ጭንቀት፣ ባስ ሲልም ወደ ድብርት ሊያስገባ ይችላል ይላሉ። ፕሮፌሰር መስፍን፤ ቫይረሱ በአካል ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ አንጎል ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖና ሊከሰቱ የሚችሉ አእምሮ ጤና ችግሮች ገና እየተጠኑ መሆኑን ይናገራሉ። ኮቪድ-19 በአእምሮ ላይ የሚያሳድረው ዘላቂ ጫና አንዳንድ ጊዜ አንጎል ሲመረዝ ከፍተኛ የሆነ የመርሳት ችግር (ዲሜንሺያ) ወይንም ከፍተኛ የአእምሮ ሕመሞች ሊከሰቱ የሚችሉበት እድል አለ ይላሉ ፕሮፌሰሩ። እንደ አእምሮ ጤና ባለሙያ፤ "ኮቪድ 19 በአካል ላይ ከሚያደርሰው ችግር በላይ፤ ከወረርሽኙ መረጋጋት በኋላ የሚመጣው የአእምሮ ጤና ችግር ለብዙ ዓሥርት ዓመታት ይቀጥላል ብለን እናምናለን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኮቪድ -19 ተይዘው ሕመም የጠናባቸውና የትንፋሽ ማገዣ መሣሪያ ላይ ያሉ ሰዎች በአብዛኛው የመትረፍ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ያስታወሱት ፕሮፌሰር መስፍን፤ በመተንፈሻ ታግዘው ጤናቸው ሲመለስ ደግሞ ለከፍተኛ ጭንቀት እንደሚዳረጉ ማስተዋላቸውን ገልፀዋል። እነርሱ በመሣሪያ እየታገዙ ተንፍሰው ሲድኑ፤ ሌሎች ግን ከጎናቸው በመሣሪያ እየተረዱም መትረፍ ሳይችሉ ቀርተው ሲመለከቱ የሚደርስባቸው ሥነ ልቦናዊ ጫና እንዳለ ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች በመትረፋቸው ተመስገን ቢሉም ጭንቀትም ሆነ ድብርት ሊታይባቸው እንደሚችል ከልምዳቸው በመነሳት ያስረዳሉ። ፕሮፌሰሩ አክለውም በተለይ የሕክምና ባለሙያዎች ራሳቸውን መስዋዕት አድርገው ስለሚሠሩ ከራሳቸው አልፎ በእድሜ ለገፉ ወላጆቻቸው፣ ለቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀው ማስተዋላቸውንም ገልፀዋል። ኮሮናቫይረስ እና 'ኦሲዲ' በኮሮናቫይረስ ዘመን ጭንቀትን መቆጣጠር አለመቻል፣ መቼም ቢሆን እርግጠኛ አለመሆን በሰዎች ዘንድ ተፈጥሯል። ጥርጣሬው የሚጀምረው "ንፁህ ነኝ?" ከሚል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ "ወደ ቀደመው ሕይወቴ መመለስ እችል ይሆን?" ወደሚለው ያመራል። አካላዊ ርቀታችንን መጠበቅ ከቻልን፣ በተደጋጋሚ እጃችንን ከታጠብን፣ አገራት ያሳለፏቸውን ቤት የመቀመጥ መመሪያዎች ከተከተልን በቫይረሱ እንደማንያዝ እርግጠኛ ነን። ነገር ግን አእምሯችንን የሚነዘንዘን ጥርጣሬና እርግጠኛ አለመሆን፤ ከዚያም ጋር ተያይዞ የሚመጣው ጭንቀት ሕይወታችንን ሞልቶታል። የሚመላለሱት ሐሳቦች መጥፎ ስሜቶች ናቸው። ምናልባት ጭንቀቱ በትንሹም ቢሆን እንድንጠነቀቅ ያደርገን ነበር፤ ችግሩ ግን ከቁጥጥራችን ውጪ ይሆናሉ። "ከመጠን በላይ መፍራት ለተለያዩ የእምሮ ጤና ችግሮች ይዳርጋል" ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ አንዳንድ ሰዎች ከልክ ባለፈ ፍርሃት ተውጠው ማስተዋላቸውንም ጠቅሰዋል። ቤታቸውን ዘግተው የተቀመጡ እና እንቅስቃሴያቸውን የገደቡ፣ በተደጋጋሚ እጃቸውን በሳሙናና በውሃ የሚታጠቡ አልያም ሳኒታይዘር የሚጠቀሙ ሰዎች ከኮቪድ-19 በኋላ በሕክምና ቋንቋ ኦሲዲ (Obsessive-compulsive disorder) ለሚባለው ችግር እንደሚጋለጡ ይተነብያሉ። የማይፈለግና ለመቆጣጠር የሚያስቸግር ሐሳብ በሰዎች አእምሮ ሲመላለስ ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር) ይባላል። አንድን ነገር ሱስ በሚባል ሁኔታ በተደጋጋሚ ከማድረግ ጋር ይገናኛል። ከፍተኛ ፍርሃት የሚመጣው ስለ ቫይረሱ ያለው ግንዛቤ እና እውቀት አነስተኛ ወይንም ቁንጽል ከመሆኑ የተነሳ ነው በማለት በየጊዜው የሚሰጡ የጤና መረጃዎችን ባለሙያዎች ማዳረስ እንዳለባቸው ይመክራሉ። ሐዘንን እና መረበሽን የመቋቋም አቅም ከሰው ወደ ሰው ስለሚለያይ ስለኮሮናቫይረስ የሚተላለፉ መረጃዎች በማያስፈራራና በማይረብሽ መንገድ በአግባቡ መሰጠት እንደሚኖርበት ይናገራሉ። ሰዎች በሚሰሙት መረጃ ተረብሸው ወደ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ራስን ወደመጥላት እና ከዚያም ወደ ከፋ እርምጃ እንዳይሄዱ የመገናኛ ብዙኀን፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ወጣቶች ትክክለኛውን መረጃ ማድረስ እንደሚያስፈልጋቸው ይመክራሉ። የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ ምን ማድረግ ይቻላል? የአእምሮ ጤናን መጠበቅ የሚቻለው ልክ ሌላው የአካል ክፍል ጤና እንደሚጠበቀው መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ያስታውሳሉ። ንጹሕ አየር መተንፈስ፣ አመጋገብን ማስተካከል፣ መንፈሳዊ ሕይወትን ማጠናከር፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፣ ከሱስ መጠበቅ ጠቃሚ መሆናቸውን በማንሳት፤ ለአካላዊ ጤና የሚጠቅሙት እነዚህ ነገሮች ለአእምሮም እንደሚያስፈልጉት ይገልፃሉ። በዚህ ወቅት ከጭንቀት እና ውጥረት ራስን መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። እርስ በእርስ መተሳሰብ እንዲሁም መደጋገፍ አስፈላጊ መሆኑንም ያስታውሳሉ።
news-51296035
https://www.bbc.com/amharic/news-51296035
ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው?
ከዚህ ቀደም በሳይንስ እንደማይታወቅ የተነገረለት ቫይረስ ቻይና ውስጥ አደገኛ የሳምባ በሽታን ቀስቅሶ ወደ ሌሎች አገራትም እየተዛመተ ነው።
በመጀመሪያ ላይ ከአንድ ወር በፊት በቻይናዋ የዉሃን ከተማ መገኘቱ የተዘገበው ቫይረስ እስካሁንም ከአንድ መቶ በላይ ሰዎችን በሽታው ገድሏል። እስካሁንም በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ከ4500 በላይ ሰዎች ሲኖሩ ባለሙያዎች ይህ ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ ይገምታሉ። ይህ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር ሊውል ይችላል ወይስ አስቸጋሪና አደገኛ ሆኖ ይቆያል? ቫይረሱ ምንድ ነው? የቻይና ባለስልጣናት እንዳረጋገጡት በአገራቸው የተከሰተው በሽታ መንስኤው ኮሮና በሚባል ቫይረስ ምክንያት ነው። ቀደም ሲል ሰዎችን የሚያጠቁ ከዚህ ቫይረስ ጋር ዝምድና ያላቸውና የሚመሳሰሉ የታወቁ ስድስት አይነት የቫይረሱ ቤተሰቦች አሉ፤ አሁን የተገኘው አዲሱ ሰባተኛ እንደሆነ ተነግሯል። የበሽታው ምልክቶች? በሽታው ሲጀምር በትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ተከትሎት ይከሰታል፤ከዚያም ከሳምንት በኋላ የትንፋሽ ማጠርን በማስከተል አንዳንድ ህሙማንን የሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያስፈልጋቸው ሊያደርግ ይችላል። በአራት ሰዎች ላይ ከሚከሰተው ይህ በሽታ አንዱ እጅግ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ። በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ማስነጠስና የአፍንጫ ፈሳሽ ላይታይበት ይችላል። • በኮሮና ቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ የኮሮና ቫይረስ ቀለል ካለ የጉንፋን ምልክቶች አንስቶ እየከፋ ሲሄድ እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። የዓለም የጤና ድርጅት የበሽታው ክስተት ቻይና ውስጥ አሳሳቢ እንደሆነ ቢገልጽም፤ እንደ ኤቦላና የወፍ ጉንፋን የበሽታው ሁኔታ ዓለም አቀፍ የሕዝብ የጤና ስጋት ነው ብሎ ለማወጅ አልወሰነም። ምን ያህል አደገኛ ነው? እስካሁን ከበሽታው ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ሰዎች እንደሞቱ ታውቋል፤ ምንም እንኳን ቁጥሩ አስተማማኝ ባይሆንም በበሽታው ተይዘዋል ተብለው ከተረጋጋጡ ሰዎች ቁጥር አንጻር የሟቾቹ ቁጥር ዝቅተኛ ነው። በሽታው የተያዙ ሰዎችን ለሞት እስኪያደርሳቸው የተወሰነ ጊዜን ስለሚወስድ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል የተወሰኑት እስካሁንም ሊሞቱ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል። በተጨማሪም ምን ያህል እስካሁን ያልተመዘገቡ በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል። ቫይረሱ ከየት መጣ? በተለያዩ ጊዜያት አዳዲስ ቫይረሶች ይገኛሉ። እነሱም ሳይታወቁ ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላ ዝርያ እየተሸጋገሩ ወደሰው ይደርሳሉ። • አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ኬንያ ውስጥ ተገኘ በአሁኑ ወቅት የተከሰተው አብዛኛው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በቻይናዋ ዉሃን በተባለችው ግዛት ውስጥ ከሚገኝ የደቡብ ቻይና ባሕር አካባቢ ካለ የአሳ መሸጫ ገበያ ነው። ቫይረሱ ከየትኞቹ እንስሳት ተነሳ? የትኞቹ እንስሳት የቫይረሱ አስተላላፊዎች እንደሆኑ ከታወቀ ችግሩን ለመቆጣጠር እጅግ ቀላል እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከባሕር ውስጥ የሚገኙ እንስሳት የኮሮና ቫይረስን እንደሚሸከሙ የታወቀ ሲሆን፤ በደቡባዊ ቻይና ውስጥ የሚገኘው የባሕር ምግቦች የጅምላ መሸጫ ገበያ ውስጥ ግን ዶሮዎች፣ ጥንቸሎች፣ እባቦችና ሌሎችም እንስሳት ስለሚገኙ እነሱም የበሽታው ምንጮች ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ ይነገራል። ለምን ቻይና? በሽታው ለምን ቻይና ውስጥ ተከሰተ ለሚለው ጥያቄ የዘርፉ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ዉልሃውስ ምክንያት ሲያስቀምጡ በሕዝብ ብዛትና ተጠጋግቶ በመኖር እንዲሁም ቫይረሱን በውስጣቸው ከሚይዙ እንስሳት ጋር በሚኖር የቅርብ ንክኪ ሳቢያ ነው ይላሉ። አክለውም "በሽታው ቻይና ውስጥ ወይም ቻይና ባለችበት የዓለማችን ክፍል ውስጥ መከሰቱ ማንንም አላስደነቀም" ሲሉ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። በምን ያህል ፍጥነት ይተላለፋል? መጀመሪያ ላይ የቻይና ባለስልጣናት ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም ቢሉም አሁን ግን በዚህ መንገድ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል። ሳይንቲስቶች እንደደረሱበትም በበሽታው የተያዘ እያንዳንዱ ሰው ቫይረሱን ከአንድ እስከ ሦስት በሚገመቱ ሰዎች ድረስ ሊያስተላልፍ ይችላል። • በአዲሱ ቫይረስ የሟቾች ቁጥር አሻቀበ በተጨማሪም ቫይረሱ በእራሱ ጊዜ ተዳክሞ የሚጠፋ እንዳልሆነም ተነግሯል። የቫይረሱን መስፋፋት ለማስቆም ቻይና ውስጥ የተወሰደው እርምጃ ችግሩ የተከሰተባቸውን ከተሞች መዝጋት ነው። በሽታው መቼ ይተላለፋል? የቻይና ሳይንቲስቶች እንደሚሉት በበሽታው የተያዙ ሰዎች የበሽታው ምልክቶችን ከማሳየታቸው በፊት አንስቶ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ማስተላላፍ ይችላሉ። በበሽታው በመያዝና ምልክቶቹ መታየት በሚጀምርበት ጊዜ ያለው የመራቢያ ጊዜ ከአንድ ቀን አስከ ሁለት ሳምንት የሚወስድ ነው። ለንደን በሚገኘው ኢምፔሪያል ኮሌጅ ውስጥ የተላላፊ በሽታዎች ክፍል ውስጥ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ዌንዲ ባርክሌይ እንደሚሉት በሳምባ ላይ የሚከሰቱ በሽታዎች ምንም ምልክት ሳያሳዩ ከሰው ወደ ሰው የመተላላፍ ባህሪይ አላቸው። ነገር ግን አሁን ባለው ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ከዚህ ቀደም እንደተከሰቱት ወረርሽኞች ዓለም አቀፋዊ የበሽታ ስጋት እንዳልሆነ እየተነገረ ነው። በምን ያህል ፍጥነት ይዛመታል? አዳዲስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቀላሉ ሊለዩ የቻሉት ቻይና ሰዎቹን ለማወቅ የሚያስችላትን አቅሟን ማሻሻል በመቻሏ ነው ይባላል። ነገር ግን የወረርሽኙ የመስፋፋት መጠንን የሚያመለክት መረጃን ለማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ሆኗል። ነገር ግን ባለሙያዎች እንዳሉት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እስካሁን ከተነገረው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ብለዋል። ቫይረሱ አደገኛ ሊሆን ይችላል? የቻይና ብሔራዊ የጤና ኮሚሽን እንዳስጠነቀቀው የኮሮና ቫይረስ የመሰራጨት አቅም እየተጠናከረ ነው። ነገር ግን ከቫይረሱ ባህርይ መቀየር ጋር በተያያዘ ያለው ስጋት ግልጽ አይደለም። ስለዚህም ይህንን ለማወቅ ሳይንቲስቶች በቅርበት ክትትል እያደረጉ ያሉት። ኮሮና ቫይረስን ማስቆም ይቻላል? አሁን ባለው ሁኔታ ቫይረሱ በራሱ መንገድ አይቆምም፤ ብቸኛው ሊያስቆመው የሚችለው የቻይና ባለስልጣናት የሚወስዱት እርምጃ ነው። ሰዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ የሚያደርግ የመከላከያ ክትባትም የለውም። ብቸኛው አማራጭ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዳይገናኙ ማድረግ ነው። ይህ ማለት ደግሞ፡ ቫይረሱ እንዳለባቸው የሚያረጋግጡ ባለሙያዎች ራሱ ከበሽተኞቹ ጋር መነካካት አለመነካካታቸውን የሚያረጋግጥ ሌላ ሰፊ ሥራ ያስፈልጋል። በቻይና ሳይንቲስቶች የቫይረሱ ታካሚዎችን ሊፈውስ ይችላል ብለው ተስፋ ያደረጉበትን መድሃኒት እየተጠቀሙ ነው። ቢሆንም ግን ገና በሂደት ላይ ያለ ከመሆኑ አንጻር ሁለቱ ጸረ ቫይረስ መድሃኒቶች (ሎፒናቫይር እና ሪቶናቫይር) ለብቻቸው ወይም ከሌላ መድሃኒት ጋር ተቀምመው ፈውስ ያመጣሉ ብሎ ለመናገር አሁን ጊዜው አይደለም። እነዚህ መድሃኒቶች የሳርስና ሜርስ ወረርሽኝ ተከስቶ በነበረበት ወቅትም ጥቅም ላይ ውለው ነበር። የቻይና ባለስልጣናት የሰጡት ምላሽ? ቻይና በሌላው ዓለም ያልታየ አንድ አዲስ ነገር አድርጋለች፤ ቫይረሱ የተገኘባትን የዉሃን ግዛትን በጊዜያዊነት ሙሉ በሙሉ ዘግታለች። 36 ሚሊዮን ህዝብን የእገዳው አካል በሆኑባቸው ሌሎች ከተሞች ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጥላለች። በብዛት መሰባሰብና የቱሪዝም መዳረሻዎች ለጊዜው ክልከላ ተጥሎባቸዋል። የተወሰነው የታላቁ የቻይና ግንብ ክፍልም እንዳይጎበኝ ተዘግቷል። የቫይረሱ ምንጭ ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚገመተው የእንስሳት ግብይትም እንዳይካሄድ እገዳ ተጥሎበታል። ቫይረሱ ማዕከል ያደረጋት የዉሃን ግዛት ሁለት ሆስፒታሎችን እየገነባች ሲሆን በድምሩ 2 ሺህ 3 መቶ ሰዎችን የሚያስተናግዱ አልጋዎች ይኖሯቸዋል። በቻይና በተከሰተው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተዘጉ ከተሞች ጭር ብለዋል ዓለም ለቫይረሱ የሰጠው ምላሽ? በርካታ የእስያ አገራት ከቻይና ዉሃን ግዛት የሚመጡ ሰዎችን ምርመራ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። የዓለም የጤና ድርጅትም ከዚህም የከፋ የቫይረሱ ስርጭት ሊኖር እንደሚችል አስጠንቅቋል። ሲንጋፖርና ሆንግ ኮንግ ከዉሃን ግዛት የሚመጡ የአውሮፕላን ተጓዦች ላይ ጥብቅ ምርመራ እያደረጉ ነው፤ የእንግሊዝና የአሜሪካ ባለስልጣናትም በጉዳዩ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል። • የአፍ ጭምብል ማጥለቅ ከቫይረስ ይታደገን ይሆን? ይሁንና እንደዚህ ዓይነት ምርመራዎች ውጤታማ ናቸው ወይ? የሚለው ሌላ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ምንም ምልክት ሳይታይበት ለሁለት ሳምንታት ሊቆይ ስለሚችል፤ የመጀመሪያውን ምርመራ ካለፈ ከቀናት በኋላ በመዳረሻ አገሩ ውስጥ ህመሙ ሊጀምረው ይችላል። የሙያተኞቹ ጭንቀት? "አሁን ላይ በርካታ መረጃ እስካለን ድረስ እንዴት እንደተጨነቅን ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው።" "ምንጩ ከየት እንደሆነ እስኪረጋገጥ ድረስ ነገሮች ከባድ እንደሆኑ ይቀጥላሉ" ብለዋል በቫይረሱ ላይ እየተመራመሩ ያሉት ዶ/ር ጎልዲንግ። ሌላኛው በዘርፉ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ባል በበኩላቸው ደግሞ "ማንኛውም የሰው ልጅን የሚያጠቃ አዲስ ቫይረስ በመጣ ቁጥር ሊያስጨንቀን ይገባል፤ ምክንያቱም የመጀመሪያ የመከላከያ ደረጃውን አልፏልና" ይላሉ። "አንዴ ቫይረሱ በሰው ህዋስ ውስጥ ከገባ በኋላ ለራሱ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በፍጥነት የሚራባበትን መንገድ ያመቻችና በጣም አደገኛ ይሆናል። "ቫይረሱ እንዲስፋፋ ዕድል ሊሰጠው አይገባም" ይላሉ። ክትባት ወይም መድሃኒት አለው? እስካሁን ባለው የለውም። ምንም እንኳ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሥራዎች በሂደት ላይ ያሉ ቢሆንም፤ ምርምሮች እንደሚያሳዩት ሜርስ በተባለው የኮርኖ ቫይረስ ላይ የተቀመመው ክትባት ሥራውን ሊያቀለው ይችላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። ሆስፒታሎችም የጸረ ቫይረስ መድሃኒቶቹ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላቸውና እንደሌላቸው የማረጋገጥ ሥራ እየሰሩ ነው። ሎፒናቫይር እና ሪቶናቫይር ከተባሉ ሁለት መድሃኒቶች የተቀመመው መድሃኒት የሳርስ ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ነበር። በቻይናም ሙከራ ተደርጎበታል።
54546130
https://www.bbc.com/amharic/54546130
ማሕበራዊ ሚዲያ፡ ፌስቡክ ሐሰተኛ መረጃንና የጥላቻ ንግግርን እንዴት ነው የሚቆጣጠረው?
ፌስቡክን የመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች ለታፈኑት ድምፅ ሆነዋል፤ በርካቶች ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ሳያፈሱ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያስተላልፉ አስችሏቸዋል።
ለዘመናት በጋዜጦች፣ በቴሌቪዥን፣ በሬድዮዎች በበላይነት ተይዞ የነበረውንም የመረጃም ሆነ የዜና ምንጭነት ቀይረውታል። በግለሰብ ደረጃ የተለያዩ ዜናና መረጃዎችን በጽሑፍ፣ በምስልና በቪዲዮ ለበርካታ ሰዎች ለማድረስ ዕድልን ፈጥረዋል። በዚህም መረጃዎች በቀላሉና በአጭር ጊዜ አገራትን ብቻ ሳይሆን አህጉራትን አቆራርጠው ከበርካቶች ዘንድ ይደርሳሉ። ነገር ግን በዚህ ሂደት ይህንን የግንኙነት ዘዴ ለዕውቀትና ለበርካታ መልካም ነገሮች ከሚያውሉ ሰዎች ባሻገር ሐሰተኛ ወሬን፣ ጥላቻን፣ ጥርጣሬና ፍርሃትን እንዲሁም ለሥነ ምግባር ተቃራኒና ለሰዎች ደኅንነት አደገኛ የሆኑ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ ቡድኖችና ግለሰቦች እየተበራከቱ ነው። ይህንንም ለመከላከል የማኅበራዊ መገናኛ መድረኮቹ ባለቤት የሆኑት ተቋማት ከጊዜ ወደ ጊዜ የመገናኛ ዘዴዎቻቸውን ከእንዲህ አይነቶቹ መልዕክቶች በተቻለ መጠን ነጻ ለማድረግ የአጠቃቀም ደንቦችን በማውጣት ቁጥጥር እያደረጉ ነው። በዚህም ሳቢያ ለሰዎች ደኅንነት ጎጂ የሆኑና ሐሰተኛ ወሬዎችን በሚያሰራጩ የማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች ላይ የተለያዩ እርምጃዎች ለመውሰድ እየተገደዱ ነው። ፌስቡክ ፌስቡክ ከጥቂት ወራቶች በፊት የጥላቻ ንግግር ወይንም ሐሰተኛ ንግግሮች ናቸው ያላቸውን 22 ሚሊዮን በላይ መረጃዎችን አጥፍቷል። ድርጅቱም ይህንን የሚያደርገው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ባቋቋማቸው ማዕከላት ነው። ይህንንም አማርኛንና ኦሮምኛን ጨምሮ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ቋንቋዎች ላይ ክትትል የሚደረገው ኬንያ ባለው ቢሮ በኩል ነው። የ'ዊ አር ሶሻል' እና ፌስቡክ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ በወር አንዴ ፌስቡክን የሚጠቀሙት ሰዎች ቁጥር ከስድስት ሚሊዮን በላይ ነው። የፌስቡክ የምስራቅ አፍሪካ የማህበራዊ ጉዳዮች ፖሊሲ ኃላፊ የሆነችው ሜርሲ ኢንዴጊዋ "ለፌስቡክ ኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚዲያ ገበያ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላት አገር ናት" ትላለች። ፌስቡክ በአካባቢው ብዙ ስራዎች እየሰራ ነው የምትለው ሜርሲ፣ ኢትዮጵያ የሚገኙት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች አብዛኞቻቸው ዜናንና ሌሎች ክስተቶችን ለማግኘት ወደ ገጻቸው እንደሚመጡ ትናገራለች። "በተጨማሪም በኢትዮጵያ የእኛ ትኩረት ሰዎች በኛ ፕላትፎርም (መድረክ) እንዴት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ፣ ከዚያን በኋላ ደግሞ ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ጊዜ በሚያሳዩት ባህሪ ላይም ትኩረት እንሰጣለን" ብላለች። ይህም ማለት የጥላቻ ንግግር፣ የሐሰተኛ መረጃ እና ሌሎች ይዘቶችን ለመቆጣጠር እንዲሁም መፍትሔ ለመስጠት እየሰሩ መሆኑን ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ወቅት ተናግራለች። የፌስቡክ ማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች፣ በተለይ ደግሞ ከኢትዮጵያ የሚጠቀሙ ግለሰቦች፣ በተደጋጋሚ የሚለጥፏቸው መረጃዎች መሰረዙን በመጥቀስ ቅሬታ ያቀርባሉ። የተወሰኑ ግለሰቦች ፌስቡክ የአንድ አካል መሳሪያ ነው በማለት ሲተቹ፣ ሌሎች ደግሞ በማንነታቸው ምክንያት ትኩረት ውስጥ እንደገቡ ያምናሉ። አንዳንድ ጊዜ፣ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ እንዲሁም የአንድ ቋንቋ ቡድን አንድ ላይ በመደራጀት ሌሎች ላይ ትኩረት ሲያደርጉ ተስተውሏል። ፌስቡክ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የሐሰተኛ መረጃዎች፣ የጥላቻ ንግግሮች፣ እንዲሁም በማንነት ላይ ያተኮሩ መረጃዎች በሚለጠፉበት ወቅት እንዴት ይቆጣጠራል? በድርጅቱ የይዘት ጉዳዮች ኃላፊ (ኮንቴንት ፕሪንሲፕል) ኃላፊ የሆነችው ፈድዛይ ማድዚንጊራ አንድ መረጃ ከፌስቡክ ላይ የሚሰረዘው የተቀመጠውን የማህበረሰብ መስፈርት (ኮሚውኒቲ ስታንዳርድ) ተላልፎ ሲገኝ ነው በማለት ታስረዳለች። ይህም ፖሊስ በፌስቡክ ገጽ ላይ በግልጽ የሚገኝ በመሆኑ ማንኛውም ሰው አግኝቶ ማንበብ ይችላል የምትለው ፈድዛይ፣ በዚህ መስፈርት ስር በድርጅቱ መተግበሪያ ላይ የሚፈቀዱ እና የማይፈቀዱ ነገሮች በግልጽ መቀመጣቸውን ታስታውሳለች። "እነርሱም በ26 አበይት ርዕሶች ተከፋፍለው የሚገኙ ናቸው፣ ለዕይታ የሚረብሹ (ግራፊክ ኮንቴንት) የሆኑ ምስሎች ከተለጠፈው ነገር ጋር ሲጋጩ እንዲሁም መልካም ያልሆነ ባህሪ፣ እስከ ጥላቻ ንግግር ድረስ በዝርዝር ይዟል። የፌስቡክ የጥላቻ ንግግር ፖሊሲ ዓላማ ሰዎች በማንነታቸው ምክንያት ትኩረት ተደርጎ የሚለጠፉ መረጃዎችን ማጥፋት ነው" ትላለች። በተጨማሪም ሰዎች በማንነታቸው ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ የሚደርስባቸው ከሆነ በሚል ይህ ፖሊሲ ማስፈለጉን ታብራራለች። አንድ መረጃ ከፌስ ቡክ ላይ የሚሰረዝበት ቅድመ ሁኔታ ስታነሳ፣ "ለምሳሌ እኔ የዚምባብዌ ዜጋ ነኝ። እና አንድ መረጃ፣ እኔ ከዚምባብዌ ስለመጣሁ አልያም ጥቁር ስለሆንኩ፣ ወይንም ሴት በመሆኔ እኔ ላይ ትኩረት አድርጎ ያስፈራራኛል ወይንም የጥላቻ ንግግር ይለጥፋል ከሆነ ይህንን እናጠፋለን።" ማንኛውም ሰው ማመልከት ይችላል ማንኛውም የፌስቡክ ተጠቃሚ ስለ አንድ የፌስቡክ መረጃ ሪፖርት ማድረግ ወይንም ማመልከት ይችላል። "አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ይህንን ማድረግ እንደማንችል ነው የሚወስዱት" የምትለው ኃላፊዋ፣ አንድ መረጃን ብቻ የተመለከተ ጉዳይ ሪፖርት ማድረግ፣ የግለሰብ ወይንም ገጽን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ሪፖርት ማድረግ እንደሚቻል ለቢቢሲ አስረድታለች።። ይህንን ማድረግ የሚቻለው በቀኝ የሚገኙ ሶስት ነጥቦች ስር በመሄድ ነው። እነርሱ ሲነኩ ማመልከት ወደ ሚቻልባቸው ሂደቶች ይወስዳል። ከዚያ በዚህ ደረጃ ውስጥ አልፈው ሲጨርሱ ማመልከቻው ወደ ፌስቡክ ይደርሳል።ያ መረጃ የፌስቡክ የኮሙኒቲ ስታንደርድ ተላልፎ ሲገኝ፣ ይሰረዛል ማለት ነው። ያመለከተው ግለሰብ እንዲሰረዝ የጠየቀው መረጃ መሰረዙ መልዕክት ይደርሰዋል። ፌስቡክ በመላው ዓለም ስራቸው ይህ የሆነ ሰዎች 'ሪቪወርስ' የተባለ ቡድን ያለው ሲሆን በዚህ ቡድን ስር 30 ሺህ ያህል ሰራተኞች ይገኛሉ። "ከእነዚህ ከ30ሺህ ሰዎች አንድ ሰው፣ አንድ መረጃ ጥያቄ ሲነሳበት ከኮሙኒቲ ስታንደርድ ፖሊሲ (ከማህበራዊ አደረጃጀት ፖሊሱ) ጋር ጎን ለጎን በማመሳከር ተላልፎ ከተገኘ ይሰረዛል" ትላለች ፈድዛይ ማድዚንጊራ። ፌስቡክ እንደ ምስራቅ አፍሪካ ይህንን የሚቆጣጠር ቢሮ ናይሮቢ ውስጥ አለው። ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ ስዋሂሊ፣ እንዲሁም ሶማልኛ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎች ቀጥሮ እንደሚያሰራም አብራርተዋል። ለመሰረዝ አንድ ማመልከቻ ብቻ በቂ ነው በፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች የሚነሳው ሌላው ጉዳይ አንድ በፌስቡክ ላይ የሚለጠፍ መረጃ ማመልከቻ ባስገቡ ሰዎች ቁጥር ብዛት ነው ወይንስ ሕጉን ተላልፈው ስለሚገኙ ነው የሚሰረዘው የሚል ነው። ፈድዛይ ማድዚንጊራ እንዲህ በማለት ትገልጻለች። ከዚህ ጉዳይ ጀርባ ያለው ነገር እንዲህ ነው በማለት አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ተከታዮቻቸውን ወይንም የፌስቡክ ማህበረሰባቸውን አንድ የፌስቡክን እሴት የማይተላለፍን ጽሑፍ እንዲሰረዝ እንዲያመለክቱ ጥሪ ያቀርባሉ። ከዚህም ጋር ተያይዞ አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሪፖርቶች እናገኛለን። ይህም ደግሞ ውጤቱን አይቀይረውም። ይህንን 'የኮሙኒቲ ስታንደርድ' ተላልፎ የሚገኝ መረጃ ላይ አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው የምንፈልገው በማለት ያስረዳሉ። አንድ መረጃ የሚሰረዘው የድርጅቱን ኮሙኒቲ ስታንደርድ ስለሚተላለፍ ነው። ይህ ሳይሆን ሳይቀርና አንድ መረጃ በስህተት ቢጠፋ፣ ተጠቃሚዎቻችን ይህንን ውሳኔ ይግባኝ እንዲሉ እድል እንደሚሰጣቸው ጨምረው አስረድተዋል። የአንተ/ ወይንም የአንቺ መረጃ ተሰርዟል የሚል መልዕክት ይደርሳቸዋል። አይ እኔ የለጠፍኩት ነገር ትክክል ነው ብለው የሚቃወሙ ከሆነ ደግሞ በድጋሚ ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል። የአመልካቹ ማመልከቻ ከዚህ በፊት መረጃውን ያጠፋው የፌስቡክ ሰራተኛ ጋር ሳይሆን ለሌላ ሰራተኛ ይሰጣል። ይህም ሰው የፌስ ቡክ ፖሊሲንና የአመልካቹን ማመልከቻ ጎን ለጎን በማስተያየት ችግር ተፈጥሮ ከሆነ መረጃው ዳግም በፌስቡክ ላይ እንዲለጠፍ ያደረጋል ስትል ታብራራለች።
news-42441568
https://www.bbc.com/amharic/news-42441568
ካለሁበት 15፡ "ራሴንና ልጆቼን የሰሜን ተራሮች ላይ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር"
ፌቨን ተወልደ እባላለሁ፤ የምኖረው በፈረንሳይ ፓሪስ ነው ።
እዚህ ከመምጣቴ በፊት በአዲስ አበባ ሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት በአውሮፓውያኑ 2002 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እንደጨርስኩኝ በሊዮን ከተማ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ዕድል አግኝቼ ነበር። እዚያው የመጀመሪያ ዲግሪዬን ከጨረስኩኝ በኋላ ደግሞ ለአንድ ዓመት በዩናይትድ ኪንግደም በርሚንግሃም በትምህርት ልውውጥ መርሃግብር አሳለፍኩኝ። ከዚያ ስመለስ ግን ባለቤቴ ፓሪስ ሥራ ስላገኘ የመጨረሻውን ዓመት በፓሪስ ነው የተማርኩት። አሁን እኔም በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የባህልና የሳይንስ ተቋም (ዩኔስኮ) ኢትዮጵያ በምትወክልበት ክፍል ውስጥ እሠራለሁ። የፓሪስን ሥነ-ሕንፃ ጥበብ፣ እንደ አይፍል ማማ ያሉ ልዩ መስህቦቿን፣ አስገራሚ ታሪካዊ መገለጫዎችና ልዩ የመታሰቢያ ሃውልቶቿን ሳይ ታሪኳንና ባህሏን የምትገልጽበት መንገድ በጣም ለየት እንደሚያደርጋት አስባለሁ። ከምግቦቿ ደግሞ ታርቲፍሌት የሚባለውን ከድንች ቺዝና ከሥጋ የሚሠራ ምግብ በጣም ደስ እያለኝ ነው የምበላው። በተለይ በብርድ ጊዜ በደንብ ስለሚያሞቅ፣ ሆድም በደንብ ስለሚሞላ በደንብ ነው የምመገበው። ከፈረንሳይ ምግቦች 'ታርቲፍሌት' የተሰኘውን ምግብ ነው ከኢትዮጵያ ከምንም በላይ የሚናፍቀኝ ተሰብስቦ ቡና መጠጣቱ ሳይቻኮሉ ጊዜ ወስዶ ከሰው ጋር መወያየቱ ነው፤ እዚህ ለሁሉም ነገር ጊዜ ያጥራል። በፓሪስ ቤቴ ቁጭ ብዬ በማዕድ ቤቴ መስኮቴ በኩል የሚታየኝ አነስ ያለ ግን ዓይን የሚሞላ አረንጓዴ ቦታ ሲሆን ደስ የሚለኝ ውብ ዕይታዬ ነው። ምክንያቱም እዚህ ሀገር ሁሉም ዕይታ ከወቅቱ ጋር ሰለሚቀያየር ለውጦቹን በደንብ የሚነግረኝም፣ የሚያስታውሰኝም ይህ ቦታ ነው። የሁለት ወቅቶች ዕይታ በፓሪስ በጣም ያስገረመኝና በሀገሬ ከለመድኩት ታላላቆቻችንን የማክበር ልምድ ጋር የሚቃረነብኝ ነገር በባቡርም ሆነ በአውቶብስ ስሄድ በዕድሜ የገፉ ሰዎችን አይቼ በመነሳት ይመርቁኛል ብዬ ስጠብቅ እነርሱ ግን ትልቅ ናቸው ብዬ ማሰቤ ሲያናድዳቸው አያቸዋለሁ። የመቻል አቅማቸውን የተጠራጠርኩ አድረገው ሲወስዱ በተደጋጋሚ ስለገጠመኝ ከዚያ በኋላ ብዙ አስቤ፣ ተጠንቅቄ ነው የምነሳው። አንድ ቀን ግን በእግሬ ወደ ቤቴ ስመለስ አንዲት በዕድሜ የገፉ ምናልባትም ወደ 90 የተቃረቡ እናት መራመድ አቅቷቸው ድክም ብለው ሳይ አላስችል አለኝና ፈራ ተባ እያልኩ ተጠጋሁ። በአጋጣሚ ግን እውነትም እርዳታ የሚፈልጉ ነበሩና ደስ ብሏቸው 'እባክሽን ቤቴ ድረስ ደግፈሽኝ እንሂድ፤ እያዞረ እየጣለኝ ነው' ሲሉኝ ሀገሬ እያለሁ ይህን በማድረጌ ብቻ ይዘንብልኝ የነበረውን ምርቃት አስብኩኝ ። ሌላው የታዘብኩት እኛና ፈረንሳውያንን የሚያመሳስለን ነገር ለባህላችን የምንሰጠው ቦታ ነው። እዚህም ልክ እንደ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በባህሉ በጣም የሚኮራና ከየትኛውም ሀገር የተለየ እንደሆነ የሚያስብ ሕዝብ ነው ያለው። ይህ አቋማቸው በሥልጣኔ አለመደብዘዙ ይገርመኛል። ፌቨን ከባለቤቷ እና ከልጆቿ ጋር ሌላው ሁሌም ኢትዮጵያን የሚያስታውሱኝ ፓሪስ የሚገኙት 14 የሚሆኑት የሀገር ቤት ባህላዊ ምግብ ቤቶች ናቸው ። በሙዚየም ውስጥ ስለኢትዮጵያ ታሪክና ባህል የሚዘከርበት ቦታ ብዙ ነው። በእስካሁኑ ቆይታዬ ያዘንኩበት ነገር ልክ ትምህርቴን እንደጨረስኩኝ የትምህርትና የሥራ ልምዴን ሳደራጅ (ሲቪ ሳዘጋጅ) በወቅቱ የነፃ አገልግሎት የምሰጥበት ክፍል ኃላፊ ዕድሜዬን አይቶ 'የትዳር ሁኔታ የሚለውን ያላገባ በይው' አለኝ። ያኔ 26 ዓመቴ ነበር እና 'ለምን?' ስለው ከዚ በኋላ አግብታለች፣ ቀጣዩ ነገር ደግሞ መውለድ ነው ብለው ስለሚያስቡ ሥራ ማግኘት ከባድ ይሆንብሻል አለኝ። በሰለጠነችው አውሮፓ ይህን ስሰማ የሴት እኩልነት ጉዳይ እንዲህ ባፈጠጠ መልኩ እንዳለ መቀበል ከብዶኝ ነበር። ከዚህ ውጩ በፓሪስ ከተማ ውስጥ አንዳች ነገር የመቀየር አቅሙ ቢኖረኝ ኖሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ይልቅ መሬት ላይ ግቢ ያለው ቤት ቢኖረኝ ብዬ እመኛለሁ፤ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ኑሮ ማለት ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ ከሥራ ቦታዬ ራቅ ማለት ስላለብኝ ቤት እስክደርስ ብዙ ጊዜ ይፈጅብኛል። ነገር ግን ሁለት ልጆች ስላሉኝ ሩቅ ከሄድኩ ልጅ የሚይዝልኝ ያስፈልገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ የምችለውን ጊዜ ይገድብብኛል፤ ስለዚህ ሁለቱን ማስታረቅ ስለማልችል ለልጆቼ አደላለሁ። ሆኖልኝ ራሴን በቅጽበት ወደ ኢትዮጵያ መውሰድ ብችል እራሴንና ልጆቼን የሰሜን ተራሮች ላይ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገረቻት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦ ካለሁበት 16 ፡ 'ጭራሹኑ መጥፎ ነገሮች እንዳይከሰቱ ማድረግ ብችል ደስታዬ ወደር የለውም' ካለሁበት 17 ፡ ከሰው አልፎ ለእንሰሳት ቦታ በሚሰጥበት ከተማ ውስጥ ነው የምኖረው
news-50020038
https://www.bbc.com/amharic/news-50020038
ኪፕቾጌን በሩጫ ይገዳደሩታል?
የኪፕቾጌ የዛሬው ትንቅንቅ ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኬንያዊያን የሞት ወይ የሽርት ጉዳይ ሆኗል።
የማራቶን ክብረ-ወሰን ባለቤቱ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ዛሬ በኦስትሪያ፤ ቪዬና የሚያደርገውን የማራቶን ሩጫ ከሁለት ሰዓት በታች ለመጨረስ አቅዶ ተነስቷል። የ34 ዓመቱ አትሌት እቅዱን እንዲያሳካ ለመርዳት በርካታ አሯሯጮች የተዘጋጁለት ሲሆን ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች የመሮጥ እቅዱ ''INEOS 01፡59 ቻሌንጅ'' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። እስቲ ራስዎን ከኤሊዩድ ኪፕቾጌ ጋር ያወዳድሩ። 42 ኪ.ሜትሩን ከእርሱ ጋር ቢወዳደሩ ይዘው የሚጨርሱትን ደረጃ ይመልከቱ።
news-53352762
https://www.bbc.com/amharic/news-53352762
በአሜሪካ ከዛፍ ላይ ተሰቅሎ የተገኘው ኢትዮጵያዊው አማኒ ሞት ያስነሳው ጥያቄ
አማኑኤል ታምራት ኪልዲያ (አማኒ) በአምስት ዓመቱ ከአሜሪካ ለመጡ ነጭ ባልና ሚስት በማደጎ ተሰጠ። አዲስ አበባ የተወለደው አማኒ አማርኛ ብቻ ነበር የሚናገረው ግን የማደጎ ቤተሰቦቹ እንደሚሉት "አዕምሮው ብሩህ ስለነበር እንግሊዝኛ በአጭር ጊዜ ነው አቀላጥፎ መናገር የቻለው።"
አዲስ አገር፣ አዲስ ቤተሰብ ሁሉ ነገር "ባዕድ" ወደሆነባትም አሜሪካ፣ ኒውጀርሲ፣ ሞሪስ ከተማ በጨቅላነቱ አቀና። አማኒ በአሜሪካ ውስጥ አስራ አምስት ዓመታትን እንዲሁም በዚህች ዓለም ላይ ደግሞ ሃያ ዓመታትን ብቻ ነው መኖር የቻለው። ሊውስ ሞሪስ ፓርክ በሚባል ስፍራም ዛፍ ላይ ተሰቅሎም ሰኔ 21/2012 ዓ.ም ሞቶ ተገኘ። አማኒ የሞተበት ፓርክ ከሚኖርበት ሰፈር የአንድ ሰዓት ያህል ርቀት ላይ ይገኛል። ከምሽቱ 2፡47 አካባቢ አንድ የፓርክ ጎብኝ በድን የሆነውንና ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን አስከሬኑን በማየቱ ለፓርኩ ፖሊስ አሳወቀ። የሞሪስ ግዛት አቃቤ ሕግም አማኒ ራሱን አጥፍቷል የሚለው መደምደሚያ ላይ የደረሰው በፍጥነት ነበር። በርካቶች ግን አንድ ወጣት ጥቁር ዛፍ ላይ ተሰቅሎ መገኘት ጥያቄን አጭሮባቸዋል ምክንያቱም አሜሪካ በጥቁር ዜጎቿ ላይ ለምዕተ ዓመታት ያህል የፈፀመችው የጭካኔ ታሪክ መገለጫ በመሆኑ። አፍሪካውያን በባርነት ተግዘው እግራቸው አሜሪካንን ከረገጠባት ዕለት ጀምሮ "እምቢተኝነትን" አሳዩ ተብለው መገረፍ፣ መገደል እንዲሁም በዛፍ ላይ መስቀል በታሪክ ብቻ የሚታወቅ ሳይሆን፤ ነፃነታቸውን ከተጎናፀፉ በኋላም ዛፎች ላይ እያንጠለጠሉ መግደል የአሜሪካ እውነታ ነው። ለዘመናት ጥቁሮችን ዛፍ ላይ በመስቀልና ጥቁሮችን በማቃጠል የሚታወቀው የኬኬኬ (ኩ ክሉክስ ክላን) ከተመሰረተበት ከጎርጎሳውያኑ 1865 እስካሁን ድረስ ተመሳሳይ ግድያዎችን ይፈፅማል። ከቀናት በፊት በጠራራ ፀሐይ የነጭ የበላይነትን በሚሰብኩ ግለሰቦች ዛፍ ላይ ሊሰቅሉት ሲሉ የተረፈው ጥቁር ዜና በአሜሪካ ውስጥ መሰማትና ሌሎች ጥቁሮችም እንዲሁ በነጭ ዘረኞች ከመገደል ጋር ተያይዞ አማኒ ራሱን አጥፍቷል መባሉ ተቀባይነት አላገኘም። የአማኒ አሟሟት ትርጉም ያልሰጣቸው አካላትም ፍትህን እየጠየቁ ነው። 'ቼንጅ' በተሰኘ ድረገፅም ላይ 245 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ኢትዮጵያዊ- አሜሪካዊው ታዳጊ ፍትህ እንዲያገኝ በመጠየቅ ፊርማቸውን አኑረዋል። "በጥቁርነቱ ምክንያት ተገድሎ ይሆናል እናም ያለምንም ምርመራ ራሱን አጥፍቷል የሚለው ነገር ተቀባይነት የለውም። የተሻለ ፍትህ አማኒ ይፈልጋልም" በማለት ፅሁፉ አስፍሯል። ፅሁፉ አክሎም "መሰላልም ሆነ ሌላ ነገር በሌለበት፤ እንዴት አንድ ሰው ያለማንም እርዳታ ራሱን ከዛፍ ላይ የሚሰቅለው? አሟሟቱ ላይ የተደረገው ምርመራ እንደገና መጀመር አለበት" በማለት ጥያቄን አጭሯል። የግዛቲቱ ፖሊስ ራሱን አጥፍቷል ቢልም የብላክ ላይቭስ ማተር እንቅስቃሴ አራማጆችና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ አስተያየታቸውን እየሰጡ ያሉ ሰዎች ዘንድ "ራሱን ገድሏል" የሚለው መደምደሚያ ተቀባይነት አላገኘም። ነገር ግን የሞሪስ ግዛት ዐቃቤ ሕግ ፍሬዲሪክ ናፕ ባወጡት መግለጫ "ወንጀል ተፈፅሟል ብለን አናምንም። የህክምና ምርመራ ውጤትም እንደሚያሳየው ራሱን ማጥፋቱን" ነው ቢሉም በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ እንቅስቃሴ መፈጠሩንም ተከትሎ ከዚህ በፊት የሰጡትን መግለጫ ለመቀየር ተገደዋል። "በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚባለው ሳይሆን ምርመራው አሁንም ክፍት ነው። አጠቃለን እንዲህ ነው የሚባል ውሳኔ ላይ አልደረስንም። የመጀመሪያ መግለጫችንም የምርመራው የመጀመሪያ ውጤት ነው። አሁንም ቢሆን ከተለያዩ የፍትህ አካላት ጋር በመጣመር አሟሟቱ ላይ የሚደረገው ምርመራ ቀጥሏል" ብለዋል። በሞሪስ ግዛት የብላክ ላይቭስ ማተር መስራች ቲያና ኪምቦርግ ዐቃቤ ሕጉ መግለጫቸውን አሻሽለው ከማውጣታቸው በፊትም "የግዛቷ ዐቃቤ ሕግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም። ግልፅነት ይጎላቸዋል። ምርመራ ከመካሄዱ በፊት በሞተ ሰባ ሁለት ሰዓታት ውስጥ ራሱን አጥፍቶ ነው ብሎ መናገር ፍትሃዊነት የጎደለውና የአካባቢውን ማኅበረሰብም የናቀ ድርጊት ነው" ብላለች። አማኒ ትምህርቱን ሲያጠናቅቅ ኤፍቢአይን ወይም ሲአይኤን የመቀላቀል ህልም እንደነበር የምትናገረው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ "ገና ሃያ ዓመቱ ቢሆንም ማኅበረሰቡን ከማገልገል ወደኋላ አላለም። ከጓደኞቹም ጋር በመሆን ኒውጀርሲ ያሉ ህፃናትን ኢላማ ያደረጉትን ደፋሪዎችን የሚያጋልጥ ቡድንም መስርተው ከ30 በላይ የሚሆኑትን አጋልጠዋል" ብላለች። ህፃናት ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎችን በማጋለጡ እንደተገደለም ታምናለች። "አማኒ ለማኅበረሰቡ ይሰራ የነበረው ሥራ ደፋርና ጀግና መሆኑን ቢያሳይም አደገኛ ነበር። ምንም እንኳን ዐቃቤ ሕግ ለግድያ የሚያበቃ ምክንያት የለም ቢልም፤ እኛ ግን እሱን ዝም ማስባል የሚፈልጉ ምክንያት አላቸው። ወንጀለኞቹን ማጋለጡ ለበቀል አነሳስቷቸዋል ብለን እናምናለን" ብላለች። "ደግ አይበረክትም" አንዳንድ ሰዎች ወደዚህ ዓለም የሚመጡት የአጭር ጊዜ አላማን ለማሳካት ሲሆን፤ ዓለምን በደግነታቸው ሞልተዋት፤ ከሚኖሩት ጊዜ በላይ በርካታ ነገሮችን ሰርተው ያልፋሉ የሚባል እምነት በበርካታ አገራት ያለ ሲሆን በኢትዮጵያም "ደግ አይበረክትም" ይባላል። አማኑኤልም በኖረባት አጭር ህይወት ደግነቱ የተትረፈረፈ እንደነበር የሚያውቁት ሰዎች እንዲሁም ቤተሰቦቹ ይመሰክራሉ። "አማኒ ደግ፣ ቀና፣ ልቡ ሩህሩህና የዋህ ነበር። የሰው ሁሉ ስሜት ይሰማው የነበረ፣ የብዙዎችን ሐዘን እንደራሱ አድርጎ የሚወስድ ነበር። ትልቅ፣ ትንሽ ሳይባል ያወቀው በሙሉ ያደንቀውና ይወደው ነበር። ሁሉም ሰው ይወደኛል የሚለውን ሃሳብ ቢጠራጠርም እኛ ግን ሁሉም ይወደው እንደነበር እናውቃለን" በማለትም የማደጎ ቤተሰቦቹ ቄስ ቶም ኪልዲያና ባለቤታቸው ጃኒስ የህይወት ታሪኩ ላይ አስፍረዋል። ወንድሙና እህቶቹ ይወዱት እንደነበር እንዲሁም ወላጅ እናቱ ገነት፣ አክስቱ፣ አጎቶቹና የአጎቶቹ ልጆችም ለእሱ የተለየ ፍቅር እንደነበራቸው የህይወት ታሪኩ ላይ ሰፍሯል። ሌላኛው የትምህርት ቤት ጓደኛው ኦውን ኮውልድ እንደ አማኒ አይነት ሰው እንደማያውቅም በማዘን መስክሯል "በጣም አስቂኝ፣ ጎበዝና ለሰው ከልቡ የሚያዝን፣ ሩህሩህ ነበር። እንደሱ አይነት ሰው መቼም የማገኝ አይመስለኝም። ሁሌም ፈገግታ ከፊቱ አይጠፋም። ከሰዎች ጋር ብዙ ስንጣላም የሚያስቀን እንዲሁም የሁላችንም ሰብሳቢ እሱ ነበር" ብሏል። ሌሎችም በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ህይወቱን እየዘከሩ ያሉ ሰዎች ስለ አማኒ ተመሳሳይ አስተያየት የሰጡት ነገር ቢኖር "ለሰው ልጅ ያለው አዛኝነት ጥልቅና ሩህሩህ መሆኑን ነው።" በነጭ ባልና ሚስት በማደጎ ከቤተሰቡ ተነጥሎ ወደ አሜሪካ የሄደው አማኑኤል በሚኖርበት አካባቢ ከፍተኛ ተሳትፎን ያደርግ ነበር። ህፃናትን የሚደፍሩና፤ ኢላማ ያደረጉ ግለሰቦችን የሚያጋልጥ 'ፔዶ ጋት ኮውት' የተባለ እንቅስቃሴንም ከመሰረቱት መካከልም አንዱ ነው። እሱና ጓደኞቹ የሚያደርጉት ይህ ተግባር ደፋሪዎችን በትልልቅ መደብሮች ወይም የሕዝብ ቦታዎች ላይ በመቅጠር ቪዲዮ በመቅረፅ ለሕዝብ የሚያጋልጥ እንቅስቃሴም ነው። የእነዚህን ግለሰቦች የሚያሳፍር ሥራ ለማሳወቅም ኢንስታግራምን ይጠቀማሉ። ቡድኑ የከንቲባ ልጅን ጨምሮ ከሰላሳ በላይ ህፃናትን ኢላማ የሚያደርጉ ግለሰቦችን እንዳጋለጠና ለፍርድም እንዳቀረበም ከበርካታ ዘገባዎች መረዳት ይቻላል። ይሄ ሥራቸው በግዛቲቱ አስተዳደሪዎችንም ሆነ፣ በፖሊስ ሥራ ጣልቃ ገብተዋል ከሚሉ አካላት እንዲሁም በሚያጋልጧቸው ሰዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሮ ነበር። እናም ለዚህ ነው በርካታ ሰዎች የአማኒ ሞት ከሚታገልልለት የማኅበራዊ ፍትህ ሥራዎች ጋር ተገናኝቶ ሊሆን ይችላል ብለው የሚጠይቁት። እነዚህ ያጋለጣቸው ከ30 በላይ ግለሰቦችና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው በፖሊስ ተመርምረው እንደሆነ ከሚጠይቁት መካከል ቲያና አንዷ ናት። በአሁኑ ሰዓትስ ሊያጋልጣቸው የነበሩ ደፋሪዎችስ ነበሩ ወይ? እንዴት ወደ ፓርኩ መጣ? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው ትላለች። ቤሰተቦቹ ካሰፈሩት የህይወት ታሪኩ እንዲሁም በእሱ ዙሪያ ከተሰሩ ዘገባዎች መረዳት የሚቻለው አማኒ ለእግር ኳስና ለቅርጫት ኳስ ለየት ያለ ፍቅር እንደነበረው ነው። በተለይም ህፃን እያለ ኳስን ከእሱ መነጠልም አስቸጋሪ ነው በማለት ቤተሰቦቹ ምስክርነት ሰጥተዋል። "በተፈጥሮውም ድንቅ አትሌት ነው" የሚልም ፅሁፍ በህይወት ታሪኩ ላይ ሰፍሮ ይገኛል። ዌስት ሴንትራል የተባለ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው አማኒ፤ በትምህርት ቤትም ውስጥ ቅርጫት ኳስ እንዲሁም እግር ኳስ ይጫወት ነበር። ዌስት ሞሪስ ሴንትራል ወልፍ ፓክ ለሚባል ቡድንም ጋር እግር ኳስ ይጫወት ነበር። ለጨዋታና ለማሸነፍ ትልቅ ቦታ የነበረው አማኒ ብሩህ አዕምሮም ያለው ነበር በማለት ብዙዎች ገልፀውታል። ብዙ ጊዜ በማደጎ ከተለያዩ አገራት ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ህፃናት ፈታኝ ህይወት እንደሚኖሩና አድገውም ማንነታቸውን ፍለጋ እንደሚባዝኑ መስማት የተለመደ ነው። በተለይም ጥቁር ህፃናት በነጭ ቤተሰብ ውስጥ ሲያድጉ ልጆቹ የመጡበትን ባህልና ታሪክ አለመገንዘብ፤ መነጠላቸውን አለማሰብ እንዲሁም በሄዱባቸው አገራት የሚያጋጥማቸውን ማኅበራዊ መገለሎች እንዲሁም መዋቅራዊ ዘረኝነት እንደሚገጥማቸው በዚህ ህይወት ውስጥ ያለፉ በርካቶች ሲናገሩም ተሰምተዋል። የአማኒም የቤት ውስጥ ህይወት ቀላል እንዳልነበረ ቤተሰቦቹ ከፃፉት የህይወት ታሪክም መረዳት ይቻላል። ይሄንም አባቱ አማኒን ደግ ቢሆንም "በጥባጭ" ነው ያሉት ሲሆን "ቤት ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ለአማኒ ፈታኝ የነበረ ቢሆንም ከልባችን እንወደው ነበር። ከእኛም ሆነ ከዓለም በመለየቱ በቃላት መግለፅ የማይቻል ሃዘን ተሰምቶናልም" በሚልም የህይወት ታሪኩ ላይ ሰፍሯል። ሆኖም ግን ቤተሰቡ አማኒ ያከናውናቸው በነበሩ ተግባራቱና ማኅበረሰቡን ለማገልገል በነበረው ቁርጠኝነት ይኮሩበት እንደነበርም በፅሁፋቸው ገልፀዋል። ሪዲመር ሉተራን በተባለ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፓስተር የሆኑት አባቱ "እንደ ማንኛውም ሰው ቢሮ ውስጥ ገብቶ መስራት ለእሱ አይዋጥለትም ነበር" በየካቲት ወር ላይ የወታደርነት ስልጠና ወስዶ መመረቁን በማውሳት እንዴት ለቤተሰቦቹ ኩራትም እንደነበር ተናግረዋል። 'አርሚ ሪዘርቭስ' ከሚባለው ተቋምም የውትድርናና የፖሊስ መሠረታዊ የሚባል ስልጠናን ወስዷል። ከእሱ ጋር ይህንን ስልጠና የወሰደ ኖህ ብራመር የተባለ የልብ ጓደኛው "ስልጠናውን አስደሳች አድርጎታል። ፈገግታው እንዲሁም ቀልዱ አሁንም ፊቴ ድቅን ይላል። እሱን አለመውደድ አይቻልም፤ ምንም አይነት ድብታም ሆነ ጭንቀት አይቼበት አላውቅም። የነገረኝ ነገርም የለም" ብሏል። አማኒ የአሜሪካውን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኤፍቢአይን ወይንም ሲአይኤን የመቀላቀልም ህልም እንደነበረው ስለሱ የሚያዉቁ ሰዎች ይመሰክራሉ። በዚህ አመትም ጄምስ ማዲሰን ዩኒቨርስቲም ገብቶ ትምህርቱንም ለመከታተል በጉጉት እየጠበቀ ነበር ተብሏል። ህልሙን እውን በማድረግ የተለያዩ አስተዋጽኦዎችን ለማኅበረሰቡ ለማበረክት ይጥር የነበረው አማኒ፤ በግዛቲቱ ውስጥ ባለፉት ሁለት ወራት ዛፍ ላይ ተሰቅለው ከሞቱት ሰዎች መካከል አራተኛው ነው። ሞቱ አወዛጋቢ ቢሆንም ቤተሰቦቹ ግን ራሱን አጥፍቷል የሚለውን ውሳኔ በፀጋ ተቀብለውታል ተብሏል። ቤተሰቦቹ እንዲህ ያለ ምርመራ መቀበላቸው በበርካቶች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። ከፍተኛ ትችትም ቀርቦባቸዋል። ዐቃቤ ሕጉ አጠቃላይ እየተካሄደ ስላለው የምርመራ ሂደት ሙሉውን መረጃ ለሕዝብ ይፋ ባያደርግም የህክምና ምርመራ ውጤቶችን ግን ማጣጣል ተገቢ አይደለም እተባለ ቢሆንም፤ ቲያኒ በበኩሏ ነፃ በሆነ አካል የአስከሬን ምርመራ እንዲደረግም ጠይቃለች። "በርካታ ጥቁር አሜሪካውያን በተለያዩ ሕዝባዊ ቦታዎች ላይ በዛፍ ተንጠልጥለውና ተገድለው ተገኝተዋል። እነዚህም ያለምንም መረጃ ራስ ማጥፋት ነው በሚል ድምዳሜ ተደርሶባቸዋል፤ ይህ ተቀባይነት የለውም" ብላለች። (ምንጭ፦ ኒውጀርሲ ሂልስ፣ ቼንጅ ኦርግ፣ ሪቮልት ቲቪ፣ ሞሪስታውን ግሪን፣ፓሪስ ፓኒ ፎከስ፣ ሄቪ፣ ኒውስ ዋን፣ቴክደይ 24፣ የአማኒ የህይወት ታሪክና ከማኅበራዊ ሚዲያዎች የተጠናቀረ)
news-56719750
https://www.bbc.com/amharic/news-56719750
ፍትሕ፡ ኢትዮጵያ የግልግል ዳኝነት ሕጓን ማሻሻሏ ምን ፋይዳ ይኖረዋል?
የግልግል ዳኝነት እና የእርቅ ሥርዓት አሰራር አዋጅ ባሳለፍነው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።
በኢትዮጵያ የግልግል ዳኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሕግ ማዕቀፍ ያገኘው በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐ ብሔር ሕግ ነበር። ይህ አዋጅ ተሻሽሎ የፀደቀው ከ65 ዓመታት በኋላ ነው። ኢትዮጵያ እአአ በ1958 የወጣውን ዓለም አቀፉን የግልግል ዳኝነት ሕግ፣ ኒው ዮርክ ኮንቬንሽንን ከዓለም 162ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 33ኛ አገር በመሆን የፈረመችውም ባለፈው ዓመት ነበር። ። የግልግል ዳኝነት የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የመሳሰሉ አለመግባባቶችን የተከራካሪ ወገኖችን ሕጋዊ መብትና ጥቅም በጠበቀ መልኩ ለመፍታት የሚያስችል አማራጭ የዳኝነት ሥርዓት ነው። የግልግል ዳኝነት ከፍርድ ቤት አሰራር በምን ይለያል? አዋጁ መሻሻሉስ ምን ፋይዳ አለው? ኩባንያዎች የግልግል ዳኝነትን ለምን ተመራጭ ያደርጋሉ? አቶ ሚካኤል ተሾመ አዋጁን በማርቀቁ ሂደት ምክክር ሲጀመር በመነሻ ረቂቅ ደረጃ (Zero Draft) ከተሳተፉ የሕግ ባለሙያዎች አንዱ ናቸው። "የግልግል ዳኝነት በኢትዮጵያ ሕግ" የሚል መጽሐፍም አቶ ሲራክ አካሉ ከተባሉ ሌላ የሕግ አዋቂ ጋር በመሆን ጥናት ሠርተው አሳትመዋል። የኢትዮጵያ የማስማማትና የግልግል ዳኝነት ማዕከል ዳሬክተርም ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት የግልግል ዳኝነት አለመግባባትን መፍቻ ብቻ ሳይሆን ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታውም የጎላ ነው። የግልግል ዳኝነት ከሌላው የፍርድ ቤት ክርክር በምን ይለያል? የግልግል ዳኝነት ተከራካሪዎቹ ዳኞችን የመምረጥ፣ ውሳኔ የሚሰጥበትን ጊዜና ቦታ እንዲሁም የሚመራበትን ሕግ የመምረጥ፣ እንዲሁም ተቋማዊ ወይም ተቋም የሌለው እንዲሆን መወሰን የሚያስችል እንደሆነ አቶ ሚካኤል ይናገራሉ። አቶ ሚካኤል እንደሚሉት በግልግል ዳኝነት የክርክሩን ሂደት የመወሰንና የመምራት መብትም የተከራካሪዎቹ ነው። ይህ ለተከራካሪዎቹ ነጻነት የሚሰጥ በመሆኑ ከፍርድ ቤት ይልቅ የግልግል ዳኝነትን ተመራጭ ያደርገዋል። የግልግል ዳኝነት በሚቋቋምበት መንገድም ከፍርድ ቤት ይለያል። ፍርድ ቤት የሚቋቋመው በሕገ መንግሥቱ መሰረት ሲሆን የግልግሉ አሠራር የሚረቀቀው ግን በውል ነው። ተከራካሪዎቹ ወይም ባለጉዳዮቹ በአንድ አገር የግልግል ዳኝነት ሕግ ለመዳኘት ፈቅደው በተስማሙበት ውል ማለት ነው። የይግባኝ አጠያየቅ ጉዳይም የፍርድ ቤትና የግልግል ዳኝነት የሚለዩበት ሌላኛው ነጥብ መሆኑን ባለሙያው ይናገራሉ። በፍርድ ቤት ሥርዓት ማንኛውም ተከራካሪ የፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ይግባኝ የመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን የግልግል ዳኝነት ላይ ግን ይህ ምርጫ ነው። ተከራካሪዎቹ ይግባኝ ማለት ከፈለጉ ይጠይቃሉ። ካልፈለጉም ይግባኝ አለማለት ይችላሉ። ኩባንያዎች ከፍርድ ቤት ይልቅ የግልግል ዳኝነትን ለምን ይመርጣሉ? በዓለማችን ትልልቅ የንግድ ተቋማትና ኩባንያዎች፣ ባለሃብቶች እና ዝነኞች የሚገጥማቸውን አለመግባባቶች ለመፍታት የግልግል ዳኝነትን ተመራጭ ሲያደርጉ ይስተዋላል። ይህ ለምን እንደሆነ የጠየቅናቸው የሕግ ባለሙያው አቶ ሚካኤል፤ "ሚስጥራቸው የተጠበቀ እንዲሆን ስለሚያስችላቸው ብዙዎች የግልግል ዳኝነት ተመራጭ ያደርጉታል" ይላሉ። ባለሙያው እንደሚሉት በዚህ ሥርዓት ከሚመለከታቸው ሰዎች ውጪ ሦስተኛ ወገን ገብቶ ዳኝነቱን መከታተል አይችሉም። በፍርድ ቤት ሕግ ግን 'ልዩ' ከሆኑ ጉዳዮች ውጪ ማንኛውም ሰው ገብቶ ችሎቱን መከታተል ይችላል። በመሆኑም የግልግል ዳኝነት ነጻነት የሚሰጥ በመሆኑ የውጪ አገር ባለሃብቶች አንድ አገር ሄደው መዋዕለ ንዋያቸውን ሲያፈሱ የሚገጥማቸውን ችግር ከፍርድ ቤት ይልቅ የግልግል ዳኝነት ይፈታልናል የሚል እምነት አላቸው ይላሉ- አቶ ሚካኤል። በዚህ ሥርዓት ተከራካሪዎቹ ዳኞችን፣ የሚዳኙበትን ሕግ ፣ ውሳኔ የሚሰጥበትን መንገድ እና ተቋማዊ መሆን አለመሆኑን የመምረጥ ነጻነት አላቸው። በሌላም በኩል የግልግል ዳኝነት ወጪ ቆጣቢ ነው ይባላል። ምንም እንኳን ይህ ብዙ አከራካሪ ሃሳብ ቢሆንም። የፍርድ ቤት ሂደት የተራዘመ ጊዜ በመውሰዱ የተነሳ ለበዛ ወጪ ይዳርጋል የሚል እሳቤ አለ። በተቃራኒው የግልግል ዳኝነት መጀመሪያ ላይ ለዳኞቹና ሌሎች አስተዳዳራዊ ክፍያዎች የሚከፈለው ገንዘብ ከፍ ስለሚል ውድ ተደርጎ የሚታይበትም አግባብ አለ። ቢሆንም ግን የግልግል ዳኝነት ሌሎች ጠቀሜታዎች ስላሉት በርካቶች ተመራጭ እንደሚያደርጉት አቶ ሚካኤል ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በውጭ አገር የተሰጡ የግልግል ዳኝነት ማስፈጸም የሚረዳውንና እአአ በ1958 የወጣውን ዓለም አቀፍ ስምምነት (የኒው ዮርክ ኮንቬንሽን) ፈርማለች። ይህም በእንግሊዝኛው (Convention on the Recognition and Enforcement of Foreign Arbitral Awards) የሚባለው ነው። በመሆኑም ሌላ አገር የተሰጠን የግልግል ዳኝነት ውሳኔ አገር ውስጥ በቀላሉ ማስፈፀም ይቻላል። ሌላ አገር የተሰጠን የፍርድ ቤት ውሳኔ ግን ኢትዮጵያ መጥቶ ማስፈፀም አደጋች ነው። "የፍትሃ ብሔር ሥነ ሥርዓትና ሕግ ጉዳይ፤ የሌላን አገር ውሳኔ እንዳይፈፀም የሚያደርግበት/የማያደርግበት የኢትዮጵያ ሕግ ሊኖር ይችላል" ይላሉ ባለሙያው። የግልግል ዳኝነት ግን አፈጻጸሙ የሚገዛው በ1958 በወጣው የኒው ዮርክ ስምምነት በመሆኑ የትኛውም አገር ጉዳይን ማስፈፀም የሚያስችል ነው ይላሉ። የኒው ዮርክ ስምምነት ሌላ አገር የተሰጠ የግልግል ዳኝነት ውሳኔ፤ ባሉበት አገር ውስጥ እንዴት ይፈፀማል የሚለውን የሚያስረዳ አለም አቀፍ ስምምነት ነው። ይህ ስምምነት በአፈፃፀም ደረጃ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ነው። በአዲሱ ሕግ ምን ተካቷል? ኢትዮጵያ የግልግል ዳኝነትን በሕግ ማዕቀፍ ያስገባችው በ1952 ዓ.ም ሲሆን የተሻሻለው ከአስርት ዓመታት በኋላ ነው። አቶ ሚካኤል ይህ ሕግ ከረዥም ጊዜ በኋላ ቢሻሻልም መሰረታዊ ነጥቦችን አካቷል ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት አዲሱ ሕግ ተቋም እንዲቋቋም ይፈቅዳል። በመሆኑም በመንግሥትም ሆነ በግል ተቋማት የግልግል ዳኝነት ተቋም ማቋቋም ያስችላል። ይህም ለተከራካሪዎች የበለጠ ነጻነት ይሰጣቸዋል ይላሉ -አቶ ሚካኤል። 'ተቋም መቋቋሙ ብቻ አይደለም ለተከራካሪዎች ነጻነትን የሚያጎናጽፈው። ለተከራካሪዎች ነጻነት የሚሰጠው በሕጉ ውስጥ የተካተቱት አንቀጾችና ድንጋጌዎች ናቸው።' የግልግል ዳኝነት ሰፊና ውስብስብ ቢሆንም በሕግ ደረጃ የተደነገገው በጣም ቁንፅል ሃሳብ ነበር የሚሉት ባለሙያው፤ አሁን በተቋም ደረጃ መታሰቡ ጠንካራ ያደርገዋል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሌላ አካል ጣልቃ ገብነትን ማስቀረት እንደሚያስችል ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም በነበረው ሕግ ፍርድ ቤቶች በተለያየ መልኩ እየገቡ ዳኝነቱ እንዲቆም ፣ ዳኞች የሚመረጡበትን መንገድ የመወሰን ሥልጣን እንደነበራቸው የሚያስታውሱት ባለሙያው፤ የተሻሻለው ሕግ ግን ከፍርድ ቤቶች ይልቅ ለተከራካሪዎች የበለጠ ሥልጣን እንደሰጣቸው አስረድተዋል። የግልግል ዳኝነቱ ዝርዝር ሃሳቦችን የያዘ ዘመናዊ ሕግ ሆኖ ነው የወጣው ሲሉም ያክላሉ። ከዚህም ባሻገር በፊት ያልነበረና የንብረት እግድ እንዴት ሊፈፀም እንደሚችል፤ እንዲሁም ሦስተኛ ወገን መግባት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን በተመለከተም መልስ የሰጠ ሕግ እንደሆነ ተናግረዋል። የግልግል ዳኝነት ፋይዳ ምንድን ነው? ባለሃብቶች ወደ አንድ አገር ሄደው መስራትን ሲያስቡ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ ያስገባሉ። ሌጣ መሬት ስለተገኘ አሊያም ገንዘብ ስላለ ብቻ ገንዘባቸውን አያፈሱም። ፖለቲካዊ መረጋጋት፣ የግብር ሕግ፣ የንግድ ሕግ ፣ የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ፣ የብሔራዊ ባንክ ሕግ እና ሌሎችን ሕጎች ያጤናሉ። ያሰራኛል ወይ ብለው ይጠይቃሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ የግልግል ዳኝነት ሕግ ነው። በሥራቸው አለመግባባት ቢገጥማቸው ባሉበት አገር ሆነው የሚዳኙበት ሥርዓት። በመሆኑም ኢትዮጵያ የኒው ዮርኩ ስምምነት አካል መሆኗ ለኢንቨስተሮች [ባለሃብቶች] በር ይከፍታል። "ባለሃብቶች 'ከኢትዮጵያዊ ነጋዴ ጋር ተከራክረን ውሳኔ ቢወሰንልን እንኳን፤ በምን አግባብ? እንዴት አድርገን እናስፈፅማለን?' የሚለውን ነገር አያሰጋቸውም። " ይላሉ አቶ ሚካኤል። ይሁን እንጅ በጥንቃቄ ካልተሰራበት የሚያስከፍለው ዋጋ እንዳለም ባለሙያው ይናገራሉ። አቶ ሚካኤል እንደሚሉት ይህ የሚያጋጥመው በቸልተኝነት ውል ሲፈፀም ነው። በመሆኑም ስምምነትን የሚያረቁ፣ የሚፈርሙ፣ በጉዳዩ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች በሙሉ እያንዳንዱን ነገር ትኩረት ሰጥተው በጥንቃቄ ማየት አለባቸው ሲሉ ይመክራሉ። "በየትኛውም አገር የኢትዮጵያን ኩባንያዎችን የሚወክሉ ባለሙያዎች ኃላፊነትና ግዴታ አለባቸው። ኮንትራቶችን በቸልተኝነት የሚፈረሙ ከሆነ፤ ዋጋ መክፈል አይቀርልንም" ብለዋል።
news-42283701
https://www.bbc.com/amharic/news-42283701
ካለሁበት 13፡ ''ለእኔ ስኬት ማለት ገንዘብ ማግኘት ብቻ አይደለም''
አብዱሰላም አባጀበል እባላለሁ በአሜሪካ በኒው ዮርክ ከተማ የ'ኦሲስ ጅማ ጁስ ባር' ባለቤት ነኝ።
አብዱልሰላም ሕይወትን ለማሸነፍ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፏል ተወልጄ ያደኩት በጅማ ከተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ሸቤ በሚባል ቦታ ነው። ዕድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ ሸቤ ትምህርት ቤት በመግባት እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ ተምሬያለሁ። ከዚያም ሌላ ቦታ እስከ 8ኛ ክፍል ለመማር ዕድሉን ባገኝም በአባቴ ሞት ምክንያት ትምህርቴን ለማቋረጥ ተገደድኩ። ያደኩት በሰፊ ቤተሰብ ውስጥ ሲሆን ከእናቴና አባቴ የተወለዱ 14 እህትና ወንድሞች ሲኖሩኝ ወደ 30 የሚጠጉ ደግሞ የጉዲፈቻ እህቶችና ወንድሞች አሉኝ። አባቴ ሰዎችን ሰብስቦ ማብላትና ማጠጣት ይወዱ ነበር። ነገር ግን ሲሞቱ ያሁሉ እየጠፋ መምጣት ጀመረ። ከ8ኛ ክፍል ወደ ክሊኒክ ባለቤትነት ትምህርቴን በማቋረጥ ቤተሰቦቼን ለመርዳት ስል ሥራ መፈለግ ጀመርኩኝ። በመጀመሪያም ሳዶ ወደምትባል አካባቢ በመሄድ ከአባቴ ባገኘሁት የሕክምና ሞያ ክሊኒክ ከፈትኩኝ። የተወሰነ ያህል ከሠራሁኝ በኃላ መንግስት ፈቃድ የለህም ስላለኝ ክሊኒኩን ዘግቼ ለመሄድ ተገደድኩኝ። ሆኖም ግን ወደ ቤተሰቦቼ አልተመለስኩም። ሠርቼ ገንዘብ አገኝበታለሁ ብዬ ወዳሰብኩት በባህላዊ መንገድ ወርቅ ወደሚቆፈርበት ዲማ ወደሚባለው አካባቢ አመራሁ። እንዳጋጣሚ ሆኖ ብዙ ወርቅ ላገኘ ወዲያው ሃብታም የመሆን ዕድል አለ የሚል ነገር በልጅነቴ ሰምቼ ነበር። እኔም የሆነ ነገር አግንቼ ራሴን አሻሽላለሁ በሚል ሃሳብ ተነሳስቼ በ16 ዓመቴ ወደ ዲማ አቀናሁ። የተባለበት ቦታ ስደርስ ግን የሚወራውና እውነታው በጣም የተለያየ ነበር። ምግብ ቤት ላላቸው ሰዎች ከወንዝ ውሃ ከመቅዳት እስከ በረሃ ወርዶ ወርቅ ፍለጋ ድረስ ታግያለሁ። እንዲሁም ምግብ ሠርቼ ለሌሎች በማቅረብና የጤና ችግር ያለባቸውን ከአባቴ ሥር ሆኜ በቀሰምኩት እውቀት በማገልገል በማገኘው ገቢ ኑሮዬን ለማሸነፍ ጥረት አድርጌ ነበር። በዚያ አይነት ሁኔታም ለአንድ ዓመት ከሠራሁ በኋላ በአካባቢው ችግር በመከሰቱ ዲማን ለመልቀቅ ተገደድኩኝ። ልጅ ነህ ዲማ በነበርኩበት ሰዓት በሱርማና በአኝዋክ ሕዝቦች መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ጓደኞቼን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ተገደሉ። ስለዚህ በቡሌ ሆራ፣ ቦረና ከዚያም በጉጂ አቆራርጬ ወርቅ ወደሚቆፈርበት ሌላ ቦታ ወደ ሻኪሶ አቀናሁ። ነገር ግን እዚያ አብሬያቸው እቆፍር የነበሩ ሰዎች 'አንተ ልጅ ነህ፥ አካፋ እንኳን ማንሳት አትችልም' በማለት አባረሩኝ። ስለዚህ ሌላ መላ ማግኘት ነበረብኝ። ቁፋሮው በሚካሄድበት ቦታ ምግብ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ስለነበረ እነሱ ለምግብ የሚያስፈልገውን ካቀረቡልኝ እኔ እያበሰልኩ 30 ሰዎችን መግቤ በጋራ የሚገኘውን ገቢ እኩል ለመካፈል ሃሳብ አቀረብኩኝ፤ እነሱም ተስማሙ። በዚህ አይነት በቀን 3 ጊዜ ለ30 ሰዎች ምግብ በማብሰል ከእነርሱ እኩል የተገኘውን በመካፈል ሠራሁኝ። ከ6ወራት በኋላ ግን በአካባቢው ከነበረው አለመመቻቸት የተነሳ ወደሌላ ሃገር በመሄድ የተሻለ ሕይወት ለምን አንኖርም በማለት ከጓደኞቼ ጋር መነጋገር ጀመርን። መነጋገር ብቻ ሳይሆን በጅቡቲ በኩል አቆራርጠን ወደ ዐረብ ሃገር ለመግባት መንገድ ጀመርን። ከ5 ወራት ውጣ ውረድ በኋላም በየመን በኩል ሳዑዲ ገባን። ይሁን እንጂ ከረዥሙ ጉዞ በኋላ የሳዑዲ ድንበር ላይ እንደደረስን የሳዑዲ ፖሊሶች ይዘውን ወደ ኢትዮጵያ መለሱን። ወደ ሰው ሀገር ሄዶ የመስራት እቅዴ ሳይሳካ ቀረ። ነገር ግን ተስፋ አልቆረጥኩም። ጊዜዬን ሳላባክንም ወደ ኬንያ አቀናሁ። እዚያም ስደርስ የሰው እጅ ላለመጠበቅ ስል የተለያዩ ሥራዎችን ሠርቼአለሁ። ለ5 ዓመታትም የወንዶች የፀጉር ማስተካከያ ቤት በመክፈትና ከተጣሉ ቁሳቁሶች የጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻ በመሥራት ገቢ ለማገኘት ታትሬያለሁ። ከ5 አድካሚ የጥረት ዓመታት በኋላ እኤአ በ2004 በተባበሩት መንግሥታት ጥገኝነት ለሚጠይቁ ሰዎች በሚዘጋጀው የቤተሰብ ማገናኛ መርሃ ግብር አማካይነት ወደ አሜሪካ ኒው ዮርክ ከተማ መምጣት ቻልኩ። የአብዱልሰላም ምግብ አፍቃሪዎች ከራስ አልፎ ለሌሎች መትረፍ አሜሪካ ስገባ የልቤ ሃሳብ በሙሉ የተፈጸመ መስሎኝ ነበር፤ ነገር ግን እውነታው የተለየ ነበረ። እንዲያውም ለተወሰኑት የመጀመሪያ ወራት አየሩ፣ ሃገሩና ቋንቋው አዲስ ከመሆኑ የተነሳ ግራ እጋባ ነበር። በኋላ ግን ቀስ በቀስ ተላመድኩት። ሥራ ለመጀመር ግን ሃገሩንና ቋንቋ በመልመድ ጊዜ ማባከን አልፈለኩም። ሠርቼ ራሴን ለመለወጥ ባለኝ ከፍተኛ ፍላጎት አሜሪካ በገባሁ በ2ኛው ቀን በልብስ ንፅህና መስጫ ቤት ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ። ከዚያም በኒው ዮርክ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ ሠርችያለሁ። በመጨረሻም ለአየር መንገድ የአውሮፕላን ነዳጅ ቀጂ ሆኜ እሠራ ነበር። ከዚያ በኋላ እንዴት ራሴን ችዬ ሌሎችን ልርዳ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሰዎችን ማማከር ጀመርኩኝ። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች 'አንተ አልተማርክም እንዲሁም ገንዘብ የለህም' እያሉ ቅስሜን ሊሰብሩ ይሞክሩ ነበር። እኔ ግን በውስጤ የነበረውን ሃሳብ ለማሳካት ጠንክሬ መሥራቱን ቀጠልኩኝ። ባገኘሁት ሰዓት ሁሉ አጫጭር ስልጠናዎችን መውሰድ እና መፅሃፍ ማንበብ ቀጠልኩ። ከዛ በኋላ ነው እንግዲህ በ2012 'ኦሲስ ጅማ ጁስ ባር' የተሰኘውን ጭማቂ ቤት መክፈት የቻልኩት። በቀጣዩም ዓመት ኒው ዮርክ ውስጥ የሚገኝ ምርጥ ጭማቂ ቤት በመባል የሶስተኝነት ደረጃ በማግኘት የምስክር ወረቀት አግኝቻለሁ። ከዛም ወዲህ ድርጅቴ በየዓመቱ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን እየያዘ መጣ። አሁን ታዲያ ዓለም አቀፍ ስምና ዝና ያለው ድርጅት መሆን በምችልበት ሁኔታ ላይ እየሰራሁ ነው። የስራዬ ዋና አላማ ገንዘብ ማግኘት ብቻ አይደለም። ሰዎች ጤናማ ምግብ ማግኘት እንዳለባቸው አስባለሁ። እኔም ራሴ ከአመጋገብ የተነሳ ለስኳር በሽታ የተጋለጥኩበት አጋጣሚ ነበር። ጤናማ ምግቦች ደግሞ እንዲህ አይነት የጤና እክሎችን ለመቆጣጠር ወይም ለመቀነስ ትልቅ ሚና አላቸው። በአብዱልሰላም ጭማቂ ቤት የሚቀርቡት ምግቦች በከፊል ወደ ትምህርት ቤቶች፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ የህብረተሰብ ማእከላት በመግባት የራሴን ተሞክሮ እና ሰዎች እንዴት ጤናማ የሆነ ምግብ መመገብ እንደሚችሉ የተለያዩ የልምድ ልውውጦችን አደርጋለሁ። በአሁኑ ሰዓት ለአስር ሰዎች የአጭር እና የረዥም ጊዜ የስራ ዕድል መፍጠር ችያለሁ። እዛው ኒው ዮርክ ውስጥ ሁለተኛ ጭማቂ ቤት ከፍቻለሁ፤ በካናዳም እንደዚሁ። በተለያዩ ግዛቶች እና እዚህ ክፈት የሚል ጥያቄ እየቀረበልኝ ስለሆነ የመጪው አመት እቅዴ የእኛ ሰዎች ወደሚገኙበት እየሄድኩ ቅርንጫፎቼን አስፋፍቼ ለበርካቶች የስራ እድል መፍጠር ነው። ሀገር ቤት ሄዶ መክፈትም ምኞቴ ነው። በተጨማሪ ደግሞ ኦሲስ ፓወር ሐውስ የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅቴ መስከረም 29 2017 ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል። የዚህ ድርጅት ዓላማ የተለያዩ ሙያ ያላቸው ሰዎች ልምድ እና እውቀታቸውን መመር ለሚፈልጉ ሰዎች ያለክፍያ እንዲያሰለጥኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው። በዚህ ማዕከል ከኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ እና ከሲቲ ኮሌጅ ጋር በጋራ በመሆን ነው የምንሰራው፤ ከተቋማቱ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች እየመጡ ልምዳቸውን ያካፍላሉ። ሁሉም ሰው በተፈጥሮው ሙሉ ሆኖ የተፈጠረ ቢሆንም ካሰብነው ቦታ እንዳንደርስ ማህበረሰቡ ተፅእኖ ያደርግብናል። የምንሰራውን ነገር ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልገው ዋናው ነገር በራስ መተማመን እንዲሁም ሌሎችን አለማውቀስ፣ እና ከሰዎች አለመጠበቅ ናቸው። አሁን የምወደውን ስራ እየሰራሁ ነው። ለዛም ነው የተሳካልኝ። ለኔ ስኬት ማለት ገንዘብ ማግኘት ብቻ አይደለም። የሚወዱትን እየሠሩ ሌሎችን ማገዝ ነው ለኔ ስኬት ማለት። ገንዘብ በየትኛውም መንገድ ሊገኝ ይችላል፤ እውነተኛ ሕይወትን መኖር ግን ከገንዘብ ይበልጣል። ለበለጡ ቡልቡላ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 14፡ "ብርዱ ሲከፋ፣ ቀኑም ሲያጥር የሀገሬ አየር በስንት ጣዕሙ እላለሁ።" ካለሁበት 15፡ "ራሴንና ልጆቼን የሰሜን ተራሮች ላይ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር"
news-53544131
https://www.bbc.com/amharic/news-53544131
አሜሪካ ሲንጋፖራዊው ተማሪ የቻይና ሰላይ እንደሆነ እንዴት ደረሰችበት?
ጁን ዊ ዩ ተወዳጅ ተማሪ ነበር። ጎበዝ የፒኤች ዲ ተማሪ። ትምህርቱን ይከታተል የነበረው ሲንጋፖር ውስጥ ነበር። እርሱም ዜግነቱ የሲንጋፖር ነው።
ጁን ዊ ዩ እንዴት ሕይወቱ አቅጣጫ ቀይሮ ራሱን የቻይና ሰላይ ሆኖ እንዳገኘው ለእራሱም ይገርመዋል። የሆነ ቀን ይፋ ትምህርታዊ ገለጻ (ሌክቸር) ሰጥቶ ሲጨርስ ከታዳሚዎቹ መካከል የሆኑ ሰዎች መጥተው ተዋወቁት። "ድንቅ ነበር 'ሌክቸርህ'" ሲሉ እንትፍ እንትፍ አሉበት። "ለምን ቤይጂንግ መጥተህ ጥናትህን አታቀርብም?" ሲሉም ጋበዙት። ደስም አለው። ከሲንጋፖር ቤጂንግ በረረ። ጁን ዊ ሦስተኛ ዲግሪውን ይሰራ የነበረው በቻይና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ነበረ። የቤይጂንግ ገለጻውን አቅርቦ ሲጨርስ ደግሞ ሌሎች ሁለት ሰዎች መጡና ተዋወቁት። "ገለጻህ ማለፍያ ነው! በዚያ ላይ ብሩህ ጭንቅላት ነው ያለህ!" አሉት። ". . . እኛ የምንሰራው ቻይና ውስጥ ለሚገኝ አንድ የምርምርና የጥናት ቡድን (ቲንክ ታንክ) ነው፤ አብረን ብንሠራ ደስ ይለናል. . . ." አላቅማማም። መጀመሪያ ከዚያው ከሲንጋፖር ሆኖ አካዳሚያዊ ወረቀቶችን ይልክላቸው ጀመር። ቀስ በቀስ ለምን ከአሜሪካ ሆነህ ትንንሽ መረጃዎችን አታቀብለንም፤ እኛ ደግሞ ትልልቅ ክፍያ እናስብልሃለን አሉት። • አሠሪዎ እየሰለለዎ መሆኑን እንዴት ያውቃሉ? • በስለላ ወንጀል የተጠረጠረው ጥንብ አንሳ የተወሰነ ጊዜ እንደሰራላቸው ሰዎቹ በትክክል ማን እንደሆኑ ተረዳ፤ ጁን ዊ የቻይና የደኅንነት ሰዎች መረብ ውስጥ ነበር ሰተት ብሎ የገባው። ብዙም አልከፋውም። አብሯቸው መሥራት ቀጠለ። መጀመሪያ ከደቡብ ምሥራቅ እሲያ አገሮች የሚያገኘውን መረጃ ይልክላቸው ነበር። ቀጥሎ ግን "በአሜሪካ ዙሪያ ብቻ እንድታተኩር እንፈልጋለን" አሉት። ከዕለታት አንድ ቀን ሲንጋፖራዊው ወጣት የለየለት የቻይና ሰላይ ሆኖ ራሱን አገኘው። ስለላ ደግሞ የኋላ ማርሽ አያውቅም። ሥራውን ገፋበት። መረጃ የሚያቀብሉትን ሰዎች ያጠምዳቸው የነበረው ታዲያ ሊንክዲን (Linkdin) በተሰኘው የሙያና የሥራ መተሳሰሪያ ድራምባ ነበር። አንዴት? ሊንክድኢንን (LinkdIn) ለስለላ? የጁን ዊ ሌላኛው ስሙ ዲከንስ ይባላል። ሐሰተኛ የአማካሪ ኩባንያ ስም በማውጣት ሰዎችን ያማልል ነበር። አምስት ዓመታት በዚህ መንገድ ከሰራ በኋላ ነው ባለፈው አርብ አሜሪካና ቻይና ግንኙነታቸው በሻከረ ማግስት በቁጥጥር ሥር የዋለው። እርሱ በተማረበት የሲንጋፖር ሊ ኩዋን ዪ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የነበሩ ጓደኞቹ ዜናውን ሲሰሙ ማመን ነው ያቃታቸው። ይህ የሲንጋፖር ዩኒቨርስቲ በፐብሊክ ፖሊሲ ዘርፍ እውቅ ነው። በእሲያ አህጉር በርካታ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ፖሊሲ አውጪዎችን ያስመረቀ ነው። "በጣም ንቁ ተማሪ ነበር። እንዴት ያለ ድንቅ ልጅ! ይገርማል" ስትል ለቢቢሲ አስተያየቷን የሰጠች፣ ስሟን መጥቀስ ያልወደደች አንድ አብራው የተማረች ሴት፤ የሊን ስም በበጎ ብቻ እንደምታስታውስ ገልጻለች። • የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን ". . . ብዙውን ጊዜ እርሱ ስለ እኩልነት ነበር የሚያወራው፣ በልጅነቱ ቤተሰቡ እርሱን ለማሳደግ ያዩትን ፍዳ ይነግረን ነበር። አሁን ለቻይና ሲሰልል ነበር መባሉ ሊዋጥልኝ አልቻለም" ብላለች። ሌላ አንድ የዩኒቨርስቲው መምህር ግን ከእርሷ የተለየ ትዝታ ነው ያላቸው። ". . . ልጁ ስለእራሱ ትንሽ የተጋነነ አመለካከት ነበረው።" ጁን ዊን ለሦስተኛ ዲግሪው ሲያማክሩት የነበሩት ሰው በአካባቢው አገራት ዕውቅ ፕሮፌሰር ናቸው። ኋንግ ጂንግ ይባላሉ። ዩኒቨርስቲው በኋላ ላይ አባሯቸዋል። የተባረሩት ታዲያ አንዲት ስሟ ያልተጠቀሰን የአካባቢውን አገር የውጭ ፖሊሲዋን ለመጠምዘዝ ሞክረዋል በሚል ነበር። ፕሮፌሰሩ ከዩኒቨርስቲው ከተባረሩ በኋላ ሲንጋፖርን ለቀው ዋሺንግተን ዲሲ ሥራ ጀመሩ። አሁን ቤይጂንግ ገብተዋል። እኚህ ፕሮፌሰር ከተማሪያቸው ጁን ዊ ጋር የስለላ ግንኙነት ነበራቸው የሚል መረጃ ግን እስካሁን አልወጣም። አሁን የምርመራ ሰነዶች ይፋ እንዳደረጉት ሲንጋፖራዊው ጁን ዊ ከቻይና የደኅንነት መኮንኖች ጋር በተለያዩ የቻይና ከተሞች ለዓመታት ሲገናኝና መረጃ ሲያሾልክ ነበረ። በአንድ የግንኙነታቸው ወቅት ታዲያ ጁን ዊ በቻይና አለቆቹ ሦስት መረጃዎችን እንዲያቀርብ ተጠየቀ። እነሱም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዙርያ አሜሪካ እየሰራች ስላለው ጉዳይ፣ በአሜሪካ የንግድ ዲፓርትመንትን በተመለከተ ያሉ ነገሮች እንዲሁም አሜሪካ ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት ለማድረግ ያላት ዝግጁነት ምን እንደሚመስል. . .። ለሰላዩ ጁን ዊ አንዲህ ያሉ መረጃዎችን እንዲቃርም እገዛ ያደረገለት ሊንክዲን (Linkdin) የሙያ ትስስር መድረክ ነው። ሊንክዲን በተመሳሳይ ሙያ ዘርፍ ያሉ ሰዎችን ያስተሳስራል። በዓለም 700 ሚሊዮን ሰዎች በዚህ መንገድ ተጋምደዋል። በዚህ ዘርፍ ሰዎች ቀድሞ ስለሰሩበት ዘርፍ እንዲሁም መሥሪያ ቤት ይጽፋሉ። ለምሳሌ በርካታ በአሜሪካ መንግሥት የሲቪልና ወታደራዊ ተቋም ውስጥ የሰሩ ሰዎች ይህንኑ ልምዳቸውን በሊንክዲን ገጻቸው ያሰፍራሉ። ይህን የሚያደርጉት ታዲያ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ሥራ ካገኘን በሚል ነው። አሁን የተሰረዛው የጁን ዊ ዩ የሊንክድኢን ገጽ ይህን ማድረጋቸው ታዲያ እንደ ጁን ዊ ላሉ ለውጪ የሰለላ ተቋማት መኮንኖች መልካም አጋጣሚን ፈጥሯል። ለምሳሌ የቀድሞው የሲአይኤ መኮንን ኬቪን ማሎሪ ለቻይና መረጃዎችን በማቀበል ተጠርጥሮ 20 ዓመት እስር የተፈረደበት ሰው ነው። መጀመሪያ የቻይና ሰላዮች ያገኙት ታዲያ በሊንክዲን አማካኝነት ነበር። ይህ የአሜሪካ ብቻ ራስ ምታት አልሆነም። አንዳንድ የአውሮፓ አገራትም ቢሆኑ ዜጎቻቸው በሰላዮች ኢላማ መደረጋቸውን ደርሰውበታል። የጀርመን ደኅንነት መሥሪያ ቤት በ2017 ባወጣው አንድ ጥናት የቻይና ሰላዮች 10 ሺህ ጀርመናውያንን ኢላማ ማድረግ የቻሉት ሊንክዲን የሙያ የትስስር መድረክን በመጠቀም ነበር። • "አገሬ ነች፣. . .ሞትም ቢመጣ እዚሁ ነው የምጋፈጠው"- ኃይሌ ገብረሥላሴ • የእሁዱ ስብሰባና በኦነግ አመራር አባላት መካከል የተፈጠረው ተቃርኖ ቢቢሲ ሊንክዲን ኩባንያ በጉዳዩ ዙርያ አስተያየት እንዲሰጠው ጠይቆ ምላሽ አላገኘም። ነገር ግን ከዚህ በፊት ለተመሳሳይ ቅሬታዎች በሰጠው አስተያየት እንዲህ ዓይነት ሕገወጥ አሰራሮችን እንደሚከታተል አስታውቆ ነበር። ጁን ዊ ኢላማ ያደረጋቸው ሰዎችን በሊንክዲን ካገኛቸው በኋላ መጀመሪያ በሐሰት ከመሰረተው የአማካሪ ኩባንያ ጋር ያፈራርማቸውና ሪፖርት አንዲጽፉለት ያደርጋል። ባለሙያዎቹ የሰሩትን ሪፖርት ካጠናቀረ በኋላ ደግሞ ወደ ቻይና ይልከዋል። ጥርጣሬ እንዳይፈጥር በሚል የአማካሪ ድርጅቱን ስም የቀዳው አሜሪካ ውስጥ ካለ አንድ ሌላ እውቅ አማካሪ ቡድን ስምና የንግድ ምልክት ላይ ነበር። በዚህ መንገድ ተታለው ለጁን ዊ ጥናት ከሰሩለት ሰዎች መካከል አንዱ በአሜሪካ አየር ኃይል ውስጥ የኤፍ-35 ጄት አብራሪ የነበረ አሜሪካዊ ነው። ሰውዬው ለፍርድ ቤት እንዳመነው ለቻይናው ሰላይ የጥናት ወረቀት ያቀበለው የገንዘብ ችግር ስለገጠመው ነበር። ሌላው አሜሪካዊ ፔንታገን ውስጥ የሚሰራ የመረጃ መኮንን ነበር። ቻይናዊው ጁን ዊ ለዚህ ሰው አሜሪካ ከአፍጋኒስታን ጦሯን ብታስወጣ ቻይና ላይ የሚደርሰው የእጅ አዙር ተጽእኖ ምን ሊሆን ይችላል የሚል የጥናት ወረቀት እንዲጽፍ ነበር ያዘዘው። ጥናቱን ሲያጠናቀቅ 2 ሺህ ዶላር ከፍሎታል። ጁን ዊ አንድ በአገር ደኅንነት አልያም በንግድና ወታደራዊ ደኅንነት ላይ የተሰማራ ሰው በሊንክዲን ሲያገኝ ሊንክዲን በበኩሉ ሌሎች ተያያዥ ልምድ ያላቸው ሰዎችን ስም ዝርዝር ይዘረዝርለታል። ይህ ነበር የጁን ዊን ልፋት ያቀለለው። ቀድሞ በሊ ኩዋን ዩው ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበረው ዊሊያም ንጉየን አሜሪካዊ ነው። በ2018 በቬትናም ተቃውሞ ላይ ሳለ በቁጥጥር ሥር ውሎ ከአገር ተባሯል። ከዚያ በኋላ ዝነኛ ሆኖ ቆይቷል። ዊሊያም ታዲያ ሰሞኑን በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ሰላዩ ጁን ዊ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሊያገኘው ሞክሯል። ጁን ዊ ለፍርድ ቤት እንዳመነው በ2018 በሐሰት ላቋቋመው የአማካሪ ድርጅቱ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ሲያወጣ 400 ሰዎች ያመለከቱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 90 ከመቶ የሚሆኑት በአሜሪካ ወታደራዊና የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሠሩ ነበሩ። የእነርሱንም ዝርዝር መረጃ ዊ ለቻይና አሳልፎ ሰጥቷል። ሰላዩ ጁን ዊ ሰዎች በሊንክዲን በተሻለ ደመወዝ እንዲማልሉ ካደረጋቸው በኋላ የሚሰጡትን መረጃና የሚያጠናቅሩትን ሪፖርት ይመረምራል። በዚህ ደረጃ የሚሰጡት መረጃና የሚያጠናቅሩለት ሪፖርት አካዳሚያዊ መልክ ነው የሚይዘው። ይህ ግን ለጊዜው ነው። የኋላ ኋላ ከእነርሱ ውስጥ እጅግ ጥቂቶቹ የመንግሥትን ምስጢር እንዲያሾልኩ የማግባባትና የመመልመል ሥራ ይከናወንባቸዋል። ቻይና ቻይናዊ ያልሆኑ ዜጎችን እየመለመለች ለስለላ ተግባር ስታሰማራ ይህ የጁን ዊ ጉዳይ የመጀመሪያዋ አይደለም። ሲንጋፖር የበርካታ ማኅበረሰቦች አገር ናት። ወደ 6 ሚሊዮን ሕዝብ አላት። ከእነዚህ ውስጥ ዝርያቸው ከቻይና የሚመዘዙ ጎሳዎች ቁጥራቸው ላቅ ይላል። ሲንጋፖር ከአሜሪካ ጋር ወዳጅ ናት። የአየርና ሌሎች ወታደራዊ ማሪፍያዎች ለአሜሪካ ታቀርባለች። ሲንጋፖር ከቻይናም ጋር ጠብ የላትም። ከሁለቱ ተቀናቃኝ አገራት ጋር ያላት ግንኙነት ሚዛናዊ መሆኑ ዜጎቿ ለስለላ የተመቹ ሳያደርጋቸው አልቀረም። የሰላዩ ጆን ዊ ጉዳይም ከዚህ የሚመነጭ ነው። አሁን በቻይናና በአሜሪካ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየሻከረ መጥቶ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህ የሲንጋፖራዊው ወጣት ሰላይ ጉዳይ ምናልባት ሁለቱን አገራት ሌላ ጡዘት ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል ተሰግቷል። ሲንጋፖራዊ ሆኖ ለቻይና ሲሰልል የተገኘው ጁን ዊ ፒኤችዲውን የሚሰራበት ዩኒቨርስቲ ከዚህ በኋላ አላውቅህም ብሎታል። ዊ ገና ሦስተኛ ዲግሪውን በማጠናቀቅ ላይ ነበር። ነገር ግን ጁን ዊ የቻይና ሰላይ አለቆቹ በሚፈልጉት ደረጃ መረጃ አቀብሏቸዋል ማለት አይደለም። በቅርቡ ቻይና ደርሶ ሲመለስ አለቆቹ አንድ አሜሪካው የጦር መኮንን ለስለላ ተግባር እንዲያስፈርመው የቤት ሥራ ተሰጥቶት ነበር። ይህንን ተልዕኮውን ሊያሳካ ጥቂት እርምጃዎች ሲቀሩት ነበር አሜሪካኖች በቁጥጥር ሥር ያዋሉት። የ39 ዓመቱ ጁን ዊ በትንሹ አስር ዓመት እስር ይከናነባል ተብሎ ይጠበቃል።
news-51047946
https://www.bbc.com/amharic/news-51047946
አራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ470 በላይ ተማሪዎችና ሠራተኞች ላይ እርምጃ ወሰዱ
የ2012 የትምህርት ዘመን ከተጀመረ ከአምስት ወራት አይበልጥም። ይሁንና ከወራት በፊት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተውን የተማሪዎች ግጭት ተከትሎ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ግጭቱ ተስፋፍቶ የሞትና የአካል ጉዳት ያደረሱ ግጭቶች ሲስተናገዱ ቆይተዋል። የመማር ማስተማር ሂደቱም በከፍተኛ ሁኔታ ተስተጓጉሏል።
ዩኒቨርሲቲዎቹም በግጭቱ ተሳትፎ አላቸው ያሏቸውን ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸው ተሰምቷል። ርምጃ ከወሰዱት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የጎንደር ዩኒቨርስቲ አንዱ ነው። ዩኒቨርሲቲው በፌሰስቡክ ገጹ ባሰፈረው መረጃ መሰረት በዩኒቨርሲቲው በተከሰተው አለመረጋጋት የመማር ማስተማር ሂደቱ ሲቆራረጥ ቆይቷል። • ከፕላስቲክ የጫማ ቀለም የሚያመርቱት የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች • ዩኒቨርሲቲ ብሎ ለመጥራት የሚያስቸግሩ "ዩኒቨርሲቲዎች" ተቋሙ ከተለያዩ አካላት ጋር ባደረጋቸው ውይይቶችም አንዳንድ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የጤና ባለሙያዎች የተከሰተውን ሁከት በማነሳሳት፣ የህይወት እና የአካል ጉዳት እንዲደርስ በተለያዩ ደረጃዎች አሉታዊ አስተዋፅኦ በማድረግ፣ በተደጋጋሚ ምክር ቢሰጣቸውም ችላ በማለት ሁከት እንዲስፋፋ በማሰብ ሰራተኞችን በማነሳሳት እና ቀስቃሽ መልእክቶችን በመበተን ተሳታፊ ሲሆኑ መቆየታቸውን መረዳት ችያለው ብሏል ዩንቨርሲቲው። በመሆኑም ታህሳስ 22/2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ 2 ተማሪዎች ለአንድ አመት፣ 39 ተማሪዎች ለሁለት አመት፤ እንዲሁም 11 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ገበታቸው (ከዩኒቨርሲቲው) እንዲሰናበቱ መወሰኑን ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ለ7 መምህራን ቀላል የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ለ3 መምህራን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ለ3 መምህራን እና ለ8 የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ ከስራ እንዲሰናበቱ ወስኗል። ሌላኛው ግጭት ተነስቶ ሁለት ተማሪዎች የሞቱበት ወሎ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራውን አውከዋል ያላቸውን 335 ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና መምህር ላይ ርምጃ ወስዷል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አባተ ጌታሁን ለኢዜአ እንደገለጹት በብሔርና በኃይማኖት ሽፋን በተፈጠረ አለመረጋጋት የመማር ማስተማር ስራው ባለፉት ወራት ውስጥ ለሶስት ጊዜ መቋረጡን አውስተዋል። ባለፉት ሁለት ወራት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራው እንዳይቀጥል ፍላጎት ያላቸውን 332 ተማሪዎች፣ ሁለት የአስተዳደር ሰራተኞችና አንድ መምህር ላይ እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል። ከነዚህ መካከል 12 ተማሪዎችና ሁለት የአስተዳደር ሰራተኞች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ አንድ መምህር ከስራ መታገዱን አመልክተው ለ320 ተማሪዎች ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል። እርምጃ የተወሰዳባቸው ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና መምህሩ በዩኒቨርስቲው ውስጥና ውጭ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር ምክንያት ሆነው መገኘታቸው በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠባቸው መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም ግጭቶች በተደጋጋሚ ተነስተው በተለያዩ ጊዜያት የተማሪዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል። በተፈጠረው የጸጥታ ችግር የተለያየ ተሳትፎ በነበራቸው ተማሪዎች ላይ ርምጃ መውሰዱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል። በዚህም መሰረት ሁለት ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ፤ ሰባት ተማሪዎች እያንዳንዳቸው ለሶስት ዓመት፣ ስምንት ተማሪዎች እያንዳንዳቸው ለሁለት ዓመት ከትምህርት ገበታቸው የታገዱ ሲሆን አንድ ተባሮ የነበረ (በወቅቱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልነበረ) ነገር ግን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ውስጥ ተሳታፊ የነበረ ዩኒቨርሲቲው ክስ መስርቶበት በህግ ተጠያቂ እንዲሆን ወስኗል። • የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደቤታቸው ለመላክ ለምን ወሰነ? የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሌላኛው በግጭት ሲታመስ የነበረ ተቋም ነው። ይህንን ተከትሎም የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ታኅሳሥ 27/2012 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ ባለፉት ሁለት ወራት ከተፈጠረዉ አለመረጋጋት ጋር በተገናኘ ትምህርት እንዲስተጓጎል ፍላጎት ባላቸዉና ሁኔታዎችን በመጠቀም ችግር የፈጠሩ 51 ተማሪዎችን በመለየት እርምጃ መውሰዱን ገልጿል። በዚህም 31 ተማሪዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸዉ ሲሆን 20 ተማሪዎች ላይ ከ1 አመት እሰከ ሙሉ በሙሉ ከትምህርት መርሃ-ግብር ማገድ የሚደርስ የዲሲፕሊን ቅጣት ርምጃ መወሰዱን ዩኒቨርሲቲው በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል። ከተቋማዊ ለዉጥ ሂደቱ ጋር በተገናኘ በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ዙርያ የምክትል ፕሬዝዳንት እና የ3 ዳይሬክተሮች እንዲሁም በሌሎች ዘርፎችም የ3 ሃላፊዎችን ለዉጥ አድርጌያለሁ ብሏል ጅማ ዩኒቨርሲቲ። አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት ወራት በተከሰቱት ግጭቶች ተሳትፎ ነበራቸው ባሏቸው ከ470 በላይ ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ እርምጃ ወስደዋል።
news-56435271
https://www.bbc.com/amharic/news-56435271
የኪም ጆንግ ኡን እህትና የሰሜን ኮሪያዋ ኃያል ሴት ማን ናት?
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ነው መታየት የጀመረችው። ኪም ዮ ጆንግ ትባላለች። የታላቁና ክንደ ብርቱው የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት የኪም ጁንግ ኡን ታናሽ እህት ናት።
ኪም ዮ ጆንግ ኪም ከእህት ወንድሞቹ ማንንም እንደሷ ያቀረበው ሰው የለም። የሰሜን ኮሪያ የመንግሥት መዋቅር ግልጽ አይደለም። ማን የማን አለቃ እንደሆነ በገሀድ አይታወቅም። ሆኖም ከወጣቱ መሪ ኪም በላይ ምንም የለም። እሱ ፈላጭ ቆራጭ ነው። ሁሉም ሰው ከእሱ በታች ነው። ከእሱ በታች ከሆኑት መካከል፣ ከበታቾች መካከል ደግሞ የበላይ የሆነች አንዲት ሴት አለች፤ ስሟም ኪም ዮ ጆንግ ነው። ለዚህ ዘገባ እህት ኪም እያልን እንጠራታለን። ለመሆኑ እህት ኪም ማን ናት? እህት ኪም የታላቁ መሪ የኪም ቀጥተኛ ታናሹ ናት። ለመጀመርያ ጊዜ በግላጭ የታየችው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 ነበር። ያን ጊዜ ከወንድሟ ጋር የጠላት አገር ደቡብ ኮሪያን ልትጎበኝ ሄደች። ያን ጊዜ የክረምት ኦሊምፒክን ለማዘጋጀት ሁለቱ ባላንጣ አገራት በጋራ ደፋ ቀና እያሉ ነበር። ከዚያ በኋላ ከወንድሟ ጋር ሆና የደቡብ ኮሪያን ፕሬዝዳንት ሙን ጄ ኢንን፣ የቻይናውን ሺ ጂን ፒንግን እንዲሁም የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን አገኘች። በዚህ ጊዜ ነው ይቺ ሴት ቀላል ሰው እንዳልሆነች ዓለም መጠርጠር የጀመረው። በሚያዝያ 2020 ክንደ ብርቱው ወንድሟ ኪም ጆንግ ኡን ከቴሌቪዥን መስኮት ጠፋ። አገሬው ይህ ሰው አለቅጥ ወፍሮ ስኳሩና ደም ግፊቱ በርትቶበት ይሆን እያለ ተጨነቀ። በዚህ ጊዜ የሰሜን ኮሪያዊያን ተስፋ እሷ ነበረች፤ እህት ኪም። ፕሬዝዳንት ኪም በጠፋበት ወቅት ዓለም በሙሉ እሱን ማን ሊተካው ይሆን ሲል ስሟን ደጋግሞ አነሳ። የኪም እህት የፖለቲካ ሚና ለመጀመርያ ጊዜ ይፋ የሆነው በጥቅምት 2017 ነበር። የፖሊት ቢሮ ተለዋጭ አባል ተደረገች። ከዚያ በፊት የፕሮፓጋንዳና የንቅናቄ ሚኒስትር ምክትል ዳይሬክተር ነበረች። አሁንም ይህን ሥልጣን አልተወችውም። እህት ኪም በአሜሪካ ማዕቀብ ከተጣለባቸው የሰሜን ኮሪያ ሹማምንት ዝርዝር ላይ ስሟ ከፊት ተቀምጧል። በዚህ ጥቁር መዝገብ ስሟ ሊሰፍር የቻለው በሰሜን ኮሪያ ከሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ እጇ እንዳለበት በመረጋገጡ ነው። በዚህ ማዕቀብ ስሟ በመኖሩ ማንኛውም የአሜሪካ ኩባንያም ሆነ ግለሰብ ከእሷ ጋር የገንዘብ ንክኪ እንዳይኖረው በሕግ ይከለክላል። በእሷ ስም የተመዘገበ ንብረት በአሜሪካ ምድር ካለ እንዳይንቀሳቀስ ይታገዳል። ኪም ዮ ጆንግ በወንድሟ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶች ተሳታፊ ናት እህት ኪም ምን ያህል ኃያል ናት? በምስጢራዊቷ አገር ሰሜን አሜሪካ ማን የማን አለቃ ነው የሚለውን ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ መሆኑ እሙን ነው። ይህም በመሆኑ እህት ኪም ምን ያህል ሥልጣን ተሰፍሮ እንደተሰጣት የሚያውቀው ሰፋሪው ወንድሟ ኪም ብቻ ነው። በሐሜት ደረጃ እንደሚወራው ግን ከወንድሟ ውጪ እሷን በሥልጣን የሚበልጥ ወንድም ሆነ ሴት በመላው ሰሜን ኮሪያ እንደሌለ ነው። ምናልባትም ከኪም ቀጥሎ 2ኛዋ ተፈሪ ሰው እሷ ናት። እንደሚታመነው ከሆነ እህት ኪም ያገባችው የቾ ርዮንግ ሄ ወንድ ልጅን ነው። ቾ ርዮንግ የሰሜን ኮሪያ ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ ናቸው። ይህ ሐሜት እውነት ከሆነ እህት ኪም የበለጠ ተፈሪ የሚያደርጋት የጋብቻ ትስስር አድርጋለች ማለት ነው። ምክንያቱም በሰሜን ኮሪያ የኮሚኒስት ፓርቲን ዋና ጸሐፊነት የያዘ ሰው ሥልጣኑ የዋዛ እንዳልሆነ ማንም የሚረዳው ነው። እህት ኪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠንካራ የማስፈራሪያ ቃላትን የያዙ መግለጫዎችን ስትሰጥ ነበር። ያነጣጠሩትም በጠላት አገር አሜሪካና በጠላት ጎረቤት ደቡብ ኮሪያ ላይ ነበር። ከቀናት በፊት ሰጥታ የነበረው መግለጫም አንዱ ተጠቃሽ ነው። በዚህም 'አሜሪካ ሰሜን ኮሪያን እንዳታስቆጪ' ስትል አስፈራርታታለች። ባለፈው ሰኔ እህት ኪም የአገራቸውን ሠራዊት ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ወደሆነው የሰሜንና ደቡብ ኮሪያ ድንበር እንደምትልክ ስትዝት ነበር። ይህን መግለጫ የሰጠችው ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ የከዱ ዜጎች የሚልኩትን የተቃውሞ ፊኛና በራሪ ወረቀቶች ማስቆም አለመፈለጓን ተከትሎ ነው። ከዚህ ዛቻ በኋላ እህት ኪም የኮሪያዎች የግንኙነት ቢሮ እንዲዘጋ ማዘዟ ይታወሳል። ከቀናት በኋላም ይኸው ዛቻዋ እውን ሆነና በሰኔ 16 ከባድ ፍንዳታ ተሰማ። የደቡብ ኮሪያ የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጡት በ8 ሚሊዮን ዶላር እንዲታደስ ከደቡብ ኮሪያ ልገሳ የተደረገለት ይህ የሁለቱ ኮሪያዎች አገናኝ ቢሮ (ላይዘን ኦፊስ) ድምጥማጡ እንዲጠፋ ተደርጓል። የዚህ ጥፋት አስፈጻሚም እህት ኪም እንደሆነች ተደርሶበታል። የቀድሞው መሪ ኪም ጆንግ ኢል ልጆች የሆኑት ወንድምና እህት የኪም የዘር ሐረግ? ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ተተኪ ቢፈለግ በዝርዝሩ መጀመርያ ረድፍ የሚቀመጡት ሰዎች የኪም ቤተሰቦች እንደሚሆኑ እሙን ነው። የአገሪቱ ፕሮፓጋንዳ ለዘመናት እንደሚናገረው ሰሜን ኮሪያ የምትመራው 'ፓክቱ' በሚባለው የዘር ሐረግ ነው። ይህም ሄዶ ሄዶ አገሪቷን የመሰረቷት ኪም ኢል ሱንግ ጋር ያደርሳል። ወጣቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን በርከት ያሉ ልጆች በይፋም በምስጢርም እንዳሉት ይገመታል። ሆኖም ልጆቹ ገና ለአቅመ ሥልጣን የበቁ አይደሉም። እህት ኪም የዚህ ፓክቱ የሚባለው የዘር ሐረግ ስላላት ወንድሟ አንድ ነገር ቢሆን ከእሷ የተሻለ ለአገር መሪነት የቀረብ ሰው ላይኖር ይችላል። ኪም ዮ ጆንግ የቀድሞ የሰሜን ኮሪያ መሪ የኪም ጆንግ ኢል ትንሽዋ ሴት ልጅ ናት። ኪምና እሷ ከአንድ አብራክ ነው የተገኙት። ሌላ ኪም ጆንግ ቾል የሚባል ወንድምም አላቸው። ሆኖም ቾል ፖለቲካው ላይ እስከዚህም ነው። እህት ኪም የተወለደችው እንደ አውሮፓውያኑ በ1987 ሲሆን ከወንድሟ ኪም ጆንግ ኡን በ4 ዓመት ታንሳለች። ሁለቱም የተማሩት በውዷና በባለጸጋዋ አውሮፓዊት አገር ስዊትዘርላንድ፣ በርን ከተማ ነበር። በበርን ከተማ የተወሰኑ ዓመታትንም ኖረዋል። የስዊትዘርላንድ ባለሥልጣናት እንደሚሉት በእህት ኪም የስዊትዘርላንድ የትምህርት ቤት ቆይታ ወቅት በበርካታ ልዩ ጠባቂዎች እና ምስጢራዊ ክትትል አድራጊዎች እየተጠበቀች ነበር የተማረችውም፣ የኖረችውም። በአንድ ወቅት መጠነኛ ጉንፋን ይዟት በከፍተኛ ጥድፊያ ሆስፒታል ተወስዳ እንደነበረም ያስታውሳሉ። አንዳንድ ሪፖርቶች እንዳረጋገጡት እሷ የተለየ ጥበቃ ሲደረግላትና ገለል ብላ ስትኖር ልጅነቷን ከብዙ ወዳጅ ዘመድ ጋር ሳትገናኝ አሳልፋለች። አሁን በሰሜን ኮሪያ ያላት ኃላፊነትና የሥልጣን ድንበር ባይታወቅም በዋናነት ስትሰራ የቆየችው ግን የወንድሟን ምስልና ገጽታ ከፍ ከፍ ማድረግ ላይ ነው። የወንድሟ ኪም የፖለቲካ አማካሪው እና ልዩ ረዳቱ እንደሆነችም ከምትሰራው ሥራ ተነስቶ መገመት ይቻላል። በ2019 ኪም ከትራምፕ ጋር ቬትናም ሀኖይ ውስጥ ተገናኝተው ውይይታቸው ፍሬ ሳያፈራ ከቀረ በኋላ፤ እህት ኪም ከእይታ ተሰውራ ነበር። ይህም ምናልባት ከሥልጣኗ ተባራ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሮ ቆይቷል። ሆኖም በ2020 ወደ ፖሊት ቢሮ ተለዋጭ አባልነቷ ተመልሳ ሥራዋን ተግታ እየከወነች ነው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 አባቷ ሲሞቱ ቀብር ላይ ታየች። ከዚያ በኋላም አልፎ አልፎ ካልሆነ ታይታ አታውቅም ነበር። በ2014 ደግሞ ወንድሟ ሲመረጥ በዓለ ሲመቱ ላይ ተገኘች። ቀጣይ የሰሜን ኮሪያ መሪ? አሁን በሰሜን ኮሪያ አንዳች ኮሽታ ሲሰማ፣ የወንድሟ ከእይታ ሲሰወር ወይም ሲታመም እህት ኪም ትልቅ መነጋገርያ ትሆናለች። ሰሜን ኮሪያም ሆነ ዓለም የሚረዳው እሷ ቀጣይዋ የሰሜን ኮሪያ መሪ እንደምትሆን ነው። ነገር ግን በሰሜን ኮሪያ እንኳን ስለ መጪው ሥልጣን ስለ ዛሬም ቢሆን በእርግጡ የሚታወቅም የሚነገርም ነገር የለም። በሰሜን ኮሪያ የፖለቲካ ምስጢር ጥብቅ ሐይማኖት ነው። ለሹመት ስትጠበቅ እንደ ታላቁ የኪም አጎት በአደባባይ ልትገደልም ትችላለች። በሰሜን ኮሪያ የሥልጣን ግምት መስጠት እጅግ አስቸጋሪ ነው። ሰሜን ኮሪያ ለምን ኑክሊዬርን መረጠች?
52896214
https://www.bbc.com/amharic/52896214
"በጣም እርግጠኛ ሆነን ያወጣነው ሪፖርት ነው" አምነስቲ ኢንተርናሽናል
አምንስቲ ኢንተርናሸናል ከቀናት በፊት ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ የመንግሥት ኃይሎች ፈጽመውታል ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር አስቀምጧል።
ይህ የድርጅቱ ሪፖርት የመንግሥት፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች መነጋገሪያ ሆኗል። እነዚህ ወገኖችም በሪፖርቱ ላይ የተለያዩ ትችቶችን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። የተነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተ የአምንስቲ ኢንተርናሸናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ተክሌ ለቢቢሲ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። የኦሮሚያ ክልል ቅሬታ የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አምነስቲ ያወጣው ሪፖርት ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል። ክልሉ ሪፖርቱን የማይቀበልበት አንዱ ምክንያት፤ በአራቱ ወለጋ ዞኖች እንዲሁም በሁለቱ የጉጂ ዞኖች ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ግድያዎችን እየፈጸሙ፤ በሪፖርቱ ሳይካተቱ ለምን ቀሩ በሚል ነው። አቶ ፍሰሃ ለዚህ ክስ መልስ ሲሰጡ ግለሰቦችም ሆኑ የታጠቁ ኃይሎች የሚፈጽሙት በወንጀል የሚታይ ነው በማለት፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚፈጸሙት ግን በመንግሥት ኃይሎች ነው ይላሉ። ሰለ ሰብዓዊ መብት ጥስት ስናወራ ስለ መንግሥት እያወራን ነው ያሉት አቶ ፍሰሃ የሰብዓዊ መብትን የማስጠበቅ ኃላፊነት የሚጫነው የመንግሥት አካላት ላይ መሆኑን አጽንኦት ሰትተው ኣስረዳሉ። "ግለሰቦች ወይም የታጠቀ ኃይል የሚፈጽመውን ወንጀል መንግሥት የመከላከል ኃላፊነት አለበት። አሁን ጥያቄው መንግሥት ይህን አድርጓል ወይስ አላደረገም ነው። ይህ የሚወስደን ደግሞ መንግሥት አላደረገም ወደሚለው ነው። ይህ ደግሞ ራሳቸውን መልሶ ተጠያቂ ነው የሚያደርገው። የታጠቁ ቡድኖች ወንጀል ሲፈጽሙ ሕግ ፊት የማቅረቡ ግዴታ የመንግሥት ነው። . . .'86 ሰዎች ግድያ አልተጠቀሰም ይላሉ' ይህ እኮ የመንግሥት ውድቀት ነው የሚያሳየው" ብለዋል። እአአ 2014 አምነስቲ ኢንተርናሽናል 'በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ- የአገሪቱ መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል ንጹሃን ዜጎችን ከታጣቂዎች ጥቃት መጠበቅ አለባቸው' የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር። በኡጋንዳም በአምነስቲ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ መግለጫ ወጥቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የታጠቁ ኃይሎች በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና በጉጂ የሚያደርሱት ጥቃት ለምን ሪፖርት አልተደረገም ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ ፍሰሃ "እነዚህ መግለጫዎች የሚሉት 'ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የሚፈጸሙ ጉዳቶችን መንግሥት የመከላከል ኃላፊነት አለበት' ነው። ከላይ በተጠቀሱ ሪፖርቶች ላይ ታጣቂዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል አላልንም። መንግሥት ጥቃቶችን መከላከል ባለመቻሉ ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም ነው ያልነው። በኢትዮጵያ ታጣቂዎች ይህን ያክል ሰው ገደሉ ሲባል፤ መንግሥት መከላከል አልቻለም የሚለው ነው የሚመጣው።" የአማራ ክልል ቅሬታ የአማራ ክልል ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ "ሪፖርቱ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው ነው፤ እውቅና አንሰጠውም" ብለዋል። የክልሉ ቃል አቀባይ ሪፖርቱ ተቀባይነት የለውም ያሉበትን ምክያት ሲያስረዱ፤ የቅማንት ብሄረሰብ አስተዳደር የራስ አስተዳዳር የመመስረት ፍላጎት ጋር ተያይዞ ግጭት ተከስቷል። በግጭቱም በአማራ እና በቅማንት ላይ ጉዳት ደርሷል። ይሁን እንጂ አምነስቲ በሁለቱም ህዝቦች የደረሰውን ጉዳት በእኩል ዓይን አላየም፣ የመንግሥት ኃይል ሰላም ለማስፈን የወሰደው እርምጃ የብሄር ጥቃት አድርጎ አቅርቧል ብለዋል። "የእርስ በእርስ ግጭት በራሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አይደለም" በማለት የሚጀምሩት አቶ ፍሰሃ፤ በግጭቱ ወቅት መንግሥት የወሰደው እርምጃ ምንድነው የሚለውን እንደተመለከቱ ይናገራሉ። "ባገኘነው መረጃ መሠረት የጸጥታ አካላት በዛ የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ግልጽ በሆነ መልኩ ለአንድ ወገን ወግነው ተሳትፈዋል።" ከዚህ በተጨማሪ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች ማድረግ ሲገባቸው ያላደረጉት አለ ይላሉ አቶ ፍሰሃ። "ለምሳሌ የአካባቢው ሠራዊት ጥሪ ሲደረግለት አልመጣም። ግጭት ያለማስቆም ሁኔታ ነበረ" ይላሉ። የአማራ ክልል ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት ላይ ያቀረበው ሌላኛው ቅሬታ፤ ከሰላም እና ደህንነት ቢሮ መረጃ ቢሰጣቸው መረጃው በሪፖርቱ ላይ በአግባቡ አልተካተተም የሚለው ነው። "ጥናት ሲካሄድ ብዙ የሚነገርን ነገር ይኖራል። ለጥናቱ ይጠቅማል፤ አይጠቅምም የሚለው መለየት አለበት። ከኃላፊው ጋር በተቀመጥንበት ጊዜ ከተነገሩን ለጥናቱ የሚሆኑን ነገሮችን ነው ያስገባነው" ብለዋል አቶ ፍሰሃ። የተለያዩ ግለሰቦች እና ቡድኖች ካነሷቸው ቅሬታዎች መካከል አማራ ክልል ተከትስቶ በነበረው ግጭት የህውሃት ተሳትፎ በሪፖርቱ ሳይጠቀስ አልፏል የሚል ይገኝበታል። የአማራ ክልል ከዚህ ቀደም ጎንደር አከባቢ ግጭት በተከሰተ ወቅት ህውሃት ለሚሊሻዎች ድጋፍ ያደርጋል ሲል መውቀሱንም ይጠቅሳሉ። አቶ ፍሰሃ ግን የቅማንት ሚሊሻዎች ከሌላ አካል ድጋፍ ስለማግኘታቸው የሚያሳይ መረጃ አላገኘንም ይላሉ። አክለውም በትክከል የህውሃትም ሆነ የሌላ አካል እጅ ስለመኖሩ የሚያሳይ ማረጋገጫ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል። 'የጥናቱ ተሳታፊዎች ምላሽ ሙሉ ምልከታን የሚሰጡ አይደሉም' ሌላ በአምነስቲ ሪፖርት ላይ የቀረበው ቅሬታ በጥናቱ ተሳታፊ የሆኑ ሰዎች ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው፤ ጥናት አድራጊዎች ተሳታፊዎቹን በሚገባ አልጠየቋቸውም የሚል ነው። እንደ ምሳሌ አንድ የጥናቱ ተሳታፊ 'የሸኔ አባል ነህ ተብዬ ጉዳት ደረሰብኝ ቢል' በሪፖርቱ ላይ ጥናት አድራጊው 'የሸኔ አባል ነህ?' ብሎ ሲጠይቀው አይታይም። ይህም የሪፖርቱ አንባቢያን ሙሉ ምልከታ እንዳያገኙ አድርጓል የሚል ነው። አቶ ፍሰሃ ግን በሪፖርቱ ላይ የተጠቀሱት ሰዎች ንግግር የተወሰደው ''quotations'' እንጂ ሙሉ ቃለ መጠይቁ አይደለም ካሉ በኋላ፣ "ዝርዝር ነገር ነው የምንጠይቀው፤ ተከታታይ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለጥናቱ ግብዓት ይሆናሉ የምንላቸውን ብቻ መርጠን ነው የምናወጣው" በማለት አምነስቲ መረጃ የሚሰበስብበት፣ የሚያደራጅበት እና የሚተነትንበት የራሱ የሆነ የተራቀቀ ስርዓት እንዳለው ይናገራሉ። አምነስቲ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ላይ በተለያዩ ስፍራዎች ከሚገኙ 80 ሰዎች የጥናቱ ግብዓት መሆናቸውን በሪፖርቱ ገልጿል። የጥናቱ ተሳታፊዎች የሚሰጡት መረጃ ትክክለኛነት በምን ታጣራላችሁ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ፍሰሃ፤ በሪፖርቱ ላይ 80 ሰዎች ይጠቀሱ እንጂ ከዛ በላይ ሰዎችን ነው ያናገርነው ብለዋል። በተጨማሪም ለጥናቱ አግባብ የሆኑ መረጃዎቸን የሰጡን ብቻ ነው ያካተትነው በማለት በሪፖርቱ በብዛት የተካተቱት ጉዳት የደረሰባቸው መሆናቸውን ይገልጻሉ። ይህንን ጥናት ካሄዱ ባለሙያዎች አንድን ከስተት ከሶስት እና ከአራት ሰዎች እንደሚሰሙ፣ አንዱ የተናገረውን ከሌላኛው ጋር መተዓጣም አለመጣጣሙን እንደሚመዝኑና እውነታውን ለይተው እንደሚያወጡ አስረድተዋል። ሪፖርቱ ስህተት ሆኖ ቢገኝ ማስተካከያ ታወጣላችሁ? ጠቅላይ አቃቤ ሕጓ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ትናንት ጠዋት በፌስቡክ ገጻቸው ላይ፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን መግለጫ መመልከታቸውን ገልፀዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጓ ጨምረውም፤ "የማጣራት ስራም ጀምረናል። ሪፖርቱ እውነት በሆነበት ልክ፣ መወሰድ ያለበቸውን እርምጃዎች እንወስዳለን። ሀሰት በሆነበት ወይም በተጋነነበት አኳያ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋራ በመወያየት ሪፖርቱ እንዲስተካከል እንጥራለን" ብለዋል። አምነስቲ ያወጣው ሪፖርት መንግሥት በሚያቀርበው ማስረጃዎች ስህተት ሆኖ ቢገኝ ማስተካከያ ታደርጋላችሁ ወይ? የሚለው ለአቶ ፍሰሃ ያቀረበነው ጥያቄ ነው። "በጣም አርግጠኛ ሆነን ያወጣነው ሪፖርት ነው። ግን መንግሥት የሚያደርገው ማጣራት በገለልተኛ እና አመቺ በሆነ መልኩ የሚካሄድ ከሆነ ለመቀበል ዝግጁ ነን። ዋነኛ ዓላማችንም መንግሥት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ማድረግ ነው" አቶ ፍሰሃ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ በሚወጡ ሪፖርቶች ላይ መንግሥት የተሻለ አስተያየት ይኖረዋል የሚል እምነት እንደነበራቸው ይናገራሉ። ከመንግሥት የተሰጡ ምላሾች ግን የቀድሞውን አስተዳደር የሚመስሉ መሆናቸውን በመጥቀስ "ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ያላቸው አመለካከት መቀየር አለበት። መሬት ላይ ያለውን ነገር ለመቀየር የሚረዳው ከድርጅቱ ጋር በቀና መንፈስ መነጋገር" መሆኑን ይገልፃሉ። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርትን በተመለከተ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ ሪፖርት ሚዛኑን ያልጠበቀና በአገሪቱ ያለውን ሁኔታ ከግንዛቤ ያላስገባ ነው በማለት "ሪፖርቱ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ቁንጽል የጸጥታ ሁኔታ ትንተና ነው" ሲል ተችቶታል። ጨምሮም የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን በመግታት የዜጎችን ህይወት ለማመታደግ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት ሪፖርቱ "ጊዜያዊ የፕሮፓጋንዳ ጥቅም ለማግኘት ሲባል ወረርሽኙ የደቀነውን ከባድ አደጋና ተጽዕኖ ችላ ያለ ከመርህ የራቀና ግዴለሽነት የታየበት ነው" ሲል ወቅሷል። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ተከሰቱ ስለተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ማጣራት እንደሚያደርግ ጠቅላይ አቃቤ ሕጓ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መግለጻቸው ተዘግቧል።
52831058
https://www.bbc.com/amharic/52831058
ዶናልድ ትራምፕ ለማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰጠውን ከለላ አነሱ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰጠውን የተወሰነ ሕጋዊ ከለላ የሚያነሳ ፊርማቸውን አኖሩ። ይህ የፕሬዝዳንቱ ፊርማ ተቆጣጣሪዎች ፌስቡክና ትዊተር ላይ ክትትል በማድረግ ህጋዊ ርምጃ እንዲወስዱ እድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።
ፕሬዝዳንቱ ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት ማህበራዊ ሚዲያዎች " ቁጥጥር የማይደረግበት አቅም" ነበራቸው ሲሉ ወንጅለዋቸዋል። ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ግን ህጋዊ ተግዳሮቶች ይገጥሙታል ተብሏል። የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ወይም የፍትህ አካሉ እነዚህ ተቋማት ያላቸውን የህግ ከለላ ለማንሳት ሊሳተፉ ይገባል። ትራምፕ የማህበራዊ ሚዲያዎችን የወግ አጥባቂዎችን ድምጽ በተደጋጋሚ ያፍናሉ ሲሉ ይወነጅሏቸዋል። ረቡዕ እለት ትዊተርን የፕሬዝዳንቱ ሰሌዳ ላይ ከተጻፈው ሐሳብ ሥር "የትራምፕ መልዕክት እውነታነት ሊጤን ይገባዋል" የሚል ምልክት ካደረገ በኋላ ምርጫ ላይ ጣልቃ ይገባል ሲሉ ወንጅለውታል። ድርጅቱ መልዕክቶቹ ዳግም ሊፈተሹ እንደሚገባ የሚገልጽ መልዕክት የሚያስቀምጥባቸው ተጠቃሚ የሐሰት ወይም ያልተረጋገጠ ሐሳብ ሲጽፍ መሆኑን ገልጿል። ትዊተር ሐሙሰስ እለት የቻይናው መንግሥት ቃል አቀባይ ኮሮናቫይረስ መነሻው አሜሪካ ነው የሚል ጽሁፍ መለጠፋቸወን ተከትሎ " ስለኮቪድ-19 ያለውን መረጃ እውነታነት ያጣሩ" የሚል ማስጠንቀቂያ ለጥፎበታል። ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተከታይ አላቸው።
news-56206403
https://www.bbc.com/amharic/news-56206403
ትግራይ፡ በአክሱም የሚጠቀሰው የሟቾች ቁጥር እኛ ከያዝነው በላይ ነው-አምነስቲ
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባካሄደው ምርመራ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም ከተማ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን መሰብሰቡን ይፋ ባደረገው ሪፖርት ላይ አስታወቋል።
የአክሱም ከተማ የአምነስቲ ኢንተርናሸናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ተክሌ፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአክሱም ሕዳር 19 እና 20 2013 ዓ.ም በሰብዓዊ ዜጎች ላይ ስለደረሰው ጭፍጨፋ ተቋማቸው ያወጣውን ሪፖርት በሚመለከት ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀናቸዋል። ቢቢሲ-ላለፉት ሁለት ወይም ሶስት ወራት የአክሱም ፅዮን ቅድት ማሪያም ቤተ ክስርቲያን ውስጥ 750 ሰዎች ተገድለዋል የሚሉ ክሶች ነበሩ። ይህም በአመታዊው የንግስ ዕለት እንደነበር በተለያዩ ቡድኖች እና ሰዎች ተገልጿል። የእናንተ ሪፖርት በቤተ ክስርትያኑ ውስጥ ይህ ስለመፈፀሙ የሚያሳየው ነገር የለም። መረጃው ስህተት ነበር ማለት እንችላለን? አምነስቲ- በማህበራዊ ሚዲያ በአክሱም ጽዮን ያለውን ጽላት የኤርትራ ወታደሮች ለመውሰድ ሲሞክሩ በተፈጠረ ግርግር የሰው ህይወት ጠፍቷል በሚል ሲሰራጭ የነበረውን መረጃ የሚያረጋግጥ መረጃ አላገኘንም። ይልቁንም ከተጠቀሰው ዕለት ቀደም ብለው ባሉት ሁለት ቀናት፤ ማለትም ኅዳር 19 እና 20 አስከፊ የተባለ ጭፍጨፋ መካሄዱን ነው ያረጋገጥነው። ኅዳር 19 የተወሰኑ የህወሓት ሚሊሻዎች አክሱም ጽዮን ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ካለች አንድ ተራራ ወይም ጉብታ ላይ ወደ ኤርትራ ወታደሮች ላይ በከፈቱት ተኩስ ግጭት ተቀስቅሶ ነበር። ይህ ካበቃ በኋላ እዛው የነበረው የኤርትራ ሠራዊት ሌላ ተጨማሪ ኃይል እና የጦር መሳሪያ ተጨምሮ (ታንኮችን ጭምር) ጥቃት ሰነዘሩ። በመንገድ ላይ ያገኙትን እና በየቤቱ እያገቡ ያገኙትን ጎረምሳ ወንዶች ሲገድሉ እደነበረ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። በማግስቱም [ኅዳር 20] ይህ ድርጊት ቀጥሎ ነበር። አስከሬን ማንሳንትም አይቻልም ነበር። ኅዳር 21 2013 ዓ.ም. በአክሱም ጽዮን ክብረ በዓል ዕለት ነው እንዲቀበሩ የተደፈቀደው። ስለዚህ የነበረው ይሄ ነው። በ 21 ትልቅ ግድያ እንደነበረ የሚያስረዳ ነገር የለም፤ ይልቁንም አስከሬን መቅበር የተጀመረውም በእዛው ዕለት ነው። ቢቢሲ-ስለዚህ ከዚህ ቀደም ከጽላቱ ጋር የተያያዘው መረጃ ትክክል አይደለም ብሎ መደምደም ይቻላል? አምነስቲ- አዎ። አክሱም ጽዮን ላይ ከፅላቱ ጋር በተያያዘ ያለመግባባት እንደነበረ ነግረውናል። ብዙዎቹ ሰዎች የሚሉት ይህ ግድያ ከተፈፀመ በኋላ ከነበሩት ቀናት በኋላ ነው ይህ ያለመግባባት የተከሰተው፤ ነገር ግን ወደ ግድያ አላመራም። የቤተ-ክስርቲያኑ አባቶች ‹‹ወደ ቤተ-ክርስቲኑ የምትገቡ ከሆነ ደወል (መረዋ) እንደውላለን፤ ሕዝቡ ግልብጥ ብሎ ይወጣል፤ ይህም ትልቅ እልቂት ይፈጥራል›› በማለታቸው ሳይገቡ መቅረታቸውን ተረድተናል። እንግዲህ አክሱም ውስጥ ያሉ ብዙ ትልልቅ ሰዎችን ነው ያናገርነው። ቢቢሲ-መረጃ እና ማስረጃዎቻችሁን የሰበሰባችሁበት ስልት እና ያመሳከራችሁበት ሂደት ምን ይመስል ነበር? አምነስቲ- በቁጥር ብዙ ያለው ሰው ነው ያናገርነው። 23ቱ ሰዎች ከአክሱም ወደ ሱዳን ሸሽተው የገቡ ናቸው። በተለይ የከባድ መሳሪያ ድብደባ፣ ዘረፋ እና ግድያ ሲካሄድ አክሱም ውስጥ የነበሩ እንዲሁም ቀብር ላይ የተሳተፉ ናቸው። ሌላው አክሱም ስልክ ሲከፈት 18 የሚሆኑ የሟቾች ቤተሰቦችን፣ የአክሱም ነዋሪዎችን እና ትልልቅ ሰዎችን አነጋግረናል። በዚህም ሂደት በቅድሚያ የሟቾችን የስም ዝርዝር ሰብስበናል። ይህም አንዱን ከሌላው በማስተያየት ለማረጋገጥ ሞክረናል። ምንም እንኳን እኛ ያገኘነው የስም ዝርዝር 240 አካባቢ ቢሆንም ቁጥሩ ከዚህ ሊልቅ ይችላል። ሌላው በተለያዩ ግዜያት የተወሰዱ የሳተላይት ምስሎችን ተጠቅመናል። በተለይም የከባድ መሳሪያ ድብደባዎችን እና ሰዎች የተቀበሩባቸውን ቤተ-ክርቲያናት ላይ አዳዲስ የመቃብር ቦታዎችን በእዛ ዕለት ላይ አሳይተውናል። ስለዚህ ይህንን ተጠቅመን ነው ለማረጋገጥ የሞከርነው። ቢቢሲ-የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሠራዊት አብረው የአክሱም ከተማን ተቆጣጥረዋል ይላል ሪፖርቱ። ይህ ኅዳር 10 ማለት ነው። ከዛ በኋላ ሪፖርቱ ስለ ኢትዮጵያ ሠራዊት የሚገልፀው ነገር የለም። ሠራዊቱ ድርጊቱን ለማስቆም ወይም በተቃራኒው ያደረገው ተሳትፎን የተመለከተ ማስረጃ አላገኛችሁም? አምነስቲ- ባገኘው መረጃ መሠረት አብረው [የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሠራዊት] ነው የተቆጣጠሩት። ከዛ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ሠራዊት እስከ ኅዳር 30 ድረስ አልታየም። ሙሉ በሙሉ የአክሱም ከተማ በቁጥጥር ስር የነበረው በኤርትራ ሰራዊት ስር ነበር። የተወሰኑ የመንግሥት ተቋማትን የኢትዮጵያ ወታደሮች እጅግ ባነሰ ኃይል ሆነው ሲጠብቁ እንደነበር ተረድተናል። በዋነኛነት የከተማውን ፀጥታ መቆጣጠር እና የማስተዳደር ስራ ይሰራ የነበረው የኤርትራ ሠራዊት እንደነበር ነው እማኞች የነገሩን። ስለዚህ በተለይ በ ኅዳር 19 እና ከዛ በፊት በነበሩት ግድያዎች እና ዘረፋዎች ላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት ተሳትፎ እንደነበራቸው የሚያሳይ ነገር አላየንም። ቢቢሲ-የተቋማችሁ ጥናት መደምደሚያ ላይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሠራዊት የአክሱም ከተማን ሲቆጣጠሩ የጦር ወንጀሎችን ፈጽመዋል የሚል ነገር ተካቶበታል። የዚህ ጦርነት አንድ አካል የነበረው ህወሓትን የተመለከተ ግን ምንም መረጃ የለውም። ይህ ሠራዊት የፈፀመው የጦር ወንጀል የለም? አምነስቲ- ይህ ጥናት የሚያስረዳው ስለ አክሱም ብቻ ነው፤ ይህ ማለት ሌላው አካባቢ ላይ የህወሓት ሠራዊት ወንጀል አልፈፀመም የሚል አይደለም። ነገር ግን በአክሱም ከተማ በህወሓት የተፈፀመ የጦር ወንጀል አላገኘንም። ያም ሆኖ ግን የእኛ ትልቁ ጥረታችን እነዚህ ተፈጽመዋል የተባሉ የጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ ተፈፅመዋል የተባሉ ወንጀሎች ላይ አስፈላጊ የሆነው ምርመራ በተባበሩት መንግስታት ተመርቶ እንዲደረግ ነው። ያ ምርመራ ሲደረግ በተለይ በአካል ቦታው ላይ ሆነን ስንመረምር ተጨማሪ ማስረጃ ይገኝ ይሆናል። አሁን ባለን ማስረጃ መሠረት ግን አክሱም ላይ ያንን የሚያመለክት ማስረጃ አላገኘንም። ቢቢሲ-በትግራይ ክልል ጦርነት ላይ የሚነሳ አንድ የዓለም አቀፍ የጦርነት ሕግ ጥሰት ጉዳይ አለ። ይህም በሁለቱም ወገን የደንብ ልብስ የማይለብሱ የሚሊሻ ኃይል ተሳትፎ ነው። በዚህ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎችን እና ከተዋጊዎች ለመለየት አስቸጋሪ አድርጎታል ይባላል። ይህ የእናንተ ሪፖርት ላይ የተጠቀሰው ቁጥር እና ተግባራት ጫና እንዳያመጣ ምን ጥንቃቄዎች አድርጋችኋል? አምነስቲ- ይህንን ከግምት ውስጥ ከተናል። ሚሊሻም ቢሆን አንድ አረንጓዴ ዩኒፎርም አላቸው። በነበረው ጦርነት ወቅት ልዩ ኃይሉም የራሱ መለያ ልብስ አለው። ነገር ግን የሞቱትን ሰዎች ስንመለከት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ህፃናቶች፤ ትልልቅ አዛውንቶች እና አልፎ አልፎም ሴቶች ከቤታቸው እየወጡ ነው የተገደሉት። ያ ዩኒፎርም አላደረጉም ተብሎ የሚያስገድል ነገር የለውም። ዩኒፎርም አለማድረግ የዓለም አቀፍ የጦርነት ሕግ ጥሰት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ዩኒፎርም ስላላደረጉ ነው ሰላማዊ ሰዎችን የገደልነው የሚለው ድርጊቱን አሳማኝ አያደርገውም ወይም አያስተባብለውም። አንደኛው ወገን ሕጉን ሰላላከበረ እኔም ሕጉን አላከብርም የሚል ምክንያት ውጤት አያመጣም። ቢቢሲ- ይህ ጥያቄ የተሰነዘረው የተፈጸመውን ድርጊት ያስተባብላል ሳይሆን ሲቪሎች ተብለው የተጠቀሱ የሟቾች ቁጥር ላይ እንዲሁም ድርጊቶች ላይ ጫና ካሳረፈ በሚል ነው። ከዛ አንፃር እንደ ውሱንነት ሊነሳ ይችላል? አምነስቲ- እኛ በደንብ ማረጋገጥ የቻልነውን እና ስማቸውን ማግኘት የቻልነውን ሲቪሎችን ነው የጠቀስነው። ከዛ ውጪ ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች ይኖራሉ። የሚጠቀሰው ቁጥር እኮ እኛ ከያዝነው የሥም ዝርዝር በላይ ነው። እኛ ከያዝነው የሥም ዝርዝር ውስጥ ሲቪል የለበሱ ተዋጊዎች ይኖሩ ይሆን የሚለውን ግን፤ እሱ ላይ እኛ ያረጋግጠነው ነገር የለም። ቢቢሲ- የእናንተ ጥናት የተገደበበትን ሁለት ቀናት ተነስተን ስናሰላ አሁን ሶተኛ ወር ላይ ነን። ከዛ በኋላ በአክሱም ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? የኤርትራ ሠራዊት አሁንስ በአክሱም አለ? ድረጊቱ ቆሟል? ከቆመስ እንዴት? አምነስቲ- ጥቃቱ የቆመው የኢትዮጵያ ሠራዊት ለአክስም ጽዮን ክብረ በአል ወደ አክሱም ከጋዜጠኞች ጋር ሄዶ ነበር። በዛ ግዜ ነበር በዋነኝነት ጥቃቱ የቆመው። ከዛ አንድ ቀን ቀድሞ በ20 ሽማግሌዋች የኤርትራ ሠራዊት አዛዥን ሄደው ጥቃቱንም እንዲያቆሙ የሞቱትንም እንዲቀብሩ እንደለመኗቸው እና ይህም በእለቱ ለነበረው ድርጊት መቆም ድርሻ እንደነበረው ያለን ማስረጃ ያስረዳል። የኢትዮጵያ ሠራዊት በጣም እንደደነገጡ የሚያሳይ ነገር አለ። ይህንን ተከትሎም ከአንድ ከሁለት ቀን በኋላ የአክሱም ከተማን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ተረድተናል። ይሄ ማለት ግን አክሱም አካባቢ ግን ጥቃቶች አልነበሩም ማለት አይደለም። ሪፖርታችን ላይ አላካተትነውም እንጂ አክሱም አካባቢ ላይ ሰላማዊ ሰዎች እየተገደሉ እንደሆነ እና ያንን የሚፈጽሙት የኤርትራ ወታደሮች እንደሆኑ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ። በዚህ ላይ ግን ብዙ ማለት አልችልም፣ ገና እየመረመርነው ስለሆነ። ቢቢሲ-የጥናታችሁ ምክረ ሃሳቦች ሁለት ናቸው። አንዱ የኢትዮጵያ መንግሥት የትግራይን በሮች ይክፈት የሚል ነው። ከትላንት በስቲያ የጠቅላይ ምስትሩ ጽ/ ቤት ይህንን መፍቀዱን የሚያሳይ መግለጫ ሰጥቷል። ይህ ከሪፖርታችሁ ጋር የሚገናኝ ይመስልዎታል? አምነስቲ- የሪፖርታችንን ግኝት ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ከመታተሙ ቀድመን አጋርትናል፤ እሱን አይተውት ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት እሱን መናገር አይልም። መንግሥት በተለይም 11 የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እንዲገቡ እና አንዲዘግቡ መፍቀዱን እና የተወሰኑትም እየሄዱ እንደሆነ እናውቃለን። ይህ ጥሩ መሻሻል ነው። መሄዱ ብቻ ሳይሆን በነፃነት ተንቀሳቅሰው መረጃ እንዲሰበስቡ እና ሪፖርት እንዲያደርጉ አስፈላጊው ትብብር ሊደረግላቸው ይገባል እላለሁ። ሌላው ሰብአዊ እርዳታ ለሚሰጡ ተቋማት ያለው የቢሮክራሲ ችግር ይታወቃል። በሱ ላይም እንደተባለው ለውጥ ተደርጎ ከሆነ ጥሩ ነው። ባለፈው በዚሁ ጉዳይ ላይ ትልቅ ዘመቻ አድርገን ነበር። ከዛ በኋላ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ስምምነት ላይ ደርሰናል፤ እንዲገቡ ተፈቅዷል ተብሎ ነበር። እነዚህ የሰብአዊ እርዳታ ተቋማት ግን ችግሩ እስካሁን እንደቀጠለ እየገለፁ ነው። ስለዚህ ያለው ሁኔታ ከተሻሻለ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ተከታትሎ የተባሉትን ነገሮች ተፈፅመዋል የሚለውን መከታተል ያስፈልጋል። ቢቢሲ- በሪፖርታችሁ ለተፈጸመው ጭፍጨፋ ፈጻሚ ብሎ የጠቀሰው የኤርትራ ሠራዊትን ነው። በምክረ ሃሳባችሁ ላይ ግን ለኤርትራ መንግስት ምንም ምክረ ሃሳብ አላስቀመጣችሁም። የህግ ባለሙያ እንደመሆንዎ፤ ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሚሆነው ማነው? አምነስቲ- ይህ ጥያቄ ውስብስብ ወደ ሆነ የሕግ ፅንሰ ሃሳብ ይወስደናል። ግን የሰብአዊ መብት ሕጎች ግዛት ላይ ያተኮሩ ናቸው። በአንድ አገር የግዛት ወሰን ውስጥ ለተፈጸሙ ተግባራት ተጠያቂ የሚሆነው ግዛቱን የሚያስተዳደረው መንግሥት ነው። ይህ አንግዲህ ዋናው መርህ ነው። ግን ግዛቱ ላይ ሙሉ ቁጥጥር የማይኖርበት ጊዜ ይኖራል። ለምሳሌ የውጪ ወረራ ሲኖር ወይም የእርስ በእርስ ጦርነት ሲኖር ያለው መንግሥት የተሟላ ቁጥጥር ወይም ስልጣን ሳይኖር ሲቀር የተቆጣጠረው አካል ተጠያቂ ይሆናል። አሁን በምንነጋገርበት ጉዳይ ግን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሠራዊት በጋራ በመሆን ህወሓትን የጋራ ጠላት አድርገው ነው እየተዋጉ የነበር። ስለዚህ የኤርትራ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ የገባው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን እና አንድ ላይ በመሆን ለመዋጋት ነው። በዚህ ምክንያት የኢትየጵያ ሠራዊት ውጤታማ ቁጥጥር አልነበረውም ማለት አይቻልም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ስለተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዋነኛ ሃላፊነቱን የሚወስደው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው። ስለዚህ አብሮት የሚዋጋውን የኤርትራን ሠራዊትም ቢሆን እነሱ በሚዋጉበት ግዜ የጦርነትንም ሆነ የሰብአዊ መብቶች ሕጎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ የማድረግ ሃላፊነት የኢትዮጵያ መንግሥት ነው። ቢቢሲ-ሪፖርቱ ሕብረተሰቡ ከህወሓት ወታደሮች ጋር እንደ ዱላ፣ ቢላ እና ድንጋይ ያሉ መሳሪያዎችን ተጠቀሞ የኤርትራ ሠራዊት ላይ ጥቃት ሰንዝሯል ይላል። ህወሓት የሰነዘረው ጥቃት ላይ የሲቪሎች ተሳትፎ ነበረው ? አምነስቲ- የሲቪሎች ተሳትፎ ነበረው። በተለይ የማይኮው ጥቃት ላይ የተወሰኑ ወጣቶች የእጅ መሳሪያዎችን ይዘው ተሳትፈው ነበር። ያ ግን ስልጠናም ሆነ መሳሪያ የሌላቸው ሰዎች ናቸው። ሌላም ከአክሱም ነዋሪ ሲቪል ወጣቶች ለህወሓት ሚሊሻ ምግብ የማቅረብ ነገር ነበር። በወቅቱ በዚያ ምክንያት የተገደሉ ሰዎች አሉ፤ ጦርነቱ ካበቃ በኋላም ቤት ለቤት እየሄዱ የመግደል ነገር ነበር። ቤት ለቤት እየሄዱ ብሎም በየመንገዱ ያሉትንም የመግደሉ ነገር በዛ ምክንያት ይመስላል። የህወሓት ሠራዊትን ደግፈው ዱላ ይዘው ምግብ ስላቀረቡ የዛ ብቀላ የሚመስል ነገር አለ። ቢቢሲ- እንዲህ ከሆነ ዓለም አቀፍ የጦርነት ሕጉ ተዋጊዎችን ከሲቪሎች የሚለይበት መንገድ አለ። በሪፖርታችሁ ለህወሓት ሠራዊት ምግብ ሲያቀርብ የነበረ ሰውን አነጋግራችኋል። በጦርነቱ ውስጥ አንዱን ቡድን በሎጂስቲክ ሲረዳ የነበረ ሰው እንደማነጋገራችሁ የሪፖርቱን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ አይከተውም? አምነስቲ- ይሄ ልጅ ከዛ ሁሉ ሰው አንድ ምስክርነት ነው። የሱ ምስክርነት አይደለም ሪፖርቱን የቃኘው። ሌሎች ሰዎችን አነጋግረናል፤ የበለጠ ሪፖርቱን ያቆሙት ሌሎቹ ሰዎች ናቸው። ስለዚህ የሱ ምስክርነት የሪፖርቱ ተአማኒነት ላይ የሚያመጣው ነገር የለም።
news-54384687
https://www.bbc.com/amharic/news-54384687
ዓይን ባንክ ለ2400 ዜጎች የብሌን ንቅለ ተከላ ተድርጎ ብርሃናቸው ተመለሰ አለ
የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ዓለም አቀፍ እውቅና አጊንቷል።
የዓይን ባንኩ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ቢሮ፣ ኮንኮርዲያ በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እና በቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ የሰዎችን ሕይወት ለማሻሻል በጥምረት ለሚሰሩ ስራዎች እውቅና በሚሰጡበት ፒስሪ ኢምፓክት አዋርድ (P3 IMPACT AWARD) እውቅና አግኝቷል። የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ውስጥ በብቸኝነት በአገር ውስጥ የዓይን ብሌን በመሰብሰብ ለንቅለተከላ ማዕከላት በማሰራጨት ለዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው። የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ በዚህ ዘርፍ አሸናፊ መሆን የቻለው ከቀረቡት አምስት እጩዎች መካከል የተሻለ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነም ተገልጿል። የዓይን ባንኩ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን በዓይን ብሌን ጠባሳ እና ተያያዥ ምክንያት የተከሰተውን ዓይነ-ስውርነት ለማጥፋት እያደረግ ባለው ጥረት እና አስተዋጽኦ ይህን እውቅና እንዳገኘ የድርጅቱ ደይሬክተር የሆኑት ለምለም አየለ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ''የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባደረጋቸው የቅንጅት ስራዎች ማለትም ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር፣ ዓይን ላይ የሚሰራ ሳይትላይፍ የተባለ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት እና ሂማላያን ካታራክት ፕሮጀክት በአንድነት ባደረጉት ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የዓይን ብሌን ጠባሳ አይነስውርነት ለመከላከል ባደረጉት የቅንጅት ስራ ነው ለ2020 የፒ3 ሽልማት የበቁት።'' የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ከ17 ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ አገልግሎቱን የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን ተጫማሪ አራት ቅርንጫፎችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍቶ እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሯ ነግረውናል። ''ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲተ ሆስፒታል፣ በትግራይ ክልል ቂሀ ሆስፒታል እና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና እንዲጀመር ተደርጓል'' ባለፉት 17 ዓመታት ውስጥም የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ለ2400 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የብሌን ንቅለ ተከላ ተከናውኖላቸው ብርሃናቸው እንዲመለስ መደረጉንም ለምለም አየለ ነግረውናል። በተጨማሪም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከህልፈታቸው በኋላ የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል እንደገቡ ገልጸዋል። በዓለም ዙሪያ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዓይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት የሚሰቃዩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ወደ 300ሺህ የሚጠጉት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ቢሮ፣ ኮንኮርዲያ የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እና ቨርጂኒያ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ ጠቁመዋል። ፒስሪ ኢምፓክት አዋርድ (P3 IMPACT AWARD) የሚባለው ሽልማት የሚሰጠው የህብረተሰቡን ችግሮች ለሚፈቱና እና ማህበረሰባዊ ግልጋሎት ለሚሰጡ የመንግሥት፣ የግል እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጥምረት ለማበረታታት ነው። ዳይሬክተሯ እንደነገሩን የዓይን ብሌን ጠባሳና ተያያዥ ችግሮች የሰው ልጆችን ሙሉ ለሙሉ ማየት የተሳናቸው ያደርጋሉ። ''ነገር ግን ይህ ሙሉ በሙሉ ሊድን የሚችል ነው'' ''ይህ ሊድን የሚችለው ደግሞ ሰዎች ከህልፈታቸው በኋላ በሚለግሱት የዓይን ብሌን አማካይነት ነው። ሰዎች ከሕልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለኢትዮጵያ ዓይን ባንክ እንዲለግሱ ይጠይቃል፤ ባንኩ ደግሞ የሚለገሱ የዓይን ብሌኖችን ሰብስቦ፣ ንጽህናውና ጥራቱን ጠብቆ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አረጋግጦ ህክምናውን ለሚያከናውኑ ተቋማት በማሰራጨት ሊድን በሚችል በሽታ አይነስውር ሆነው የተቀመጡ ዜጎችን ብርሀናቸው እንዲመለስ በማድረግ ላይ ነው የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የሚሰራው'' ይላሉ ለምለም አየለ። የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ እንዲህ አይነት አለም አቀፍ እውቅናን ማግኘቱ ትልቅ ትርጉም እንዳለውም ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። ''የህብረተሰቡ ግንዛቤ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ባለበትና የሰውነት አካል ልገሳም ሆነ ንቅለ ተከላ ባህል ባልዳበረበት ሁኔታ ነው የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ እየሰራ የሚገኘው። ስለዚህ ይህን ሽልማት ማግኘታችን ትልቅ ኩራት ነው። ለወደፊት ለምንሰራው ስራም ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለን እናስባለን።'' ደይሬክተሯ አክለውም እውቅናው በተለይ ደግሞ በአፍሪካ በዓይን ብሌን ልገሳና ንቅለ ተከላ ዘርፍ ፈር ቀዳጅ እንደመሆኑ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት ምሳሌ ለመሆንና የልቀት ማዕከል ለመሆን ለሚያደርገው ጥረት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ከ17 ዓመታት በፊት የተቋቋመ ተቋም ሲሆን ሲቋቋምም ዋና አላማው ሊድን በሚችል በብሌን ጠባሳና ተያያዥ ችግሮች የሚመጣ ማየት አለመቻልን ለመከላከልና ህክምናው በኢትዮጵያ እንዲጀመር ማድረግ ነበር። መሠረታዊ ስራውም ሕብረተሰቡን ስለ ብሌን ልገሳ ማስተማር፣ ከትምህርት ባሻገር ደግሞ ከሕልፈት በኋላ የተለያዩ ፈቃደኛ ሰዎችን የዓይን ብሌን መሰብሰብ ከዚያም ንቅለ ተከላውን ለሚያከናውኑ የሕክምና ተቋማት ማሰራጨት ነው።
news-45004239
https://www.bbc.com/amharic/news-45004239
አካል ጉዳተኛነት፡ ትኩረት የተነፈገው የብዙ ኢትዮጵያውያን እውነታ
ኬንያዊቷ አን ዋፉላ ስትራይክ ታዋቂ የፓራሊምፒክ ተወዳዳሪ ስትሆን የሕይወትታሪኳን በመጽሐፍና በዘጋቢ ፊልም ለሕዝብ አቅርባለች። የዛሬ 47 ዓመት የሁለት ዓመት ህጻን እያለች በያዛት የልጅነት ልምሻ (ፖልዮ) ምክንያት አካል ጉዳተኛ የሆነችው አን በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፋ ስኬትን እንደተጎናፀፈች ዛሬ በሙሉ ልብ ትናገራለች።
ኢትዮጵያውያን አካል ጉዳተኞች እንደ አን ጥሩም ሆነ መጥፎ ተሞክሯቸውን የሚናገሩት መቼ ይሆን? ኢትዮጵያ ውስጥ አካል ጉዳተኛ መሆን ምን ማለት ነው? በትምህርትም ሆነ በሥራ ዓለም ምን ዓይነት ውጣ ውረድስ ይገጥማቸዋል? አካል ጉዳትና ኢትዮጵያውያን ''እንደ ዕድል ሆኖ በቤተሰቤም ሆነ ባደግኩበት ሰፈር በአካል ጉዳተኛነቴ የደረሰብኝ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አልነበረም። እንዲያውም አካል ጉዳተኛ መሆኔንም አላውቀውም'' የሚለው አንዱዓለም ከበደ አንድ እጁና ሁለት እግሮቹ ጉዳተኛ ናቸው። ከሚያከናውናቸው ተግባሮችና በአካባቢው ከነበረው ተቀባይነት የተነሳ አካል ጉዳትኝነቱን የዘነጋው አንዱዓለም፤ ብዙ አካል ጉዳተኛ ጓደኞቹ ግን ስለሚገጥሟቸው የተለያዩ ችግሮች እንደሚነግሩት ይገልጻል። • ''እግሬን ባጣም ትልቁን ነገር አትርፌ ለትንሹ አልጨነቅም'' • ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ? መላኩ ተክሌ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማዕከል በመባል የሚታወቀው መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ነው። መላኩ አካል ጉዳተኛ ሲሆን ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር ክራንች ይጠቀማል። የሚሠራበት ድርጅት አካል ጉዳተኞች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እንዲሳተፉ ለማድረግ የሚተጋ ነው። ከሥራዎቻቸው መካከል አካል ጉዳተኞችን የሚያካትት ትምህርት፣ ጤና፣ መተዳደሪያና የማህበረሰብ ልማት ይገኙበታል። ድርጅቱ በአጠቃላይ ወደ 48 ሠራተኞች አሉት። ከሠራተኞቹ መካከል ደግሞ 20ዎቹ አካል ጉዳተኛ ከእነሱም ውስጥ 19ኙ ሴቶች ናቸው። የአካቶ ትምህርት ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆነቸው እመቤት ግርማ ''ሴት አካል ጉዳተኞች በሁሉም መስኮች እኩል መካተታቸውን ለማረጋገጥ እንጥራለን። ይህም ደግሞ በሚሰጡ ሥልጠናዎችም ሆነ በማንኛውም አገልግሎት ቢያንስ 50 በመቶ ሴቶች እንዲሆኑ ይጠየቃል'' ትላለች። እንደ ኢትዮጵያ እያደጉ ባሉ ሃገራት ውስጥ አካል ጉዳተኛ ለሆነ ሰው ብዙ አዳጋች ነገሮች አሉ የምትለው እመቤት፤ ፈተናዎቹ ለሴት አካል ጉዳተኞች እጥፍ እንደሚሆኑ ትጠቁማለች። ትምህርት ካለማግኘት አንስቶ እስከ ሥራው ዓለም ድረስ ለአካል ጉዳተኞች ብዙ የሚከብዱ ነገሮችን ታነሳለች። ለአካል ጉዳተኞች ተብለው የሚዘጋጁ የትምህርት ማሟያ መጻሕፍት አቅርቦትና የትምህርት ዕድል የማግኘት አጋጣሚው በጣም ጠባብ በመሆኑ በትምህርታቸው ገፍተው የሚሄዱ የአካል ጉዳተኞች ቁጥር እየመነመነ እንደሚመጣም ታስረዳለች። የመረጃና የምቹ አገልግሎቶች ውስንነት? በቅርቡ በእንግሊዟ ለንደን ከተማ አለም አቀፍ የአካል ጉዳት ጉባኤ ተካሂዶ ነበር። በጉባኤው ላይ ከተነሱ ነጥቦች አንዱ የአካል ጉዳተኞች ቁጥር አለመታወቁ ተጠቅሷል። አቶ መላኩ ተክሌ እንደሚሉት ከዓመታት በፊት በወጣው የተባበሩት መንግሥታት የአካል ጉዳተኞች ሪፖርት መሠረት፤ በዓለም ላይ ካሉት 1 ቢሊዮን አካል ጉዳተኞች መካከል 15 በመቶዎቹ በታዳጊ ሃገራት ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 15 በመቶ የሚሆኑት በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ''በማህበረሰቡ ዘንድ በቂ መረጃ የለም'' የምትለው እመቤት፤ ብዙ አካል ጉዳተኞች ከልጅነታቸው ጀምሮ እንደሚገለሉ ታክላለች። በየቤቱ ተደብቀው የሚያድጉ አካል ጉዳተኛ ልጆች ከማህበረሰቡ ጋር ከተቀላቀሉ በኋላ መድሎና መገለል ይደርስባቸዋል። ብዙ ሁኔታዎችም አልጋ በአልጋ አይሆኑላቸውም። ''እነዚህ ችግሮች ሁሉንም አካል ጉዳተኞችን የሚያጋጥሙ ቢሆኑም በሴቶች ላይ ግን ይብሳል። ከቤት መውጣት አይፈቀድላቸውም እንደውም እርባና እንደሌላችው ይቆጠራሉ። እነዚህን ተግዳሮቶች ቢያልፉ እንኳን አካባቢያቸው ምቹ አይሆንም'' ትላለች። ባለሙያዎች ከዚህ በተጨማሪም አካል ጉዳተኞች ለራሳችው ያላችው ዝቅተኛ አመለካከትም ይጨመርበታል ይላሉ። "አቅማቸውን እንዲጠራጠሩ ይደረጋሉ" የምትለው እመቤት ለአካል ጉዳተኞች በቂ መረጃ አለመኖሩም ችግር መሆኑን ትገልጻለች። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" አቶ ረታ ጌታችው በእንግሊዝ ሃገር ሊድስ ከተማ የማስተርስ ዲግሪውን በአካል ጉዳት ላይ እያሰራ ሲሆን እሱም ''ይህች ዓለም የአካል ጉዳት ለሌለባቸው ሰዎች ምቹ ሆና የተሠራች ናት'' ይላል። አቶ ረታ አካል ጉዳተኛ ባይሆንም ለአካል ጉዳተኞች ጉዳይ በቂ ቦታ አለመሰጠቱ ኢ-ፍትሐዊ ነው ይላል። ከመረጃ አንስቶ እስከ መንገድና የሃገር ኢኮኖሚ ድረስ አካል ጉዳተኞችን የማካተት ሥራ መሰራት አለበት ይላል። አክሎም አካል ጉዳተኞች ያሉበት ቦታ በበቂ ሁኔታ አይታወቅም ይላል። በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው መገለል ለማስረዳት አካል ጉዳተኛ ልጅ እንዳላቸው ለማሳወቅ እንኳን የሚያሳፍራቸው ወላጆች እንዳሉ ይገልፃል። ''እነሱም ላይ አልፈርድም። ምክያቱም ከዚህ ቀደም አካል ጉዳተኛ ልጅ እንዳላችው ያሳውቁ ሰዎች ብዙ ችግር ሲደርስባቸው አይተዋል'' ይላል። ወሲብና አካል ጉዳተኝነት አቶ መላኩ ''የጤና ባለሙያዎች ከሕብረተሰቡ የወጡ እንደመሆናቸው፤ አካል ጉዳተኞች ወይ ለወሲብ ብቁ እንዳልሆኑ አለበለዚያም ከመጠን ያለፈ ፍላጎት እንዳላቸው አድርገው ያስባሉ'' በማለት ያሉትን ሁለት ጽንፍ አመለካከቶች ይጠቅሳሉ። አያይዘውም የጤና ተቋማት የተለያየ አካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎችን እንደ ጉዳታቸው አይነት ሊያስተናግዱ የሚችሉበት መንገድ እንዲዘረጉ ይጠቁማሉ። "መስማት ቢሳነኝም ከእርስዎ በላይ ብዙ ቋንቋ እችላለሁ" አቶ ረታ ስለ ወሲብ ሲነሳ ተያይዞ ስለሚያጋጥመው ያልተፈለገ እርግዝናም እንደ ሃገር ሊወራበት ይግባል ይላል። "በኢትዮጵያ ይህ ጉዳይ አስቸኳይ ሆኖ አይታይም። ምክንያቱም በመጀመሪያ ድህነትን ማሸነፍ አለባቸው የሚል አመለካከት አለ"። ሲል ይገልጻል። መሠረት ይርጋ ከአካል ጉዳተኞች ጋር የዳንስ ቡድን በማቋቋም በእንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን በራሳቸው እንዲተማመኑ ለማድረግ እንደሚሠሩ ትናገራለች። ከሷ የዳንስ ቡድን ውስጥ ሁለቱ አካል ጉዳተኛ ሴቶች አራቱ ደግሞ ወንዶች እንደሆኑ የምትናገረው መሠረት፤ በየጊዜው ስለሚያጋጥሟቸው እክሎች እንደሚወያዩም ትገልፃለች። እንደ ምሳሌ ከምትጠቅሳቸው ገጠመኞች በአንዱ፤ ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች አካል ጉዳተኛ ተማሪዋ ተደፍራ ላልተፈለገ እርግዝና ትዳረጋለች። ሰውነቷ እርግዝናውን ለመቋቋም ቢቸገርም ወልዳ ልጇን ለመሳም በቅታለች። ወልዳ መደሰት የቻለችው የመሠረትና ሌሎችም በዙሪያዋ የነበሩ ሰዎች ጥረት ታክሎበት ነው። መሰረት ወደኋላ መለስ ብላ ስታስታውስ ተማሪዋ ራሷን ለማጥፋት ሁሉ ታስብ እንደነበረ ትናገራለች። ''በጣም የሚያሳዝነው ወደ ጤና ጣቢያ ይዘናት በሄድንበት ወቅት ብዙ የጤና ባለሙያዎች 'ቢቀርባትስ' በማለት ሲያጉረመርሙ ነበር'' በማለት ስሜትን የሚጎዳውን አስተያየት ትጠቅሳለች። ኢትዮጵያ ውስጥ በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ መሠራት ያሉባቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ አቶ ረታ አስረግጠው ይናገራሉ። መሠረትም ይቀራሉ ከምትላቸውን ነጥቦች መካከል ግንዛቤ መፍጠርን በዋነኝነት ታስቀምጣለች። "በአለም ዙሪያም ገና ብዙ የሚቀሩ ጉዳዮች አሉ። ኢትዮጵያ እንደ አገርና ኢትዮጵያውያን እንደ ማህበረሰብ ከበፊቱ በተሻለ ለአካል ጉዳተኞች ምን ዓይነት ቦታ መሰጠት እንዳለበት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል" ይላሉ አቶ ረታ።
news-52000796
https://www.bbc.com/amharic/news-52000796
ልንቀበላቸው የማንችላቸውን ነገሮች እንድንቀበል ግፊት ሲደረግ ነበር ፡ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
ኢትዮጵያ እገነባችው ባለው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለዓመታት ሲደረግ የነበረው ድርድር እስካሁን መቋጫ ሳያገኝ ቆይቷል። ተስፋ ተጥሎበት የነበረውና አሜሪካና የዓለም ባንክን ያካተተው ድርድር ታሰበውን ውጤት ሳያሳካ በመጨረሻው ላይ ኢትዮጵያ ጥቅሜን የሚነካ ነው ያለችውን ሰነድ ሳትፈርም በእንትልጥል ቀርቷል።
ይህ ዋሽንግተን ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ድርድር ግብጽን የሚደግፍ ኢትዮጵያ ላይ ደግሞ ጫናን የሚያሳድር እንደነበረ በስፋት ሲነገር ቆይቷል። በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል ሲካሄድ ስለቆየው ድርድር የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙርያ በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል ውይይቶች ሲከናወኑ መቆየታቸውይታወቃል። እነዚህ ውይይቶች ምን ደረጃ ላይ ነው ያሉት? አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፡ የሕዳሴ ግድብ የድርድር ሒደት አሁን ወደ መጨረሻ አካባቢ ደርሷል። ይህ የድርድር ሒደት የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ አንስቶ የነበረ ነው። ግድቡን እንደጀመርን ግብጾችና ሱዳኖች የሚያሳስበን ጉዳይ አለ የሚል ጥያቄ በማነሳታቸው ግድቡ የታችኞቹ አገራትን የመጉዳት ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት መሆኑን ለማስረዳት ሞክረናል። ከዚህ አኳያ የታችኞቹ ተፋሰስ አገራት ይህንን እንዲያውቁትና ውይይቶች እንዲካሄዱ፣ ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች ካሉ ግልፅ እንዲሆኑ፣ የሚያስፈልግ ጥንቃቄ አለ የሚሉትም ጉዳይ ካለ ለዚህ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ በጣም ግልፅ በሆነ መንገድ ነው ኢትዮጵያ አቅዳ ግድቡን የጀመረችው፤ ከዚያ እነርሱ ጥያቄ ሲያነሱም ወደ ውይይት ያመራችው። ግድቡ እንደተጀመረ ከጥራቱ ጋር በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል፣ አይኖረውም በሚለው ጉዳይ ላይ የግድቡን ደኅንነት በተመለከተ ጥያቄዎችን ሲያነሱ ይህንን ለማረጋገጥ ከአውሮፓ የጀርመን፣ የፈረንሳይ፣ የእንግሊዝ አንዲሁም ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካ፣ የግብፅ፣ የሱዳን እና የኢትዮጵያ ባለሞያዎች እንዲገምግሙት ኢትዮጵያ ዝግጁ ሆናለች። ከዚያ በኋላ በተለያዩ ዙሮች በተለያዩ አካላት ድርድሮች ሲካሄዱ ቆይቷል። ድርድሩ አንዳንድ ጊዜ ደህና ሲሄድ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲቋረጥ እ.ኤ.አ እስከ መስከረም 2018 ድረስ ሲከናወን ቆየና መስከረም ላይ አንድ ደረጃ ላይ ተደረሰ። ለመፈራረም ዝግጁ ሆኖ እንፈራረም ሲባል የግብጽ ተደራዳሪዎች አሁን አንፈራረምም አገራችን ሄደን መመካከር አለብን ብለው ለፊርማ የተዘጋጀን ሰነድ ትተው ሄዱ። በእርሱ ምክንያት ተቋርጦ ቆየ፤ ቀጥሎም ሱዳን ውስጥ አብዮት ተነሳ። በኋላ እ.ኤ.አ. ኦገስት አንድ 2019 ግብጾቹ ድርድሩን ለማስቀጠል የሚያስችል ረቂቅ ሃሳብ አለን ብለው ይዘው ቀረቡ። ይህ ሃሳብ ግን ከዚያ ቀደም ከነበሩ ድርድሮች ጋር ግንኙነት ያልነበረው ነው። ኢትዮጵያ የውሃ መጠን ዋስትና ትስጠን የሚል እንዲሁም አስዋን ግድብ በሚጎድልበት ጊዜ በሚሞላበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ላይ እንድረስ የሚሉ ተቀባይነት የሌላቸውን ሃሳቦችን ይዘው ቀረቡ። ይሄንን ተከትሎ ኢትዮጵያም የራሷን፣ ሱዳንም የራሷን ሃሳቦች ይዘው መስከረም 2019 ድርድር ተጀመረ። በተወሰኑ ጉዳዮች ስምምነት ሲኖር፣ በተወሰኑት ላይ መፋጠጥ ሲመጣ፣ የግብጽና የኢትዮጵያ መሪዎች ሩሲያ፤ ሶቺ ውስጥ ተገናኝተው የቴክኒክ ውይይቱ እንዲቀጥል ተስማሙ። በዚህ መኃል የአሜሪካ መንግስት ድርድራችሁን ላግዛችሁ የሚል ጥያቄ አቀረበ። እኛም ግብዣው ሲቀርብልን ወደዚያው ሄድን። የአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ እያገዙ ዋነኞቹ ተደራዳሪዎች ማለትም ሦስቱ አገራት ደግሞ በነጥብ በነጥብ እየተወያዩ ብዙ ልዩነቶችን ማጥበብ ተቻለ። ወደ መጨረሻው ግን ስምምነት ላይ ሙሉ በሙሉ ሳንደርስ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ እንፈራረምም የሚል ሃሳብ ይዘው ቀረቡ። ስምምነት ሳያልቅ ልዩነት ባለን ጉዳዮች ላይ እንድንፈራረም ማድረጉ ተገቢነት የለውም ብለን ነገርናቸው። ይህ በዚህ እንዳለ ሌላ ዙር ውይይቱ ቀጠለ። አሁንም ያንኑ አቋም ያዙ። ይሄኔ የአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስትር 'እናንተ መስማማት ስላልቻላችሁ እኔ በዓለም ባንክ አጋዥነት ሁላችሁንም የሚያስማማ የስምምነት ሰነድ አዘጋጅቼ አቀርባለሁ' አሉ። 'ይህ በፍፁም አይሆንም፤ ተደረዳሪዎቹ እኛ ነን። እኛው ተደራድረን፥ ተነጋግረን መፍታት ነው ያለብን እንጂ፤ ሌላ ወገን አዘጋጅቶ በዚህ ተስማሙ ብሎ የሚሰጠን ከሆነ እኛ አንቀበለውም' አልን። በተለይ ግብጾቹ ወዲያውኑ እንቀበለዋለን አሉ። እኛ ደግሞ እንደዚህ ያለ አሰራር መርኅን የተከተለ አይደለም። መጀመሪያ የተነሳንበትን ዓላማ የሚያሳካ አይደለም። አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ታዛቢዎች ናቸው እንጅ ፅሁፍ አዘጋጅተው ለእኛ የሚያቀርቡ አይደሉም። ሚናቸው ተቀላቅሏል፤ ድርድሩ አቅጣጫውን ስቷል። በዚህ ዓይነት አካሄድ እኛ ልንገባ አንችልም' የሚል ሃሳብ አቀረብን። በዚህ ምክንያት ድርድሩ አሁን ቆሟል። በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ከድርድሩ ጋር በተገናኘ ከዚህ በኋላ ምንድን ነው የሚጠበቀው ? አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፡ እኛ ተደራድሮ መስማማት ይቻላል ብለን እናምናለን። ለዚህ ግን ከግብጾች የሚጠበቅ አንድ ነገር አለ። ይህ ውሃ የኢትዮጵያም፣ የግብፅም፣ የሱዳንም ስለሆነ ኢትዮጵያ በዚህ ውሃ የመጠቀም መብቷ የተከበረ ነው ብለው አምነው በጋራ ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የጥቁር አባይን ውሃ ለመጠቀም ዝግጁ እስከሆኑ ድረስ ሌላ አሸማጋይም ሳያስፈልግ መስማማት ይቻላል። በሚያለያዩ ጉዳዮች ላይ መነጋገር ይቻላል። ስምምነት መድረስ የማይቻለው አንዱ የሌላውን መብት ሲክድ ነው፤ በተለይ በግብጽ በኩል የቅኝ ግዛት ዘመንን ውርስ ለማስቀጠልና እ.ኤ.አ በ1959 ከሱዳን ጋር የተፈራረሙትን ኢፍትሃዊ የሆነ የውሃ ድርሻን ጠብቆ ለማስቀጠል የሚያስችል ስምምነት ለመድረስ የሚያደርጉትን ሙከራ ማቆም ይኖርባቸዋል። ከዚህ ባሻገር ከውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ጋር የተያያዙ እንዲሁም መሰል ጉዳዮች ላይ የታጠረ ንግግር አድርጎ መስማማት እስከተቻለ ድረስ በኢትዮጵያ በኩል መቼውንም ቢሆን በራችን ክፍት ነው። ሌላ አካል ረቂቅ አቅርቦልን፣ በዚያ ረቂቅ ላይ መደራደር ሳይሆን እኛው የየራሳችንን ፍላጎት በሚያንፀባርቅ መንገድ አንድ በአንድ ተነጋግረን ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል። በዚህ ድርድር ላይ የአሜሪካን እና የዓለም ባንክን ተሳትፎ እንዴት ገመገማችሁት? የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያ ስምምነት እንድትፈርም ጫና ለማሳደር ሞክሯል የሚሉ ዘገባዎች ወጥተው ነበርና በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ምልከታ ምን ይመስላል? አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፡መጀመሪያ አካባቢ አሜሪካኖቹ በታዛቢነት በድርድሩ ተራርቀው የነበሩ አቋሞችን እያጠበብን እንድንመጣ አግዘውናል። ይሄ የሚካድ አይደለም። ነገር ግን በሒደት አሜሪካኖቹ ድርድሩ ቶሎ እንዲቋጭ ፈለጉ። ድርድሩ ቶሎ አልቆ አንድ ትልቅ ነገር እንደቋጩ አድርገው ለማየት ፈለጉ። በእኛ በኩል ደግሞ ይሄ የአባይ ስምምነት በአሁኑ ትውልድ ብቻ ሳይሆን በመጪው ትውልድም ላይ የራሱ ተፅዕኖ የሚኖረው ስምምነት ስለሆነ በጥንቃቄ መታየት አለበት ብለን ነው የምናመነው። 'በጥድፊያ መሆን የለበትም፤ እንደገና ደግሞ በድርድሩ ሒደት ዋነኞቹ ተዋናዮች መሆን ያለብን ባለቤቶቹ ሦስቱ አገራት ነን፤ በመሆኑም የእናንተ ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ በእኛ ላይ ማሳደር ፍትሃዊ የሆነ ስምምነት ላይ እንድንደርስ አያደርገንም' የሚል ነው ልዩነታችን። መጀመሪያ አካባቢ በሄዱበት አካሄድ በሰከነ መንገድ ሦሰቱም አገራት በየራሳቸው ከሚለከታቸው አካላት ጋር እየተመካከሩ ስምምነት ላይ መድረስ የሚቻልበት ዕድል ነበረ። ነገር ግን በአቋራጭ አንዳንዶቹን በፍፁም እኛ ልንቀበላቸው የማንችላቸውን ነገሮችንም እንድንቀበል ግፊት ማድረጉ እየተጠናከረ ሲሄድ ይሄ ልክ አይደለም አልናቸው፤ እነርሱ ደግሞ መስማማት አለባችሁ የሚል አቋም ያዙ። ወደመጨረሻ አካባቢ ሙሉው የአሜሪካ መንግሥት ብዬ ለመውሰድ ባልችልም በተለይ የገንዘብ ሚኒስትሩ (የትሬዠሪ ዲፓርትመንት ኃላፊው) ግፊታቸውን ጠንከር እያደረጉ መጡ። ይሄ ደግሞ ትክክል አይደለም፤ ተቀባይነትም የለውም። ስለዚህ ኢትዮጵያ አሜሪካ ወይንም የዓለም ባንክ ወደ አደራደሪነት ቢመለሱ ችግር አይኖርባትም ማለት ነው? አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፡ማንኛውም የሚካሄድ ድርድር በመርኅ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት የሚል እንጂ፤ ኢትዮጵያ በአደራዳሪነት ማን መጣ? ማን ሄደ አይደለም ዋናው ጉዳዩዋ። ይህ ድርድር ደግሞ ሦስቱን ባለጉዳይ የሆኑትን አገራት የሚተካ መሆን የለበትም። እንዲህ ያለ ሙከራ ጠቃሚ የሆነ ድርድር ላይ እንድንደርስ አያደርገንም። ለወደፊቱም ጠንቅ ጥሎ የሚያልፍ ድርድር ነው የሚሆነው። ሌሎች ሊያግዙን ይችላሉ፤ ሊደግፉን ይችላሉ። እኛን ሊተኩን ግን አይችሉም። ግብጽ ዘጠና ከመቶ ገደማ የንፁህ ውሃ ፍላጎቷን የምታሟላው ከአባይ ውሃ ነው። ስለዚህ ግድቡ የውሃ ፍላጎቴ ላይ አደጋ ይጋርጣል የሚል ስጋት አላት። ይህንን ስጋቷ ተገቢ አይደለም? አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፡ግብጾች እኛ ፍትሃዊ አይደለም ያልነውን ስምምነት እንድንፈርም ይፈልጋሉ። እኛ ደግሞ የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ ስለሆን አንፈርምም ብለናል። ይህንን መሰረት አድርገው የተለያዩ ዘመቻዎች እያካሄዱ ነው። ይህ ዘመቻ ይሳካላቸዋል፣ አይሳካላቸውም ሌላ ጉዳይ ሆኖ፤ የያዙት መንገድ ግን ትክክል አይደለም የሚል እምነት አለን። እኛ ተደራድረን ችግሩን ማቃለል ስንችል፣ በዲፕሎማሲ ጫና፣ በተለያየ መንገድ በሚደረግ ግፊት ኢትዮጵያ የሚጎዳትን ስምምነት ትፈርማለች ብለው እያሰቡ ከሆነ ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነገር ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ የማንንም ጥቅም አልተጋፋችም። የማንንም ጥቅም አትጋፋም። ይህ ግድብ እየተገነባ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። በዚህ ግድብ የሚከማቸው ውሃ ከኢትዮጵያ መንጭቶ የሚከማች ነው፤ የኢትዮጵያን የራሷን ድርሻ ነው እንጂ የግብጽን ድርሻ አይደለም የምታከማቸው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ድሃውም ሳይቀር አዋጥቶ እየተሰራ ያለ ግድብ ነው። ይህንን ግድብ በሚመለከት የሚደረግ ስምምነት የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም በሚያረጋግጥ መልኩ ካልሆነ በስተቀር በሌላ በማንኛውም ጫና፣ በማስፈራራት በመሳሰለው የማይሆን ነው። የሚሻላቸው ከወንድሞቻቸው ጋር ተመካክሮ ጉዳዩን ለማቃለል መሞከር ነው። የኢትዮጵያ ዓላማ አባይን የግጭትና የንትርክ አጀንዳ ማድረግ አይደለም። እርሱ ያለፈና ኋላቀር በሆነ አኳኋና ሲሄዱበት የነበረው ነው። አባይ የትብብር ምንጭ እንዲሆን ነው የኢትዮጵያ ፍላጎት። ግድቡ የሚያመነጨው ኃይል ለኢትዮጵያም፣ ለሱዳንም ከፈለጉ ለግብጾችም ሊሆን የሚችል ነው። ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ ደፋ ቀና እያለች ያለች አገር ናት። ብቻዋን ሳይሆን ከጎረቤቶቿ ጋር ተሳስራ ለማደግ ነው እየሰራች ያለችው። በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ አባይ የትብብር ምንጭ፣ የትብብር ወንዝ እንዲሆን ነው ፍላጎታችን። የግብጾች ብዙ ቦታ መንቀሳቀስ ብዙ ጥቅም ያለው አይመስለኝም።
news-53847303
https://www.bbc.com/amharic/news-53847303
ጥቁር ቆዳ ውበት ነው ካልን ለምን ፈጣሪ ቀይ እንዲያደርገን እንጸልያለን?
ጥቁር መሆን ውበት ነው የምንለው እውነት ነው ወይስ ስናስመስል?
‹ከለሪዝም› ይሉታል እነሱ፡፡ እኔ ለዚህ ጽሑፍ መግባቢያነት ‹‹የቅላት ዘረኝነት›› እንድለው ፍቀዱልኝ፡፡ በአንድ ኅብረተሰብ ውስጥ ቆዳው ‹ፈካ፣ቀላ፣ነጣ› ላለ ሰው የሚሰጥ ሻል ያለ ቦታ ነው የቅላት ረዘኝነት፡፡ ለዚያ ሰው የሚሰጠው ከፍታ እንዴት ይለገጻል? በብዙ መልኩ፡፡ በአመለካከት ብቻ አይምሰላችሁ፡፡ ሁለመና ነው ነገሩ፡፡ ዕድል፣ ሥራ፣ መወደድ፣ ቁንጅና፣ ቅቡልና ወዘተ…፡፡ ጠቆር የምትል ሴት ስትወለድ፣ ‹‹አይ…! ይሁን መቼስ ምን ይደረጋል?›› የሚል ማኅበረሰብ፣ የቅላት ዘረኝነት ተጠቂ ነው፡፡ ቢያስተባብለውም፣ ባያስተባብለውም፡፡ አብዛኛው የዓለም ማኅበረሰብ በዚህ ‹የቅላት ዘረኝነት› የተበከለ ነው፡፡ ለምሳሌ ሐርሻሪን እንስማት፡፡ ኒው ዚላንድ ነበር የምትኖረው፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ ሕንድን ስትጎበኝ ደነገጠች፡፡ ሕዝቡ በሙሉ ቆዳውን ፈቅፍቆ ቢያነጣው ደስ የሚለው ዓይነት ነው፡፡ ሐርሻሪን ቤተሰቦቿ ከሕንድ ናቸው፡፡ እዚያ በሄደችበት የምታየውን ማመን ነው ያቃታት፡፡ ከኒው ዚላንድ ወጥታ አታውቅም ነበር ከዚያ በፊት፡፡ ለዚያ ይሆናል የደነገጠችው፡፡ በሕንድ የጎዳና ላይ ግዙፍ የደጅ ማስታወቂያዎች (ቢልቦርዶች) በብዛት አገልግሎት ላይ ይውላሉ፡፡ ብዙዎቹ መጪዎቹን አዳዲስ ፊልሞች የሚጠቁሙ ናቸው፡፡ ሁሉም ላይ በቆዳ ቀለም ፈካ ያለች የአንዲት ሴት ምሥል ይታያል፡፡ ቦሊዉድ ጥቁር ቆዳ ያላት ሴት ድርሽ እንዳትል የተባለ ነው የሚመስለው፡፡ ከደጅ ቤት ስትገባ ነገሩ ባሰባት፡፡ ቴሌቪዥኑን የሞሉት ቀላ ያሉ ሕንዳዊያን ናቸው፡፡ ማስታወቂያውን የሚሠሩት ቀላ ያሉ ሕንዳዊያን ናቸው፡፡ ድራማው፣ ዜና አንባቢዎቹ፣ ተዋኞቹ፣ የመርሀግብር አጋፋሪዎቹ…በሙሉ ቅላት፣ንጣት፣ ፍካት…ይታይባቸዋል፡፡ ፍካት ስንል ራሱ አዎንታዊ ነው፡፡ ተቃራኒው መጠየም፣ መክሰል፣ መደብዘዝ ነው፡፡ ሁሉም አሉታዊ ይመስላሉ፡፡ እኛ ራሱ ስለ ከለሪዝም እያወራን፣ ራሳችን ዘረኞች ሆነን አረፍነው? ዘረኛ የቅባት ማስታወቂያዎች የቆዳ ቅባት ማስታወቂያው ሁሉ አንድ አይነት ይዘት ያለው መልእክት ይለፍፋል፡፡ ‹‹ቆዳችሁን የሚያፈካ…ቅባት›› በሚል ተመሳሳይ ሐረግ የማይደመደም ማስታወቂያ በአገሩ ጠፋ፡፡ እንዲያውም አንደኛው ማስታወቂያ ቃል በቃል እንዲህ ይላል፡- "ሴቶች ጥሩ ባል፣ ጥሩ ሥራና የተሟላ ደስታን እንዲያገኙ ቆዳቸውን የሚያፈካ ቅባት ይጠቀሙ" ማስታወቂያው ይህን የሚሰብከው ያለምንም ሀፍረት ነው፡፡ አድማጩም፣ ተመልካቹም ‹ታዲያ ይሄ ምን ቸግር አለው?› ይላችኋል፡፡ ችግርማ አለው፡፡ ችግሩ ዘረኛ መሆኑ ነው፡፡ ችግሩ ችግር መሆኑን እስክንረሳ መሰበካችን ነው፡፡ ‹‹በዓለም ግዙፎቹ ቆዳ አምራቾቹ ጋርኒየር (Garnier) እና ሎሪያል (L'Oreal) በኒው ዚላንድም አሉ፡፡ እኔ ግን አንድም ቀን እንዲህ ብለው ምርታቸውን ሲያስተዋውቁ አይቼ፣ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ›› ትላለች ሐርሻሪን፡፡ ሐርሻሪን ‹‹የሕንድ ፌሚኒስቷ ገጽ›› የሚል ኢኒስታግራም አላት፡፡ በዚያ በኩል ‹‹የቅላት ዘረኝነበት››ን ለመታገል ትተጋለች፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን በሚኔሶታ መገደል ተከትሎ ተጋግሎ በነበረው የጥቁሮች እንቅስቃሴ የተነሳ በሰኔ 2020 ዓ.ም ላይ እነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች ምርቶቻቸው ላይ ‹‹ቀይ ቆዳ እንዲኖርሽ…›› የሚሉ ዘረኛ ሐረጎችን ከማስታወቂያቸው ለማንሳት ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡ ይህንንም በከፊል አድርገውታል፡፡ ሆኖም አስተሳሰብ በአንድ የማስታወቂያ ሐረግ መነሳት በአንድ ጀምበር ይፋቃል እንዴ? አይፋቅም፡፡ ስለዚህ የቅላት ዘረኝነት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ጋርኒየር አብዛኛዎቹን ምርቶቹን የሚሸጠው በኢሲያ አህጉር ነው፡፡ ምርቶቹን የሚታወቁት ቆዳን በማፍካት ነው፡፡ ይህ ‹‹የቅላት ዘረኝበት›› በኢሲያ አገሮች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጉዳዬ የሚለው አልነበረም፡፡ ነውርም ሆኖ የሚታየው ሰው አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡ በቃ ቀይ ሴት፣ ከጥቁር ሴት አንጻር ውብ ናት፣ ውብ ናት፤ አለቀ ፣ደቀቀ፡፡ ጥቁር ሴት ደግሞ ‹‹መቼስ ምን ይደረጋል…እግዚአብሔር ካመጣው…›› ነገር፡፡ ለምን ጠቆርኩ ብሎ ራስን ማጥፋት የቅላት ዘረኝነት በአንድ ኅብረተሰብ ውስጥ ሲፀርስ ውጤቱ አደገኛ ነው፡፡ ሕጻናት ቆዳቸው ሲጠቁር አካል ጉዳተኛ እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ ፈጣሪ የረገማቸው ይመስላቸዋል፡፡ ገና ታች ክፍል እያሉ ከእናታቸው የሚያቀላ ቅባት ሰርቀው ተደብቀው እየተቀቡ በእኩዮቻቸው ዘንድ ቅቡልነት ለማግኘት ይተጋሉ፡፡ ምክንያቱም ከቴሌቪዥኑ የሚማሩት ይህንኑ በመሆኑ። ይህ በኢሲያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ አገራትም የሚታይ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ጸሎታቸው ‹አምላኬ ሰው በልኬ›፣ ከሚለው ቀጥሎ ‹አምላኬ ቆዳየን ትንሽ አንጣልኝ› የሚል ሆኗል፡፡ ከላይ የሚታየው የቢልቦርድ ምስል በአይቬሪኮስት የተሰቀለ ነው፡፡ ይህንኑ የሚመሰክር፡፡ ቀድሞ ጭራሽ አጀንዳ እንኳን ያልነበረው ይህ ‹የቅላት ዘረኝነት› አሁን ብዙዎች እንዲያወሩበት ሆኗል፡፡ ይህ የኅብረተሰብ መንቃት የተፈጠረው በአጋጣሚ ነው፡፡ ወይም አይደለም፡፡ የጆርጅ ፍሎይድ ሞት ብዙ የቀለም ጉዳዮች ወደ ሚዲያ እንዲመጡ ማድረጉ ግን እሙን ነው፡፡ ማኅበራዊ የትስስር መድረኩ ክርክሩን አጧጧፈው፡፡ አሁን አሁን ጥቁር ቆዳ ያላቸው ሰዎች በቅባትም ሆነ በሽቦ ቆዳቸውን መፈተግ እንደሌለባቸው እያሰቡ መጥተዋል፡፡ ተፈጥሮ የሰጠቻቸው ቆዳ ችግር እንደሌለበት እየተገለጠላቸው ነው፡፡ የሕዝብ ንቃት ሁልጊዜም ለለውጥ ወሳኝ ነው፡፡ ለምሳሌ ለስንትና ስንት ዓመታት በገበያ የቆየው ዩኒሊቨር (Unilever) ለምሳሌ እነዚህን የቅላት ዘረኝነት የሚደግፉ ምርቶቹን ‹‹አይለመደኝም›› ብሎ ማስታወቂያውን በዚያ መንገድ ማስነገር አቁሟል፡፡ ምርቶቹንም ስማቸውን ለመቀየር ተገዷል፡፡ ለምሳሌ ፍካት (fairness), ንጣት (whitening)፣ ድምቀትና ቅላት (lightening) የሚሉትን ስሞች አስወግዷል፡፡ ፌየር ኤንድ ላቭሊ (Fair & Lovely) ሚሊዮን ዶላሮችን የሚያስገባት ምርቱ ነበር፡፡ ስሙን ቀይሮታል፡፡ ግሎው ኤንድ ላቭሊ (Glow & Lovely) በሚል፡፡ ስሙ አልሸሹም ዞር አሉ ቢመስልም አንድ አበረታች እርምጃ ሆኖ ሊወሰድለት ይችላል፡፡ ዩኒሊቨር በነዚህ ምርቶቹ እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ ያፍስባቸዋል፡፡ በቬርሞንት ዩኒቨርስቲ የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት ኒኪ ካና የስም ለውጡ አሁንም የቅላትን በጎነት የሚሰብክ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ እጅግ ገናና ምርት ስለሆነ የስም ለውጥ ለማድረግ መጨከኑ በራሱ የሚደነቅ ሆኖ የትርጉም ለውጡ ግን አይታየኝም›› ይላሉ፡፡ ለዓመታት ደንበኞቻቸው ፊታቸውን ማቅላት የሚሹ ሰዎች ሆነው ቆይተዋል፡፡ ድምቀት (Glow) የሚለው ቃል የተሳሰረው ከቅላት ጋር ነው፡፡ ስለዚህ ማድረግ ያለባቸው የምርቱን ስም መቀየር ሳይሆን ምርቱን ከገበያ እስከናካቴው ማስወደግ ነበር ባይ ናቸው ፕሮፌሰሩ፡፡ የመቅላት አባዜ ምን ይዞ ይመጣል? ጥናቶች ብዙ ተሰርተዋል፡፡ የመቅላት ዘረኝነትና የመቅላት አባዜ ዙርያ፡፡ ዋንኛው የጥናቱ ውጤት የአእምሮ ጤና ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በኢሲያዊና በአፍሪካዊ ሴቶች የተደረገ አንድ ሰፊና ጥልቅ ጥናት ‹‹ድብታ ውስጥ የመግባት እና የአእምሮ ጤና መቃወስ የቆዳ ቀለምን በጸጋ ካለመቀበል ጋር ተሳስሮ ታይቷል፡፡ በአንዳንድ ውስን አጋጣሚዎች ደግሞ ለቆዳ ቀለም መጠየም ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ያለመፈለግ ስሜት፣ ዋጋ የማጣት ስሜት፣ የራስ ዋጋቸውን አውርደው፣ ዋጋቸውን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን የሚፈጠፍጡም አልጠፉም፡፡ ‹ኅብረተሰብ የማይፈልገኝ ከሆነ ለምን እኖራለሁ› ነው ነገሩ፡፡ በኔትፍሊክስ የሚታየው አንድ ተከታታይ የሪያሊቲ አውደ ትእይንት ትኩስ ክርክር ፈጥሯል፡፡ ትእይንቱ ‹‹ኢንዲያን ማችሜኪን›› ይባላል፡፡ የትእይንቱ አሰናጅ የፍቅር ጓደኛ ማደን ነው ሥራዋ፡፡ በትእይንቱ የምታገናኛቸው፣ የምትመርጣቸው በሙሉ ፈካ ያለ ቀለም ያላቸው ወንዶችና ሴቶች መሆናቸው ለጦፈ ክርክር ምክንያት ሆኗል፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ እንዲህ ዓይነቱ ነገር እንደ ትክክል የሚቀበል ማኅበረሰብ አሁን ‹‹ግን ለምን?›› ማለት ጀምሯል፡፡ ጥቁር ሴትስ? ጥቁር ወንድስ? ጠቆር ማለት መጉደል ነው? መበደል ነው? ክፉ እጣ ነው? ማን ነው ያለው? ደግነቱ ኅብረተሰቡ አይደለም ካለ መሆኑ ያበቃል፡፡
55426025
https://www.bbc.com/amharic/55426025
በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ዛሬ [ረቡዕ ታህሳስ 14/2013] ንጋት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ከ90 በላይ ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ።
የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ በበኩላቸው ጥቃቱ ስለመፈፀሙ መረጃው እንደሌላቸው የተናገሩ ሲሆን፣ የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ግን ጥቃቱ መፈፀሙን አረጋግጠው የሟቾች ቁጥር እስካሁን ድረስ ባይታወቅም "በጣም ከፍተኛ መሆኑን" ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ በአካባቢው የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ተሰማርቶ ሰላም የማስከበር ሥራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ መለሰ አክለው ተናግረዋል። ከጥቃቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተገኝተው ከመተከል ዞን ነዋሪዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አካባቢውን ወደ ሠላም የመመለሱ ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ መናገራቸው ተዘግቦ ነበር። ነዋሪዎች ምን ይላሉ? በርካታ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት ተከትሎ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የቡለን ከተማ ነዋሪ ጥቃቱ ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ ሌሊት 11 ሰዓት አካባቢ መፈፀም እንደጀመረ ገልፀው፤ እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ቀጥሎ ነበር ብለዋል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት ነዋሪ ጨምረውም በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ቤተሰቦች ለቅሶ ላይ መሆናቸውን ገልፈው፤ በጥቃቱ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ይናገራሉ። "እስካሁን 100 አስክሬኖች ተገኝተዋል፤ የጠፉ አስክሬኖችም አሉ። ወደ ቡለንም 70 አስክሬኖች መጥተው ተመልክቻለሁ" ሲሉ የተመለከቱት ነዋሪ ገልጸዋል። በጥቃቱም የጓደኛቸው አባት መገደላቸውን የተናገሩት ነዋሪው፤ "ቤት እየጠበቀ እያለ ነው ተኩሰው የገደሉት። አርሱ መሳሪያ ቢኖረውም፤ እነርሱ ብዙ ስለነበሩ እራሱን መከላከል አልቻለም" ሲሉ የተገደሉበትን ሁኔታ አስረድተዋል። ሌላ ያነጋገርናቸው ነዋሪ ደግሞ "ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ነው ታጣቂዎች ወደ በኩይ ቀበሌ የገቡት" ይላሉ። ጥቃቱ በከባድ መሳሪያ በመታገዘ ጭምር መፈፀሙን የገለፁት ነዋሪው፤ እስካሁን ድረስ ከ96 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና 28 ቤቶችና በርካታ የእህል ክምሮች መቃጣላቸውን አስረድተዋል። ነዋሪው አክለውም በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቡለን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን በስፍራው ተገኝተው ማረጋገጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አስክሬኖች በሸራ ተጠቅለው በየሜዳው ወድቀው ነው ያሉት፤ ገና ጫካ ያለው አልተሰበሰበም። ቡለን የመጡት ቁስለኞችም ከ20 በላይ ይሆናሉ። ሆስፒታል ሄጀ በዓይኔ ነው ያየኋቸው፤ በአሰቃቂ ሁኔታ ጉዳት የደረሰባቸው ሁሉ አሉ" በማለትም ጥቃቱ በስለት፣ በመሳሪያና በቀስት መፈፀሙን ገልፀዋል። በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎችን በተመለከተ እማንነታቸውን የሰጡት እኚህ ነዋሪ በዐይናቸው 96 አስክሬኖች መመልከታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው የአካባቢው ተወላጅ አይደሉም በተባሉ ነዋሪዎች ላይ መሆኑን ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን ተመሳሳይ ጥቃት ሲፈጸም ወራት ተቆጥረዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ማክሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከፌደራልና ከክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ገልጸዋል። ቅሬታቸውንም ሲያስረዱ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያወያዩት ችግሩ በሌለበት አካባቢ ነው። ችግሩ ያለው ዲባጤ ቡለንን ጨምሮ በሦስት ወረዳዎች ነው። ከሦስቱ ወረዳዎች የተወከለና ሁኔታውን የሚያስረዳ ሰው እንኳን በውይይቱ አልተወከለም፤ ተወካዮች እንዳይሄዱም በክልሉ መንግሥት ተፅዕኖ ተደርጓል" ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን የነዋሪውን ቅሬታ ግን ከክልሉ መንግሥት ኃላፊዎች ማረጋገጥ አልቻልንም። የሆስፒታል ምንጮች በመተከል የቡለን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ እና ስማቸው ለደኅንነታቸው ሲባል እንዳይገለፅ የጠየቁ ባለሙያዎች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ወደ ሆስፒታላቸው ከቀኑ አምስት ሰዓት ጀምሮ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ ሰዎች የመጡ ሲሆን ብዛታቸው እስከ አርባ ይደርሳል ብለዋል። በጥይት፣ በስለት እና በቀስት ተመትተው ወደ ቡለን ሆስፒታሉ ከመጡ የትቃቱ ሰለባዎች መካከል ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው እንደሚገኙበት አክለው ገልፀዋል። ወደ ሆስፒታሉ የመጡት ሰዎች በጥይት እንዲሁም በቀስት መመታታቸውን የሚናገሩት ቢቢሲ ያናገራቸው የጤና ባለሙያ፤ ሆስፒታል ከደረሱት መካከል አንዲት ታዳጊ ሕጻን መሞቷን አረጋግጠዋል። ግጭት በተከሰተበት አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ወደ ሆስፒታል ከመጡ ሰዎች መስማታቸውን የገለፁት የሕክምና ባለሙያው፣ ጥቃት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታሉ የመጡት የጥቃቱ ሰለባዎች በጥቃት ፈጻሚዎቹ ተከበው ተኩስ የተከፈተባቸው ነዋሪዎች ያሰሙትን የድረሱልን ጩኸት ሰምተው የሄዱት መሆናቸውን መስማታቸውን ተናግረዋል። የቡለን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተደጋጋሚ በአካባቢው በሚፈጠሩ ግጭቶች ጥቃት የሚደርስባቸውን ሰዎች ተቀብሎ የሚያክም ሲሆን መሰረታዊ የሕክምና ቁሳቁሶችን ለማሟላት በፀጥታ ችግር ምክንያት እንዳልቻለ የሕክምና ባለሙያው ተናግረዋል። ለሆስፒታሉ ግዢ የሚፈፀመው ባሕር ዳር እንደነበር የገለፁት ባለሙያዎች ከቡለን-ቻግኒ ያለው መንገድ በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ዝግ በመሆኑ ይህንን ማድረግ ሳይችሉ መቅረታቸውን ገልፀዋል። በዚህ የተነሳም በሆስፒታሉ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ለመጡ ሰዎች ተገቢውን ሕክምና ለመስጠት እየተገሩ እንደሆነ ጨምረው አመልክተዋል። በአካባቢው ካለፈው ዓመት ማብቂያ ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት በነዋሪዎች ላይ እንደሚደርስ የሚናገሩት የሕክምና ባለሙያው እንዲህ በጅምላ ጉዳት ደርሶባቸው በርካታ ሰዎች ለህክምና ሲመጡ የአሁኑ ሁለተኛው መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ በርካታ ብዙ ሰዎች የተጎዱት ከሳምንታት በፊት ከቡለን ወደ ቻግኒ የሚሄድ መኪና ላይ ጥቃት በደርሰበት ወቅት ብዙ ሰዎች በተገደሉና ወቅት መሆኑን ጠቅሰዋል። በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው የመተከል ዞን ውስጥ በታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ወራትን አስቆጥሮ፤ አሁንም ድረስ በተለያዩ ጊዜያት በሚፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ለሞትና ለጉዳት እየተዳረጉ ይገኛሉ። ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰነውና በሰባት ወረዳዎች በተዋቀረው የመተከል ዞን የተለያዩ ብሔረሰቦች ይኖራሉ። በዋናነት የጉሙዝ፣ የሽናሻ፣ የአማራ፣ የአገው፣ የኦሮሞና የበርታ ብሔሮች ይገኙበታል። በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጸሙ ጥቃቶች ማንነትን የለየና በተወሰኑት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችና ከዚህ በፊት የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የአካባቢው ባለስልጣናት ጥቃቱን የሚፈጽሙት ኃይሎችን "ጸረ ሠላም" ከማለት ውጪ ማንነታቸውና የጥቃቱ አላማ በግልጽ አይታወቅም። በተለያዩ ጊዜዎች በጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች የተለያየ ቁጥር ያላቸው በጥቃቶቹ ተሳትፈዋል የተባሉ ታጣቂዎች መገደላቸው ሲዘገብ ቆይቷል። በአካባቢው ለወራት በዘለቀው ጥቃት ሳቢያ ጸጥታውን ለመቆጠጠርና በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጸሙትን ጥቃቶች ለማስቆም ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ የፌደራል መንግሥት ጦር ሠራዊትና የክልሉ የጸጥታ አካላት የተካተቱበት ኮማንድ ፖስት ተደጋጋሚ ጥቃት በሚፈጸምባቸው አካባቢዎች መዋቀሩ ይታወሳል። ነገር ግን አሁንም ድረስ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፉ ተከታታይ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ነው። አሁን የተፈጸመውና ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ጥቃት በአካባቢው ከተፈጸሙት ሁሉ የከፋው እንደሆነ ይነገራል።
52281072
https://www.bbc.com/amharic/52281072
ኮሮናቫይረስ፡ "ቀጣፊ ዋሾ ነሽ፣ አሳፋሪ ሰው ነሽ" ዶናልድ ትራምፕን ያስቆጣችው ጋዜጠኛ
የዶናልድ ትራምፕ ጋዜጣዊ መግለጫ ራሱን የቻለ የኮሜዲ ትዕይንት መልክ የሚይዝበት ጊዜ ብዙ ነው። የትናንት ምሽቱ ከነዚህ የሚመደብ ነው፡፡ በዋሺንግተን ሰኞ ከሰዓት ነው የተደረገው፤ በኛ ሌሊቱን።
በትራምፕ ጋዜጣዊ መግለጫ ታሪክ ዘለግ ያለ ሰዓት ወስዷል የተባለት ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ በድራማዎች የተሞላ ነበር። በድምሩ 2 ሰዓት ከ 24 ደቂቃ የወሰደ መሆኑም ልዩ ያደርገዋል። ወትሮም ትራምፕ ጠላቶቼ ከሚሏቸው ጋዜጠኞች ጋር የሚያደርጉት ቆይታ አንዳች አስቂኝ ክስተት አያጣውም። ለምሳሌ ባፈለው አርብ በፈረንጆች ስቅለት ዕለት በነበራቸው መግለጫ ጋዜጠኞቹን፣ "እስኪ ዛሬ እንኳ እርስ በርስ እንተሳሰብ፤ ስቅለት ነው፤ እስኪ ዛሬ እንኳ ጨዋ ሁኑ…" ብለው ነበር መድረኩን ለጥያቄ የከፈቱት። ዶናልድ ትራምፕ "ተራ ጉንፋን ነው፤ በራሱ ጊዜ ብን ብሎ እንደ ተአምር ይጠፋል" ሲሉት የነበረው ቫይረስ 600ሺህ የሚጠጋ ዜጋቸውን አጥቅቷል። ከ20ሺ በላይ አሜሪካዊያንን ገድሏል። አሁንም ቢሆን ግን እርሳቸው ስለ ስኬታቸው እንጂ ሌላ ማውራት አይወዱም። ከሰሞኑ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዶናልድ ትራምፕ ፈጣን እርምጃ እንዲወስዱ በቂ መረጃ ቀርቦላቸው እንደነበር፣ በቂ ምክር ተሰጥቷቸው እርሳቸው በመዘናጋታቸው ነው ይህ ሁሉ ጥፋት የደረሰው የሚል ይዘት ያለው ሰፊ ዘገባ ይዞ መውጣቱ ፕሬዝዳንቱን ክፉኛ ሳይረብሻቸው አልቀረም። ለዚህም ይመስላል ሰፊ ጊዜ ወስደው በጊዜ ሰንጠረዥ ሳይቀር መቼ ምን እንዳደረጉ እስኪሰለች ድረስ ደጋግመው ሲናገሩ የነበረው። በትናንቱ የጋዜጣዊ መግለጫ መድረክ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣን በቻሉት አቅም ሁሉ ወርፈውታል። "ቀጣፊ!" ብለውታል። • ኮሮናቫይረስ ለምን ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶችን ያጠቃል? ወረርሽኙን በመከላከሉ ሂደት ስማቸው ገዝፎ የሚነሳው ዶ/ር ፋውቺን ከሥራ ሊያባሯቸው ይችላሉ የሚለው ዜና ከወጣ በኋላ በተደረገው በዚህ ዘለግ ያለ የጋዜጠኞችና የትራምፕ ጥያቄና መልስ ክፍለ ጊዜ ጎልቶ የወጣው ታዲያ የፓውላ ሬይድና የትራምፕ ፍጥጫ ነው። ፓውላ ሬይድ የሲቢኤስ ጋዜጠኛ ናት። ትናንት ዶናልድ ትራምፕን በጥያቄ ተናንቃቸው ነበር። እርሷን ለመስደብ ያደረሳቸውም ፈታኝ ጥያቄዎቿን ያለማቋረጥ በመሰንዘሯ ነው። በቂ ሥራ ከጃንዋሪ ወር ጀምሮ ሠርቻለሁ ልወቀስ አይገባም የሚሉትን ትራምፕን በፌብሪዋሪ ወር ምን ሲሰሩ ነበር? በር ለመዝጋት ለምን ዘገዩ? ስትል ጠይቃቸዋለች። ትራምፕ ነገሩን ቸል ብለው ስለስኬታቸው ማውራት ሲጀምሩ እያቋረጠች ፋታ ነሳቻቸው። ይህ የሁለቱ ምልልስ የሚሊዮኖችን ቀልብ ስቧል። በግርድፉ ይህን ይመስላል። ትራምፕ፡- "በጃንዋሪ 11 አንድም ታማሚ በአሜሪካ አልነበረም። ይሄ የናንተ ዋሾ ሚዲያ ዝም ብሎ ይቀባጥራል። 'ኦ… ፕሬዝዳንቱ ቀደም ብሎ ነገሮችን መቆጣጠር ነበረበት' ይላል። ልንገራችሁ አይደል? እኔ መጀመርያ ነው እርምጃ የወሰድኩት። እርምጃ ፈጥኜ ስወስድ ደግሞ ይቺ ናንሲ ፒሎሲ የምትባል ሴትዮ እና ይሄ እንቅልፋሙ ጆ ባይደን ደርሰው ይተቹኛል። "…እንዲያውም በአየር መንገዶች ቁጥጥር እንዲደረግ በማድረጌ መጤ ጠል ሲሉኝ ነበር። በጃንዋሪ 21 ነው የመጀመርያው የቫይረሱ ተጠቂ የተገኘው። አንድ ሰው እንኳ አልሞተም። በዚህ ጊዜ ለምን የዓለሙን ትልቁን ኢኮኖሚ አልዘጋህም ነው የምትሉኝ? ምን ነክቷችኋል እናንተ ሰዎች? "…የዓለምን ቁጥር አንድ ኢኮኖሚ፣ ቻይናን የሚያስከነዳውን ኢኮኖሚ፣ የታላቋን አሜሪካንን ኢኮኖሚ፣ ታላቁን ቀጣሪ ኢኮኖሚ…በዚያ ወቅት ለምን አልዘጋህም ነው የምትይኝ? ደግሞ ትልቅ ኢኮኖሚ የገነባሁት እኔ ነኝ። በጃንዋሪ 31 በዚች ታላቅ አገር አንድ ሰው ሳይሞት ነው በር የዘጋሁት። • ቻይና ከኮሮናቫይረስ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በቅርብ የታዘበው ኢትዮጵያዊ ዶክተር "…ቶሎ በር ስዘጋ ደግሞ እናንተ ሐሳዊ መረጃ ፈልፋዮች የትችት መዓት ታደርሱብኛላችሁ፤ የሚገርም እኮ ነው፤ ስፈቅድም መከራ፣ ስከለክልም መከራ… "…እንቅልፋሙ ጆ ባይደን ምን አለኝ መሰለቻሁ!? ዘረኛ አለኝ፣ ከቻይና ሰው እንዳይመጣ ስላልኩ እኮ ነው እንዲህ የሚለኝ። ያቺ ፒሎሲ ደግሞ መጤ ጠል አለችኝ። ከዚያ ትንሽ ቆይቶ ባይደን መግለጫ አወጣ፣ ሰው ነው የጻፈለት ለነገሩ። ትራምፕ በር መዝጋቱ ትክክል ነበር ብሎ ጻፈ። እሱ አልጻፈውም፤ ጓደኞቹ ናቸው በሱ ስም የሚጽፉለት። "…ይሄ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የለየለት ቀጣፊ ነው፤ የታወቀ ዋሾ። ፕሬዝዳንት ትራምፕ እርምጃ ለመውሰድ ዘግይቷል ይለኛል ደግሞ…ቀጣፊ። ለነገሩ ስለኔ ካልጻፈ ይዘጋል። አይሸጥለትማ…ማን ገዝቶ ያነባል እሱን… ትራምፕ ከዚህ በኋላ መብራቱ እንዲጠፋ አዘዙ፤ ጋዜጠኞቹን ፊልም እንዲመለከቱ ጋበዙ። የተቀነባበረ የቲቪ ምሥል ነው። በምሥሉ ላይ የተለያዩ ሰዎች በተለይም የተለያዩ የአሜሪካ ግዛት ገዢዎች እርሳቸውን ሲያንቆለጳጵሱ ይታያል። የሚገርመው ይህ ቪዲዮ ሲተላለፍ ትራምፕ ከፊት ለፊት ቆመው ጋዜጠኞቹ በትኩረት እንዲመለከቱት ያበረታቱ ነበር። አንዳንድ ገዢዎች ስለርሳቸው ታላቅነት ሲናገሩም ወደ ጋዜጠኞች እየዞሩ ይጣቀሱ ነበር፤ ከፈገግታ ጋር። ይህ አጭር ዘጋቢ ፊልም እንዳለቀ አንድ ጋዜጠኛ እጁን አውጥቶ "ክቡር ፕሬዚዳንት! ይህንን የሙገሳ ቪዲዮ ማን አቀነባበረልዎ፤ የምርጫ ዘመቻ ላይ ያሉ ይመስላሉ? ሲል ጠየቃቸው። ትራምፕ፡-"እኛው ነን የሠራነው፤ በ2 ደቂቃ ነው ያቀናበርነው። ከፈለክ የዚህ ዓይነት ሺ ላሳይህ እችላለሁ" ጋዜጠኛ፡-"ለምን ያን ማድረግ አስፈለገዎ" ትራምፕ፡-"ምክንያቱም ቀጣፊ ሚዲያዎች አስቸገራችሁኝ።" ጋዜጠኛ፡- "በመንግሥት በጀትና በዋይት ሃውስ ሰራተኞች ነው ይህን ቪዲዮ የሚያሰሩት" ትራምፕ፡- "የተቀናበረ ቪዲዮ አትበለው፤ የሰዎችን ንግግር ነው ቀጣጥለን ያሳየናችሁ." ትራምፕ በድጋሚ ስሜታዊ ሆነው መናገር ጀመሩ "እኔ የምለው፤ እንዴት ነው ማንም ሰው ሳይሞት ማንም ሰው በቫይረሱ ሳይያዝ በታሪክ በዓለም ትልቁን ኢኮኖሚ ለምን አልዘጋህም እያላችሁ የምትወቅሱኝ? የሲቢኤስ ጋዜጠኛ እጇን አወጣች፡- • በኮቪድ - 19 የሞተ ሰው የቀብር ሥነ- ሥርዓት እንዴት መፈጸም አለበት? "ክቡር ፕሬዝዳንት፣ እርስዎ እየተተቹ ያሉት እኮ እርምጃ ለመውሰድ ጊዜ ገዝተዋል ተብለው ነው። በዚያ በሚሉት ወቅት አልጋ ለማዘጋጀት፣ ሆስፒታል ለመገንባት፣ የምርመራ መሳሪያዎችን ለማዘጋጀት አልተጠቀሙም ነው የተባሉት። በአሁን ሰዓት 20 ሚሊዮን አሜሪካዊያን ሥራ ፈተዋል…ሺዎች ሞተዋል። እርስዎ ነዎት… ትራምፕ ተቆጡ፡- "አንቺ አሳፋሪ ጋዜጠኛ ነሽ። ነገሩን ያስቀመጥሽበት መንገድም አሳፋሪ ነው። እስኪ ዝም በይ አንድ ጊዜ…፤ማንም ያላደረገውን አድርጊያለሁ፤ ስላደረኩት… ጋዜጠኛዋ አቋረጠቻቸው፤ "በጃንዋሪ ሳይሆን በፌብሪዋሪ ምን ሰሩ ነው የተባሉት፤ ሥራ ቢሰሩማ ኖሮ ያ ሁሉ ሰው ባልሞተ… "ይቅርታ ይቅርታ፣ ራስሽ ዘግበሽዋል እኮ፣ አንድም ሰው አልሞተም፣ አንድም ሰው አልተያዘም፤ እንዴት አገሩን ልዝጋው በዚህ ወቅት…ንገሪኝ…እንዴት ይህን ታላቅ አገር ልዝጋ ጋዜጠኛዋ አቋረጠቻቸው በድጋሚ፡- "አሁንም ያልጠየቅዎትን ነው የሚመልሱት፤ በፌብሪዋሪ ምን አደረጉ ነው እያልኩ ያለሁት…" ትራምፕ፡- "በጣም ብዙ! በጣም ብዙ ነገር ነው ያደረኩት…ምን የላደረኩት አለና…እንዲያውም ዝርዝሩን በጽሑፍ ልሰጥሽ እችላለሁ… ጋዜጠኛዋ፡- "እሱን አኮ ነው ይንገሩኝ ያልኮት… ትራምፕ ተናደዱ፤ አንድ ነገር ልንገርሽ ? ቀጣፊ ነሽ፣ አንቺም ያንቺ ሚዲያም ዋሾዎች ናችሁ። እኔን እንደዚያ ከምትጠይቂ ለምን ጆ ባይደን ይቅርታ ጠየቀኝ። ለምን ዲሞክራቶች አደነቁኝ…ቀድሜ እርምጃ ስለወሰድ አይደለም ጆ ባይደን… ጋዜጠኛዋ በድጋሚ አቋረጠቻቸው፡- "ስለ ጆ ባይደን ማንም አልጠይቅዎትም ክቡር ፕሬዝዳንት… ትራምፕ፡- "ቆይኝ ቆይኝ…እንደ አንዳንድ አገሮች በሩን ከፍቼው ብቆይማ ሚሊዮኖች ይረግፉ ነበር፤ ያን አላደረኩም። ቶሎ ብዬ እርምጃ በመውሰዴ የሚሊዮኖችን ሕይወት ታድጊያለሁ። ችግሩ እናንተ ዋሾ ጋዜጠኞች አትዘግቡም። ዋሾ ነሽ…ቀጣፊዎች ናችሁ…ፌክ ኒውስ…
49354707
https://www.bbc.com/amharic/49354707
“ከተማ አስተዳደሩ የወሲብ ንግድን በህግ ወንጀል የማድረግ ስልጣን የለውም” የህግ ባለሙያ
ከሰሞኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር የጎዳና ልመናና የወሲብ ንግድን ለማገድ ረቂቅ ህግ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በብዙዎች ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ከእግዱ አላማ አንስቶ እስከተደረጉ ዝግጅቶች፣ እንዲሁም የአስተዳደሩ ስልጣን ባሉና በተያያዙ ጉዳዮች ውይይቶች ቀጥለዋል።
ረቂቅ ህጉ በአሁኑ ወቅት ለካቢኔ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ብቻውን መወሰንም ስለማይችል ባለድርሻ አካላት በተለይም የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተያየት እንዲሰጡበትም እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ፌቨን ተሾመ አስረድተዋል። •''ለሴቶች ቦክስ ምን ያደርጋል እያሉ ያንቋሽሹናል'' የኢትዮጵያ ህግ የወሲብ ንግድን የማይከለክል ሲሆን ይህንንም ወንጀል ለማድረግ ጉዳዩ የሚመለከተው የከተማ አስተዳደሩን ሳይሆን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን እንደሆነ የህግ ባለሙያ፣ አማካሪና የስርአተ ፆታ መብት ተሟጋቿ ሰብለ አሰፋ ትናገራለች። የበርካታ ሃገራት ልምዶች ሲታይም የወሲብ ንግድን ህገወጥ ለማድረግ የሚጠቀሙት የወንጀል ህጉን ሲሆን ይህንንም ኃላፊነት የተሰጠው ማእከላዊው መንግሥት ሲሆን በኢትዮጵያም የወሲብ ንግድን ወንጀል ማድረግ የሚቻለው በወንጀል ህጉ መሰረት ሲሆን ይህም ስልጣን የተሰጠው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሆነም ታስረዳለች። "ስልጣኑ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠበት ምክንያት እንደራሴዎቹ የብዙኃኑ ተወካይ ናቸው። ማህበረሰቡን ያማከለና በጥናት የተመሰረተ ህግ ነው የሚያወጡት የሚል ግንዛቤ ስላለ ነው" ትላለች። •ከ125 በላይ የተጠፋፉ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦችን ያገናኘችው አሜሪካዊት ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የወሲብ ንግድን የሚያግድ ህግ ይውጣ ቢባል እንኳን በዘፈቀደ ሳይሆን በበርካታ ጥናቶች ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥታ የምትናገረው ጉዳይ ነው። የወሲብ ንግድን መከልከል ጉዳይ ሲነሳ ይህ የመጀመሪያው እንዳልሆነ የምትናገረው ሰብለ በተለይም የወንጀል ህጉ በ1997ዓ.ም ሲሻሻል የወሲብ ንግድና ፅንስ ማቋረጥን የመከልከል ጉዳይ በጣም አነጋጋሪ ሁኔታም እንደነበር ትጠቅሳለች። በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ፈቅደው የሚገቡበት ባለመሆኑ ወደዛ የሚመራቸው ማህበራዊ ችግሮች ባልተፈቱበት ሁኔታ ድርጊቱን ህገወጥ ማድረጉ "ከህመሙ ይልቅ የህመሙ ምልክት ላይ ማተኮር"፤ ከዚህም በተጨማሪ ሰፋ ያለውን የፖሊሲ ጉዳይ እልባት ሳያገኝና ሴቶቹን ወደዛ የሚገፋፋቸውን ውስብስብ ነገሮች መፍትሔ ሳይሰጥና ተገቢውን የማብቃት ስራ ሳይሰራ ዝም ብሎ ማገድ ትክክል አለመሆኑ ግንዛቤ ተወስዶበት በቂ ጥናት ተሰርቶ ህጋዊ እንዲሆን መደረጉንም ትናገራለች። በወቅቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን ነገር በአግባቡ እንደተመለከተውና ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚሉ ባለድርሻ አካላት የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም የሴቶች መብት ተሟጋቾች ጥናት የተሳተፉበት ጥናት መቅረቡን ታስረዳለች። ከዚህም በተጨማሪ በየከተማው ውይይት ተደርጎ ባለው የሃገሪቷ ሁኔታ የሚሻለው ህጋዊ አድርጎ መቀጠል ነው በሚል ተወስኗል ትላለች። "የከተማ አስተዳደሩ በራሱ ይህንን እከላከላለሁ ሲል ወንጀል እያደረገው ነው ያንን ለማድረግ ስልጣኑ የለውም። ስልጣኑ ያለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው" ትላለች። በወሲብ ንግድ ላይ መሰማራት ሴቶቹ መርጠው ይገቡበታል ተብሎ የሚታሰብ ባለመሆኑ ለጎዳና ልጆች እንደታሰበው ለሴቶቹም የገቢ ማግኚያ መንገድ መቀየስ ሲገባው ይህ አለመሆኑ "በጣም አደገኛ አካሄድ ነው፤ የሴቶቹን መብት እየተጋፋ ነው" በማለት ታስረዳለች። በተደጋጋሚ የፀጥታ ኃይሉ ጎዳና ላይ በወሲብ ንግድ የተሰማሩትን "የሕግ አግባብ" ሳይኖር ለመከልከል እርምጃ መውሰዱን በመጥቀስ አንዳንዶች ትችት ያቀርባሉ። አሁን ደግሞ መንግሥት ህግ አርቅቆ ለፀጥታ ኃይሉ የማስከበር ኃላፊነቱን የሚሰጥ ከሆነ እነዚህን ተጋላጭ የማህበረሰቡ አባላት ላይ ተገቢ ያልሆነ ኃይል እንዲጠቀሙ በር ይከፍታል የሚሉም አልታጡም። ለሰብለም ክልከላው ሲደረግ አፈፃፀሙ እንዴት ነው የሚለው ጥያቄ ከበድ ያለ ሊሆን እንደሚችል ትናገራለች። በረቂቅ ህጉ መሰረት የጎዳና ወሲብ ንግድን ለመከላከከል ቅጣጡ ተፈፃሚ የሚሆነው በንግዱ ላይ የተሰማሩት ሴቶች ናቸው። "የከተማ አስተዳደሩ ፖሊሶችን እየላከ ጎዳና ላይ ያሉ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችን ከሆነ ኢላማ የሚያደርገው ይሄ ክልከላ ሳይሆን አላማው ምንድን ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ይህ ከሆነም አፈፃፀሙም ከባድ ነው፤ ለከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የፆታዊ ጥቃት ለመሳሰሉት የሚዳርግ ነው፤ እንደ ወንጀለኛም እንዲቆጠሩ ይዳርጋል። "ትላለች። ሰብለ እንደምትለው የወሲብን ንግድ ህገ መንግስቱ ስለማይከለክለው በዚያ መሰረት ወንጀል ተደርጎ አልተቆጠረም ማለት ይህ አንድ የስራ መስክ ሊሰማሩበት የሚገባ ጉዳይ ሲሆን መከልከል ደግሞ የሴቶቹን ህገ መንግሥታዊ መብት የሚጣረስ ነው ትላለች። "ይህ ኢ-ህገ መንግሥታዊ ነው። ህገ መንግሥቱም ስለማይከለክለው እንደ አንድ የገቢ ማግኛ የኢኮኖሚ መስክ የመምረጥ ህገ መንግሥታዊ መብት አላቸው። የከተማ አስተዳደሩም የመከልከል መብት የለውም" የምትለው ሰብለ የከተማ አስተዳደሩ በከፍተኛ ሁኔታ እንደገና ሊያጤነው የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ አስተያየቷን ሰጥታለች። ረቂቁ እንዲሁ ከመንግሥት ስለመጣ ብቻ መጫን ሳይሆን ከህብረተሰቡ ጋር ለመተማመን እየተሰራ መሆኑንና ከዚያ በኋላም ወደ ምክር ቤት ተልኮ አዋጁ ሥራ ላይ እንደሚውል የሚናገሩት ፌቨን ተሾመ ናቸው። የጎዳን ልመናን በተመለከተ አምራች ኃይሉ ወደ ሥራ እንዲገባና በተለይም ለጎዳና ተዳዳሪዎቹ ከዚህ ህይወት እንዲወጡም በዘላቂነት ማቋቋም የሕጉ አላማ እንደሆነ ገልፀዋል። •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት እንደ ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ከሆነ በአሁኑ ወቅት አስተዳደሩ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለማገዝ የራሱን 'ሶሻል ፈንድ' አቋቁሞ እየሰራ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ማህበረሰቡ በተናጠል የሚሰጠውን ገንዘብ ተቋማዊ አሰራር ዘርግቶ በዚያ መንገድ እርዳታው እንዲገለስና ፕሮጀክቶችም ተቀርፀው እነሱ የሚጠቀሙበት መንገድ ተቀይሷል ይላሉ። "የማይከለከል ከሆነ አስቸጋሪ ነው። ልመና እንደባህልም እየተወሰደ ስለሆነ ከዚህ ህይወት መውጣት ያለመፈለግ አዝማሚያዎች አሉ። በርካታ ወጣቶችም ከተለያዩ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ለልመና ሲባል ይመጣሉ። ይህ እርምጃም ነገ ተረካቢ ትውልድ ከማፍራት አንፃር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብሎ አስተዳደሩ ያምናል" ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ አዲስ አበባ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ ከመሆኗም አንፃር ለሃገር ገጽታም መታሰብ እንዳለበትም አስረድተዋል። ከዚህም አንፃር የጎዳና ላይ ልመና ብቻ ሳይሆን የጎዳና ላይ የወሲብ ንግድ ልቅ መሆኑ አግባብ እንዳልሆነ ጠቅሰው፤ በተለይም የወሲብ ንግድ ከባህል አንጻር እንዲሁም ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። •ሰሜኒያ ሴት ስፖርተኞች ደግፈዋት እንደማያውቁ ተናገረች "የወሲብ ንግድ ኢትዮጵያዊ እሴት ስላልሆነ፤ እንደ ዋና ከተማ ዜጎች ከውጭ ሃገር የሚመጡባት ለሃገሪቷም መውጪያና መግቢያ በር እንደመሆኗ መጠን እንደዚህ አይነት ተግባር ያልተበራከቱባት ብሎም የሌሉባት ከተማ ለማድረግ ታቅዷል" ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ የወሲብ ንግድ መበራከት በከተማዋ ያለውን የኤች አይ ቪ ስርጭትን እንደሚጨምረው ጥናቶች ስለሚጠቁሙ ይህንንም ለመከላከል የወሲብ ንግድን መቆጣጠርም እንደሚያግዝ ያስረዳሉ። •ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠየቁት ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ረቂቅ ህጉ ላይ ከልመና ጋር በተገናኘ ተጠያቂ የሚሆነው ወይም የሚቀጣው ሰጪው እንደሆነ ጠቅሰው የጎዳና ተዳዳሪዎችንም የማገገሚያ ማዕከል ተዘጋጅቶ ወደዚያ ገብተው የሥነ ልቦና ትምህርት፣ የሞያ ስልጠና እንዲያገኙና ወደ ሥራ እንዲገቡ የማቋቋም ሥራዎች ይሰራሉ ብለዋል። "በመቆጣጠርና በመከልከል የሚፈለገው ላይ ስለማይደረስ፤ ከማስገደዱ በላይ የግንዛቤ ሥራ መቅደም አለበት። በተለይ የሃይማኖት ተቋማት እዚህ ላይ ከፍተኛ ሚና ስላላለቸው መተማመን ላይ መደረስ አለበት" ይላሉ አክለውም። "በዚህ ሁኔታ የሐይማኖት አባቶች ትብብር ካላደረጉ የሚሳካ ስላልሆነ፤ ተቋማትን ማወያየትና የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ውይይቶች ይደረጋሉ። ከህብረተሰቡ ጋር መተማመን ከተደረሰ በኋላ ነው ወደ ማፅደቁ የምንሄደው" ብለዋል። የወሲብ ንግድን በተመለከተ ረቂቅ ሕጉ ራሳቸው በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩትን ለመቅጣት ያሰበ ሲሆን፤ ከዚያም በተጨማሪ የምክር አገልግሎት የመስጠት ከሚገኙበት አካባቢ እንዲነሱና ህይወታቸውን እንዲቀይሩ የማድረግ ሥራ ይሰራል ብለዋል። በቀድሞ የወሲብ ንግድ ትተዳደር የነበረችው ምፅዋ የረቂቅ ሕጉን ሐሳብ ደግፋ "በጣም የሚያስከፋ ሥራ ነው። ግን ለእነዚህ ሰዎች ምንድን ነው የሚደረግላቸው? ብዙዎች የልጆች እናትና የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደመሆናቸው መጠን መንግሥት ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል" በማለት አስተያየቷን ሰጥታለች። "እየተገረፉ፣ እየታሰሩ፤ እርቃናቸውን ብርድ ላይ ብዙ ነገር እየደረሰባቸው ነው እያሳለፉ ያሉት" የምትለው ምፅዋ፤ በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች የፀጥታ ኃይሎች በደል እንደሚያደርሱባቸው ጠቅሳ መስተካከል እንዳለበትም ትናገራለች። •በአዲስ አበባ ተማሪዎች በዲዛይነሮች የተዘጋጀ የደንብ ልብስ ሊለብሱ ነው እንዲህ አይነት ሕግ ሲረቅ መንግሥት የሚጠበቅበትን ማከናወን አለበትና በወሲብ ንግድ ተሰማርተው የነበሩ ግለሰቦች ምንም አይነት እርዳታ እንደማይደረግላቸውም ትጠቅሳለች። "እኛ አሁን በቀበሌ ደረጃና የተለያዩ የመንግሥት መዋቅሮች ያውቁናል። ግን ምንም የሚደረግልን ነገር የለም፤ እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ እያለን እርዱን ብለን የምናለቅስበት ጊዜ ነበር፤ በቅድሚያ ማደራጀትና ማስተማር ያስፈልጋል" ትላለች። ከዚህም በተጨማሪ ብዙዎቹ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሰዎች በሱስ የተጠቁ ከመሆናቸው አንፃር ያንን ነገር ለማስወገድ መጀመሪያ መሰራት እንዳለበትና የትራንስፖርትና የእለት ጉሮሯቸውን ለመሸፈን የሚያስችል ድጎማም ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ተግባር እንደሆነ አበክራ ትናገራለች። "ረቂቅ ሕጉ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን መጀመሪያ የህብረተሰቡን ችግር መረዳት አለበት። እኛም የወጣነው በፈታኝ ሁኔታ ነው" ትላለች። ለረዥም ዓመታት በወሲብ ንግድ ተሰማርታ የቆየችው ሐይማኖት ከምፅዋ የተለየ ሀሳብ የላትም። እሷም በሁኔታው ተደስታ ነገር ግን የድጋፍ ሥራ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ታስረዳለች። መንግሥት ትኩረት አድርጎ በእውቀት፣ በትምህርት፣ እንዲሁም ሰርተው የሚበሉበትንና የሚደራጁበትን ቦታ በማሰብ ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚገባ ገልፃለች። "ድጋፍ ከሌለ ከዚያ ህይወት መላቀቅ እጅግ በጣም ከባድ ስለሆነ፤ እኔ ራሱ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ነው መውጣት የቻልኩት፤ እኔ ራሱ በድጋፍ ሰጪ ድርጅት ነው መውጣት የቻልኩት" ብላለች። መንግሥት ይህንን ሕግ ሲያፀድቅ ዝግጅት አድርጎ ሊሆን እንደሚችልም ግምቷን አስቀምጣለች። "በአንዴ አቁሙ የሚል ነገር የለም። ምን ሊበሉ፣ ምን ሊጠጡስ፤ ቤት ኪራዩስ፤ ቦታ፣ ትምህርት፣ ገንዘብ አዘጋጅቷል ብዬ አስባለሁ። ካለዚያ ግን የታሰበውን ውጤት አያመጣም። ዝግጅት ሳይደረግ ያፀድቁታል ብዬ አላስብም" ትላለች። በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ግለሰቦች ከተጠቃሚው እስከ ፖሊስ ድረስ ግፍ እንደሚደርስባቸውም ትናገራለች። "ማንኛውም አይነት ችግር ቢደርስ ተሰሚነት የላቸውም፤ በዳይ እኛ ተደርገን ነው የምንታየው። ስንደበድብ፣ ጫካ ስንጣል፤ በጣም ራቅ ካለ ስፍራ ከአዲስ አበባ ውጪ ይጥሉ ነበር፤ ይህ ሁኔታ በአሁኑ አሰራር ይቀየራል" ብላ ታስባለች።
news-44882464
https://www.bbc.com/amharic/news-44882464
ስለኤርትራና ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አምባሳደር
ኤርትራን ነፃነቷን ማግኘቷን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ዕውቅናን ለመስጠት የመጀመሪያው ሆነ። አቶ አውዓሎም ወልዱም በ1986 ዓ.ም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አሥመራ ላይ ተሾሙ። የመጨረሻ አምባሳደር ይሆናሉ ብሎ ግን የጠበቀ አልነበረም።
ከሰባት ዓመታት ቆይታ በኋላ ግን የሁለቱ ሃገራት ጦርነቱ በመቀስቀሱ የመጨረሻው አምባሳደር ሆነዋል። "ሁለቱ ሃገራት በነበራቸው ግንኙነት እንደ ሁለት ሃገራት ሳይሆን እንደ አንድ ሃገር ነበሩ" የሚሉት አቶ አውዓሎም የኤርትራ መንግሥት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ ፖለቲካና ሌሎች ጉዳዮች ጣልቃ ይገባ ነበር ይላሉ። • ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ቢቢሲ አማርኛ፡ ከጦርነቱ በፊት የነበረው የሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዴት ይታያል? አቶ አውዓሎም፡ ኤርትራ እንደ ሃገር ሆና ብትቆምም የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው እንደ ሁለት ሃገራት አልነበረም። በተለይ የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው ከኢትዮጵያ ብዙ ሃብትን በመውሰድ ነው። በቀላል አማርኛ ለመግለፅ ኢትዮጵያን እንደ የጓሮ አትክልት ስፍራ ነው የወሰዷት። ከዚያም በተጨማሪ በንግዱም ዘርፍ ሆነ በሌሎች ጉዳዮች የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት ያሳይ ነበር። በተለይም በንግዱ ዘርፍ የኢትዮጵያ ሃብት የሆኑትን ልክ እንደ አንድ አምራችና ላኪ በመሆን ለምሳሌ የቡና ምርቶችን፣ ሰሊጥ፤ በኮንትሮባንድና የወርቅ ንግድ ይሳተፉ ነበር። የውጭ ምንዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥት ይፋዊ ካስቀመጠው የልውውጥ መጠን ውጭ እነሱ በከፍተኛ ደረጃ በጥቁር ገበያ ዘርፍ ኤምባሲው እሱን ይሰራ ነበር። ብዙ እልባት ያላገኙና ግልፅ ያሉ አካሄዶች ነበሩት። የጋራ የገንዘብ መገበያያ ፣ የወደብ አጠቃቀም የጠራ አካሄድ አልነበረውም። ከዚህም በተጨማሪ በሁለቱ ሃገራት የሚገኙት የየሃገራቱ ህዝቦችን በተመለከተ በዝርዝር ተሂዶ የእነሱ መብትና የሥራ ስምሪት በሚገባ ተለይቶ የሄደበት ሁኔታ አልነበረም። የድንበር አከላለሉም በውዝፍ የቆየ ሥራ ነበር። ብዙ ክፍተቶች ተፈጥረው ነው ግንኙነቱ የተመሰረተው፤ በጊዜው ልክ እንደ ሌሎች አገሮች እንደ ሁለት ሃገር ሆነው የሚሄዱበት ሁኔታ ከጅምሩ አልተሰመረም፤ አልተቀየሰም። ኢህአዴግም ሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ሥራ አልሰሩም። ኢህአዴግ እንደ መንግሥት እኔም በነበርኩበት ወቅት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ኃላፊነታችንን ተወጥተናል የሚል አቋም የለኝም። እነዚህ ሁሉ ክፍተቶች ለጦርነቱ እንደ ቆስቋሽና መነሻም ነበሩ። • ኤርትራዊያን የሚሿቸው አምስት ለውጦች ቢቢሲ አማርኛ፡ የኤምባሲው ሚና እንደ ሌሎች ሃገሮች ነበር? ወይስ ከኤርትራ ጋር በነበረው ግንኙነት ሚናው ይለያል? አቶ አውዓሎም፡ ለየት ይላል ምክንያቱም የምፅዋና የአሰብን ወደቦች ብቸኛው ተጠቃሚ የኢትዮጵያ መንግሥት ስለነበር በሁለቱንም ወደቦችና ላሉት ሥራዎች በሙሉ እንደ በላይ ሃላፊ ሆኖ የውስጥና የውጭ ገቢውን የሚቆጣጠረው ኤምባሲው ነበር። ከአሥመራ ውጭ በአሰብና በምፅዋ ኢትዮጵያ ቆንስላ ነበራት። ኢትዮጵያና ኤርትራ በጋራ ኖረው ሁለት አገር ስለሆኑ፤ በሁለቱም አካባቢ የሁለቱም ህዝቦች ነዋሪዎች አሉ። በዚህም ምክንያት ትንሽ ዘርዘር ያለና እስከ አሰብ ድረስ ሙሉ ዕውቅና ያላቸው በኢትዮጵያ በጀት የሚተዳደሩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ባንክ፣ የጉምሩክ ሥራዎች፣ መሬት ላይ ነበሩ። ከዚህም በተጨማሪ የድንበር ማካለል ጉዳይ፣ በጋራ ብር የመጠቀም ሁኔታ፣ ንግድን የመሳሰሉት ጉዳዮች በጋራ መወሰን ያለባቸው ናቸው። በሌሎች ሃገሮች ያሉትን ኤምባሲዎቻችንን ስናይ ምንም እንኳን በኢኮኖሚውም ሆነ በማህበራዊ ዘርፎች ሁለትዮሽ ግንኙነት ቢኖረንም እንደ ሁለት ሃገራት ነው ስምምነቶቹም ሆነ የንግድ ሽርክናዎች የሚመሰረቱት፤ ከኤርትራ ጋር ለየት ያለ ግንኙነት ነበረን። ቢቢሲ አማርኛ፡ የሁለቱ ሃገራት ህዝቦችስ በሚጓጓዙበት ጊዜ የኤምባሲው ሚና ምን ነበር? አቶ አውዓሎም፡ በአጎራባች አካባቢ ባሉ ለምሳሌ በአፋርና በትግራይ አካባቢዎች፤ ህዝቡ በአቅራቢያው ባሉት መስተዳድሮች የራሳቸውን አሰራር ፈጥሮ በነፃ እንዲንቀሳቀስ ተደርጓል። የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማዳበር በድንበር አካባቢ የነበረው የቁጥጥር ሁኔታ ቀለል ያለና ነፃነት ያለው ነበር። በተረፈ ግን በአውሮፕላን የሚጓጓዙት አየር ማረፊያዎቹ ላይ ሲደርሱ ቪዛ የሚያገኙበት መንገድ ተመቻችቶ ነበር። ሳይተገበር ጦርነቱ ተነሳ እንጂ በሂደትም የነፃ ቀጠና እንዲሆን ተወስኖ ነበር። ቢቢሲ አማርኛ፡ የጦርነቱን መነሻ የመጀመሪያ ዓመታት እንዴት ያዩዋቸዋል? አቶ አውዓሎም፡ የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት እንደ ጫጉላ አይነት ነበር። በዝርዝር ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የሄድንበት ሁኔታ አልነበረም። ለምሳሌ የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥት ሳያማክር ነው የራሱ መገበያያ ገንዘብ ናቅፋ ያሳተመው። ይህንንም ሁኔታ ተከትሎ እንደማንኛውም ሃገር የመገበያያ ገንዘብ ሁለቱ ሃገራት በመረጡት እንገበያይ ማለቱ ጦርነቱን ቀስቅሶታል። የባድመ ጉዳይና የድንበር ማካለሉ ጉዳይ እንደ ችግርም አጀንዳም አልነበረም። ከጦርነቱ መቀስቀስ ጀርባ መነሻ ያሉት በሙሉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ነበሩ። የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን በመጨረሻ አይቶታል። • ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የኢትዯጵያና የኤርትራ ሕዝቦች አንድ ናቸው አሉ ቢቢሲ አማርኛ፡ ጦርነቱ ሲነሳ እርስዎ በወቅቱ የት ነበሩ? በአሥመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዕጣ ፈንታስ ምን ሆነ? አቶ አውዓሎም፡ ጦርነቱ ከመጀመሩ ከቀናት በፊት አዲስ አበባ አንድ ስብሰባ ነበር። ድንበር ማካላል የሚባል አንድ የተዋቀረ ኮሚቴ ነበር። እኔም ከልዑካኖቹ ጋር አዲስ አበባ ነበርኩ። የኤርትራ ልዑካንም ሳይነግሩን ተመለሱ ከቀናት በኋላ ጦርነቱ ተነሳ። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይገኝ የነበረው አሥመራ ማሪናዮ የሚባል አካባቢ ሲሆን፤ የድሮ የባሕር ኃይል መስሪያ ቤት የነበረና የኤርትራ ህዝበ-ውሳኔውም የተካሄደው እዚሁ ነው። ያው ኤምባሲው ተዘጋ፤ ዋነኛ ንብረት የምንላቸውንም በመርከብ ጭነን ተመለስን። ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት በሲኤምሲ አካባቢ ወደ 23 ሺ ካሬ ሜትር ለኤርትራ ኤምባሲ ግንባታ ሊያካሂዱ እቅድ ላይ የነበሩ ሲሆን፤ እኛም አሥመራ አየር ማሪፊያ አካባቢ 23 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጥቶን ካርታው ወጥቶ ሥራ ለመጀመር እቅድ ላይ ነበርን። • የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? ቢቢሲ አማርኛ፡ አሁን ሁለቱ ሃገራት የሰላም ስምምነት ላይ ናቸው። ለወደፊትስ ምን ዓይነት ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል? የኤምባሲዎቹስ ሚና ምን ሊሆን ይገባል? አቶ አውዓሎም፡ ሰላምና ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ተፋጠው የነበሩ ሃገራት ከጠላትነት ወጥተው፣ ከጦርነት ወጥተው ግንኙነት መጀመራቸው ግንኙነት መጀመራቸው መልካም ነው። ነገር ግን አሁንም ለጦርነቱ ምክንያት የነበሩ ጉዳዮች ተዳፍነው በጭራሽ ውይይት ሳይደረግባቸው ወደ ሰላም መምጣታቸው መጥፎ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ሁለቱም ሃገራት ሞቅ ሞቅ ያለ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ዘላቂነትን ለመፍጠር በጥልቀት የውይይትና ሥራ ያስፈልገዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከተቻለ የአሰብ ወደብ ባለቤትነት ጥያቄ ማቅረብ አለበት። የዛን ያህል ርቀት የኢትዮጵያ መንግሥት ይሄዳል የሚል ግምት የለኝም ነገር ግን የአሰብን ወደብ እንደ ጥያቄ ማንሳት አለበት። የሰላም መዝሙሩ እንዳለ ሆኖ መሰረታዊ እልባት ካልተገኘለት ትርጉም ያለው ግንኙነት ይሆናል የሚል ዕምነት የለኝም። እንደ ሁለት ሃገራት የኢኮኖሚ ሽርክና፣ወደብን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ አቅጣጫ ቢያስቀምጡ ጋራ የፖለቲካና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች በጣም ከፍተኛ በሆነ ተጠቃሚ ይሆናሉ። የአልጀርስ ስምምነት እንዳለ ሆኖ መሬት ላይ በአፋርም ሆነ በትግራይ ሁለቱ ከጦርነቱ በፊት በነበረው የየራሳቸውን መስተዳድር እንደነበረ ሆኖ ቢቀጥል ጥሩ ነው እላለሁ።
46625732
https://www.bbc.com/amharic/46625732
"ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ
በገዳ ስርዓት ላይ ጥልቅ የምርምር ስራን በመስራት ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ፈር ቀዳጅ ናቸው። ኢትዮጵያ ያላትን ሀገር በቀል የአስተዳደር ሁኔታም ከ45 ዓመታት በፊት በፃፉት "ኦሮሞ ዴሞክራሲ፡ አን ኢንዲጂኒየስ አፍሪካን ፖለቲካል ሲስተም" (OROMO DEMOCRACY : An Indigenous African Political System) በሚለው መፅሀፋቸውም ማሳየት ችለዋል።
ታኅሳስ 9/2011 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬታቸውን ያገኙት ፕሮፌሰር አስመሮም ስለገዳ ስርዓት እንዲሁም መሰል ሃሳቦች ላይ ያጠነጠነ ቆይታ ከቢቢሲ ጋር አድርገዋል። • የቢላል አዛን የናፈቃቸው ሀበሾች • ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፉት ጀርመናዊ ፕሮፌሰር ዱካ አልተገኘም ቢቢሲ፡ የገዳ ስርዓትን ለመመርመር ያነሳሳዎት ምንድን ነው? ፕሮፌሰር አስመሮም፡ መጀመሪያ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ስለ የኤርትራ ባህላዊ ስርዓት ማጥናት አቅጄ ነበር። ወቅቱ እንደ አውሮፓውያኑ 1961 ሲሆን የህዝባዊ ግንባር ኃርነት ኤርትራ እንቅስቃሴ ኤርትራ ውስጥ የተጀመረበት ጊዜ ከመሆኑ አንፃር በጊዜው የነበሩት የትምህርት ሚኒስትር ኤርትራ ሄደህ ጥናት እንድታደርግ አንፈቅድልህም አሉኝ። ምንም አማራጭ አልነበረኝም ተመልሼም ወደ አሜሪካ ሄድኩኝ። በአንድ አጋጣሚ ቤተ መፃህፍት ቁጭ ብየ ስጨነቅ የቤተ መፃህፍቷ ሴትዮ አንተ ከኢትዮጵያ አይደለም እንዴ የመጣኸው የሚል ጥያቄ ጠየቀችኝ። አዎ የሚል ምላሽ ስሰጣትም አንድ መፅሀፍ ከኢትዮጵያ በቅርቡ እንዳሰተሙ ነገረችኝ። ኤንሪኮ ቸሩሊ የተባለ ጣሊያናዊ ፀሀፊ የፃፈውን 'ፎክ ሊትሬቸር ኦፍ ዘ ጋላ' (Folk-literature of the Galla of Southern Abyssinia) የተሰኘ መፅሀፍ ሰጠችኝ። መፅሀፉን ሳነበው በጣም ነበር ያስደመመኝ፤ በመፅሀፉ ውስጥ የገዳ ስርዓትም ሰፍሯል። እናም መነሻ የሆነኝ እሱ ሲሆን፤ አሱ የጀመረውንም ከዳር ለማድረስ ቆርጬ ተነሳሁ። ቢቢሲ፡ በአካባቢው ምን ያህል ቆዩ? ፕሮፌሰር አስመሮም፡ ሁለት ዓመት ያህል በኢትዮጵያ በኩል ቆይቻለሁ። ደርግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ መመለስ አልቻልኩም። እናም ተሻግሬ በኬንያ በኩል ሶስት ዓመት ቆየሁኝ። ቢቢሲ፡ ገዳ ስርዓትን ሲመራመሩ በጣም ያስደነቀዎት ነገር ምንድን ነው? ፕሮፌሰር አስመሮም፡ በምስራቃዊ አፍሪካ በሙሉ የዕድሜ አደረጃጀት ስርዓት አላቸው። ይህ ፖለቲካዊ ሳይሆን ማህበራዊ ስርዓት ነው። ስርዓቱም የተዘረጋው አንድ ሰው ወደ ሌላኛው በእድሜ የሚሸጋገርበትን ለመቀየስ ነው። •በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት በኦሮሞ በኩል ግን ያንን ማህበራዊ ስርዓት ወደተሟላ የፖለቲካ ስርዓት ቀየሩት። በገዳ ፖለቲካ ስርዓት መሠረት ስልጣን ሲወስዱ ገዳ የሚባል መጠሪያ ይኖራቸዋል። የስልጣን ጊዜያቸውም ተገድቦ በመንበረ ስልጣንም ላይ የሚቆዩት ለስምንት ዓመታት ብቻ ነው። የሕይወት ሙሉ ፕሬዚዳንት የሚባል ነገር በኦሮሞ ዘንድ የለም (ሳቅ)። እንዲያውም መጭው አባ ገዳ ገቢውን አባ ገዳ በቀና ስልጣኑን እንዲቀበል ያስገድደዋል። የኦሮሞ የጊዜ አቆጣጠር የተፈጠረውም ለዚያ ነው። በኦሮሞ (በቦረና) ጊዜ አቆጣጠር መሰረት ቦረናዎች ሰባት ከዋክብትና ጨረቃ አብረው የሚወጡበትን ወርና ቀን በመታዘብ ብቻ ያውቁታል። በውስጡ ሥልጣንን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘዴ አለው። የገዳ ስርዓት አራት ክፍሎች ያሉት ሲሆን ለምሳሌ ስድስት አባላት ያሉትን ጉሚን ብንወስድ የመላው ቦረና ጉባኤ ማለት ሲሆን ህግ ወሳኝና ከሁሉም በላይ የሆነ አካል ማለት ነው፤ ከባለሥልጣናቶቹም ጭምር። በጣም የሚያስገርመው፤ ውሳኔ ላይ የሚደረሰው በስምምነት ነው። በምርጫ በአንድ ድምፅ በለጥኩኝ ብሎ ውሳኔ ማስተላለፍ አይቻልም በተቃራኒው ተማክረው ውሳኔ ላይ መድረስ አለባቸው። አዳዲስ ዲሞክራሲ ያላቸው ሀገሮች በወንበር ሲደባደቡ እናያለን፤ ይህ በገዳ ስርዓት ሊሆን አይችልም። እንኳን ይሄ ሊሆን ሰው ተራ ተሰጥቶት (ንግግር ለማድረግ) አባ ገዳውን ጨምሮ ማንም ሰው ሊያቋርጠው አይችልም። • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" ስርዓት ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ቋንቋ አላቸው። የኢትዮጵያ ቋንቋ ተመራማሪዎች የዴሞክራሲ ቋንቋን ለማጥናት መሄድ አለባቸው። እኔ ቋንቋውን ስለማልችል ማድረግ አልችልም። ይህንን ትልቅ ሳይንሳዊ ስርዓት መሆኑን ለማስረዳት ችያለሁ። ቢቢሲ፡ የኦሮምኛ ቋንቋ ሳይችሉ ጥናቱን ማካሄድ ከባድ አልነበረም? ፕሮፌሰር አስመሮም፡ እውነት ነው ከባድ ነው። ነገር ግን አማርኛም አቀላጥፎ መናገር የሚችል አንድ ጎበዝ የሆነ አስተርጓሚ ነበረኝ። እሱ ያልኩትን ያስተረጉማል። እናም ማታ ማታ እንፅፈዋለን። በኦሮምኛም ሆነ በእንግሊዝኛ የተሟላ መረጃ ማግኘት ችያለሁ። ቢቢሲ፡ የገዳ ስርዓት ዘመናዊ አስተዳደር ሊሆን ይችላል? ፕሮፌሰር አስመሮም፡ በደንብ፤ በአሁኑ መፅሀፌ የመጨረሻ ምዕራፍ 'ገዳ ኢን ዘ ፊውቸር ኦፍ ኦሮሞ ዴሞክራሲ' የምጠቅሰው ይህንኑ ነው። የወደፊቱ ትውልድ እንዴት ይጠቀምበታል የሚለውን ግልፅ አድርጎ የሚያመላክት ነው። እስካሁን በሰራሁት ጥናት ስርዓቱን በደንብ መመርመር እንጂ ወደፊት የሚያራምድ ሀሳብ አላቀረብኩም። ጉድለት ይሄ ነው ወይም ነቀፌታየ ይሄ ነው በሚል እንዲሁም ይሻሻል የሚል ሀሳብ አላቀረብኩም። ይህኛው መፅሀፍ ግን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እንዴት መፍጠር ይቻላል የሚለውን ስትራቴጂ ይቀይሳል። እኔ ሀሳቤን አቅርቤያለሁ እንግዲህ የኦሮሞ ሊቃውንት ተከራክረውበት አሻሽለው ግብር ላይ ሊያውሉት ይችላሉ። ቢቢሲ፡ የገዳ ስርዓት ውስጥስ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮችስ ምንድን ናቸው? ፕሮፌሰር አስመሮም፡ ገዳ የተሟላ የፖለቲካ ስርዓት ቢሆንም ሁለት ጉዳዮች መስተካከል ይገባቸዋል። አንደኛው በስርዓቱ ውስጥ ሴቶች ሙሉ በሙሉ የሉም፤ ሊካተቱም ይገባል። ሁለተኛው፤ ስርዓቱ በትውልድ የተከፋፈለ ነው። በዚህ ትውልድ ክፍፍልም መሰረት ልዩነቱ እስከ 50 ዓመት ሊደርስ ይችላል። በጣም ሰፊ የዕድሜ ልዩነት ስላለ ለብዙ ስራ መጠቀም ከባድ ያደርገዋል፤ ሰራዊትም ማዘጋጀት አይቻልም። ቢቢሲ፡ ስለ አዲሱ መፅሀፍ ጥቂት ይንገሩን ፕሮፌሰር አስመሮም፡ አዲሱ መፅሀፌ አራት አዳዲስ ምዕራፎች የተጨመሩበት ሲሆን፤ የመጀመሪያው መፅሀፌ ከአርባ አምስት አመታት በፊት እንደመፃፉ በነዚህ አሥርት አመታት የተደረገው ለውጥ በሙሉ ተካቶበታል። 'ገዳ ኢን ዘ ፊውቸር ኦፍ ኦሮሞ ዴሞክራሲ' የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። ዲሞክራቲክ ኢንስቲትዩሽንስ ኦፍ ዘ ቦረና ኦሮሞ (ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በቦረና ኦሮሞ) የሚለው የመጨረሻው ምዕራፍ ነው። ወደፊት ምን ሊሆን ይገባዋል የሚለውንም አቅጣጫ አመላካች ነው። ይህ መፅሀፍ የተፃፈው ለመጪው ትውልድ ነው። ማስታወሻነቱም ለቁቤ ትውልድና ለቄሮ ነው። ምክንያቱም በስራ ላይ የሚያውለው መጪው ትውልድ ስለሆነ ነው። የአሁኑ ትውልድ ብዙ ኃሳብ አለው ነገር ግን ሁሉም የተውሶ ዕውቀት ነው። የኛ ዴሞክራሲ የእንግሊዝ ስርዓት ነው፤ ለጊዜው ሊያገለግል ይችላል። ነገር ግን የባዕድ ስርዓት ሰው እንደራሱ አያየውም፤ በሱም አይገዛም። እንደራሳቸው ቅርስም አያዩትም። እሱን የሚያፋልስ ኃይል ሲመጣ ምን ይሆናል? ምንም ማድረግ አይቻልም። የራሳቸው ከሆነ ግን ትግል ይጀመራል። በሁሉም ስርዓት መሠራታዊ የዲሞክራሲ መርሆች አሉ። ለምሳሌ በአማራ ባህል አንድ አባባል አለ፤ ይህም 'በሺ ዓመቱ ርስት ለባለቤቱ' የሚል ነው። ኃያላን መጥተው መሬቱን ሊወስዱ ይችላሉ ሆኖም ግን ርስት ለባለቤቱ መመለሱ አይቀርም። እነዚህ ሀገር በቀል የዴሞክራሲ መርሆች ሊበለፅጉ ይገባል። ከስድስት ሳምንታት በኋላ መፅሀፉ ይወጣል፤ እናም ተመልሼ የምመጣ ሲሆን፤ የመፅሀፍ ጉብኝትም በተለያዩ የኦሮሞ ዩኒቨርስቲዎች ላይ አካሂዳለሁ።
news-48735458
https://www.bbc.com/amharic/news-48735458
ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው
ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ባህር ዳር ውስጥ የተከሰተው ነገር ለብዙዎች ያልተጠበቀ ነበር። ድንገት ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ አካባቢ የተሰማው ተኩስ ለሰአታት ቀጥሎ ከተማዋን ያደናገጠ ሲሆን፤ ምን እንደተከሰተ ሳይታወቅ ቆይቶ የተኩስ ልውውጡ በሌሎች አካባቢዎችም አጋጥሟል።
የተኩሱ ምክንያት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መሆኑ በፌደራል መንግሥት ከተነገረ በኋላ እንደ ባህር ዳሩ ከባድ ባይሆንም አዲስ አበባ ውስጥ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዡ መኖሪያ ቤት አካባቢም ተኩስ ተሰምቶ ነበር። • ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ • መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች • የሰኔ 16ቱ ጥቃትና ብዙም ያልተነገረላቸው ክስተቶች በሁለቱ ከተሞች የተከሰተው ነገር በተቀራራቢ ጊዜ ያጋጠመ መሆኑ ደግሞ ምናልባት ተዛማጅ ጉዳዮች ሊሆኑ እንደሚችሉ ሲጠረጠር ነበር። ቅዳሜና ዕሁድ ምን ተከሰተ? ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቃቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ባህር ዳር ቅዳሜ ሰኔ 16/2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ቅዳሜ ሰኔ 16/2011 ዓ.ም ዕሁድ ሰኔ 17/2011 ዓ.ም የመከላከያ ሠራዊት በባህር ዳር ከተማ ከተሰማራ በኋላ ከመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ፈጻሚዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋሉ እንዳሉና ያልተያዙ ሰዎች እንዳሉም እየተገለጸ ነው። የአማራ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ላቀ አያሌው ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ እንዳልተያዙና እየተፈለጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። አዲስ አበባ ውስጥ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዡና ላይ በሌላ ጄነራል ላይ ጥቃት የፈጸመው ጠባቂ መያዙ የተገለጸ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌሊት ላይ በሰጡት መግለጫ በድርጊቱ እጃቸው ያለበት በሙሉ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አመልክተዋል።
news-44454107
https://www.bbc.com/amharic/news-44454107
"አሜሪካ ምኞቷ ሞላላት"፡ ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ያደሩጉትን ውይይት "እምነት የተሞላበት ፣ቀጥተኛና ውጤታማ ነበር" ሲሉ አሞካሹት።
በስምምነቱ አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን የጦር መሳሪያ ፉክክር ለማቆም እንዲሁም ሰሜን ኮሪያም የሚሳይል ሙከራ የምታደርግበትን ክልል ለማጥፋት ቃል ገብተዋል። የኮሪያን ሰርጥ ከኑክሌር መሳሪያ ነፃ ማድረግም በስምምነታቸው ውስጥ ተካቷል። በሰብዓዊ መብት ዙሪያ በተለይም ዜጎችን በግዞት መልክ የሚደረግን የጉልበት ብዝበዛን አስመልክተው ጉዳዩን ከኪም ጋር በነበራቸው የሁለትዮሽ ውይይት አንስተዋል። ኪም የኮሪያን ሰርጥ ከኑክሌር ነፃ ለማድረግ እንደማያመነቱ በንግግራቸው አረጋግጠዋል፤ ይህ ጉዳይ አሜሪካም አጥብቃ ስትሻው የነበረው ነው። ሁለቱ አገራት ወደፊት ለሚመሰርቱት አዲስ ግንኙነት እንደሚተባበሩና አሜሪካም ለሰሜን ኮሪያ የደህንነት ዋስትና እሰጣለሁ ብላለች። የአሜሪካ ተቀማጭ ፕሬዚዳንትና የሰሜን ኮሪያው መሪ ሲገናኙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ።
news-52267350
https://www.bbc.com/amharic/news-52267350
ኮሮናቫይረስ፡ ቢሊየነሩ ቢልጌትስ የኮሮናቫይረስ ሊከሰት እንደሚችል እንዴት ቀድመው ሊያውቁ ቻሉ?
የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ በሀብት ዓለምን ይመራል። 56 ዓመቱ ነው። አግብቶ ፈቷል። አራት ልጆች አሉት። ሀብቱ 124.7 ቢሊዮን ዶላር አልፏል።
ቢል ጌትስ ይከተላሉ። ዕድሜያቸው 64 ነው። ከባለቤታቸው ሜሊንዳ ሦስት ልጆችን አፍርተዋል። 104.1 ቢሊዮን ዶላር ሀብት አላቸው። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ግን የየትኛውም ቢሊየነር ስም እንደ ቢልጌትስ ተደጋግሞ አይነሳም። ለምን? እርግጥ ነው ከ2 ወራት በፊት በቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኩል 100 ሚሊዮን ዶላር ለኮሮናቫይረስ ሕክምናና ተያያዥ ጉዳዮች ወጪ እንደሚያደርጉ ይፋ አድርገዋል። ሆኖም በዚህ በጎ ተግባራቸው አይደለም ይበልጥ ስማቸው እየተነሳ ያለው። • በድብቅ በተዘጋጀ ድግስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 6 ሰዎች ቆሰሉ ምክንያቱም ቢል ጌትስ ወትሮም መስጠት ብርቃቸው አይደለም። እንዲያውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማይክሮሶፍት ኩባንያ ያላቸው ድርሻ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። አብዛኛውን ድርሻቸው ሽጠውታል፤ ወይም አሳልፈው ሰጥተዋል። አሁን በእጃቸው የቀረው ከጠቅላላው 2 እጅ እንኳ አይሞላም። ሀርቫርድን ጥለው ወጥተው ከአጋራቸው ፖል አለን ጋር የመሠረቱት ማይክሮሶፍት ኩባንያ የቦርድ አባልም ነበሩ፤ ለረዥም ዘመን። እሱንም ኃላፊነታቸው ከሳምንት በፊት በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። ጌትስ እጅግ ለጋስ ከመሆናቸው የተነሳ እስከዛሬ 36.8 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የማይክሮሶፍ ኩባንያን ስቶክ በእርዳታ መልክ ሰጥተዋል። ታዲያ ሰውዬውን ከኮሮናቫይረስ ጋር የሚያገናኛቸው ምንድነው? የሴራ ፖለቲካ አራማጆች ኮሮናቫይረስ በአንዳች አሻጥር የተፈጠረ የቤተ ሙከራ ውጤት እንጂ ከቻይና ሁቤይ ግዛት፣ ከዉሃን ከተማ የእንሰሳት ሥጋ ተዋጽኦ ጉሊት የተነሳ አይደለም ይላሉ። ሴራቸውን ፈትለው ሲጠልፉትም እንዲያውም ቢልጌትስ በቤተ ሙከራ ራሱ የፈጠረው ቫይረስ ነው ይላሉ። ለምን ሲባሉ መድኃኒቱን ራሱ አምርቶ ለመቸብቸብ ሲሉ ይመልሳሉ ከፊሎቹ፤ ሌሎች ደግሞ የዓለምን ሕዝብ ለመቀነስ ሊሆን ይችላል ይላሉ። የዴይሊ ሾው አሰናጅ ትሬቨር ኖዋ በቅርቡ ለቢልጌት ባደረገው ቃለ ምልልስ የመጀመርያ ጥያቄ ያደረገውም ይህንኑ የሴራ ሸራቢዎችን ጥርጣሬ ነው። "ቢል፣ ኮሮናን 'ብዬ ነበር' ለማለት ራስህ የፈጠርከው ቫይረስ ነው ይባላል፤ ለመሆኑ ከ5 ዓመት በፊት የተነበይከው በትክክል ስለዚህ ቫይረስ ነበር ወይስ ስለሌላ ተመሳሳይ ቫይረስ?" ሲል ጠይቆታል። ቢል ጌትስ ሲመልሱም "እኔ ኮሮናቫይረስ ዛሬ ልክ አሁን በተፈጠረበት ጊዜ ይፈጠራል ብዬ አልተነበይኩም፤ ይህ እንደሚሆንም አላውቅም ነበር። ያን ትንቢት የተናገርኩት መንግሥታት ለማይቀረው ወረርሽኝ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለማበረታታት ነበር፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ያ ሳይሆን ቀርቶ የፈራሁት ደረሰ" ብለዋል። • ቻይና ከኮሮናቫይረስ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በቅርብ የታዘበው ኢትዮጵያዊ ዶክተር ኮማኪው ትሪቨር ኖዋ ሌላ ጥያቄን አስከተለ፡ "አንተ አንድ ግለሰብ ነህ? እንዴት ነው መንግሥታት እንኳ ሊያውቁ ያልቻሉትን ልታውቅ የቻልከው?" ቢል ጌትስ ሲመልሱ፣ "እኔ ብቻ አይደለሁም ስጋቴን ቀድሜ የገለጽኩት፤ እኔ በፈራሁት ያህል ይህ እንዳይደርስ ስጋታቸውን ሲያሰሙ የነበሩ ብዙ ሳይንቲስቶች ነበሩ፤ አንዱ ዶ/ር ፋውቺ ነው" ብለዋል። ጨምረውም፤ "ኢቦላ፣ ዚካ፣ ሳርስና መርስ መጥተው ሄደዋል፤ እድለኞች ነን እልቂት ባለማድረሳቸው። በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፍ የሚችል ወረርሽኝ ወደፊት ቢከሰት ሊያስከትል የሚችለውን ነገር ሳስብ እንቅልፍ ይነሳኝ ነበር፤ ያንን ጭንቀቴን ነው የተናገርኩት. . . " ብለዋል ቢልጌትስ። የሴራ ፖለቲካ በመረጃ ላይ የማይመሰረት የቢሆን ዓለም በመሆኑ የቢል ጌትስ ምላሽ ለብዙዎች የሚታመን ላይሆን ይችላል። ሴራ አራማጆች ቁልፍ ጉዳይ አንስተው ያሻቸውን ሰውና ክስተት አንዱን ካንዱ ይሸርባሉ። ከዚያ ስሜት እንዲሰጥ ከስጋት ጋር ያስተሳስሩታል። ቢል ጌትስ ይህ እንደሚመጣ ቀድመው ማወቃቸው የሴራ ፖለቲካ አራማጆች ሁነኛ አጀንዳ ከሆኑ ሰነባብተዋል። "ቢሊየነሮች ድሃውን የዓለምን ሕዝብ ለመቀነስ" ስለማሴራቸው የቢልጌትስን ንግግር እንደ አንድ ማስረጃ የሚያቀርቡትም ለዚሁ ነው። • ልናውቃቸው የሚገቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር ይዘቶች "ኮምፒውተር ይፈጥራሉ፤ ከዚያ መተግበሪያውን፣ ከዚያ ቫይረሱን፤ አሁን ደግሞ ይህን ወደ ሰው በማምጣት ወረርሽኝ ፈጥረው፣ ከዚያ ክትባቱን፣ ከዚያ መድኃኒቱን እያሉ በዓለም ሕዝብ ይጫወታሉ" ይላል የሴራ ትንተና አራማጆች ክስ። ቢል ጌትስ በ"ቴድቶክ" ምን ነበር የተነበዩት? ቴድቶክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች በሰዓት የተገደበ ንግግር የሚያደርጉበት ዓለም አቀፍ መድረክ ነው። ቢል ጌትስ ከአምስት ዓመት በፊት ያደረጉትን ይህን ንግግር ከ25 ሚሊዮን ሰዎች በላይ በዩቲዩብ መስኮት ተመልክተውታል። ቢል ከባለቤታቸው ሜሌንዳ ጌትስ ጋር እርግጥ ነው ይህ በፈረንጆች ማርች፤ 2015 በካናዳ ቫንኩቨር ቢል ጌትስ ያደረጉት ንግግር "እኚህ ሰው ነብይ ነበሩ እንዴ?" የሚያስብል ነው፤ ያለማጋነን። ያኔ ማንም ልብ ያላለው ይህ አስገራሚ ንግግራቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ሚሊዮኖች በድጋሚ እየተመለከቱት ነው። የዚህ ንግግራቸው ጭብጥ በመጪው ጊዜ የዓለም ስጋት ኒውክሌር ቦምብ ሳይሆን ቫይረስ ነው የሚል ነው። በቅርብ ዓመት አንዳች የቫይረስ ወረርሽኝ መጥቶ ሺዎችን እንደሚገድልም ይተነብያሉ። ይህን ለማስረዳትም አንድ በርሜል እያንከባለሉ ነበር ወደ መድረኩ የወጡት። "ልጅ ሳለሁ ዋንኛው ስጋት የኑክሌር ጦርነት ነበር፤ በቤታችን ጓሮ ምድር ቤት ውስጥ ውሃና ምግብ ማጠራቀሚያ እንዲሆነን ይህንን በርሜል እናስቀምጥ ነበር" ሲሉ ንግግራቸው ጀምራሉ። አሁን ግን ኒውክሌር ሳይሆን ቫይረስ ነው የዓለም ስጋት ሲሉ ትንቢታቸውን ይቀጥላሉ። • ጁሊያን አሳንጅ በድብቅ የወለዳቸው ሁለት ልጆች "ተገኙ" "ለዚያ አይቀሬ የቫይረስ ወረርሽኝ አሁን ዝግጅት ካልጀመርን ኋላ ጉድ ነው የሚፈላው" ሲሉም ንግግራቸውን ይቋጫሉ። እንዴት ታያቸው? ትናንት ምሽት ደግሞ ከቢቢሲ ብሬክፋስት የቴሌቪዥን መሰናዶ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር ቢል ጌትስ። በዚህ ቆይታቸው ያሰመሩበት ነጥብ "ዓለም ለዚህ ወረርሽኝ ቀደም ብሎ ተዘጋጅቶ ቢሆን ኖሮ፣ እንዲሁም ሳይንቲስቶች የሚሉትን ነገር ቀደም ብሎ ሰምቶ ቢሆን ኖሮ. . . ይህ ሁሉ ጥፋት ባልደረሰ ነበር።" አሁን ባለው ርብርብም ቢሆን ጥቂት አገራት ናቸው አስር ከአስር የሚያገኙት፤ አብዛኛው አገር ለወረርሽኙ የሰጠው ምላሽ በጣም ደካማ ነው ሲሉ ተችተዋል። "የዓለም መንግሥታት በቅንጅት መሥራት ነበረባቸው" ሲሉ በተጨባጭ ምን ማድረግ ነበረባቸው? ተብለው የተጠየቁት ቢል ጌትስ ወረርሽኙ እስካሁን ሁለት ምዕራፎች እንደነበሩት በማብራራት ጀምረዋል። የመጀመርያው ቫይረሱ ከቻይና ሳይወጣ የነበረው ጊዜ ሲሆን ሁለተኛው አብዛኛዎቹን ሀብታም አገራትን ካጠቃ በኋላ ያለው ጊዜ ሲሉ ከፍለውታል። የሀብታም አገራቱ ሁኔታ በመጪው የፈረንጆች በጋ መጀመርያ አካባቢ እየተሻሻለ እንደሚመጣም ተንብየዋል። • ነዳጅ አምራች አገራት በታሪክ ከፍተኛ የተባለለት ስምምነት ላይ ደረሱ "አስፈሪው የወርርሽኙ ምዕራፍ የሚሆነው በታዳጊ አገራት በሽታው የተቀሰቀሰ ዕለት ነው" የሚሉት ቢል ጌትስ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያን ጊዜ የሰበሰበውን ቬንትሌተርም ሆነ ሌሎች የሕክምና መሣሪያዎች በእርዳታ ወደ ታዳጊ አገራት ካላስተላለፈ አስፈሪ ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል። ቻይና ገና ከአሁኑ ያን እያደረገች እንደሆነ በመጥቀስ እውቅና ሰጥተዋት አልፈዋል። ቢል ጌትስ ስለታዳጊ አገራት ስጋት ገብቷቸዋል ከቢቢሲ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ቢል ጌትስ ታዳጊ አገራት ይህን ወረርሽኝ ለመቋቋም አንዳችም አቅም እንደሌላቸው አረጋግጠዋል። በሽታውን ታዳጊ አገራት እንዲቋቋሙት በሀብታም አገራት ካልታገዙ በድጋሚ ወረርሽኙ ወደ ሀብታም አገራት ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችልም ስጋታቸውን አጋርተዋል። ክትባት በትክክል መቼ ሊደርስ ይችላል? ሲል የቢቢሲ ብሬክፋስት አሰናጅ ጋዜጠኛ ሲጠይቃቸው፤ ቢል ጌትስ ቢያንስ 10 ኩባንያዎች እጅግ ተስፋ ሰጪ ምርምር እያደረጉ እንደሆነ ጠቅሰው ክትባቱን ተግባራዊ ለማድረግ በትንሹ 18 ወራት እንደሚያስፈልግ አስምረውበታል። ይህም የሚሆነው መንግሥታትና የመድኃኒት ቁጥጥር ኤጄንሲዎች ወትሮ ለመድኃኒት ሙከራ አስገዳጅ ሂደት የነበሩ ነገሮችን ካለው አጣዳፊ ሁኔታ በመነሳት ማንሳት ሲችሉ እንደሆነም ተናግረዋል። "ለምሳሌ በተለመደው አሰራር አንድ አዲስ መድኃኒት ከተወሰደ ከ2 ዓመት በኋላ ምን የጎንዮሽ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚለው ነገር የመድኃኒት ምርት በገፍ መመረት ከመጀመሩ በፊት መጠናት አለበት። ይህ ግን አሁን ካለው ጥድፊያ አንጻር በኮሮናቫይረስ ክትባት ሂደት ሊተገበር የሚችል አይደለም" ብለዋል ቢል ጌትስ። ብዙ ጥብቅ የነበሩ የመድኃኒት ምርት ሂደቶች ደረጃዎች ሕይወትን ለመታደግ ሲባል ሊታፈሉ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በቴድቶክ መድረክ ያደረጉት ንግግር አሁን ስለተከሰተው ወረርሽኝ የሚተነብይ እንደነበር ያስታወሰው የቢቢሲ ጋዜጠኛ "ያን ጊዜ ምነው የዓለም መንግሥታት ሰምተውኝ ቢሆን ኖሮ" የሚል ስሜት ተፈጥሮባቸው እንደሆነ ጠይቋቸው ነበር። • ትራምፕ ጨረቃ ላይ ማዕድን ቁፋሮ እንዲጀመር ለምን ፈለጉ? ቢል ጌትስ ሲመልሱ መንግሥታት ጦርነት ቢከሰት ብለው በጋራም ሆነ በተናጥል የጦር ልምምድ እንደሚያደርጉ አስታውሰው፣ ጦር ሜዳ ከሚያልቀው ሕዝብ በላይ ለሚጨርስ የተህዋሲያን ወረርሽኝ ግን ምንም ግድ አልነበራቸውም፣ በጀትም አይመድቡም ነበር ብለዋል። ኮሮናቫይረስ ካለፈ በኋላ ዓለም የሚቀጥለውን ወረርሽኝ እንደከዚህ በፊቱ እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ ይጠብቅ ይመስልዎታል ወይ? ተብለው የተጠየቁት ቢል ጌትስ "ይህ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል። ኮማኪው ትሬቨር ኖዋ ቢል ጌትስን እንግዳ ባደረገበት መሰናዶው ለቢል ጌት በመጨረሻ ካቀረበላቸው ጥያቄዎች መሀል አንዱ የሚከተለው ነበር፡- "ይህ እንደሚመጣ ተንብየው ሆኖልዎታል? ቀጥሎ የሚመጣብንን መቅሰፍት ሊነግሩን ይችላሉ? ከአሁኑ እንድንዘጋጅ?" ቢል ጌትስ ጥያቄውን በፈገግታ ነበር የመለሱለት። ዓለም ከኮረናቫይረስ ቅጣት በቂ ትምህርት መውሰዱን ያመኑ ይመስላሉ።
news-56827447
https://www.bbc.com/amharic/news-56827447
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡ ጥቃት የፈጸመው 'የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ' ነው ሲል የክልሉ ፖሊስ ገለጸ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ውስጥ የሴዳል ወረዳ ከተማ የሆነችውን ዲዛንን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ያዋለው የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ (ጉሕዴን) መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ገለጸ።
ጥቃቱ የተፈጸመበት የካማሺ ዞን ከመተከል ዞን በስተደቡብ የሚገኝ ነው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ምስጋናው እንጂፋታ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ታጣቂው በክልሉ ውስጥ ካሉ ሦስት ዞኖች በካማሺ ውስጥ የሚገኘውን የሴዳል ወረዳ ከተማን ተቆጣጥሮታል። በምዕራብ ኢትዮጵያ ቤኒንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ካማሺ ዞን ውስጥ የሚገኘው ሴዳል የወረዳ በታጣቂዎች ቁጥጥር ሰር መዋሉን ቀድሞ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ነው። ነገር ግን የኮሚሽኑ መግለጫ ታጣቂው ኃይል የተቆጣጠረው ሴዳል ወረዳን ነው ቢልም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ግን ወረዳው ሳትሆን የወረዳው ከተማ ዲዛ መሆኗን ለቢቢሲ ገልጿል። የሴዳል ወረዳ ላለፉት ሦስት ሳምንታት "ከፍተኛ ስጋት" ውስጥ እንደነበረች የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው እንጂፋታ ለቢቢሲ የገለጹ ሲሆን፤ ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ላይ ታጣቂዎቹ ከሰኞ ሚያዝያ 11/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሴዳል ወረዳን "ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ መቆጣጠራቸውን" ደረሱኝ ያላቸው መረጃዎችን ጠቅሶ ገልጿል። ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ጥቃት ፈጻሚው የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲ ንቅናቄ (ጉሕዴን) መሆኑን ጠቅሰው፣ ከሴዳል ወረዳ ከመለመላቸው በርካታ ወጣቶች ጋር በመሆን ጥቃቱን ፈጽሟል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ታጣቂው ኃይል ከዚህ ቀደም በመተከል አካባቢ የተለያዩ ጥቃቶች መፈፀሙን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ "የጉሙዝ ሕዝብን ነጻ እናወጣለን" በሚል እንደሚንቀሳቀስ አስረድተዋል። ጉሕዴን ከዚህ በፊት በሕጋዊነት ለመንቀሳቀስ ተመዝግቦ የነበረ ተፎካካሪ ፓርቲ መሆኑን እና በአምስተኛው ምርጫ ላይም የተሳተፈ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ፓርቲው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሙሉ በሙሉ ወደ ትጥቅ ትግል መግባቱንም አብራርተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት ከሱዳን 25 ኪሎ ሜትር በሚርቅ ስፍራ ላይ 'መርሾ' የሚባል ቀበሌ ውስጥ እነዚህ ታጣቂዎች የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ እንዲሁም ሦስት ንፁሃን ዜጎች ገድለው እንደነበር ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። እንደ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ በርካታ ነዋሪዎች፣ የወረዳው አስተዳደር እና ፖሊስ አካባቢውን ጥለው ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ሸሽተዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንም ይህንኑ አረጋግጦ የሴዳል ወረዳ ከተማ ሙሉ በሙሉ በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ስር መዋሏንና በዚህም የሞቱና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም ብሏል። ቢቢሲ የቡድኑን አመራሮችንም ሆነ አባላት በማግኘት ስለቀረበባቸው ክስና ስለተፈጸመው ጥቃት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ከሴዳል ከተማ የተፈናቀሉ ሰዎች ምን ይላሉ? ከሴዳል ወረዳ ሸሽተው በምዕራብ ወለጋ ወደምትገኘው መንዲ ከተማ የሸሹት አቶ ተክሌ ኪባ ማክሰኞ ዕለት ጠዋት ወደ 11 ሰዓት ገደማ ተኩስ መከፈቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ማክሰኞ ጠዋት 11 ሰዓት አካባቢ ተኩስ ተጀመረ። ጦርነቱ ሲጀመር እኛ ቤት ውስጥ ነበርን። ከሁለት ሰዓት እስከ ሶስት ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ጦርነቱ ከተካሄደ በኋላ ማንነቱ ያልታወቀ አካል ቤት ለቤት በመግባት ሰዎችን በማስወጣት ሌሎቹን በመግደል ቀሪዎቹን አርዷል" በማለት የነበረውን ሁኔታ ይናገራሉ። በከተማው ሆቴል እንደነበራቸው የሚናገሩት አቶ ተክሌ፣ እነዚሁ ታጣቂዎች ወደ ሆቴላቸው በመግባት ተኝተው የነበሩ አስር ሰዎችን ይዘው መሄዳቸውን ተናግረዋል። "ቤቴን እና በደጃፌ የነበረውን መኪናዬን እሳት ካያያዙበት በኋላ ልጄንና ከእኔ ጋር የነበሩትን ሠራተኞች ይዤ በጀርባ በኩል ወደ ጫካ ሸሸን" በማለት እንዴት እንዳመለጡም ይናገራሉ። አቶ ተክሌ ባለቤታቸውን እና ልጃቸውን ከእርሳቸው ጋር ሲሰሩ የነበሩ ሶስት ሰዎች ይዘው ማምለጣቸውን ይናገራሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ 'የበርካታ' ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይናገራሉ። ይህ የታጠቀ አካል የመንግሥትን የፀጥታ መዋቅር በመስበር፣ የሳድሌ ወረዳ ከተማ የሆነችውን ዲዛ መቆጣጠሩን የሚናገሩት ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው እንጂታ የክልሉ ልዩ ፖሊስ ኃይል ማነስ እንዲሁም የጦር መሳሪያ አቅርቦት እጥረት ለሰላም አስከባሪዎቹ መሸነፍ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። የሴዳሌ ወረዳ ነዋሪዎች በታጣቂዎች ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል ቀድሞ መረጃ እንደነበራቸው እና ይህንንም ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቃቸውን ተናግረዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ ጥቃቱ የተፈፀመው "ፀረ ሰላም" ባሏቸው ኃይሎች መሆኑን አመልክተው፤ እነዚህ ታጣቂዎች በአጎራባቹ የመተከል ዞን ውስጥ ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩና አሁን ወደ ሴዳል በማቅናት ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጸዋል። በታጣቂዎችና በክልሉ የፀጥታ ኃይል መካከል "ከፍተኛ የኃይል አለመመጣጠን አለ" ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ በክልል የፀጥታ ኃይል ላይ እንዲሁም በንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ታጣቂው ኃይል ያደረሰውን ጉዳት ለመመከት ክልሉ ያሰማራው የፀጥታ ኃይል ጋር በቂ እንዳልሆነ የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ ይህንንም በወቅቱ ባደረጉት ግምገማ ለመከላከያ ማሳወቃቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን ታጣቂው ኃይል በወረዳው ስር ወደሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በሚጠጋበት ወቅት የክልሉ ፖሊስ፣ ሚሊሻ እና ልዩ ኃይል ተቀናጅተው ለመመከት ጥረት ቢያደርጉ አለመሳካቱን ገልፀዋል። አያይዘውም የክልሉ ልዩ ኃይል በሰው ኃይልና በጦር መሳሪያ በአግባቡ አለመደራጀቱን ተናግረዋል። በካማሺ ዞን የተከሰተው ምንድን ነው? ታጣቂዎች ለተከታታይ ቀናት በካማሺ ዞን ውስጥ በሚገኘው የሴዳል ወረዳ ላይ የሰነዘሩትን ጥቃት ተከትሎ ወረዳዋን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። ስፍራው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደቡባዊ ክፍል ውስጥ የሚገኝ አካባቢ ሲሆን በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ወድቃለች በተባለችው የሴዳል ወረዳ ውስጥ ከ25 ሺህ በላይ ነዋሪዎች እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ጠቅሷል። ታጣቂዎቹ በወረዳው ላይ በሰነዘሩት ጥቃትም በርካታ ነዋሪዎች፣ የወረዳው አስተዳደር እና ፖሊስ አካባቢውን ጥለው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለመሸሽ መገደዳቸውን ጨምሮ አመልክቷል። በጥቃቱም ወረዳውን የተቆጣጠረው ታጣቂ ቡድን የመንግሥት እና የግለሰብ ንብረቶችን ማውደሙን፣ የአካባቢውን ነዋሪዎች፣ የወረዳውን እንዲሁም የዞን አመራሮችን ጨምሮ የመንግሥት ሠራተኞችን የገደለና ያገተ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል። ኮሚሽኑ ስለሁኔታው ያነጋገራቸው የሴዳል ወረዳ ነዋሪዎች የታጣቂው ኃይል በአቅራቢያ ካለው የመንግሥት ኃይል አቅም በላይ መሆኑን ገልጸው፤ ድጋፍ ለመስጠት ተልኳል የተባለው ተጨማሪ የፀጥታ ኃይልም ወደ ስፍራው እንዳልደረሰ ተናግረዋል ብሏል። ኢሰመኮ በዚህ መግለጫው ላይ ጥቃት ፈጽሞ ወረዳዋን በመቆጣጠር ግድያና የተለያዩ ጥፋቶችን ስለፈጸመው ታጣቂ ኃይል ማንነት ያለው ነገር የለም። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት በአፋጣኝ የአካባቢውና የክልሉን የፀጥታ ኃይል በማጠናከር ተጨማሪ የሰዎች ሞትና የከፋ ሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንዳይከሰት እንዲከላከል ጥሪውን አቅርቧል። ኮሚሽኑ እንዳለው "ይህ ክስተት በክልሉ የቆየው የጸጥታ ችግር እየተባባሰና መልኩን እየቀየረ መምጣቱን የሚያሳይ" መሆኑን ጠቅሶ ይህም ከፍተኛ ስጋት የሚያሳድር ክስተት መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም በአካባቢው የተከሰተውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑንና ከሚመለከታቸው የፌዴራል እንዲሁም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳደር አካላት ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑን ገልጿል። የቤኒሻንጉል ክልል መንግሥት ረቡዕ እለት ባወጣው መግለጫ በተለያዩ ጊዜያት ችግሮች ሲከሰቱ "የውጭ ኃይሎችና የውስጥ ተባባሪዎቻቸው ወደ ባሰ ውጥንቅጥ እና የቀውስ አዙሪት ሊከቱን ጥረት ማድረግ ጀምረዋል" ብሏል። ጨምሮም እነዚህ አገሪቱን ወደ ባሰ ውጥንቅጥ ውስጥ ለመክተት የሚጥሩ ያላቸው ነገር ግን ስማቸውን ያልገለጸው "የጥፋት ቡድኖች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል" ገልጿል። የፌዴራል መንግሥቱም ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ "ጽንፈኛ ኃይሎች የሚያራምዱትን የጥፋትና የብጥብጥ አጀንዳ ሥርዓት እንዲያስይዝ" ጠይቋል። ነገር ግን ይህ የክልሉ መግለጫ በካማሺ ዞን ስለተፈጸመው ጥቃት በተለይ ያለው ነገር የለም። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሦስት ዞኖች የሚገኙ ሲሆን እነሱም መተከል፣ ካማሺ እና አሶሳ የሚባሉ ናቸው። በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ከዚህ ቀደም በታጣቂዎች በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ሰዎች ከሞትና ለመፈናቀል ሲዳረጉ መቆየታቸው ይታወሳል። ከእነዚህም መካከል ለረጅም ጊዜ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲፈጸሙበት የቆየው የመተከል ዞን በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን፤ ይህንንም ለመቆጣጠር በሚል የክልሉና የፌደራል መንግሥት የጸጥታ አካላት በጥምረት የሚመሩት የዕዝ ማዕከል (ኮማንድ ፖስት) በዞኑ ውስጥ ከተቋቋመ ወራት ተቆጥረዋል። ከአራት ወራት በፊት ታኅሣሥ 14/2013 ዓ.ም በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ኢሰመኮን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለሥልጣናት ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ይህንና ሌሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በድርጊቱ ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ በክልልና በፌደራል መንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውና በርካታ የታጠቁ ሽፍቶች እንደተገደሉ ተገልጾ ነበር። የክልሉ መስተዳደር ጥቃቱን የሚፈጽሙት "ጸረ ሰላም ኃይሎችና ሽፍቶች" ናቸው ከማለት ውጪ ጥቃቱን የሚፈጽመው ኃይል ምን አይነት ቡድንና አላማው ምን እንደሆነ አስካሁን በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም። ነገር ግን በበርካታ አካባቢዎች በሚፈጸሙ ጥቃቶች የሚገደሉና የሚፈናቀሉ ሰዎችን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ድርጊቱ የብሔር ማንነትን የለየ መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለእርሻ የሚውል ሰፊ ለም መሬት ያለበት አካባቢ ሲሆን ለዓመታት የዘለቀው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽን እያወዘገበ ያለው በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ግዙፉ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የሚገኝበት ክልል ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ከሁለት ዓመት በፊት ባወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በክልሉ ወደ 1.1 ሚሊዮን እንደሚጠጋ ሕዝብ ይገኛል።
news-44948939
https://www.bbc.com/amharic/news-44948939
ፌስቡክ በቻይና ቢሮውን ሊከፍት ነው
ፌስቡክ ድረገፁ እንዳይታይ በታገደበት ቻይና ቢሮ መክፈት የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ። ድርጅቱ እንዳለው ቢሮው ቻይናዊያን የዴቬሎፐሮችንና የፈጠራ ባለሙያዎችን ለማገዝ እንዲሁም መነሻ የሚሆናቸውን ነገር ለማመቻቸት ያገለግላል።
የቢሮው መከፈት እውን ከሆነ ፌስቡክ በቻይና እግሩን ሲያስገባ የመጀመሪያው ይሆናል። ነገር ግን ከቻይና መንግሥት ድረገፅ ላይ የምዝገባ ፍቃዱ ዝርዝር ስለተነሳ ትንሽ ወሰብሰብ ያለ ነገር እንደሚኖር ኒው ዮርክ ታይምስ ጠርጥሯል። • ፌስቡክ ግላዊ መረጃን አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ • ፌስቡክን ለልጆች? • ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ • በፌስቡክ ማስታወቂያ የተሳካ ጋብቻ ቻይና በአለማችን ትልቋ የማህበራዊ ሚዲያ ገበያ ብትሆንም እንደ ትዊተር፣ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ ያሉ ድረገፆች በሀገሪቱ ስለተዘጉ መጠቀም አይቻልም። ከዛ ይልቅ ለቻይናውያን ብቻ ተብለው በሀገሬው የተሰሩ እና በቻይና መንግስት ቁጥጥር የሚደረግባቸው እንደ ዌይቦ፣ ሬይነርን እና ዩኩት የሀገሬውን የማህበራዊ ድረገፅ ፍላጎት ለማገልገል ጥቅም ላይ ውለዋል። የፌስቡክ መስራች የሆነው ማርክዙከንበርግ በተደጋጋሚ የቻይና ባለስልጣናትን ለማማለል ማንድሪን እስከመማር ድረስ ደርሷል። የፌስቡክ አቻ በደቡባዊ ቻይናዋ ከተማ ሀንግዡዋ የተመዘገበ ሲሆን የ30 ሚሊየን ፓውንድ ካፒታል አለው።
news-43300068
https://www.bbc.com/amharic/news-43300068
‘ቤቴን ከ28 ስደተኞች ጋር እጋራለሁ’
የናይጄሪያ የአደጋ ጊዜ ሃላፊዎች እንደሚሉት ካለፈው ጥቅምት ወዲህ ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ሃገሪቱን ከካሜሮን ጋር በሚያዋስናት ድነበር በኩል መግባታቸው ሲገልጹ ይህ ቁጥርም እያደገ ነው ብለዋል።
ፍራንክ ኦኮሮ ደሞዙን ቤተሰቡንና 28 ስደተኞችን ለማስተዳደር ያውለዋል ስደተኞቹ በደቡባዊ ሃገሪቱ ክፍል ተገንጣዮች የራሳቸውን ግዛት "የአምባዞኒያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ" ብለው መመስረታቸውን ተከትሎ ደም አፋሳሽ ዘመቻ በቶሩ ስለተከፈተባቸው ነው። በደቡባዊ ናይጄሪያ በምትገነው አግቦኪም ቢቢሲ 28 ስደተኞችን በቤቱ ያስጠጋውን እና የአራት ልጆች አባት የሆነውን ፍራንክ ኦኮሮን አግኝቶታል። የ57 ዓመቱ ፍራንክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር እና እምነቱም ጠንካራ ነው። ደሞዙን እና ከካካዋ እና ከከሳቫ እርሻ የሚያገኘውን ገቢም ብዛት ያላቸውን እንግዶቹን ለማስተናገድ እየተጠቀመበት ነው። አንዳንዶቹ ካሜሮናዊት ሆነችው የሚስቱ ዘመዶች ሲሆኑ ሌሎች ግን ምንም ግንኙነት የላቸውም። በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆናቸው ነው አብረውት እንዲሆኑ የፈቀደው። ለሁሉም የሚበቃ ማረፊያ ቦታ ማዘጋጀት ግን አዳጋች ነው። "መሬት ላይ ምንጣፍ እንዘረጋላቸዋለን" ይላል። "ሁሉም ህጻናት መሬት ይተናሉ ወይም ደግሞ እናቶቻቸው አቅፈዋቸው በሰላም ተኝተው ጠዋት እንዲነቁ ነው የምፈልገው።" እንግዶቹ የሚሰራውን የትኛውም ሥራ ያግዙታል። ይህ ማለት "በመርህ ደረጃ የማይሰሩ አይበሉም" ማለት ነው። አብዛኛዎቹ ስደተኞች ሴቶች እና ህጻናት ናቸው እንደገበሬ ብዙ የሚሰሩ ሥራዎች አሉ። "አምላክ በትልቁ እየረዳን ነው" ይላል ፍራንክ። "የቤቱ አባወራ እንደመሆኔ ሁኔታውን ለመቋቋም እኔ ብዙ መጣር ይኖርብኛል" ሲል ያምናል። የሰፊው ቤተሰብ ወይንም የሌሎች ደግ አሳቢዎች ድጋፍ ባይኖር ኖሮ ስደተኞቹ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋጥማቸው ነበር። ከአካባቢውም ሆነ ከዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ የሚያገኙት አንዳንዴ ነው። መሠረታዊ የጤና አገልግሎትም አያገኙም። ልጆቻቸውም የትምህር ዕድል አያገኙም። ከዚህ ውጭ ያላቸው አማራጭ ግን ወታደራዊ ትቃት በሚፈጸምባት ካሜሮን መቆየት ነው መሆኑን ይገልጻሉ። 'በቁጥቋጦ ውስጥ ለስምንት ቀናት ተጉዣለሁ' ወጣት የሆነው አባት ሬኔ ወታደሮች መንደራቸውን ሙሉ በሙሉ አጥፍተው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ከባለቤቱና ከልጆቹ ጋር መለያቱን ለቢቢሲ አስታውቋል። ምስጋና ለአንድ ሞተረኛ ቅን ሰው ይሆንና የሚወዳቸው ሰዎች ከረዥም ጉዞ በኋላ ወደ የናይጄሪያ ድንበርን አልፈው መግባት ችለዋል። እሱ ግን ግጭቱን ለማምለጥ ከሳምንት በላይ በቁጥቋጦ ውስጥ ለመጓዝ ተገዷል። በዚህ ወቅትም ህይወቱን ለማቆት ከቻካ ውስጥ ፍራፍሬ በመልቀም እና የወንዝ ውሃ ለመጠታት ተገዷል። ለሁለት ቀናትም በየቦታው ሲማስን ቆይቶ ነው እግረኛ መንገድ ያገኝው። መንገዱ በናይጄሪያዋ ክሮስ ሪቨር ግዛት ወደምትገኘው ባሱ መንደር የወሰደችው ሲሆን ዕድለኛ ሆኖም ቤተሰቦቹን አግኝቷል። ሬኔ ለሳምንት ያህል ቁጥቋጦ ውስጥ ሲጓዝ ቆይቷል አሁን ከካሜሮን 27 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው ኢኮም ከተማ ነው ተጠልለው የሚገኙት። "በምንደራችን በሠላም ነበር የምንኖረው። በድንገት ወታደሮች ማህበረሰባችንን ወረሩት። በደቂቃዎች ውስት ጥይት ተኩስ ድምጽ ሰማን። ወደ ግራ ወደ ቀኝ መሮጥ ጀመርን። ለስምነት ቀናት በደን ውስጥ ሮጫለሁ።" እንደ 32 ዓመቱ ሰው ከሆነ ይህ ህይወቱ መጥፎ ልምድ ነው። በደን እና በተራራ ላይ ሲጓዝ እግር ላይ ደረሰውን ጉዳት የሚያሳየውን ቁስል አሳይቶኛል። ሬኔ በስደት ጉዞው ወቅት እግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበታል እንደ ብዙ ስደተኞች በማህበረሰቡ አካባቢ ሠላም እሰኪሰፍን ድረስ ወደ ካሜሮን መመለስ አይፈልግም። 'ራቁቴን ወደ ወንዝ ወረወሩኝ' የተሰደዱት ሴቶች በካሜሮን ጦር ጥቃት እንደደረሰባቸው ይገልጻሉ። በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል የምትገኘውንጉማ እሷና ሌሎች ሴቶች በካሜሮን ጦር "ተደብድበው፣ ራቁታቸውን ወደ ወንዝ ውስጥ ተወርውረዋል።" ሌሎች ስደተኞችን ጨምሮ እነሱም ወደ ናይጄሪያ መግባት የቻሉት በጀልባ ነው። ንጉማ ወታደሮች እንደደበደቧት ተናግራለች ሬጂና ደግሞ ግጭት በተቀሰቀሰበት ወቅት ወደ ቤቷ ሮጣ በመሄድ ልጆቿን ልታድን ስትሞክር በሶስት ወታደሮች እንድትቆም ተደርጋለች። ወደ ቤቷ ስትደርስ በወታደሮች መያዟን ገልጻለች። "ባልህ ያልሆነ ሰው ጡትህን ሲይዝህ፤ ወደራሱ አጥብቆ ሲይዝህ... ወታደሮች ድፍራሉ ሲባል ስለሰማሁ መጮህ ጀመርኩ።" "ልጆቼ እየሮጡ ሲመቱ የጦሩ ባልደረባ አይቷቸው ቤቴ ኮሪደር ላይ ለቀቀኝ።" ብዙዎቹ ወደ ናይጄሪያ የሸሹ ስደተኞች በተቀሰቀሰው ግጭት ያዩት ነገር አሁንም ጭንቀት እንደሚፈጥርባቸው ይገልጻሉ። "ነጻነታችን ከታወጀ ወደ መንደሬ እመለሳለሁ" ትላለች ረጂና። "ጦርነቱ የማያበቃ ከሆነ ግን አልመለስም። ምክንያቱም ወታደሮቹን እፈራለሁ። እነዛ ትልልቅ የጦር መሣሪያዎች ልቤ ውስጥ ህመም አኑረዋል።" "የመሣሪያ ተኩስ ድምጽ ስሰማ የሞትኩ ያህል ልቤ ወደ ውስጥ ትገባለች። እነዛ መሣሪያዎች እያሉ ካሜሮን ውስጥ መኖር አልፈልግም።" ሬጂና ቶርነቱ ካልቆመመ ወደ ካሜሮን እንደማትመለስ አስታውቃለች በስደተኞቹ መካከል ስለ ካሜሮን እና ስለተሰደዱባት ናይጄሪያ ትልቅ ጥርጣሬ አለ። በካሜሮን በኩል ባለወ የጦሩ ጥቃት ምክንያት ስደተኞች አሁን ወደ ናይጄሪያ ለመሻገር ያላቸው መንገድ ጠባብ ነው። ህጋዊዎቹ መንገዶች የሚቻሉ አይደሉም። ስለዚህ ድንበሩን ለማቋረጥ ግዴት ሚሆንባቸው ሰዎች በቁጥቋጦ ውስጥ መጓዝ ብቸና አማራጫ\ቸው ነው። ግጭቱ በምን ምክንያት ነው? አብዛኛው ህዝብ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ በሆነባት ካሜሮን አነስተኛ ቁጥር ያላቸው እንግሊዘኛ ተናጋሪ ካሜሮን አካባቢ ነዋሪዎች እንደተገለሉ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ይገልጻሉ። በአውሮፓዊያኑ 2016 በተወሰኑ እንግሊዘኛ ተናጋሪ አካባቢዎች ከወና ወና መንግስታዊ ስራዎች ተገለናል፤ ፈረንሳይ ቋንቋ እና ፍትህ ዘዴ ተጭኖብናል በሚል ላይ ተቃውሞ ተጀመረ። መንግሥት ለዚህ ምላሽ የሰጠው ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ነው። ከዚህ ባለፈ በእንግሊዘኛ ተናጋሪ አካባቢዎች ለረዥም ወራት ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደርጓል። ሆኖም ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን አንዳንዶች ነጻነት ታውጆ "የአምባዞኒያ ፌደራል ሪፐብሊክ" በእንግሊዘኛ ተናጋሪ የሰሜን ምእራብ እና ደቡብ ምዕራብ አካቢዎች እንዲመሠረት ጠየቁ። አንዳንዶች የትጥቅ ትግል የጀመሩ ሲሆን ብዙ ቁጥር ያላቸው ጸጥታ አባላትም ተገደሉ። መንግሥት ሰብዓዊ መብት አያያዝ ጥሰት መኖሩን ያስተባብላል። ጦሩ የሃገሪቱን ሉዓላዊ አንድነት ብቻ እየጠበቀ ነው ይላል። መንግሥት በየትኛውም ቅሬታ ዙሪያ ለመነጋገር በሩ ክፍት ቢሆንም የትኛውንም የመገንጠል ወይም የአመጽ ተግባር እንደማይቀበል ካሜሮን መንግሥት ቃል አቀባይ ኢሳ ቺሮማ ባካሪ አስታውቀዋል። ናይጄሪያ በሰሜናዊ ሃገሪቱ ክፍል በኮ ሃራምን ጥቃትን የሸሹ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮችን ጉዳይ በመፍታት ላይ እያለች ካሜሮን ስደተኞች መጨመር ችግሩን አባብሶታል። ጆን ኢናኩ-በክሮስ ሪቨር ግዛት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኃላፊ አብዛኛዎቹ በደቡባዊ ክሮስ ሪቨር ግዛት እና ማዐከላዊ ቤኑ ግዛት ነው የሚገኙት። "እስካሁን ያለው ልምድ አስቸጋሪ ሲሆን ሰዎች ቁጥር መጨመሩም በጣም የሚያሳዝን ነው። በተለይ ደግሞ በጀቱ ያላካተታቸው ሰዎች ሲሆኑ የከፋ ይሆናል። አይደለም ለመመገብ ለማሰባበሰብም አስቸጋሪ ነው" ሲሉ በክሮስ ሪቨር ግዛት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኃላፊ ጆን ኢናኩ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እና ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ስደተኞቹን ለመርዳት ከሚሞክሩት መካከል ይጠቀሳሉ። የካሜሮን ስደተኞችን በጉልበት ከናይጄሪያ ለመመለስ የሚደረግ ጥረት ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስ በመሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስጠንቅቋል። እንግለዘኛ ተናጋሪዎች ባለቡት ካሜሮን ክፍል ያለው ውጥረት አሁንም ከፍተኛ ሲሆን በናይጄሪያ ያሉ ስደተኞች ምን ኣህል እንደሚቆኡ አልታወቀም። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ቋሚ መጠለያ በየጊዜው እየጨመረ ለሚገኙት ስደተኞች ለማቋቋም ለማስራት እያሰቡ መሁን እየገለጹ ነው። እንደጀራተኞቹ ከሆነ ሠላም የማይመጣ ከሆኑ በመጪዎቹ ጥቂት ወራት የስደተኞች ቁጥር ከሚሊዮን ሊበልጥ ይችላል። እንደዚህ ከሆነ ደግሞ በፍራንክ ቤት በእንግድነት የተገኙት ሰዎች ላልተወሰነ ጊዜ በዛው ሊቆዩ ነው።
46779166
https://www.bbc.com/amharic/46779166
"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ
የ14 አመቷ ታዳጊ አበራሽ በቀለ ጠልፎ አስገድዶ የደፈራትን ግለሰብ መግደሏ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ ነበር። አበራሽ በግድያ ክስ ተመስርቶባት ማረሚያ ቤት የነበረች ሲሆን የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ጥብቅና ቆመውላት ነፃ ሆናለች።
ይህንን እውነተኛ ታሪክም ዕውቅና በመስጠት ከጥቂት አመታት በፊት ዘረሰናይ ብርሃኔ መሐሪ ወደ ፊልም በመቀየር አዘጋጅቶታል። ፊልሙ ታዋቂዋን የሆሊውድ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊን በኤክስኪውቲቭ ፕሮዲውሰርነት ከማሳተፉ በተጨማሪ ሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫልን ጨምሮ ብዙ ሽልማቶችን ማግኘት ችሏል። • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" ከዚህ ፊልም ስኬት ጀርባ ያለው ዘረሰናይ በአሁኑ ወቅት በትልቅ በጀት 'ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ' የሚል ፊልም እየሰራ ነው። በዚህ ፊልም ላይ ታዋቂዋ ዳኮታ ፋኒንግን ጨምሮ የአኳ ማን ተዋናዩ ያያ አብዱል ማቲን፣ የቢግ ባንጉ ኩናል ናይር የተሳተፉበት ሲሆን ከኢትዮጵያም ታዋቂዋ ሙዚቀኛ ዘሪቱ ከበደ ተሳትፋበታለች። ከዩኒቨርስቲ ኦ ኦፍ ሳውዘርን ካሊሮርኒያ በፊልም የተመረቀው ዘረሰናይ ብርሃነ በአዲሱ ፊልሙና በሙያው ዙሪያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፦ ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ የተሰኘው ፊልም ቀረፃው ተጠናቋል ? ዘረሰናይ መኃሪ፦ ቀረፃው ተጠናቋል። ወደ አራት ሳምንት የሚሆን አየርላንድ የቀረፅን ሲሆን በመቀጠልም ድሬዳዋና ሐረር ከተሞች ለ17 ቀናት ያህል ቆይተን ቀረፃውን አጠናቀናል። በዚህ አይነት ደረጃ ፊልም ሲሰራ ሂደቱ በጣም የተለየ ነው። ለሂደቱ አዲስ ባልሆንም በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረን ቀረፃ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የፊልም ባለሙያዎችን ከሆሊውድ ተዋናዮች ጋር ለማዋሃድ መስራት ነበረብን። ብዙ ፈታኝ ጉዳዮች ቢያጋጥሙንም ካሰብነው በላይ በሚያኮራ መንገድ ነው የጨረስነው። •የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን ቢቢሲ፦ በጣም ትልቅ በጀት ያለው እንደመሆኑ መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ መቅረፅ ፈታኝና በጎ ነገሮቹ ምን ነበሩ? ዘረሰናይ፦ ጥሩነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ መቅረፅ መቻላችን በምስል ደረጃ ብዙ አስደማሚ ነገሮችን ሰጥቶናል። በሚገርም ሁኔታ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሞሮኮን አስመስለን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የቀረፅነው። ያለን የመልክአ ምድር ብዛትና አይነት የትኛውንም አገር ማስመሰል ይቻላል። ነገር ግን ሌሎች ሃገሮች ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ብንቀርፀው ደግሞ ጥቅማጥቅሞች ይኖሩት ነበር። ፊልሞች ወደየሃገሮቻቸው እንዲመጡና መዋዕለ ንዋያቸውን በሀገሮቻቸው ላይ እንዲያፈሱ የዘረጉት ስርአት አለ። ከግብር እፎይታ ጀምሮ የፊልም ቁሳቁሶች በነፃ ነው የሚገቡት፤ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለ፤ የፊልም እቃዎቹ እንደልብ ነው። ሆኖም ግን የፊልሙ ታሪኩ ሐረርና ድሬዳዋ ስለሆነ የሚያጠነጥነው፤ ቦታዎቹ ያላቸውን ታሪካዊ ምስል በሌላ ቦታ መተካት አይችልም። ኢትዮጵያ ውስጥ መምጣታችን በገንዘብ ደረጃ ጎድቶናል፤ ዕቃው በሙሉ ከአየርላንድ ተጭኖ ነው የመጣው። ከዚህም በተጨማሪ ሰላሳ ስድስት የፊልም ባለሙያዎች አስመጥተናል። ያ ሁሉ ጉድለት እያለ በምስል ደረጃ የሚሰጠንን ነገር መተካት አንችልም። በሱ በጣም ደስተኛ ነኝ። ከዚህ ሁሉ በላይ ትልቁ ችግራችን የነበረው የፊልም ገንዘብ (ፊልም ፋይናንሲንግ)ና የሶስተኛ ሀገር ስምምነት ( ሰርድ ካንትሪ ትሪቲ ) የለም። ለምሳሌ ሁለቱ ሃገራት አየርላንድና ካናዳ በመካከላቸው ስምምነት ስላላቸው መንግሥት በጥበብ (አርት ኢንዳውመንት) በኩል ድጋፍ አድርጎላቸዋል። ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር እንዲህ አይነት ስምምነት ያስፈልጋታል። ያ ደግሞ ለኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች ብዙ በር ሊከፍትልን ይችላል። ምክንያቱም እንደሚታወቀው ለፊልም የተመደበ ገንዘብ (ፊልም ፋይናንሲንግ) የለም። ማንም ሰው በራሱ ያለውን መኪና ሸጦ፣ ወይም ደግሞ ቤቱን አስይዞ ነው ፊልም የሚሰራው። እንደዛም ሆኖ የሚሰሩት ፊልሞች ከአገር ውጭ መታየት ባይችሉም ሀገር ውስጥ በሚታዩበት ወቅት ትርፉ ይህ ነው ባይባልም ገንዘብ ያስገኛሉ። ድጎማ ቢኖር፣ ለማስታወቂያ ገንዘብ ቢኖር፤ ታሪኩ ሲፃፍ ጀምሮ ፊልሙን ለማዳበር የሚደግፍ ቢኖር የሰውም የማየት ፍላጎት ሆነ ለፊልም ባለሙያዎች የሚከፈለው ገንዘብ የላቀ ይሆናል። ሌላ ስራ እንዳይሰሩና በዚህ በያዙት ሙያ ቀጥለው ሙያቸውን እንዲያዳብሩ ማድረግ ይቻላል። ምንም እንኳን የተለያዩ የሚኒስትር ቢሮዎች ድጋፍ አድርገውልን ቀለል ቢልልንም፤ የፊልም እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት በጣም ከባድ ነበር። ቢቢሲ ፦'ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊን' ወደ ማዘጋጀቱ ስራ እንዴት ገባህ? ለፊልም እንዲመች አድርገህ የፃፍከው አንተ ነህ ወይስ የመፅሀፏ ደራሲ ለዳይሬክተርነቱ ሚና መረጠችህ? ሂደቱን አጫውተን ዘረሰናይ፦ ታሪኩን ያነበብኩት ከአራት አመት በፊት በርሊን የመጀመሪያ ፊልሜን ድፍረትን ልናሳይ በርሊን ሄደን እያለ ነው። መፅሀፉ የተፃፈው በካሚላ ጊብ ሲሆን፤ ሁለት ካናዳውያን ፕሮዲውሰሮች ከደራሲዋ ጋር ተስማምተው ለፊልም እንዲመች አድርገው ፃፉት። በዛን ጊዜ አዘጋጅ እየፈለጉ በነበረበት ወቅት በአጋጣሚ ድፍረትን መመልከታቸውና ድፍረትም የተመልካች ሽልማት ማሸነፉ፤ ከዚያም በፊት ሰንዳንስ ላይም አሸንፎ መምጣቱን በማየት እንዳዘጋጅ ጠየቁኝ። ፅሁፉን ለማንበብ ሁለት ሰዓትም አልፈጀብኝም ፤ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠሁ በመሀል ነው ያነበብኩት፤ እዛው ነው በፍጥነት ነው ፊልሙን ለመስራት የወሰንኩት። ታሪኩን እኔ አልፃፍኩትም። መፅሀፉ ላይ ከነበረው ወደ እይታ እንዴት ይመጣል በሚለው መንገድ አንዳንድ ጉዳዮችን የአርትኦ ስራ (ኤዲት) ሰርቻለሁ። ቢቢሲ፦ ስለ ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ ትንሽ ንገረን? ለምን ፊልሙን መረጥከው? ዘረሰናይ፦ ልብወለድ ታሪክ ነው። ነገር ግን ታሪኩን የሰማው ሰው በሙሉ እውነተኛ ታሪክ ነው ብሎ ነው የሚያስበው። ታሪኩ የ1966 አብዮትን ለሚያውቅና ለኔና ከኔም ከፍ ላሉት የቅርብ ታሪክ ነው።መቼቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረገ ፊልም ነው። በዛን ጊዜ እምነቷን ወደ እስልምና የቀየረች አንዲት የሃያ አመት እንግሊዛዊት ከሞሮኮ የቢላል አልሀበሺን የትውልድ ቦታ ለማየት ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለች። በኢትዮጵያ ቆይታዋም ኢትዮጵያውያኖች መኖሪያ ሰጥተዋት፤ እየኖረች እያለ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ዶክተር ጋር ግንኙነት ትመሰርታለች። በመሀል ለውጡ ተከሰተ፤ እሷ ደግሞ ብትወለድበትም ወደማታቀው ወደ እንግሊዝ አገር ትመለሳለች። ታሪኩ የሚያጠነጥነው ኢትዮጵያ እንዲሁም ሞሮኮ ውስጥ የነበራትን ቆይታ እንዲሁም እንግሊዝ አገር በስደት ከሄደች በኋላ የነበራትን ህይወት ነው። ዋናዋ ገፀ ባህርይ እራሷን እንደ ኢትዮጵያዊ አድርጋ የምትቆጥር ሲሆን እንግሊዝም ከሄደች በኋላ ከኢትጵያውያን ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራት። ቢቢሲ፦ የአብዮቱን ጊዜ ማወቅህና ኢትዮጵያዊ መሆንህ ፊልሙን በተሻለ መንገድ እንድነግር ረድቶኛል ብለህ ታስባለህ? ዘረሰናይ፦ በጣም፤ ፀሀፊዋ ነጭ ነች። የባህል አንትሮፖሎጂ ተማሪ እያለች ኢትዮጵያ ውስጥ በሰባዎቹ መጥታ ስለ ሀረር ሴቶች ፅፋለች። ወደ ኃገሯም ከተመለሰች በኋላ ይህንን መፅሀፍ ፃፈች። የዛን ጊዜ የነበረውን ታሪክ ማወቄና መስማቴ፤ በተለይም ኢህአፓና መኤሶን ውስጥ የነበሩ ግለሰቦችን ታሪክ ማወቄ ለኔ ፊልሙን እንዳዳብረው በትልቅ ደረጃ ረድቶኛል። ምክንያቱም ፊልሙ ላይ በተለይ ኢትዮጵያዊው ገፀ ባህርይ ዶ/ር አዚዝ ከዶክተርነቱና ከፈረንጇ ጋር ካላት ግንኙነት ውጭ ስለሱ ማንነት የሚታወቅ አልነበረም። ምን ያህል ለአገሩ፣ ለነበረው ለውጥ እንደሚቆረቆር እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች መፅሀፉ ላይ የጎሉ አልነበሩም። ከማቃቸው ታሪኮች፣ ካነበብኳቸው መፃህፍት ወስጀ ገፀባህርዩን በደንብ አዳበርኩት። በዛን ጊዜ የነበሩ ወጣቶች እኛ ያልነበረንን አይነት ኃይል ነበራቸው። ያገሪቷን ፖለቲካዊ መንገድ መቀየርና ማሽከርከር የቻሉ ወጣቶች ነበሩን። እናም እሱ ነገር ተድበስብሶ እንዲያልፍ አልፈለግኩም። የኢትዮጵያን ቦታ በታሪክ ላይ ማወቅ፤ ባህላችንን፤ ታሪኩን ከማያውቅ ሰው በበለጠ ፊልሙን እንድሰራ ረድቶኛል። ይሄ እንግዲህ ፊልሙ ሲወጣ የምናየው ይሆናል። ቢቢሲ፦ ምዕራባውያን ወይም ነጭ የፊልም ጸሀፊዎችና አዘጋጆች ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካን ታሪክ የሚያዩት በራሳቸው መነጽር (ዋይት ጌዝ) ነው ተብለው ይተቻሉ። የአፍሪካውያን ታሪክ በነጮች ሲፃፍ ወይም ሲዘጋጅ ባህሉን ካለማወቅ በደንብ መንገር አይችሉም ይባላል። ስለዚህ ምን ታስባለህ? ዘረሰናይ፦ አብዛኛውን ጊዜ እውነት ነው። አውሮፓውያን ወይም ነጭ አዘጋጆች የአፍሪካን ታሪክ ሲናገሩ ከራሳቸው እይታ ነው። ይሄ ችግር ያመጣል። በተለይ "ድፍረት"ን ከሰራሁ በኋላ አንድ ዓመት ያህል በየፌስቲቫሉ እየሄድን ፊልሙን ስናሳይ ብዙ ጊዜ ተናግሬዋለሁ። አፍሪካውያኖች የራሳችንን ታሪክ መናገር መቻል አለብን። የአፍሪካዊን ታሪክ የራሳችን ታሪክ የማድረግ ግዴታም አለብን። በሌላ በኩል ነጮቹ ለምን እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ የሚገቡት ስንል ከኋላቸው ይህንን የሚያደርጉ በጣም ብዙ ትልቅ ሀይሎች አሉ። አንድ ነጭ አዘጋጅ አፍሪካዊ ፊልም መሥራት የሚፈልግ ከሆነ ፊልሙ ፊልም የሚያስብለው በመጨረሻ ወጥቶ ለሕዝብ ሲታይ ነው። ሰው እይታ ጋር ለመቅረብ በጣም ብዙ ገንዘብ ይፈጃል። አንድ ፊልምን ለመስራት ከሚያበቁት ነገሮች መካከል ትልቁ ነገር ፊልሙ የሚሰራጭበት መንገድ ነው። እነዚህ ነገሮች መጀመሪያ ካልተስተካከሉ ፊልሙ ስኬታማ ሆኖ አይወጣም። ስለዚህ አሰራጮች (ዲስትሪቢውተርስ) ኃይል ስላላቸውና አስቀድመው ገንዘብ መስጠት ስለሚችሉ የፊልም ሰሪውን አካሄድ መቀየር ይችላሉ። ማየትና መሸጥ የሚፈልጉት ፊልሙን ሊያይ ይችላል ብለው የሚገምቱት ዓለም ላይ ያለውን ነጭ ተመልካች ስለሆነ፤ ነጮች በሚያዩትና በሚገባቸው መንገድ ነው ፊልሙን መሥራት የሚፈልጉት። ለምሳሌ የማልረሳውና ያስደነገጠኝ ትልቅ ነገር አለ። "ድፍረት" ሰን ዳንስ እንዳሸነፈ ስርጭት እየተስማማን እያለ አንድ ጣልያናዊት አሰራጭ በጣም ፊልሙን ወደደችውና ተደራደረች። ፊልሙን በዓለም ለማሳየትም የ "ወርልድ ዋይድ ራይትስ' መብቱንም መውሰድ ፈለገች። ድርጅቷ ያለው ጣልያን ቢሆንም ጣልያን ሀገር ማሳየት አልፈለገችም። ለምን? ስላት፣ ፊልሙ ውስጥ ምንም ነጭ ገፀባህርይ ስለሌለ ፊልሙን ጣልያን ሀገር ለማሳየትና ለመሸጥ በጣም ይከብዳል አለች። ያላቸው አስተሳሰብ ወይም አንድን ነገር ለመገንዘብ እነሱን የሚመስል ሰው እዛ ውስጥ መኖር አለበት የሚለው ነገር ነው። በጣም አስደነገጠኝ። ከዛ በተጨማሪ ጃፓን ሀገር "ድፍረት" በየቴአትር ቤቱ ለማሳየት የስርጭቱን መብት ከወሰዱ በኋላ ፖስተሩን መቀየር ፈለጉ። ፖስተሩ ላይ የ13 ዓመት ኢትዮጵያዊት ታዳጊ ነው ያለችው። ተመልካች እሱን ካየ አያይልንም ብለው የአንጀሊና ጆሊን ፎቶ እናድርግበት ወይ? ብለው ጠይቀውናል። ለተግባራቸው ምክንያት እየሰጠሁ አይደለም ነገር ግን ሌላ ግፊት ሳይኖርባቸው አፍሪካን በአንድ መነጽር ብቻ የሚያዩ ሌሎችም አዘጋጆች አሉ። ለምሳሌ የኢትዮጵያን ባህልና የናይጄሪያን ባህል አንደ አይነት አድርገው፣ አጣምረው ማሳየት የሚፈልጉ አዘጋጆችም አሉ። የስርጭት መንገዱ እስካሁን በብዛት የተያዘው በነጮችና ለነጮች የሚቀርብ ስለሆነ፤ አንደኛ አፍሪካን እንደ ገበያ አይዩንም። ስለዚህ የነጭ ፊልም ባለሙያዎች ፊልም ሲሰሩ አፍሪካን ለሌላው ሕዝብ እንዴት አድርገው እንደሚያሳዩ ነው። ለዛም ነው እንደዚህ አይነት ፊልሞች ሲሠሩ ታሪኩን በትክክል የመንገር ታሪኩን በደንብ አድርጎ የመወከል ኃላፊነት ያለብን። በዛም ላይ ደግሞ የፈጠራ ችሎታችንን፣ ታሪክ መንገር የምንችል ሰዎች መሆናችንን፣ከሌላው ሀገር ያላነሰ መሆኑን ማሳየትም አብሮ ይመጣል። ቢቢሲ፦ የአፍሪካ ፊልም ቢሆኑም ብዙ ጊዜ በነጮች የተሞሉ ወይም ዋናው ነጭ ተዋናይ እንደ ጀግና ተስሎ ጥቁር ህዝቦችን የሚታደግ ፊልሞች ለረጅም ጊዜ እናይ ነበር። በባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን እንደ ብላክ ፓንተር በጥቁር ተዋንያን የተሞላ ፊልሞችም መታየት ችለዋል። ኔትፍሊክስ ከደቡብ አፍሪካ ፊልም መውሰዱ እና ሌሎች አፍሪካዊ ፊልሞችን ለመውሰድ ክፍት ማድረጉም የተወሰነ እንደተከፈተ የሚያሳይ ይመስላል። "ድፍረት" የነበረውን ዓለም አቀፍ እይታን በማየት፣ አሁንስ ለኢትዮጵያዊ አዘጋጆች ምን ያህል ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ክፍት ነው ብለህ ታስባለህ? ዘረሰናይ፦ በጣም ውስን ነው። ያም የሆነበት ምክንያት አፍሪካ ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በኢንቨስትመንት ወደ ፊልም ማምጣት የሚችሉ በጣም የተወሰኑ ሀገሮች ብቻ ናቸው። አንደኛ ሥራችን እስካልታየ ድረስ ማንነታችን አይታወቅም። በኔ ላይ የደረሰው ትልቅ ምሳሌ ነው። "ድፍረት"ን ሰራሁ፤ ፊልሙ እድል አግኝቶ ከዓለም ሁለተኛ ትልቅ የሚባል ፌስቲቫል ላይ መሳተፍ ቻለ እናም እዛም ማሸነፍ በመቻሉ የፕሮዲውሰሮችና የአዘጋጆች ቀልብ ያዘ። ይህንን ስል በኢትዮጵያዊነቴ ወይም በጥቁርነቴ አዝነውልኝ ያደረጉት አይደለም። በስተመጨረሻ ለማናቸውም ቢሆን ቢዝነስ ነው። ባህላችንን ወይም ታሪካችንን መንገር እንዳለ ሆኖ በሌላ መንገድ ደግሞ ስኬታማ ነገሮች ማድረግ መቻል አለብን። ለምሳሌ "ብላክ ፓንተር"ን የፃፈውንና ያዘጋጀውን ራየን ኩግለርን እንውሰድ እኔና እሱ አንድ ትምህርት ቤት ነው የተማርነው። "ብላክ ፓንተር" ሦስተኛ ፊልሙ ሲሆን ከዛ በፊት "ፍሩት ቬል ስቴሽን " እና "ክሪድ" የተሰኙ በትንሽ በጀት ፊልሞች ሰርቷል። ይህ እድል ሲሰጠው ደግሞ ከዛ በፊት በነበሩት ፊልሞቹ አብዛኛው ጥቁር ተዋናዮችን አሳትፎ ስኬታማ ስለሆነ ነው። 99% ጥቁር ተዋናዮች ያሉበት አሜሪካዊ ፊልም ፊልም ተሰርቶ ሲወጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የፊልም የደረጃ ሰንጠረዥ በመቆጣጠር ገንዘብም ማግኘት እንደሚችል አሳየ። የኔትፍሊክስም አፍሪካ መምጣትና ከደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያ ፊልም መውሰዳቸው የሚያሳየን ለኛ አዝነውልን ወይም ደግሞ የአፍሪካ ታሪክ እንዲህ ነው ብለው የሚመጡበት ሳይሆን ሁሉም ነገር ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው። የአፍሪካ ህዝብ እንደ ትልቅ ገበያ መታየት ጀምሯል። ፊልሞችን ማየት ብቻ ሳይሆን የራሳችንንም ታሪኮች ወደ ውጭ ማውጣት የሚችል ተቋማት መፍጠር እንችላለን። የኢትዮጵያን ፊልሞችን ብናይ በኃይሌ ገሪማ በኩል ስማችን ሲጠራ ቆይቷል። ከዚያም በኋላ ድፍረት፣ ላምብ፣ አትሌቱ በሄዱበት ቦታ አሸናፊ መሆናቸውና ለስርጭት መብቃታቸው በር ከፋች ሆኗል። ከማንኛውም አለም የበለጠ ታሪክ አለን ነገር ግን እሱን መቀየር ካልቻልን የሌሎችን ስራ ተመልካች ወይም የኛን ታሪክ በሌላ እንዲሰራ መፍቀድ ነው። ቢቢሲ፦ በግልህ ፊልም እንደሚሰራ ሰው ፈተናዎቹ ምንድን ናቸው? ዘረሰናይ፦ በጣም መአት ችግሮች ናቸው (ሳቅ) ። ከየት ልጀምር መኖሪያየን ኢትዮጵያ ካደረግኩ ሶስት አመት ሆኖኛል። አሜሪካም እያለሁ ለፊልም ገንዘብ ማግኘት ችግር ነው። ለፊልም ገንዘብ የሚሰጡ ብዙ ተቋማት አሉ። ፊልም ላብራቶሪዎችና ፊልም ፌስቲቫሎች አሉ። ነገር ግን ውድድሩ በጣም ፈታኝ ነው። ከአምስት ሺ ያላነሱ ፎርሞች ይሞላል፣ የፀሀፊው ማንነት፣ ዳይሬክተር ታይቶ አስርና ሃያ ለሚሆኑት ብቻ ተጣርቶ ድጋፍ ይሰጣል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ መስራት ከዚህ የከበደ ነው። ድፍረትን ለመስራት ስምንት አመት ወስዶብናል። አንደኛ አፍሪካዊ (ኢትዮጵያዊ) ታሪክ መሆኑ ብዙ ሰው ሊቀበለው አልፈለገም። ሁለቱ መሪ ተዋንያን ሴቶች መሆናቸውን ደግሞ ሌላው ፈታኝ ጉዳይ ነበር። እኔ ታሪኩን ብቻ ነው ያየሁት የጄንደር (የሥርአተ ፆታው) ፖለቲካው አልገባኝም ነበር። እድለኛ ነኝ የምለው ፕሮዲውሰሯን ምህረት ማንደፍሮን ማግኘቴ ነው። ዋናውን መንገድ ትተን ፊልሙን መደገፍ የሚችሉ ሰዎች ስናፈላልግ የመጀመሪያውን ድጋፍ ያገኘነው ከታዋቂዋ ሰዓሊ ከጁሊ ምህረቱ ነው። አንድ ስዕሏን ሸጣ ድጋፍ አደረገችልን። ምንም እንኳን ጥሩ ታሪክ እስካለው ድረስ ድጋፍ የሚያደርጉ አይታጡም የሚል እሳቤ ቢኖርም እውነታው ግን ታሪክን እንደ ገንዘብ ዕድል አይቶ ድጋፍ የሚያደርግ አለመኖሩ ነው። ቢቢሲ፦ ብዙዎች የሚያውቁህ በድፍረት ፊልም ነው ከድፍረት በፊት የሰራሃቸው ፊልሞች አሉ። ስለነሱ እስቲ ትንሽ ንገረን? ዘረሰናይ፦ እኔ አብዛኛውን ጊዜ የኖርኩት አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ነው። የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየሰራሁ ነበር። እነዛ ስራዎች አሁን ለደረስኩበት ደረጃ አብቅቶኛል። በትንሹ ከፕሮዳክሽን አሲስታንት እስከ ፕሮዲውሰርነት የተሳተፍኩ ሲሆን የኔን ስም ይዘው ባይወጡም ከዋርነር ብራዘርስ፣ ፎክስ ስቱዲዮ፣ ፓራማውንት ጋር ሰርቻለሁ።
news-50172418
https://www.bbc.com/amharic/news-50172418
ጨቅላ ልጅዎትን ከአቅም በላይ እየመገቡ ይሆን?
እንደው ሳያስተውሉት ልጅዎን ከሚገባው በላይ እየመገቡ ይሆን?
የሕፃናት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከ21ኛው ክፍለ ዘመን የጤና እክሎች መካከል አንዱ ነው ይላል የዓለም ጤና ድርጅት። ታድያ እንደሚያስቡት ያደጉ አገራትን ብቻ የሚያጠቃ ችግር አይደለም። ከመጠን ያለፈ ውፍረት የምጣኔ ሃብት ዕድገታቸው ዝቅ ባለ አገራትም በሰፊው ይታያል። • የኢትዮጵያ ተረት ገፀ-ባህሪን በአኒሜሽን • የአገልግል ምግብ አምሮዎታል? ሕፃናት ከመጠን በላይ እንዲወፍሩ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ዋነኛው ከመጠን በላይ መመገብ ነው። ለዚህ ደግሞ ተጠያቂው ቤተሰብ ወይም አሳዳጊ ነው። ታድያ ሕፃናት ምን ያህል መመገብ እንዳለባቸው እንዴት እናውቃለን? የሚመገቡት የምግብ ዓይነትስ? እነሆ አራት መላዎች። የጡት ወተት የእናት ጡት ወተት ለሕፃናት የመከላከል አቅም ይሰጣቸዋል። የጡት ወተት ከተወለዱ በኋላ ለስድስት ወራት ያገኙ ሕፃናት ከተላላፊ በሽታዎች የመጠበቅ ዕድላቸው የሰፋ ነው። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና • ለሰው ልጅ ምርጡ ምግብ እንቁላል ይሆን? ለዚህ ነው ለስድስት ወራት ከጡት ወተት ውጭ የማይሞከረው። አልፎም ለመጀመሪያዎቹ 12 ወራት የላም ወተት ባይመግቧቸው ይመከራል። ይህ የሚመከረው የላም ወተት ያለው የአይረን መጠን ዝቅ ያለ ስለሆነ ነው። ደረቅ ምግብ ሕፃናትን ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት የጡት ወተት ከተመገቡ በኋላ ደረቅ ምግብ እንደሚገቡ ማድረግ አይረን የበዛባቸው ምግቦች መመገብን ይመከራል። ሕፃናት ከጡት ወተት ወደ ደረቅ ምግብ ሲተላለፉ ዳተኝነት ይታይባቸው ይሆናል። እንዲሁም ላይለምዱትም ይችላሉ። ነገር ግን ማስለመድ የግድ ነው። ታድያ የጡት ወተቱ እንዳይረሳ። ጨው እና ስኳር ካላቸው ምግቦች ማራቅ ሥጋና መሰል ምግቦች እንዲሁም ለስላሳ መጠጦች ብዙ ካሎሪ አላቸው። ሕፃናት ይህንን ከለመዱ ለጤናማ ምግብ ያላቸው አምሮት ይዘጋል። ጭማቂም ቢሆን አይመከርም። ምንም እንኳ ጁስ ከፍራፍሬ ቢመጣም ሲብላላ ወይም ሲጨመቅ ብዙ ስኳር ስለሚወጣው ለሕፃናት አይመከርም፤ በተለይ ደግሞ የታሸጉ ጭማቂዎች። ምንም እንኳ ሕፃናት ለብስኩታ ብስኩት ያላቸው ፍቅር ከፍ ያለ ቢሆንም በውስጡ ያለው ጨው የሚመከር አይደለም። ለውዝ እና እንቁላል ሕፃናት ከስድስት ወራቸው በኋላ ለውዝ እና የዶሮ እንቁላል ቢመገቡ ይመረጣል። • ለቤተሰብ ምግብ ወይስ ለህክምና ይክፈሉ? • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ይህ ከአለርጂ ጋር እንጂ ከመጠን ካለፈ ውፍረት ጋር ብዙም ግንኙነት የለውም። የጤና ባለሙያዎች ሕፃናት ለውዝና እና እንቁላል ዘግይተው መመገብ ከጀመሩ ለአለርጂ ሊጋለጡ ይችላሉ ባይ ናቸው። ስለዚህ ከእነዚህ ምግቦች ጋር በጊዜ ማስተዋወቅ የተገባ ነው። በተለይ ደግሞ ከስድስተኛ ወራቸው በኋላ። ነገር ግን ቤተሰቦት ውስጥ ለእነዚህ ምግቦች አለርጂ ያለበት ሰው ካለ የሕክምና ባለሙያ ማማከሩ የሚጎዳ አይደለም። ለነገሩ የሕክምና ባለሙያ ማማከር ለዚህ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ይመከራል። • ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች
news-51414511
https://www.bbc.com/amharic/news-51414511
የኮሮናቫይረስ ስጋት ባጠላበት በርካቶች በአንዴ ተሞሽረሩ
በደቡብ ኮሪያዋ ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ስጋት ባጠላበት በሺዎች የሚቆጠሩ ጥንዶች አንድ ላይ ተሞሸሩ።
ከመዲናዋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ከተማ በተዘጋጀው የሠርግ ስነ-ስርዓት ላይ ሙሽሮች አፍን እና አፍንጫ መሸፈኛ 'ማስክ' አድርገው ታይተዋል። ቀላል የማይባሉት ሙሽሮችና የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ማስክ በማድረግ ከቫይረሱ እራሳቸውን ለመጠበቅ ሲሞክሩ የታዩ ሲሆን በሽታው ያላሰጋቸው 'ማስክ' ለምኔ ብለዋል። ከ60 አገራት የተሰባሰቡ ወደ 6ሺህ የሚጠጉ ጥንዶች በዝግጅቱ ላይ ትዳር መስርተዋል። የዝግጅቱ ታዳሚዎቹ ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የደም ሙቀታቸው ተለክቷል።
news-46944131
https://www.bbc.com/amharic/news-46944131
ግብጽ የሴቶችን የወሲብ ፍላጎት ለማሳደግ 'የሴቶች ቫያግራን' ለገበያ ማቅረብ ጀመረች
ግብጽ የሴቶችን የወሲብ ፍላጎት ለማሳደግ በማሰብ 'የሴቶች ቫያግራን' በማምረት እና ለገብያ በማቅረብ የመጀመሪያዋ አረብ ሃገር ሆነች። ወግ አጥባቂ በሆነችዋ ሃገረ ግብጽ፤ የምርቱ ፈላጊዎች ቁጥር ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል የሚሉ በርካቶች ቢሆንም አምራቾች ግን ገበያው ደርቶልናል እያሉ ነው።
ግብጽ የሴቶችን የወሲብ ፍላጎት ለማሳደግ በማሰብ 'የሴቶች ቫያግራን' በማምረት እና ለገብያ በማቅረብ የመጀመሪያዋ አረብ ሃገር ሆነች። ''እንቅልፍ እንቅልፍ አለኝ፤ ልቤም በፍጥነት ይመታ ነበረ።'' ግብጻዊቷ ላይላ ይህን ያለችው ''የሴቶች ቫያግራ'' ከወሰደች በኋላ ነበር። • የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? 'ፈሊባንሴሪን' የተሰኘው ኬሚካል ለአሜሪካ ገብያ የቀረበው ከሶስት ዓመታት በፊት ነበር። በቅርቡም አንድ የግብጽ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ምርቱን አምርቶ ለገበያ ማቅረብ ጀምሯል። ላይላ- ስሟ የተቀየር- ወግ አጥባቂ በ30ዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ የቤት እመቤት ናት። ላይላ በግብጽ ስለ ግብረ ስጋ ግንኙትም ሆነ ስለ ወሲብ ፍላጎት በግልጽ ማውራት እጅግ ሲባዛ ነውር ነው ትላለች። ምንም አይነት የጤና እክል የሌለባት ለይላ ከ10 ዓመታት የትዳር ቆይታ በኋላ ይህን መድሃኒት ለመጠቀም ፍላጎቱ አደረብኝ ትላለች። ላይላ መድሃኒቱን ያለ ሃኪም የመድሃኒት ማዘዣ ከመድሃኒት ቤት መግዛቷን ታስረዳለች። ''ፋርማሲስቱ ለጥቂት ሳምንታት አንድ እንክብል ከመኝታ በፊት እንድወስድ ነገርኝ። ምንም አይነት የጎንዮሽ ችግሮችን እንደማያስከትል ጨምሮ ነግሮኛል'' ትላለች። ''እኔ እና ባለቤቴ ምን ሊከሰት እንደሚችል ማየት ፈለግን። አንዴ ሞከርኩት። ከአሁን በኋላ ግን ዳግመኛ አልሞክረውም።'' በግብጽ የፍቺ መጠን እያሻቀበ ነው። ለፍቺ ቁጥር መጨመር እንደ ምክንያት እየቀረቡ ካሉ ምክንያቶች መካከል ደግሞ አንዱ በጥንዶች መካከል በወሲብ አለመጣጣም ነው። የሴቶች ቫያግራ አምራች ኩባንያው እንደሚለው ከሆነ ከአስር የግብጽ ሴቶች ሶስቱ ለወሲብ አነስተኛ ፍላጎት ያሳያሉ። ኩባንያው በግብጽ እንዲህ ባሉ ጉዳዮች ላይ ትክክለኛውን ቁጥር ማወቅ አዳጋች መሆኑን በመግለጽ ይህ አሃዝ ግምታዊ መሆኑን ያሳስባል። መድሃኒቱን እየሸጡ የሚገኙ ፋርማሲዎች ከአሁኑ ግበያው እየደራላቸው እንደሆነ ይናገራሉ። ለወሲብ አነስተኛ ፍላጎት ያላቸው ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ በሆነባት ሃገር ''ይህ አይነት ህክምና እጅግ ወሳኝ ነው'' በማለት የኩባንያው ተወካይ አሽራፍ አል ማራጋይ ይናገራሉ። አሽራፍ አል ማራጋይ መድሃኒቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደማያስከትል እና ውጤታማ እንደሆነ በመግለጽ የድብርት እና የድካም ስሜቶች ከጊዜ በኋላ እንደሚጠፉ ይናገራሉ። የመድሃኒቱ አምራች ኩባንያ ይህን ይበሉ እንጂ በርካታ ፋርማሲስቶች እና ሃኪሞች በሃሳባቸው አይስማሙም። በጉዳዮ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የፋርማሲ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነ፤ እንክብሉ ለአነስተኛ የደም ግፊት ሊዳርግ ይችላል። የልብ እና የጉብት ችግር ያለባቸው ሴቶች ላይም ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ይላሉ። በግብጽ መዲና ካይሮ የፋርማሲ ባለሙያ የሆኑት ሙራድ ሳዲቅ መድሃኒቱን ለሚገዙ ደንበኞቻቸው እንክብሉ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ቢያስረዱም ''ሰዎች ግን መድሃኒቱን ለመግዛት ይገዳደራሉ'' ይላሉ። ''በቀን ቢያንስ 10 ሰዎች መድሃኒቱን ይገዛሉ። በርካቶቹ ደግሞ ወንዶች ናቸው። በመድሃኒት ቤቶች ውስጥ ሴቶች መድሃኒቱን መጠየቅ ያፍራሉ።'' ኬንያዊው በኮንዶም ምክንያት መንግሥትን ከሰሰ ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች 'ሁሉም ነገር አእምሯችን ውስጥ ነው' በሙራድ ሳዲቅ መድሃኒት ቤት ውስጥ የሴቶች ቫያግራ ''ሃምራዊው እንክብል'' በማለት የሚያስተቃውቅ ምስል ይታያል። በግብጽ ለወንዶች ታስቦ የሚሰራው ቫያግራ ''ሰማያዊው አንእክብል'' ተብሎ በግብጻዊያን ዘንድ ይጠራል። የአንክብሉ አምራች ''የሴቶች ቫያግራ'' የሚለው ሐረግ ትክክል አይደለም ይላሉ። የአምራች ኩባንያው አምራች አሽራፍ አል ማራጋይ ይህን ስያሜ ይዞ የመጡት መገናኛ ብዚሃን እንጂ እኛ አይደለንም ይላሉ። ለወንዶች ታስቦ የሚሰራው እንክብል ወደ ብልት የሚሄደወን የደም ዝውውር በማሻሻል የብልት አለመቆም ችግርን ይቀርፋል፤ ለሴቶች ታስቦ የተፈበረከው 'ፈሊባንሴሪን' ደግሞ በአእምሮ ውስጥ የንጥረ ነገሮችን ውህድ በማመጣጠን የወሲብ ስሜትን ከፍ ያደርጋል። 'ፈሊባንሴሪን' በአእምሮ ውስጥ የንጥረ ነገሮችን ውህድ በማመጣጠን የወሲብ ስሜትን ከፍ ያደርጋል። '' 'የሴቶች ቫያግራ' አሳሳች ቃል ነው'' ትላለች የወሲብ አማካሪዋ ሄዳ ቆትባ። የወሲብ አማካሪዋ እንደምትለው በእንክብሉ ላይ እምነት ስላላደረባት ታካሚዎቿ እንክብሉን እንዲጠቀሙ አትመክርም። ''አካላዊ ወይም አእምሯዊ ችግር እያጋጠሟት ላለች ሴት፤ ይህ እንክብል በምንም አይነት ሁኔታ መፍትሄ ለሆን አይችልም'' ትላላች ሄዳ ቆትባ። ''ለሴት ልጅ ወሲብ ስሜታዊ ሂደት ነው። ሁሉም ነገር የሚጀምረው አእምሮ ውስጥ ነው። አንዲት ሴት ባሏ እንክብካቤ የማያደርግላት ከሆነ በወሲብ ሊጣጣሙ አይችሉም። ይህን አይነት ችግር ደግሞ መድሃኒት አይቀርፈውም።'' የወሲብ አማካሪዋ እንደምትለው ከሆነ ይህ እንክብል ከሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት ጋር አንጻር መጥፎ ጎኑ ያመዝናል በማለት ታስጠነቅቃለች። በርካታ ግብጻውያን ሴቶች አሁንም ቢሆን ስለ ወሲብ ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በግልጽ አያወሩም። ለይላም ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በወሲብ ያመይጣጣሙ በርካታ ባለትዳር ሴቶችን ታውቃለች። ላይላ ''አፍቃሪ እና ተንከባካቢ የሆነ ባለቤትሽ በወሲብ ደካማ ቢሆን የሚያስፈልገውን የህክምና ድጋፍ እንዲያገኝ ትረጂዋለሽ። በሌላ በኩል ደግሞ ተንከባካቢ እና አፍቃሪ ያልሆነ ባል አልጋ ላይ ምንም ያክል ጎበዝ ቢሆን እንኳ ከእሱ ጋር የሚኖርሽ የወሲብ ፍላጎት እየቀነሰ ይሄዳል። ወንዶች ግን ይህ የሚገባቸው አይመስለኝም'' ብላለች።
news-43885706
https://www.bbc.com/amharic/news-43885706
እራስን መፈለግ፣ እራስን መሆን ፣ እራስን ማሸነፍ
ጥበብን ለዕለት ጉርስ ማግኛ ሳይሆን እራስን ለመግለጥ ብቻ ትጠቀምበት እንደነበር ትናገራለች ሐይማኖት። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግባት የመረጠችው የቤተሰቦቿን ደስታ ላለማክሸፍ ብላ እንጂ በርግጥም በተማረችበት ሙያ ተቀጥራ መንፈሷንም ኪሷንም በእርካታ መሙላት እንደማትችል ቀድሞ ገብቷት ነበር።
በቅድሚያ ሠዓሊ እንደምሆን አውቅ ነበር የምትለው ሐይማኖት የሥዕል ችሎታ እንደነበራት እና እንደምትስልም ወደ ኋላ መለስ ብላ ታስታውሳለች። እርሷ ወደ ሥዕሉ ብትሳብም ቤተሰቦቿ ግን ለኪነ-ጥበቡ ያላቸው ግንዛቤ ተሰጥኦዋን በትምህርት እንዳታስደግፈው አድርጓታል። ከዚህም ባለፈ እርሷ የሕግ ትምህርት ቤት ብገባ ብላ ታስብ ስለነበር ያ ሳይሆን ሲቀር የቤተሰቦቿን ደስታ ብቻ ለማሳካት የአስተዳደር ሙያ አጥንታ ተመረቀች። በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ እያለች ወዳጆቿ በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ነበሩ። እነርሱ በሚያዘጋጇቸው የተለያዩ አውደ-ጥበቦች ላይ እየተገኘች ተሰጥዖዋን ለማሳየት ትጥር ጀመር። የሥዕል ችሎታዋንም ለማዳበር አጫጭር ኮርሶችን ወስዳለች። እናትና ልጅ ጎዳና ላይ እየሄዱ ያነሳችው ይህ ፎቶግራፍ መቼም አይረሳትም የፎቶግራፍ ጥበብ ሐይማኖት ሠዓሊ የመሆን ፍላጎቷን የመኮትኮትና የማሳደግ ሕልሟ በውስጧ እንዳለ ቢሆንም ፎቶ ግራፍ የማንሳት ጥበብ ዝንባሌዋ ደግሞ እያየለ መጣ። ስለዚህ የተለያዩ ፎቶዎችን በስልኳ እያነሳች ለባልንጀሮቿ ታሳይ ጀመር። ከጓደኞቿ የምታገኘው አድናቆትና ውዳሴ ልቧን ያሸፍተው ጀመር። ከዚያ በኋላ መደበኛ ካሜራ በመጠቀም ስሥዬ ሆይ ብላ ፎቶ ማንሳቱን ገባችበት። ሐይማኖት ፎቶ ስታነሳ እንደሠርግ እና ልደት ያሉ ከበራዎች ላይ ተገኝታ ማንሳት ምርጫዎቿ እንዳልሆኑ ትናገራለች። ከዛ ይልቅ የጎዳና ላይ ትዕይንቶችን እየተከተሉ እና እየፈለጉ በማንሳት የምትፈልጋቸው ቁምነገሮች ጎልተው በሌሎች ዓይን እንዲታዮላት ትፈልጋለች። ባለፈው ዓመትም ያነሳቻቸውን ፎቶዎች ሰብሰብ አድርጋ ለሕዝብ እይታ እንዳበቃች ታስረዳለች። እነዚህ ፎቶዎች ስሜቷን ለመግለጥ ብቻ ሳይሆን የዕለት ጉርሷንም ለመሸፈን ረድቷታል። ሐይማኖት ሥራዎቿን ለማስተዋወቅ የማህበራዊ ድረ-ገፆችን እንደመንገድ እንደምትጠቀምበት ትናገራለች። ካነሳቻቸው ምስሎች ባጠቃላይ የማትረሳው እናትና ልጅ ጎዳና ላይ እየሄዱ ያነሳችውን ነው። ይህንን ፎቶ ስታስታውስም ፎቶ ማንሳት በሽርፍራፊ ሰከንድ ውስጥ ያሉ ኹነቶችን ቶሎ ለቀም አድርጎ መያዝ ነው። ያ ፎቶም እነዚያን ሽርፍራፊ ሰኮንዶችን ያስቀረሁበት ስለነበር በርካቶች ወደውታል ትላለች። የተለያዩ የዲዛይን ጥበብ ሥራዎቿ የዲዛይን ጥበብ ሐይማኖት በተማረችበት ሙያ ለሁለት ዓመት ያህል በተለያየ ቦታ ተቀጥራ ሠርታለች። የፎቶግራፍ ጥበብን እንደ የሕይወት ጥሪ ተቀብላ የጎዳና ላይ ፎቶዎችን እያነሳች እና ፎቶዎችን እየሸጠች ደግሞ በቋሚ ገቢ ማግኛነት መጠቀም እንደማትችል ተረዳች። ይሄኔ እራሷን በእራሷ ወዳስተማረችው የተለያዩ ነገሮችን የማስዋብ ሙያ ፊቷን አዞረች። በሁለት ዓመት ውስጥ ሦስት ሥራዎችን ቀያይሬ ነበር የምትለው ሐይማኖት፤ ቋሚ የወር ገቢ የምታገኝበትን ሥራዋን ትታ ወደጥበብ ሥራዎች ፊቷን ስትመልስ ቤተሰቦቿም ሆነ ወዳጆቿ "ሐይማኖት ምን ነክቶሻል" የሚል ተግሳፅ እንደገጠማት ታስረዳለች። ማንም በተሰጥዖዋ ውስጥ እራሷን እንድትፈልግ እና እራስዋን እንድትሆን እንዳላበረታታት የምትናገረዋ ሐይማኖት ይህ ደግሞ ፈታኝ እንደነበረባት አልሸሸገችም። የተለያዩ ነገሮችን እየሠራሁ ለእራሴም ሆነ ለባልንጀሮቼ እሰጥ ነበር የምትለው ሐይማኖት፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የሠራቻቸውን ጆሮ ጌጦች ይዛ በአካባቢዋ ወደሚገኘው 'ድንቅ የአርት ጋለሪ' አመራች። ''እውነቱን ለመናገር ሥራዎቼ ጥሩ አልነበሩም። አዲስ ነገር ለመሥራት ሙከራ ያደረኩባቸው ነበሩ" የምትለዋ ሐይማኖት በአርት ጋለሪው ያገኘቻቸው ሰዎች ምክር እንደለገሷት አትረሳም። እነዚያን ምክሮች ወስዳ የእራሷን የእጅ አሻራዎች በማሳረፍ መሥራት ቀጠለች። በኋላም በጥሩ ሁኔታ የሠራቻቸውን ጌጣ ጌጦች እዛው ጋለሪ ውስጥ መሸጥ ጀመረች። ሐይማኖት ሥራዎቿን ለማስዋብም ሆነ የእራሷን አሻራዎች ለማሳረፍ የምዕራብ አፍሪካዊያንን የተለያዩ ውጤቶች እንደምትጠቀም ትናገራለች። ሁልጊዜም ቢሆን አዲስ ነገር ለመሞከር እና እራሷን ለማስተማር እንደምትተጋም ታስረዳለች። አነስተኛ ጌጣ ጌጦችን ብቻ ሳይሆን የእራስጌ መብራቶችን፣ የትራስ ጨርቆችን ጥለቶችን በመጠቀም እያስዋበች ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ሃገር ደንበኞቿ ትሸጣለች። የተለያዩ የእጅ ሥራዎቿ የእጅ ሥራ ውጤትና ኢትዯጵያውያን እኛ ሃገር በእጅ ለሚሠሩ ውጤቶች የሚተመነው ዋጋ እጅግ በጣም ዝቅ ያለ ስለሆነ ብዙ ደንበኞች ለማግኘት ያስቸግራል ትላለች ሐይማኖት። ስለዚህ ሥራዎቿን ለመግዛት ከኢትዮጵያውያን ይልቅ የውጭ ሃገር ዜጎች ይደፍራሉ። ተቀጥሮ መሥራት በገቢ ደረጃ የምትተማመንበት ነገር እንዲኖር ያደርጋል የምትለዋ ሐይማኖት፤ ቋሚ የወር ገቢን ትቶ የእራስን ተሰጥዖ ተጠቅሞ ገቢ ማግኘት ፈተና እንደሆነም አልሸሸገችም። በመቀጠልም ሐይማኖት ገበያ ለማግኘትም ሆነ ቋሚ የመሥሪያ እና የመሸጫ ቦታ እንዲኖራት ጥረት እያደረገች እንደሆነ ትናገራለች። ነገር ግን ጥረቷን እንደሥራ ፍሬዋ በመውሰድ እና በምታገኛቸው ትናንሽ ውጤቶች ''ደስተኛ በመሆን ዛሬን እየኖርኩ ነገን ትልቅ አልማለሁ'' ትላለች። አሁን ከተማዋ ውስጥ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ለሥራዎቿ ገበያ ለማግኘት እንዳገዛት ታስረዳለች። በተለይ አውደ-ርዕዮች ሲበዙ እና ቀን እና ለሊት ከእንቅልፍ ተፋትታ የምትሠራቸው ሥራዎች የበለጠ እንደሚመስጧት ትናገራለች። ሐይማኖት ሆነልኝ ውልደቷ እድገቷ አዲስ አበባ ነው።
news-41429856
https://www.bbc.com/amharic/news-41429856
''እዚህ ነው ዓይኔን ያጣሁት፤ ወደ ስፍራው ስመጣ የእሷን ዓይን የማይ ይመስለኛል''
በርካቶች የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በተሰበረ ስሜት ነው የሚያከበሩት።
ከነዚህም መካከል አብዲሳ ቦረና ይገኝበታል። መስከረም 22/2009 ዓ.ም አብዲሳ ከነፍሰ-ጡሯ የትዳር አጋሩ ሲፈን ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የኢሬቻን በዓል ለማክበር ወደ ቢሾፍቱ አቀና። አብዲሳ ''ትዳር ከመሰረትን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የምንናከብረው የኢሬቻ በዓል ስለሆነ እጅግ ደስተኛ ነበርን። ሁለታችንም በባህል ልብስ አጊጠን የበዓሉ ተካፍይ ለመሆን ወደ ሥፍራው ሄድን'' ይላል። አብዲሳ በዓሉ በሚከበርበት ቦታ ላይ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ ቀኑን እንዲህ ሲል ያስታውሳል ''በበዓሉ ሥፍራ ከሲፈን እና ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር ሆነን ጥቂት ከቆየን በኋላ፤ ቀኑ ፀሃያማ ስለነበር ሲፈንም ነፍሰ ጡር ስለሆነች ለእሷ ደህንነት ስንል ዛፍ ጥላ ስር ለመሆን ቦታ ቀየርን። ጥቂት እንደቆየን እኔና ወንድሜ ወደ ሃይቁ ተጠግተን ፎቶግራፍ ማንሳት ስለፈለግን፤ ሲፈን ከጓደኞቼ ጋር ወደ ከተማ ተመልሳ እዛው እንድንገናኝ ተስማምተን ተለያየን''። እስከ ወዲያኛው መለየት አብዲሳ ባለቤቱን እንዲህ በቀላሉ የተለየው ዳግመኛ ዓይኗን ላያይ ነበር። ''እንደተለያየን ተኩስ ተጀመረ'' ይላል አብዲሳ። ''ከመድረኩ ጀርባ ተኩስ ሲጀመር ሁሉም ህይወቱን ለማዳን ሩጫ ያዘ። ከዛ በኋላ እጅግ አሰቃቂ ነገር ተፈጠረ።'' ''ባለቤቴ እና ጓደኞቼ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ በተደጋጋሚ ስልክ ብሞክርም ሊሰራልኝ አልቻለም። ከብዙ ጥረት በኋላ የጓደኛዬ ስልክ በመስራቱ፤ ተጎድቶ ሆስፒታል እንደገባ ተነግሮኝ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል አመራሁ'' ይላል። ሆስፒታል ደርሶ የጓደኛውን ስም እየጠራ ፍለጋ ጀመረ። እስከዛ ሰዓት ድረስ ግን ሲፈን ደህና እንደሆነች ነበር የሚያውቀው። በድንገት ያልጠበቀውን ነገር ተመለከተ። ''የነፍሰ ጡሯ ባለቤቴን የሲፈንን አስክሬን ከሌሎች ሰዎች አስክሬን ጋር በአንድ ድንኳን ውስጥ አየሁ። ሰዎች ይዘው ሊያረጋጉኝ ሲሞክሩ አስታውሳለሁ። ከዚያ በኋላ ግን ምን እንደተፈጠረ የማውቀው ነገር የለም'' ይላል። የብዙዎች ደስታ ወደ ሃዘን የተቀየረበት ቅፅበት 'ሂውማን ራይትስ ዋች' የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን የ2009 ዓ.ም የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት ''ፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀማቸው እና መውጫ መንገዶችን በመዝጋታቸው በተፈጠረ ግርግር በመቶዎች ሊቆጠሩ የሚችሉ ሰዎች ተረጋግጠው ሞተዋል'' ብሏል። በባለ 33 ገፁ ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰው፤ ተረጋግጠው ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በጥይት ተመተው የተገደሉም እንዳሉ ቡድኑ አረጋግጫለሁ ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለጠፋው ህይወት ፀረ-ሰላም ያላቸውን ኃይሎች ተጠያቂ አድርጎ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም የፀጥታ ኃይሎችን ''ስላምና መረጋጋትን'' አሰፍነዋል በማለት አመስግነው እንደነበር ሪፖርቱ አስታውሷል። በዕለቱ የሞቱትን ሰዎች ቁጥር የኢትዮጵያ መንግሥት 55 ነው ሲል፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ደግሞ 678 ያደርሰዋል። ሲፈንና አብዲሳ ለሲፈን ሞት ተጠያቂው ማነው? ''ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የነበርው ክስተት፤ ሆን ተብሎ እና ታቅዶ የተፈፀመ እንጂ በአጋጣሚ የሆነ ነገር አልነበረም።'' የሚለው አብዲሳ፤ ለባለቤቱም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የሆነው አካል ለፍርድ እንዳልቀረበ በምሬት ይናገራል። ስለባለቤቱ አሟሟት በይፋ በመናገሩ ምክንያት ማንነታቸውን የማያውቃቸው ግለሰቦች ''አንተንም አንጨምርሃለን (ከሟቾች ጋር)'' እያሉ ያስፈራሩት እንደነበረ ለቢቢሲ ተናግሯል። ከዚህም በተጨማሪ የእሷ ህይወት ከማለፉ ከ5 ወራት ቀደም ብሎ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ይማር የነበረ ታናሽ ወንድሟ በኦሮሚያ ክልል በነበረው ተቃውሞ ህይወቱ አልፏል። በዚህም ምክንያት ሲፈንም ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ እንደነበረች የሚያስረዳው አብዲሳ ''ከእኔ በላይ ደግሞ የሲፈን ቤተሰብ ሁለት ልጆቻቸውን በግፍ ተነጥቀዋል'' ሲል ያማርራል። ''ህይወትን አብረን ጀምረን፣ ቤተሰብ መሥርተን፣ በስማችን የሚጠሩ ልጆች ወልደን ለመኖር ብዙ እቅድ ነበረን። የህይወቴ አቅጣጫ ግን እዚህ ቦታ ላይ ተቀየረ። ይህ ስፍራ ዓይኔን ያጣሁበት ቦታ ነው'' ይላል አብዲሳ። በተጨማሪም ባለቤቱ ሲፈንን ወደተነጠቀበት ሆራ አርሰዴ ሲሄድ ''ዓይኗን የማይ ስለሚመስለኝ፤ መቼም ለኢሬቻ በዓል አልቀርም።'' በማለት በሃዘን የተሰበረውን ልቡን ይዞ ዘንድሮም ወደ ቢሾፍቱ ይሄዳል።
news-53200632
https://www.bbc.com/amharic/news-53200632
በመንግሥት አካላት ጥቃት ተፈጸመባቸው ግለሰቦች ሲታሰቡ
ትናንት በተለያዩ አካላት ስቃይ የደረሰባቸው ሰዎች የሚታሰቡበት እና ድጋፍ የሚደረግላቸው ቀን ነበር፡፡ ቀኑን በማስመልከት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “በሰዎች ላይ ስቃይ የሚፈጽሙ ሰዎች ከነበደላቸው መተው የለባቸውም፤ በሰዎች ላይ ስቃይ እንዲፈጸም የፈቀዱ ሥርዓቶችም መፍረስ ወይም ሥር ነቀል ለውጥ ሊካሄድባቸው ይገባል” ብለዋል።
የተለያየ መልክ ያላቸው እና ሆነ ተብሎ የሚፈጸሙ ስቃዮች፤ ዓላማቸው በሚሰቃየው ግለሰብ ላይ አካላዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ጫና ማድረስ ነው። መሰል ጥቃት ከደረሰባቸው ሚሊዮኖች መካከል አንዱ ደግሞ ዮናስ ጋሻው ነው። ዮናስ በመንግሥት የጸጥታ አካላት በደሰበት ጥቃት ለከፋ ጉዳት መዳረጉ ይታወሳል። ጥቂት ስለ ዮናስ ዮናስ ጋሻው ተወልዶ ያደገው በፍኖተ ሰላም ከተማ ሲሆን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አጠናቋል፡፡ ለእስር የተዳረገው ተመርቆ መስራት በጀመረ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፣ በ2009 ዓ.ም ነበር፡፡ በእስር ቤቶች ውስጥም ለጆሮ የሚከብድ አሰቃቂ በደል እንደተፈጸመበት፣ ከእስር ከተለቀቀ በኋላ በአካል ቀርቦ ለተለያዩ መገናኛ ብዙኀን ተናግሯል፡፡ የእግሮቹ ጣቶች ጥፍር በፒንሳ እንደተነቀሉ፤ ብልቱ ላይ በውሃ የተሞላ ኮዳ በማንጠልጠል ማኮላሸት እንደተፈጸመበት፤ ራሱን ችሎ መቆም እስከሚያቅተው ድብደባ እንደደረሰበት በዝርዝር አስረድቷል፡፡ በደረሰበት ድብደባ በጀርባው መተኛት እንደማይችልና ሽንት ቤት እንኳን ለመሄድ በሰው ድጋፍ እንደነበር በወቅቱ ለቢቢሲ ገልጿል፡፡ እርሱ እንዳለው በደሉ አካላዊ ብቻ ሳይሆን ሥነልቦናዊ ጉዳቱም ከፍተኛ ነው፡፡ በማንነቱ ይሰደብና ይዘለፍ ነበር፡፡ • በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃና ግፍ ለተፈጸመባቸው ካሳ ሊጠየቅ ነው • ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የ114 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ማን ናቸው? መንግሥትን በቃል ከመተቸት ውጪ፤ ለደረሰበት ስቃይ የሚያበቃ ተግባር ፈጽሞ እንደሆነ ራሱን እስከሚጠራጠር ድረስ ግፍ እንደተፈጸመበትም ተናግሯል፡፡ በደሉ በእርሱ ብቻ ሳያበቃ ቤተሰቡም በደል እንደደረሰባቸውና እናትና ወንድሙን በሞት እንዳጣ፤ አባቱ ደግሞ የት እንዳሉ እንደማያውቅ በተደጋጋሚ ገልጿል፡፡ የሽብር ክስ ተመስርቶበት የነበረው ዮናስ፤ ከእስር የተለቀቀውም የዶ/ር ዐብይ ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ከሁለት አመታት በፊት ነበር፡፡ በወቅቱም "በቁሜ የሞትኩ ያክል ቢሰማኝም፤ ይህንን ለውጥ በማየቴ ደስተኛ ነኝ" ሲል ስሜቱን ገልጾ ነበር፡፡ ዮናስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? በማን እገዛ? ቢቢሲ ያነጋገረውና በአሁኑ ወቅት ለህክምና አሜሪካ የሚገኘው ዮናስ ጤናው እየተሻሻለ እንደሆነ ገልጾልናል፡፡ ሙሉ ጤናማ አካሉን ይዞ እስር ቤት የገባው እና ዊልቸር ላይ ሆኖ፤ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ከእስር የወጣው ዮናስ፤ አሁን ላይ በተደረገለት ህክምና የሰውነቱ መንቀጥቀጥ እንደቆመለት፤ አነጋገሩም እየተስተካካለ እንደመጣ ነግሮናል፡፡ አልታጠፍ አልዘረጋ ላለው እግሩም የህክምና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጾልናል፡፡ "ይህንን የፈጸሙብኝ አካላት ለጥቅማቸው ሲሉና ሥልጣናቸውን በመፈለግ በእኔ ላይ ያደረጉት ነገር ይኖራል፤ በሌላ በኩልም እኔ እንደዚያ መሆኔ ምንም አድርጌ ባይሆንም፤ ለከፈልኩት ዋጋ ሕዝብ ስለካሰኝ ደስ ብሎኛል፡፡" ይላል፡፡ በደል ስለፈጸሙበት ሰዎች ያለውን ስሜት የተጠየቀው ዮናስ፤ "እነሱ ላደረጉት ነገር እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው፤ እነርሱ ያደረሱብኝን ጉዳት ሕዝቡ እንድረሳ አድርጎኛል፤ ሁሉንም ሰው በእኩል ዐይን አላይም" ሲል መልሷል፡፡ ዮናስ ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግም ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች የገንዘብ መዋጮ አድርገውለታል። ለዮናስ ህክምና ገንዘብ ሲያሰባስቡ ከነበሩት መካከል ዮሐንሰ ሞላ አንዱ ነው። ዮናስ በወቅቱ ድጋፍ አድርጉልኝ ብሎ አለመጠየቁን የሚያስታውሰው ዮሐንስ ፤ በግሉ ተነሳሽነት በፌስቡክ ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራ እንደጀመረ ያስታውሳል፡፡ • የህዳሴ ግድብ ድርድርና ለፀጥታው ምክር ቤት የተላኩት ደብዳቤዎች • ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በቀጣዮቹ ሳምንታት ድርድራቸውን ለማጠናቀቅ ተስማሙ "ጓደኞቼን አስተባብሬ ገንዘብ ማሰባሰብ ጀመርኩ፤ ከዚያም ባልጠበቅኩት መንገድ በርካታ ሰዎች ገንዘብ ለገሱ" ይላል፡፡ ገንዘቡ ከፍ እያለ ሲመጣም ለዮናስ እንደነገረውና እርሱም ደስተኛ እንደነበር ገልጾልናል፡፡ ከዚያም ገንዘብ ማሰባሰቡ ቀጥሎ 98 ሺህ ዶላር ደረሰ፡፡ አሜሪካ ሄዶ እንዲታከም ለማድረግም የሚያስፈልጉ ነገሮችን በማሟላት ከተባበሩት መካከል ዶ/ር ጌታቸው ወልደሄር የተባሉ ግለሰብን ይጠቅሳል፡፡ ይህን ተግባር ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳው የተጠየቀው ዮሐንስ፤ "ጥቃቶች በሰው ልጆች ላይ ይደርሳሉ፡፡ ጥቃት አድርገን የማንወስዳቸው ሁሉ ጥቃቶች ይደርሱብናል፡፡ እኔ ራሴ ለመኖር በማደርገው የህይወት መስተጋብሮች ሃሳቤን መግለጽ እየፈለኩ፣ ሃሳብህን መግለጽ አትችልም እየተባልኩ ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፌያለሁ፡፡ ህመሙ ይገባኛል. . . " ሲል ምላሹን ሰጥቷል። አክሎም ". . .ዮናስ ደግሞ ከጥቃት ያስጥለኛል ብሎ ያመነው መንግሥት፤ ይህን በደል አድርሶበታል፡፡ የደረሰበት በደልም አንድ ሰው ላይ ሊደርሱ የሚገቡ ናቸው ብሎ ማሰብም ይከብዳል፡፡" በማለት ከደረሰበት አካላዊ ጥቃት ባሻገር እናቱና ወንድሙ በዚሁ ጉዳይ መሞታቸውን፤ አባቱ ያሉበት አለመታወቁን ሲሰማ የራሱን ጭንቀት ለማስታመም እንዲሁም አይዞህ ለማለትና ሰው እንዳለ ለማሳየት ያደረገው እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ከፍተኛ ስቃይ እና ህመምን ያሳለፈው ዮናስም "ሰዎች ከህመሜ እንድድን ያደረጉትን ጥረት ሳይ፤ የበደሉኝን ይቅር እንድላቸው አድርጎኛል" ብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በእስረኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጸም እንደነበር ጠቅሰው ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ ለስቃይና ለእንግልት የተዳረጉ እነዚህ የቀድሞ እስረኞችም መንግሥትን ካሳ እንጠይቃለን ብለው ነበር፡፡ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪና የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አምሃ መኮንንም፤ በወቅቱ ተጎጂዎች ካሳ የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት እየሰሩ እንደሆነና ጉዳያቸው በአገር ውስጥ ፍርድ ቤቶች መልስ የማያገኝ ከሆነም ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ድረስ ለመሄድ እንደተዘጋጁ መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡
news-48889733
https://www.bbc.com/amharic/news-48889733
“በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ
የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጠበቃ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በሂውማን ራይትስ ዋች ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግሏል።
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2011 እስከ 2016 የተቋሙ የአፍሪካ ክንፍ ዋና ዳይሬክተር ነበር። ኦክስፋም፣ አርቲክል 19፣ የዓለም ባንክ እና ዩኤስኤድን አማክሯል። በበርካታ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ የሠራው ዳንኤል፤ የ97ቱ ምርጫ ነጻ እንዲሆን እንዲሁም ሰብአዊ መብት እንዳይጣስ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። ከምርጫው በኋላ የተፈጠረውን ቀውስ ለማርገብም ሞክሯል። በዚህም ለእሥር ተዳርጎ ነበር። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2009 ላይ ላይ 'አሊሰን ደስ ፎርጅስ አዋርድ ፎር ኤክስትራኦርዲነሪ አክቲቪዝም' የተሰኘ ሽልማት አግኝቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀሪያ ዲግሪውን በሕግ፣ ሁለተኛ ዲግሪውን ደግሞ በሪጅናል ዴቨሎፕመንት ስተዲስ አግኝቷል። በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በሌጋል ስተዲስ ሁለተኛ ዲግሪ የያዘ ሲሆን፤ ፒኤችዲውን በዓለም አቀፍ ሕግ አግኝቷል። ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ባለፈው ማክሰኞ ሰኔ 25/2011 ዓ. ም. በኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆኖ ተሹሟል። ይህንን ተከትሎም ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል፤ እነሆ . . . እሾማለሁ፤ ያውም ባሰረህ በኢህአዴግ መንግሥት እሾማለሁ ብለህ አስበህ ታውቃለህ? ይህ ቀን ይመጣል ብለህ ታስብ ነበር? ዳንኤል በቀለ፡ ይህ ቀን ሊመጣ ይችላል ብለህ ታስብ ነበረ ወይ? ለተባለው ኢትዮጵያ ውስጥ የዚህ አይነት ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብለህ ታስብ ነበር ወይ? ማለት ከሆነ፤ አስብ ነበር። እንደሚመጣ ይሰማኝ ነበር። እኔ ራሴ ግን ያለሁበትን ሁኔታ ከሆነ ይህንን በተለየ አስቤው አላውቅም። ይሄኛውን [በኢህአዴግ መንግሥት መሾምን] በጭራሽ አስቤ አላውቅም በእውነት። እመኝ የነበረው ለአገሬ የሰብአዊ መብት መከበር፣ የሰብአዊ መብት መስፋፋት ወይም የዴሞክራሲ መዳበር ወይም በአጠቃላይ ለአገሬ ሰላም፣ እድገት፣ ብልጽግና በማንኛውም አይነት መንገድ አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁና ፍቃደኛ መሆኔን አስበዋለሁ። ረዥም ጊዜ የሠራሁት በሲቪል ማኅበር ድርጅቶች ውስጥ ስለነበረ፤ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ አስተዋጽኦ ላደርግ እችላለሁ እያልኩ አስባለሁ እንጂ የዚህ አይነቱን ሹመት፣ የዚህ አይነቱን ኃላፊነት በተለይ በኢህአዴግ መንግሥት ሊሆን ይችላል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። • አምነስቲ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለውጥ እንዲደረግበት ጠየቀ ነገር ግን ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የኢህአዴግ አስተዳደር በነበረበት ዴሞክራሲያዊ ያልሆነና የሰብአዊ መብቶችን በሚረግጥ መንገድ የነበረው አስተዳደር ግን ዘላቂ እንዳልሆነ፣ ማንኛውም ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ ሥርዓት በአንድ ወቅት ላይ ከውስጡ የለውጥ ሀዋርያት ሊወለዱ እንደሚችሉ፣ ከውስጡ የሚወለዱ የለውጥ ሀዋርያት ደግሞ የተሀድሶ አጀንዳ ሊመሩ እንደሚችሉና በእንደዚህ አይነት መንገድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል አስብ ነበር። በእርግጥ ደግሞ ሌላ የሚያስፈራ፣ ሌላ አሳሳቢ ሁኔታም ሊፈጠር ይችል ይሆን ነበር የሚለው ስጋት እንደተጠበቀ ሆኖ ማለት ነው። ከ1997 ምርጫ በኋላ ከተነሳው ቀውስ ጋር ተያይዞ ለሁለት ዓመት ያህል ታስረሀል። ያንን የእስር ጊዜ እንዴት ነው የምታስታውሰው? ዳንኤል በቀለ፡ የእስሩን ዘመን እንዴት ታስታውሰዋለህ ለሚለው፤ መቼም እንደሚታወቀው እስር አስቸጋሪ ጊዜ ነው፤ ጥሩ ጊዜ አይደለም። በተለይ የኢትዮጵያ እስር ቤት እና በተለይ ደግሞ ያኔ እኛ ታስረን የነበረበት ጊዜ አስቸጋሪና ከባድ ጊዜ ነበር። ነገር ግን እኔ ከማስታውሰው ነገር ውስጥ አንዱ ከራሴ የሚበልጥ በቤተሰቤ ላይ የተፈጠረው ችግርና መጉላላት ሁልጊዜም አልረሳውም። አሁንም ሰው ሲታሰር ብዙ ጊዜ ስለቤተሰቦቻቸው አስባለሁ። ከዚያ በተረፈ ግን እስር ጥሩ ነገር ባይሆንም ያንን እስር አሁን የማስታውሰው በምሬት፣ በንዴት፣ በቁጭት፣ በበቀል ስሜት ሳይሆን ይልቁንም በሕይወት ውስጥ ሊያጋጥም እንደሚችል አንድ ችግር፣ አንድ መሰናክል ከዛም ደግሞ የምወስደውን ትምህርት ወስጄ ሕይወትን መቀጠል እንደሚቻል በማስታወስ ነው። በእስር ቤት ውስጥ በነበርኩ ጊዜ ደግሞ የራሴን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ በርካታ እስረኞች የሚገኙበት ቦታ ምን እንደሚመስልም ለማየትም የሚያስችል ሁኔታ ስለሆነ፤ በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ ያሉ እስረኞች አይነታቸው፣ ብዛታቸው፣ የታሰሩበት ጉዳይ አይነት፣ የእስር ቤቱ አያያዝ የመሳሰለውን ነገር ሁሉ ለማየት እድል ይሰጣል። ስለዚህ ከዚያ አንጻር አንድ ላየው የማልችለው የነበረ ነገርን እንዳይ እድል የሰጠኝ ይመስለኛል። እስር ጥሩ አይደለም ግን ነገሩ እዚያ ውስጥ ሆነሽ ከተገኘሽ ግን የሚያሳይሽን ነገር መመልከት ጥሩ ነው። እና ያንን ስላሳየኝ ጠቃሚ ትምህርት ሰጥቶኛል ብዬ አስባለሁ። ለዓመታት የኢትዮጵያን ሰብአዊ መብት አያያዞችን ስትተች ነበር። በቅርቡ ደግሞ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነሃል። ይህንን ቦታ ስትቀበል ምን አይነት ማሻሻያዎችን ከግምት ውስጥ አስገብተህ ነው? የእስረኞች መፈታት የመሳሰሉ ያየናቸው ማሻሻያዎች አሉ። ዳንኤል በቀለ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በእውነቱ ከሆነ ከዛሬ አንድ ዓመት ገደማ ወዲህ ይህ የለውጥ አመራር ወደ ኢትዮጵያ አመራር ላይ ከመጣ በኋላ የታዩት ለውጦች ሊካዱ የሚችሉ አይመስለኝም። ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ በጣም መሰረታዊ የሆነ በታሪካችን ምናልባት ለየት ያለ ነው በሚባል ደረጃ ከፍተኛ ለውጥ ታይቷል። በተደጋጋሚ የሚገለጸው ያላግባብ የታሰሩ ሰዎች ከእስር ከመለቀቅ አንስቶ የፖለቲካ ሜዳው ለሁሉም ክፍት መደረጉና ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ተሳትፎ መብት ሁሉንም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ያገባናል፣ ይመለከተናል የሚሉ ተገለው የነበሩ ሰዎች ሁሉ በሚያቅፍ መንገድ በሩ ተከፍቷል። በምንም አይነት ሁኔታ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ በተከፈተው የፖለቲካ ሂደት የተገለለ ሰው ወይም ቡድን አለ ብሎ ለማለት የሚቻል አይመስለኝም። ሰፊ ድንኳን ነው የተጣለው፤ ሰፊ በር ነው የተከፈተው፤ ስለዚህ በአገራችን ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉ ሰዎች ሁሉ ሊሳተፉ የሚችሉበት እድል ተፈጥሯል ብዬ አምናለሁ። • በኢትዮጵያ የአዕምሮ ህሙማን ሰብዓዊ መብት እየተጣሰ ይሆን? ይህ የተፈጠረው እድልም የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታን ትልቅ በሚባል ደረጃ አሻሽሎታል፤ ለውጦታል። ነገር ግን ይህ ማለት የሰብአዊ መብት ችግሮች በሙሉ ተፈትተዋል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ችግር የለም ማለት አይደለም። ይልቁንም እጅግ ሰፊ፣ውስብስብ፣ ጥልቅ፣ የሆኑ የሰብአዊ መብት ችግሮችም፤ የፖለቲካ ቀውስም፣ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥም የምንገኝ መሆኑ ሊካድ አይችልም። የተፈጠረው አዲስ የተሃድሶ ወይም የለውጥ ሥራ ግን እነዚህን ሁሉ ችግሮቻችንን በመተጋገዝና በመተባበር ከሠራን ልንለውጣቸውና ልናሻሽላቸው የሚያስችል እድል አለ ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ በታሪካችን ብዙ ጊዜ ዕድል ይፈጠራል፤ እድሎች ግን ሲጠፉ ተመልክተናል። ይህ እድል መጥፋት ያለበት አይመስለኝም። ስለዚህ አሁን በተፈጠረው ዕድልና ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አገራችንን ወደፊት ለማራመድ አብረን መሥራት አለብን በሚል እምነት ነው ይህንን ሹመት ተገቢ ነው ብዬ የተቀበልኩት። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መንግሥት የሚፈፅማቸውን ጥሰቶች በማለባበስ ለዓመታት ይተቻል። ብዙ ቅሬታዎች ሲቀርብበት የነበረም ድርጅት ነው። እነሱ ክፍተቶች ተስተካክለዋል? ገምግመኸው ከሆነ በምን ሁኔታስ መስተካከል ይችላሉ? ዳንኤል በቀለ፡ እነዚህ ክፍተቶች አልተስተካከሉም። ገና ወደፊት የሚስተካከሉ እንጂ አሁን የተስተካከሉ አይደሉም። አሁን የተጀመረው ነገር እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ የዲሞክራሲያዊ ተቋማት የሚባሉ እንደ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ምርጫ ቦርድ የመሳሰሉ የአገሪቱን የዳኝነት አካልን የመሳሰሉ ተቋማትን እውነተኛ፣ ገለልተኛ፣ ነፃ፣ ጠንካራና ውጤታማ ተቋም ለማድረግ የሚያስችል እድል ተፈጥሯል። ይህንንም ለማድረግ የሚያስችሉት የመጀመሪያዎቹ እርምጃዎች መወሰድ ተጀምረዋል። የለውጡ አመራሮች የፖለቲካ ፈቃደኝነታቸውና የፖለቲካ ቁርጠኛነታቸው ለእነዚህ ተቋማት የሚያስፈልገውን አመራር ለመፍጠር፤ ለሥራው ይሆናሉ ብለው የሚያስቧቸውን ግለሰቦች መምረጥ መጀመር መቻላቸው በእውነቱ አንዱ ትልቅ እርምጃ ነው ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ ተቋማቱን ተአማኒ፣ ተቀባይነት ያላቸውና ውጤታማ ለማድረግ ገና የመጀመሪያው እርምጃ ወይም የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ እንጂ፤ ሥራው ተጀመረ እንጂ ፈፅሞ አልተጠናቀቀም። ግን የተፈጠረው ዕድል ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ስለሆነ እጅግ በጣም ተስፋ ሰጪ ነው ብዬ አምናለሁ። በቅርቡም ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ በሰብአዊ መብት ኮሚሽን ላይ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲደረግ ጠይቋል። ኮሚሽኑ ምን አይነት መዋቅራዊ ለውጥ ነው ማምጣት ያለበት? መስተካከል ካለበት በምን መንገድ ነው መስተካከል ያለበት? ዳንኤል በቀለ፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት አይቸዋለሁ። በእኔም አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን መዋቅራዊም ሆነ አሠራራዊ የለውጥ ማሻሻያ ሊያደርግ ይገባዋል የሚል እምነት አለኝ። ነገር ግን ወደ እንደዚህ አይነት የተቋም ማሻሻል፣ ማጠናከር፣ ማደስና የአሠራር ለውጥ ጉዳዮች ውስጥ ከመግባታችን በፊት ትንሽ በጥሞና ማድመጥ፣ ማጥናትና መጠየቅ ያስፈልጋል። • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ጥሩ የሚባሉ ልምዶችን መመልከትና መፈተሽ ያስፈልጋል። ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ሊደረግ የሚገባውን መዋቅራዊ ለውጥ ይሄ ነው ይሄ ብዬ ለመናገር ዝግጁ አይደለሁም። ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት መንግሥታዊ የሆኑና መንግሥታዊ ያልሆኑ፣ የልማት አጋሮችና ህብረተሰቡንም በአጠቃላይ ሁሉንም በሚያካትት መልኩ ችግሮቹ ምንድን ናቸው? እድሎቹስ? የሚለውን ማየት ያስፈልጋል። በዚያ ላይ ተመስርቶ የመዋቅር ለውጥና የአሠራር ለውጥ ለማድረግ እንችላለን። ምንም እንኳን ብዙ ማሻሻያዎች ቢደረጉም አገሪቱ ውስጥ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ በብሔራቸው የሚፈናቀሉበት፣ የመንቀሳቀስ መብት የተገደበበት ሆኗልና እንደው እንደ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንስ ተግዳሮቶች ብለህ የምታስባቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ዳንኤል በቀለ፡ ችግሮቹ ብዙ ናቸው። የተወሰነውን ለመጥቀስ ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ ተቋማት አለመኖራቸው በጣም ትልቅ ችግር ነው፤ ምክንያቱም በወንጀል ፍትህ አስተዳደር፣ በዳኝነት ሥራ፣ በፖሊስና በፀጥታ ኃይሎች ብዙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት ሁኔታ አለ። ያለው የፖለቲካ ሂደት ብሔርን መሰረት ያደረገ፣ የተካረረ የፖለቲካ ውጥረት መኖሩ ያስከተለው ግጭት፣ የፈጠረው የብዙ ሕዝብ መፈናቀል፣ መሞትና ከኑሮው መስተጓጎል ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጠረው ለውጥ ጋር ተያይዞ በርካታ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የደህንነት ክፍተት መፈጠሩ ማለትም ሕግና ሥርዓትን ማስከበርን ጨምሮ ማለት ነው። አንዳንድ አካባቢዎች ሕግና ሥርዓትን ማስከበሪያ ተቋማት በመዳከማቸው ወይም በመጥፋታቸው የተነሳ የደህንነት ክፍተት ተፈጥሯል። የአገራችን የፖለቲካ ቀውስ ገና መፍትሔ አለማግኘቱ፤ እነዚህ ሁሉ ደግሞ በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ላይ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ናቸው። ይሄ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። አሁን ካለንበት የፖለቲካ አንፃርም እነዚህን ሁሉ ነገሮች ከግንዛቤ ውስጥ ከቶ ሰብአዊ መብት አያያዝን ለማሻሻል እንዴት አድርጎ ይቻላል የሚለው ከባድ ነው። በአጠቃላይ ከፖለቲካችን፣ ከኢኮኖሚያችንና ከማኅበራዊ ሁኔታችን ጠባይ የተነሳ የሚፈጠሩት ችግሮች በሰብአዊ መብት ሁኔታም ላይ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ናቸው። ይህ ትልቅ እንቅፋት ወይም መሰናክል ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ብዙዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ ባደረጓቸው ተግባራት እንደ እስረኞች መፍታት የመሳሰሉት ያመሰግኗቸዋል። ከዓመት በኋላ በብዙዎች ዘንድ አፋኝ በተባለው በፀረ ሽብር ሕግ ሰዎች እየተጠየቁ ነው፤ እንዲሁም በእስክንድር ነጋ የሚመራው ራሱን የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ብሎ የሚጠራው አካልም መንግሥት በነፃ እንዳልንቀሳቀስ አድርጎኛል ይላል። መንግሥት ላይ የሚሰሙ ትችቶችን እንዴት ታያቸዋለህ? ዳንኤል በቀለ፡ ሙሉ በሙሉ ያጠናሁትና ያልመረመርኩት ቢሆንም በተወሰነ መንገድ የተነሱትን ሃሶቦች በሚመለከት አድምጫለሁ እና እነዚህ አሳሳቢ ጉዳዮች ናቸው። በጣም በጥንቃቄ መጣራት የሚያስፈልገው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለምሳሌ የፀረ ሽብር ሕጉ ኢትዮጵያ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ከፍተኛ ትችት የቀረበበትና አሁንም የለውጥ እርምጃ መወሰድ ከተጀመረበት በኋላ ሊሻሻሉ ይገባል ተብለው ከታሰቡት ሕጎች ውስጥ አንዱ እሱ ነው። የማሻሻል ሥራም ተጀምሮ የተወሰነ ደረጃ የደረሰ መሆኑ ይታወቃል። እና ያንን ሕግ መሰረት ተደርጎ ሊቀርብ የሚችል ወይም የሚገባ ክስ ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራል ብዬ አልገምትም፤ መኖርም የለበትም። ተፈፀመ የተባለ ወንጀል ካለ ሌሎች አግባብነት ባላቸው የወንጀል ሕግ ሊጣራ ወይም ሊመረመር ይገባል። እንጂ እጅግ የተወቀሰ፣ የተነቀፈና ሊሻሻልም እንደሚገባው ታምኖ የመሻሻል እርምጃ የተጀመረበት ሕግ በአሁኗ ኢትዮጵያ ውስጥ የወንጀል ክስ ለማቅረብ መሰረት ይሆናል ብዬ አልገምትም። እንደዚህም አይነት እርምጃ መወሰድ ተጀምሮ ከሆነ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። ዝርዝሩን በደንብ ባላውቀውም ትክክል ነው ብዬ አላምንም። ወደ ትችቶቹ ስመጣ አሁን ባለው የኢትዮጵያ አስተዳደር የተቃውሞ አስተሳሰብ ሊኖር እንደሚችል እገምታለሁ። ያም ሁኔታ በራሱ መጥፎ አይደለም። ሁሉም ሰው አንድ አይነት አስተሳሰብ ይኖረዋል ተብሎ መጠበቅ የለበትም፤ ሊሆንም አይችልም። ስለዚህ በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ እስከተገለፀ ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በሚመሩት መንግሥት ላይ ተቃውሞ ቢነሳ፣ ትችት ቢቀርብና የተለየ ሃሳብ ቢስተናገድ በራሱ እንደ ችግር ወይም እንደ መጥፎ ነገር የሚታይ አይደለም። ይልቁንም ይበረታታል፤ የተለያዩ ሃሳብ መኖራቸው መልካም ነው። በጣም አበክሬ የምናገረው ግን የተፈጠረው እድል በጣም ትልቅ ነው። ይህንን እድል እንዳናበላሽ በጥበብና በማስተዋል መስራት ያለብን ይመስለኛል። የአገራችን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በመክተት እንዴት ነው በመተጋገዝና በመተባበር ወደፊት መሄድ የምንችለው የሚለውን ማሰብ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። እስሮችም ሆነ ሌሎች መንግሥት የሚወስዳቸው እርምጃዎች ከብሔር ጋር ይተሳሰራሉ። እንደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያለው ሪፖርት በሚያወጣበትም ጊዜ አንደኛው ብሔር ሊያኮርፍ ይችላል። ሁሉም ነገር በብሔር መነጽር ስለሚታይ ማለት ነው። እንደ መፍትሔ ወይም እንደ አቅጣጫ የምታስቀምጣቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው? ዳንኤል በቀለ፡ በጣም ሰፊና ከባድ ጥያቄ ነው። በአጭሩ በቀላሉ ሊመለስ የሚችል ነገርም አይመስለኝም። ለብቻዬም የምመልሰው ነገር አይደለም። በርካታ ባለድርሻ አካላት በጋራ በመተባበር ሊሠሩበት የሚገባም ነገር ይመስለኛል። ነገር ግን እንደው ምናልባት አግባብነት ያለው አንድ ነጥብ ለማንሳት የምፈልገው ቢኖር፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከብሔር ጋር የተያያዘ የተወሳሰበ የፖለቲካ ጥያቄ ቢኖርም፤ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሊስማሙበት የሚገባው ወይም ሊያስማማቸው ይገባል ብዬ ተስፋ የማደርገው አንድ ነገር ግን የሰብአዊ መብት ጉዳይ ከብሔር ጋር የተያያዘ አይደለም። የማንኛውም የሰው ልጆች ሁሉ መብት ነው። ስለዚህ የትኛውም አይነት በብሔር ፖለቲካ የተደራጁ ወይም በሌላ አይነት መልክ ፖለቲካ የተደራጁ ቡድኖች በሙሉ በያሉበት፣ በየሚሠሩበት አካባቢ ሊቆሙለት የሚገባ አንድ መርህ ነው ብዬ የማስበው ነገር የሰዎች መብት መከበር ነው። የሰዎች መብት መከበር ደግሞ ማለት የአንድ አካባቢ ተወላጆች የሚባሉ ሰዎች መብት ብቻ ሳይሆን የማንኛው ሰው መብት ማለት ነው። በአንድ ክልል የሚኖሩ ሰዎች የሌላውን ሰው መብትም ካላከበሩ እነዚያ ሰዎች እነሱም በሌላ አካባቢ የሚከበር መብት አይኖራቸውም ማለት ነው። ስለዚህ ሁሉም የፖለቲካ ቡድኖች ወይም አደረጃጀቶች እነዚህ ከዚህ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ አስተሳሰቦች በሙሉ ሊስማሙበት፣ ሊቆሙበት፣ ሊታገሉለት የሚገባ ነገር የሰብአዊ መብት መከበር ነው። የሰብአዊ መብት ለሁሉም ነው። ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የሰው ልጆች ሊከበር የሚገባው ነገር ነው። እና ትንሽ ተስፋ የማደርገው ነገር ብዙ የማስተማር፣ የማሳወቅ ሥራ ሊጠይቅ ይችላል። ነገር ግን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቡድኖች፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና ህብረተሰብ በሙሉ በሰብአዊ መብት ጉዳይ ላይ ሊስማማ ይችላል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በጣም ከባድ ችግር ወይም እንቅፋት እንዳለውም እገነዘባለሁ።
news-54378309
https://www.bbc.com/amharic/news-54378309
ብሪታኒያ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩቅ ደሴት ለመላክ እያሰበች ይሆን?
ብሪታኒያ የጥገኝነት አመልካች ስደተኞችን የት ላስቀምጣቸው በሚለው ጉዳይ ላይ እየተብሰለሰለች ይመስላል፡፡
ፋይንናንሻል ታይምስ ጋዜጣ አገኘሁት ባለው አንድ የሾለከ መረጃ ከሆነ ለጊዜው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ጀልባዎችን ጭምር የስደተኞች ማቆያና ቢሮ የማድረግ ሐሳብ አለ፡፡ ስደተኞችን አጭቀው ከፈረንሳይ የሚመጡ ታንኳዎችንም በምን መልኩ ልናስቆማቸው እንችላለን የሚለው ጉዳይ በጥሞና እየታየ ነው፡፡ አውቶቡሶች ሲያረጁ ዳቦ መሸጫ እንደሚደረጉት ሁሉ አሮጌ ታንኳዎች (ferries) የስደተኞችን ጉዳይ ለማየትና ለማቆያነት እንዲውሉ ለማድረግ ዩኬ እያጤነች ነው ተብሏል፡፡ ሪፊዩጂ አክሽን የተሰኘ ድርጅት ባወጣው አንድ አሐዛዊ መረጃ ባለፈው ዓመት ብቻ 35ሺህ 566 ሰዎች በዩናይትድ ኪንግደም የአስጠጉን ማመልከቻ አስገብተዋል፡፡ ይህ ቁጥር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየቀነሰ እንጂ እየጨመረ አልመጣም፡፡ ከፍተኛ የጥገኝነት ጥያቄ ቀርቦ የነበረው ግን በ2002 እንደነሱ አቆጣጠር ሲሆን ያን ዓመት ብቻ 84ሺህ ሰዎች ብሪታኒያ ጥገኝነት አመልክተው ነበር፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የጥገኞችን ጥያቄ የሚያስተናግድበትን ሁሉንም አማራጮች እያየ ነው ተብሏል፡፡ የሌበር ፓርቲ ይህንን ሐሳብ አምርሮ ተቃውሞታል፡፡ ጥገኝነት አመልካቾችን ሥራ ባቆሙ ጀልባዎች እያጎሩ የማንገላታቱን ሐሳብ ‹‹በፍጹም ያልተገባ ድርጊት› ብሎታል፡፡ በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አንድ ከፍተኛ ኃላፊ ግን በዩኬ የጥገኝነት ጥያቄዎች የምናስተናግድበትን ሁሉንም አማራጮች እያየን ነው ሲሉ ሐሳቡ እንዳለ የሚጠቁም መረጃን ሰጥተዋል፡፡ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ፕሪቲ ፔተል በበኩሏ የሚመለከታቸውን የበታች ባለሥልጣናት ጥገኝነት አመልካች ስደተኞች ከዩኬ ውጭ ባሉ ቦታዎች ሆነው ጉዳያቸውን የሚከታተሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንዲሠሩ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ታዲያ የስደተኞች ማረፍያ የት ይሁን የሚለው ነው፡፡ አሮጌ ጀልባዎች የታሰቡትን ለዚሁ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ፋይናንሺያል ታይምስ ያወጣው ዘገባ ነገሩን መነጋገርያ አድርጎታል፡፡ ይኸውም የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስደተኞች ራቅ ባሉ ደሴቶች አስቀምጦ ጉዳያቸውን የዩኬን ምድር ሳይረግጡ እንዲከታተሉ የማድረግ ሐሳብ እየተጤነ ስለመሆኑ ዘገባው ያትታል፡፡ ስደተኞችን አርቀን እናስቀምጣቸው የሚለውን ሐሳብ ተከትሎ የት የሚለው ጥያቄ ነው ያልተመለሰው፡፡ አሴሸን ደሴት አንዷ እጩ ናት፡፡ ይቺ ደሴት ከዩኬ ርቃ በአትላንቲክ ውቅያኖስ የምትገኝ ናት፡፡ እንዲያውም ከእንግሊዝ ይልቅ ለብራዚል ትቀርባለች፡፡ ብሪታኒያ ጥገኝነት አመልካቾችን እዚያች ሩቅ ደሴት ልኮ በማቆየት ጥገኝነታቸው አዎንታዊ ምላሽ ሲያገኝ ብቻ የብሪታኒያ ምድር እንዲረግጡ የማድረግ ሐሳብ ሳይኖር አይቀርም ይላሉ የጋዜጣው ምንጮች፡፡ ይህ ሐሳብ በባለሥልጣናት ደረጃ ሲውጠነጠን የመጀመርያው አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም ሐሳቡ ተነስቶ ውድቅ ተደርጎ እንደነበረ ይኸው ጋዜጣው አስታውሷል፡፡ ሆኖም አሁን ሐሳቡ መልሶ እየተንሸራሸረ ነው፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ ምናልባት ከሥራ ውጭ የሆኑ ጀልባዎች ለስደተኞች አገልግሎት ጉዳዮች የማዋሉ ነገር እየተጤነ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡ ታንኳዎቹ የስደተኛ መኖርያ ይደረጉ ወይስ የስደተኞች ጉዳይ የሚታዩባቸው ቢሮዎች ዘገባው በግልጽ አላብራራም፡፡ ጋዜጣው ጨምሮ እንዳለው ሌሎች ከስኮትላንድ በብዙ ማይል ርቀው የሚገኙ ደሴቶችን እንደ ስደተኛ ጊዝያዊ ማቆያ የመጠቀሙ ሐሳብ ዳግም እየተጤነ ነው፡፡ የስኮትላንድ ሚኒስትር ኒኮላ ስተርጂዮን ግን ይህን ሐሳብ በትዊተር ሰሌዳቸው ክፉኛ ተችተውታል፡፡ ‹‹ሰዎችን እንደ ከብት የሚመለከትን ማንኛውንም ሐሳብ ውድቅ አደርጋለው›› ሲሉም ዝተዋል፡፡ በተወካዮች ምክር ቤት የማኅበረሰብ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ስለጉዳዩ የተጠየቁት ማቲው ራይክሩፍ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣው አገኘሁት ባለው መረጃ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ሆኖም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው ሁሉንም አማራጮች እየተመለከተ እንደሆነ አልካዱም፡፡ ‹‹ብዙ አገሮች እየተመለቱት ያሉትን አማራጮች እኛም እያየናቸው ነው፡፡ ለጊዜው ምንም ውሳኔ ላይ አልደርስንም›› ብለዋል፡፡ ሆኖም ዩኬ ሁሉንም ዓለም አቀፍ የስደተኛ አያያዝ ደንቦችን ታሟላለች፣ ስጋት ኤግባችሁ ብለዋል፡፡ የሌበር ፓርቲ ተጠሪና የአገር ውስጥ ሚኒስትር ተቆጣጣሪና ተጠባባቂ ሚኒስትር አባል ኒክ ቶማስ ፓርቲያቸው ይሄ ሰዎችን በታንኳዎች የማኖርን ሐሳብ በፍጹም እንደማይቀበለው፤ ሐሳቡም አሳፋሪ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የስኮቲሽ ናሽናል ፓርቲ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጆናና ቼሪ እንደምትለው ደግሞ ስደተኞቹን ከዩናይትድ ኪንግደም አርቆ የማስቀመጥ ሐሳብ እውነት ከሆነ ‹የሰው ልጅን እንደ ከብት ከመቁጠር አይተናነስም፤ እንቃወመዋለን›› ብላለች፡፡ ነገር ግን የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ተወካይ የምክር ቤት አባል አዳም ሆሎዌይ የአገር ውስጥ ሚኒስትር የታንኳም ሆነ የደሴቶችን አማራጭ ማየቱ ትክክልና ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ለምን ሲባሉ ምክንያቱም ስደትን ወደ ዩኬ ለሚያስቡ ሰዎች ተስፋ ያስቆርጣቸዋል ሲሉ መልሰዋል፡፡ የምክር ቤት አባሉ አዳም ለዕውቁ ቢቢሲ ሬዲዮ ፎር ፕሮግራም እንደተናገሩት ‹‹ስደተኞች ወደ እንግሊዝ መሰደድን ሲያስቡ 'ሆቴል አርፈን ጉዳያችን ይታያል፣ እንግሊዝ እየኖርን ሁሉ ነገር እየቀረበልን ተንደላቀን እንቆያለን' የሚለውን አስተሳሰብ መስበር አለብን ብለዋል፡፡ የምክ ቤት አባሉ አዳም ጨምረው እንዳሉት ብሪታኒያ ልክ እንደ አውስትራሊያ ስደተኞችን የማያበረታታ፣ እንዲያውም ተስፋ የሚያስቆርጥ አካሄድን መከተል አለባት፡፡ ይኸውም ከእንግሊዝ ምድር ራቅ ብሎ ወደሚገኙ ደሴቶች ስደተኞችን አርቆ የማስቀመጥ ሐሳብ ነው፡፡ ይህ አሰራር ሊኖራት ይገባ ነበር ብለዋል፡፡ አውስትራሊ በሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ትችትን ያስተናገደ የስደተኞች አያያዝን የምትከተል አገር ናት፡፡ ወደ አገሯ ለመግባት የሚሞክሩ ዜጎችን ናውሩ ደሴት ወይም ፓፓዎ ኒውጊኒ ደሴት ትልካቸዋለች፡፡ በብሪታኒያ ስደተኞችን የት እናድርጋቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይቱ እየተጧጧፈ የመጣው ከጎረቤት አገራት በታንኳ በእንግዝ ቻናል በኩል በአንድ ቀን ብቻ 400 ሰዎች ከገቡበት ከመስከረም ወዲህ ነው፡፡ የአገር ውስጥ ጉዳዮች መሥሪያ ቤት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአጎራባች አገሮች በትንንሽ ታንኳዎች ተሳፍረው ወደ ብሪታኒያ የሚገቡ ስደተኞችን ለማስቆም አዳዲስ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳውቋል፡፡ ነገር ግን እስካሁን ይፋ የሆነ አዲስ የቁጥጥር መንገድ የለም፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ 7ሺ የሚሆኑ ስደተኞች 500 በሚሆኑ ትንንሽ ታንኳዎች ተሳፍረው ብሪታኒያ መግባት ችለዋል፡፡ በእንግሊዝ ጥገኝነት ጠያቂዎች ተቀባይነት ለማግኘት ካሻቸው ወደ ትውልድ አገራቸው ቢመለሱ በዘራቸው፣ በማንነታቸው፣ በአስተሳሰባቸው፣ በጾታቸው ወይም በተመሳሳይ ጾታ የፍላጎት ምርጫቸው ወይም በሃይማኖታቸው ምክንያት ከባድ አደጋ እንደሚደርስባቸው መንግሥትን ማሳመን አለባቸው፡፡ የስደተኛ ጉዳይ ቢሮ የአመልካቾችን መረጃዎች ከፈተሸና ከመረመረ በኋላ በ6 ወራት ውስጥ የጥገኝነት ጥያቄው ተቀባይነት ሊሰጥ ወይም ውድቅ ሊያደርግ ይጠበቃል፡፡ ሆኖም የአመልካቾች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ አሁን አሁን ውሳኔዎች በከፍተኛ ሁኔታ ይዘገያሉ፡፡ የጥገኝነት አመልካቾች ማመልከቻቸው ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ የመሥራት ፍቃድ አይሰጣቸውም፡፡ ሆኖም መጠለያን መንግሥት ያቀርብላቸዋል፡፡ አመልካቾች መጀመርያ በቡድን የጋራ መኖርያዎች ውስጥ (ሆስቴል) ካረፉ በኋላ ቀስ በቀስ ቋሚ መኖርያ እንዲያገኙ ይደረጋል፡
news-46120867
https://www.bbc.com/amharic/news-46120867
«በቋንቋው ሳያስተምር ያደገ ሃገር እኔ አላውቅም» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ እነሆ መንፈቅ አለፋቸው። ታድያ ጠቅላዩ መንበረ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ሃገሪቱን ያሳድጋሉና መሆን አለባቸው ብለው ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል ምጣኔ ሃብታዊ ይዘት ያላቸው ይገኙበታል።
ቴሌንና አየር መንገድን የመሰሉ አሉ የሚባሉ የመንግሥት ድርጅቶችን ወደግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር ከመወጠን አንስቶ ከጎረቤት ሃገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት እስከማጠናከር ድረስ። የዳይስፖራ ትረስት ፈንድ (የአደራ ገንዘብ እንበለው) እና ለአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን ቪዛ አየር መንገድ ሲደርሱ መስጠትን ጨምሮ ያሉ ከዚህ በፊት የማናውቃቸው ክንውኖች መታየት ጀምረዋል። • ጫትን መቆጣጠር ወይስ ማገድ? በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማክሮና ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚክስ ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ያከናወኗቸው ጉዳዮች መልካም ሆነው ሳለ በምጣኔ ሃብት ጉዳይ አማካሪ ያሻቸዋል ይላሉ። እውን ጠቅላዩ ወደሥልጣን ከመጡ ወዲህ የምጣኔ ሃብት ፖሊስ ለውጥ አይተናል ወይ? ትልቁ ጥያቄ ነው። «የምር የሆነ የፖሊሲ ለውጥ የለም ግን ሃሳብ አለ፤ የመለወጥ አዝማሚያ ታያለህ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጡ ወዲህ ይህ ነው ፖሊሲዬ በዚህ መልኩ ነው የምሄደው ያሉን ነገር የለም። ሃዋሳ በነበረው ጉባዔ (የኢህአዴግ) ላይም የተናገሩት ይሄንኑ ነው። በፊት የነበረው የኢኮኖሚ አስተሳሰብ እንዳለ እንደሚቀጥል ነው ፍንጭ የሰጡት።...» « ...በአንፃሩ ደግሞ ከዚያ ቀድም ብሎ አንዳንድ ትላልቅ የምንላቸውን የመንግሥት ኩባንያዎች በከፊል ለመሸጥ ሃሳብ እንዳላቸው አሳውቀዋል። ይህ የሚያሳይህ በፊት ከነበረው ለየት ባለ መልኩ ከፈት በማድረግ፤ የመንግሥት ሚና ብቻ ከጎላበት ኢኮኖሚ የግሉም ዘርፍ የሚሳተፍበት ኢኮኖሚ ለመመሥረት ቢያንስ ሃሳብ እንዳላቸው ያሳያል» ይላሉ ፕሮፌሰሩ። • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? የመንግሥት ድርጅቶችን የመሸጥ ጉዳይ ግን አከራካሪነቱ እንደቀጠለ ነው፤ 'ሃገር መሸጥ ነው' በሚሉና 'እንዲህ ካልሆነ አናድግም' የሚል ሃሳብ በሚያነሱ መካከል። ለፕሮፌሰር አለማየሁ ግን ዋናው ጉዳይ ወዲህ ነው፤ መለየትና ማመቻቸት። «ወደ ገበያ ተኮር ኢኮኖሚ የምንሄድበት ዋናው ምክንያት ውድድር ለማምጣት ነው፤ ውድድር ለማምጣት ደግሞ መወዳደሪያ ሜዳውን ማስተካከል አለብን። ውድድሩን የሚመራ፤ የሚቆጣጠር አካል ማደርጀት ያስፈልጋል። አለበለዚያ ዝም ብሎ ከመንግሥት ወደ ግል መሄድ፤ 'ሞኖፖሊውን' ከመንግሥት ወደግል መቀየር ነው። የግል ሞኖፖል ደግሞ ተጠያቂነት የለበትም፤ ብሩን የት ያጥፋው የት አይታወቅም፤ የሞራል ኃላፊነትም የለበትም።» ምሁሩ «ምሳሌ ልስጥህ...» ይላሉ፤ «ምሳሌ ልስጥህ፤ ኢትዮ-ቴሌኮም በጣም ደካማ ነው፤ እናውቀዋለን። ሶማሊያ እንኳን ያለው የቴሌኮም አገልግሎት የተሻለ ነው። ኬንያማ አንደርስባቸውም። ስለዚህ እንደ ቴሌኮም ዓይነቱን ምን ማድረግ ነው? በከፊል መሸጥ። ችሎታው ላላቸው፤ ቢቻል ደግሞ አፍሪቃዊ ለሆኑ ድርጅቶች፤ በዚያውም ቀጣናዊ ግንኙነቱን ማጠናከር። እንደዚህ አድርጎ ተወዳዳሪነቱን ማጎልበት። ይህንን ውድድር የሚቆጣጠር ሥርዓት መዘርጋት፤ ከዚያ ለውድድር መክፈት። እንዲህ ነው መሆን ያለበት።» «አሁን በሌላ በኩል ደግሞ ስትመጣ አየር መንገድ አለ። አየር መንገድ በእኔ እምነት እንኳን ሊሸጥ፤ ለመሸጥ መታሰብ ራሱ የለበትም። ምክንያቱም በጣም ትርፋማ የሆነ ድርጅት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም ተወዳዳሪ የሆነ ድርጅት ነው፤ በጣም! ያለው ንብረት ወደ 80 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፤ ዕዳው 60 ቢሊዮን ገደማ ነው። ስለዚህ ንብረቱ በአያሌው ይበልጣል። በመንገደኛ የሚያገኘው ገቢ 'ቶፕ' ሰባት ከምትላቸው የአሜሪካ አየር መንገዶች ይበልጣል።» «ይህ እንግዲህ ኢኮኖሚያዊ መከራከሪያ ነው፤ ወደ ባህላዊው ስትመጣ አየር መንገድ ቅርሳችን ነው፤ ዓለም ላይ ምንም ሳይሳካልን ሲቀር እንኳ አየር መንገዳችን ስኬታማ ነበር፤ ምልክታችን ነው። 'ፕራይቬታይዜሽን ለውድድር ነው ካልን፤ በትንሽ ዋጋ ህዝቡን ለማገልገል ነው የምንል ከሆነ አየር መንገድን መሸጥ አዋጭ አይደለም። እኔ እንደ ኢኮኖሚስትም እንደ ዜጋም አልቀበለውም።» ምክረ ሃሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በርካታ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችን ያካተተ የህግ አማካሪ ያዋቀሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መሰል ውሳኔ በምጣኔ ሃብቱ በኩል እንዲያሳልፉ መወትወት ከተጀመረ ውሎ አድሯል። እውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ያስፈልጋቸዋል ወይ? የሚል ጥያቄ የሚያነሱም አልጠፉም። «ምንም ጥያቄ የለውም. . .» ይላሉ ፕሮፌሰር አለማየሁ። «ምንም ጥያቄ የለውም፤ አማካሪ ያስፈልጋቸዋል። ያደገ ሃገር ሆኖ ያለአማካሪ ያደገ እኔ አላውቅም። ከዚህም አንድ ደረጃ ፈቅ ማድረግ እችላለሁ። ያደገ ሃገር ሆኖ በቋንቋው ሳያስተምር ያደገ ሃገር እኔ አላውቅም። ቻይና ብትል ጃፓን፤ ጀርመን፣ አሜሪካ. . .እኔ አስተማሪ ስለሆንኩ ተማሪዎቼን ሳያቸው ከትምህርቱ እኩል ቋንቋ ችግር ነው። እንኳን የኢኮኖሚ አማካሪ ይቅርና ማለቴ ነው።» «ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉን ነገር መሆን አይችሉም፤ ኢኮኖሚው ደግሞ የረቀቀ ነው። መዓት ፈርጆች አሉት። በእኔ ግምት ማንኛውም መሪ ያለኢኮኖሚ አማካሪ እሠራለሁ ካለ አልገባውም ማለት ነው።» ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት. . . ጠቅላዩ ከተመረጡ ወዲህ የመጀመሪያ ካሏቸው ሥራዎች መካከል ወደጎረቤት ሃገራት ብቅ ብሎ ወዳጅነትን ማጠንከር ነበር። ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ. . . ታሪካዊ የሆነው ከኤርትራ ጋር የተደረገው እርቀ ሰላም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዘመን ከተከወኑ መካከል እንደስማቸው አብይ ሆኖ የሚጠቀስ ነው። «የኛ ፖለቲካ እንደምታውቀው በጣም እየጠበበ፤ እየጠበበ እየሄደ ወደ ጎሳ፤ ከጎሳ ደግሞ ቀጥሎ ወደ መንደር፤ ከመንደር ደግሞ ወደ ቀበሌ መሄዱ አይቀርም በዚሁ ከቀጠለ። ሊህቃን ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ሰዎችን የሚያደራጁበት መንገድ ነው የሚፈልጉት። ብትፈልግ ሶሻሊዝምና ካፒታሊዝም ይልሃል፤ ብትፈልግ ቀይ ሽብር፣ ነጭ ሽብር ይልሃል፤ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ቤኒሻንጉል ይልሃል፤ ማደራጃ ነው የሚፈልጉት በእኔ እምነት። ቀጣናዊ የሆነው የኢኮኖሚ አስተሳሰብ ከእንደዚህ ዓይነት አናሳ ከሆኑ አስተሳሰቦች አውጥቶ በሰፊው እንድናይ ስለሚያደርገን ከፖለቲካ አንፃር ጥሩ መነፅር ነው ብዬ ነው የምገምተው።» • "በፍትህ ተቋማት ላይ የለውጥ እርምጃ ይፋ ይሆናል" ጠ/ሚ ዐብይ «አሁን ወደ ኤርትራ እንምጣ. . . ነፃ የሆነ የህዝብ ፍሰት፤ ነፃ የሆነ የካፒታል ፍሰት፤ ነፃ የሆነ እንቅስቃሴ የመጨረሻው የዕድገት ደረጃ ነው። አውሮጳውያን ከ50 ዓመታት በላይ ነው ያ ጫፍ ለመድረስ የፈጀባቸው። በኢትዮጵያና በኤርትራ ጉዳይ ግን ባለፉት ጥቂት ወራት የሆነው የ50 ዓመቱን በአንድ ቀን እንደማድረግ ነው። የኔ ሪኮሜንዴሽን (ምክር) ምንድነው፤ ቆንጆ ነው ሃሳቡ፤ ህዝብን ከህዝብ ለማቀራረብ የሚደረገው፤ ነገር ግን ኤክስፐርቶች (ባለሙያዎች) ያስፈልጉናል። በዚህ መንገድ ነው የምንሄደው፤ በመርህ ደረጃ ሁላችንንም ተጠቃሚ የሚያደርግ፤ የሰላሙን ዘላቂነት የሚያረጋግጥ ሥርዓት ይህ ነው ብለው የሚመክሩ 'ኤክስፐርቶች' ማዘጋጀት ነበረባቸው የሚል ሃሳብ ነው ያለኝ።» እነ ዓለም ባንክ ይታመናሉ? የዓለም ባንክ፣ የዓለም የገንዘብ ተቋም እና መሰል አበዳሪ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት ይህን ያህል የሻከረ የሚባል አይደለም። በቅርቡ የዓለም የገንዘብ ተቋም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የፈረንጆች ዓመት መልካም የሚባል ዕድገት ታስመዘግባለች የሚል ትንበያ ይዞ ብቅ ብሏል። የዓለም ባንክም ለወዳጄ ኢትዮጵያ ያለሆነ ዶላር አፈር ይብላው በሚል 1.2 ቢሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቷል። «እኔ እነ ዓለም ባንክ ብድር ሲፈቅዱ ሃሳብ ነው የሚገባኝ። ለምን ብትለኝ፤ ከጀርባ የሆነ ነገር አለ ማለት ነው። እንጂ ዝም ብለው አይፈቅዱልህም። ወይ ፕራይቬታይዝ አድርግ ብለውሃል ወይ የሆነ ነገር ሽጥ ብለውሃል ማለት ነው። እነሱ የቆሙላቸው የምዕራብ ሃገር ድርጅቶች ከኋላ ሊገዙ ተሰልፈዋል ብዬ ነው የማስበው። ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርታችን 60 በመቶ ዕዳ ነው። ይህ አሁን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ችግር አይደለም፤ የበፊቶቹ እንጂ፤ ቢሆንም ይህንን ዕዳ ወርሰውታል።» ምሁሩ ሲቀጥሉ «አሁን እንዴት ይፍቱት ነው ዋናው ቁም ነገር» ይላሉ። «እኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ብሆን፤ እግዚአብሔር አያድርገኝና (ሳቅ. . .)፤ ምንድነው የማደርገው፤ ምዕራብም ምስራቅም አልልም። ከኢትዮጵያ ጥቅም አንፃር ነገሮችን አይቼ ጠቃሚው ላይ ትኩረቴን አድርጌ ፖሊሲዬን በዛ ነበር የምቀርፀው።» ምጣኔ ሃብቱን ማሳደጉ ይቅርብንና ሰላሙ ይቅደም የሚሉ ድምፆች መሰማት ከጀመሩ ውለው አድረዋል። ለፕሮፌሰር አለማየሁ እና መሰሎቻቸው ግን መፍትሄው ሁለቱን አንድ ላይ ማስኬድ ነው። «ሁሉቱን አንድ ላይ ነው ማስኬድ ያለብን። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ያመጣው (ወደሥልጣን) ፖለቲካ ብቻ አይደለም፤ ኢኮኖሚውም እንጂ። ለምሳሌ ወጣት ሥራ አጦችን እንውሰዳቸው። ኦፊሻል ቁጥሩ 25 በመቶ ሥራ አጥ ወጣቶች እንዳሉ ነው የሚያሳየን። እኔ ያደረግኩት ጥናት እንደሚያሳው 40 በመቶ የሚሆኑ ወጣቶች ኢ-መደበኛ በሚባለው ዘርፍ ውስጥ ነው ያሉት፤ ሥራ አጥነት ማለት በሌላ ቋንቋ። ስለዚህ ለዚህ ሥራ አጥ ወጣት ሥራ ካልሰጡት ሊነሳባቸው ይችላል። ፋንዳሜንታል (መሠረታዊ) ችግሩ ምንድነው? ድህነት፣ ሥራ አጥነትና ፍትሃዊ ያልሆነ የገቢ ሥርጭት ነበር። ለኔ አብይን ካመጣው አብዮት ጀርባ ይሄ ጥያቄ አለ። ከላይ ያለው 'አይድዮሎጂ' ላዕላይ መዋቅሩ ነው። ውስጡ ግን ይሄ ነው። ስለዚህ ከፖለቲካው እኩል ኧረ እንደውም በበለጠ ይህንን ችግር ለመፍታት መንገድ ካልጀመሩ እሳቸውም ላይ ይመጣል።» • "ምንም ከህዝብ የሚደበቅ ነገር አይኖርም" የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ አብዲሳ
43242907
https://www.bbc.com/amharic/43242907
የአፍሪካ አገራት ከህፃናት የተመጣጠነ ምግብ አንፃር የልማት ግብን አያሳኩም
አንድም የአፍሪካ አገር በ2030 የህፃናት የተመጣጠነ ምግብ ጉድለትን የማስወገድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያስቀመጠውን የዘላቂ ልማት ግብን እውን እንደማያደርጉ የህፃናት እድገት ላይ የተሰሩ ሁለት ሰፊ ጥናቶች ጠቆሙ።
ይህ ግብ ከተመድ ዘላቂ የልማት ግቦች መካከል አንዱ ነው። አገራቱ ግቡን እውን ለማድረግ እንደማይችሉ ጥናቶቹ ቢያመለክቱም ቢያንስ በእያንዳንዱ የአፍሪካ አገር የህፃናት ጤና የተሻሻለ የሚሆንበት አንድ አካባቢ መኖሩን አስቀምጠዋል። ጥናቶቹ በመሰረታዊነት የሚያተኩሩት የህፃናት እድገትና በመውለድ እድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ሴቶች የትምህርት ተደራሽነትን ነው። ይህ የሆነው እነዚህ ነገሮች ከህፃናት ሞት ጋር ተያያዥነታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ነው። "እነዚህ ሁለት ነገሮች አንድላይ ህዝብ የቱ ጋር ጤናማ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነም ጠቋሚዎች ናቸው" ይላሉ፤ የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲው የዓለም አቀፍ ጤና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሲሞን ሃይ። ጥናቱ የአፍሪካ አገራት ግቡን እውን ማድረግ አይችሉም ቢልም ግን የህፃናት የተመጣጠነ ምግብ ችግርን በመቅረፍ ረገድ ብዙዎቹ ከሰሃራ በታች ያሉ፤ ምሥራቃዊና ደቡባዊ የአፍሪካ አገራት መሻሻሎች ማሳየታቸውን ይጠቁማል።
news-49671793
https://www.bbc.com/amharic/news-49671793
"ፍቅር እስከ መቃብርን አልረሳውም" ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም
በ2010 ዓ. ም. የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፤ በትግራይ ክልል ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክልል ባሉ የተለያዩ መዋቅሮች ውስጥ ከ1995 ዓ. ም. ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል።
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ካሉት ጥቂት ሴቶች አንዷ ሲሆኑ፤የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ከመሾማቸው በፊት የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የደቡብ ምሥራቅ ዞን አስተዳዳሪ፣ የትግራይ ክልል የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም በፓርቲያቸው ውስጥም የገጠር ዘርፍ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል። አስመራ የተወለዱት ወ/ሮ ኬሪያ፤ በትምህርት ዝግጅታቸውም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኢንቫይሮሜንታል አንትሮፖሎጂ ሰርተዋል። ቢቢሲ አማርኛ በዓሉን ምክንያት በማድረግ አፈ ጉባኤዋ እንዴት ነው የሚያሳልፉት? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች አንስተንላቸዋል። • ከነፍስ የተጠለሉ የዘሪቱ ከበደ ዜማዎች በዓላትን እንዴት ያሳልፋሉ? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ በዓል ለሴትና ለወንድ አንድ አይደለም። በተለይ በከፍተኛ ደረጃ አመራር ላይ ስትደርሺ ያው መቼም ሥራ አቋርጠሽ የቤት፣ የበዓል ላዘጋጅ አትይም። ነገር ግን ሁለቱንም አደራርበን ነው የምንሠራው። ስለዚህ የቤቱም እንዲሟላ የእረፍት ሰአትሽን፣ የመኝታ ጊዜሽን ዋጋ የምትከፍይበት ጊዜ አለ። የቤቱንም ሆነ የሥራም ደግሞ እንዳይደናቀፍ በተሟላ መልኩ የመምራት ኃላፊነት አለ። ሁለቱንም በሚያቀናጅና በሚያስማማ መንገድ መሆን አለበት። በተለይ አዲስ ዓመትን ለየት ባለ መንፈስ፣ አስተሳሰብ እና ዝግጅት ለሥራ ብቻ ሳይሆን ለሕይወትም፣ ለቤትም፤ እንዴት እንደምትመሪው የምታቅጅው፤ ሁለቱንም የቤትና አደባባይ አቀናጅተሽ በአዲስ መንፈስ የምትቀበይው በዓል ነው። • የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ • "ሰዓረ ሙዚቃ በጣም ያዝናናው ነበር" ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ ስለዚህ በተለይ የዘንድሮው አዲስ ዓመት ደግሞ በአገራችን ላይ የሚታዩ ብዙ ነገሮችም ስላሉ እነዚህን አዳጋች ነገሮችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል፤ የተሻለ ነገር እንዴት መሥራት እንዳለብን ከወዲሁ በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ አሰራር፤ አገራችን፣ ሕዝባችን ሰላም እንዲሆን፤ የተረጋጋ ኑሮና ሕይወት እንዲመራም ጭምር የምታስቢበት ነው፤ በዛ በደስታ ውስጥ ሆነሽ ማለት ነው። በዓል ላይ ምን ያደርጋሉ፤ ቤት ውስጥ እንዴት ነው የሚያሳልፉት? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ አንዳንድ ሰዎችን ምን ትታዘቢያለሽ? ወደ ከፍተኛ አመራር ስትደርሺ ቤትሽ ገብተሽ ምንም እቃ እንደማታነሺ አድርገው የሚወስዱ አሉ። ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው። ለሴት ልጅ በተለይ በኛ አስተዳደግ፣ በባህሉም፣ በእሳቤውም ብዙ ያልተቀረፉ ችግሮች አሉ። ስለዚህ ሴት ልጅ ከፍተኛ አመራርም ትድረስ የትኛውም ቦታ ላይ ብትሆን ቤት ስትገባ የሚጠበቅባት የቤት ውስጥ አገልግሎቶች አሉ። የግድ ወደቤቷ፣ ወደጓሮ መግባቷ አይቀርም። ምንም እንኳን የቤት ሠራተኛ ቢኖርም፤ ያው ምን እንደተዘጋጀ፣ እንደጎደለ፣ ምን እንደተሟላ አያለሁ። ማገዝ የሚያስፈልጉና መስተካከል የሚያስፈልጉ ነገሮችን ታስተካክያለሽ። • ''አባቴ የቼልሲ ደጋፊ ነበር'' የሜጄር ጄኔራል ገዛዒ አበራ ልጅ ልጆችም፣ ባለቤትም አለ። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች በቤትም ጭምር ተጨማሪ ሰዓት የምትሠሪው አለ፣ ተጨማሪ የምትከፍይው ጊዜና የምትከፍይው ጉልበት አለ፤ ለየት ያለ ለሴት። ወንድ ግን ዞሮ ዞሮ ቤት የተሠራለትን ቁጭ ብሎ የሚጠብቅ ነው። ምናልባት የአሁኑ ትውልድ የሚያግዙ ወንዶች ሊኖሩ ይችላሉ። ለኛ ግን በቤትም ጭምር ትልቅ ኃላፊነት ነው የተጣለብን። በተለይ በበዓል ለሴት ልጅ ተጨማሪ ሥራው ከፍተኛ ነው። የተለያዩ ክብረ በዓላት አሉ። ለርስዎ ለየት ያለው የትኛው ነው? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ ከእምነት ጋር ከተያያዘ ያው አረፋና ኢድ አልፈጥር ነው። ግን ከባህላችንና ከአገራችን ከሆነ አዲስ ዓመት ደስ ይለኛል። አዲስ ዓመትን በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ አስተሳሰብ ከሁሉም ሕዝብ ጋር በጋራና በደስታ የምንቀበለው ስለሆነና የዘመን መለወጫም ስለሆነ እሱም ትልቅ በዓል ነው። በዓል ሲነሳ ብዙ ጊዜ የሚነሳው ምግብ ነው እና እርስዎ የሚወዱት ምግብ አለ? በአጠቃላይ የሚወዱት ምግብ ምንድን ነው? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ እኔ አብዛኛውን ጊዜ ምግብ አልመርጥም፤ ከሁሉም በላይ የምወደው ምግብ ግን ሩዝ በስጋ ነው። ባህላዊ፣ የተለመደ ምግባችን ሽሮም እወዳለሁ። በተለይ ከመጀመሪያው ተመጥኖ፣ ቅመም ገብቶበት፣ በደንብ በስሎ፣ የተከሸነ ሽሮ በጣም ነው የምወደው። ሁሉንም ምግብ እሠራለሁ፤ እችላለሁ ያው ሴት ልጅ የምትችለውን (ሳቅ) ከበዓል ምግብስ የሚወዱት? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ ከበዓል ምግብ ዶሮ ነው የምወደው። በዓል ሲመጣ ከሁሉም በፊት ቀድማ የምትሠራው ዶሮ ናት። ለሴት ልጅ ያው ጣጣዋ ብዙ ነው። ዶሮ ለመሥራት ትንሽ ጉልበትና ጊዜ ትፈልጋለች። ያው በበዓል ላይ ዶሮ፣ ብርዝ፣ አብሽ የሚባልም አለ (በተለይ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ)፤ እነዚህ ጊዜ የሚፈልጉና አስቀድመሽ የምትሠሪያቸው ናቸው። • መከላከያ የሶሪያ እና የየመን ዜጋ የሆኑ የአይኤስ አባላትን በቁጥጥር ሥር አዋልኩ አለ ድፎ ዳቦና ሁሉም ነገር እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። በበአሉ ጊዜ ደግሞ ቄጠማውም፣ ፈንዲሻውም፣ ከረሜላውም፣ ብስኩቱም ይዘጋጃል። ይሄ ሁሉ ሲሟላ ነው በአል፣ በአል የሚሸተው። በትርፍ ጊዜዎ ምን ያደርጋሉ? ፊልም ያያሉ? ሙዚቃ ያዳምጣሉ? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ ሙዚቃ ያንን ያህል አላዳምጥም። ድሮ ብዙ ሙዚቃዎችን አደምጥ ነበር። በአሁኑ ሰአት የማዳምጥበት ጊዜ የለም (ሳቅ)፤ ድሮ ግን የአስቴር አወቀን ሙዚቃ አዳምጥ ነበር። በአሁኑ ሰአት የተወሰኑ ፊልሞች አያለሁ። በርግጥ እያቆራረጥኩ ነው የማየው። መጽሐፍ ያነባሉ? አሁን እያነበቡት ያለ መጽሐፍ አለ? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ መጽሐፍ አነባለሁ። አብዛኛውን ጊዜ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው የማነበው፤ በአገር ውስጥ የሚታተሙትን እንዲሁም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ያዘጋጃቸው የነበሩ ፅሁፎችን አነባለሁ። ሌላው ደግሞ ከአገራችን ተመሳሳይ ሥርአት ያላቸው አገራት የሚከተሉትን ርዕዮተ ዓለም አነባለሁ። በተለይም ከፌደራሊዝም ሥርአት ጋር ተያይዞ የማነባቸው አንዳንድ ፅሁፎች አሉ። • 2011፡ በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት • በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ ለመዝናናት ልብወለድ አያነቡም? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ 'ፊክሽን' ድሮ አነብ ነበር (ሳቅ)፤ በተለይ ድሮ ትምህርት ጨርሰን ክረምት ላይ ሲሆን ብዙ ልብወለዶች አነብ ነበር። ካነበቡት ልብወለድ መፅሀፎች የማይረሱት አለ? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ ያው 'ፍቅር እስከ መቃብር' ን አልረሳውም (ሳቅ) በአንድ ጊዜ ጀምሬ ሳላቋርጥ የጨረስኩት ነው። እሱን ነው በብዛት የማልረሳው ያዘኑበትና የተደሰቱበት የሚያስታውሱት ቀን አለ? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ አለ ግን...ይኼ እንኳን ቢቀር ይሻለኛል። መጀመሪያ ከእንቅልፍዎ ሲነሱ ወይም ሲተኙ የሚያደርጉት ተመሳሳይ ነገር አለ? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ ከአልጋየ ተነስቸ መጀመሪያ ሁልጊዜም እሰግዳለሁ። ማምሸት እወዳለሁ፤ እና ስተኛም የማነበውን ነገር አንብቤ ነው የምተኛው፤ የሚወዱት ጥቅስ አለ? ሁልጊዜም ከህሊናዎ የማይጠፋ? ወይም እንደ ሕይወት መርህ የሚጠቀሙበት? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ አለ! በትግርኛ ስለሆነ፤ በአማርኛ ሲተረጎም ትርጉሙን ሊያጣ ይችላል። ለበዓሉ ምን መልዕክት አለዎት? ለኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን ይመኛሉ? ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፡ ያው በዓሉን በተለያየ መንገድ ነው የምናከብረው፤ በተለይ የአሁኑን በአል ከወትሮው ለየት የሚያደርገው በሕዝቦች መካከል የነበረው አብሮነት፣ መቻቻልና መከባበር፣ መፈቃቀርና መደጋገፍ ትንሽ የላላበት ጊዜ ባለበት ነው የምናከብረው። ትልቁ ነገር አገራችን የልማት፣ የሰላም ተምሳሌት፣ የዕድገትና የብልፅግና ተምሳሌት የምትሆነው በሕዝቦቿ ላይ ያለው አንድነት፣ መቻቻልና መከባበር ሲጠነክር ነው። ያለፈውን ብዙ ችግሮቻችን እንዳሉ ትተን ለሚቀጥለው ለ2012 ዓ. ም. የሰላም፣ የብልፅግናና የእድገት እንዲሆንልን እመኛለሁ። አገራችን ብዙ ችግሮች እንዲሁም እድሎች አሉ። እድሎቻችንን በደንብ አስፍተን መጠቀም፤ በተለይ ከሚለያዩን አንድ የሚያደርጉንን ትኩረት አድርገን፤ የሕዝቦች አንድነት የሚጠናከርበት፤ ሁላችንም የየራሳችንን ድርሻ መወጣት አለብን። ሰላም የሚፈጠረው በእያንዳንዱ ዜጋ ሰላም በሥነ ልቦናው፣ በአእምሮው ሲፈጠር ነው። ሁላችንም በሥነ ልቦናና በአዕምሯችን ሰላም ፈጥረን ከሌሎች ጋርም ሰላም ሆነን አገራችን የሰላምና የእድገት ተምሳሌት እንድትሆን ሁላችንም መጣር እንዳለብን ቃል የምንገባበት መሆን አለበት።
news-45544578
https://www.bbc.com/amharic/news-45544578
በጀርመን በርሊን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢሊዩድ ኪፕቾጌ የዓለምን ክብረ ወሰን ሰበረ
ኬንያዊው ኢሊዩድ ኪፕቾጌ በጀርመን በርሊን በተካሄደው የማራቶን ውድድር 2፡1፡39 ሰከንድ በመግባት የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብሯል። የ 33 ዓመቱ አትሌት በአውሮፓውያኑ 2014 በአገሩ ልጅ ደኒስ ኪሜቶ ተይዞ የነበረውን ሰዓት በ1፡20 ሰከንድ አሻሽሎ ክብረ ወሰኑን የራሱ አድርጓል።
ኬንያዊው አትሌት ኢሊዩድ ኪፕቾጌ • ኦፌኮና ሰማያዊ መንግሥት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ • የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል ውድድሩን ባጠናቀቀበት ጊዜም "የዛሬውን ቀን ለመግለፅ ቃላት ያጥረኛል፤ የዓለምን ክብረ ወሰንን በመስበሬ ደስተኛ ነኝ" ሲል ተናግሯል። ኪፕቾጌ በዚህ ዓመት መጀመሪያ በለንደን የተካሄደውን ማራቶን ለሶስተኛ ጊዜ አሸንፏል። በረጅም ርቀት የኦሎምፒክ አሸናፊም ነው። • ቄሮ፣ ሴታዊት፣ ፋኖ…የትውልዱ ድምጾች • 'በእኔ በኩል ሒሳቤን ዘግቻለሁ ' አቶ ታምራት ላይኔ • ድንበር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለቀው ይወጣሉ "በጣም ከባድ ነበር፤ የራሴን ፍጥነት ነበር የምከተለው፤ አሰልጣኘን አምነዋለሁ፤ ያ ነው በመጨረሻዎቹ ኪሎ ሜትር አፈትልኬ እንዲወጣ ያስቻለኝ ሲል ተናግሯል። በሴቶች ምድብ ኬንያዊቷ ግሌዲየስ ቸሮኖ 2፡18፡11 ሰከንድ በመግባት ድልን ተቀዳጅታለች። በሁለተኛ ደረጃነት ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሩቲ አጋ 2፡18፡34 በመግባት ስታጠናቅቅ፤ ታሸንፋለች ተብላ በጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በ2:18:55 በመግባት በሶስተኛ ደረጃ ውድድሩን ጨርሳለች።
news-52088102
https://www.bbc.com/amharic/news-52088102
ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 መዛመትን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ እመርታ ያሳዩ ስድስት ምርቶች
የኮሮና ቫይረስ መዛመት እያሻቀበ ባለበት በአሁኑ ወቅት በንግዱ አለም ላይ ከፍተኛ ጫናን አሳርፏል፤ ንግዶች አሽቆልቁለዋል፣ አንዳንዶችም ላያንሰራሩ ወድቀዋል። የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን እንዲሉ የኮሮና ቫይረስ መዛመትን ተከትሎ ንግዳቸው በከፍተኛ ሁኔታ እመርታ ያሳዩም ዘርፎች አሉ።
" አብዛኛውን ጊዜ በገና ወቅት ስራ ይበዛብናል" የሚለው በበይነመረብ (ኢንተርኔት) ላይ የቡና ሽያጭ አቅርቦት ባለቤት የሆነው ግለሰብ በአሁኑ ወቅት ሽያጫቸው በእጥፍ እንደጨመረ አልደበቀም። እንዲሁም የተለያዩ ስፖርታዊ ቁሳቁሶችን የሚያቀርብ አንድ ድርጅትም በሸማቾች ፍላጎት እንደተጨናነቁ አሳውቋል። " ያለንን የጠረጴዛ ቴኒስ ሸጠን ጨርሰናል፤ አዲሱ የመፀዳጃ ወረቀት( ሶፍት) ነው ማለት ይቻላል" በማለት በቀልድ መልኩ ተናግሯል። • ኮሮናቫይረስን ለማሸነፍ ከኢቦላ በሽታ ምን ልምድ መውሰድ ይቻላል? ቤተሰቦች በአንድ ቤት ውስጥ ታፍነው ከቤት መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ ምን ማድረግ ይችላሉ፤ አዕምሯቸውን እንዲሁም አካላቸውን የሚያነቃቃ ነገር ይፈልጋሉ። በዚህ ወቅት ሽያጫቸው በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀቡ ያሉ ምርቶች የትኞቹ ናቸው? ሳይክሎችና ስፖርታዊ ቁሳቁሶች አካላዊ እንቅስቃሴም ለማድረግም ሆነ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመጓጓዝ ሳይክሎች ተመራጭ ሆነዋል። "ብዙዎች ነፃ ሆኜ መጓዝን እፈልጋለሁ ብለው ሲያስቡ ሳይክሎችን ይመርጣሉ" በማለት ብሮምተን የተባለው የሳይክል ኩባንያ ስራ አስፈፃሚ ዊል በትለር አዳምስ ይናገራሉ። በተለይም በእንግሊዝ ባሉ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ጋር ሲወዳደር አስራ አምስት በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከዚህም በተጨማሪ ታዋቂው የለንደን ሳይክል መጠገኛም እንደቀድሞው ስራ አልጎደለበትም፤ ያረጁ ሳይክሎችን የህዝብ መመላለሻ ትራንሰፖርቶችን እንዲያስወግዱ በማለት ለደንበኞቻቸው ይጠግናሉ። ሪቴይለን ሃልፎርድስ የተባለው ድርጅትም በሳይክል ሽያጭ ከፍተኛ ጭማሪ እንዳስመዘገበ ሪፖርት አድርጓል "ከቤታቸው መውጣት የማይችሉ ሰዎችም ቤታቸው ውስጥ ሆነው አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይፈልጋሉ" ብሏል። በቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ስፖርታዊ ቁሳቁሶች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ሚንቴል የተባለው በገበያ አቅርቦት ላይ ምርምር የሚሰራውን ድርጅት ኃላፊ ቶቢ ክላርክ በበኩሉ ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ስፖርታዊ ቁሳቁሶች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን፤ ወደ ስፖርት ቤቶች መሄድ ስለማይችሉም እሱን ለማካካስ በመፈለግ ይመስላል" ብሏል። የቤትና የውጭ መጫወቻዎች የተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታ አይነቶችን የሚያቀርበው አንዲ ቤሬስፎርድ እንደሚለው ከነበራቸው የክምችት ክፍል የጠረጴዛ ቴኒስ ሙሉ በሙሉ እንደተሸጠና ለዚህ ሳምንት ታዞ የነበረው ተሸጦ እንዳለቀ ነው። "በዚህ ሳምንት 124 የጠረጴዛ ቴኒሶች ሸጫለሁ፤ በዚህ ወቅት አምና የሸጥኩት 15 ብቻ ነው" • ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ በተለይም መንግሥት ትምህርት ቤቶች ይዘጉ የሚለውን እወጃ ተከትሎ ሽያጮች በከፍተኛ ሁኔታ ነው የጨመሩት። ከጠረጴዛ ቴኒስ በተጨማሪ የፑል ጠረጴዛዎችም በሸማቾች በከፍተኛ ሁኔታ እንደተቸበቸቡ አንዲ ገልጿል። ከነበረውም 500 የፑል ጠረጴዛ ግማሹን፣250፣ ሸጧል። የቤት የእጅ ስራ መስሪያዎችና ለአትክልት ስፍራ የሚውሉ ዘሮች ጀስት ሲድ የተባለ ድርጅት የተለያዩ አዝርዕት እንዲሁም አትክልት ዘሮችን ያቀርባል። ነገር ግን ከሰሞኑ ዘሮችን ማቅረብ እንደማይችል ድርጅቱን ወክሎ ፊል ጆንስ ተናግሯል። ለዚህም እንደ ምክንያትነት ያቀረቡት ካሮት፣ ሰላጣና ቲማቲም የመሳሰሉ ዘሮች አቅማቸው ከሚፈቅደው በላይ በገፍ በመጠያቃቸው ነው። ጀስት ሲድ ብቻ አይደለም ሁለቱ ትልልቅ የዘር አምራች ኩባንያዎች ማርሻልስና ሰተንስም ስልካቸውን መመለስ አቁመዋል። • ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ እስከ ሠኔ ድረስ ከኮሮና ታገገምላች አሉ ለአንዳንድ ሸማቾች አትክልቶች ሊያጥሩ እንደሚችሉ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ በመግባት የሚገዙ ቢኖሩም፣ ለአብዛኛው ግን ዘሮችን የሚገዙት በትርፍ ጊዜያችን ምን እናድርግ በሚል እንደሆነ ፊል ይናገራል። ሌላኛው የዘር አከፋፋይ ፍራንቺ ሲድስም ድረገፁን ለአጭር ጊዜ ከአገልግሎት ውጭ ያደረገ ሲሆን "ብዙዎች በፍራቻ በገፍ እየገዙም ነው" የሚል ምላሽም ሰጥቷል። አትክልቶችን ከመትከል በተጨማሪ ብዙዎች በአንድ ቤት ውስጥ መታፈን ከሚያመጣው ድብርት ለመላቀቅ ወደ ሹራብ ስራ እንዲሁም ልብስ ስፌት እየተመለሱም ነው ተብሏል። በለንደን ተቀማጭነቱን ያደረገ እንደ መደብርም የልብስ ስፌት ቁሳቁሶች ከባለፈው አመት ጋር ሲወዳደር በ380 በመቶ ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን እንዲሁም የእጅ ስራ መሳሪያዎች በ228 በመቶ ጭማሪም አሳይተዋል ተብሏል። መፃህፍት በአሁኑ ሰዓት ብዙዎች ከስራ ውጭ ቤታቸው ተቀምጠው ጊዜ በተትረፈረበት ሰዓት ወቅት መፃህፍትን በማንበብ ማሳለፍ አንዱ መንገድ ሆኗል። በተለይም የተለያዩ ሳይንሳዊ ልብወለድ ስራዎች በተለይም ስለ ወርርሽኝ የተፃፉት ተፈላጊነታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። • ስለኮሮናቫይረስ እስካሁን ያላወቅናቸው ዘጠኝ ነገሮች ከአማዞን እንግሊዝ የተገኘን መረጃ ብናይ በዚህ ሳምንት በሽያጭ ደረጃ ሁለተኛ የሆነውን ብናይ 'The Eyes of Darkness' የተባለው መፅሀፍ ነው። ደራሲው ዲን ኩንትዝ ሲሆን የተፃፈበት ወቅትም እንደ ጎርጎሳውያኑ 1981 ነው። ውሃን- 400 ስለተባለ ቫይረስ የሚተርከው ይህ መፅሀፍ አሁን ስላለው ኮሮና ቫይረስ ትንቢት ነውም ተብሏል። ሌላኛው በከፍተኛ ሁኔታ እየተሸጠ ያለው መፅሀፍ በታዋቂው ፈረንሳያዊ ደራሲ አልበርት ካሙዝ የተፃፈው 'The Plague' የተሰኘው ነው። የእንግሊዙ አሳታሚ ፔንግዩን እንደሚለው በየካቲት መጨረሻ ሳምንት ላይ የነበረው ሽያጭ በ150 ፐርሰንት የጨመረ ሲሆን፤ እንደገና ወደማተምም ስራ ተገብቷል። መፅሀፉ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቸበቸበ ያለው በፈረንሳይና በጣልያን ነው። የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ከተለያዩ ትልልቅ መደብሮች (ሱፐር ማርኬቶች) የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው 1.2 ቢሊዮን ዶላር ግምት የሚያወጣ የምግብ ክምችት በየሰው ቤት ይገኛል። ይሄ ሁሉ ግን የት ይሄዳል? ማስቀመጫ ሊኖረው ይገባል። በዚህም ምክንያት የተለያዩ መጠን ያላቸው ፍሪጆችም ሆነ ማቀዝቀዣዎችን በተለያዩ ድረገፆች እየተፈለጉ በመሸመት ላይ ናቸው። ፍሪጆች ብቻ አይደሉም ላፕቶፖችም ተፈላጊ ከሆኑት ቁሳቁሶች መካከል ሲሆን በተጨማሪ የቢሮ ቁሳቁሶችም እንዲሁ። በቤታቸው ሆነው የሚሰሩ ሰዎች ሶፋ ላይ ተንሰራፍተው መስራት ስለማይመች የቢሮ እቃዎቻቸውን እያስመጡ ነው። • በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች ዲክሰንስ ካርፎን የተባለው ድርጅት እንዳሳወቀው ቤት ውስጥ ሆነው ለመስራት የሚያመቹ ላፕቶፖች፣ ማተሚያዎች እንዲሁም ለቤት መዝናኛ የሚሆኑ ቴሌቪዥኖች የተለያዩ የመጫዎቻ አይነቶችና እንዲሁም ማቀዝቀዣዎች፣ የማእድ ቤት ቁሳቁሶች በ23ፐርሰንት ጭማሪ አሳይቷል። ቡና የኮሮና ቫይረስ መዛመትን ተከትሎ ባሳየው የፍላጎት ማሻቀብ ምክንያት ሬቭ ኮፊ ተጨማሪ ሰራተኞችን ለመቅጠር ተገዷል። "አስራ አንድ ሰራተኞች ብቻ ነበሩን፤ ያለው ፍላጎት በእጥፍ በመጨመሩ ምክንያት አምስት ሰራተኞች አስፈልገውናል" በማለት ቪኪ ሆጅ የድርጅቱ ኃላፊ ተናግራለች። "ከዚህ ቀደም ብዙዎች ቡናችንን ይገዙት የነበረው ለቢሮ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ለቤታቸው ነው" በማለት ቪኪ ገልፃለች። "ምናልባት ለምሳሌ አንድ ሰው ቡና ከቢሮ ቢያዝ አስር ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው ሆነው ያዛሉ" ትላለች ምንም እንኳን አንዳንድ የንግዱ ዘርፎች ጥሩ እየሰሩ ቢሆንም ቀውሱ እስካልተፈታ ድረስ ነገሮች በዚህ አይቀጥሉም። የተለያዩ ስፖርታዊ ቁሳቁሶችን የሚሸጠው አንዲ ተጨማሪ የጠረጴዛ ቴኒሶችን ትእዛዝ እንዳይቀበል ያደረገው ምክንያት በፈረንሳይ፣ በስፔንና ጣልያን ያሉ ፋብሪካዎች በመዘጋታቸው ነው። በዚህ ሳምንት መጨረሻም ቤት ለመቆየት ሃሳብ ያለው አንዲ አርባ ሰራተኞችን ያስተዳድራል። አርባ ሰራተኞቹን እንዲሁ ዝም ብሎ ከመበተን መንግሥት ደመወዛቸውን እንዲከፍላቸው የመጠየቅ ሃሳብ አለው። ቪኪም በስጋት ላይ ናት ያላቸው ቢዝነስ ጥቃቅንና አነስተኛ ከሚባሉት አንዱ ከመሆኑ አንፃር በቅርቡ ሊዘጋ ይችላልም ትላለች።
news-53675953
https://www.bbc.com/amharic/news-53675953
የአሜሪካ ምርጫ፡ ባይደን ወይስ ትራምፕ? ቅድመ ምርጫውን ማን እየመራ ነው?
ከሰዓታት በኋላሬ፤ አሜሪካውያን ቀጣይ መሪያቸውን ይለያሉ።
ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣናቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ? ወይስ ይቀጥላሉ? የሚለው የሚለይበት ቀን። ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው ከዴሞክራቱ ጆ ባይደን ጋር አንገት ለአንገት የተናነቁት ፕሬዝደንት ትራምፕ ቁርጣቸውን የሚያውቁት ከሰዓታት በኋላ ነው። ባይደን ከ1970ዎቹ ጀምሮ የአሜሪካን ፖለቲካ ቅርጥፍ አድርገው የበሉ ሰው ናቸው። ከትራምፕ አስተዳደር በፊት የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። ማን ይረታ ይሆን? ጥቅምት 24 ያገናኘን። ነገር ግን የአሜሪካ የምርጫ ትንቅንቅ የምርጫ ዕለት ብቻ የሚታይ አይደለም። የቅድመ ምርጫ ምርጫም አለው። ድምፅ ሰብሳቢ ድርጅቶች የትኛውን ዕጩ ነው የምትመርጡት እያሉ ከአሜሪካውያን የሚሰበስቡትን ድምፅ ይፋ የሚያደርጉበት ነው ቅድመ ምርጫ ማለት። እና በዚህ ቅድመ ምርጫ ማን እየመራ ነው? ትራምፕ ወይስ ባይደን? በአጠቃላይ የሕዝብ አስተያየት ምዘና ቀዳሚው ማነው? ዴሞክራቶች ባይደን 52% ሪፐብሊካኖች ትራምፕ 44% ጠቋሚ መስመሮቹ የተናጠል የድምጽ መስጫዎችን አማካይ ውጤት ያሳያሉ የተናጠል የሕዝብ አስተያየት የተናጠል ምርጫን መሰረት በማድረግ የተገኘ አማካይ የሕዝብ አስተያየት አዝማሚያ 30 days until የምርጫ ቀን የቢቢሲ የሕዝብ አስተያየት የምርጫ ምዘና ባለፉት ሰባት ቀናት የተሰጡ ድምጾችን በመመልከት አማካይ አሃዞችን በመያዝ የምርጫ አዝማሚያዎች ያመለክታል። በዋነኛ የፉክክር ግዛቶች የተገኙ አዳዲስ አማካይ ውጤቶች ሙሉውን ለመመልከት እባክዎን ብሮውዘርዎን ያሻሽሉ ምንጭ: US Census አሃዞቹ በመጨረሻ የተሻሻሉት፡ 03/11 የቅድመ ምርጫ ድምፆች የትኛው ዕጩ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው ማሳያ ናቸው። ነገር ግን ምርጫውን አሸናፊ ማነው የሚለውን በትክክል ላይገምቱ ይችላሉ። ለምሳሌ፤ በጎርጎሳውያኑ 2016 ሂላሪ ክሊንተን በቅድመ ምርጫው ትራምፕን አስከንድተው ሲመሯቸው ነበር። ነገር ግን በዋናው ምርጫ መሸነፋቸው አይዘነጋም። ለነገሩ በዋናውም ምርጫ ቢሆን ሂላሪ ክሊንተን ከትራምፕ በሶስት ሚሊዮን የላቀ ድምፅ ማምጣታቸው አይዘነጋም። ቢሆንም አሜሪካ 'ኢሌክቶራል ኮሌጅ' ሥርዓትን ስለምትጠቀም ብዙ ሰው ድምፅ የሰጠው ዕጩ ያሸንፋል ማለት አይደለም። በዘንድሮው ቅድመ ምርጫ ድምፅ ጆ ባይደን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕን እየመሩ ይገኛሉ። በተሰበሰቡት ድምፆች መሠረት ባይደን ከትራምፕ ቢያንስ በ10 ነጥቦች ልቀው ይገኛሉ። ዋነኛ የፉክክር ግዛቶች አሜሪካውያንና ዓለም ከ2016 ምርጫ የተማሩት ነገር ቢኖር ብዙ ድምፅ ማግኘት ማለት ምርጫ ማሸነፍ ማለት አለመሆኑን ነው። በአሜሪካ ምርጫ ለማሸነፍ ወሳኝ የሚባሉ ግዛቶች አሉ። ፕሬዝደንታዊ ዕጩዎች እነዚህን ግዛቶች ለማሸነፍ የሞት ሽረት ትንቅንቅ ያደርጋሉ። የአሜሪካ ግዛቶች በአጠቃላይ 538 ድምፆች ተከፋፍለው ይዘዋል። ነገር ግን እኒህ ድምፆች ለ50ዎቹ ግዛቶች እኩል የተከፋፈሉ አይደሉም። የምርጫ አውድማ የሚባሉት እኒህ ግዛቶች ከሌሎች ግዛቶች የበለጠ ድምፅ አላቸው። እስካሁን ድረስ የተሰበሰቡት ድምፆች እንደሚጠቀሙት ባይደን በሚቺጋን፣ ፔንሲልቫኒያ እና ዊስኮንሲን ግዛቶች የተሻለ ተቀባይነት አላቸው። ትራምፕ ከእነዚህ ግዛቶች በሰበሰቡት ድምፅ ነው በጠባብ ውጤት ያለፈውን ምርጫ መርታት የቻሉት። ጆ ባይደን፣ በእነዚህ ግዛቶች ብቻ ሳይሆን ባለፈው ምርጫ የትራምፕ ናቸው ተብለው በነበሩት ኦሃዮና ቴክሳስ ግዛቶችም የተሻለ ተቀባይነት አግኝተዋል። ኮሮናቫይረስና ትራምፕ ፕሬዝደንት ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና የሰጡት ምላሽ በብዙዎች ዘንድ እንዲተቹ አድርጓቸዋል። ትራምፕ መጋቢት ላይ በወረርሽኙ ምክንያት ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ሲደነግጉ ተቀባይነታቸው ጨምሮ ነበር። 55 በመቶ አሜሪካውያን በወቅቱ ድምፃቸውን ለእሳቸው ሊሰጡ እንደሚችሉ አንድ ድምፅ ሰብሳቢ ድርጅት አሳውቆ ነበር። ነገር ግን በቅርቡ የተሰበሰበ አንድ ድምፅ እንደሚጠቁመው የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ጭምር ትራምፕን ፊት ነስተዋቸዋል። ለዚህም ነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወረርሽኙ ላይ ያላቸውን አቋም እያለሳለሱ ያሉት [ጭምብል መልበስን ጨምሮ] ይላሉ ባለሙያዎች። ቅድመ ምርጫዎች ለባይደን ያደሉ ይምሰሉ እንጂ ምርጫው ሲቃረብ ነገሮች የተለየ ቅርፅ ሊኖራቸው ይችላል። ለዚህም ነው ብዙዎች ቅድም ምርጫውን ተውትና ጥቅምት 24 እንገናኝ የሚሉት።
news-50020788
https://www.bbc.com/amharic/news-50020788
17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ
ቀድሞኝ ዶሃ የከተመው የሥራ ባልደረባዬ አንድ መልዕክት ስልኬ ላይ አኖረልኝ። 'ልብስ ይዘህ እንዳትመጣ' የሚል። መጀመሪያ መልዕክቱ ፈገግ አሰኘኝ። የወዳጄ መልዕክት ቀጭን ትዕዛዝ መሆኑ የገባኝ የዶሃን አየር ፀባይ በተመለከተ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ድረ ገፆች ጎራ ባልኩበት ጊዜ ነው።
ሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንኳን እኔ 'ሦስተኛ ዓለም' ከሚሉት ቀጠና የመጣ ይቅርና አሜሪካውያንና እንግሊዛዊያንን በአግራሞት አፍ ያስከፍታል። እንዴት ያን የሚያክል ህንፃ እንደ ቤተ-መቅደስ በመልካም መዓዛ ይታወዳል? ሀሉም ነገር ተብለጨለጨብኝ። • በቤተ መንግሥት ግቢ የተገነባው አንድነት ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል? • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ ዶሃ የገባሁት ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ ነበር። ቪዛና ሌሎቹ ኮተቶቼን አጠናቅቄ ከአየር መንገድ ስወጣ 2 ሰዓት ገደማ ሆኗል። ልክ ከአየር መንገዱ ስወጣ የተቀበለኝ ጥፊ ነው። አዎ ጥፊ! ወበቁ ይጋረፋል። ያስደነግጣል። "ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነው የመጣኸው?" አንድ በደንቡ የለበሰ ሰው ጠየቀኝ። "አዎ!"። "በል ተከተለኝ" . . . ምን አማራጭ አለኝ. . . በፈገግታ የተሞላው ቃጣሪ [የኳታር ዜጋ] ለአንድ ሕንዳዊ አቀበለኝ። "ጌታዬ፤ ወደ ሆቴል ነው ወደ ስታድዬም?"። ኧረግ 'ጌታዬ'፤ ኧረ ልጅ ዓለም በለኝ ልለው አሰብኩና ከአፌ መለስኩት። የሆቴሌን ስም የነገርኩት ሕንዳዊ ሹፌር ሻንጣዎቼን የመኪናው ሳንዱቅ ውስጥ ጨምሮ ጉዞ ጀመርን። • በበዴሳ ከተማ ታዳጊውን ለመታደግ የሞከሩ 4 ሰዎች የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ ልክ ወደ መኪናዋ ስዘልቅ የተሰማኝ ቅዝቃዜ. . . የሆነ ነገር አንቆኝ ስታገል ቆይቼ በስተመጨረሻ የተገላገልኩ ያክል ተሰማኝ። የዶሃ መለያዋ ምንድነው? ቢሉ ሰው ሰራሽ ማጤዣዋ [ኤሲ] እልዎታለሁ። ከኤርፖርት ወደ ሆቴል የነበረውን ጉዞ በሕንፃዎች መካከል እየተሹለኮለክን አለፍነው። የሕንፃ ጫካ አይቶ፤ 'ቬጋስ ተንቆጥቁጣ' ሲል ያቀነቀነው ዘፋኝ ዶሃን አላያትም ማለት ነው? እያልኩ ወደ ማረፊያዬ ደረስኩ። ኤሲ፣ ኤሲ፣ ኤሲ. . . ኑሮ በዶሃ በኤሲ የተቃኘ ነው። ወደ መኪና ሲገቡ ኤሲ፤ ወደ መገበያያ ሥፍራ ሲገቡ ኤሲ. . . ሌላው ቀርቶ 50 ሺህ ውጦ አላየሁም የሚለው ኻሊፋ ዓለም አቀፍ ስታድዬም ኤሲ ተገጥሞለታል። ለ50 ሺህ ሰው አየር ማቀዝቀዣ! የዶሃ ሰው የምዕራብ እስያዊቷ ሃገር ኳታር የሕዝብ ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ይገመታል። ከዚህ ውስጥ አረብ ወይም ቃጣሪ ተብለው የሚጡት የአገሪቱ ዜጎች 15 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ሲነገር፤ የተቀሩቱ ከሌሎች አገራት የመጡ ዜጎች ናቸው። የሕንድ፣ ኔፓል፣ እና ፊሊፒንስ ዜጎች ኳታርን ሞልተዋታል። በንጉሳዊ አገዛዝ የምትተዳደረው ኳታር በዓለም ሦስተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ያለባት አገር ነች። የዜጎቿ የነብስ ወከፍ ገቢም በዓለም አሉ ከሚባሉት የሚመደብ ነው። ዶሃ ውስጥ ያለ ፓስፖርት ወይም ሕጋዊ ማስረጃ መንቀሳቀስ ቀላል አይደለም። ይህንን ስል በየመንገዱ ፖሊስ እያስቆመ 'ፓስፖርት ወዲህ በል' ይላል ማለቴ አይደለም። ዶሃ የመጀመሪያ ተግባሬ የነበረው ሲም ካርድ ማውጣት ነበር። ወደ አንዱ የቴሌኮም ድርጅት ሄጄ ሲም ካርድ ፈልጌ ነው አመጣጤ ማለት፤ 'ፓስፖርት እባክዎን ጌታዬ'፤ ኧረ ልጅ ዓለም ይበቃል. . .አሁንም በውስጤ። ሰውዬው ፓስፖርቴን ከተቀበለ በኋላ ወደ አነስተኛ ማሽን ሲያስጠጋት ሚስጥሬ ሁሉ ስክሪኑ ላይ ተዘረገፈ። የትውልድ ቀንና ቦታ፤ ለምን ያህል ጊዜ ዶሃ እንደመጣሁ. . . • ስቶርምዚ በካምብሪጅ የጥቁር ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ አድርጓል ተባለ ቀጣይ ተግባሬ ደግሞ ዶላር ወደ ኳታሪ ሪያል መመንዘር። እዚህም ያስተናገደኝ ሰው ፓስፖርቴን ለአንድ ማሽን ቢያቀብል ሙሉ መረጃዬ ተዘረገፈ። አንድ ዶላር በ3 ሪያል ሂሳብ መንዝሬ ሳበቃ የዶሃ መንግሥት እንዴት የዜጎቹን ሚስጥር እንደሚቆጣጠር እየገረመኝ ሹልክ አልኩ። 'ሕጉን ካከበርክ. . .' ዶሃ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች ጥያቄ ይወዳሉ። በተለይ ሕንዶችና እና ኔፓሎች። ጋዜጠኛ እኔ ሳልሆን እነሱ ነበር የሚመስሉት። ታዲያ ጨዋታቸው ደስ ይላል። 'ከየት ነው የመጣኸው?' የሁሉም ጥያቄ ነች። ከዚህ ነው የመጣሁት፣ አመጣጤ ደግሞ ለዚህ ነው. . . እኔም መልሴን አዘጋጅቼ መጠባበቅ ያዝኩ። ከሆቴል ወደ ስታድዬም መሄድ ነበረብኝና 'ኡበሬን' መዥረጥ አድርጌ ታክሲ ብጠራ ፀጋይ ከች። የአገር ሰው መቼም የሃገር ነው ብዬ ተንገብግቤ ነበር ፀጋይ 'ሰላም ነህ ወንድሜ?' ስል እጄን የሰጡት። ፀጋይ አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋው እንደሆነ ቢያሳብቅም አቀላጥፎ ይናገራል። ፀጋይ ኤርትራዊ ነው። ዶሃ ከከተመ በርካታ ዓመታት ሆነውታል። ባለቤቱና ልጆቹ ኑሯቸው አስመራ ነው። በዓመትም ይሁን በሁለት እየተመላለሰ እንደሚጎበኛቸው አጫወተኝ። ታድያ ኑሮ በዶሃ እንዴት ነው?፤ "ይገርምሃል እኔ ዶሃን በደንብ ነው የማውቃት። መቼም ቃጣሪዎች በቁጥር ትንሽ እንደሆኑ ታውቃለህ። ግን ገንዘቡ ያለው በእነርሱ እጅ ነው። እዚህ አገር የማታገኘው ዓይነት የውጭ ዜጋ የለም። ከአፍሪቃ እና እስያ ሃገራት የሚመጡት ተውና ከአሜሪካ እና ከአውሮጳ ሳይቀር እዚህ መጥተው የሚሠሩ ብዙ ናቸው።" • የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው ፀጋይ የማይጠገብ ጨዋታውን እየመገበኝ ስታድየም ደረስን። ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን። ከዚያ ቀን በኋላ ወደ ምፈልገበት ቦታ ሲያደርሰኝ የነበረው ፀጋይ ነበር። ጨዋታው የሚጠገብ አይደለም። ስለ ዶሃ ብዙ አጫወተኝ። አንገቴን እስኪያመኝ ቀና ብዬ የማያቸው መጨረሻ የሌላቸው ሕንፃዎችን ከነስማቸው እየዘረዘረልኝ ጉዞዬን አሰመረው። "እዚያ ጋር ይታይሃል? ፎቶ እና ቪድዬ ማንሳት ክልክል ነው የሚል የተለጠፈበት አጥር?"። ወደ ጠቆመኝ ቦታ እየተመለከትኩ ጭንቅላቴን በአዎንታ ወዘወዝኩ። "የአልጃዚራ ዋና መሥሪያ ቤት ነው። ገና ምኑን አይተህ፤ መጨረሻ የለውም።" እውነትም መጨረሻ የለውም። በዶሃ ቆይታዬ ፖሊስ ያየሁት ስታድየም ዙሪያ ብቻ ነው። ዶሃ ተፈልጎ የማይገኘው ሌላው የትራፊክ አደባባይ ነው፤ አዎ! አደባባይ። ብዙዎቹ መንገዶቹ ማሳለጫቸው መስቀለኛ ነው። በአቅጣጫ ጠቋሚ የትራፊክ መብራቶች ተሞልተዋል። ታዲያ፤ መሽቷል፣ አልያም ትራፊክ የለም በሚል ተልካሻ ምክንያት መብራት መጣስ ጣትን ወደ እሳት እንደመስደድ ነው። አንድ ጋናዊ ሹፌር እንደነገረኝ የትራፊክ መብራት መጣስ እስከ 6000 የቃጣር ሪያል ያስቀጣል። ወደ 59 ሺህ ብር ገደማ ማለት ነው። ተሽከርካሪዎች ጥፋት መፈፀም አለመፈፀማቸውን መርምረው የሚያሳብቁ ካሜራዎች በየቦታው ተተክለዋል። "እያየህ ግባበት ነው" ያለው ፀጋይ ወዶ አይደለም። • ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች ፀጋይም ሆነ ሌሎች ያጋጠሙኝ አሽከርካሪዎች እንዲሁም የዶሃ ነዋሪዎች በአንድ ጉዳይ ይስማማሉ። ዶሃ ለኑሮና ሥራ ምቹ ናት። ዋናው ነገር ሕጉን ማክበር ነው። ሕግ ጥሰው የተገኙ እንደሆነ የፀጥታ ሰዎች ካሉበት መጥተው ነው የሚለቅምዎት ሲሉ ብዙዎች ያስረዱኝ። የሃበሻ ኑሮ በዶሃ ዶሃ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንዳሉ ፀጋይ አጫውቶኛል። እኔም ወዲያ ወዲህ ስቅበዘበዝ ያገኘኋቸው እና ለሰላምታ የተጠመጠምኩባቸው የዶሃ ምድር ይቁጠራቸው። ኳታር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 25 ሺህ ይገመታል። ይህም የጠቅላላው ሕዝብ ቁጥሩን 0.8 በመቶ ድርሻ ይይዛል። በቤት ሠራተኝነት የተሰማሩ፣ አሽከርካሪዎች፣ የጥበቃ ሠራተኞች. . . እንዲሁም ሌሎች የሥራ መስኮች ኢትዮጵያውያን ተሠማርተው ኑሯቸውን የሚገፉባቸው መስኮች ናቸው። ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን 'ፕሮፌሽናል' ተብለው የሚጠሩ የሥራ መስኮችም ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ። እርግጥ ነው የአትሌቲክስ ቡድናቸውን ለመደገፍ ኻሊፋ ስታድየም የተገኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በርካታ ነበር። በባንዲራ ጉዳይ ጎራ ከፍለው ቢቀመጡም። ምን ያህል ኤርትራውያን ኳታርን መጠለያቸው እንዳደረጉ ግን ውል ያለው መረጃ የለም። ፀጋይ፤ ቢበዛ 5 ሺህ ገደማ ብንሆን ነው ሲል አጫውቶኛል። • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች እንደው አንድ ቀን የቡና ጥም ከዶሃ ሙቀት ጋር ተቀላቅሎ ቢያንገላታኝ ስታርባክስ የተሰኘ ቡና መሸጫ ሱቅ ገባሁ። ታዲያ ከፊት ለፊት የተቀበለኝ ኢትዮጵያ የሚል ስም ደረቱ ላይ የለጠፈ የታሸገ ቡና ነው። ጀበናችንም ከረጢቱ ላይ ተስላ ትታየኛለች። ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ኮለምቢያ አለች። በገዛ ቡናችን እንደባይተዋር ተሰልፌ ተራዬ ሲደርስ ሸምቼ ወንበሬን ስቤ ተቀመጥኩ። አንድ 'ሱፐርማርኬት' ገብቼ ቡናዎች ከተደረደሩበት ሥፋራ ባቀናም የኢትዮጵያ ስም የተለጠፈበት አንድ እሽግ አይቻለሁ። የሚደንቀው ነገር የኢትዮጵያን ስም እንደ ታርጋ የሚጠቀሙት እኒህ እሽግ ቡናዎች ዋጋቸው ከሌሎቹ ወደድ ያለ መሆኑ ነው። ኳታር 2022 ምናልባት እኔ ነገሮች ተመቻችተውልኝ ስለጎበኘኋት ይሆን? ብቻ ዶሃ አትጠገብም። ጊዜ ቢያጥረኝ እንጂ ከእግር እስከ ራሷ ብጎበኛት ደስታዬ ወደር አልነበረውም። በቻልኩት መጠን ግን በርካታ ሥፍራዎችን ሲቻል ወደ ውስጥ ዘልቄ ሳይሆን ሲቀር ከቅርብ ርቀት ማየት ችያለሁ። የዶሃ ቅርሶች አብዛኛዎች ሰው ሰራሽ ናቸው። ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች፣ የሕንድ ውቅያኖስ ላይ የተንሳፈፉ ሆቴሎች፣ ሌላው ቀርቶ ሰው ሰራሽ ደሴቶችና ጫካዎች የከበቧት ናት፤ ዶሃ። • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ ቃጣሪዎች ዶሃ የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ ማሳያዎች ብዙዎች ናቸው። ከብዙ ሃገራት ተቃውሞ ቢገጥመውም የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማህበራት ፌዴሬሽን የዘንድሮውን ውድድር ከማምጣት አልተቆጠበም። በገንዘብ ገዙት እንጂ እንዴት በዚህ በረሃ ላይ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል እያሉ ሃሜት እና ምሬት ሲያሰሙ ያደመጥኳቸው አሉ። ነገር ግን ኳታር ዝግጅቱን በድል ጀምራ በድል አጠናቃዋለች። የመጀመሪያዎቹ ቀናት የተመልካች ድርቅ መቶት የነበረው ግዙፉ ስታድየማቸው እያደር ደምቆላቸዋል። አሁን ሁሉም 2022ን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው። የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን። 'ገንዘብ ካለ. . . 'የሚለውን አባባል እውን ያደረጉት ቃጣሪዎች የሚሳናቸው ያለ አይመስልም።
46860386
https://www.bbc.com/amharic/46860386
በምዕራብ ኦሮሚያ ምን ተከሰተ?
ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ፤ ማለትም ጥር 4 እና 5፣ 2011 ዓ. ም. በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ባንኮች እንደተዘረፉና ንብረታቸው እንደወደመ እንዲሁም የወረዳ ጽህፈት ቤቶች በእሳት እንደጋዩ ተነገረ።
በሆሮ ጉዱሩ ዞን፤ ሆሮ ቡሉቂ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ሰባት መሥሪያ ቤቶችን የያዘ የወረዳ ጽህፈት ቤት መቃጠሉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ተረፈ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ደሳለኝ የታጠቁ ኃይሎች የሆሮ ቡሉቂ ወረዳ ዋና ከተማ ወደሆነችው ሰቀላ ከተማ በመግባት መሥሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውንና አዋሽ ባንክን መዝረፋቸውን ይናገራሉ። ''እነዚህ የታጠቁ ቡድኖች የአዋሽ ባንክ ሥራ አስኪያጅን ቤቱ ድረስ ሄደው በማምጣት ባንኩን አስከፈቱት።'' የሚሉት አቶ ደሳለኝ፤ ባንኩ ቢከፈትም የካዝናው ቁልፍ የባንኩ ሥራ አስኪያጅ እጅ ስላልነበረ ካዝናውን መክፈት ባለመቻላቸው ያገኙትን ገንዘብ ሰብስበው የባንኩን ሥራ አስኪያጅ አፍነው መሄዳቸውን ያስረዳሉ። በተጨማሪም ከባንኩ ጥበቃዎች ሁለት ክላሺንኮቭ መዝረፋቸውን ይናገራሉ። • የአቢሲኒያ ባንክ የዝርፊያ ድራማ • የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ሰማኒያ ሚሊዮን ብር እንዴት ተዘረፈ? የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምዕራብ ዲስትሪክት ተጠባባቂ ሀላፊ አቶ ግርማ ጪብሳ፤ የባንክ ሠራተኞች በተለመደው ሁኔታ ደንበኞችን እያስተናገዱ ሳሉ ከረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ ታጣቂዎች ወደ ባንኩ እንደገቡ ይናገራሉ። በአጠቃላይ በምዕራብ ኦሮሚያ እና በቄለም ወለጋ በሚገኙ አሥር የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አቶ ግርማ ይናገራሉ። ሀላፊው፤ አምስት ቅርንጫፎች መዘረፋቸውን እንዲሁም በተቀሩት አምስት ቅርንጫፎች ውስጥ የሚገኙ መገልገያ ቁሳ ቁሶች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ኤቲኤም (ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች) እና ኮምፒዩተሮች መሰባበራቸውንም ገልጸዋል። ገንዘብ ከተዘረፈባቸው አምስት ቅርንጫፎች መካከል በሁለቱ አራት ሠራተኞች ታግተው እንደነበረ እና ሁለቱ እንደተለቀቁ አቶ ግርማ ጨምረው ተናግረዋል። "የተቀሩት ሁለት ሠራተኞች ስላሉበት ሁኔታ ግን ማወቅ አልቻልንም" ብለዋል። በአካባቢው የደህንነት ስጋት ስላለ የደረሰውን ጉዳት ወደ ቅርንጫፎቹ ሄደን ለማጣራት አልቻልንም። መረጃም ተሟልቶ አልቀረበም የሚሉት አቶ ግርማ፤ እስካሁን በባንኩ እና በሠራተኞቹ ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን አለመታወቁን ይናገራሉ። "ጥቃቱን ያደረሱት የታጠቁ ቡድኖች መሆናቸውን ሰምተናል። ይሁን እንጂ ዘረፋውን የፈጸመው አካል ይሄ ነው ብዬ መናገር አልችልም" በማለት አክለዋል። በተመሳሳይ በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ በርካታ ቅርንጫፎች እንዳሉት የሚያናገሩት የባንኩ የገበያ ጥናት እና የንግድ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ በለጠ ዋቅቤካ፤ በባንኮቹ ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ ጠቅሰው፤ እስካሁን ምን ያህል የባንኩ ቅርንጫፎች እንደተዘረፉና ጥቃት እንደደረሰባቸው የጠራ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል። የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መለያዎች የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ገመቺስ ተመስገን፤ ቅዳሜ ዕለት በዞኑ በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ውስጥ በመንግሥት እና በግል ባንኮች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ዘረፋ እንደተፈጸመ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ ኅብረት ባንክ እና አዋሽ ባንክ እንደተዘረፉ ገልጸዋል። አቶ ገመቺስ እንደሚሉት፤ ዘረፋዎቹ የተፈጸሙት የሀገር መከላከያ ሠራዊት በሌለባቸው ስፍራዎች ነው። ከባንክ ዘረፋው ጋር ተያይዞ ታፍነው የተወሰዱ የባንክ ሠራተኞች እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ገመቺስ፤ ከመካከላቸው የተለቀቁ እንዳሉና፤ እስካሁን የት እንደደረሱ የማይታወቁ ሠራተኞችን እያፈላለጉ መሆኑን አስረድተዋል። ይህን ጥቃት እየሰነዘረ ያለው የኦነግ ታጣቂ ነው የሚሉት አቶ ገመቺስ ''ከኦነግ ውጪ በእዚህ አካባቢ የታጠቀ ኃይል የለም'' ሲሉ ተናግረዋል። የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የኦፕሬሽን ኃላፊ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ባለፈነው አርብ በሰጡት መግለጫ፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ላለው የጸጥታ መደፍረስ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን (ኦነግ) ተጠያቂ ያደርጋሉ። ምክትል ኤታማዦር ሹሙ፤ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦነግ ጦር ላይ መከላከያ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ተናግረው ነበር። • ኦዲፒ፡ ኦነግ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፤ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ በኦሮሚያ በተለያዩ ስፍራዎች ይዘርፋል፣ አዲስ የኦነግ ጦር ይመለምላል፣ የክልል የመንግሥት ተቋሞችን ሥራ ያስቆማል፣ እንዲሁም የአካባቢውን አመራሮችን ይገድላል ሲሉ ተናግረዋል። • በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል? የኦነግ ምላሽ አቶ ሚካኤል ቦረና የኦነግ ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸው። አቶ ሚካኤል ኦነግ ለበርካታ ዓመታት የኦሮሞን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት ሲታገል የቆየ ድርጅት ነው። ኦነግ በምንም አይነት ሁኔታ እንዲህ ያለ ተግባር አይፈጽምም ይላሉ። አቶ ሚካኤል የተፈጸመው ተግባር ሆነ ተብሎ የኦነግን ስም ለማጥፍት ነው ያሉ ሲሆን፤ ''መንግሥት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ በርካታ ጦሩን አሰማርቷል፤ በየአካባቢው እየተካሄደ ስላለው ነገር ሙሉ መረጃ ለማግኘት ቸግሮናል'' ይላሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የኦነግ የምዕራብ ዕዝ የጦር አዛዥ ኩምሳ ዲሪባ ወይም በቅጽል ስሙ መሮ፤ የክልሉ መንግሥት ኦነግ ላይ ያቀረበውን ወቀሳ በማስመልከት ለቢቢሲ ይህን ብሎ ነበር። ''. . . የተኩስ አቁም ስምምነቱን ከደረስን በኋላ ኦነግ በራሱ ተነሳሽነት መንግሥት ላይ ተኩስ ከፍቶ አያውቅም፤ አጸፋዊ እርምጃ ካልወሰድን በቀር። ይህ ሁሉ ክስ ግን ሃሰተኛ ነው። መንግሥት ይህን ክስ የሚያቀርበው በዚህ አካባቢ ላይ ጦሩን በማዝመት ጦርነት ለመክፈት ቅድመ ዝግጅት ሲያከናውን ነው እንጂ ኦነግ ያፈረሰው የመንግሥት ሥርዓት የለም፤ የዘረፈውም የጦር መሳሪያ የለም።'' የአየር ጥቃት ዕሁድ ጠዋት የሀገር መከላከያ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የኦነግ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝሯል የሚል መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር። የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ገመቺስ ተመስገን በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ጠይቀን፤ ''ይህ መረጃ እስካሁን አልደረሰኝም። በምዕራብ ኦሮሚያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይንቀሳቀሳል። በተለያዩ አጋጣሚዎችም ከኦነግ ሠራዊት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል። ዕሁድ ዕለት የአየር ጥቃት ተሰንዝሯል ወይም አልተሰነዘረም ማለት አልችልም'' ብለዋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የአየር ጥቃት የተፈጸመው በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች አዋሳኝ ድንበር ላይ መሆኑ በስፋት ተነግሯል። ይሁን እንጂ ያነጋገርናቸው የአከባቢው ነዋሪዎች "የአየር ጥቃት ተፈጽሟል ሲባል ሰማን እንጂ ያየነው ነገር የለም" ይላሉ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፤ የአየር ጥቃት ሲፈጸም ባይመለከቱም በአከባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮች በብዛት ስለሚመላለሱ ከፍተኛ ስጋት ገብቷቸዋል። የኦነግ ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ቦረና ግን መንግሥት በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች ውስጥ የአየር ጥቃት እየሰነዘረ ነው ሕዝቡም እየተጎዳ ነው ብለዋል። አቶ ሚካኤል እንደሚናገሩት፤ የኦነግ ጦር የነበረበትን ስፍራ ሳይለቅ እራስን የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ነው። ከፌደራል መንግሥት እንዲሁም ከመከላከያ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
news-53328681
https://www.bbc.com/amharic/news-53328681
“ከቀን ሥራ ጀምሬ ለ30 ዓመታት ያፈራሁት ንብረት ነው የወደመብኝ” የባቱ ነዋሪ
የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ሁከቶች ተከስተው ነበር። በዚህም የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል። አሁን መጠኑ በውል ያልታወቁ ንብረትም ወድሟል።
አለመረጋጋቱ ክፉኛ ካናወጣቸው የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካከል ከአዲስ አበባ 165 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቃ የምትገኘው የባቱ (ዝዋይ) ከተማ አንዷ ናት። በዚህም በከተማዋ ታዋቂ ከሚባሉት ተቋማት መካከል የሚገኙት የአባይ ሆቴል ባለቤት አቶ ሰለሞን ማሞ እና በድርጅቴ ስም ጥሩኝ ያሉት የቫሊ ላንድ ሆቴል ባለቤት ለአስርተ ዓመታት ያፈሩት ንብረታቸው በግፍ እንደወደመባቸው ይናገራሉ። "ሁከቱ ሲነሳ የድምፃዊውን መሞት እንኳን አልሰማንም" አቶ ሰለሞን ማሞ ይባላሉ። ተወልደው ያደጉት በዝዋይ ከተማ ሲሆን ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት እናታቸው የተወለዱትም የኖሩትም እዚያው ከተማ ውስጥ ነው። ከዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ፤ የቀን ሥራ ከመስራት ተነስተው በርካታ ንብረቶችን እንዳፈሩ እና 6 ሱቆች፣ ፎቶ ቤት፣ ሆቴል (አባይ ሆቴል)፣ መጋዘን፣ ባለቤታቸው የሚሰሩበት ልብስ ቤት እንደነበራቸው ይናገራሉ። አቶ ሰለሞን እንደሚሉት የዚያን ዕለት ቀን ላይ ሥራ በዝቶባቸው ስለዋሉ፤ ወደ ቤት የገቡት የንግድ ድርጅቶቻቸውን ሂሳብ እንኳን ሳይሰሩ ነበር። ምንም የሰሙት ነገር አልነበረም። ከዚያ ግን ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ገደማ ስልካቸው ጠራ። በዚያ ውድቅት ሌሊት ስልክ ላለማንሳት ቢወስኑም ከእንቅልፋቸው መነሳታቸው አልቀረም። በዚህ ወቅት ጩኸት ሰሙ። ጩኸቱ ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ በር ከፍተው ሲወጡ "ከፍተኛ የጩኸት ድምፅ ይሰማል ነበር" ይላሉ። እንዳሉን ከሆነ የሆነ አደጋ የተፈጠረ አሊያም ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ እንደተከሰተ ነበር የገመቱት። ሁኔታው ምን እንደሆነ ስላልተገለጠላቸው ተመልሰው ወደ ቤት በመግባት ወደ ተደወለላቸው ስልክ መልሰው ደወሉ። ይህን ጊዜ ነበር የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል የሰሙት። የሰሙት መርዶ ድንጋጤና ሃዘን ቢፈጥርባቸውም፤ እየጨመረ የመጣው ጩኸትም ቀልባቸውን በተነው። "ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር መደዋወል ጀመርን" ይላሉ። ሆቴሎች፣ መኪናዎች እየተቃጠሉ እንደሆነ መረጃ ደረሳቸው። የስልክ መረጃ ልውውጡም ቀጠለ። ብዙም ሳይቆይ ከጎናቸው ያለ ሆቴልና የሆቴሉ ባለቤት መኖሪያ ቤት ተቃጠለ። ባለቤቶቹ እርዳታ ቢማፀኑንም፤ በወቅቱ ሊደርስላቸው የቻለ አካል እንዳልነበር አቶ ሰለሞን ይገልፃሉ። ሁኔታው እየከፋ መጣ በየቦታው የቃጠሎ ዜና መጉረፍ ጀመረ። እርሳቸውም ሊታደጉኝ ይችላሉ ያሏቸው ሰዎች ጋር ደጋግመው ቢደውሉም፤ የሁሉም ስልክ ዝግ ነበር። በዚህ ሁኔታ ቀጥሎ ከማለዳው 12 ሰዓት ሆነ። በዚህ ጊዜ እርሳቸው ሆቴል የሚያድሩ ሠራተኞች ጋር ደውለው "ውጡና እራሳችሁን አድኑ" ሲሉ መልዕክት አስተላለፉ። ትንሽ ቆይቶም በችግር ላሳደገቻቸው እናታቸው መታሰቢያነት በእናታቸው ስም 'አባይ' ሲሉ የሰየሙት ሆቴላቸው መቃጠል ጀመረ። "በዚህ ጊዜ የሆቴሉ ሠራተኞችና ጎረቤቶች ጉዳቱ እንዳይከፋ ሲሊንደሮችን ለማውጣት ሲሞክሩ እነርሱም ላይ ድብደባ ደረሰባቸው" ይላሉ። ታዲያ ይህን ያዩ ጎረቤቶቻቸው ከባለቤታቸውና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳስወጧቸውና ሕይወታቸውን እንደታደጉላቸው ይናገራሉ። መኖሪያ ቤታቸውንም እንደተሰባበረ ጠቅሰው፤ በግምት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት እንደወደመባቸው ይገልፃሉ። የንግድ ድርጅቴ ታዋቂ ስለሆነ በድርጅቴ ስም ልጠራ ያሉት ሌላኛው ተጎጂ ደግሞ የቫሊ ላንድ ሆቴል ባለቤት ናቸው። እርሳቸውም እንደ አቶ ሰለሞን ሁከቱ ሲፈጠር እርሳቸውን ጨምሮ ከ6 የቤተሰብ አባላቸው ጋር ቤት ውስጥ ነበሩ። ከሌሊት ሰባት ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ ድምፅ እየተሰማ ነበር ይላሉ። ሁከቱ ሲነሳ ግን የድምፃዊውን መሞት እንኳን እንዳልሰሙ ይናገራሉ። በባቱ ከተማ ተወልደው እንዳደጉ የሚናገሩት ግለሰቡ፤ "ከቀን ሥራ፤ ከልዋጭ ልዋጭ፤ ከቆራሌው ጀምሬ ነው ይህንን ከተማ ሳለማ የኖርኩት" ይላሉ - በ30 ዓመታት ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረትም እንደወደመባቸው በምሬት ይገልጻሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት ቫሊ ላንድ ሆቴሎች ተቃጥለውባቸዋል። ቁጥር አንዱ ከሁለት ዓመት በፊት የተከፈተ ሲሆን 51 የመኝታ ክፍሎች ነበሩት፤ ቁጥር ሁለቱ ደግሞ አዲስ ሊያስመርቁ ያዘጋጁት 50 ክፍሎችን የያዘ ሆቴል ነበር። ከዚህም ባሻገር መጋዘን ሙሉ እቃ፣ ቢራ የጫነ አይሱዙ መኪና እና መኖሪያ ቤታቸው እንደተቃጠለባቸው በመግለፅ "አንድም ንብረት የለኝም፤ ከሰው ጋር ተጠግቼ ነው ያለሁት" ሲሉ በደረሰው ጥፋት በጣም ማዘናቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። "በወረርሽኙ ለችግር የተጋለጡትን ለመርዳት የተገዛው እህልም ተቃጥሏል" ባለሃብቶቹ ከኅብረተሰቡ ጋር ጥብቅ ትስስር እንዳላቸውና ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት የከፋ ችግር አጋጥሟቸው እንደማያውቅ ይናገራሉ። አቶ ሰለሞን እንደሚሉት በአገሪቷ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎችን ለመደገፍ በተዋጣው 500 ሺህ ብር የተገዛ እህል ጭምር ነው የተቃጠለው ይላሉ። ንብረታቸውን ሁሉ ያጡት አቶ ሰለሞን ቤተሰባቸው ከዘመድ ጋር እንደተጠጉ እንዲሁም ከእርሳቸው ጋር ይሰሩ የነበሩ 45 ሠራተኞቻቸውም መበተናቸውን አስረድተዋል። "የልማት አምባሳደር ተብዬ የተሸለምኩበት ከተማ ናት፤ ይህንን ጥቃት ምን እንዳመጣብኝ አላውቅም" የሚሉት የቫሊ ላንድ ሆቴል ባለቤት በበኩላቸው፤ ከ170 በላይ ሠራተኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸውም እንደተበተኑ በመግለፅ "ለስንት ሰው የምተርፍ ሰው፤ ዛሬ ራሴንም ማስጠለል አቅቶኝ ነው ያለሁት" ሲሉ በተሰበረ ስሜት ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ከስንዴ ውስጥ ያለ እንክርዳድ" ጥቃቱ ሲፈፀም ተጎጂዎችን ለመታደግ ሲጥሩ የነበሩ የአካባቢው ነዋሪዎችን መኖራቸውን የሚጠቅሱት የቫሊ ላንድ ሆቴል ባለቤት፤ "ከስንዴ ውስጥ እንክርዳድ ይኖራል" በማለት ጥቃቱን ተከትሎ ድርጊቱን የአንድ ማኅበረሰብን ድርጊት ማድረግ እንደማይገባ ይገልፃሉ። በወቅቱ ከቤታቸው ሊወጡ የቻሉትም በአካባቢው ነዋሪዎች እርዳታ መሆኑን ይናገራሉ። አክለውም "ጥቃት አድራሾቹ የድምፃዊውን ሞት እንደ አጋጣሚ ተጠቀሙበት እንጂ፤ ድርጊቱ ከዚህ በፊት የተጠናና የተቀነባበረ ይመስላል" ሲሉም ሁኔታውን ይገልጹታል። "አዕምሮው የተበላሸ ትውልድ አለ" የሚሉት አቶ ሰለሞንም፤ የተመረጡና የሚሰሩ ሰዎች ኢላማ እንደተደረጉ እንዲሁም ጥቃቱን የፈፀሙት ቡድኖች በጣም የተደራጁ እንደሚመስሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቃቱን ለመከላከልና ሰዎችን ለመታደግ ሲረባረቡ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩ የሚጠቅሱት አቶ ሰለሞን፤ ምንም እንኳን ዕድሜ ልክ ለፍተው ያፈሩት ንብረት ቢወድምባቸውም ጎረቤቶቻቸው ጥፋቱን ለማስቆም ላደረጉት ጥረት ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ከመግለጽ አልተቆጠቡም። አቶ ሰለሞን አክለውም በዕለቱ ጥቃቱ ከጀመረበት ከሌሊቱ 7 ሰዓት አንስቶ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ያዩት የከተማው የፀጥታ አካል እንደሌለና ምሽት 12 ሰዓት ላይ መከላከያ ከገባ በኋላ በተወሰነ መልኩ ውድመቱ ጋብ ማለቱን ያስታውሳሉ። የቫሊ ላንድ ባለቤት ግን ወዳጆቻቸው የፀጥታ አካላትን ጠርተው በእነርሱ እርዳታ እርሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከሞት እንዳተረፉላቸው ያስረዳሉ። በከተማው ብዙ ሆቴሎችና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የጠቀሱት ባለሃብቱ፤ "ከተማዋ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት ናት፤ ተመርጦ ነው ጉዳት የደረሰብኝ ለማለት እቸገራለሁ፤ የማውቀው ንብረቴ ብቻ እንደወደመ ነው" ብለዋል። የአሁኗ ዝዋይ ከተማ በባለሃብቶቹ ዕይታ አቶ ሰለሞን በከተማዋ ላይ በአንድ ቀን ብቻ የተፈጸመው ጥቃት ባቱን 20 እና 30 ዓመታት ወደ ኋላ መልሷታል ብለው ያምናሉ።የቫሊ ላንድ ባለቤትም ከዚህ የተለየ ሃሳብ የላቸውም። "ከተማዋ በ20 ዓመታት እንኳን የምታንሰራራ አይመስልም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሁለቱም የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት በአካባቢው በተፈጠረው ስጋት በጥቃቱ የተጎዳውም ሆነ ያልተጎዳው ከተማዋን ጥሎ እየወጣ እንደሆነም ይናገራሉ። "እንዲህ ዓይነት ነገር ካለ ሰውስ እንዴት ነው ወደ ግንባታ ፊቱን የሚያዞረው? ሰው እንዴት የአገር ሃብት ያወድማል? ነፍሴን ይዤ የወጣሁ ሰው፤ እንዴት ነው ወደ ልማት መመለስ የምችለው?" ሲሉም ይጠይቃሉ። ባለሃብቶቹ ይህንን ጉዳት ያደረሱት ሰዎች ለሕግ እንዲቀርቡ፤ መንግሥትም አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል። በከተማዋ ውስጥ ሰኞ ሰኔ 22 ከሌሊቱ ጀምሮ ማክሰኞ እስከ አመሻሹ ድረስ በተፈጸመው ጥቃትና የንበረት ውድመት በባቱ ከተማ ላይ የደረሰው ውድመት ጥቂት የሚባል አይደለም። ኃይሌ ሪዞርት፣ ቤተልሔም ሆቴል እንዲሁም ሌሎች በከተማዋ የሚገኙ በርካታ ትላልቅ ሆቴሎችና የንግድ ተቋማት መውደማቸውንም አቶ ሰለሞንና የቫሊላንድ ባለቤት ለቢቢሲ ገልጸዋል። እስካሁን የደረሰውን ውድመትና ጉዳት ለማወቅ የከተማዋ ባለስልጣናት በየቦታው እየሄዱ በመመዝገብ ላይ ሲሆኑ፤ ቢቢሲም ስለደረሰው ውድመት ከኃላፊዎቹ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
news-53763558
https://www.bbc.com/amharic/news-53763558
ልዩ ኃይል፡ የአገር አንድነት ስጋት ወይስ የሕዝብ ደኅንነት ዋስትና?
በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች የራሳቸውን የልዩ ኃይል ፖሊስ ማደራጀት ከጀመሩ ዓመታት ቢሆናቸውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መደበኛ ሠራዊት በሚመስል መልኩ እየሰለጠኑና እየተደራጁ መሆናቸው ይነገራል።
የኦሮሚያ እና የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ከዚህ አንጻር በርካቶች፤ ክልሎች የራሳቸውን ልዩ ኃይል አደራጅተውና አስታጥቀው ማሰማራታቸው ለአገር ደኅንነት አደጋ ነው፤ የእነዚህ ኃይሎች አደረጃጀትም ሕጋዊ መሠረት የሌለው ነው በማለት ይከራከራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የልዩ ኃይል ፖሊሶችን ጥቅም ከግምት በማስገባት የአንድን ክልል ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ ከፖሊስ ባሻገር ይህ ሠራዊት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበርክት እንደሚችል የሚሞግቱ አሉ። በኢትዮጵያ የልዩ ፖሊስ አመሰራረት ምን ይመስላል? የአምነስቲ የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሐ ተክሌ፤ በኢትዮጵያ የተመሰረተው ልዩ ኃይል በ1998 ዓ.ም የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ መሆኑን ይናገራሉ። "ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ጋር ከነበረውን የሽምቅ ውጊያ ጋር በተያያዘ ነበር ይህ ልዩ ኃይል የተደራጀው። ከዚያም በኋላ በኦሮሚያና በአማራ እንዲሁም በሌሎች ክልሎችም ልምዱ ተስፋፍቶ ቀጥሏል” ይላሉ። የሶማሌ ክልል ተወላጅና ሁለት ጊዜ የሕዝብ ተወካዮች የምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ጀማል ድሪ ሃሊስ ከዚህ ቀደም የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አመሰራረትን በተመለከተ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በክልሉ የነበረውን የአማጺያን እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ነበር። ''በአካባቢው ይንቀሳቀስ የነበረውን የኦብነግ ኃይልን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለመደምሰስ ብዙ ጥረት አድርጎ ውጤታማ መሆን አልቻለም'' የሚሉት አቶ ጀማል፤ በወቅቱ በክልሉ የተሰማራው የአገር መከላከያ ሠራዊት የአካባቢውን ቋንቋና ባህል ስለማያውቅ የአማጺያኑን ከሲቪሉ ሕዝብ ለመለየት አልቻለም ነበር ይላሉ። በ2007 (እአአ) ላይ የክልሉን ፖለቲካዊ ምህዳር የቀየር ሁኔታ እንደተከሰተ የሚናገሩት አቲ ጀማል "ኦብነግ ነዳጅ ፍለጋ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ከ70 በላይ ቻይናውያንና በርካታ ኢትዮጵያውያንን ገደለ። በዚህም የፌደራሉ መንግሥት ኦብነግ ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ተነሳ” ይላሉ። ለዚህም ሁነኛ አማራጭ የነበረው በሶማሌ ክልል ችግር ሆነው የቆዩትን ሥራ አጥ ወጣቶችን በማደራጀት ሰልጠና ሰጥቶና አስታጥቆ ኦብነግ ላይ ማዝመትና የአማጺውን እንቅስቃሴ በእነዚህ ወጣቶች መቆጣጠር እንደነበረ አቶ ጀማል አስታውሰዋል። የክልሉ መንግሥት ለ30ኛ ዙር የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላትን ባስመረቀበት ወቅት የልዩ ኃይል አመሰራረት ሕጋዊ መሠረት ከልዩ ፖሊስ አመሰራረት ጋር አብሮ ከሚነሱት ጉዳዮች መካከል እንዱ ሕጋዊ መሠረቱ ነው። የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 52 የክልሎች ስልጣንና ተግባር ይደነግጋል። የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 52/ሰ ክልሎች የክልላቸውን የፖሊስ ኃይል ያደራጃሉ፣ ይመራሉ፣ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃሉ ይላል። ይሁን እንጂ ይህ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ ለአተረጓጎም ክፍት መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌደራሊዝምና የሰብዓዊ መብቶች መምህር ሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር)ይናገራሉ። "ከመደበኛ ፖሊሱ በተጨማሪ ክልሎች ሌላ ፖሊስ እንዲያደረጁና እንዲያሰማሩ ይፈቅዳል ብለው የሚተረጉሙ አሉ። የለም ይህ አንቀጽ የሚለው ክልሎች ሰላምና ጸጥታ የሚያስከብሩት መደበኛ ፖሊስን ተጠቅመው ነው ብለው የሚከራከሩ ወገኖችም አሉ" ይላሉ። ስለዚህም ኃይል አመሰራረት ሙሉ በሙሉ ሕገ-ወጥ ነው ለማለትም ሆነ ሕጋዊ ነው ለማለት አስቸጋሪ እንደሆነ ሲሳይ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። "ሙሉ በሙሉ የሕግ መሠረት የለውም ብሎ ለመከራከር ያስቸግራል። ሕገ-መንግሥታዊ መሠረት አለው ለማለትም ድንጋጌዎች ግልጽነት ይጎድላቸዋል።" የፌደራሉ መንግሥት ከትጥቅ አያያዝና አደረጃጀት ጋር የተያያዘ ግልጽ ፖሊሲ በማውጣት ሕገ-መንግሥቱ ላይ የተጠቀሰውን አንቀጽ በዝርዝር ሕግ መብራራት እንደሚገባውም ሲሳይ (ዶ/ር) ይናገራሉ። የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል አደም መሐመድ ግን ከቀናት በፊት በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ፤ የልዩ ኃይሎች አመሰራረት ሕጋዊ ማዕቀፍ እንደሌለው ተናግረዋል። "የልዩ ኃይሉ አደረጃጀት ከሕገ-መንግሥቱ አንጻር ከታየ ሕጋዊ ማዕቀፍ የለውም" ብለዋል ኢታማዦር ሹሙ። ልዩ ኃይሎች ወገንተኛ ናቸው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሸናል በኢትዮጵያ በተለይ በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል መመስረት ከጀመረ ወዲህ፤ በልዩ ፖሊሶች የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲመዘግብ ቆይቷል። የክልል ልዩ ኃይሎች የሚወስዷቸው እርምጃዎች ላይ ወገንተኝነት ይታይባቸዋል። በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰትም ይፈጽማሉ፤ ስለዚህም የክልል ልዩ ኃይሎች መበተን አለባቸው በማለት የሚሞግቱ በርካቶች ናቸው። ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ-ኢዜማ ይገኝበታል። የፓርቲው የሕዝብ ግነኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ፤ "ፓርቲያችን ከልዩ ኃይል ፖሊስ አንጻር ያለው ችግር የመጀመሪያው መሠረታዊ ጉዳይ ከአመሰራረቱ ጋር ይያያዛል” ይላሉ። አቶ ናትናኤል የልዩ ፖሊስ አመሰራረት ምንም አይነት ሕጋዊ መሠረት እንደሌለው ይናገራሉ። "ከዚህ በተጨማሪ ኃይሉ ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ መታዘብ እንደቻልነው፤ እራሱን [ልዩ ኃይል] የአንድ ብሔራ ጠባቂ አድርጎ በማየት በተደራጀበት ክልል የሚኖሩ የሌላ ዘውግ ማንነት ያላቸውን ማጥቂያ መሳሪያ ሲሆን፣ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር እንቅፋት ሲሆን ተመልክተናል" ይላሉ። የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚው አቶ ፍሰሐም፤ ከዚህ ቀደም የክልል ልዩ ኃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ያስታውሳሉ። አቶ ፍሰሐ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በሶማሌ ክልል እንዲሁም በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበር ላይ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸሙን ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይልም አምነስቲ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት ላይ በሁሉቱ የጉጂ ዞኖች ላይ፤ "ከሕግ ውጪ ሰዎችን እንደሚገድሉና ቤቶች እንደሚያቃጥሉ መዝግበናል" ብለዋል የአምነስቲው አጥኚ። የአማራ ክልል ልዩ ፖሊስም በተመሳሳይ፤ በተለያዩ ቦታዎች በተከሰቱ ግጭቶች ላይ ተሳትፎ እንደነበረው አቶ ፍሰሐ ጠቅሰው "ለአንድ ወገን በመወገን ጥቃቶችን አድርሰዋል፣ ቤቶችን አቀጥለዋል፣ ሰዎችንም ከሕግ ውጪ አስረዋል" ይላሉ። ልዩ ኃይል መበተን አለበት የክልሎች ልዩ ኃይል የሚያደርሰውን ጥፋት ለማስቆም፤ የፌደራሉ መንግሥት በየክልሉ ያሉትን የተደራጀና የታጠቀን ልዩ ኃይል መበተን እንደሚኖርበት የኢዜማው አቶ ናትናኤል እና የአምነስቲው አጥኚ አቶ ፍሰሐ ይሞግታሉ። "የክልል ልዩ ኃይል የሚባለው ፈርሶ ወይ ወደ መደበኛ ፖሊስ፣ ወይ ወደ መከላከያ ሠራዊት ወይም ደግሞ ወደ ፌደራል ፖሊስ ውስጥ እንዲጠቃለልና በዚያ ዕዝ ስር እንዲተዳደር ነው በተደጋጋሚ ስንጠይቅ የቆየነው" ይላሉ የኢዜማ የሕዝብ ግነኙነት ኃላፊው አቶ ናትናኤል። አቶ ፍሰሐም በበኩላቸው፤ “መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥቃት ከማድረሳቸውና ለተፈጸሙት ድርጊቶች ተጠያቂ ሲሆን ከአለማየታችን አንጻር ይህ የፖሊስ ኃይል እንዲበተንና አስፈላጊ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀናል" ሲሉ በአምነስቲ በኩል የቀረበውን ሃሳብ ጠቅሰዋለ። የልዩ ፖሊስ ኃይል ወሳኝነት አያጠያይቅም የክልል ልዩ ኃይሎች ይበተኑ፤ የሚለው ሃሳብ ለጸጥታ አማካሪው ለብርጋዴየር ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ የሚዋጥ አይደለም። ብ/ጀ ኃይሉ የልዩ ፖሊሶች ወሳኝነት ላይ ጥርጣሬ የላቸውም። በልዩ ኃይል ተፈጸሙ ለሚባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም ምክንያት አስተዳደራዊ ችግር እንጂ የልዩ ኃይሉ አይደለም ይላሉ። በክልሎች ያሉት የልዩ ኃይል ሠራዊት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፈጽማሉ እንዲሁም ወገንተኛ ናቸው ለሚለው ችግሩ፤ “የመንግሥታዊ መዋቅር፣ የቢሮክራሲ እና የአስተዳደር ችግር ነው እንጂ የልዩ ኃይሉ ችግር አይደለም” ይላሉ። ብ/ጀ ኃይሉ ሃሳባቸውን በዝርዝር ሲያስረዱ “ልዩ ኃይል በትዕዛዝ የሚሄድ ኃይል ነው። ልዩ ኃይሉን የሚመሩ ክልሎች ወይም ፓርቲዎች በትክክል በክልሎችና በፌደራል ሕገ-መንግሥት መሠረት ሕግን ተከትለው ልዩ ኃይሉን ቢመሩ ችግር አይፈጠርም” ብለው ያምናሉ። ለዚህም እንደመፍትሔ የሚያስቀምጡት ለሚከሰቱ ችግሮች "የሕግ የበላይነት በሠራዊቱ አዛዦች ላይ ቢተገበር፤ ልዩ ኃይሉም ከዚያ አንጻር ነው የሚቃኘው" ይላሉ። ብ/ጀ ኃይሉ "በአንዳንድ ክልሎች የተስተዋሉት ችግሮች እንዳይከሰቱ የልዩ ኃይሉን ተልዕኮ ማስተካከልም ያስፈልጋል" ባይ ናቸው። "የክልል ልዩ ኃይል ብቻ ሳይሆን የሚሰጠው ተልዕኮው ከተበላሸ መከላከያም ሊበላሽ ይችላል።" በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በፌደራል ሥርዓት በሚተዳደሩ አገራት ውስጥም ይህ አይነት አደረጃጀት እንዳለ የሚያስረዱት ብ/ጀ ኃይሉ፤ በኢትዮጵያ ያውን የልዩ ኃይል ፖሊስ ኃይል ተልዕኮና ኃላፊነት ማጥራት፣ እንዲሁም አባላቱ የሚሰለጥኑበት የጦር ሥነ ምግባርና የጦር ርዕዮተ-ዓለም ዳግም መከለስ እንዳለበት ያሳስባሉ። መከላከያና ፌደራል ፖሊስ እያሉ ልዩ ፖሊስ ለምን ተፈጠረ? በአንድ ክልል የሚከሰትን የጸጥታ መደፍረስን ፖሊስ ወይም የሚሊሻ የጸጥታ መዋቅር ማስቆም ቢሳነው የፌደራል ፖሊስ አልያም መከላከያ ሠራዊት ወደ ክልሉ ዘልቆ በመግባት ሰላም የሚያስከብሩበት ዕድል እያለ ልዩ ኃይልን መመሠረት አስፈላጊነት በተመለከተ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ ይነሳል። ብርጋዴየር ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ እንደሚሉት የፖሊስ መደበኛ ሥራ የተለመደው የወንጀል መካላከል ሥራ እንደሆነ ጠቅሰው፤ የመከላከያ ሠራዊት ሥራም ድንበር ላይ ሆኖ የውጪ ጠላትን መከላከል ነው ይላሉ። ከዚህ አንጻር የልዩ ፖሊስ ተልዕኮም የተደራጁ ኃይሎችን መመከት እንደሆነ በመጥቀስ "ፖሊስ የዕለት ተዕለት ጥቃቅን የሆኑ ቴክኒካል ሥራዎችን ነው የሚሰራው። እንደ ኢትዮጵያ ሰፊ የቆዳ ስፋትባለ ባለው አገር ውስጥ ያለን ግዙፍ መከላከያ ሠራዊትን አንድን የተደራጀ ኃይል ለመደምሰስ ከድንበር ማንቀሳቀስ አዋጭ አይደለም" በማለት በክልል ያሉ ልዩ ኃይሎችን አስፈላጊነት ይጠቅሳሉ። ብርጋዴር ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ ጨማረውም አንድ ኅብረተሰብ ውስጥ የሚንቀሳቀስን የተደራጀ ኃይል ለመቆጣጠርና ለመደምሰስ፤ የመከላከያ ሠራዊትን ከመጠቀም ይልቅ፤ የማኅበረሰቡን ባህል፣ ባህሪና ሥነ-ልቦና የሚረዳ ኃይል ማደራጀቱ ለሚተገበሩ ተልዕኮዎች ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ያስረዳሉ። ልዩ ኃይሎች የትጥቅ ሁኔታ በቅርቡ የትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ ባካሄዳቸው ወታደራዊ ትዕይነት ላይ፤ የልዩ ኃይል አባላቱ መካከለኛ እና የቡድን የጦር መሳሪያዎችን ታጥቀው ታይተዋል። የሌሎች ክልል ልዩ ፖሊሶችም በተመሳሳይ የቡድን የጦር መሳሪያዎችን ታጥቀው እንደሚገኙ በመጥቀስ፤ ልዩ ፖሊሶች ከሚሰጣቸው ተልዕኮ አንጻር የታጠቁት የጦር መሳሪያ ከባድ መሆኑን ብርጋዴር ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ ይናገራሉ። የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሐመድ ግን ለብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲናገሩ ልዩ ፖሊሶች በኃይል ታጥቀዋል ማለት አይቻልም ብለዋል። “ልዩ ኃይሎች ከባድ የጦር መሳሪያ ታጥቀዋል ሲባል ግራ ይገባኛል። የትጥቅ ደረጃ አለ ማለት ባይቻልም፤ ከባድ ጦር መሳሪያ የተባለው የቡድን መሳሪያ ለማለት ተፈልጎ ይመስለኛል። የቡድን መሳሪያ የላቸው የክልል ልዩ ኃይሎች ሊኖሩ ይችላሉ" በማለት የትጥቁን ዓይነት ገልጸውታል፤ ኢታማዦር ሹሙ።
45147962
https://www.bbc.com/amharic/45147962
አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ
አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ምን ያህል ስኬታማ ናቸው? በርካታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጨዋቾች አውሮፓውያን ናቸው። አፍሪካውያን እግር ኳሰኞች ከእሲያ እና ደቡብ አሜሪካ ተጨዋቾች የበለጠ በፕሪሚየር ሊጉ ቁጥር አላቸው።
አፍሪካውያን ተጨዋቾች ለሚጫወቱባቸው ክለቦች የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሱ ቀላል የማይባል አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ናይጄሪያና ሴኔጋል ደግሞ 39 እና 35 ተጫዋቾችን በሊጉ በማሳተፍ የቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ። ዝቅተኛ የሚባል የተጫዋች ቁጥር ያላት ጋና ስትሆን ቁጥራቸውም 26 ነው። • የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ: የላውሮ ግምት • ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን? • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ የአይቮሪ ኮስት እግር ኳሰኞች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች ሃገራት በላይ አስራ ሁለት ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ቀዳሚ ናቸው። በሁለተኝነት የምትከተላት ደግሞ ናይጄሪያ ስትሆን፤ በአጠቃላይ 11 ሜዳሊያዎችን በእንግሊዝ ውድድሮች ማግኘት ችለዋል።
49969037
https://www.bbc.com/amharic/49969037
ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ንግግር አንዳንድ ነጥቦች
በትናንትናው ዕለት ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው በ2012 ዓ.ም በሠላም፣ በፍትሕ ማሻሻያ ሥርዓቶች፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን ዘርዝረዋል።
በንግግራቸው ወቅትም መንግሥት ባለፈው ዓመት 2011 ዓ.ም በፖለቲካ፣ በዲሞክራሲ፣ በሰብአዊ መብት አያያዝ፣ በፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣ በፍትሕ ሥርዓትና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የነበረውን ሀገራዊ ጉድለት ማስተካከል የጀመረበት መሆኑን አንስተዋል። • እንቅስቃሴ አልባዋ ምጽዋ ምጣኔ ኃብት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን ተግባራዊ ማድረግ የዚህ ዓመት ቀዳሚ ተግባር እንደሚሆን የተናገሩት ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ፣ ዋና ዓላማውም የማክሮ ኢኮኖሚውን ጤንነት መጠበቅ፣ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ማሳደግና ለዜጎች በቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ የሥራ ፈጠራ ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን ገልፀው "የተጀመረው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለወጣቶቻችን የሥራ ዕድሎችን የማመቻቸትና የማፈላለግ ተግባራት ይበልጥ ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል" ብለዋል። በዚህ ዓመትም የተመረጡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይንም በሙሉ ወደግል የማዘዋወሩ እንዲሁም በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን የመተግበሩ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። • ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ የቴሌኮም ሴክተር እንዲሁም በስኳር ኮርፖሬሽን ሥር የሚገኙ የተወሰኑ ኩባንያዎችና ፕሮጀክቶች በዚህ ዓመት በከፊል ወይንም በሙሉ ወደ ግል ይዛወራሉ ሲሉም አክለዋል። የዋጋ ንረት አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህበረተሰብ ክፍሎች በተለይ እንደሚጎዳ የገለፁት ፕሬዝዳንቷ፣ መንግስት የመሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን በበቂ መጠን ከውጭ በማስገባት የዋጋ ንረቱ ሸማቾችን እንዳይጎዳ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል ሲሉ ቃል ገብተዋል። የዜጎች መፈናቀልና ግጭት ከለውጡ ዋዜማ ጀምሮ በኃገሪቷ ውስጥ ግጭትና መፈናቀል የሰፈነበት፤ ውስጣዊ መረጋጋት ኃገሪቷን የፈተነበት ጊዜ መሆኑን አስታውሰው "ግጭቶቹን ተከትሎ የመጣው የውስጥ መፈናቀልም በታሪካችን ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ምዕራፍ ሆኗል" ብሏል። ምንም እንኳን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የሌላ ኃገራት ዜጎች መጠለያ ብትሆንም "በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች፣ በገዛ ሀገራቸው ተፈናቃይ የሆኑበትን አሳዛኝ የታሪክ ገጽ አልፈናል።" ብለዋል። ሠላምና መረጋጋትን ማረጋገጥን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ በርከት ያለ ስራ መሰራቱን ያስታወሱት ርዕሰ ብሔሯ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ባለፈው አንድ ዓመት በጋራ ባደረጉት ርብርብ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የነበረው የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ከመቶ ሺ የማይዘል ሆኗል ብለዋል። በ2012 ዓ.ም በመልሶ ማስፈርና ዘላቂ ማቋቋም መርሐ ግብር ወደ ቀያቸው የተመለሱ ዜጎችን ወደተሟላ መደበኛና የተረጋጋ ኑሮ የመመለስ ተግባር በትኩረት የሚሰራበት መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም የደኅንነት ተቋማት ችግሮች ከመከሠታቸው በፊት ቀድመው "የማነፍነፍ ዐቅማቸው" እንዲያድግና ችግር ሲከሠትም በአጭር ጊዜ የማስቆም ብቃታቸው እንዲጎለብት የሚያስችሉ የአቅም ማሻሻያ ተግባራት ይሠራሉ ብለዋል። በዚህ ረገድ ፌደራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊሶችና፣ የመከላከያ ሠራዊቱ አቅማቸውን የሚያጠናክር ሥራ ይሰራሉ ሲሉ ተናግረዋል። ምርጫ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በ2012 የሚከናወነው ሀገራዊ ምርጫ ሦስት ዕሴቶችን መሠረት ያደረገ እንዲሆን መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ለዚህም ምርጫው በተቻለ መጠን ከዚህ በፊት ያጋጠሙ ግድፈቶችን በሚያርም መልክ እንዲከናወን፣ ነጻና ዲሞክራያዊ ፤ ተአማኒና ተቀባይነት ያለው እንዲሆንና የፖለቲካ ልሂቃንንና የምልዐተ ሕዝቡን ተሳትፎ ያረጋገጠ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል። • በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ አክለውም መንግሥት የምርጫውን ሂደት ለማሰናከልና ለማጠልሸት የሚከናወኑ ሕገ ወጥ ተግባራትን በሕግና በሥርዓት የሚያስተካክል ይሆናል ብለዋል። ከሀገራዊ ምርጫው ባሻገር የሚከናወኑ የሕዝበ ውሳኔ ሂደቶችም ምርጫውን በተመለከተ በተቀመጡት ሦስቱ ዕሴቶች መሠረት የሚከናወኑ ይሆናሉ ሲሉ አረጋግጠዋል። የፍትሕ ሥርዓቱ ማሻሻያዎች የፍርድ ቤት ማሻሻያዎችን ለማከናወን የሦስት ዓመታት መርሐ ግብር ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱን ያስታወሱት ፕሬዝዳንቷ፣ በዚህም መሠረት በሦስት ዘርፎች የሚከናወን የፌዴራል ፍርድ ቤቶችና የዳኝነት ማሻሻያ ዕቅድ ተቀርጿል ብለዋል። የዳኝነት ነጻነትን፣ ተጠያቂነትንና ግልጽነትን ማጠናከር፣ የፍትሕ ተደራሽነትን ማስፋትና የሕግ ዕውቀት እንዲዳብር ማድረግ፣ እንዲሁም የዳኝነትን ውጤታማነትና ቅልጥፍና ማሻሻል የማሻሻያው ዋና ዋና ትኩረቶች መሆናቸውንም አስቀምጠዋል። ውጤታማ እና ቀልጣፋ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ለማጠናከር በተያዘው ዕቅድ ደግሞ የፌደራል ፍርድ ቤቶችን አደረጃጀትና ሥልጣን የሚወስኑ ዓዋጆችን ማሻሻያ የማጠናቀቅ፤ የየአዋጁን ማሻሻያ ተከትሎ የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደርን የተሻለ ለማድረግ አስፈላጊ አደረጃጀትን የመዘርጋትና ደንቦቹን ማውጣት ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል ፕሬዝዳንቷ። ሕዝቡ ወደ ፍርድ ቤቶች የሚያቀርበውን ከፍተኛ የአገልግሎት ጥያቄ ለመመለስ የሚያሥችል፤ በዓመት እስከ ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ (250,000) መዛግብት ለማስተናገድ የሚያስችል አወቃቀር መፍጠር መታሰቡንም ገልፀዋል። • "ቤተ መንግሥቱን ለማስዋብ ለሙያችን የሚከፈለን ገንዘብ የለም" መስከረም አሰግድ አክለውም የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መምሪያ፣ የቁጥጥርና ክትትል ክፍሎችን በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች ማቋቋም እና ማደራጀት፤ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓትን ማጠናከር፤ የዳኝነት አገልግሎት ሥራ ደጋፊ የሆኑትን የአስተዳዳር አካላት ውጤታማነት ማረጋገጥ ዋነኞቹ ትኩረቶቹ ናቸው ብለዋል። የውጪ ግንኙነት በ2011 ዓ.ም ብቻ በተለያዩ ሀገራት በእስር እና በእንግልት ላይ የነበሩ ከ90 ሺህ በላይ ዜጎቻችን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ያስታወሱት ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሥራ ሥምሪት ስምምነቶችን መደራደርና ከተወሰኑት ጋር ስምምነትን ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል። ከጎረቤት ሀገራትና ከሌሎችም የአፍሪካ ሀገራት ጋር ቀስ በቀስ እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚያዊ ጥምረት ለመፍጠር የሚያግዙ የነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነቶች እና ያለ ቪዛ ወደ ሀገር ውስጥ መግባትን የመፍቀድ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑንም ተናግረዋል። • በኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የደረሱት ሥምምነት ምንድን ነው? "የውጭ ግንኙነት መርሃችን ፉክክርንና ትብብርን ባማከለ መልኩ እንዲከናወን ታስቧል" ያሉት ፕሬዝዳንቷ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን አሸናፊ ሆኖ መውጣትም ያስፈልጋል በማለት፣" ለዚህ ደግሞ የውጭ ግንኙነታችን በውስጥ ጥንካሬያችን ላይ ይወሰናል፡፡ ጠንካራ አንድነት፣ ጠንካራ ኢኮኖሚ፣ ጠንካራ የፖለቲካ ሥርዓትና ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ሲኖረን የውጭ ግንኙነታችንም በዚያው ልክ ጠንካራ ይሆናል፡፡ በዓለም አቀፍ መስኮች ተፎካካሪ ኃይል ሆነን ለመውጣትም እንችላለን" ሲሉ ተናግረዋል።
news-45166880
https://www.bbc.com/amharic/news-45166880
ታይዋናዊ ቱሪስት ኬንያ ውስጥ ፎቶ ሊያነሳው በነበረው ጉማሬ ተነክሶ ሞተ
ታይዋናዊ ቱሪስት ኬንያ ውስጥ ጉማሬ ፎቶ ለማንሳት ሲሞክር ጉማሬው ደረቱ ላይ ነክሶ ገድሎታል። የ 66 ዓመቱ ቻንግ ሚንግ ቻውንግ 'ሌክ ናይቫሻ' በተሰኘው የዱር እንስሳት ማቆያና መዝናኛ ውስጥ ነበር ጉማሬውን ፎቶ ለማንሳት የሞከረው።
ስል ጥርስ ያለው ጉማሬ አደገኛ እንስሳ ነው ጉማሬው ሌላ ታይዋናዊም ነክሷል። የአይን እማኞች እንደተናገሩት ሁለቱ ቱሪስቶች ጉማሬውን ፎቶ ለማንሳት በጣም ተጠግተውት ነበር። ህይወቱ ያለፈው ጎብኚ በጉማሬው ከተነከሰ በኃላ ወደ ህክምና መስጫ ቢወሰድም ብዙ ደም ስለፈሰሰው ሊተርፍ አልቻለም። • ካልጠፋ ዘመድ ከአዞ ጋር ፎቶ የተነሳችው አሜሪካዊት ው ፔንግ ቴ የተባለው ሌላው ታይላንዳዊ የደረሰበት ጉዳት ለክፉ የሚሰጥ አልነበረም። የኬንያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ቱሪስቶቹ ቻይናውያን ናቸው ብለው ቢገምቱም የኃላ ኃላ የታይዋይን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ታይዋናውያን መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የሌክ ናይቫሻ ባለ መርከቦች ማህበር አስተዳዳሪ ዴቪድ ኪሎ ለኬንያው ስታር ጋዜጣ እንደተናገሩት የአካባቢው ሐይቅ የውሀ መጠኑ ከፍ ስላለ ጉማሬዎች ከሐይቅ እንዲወጡ ግድ ብሏቸዋል። ከሐይቁ ወጥተው በሆቴል አቅራቢያ ስለሚዘዋወሩም በቀላሉ ከሰዎች ጋር ይገናኛሉ። ከአጥቢ እንስሳት መካከል እጅግ አደገኛው ጉማሬ ነው። በአካባቢው በዚህ ዓመት ብቻ ስድስት ሰዎች በጉማሬ ተገድለዋል። ጉማሬዎች እስከ 2,750 ኪሎ ግራም ድረስ ሊመዝኑ ይችላሉ። አፍሪካ ውስጥ በየዓመቱ 500 ሰዎች በጉማሬ ተበልተው ይሞታሉ። ታይዋናዊው ጎብኚ የሞተባት ኬንያ አምና 1.4 ሚሊዮን ሰዎች ጎብኝተዋት ከቱሪዝም 1.2 ቢልየን ዶላር ገቢ አግኝታለች።
news-56620482
https://www.bbc.com/amharic/news-56620482
በትግራይ ስለተፈጸመው ግድያ በሚያሳየው ቪዲዮ ላይ የተደረገው ምርመራ ምን ያሳያል?
የቢቢሲ 'አፍሪካ አይ' ፕሮግራም ባደረገው ምርመራ በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጸመ አንድ ጭፍጨፋ በኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት መፈጸሙን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች አግኝቷል። በዚህም ቢያንስ 15 ወንዶች የተገደሉበትን ትክክለኛውን ቦታ ለመለየት ችሏል።
የታጠቁና የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ያልታጠቁ ወንዶችን ከአንድ የገደል አፋፍ ላይ በመውሰድ አንዳንዶቹን ላይ በቅርብ ርቀት በመተኮስ አስከሬኖችን ወደ ገደል ገፍተው ሲጨምሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታይቶ ነበር። ቢቢሲ ይህ ድርጊት የተፈጸመው የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት ኃይሎችን እየተዋጋ ባለበት ትግራይ ክልል ውስጥ ማኅበረ ዴጎ ከተባለች ከተማ አቅራቢያ መሆኑን አረጋግጧል። ቢቢሲ ያገኛቸውን ማስረጃዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት በማቅረብ ምላሽ የጠየቀ ሲሆን መንግሥት "በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ነገሮችና ክሶች እንደ ማስረጃ ሊወሰዱ አይችሉም" በማለት "ገለልተኛ ምርመራዎችን ለማካሄድ የትግራይ ክልል ክፍት ነው" ሲል መልሷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው እንደተናገሩት፣ ትግራይ ውስጥ በኢትዮጵያ ሠራዊት ተፈጸሙ ስለተባሉት ጥፋቶች አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች በሕግ እንደሚጠየቁ መናገራቸው ይታወሳል።
51867053
https://www.bbc.com/amharic/51867053
ለተከታታይ ስምንት ዓመታት የህዳሴ ግድቡን ቦንድ የገዙት ኢትዮጵያዊ
ወላጆቹ ስድስት ልጆች ወልደዋል፤ ሁሉም ሊያድጉላቸው ግን አልቻሉም። አንድ በህይወት የተረፈላቸውን ልጃቸውን ግን፤ እንደ ሴት 'አንቺ' ብለው እየጠሩ አሳደጉት። ሰባት ዓመት ሲሞላው ደግሞ ኪሮስ የሚል ስም አወጡለት።
"የአባይ ውሃ ለኔ ፀበሌ ነው፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ፀበል ነው" እናቱ ግን፤ ልጄ አንድ ብቻውን ስለሆነ 'ሁለት ሰባት [14 ዓመት] እስኪሞላው አንቺ ነው የምለው' ብለው አንቺ ማለታቸውን ቀጠሉ። 'ልክ 14 ዓመት ሲሞላኝ፤ እናቴ 'አንተ' ብላ ጠራችኝ፤ በዛው ለትግል ወደ በረሃ ወጣሁ' የሚሉት አቶ ኪሮስ አስፋው፤ በ1972 ዓ.ም ህወሓትን እንደተቀላቀሉ ያስታውሳሉ። • የግዙፉ ግድብ ግንባታ፡ የኢትዮጵያና ግብፅ ቅራኔ • ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን? ከሁለት አመት በኋላ ግን የሻእቢያ ሰራዊትን ለመደገፍ ሳሕል ላይ በተካሄደው ጦርነት ለመሳተፍ ከሄዱት ታጋዮች አንዱ ስለነበረ፤ ጭንቅላታቸው ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው። በዚህ ጉዳት፤ ለስድስት ወራት ራሳቸውን ስተው ቆዩ ፤ አንድ አይናቸውም በዚሁ አደጋ ጠፋ። ከስድስት ወራት ህክምና በኋላ ያገገሙት አቶ ኪሮስ፤ ወደ ትግራይ ተመልሰው ፊደል ቆጥረው፣ ዳግም ወደ ኤርትራ በመሄድ የህክምና ትምህርት አጥንተው ተመለሱ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ማእከላይ ዞን አብዪ አዲ ከተማ በሚገኘው የአብዪ አዲ ሆስፒታል ነርስ ሆነው ሲሰሩ ቆይተው አሁን በፊዚዮቴራፒ ማዕከል እያገለገሉ የሚገኙ አካል ጉዳተኛ ናቸው አቶ ኪሮስ። ኪሮስ አስፋው፤ ለተከታታይ 8 አመታት ያለማቋረጥ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ቦንድ በየወሩ በግማሽ ወርሃዊ ደመወዛቸው እየገዙ ይገኛሉ። ቢቢሲ፤ ዓብዪ ዓዲ ላይ 'ኪሮስ ቦንድ' ብለው የሚጠሩዎት ሰዎች እንዳሉ ሰማሁ፤ ለምንድን ነው? ኪሮስ አስፋው፤ የድሮ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ህያው ከሚያደርጉት ስራዎቹ አንዱ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የወሰደው ቆራጥ ውሳኔ ነው። የግድቡ ግንባታ ሲያበስሩ ካላቸው ሦስት ነገሮች በገንዘብ፣ ጉልበትና ሞያ ራሳችን የምንገነባው ግድብ ነው ማለቱን መቼም አልረሳም። በዚህ ምክንያት ግድቡ ተሰርቶ እስኪያልቅ የወርሃዊ ደሞዜን ግማሹ እሰጣለሁ የሚል ቃል ገባሁ። ቃሌን በማክበር እነሆ ስምንት አመት ሙሉ ቦንድ እየገዛሁ ነው። ቢቢሲ፤ ምን ያክል ቦንድ አለዎ ማለት ነው? ኪሮስ አስፋው፤ ባጠቃላይ 95 ቦንድ ገዝቻለው፤ የመጨረሻዋ 25 የካቲት 2012 የገዛኋት ናት። ቢቢሲ፤ ይሄን ያክል ለቃልዎ ተገዢ እንዲሆኑ ያስቻለዎት ምንድን ነው? ኪሮስ አስፋው፤ ቃሌ ለአባይ ነው የሰጠሁት። የበረሃው ትግልም የገባሀው ቃል እንደማይታጠፍ አስተምሮናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ግድቡ እንዲሰራ ይፈልጋል፤ ተሰርቶም ለህዝብ ጥቅም ይውላል ብዬ አምናለሁ። እኔ ይሄ ሁሉ ቦንድ ለመግዛት ገንዘብ ተርፎኝ ወይም የሚያግዘኝ ሰው ኖሮ ሳይሆን፤ አባይ ተገንብቶ ጥቅም ላይ ሲውል እኔም ተጠቃሚ እሆናለሁ የሚል እምነት ስላለኝ ነው። ቢቢሲ፤ ከግድቡ እንደ ግለሰብ ምን እጠቀማለሁ ይላሉ? ኪሮስ አስፋው፤ በቀጥታ ተጠቃሚ ባልሆንም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠቃሚ ሲሆን እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ጥቅሙ ይደርሰኛል እላለሁ። ግድቡ ወደ ሚገነባበት ቦታ ሂጄ ምን ይዤ መጣሁ መሰለሽ፤ አንድ ድንጋይና ከወንዙ በላስቲክ ኮዳ የቀዳሁት ውሃ ይዤ መጥቻለሁ። • ሦስቱ ሃገራት በዋሽንግተን ምን ተስማሙ? ቢቢሲ፤ ለምን? ኪሮስ አስፋው፤ ድንጋዩ ግድቡ የሚገነባበት ቦታ እጅግ አስቸጋሪና ጠንካራ መሆኑን፤ እኛም ይህን እውን ለማድረግ ያለን እምነት ጽኑ መሆኑን ለማሳየት ነው። ውሃው ግን የአባይ ጸበል ነው። አንድ ሰው የሚካኤል፣ የማርያም ወዘተ . . . ብሎ የሚያምንበት ጸበል ይጠቀማል። እኔ ከአባይ ያመጣሁት ውሃ ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መድሃኒት ነው ብዬ ስላመንኩ ነው። ቢቢሲ፤ እሺ ቅድም ወደ ጀመርነው ወሬ እንመለስ ኪሮስ አስፋው፤ መልካም፤ ስለዚህ እንደ ሰው አስፈላጊውን ገንዘብ ከህዝቡ ተሰብስቦ ግድቡ ይገነባል። ከተገደበ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ይጠግባል፤ ከምን ነገር በላይ ግን የመለስ አደራ መወጣት እፈልጋለሁ። የኢትዮጵያ ችግር ገንዘብ ሳይሆነ፤ ፖለቲካና ሰላም ማጣት ነው። እንደጀመርነው ብንቀጥል ኑሮ አሁን ሁለተኛ አባይ ጀምረን ነበር እላለሁ። በተያዘለት ጊዜ አልቆ፣ ተመርቆ ስራ ቢጀምር ብዙ ተጠቅመን ነበር። ግን ባለው የፖለቲካ አመራር ችግር እስከ አሁን ወደ ኋላ እየተጎተተ ሲደናቀፍ ቆይቷል። ችግሮች ቢገጥሙንም ግን ይገነባል። ቢቢሲ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን እንደመጡ ግድቡ የፕሮፖጋንዳ ስራ ሲሰራበት እንጂ ሲገነባ እንዳለነበረ በመግለጽ፤ ገንዘቡም በሙስና መጥፋቱን ጠቁመዋል። በዚህ ምክንያት በ10 አመት እንኳ አያልቅም ብለው ነበር። ፕሮጀክቱን ሲመሩ የነበሩት ኢንጀነርም በመኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል። በወቅቱ እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ ተስፋ አልቆረጡም? ኪሮስ አስፋው፤ ልክ ነው፤ ይህ ስሰማ አዝኛለሁ። ከዚህ ሁሉ ልብ የሚሰብር ንግግር በኋላ ቦንድ መግዛት ማቆም አላቃተኝም። ግን ይህ አመራር የአባይ ግንባታ የማያምንበት ከሆነ፤ በግድቡ አስፈላጊነት እምነት ያለበት አመራር መጥቶም ቢሆን ያልቃል የሚል እምነት ማስቀደም እንዳለብኝ አወቅኩ። • ትራምፕ ህዳሴ ግድብ ሲያልቅ እመርቃለሁ ማለታቸው ተሰማ የኢንጅነሩና የመለስ ሞት ለእኔ አንድ አይነት ናቸው፤ በቃ የኢንጅነር ስመኘው በቀለ መሞት ግድቡ እንዳይሰራ ማድረግ ይሆን እንዴ የሚል ስሜት ፈጥሮብኛል። በዚህ ደንግጬ፣...አዝኜ፣ አልቅሻላሁ፤ ግን መልሶ እንጽናናለን። እኔ ታጋይ ነኝ። በትግል ወቅት ታላላቅ መሪዎቻችን ሲሞቱ አዝነን እናለቅስና፤ አሁንስ ማን ይመራናል እንል ነበር። ሆኖም ግን ሌሎች ጀግና መሪዎች ይተኩና ትግሉን መርተው፣ አሸንፈናል። ስለዚህ ግድቡን መርተው ማሳካት የሚችሉ ጀግና ለመኖራቸው ተስፋ አልቆርጥም። አባይም በህዝብ ተሳትፎ ያልቃል፤ እነሱ ወደ 'ኔጋቲቭ' እኛ ደግሞ ወደ 'ፖዘቲቭ' እየገባን መንገድ ላይ እንገናኛለን። ቢቢሲ፡ ከማን ጋር? ኪሮስ አስፋው፤ የአባይ ግድብ እንዳይገነባ ሲያደርጉ ከነበሩና፣ ገንዘባቹ ተበልቷል በማለት ተስፋ እንድንቆርጥ ካደረጉን ጋር። ቢቢሲ፤ አሁን ግን በወሬ ብቻ አይደለም፤ ከግብጽ፣ አሜሪካና ሌሎች ትልልቅ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለችውን ግድብ የመጠቀም መብቷን ወደ ምታጣበት መስመር እንድትገባ ጫና እየተደረገባት ነው ብለው ምሁራን እየገለጹ ነው፤ ይህ እርሶን ጨምሮ ህዝቡ ለአመታት የከፈለው ገንዘብ ሜዳ ላይ እንዳይቀር አያሰጋዎትም? ኪሮስ አስፋው፤ ለእኔም በግሌ እኮ ብዙ ነገር ደርሶብኛል። ከህጻን ልጅ ጀምሮ ብዙ ሰዎች እየመጡ አባይ ተሽጧል፣ አባይ ተከልክሏል፣ አባይ ተወርሷል፣ ገንዘብህ ጠፍቷል ይሉኛል። መሪዎቻችን በግድቡ ዙርያ ቆራጥ የሆነ አመራርና አቋም ባለማሳየታቸው አሁን እነዚህ አገራት እየፈከሩ ነው፤ ግን ትርጉም ስለ ሌለው ይሄም ያልፋል። • ኢትዮጵያ፤ የአሜሪካንን መግለጫ ተከትሎ ብሔራዊ ጥቅሜን አሳልፌ አልሰጥም አለች ቢቢሲ፤ እንዴት ትርጉም አይኖረው? ሃያላን አገራት አይደሉም? ኪሮስ አስፋው፤ ቢሆኑስ? የእኔ የቃል እምነት መለስ ያልቃል ማለቱ ነው። አሜሪካም ትሁን ግብጽ እንዲሁም ከራሳችን የግድቡን ግንባታ ሊያደናቅፉን ይችላሉ፤ ግን እንሻገረዋለን የሚል ጠንካራ እምነትና ጽናት እንዲኖረን በማድረግ አበርትቶን አልፏል። እኔም ከዚህ ቃል ነው የምነሳው፤ በማንኛውም አጋጣሚ ያልቃል የሚለው እምነቴን ይዤ ነው የምጓዘው። ቢቢሲ፤ ኑሮ በተወደደበት [በዚህ] ወቅት ግማሽ ወርሃዊ ደመወዝ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ብሎ መክፈል አይከብድም? ኪሮስ አስፋው፤ 'ሃብታም እንደሚበላለት፤ ድሃም እንደሆነለት' ይላሉ ወላጆቻችን። ግድቡ ሲያልቅ በተዘዋዋሪ ገንዘቡ እኔ ጋር ይደርሳል። እግዜር ይመስገን ሳልበላ አልዋልኩም፣ አላደርኩም። ልጆቼም ይማራሉ፣ ቤትም አለኝ። ሁሌም የምልከው ገንዘብ ደግሞ፤ ልክ ወደ ልጄ የላኩት ያክል ነው የሚሰማኝ። ስለ ሆነም አካባቢዬ ያለው ባንክ ማረጋገጫ ቦንድ ቢሰጠኝም፤ ስልክ ደውዬ ግን ደርሷል ብየ ጠይቄ አረጋግጣለሁ። እርካታ ይሰጠኛል። ቢቢሲ፤ ግድቡ የሚጠይቀው ገንዘብ ግን በመቶዎች ሳይሆን በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ነው ኪሮስ አስፋው፤ አውቃለሁ፤ ግን የኢትዮጵያ ህዝብም እኮ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ነው። ቦንድ መግዛት የቻለውን ከገዛ፣ ያልቻለውን ደግሞ በቀን አንድ ብር ከሰጠ በአመት ስንት ሚሊዮን ብር ይገኛል? ይህ በየአመቱ ተደምሮ ግድቡን መገንባት የሚችል ገንዘብ ይፈጥራል። ቢቢሲ፤ ስለዚህ? ኪሮስ አስፋው፤ ስለዚህማ ግድቡ የሚገነባው፤ ገንብተን መጨረስ እንችላለን የሚል እምነት በህጻን፣ አዋቂ፣ ወጣትና የአገር መሪ ልቦና ውስጥ መኖር አለበት። የተበላሸው ፖለቲካዊ አስተሳሰባችንም መለወጥ ይገባዋል። ለብሄርና ሃይማኖታዊ ግጭት፣ መከፋፈልና መራራቅ የዳረገንን ፖለቲካ መስበር አለብን። የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰሞኑ ያሳየውን ወኔ አስደስቶኛል፤ መንግስትም ወደ ፊት ባናውቅም አሁን አሜሪካ ያቀረበችለት ሰነድ ባለመፈረሙ እፎይታ ሰጥቶኛል። • አሜሪካ ከህዳሴ ግድብ አደራዳሪነት እንድትወጣ የሚጠይቀው የዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ በቀጣይም አንፈተንም ማለት ግን አይደለም፤ አሁን የምናያቸው ችግሮች በሙሉ ተደምረው ግን ተስፋ የምናደርግበት የህዳሴአችን ግድብ የሚጎዳ መሆን የለበትም፤ ያ ያሰጋኛል። የፈለገው ፖለቲካዊ ልዩነት ቢፈጠርም አባይ ግን አንድ ሊያደርገን ይገባል። ፈተናዎች አሸንፈን የግድቡ ፍጻሜ የምናይበት ቀንም በተስፋ እጠብቃለው።
47900152
https://www.bbc.com/amharic/47900152
ለዘመናት በስልጣን ላይ ያሉት ስድስቱ አፍሪካውያን መሪዎች
አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች ሳይወዱ በግድ በህዝባዊ ተቃውሞ አልያም ሞት ካላሸነፋቸው በቀረ ስልጣን አሳልፈው ሲሰጡ ማየት የተለመደ አይደለም። ለዚህም የዚምባብዌው ሮበርት ሙጋቤ፣ የሊቢያው ሙአመር ጋዳፊ እንዲሁም ትናንት ከስልጣን የተነሱት የሱዳኑ ኦማር አልበሽር ማሳያ ናቸው።
ከግራ ወደ ቀኝ፦ ቲዮዶር ኦኒያንግ-ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ፖል ቢያ-ካሜሩን፣ ዩዌሪ ሙሴቪ- ኡጋንዳ፣ ኢድሪስ ዴቢ-ቻድ፣ ኢሳያስ አፈወርቂ-ኤርትራ፣ ዴኒስ ሳሶኡ ናጉኤሶ-ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ ዛሬስ ለዘመናት በስልጣን ላይ ተደላድለው እንደሉ የሚገኙ የሚገኙ የአፍሪካ መሪዎች እነማን ናቸው? 1. ቲዮዶር ኦኒያንግ ጉኤማ ባሶጎ፦ የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝደንት ቲዮዶር ኦኒያንግ ጉኤማ ባሶጎ በመካከለኛው አፍሪካ የምትገኘውን ኢኳቶሪያል ጊኒን ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል። ይህም ለ40 ዓመታት ያክል ማለት ነው። ቲዮዶር ወደስልጣን የመጡት አጎታቸውን በመፈንቅለ መንግሥት ከስልጣን ካባረሩ በኋላ ነበር። ከስልጣን የተባረሩት የቲዮዶር አጎት በመንበራቸው ላይ ሳሉ ፈጽመውተል ለተባሉበት ወንጀል የሞት ብይን ተፈጽሞባቸዋል። • የሙጋቤ ሕይወት በምስል ቲዮዶር በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ''እጅግ ጨካኙ መሪ'' ተብለው ተፈርጀዋል። ቲዮዶር ከድሃ ሃገራቸው ሀብት ዘርፈው በፈረንሳይ ቪላዎች ገንብተዋል፤ ቅንጡ መኪኖችን ገዝተዋል ተብለው በፈረንሳይ መንግሥት ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው። ቲዎዶር ልጃቸውንም የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት አድርገው ሾማዋል። የቲዮዶር ልጅም ቢሆን በአሜሪካ በስሙ ተመዝገቦ የሚገኘው ንብረት ከሀገሪቱ በተሰረቀ ንብረት ነው የተገዛው በማለት የአሜሪካ መንግሥት የምክትል ፕሬዝዳንቱን ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ ጉዳዩን ፍርድ ቤት ቢወስደውም የቲዎዶር ልጅ ግን ንብረቱን ያፈራሁት በህጋዊ መልኩ በተገኘ ገቢ ነው በማለት እየተከራከረ ይገኛል። 2. ፖል ቢያ፦ የካሜሩን ፕሬዝደንት ፖል ቢያ ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ ካሜሮንን በፕሬዝደንትነት እየመሩ ይገኛሉ። በወቅቱ የካሜሩን ፕሬዝደንት ከነበሩት ፕሬዝደንት አሀመዱ አሂድጆ ጋር መልካም ግነኙነት የነበራቸው ቢያ ፕሬዝደንት ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የካሜሮን ጠቅላይ ሚንስትር በመሆን አገልግለዋል። በወቅቱ የነበረው የካሜሮን ህግ ጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬዝደንቱ ተተኪ ይሆናሉ ይላል። ፕሬዝደንት አሂድጆ ባልተጠበቀ ሁኔታ በፍቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ፖል ቢያ መንበረ ሥልጣኑን ተቆጣጠሩ። ቢያ 1976 ላይ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ቢደረግባቸውም ሳይሳካ ቀርቷል። መንበረ መንግሥታቸው ተቃውሞ የማይለየው ቢያ፤ ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገው እና በተቀውሞ በታጀበው ምርጫ ለ7ኛ ጊዜ አሸንፊያለሁ በማለት ካሜሮንን ማስተዳደራቸውን ቀጥለዋል። 3. ዩዌሪ ሙሴቪኒ፦ የኡጋንዳ ፕሬዝደንት ሙሉ የመዝገብ ስማቸው ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ ሲሆን ከ1976 ጀምሮ ኡጋንዳን በፕሬዝደንትነት ሲመሩ ቆይተዋል። ሙሴቪኒ ወደ መንበረ ስልጣን የመጡት በጭካኔ የሚታወቀውን የኢዲያሚን ዳዳ መንግሥትን ከስልጣን በማባረር ነበር። ሙሴቪኒ ወደ ስልጣን ሲመጡ በወሰዷቸው እርምጃዎች በምዕራባውያን ሃገራት ዘንድ ተቀባይነትን አግኝተው ነበር። ሙሴቪኒ ኤችአይቪ ኤድስን በመከላከል ረገድ ያስመዘገቡት ድል ብዙ ጊዜ ይወሳላቸዋል። በሰሜን ዩጋንዳ፣ ሱዳን እና ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ በስፋት የሚንቀሳቀሰው እና በጆሴፍ ኮኔ የሚመራው ''ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ'' ለሙሴቪኒ ፈተና ሆኖ ቆይቷል። • ኦማር አል-ባሽር: ከየት ወደየት? ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚዎች ዩጋንዳ በመድበለ ፓርቲ ዲሞክራሲ እና በአስርቱ ትዕዛዛት እንድትመራ ማድረግ ዓላማቸው አድርገው ይታገላሉ። የሙሴቪኒ እና የአሜሪካ ጦር የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ መሪ የሆነውን ጆሴፍ ኮኔን ለመግደል በርካታ ኦፕሬሽኖችንን ቢያደርግም እስካሁን ጆሴፍ ኮኔ ያለበት አይታወቅም። ሙሴቪኒ በቅርቡ በሕገ-መንግሥቱ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን ስልጣን ላይ የመቆየት የዕድሜ ጣሪያን ለማስቀነስ እና መንበረ ስልጣን ላይ ለመቆየት ባደረጉት ጥረት ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። 4. ኢድሪስ ዴቢ፦ የቻድ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ቻድን ላለፉት 29 ዓመታት ሲመሩ ቆይተዋል። ኢድሪስ ዴቢ በአሜሪካ እና ፈረንሳይ ድጋፍ ስልጣን ላይ የወጡትን ፕሬዝደንት ሃይሴኔ ሃብሬ በማስወገድ ነበር ስልጣኑን የተቆናጠጡት። ስልጣን ላይ ከወጡ ከስድስት ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ መድብለ ፓርቲ በመመስረት ሃገራዊ ምርጫ አሸነፉ። አነስተኛ የህዝብ ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገረው ዴቢ፤ የራሳቸውን ጎሳ ከሃገር ያስቀድማሉ ሲባሉ ይወቀሳሉ። የጉበት ህመም ወደ ፈረንሳይ ለህክምና በተደጋጋሚ የሚያመላልሳቸው ዴቢ፤ በቅርቡ ፓርላማው የስልጣናቸውን ኃያልነት የሚጨምር ህግ አስተላልፏል። 5. ኢሳያስ አፈወርቂ፦ የኤርትራ ፕሬዝደንት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የትኛውም ቃለ መጠይቅ ምንም አይነት ነገር ስለ ግለ ህይወታቸው አውርተው የማያውቁት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ጥቂት የሚባሉ ሰዎች ብቻ ስለ እርሳቸው ያውቃሉ። ኢሳያስ አፈወርቂ በ1936 ዓ.ም በአስመራ ከተማ ነው የተወለዱት። የሁለተኛ ደርጃ ትምህርታቸውን በልዑል መኮንን ሁለተኛ ደርጃ ት/ቤት ተከታትለዋል። ያስመዘገቡት ከፍተኛ ነጥብ የቀድሞ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአሁኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ትምህርት እንዲከታተሉ ቢያስችላቸውም በ1958 ዓ.ም ትምህርታቸውን አቋርጠው የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባርን ለመቀላቀል ወደ ሱዳን ተጓዙ። • "ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባር አባል ከነበሩት ሳባ ኃይሌ ጋር ትዳር መስርተው የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት ሆነዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ ለረጅም ዓመታት በሃገር መሪነት በስልጣን ላይ የቆዩ መሪ ብቻም ሳይሆኑ በቁመት ረጅም ከሚባሉት የሃገር መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው። የ1985ቱን ህዝበ-ውሳኔን ተከትሎ ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት እና የብሔራዊ ምክር ቤቱ ዋና ጸሀፊ ሆነው የተመረጡ ሲሆን፤ ይህም የመንግሥትን የሥራ አስፈጻሚ እና የፍትህ አካሉን በቁጥጥራቸው ስር እንዲሆን አስችሏቸዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመሩት ህዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሃገሪቱ የሚገኘው ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ሲሆን ከመስራቾቹ መካከልም አንዱ ናቸው። በ1989 ዓ.ም ጸድቆ የነበርው ሕገ-መንግሥትም ሥራ ላይ ሳይውል ቀርቷል። በኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው የኤርትራ መንግሥት በተለያዩ አጋጣሚዎች በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና በሃገሪቱ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ አላመጣም ተብሎ በተደጋጋሚ ይወቀሳል። • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? 6. ዴኒስ ሳሶኡ ናጉኤሶ፦ የሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕሬዚደንት ዴኒስ በሃገሪቱ ጦር አማካኝነት በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕሬዚደንት ተደርገው ተሰየሙ። ከ14 ዓመታት የስልጣን ዘመን በኋላ በተካሄደ ምርጫ ተሸነፉ። ይህ ያልተዋጠላቸው ዴኒስ ሳሶኡ ናጉኤሶ ከ5 ዓመታት በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት ስልጣን ላይ ወጡ። ከሶስት ዓመታት በፊት በተደረገ ምርጫ ለ7ኛ ጊዜ ምርጫ አሸንፌያለሁ በማለት ስልጣን ላይ ተደላድለው ተቀምጠዋል። በአጠቃላይ ለ38 ዓመታት ገደማ ስልጣን ላይ የቆዩት ዴኒስ የስልጣን ላይ ቆይታቸውን ለማራዘም በማሰብ ሕገ-መንግሥቱ እንዲሻሻል ማድረጋቸው ክፉኛ አስኮንኗቸዋል። • የኢትዮጵያና አሜሪካ የተለየ ግንኙነት እስከምን ድረስ? አየር ወለዱ ኮረኔል ለምዕራባውያን ሃገራት ነዳጅ እንዲያወጡ ፍቃድ በመስጠት ይታወቃሉ። ይህም ብቻ ሳይሆን ዴኒስ ሳሶኡ እጃቸው በሙስና ተጨማልቋል የሚል ክስ በተደጋጋሚ ይነሳባቸዋል። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ዴኒስ በፈረንሳይ ቅንጡ ቪላዎች እና መኪኖችን አፍርተዋል በሚል ለቀረበባቸው ክስ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበረ።
news-56867426
https://www.bbc.com/amharic/news-56867426
ኮሮናቫይረስ፡ ስለኮሮናቫይረስ ሐሰተኛ መረጃና ወሬዎችን የሚፈጥሩትና የሚያሰራጩ ሰባት አይነት ሰዎች
ኮሮናቫይረስን በሚመለከት የሚለቀቁ የሴራ ትንተና፣ የተሳሳተ መረጃ እና መላ ምቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ብዙዎች ሲያጋሯቸው ይስተዋላል። ነገር ግን እነዚህን መረጃዎች የሚያመነጨው ማነው? የሚያሰራጨውስ?
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በብዛት የተሰራጩ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሳሳች መረጃዎችን ተመልክተናል። ይህም እነዚህን መረጃዎች ማን እንደሚያሰራጫቸው መነሻ ሀሳብ ሰጥቷል። ምን እንደሚያነሳሳቸውም ያሳያል። ከዚህ በታች የተሳሳቱ መረጃዎችን የሚያስጀምሩ እና የሚያሰራጩ ሰባት አይነት ሰዎችን ተለይተዋል። "ቀልደኞች" በአንድ ወቅት የእንግሊዝ መንግሥት ዌምብሌይ ስታዲየም ውስጥ የለንደን ነዋሪዎችን ለመመገብ ላዛኛ እያበሰለ ነው የሚል መረጃ ሲለቀቅ በርካቶች እንደቀልድ እንኳን አልወሰዱትም ነበር። በሌላ አጋጣሚ ደግሞ አንድ ግለሰብ መንግሥት ያስቀመጣቸውን ገደቦች በመጣስ ከቤቱ ብዙ ጊዜ በመውጣቱ ተቀጣ የሚል መረጃና ለማሳመኛ ደግሞ የሐሰት ምስል ተጠቅሞ ነበር። እሱ እንደሚለው ይህ መረጃ ሰዎች ከቤት መውጣት እንዲፈሩ ያደርጋል በሚል ነበር። ኢንስታግራም በተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚከተሉትን ሰዎች ይህንን መረጃ እንዲያጋሩ የጠየቀ ሲሆን መረጃው ግን ከኢንስታግራም አልፎ በፌስቡክም በርካቶች ሲጋሩት ነበር። ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ሰዎችም መረጃውን እውነት አድርገው ወስደውት ነበር። "በሰዎች ዘንድ ድንጋጤ መፍጠር አልፈልግም'' ይላል መረጃውን መጀመሪያ ላይ ያጋራው ግለሰብ። ስሙን ግን መናገር አልፈለገም። "ነገር ግን እነዚህ ሰዎች እውነተኛ ያልሆነውን ምስል መለየት ካልቻሉ ከበይነ መረብ መረጃ የሚያገኘበትን መንገድ በደንብ መመርመር አለባቸው'' ብሏል። "አጭበርባሪዎች" በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በርካታ አጭበርባሪዎች ከመንግሥት የሚላኩ በማስመሰል የተለያዩ የጽሁፍ መልዕክቶችን ለዜጎች ሲልኩ ነበር። ዋነኛ ዓላማቸው ደግሞ ሰዎችን አሳስቶ ገንዘብ ማግኘት ነው። ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ አንድ መረጃ አጣሪ ቡድን ባደረገው ምርመራ መሰረት አንድ አጭበርባሪ መንግሥት ለዜጎች ድጎማ ለማድረግ ስላሰበ የባንክ መረጃችሁን ላኩ የሚል የጽሁፍ መልዕክት ሲልክ ነበር። የአጭበርባሪው የጽሁፍ መልዕክት በፌስቡክ በርካቶች ተጋርተውታል። ይህ መልዕክት ለዜጎች ሲላክ የነበረው የጽሁፍ መልዕክትን በመጠቀም ስለነበር ከጀርባው ማን እንዳለ ለማወቅ አስጋቸሪ ነበር። ከጥቅምት ወር ጀምሮ ደግሞ አጭበርባሪዎች በተለያዩ መንገዶች ገንዘብ ለማግኘት ስለኮሮናቫይረስ የተሳሳቱ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ነበር። አንዳንዶቹ ኢሜል በመጠቀም ሰዎች ስለ ክትባቱ ለማወቅ ከፈለጋችሁ ይህንን ተጫኑ በማለት የሰዎችን የባንክ መረጃ ለማግኘት ሞክረዋል። በሌሎች አጋጣሚዎች ደግሞ መንግሥት በወረርሽኙ ምክንያት በየወሩ የሚወስደውን ግብር አቋርጧል፤ ከዚህ በፊት የተቆረጠባችሁ እንዲመለስላችሁ ከፈለጋችሁ የባንክ መረጃችሁን ንገሩን የሚሉ አጭበርባሪዎችም አልጠፉም። "ፖለቲከኞች" ስለኮሮናቫይረስ እና ስለክትባቱ የተሳሳቱና ሐሰተኛ መረጃዎችን ከበይነ መረብ ጀርባ ተደብቀው ከሚያሰራጩ ብቻ የሚመጣ አይደለም። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ግንቦት ወር ላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ፀሐይ ላይ ማሞቅ አልያም ኬሚካሎችን መውጋት ከበሽታው እንዲድኑ ሊያደርጋቸው ይችል ይሆን ብለው ነበር። ፕሬዝዳንቱ በኋላ ላይ የሰጡት አስተያየት እንደ ቀልድ እንደሆነ ገልጸዋል። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ይህንን ግምታቸውን ከተናገሩ በኋላ በርካታ ሰዎች ወደ መረጃ ማዕከላት በመደወል እራሳቸውን በተመሳሳይ መንገድ ከበሽታው ማዳን ይችሉ እንደሆነ ሲጠይቁ ነበር። መሰል መረጃዎችን ያሰራጩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ብቻ አይደሉም። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ የኮሮናቫይረስ መጀመሪያ ላይ ወደ ዉሃን ከተማ የመጣው ምናልባት "በአሜሪካ ወታደሮች ሊሆን ይችላል" ብለው ነበር። የሩሲያው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ደግሞ ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተለያዩ የሴራ ትንተናዎችን ሲያደርግ የነበረ ሲሆን የክሬምሊን ደጋፊ የሆኑ የትዊተር ገጾችም ቢሆኑ ተመሳሳይ መረጃ ሲያሰራጩ ነበር። በአሜሪካ አሪዞና ግዛት የዓሳ ገንዳ ማጽጃ ኬሚካል ኮሮናቫይረስን ይፈውሳል የሚል ዜና ያነበቡ ጥንዶች ኬሚካሉን ጠጥተው ሆስፒታል ገብተዋል። ለዚህ አንዱ ተጠያቂ የሚሆኑት እንደመጣላቸው ይናገራሉ የሚባሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሳይሆኑ አይቀሩም። "የሴራ ተንታኞች" ስለኮሮናቫይረስ ባለሙያዎቹ እንኳን እርግጠኛ መረጃ መስጠት አለመቻላቸው የሴራ ትንታኔ ለሚሰጡ ሰዎች አመቺ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል። ለምሳሌም በሴራ ላይ በተመሰረተ የተሳሳተ መረጃ ምክንያት በዩናይትድ ኪንግደም 70 የሚሆኑ የሞባይል ስልክ ኔትወርክ ማማዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ 5ጂ ቴክኖሎጂ ነው ቫይረሱን ያመጣው የሚለው ወሬ ነው። ዩጎቭ እና ዘ ኢኮኖሚስት ባለፈው ወር ባደረጉት አንድ ጥናት እንዳመለከቱት 13 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካውያን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ውሸት ነው ብለው ያምናሉ። 49 በመቶዎቹ ደግሞ ሰው ሰራሽ ሊሆን ይችላል ብለዋል። በአንድ ወቅት ደግሞ እንግሊዝ ውስጥ የክትባት ሙከራ ላይ አንድ በጎ ፈቃደኛ በሂደቱ ላይ ህይወቱ አልፏል የሚል መረጃ ተሰራጭቶ ነበር። በዚህ ምክንያት ክትባቱ ሰዎችን ለመግደል የተሰራ ነው የሚል የሴራ ትንታኔ ተሰራጭቶ ነበር። የሬዲዮ ሞገዶችን በመጠቀም ለሞባይል ስልክ አገልግሎት የሚውለውን የ5ጂ ቴክኖሎጂ በስፋት እየተሰራጨ ላለው የኮሮናቫይረስ ተጠያቂ በማድረግ ይህንን ሐሰተኛ መረጃ በስፋት እያሰራጩ ያሉት ሰዎች የሴራ ንድፈ ሐሳብን መሰረት አድርገው ነው። ይህ ወሬ መሰራጨት የጀመረው በጥር ወር መጨረሻ አካባቢ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ታማሚ አሜሪካ ውስጥ በተገኘበት ሰሞን ሲሆን፤ ክስተቱ ከ5ጂ ኔትወርክ ጋር ግንኙነት እንዳለው በፌስቡክ በኩል ሲወራ ነበረ። የሚሰራጨውም ወሬ ሁለት ገጽታ የነበረው ሲሆን አንደኛው 5ጂ የተፈጥሮ በሽታን የመከላከያ አቅምን በመቀነስ ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ ያደርጋል የሚሉ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ቫይረሱ በቀጥታ በ5ጂ ቴክኖሎጂ በኩል ይተላለፋል ሲሉ ያልተረጋገጡ መልዕክቶችን በስፋት አሰራጭተዋል። "ውስጥ አዋቂዎች" አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተሳሳተ መረጃ የሚመጣው ታማኝ ከሆኑ ምንጮች ነው። ለምሳሌ ዶክተሮች፣ መምህራን አልያም የጤና ማዕከላት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ተናገሩት እየተባለ የተሳሳተ ወሬ ይዛመታል። በአንድ ወቅት እንግሊዝ ውስጥ አንዲት የአምቡላንስ ሠራተኛ ተናገረችው ተብሎ "ወጣቶች በብዛት እየሞቱ ነው'' የሚል የድምጽ መልዕክት ተሰራጭቶ ነበር። ቢቢሲ ይህንን የድምጽ መልዕክት አስተላልፋለች የተባለችውን ሴት ለማነጋገር ቢሞክርም የእውነትም የጤና ሠራተኛ መሆኗን ማረጋገጥ አልቻለም። ነገር ግን መረጃው ሙሉ በሙሉ ሐሰት ነው ብሎ መደምደምም ይከብዳል። "ዘመዶች" ብዙ ጊዜ ሰዎች ስለቤተሰቦቻቸው አልያም ስለወዳጆቻቸው ሲያስቡ ይጨነቃሉ። በተለይ ደግሞ በዚህ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን በሚያስጨንቅበት ወቅት። እናም አንዳንድ ሰዎች ጠቃሚ ነው ብለው የሚያስቡን መረጃ ለቤተሰብና ወጃጆቻቸው ያገራሉ። መረጃ ማጋራቱ በራሱ መጥፎ ባይሆንም መረጃው ግን ምን ያህል ተአማኒና እውነተኛ ነው የሚለውን ሳያጣሩ ለሌሎች ማጋራት አደገኛ ውጤትን ሊያስከትል ይችላል። እንግሊዛዊቷ ዳኒኤል ቤከር የዚህ ጉዳይ ሰለባ ነበረች። በአንድ ወቅት ፌስቡክ ላይ ያገኘችውን መረጃ ምናልባት እውነት ከሆነ በማለት ለብዙ ሰዎች አጋርታ ነበር። "መጀመሪያ ላይ ትንሽ አሳስቦኝ ነበር። ምክንያቱም እምብዛም ከማላውቃት ሴት ነበር መልዕክቱ የተላከልኝ'' ትላለች። "መልዕክቱ ጠቃሚ ስለመሰለኝ ልጅ ላላት እህቴ ላኩላት።'' እነዚህ ሰዎች የሚያገኙትን መረጃ ለሚወዷቸው ሰዎች ለማጋራት መቸኮላቸው የሚያስገርም አይደለም። ነገር ግን ሁሉም የሚባለው ነገር ግን እውነት ነው ማለት አይደለም። "ታዋቂ ሰዎች" ኮሮናቫይረስን በተመለከተ የተሳሳቱ እና እውነት ላይ መሰረት ያላደረጉ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ ሰዎች መካከል የምናደንቃቸውና የምንወዳቸው ሰዎችም ጭምር ይገኙበታል። ብዙ ጊዜ በይነ መረብ ላይ የሚያገኙትን መረጃ ማጋራት የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን በርካታ ተከታዮች ያላቿው ሰዎች እንዲህ አይነት ነገሮች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ምክንያቱም አንድ ተራ ሰው የተሳሳተውን መረጃ ሲያጋራና ታዋቂ ሰዎች ሲያጋሩት መልዕክቱ የሚያገኘው ተቀባይነት ተመሳሳይ አይደለም። ሮይተርስ የዜና ወኪል በቅርቡ በሰራው አንድ ጥናት መሰረት በመላው ዓለም ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ጀርባ የታዋቂ ሰዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አሳይቷል። የሞባይል ስልክ አገልግሎትን ፈጣንና ዘመናዊ ያደርገዋል ተብሎ የታመነበት የአምስተኛው ትውልድ [5ጂ] ቴክኖሎጂ የኮሮናቫይረስን እያሰራጨ ነው በሚል በተናፈሰው ወሬ ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎች ነበሩበት። አዲሱ ቴክኖሎጂ በሽታውን እያስተላላፈ ነው የሚሉ መላምቶችን የያዙ መልዕክቶች ዕውቅና ባገኙና በመቶ ሺህዎች ተከታይ ባሏቸው የፌስቡክ፣ የዩቲዩብና የኢንስታግራም አካውቶች በኩል ሳይቀር በስፋት ሲሰራጩ ነበር። ነገር ግን ሳይንቲስቶች ይህ በኮቪድ-19 እና በ5ጂ አገልግሎት መካከል አለ የተባለው ግንኙነት "ፍጹም የማይረባ" ከመሆኑ በተጨማሪ ከሥነ ፍጥረት እሳቤ አኳያም ሊሆን የማይችል ነው ብለዋል። አሁንም ድረስ ኮሮናቫይረስ አውሮፓውያን የሸረቡት ሴራ እንጂ እውነት አይደለም ብለው የሚያምኑ ሺህዎች ናቸው። አሁንም ድረስ ኮሮናቫይረስን የወለደው 5ጂ ኔትወርክ ነው የሚሉ አሉ። አሁንም ድረስ 'አልኮል ኮሮናቫይረስን ድራሹን ያጠፈዋል' ብለው ጉሮሯቸው እስኪሰነጠቅ የሚጨልጡ በርካቶች ናቸው። ከኢትዮጵያ እስከ ማዳጋስካር፣ ከታይላንድ እስከ ብራዚል፣ ከአሜሪካ እስከ ታንዛኒያ በሐሳዊ ወሬ ያልናወዘ፣ መድኃኒት ያልጠመቀ የለም። ሳይንስ መፍትሔ የለውም ብለው ከደመደሙት ጀምሮ አምላክ ያመጣው መቅሰፍት ነው ራሱ ይመልሰው ብለው ሕይወታቸውን በተለመደው መልኩ የቀጠሉ የዓለም ሕዝቦች ብዙ ናቸው።
news-45376843
https://www.bbc.com/amharic/news-45376843
"አቶ በረከት የኪራይ ሰብሳቢነት ፊታውራሪና ነፍስ አባት ናቸው" አቶ መላኩ ፈንታ
የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ በከፍተኛ ሙስና ክስ ተመስርቶባቸው ለአምስት ዓመታት የታሰሩ ሲሆን ከእስር የተለቀቁት ከጥቂት ወራት በፊት ነው። በቀድሞ ፓርቲያቸው ብአዴን ውስጥ እየተወሰደ ስላለው እርምጃና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አቶ መላኩ ፈንታ ጥያቄ፦ በአሁኑ ወቅት በብአዴን እየተካሄደ ያለው ለውጥ የምን ውጤት ነው ይላሉ? አቶ መላኩ፦ እስር ቤት እያለሁ፣ ከወጣሁም በኋላ በብአዴንና በሌሎች ፓርቲዎች እንዲሁም በኢህአዴግ ውስጥ እየተደረጉ ያሉ ሁኔታዎችን ሳጤን በሕዝብ የመጣን ለውጥ አምኖ የመቀበልና ያለመቀበል የተለያየ ነገር ይታየኛል። ለውጡን ተቀብለን እንምራ የሚል እና መቀበል ያልቻለም አለ። ከዚህ አንፃር በቅርቡ ብአዴን እየወሰደ ያለውን እርምጃ፣ ስለ ውሳኔዎቹ የሚሰጣቸው መግለጫዎች፣ እንዲሁም ከአንዳንድ አባሎቹ ከምሰማው [ተነስቼ] ፓርቲው በትክክልም ሕዝብ ያመጣውን ለውጥ ተቀብዬ እመራለሁ ያለ ይመስለኛል። ነገር ግን በዚህ ውስጥ ለውጥን በመቀበልና ባለመቀበል እንዲሁም በመተካካት ጉዳይ መሳሳብ፣ መገፋፋት ይታያል። እስከማውቀው ድረስ የመተካካት ዕቅድ እኔ ከመታሰሬ በፊት የወጣ ነው፤ ትርጉም ባለው መልኩ ተፈፅሟል ማለት ግን የሚቻል አይመስለኝም። ከተተካን መውጣት አለብን ብለው የወጡት አቶ ተፈራ ዋልዋ ብቻ ናቸው። ለእኔ እውነተኛ መተካካትን ተግባራዊ ያደረጉት [እርሳቸው ናቸው]። ሌላው ግን ከኋላ ሆኖ የመምራትና የመቀጠል ፍላጎት አለው።ይሄ ነገር ነው አሁን መሳሳብን እየፈጠረ ያለው። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» የወጣቱን አዲሱን የፓርቲ አመራር አምኖ መልቀቅና መሰናበት ያለባቸው ሰዎች አሉ።በእርግጥ ለተፈጠረው ብዙ ጥፋት ተጠያቂ እንደረጋለን በሚል ስጋት ለውጡን የማይፈልጉት ያሉ ይመስለኛል። አንዳንዶቹ ደግሞ በታሪክ መኖር የሚፈልጉ ይመስለኛል። አንዳንድ ምዕራፎችን ለመዝጋት ታሪክ ጥሩ ነው። ባለፈው የተከፈለ መስዋዕትነት አለ፤ ክብር ሊሰጠው የሚገባ ነው።አሁን ደግሞ ወቅቱ የሚጠይቀው ነገር አለ።ወቅቱ ሕዝብ ልማት፣ ዲሞክራሲና ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እየጠየቀ ያለበት ነው። በነጻነት ሐሳብ መግለፅ የሚቻልባት አገር ትፈጠር፣ የሞግዚታዊ ስሜትና አስተሳሰብ አይጫንብኝ እያለ ነው። ይህን ነባራዊ ሁኔታ አምኖ መቀበልና ለዚህ ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። በብአዴንም [ኾነ]በኢህአዴግ እየተደረገ እንዳለው ለዚህ ዝግጁ የሆኑት መቀጠል አለባቸው፤ ያልሆኑት ደግሞ በክብር መሸኘት፣ ተጠያቂ መሆን ያለባቸውም መጠየቅ ያለባቸው ይመስለኛል።በፓርቲዎች እየተደረገ ያለው ፍትጊያ እነዚህን ማዕከል አድርጎ እየሄደ ይመስለኛል። ጥያቄ፦ ስለዚህ ብአዴን በአቶ በረከት ስምኦንና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ የወሰደው እርምጃ ትክክል ነው እያሉ ነው? አቶ መላኩ፦ በእኔ እምነት የዘገየ ካልሆነ በቀር በጣም ትክክለኛ እርምጃ ነው። እንደ አቶ በረከት ዐይነቱ ስለ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ስለ ጸረ ሙስና ትግል የሚዘምሩ ናቸው፤ በመድረክ ላይ፤ በተግባር ግን የኪራይ ሰብሳቢነት ፊታውራሪና ነፍስ አባት ናቸው። ለዚህ ነው የተወሰደው እርምጃ ዘግይቷል የምለው። የሕዝብን ጥያቄ ይዤ እመራለው የሚል ኃይል እየተፈጠረ ነው።የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ ቆርጦ የመጣ ፤ ከሞግዚታዊ አስተሳሰብ ልላቀቅ ያለ ኃይል በእነሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ የዘገዩ ካልሆኑ [በስተቀር] በጣም ተገቢ ናቸው። • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" ጊዜው ሲፈቅድና በተረዱበት ጊዜ እርምጃ መውሰዳቸው አመራሮቹን ሊያስመሰግናቸው ይገባል። አመራሮቹ ይህን እያደረጉ ያሉት የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ እስከሆነ ድረስ የብአዴን አባሎች፣ ሕዝብና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሁሉ ሊደግፏቸው ይገባል የሚል እምነት ነው ያለኝ። ጥያቄ፦ለአቶ በረከትና አቶ ታደሰ መታገድ ምክንያት በጥረት ላይ የፈፀሙት ጥፋት እንደሆነ ብአዴን አስታውቋል።እርስዎ ደግሞ ጥረትና ኤፈርትን ወደ ግብር ሥርዓቱ እንዲገቡ ለማድረግ ቆርጠው መነሳትዎ ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ግጭት ውስጥ እንደከተትዎ ቀደም ሲል ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ተናግረው ነበር? በእርግጥ ጥረት ግብር እንዲከፍል ማድረግ ችለው ነበር? አቶ መላኩ፦መጀመሪያ ላይ ጥረትንም ሆነ ኤፈርትን ወደ ግብር ሥርዓት ማስገባት ተግዳሮት ነበረው። በመጨረሻ ግን ሁለቱንም ማስገባት ችለናል። የጥረት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ዮሴፍ ረታ ነገሩ እንዲሳካ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍለዋል።ከሳቸው ጋር ተረዳድተን ጥረትን ግብር ሥርዓት ውስጥ ማስገባት ችለናል። ታክስ ብቻ ሳይሆን የልማት ባንክ ቦርድ ሰብሳቢም ስለነበርኩኝ ብድር በመክፈል እንደማንኛውም ተበዳሪ ወደ ሥርዓት እንዲገቡ የማድረግ ሥራ ሠርቼ ነበር።አሁን [ያለፉት]አምስት ስድስት ዓመታት መረጃ የለኝም። መጀመሪያ 'ኪራይ ሰብሳቢውን ሳትታገሉ ግብር ክፈሉ፣ ታክስ ክፈሉ እያላቹ ለምን ክንዳችሁ እኛ ላይ ያርፋል' የሚል ሽፋን ነበር። የኛ ነጥብ ደግሞ ማንኛውም ግብር ከፋይ ነኝ ያለ፣ በሥርዓቱ ብድር ተበድሬ እከፍላለው ያለ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በሥርዓቱ መዳኘት አለበት የሚል ነበር። አሁን እየሰማሁ እንዳለሁት ግን ግለሰቦቹ እየተጠየቁ ያሉት ጥረትን ይመሩ በነበረበት ወቅት ድርጅቱ ውስጥ በነበረ ሙስናና ብልሹ አሠራር ነው። በርግጥ ከመታሰሬ በፊት የማውቀው ፣ እሰማ የነበረውና አባላትም ያነሱ የነበሩት ነገር ነው። በጥቅሉ ያደረጉትን የኦዲት ሪፖርት እና ጥናት ባላውቅም ለረዥም ጊዜ ድርጅቱ የቤተሰብ ቤት፣ ግለሰቦች እንደፈለጉ የሚመሩት ድርጅት ሆኗል ተብሎ ጥያቄ ሲነሳ ነበር። የሕዝብ የሚባል ድርጅት የቤተሰብ ሆኗል ከተባለ በድርጅቱ ብልሹ አሠራር ለመንገሡ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ትንታኔ አያስፈልገውም።ውጤታማነቱም ከሌሎች ተመሳሳይ ኢንዶመንቶች አንፃር ሲታይ ለብልሹ አሠራር የተጋለጠ እንደነበር መገመት የሚቻል ይመስለኛል። ጥያቄ፦ ብአዴን ለህወሓት ፍላጎት ይገዛ ነበር፤ ግንኙነታቸውም የአቻ ፓርቲዎች አልነበረም ይባላል።እርስዎ ፓርቲው ውስጥ እያሉ ግንኙነታቸው እንዴት ነበር? አቶ መላኩ፦ይህን ነገር በሁለት መንገድ መመልከት ይቻላል።በአንድ በኩል ብአዴን በራሱ ለክልሉ ሕዝብ ተጠቃሚነት ያደረጋቸው ነገሮች [እንዳሉ ሁሉ] ተጠያቂ የሚሆንባቸው ነገሮችም አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የህወሓት የበላይነት የሚታይበት ሁኔታ ነበር።እናም ይህን ሕዝቡም አባላቱም ያነሱት ነበር። ይህን ያነሱ ብዙ አባላት ስደትና እስራት ደርሶባቸዋል። የህወሓትን የበላይነት ተልእኮ ወደ ብአዴን ይዘው የሚመጡት ደግሞ እንደ አቶ በረከት ያሉት ነበሩ።አሁን ላይ ቆሜ ሳየው በዚህ መልኩ ብዙ ተልዕኮዎችን አስፈፅመዋል። እንደሰማሁት የብአዴን አባላት እንዲሁም የሌሎች ፓርቲዎች አባላት በኢህአዴግ ጉባኤ ላይ የህወሓትን የበላይነት ጉዳይ አንስተው ተወያይተዋል።ይህ ጊዜው ሲፈቅድ የመጣና አከራካሪ ጉዳይ ነበር።ይህ ሕዝብ ያመጣው ለውጥ ከዚያ እውነታ የተነሳም ነው። የህወሓት የበላይነት የለም ብሎ መደምደም አይቻልም።በተመሳሳይ ብአዴን ሙሉ በሙሉ ለህወሓት ተገዥ ነበር ማለትም አይቻልም። በጥቅሉ ግን አሁን የህወሓት የበላይነት ጉዳይ የፓርቲዎች ትልቅ የትግል አጀንዳ እንደሆነ ይሰማኛል። ጥያቄ፦ ከዚህ ቀደም አሁን ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ከታገዱት አቶ በረከት ስምኦን ጋር ስለተነካካችሁበት ነገር ተናግረው ነበር።እሳቸውም ሰሞኑን እርስዎን በግል ለማጥቃት ያደረጉት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።ይልቁንም የእርስዎ ምክትል የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ 'ሰዎችን እያስለቀሰ ነው፤ አንድ ነገር አድርግ' እንዳልዎ ነው እየገለፁ ያሉት።እዚህ ላይ የሚሉት ካለ? አቶ መላኩ፡- ይህን ማለታቸውን አልሰማሁም፤ ግን ከባህሪያቸው አንፃር ቢሉም አይገርመኝም።የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም አባሉ ስለ መላኩ ጉዳይ ይገለፅልን፤ ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተመረጠው ከሙስና የፀዳ ተብሎ ነው ሲላቸው፣ 'ሙስና ውስጥ ገብቷል፣ መረጃ አለ፤' እያሉ ሲያብራሩ የነበሩት እሳቸው ናቸው።ስለዚህ የአሁኑ እሱ ላይ አጀንዳ የለኝም ማለታቸው የማይመስል ነገር ነው። ወደ ሙስና ገብቼ አጥፍቼም ከሆነ ማወቅ ያለበት ጉዳዩ ቀርቦ መገምገምም ያለብኝ፣ የፓርቲው ሊቀ መንበር ምክትሉም አውቀው መድረክ ላይ ነበር።ነገር ግን አብዛኛው የብአዴን አመራር ነገሩን የሰማው ከሚዲያ ነው።እሳቸው ግን የጀርባ ፈላጭ ቆራጭ ስለነበሩ ያኔ ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር። • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? የአቶ ገብረ ዋህድን ጉዳይ [በተመለከተ] እውነት ነው አንስተውልኛል፤ እሳቸውም ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የህወሓት አመራሮች [አንስተውልኛል]።እኔ ግን ጉዳዩ ላይ ተጨባጭ ማስረጃ ስላላገኘሁ ለሾመው አካል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርቤያለሁ ብያቸዋለሁ።በድጋሚ ይህንኑ ጉዳይ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ አንስተውብኝ 'ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሳወቅ የሚጠበቅብኝን አድርጌያለሁ' ብዬ መልሼላቸዋለሁ። ከአቶ ገብረዋህድ ጉዳይ ጋር አዳብለው ያነሱልኝን ጉዳዩች ግን ህሊናቸው ያውቃል።ለሚዲያ አካላት ማስታወቂያ በመስጠት ሕይወት እንዲኖራቸው የሚያደርጉ እንደ አቶ ከተማ ከበደ ያሉ ባለሐብቶችን፣እየሱስ ወርቅ ዛፉ፣የህብረት ባንክ ፕሬዝዳንት የነበሩትንና ሌሎችን 'የታክስ ጉዳይ ፈልገህ እሰር' ብለውኝ፣ 'በታክስ ፈልጌ አላስርም' ብያቸዋለሁኝ። 'የኮሚኒኬሽን ኃላፊ እርስዎ ነዎት፤ ሚዲያ ሕግም አለዎት፤ ራስዎ የሚያደርጉትን ያድርጉ' ብያቸዋለሁ።ይህን ያሉኝ የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊውን ይዘው ነበር። በወቅቱ ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርቤም ነበር። የባንክ ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ሌሎች ሌሎች ሰዎችንም በተደጋጋሚ እሰር ብለውኝ እምቢ ብያቸዋለሁ። በተቃራኒው ታክስን ተፈፃሚ ላደርግ ስል 'ይሄ እኮ ልማታዊ ባለሐብት ነው' እያሉ ቢሮ ድረስ አስጠርተው አነጋግረውኛል።ይህንንም የብአዴን ሥራ አስፈፃሚ ሂስና ግለ ሂስ መድረክ ላይ አቅርቤያለሁ። ጥያቄ፦ ወደ ፖለቲካ የመመለስ ሐሳብ አለዎት? አቶ መላኩ፦ ትበሰብሳታለህ ተብዬ ነበር የገባሁት፤ እንድበሰብስ ተፈርዶብኝ የሄድኩ ሰው ነኝ። እስከዚህ ድረስ ነበር ነጻነታችንን አጥተን የነበረው። በአገሪቱ የመጣው ለውጥ ትልቅ ነው።በዚህ ውስጥ አገሬንና ሕዝቤን መርዳት እፈልጋለው። ግን ፖለቲካ ውስጥ ገብቼ ነው? ሌሎች መንገዶች አሉ? የሚለውን እያሰብኩ ነው።ለራሴም ጊዜ እየሰጠሁ ነው። ክብር ለሰጠኝ፣ ፍቅር ለሰጠኝ ሕዝብ የማገለግለበትን መንገድ ዐይቼ የምወስን ይሆናል። ጥያቄ፦ ወደ ብአዴን መመለስን ያስባሉ ታዲያ? በዛሬው ብአዴን ውስጥ ራስዎን ሊያዩ አልሞከሩም? አቶ መላኩ፦ወደ ፖለቲካ መመለስን በማይበት ጊዜ አንደኛው አማራጭ እሱ ስለሆነ አስበዋለው። ጥያቄ፦ በአሁኑ ወቅት ከብአዴን አመራሮች ማለትም ከቀድሞ ጓዶችዎ ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት ነው ያለዎት? አቶ መላኩ፦ተቋማዊ ባይሆንም ከብአዴን የቀድሞ አዲስ አመራሮች እንዲሁም ከአባላቱ ጋር በስልክም በአካልም እገናኛለሁ። እንደተፈታሁም ሁሉም በአካልም በስልክም እንኳን ደስ አለህ ብለውኛል። 'ያንተ የለየለት መታሰር ቢሆንም ላለፉት ሦስትና አራት ዓመታት እኛም ታስረን ነበር።የከፈልከውን መሰዋዕትነት አንረሳም፤ ሥራ አስፈፃሚው ውስጥ እንዳለህ ነበር የምናስበው' ብለውኛል። ያለፈውን ትቼ ወደፊት እንድሄድ ምክርም ማበረታቻም ይሰጡኛል፤ እኔም ከማያቸው ከምሰማቸው ነገሮችም በመነሳት እንዲህ ቢሆን ባይሆን እያልኩ አስተያየቴን እሰጣቸዋለሁ፤ እንወያያለን።
news-46429666
https://www.bbc.com/amharic/news-46429666
ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ለረቡዕ ተቀጠሩ
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እስር ላይ ያሉት የቀድሞው የሜቴክ ዋና ስራ አስኪያጅ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውና ወንድማቸው ኢሳይያስ ዳኘው፣ የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ የደህንነት አቶ ተስፋየ ኡርጌ በዛሬው ዕለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
በዛሬው ፍርድ ቤት ውሎም ሌላኛው በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የቀረቡት አቶ አለም ፍፁም ሲሆኑ ሪቬራ ሆቴልን ዋጋውን ከፍ አድርጎ ለሜቴክ በመሸጥም ፖሊስ ክስ አቅርቦባቸዋል። የፖሊስ ክስ እንደሚያሳየውም ክፍት ባልሆነ ጨረታ ያላቸውን ግንኙነት ያላግባብ በመጠቀም ሆቴሉ ሊያወጣው ከሚችለው በላይ በ67 ሚሊዮን ብር ሸጠዋል ይላል። •ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከጠበቃቸው ጋር ፍርድ ቤት ቀረቡ •ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች •"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ አምስት ግለሰቦች በምስክርነትና፤ በተጠርጣሪውና በሜቴክ መካከል የነበረ ቃለጉባኤን እንደ ተጨማሪ መረጃነት ፖሊስ አቅርቧል። ፖሊስ ለተጨማሪ ምርምራ 14 ቀነ ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን፤ተጠርጣሪው መረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ እንዲሁም ከሐገር ውጭ ሊወጡ ይችላሉ በሚልም የዋስ መብታቸው እንዲከለከሉ ጠይቋል። አቶ አለም በቦሌ አካባቢ በግንባታ ላይ ያለ ባለ አራት ኮከብ ባለቤት ሲሆኑ ጠበቃቸውም የንግድ ሰው በመሆናቸውም ሊያዋጣቸው በሚችል መሸጥና መግዛት ይችላሉ በሚል ተከራክረዋል። ጠበቃቸው በተጨማሪ ፖሊስ እንደመረጃነት ያቀረበው ሰነዶች ከመሆናቸው አንፃር ተጨማሪ አስራ አራት ቀነ ቀጠሮ እንደማያስፈልግ ገልፀዋል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የአቶ አለምን ዋስ መብታቸውን በተመለከተ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ይዟል። በሌላ በኩል 14 ሚሊዮን ብር በህገወጥ መንገድ ከባንክ ሊያወጡ ነበር በሚል ፖሊስ የጠረጠራቸው አቶ ገመቹ ጫላ ላይ ፖሊስ ያለውን መረጃ አጠናቆ ነገ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ፍርድ ቤት አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ የሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘውና ወንድማቸው ኢሳይያስ ዳኘው ጉዳይን ለመመልከት ጊዜ ባለመኖሩ ለረቡዕ ህዳር 26 ቀጠሮ ይዟል። በሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ የተጠረጠሩት የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ አዲስ የሙስናና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክሶች ቀርበውባቸዋል። አቶ ተስፋየ ፖሊስ ላቀረበባቸው ክስ ምላሽ ለመስጠት ፍርድ ቤቱን የሁለት ቀናት ቀጠሮ በጠየቁት መሰረት ለረቡዕ ህዳር 26 ምላሻቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
news-47025318
https://www.bbc.com/amharic/news-47025318
'ለሼህ አላሙዲ መፈታት የጠቅላይ ሚንስትሩ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር'
በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና የሳዑዲ ዜግነት ያላቸው ቢሊየነሩ ሼህ ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ትናንት ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ከሪያድ ወደ ጅዳ በማቅናት ከቤተሰባቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
የሳዑዲ መንግሥት ያካሄደውን የፀረ-ሙስና ዘመቻን ተከትሎ ከበርካታ ንጉሣዊ ቤተሰቦች እና ከበርቴዎች ጋር ተይዘው ከ14 ወራት በላይ በእስር ያሳለፉት አላሙዲ እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለቢቢሲ ተናገረዋል። አቶ ተካ ''ትናንት (እሁድ) በስልክ ተገናኝተናል። ጤናቸው በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል'' ያሉ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ መቼ ሊመጡ ይችላሉ ተብለው ለተጠየቁት ''ወደ ኢትዮጵያ መምጣቸው አይቅርም፤ ነገር ግን መቼ እንደሚመጡ በእርግጠኝነት መናገር አልችልም'' ሲሉ የአላሙዲ ጠበቃ አቶ ተካ አስፋው ተናግረዋል። • አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ፍርድ ቤት ቀርበው ምን አሉ? ካለፈው ግንቦት 2009 ዓ.ም ጀምሮ አሊ-አላሙዲ ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደቆዩ የሚናገሩት አቶ ተካ ''ጠቅላይ ሚንስትራችን ከአንዴም ሁለቴ ቦታው ድረስ ተገኝተው ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድረገዋል። ከዚያም በኋላ በነበራቸው ግንኙነት ከፍተኛ ጥረት እንዳደረጉ ነው የምናውቀው። ለመፈታታቸው የእሳቸው ጥረት እንዳለበት ነው የተረዳነው'' ብለዋል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የፌስቡክ ገጽ የባላሃብቱን ከእስር መፈታት ይፋ ባደረገበት ጽሁፍ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ግንቦት 2010 ዓ.ም ሞሐመድ ሁሴን አሊ-አላሙዲ ከእስር ለማስፈታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን እና በቅርቡም ወደ አገራቸው ይመለሳሉ በማለት በሚሊኒያም አደራሽ ያደረጉትን ንግግር አስታውሷል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ጨምሮም አሊ-አላሙዲ በሰላም እንዲመለሱ መልካም ምኞታችንን አንገልጻለን በማለት አስፍሯል። ከ14 ወራት በፊት ከአላሙዲ ጋር በሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ከነበሩት መካከል ጥቂት የማይባሉ ከበርቴዎች መጠኑ በይፋ ያልተገለጸ ነገር ግን ካላቸው ሃብት ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ ለሳዑዲ መንግሥት ሰጥተው ከወራት በፊት ከእስር መውጣታቸው ይታወሳል። • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ ከዚህ አንጻር ሼህ አላሙዲንም ከእስር ለመፈታት ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለዋል ወይ ተብለው የተጠየቁት ጠበቃቸው አቶ ተካ ''ከፍለዋል ብዬ ለመናገር ይከብደኛል። የተፈቱበትን አኳኋን ዝርዝር ሁኔታ ሰለማላውቅ ይሄ ነው ብዬ መናገር አልችልም። እኔ ግን ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለዋል ብዬ አላምንም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን ለመፈታታቸው የማይናቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል'' ብለዋል። ጥቂት ስለሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ እንደ ፎርብስ መጽሔት ከሆነ ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከሳዑዲ ዜጋው አባታቸው እና ከኢትዮጵያዊት እናታቸው በደሴ ከተማ ነው የተወለዱት። ፎርብስ የአሊ አል-አሙዲን እድሜን 72 የሚያደርስ ሲሆን የሃብት ምንጫቸውን ሲገልጽ ''የነዳጅ ዘይት፣ የተለያዩ ምንጮች እና በእራሳ ጥረት'' ሲል ያስቀምጠዋል። የሳውዲ አረቢያ ዜግነት ያላቸው ሼህ ሞሃመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ቋሚ የመኖሪያ አድራሻቸው ጂዳ ሳዑዲ አረቢያ ሲሆን፤ መጋቢት 2017 በነበረው በፎርብስ የቱጃሮች ዝርዝር ውስጥ አሊ አል-አሙዲ የተጣራ 10.3 ቢሊዮን ዶላር ንብረት በስማቸው በማስመዝገብ ከዓለም 159 ደረጃ ላይ ተቀምጠው ነበር። ይሁን እንጂ ፎርብስ እአአ ማርች 2018 ላይ ሼህ ሞሃመድ ሁሴን አል-አሙዲን ሃብታቸው የትኛው እንደሆነ በትክክል ማጣራት አልቻልኩም በማለት ከቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ሰርዟቸዋል። • ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች የደርግ ሥርዓት ተወግዶ ኢህአዴግ አገሪቷን ከተቆጣጠረ በኋላ ወደ ትውልድ ሃገራቸው በመምጣት መዋዕለ ንዋያቸውን የፈሰሱት ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ፤ በኢትዮጵያ በተለያዩ የመዋዕለ ነዋይ ዘርፎች ተሰማርተው ግዙፍ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን የሚያካሂዱ በርካታ ኩባንያዎች አሏቸው። ሼህ ሙሐመድ የሐብት ምንጭ በዋነኛነት የነዳጅ ዘይት ይሁን እንጂ በማዕድን፣ በግብርና፣ በሆቴል፣ በግንባታ፣ በሪልስቴት፣ በሆስፒታል፣ በሥልጠናና ምርምር፣ በፋይናንስ እና በመሳሰሉት ዘርፎች በተለይ በአሜሪካ፣ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በስዊድን ተሰማርተው ይገኛሉ። ግለሰቡ በዓለም ዙሪያ ባሏቸው ኩባንያዎቻቸው ውስጥ ከ200 ሺ በላይ ለሆኑ ሠራተኞች ሥራ መፍጠር የቻሉ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ ተቋሞቻቸው ቁጥርም ከ70 በላይ መድረሱን በዚህም ከ40ሺ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የሥራ ዕድል ማስገኘታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ከውጪ ቋንቋዎች አረብኛ፣ እንግሊዝኛና ጣሊያንኛ ይናገራሉ። ከአገር ውስጥ ደግሞ አማርኛ እና ትግርኛ ቋንቋን አቀላጥፈው ይናገራሉ። አላሙዲ በስዊዲንና ሞሮኮ የነዳጅ ማጣሪያዎችን በመግዛትና ቅርንጫፎችን በመክፈት ሥራቸውን ከማስፋፋታቸው በፊት በኮንስትራክሽን (ሪልስቴት) ዘርፍ ተሰማርተው ነበር። በአሁኑ ወቅት በስዊድን ስመጥር ከሆኑ የውጪ ባለሃብቶች መካከል የሚጠቀሱም ናቸው። የንጉሣዊያን ቤተሰቦችና ቱጃሮች እስር ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ስለታሳሪዎቹ ማንነት ዝርዝር የሆነ ይፋዊ መግለጫ ባይሰጥም ከጥቅምት 26/2010 ዓ.ም ጀምሮ በሳዑዲ በሙስና ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት ልዑላን፣ ሚኒስትሮችንና የቀድሞ ሚኒስትሮችን እንዲሁም ሼህ ሙሐመድ አሊ አላሙዲንን ጨምሮ ነጋዴዎች ይገኙበት ነበር። በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው በሚገኙት ግዙፍ ተቋሞቻቸው ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቀጥረው የሚያሰሩት የባለጸጋው አላሙዲን መታሰር በተሰማበት ጊዜ በድርጅቶቻቸው ውስጥ ስጋትና ግራ መጋባትን አስከትሎ ነበር። • ሳዑዲ ሴቶች እንዳያሽከረክሩ ጥላ የነበረችውን እገዳ ልታነሳ ነው የባለሃብቱ ተቋማት ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ያላቸውን አስተዋጽኦ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲያወድስ የሚሰማው የኢትዮጵያ መንግሥትም፤ ግለሰቡ ድንገት መታሰር የተሰማውን ብዙም ሳይዘገይ ነበር ይፋ ያደረገው። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ኃይለማርያም ደሳለኝ ከግለሰቡ መታሰር ከቀናት በኋላ ስልጣናቸውን ከቋፍ ላይ አድርሶት ከነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር አያይዘው በሰጡበት መግለጫ ላይ መንግሥታቸው ጉዳዩን በተመለከተ እጁን አጣምሮ እንዳልተቀመጠ ገልጸው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለአላሙዲ የእስር ምክንያት ባይናገሩም ''ሳዑዲ አረቢያ ሉዓላዊ ሃገር ነች እኛ ጣልቃ መግባት አንችልም። በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ስለ ጉዳዩ ማጣራት እያካሄድን ነው" በማለት እስሩ በኢትዮጵያ ባላቸው ሥራ ላይ ምንም እንቅፋት እንደማይፈጥር መንግሥታቸው እምነቱ እነደሆነ ተነግረው ነበር። ከወራት በኋላ ኃይለማሪያምን ተክተው የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መንበር የተረከቡት ዐብይ አህመድም ወደ ሳዑዲ አረቢያ በተጓዙበት ወቅት ስለሼህ አላሙዲ ጉዳይ ከሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸውንና በቅርቡ ከእስር እንደሚወጡ ቃል እንደገቡላቸው ተናግረው ነበር። ቢሆንም እንደተባለው ግለሰቡ ከእስር ሳይወጡ ለወራት ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ቆይተው ባለፈው ሳምንት መረሻ ላይ ነው መለቀቃቸው የተሰማው። ቢሆንም ግን የሼህ አላሙዲን የቅርብ ሰዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለግለሰቡ መፈታት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሚና ከፍተኛ ነው። ከእስሩ ጀርባ ያሉ ጥርጣሬዎች በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የሳዑዲ አረቢያ ሃያላን ግለሰቦችን ወደ እስር ቤት ወደተቀየረው ቅንጡው የሪትዝ ካርልተን ሆቴል ያስገባቸው የእስር ዘመቻ ከተካሄደ በኋላ የሳዑዲ መንግሥት ባወጣው መግለጫ የፀረ ሙሳና እንቅስቃሴው ''ገና የመጀመሪያው'' ነው በማለት ቀጣይነት እንደሚኖረው ፍንጭ ሰጥቶ ነበር። ይህ እርምጃም የሳዑዲን የመንግሥት ከፍተኛ ስልጣን በቅርቡ የተቆናጠጡት ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን አዲሱን የፀረ-ሙስና ቡድን በመምራት በሃገሪቱ ሊያመጡ ላሰቡት ለውጥ ምን ያህል ስልጣን እንዳላቸውና ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ ያሳያል ተብሎ ነበር። የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም የፀረ-ሙስና ቡድኑን ተግባር ደግፈዋል። ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ''በልዑል አልጋ ወራሹ ላይ ትልቅ መተማመን አለኝ የሚሰሩትን ያውቃሉ'' ሲሉ አስቀምጠው ነበር። • በሳዑዲ 'አንድ ወንድ እኩል ይሆናል ሁለት ሴት' ሳዑዲ አረቢያን በቅርበት የሚያውቃት የቢቢሲው የደህንንት ዘጋቢ ፍራንክ ጋርድነር ከሙስና ጋር በተያያዘ በርካታ ቱጃሮች በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ወቅት "አሁን በሳዑዲ አረቢያ እየተካሄደ ያለውን ማወቅ እና የወደፊቱን መገመት እጅግ አስቸጋሪ ነው። በሳውዲ ከ85 ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ አይነት ለውጥ እየታየ ነው" ሲል ተናግሮ ነበር። "የልዑሎቹ፣ የሚንስትሮቹ አልያም የነጋዴዎቹን እስር ከሦስት ዓመት በፊት ሆኖ ማሰብ አይቻልም ነበር" የሚለው ፍራንክ የልዑል አልጋ ወራሸ ሞሐመድ ቢን ሳላህ ወደ ስልጣን መምጣት ሃገሪቱን ወደተለየ አቅጣጫ እየወሰደ ይገኛልም ብሏል። የዘመቻ እስሩ መካሄዱን ተከትሎ በታሳሪዎቹ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ገንዘብም ሆነ ንብረት እንዳይንቀሳቀስ እገዳ እንደተጣለ የሳዑዲ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ገልጾ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ዘመቻውን የሚያካሂደው የፀረ-ሙስና ቡድን በማንኛውም ግለሰብ ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣት እና የጉዞ እገዳ የመጣል ስልጣን ተሰጥቶት ስለነበር ከእስር ውጪ የሚገኙ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች በስጋት ውስጥ ከዓመት በላይ ቆይተዋል። የሙስና ምርመራውና እስሩ በሃገሪቱ ስር እየሰደደ የመጣውን ችግር ለመዋጋት የተጀመረ እንደሆነ ቢነገርም፤ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ዘመቻው በሳዑዲ ንጉሣዊያን ቤተሰቦች መካከል ባለ የፖለቲካ ሽኩቻ ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሰልማን ስልጣን ለመቆጣጠር የወሰዱት እርምጃ ነው ይላሉ። ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሰልማን ማናቸው? ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሰልማን ወላጅ አባታቸው እአአ 2015 ንጉሥ ከመሆናቸው በፊት የ33 ዓመቱ አልጋ ወራሽ ብዙዎች ዘንድ አይታወቁም ነበር። አባታቸው ንጉሥ ከሆኑ በኋላ ግን ሞሐመድ ቢን ሳላህ በነዳጅ ሃብቷ በበለጸገችው ሳውዲ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን ችለዋል። የአጎታቸው ልጅ የሆኑትን ሞሐመድ ቢን ናይፍን በመተካት ነበር ልዑል አልጋ ወራሽ ተደርገው የተሾሙት። ሞሐመድ ቢን ሰልማን እአአ ነሃሴ 1985 በሪያድ የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከኪንግ ሳዑድ ዩኒቨርሲቲ በህግ አግኝተዋል። በ2009 ዓ.ም የሪያድ አስተዳዳሪ ለነበሩት ወላጅ አባታችው ልዩ አማካሪ ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ ሞሐመድ ቢን ሰልማን በተለያዩ የሥራ ድርሻዎች የሳዑዲ አረቢያን መንግሥት አገልግለዋል። ሞሐመድ ቢን ሰልማን ወደ ስልጣን መምጣት የጀመሩት በ2013 በሚንስትር ማዕረግ ልዑል አልጋ ወራሽ ተብለው ከተሰመዩ በኋላ ነበር። • ኻሾግጂ የዓመቱ ምርጥ ሰው ዝርዝር ውስጥ ተካተተ ከዚያ በፊት የሞሐመድ ቢን ናይፍ አባት የሆኑት ናይፍ ቢን አብዱል አዚዝ መሞታቸውን ተከትሎ ሞሐመድ ቢን ሰልማን አልጋ ወራሽ ተብለው ተሰይመው ነበር። ሞሐመድ ቢን ሰልማን የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያ እርምጃቸው የነበረው እአአ በ2015 የየመን ፕሬዝዳንት በሁቲ አማጺያን ተገፍተው ሃገር ጥለው ከተሰደዱ በኋላ፤ ከሌሎች የአረብ ሃገራት ጋር በመሆን የጦርነት ዘመቻ የመን ላይ መክፍት ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ሞሐመድ ቢን ሰልማን ንጉስ ሰልማንን በመወከል በተለያዩ የዓለም ሃገራት ይፋዊ የሥራ ጉብኝቶችን አድርገዋል። በቻይናና በሩሲያን የጎበኙ ሲሆን በዋሺንግተንም ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኘተው መክረዋል።
47577005
https://www.bbc.com/amharic/47577005
«ጥቁሩ ሰንዱቅ» [BlackBox] ለምን ፈረንሳይ ተላከ?
ከእሑዱ አሳዛኝ የአየር መንገድ አደጋ ጋር በተያያዘ ጥቁሩ የመረጃ ሰንዱቅ ከሁለት ቀናት በኋላ መገኘቱ ይታወሳል። ትናንት ደግሞ ለምርመራ ወደ ፈረንሳይ መላኩ ተዘግቧል። ለመሆኑ ለምን ፈረንሳይ ተመረጠች? ለምን የጥቁር ሰንዱቁን መረጃ ለሌላ አገር አሳልፈን እንሰጣለን? ቦይንግ ለምን የመረጃ ሰንዱቁን ለመመርመር ፍላጎት አሳየ? የአብራሪዎች ሚና በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ምን ይመስላል? በነዚህ ቁልፍ ጥያቄዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ለሁለት ዐሥርታት አብራሪዎችን የማስተማር ልምድ ያላቸውን ካፒቴን አማረ ገብረሃናን አነጋግረናቸዋል። ካፒቴን አማረ በአየር ኃይል ከ26 ዓመት በላይ ሠርተዋል። በሲቪል አቪየሽን የፍላይት ሴፍቲ ዲፓርትመንትን ደግሞ በዳይሬክተርነት ለ14 ዓመት መርተዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ8ዓመት በበረራ ትምህርት ቤት አስተምረዋል። አሁን በአቢሲኒያ በረራ ምክትል ኃላፊ ናቸው።
ጥቁሩን የመረጃ ሰንዱቅ በተመለከተ ጥቁሩ ሰንዱቅ ሁለት ቅንጣት አለው። አንዱ ፍላይት ዳታ ሪኮርደር ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ኮክፒት ቮይስ ሪኮደር ነው። እነዚህ ሁለቱ በአደጋ ጊዜም ሆነ በሌላ ተፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ቁልፍ መረጃዎችን ይዘው የሚቆዩና አስፈላጊ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ደግሞ መረጃው ተገልብጦ ጥቅም ላይ ማዋል እንዲቻል ሆነው የተሠሩ ናቸው። ሁለቱ ቅንጣቶች የበረራን ጠቅላላ ሁኔታ መዝግበው ይይዛሉ። ለምሳሌ አውሮፕላኑ ምን ያህል ፓወር ሴቲንግ ላይ እንደነበረ፣የኢንጂኑ ፓራሜትሮች የት ላይ እንደነበሩ፣ እንዲሁም ጠቅላላ የፍላይት ኮንድሽኑ ማለትም የጄቱ ፍጥነት፣ ከፍታው፣ አቅጣጫው በምን ሁኔታ ላይ እንደነበረ በጠቅላላው ሰፋ ያለ መረጃን አጭቀው ይይዛሉ።እነዚህን መረጃ መዝጋቢዎች የ25 ሰዓት መረጃን የመመዝገብ አቅም አላቸው። ቮይስ ሪኮርደር ደግሞ በጋቢና ውስጥ በረዳቱና በአብራሪው እንዲሁም በሌሎች የአውሮፕላኑ ሠራተኞች መካከል የተደረገን ንግግር ቀድቶ የሚይዝ ቅንጣት ነው። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት ጥቁሩ ሰንዱቅ ለምን አይሰበርም? ቅርፊቱ መረጃውን መጠበቅ የሚችል ጥንካሬ እንዲኖረው ተደርጎ የተሠራ ነው። እሳትን ብቻ ብንመለከት ከ1ሺ ዲግሪ ሴንትግሬድ በላይ የእሳት ነበልባልን መቋቋም የሚችል ነው። ጂ-ፎርስ ለምሳሌ አውሮፕላኑ ሲከሰከስ መሬት በሚመታበት ጊዜ ከነበረው ፍጥነት ወደ ዜሮ ፍጥነት በሚመጣበት ጊዜ በዕቃው ላይ የሚያርፍ ሃይል አለ። ይህ ግራቪቴሽናል ፎርስ ይባላል። የጥቁሩ ሰንዱቅ የላይኛው ክፍል ግን ወደ 3ሺ አራት መቶ ጂ-ፎርስ መቋቋም የሚችል ነው። በተለይም እንዳሁኑ ዓይነት አደጋ ከበረራ ሠራተኞችም ሆነ ከተሳፋሪዎች መረጃ ማግኘት አዳጋች በሆነባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም ተዛማጅ መረጃ በማይገኝበት ደረጃ ብቸኛው የመረጃ ምንጭ ይኸው ሰንዱቅ ይሆናል። የአደጋ ምርመራ ለመጀመር ከፍተኛ ፍንጭ ይሰጣል። ይህ ነገር ሲገኝ እንደትልቅ ግኝት የሚቆጠረውም ለዚሁ ነው። የሰንዱቁ ክብደት ከባድ አይደለም። አንድ መሐከለኛ የመኪና ባትሪ ቢያክል ነው። ኾኖም ውስጡ ከባድና ውስብስብ የቴክኖሎጂ ውጤትን የያዘ ነው። በአውሮፕላኑ ውስጥ የት ነው የሚቀመጠው? ይህ እቃ የሚቀመጠው የአውሮፕላኑ ጭራ አካባቢ ነው። ያለ ምክንያት አይደለም። ብዙ ጊዜ አደጋ የደረሰበት እውሮፕላን ጭራው አካባቢ ደህና ይሆናል። ለዚያ ነው አንዳንድ ሰዎች የአውሮፕላኑ ጭራ አካባቢ መቀመጥ የሚመርጡት። ብዙውን ጊዜ ቶሎ የሚገኘው ለምንድነው? ልክ ፈንጂ ማምከኛ ፈንጂዎች ያሉበት ከባቢ ሲደርስ ምልክት እንደሚኖረው ሁሉ ይህም ሰንዱቅ በሆነ ራዲየስ በመሣሪያ ሲጠጉት አለሁ የሚል ምልክት ይልካል። ይህ ምልክት ለተወሰነ ጊዜ ያህል የሚቆይ ነው። ብላክ ቦክሱ በተለይ ውሀ ውስጥ ከወደቀ የራሱ ሲግናል ወይም ሴንሰር ባትሪው እስኪያልቅ ድረስ ምልክት ስለሚሰጥ የት እንዳለ ለማግኘት ይቻላል። የት ይፈተሽ የሚለው ለምን ያጨቃጭቃል? • ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል ይህ ማክስ-8 አውሮፕላን የቦንይንግ ሥሪት ነው። ምናልባትም አሜሪካን ሄዶ ቢመረመር የራሱ የሆነ ቅሬታ ሊፈጥር ይችላል። በትክክል መረጃ ሊደብቁ ይችላሉ የሚለው ስጋት መኖሩ አይቀርም። በመሠረቱ አቪየሽን ውስጥ የምትደብቀው ነገር መኖር የለበትም። ትክክለኛው መደረግ ያለበት ነገር አደጋው በምን ምክንያት ደረሰ የሚለውን አውቆ፣ አስፈላጊውን እርምጃ ቶሎ ወስዶ፣ መደረግ ያለበት ነገር ተደርጎ፣ ግራውን የተደረጉ አውሮፕላኖች ወደ ሥራ እንዲመለሱ፣ በመመረት ላይ ያሉትም ማድረግ ያለባቸውን እንዲተገበሩ ነው የሚፈለገው። ሆኖም በሁሉም ዘንድ ማለት ይቻላል ጥርጣሬ አይኖርም አይባልም። ሌሎች በጉዳዩ ላይ የተለያየ ፍላጎት ያላቸው አካላት አሉ። ቦይንግ ራሱን መከላከል የሚፈልግ ድርጅት ነው። ፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር በዚህ አውሮፕላን ሥሪት ላይ የነበረውን ነገር ብዙ ያውቃል። ለምን ቶሎ እርምጃ አልወሰደም በሚል የተለያዩ ትችቶች ሊደርሱበት እንደሚችሉ ያውቃል። ስለዚህ ራሴ ልመርምረው የሚል አካሄድ ሊኖር ይችላል። የኢትዯጵያ አየር መንገድም የራሱ ፍላጎቶች አሉት። ወደ መላምት ውስጥ ሳይገባ ቶሎ የችግሩ ምንጭ እንዲታወቅለት ይፈልጋል።በዚህ ምክንያት ነው፣ በዚያ ምክንያት ነው ፈረንሳይ የተላከው ለማለት ግን በቂ መረጃ የለኝም። ኢትዮጵያ ብላክቦክሱን ራሷ መመርመር አትችልም? እንደዚህ ዓይነት ፋሲሊቲ(የመመርመሪያ ግብአት) በተወሰነ ቦታ ነው እንጂ በሁሉም አየር መንገዶች ውስጥ አይገኝም። በርግጥ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደዚህ የሆነ ዳታ የሚያወጣበት መንገድ አይኖረውም ማለት አይቻልም። ኖርማል ኦፕሬሽን ላይ የሚጠቀምበት ነገር ይኖራል የሚል ግምት አለኝ። ከአደጋ ጋር በሚያያዝበት ጊዜ ግን ነገሩ ከበድ ይላል። ስለዚህ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ኢቲ የራሱ ፍላጎት አለው፤ ቦይንግ የራሱ ፍላጎት አለው፤ ተቆጣጣሪው የራሱ ፍላጎት አለው። በነዚህ ሁኔታዎች ታዲያ ከነዚህ የተለያየ ፍላጎት ካላቸው ቡድኖች ውጭ ሆኖ በገለልተኝነት ዳታውን እንዲመረመር ቢደረግ ጥሩ ነው የሚል አመለካከት ይኖራል። እና ቴክኖሎጂው እጅግ በጣም ውስብስብ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ዓይነቱን ነገር አደጋ ሲደርስ ብቻ አገልግሎት ላይ ለመዋል ቴክኖሎጂውን ማቆየት አዋጪ ላይሆን ይችላል። ምክንያቱም አደጋ ከስንት አንዴ ነው የሚደርሰው። በጣም በተደራጀ ሁኔታ የተወሰነ ቦታ ላይ ለዚያ በሰለጠኑ ሰዎች የሚተገበር ሲስተም ቢኖር የተሻለ ይሆናል ከሚል ግምት ይመስለኛል። ለአብራሪዎች የትኞቹ ሰዓታት ከባድ ናቸው? ማብረር ትልቅ የሥራ ጫና ያለበት ተግባር ነው ማለት ይቻላል። መረጃዎች እንደሚነግሩን በተለይ መነሳትና ማረፍ ላይ ጫናውም አደጋውም ይበረታል። ሁለቱም አብራሪዎች ጫና ውስጥ የሚገቡት በዚህ ጊዜ ነው። ከፍታ እየጨመረ በመጣ ቁጥርና የሚፈለገው ከፍታ ላይ ሲደርስ ግን አብራሪው በአመዛኙ የመቆጣጠር (ሞኒተሪንግ) ሥራ ነው የሚሠራው። በተለይም በነዚህ ዘመናዊ አውሮፕላኖች ጫናው ዝቅ ያለ ነው። አደጋውም ሥራውም የሚበዛው መነሳትና ማረፍ ላይ ነው። የአብራሪነት ሥልጠናውም የሚያተኩረተው በዚሁ ዙርያ ነው። የመጀመርያዎቹ ስድስት ደቂቃዎች ምን ይመስሉ ይሆን? ይህ አውሮፕላን ተነስቶ በ6 ደቂቃ ውስጥ ነው ችግር ውስጥ የገባው። ከመንደርደር (ቴክኦፍ) ጀምሮ ያቺ 6 ደቂቃ ምን ያህል ጫና እንደነበረ መገመት የሚያስቸግር አይደለም። እኔ ሳስበው አብራሪዎቹ በከፍተኛ ደረጃ ሲታገሉ እንደነበረ ይታየኛል። አንደኛ ገና ተንደርድሮ የመነሳት (ቴክ ኦፍ) ምዕራፍም አላጠናቀቁም። ሁለተኛ ይሄ ችግር ደረሰባቸው። እና ምን ያህል ፈታኝ ትግል ያደርጉ እንደነበረ መገመት ይቻላል። • ትጥቅ የፈቱ የኦነግ ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ ናቸው የረዳትና የዋና አብራሪ የሥራ ድርሻ ይለያያል? የሥራ ክፍፍል አለ። ዋናው አብራሪ [ፓይለት ፍላይንግ] እና እረዳቱ [ፓይለት ኖት ፍላይንግ] ብለን እንከፍላቸዋለን። ሁለቱም መቀናጀታቸው ነው ለተፈለገው ውጤት የሚያበቃቸው። አንዱ ያለአንዱ አይሆንም። ፓይለት ኢን ኮማንድ(ዋናው) ብዙ ጫና አለበት። ምክትሉም እንዲሁ። ረዳት አብራሪ ቁጥጥርን ጨምሮ የዋናውን ሥራ ይጋራል። በሁለቱ መሀል ከፍተኛ የሆነ ቅንጅት መኖር አለበት። በመነሳት ምዕራፍ ሁለቱም በጣም በሥራ ይጠመዳሉ። በዝርዝር የተከፋፈለ ሥራ አላቸው። የሁለቱን ሥራ በፐርሰንት ማስቀመጥ ያስቸግራል። በአጭሩ ማለት የምንችለው የስራ ድርሻቸው ተመጋጋቢ ነው። ዋናውና ረዳታ አብራሪው በሙሉ በረራ ሃላፊነት ሊቀያየሩ የሚችሉ ሲሆን ውሳኔ የሚያስተላልፈው ግን ዋናው ይሆናል። ረዳት አብራሪው ዋና አብራሪው ሲደክመው የሚመጣ ሰው አይደለም? አይደለም አይደለም። በፍጹም። ረዳቱን ፓይለት ዋናው ያዘዋል። በስራ ሃላፊነት ዝርዝራቸው መሠረት ነው የሚሠሩት። ረዳቱ ደግሞ ያ መሠራቱን ይነግረዋል። እንጂ ዋናው አብራሪ ሲበር ሌላው አብራሪ የሚተኛ አይደለም። በአውሮፕላኑ ጋቢና ከሁለቱ ሌላ ሰው ይኖራል? በአሁኑ ጊዜ የለም። ቀደም ሲል ፍላይት ኢንጂነር የሚባል ሦስተኛ ሰው ይገባ ነበር። የራሱ የሆነ የመቆጣጠር ሥራ ድርሻ ነበረው። ይህ ግን የመጀርመያ ትውልድ አውሮፕላኖች ላይ፣ እነ 727፣ 720፣ 707 የሚባሉት ላይ የነበረ ነው። አሁን ግን የሁለት ሰው ሚና ብቻ ነው ያለው። ሦስተኛው ሰው ቀርቷል። አብራሪዎች የጤና ምርመራ ለማድረግ ይገደዳሉ? ይሄማ ምኑ ይጠየቃል። አንድ አብራሪ በጤና ብቁ መሆን አለበት፤ለማብረር። ጤና መታወክ አንዱ የአደጋ መንስኤ ነዋ። ከበረራ በፊት ጤናቸው ይረረጋገጣል። እንደ ዕድሜአቸው ሁኔታ በ6 ወርም ፣ በዓመትም ፣ በሦስት ወርም ሙሉ ጤና ምርመራ ሊወስዱ ይችላሉ። ሜዲካል ሠርተፍኬት ከሌለ ማብረርም አይቻልም። ይሄ ሁሉም የሚያውቀው ነገር ነው። የአብራሪነት ፍቃድም አይታደስም። የተሟላ የጤና ሁኔታ ማረጋገጥ ማንም የማይሽረው ጉዳይ ነው።
news-45004240
https://www.bbc.com/amharic/news-45004240
አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው?
''አንበሳ እወዳለሁ ፤ የማልወድበት ምክንያት አይታየኝም''
ሪቻርድ ቱሬሬ እንስሳቱን ከእንበሳ ለመከላከል የሚያስችል ዘዴ ሲያፈልቅ ገና ታዳጊ ነበር። ''ላሞቼ ደህና ከሆኑና ከተጠበቁልኝ ከአንሰቦቹ ጋር ያለምንም ችግር መኖር እንችላለን።" ይህን ከአንድ የኬንያ ማሳይ እረኛ መስማት ያልተመለደ ነገር ነው። ዋነኛው ሥራቸው በማናቸውም መንገድ ቢሆን ላሞቻቸውን ከጥቃት መከላከል ነው። የ18 ዓመቱ ሪቻርድ ቱሬሬ ግን እንደማንኛውም የማሳይ እረኛ አይደለም። በወቅቱ ቤተሰቦቹ በአንድ ሳምንት ከ9 ያላነሱ ከብቶቻቸው በአንበሶች ተበልተውባቸው ስለነበር የ11 ዓመት ልጅ እያለ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ አንበሶችን ከከብቶች በረት የሚያባርር መብራት ፈጠረ። • የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች እያንዳንዱ ላም እስከ 1000 ዶላር ዋጋ ያሚያወጣ በመሆኑ ቤተሰቦቹ ኪሳራውን መቋቋም ተስኗቸው ነበር። ''በከብቶቻችን ላይ የሚፈጸሙት ጥቃቶች መጠነ ሰፊና በየቀኑ የሚያጋጥሙን ነበሩ" ይላሉ የሪቻርድ እናት ቬሮኒካ። ''ከመብራቶቹ በኋላ ግን ከአንበሶቹ ጋር ምንም ችግር አልገጠመንም።'' ሪቻርድ ይህንን ፈጠራውን ስኬታማ ለማድረግ የተወሰነ ጊዜ ፈጅቶበታል። በመጀመሪያ ሰው የሚመስሉ ቅርጾችን በአካባቢው ቢያቆምም አንበሶቹ ከቁብ ሳይቆጥሩት ቀሩ። በመቀጠል ደግሞ አንበሶቹ የእርባታውን የውስጥ ክፍል ማየት እንዳይችሉ ጥቁር መከለያ ቢሰራም የላሞቹን ጠረን ከማሽተት አላገዳቸውም። አንድ ቀን ግን የእጅ ባትሪ ይዞ በተንቀሳቀሰበት ምሽት አንበሶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማጥቃት ሳይመጡ ቀሩ። ሪቻርድም የእጅ ባትሪውን የሚንቀሳቀስ በማስመሰል ስላዘጋጀው ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አጥቶ ከመጠበቅ የገላገለውን 'ላየን ላይትስ' መብራትን ሰራ። አንበሶች በርካታ ከብቶችን ይገድላሉ ራስን ማስተማር "ነገሮችን በመሰባበር ነው ስለ ኤሌክትሮኒክስ መማር የጀመርኩት" ይላል ሪቻርድ። ''የእናቴን አዲስ ሬድዮ ሰብሬ በጣም ተናዳ ልትገድለኝ ደርሳ ነበር።'' በእያንዳንዱ ስሪት ላይ አዳዲስ ማሻሻያዎችን እያደረገ አሁን 'ላየን ላይትስ' በሪቻርድ ማህበረሰብና በሌሎች አካባቢዎች በ750 መኖሪያዎች ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። "ሰዎች እንዴት እንደሚሰሩ በውል ስለማያውቁ ብዙ ጊዜ መብራቶቹን ለመጠገን እጥራለሁ'' ብሏል ሪቻርድ። '' ራሳቸው ለመጠገን ጥረት ያደርጋሉ፤ ይህን ሳይ አሰራሩን አውቶማቲክ የማድረግ ሃሳብ አመነጨሁ። 'ላየን ላይትስ 2.0' ን ለመስራት 200 ዶላር ወይም 150 ፓውንድ ይፈጃል። ብዙ ጊዜ ከዚህ ወጪ ግማሹ መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረሰናይ ድርጅቶች ቀሪው ደግሞ በከብት አርቢዎቹ ይሸፈናል። ይህ ስሪት 16 የተለያዩ የመብራት አማራጮች አሉት። የሪቻርድ የመጨረሻው የተሻሻለ ፈጠራ በደመና ምክንያት የፀሐይ ኃይል አቅም ሲቀንስ ቤት ውስጥ የተሰራ ለቀናት የሚቆይ የነፋስ ማጦዣ አለው። ሪቻርድ ብዙ ጊዜ እራሱ እየሄደ መብራቶቹን መጠገን አለበት የላም ባንኮች ሪቻርድ የሚኖርበት ማህበረሰብ የሰዎችና የዱር እንስሳት ግጭት በተደጋጋሚ የሚከሰትበት ነው። በናይሮቢ ብሔራዊ ፓርክና በኪቴንጌላ ከተማ መካከል የሚገኘውን ''የማህበረሰቡ መሬት" ከፓርኩ የዱር እንስሳት የሚለየው አነስተኛ ወንዝ ብቻ ነው። ሁልጊዜ ማታ ማታ የዱር እንስሳትና የሜዳ አህያ ለምለም የግጦሽ መሬት ፍለጋ መሬታቸውን ያቋርጣሉ፤ አንበሶችም ወዲያው ይከተላሉ። ''አንበሶች ትልቅ ችግር ናቸው። ለእነርሱ ላሞችና በጎችን መግደል በጣም ቀላል ነው፤ በተለይ ደግሞ በማታ '' ይላሉ የማሳይ ማህበረሰብ ሰባኪና አርብቶ አደሩ ሬቨረንድ ካልቪን ታፓያ። "ሆኖም ላሞችና በጎች ለእኛ ባንኮቻችን ናቸው፤ ገንዘባችንን የምናከማቸው እነርሱ ጋር ነው።" ሪቻርድ እስካሁን ከመንግሥት ምንም ዓይነት የገንዘብ ድጋፍ ባያገኝም የእርሱ ፕሮጀክት የሀገሪቱን ብሄራዊ ፓርኮች ለሚያስተዳደረው የኬንያ የዱር እንስሳት አገልግሎት እገዛ እያደረገ እንደሆነ ያስባል። ድርጅቱ እንደሚለው ላለፉት አስር ዓመታት ኬንያ በየዓመቱ 100 አንበሶችን እያጣች ሲሆን አሁን በዱር 1700 የሚሆኑት ብቻ ቀርተዋል። ከእነዚህ ሞቶች መካከል የተወሰኑት በሰዎች ምክንያት የተከሰቱ ናቸው። የሪቻርድ ቱሬሬ ሃሳብ ዓለምን አዳርሷል በቀል በአውሮፓውያኑ 2012 ሁለት ሴት አንበሶችና ሁለት ደቦሎች በኪቴንጋ መኖሪያ ቤቶችን በመውረራቸው ግር ብለው በወጡባቸው ሰዎች ተገድለዋል ። የሪቻርድ 'ላየን ላይት' ልክ እንደርሱ ሁሉ ማህበረሰቡ ከብቶቹን እንዲከላከል እስካስቻለው ድረስ አንበሶችንም ከሰው ጥቃት ይታደጋቸዋል። ''ከአውሮፓውያኑ 2010 ጀምሮ ከበፊቱ ይልቅ ለበቀል ተብለው የሚፈጸሙ የአንበሶች ግድያ ተበራክቷል'' የዱር እንስሳት ባለሙያዋ የአፍሪካ ጥበቃ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ሉሲ ዋሩይነጊ አንደሚናገሩት። ''ለማሳዮችም ሆነ ለዱር እንስሳቱ የቀረው መሬት አነስተኛ በመሆኑ ከበፊቱ ይልቅ አሁን ተቀራርበዋል" "አሁን የተጎዱትን የሚደግፍ አማራጭ ስርዓት አልተዘረጋም፤ 'ላየን ላይትስ' እንደሞከረው በአንበሶችና በሰዎች መካከል የሚፈጠረውን ግጭት ለመከላከል እንኳ ጥረት አልተደረገም።" በ2014 የኬንያ መንግሥት በሰዎችና በዱር እንስሳት መካከል በሚፈጠር ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን የካሳ ተጠቃሚ የሚያደርግ ህግ አውጥቶ ነበር። ይሁንና በተግባር የሚካሱት ጥቂት ክስተቶች ብቻ በመሆናቸው አሁንም ጥያቄዎች እንደተከማቹ ናቸው። ''የእንስሳት፣ የንብረትና የሰብል ካሳን ሙሉ በሙሉ መፈጸም አልቻልንም ምክንያቱም ገና በፓርላማ ያልጸደቁ መመሪያዎች አሉ'' ብለዋል በናይሮቢ ብሔራዊ ፓርክ ያሉ የማሀበረሰብ ጠባቂ፡፡ ሪቻርድ ቤት ውስጥ ያገኛቸው የነበሩ የተወሰኑ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይገጣጥም የሪቻርድ የፈጠራ ሥራ በብዙ መልኩ ህይወቱን ቀይሮታል። በናይሮቢ በሚገኝ ስመ-ጥር ትምህርት ቤት በነጻ የመማር ዕድልም አስገኝቶለታል። ቻይናዊውን የአሊባባ መስራች ጃክ ማ እንዲያገኝው ተጋብዞ ለክብሩ የተዘጋጀውን ትምህርት ተከታትሏል። እርሱም በኬንያ ስመ-ጥር ሆኗል። እስከ አርጀንቲናና ህንድ ድረስ ያሉ ሌሎች ማህበረሰቦችም የእርሱን የፈጠራ ውጤት መሰረት አድርገው የተሰሩ መብራቶችን ይጠቀማሉ። ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋል የሪቻርድ ሃሳብ አድማስ ቢሻገርም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አንደ አንድ ወጣት የፈጠራ ሰው የሚደረግለት ድጋፍም ሆነ የ'ላየን ላይትስ' መብራት አፈጻጸም ቀንሷል። ኬንያ እንደእርሱ ላሉ ወጣት የፈጠራ ሰዎች ከዚህ የተሻለ ድጋፍ ማድረግ እንደምትችል ያምናል። "በኬንያ ከእኔም የተሻለ አስደናቂ ሃሳቦች ያሏቸው ብዙ ወጣቶች አሉ፤ የሚፈልጉት ድጋፍ ብቻ ነው'' ብሏል ሪቻርድ ። "ይህ ሃሳብ በጣም አሪፍ ነው፤ 'የኬንያን ብሎም የዓለምን ማህበረሰብ እንዲያግዝ እናሳድገው' የሚላቸው ሰው ይፈልጋሉ።" ሪቻርድ ቱሬሬ የፍየሎቹን ደህንነት መጠበቅ ይፈልጋል። ''እንደ'ላየን ላይትስ' ያሉ ፈጠራዎች ለኬንያ ብቻ አይደለም የሚያስፈልጉት" ይላሉ ሉሲ ዋሩይነጊ። "የሰብዓዊ ልማት በመላው ዓለም በፍጥነት እያደገ በመሆኑ መንግሥታት ከዱር አራዊት ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት የተገደዱ ማህበረሰቦቻቸውን ማገዝ አለባቸው።" "መንግሥታት የፈጠራ ሰዎች ተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉ ሃሳቦችን እንዲያካፍሉ መድረኮችን ማመቻቸት አለባቸው'' ሲሉ ያክላሉ። ''እነዚህን ሃሳቦች ወደ ንግድ ሥራ በማሳደግ እንደ ሪቻርድ ያሉ ሰዎች ማህበረሰባቸውን በመደጎም እነርሱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ።'' ሪቻርድ እንደ 'ላዮን ላይትስ' ፈጣሪነቱ በአግባቡ ተጠቃሚ ካልሆነባቸው ምክንያቶች መካከል፤ ምንም እንኳ በ15 ዓመቱ የኬንያ በዕድሜ ትንሹ የፈጠራ ባለቤት ቢሆንም ሃሳቡን በጊዜ አለማስመዝገቡ ነበር። ይህንን ስህተት በድጋሚ እንደማይሰራ ይናገራል፤ አሁንም በርከት ያሉ የፈጠራ ስራዎቹ በሂደት ላይ ናቸው። "ይህ ነው የምወደው ሥራ። ቴክኖሎጂ እወዳለሁ፤ እጆቼን መጠቀምና ተግባራዊ ሥራ ላይ መሳተፍም ያስደስተኛል፤ ወደፊት መራመድ እንድችል የሚያግዘኝም ይሄው ነው።" ይህ የአፍሪካ ዋነኛው የፈጠራ አካባቢ ይሆን?
47127328
https://www.bbc.com/amharic/47127328
ማህበራዊ መስተጋብር ያፈረጠመው የቤቲ ዋኖስ የኮሜዲ ህይወት
የሁለት ስም ባለቤት ናት፤ እንደ እርሷ አባባል ከሆነ የብርና የብዕር። ቤቲ ዋኖስ እንጀራዋን የምትጋግርበት መጠሪያዋ ሲሆን ቤቴልሄም ጌታቸው ደግሞ ወላጆቿ ያወጡላት፣ ሰነድ የያዘው መጠሪያዋ።
ቤቴልሄም ጌታቸው ገና አፍላ ሳለች የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሆና የሚኒ ሚዲያ ክበብ አባል እንደነበረች ታስታውሳለች። ያኔ "መጥፎ ጓደኛ" የሚል የእራሷን ድርሰት ፅፋ በልጆች ዓለም የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ማቅረቧን ትናገራለች። ቤቲ ድምጿ ወፍራም ስለሆነ በድርሰቱ ላይ ወንድ ሆና ነበር የተወነችው። ከዚያ በኋላ ደግሞ ፈርጥ የቲያትር ቡድን ውስጥ ከድምፃዊ አብነት አጎናፍር ወንድም ካሳሁን አሰፋ ጋር መተወን ጀመረች። መርካቶ - "አንድ ህልም ለ20 የሚታይበት ሰፈር" ቤቲ ልጅነቷን ስታስታውስ ተወልዳ ያደገችበት ሰፈርን አትረሳም። ለሙያዬ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል የምትለው ይህ ሰፈር ችምችም ያሉ ቤቶች የሚገኙበት፣ ማህበራዊ ህይወቱ የተሟሟቀ ነው። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን • ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ? • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ • “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ ከአዲስ አበባ የትኛውም አቅጣጫ ሰው ወደ መርካቶ ይፈሳል። ከሀገሪቱ የትኛውም አቅጣጫ ሰው ይጎርፋል። መርካቶ ሞላሁ አትልም፤ ሁሉንም ተቀብላ ማህበራዊ ህይወቷን አዛንቃ ለልጆቿ ታቀብላለች። እንደ ቤቲ ከሆነ ሕይወት በመርካቶ ፈዝዛ አታውቅም። ከነሙሉ ወዟ ትገማሸራለች። መርካቶ ለሐሜት አትመችም ትላለች ቤቴልሔም። ስሟን በክፉ ከማንሳት በጥበብ ማነሳሳት ይቀላታል። በዚች ትንሿ ኢትዮጵያ ድራማ ያልሆነ ነገር አይታያትም። ትራጀዲ ገጥሞት የሚንሰቀሰቅ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ፣ የሚያፍነከንክ ገጠመኝ ያለው የጎረቤት ልጅ በአውቶብስ ተራ አይጠፋም ባይ ናት። በመርካቶ ሕይወት ሚስቶ ናት ። የተለያዩ ክልል ሰዎችን አነጋገር ለመቅዳት፣ ኢትዮጵያን ሳይዞሩ ደጃፋቸው ድረስ መጥታ ለመመልከት መርካቶዎች የታደሉ መሆናቸውን ትመሰክራለች። ጥበብ ናት መርካቶ፣ ጥበበኞችም ሞልተውባታል የምትለው ቤቲ ዋኖስ ኮመዲን እንጀራዬ ያለችው ፕሮ ፕራይድ ውስጥ ነው። ፕሮ ፕራይድ የተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት የከተማ ድህነትን ለመቀነስና የፀረ ኤች ኤይቪ ስራዎችን ለመስራት መርካቶ ውስጥ እግሩን ሲያስገባ ቤቲ የባህል ቡድኑ አባል ሆና ተቀላቀለች። "ያኔ እኔም ደምሴም ብቻችንን ነበር የምንሰራው" ትላለች ቤቴልሄም። የሁለቱ ኮመዲያን ለየብቻ መስራት ግን ቡድኑን ያስተባብር ለነበረው ነብዩ ለሚባል ጓደኛቸው አልተዋጠለትም። ሁለቱ ቢጣመሩ አዲስ ነገር እንደሚሆንና ለእነርሱም የሙያ እድገት፣ ለተመልካቾችም አዲስ ነገር ማቅረብ እንደሆነ ተሰማው። እንዲጣመሩ ሀሳብ አቀረበ፤ ሀሳቡን ተቀበሉት። ዳቦ ባይቆረስም ዋኖሶቹ ተባሉ። "ዋኖስ የወፍ አይነት ናት ሌሎችን ወፎች የምታዝናና" ትላለች ቤቲ። በ1993 የአለም የኤድስ ቀን እንደ አዲስ አመት ነበር የሚከበረው ትላለች ጊዜውን ስታስታውስ። ትልልቅ ዝግጅቶች በየአዳራሹ፣ ድንኳኖች በየቀበሌው ተጥለው፣ ግድግዳዎች በተለያዩ ፖስተሮች አጊጠው፣ ቲሸርት፣ ኮፍያ ተዘጋጅቶ ሙዚቃ፣ ጭውውት እየቀረበ ይከበር ነበር። እርሷ ታዲያ ያኔ ፕሮፕራይድ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ከሽመልስ በቀለ ጋር መድረክ የመምራት እድል አገኘች። ሽመልስ አደነቃት። በፊትም የጥበብ ጥሪ አለኝ ብላ በየመድረኩ ላይ መክሊቷን ትፈልግ ነበር የዛን እለት አገኘችው። ኮመዲያን ቤቴሊሄም ጌታቸው በኮሜዲ አለም ስሟን ፃፈች። ቀጣዩ ስራ የተፃፈው ስሟ በጊዜ ድሪቶ እንዳይደበዝዝ ተግቶ መስራት ነው። ለዚህ ደግሞ የዋኖሶች አዲስ ጥምረት አገልግሏታል። የዋኖሶችን አዲስ ጥምረት በትርኢት መካከል መፈተን ሲፈልጉ ደግሞ ሜጋ የኪነጥበባት ማዕከል መድረክ አገኙ። 19 94 አ.ም የዘመን መለወጫ በዓል ምሽት ዋኖሶቹ አዲስ የኮመዲያን ጥንዶች ሆነው ብቅ አሉ። የአድማጭ ተመልካቹ ምላሽም የሞራል ስንቅ ሆኖ ለቀጣይ ጉዟቸው አገዛቸው። ያኔ የነበረውን ጊዜ ስታስታውስ "ቀልድ ይደገም ተብሎ አያቅም፤ ያኔ ግን ይደገም ሁሉ ተብሎ ደግመን አቅርበናል" ትላለች። ዋኖሶቹ፣ በዘመኑ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኮመዲያን አለባቸው ተካ በሚቀርበው አለቤ ሾው ላይ ሲቀርቡ ደግሞ መልካቸውም ስማቸውም በአድናቂዎቻቸው ትዝታ ውስጥ ታተመ። ሽመልስ በቀለም በትርኢቱ ላይ ካያት በኋላ መክሊቷን አውጥታ መጠቀም መጀመሯን አንስቶ አበረታታት። ይህ ማበረታቻ በስራዋ ብርቱ መሰረት እንደሆናት ትናገራለች። የዋኖሶቹ ጥምረት የኢትዮጵያ የጥበብ አድባር በታዳሚዎቹ ላይ የሳቅ ሸማ የሚደርቡ ከያኒያንን አብቅላለች። በየጭውውቱ፣ በየቴያትር መድረኩ ለተመልካች የሳቅ ቀለብ የሚሰፍሩ ባለሙያዎች አልጠፉም። እንግዳ ዘር ነጋ፣ በላይነሽ አመዴ፣ ዘነበች ጭራ ቀረሽ አፈሩን ያቅልላቸው ተብለው ጎልተው የሚጠቀሱ ጎምቱ ባለሙያዎች ናቸው። እነዚህን የጥበብ ባለሙያዎች ያበቀለች አድባር ግን ማህፀኗ ሴት ስታንዳፕ ኮመዲያን ያፈራ አይመስልም። የስታንዳፕ ኮመዲያኑ ዘርፍ የሴት ኮመዲያን ድርቅ የመታው ነው። ቤቲ "በርግጥ ኮመዲን በጭውውት መልክ የሚሰሩ ነበሩን። በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ እነ እንግዳዘር ነጋ የነበራቸው አስተዋፅኦ ቀላል አልነበረም። እነበላይነሽ አመዴ እነ ጭራ ቀረሽ በየትያትር መድረኩ ላይ ተክነውበት አፍነክንከውናል። ስታንዳፕ ኮመዲያን ግን አልነበረንም" ትላለች። እርሷ ከኮሜዲያን ደምሴ ጋር ተጣምራ ስትመጣ የመጀመሪያዋ ሴት ስታንዳፕ ኮመዲያን ሆነች። ደምሴና እርሷ ሲመጡ አዲስ ሆነው ጥምረታቸው ተወዳጅነት አፈራ። ሴት ስታንድ አፕ ኮመዲያን ባልተለመደበት ሀገር አይኖች ሁሉ ቤቲ ዋኖስ ላይ አረፉ። ይህ ጥምረት ግን ብዙ አልቆየም፤ ከሙያ አጋሯ ጋር ባለመግባባት ተቋጨ። ኩምድናና ሴትነት ቤቲ ከሙያ አጋሯ ጋር ከተለያየች በኋላ በየመድረኩ ደጋግመን አላየናትም። ምነው ተብላ ስትጠየቅ ልጅ መውለድና ማሳደግ ባተሌ አድርጓት እንደነበር ትገልፃለች። ከዚያ በኋላ ግን ትንንሽ ጸሐዮች የሬዲዮ ድራማ ላይ በመሳተፍና የራሷን ስራዎች በመስራት ላይ ትገኛለች። በሳቅ ገበታ ላይ ወንድ ኮሜዲያን ተሰብስበው የድርሻቸውን ሲቋደሱ ሴቶችን አለማየታችን ስለምን ነው? ብለን ጠይቀናል። ኮመዲ ለሴቶች ፈታኝ ነው የምትለው ቤቴልሄም አንዱ ልፋት መጠየቁ ነው ስትል ታስረዳለች። "ኮመዲን አቅልሎ ማየት፣ በዙሪያ ያሉ ወዳጆች፣ ጓደኞችና ቤተሰብ ስለሳቁ ሰፊውን ጀማ አስቃለሁ ብሎ መዘናጋት ሴትነት ላይ ሲታከልበት ፈታኝ ያደርገዋል።" ሌላው በመጀመሪያው መድረክ ሳይሳካ ሲቀር ደንግጦ መቅረት፣ ረዥም መንገድ ለመሄድ፣ መውደቅ መነሳቶችን ለማለፍ ቅስም ማጣት ሴት ኮመዲያንን እንዳናይ አድርጎናል ባይ ናት። ሴት በቤት ውስጥ፣ በማህበረሰቡ መካከል ጭምት እንድትሆን በሚፈለግበት ባህል ውስጥ ልል የሆነ ማህበራዊ መስተጋብር የሴት ኮሜዲያን ሌላ ፈተና ነው ስትልም ተጨማሪ ነጥቦችን ትዘረዝራለች። "እኔ ግርግር እወዳለሁ። መርካቶ እንኳን ባልሆን የራሴን መርካቶ በየሄድኩበት እፈጥራለሁ" የምትለው ቤቴልሄም የማህበራዊ መስተጋብርን አስፈላጊነት አጽንኦት ትሰጠዋለች። "ኮመዲ የጤፍ ዝናብ ነው" የምትለው ቤቲ "የጤፍ ዝናብ ሲወርድ ትንንሽ ነው፤ ምን ያህል እንደበሰበስክ የምታውቀው መድረሻህ ላይ ስትሆን ነው። ለኮመዲም የማህበራዊ ህይወት ግብዓት ጠንካራ ከሆነ ከህይወት ልምድና ከማህበራዊ መስተጋብር የሚቃረመው ትንንሽ ነገር በበቂ ሁኔታ ማቆሩ የሚታወቀው ከህዝብ ፊት ቀርቦ ምላሽ ሲገኝ ነው" ባይ ናት። ፈጠራ የሴት ኮመዲያን ጉልበት መሆን አለበት ስትል ኮሜዲያንነትን መክሊታቸው ለማድረግ ለሚፈልጉ ሴቶች ተጨማሪ ነጥቦችን ትጠቅሳለች። "ዓለምን ወንዶች ከሚያዩበት ውጪ ማየት፣ ነገሮችን በግልባጩ በመረዳት ከእያንዳንዱ የህይወት ዘለላ የሳቅ ቅንጣት መፈለግ ያስፈልጋል" ትላለች። ማህበረሰቡ ሴትን ፈጣጣ ናት ሲል ያሸማቅቃል የምትለው ቤቲ "አይናፋር ሆኖ ኩምድና ስለማይታሰብ፣ አንገትን ቀና አእምሮን ሰላ ማድረግ ለሴት ኮመዲያን አስፈላጊ ነው።" ሌላው ከሙያ አጋሮች የሚመጣ ግፊያን ጉሽሚያ መቋቋም እንደሚያስፈልግም ትመክራለች። ሴት አጋዥ እንጂ፣ ራሷን ችላ መድረክ ላይ እንድትቆም የማይፈልጉ የሙያ ባልደረቦች ሊገጥሙ እንደሚችሉ ታስታውሳለች። የኮሜዲያን ኑሮ እንደቀልድ ስለሚታይ ለየትኛውም ቁምነገር አለመታሰባቸው፣ እንደ ዋዛ፣ ፈዛዛ፣ ቧልት ወዳድ፣ መቆጠር ለሴቶች ይበልጥ ፈታኝ መሆኑንም ትጠቅሳለች። መውለድና የኮሜዲ ህይወት ከዚህ በፊት መስመር የለቀቁ ቀልዶች ከነበሩኝ ዛሬ ልጅ ኖሮኝ አላስባቸውም የምትለው ቤቲ ልጅ ኃላፊነትን ይዞ ይመጣል ስትል ከወለደች በኋላ በስራ ህይወቷ ላይ ያለውን ለውጥ ትናገራለች። የራስን ልጅ በማሰብ መስመሩን ያልሳተ ቀልድ ለማቅረብ እንደምትታገልም ስታስረዳ በዝግጅቷ ውስጥ ልጇን ማዕከል እንደምታደርግ ስታብራራ "ልጆች ራሳቸው የቀልድ አቀባዮች ይሆናሉ" በማለት ነው። ከልጇ ጋር ስትጫወት የኮመዲ ሀሳቦችን እንደምታገኝ የምትናገረው ቤቲ ዋኖስ ስራዎቿን ስታቀርብ መጀመሪያ ራሷ መሳቅ እንዳለባት በመቀጠል ጓደኞቿ ከዛም ለልጇ በማውራት ምላሻቸውን ለማግኘት እንደምትሞክር ትገልፃለች። ቤቲ ዋኖስ በዩ ቲዮብ የሚቀርብ የኮመዲ ስራ፣ የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ እና የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ለመስራት ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ነግራናለች።
news-53580506
https://www.bbc.com/amharic/news-53580506
የጉግል፣ የፌስቡክ የአፕልና የአማዞን ሥራ አስፈጻሚዎች ቃላቸው ሊሰጡ ነው
አራቱ የዓለም ግዙፍ ኩባንያ ባለቤቶችና ሊቃነ መናብርት በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ቀርበው ቃላቸውን ይሰጣሉ፣ ይመረመራሉ። ይህ የሚሆነው ነገ ረቡዕ በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ ነው።
ሰንዳር ፒቻይ፣ ማርክ ዙከርበርግ፣ ጄፍ ቤዞስ እና ቲም ኩክ ይህ በታሪክ ውስጥ ሆኖ የማያውቅ አጋጣሚ ነው። የፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ፣ የጎግል አለቃ ሰንዳር ፒቻይ፣ የአፕል ኩባንያ ሊቀመንበር ቲም ኩክ እና የአማዞን ኩባንያ ሊቀመንበርና መሥራች የዓለም ቁጥር አንድ ቢሊየነር ጄፍ ቤዞስ ናቸው፤ ምክር ቤት ቀርበው በጥያቄ የሚፋጠጡት። ከአራቱ ኃያላን መሀል ጄፍ ቤዞስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሲቀርብ ይህ የመጀመርያው ይሆናል። ሌሎቹ ከዚህ ቀደም ቢቀርቡም በአንድነት አብረው ለጥያቄ ሲጠሩ ግን ይህ በታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል። ምክር ቤቱ ግዙፎቹን ኩባንያዎች ለጥያቄ የጠራቸው ከሚገባው በላይ ግዙፍ መሆናቸውና ይህም ግዝፈታቸው ምናልባት ሊያስከትል የሚችለውን የንግድ ተወዳዳሪነት አለመኖር ጉዳት ለመገምገም ነው። ምርመራው በዚህ ወቅት እንዲጠራ ያደረገው አንዱ ምክንያት በርካታ የዓለም ንግድ እየተብረከረከ ባለበት ሰዓት እነዚህ ኩባንያዎች ግን ከዕለት ዕለት እያበጡ መምጣታቸው የፈጠረው ጥያቄ ነው። አራቱ ግዙፍ የዓለም ኩባንያዎች የሚያንቀሳቅሱት ሀብት ከ5 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይገመታል። በርካታ የንግድ ተቋማት በእነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች ላይ ቅሬታ አላቸው። ከእነዚህ መካከል የተወሰኑት ከነገ ጀምሮ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ይደመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቁጥር አንድ ቢሊየነሩ ጄፍ ቤዞስ ለምክር ቤቱ የሚያቀርበውን ንግግር ከወዲሁ በማኅበራዊ ሚዲያ አጋርቶታል። "ደንበኞቻችን ለምርቶች ያላቸው ፍቅር ለዚህ አብቅቶናል፤ ትልልቅ ተግባር እንድንፈጽም ያደረገንም ይኸው ነው። 10 ሰዎች እያለን ምን መስራት እንደምንችል አውቅ ነበር፣ አንድ ሺህ ስንሆን ከዚያም 10 ሺህ ስንሆን ምን ማድረግ እንደነበረብን አውቅ ነበር፤ አሁን ከሚሊዮን በላይ ስንሆን ደግሞ ምን ማድረግ እንዳለብን አውቃለሁ" ብሏል ቤዞስ ቀደም ብሎ ባሰፈረው የመግቢያ ንግግሩ። "አማዞን መመርመር እንዳለበት ይሰማኛል። ሁሉም ግዙፍ ተቋም ሊመረመር ይገባል። የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት ሊፈተሹ ይገባል። የእኛ ኃላፊነት እነዚህን መጠይቆች በአስተማማኝ ሁኔታ ማለፍ መቻል ይሆናል" ብሏል ቤዞስ። መውደቅ እስኪያቅታቸው ድረስ የገዘፉት ኩባንያዎች በእነዚህ ኩባንያዎች ላይ ከሚነሱ ቅሬታዎች አንዱ ኩባንያዎቹ አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን ኢንርኔቱን መቆጣጠራቸው ነው። መጫወቻ ሜዳው የእነርሱ መሆኑ ሌሎችን ለመጨፍለቅ ሳያስችላቸው አልቀረም። ይህን ግልጽ ለማድረግ ለምሳሌ አማዞን የሌሎችን ምርቶች በሚሸጥበት ድረገጽ የራሱን ምርት እያሞገሰ ያስተዋውቃል። ይህ በራስ ሜዳ እየተጫወቱ የጆተኒ በረኛን ገልብጦ ባለጋራ ላይ ጎል ማስቆጠር እንደማለት ነው። አፕልም ከዚህ ክስ አይድንም። አፕል ኩባንያ በእርሱ ምርቶች ላይ ለሚጫኑ ለምሳሌ ስልክ ላይ የመተግበሪያ ቋት (App Store) ሼልፍ ላይ ለሚደረደሩ መተግበሪያዎች ከሽያጫቸው 30 እጅ ይቆርጥባቸዋል። ይህም ለራስ ሲቆርሱ. . . የሚያሰኘው ነው። ገና ጀማሪ የሆኑ መተግበሪያ ፈጣሪዎች በአፕል ላይ ከሚያነሷቸው ቅሬታዎች አንዱ "የሰራነውን መተግበሪያ የት ወስደን እንሽጠው ታዲያ?" የሚል ነው። በዓለም ላይ ለዘመናዊ ስልኮች የስልክ መተግበሪያ መሰረት ልማት የሚያቀርቡት ጉግልና አፕል ናቸው። አፕል አይኦኤስ (iOS) ሲዘረጋ ጉግል በበኩሉ አንድሮይድ (Android) የስልክ መተግበሪያዎች መሰረተ ልማት ዘርግቷል። ይህ ማለት አዲስ መተግበሪያ ፈጣሪዎች ከሁለቱ ግዙፍ ኩባንያዎች ጋር ሊወዳደሩ የማይችሉበትን ሁኔታ ተፈጥሯል ማለት ነው። ይህ በሌላ ቋንቋ የሰፈሩን ኮብልስቶን ያነጠፍኩት እኔ ስለሆንኩ ወደዚህ ሰፈር የምትመጡ መንገደኞች ካልከፈላችሁኝ ክንፍ አውጥታችሁ ብረሩ እንጂ ኮብልስቶኔን አትርገጡ እንደማለት ይሆናል። ይህ የጉግልና የአፕል የገበያ ቁጥጥርን የሚያሳይ ምስስሎሽ ነው። ጉግል በበኩሉ ሰዎች አንድን ነገር ፍለጋ ድረገጹን በሚያስሱበት ወቅት ለራሱና ለአጋሮቹ ምርቶች ቅድሚያ በመስጠት፣ ተወዳዳሪ ማሰሻዎችን ጠቅልሎ በመግዛትና በመጨፍለቅ ሌሎች ተወዳዳሪ ኩባንያዎችን አክስሟል በሚል ይከሰሳል። ጉግል ከዚህ በፊት ለዚህ ድርጊቱም ቅጣት ተጥሎበትም ያውቃል። ጄፍ ቤዞስ፣ ቲም ኩክ፣ ማርክ ዙከርበርግ እና ሰንዳር ፒቻይ "ቅዳው፣ ግዛው ግደለው" አራቱ ግዙፍ የዓለማችን ኩባንያዎች ይከተሉታል የሚባለው ምስጢራዊ የንግድ ስልት በምክር ቤቱ ይነሳሉ ከሚባሉት ጥያቄዎች መካከል ይገኝበታል። ይህ የንግድ ስልት፣ "ቅዳ፣ ግዛ፣ ግደል" በሚል ይታወቃል። አዲስ ተወዳዳሪ ምርት ወደ ገበያ ሲመጣ ከተቻለ ተመሳሳዩን አገልግሎት የሚሰጥ ሌላ ተወዳዳሪ ምርት በማምጣት ማዳከም፣ ከዚያም ድርጅቱ ሲዳከም መግዛት፣ በመጨረሻም ከገበያ ማስወጣት እነዚህ አራቱ ድርጅቶች ሁልጊዜም ይከተሉታል ተብሎ የሚታሰብ ስልት ነው። ይህም ስልት ነው ያለተቀናቃኝ ዘወትር ትርፍ አጋባሽ ያደረጋቸው ይባላል። አራቱ ኩባንያዎች ማለትም ፌስቡክ፣ አማዞን፣ ጉግልና አፕል የሚወዳደሯቸውን ኩባንያዎች ቶሎ ጠቅልለው በመግዛት ይታወቃሉ። ይህ የተወዳዳሪነት ሕግን የሚጥስ አሰራር እንደሆነ ይነገራል። አንድ ድርጅት ወደ ሞኖፖሊ አሰራር ገብቷል የሚባለው አንድ ሸማች ለአገልግሎት ወይም ለምርት ለዚያ ኩባንያ የከፈለው ዋጋ አማራጭ በማጣቱ ለመክፈል ሲገደድ ነው። ይህ ወደ ሞኖፖሊ የመጠጋት ነገር በሌሎች ኩባንያዎች ላይ በቀላሉ ለይቶ መንቀስ እንደሚቻለው በቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ያን ማድረግ ከባድ ሆኗል። አንደኛው ምክንያት የጸረ ተወዳዳሪነት ሕጉ የማያሻማ ትርጉም አለመስጠቱ ነው። ይህም ሁኔታ አራቱን ድርጅቶች ለሕግ ለማቅረብ ፈተና ሆኖ ቆይቷል። ነጻ አገልግሎት በመስጠት ሸማችን መበዝበዝ ለምሳሌ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና ዋትስአፕ አገልግሎቶቻቸውን ለተግልጋይ የሚያቀርቡት በነጻ ነው። ነጻ በሆነ አገልግሎት ውስጥ የሞኖፖሊን ሕግ አንስቶ ክስ መመስረት ቀላል አይሆንም። አማዞን በበኩሉ ሌሎች ተወዳዳሪዎችን ለመዘረር በምርቶቹ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ያደርጋል። በራሱ ገጽ ላይ ምርታቸውን የሚሸጡት ይህን መቋቋም ይሳናቸዋል። ምክንያቱም አማዞን በሸጡት ምርት ልክ ትርፍ ስለሚጋራቸው ነው። ለምሳሌ የጉግል ነገረ-ማሰሻው (search engine) ነጻ ነው። ሌላው የጉግል ንብረት የሆነው ዩትዩብም እንዲሁ ነጻ አገልግሎት ነው የሚሰጠው። ለስልክ የሚሆኑ መተግበሪያዎችንም ከጉግል ለማውረድ ከሞላ ጎደል ነጻ ነው። ይህ ታዲያ ምን ችግር አለው ይሉ ይሆናል? ክርክሩም የሚነሳው ከዚሁ ነው። ተቺዎች እንደሚሉት እነዚህ ኩባንያዎች አገልግሎቱን ነጻ ያደረጉት ተወዳዳሪዎች ድርሽ እንዳይሉባቸው እንጂ ለጋስ ሆነው አይደለም። በነገው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ይኸው ጉዳይ ለአራቱ ኃያል ሊቃነ መናብር ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል። ከሸማች መብትና ከኢፍትሀዊ ውድድር ጋር ከተያያዙ ጥያቄዎች ባሻገር የፌስቡኩ ማርክ ዙከርበርግ የጥላቻ ንግግሮችን ከገጹ በቶሎ ለምን እንደማያነሳ ጥያቄ ይቀርብለታል ተብሎ ይጠበቃል። ፌስቡክ በተለያዩ አገራት የጥላቻ ንግግሮችን ቸል በማለቱ ፖለቲካዊ ጥፋቶች እየደረሱ እንደሆነ ይነገራል። የጆርጅ ፍሎይድን የግፍ ግድያ ተከትሎ ፌስቡክ በጥቁሮች ላይ ከነጭ አክራሪዎች የሚሰነዘሩ የጥላቻ ንግግሮችን ቶሎ ለማንሳት ዳተኛ መሆኑ ክፉኛ ሲያስተቸው ቆይቷል። የፌስቡክን ድርጊት ለመቃወም ግዙፍ ኩባንያዎች ማስታወቂያዎቻቸውን ከፌስቡክ ላይ ለማንሳት እስከመወሰን አድርሷቸዋል። በነገው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፊት የሚቆመው ማርክ ዙከርበርግ "ለመሆኑ የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ምን ለማድረግ አስበኻል?" የሚል ጥያቄ ይጠብቀዋል።
news-57109336
https://www.bbc.com/amharic/news-57109336
የአማኑኤል አባት፡ የልጄን አስክሬን እጁ ወደ ኋላ ታስሮ አደባባይ ላይ አየሁት
ከቀናት በፊት በደምቢ ዶሎ ከተማ በአባባይ በመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች የተገደለው ወጣት ወላጅ አባት፤ የልጃቸውን አስክሬን እጁ ወደ ኋላ ታስሮ አደባባይ ሆኖ ማየታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
የአማኑኤል አባት ልጃቸው ቤተ-ክርስቲያን ያደገ ዲያቆን ነበር ይላሉ። ሰኞ ግንቦት 2 ባለስልጣናት የአባ ቶርቤ አባል ነው ያሉት ወጣት በአባባይ መገደሉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የዓይን እማኞች አማኑኤል የተባለው ወጣት በአባባይ መገደሉን ሲናገሩ፤ የመንግሥት ባስልጣናት በበኩላቸው 'የአባ ቶርቤ' አባል ነው የሚሉት ወጣት በአደባባይ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ይላሉ። የወጣቱ ያለ ፍርድ ሂደት መገደሉ አሳሳቢ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ አውጥቷል። የወጣቱ ከፍርድ ውጭ መገደሉ እና በአደባባይ ለሕዝብ እንዲታይ የተደረገበት ሁኔታ በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶችን ያስቆጣ ጉዳይ ሆኖ አልፏል። የአማኑኤል አባት ምን ይላሉ? የአማኑኤል አባት አቶ ወንድሙ ከበደ የልጃቸውን መገደል ሳይሰሙ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ወደ መኖሪያ ቤታቸው መጥተው ፍተሻ ማድረጋቸውን ይናገራሉ። "ምንድነው የተፈጠረው ብዬ ስጠይቅ፤ 'የሆነውን አታውቅም?' ብለው ጠይቁኝ" ይላሉ። "አዎ አላውቅም ስላቸው 'የሆነው ታወቃለህ' አሉኝ" በማለት ይናገራሉ። የጸጥታ ኃይሎቹ መኖሪያ ቤታቸውን ከፈተሹ በኋላ እርሳቸውን እና ባለቤታቸውን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመኪና መሄድ መጀመራቸውን ይናገራሉ። "አደባባዩ ጋር ስንደርስ ባለቤቴ 'ልጄ ልጄ' እያለች መጮህ ጀመረች። 'ልጄ ነው ልጄ ነው' ስትል ወታደሮቹ 'አዎ ልጅሽ ነው' አሏት" አቶ ወንድሙ ከበደ የልጃቸውን አስክሬን አደባባይ ላይ ማየታቸው በእርሳቸው እና በባለቤታቸው ላይ ድንጋጤን እንደፈጠረ ይናገራሉ። "የልጄን አስክሬን እጁ ወደ ኋላ እንደታሰረ አየሁት" በማለት ይናገራሉ። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘዋቸው መሄዳቸውን ያስረዳሉ። ከዛም የልጃቸው አስክሬን ወዳለበት ስፍራ መልሰው እንደተወሰዱ ይናገራሉ። የልጃቸው አስክሬን ባለበት አደባባይ ከደረሱ በኋላ የአማኑኤል እናት ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው እንደነበረ ይናገራሉ። "እሷ እራሷን መቆጣጠር አልቻለችም። ትንከባለላለች፤ ትጮሃለች። በጣም እየጮኃች 'እኔንም ግደሉኝ' ስትል አትረብሹ ብለው ደበደቡን" ይላሉ። የአማኑኤል አባት የልጃቸውን አስክሬን ለማንሳት ስላልተፈቀደላቸው "ወደ ቤት ተመልሰን ማልቀስ ጀመርን" ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ያስረዳሉ። ከቆይታ በኋላ የአገር ሽማግሌዎች አስክሬኑን አንስተው ወደ መኖሪያ ቤት ካመጡላቸው በኋላ ቀብር መፈጸሙን ይናገራሉ። አማኑኤል ማን ነበር? የአማኑኤል አባት ልጃቸው የ17 ዓመት ወጣት እና የ10ኛ ክፍል ተማሪ እንደነበረ ይናገራሉ። ልጃቸው ላይ ስለ ቀረበው ክስ ምንም እንደማያወቁ የሚናገሩት አባት፤ ልጃቸውን ቤተ-ክርስቲያን ያደገ ዲያቆን ነበር ሲሉ ያስታውሱታል። ስለ አማኑኤል ግድያ የምናውቀው 'የአባ ቶርቤ' አባል ነው የተባለው አማኑኤል ሰኞ ግንቦት 2 2013 ዓ.ም. በደምቢ ዶሎ ከተማ በሚገኝ አደባባይ ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተገድሏል። ወጣቱ ከመገደሉ በፊት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚኒኬሽን ጸ/ቤት የፌስቡክ ገጽ ላይ ተለጥፎ ነበር። ኮሚኒኬሽን ቢሮው ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲል ጽፏል። ወጣቱ ከመገደሉ በፊት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ ይታያል። ቪዲዮን እየቀረጸ የሚገኘው ሰው የወጣቱን ስም እና የትውልድ ስፍራውን ይጠይቀዋል። አደባባይ ፊትለፊት የቆመው ወጣት ስሙ አማኑኤል ወንድሙ ከበደ እንደሚባል እና ትውልዱ ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። እጁ ወደ ኋላ የታሰረው ወጣት አንገቱ ላይ ሽጉጥ ተንጠልጥሎ ይታያል። በወጣቱ እግር ላይ እና በዙሪያው ደም የሚታይ ሲሆን ልብሱም በጭቃ ተለውሷል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። ወጣቱ ለምን ተገደለ? የከተማው ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ ይህ ወጣት የመንግሥት ባለስልጣናት በመግደል የሚታወቀው "አባ ቶርቤ' የተሰኘው ህቡዕ ቡድን አባል ነበር። ወጣቱ በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊትም ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር "በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከቀናት በፊት በደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔትዎርክ ጋዜጠኛ የነበረውን ሲሳይ ፊዳ የገደለው የአባ ቶርቤ ቡድን ነው ሲል አክሏል። የዓይን እማኝ ምን ይላሉ? የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅሰውወጣቱ በአደባባይ ሲገደል ማየታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አማኑኤል ሕዝብ የሚወደው ልጅ ነበር" ካሉ በኋላ፤ በጥይት ተመትቶ ከተያዘ በኋላ "ሲገደል በዓይናችን አይተናል" ብለዋል። እኚህ ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አካላት ወጣቱ ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ወጣቱ ከአንድ ሱቅ እቃ እየገዛ ነበር ይላሉ። ይህ ነዋሪ በአደባባይ ከተገደለው ወጣት በተጨማሪ በተመሳሳይ ቀን ሌሎች ሁለት ወጣቶች በጥይት ተመትተው ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ሌላ ስፍራ ስለመወሰዳቸው አውቃለሁ ብለዋል። የመንግሥት አካል ምን ይላል? የቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ ወጣቱ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ይላሉ። አቶ ተሰማ "ተጠርጣሪ አይደለም" በማለት የወጣቱን ወንጀለኛነት በማረጋገጥ የተወሰደው እርምጃ አግባብ ስለመሆኑ ይሞግታሉ። በተመሳሳይ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በክልሉ ህዝብን እያሸበሩ ነው የሚሏቸው አካላት ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ በአፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። "በከተሞች ሰውን እየገደሉ ህዝብን ማሸበር የነሱ የእለት ተእለት ተግባር ነው። እነሱ የሚያደርጉት መግደል ነው። ሰላምን ለማስከበር የሚሄደው ኃይል እነዚህ አካላትን አጋልጦ እርምጃ ወስዶ ሊቆጣጠር ይገባል የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ የተወሰደው እርምጃ የትኛውም አይነት ይሁን ህዝብን አሸብሮ፣ አስፈራርቶ እቆጣጠራለሁ የሚለው ኃይል ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።" ብለዋል። ግድያውን ተከትሎ ማን ምን አለ? አማኑኤል ፍርድ ሳይሰጠው በአደባባይ መገደሉ አሳሳቢ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ አውጥቷል።። በወንጀል ተጠርጥሯል የተባለው አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያና በአደባባይ ለሕዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ አሳስቦኛል ብሏል ኮሚሸኑ። በማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ግድያውን በመቀውም ለግድያው ተጠያቂ የሆኑ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ሲጠይቁ ነበር። ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ኮሚሽኑም ጠይቋል። አባ ቶርቤ ማነው? "አባ ቶርቤ" የኦሮምኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ባለ ሳምንት" ማለት ነው። ይህ ቡድን በኦሮሚያ የተለያዩ ስፍራዎች ታጥቆ ከሚንቀሳቀሰው በቅርቡ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ ከሚጠራው አካል ጋር ግንኙነት እንዳለው የክልሉ ባለስልጣናት ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሐመድ "አባ ቶርቤ ማለት የአሸባሪው ሸኔ የከተማው ክንፍ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በከተማ ደግሞ 'አባ ቶርቤ' እና 'ሶንሳ' ተብሎ የሚጠራ ቡድን አለው። እነዚህ ቡድኖች በተቻላቸው መጠን ግድያ በመፈጸም ሽብር ለመፍጠር የሚሞክሩ ናቸው ሲሉ ተናግረው ነበር። አቶ ጅብሪል መሐመድ እንደሚሉት የዚህ ቡድን አባላት ምንም አይነት የተለየ ስልጠናም ሆነ መሳሪያ የላቸውም። የሚጠቀሙት ስልት፤ ማህበረሰቡን በመምሰል፤ ለማምለጥ በሚያመቻቸው ቦታ በድንጋት አደጋ አድርሰው ይሰወራሉ" ብለው ነበር አቶ ጅብሪል።
news-55763866
https://www.bbc.com/amharic/news-55763866
የኮቪድ ክትባት ሽሚያ፡ ሀብታም አገሮች አፍሪካን ለምን ረሷት?
አፍሪካ ክትባቱን ለማግኘት ሳምንታት ወይም ወራት ልትጠብቅ ግድ ይላታል፡፡
ይህን ያሉት ለአፍሪካ ክትባቱን ለማስገኘት እየጣሩ ያሉ ድርጅቶች ናቸው፡፡ እስከአሁን 900 ሚሊዮን ጠብታ ተገኝቷል፡፡ ይህ የተገኘው ከተለያዩ አገራትና ለጋሾች በተደረገ ልገሳና ርብርብ ነው፡፡ 900 ሚሊዮን ጠብታ የአፍሪካን 30 ከመቶውን ለመከተብ እንኳ የሚበቃ አይደለም፡፡ የአፍሪካ ሕዝብ ብዛት አንድ ቢሊዮን ሦስት መቶ ሚሊዮን ደርሷል፤ አሁን፡፡ ይህን ያህል ሕዝብ ያላት አህጉር አፍሪካ በቂ ክትባት ሳታገኝ ታዲያ ሀብታም አገራት ግን ክትባቱን ከወዲሁ እየገዙ ማጠራቀም ይዘዋል፡፡ ክትባቱን ለመግዛት ስምምነት መፈረም የጀመሩት ገና ድሮ ነው፡፡ ክትባቱ ሳይፈለሰፍ፡፡ ተስፋ ሰጪ ምርምሮችን በተመለከቱ ቁጥር ቶሎ ብለው ያስፈርማሉ፡፡ ‹ቅድሚያ ለኔ› እያሉ፡፡ ይህም ማድረግ የማይችሉ የአፍሪካ አገራት እየተቁለጨለጩ ነው የቆዩት፡፡ ሀብታም አገራት ክትባቶቹ መመረት ሲጀምሩ እየገዙ ማጠራቀማቸው ብቻም ሳይሆን ለድሀ አገራት እጃቸውን ለመዘርጋት ዳተኞች ሆነዋል፡፡ በአጭሩ አፍሪካና ሌሎች የኢሲያ ድሀ አገራት ገሸሽ ተደርገዋል፡፡ ለአፍሪካ ክትባቱ እንዲርቅ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ ያልተቆራረጠ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት(Cold Chain) አለመኖር ነው፡፡ ያልተቆራረጠ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት ማለት አንድ ክትባት ከምርት ጀምሮ ለማጓጓዝ ወደ አውሮፕላን እስኪሄድ፣ በአውሮፕላን እስኪጫን፣ ከአውሮፕላን ሲራገፍ እና ለሕዝብ እስኪዳረስ መጋዘን ሲከማች ከመነሻ እስከ መድረሻ እጅግ ቀዝቃዛ በሆነ ቅዝቃዜ ብልቃጥ የማስቀመጥ ሂደት ነው፡፡ ክትባቶቹ የሚቀመጡበት የማቀዝቃዣ ዓይነት ውስብስብ መሆን የክትባት ሥርጭቱን ፈታኝ አድርጎታል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ስኬታማ የተባሉት ፋይዘርም ሞደርናም ከፍተኛ ማቀዝቀዣ የሚፈልጉ የክትባት ዓይነቶች ናቸው፡፡ ይህ ለአፍሪካ አገራት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል፡፡ አንድም ክትባቱ አልተገኘ፣ ሁለትም ማጓጓዣና ማስቀመጫም አልተበጀ፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ባለፈው ሳምንት ‹ዓለም የሞራል ልእልናዋ ላሽቋል፤ ለዚህ ስግብግብነት ዋጋ እየከፈሉ ያሉት ደግሞ በድሀ አገራት የሚኖሩት ናቸው› ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ይህን ያሉት ሀብታም አገራት ክትባቱን ከእቅፋቸው ለመልቀቅ ባለመፍቀዳቸው ነው፡፡ በዚህ ረገድ ዶ/ር ቴድሮስ ብቻም ሳይሆኑ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ፍትሐዊ ክፍፍል ይኑር ሲሉ ጥሪ እያሰሙ ነው፡፡ መድኃኒት ከተገኘ እስከዛሬ ድረስ በ49 አገራት 40 ሚሊዮን ጠብታዎች ተሰጥተዋል፡፡ በአፍሪካ ግን እስከዛሬ 25 ጠብታ ብቻ ነው የተሰጠው፡፡ ይህ ቁጥር በእርግጥም የድህነትን አስከፊ ገጽታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ስለዚህ ሀቅ ሲናገሩ፣ ‹‹…25 ሚሊዮን አላልኩም፣ 25ሺም አላልኩም፣ 25 ጠብታዎች ብቻ›› ሲሉ ነው ነገሩ እንዴት አሳሳቢ እንደሆነ የገለጹት፡፡ እስከአሁን ከዋና ዋናዎቹ የክትባት ዓይነቶች አንዳቸውም በአፍሪካ ምድር ለሰው አልተሰጡም፡፡ በአውሮፓ ግን የመጀመርያው ጠብታ ከ2 ወር በፊት ነው የተጀመረው፡፡ ይህ የሀብታምና ድሀ አገራትን ልዩነት እና የዓለም ሥርዓት አድሏዊነትን ፍንትው አድርጎ ያሳየ አጋጣሚ ነው፡፡ ሰልፍ እየጣሱ የሚገቡ አገራት ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አሊያንስ የሚባል አንድ የመብት ተቆርቋሪ ቡድን ባወጣው መረጃ የዓለምን ሕዝብ 14 ከመቶ ብቻ የሚሸፍኑ ሀብታም አገራት 53 ከመቶ የሚሆነውን ክትባት በእጃቸው አስገብተዋል፡፡ ይህ አሀዝ የ2012 የሞደርና ክትባት ምርትን እና 96 ከመቶ የሚሆነውን የፋይዘር ቀጣይ ወራት ምርትን ይጨምራል፡፡ በዚህ መረጃ መሰረት ካናዳ ከብልጹግ አገራት በመጀመርያ ረድፍ የምትገኝና ክትባቱን በገፍ የወሰደች አገር ናት፡፡ ካናዳ የሰበሰበችው የክትባት መጠን እያንዳንዱን ካናዳዊ 5 ጊዜ ደጋግሞ ለመከተብ የሚያስችል ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የብልጹግ አገራት ራስ ወዳድነት አፍሪካ ለሀብታም አገራት ሸቀጥ ማራገፍያነት ካልሆነ ውልብ የምትልባቸውም አትመስልም፡፡ ይህ ነገር በፈረንጆቹ 1990ዎቸ አካባቢ ለኤች አይቪ ኤድስ ታማሚዎች ዕድሜ ማራዘምያ በአሜሪካ መድኃኒት የተገኘ ወቅት የሆነውን የሚያስታውስ ነው፡፡ ያን ጊዜ አፍሪካ ምንም እንኳ አብዛኛዎቹ ታማሚዎች የሚገኙባት አህጉር የነበረች ቢሆንም መድኃኒቶቹን ለማግኘት ግን 6 ዓመታትን ወስዶባታል፡፡ ይህም የሆነው ሀብታም አገራት መድኃኒቱ ከሚያስፈልጋቸው በላይ ማጠራቀም ስለጀመሩ ነበር፡፡ ሌላው ምክንያት ደግሞ መድኃኒቱ የሚመረትበት ዋጋ ሰማይ መንካቱ ነው፡፡ በ10 ዓመት ውስጥ በአፍሪካ 12 ሚሊዮን ሰዎች ከኤች አይ ቪ ጋር በተያያዘ ሞተዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ መድኃኒቱ በወቅቱ ደርሶ ቢሆን ብዙዎችን ዕድሜ ማራዘም በተቻለ ነበር፡፡ መድኃኒቱ የደረሰው ግን ከ6 ዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ነበር፡፡ ዩኤን ኤይድስ ዳይሬክተር ዊኒ ቤያንዪማ ለኮቪድ ክትባት ፍትሐዊ ክፍፍል እንዲኖር ከሚታገሉት ሰዎች አንዱ ናቸው፡፡ ‹‹እኛ መድኃኒት አምራቾች ይክሰሩ አይደለም እያልን ያልነው፡፡ ልክ ዕድሜ ማራዘምያ በሕዝቦች የተባበረ ጥረት ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለው ይህንንም እንደዚያ እናድርግ ነው የምንለው›› ብለዋል ለቢቢሲ፡፡ ከኤች አይ ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ባደረጉት ከፍተኛ ግፊት አገሮች የዕድሜ ማራዘምያ እንዲመረት በመፍቀዳቸውና መድኃኒት አምራቾች ፍቃድ በመስጠታቸው ዋጋው ሊወርድ ችሏል፡፡ ለምሳሌ አንድ የዕድሜ ማራዘምያ መድኃኒት ለመግዛት የዓመት ወጪ መጀመርያ አካባቢ ከ10ሺህ ዶላር በላይ ነበር፡፡ በኋላ ነው ወደ 100 ዶላር ነው ዝቅ እንዲል የተደረገው፡፡ ዊኒ አሁንም የሚሉት ለኮቪድም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪው በትርፍ ብቻ እንዳይቅበዘበዝና ሰብአዊነት እንዲያስቀድም ነው እየጠየቁ ያሉት ዊኒ ቤያንዩማ፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ እንደተናገሩት አንዳንድ አገሮች ስለ እኩልነትና ፍትሐዊ ክፍፍል እያወሩም ራሳቸውን ያስቀድማሉ፡፡ ብልጹግ አገራትና ኩባንያዎች የሁለትዮሽ ስምምነቶቻቸውን ውስጥ ውስጡን ይፈራረማሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ለድሀ አገራት ክትባቱን ያደርሳል የተባለው ‹ኮቫክስ› ፕሮጀክት በአገሮችና በመድኃኒት አምራቾች ገሸሽ እየተደረገ ነው፡፡ ‹‹ወረፋ ሳይጠብቁ የሚገቡ አገሮች አሉ፤ መድኃኒት አምራቾች ደግሞ ዋጋ እየጫኑ ነው›› ሲሉ ወቅሰዋል ዶ/ር ቴድሮስ፡፡ በቫክሲን አሊያንስና የዓለም ጤና ድርጅት ጥምረት የሚሠራው ኮቫክስ ክትባቱን በፍትሐዊነት ለዓለም ለማድረስ የተቋቋመ ነበር፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት የክትባት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ሪቻርድ ሚጎ እንደተናገሩት ደግሞ አብዛኛዎቹ አገሮች ከመድኃኒት አምራቾች ጋር ስምምነት የተፈራረሙት መድኃኒቱ ገና ፈዋሽ መሆኑ ሳይረጋገጥና ወደ ምርት ሳይገባ ነው፡፡ ‹ለምን ኮቫክስ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ አልቻለም?› ተብለው በጋዜጠኞች የተጠየቁት ዶ/ር ሪቻርድ ገንዘብ ማፈላለግ የመጀመርያው ተግባሩ ስለነበረ ነው ብለዋል፡፡ እስካሁን ለድሀ አገራት ክትባቱን ለማድረስ እንዲቻል በኮቫክስ በኩል 6 ቢሊዮን ዶላር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ የሚያስፈልገው ገንዘብ ግን 8 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ በዚህ ገንዘብ 92 የሚሆኑ ድሀና መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገራትን ለማገዝ ታስቧል፡፡ እስከአሁን ለነዚህ 92 አገራት የሚሆን 2 ቢሊዮን ዶዝ ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን 600 ሚሊዮኑ ደግሞ ለአፍሪካ የሚደርሳት ነው፡፡ የአፍሪካ ኅብረት አባል አገራት ከአበዳሪዎች የተዘጋጀ 7 ቢሊየን ዶላር ፈንድ እንዲያመለክቱ መክሯል፡፡ ይህም 270 ሚሊዮን ጠብታዎች ለማግኘት ይረዳል፡፡ ለድሀ አገራት ፈተናው ክትባቱን ማግኘት ብቻ አይደለም፡፡ የማጓጓዙና ለክትባቱን የማከማቻ ምቹ ቦታ ማግኘት እጅግ ፈተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ ፋይዘር ክትባት 70 ዲግሪ ከዜሮ በታች በሆነ ማቀዝቀዣ ነው መቀመጥ ያለበት፡፡ ይህን ማሳካት ለየትኛውም ድሀ አገር እንደሚታሰበው ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ለጊዜው ዩኒሴፍ በኮቫክስ በኩል ይህን የማጓጓዙን ሥራ እንዲወጣ አደራ ተጥሎበታል፡፡ ዩኒሴፍ ወትሮ የልጆችን ክትባቶች በማዳረስ ነው የሚታወቀው፡፡ አሁን ያን ልምዱን ተጠቅሞ የዚህን የጉዞ መሠረተ ልማትና ግብአት (ሎጂስቲክ) በማጓጓዝ ከባድ አደራ የተሰጠው ሲሆን ይህም ከዚህ በፊት ካሳካቸው ሁሉ እጥፍ የሚሆን አቅሙን የሚጠይቅ ነው፡፡ ክትባቱ ለብልጹግ አገራት ፊት አልሰጠም፡፡ሰዎችን በሀብት ደረጃ አልለየም፡፡ አሜሪካ ምናልባት በሚቀጥለው ወር በተህዋሲው የሟቾች ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን ትደርሳለች፡፡ ይህ ይሆናል ያለ ማንም አልነበረም፡፡ አፍሪካ ክትባቱ ቢዘገይባትም ለጊዜው ሳይንስ ባልተረዳው መንገድ ክትባቱ የጨረሰባት ዜጋ ብዛት ግን ከተፈራው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ተፈጥሮ እያካካሰች ይሆን?
news-56474380
https://www.bbc.com/amharic/news-56474380
ቱርክ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ውስጥ ያላት ሚና ሲቃኝ
ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላት ግንኙነት መጠናከር ካለችበት ቀውስና እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ እየተፈጠሩ ካሉ ነገሮች ጋር ተያይዞ የተለያዩ አንድምታዎች እንዳሉት ተንታኞች እየተናገሩ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የቱርኩ አቻቸው ሜቭሉት ካቩሶግሉ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የቱርኩ አቻቸው ሜቭሉት ካቩሶግሉ በቱርክ ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውም "የተሳካ ተልዕኮ" በማለት ነበር አንድ ከፍተኛ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት የጠሩትት። ቱርክና ኢትዮጵያ ይፋዊ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 125ኛ ዓመት መታሰቢያን አስመልክቶ የተገናኙት ሁለቱ ባለስልጣናት በዋነኝነት አጀንዳ አድርገው የተወያዩት 'በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል በተከሰተው የድንበር ይገባኛል ውጥረትና የደኅንነት ትስስራቸውን በማጠናከር' ላይ እንደነ የቱርክ ዜና ወኪል አናዶሉ ዘግቧል። በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ማሰቧ 'ስልታዊ' [ስትራቴጂክ] እንደሆነ የሚገልጹት ተንታኞች፤ ይህም በአፍሪካ ውስጥ ምጣኔ ሀብታዊና ወታደራዊ ግንኙነቷን እያጠናከረች ያለችው ቱርክ ሁሌም በሚቀያየረው የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ውስጥ የኃይል ሚዛን መመጣጠን ልትፈጥር እንደምትችልም ያምናሉ። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ሚድል ኢስት ኢንስቲትዩት የቱርክ ጥናቶች ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ጎኑል ቶል እንደሚሉት ቱርክ በውጭ ያላትን ተጽእኖ ለማስፋት እየሰራች እንደሆነ ነው። በተለይም ከ2015 (እአአ) ጀምሮ ያወጣችውን ፖሊሲ ተከትሎ ይህ እንደሚስተዋል ያስረዳሉ። ቱርክና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና እንዳሉት አገራት ኢትዮጵያና ቱርክ ታሪካዊና ባህላዊ ግንኙነቶች አላቸው። ምንም እንኳን በወታደራዊው የደርግ ሥርዓት ወቅት ይህ ግንኙነት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በኢህአዴግ መራሹም ሆነ አሁን ባለው አስተዳደር ቱርክና ኢትዮጵያ መልካም የሚባል ግንኙነት አላቸው። ለረዥም ዘመናትም ግንኙነታቸው በአብዛኛው በምጣኔ ሀብቱ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው። ለምሳሌ ያህል ቱርክ በኢትዮጵያ ውስጥ ያፈሰሰችውን መዋዕለ ነዋይ ስንመለከት 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ይናገራሉ። ይፋዊ የሆኑ ሪፖርቶችንም በምናይበት ወቅት በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ንዋይ የምታፈሰው ቱርክ፣ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ደረጃ ከኃያሏ ቻይና ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የቱርክ ኩባንያዎች 20 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች አሏቸው። ይህም አሃዝ በአገሪቱ ውሰጥ ካሉ ግንባር ቀደም የግል ቀጣሪዎች መካከል እንደሚያስቀምጣት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ አስታውቋል። በቱርክ መዲና አንካራ የኢትዮጵያ አዲስ ኤምባሲ ህንፃ በሚመረቅበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሜቭሉት ካቩሶልጉ፤ ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የምታደርገውን ትግል አድናቆት ችረውታል እንዲሁም አገራቸው በዚህ ዘርፍ እንደምትተባበርም ቃል ገብተዋል። የሁለቱ አገራት ግንኙነት ለዘመናት በአብዛኛው በምጣኔ ሀብቱ ዘርፍ ላይ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም፤ በቅርቡ ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላትን ግንኙነት ደኅንነትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ እንዲሆን ፍላጎት መኖሩን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል። ቱርክ ከግብጽና ከሱዳን ጋር ያላት ግንኙነት በግብጽና በቱርክ መካከል ያለው ግንኙነት የሻከረ በሚመስልበት ሁኔታ የኢትዮጵያና የቱርክ ግንኙነት መጠናከር ዝም ብሎ የሚታይ እንዳልሆነ የዘርፉ ተንታኞች የሚናገሩት ነው። ለዓመታት ሊቋጭ ያልቻለው የህዳሴ ግድብ ድርድር የግብጽና ኢትዮጵያን ግንኙነት ውጥረት የነገሰ እንዲሆን አድርጎታል። "ግብጽና ቱርክ ቁልፍ በሚባሉ የምሥራቅ ሜዲትራንያን የጋዝ ሃብትን በተመለከተ ወይም ሊቢያ ጉዳይ እንዲሁም በቅርቡም በሱዳን ጉዳይ ላይ ተፃራሪ አቋም ነው ያላቸው" የሚሉት የአፍሪካ ቀንድ ተንታኙ አብዱራህማን ሰይድ ናቸው። ቱርክ ከሱዳን ጋር ያላትን ግንኙነት ስንመለከት ከአዲሱ የሱዳን አስተዳደር ጋር እየተቀየረ እንደሆነ አብዱራህማን ያስረዳሉ። የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር በስልጣን በነበሩበት ወቅት ቱርክ ከሱዳን ሱዋኪም የተባለችን ደሴት በሊዝ ተከራይታ ነበር። በቀይ ባሕር ላይ የምትገኘው ይህች ደሴት በቀጠናው ላይ ቁልፍና ስትራቴጂካዊ የምትባል ስፍራ ናት።'' "በሱዳንና በግብጽ እንዲሁም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው ግንኙነት እየተጠናከረ ይመስላል። ሁለቱ አገራት ደግሞ ቱርክን ክፉኛ የሚቃረን አቋም ነው ያላቸው። "ስለዚህም ቱርክ በሱዳን ላይ ያላትን ተፅእኖ በግብጽ ምክንያት እንዲሁም በተወሰነ መልኩ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ምክንያት አጥታዋለች" በማለት አብዱራህማን ያስረዳሉ። በተቃራኒው በእንግሊዝ ኪል ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የሕግ መምህር የሆኑት አወል አሎ (ዶ/ር) በበኩላቸው "ቱርክ አሁንም ቢሆን በሱዳን ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ማድረግ እንደምትችል" ይናገራሉ። አሁን ለምን? በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በሰሜናዊ ክፍሏ ትግራይ ውስጥ በፌደራል መንግሥቱና በክልሉን አስተዳድር መካከል በነበረው ግጭት ምክንያት የተከሰተውን ቀውስ ለመቆጣጠር እየጣረች ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከሱዳን ጋር የድንበር ይገባኛል ውዝግብንም ገጥሟታል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እያደረገች የነበረውን ወታደራዊ ዘመቻ የፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም ሱዳን በድንበር በኩል ሰፊ ግዛት እንደያዘች ተናግረዋል። ጨምረውም ሁለቱን አገራት የሚያወዛግበውን ይህንን ግዛት ለመቆጣጠርም ሱዳንን እየገፋት ያለው "ሦስተኛ ወገን" ነው ሲሉ ወንጅለዋል። "የሱዳን መንግሥት ወታደራዊ ክንፍ የጫረው ግጭት ለሱዳን ሕዝብ የማይጠቅምና የሦስተኛ ወገን ፍላጎትን የሚያስፈጽም ነው" በማለት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቶ ነበር። በሌላ ወገን ሱዳን በበኩሏ ባለው የድንበር ውዝግብ ውስጥ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፋለች በማለት ብትወነጅልም ኤርትራ በበኩሏ ይህንን አትቀበለውም። በርካታ ምዕራባውያን አገራት በትግራይ ክልል ያለው ግጭት ተዛምቶ ቀጠናዊ ቀውስ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን እየገለፁ ሲሆን፤ ለዚህ ደግሞ የወሳኝነቱን ቦታ የያዘችውና ቁልፍ ሚና መጫወት የምትችለው ሱዳን እንደሆነች ተንታኞች ይናገራሉ። ኢትዮጵያ በገጠሟት የተለያዩ ተግዳሮቶች ምክንያት የተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላትን ትኩረት ስባለች። ተንታኞቹ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ጠንካራ አጋሮች ያስፈልጓታል። አወል (ዶ/ር) እንደሚሉትም ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላት ግንኙነት "አገሪቷ በአሁኑ ወቅት ከምትጋፈጣቸው ችግሮች ጋር የተያያዘ" እንደሆነ ያስረዳሉ። ይህንንም ውሳኔ ስልታዊ [ስትራቴጂክ] እንደሆነም ይናገራሉ። "ቱርክና ግብፍ መልካም ግንኙነት የላቸውም። ኢትዮጵያ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሱዳን ላይ ጫና ማሳረፍ ትፈልጋለች" በማለት ያስረዳሉ። በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የድንበር ይገባኛል ውዝግብን ለመፍታት ቱርክ የማደራደሩን ሚና ብትጫወት ኢትዮጵያ እንደምትቀበለው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለቱርኩ ዜና ወኪል አናዶሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያና ቱርክ ግንኙነት ወታደራዊ መልክ ይኖረው ይሆን? ኢትዮጵያና ቱርክ በቅርቡ ምን አይነት ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል የሚለው ግልፅ አይደለም። አወል (ዶ/ር) እንደሚያምኑት የሁለቱ አገራት ወቅታዊ ግንኙነት "በጥቅም የተሳሳረ" መልክ ያለው እንደሚመስል ነው። ይህም ማለት ቱርክ በሱዳን ላይ ምን አይነት ጫና ታሳርፋለች ከሚለው ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችል ቢገልጹም ያ ለመሆኑ ግን ጥርጣሬ እንዳላቸው ጠቁመዋል። አብዱራህማን በበኩላቸው ከትግራይ ቀውስና ከሱዳን ጋር ካለው ውጥረት ጋር ተያይዞ ድጋፉ ወታደራዊ ሊሆን እንደሚችል ይገልፃሉ። "በአሁኑ ጊዜ ቱርክ ከኢትዮጵያ ብዙ የራቀች አይደለችም። ለዚህ ደግሞ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ውስጥ የጦር ሰፈርም አላት።" "ቱርክ ወታደራዊው ዘርፍ በተለይም ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕላኖችን) በማምረት በኩል ጠንካራ አገር ሆናለች" የሚሉት አብዱራህማን በቅርቡም በአዘርባጃንና በአርሜኒያ መካከል በተደረገው ግጭት የቱርክ ድሮኖችን ጥቅም ላይ መዋላቸው እንዴት የጦርነቱን ውጤት እንደቀየሩት እንደምሳሌ ይጠቅሳሉ። "በዚህ በኩልም የኢትዮጵያ ፍላጎት ሊኖር ይችላል" በማለትም ያስረዳሉ።
43665520
https://www.bbc.com/amharic/43665520
ለፍርድ የቀረቡ አፍሪካውያን መሪዎች
አርብ መጋቢት 28 ቀን 2010 ዓ.ም የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በሙስናና በሌሎች ተጨማሪ ክሶች ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
በተመሳሳይ የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ በዚሁ ቀን በቀረበባቸው የሙስና ክስ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በታዘዘው መሰረት እጃቸውን ለፖሊስ ሰጥተዋል። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እንዲሁም በአፍሪካ ስልጣን የለቀቁ መሪዎች ክስ እየተመሰረተባቸው ለፍርድ እየቀረቡ ነው።የቀድሞውን የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚን ጉዳይም ምሳሌ ማድረግ ይቻላል። የቀድሞ የደቡብ ኮሪያዋ ፕሬዝዳንት ፓርክ ጄውን ሃይም ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ችሎት ቀርበው 24 ዓመት እስር የተፈረደባቸው አርብ እለት ነበር። እስከ ዛሬ ተከሰው ከተፈረደባቸው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በተጠቀሱት ጊዜያት የተለያዩ አፍሪካ አገራትን ያስተዳደሩ መሪዎች በቀዳሚነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።
news-55036273
https://www.bbc.com/amharic/news-55036273
በሴት ፖለቲከኞች ጥምረት የምትመራው ስኬታማዋ ፊንላንድ ስትቃኝ
የዓለም አይን በሙሉ ወደ ፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትርና ጥምር መንግሥታቸው አዙሯል።
ፊንላንድ አምስት ፓርቲዎችን በያዘ በሴቶች ጥምር መንግሥትና በሴት ጠቅላይ ሚኒስትር የምትመራ አገር ናት። አምስቱም የፓርቲ አመራሮች ሴቶችና ወጣቶች ናቸው። የጥምር መንግሥቱ አመራሮች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ያሳዩት እርጋታ እንዲሁም ቁርጠኝነት ምስጋና ተችሯቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሳና ማሪን ከሚዲያዎች አፍ አትጠፋም፤ የግል ህይወቷም መወያያ ነው። የጫጉላ ጊዜዋን በአንድ ሳምንት ብቻ አቋርጣ ስትመጣና ወደ ሥራ ስትመለስ የአገር መሪ መሆን ቀላል አይደለም በሚል ውሳኔ ነበር። የቀድሞ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችና የ16 ዓመት የፍቅር ጓደኛዋን ያገባችው ነሐሴ ወር ላይ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ባለበት ወቅት ሠርግ መደገሳቸውም መደነቅን ፈጥሯል። ባለትዳሮቹ ኤማ የምትባል ልጅም አለቻቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ባለቤቷን ማርከስ ራይኮኔንን ከጎኗ ሻጥ ያደረገችበት የሠርግ ፎቶም እንዲሁም ከዚህ ቀደምም ኤማን ስታጠባ የሚያሳዩ ፎቶዎች በኢንስታግራም ገጿ ላይ ማጋራቷ የበርካታዎችን ቀልብ ስቧል። ባለትዳሮቹ ፈገግ ብለው፣ እጅ ለእጅ ተጠላልፈው ሄልሲንኪ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸውና በተንጣለለው ቪላ ላይም ይታያሉ። የፖለቲካ መፅሔት አዘጋጆች፣ የፋሽን ጦማሪዎች፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲያው በአጠቃላይ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ፎቷቸውን ተቀባበለውታል። ከሰሞኑ ደግሞ በርካታ ጋዜጠኞች የሬናይሰንስ ዘመን ሕንፃ በሆነው የፊንላንድ መንግሥት መቀመጫ ተሰባስበው ነበር። የጥምር መንግሥቱ የሚያካሂዱትን ስብሰባ ይጠብቃሉ። "መናገር የምፈልገውን ነገር ቀድሜ አላዘጋጅም" ትላለች ለቢቢሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ጋዜጠኞቹን እየተጠጋች። በሴት ጠባቂዎቿም ታጅባ "ስለ ማንኛውም ነገር መጠየቅ ይችላሉ። በአጭሩም እመልሳለሁ።" በዚህ ሳምንት ምናልባት ብዙው ጥያቄ የግል ህይወቷ ላይ ያነጣጠረ ይሆን? ቢቢሲ ጠቅላይ ሚኒስትሯን የጠየቃት ጥያቄ ነበር። "አይደለም። በአገሪቷ ውስጥ በርካታ ነገሮች እየተከናወኑ እንደመሆኑ መጠን ስለነሱ ጉዳዮች ማወቅ እንደሚፈልጉ እርግጠኛ ነኝ" በማለት አፅንኦት በመስጠት ከተናገረች በኋላ "መጨረሻ ላይ ምናልባት የግል ህይወቴ ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን ይጠይቁ ይሆናል" ብላለች። አንዳንዶቹ ሪፖርተሮች ጭምብላቸውን አጥልቀዋል። ትልልቅ ማይክራፎንም የያዙም ነበሩ። የተሰበሰቡትን ሪፖርተሮች ስትጠጋቸውም የሁሉም ቀልብ እሷ ላይ አተኮረ። ለስብሰባው ከሁሉም ቀድማ የደረሰችው የመጀመሪያ ፖለቲከኛ እሷ ነበረች። ልክ ብላለች የፊንላንድ ሚዲያ አገሪቷ ላይ ስላለሉት አንገብጋቢ ጉዳዮች ጥያቄዎችን ማዥጎድጎድ ጀመሩ። ከዚያም ወደ ስብሰባዋ አቀናች። አራት ሰዓታት ከፈጀው ስብሰባ በኋላም ለጋዜጠኞች ጥያቄዎች ለመመለስ ቆመች። ወደ ቤቷ ለመሄድም የመጨረሻዋ ፖለቲከኛ ነበረች። የጠቅላይ ሚኒስትሯ የመጀመሪያ ፎቶ በዓለም ዘንድ መነጋገሪያ የሆነው ሥራዋን 'ሀ' ብላ በጀመረችበት ወቅት በአውሮፓውያኑ ታኅሳስ 2019 ነበር። በወቅቱ የ34 ዓመቷ ጠቅላይ ሚኒስትር የግራ ዘመም ጥምር ፓርቲዋ መሪ ፖለቲከኞች ጋርም ፈገግ ብላ የተነሳችው ነው። ከአምስት ፓርቲዎች የተውጣጣው ጥምር ፓርቲ መሪዎች መካከል በወቅቱ እንደኛዋ ብቻ ናት ከ34 ዓመት በላይ የሆነችው። በምክር ቤቱ መድረክ ላይ ባደረገችው ንግግርም "የወጣቱ ትውልድ ተወካይ ነኝ" አለች። ዓለም አቀፉ ሚዲያም በፊንላንድ ላይ ማተኮሩን እንደ በጎ ተግባር እንደምትመለከተው ተናገረች። "ለቀሪው ዓለም ፊንላንዳውያን ምን አይነት ህዝቦች እንደሆን ለማሳወቅም እድል ይፈጥርልናል" አለች። በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በፖለቲከኞች ደረጃ ብቻ አይደለም እውቅናን ያተረፈችው። 'ሬጅ ኤጌይንስት ዘ ማሺን' የተባለው የአሜሪካ ሮክ ባንድ ጊታር ተጫዋች ቶም ሞሬሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን አድናቂያችን ናት በማለት የጥምር ፓርቲውን ፎቶ በኢንስታግራም ገፁ ላይ ለጠፈ። እሷም በምላሹ ያው እንደ ዘመኑ ፎቶውን በመውደድ (ላይክ በማድረግ) ያላትን አድናቆት ገለፀች። ሚዲያዎችም "ፌሚኒዝም የደረሰበትን ደረጃ በማወደስ፣ የፊንላንድ ፓርላማና የሥርዓተ ፆታ እኩልነት ፈር ቀዳጅ፣ ስንጠብቀው የነበረው የሴቶች አገዛዝ" በማለትም መፃፍ ጀመሩ። አንዳንዶችም ጥምሩን መንግሥት በማንቋሸሽ ፆተኛ በሆነ መንገድ አመራሮቹ ሳውና ውስጥ ገብተው ሲታጠቡ የሚያሳይ ምስል ይዘው የወጡ አልታጡም። ሆኖም ቀረም ፊንላንድ የፌሚኒስት "ዩቶፕያ"፣ ደሴት ናት ተባለች። ፊንላንድ ግን ሴት ዜጎቿን ከወንድ እኩል አድርጋ ማየትና እድል መስጠት የጀመረችው አሁን አይደለም። በዓለም ታሪክም ሴቶች እንዲመርጡም ሆነ በፓርላማ ድምፅ እንዲኖራቸውም ፈር ቀዳጅ ናት ፊንላንድ። በርካታ ምዕራባውያን አገራት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ቢሆንም ሴቶች እንዲመርጡ የፈቀዱት፤ ፊንላንድ ግን በአውሮፓውያኑ 1906 ነው። በቀጣዩም ዓመት 19 ሴቶች ለፓርላማ አባልነት ተመረጡ። በአውሮፓውያኑ 2000 የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንት ታርጃ ሃሎኔን መረጠች። ከሦስት ዓመታት በኋላ፣ በ2003 አኔሊ ጃቴንማኪ የመጀመሪያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆና ተመረጠች። ከዚያም በኋላ ሌላ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበራት ፊንላንድ በ2019ም በዕድሜ ትንሿ የሆነችውን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪንን መረጠች። ስልጣኑን የተቀበለችው ከጠቅላይ ሚኒስትር አንቲ ሪን ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፖስታ ቤት የተነሳውን የሥራ ማቆም አድማ መቆጣጠር ባለመቻሉም ነው እሷ የተመረጠችው። የግራ ዘመሙ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ በእድሜ ትንሽ የሆነችውን ማሪንን ይመርጣል ብሎ አልጠበቀም ነበር። ሳና ማሪን ቢቢሲ በዚህ ዓመት ተፅእኖ ፈጣሪ ብሎ ካካተታቸው 100 ሴቶች አንዷ ናት የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነው ብሎ ሲያውጅ በጠቅላይ ሚኒስትር ማሪን የሚመራው ምክር ቤቱ ለቫይረሱ ተዘጋጅቶ ነበር። ድርጅቱ ወረርሽኙን ባሳወቀ በቀናት ውስጥ ፊንላንድ ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴን ማገድ ብቻ ሳይሆን ለጦርነት የምትጠቀምበትን ድንገተኛ የተባለውን 'ኢመርጀንሲ ፓወርስ አክት' ተግባራዊ አደረገች። ይህንን መመሪያ አገሪቱ የተጠቀመችበት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ሲሆን ለሠራተኞች የሚከፈለውን ደመወዝ ጨምሮ፣ ተጨማሪ ሠራተኞችን በተለያዩ አገልግሎት ማሰማራትም ይገኝበታል። መመሪያው በተለያዩ ሚዲያዎች ቢወገዝም ሕዝቡ ግን ደግፎት ነበር። የፊንላንድ ዜጎች በቤታቸው እንዲወሰኑ፣ ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች እንዲመረመሩና ተከታታይ የበይነ መረብ ክትትሎችም ተጠናከሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪንና አራት ከፍተኛ የምክር ቤቱ አባላት በየሳምንቱ ስለ ኮሮናቫይረስ መግለጫ ይሰጣሉ፤ ከሚዲያም ሆነ ከዜጎች ጋር ውይይትና ጥያቄና መልስ ያካሂዳሉ። ከህፃናትም ጋር እንዲሁ። ከታይዋን፣ ጀርመንና ኒውዚላንድ መሪዎች ጋር በመደመር ተወደሰች። በዓለም ላይም ሴት መሪዎች የበለጠ ቀውሱን መቆጣጠር ችለዋልም የሚል ስም አሰጣቸው። 5.5 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ፊንላንድ በኮሮናቫይረስ የሞተባት ሰው ቁጥር 370 ብቻ ነው። መሪዋ እንደሚሉት መንግሥታቸው በሳይንስ የተመሰረተ መመሪያዎችን ከመጠቀም በተጨማሪ ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ያለው አመኔታና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መከተሉ ከዚህ ወረርሽኝ ለመውጣት እንደጠቀማቸውም ይናገራሉ። በሚዲያዎች ሲወቀስ የነበረው ኢመርጀንሲ አክት በሰኔ ወር ቢነሳም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የሴንተር ፓርቲ መሪ የ33 ዓመቷ ካትሪ ኩሉሙኑ ከስልጣን መልቀቋ አመራሩን በተወሰነ መልኩ አብረከረከው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከገንዘብ ቅሌት ጋር በተያያዘም ነበር የለቀቀችው። በእሷ ቦታ አኒካ ሳሪኮ ተተካች። ጥምር ፓርቲው በይፋ በሚያወጣቸው መግለጫዎች ስምምነት ላይ ያለ ቢመስልም በፓርቲዎቹ መካከል አለመግባባትም ነበር ተብሏል። በታዳጊነቷ ጠቅላይ ሚኒስትርነትም ሆነ በፖለቲካው እሳተፋለሁ የሚል የሩቅ ህልምም አልነበራትም። እንደ በርካታ ፊንላንዳውያን "አሳዛኝ የቤተሰብ ታሪክ ነው ያለኝ" በማለትም ከአራት ዓመት በፊት የግል ህይወቷን በፃፈችበት ጦማር ላይ አስፍራለች። በፊንላንድ ደቡብ ምዕራብ በምትገኝ ፒርካላ በምትባል ትንሽ መንደር ነው ያደገችው። ያደገችውም ከእናቷና ከእናቷ የህይወት አጋር ነው። ምንም እንኳን በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ቤተሰብ ውስጥ ማደጓ ነፃነትን ቢፈጥርላትም በከፍተኛ የገንዘብ ጫና ውስጥ እንደነበሩ ትናገራለች። በማደጎ ውስጥ ያደገችው እናቷ ከሰካራም ባለቤቷ፣ ከማሪን አባት ጋር መፋቷቷን ተከትሎም ከመንግሥት በሚሰጣት ድጎማ ነበር የምትኖረው። ሳና ማሪንም ቤተሰቡን ለመደገፍ ገና በልጅነቷ የሥራውን ዓለም ተቀላቀለች። በትምህርቷ ይህ ነው የሚባል አመርቂ ውጤትም አታሳይም ነበር። ፓሲ ኬርቪኔን የተባለች የሁለተኛ ደረጃ መምህሯም "መካከለኛ ተማሪ " ነበረች ብላለች። የፖለቲካ ህይወቷ የተጠነሰሰው በሃያዎቹ እድሜ ላይ እያለች ነው። የእሷንም ብቻ ሳይሆን በአካባቢዋ ያሉትንም መቀየር እንደሚቻል ተረዳች። ለጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን የእኩልነት ፕሮግራም መነሻው ይህ ነው። ቤተሰቦች ልጆቻቸውን የመንከባከብ ኃላፊነት በእኩልነት እንዲወጡ በፖሊሲ ደረጃ ማርቀቅ፣ የቤት ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል ከፍተኛ ቅጣት መጣል፣ በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን የክፍያ ልዩነት ማስቀረት እንዲሁም ከደሃና ስደተኛ ቤተሰቦች ለሚመጡ ህፃናት የትምህርት እድል መስጠት መንግሥቷ የሚጠቅስላት አመርቂ ሥራዎች ናቸው። እንዲሁም በፆታዊ ማንነት ጋርም በተያያዘ እኩልነት መስፈን አለበትም ትላለች። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በሰራችው ሥራ በሕዝቧ ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ተቀባይነት የጨመረ ቢሆንም ከዓለም አቀፉ ብላክ ላይቭስ ማተር እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ መንግሥቷ ትችቶችን አስተናግዷል። ምንም እንኳን በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያለውን ኢ-ፍትሃዊነት ለመቅረፍ መንግሥት ቢሰራም ጥቁሮች ላይ ያለውን ጫና ቦታ አልሰጠም በማለት ጥቁር ፊንላንዳውያን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ወቅሰዋል። በፊንላንድ ውስጥ ከሚኖሩ ጥቁሮች መካከል 63 በመቶ የሚሆኑት ተደጋጋሚ የዘረኝነት ጥቃት እንደሚደርስባቸውም የአውሮፓ ካውንስል ከሁለት አመታት በፊት ያወጣው ሪፖርት ያሳያል፤ ይህም በአውሮፓ ከፍተኛው ነው። በፊንላንድ ፓርላማም ውስጥ አንዲት ጥቁር ሴት ብቻ መሆኗ አገሪቷ ገና ከፍተኛ የቤት ሥራ እንደሚጠብቃት አሳይ ነው ተብሏል።
news-56206406
https://www.bbc.com/amharic/news-56206406
125ኛው የአድዋ ድል በዓል፡ አድዋን በሎሬት ፀጋዬና በእጅጋየሁ ሽባባው ሥራዎች ውስጥ
የዓድዋን ጦርነትና ድል በጥሞና ስንቃኝ፣ የእንባ ጤዛና የሳቅ ዜማ በትይዩ ያፏጩብናል፡፡ በአንድ አፋፍ ከረዥም ዓመታት በፊት በደም የተነከረ መስዋዕትነት፣በሌላው በቋያ እሳት ተፈትኖ አልፎ፣ዓለምን ያስደነቀና የነቀነቀ የድል ብስራት ወርቅ ሆኖ ሲወጣ በመንታነት ይከሰቱልናል፡፡
ስመ ገናናዋ የዓድዋ መዝሙር እናት እጅጋየሁ ሽባባው እንዲህ የተቀኘችው በከንቱ አይደለም፡፡ በኩራት፣በክብር፣በደስታ፣በፍቅር፣ በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፤ ደግሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን፡፡ ይህ ድብልቅልቅ ስሜት፣ረቂቅ ትውስታ ሁለት ገጽታ ያለው የሁሌ ትዝታ፣ መዝሙርና ሙሾ ነው፡፡ በጦርነቱ ዕለት እንኳ ከዚያ አስደናቂ ድል በኋላ በዐጼ ምኒልክ፣በራስ መኮንንና ሌሎችም ጀግኖች ፊትና ልብ ላይ የሚንቀዋለል ስሜት ነበር፡፡ ከዚያ አስደናቂ ድል በኋላ የወደቁት እነ ፊታውራሪ ገበየሁ አባገራውን የመሳሰሉ ጀግኖች ሞት ለጓዶቻቸው ሕመም ነበር፡፡…ሰው ከፍሎ፣ውድን ሰጥቶ ሌላ ውድ ነገር መቀበል ቀላል አልነበረም!! ጀግኖቻችን የዓለም ዕብሪተኛ በስላቅ ምላሱን አውጥቶ እንዳያላግጥብን፣ የተሳለልንን ቢላ ነጥቀው፣ ቀንበሩን ከጫንቃችን የሰበሩት በራሳቸው ደም ነው፤ የድል ዜና ያሰሙን፣ ገድሉን የፈጸሙትና በታሪካችን ላይ ዘውድ የደፉት ከጠላት ጋር ተናንቀው ደምና ላብ ከፍለው ነው፡፡ እናም ዛሬ ሲታሰቡን የማያረጁና በታሪካችን ገጾች የማይደበዝዙ ዝርግፍ ጌጦቻችን ሆነው ነው፤ ስለዚህ ሁሌም እንኮራባቸዋለን፡፡ ታዲያ ይህንን አንገት ቀና የሚያደርግ የነጻነት ተጋድሎ፣ ጭንጫ መሬት ላይ የወደቀ ዘር ሆኖ አልቀረም፡፡ ይልቅስ በከያኒዎቻችን ልብ በቅለውና አድገው፣ እሸት ሆነው፣ አብበው ፈክተዋል፤ በዜማ አጊጠው፣በጥበብ ተቀምመው፣ በልባችን በውብ ቀለም እንደ ጅረት ፈስሰዋል፡፡ ከነዚህ ድሉ ከወለዳቸው ከያንያን ውስጥ ስለ ዓድዋም ከፍ ባለ ጥበባዊ ቁመና፣ በሠፊ ምናብ ክንፍ ቅኝት የምናደንቃቸው ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረመድህንና እጅጋየሁ ሽባባው፣ ሌሎችም ወጣት ከያንያን አባቶቻችንን ከዘከሩበት ስራ በጥቂቱ መዳሰስ የወቅቱ ጥያቄና የኔም የዚህ ጽሑፍ ዓቢይ ጉዳይ ነው፡፡ በርግጥም ከታሪክ አንጻር የዓድዋን ድል ያህል ግዙፍና ለማንጸሪያነት የሚበቃ ሰማይ ጠቀስ ታሪክ፣ አሻራ ያለው ድንቅ የማይዳሰስ ሀውልት የለንም፡፡ ዓድዋ ዓለም ዐቀፍ ግርማ ያገኘ፣የታሪክ ሰነዶችን ያጣበበ የዓለማችን ታላቅ ገድል ነው፡፡ ሰለዚህም በየስፍራው በየሀገሩ ብዙ ተጽፎለታል፤ ብዙ ተዘምሯል፡፡ እኛ ጋ ሲመጣም በያመቱ፣አንዳንዴም በያጋጣሚው በጥበብ ሰዎች ብዕር ይዘመራል፡፡ ከወጣቶቹ የሆሄ ስነጽሑፍ ሽልማት የግጥም ዘርፍ የአንደኛው ዙር ተሸላሚ የሆነው ወጣት አበረ አያሌው ‹‹ፍርድ እና እርድ›› በሚለው መጽሐፉ፣ ስለ ዓድዋ እንዲህ ያለው ለዐለም ዐቀፋዊነቱ ክብር ይመስለኛል፡፡ አድዋ ሰፈር አይደለም-አድዋ መንደር አይደለም ሀገር ነው ከነታሪኩ-አህጉር ነው፣ሰ……ፊ ዓለም፡፡ እነምኒልክ ጦር ይዘው-ከመድፍ የተዋደቁ ጎራዴ መዘው የሮጡ-በጠብ-መንጃ አፍ ያለቁ ለጓጉለት ነፃነት -ደማቸውን ያፈሰሱ ለሰፈር ብቻ አይደለም-ያህጉር ድል አታንኳሱ፡፡ይላል፡፡ ይህ ግዝፈቱን ማሳያ ነው፡፡ ዓድዋ በርግጥም ሩቅ፣ ለምናብም ልጥጥ ነው፡፡ ነግረው አይጨርሱትም፤ አፍሰው በጎተራ አያኖሩትም፡፡ እንደ ዋርካ ባለ ብዙ ቅርንጫፍ፣ በእልፍ ቃል የማይገለጥ፣ከአእምሮ በላይ ነው፡፡ የአንዲት ደሃ ሀገር የገበሬ ጦር ዘመናዊ ስልጠና የወሰደ የአውሮፓዊት ሀገር ጦር አሸነፈ ማለት እንደ ተረት የሚቆጠር ነው፡፡…ግን በእውኑ ዓለም እውን ሆኖ ዓለምን አደናግሯል፡፡ ስለዚህ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ችቦ፣ የአሸናፊነት ማሳያ ፊልም፣ የማይጠበቅ ተዐምር ብንለው ያስኬዳል፡፡! ስመ ጥሩ ከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁንም ‹‹ጥቁር ሰው››ብሎ በሰየመው አልበም ስለ ምኒልክ ያቀነቀነው፣ ስለ ቀለሙ ሳይሆን ድንበር የለሽነቱን ለማሳየት ይመስለኛል፡፡ ዓድዋ ድንበር የሌለው ድል፣ ጥቁር ሕዝቦችን ከተኙበት ለነጻነት ያባነነ የማንቂያ ደወል ነው፡፡ በርግጥም ያለጥርጥር የዓድዋ ድል ጥቁር ሕዝቦች ለአምባገነን ነጮች "አንገዛም!" በሚል ቁጣ ማንነታቸውን በጦር ፍልሚያ የታደጉበትና ክብራቸውን ያስጠበቁበት ጦርነት የወለደው ተዐምራዊ ገድል ነው፡፡ ወጣት፣ ጎልማሳ፣ ሙስሊም ክርስቲያን ነጻነትን ከሕይወት በላይ የተረጎመበት ዓለም አቀፍ ሰነድ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ድል የኪነጥበቡ ቤት፣ የከያኒው ልብ ‹‹እንዴት ዘመረው? እንዴት ዘከረው?›› ብሎ መቃኘት ጠቃሚ በመሆኑ ነው እንዲህ የምናየው፡፡ ስለዚህም በዚህ የጥበብ ዓለም ቅኝት ዓይኖቻችንን ኩለን የታሪካችንን ሰነድ፣ የሰንደቃችንን ግርማ አጥርተን ልናይ እመኛለሁ፡፡ እናም ወደ መሙ ለመግባት በእጅጋየሁ ስንኞች እጀምራለሁ፡፡ የሰው ልጅ ክቡር፣ ሰው መሆን ክቡር ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፤ "ሰው" የሚለው ቃል ሁለንታዊ (Universal) ነው፡፡ ዓለምን ሁሉ የሚሞላ ሰፊ ማዕቀፍ ነው፤ "ሰው ክቡር" ስትል ደግሞ የሰው ክብሩ ከነጻነቱ ይጀምራል፡፡ በነጻነት መኖር ሰዋዊና ሕሊናዊ ነው፡፡ ይህ ሀሳብ የሚወስደን ቶማስ ጀፈርሰን ዋነኛ መርሁ ያደረገው የሰው ልጅ ነጻ ሆኖ የተፈጠረ ፍጡር ነው የሚለውን ጉዳይ አጽንዖት ወደ መስጠት ነው፤እኔም አባቶቼም፣ሌሎች ያገሬ ልጆችም በዚህ ስለምናምን ባርነትን እስከ ዛሬ ባርነትን አሻፈረኝ ብለናል፡፡ ዓድዋ የዚያ እምቢታ ማሳያና ውጤት ነው፡፡ በገሃድ እንደታየው፣ ለነጻነት ክብር ዓድዋ ላይ "ሰው"ን ሰው ለማድረግ ሰው ሞቷል፤ ለመንፈስ ልዕልና ሕይወቱን በጦር ሜዳ አፍስሷል፤ ደሙን ሜዳ ላይ ደፍቷል፡፡ አዎ፤በሞት ጥርስ ጫፍ ላይ የተንጠለጠለው የመጨረሻ ተስፋችንን፣ለማለምለም በቋፍ ላይ የነበረውን ሉዐላዊነታችንን ለማስከበር በጊዜው ቤዛ የሆኑልን አባቶች ሺህዎች ናቸው፡፡ እናም ዓድዋ ላይ አንዱ የሌላውን መስቀል ተሸክሞ አልፏል፤አንዱ ለሌላው ልዕልና ሞቷል፡፡ ወርቅ የሆነ ሰው በእሳት አልፎ፣ አፈር ሆኗል፤ ይህ ሁሉ ግን ሌሎችን ወርቅ አድርጎ ለማኖር ነው፡፡ እጅጋየሁ ሽባባው፣ የተሰጠኝ ሕይወት ዛሬ በነጻነት፣ ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት ትላለች! ጸጋዬ ገ/መድህን ደግሞ ‹‹እሳት ወይ አበባ›› በሚል መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይላል፤ ዓድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ የደም ትቢያ መቀነትዋ በሞት ከባርነት ስርየት በደም ለነጻነት ስለት አበው የተሰውብሽ ለት ይህም አንጓ ወደ ኋላና ወደፊት የሚያይ፣የሚያጠንጥን፣ ከመስዋዕትነቱ ሜዳ እስከ ነጻነቱ አፅናፍ የሚተርክ ነው፤ በዚህ አንጓ መስዋዕትነቱ መቆየቱን የሚያሳየው የፈሰሰው ደም ደርቆ ትቢያ ሆኖ፣ ከአፈር ጋር አፈር መሆኑ ነው፡፡ የደረቀው ደም ግን ተበትኖ አልቀረም፤መቀነት ሆኖ ኢትዮጵዊ አንድነታችንን አስጠብቆልናል፤ሕልውናችንን በታሪክ ዳንዳ ከፍ አድርጎ ሰቅሎታል፡፡ በደም ውስጥ ሕይወት አለ፤ሕይወት ለነጻነት ተከፍሏል፤ ለባርነት ስርየት ፈስሷል፡፡ ምሱን የተቀበለው የዓድዋ ምድር ርስትነቱ ፀንቷል፡፡ ቦታው ዓድዋ፣ኪዳኑ መስዋዕትነት ነው፡፡ ሰንደሉ ትውልድ ጤሶ እስከ ዛሬ በሀገርና በዓለም አድማሳት ይናኛል፡፡ "…ዛሬም ለእኛ የሽቱ ያህል መዓዛ፣ ለማይወዱን ደግሞ የሞት ያህል ክርፋት ሆኖ ይኖራል፡፡ አባቶቻችን ጠባሳው ሕመም እንዳይሆን፣ በድል የክብር ቀለም ቀብተው፣ከፍ አድርገው ሀውልቱን ከታሪክ ጋር ገምደውታል፡፡ ስለዚህም ከያንያኑ ደም ተከፍሎበታል !... ሰው ተከፍሎበታል!... ይሉናል! ያንን የደም ዋጋ፣ ያንን ታላቅ ተጋድሎ፣ ያንን እንደ ችቦ በታሪክ ውስጥ የሚነድድ ደም እጅጋየሁ ሽባባው እንዲህ ትገልጸዋለች፡፡ በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፤ በክብር ይሄዳል፤ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ፡፡ ዓድዋ ነፍስን ለሌሎች ነፍስ የመስጠት ተዐምር ነው፡፡ ይህንን የሚያደርግ ደግሞ የጀግና ልብ ሩቅ ተመልካች ዓይን ነው፡፡ የከበረች ምድሩን አሳልፎ የማይሰጥ፤ የነጻነቱ ትዕምርት የሆነው የባንዲራው ቀለም በልቡ የታተመ፤ ስለዚህ ሕልሙ ሀገሩ ፤ ክብሩም ነጻነቱ የሆነ፡፡ ስለ ወገኖቹ በቋያ እሳት አልፎ፤ ነበልባል ሆኖ ነድዶ ሲያበቃ ነበልባሉን በታሪክ አንገት ላይ የድል ጉንጉን አበባ አድርጎ ያጠለቀ፣የትዝታውን አመድ በታሪክ ገጾች ላይ ወርቃማ ቀለም አጥቅሶ ያሰፈረ፣ኩሩ ትውልድ መሆኑን ነግረውናል፡፡ ይህንን ደግሞ ሴቶች እናቶቻችን ሳይቀሩ በገቢር አሳይተውታል፡፡ በጦር ሜዳ ከተሰለፉት ሌላ ለቁስለኞች ውሃ በማቅረብ፣ቁስላቸውን በመጠገን፣አዝማሪዎቹ ጀግኖችን በማደፋፈር፣ ጀግንነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ሲጠቀለል የዓድዋ ጦርነት መነሻ ምንጩ "አትንኩን!" ነው፡፡ ‹‹አትንኩን›› ቢሆንማ ቤቱ ተቀምጦ ባልተነካ!... "አትንኩን!" ያለው ግን ትግራይ ያለው ወገኑ ሲነካ ስላመመው ነው፤ ሰሜኑ፣ደቡቡ፣ምስራቁ፣ምዕራቡ ሲነካ "አትንኩን!" ብሎ በቁጣ ቤቱን ጥሎ ወጥቷል፡፡ ይህ ውለታ ያልጠፋት ከያኒ እንዲህ ታቀነቅናለች፡- የተሰጠኝ ሕይወት ዛሬ በነጻነት፣ ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣ ስንት ወገን ወደቀ በነጻነት ምድር ትናገር ዓድዋ ትናገር ትመስክር! ትናገር ዓድዋ ትናገር አገሬ እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ፡፡ --በዘይቤ አሽቆጥቁጣ ዓድዋን ለእማኝነት ትጋብዛለች፡፡ በዛሬው የነጻነት ሰንደቅ ስር በሚፍለቀለቅ የነጻነት ዜማ፣ በሀገር አደባባዮች ላይ ለመቆም ትናንት የተከፈለ ውድ ዋጋ አለ፡፡ ዛሬ እሸት እሸት ለሚሸትተው ተስፋ ትናንት የከሰለ የወገን አጽም ነበር፡፡ በዚያ ዐውደ ውጊያ የብዙ ጀግኖች አጥንት እንደ ችቦ ነድዷል፤ያ የብርሃን ወጋገን ግን ዛሬ በጸና ስነልቡናዊ ማንነትና ክብር ሁላችንንም አቁሞናል፡፡ እጅጋየሁ ሽባባው ለዚህ ምስክሯ የዓይን እማኟ ዓድዋ ናት እያለችን ነው፡፡... ዓድዋ ተራራው -አድዋ - ሰማዩ ፣ ሰማዩን የሳመው የተራራው ከንፈር … ከውስጡ የሚመነጨው የትዝታ ገሞራ - ፊታውራሪ ገበየሁ - ገብቶ ሲነድድ - መዓዛው ለዛሬ ጣፋጭ- የነጻነት ዜማ … የባርነት ስርየት ነው:: የመትረየስ እሳት ምላስ ያነደደው ተራራ፣አፈሩን የዛቀው መድፍ ግራና ቀኙን የተጎሰመው ነጋሪት ድምጽ ያሸበረው ቁጥቋጦ የተሳከረውን ድብልቅልቅ ዋጋ፣ ስሌቱን የታሪክ ድርሳናት ብቻ ሳይሆኑ ዓድዋ ራሱ ይተርከው ብላለች፡፡ ከያኒዋ "ትናገር … ትናገር!; ያለችው በአጽንዖት ነው፡፡ ያኔ የነበረችው፣ ዛሬም በጉያዋ ስር ያንን ተዐምር ያቀፈችው እርሷ ናት!... የነደደ ፊቷ … የከሰለ ልቧ … ያንን ጠባሳ በእንባ እያጠቀሰ ሳይሆን በሳቅ እየፈካ ይናገረዋል!... እንባችንን አባቶቻችን አልቀሰው በሳቅ መንዝረው ሰጥተውናል! አፈር ሆነው ወርቅ አውርሰውናል! ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እንዲህ ይላል፤ ዓድዋ ሩቅዋ የአለት ምሶሶ አድማስ ጥግም ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ የማይፈርስ ምሶሶ አድርገዋት ያለፉት፣ የማይደረስበት አድማስ አድርገው ታሪኳን የጻፉት ኩሩ ትውልድ ነበሩ፡፡ እንደ ጧፍ የነደዱ የማይገሰሥ ክብር፣ የማይናድ ገድል ጽፈው ያለፉ!...እነዚህ ጀግኖች ግን በየአቅጣጫው የተመሙት ሞተው እናን በክብር ለማኖር ነው፡፡ እናም እጅጋየሁ ሽባባው ዓድዋን እንዲህ ታሞካሻታለች፤ ዓድዋ ዛሬ ናት ዓድዋ ትናንት መቼ ተረሱና የወዳደቁት ምስጋና ለእነሱ የዓድዋ ጀግኖች ለዛሬ ነጻነት ላበቁኝ ጀግኖች የጥቁር ድል አምባ ዓድዋ አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ ተናገሪ የድል ታሪክ አውሪ ስለ ዓድዋ በዜማ አቀንቅና አላበቃችም፤ስለ ዋነኞቹ ጀግኖች አውስታለች፤"ምስጋና!" ብላ የክብር ዘውድ ደፍታላቸዋለች፤አበባ ጉንጉን አጥልቃላቸዋለች፤ሻማ ለኩሳለች፡፡ የስንኟ ጅማሬ ከሰው ልጅ ጥቅም ተነስቶ ወደ ጥቁር ሕዝቦች ከዚያም ወደ አፍሪካ አፍንጫ ደርሷል፤ የድሉን አበባ እያሸተተች፣ ጀግኖች በነሰነሱት የነጻነት ጉዝጓዝ በክብር አዚማለች፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ - የጥቁር ሕዝቦች ከፍታ ችቦ ለኳሽ!... ጋሽ ጸጋዬም ዋ!... ዓድዋ ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል ማስቻል ያለው አባ መቻል በዳኘው ልብ በአባ መላው በገበየሁ በአባ ጎራው በአባ ናፍስ በአባ ቃኘው በለው ብሎ፤ በለው በለው ጸጋዬ ወደ ሽለላና ቀረርቶ ይሻገራል፤ጀግኖቹን በፈረሳቸው ስም እያደጋገመ በሽለላና ቀረርቶ ቃና - #በለው በለው!; ይላል፤ ያንን የትንቅንቅ ቀን፣ ያንን የመስዋዕትነት ምድጃ፣ ያንን ጀግኖች የጨሱበትን ደመራ ያወዛውዛል - ዓድዋ!... ዓድዋ የጀግኖች ቃል ኪዳን ውርስ! ወርቅ አፈር ሆኖ፣ወርቅ የተወለደበት ማሕጸን!! *ደራሲና ሃያሲ ደረጀ በላይነህ ከዚህ ቀደም ዘጠኝ የግጥም፣የወግ እና የልብ ወለድ ሥራዎች አሳትሟል። በተለያዩ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ላይ ሂሳዊ ዳሰሳ በማቅረብም ይታወቃል። በቅርቡም "ኂሳዊ ዳሰሳ" የተሰኘ የተለያዩ ስነ ጽሁፋዊ ሂሶችን የያዘ መጽሐፍ ለንባብ አብቅቷል።
42645132
https://www.bbc.com/amharic/42645132
'ለመጥፋት አደጋ የተጋለጠው' የኢትዮጵያ ህትመት ሚድያ
ነዋሪነቷን ኬንያ መዲና ናይሮቢ ያደረገችው አልባብ ሰይፉ ዘወትር ማለዳ ከመኖሪያ ቤቷ ወደ ሥራ ስታቀና አንድ ነገር ትታዘባለች። የትራፊክ መጨናነቅ የማይለያት ናይሮቢ ነዋሪዎች በህዝብ ትራንስፖርትም ሆነ በግል መኪናዎቻቸው ሆነው ጋዜጣ እያገላብጡ ሲጓዙ።
"ናይሮቢያዊያን ከጋዜጣ በሚያገኙት መረጃ ከወቅቱ ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እኩል ሲራመዱ ሳይ በጣም እቀናለሁ" ትላለች። በ1902 ዓ.ም. "አዕምሮ" የተሰኘችው ጋዜጣ መታተም ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያን እየተፈራረቁ የመሯት መንግሥታት በብዙሃን መገናኛ በተለይ ደግሞ በህትመት ሚድያ ላይ የራሳቸውን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳሳደሩ እሙን ነው። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል ኃላፊ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካው 'ኒው ሜክሲኮ' ዩኒቨርሲቲ በተጋባዥ ፕሮፌሰርነት የሚያገለግሉት ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ እንደሚሉት "የህትመት ሚድያ ከኢህአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ያህል አዎንታዊ ለውጥ ቢያስመዘግብም አሁን ላይ ግን 'ለአደጋ የተጋለጠ' ሆኗል።" ድህረ 97 ተከትለውት በመጡ ክስተቶች ዘወተር የሚወሳው የ1997ቱ ምርጫ በፕሬሱ ላይም ውጤቱ ጉልህ ነበረ። "ለእኔ ከ97ቱ ምርጫ በኋላ ያለው የህትመት ሚድያ የሞተ ነው" ሲል በቅርቡ ከእሥር የተለቀቀው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይናገራል። "ከምርጫው በኋላ በተለይ የግሉ ፕሬስ ከገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደርስበት ጫና እጅግ እያየለ በመምጣቱ በርካታ የግል ጋዜጦች ከጨዋታ ውጭ ሊሆኑ ችለዋል" ይላል። "ድህረ 97 መንግሥት የፀረ-ሽብር፣ የሲቪክ ማሕበረሰብ እንዲሁም የብዙሃን መገናኛን በተለመለከተ ባወጣቸው ህግጋት ብዙሃን መገናኛዎች ላይ ብርቱ ክንዱን ያሳረፈበት ጊዜ ነው" የሚሉት ደግሞ ዶክተር አብዲሳ ናቸው። "እነሆ ከዚያ ወቅት አንስቶ የግሉ ሚድያ በተለይ የህትመት ዘርፉ ማገገም አልቻለም።" ለአምስት ዓመታት ያክል በየወሩ ሲታተም የቆየውና የአስቸኳይ ጊዜ ዘዋጁ መባቻ ላይ የተቋረጠው 'የአዲስ ስታንዳርድ' መፅሄት መሥራችና ዋና አዘጋጅ የሆነችው ጋዜጠኛ ፀዳለ ለማ መሰል ህግጋት የህትመት ሚድያው እንዲዳከም የበኩላቸውን እንደተጫወቱ ትስማማለች። "ህግጋቱ ካሳደሩብን ጫና አንፃር አንዳድንድ ጊዜ የትኛውን አትመን የትኛውን እንደምንተው ሁሉ አናውቀውም ነበር" ትላለች። የቴክኖሎጂ ተፅዕኖ አንዳንዶች የቴክኖሎጂው ዕድገት ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም ሃገራት ለህትመት ሚድያ መዳከም ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ። "ሰዉ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በግል ስልኩና በኮምፒውተር በቂ መረጃ ማግኘቱ ለህትመት ሚድያ መቀዛቀዝ ምክንያት ነው ብዬ አላምንም" ትላለች አልባብ። "እስቲ ያለሁበትን የናይሮቢ ከተማ ሁኔታ እንመልከት. . .ኬንያ በቴክኖሎጂ በተለይ በኢንተርኔት አቅርቦት ከኛ በጣም የላቀች ብትሆንም አሁንም ድረስ ዜጎቿ ጋዜጣ ሲያነቡ አያለሁ" ባይ ነች። ጋዜጠኛ ፀዳለም ሆነ ተመስገን ደሣለኝ በአልባብ ሃሳብ ይስማማሉ። ሁለቱም የህትመት ሚድያው መዳከም ሰዉ ወደ በይነ-መረብ እንዲያጋድል አስገደደው እንጂ አሁንም የህትመት ውጤቶች አንባቢ ሞልቷል ይላሉ። 'የሆርን አፌይርሱ' ዳንኤል ብርሃነም ተመሳሳይ ሃሳብ አለው። "ሰው 'ከኦንላይን' የሚያገኘው መረጃ አርኪ ስለሆነ ነው ጋዜጦች እና መፅሔቶች ገዢ ያጡት ብዬ አላስብም። ሁኔታዎች ተመቻችተው የህትመት ውጤቶች አንጀት ላይ ጠብ የሚል ጉዳይ ይዘው ቢመጡ አንባቢ እንዳማያጡ እምነቴ ነው" ሲል ይደመጣል። "ይልቁንስ መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት አናሳ በመሆኑ የህትመት ሚድያ በኢትዮጵያ እጅግ ተዳክሟል" ይላል። "የፀረ ሽብር ህጉም በተወሰነ መልኩ ለዘርፉ መዳከም ሚና እንደተጫወተ አስባለሁ፣ ነገር ግን ህጉ አያስፈልግም ብዬ አላስብም" ሲል ይሞግታል። ራስን ጠልፎ መጣል ዶ/ር አብዲሳ የህትመት ሚድያ ዘርፍ አሁን ላጠላበት መቀዛቀዝ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶችን ይጠቅሳሉ። "ከውስጣዊው ምክንያቶች አንዱ ከጋዜጠኞች ይታይ የነበረው ሙያዊ ሥነ-ምግባር ጉድለት ነው። አዲሱን ሥርዓት ለመጋፈጥ በሚል የተወለደው የግሉ ሚድያ ጅምላ ወቀሳ፣ ግጭት ቀስቃሽና ስም አጥፊ የሆኑ ይዘቶች ይታዩበት ነበር። ይህ ሁኔታ የግል ሚድያውን ራሱን ጠልፎ እንዲጥል ከማገዙም በላይ መንግሥት ጡጫውን እንዲያበረታ መንገድ ከፍቷል።" "በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ላይ ሃገሪቱን የሚመራው መንግሥት የሚድያውን ባህርይ ባለመረዳቱ ምክንያት ዘርፉ እንዲያብብ ከማድረግ ይልቅ፤ በተቃራኒ እንደቆመ አካል ማየቱ ለህትመት ሚድያ ቁልቁለት መጓዝ እንደ ውጫዊ ምክንያት የሚጠቀስ ነው" ሲሉ ይተንትናሉ። ነገር ግን የግሉ ህትመት ዘርፍ ራሱን ጠልፎ ሲጥል ወይም ከሙያ ሥነ-ምግባር ፈቀቅ ሲል "መንግሥት ክንዱን ከማፈርጠም ይልቅ በሌሎች ሃገራትም እንደሚሆነው በፕሬስ ካውንስል እንዲዳኝ ቢደረግ የት በደረስን" ባይ ናት ፀዳለ። ተመስገንም ቢሆን "የህትመት ዘርፉ ከጥፋት የፀዳ ባይሆን እንኳ ይህ ለመንግሥት ጡጫ መበርታት ምክንያት ሊሆን አይገባም" ይላል። በ1999 ዓ.ም የተመሠረተው 'አዲስ ነገር' ጋዜጣ እስከ 30 ሺህ ኮፒ በመሸጥ በኢትዮጵያ የግል ህትመት ሚድያ ዘርፍ የጎላ እመርታ ማሳየት ከቻሉ ጋዜጣዎች አንዱ ነበር። ነገር ግን ከ2002 ምርጫ ጥቂት ወራት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ከታተመ በኋላ አዘጋጆቹ ከመንግሥት ጫና ደርሶብናል በማለት ጋዜጣው መዘጋቱንና 'ፍርደ ገምድልነትን' በመፍራት ከሃገር መሸሻቸውን አሳወቁ። በተመሳሳይ በርካታ አንባቢያን እንደነበሩት የሚታመነውና 'ፍትህ' ጋዜጣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈተ-ሕይወት ይፋ ከመሆኑ በፊት ሞታቸውን የተመለከተ ዜና በመሥራቱ ምክንያት ወደ 30 ሺህ የሚደርስ ዕትም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲቃጠል ከተደረገ በኋላ ከገበያ ውጭ እንደሆነ አዘጋጁ ተመስገን ደሳለኝ ያስታውሳል። ዕለታዊ አዲስ፣ ኢትኦጵ፣ ሞገድ፣ ልሳነ-ሕዝብ፣ ምኒልክ፣ ጦቢያ፣ ሳተናው፣ ነፃነት፣ አውራንባ ታይምስ፣ መብረቅ፣ ሰይፈ ነበልባል፣ ፍትህ፣ ፋክት፣ አዲስ ታይምስ፣ አዲስ ነገር. . . ከብዙ በጥቂቱ አንድ ሰሞን ብቅ ብለው የጠፉ የህትመት ውጤቶች ናቸው። ወደፊት. . .? ከእነዚህ የህትመት ውጤቶች በኋላ በኢትዮጵያ ይሄ ነው የሚባል በተለይ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚሠራና በግሉ ዘርፍ የሚተዳደር ጋዜጣም ሆነ መፅሔት አልተስተዋለም። ፎርቹን፣ ሪፖርተርና አዲስ አድማስን የመሳሰሉ ጋዜጦች በገበያው ላይ መቆየት ቢችሉም ጠንካራ የሚባል ፖለቲካዊ ዕይታ የሚንፀባርቅባቸው ግን አይደሉም ስትል ፀዳለ ትሞግታለች። አዲስ ስታንዳርድ በአሁኑ ወቅት በድረ-ገፅ ይዘቱን የሚያሰራጭ ሲሆን "ሁኔታው ቢመቻችልን ወደ ህትመት የማንመልስበት ምንም ምክንያት የለም" ትላለች ዋና አዘጋጇ። "መንግሥት በመጀመሪያ ደረጃ ዘርፉን ጠፍረው የያዙትን ህግጋት ማሻሻል አለበት። ጋዜጠኞች የሽብር ወንጀል በመፈፀም ከተጠረጠሩ ግለሰቦች እኩል የሚዳኙበት ሃገር ላይ ነው ያለነው። ከዚያም አልፎ መንግሥት ራሱን በሚድያ ፉክክር ውስጥ ማስገባቱ ሌላኛው ትልቅ ፈተና ነው።" እንደ ዶ/ር አብዲሳ ከሆነ "ለመንግሥት 'ብዝሃነት' ማለት ከብሔር ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ብዝሃነት ከአስተሳሰብና ፍልስፍና ጋር ትልቅ ቁርኝት ያለው ነገር ነው። ሚድያውን እንደ ባላጋራ ከማየት ይልቅ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ማገዝ አስፈላጊ ነው።" ስለዚህ መንግሥት የግሉን ህትመት ሚድያ አላንቀሳቅስ ያሉትን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እንቅፋቶችን ለማስወገድ ያለው ዝግጁነትና የሃሳብ ልዩነትን ለማስተናገድ ፈቃደኛ መሆኑን ማሳየት የብዙዎች ጥያቄ ነው። "መቼ ይሆን የሃገሬ ሰዎች እንደልባቸው ጋዜጣ እያገላበጡ ወደ የፊናቸው ሲያመሩ የማየው?" ብላ የምትጠይቀው ደግሞ አልባብ ናት።
news-47849680
https://www.bbc.com/amharic/news-47849680
በሰሜን ሸዋ ዞኖች የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዘ
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት መግለጫ ተሰጥቷል። መግለጫው በአካባቢው የተፈጠረውን አለመረጋጋት ጠቅሶ "የተከሰተውን የሰላም መደፍረስ ለማረጋጋትና የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት አስፈላጊውን ሕጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ" ትእዛዝ አስተላልፏል።
ከሰሞኑ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የተከሰተው አለመረጋጋት ወደ ሰሜን ሽዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ተሸጋገሮ የሰው ህይዎት መጥፋቱ፣ ንብረት መውደሙ እና ዝርፊያ መፈፀሙ ተነግሯል። አቶ ሰማቸው የተባሉ የማጀቴ ከተማ ነዋሪ እንደተናገሩት ከትናንት ጀመሮ በተደራጀ መልኩ የቡድን መሳሪያ የታጠቁ አካላት በንጹሃን ዜጎች ላይ ሲተኩሱ ውለዋል፤ በዚህም 14 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሁለቱ የፖሊስ አባላት ናቸው ብለዋል። አሁንም ስጋት በመኖሩ ነዋሪው አካባቢውን ለቅቆ ወደ ገጠር ቀበሌዎች እየተሰደደ ነው ያሉት አቶ ሰማቸው በዚህ ሰአት የሚካሄድ ተኩስ የለም ነገር ግን የጸጥታ አካላት ባለመድረሳቸው ስጋት አለን ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በሰሜን ሸዋ በተከሰተ ግጭት ህይወት ጠፍቷል ንብረት ወድሟል • በትሪፖሊ አቅራቢያ በተደረገ ውጊያ የ21 ሰዎች ሕይወት ጠፋ ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪና ስሙን መግለጽ ያልፈለገው ግለሰብ ደግሞ "ከትናንት ጀምሮ ባልተዘጋጀንበት ሁኔታ ከቀያችን ድረስ መጥተው ተኩስ ከፈቱብን ባለን አቅም ስንከላከል ለጊዜው ከሁለታችንም ወገን ቁጥራቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ሞተውብናል" ብሏል። የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ካሳሁን እምቢአለ እንደገለጹት ደግሞ የጸጥታ አካላት በሁሉም ቦታ ደርሰዋል። አስፈላጊ ከሆኑ አካላት ጋርም እየተነጋገርንና ነገሮች ወደ ቀደመ ሰላማቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ እያመቻቸን ነው ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ትናንት በነበረው ግጭት አንድ ቤተ ክርስቲያን የተቃጠለ መሆኑን የተናገሩት የመምሪያው ኃላፊው በሌላ አካባቢ ቤተክርስቲያንም የማቃጠል ሙከራ ተካሂዶ ባይሳካም በዙሪያው የሚገኙ ቤቶች ግን ተቃጥለዋል ብለዋል። አጣዬ ላይ የግለሰብ ቤቶች እንደተቃጠሉና ዝርፊያም እንደተፈጸመ አብራርተዋል። "ኦነግ ያደራጃቸው ናቸው ይህን የፈጸሙት" የሚሉት አቶ ካሳሁን "አላማቸውም ሽብር መፍጠርና ዝርፊያ ማካሄድ ነው" ብለዋል። በዚህ ወቅት በስፍራው የሚገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እንደገለጹት ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሁሉም አካባቢዎችን ማረጋጋት ተችሏል። አክለውም ሁኔታውን ዘላቂ ሰላም እንዲኖረው ለማድረግም ከሃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ብለዋል። ትናንት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ደብረ ብርሃንም ከፍተኛ የሆነ ህዝብ ጎዳና ወጥቶ ችግሩን ሲቃወም መስተዋሉን ከስፍራው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ነግረውናል። ዛሬ በአጣዬ ማጀቴና ካራቆሬ አንጻራዊ መረጋጋት የታየ መሆኑን የተናገሩት አቶ ካሳሁን ከባንኮችና አንዳንድ ተቋማት ውጭ ሌሎች አገልግሎቶች መደበኛ ስራቸውን በመስራት ላይ ናቸው ብለዋል። በስፍራው የመከላከያ ሠራዊትም ደርሷል ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ የሚገኙ 500 የሚሆኑ የአካባቢው ተወላጆች ድርጊቱን በማውገዝ ዛሬ ጠዋት ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል። መግለጫውን የሰጡት ተሰብሳቢዎች ተወካይ አቶ ደጀን መንገሻ በአካባቢው የተፈጠረ ግጭት አነሳስቷቸው መሰባሰባቸውን ጠቅሰው መግለጫው በቦታው ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግድያ፣ አፈናና ዘረፋን አስመልክቶ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራና ሠላም እንዲመጣ ለመጠየቅ ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል። ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ በአጣዬ፣ ማጀቴ፣ ካራ ቆሬ፣ እና በአካባቢው በንፁሃን ላይ የተከፈተው ተኩስ፣ ግድያ፣ ዘረፋና አፈና እንዲቆም መንግስት ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ፣ በሕይወትና ንብረት ላይ አደጋ ያደረሱ የተደራጁና የታጠቁ ኃይሎች በአፋጣኝ ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ጥቃቱን በማውገዝ መንግስት ከህዝብ ጎን እንዲቆም፣ በቦታው በቂ የፀጥታ አካላት ተመድቦ ቦታውን እዲያረጋጋ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አፋጣኝ ሰብዓዊና ቁሳዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው ጥሪ ለማቅረብና ሟቾቹንም በፀሎት ለማሰብ ነው ሲሉ ዐብይ የመግለጫውን ይዘቶች ዘርዝረዋል። አቶ ደጀኔ እንዳሉት በተለይ በማጀቴ፣ ካራ ቆሬ፣ አንፆኪያ አካባቢዎች ከዚህ ቀደምም በግጦሽም ሆነ በውሃ ሲጋጩ፣ በሽማግሌ ሲፈታ የኖረ ነው በማለት ሕዝቦቹ ተሳስበውና ተከባብረው የሚኖሩ ናቸው፤ ነገር ግን "አሁን የተፈጠረው ግን ታስቦበት፣ ታቅዶና ተጠንቶ የተደረገ ነው፤ ተራ ግጭት አይደለም" ሲሉም ያክላሉ። ስልጠና ተካሂዶ፣ ከግለሰብ የማይጠበቅ መሳሪያ ተታጥቀው፣ ቦታና ምሽግ ይዘው ህዝቡን ሲያጠቁ ነበር የሚሉት ተወካዩ የተደራጀና ሌላ ዓላማ ያለው ኃይል እንዳለ ተረድተናል ብለዋል። "የክልሉ ልዩ ኃይልም ሆነ መከላከያም የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ገብተዋል ፤ነገር ግን ቦታው ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት በሚገባው ልክ የተረዱት አይደለም፤ የተላከውም ኃይል በቂ አይደለም" ሲሉ የጉዳዩን አሳሳቢነት ያስረዳሉ። አሁንም በአጣዬ ዙሪያ አላላ የተባለው አካባቢ የታጠቁ ኃይሎች ጥቃት እያደረሱ እንደሆነ መረጃ እንደደረሳቸውም ነግረውናል። "ሕዝቡ ከኖረበት፣ ከአገሩ፣ ከርስቱ ነው እየተፈናቀለ ያለው" የሚሉት አቶ ደጀን መንግስት ይህንን ኃይል ያደራጀው አካል በመመርመር ሥር ነቀል ለውጥ እንዲያመጣ አሳስበዋል። በቀጣይም ኮሚቴ አዋቅረው ለኢህአዴግ ፅ/ቤት፣ ለአዴፓ ፅ/ቤትና ለጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ኃሳባቸውን ለማቅረብ እንደተዘጋጁ ገልፀውልናል። ሁለት ኃይማኖት አንድ ትዳር!
news-56036400
https://www.bbc.com/amharic/news-56036400
በትግራይ የተከሰተው ግጭት አንኳር ነጥቦች ሲዳሰሱ
በትግራይ ክልል በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የተጀመረው ግጭት መቶ ቀናትን ደፍኗል።
በፌደራልና በክልሉ ኃይሎች መካከል በተካሄደ ግጭት ምክንያትም በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ማጋጠሙን የተለያዩ ዓለማ አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በሪፖርቶቻቸው አመልክተዋል። የግጭቱን መንስዔ እና ከግጭቱ በኋላ የተከናወኑ አበይት ጉዳዮችነ በወፍ በረር ለመቃኘት ሞክረናል። የግጭቱ አጀማመር በፌደራል መንግሥትና ህውሓት በሚመራው የትግራይ መንግሥት መካከል እየተባባሰ የመጣው አለመግባባት በጥቅምት 24 2013 ዓ.ም ላይ ወደ ግልጽ ግጭት ማምራቱ ይታወሳል። በ2011 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ የቀድሞው ኢህአዴግ እንደሚዋሃድ ውሳኔ ላይ በመድረሱ ህወሓት ይህንን ባለመቀበል ከውህደቱ ራሱን መነጠሉን አስታወቀ። ኢህአዴግ ራሱን ወደ ብልጽግና መቀየሩን ይፋ ባደረገበት ወቅትም ፖለቲካዊ ፍቺው ይፋ ሆነ። ብልጽግና ሃገሪቱን የሚመራ ፓርቲ ሆኖ ሲቀጥል ህወሓት በበኩሉ ትግራይን ማስተዳደር ቀጠለ። በ2012 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነሐሴ ወር መካሄድ የነበረበት አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት መራዘሙን ይፋ ሲያደርግ፣ ህወሓት በበኩሉ 'ቫይረሱን እየተከላከሉ ምርጫ ማካሄድ ያቻላል' በሚል መከራከሪያ ምርጫውን የማራዘም ውሳኔ ሳይቀበለው ቀረ። የፌደሬሽን ምክር ቤትም የምርጫ ቦርድ ውሳኔን በማጠናከር የፌደራልና ክልል መንግሥቶች የስልጣን ዘመን እንዲራዘም ውሳኔ አስተላለፈ። ህወሓት እና የትግራይ ክልል ምክር ቤት በበኩላቸው የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ "ህጋዊ አይደለም" በማለት ውድቅ አደረጉ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ቦርድን እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ማጽደቁን ተከትሎ የትግራይ ክልል መንግስትም ክልላዊ ምርጫ እንደሚያካሂድ ውሳኔውን በሰኔ 2012 ዓ.ም ላይ ይፋ አደረገ። ምርጫውንም በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፉን ህወሓት ይፋ አደረገ። በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የሚመራ መንግሥትና የፌደሬሽን ምክር ቤት ግን በትግራይ የተካሄደውን ምርጫ "ህጋዊነት የሌለውና ትርጉም አልባ" መሆኑን በመግለጽ እውቅና እንደማይኖረው አስታውቀዋል። ከዚህ በኋላ የሁለቱ መንግሥታት አለመግባባት እየተካረረ ሄዶ ጥቅምት 24 2013 ምሽት ጠቅላይ ሚንስትሩ የትግራይ ኃይሎች በክልሉ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ "ህግ የማስከበር ዘመቻ" ያሉትን ወታደራዊ እርምጃ ማዘዛቸውን አስታወቁ። የኢትዮጰያ መከላከያ ሠራዊት ግጭቱ በተጀመረ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ፣ ሕዳር 19 2013 ዓ.ም የመቀለ ከተማን ተቆጣጠረ። ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ በተመሳሳይ ቀን በሰጡት መግለጫ "ህግ የማስከበር ዘመቻው" በድል መጠናቀቁን በማሳወቅ የሚቀረው የህወሐት መሪዎችን በቁጥጥር ስር የማስገባት ስራ ብቻ እንደሚሆን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜም በተለያዩ አካባቢዎች አልፎ አልፎ ውጊያዎች እንደሚካሄዱ የሚገልጹ መረጃዎች እየወጡ ነው። በትግራይ ክልል ላይ በተካሄደው ጦርነት በሁለቱም ሐይሎች በኩል ስንት ተዋጊዎች እንደተገደሉ በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ከፍተኛ የሰው ኃይልና የንብረት ውድመት መድረሱ ግን ይገመታል። በቁጥጥር ሥ የዋሉ የህወሓት አመራሮች። አቶ አባይ ወልዱ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አብረሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ ሰለሞን ኪዳነ (ዶ/ር) እና አቶ ስብሐት ነጋ የተገደሉና የታሰሩ የህወሐት አመራሮች የፌደራል መንግሥት ጸጥታ ሀይሎች እንዳስታወቁት በርካታ የህወሐት መስራቾችና አመራሮች እንዲሁም በአገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን ላይ ያገለገሉ ተገድለዋል፤ ታስረዋልም። መከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃ ከተገደሉት መካከልም ለ20 ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ያገለገሉት ከህወሐት መስራቾች አንዱ የነበሩት አምባሳደር ስዩም መስፍን ይገኙበታል። አብረዋቸው በሚንስትርነት ደረጃ ያገለገሉ አቶ አባይ ጸሃዬና የህወሐት ሥራ አስፈጻሚ አባል የነበሩት አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ተገድለዋል። ከከፍተኛ የህወሐት አመራሮች መካከል አንድ የሆኑት እና አንጋፋ ፖለቲከኛ አቶ ስብሐት ከባለቤታቸው ሌ/ኮ ሪቺና እንዲሁም እህታቸው ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል። በተጨማሪም ለዓመታት የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት በመሆን ያገለገሉት አቶ አባይ ወልዱ እንዲሁም ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የህወሐት ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ አባል የነበሩት አብርሃም ተከስተ [ዶ/ር] የሚገኙባቸው በርካታ የክልሉ አመራሮች በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸው ፍርድ ቤት እየታየ ነው። ጦርነቱ ያስከተለው ሰብአዊ ቀውስ! በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በክልሉ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስና መፈናቀል ማስከተሉን የመንግስት አካላት እንዲሁም የእርዳታ ድርጅቶች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። ከ2.3 ሚልዮን ሰዎች በክልሉ ውስጥ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ከ60 ሺህ በላይም ወደ ሱዳን በመሸሽ በስደተኛ ካምፖች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። እንደ ተባበሩት መንግሥታት አሃዝ 4.5 ሚልዮን ህዝብ በላይም በክልሉ አስቸኳይ የምግብና ህክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት አግልግሎት መስጠት አቁመው ቆይተዋል። ግጭቱ ከተጀመረ ከሁለት ወር በኋላ አምስት ሆስፒታሎች ብቻ አገልግሎት መስጠት ጀምረው እንደነበረ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመለክታል። የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎቶች በመቋረጣቸውም ስለጦርነቱና በክልሉ ስለሚፈጠሩ ነገሮች መረጃ ለማግኘት የማይቻል ነገር ሆኖ ቆይቷል። የኤሌትሪክ አገልግሎትም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ነበር። ከጥር ወር የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ግን የስልክና የትራንስፖርት አገልግሎት በተወሰኑ ከተሞች ሊመለስ ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ክልል በአራት የስደተኞች መጠለያዎች የነበሩ ኤርትራውያን ስደተኞችም በከፍተኛ አደጋ ላይ መውደቃቸው ይገለጻል። መጠለያዎቹ ውጊያው በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ስለሆኑ ለስደተኞቹ የሚሆን እርዳታ ማድረስ ባለመቻሉ እጅግ አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ መቆየታቸው ይታወቃል። የተባበሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ሕብረትና አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ አካላት በትግራይ ውስጥ ተፈጽመዋል የሚባሉ ጾታዊ ጥቃቶች፣ ግድያዎች፣ እገታና ዘረፋ የሚገኙባቸው ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በነጻና ገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጥያቄ እያቀረቡ ነው። የኤርትራ ተሳትፎ የህወሐት መሪዎች ውጊያው በተጀመረ ማግስት የኤርትራ ሰራዊት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ድብደባዎች እንዳካሄደና በርካታ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ትግራይ መግባታቸውን ሲከሱ ተሰምተዋል። የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በተለያየ ጊዜ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ የሚጠይቅ መግለጫ አውጥተዋል። የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ዑስማን ለሮይተርስ በሰጡት ምላሽ ግን ኤርትራ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ላይ እንደማትገባ ተናግረው ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥትም የኤርትራ ጦር በትግራዩ ግጭት እንዳልተሳተፈ ሲያስተባብል ቆይቷል። የህወሓት ኃይሎች በተደጋጋሚ ወደ ኤርትራ ሚሳዔል ቢያስወነጭፍም የኤርትራ መንግስት ስለጥቃቶቹ የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም። በማይካድራ የተገደሉ ሰዎች አስክሬን በዚህ መሰል አልጋዎች ሲሰበሰቡ ነበር በማይካድራ የተፈጸመው ግድያ በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ውስጥ በምትኘው ማይካድራ ከተማ በተፈጸመው ጭፍጨፋ ከ600 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ቡድኖች አስታውቀዋል። ማይካድራ ከተማ የተፈጸመው ጥቃት በአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና 'ሳምሪ' በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን መፈጸሙንም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል። ኮሚሽኑ ይህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት "በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል እና የጦር ወንጀል ሊሆን እንደሚችል" ያመለከተ ሲሆን፤ ለዚህም ኢሰመኮ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በበኩላቸው የፌደራል መንግሥት የምዕራብ ትግራይን "ነፃ ካወጣ" በኋላ የህወሓት ታጣቂዎች በማይካድራ ከተማ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን "በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል" ብለዋል።
news-44625357
https://www.bbc.com/amharic/news-44625357
ማቻርና ሳልቫ ኪር ከፊል ስምምነት ላይ ደርሰዋል
የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና የአማጺያኑ መሪ ሪክ ማቻር በከፊልም ቢሆን አንዳች ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰማ። ማቻርና ኪር ስምምነት የደረሱባቸው ነጥቦች ግን ለጊዜው አልተገለጹም።
የሁለቱ ተፋላሚዎች የስምምነት መልካም ዜና የተሰማው ከካርቱም ሲሆን የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልማዲሪ ሙሐመድ አሕመድ «በተወሰኑ ጉዳዮች» ላይ ብቻ ስምምነት መፈጸማቸውን ተናግረዋል። በደቡቡ ሱዳን የርስበርስ ጦርነት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለዋል። ከ4 ሚሊዮን የማያንሱ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ይህ የሰላም ስምምነት በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የቀረበ ሲሆን በቅርቡ አዲስ አበባ በተደረገ የአባል አገራት መሪዎች ስብሰባ ውጤታማ ሳይሆን ቀርቶ ነበር። ሁለቱ ተፋላሚ መሪዎች ባለፈው ሳምንት የፊት ለፊት ንግግር ሲጀምሩ በአካል ለመገናኘት ከሁለት ዓመታት በኋላ የመጀመርያቸው ነበር።
news-47966984
https://www.bbc.com/amharic/news-47966984
የአድዋ ማዕከል የአዲስ አበባ እምብርት ላይ ሊሰራ ነው
ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በጭቆና ስር ለነበሩ አፍሪካውያንም ሆነ ለጥቁር ህዝቦች የሰውነት ክብር መለኪያ የተረጋገጠባት የአድዋ ድል በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ፋይዳ አለው። ይህንንም ለማጉላት ከሰሞኑ የአዲስ አበባ መስተዳድር የአድዋን ድል የሚዘክር ማዕከል በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ እንደሚሰራ አስታውቋል።
የማዕከሉ አስፈላጊነት በአሁኑ ወቅት ሀገሪቷ ካጠላባት መቃቃርና መከፋፈል ለማውጣት ህዝቡን የሚያስተሳስር ታሪክን ወደ ኋላ መቃኘት አስፈላጊ መሆኑ አንዱ ምክንያት መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ይናገራሉ። •መከፋፈል ያጠላበት ጉዞ አድዋ •"ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች በተለይም ዕድሜ፣ ብሔር፣ ፆታ፣ ሀይማኖት ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው የተሰባሰቡባት አድዋ በታሪክም ሆነ የህዝቡን አንድነት ለመመለስ ከፍተኛ ሚና እንዳላት ኃላፊው ይናገራሉ። "አድዋ የድል ትርክት ብቻ ሳይሆን የአንድነት፣ የነፃነት፣ የፍትህ፣ የሰብአዊነትና ሌሎች ገዢ ሀሳቦችን ተምሳሌት ናት" የሚሉት ኃላፊው አድዋን ለመዘከር ምን አይነት ማዕከል ያስፈልጋል በሚለው ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የመጀመሪያውን ምክረ ኃሳብ መቅረቡን ተናግረዋል። በምክረ ኃሳቡ መሰረት ማዕከሉ ሊያካትታቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል በወቅቱ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች፣ ስንቆች፣ ትጥቆች በአጠቃላይ የጦርነቱን ሁኔታ የሚያሳይ የጦርነቱ መዘክር ሙዚየም፤ በአድዋ ድል ላይ የተፃፉ መፃህፍት፣ የኪነ ጥበብ ውጤቶች፣ ሙዚቃዎች፣ ፊልሞች፣ ተውኔቶች ተከማችተው ለህዝብ የሚቀርብበት ቦታ፤ በተለያዩ ሰዓሊያንና ቀራፂያን የሚቀርቡ በአድዋም ሆነ በሌሎችም ሀሳቦችም የሚሰሩ ስራዎችን የሚታዩበት ቋሚ የሆነ ጋለሪ፣ ትልቅ ቤተ መፃህፍት፤ ለሲኒማ፣ ለትያትር እንዲሁም ለማንኛውም ክዋኔ ጥበባት የሚያገለግል ሁለገብ የሆነ አዳራሽ፤ ምግብ ቤቶች ናቸው። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ሌሎች ሃገራት ላይ እንዳለው የርቀቶች መነሻ ወይም የአገሪቷ እምብርት ተብሎ የሚወሰደው ቦታ ላይ ህንፃውን ለመስራት ታስቧል። በኢትዮጵያ የተለያዩ የከተሞች ርቀት የሚለካው አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ ሲሆን ይህ ዜሮ ኪሎ ሜትር (እምብርት ) ተብሎ የሚታወቀው ቦታ ላይ ማዕከሉ ይሰራል። በዚህም ቦታ ላይ"ሁሉ ከዚህ ይጀምራል" የሚል ፅሁፍ የሚኖረው ሲሆን ሁሉንም የሚያሰባስብ ቦታ ሊሆን እንደታቀደም ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ገልፀዋል። •ሰላሳ ሰባት ማዳበሪያ ዕፀ ፋርስ ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል ተያዘ "በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምስራቅ፣ በምዕራብ ያለነው ኢትዮጵያውያን አንድ የሚያደርገን የሚያስተሳስረን ነገሮች ቢኖሩም በዚህ ጥበባዊ መንገድ የምንተሳሰርበት ሁኔታ ሲፈጠር አብረን ቆመን ሁላችንም ከዚች ቦታ ነው የምንነሳው፤ ስለዚህ ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ አድዋ ደግሞ ሁላችንም የተሳተፍንበት ነው" ይላሉ። የማዕከሉ ዲዛይን ጋሻ እንዲመስል ተደርጎ የታሰበ ሲሆን ከዚህም ጀርባ ያለው ፅንሰ ሃሳብ አለኝታነትን፣ መከታነትን እንዲወክል ቢሆንም የመጨረሻው ዲዛይን እንዳልሆነ ግን ኃላፊው ገልፀዋል። ዲዛይኑም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች ማህበረሰቡን እንዲያሳትፉ በሚል እሳቤ ውይይቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በትናንትናው ዕለትም ከሀይማኖት አባቶች፣ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከምሁራን፣ ከኪነ ጥበብ ሰዎች፣ አርበኞችና ከተውጣጡ የማህበረሰቡ አባላት ግብአት መሰብሰቡን ኃላፊው ነግረውናል። ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ እንደሚሉት ምን ያህል ወጭ እንደሚያስፈልግ አሁን ባለው ሁኔታ ባይታወቅም "የአድዋን ታሪክ አስፈላጊነት፣ ለትውልድ የሚሰጠውን መንፈሳዊ ጥቅምና ለአገራችን የሚኖረውን ታላቅ እሴት በማሰብ ማንኛውንም ወጪ ለመሸፈን ከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኝነት አለው" ብለዋል።
news-54004613
https://www.bbc.com/amharic/news-54004613
የቻይና ስም በደቂቅ የተፃፈበት አዲሱ የታይዋን ፓስፖርት
የታይዋን ባለሥልጣናት አዲስ ፓስፖርት ይፋ አድርገዋል።
የታይዋና የቀድሞ ፓስፖርት (ግራ) እና አዲሱ ፓስፖርት (ቀኝ) ፓስፖርቱ ‘ታይዋን’ የሚል በደማቅ የተፃፈበት ሲሆን ‘ሪፐብሊክ ኦፍ ቻይና’ የሚለው በደቃቅ ፅሑፍ ታትሞ ይታያል። ባለሥልጣናቱ ይህን ያደረግነው የታይዋን ዜጎች ከቻይና ዜጎች ጋር እንዳይምታቱ በማሰብ ነው ብለዋል። ደሴቲቱ ነፃ ሃገር ነኝ ብትልም ቻይን ግን እራሷን ከቻይና ለመገንጠል ጥረት የምታደርግ ግዛት አድርጋ ነው የምትቆጥራት። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አዲሱ ፓስፖርት ታይዋንን ‘የቻይና አንድ ክፍል ከመሆን የሚያተርፋት አይደለም’ ብለዋል። የታይዋን ባለሥልጣናት ዕለተ ረቡዕ ደመቅ ባለ ሥነ-ሥርዓት ነው አዲሱን ፓስፖርት ያስተዋወቁት። የታይዋን ኦፌሴላዊ መጠሪያ የሆነው ‘ሪፐብሊክ ኦፍ ቻይና’ ከፓስፖርቱ ሽፋን ላይ ተነስቶ በምትኩ 'ታይዋን' የሚለው ስያሜ በትላልቅ ፊደላት ሰፍሯል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ማስጨነቅ ከጀመረ ወዲህ ‘ዜጎቻችን ጎልተው እንዲታዩና ከቻይና ዜጎች ጋር እንዳይምታቱ እየሰራን ነው’ ሲሉ የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሴፍ ዉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል በርካታ ሃገራት ከቻይና የሚመጡ ሰዎች ላይ እግድ በመጣላቸው ምክንያት ይህንን ለማስወገድ የተደረገ እርምጃ መሆኑን ባለሥልጣናት ይናገራሉ። በተለይ ከኮሮናቫይረስ ወረረሽኝ በኋላ ታይዋን ከቻይና ጋር የለየለት ጠብ ገጥማለች። ታይዋን ወረርሽኙን በተቆጣጠረችበት መንገድ ከበርካታ መንግሥታት አድናቆት ብታገኝም የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት አባል ሃገር ግን አይደለችም። ቻይና፤ ታይዋን ከድርጅቱ እንቅስቃሴዎች ያገደቻት ከ2016 [በአውሮፓውያኑ] ጀምሮ ነው። ታይዋን ከአውሮፓውያኑ 1949 ጀምሮ ራሷን በራሷ ስታስተዳድር ቆይታለች። የራሷን ዴሞክራሲያዊ ምርጫም ታካሂዳለች። የራሷ የሆነ ጦር ሠራዊትና የመገበበያ ገንዘብም አላት። ነገር ግን በአንድ ቻይና ፖሊሲ መሠረት ቻይና ታይዋንን የራሷ ግዛት አድርጋ ትቆጥራታለች። አንድ ቀን የታይዋን ግዛት ወደ ቻይና ትመጣለች - አስፈላጊ ከሆነም በኃይል ትላለች ቻይና። የታይዋን ፕሬዝደንት ሳይ ኢንግ-ዌን ቻይና ‘እውነታን እንደትቅበልና’ ለታይዋን ክብር እንድታሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተወሰኑ የዓለማችን ሃገራት ታይዋንን እንደ ሃገር ይቆጥሯታል። ነገር ግን እንዲህ ያደረጉ ሃገራት በቻይና ጥርስ ተነክሶባቸዋል። በቅርቡ አንድ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ታይዋንን መጎበኝታቸው አይዘነጋም።
news-45036019
https://www.bbc.com/amharic/news-45036019
አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በቤተሰቦቹና በሙያ አጋሮቹ ዓይን
"ለኔ ወንድሜ ጓደኛዬ ነው። አባቴም ነው።" ግርማ ተክለማርያም
ግርማ ተክለማርያም የፍቃዱ ወንድም ነው። ፍቃዱ ከወንድምነት ባሻገር ጓደኛውም እንደሆነ ይናገራል. . . "ለኔ ወንድሜ፣ ጓደኛዬ ነው። ከዚያ በላይ አባቴም ነው።" ይላል። ፍቃዱ ጥሩ ጤንነት ላይ ነበር ፤ እየተሻለውም ነበር። የፍልሰታን ጾም ልጨርስና ወደ አዲስ አበባ እመጣለሁ ብሎ አስቦ በነበረበት ሁኔታ ነው በሞት የተለየው። •ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? •40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ •ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ በገዳም ህግ ገዳም ውስጥ ያረፈ ሰው አስከሬን ከገዳም አይወጣም። ነገር ግን ገዳሙ ትልቅ ትብብር አድርጎልናል። ፍቃዱ የህዝብ ልጅ ነው። ስለዚህ ህዝብ በይፋ እንዲቀብረው አስከሬኑን ሰጥተውናል። ጸበል ቦታ ሳለ አንድ ወር ከሰባት ቀን አብረው ቆይቻለሁ። ባለቤቱም ነበረች። በየግዜው በስልክ አገኘው ነበር። ከህክምና በፊት የተወሰነ ጊዜ ስላለው ወደ ኩላሊት እጥበት ከመግባቱ በፊት ሀይማኖታዊ ህክምና ላድርግ አለና ተስማማን። ሀይማኖቱ ላይ ጠንካራ አቋም ነበረው። ሀይማኖታዊ ህክምናውን እያደረገ ጤናው ተመልሶ ነበር። ከዚያ ሲመለስ ከኢትዮጵያ ውጪ ህክምናውን ሊቀጥል ወስኖ ነበር። •''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ •ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሙሉ የህክምና ወጪውን ችዬ በነጻ ለማሳከም ፍቃደኛ ነኝ አለ። በማመስገን ተቀበልን። ጳውሎስ ሆስፒታል ንቅለ ተከላ የሚደረግላቸው ሰዎች ኩላሊት ከቅርብ ዘመዶቻቸው የተሰጣቸው ብቻ ናቸው። እኔና ሌሎችም ቤተሰቦች በጤና እክል ምክንያት ኩላሊት መስጠት አልቻልንም። ኩላሊት ፍለጋ ወደሚድያ የተወጣው ለዚህ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን ከውጪና ከሀገር ውስጥም ከ100 ሰው በላይ ኩላሊት ለመስጠት ፍቃደኛ ሆነ። ስለዚህ የሀገር ውስጥ ህክምና ቀርቶ ውጪ ለህክምና ለመሄድ ነበር። ትላንት አይኑን ልመልከት ብዬ የአውሮፕላን ትኬት ቆርጬ ሄጄ ነበር። ግን ኮምቦልቻ ላይ ዝናብ ስለዘነበ አውሮፕላኑ ማረፍ አልቻለምና ወደ አዲስ አበባ ተመለሰን። "ፍቄ የሀገር ቅርስ ነው። የሁሉም አባት ነው" ዮርዳኖስ ለፍቃዱ እንደ ልጅ ቅርቡ ነው። ፍቃዱ የሱ ብቻ ሳይሆን የሀገር ቅርስ እንደሆነ እንዲህ ያወሳል. . . ከትንሳኤ በአል በኃላ ወደ ጸበል ሄደ። ጳውሎስ ሆስፒታል ቀጠሮ ላይ ነበር። የቀጠሮው ግዜ እስከሚደርስ 'ቤቴ አልቀመጥም ጸበል ቦታ ገብቼ እግዚአብሄርን እማጸናለሁ' ብሎ ነበር። ከበቂ በላይ ገንዘብ ተሰባስቧል። እሱም ደስተኛ ነበር። የሌላ ሰው ኩላሊት ወስጄ ባልተርፍስ የሚል ስጋት ግን ነበረው። ትላንት ወደ 11 ሰዓት ነው ሞቱን የሰማነው። ፍቄ የሀገር ቅርስ ነው የሀገር ባለውለታ ነው። ፍቄ ከምንም በላይ አባት ነው። የሁሉም ሰው አባት ነው። "መጨረሻ የተናገረው በርቺ የሚል ቃል ነበር" ፍቃዱ ህክምና እንደሚያስፈልገው ከታወቀ ጊዜ አንስቶ ኮሚቴ ተቋቁሞ ገንዘብ ሲያሰባስቡ፣ ኩላሊት የሚለግስ ሲፈልጉም ነበር። በዚህ ሂደት ወቅት እንደ ፍቃዱ በኩላሊት ህመም ትሰቃይ የነበረቸው የሜላት አሰፋ ጉዳይ በማህበራዊ ድረ ገጾች ይዘዋወር ጀመር። ሜላት በኩላሊት ህመም ምክንያት ትምህርቷን ከአስረኛ ክፍል ለማቋረጥ ተደዳለች። ፍቃዱ ስለ ሜላት ሲሰማ 'ወጣትን መታደግ ይሻላል' ብሎ ለህክምናው ከተሰባሰበለት ገንዘብ 200,000 ብር ለሜላት እንዲሰጥ አደረገ። ሜላት ስለ ፍቃዱ እንደምትናገረው. . . ያኔ የፍቃዱ ጥሪ የመጣልኝ በጌታነህ ጸሀዬ በኩል ነበር። ገንዘቡን የሰጠኝ ምንም ባልጠበቅኩበት ወቅት ነበር። በሰዓቱ እጄ ላይ ብር አልነበረኝም። ሲጠራኝ እንዲሁ ሊያናግረኝ የፈለገኝ ነበር የመሰለኝ። መልካም ነገር ነው ያደረገልኝ፤ አመሰግነዋለሁ። በኛ ሀገር የኩላሊት እጥበት ወጪ ከባድ ነው። እሱ ግን ረዳኝ። ከሀገር ውስጥም ከውጪም ሰዎች ባሰባሰቡልኝ ገንዘብ እየታከምኩ ነው። አሁን በኮርያ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት እየተከታልኩ ነው። ከረዳኝ በኃላ በስልክ አንገናኝ ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ የተነጋገርነውን አስታውሳለሁ። 'በርቺ' የሚል ቃል ነበር የተናገረው። 'እንድናለን' ይለኝ ነበር። ድኖ እንገናኛለን ብዬ ነበር። ነገር ግን አልሆነም። "በጣም ግሩም፣ ድንቅና ብርቅ አርቲስት ነበር" ተስፋዬ አበበ (ፋዘር በሚል የቁልምጫ ስምም ይጠራሉ) በቴአትርና በሙዚቃ ዘርፍ በጽሁፍና በዝግጅትም ይታወቃሉ። እውቁ የተስፋዬ የስልጠና ማዕከል የበርካታ ተዋንያንና ጸሀፊ ተውኔቶች መነሻ ነው። ከነዚህ አንዱ ደግሞ ፍቃዱ ነው። ፋዘር ስለ ፍቃዱ ሲናገሩ. . . በልጅነቱ የሰለጠነው እኔጋ ነበር። ያኔ ሱራፌል ጋሻው ከሚባል ጓደኛው ጋር የመጣው በ 1965 ዓ. ም. ነበር። እኔጋ ከመምጣቱ በፊት በትምህርት ቤቱ ሙዚቃ ይጫወት ነበር። ከተዋናይነቱ ባሻገር መለስተኛ ድምጻዊም ነው። እኔጋ ሲመጣ ልጅ ቢሆንም እንደልጅነቱ ሳይሆን ሁሉም ነገር ላይ ይሳተፍ ነበር። በዝማሬና በአጫጭር ድራማ ውስጥም ይገባል። ከእድሜው በላይ የሚያስብ ነበር። ከዛ እሱ፣ ስዩም ተፈራና ሱራፌል ጋሻው ወደ ማዘጋጃ ቤት ሄዱ። በሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን "ቴዎድሮስ" ቴአትር ላይ አጼ ቴዎድሮስን ሆኖ ትልቅ ስራ የሰራ ጀግና አርቲስት ነው። በጣም ግሩም፣ ድንቅና ብርቅ አርቲስት ነበር። የፊልም ኢንዱስትሪው እየተስፋፋ ከመጣ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ትልልቅ ፊልሞች ሰርቷል። በጣም በቅርቡ ደግሞ ከኔ ጋር "መለከት" በተባለ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ ይሰራ ነበር። •40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ •ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ ፍቃዱ በገሀዱ አለም ውስጥ ሰውን አክባሪና ታማኝ ነበር። ለጥበቡ የቆመ ለጥበቡ የቆመ ሰው ነበር። ነገር ግን በኩላሊት ህመም ምክንያት ትልቅ አደጋ ደረሰበት። ለህልፈት በቃ። እናም ሁላችንም ሀዘን ላይ ነው ያለነው። ቴአትር ሲሰራ እውነታን ይዞ፣ እውነታን አስመስሎ ነው። ሆኖ ነው የሚጫወተው። በተለይ የማደንቀው ቴዎድሮስን ሆኖ ሲጫወት ነው። አጼ ቴዎድሮስን ሆኖ ሲጫወት ሰውነቱ ሁሉ ይለወጣል። በቃ ፍጹም ቴዎድሮስን ነው የምናገኘው። ቴዎድሮስ በጣም መወደድና አድናቆት ያተረፈበት ስራ ነው። እኔም በጣም የማከብረው የማደንቀው በዛ ስራ ነው። ፍቄ ሩህሩህ፣ ልበ ግልጽ ነው። የታመመ የሚጠይቅ፣ እከሌ ሞተ ሲባል ፈጥኖ የሚደርስም ነው። •"የእሱ አባት ኩራዝ የላቸውም፤ እሱ ግን ኢትዮጵያን ሊያበራ ነው የሞተው" ፍቄ ቁጭ ብለው ሲያዋሩት 'የገበታ አርቲስት ነው'። የሚያመጣቸው ጨዋታዎች ያስፈነድቃሉ። አኩርፎ የሚቀመጥ ባህሪ ያለው አይደለም። "መጨረሻ ወደ ገዳም ሊሄድ ሲል ደውሎ በጣም ትልቅ የአባት ምርቃት መረቀኝ" የቴዎድሮስ ተሾመ "ጉዲፈቻ" ፊልም ከፍቃዱ ተጠቃሽ ስራዎች አንዱ ነው። ቴዎድሮስ ፍቃዱ የኩላሊት ህመም ከገጠመው በኃላ ለመታከሚያ የሚሆን ገንዘብ እያሰባሰበ የነበረው ኮሚቴ ውስጥ ይገኝበታል። ይህንንም ብሎናል. . . በኮሚቴው ገንዘብ እንዲሰባሰብለት አድርገን ነበር። ከበቂ በላይ ገንዘብ ተሰብስቦለትም ነበር። ከሁለት ወይም ሶስት ወር በፊት አብረን ወደ ህንድ ሄደን ነበር። ህመሙ የጸና እንደሆነና መታከም አንዳለበት ተረጋግጦ ነበር። 'ቶሎ ኩላሊት የሚለግስ ሰው ይዛችሁ ኑ' ብለውን ነበር። አዲስ አባባ ከመጣም በኃላ እንደ መድከም ሲለው ሸበሌ የሚባል ክሊኒክ ወስደውት ነበር። እዛ ማደር እንዳለበትና ህክምና ማድረግ እንዳለበት ቢነግሩትም መጀመሪያ ጸበል ልጠመቅ ብሎ ወደ ወሎ ሄደ። ገንዘብ ተዋጥቶለታል ኩላሊት የሚሰጥም ተገኝቶለታል። መጥቶ እንዲታከም እየነዘነዝን ነበር። የእግዚአብሄር ፈቃድ ሆነ ብለን እንለፈው እንጂ ህክምና እንዳያደርግ የሚያደርግ ነገር አልነበረም። ይመጣል ተብሎም እየጠበቅን ነበር። ትላንት ማታ ዜና እረፍቱን ሰማን። በጣም ያማል። አባት ነው። አማካሪ ነው። ጓደኛ ነው። መጨረሻ ላይ ወደ ገዳም ሊሄድ ሲል ደውሎ በጣም ትልቅ የአባት ምርቃት መረቀኝ። ላደረግከው ነገር እግዚአብሔር ይባርክህ አለኝ። ተመልሼ እመጣለሁ። የልፋትህን ውጤት አሳይሀለሁ ብሎኝ ነበር። እርዳታ ሲያሰባስብ የነበረው ኮሚቴ ከቤተሰብ ጋር ለቀብሩ መደረግ ያለበትን ቅድመ ሁኔታ እያመቻቸ ነው። በ 1948ዓ. ም. የተወለደው ፍቃዱ ነገ 8 ሰዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ስርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል። ከቀብሩ በፊት ከ5 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በብሄራዊ ቴአትር መታሰቢያ መርሀ ግብር ይኖራል።
47579808
https://www.bbc.com/amharic/47579808
ደቡብ ክልል አዲስ ለተፈናቀሉ 54 ሺህ ጌድዮዎች የፌደራል መንግሥትን ድጋፍ ጠየቀ
የደቡብ ክልል በወሰን ግጭት ከኦሮሚያ ክልል አዲስ ለተፈናቀሉ 54 ሺህ ስምንት መቶ 64 ጌድዮዎች እርዳታ እንዲልክለት የፌደራል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንን የጠየቀው መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ እንደሆነ የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙት ሃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
እነዚህ አዲስ ተፈናቃዮች በገደብ፣ ዲላ አቅራቢያ ጫጩ በሚባል እንዲሁም ጎቲቲ በተሰኘ ሌላ አካባቢ እንደሚገኙም ገልፀዋል። እነዚህ ተፈናቃዮች የተፈናቀሉበት ጊዜን በሚመለከት ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ደበበ "እኛ በዚህ ቀን ለማለት ይቸግረናል። ግን ደብዳቤው እንደደረሰን ወዲያው እርዳታ ልከናል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት ይህ የተላከው እርዳታ ለወዲያው ማስታገሻ ሲሆን ወደ ቦታው ሁኔታውን ለማጣራት ባልደረቦቻቸው መላካቸውንና በቀጣይ አስፈላጊው እርዳታ እንደሚላክ ጠቁመዋል። በጌድዮ ዞን ገደብ ወረዳ አንድ ተራዶ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ ግለሰብ ከመንግስት የሚገኘው እርዳታ እያነሰ ተቋርጧል የሚባልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ደበበ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት 208 ሺህ የሚሆኑ የጌድዮ ቋሚ ተፈናቃዮች ሲኖሩ እነዚህ ተፈናቃዮች ቀደም ሲል 860 ሺህ ከነበሩት የጌድዮ ተፈናቃዮች ብዙዎቹን ወደ ቀያቸው መመለስ ሲቻል በተለያየ ምክንያት ሳይመለሱ የቀሩ ናቸው። • ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል በላፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ብዙዎች በግጭት ምክንያት መፈናቀላቸው የሚታወቅ ነው።በተመሳሳይ መልኩ የተፈናቀሉ ጌድዮች ቁጥር ግን ከሌሎች በማይወዳደር መልኩ እጅግ ከፍተኛ ሊባል የሚችል ነው።ነገር ግን ምንም እነኳ ቁጥራቸው ከፍተኛ፤ ያሉበት ሁኔታም አስከፊ ቢሆንም መንግስት የጌደዮ ተፈናቃዎችን ችላ ብሏቸዋል የሚል ጮኸት ከመቼው በላይ እየተሳማ ነው። በአስከፊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ የጌድዮ ተፈናቃዮችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችም በማህበራዊ ሚዲያ ብዙዎች እየተጋሯቸው ነው።
news-45755908
https://www.bbc.com/amharic/news-45755908
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ የቀረበው የደፍሮኛል ውንጀላ ናይኪ እጅጉን እንዳሳሰበው ገለፀ
ናይኪ በእግር ኳስ ተጫዋቹ ክሪስቲያኑ ሮናልዶ ላይ የቀረበው የወሲብ ቅሌት ክስ እጅጉን እንዳሳሰበው ገለፀ። ይህ ግዙፉ የስፖርት ትጥቆች አምራች ኩባንያ ከሮናልዶ ጋር የ1 ቢሊየን ዶላር የኮንትራት ስምምነት የነበረው ሲሆን አሁን ግን "ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው" እንደሆነ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ገልጿል።
ሌላኛው የስፖርት ትጥቆች አምራች ኢኤ ስፖርትስ ከሮናልዶ ጋር ተመሳሳይ የስራ ውል ያለው ሲሆን እርሱም ጉዳዩን በአንክሮ እየተመለከተው መሆኑን አልሸሸገም። ናይኪ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው "የቀረበበት ውንጀላ እጅጉን ያሳስበናል ስለዚህ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልነው ነው" ሲል ኢኤ ስፖርትስ በበኩሉ " በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ የቀረበውን ዝርዝር ውንጀላ በሚገባ ተመልክተነዋል፤ ከድርጅታችን ጋር የሚሰሩ ስፖርተኞች የድርጅታችንን እሴቶች በሚጠብቅ መልኩ መንቀሳቀስ ስላለባቸው ጉዳዩን በቅርበት እያየነው ነው" ብሏል። • ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘች • ሞርጋን ፍሪማን በፆታዊ ትንኮሳ ለቀረበባቸው ውንጀላ ይቅርታ ጠየቁ • የኒውዮርኩ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፈፀሙት በተባለ ጥቃት ሥራ ለቀቁ በሌላ ወገን ደግሞ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የሚጫወትበት የጣልያኑ ስፖርት ክለብ ጁቬንቱስ ከተጫዋቹ ጎን ቆሟል። ክለቡ በቲውተር ገፁ ላይ እንዳሰፈረው " ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ሙያዊ ስነምግባሩንና ያለውን መሰጠት በሚገባ እያሳየ ነው። ይህም በጁቬንቱስ ውስጥ በሁሉም ዘንድ እንዲከበር አድርጎታል" ብለዋል። የእግር ኳስ ቡድኑ በሐምሌ ወር ከማድሪድ በ99 ሚሊየን ፓውንድ ነው የገዛው። የ33 ዓመቱ የእግር ኳስ ኮከብ በ2009 በላስቬጋስ ካትሪን ማዮግራ ደፈረኝ የሚል ክስ ስታቀርብ ሽምጥጥ አድርጎ ክዶ ነበር። የ34 ዓመቷ እና ቀድሞ በመምህርነት ስራ ትተዳደር የነበረችው ካትሪን ማዮግራ፣ አሁን ጉዳዩን ወደ ህግ ፊት በድጋሚ ያመጣችው በ#ሚቱ (#Me Too) እንቅስቃሴ ተነሳስታ እንደሆነ ጠበቃዋ መግለፃቸው ይታወሳል።
56192208
https://www.bbc.com/amharic/56192208
"በምርጫ ወቅት በመመታቴ የስምንት ወር ፅንሴ ጨነገፈ" ፖለቲከኛዋ አስካለ
ሰኔ፣ 1984 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፏቸው ሶስት አስርት አመታትን ላስቆጠሩት ወይዘሮ አስካለ ኃይሌ የምትረሳ ወር አይደለችም።
ፓርቲያቸውን ወክለው የመጀመሪያ ምርጫ የተወዳደሩባት እንዲሁም በሰደፍ ተመትተው የስምንት ወር ፅንሳቸው የጨነገፈችባት ወቅት ናት። በአሁኑ ወቅት 29 አመት ይሆናት ነበር በማለትም በኃዘን " በሆዴ ውስጥ የነበረችው ልጅ አልተፈቀደላትም" ይላሉ ከቢቢሲ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ። 'ልጃቸውን' እንዴት አጡ? ወቅቱ 1984 ዓ.ም ነበር። የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ስልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ የሽግግር መንግሥት ተመሰረተ፤ በሽግግር ወቅቱም እንደ ህገ መንግሥት የሚያገለግል ቻርተር ፀድቋል። በቻርተሩ መሰረት ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከታዋቂ ግለሰቦችና ከሌሎች አባላት የተውጣጡ ከ87 የማይበልጡ የምክር ቤት አባላትን ይዟል የሽግግር መንግሥቱ የተወካዮች ምክር ቤት። ከዚህም ጋር ተያይዞ ነበር የብሔራዊ፣ ክልላዊ፣ የዞን እና የወረዳ ምክርቤት ምርጫዎችን ለማካሄድ ሰኔ ቀን ቀጠሮ የተቆረጠው። የሽግግር መንግሥቱ ተሳትፎ የነበረው ኦነግ ለሰኔ የተቀጠረው ምርጫ የሚያበቃ ዝግጅት የለም ብሎ ከምርጫ የወጣበት ወቅት ነበር። ወይዘሮ አስካለም የትጥቅ ትግል ያካሂድ የነበረውን የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት ኢዲዩን ወክለው ነበር የመጀመሪያ ምርጫ ላይ የተሳተፉት። በወቅቱ ክልል 14 በነበረችው አዲስ አበባ ለወረዳ ምክር ቤት አባልነት ወረዳ 13 ቀበሌ 03ን ወክለው እጩ ተወዳዳሪ ነበሩ። የምርጫው ቀንም ደረሰ። እሳቸውም ሆነ ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ከምርጫ ጣቢያው ገለል ብለው ነበር። ወይዘሮ አስካለ እንደሚሉት የብሔራዊ፣ ክልላዊና የወረዳ ምክር ቤት አባላት ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት በምርጫው ቀን እጩ ተወዳዳሪዎች ከምርጫ ጣቢያው 500 ሜትር ርቀት መገኘት አለባቸው የሚል አንቀፅ አስፍሯል። እሳቸውም ሆነ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ይሄንን ህግ ቢያከብሩም የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ እጩ ተወዳዳሪ በምርጫ ጣቢያ "እንደፈለገች እየገባች፣ እየወጣች ነው" ሲሉ ያስቀመጧቸው ታዛቢዎች ጥቆማ ላኩባቸው። የምርጫው ጣቢያ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት አካባቢ ሲሆን ወይዘሮ አስካለ ሁኔታውን ሲሰሙ ወደቦታው አቀኑ። በቦታው ለነበሩት የምርጫ ሂደቱን የሚቆጣጠሩት የፀጥታ ኃይሎች ለምን የገዢውን ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ እንደሚያስገቡ ጠየቁ። "የሚታይ ሁኔታ ካለ እኛም እንይ አሉ" የፀጥታ ኃይሎቹ በምላሹ ዘወር በሉ ብለው ማስፈራራት ጀመሩ። እሰጣገባውም በዚያ መንገድ ተጀመረ። እሳቸውም "በምን ምክንያት እኔን ብቻ ታባርረኛለህ? እኔ እኮ እጩ ነኝ። የኦህዴድ/ ኢህአዴግ እጩ ተወዳዳሪ ከገባች፤ እኔ የማልገባበት ምክንያት ምንድን ነው ብዬ ለመግባት ስሞክር ዘወር በይ ብሎ ገፋኝ፤ በሰደፉ ሆዴን መታኝ" ይላሉ። "ያኔ ግብታዊ ነበሩ፤ ስርአት የላቸውም፤ ነገሩ ያኔም አሁንም ያው ናቸው። የመሳሪያ ባለቤትነት ያለው ሁሉ በኃይል ነው" ይላሉ በወቅቱ የስምንት ወር ነፍሰጡር የነበሩት ወይዘሮ አስካለ በሰደፍ ከተመቱባት እለት ጀምሮ በትንሹ ደም ይፈሳቸው ጀመር። "ያው ምንድን ነው እያልኩ እጨነቅ ነበር" የሚሉት ወይዘሮ አስካለ ከምርጫው አስራ አምስት ቀናት በኋላም የሚፈሳቸው ደም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ፤ አንዲት ዕለት፣ ሐምሌ 5፣ 1984 ዓ.ም የደም አበላ አደረጋቸው። ነፍስ ውጪ፣ ነፍስ ግቢ ሆነ። ወደ ህክምና ቦታ ተወሰዱ። "እኔ ከሞት ተረፍኩኝ ግን በሆዴ ውስጥ የነበረችው ልጅ አልተፈቀደላትም" ይላሉ። እሳቸው በህክምና ኃይል ህይወታቸው ቢተርፉም በአጭር የተቀጨችውን ልጃቸውን ሲያስቡ ያንገበግባቸዋል። ምንም እንኳን ህፃኗ በፅንስ ብትጨነግፍም ወይዘሮ አስካለ ፅንሷን ሴት እንደሆነች አድርገው ነው የሚናገሩት። የፅንሱ መጨንገፍ የእግር እሳት ብቻ ሳይሆን ወደ ቆራጥ ትግል እንዲገቡ ምክንያት መሆኑንም በሙሉ ልብ ነው የሚናገሩት። ከሽግግር መንግሥት ምስረታው እስካሁን ባለው የፖለቲካ ህይወታቸው ቆይታ ያዩት ውጣ ውረድ ይህ ነው የሚባል አይደለም። የምርጫ ተሳትፎ ሴቶችን ባገለለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን በምርጫ ለማሸነፍም በርካታ ትግሎችን አድርገዋል። ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ አገሪቷ ባካሄደችው ብሔራዊ ምርጫዎች ተሳትፈዋል- ከ1987 ዓ.ም ምርጫ በስተቀር። ሆኖም በተሳተፉባቸው ምርጫዎች እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሚያገኙት ድምፅ በቁጥር አናሳ ነው። "1፣ 2፣3 እያሉ ነው የሚለጥፉልን፤ በጣም ከሚገርመኝና ከሚያስደንቀኝ ታሪክ ልንገርሽ፤ እኔ ባለቤቴ፣ ልጆቼ አይመርጡኝም? ጎረቤቴና እህቴ አይመርጡኝም፤ አምስት ቤተሰብ ቢኖረኝ የአምስቱ ድምፅ የት ሄደ? ጌታ ያሳይሽ እስቲ! እና እንዲህ አድርገው እየቀለዱብን አጫፋሪ ሆነን እንደ ሙሽራ አጅበናቸው ነው የኖርነው" ይላሉ። "ትክክለኛ ምርጫ የተደረገው በ1997 ዓ.ም ነው፤ ከዛ በፊት የተደረጉ ምርጫዎች የይስሙላ ናቸው።" ይላሉ ሆኖም ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ ምርጫ ቅስቀሳዎችን አካሂደዋል። የምርጫ ቅስቀሳ ወጎች ለወይዘሮ አስካለ ቅስቀሳ ሲነሳ ዋነኛ መሰረት እድሮች እንደሆኑ ይናገራሉ። "መቼም መነሻችን የሴት እድር ናት" ይላሉ። ከእድሮች በተጨማሪም እቁብ፣ ከጎረቤት ጋር ሆነው ቡና በማፍላት በዋነኝነት ሴቶችን በመጥራት ፓርቲያችን ያቀደውን ያስረዳሉ። በየመንደሩም የየራሳቸውን ደጋፊ ሰዎች አሰማርተው በየወረዳው፣ በየቀበሌውና በየሰፈሩ በዚህ ሰዓት ለቅስቀሳ ይመጣሉ ተብሎ ይነገራል። በሚወዳደሩባቸው ወረዳዎች ላይ ከታዛቢዎች ጋር አብረው ይዞራሉ። ምንም እንኳን የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ መንግሥት የሚከተሏቸው ርዕዮተ ዓለማትም ሆነ የሚያወጧቸው ፖሊሲዎችም ሆነ በተደጋጋሚ የሚሰሙ ቃላት ኒኦ ሊበራሊዝም፣ ዲሞክራሲ፣ ፌዴራሊዝም ከበርካታ ኢትዮጵያውያን የተነጠሉ ቢሆንም ወይዘሮ አስካለ ማህበረሰቡ በሚገባውና በሚረዳው መልኩ እንደሚያስረዱ ይናገራሉ። አንድ መንደር ውስጥ ውሃ፣ ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት ከሌለ ፓርቲያቸው በወረዳው ያለውን ችግር የሚቀረፍበትን ከምሁራኖች እንዲሁም ከመንግሥት ጋር በመደራደር ያስፈፅማል ይላሉ። እሳቸውን ቢመርጡ የሴቶችን ጥያቄዎች ወደፊት በማምጣት እንዲሁም ኃገራዊ ጉዳዮችን ጥያቄ በማቅረብና በመከራከር ወደ ውጤት የሚገቡበትን መንገድ እንደሚቀይሱና ከተጠናከሩም ለመንግሥትነት የማይበቁበት ምክንያት እንደሌለም ያስረዳሉ። በተለያዩ ቦታዎች ሲቀስቅሱ አንዳንድ ሴቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችም ያስደነግጣቸው እንደነበር ያወሳሉ። "ምን ለራስሽ ጥቅም ነው ብትመረጭ፤ 'እዛ ከገባሽ በኋላ መች ዘወር ብለሽ ታይናለሽ? እኛ እንደሆነ ከዚች ከችግራችን አንወጣም፤ አውቃችሁ ነው፤ ደግሞ የናንተ የፖለቲካ ድርጅት ምን ያህል ከመንግሥት ጋርስ ተደራድሮ የማስፈፀም አቅም አለው ብለው ያስደነግጡሻል" የሚሉት ወይዘሮ አስካለ አንዳንዶችም "እናንተ ዝም ብላችሁ እንዲያው ለራሳችሁ ጥቅም ነው። አንድ ስራ አጥ ስራ ለማስያዝ ከሆነ በጣም ጥሩ ነው እንመርጥሻለን" የሚሉ እንዲሁም "ከናንተ ጋር ስራ አንፈታም ብለው ጥለውንም የሚሄዱ ሰዎች አሉ" ይላሉ። ለዘመናት በፖለቲከኞች ባዶ ቃል መግባት የተሰላቹ ነዋሪዎች በርካቶች እንደሆኑ ይናገራሉ። የሴቶች ወደ አደባባይ መውጣት እንደ ነውር ተደርጎ በሚታይበት ሁኔታ እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ ያሉት ማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊና ሌሎች መዋቅሮችም ሴቶች በፖለቲካው እንዳይሳተፉ እክል ሆነዋል። ከዚህም በተጨማሪም በርካታ ሴቶችም ትዳር አጋሮቻቸውን ፍቃድ ማግኘት እንዲሁ ቁልፍ ነገር መሆኑንም ወይዘሮ አስካለ ይረዳሉ። በአንድ ወቅት ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ጉራራ ጊዮርጎስ የሚባል ቤተክርስቲያን አካባቢ ቅስቀሳ እያካሄዱ ነበር። ቅስቀሳውን እያደረጉ የነበረው በህብረት ሲሆን እሳቸውን ጨምሮ ሶስት ወንዶችና ሶስት ሴቶች ሆነው ነው። በቅርበት የሚያውቋትንም ጓደኛቸውንም የሰፈሩን ሴቶች ሰብስባ እንድትጠብቃቸው ነገሯት። ቤቷ አካባቢ ሲደርሱ "ማን አለ?" ብለው መልዕክተኛ ላኩ። እሷም ከግቢው ወጣ ብላ ተጨንቃ መጣች። በወቅቱ ባለቤቷ ለምሳ እንደመጣና እሱ ስራ እስኪሄድ እንዲጠብቁ ነገሯቸው። ወይዘሮ አስካለ እንደሚሉት ባለቤቷ እንዲህ አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ውስጥ በጭራሽ እንድትገባ አይፈልግም። ባለቤቷም እስኪሄድ ሌላ ሰፈር ሄደው የአካባቢውን ሴቶች ሰብስበው ምርጫ እንዴት እንደሚመረጥ፤ ስለ ምልክቶቹ ተናገሩ። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ጓደኛቸው ልጆች ሄዶ ባለቤቷ እንደሄደና መምጣት እንደሚችሉ ተነገራቸው። በቦታው ሲደርሱም በጓሯቸው በርካታ ሴቶችን ሰብስባ ጠበቀቻቸው፤ የምርጫ ቅስቀሳውም ሆነ እንዴት እንደሚመረጥ እየተወያዩ ባሉበት ወቅት የጓደኛቸው ባለቤት እቃ ረስቶ ተመልሶ መጣ። "ምን አባቴ ይዋጠኝ፤ የሰው ትዳር አፈረስኩ ብዬ ተጨነቅኩኝ" ይላሉ። "እሱም አስካለ ምን ሆነሻል አለኝ? እዚህ ለቅስቀሳ መጥቼ ከእንግዶች ጋር ውሃ ጠምቶን ነው አልኩኝ የእህቴ ቤት ነው ብየ መጣሁ አልኩት፤ ውሃ ክፍል እኔ ቤት የተዘረጋ መሰላችሁ እንዴ አለኝ እና በዚህ አለባብሰን አለፍነው፤ እኛም ጨርሰን ወጣን። መቼም እድሜ ልኬን አልረሳውም። " ይላሉ ከዚህ ቀደም በእግራቸው ቤት ለቤት በመዞር፣ በሴት እድር፣ በእቁብ፣ በመተዋወቅና በጓደኝነት የነበረው የምርጫ ቅስቀሳ የተቀየረው በ1997 ዓ.ም ምርጫ ነው። የ1997 ዓ.ም ምርጫ ቅስቀሳዎች በይፋ የሆኑበትና በመኪናም እንዲሁም ያለ እረፍት የቀሰቀሱበት ወቅት ሲሆን መራጭም እንደዚያ የተነሳሳበት ወቅት የለም ይላሉ። በተናጠል ሳይሆን በተደራጀ መልኩ በራሪ ወረቀት እየበተኑ ይቀሰቅሱ ጀመር። የ1997 ዓ.ም ቅስቀሳው ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ፓርቲዎች ተደራጅተው የመጡበት ወቅት ነበር። የወይዘሮ አስካለ ፓርቲ ኢዲዩም የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ህብረት የተባለውን ፓርቲ ከመሰረተቱት 15 ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። ፓርቲያቸው በዚህ ወቅት በተለያዩ የክልል ከተሞች እንዲሁ እየተዘወዋወሩ ቀስቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ወይዘሮ አስካለ ከ15 በላይ የክርክር መድረኮች ከነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ዶክተር መረራ ጉዲና ጋር በመሆን ከተለያዩ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋርም በመድረክ ላይ ተከራክረዋል። በተለይም የምርጫ ቅስቀሳዎች ሲነሱ ሚያዝያ 30፣ 1997 ዓ.ምን ያስታውሱታል። ቅንጅት ሰላማዊ ሰልፍ የጠራበትና ህዝቡ ግልብጥ ብሎ የተመመበትና፣ በረዶ፣ ዶፍ እየወረደበት ለለውጥ የዘመረበት ወቅት ነው ይላሉ። ባለቤታቸውን በሞት ያጡት ወይዘሮ አስካለ አምስት ልጆቻቸውን የማሳደግ ኃላፊነቱም የተጣለው በሳቸው ላይ ነው። በዚህ ወቅትም ሙሉ ቀን ሲቀሰቅሱ ይውላሉ። ሌሊት ምግብ ሰርተው ወደ 10፡30 አካባቢ ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ለነበረው ልጃቸው ምግብ ለማድረስና ለማየት ይሄዳሉ። "ሌሊት እንቅልፍ አይወስደኝም፤ ጭንቀቱም ደግሞ ብዙ ነው፤ ልጄን አፍነው ወሰዱት ይሆን? እንዲህ አደረጉት ይሆን ? እያልኩ በጭንቀት እብሰከሰካለሁ "የምን እንቅልፍ አመጣሽብኝ፤ ያን ጊዜ ሳስበው በጣም ይሰማኛል፤ ስሜቴን ይነካኛል" በሳግ በተቆራረጠ ድምፅ "ሴት ፖለቲከኛ መሆን ትልቅ አደጋ አለው" የሚሉት ወይዘሮ አስካለ በተለይም በርካታ ሴቶች የቤተሰብ፣ መስሪያ ቤት እንዲሁም ሌሎች ኃላፊነት አደራርበው በፖለቲካው መሳተፍ በጣም ከባድ እንደሆነም ይናገራሉ። "ሆደ ሰፊነት፤ ልበ ሙሉነት ያስፈልጋል። ተስፋ ያለ መቁረጥ ያስፈልጋል። ይሄ ይገጥመኝ ይሆን? ራስሽን ማሳመን አለብሽ" ይላሉ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች በባለፉት አመታት በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ቢሯቸው ከመዘጋት ጀምሮ፣ የአባላት እስር፣ ማስፈራራሪያዎች እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ። በተለይም ምርጫዎች በሚቃረቡበት ወቅት በየሰፈሩ ፓርቲያቸውን ለማጠልሸት ይሰሩ የነበሩ ስራዎች በርካታ ናቸው ይላሉ። የምርጫ ፖስተሮቻቸው ላይ ንብ በመለጠፍ እንዲሁም ሌሎችንም ተግባራት ያከናውኑ ነበር የሚሉ ሲሆን ምርጫ ቦርድም ጋር ከሰው ነበር። በተለይ ሴት ተቃዋሚ አባላት ከሆኑ የሴቶች ማህበር መታወቂያ እንዳያገኙ በማድረግና ተቃዋሚ ሴቶችን በማግለል ጫና ያደርሱ እንደነበር ያስታውሳሉ። በተለያዩ ማህበራት ውስጥ በሚገኙ ድርጅቶችም የተቃዋሚ ሴቶችን እንደ ጠላት በማሳየት "ሰውን በጥቅማጥቅም ይዘውት ነበር" ይላሉ። "የኢህአዴግ ማስፈራሪያ ብትሰፍሪው ብትሰፍሪው የሚያልቅ አይደለም፤ አይደለም ሌላውን ህዝብ እንዳይመርጥሽ ማድረግ ይቅርና ቤተሰቦችሽ መሃል ገብቶ አንጃ ይፈጥርብሻል። ይሄ መንግሥት የመጣው ለናንተ ነው፤ የናታችሁ ለኢዲዩ ማገልገል፤ ኢዲዩ ዘውድ አስመላሽ ድርጅት ነው" ይላሉ ኢዲዪ ፊውዳላዊና የቡርዧ ስርአት ከማለትም በተጨማሪ በ1997 ዓ.ም በነበረው ምርጫ በወቅቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ኃብት ተማሪ የነበረው ልጃቸውን ጠርተው እንዳስፈራሩትም ይናገራሉ። " የኢዲዩን እንዲሁም የእናትህን አላማ ትደግፋለህ ወይ ብለው አስፈራሩት፤ በእናትህ ላይ ሰላይ ሁን ነው የምትሉኝ፤ ብሎ ጠየቃቸው? አላደርገውም፤ እኔ የራሴ ምርጫ አለኝ ያንን ደግሞ አላደርገውም የሚል ምላሽ ሰጥቷቸዋል" ማስፈራሪያና ዛቻ በሳቸው እንዲሁም በልጃቸው ላይ ደርሷል የሚሉት ወይዘሮ አስካለ "ቤተሰቦቼ ላይ ከፍተኛ ስቃይ አድርገዋል" ይላሉ። እሳቸውም ቢሆን በየጊዜው በተደጋጋሚ ታስረዋልም፤ ተፈትተዋልም። አስራ አምስት ቀን፣ ሃያ ቀናት በተደጋጋሚ ይታሰራሉ፤ ከዚያም ይፈታሉ። የፖለቲካ ህይወት ወይዘሮ አስካለ ኃይሌ አለሙ ተወልደው ያደጉት አዲስ አበባ ሲሆን የፖለቲካ ህይወታቸውም የሚጀምረው በ1960ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት ነው። መሬት ላራሹ በሚል የትግል ችቦ ሲቀጣጠል በወቅቱ የፈለገ ህይወት ዮርዳኖስ ተማሪና ገና ፍሬ ልጅ ቢሆኑም "ድንጋይ ወርውሬያለሁ" ይላሉ። ትምህርታቸውን ጨርሰው አዲስ አበባና ውሃና ፍሳሽ ከተቀጠሩ በኋላ "ሴት በሴትነቷ ትከበር፤ አይቻልምና ያለሷ ለመኖር" የሚሉ መዝሙሮች የሴቶችን ጥያቄዎች ላይ አጫሩባቸው። የሴቶች የውይይት ክበብም ተሳታፊ ሆኑ፤ የማርክሲዝምና ሌኒኒዝም ፅንሰ ሃሳቦችና ትምህርቶች መውሰድ ጀመሩ። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር የአብዮት ጥበቃም ስልጠናም ወስደዋል፤ "አብዮተኛም ሆንኩ" ይላሉ። የሰራተኛው ጥቅም መከበር አለበት በሚልም ቋሚ ተከራካሪ ሆኑ፤ የወዛደሩንም ጥቅም ለማስከበር የሰራተኛ ማህበሩንም ተቀላቀሉ፤ ከመምሪያ ኃላፊዎችና ከስራ አስኪያጆች ጋርም መላተም ጀመሩ። በዚህም መሃል ማግባትና መውለድ መጣ ትንሽ እረፍት መሃል ላይ ወሰዱ። ልጅም እያሳደጉ ትግላቸውን ቀጠሉ። በስደት ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት (ኢዲዩ)ፓርቲ ሃገር ውስጥ ሲገባ፤ ባለቤታቸውም የፓርቲው አቀንቃኝ ናቸው በሚል በተደጋጋሚ ለዘብጥያ ተዳርገዋል። ባለቤታቸው ከሞቱ በኋላ ወይዘሮ አስካለ ኢዲዩን ተቀላቀሉ። በኢዲዩም ከታች እስከ ከፍተኛ አመራር ደርሰዋል። በተለይም በ1997 ዓ.ም በኢዲዩ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ወ/ሮ አስካለ ዋና ፀሐፊ መሆንም ችለው ነበር። በአመታት ውስጥ በፖለቲካ ፓርቲ ተሳትፏቸው ያዩት ነገር ቢኖር ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ቢሆኑም ሴት አባላታቶቻቸውን ከቁጥር ማሟያ ውጭ እንደማያዩዋቸው ነው። ሆኖም በተዘረጋው ስርአት ውስጥ የራሳቸውን አስተዋፅኦ ለማርበክት መታገላቸውን ይናገራሉ። እስከ 2001 ዓ.ም ድረስም በኢዲዩ ሲታገሉ ነበር። ከዚያ በኋላ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰነጣጠቅና መበታተንም ተከተለ። ብዙ የፖለቲካ ፖርተዎች ተበታተኑ የኢትዮጵያ ፍትህና ዲሞክራሲ ሃይሎች ግንባር፣ ኢፍድሃግን መሰረቱ ስራ አስፈፃሚ ነበሩ። ድርጅቱ ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ፍርድ ቤትም ደረጃ ተከራክረው ነበር። ከዚያ በኋላ ለአመታት ትንሽ ገለል ብለው ወደራሳቸው ንግድ ተመልሰው በወጪ ንግድ ተሰማርተው ነበር። በግዞት ላይ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ውስጥ ተመለሱ ሲባል ከአራት አስርት አመታት በፊት የተመሰረተው ህብረ ህዝብምና ህብረትን ከመሰረቱት ውስጥ አንዱ የሆነው ፓርቲ ሲመለስ እሱን ተቀላቀሉ። በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና በአገር ውስጥም የድርጅቱ ተወካይ ናቸው። በአሁኑ ወቅት አገሪቷ ባለችበት የአለመረጋጋትና የፀጥታ ሁኔታ ምርጫ ቅስቀሳም ሆነ ለመወዳደደር ፈታኝ እንደሆነ የሚናገሩት ወይዘሮ አስካለ በአሁኑ ምርጫ እንደማይወዳደሩ ይናገራሉ። ሆኖም በሌሎች መድረኮች ትግላቸውን እንደሚቀጥሉም አፅንኦት ይሰጣሉ። "ሰው ሲፈጠር ለሞት ነው የተዘጋጀው፤ ተልከስክሶ ከመሞት ታሪክ ሰርቶ መሞት የተሻለ ነው" እኔ ዛሬም፣ ነገም አልተኛም ወጣቶቻችን እንዲወጡ ነው የምንፈልገው፤ ያ ትውልድ ተብለን እያለፍን ነው።"ይላሉ።
48237005
https://www.bbc.com/amharic/48237005
"ምርጫው እንዲራዘም እንፈልጋለን" የኢዜማ ምክትል መሪ አቶ አንዷለም አራጌ
የቀድሞው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የመላ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄና አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ራሳቸውን አክስመው የመሰረቱት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ትላንት መሪና ምክትል መሪ መርጧል። ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበርም ሾሟል።
አመራሮቹ ፓርቲው ሁለት ዓይነት የአመራር አወቃቀር አለው ብለዋል። በዚህም መሰረት የፓርቲው ሊቀ መንበር እና የፓርቲው መሪ የተለያዩ ናቸው። የፓርቲው ሊቀ መንበር የፓርቲውን የአደረጃጀትና የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ የሚመራ ሲሆን፤ የፓርቲው መሪ ፓርቲው ለፖለቲካ ስልጣን የሚያደርገውን ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴና በመንግሥት ስልጣን ውስጥ የፓርቲውን አቋም የሚያስፈፅም አካል ነው በማለትም ያብራራሉ። • ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢዜማ መሪ ሆነው ተመረጡ ፓርቲው አሸንፎ ስልጣን ቢይዝ የመንግሥትን ሥልጣን እና የፖለቲካ ስልጣንን ለመለያየት ታስቦ የተዋቀረ አደረጃጀት ነው። በዚህም መሰረት የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ፤ የፓርቲው መሪ ደግሞ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ሆነው ተመርጠዋል። ስለፓርቲው አቋም፣ ስለቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ከፓርቲው ምክትል መሪ አቶ አንዷለም አራጌ ጋር ቆይታ አድርገናል። የብሔር ፓለቲካ ገኖ በወጣበት በዚህ ጊዜ የዜግነት ፖለቲካን ይዛችሁ ወደፊት ለመራመድያሰባችሁት እንዴት ነው? የምትተማመኑትስ ምንድን ነው? አቶ አንዷለም አራጌ፡ በፕሮግራምና በደንብ የያዝነው እምነት አለ። ለብሔር ጉዳይ ብለን ያነሳነው ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን ወደተሻለ አቅጣጫ ይወስዳታል ብለን የምናምነውን በዜግነት ላይ መሰረት ያደረገ ፖለቲካ ነው የምናራምደው። ይህ ደግሞ እያንዳንዱን ዜጋ ይመለከታል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሚወከልበት ነው። በእያንዳንዱ [ሰው] ቤት ውስጥ የሚገባ ነገር ነው። ሕዝቡ በተፈጥሮው ሕብረ ብሔራዊ ነው። በመልኩ፣ በአኗኗሩ፣ በባህሉ፣ በእምነቱና በሁሉ ነገር ተሰባጥሮ የሚኖር ሕዝብ ነው። ሕዝቡ ውስጥ ያለውን ነገር መልሰን ለሕዝቡ ነው የምንነግረው። ሕዝቡ ልብ ውስጥ ያለውን መልሶ መንገር አያከስርም። በቀላሉ ፍሬ ያፈራል ብዬ አስባለሁ። በብሔር ፓለቲካ የተሰማሩት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንም ቢሆኑ ከዚህ አስተሳሰብ ጨርሰው ይርቃሉ ብዬ አላስብም። በተለያዩ ወቅቶች የተነሱ ግጭቶች ሊያሻቅቡ ይችላሉ። ግን ውሎ አድሮ ሥራውን ሲያዩት እነሱም ወደቀናው መንገድ ይመለሳሉ ብዬ አምናለሁ። ለምሳሌ ቅንጅትን ብናይ ሕዝቡን አሳምኖ፤ የሕዝቡን ድጋፍ አግኝቶ ኢህአዴግን መገዳደር ቀላል ነበር የሆነለት። አሁን ግን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ተቀባይነት አላቸው። ኢህአዴግ ይህን ያህል ተቀባይነት ያለው መሪ ባለው ሁኔታ ፓርቲውን መገዳደር ቀላል ይሆናል? አቶ አንዷለም አራጌ፡ በእርግጥ [ቀድሞና አሁን ከኢህአዴግ ጋር መፎካከር] ልዩነት አለው። ዶ/ር ዓብይ ጋር ያለው ቀናነት፣ አርቆ አሳቢነት፣ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በኢህአዴግ ውሰጥ ከተለመደው የተለየ ነው፤ በጎ ነገር ነው። ለዛ ሁላችንም ድጋፋችንን ቸረናቸዋል። ነገር ግን ኢህአዴግ የሚከተላቸው አላማዎቹና መርሆቹ አሁንም እንደቆሙ ናቸው። ለውጡም ቢሆን ከዶክተር ዓብይ ብዙ አልወረደም። በ547ቱም ወረዳዎች የሚወዳደሩት ዶ/ር ዓብይ ብቻ አይደሉም። ዶ/ር ዓብይ የሚወከሉት በአንድ ወረዳ ላይ ነው። ሕዝቡ በየወረዳው የሚመርጣቸው ሰዎች ውድድር የሚካሄደው ኢህአዴግ በሚያቀርባቸውና እኛ [በምናቀርባቸው ተፎካካሪዎች] አላማ፣ ማንነትና ሥነ ምግባር መካከል ነው። በብዙ ቦታዎች እናሸንፋቸዋለን ብዬ አምናለሁ። አልጠራጠርም። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ደጋፊ ማነው? ተከታያችን ማነው ትላላችሁ? አቶ አንዷለም አራጌ፡ የኛ ደጋፊ በሕብረ ብሔራዊ አስተሳሰብ፣ በኢትዮጵያ አንድነት፣ በኢትዮጵያ ታሪክ የሚኮራው፣ አሁንም በኢትዮጵያ ተስፋ የሚያምነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ኢትዮጵያውያን ሁሉ የኛ እምነት ደጋፊዎች ናቸው። እኛ የምናወራው ስለአንድ ብሔር፣ ስለአንድ ክልል ወይም ስለአንድ ቀበሌ አይደለም። እኛ የምናወራው ስለጠቅላላ ሀገራችን፣ ስለጋራ ተስፋችን፣ ስላለፈው በጎም መጥፎም ታሪካችን [እና] የዚያ ሕብር፣ የዚያ ግማጅ መሆናችንን ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ የዚህ ሁሉ ነገር ወራሽና አስፈጻሚም ስለሆነ አብዛኛው የኛ ደጋፊ ነው ብለን እናምናለን። በአስተሳሰብ ልዕልና የሚያምን፣ በአመክንዮ ልዕልና የሚያምን እና ለኢትዮጵያ ያለንን ፖሊሲ መዝኖ ይበጃል፤ አይበጅም ብሎ ፍርድ መስጠት የሚችል፤ ቀና አስተሳሰብ፣ በጎ ህሊና ያለው ሁሉ የኛ ደጋፊ ነው ብለን እናምናለን። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ የሚታወቁ ሰዎችን ወደአመራር አምጥቷል። በሌሎች ፓርቲዎች መከፋፈልና መፈራረስ ውስጥ የነበሩ ሰዎች አሁን የኢዜማ ፊት ሆነው መምጣታቸው አሉታዊ ነገር ያስከትላል የሚል ስጋት አላችሁ? አቶ አንዷለም አራጌ፡ እኛ ስጋት የለብንም። የድሮ ነገር ሲነሳ እንኳን በኛ መካከል አይደለም፤ ትላንት ልጆቻንን ሲያስለቅሱ የነበሩ፤ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በየመንገዱ፣ በየታዛው የገደሉ ኢህአዴግ ውስጥ ያሉ ሰዎችንም ይቅር ብለናል። ስለዚህ በይቅርታ እናምናለን። በፍቅር እንጸናለን። ሰዎችን የምንመዝነው ለዛሬዋና ለነገዋ ኢትዮጵያ በሚኖራቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እንጂ ትላንት የነበሩበትን በደል ሁሉ እየቆጠርን በዛ ልንመዝናቸው አንሞክርም። የሰው ልጅ ትልቁ የሰብዕናው አካሉ ካለፈው ማንነቱ የመማር አቅሙ ነው። ስለዚህ የኛ ደጋፊ እነዚህን መሪዎች ሲመርጥ ይህንን ሁሉ ግንዛቤ ውስጥ በመክተት ነው ብዬ አምናለሁ። ሁላችንም የተለያየ ፓርቲ ውስጥ ነበርን። መራጩ ግን ያለውን ሉአላዊ ስልጣን ተጠቅሞ መርጧል። ሕዝቡም የይቅርታ መንፈስና ልብ አለው። መቻቻልን፣ አንድነትን ይደግፋል። ትላንት ላይ ሳይሆን ዛሬ ላይ ቆሞ ነገን ማየት ይፈልጋል ብለን እናምናለን። ስለዚህ ችግር ያመጣል ብለን አናስብም። ብዙ አዳዲስ መሪዎችም አሉ። አሁን የመጀመሪያው ጉባዔ ስለሆነ እንጂ ነገ ከነገ ወዲያ ታላላቅ መሪዎች የሚያፈራ ፓርቲ ነው የፈጠርነው። አሁን አመራር ውስጥ የተወሰነ ልምድ ያላቸው ሰዎች መካተታቸው ለድርጅቱ ጥንካሬ እንጂ ድክመት አይሆንም ብዬ ነው የማምነው። • የኦሮሞ ፓርቲዎች የጋራ ፎረም ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደረሱ በቀድሞ ፓርቲዎች መከፋፈል ውስጥ የነበሩና አንዳንዶች 'የከሰሩ ፖለቲከኞች' የሚሏቸውን ወደ ፓርቲው አመራር ማምጣታችሁ ጥሩ አይደለም የሚል አስተያየት አለ? አቶ አንዷለም አራጌ፡ የምንታገለው ስለሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነት ነው። ነገ ከዚህም በላይ በጠነከሩ ቃላት የሚገለጹ ሰዎች ምርጫ ሊያሸንፉ ይችላሉ። የዴሞክራሲ ውበቱ ደግሞ ተሸናፊና አሸናፊ ይኖራል። ተሸናፊው ጊዜውን ጠብቆ ለማሸነፍ ይሠራል። የከሰሩ ፓለቲከኞች ሌላም ስም ሊሰጥ ይችላል። ግን እነዚህ የሚባሉትም ሰዎች ኪሳራ ከማን አንጻር እንደሚለካ አናውቅም። በዚ ሀገር እንደዚህ አይነት የሚያሳፍር ነገር መስማት የተለመደ ነው። ትላንት ብዙ ነገር ሲሠሩ የነበሩ ሰዎች ሌሎችን በባንዳነት፣ ሌሎችን በገዳይነት ሲከሱ እናውቃለን። እንደዚህ አይነት መፈራረጅና ጭቃ መቀባባት ውስጥ መግባት አንፈልግም። እንዲያውም የከሰረ ማለት ይሄ ነው። በጣም ከሥነ ምግባር የወጣና ጸያፍ በሆነ የፖለቲካ ስርአትና ብሂል ውስጥ መቆየት አንፈልግም። ፓለቲካው መታደስ አለበት። መዘመን አለበት። ሀሳብ ላይ ትኩረት አድርጎ መታገል ተገቢ ነው ብለን እናምናለን። የኛ አባላት ግን ሉአላዊ መብታቸውን ተጠቅመው ይበጁኛል ያሏቸውን ሰዎች መርጠዋል። ስለዚህ እሱን ሁልጊዜ እናከብራለን። ዜጋው ሰውን የመመዘን አቅም አለው። የከሰረ ፓለቲከኛ ብሎ የሚሳደበው ሰው፤ የመሳደብ መብት ባይኖረውም፤ ሀሳቡን የመግለጽ መብት እንዳለው ሁሉ፤ የመምረጥ መብት ያላቸው ዜጎች፣ መሪዎቻቸውን መርጠዋል። ዋናው ያ ነው። በሚመረጥ ሰው ሁሉንም ማስደሰት አይቻልም። • "በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ቀደም ሲል ተቃዋሚዎችን በፕሮፓጋንዳም ይሁን በተለያዩ መንገዶች የሚገዳደረው ገዢው ፓርቲ ነበር። አሁን ግን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዋናዮች በዝተዋል። አክቲቪስቶችና ተጽዕኖ ፈጣሪ ቡድኖችም አሉ። በማኅበራዊ ሚዲያም በጣም ጠንካራ እንቅስቃሴ አለ። በዚህ የፖለቲካ ጨዋታው በተቀየረበት ጊዜ ራሳችሁን ለማስተዋወቅና የሚሰነዘርባችሁን ለመመለሰ ምን አይነት ስልት ለመከተል አስባችኋል? አቶ አንዷለም አራጌ፡ እኛ እየሞከርን ያለነው አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስተዋወቅ ነው። በኛ በኩል መንገዳችን ፍቅር ነው። ያንን ደግሞ በተግባር እናሳያለን። ኢትዮጵያውያን ስንል የሚደግፉን፣ የሚመስሉንን ብቻ አይደለም። እንዲያውም ሀሳባቸው ከኛ የሚለየውንም በጣም እናከብራለን። ለነሱ ጆሮ እንሰጣለን። ምክንያቱም ያለንን የሚደግሙልን ሳይሆን የሌለንን የሚነግሩን ሰዎች ናቸው። እኛ ያላየነው እነሱ ጋር ያለው ምንድንነው ብለን ትኩረት ሰጥተን እንከታተላለን። ሁልጊዜም የሀሳብ ልዩነት እንዲኖረን እንፈልጋለን። ምክንያቱም ሕዝብ የሚጠቀመው ከሀሳብ ልዩነት ነው። አንድ ላይ ተመሳሳይ ነገር ብናስተጋባ ትርጉም የለውም። ይህን የምናደርገው በፍቅርና በስርዓት ነው። ለኛ አክቲቪስትም፣ ሌላ ዘርፍ ተከትሎ እምነቱን የሚያራምድም አንድ ነው። በቀናነት እናስተናግዳለን። ጭቃ መቀባባት አልጠቀመንም። ገና ከምስረታው ቅሬታዎች እየተነሱባችሁ ነው። የሚሰነዘርባችሁን ነገር ፍቅር ብቻ ይመልሰዋል? አቶ አንዷለም አራጌ፡ ፍቅር ውስጥ ምክንያት አለ። ዝም ብሎ እንወዳችኋለን አይደለም። ፍቅር ውስጥ የምናደርገውን ነገር በንጽህና፣ በትህትናና በፍቅር እናደረገዋለን። እኛ እውነት የምንለውን ነገር በፍቅር፣ በትህትናና በክብር እናቀርባለን። ሕዝቡ ይፈርዳል። ያለንን ነገር የምናቀርበው ከሥነ ምግባር ባፈነገጠ ሁኔታ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በማይመጥን ሁኔታ ጭቃ በመቀባባት፣ ነውረኛ የሆነ አቀራረብ በመከተል አይደለም። እኛ ኢትዮጵያውያን አስተዳደጋችን ባህላችንም እንደዚህ ነው ብለን አናምንም። ለሀሳባቸው ክብር እንሰጣለን። ለሀሳባቸው ትኩረት እንሰጣለን። ግን ያንን በፍቅር፣ በንጽህና፣ በትህትናና በአክብሮት ምላሽ እንሰጣለን። ሀገራዊው ምርጫ እንደታሰበው በሚቀጥለው ዓመት የሚካሄድ ከሆነ ኢዜማ ዝግጁ ነው? ለመሳተፍ ያህል ሳይሆን ለማሸነፍ ወደምርጫ የመግባት አቅም አለው? አቶ አንዷለም አራጌ፡ እንኳን የዚህ ሀገር ፓርላማ የሌላውም ሀገር ፓርላማ ደመወዝ ብዙም የሚያስቀና አይመስለኝም። ገንዘብንም ታርጌት [ኢላማ] አድርጎ መኖር ከአንድ የመርህ ሰው የሚጠበቅ አይደለም። እኛ የምናስቀድመው ሀገራችንን ነው። እኛ የምናስቀድመው ለውጥን ነው። ሀገራችን በተስተካከለ የለውጥ ጎዳና ላይ እንድትሆን፤ አሁን የተጀመረው መንገድ በደንብ ተጠርጎ ይህችን ሀገር ለዘመናት ከቆየችበት የድክርት ጨለማ ታሪክ አውጥተን ብርሀን ወደነገሠበት የዴሞክራሲ ምድር ልናሻግራት እንፈልጋለን። ትልቁ ህልማችን እንዲወለድ፤ ስጋና ደም እንዲለብስ የምንፈልግው ይህንን ነው እንጂ፣ ምርጫ ማሸነፍ ሁለተኛ ነገር ነው። እኛ [ምርጫው] መራዘም አለበት [እንላለን]። ምክንያቱም [ያለን] ትልቅ አላማ የታሪክን ወንዝ የመቀየር አላማ ነውና በደንብ ተዘጋጅተን፣ የተቋማቱ ምሰሶዎች ቆመው፣ በማያዳግም ሁኔታ ለሁልጊዜም አርአያ የሚሆነን ምርጫ እንድናደርግ [እንፈልጋለን]። ያለፉት አይነት ምርጫ እንዳይደገም እንፈልጋለን። ምርጫው የሚደረግ ከሆነ ግን፤ በግድ ይሁን ተብሎ ብንወዳደር እኛ በ312 ወረዳዎች በጣም ጠንካራ የሚባል አደረጃጀት ፈጥረናል። ምክር ቤቶች ፈጥረናል። በቀሩት ወረዳዎችም በአጥጋቢ መልኩ መንቀሳቀስ እንችላለን። ሕዝብ በጣም እንደሚደግፈን እናምናለን። ሕዝብ ያውቀናል። ይህንን በድፍረት የምናገረው በፍርደ ገምድልነት ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀሳብ ይዘን እንደተነሳን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀሳብ፣ እምነቱን ተስፋው አብሮ ተከባብሮ መኖር እንጂ መገዳደልና መለያየት ስላልሆነ ነው። እኛ ደግሞ የዚህ ሀሳብ ደጋፊዎችና አራማጆች ስለሆንን ሕዝቡ ለእምነቱ፣ ለተስፋው ዘብ ይቆማል፣ ይታገላል ብለን እናምናለን። ስለዚህ በቀረው ጊዜም ቢሆን ተደራጅተን መታገል እንችላለን። ማሸነፍ እንችላለን ብለን እናምናለን።
news-52766056
https://www.bbc.com/amharic/news-52766056
ከ81 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአማራ ክልል አስታወቀ
ባለፉት ዓመታት በአማራ ክልል እና በሌሎች አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ተፈናቅለው የነበሩ ከ81 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ መቻሉን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጃለም አስታውቀዋል።
"ከነዚህም ውስጥ 74 ሺህ 273 ሺህ በላይ በክልሉ እንዲሁም 6ሺህ 836 ከክልሉ ውጭ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል" ብለዋል። በተከሰቱት ግጭቶች የሰው ህይወት ማለፉን፣ አካል መጉደሉን እና ንበረት መውደሙን የገለጹት በዚህም ምክንያት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመጠለያ ካምፖች ለመኖር መገደዳቸውን አስታውቀዋል። ተፈናቃዮቹ ወደቀዬአቸው ሲመለሱ እስከ 4 ወራት የሚደርስ ቀለብ እና ለእርሻ የሚሆን ግብዓት እንደተሟላላቸውም ገልጸዋል። ከአማራና ቅማነት እንዲሁም በጃዊ አካባቢ በነበሩ ግጭቶች 7 ሺህ በላይ ቤቶች መቃጠላቸውን አመልክተው ከ5200 ሺህ በላይ ቤቶች እንደገና ሲገነቡ፣ ከ130 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችም ጥገና ተደርጎላቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን አስታውቀዋል። "ከቤንሻንጉል ክልል ተፈናቅለው ያልተመለሱ 4ሺህ 720 ዜጎች አሉ። ከክልሉ መንግስት ጋር በተደረገ ውይይት ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ ፍላጎት አለ። ቻግኒ አካባቢ የነበሩ እና 4 ሺህ የሚያህሉ ሰዎች ባለፉት ቀናት ተመልሰዋል። ክልሉ ሁኔታዎችን አመቻችቶ ለመመለስ እየሰራ ነው። በሚመጡት ጥቂት ቀናት ቀሪዎቹ እንዲመለሱ እየተሠራ ነው" ብለዋል። ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ከተፈናቀሉት ሁሉም በሚባል ደረጃ ወደ ቀዬአቸው መግባታቸውን አስታውቀዋል። ለተፈናቃዮች የሚሆን ድጋፍ ለማሰባሰብ በተካሄደው ሥራ 720 ሚሊዮን ብር ቃል የተገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነውን መሰብሰብ መቻሉንም አስታውቀዋል።
news-54612589
https://www.bbc.com/amharic/news-54612589
ጣልያን፡ አረንጓዴ ፀጉር ይዞ ተወለደው ቡችላ
ጣልያን ውስጥ አረንጓዴ ቀለም ያለው ቡችላ መወለዱ ተሰማ።
ቡችላው በግብርና ሥራ የሚተዳደረው የክርስትያን ማሎቺ ሲሆን፣ ውሻው ስፔላቺያ ስድስት ቡችሎችን በተገላገለች ጊዜ አንዱ አረንጓዴ ፀጉር ይዞ መወለዱ ተነግሯል። ይህ ከሌሎች ቡችሎች ለየት ብሎ የተወለደው ቡችላ ፒስታችዮ የሚል ስም ተሰጥቶታል። የፒስታቺዮ እናት አምስት ወንድምና እህቶች አብረውት ተወልደዋል። በጣሊያንዋ ሳርዲና ከተማ የተወለደው ይህ ቡችላ ወንድምና እህቶቹ በአጠቃላይ ልክ እንደናታቸው ነጭ ፀጉርን ይዘው መወለዳቸው ተረጋግጧል። የእንስሳት ሕክምና ባለሙያዎች ለፒስታችዎ አረንጓዴ ፀጉር ይዞ መወለድ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። እንዲህ አይነት አረንጓዴ ፀጉር ይዞ መወለድ እጅጉን ያልተለመደ ነው ያሉት ባለሙያዎቹ ነገር ግን አይፈጠርም ማለት አለመሆኑን ፒስታችዎን ማስረጃ አድርገው አስረድተዋል። ቡችላው በእናቱ ማሕፀን ውስጥ ሳለ ቢልቨርዲን ከሚባል አረንጓዴ ፒግመንት ጋር ንክኪ ነበረው ማለት ነው ብለዋል። የፒስታቺዮ አረንጓዴ ፀጉሮች ግን አብረውት አይቆዩም፤ የእናቱን ነጭ ፀጉር ወደመያዝ ከአሁኑ እየሄዱ ነው። ገበሬው ማሎቺ የፒስታቺዮ ወንድምና እህቶች በሙሉ ውሻ እንፈልጋለን ላሉ ሰዎች ለመስጠት ወስኗል። ነገር ግን ፒስታቺዮን በጎች በመጠበቅ ያግዘኛል እኔው አሳድገዋለሁ ሲል ተናግሯል። ደግሞም ይላል ገበሬው ማሎቺ፣ አረንጓዴ የመልካም እድል ምልክት ነው። በማለት በቀሪው 2020 መልካም ነገር እንደሚገጥመኝ የሚጠቁም ቢሆንስ ብሏል።
44038787
https://www.bbc.com/amharic/44038787
ማንበብና መጻፍ ሳይችል 17 ዓመት ያስተማረው መምህር
'ማንበብና መጻፍ ዋናው ቁም ነገሩ' የሚለውን ብሂል የሚያጠይቅ ታሪክ ነው።
ትምህርት ለማስተላለፍ ከሚያስፈልጉ ክህሎቶች መካከል ማንበብ እና መጻፍ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። ታድያ ሁለቱን መሰረታዊ የእውቀት ማሸጋገሪያዎች ሳይችሉ ለ17 ዓመታት ማስተማር ይቻላልን? ጆን ኮርኮራን "ማንበብና መፃፍ ሳልችል ለዓመታት አስተምሬያለሁ" ይላል። እንዴት? ለሚለው ጥያቄም ምላሽ አለው። ጆን የመምህርነት ሙያን የተቀላቀለው እንደ አውሮፓውያኑ በ1960ዎቹ ነበር። ልጅነቱን በአሜሪካዋ ኒው ሜክሲኮ አሳልፎ፤ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ከተመረቀ በኋላ ለ17 ዓመታት አስተምሯል። ያደገው በምድር ላይ ማንኛውንም ነገር የመከወን ችሎታ እንዳለው በቤተሰቦቹ እየተነገረው ነበር። እሱም 'የሚሳነኝ አንዳችም የለም' በሚል ልበ ሙሉነት አደገ። ምኞቱ እንደ ታላላቅ እህቶቹ የተጨበጨበለት አንባቢ መሆን ነበር። ትምህርት ቤት በገባባቸው የመጀመሪያ ዓመታት የንባብ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች እምብዛም አልነበሩም። መምህራን እሱና የእድሜ እኩዮቹ ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ ያሳስቧቸዋል። ሰልፍ ላይ 'ከንዳ አውርድ' ከማለት ባለፈ የሚጠበቅባቸውም አልነበረም። ንባብ ለመቻል ፈጣሪን መማፀን ጆን ሁለተኛ ክፍል ሲደርስ ትምህርት ጠነከረ። ተማሪዎች ንባብ ይለማመዱ ጀመር። ለእሱ ግን ንባብ ፈፅሞ ግራ አጋቢ ነበር። "መጻሕፍት ስከፍት የማየው ነገር አይገባኝም።" ሲል ያስታውሳል። በልጅ አእምሮው መፍትሔ ሆኖ የታየው ፈጣሪን መማፀን ነበር። ዘወትር ከመተኛቱ በፊት ከእንቅልፉ ሲነቃ በንባብ ተክኖ ይነሳ ዘንድ ፈጣሪ እንዲያግዘው ይለማመናል። ከፀሎቱ በኋላ መጻሕፍት ቢያገላብጥም የጠበቀው ተአምር አልተከሰተም። እጣ ፈንታው ማንበብ የማይችሉ ተማሪዎች ማለትም 'የሰነፎች ጎራ'ን መቀላቀል ነበር። ምድቡን መቀላቀሉ ሰነፍ ተማሪ ስለመሆኑ 'ምስክር' የሆነ ቢመስለውም፣ መምህራኑ ግን ተስፋ አልቆረጡም። 'የኋላ ኋላ ንባብ ይገለጥለታል' ብለው ስላመኑ ከአንዱ ክፍል ወደ ሌላው እንዲሸጋገር ወሰኑ። አራተኛ፣ አምስተኛ . . . ክፍል መጨመሩን ቀጠለ። የንባብ ነገር ግን አልሆንልህ አለው "ለእኔ ትምህርት ቤት መሔድ የጦርነት አውድማ እንደመሔድ ነበር" ይላል። ተስፋ መቁረጥ የወለደው አመጸኛነት አምስተኛ ክፍል ሲደርስ ንባብ ባለመቻሉ ተስፋ ቆረጠና ትምህርት ቤቱን መጥላት ጀመረ። ሰባተኛ ክፍል ላይ ብስጭቱን ከተማሪዎች ጋር በመጋጨት ይገልፅ ጀመር። ባህሪው ከትምህርት ቤት ለመባረርም አበቃው። "መሆን የማልፈልገውን አይነት አመጸኛ ሰው ሆኜ ብገኝም፤ ምኞቴ ጎበዝ ተማሪ መሆን ነበር። ያሰብኩት ሊሳካልኝ አልቻለም እንጂ" ሲል ወቅቱን ይገልፃል። ስምንተኛ ክፍል ሲደርስ መምህራን የሚያዙትን ባጠቃላይ በመፈፀም ራሱን ለመቀየር ሞከረ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን የመወጣት ተስፋውም አንሰራራ። ሆኖም ንባብና ጆን መሀከል ያለው ጉድጓድ ሊጠብ አልቻለም። በተቃራኒው በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጎበዝ ስለነበር ሯጭ መሆን ይመኝ ነበር። በተማሪዎች ዘንድ ከመወደዱ የተነሳ የቤት ሥራውን የሚሰሩለት ጓደኞቹ ነበሩ። በፈተና ወቅት፣ የክፍል ጓደኞቹ መልስ በመስጠት እንዲያልፍ ይረዱታል። ጆን ግን ስሙን ከመጻፍ ያለፈ ችሎታ አልነበረውም። "የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ብሆንም የንባብ ችሎታዬ የሦስተኛ ክፍል ተማሪ እንኳን አይሆንም ነበር" ይላል። "ከኮራጅነት ወደ ወንጀለኛነት ተሸጋገርኩ" ጆን በሩጫ ዘርፍ ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ ዩኒቨርስቲ ገባ። ኩረጃንም ቀጠለበት። ቀደም ያሉ ዓመታት ፈተናዎችን መልስ በመሸምደድ መፈተንን ዋነኛ አማራጩ አደረግ። የመምህራንን ቢሮ ሰብሮ በመግባት የጥያቄ ወረቀት መስረቅ ሌላው መንገድ ነበር። የአንድ መምህርን የፈተና ጥያቄ ለመስረቅ ጓደኞቹን ጭምር ማሰማራቱን ሲያስታውስ "ከኮራጅነት ወደ ወንጀለኛነት ተሸጋገርኩ" በማለት ነው። ከፈተናዎቹ አንዱን የሰረቀው ቁልፍ ሰሪ ቀጥሮ የመምህሩን ቢሮ በተመሳሳይ ቁልፍ በማስከፈት ነበር። ፈተናውን ለማለፍ ብቸኛ አማራጩ እንደሆነ ቢያምንም ስርቆት ህሊናውን ይቆጠቁጠው ጀመር። "ፈተናውን ከሰረቅኩ በኋላ አለቀስኩ" ቢልም፤ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም መመረቅ የተሻለ ህይወት ለመምራት ቁልፍ እንደሆነ በማመን ዲግሪ ለማግኘት ኩረጃን ገፋበት። እንደምንም ብሎ ከተመረቀ በኋላ የመምህራን እጥረት ያለበት አካባቢ የማስተማር እድል አገኘ። ማንበብ ሳይችል መምህር የመሆኑን ተቃርኖ "ማንም ሰው አንድ መምህር ማንበብ አይችልም ብሎ አያስብም" ሲል ይናገራል። ማንበብ ሳይችሉ ማስተማር አስተማሪ ሳለ ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተጨማሪ የማህበረሰብ ሳይንስ ማስተማር ይጠበቅበት ነበር። አንድም ቀን ጥቁር ሰሌዳ ላይ ፅፎ አያውቅም። በእሱ ክፍለ ግዜ የፅሁፍ የትምህርት መርጃዎች ጥቅም ላይ አይውሉም። በምትኩ ለተማሪዎቹ ብዙ ቪድዮ እያሳየ እንዲወያዩ ያደርጋል። ማንበብ አለመቻሉን ከተማሪዎቹ መደበቅ ነበረበትና ከተማሪዎቹ መሀከል ጎበዝ ተማሪዎችን መርጦ እንዲያነቡለት ያዛል። ተማሪዎቹ በላቀ ችሎታቸው እንደተመረጡ ከመገመት በዘለለ መምህራቸው ማንበብ እንደማይችል አልተጠራጠሩም። ለተማሪዎቹ የሚቆረቆርና እውቀት እንዲያገኙ የሚፈልግ መምህር በመሆኑ በራሱ ቢኮራም፤ በማስመሰል በመኖሩ ጥፋተኝነት ይሰማዋል። "ማስተማር አይገባኝም ነበር። ዘወትር የጥፋተኛነት ስሜት ያንገበግኝ ነበር። ቢሆንም ሚስጥሬን ለማንም ለመናገር አልደፈርኩም" ሲል ይናገራል። "ካቲ፤ ማንበብ አልችልም" ጆን ባለቤቱ ካቲን የተዋወቃት መምህር ሳለ ነበር። 'ባልና ሚስት መሀል ሚስጥር የለም' ብሎ አንድ ምሽት ባለቤቱን "ካቲ፤ ማንበብ አልችልም" አላት። 'ብዙ አላነብም' እንጂ 'ፈፅሞ ማንበብ አልችልም' ማለቱን አልተገነዘበችም። ከዓመታት በኋላ ለሦስት ዓመት ልጁ መጸሐፍ 'እያነበበ' እንደሆነ ሲያስመስል ባለቤቱ ሚስጥሩን ደረሰችበት። ለልጁ መጸሐፉን ሲተርክ የሚደመጠው ታሪክና የመጸሐፉ ይዘት እንደሚለያይ ባለቤቱ ደረሰችበት። ማንበብ እንደማይችል ስታውቅ ንባብ በሚሻባቸው ቦታዎች መርዳቷን ከመቀጠል ባለፈ ቅሬታ አላሰማችም ነበር። ሚስጥሩን የምታውቅ ብቸኛ ሰው ባለቤቱ ሆናም ዓመታት አለፉ። እድሜው ወደ አርባዎቹ ሲጠጋ ማስተማር አቆመ። ካቆመ ከአምስት ዓመት በኋላ ህይወቱን የሚለውጥ አጋጣሚ ተፈጠረ። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የጆርጅ ቡሽ ባለቤት ባርባራ ቡሽ፤ ማንበብ ስለማይችሉ ጎልማሶች በቴሌቪዠን ሲናገሩ የሰማበትን ቅፅበት አይዘነጋውም። በ47 ዓመቱ ማንበብና መጻፍ የማይችል ብቸኛ ሰው እንደሆነ ያስብ ነበር። ከባርባራ ንግግር ግን ብዙዎች ማንበብ ሳይችሉ እድሜያቸው እንደሚገፋ ተገነዘበ። የንባብን ሀሁ በ47 ዓመት በአንድ የመገበያያ ማዕከል ውስጥ ማንበብና መጻፍ ስለማይችል ጎልማሳ ወንድማቸው የሚያወሩ እህትማማቾች አገኘ። ወንድማቸው በአቅራብያው በሚገኝ ቤተ-መጻሕፍት የንባብ ትምህርት እየወሰደ ነበር። ጆን ይህንን አስደሳች ዜና ከሰማ በኋላ ግዜ ሳያጠፋ ወደ ቤተ-መጻሕፍቱ አመራ። በቤተ መጻሕፍቱ የምትሰራ የ65 ዓመት በጎ ፍቃደኛ ንባብ ልታስተምረው ወደደች። "መምህሬ ማንበብ ስለምትወድ ሁሉም ሰው ንባብ እንዲችል ትፈልጋለች። ንባብን ከስር ከመሰረቱ ታስተምረኝም ጀመር" ይላል። ወረቀት ላይ አረፍተ ነገር መመስረት ባይችልም በርካታ ሊጽፋቸው የሚፈልጋቸው ሀሳቦች ነበሩት። መምህርቱ ስሜቱን በግጥም እንዲገልፅ በማድረግ ትምህርቱን ገፋችበት። "ማንበብ ለመማር ሰባት ዓመት ወሰደብኝ። በስተመጨረሻ ማንበብ ስችል ገነት የገባሁ ያህል ነው የተሰማኝ። ከደስታ ብዛት አልቅሻለሁ። ሙሉ ሰው እንደሆንኩ ተሰማኝ" ሲል ይናገራል። የንባብ መምህርቱ የህይወት ታሪኩን በአደባባይ እንዲናገር ያበረታታችው ታሪኩ ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን ሰዎች እንደሚያነሳሳ በማመን ነበር። ታሪኩን ለህዝብ ለማካፈል ጥቂት ቢያቅማማም ሰዎች በታሪኩ እንደሚማሩ ተስፋ አድርጎ ለመናገር ወሰነ። ተሞክሮውን በመገናኛ ብዙሀን ካካፈለ በኋላ በአሜሪካ ታዋቂ በሆኑ የቴሌቭዥን መርሀ ግብሮች ተጋበዘ። በሌሪ ኪንግ፣ በኦፕራ ዊንፍሬይና ሌሎችም መሰናዶዎች አሜርካውያን ታሪኩን ሰሙ። ጆን "ለመማር መቼም አይረፍድም" ሲል መልዕክቱን አስተላልፎ፤ "ለ 48 ዓመታት እስረኛ ነበርኩ። በስተመጨረሻ ግን ነፃ ወጣሁ" ይላል።
50499540
https://www.bbc.com/amharic/50499540
ኢትዮጵያ፡ ወገኖቹን ለመርዳት ጠመኔ የጨበጠው ሐኪም
ተማሪ አህመድ አብዲ ዶህ በሶማሌ ክልል የሚገኘው ዋርዴር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ነው። በሚማርበት ትምህርት ቤት ውስጥ ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሆስፒታል ሲያገለግሉ የሚያውቃቸው ዶ/ር መሐመድ የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጡ ነው።
የሕክምና ባለሙያው ወደ ትምህርት ቤታቸው መጥተው ለእርሱና ለክፍል ጓደኞቹ የባዮሎጂና የኬሚስትሪ ትምህርቶች ላይ እገዛ ሲያደርጉላቸው ሲያይ ተደንቋል። • ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት በዋርዴር አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር መሐመድ አሊና ዶ/ር አህመድ ናስር አብዱርህማን ዘወትር ቅዳሜና እሁድ ወደ ዋርዴር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጠመኔ ይዘው ይሄዳሉ። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ስለተላላፊ በሽታዎች፣ ስለንጽህና አጠባበቅ አልያም ስለ ሥነ ተዋልዶ ጤና ለማስተማር ሳይሆን የሚገኙት፤ መደበኛ የትምህርት ሥራውን ለማገዝ ነው። ውለታን የመመለስ ጉዞ ዋርዴር ከጅግጅጋ 520 ኪሎ ሜትሮች ርቃ የምትገኝ ከተማ ነች። ከጅግጅጋ ተነስቶ ወደ ከተማዋ መምጣት የሚፈልግ ቀብሪ በያን፣ ደገሃቡርን፣ ቀብሪ ደሃርን ማለፍ ይጠበቅበታል። በዚች የገጠር ከተማ በሚገኘው በዋርዴር አጠቃላይ ሆስፒታል ከሚያገለግሉት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል ዶ/ር መሐመድ አሊ አንዱ ናቸው። ተወልደው የፊደል ዘር የለዩትም በዋርዴር መጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሆኑን ይናገራሉ። • ወላጆች ለልጆቻቸው የሚመኟቸው ኢትዮጵያዊ መምህር ዶ/ር መሐመድ በሚማሩበት ወቅት በትምህርት ቤታቸው የመምህራንና የትምህርት መርጃ መሳሪያ እጥረት በመኖሩ በትምህርታቸው ላቅ ያሉ ተማሪዎች ደከም ያሉትን በመርዳት ያስጠኑ እንደነበር ያስታውሳሉ። "እኛን ከሚያስጠኑን መካከል እኮ አንዱ መሐመድ ፋራህ ነው። አሁን በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ውስጥ መምህር ነው" የሚሉት ዶ/ር መሐመድ፣ ከዚህ በተለየ ደግሞ በግላቸው ከትምህርት ሰዓት ውጪ የሚያስጠኑ ግለሰቦች ጋርም በመሄድም ያጠኑ እንደነበር ይናገራሉ። በሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ተወልደው በተለያዩ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ምሁራን የአካባቢውን ተማሪዎች መማሪያ ክፍላቸው በመገኘት ሲያበረታቱ በአንድ ወይንም በሁለት ክፍል ይቀድሟቸው የነበሩ የትምህርት ቤት ጓደኞቻቸው ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂና ኬሚስትሪ በማስጠናት በትምህርታቸው እንዲጠነክሩና አሁን የደረሱበት እንዲደርሱ አግዘዋቸዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጥሩ ውጤት አጠናቀው ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመግባት ሕክምና አጠኑ። ከተመረቁ በኋላም እንዲያገለግሉ የተመደቡት የቀለም ዘር በለዩበት፣ እጃቸው እስክርቢቶ ጨብጦ ከወረቀት ባገናኘበት ዋርዴር ሆነ። • ተማሪዎች መገረፍ አለባቸው የሚሉት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት እርሳቸውና ጓደኞቻቸው ከትንሽ ብላቴናነት ተነስተው ዶክተር እስኪሆኑ ድረስ በፍቅር አቅፋ፣ በእውቀት እንዲጎለምሱ ያደረገችው ዋርዴር እንደቀድሞው ሆና አልጠበቀቻቸውም። መስኩ፣ ተራራው ትምህርት ቤቱ ያው ቢሆንም አንድ ነገር ግን ተለውጧል። ዶ/ር መሐመድ አንደሚሉት የተለወጠው ነገር ከዶሎ ዞን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚገቡት አፍላ ወጣቶች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እያነሰ መሄዱ ነበር። "የተወሰን ነው ምህንድስና፣ የተወሰኑት በሂሳብ ሙያ፣ ቀሪዎቻችን ደግሞ ሕክምና አንዳንዶቹም ዩኒቨርስቲ መምህራን ሆነን ሳለ በአካባቢያችን ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማነሱ አሳሰበን" ይላሉ ዶ/ር መሐመድ። ያለ መፍትሔ የማይመጣው ችግር ከዚያም ሰብሰብ ብለው፤ ለመሆኑ ባለፉት ስድስትና ሰባት ዓመታት ከአካባቢያችን ወደ ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች ቁጥር ምን ያህል ይሆናል ሲሉ ጥናት አደረጉ። ያገኙት ውጤት ከገመቱት በታች መሆኑን የሚናገሩት ዶ/ር መሐመድ፤ መፍትሄ ያሉትን አስቀመጡ። ለመሆኑ ተማሪዎቹ ጥሩ ውጤት ላለማምጣታቸው ምክንያታቸው ምንድን እንደሆነ ለያችሁ? ዶ/ር መሐመድ፡ አዎ፤ የትምህርት አሰጣጡ ድክመት፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች አቅርቦት አለመኖር፣ የመምህራን እጥረት እንዲሁም አቅም ማነስ መሆናቸውን ለይተናል። • በዋግ ኸምራ አስተዳደር 7 የዳስ ት/ቤቶች አሉ ለይተው ላስቀመጧቸው ችግሮች መፍትሄ ያሉትን ሲዘረዝሩ፤ ለተማሪዎቹ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ቀዳሚው መሆኑን አስቀመጡ። ለማጠናከሪያ ትምህርቶቹ ደግሞ ከሳይንስ ትምህርቶች ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ ሒሳብና ፊዚክስ ሲመረጡ ከማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ኢኮኖሚክስ፣ ታሪክና ጂኦግራፊ ተመርጠ። ከቋንቋ እንግሊዘኛም እንዳለበት ዶ/ር መሀመድ ይናገራሉ። በተማሪዎቹ መካከል የፉክክር መንፈስ ለማኖር በማሰብም ውድድር እንደሚያዘጋጁ፣ እጅ ከሚያጥራቸው ቤተሰቦች ለሚመጡ ተማሪዎች ደግሞ አቅም በፈቀደ ድጋፍ ለማድረግ ወሰኑ። አቶ መሐመድ ፋራህ በጂግጂጋ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር ናቸው። ወርዴር ዞን ተወልደውና ተምረው በጅግጅግና በወርዴር የሚገኙ ምሁራን ተገናኝተው በትውልድ ቀያቸው የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት አቀባበል ላይ ያለባቸው ችግር ላይ መወያየታቸውን ያስታውሳሉ። ከዚህ በመቀጠልም የዞናቸው ተወላጅ የሆኑ ምሁራን በጎ ፈቃደኞችን ለማስተባበር ኃላፊነቱን ከወሰዱት መካከል አንዱ እርሳቸው ናቸው። ከዋርዴርና አካባቢዋ፣ ዶሎ ዞን፣ የተወለዱና በተለያዩ መስኮች ተመርቀው ሥራ የያዙ እንዲሰባሰቡ ጥሪ በማቅረብም ከ150 በላይ ሰዎች ምላሽ ማግኘታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ስምንት ሰዎች ደግሞ ይህንን በጎ ሀሳብ ለማስተባበር በኮሚቴነት ተመረጡ። • ተነግረው ያላበቁት የ'ጄል' ኦጋዴን የሰቆቃ ታሪኮች ከዚያም 'ዶሎ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን' በሚል ለስብስባቸው ስም ሰጡ። የሚያደርጉት ድጋፍ በእውቀት፣ በገንዘብ ወይንም በጉልበት ሊሆን እንደሚችል አቶ መሐመድ ፋራህ ያብራራሉ። ዶ/ር መሐመድ ከሆስፒታል ሥራው በሚተርፈው ሰዓትና በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በዋርዴር ትምህርት ቤት በመገኘት የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የወሰነው ከዚህ መሰባሰብ በኋላ እንደሆነ ይናገራል። ዶ/ር መሐመድ አሊ በማስተማር ብቻ ሳይሆን የዚህ ኮሚቴ አባል በመሆንም ይሰራል። ኮሚቴው ከተወላጆቹ ገንዘብ በማሰባሰብ ዓላማውን ለመደገፍ እንደሚሰራ የገለፁት ዶ/ር መሐመድ የአካባቢው ማህበረሰብም የተቻለውን ያህል ለመደገፍ ፈቃደኛ መሆኑን ያብራራሉ። ዶ/ር መሐመድ ባዮሎጂና ኬሚስትሪ ለማስተማር ሲወስኑ፤ በሚሰሩበት ሆስፒታል እያገለገሉ የሚገኙ ሌሎች ሐኪሞች እነ ዶ/ር አህመድ ናስር እና ተማሪዎቹን ታሪክ ለማስተማር ኃላፊነት የወሰዱት የሒሳብ ባለሙያው ካፊ አህምድ በማስተማሩም ሀሳቡን በመደገፉም አብረዋቸው ለመሆን ተስማምተዋል። ዶ/ር... አብዛኛውን ጊዜ ተማሪዎች ወገቤን የሚሉት ሒሳብ ላይ ነው። እርስዎ ለምን ባዮሎጂና ኬሚስትሪን ማስተማር መረጡ? ሒሳብ ለምን አያስተምሩም ዶ/ር መሐመድ፡ እኔ ብቻ ሳልሆን አብዛኛው የሕክምና ተማሪ ሒሳብ ላይ እምብዛም ነው። [ሳቅ] ባዮሎጂና ኬሚስትሪ ግን የተካንኩበት ነው። ተማሪ አህመድ አብዲ እነዚህን በጎ ፈቃደኞች ሲመለከት፣ እንደሚበረታታ ይናገራል።"እኛም ለሌሎች አርአያ እንድንሆን፣ ሌሎችን እንድናግዝ እያነሳሱን ነው" በማለት ከእነሱ ቀዬ ወጥተው ተመልሰው ማህበረሰባቸውን በማገዛቸው የተሰማውን ደስታ ይገልጻል። የዋርዴር ሁለተኛ ደረጃ መምህራኖችም ቢሆኑ ረዳት በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን አቶ መሐመድ ፋራህ ያስረዳሉ። ዶ/ር መሐመድ አሊ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው ተፈናቅለው የመጡ ሰዎች ያሉ ሲሆን የማጠናከሪያ ትምህርቱና የቁሳቁስ ድጋፉ ለእነርሱም ይሰጣል። እንደ አቶ መሐመድ ፋራህ ከሆነ በዞኑ ስር በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት ለማቋቋም፣ ትልቅ ቤተ መጻህፍት ለመክፈት እቅድ አላቸው። የአካባቢው አስተዳደርና ማህበረሰብ ምን ይላል? እነ ዶ/ር መሐመድ ለተወለዱበት አካባቢ በገንዘባቸው፣ በእውቀታቸውና በጉልበታቸው አስተዋጽኦ ለማድረግ ወስነው ወደ ትውልድ ቀያቸው በሄዱበት ወቅት ከአካባቢው አስተዳደሮችና ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር መወያየታቸውን በመጥቀስ በጥሩ መግባባት እንደተቀበሏቸው ይጠቅሳሉ። "ዶሎሎ ከጅግጅጋ በጣም ሩቅ ነው የምትገኘው። መምህራን ደግሞ ቅርብ ከተሞች ላይ ለመስራት ነው የሚፈልጉት" በማለትም መንግሥት መምህራንን ቢመድብም እጥረት መኖሩን የሚናገሩት አቶ መሐመድ ፋራህ፤ እነርሱ ያለውን ክፍተት በመሙላት እንደሚያግዙ ያስረዳሉ። በዋርዴር ከተማ ሁለት በአጠቃላይ ዞኑ ደግሞ 19 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። • ሁለት መልክ ያለው የጅግጅጋ የአንድ ዓመት ክራሞት በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የቤተ ሙከራና የቤተ መጻህፍት እጥረት ስላለ የተማሪዎችን አቅም ለማሳደግ ተጨማሪ ድረጋፍ እንደሚያስፈልግ የሚገልጹት አቶ መሐመድ፤ የማጠናከሪያ ትምህርቱን ቅዳሜ አንደሚሰጡ ገልፀው በእውቀታቸው ማገልገል ያልቻሉ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው እንደሚያግዟቸው ያስረዳሉ። በዋርዴር የተወለዱ እና በጅግጅግ የሚኖሩ በወር አንዴ አልያም ሁለቴ ወደ ስፍራው በመሄድ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀው፤ በከተማዋ የሚኖሩና በጤና፣ በትምህርትና በሌሎች ቢሮዎች የሚሰሩ ደግሞ በየሳምንቱ ያስተምራሉ ብለዋል። አቶ መሐመድ እንዲህ አይነት የበጎ ፈቃድ ሥራ በሰፊው በዞናቸው እንዲሁም በክልሉ እንዲለመድ ፍላጎት እንዳላቸው በመጥቀስም ሌሎች የእነርሱን ጅማሮ ተከትለው መሰባሰብና ሃሳቦችን ማዋጣት መጀመራቸውን ተናግረዋል። ተማሪ አህመድ በበኩሉ የፈተና ወቅት እየደረሰ መሆኑን በማስታወስ፤ በዚህ ዓመት ባገኘው የማጠናከሪያ ትምህርት ድጋፍ ታግዞ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ተስፋ እንደሚያደርግ ለቢቢሲ ገልጿል።
50385143
https://www.bbc.com/amharic/50385143
የሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶች በደህንት ስጋት ተዘጉ
በሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶች በደህንነት ስጋት ተዘግተዋል።
ፖሊሶች በዩኒቨርስቲዎች ቅጥር ጊቢ ገብተው ተማሪዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ የተኮሱ ሲሆን፤ በባቡር ጣቢያዎች ተሳፋሪዎችን እየፈተሹ በመሆኑም መጨናነነቅ ተፈጥሯል። ባለፈው ሰኞ ከፍተኛ ተቃውሞ መካሄዱ ይታወሳል። • ''ፕሬዝደንት ትራምፕ እባክዎ ሆንግ ኮንግን ይታደጉ'' ሰልፈኞች • ተቃውሞ በቻይና፡ መንግሥት 'የውጭ ኃይሎችን' እየወቀሰ ነው • የሆንግ ኮንግ 'የተቃውሞ' ኬክ ከውድድር ታገደ አንድ የመብት ተሟጋች በፖሊስ የተተኮሰበት ሲሆን፤ ሌላ ተሟጋች ደግሞ በእሳት ተቃጥሏል። ሁለቱም በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። ዛሬ በርካታ ትምህርት ቤቶች የደህንት ስጋት በመኖሩ እንደሚዘጉ ለተማሪዎቻቸው ቤተሰቦች በአጭር የጽሁፍ መልዕከት አስታውቀዋል። የሆንግ ኮንጓ ካሪ ላም በበኩላቸው አለመረጋጋት ቢኖርም ትምህርት ቤቶች እንደማይዘጉ ገልጸዋል። ሰኞ ተማሪዎችና ፖሊሶች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የባቡር አገልግሎት ተስተጓጉሎ፣ መንገዶች ተዘግተውም ነበር። በ 'ቻይኒዝ ዩኒቨርስቲ' ተቃዋሚዎች ፖሊሶች ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ፖሊሶች ደግሞ በምላሹ የፕላስቲክ ጥይት ሲተኩሱ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት አቋርጠዋል። ሰኞ ከ260 በላይ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን፤ ተቃውሞው ከጀመረበት ጊዜ እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 3,000 ደርሷል። ካሪ ላም ተቃዋሚዎች "የሕዝብ ጠላት" ናቸው ሲሉ፤ አሜሪካ ደግሞ ሆንግ ኮንግ የገባችበት ውጥንቅጥ አሳስቦኛል ብላለች። የሆንግ ኮንግ እስረኞች ለቻይና ተላልፈው ይሰጡ የሚል ረቂቅ አዋጅን በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ፤ ረቂቁ ውድቅ ቢደረግም እንደቀጠለ ነው። የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ዴሞክራሲ ይስፈን፣ ፖሊሶች ለተግባራቸው ተጠያቂ ይደረጉ ሲሉ ድምጻቸውን ማሰማቱን ቀጥለዋል።
news-56968686
https://www.bbc.com/amharic/news-56968686
የ'ሸኔ' እና ሕወሓት በሽብር መፈረጅ አንድምታው ምንድን ነው?
ቅዳሜ ዕለት የሚንስትሮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና 'ሸኔ' በሽብርተኛነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ማስተላለፉን ይታወሳል።
የደንብ ልብስ የለበሱ እና የታጠቁ ሰዎች መኪና ላይ ተጭነው። በቀጣይ የሚንስትሮች ምክር ቤት በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 77 በተሰጠው ስልጣን መሠረት፤ "ህወሓት" እና "ሸኔ" ቡድኖችን በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሃሳቡን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይልካል። ፓርላማውም የሚንስትሮች ምክር ቤት ሃሳብን ተቀብሎ ቡድኖቹን 'አሸባሪ' ብሎ ለመፈረጅ ሁለት ሶስተኛ ድምጽ መሰጠት አለበት። ለመሆኑ አንድን ቡድን አሸባሪ ብሎ መፈረጅ ለምን ያስፈልጋል? ለዚህ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጡን ከዓመት በፊት ተሻሽሎ የፀደቀውን የሽብር ሕግ የማርቀቅ ተግባር ላይ የተሳተፉት እና የዐቃቤ ሕጉን የአማካሪ ጉባኤ ጽህፈት ቤት የሚመሩትን አባድር ኢብራሂምን (ዶ/ር) ጠይቀናል። አባድር (ዶ/ር) መንግሥት የተለያዩ የወንጀል ተግባራትን ለመከላከል ዝርዝር ክትትል ማድረግ የማይችልበት ሁኔታ ሲፈጠር አንድን ቡድን አሸባሪ በማለት ሊፈርጅ እንደሚችል ያብራራሉ። አባድር (ዶ/ር) አንድን ተግባር 'ሽብር' ለማለት "የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የርዕዮተ ዓለም ዓላማን ለማራመድ በማሰብ ህዝብን ወይም የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍልን ለማሸበር አስቦ የተፈፀመ ተግባር ሲሆን" አክለውም "መንግሥትን፣ የውጭ አገር መንግሥትን ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅትን ለማስገደድ ህይወትን ለአደጋ ማጋለጥ፣ የአካል ጉዳት ማድረስ፣ ማገት ወይም መጥለፍ፣ ንብረትን እንዲሁም የማህበራዊ አገልግሎቶችን ማስተጓጎል" የሚሉትን ጨምሮ የተቀመጡ አምስት ክልከላዎች ተጥሰው ሲገኙ የሽብር ወንጀልን ያቋቁማሉ ሲሉም ይገልፃሉ። በተጨማሪም አባድር (ዶ/ር) አንድ ድርጅት እነዚህን ተግባራት አላማው ካደረገ፣ የድርጀቱ አመራር ወንጀሉን በአሰራር ወይም በግልጽ የተቀበለው ከሆነ፣ በአሰራር ወይም በአፈፃፀም ወንጀሉ የድርጅቱ መገለጫ ከሆነ፣ አንድ ቡድን አሸባሪ ተብሎ ሊሰየም እንደሚችል ለቢቢሲ አስረድተዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት አንድ ድርጅት 'አሸባሪ' ተብሎ እንዲፈረጅለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፤ ድርጅቱን አሸባሪ ያስባሉ ተግባራት እና ድርጅቱ በዚያ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ በግልጽ ማሳየት ይገባል ሲሉም አባድር ያብራራሉ። ይህንን ማስረጃ ይፋ ማድረግ የደህንነት ስጋት ያለው ነው ተብሎ ሲታመን ግን ዝርዝር ጉዳዮች ላይቀርቡ እንደሚችሉ ሕጉ ደንግጓል። ድርጅቱ ከላይ በተጠቀሱት ሶስት ተግባራት ቢያንስ በአንዱ መሳተፉ መረጋገጥ እንደሚገባውም ባለሞያው ያስረዳሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድርጅቱ ወይም ሌላ አካል አስተያየቱን የሚያቀርብበትን በቂ ጊዜ በመስጠትና የጊዜ ገደብ በመግለጽ አግባብ ባለው መገናኛ ዘዴ ጥሪ ማስተላለፍ አለበት ሲል አዋጁ ይደነግጋል። በአሸባሪነት ሊፈረጅ ሃሳብ የቀረበበት ድርጅትም ለምክር ቤቱ አስተያየት ለማቅረብ የማያስችሉ እና ሚስጥራዊ ከሚባሉ ጉዳዮች በስተቀር ማስረጃዎችን የማወቅና የማግኘት መብት አለው። እንዲሁም የውሳኔ ሀሳቡን ለመቃወም ለምክር ቤቱ ማንኛውንም ማስረጃ ለማቅረብ መብት እንዳለው አዋጁ ይደነግጋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት [ሰኞ] ይህንን ጥሪ በመገናኛ ብዙሃን አቅርቧል። ይህ የውሳኔ ሃሳብ ሲፀድቅም በአዋጁ መሠረት የመጀመሪያው ውጤት ድርጅቱ ካልፈረሰ እና ህጋዊ ሰውነት ካለው፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ድርጅቱ እንዲፈርስ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት በማመልከት እንዲፈርስ ያደርጋል። እንዲሁም የድርጅቱን ንብረት መንግሥት እንዲወርሰው ይደረጋል ሲል አዋጁ ይደነግጋል። መንግሥት ከዚህ ቀደም ስህተቱ ምን ይማር? መንግሥት እነዚህ ሁለት ድርጅቶችን በአንድ ግዜ ሽብርተኛ ለማለት ያስብ እንጂ በሁለቱ ድርጅቶች ላይ የሚኖረው ውጤት ተለያይቶ መታየት አለበት ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሕግ ባለሙያ ይገልጻሉ። ከዚህ ቀደም መንግሥትን የሚቃወም አሸባሪ እየተባለ በዚህ ትርጉም ስር ወድቆ ነበር የሚሉት ባለሙያው መንግሥትን መቃወም ሽብር ሆኖ መታየት የለበትም ሲሉም ያስረዳሉ። "ሲቪል መሆን የሚጠበቀው የፖለቲካ ግንኙነት፤ በህግ፣ በወታደር እና በፖሊስ መተዳደር የለበትም። በተለይ አተገባበር ላይ እንዳይኖር መደረግ አለበት" በማለት ገልፀዋል። "ከዚህ ቀደም የተሻረውን የፀረ-ሽብር ሕግ መንግሥት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ የፀጥታ ግንኙነት የሚወስድበት ነበር። ይህ አሁን ላይ መደገም የለበትም" ብለዋል። "በተለይም በመንግሥት እና በእነዚህ ሁለት ተቋማት መካከል ከዚህ በኋላ ድርድር፣ እርቅ ወይም ምንም አይነት ስምምነት ማድረግ የማይታሰብ ያደርገዋል" ሲሉም አክለዋል። በተለይም በትግራይ ክልል ያለውን ችግር መሰረቱን ከመፍታት ይልቅ አንድ በአንድ የሚታዩ የፍርድ ቤት ጉዳይ ያደርገዋል። ይህም ህጋዊ የወንጀል ድርጊት እና በጥቃቶች ላይ መልስ የመስጠት ሂደት ይሆናል። በተጨማሪም በአገር ውስጥ ያሉ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም የውጪ አካል ለማስታረቅ ወይም ለመደራደር የሚያደርገውን ጥረት ወንጀል እንደሚያደርገውም ያስረዳሉ። በተለይም አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ የውጪ መንግሥታት በትግራይ ክልል ያለው ግጭት በስምምነት እንዲቋጭ ሲቀርቡ የነበሩ ጥያቄዎችን ለመዝጋት የታሰበ ይመስላልም ሲሉ አስረድተዋል። በአሸባሪነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሃሳብ የተላለፈባቸው 'ሸኔ' እና ህወሓት ማን ናቸው? ሸኔ የሚንስትሮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ እንዲፈረጅ ሃሳብ ያቀረበው "ሸኔ" ቡድንን ነው። በአሁኑ ወቅት በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ በስፋት ስለሚንቀሳቀሰው እና የመንግሥት ባለስልጣናት፤ 'ኦነግ ሸኔ' ብለው ስለሚጠሩት ታጣቂ ቡድን የሚታወቀው የሚከተለውን ነው። መንግሥት በተለይ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት 'ኦነግ ሸኔ' በሚል የሚጠሩት ታጣቂ ኃይል ራሱን "የኦሮሞ ነጻነት ጦር" በማለት ይጠራል። 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር' ለበርካታ አስርት ዓመታት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ የጦር ክንፍ ሆኖ ቆይቷል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህምድ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ከገቡ በኋላ የኦሮሞ ነጻነት ጦር (መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው ቡድን) ከፓርቲው ተገንጥሎ በትጥቅ ትግሉ እንደሚቀጥል ይፋ አደረገ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ-መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦሮሞ ነጻነት ጦር (ኦነግ ሸኔ) በእርሳቸው እንደማይታዘዝ ይፋ አድርገው ነበር። ሸኔ የምትለዋ መጠሪያ ከየት መጣች? ሸኔ- ማለት 'ሸን' ከሚለው የኦሮምኛ ቃል የመጣ ነው። 'ሸን' ማለት አምስት ማለት ነው። 'ሸኔ' ማለት ደግሞ አምስቱ እንደማለት ነው። በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ አምስት አባላት ያሉት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 'ጉሚ ሸኔ' ተብሎ ይጠራል። ጉሚ ሸኔ ማለት 'አምስት አባላት ያሉት ጉባኤ' እንደማለት ነው። ፓርቲው ግን ከ5 በላይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አባላት ሊኖረው ይችላል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን መሪ እንደሆነ የሚታመነው ኩምሳ ድሪባ በትግል ስሙ በስፋት የሚታወቀው ጃል [ጓድ] መሮ፤ ለኦሮሞ ነጻነት እንታገላለን ይላል። በተለያዩ ወቅቶች መንግሥት በዚህ ቡድን ላይ በሳምንታት ውስጥ 'እርምጃ' እወስዳለሁ ቢልም፤ በቡድኑ አባላት ተፈጽመዋል በሚባሉ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገድለዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል። መንግሥት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ቡድን በርካታ የመንግሥት ባለስልጣናት እና የፖሊስ አባላት ላይ ግድያ እና የባንክ ዝርፊያ መፈጸሙን ይገልጻል። መንግሥት ከዚህ ቀደም ይህ ቡድን በህወሓት ድጋፍ እንደሚደረግለት እና በትግራዩ ግጭትም ለህወሓት ወግነው ሲዋጉ ነበሩ ያላቸውን 'የኦነግ ሸኔ' ታጣቂዎችን መማረኩን አስታውቆ ነበር። ኦነግ-ሸኔ የሕዝብ 'ጠላት ነው' የቦረና አባ ገዳ የሆኑት ኩራ ጃርሶ ኦነግ-ሸኔን የሕዝብ ጠላት ነው ሲሉ ቡድኑን ማውገዛቸው ይታወሳል። አባ ገዳ ኩራ በታጣቂ ቡድኑ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ሠላማዊ ሰዎች በመገደላቸው ቡድኑን ጠላት ብሎ መፈረጁ እንዳስፈለጋቸው ተናግረዋል። የቦረና አባ ገዳ በማኅበረሰባቸው ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው ሲሆኑ የሚያስተላልፉትም መልዕክት ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው። ህወሓት ህወሓት በሽምቅ ውጊያ ወደ አገር መሪነት ከዛም ወደ የክልል አስተዳዳሪነት በመጨረሻም ወደ ሽምቅ ወጊያ ተመልሷል። ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ዋነኛው ተዋናይ ሆኖ የቆየው ህወሓት ባለፈው ጥቅምት ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ሰውነቱን አጥቶ እንዲሰረዝ ተደርጓል። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የንጉሡ አስተዳደር ወድቆ ወታደራዊው መንግሥት ወደሥልጣን መውጣቱን ተከትሎ ነበር የካቲት 11/1967 ዓ.ም የትጥቅ ትግል መጀመሩን ያስታወቀው። ለህወሓት የትጥቅ ትግል መነሻ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያቋቋሙት ማገብት (ማህበረ ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ) የተባለው መደበኛ ያልሆነ ቡድን ነበር። ማገብት በስምንት አባላት የተመሠረተ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በሪሁ በርሀ (አረጋዊ በርሄ ዶ/ር)፣ አምባዬ መስፍን (ስዩም መስፍን) እና አመሃ ፀሃዬ (አባይ ፀሃዬ) ተጠቃሽ ናቸው። ከደርግ ጋር የሚደረገው ጦርነት ወደ ሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ሲሸጋገር በየአካባቢዎቹ ያሉትን ሕዝቦች ይወክላሉ የተባሉ ድርጅቶችን ማቀፍ እንዲሁም ሊወክሉ ይችላሉ የሚባሉ እንዲቋቋሙ ህወሓት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። ይህንንም ተከትሎ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን)፣ ከኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ጋር በመጣመር ኢሕአዴግ የተባለውን ግንባር ፈጠረ። በህወሓት የበላይነት ይመራ የነበረው ኢሕአዴግ የደርግ መንግሥትን ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ ለ27 ዓመታት አገር መምራት ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን በግንባሩ ውስጥ ለዓመታት የቆየው ቅሬታ ስር እየሰደደና እየጎላ መጣ። በመጨረሻም ኢህአዴግ ከስሞ የብልጽግና ፓርቲ ሲተካው ህወሓት በአዲሱ ስብስብ ውስጥ ላለመግባት ከመወሰኑ ባሻገር "ውህደቱ ሕጋዊ አደለም'' በማለት ተቃውሞውን አስምቶ ነበር። ህወሓት ከፍተኛ አመራሮቹን ይዞ ወደ ትግራይ ካቀና በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የነበረው ግንኙነት ከመሻከር አልፎ ወደ ግጭት አምርቷል። ከ6 ወራት በፊት በተጀመረው ጦርነት የፌደራሉ መንግሥት 'ህወሓት አብቅቶለታል' ሲል አውጇል። የቡድኑ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች ተጠርጥረው የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ወራት ተቆጥረዋል። በርካታ የህወሓት አመራሮች በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውና ሌሎች ደግሞ መገደላቸው የአገሪቱ ሠራዊት መገለጹ ይታወሳል።
news-49752460
https://www.bbc.com/amharic/news-49752460
"ዛሚ አልተሸጠም፤ በትብብር እየሠራን ነው" ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ
ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቴአትር ጥበባት ተመርቀዋል። የኮሌጅ ተማሪ ሳሉ ጀምረው በሚዲያ ላይ መሳተፍ የጀመሩት ሚሚ፤ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በትርፍ ጊዜ ይሠሩ ነበር። ከተመረቁ በኋላም የኢትዮጵያ ፊልም ኮርፖሬሽንን ተቀላቅለው ዘጋቢ ፊልሞችን ሠርተዋል።
የትምህርት እድል አግኝተው ወደ አሜሪካ፤ ኒዮርክ አቅንተዋል። በወቅቱ በአገሪቱ ውስጥ የነበረው የፖለቲካ ሁኔታ [ከደርግ መውደቅ በኋላ] ያላማራቸው ሚሚ፤ እዚያው ለመቆየት ወስነው በአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ፕሮግራም ተቀጥረው በጋዜጠኝነት ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል። • የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ • "ወፍራም ሴቶች ለአገርም ለቤተሰብም ሸክም ናቸው" የግብፅ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ከአሜሪካ ከተመለሱ በኋላም ዛሚ 90.7 ራዲዮ ጣቢያን አቋቁመው እየሠሩ ይገኛሉ። ይህ ራዲዮ ጣቢያ የተለያየ የፖለቲካ አቋም ባላቸው አካላት ትችቶች ሲዘነዘሩበት ቆይቷል። በተደጋጋሚ ሊዘጋ ነው የሚል ዜናም ተሰምቷል። አሁን ደግሞ በእጅ አዙር ተሸጧል፤ አልተሸጠም የሚሉ ውዝግቦች ይነሱበታል። አዲስ ዓመትን አስመልክተን ከሚዲያ የራቁ ሰዎችን ስናፈላልግ ጋዜጠኛ ሚሚን አግኝተን ስለ ጣቢያውና ስለ ግል ሕይወታቸው ጠይቀናቸዋል። አሁን የት ነው ያሉት? አሜሪካን አገር ነው ያለሁት። የጤና ምርመራ ላይ ነኝ። በየዓመቱ የጤና ምርመራ አደርጋለሁ። የጤንነት ሁኔታዎ እንዴት ነው? በጣም ደህና ነኝ። በጣም በሚገርም ዓይነት ባለፈው ጊዜ ዐይኔን ቀዶ ሕክምና አድርጌ ነበር። የሚገርመው የምርመራ ውጤቴንም ተቀብያለሁ፤ በጥሩ ጤንነት ላይ ነው ያለሁት [ሳቅ] በዚህ እድሜ የሚመጡ ብዙ ነገሮች አሉ- በእኔ እድሜ። ስለዚህ ከዚያ አንፃር፣ እ. . . ከሥራዬ ውጥረት መብዛት አንፃር ሲታይ፤ እነዚህ አስፈሪ የሆኑት እንደ ስኳር፣ ግፊት ምናምን ያሉት የሉብኝም። በዚያ ተደስቻለሁ። የሚገርምሽ ስፖርት አልሠራም። ምን አልባት አመጋጋብ ሊሆን ይችላል። አሁን በምን ሥራ ላይ ነው ያሉት? አሁን ዛሚ 'ሪብራንድ' እየተደረገ ነው። እንደገና ደግሞ ጋዜጠኞችን በዘለቄታዊ የሥልጠና ተቋም የመገንባት ሥራ ላይ ነው ያለሁት። ብዙ ሥራዎች ላይ ነው ያለሁት፤ አሁን ሕክምና ላይ ብሆንም። የማማከር ሥራዎችን ይሠራሉ ሲባል ሰማሁ። ማንን ነው የሚያማክሩት? እሠራለሁ። ግን በአሁኑ ሰዓት መጥቀስ አልፈልግም። ብዙዎቹ ገና በተለያየ ደረጃ ላይ ስለሆኑ፤ እሱን አሁን መዘርዘሩ ጥሩ አይሆንም። ገና ነው። አሁን ለመናገር ጊዜው አይደለም፤ ግን ሥራ አልፈታሁም ለማለት ነው [ሳቅ]። ዛሚ ራዲዮ ጣቢያ 'ተሸጧል' እየተባለ ይወራል። እውነት ነው? ዛሚ ብዙ ጊዜ የአየር ሰዓት ወስደው የሚሠሩ አጋር ድርጅቶች አሉት። በተለያየ መንገድ አብረውን የሚሠሩ በርካታ ድርጅቶች አሉ። ስለዚህ ከብዙ ሰዎች ጋር እንሠራለን። ዛሚ የሚዲያ ተቋም እንደመሆኑ መርሁን እና ሥነ ምግባሩን ከሚያከብሩ፣ አላማው ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም እንደመሆኑ ያንን ማድረግ ከሚፈልጉ፣ መሠረታዊ በሆኑት የጋዜጠኞች መስፈርቶች ዙሪያ ከሚንቀሳቀሱ፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ለህብረተሰባችን አገልግሎት ከሚሰጡ፣ መስጠት ከሚፈልጉ፣ ከማናቸውም ወገኖች ጋር በትብብር እንሠራለን። ስለዚህ 'ሪብራንድ' እያደረግን [እንደገና እያደራጀን] ነው። ሌሎች ጣቢያዎችም እኮ እንደዚህ ያደርጋሉ። ለምን በዛሚ ላይ ትንሽ ለየት እንደሚል ባይገባኝም፤ በትብብር እንሠራለን- ከተለያዩ ወገኖች ጋር። የአየር ሰዓት መስጠት የተለመደ ነው። ስለዚህ 'በትብብር' ሲሉኝ የአክሲዎን ሽያጭ ነው ማለት ነው? ትብብር ሲሉ ግልፅ ቢያደርጉልኝ? የአክሲዎን ሽያጭ አይደለም። በትብብር የሚሠራባቸው ብዙ ዓይነት መንገዶች አሉ። እነዚህን ደረጃ በደረጃ በቢዝነስ ክፍሉ ነው የሚሠሩት። ይህ ደግሞ በቀጥታ የሚመለከተው አቶ ዘሪሁን ተሾመን [ባለቤታቸው] ነው። እኔን የፕሮግራም፣ የሙያው ጉዳይ ነው የሚመለከተኝ። ከዚህ ቀደምም የምሠራው በዚያው መስመር ነው። ነገር ግን በ'ሪብራንዲንጉ' ሂደት ውስጥ፤ በርካታ ለውጦች. . . አዳዲስ ፕሮግራሞች፣ አዳዲስ አጋሮች እ. . . አሰባስበን እንግዲህ ተጀምሯል። ከማን ጋር ነው በትብብር እየሠራችሁ ያላችሁት? ከተለያየ አካላት ጋር። በርካታ ናቸው። • ዛሚ ሬዲዮ ሊዘጋ ይሆን? • "የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ" መሐመድ አደሞ ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሥልጠናዎችን ይሰጡ እንደነበር አውቃለሁ። እስካሁን ለምን ያህል የሚዲያ ባለሙያዎች ሥልጠና ሰጡ? በጣም ብዙ ነው። ገና ዛሚ ሳይቋቋም በነበሩት ሁለት ዓመታት በየክልሉ እየዞርኩ ሳሰልጥን ነበር። ከዚያ ይጀምራል እንግዲህ። በጣም ብዙ ነው። በጊዜው አገልግሎት ላይ ለነበሩ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች፣ ለማህበረሰብ ራዲዮ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች፣ አዲስ ለተቋቋሙ መገናኛ ብዙኃን ከዚያ ደግሞ በዛሚ ሥር በየዓመቱ ሥልጠናዎችን እሰጥ ነበር። ቁጥሩን ግን በፍፁም አላውቀውም። ግን ከ300 በላይ ይሆናል። አሁንም ይሄንን ሥልጠና በደንብ በተደራጀ መልኩ ለማድረግ አስበናል። በትርፍ ጊዜዎ ምንድን ነው የሚያደርጉት? ብዙ ጊዜ መዝናኛ የምለው ፊልም እና መጽሐፍ ነው። ጊዜ ካገኘሁ እነዚህ ሁለቱ ላይ ነው ጊዜየን የማሳልፈው። አሁን ለጊዜው እንግሊዝኛ መጻሕፍት ናቸው እያነበብኳቸው ያለሁት። Sapiens [ሳፒያንስ] በተከታታይ የወጣ ሁለት መጽሐፍ አለ። አንዱን ጨርሼ አንዱ ላይ ነው ያለሁት። የማንን ሙዚቃ ይወዳሉ? እ . . . ይለያያል። አዳዲስ ዘፈኖች በጣም እከታተላለሁ። ወጣቶቹ ደስ ይሉኛል። ባህላዊ የሆኑ ዘፈኖችን እሰማለሁ፤ አያለሁ። ወደፊት ምንድን ነው እቅድዎት? መጽሐፍ ለመጻፍ እቅድ አለኝ። 'ሻዶው ራይተር' [ጸሐፊ] እየፈለኩ ነው። አፅመ ታሪኩ ወጥቷል። ጎበዝ ፀሐፊ እየፈለኩ ነው። ያው ቁጭ ብዬ መጻፍ ስለማልችል፤ ሥራ ላይም ስለሆንኩኝ እ. . . የሚያግዝ ጸሐፊ ባገኝ ይበልጥ ይፋጠናል ብየ አስባለሁ። መጽሐፉ በምን ላይ የሚያተኩር ነው? ሙያዬ ከግለ ታሪኬ ጋር በጣም የተያያዘ ስለሆነ ሁለቱንም የያዘ፤ ለሌሎችም ትምህርት ሊሆን የሚችል የሕይወት ምዕራፌን አጋራለሁ ብዬ አስባለሁ። የግል ሕይወትዎስ? በትዳር 25 ዓመት ቆይቻለሁ። ሩብ ምዕተ ዓመት [ሳቅ] ሁለት ልጆች አሉኝ። አንዱ ትልቅ ነው። አሜሪካ ነው የሚኖረው። አብራኝ ያለችው ደግሞ ዘጠኝ ዓመቷ ነው። በጣም ደስተኛ ነኝ። በግል ሕይወቴ ደስተኛ የሆንኩት፤ በቤቴ በጣም ደጋፊ የሆነ ቤተሰብ ስላለኝ ነው። በጣም ተግዳሮት የበዛበት ቢሆንም፤ እስከዛሬ ድረስ ያለሁትም በዚያ ምክንያት ነው። ትልቁ ድጋፌ ያ ነው። በሥራዬ ተግዳሮት አለብኝ ብለውኛል። የፈተነዎት ምንድን ነው? ብዙ ነገሮች አሉ። [ሳቅ] ብዙ ተግዳሮቶች አሉ። የሚጠበቁ፣ የማይጠበቁ፣ ድንገት የሚመጡ ተግዳሮቶች አሉ። ብዙ ናቸው። በተለይ እንደኛ ዓይነት ሙያ ውስጥ በምትኖሪ ጊዜ፤ ብዙ ፈተናዎች አሉ። ይሄ ነው፤ ይሄ ነው አልልም። ሙያችን አልጋ ባልጋ የሆነ ሙያ አይደለም። ስለዚህ ብዙ ፈተናዎችና ችግሮች አሉበት። ዛሚ በእጅ አዙር ተሸጧል? ዛሚ 90.7ን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜ የተለያዩ መረጃዎች ይወጣሉ። ከዚህ ቀደም ሊዘጋ ነው ተብሎ የራዲዮ ጣቢያው ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከሆኑት አቶ ዘሪሁን ተሾመ ጋር ቃለ ምልልስ ማድረጋችን ይታወሳል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ዛሚ 90.7 በነበረበት ቁመና አይቀጥልም፤ በእጅ አዙር ተሸጧል የሚሉ ወሬዎች ይናፈሳሉ። ወሬው የገዥውን ስም እስከመጥቀስ የደረሰም ነበር። ከወ/ሮ ሚሚ ጋር ቃለ ምልልስ ስናደርግ፤ እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን የሚመለከተው የጣቢያው ባለቤትና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን ተሾመ [ባለቤታቸው] ነው ስላሉን ወደ እርሳቸው ደውለን ነበር። ዛሚ ተሸጧል? አልተሸጠም! ስሙን ለውጠነዋል። አመራር ቀይረናል። አዳዲስ ፕሮግራሞች አምጥተናል። ፉክክሩ እየበረታ ነው። ይህንን ካጠናከርን በኋላ ደግሞ ፍላጎት ላለው የተወሰነ አክሲዮን ለመሸጥ አቅጣጫ ይዘናል። ስሙን መለወጥ ለምን አስፈለገ? እንደምታውቂው አገራችን ላይ ፍረጃ ምናምኖች አሉ- አንደኛው እሱ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ዛሚ የሚለው ስያሜ በዋነኛነት የሚወክለው የሁለት ግለሰቦችን ስም የመጀመሪያ ፊደል ነው [የእኔና የባለቤቴን]። አሁን ያስቀመጥነው አቅጣጫ ደግሞ፤ ሌሎች ፍላጎት ያላቸው ሁለት ያህል የአክሲዎን ባለድርሻ አካላት እንዲገቡ እንፈልጋለን። ፍረጃ ሲሉኝ? ከአንድ ፖለቲካ ወገን ጋር ማያያዝ ወ.ዘ. ተ። ስለሆነም ያንን ጥላም ለመግፈፍ ነው። በዋናነት ግን ለሁሉም አስማሚ የሆነ፤ በእናንተ ስም ብቻ ነው የማይባል፤ ወደፊት ያቀድነው ከተሳካ እና የሚመጡ የአክሲዎን ባለድርሻዎች ከኖሩ እነሱንም ለማበረታታት ጭምር ነው። ስሙ ከዛሚ ወደ አዋሽ ነው የተለወጠው። ስያሜውን እንዴት አገኘ? እኔ ነኝ ያወጣሁለት። አዋሽን የመረጥንበት የራሱ መነሻ አለው። አዋሽ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ወንዝ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚያበቃው። ስለዚህ በዚህ ደረጃ ካየሽው ታማኝ ማለት ነው። ከአገሩ የማይወጣ፤ ላገሩ የሆነ። ሌላው አዋሽ ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ የሚፈስ በመሆኑ ነው። በሌላ በኩል ጉራጌን፣ ደቡብን፣ ኦሮሚያን፣ የተወሰነ የአፋር ቦታ፣ ሶማሌን፣ እንዲሁም የአማራን የተወሰነ ቦታ ይነካል። በመሆኑም ታማኝ፣ ጥልቅ፣ ሕብረ ብሔራዊ ወይም አስተሳሳሪ ማለት ነው። ስለዚህ ጣቢያው ላይ ሲተላለፉ የነበሩ የፕሮግራሞች ቅርፅና ይዘት ተለውጧል? ተለውጠዋል። አዳዲስ አጋር ድርጅቶች ገብተዋል። የመዝናኛ ፕሮግራሞች በርከት ብለዋል። 'የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ' በአዲስ ቅርፅ፣ በአዲስ ሰዎች ይጀምራል። 'የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ' ፕሮግራም በማን ይመራል ማለት ነው? ገና ሰው አልመደብንለትም፤ ግን አዲስ ዳይሬክተር ሾመናል። እሱም ሊመራው ይችላል። ታዋቂ ሰዎችም እየተሳተፉበት የጦፈ የክርክር መድረክ ሆኖ ነው የሚቀጥለው። ጋዜጠኛ ሚሚስ? ወ/ሮ ሚሚ ለጊዜው ሥልጠና እና ማማከር ላይ ነው ያለችው። የሥልጠናውን ዘርፍ የያዘችልን እሷ ነች። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን እሷም መመለስ ትችላለች። ስለዚህ እስካሁን አብሯችሁ የሚሠራ አካል የለም? መቶ ፐርሰንት። በነገርሽ ላይ በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ራዲዮ ጣቢያ መሸጥ አይቻልም። ስለዚህ በእርግጠኝነት የምነግርሽ እስካሁን ድረስ የሞከርነው ከናሁ ቴሌቪዥን ጋር ነበር። ከእነርሱ ጋር አልተግባባንም፤ ስላልተግባባን የደረስነው ስምምነት እንዲፈርስ አድርገን፤ አሁን በግልግል ዳኝነት ላይ ነን። በምንድን ነው ያልተግባባችሁት? በአከፋፈል ሒደት. . . ምናምን ወዘተረፈ። ግልግል ላይ ያለ ነገር ስለሆነ ወደ ዝርዝሩ ልገባ አልችልም፤ ግን የግልግል ዳኝነት ላይ ነን። አብረዋችሁ ሊሠሩ የሚችሉት እነማን እንደሆኑ ይታወቃሉ? ድርጅትም ከሆነ? አይታወቁም። ግን እስከ ሁለት ነው የሚሆነው። እስካሁን ድረስ በግል ያነጋገርነው አካል የለም፤ ግን ለማድረግ እየሞከርን ነው። ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ይኖራሉ ብለን እንገምታለን።
news-53044856
https://www.bbc.com/amharic/news-53044856
ኮሮናቫይረስ፡ ወንጀለኛን ከማደን ጋር የሚመሳሰለው ወረርሽኝን የመቆጣጠሪያ መንገድ
አንድ ቫይረስ ከየት ተነሳ የሚለው ነገር ነፍሰ ገዳይን ለማደን ከሚደረገው ሂደት አይለይም። ፖሊስ ወንጀል የተፈጸመበት ሄዶ አካባቢውን ማጠር አለበት። የኅብረተሰብ ጤና ሰዎችም እንደዚያው ነው የሚያደርጉት።
ፖሊስ ምስክሮችን ቶሎ ይዞ መመርመር አለበት። የጤና ባለሞያዎችን ቶሎ ታማሚዎችን ወይም የታማሚ ቤተሰቦችን መመርመር አለባቸው። ገዳዩን ለማግኘት ዱካውን ፍለጋ ሩጫ ያሻል። ቫይረስም እንደዚያ ነው። ምንም እንኳ የቫይረሱን ጭራ ለመያዝ ዓለም አቀፍ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ነፍሰ ገዳዩ ቫይረስ አሁንም ሺህዎችን እየገደለ ነው። አሁን ቫይረሱ የመጀመርያውን ጥቃት ካደረሰ መንፈቅ ሆኖታል። ሳይንቲስቶች እስካሁን ምን ላይ ደርሰው ይሆን? መዳኛውን ባያገኙም መነሻውን ደርሰውበት ይሆን? ቫይረሱን ወደ ሰው ያጋባው የትኛው እንሰሳ ነው? ቁልፉ ነገር መነሻውን ማወቅ ነው። መድረሻው ግን ይደረስበታል። ከየት ተነሳ? የሚለው ሲመለስ የት ድረስ ይሄዳል? ለሚለው ከፊል ምላሽ ይገኛል። ከምን ተነሳ? የሚለው ሲታወቅ በምን ፍጥነት እንደሚጓዝም ፍንጭ ይኖረናል። ነገር ግን ይህ ኮሮናቫይረስ ገና ከመነሻው ነው ጥቃቱን ያፋፋመብን። ከየት ተነሳ? የሚለውን ለማጥናትም ጊዜ አልሰጠም። ለቁጥጥርም ጊዜ አልሰጠም። ቻይናዊያን ለአዲስ ዓመት በሚሰናዱበት ወቅት ዶክተር ሊ ዌንሊያንግ በዉሃን ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ውስጥ እየሰሩ ነበር። ሰባት ታማሚዎቻቸው ላይ የሳንብ ምች የሚመስል ምልክት ያሳያሉ። ዊቻት በሚባለው የማኅበራዊ ሚዲያ ወሬ ማድመቂያ ላይ ዶ/ር ሊ ለጓደኞቻቸው ፍርሃታቸውን አጋሯቸው። እርሳቸው ለጓደኞቻቸው ኮቪድ-19 ተከሰተ አላሉም። መቼ አወቁትና። የጠረጠሩትን ነገሯቸው። የሳርስ ወረርሽኝ በድጋሚ ሳይከሰት አይቅርም ሲሉ ለባልደረቦቻቸው አረዳቸው። ያን ጊዜ ዶ/ር ሊ ያልተረዱት ግን እነዚህ 7ቱ ህሙማን ላይ ይታይ የነበረው ነገር ሳርስ አገርሽቶ ሳይሆን አዲሱ የኮቪድ-19 የመጀመሪያ ወረርሽኝ ነበር። ይሄ ሳርስም ያኔ በ2003 ከቻይና ነበር የተነሳው። ከዚያ በኋላ በ26 አገራት ተሰራጭቶ 8 ሺህ ሰዎችን አጥቅቷል። ዶ/ር ሊ በዊቻት በኩል ለጓደኞቻቸው ስጋታቸውን በመግለጻቸው ብቻ በሦስተኛው ቀን ካሉበት ፖሊስ ከቸች አለ። ሌሎች 8 ሰዎች ጋር አብሮ አሰራቸው። ክሱ የነበረው ታዲያ የሐሰት ወሬ አሰራጭተዋል የሚል ነበር። ይህ በቻይና መገናኛ ብዙሃን ጭምር የተዘገበ ጉዳይ ነው። ኋላ ላይ ከእስር ሲፈቱ፤ ዶ/ር ሊ ራሳቸው በኮሮናቫይረስ ተህዋስ ተይዘው ነበር። ከዚያ ወዲያ በሕይወት ለመቆየትም ዕድለኛ አልነበሩም። በጥቅምት 7፣ በተወለዱ በ34 ዓመታቸው በአጭር ተቀጩ። ዶ/ር ሊ የአንድ ልጅ አባት ነበሩ፤ ሚስታቸውም እርጉዝ ነበረች። የህክምና ባለሙያዎች ዉሃን ውስጥ ኮቪድ-19 ታማሚዎችን ሲያክሙ ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ታኅሳስ ወር መጨረሻውን ሙሉ እንደ ዶ/ር ሊ ሁሉ ሌሎች ነርሶችም የሆነ ወረርሽን የሚመስል ነገር እንደተከሰተ ሲያስጠነቅቁ ነበር። መጀመሪያ የነቁት ግን የጤና ሠራተኞች ነበሩ። የጤና ሠራተኞቹ ታማሚዎች ከአንድ ቦታ የሚመጡ እንደሆነ አስተዋሉ። ሁሉም ሁዋናን ከሚባው የዓሣና የባሕር ውስጥ እንሰሳት ገበያ የመጡ ሰዎች ነበሩ። ይሄ የዓሣ ገበያ ታዲያ በዉሃን አዲስ ሰፈር የሚገኝ ሲሆን ዶሮ፣ ዓሣና ሌሎች ተሳቢና ተራማጅ እንሰሳት ሳይቀሩ ከነነፍሳቸው የሚሸጡበት ቅልጥ ያለ ሥጋ ተራ ነው። በታኅሳስ ወር መጨረሻ የዉሃን ከተማ የጤና ኮሚሽን የሆነ ወረርሽኝ መከሰቱን አምኖ ለቤይጂንግ ሪፖርት አደረገ። በቀጣዩ ቀን ያ የዓሣ ገበያ ተዘጋ። በዚህ ሁኔታ ወንጀለኛው ብዙ ጉዳት አድርሶ ከሄደ በኋላ ነው ፖሊስ የወንጀሉን ሥፍራ የከበበው እንደማለት ነው። ዛሬ ሳይንቲስቶች በጋራ ያመኑት ነገር ቢኖር ከፍተኛ ወረርሽኝ በዚያ የዓሣ ገበያ መከሰቱን ነው፡፡ ቫይረሱ የመነጨው ከዚያ ገበያ ነው ወይ የሚለው ግን አከራካሪ ሆኗል። እርግጥ ነው በዚያ ገበያ ከሰዎችም ሆነ ከእንሰሳት ናሙና ተወስዶ ሁሉም ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ምናልባት የመጀመርያው ሰው የተያዘው ቫይረሱ ይፋ ከመደረጉ አራት ሳምንታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ተገምቷል። ይህም በታኅሣሥ 1/ 2019 መሆኑ ነው። ያን ጊዜ የተከሰተው መጀመሪያ በዚያ የዓሣ ገበያ ስለመሆኑ ግን መረጃ የለም። በመስከረም ወር በዉሃን ከተማ በርካታ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነ ቢታወቅም፤ ማንም በዚያ ፍጥነት ዓለም ላይ ይሰራጫል ያለ አልነበረም። አይደለም በመላው ዓለም፣ ቫይረሱ ቻይናን ያዳርሳል ያለም አልነበረም። በመስከረም 11/2019 የመጀመሪያው ሞት በቻይና በተመዘገበ በ9 ቀናት ውስጥ ቫይረሱ ድንበር ተሸገረና ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያና ታይላንድ መድረሱ ተሰማ። ቫይረሱን ለመያዝ መርማሪዎች እግር በእግር ቢከተሉትም ሁልጊዜም ቀድሞ ሌላ ስፍራ ይገኛል። ባለፉት 6 ወራት 188 አገራትን ያዳረሰውም በዚሁ መንገድ ነው። አሁን 7 ሚሊዮን ሕዝብን በክሏል። ዶክተር ሊ ዌንሊያንግ የገዳዩን ቫይረስ ማንነት ማወቅ የአንደርሰን ቤተ ሙከራ ኃላፊ ፕሮፌሰር ክርስቲያን እንደሚሉት የመጀመሪያው ሥራ ገዳዩ ቫይረስ ማን ነው ብሎ ማግኘት ነው። ቫይረሱ ከእንሰሳት ወደ ሰው እንዴት ሄደ? ከሰው ወደ ሰው እንዴት ነው የሚተላለፈው? የሚለው የሚታወቀው ከዚያ በኋላ ነው። በመስከረም መጨረሻ በዉሃን ኢንስቲትዩት ኦፍ ቪሮሎጂ [በቫይረስ ላይ ምርምር በሚደረግበት ተቋም] ውስጥ የተደረገውም ይኸው ነው። ከሰው አፍንጫ ፈሳሽ በተወሰደ ናሙና የቫይረሱ ዘረመል ቅርጹ ተደረሰበት። የቫይረሱ የዘረመል ቅጥልጥል ኮዱ ሲገኝ የቫይረሱ አፈጣጠር ተገኘ ማለት ነው። እንዴት እንደሚሰራጭም የሚታወቀው የዘረመል ቅጥልጥል ኮዱ ሲታወቅ ነው። የዘረመል ኮድ የፊደሎች ቅጥልጥል ነው። ለምሳሌ የአንድ ሰው የዘረመል ኮድ በ3 ቢሊዮን ጄኔቲክ ፊደሎች ነው የሚወከለው። አንድ ተራ የጉንፋን ቫይረስ ለምሳሌ 15 ሺህ ፊደሎች ይወክሉታል። ይህ የፊደል ውክልና ቫይረሱ ባሕሪውን፣ እንዴት እንደሚዋለድ፣ በምን ፍጥነት እንደሚዋለድ ይነግረናል። አንድን የቫይረስ ዘረመል ኮድ ፈልፍሎ ለማግኘት ወራት ሊወስድ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ዓመታትንም ይወስዳል። በዚህ ረገድ ግን እድለኞች ነን። የኮቪድ-19 ቫይረስ ዘረመል ኮድ የተገኘው በመስከረም 10 ሲሆን የወሰደው ጊዜም በጣም አጭር ነበር። ይህን የዘረመል ቅጥልጥል ኮድ የፈቱት ደግሞ በዉሃን ቪሮሎጂ ኢንስቲትዩት ፕሮፌሰር ዮንግ ዣንግና የመሩት ቡድን ነው። ልክ የዘረመል ቅጥልጥሉ ሲገኝ ቫይረሱ ከኮሮናቫይረስ ቤተሰብ የሚመደብ ዓይነት ቫይረስ መሆኑ ተደረሰበት፤ 80 ከመቶ ደግሞ ከሳርስ ጋር ተፈጥሮው እንደሚመሳሰል ታወቀ። በተለምዶ ኮሮናቫይረስ የሚባለው በዘርፉ ባለሙያዎች ለብዙ ቫይረሶች የተሰጠ የወል ስም እንጂ የአንድ ልዩ ቫይረስ ስም አይደለም። ባለብዙ ዝርያው ኮሮናቫይረስ የዚህ ቫይረስ ዝርያዎች በአሳማ፣ በግመል፣ በሌሊት ወፍ እንዲሁም በድመት ላይ ጭምር በስፋት ይገኛል። ኮቪድ-19 የኮሮናቫይረስ ቤተሰብ አንድ አባል ብቻ ነው። ከእንሰሳት ወደ ሰው በመተላለፍ ደግሞ ከኮሮናቫይረሶች 7ኛ ነው። የዘረመል ቅጥልጥል ኮዱ ከተገኘ በኋላ ሁለተኛው እንቆቅልሽ አንዴት እንደርስበታለን የሚል ነው። ይህም ስለመመርመሪያ ሂደቶች እንድናውቅ ያደርገናል። በወንጀል ምርመራ ሂደት ሦስተኛው ወንጀለኛን የማደን ሂደት ወንጀለኛውን በቁጥጥር ማዋል ነው። በተመሳሳይ ቫይረሱን ለመያዝ በመላው ዓለም ፖሊሶች እየተራወጡ ነው። ወንጀለኛው ተያዘ የምንለው ደግሞ ክትባቱ ሲገኝ ነው። ፕሮፌሰር አንደርሰን እንደሚሉት በርካታ ጥናቶች ይህ ቫይረስ ከሌሊት ወፍ እንደመጣ ይጠቁማሉ። ምክንያቱም በሌሊት ወፍ ውስጥ በርካታ ተመሳሳይ ቫይረሶች ይገኛሉና ነው። መላምቱ እውነት ከሆነ አሁን ማወቅ ያቃተን፤ እንዴት ከሌሊት ወፍ ወደ ሰው እንደተሸጋገረ ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። የፕሮፌሰር አንደርሰን የጥናት ቡድን ከሌሊት ወፍ የመጣ ሌላ የኮሮናቫይረስ አባል የሆነ ቫይረስ አግኝቷል። የዚህ ቫይረስ የዘረመል ቅጥልጥል ኮዱ ከኮቪድ-19 የሚለየው በትንሹ ነው። "96 ከመቶ አንድ ናቸው ማለት ይቻላል" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ሌላው ደግሞ ፓንጎሊን በሚባሉ አጥቢ እንሰሳትም ላይ ተመሳሳይ ቫይረስ ተገኝቷል። አንዱ መላምት የሚሆነው ታዲያ ቫይረሱ ከሌሊት ወፍ ተነስቶ ወደ ፓንጎሊኖች ተሻግሮ ከዚየ የተወሰነ ፕሮቲን አግኝቶና ዳብሮ ይሆን ወደ ሰው የመጣው? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ምርምሩ ቀጥሏል። የሚገርመው በቻይና ይህን የዘረመል ቅጥልጥሉን ያገኙት ፕሮፌሰር ዣንግ ከዚህ ስኬታማ ሥራ በኋላ ቤተ ሙከራቸው ታሽጎባቸዋል፤ ባልደረቻቸውም ኮዱን ለዓለም ባሳወቁ በ2ኛው ቀን ፖሊስ ወስዷቸዋል። ፍቃዳችውንም ሰርዞታል። የቻይና መገናኛ ብዙሃን እንደዘቡት ይህ ለምን እንደተደረገ የተሰጠ ምንም ምክንያት የለም። የፕሮፌሰር ዣንግ የዘረመል ቅጥልጥል ባይኖር ኖሮ አሁን የተሰሩት ነገሮች አንዳቸውም ሊሳኩ አይችም ነበር ይላሉ ፕሮፌሰር አንደርሰን። የቫይረስ ዘረምል ቅጥልጥል ኮድ ሳይገኝ አንዳችም ሥራ መስራት አይቻም ነበር። ወንጀለኛውን ማሳደድ ደቡብ ኮሪያ 51 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት አገር ናት። ቫይረሱን አሳዶ በመያዝ ተሳክቶላታል የምትባለው እርሷ ናት። ይህን ያሳካችው ወንጀለኛን አድኖ የመያዝ ችሎታ ያላቸውን ትንንሽ የቫይረስ ወታደሮችን በማሰልጠኗ ነው። እነዚህ ወንጀል አዳኞች ሥራቸው ሌላ አይደለም። አንድ ሰው ቫይረሱ ተገኘበት ሲባል የዚያን ሰው ንክኪና የእንቅስቃሴ ታሪክ ቶሎ አግኝቶ እርምጃ መውሰድ ነው። እነዚህ አዳኞች ማን ራሱን ማግለል እንዳለበት፣ ማን መንቀሳቀስ እንደሚችል፣ የትኛው ሕንጻ ሙሉ በሙሉ መታሸግ እንዳለበት፣ የትኛው ገበያ መዘጋት እንዳለበት ቶሎ ውሳኔ ይሰጣሉ። በዚህ ሁኔታ ቫይረሱን መፈናፈኛ አሳጡት። እግር በእግር አሳደዱት። ደቡብ ኮሪያ ተጨበጨበላት። ይህ ስኬት እያለ ነው ታዲያ በጥቅምት መጨረሻ አንዲት የኮሪያ ከተማ ድንገት በቫይረሱ የተወረረችው። በጥቂት ቀናት ውስጥ ሺህ ሰዎች ተያዙ ተባለ። ይህቺ ከተማ ዴጉ ትባላለች። አንዲት ሴት ናት ይቺን ከተማ የበከለቻት። ብቻዋን! ለዚህች ሴትዮ "ታማሚ 31" የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷታል። ይህች ሴት በጥቅምት 17 ቫይረሱ እንዳለባት ታወቀ። እነዚህ ቫይረስ አዳኞች ያዳረሰቻቸውን ቦታዎች በሙሉ ሲመረምሩ በ10 ቀናት ውስጥ አንድ ሺ ሰዎችን ነካክታለች። ምስጋና ለአዳኞች እንጂ ሴትዮዋ ታደርስ የነበረው ጉዳት ከዚህም በላይ በሆነ ነበር ተብሏል። እነዚህ አዳኞኝ የስልክ መተግበሪያን፣ ጂፒኤስን [የቦታ አመልካች መሳሪያ]፣ የክፍያ ካርዶችን እነ ክሬዲት ካርድን ጭምር ይጠቀማሉ። ይቺ ሴትዮ መጀመሪያ የሺንቼኖጂ ቤተክርስቲያን አባል መሆኗን አልተናገረችም ነበር። እነዚህ አዳኞች ናቸው የደረሱበት። ያደረሰቸው ጉዳትም ከፍተኛ የሆነው ለዚያ ነው። ይህ ቤተክርስቲያን 300 ሺህ አባላት አሉት። የቤተክርስቲያኑ መሪ ሊ ማን ሂ ይባላሉ። ዳግማዊ ክርስቶስ ናቸው ተብሎ ይታመናል። መጽሐፍ ቅዱስን የመተርጎም ሥልጣን ያላቸውም እሳቸው ብቻ ናቸው ብለው ያምናሉ ተከታዮቹ። ይህ ቤተክርስቲያንና የሚያራምደው እምነት ደቡብ ኮሪያ ከሚገኙ በአብዛኞቹ ክርስቲያኖች ዘንድ ያፈነገጠ የሚባል ነው። ይህቺ "ታማሚ 31" በሚል ቅጽል የምትታወቅ ሴትዮ የዚህ ቤተክርስቲያን አባል መሆኗ ብቻ አልነበረም ችግር የፈጠረው። የህመሙን ምልክት እያሳየች በ10 ቀናት ብቻ አንድ ሺህ ሰዎችን ጋር በተለያየ መንገድ ተገናኝታለች። ጥቅምት 7 ላይ የመኪና አደጋ ደረሰባትና ሆስፒታል ገባች። ሆስፒታል ውስጥ ደግሞ ከ128 ሰዎች ጋር ንክኪ ነበራት። እቃ ላምጣ እያለች ከሆስፒታል ወጥታ ብዙ ሰዎች ጋር ተገናኝታለች። በኋላም ምሳ በልቼ መጣሁ እያለች ጓደኞቿን ታገኝ ነበር። በመጨረሻም ተደብቃ ወጥታ እዚህ ቤተክርስቲያን ተገኘችና ከሺህ ሰዎች ጋር ታደመች። ትልቁ ችግር የተከሰተው ደግሞ የዚህ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ራሳቸውን መደበቃቸው ነው። ዴጉ ከተማ ከፍተኛ ተጠቂ የሆነችውም በዚሁ ምክንያት ነበር። ዋናው የአደኑ ሂደት የተያዘውን ሰው የጉዞ ታሪክ ለማግኘት በፍጥነት ምርመራ በማድረግ በሚያዚያ ወር በዴጉ ከተማ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ዜሮ ሆነ። ሌሎች አገሮች ግን ይህን የዴጉን ስኬት ማሳካት አልተቻላቸውም። አንዲት የጉዞ ታሪኳን የደበቀች ሴት ይህን ሁሉ ጉዳት የምታደርስ ከሆነ የሰዎችን የእንቅስቃሴ ታሪክ በቴክኖሎጂ ለማደን የማይችሉ አገራት ቫይረሱ እንዴት ሊዛመት እንደሚችል መገመት ከባድ ይሆንባቸዋል።
51595882
https://www.bbc.com/amharic/51595882
በቡናም በመልካም ተሞክሮዎችም ሰዎችን የሚያነቃቃው ወጣት
ፊልሞን ተስፋስላሴ ይባላል። ቡና መቁላት እና መቅመስ ሙያው ነው። በአገረ ቱርክ ለስድስት ወራት ያህል ስልጠና ወስዶ የስራ ልምምድም አድርጓል፤ ከዚያ መልስም የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የሚሰጠውን የሦስት ወራት ስልጠና ተከታትሎ ቡናን የመቅመስ እና የመቁላትን ሙያዊ ዕውቅናን አግኝቷል።
ፊልሞን እና ጓደኞቹ ካፌውን ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ ሲከፍት ሁሉም ያላቸውን ከኪሶቻቸውን አዋጥተው ወደ ሠላሳ ሺህ ብር ገደማ አሰባስበው ነበር ሙያው በተለይ ወደውጭ አገር የሚላክን ቡና በተገቢው ልኬታ መቁላትን እንዲሁም የጥራት ደረጃውን ለመለየት መቅመስን እንዲካን አስችሎታል። ይህ ከቡና ጋር ያለው ቅርርብ ነው ለአሁን ሥራው መንገድ የጠረገው። • «ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ • የ27 አስደናቂ ፈጠራዎች ባለቤት የ17 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ አሁን ከዕለታዊ ጊዜው ሰፋ ያለውን የሚወስደው በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ በሚባለው አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር በአንድ የቀድሞ መጋዘን የከፈተውን ካፌ ማስተዳደር ነው። ካፌው የአካባቢው ወጣቶች ቡና ከመጠጣት ባሻገር ነፃ የዋይፋይ አገልግሎት የሚያገኙበት፥ ተደርድረው ከተቀመጡ መፅሐፍት ያሻቸውን ተውሰው የሚያነቡበት እንዲሁም በወር አንዴ የሚያነቃቁ ንግግሮችን የሚያደርጉ እንግዶች ተጋብዘው የህይወት ተሞክሯቸውን የሚያጋሩበት እና የጃዝ ሙዚቃ ምሽቶች የሚስተናገዱበት ስፍራ ነው። ቡና ለኢትዮጵያዊያን አነቃቂ መጠጥ ብቻ አይደለም ይላል ፊልሞን፤ የኑሮ ዘይቤም ነው። በተለይ ቀደም ባለው ጊዜ "የማኅበራዊ ክንውኖች ማዕከል ነበር። ሰዎች ተገናኝተው መረጃ የሚቀባበሉበት፥ ሕይወት የሚከሰትበት መናኸሪያ ነበር። በደስታ በሐዘንም ሰዎችን አንድ አድርጎ የሚያሰባስብ ስርዓት ነበር" ሲል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ያስታውሳል። ፊልሞን ይህ ቡና ተፈልቶ፣ ሰብሰብ ብሎ ኃሳብን የመቀያየር ልማድ በከተሞች አካባቢ እየጠፋ መምጣቱ እንደሚያስቆጨው ይገልፃል፤ ከጓደኞቹ ጋር በከፈተው ካፌ እየታጣ ነው የሚለውን ማኅበራዊ ስሜት ለመኮረጅ የሚጥር ይመስላል። ፊልሞን እና ጓደኞቹ ካፌ የከፈቱበት ቦታ ከሁለት ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ተዘግቶ የከረመ መጋዘን ነበር መጋዘኑ. . . አሁን ፊልሞን እና ጓደኞቹ ካፌ የከፈቱበት ቦታ ከሁለት ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ተዘግቶ የከረመ መጋዘን ነበር። ዝግ በመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች ቆሻሻ ይጣል እና ይከመርበት፣ ሥራ የሌላቸው ወጣቶችም እርሱ "አልባሌ" ያለቸውን ተግባራት ይከውኑበት ነበር። "ቦታው ለመጥፎ ነገር የተጋለጠ አካባቢ ነበር" ይላል። • "ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው" • የረሳነውን ነገር የሚያስታውስ መሣሪያ የፈጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ቦታውን በዚህ መልኩ ቀይሮ አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ ግን የነበረው ውጣ ውረድ ታዲያ ቀላል አልነበረም። የመጀመሪያው ፈተና ቦታው ላይ መጋዘኑን ራሱን የመስሪያ ቦታ ለማድረግ ፈቃድ ማግኘት ነበር። "በእኛ አዕምሮ ለሁለት ዓመታት ተዘግቶ የቆየን መጋዘን ለሚሰራ ሰው መስጠት ቀላል ውሳኔ የሚሆን ነበር የመሰለን" ይላል በወቅቱ እርሱ እና ጓደኞቹ የነበራቸውን እሳቤ ሲያስታውስ። መጋዘኑ በአካካቢው የመንግስት አስተዳደር ባለቤትነት የተያዘ በመሆኑ፣ ከሚመለከተው አካል የመስሪያ ፈቃድ ለማግኘት ሰባት ወራት ገደማ መመላለስን ጠይቆታል። "አንደኛው እና ዋናው ችግር እርሱ ነበር፤ ሰዎች እንዲሰሩ መፍቀድ። ለዚያው ኃላፊነቱን ራሳቸው ወስደው፣ ሊመጣ የሚችለውን ኪሳራ ራሳቸው ተጋፍጠው እና በራሳቸው ወጭ እንስራ ላሉ ሰዎች።" ፈቃዱ ከተገኘም በኋላ ሌሎች ተግዳሮቶች አፍጥጠው መጠበቃቸው አልቀረም። • የንድፈ ሐሳብ ትምህርትን ወደ ተግባራዊ ዕውቀት ለመለወጥ የሚተጋው የፈጠራ ባለሙያ • ከባህላዊ ጃንጥላ እስከ እንጀራ ማቀነባበሪያ፡ የ2011 አበይት ፈጠራዎች ለምሳሌ መጋዘኑ ዘለግ ላለ ጊዜ ተዘግቶ እንደመቆየቱ ውሃ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎትን የመሳሰሉ አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች አልነበሩትም። እነርሱን ለማሟላትም የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ደጋግሞ ደጅ መጥናት አስፈልጓል። ቦታው ቡና ይቆላበታል፤ ይፈላበታል፤ ይታሸግበታል፤ ምግብ ይሰናዳበታል። "እንደዚያ ቆሻሻ የነበረን ቦታ አሁን ለምግብ ማቀነባበሪያነት ነው የተጠቀምንበት። ሙሉ በሙሉ ነው የለወጥነው።" በበርካታ ጀማሪ የንግድ ተቋማት ላይ የሚስተዋለው የብድር አገልግሎት እጦት ሌላኛው ማነቆ ነበር። ፊልሞን ለወጣቶች እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ አደረጃጀት ለተዋቀሩ የንግድ እና የአገልግሎት ተቋማት ከመንግስት ይሰጣል የሚባለውን ብድር ማግኘት "ላም አለኝ በሰማይ..." ላይ ነው የሆነብን ይላል። "የሚታይ ለውጥ አምጥተናል። ማስያዣ አለን። አርዐያ መሆን የምንችል ተቋም ነን። ይሄንን ለእነርሱ ማብራራት ራሱ ችግር ነው።" የበጎ እሳቤ መድረክ. . . ፊልሞን በካፌው ውስጥ መፅሐፍትን ደርድሮ ማንበብ ለሚፈለግ ሰዎች እንዲዋሱ የማድረግ ኃሳብ ከተገልጋዮች እንደመጣ ይናገራል። መፅሐፍቱንም እንዲሁ ከደንበኞች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሰባሰበ ለቢቢሲ አስረድቷል። "መልሶም የሚጠቀመው የአካባቢው ማኅበረሰብ ነው።" በቀን ሁለት መቶ ገደማ ደንበኞች ቦታውን ይጎበኛሉ። በወር አንዴ የሚከናወነው የማነቃቂያ መርኃ ግብር ግን ከራሱ የሕይወት ተሞክሮ መመዘዙን ይገልፃል። "እኔ እንደወጣት ያለፍኩባቸው፥ የተነቃቃሁባቸው፥ የተጠቀምኩባቸው ብዙ ተመሳሳይ መርኃ ግብሮች ነበሩ።" ሰዎች ያለፉበትን ውጣ ውረድ፣ ተሞክሯቸውን መስማት እና ምስክርነታቸውን ማዳመጥ ከምክርም በዘለለ እንደሚለውጥ በራሴም ሕይወት ላይ አይቼ አውቀዋለሁ ይላል ፊልሞን። እናም "ሰው እንጋብዛለን፤ ልምዳቸውን፣ የስኬት ታሪካቸውን ይነግሩናል።" መርኃ ግብሩን ማድረግ ከጀመሩ አንስቶ ከሰባት ላላነሱ ጊዜያት አከናውነዋል እርሱ አንደሚለው። የወደፊት ጉዞ ፊልሞን እና ጓደኞቹ ካፌውን ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ ሲከፍት ሁሉም ያላቸውን ከኪሶቻቸውን አዋጥተው ወደ ሠላሳ ሺህ ብር ገደማ አሰባስበው ነበር። የነበራቸው መሣርያም ከማሽን ጎን የምትቀመጥ ትንሽ የኤስፕሬሶ መፍጫ ብቻ ነበረች። ቡናውን ለማስቆላት ግን ማሽኑ ላላቸው ሌሎች ድርጅቶች መክፈል ነበረባቸው። በጊዜ ሒደት ያገለገሉ ማሽኖችን ረከስ ባለ ዋጋ በመግዛት ቡናውን ራሳቸው መቁላት ጀመሩ። አሁን በራሳቸው ቡናውን ቆልተው፥ ያፈላሉ፥ ለገበያ የሚቀርብ ዱቄትም ፈጭተው ያሽጋሉ። የተቆላ እና የተፈጨ ቡናቸውን ለአርባ የተለያዩ ካፌዎች ያቀርባሉ- ፊልሞን ለቢቢሲ እንደገለፀው። የባለቤትነት ድርሻ ያላቸውን እንዲሁም ተቀጥረው የሚሰሩትን ጨምሮ ለአስራ አራት ወጣቶች ቋሚ የእንጀራ በር ከፍተዋል። በዚህ የመቆም ፍላጎቱ ግን የላቸውም። ምርታቸውን ወደውጭ አገራት ለመላክ ፈቃዱን ወስደዋል፤ የሚቀረው አቅም ማደበር ነው። ቡናን በመቁላት እና በመቅመስ የወሰዳቸው ትምህርቶች እና የሥራ ተሞክሮዎች "በጣም ጠቅመውናል" ባይ ነው ፊልሞን። "ከዕውቀት ተነስተን እንድንሰራ፥ የሚጎድለንን እንድናሻሽል፥ ጥራትን እንድንሽት ረድቶናል።"
news-47799378
https://www.bbc.com/amharic/news-47799378
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ 6 ዋና ዋና ዕቅዶች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ከፍተኛው የሃገሪቱ የስልጣን መንበር የመጡበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ባለፉት አስራ ሁለት ወራት በመንግሥታቸው ስለተከናወኑት ተግባራትና ስላጋጠሙት ተግዳሮቶች ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጠቀሷቸው የመንግሥታቸው ስኬቶች መካከል ባለፉት 100 ዓመታት በአንድ ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ አግኝታ የማታውቀውን የውጪ ምንዛሬ መጠን በ7 ወራት ውስጥ 13 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት እንደቻለችና በዚህ ጊዜም 8 ቢሊዮን ዶላር ለግሉ ዘርፍ መቅረቡን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱት መፈናቀሎች ካጋጠሙ ችግሮች ውስጥ በቀዳሚነት ጠቅሰው በፖለቲካ ኃይሎች መካከል ያለው መጠላለፍ ሃገሪቱ እያካሄደች ላለው ለውጥ እንቅፋት እንደሆነም ጠቁመዋል። • መፈናቀል፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ዓመት ፈተናዎች አንዱ • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ የስልጣን ዘመናቸው ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከ ዳር በጋራ በመቆም በማይግባቡበት እየተወያዩ ኢትዮጵያዊነትን የሚያደምቁበት ዓመት እንዲሆን ጥሪ አቅርበው፤ በቀጣይነት መንግሥታቸው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አስቀምጠዋል። • የጠቅላይ ሚንስትሩን የአንድ ዓመት የስልጣን ዘመን እንዴት ይመዝኑታል? የሕግ የበላይነትን በተመለከተ ሁሉም ሕግ የሚያስከብሩና ሕግ የሚተረጉሙ አካላት ከተሻሻሉት ሕጎች በተጨማሪ እያንዳንዱን ዜጋ ከጥቃት የሚከላከሉ ሃቀኛ ፍትህን ከፍርድ ቤቶች የሚያስገኙ ሥራዎች በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲያቆሙ ማድረግም የዕቅዳቸው አካል አድርገው ጠቅሰዋል። 2. የሥራ ዕድል ፈጠራ ሌላኛው በቀጣይ አንድ ዓመት ሊያሳኩ ካቀዱት መካከል ይገኛል። ገለልተኛ ተቋማትና ጠንካራ መንግሥትን በመገንባት የውጪ ባለሀብቶች በተለያዩ መስኮች እንዲሰማሩ በማድረግ ለወጣቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ማድረግ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠውም ተናግረዋል። እንዲሁም የማዕድን ዘርፍን ማጎልበትና የውጪ ምንዛሪን ማስገኘት ከዕቅዳቸው መካከል ይገኝበታል። • ኢትዮጵያዊያን ቶሎ አያረጁም? 3. የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይም ሌላኛው ዕቅዳቸው ነው። እነዚህ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደነበሩባቸው ቦታ እንዲመለሱ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እንዲቋቋሙ መንግሥት ከሕዝቡ ጋር በመሆን እንደሚሰራ ተናግረዋል። 4. በግብርናው ዘርፍ በዚህ ዓመት በትናንሽና በመካከለኛ የመስኖ ሥራ ላይ የተጀመሩት ሥራዎችና ጥናቶችን አጠናክሮ ፍሬያማ ለማድረግም አልመዋል። 5. በቱሪዝም መስክ በመጪው መስከረም ወር የብሔራዊ ቤተ መንግሥት ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረግና የአዲስ አበባን ገጽታ ለመቀየር እየተሰራ ያለው ፕሮጀክትም በመጪው ዓመት አንድ አራተኛው ተጠናቆ ክፍት እንደሚሆን ተናግረዋል። 6. በሚቀጥለው ዓመት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰረት የሚኖረው ምርጫ ፍጹም ነጻና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲከናወን በማድረግ በአፍሪካ ደረጃ አርዓያ እንዲሆን ይሰራልም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ መንግሥታቸው ሊሰራ ያቀዳቸውን ጉዳዮች ካስቀመጡ በኋላ ባለፈው አንድ ዓመት ሕዝቡ እየጠበቀ የጎደለና ያልተሟላ ነገር ካለ ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቀዋል። • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? • የጌዲዮ ተፈናቃዮች ሁኔታ በፎቶ ሕዝቡ ተስፋ አድርጎ በአስተዳደራቸው በኩል ያልተፈጸሙ ነገሮች ካሉ በዳተኝነትና በንዝህላልነት ሳይሆን ምናልባት ከዕውቀት ማነስና ከሁኔታዎች አለመመቸት እንደሚሆን ተናግረው፤ ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሲወጡ እንደቆዩ ተናግረዋል።
54367503
https://www.bbc.com/amharic/54367503
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፡ "በታሰርኩበት ጊዜ በከዘራ እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር"- ርዕዮት አለሙ
"አንድ ትውልድ ይወለዳል ፤ በጊዜው እንደጊዜው ያድጋል፤ ያልፋል፤ በሌላ ትውልድ ይተካል፤ አዲሱም ትውልድ የተረከበውን ቅርስ ይዞ ይነሣና በራሱ ጥረት አዳዲስ ሥራዎችን ሠርቶ ይጨምርበትና ያድጋል፤ አዲስ ነገርን ትቶ ያልፋል፤ የቀደመው ትውልድ ተፈጥሮና ኑሮው ከሚያስገድደው በላይ ለሚቀጥለው ትውልድ መስዋ ዕ ት መሆን አይችልም፤ አይጠበቅበትምም፤ በምጽዋትና በሞግዚት አስተዳደር የሚኖር ትውልድ ሊሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፈው ዕዳ ብቻ ነው ። "
ይህ የተወሰደው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ለአስርት ዓመታት ያህል በፅሁፋቸው፣ በንግግራቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሰላማዊ ትግልን ዋና ማዕከል አድርገው ሲሞግቱ ከነበሩት የአደባባዩ ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ከፃፉት ነው። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከሁለት ሳምንት በፊትም "ትውልዶች" ብለው በፌስቡክ ገፃቸው መጨረሻ አካባቢ ከፃፉት የተቀነጨበ ነው። በርካቶች የቀለም ቀንድ ብለው የሚጠሯቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ደራሲ፣ ፖለቲከኛ፣ የጂኦግራፊ መምህሩ ፕሮፌሰር የአገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊና መፃኢ ተስፋንም በተመለከተ "ተዝቆ ከማያልቀው" ዕውቀታቸው ሙያዊ ትንታኔን በመስጠት ዘመናትን ተሻግረዋል። በቅርብ የሚያውቋቸውና ለሰዓታት ውይይት ያደረጉ ሰዎች እውቀታቸው ባህር ነው ይሏቸዋል። በተደጋጋሚ በሚያደርጓቸው ቃለ መጠይቆች ነፃነት በምንም የማይለወጥ መሆኑን፣ ለሆድ መገበር የሚለውን አጥብቀው ሲቃወሙም ይሰማሉ። ለሚያምኑበት ነገር የማይደራደሩ፣ በአቋማቸው የፀኑ፣ ለአላማቸው ሟች የሚባሉት ፕሮፌሰር መስፍን በዘመናት ውስጥም በፅሁፋቸው፣ በአስተምህሮታቸው እንዲሁም የእድሜ ባለፀጋ ከሆኑ በኋላም የመጣውን ፌስቡክ ተቀላቅለው በተገኘው መድረክ ሁሉ ሲፅፉ፣ ሲተቹ ኃይለ ቃልም በመናገር ይታወቃሉ። በዚህም ሁኔታ በአስተሳባቸው በርካቶች የአገር ዋርካ፣ ጭቆናን የሚጠየፉ፣ ትውልድን ለማንቃት የማይታክቱ የአፃፃፍ ችሎታቸውን በማወደስ፣ የሰብዓዊ መብት ፋና ወጊ የሚሏቸውን ያህል የመርማሪ ኮሚሽን ሊቀ-መንበርነታቸው ጋር ተያይዞም ከ60ዎቹ ግድያ ጋር ነቀፌታቸውን የሚያሰሙ አሉ። "ኢትዮጵያዊ ሁሉ መብቱ እንዲከበር የታገለ ሰው"- ዶክተር ኃይሉ አርአያ ፕሮፌሰር ወይም የቀድሞ ተማሪዎቻቸው እንደሚጠሯቸው ጋሽ መስፍን በአደባባይ በመሞገትና ሃሳባቸውንም በማንፀባረቅ በርካታ ትውልዶችን ማስተሳሰር እንዲሁም ሃሳቦችም ማምጣት የቻሉ ሰው መሆናቸውንም ለበርካታ አስርት ዓመታት የሚያውቋቸው ዶክተር ኃይሉ አርአያ ይናገራሉ። ኢህአዴግ ስልጣን በተቆጣጠረ ማግስት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)ን ያቋቋሙት ፕሮፌሰር መስፍን በአገሪቱ ውሰጥ ይደረግ የነበረውን የመብት ጥሰት ይፋ በማውጣት መስራታቸውንም በማስታወስ "ኢትዮጵያዊ ሁሉ መብቱ እንዲከበር የታገለ ሰው ነው" ይሏቸዋል። ለዓመታትም መሰረታዊ የሚባለውን የሰብዓዊ መብት እንዲከበርም ከፍተኛ ጥረትና አስተዋፅኦ እንዳደረጉም ዶክተር ኃይሉ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርነት ጀምሮ ወደ ፖለቲካው መድረክም ጎራ ባሉበት ወቅትም በአንድነት ፓርቲ አብረዋቸው የነበሩት ዶክተር ኃይሉ ፕሮፌሰሩ ሃሳባቸውን የሚገልፁበት መንገድና ስለ ቀናነታቸው አውርተው አይጠግቡም። "በብዙ መንገድ ነው መስፍንን የማውቀውና የምወደው። አንዱ እሱን የምወድበት አቋም በሚያምነው ነገር የመፅናቱ ጉዳይ ነው" የሚሉት ዶክተር ኃይሉ የሚያስቡትንም ሆነ የሚያምኑበትን ከመናገር ወደ ኋላ የማይሉ፣ እውነትና ትክክለኛ ነው ብለው ያሰቡትንም ማንም ቢቃወም ከመግለፅ ወደ ኋላ አይሉም ይሏቸዋል። "ሐሳቡን በትክክልና ቀና በሆነ መንገድ በሚያቀርብበት ጊዜ ሰዎች ይነካሉ፤ ይቆጣሉ። የተለየ ባህርይ ነው የሚሰጡት፣ ሰውንም ያስቀይማል ግን እውነቱንና ትክክለኛ ነገር ነው የሚናገረው" ይላሉ። አንዳንዶች ፕሮፌሰሩ የሚናገሩትን ጉዳይ በተሳሳተ መንገድ የሚተረጉሙት በመኖራቸውም በሃሳብ ከሰዎች ጋር እንደሚጋጩ የሚናገሩት ጓደኛቸው ዶክተር ኃይሉ ብቻ አይደሉም። ስለሳቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚባሉና የሚፃፉ ጉዳዮችም ለዚህ አባሪ ናቸው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ በተሰጠው ምርጫ 1997 ጋርም ተያይዞ ቀስተ ደመና የተባለ የፖለቲካ ፓርቲ የመሰረቱት ፕሮፌሰሩ በአንድነት ፓርቲ ውስጥም ከዶክተር ኃይሉ ጋር አንድ ላይ ነበሩ። በሃሳብ ከፓርቲውም ጋር ሆነ ከሳቸው ጋር ቢለያዩም፤ እንዲሁም ትክክል አይደለም ብለው ቢያምኑም "የተናገረው ነገር በእኔ ሃሳብ፣ በእኔ በኩል ትክክል አይደለም። ነገር ግን የሚያምንበትን ነገር በመግለፁ አቋሙን አደንቅለታለሁ፤ አከብርለታለሁኝ" ይላሉ። በሃሳብ መለያየት እንዳለ ሆነ በቅንነትና በምሉዕነት መግለፃቸውን ለሳቸው ከበሬታ እንዲኖራቸው እንዳደረጋቸውም ደጋግመው ዶክተር ኃይሉ ይናገራሉ። "ሃሳቡን የመግለፁን መንፈስ፣ ቅንነቱን አደንቅለታለሁ። በዚህ ምክንያት በጣም እወደዋለሁ" የሚሉት ዶክተር ኃይሉ የፕሮፌሰር መስፍን ዋናው ትኩረታቸው የተሻለች ኢትዮጵያ፣ በድህነትና በጭቆና የሚደቆሰው ሕዝብ የተሻለ ኑሮና ነፃነትን የሚያገኝበትን የወደፊትን መፍጠር ህልማቸው ነበር። በአንዳንዶች ዘንድ 'የኔታ' ተብለው የሚጠሩት ፕሮፌሰር ዕድሜያቸውን በሙሉ ከወጣቶች ጋር ያሳለፉ፣ በዕድሜ የልጅ ልጆቻው ከሚሆኑ ጋር የቅርብ ጓደኝነት ያፈሩና በአገሪቱ ራዕይም አብረው የሚወጥኑና የሚሟገቱም ናቸው። "በታሰርኩበት ጊዜ በከዘራ እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር"- ርዕዮት አለሙ ከነዚህም መካከል ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ አንዷ ናት። በከፍተኛ ሃዘን ተውጣ ያለችው ርዕዮት አለሙ ስለ ፕሮፌሰር መስፍን ጥቂት ነገር ንገሪን ብሎ ቢቢሲ በጠየቃት ወቅትም "ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩኝ መገለፅ እንዳለበት ላልገልፀው እችላለሁ" ብላለች። ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር በጣም ቅርበት የነበራቸው ሲሆን እሷ ብቻ ሳትሆን የእሳቸውን አላማ የሚደግፉ ወጣቶችም ጋር አብረው ይሰባሰቡም፤ ይገናኙም ነበር። በተለይም ደግሞ በበዓላት ወቅት አብረው ያከብራሉ፤ የእሳቸውንም ልደት እንዲሁ አንዳንድ ዝግቶጅም ላይ አብረው ማሳለፋቸው ከፍተኛ ቅርበት እንደፈጠረላቸውም ርዕዮት ታስረዳለች። "ትዝ የሚለኝ ትልልቅ መፃህፍት (እንግሊዝኛቸው ሁሉ ከበድ ከበድ የሚል) ይህንን አንብበሽ ጨርሰሽ እንወያይበታለን፤ እያለ በዚህ አይነት መንገድ ሁሉ ወጣቶችን ለማብቃት የሚያደርጋቸው ጥረት ትዝ ይለኛል" በማለት ሳግ በተናነቀው ድምጿ ትናገራለች። በታሰረችበት ወቅትም በርካታ ጊዜዎች እንደጎበኟትም ታስታውሳለች። "በታሰርኩ ጊዜ እንደዚያ ከዘራ ይዞ ሁሉ እየመጣ ይጠይቅ ነበር ከወጣቶች ጋር አብሮ፤ በታሰርኩባቸው ዓመታት ልደቶቼ ሲታሰቡ በተለያዩ ቦታዎች ይገኝ ነበር" ትላለች። ስትፈታም እስር ቤት በር ላይ ቆመው ከጠበቋትና ከተቀበሏትም መካከል ፕሮፌሰር መስፍን አንዱ ነበሩ። መፅሃፏም ሲወጣ ከጀርባው ማስታወሻ የፃፉላት እሳቸው ናቸው። "በዚያ እድሜው፤ ምን ያህል አገርሽን አክብረሻል ብሎ ሲያስብ? ምን ያህል እንደሚያከብርሽ እሱን የሚያህል ትልቅ ሰው። እኔ እንግዲህ ከእሱ ጋራ በምንም በምንም የማልወዳዳር ሰው በዚያ መጠን ሲያከብር ምን አይነት ሰው እንደሆነ መረዳት ይቻላል" በማለትም ለሰው ልጅ የነበራቸውን ከበሬታም ጥልቅ እንደነበረ ታዝባለች። "ወገንተኝነትን የሚፀየፍ ነበር" የምተለው ርዕዮት "ኢትዮጵያ በማለት እድሜ ልኩን የኖረላት፣ የተሰቃየላት፣ ያከበራት ለእሱ ከምንም በላይ የሆነች አገር ነች።" "እሱ ከዚህ ጎሳ ነው፣ ከዚህ ነው፤ የእሱ ጉዳይ አይደለም። ሰው የተባለ ፍጡር ሁሉ ተጎዳ ሲባል ራሱ እንደተጎዳ አድርጎ የሚያስብ፣ የሚያመው እንደዚህ አይነት ትልቅ ሰው ነው ያጣነው" ትላለች። ከዚያም በተጨማሪ በአኗኗራቸው ላይ ለቁሳዊ ህይወትም ሆነ ለሃብት ምንም አይነት ቦታ የማይሰጡም እንደነበሩም ትናገራለች። "አንዳንዴም የሚጠየፍ ነው የሚመስለኝ እና እንዴት ሆኖ እድሜ ልኩን በአንዲት አፓርትመንት እንደኖረ ሲታሰብ በእሱ የእውቀት ደረጃ የትኛውም ዓለማዊ ደረጃ ያሉ ሰዎች መድረስ የሚችሉበት ነገር ሲታሰብና እሱ እንዴት እንደኖረ ሳስብ በቃ ጉዳዩ አይደለም" በማለትም በሐዘን በተሞላ ድምጿ ታላቅ ስለምትላቸው ፕሮፌሰር ምን አይነት ሰው እንደነበሩም ትናገራለች። በተለያየ ትውልድ ላይ ያሉት ዶክተር ኃይሉም ሆነ ርዕዮት የሚሉትም ፕሮፌሰሩ "ራሳቸውን ሆነው የኖሩ" ሃሳባቸውን በግልፅ የሚያንፀባርቁ ነበሩ። "በምንም አይነት ሁኔታም ሆነ ጉዳይ አለማመቻመች፤ ሃሳቡ ጋር መስማማት አለመስማማት ይቻላል። እሱ ላመነበት እውነት ነው ላለው ነገር፤ ደረስኩበት ላለው እውነት መኖር የሚችል ራሱን ሆኖ የኖረ ሰው ነው" በማለትም ያላትን ክብርና ፍቅር ትገልፃለች። ከእሷም ጋር ቢሆን የሃሳብ ልዩነቶች ያሏቸው ሲሆን በአንዳንድ መድረኮችም ላይ በግልፅ ተነጋግረዋል። በልዩነቶቻቸውም መካከል ተከባብረውም ቀጥለዋል። ቅርበታቸው ከርዕዮት ጋር ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቧም፣ ከእህቷምም፣ ከአባቷም ከእናቷም ጋርም በጣም ቅርብ ግንኙነት ነበራቸው ነው። "ነጻ ሆኖ መኖር፣ በድፍረት ማሰብን ያስተማሩን" አቶ ይልቃል ጌትነት "ጋሽ መስፍንን የማውቃቸው" ይላል ፖለቲከኛው ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) ስለ ፕሮፌሰር መስፍን ሲናገር። እርሱ ፕሮፌሰር ብሎ ጠርቷቸው እንደማያውቅ በመግለጽም ማዕረግ ስለሚያራርቅ "እንደ አንድ ወዳጅ ፣ መምህር፣ የልብ ወዳጅ" ጋሼ መስፍን በማለት እንደሚጠራቸው ይገልጻል። አቶ ይልቃል ፕሮፌሰር መስፍንን በቅርበት ማወቅ የጀመረው በምርጫ 97 እስር ቤት ገብተው ከወጡ በኋላ መሆኑን ያስታውሳል። በወቅቱ አንድነት ፓርቲን ለመመስረት ዝግጅት ላይ እንደነበር የሚያስታውሰው ይልቃል (ኢንጂነር)፣ እውቂያቸው ለ12 ዓመት ያህል እንደሚያውቋቸው ጊዜውን በማስላት ይናገራል። ፕሮፌሰር ከይልቃል (ኢንጂነር) ጋር በነበራቸው ወዳጅነት ወቅት ልዩ ጥልቅ ፍላጎት እንዳላቸው የሚነግሩኝ የነበረው በማለትም የኀብረተሰብን እና የግለሰብን ሥነልቦና ማወቅ እንደሆነ ይገልጻል። ጋሽ መስፍን የሚያምኑበትን በድፍረት የሚናገሩ ሰው ብቻ አይደሉም ያለው ይልቃል "ኃላፊነት የሚሰማቸው፣ የሚያስተምሩትና የሚናገሩት ነገር ላለው ማኅበራዊ ስሪት ምን ይጠቅማል ብው የሚያስቡ፣ አንዳንድ ጊዜ እውነትም ቢሆን እንኳ ለአገርና ለሕዝብ ጉዳት አለው ብለው ካመኑ የማይናገሩ፣ ኃላፊነት የሚሰማቸው የአደባባይ ምሁር ነበሩ" ይላል። ይልቃል ፕሮፌሰር መስፍን በሕንድ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ሲሰሩ በዋናነት ጂኦግራፊ ያጥኑ እንጂ ፍልስፍናንም መማራቸውን በማንሳት እና ብዙ ያነበቡ መሆናቸውን በመጥቀስ ያላቸው እውቀት ዘርፈ ብዙ የሆነ እንደሆነ ይገልጻል። ለማስተማር፣ ለማሳወቅ፣ ብቻ ለመቆም ያላቸው ጽናትን ከሚያደንቁላቸው መካከል መሆኑን ይናገራል። በኢትዮጵያ ስለድርቅ ለሰባት ዓመት ያህል በማጥናት የጻፍዋቸው ጥናቶች ከድርቅ ባሻገር ችጋርን (Famine) በማንሳትም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ማጣቀሻ ሆኖ ለማስተማሪያነት እንደሚያገለግል ገልፀዋል። በጥናታቸው መደምደሚያ ላይ ነጻነትና ችጋር ተያያዥ መሆናቸውን በማንሳት የኢትዮጵያ ገበሬ ነጻ እስካልወጣ ድረስ ችጋር ከአገሪቱ አይጠፋም ብለው በጥናታቸው መደምደማቸውን፣ የችግሮቻችን ምንጭ ከፖለቲካ እና ነጻነት ማጣት መሆኑን በእነዚሁ ጥናቶቻቸው በሚገባ መግለጻቸውን ያስታውሳል። ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ እውነትንና ሳይንስን መሰረት አድርጎ በመናገር ፣ የሕብረተሰብ ሥነልቦናን፣ የማስተማር ልዩ ችሎታ፣ አድማጭን በሚዋጅ መልኩ ኅብረተሰብን ተገንዝቦ የማስተማር ችሎታቸው የላቀ መሆኑን ከሚያስታውሳቸው መካከል መሆኑን ይመሰክራል። ነጻ ሆኖ የመኖር፣ በድፍረት የማሰብ፣ ትልቅ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች መሆናቸውን የእርሳቸው መገለጫዎች መሆናቸውንም ያክላል።