context
stringclasses
367 values
question
stringlengths
10
114
answer
stringlengths
1
90
answer_start
int64
0
3.22k
ጋና ጋና በአፍሪካ አትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት። የጋና ስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይም ትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ 1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑ ማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያ አሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ። ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ። የጋና ዋና ምርቶች ካካዎ፣ ዘይት፣ አልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል። እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤ፣ ጐርጠብ፣ የስኳር ድንች፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ኦቾሎኒ፣ ባሚያና ሩዝ ይሠራል።
ቮልታ ሐይቅ የት ይገኛል?
በጋና
815
ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ እንግሊዝ ሀገር አንደደረሰም የወቅቱ የእንግሊዝ ንግስት ከነበረችው ንግስት ቪክቶሪያ ጋር ተገናኘ፡፡ ንግስቲቱም ልዑሉ የፈለገው እና ያሻው ይደረግለት ዘንድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡ ልዑሉ በመቅደላ የነበረውን እልቂት በመጠኑም ቢሆን በማየቱ እና የአባቱ እና የእናቱ ተከታታይ ሞትም በልጅ አዕምሮው ሊቀበለው ከሚችለው በላይ ስለነበር እጅግ ታውኮ እንደነበር በተደጋጋሚ ተፅፎ እናገኛለን፡፡ በ1861 ዓ.ም ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ አንዲት ከተማ አዛዥ ሆኖ ስለተሾመ የ8 ዓመቱን አለማየሁን እና ሚስቱን ይዞ ወደዛው አቀና፡፡ በሄዱበት ሀገርም አለማየሁ ትምህርቱን መከታተሉን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን ከመደበኛው ትምህርት በዘለለም ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንም ያዘወትር ነበር፡፡ 1867 ዓ.ም አለማየሁ ወደ ራግቢ ትምህርት ቤት ተዛወረ፡፡ በዚህም ከቄስ ብሌክ ቤት ወጥቶ ወደ ሊው ዋርነር ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በዚህ ግን ደስተኛ ስላልነበር በቀጣዩ አመት ሚስተር ድራፐር ቤት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ቄስ ብሌክም ካዩት የልዑሉ ባህሪ በመነሳት ልዑሉ ወታደርነት ላይ ቢያተኩር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ በዚህም ንግግር መሰረት የወታደር ትምህርት ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በአንድ ወቅት አለማየሁ ወደ ሊድስ በመሄድ በሰር ራምሰን ቤት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት በመርዝ ተመረዘ። መርዙ ህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከሩብ በተወለደ በ19 ዓመቱ ከዚህ አለም እንዲሰናበት አደረገው፡፡ አስከሬኑም ዊንድሶር ባለው የነገስታት መቀበርያ በክብር አረፈ፡፡ በመቃብሩም ላይ “የሀበሻው ልዑል አለማየሁ” የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበት እስካሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል፡፡
ልዑል አለማየሁ ከመደበኛ ትምህርቱ ውጪ ምን ያዘወትር ነበር?
ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንም
413
ውትድርና የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት ሀገሯን የመከላከል፣ የሀገሯን ፍላጎት የማስጠበቅ እና ፀጥታ አስጠባቂ ጥረቶችን የመደገፍ ግዴታ አለበት። ሠራዊቱ የምድር፣ የባህርና የአየር ኃይል አለው። ሠራዊቱ ከነፃነት ጀምሮ በሀገሯ ታሪክ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በተለያዩ ጊዜያት የውትድርና ጁንታዎች ሥልጣን በመያዝ አገሯን አስተዳድረዋል። የናይጄራያ ሠራዊት በፀጥታ ጠባቂነት ደረጃ ከ1995 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በላይቤሪያ (1997 እ.ኤ.አ.)፣ አይቮሪ ኮስት (ከ1997 እስከ 1999 እ.ኤ.አ. ) እና ሲየራ ሊዮን (ከ1997 እ.ኤ.አ. 1999 እ.ኤ.አ.) ተሰማርቷል። ምጣኔ ሀብት በግብርና ናይጄሪያ በዋናነት ለአለም የምታቀርበው ምርቶች በተለይ ካካውና ጎማ ናቸው። እንዲሁም ፔትሮሊየም ከሚያቀርቡት አገራት 12ኛ ነች። በተጨማሪ፣ የመኪና ሥራ ድርጅት (ኢኖሶን ተሽከርካሪ መፈብረክ) ይኖራል። መልከዓ ምድር ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ በጊኒ ባሕረ ሰላጤ ላይ ትገኛለች። የቆዳ ስፋቷ 923,768 ካሬ ኪ.ሚ. ሲሆን ከዓለም ፴፪ኛዋ ትልቅ ሀገር ናት። ድንበሯ 4,047 ኪ.ሜ. ርዝመት ሲኖረው ከቤኒን 773 ኪ.ሜ.፣ ኒጄር 1,497 ኪ.ሜ.፣ ቻድ 87 ኪ.ሜ.፣ ካሜሩን 1,690 ኪ.ሜ. ትዋሰናለች። በተጨማሪም 853 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ጠረፍ አላት። በናይጄሪያ ውስጥ ከፍተኛው ቦታ ቻፓል ዋዲ ተራራ ሲሆን ከፍታው 2,419 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ነው። የአገሯ ዋና ወንዞች ኒጄር እና ቤንዌ ሲሆን ወደ ኒጄር ደለል ይፈሳሉ።
በናይጄሪያ ከፍተኛው ቦታ በምን ያህል ከፍታ ላይ ይገኛል?
2,419 ሜትር
763
ላይቤሪያ ላይቤሪያ (እንግሊዝኛ፦ Liberia)፣ በይፋ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ፦ Republic of Liberia)፣ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በጊኒ፣ ኮት ዲቯር፣ ሴራሊዮን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። ላይቤሪያ የቅኝ ግዛት ሆና በ1822 እ.ኤ.አ. ከአሜሪካ በመጡ ነጻ የወጡ ባሪያዎች የተመሠረተች ሲሆን በአካባቢው ግን የተለያዩ ብሔሮች ለብዙ ምእተ አመታት ኖረዋል። መሥራቾቹ ዋና ከተማቸውን ሞንሮቪያ ብለው ለአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጄምስ ሞንሮው ሰይመውታል። ሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፴፱ ዓ/ም ነጻነት አወጁና ግዛቷ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ሆነች። በ1980 እ.ኤ.አ. በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት የላይቤሪያ አመራር ከወረደ በኋላ ከ1989 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ድረስ ሀገሩዋ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀሉና የሀገሩዋን ኢኮኖሚ ያቃወሱ ሁለት የእርስ-በርስ ጦርነቶችን አይታለች። የአንትሮፖሎጂ ምርምር እንደሚያሳየው ከሆነ፣ በላይቤሪያ ላይ ከ12ኛው ክፍለ-ዘመን ወይም ከዛ በፊት ጀምሮ ሰው ሠፍሯል። መንዴ (Mende) የሚባል ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ ምዕራብ ሲስፋፉ፣ ሌሎች ታናናሽ ብሄረሰቦችን ወደ ደቡብ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ገፍተዋቸዋል። ዴዪ፣ ባሳ፣ ክሩ፣ ጎላ እና ኪሲ የሚባሉ ጎሳዎች በአካባቢው ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደነበሩ በማስረጃ ይታወቃል። ይህ ፍልሰት የጨመረው የማሊ ግዛት በ1375 እ.ኤ.አ. እና የሶንጋይ ግዛት በ1591 እ.ኤ.አ. ሲዳከሙ ነው። በተጨማሪም ወደ ውስጥ ያለው ሥፍራ ወደ በርሃነት እየተለወጠ ስለመጣ፣ ነዋሪዎቹ ወደ እርጥቡ ፔፐር ጠረፍ (Pepper Coast) እንዲሄዱ ተገደዱ። ከማሊና ሶንጋይ ግዛቶች የመጡ አዳዲስ ነዋሪዎች ጥጥ ማሽከርከር፣ ልብስ መስፋት፣ ብረት ማቅለጥ እና ሩዝና ማሽላ ማብቀልን የመሳሰሉ ጥበቦች ለቦታው አስተዋወቁ። መኔ ሰዎች (ከመንዴ ወታደሮች የመጡ) አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ ቫይ የሚባል የማሊ ግዛት ከፈረሰ በኋላ ለመሰደድ የተገደደ ብሔር ወደ ግራንድ ኬፕ ማውንት (Grand Cape Mount) የሚባለው ሥፍራ ፈለሱ። የክሩ ብሔር የቫይን ፍልሰት ተቃወሙ። ከመኔ ብሔር ጋር አንድ ላይ በመሆንም የቫይ ብሔርን ከግራንድ ኬፕ ማውንት አልፈው እንዳይስፋፉ አገዱ። በጠረፍ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ታንኳ ሰርተው ከካፕ-ቨርት እስከ የወርቅ ጠረፍ (Gold Coast) ድረስ ካሉት ሌሎች ምዕራብ አፍሪካውያን ጋር ይገበያዩ ነበር። የክሩ ጎሳ በመጀመሪያ ለአውሮፓውያን ሰው ያልሆኑ ነገሮችን ይሸጡ ነበር። ግን በኋላ በየአፍሪካ ባሪያ ንግድ ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ። የክሩ ሠራተኞች ቦታቸውን ትተው በትልቅ እርሻዎችና የግንባታ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል። አንዳንዶቹም የስዊዝና ፓናማ መስኖዎች ለመገንባት ረድተዋል። ሌላ ግሌቦ የሚባሉ ሰዎች የመኔ ጎሳ አካባቢያቸውን ሲወር፣ በኋላ የላይቤሪያ ወደ ሚሆነው ጠረፍ አመሩ። በ1461 እ.ኤ.አ. እና 17ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ መካከል ፖርቱጋላዊ፣ ሆላንዳዊና ብራታንያዊ ነጋዴዎች በላይቤሪያ የንግድ ቦታ አቋቁመው ነበር። በተጨማሪም የአንድ የሚጥሚጣ አይነት ፍሬ በመብዛቱ ፖርቱጋላዊያን አካባቢውን Costa da Pimenta (ኮስታ ዳ ፒሜንታ) ማለትም የፍሬ ጠረፍ ብለው ሰይመውት ነበር። በ1822 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የቅኝ መግዛት ማህበር ላይቤሪያን ባሪያ የነበሩ ጥቁር ሰዎች የሚላኩበት ቦታ አድርጎ አቋቋመ። ከሌሎች ባሪያ ያልነበሩ ጥቁር አሜሪካውያንም ወደ ላይቤሪያ ለመሄድ የመረጡ ነበሩ። ወደ እዛ የሄዱት አሜሪካዊ ላቤሪያዊያን በመባል ይታወቃሉ። በሐምሌ 20 ቀን 1839 ዓ.ም. እነዚህ ሰፋሪዎች የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ነፃነትን አወጁ። አርባ ከመቶ የሚሆነው የሀገሩ ሕዝብ ክርስቲያን ነው። ሌላ ሀያ ከመቶ የሚሆን ሕዝብ የራሱ የአገሬው ሀይማኖት አለው። የቀረው አርባ ከመቶ ሕዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው። የላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሞንሮቪያ ይገኛል። በ1862 እ.ኤ.አ. የተከፈተ ሲሆን ከአፍሪካ ቀደምት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው። በእርስ-በርስ ጦርነት ጊዜ በጣም የተጎዳ ሲሆን አሁን እንደገና እየተገነባ ነው። ከቲንግተን ዩኒቨርሲቲ በየአሜሪካ ኢጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን በ1889 እ.ኤ.አ. ተመሥርቷል። ግቢው በሱዋኮኮ፣ ቦንግ የአገዛዝ ክፍል ይገኛል።
ላይቤሪያ የምትገኝበት አህጉር የት ነው?
አፍሪካ
85
አሪዞና አሪዞና (Arizona) በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ክፍላገር ነው። ኒው ሜክሲኮ ፣ ዩታህ ፣ ኔቫዳ ፣ ካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ያዋስኑታል። የአሪዞና ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ የ30 ሰው ሴኔት እና የ60 ሰው ምክር-ቤት አለው። የሪፑብሊካን ፓርቲ በስቴቱ ዋነኛው ፓርቲ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. የአሪዞና ስቴት ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ በጀት 14.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በጀት ደግሞ 13.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። የስቴቱ ሴኔተሮች እና ምክር-ቤት ተወካዮች ለሁለት-ዓመት ጊዜ ላልተወሰነ ብዛት ይመረጣሉ። ከ4 ጊዜ በላይ በተካካይ መመረጥ ግን አይችሉም። የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በአስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን ለ4 ዓመት ሥልጣን ላይ ይቆያል። ያልተወሰነ ጊዜ መወዳደር ሲቻል ከሁለት ጊዜ በላይ ግን በተካካይ መመረጥ አይፈቀድም።
የአሪዞና ሕግ አውጪ የ30 ሴኔት አባላትና የስንት ምክር ቤት አባላት ውቅር ነው?
የ60
131
ኢትዮ ሬይን ሜከርስ ኢትዮ ሬይን ሜከርስ (Ethio Rain Maker) በኢትዮጵያ ውስጥ ዛፎች በመትከል ረሃብን ለመከልከል የተቋቋመ ቡድን ነው። አሁን ወደ ምድረ በዳ መጥተው በወንድማማችነት ገነት ይሠራሉ። በድርቅ አፈር ውስጥ የሚተክሉት ዘር ታላቅ ደን ይሆናል፤ ምድሪቱ እንደገና በሙሉ እስክትሸፈን ድረስ ረጀም ዛፎች በዝተው አረንጓዴ ክንፎቻቸውን ይዘረጋሉ። ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም መገናኛ ብዙሃን በረሃብ ስትጠራ፣ ህዝቦችዋ በጠኔ ሲሰቃዩ ዘመናት ተቆጥረዋል። የወገኖቻችን ስቃይ፣ የሀገራችን ኋላ ቀርነት በኢትዮጲያዊነታችን እያንዳንዳችንን ይመለከተናል። ላለፉት ሰላሳ አመታት በጎ አድራጊ ድርጅቶች በአይነትም ሆነ በጥሬ ገንዘብ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደረዱን መረጃ አውጥተዋል። የኛ ስቃይ ግን አላበቃም። መከር ሲመጣ ሰብል ከማጨድና ምርት ከመሰብሰብ ይልቅ ለልመና እጁን የሚዘረጋ ኢትዮጲያዊ ቁጥር በሶስት እጥፍ ጨመረ። ይህ ሂደት መቆም አለበት። እንዴት? አበው “ነገርን ከስሩ …” እንደሚሉት የሁሉም ችግር መፍትሔው ያለው ከመነሻው ላይ ነው። የኛ ረሐብ መንስዔው ምንድነው? በአጭሩ ለመግለጽ ያህል ለረሐባችን መንስዔ የዝናብ አለመኖር (ድርቅ) መሆኑን ከረሐባችን ታሪክም ሆነ ጥናቱን ካካሄዱት ምሁራን መረዳት ይቻላል። ዛሬም ቢሆን ገበሬው ዝናብ በማጣቱ ሰብሉ መበላሸቱን ከአንደበቱ እየሰማን ነው። ጦርነትን ለማቆም የጦርነት መነሻ ሃሳቦችን ማስወገድ እንጂ ጦርነትን ከጦር ሜዳ ማስቆም እንደማይቻል ሁሉ የሃገራችንንም ረሃብ ከመንስዔው እንንቀለው። ኢትዮ ሬይን ሜከርስ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ደን ማደነን (አፎረስቴሽን) ችግራችንን ከመቅረፊያ መንገዶች አንዱ እንደሆነ በማመን የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ችግኞችን መትከል ጀምሯል። በ1995 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ጋር በመተባበር በእንጦጦ የተፈጥሮ መናፈሻ አስር ሺህ ችግኞችን ተክሎ ሰባ ሁለት ከመቶው (7167) ፀድቋል። በ1996 ክረምት ደግሞ ሀምሳ ሺህ ችግኞችን ለመትከል አቅዶ ሀያ ከመቶው ተጠናቋል። በአሰላ፣ በመቀሌና በባህር ዳር አንድ ሺህ ዛፎችን የሚይዙ የተፈጥሮ መናፈሻዎችንን በመስራት ላይ ነን። በ1997 ለሀገራችን የሺህ አመት ስጦታ እንስጥ በሚል መነሻ ሀሳብ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ አንድ ዛፍ ተክሎ የሚንከባከብበትን እቅድ አውጥተናል። ከነዚህም አንዱ አንድ ዛፍ ለአንድ ተማሪ ነው። የሃገራችን የዘመናት ችግር በአንድ አመትና በጥቂት ሰዎች ጥረት አይፈታም። ለዚህ አላማ መሳካት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥረትና እገዛ ያስፈልጋልና ሃገራችንን ከረሐብ ለመታደግ አብረን ዛፍ እንትከል። እንንከባከብም።
ኢትዮ ሬይን ሜከርስ በ1996ዓ.ም. ለመትከል ካቀዱት ምን ያህሉን አሳኩ?
ሀያ ከመቶው
1,109
አማራ (ክልል) አማራ (ክልል 3) ከዘጠኙ የኢትዮጵያ ክልሎች አንዱ ሲሆን ከ 1994 በፊት አራት የሀገሪቱን ዋና ወና ክፍለ ሀገራት የ ካትት ነበር እነሱም በጌምድር ጐጃም ወሎና ሸዋ ነበሩ ።የአማራ ብሔራዊ ክልል ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ በ8° 45 እስከ 13° 45 ሰሜን የኬንትሮስ እና በ35° 46 እስከ 40° 25 ምስራቅ የኬንትሮስ መስመር ውስጥ ይገኛል። በምስራቅ የአፋርና የኦሮሚያ ክልሎች፣ በምዕራብ ሱዳን እና ቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል፣ በሰሜን የትግራይ ክልልና በደቡብ የኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል። የቆዳ ስፋቱ ፻፶፯ሺ፸፮ ካሬ ሜትር ሲሆን ከአገሪቱ አሥራ አምስት በመቶ ድርሻ ይይዛል። የክልሉ ሕዝብ ብዛት ደግሞ በ፳፻፪ ዓ/ም 20,875,456 እንደነበር የተገመተ ሲሆን ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ 33.9% አካባቢ ድርሻ ይይዛል ተብሎ ይገመታል። ክልሉ በ፲ ዞኖችና በ፻፷፮ የገጠርና የከተማ ወረዳ አስተዳደሮች የተከፋፈለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ፴፰ የሚሆኑት የከተማ አስተዳደሮች ናቸው። የአማራ፣ የአገው፣ የኦሮሞና የሌሎች ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት ክልል ነው። እንዲሁም የአማራ ክልል አሁን ላይ የክልል ከተማው ባህር ዳር ነው። በክልሉ አልፎ አልፎ ከሚታዩ የመንግሥትና የማኅበራት ደኖች፣ በደሴቶች፣ በአብያተ ክርስቲያናት፣ በወንዞች ዳርቻና ሰው ሊደርስባቸው በማይችሉ ገደላማና ተራራማ ስፍራዎች ከሚገኙ ጥቂት ደኖች በስተቀር ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የደን ሀብት ጋር በቅርብ የተያያዘ ነው። በዚህ ረገድ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ እንደ ቀይ ቀበሮ፣ ዋልያ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እንዲሁም በምዕራባዊው የክልሉ አካባቢ ዝሆን አንበሳና ነብር፣ ሰጐንና የተለያዩ አዕዋፋት በስተቀር ከፍተኛ የዱር እንስሳት ክምችት ካለመኖሩም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጥቂት የደን ቅሪቶችና ዋሻዎች የነበሩት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አራዊቶችም ለዘመናት በደረሰው የደን መጨፍጨፍና መራቆት ምክንያት ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ እንደተሰደዱ ይታወቃል። ክልሉን የማዕድን ሀብት አስመልክቶ በሚገባ የተጠናከረ ጥናት ባይኖርም ከክልሉ ስነ-ምድራዊ ሁኔታዎችና ከተካሄዱ አንዳንድ ጠቋሚ ጥናቶች መረዳት እንደሚቻለው በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ማዕድናት እንደአሉ ይገመታል። በዚህም መሠረት በሰሜን ሸዋ የኦፓል ማዕድን፣ በሰሜን ጐንደር፣ በጭልጋና በደቡብ ወሎ በአምባሰል ወረዳ የድንጋይ ከሰል ክምችት እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ለግንባታ ሥራ የሚውል በቂ የድንጋይ፣ የኖራ ድንጋይ፣የሸክላ አፈር፣ ጅኘሲየም፣ የጌጣጌጥ ማዕድናት እንዲሁም በዓባይ ሸለቆ የዕብነ በረድ ሐብቶች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይሁን እንጅ በውል የሚታወቀው ሐብትም ቢሆን በበቂ ሁኔታ አልለማም።
በኢትዮጵያ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የት ክልል ይገኛል?
አማራ (ክልል 3)
10
ዶናልድ ጆን ትራምፕ ዶናልድ ጆን ትራምፕ (ጁን 14 ቀን 1946 እ.ኤ.አ. ተወለደ) አሜሪካዊ ነጋዴ ፣ ፖለቲከኛ ፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቹ ታዋቂ እና 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፕሬዚደንት ነው። ሥልጣኑንም እ.ኤ.አ. በጃኑዌሪ 20 ቀን 2017 ተረክቧል። በክዊንስ ኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው አቶ ትራምፕ በሪል እስቴት ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የፍሬድ ትራምፕ ልጅ ነው። በኮሌጅ እያለም ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ በተባለው ድርጅት ይሠራ ነበር። በእ.ኤ.አ. 1968 ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ ያንን ድርጅት ተቀላቀለ። በእ.ኤ.አ. 1971 ደግሞ ሙሉ ሥልጣን ከተሠጠው በኋላ የድርጅቱን ስም ወደ "ዘ ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን" ለወጠው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ካሲኖዎችን ፣ የጎልፍ ሜዳዎችን ፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች በእርሱ ስም የሚጠሩ ንብረቶችን አፍርቷል። እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2015 ድረስ ዘ አፕሬንቲስ የተባለ ፕሮግራምን በኤን ቢ ሲ ላይ ያቀርብ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የሪፎርም ፓርቲ እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ ቴድ ክሩዝ እና ጆን ካሲች ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታወጀ። በእ.ኤ.አ. ኖቬምበር 8 ቀን 2016 ላይ የፕሬዚደንትነት ምርጫውን አሸነፈ። ማሸነፉንም ተከትሎ ብዙ የተቃውሞ ሠልፎች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በ70 ዓመቱም ሥልጣን ላይ በመውጣቱ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ፕሬዚደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ያደርገዋል።
ትራምፕ የት ተወለደ?
በክዊንስ ኒው ዮርክ ከተማ
169
የእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት የእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት በእስክንድርያ፣ ግብጽ በጥንት (54-373 ዓም ያህል) የተገኘ የክርስትና ሥነ መለኮት ትምህርት ተቋም ነበረ። ተቋሙን የመሠረተው የኢየሱስ ሐዋርያ እና መጀመርያው የእስክንድርያ ጳጳስ፣ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ በ54 ዓም እንደ ሆነ ተጽፏል። የተቋሙ መጀመርያው መሪ በኋላ የእስክንድያ ፮ኛው ጳጳስ የሆነው ዩስቱስ እንደ ተሾመ ይታመናል። ተቋሙ ያስተማረው ከሥነ መለኮት፣ መጽሐፍ ቅዱስና ክርስትናን ጭምር፣ የግሪክኛና የሮማይስጥ ስነ ጽሁፍ፣ ሥነ ጥበብ፣ ስነ አመክንዮ፣ ሥነ ቁጥርና ስነ-ተፈጥሮ ጥናቶች ነበሩ። ለዕውሮችም ማስተማርያ አገልግሎት አቀረቡ። በፓንታይኖስ መሪነት (173-182 ዓም) ተቋሙ ስለ ትምህርቱ ዝነኛ ሆነ። ፓንታይኖስ በክርስትና ከመጠመቁ በፊት፣ የግሪኮች «ስቶዊሲሲም» ፍልስፍና ተከታይ ሆኖ ነበር። ፓንታይኖስ የግሪክ ፍልስፍና ከክርስትና ርዕዮተ አለም ጋር እንዳዋሐደ ይታስባል። ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ ከ182-194 ዓም በተቋሙ መሪነት ተከተለው። ብዙ አረመኔዎች በዚያን ጊዜ ለትምህርት ስለመጡ ከፍልስፍና መሠረት ጀምሮ የክርስትናን ትምህርት ያሳውቃቸው ነበር። በ194 ዓም የሮሜ መንግሥት ቄሣር በክርስቲያኖች ላይ ስላዘረጋው ማሳደድ፣ ቀሌምንጦስ ለጊዜው ከእስክንድርያ ሸሸ። እሱም የጻፋቻው ትልቅ መጻሕፍት ተርፈውልናል። የቀሌምንጦስ ተከታይ ኦሪገኔስ በመከራ ጊዜ ቢሆንም ተቋሙን በ195 ዓም ዳግመኛ አቆመ። ኦሪገኔስ ደግሞ ብሉይ ኪዳን በስድስት ትይዩ ዕብራይስጥና ግሪክኛ ትርጉሞች (ሄክሳፕላ) ያሳተመው እና ብዙ አንድምታ የጻፈው ዝነኛ መምህር ነው። በ373 ዓም በተካሄደው በቁስጥንጥንያ ጉባኤ፣ የጵጵሳት ቅድምንትነት ለሮሜ ፓፓ፣ ከርሱም ቀጥሎ ለአንጾኪያ ጳጳስ እንዲሰጥ የሚል ብያኔ ወረደ። ስለሆነም፣ የእስክንድርያ ጳጳስ የቀድሞ ቀድምትነቱን በማጣቱ፣ በእስክንድርያ ከተማ ውስጥ ትልቅ ሁከት ደረሰ። በዚያም ጊዜ በተደረገው ጉዳት የማስተማርያ ተቋሙ ጠፋ።
ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ የእስክንድርያ ትምህርት ተቋምን ከመቼ እስከ መቼ መራ?
ከ182-194 ዓም
560
በዚህ በ፲፭ኛው መቶ ዓ.ም. ላይ የቱርክ፣ የመስኮብ፤ የጀርመን፤ የእንግሊዝ፤ የፈረንሳይና የኤስፓኝ መንግሥታት እንደ ኃያላን መንግሥታት መቆጠራቸው አልቀረም። ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ የፖርቱጋል መንግሥት በሌላው እንኳን ባይሆን በመርከብና አገር በመያዝ ከቀሩት ይበልጥ ነበር። የቀሩት የኤውሮፓ መንግሥታት እዚያው ወሰናቸው ላይ ገዥነታቸውን ለማጽደቅ እርስ በርሳቸው ሲጨቃጨቁ የፖርቱጋል መንግሥት ግን ደኅና ደኅና መርከቦችን አዘጋጅቶ እየላከ ከመንግሥቱና ከኤውሮፓ ርቆ የሚገኘውን የአሜሪካን፤ የእስያን፤ የአፍሪካን አገሮች ያስመረምር ነበር። መርማሪዎቹም እነቫስኮ ደጋማ፤ እነፔሬዝ፤ እነአንድራድ፤ እነካብራል በመርከብ እየሄዱ ለመከላከል ጉልበት የሌለውንና በጠባዩ ሀብት ያለበትን አገር መርምረው ሲመለሱ መንግሥቱ ወታደር በመርከብ እየላከ ብዙ አገር ያዘ። በሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፭፻ እ.ኤ.አ. ፔድሮ አልቫሬዝ ካብራል የተባለው የፖርቱጋል መኮንን በትልቅ መርከብ ሄዶ ይን ጊዜ ለቀረው ዓለም ያልታወቀውን የብራዚልን አገር አስገበረና በፖርቱጋል መንግሥት ስም ቅኝ አገር አደረገው። ከዚያም አገር በተገኘው ወርቅ መንግሥቱ ሀብታም ሆነ። እንደዚሁም የመጀመሪያ የንጉሥ እንደራሴ የተባለው ፍራንቼስኮ ዳልሜዳ ወደ ህንድ አገር ሄዶ አገሩን ያዘ። ከተማውንም በጎአ አድርጎ ህንድንም የፖርቱጋል የቄሣር ግዛት አደረገና አገር ገዥውም የንጉሥ እንደራሴ ይባል ጀመር። ከዚያም በትልቁ ውቅያኖስ ውስጥ የሚገኙትን ደሴቶች ኑቤል ጉኔንና ዛሬ ፊሊፒን የሚባለውን አገር በየጊዜው በጦር ኃይል አስገበራቸው። በዚሁ አኳኋን ወደ ኢትዮጵያም እነኮቪልሐኦ ቀደም ብለው በዓፄ እስክንድር ዘመን መጥተው እንደመረመሩትና የኢትዮጵያ መንግሥት በዚያ ጊዜ በነሱ አጠራር የቄሱ የዮሐንስ መንግሥት አለ ብለው አውርተው እንደነበረ ሌላ የፖርቱጋል የጦር መርከብ በአፍሪካ ድንበር በቀይ ባሕር ላይም እየተመላለሰ አስቀድሞ ከያዙት ከቱርኮችና ከግብጾች እየተዋጋ አንድ ጊዜም እየተሸነፈ አንድ ጊዜም እያሸነፈ ብዙ ጊዜ ተመላለሰ። በዚህ ሁሉ ምክንያት የፖርቱጋል መንግሥት ታላቅነት በሌላው ዓለም እንደ ታወቀ እንደዚሁም ፩ኛ ትልቅ መንግሥት መሆኑ ፪ኛ ክርስቲያን መሆኑ ኢትዮጵያ ባሉት የውጭ አገር ሰዎች አፍ እየተነገረ ዝናው በኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት ዘንድ መሰማት ቻለ።
የፖርቱጋል መኮንን የሆነው በትልቅ መርከብ ሄዶ በራዚልን ቅኝ ሀገር እንድትሆን ያደረጋት ሰው ማን ይባላል?
ፔድሮ አልቫሬዝ ካብራል
499
ሳህሌ ደጋጎ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል። በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ መሆኑን የሕይወት ታሪኩ ላይ ተጠቅሷል። ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ (በተቋቋመ ጊዜ ) በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁር ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር። ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ፣ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል።
ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ የትኞቹን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወቱ ነበር?
ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ”
597
ቀጭኔ ከዝሆን በስተቀር ማንኛውም ሌላ እንስሳ ሊደርስ በማይችልበት ከፍታ ላይ የሚገኙ ረዣዥም ቀንበጠቦችን ለመብላት የሚያስችል አስደናቂ አፈጣጠር አላት። ልዩ የሆነ የመቆንጠጥ ችሎታ ያለው የላይኛው ከንፈሯና እንደተፈገለው የሚተጣጠፍ ችሎታ ያለው ምላሷ ሹል በሆኑ እሾሆች የታጠሩ ቅጠሎችን ለመቀንጠብ ያስችሏታል። ቀጭኔዎች በቀን እስከ 34 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕፅዋት መመገብ ይችላሉ። የተለያዩ ዕፅዋትን የሚበሉ ቢሆኑም ይበልጥ የሚመርጡት በአፍሪካ ሜዳዎች የሚገኙትን እሾሃማ ግራሮች ነው። አንድ ወንድ ቀጭኔ ምግብ ለመፈለግ ምላሱን እስከ 42 ሳንቲ ሜትር መዘርጋት ይችላል። የቀጭኔ አንገት በጣም አስደናቂ የሆነ የመተጣጠፍ ችሎታ አለው። ይህም ላይኛዎቹን የዛፍ ቅርንጫፎች ለመቀንጠብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ረዥሙን ራሷን እንደ ልቧ ለማዘንበልና ለማዟዟር ያስችላታል። ለቀጭኔ ወደ ላይ መንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት ግን ይከብዳታል። ወደ ውኃ ጉድጓድ በምትቀርብበት ጊዜ የፊት እግሮቿን ቀስ በቀስ ከፍታ ካራራቀቻቸው በኋላ ወደ ውኃው ለመድረስ እንድትችል ሁለት ጉልበቶቿን አጠፍ ታደርጋለች። ቀጭኔዋ እንዲህ ባለው አመቺ ባልሆነ ሁኔታ እያለች ረዥም አንገቷን እስከ መጨረሻ ትዘረጋለች። ደግነቱ ግን ከምትመገባቸው ቅጠላ ቅጠሎች በቂ እርጥበት ስለምታገኝ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አያስፈልጋትም። የቀጭኔ አንገትና ትከሻ የቅጠል ቅርፅ ባላቸውና ቀጫጭን በሆኑ ነጭ መስመሮች ያጌጠ ነው። ቀለማቸው የተለያየ ሲሆን ከወርቃማ ዳለቻ አንስቶ እስከ ቡናማ እንዲያውም ጠቆር እስካለ ቀለም ይደርሳል። የቀጭኔ ዕድሜ እየገፋ በሄደ መጠን ቀለሟም እየጠቆረ ይሄዳል። ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው። አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ ልጅዋን ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት ከተሸከመች በኋላ ሁለት ሜትር ቁመት ያለው ግልገል ትወልዳለች። ግልገሏ በምትወለድበት ጊዜ ራስዋን ታስቀድምና ከሁለት ሜትር ከፍታ ላይ ወደ መሬት ትወረወራለች። ይሁን እንጂ በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባት እየተውተረተረች ትነሳና ጡት ለመጥባት ዝግጁ ትሆናለች። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ በደመ ነፍስ ተመርታ የግራር ቀንበጦችን መለቃቀም ስለምትጀምር ብዙም ሳትቆይ ረዥም እርምጃ ያላትን እናትዋን ተከትላ ለመሄድ የሚያስችል ጉልበት ታገኛለች። አንዲት የቀጭኔ ግልገል በጣም ውብ መልክ ሲኖራት የወላጆችዋ አነስተኛ ግልባጭ ነች። ቁመቷ ከቀጭኔ ርዝመት ጋር ሲወዳደር አጭር ብትሆንም ከብዙ ሰዎች ቁመት ግን ትበልጣለች። በእናቷ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ተማምና አላንዳች መሸበር አካባቢዋን የምትማትረው ግልገል ላያት ሁሉ ልዩ መስህብ አላት። ግልገል ቀጭኔዎች በተወለዱበት ወራት በግልገል መዋያ ተሰባስበው ሙሉውን ቀን ዕረፍት በማድረግ፣ በመጫወትና በአካባቢያቸው የሚሆነውን ነገር በመመልከት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የቀጭኔ ግልገል ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት ያድ⁠ጋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሜትር የሚያክል ቁመት ሲጨምር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል። በአንድ ሳምንት ብቻ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ሊያድግ ይችላል! እናትዬው ለልጅዋ ከፍተኛ ጥበቃ የምታደርግ ሲሆን ልጅዋ የተወሰነ ርቀት እንድትዘዋወር ብትፈቅድላትም ሩቅ የማየት ችሎታ ስላላት በዓይኗ ትከታተላታለች። ቀጭኔ ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ስላላት ከአንበሳ በቀር የሚያጠቃት ጠላት የለም። ቢሆንም ይህችን የምታምር ፍጥረት የሰውን ያህል በብዛት አድኖ የገደለ የለም። ቀጭኔ በሚያምር ቆዳዋ፣ በሚጣፍጥ ሥጋዋና አንዳንዶች ምትሐታዊ ኃይል አለው በሚሉት ረዥምና ጥቁር ጭራዋ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ ስለሆነች በአሁኑ ጊዜ የዚህች ሰላማዊ ፍጡር የወደፊት ሕልውና ስጋት ላይ ወድቋል። በአንድ ወቅት በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች እንደ ልብ ትታይ የነበረችው ቀጭኔ በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው በቂ ጥበቃ በሚደረግላት ፓርኮች ብቻ ሆኗል። የቀጭኔ አካላዊ ቅርጽና ግዝፈት ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል። በጣም ትልቅ ቁመትና ረዥም አንገት ስላላት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖራትና ወደ ሁሉም የአካሏ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ማድረግ የማይቻል ነገር ሊመስል ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀጭኔ አንገቷን ወደ መሬት ስታጎነብስ በስበት ኃይል ምክንያት ብዙ ደም ወደ ጭንቅላቷ ፈስሶ አንጎሏን ማጥለቅለቅ ነበረበት። ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ደሟ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ልቧ ተመልሶ ራሷን እስከ መሳት ሊያደርሳት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ነገር አይደርስም። ለምን? የቀጭኔ የደም ዝውውር ሥርዓት በዓይነቱ ልዩ ለሆነው ለዚህች እንስሳ ቅርጽና መጠን እንዲያገለግል ሆኖ በታላቅ ጥበብ የተሠራ ነው። ልቧ ራሱ በጣም ትልቅ ሲሆን ደሙን ሦስት ሜትር ተኩል ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ አንጎላ ለመግፋት የሚያስችል አቅም አለው። በደቂቃ እስከ 170 ጊዜ የሚመታውና 7 ሳንቲ ሜትር ያህል ውፍረት ባለው ጡንቻ የተገነባው የቀጭኔ ልብ ከሰው የደም ግፊት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ግፊት ያመነጫል። ወደ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው ካሮቲድ የተባለው የደም ቧንቧና ከአንጎል ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም የሚሸከመው ጀጉላር የተባለው የደም ቧንቧ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚያስችል መጠን ሊኖራቸው ይገባል። በእርግጥም እነዚህ የደም ቧንቧዎች ከ2.5 ሳንቲ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው ከመሆኑም በላይ ጠንካራና የመለጠጥ ችሎታ ባላቸው ሕዋሳት የተገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንካሬና የመለመጥ ችሎታ አላቸው። ቀጭኔ ከጭንቅላቷ ጎንበስ በምትልበት ጊዜ ወደ አንጎሏ የሚሄደውን የደም ፍሰት የሚቆጣጠሩ ልዩ መቆጣጠሪያዎች አሏት። አንጎልና አንገት በሚገናኙበት ቦታ ላይ ትልቁ ካሮቲድ የደም ቧንቧ ሬቴ ሚራቢሌ ተብሎ ከሚጠራ አስደናቂ የሆነ መረብ መሰል አካል ይገናኛል። በከፍተኛ ኃይል ተገፍትሮ የመጣው ደም እዚህ ጋር ሲደርስ በጣም በርካታ ወደሆኑ ትናንሽ የደም ሥሮች እንዲገባ ስለሚደረግ የደሙ ግፊት ተስተካክሎ በአንጎል ላይ ጉዳት የማያስከትል ይሆናል። ቀጭኔዋ ራስዋን ጎንበስ በምታደርግበት ጊዜ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው መረብ ይለጠጣል፤ ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ይኮማተራል። ይህም የስበት ኃይል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና የደም ግፊቷ በእጅጉ ቀንሶ ራሷን የምትስትበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳታል። የሳይንስ ሊቃውንት በጣም አስደናቂ ርዝመት ያለው የቀጭኔ አንገት ያሉት አከርካሪዎች ቁጥር ከአይጥ ወይም ከብዙዎቹ አጥቢ እንስሳ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቁ በጣም ተደንቀዋል! ይሁን እንጂ የቀጭኔ አከርካሪዎች በጣም ረዣዥሞችና እርስ በርሳቸው ልዩ በሆነ ሁኔታ የተሰካኩ በመሆናቸው እንደ ልብ ሊተጣጠፉ ይችላሉ። ቀጭኔ አንገቷን መጠምዘዝና ማጠፍ ስለምትችል ሁሉንም የአካሏን ክፍሎች ለመላስም ሆነ ረዣዥም የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ለመድረስ ትችላለች።
ወደ ቀጭኔ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው የደም ቧንቧ ምን ይባላል?
ካሮቲድ
2,864
የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። ውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ። ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ውለታ ለማ ያሸነፉበት የውድድር በየስንት ጊዜው ይካሄዳል?
በየዓመቱ
129
አዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዕውቁና አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ በውጭ አገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች ወጣቶችን በሳይንስ በማነጽ ተግባር እንዲሰማሩ፤ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር ጥላሁን በቻይና ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የአፍሪካ ሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል ሊያቋቁሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚዘጋጀው ወርኃዊ የሳይንስ ገለጻ መድረክ ወጣቱን ትውልድ ማስተማርና ማነጽ ለኢትዮጵያ ተስፋ፤ የቻይና ተምሳሌትነት በሚል ትናንት ምሽት ገለጻ አድርገዋል። በአውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 1943 በኢትዮጵያ የተወለዱት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች አጠናቀው በቀድሞው የአለማያ እርሻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት በኮሌጅ ቆይታቸው ባሳዩት የላቀ ውጤትም አሜሪካን አገር በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህር ቤት ተልከው ትምህርታቸውን በማጥናት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት አስተምረዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላም ወደ ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በደቂቀ ሥነ ሕይወት መስክ በማጥናት በአውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1980-2006 በተማሩበት ካሊፎርኒያ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አስተምረዋል፤ ተመራምረዋል። እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ደግሞ የዲስቲንጉሽድ ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.አ.አ ከ1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል በማቋቋም በዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በተማሩበት ካሊፎርኒያ ዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከ1980-2006 ከምን እስከ ምን ማዕረግ ደረሱ?
ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት
915
እንደ ፕላቶ ዘገባ፣ የሶቅራጠስ እናት ፌናርት የተሰኘች አዋላጅ ነበረች። ሶቅራጠስ እናቱ ሴቶች ልጅ እንዲወልዱ እንደምትረዳ ሁሉ እርሱ ደግሞ ሰዎች አዳዲስ አሳቦችን እንዲወልዱ ለመርዳት እንደሚሞክር መናገሩ ይጠቀሳል። የሶቅራጠስ አባት ድንጋይ አናጢ የነበረው ሶፍሮኒስከስ እንደነበር ይጠቀሳል። ሶቅራጠስ በዘመኑ ድሃ የነበረ ሲሆን ለዚህ ምክንያቱ ከገንዘብ ይልቅ እውቀት ይበልጣል ብሎ ስለሚያምን ነበር። ሶቅራጠስ ስራ እንደማይሰራና በፍልስፍና ሃሳብና ክርክር ጊዜውን እንደሚያሳልፍ ፕላቶ ዘግቦት ይገኛል። ዛንቲፕ የተሰኘች ከርሱ በዕድሜ በጣም የምታንስ ሴትን አግብቶ ሶስት ልጆች እንደነበሩት ፕላቶ ጽፏል። ሶቅራጠስ 70 ዓመት በሞላው ጊዜ የአቴና መንግስት እንዲያዝና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረገ። በወቅቱ ሁለት ክሶች ሲቀርቡበት አንደኛው "በትምህርትህ ወጣቱን አበላሽተሃል" የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ለግሪክ ጣዖታት አልተገዛህም" የሚል ነበር። እንደ ፕላቶ ዘገባ ግን ሶቅራጠስ የግሪክ ጣኦታት አምላኪ ነበር። በአንድ አንድ ተመራማርወች ዘንድ የአቴንስ መንግስት ያቀረባቸው ክሶች በውሸት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የሆኖ ሆኖ፣ ክሪቶ የተሰኘው የፈላስፋው ጓደኛ ለጠባቂወቹ ጉቦ በመስጠት እንዲያመልጥ ሁኔታውን አመቻችቶ ነበር። ሶቅራጠስ ግን እምቢ በማለት ቀረ እንጂ አላመለጠም። ሶቅራጠስ ለፍርድ በቀረበ ጊዜ ሰፊ የሆነ የመከላከያ ክርክር በማቅረብ የአቴናን መንግስት ክስ ውድቅ ለማደርግ ሞክሯል። ከዚህ በኋላ ዳኞቹ ምን አይነት ቅጣት እንዲበይኑበት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት፣ ለአቴና ህብረተሰብ ካበረከተው ጥሩ ተግባራቱ አንጻር በቀሪው ዘመኑ ሁሉ ነጻ እራት እንዲያመጡለት ተናገረ። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ወይ በቅጣት እንዲለቀቅ ወይንም ደግሞ እንዲገደል የእጅ ምርጫ አደረገ። ውጤቱም ሶቅራጠስ እንዲገደል የሚል ሆነ። ይሁንና ሶቅራጠስ ሞትን አይፈራም ነበር። ሞቱን ለማስቀረት ይቅርታም ሆነ ሌላ ማባበያ አላቀረበም። በርሱ ሥነ ምግባር መሰረት ላመነበት ነገር እስከመጨረሻ መቆሙ ሰናይ ድርጊት ነበር። ስለሆነም ሄምሎክ የተሰኘ መርዝ ጠጥቶ እንዲሞት ስለታዘዘ፣ መርዙን በመጠጣት አለፈ።
የሶቅራጥስ እናት ፌርናት ምን ሙያ ነበራት?
አዋላጅ
35
ሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡ ከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው። ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው። ሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው። የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮም፣ ዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ። የአገር ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከብዙ ኗሪ ቋንቋዎች 11ዱ በተለይም ዎሎፍኛ አገራዊ ዕውቅና አላቸው። ሌሎቹ ባላንታኛ፣ ማንዲንክኛ፣ ፑላርኛ (ፉላኒኛ)፣ ሰረርኛ፣ ሶኒንክኛ፣ ኖንኛ፣ ማንካኛኛ፣ ማንጃክኛ፣ ጆላኛ እና ሀሣኒያ አረብኛ ናቸው። ፖርቱጊዝኛም በትምህርት ቤት ይማራል፣ የካቦ ቨርዴ እና የጊኔ-ቢሳው ኅብረተሠቦችም ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል ይናገራሉ። ከሴኔጋል ሕዝብ 94% የእስልምና አማኞች፣ 5% ክርስትና (ባብዛኛው ካቶሊክ)፣ 1% የኗሪ አርመኔነት ተከታዮች ናቸው። የመንግሥት ሃይማኖት የለውም። በሴኔጋል ልማዳዊ ባሕል ግሪዮት የተባሉ ሽማግሎች ታሪኮቻቸውን በአፍ ቃል ይደግማሉ። ሴኔጋል ለሙዚቃዊ ስልቶቹ ይታወቃል፤ በተለይ የሚወድደው ዘመናዊው ስልት ምባላክስ ተብሏል። በሴኔጋል አበሳሰል በተለይ አሣ፣ ዶሮ፣ በግ፣ አተር፣ ዕንቁላል፣ በሬ ይጠቀማሉ፤ እስላም አገር እንደ ሆነው መጠን ግን አሳማ አይበላም። ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ስኳር ድንች፣ ምስር፣ ጥቁር-ዐይን አተር ደግሞ በሴኔጋል አበሳሰል በሰፊ ይገኛሉ። በእስፖርት በኩል፣ ከሁሉ የሚወደደው ባህላዊው የሴኔጋል ትግል ግጥሚያ ሲሆን፣ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ ደግሞ እጅግ ይወደዳሉ።
በሴኔጋል ምን ያህል የፖለቲካ ድርጅቶች አሉ?
ከ፹ በላይ
5
ዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
ዩጋንዳ የአሁኑን ቅርጽ የያዘችው መች ነው?
በ1914 እ.ኤ.አ.
403
ግሥላ ግሥላ በእስያ፣ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኝ አጥቢ አውሬ ነው። በእስያ የተገኘው ነብር የግስላ ቅርብ ዘመድ ሆኖ፣ በአነጋገር «ግስላ»ና «ነብር» የሚሉ ስሞች ሊለዋወጡ ይችላሉ። የአንድ ጎልማሳ ግሥላ ክብደት ከ35 እስከ 80 ኪ.ግ ሲደርስ በርዝመት ከ90 ሴ.ሜ እስከ 1,60 ሜ.ና በአፍሪካ የሚገኘው ዘር እስከ 1,90 ሜ ይደርሳል ። ከመሬት እስከ ሆዱ ከ50 እስከ 70 ሴ.ሜ ቁመት ሲኖረው ጭራው ደግሞ እስከ 100 ሴ.ሜ ርዝማኔ ያሳያል ። ሴቲቱ ከወንዱ አነስ ትላለች ። በዱር ሲኖር እስከ 10 አመት እንደሚኖር ሲታወቅ በሰው ተይዘው ሲኖሩ እስከ 20 አመት እድሜ ያስመዘገቡ ግሥሎች አሉ።
የግስላ የጭራው ርዝማኔ ስንት ሴ.ሜ ይሆናል?
100 ሴ.ሜ
283
ሴኔጋል ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒና ጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 14 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል። የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ። በአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋል፣ ኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።
ዳካር የሴኔጋል ምንድን ነው?
ርዕሰ ከተማ
300
ለአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ወሳኝ የሆነው ነጥብ መባጃ ሐመር ነው፡፡ መባጃ ሐመር መባጊያ ሐመር እየተባለም ይጠራል፡፡ መባጊያ ሐመር ሲሆን የበጋ መመላለሻ የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡ በሌላ በኩል መባጃ በራሱ ማቆያ፣ ማክረሚያ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ሐመር መርከብ፣ መጓጓዣ የሚለውን ትርጉም ያስገኛል፡፡ መባጃ ሐመር የመጥቅዕና የዕለታት ተውሳክ ድምር ሆኖ አጽዋማትና በዓላት የሚውሉበትን ቀን ያመለክታል፡፡ በሐመር የተመሰለውም አጽዋማትና በዓላት ወደ ላይና ወደታች የሚመላለሱበት ሥርዓት /መርከብ/ ስለሆነ ነው፡፡ በአጠቃላይ መባጃ ሐመር ማለት የአጽዋማትንና የበዓላትን መዋያ ወይም መግቢያ ቀን ለማወቅ የሚያገለግል ልዩ ቁጥር ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አራቱ በመባጃ ሐመር መሠረት በየዓመቱ እየተቀያየሩ ወይም ቀመር እየተሠራላቸው የሚወጡ ሲሆን፣ ሦስቱ ግን ያለ መባጃ ሐመር በየዓመቱ በተመሳሳይ ወቅት ይባጃሉ፡፡ በመባጃ ሐመር የሚባጁት አራት አጽዋማት ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌና ጾመ ሐዋርያት ሲሆኑ፣ ያለ ማባጃ ሐመር በየዓመቱ ቋሚ ጊዜ ይዘው የሚብቱት ሦስቱ አጽዋማት ደግሞ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ገሃድና ጾመ ማርያም /ፍልሰታ/ ናቸው፡፡ ከላይ በተመለከትነው መሠረት መባጃ ሐመር የአጽዋማትና የበዓላት ማስገኛ ልዩ ቁጥር ነው ካልን ቁጥሩ እንዴት እንደሚገኝ ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ እንደምራለን፡፡
መባጃ ሐመር ሳያስፈልጋቸው ቋሚ ጊዜ ጠብቀው የሚጀምሩ አጽዋማት የትኞቹ ናቸው?
ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ገሃድና ጾመ ማርያም /ፍልሰታ/
628
ነሐሴ ፳፯ ነሐሴ ፳፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፰ ዕለታት ይቀራሉ። ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ። ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አረፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ነጻነትን አስከትሎ በጃዋሃርላል ኔህሩ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ የሕንድ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት።
የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ ላይ የፈረደበት በስንት ዓመተ ምህረት ነው?
፲፱፻፺ ዓ/ም
657
ናይጄሪያ ናይጄሪያ በይፋ የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ አገር ናት። በሕዝብ ብዛትም ከአፍሪቃ አንደኛ ናት። ከቤኒን ፣ ቻድ ፣ ካሜሩን ፣ ኒጄር ፣ እና ከጊኒ ባሕረ ሰላጤ ጋር ድንበር ትካለላለች። በናይጄሪያ ውስጥ ትልቁ ብሔሮች ሀውዛ ፣ ኢግቦ እና ዮሩባ ናቸው። ግማሹ ሕዝብ እስላም ሲሆን ሌላው ግማሽ ደግሞ የክርስትና እምነት ይከተላል። ትንሽ የሕዝቡ ክፍልም ባህላዊ ሃይማኖቶችን ይከተላል። የሳይንስ ጥናት እንደሚያሳየው ናይጄሪያ ከ፱ሺህ ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ ነዋሪዎች እንደነበሩባት ያሳያል። በቤንዌ እና ክሮስ ወንዞች አካባቢ ያለው ሥፍራ የባንቱ ፍልሰቶች መነሻ እንደ ነበረ ይታመናል። የናይጄሪያ ስም ከኒጄር ወንዝ ነው የተወሰደው። ናይጄሪያ በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ስትሆን ከዓለም ደግሞ ሰባተኛ ናት። የናይጄሪያ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። የዓለም አቀፍ ገንዘብ ፈንድ እንደሚገምተው የናይጄሪያ ኢኮኖሚ በ2011 እ.ኤ.አ. በ8% ያድጋል።
ናይጄሪያ ስያሜዋ የተወሰደው ከምንድን ነው?
ከኒጄር ወንዝ
410
ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት ቀረቡ። በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ  ኢትዮጵያን በመወከል  ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ነው የተነገረው። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋና የቋንቋ ጥናት ክፍል ለረጅም ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።
ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም በሚንስቲር ማዕረግ የማን አማካሪ ሆነው ሰርተዋል?
የጠቅላይ ሚኒስትሩ
87
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
ንጉሥ ሎቤንጉላ ለብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ የሰጠው ፈቃድ የምን ነበር?
የማዕደን ማውጣት
826
ቺኑዋ አቼቤ በሙሉ ስሙ ሲጠራ አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ይሰኛል። ምናልባትም ናይጄሪያ ካሉዋት ምርጥ ፀሃፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የሚሰለፍ ሳይሆን አይቀርም። በ1930 እ.ኤ.አ. ኦጊዲ በተባለች የናይጄሪያ ግዛት ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ ተወለድ። በ1953 እ.ኤ.አ. ከለንደን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ለአቼቤ ድንቅ ሥራ የተባለለት "Things Fall Apart" 50 ወደሚሆኑ የአለም ቁዋንቁዋዎች የተተርጎመ ሲሆን ወደ 10,000,000 ቅጂዎች እንደተሸጡለት ይነገራል። አቼቤ ከአፍሪካ ፀሃፍት ሁሉ ሥራው በበዙ ቁዋንቁዋዎች በመተርጎም ክብረ ወሰኑን እንደያዘ ነው። ብዙዎችም ይኸው ድርሰቱ በአለም እስከዛሬ ከተደረሱ ምርጥ ልበ-ወለዶች መካከል እንደሆነ ይስማማሉ። አቼቤ ከ30 ከሚበልጡ ዩኒበርስቲዎች የክብር ዶክትሬት የተቀበለ ሲሆን ብዙ ሽልማቶችንም ከተለያዩ ድርጅቶች አግኝቷል። ይሁንና እስከ አሁን ድረስ የኖቤል ሽልማት ለማግኘት አልታደለም። ይኸውም በብዙው ጽሁፉ የመራቡን አለም ዘረኛነት የሚተች በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል። በ1990 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ከወገቡ በታች መንቀሳቀስ የተሳነው ሲሆን ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኘው የባርድ ኮሌጅ የቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ፕሮፌሰር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ወላጅ እናት እና አባት ማን ይባላሉ?
ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ
140
የሠውነት ማጎልመሻ ትምህርተ ፕሮፌሽናል በ young men’s Cristian association tinning school በአሁኑ መጠሪያው spring filed college ውስጥ አሰልጣኝ የነበሩት ካናዳዊ ጀምስ ኒስዝ እኤአ ከዲሴምበር 1891 ቀደም ብሎ የጂም ትምህር ቤት ክፍልን በዝናባማ ወቅትም ለማስቀጠል ፈለጉ፡፡ ተማሪዎቹ ክረምቱንም በተሻሎ የሰውነት ጥንካሬ እንዲያሳፉ በሚል በርካታ ሀሳቦች አስበው በኋላም ከበርካታ ሀሳቦች ውስጥ የባስኬት ቦልን በመምረጥ 10 ጫማ ወይም 3 ሜትር ከፍታ ያለው የባስኬት ቦል መረብ መስቀያ አዘጋጁ፡፡ ለባስኬት ቦል መጫወቻ ተብሎ የተዘጋጀው የመጀመሪያ ኳስ ብራውን ወይም ቡናማ ቀለም ሲኖረው እኤአ በ1950ዎቹ መጨረሻ ላይ ግን ቶኒ ሂንክል የተባለ ሰው ለተጫዋቾቹ ግልፅ ሆና መታየት አለባት በሚል የኳሷ ቀለም ወደ ብርቱካናማ ቀለም እንዲቀየር አደረገ የተቀየረውም ቀለም እስካሁን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በ1892 ከገና እረፍት መልስ ለመጀመሪያ ጊዜ የባስኬት ቦልን የተጫወተው ፍራንክ ማሀን ሲሆን በወቅቱ ስያሜውን ምን እንደሚሉት ኒስሚዝን ጠየቃቸው እሳቸውም ውድድሩን የማስጀመር ሀሳብ እንጂ ስለስያሜው አላሰብኩበትም ሲሉ መለሱለት፡፡ ፍራንክ ለምን ኒስሚዝ ኳስ አይሉትም ሲል ሀሳብ አቀረበ፡፡ ኒሚዝም ከሳቁ በኋላ እንዲህ አይነት ስያሜዎች ጨዋታውን ይገድሉታል ብለው መለሱለት፡፡ ፍራንክም መልሶ ለምን ባስኬት ቦል አንለውም አለ፡፡ ኒስሚዝም ባስኬት አለን ኳስም አለን ስለዚህ ባስኬት ቦል መባሉ ለኔ ተስማምቶኛል፤ ጥሩ ይመስለኛል ብለው አፀደቁለት፡፡ የመጀመሪያው የባስኬት ቦል ውድድርም ኒዮርክ ውስጥ በሚገኝ YMCA ጂምዚየም ውስጥ እኤአ በጃንዋሪ 1892 በ9 ተጫዋቾ ተጀመረ፡፡ በወቅቱ የእግር ኳስ 10 ተጫዋቾ በ1 ቡድን የሚጫወቱበት ወቅት ስለነበር ሀይለኛ የበረዶ ግግር የእግር ኳስ ጨዋታቸውን እንዳያከናውኑ ስላስቸገራቸው ወደቤት ውስጥ ገብተው 10ሩ ተጫዋቾ በሁለት በመከፈል 5 5 ሆነው መጫወት ባስኬት ቦልን ወይም የቅርጫት ኳስን ጀመሩ፡፡ በ1897 -1898 በአንድ ቡድን የተጫዋቾ ብዛት 5 ሆኖ ፀደቀ፡፡ እኤአ በ1980ዎቹ እና በ1990ዎ ውስጥ ፕሮፌሽናል ውድድሮችን በማካሄድ የስፖርቱን ተወዳጅነትና እውቅና ከፍ እንዲል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ እና የምንግዜም ምርጥ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች የሚባሉት 3 ተጫዋቾ ላሪ በርድ፤ ኢረን ማጂክ ጆንሰን እና ማይክል ጆርዳን ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ ፌብርዋሪ 17፣1963 በአሜሪካዋ የኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው ማይክል ጆርዳን በአለማቀፍ ደረጃ ብዙ ሽልማቶችን ተቀዳጅቷል፡፡ ብዙ ሰዎች ከምርጥ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሳይሆን መቼም ተወዳዳሪ የማይገኝለት ተጫዋች ነው በማለት ያሞግሱታል፡፡ ከሴቶች እውቅ የባስኬት ቦል ተጫዋቾች ውስጥ አንዷ የሆነችው የአሜሪካ ፕሮፌሽናል ባስኬት ቦል ተጫዋች ማያ አፕሪል ሞኖር በርካታ የብሄራዊ ቻምፒየን ሺፕን በማሸነፍ የጆን ዎደን አወርድ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ እኤአ በ1932 ስምንት ሀገራት የብሄራዊ ባስኬት ቦል አሶሼሽን FYBA አቋቋሙ፡፡ ስምንቱ መስራች ሀገራት አርጀንቲና ፤ Czechoslovakia ፤ ግሪክ ፤ ጣሊያን ፤ lasiva፤ ፓርቹጋል ሮማንያ እና ሲውዘርላንድ ናቸው፡፡ ሴቶች በባስኬት ቦል ውድድር ላይ መሳተፍ የጀመሩት በ1892 በስሚዝ ኮሌጅ ውስጥ ነበር፡፡ በወቅቱ ሰንዳ በርሶን የተባለች የሰውነት ማጎልመሻ መምህር የኒስሚዝን የባስኬት ቦል ህጎች ለሴቶች እንዲሆኑ አድርጋ አስካከለቻቸው፡፡ በአጭሩ በአዲሱ ስፖርት በመማረኳ ስለውድድሩ ከኒሰሚዝ ብዙ ለመማር ትፈልግ ነበር፡፡ በመጋቢት 21 1893 የመጀመሪያው የሴቶች ባስኬት ውድድርን አዘጋጀች፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የባስኬት ቦልን የተጫወቱት ማን ናቸው?
ፍራንክ ማሀን
576
ኤስፔራንቶ ኤስፔራንቶ (Esperanto) ከሁሉም አለማቀፋዊ ሠው ሰራሽ ቋንቋዎች እጅጉን የተስፋፋ ቋንቋ ነው። በ1859 እ.ኤ.አ. በዛሬይቷ ፖሎኝ የተወለደውና በሞያው የአይን ሀኪም የሆነው ሉድዊክ ሌይዛር ዛመንሆፍ በ1887 እ.ኤ.አ. ቋንቋውን ለህዝብ አሳወቀ። አላማው ኤስፔራንቶን በቀላሉ ሊማሩት የሚቻል፣ የጋራ የሆነና ለአለማቀፋዊ መግባባት የሚረዳ ግን ያሉትን ቋንቋዎች የማይተካ ቋንቋ ማድረግ ነበር። ኤስፔራንቶ ከ1,600,000 በላይ ተናጋሪዎች ቢኖሩትም የቋንቋው ደጋፊ ያልሆኑ እንግሊዝኛን ከመስፋፋቱ አንፃር ለአለማቀፋዊ ቋንቋነት በተሻለ ይመርጡታል።
ኤስፔራንቶ የተሰኘውን ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ ያስተዋወቀው ሉድዊክ ሌይዛር ዛመንሆፍ ሙያው ምን ነበር?
የአይን ሀኪም
106
ድረ ገጽ መረብ የድረ ገጽ መረብ (ወይም ኢንተርኔት) በጣም ብዙ የኮምፒዩተር አውታሮችን የያዘ የመገናኛ መረብ ነው። በመረቡ ውስጥ ብዙ ድረ ገጽ ይገኛሉ። ከዚያ በላይ በርካታ የመነጋገርና መገናኘት መንገዶች አሉ። ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ክፍለ-ኢንተርኔት «USENET» የሚባለው አገልግሎት ነው። ይህ በ1973 ዓ.ም. (1980 እ.ኤ.አ.) አካባቢ ሲጀመር በተለይ ለዩኒቨርሲቴዎችና ኮሌጆች ብቻ የታወቀ መገናኛ ሆኖ ቆየ። ይህ ጽሑፍ በተገናኙት ኮምፒውተሮች ላይ መልጠፍ የሚፈቅድ ሥርዓት ብቻ እንጂ ስዕል ወይም ሌላ ነገር አልነበረም። መጀመርያው e-mail አድራሳዎች የተሰጡት ከዚያ ዘመን ነው። ዛሬም ብዙዎች ተጠቃሚዎቹ ግን ስንኳ ስለ USENET መኖሩን አያውቁም። መጀመርያው ድረ ገጽ የተፈጠረው በ1983 ዓ.ም. (1990 እ.ኤ.አ.) ሆነ።
ብዙ የኮምፒዩሮችን የያዘ የመገናኛ መረብ ምን ይባላል?
የድረ ገጽ መረብ
10
አክሱም አክሱም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክ/ሃገር ከአድዋ ተራራዎች አጠገብ የምትገኝ ከተማ ነች። በክርስቶስ ልደት በፊት ተመስርቶ የነበረው የአክሱም ስርወ መንግስት ማእከል ነበረች የአክሱም ስርወ መንግስት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እየተዳከመ ሲመጣ የማእከላዊው መንግስት ወደ ደቡብ ተንቀሳቀሰ። ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የከተማው ነዋሪ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ነው። የተቀሩት ነዋሪዎች የሱኒ እስልምና ተከታዮች ናቸው። ባላቸው ታሪካዊ ተፈላጊነት ከተማ ውስጥ የሚገኙት የአክሱም ስርወ መንግስት ቅሪቶች UNESCO በ1980 የአለም ቅርስ ቦታ ተብለው ተሰይመዋል ። አክሱም በኢትዮጵያ የ ትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በማዕከላዊ ዞንና በላዕላይ ማይጨው ወረዳ ይገኛል።
አክሱም በኢትዮጵያ በየትኛው ክልል ትገኛለች?
በትግራይ
21
በሕንድ ንጉሥ አሾካ መንግሥት የአሾካ አዋጆች ሕግጋት በ264 አክልበ. መሠረቱ። ከምዕራቡ ሮማ መንግሥት ውድቀት ደግሞ ወደ ተረፈው ሕዋእ ውስጥ ከፈለሱት ጀርመናውያን ወገኖች አብዛኛው የራሳቸውን ሕጎች ዝርዝር በጽሑፍ አወጡ። በተለይ የሚታወቁም የቪዚጎቶች አለቃ ዩሪክ ሕግ (463 ዓ.ም.)፣ የቡርጎንዳውያን ሕግጋት (እኚህ ለጀርመናውያንና ለሮማውያን የተለያየ ፍትሕ ነበራቸው)፣ የአላማናውያን ሕግጋትና፣ የፍራንኮች ሕግጋት ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የተጻፉት ከ492 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። በ498 ዓ.ም. የቪዚጎቶች አለቃ 2ኛ አላሪክ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስና አንዳንድ የተለያዩ የቀድሞ ሮማ ሐገጋት አከማችተው አዋጁአቸው። ከዚህም በኋላ የታዩ ሕጎች የሎምባርዶች ሕግጋት (635 ዓ.ም.)፣ የቪዚጎቶች አዳዲስ ሕግጋት (646 ዓ.ም.)፣ የአላማናውያን አዳዲስ ሕግጋት (722 ዓ.ም.) እና የፍሪዝያውያን ሕግጋት (777 ዓ.ም.) አሉ። በአውሮፓ አኅጉር ላይ የተጻፉት እነኚህ ፍትሖች ሁሉ በሮማይስጥ ቢጻፉም፣ በእንግሊዝ አገር ግን የተጠቀሙት ሕጎች ከኬንት ንጉሥ ኤጠልቤርት ሕጎች (594 ዓ.ም.) ጀምሮ በጥንታዊ እንግሊዝኛ የተቀነባበሩ ነበሩ። በ885 ዓ.ም. ታላቁ አልፍሬድ ይህንንና ሁለት የድሮ ፍትሖች ከሕገ ሙሴና ከሕገ ወንጌል ጋራ አጋጥመው የእንግሊዝ ሕገ መንግሥት ዶም ቦክ ሠርተዋል።
በ885ዓ.ም. የድሮ ሕጎችን፣ የኦሪትና የወንጌል ሕግጋትን በመጠቀም አዲስ የእንግሊዝ ሕገ መንግሥት ያዘጋጀው ንጉሥ ማን ይባላል?
አልፍሬድ
665
የአመራር ክፍሎች ናይጄሪያ በሠላሳ ስድስት ክፍላገራት እና አንድ የፌዴራል ግዛት ተከፍላለች። እነዚህ ክፍላገራት ወደ ፯፻፸፬ የአካባቢ ግዛቶች ተከፍለዋል። ስድስት የናይጄሪያ ከተሞች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አሉባቸው። እነዚህም ሌጎስ፣ ካኖ፣ ኢባዳን፣ ካዱና፣ ፖርት ሀርኮርት እና ቤኒን ከተማ ናቸው። ሌጎስ ከ፰ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲኖሩባት ከሣህራ በታች በአፍሪካ ትልቁ ከተማ ናት። ብሔረሰቦች በናይጄሪያ ውስጥ ከ፪፻፶ በላይ ብሔሮች ይገኛሉ። ትልቆቹ ብሔሮች ፉላኒ ወይም ሀውዛ፣ ዮሩባ እና ኢግቦ ናቸው። ከእነሱ ቀጥሎ ደግሞ ኤዶ፣ ኢጃው፣ ካኑሪ፣ ኢቢብዮ፣ ኑፔ እና ቲቭ ይገኛሉ። በናይጄሪያ ውስጥ የተቆጠሩት ቋንቋዎች ፭፻፳፩ ይሆናሉ። ከእነዚህም ውስጥ ፭፻፲ቹ መደበኛ ተናጋሪዎች አሏቸው። ሁለት ቋንቋዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ብቻ ነው የሚነገሩት። ዘጠኙ ደግሞ ተናጋሪ የሌላቸው የጠፉ ቋንቋዎች ናቸው። ከእንግሊዝኛ በኋላ ዋናዎቹ ልሳናት ዮሩብኛ፣ ሐውዝኛና ኢግቦኛ ናቸው።
በናይጄሪያ ምን ያህል የታወቁ ቋንቋዎች አሉ?
፭፻፳፩
397
ጣና ሐይቅ ጣና ሐይቅ ቅዱሱ ሐይቅም ይባላል። ከኢትዮጵያ አንደኛ እና ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል። በቁጥር ከ35 በላይ ደሴቶች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥም 22ቱ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት ናቸው። ባንዳንዶቹ ላይም (ለምሳሌ በዳጋ ደሴት) የድሮ የኢትዮጵያ መሪዎች መቃብሮች ሲገኙ ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ለመጀመሪያ ያስተዋወቀው አቡነ ሰላማ መቃብርም በዚሁ ሃይቅ ይገኛሉ። የጣና ሃይቅን የሚመግቡ 3ቱ ዋና ወንዞች ርብ፣ ጉማራ ወንዝ ና ትንሹ አባይ በመባል ይታወቃሉ። አሁን ባለው ይዞታ የጣና ሃይቅ 1,454 ቶን አሳ በአመት ይመረታል። ነገር ግን ይሄ የምርት ሃይቁ ያለምንም ችግር ሊያስተናግድው ከሚችለው 15 በመቶው ያህል ብቻ ነው።
የጣና ሐይቅ ምን ያህል የወለል ስፋት አለው?
3,500 ካሬ ኪ.ሜ.
92
የቻይናው ግዙፉ የቴሌኮም  ኩባንያ ሁዋዌ በፈረንጆቹ 2019 240 ሚሊየን ስልኮችን ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ኩባንያው የሽያጭ ገቢው 850 ቢሊየን ዩዋን ወይም 122 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል ፡፡ ሽያጩ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ 18 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን፥ የተጠበቀውን ያክል ገቢ አለመገኘቱም ተመላክቷል ፡፡ የኩባንያው  መሳሪያዎቹን በመጠቀም ስለላ ሊያካሂድ ይችላል በሚል በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ባለሥልጣናት  ላይ ስጋትን በመጫሩ ከአሜሪካ የግንኙነት መረቦች በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዛዝ መታገዱ ይታወሳል ፡፡ ይህም ለሁዋዌ አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሮ  ቆይቷል፡፡ ኩባንያው በ2020ም የተፈጠረውን ችግር በመቋቋም ገበያው ላይ መቆየት ተቀዳሚ አላማው መሆኑን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል። ምንጭ፡-www.cnet.com/
የቻይናው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ በፈረንጆቹ 2019 ምን ያህል ስልኮችን ለገበያ አቀረበ?
240 ሚሊየን
38
የእብድ ውሻ በሽታ የእብድ ውሻ በሽታ የየቫይረስ በሽታ ሆኖ ከፍተኛ የየአንጎል መጉረብረብን በሰዎች እና በሌሎች ደመ-ሞቃት እንስሳት ላይ የሚያስከትል ነው። ቅድሚያ ምልክቶቹ ትኩሳት እና በተነከሱበት ቦታ ማሳከክ/ማቃጠልን ያካትታል። እነዚህ ምልክቶች ከሚከተሉት አንድ ወይም የበለጡ ምልክቶች አስከትለው ይመጣሉ- ሃይል የታከለባቸው የሰውነት እንቅስቃሴዎች፣ ከቁጥጥር ወጭ የሆ መሸበር፣ የውሀ ፍራቻ, የሰውነት ክፍለን ለማንቀሳቀስ አለመቻል፣ ግራ መጋባት፣ እና ህሊናን መሳት። ምልክቶቹ ከታዩ በኋላ፣ የእብድ ውሻ በሽታ በአብላጫው ሁልጊዜ ሞትን ያስከትላል። በበሽታው በመያዘዎ እና ምልክቶቹ መታየት የሚጀምሩበት የጊዜ ገደብ በአብዛኛውን ጊዜ ከአንድ እሰከ ሶስት ወራት ባሉት ጊዜ ውስጥ ነው። ሆኖም ግን፣ ይህ የጊዜ ገደብ ከሳምንት ባነሰ እና ከአመት በበለጠ ጊዜ ሊለያይ ይችላል። የጊዜ ገደቡ የሚወስነው የበሽታ አምጭው ረቂቅ ህዋስ ወደ የማዕከላዊ የነርብ ስርዓትለመድረስ በሚፈጅበት እርቀት ነው። የእብድ ውሻ በሽታ በአለም ዙሪያ በአመት ከ26,000 እሰከ 55,000 ሞቶች ምክንያት ነው። ከ95% በላይ እነዚህ ሞቶች የተከሰቱት በኢሲያ እና አፍሪቃነው። የእብድ ውሻ በሽታ ከ150 ሀገራት በላይ እና ከአንታርቲካ በቀር በሁሉም አሀጉራት ይገኛል። ከ3 ቢሊዮን ሰዎች በላይ የእብድ ወሻ በሽታ በሚከሰትበት የአለማችን ከፍሎች ውስጥ ይኖራሉ። እጅግ በአብዛኛው አውሮፓ እና አውስትራሊያ፣ የእብድ ወሻ በሽታ የሚገኘው በሌሊት ወፎች ላይ ነው።
የእብድ ውሻ በሽታው ምልክት በምን ያህል ጊዜ ይታያል?
በአብዛኛውን ጊዜ ከአንድ እሰከ ሶስት ወራት ባሉት ጊዜ ውስጥ
396
የፌስቡክ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ ሀገራት ሀሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን የሶስተኛ ወገን የትክክለኛነት ማረጋገጫ ፕሮግራም (Third-Party Fact-Checking Program) መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው ፕሮግራሙን ካስጀመረባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ዛምቢያ፣ ሶማሊያ፣ ቡሪኪና ፋሶ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኮትዲቯር፣ ጊኔ ኮናክሪ እና ጋና ይገኙበታል፡፡ ሶስተኛ ወገን የመረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጫ ፕሮግራም ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመግታት የሚያስችል እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በዚህም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በማህበራዊ ሚዲያው ጥራት ያለው መረጃ የሚያገኙበትን አሰራር የሚያሻሽል እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
የፌስቡክ ኩባንያ ሀሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን ምን አይነት ፕሮግራም አስተዋወቀ?
የሶስተኛ ወገን የትክክለኛነት ማረጋገጫ ፕሮግራም
63
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012(ኤፍቢሲ) ቻይና በዋና ከተማዋ ቤጂንግ እና በሀቤይ ግዛት ዘሃንግጃኩ መካከል የተዘረጋውን ፈጣን ባቡር ለገልግሎት ክፍት ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል። ቻይና የፈጣን ባቡሩን ለአገልግሎት ክፍት የምታደርገው በአውሮፓውያኑ 2022 የምታስተናግደውን የክረምት ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ተነግሯል። ፈጣኑ ባቡር በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን፥ በዓለማችን ላይ የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ ባቡር እንደሚሆንም ተነግሮለታል። የ 174 ኪሎ ሜትር ያለው የባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቱ ለ2022 የክረምት ኦሎምፒክ እና የፓራሎምፒክ  ታስቦ የተሰራ መሆኑም ታውቋል። የባቡር መስመሩ የክረምት ኦሎምፒኩን በሚያስተናግዱት በሁለቱ ከተሞች መካከል የነበረውን የ3 ሰዓት መንገድ ወደ 47 ደቂቃ የሚቀንስ መሆኑ የቻይና ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል። ምንጭ፦ newsus.cgtn.com
የ2022 የክረምት ኦሎምፒክ አዘገጋጅ ማናት?
ቻይና
29
ቱርክመንኛ ቱርክመንኛ (Türkmen) የቱርክምኒስታን ብሔራዊ ቋንቋ ነው። በቱርክመኒስታን 3,430,000 ተናጋሪዎች ሲኖሩ ከቱርክመኒስታን ውጭ ደግሞ 3 ሚሊዮን የሚያሕሉ ተናጋሪዎች በተለይም በኢራን (2 ሚሊዮን) በአፍጋኒስታን (500,000) እና በቱርክ (1000) አሉ። ቱርክመንኛ በቱርኪክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይከተታል። ይህም አንዳንዴ በትልቁ አልታይ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይደመራል። ቀድሞ የተጻፈበት ወይም በቂርሎስ ወይም በ አረብ ፊደሎች ነበር፤ አሁን ግን የቱርክመኒስታን መሪ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ አዋጀ። በ1994 አ.ም. ደግሞ የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ እንደ አቶ ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።
በቱርክምኒስታን ምን ያህል የቱርክመንኛ ቋንቋ ተናጋሪ አለ?
3,430,000
57
በ628 ዓክልበ.፣ ድራኮ የሚባል ጸሃፊ የአቴና ከተማ ሕግጋት ጻፈ፤ ይህም ሕግ እጅግ ጨካኝ ሆኖ ይሙት በቃ ለማንኛውም ጥፋት ወሰነ። በ600 ዓክልበ.፣ የአቴና አለቃ ሶሎን አዲስ ሕገ መንግሥት ፈጠረ። የሰራተኞች ሸክም አቀለለ፣ ነገር ግን ባላባትነት በልደት ሳይሆን በንብረት ብዛት እንዲቈጠር አስደረገ። ክሊስቴኔስ እንደገና በ516 ዓክልበ. በዴሞክራሲያዊ መሠረት የተሻሸለ ለአቴና ሕገ መንግሥት አወጣ። የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ በ350 ዓክልበ. ግድም የሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ዐወቀ። በጽሑፎቹ የአቴና፣ የስፓርታና የካርታግና ሕገ መንግሥቶች ያነጻጽራል። በመደምደሚያው የተሻለው ሕገ መንግሥት ከንጉሣዊ፣ ከመኳንንታዊና ከሕዝባዊ ወገኖች የተደባለቀ መሆኑን ገመተ። በሀሣቡ በመንግሥት የሚከፋፈሉ ዜጎች ከማይከፋፈሉ ከባርዮችና ዜጎች ካልሆኑ ሰዎች ልዩነት አደረገ። ሮማውያን መጀመርያ «12ቱ ሰንተረዦች» የተባለውን ሕገ መንግሥት ያወጡ በ457 ዓክልበ. ነበር። ከዚያ በኋላ አንዳንዴ የተለያዩ ሕጎችና ትእዛዛት ይጨምሩበት ነበር እንጂ እስከ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስ ድረስ (430 ዓ.ም.) ሌላ ክምቹ ሕገ መንግሥት አልኖረም ነበር። በኋላም በምሥራቁ መንግሥት (ቢዛንታይን) በኩል መጽሐፈ ዩስጢኒያኖስ (526 ዓ.ም.) ለአውሮፓ ከፍ ያለ ተጽእኖ ነበረው። ይህም በምስራቁ ነገሥታት 3ኛ ሌዎን ኢሳውራዊ «ኤክሎጋ» (732 ዓ.ም.) እና በ1ኛ ባሲሌዎስ «ባሲሊካ» (870 ዓ.ም.) በተባሉት ሕገ ፍትሐን ተከተለ።
ድራኮ የአቴና ሕግጋትን መች ጻፈ?
በ628 ዓክልበ
0
ፋሽስት ቅዲስቲቱዋን ኢትዮጵያን ለማዋረድ ለመዝረፍና ለመግዛት ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ዝግጅቱን አጠናቆ በ1928 ዓም 300, 000 ሰራዊት 160 ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች 450 ታንኮች 2000 የመጉዋጉዋዣ መኪናዎችን በማሰማራት ድንበር አልፎ ጦርነት በመክፈት ከገጠር እስከ ከተማ ህዝቡን ያለ እርህራሄ ጨፈጨፈ። በዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ላይ የመጀመሪያውን ህይወት ያለዉን ነገር ሁሉ የሚያጠፋውን “ማስተርድ ጋዝ” የሚባል ኬሚካል መሳሪያ በመጠቀም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ፈጸመ። በዚያን ክፉ ቀን የነጻነትና የሀገር ትርጉም የገባቸው የቁርጥ ቀን ልጆች በየአካባቢያቸው ፋኖዎችን በመምራት የእብሪተኛዉን የፋሽ ስት ጦር መግቢያ መዉጫ በማሳጣት ኢትዮጵያ ዉስጥ በሰላም መኖር እንደማይችል ተስፋ አስቆርጠዉታል። ከነዚህ ነበልባል የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች መካከል ጠላትን በተከታታይ ዝርክርኩን አዉጥተው ከደቡብ ያሳደዱትና በመጨረሻው ዉጊያ ላይ ኢትዮጵያዊ በሚመስሉ የተሀሬ ስርጎ ገብ ባንዶች ቆሰለው የተያዙትና በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ዉዱ የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ልጅ ራስ ደስታ ዳምጠው ነበሩ።
ጣልያን ኢትዮጵያን ለመውረር ድጋሚ የመጣበት ዓመት መቼ ነው?
በ1928
64
125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለማክበር የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ካሳው አሶሳ ከተማ ገቡ። በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራርም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በዓሉም ከዛሬ ጀምሮ በፓናል ውይይት እና ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘት እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ማነው?
አቶ አሻድሌ ሀሰን
94
ደቡብ አፍሪካ በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ። ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውን፣ ብሉምፎንቴንና ፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው። ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው። የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ። የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካ ፓርላሜንቱ የሚገኘው የት ከተማ ነው?
በኬፕ ታውን
409
ጋሞጐፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ከ1955 እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ የጋሞ ጐፋ ጠቅላይ ግዛት፣ የሰሜን ኦሞ አስተዳደር አካባቢና ከዚያም የሰሜን ኦሞ ርዕሰ ከተማ በመሆን ለቀድሞዎቹ የጋሞ፣ የጐፋ፣ የጋርዱላና ሐመር ባኮ አውራጃዎች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ማዕከል ሆና ያገለገለች ስትሆን ከ1993 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ዓመታት ደግሞ አስራ አምስት ወረዳዎችንና ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን አቅፎ ለያዘው ጋሞ ጐፋ ዞን ዋና ከተማ በመሆን እያገለገለች የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የዘይሴ ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሄረሰቦችን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ ሌሎች የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ተወላጆች ተከባብረውና ተቻችለው በፍቅርና በሰላም የሚኖሩባት አርባ ምንጭ ከተማ በቀለማት አደራደሩ ትኩረትና ተወዳጅነት የማይለየው የጋሞ ብሔረሰብ የክብርና የማዕረግ ልብስ እንዲሁም መታወቂያው የሆነውንና ዱንጉዛ በመባል የሚታወቀው ባህላዊ ልብስ ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ የሸማ ጥበብ አልባሳት ሥራዎች መፍለቅያ አካባቢዎች እምብርት ከመሆኗም በተጨማሪ በባህላዊ ቤት አሰራራቸው በለቅሶና ሠርግ ስርዓታቸው በባህላዊ የማምረቻና የመገልገያ ቁሳቁሶቻቸው የብዙዎችን አድናቆትና አግራሞትን ላስጫሩት የጋሞ፣ የጐፋ፣ የዘይሴ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሔረስብ ህዝቦች መዲና ነች፡፡    ከባህር ወለል በላይ ከ1,300 እስከ 1,500 ሜትር ከፍታ ላይ ስትገኝ  የአርባ ምንጭ ከተማ አየር ንብረት በተለምዶ ቆላማ የሚሉት አይነት ሲሆን፤ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠኗ 240c ነው፡፡ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኗ 900 ሚሊ ሜትር ሆኖ ግንቦት፣ ሰኔ፣ መስከረምና ጥቅምት ወራት ከፍተኛ የዝናብ መጠን በዓመቱ ውስጥ የሚመዘግብባቸው ወራት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡  በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ስፍራ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን መንትያዎቹ የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ፤በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን   የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያ  እና የተፈጥሮ ደኖችን  ሌሎች ከህሊና ጓዳ የማይፋቅ ትዝታን ጥለው የሚያልፉ ሃብቶች ባለቤት ናት በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ከተማ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን ፤ የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያን በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት እና የተፈጥሮ ደኖችን ይገኛሉ፡፡ የዞኑን አስደናቂ የቱሪስት መስህቦች እንግዶቻችንን በማስጎብኘት ከታዋቂ የዓሳ ምርታችን ፣ ከማንጎ ፤ ከሙዝ እና በአፕል ማሳችን እየተንሸራሸርን የማይረሱ ትዝታዎችን ጥለው ያልፋሉ፡፡
አርባ ምንጭ የየትኛው ዞን ዋና ከተማ ናት?
ጋሞ ጐፋ
44
ውትድርና የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት ሀገሯን የመከላከል፣ የሀገሯን ፍላጎት የማስጠበቅ እና ፀጥታ አስጠባቂ ጥረቶችን የመደገፍ ግዴታ አለበት። ሠራዊቱ የምድር፣ የባህርና የአየር ኃይል አለው። ሠራዊቱ ከነፃነት ጀምሮ በሀገሯ ታሪክ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በተለያዩ ጊዜያት የውትድርና ጁንታዎች ሥልጣን በመያዝ አገሯን አስተዳድረዋል። የናይጄራያ ሠራዊት በፀጥታ ጠባቂነት ደረጃ ከ1995 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በላይቤሪያ (1997 እ.ኤ.አ.)፣ አይቮሪ ኮስት (ከ1997 እስከ 1999 እ.ኤ.አ. ) እና ሲየራ ሊዮን (ከ1997 እ.ኤ.አ. 1999 እ.ኤ.አ.) ተሰማርቷል። ምጣኔ ሀብት በግብርና ናይጄሪያ በዋናነት ለአለም የምታቀርበው ምርቶች በተለይ ካካውና ጎማ ናቸው። እንዲሁም ፔትሮሊየም ከሚያቀርቡት አገራት 12ኛ ነች። በተጨማሪ፣ የመኪና ሥራ ድርጅት (ኢኖሶን ተሽከርካሪ መፈብረክ) ይኖራል። መልከዓ ምድር ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ በጊኒ ባሕረ ሰላጤ ላይ ትገኛለች። የቆዳ ስፋቷ 923,768 ካሬ ኪ.ሚ. ሲሆን ከዓለም ፴፪ኛዋ ትልቅ ሀገር ናት። ድንበሯ 4,047 ኪ.ሜ. ርዝመት ሲኖረው ከቤኒን 773 ኪ.ሜ.፣ ኒጄር 1,497 ኪ.ሜ.፣ ቻድ 87 ኪ.ሜ.፣ ካሜሩን 1,690 ኪ.ሜ. ትዋሰናለች። በተጨማሪም 853 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ጠረፍ አላት። በናይጄሪያ ውስጥ ከፍተኛው ቦታ ቻፓል ዋዲ ተራራ ሲሆን ከፍታው 2,419 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ነው። የአገሯ ዋና ወንዞች ኒጄር እና ቤንዌ ሲሆን ወደ ኒጄር ደለል ይፈሳሉ።
ኒጄርና ቤንዌ የት ሀገር የሚገኙ ወንዞች ናቸው?
በናይጄሪያ
723
ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ-10 የሚያቀርብውን የደህንነት ጥገና በ2025 ማቅረብ እንደሚያቆም እና በዚህ ወር መጨረሻ የዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዋና ማሻሻያ ይፋ ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ ኩባንያው ከዚህ ቀደም ዊንዶውስ 10 ማሻሻያ ይፋ ሲያደርግ የመጨረሻው ኦፕሬቲንግ ሲስተም  ነው ቢልም አሁን ላይ ግን ሃሳቡን እንደቀየረ ይፋ አድርጓል። ከዚህ ጋር ተያይዞም ኩባንያው ከፈረንጆቹ ጥቅምት 14 ቀን 2025 ጀምሮ ለሆምም  ሆነ ለፕሮፌሽናል ቨርዥኖች አዳዲስ ዝመናዎች ወይም የደህንነት ጥገናዎች አይኖሩም ብሏል፡፡ ምንም እንኳን የዊንዶው-7 ተጠቃሚዎች ከፈረንጆቹ 2020 ወዲህ የደህንነት ዝመና ቢቋረጥም የንግድ ድርጅቶች ለዊንዶውስ-7 ፕሮፌሽናል እና ዊንዶውስ 7 ኢንተርፕራይዝ ዝመናዎችን ለማግኘት ለማይክሮሶፍት ክፍያ እየፈጸሙ ነው። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት አዲሱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከ11 ቁጥር ይልቅ ስም እንደሚሰጠው እየገለጹ መሆኑን ቢቢሲ በድረ-ገጹ ማስነበቡን ኢመደኤ ዘግቧል።
ማይክሮሶፍት ለየትኛው ዊንዶ የሚያቀርብውን የደህንነት ጥገና በ2025 እንደሚያቆም ያሳወቀው?
ለዊንዶውስ-10
9
አንድ ወጣት ተማሪ ከወዳደቁ ቁሳቁሶች በውሃ ላይ የሚነዳ የብስክሌት ጀልባ መስራቱ ተገለጸ፡፡ ጌታባለው መኩሪያው የተባለው ወጣት በባህርዳር ዩኒቨርስቲ 3ኛ ዓመት የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወጣቱ የወዳደቁ ፒፒሲ ትቦዎች፣ የላሜራ ብረቶችና ፌሮዎች እንዲሁም አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የብስክሌት አካላትን ተጠቅሞ ነው የብስክሌት ጀልባ (Pedal-Boat) መስራት የቻለው፡፡ ጌታባለው መኩሪያው ከወዳደቁ ቁሳቁሶች የሰራውን የብስክሌት ጀልባ በውሃ ላይ በመንዳት ሙከራ ማድረጉም ተገልጿል፡፡
በዉሃ ላይ የሚሄድ ብስክሌት ፈጠራ ባለቤት ጌታባለው መኩሪያ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምን ተማሪ ነው?
የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ
102
ጋሊልዮ ጋሊልዮ ጋሊሊ ታህሳስ 15, 1564 – ጥር 8, 1642 የነበረ የጣሊያን ሥነ-ፈለክ አጥኝና ተመራማሪ ነበር። ጋሊልዩ በዘመኑ የራሱን አጉሊ መነጽር በመስራት ጨረቃ ተራራ እንዳላት፣ ጁፒተር የተባለው ፈለክ ልክ እንደ መሬት የራሱ የሆኑ 4 ጨረቃወች እንዳሉት፣ ረጨቶች ከከዋክብት ስብስብ እንደተሰሩ፣ ፀሐይ ጥቁር ነጠብጣቦች እንዳሏት፣ ቬነስ ልክ እንደ ጨረቃ የተለያየ ቅርጽ በጥልቁ እንደምትይዝ የመሰከረና በኋላም መጽሃፍ ጽፎ ያሳተመ ሳይንቲስት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ጋሊልዮ የተፈጥሮ ህጎችን/ጉልበቶችን አጥንቷል። በትውፊት እንደሚነገር ጣልያን ውስጥ ባለው የተንጋደደው የፒሳ ግንብ ላይ በመውጣት፣ የተለያዩ ክብደት ያላቸውን የብረት ኳሶች ወደመሬት በመልቀቅ፣ ሁሉም በዕኩል ሰዓት መሬትን እንደሚመቱ አረጋግጧል። ከዚህ በመነሳት እስከሱ ዘመን ይሰራበት የነበረውን የአሪስቶትል አስተሳሰብ (ከባድ ነገሮች ከቀላል ነገሮች በበለጠ ፍጥነት ወደመሬት ይወድቃሉ) ፉርሽ አድርጓል። ሆኖም ግን በጊዜው የአሪስቶትል አስተሳሰብ በህብረተሰቡ ህሊና ውስጥ በጥብቅ ስለሰረጸ ቆይቶ ኢሳቅ ኒውተን የጋሊልዮን አስተሳሰብ ልክ መሆኑን በግስበት ጥናቱ እስካረጋገጠበት ድረስ የአሪስቶትል አስተሳሰብ ተቀባይነት ነበረው። ጋሊልዩ ከሱ ቀድሞ የተነሳውን የኮፐርኒከስን ሃሳብ (መሬት ሳትሆን ፀሓይ የአለም መካከለኛ ናት) በመደገፉ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለእስር ተዳርጎ ነበር። ይህም በዚያ ዘመን የነበሩ የቤ/ክርስቲያኒቱ አዋቂወች ያምኑት እንደነበረው መሬት ቆማ ሌላው አለም ሁሉ በመሬት ዙሪያ ይሽከረከራሉ የሚለውን ስለተቃወመ ነበር። ከዚህ በኋላ እስከ አረፈበት 1642 ድረስ የቤት እስረኛ ሆኖ ዘልቋል። በቅርቡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የሮማው ፓፓ ጆን ፓውል 2ኛ ጋሊልዮን "የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት] አባት" በማለት የካቶሊክ ቤ/ክርስቲያ ከ400 አመት በፊት በጋሊልዮ ላይ ለፈጸመችው ግፍ ይቅርታ ጠይቀዋል።
በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋሊልዮ ለእስር ያበቃው ምን ነበር?
ከሱ ቀድሞ የተነሳውን የኮፐርኒከስን ሃሳብ (መሬት ሳትሆን ፀሓይ የአለም መካከለኛ ናት) በመደገፉ
702
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012(ኤፍቢሲ) ቻይና በዋና ከተማዋ ቤጂንግ እና በሀቤይ ግዛት ዘሃንግጃኩ መካከል የተዘረጋውን ፈጣን ባቡር ለገልግሎት ክፍት ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል። ቻይና የፈጣን ባቡሩን ለአገልግሎት ክፍት የምታደርገው በአውሮፓውያኑ 2022 የምታስተናግደውን የክረምት ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ተነግሯል። ፈጣኑ ባቡር በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን፥ በዓለማችን ላይ የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ ባቡር እንደሚሆንም ተነግሮለታል። የ 174 ኪሎ ሜትር ያለው የባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቱ ለ2022 የክረምት ኦሎምፒክ እና የፓራሎምፒክ  ታስቦ የተሰራ መሆኑም ታውቋል። የባቡር መስመሩ የክረምት ኦሎምፒኩን በሚያስተናግዱት በሁለቱ ከተሞች መካከል የነበረውን የ3 ሰዓት መንገድ ወደ 47 ደቂቃ የሚቀንስ መሆኑ የቻይና ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል። ምንጭ፦ newsus.cgtn.com
በቤጂንግ እና ዘሃንግጃኩ መካከል የተዘረጋውን ፈጣን ባቡር በከተሞቹ መካከል የነበረውን የስንት ሰዓት መንገድ ወደ 47 ደቂቃ ይቀንሰዋል?
የ3 ሰዓት
439
ኃይሌ ገብረሥላሴ ኃይሌ ገብረሥላሴ በ ሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፷፭ (1965) ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ፣ አርሲ ክፍለ ሀገር የተወለደ አቻ ያልተገኘለት ድንቅ የረጅም ርቀት ኢትዮጵያዊ ሯጭ ነው። ኃይሌ በሩጫ ዘመኑ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ፣ በግማሽ ማራቶን፣ በማራቶንና እንዲሁም በሌሎቹ የሩጫ ዓይነቶች ከ ፲፩ በላይ የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብሯል። ኃይሌ በሩጫ ችሎታው ጠንካራ የሆነበት ምናልባትም ከመንደሩ ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ነው ተብሎ ቢታመንም የተፈጥሮ ጥንካሬው ዓለምን ያስደነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ኃይሌ ሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከመሆኑም በላይ በ፴፫ ዓመት ዕድሜው ፪ ሰዓት ከ፬ ደቂቃ በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለምን ማራቶን ክብረ-ወሰን ሊሰብር ችሏል። ኃይሌ ገብረሥላሴ እስካሁን ድረስ ፳፮ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን ሰብሯል። ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ በሲድኒ እና በአትላንታ ኦሊምፒኮች በ፲ ሺህ ሜትር ሩጫዎች ወርቅ አስመዝግቧል። በ ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. ኤንዱራንስ (Endurance) የተባለ ስለ እራሱ የእሩጫ ድል ፊልም ተሠርቷል።
ሯጭ ኃይሌ የአሥር ሺህ ሜትር ርቀት ሩጫ የወርቅ ሜዳልያ ያገኘው የት በተካሄደው ኦሎምፒክ ነበር?
በሲድኒ እና በአትላንታ
490
ቱርክመንኛ ቱርክመንኛ (Türkmen) የቱርክምኒስታን ብሔራዊ ቋንቋ ነው። በቱርክመኒስታን 3,430,000 ተናጋሪዎች ሲኖሩ ከቱርክመኒስታን ውጭ ደግሞ 3 ሚሊዮን የሚያሕሉ ተናጋሪዎች በተለይም በኢራን (2 ሚሊዮን) በአፍጋኒስታን (500,000) እና በቱርክ (1000) አሉ። ቱርክመንኛ በቱርኪክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይከተታል። ይህም አንዳንዴ በትልቁ አልታይ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይደመራል። ቀድሞ የተጻፈበት ወይም በቂርሎስ ወይም በ አረብ ፊደሎች ነበር፤ አሁን ግን የቱርክመኒስታን መሪ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ አዋጀ። በ1994 አ.ም. ደግሞ የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ እንደ አቶ ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።
የቱርክምኒስታን ብሔራዊ ቋንቋ ምንድን ነው?
ቱርክመንኛ
7
እንደ ፕላቶ ዘገባ፣ የሶቅራጠስ እናት ፌናርት የተሰኘች አዋላጅ ነበረች። ሶቅራጠስ እናቱ ሴቶች ልጅ እንዲወልዱ እንደምትረዳ ሁሉ እርሱ ደግሞ ሰዎች አዳዲስ አሳቦችን እንዲወልዱ ለመርዳት እንደሚሞክር መናገሩ ይጠቀሳል። የሶቅራጠስ አባት ድንጋይ አናጢ የነበረው ሶፍሮኒስከስ እንደነበር ይጠቀሳል። ሶቅራጠስ በዘመኑ ድሃ የነበረ ሲሆን ለዚህ ምክንያቱ ከገንዘብ ይልቅ እውቀት ይበልጣል ብሎ ስለሚያምን ነበር። ሶቅራጠስ ስራ እንደማይሰራና በፍልስፍና ሃሳብና ክርክር ጊዜውን እንደሚያሳልፍ ፕላቶ ዘግቦት ይገኛል። ዛንቲፕ የተሰኘች ከርሱ በዕድሜ በጣም የምታንስ ሴትን አግብቶ ሶስት ልጆች እንደነበሩት ፕላቶ ጽፏል። ሶቅራጠስ 70 ዓመት በሞላው ጊዜ የአቴና መንግስት እንዲያዝና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረገ። በወቅቱ ሁለት ክሶች ሲቀርቡበት አንደኛው "በትምህርትህ ወጣቱን አበላሽተሃል" የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ለግሪክ ጣዖታት አልተገዛህም" የሚል ነበር። እንደ ፕላቶ ዘገባ ግን ሶቅራጠስ የግሪክ ጣኦታት አምላኪ ነበር። በአንድ አንድ ተመራማርወች ዘንድ የአቴንስ መንግስት ያቀረባቸው ክሶች በውሸት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የሆኖ ሆኖ፣ ክሪቶ የተሰኘው የፈላስፋው ጓደኛ ለጠባቂወቹ ጉቦ በመስጠት እንዲያመልጥ ሁኔታውን አመቻችቶ ነበር። ሶቅራጠስ ግን እምቢ በማለት ቀረ እንጂ አላመለጠም። ሶቅራጠስ ለፍርድ በቀረበ ጊዜ ሰፊ የሆነ የመከላከያ ክርክር በማቅረብ የአቴናን መንግስት ክስ ውድቅ ለማደርግ ሞክሯል። ከዚህ በኋላ ዳኞቹ ምን አይነት ቅጣት እንዲበይኑበት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት፣ ለአቴና ህብረተሰብ ካበረከተው ጥሩ ተግባራቱ አንጻር በቀሪው ዘመኑ ሁሉ ነጻ እራት እንዲያመጡለት ተናገረ። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ወይ በቅጣት እንዲለቀቅ ወይንም ደግሞ እንዲገደል የእጅ ምርጫ አደረገ። ውጤቱም ሶቅራጠስ እንዲገደል የሚል ሆነ። ይሁንና ሶቅራጠስ ሞትን አይፈራም ነበር። ሞቱን ለማስቀረት ይቅርታም ሆነ ሌላ ማባበያ አላቀረበም። በርሱ ሥነ ምግባር መሰረት ላመነበት ነገር እስከመጨረሻ መቆሙ ሰናይ ድርጊት ነበር። ስለሆነም ሄምሎክ የተሰኘ መርዝ ጠጥቶ እንዲሞት ስለታዘዘ፣ መርዙን በመጠጣት አለፈ።
ሶቅራጥስ ጊዜውን የሚያሳልፈው ምን በማድረግ ነበር?
በፍልስፍና ሃሳብና ክርክር
272
ኢትዮጵያ  በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የዓለም አቀፍ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዚየም ልታካሂድ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ። ዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዚየምና የአፍሪካ አስትሮኖሚ ማኅበር የምክክር መድረክ ከመስከረም 26-30 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ እንደተብራራው በሁለቱ መድረኮች ከ30 አገራት ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶች፣ ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎችና ባለድርሻ ተቋማት ሾለ አስትሮኖሚና ስፔስ ሳይንስ ይመክራሉ። በኢንስቲትዩቱ የአስትሮኖሚና አስትሮፊዚክስ ምርምር ክፍል ኃላፊ ዶክተር ማሪያና ፖቪች እንዳሉት በዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት በተለያዩ አገራት በየዓመቱ የሚዘጋጁ ሲምፖዚየሞች አሉ። ኅብረቱ መቶኛ ዓመቱን እያከበረ ይህንንም ክብረ በዓል ያከናወናቸውን ስራዎችና ስኬቶች እየገመገመ በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ ነው። እስካሁን 355 ሲምፖዚየሞች የተካሄዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሲምፖዚየሙን የምታካሂድ ሶስተኛዋ የአፍሪካ አገር ስትሆን በደቡብ አፍሪካና ቡርኪናፋሶ መሰል ሲምፖዚየም ተካሂዷል። ሲምፖዚየሙ በዘርፉ ልምድና እውቀት ያካበቱ ተመራማሪዎች ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በሳይንስ ዘርፍ እየከወኗቸው ያሉ ተግባራትን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስገንዘብ የሚያስችል ነው ብለዋል። የምስራቅ አፍሪካ አስትሮኖሚ ለልማት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ አለምዬ ማሞ በበኩላቸው እንደገለጹት የአፍሪካ አስትሮኖሚ ማኅበር የሚያዘጋጀው የአፍሪካ አስትሮኖሚ የሳይንስ ምክክር መድረክ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል። መድረኩ በአፍሪካ አስትሮኖሚ ምን አይነት አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚችል የሚያመላክት ራዕይና ስትራቴጂ ሰነድ የሚነደፍበት ይሆናል ነው ያሉት። የማኅበሩን እንቅስቃሴ ለሳይንስና ለጠቅላላ ማኅበረሰቡ ማስተዋወቅ፣ የአህጉሪቱ ወጣት ተመራማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማስቻል፣ በአፍሪካ በአስትሮኖሚና ስፔስ ሳይንስ ዘርፍ የሚሰሩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ማጎልበት የመድረኩ ዓላማዎች መሆናቸውን አንስተዋል። መድረኩ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብርና ትስስር መፍጠር ያስችላልም ነው ያሉት። ነገና ከነገ በስቲያ አራት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ በዘርፉ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪያቸውን እየሰሩ ላሉ ተማሪዎች የእውቀትና ክህሎት ስልጠናም ይሰጣል። ከሁለቱ መድረኮች ጎን ለጎን በተመረጡ 10 የህዝብ ትምህርት ቤቶች በተግባር የታገዘ አስትሮኖሚን የማስገንዘብ ሾል እንደሚሰራም ተገልጿል። ለበርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሾለ አስትሮኖሚ ሳይንስ ግንዛቤ የመፍጠር እንዲሁም ለሁለተኛ ደረጃ መምህራን የሚሰጥ ስልጠና መኖሩም ተጠቁሟል።    
በአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ በየትኛው ካምፓስ ለሚገኙ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነው ስልጠና ለመስጠት የታሰበው?
አራት ኪሎ
1,321
ክሻትሪያ ክሻትሪያ የህንዳውያን ኅብረተሠብ በተለያዩ 4 መደባት የሚከፋፈልበት አንዱ የህብረተሰባዊ ክፍል (ካስት) ነው። በዚህ አከፋፈል ዘዴ የወታደሮችና የገዢዎች ክፍል እሱ ነው። ክሻትሪያ ከብራህሚን (ቄሳውንትና አስተማሮች) በታችና ከቫይስያ (ነጋዴዎች) እንዲሁም ከሹድራ (ሠራተኞች፣ አገልጋዮች) በላይ ሆኖ ይቆጠራል። በመጀመርያ በጥንት ይህ ደረጃ በሰው ችሎታ፣ ተግባርና ጸባይ ምክንያት ሊገኝ የቻላ ሲሆን፣ በዘመናት ላይ ግን የተወረሰ ማዕረግ (በዘር የሚዛወር) ብቻ ሆነ። በአንዳንድ ወቅት ደግሞ የክሻትሪያ (መኳንንት) ክፍል ከብራህሚኖች (ቄሳውንት) ክፍል ይልቅ ላየኛነቱን ይይዝ ነበር። ብራህሚኖችም በኋላ የበለጡት ከትግል በኋላ እንደ ሆነ ይታመናል። የቃሉ ሥር በሕንዳዊ-ኢራናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ «*ክሺ» 'መግዛት' ሲሆን ለዚሁ ብዙ የተዛመዱ ቃሎች (እንደ ሳንስክሪት «ክሻትራ» 'ግዛት') ይኖራሉ። በጥንታዊ ፋርስኛ በኩል «ሕሻጥራ» ማለት 'ሃይል፣ መንግሥት' ነበረ፤ የ«ሕሻያጢያ» ትርጉም የፋርስ ንጉሠ ነገስት ሆኖ ከዚህ በዘመናዊ ፋርስኛ ንጉሥ ሻህ ይባላል። በአማርኛ፣ ቼዝ (ሰንጠረዥ) የሚባል ጨዋታ ስም ከዚህ የመጣ ነው። በተጨማሪ በፋርስ ታሪክ የጠቅላይ ግዛት ወይም አገረ ገዥ ማዕረግ «ሕሻጥራ-ፓዋ» (የግዛት ጠባቂ) በኋላ «ሳትራፕ» ሆነ። ሌሎች ቃላት በታይላንድኛ «ካሳት» 'ንጉስ' በመላይኛም «ሳትሪያ» 'ጀግና' ከ«ክሻትሪያ» የተነሡ ናቸው።
የህንዳውያን የወታደሮችና የገዢዎች ክፍል ምን ተብሎ ይጠራል?
ክሻትሪያ
0
ነሐሴ ፳፯ ነሐሴ ፳፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፰ ዕለታት ይቀራሉ። ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ። ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አረፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ነጻነትን አስከትሎ በጃዋሃርላል ኔህሩ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ የሕንድ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት።
መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ የተቀበረበት ቤተክርስቲያን የት ይገኛል?
አረፎ አንኮበር
479
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እስካሁን ግብይት የሚያስፈጽመው ግዥና ሻጭን መድረክ ላይ በማገናኘት በድምፅ ዋጋ በመንገርና በመጫረት ነው፡፡ ይህ የተለመደው አሠራር የበለጠ ውጤታማ የሚሆነው ግን በድረ ገጽ ግብይት ሲደረግ በመሆኑ ይህንን የድረ ገጽ ግብይት ለማስጀመር ከሦስት ዓመት በፊት ሥራው የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሥራው ተጠናቅቆ ወደ ትግበራ ሊገባ ችሏል፡፡ በተለመደው የመድረክ የግብይት አሠራር በቀን የሚፈጸመው የግብይት መጠን ከ200 እስከ 300 የሚደርስ ነው፡፡ ይህም የግብይት መጠኑ ውሱን መሆኑን ያሳያል፡፡ ስለዚህ የድረ ገጽ ግብይት መጀመሩ ግን ይህንን በመለወጥ ከፍተኛ አቅም ይሰጣል፡፡ ይህም አሠራሩን ተግባራዊ ከማድረጉ በፊትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባለው ተቋም ጭምር ዕውቅና አግኝቶበታል፡፡ እንደ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ያሉ ተቋማትም ይህንን አገልግሎት ፈትሸው ማረጋገጫ ተሰጥቶት እየተሠራበት ስለመሆኑም የምርት ገበያው የሥራ ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡ ይህንን ዘመናዊ አገልግሎት ሥራ ለማስጀመር ከመጀመሪያው ጀምሮ የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየው የኢንቨስትመንት ክላይሜት ፋሲሊቲ ፎር አፍሪካ (ICF) የተባለው ተቋም ሲሆን፣ ለዚህ ፕሮጀክት 2.2 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ይህ ግብይት በቡና የተጀመረ ሲሆን፣ ሁሉም በዚህ የግብይት ሥርዓት እንዲጠቀሙ ይደረጋል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ አዲስ በመሆኑ በዚህ ለመጠቀም ተገበያዮች ሥልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ እስካሁንም 380 ተገበያዮች በድረ ገጽ ለመገበያየት ሥልጠና ወስደው ብቁ መሆናቸው ተረጋግጦ ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የድረ ገጽ የግብይት ሥርዓትን ለማበልጸግ የገንዘብ ድጋፍ ያገኘው ከማን ነው?
የኢንቨስትመንት ክላይሜት ፋሲሊቲ ፎር አፍሪካ (ICF)
625
ኤዎስጣጤዎስ በግዕዝ ኤዎስጣቴዎስ ወይም ዮስጣቴዎስ፣ ከሐምሌ ፭ ቀን ሺ፪፻፷፭ – ሺ፪፫፵፬ በኢትዮጵያ ሰለሞናዊ መንግሥት አገዛዝ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ታላቅ መሪ የነበሩ አባት ናቸው። በጣም አጥብቀው ከሚያስተምሩት ትምህርት ስለ ሰንበት መከበር ነበረ። ተከታዮቻቸው የኤዎስጣጤዎስ ቤት ወይም በግል ሲጠሩ ኤዎስጣጤዎሳውያን ይባሉ ነበር ለተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ናቸው። የኤዎስጣጤዎስ መጀመሪያ ስማቸው ማዕቀበ እግዚእ ሲሆን ከእናታቸው ከስነሕይወትና ከአባታቸው ከክርስቶስ ሞዐ ሐምሌ ፳፩ ቀን ፩ሺ፪፷፭ ተወለዱ። እኒህም ደጋግና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ነበሩ ። ኤዎስጣጤዎስ የታወቀውን ደብራቸውን (ደብረ ፀራቢን) የመሠረቱት የተወለዱበት ቦታ እዛው (እንድርታ) እንደሆነ ገድላቸው ይገልፃል። በወጣትነታቸው ዘመን በሺ፪፸፪ አካባቢ ከአጎታቸው አባ ዳንኤል (የደብር ስማቸው አባ ዘካርያስ) ቆርቆር (ደብረ ማርያም) አስተዳዳሪ ጋር እንዲኖሩ ወደ ገራልታ ይላካሉ። አባ ዳንኤልም ኤዎስጣጤዎስን ተቀብለው ተገቢውን የሃይማኖት ትምህርትና የደብር ሕይወትን ካስተማሩ በኋላ ማዕቀበእግዚእ በ፲፭ ዓመቱ ቅስና ሥራዬ መሆን አለበት ብሎ በወሰደው ውሳኔ መሠረት ስሙ ኤዎስጣጤዎስ ተብሎ ተሰየመ። ኤዎስጣጤዎስ ከአባ ዳንኤል የቅስና መዐረጋቸውን ካገኙ በኋላ የራሳቸውን ደብር በ(ሰራይ) መሠረተው በዚያም በማስተማር ብዙ ተማሪዎችን አፈሩ ። በሰንበት ላይ ያተኮረ አመለካከታቸውን ለይተው ያስተምሩ ነበር ፣ የሚቃወማቸው አቡነ ያእቆብ ፫ኛው አስኪመጣ ድረስ። ከዛ ግን ከተከታዮቻቸው ከባካርሞስ ፣ መርቆርዮስ ፣ ገብረእያሱ ጋር ኢትዮጵያን ለቀው ወደ ግብፅ (ካይሮ) ገብተው በአሌክሳንድሪያው ጳጳስ ቢንያም ፪ኛው ፊት በሰንበት ባላቸው አመለካከት ፀንተው ከዛም ወደ ኢየሩሳሌም አምርተው በመጨረሻም የሕይወታቸው ማብቂያ ወደ ሆነችው አርሜኒያ ገብተው ኖሩ።
ኤዎስጣጤዎስ አጥብቀው የሚያስተምሩት ትምህርት ምንድን ነው?
ስለ ሰንበት መከበር
146
ኃይሌ ገብረሥላሴ ኃይሌ ገብረሥላሴ በ ሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፷፭ (1965) ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ፣ አርሲ ክፍለ ሀገር የተወለደ አቻ ያልተገኘለት ድንቅ የረጅም ርቀት ኢትዮጵያዊ ሯጭ ነው። ኃይሌ በሩጫ ዘመኑ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ፣ በግማሽ ማራቶን፣ በማራቶንና እንዲሁም በሌሎቹ የሩጫ ዓይነቶች ከ ፲፩ በላይ የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብሯል። ኃይሌ በሩጫ ችሎታው ጠንካራ የሆነበት ምናልባትም ከመንደሩ ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ነው ተብሎ ቢታመንም የተፈጥሮ ጥንካሬው ዓለምን ያስደነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ኃይሌ ሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከመሆኑም በላይ በ፴፫ ዓመት ዕድሜው ፪ ሰዓት ከ፬ ደቂቃ በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለምን ማራቶን ክብረ-ወሰን ሊሰብር ችሏል። ኃይሌ ገብረሥላሴ እስካሁን ድረስ ፳፮ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን ሰብሯል። ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ በሲድኒ እና በአትላንታ ኦሊምፒኮች በ፲ ሺህ ሜትር ሩጫዎች ወርቅ አስመዝግቧል። በ ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. ኤንዱራንስ (Endurance) የተባለ ስለ እራሱ የእሩጫ ድል ፊልም ተሠርቷል።
ኃይሌ ገብረሥላሴ በሲድኒና በአትላንታ ኦሎምፒኮች የወርቅ ሜዳልያ ያገኘው በምን የሩጫ ዓይነት ነው?
በ፲ ሺህ ሜትር ሩጫ
512
የፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ምርምሮች በቫይረስ ጥቃት በእንስሳትና በሰው ላይ ለሚከሰቱ በሽታዎች በዘረመል ምህንድስና ጥበብ ክትባት ወይም መከላከያ መድሃኒት ግኝቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው። በዚህም የበርካታ በሽታዎች ክትባትና መድሃኒት ግኝቶች ባለቤት ሲሆኑ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ያደረጋቸው ደስታ በተሰኘውና ከ100 ዓመት በፊት በአውሮጳና በአፍሪካ ከፍተኛ ዕልቂት ላደረሰው የከብቶች መቅሰፍት በሽታ ክትባት መፈልሰፋቸው ነው። ይህን ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በርካታ የምርምር ተቋማት ደክመው ያላሳኩትን የደስታ በሽታ ክትባት ማግኘታቸው በህክምና ግኝቶች መስፈርት አንቱ አስብሏቸዋል፤ ዓለምንም በደስታ በሽታ ከሚደርሰው እልቂት ታድገዋል። በእንግሊዝና በጣሊያን ወታደሮች ሴራ ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ከብቶች በተዛመተው የደስታ በሽታ እ.አ.አ ከ1888-1892 ለአራት ዓመታት በኢትዮጵያ በደረሰው እልቂት ከፍተኛ ረሀብ መከሰቱን ያስታወሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን የምርምራቸው መነሻ ከወላጆቻቸው ስለ ከብት መቅሰፍት ሲሰሙ ማደጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሰውና በእንስሳት ህክምና ዕውቀት በሁለቱም ሰይፍ የተካኑት አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ ለኤች አይ ቪ/ኤዲስ ቫይረስ ክትባት ለማግኘትም ደክመዋል። ከ124 በላይ የሚሆኑ የምርምር ግኝቶች በስመ ጥር ዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔቶች የታተሙላቸው ሲሆን በአሜሪካና በቻይና በሚገኙ በርካታ ተቋማትም የአካዳሚ አባልነት ተመርጠዋል፤ በአማካሪነትም እየሰሩ ይገኛል። በተማሩበት ብሎም ባስተማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጨምሮ በአሜሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ዕውቅናና ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን ለአብነትም የዩኒቨርሲቲዎች የምርጥ አስተማሪነትና ተመራማሪነት ሽልማት፣ የእንስሳት ህክምና ዘርፍ ከፍተኛውን ዓለም አቀፍ ሽልማት፣ የልዩ አገልግሎት ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል። እርሳቸው ባቋቋሙትና በዳይሬክተርነት በሚመሩት የዓለም አቀፉ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የምርምር ማዕከል ከተለያዩ ታዳጊ አገራት በርካታ ሳይንቲስቶችንም አፍርተዋል። በትምህርትና ምርምር ዘመናቸው የነጮችን የዘረኝነት ጫና በመቋቋም ከስኬት ማማ ላይ የደረሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ አሁን ላይ በማደግ ላይ በሚገኙ አገራት ወጣት ሳይንቲስቶችን በማስተማርና በማበረታት ላይ ትኩረት አድርገው በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ የፈለሰፉት ለእንስሳት የሚሆን ክትባት የምን በሽታ መድኃኒተ ነው?
የደስታ በሽታ
326
ሩሲያ ለአለም አቀፍ በይነመረብ አማራጭ የሚሆን አር ዩ ኔት  የተሰኘ ኢንተርኔት  በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን  የሀገሪቱ  መንግስት አስታውቋል ፡፡ ይሁን እንጂ  የተከናወነውን ሙከራ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ አለመሰጠቱ  በዘገባው ተመላክቷል። እንደ ሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር  መረጃ ፥ማንኛውም ተጠቃሚ  በተደረገው ሙከራ ወቅት  ምንም አይነት ለውጥ ማስተዋል አለመቻሉን አስታውቋል፡፡ የሙከራ ውጤቱም  ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት  ቭላድሚር ፑቲን ይቀርባል ነው የተባለው ፡፡ ምሁራኖችበ አንዳንድ ሀገሮች በበይነ መረብ የሚደርስ ጥፋትን እንዳለ ይጠቅሳሉ። በጥናቱ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒተር ሳይንቲስት የሆኑት ፕሮፌሰር አላን ውድዋርድ እንዳሉት፥ በሚያሳዝን ሁኔታ የበይነመረብ  ሰርጎ ገቦች መበራከት የሩሲያ የጉዞ አቅጣጫ ሌላ ደረጃ እያደረሰ ነው። ቁጥራቸው እየጨመረ ያሉ ሃያላን መንግስታት ዜጎች የሚያዩትን መቆጣጠር የሚፈልጉ ስለመሆናቸው ከኢራን እና ከቻይና መመልከት ይቻላል። ይህ ማለት ሰዎች ሀገራቸው ውስጥ ስለሚሆነው ነገር የመነጋገር እድል አይኖራቸውም፡፡ የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው  ባለስልጣኖች እና የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ውጤታማ ምላሽ በመስጠት   አደጋዎች እና ስጋቶችን ማስወገድ እንዲሁም በሁለቱም በይነመረብ እና ቴሌኮሙዩኒኬሽን አውታር መረብ ውስጥ የተስተካከለ አሠራር  በሩሲያ ፌዴሬሽን እንዲኖር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው ተነግሯል።
ሀገራት የራሳቸውን የበይነ መረብ መተግበሪያ መስራታቸው ችግሩ ምንድን ነው?
ሰዎች ሀገራቸው ውስጥ ስለሚሆነው ነገር የመነጋገር እድል አይኖራቸውም
554
የፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ምርምሮች በቫይረስ ጥቃት በእንስሳትና በሰው ላይ ለሚከሰቱ በሽታዎች በዘረመል ምህንድስና ጥበብ ክትባት ወይም መከላከያ መድሃኒት ግኝቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው። በዚህም የበርካታ በሽታዎች ክትባትና መድሃኒት ግኝቶች ባለቤት ሲሆኑ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ያደረጋቸው ደስታ በተሰኘውና ከ100 ዓመት በፊት በአውሮጳና በአፍሪካ ከፍተኛ ዕልቂት ላደረሰው የከብቶች መቅሰፍት በሽታ ክትባት መፈልሰፋቸው ነው። ይህን ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በርካታ የምርምር ተቋማት ደክመው ያላሳኩትን የደስታ በሽታ ክትባት ማግኘታቸው በህክምና ግኝቶች መስፈርት አንቱ አስብሏቸዋል፤ ዓለምንም በደስታ በሽታ ከሚደርሰው እልቂት ታድገዋል። በእንግሊዝና በጣሊያን ወታደሮች ሴራ ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ከብቶች በተዛመተው የደስታ በሽታ እ.አ.አ ከ1888-1892 ለአራት ዓመታት በኢትዮጵያ በደረሰው እልቂት ከፍተኛ ረሀብ መከሰቱን ያስታወሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን የምርምራቸው መነሻ ከወላጆቻቸው ስለ ከብት መቅሰፍት ሲሰሙ ማደጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሰውና በእንስሳት ህክምና ዕውቀት በሁለቱም ሰይፍ የተካኑት አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ ለኤች አይ ቪ/ኤዲስ ቫይረስ ክትባት ለማግኘትም ደክመዋል። ከ124 በላይ የሚሆኑ የምርምር ግኝቶች በስመ ጥር ዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔቶች የታተሙላቸው ሲሆን በአሜሪካና በቻይና በሚገኙ በርካታ ተቋማትም የአካዳሚ አባልነት ተመርጠዋል፤ በአማካሪነትም እየሰሩ ይገኛል። በተማሩበት ብሎም ባስተማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጨምሮ በአሜሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ዕውቅናና ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን ለአብነትም የዩኒቨርሲቲዎች የምርጥ አስተማሪነትና ተመራማሪነት ሽልማት፣ የእንስሳት ህክምና ዘርፍ ከፍተኛውን ዓለም አቀፍ ሽልማት፣ የልዩ አገልግሎት ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል። እርሳቸው ባቋቋሙትና በዳይሬክተርነት በሚመሩት የዓለም አቀፉ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የምርምር ማዕከል ከተለያዩ ታዳጊ አገራት በርካታ ሳይንቲስቶችንም አፍርተዋል። በትምህርትና ምርምር ዘመናቸው የነጮችን የዘረኝነት ጫና በመቋቋም ከስኬት ማማ ላይ የደረሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ አሁን ላይ በማደግ ላይ በሚገኙ አገራት ወጣት ሳይንቲስቶችን በማስተማርና በማበረታት ላይ ትኩረት አድርገው በመስራት ላይ ይገኛሉ።
እ.ኤ.አ ከ1888-1892 ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ከብቶች በተዛመተው የደስታ በሽታ በደረሰው እልቂት ከፍተኛ ረሀብ የተከሰተው በማን ሴራ ነበር?
በእንግሊዝና በጣሊያን ወታደሮች
411
ኤርትራ ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አገሮች አንዷ ስትሆን በስሜን-ምዕራብ ከሱዳን፣ በሰሜን-ምስራቅ ከቀይ ባህር፣ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ በደቡብ-ምስራቅ ጅቡቲ ጋር ድንበር ትካለላለች። ኤርትራ የሚለው ስም ከላቲን የተወሰደ እና ስረ-መሰረቱ የግሪክ ሐረግ ሲሆን ትርጉሙም ቀይ ማለት ነው። ይህን ስም ለአካባቢው የሰጡት ጣሊያኖች በጥር ፲፰፻፺ ቅኝ ግዛታቸውን ሲያውጁ ነበር (ተመሳሳይ ስም በጀርመኖች 1870 እና ግብጾች ፲፰፻፷ወቹ በጥቅም ላይ ውለዋል፣ ነገር ግን የትኛውን ክፍል ስሙ እንደሚመለከት ግልጽ አልነበረም)። ኤርትራ፣ እንደ ሐገር፣ በጣሊያኖች ከተመሰረተች በኋላ በ5 ልዩ ሂደቶች ውስጥ በማለፍ ነው ያሁኑን ቁመናዋን የያዘችው። ከ1890 በፊት የነበረው የአካባቢው ታሪክ በ«ኤርትራ» ስር የሚጠና ባህይሆንም ስለአዲሱ ኤርትራ ግንዛቤ ስለሚያስጨብጥ ታሪክ ተመራማሪዎች ከ፲፰፻፺ በፊት ያለውንም ታሪክ ማጥናት ተገቢ እንደሆነ ይስማማሉ። በ1860ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ፣ የግብጹ መሪ ኢስማኤል ከዴቭ ፓሻ በናይል ተፋሰስ ላይ ሰፊ የግብጽ ቅኝ ግዛት ለማበጀት ተነሳ። ለዚህ አዲሱ ግዛቱ ካርቱምን ዋና ከተማው በማድረግ የሱዳን ግዛቱን አጸና። ቀጥሎም የቀይ ባህርን ጠረፎች በ1865 ከተቆጣጠረ በኋላ በ1870ዎቹ መጀመሪያ ሐረርንና ተሻግሮ ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ግዛቶችን አበጀ። እንግዲህ በኒህ ግዛቶቹና በሱዳን መካከል የነበረው ብቸኛ መገናኛ መንገድ ካርቱም-ከሰላ- ከረን -ምፅዋ ብሎ የሚዘልቅ ነበር። ስለሆነም በ1872 ይህን ስልታዊ መንገድ የክዴቭ ፓሻ ሰራዊቶች ተቆጣጠሩ። መቆጣጠር ብቻ አይደለም በየመንገዱ ምሽግ እየሰሩና የአውሮጳ ምስዮናውያንን እርሻ ቦታ እየሰጡ ቅኝ ግዛት አበጁ። በዚህ ሳይቆጠቡ፣ የመንገዱን ደህንነት ዋስትና ለማስጠበቅ ሲሉ የአካባቢውን ደጋማ ክፍል መያዝ ግድ አላቸው። ደጋማው ክፍል በዚህ ወቅት በአጼ ዮሐንስ ግዛት ስር ነበር።
ኤርትራ በሰሜን-ምሥራቅ የምትዋሰነው ከየትኛው ባህር ጋር ነው?
ከቀይ ባህር
65
ሳዑዲ አረቢያ የሣውዲ አረቢያ ግዛት 28.7 ሚሊዬን የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡ ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ ኤዥያ ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡ የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡ ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡ የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡ አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡ የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በ1932 እ.ኤ.አ. በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡ ኢብን ሣኡድ ቀድሞ በ1894 ዓም (1902 እ.ኤ.አ.) ከብሪታንያ ግዛት ከኩወይት ዘምቶ ሪያድን ያዘ። ኢብን ሳኡድ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስልምና ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ የነዳጅ አምራች ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ሀይድሮ ካርቦን ክምችት ካላቸው አገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሀገሪቱ ባለው የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛ ክምችት ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ እና የህዝብ ቁጥር እድገት ከያዙ ሀገራት ጋር ትመደባለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ G-2ዐ ተብለው ከሚታወቁት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የሀገራት ቡድን ውስጥ ብቸኛዋ የአረቡ ዓለም አገር ናት፡፡ ይህም ቢሆን የሣውዲ ኢኮኖሚ በአብዛኛው በአንድ ቡድን የተያዘ ነው፡፡ የሣውዲ አረብያን ፈላጭ ቆራጭ በሆነ የመንግስት ስርዓት በመመራት “ነጻነት የለም” በሚል “ነጻነት ቤት” በሚል በሚታወቀው ድርጅት ተሰይማለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ለጦር ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያወጡ አገሮች ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2ዐ1ዐ-2ዐ14 በስኘሪ ተብሎ በሚታወቅ ድርጅት በተደረገው ጥናት ሣውዲ አረቢያ ዓለም ላይ ከሚገኙ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ደረጃ በማስገባት ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡ ሣውዲ አረቢያ በአካባቢው ካሉ ሀገሮች በዓለም ላይ ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማድረግ ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የኦፔክ፣ ጂሲስ እና የእስላም ግሩፕ አባል ናት፡፡
የበፊቱ አራቱ ሳውዲ አረብያ ግዛቶች የትኞቹ ናቸው?
ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን
449
ፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ "The Nation"፣ "The Chinese Recorder"፣ "Asia" እና "The Atlantic Monthly" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል።
የፐርል በክ የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ ያገኘችው በስንት ዓመተ ምህረት ነበር?
በ1935 ዓ.ም
905
ባለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል። በዚህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ተደርሶ የነበረው ስምምነት ወደ ትግበራ ገብቷል። ባለፉት ስደስት ወራት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች መረጣ እና ተመሳሳይነት ልየታም ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህ መሰረት 25 የህንድ የቴክኖሎጂ ባላሙያዎችና ድርጅቶች ከ57 የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መመስረታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በቅንጅት በመስራት ታምናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር፥ የሁለቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጥምርታ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የቴክኖሎጂው ዘርፍ የእውቀት ሽግግር እንዲያመጣ፣ ሃብት እና የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ ኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራንግ ስትራቫስታቫ በበኩላቸው፥ኢትዮጵያ እና ህንድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመሩት ስራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን ተናግረዋ። በኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ፕሮግራም በሚቀጥሉት አምስት አመታት 50 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ለመፍጠር እቅድ መያዙ ተመላክቷል። ባለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል። በዚህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ተደርሶ የነበረው ስምምነት ወደ ትግበራ ገብቷል። ባለፉት ስደስት ወራት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች መረጣ እና ተመሳሳይነት ልየታም ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህ መሰረት 25 የህንድ የቴክኖሎጂ ባላሙያዎችና ድርጅቶች ከ57 የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መመስረታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በቅንጅት በመስራት ታምናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር፥ የሁለቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጥምርታ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የቴክኖሎጂው ዘርፍ የእውቀት ሽግግር እንዲያመጣ፣ ሃብት እና የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ ኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራንግ ስትራቫስታቫ በበኩላቸው፥ኢትዮጵያ እና ህንድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመሩት ስራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን ተናግረዋ። በኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ፕሮግራም በሚቀጥሉት አምስት አመታት 50 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ለመፍጠር እቅድ መያዙ ተመላክቷል።
ኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ላይ ምን ያህል የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ተሳተፉ?
57
291
ፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ "The Nation"፣ "The Chinese Recorder"፣ "Asia" እና "The Atlantic Monthly" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል።
ፐርል በክ የስነ-ጽሑፍ ስራዎቿን ማሳተም የጀመረችው ከስንት ዓመተ ምህረት ጀምሮ ነው?
ከ1920ዎቹ ጀምራ
506
አብርሀም ሊንከን (የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፰ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም.) ድረስ የኖሩ ከ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትተው ተገደሉ። የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜሪ ቶድን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር መኖር ትንሽ የተቸገሩ ቢሆነም ከጊዜ ብዛት ግን ለምደዉ 4 ወንድ ልጆችን በተከተሉት አመታት ወለዱ። በ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን ሪፐብሊካን ፓርቲ መሥርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም. የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ። በጦርነቱ የስሜን ሠራዊት ከብዛታቸው የተነሣ በአራት ዓመት ውስጥ አሸነፉ። በዚህ ጊዜ ላይ ሊንከን ለአመጸኖቹ ባርዮች ነጻነት አዋጁ። ያላመጹ ዜጎች ባርያዎች ግን በዚያን ጊዜ ነጻ አልወጡም። በ፲፰፻፶፮ዓ.ም.ምርጫ ሊንከን በቀላል ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ተመረጡ። በሚያዝያ ፪ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. የኮንፌደራት ሠራዊት እጁን ሰጠ። ነገር ግን ሚያዝያ ፯ ቀን የመድረክ ትርዒት ሲያዩ በነፍሰ ገዳዩ በጆን ዊልክስ ቡዝ እጅ በጥይት ተመትተው በማግሥቱ ሞቱ። ከዚህም ትንሽ በኋላ ባርነት በሕግ በሙሉ ተክለክሎ የተረፉት ባርያዎች ነጻነት አገኙ።
አብርሃም ሊንከን በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለየትኛው ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ?
ለኢሊኖይ
276
ተክለጻድቅ መኩርያ ተክለጻድቅ መኩርያ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አሳግርት ልዩ ስሙ ሳር አምባ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ መጀመሪያ ከአባታቸውና ቀጥሎም በአጥቢያቸው ባህላዊውን ትምሕርት እስከቅኔ ያለውን ቀስመዋል። ከዚያም አዲስ አበባ መጥተው አሊያንስ ፍራንሴዝና ተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ገብተው የጊዜውን የትምሕርት ደረጃ አጠናቀዋል። ኢጣልያ አገራችንን የወረረች ጊዜም በየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ፍጅት ተይዘው ወደ ሶማሌ ደናኔ ተግዘው ለሦስት ዓመታት ታስረዋል። ከነጻነትም መልስ አገራቸውን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል። መጀመሪያ ተቀጥረው ያገለገሉት በትምሕርትና ሥነጥበብ ሚኒስቴር ነበር። እዚያም ሳሉ በአገራችን ሰው የተጻፈ የአገራችን ታሪክ አንድም ባለመኖሩ በቁጭትና በመቆርቆር ነበር ‘መጻፍ አለብኝ’ ብለው በደንብ ከሚታወቀው ከቅርቡ ጊዜ በቅጡ ወደማይታወቀው የሩቁ ዘመን መጻፍ የጀመሩት። የመጀመሪያውን መጽሐፍ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ” የሚለውን በ ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. አሳተሙ። ከጫፍ እስከ ጫፍ ጽፈው የመጨረቻውን መጽሐፍ፣ የታሪካችን መጀመሪያ የሚሆነውን “የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ-አክሱም-ዛጉዬ እስከ ዓፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት” የሚለውን በ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. አቅርበዋል። እኒህኑ መጻሕፍት ትምሕርት ሚኒስቴር ታሪክ ለማስተማሪያ በትምሕርት ቤት ተጠቅሞባቸዋል። ተክለጻድቅ ከታሪክ ውጭ የጻፏቸው “የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ” እና በሚዮቶሎዢያ (አፈ ታሪክ) ላይ ያተኮረ “ከጣዖት አምልኮ እስከ ክርስትና” የሚሉም መጽሐፎች አሏቸው። ተክለጻድቅ በምድር ባቡር በዋና ጸሐፊነት፥ በቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዋና ሥራ አስኪያጅነት፥ እንዲሁም በፈረንሳይ፥ በእስራኤል፥ በዩጎዝላቪያ በዲፕሎማሲ ሥራ በመጨረሻም የትምሕርትና የባህል ሚኒስቴር ሆነው አግልግለዋል። በፈቃዳቸው ጡረታም ከወጡ በኋላ በምርምር የታገዙ ሦስት ታላላቅ የታሪክ ሥራዎችን አቅርበዋል። ተክለጻድቅ ከረጅም የአገልግሎት ዘመን በኋላ በተወለዱ በ ሰማንያ ስድስት ዓመታቸው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. አርፈዋል።
ተክለጻድቅ መኩርያ አዲስ አበባ መጥተው ትምህርታቸውን የት ተከታተሉ?
አሊያንስ ፍራንሴዝና ተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት
180
ዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
በዩጋንዳ በሁለተኛነት ደረጃ የሚነገረው ቋንቋ ምንድን ነው?
የአቴሶ ቋንቋ
1,455
ታንዛኒያዊው ደራሲ አብዱልራዛቅ ጉራህ የ2021 የኖቤል የሥነ ጽሑፍ አሸናፊ መሆናቸውን የስዊድን አካዴሚ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1986 ዎሌ ሾይንካ በሥነ ጽሑፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑ ከ35 ዓመታት በኋላ አብዱልራዛቅ ጉራህ ሁለተኛው ጥቁር አፍሪካዊ ያሰኛቸውን ክብር ተቀዳጅተዋል፡፡ በመላው አፍሪካ ደረጃ ስድስተኛ ተሸላሚ ናቸው፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ አብዱልራዛቅ ለአሸናፊነታቸው ከስዊድኑ የኖቤል ሽልማት ድርጀት 10 ሚሊዮን ክራውን ወይም 1.14 ሚሊዮን ዶላር ያገኛሉ፡፡ የ73 ዓመቱ አዛውንት ጉራህ ጎልተው የሚታወቁትን ‹‹ፓራዳይዝ›› (Paradise) እና ‹‹ዲዘርሽን›› (Desertion) ጨምሮ የ10 ልብ ወለዶች ደራሲ ናቸው፡፡
ደራሲ አብዱልራዛቅ በ2021 የሥነ ጽሑፍ ኖቤል ተሸላሚነታቸው የታወቀው መቼ ነበር?
መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም.
66
ሊንጋላ ሊንጋላ (Lingala) ከባንቱ ቋንቋዎች ቤተሠብ አንድ ነው። የሚናገርበት በተለይ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ስሜን-ምዕራብ ክፍል፣ በኮንጎ ሪፑብሊክም፣ እንዲሁም በአንጎላና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ነው። ተናጋሪዎቹ 10 ሚልዮን ናቸው። የሊንጋላ መነሻ ቦባንጊ በተባለ ቋንቋ ነበር። ከኮንጎ ነጻ መንግሥት አስቀድሞ ቦባንጊ የአከባቢው መደበኛ ቋንቋ ይሆን ነበር። የቤልጅክ ንጉስ አገሩን ከያዙ በኋላ የቀኝ አገሩ መንግሥት ለማስተዳደርና ለመሰበክ ቋንቋውን ጠቃሚ ሆኖ አገኙት። ካለፈው ቦባንጊ እንዲለይ የአዲሱን ቋንቋ ስም ባንጋላ ብለው ጠሩት። ሚስዮናዊዎቹ ወዲያ (1900 አ.ም.) ባንጋላን ዳግመኛ ሲያሻሽሉ "ሊንጋላ" እንዲህ ተፈጠረ። ሊንጋላ ከፈረንሳይኛ ብዙ ቃሎች ተበድሮ ደግሞ ከፖርቱጊዝ ተጽእኖ አለ (ለምሳሌ "ማንቴካ" = ቅቤ፤ "ሜሳ" = ጠረጴዛ፤ "ሳፓቱ" = ጫማ) ከእንግሊዝኛም ተጽእኖ አለ ("ሚሊኪ" = ወተት፤ "ቡኩ" = መጽሐፍ)።
የሊንጋላ ቋንቋ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በየትኛው አካባቢ ይነገራል?
ስሜን-ምዕራብ
75
ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ እንግሊዝ ሀገር አንደደረሰም የወቅቱ የእንግሊዝ ንግስት ከነበረችው ንግስት ቪክቶሪያ ጋር ተገናኘ፡፡ ንግስቲቱም ልዑሉ የፈለገው እና ያሻው ይደረግለት ዘንድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡ ልዑሉ በመቅደላ የነበረውን እልቂት በመጠኑም ቢሆን በማየቱ እና የአባቱ እና የእናቱ ተከታታይ ሞትም በልጅ አዕምሮው ሊቀበለው ከሚችለው በላይ ስለነበር እጅግ ታውኮ እንደነበር በተደጋጋሚ ተፅፎ እናገኛለን፡፡ በ1861 ዓ.ም ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ አንዲት ከተማ አዛዥ ሆኖ ስለተሾመ የ8 ዓመቱን አለማየሁን እና ሚስቱን ይዞ ወደዛው አቀና፡፡ በሄዱበት ሀገርም አለማየሁ ትምህርቱን መከታተሉን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን ከመደበኛው ትምህርት በዘለለም ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንም ያዘወትር ነበር፡፡ 1867 ዓ.ም አለማየሁ ወደ ራግቢ ትምህርት ቤት ተዛወረ፡፡ በዚህም ከቄስ ብሌክ ቤት ወጥቶ ወደ ሊው ዋርነር ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በዚህ ግን ደስተኛ ስላልነበር በቀጣዩ አመት ሚስተር ድራፐር ቤት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ቄስ ብሌክም ካዩት የልዑሉ ባህሪ በመነሳት ልዑሉ ወታደርነት ላይ ቢያተኩር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ በዚህም ንግግር መሰረት የወታደር ትምህርት ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በአንድ ወቅት አለማየሁ ወደ ሊድስ በመሄድ በሰር ራምሰን ቤት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት በመርዝ ተመረዘ። መርዙ ህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከሩብ በተወለደ በ19 ዓመቱ ከዚህ አለም እንዲሰናበት አደረገው፡፡ አስከሬኑም ዊንድሶር ባለው የነገስታት መቀበርያ በክብር አረፈ፡፡ በመቃብሩም ላይ “የሀበሻው ልዑል አለማየሁ” የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበት እስካሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል፡፡
ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ ከተማ አዛዥ ሆኖ በተሾመበት ወቅት ልዑለ አለማየሁ የስንት ዓመት ልጅ ነበር?
የ8
313
ዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘውድ እንደጫኑ የአገሪቱን የመጀመሪያ ሕገ-መንግሥት እንዲዘጋጅ አዝዘው በዘውዱ አንደኛ ዓመት በዓል ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. በአዲሱ ምክር ቤት (ፓርላማ) ለሕዝብ ቀረበ። ከዚህም በላይ ብዙ የቴክኖዎሎጂ ስራዎችና መሻሻያዎች ወደ ኢትዮጵያ ከውጭ አገር አስገቡ። በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. የሙሶሊኒ ፋሺስት ሠራዊት ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ጃንሆይ ሕዝባቸውን ወራሪውን በሙሉ ለመቃወም እንዳስነሡና የከተት ዐዋጆቻቸው በታሪክ ገጾች ይዘገባሉ። በዐዋጅ መሠረት የዘመቻው ጊዜ እስቲያልቅ ድረስ ለሚታግሉ ነጋዶች ከቀረጥ አስተስርየት ሰጣቸው። እራሳቸው በቆራጥነት ከታገሉ በኋላ የጠላቱ ጦር ኅይል ግን በመጨረሻ ወደ እንግሊዝ አገር ለጊዜው አሰደዳቸው። ወደ ጄኔቭ ስዊስ ወደ ዓለም መንግሥታት ማኅበር ሄደው ስለ ጣልያኖች የዓለምን እርዳታ በመጠየቅ ተናገሩ። የዓለም መንግሥታት ግን ብዙ አላደረጉም። በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ግን አውሮፓ ሁሉ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተያዘ። የእንግሊዝ ሠራዊቶች ለኢትዮጵያ አርበኞች እርዳታ በመስጠት ጣልያኖች ተሸንፈው በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ኢትዮጵያን ተዉ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ አዲስ አበባን እንደገና የገቡበት ቀን ከወጡበት ቀን በልኩ ዕለት አምስት ዓመት በኋላ ነበረ። ከዚህ በኋላ በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የሕዝቦችን መብቶችና ተከፋይነት በመንግሥት አስፋፍቶ ሁለቱ ምክር ቤቶች እንደመረጡ አደረገ። በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ግርማዊነታቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአዲስ አበባ እንዲመሠረት ብዙ ድጋፍ ሰጡ። በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ወደ ካሪቢያን ጉብኝት አድርገው የጃማይካ ራስታዎች ተገኛኙ። በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. በማርክሲስት አብዮት ደርግ ሥልጣን ያዙና እሳቸው በእሥር ቤት ታሰሩ። በሚከተለው ዓመት ከተፈጥሮ ጠንቅ እንደ አረፉ አሉ ፤ ሆኖም ለምን እንደ ሞቱ ስለሚለው ጥያቄ ትንሽ ክርክር አለ። ብዙ ራስታዎች ደግሞ አሁን እንደሚኖሩ ይላሉ። የዓፄ ኃይለ ሥላሴ የትውልድ ስም ልጅ ተፈሪ መኮንን ነው። ስመ-መንግሥታቸው ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነበር። ሞዓ አንበሣ ዘእምነገደ ይሁዳ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የሚለው የሰሎሞናዊ ሥረወ-መንግሥት ነገሥታት መጠሪያም በንጉሠ-ነገሥቱ አርማ እና ሌሎች ይፋዊ ጽሑፎች ላይ ከመደበኛው ማዕረግ ጋር ይጠቀስ ነበር። ጃንሆይ ፣ ታላቁ መሪ እና አባ ጠቅል በመባልም ይታወቁ ነበር።
የጣልያን ፋሺስት ጦር ኢትዮጵያን በመውረሩ ምክንያት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በስደት ስንት ዓመት ቆዩ?
አምስት ዓመት
678
አንበሳ አንበሳ ጡት አጥቢ የእንስሶች መደብ ውስጥ ሲሆን ግዙፍ ድመቶች ከሚባሉት 4 አራዊት አንዱ ነው። ከነዚህም መካከል ነብር ከሚባለው ግሥላ መሳይ አውሬ ቀጥሎ በቁመቱና ክብደቱ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አንበሳ ዛሬ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በህንድ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በታሪክ እስያና በደቡብ አውሮፓ እንደነበርና እንደጠፋ ይታወቃል። አንበሶች በጣም ቁጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሙጭሊትን ያህል ገራምና ተጫዋች ይሆናሉ። ሲጠግቡ በዝግታ የሚያንኮራፉ ቢሆንም እንኳ እስከ ስምንት ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሰማ በሚችል ኃይለኛ ድምፅ ሊያገሡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰነፎችና ልፍስፍሶች ይመስሉ ይሆናል፤ ሆኖም በሚያስገርም ፍጥነት የመንቀሳቀስ ችሎታ አላቸው። የሰው ልጅ፣ አንበሳ ባለው ድፍረት ለዘላለም ሲወሳ እንዲኖር አድርጓል፤ በመሆኑም ደፋር ሰው አንበሳ ተብሎ ይጠራል። አንበሶች በማኅበር ከሚኖሩት የድመት ወገን የሆኑ እንስሶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በትልልቅ መንጋ ተከፋፍለው የሚኖሩ ሲሆን እያንዳንዱ መንጋ ከጥቂት አባሎች አንስቶ ከ30 በላይ ሊደርስ ይችላል። አንድ መንጋ የጠበቀ ዝምድና ያላቸው በርከት ያሉ ሴት አንበሶች ይኖሩታል። አንድ ላይ ይኖራሉ፣ ያድናሉ እንዲሁም ይወልዳሉ። ዕድሜ ልካቸውን ሊዘልቅ የሚችለው ይህ የጠበቀ ትስስር ለመንጋው ጠንካራ መሠረት የሚጥል ከመሆኑም በላይ ለመንጋው ሕልውና ጥሩ ዋስትና ይሆናል። እያንዳንዱ መንጋ እየተዘዋወሩ የሚጠብቁና የመንጋውን የክልል ወሰን የሚያወጡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ለአካለ መጠን የደረሱ ወንድ አንበሶች ይኖሩታል። እነዚህ ዕጹብ ድንቅ የሆኑ አውሬዎች ከጥቁሩ የአፍንጫቸው ጫፍ አንስቶ እስከ ጭራቸው ጫፍ ድረስ ከሦስት ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን ከ225 ኪሎ ግራም በላይ ሊመዝኑ ይችላሉ። ቤተሰቡን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ወንዶቹ ቢሆኑም አመራር የሚሰጡት ግን ሴቶቹ ናቸው። ወደ ጥላ ሥፍራ መሄድን ወይም አደን መጀመርን በመሳሰሉት ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ መንጋውን ለአንድ ዓይነት እንቅስቃሴ የሚያነሳሱት ሴቶቹ አንበሶች ናቸው። ሴት አንበሶች በአብዛኛው በየሁለት ዓመቱ ይወልዳሉ። ግልገሎቹ በሚወለዱበት ጊዜ ምንም ዓይነት አቅም አይኖራቸውም። ግልገሎችን ማሳደግ የሁሉም የጋራ ሥራ ነው፤ በመሆኑም ሴቶቹ አንበሶች በሙሉ በመንጋው ውስጥ ያሉትን ግልገሎች ይጠብቃሉ እንዲሁም ያጠባሉ። የግልገሎቹ ዕድገት ፈጣን ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ መሮጥና መቦረቅ ይጀምራሉ። ልክ እንደ ሙጭሊቶች እየተንደባለሉ ይጫወታሉ፤ ከሚያጫውቷቸው ጋር ይታገላሉ፤ እንዲሁም በረጃጅሙ ሣር ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይዘላሉ። እያንዳንዱ የሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ ስሜታቸውን ይማርከዋል፤ ቢራቢሮዎችን ለመያዝ ይዘላሉ፣ ትናንሽ ነፍሳትን ያሳድዳሉ፣ ከየጭራሮና ከየሐረጉ ጋር ይታገላሉ። ይበልጥ ስሜታቸውን የሚማርከው ግን እነርሱን ለማጫወት እናታቸው ወዲያና ወዲህ የምታወናጭፈው ጭራዋ ነው። እያንዳንዱ መንጋ የሚኖርበት በደንብ የተከለለ ቦታ ያለው ሲሆን ይህ መኖሪያ ብዙ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ሊኖረው ይችላል። አንበሶች ውኃ እንደ ልብ ባለበትና ከቀትር ሐሩር የሚከላከል ጥላ በሚያገኙበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ መኖር ይመርጣሉ። በእንዲህ ዓይነቱ ሥፍራ ከዝሆኖች፣ ከቀጭኔዎች፣ ከጎሽና ከሌሎች ሜዳማ በሆኑ ሥፍራዎች ከሚኖሩ እንስሶች ጋር በአንድነት ይኖራሉ። አንበሳ አብዛኛውን ጊዜውን በእንቅልፍ ጥቂቱን ጊዜ ደግሞ በአደንና በተዋስቦ ያሳልፋል። እንዲያውም አንበሶች በቀን ውስጥ ወደ 20 የሚጠጋውን ሰዓት የሚያሳልፉት በዕረፍት፣ በመተኛት ወይም በመቀመጥ ነው። ከባድ እንቅልፍ ተኝተው ሲታዩ ሰላማዊና ለማዳ ይመስላሉ። ይሁን እንጂ በዚህ መታለል የለብህም፤ አንበሳ እጅግ ቁጡ ከሆኑት አራዊት መካከል አንዱ ነው!
የአንበሳ እንስሶች መደብ ውስጥ ከየትኛው መደብ ነው የሚመደበው?
ጡት አጥቢ
10
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ስብሐት (ስብሐት ለአብ) ገብረ እግዚአብሔር (ሚያዝያ 27 [1928]ዓ.ም. - ሰኞ፣ ቀን ትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደ ፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው። ስብሐት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ በመነን መጽሄት የዝግጅት ክፍል ውስጥ ሰርቷል። በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲቋቋም በአርታኢነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በመንግሥት ትእዛዝም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን የካርል ማርክስ ሥራ የሆነውን ካፒታልን ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመመለስ ሥራ ላይ ተሳትፏል። ብዙዎቹ የስብሐት ሥራዎች በተጻፉበት ጊዜ ለመታተም ባይታደሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የህትመትን ብርሃን ለማየት በቅተዋል። ጽሁፎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይታተሙ ለመቆየታቸው ዋነኛው ምክንያቱ ስብሐት በመጽሐፉ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ባህል ያደገ አንባቢን አይን የሚያስፈጥጡ፣ ጆሮ የሚያስይዙ በመሆናቸው ነው። በገበያ ላይ በቅርብ የወጡት ድርሰቶቹ ከመጀመሪያ ቅጂያቸው ብዙ ለውጥ እና የአርትኦት ሥራ የተደረገባቸው እንደሆኑ ይነገራል። ስለዚሁ ጉዳይ ለአዲስ ላይቭ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገር «በጨለማ ያልተደረገውን ነገር አንድም የጻፍኩት የለም... ያለውን እንዳለ ነው የምጽፈው» ብሏል። ይህንኑም ከኤሚል ዞላ የአጻጻፍ ዘይቤ የወሰደው እንደሆነ ይናገራል። ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ደራሲ፣ አርታኢ፣ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም - የልብ-ወለድ ድርሰት ገጸባህርይም ነው። ደራሲው የተሰኘው የበአሉ ግርማ ልብ-ወለድ በስብሐት ህይወት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው። ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች አባት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነው።
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር መቼ ተወለደ?
ሚያዝያ 27 [1928]ዓ.ም
46
በርግጥም የመጀመሪያው በሰፊው ተግባራዊ የሆነ የቴሌቭዥን ስርዓት ስራ ላይ የዋለው በጀርመን አገር ሲሆን ይኸውም በ1929 እ.ኤ.አ. ነው። በ1936 እ.ኤ.አ. (1928 ዓም) ጀርመን ሃገር ተደርጎ የነበረውን የኦሎምፒክ ውድድር በቴሌቭዥን ሊሰራጭ ቻለ፣ ህዝቡም ውድድሩን እቤቱ ሆኖ ቀጥታ ሲካሄድ ለማየት ቻለ። ከዚያ መጀመርያው ጥቁርና-ነጭ ፕሮግራሚንግ በዩናይትድ ኪንግደም 1928 ዓም፤ በአሜሪካ 1933 ዓም ተደረገ። በአፍሪካ መጀመርያው ጣቢያዎች በ1952 ዓም በናይጄሪያና ደቡብ ሮዴዝያ (አሁን ዚምባብዌ) ተሰራጩ፣ በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት (ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) የጀመረው በ1956 ዓም ሆነ። ሁለት አገራት - እነርሱም ቱቫሉና ኪሪባስ - ምንም የራሳቸውን ቴሌቪዥን አሁን አያሰራጩም፤ ሆኖም የሌላ አገር ስርጭት እዚያ ሊታይ ይችላል። ከዚያ ቤርድ በግንቦት 26 ቀን 1920 (ጁላይ 3, 1928 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የከለር ቴሌቪዥን ስርጨት ሙከራ አደረገ። ነገር ግን ከለር ቴሌቪዥን ቢፈጠረም ለሚከተሉት ብዙ ዓመታት ስርጭት ባብዛኛው ጥቁርና ነጭ ብቻ ሆኖ ቀረ። ይሄው ቴክኖዎሎጂው በጣም ውድ፣ በጣም ከባድና በትክክል ያልተስተካከለ ስለ ሆነ ነው። በየጥቂቱ ከ1946 ዓም (1954 እ.ኤ.አ.) ጀምሮ አገራት ወደ ከለር ስርጭትና ከለሩን ማሳየት የሚችል ቴሌቪዥን ወደ መሸጥ ይዛወሩ ጀመር። በጥር ወር 1946 ዓም NBC የተባለው አሜሪካዊ ስርጭት ጣቢያ በከፊሉ ወደ ከለር ተሸጋገረ፤ ብዙ ሰዎች ግን ያንጊዜ ከለር ማሳያ ቴሌቪዥን ለመግዛት ገና አልቻሉም ነበር። ከ1955 እስከ 1959 ዓም ድረስ ሌሎቹ ትልልቅ አሜሪካዊ ጣቢያዎች ABC እና CBS ደግሞ ወደ ከለር ተዛወሩ፣ የከለርም ተቀባዮች ዋጋ እየተቀነሰ የሚይዩት ሕዝብ ቁጥር ደግሞ ከዚህ በኋላ እየተጨመረ ሄደ፤ ከረጅሙ ጥቁርና-ነጭ ዘመን ቀጥሎ ከለርም በኅብረተሠብ ያመጣው ለውጥ ለግዙፍነቱ በኋላ ኢንተርኔት እንደ ሆነ ያሕል ነው። ጃፓን በ1952 ዓም፣ ሜክሲኮ በ1955፤ ካናዳ በ1958፣ የአውሮፓ ኅብረትና የሶቪዬት ሕብረት በ1959፣ ኮት ዲቯር በ1962፣ አውስትራሊያ በ1967 ከለር ስርጭትን ጀመሩ። በኢትዮጵያም ከለር ስርጭት ከ1976 ዓም ጀምሮ ተገኝቷል። በ1977 ዓም ሮማኒያ ከጥቁርና-ነጭ ስርጭት ወደ ከለር ማሰራጨት የለወጠ በዓለም መጨረሻው ሃገር ሆነ።
በአፍሪካ የመጀመሪያው የቴሌቪዥን ስርጭት የተደረገው የት ነው?
በናይጄሪያና ደቡብ ሮዴዝያ (አሁን ዚምባብዌ)
294
አዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዕውቁና አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ በውጭ አገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች ወጣቶችን በሳይንስ በማነጽ ተግባር እንዲሰማሩ፤ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር ጥላሁን በቻይና ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የአፍሪካ ሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል ሊያቋቁሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚዘጋጀው ወርኃዊ የሳይንስ ገለጻ መድረክ ወጣቱን ትውልድ ማስተማርና ማነጽ ለኢትዮጵያ ተስፋ፤ የቻይና ተምሳሌትነት በሚል ትናንት ምሽት ገለጻ አድርገዋል። በአውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 1943 በኢትዮጵያ የተወለዱት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች አጠናቀው በቀድሞው የአለማያ እርሻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት በኮሌጅ ቆይታቸው ባሳዩት የላቀ ውጤትም አሜሪካን አገር በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህር ቤት ተልከው ትምህርታቸውን በማጥናት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት አስተምረዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላም ወደ ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በደቂቀ ሥነ ሕይወት መስክ በማጥናት በአውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1980-2006 በተማሩበት ካሊፎርኒያ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አስተምረዋል፤ ተመራምረዋል። እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ደግሞ የዲስቲንጉሽድ ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.አ.አ ከ1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል በማቋቋም በዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ 3ኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት በምን ላይ ነው?
በደቂቀ ሥነ ሕይወት
833
ማርክ ትዌይን ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ ወይም በብእር ስሙ ማርክ ትዌይን አሜሪካ ካፈራቻቸው ድንቅ ጸሃፍት መካካል የሚመደብ ደራሲ ነው። ትዌይን በኖቬምበር 1835 ዓ.ም. ሚዙሪ በተባለችው የአሜሪካ ግዛት ተወለደ። 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር የኖረው ሃኒባል በተባለች እና ሚሲሲፒ ላይ በተቆረቆረች ትንሽ ከተማ-አከል ቦታ ነው። አባቱ በ1847 ሲሞት ትዌይን ትምህርቱን በማቋረጥ በማተሚያ ቤት ውስጥ በሰልጣኝነት ተቀጠረ። ይህን ስራውን በ1857 በመተው የእንፋሎት ጀልባ ነጂ በመሆን መስራት ጀመረ። በዚሁ ስራ በቆየባቸው አመታት ነው ኋላ ላይ አድናቆትን ላተረፉለት የስነ-ጽሁፍ ስራዎቹ የሚሆኑትን እውቀቶች ለማሰባሰብ የበቃው። እሱ ራሱም እንዳለው በዚሁ ስራ ላይ ነው "ማንኛውንም በልብ-ወለድ፣ በግለ-ታሪክም ሆነ በታሪክ ላይ ሊገኙ የሚችሉ የሰው ባህርያትን" ሊያጠና የበቃው። በ1861 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የእርስ-በርስ ጦርነት በመቀስቀሱ ምክንያት ማንኛውም አይነት የመርከብ ላይ ጉዞ ሲስተጓጎል ትዌይንም ስራውን ለመልቀቅ ተገዷል። ከዚህ በኋላም በውትድርና ወዶ-ገብነት፣ በወርቅ ማእድን ፈላጊነት፣ በጋዜጠኝነት ወዘተ ስረቷል። በ1869 ዓ.ም የመጀመሪያ ዋነኛ ስራው የሆነውን "The Innocents Abroad" ለማሳተም በቃ። ይኽ ድርሰት ክሌመንስ ራሱ በአውሮፓ እና በእየሩሳሌም ባካሄዳቸው ጉብኝቶች ላይ የተመሰረተ ነው። በ1870 ዓ.ም ኦሊቭያ ላንግዶንን በማግባት ኑሮውን ኮኔቲከት በተባለችው ግዛት አድርጓ በዛው ለ17 ዓመታት ኖሯል። በነዚህ 17 ዓመታት ነው አድናቆት ያተረፉለት ስራዎቹን ማለትም "Roughing It"፣ "The Adventures of Tom Sawyer"፣ Life on the Mississippi"፣ እና ከሁኡ የላቀ የተባለለት ድርሰቱን "The Adventures of Huckleberry Finn"ን ያሳተመው። ትዌይን በ1910 ዓ.ም አርፎ ሬዲንግ፣ ኮኔቲከት ውስጥ በድኑ አርፏል።
ከትዳር አጋሩ ጋር ኑሮውን ለ17 ዓመታት ያሳለፈባት ግዛት ማን ትባላለች?
ኮኔቲከት
820
ሮማንሽ ሮማንሽ ወይም ሩማንች (Rumantsch) ከስዊስ አገር 4 ብሔራዊ ቋንቋዎች 1ዱ ሆኖ ሌሎቹ 3 ጀርመንኛ ጣልኛና ፈረንሳይኛ ናቸው። ከሮማይስጥ የታደገ ቋንቋ በመሆኑ የሮማንስ ቋንቋ ቤተሠብ አባል ነውና በተለይ የሚመስለው ፈረንሳይኛ ወይም እጣልኛ ነው። የሚናገረው በግራውብውንደን (ግሪዞን) ካንቶን ስዊስ በሚኖሩ 60,000 ሰዎች ነው። ይህ ከስዊስ አገር ሕዝብ ብዛት 1% ብቻ ሲሆን ከስዊስ አገር ብሔራዊ ቋንቋዎች ሁሉ ትንሹ ነው። እንኳን በስዊስ አገር ከሚኖሩት ስርቦ-ክሮዌሽኛ ተናጋሪዎች ቁጥር ብዛት (111,000) በግማሽ ያንሳል። በስሜን እጣልያ አገር ዛሬ ለሚናገሩ ቋንቋዎች ለፍሪዩልያንና ለላዲን ቅርብ ዘመድ ነው።
ሮማንሽ ቋንቋ በስዊስ ምን ያህል ተናጋሪዎች አሉት?
60,000
202
በዚህ በ፲፭ኛው መቶ ዓ.ም. ላይ የቱርክ፣ የመስኮብ፤ የጀርመን፤ የእንግሊዝ፤ የፈረንሳይና የኤስፓኝ መንግሥታት እንደ ኃያላን መንግሥታት መቆጠራቸው አልቀረም። ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ የፖርቱጋል መንግሥት በሌላው እንኳን ባይሆን በመርከብና አገር በመያዝ ከቀሩት ይበልጥ ነበር። የቀሩት የኤውሮፓ መንግሥታት እዚያው ወሰናቸው ላይ ገዥነታቸውን ለማጽደቅ እርስ በርሳቸው ሲጨቃጨቁ የፖርቱጋል መንግሥት ግን ደኅና ደኅና መርከቦችን አዘጋጅቶ እየላከ ከመንግሥቱና ከኤውሮፓ ርቆ የሚገኘውን የአሜሪካን፤ የእስያን፤ የአፍሪካን አገሮች ያስመረምር ነበር። መርማሪዎቹም እነቫስኮ ደጋማ፤ እነፔሬዝ፤ እነአንድራድ፤ እነካብራል በመርከብ እየሄዱ ለመከላከል ጉልበት የሌለውንና በጠባዩ ሀብት ያለበትን አገር መርምረው ሲመለሱ መንግሥቱ ወታደር በመርከብ እየላከ ብዙ አገር ያዘ። በሚያዝያ ፳፩ ቀን ፲፭፻ እ.ኤ.አ. ፔድሮ አልቫሬዝ ካብራል የተባለው የፖርቱጋል መኮንን በትልቅ መርከብ ሄዶ ይን ጊዜ ለቀረው ዓለም ያልታወቀውን የብራዚልን አገር አስገበረና በፖርቱጋል መንግሥት ስም ቅኝ አገር አደረገው። ከዚያም አገር በተገኘው ወርቅ መንግሥቱ ሀብታም ሆነ። እንደዚሁም የመጀመሪያ የንጉሥ እንደራሴ የተባለው ፍራንቼስኮ ዳልሜዳ ወደ ህንድ አገር ሄዶ አገሩን ያዘ። ከተማውንም በጎአ አድርጎ ህንድንም የፖርቱጋል የቄሣር ግዛት አደረገና አገር ገዥውም የንጉሥ እንደራሴ ይባል ጀመር። ከዚያም በትልቁ ውቅያኖስ ውስጥ የሚገኙትን ደሴቶች ኑቤል ጉኔንና ዛሬ ፊሊፒን የሚባለውን አገር በየጊዜው በጦር ኃይል አስገበራቸው። በዚሁ አኳኋን ወደ ኢትዮጵያም እነኮቪልሐኦ ቀደም ብለው በዓፄ እስክንድር ዘመን መጥተው እንደመረመሩትና የኢትዮጵያ መንግሥት በዚያ ጊዜ በነሱ አጠራር የቄሱ የዮሐንስ መንግሥት አለ ብለው አውርተው እንደነበረ ሌላ የፖርቱጋል የጦር መርከብ በአፍሪካ ድንበር በቀይ ባሕር ላይም እየተመላለሰ አስቀድሞ ከያዙት ከቱርኮችና ከግብጾች እየተዋጋ አንድ ጊዜም እየተሸነፈ አንድ ጊዜም እያሸነፈ ብዙ ጊዜ ተመላለሰ። በዚህ ሁሉ ምክንያት የፖርቱጋል መንግሥት ታላቅነት በሌላው ዓለም እንደ ታወቀ እንደዚሁም ፩ኛ ትልቅ መንግሥት መሆኑ ፪ኛ ክርስቲያን መሆኑ ኢትዮጵያ ባሉት የውጭ አገር ሰዎች አፍ እየተነገረ ዝናው በኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት ዘንድ መሰማት ቻለ።
የመጀመሪያ የንጉሥ እንደራሴ የተባለው ፍራንቼስኮ ዳልሜዳ የያዛት ሀገር ማን ትባላለች?
ህንድ
695
ቦትስዋና ቦትስዋና ወይም በይፋ የቦትስዋና ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ Republic of Botswana ሰጿና፡ Lefatshe la Botswana) በደቡባዊ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ አገር ናት። ቦትስዋና የቀድሞ የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ስትሆን ነፃነቷን በመስከረም ፳ ቀን ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. ከተቀዳጀች በኋላ መሪዎቿ በነፃ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ተመርጠዋል። ቦትስዋና ሜዳማ ስትሆን ከሰባ ከመቶ በላይ በካለሃሪ በርሃ የተሸፈነች ናት። በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ከደቡብ አፍሪካ፣ በምዕራብና ሰሜን ከናሚቢያ እና በሰሜን ምሥራቅ ከዚምባብዌ ጋር ትዋሰናለች። ከዛምቢያም ጋር በደንብ ያልተወሰነ ቢበዛ በመቶ ሜትር የሚቆጠር ወሰን አላት።
ቦትስዋና በምዕራብና ሰሜን ምሥራቅ የምትዋሰነው ከማን ጋር ነው?
ከናሚቢያ
308
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በጥሩ ጎናቸው ከሚነሱ የቅርብ ጊዜያት ተጫዋቾች መካከል አዳነ ግርማ ይገኝበታል።ተጫዋቹ በበርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታንም ይዟል።አዳነ ግርማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን መነቃቃት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ተጫዋቹ በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ለ10 ዓመታት በመጫወትም አንጋፋ ለመሆን በቅቷል። አዳነ ግርማን ስናስብ ሁለት ጨዋታዎች ሁሌም ከፊታችን ድቅን ይላሉ።ደቡብ አፍሪካ ላስተናገደ ችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡደን ከሱዳን አቻው ጋር ሲጫወት በግንባሩ ገጭቶ ያስቆጠራት ግብ መቼም ቢሆን አዳነ እንዲታወስ ያደረገችም የምታደርግ ናት።ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ያረገችው ወሳኝ ግብም ሆናለች። በአፍሪካ ዋንጫው ከ 39 ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛምቢያ ላይ ያስቆጠራት ግብም አዳነን ሁሌም እንድናስበው ያረገች ሌላዋ ግቡ ናት። ተጫዋቹ ከዋልያዎቹ ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገና የቡድኑ ምሰሶ እንደነበርም ይታወቃል።በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዘመን አዳነ ቡድኑን በአምበልነት መርቷል። የአትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሰውነት ቢሻው የተረከቡት አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ቡድኑን እንደ አዲስ ሲያዋቅሩ አዳነ ግርማን መቀነሳቸው ሲሰማ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ ቅሬታ ቢፈጠርም፣ ተጫዋቹ ግን ውሳኔውን አሜን ብሎ ነው የተቀበለው። በወቅቱም አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ለተጫዋቹ መቀነስ ምክንያታቸው ያደረጉት የተጫዋቹ «ብቃትና አቅም ወርዷል» የሚል ነው። ተጫዋቹ ግን በወቅቱ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ያረጋገጠው ምንም አይነት የአቋም መዋዠቅም እንደሌለበት ነው። የብቃት መውረድ እንዳላሳየም ገልጿል። የመቀነሱ ሚስጥር ለሱም እንቆቅልሽ እንደሆነበት ነበር ያስታወቀው። ይህን ተከትሎ ራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው አዳነ በአዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሰሞኑን ጥሪ ተደርጎለት ነበር:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ በአጥቂ እጥረት ላይ ቢገኝም አዳነ ግርማ ከቤተሰቦቼ ጋር ተመካክሬ የወሰንክይት ውሳኔ ነው በሚል ለብሔራዊ ቡድኑ እንደማይጫወት አስታውቋል:: በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሁለት የተደለደለውና በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጀሪያ አቻው ጋር ላለበት የምድቡ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን መጥራቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ሁለት ተጫዋቾችን ከአገር ውጭ ቀሪዎቹን 22 ደግሞ ከአገር ውስጥ ሊጎች የመረጡ ቢሆንም የአዳማ ከነማው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ባጋጠመው ጉዳት ከቡድኑ ውጭ ሆኗል። እርሱን ለመተካት ሳልሃዲንና አዳነን ቢጠሩም እምቢ ተብለዋል:: ሆኖም ግን አሰልጣኙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የመረጧቸውን አምስት ተጫዋቾችና ከአገር ውጭ ከሚጫወቱት ሕመልስ በቀለና ጌታነህ ከበደ በስተቀር 15 ተጫዋቾችን ይዘው ልምምዳቸውን ዛሬ ጀምረዋል።
አዳነ ግርማ ኢትዮጵያ ስንተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ከዛምቢያ ጋር ስትጫወት ግብ አስቆጠረ?
29ኛው
279
በሊትር እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ የምትችል ተሸከርካሪ በኢትዮጵያዊ ወጣት መሰራቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ነዋሪ የሆነው ታዳጊ አጃዬ ማጆር ተሸከርካሪዋን ከወዳደቁ ብረቶች እንደሰራት ተነግሯል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባደረገለት ድጋፍ የተሰራችው  የባለ ሁለት እግር ተሸከርካሪ ሞተርን በመጠቀም የተሰራች ሲሆን ወደ ኋላ መሄድ እንድትችል ተደርጋ ተሻሽላ ተሰርታለች፡፡ አራት ኩንታል ክብደት ያላት ተሽከርካሪዋ እስከ 4 ሰዎች የመጫን አቅም ያላት ሲሆን በአንድ ሊትር እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች ተብሏል፡፡ ታዳጊው የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ መኪና መስራቱ ተገልጿል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለታዳጊው የተለያዩ ድጋፎችን  እንደሚያደርግ  ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በኢትዮጵያዊው ወጣት የተሰራው ተሽክርካሪ በሊትር ስንት ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል?
40 ኪሎ ሜትር
10
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር፣ በጠላት ወረራ ዘመን የተመሠረተ ድርጅት ሲሆን፤ እስከ አሁን ድረስ ያሉት አዛውንት አባላቱ በዚያው የአምሥት ዓመት ትግል ዘመናት፣ መኳንንቱ፤ የጦር መሪዎቻቸውና ንጉሠ ነገሥቱም ጭምር እነዚያን ወጣት ኢትዮጵያውያን አንጀታቸውን ለረሀብ፤ እግራቸውን ለሾኽ ለጠጠር፤ ግንባራቸውን ለእርሳስ አጋልጠዋቸው በካዷቸው መራር ዘመን፤ ሞትም ቢመጣ እናት አገራችንን አሳልፈን ለጠላት አንሰጥም፤ ነፃነታችንን ለጊዜያዊ ሹመት፣ ሽልማት አንለውጥም ብለው የተጋፈጡ ጀግኖች ናቸው። ደጃዝማች ከበደ ተሰማ፤ “የታሪክ ማስታወሻ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ፤ ይህ ማኅበር በአርበኝነት ዘመን በሸዋ ክፍለ ሀገር በ፲፱፻፴፩ ዓ/ም «የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ማኅበር» በሚል ስም ተሠይሞ የተቋቋመ ማኅበር እንደነበርና ዓላማውም «የአርበኞችን ክብ በማበረታታትና በየሀገሩ ካሉ አርበኞች ጋር በመላላክ የሚገኘውን ሥራ ፍሬ» እርስ በርስም ሆነ በስደት ላይ ከነበሩት ንጉሠ ነገሥት ጋርም መካፈል እንደነበር ይገልጻሉ። ከመሥራች ማኅበረተኞቹ በከፊሉ፦ ራስ አበበ አረጋይ፤ ወንድማማቾቹ ደጃዝማች ፀሐዩ እና ደጃዝማች ተስፋዬ ዕንቁ ሥላሴ፤ አቶ እምአእላፍ ኅሩይ፤ ደጃዝማች ኃብተ ሥላሴ በላይነህ፤ ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያት ይገኙባቸዋል። በመጀመሪያ ጊዜ የነበሩት መሥራቾች ሃያ ዘጠኝ አባላት ሲሆኑ በኋላ ጊዜ ግን ብዙ ማኅበረተኞች እየተጨመሩ የአባሎቹ ቁጥር ከሦስት መቶ በላይ ሆኖ ነበር። የጠላት ኃይል ተሸንፎ የአገሪቱ ነፃነት ከተመለሰ በኋላ፣ አርበኞቹ በየአውራጃውና በየጠቅላይ ግዛቱ ተሰማርተው ስለነበረና ማኅበሩም በመከራው ዘመናት የተቋቋመበት ዓላማ በነፃነት ጊዜ አላስፈላጊ በመሆኑ፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ማኅበር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሳያሳይ ብዙ ዓመታት አሳለፈ። ሆኖም በሚያዝያ ወር ፲፱፻፶፬ ዓ/ም ጄኔራል ነጋ ኃይለ ሥላሴ «ከሥራ ባልደረቦቻቸውና ከዕውቅ አገር አፍቃሪዎች ጋራ፥ "ጥንታዊት ኢትዮጵያ ሀገራዊ የዠግኖች ማኅበርን" በታደሰ ሀገራዊ ዓላማና በተሻሻለ ደንብ አቋቋሙ። ኾኖም፥ ድርጅቱ እስከ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ/ም ድረስ ከመንግሥት ዕውቅናን ስላላገኘ ሥራው በዚሁ ምክንያት ለጊዜው ተገታ።» ጄኔራል ነጋ በዚህ ዕለት ሕጋዊ ዕውቅና ያገኘውንና ለፍጹም ሰላማዊና ሀገራዊ ዓላማ፤ ለበጎ አድራጎት የተጀመረውን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ሀገራዊ የዠግኖች ማኅበር፤ ጠቅላይ ሥራ አመራር ሸንጎ ሊቀ-መንበር ኾነው የማኅበሩን ሥራ በሰፊው በማንቀሳቀስ ባጭር ጊዜ ውስጥ ፬ሺ የፈረሙ አባላትን ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ እንዳስገኙ፥ አሁንም መንግሥታዊ እንቅፋት ገጥሞት ከሕገ-ወጥ በሆነ እርምጃ ፥ የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት በጸጥታ ኀይሎች እንዲዘጋ ተደረገ።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር የተዘጋበት ምክንያት ምንድን ነው?
ከመንግሥት ዕውቅናን ስላላገኘ
1,212
የማይዳሰሱ (ኢንታንጀብል) ባህላዊ ቅርሶችን የሚመለከተው የዩኔስኮ አካል በይነ መንግሥታዊው ኮሚቴ 10ኛ ስብሰባውን ከኅዳር 20 እስከ ኅዳር 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በናሚቢያ መዲና ዊንድሆክ በተደረገው 10ኛ የዩኔስኮ ጉባዔ ለውሳኔ ከቀረቡት 35 (ሠላሳ  አምስት) ባሕላዊ ቅርሶች መካከል የሲዳማ ብሔር የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ የሆነው ፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ የ2003 የኢንታጀብል ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ዓለም አቀፍ ስምምነት መስፈርቶችን አሟልቶ በመገኘቱ አባል አገሮች ውይይት ካደረጉበት በኋላ ፍቼ ጫምባላላ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ከመስቀል በዓል ቀጥሎ የኢትዮጵያ ሁለተኛው የማይዳሰስ ዓለም አቀፍ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ ሕዳር 22 ቀን 2008 ዓ.ም በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር 9፡40 በፋይል ቁጥር (01054) በውሳኔ ቁጥር 10.com.10.b.16 ተመዝግቧል፡፡ በ2004 በጀት ዓመት የመስቀል በዓል አከባበርን በዩኔስኮ ማስመዝገብ የሚያስችል የጥናት ሰነድ ተዘጋጅቶ ለዩኔስኮ የተላከ ሲሆን በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ከህዳር 23-28 ቀን 2006 ዓ.ም በተካሄደው 8ኛው የዩኔስኮ የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ የኢንተርገቨርንመንታል ኮሚቴ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔ መሰረት የመስቀል በዓል አከባበር በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡ በ2006 የበጀት ዓመት የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው ፊቼ ጫምበላላን በሰው ልጆች ወካይ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ የሚያስችል የጥናት ሰነድ (ኖሚኔሽን ፋይል) ተዘጋጅቶ ለዩኔስኮ የተላከውና ህዳር 22 ቀን 2008 ዓ.ም የተመዘገበው የተደረገው  ፊቼ ጫምበላላ ሰነዶች በሚከተለው የዩኔስኮ ድረ ገጽ ላይ ለመላው ዓለም ተለቀው ይገኛል፡፡ በተመሳሳይም በ2007 የበጀት ዓመት ኦሮሞ ህዝብ የማንነት መገለጫ የሆነው የገዳ ስርዓትን በሰው ልጆች ወካይ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ለማካተት የሚያስችል የኖሚኔሽን ሰነድ ተዘጋጅቶ ለዩኔስኮ መጋቢት 2007 ዓ.ም ተልኳል፡፡
የተመዘገበበት የፋየል እና የውሳኔ ቁጥር ስንት ነው?
በፋይል ቁጥር (01054) በውሳኔ ቁጥር 10.com.10.b.16 ተመዝግቧል፡፡
461
ባሕር-ዳር ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች። ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎሜትር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት። ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ "ከባሕሩ-ዳር" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል። ባሕር-ዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕር-ዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር-ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር-ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር-ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ።
ባሕር ዳር ከተማ ከጣና ሐይቅ በየትኛው አቅጣጫ ትገኛለች?
ደቡባዊ
121
ጨኖ ጨኖ ግራጫ ቢጤ የሆነ፣ ፈርጠም ያለ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ አፍሪቃ፣ በተጨማሪም በኮንጎ ደኖች የሚገኝ ዝንጀሮ ነው። በኢትዮጵያ የሚገኘው ዓይነት ጨኖ የፀጉሩ ቀለም ግራጫና ጥቁር የሆነ፣ ፊቱ የጠቆረ ሰማያዊ የሆነ፣ አገጭና አንገቱ ነጭ ነው። የወንዶቹ ክብደት እስከ 12 ኪ.ግ. ሲሆን፤ አማካዩ 4.5 ኪ.ግ ይመዝናሉ። ጨኖ የደን ዝንጀሮ ነው። የደን ዝንጀሮች ብዙ ጊዜ ከዝናባማ ሥፍራዎች ደኖች ውጪ አይገኙም። ጨኖ ግን ከነዚህ ደኖች ውጪም በሚገኙ ደኖች ውስጥ ይኖራል። በኢትዮጵያ፣ በጎደሬ ደን ውስጥ፣ ቴፒ አጠገብ ሜጢ አካባቢ ይገኛሉ። በተራራማ ሥፍራዎች ደኖችም እስከ 3000 ሜትር ከፍታ ድረስ ይገኛሉ። እጅጉን በዛፍ ላይ የሚገኝ ዝንጀሮ ነው። የሚገኘው በደን ዛፎች ግማሽ ላይ ነው። በተለያዩ ዓይነት ተግባሮች መገለጫ የሚሆኑ ሰባት ዓይነት ድምፆች አሏቸው። በቡድናቸው ውስጥ የሚታየው አብዛኛው ፀብ፣ በዋናው ወንድና ለአካለ መጠን ባልደረሱና ጎረምሳ ወንዶች መሃል የሚታየው ነው። በሴቶቹና ሕፃናትን በሚገድሉ ወንዶች መኻከል ከባድ ግጭት ያድጋል። በቡድኖች መኻከል የሚደረግ ግጭት የሚሆነው አልፎ አልፎ ነው። እንዲህ ያለ ግጭት የሚነሳው በድንበር አካባቢ በምግብ ሽኩቻ የተነሳ ነው። የእርግዝና ጊዜአቸውን 140 ቀን ነው። የልጆቻቸውን እድገትም ቀስ ያለ ነው። ከወለዱ ወዲያ ለሚቀጥለው እርግዝና 15 ወራት መቆየት አለባቸው።
ጨኖዎች ከወለዱ በኃላ ለቀጣይ እርግዝና ምን ለያህል ጊዜ መቆየት አለባቸው?
15 ወራት
771
ሳህሌ ደጋጎ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል። በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ መሆኑን የሕይወት ታሪኩ ላይ ተጠቅሷል። ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ (በተቋቋመ ጊዜ ) በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁር ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር። ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ፣ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል።
ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ በ1942 ዓ/ም የት ተቀጠሩ?
ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ
237
ቱርክ በዊኪፒዲያ ላይ ላለፉት ሶስት ዓመታት ጥላው የነበረውን እገዳ በማንሳት ተጠቃሚዎች ድረ ገፁን ማግኘት እንዲችሉ ፈቀደች። የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት እገዳው የመናገር መብትን ይጥሳል ሲል እግዱ እንዲነሳ ውሳኔ አሳልፏል። ዊኪፒዲያ በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 2017 የቱርክን መንግስት የሚተች ፅሁፍ ለማንሳት ፈቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ የቱርክ መንግስት እገዳ ማሳላፉ ይታወሳል። በወቅቱ በዊኪፒዲያ ላይ የሰፈረው ፅሁፍ የቱርክ መንግስት ከአይ ኤስ እና አል ቃይዳ ጋር ትብብር አለው የሚል መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። ይህንን ተከትሎም እገዳው ላለፉት 991 ቀናት ተግባራዊ ሆኖ መቆየቱን የኢንተርኔት ክትትል ተቋም የሆነው ኔትብሎክስ አስታውቋል። እገዳው በሂደት ቀስ በቀስ የሚነሳ በመሆኑ እና የተወሰኑ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ዊኪፒዲያን ለመመለስ እየሰሩ በመሆኑ በቱርክ የሚገኙ ሁሉም ተጠቃሚዎች ድረ ገፁን ማግኘት አይችሉም ተብሏል፡፡ ዊኪፒዲያ በበርካታ የዓለም ሀገራት ሳንሱር የሚደረግ ሲሆን በቻይና አሁንም ታግዶ ይገኛል።
የኢንተርኔት ክትትል ተቋም ማን ይባላል?
ኔትብሎክስ
399
ኒኑስ ኒኑስ በጥንታዊ የግሪክ ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ የነነዌ መስራችና የአሦር ንጉስ ነበረ። ለዘመናዊ ሥነ ቅርስ የታወቀ አንድ ግለሰብ አይመስልም፤ ዳሩ ግን የአያሌ ታሪካዊ ወይም አፈ ታሪካዊ ግለሰቦች ትዝታ በአንድ ስም በግሪኮች በኋለኛ ዘመን እንደ ተዘከረ አሁን ይታስባል። የንጉሥ ኒኑስና ሚስቱ ንግሥት ሴሚራሚስ ስሞች በጽሁፍ መጀመርያ የተገኘው ክቴስያስ ዘክኒዱስ (400 ዓክልበ. ገዳማ) በጻፈው በፋርስ አገር ታሪክ ነው። ክቴስያስ ለ2 አርጤክስስ (2 አርታሕሻጽታ) የመንግሥት ሀኪም ሆኖ የፋርስ ነገሥታት ታሪካዊ መዝገቦች አንብቤያለሁ ብሎ አሳመነ። ከዚህ በኋላ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ የክቴስያስን ወሬ አስፋፋ። የአለም ታሪክ ሊቃውንት እስከ 1880ዎቹ ድረስ የኒኑስ ታሪክ ዕውነት መሆኑን ይቈጠሩት ነበር። በዚያን ጊዜ የኩኔይፎርም ጽሕፈት ፍች ስለ ተፈታ፣ በሜስፖጦምያና በነነዌ ብዙ ቅርሶችም በመገኘታቸው፣ የአሦር ትክክለኛ ታሪክ ዕውቀት ተጨመረልን። ኒኑስ የቤሉስ ወይም ቤል ልጅ ተባለ፤ ይህም ምናልባት በሴማዊ ቋንቋ ሥር «ባል» (ጌታ) የመሰለ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። በካስቶር ዘሮድስ ዘንድ ኒኑስ ለ52 ዓመታት ነገሰ፤ ክቴስያስም እንዳለው መጀመርያው ዓመተ መንግሥቱ 2198 ዓክልበ. ነበረ። በ17 አመታት ውስጥ ኒኑስ በአረቢያ ንጉስ አርያዎስ እርዳታ ምዕራብ እስያን በሙሉ እንዳሸነፈ ተብሏል። ከዚህ ቀጥሎ የአርመን ንጉስ ባርዛኔስን (ይቅርታ የሰጠውን) እና የሜዶን ንጉስ ፋርኖስን (በስቅለት ይሙት በቃ የሰጠውን) ድል በማድረግ የአለም መጀመርያ ንጉሠ ነገስት እንደ ሆነ ተብሏል።
የኑኒስ ሚስት ማን ትባላለች?
ንግሥት ሴሚራሚስ
188
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012(ኤፍቢሲ) ቻይና በዋና ከተማዋ ቤጂንግ እና በሀቤይ ግዛት ዘሃንግጃኩ መካከል የተዘረጋውን ፈጣን ባቡር ለገልግሎት ክፍት ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል። ቻይና የፈጣን ባቡሩን ለአገልግሎት ክፍት የምታደርገው በአውሮፓውያኑ 2022 የምታስተናግደውን የክረምት ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ተነግሯል። ፈጣኑ ባቡር በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን፥ በዓለማችን ላይ የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ ባቡር እንደሚሆንም ተነግሮለታል። የ 174 ኪሎ ሜትር ያለው የባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቱ ለ2022 የክረምት ኦሎምፒክ እና የፓራሎምፒክ  ታስቦ የተሰራ መሆኑም ታውቋል። የባቡር መስመሩ የክረምት ኦሎምፒኩን በሚያስተናግዱት በሁለቱ ከተሞች መካከል የነበረውን የ3 ሰዓት መንገድ ወደ 47 ደቂቃ የሚቀንስ መሆኑ የቻይና ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል። ምንጭ፦ newsus.cgtn.com
የቻይና ዋና ከተማ ማን ናት?
ቤጂንግ
42
አባይ ሀገሬው አባይ ብሎ ይጠራዋል፣ አባይ ማለት ታላቅ ማለት ነው። ከወንዞች ሁሉ አብይ ነው። የበኩር ልጅን አባይነህ ይሉታል ታላቅ ነህ ማለታቸው ነው። አባይ ከወንዞች ሁሉ ታላቁ ነው። የቀዬው ሰው አባይ ብሎ በአክብሮት ይጥራው እንጂ፣ ስሙ ግዮን ነው። ግዮን በመፅሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት ምዕራፍ ሁለት ቁጥር 10 እና 13 ላይ ከኤደን ገነት ከሚወጡት አራት ወንዞች አንዱ ሆኖ ተፅፏል። ይህ ወንዝ የኢትዮጵያን ምድር ይከብባል ሲልም ይናገራል። ግዮን የሚለው ቃል የግዕዝ ሲሆን በዕብራይስጥ ጊሖን፣በፅርዕ (ግብፅ) ጌዖን ይባላል። ትርጓሜውም “ዘየሐውር፡ በኃይል፡ ወይርም በድምፀ ማዩ ዐቢይ ወግሩም ማለት ነው።” ወደ አማርኛ ሲገለበጥ “ የውሃውን ብዛት፣ የመልካውን(የወንዙን) ስፋት፣ያካሄዱን ኅይል፣ የጩኸቱን ግርማ፣ ፏፏቴውንና ተመማውን(አፈሳሰሱ)፣ ድምፁ እንደ ነጎድጓድ መሆኑን ያሳያል”። ባለፉት 6 ሚሊዮን ዓመታት በተለያዩ የመሬት ነውጦች ምክንያት የአባይ ሸለቆ ብዙ ጊዜ ተቀያይሯል። Eonile የተፈጠረው ከ5.4 ሚሊዮን ዓመት ገደማ የሜዲትራኒያን ባሕር ተኖ ኃይለኛ ዝናብ በመከሰቱ ምክንያት በወረደው ዝናብ ነው። ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ይፈስ የነበረው አባይንኳ ከ 5 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በተከሰተ የመሬት መናድ ምክንያት አቅጣጫውን ቀይሮ ወደሰሜን መፍሰስ ጀምሯል። የጣና ሐይቅን የፈጠረው እሳተ ገሞራም የዛሬ 2.6 ሚሊዮን ዓመት የተከሰተ ነበር። ከሕንድ ውቅያኖስ የሚነሳው እርጥበታማ አየር በኢትዮጵያ ተራራማ ክፍል ሲያልፍ የሙቀት መጠኑ እየቀዘቀዘ ይመጣል። ጉም ምድርን እንደሚያጠጣ፣ ያም ከሕንድ ውቅያኖስ የነፈሰው እርጥበት አዘል አየር፣ ሳይዘንብ የግሸንን ተራራን ያጠጣል። ከግሸን ተራራ ስር፣ ከሰቀላ ወረዳ የፈለቀው ምንጭ በግሸን ሜዳ ላይ ግልገል አባይን ሆኖ ይፈሳል። ግልገል አባይ, በግሸን ሜዳ ላይ ሮጦ ከጣና ሐይቅ ሲስርግ በጣና ተውጦ አይቀርም። በጣና ላይ ተንሳፎ፣ ወደ አባይ ሸጥ ይንደረደራል። አባይ ከጣና ወጥቶ አርባ ኪሎ ሜትር ከተጓዘ በኋላ የአባይ ፏፏቴጋ ሲደርስ 37 ሜትር ቁልቁል ቋጥኝ ላይ ይፈጠፈጥና ሽቅብ አየሩ ላይ ተበትኖ ዳግም ቁልቁል ይወርድና ጥልቀቱ 1200 ሜትር፣ ስፋቱ 24ኪ.ሜ ወደሆነው የአባይ ሸለቆ ውስጥ ይገባና በታላቁ የአባይ ገደላማ ሸለቆ፣ በእናቱ በኢትዮጵያ ሆድ ውስጥ 800 ኪሎ ሜትር ይጓዛል። ይህ ዑደት ላለፉት 5000 ዓመታት አልተለወጠም። በ460 ታሪክ ፀሐፊው ሔረዶቱስ አባይ ከሁለት ትላልቅ ተራሮች እንደሚፈልቅ ያምን ነበር። በኋላም ንጉሠ ነገሥት ኔሮ፣ አሽከሮቹ የአባይን ወንዝ እንዲከተሉ ትዕዛዝ ሰጥቷቸው መልዕክተኞቹ የሱዳን ከተማ የሆነችው ሲናር ሲቲ ከሚገኘው የሱድ ማጥ ደርሰው አባይ ከዛ ነው የሚመነጨው የሚል መልስ ይዘው ተመለሱ። ከአራተኛው እስከ አሥራ ሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የኢትዮጵያ ተራሮች የአባይ መፍልቂያ መሆናቸውን የገመተ የውጭ ዜጋ አልነበረም።
አባይ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸው ምንጩ ከየት ነው?
ከኤደን ገነት
207
ሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው። ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ የእንግሊዝን አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ። ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በሩሲያኖች የተገነባው የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ እራሳቸውን ከሥልጣናቸው አስወገዱ። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - አቶ ለገሰ ዜናዊ አስረስ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አድዋ ላይ ተወለዱ።
በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ያከተመው መቼ ነው?
፲፱፻፴፯ ዓ/ም
467
ኤንመርካር ኤንመርካር በሱመር (ሳንጋር) ነገስታት ዝርዝር ዘንድ የኡሩክ (ኦሬክ) ከተማ መስራች ነበረ። በዚያ ዝርዝር ጽህፈት 420 (ወይም በሌላ ቅጂ 900) ዓመታት እንደ ነገሰ ይላል። ደግሞ አባቱ የኡቱ ልጅ መስኪያጝካሸር ወደ ባሕር ገብቶ ኤንመርካር መንግስቱን ከኤአና ከተማ እንዳመጣ ይጨምራል። የኤንመርካር ስም በሌላ የሱመር ጽሑፍ ደግሞ ተገኝቷል። «ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ» በተባለው ተረት እሱ የኡቱ ልጅ ይባላል። (ኡቱ በሱመር እምነት የጸሓይ አምላክ ነበር።) ይህ ተረት የሰው ልጅ ልሳናት መደባለቁን ይናገራል። ኡሩክን ከመመስረቱ በላይ ታላቅ መስጊድ በኤሪዱም እንዳሰራ ይተረታል። ለመሆኑም፣ አራታ እንዲገዛለት የሚለው መልእክት በአፍ መናገር ስለሚከብድ፣ ኤንመርካር ጽሕፈት በሸክላ ጽላት ላይ መጻፍ እንደ ፈጠረ ይላል። በተጨማሪ በዚሁ ጽሑፍ ኤንመርካር የዙሪያው አገሮች ልዩ ልዩ ልሳናት እንደገና አንድ እንዲሆኑ ይጸልያል። እነዚህ አገራት ሹቡር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙርያ) እና የማርቱ አገር ናቸው። ከዚህ በላይ የኤንመርካርን መንግሥት የሚገልጹ ሦስት ተጨማሪ ጽሑፎች አሉ። «ኤንመርካርና ኤንሱሕጊርዓና» የሚባል ተረት የኤንመርካርና የአራታ መቀያየም ሲገልጽ፣ ሐማዚ ተሸንፎ እንደ ነበር ይጠቅሳል። በ«ሉጋልባንዳ በተራራ ዋሻ»፣ ኤንመርካር በአራታ ላይ ዘመቻ ሲመራ ይታያል። አራተኛውና መጨረሻውም ጽላት፣ «ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ» ኤንመርካርና ሠራዊቱ በአራታ ዙሪያ ለ1 አመት እንደ ከበቡት ይላል። ለመሆኑ ኤንመርካር 50 አመት ከነገሰ በኋላ፣ የማርቱ ሕዝብ (አሞራውያን) በሱመርና በአካድ ሁሉ ተነሥተው ኡሩክን ለመጠብቅ ግድግዳ በበረሃ መስራት እንደ ነበረበት ይጠቅሳል። በነዚህ መጨረሻ 2 ጽላቶች፣ ከኤንመርካር ጦር አለቆች አንድ የሚሆን ሉጋልባንዳ የሚባል ሰው ይተረታል። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ይህ ሉጋልባንዳ «እረኛው» ኤንመርካርን ወደ ኡሩክ ዙፋን ተከተለው። ይህ ሉጋልባንዳ ደግሞ በጊልጋመሽ ትውፊት በተባለው ግጥም ዘንድ የኋለኛው ኡሩክ ንጉሥ የጊልጋመሽ አባት ነበረ። ዴቪድ ሮኅል የሚባል አንድ የታሪክ ሊቅ የኤንመርካርና የናምሩድ ተመሳሳይነት አመልክቷል። «-ካር» የሚለው ክፍለ-ቃል በሱመር ቋንቋ ማለት «አዳኝ» ነው። ኡሩክ ከተማ የተመሠረተ በኤንመር-ካር ነበር ሲባል፣ ደግሞ ናምሩድ፣ አዳኝ፣ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 10 ዘንድ ኦሬክን ሰራ። በሌላ ትውፊቶች ዘንድ ይህ ናምሩድ የባቢሎን ግንብ መሪ የሆነ ነበር። በተጨማሪም አቶ ሮህል የኤሪዱ መጀመርያ ስም «ባቤል» እንደ ነበር ያምናል፤ እዚያም የሚገኘው የግንብ ፍረስራሽ የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ መሆኑን ገመተ። «ባቢሎን» ማለት የኤሪዱ መጠሪያ እንደ ነበር የሚል ማስረጃ በሌሎችም ጥናቶች አለ። ሮማዊው ጸሐፊ ክላውዲዩስ አይሊያኑስ በጻፈ አንድ ትውፊት ዘንድ (200 ዓ.ም. ግድም)፣ የባቢሎን ንጉስ «ኤወኮሮስ» የተከታዩን «ጊልጋሞስ» አያት ይባላል። ይህ «ጊልጋሞስ» ማለት የኡሩክ ንጉስ ጊልጋመሽ መሆኑን የአሁኑ ሊቃውንት ስለ ገነዘቡ፣ እንዲሁም «ኤወኮሮስ» ማለት ኤንመርካር ሳይሆን አይቀርም የሚል አስተሳሰብ ያቀርባሉ። ከዚህ በላይ የከላውዴዎን ታሪክ ጸሐፊ ቤሮሶስ በጻፈው ዝርዝር መሰረት፣ ከማየ አይህ ቀጥሎ የከላውዴዎንና የአሦር መጀመርያው ንጉስ «ኤወኮዮስ» ይባላል፤ ስለዚህ የዚሁ «ኤወኮዮስ»ና የናምሩድ መታወቂያ አንድ ናቸው የሚለው አሳብ ለረጅም ዘመን የቆየ ነው።
በሱመር እምነት መሰረት ኡቱ ምንድን ነው?
የጸሓይ አምላክ
285
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
የድንጋይ ዘመን አዳኞች በዚምባቡዌ ከስንት ዓመት በፊት ይኖሩ ነበር?
ከአምስት ሺህ
217
ከዛሬ ፶00 ዓመት በፊት የሶሎሞን ስረወ መንግስት ሸዋ (መንዝንና ተጉለት) ላይ  ሆኖ ለረጅም ዘመን ኢትዮጵያን ካስተዳደረ በሁዋል  የግራኝ መሃመድ ወረራ በአጼ ልብነድንግል ዘመን ተካሄደ።  ኢትዮጵውያን በግራኝ መሃመድ ወረራ የተነሳ ከፖርቱጋሎች ጋር ግንኙነትን መሰረቱ፡ በ፩፮፴ ተጀምሮ ለረጅም ጊዜ የተካሄደው ግጭት ከውጪ የመጡትን ሚሲዮናዊያን በሙሉ ከኢትዮጵያ በማባረር ሰላም ተመልሷል፡፡ ይህ የከፋ የግጭት ጊዜ ኢትዮጵያ የውጭ ክርስትያኖች ላይ እና አውሮፖውያኖች ላይ እስከ ሀያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ፊቷን እንድታዞር አስተዋጾ ከማድረጉም በተጨማሪ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ ከመላው አለም ተገልላ እንድትቆይ አድርጓታል፡፡ ከ1700 ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አገዛዝ ሳይኖሯት ቆይታለች፡፡ ይህም “ዘመነ መሳፍንት”  ሲሆን በ1869 አፄ ቴዎድሮስ መሳፍንቶቹን ሁሉ አስገብረው ኢትዮጵያን አንድ አድርገዋል
ኢትዮጵያን ለረጅም ዘመን ያስተዳድር የነበረው የሰለሞን ስርወ መንግስት መቀመጫው በየት ነበር?
ሸዋ (መንዝንና ተጉለት)
32
አማ አታ አዪዶ ክሪስቲና አማ አታ አዪዶ በማርች 23፣ 1942 እ.ኤ.አ. ጋና ውስጥ ተወለደች። ትምህርቷን በዌስሊ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት፣ በመቀጠልም በጋና ዩኒቨርስቲ ተከታትላ በ1964 ዓ.ም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች። የመጀመሪያ የድርሰት ስራዋ የሆነውን «The Dilemma of a Ghost»ን በዚያ ዓመት ለማጠናቀቅ የበቃች ሲሆን ይሄው ድርሰቷ በሎንግማን አሳታሚ ድርጅት አማካይነት በቀጣዩ ዓመት ታትሞላታል። አዪዶ በልብ-ወለድ ደራሲነት ብቻ አይደለም እውቅናን ያተረፈችው፤ በጸሃፌ-ተውኔትነት እና ገጣሚነትም እንጂ። ጽሁፎቿ በአብዛኛው የዘመኑ የአፍሪካ ሴቶች ስላላቸው ሚና እና የምእራባዊው ባህል ስለሚያሳድርባቸው ኢርቱእ ተጽኖ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው። አዪዶ በ1982 የጋና የትምህርት ሚኒስትር ሆና ብትሾምም በስራው ላይ የቆየችው ለ18 ወራት ያህል ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት በብራውን ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ጥናት ክፍል ውስጥ ተጋባዥ ፕሮፌሰር በመሆን ትሰራለች።
አማ አታ አዪዶ ክሪስቲና የመጀመሪያ ዲግሪዋን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያገኘችው በስንት ዓመተ ምህረት ነው?
በ1964 ዓ.ም
117
ሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው። ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ የእንግሊዝን አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ። ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በሩሲያኖች የተገነባው የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ እራሳቸውን ከሥልጣናቸው አስወገዱ። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - አቶ ለገሰ ዜናዊ አስረስ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አድዋ ላይ ተወለዱ።
የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ የሚገረው ምንድን ነው?
የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ
580
የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች አሉ። እነዚህም መሣሪያዎች የጅማት፣ የትንፋሽና የምት ተብለው ወደ ሶስት ይከፈላሉ። የክር ሙዚቃ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በንዝረት ነው፤ ክራር መሰንቆ ከዚህ የሙዚቃ መሳርያዎች ወገን ይመደባሉ፡፡ የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በትንፋሽ ኃይል ነው ምሳሌ ዋሽንት። የምት የሙዚቃ መሣርያ እንደ ከበሮ ሲመቱ ድምጽ የሚያወጡ ናቸው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የባህል ሙዚቃ መሳሪያዎች ስንት መደብ አላቸው?
ሶስት
97
ፋሲለደስ ዓፄ ፋሲለደስ ወይም ዓፄ ፋሲል (የዙፋን ስማቸው ዓለም ሰገድ) ከአባታቸው አፄ ሱሰኒዮስ እና እናታቸው ልዕልት ስልጣነ ምገሴ በመገዛዝ፣ ሸዋ ህዳር 10፣ 1603 (እ.ኤ.አ) ተወለዱ። የነገሱበትም ዘመን ከ1632 እስከ ጥቅምት 18, 1667 (እ.ኤ.አ) ነበር። በስረፀ ክርስቶስ በተመራው አመፅ ምክንያት በ1630 ፋሲለደስ ለንግስና ቢበቃም፣ ዘውዱን ግን እስከ 1632 አልጫነም ነበር። ሲመተ ንግስናው በ1632 እንደተገባደደ የመጀመሪያው ስራው የተዋህዶ ቤ/ክርስቲያንን የቀድሞው ቁመና መመለስና የካቶሊኮችን መሬት በመቀማት ከደንካዝ በማባረር በፍሪሞና እንዲወሰኑ ማድረግ ነበር። ወዲያውም በማከታተል ከግብፅ አገር አዲስ ጳጳስ እንዲላክለት በማድረግ በአባቱ ዘመን እንዲደበዝዝ ተደርጎ የነበረውን የግብፅና ኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት እንዲጸና አደረገ። በኬኒያ የሚገኘው የሞምባሳ ወደብ በፖርቱጋሎች መደብደቡን ሲሰማ፣ የሮማው ፓፓ ከበስትጀርባው ያለበት ሴራ ነው በማለት በምድሩ የነበሩትን የካቶሊክ ጀስዊቶች በመሰብሰብ አባረራቸው። አፄ ፋሲል አዘዞ ተብላ በምትታወቀው ከጎንደር ከተማ 5 ማይል ርቃ በምትገኘው ከተማ ጥቅምት18፣1667 እ.ኤ.አ. (ጥቅምት 10፣ 1660) ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አስከሬናቸውም የአገሪቱ መላ ህዝብ ባዘነበት ሁኔታ በቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም፣ ጣና ሃይቅ ውስጥ ደጋ ደሴት ተብላ በምትታወቀው ደሴት የዘላለም እረፍት አገኘ።
አፄ ፋሲል ለምን ያህል ጊዜ በንግስና ቆዩ?
ከ1632 እስከ ጥቅምት 18, 1667 (እ.ኤ.አ)
138
ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ በሌላ አጠራሩ ታላቁ ቅዱስ ባስሊዮስ በቀጰዶቂያ የቄሣርያ ኤጲስ ቆጶስ ነበር። የንቂያን የሊቃውንት ጉባዔ የሚደግፍና አርያኒዝምንና የአፖሊናረስን ተከታዮችን የክርስትና አመለካከት ተቃውሞ ትክክለኛውን መንገድ ያስተማረ ታላቅ አሳማኝ የሃይማኖት ፈላስፋና መሪ ነበር ። ቅዱስ ባስሊዮስ ከሃይማኖት ፈላስፋነቱ ሌላ ድሆችንና ኑሮን ማሸነፍ ያቃታቸውን በመንከባከብ ይታወቃል ። በተጨማሪም የማኅበራዊ ኑሮ ፣ የሥርዐተ ጸሎትና የጉልበት ሥራ ለገዳማዊ ኑሮ መመሪያን መሥርቷል። ባስሊዮስ ከቅዱስ ጳኩሚስ ጋር የማኅበራዊ ገዳማዊነት አባት ተብሎ በምሥራቃዊ ክርስትና ይታሰባል ። ዳሮግን በምሥራቅም በምዕራብም በቅዱስ ደረጃ ነው የሚከበረው ። እነዚህ ሁለት ጎራዎች ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት የሚለውን ስያሜ ከዮሐንስ አፍወርቅና ከግሬጎሪዮ ናዚያንዘስ ጋር ሰተውታል። ባስሊዮስ ከቀዳማዊ ባስሊዮስና ከኤሚልያ የቄሣሪያዋ በ፫፻፳ ዓም አካባቢ በቀጰዶቂያ ተወለደ ። እናትና አባቱ እግዚአአብሔርን በጣም የሚወዱና ጸሎተኞች የነበሩ ሰዎች ነበሩ ። የእናቱ አባት ከቆስጠጢኖስ ፩ኛ በክርስትና ማመን በፊት ሰማዕት ሆኖ ያለፈ ሰው ነበረ። ጸሎተኛ ባልቴቱ ማክሪናም የጎርጎርዮስ ታውማታርገስ (የኒዎ ቄሣርያን ቤተክርስቲያን በአቅራቢያው የመሠረተ) ተከታይ የነበረች ባስሊዎስንና አራቱን ወንድሞቹንና እህቱን ፣ ወጣትዋ ማክሪና ፣ ናውክራቲየስ ፣ ጴጥሮስ የሰባስቴውንና ፣ ጎርጎርዮስ የኒሳውን (ወደፊት ታላቅና የተከበሩ ቅዱሳን የሚሆኑ) በክርስትና ሃይማኖት ሥርዐት አሳደገች ። ባስሊዮስ በቄሣርያ ማዛካ ቀጰዶቂያ በአሁኑ ዘመን አጠራር ካይዜሪ (ቱርክ) ትምህርት ቤት በ፫፻፵፪ ፵፫ ዓ.ም.አካባቢ ተምሩዋል ። እዛም ጎርጎርዮስ ናዚያንዘስን የረጅም ጊዜ ጉዋደኛ የሚሆነውን ተዋውቋል። ባስሊዮስና ጎርጎርዮስ አንድላይ በመሆን ለከፍተኛ ትምህርትና በተጨማሪ የሊባኒየስን ትምህርታዊ ንግግር ለማጥናት ወደ ቁስጥጥኒያ አምርተዋል ። ሁለቱ በአቴንስ በ፫፵፪ ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ ለስድስት ዓመት ተቀምጠዋል። በዛም ቆይታቸው ጁሊያን ዘአፖስቴት ወደፊት ንጉሥ የሚሆን ተማሪ ተዋውቀዋል። ባስሊዮስ አቴንስን በ፫፵፰ ለቆ ወደ ግብፅና ሶርያ ከተጉዋዘ በኋላ አገሩ ቄሣርያ የሕግ ሥራ በመለማመድና የንግግር ችሎታ ሲያስተምር ቆየ።
ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ የትውልድ ስፍራቸው በየት ነው?
በቀጰዶቂያ
51
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተገኝተዋል። በሰመዕታት መታሰቢያ ቀን የካቲት 12 ቀን በየአመቱ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፤አባት አርበኞች፤ እና የህብረተሰብ ክፍሉ በስድስት ኪሎ ታስቦ ይውላል፡፡
በአዲስ አበባ የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን በየት ቦታ ይዘከራል?
በስድስት ኪሎ
243