id
stringlengths 9
150
| url
stringlengths 42
183
| title
stringlengths 11
101
| summary
stringlengths 45
356
| text
stringlengths 439
6.59k
|
---|---|---|---|---|
a_g20-toronto-canada-meeting-06-28-10-97331599_1460839 | https://amharic.voanews.com/a/g20-toronto-canada-meeting-06-28-10-97331599/1460839.html | የG20 አገሮች መሪዎች በቶሮንቶ ካናዳ ተሰባሰቡ | በሶስት ዓመታት ውስጥ የባጀት ኪሳራቸዉን በግማሽ እንዲቀንሱ ፣ እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር እስከ 2016 ደግሞ ከኢኮኖሚ እድገታቸዉ ጋር በማጣመር ተጨማሪ የባጄት ኪሳራ ቅነሳ ማድረግ አለባቸዉ አሉ። | የዓመት የባጄት ኪሳራቸውን እየቀነሱ የኢኮኖሚ እቅዳቸውን ከግብ የማድረስ ግዴታ እንዳለባቸው መክረዋል ስምንት በኢኮኖሚ ከበርቴ የሆኑ እና ኢኮኖሚያቸዉ እየመጠቀ ያለ እንደ ቻይናና ህንድ ያሉ ታዳጊ አገሮችን የጠቀለለ የ G 20 መሪዎች ጉባኤ በቋፍ ያለ የዓለም ኢኮኖሚ አሁንም ማነቃቂያ እንደሚያሰፈልገውና የበጀት ኪሳራቸውን ለመቀነሰ ግን የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ እንዳለባቸው ተስማምተዋል። ጉባኤዉን ባስተናገደችው አገር ካናዳ ባቀረበችው እቅድ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ስቲቨን ሀርፐር የኢኮኖሚ ተሃድሶው እንዲቀጥል፣ አገሮች ባለፈዉ ዓመት ጉባኤ በፒትስበርግ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ፣ የዓለም ገበያን ለማረጋጋት መሪዎቹ የተቀነባበረ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። የG 20 አገሮች የዓመት የባጄት ኪሳራቸውን እየቀነሱ የኢኮኖሚ እቅዳቸውን ከግብ የማድረስ ግዴታ እንዳለባቸው መክረዋል። የG20 እና G8 መሪዎች በጉባኤዉ ፍጻሜ ላይ ያወጡት መግለጫ በአያሌ አገሮች የስራ አጡ ህዝብ ቁጥር ከሚገባው በላይ ከፍተኛ ስለሆነ፣ የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ማገገም በቋፍ ያለና ኑሮ ላይ ያስከተለው ቀውስም እንደሃገሮቹ የተለያየ ነው ይላል። የግል ንግዶችን የብድር ፍላጎት ለማሙዋላትና ኢኮኖሚውን እንደገና ለማንሰራራት የማነቃቂያ እርምጃ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸዉ ተጠቅሷል። በዓለም እኩል የማይራመዱና ወጣ ገባ የኢኮኖሚ አያያዞች፣ በተለይም የአገሮች የባጄት ኪሳራ ወደ ማገገም የተያዘዉን አቅጣጫም ሊቀለብሱ እንደሚችሉ የG20 መሪዎች ይናገራሉ። ፕሬዚደንት ኦባማና ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት፣ የኢኮኖሚ እድገቱ አንድ ተጨባጭ ውጤት ሳያሳይ፣ በመንግስታት የሚወሰዱ የማነቀቂያ እርምጃዎች እንዳይቋረጡ ፣ ያ ከሆነ ግን እንደገና የዓለም ዋጋ ግሽበት እንደሚከስት ያስጠነቅቃሉ። በጉባኤዉ ፍጻሜ ላይ ባደረጉት ንግግር ፥ በዚህ ነጥብ ላይ ስላለዉ የሃሳብ ልዩነት ፕሬዚደንት ኦባማ ተጠይቀዉ በተለያዩ አገሮች የሚታየው የኢኮኖሚ ማገገም አሁንም በቋፍ ያለ እንደሆነና ተሃድሶ ላይ ለመድረስም ገና ብዙ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል። የጉባኤዉ መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ የምትከተላችውን ልዩ ልዩ ፖሊሲዎች ያንጸባርቃል የሚሉት ፕሬዚደንት ኦባማም ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ የማንፈልግ ከሆነ ግን “በመካከለኛና ረጅም ጊዜያት በመተመን ከባድ የባጄት ኪሳራ ቅነሳ መጋፈጥ ይኖርብናል፤” ይላሉ። የሚቀጥለዉ የG 20 መሪዎች ጉባኤ በመጪው ህዳር ወር በሶል ደቡብ ኮሪያ ይደረጋል። |
a_amnesty-open-letter-to-the-ethiopian-parilament-voa-03-01-18_4276606 | https://amharic.voanews.com/a/amnesty-open-letter-to-the-ethiopian-parilament-voa-03-01-18/4276606.html | አምነስቲ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ። | “አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው። አሁን ላለው ችግር መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ።” ሳሊ ሼቲ የአምነስቲ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር። | ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ለኢትዮጵያ ፓርላማ አባላት ግልጽ ደብዳቤ ልኳል። የምክር ቤቱ አባላት ነገ አርብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ለመምከር እየተዘጋጁ ባሉበት በዚህ ወቅት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ይበልጥ እንዲያስቡ ጥሪ እናቀርባለን፤ ብሏል። በነገው የፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዙሪያ ክርክር የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አብይ ትኩረት እንዲሆን ነው፤ አምነስቲ በግልጽ ደብዳቤው የጠየቀው። የኢትዮጵያ ፓርላማ አዲሱ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀድሞውንም የጠበበውን በሃገሪቱ ያለውን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት፤ የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶች ይበልጥ እንዳያጠፋ ማረጋገጥ አለበት” ሲል የሚንደረደረው የአምነስቲ መግለጫ የብሔራዊው ሸንጎ በነገው ዕለት ሲከፈት አባላቱ በሚያደርጉት ክርክር ወቅት፤ “አሳሳቢውንና የከፋውን” የአገሪቱን ሁኔታ በቅጡ እንዲያጤኑ አሳስቧል። “አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው” ሲሉ፤ የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር ሳሊ ሼቲ ለፓርላማ አባላቱ በላኩት ደብዳቤ “መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ” ያሉበትን አቶ ፍስሃ ያብራራሉ። ይበልጥ የሚያሳስበን ደግሞ የጸጥታ ኃይሎች አስፈላጊ ያሉትን ኃይል እንዲጠቀሙ መታዘዙ ነው፤ ይላሉ አቶ ፍስሃ። “ሁላችሁም” ዋና ሥራ አስፈጻሚውን ዋቢ ያደረገው የአምነስቲ መግለጫ፤ (የፓርላማ አባላትም ጭምር ማለታቸው ነው) “ሁላችሁም በሕግ እንድተዳደሩ፤ የሕዝቡን ፍቃድ እንድታከብሩና ለሕሊናችሁ እንድትገዙ፤ የሃገሪቱ ሕገ-መንግስት ግድ ይጠይቃል። በአስቸኳይ አዋጁ ጉዳይ ውሳኔ በምትታሳልፉበት ወቅት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብዓዊ መብት መከበር ሙሉ ትኩረት መስጠት በእጅጉ አስፈላጊ ነው። ” ብለዋል። |
a_india-covid19-surpases-20-million-second-wave-continues-05-04-21_5878097 | https://amharic.voanews.com/a/india-covid19-surpases-20-million-second-wave-continues-05-04-21/5878097.html | መቆሚያ ያልተበጀለት የህንዱ ሁለተኛ ዙር የኮቪድ 19 ማዕበል | “አጋዥ ከማጣት የመጣ አይደለም። ጨርሶ ከመውደቅ ደረጃ መድረሱ እንጂ! ለሌላ ለማዘን ከምንችልበት ቦታ አይደለንም። እዚህ ታካሚዎች እየሞቱብን ነው። ይሄ የተለየ ድብቅ ምክኒያት የከሰተውም አይደለም።በተጨባጭ የሚታይ ነገር ነው። ሁሉም ያውቀዋል፡፡ አገረ ገዥው ያውቁታል። አስተዳደሩም ያውቀዋል። ሁሉም ያውቀዋል፡፡” ዶ/ር ሩሺ ጉብታ በማዕከላዊ ኒው ዴልሂ የሚገኝ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን ሃኪም። | ዋሺንግተን ዲሲ — ህንድን እያናወጠው ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዛሬ 13ተኛ ቀን በተከታታይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ለቫይረሱ መጋለጡ ተዘግቧል። በአንድ ቀን ዕድሜ 357 ሺህ 229 አዲስ ለኮረናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች መዘገባቸውን የጤና ሚንስትር በዛሬው ዕለት አስታውቋል። ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በደቡባዊ እስያዊቱ አገር በኮቪድ-19 ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ከ3449 በላይ ሰዎች ናቸው። በጃን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮረናቫይረስ መረጃ ማዕከል አሃዞች መሰረት ባሁኑ ወቅት በህንድ ለቫይረሱ የተጋለጠው ሰው ቁጥር ሃያ ሁለት ሚልዮን ነጥብ ሁለት በዚያች አገር በኮቪድ ሳቢያ ህይወቱ ያለፈው ሰው ቁጥር 222,408 ደርሷል። ያም ህንድን በወረርሽኙ ጥናት እና ለቫይረሱ በተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ ሁለተኛዋ አገር ያደርጋታል። በሟቶች ቁጥር ደግሞ ሶስተኛዋ አገር ናት። በአንድ የኒው ዲልሂ ሆስፒታል ሃኪሞች የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ቀውስ የሕክምና መስጫ ተቋሙ ከሚችለው በላይ ለማስተናገድ የተገደደበት ሁኔታ መፈጠሩን ይናገራሉ። ዶ/ር ሩሺ ጉብታ በአንድ ማዕከላዊ ኒው ዴልሂ በሚገኝ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን መርጃ ክፍል ሃኪም ናቸው። “አጋዥ ከማጣት የመጣ አይደለም። ጨርሶ ከመውደቅ ደረጃ መድረሱ እንጂ! ለሌላ ለማዘን ከምንችልበት ቦታ አይደለንም። እዚህ ታካሚዎች እየሞቱብን ነው። ይሄ የተለየ ድብቅ ምክኒያት የከሰተውም አይደለም። በተጨባጭ የሚታይ ነገር ነው። ሁሉም ያውቀዋል፡፡ አገረ ገዥው ያውቁታል። አስተዳደሩም ያውቀዋል። ሁሉም ያውቀዋል፡፡ ” ብለዋል። ዶ/ር ጉብታ አክለውም መሠረታዊ የኦክስጂን አቅርቦት ያለመኖሩን እና ያላቸውም በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ሊያልቅባቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ትናንት የሆስፒታላቸው የድንገተኛ ክፍል ሞልቶ ስለነበር ከኮቪድ 19 ውጭ ሌሎች የድንገተኛ እርዳታ የሚሹ ታካሚዎችን ተቀብለው መርዳት ሳይቻላቸው መቅረቱን አስረድተዋል። በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሆስፒታሎች የህሙማን መቀበያ እና መርጃ መኝታዎች በመሙላታቸው እና ከፍተኛ የኦክስጂን አቅርቦቶች ዕጥረት በመፈጠሩ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች እንዲጨምር ማድረጉ ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ህንድ በገጠማት ችግር ሳቢያ ለደሃና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገሮች የሚሰራጨውን ክትባት የሚያመርተው የመድሃኒት ኩባንያ ብዙ ተስፋ እንደተጣለበት ማቅረብ በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ ባለመሆኑ የዩናይድ ስቴትሱ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ሞደርና በዓለም ጤና ድርጅት አማካኝነት ለተቋቋመው ዓለም አቀፍ የክትባት ፕሮግራም COVAX የCOVID-19 ክትባቱን መጠኑ 500 ሚሊዮን የሚደርስ ክትባት ለማቅረብ ቃል መግባቱን በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል። |
a_opposition-wants-new-election-06-03-10-95522759_1458002 | https://amharic.voanews.com/a/opposition-wants-new-election-06-03-10-95522759/1458002.html | የኢትዮጵያው ምርጫና የተቃዋሚዎቹ የዛሬ አቋም | የመንግሥት ባለሥልጣናት የገዥው ፓርቲ አጠቃላይ ድል የሕዝቡን ፍላጎት ያሣየ ነው ቢሉም ተቃዋሚዎቹ ግን ምርጫው ተሠርቋል በሚል አቋማቸው እንደፀኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት አዲስ ምርጫ ጠይቀዋል፡፡ | "ፍትሐዊ ምርጫ ቀልድ ነበር" - ኢፍዴኃግ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስምምነት የሌላቸው 65 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ከተደረሰባቸው ሰባሪ ሽንፈት ለማገገም እየተፍጨረጨሩ እንደሆነ ይታያል፡፡ ብዙዎቹ ግን በአንድ ጉዳይ ላይ ወደአንድ ሠልፍ እየገቡ ይመስላሉ - በምርጫው ውጤት፡፡ ከ547ቱ የፓርላማ መቀመጫዎች አሥር ከመቶ የማይሞሉትን የተቃዋሚ የሚባሉ መቀመጫዎች በብዙ መንገድ ነው የሚቀራመቷቸው፡፡ የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረቱ የኢትዮጵያ የፍትሕና የዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር አዲስ ምርጫ መካሄድ አለበት የሚለውን አቋም ተቀላቅሏል፡፡ ይህንን አቋም የሚያራምዱት ወገኖች ገዥው ፓርቲ ምርጫውን አጭበርብሯል፤ ዕጩዎቻቸውና ድምፅ ሰጭዎች ተዋክበዋል፤ እንዲሸማቀቁ ተደርገዋል ባይ ናቸው፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ደግሞ ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን መናገር እንደሚችሉ ቢናገሩም ድጋሚ ምርጫ የሚባል ነገር ግን የሚታሰብ ነገር እንዳልሆነ ያሣስባሉ፡፡ - ብለዋል የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትሩ በረከት ስምዖን - ይሁን እንጂ ደርሰዋል የሚባሉ ችግሮችን በገሃድ የሚያሣዩ ቁጥራቸው የበዛ ማስረጃዎች በእጃቸው እንደሚገኙ ታዛቢዎቻቸው ከብዙ የምርጫ ጣቢያዎች መባረራቸውን እየተናገሩ ነው፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ወደምርጫው ፉክክር የገቡት መንግሥት ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ ስለነበረ ቃሉን ይጠብቃል በሚል እምነት እንደነበረ አመልክተዋል፡፡ "ያ የፍትሐዊ ምርጫ ቃል ግን ቀልድ ሆኖ ቀረ" ብለዋል የፍትሕና የዴሞክራሲ ኃይሎች ግንባር ዋና ፀሐፊ ገረሱ ጋሳ፡፡ - ሲሉም አክለዋል፡፡ የምርጫው ሂደት አያያዝና አሠራር እራሱ በተፈጥሮው ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የማይመች፣ ለገዥው ፓርቲ የሚያዳላ እንዲሆን ተደርጎ የተዋቀረ እንደሆነ ይናገራሉ ዋና ፀሐፊው፡፡ ትልልቆቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው የሚባሉት መድረክና የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ባለፈው ሣምንት ጠይቀዋል፡፡ በፓርላማው ውስጥ በንቃት ይሣተፍ የነበረው የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም ቢሆን መንግሥትን አካሂዷል በሚላቸው የሰፉ ችግሮች ሲከስ ተደምጧል፡፡ ሌላ ዙር ምርጫ እንዲካሄድ ከመጠየቅ ግን ተቆጥቧል፡፡ |
a_amh-horn-drought-moyale-cattle-death-10-11-11-131540858_1462986 | https://amharic.voanews.com/a/amh-horn-drought-moyale-cattle-death-10-11-11-131540858/1462986.html | በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በተጨማሪ የዝናብ እጥረት ተባብሷል | በቦረና ዞን ክፉኛ በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የመስከረም አጋማሹ ዝናብ ዘግይቷል | ከአዲስ አበባ 705 ኪሜ ወደ ኢትዮጵያ ኬንያ ድንበር ሞያሌ መንገድ ጸሃይ በርትታለች። ክው ብለው በደረቁት የግራር ዛፎችና ቁጥቋጦዎች ያለከልካይ የሚነፍሰው ንፋስ ደማቅ ብርቱካናማውን አፈር እንዳሻው ይገልጠዋል። ድርቁ አካባቢውን አረንጓዴ ቀለም አይቶ የማያውቅ በረሃ አስመስሎታል። ግራና ቀኝ በቀይ አፈር አጃቢነት ከተነጠፈው አስፋልት ቀለሙ በለቀቀ ጥቁርና ነጭ ቀለም 705 ኪሎሜትር የሚል የኮንክሪት አምድ ቆሟል። ከአዲስ አበባ 705 ኪ.ሜ መሆኑን ከሚያሳየው ምልክት ስር አንዲት ደባራ ላም ወድቃለች። ከወደወገቧ ጥቁር ቡናማ ከወደ እግሮቿ ሳያር የተቆላ ቡና መሰል -- ደባራ ቀለም አላት። መቼ እንደሞተች ባይታወቅም። ስጋዋ በጸሃይ ሃሩር ፈሳሹን አትንኖ ቆዳዋ ከአጽሟ ጋር ተጣብቋል። ሽታ የሚባል ነገር የለም። ቀድሞውንም ለሁለት አመት ያህል የዘለቀው ድርቅና የጸሃዩ ብርታት የሚሞቱትን ከብቶች በቀናት ውስጥ ያደርቃቸዋል። ከብቶቻቸው የሚሞቱባቸው አርብቶ አደሮች ሳር ፍለጋ ከሞት የተረፉትን ለማዳን ስለሚገሰግሱ፤ ቆም ብሎ ቆዳ ለመግፈፍ ጊዜውን አንዳንዴ ደግሞ አቅሙ አይኖራቸውም። 705ኛው ኪሎሜትር በቦረና ዞን የሚታየውን ድርቅና ከፍተኛ የሆነ የእንስሳት ሞት በግልጽ ያሳያል። ከ1.5 ኪሎሜትር እስከ 2 የሚሆን ርቀት ውስጥ 16 የሞቱ የከብት ቅሪቶችን ቆጥረናል። ይሄ እንግዲህ በመንገዱ ዳር ያየንው ብቻ ነው። ውስጣ ውስጡን ያለቀውን፣ ወድቆ የሚታየውን የእንስሳት ቅሪት አድማስ ይቁጠረው። የሚበዛው ነዋሪ ከከብት እርባታ በሚገኙ ተዋጽዖዎች የሚተዳደርበት ቦረና ከ60-75 ከመቶ የሚሆኑ ከብቶች መሞታቸው ይገመታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለው ከሆነ የሚያዝያው ወር የገና ዝናብ ለሁለተኛ ጊዜ ሳይጥል በመቅረቱ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ከብቶች ሞተዋል። “የእንስሳት ሞቱ በከብት ብቻ አልተወሰነም። ግመልም፣ ፍየልም የጋማ ከብቶችም ሞተዋል። ” ይላሉ ሊበን አሬሮ የቦረና ዞን አርብቶ አደር ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ። “በድርቁ ሳቢያ የሞቱትን ከብቶች ጠቅላላ ቁጥር ለማወቅ ጥረት ቢያዝም፤ እስካሁን ይሄን ያህል ለማለት የሚያስችል መረጃ አላሰባሰብንም። የሞቱት ከብቶችን ቁጥር የኢትዮጵያ መንግስት በቁጥር ማስቀመጥ ባይችልም። በአካባቢው ለተረጂነት የተጋለጡ ሰዎችን ቁጥር በአግባቡ ይገልጻል። በአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና በሴፍቲ ኔት ከሚረዱት ሰዎች በተጨማሪ ለእናቶችና ህጻናት፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋዊያን የሚሰጠው እርዳታ ሲጨመር ግማሽ የሚሆነው የቦረና ህዝብ እርዳታ እየተሰጠው ይኖራል። ከ705ኛው ኪሜ ቀድሞ አልፎም እስከ ኬንያ ድንበር እንዲሁ የቀውስ ቀጠና ነው። ሰሜን ኬንያም ቢሆን በዚህ ድርቅ ክፉኛ ተጠቅቷል። በሳምንታት የዘገየው የሃገያ ዝናብ ካልጣለ፤ አካባቢው ወደከፋ የሰብዓዊ እልቂት እንዳያመራ ተሰግቷል። |
a_ethiopia-election-re-run_1458682 | https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-election-re-run/1458682.html | «በአብዛኛው ታዛቢዎቻችን በሌሉበት ተካሄደ፤» ሲሉ፥ የገለፁት የግንቦት 15ቱ ምርጫ እንዲደገም ሁለት ዋነኛ ተቃዋሚ ቡድኖች አስታወቁ። | «ነፃና ገለልተኛ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገርና ታዛቢዎች፤ በተገኙበት ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ እንጠይቃለን፤» - መድረክ | «የምርጫው ሂደትም ሆነ የድምፅ መስጫው ቀን፥ ነፃና ፍትሃዊ ባለመሆናቸው፤ ታዛቢዎቻችን ተደብድበው በመባረራቸው በብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን ውጤት አንቀበልም። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ በተከታታይ በሰጧቸው መግለጫዎች በምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን ውጤት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል። ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ይፋ ካደረገና ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም ድሉን ማክበር ከጀመረ በኋላ የመጀመሪያው በሆነው ይፋ የተቃዋሚዎች መግለጫ ሁለቱ ተቃዋሚ ቡድኖች ውጤቱን የማይቀበሉበትን ምክኒያትና አማራጭ ያሉትን በመግለጫቸው ዘርዝረዋል። «የምርጫው ሂደትም ሆነ የድምፅ መስጫው ቀን፥ ነፃና ፍትሃዊ ባለመሆናቸው፤ በመላው አገሪቱ በሚገኙ አብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎችም ታዛቢዎቻችን ተደብድበው በመባረራቸው በብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ይፋ የተደረገውን ውጤት ላለመቀበል ወስነናል፤» ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በውጭ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ያቆብ ልኬ አማካኝነት አስታውቋል። ይሄንን ውሳኔውን ትላንት ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ለምርጫ ቦርድ ማሳወቁን የገለፀው መኢአድ፥ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫዎችም በተቻለ ፍጥነት በድጋሚ እንዲካሄዱ መጠየቁን አመልክቷል። ኢህአዴግን አሸናፊ ያደረገውንና በቦርዱ ይፋ የሆነውን ውጤት እንደማይቀበል ከመኢአድ በተመሳሳይ ዛሬ ከቀትር በኋላ ያስታወቀው የስምንቱ ተቃዋሚ ቡድኖች ጥምረት መድረክ በበኩሉ፥ ነፃና ገለልተኛ የሆኑ የአገር ውስጥና የውጭ አገርና ታዛቢዎች፤ በተገኙበት ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ጠይቋል። «ከኢህአዴግ ሌላ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ የማይፈልግ ተቃዋሚ ፓርቲ ሊኖር አይችልም፤» ብሎ እንደሚያምን መድረክ በሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አማካኝነት መድረክ ገልጧል። |
a_voa-amharic-news-05-22-2020_5442495 | https://amharic.voanews.com/a/voa-amharic-news-05-22-2020/5442495.html | ቪኦኤ አማርኛ - የቅዳሜ፤ ግንቦት 22/2012 ዜና | በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ተጋላጭ ከአንድ ሺህ በላይ ሆነ ከቤይሩት ተጨማሪ 323 ሃገራቸው ገቡ የጆርጅ ፍሎይድ መገደል ዓለም አቀፍ ንግግር እየሆነ ነው | ኢትዮጵያ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ ስድሣ መብለጡን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የኮቪድ 19 ሞት ቁጥር ስምንት መድረሱን በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፊርማ የወጣው የዛሬ መግለጫ ያሳያል። መግለጫው ዛሬ እስከወጣበት ጊዜ በነበሩት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረጉ 5 ሺህ 34 የላብራቶሪ ምርመራዎች ለቫይረሱ መጋለጣቸው የተረጋገጠው ዘጠና አምስት ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች አጠቃላይ ቁጥር ዛሬ 1063 ደርሷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮቪድ 19 የዓለም መዛመት ቁጥር ወደ ስድስት ሚሊየን መጠጋቱን ዓለምአቀፉን ሁኔታ በቅርብ እየመዘገበ ያለው የጆንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የኮሮናቫይረስ መረጃ ማዕከል ዛሬ አስታውቋል። በማዕከሉ መረጃ መሠረት በዓለም ዙሪያ 365 ሺህ 800 ሰው በኮቪድ 19 ምክንያት ሞቷል። ሠንጠረዡን እየመራች ባለችው ዩናይትድ ስቴትስ የተጋላጩ ቁጥር አንድ ሚሊየን 750 ሺህ፤ የሞቱ ቁጥርም አንድ መቶ ሁለት ሺህ 900 መድረሱን ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል። ከ135 ሺህ በላይ ተጋላጮች እንዳሉባት ዛሬ ጠዋት በተነገረው አፍሪካ ከሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ በላይ ሰው በኮቪድ 19 ምክንያት መሞቱ ተገልጿል። ቤይሩት ውስጥ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ተመዝግበው ሲጠባበቁ የነበሩ ተጨማሪ 323 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ተመልሰዋል። ኢትዮጵያዊያኑ የተመለሱት ለመጓጓዣና ለተለያዩ ወጭዎች የከፈሉት 550 ዶላር ተመልሶላቸው መሆኑን በሊባኖስ የኢትዮጵያ በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል አስታውቋል። ከሁለት ቀናት በፊት እንዲመለሱ የተደረገውን ጨምሮ አጠቃላይ ቁጥር 658 መድረሱን የቆንስላ ጄነራል ፅህፈት ቤቱ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባወጣው ዝርዝር መግለጫ ላይ አመልክቷል። ኢትዮጵያዊያኑ ከቤይሩት ከመነሳታቸው በፊት አስፈላጊው የኮቪድ 19 ፍተሻ እንደተደረገላቸውና አዲስ አበባ ሲደርሱም ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚቆዩባቸው ሁኔታዎች የተመቻቹላቸው መሆኑን፤ የአሥራ አራት ቀናት የቆይታ ጊዜያቸውን ከጨረሱ በኋላም እስከመኖሪያ ቀዬዎቻቸው የሚደርሱበትና ከየማኅበረሰባቸው ጋር የሚቀላቀሉባቸው ዝግጅቶች መደረጋቸውንም ፅህፈት ቤቱ ገልጿል። በዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ምዕራብ ግዛቷ ሚኔሶታ ከተማ ሜኔአፖሊስ ውስጥ በነጭ ፖሊሶች የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ጊዳይ ባስነሳው ቁጣ ተቃዋሚዎቹ በከተማዪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ተቋማት ላይ እሳት አንስተዋል። በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ባልታየ ሁኔታ አፍሪካ ዋና ከተሞች ውስጥ የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች የበረታ ይዘት ያላቸውን መግለጫዎች እያወጡ ናቸው። አሜሪካ ምድር ላይ የተፈፀመው አድራጎት በመላ አፍሪካ ቀጣና ቅሬታን ማጫሩም ተዘግቧል። የኤምባሲዎቹ መግለጫዎች እየወጡ ያሉት የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር መሳ ፋኪ ማሃማት በጆርጅ ፍሎይድ ላይ የተፈፀመውን አድራጎት በዩናይትድ ስቴትስ ጥቁር ዜጎች ላይ እየቀጠለ ያለ የመድልዎ አድራጎት ሲሉ ውግዘት ካሰሙ በኋላ ነው። በኮንጎ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃመር ባወጡት መልዕክት የጆርጅ ፍሎይድ ሜኔአፖሊስ ውስጥ በአሳዛኝ ሁኔታ መገደል የረበሻቸው መሆኑን ጠቁመው የሃገራቸው የፍትሕ ሚኒስቴር ለጉዳዩ ከፍተኛ ቅድሚያ ሰጥቶ ወንጀል ምርመራ እያካሄደበት መሆኑን ገልፀዋል። ኬንያ፣ ዩጋንዳና ታንዛኒያ ያሉት የአሜሪካ ኤምባሲዎችም የየራሳቸውን መልዕክቶች አውጥተዋል። እንድ ነጭ ፖሊስ አንገቱ ላይ በጉልበቱ ተጭኖት በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ጥቁሩ ጆርጅ ፍሎይድ መሞት በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ተቃውሞዎችን እያቀጣጠለ መሆኑ ተዘግቧል። ሰልፈኞቹ ሚኔአፖሊስ ውስጥ የንግድ ተቋማትን፣ ተሽከርካሪዎችንና ፖሊስ ጣቢያ በእሳት አጋይተዋል። በሜኔአፖሊስና በአጎራባቿ ሴንት ፖል ከተሞች 500 ብሄራዊ ዘብ የተሠማራ ሲሆን ነገ ቁጥሩ ወደ 1700 ከፍ እንደሚል ተገልጿል። |
a_article----112273904_1460523 | https://amharic.voanews.com/a/article----112273904/1460523.html | ሁለት ጥበበኛ እጆች | አብዱረዛቅ ረሽድ ወይንም በመድርክ ስሙ አብዲ ዘ-ጀግለር ታዋቂ የሰርከስ ትርዒት ባለሙያ ነው። ስለትግሉና ስኬቱ ከመስታዎት ዝግጅት ጋር ተወያይቷል። | ተወልዶ ያደገው ናዝሬት ከተማ ነው። አብዱረዛቅ ረሽድ አደም ገና በስምንት ዓመቱ የሰርከስ ልምምድ ለማድረግ ከትምህርት ቤት መልስ ከበጎ ፈቃድ አሰልጣኙ ሙያ ሊቀስም ሲሄድ ቤተሰቦቹ ደስተኞች አልነበሩም። “ይሄንን ቧልትና ዝላይ ትተህ በትምህርትህ በርታ” ነበር የወላጆቹ ምክር። በየቀኑ ወሳኝ ክህሎቶቹን እየተማረ የነበረው አብዲ ግን ተደብቆም ቢሆን ከልምምድ አይቀርም ነበር። “ቤተሰቦቼ ጊዜየን የከንቱ የማሳልፍ ይመስላቸው ነበር” ይላል አብዲ። የኋላ ኋላ ቤተሰቦቹን ከትርዒቶቹ አንዱን እንዲመለከቱለት ጋብዟቸው ስራውን ካዩ በኋላ ድጋፋቸውን ሰጡት። ዛሬ ይሄ ታዳጊ ወጣት የ27 ዓመት ሰው ነው። በስራውም ቢሆን በልጅነቱ ያደረበትን የሰርከስ ፍቅር ወደ ፕሮፌሽናል ሙያ ቀይሮት ታዋቂ ሆኗል። ሲጀምር ሰርከስ ናዝሬት ፥ ከዚያ ሰርከስ ኢትዮጲያ ፥ ዛሬ ደግሞ በዓለም ላይ የታወቀ ባውንሲንግ ጀግለር ወይም በርካታ ኩዋሶችን በማንጠር በቅንብር እየቀለበ በታላላቅ የዝናኛ ማዕከላት እና በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ከተሞች ስራውን ያቀርባል። ለሰርከስ ትርኢቱ ወዲህ ወደዩናይትድ ስቴትስ መጥቶ በዋሽግተን ዲሲ እና በተለያዩ በርካታ ከተሞች እየተዘዋወረ ነው። በታወቀው በኬኔዲ ሴንተር ዝግጅቱን ከአውሮፓ ከተሰባሰብ የሰርከስ ቡድን ጋር አቅርቧል በሌሎችም ከተሞች እንዲሁ እየተዘዋወረ ዝግጅቶቹን ያቀርባል። ከመስታዎት ዝግጅት ጋር ያደረገውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ። |
a_amh-ethiopians-eritreans-libya-02-25-11-116949553_1458016 | https://amharic.voanews.com/a/amh-ethiopians-eritreans-libya-02-25-11-116949553/1458016.html | ሁለት ኢትዮጵያዊያን በሊቢያ መሞታቸውንና በርካታዎች መሰወራቸውን ስደተኞቹ አስታወቁ | በጸረ-መንግስት ተቃውሞ በታወከችው ሊቢያ አፍሪካዊያን ስደተኞች ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰባቸው ይገኛል። በተለይ ከመንግስቱ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ከተሞች ጥቃቱ አይሏል። | የጋዳፊ ቅጥረኞች ናችሁ በሚል ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ጥቃት እየደረሰባቸው ነው በጸረ-መንግስት ተቃውሞዎች የተናወጠችውን ሊቢያ ለቀው ለመውጣት በርካታ ሽህ የውጭ አገር ስደተኞች በአውሮፕላን፤ በመርከብና በእግር እየተመሙ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በከባድ ችግር ውስጥ ወድቀዋል። በዚህ ግጭት መሀል የተያዙት በሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች የሞማር ጋዳፊ ቅጥረኛ “ጥቁር የውጭ አገር ወታደሮችሁ” ናቸው በሚል ለድብደባ፣ ዘረፋና ግድያ መጋለጣቸውን ይናገራሉ። በጸረ-መንግስት ተቃውሞ በታወከችው ሊቢያ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ከቤታቸው አይወጡም። ወጥቶ ለቤተሰብ፣ በተለይ ለልጆች የሚቀመስ እህል ውሃ መግዛት እንዳልቻሉ ይናገራሉ። እነዚህ ስደተኞች በአንድ በኩል በሁከት በሌላ በኩል የጋዳፊ ቅጥረኛ የውጭ አገር ተዋጊዎች ላይ ባለው ጥላቻ ከባድ ችግር ላይ ወድቀዋል። “ጥቁር መንገድ ላይ ከወጣ መግደል ነው” ይላል በሊቢያ ለ9አመት የኖረው ኢትዮጵያዊ ሳሚ። ወደ ሱቅ ሄዶ ምግብና ውሃ መግዛት በህይወት ዋጋ የሚያስከፍልበት ደረጃ ደርሰናል ይላል። “ለቤተሰባቸው ምግብ ሊገዙ የወጡ ሶስት ኢትዮጵያዊያን አንዱ የአሩሲ ልጅ ነው። እግሩን በጥይት መትተው ይዘውት ሄደዋል” ይላል ሳሚ። በመንግስት ቁጥጥር ስር በማይገኙ ከተሞች። ማለት የጸረ-ጋዳፊ ተቃዋሚዎች ነጻ ባወጧቸው ከተሞች በጥቁር አፍሪካዊያን ላይ ያለው ቁጣ በጣም ያየለ ነው። ሳሚ ሁኔታው ከቆየ ጥላቻ የመነጨ ቢሆንም፤ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ ፓስፖርት ያላቸው ሰዎች በጋዳፊ ቅጥረኛ ተዋጊነት ተጠርጥረው ከተያዙ ወዲህ ቁጣው ወደ ጥቃት ተለውጧል። በጠቅላላው ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ እነዚህ ስደተኞች ከባድ የሆነ ችግርና ጥቃት ይደርስባቸዋል በሚል ተሰግቷል። የሊቢያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች መስሪያቤትን ከሀገር እንዲወጣና ስራውን እንዲያቆም ማድረጉ ይታወሳል። በዚህ እርምጃ ወደ 12ሽህ የሚሆኑ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ሌሎች ስደተኞች አስተባባሪ አጥተው ቆይተዋል። ከነዚህ መከከል በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ይገኙበታል። UNHCR እና ሌሎች አለማቀፍ የስደተኛ ተቆርቛሪ ድርጅቶች በሌሉበት ሁኔታ፤ አገሮች ዜጎቻቸውን በአውሮፕላን በመርከብና በመኪና እያስወጡ ባለበት ወቅት፤ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን፣ ሱዳናዊያን እና ሌሎችም በከባድ ችግር ላይ ናቸው። አንድ በጣሊያን መሰረቱን ያደረገ አጄንሲያ አበሻ የተባለ ማህበር፤ የአውሮፓ ህብረት በተለይ ደግሞ የጣሊያን መንግስት ዜጎቻቸውን ከሊቢያ ሲያወጡ፤ ኢትዮጵያዊያኑንና ኤርትራዊያኑን አብሮ ከሀገር እንዲያወጣ በመማጸን ላይ ነው። “ከአውሮፓዊያን ዜጎች ጋር አብሮ የመውጣት እድል እንዲሰጣቸው ጠይቀናል” የሚሉት አባ ሙሴ ዘርዓይ አጀንሲያ አበሻ የተባለው ማህበር መስራች ናቸው። የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በትሪፖሊ ለሚገኘው ኢምባሲ ሁኔታውን እንዲያሳውቅና የስደተኞቹ ደህንነት እንዲጠበቅ ያቀረቡት ጥያቄ፤ በጣሊያን መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አላገኘም። የስደተኞቹ ቁጥር በርካታ በመሆኑ ከሊቢያ ማውጣቱ ከባድ እንደሆነ መልስ ተሰጥቷቸዋል። አባ ሙሴ ትግላቸውን አላቆሙም። ህጻናት ልጆች ላላቸው ቅድሚያ እንዲሰጥ የተረፉትን ደግሞ ወደ ጎረቤት አገሮች እንዲዛወሩ እየወተወቱ ነው። አባ ሙሴ በዚህ ትግላቸው ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠይቀዋል። |
a_ethiojazz-music-young-ethiopia-_3187096 | https://amharic.voanews.com/a/ethiojazz-music-young-ethiopia-/3187096.html | አዳጊ ወጣት የጃዝ ሙዚቃ ተጫዋቾች-በካሊፎርኒያ | “Young Ethio-jazz Band” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ተወልደው ያደጉት በዩናይትድ ስቴትስ ኦክላንድ ካሊፎርኒያ ነው። እድሜያቸው ከዐስራ ሦስት እስከ ዐስራ ስምንት የሆኑት አነዚህ ወጣቶች በጋራ ሙዚቃን መጫወት የጀመሩት የዛሬ አራት ዓመት ነው።"ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ" ይላል ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ። | ዋሽንግተን ዲሲ — ኢትዮጵያዊ ዜማዎችን በተለያዩ መድረኮች በመጫወት ለውጭው አድማጭ ኢትዮጵያዊነታቸውና ባህላቸውን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ። በተለይም የኢትዮ-ጃዝ የሙዚቃ ስልት የሆነውን የዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ ሙዚቃዎችን በመድረክ በመጫወት ይታወቃሉ። 'Young Etho-jazz band' ያንግ ኢትዮ-ጃዝ ባንድ የተመሰረተው በአዳጊዎቹ ወላጆች የጠነከረ ጓደኝነትና ኢትዮጵያዊነትን ለልጆቻቸው ለማስተላለፍ ካላቸው ፍላጎት ነበር። ከሙዚቃ ባንድ አባላቱ የአንዱ ልጅ አባት የሆነው አቶ ሲራክ ተግባሩ በተለየ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለወጣቶቹ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል። የሳክስፎን የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች የሆነው አቶ ሲራክ ልጆቹን በማሰባሰብና በመኖሪያ ቤቱ የሙዚቃ ልምምድ እንዲያደርጉበት ከማዘጋጀት ጀምሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ፣ አጠቃላይ የሙዚቃን ህግና የሙዚቃ መሳሪያውን በማስተማር ላይ ይገኛል። በቅርቡም ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሴት አዳጊ ወጣቶችን በማሰባሰብ የኢትዮጵያን ሙዚቃ የማስተማር እቅድ አለው። “መሆን የምትመኙትን ለመሆን ጣሩ፤ ራሳችሁን ኢትዮጵያዊነታችሁን ለማስተዋወቅ አትፈሩ። ” ዮሃንስ ከሙዚቃ ባንድ አባላት አንዱ የተናገረው ነው። መስታወት አራጋው የሙዚቃ ባንድ አባላቱን አነጋግራቸዋለች። ሙሉ ዝግጅቱን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ። |
a_amh-unsc-eritrea-react-12-6-11-135127608_1458866 | https://amharic.voanews.com/a/amh-unsc-eritrea-react-12-6-11-135127608/1458866.html | ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ተጨማሪ ማእቀብ የጣለብኝ ለዩናይትድ ስቴይትስ ስለማላጎበድድ ነው አለች | ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ የምትፈጥረውን አለመረጋጋት ለመግታት በሚል ያለፈው ውሳኔ 2023 በኤርትራ የማእድን ኢንዱስትሪና በውጭ አገር የሚኖሩ ኤርትራዊያን የሚከፍሉት ቀረጥ ለአፍራሽ ተግባር እንዳይውል ያቅባል። | ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቪዛ ማግኘታቸውን ዩናይትድ ስቴይትስ ገለጸች በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማእቀብ ከመጣሉ በፊት የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ህብረት IGAD መሪዎችና ተወካዮቻቸው በአዲስ አበባ በቪዲዮ መልእክት የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ማእቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል። የጸጥታው ምክር ቤት አባላት አንዲያስቡበትና ድምጻቸውን እንዲሰጡበት የረፍት ጊዜ ከወሰደ በኋላ በናይጀሪያና ጋቦን አርቃቂነት የቀረበው ስምምነት 2023 በ13 የድጋፍ ድምጽና በቻይናና ራሻ ተአቅቦ ጸድቋል። በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴይትስ አምባሳደር ሱዛን ራይስ ይሄ ስምምነት ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ የምትፈጥረውን አለመረጋጋትና ለአሸባሪዎች የምትሰጠውን ድጋፍ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደሚያወግዝ ያሰምርበታል ብለዋል። “ከዚህ በፊት የነበረውን ስምምነት 1907 ያጠናክራል፥ እናም በኤርትራ ላይ ተጨማሪ ማእቀቦችን ይጥላል። ከዚያም በተጨማሪ ከማእድን ዘርፍና በውጭ አገር ከሚኖሩ ኤርትራዊያን የሚሰበሰበውን ቀረጥ ላልተፈለገ ለእኩይ ተግባር እንዳታውል ያቅባል” ብለዋር አምባሳደር ራይስ። ጀርመንም በዚሁ ውሳኔ ላይ የኤርትራ መንግስት የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ህብረት IGAD ለመግባት ያቀረበው ጥያቄ ተፈጻሚ እንዲሆን ጠይቃ፤ ኤርትራ በበኩሏ ከጎረቤቶቿ ጋር እንድትስማማ ገልጻለች። ውሳኔ 2023 ለኤርትራ ይፋ የፖለቲካ መልእክት የያዘ ነው ያሉት በተ.መ.ድ የጀርመን ቋሚ ልዑክ ፔትር ዊቲግ ኤርትራ “ጎረቤቶቿ መረጋጋት እንዳይኖራቸው የምታደረገውን እንቅስቃሴ ትታ፤ በትብብር መኖር አለባት” ብለዋል። ቻይናና ራሻ በውሳኔው እጃችን የለበትም ሲሉ በውሃ ታጥበው የተዓቅቦ ድምጽ ሰጥተዋል። የጸጥታው ምክር ቤት የወቅቱ ፕሬዝደንት የራሻ ፌደሬሽን አምባሳደር ቭ መንግስታቸው በኢጋድ አባሎች የቀረቡት አቤቱታዎች እንደሚያሳስቡት ገልጸው ቪታሊ ቸርኪን በአንዳንድ ለውሳኔ የቀረቡ ጉዳዮች ላይ ግን በቂ ማስረጃ አልነበረም፤ በተለይ ኤርትራ በአዲስ አበባ የአፍሪክ ህብረት ስብሰባ ላይ ፈንጅ ለማፈንዳት አሲራለች የተባለው የተረጋገጠ መረጃ የለውም ብለዋል። “ምርመራው እንዴት እንደተከናወነ አናውቅም፣ እንዴት እንድተጠናቀቀና በዚህ ጉዳይ ላይ የፍርድ ሂደት ስለመኖሩ የምናውቀው ነገር የለም። ስለዚህ እንዲህ ያለ ከባድ ውንጀላ ለማካተት የተረጋገጠ ማስረጃ ያስፈልግ ነበር። አንድ የሁኔታ አጣሪ ቡድን ይሄን አረጋግጧል ተብሎ ያለበቂ ማስረጃ ማቅረብ ተገቢ አመለካከት አይደልም። በዚያ ላይ የኛ ባለሙያዎች የሁኔታ አጣሪውን ብቃት ሙሉ ድጋፍ አልሰጡትም። አምባሳደር ቼርክን አክለውም ምንም እንኳ ራሻ በውሳኔው ገለልተኛ ብትሆንም፤ ለኤርትራ የተሰጠው ጊዜና ውሳኔው የተላለፈበት መንገድ፤ ህጋዊ ነው አሰራሩም ፍትሃዊ ነው ብለዋል። “ኤርትራ በስልክም ቢሆን አቋሟን እንድታሳውቅ እድሉ ተሰጥቷት ነበር። ይህንን እድል ሊወስዱ በቻሉ ነበር። የአካባቢው መሪዎች በቪዲዮ መልእክታቸውን አሳልፈዋል። ወይንም ደግሞ እዚህ ባሉት ቋሚ መልእክተኛቸው በኩል ተቃውሟቸውን ሊያሰሙ ይችሉ ነበር። እነርሱ ሃሳባቸውን ለመናገር አልፈለጉም፤ ውሳኔው የራሳቸው ነው” ብልዋል ቸርኪን። የጸጥታው ምክር ቤት ኤርትራ አቋሟን እንድታስረዳ በማሰብ ነበር ለባለፈው ሳምንት ታቅዶ የነበረውን የድምጽ መስጫ ቀነ ቀጠሮ ለሰኞ ያዛወረው። ኤርትራም አስቀድማ በፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኩል መልእክት ለማሳለፍ ጠይቃ ነበር። የመንግስቱ ቃል አቀባይ አቶ አሊ አብዱ እንደሚሉት የኤርትራ ባለስልጣንት አስመራ በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ቪዛ ማግኘት አልቻሉም። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሱዛን ራይስ አገራቸው ለልዑካኑ በ24 ሰዓት ውስጥ ቪዛ መስጠቷል ይናገራሉ። “አርብለት አስመራ በሚገኘው ኢምባሲያችን ለ13 ሰዎች ቪዛ ጠየቁን። አስሩን ቪዛዎች ወዲያውኑ ሰጠናቸው። የተቀሩትን 3 ቪዛዎች በማግስቱ ከአራስት ሰዓት በፊት ሰጠናቸው። ሁሉም ቪዛዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ተሰጥተዋል። የፕሬዝደንት ኢሳያስ ቪዛ ወዲያውኑ በሰዓታት ውስጥ ነው የተሰጠው። የኤርትራ መንግስት እነዚህን ሁሉ ከእውነት የራቁ ናቸው ይላል። |
a_eritrean-sanctions-united-nations-07-21-10-98943239_1460405 | https://amharic.voanews.com/a/eritrean-sanctions-united-nations-07-21-10-98943239/1460405.html | የኤርትራ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጣለባትን ማእቀብ እንዲያነሳ ጠየቀች | ኤርትራ ይህንን ጥያቄዋን ያቀረበችው ከጅቡቲ ጋር ያላትን የድንበር ግጭት በውይይት ለመፍታት የጀመረችውን ጥረት ካወደሰ በኋላ ነው። | አንድ የዩናይትድ ስቴይትስ የረጅም ጊዜ የህግ አውጭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራን አሸባሪዎችን ከሚረዱ አገሮች ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንድትገባ ጠይቀዋል ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን-ኪሙን ቢሮ የወጣው ሪፖርት ኤርትራ ከጎረቤቶቿና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ እየተነጋገረች መሆኑን ጠቁሟል። በተለይ ኤርትራ ከጅቡቲ ጋር ያላትን የድንበር ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመቋጨት መወሰኗ ይበል የሚያሰኝ ጅምር መሆኑን አትቷል። የጸጥታው ምክር ቤት በኒው ዮርክ ሲሰበሰብ በጉዳዩ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሀፊ ሊን ፓስኮ ኤርትራ ወታደሮቿን ከአወዛጋቢው ድንበር ማስወጣቷንና አደራዳሪዋ ቃታር ወታደራዊ ታዛቢዎችን በቦታው ማስፈሯን አረጋግጠዋል። “ኤርትራና ጅቡቲ የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት በቃታር መንግስት አደራዳሪነት የወሰዷቸውን ወሳኝ እርምጃዎች እናደንቃለን። ዋና ጸሀፊው የተባበሩት መንግስታት እርዳታ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፤ ሊረዳ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፣” በማለት ሊን ፓስኮ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር አርአያ ደስታ ከጅቡቲ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ጉልህ እመርታ ነው ብለውታል። ነገር ግን የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጣለው ማእቀብ ፍትሃዊ አይደለም በማለት አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “ኤርትራ ለሰላምና ደህንነት ከፍተኛ አትኩሮት ትሰጣለች። በዚህ ምክንያት በአካባቢዋ በሚደረጉ ፍሬአማ ውይይቶች ትርጉም ባለው መልኩ ተሳትፎ እንዳታደርግ መታገድ የለባትም። ዘለቄታ ያለው ሰላምን በሚያመጡ እንቅስቃሴዎች ሁሉ የኤርትራ ተሳትፎ መረጋገጥ አለበት፣” ብለዋል አምባሳደር አርአያ ደስታ። “ከጅቡቲ ጋር በቃታር መንግስት ሸምጋይነት ያገኘናቸው የዲፕሎማሲ ፍሬዎችን ማጤን ያስፈልጋል። በሶማሊያ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን የምናደርገውን ጥረትም ተመልክቶ የጸጥታው ምክር ቤት የጣለብንን መአቀብ እንዲያነሳ እንጠይቃለን። በአስተርጓሚ የተናገሩት የጅቡቲ ተወካይ ካድራ አህመድ ሃሰን በኤርትራ ላይ የተጣለው ማእቀብ የሰላም ውይይት እንዲጀመር በር ከፍቷል ብለዋል። “የተያዘው ጥረት አበረታች ቢሆንም፤ ረጅም መንገድ ይጠብቀናል። በሚቀጥሉት ወራት በሁለታችንም በኩል ቀጣይነት ያላቸው ስራዎችን መስራት ይጠበቃል። የተወያየንባቸው ነጥቦች በእጅጉ ወሳኝ ናቸው፤ የምርኮኞች ጉዳይ፣ የጠፉ ሰዎች ጉዳይና ድንበሩን በካርታ አስምሮ በምድር በችካል እስከመከለል ይሄዳል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን ጊ-ሙን ቢሮ ያወጣው ሪፖርት ኤርትራ የጀመረቻቸውን ጥረቶች አበረታች ናቸው ቢልም፤ የጸጥታው ምክር ቤት ማእቀቡን ሲጥል ያስቀመጣቸውን ሁኔታዎች ለማሟላት ብዙ መስራት እንደሚጠበቅባት ጠቁሟል። ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤርትራ መልካም ጅምሮቿን የሚያበረታቱ ምላሽ ብታገኝም ከዩናይትድ ስቴይትስ በኩል ግኝ ተጨማሪ ጫና እንዲደረግ የህግ አውጭዎች እየወተወቱ ነው። በዩናይትድ ስቴይትስ የህግ አውጭ ክፍል ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ኮንግረስማን ኤድ ሮይስ ኤርትራ አሸባሪዎችን ከሚረዱ አገሮች ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንድትገባ ጠይቀዋል። ኮንግረስ ማን ሮይስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን በጻፉት ደብዳቤ በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ ሀምሌ 4 ቀን የደረሰውን ፍንዳታ ያቀነባበሩ የአል-ቃይዳ አጋሮች ጋር ይሰራል ያሉት የኤርትራ መንግስት ላይ ጫና እንዲደረግ ጠይቀዋል። በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አል-ሸባብ የተባለ የአሸባሪዎች አንጃ በዩጋንዳ ለ76 ሰዎች ህይወት መጥፋት መንስኤ የሆኑትን ጥቃቶች ማከናወኑን አስታውቋል። ድርጊቱም የተከናወነው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል አብዛሀኛው ወታደሮች ከዩጋንዳ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ነው። ታዲያ በኮንግረሱ የሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የጸረ-ሽብርተኝነት፣ የጸረ-ኑክሌር ግንባታና የንግድ ንኡስ ኮሚቴ ተሰሚነት ያላቸው ኮንግረስማን ሮይስ በጻፉት ደብዳቤ “ኤርትራ ለአልሸባብ የምትሰጠው ድጋፍ በአግባቡ በመረጃ የተረጋገጠ ነው” ሲሉ አልሸባብ በአሜሪካ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል። ኤርትራ አሸባሪዎችን ከሚደግፉት አገሮች መካከል ከተፈረጀች ከኩባ፣ ኢራን፣ ሱዳንና ሶሪያ ጋር ትቀላቀላለች። በእነዚህ አገሮች የተጣሉ የዲፕሎማቲክ፣ ኢኮኖሚና የጦር መሳሪያ ማእቀቦች በኤርትራ ላይ ሊጫኑባት ይችላሉ። ኤርትራ ለሶማሊያ ሸምቅ ተዋጊዎች እርዳታ ትሰጥ እንደነበረ መረጃዎች አሉ። ነገር ግን በናይኖቢ የInternational Crisis Group ስራአስኪያጅ E.J. Hogendoorn ኤርትራ የኢትዮጵያን ወታደሮች ይዋጉ ለነበሩ ሸማቂዎች እርዳታ መስጠቷ ቢታወቅም፤ በቀጥታ ለአሸባሪዎቹ የአል-ሸባብ ተዋጊዎች የምታደርገው እርዳታ የለም ይላሉ። “በዚህ ጊዜ ኤርትራ አል-ሸባብን እንደምትረዳ የሚያሳይ ትንሽ እንኳን ማረጋገጫ አልተገኘም። በሶማሊያ የነበረውን የኢትዮጵያን ጦር በእጅ አዙር የሚወጉ ሀይሎችን ታስታጥቅ እንደነበረ መረጃ አለ። ያሉን መረጃዎች የሚጠቁሙት ኤርትራ ሂዝቡል-ኢስላምን እንጂ አል-ሸባብን አትደግፍም። የሂዝቡል ኢስላም እንቅስቃሴዎች በእርግጥ አሳሳቢ ናቸው። ነገር ግን ሂዝቡል ኢስላም በቀጥታ በጎረቤት አገሮች ላይ የሽብር ጥቃቶችን ማቀነባበሩን የሚያሳዩ መረጃዎች የሉም። ሂዝቡል ኢስላም ከአል-ሸባብ ጋር ግንባር ፈጥሮ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለውን የሶማሊያ መንግስት ይወጋል። ሁለቱ ቡድኖች በሶማሊያ እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ይንቀሳቀሱ እንጂ አብዛሃኛውን የሶማሊያ አካባቢዎች የሚያስተዳደረው አል-ሸባብ ነው። አልሸባብ በዩናይትድ ስቴይትስ ጥቅሞች ላይ ከዚህ በፊት ይዝት እደነበር የገለጹት በናይኖቢ የInternational Crisis Group ስራአስኪያጅ E.J. Hogendoorn እሳካሁን ድርጅቱ ከዩናይትስ ስቴይትስ ጥቅሞች ይልቅ የምስራቅ አፍሪካ አገሮችን ሰላምና ጸጥታን በማወክ ረገድ አፍራሽ ሚና መጫወቱን ይገልጻሉ። |
a_rockwell-exhibit-contest10-13-10-104895464_1460770 | https://amharic.voanews.com/a/rockwell-exhibit-contest10-13-10-104895464/1460770.html | የአሜሪካዊያን ኑሮ በየኖርማን ሮክዌል ስእሎች | በእርሳስና በዘይት በሚስላቸው እውነት መሰል ስእሎች በዋሽንግተን ዲሲ በመታየት ላይ ናቸው። በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኢምባሲ የጥበብ ውድድር ከፍቷል። | በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናትድ ስቴይትስ ኢምባሲ በሚቀጥለው አመት የሚከበረውን የፕሬዝደንት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት “የአራቱ ነጻነቶች” ንግግር አስመልክቶ የጥበብ ውድድር አዘጋጅቷል። የፕሬዝደንቱ ንግግር የመሰጠው አሜሪካዊ ሰአሊ ኖርማን ሮክዌል በ1935 ዓ.ም “የአሜሪካ ኑሮ” በሚል አራት የስእል ራብአይ ለትእይንት አብቅቷል። እነዚህ ታዋቂ ስእሎች በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ እየታዩ ይገኛሉ። በዋሽንግተን ዲሲ እምብርት የሚገኘው የስሚትሶኒያን ማእከል የታዋቂውን አሜሪካዊ ሰአሊ ኖርማን ሮክዌል ስራዎች ለትእይንት አቅርቧል። “የአሜሪካ ኑሮ” በሚል የተሳሉት አራቱ ስእሎች በፕሬዝደንቱ “የአራቱ ነጻነቶች” ንግግር የተቃኙ ናቸው። የሃይማኖት ነጻነት፣ የመፈልግ ነጻነት፣ ከፍራቻ ነጻ መሆንና የመናገር ነጻነት ናቸው አራቱ ነጻነቶች። አንደኛው ስእል በህዝብ መካከል አንድ ሰው ተነስቶ ሲናገር ያሳያል። ሰዎች ተሰባስበው ሲጸልዩ፣ ቤተሰቦች በምግብ በተሞላ የምግብ ገበታ ላይ ተቀምጠውና ባልና ሚስት ልጆቻቸውን ሲያስተኙ የሚያሳዩ ናቸው ስእሎቹ። አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ የፕሬዝደንት ሩዝቬልት ንግግር የተደረገበትን 70ኛ አመት በሚቀጥለው አመት መከበሩን አስመልክቶ ነው ይሄንን የስእል ውድድር የሚያካሂደው። በኤግዚቢሽኑ ከቀረቡት የኖርማን ሮክዌል ስራዎች በርካታዎቹ በአሜሪካዊው ፊልም ሰሪ ጆርጅ ሉካስ ባለቤትነት ያሉ ናቸው። “ስለእውነተኛ በየለቱ የምናያቸው ሰዎች ነው የሚያወራው በፍሬም ውስጥ የሚያሳየን” ይላላ ጆርጅ ሉካስ “ይሄንን ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ታዋቂው የፊልም ሰሪ ስቲቨን ስፒልበርግም የኖርማን ሮክዌል አድናቂ ነው። ይህወትን በሲኒማ እንደምናሳየው ሮክዌል በእርሳስ በሚሞነጫጭራቸውና በዘይት ቀለም በሚስላቸው ስራዎቹ ኑሮን ቅልብጭ አድርጎ ያሳያል ይላል። በተለይ አሜሪካዊያኑን ኑሮ። ፕሬዝደንት ሩዝቬልትና ሰአሊው ኖርማን ሮክዌል ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ነበራቸው። አጼ ሃይለ-ስላሴ በ1935ዓም ለፕሬዝደንት ሩዝቬልት አሁን በሽሮሜዳ የሚገኘውን የአሜሪካ ኢምባሲ እንዲሰራ መሬቱን ሰጥተዋል። ሰአሊው ሞርማን ሮክዌል ወደ ኢትዮጵያ በ1945ዓም ተጉዞ ነበር። በዚያን ጊዜ በሰላም ጓድነት ይሰሩ የነበሩ አሜሪካዊያንን ስራ በቡርሹ ለማስቀረት ነበር ሮክዌል ወደ ኢትዮጵያ ያቀናው። በደሴ ከተማ አቅራቢያ አንድ አሜሪካዊ የሰላም ጓድ የቤተሰቡ አካል ሆኖ በሚኖርበት መንደር እርሻ ከሚያርስ ኢትዮጵያዊ ገበሬ ጋር ሆኖ የሳለው ስእል ከፍተኛ አድናቆት የተቸረው ስራው ነው። ወደ ኋላ ስእሉ በዩናይትድ ስቴይትስ የፖስታ ድርጅት ቴምብር ሆኖ ወጥቷል። ያሜሪካ ኢምባሲ ለዚህ ውድድር የ25ሽህ ብር ሽልማት አዘጋጅቷል። የማመልከቻ ቀኑ የሚያልፈው በአውሮፓዊያኑ አመት 2010 የመጨረሻ ቀን ዲሴምበር 31 ቀን ነው። |
a_amh-ak-us-midterm-elections-global-implications-analysis-106476383_1458441 | https://amharic.voanews.com/a/amh-ak-us-midterm-elections-global-implications-analysis-106476383/1458441.html | የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤቶች ምርጫና ዓለም አቀፍ አንድምታው | ሪፐብሊካኖች ምርጫውን አሸንፈው ሁለቱንም ምክር ቤቶች ወይም አንዱን ብቻ እንኳን ከቆጣጠሩ፥ የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች አስመልክቶ በርከት ያሉ ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ። | በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ማክሰኞ ጥቅምት 23 የሚካሄዱት Midterm Elections በመባል የሚታወቁት የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በአሁኑ ወቅት አብላጫውን የሁለቱን ምክር ቤቶች የኅግ አውጪውንና የእንደራሴዎች ምክር ቤቶች፤ መቀመጫዎች ለያዘው የፕሬዝዳንት ኦባማ የዲሞክራቶች ፓርቲ ፈተና ይደቅናል፤ ተብሎ ተገምቷል። የሪፐብሊካኑ ፓርቲ የብልጫውን ድምፅ ያገኝ ይሆናል፤ የሚል ሠፊ ግምት በተያዘባቸው በእነኚህ የአጋማሽ ጊዜ ምርጫዎች፤ በርካታ መቀመጫዎችን ያጡ ይሆናል የተባሉት ዲሞክራቶች፥ ከተቀናቃኛቸው በሚገጥማቸው ፈተና፥ ከዲሞክራቱ ፓርቲ የሆኑት ፕሬዝዳንት ኦባማ በቀጣዩ የሁለት ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው ለማሳካት ያቀዷቸው ውጥኖች «ይደናቀፋሉ፤» የሚል ግምት አሳድሯል። እንደ ቅድመ ምርጫ ትንበያዎቹ ሪፐብሊካን የሁለቱንም ምክር ቤቶች አብላጫ መቀመጫዎች ከያዙ፥ የተባሉት ለውጦች፥ በአገር ውስጥ ጉዳዮች ብቻ ሳይወሰኑ፥ የዩናይትድ ስቴትስን የውጭ ፖሊሲ ጨምሮ፥ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምታጨወታቸው «ዋና ዋና የሚሰኙ ሚናዎቿም ይንፀባረቃሉ፤» እየተባለ ነው። በርዕሱ ዙሪያ ትንታኔ የሚሰጡን የፖለቲካ ሳይንቲስት ጋብዘናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የህግ ባለ ሞያ ናቸው። |
a_osaman-mohammed092910-104029894_1460868 | https://amharic.voanews.com/a/osaman-mohammed092910-104029894/1460868.html | የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን መሀመድ ሳለህ የኤርትራ መሬት በኢትዮጵያ በህገ ወጥ ሲያዝ ባለማስለቀቅ የመንግስታቱን ድርጅት ወነጀሉ | ዉዝግቡ የሚመለከታቸዉ አካላት ሃላፊነት ካልሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማደራደር ስልጣን የለዉም ብለዋል አቶ ስዩም መስፍን ። | አቶ ኦስማን የግጭት መቀጠል ለኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች ከባድ ሸክም ከመሆኑም በላይ የአካባቢዉን ሁኔታ የሚያወሳስብ ነዉ ሲሉ,የኢትዮጵያዉ አቻቸዉ አቶ ስዩም መስፍን በበኩላቸዉ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንበሩን ለማካለል ያቀረበዉ ዉሳኔ ላይ ”አልወያይም” ያለችዉ ኤርትራ ናት ብለዋል። የኤርትራ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን መሀመድ ሳለህ የኤርትራ መሬት በህገ ወጥ በኢትዮጵያ ሲያዝ፣ አይቶ እንዳላዬ ቸል በማለት የመንግስታቱን ድርጅት ከሰዋል። ኢትዮጵያ የኤርትራን ነጻ ግዛት እንደያዘች ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዚህን እርምጃ አሳሳቢነት ቸል ማለቱን መርጦአል። የኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር አካላይ ኮሚሽን ዉሳኔዉን ከሰጠ ስምንት ዓመታትና ኮሚሽኑ ሃላፊነቱን አጠናቆ ያካለለዉን ካርታ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካሳወቀ በሁዋላ፣ የኢትዮጵ ከህግ ዉጭ የኤርትራን ግዛት መቆጣጠርና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩን ቸል ማለት፣ የሁለቱ አገሮች ግጭት መቀጠል ለኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች ከባድ ሸክም ከመሆኑም በላይ የአካባቢዉን ሁኔታ የሚያወሳስብ ነዉ ብለዋል። የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ዛሬ በመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ከ1990 ዎቹ ወዲህ ኤርትራ በርካታ ጎሬቤቶችን ወራለች፣ የመንግስታቱ ድርጅት ድረ ገጽ የኤርትራ መንግስት ያለ ምንም ትንኮሳ ኢትዮጵያን ወሮ ኢትዮጵያ ተከላክላ የኤርትራን ሰራዊት መመለስዋን ያሳያል ሲሉ በዋቢነት ጠቅሰዋል። ምንም እንክዋን የተባባበሩት መንግስታትን ህግ ጥሳ ኢትዮጵያን ብትወርም ኤርትራ ዛሬ ኢትዮጵያ ወረረችኝ የሚል ዘመቻ ይዛለች ብለዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንበሩን ለማካልል ያቀረበዉ ካርታ ላይ፤ ቁጭ ብለን እንወያይ በሚለዉ የኢትዮጵያ ጥያቄ ያልተስማማችዉም ኤርትራ ናት ብለዋል። ”ድንበሬ ተያዘ” የሚለዉ የኤርትራ ግምት ነዉ ያሉት አቶ ስዩም መስፍን ዉዝግብ ካለ፣ ዉዝግቡ የሚመለከታቸዉ አካላት ሃላፊነት ካልሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማደራደር ስልጣን የለዉም ብለዋል። ዘገባውን ያድምጡ! |
a_amhara-landslide-08-24-10-101405284_1461942 | https://amharic.voanews.com/a/amhara-landslide-08-24-10-101405284/1461942.html | በአማራ ክልል የመሬት መንሸራተት 19 ሰዎችን ገደለ | በመርሳ ከተማ በደረሰው የመሬት መንሸራተት 14 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ 24 ቆስለዋል። በውርጌሳ ዙሪያ አምስት ሰዎች ሞተዋል። | አከታትሎ የጣለ ዝናብ ያደረሰው የጎርፍ አደጋ በሀብሩ 2ሽህ ሰዎችን አፈናቅሏል አቶ አሰፋ ነጋሲ በሀብሩ ወረዳ በመርሳ ከተማ ለረጂም ጊዜ የኖሩ የአገር ሽማግሌ ናቸው። አበይ ተራራ በሚባለው ስፍራ ከሰሩት ቤታቸው ቁልቁል ከተማዋን እየተመለከቱ የህዝቡ ብዛት ከጥቂት ሽዎች ወደ አስር ሽዎች ሲያድግ ተመልከተዋል። በግብርና ስራ የተሰማሩት አቶ አሰፋ ቤት እሁድ ሌሊት በመሬት መንሸራተት ፈርሷል። አቶ አሰፋ ምሽቱን አነስ ባለች ቤት ስላሳለፉ በአደጋው ጉዳት አልደረሰባቸውም። በዋናው ቤት ውስጥ የነበሩት ባለቤታቸው፣ ልጃቸውና የልጅ ልጃቸው ገበሬያቸውን ጨምረው ህይወታቸው አልፏል። የድረሱን ጥሪ “እሪታውን” ጎረቤቶች ሲያሰሙ፤ የአካባቢው ሰውና ወዳጅ ዘመዶች ለእርዳታ ወደ አቶ አሰፋ ቤት ፍርስራሽ የተቀበሩ ሰዎችን ሊያድኑ ያመራሉ። በዚህ ጊዜ ነው ትልቁና ብዙዎችን የጎዳው መንሸራተት የደረሰው። “እንደ ደማሚት መሬቱ ተገምሶ እላያችን ላይ ወደቀ ሲሉ” ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ተናግረዋል። የመሬት መንሸራተቱ 14 ሰዎችን ሲገድል ከ24 ያላነሱ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ አስከትሏል። “ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በወልዲያ ሆስፒታልና በመርሳ ጤና ጣቢያ በመታከም ላይ ይገኛሉ” ሲሉ የመርሳ ከተማ አስተደደር ባለስልጣን አቶ ሙሀመድ ያሲን ተናግረዋል። “በአካባቢው የጎርፍ አደጋም ደርሷል… በተለይ በቡሆሮና በውርጌሳ አካባቢ ባለው ተደምሮ ከሁለት ሽህ በላይ ህዝብ የተፈናቀለ መሆኑን ነው መረጃው የሚያሳየው። ” ብለዋል አቶ ሙሀመድ። በጎርፉ ለተጎዱ ገበሬዎች የእርዳታ አቅርቦትና የመልሶ ማቋቋም ስራን ለማስተባበር እየጣረ መሆኑን የአካባቢው አስተዳደር ይናገራል። በወረዳው ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ችግር ደርሶ ስለማያውቅ አቅርቦት ለማዳረስ የሚያስችሉ መሰረቶችና ልምዶች የሉም። ይሄም የእርዳታ አቅርቦቱን ሊያጓትተው ይችላል በሚል ስጋት አለ። የአካባቢው አስተዳደር ግን በቀጣይነት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቋል። |
a_ethiopia-press-review-8-23-13_1735792 | https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-press-review-8-23-13/1735792.html | ኢትዮጵያ በጋዜጦች | የሱዳንና የሶማልያ ፕረዚዳንቶችን የመሳሰሉት በዝክረ መለስ ስነ-ስርአት የተሳተፉት የአፍሪቃ መሪዎች “የአፍሪቃ ድምጽ” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርን አሞግሰዋል። | ዋሽንግተን ዲሲ — ዋሽንግትተ ፖስት ጋዜጣ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርመለስ ዜናዊ ህልፈት አንደኛ አመትን ለማሰብ ስለተደረገው ስነስርአት ባወጣው የአሶሼተድ ፕረስ ዘገባ አቶ መለስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ አንድ አመት ቢያልፍም የተለወጠ ነገ የለም ይላል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አመቱን ሙሉ ሲሞገሱ ቆይተዋል። ምስላቸውም በሀገሪቱ ዙርያ በሚገኙት የመንግስት መስርያ ቤቶች እንደተሰቀለ ነው ይላል ጋዜጣው ላይ የወጣው ዘገባ። በሀገሪቱ ዙርያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርአት ተደርጎላቸዋል። ለሳቸው ማስታውሻም ከአርባ ስምንት በላይ የመናፈሻ ቦታዎች ተመስርተዋል። በመዲናይቱ አዲስ አበባም የሳቸው ስራዎች የሚዘከሩበት ቤተ መዘክር ለመገንባት መሰረተ-ዲንጋይ ተጥሏል። የሱዳንና የሶማልያ ፕረዚዳንቶችን የመሳሰሉት በዝክረ መለስ ስነ-ስርአት የተገኙት የአፍሪቃ መሪዎች “የአፍሪቃ ድምጽ” በማለት አቶ መለስን እንዳሞገሱ ዋሽንግትተ ፖስት ጋዜጣ ላይ የወጣው የአሶሼትድ ፕረስ የዜና አገግሎት ዘገባ ጠቅሷል። ሌሎች ርእሶችም ተካተዋል። ከሚቀጥለው ድምጽ ያድምጡ። |
a_the-idea-series-ethiopian-history-selective-memory-a-historian-view-voa-dr-shimelis-bonsa-with-alula-kebede-july-2017_3968766 | https://amharic.voanews.com/a/the-idea-series-ethiopian-history-selective-memory-a-historian-view-voa-dr-shimelis-bonsa-with-alula-kebede-july-2017/3968766.html | ታሪክ ‘ባስታዋሹ’ መነጽር እና ...በታሪክ ምርምርና ፋይዳ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሌሎች ወጎች | “ክርክሩ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን መነጋገሪያ መድረክ የት ነው? እያንዳንዱ ሰው ከራሱ መንገድ ነው የሚጽፈው። በታሪክ ሞያ ውስጥ ይሄን ምንድን ነው የምንለው? መርጦ ማስታወስ እና መርጦ መርሳት። የተወሰኑ ነገሮች ተመርጠው ይታወሳሉ። ተመርጠውም ይረሳሉ። ታዲያ እነኚህ ጨርሶ እውነታ የላቸውም ማለት አይደለም። ነገር ግን ጎዶሎ እውነታዎች ነው የሚሆኑት። የራስን ፍላጎት ለማስፈጸም ነው የሚውሉት።” ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ። | አዎን! ይህም “ሃሳብ እንደ መንገድ .. በማስረጃ የተደገፉ ጠቃሚ ወጎች” በሚል አብይ ርዕስ የተጀመረው አዲስ ተከታታይ ወግ አካል ነው። የታሪክ ትንተና በፈቃድና ከጥቅም አንጻር ሲተረጎም? ... ታሪክ ባስታዋሹ መነጽር ነገር ግን በብዙዎች ህይወት ላይ የሚኖረው አንድምታ እንደምን ይታያል? የታሪክ ምርምር ተጨባጭ ፋይዳስ በእርግጥ ምንድን ነው? እንግዳችን ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ ናቸው። በState University of New York - Stony Brook የአፍሪካ ዘመናዊ ታሪክና ፖለቲካ እንዲሁም የከተማ ጉዳዮች መምህር ናቸው። በፕሬስ፥ በሴቶች ጉዳይ፣ ፍልሰት፣ በከተሜነትና ከተማ ነክ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረጓቸው በርካታ ጥናትና ምርምሮች ለህትመት በቅተዋል። “ከተማ እንደ አገር” የሚለውን ጨምሮ በከተማ በመንግስትና በሕብረተሰብ መሃል ያለውን መስተጋብር በሚመረምሩ የጥናት ሥራዎቻቸው፤ በሰሞንኛ አነጋጋሪ ታሪክ ቀመስ ጉዳዮች እና በታሪክ ምርምርና ፋይዳ ዙሪያ የተካሄደውን ባለ ሦሥት ክፍሎች ተከታታይ ውይይት ከዚህ ያድምጡ። |
a_article-------------114307439_1460381 | https://amharic.voanews.com/a/article-------------114307439/1460381.html | ቻይና ከዩናይትድ ስቴይትስ ጋር የጠበቀ የንግድ ግንኙነት እንጂኖራት ፕሬዝደንት ሁ ጥሪ አቀረቡ | ዩናይትድ ስቴይትስን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ጂንታው አገራቸው ከአሜሪካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራት እንደምትፈልግ ገልጸው፤ ቻይና አጋር እንጂ ስጋት አይደለችም ብለዋል። | የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ጂንታው በዩናይትድ ስቴይትስ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ1989ወዲህ በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስታዊ ልዑካንን በመምራት የቻይና ፕሬዝደንት ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ ሲጓዝ ሁ የመጀመሪያው ናቸው። በዚህ ጉብኝታቸው ሚስተር ሁ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአንድሩውስ ወታደራዊ የአውሮፕላን ማረፊያ በምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ዛሬ በዋይት ሀውስ ቤተ-መንግስት ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። የአሜሪካ ኩባንያዎችና ድርጅቶች ዋጋው ከወረደው የቻይና ገንዘብ ጋር በዶላር ለገበያ ውድድር መቅረብ ከብዶናል በሚል ሮሮ ማሰማት ከጀመሩ ቆይተዋል። በይፋ የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስትና የመገናኛ ብዙሃን ችግሩን አስመልክቶ መላ መምታት ከጀመሩ አንድ አመት አልፎታል። እስካሁን የተለወጠ ነገር የለም። የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ከዩናይትድ ስቴይትሱ አቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር በንግድ ዙርያ ሲመክሩ ሰንብተዋል። በሰፊው ውይይት ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቀው ጉዳይ ቻይና የሀገር በቀል ድርጅቶቿን ታበረታታለች ለውጭ ሀገር ኩባንያዎች ገበያ በተለያዩ የቢሮክራሲና የህግ ማነቆዎች ገበያ እንዳያገኙ ትጥራለች በሚል አሜሪካዊያን ነጋዴዎች ያማርራሉ። በተለይ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በማደግ ላይ ያለውን ያቻይናን ኢንዱስትሪ የገበያቸው መዳረሻ ለማድረግ ይፈልጋሉ፤ ግን ማነቆዎቹ በዝተውባቸዋል። ሚስተር ኦባማ ያቻይናንና አሜሪካን የትምህርት፣ የቴክኖሎጂ፣ የንግድና የቱሪዝም ግንኙነት መጠናከር አስመልክተው፤ በብዙዎቹ መስኮች ተወዳዳሪዎች ብንሆንም በብዙዎቹ ደግሞ አብረም መስራት እንችላለን ብለዋል። ሚስተር ሁ ጂንታውም በበኩላቸው ወደ ዩናይትድስቴይትስ የመጡት የሁለቱን አገሮችና ህዝቦች ትብብር፣ አጋርነት፤ እንዲሁም እርስ-በርስ መተማመን ለማጠናከር መሆኑን ተናግረዋል። ሚስተር ሁ ይሄ ግንኙነት በጸና መሰረት ላይ መቆም ያለበት መሆኑን ገልጸዋል። |
a_the-purpose-of-education-experts-discuss-the-state-of-education-in-ethiopia-with-voa-alula-kebede-march-1-2021_5799589 | https://amharic.voanews.com/a/the-purpose-of-education-experts-discuss-the-state-of-education-in-ethiopia-with-voa-alula-kebede-march-1-2021/5799589.html | ለምን እንማራለን? | "..ራሳችን በራሳችን የመሠረትነው ትምህርት ከኖረን ቆይቷል።.." ዶ/ር ሃዋኒ ንጉሴ "የራሳቸው ነጻነት ኖሯቸው ማሰብ መፈተሽ እንዲችሉ - ተዓማኒነት ያለውን ከሌለው መለየት የሚያስችል የአስተሳሰብ ችሎታ፥ የሰው መብት የሚያከብር ፍጡር እንዲሆኑ ለማድረግ የምንጠቀምበት ሂደት ነው።" ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ። "..ከዛሬ የተሻለ ነገ እንዲኖረን የሚረዳ እና ችግርን የሚፈታ መሆን አለበት ብዬ ነው የማምነው።.." ዶ/ር ፋንታሁን አድማስ። | ዋሽንግተን ዲሲ - ሎሳንጀለስ - ሺካጎ - አዲስ አበባ — በዝግታ … በጊዜ ውስጥ በሚገበይ እውቀት ሁነኛ ለውጥ ማምጣት ቻሉና “ለአንዳች ቁም ነገር ማብቃቱ” የታወቀና ሁሌም የሚጠበቅ ትሩፋቱ ይመስላል። ኑሮን ለማሸነፍ የሚበጅ ክህሎት ማጎናጸፉና የሰው ልጆችን ህይወት ለማሻሻል ዓይነተኛ መንገድነቱ ሳይሆን ዕድሉን ማግኘት ያለማግኘት ነው ጥያቄው። የመልካም ፍሬዎቹን መበርከት: የመንገዱን ማለቂያ ያለው ያለመምሰል እና ጉዞው የዕድሜ ልክ የሆነውን ያህል ግን አንዳንዶች በዙሪያቸው ያለውን ዓለም አይተው መለስ ሲሉ “በእርግጥ ከትምህርት የጠበቅነውን እያገኘን ነው? ” በሚል መጠየቃቸው አልቀረም። ለመሆኑ መላውስ ምን ይሆን? ፍለጋው ቀጥሏል። የትምህርት ጥራት ወይም ይዘት እዚህ ውስጥ ድርሻው ምን ይሆን? ሦስት የትምህርት ጉዳይ አዋቂዎች ለውይይት ጋብዘናል። ዶ/ር ሃዋኒ ንጉሴ ከሎሳንጀለስ ዶ/ር አዳነ ገበያው ካሳ ከሺካጎ እና ዶ/ር ፋንታሁን አድማስ ከአዲስ አበባ ናቸው። የትምህርትን ትርጏሜ: ፋይዳ እና ጥራት ይፈትሻሉ። |
a_amh-ned-havel-1-11-2012-137122993_1460387 | https://amharic.voanews.com/a/amh-ned-havel-1-11-2012-137122993/1460387.html | በኢትዮጵያ መንግስት የሚዋከቡና የሚታሰሩ ተጠቂዎች ቢመስሉም አሸናፊዎች ናቸው ሲሉ ብርቱካን ሚደቅሳ ተናገሩ | በዋሽንግተን ዲሲ በተሰናዳ የቀድሞው የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ቫትስላቭ ሃቨል መታሰቢያ የብርማዋ አንሳንሱቺ፣ ፕሬዝደንት ኦባማ፣ ዳሊ ላማና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች መልእክት አስተላልፈዋል | በታህሳስ ወር በህመም የሞቱት የቀድሞው የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ቫትስላብ ሃቨል፤ ቼኮስላቫኪያን ከኮሚውኒስት አገዛዝ ነጻ ለማውጣት “የቬልቬት አብዮት” በመባል በሚታወቀው ሰላማዊ ትግል በ1981ዓም የቼኮዝላቫኪያ ፕሬዝደንት ሆኑ። በ1985 ቼኮዝላቫኪያ ለሁለት ተከፍላ ስሎቫኪያና ቼክ ሪፐብሊክ ስትባል፤ የመጀመሪያው የቼክ ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። ቫትስላቭ ሃቨል በመላው አለም የሚታወቁት በፖለቲካቸው ብቻ አይደለም። እንዲያውም ሃቨል ከምንም በላይ እራሳቸውን የሚገልጹት፤ ጸሃፊ ተውኔት አድርገው ነው። የሃቨል ተውኔቶች ታዲያ፤ ፍሬ ከርስኪ አልነበሩም፤ መሰረታቸው እውነት ሆኖ የቼኮችን ህዝና የዓለምን ህዝብ አንድ የሚያደርጉ ሰብዓዊ ባህርያትና ፍላጎቶች ጣራና ድግድዳ ሆነው የተዋሃዱባቸው ናቸው። የተውኔቶቹ ክዳን ደሞ፤ ነጻነት፣ ተስፋና ዴሞክራሲ ነበሩ። ቼኮዝላቫኪያ የተፈጠረችው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ሲሆን፡ አስቀድማ በጀርመኖች ጠንካራ እጅ ትገዛ የነበረችው የምስራቅ አውሮፓ አገር፤ ቀጥላ በራሻ ኮሚኒስቶች እጅ ወደቀች። በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ቼኮዝላቫኪያ የምእራባዊያንና የምስራቅ ሶሻሊስቶች የመቆራቆሻ ሜዳ ነበረች። በዚህ የቁርሾ ጊዜ የኖሩት ሃቨል፤ ስራዎቻቸው የጊዜውን ሁኔታዎች ያሳዩ ነበር። ይሄ ታዲያ በሶሻሊስቶቹ አልተወደደላቸውም። በተለይ ስለ ግለሰቦች ነጻነት፣ እኩልነትና ዜጎች እራሳቸውን ለማስተዳደር ያላቸውን መብቶች የሚያሳዩ መልእክቶች ለተደጋጋሚ እስራትና ወከባ ዳርጓቸዋል። በ1980ዎቹ ሃቨልና መሰል ዜጎቻቸው በሰላማዊ መንገድ የሶሻሊዝም አስተዳድርን ለመጣል ተደራጅተው ተንቀሳቀሱ። መሳሪያቸው ንግግር፣ ብእርና ጠብቆ የህዝቡን ብሶት የማደራጀት ብቃት ነበር። ተሳካላቸው። አንድም ሰው ሳይሞት “በቬልቬት አብዮት” የሰላማዊ ትግል ሶሻሊስቶችን አሽቀንጥረው ጣሉ። በዚያን ወቅት በቼኮዝላቫኪያ የዩናይትድ ስቴይትስ አምባሳደር ዊሊያም ሉርስ፤ ሃቨል ፕሬዝደንት ከመሆናቸው አንድ ቀን አስቀድሞ አብረዋቸው እራት በልተው ነበር። “የቆዳ ጃኬት ለብሰው በየመንገዱ ሰልፍ ያስተባብሩ የነበሩ የፋብሪካ ሰራተኞች፤ በአዲሲቱ ቼኮዝላቫኪያ የካቢኒ ሚኒስትሮች ሆኑ” ብለዋል። ለዴሞክራሲ በሚሰራው National Endowment for Democracy ባሰናዳው የሃቨል መታሰቢያ ፕሬዝደንት ኦባማ በአካል ባይገኙም በቢል ክሊንተን አስተዳድር ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት ማድሊን ኦልብራይት መልእክታቸውን እንዲያነቡ ጠይቀዋቸዋል። “ሁላችሁም ጋር በአንድነት የቫትላቭ ሃቨልን ህይወትና ስራዎች ስዘክር ደስታ ይሰማኛል። ከጸሃፊ ተውኔትነት፣ ወደ ፖለቲካ እስረኛነት፣ ከዚያ ወደፕሬዝደንትነት ያደረጉትጉዞ፤ ነጻነትን ለሚሹ የአለም ህዝቦች አርዓያ ሆኗል። በዋሽንግተን ዲሲ ሃቨልን ለማስታወስ በተሰናዳው ዝግጅት በርካታ የአለም ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎችና መልእክተኞች ተገኝተዋል። ከኩባ፣ እስከ ሞንጎሊያ፣ ቲቤት፣ በርማ፣ ኢትዮጵያ፣ አሜሪካና ቼክ የታወቁ ስሞች ይህንን የነጻነት ሰው ዘክረዋል። የቲቤት ህዝቦች የመንፈሳዊ መሪ ዳሊ ላማ በጽሁፍ መልእክታቸውን ልከዋል። “ከቲቤታዊያን ጎን ተሰልፈዋል። በጋራ ያረቀቁት የሰብዓዊ መብት ቻርተር 77 በአገራቸው ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ዜጎችም ትልቅ ለውጥ ያመጣ ነው። በቅርቡ ቻርተር 8 የሚባል ተመሳሳይ ህግ በቻይና ረቋል። በቃላት ብቻ ሳይሆን ጓደኝነታቸውን በተግባር አሳይተዋል። የቻይና ተቃዋሚ ሉ ሻቦ ከእስር እንዲፈታም ተከላክለዋል” ይላል የዳሊ ላማ መልእክት። ቫትስላቭ ሃቨል የጤንነት ሁኔታቸው እያስቆለቆለ ባለበት ወቅት በጋዜጠኞች ተከበው ፕራግ ለሚገኘው የቻይና ኢምባሲ ሉ ሻቦን መንግስቱ እንዲለቅ ደብዳቤ አስገብተዋል። ሃቨል ጤንነታቸው እያሽቆለቆለ በመጣበት ጊዜም የሌሎችን ህዝቦች ትግል አልረሱም። በበርማ ከወታደራዊ አገዛዝ ጋር ተፋጠው በእስርና በወከባ የሚጎሳቆሉት አን ሳን ሱቺ ሃቨል ካረፉ ከሁለት ቀናት በኋላ ደብዳቤ ደረሳቸው። “ለ50 አመታት ከዘለቀ አምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ ወጥቶ ሁሉን አቀፍ፣ ዴሞክራሲያዊ አስተዳድር የመመስረቻው መንገድ ከባድ ነው። እኛም 50 ዓመታት በጭቆና ኖረናል። መጀመሪያ ጀርመኖች፤ ከዚያ ኮሚኒስቶች። የቬልቬት አብዮት ከተሳካ ከ22 ዓመታት ቢያልፉም አሁንም የፈለግንው ቦታ አልደረስንም። በዚህ የመታሰቢያ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያዋ አን ሳን ሱቺ በመባል ወደ መድረክ የተጠሩት ለዴሞክራሲ በሚሰራው National Endowment for Democracy ጥናት በማድረግ ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊት ተቃዋሚና የዴሞክራሲ አቀንቃኝ ብርቱካን ሚደቅሳ፤ የኢትዮጵያን ጉዳይ ከአለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር በማጣቀስ ንግግር አድርገዋል። ወይዘሪት ብርቱካን የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን በምርጫ 97 ከመሩ በኋላ ለሁለት አመት ያህል በታሰሩበት፤ ቆይቶ ደግሞ የይቅርታ ወረቀታቸው ተቀዶ ለብቻቸው በታሰሩትበ ወቅት፤ ተስፋ ይሰጣቸው የነበረው የቫትስላቭ ሃቨል ጽሁፎች እንደሆኑ ያስታውሳሉ። “ጉልበት የሌላቸው ህዙሃን ሃይል The powerof the Powerless በሚል ቫትስላቭ ሃቨል የጸፉት መጽናኛና መበረታቻዪ ነበር። ነጻና የተከበረ የሰው ይህወት ለመምራት ያለኝን ቁርጠኝነት አጠንክሮታል። አንድ ግለሰብ ጭቆናን እምቢ ሲል፤ የሚያሳልፈው መልእክት ከተሳካ አብዮት ጋር የሚስተካከል ትርጉም አለው። አንድም ሰው ሆነ ብዙ ሰዎች ያለውን ስርዓት ማንገጫገጫቸው፤ የእንቅስቃሴዎች ሁሉ የመጀመሪያ እርምጃ ነው” ብለዋል ብርቱካን ሚደቅሳ። ወይዘሪት ብርቱካን፤ የሃቨልን የሰላማዊ አብዮትና የዴሞክራሲ ፍልስፍናዎች ከኢትዮጵያ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታዎች ጋር አነጻጽረዋል። “የኢትዮጵያ መንግስት የሚቃወሙትን ሁሉ ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ብዙ ሳይተች በጭካኔ ቢያዋክብም፤ እነዚህ ተጠቂዎች ደካማና ረዳት አልባ ቢመስሉም፤ ለኔ አሸናፊዎች ናቸው። ምክንያቱም በውሸት አንኖርም ሲሉ ስርዓቱን በመቃወማቸው። በኢትዮጵያ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና መሰሎቹ ይፈቱ ሲሉ ወይዘሪት ብርቱካን በንግግራቸው ጠይቀዋል። በዚህ ስነስርዓት ከኩባ ኦስዋልዶ ፓያ፣ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማድሊን ኦልብራይት፣ ከቻይና ሊ ሻሮንግ፣ እንዲሁም ከሌሎች ለዴሞክራሲ ትግል ከሚደረግባቸው አካባቢዎች “ተቃዋሚዎች” ንግግር አድርገዋል። |
a_ethiopia-health-11-12-10-109949584_1458542 | https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-health-11-12-10-109949584/1458542.html | የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ለማሳደግ ዩናይትድ ስቴይትስ ተጨማሪ እገዛ እያደረገች ነው | ኢትዮጵያ በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት የግሎባል ሄልዝ ኢኒሺየቲቭ በጤና ዙሪያ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው ከተመረጡ ጥቂት አገሮች አንዷ ነች። | በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን በሚገኘው የባቲ የጤና ጣቢያ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኛ የሆነችው ዘቢባ ሰይድ መድሃኒቶችን ከመድሃኒት ቤት ለመውሰድ መጥታለች። መድሃኒት ቤቱ ተጨናንቋል። ከኦሮሚያ ዞንና ከቅርበቱ አንጻር ከአፋር ክልል የሚመጡ ተገልጋዮች በጤና ጣቢያው ይገኛሉ። ይሄንን መሰል የጤና ጣቢያ በተለይ በገጠር አካባቢ ማግኘት አይቻልም። ለዚህ ነው የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ምንስቴር የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ያሰማራው። እንደ ዘቢባ መሰል ከ32ሽህ በላይ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በመላው ኢትዮጵያ ከወረዳ እስከ ጎጥ ድረስ ከማህበረሰቡ ጋር እየኖሩ ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል፤ አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት በመስጠትና ከአቅማቸው በላይ የሆኑትን ጉዳዮች ወደ ክሊኒኮች፣ ጤና ጣቢያና ሆስፒታሎች መላክ ነው ስራቸው። ይሄ ስልት የተዋጣለት እንደሆነ በባራክ ኦባማ አስተዳድር በጤና ጉዳዮች የዋይት ሃውስ የበጀት አማካሪ ዶክተር ዝክየል ኢማኑዌል የተናገሩት። “እዚህ በአግባቡ እየሰሩና ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ነገሮችን አስተውያለሁ። በተለያዩ የጤና ኬላዎች ብዙ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን ተመልክቻለሁ። ይሄ በእውነቱ በኢትዮጵያ ከሚታዩ ትልቅ እመርታዎች አንዱ ነው። ውጤታማ ነው። ሀገሪቱ 32 ሽህ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን በአጭር ጊዜ አሰልጥና ወደ ገጠር ቀበሌዎች በመላክ የሚደነቅ ስራን ሲሰሩ ተመልክተናል። ማህበረሰቡን ያስተምራሉ፣ መሰረታዊ የጤና አገልግሎትም ይሰጣሉ። የወባ በሽትን በመከላከል ረገድና የቤተሰብ ምጣኔን በተመለከተ የተሰሩ ስራዎች በእጅጉ የሚደነቁ ናቸው” ብለዋል። ዶክተር ዚክ ኢማኑዌል በጎበኟቸው የአመያና ዎንጭ ወረዳዎች ከአንደ አመት በፊት የወባ መከላከያ አጎበሮች ተከፋፍለው ነበር፣ የወባ በሽታ መለላከልና ህክምና አገልግሎትም በዚሁ አመት ተስፋፍቷል። ውጤቱ በወባ በሽታ የተጠቁት ሰዎች ቁጥር በ90 ከመቶ ቀንሷል፤ ከሁለት አይነት የወባ ተውሳኮች ማለት ከቫይቫክስና ፋልሲፋረም የሚሞቱ ሰዎችም ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል። “በግልጽ እንደሚታየው የአልጋ አጎበሮች ስርጭት፣ የማህበረሰቡ ግንዛቤ መጨመር፣ መድሃኒት መርጨት፣ ፈጣን የምርመራ አገልግሎቶች መስፋፋት ለተገኘው ውጤት ተጠቃሽ ናቸው። አስቀድሞ በሽታው ከታወቀና የመከላከያ መንገዶች ካሉ፤ የወባ በሽታን መቀነስ ይቻላል” ሲሉ ዶክተር ኢማኑዌል ተናግረዋል። ሌላኛው በጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የተገኘው ለውጥ የወሊድ መቆጣጠርና የእናቶችና ህጻናት በእርግዝና ጊዜ፣ በወሊድና፣ ከወሊድ በኋላ የሚኖር የጤና ክትትል ነው። ይሄንን ስራ ነው የኦባማ አስተዳድር የጤና አማካሪ የሆኑት ዶክተር ዚክ ኢማኑየል ያወደሱት። “በጣም የሚያስመሰግንና የሚያኮራ ነው። ይሄ የሚያሳየው የተሟላ መርሃ ግብር ተቀርጾ በስራ ላይ ከዋለ የሚያስገርም ለውጥ እደሚያመጣ ነው። ዶክተር ኢማኑዌል ይህንን ይበሉ እንጂ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ጥራት ዙሪያ የሚያሳስቧቸው ነገሮች እንዳሉ ሳይጠቁሙ አላለፉም። ከጤና ጥበቃ ምኒስትር ዶ.ር. ቴድሮስ አድሃኖም ጋርም በተገናኙበት ወቅትም ይህንንኑ ማሳባቸውን ገልጸዋል። “በሳምንቱ መጀመሪያ ከሚኒስትሩ ጋር ስንገናኝ ያለምንም ገደብ የማይሰራውንና ሊሻሻል የሚገባ የምለውን እንድነግራቸው አበረታተውኝ ነበር” ይላሉ የቀድሞው የዋይት ሀውስ ቺፍ ኦፍ ስታፍ ራም ኢማኑዌል ወንድም ዚክ ኢማኑዌል ። “ያም ሆኖ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ከፍተኛ እንቅፋቶች ተጋርጠውበታል። የመጀመሪያው መሰረተ-ልማት ነው። ይሄንን ስል የጤና መሰረቶች=ማለት የጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች እንዲሁም ዶክተሮችና ነርሶች ብዛት ሳይሆን፤ ሌሎችንም ያካትታል። መንገዶች፣ የውሃ የመብራትና የመሳሰሉት አገልግሎቶች አለመኖር አሁንም ከፍተኛ ችግር ነው። ከዚህም በተጨማሪ በመላው ኢትዮጵያ የመከላከልና የመጀመሪያ ደረጃ ህክምናን ለማስፋፋት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም የጤና ዘርፉ አሁንም ቢሆን ከፍተኛ የጥራት ችግሮች ይታዩበታል ሲሉ ዚክ ኢማኑዌል ተናግረዋል። ዶክተሮች፣ የጤና መኮንኖችና ነርሶች ቁጥር መጨመር እንዳለበትና ፤ ሀገር ለቀው በሚሄዱ ልምድ ባላቸው ሃኪሞች እግር ሌሎችን ለመተካት የተሻሉ ባለሙያዎችን ማሰልጠን እደሚሻ ተናግረዋል። ለሁሉም የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። “በዚች አገር ከፍተኛ መዋእለ-ንዋይ እያፈሰስን ነው። በየአመቱ ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ዶላር ለጤና እንሰጣለን። ይች አገር ቁልፍ አጋር ነች። ብዙዎቻችሁ አንደምታውቁት ባለፈው አመት ፕሬዝደንት ኦባማ የግሎባል ሄልዝ ኢኒሺየቲቭን መስርተዋል። የዚህ መርሃ-ግብር አንዱ አሰራር በጤና ዙሪያ ከፍተና ለውጥ ያመጣሉ ብለን ያሰብናቸውን ጥቂት አገሮች እንድንመርጥ ነው። ኢትዮጵያ በዚህ መርሃ ግብር ከተመረጡት ጥቂት አግሮች አንዷ ናት። ተጨማሪ ገንዘብና የቴክኒክ እገዛም ለማድረግ ተዘጋጅተናል። በዚህም ጠንካራ እመርታዎችን ለማግኘትና የጤና አገልግሎቱን ለማሻሻል ከመንግስቱ ጋር አብረን እንሰራለን። በጤና አገልግሎቱ ዙሪያ በወባ በሽታ፣ በኤች አይ ቪ ኤድስ፤ በእናቶችና ህጻናት ጤና ጥበቃ ዙሪያ የመረጃ ማሰባሰብ ስራዎች አሁን ካሉበት ዝቅተኛ ደረጃ እንዲሻሻሉም ዚክ ኢማኑዌል አሳስበዋል። |
a_unga-obama-ahmadinejad--103885994_1461881 | https://amharic.voanews.com/a/unga-obama-ahmadinejad--103885994/1461881.html | "ታሪክ የነፃነት ወገን ነች" - ፕሬዚዳንት ኦባማ ለተመድ ያደረጉት ንግግር | "በመስከረም 94ቱ ጥቃት ውስጥ የአሜሪካ መንግሥት እጅ አለበት" - ፕሬዚዳንት አሕመዲነጃጅ ለተመድ ያደረጉት ንግግር | ኒው ዮርክ ላይ ሲካሄድ በሰነበተውና 14ዐ የሚሆኑ የመንግሥታትና የሃገሮች መሪዎች በተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሐሙስ ውሎ ላይ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፕሬዚዳንቶች ተናግረዋል፡፡ ኒው ዮርክ ላይ ሲካሄድ በሰነበተውና 14ዐ የሚሆኑ የመንግሥታትና የሃገሮች መሪዎች በተገኙበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የሐሙስ ውሎ ላይ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ፕሬዚዳንቶች ተናግረዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሃገራቸውን ሠላም፣ የውጭ ፖሊሲና ሰብዓዊ መብቶችን ያካተተ ሰፊ አድማስ ያለው ንግግር ነው ያደረጉት፡፡ በዚህ ንግግራቸው ፕሬዚዳንቱ በሴቶች ላይ የሚካሄደው አመፃ እንዲያከትም ዓለም እንዲተባበር አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ለያዙት የመካከለኛው ምሥራቅ የሠላም ጥረትም መሪዎቹ ድጋፍ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል፡፡ ከሁሉም ዓይነት የአስተዳደር ሥርዓቶች አሸናፊው ዴሞክራሲ መሆኑን ታሪክ እንደሚመሰክርም ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ መድረክ ላይ የተናገሩት የኢራን ፕሬዚዳንት ማኅሙድ አሕመዲነጃድ በመስከረም 1994ቱ ጥቃት ውስጥ የራሷ የዩናይትድ ስቴትስ እጅ አለበት ብለው ብዙ አሜሪካዊያንና ብዙ መንግሥታትም እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ ይህ የኢራኑ መሪ ንግግር በዩናይትድ ስቴትስ፣ በብዙ የአውሮፓና የሌሎችም አካባቢዎች ልዑካን ዘንድ ቁጣን አጭሯል፡፡ ብዙዎቹም ንግግራቸውን እየረገጡ ከአዳራሹ ወጥተዋል፡፡ ዝርዝሩን በ"የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባዔ ያድምጡ፡፡ |
a_article----------amh-ak-crossfire-freedom-of-speech-2-18march2011-118338139_1458396 | https://amharic.voanews.com/a/article----------amh-ak-crossfire-freedom-of-speech-2-18march2011-118338139/1458396.html | የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ የዛሬ ይዞታውና አካሄዱ፤ ከየት ወደ የት? | «እኔ ባለኝ ግንዛቤ፥ የንግግር ነፃነት ዛሬ በኢትዮጵያ አለ፤» አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ። «የንግግር ነፃነት ለተወሰኑ ብቻ የተሰጠ የኢህአዴግን ዓላማ ለማስፈፀም ብቻ የዋለ እንጂ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የለም፤» አቶ ግዛው | «የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፤ ወቅታዊ ይዞታና አንድምታው፤» በእሰጥ አገባ የተጀመረው የሁለት ወገን ክርክር ቀጥሏል። የክርክሩ ተሳታፊዎች፥ አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ከአዲስ አበባ፤ አቶ ግዛው ለገሰ ደግሞ ከዚህ ከዋሽንግተን ዲሲ ናቸው። አቶ ተስፋዬ ”የንግር ነፃነት“ ዛሬ በኢትዮጵያ «ተረጋግጧል፤» ሲሉ፤ አቶ ግዛው በበኩላቸው፤ ከዓመታት በፊት ብልጭ ብሎ የነበረውና እንዲያድግ፥ እንዲጎለብት ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ዛሬ ጨርሶ ተዳፍኗል፤ ይላሉ። የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ ከማጡ ወደ ድጡ? ወይስ በእርግጥ «ሁነኛ፤» የሚሰኝ ነፃነት ዕውን እየሆነ ይሆን? የማይመሳሰሉና ፍፁም የተለያዩ ዕይታዎች የተንፀባረቁበት የሁለት ወገን ክርክር እንደጦፈ ቀጥሏል። ለዝርዝሩ የሳምንቱን ምጥን ዝግጅት ያዳምጡ፤ |
a_obama-african-youth-leaders-white-house-08-04-10-99977454_1460122 | https://amharic.voanews.com/a/obama-african-youth-leaders-white-house-08-04-10-99977454/1460122.html | ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የአፍሪካ ሀገሮችን የወከሉ ወጣት መሪዎችን ተቀበሉ | ወጣቶቹ ከሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን እና ከአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን ጋር ጀምረው ከቀትር በኋላ ደግሞ በዋይት ሃውስ ከፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ጋር በዋይት ሐውስ ምስራቅ ክፍል ውይይት አድርገዋል። | ከአሜሪካውያን አቻዎቻቸው ጋር እየተወያዩ ራዕያቸውን እያካፈሉና ልምድም እየቀሰሙ ናቸው በዚህ መልክ ነበር ፕሬኢዘንት ባራክ ኦባማ ወደ መቶ ሃያ የሚደርሱት እና በየሀገሮቻቸው የባህል ልብሶች ደምቀው በማራሹ ዙሪያ ተቀምጠው የጠበቋቸውን ወንዶችና ሴቶች የአህጉረ አፍሪካ ወጣት መሪዎች የተቀበሏቸው። ፕሬዚደንት ኦባማ ለዚህ መወያያ መድረክ ወጣቶቹን የጋበዟችው ይህ የአውሮፓውያን ሁለት ሺህ አስር ዓመተ ምህረት አስራ ሰባት የአፍሪካ ሀገሮች ከቅኝ አገዛዝ ተላቀው ነጻነታችውን የተጎናጸፉበትን ሃምሳኛ ዓመት መታሰቢያ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ከወጣቶቹ ጋር እናንተስ የቀጣዮቹ ሃምሳ ዓመታት ራዕያችሁ ምንድነው? በሚለው ዙሪያ ለማወያየት ነው። የሃይማኖታዊ ተቋማት ፥ የሲል ማህበረሰባት የልማት እንዲሁም የንግድ ስራዎች መሪነታችሁን አስመስክራችኋል። ታላቅ ተስፋም ይጠብቃችኋል ። አያሌ እሪካውያን ለብዙ ጊዜ ያከናወኑትን የምትወክሉ ናችሁ። በርግጥም አፍሪካ ብዙ ጊዜ ልብ የማይባልላትን ወደሃያ አንደኛው ምዕተ በምታደርገው ግስጋሴ ያላትን ተስፋ የምታሳዩ ናችሁ ብለዋቸዋል። ስለዚህም አሉ ጠንካራ እና በራሱዋ የምትተማመን አፍሪካ ታስፈልገናለች። ዓለምን የናንተን አፍሪካ ዓቅም ትፈልጋለች ፥ ሸሪካችሁ ለመሆንም ብለዋል። ስለዚህም ዛሬ በመካከላችን ያን ሽርክና ለማጠናከር የሚሰሩ የአስተዳደሬ አባላትም አሉ። ደስ ብሎኛል። ለዚህ ለዛሬው ስብሰባችን ካሁን የሚመረጥ ጊዜ አይኖርም ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚደንት በአፍሪካ ዙሪያ አስራ ሰባት ሀገሮች የቅኝ ገዥዎች ባንዲራ ወርዶ የራሳቸው የነጻነት ሰንደቅ ዓላማቸውን በማውለብለብ በደስታ የፈነደቁበት ሃምሳኛ ዓመት ታሪካዊ ክብረ በዓል በመሆኑ ነው ብለዋል። ፕሬዚደንቱ አያይዘው ዛሬም ቢሆን በአህጉሪቱ ዜጎች በፈታኝ ህይወት ውስጥ እንደሚያልፉም አንክድም ። ለልጆቻችን የለት ጉርስ እና ስራ ለማግኘት ያለባቸው ውጣ ውረድ እናውቃለን ብለው አዘውትሮ በዓለም መድረኮች የሚንጸባረቀው የአፍሪካ ገጽታም ይህ መሆኑንን እንረዳለን ብለዋል። በጋና እና ቦትስዋና ብልጽግና እየተመዘገ ነው ሲሉም ፕሬዚደንት ኦባማ ተናግረዋል። ደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን በስኬት ማከናወኑዋም አሉ ፕሬዚደንት ኦባማ ምንም እንኩዋን ወደአሸናፊነት የዘለቁት አውሮፓውያን የእግር ኳስ ቡድኖች ይሁኑ እንጂ የዓለም ዋንጫው ባለድል ግን አፍሪካ መሆንዋ ሲወሳላት እንደቆየ አስታውሰዋል። ወጣቶቹን መሪዎች የቀጣዮቹን ሃምሳ ዓመታት አፍሪካን የመገንባት ኃላፊነት የናንተ ነው ሲሉ ኣሳስበዋቸዋል ። አሜሪካ አብራችሁ ትቆማለች በማለትም ለአህጉራችሁ ግልጽነትንና ሙስናን ለማስወገድ እንዲሰሩ አሳስበዋቸዋል። መጪዎቹ የአፍሪካ መሪዎች እንዲህ ያለውን ግልጽነት ከልባቸው በመከተል ሙስና አስወጋጅ ርምጃዎችን የሚወስዱ ናችው። እንደHIV AIDS ካሉ በሽታዎች ራሳቸውን የሚጠብቁ የዜጎቻችን ሁሉ በተለይም የሴቶችን መብት የሚያስከብሩ ናቸው በማለት ካስገነዘቡ በኋላ የወደፊት ዕጣ ፈንታችሁ በናንተው ስራ ላይ ነው ብለዋል። ፕሬዘንት ኦባማ ከወጣት አፍሪካውያኑ መሪዎች በርካታ ጥያቄዎችን በመቀበል አስተናግደዋል ፥ HIV AIDS ወረርሺኝ ፥ የአፍሪካ ሀገሮች የተማሩ ዜጎች ከሀገር ተሙዋጦ መውጣትን ፥ የሴቶች መብትንና ሌሎችንም ጥያቄዎችን አንስተውባባቸዋል። ደካማ አፍሪካ እና ብርቱዋ አሜሪካ ዕውን በዕኩልነት ላይ የተመሰረተ ሽርክና ሊኖራቸው ይችላል የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸዋል። አፍሪካውያኑ ወጣት መሪዎች ዛሬም በተሰናዱላቸው ልምድ መቅሰሚያ ራዕይ መጋሪያና ትውውቅ መፍጠሪያ ፕሮግራሞች መካፈላችውን ቀጥለዋል። ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ፥ በአሜሪካ የሰላም ጉዋድ እና በተለያዩ ህዝባዊ ድርጅቶች መርሃ ግብሮች የነበሩዋቸው ሲሆን ነገ ሐሙስም ይቀጥላሉ። |
a_th-annual-golden-globe-jan-7-2018-voa-alula-kebede_4198709 | https://amharic.voanews.com/a/th-annual-golden-globe-jan-7-2018-voa-alula-kebede/4198709.html | ኦፕራ ዊንፍሬ በዘንድሮው የምርጥ-ምርጥ የቴሌቭዥንና የሲኒማ ሥራዎች ሽልማት ጎልደን ግሎብ | “እነኚያ ሬሲ ቴይለር’ን ሊያጠፉ የሞከሩ ሰዎች በሕግ ሳይጠየቁ ቀርተዋል። ሬሲ ቴይለር ዘጠና ስምንተኛውን የልደት በዓሏን ለማክበር ጥቂት ሲቀራት ከአሥር ቀናት በፊት ነው ያረፈችው። አይደፈሬ ነገር ግን ርሕራሄ በሌላቸው ወንዶች በተደፈረ ባሕል ውስጥ አያሌ ዓመታት ኖራ አለፈች። በእነኚያ አይጠየቄ ወንዶች የደረሰባቸውን ጥቃት ለመናገር የደፈሩ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶችም ሰሚ ሳይኖራቸው ለረዥም ዘመናት ዘለቁ። ዛሬ ግን ያ ሰዓት ያበቃ ይመስላል።” ኦፕራ ዊንፍሬ። | ዋሺንግተን ዲሲ — በቀይ ምንጣፍ ላይ የተንጣለለ የጥቁር ባሕር ተመስሏል። በሆሊውድ እና በመላዋ አገሪቱ በተለያዩ የሥራ ቦታዎች በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ሥር የሰደደ ወሲባዊ ወከባ ለመፋለም ለሚንቀሳቀሰውን ታይም ኢዝ አፕ የተባለውን የመብት ተሟጋች ቡድን በመደገፍ ጥቁር የለበሱ በሥነ ሥርዓቱ የተገኙ ሴቶች የለበሱት ልብስ የከሰተው ገጽታ ነው። በቴሌቭዥን እና በሲኒማው መስክ ባለፈው ዓመት የተሰሩ ምርጥ ሥራዎችን የሚዘክረው የሆሊውዱ የውጭ ፕሬስ ማኅበር የሚያሰናዳውና እንደ ወትሮው ሁሉ ለየት ባለ ጉጉት የተስተናገደው የትላንቱ የጎልደን ግሎብ ሥነ ሥርዓት፤ ሆሊውድ በሴቶች ላይ በሚፈጸሙት እና ለዓመታት በዘለቁት የወሲባዊ ወከባ ጥቃቶች ቅሌት ከተናጠች ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑ ነው። የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ባለፈው የጥቅምት ወር አስገድዶ የመድፈር ጥቃትን ጨምሮ በያኔው ገናና እና ከፍተኛ ተሰሚነት የነበረው የፊልም አቀናባሪ ሃርቬይ ዋይንስቲን “ተፈጽመዋል” በተባሉ ለአሥርት ዓመታት የዘለቁ፤ ወሲባዊ ወከባዎች ውንጀላ ያተተ ዝርዝር ዘገባ ተከትሎ፤ ሌሎች በርካታ ገናናዎችንና አይደፈሬዎችን ያንበረከኩ ያልተጠበቁ ድምጾች፤ ክሶችና ስሞታዎች በየቀኑ ይዥጎድጎዱ ጀመር። በትላንቱም ጎልደን ግሎብ የሥነ ሥርዓቱ አስተናጋጅ፤ ታዋቂ የምሽት የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና ኮሜዲያን ሲት ማየር ይሄንኑ የወሲባዊ ቅሌት ሥሜት ባዘሉ የሰሉ ሥላቆች የምሽቱን መድረክ መጋረጃ እንዲህ ሲል ከፈተ። “በዚህ ክፍል ውስጥ የሌለውን ግዙፍ ጉዳይ የማስተዋወቂያው ሠዓት ይመስለኛል። ሃርቬይ ዋይንስቲን በዛሬው ምሽት ከዚህ የለም። እንደ ሰማሁት ጭምጭምታ ከሆነ እብድና አብረውት መሥራት የሚቻል ሰው አይደለም። ሃሳብ አይግባችሁ ከአንድ ሃያ ዓመታት በኋላ ተመልሶ ይመጣል። በሕልፈታቸው መታሰቢያ በታዳሚው ጩኰት ከመድረኩ እንዲወርዱ በመጠየቅ የመጀመሪያው ሰው ይሆናሉ። እንዲያ ነው የሚመስለው ነገሩ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1914 እስከ 1958 በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ70 በላይ ፊልሞችን በሰራውና የአሜሪካ የፊልም አባት በሚል ቁልምጫ በሚታወቀው ዕውቁ የፊልም ዲሬክተር እና አቀናባሪ ሴሲሊ ቢ ዴሚሌ ሥም የተሰየመውን ለዕድሜ ልክ ሥራዎች የሚሰጥ ሽልማት የዘንድሮ ተሸላሚ የፊልም ተዋናይዋ አቀናባሪና የቴሌቭዥን ሠው ኦፕራ ዊንፍሬ ሽልማቱን በተቀበለችበት ወቅት ያሰማችውም ንግግር አዳራሹን ከዳር እስከ ዳር ያቀጣጠጠለ ነበር። ኦፕራ በዚያ የብዙዎችን ቀልብ በልዩ ሥሜት በናጠ ንግግሯ ከሰባ ዓመታት በፊት በነጭ አሜሪካውን ወረበሎች በቡድን የተደፈረች አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት አስታወሰች። “እነኚያ ሬሲ ቴይለር’ን ሊያጠፉ የሞከሩ ሰዎች በሕግ ሳይጠየቁ ቀርተዋል። ሬሲ ቴይለር ዘጠና ስምንተኛውን የልደት በዓሏን ለማክበር ጥቂት ሲቀራት ከአሥር ቀናት በፊት ነው ያረፈችው። አይደፈሬ ነገር ግን ርሕራሄ በሌላቸው ወንዶች በተደፈረ ባሕል ውስጥ አያሌ ዓመታት ኖራ አለፈች። በእነኚያ አይጠየቄ ጉልቤ ወንዶች የደረሰባቸውን ጥቃት ለመናገር የደፈሩ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶችም ሰሚ ሳይኖራቸው ለረዥም ዘመናት ዘለቁ። ዛሬ ግን ያ ሰዓት ያበቃ ይመስላል። የእነኚያ ጉልበተኞች ጊዜ አለፈ። አዎን! አለፈ። ” ብላለች። በርካታ እንስት ተዋናዮች ከሴቶች መብት ተሟጋቾችና የዘር ልዩነትን በመቃወም የፍትሕ ጥሪ ለማሰማት ከተሰለፉ ብዙዎች ጋር በመሆን ነው። አነጋጋሪውና ቀልብ ሳቢያ የኦፕራ ንግግራ የመጪዋ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የመሆን ዕቅድ መጀመሪያ አድርገውም ወስደውታል። ይህን አስመልክቶ በኦፕራ በኩል የተባለ ነገር በሌለበት በእርግጥ የሚሆነው ወደፊት ይሆናል የሚታወቀው። |
a_covid-main_5545788 | https://amharic.voanews.com/a/covid-main/5545788.html | የኮሮናቫይረስ የምራቅ ምርመራ ጸደቀ | የዩናይትድ ስቴትስ የሳይንስ ምሁራን ሆስፒታል ከሚገኙት የኮቪድ 19 በሽተኞች በ 4.8 ሜትር ርቆ የቫይረሱን አካል ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ የሚለው እምነት የተሳሳተ መሆኑን የሳይንስ ጠቢባኑ ሲያስረዱ የነበረው የተሳሳተ ግንዛቤ ብዙ ሰዎችን ለቫይረሱ እያጋለጠ ሳይሆን አንዳልቀረ ጠቁመዋል። | ዋሽንግተን ዲሲ — ጥናቱ የተካሄደው በፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ክፍል ሲሆን ገና በሌሎች የሙያው ምሁራን እንዳልተገመገመ ተገልጿል። የአሜሪካው የል ዪኒቨርሲቲ ያፈለቀውን የኮቭድ 19 ቫረስን በምራቅ የመመርመሩ ዘዴ በአስቸኳይ ጊዜ ወቅት እጥቅም ላይ እንዲውል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ትላንት አጸደቀው። በምራቅ የሚደረገው ምርመራ ከ 24 ሰአታት ባነሰ ፍጥነት ውጤቱ ሊገኝ እንደሚችል ዋጋውም ርካሽ እንደሆነ ወደ $10 ዶላር ገደማ መሆኑ ተገልጿል። አዲሱ የምርመራ ዘዴ የፀደቀው አንዳንድ የፌደራልና የጤና ባለስልጣኖች በሀገሪቱ የቫይርሱ ምርመራ እንዲበራከት እየጠየቁ ቢሆንም በየቀኑ የሚደረግ የቫይረሱ ምርመራ እንደቀነሰ በተገለጸነት ወቅት ነው። ዩናይትድ ስቴትስ በኮቪድ-19 ህሙማንና በሙታኑ ብዛት ከአለም ቀዳሚ ቦታ መያዝዋ በቀጠለበት ወቅት ነው ይህ የሆነው። በአለም ደረጃ የኮቪድ 19 በሽተኞች ብዛት እስከ ዛሬ ንጋት በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ 21 ሚሊዮን በላይ መሆኑን ስለጉዳዩ የሚከታተለው የጆንስ ሆፕኪንስ ዪኒቨሲቲ አስታውቋል። ከ5.3 ሚልዮን በላይ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ3.3 ሚልዮን ደግሞ በብራዚል መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው አሀዝ አመልክቷል። የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በገለጸው መሰረት ህንድ ከ 2.5 ሚልዮን በላይ በኮቪድ የተያዙ በሽተኞች አሏት። ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች በሞት ተለይተዋል። |
a_hr-128-ethiopian-human-rights-us-congressman-cofman-01-30-18_4231874 | https://amharic.voanews.com/a/hr-128-ethiopian-human-rights-us-congressman-cofman-01-30-18/4231874.html | በUS ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ረቂቅ ሕግ ቀጣይ እጣ እና ሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች | “ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ላላት በብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ላተኮረ ግንኙነቷ ቅድሚያ በመስጠት ለረዥም ጊዜ በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አይታ እንዳላየች ስታደርግ ቆይታለች። ያ ፍጹም የተሳሳተ ነገር ነው። በመሆኑም ይሄ ያን ስህተት የማመን የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ዜጎቹ ላይ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።” ኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን የUS የተወካዮች ምክር ቤት አባል። | ዋሽንግተን ዲሲ — በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ግፊት ለማድረግ በሚል ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ሕግ ቀጣይ ሂደት ዙሪያ የተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባኤ ነው የቀጣዩ ዘገባ መነሻ። ባሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚታየው ሁኔታ ካልተለወጠ HR-128 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሙሉ ምክር ቤቱ የሚተላለፍና ሊጸድቅ የሚችል መሆኑ ነው፤ በምክር ቤቱ የብዙኃኑ ፓርቲ ተጠሪ በተገኙበት በተካሄደው ጋዜጣዊ ጉባኤ የተገለጸው። በኢትዮጵያ ተፈጽመዋልና እየተፈጸሙ ናቸው የሚላቸውን የመብት ጥሰቶች የሚያወግዘው ባለፈው ዓመት በየካቲት ወር መጀመሪያ የቀረበው ይህ የሕግ ረቂቅ፤ በኢትዮጵያ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ከበሬታ መረጋገጥ እና ብሎም ሁሉን አቀፍ አስተዳደር መፈጠር የታለመ መሆኑን ይዘረዝራል። ኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን በUS የተወካዮች ምክር ቤት የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ስድስተኛው የምክር ቤታዊ የአስተዳደር ክልል ተወካይ ናቸው። ረቂቅ ሕጉ ያለበትን ሁኔታ እንዲያስረዱ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ፤ ከምክር ቤቱ አመራር አባላት ጋር ባደረግናቸው ንግግሮች “በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትና አስተዳደር ጉዳዮች ያሉትን አማራጮች ለማየት ከሚያስችለን ስምምነት ላይ ደርሰናል፤” ይላሉ። “የኢትዮጵያ መንግስት እስረኞችን እየፈታ ነው፤ አንዳንድ መሻሻሎችንም እያደረገ ነው፤ እናም በረቂቅ ሕጉ ላይ ድምጽ ከመ’ሰጠቱና ከመጽደቁ አስቀድሞ ነገሮችን ወደሚፈለገው አቅጣጫ ይወስዳል፤” የሚል አስተያየትም ተነስቷል። በእርግጥ እኔ በዚያ ግምት አልስማም። ለሁሉም የምናየው ይሆናል። ካልሆነም ረቂቅ ሕጉ እውን ወደሚሆንበት መንገድ እናመራለን። ” የሚሉት ኮንግሬስማን ኮፍማን የጊዜ ገደቡ እየተጤነ መሆኑንም ጨምረው ገልጠዋል። ሁኔታዎች ተሥፋ እንደተጣለባቸው ባይይዙና ቀደም ብለው እንደገለጹት የሕግ ረቂቁን ተፈጻሚ ወደሚያደርገው አማራጭ የሚኬድ ቢሆን፤ በእርግጥ ሕጉ ምን ዓይነት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት ያስገኝ ይሆን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም ኮፍማን እንዲህ ይመልሳሉ። “ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ላላት በብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ለሚያደርገው ግንኙነቷ ቅድሚያ በመስጠት በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለረዥም ጊዜ አይታ እንዳላየች ስታደርግ ቆይታለች። ያ! ፍጹም የተሳሳተ ነገር ነው። በመሆኑም ይሄ ያን ስህተት የማመን የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ዜጎቹ ላይ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የመቶ ሚልዮን ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው፤ በአፍሪቃ ቀንድ ዋነኛዋ የዩናይትድ ስቴትስ ሃጋር የሆነችው ኢትዮጵያ፥ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መሆኗ እየተዘገበ ነው። ለመሆኑ ያች ሃገር ቀውሱ ተባብሶ የከፉ ሁኔታዎች ውስጥ እንዳትወድቅ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሊወስዳቸው የሚችላቸው እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን? ለሚለውም ኮፍማን ጥረታቸው ያ እንዳይሆን መሆኑን ያስረዳሉ። “ቀውስ በተንሰራፋበት የሚሆነውን እናውቃለን። እርግጥ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግስት የገዛ ዜጎቹ ላይ ሽብር እየፈጸመ ነው። መንግስት አልባነት በኢራቅ ይሁን በሊቢያ ያደረገው ቢኖር፤ የአሸባሪዎች መፈልፈያ መሆን ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታዎቹን መለወጥ አለበት። የዚህ ረቂቅ ሕግ መመሪያም ሆነ ሌላው እየሠራን ያለነው ያን ለመከላከል ነው። ” ይላሉ። |
a_amh-wfp-horn-drought-9-12-11-125447933_1461018 | https://amharic.voanews.com/a/amh-wfp-horn-drought-9-12-11-125447933/1461018.html | በደቡብና ምስራቅ ኢትዮጵያ ከተራቡ ሰዎች በተጨማሪ ሶማሊያዊያን ስደተኞች እርዳታ ይሻሉ | በምስራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ የተራቡ ዜጎችና ስደተኛ ሶማሊያዊያንን ህይወት ለማዳን ከፍተኛ እርዳታ እንደሚያስፈልግ WFP አስታወቀ። ኬንያን ጨምሮ 10 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። | የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በ60 አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ ተመትተዋል፡፡ በዚህም መሰረት በአደጋው የተጋለጠውን ህዝብ ለመታደግ ከፍተኛ እርዳታ እንደሚያስፈልግ WFP ገልጿል። በአፍሪቃ ቀንድ በተከሰተው ድርቅ ለከፋ አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን ለመድረስ የያዘውን ጥረት መጨመሩን የተባበሩት መንግስታት ድርግት የምግብ ፕሮግራም WFP አስታወቀ። የአሜሪካ ድምጹ ጋቢ ጆስሎ ከናይሮቢ ባጠናቀረው ዘገባ እንደጠቆመው፤ የተጎዱትን ወገኖች በአስቸኳይ ለመድረስ የሚያስፈልገውን እርዳታ ለማሟላት ድርጅቱ ለተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ጥሪ አቅርቧል። ይህን ያስታወቁት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስነህዝብ የስደተኞችና የፍልሰት ጉዳይ ጽ/ቤት ም/ል ረዳት ጸሃፊ ዶ/ር ሪበን ብርጌቲ ናቸው፡፡ ከዶናልድ ቡዝ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደርና ከዶናልድ ስታይበርግ የአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ተራዲኦ ድርጅት ም/ል አስተዳዳሪ ጋር በጋራ ትላንት አመሻሹ ላይ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያ ውስጥ እየተባባሰ በመጣው ድርቅና ጦርነት የተነሳ ብዙ ሱማሊያውያን ወደኢትዮጵያና ኬንያ እየተሰደዱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ረዳት ጸሃፊው በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በዶሎ አዶ የሰደተኞች ካምፖች የተመለከቱትን ገጽታ አስረድተዋል፡፡ “ዛሬ በዶሎ አዶ የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ የስደተኞች ቁጥር ወደመቶ ሺህ ይጠጋል፡፡ የስደተኞች ጎርፍ በዚሁ ከቀጠለ በአመቱ መጀመሪያ ላይ በእጥፍ ይጨምራል፡፡ ወደ ካምፑ የሚመጡትም በአካልና በጤና የተጎሳቆሉ ናቸው፡፡ በአልተመጣጠነ ምግብ ምክንያት የሚደርሰው ጉዳትም ከ45 እስከ 50 በመቶ ይሆናል፡፡ ይህ በህጻናቱ መካከል 20 በመቶ ይደርሳል፡፡ በሱማሊያ ያለው ግጭት ድርቁን እንዳባባሰውም ተናግረዋል፡፡ አሁን በምስራቅ አፍሪካ የደረሰው ድርቅ በ60 አመታት ውስጥ ያልታየ መሆኑን በመግለጫው ላይ ተገልጿል፡፡ ይህ መቅሰፍት እንደሚመጣም በአሜሪካ መንግስት አስቀድሞ ይታወቅ እንደነበረ የአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ተራዲኦ ድርጅት ም/ል አስተዳዳሪ ዶናልድ ስታይበርግ ተናግረዋል፡፡ ይህ የታወቀውም በሳተላይትና ምድር ላይ በተገኙ መረጃዎች ሳይንሳዊ ትንታኔ መሰረት ነው፡፡ የተፈራው ድርቅም ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ መከሰት ጀመረ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ እርዳታ የሚሹ ዜጎች ቁጥር በሚሊዮኖች መቆጠር ጀምሯል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዶሎ አዶ የሱማሊያ ስደተኞች ጣቢያዎች ውስጥ በየቀኑ ከ2-3 ወይም ከ10 ሺዎች ውስጥ 7 ህጻናት እንደሚሞቱ ተናግረዋል። የዶሎ አዶ ጣቢያዎች ከአሜሪካ ባለስልጣናት በተጨማሪ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ተወካዮች፥ የኢትዮጵያ መንግስት የስደተኞችና ስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር ተወካዮች፥ የዩናይትድ ኪንግደም አለማቀፍ ክፍል፥ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እንዲሁም የሲዊዲንና የጃፓን መንግስት ተወካዮች ጎብኝተዋቸዋል። |
a_election-followup-opposition-06-08-10-95900214_1462506 | https://amharic.voanews.com/a/election-followup-opposition-06-08-10-95900214/1462506.html | ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላም ወከባና እንግልቱ ቀጥሏል፤ በሚለው ተቃዋሚና መንግስት አሁንም እየተወዛገቡ ነው | «ማንም ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዳይዋከብ፤ የልማት ሥራው እንዳይስተጓጎል ግልፅ የመንግስት መመሪያ ወጥቷል፤» አቶ መስፍን አሰፋ። | የምርጫው ማግስት ወከባና እንግልት እንደቀጠለ ነው፤ ሲል የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ገዢውን ኢህአዴግን ይወነጅላል። ኢህአዴግ በበኩሉ «ከምርጫው ጋር በተያያዘ በማንም ላይ እየተወሰደ ያለ ዕርምጃ የለም፤» ሲል ያስተባብላል። ብሄራዊው የምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መሠረት ምርጫው ሙሉ በሙሉ በኢህአዴግ አሸናፊነት ቢጠናቀቅም፤ «ለታዛቢነት ያቀረብኳቸውና ደጋፊዎቼ ከሥራ መታገድ፥ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ነው፤» ሲል፥ ተቃዋሚው የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ገዢውን ኢህአዴግን ወንጅሏል። ችግሮቹ ተከሰቱ የተባለበት የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር በበኩሉ፥ «ለተቃዋሚው ወገን በምርጫ ታዛቢነት መንቀሳቀስም ሆነ ደጋፊ ወይም አባል መሆን የዜጎች መብት ነው፤ እናም በዚህ ሳቢያ በማንም ላይ ዕርምጃ አልተወሰደም፤» ሲል ውንጀላዎቹን አስተባብሏል። «ማንም ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዳይዋከብ፤ የልማት ሥራው እንዳይስተጓጎል ግልፅ የመንግስት መመሪያ ወጥቷል፤» ሲሉ፥ መንግስታቸውን የተከላከሉት የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ የመረጃና ኅዝብ ግንኙነት ሥራ ሂደት መሪውን አቶ መስፍን አሰፋን ናቸው። «ደጋፊዎቻችን ለስራ አጥነት እየተዳረጉ ነው፤» የሚሉት የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ ዋና ፅህፈት ቤት ረዳት ኃላፊ አቶ ኦልባና ሌሊሳ ግን፤ ባለሥልጣናቱ ሳያውቁ የሚፈፀም ምንም እንደሌለ ተናግረው፤ ለችግር የተጋለጡት ወገኖች ከአንዱ የመንግስት ቢሮ ወደ ሌላው ለአቤቱታቸው ሠሚ ሳያገኙ እየተንከራተቱ ነው ብለዋል። የተቃዋሚ ዕጩዎች፥ ስለ ተሸነፉበት ምርጫ ነፃና ትክለኛነት እንዲመሰክሩ፤ በተቃዋሚ የምርጫ ታዛቢነት የተሳተፉት ደግሞ ይቅርታ ጠይቀው ከፈረሙ ብቻ ስራቸውን የሚያገኙ መሆናቸው እየተገለፀላቸው መሆኑን አቶ ኦልባና ዘርዝረዋል። «ለምሳሌ ያህል አቶ ጣሂር ደርሲሶ የተባሉ ታዛቢያችን በምርጫው ዋዜማና በዕለቱ ዕለት በወረዳው የኦህዲድ ፅ/ቤት የታዘዙ ሠዎች በአባታቸው ቤት ውስጥ በሰንሰለት አስረው በታዛቢነታቸው እንዳይሰሩ አድርገዋቸዋል፤» ሲሉ ከምርጫው አስቀድሞም ለተመረጡበት የታዛቢነት ሚና እንዳይበቁ በደጋፊቸው ላይ «ደረሰ፤» ያሉትን ህገ ወጥ ዕርምጃ የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬሱ ተጠሪ በዋቢነት አንስተዋል። ከምርጫው በፊትም ሆነ በምርጫው ወቅት እንዲህ ያሉት ተመሳሳይ ክሶች በተቃዋሚዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፤ ነገር ግን ወደ ማጣራቱ ሲኬድ ዕውነተኛ ሆኖ አይገኝም፤ የሚሉት የኦሮሚያ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ የመረጃና ኅዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መስፍን ደግሞ «የክሶቹን መሠረተ ቢስነትም ህዝቡ ያውቃል፤» ይላሉ። በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች «እየተፈፀሙ ናቸው፤» የተባሉትን አንዳንድ ክሶች የሚያጣሩ መሆናቸውን አቶ መስፍን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል አመልክተዋል። |
a_uganda-blast-0712-10-98264739_1462920 | https://amharic.voanews.com/a/uganda-blast-0712-10-98264739/1462920.html | በዩጋንዳ በደረሰ ፍንዳታ 74 ሰዎች ተገደሉ | በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በደረሱ ተከታታይ ፍንዳታዎች ከ70 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። | አስር ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን መሞታቸው ተዘግቧል ትናንት እሁድ ማታ የአለም ዋንጫ ፍጻሜን በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ሲመለከቱ ነበር ተከታታይ ፍንዳታዎች የኳስ አፍቃሪዎቹ የተሰበሰቡባቸውን ሁለት ስፍራዎች ያናወጡት። አንደኛው የዩጋንዳ ራግቢ ክበብ ሲሆን፤ ሁለተኛው በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን፣ የሌላ አገሮች ዜጎችና ዩጋንዳዊያን የተሰባሰቡበት የኢትዮጵያዊያን የገጠር ምግብ ቤት ነበር። “የመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታ በማብቃት ላይ ሳለ ነው ፍንዳታው የተከሰተው…ወዲያው ሰው መጮህ ጀመረ፣ ከአካባቢው ለመራቅ በነጫጭ የፕላስቲክ ወንበሮች ላይ እየዘለለ ነበር የሚሄደው፣” ሲል ላለፉት ስድስት ወራት በካምፓላ የኖረውና ለጋዜጠኝነት ትምህርት ወደዚያው ያመራው ተስፋለም ወልደየስ ለቪኦኤ ተናግሯል። በተመሳሳይ ሰአት በዩጋንዳ ራግቢ ክበብ የደረሱ ፍንዳታዎችም እንዲሁ በርካታዎችን አቁስለዋል። ዛሬ ማለዳ የዩጋንጋ ፖሊስ ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫ የሟቾቹ ቁጥር 74 ሲደርስ ከሰባ የማያንሱ ደግሞ ቆስለዋል። መሟቾቹ መካከል ወደ አስር የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን እንደሚገኙበት ታቋል። በተለያዩ ዜጎች የሚዘወተረው የኢትዮጵያ ምግብ ቤት የደረሰው ፍንዳታ አንድ-አሜሪካዊ መግደሉም ተዘግቧል። “አንድ አሜሪካዊ ሞቷል። ጉዳት የደረሰባቸውን አሜሪካዊያን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማጠያየቅ እየሞከርን ነው፣” ሲሉ በካምፓላ የዩናይትድ ስቴይትስ ኢምባሲ ቃል አቀባይ ጆዋን ሎካርድ ተናግረዋል። ጥቃቱን ተከትሎ በርካታ መሪዎች መግለጫ አውጥተዋል። የዩናይትድ ስቴይትሱ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ “አሳፋሪ የፈሪዎች ተግባር ሲሉት” የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን የዩጋንዳ መንግስት ወንጀለኞቹን ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል-አቀባይ በረከት ስም-ኦን በአልሸባብ የተሰነዘረ “የፈሪ ዱላ” ብለውታል። የዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አገራቸው በሞቃዲሹ ካላት ሀላፊነት አታፈገፍግም ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ይህንን የተናገሩት አስቀድሞ የነበረውን ጥርጣሬ በመመርኮዝ ነው። ጉዳቱ እንደደረሰ- በአል-ቃይዳ የሚታገዘው የሶማሊያ የሽብርተኞች ቡድን አል-ሸባብ የአጥፍቶ ማጥፋት ጥቃቱን በማቀነባበር በመጠርጠሩ ነው። ከአል-ቃይዳ ጋር ግንኙንት እንዳለው የሚነገረው የሶማሊያ አንጃ አል-ሸባብ ጥቃቱን መፈጸሙን ሰኞለት አምኗል። “በካምፓላ የተከሰተው አገሪቱ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ስራ ላይ ከመሰማራቷ ጋር የተያያዘ ነው፣” ሲሉ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽነር ራምታኔ ላማምራ ዛሬ በአዲስ አበባ ተናግረዋል። ሚስተር ላማምራ ጥቃቱ የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ በአስቸኳይ ሊያሰፍር ያሰባቸውን የ2ሽህ ወታደሮችና አጠቃላይ የ8ሽህ ግብረ-ሀይል እቅድ አያስተጓጉለውም፤ እንዲያውም ከምን ጊዜውም በበለጠ ሁኔታ በሶማሊያ የሚኖረንን ስራ ያጠናክረዋል ብለዋል። በካምፓላ ከደርግ አስተዳደር ጀምሮ በአሁኑ መንግስትም ጭምር በፖለቲካ ስደትና በንግድ የሚኖሩ በሽዎች የተቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ይገኛሉ። |
a_amh-debt-us-7-20-11-125912468_1459491 | https://amharic.voanews.com/a/amh-debt-us-7-20-11-125912468/1459491.html | የዩናይትድ ስቴይትስ የብድር ጣራ በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካኖች መካከል ያስነሳው ውዝግብ ቀጥሏል | የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት እንዲበደር የሚፈቀድለት የ14.3 ትሪሊየን ዶላር ጣራ እንዲነሳለት የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አስተዳድር የህዝብ ተወካዮችን በኮንግረስ በመጠየቅ ላይ ነው | የዩናይትድ ስቴይትስ የብድር ጣራ መነሳትና አለመነሳት የሰሞኑ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት ሆኖ ነው የሰነበተው። የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ አስተዳደር በበጀት መጓደል የገጠሙትን እክሎች ሊያስተካክል፤ የመንግስቱን ወጭ በመቀነስ ላይ ባለበት ወቅት፤ አገሪቱ ተጨማሪ ብድር የምታገኝበትና፤ ከዚህ ቀደመ የቆዩ ብድሮቿን ለመክፈል እንድትችል፤ ተጨማሪ ብድር የማግኘት እድሏ በህግ ቋጠሮ ተበጅቶለታል። የባራክ ኦባማ አስተዳድር የአሜሪካ የብድር ጣራ ካልተነሳ አገሪቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ትወድቃለች በሚል አምርሮ በመከራከር ላይ ይገኛል። የህዝብ ተወካዮች በሚገኙበት ኮንግረስም ክርክሩ በዴሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች ጦፏል። ዴሞክራቶቹ ከኦባማ ጎን ተሰልፈዋል፤ ሪፐብሊካኖቹ የብድር ጣራውን አናነሳም ብለዋል። በትናንትናውለት ፕሬዝደንት ኦባማ በዋይት ሃውስ ቤተመንግስት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ አስተዳደራቸው ከኮንግረስ መሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት መጠነኛ እመርታዎች ቢታዩም፤ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ነገሮች እየጠበቡ መሄዳቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። ለሳምንታት የዘለቀው ክርክር በዴሞክራቶችና በሪፐብሊካኖች በይፋ በመገናኛ ብዙሃንና በዝግ በሚደረጉ ድርድሮችና ስብሰባዎችም ጭምር ሲስተጋቡ ቆይተዋል። የዩናትድ ስቴይት የነጻነት ቀን በሰኔ ወር ማብቂያ ላይ ሲከበር ፕሬዝደንት ኦባማ በብድር ጣራው ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሄ ያሻዋል ብለዋል። “ባለፉት አስርት አመታት ዋሽንግተን የአገሪቱን ብድር ጣራዊን ካስነካችው በኋላ፤ አሁን ተቀማጭ ገንዘባችንን መጨመር ይገባናል” ብለዋል ኦባማ። ፕሬዝደንቱ አክለውም ሁሉንም ዘርፎች ተመልክቶ የቀረጥ እፎይታ በበጀቱ መካተት እንደሚገባውና አስተዳደራቸው ሁሉንም ተመልክቶ ገንዘብ የሚባክንባቸውን ፕሮጀክቶች በማቆም ገንዘብ እንደሚቆጥብ ገልጸዋል። የዩናይትድ ስቴይትስ ኢኮኖሚ ከአለም የገንዘባ ውድቀት ወዲህ ከገባበት አዘቅት ለመውጣት በሚፍጨረጨርበት ወቅት፤ መንግስቱ የበጀት አለመመጣጠን ገጥሞታል፣ በዚያ ላይ የብድር ጣራው ሰማይ ነክቷል። ሪፐብሊካኖች ለዚህ ችግር መፍትሄው፤ መንግስት ወጭውን መቀነሱ ነው ይላሉ። “የሌለንን ገንዘብ ልናወጣ አንችልም። ከዋሽንግተን የሚመጣ አንድ ዶላር ውስጥ 42 ሳንቲሙ በብድር የተገኘ ነው። ከዚህ ውስጥ 47 ከመቶው ከውጭ የተገኘ ብድር ነው፤ ቻይና ቁጥራ 1 አበዳሪያችን ናት” ብለዋል በኮንግረስ የበጀት ኮሚቴ ሊቀ-መንበር ሪፐብሊካን ፖል ራያን። ዴሞክራቶቹ በበኩላቸው የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት የቀረጥ ገቢ ከ1950ዎቹ ወዲህ በጣም ዝቅ ያለ መሆኑን ይጠቅሳሉ። “በምናደርጋቸው ድርድሮች እንዳየንው፤ ሪፐሊካን ጓዶቻችን የአገሪቱን ኢኮኖሚ አዝቅት ውስጥ ማስገባት ግድ አይሰጣቸውም። እንዲያውም ባንጻሩ የቀረጥ እፎይታዎች እንዲነሱ ፈጽሞ አይፈልጉም” ብለዋል የኒውዮርኩ ዴሞክራት ሴናተር ቻርልስ ሹመር። ሪፐብሊካኖች የመንግስትን ገቢ ለመጨመር ቀረጥ መጨመር የሚለውን አሳብ አይደግፉትም። የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት ያለበትን የ1.5 ትሪሊየን የበጀት መጓደል ከማሟላት ይልቅ፤ የቀረጥ ገቢው ሲጨምር ተጨማሪ ገንዘብ ያወጣል ሲሉ አጥብቀው ይከራከራሉ። “ችግራችን ትንሽ ቀረጥ መክፈላችን አይደለም። ከዚህ ሁሉ የፖለቲካ ክርክር በኋላ አሜሪካኖች ከሀምሌ 26 በፊት ውሳኔ ማሳለፍ ይኖርባቸዋል። የብድር ጣራውን ማንሳት፤ አለማንሳት፤ የበጀት መጓደሉ እንዴት እንደሚስተካከልና የቀረጥ ጉዳይ ከዚች ቀን በፊት ውሳኔ ማግኘት ይገባቸዋል። ፕሬዝደንት ኦባማና አስተዳደራቸው ተስፋ ሰንቀዋል። ከምርጫና ከድምጽ ማግኘት አንጻር የሚደረጉ የፖለቲካ ክርክሮች ቢበረቱም፤ በስተመጨረሻ የብድር ጣራው እንደሚነሳ እምነት አላቸው። “ዴሞክራሲ ሁሌ የተዋበ አሰራር አይደለም። እንከራከራለን በሃሳብ አንስማማም፤ ነገር ግን በተደጋጋሚ ያረጋገጥንው ነገር ቢኖር ችግሮችን ለመፍታት አብረን እንደምንሰራ ነው። በሁሉም ጉዳዮች ላይ አይን ለአይን ባንተያይም አገራችንን እንወዳለን፣ በወደፊት ተስፋዋም የጋር እምነት አለን። ይሄንን ስሜት ነው አሁን ልናስተጋባ የሚገባን” ብለዋል ፕሬዝደንት ኦባማ። በሴኔቱ ተቀባይነት ያላቸው ፖለቲከኞች ተሰባስበው ጉዳዮን ለመሸምገል ጥረት ይዘዋል። እነዚህ ፖለቲከኞች የመንግስቱን ወጭ ለመቀነስና ዩናይትድ ስቴይትስ ብድሯን የምትከፍልበትን መንገድ ለማመቻቸት ጥረት ይዘዋል። |
a_eu-election-observers-report-05-25-10-94872039_1458991 | https://amharic.voanews.com/a/eu-election-observers-report-05-25-10-94872039/1458991.html | የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን የኢትዮጵያ ምርጫ ሰላማዊ ቢሆንም በእኩል ሜዳ አለመደረጉን ገለጸ | ምርጫው ከፍተኛ ብዛት ያላቸው መራጮች የተሳተፉበትና ሰላማዊ ቢሆንም እየጠበበ በሄደው የፖለቲካ ምህዳርና እኩልነት በጎደለው የመወዳደርያ ሜዳ መዘፈቁ አልቀርም ሲሉ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ገለጹ። | ባለፈው እሁድ ግንቦት 15 ቀን 2002 አም በኢትዮጵያ የተካሂደውን ምክር ቤታዊ ምርጫ የተከታተለው የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ታይስ በርማን የምርጫውን ሂደት ጠንካራና ደካማ ጎን ሲገመግሙ አራተኛው አጠቃላይ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ መጠናቀቁን ባለድርሻ አካላት በአንድነት ተቀብለውታል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድም ምርጫውን በበቂ ሁኔታ አስተዳድሯል። ይሁንና በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚነሱትን የኢወገኝተኛነት ጥያቄን ለመመለስ አልቻለም ብለዋል በርማን። ታይስ በርማን ይህን ያሉት ዛሬ ማክሰኞ በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ከእኩለ ቀን በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ሚስተር በርማን በተጨማሪም “በገዢው ፓርቲና በመንግስታዊ አስተዳደር መካከል መኖር የሚገባው ልዩነት በብዙ የተለያዩ ቦታዎች ደብዝዞ ታይቷል። የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን የመንግስት ንብረቶች ለገዢው ፓርቲ የምርጫ ዘመቻ መገልገያነት መዋላቸውን አስተውሏል። ቡድኑ የ 2002 የምርጫ ሜዳ በበቂ ሚዛን አልጠበቀም። በብዙ ቦታዎች ለገዢው ፓርቲ ያጋደለ ነበር የሚል እምነት አለው። ” በማለት ገምግመዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ቴክኒካዊ ችግሮችን ብቃት ባለው ሙያዊ ተግባር ተወጥቷል። በማለትም አመስግነዋል። ሙሉ የምርጫ ጣብያዎች ዝርዝርን የመሳሰሉት መረጃዎች አለመኖራቸው ግን በሂደቱ ግልጽነት ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል ብለዋል። ስለሚድያ ሲናገሩ ደግሞ የአሜሪካ ድምጽ ሪድዮ የአማርኛ አገልግሎት መታፈንም የመራጮችን ከዘርፈ ብዙ ምንጮች ኢንፎርመሻን የማግኘት ዕድል ቀንሷል ብለዋል የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን መሪ ታይስ በርማን። |
a_oromya-flood-08-27-10-101798503_1459111 | https://amharic.voanews.com/a/oromya-flood-08-27-10-101798503/1459111.html | በኦሮሚያ ክልል የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪዎች በጎርፍ ተጠቃን ይላሉ፤ አስተዳደሩ ጉዳቱ መጠነኛ ነው ብሏል | በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ በአማራ ክልል ከ37 ሰዎች በላይ የገደለው የጎርፍ አደጋ በኦሮሚያም ተከስቷል። | በኦሮሚያ በህይወት ላይ ጉዳት አልደረሰም በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ጎርፍ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። በአካባቢው የሚገኝ የሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤት ክፉኛ በጎርፍ መመታቱን ቦሩ ሮባ የተባሉ የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪ ለቮኦኤ ገልጸዋል። “የደረሰው ጉዳት በጣም ከባድ ነው። ጉዲና ቱምሳ GTS የተባለ ሃይስኩል (ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) አለ። ያን ትምህርት ቤት እንዳለ ወስዶታል (ጎርፍ)” ብለዋል አቶ ቦሩ ሮባ። የምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳድር በበኩሉ መጠነኛ ጎርፍ በመተሃራ ከተማ አቅራቢያ እንደነበረና ያስከተልው ከፍተኛ ጉዳት እንደሌለ ለቪኦኤ አብራርቷል። የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብራሃም አዱላ ጉዳቱ መጠነኛ ነው ብለዋል። “የፈንታሌ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው መተሃራ አቅራቢያ በሰቃ ሀይቅ የሚባል የተፈጥሮ ሃይቅ አለ። በበጋው ወር ውስጥም አልፎ አልፎ ዝናብ ይዘንብ ስለነበረ፤ መጀመሪያ ካለው የውሃ ይዘቱ የጨመረበት ሁኔታ አለ፤” ብለዋል። በመተሃራ የስኳር ፋብሪካና በግል የከብት ማደለቢያ አካባቢ የተወሰነ ጥፋት መድረሱንና የሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤት በጎርፍ መጥለቅለቁን የተናገሩት አቶ አብርሃም አዱላ፤ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጠዋል። ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል አከታትሎ የጣለው ዝናብ በአምስት ወረዳዎች 37 ሰዎችን ሲገድል ከ6ሽህ በላይ ሰዎችን ማፈናቀሉን የክልሉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የአስቸኳይ ጊዜ ሰራተኞች የተጎጂዎቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል በመግለጽ ላይ ናቸው። የክረምቱ ዝናብ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ድርጅት አስታውቋል። |
a_henok-youth-white-house-08-03-10-99888544_1460928 | https://amharic.voanews.com/a/henok-youth-white-house-08-03-10-99888544/1460928.html | ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ከወጣት የአፍሪካ ሃሳብ አፍላቂዎችና መሪዎች ጋር ተገናኙ | የአፍሪካ የወደፊት የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የምህበራዊ ተቋማት መሪ የሆኑ ወጣቶች እርስ በርስ ልምድ ይለዋወጣሉ፤ ከታላላቆቻቸውም ተሞክሮ ይካፈላሉ። | ጉባኤው እስከ ሀሙስ ድረስ ይቀጥላል ከ45 የአፍሪካ አገሮች የተሰባሰቡት 115 ወጣቶች ዛሬ ማለዳ በውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ለአራት ቀናት የሚዘልቀውን ውይይታቸውንና የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብራቸውን ጀምረዋል። እነዚህ በሚኖሩበት አገር በአነስተኛና ከፍተኛ የማህበራዊ መሪነት ጉልህ ሚና የተጫወቱ ወጣቶች ለአፍሪካ የወደፊት ተስፋዎቿ፣ አሁን ደግሞ የእድገት ክንዶቿ ናቸው ሲሉ የዩናይትድ ስቴይትስ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን በስብሰባው መክፈቻ ተናግረዋል። በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ-ግዛት ነጻ የወጡበትን 50ኛ አመት በማክበር ላይ ባሉበት ወቅት የወደፊትና የአሁን የአህጉሪቷን መሪዎች አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አምነው ነው ፕሬዝደንት ኦባማ በዋይት ሃውስ እነዚህን ወጣቶች ለውይይት የጠሩት። ወደ ዋይት ሃውስ ከማምራታቸው በፊት ግን እነዚህ ወጣቶች እርስ በርስ በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይተዋል። በርካታ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶችና ልምዶችን ከየአገራቸው ይዘው የመጡት ወጣቶች እርስ በርስ እየተማማሩ ችግሮቻቸውን ከባለሙያዎች ጋር እየተወያዩ አርፍደዋል። ከኢትዮጵያም 4 ተሳታፊዎች መጥተዋል። አንዳንዶቹ በወጣቶች ማህበር የተሰባሰቡ አቀንቃኞች ሲሆኑ፤ ሌሎቹ ደግሞ እጅጊያቸውን ሰብስበው በስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው። ይሄ ስብሰባ ታዲያ ለሁሉም ነው። ግንዛቤ መፍጠር፣ አቅም መገንባትና የተሰሩ ተግባራዊ ስራዎችን ደግሞ ለሌሎች ማሳየት ነው አላማው። እኛ የወጣት ጉዳይን ይዘው በየስብሰባው ለሚሳተፉ ቦታ የለንም፤ በስራ የተሰማራችሁ ካላችሁ ግን ስራችሁን አሳዩንና ወደ ትልቅ ደረጃ እናድርሰው ሲሉ የተናገሩት ደግሞ TED የተባለው የፈጣሪ ጭንቅላት ያላቸውን አፍሪካዊያን ወጣቶች የሚያግዝ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ለምሳሌ በመንደራቸው ከንፋስ መዘውር የሚሰራ የሀይል ማመንጫ እንደገነባው የማላዊው የ12 አመት ወጣት ዊሊያም ኳምክእ`ምባ አይነት ፈጣሪዎችን ያግዛል። በቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚገኙ እድገቶችን፣ ማህበራዊ ችግሮችን የመፍቻ አዲስ መንገዶችን፤ ሰርቶ የማደርና ኑሮን የማሸነፍ ውጤቶችን ያበረታታል። በዚህ ጉባኤ የሚሳተፉት ወጣቶች ታዲያ እንዲህ ያለ ድጋፍ ከሚሰጡ ድርጅቶች ተወካዮችም ጋር ይወያያሉ፣ ሃሳብ ይለዋወጣሉ፣ ተዋውቀውም ወደፊት ለሚሰሩት ስራ ድጋፍ ያመቻቻሉ። ይህንን ነው ፕሬዝደንት ኦባማም የአፍሪካ ወጣቶች እንዲያደርጉ አስበው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የጠሯቸው። |
a_amh-wfp-famin-7-21-11-125957683_1459934 | https://amharic.voanews.com/a/amh-wfp-famin-7-21-11-125957683/1459934.html | በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ከብቶች እየሞቱ ነው | በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ፣ በሶማሊያና በኬንያ የተከሰተው ድርቅ ወደርሃብ በመሸጋገር ላይ በመሆኑ ከፍተኛ እልቂት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ የዓለም የምግብ ድርጅትና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስጠነቀቁ። | በሶማሊያ የተከሰተው ድርቅ ወደርሃብ መሸጋገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ እርዳታ በማይደርስባቸው የሶማሊያ ደቡባዊ ቀጣናዎች ድርቅ ያስከተለው ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት ዕለቂት ሊያስከትል ወደሚችል ርሃብ መሽጋገሩን የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይፋ አደረጉ። የአፍሪካ ህብረትና የዓለሙ ድርጅት የደረሰውን ሰባዊ ቀውስ ለመታደግ በትብብር እንዲንቀሳቀሱ ጠየቁ። የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጆሴት ሽራም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ኢራስተስ ሞኤንቻ ጋር በመሆን በአፍሪካ ህብረት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው ድርቅና ያስከተለው ቀውስ መከታተል ድርጅታቸው በዓለም ላይ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። ድርቁ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶማሊያ ኬንያና ኡጋንዳ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። የዚህ ሰባዊ ቀውስ ዋና ተጠቂ የደቡብ ሱማሊያ ክፍል ነው ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። “ ሁኔታው ከባድ ጥፋት እያስከተለ ነው። ሆኖም በቁጥጥር ስር ነው። የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ እየጨመረ ነው። ስለሆነም በማንደርስባቸው አካባቢዎች ካልሆነ በስተቀር የሰው ህይወት አልጠፋም” ብለዋል ሽራም። “እንዳለን መረጃ ከሆነ ሰባ በመቶ የሚሆነው የሶማሊያ ህዝብ ዕርዳታ ማግኘት በሚችልበት ሁኔታ ላይ አይደለም። ይህ ደግሞ ሰባዊ ቀውስ ፈጥሯል። በታሪክ እንደታየው ድርቁ እየከፋ በሄደ ቁጥር ሰባዊ ቀውሱ እየከፋይሄዳል ይላሉ ሽራም። በአፍሪካ ቀንድ ድርቁ በስፋት የደረሰ ቢሆንም የሰው ህወት አልጠፋም ያሉት ጅሴት ሽራም መድረስ ያልተቻለባቸው የሱማሌ አካባቢዎች ግን ድርቁ ወደርሃብ ተሸጋግሯል። “የአሰራር ፕሮቶኮል የምንመሰርትበትን ብልሃት በማፈላለግ ያስቸኳይ ጊዜ እርዳታዎች አከማችተን በደቡብ ሱማሊያ የችጋር ቀጣናዎች ተብለው ወደተለያዩ አካባቢዎች ለመድረስና ሕይወት ለማዳን እየሞከርን ነው። ሚስ ሽራም ይህን ቀውስ ለመፍታት የሚያስፍልገውን እርዳታ ለመሰብሰብ በፍጥነት መንቀሳቀስ ይገባል ብልዋል። “የእርዳርታውን ቁሳቁስ ባስቸኳይ ማሰባሰብ ያስፈልጋል። አሁን ያለን ጉድለት $190 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይሄ ደግሞ ለተጠበቀው 6 ሚሊዮን እርዳታ ጠባቂ ህዝብ ነበረ። በግንቦትና ሰኔ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ስላልጣለ ይህ የርዳታ ጠባቂ ቁጥር ወደ 11 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይጠበቃል። ይሄ በደቡብ ሶማሊያ ያሉትን ለመድረስ ተስፋ በማድረግ ነው። ድርቁ በኢትዮጵያ ያስከተለውን ችግርም በጥልቀት ዘርዝረዋል። “በኢትዮጵያ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ በሚገኙ ሰፊ አካባቢዎች ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በተለይም አርብቶ አደሩ በቀውስ ውስጥ ይገኛል። ይኽ ቀውስ ለረጅም ጊዜ የቆየ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታትም ብዙዎች ከብቶቻቸውን አጥተዋል። ሌሎች በርካቶችም ያላቸውን ሁሉ ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ አጥተዋል። እናም በአርብቶ አደሮች ላይ የደረሰው ቀውስ በጥልቁ ያሳስበናል። ዳይሬክተሯ ድርቁ ያስከተለውን ቀውስ ለመቋቋም ከአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጋር በጥልቀት ተወያይተዋል። የህብረቱ ረዳት ኮሚሽነር ኢራስተስ ሞኤንቻም ስለውይይታቸው ትኩረት ይህን ብለዋል። “ትኩረታችን አሁን በምናየው ቀውስ ላይ ብቻ አይደለም። እንዲህ አይነት ሁኔታን እንዴት መከላከልና ማለዘብ እንችላለን በሚለው የወደፊቱን ጊዜ ጭምር ነው። አቅምን በመገንባት ላይ ዘላቂነት ያላቸው መፍትሄዎች በመዘርጋት ላይ ነበር አተኩረን የተነጋገርነው። 13 የድርጅቱ ሰራተኞች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በስራላይ እንዳሉ መገደላቸውን ጆሴት ሽራም አውስተው የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተባብረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል |
a_voa-radio-mag-stories-with-alula-kebede-and-addisu-abebe-11-22-15_3073955 | https://amharic.voanews.com/a/voa-radio-mag-stories-with-alula-kebede-and-addisu-abebe-11-22-15/3073955.html | የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች፥ አዲሱ ሰባት ኪሎ መጽሔት፥ እና ሌሎች ሙዚቃ ነክ ወጎችና የሃሳብ መስመሮች፤ | የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ። | “ሰባት ኪሎ” የሚል ሥያሜ ስለ ሰጡትና በቅርቡ ለንባብ ስለ በቃው መጽሔታቸው፥ ጋዜጠኝነት በስደትና መንገዶቹ የሚያወጉን እንግዶች፤ ከቀድሞዎቹ አዲስ-ነገሮች ሁለቱ ለራዲዮ መጽሔት ወግ ተሰይመዋል። ከዓመታት በፊት “መርካቶ ሰፈሬ፤” በተሰኘችው ዜማው ከሙዚቃ አድናቂዎች ጋር የተዋወቀው ድምጻዊ አብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ” በሚል ሥም ያወጣውን አዲስ አልበም ይዞ ብቅ ብሏል። በእንግሊዥናው ምሕጻረ ቃል AFRIMA በመባል ለሚታወቀው “የመላው አፍሪቃ ዓመታዊ የሙዚቃ ሽልማት” ለሁለተኛ ጋዜ ከተመረጠችው ድምጻዊት ጸደኒያ ገብረማርቆስ ስለ ሽልማቷ፥ የውድድሩ ሂደትና ሌሎች ተዛማች ርዕሶች እንነጋገራለን። “የሃሳብ መስመር” ... የተለያዩ ጉዳዮችንና ሁኔታዎችን የሚመለከቱ ጭብጦች መናሃሪያ ነው። እውነት ምንድ ናት? በሚል ጥያቄ ዙሪያ ያጠነጥናል። ሕዳር ይታጠናል። የዕለቱ የታሪክ ማስታወሻ ከአዲስ አበባ ተቀናብሯል። የሳምንቱን የራዲዮ መፅሔት ወጎች እነሆ፤ |
a_a-53-2008-04-30-voa2-93031129_1457722 | https://amharic.voanews.com/a/a-53-2008-04-30-voa2-93031129/1457722.html | African Athletics Championships DAY 1: Ethiopia Sweeps Medals in the Men’s 10,000 meters | Gebreegziabher Gebremariam led the Ethiopian trio to victory and finishing the10,000 meteres in 28:17.11. | 10,000 m - MENS FINAL RANK NAME NAT 1. Gebregziabh. GEBREMARIAM ETH 28:17.11 2. Ebrahim JEILAN ETH 28:30.66 3. Eshetu WONDEMU ETH 28:56.36 4. John KORIR KEN 29:07.33 5. Bernard SANG KEN 29:47.61 6. Julius KIPTOO KEN 30:12.10 SHOTPUT - MENS FINAL RANK NAME NAT RESULT 1. Abdu Moaty MOUSTAFA EGY 18.06 2. Yasser IBRAHIM EGY 17.39 3. Janus ROBBERTS RSA 16.44 HAMMER - WOMENS FINAL RANK NAME NAT RESULT 1. Marwa HUSSIN EGY 62.26 2. Florence EZEH 61.26 3. Funke ADEOYE NIG 57.02 |
a_inventions-for-though-times-3d-printers-ppe-faruk-mubarek-with-voa-alula-kebede-may-2020_5437346 | https://amharic.voanews.com/a/inventions-for-though-times-3d-printers-ppe-faruk-mubarek-with-voa-alula-kebede-may-2020/5437346.html | ሕይወት ለማዳን የዋለ ጥበብ እና አሳቢነት | “እንደሚታወቀው አገራችን ደካማ የሚባል የጤና ሥርዓት ነው ያላት አገር ነች። ከዚህ በፊት በተክለምዶ የተለያዩ እርዳታዎች ከውጭ ይመጡ ነበር። አሁን ግን ያደጉትን አገሮች ብንመለከት አራቸውን ዘግተው ራሳቸውን ለማዳን እየተረባረቡ ናቸው። ‘የስሪ ዲ ኮሚኒቲዎች’ እና ቴክኖጂውንም ሳይ ደግሞ ብዙው የውሚሰሩት ራሳቸውን ለመጥቀም ነው። ስለዚህ እኛም ለምን ይሄንን ወስደን ራሳችንን ለምን አናድንም ከሚል ነው የተነሳሁት።” ፋሩቅ ሙባረክ። | ዋሽንግተን ዲሲ - አዲስ አበባ — ክፍል ሁለት ከጊዜያችን ብርቱ ፈተናዎች አንዱ ለሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ የሚውሉ ሁነኛ መላ ፍለጋ የሚደረገው ጥረት በሁሉም አቅጣጫ ቀጥሏል። በዚህ መላውን የሰው ልጆች በገጠመ ፈተና እንደየተሰማሩበት ሞያና እንደየክህሎቶቻቸው የተያዘው ጥረት አጋዥ ለመሆን የበኩላቸውን ለማድረግ ደፋ ቀና የሚሉት ብዙዎች ናቸው። የወረርሽኙን የጥድፊያ መዛመት ለመግታትት ሁነኛ የመከላከያ ብልሃቶችን በመቀየስ አገራዊውን ጥረት ከሚያጎለብቱት፤ ከፍተኛ እጥረት የሚታይባቸውን አስፈላጊ ቁሳቁሶች እጥረት ለመቀነስ የሚያግዙ መላዎችን እስከሚፈነጥቁት ይዘልቃሉ። የኮቪድ 19 ህሙማንን ለመርዳት በግንባር የተሰለፉትየሕክምና ባለሞያዎች ለበሽታው እንዳይጋለጡ ለማድረግ በታለመ ጥረት '3D ፕሪንተር' በመባል የሚታወቀውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የመከላከያ ቁሳቁሶችን በመስራት ላይ የሚገኝ ወጣት ነው። ፋሩቅ ሙባረክ ይባላል። ስለ ስራውና ለዚህ መልካም ዓላማ ያነሳሱትን ምክኒያቶች ጨምሮ ሊያጫውተን ከአዲስ አበባ በስልኩ መስመር ብቅ ብሏል። የቃለ ምልልሳችንን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ። ክፍል አንድ |
a_south-sudan-independence-7-11-2011-125348308_1459557 | https://amharic.voanews.com/a/south-sudan-independence-7-11-2011-125348308/1459557.html | የደቡብ ሱዳን አስተዳድር ከጎረቤቶቹ ጋር አብሮ ለመስራት እጁን ዘረጋ | ሀምሌ 2 ቀን 2003ዓም የአለማችን አዲሲቱ አገር ደቡብ ሱዳን ተወለደችበት እለት ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ባሰሙት ንግግር አገራቸው የመልካም ጉርብትናና የትብብር እጇን እንደምትዘረጋ ገልጸዋል። | ቅዳሜለት በመዲናዋ ጁባ በተደረገ ስነስርዓት በአስር ሽዎች የተቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ዜጎች በአለም መሪዎች ታዛቢነት የአዲስ አገር ምስረታ በዓላቸውን አክብረዋል። ከዋዜማው ጀምሮ ማምሻውን በጸሎትና በባህላዊ ጭፈራዎች ደምቆ ያመሸው የነጻነት ዋዜማ፤ ቅዳሜ ማለዳ ባንዲራ ይዘው ለነጻነት ክብረበዓሉ በወጡ ዜጎች ታጅቦ፣ በአለም መሪዎች ታዛቢነት ተበስሯል። የደቡብ ሱዳን አስተዳድር ፕሬዝደንት የነበሩት ሳልቫ ኪር፤ የአዲሱቱ አገር ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ ማሃላ ፈጽመዋል፤ ሃገሪቱ የምትተዳደርበትን ህገ-መንግስትንም በፊርማቸው አጽድቀዋል። ፕሬዝደንት ኪር በትረ-ስልጣኑን ከተረከቡ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ ደቡብ ሱዳናዊያን ለዛሬዋ የነጻነት ቀን እውን መሆን ለከፈሉት መስዋእትነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በተለይ የሱዳን ህዝቦች የነጻነት ጦር (SPLA) ን የመሰረቱትን ጆን ጋራንግ አመስግነዋል። “ለ56 ዓመታት የጠበቅናት ቀን ናት። ህልማችን ዛሬ እውን ሆኗል” ብለዋል ኪር “ውድ ጓዶቼ የዛሬዋ ቀን ለነጻነት ለወደቁ ጀግንኖቻችን ልባዊ የሆነ ምስጋናና አክብሮት የምናቀርብበት ሊሆን ይገባል። ከዚህ ንግግር አስቀድሞ የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽር ባሰሙት ንግግር፤ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክን እውቅና የሰጠችው የመጀመሪያዋ አገር ሱዳን መሆኗን ተናግረዋል። ለአዲሲቷ አገር መልካም እድል የተመኙት አል-በሽር፤ መንግስታቸው አሁን ጎረቤት ከሆነችው ደቡብ ሱዳን መልካም ንግኙነት እንደሚሻም ይፋ አድርገዋል። ደቡብና ሰሜን ሱዳን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍርጫቸው የቆየ ነው። ሱዳን ከግብጽና ከብርታንያ ጥምር የቅኝ አገዛዝ እንደ እ.ኤ.አ በ1956 ዓም ነጻ ከወጣች ወዲህ በሱዳን ሰላም አልታየም። የቀደሙ የትጥቅ ትግሎችን ተከትሎ የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጭ ጦር (SPLA) በዶ.ር ጆን ጋራንግ ከተመሰረተ ወዲህ፤ ከሁለት አስርት አመታት በላይ በደቡብና ሰሜን ሱዳን መካከል መሪር ውጊያ ተካሂዷል። በነዚህ የጦርነት ዘመን ደቡብ ሱዳናዊያን ተሰደዋል፣ ተርበዋል ተጠምተዋል። “ይቅር እንላለን ግን አንረሳም! ” ብለዋል ኪር። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር አክለውም ከጎረቤቶቻቸው ጋር በሰላም፣ በልማትና አብሮ በመስራት የሚያተኩር ግንኙነት ለመፍጠር መንግስታቸውና ህዝቦቻቸው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። “ከሱዳን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር እንዲሁም ከሁሉም ጎረቤቱቻችን ጋር በህብረት ከህዝባችን ጋር በጸባይም ሆነ በምግባርም የሰመረ ግንኙነት እንዲኖረን፣ በሰላም መልካም የጉርብትና እጆቻችንን እዘረጋለን” ብለዋል ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር። በደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የነጻነት በአል ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪሙን፣ የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦማር አልበሽርና ሌሎችም የአለም መሪዎች ተገኝተዋል። |
a_usaid-officials-ethiopia-127886433_1462105 | https://amharic.voanews.com/a/usaid-officials-ethiopia-127886433/1462105.html | የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት አሞገሱ | የ United States የአለም አቀፍ ረዴት ባለስልጣን በኢትዮጵያ ረሀብ እንዳልጋባ ገለጹ | የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ገለጹ። አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎችም እርዳታውን እያገኙ ናቸው ብለዋል ባለስልጣናቱ። በ United States አለም አቀፍ የተራዶ ድርጀት ከፍተኛ ምክትል የእርዳታ አስተባባሪ Gregory Gotlied በአዲስ አበባ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሲም አልሱ፣ “በኢትዮጵያ ረሃብ የለም እንላለን። አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በሱማልያ ያለውን ሁኔታ አይመስልም። ያ ረሃብ ነው። የእነዚህ በተመጣጠነ ምግብ እጦት ከሚታይ ጉዳት በላይ ነው። እዚህ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ አይነት ሁኔታ የለም። እና በዚያ ረገድ እዚህ ይሻላል። " ሲሉ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ አብራርተዋል። ኤቶጵያ ውስጥ በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጎዱ ህጻናት ክሊኒክ ሄደው ተገቢውን ህክምና እንደሚያገኙ ከምግብ ዋስትና አኳያም ተስፋ የሚያሳድሩ አዝማምያዎች አሉ ሲሉ የአሜሪካው ባለስልጣን አስገንዝበዋል። |
a_meles-press-conference-05-27-10-95042384_1462514 | https://amharic.voanews.com/a/meles-press-conference-05-27-10-95042384/1462514.html | ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችን ነቀፉ፤ | "የምርጫው ውጤት ትብብራችንን ለመቀጠል የሚያስችል አይደለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ - መልካም፤ እስከዛሬ ላደረጉልን እርዳታ እያመሠገንን ወደፊት መቀጠል ነው፡፡" መለስ ስለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አቋም ሲናገሩ፡፡ | መለስ ዜናዊ “የአውሮፓ ኅብረት ታዛቢዎች የፖለቲካ ድምዳሜውን ለራሣቸው ዓላማ በሚመጥን መልኩ የሰፉት ስለሆነ እኛ ልንለብሰው አንችልም’ አሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ትላንት በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርተዋል፡፡ የሃገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች ያነሷቸው ጥያቄዎች ከምርጫው ጋር የተያያዙ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከል አንዱ ካለፉት ምርጫዎች ሁሉ በተለየ ሁኔታ ገዥው ፓርቲ ከሁለት መቀመጫዎች በስተቀር የፓርላማውን መቀመጫዎች ጠቅልሎ መውሰዱ "በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደትና በብዙኅነት አቅጣጫ ላይ አደጋ የለውም ወይ? " የሚል ነበር፡፡ እንዲያውም በቻይና እንደሚታየው ዓይነት የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ሊፈጠር እንደሚችልም ተመላክቷል - በጥያቄዎቹ፡፡ ይህንን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችም ሲሉት ነበረ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን በዚህ ፈፅሞ አይስማሙም፡፡ "በኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ሥርዓት ሊፈጠር የሚችልበት ሁኔታ ፈፅሞ የለም፡፡ በሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ መኖር ምክንያት ይህ በምንም ዓይነት ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ ምናልባት እንደስዊድን ያለ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ወይም እንደጃፓኑ ሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ተፅዕኖ የሠፈነበት ሥርዓት ለአንድ አሠርት ዓመት ወይም ወደዚያ የሚጠጋ ጊዜ ሊኖር ይችላል፡፡ ግን በምንም ዓይነት በኢትዮጵያ የአንድ ፓርቱ ሥርዓት ሊፈጠር አይችልም፡፡ የዘንድሮው ምርጫ ውጤት በሠላማዊና ሕጋዊ መንገድ በሃገሪቱ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ኃይሎችን የሚያዳክምና ፅንፈኛ ለሚባሉ የፖለቲካ ኃይሎች አመቺ ሁኔታን ሊፈጥር ይችላል የሚለውን ክርክርም አቶ መለስ ዜናዊ ጨርሶ አይቀበሉትም፡፡ እንዲያውም ፓርቲያቸውም ሆነ የሚመሩት መንግሥት የሚከተሏቸው ፖሊሲዎች ፅንፈኛ የሚባሉ ኃይሎችን እንኳ እያለዘበ ወደ ሕጋዊና ሠላማዊ የፖለቲካ መስመር እያስገባ መሆኑን በመግለፅ ይከራከራሉ፡፡ እንደምሣሌም ከጥቂት ወራት በፊት ከመንግሥት ጋር የተፈራረመውን የምዕራብ ሶማሌ ነፃነት ግንባርና በቅርብ ጊዜ ደግሞ ተመሣሣይ ስምምነት ሊፈርም ነው ያሉትን የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር አንድ አንጃም ይጠቅሣሉ፡፡ የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ግንቦት 18 ቀን 2002 ዓ.ም ካወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀበሉት የተዘረዘሩትን "ጥሬ ሃቆች" ያሏቸውን ብቻ ነው፡፡ በእነርሱም ላይ እንኳ አንዳንድ የተዛቡ ነገሮች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ መደምደሚያውን በተመለከተ ያላቸውን ቅሬታ ግን አልሸሸጉም፡፡ "ከሞላ ጎደል በትክክል አስቀምጠውታል፤ ድምዳሜውን ከፖለቲካ ዓላማቸው ጋር አብሮ በሚሄድ ልክ ሰፍተው አስቀምጠውታል፡፡ የፖለቲካ ድምዳሜውን ለራሣቸው ዓላማ በሚመጥን መልኩ የሰፉት ስለሆነ እኛ ልንለብሰው አንችልም፡፡ ጥሬ ሃቁ ግን ጥሬ ሃቅ ስለሆነ ልንቀበለው የምንችል ነው፡፡ " ብለዋል፡፡ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ አስተያየቱን የሰጠው የአውሮፓ ኅብረት ታዛቢ ቡድን ብቻ አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው ከሚባሉት መንግሥታት መካከል የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትም አስተያየቱንና ውጤቱ ያሣሰበው መሆኑን ገልጿል፡፡ ደግሞም የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሰብዓዊ እርዳታ በሰፊው ይለግሣል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን እንዴት እንደሚመለከቱትም ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ሃገሪቱ ያላት ግንኙነት በሁለቱም ሃገሮች የጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ መሆኑን አበክረው ያስረዱት አቶ መለስ ይህ መልካም ግንኙነት ወደፊትም እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ አረጋግጠዋል፡፡ "ግን - አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ - ኢትዮጵያ በሞግዚት የምትተዳደር ሃገር አይደለችም፡፡ ዩናይትድ ስቴትስም በዚህ ረገድ አንድ ጥርጣሬ የላትም፡፡ "ዩናይትድ ስቴትስ የታክስ ከፋዮቿን ገንዘብ ይሆናል እርሷ ባሻት ሁኔታ ልትጠቀምበት ሙሉ መብቷ ነው፡፡ የምርጫው ውጤት ትብብራችንን ለመቀጠል የሚያስችል አይደለም ብለው የሚያስቡ ከሆነ - መልካም፤ እስከዛሬ ላደረጉልን እርዳታ እያመሠገንን ወደፊት መቀጠል ነው፡፡ ይሁንና ' ከዚህ ወይም ከዚያ ሃገር የሚመጣው የእርዳታ እህል ከቆመ የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሃብ ያልቃል' ብለው የሚያስቡ ሰዎች ካሉ ይህቺ ሃገር እንደት እንደምትተዳደር ምንም የማያውቁ ናቸው፡፡ ረቡዕ መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ አልነበሩም፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን መግለጫዎችን ሰጥተዋል፡፡ ሁሉም በምርጫው ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡ ከአፍሪካ ሕብረት ታዛቢዎች በስተቀር የተቃዋሚዎቹና የመንግሥት ባለሥልጣናቱ መግለጫዎች ቢያንስ መንፈሣቸው የሚጣጣም አይደለም፡፡ ይህ አለመጣጣም እንዲረግብ የማንም ጤናማ ሰው ምኞት ነው፡፡ ታሪክ ግን በምኞት አይሠራም፡፡ መለስካቸው አምሃ - ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ከአዲስ አበባ፡፡ |
a_amh-onlf-sweeds-ethiopia-7-5-11-125030254_1463114 | https://amharic.voanews.com/a/amh-onlf-sweeds-ethiopia-7-5-11-125030254/1463114.html | ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በኦጋዴን በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ቆስለው ታሰሩ | በሰሜናዊቷ የሶማሊያ ራስ ገዝ ፑንትላንድ በኩል ድንበር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ያቀኑት ስዊድናዊ የፎቶ ጋዜጠኞች በኦብነግ አማጺያን አጃቢነት ድንበር ሲሻገሩ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ቆስለው ታስረዋል። | ሰኔ 23 ቀን ኢትዮጵያን በሚያዋስነው የፑንትላንድ ድንበር በጋልቃዮ በኩል ሁለቱ ስዊድናዊ ጋዜጠኞች ከከኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጭ ግንባር (ኦብነግ) ታጣቂዎችና ሌሎች አጋዦቻቸው ጋር ሲጓዙ ነበር የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በደረሳቸው መረጃ መሰረት ተከታትለው ያገኟቸው። ወዲያውኑ ተኩስ ተከፈተ። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ስምዖን የሆነውን ለVOA እንዲህ ያስረዳሉ። “ተኩስ ነበር። በዚህ የተኩስ ልውውጥ 15 የአሸባሪ ድርጅቱ ታጣቂዎች ወዲያውኑ ተገድለዋል። ስድስቱ ተማርከዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሁለት የውጭ አገር ዜጎች ተይዘዋል” ብለዋል አቶ በረከት ስምዖን። አቶ በረከት “ሁለቱ የውጭ አገር ዜጎች” ያሏቸው ዮሃን ፐርሰን እና ማርትን ሽቢየ የተባሉ የስዊድን ዜጎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በፑንትላንድ በኩል ጋዜጠኞቹን ለማሳለፍ አጃቢዎችና መሪዎች መላኩን ያስታወቀው በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻአውጭ ግንባር (ኦብነግ) ከጋዜጠኞቹ ጋር ከሰኔ 24 ቀን ወዲህ ግንኙነቱ መቋረጡንና፤ የኢትዮጵያ ሃይሎች የጋዜጠኞቹን ረዳቶች ገድሎ፤ ስዊድናዊ ጋዜጠኞቹን አስሯል ሲል በዛሬውለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አቶ በረከት ስምዖን የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ሁለቱን ጋዜጠኞችና ሌሎች 21 ሰዎች ከማግኘታቸው በፊት በጋልቃዮ በኩል ወደ ኦጋዴን ለመግባት ሲሞክሩ በጀሌዎና በሊወርድ የአካባቢው ፖሊስና የጸጥታ ሃይሎች ድርሰው ተኩስ እንደከፈቱባቸው ነው የተናገሩት። በዚህ የተኩስ ልውውጥ መካከል ሁለቱም ጋዜጠኞች ቆስለዋል። “በተኩስ ልውውጡ አንዱ….በእርግጥ ሁለቱም በመጠኑ ቆስለዋል። አንዱ ትንሽ ጠለቅ ያለ ቁስል አለው፤ ግን ለሞት የሚያበቃው አይደለም” ብለዋል አቶ በረከት። በዛሬውለት መግለጫ ያወጣው ኦብነግ በኢትዮጵያ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀ ነው። ድርጅቱ እንደሚለው ሁለቱ ጋዜጠኞች “ኮንቲነንት ፎቶጆርናሊስት ኤጀነሲ” ለተባለ የፎቶ አንሽ ጋዜጠኞች ድርጅት የሚሰሩ ናቸው። በፑንትላንድ በኩል ጋዜጠኞቹ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞች ወደ ኦጋዴን ሄደው እንዳይዘግቡ በመከልከሉ እንደሆነ ኦብነግ አስታውቋል። ይሄም የሚደረገው የኢትዮጵያ ወታደሮች በኦጋዴን የሚፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ረገጣና ግድያ ለማድበስበስ እንደሆነ ኦብነግ በመግለጫው አስታውቋል። አቶ በረከት ስምዖን መንግስታቸው ለውጭ አገር ጋዜጠኞች የሚሰጠው የዘገባ ፈቃድ እንዲህ ያለ መንግስታቸው እንደሚያምነው “የልዖላዊ ድንበርን የመሻገር ወንጀል አያካትትም” ብለው ጋዜጠኞቹ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ገልጸዋል። “እነዚህ ሰዎች ህጋዊ ፓስፖርት የላቸውም። ከዚያ በተጨመሪ ከአሸባሪ ድርጅት ጋር ሲሰሩ ተይዘዋል። ስለዚህ ህጉ በሚደነግገው መሰረት፤ ህገ-ወጥ ናቸው ስለዚህ እንደ ህገወጥ እናያቸዋለን” ብለዋል አቶ በረከት ስምዖን። አቶ በረከት አክለውም ከሁለቱ ጋዜጠኞች መካከል ዮሃን ፐርሶን ከዚህ በፊት በኦጋዴን መያዙን ተናግረዋል። “ሚስተር ጆን በድንበሩ በኩል ተሾልኮ ሲገባ ይሄ ሶስተኛ ጊዜው ነው። ይሄን አምኗል። በ2000ዓም በአካባቢው ፖሊስ ተይዞ ነበር። ለአካባቢው ፖሊስ የነገረውን ከግምት በማስገባት ወዲያውኑ ተለቋል። ከዚያም በኋላ ስለ ኦብነግና የኢትዮጵያ መንግስት የተሳሳተ መረጃ ሲያሰራጭ ቆይቷል። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ለኢትዮጵያ መንግስት መረጃውና አቀብሏል ያለው የፑንትላንድ አስተዳድርና የኢትዮጵያ መንግስት ላይ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድርጊቱን በማውገዝ መተባበር አለበት ብሏል። የኢትዮጵያ መንግስትም ታጋቾቹን እንዲለቅ ጫና ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል ኦብነግ። ኢትዮጵያ በቅርቡ ባወጣችው የጸረ-ሽብር ህግ፤ መንግስቱ አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ነፍጥ ካነሱ አንጃዎችና ከተወሰኑ ተቃዋሚዎች ጋር ጋዜጠኞች እንዳይሰሩ ይከለክላል። ባለፈው ሳምንት የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬና የፍትሕና አዲስ ፕሬስ ጋዜጦች፣ የፖለቲካ አምደኛ ወይዘሪት ርዕዮት ዓለሙ ታስረው ለፍርድ ቀርበዋል። በኒውዮርክ መሰረቱን ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲ.ፒጄና የመብት ተሟጋች ቡድኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችን “አሸባሪዎች” በሚል እንዲያስር የሚያደርገው ህግ ለመብት ረገጣና ለአፈና የተመቼ ነው ሲሉ ጉዳዩ በብርቱው እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል። ሲ.ፒ.ጄ በጸረ-ሽብር ህግ ጋዜጠኞችን አሸባሪዎችን አነጋግራችኋል አብራችሁ ሰርታችኋል በማለት ማዋከብና ማሰር በኢትዮጵያ እንዲቆም ጠይቋል። |
a_ethiopia-edp-election-95273224_1458296 | https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-edp-election-95273224/1458296.html | የ2002ቱ አጠቃላይ ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ አልነበረም፤ በበርካታ ችግሮች የተሞላም ነበር፤ ሲል ኢዴፓ አስታወቀ | ምርጫው ተመልሶ ቢደገምም፤ በዴሞክራሲ ተቋማቱ የሚታዩ ግድፈቶች በድጋሜ ለገዥው ፓርቲ ያዳላሉ ሲሉ የኢዴፓ አመራሮች አስታውቀዋል። | ከህግ ውጭ ከአንድ በላይ የኢህአዴግ ወኪል ታዛቢ በየምርጫ ጣቢያዎች ተመድቦ እንደነበር ይላል ኢዴፓ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ 547 መቀመጮች ካሉት የአገሪቱ ፓርላማ ከ99.6 በመቶ በላይ የሚሆነውን ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ተቃዋሚዎች ውጤቱን አስመልክቶ ያላቸውን አስተያየት በመግለጫዎች ጭምር እያስታወቁ ነው። በሸንጎው ወንበሮች ባያሸንፉም የተሻለ ድምፅ ማግኘታቸው ከተነገረላቸው ሁለት ዋነኛ ተቃቃሚዎች አንዱ የሆነው ኢዴፓም በዛሬው ዕለት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ አቋሙን ይፋ አድርጓል። የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ልደቱ አያሌው፥ ዋና ፀሃፊው አቶ ሙሼ ሰሙና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ መስፍን መንግስቱ በተገኙበት ኢዴፓ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ጋዜጠኞች በሠጠው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫው፤ ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ፥ ገዢው ኢህአዴግ የፈፀማቸው ስህተቶችና ድክመቶች ዋነኞቹ መንስኤዎች ናቸው፤ ብሏል። «መራጮች አስቀድሞ በተወሰነላቸው ሠዓት፥ በአምስት ሠው ተቧድነውና ማንን መምረጥ እንዳለባቸው አለቃ ተመድቦ በጫና እንዲመርጡ መደረጋቸው፤ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎችም ቀድሞ ከተመዘገበው በላይ ድምፅ የተሰጠበት ሁኔታ መከሰቱ፤» በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ከተፈፀሙ የህዝብን የመምረጥ መብት ከሚጋፉ ሁኔታዎች ውስጥ መሆናቸውን ኢዴፓ ገልጧል። «በአንዳንድ አካባቢዎች ከህግ ውጭ ከአንድ በላይ የኢህአዴግ ወኪል ታዛቢ በየምርጫ ጣቢያዎች እንዲመደብ መደረጉና በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎችም የተቃዋሚ የምርጫ ታዛቢዎች ያለ አግባብ እንዲባረረሩ መደረጉ፤ ከእንከኖቹ ጥቂቶቹ ናቸው፤» ሲል ኢዴፓ አመልክቷል። የገዢው ፓርቲ ድክመቶችና ስህተቶች ያላቸውን በአሃዝ ሠላሳ አንድ ያደረሳቸውን ነጥቦች የዘረዘረው ኢዴፓ በችግሮቹ ስፋትና ተቋማዊ ይዘት ምክኒያት ድጋሚ ምርጫ መፍትሄ አያመጣም ሲል ይልቁን ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ድርድር በተቋማቱ ላይ እንዲጀመር ጠይቋል። |
Dataset Card for LR-Sum
LR-Sum is a automatic summarization dataset of newswire text with a focus on less resourced languages with a cc-by 4.0 license.
Dataset Details
Dataset Description
LR-Sum is a permissively-licensed dataset created with the goal of enabling further research in automatic summarization for less-resourced languages. LR-Sum contains human-written summaries for 39 languages, many of which are less-resourced. The data is based on the collection of the Multilingual Open Text corpus where the source data is public domain newswire collected from from Voice of America websites. LR-Sum is released under a Creative Commons license (CC BY 4.0), making it one of the most openly-licensed multilingual summarization datasets.
- Curated by: BLT Lab: Chester Palen-Michel and Constantine Lignos
- Shared by: Chester Palen-Michel
- Language(s) (NLP): Albanian, Amharic, Armenian, Azerbaijani, Bengali, Bosnian, Burmese, Chinese, English, French, Georgian, Greek, Haitian Creole, Hausa, Indonesian, Khmer, Kinyarwanda, Korean, Kurdish, Lao, Macedonian, Northern Ndebele, Pashto, Persian, Portuguese, Russian, Serbian, Shona, Somali, Spanish, Swahili, Thai, Tibetan, Tigrinya, Turkish, Ukrainian, Urdu, Uzbek, Vietnamese
- License: CC-BY 4.0
Dataset Sources [optional]
Multilingual Open Text v1.6 which is a collection of newswire text from Voice of America (VOA).
- Paper: https://aclanthology.org/2023.findings-acl.427/
- Repository: https://github.com/bltlab/lr-sum
Uses
The dataset is intended for research in automatic summarization in various languages, especially for less resourced languages.
Direct Use
The data can be used for training text generation models to generate short summaries of news articles in many languages. Automatic evaluation of automatic summarization is another use case, though we encourage also conducting human evaluation of any model trained for summarization.
Out-of-Scope Use
This dataset only includes newswire text, so models trained on the data may not be effective for out of domain summarization.
Dataset Structure
Each field is a string:
{
'id': Article unique id
'url': URL for the news article
'title': The title of the news article
'summary': The summary of the article
'text': The full text of the news article not including title
}
Dataset Creation
Curation Rationale
Research in automatic summarization for less resourced languages.
Source Data
Voice of America (VOA)
Data Collection and Processing
See our paper for details on collection and processing.
Who are the source data producers?
Voice of America (VOA)
Annotation process
The summaries are found in news article meta data. More detail about the curation process can be found in our paper.
Who are the annotators?
The summaries are found in the news article meta data. The authors of the summaries are authors and staff for VOA.
Personal and Sensitive Information
The only sensative personal information would be information already published in news articles on VOA. See VOA's mission and values
Bias, Risks, and Limitations
The content in this dataset is newswire. See VOA's mission and values for more detail about the journalistic integrity and policy.
Recommendations
The data is newswire text. Training text generation models on this dataset will have similar risks and limitations to other text generation models including hallucinations and potentially inaccurate statements. For some languages that have fewer examples, issues with text generation models are likely to be more pronounced. The dataset is primarily released for research despite having a permissive license. We encourage users to thoroughly test and evaluate any models trained using this data before putting them into production environments.
Citation
If you make use of this dataset, please cite our paper using this bibtex:
BibTeX:
@inproceedings{palen-michel-lignos-2023-lr,
title = "{LR}-Sum: Summarization for Less-Resourced Languages",
author = "Palen-Michel, Chester and
Lignos, Constantine",
editor = "Rogers, Anna and
Boyd-Graber, Jordan and
Okazaki, Naoaki",
booktitle = "Findings of the Association for Computational Linguistics: ACL 2023",
month = jul,
year = "2023",
address = "Toronto, Canada",
publisher = "Association for Computational Linguistics",
url = "https://aclanthology.org/2023.findings-acl.427",
doi = "10.18653/v1/2023.findings-acl.427",
pages = "6829--6844",
abstract = "We introduce LR-Sum, a new permissively-licensed dataset created with the goal of enabling further research in automatic summarization for less-resourced languages.LR-Sum contains human-written summaries for 40 languages, many of which are less-resourced. We describe our process for extracting and filtering the dataset from the Multilingual Open Text corpus (Palen-Michel et al., 2022).The source data is public domain newswire collected from from Voice of America websites, and LR-Sum is released under a Creative Commons license (CC BY 4.0), making it one of the most openly-licensed multilingual summarization datasets. We describe abstractive and extractive summarization experiments to establish baselines and discuss the limitations of this dataset.",
}
Dataset Card Authors
Chester Palen-Michel @cpalenmichel
Dataset Card Contact
Chester Palen-Michel @cpalenmichel
- Downloads last month
- 145