id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-48672456
https://www.bbc.com/amharic/news-48672456
የኢንትርኔት መቋረጥ፡ የሕግ ባለሙያዎች ኢትዮ-ቴሌኮምን ለመክሰስ አቅደዋል
ሃገር አቀፍ ፈተና በመጣ ቁጥር ከተፈታኞች ቀጥሎ ጭንቀት ውስጥ የሚገባው የበይነ-መረብ [ኢንተርኔት] ተጠቃሚው ነው።
ባለፈው ሳምንት፤ ማክሰኞ የሆነው ይህ ነው። ሃገር አማን ብለው ዓለም እንዴት እንዳደረች ለመቃኘት የጎገሉ አንጀት የሚያርስ መረጃ ማግኘት አልቻሉም። ኧረ እንደውም ምንም ዓይነት መረጃ ማግኘት ይቅርና የሞባይልም ሆነ ኮምፒውተር ስክሪናቸው ላይ ብቅ ሊል አልቻለም። ተጠቃሚው የሞባይልና ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ የገባው ዘግየት ብሎ ነው። ኢንተርኔት ብትጠበቅ የውሃ ሽታ ሆና ቀረች። ከሰዓት በኋላ አካባቢ ግን ብቅ አለች። ደግሞ በነገታው አንዲሁ. . .ኢትዮ-ቴሌኮም ምን ገጠመህ? ተብሎ ቢጠየቅ እኔ 'ማውቀው ነገር የለም ሆነ ምላሹ። እንደው ክቡር ሚኒስትሩ ያውቁ ይሆን ቢባል 'ኢትዮ-ቴሌኮም እንጂ እኛ ምን አገባን' ነበር ለመገናኛ ብዙሃን የተሰጠው መልስ። • የኢንተርኔቱን ባልቦላ ማን አጠፋው? እርግጥ ሰዎች የኢንተርኔት መቋረጡ ከሃገር አቀፍ ፈተናዎች ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል [አምና፣ አቻምና የተከሰተውን ልብ ይሏል]፤ ይህ ግን መላ ምት እንጂ የተጨበጠ መረጃ አይደለም። ሐሙስ ዕለት ከኢንተርኔቱ አልፎ አጭር የፅሑፍ መልዕክት አገልግሎት እንደተቋረጠ ተሰማ። 'ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላማ እንዲህ ዓይነት ነገር አይታሰብም?' ያሉ ሁኔታው ግራ አጋባቸው። በጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው ኢንተርኔት አርብ ጀምበር ልትጠልቅ ስታኮበኩብ ገደማ ብቅ አለች። አጭር የፅሑፍ መልዕክቱ ግን እንደቀለጠ ቀረ። አሁንም ቢሆንም የኢንተርኔት አገልግሎት ተመልሶ ያልመጣባቸው ሥፍራዎች እንዳሉ ይነገራል። «ኢትዮ-ቴሌኮምን እከሳለሁ» የሕግ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ እንየው በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር እና የዲጂታል መብት አማካሪ ናቸው። ከሰሞኑ በተፈጠረው ጉዳይ ኢትዮ-ቴሌኮም በሕግ ሊጠየቅ ይገባል ከሚሉ ሰዎች መካከል ናቸው። «ኢንተርኔት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከመጡ ወዲህ እንኳ አራት ጊዜ ያክል ተቋርጧል። እርግጥ ጉዳዩ እንደ ቅንጦት ነው የሚታየው። በሕግ ባለሙያዎች አንድም አንገብጋቢ ከሚባሉ ጉዳዮች ተርታ አይመደብም። ወደሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስትመጣ ግን መንግሥት መሰል ድርጊቶችን ሲፈጽም ይከሰሳል። ብሩንዲ ብትል፣ ታንዛኒያ ሆነ ኡጋንዳ ብትሄድ ኢንተርኔት ሲቋረጥ ይከሳሉ። እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን በቀላል አይልፏቸውም ሌሎች ሃገራት። እኛ ጋር ግን እንደ ቀልድ ነው የሚታየው፤ ማንም ተጠያቂ አይሆንም።» እርግጥ አቶ ዮሐንስ እና ሌሎች የሕግ ባለሙያዎች ጉዳዩ ውልብ ያለላቸው ከሰሞኑ ነው፤ ሂደቱም ገና ጅማሬ ላይ ነው። ቢሆንም እንደውም ሃሳቡን ማጫር በራሱ አንድ እርምጃ ነው ይላሉ ባለሙያው። «እንደው ውይይቱን ብናስጀምረው ብለን ነው። በቀጣይ መንግሥትም ይሁን ኢትዮ-ቴሌኮም፤ አሁን ደግሞ ሌሎች 'ኔትዎርክ ፕሮቫይደሮች' እየመጡ ስለሆነ [ፕራይቬታይዝ እየተደረገ ስለሆነ] ወደፊት ለሚያጋጥሙ የተለያዩ ክስተቶች አላግባብ በሆነ መልኩ ከሕግ ውጭ መሰል ድርጊት እንዳይጸሙም ነው።» ምን ተብሎ ይከሰሳል? ባለፈው ሳምንት እንደ ፌስቡክና ትዊትር ያሉ ማህበራዊ ድር አምባዎች ጭር ብለው ነው የከረሙት [ዕድሜ ለኢንተርኔት መቋረጡ]። ከሃገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ግን ተቃውሟቸውን 'በነፃነት' ሲገልጹ ከርመዋል። ኢትዮ-ቴሌኮም ተከሰሰ እንበል. . .በዋናነት ክሱ የሚሆነው ምንድን ነው? የመረጃ ነፃነት መግፈፍ? ተጠቃሚዎች ለገዙት 'ዳታ' ሳይጠቀሙበት መክሰሩ ነው? ግራ ያጋባል። «እርግጥ ነው ኢንተርኔት መዘጋት ብዙ ችግር ፈጥሯል። ግን እኛ በዋናነት ከምንም በላይ የመናገር ነፃነት፤ ሁለተኛ ደግሞ መረጃ የማግኘት መብት ላይ ነው የምናተኩረው። ምናልባት ሌሎችም ክሱን ፋይል ስናደርግ የሚቀላቀሉን ካሉ ያስከተለውን ኪሳራን ልናካታት እንችላለን። ለምሳሌ አንድ ሪፖርት ኢንተርኔት መቋረጥ ሃገሪቱን 4.5 ሚሊዮን ዶላር በቀን ያሳጣታል ይላል። ይህ ማለት የማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ መብቶችንም ይነካል ማለት ነው።» «የተደራጁ ማህበራት ቢኖሩን. . .» ይላሉ አቶ ዮሐንስ፤ «የተደራጁ ማህበራት ቢኖሩን ክሱ በተነፃፃሪ ቀላል ይሆን ነበር። ለምሳሌ የብሎገሮች [ጦማሪያን] ማህበር ቢኖር በኢንትርኔት መቋረጡ የደረሰባቸውን ተፅዕኖ አስረድቶ ክስ ማቅረብ ይቻላል። ሌሎችም አሁን ስማቸውን መጥቀስ የማያስፈልግ ማህበራት እና የግል ተቋማትም ይመለከታቸዋል።» እርግጥ ነው ቴሌ ቢከሰስ የክሱ ፋይል በርካታ ወረቀቶች እንደሚፈጅ ይታሰባል። ከምጣኔ ሃብት፣ ከማህበራዊ ትስስር፣ እና ከሰብአዊ መብት ጥሰት አንፃር ጉዳዩን ማየት ይቻላልና። • ኢትዮ-ቴሌኮም፡ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ? ምናባዊ ክስ ኢትዮ-ቴሌኮምን የመክሰስ ሂደቱ ገና እንጭጭ ቢሆንም፤ ሃሳቡ ግን መንሸራሸር ጀምሯል። ድርጅቱ ከሰሞኑ ለፈፀመው ድርጊት በፍርድ አደባባይ ሊቆም እንደሚገባ በርካታ የሕግ ሰዎች ይስማማሉ። 'ኢትየ-ቴሌኮም ሊከሰስ እንደሆነ ሰምተው ይሆን?' ብለን የጠይቅናቸው ታዋቂው የሕግ ሰው አቶ አምሃ መኮንን «እርግጥ ጉዳዩ ለእኔ አዲስ ነው ግን ኢትዮ-ቴሌኮም መከሰስ እንዳለበት አምናለሁ» የሚል ምላሽ ነበር የሰጡን። • ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት? እስቲ ክሱ ፋይል ተደረገ እንበል። የፍርድ ቤት ምላሽ ምን ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ? ለሕግ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ ያቀረብነው ጥያቄ። «ፍርድ ቤቱ ሥልጣን የለኝም ሊለን ይችላል። ጥቅም የላችሁም ሊል ይችላል። በፍትሀ-ብሔር ጉዳይ ወይንም በሕዝብ ጥቅም ጉዳይ አንድ ክስ ሲቀርብ ጥቅም ሊኖር ይገባል። ጥቅም የሚባለው የንብረት ወይንም መብት ማስከበር ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን አሁን እኛ የምናቀርበው 'ስትራቴጂክ ሊቲጌሽን' [ሰብዓዊ መብትን ለማስከበር የሚቀርብ ክስ] ስለሆነ የሕዝብ ጥቅም ጉዳይ ነው። ሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 37 ላይ ፍትህ የማግኘት መብት የሚለውን መሠረት አድርገን ነው ክሱን ለማቅረብ የምንሞክረው።» ክሱ ተሳካም አልተሳካ፤ ፍርዱ የሕግ ባለሙያዎቹ የሚሹት ሆነም አልሆነ፤ አንድ ጉዳይ ግን ግልፅ ይመስላል። ሰማይ አይታረስም ንጉሥ አይከሰስ ተደርምሶ፤ ሰማይ ባይታረስ ንጉሥ ግን ይከሰስ ሆናል። ንጉሡ ኢትዮ-ቴሌኮም መሆኑ ነው እንግዲህ።
news-54415189
https://www.bbc.com/amharic/news-54415189
ስደት፡ ወደ ጂቡቲ በመመለስ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሞታቸው ተሰማ
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ኢትዮጵያዊያን ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ ስደተኞችን የያዘች ጀልባ ባሕር ላይ አደጋ ደርሶባት ስምነቱ ሲሞቱ በርካቶች የደረሱበት አለመታወቁን ገለጸ።
በጅቡቲ ባሕር ዳርቻ አቅራቢያ አደጋው በደረሰባት ጀልባ ላይ ተሳፍረው ከነበሩት ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ይሆናሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን፤ ከመካከላቸውም ስምንት ስደተኞች ሲሞቱ 12ቱ ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁን ድርጅቱ አመልክቷል። በባሕር ላይ በደረሰው አደጋ ለሞት ከተዳረጉትና የደረሱበት ሳይታወቅ ከቀሩት ውጪ የ14 ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ የተቻለ ሲሆን፤ ሌሎቹንም ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው። ለስደተኞቹ ሞት ምክንያት የሆነቸው ጀልባ ሰዎቹን አሳፍራ በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካይነት በግድ እንድትንቀሳቀስ ከተደረገች በኋላ አደጋው መከሰቱ ተገልጿል። አደጋው የገጠማት ጀልባ ከሰላሳ በላይ ሰዎችን አሳፍራ እንደነበረ የተነገረው ሲሆን በጀልባዋ ላይ ተሳፍረው ከነበሩት ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ይሆናሉ ተብሎ እንደሚገመት የስደተኞቹ ድርጅት መግለጫ አመልክቷል። በባሕር ላይ በደረሰው አደጋ ለሞት የተዳረጉትና የደረሱበት ያልታወቁት እነዚህ ስደተኞች ከየመን ወደ ጅቡቲ እየተመለሱ የነበሩ ናቸው ሲል መረጃው አክሎ ገልጿል። የአካባቢው አገራት በሁለት ጎራ ተከፍለው በሚደግፉት ለዓመታት በተካሄደ የእርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው የመን ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ለከባድ ችግር መጋለጣቸው በተደጋጋሚ እየተነገረ ነው። በባሕር ላይ ሳሉ በጀልባቸው ላይ አደጋ የደረሰባቸው ስደተኞችም የመን ውስጥ ካለው ጦርነት ለመሸሽ ወደ ጂቡቲ እየተመለሱ ያሉ ስደተኞች ሳይሆኑ እንደማይቀር ተገምቷል። ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር በሚል ከ14 ሺህ በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች ከአገሯ ማስወጣቷ የተገለፀ ሲሆን እነዚህ ስደተኞች በየመን መንቀሳቀሻ አጥተው ይገኛሉ።
news-50358804
https://www.bbc.com/amharic/news-50358804
ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ ልታጸድቅ ነው
የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ጥቅምት 29/2012 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ።
ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚፈጥረውን ችግር አሁን አገሪቱ ባሏት ሕጎች መፍታት የማይቻል በመሆኑ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቦ ነው ውይይት የተደረገበት ተብሏል። • “ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ • ቴክቫህ ኢትዮጵያ፡ የፀረ ጥላቻ ንግግር የወጣቶች እንቅስቃሴ የሚኒስትሮች ምክር ቤት "የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ህይወት ስምረት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለአገራዊ አንድነት፣ ለሰብዓዊ ክብር፣ ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን" ጠቅሶ በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት መነጋገሩን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ማስተካከያዎችን በማድረግ ተቀብሎ ይጸድቅ ዘንድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል። መግለጫው ጨምሮም "በተለይ በአሁኑ ወቅት በሕብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለአገርም ስጋት የደቀኑ መሆናቸውን" ጠቅሷል። • የጥላቻ ንግግርን የሚያሠራጩ ዳያስፖራዎች እንዴት በሕግ ሊጠየቁ ይችላሉ? • ''ኢትዮጵያን ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል ሌላ መሪ የለም'' የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዝዳንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተመራው በዚህ መደበኛ ስብሰባው ላይ ከዚህ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ በተጨማሪም በሌሎች ረቂቅ ደንቦችና አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔን አሳልፏል። ምክር ቤቱ የተመለከታቸው ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ፣ የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓትን ለመደንገግ በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ እና በኢትዮጵያና በጅቡቲ መንግሥታት መካከል የተፈጥሮ ጋዝ ቧንቧ መስመር ለማስተላለፍ የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ በዛሬው 75ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ በአጀንዳነት ይዞ የተመለከታቸው ጉዳዮች ላይ መወያየቱንና ማሻሻያ የሚያስፈልጓቸው ላይ ማስተካከያዎች እንዲካተቱ በማድረግ ረቂቅ አዋጆቹ እንዲጸድቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲመራ ረቂቅ ደንቦቹን ደግሞ ሥራ ላይ እንዲውሉ ውሳኔ አሳልፏል።
44558119
https://www.bbc.com/amharic/44558119
"ወትሮም ቢሆንም የትጥቅ ትግል ፍላጎት የለንም" ግንቦት 7
ከጥቂት ቀናት በፊት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረቡት ማብራሪያ ላይ "የጥትቅ ትግል ያለፈበት ስልት ነው" ማለታቸው ይታወሳል።
ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትሩ በጎረቤት ሃገራት ሆነው የትጥቅ ትግል አማራጭ አድረገው የሚገኙ ቡድኖች ወደ አገር ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅረበው ነበር። ይህንን የጠቅላይ ሚንስትሩን ጥሪ ተከትሎም አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ''የስለጠነ ፖለቲካ'' የምንመርጠው፣ የምናውቀውና የምንመኘው የትግል ስልት ነው'' ብሎ ባወጣው መግለጫ የጠቅላይ ሚንስትሩን የሰላም ጥሪ መቀበሉን ገልጿል። ግንቦት 7 ትናንት ባወጣው ልዩ መግለጫ "የትጥቅ ትግል እንዲሁም ግንባሩ ጥይት የተኮሰው ለመከላከል እንጂ አንደ ህወሃት ስልጣን ለመያዝ"ተልሞ እንዳልሆነ አስምሯል። ዶ/ር ታደሰ ብሩ የአርበኞች ግንቦት 7 የሥራ አስፈጻሚ አባል እና የህዝባዊ እምቢተኝነት ክንፍ ኃላፊ "ድሮም ቢሆን የትጥቅ ትግል ፍላጎት አልነበረንም፤ በመሣሪያ ትግል የፖለቲካ ግብ የማሳካት ፍላጎትም ዓላማም ኖሮን አያውቅም። ይልቁንስ ከጉልበተኛ መንግሥት ራሳችንን እንከላከላለን የሚል ነበር እንጂ መሣሪያን ተጠቅመን ሥልጣን እንያዘለን የሚል አቋም ኖሮን አያውቅም" ይላሉ። በቅርቡ ከእሥር የተለቀቁት የግንቦት 7 መሥራች አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 'ግንቦት 7 አንድም ጥይት ተኩሶ አያውቅም' ማለታቸው አይዘነጋም። ይህንን በተመለከተ ምላሽ የሰጡት ዶ/ር ታደሰ "ምናልባት ራሳችንን ለመካለከል ጥይተ ተኩሰን እናውቅ ይሆናል እንጂ ዓለማችንን ለማሳካት ብለን አድርገነው አናውቅም" ይላሉ። "ዋነኛ ስትራቴጂያችን ሕዝባዊ እንቢተኝነት ነው» የሚሉት ኃላፊው "አፋኝ የሆነና ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ላይ ጥይት የሚተኩስ መንግሥት ባለ ጊዜ ራሳቸውን መካለከል የሚችሉ ቡድኖች ያስፈልጋሉ፤ ለዚህ ደግሞ መደራጀት ያስፈልጋል፤ መሰልጠንም ግድ ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። አርበኞች ግንቦት 7 ይህንን መግለጫ ያወጣው መሽጎባት የምትገኘው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ለመፍጠር መወሰኗን ተከትሎ ነው የሚሉ ትንታኔዎች መሰማት ጀምረዋል። ዶ/ር ታደሰ ግን "ይህን ውሃ አያነሳም" ይላሉ። "እንደውም እኛ ስምምነቱን በበጎ ጎኑ ነው የምንመለከተው። በዶ/ር አብይ በምትደዳረው ኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሚኖረው መቀራረብ ከሁለቱ ሃገራት አልፎ ለቀጣናው መረጋጋት ጠቀሜታ አለው ብለን እናምናለን" ይላሉ። ወደ ሃገር ቤት የመመለስ ነገር. . . ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በውጭ ሃገራት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ማቅረባቸው የሚዘነጋ አይደለም። ይህንነወ ተከትሎም በተለይም ለኦሮሞ ነፃነት የሚታገሉ አንዳንድ ፓርቲዎች ልዑካንን መላክ መጀመራቸውም ተዘግቧል። "እስካሁን የማውቀው ይፋ የሆነ ነገር ባይኖርም እርምጃውን በቀና መልኩ ነው የምናየው፤ በዘመናዊ ፖለቲካ የመሳተፍ ፍላጎታችንም ፅኑ ነው። ቢሆንም አሁን የተጀመረው እንቅስቃሴ ዘላቂ መሆኑን ማረጋገጥ አንፈልጋለን። ለምሳሌ የፀረ-ሽብር ሕጉና ሌሎች አፋኝ ሕግጋት መነሳት አለባቸው። ግንቦት 7፣ ኦነግና አብነግና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ላይ የተፈረጀው ፍረጃም መነሳት አለበት በለን እናምናለን" ይላሉ። ግንቦት 7 በመግለጫው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እያከናወኗቸው ያሉ ተግባራትን እንደሚያደንቁ አስታውቋል። "ምንም እንኳ ነገሮች በአንድ ጀምበር ይከናወናሉ ብለን ባናምንም ወደፊት የተሻለ ተቋማዊ ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ አለን"ይላሉ ዶ/ር ታደሰ፤ ወደ ሃገር ቤት የመመለሳቸው ጉዳይ በመፃኢ ኹነቶች ላይ የተንጠለጠለ እንደሆነ በማስረገጥ። አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወደቀደመ ሥራቸው መመለሳቸውን ያሳወቁት ዶ/ር ታደሰ «መግለጫውን ያወጣነው እሳቸው ስለተመሱ ግን አይደለም» ይላሉ። «አሁን ይፋ ያደረግነው አቋም በፊት የነበረ ነው፤ አሁንም ደግሜ የምለው ሕዝባዊ እንቢተኝነታችንን ለመደገፍ እና ራሳችንን ለመከላከል ያደረግነው እንጂ የትጥቅ ትግል ፍላጎት የለንም» ሲሉ ያስረግጣሉ።
news-52948483
https://www.bbc.com/amharic/news-52948483
የዲሲ ከንቲባ ወደ ትራምፕ ቤተ-መንግሥት የሚወስደውን 'ብላክ ላይቭስ ማተር' ሲሉ ሰየሙት
የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ የሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ወደ ትራምፕ ቤተ-መንግሥት የሚወስደውን መንገድ ብላክ ላይቭስ ማተር [የጥቁሮች ሕይወታ ዋጋ አለው] ሲሉ ሰየሙት።
ወደ ቤተ-መንግሥቱ የሚያቀናውን መንገድ ዴሞክራቷ ጥቁር አሜሪካዊት ከንቲባ ሚዩሪዬል ባውዘር 'የጥቁር ሕዝቦች ሕይወት ዋጋ አለው' የሚል በቢጫ ቀለም ገዘፍ ብሎ የተፃፈበት ወደ ዋይት ሐውስ የሚያቀና መንገድ መርቀው ከፍተዋል። ከንቲባዋ ፕሬዝደንት ትራምፕ የፌዴራል ሠራዊት ወታደሮችን ከዋሽንግተን እንዲያስወጡ አዘዋል። ከንቲባዋ ይህንን ያደረጉት የጥቁር አሜሪካዊው በጆርጅ ፍሎይድን ሞት ምክንያት የተቀጣጠለው ተቃውሞ ዋሽንግተን ዲሲ መድረሱን ተከትሎ ነው። ዋሽንግተን በተቃውሞ መታመሷን ተከትሎ ፕሬዝደንት ትራምፕ በሺህ የሚቆጠሩ የፌዴራል መንግሥት ወታደሮች ከተማዋን እንዲቆጣጠሯት ማዘዛቸው አይዘነጋም። ፕሬዝደንቱ ሰልፈኞች ከመንገድ ገለል እንዲረጉት ከአንድ ቤተ-ክርስትያን ፊት ለፊት ፎቶ ለመንሳት ነበር። የፕሬዝደንቱ ድርጊት ብዙዎችን ያስቆጣ ሲሆን ከግራም ከቀኝም ትችት እንዲዘንብባቸው ምክንያት ሆኗል። ዋይት ሐውስ ግድም የሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ-ክርስትያንን ተከትሎ ወደ ቤተ-መንግሥቱ የሚያቀናውን መንገድ የሰየሙት ከንቲባዋ "እኛ የዋሽንግተን ሰዎች በሰላም ተቃውሟችንን ማሰማት እንሻለን። አልፎም መንገዱ ዜጎች የጭቆና ድምፃቸውን ለመንግሥት የሚያሰሙበት እንዲሆን እንፈልጋለንን" ሲሉ ተደምጠዋል። ነገር ግን ከንቲባዋ ትችት አላጣቸውም። ብላክ ላይቭስ ማተር ግሎባል ኔትወርክ የተሰኘው የጥቁር አሜሪካውያን መብት ተከራካሪ ቡድን የከንቲባዋ ድርጊት አጀንዳ አፍራሽ ድራማ ነው፤ ዋናውን የፖሊሲ ለውጥ ጥያቄ አያካትትም ሲል ተችቶታል። ምንም እንኳ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ጥቁር አሜሪካውያን ቁጥራቸው ከነጭ አሜሪካውያን ቢልቅም በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ አለመመጣጠን እንዳለ ይነገራል። ትራምፕ፤ በትዊትር ግድግዳቸው ላይ ከንቲባዋ የፌዴራል ሠራዊት አባላትን የማያንቀሳቅሱ ከሆነ በርካታ ወንዶችና ሴቶች ወደ ዲሲ አመጣለሁ ሲል ለጥፈዋል። ወንዶችና ሴቶች ሲሉ እነማንን ማለት እንደፈለጉ ግን በግልፅ አላስቀመጡም። ከንቲባዋ ባለፈው ሐሙስ ፕሬዝደንቱ የጦር ሠራዊታቸውን ከከተማዋ እንዲያስወጡ የሚያትት ደብዳቤ መፃፋቸው አይዘነጋም። አልፎም አሜሪካ የጣለችው የሰዓት እላፊ ዲሲ ውስጥ እንደማይሰራ አሳውቀዋል። ወታደር አንፈልግም፤ ፖሊስ ሰላማዊ ተቃውሞችን ማስተናገድ ይችላልም ብለዋል። ዋሽንግተን ፖስት እንደፃፈው ከሆነ ቢያንስ 16 ተቋማት ወታደሮቻቸውን ወደ ዲሲ ልከዋል። ከእነዚህም መካከል የሃገር ውስጥ ፀጥታ፣ ኤፍቢአይ፣ የኢሚግሬሽንና ገቢዎች ድርጅት፣ የአገር መከላከያ ሠራዊትና ብሔራዊው ዘብ ይገኙበታል። ዋሽንግተን ዲሲ ግዛት አይደለችም። ከንቲባዋ እንደ ግዛት አስተዳዳሪዎች ያለ ሠራዊት የማስገባትና የማስወጣት ስልጣን የላቸውም። የከተማዋ ብሔራዊ ዘብ ተጠሪነቱ ለመከላከያ ሚኒስቴር ነው።
news-56170346
https://www.bbc.com/amharic/news-56170346
በእነ አቶ ጃዋር የሕክምና ጉዳይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝን ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ሰዎች የሕክምና ጉዳይን በማስመልከት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በመረጡት የግል ሃኪም እና የግል ሕክምና ጣቢያ እንዲታከሙ መፍቀዱን በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ነበር። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ተከሳሾች ግን በመረጡት ሃኪም የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያለባቸው በግል ሆስፒታል ሳይሆን ተከሳሾች ታስረው በሚገኙበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ከእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች መካከል አቶ ሚኪያስ ቡልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነን ጨምሮ ሌሎች በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ ተከሳሾች ከ25 ቀናት በላይ በረሃ አድማ ላይ እንደሚገኙ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። ተከሳሾቹ እያደረጉት ባለው የረሃብ አድማ ምክንያት የቅርብ የጤና ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው የተከሳሾች የግል ሃኪም ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ተከሳሾች 'ለደህንነታችን እንሰጋለን' በማለት በመንግሥት የሕክምና አገልግሎት መስጫ ስፍራ ለመታከም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የተከሳሽ ጠበቆች እንደሚሉት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ በግል የጤና ተቋም እንዳይታከሙ የተከራከረው የተከሳሾችን ደህንነት በግል ሆስፒታል ማረጋገጥ አይቻልም በሚል ነው። የዛሬው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ "የላንድ ማርክ ሃኪሞች ተደራጅተው ተከሳሾች ባሉበት በመምጣት ሕክምና እንዲሰጣቸው ነው" በማለት ጠበቃው አቶ ሚኪያስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ፍርድ ቤቱ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታ የሕግ መሠረት የለውም ብሎ ውድቅ ካደረገ በኋላ ተከሳሾች ማረሚያ ቤት ሆነው ይታከሙ መባሉ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው" በማለት የተከሳሽ ጠበቆች በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ደስተኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል። ጠቃው እንደሚሉት ደንበኞቻቸው ሆስፒታል ተኝተው መታከም የሚያስፈልጋቸው ከሆነ፣ የሆስቲታል ማሸኖች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ እንዲሁም በጤና ባለሙያ የቅርብ ክትትል ቢያስፈልጋቸው በማረሚያ ቤት ሆነው መታከማቸው ይህን ስለማያሟላ፤ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤቱ መልሰው እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም እነ አቶ ጃዋር የረሃብ አድማውን እንዲያቆሙ በሃይማኖት አባቶች እና ፖለቲከኞች ቢጠየቁም ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወሳል። ከእነ አቶ ጃዋር ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ጠበቆች እና የቤተሰብ አባላት ምግብ እንዲበሉ ሲጠይቋቸው ቢቆዩም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የረሃብ አድማ ለምን? እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ መሆኑን ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የረሃብ አድማው ተከሳሾችን የከፋ አደጋ ላይ እንዳይጥል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ አስነብቧል።
news-44000234
https://www.bbc.com/amharic/news-44000234
ቢል ኮዝቢና ፖላንስኪ ከኦስካር አካዳሚ ተባረሩ
የፊልሙ ዘርፍ ፈርጦች የሚሞገሱበትን የኦስካር ሽልማት የሚያዘጋጀው 'ሞሽን ፒክቸር አርትስ ኤንድ ሳይንስ' የተሰኘው ተቋም ተዋናዮቹን ያባረራቸው የድርጅቱን መርህ ተከትሎ መሆኑን አሳውቋል።
በተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ የሚታወቀው ጥቁር አሜሪካዊው የጥበብ ሰው ቢል ኮዝቢ ወሲባዊ ጥቃት ፈፅሟል በሚል እሥር የተፈረደበት ባለፈው ወር ነበር። የፊልም አዘጋጅና የኦስካር አሸናፊው ሮማን ፖላንስኪ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 1977 የ13 ዓመት ታዳጊን አስገድዶ መድፈሩን አምኗል። የቢቢሲው ጄምስ ኩክ እንደዘገበው፣ ኮዝቢና ሮማን ከኦስካር ባለሟልነት ስለመባረራቸው ያሉት ነገር ባይኖርም፣ የኮዝቢ ባለቤት ካሚሌ "ፍርዱ ትክክለኛ አይደለም" ብላለች። ሮማን ጥቃት ማድረሱን ካመነ በኋላ ተቋሙ በአፋጣኝ አለማባረሩ፣ የተቋሙን ቦርድ አባላት በማህበራዊ ድረ ገፅ ሲያስተቻቸው ነበር። የወሲባዊ ጥቃት ክሶች የሆሊውድን መንደር የናጡት በቢል እና በሮማን ጉዳይ ብቻ አይደለም። በርካታ ሴቶች የወነጀሉት ፕሮዲውሰሩ ሀርቪ ዋንስታይንም ይገኝበታል። ባለፈው አመት ሀርቪም ከኦስካር አካዳሚ መባረሩ ይታወሳል። ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ፍትሕ ለማግኘት #MeToo ወይም 'እኔም' የተሰኘ ንቅናቄ ጀምረዋል። ንቅናቄው ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች አደባባይ ወጥተው አጥቂዎቹን ለመክሰስ ድፍረት እንዲያገኙ ያበረታታል። ንቅናቄው ሀርቪ ዋይንስታይንን የመሳሰሉ የሙያና የገንዘብ ጉልበታቸውን ተጠቅመው በርካታ ሴቶችን ያጠቁ ወንዶችን ለፍርድ በማቅረብም ቀጥሏል። ኮዝቢና ሮማን ከኦስካር አካዳሚ የተባረሩበት ውሳኔ የኦስካር አካዳሚ የቦርድ አባላት ለሁለት ቀናት ውይይት ካደረጉ በኋላ ነበር ከውሳኔ የደረሱት። አባላቱ ውሳኔውን ትላንት ሲያስተላልፉ "ቦርዱ ኮዝቢና ሮማንን ከአካዳሚው አባልነት የሰረዛቸው የተቋሙን ህግጋት ተከትሎ ነው። አባላት የቦርዱን ደንብ ከማክበርም ባሻገር የሰዎችን ሰብአዊ መብት እንዲያከብሩ እንሻለን" በማለት ነበር። ባለፉት 91 ዓመታት ተቋሙ በአራት ግለሰቦች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። እ.አ.አ 2004 ላይ ተዋናዩ ካርሚን ካርዲ ለህዝብ ዕይታ ያልበቃ ፊልም ለጓደኛው በመላኩ ተባሯል። በሮማን ላይ የተወሰደው እርምጃ መዘግየት የ84 አመቱ ፀሐፊ፣ አዘጋጅና ተዋናይ ሮማን፣ ሳማንታ ጌሚር የተባለች ሴትን አስገድዶ መድፈሩን ካመነ አራት አስርታት ተቆጥረዋል። በወቅቱ ፈረንሳይ-ፖላንዳዊው ሮማን የታሰረው ለ42 ቀናት ብቻ ነበር። ከአሜሪካ ወደ ፈረንሳይ ሸሽቶ ፍርዱን ካመለጠ በኋላ ዳግም አልተመለሰም። የአሜሪካ መንግስት ለማስመለስ ያደረገው ጥረትም በፈረንሳይና ፖላንድ እምቢተኝነት ሳብያ ከሽፏል። አሜሪካ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ 2010 ሮማንን ከስዊዘርላንድ ወስዶ ለፍርድ ለማቅረብ ያደረገችው ጥረት ባይሳካም፣ ለዘጠኝ ወር ከቤት ያለመውጣት (ሀውስ አረስት) ተፈርዶበታል። ጥቃቱ የደረሰባት ሳማንታ፣ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት "ይቅር ብዬዋለሁ፣ ክሱን ይቋረጥና በሰላም ልኑር" ብትልም ተቀባይነት አላገኘችም። ይህ ሁሉ ሲሆን፣ ሮማን ለ40 ዓመታት ከኦስካር አካዳሚ አለመባረሩ ጥያቄ አጭሯል። "የ13 አመት ታዳጊ ተደፍራ፣ ሮማንም ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ እርምጃ አለመወሰዱ፣ ተቋሙ ሰብአዊ መብት ስለማክበሩ ጥያቄ ያስነሳል" ተብሎም ተወንጅሏል። ከስምንት ሺ በላይ አባላት ያሉት ተቋሙ፣ በቅርቡ መተዳደርያ ደንቡን ቢያሻሽልም ከወቀሳ አላመለጠም። #MeToo የተሰኘውና ሌሎችም ንቅናቄዎች የፊልም ዘርፉን ጥላሸት ቀብተውታል። ከፍርዱ በኋላ የተባረረው ኮዝቢ የ80 ዓመቱ ቢል ኮዝቢ ወንጀለኛ ሆኖ የተገኘው በሶስት የወሲባዊ ጥቃት ክሶች ነው። እያንዳዳቸው የአስር አመት እስራት ያስፈርዱበታል። እ.አ.አ በ2004 የቀድሞዋ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች አንድርያ ኮንስታንድ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ በማድረሱ ተከሷል። ፍርድ ቤቱ ከውሳኔ ሳይደርስ ነበር ሁለተኛ ክስ የተከተለው። ሞሽን ፒክቸር አርትስ ኤንድ ሳይንስ፣ ቢልን ከኦስካር አካዳሚ ያባረረው የእስር ፍርድ እንደተበየነበት ነው። "ዘ ኮዝቢ ሾው" የተሰኘው አስቂኝ የቴሌቭዠን ድራማ ላይ ቢል አባት ሆኖ ሲተውን፣ "የአሜሪካ አባት" የተሰኘ የአክብሮት ቅፅል ስም አትርፎ ነበር። በወቅቱ በአሜሪካ ቁጥር አንድ ተከፋይም ነበር።
news-51299517
https://www.bbc.com/amharic/news-51299517
የሶሪያ ጦር ወሳኝ ያላትን ከተማ ከታጣቂ ኃይሎች ነጻ ማውጣቱን አስታወቀ
የበሽር አላሳድ ጦር በኢድሊብ ግዛት የምትገኘው ማራት አል-ኑማን የተሰኘች ስትራቴጂካዊ ከተማ ከታጣቂ ኃይሎች ነጻ ማውጣቱን አስታወቀ።
የሶሪያ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የአገሪቱ ጦር ከከፍተኛ ውጊያ በኋላ ከተማዋን መቆጣጠሩን አውጇል። በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች መካከል በከተማዋ የተደረገውን ጦርነት ሽሽት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ቱርክ ድንበር ተጠግተዋል። ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው የበሽር አላሳድ ጦር ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ከፈንጂ እና ከሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች እያጸዳ መሆኑ ተነግሯል። መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም የደረገው የሶሪያ ኦብዘርቫቶሪ ፎር ሂዩማን ራይትስ የተሰኘ ድርጅት እንዳለው ከሆነ፤ ከተማዋን ተቆጣጥረዋት የነበሩት ታጣቂ ኃይሎች ከሳለፍነው አርብ ጀምሮ ከተማዋን ጥለው መውጣት ጀምረው ነበር። በሩሲያ አየር ኃይል የሚደገፉት የበሽር አላሳድ ወታደሮች ከተማዋን እና በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ 25 መንደሮችን መቆጣጠራቸውን ይሄው ድርጅት አስታውቋል። ማራት አል-ኑማን የተኘችውን ስትራቴጂካዊ ከተማን ለመቆጣጠር በተደገው ጦርነት 147 የሶሪያ መንግሥት እና 151 የታጣቂ ኃይሎች ወታደሮች መገደላቸው ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት በሶሪያ የሚደረጉት ጦርነቶች ለበርካታ ንጹሃን ዜጎች ሞት እና መፈናቀል ምክንያት እንደሆኑ አስታውቋል። ባሳለፈው አንድ ወር ብቻ በሁለቱ ኃይሎች መካከል እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ጠንካራ ጦርነት አስክ 358 ሺህ የሚደርሱ ዜጎች ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። ወቅቱ በሶሪያ ከፍተኛ ቅዝቃዜ የሚመዘገብበት መሆኑ የተፈናቃዮቹን ህይወት አደጋ ላይ እንደሚጥል የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል።
56954698
https://www.bbc.com/amharic/56954698
ከሕንድ የሚመለሱ አውስትራሊያውያን እስር ወይም የገንዘብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተባለ
ከሕንድ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ አውስትራሊያውያን እስከ አምስት ዓመት እስራት እና የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የአውስትራሊያ መንግስት ገለጸ።
የአገሪቱ መንግሥት ከሕንድ ወደ አውስትራሊያ የሚደረግ ጉዞ ሕገ-ወጥ ነው ብሏል። የአውስትራሊያ የጤና ሚንስትር መንግሥት ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው በሕንድ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መጨመርን ተከትሎ ነው ብለዋል። አውስትራሊያ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከሕንድ የሚመጡ በረራዎችን በሙሉ አግዳለች። 9,000 የሚደርሱ አውስትራሊያዊያን በሕንድ ሲኖሩ ከእነዚህ ውስጥ 600 የሚሆኑት ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ተብለው ተለይተዋል። አውስትራሊያውያን ወደ አገራቸው በመመለሳቸው በወንጀል ሲከሰሱ ይህ የመጀመሪያው እንደሚሆን የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። አንድ አውስትራሊያዊ የሕክምና ዶክተር የመንግሥት ውሳኔ ከሕንድ የሚመለሱ ሰዎች ከሚያደርሱት ስጋት ጋር የማይመጣጠን ነው ብለዋል። "ቤተሰቦቻችን ሕንድ ውስጥ እየሞቱ ነው ... እነሱን ለማውጣት ምንም መንገድ አልተመቻቸም። ይህ ምንም ድጋፍ ሳይደረግላቸው መተው ነው" ሲሉ የህክምና ባለሙያው ዶ/ር ቪዮም ሻርመር ገልጸዋል። ማንኛውም ዜጋ አውስትራሊያ ለመግባት ካቀደበት ቀን በፊት ባሉት 14 ቀናት ውስጥ በሕንድ ከነበረ ወደ አውስትራሊያ መግባት አይችልም። ውሳኔውን አለመተግበር ለአምስት ዓመት እስራት ወይም ለ 37,000 ፓውንድ ቅጣት ወይም በሁለቱም ያስቀጣል። ውሳኔው ግንቦት 15 ቀን እንደሚገመገም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የጤና ሚኒስትሩ ግሬግ ሃንት በመግለጫቸው "መንግሥት እነዚህን ውሳኔዎች በቀላል አልወሰነም" ብለዋል። ሚኒስቴሩ ቬንትሌተሮችን እና የመከላከያ አልባሳትን ጨምሮ አስቸኳይ የህክምና አቅርቦቶችን ለመላክ ከሕንድ ጋር መስማማቱን ገልጿል። መግለጫው አክሎ "ለሕንድ ህዝብ እና ለሕንድ-አውስትራሊያዊ ህብረተሰባችን ሃዘናችንን እንገልጻለን" ብሏል። በሕንድ የቫይረሱ ስርጭት ወደ 19 ሚሊዮን ከፍ ሲል የሟቾቹ ቁጥር 200 ሺህ ደርሷል። ባለፈው ሳምንት በየቀኑ ከ 300 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ነበር።
news-49109707
https://www.bbc.com/amharic/news-49109707
ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው
ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሥራ ስምሪት መጀመሩንና ወደ እስያና አውሮፓም የሠለጠነ የሰው ኃይል ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ዳይሬክተር ጀኔራል ብርሃኑ አበራ ለቢቢሲ ገለፁ።
በዚህ የውጭ ሃገር ሥራ ስምሪት በተለይ በኮንስትራክሽን ሙያ ላይ እውቀቱና ልምዱ ያላቸውን ባለሙያዎችን ለመላክ እንደታሰበም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ሥራ ቀጣሪው የሚፈልገው የሥራ ዘርፍ ስላልተገለጸ በየትኞቹ የኮንስትራክሽን ዘርፎች ላይ እንደሆነ ዝርዝሩን ገና አለመለየታቸውን አክለዋል። "በየዓመቱ በርካታ ባለሙያዎች ከቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛዎችና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስለሚመረቁ የአቅርቦት ችግር የሚኖር አይመስለኝም" የሚሉት ዳይሬክተሩ ወደ እነዚህ ሃገራት ብቻ ሳይሆን ወደ ሌሎች ሃገራትም ስምምነቱን ለማስፋት ሃሳብ አለ ይላሉ። • 1 ቢሊየን ዶላሩ ስንት ችግር ያስታግሳል? ይህንንም ለማድረግ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሥራ ፈጠራ ኮሚሽንና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተካተቱበት የጋራ ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል። ኮሚቴው የተለያዩ ሃገራትን የሠራተኛ ፍላጎት ያጠና ሲሆን ፖላንድ፣ ጃፓን፣ ካናዳ፣ ጀርመንና ሩሲያ ከፍተኛ የሰው ኃይል ፍላጎት እንዳላቸው ተለይቷል። በመሆኑም ወደ እነዚህ ሃገራት በፍጥነት ሠራተኛ ይላካል ተብሎ ታሳቢ መደረጉን አቶ ብርሃኑ ይናገራሉ። ዳይሬክተሩ እንደሚሉት ጃፓን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ሃገራት ክፍት የሆነ 350 ሺህ የሥራ እድል እንዳላት አስታውቃለች። ይህንን እድል ለመጠቀምም የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቶ መላኩንም ገልጸዋል። በተመሳሳይ መልኩ ካናዳም ከ150 ሺህ ያላነሰ የሥራ እድል እንዳለ የተገለፀ ሲሆን ይህንን ታሳቢ አድርጎ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አክለዋል። ይህ የሥራ እድል በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ተወዳዳሪዎች በእኩል መልኩ የሚቀርብ ሲሆን የመምረጫ መስፈርቱም የተፈለገው የሥራ ዓይነት ከተለየ በኋላ የሚወሰን እንደሚሆን ገልፀውልናል። • ከስራ አጥነት ወደ ራስን ቀጣሪነት የሥራ ስምሪቱ በአንድ ጊዜ ብቻ ተልኮ የሚቋረጥ ሳይሆን ወደተለያዩ ሃገራት እየሰፋ እንደሚሄድም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። በቅርቡ 13 ሠራተኞች ወደ ኳታር፣ 6 ሠራተኞች ደግሞ ወደ ዮርዳኖስ የተላኩ ሲሆን ወደ ሳዑዲ አረቢያ 58 ሠራተኞችን ለመላክ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል። እነዚህ ግለሰቦች በቤት ሠራተኝነት የሚሰማሩ ሲሆን ሕጋዊ ፈቃድ በተሰጣቸው ኤጀንሲዎች የተለዩ ናቸው። በተለይ በአረብ ሃገራት በአሠሪና ሠራተኛ መካከል በሚፈጠሩ ችግሮች በርካቶች ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ሲሆን በቅርቡም በርካቶች ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውና በዚህም ምክንያት የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት ታግዶ መቆየቱ አይዘነጋም። አሁንም እንደዚህ ዓይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ ምን ሰርታችኋል? ያልናቸው ዳይሬክተሩ ከተቀባይ ሃገራት መንግሥታት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ለማድረግ የተወሰነው እንደዚህ ዓይነት ችግሮችን ለመፍታት ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህ በፊት ታግዶ የነበረው የውጭ ሃገር ሥራ ስምሪት የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ ችግሮችንና የአደረጃጀት ክፍተቶችም ቀድመው ተፈተዋል ብለዋል። በመሆኑም በሁለትዮሽ ስምምነቱ ተቀባይም ሆነ ላኪ ሃገራት የሚወስዱት ኃላፊነት በመኖሩ እንደዚህ ዓይነት ችግሮች እንደማያጋጥሙ አረጋግጠዋል። • የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን፡ ኢትዮጵያን መጠጊያ ያደረጉ የስደተኞች ታሪክ ከዚህም በተጨማሪ በሕጋዊ መንገድ ከሄዱ በኋላ ባሉበት የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም ጉዳይ ሆነ ችግር ሊከታታልና ችግራቸውን ሊፈታ የሚችል ባለሙያ [Labour attache] በየሃገራቱ ለመመደብ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል። ባለሙያዎቹ የሥራ ገበያውን ከማጥናት ባሻገር የዜጎችን መብትና ደህንነት እየተከታተሉ ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ክትትል ያደርጋሉ። "ባለሙያዎቹ ከጥቂት ወራት በኋላ ይመደባሉ" ብለዋል። ስለ ሥራው ዘላቂነት በተመለከተ ሃሳብ ያነሳንላቸው አቶ ብርሃኑ የሚደረገው የሥራ ውል ኮንትራት [ጊዜያዊ] ቢሆንም እንደሁኔታው የሚታደስባቸው አጋጣሚዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አስረድተዋል። በኢትዯጵያ የሥራ አጦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ በተለያየ ጊዜ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። ይሁን እንጂ በዚህ መልኩ በተለያየ ደረጃ የተማሩ ሰዎችን ወደ ውጭ ሃገራት መላክ የሃገር ውስጥ አቅምን አያዳክምም ወይ ያልናቸው ዳይሬክተሩ፤ "የመንግሥት አቅጣጫ ዜጎች በሃገራቸው ላይ ሰርተው መለወጥ እንዲችሉ ቢሆንም ወደ ውጭ ሃገር ሄደው ሠርተው መለወጥ ለሚፈልጉ መብታቸው፣ ክብራቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ መሄድ እንዲችሉ ነው እየተሰራ ያለው" ብለዋል። ከዚህም ባሻገር በሃገር ውስጥ ያለውን የሠራተኛ ፍላጎት አርክቶ ለሚተርፈው ደግሞ የሥራ እድሉን መፍጠር እንደሚያስፈልግ አስተያታቸውን ሰጥተዋል። በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ 50 ሺህ የሚጠጉ ሠራተኞችን ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለመላክ እቅድ እንደተያዘ አስታውቀው ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን ወደ ኤዥያና አውሮፓ ሃገራትም የሠለጠነ የሰው ኃይል ለመላክ እንደታሰበ መናገራቸው ይታወሳል።
news-40940151
https://www.bbc.com/amharic/news-40940151
ፓስፖርት፡ የሰዎችን እንቅስቃሴ የወሰነ ሰነድ
በታሪክ ውስጥ ፓስፖርት ሁሌም የነበረ ነገር አይደለም። ፓስፖርት ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ የሚረዳ በሃላፊዎች ፈቃድ የሚሰጥበት ማስረጃ ነው። ይህን ማስረጃ መጠቀም የተጀመረው ከብዙ ዓመታት በፊት ነው።
በቀደም ሲል በፈረንሳይ ዜጎች ሃገራቸውን ሲለቁ ብቻ ሳይሆን ከከተማ ወደ ከተማ ሲንቀሳቀሱም ማስረጃ ሊኖራቸው ይገባ ነበር። አሁን አሁን የበለጸጉ ሃገራት ሙያ የሌላቸው ሰዎች ወደ አገራቸው እንዳይመጡ የሚከለከሉ ቢሆንም ቀደም ሲል ግን ሙያ ያላቸው ሰዎች አገራቸውን ለቀው እንዳይወጡ ያደርጉ ነበር። ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የመጓጓዣ ዓይነቶች ዕድገት ጉዞን ፈጣንና ርካሽ አድርጓል። በወቅቱ ቁጥጥር የሚበዛባቸው የጉዞ ማስረጃዎች ደግሞ ብዙም አስፈላጊ ተቀባይነት አልነበሩም። በ1890ዎቹ ማንኛውም ነጭ የሆነ ሰው አሜሪካን ያለምንም ፓስፖርት መጎብኘት ይችል ነበር። በ1890ዎቹ አሜሪካን ለመጎብኘት ፓስፖርት አያስፈልግም ነበር በወቅቱ አንዳንድ የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ያለፓስፖርት የመንቀሳቀስ መብትን በህገመንግስታቸው ውስጥ አስፍረዋል። ጃፓንና ቻይና በበኩላቸው ወደ መሃል ሃገር የሚገቡ የውጭ ዜጎች ፓስፖርት እንዲይዙ ይጠይቁ ነበር። በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያም ቢሆን ወደ ሃገራቸው የሚገቡና የሚወጡ ሰዎችን ፓስፖርት የሚጠይቁ መንግሥታት ቁጥር አነስተኛ ነበር። አሁን ግን እንደዚህ ያሉ አገራት መኖራቸው አጠራጣሪ ደረጃ ላይ ደርሷል። ፓስፖርትና ስደተኞች እአአ መስከረም 2015 ጠዋት መዳረሻዋን በግሪክ ደሴቷ ኮስ ያደረገች ጀልባ ከቱርክ ቦድረም ትነሳለች። ጀልባዋ ላይ አብዱላህ ኩርዲ የተባለ ግለሰብ ከሚስቱና ከሁለት ልጆቹ ጋር ተሳፍሯል። በጉዞው ወቅት ጀልባዋ በመስመጧ ከመላው ቤተሰብ አብዱላህ ብቻ ይተርፋል። የሦስት ዓመት ልጁ የአይላን ኩርዲ ሬሳ በውሃ ተገፍቶ ወደ ባህር ዳርቻ ከወጣ በኋላ ፎቶው የስደት ምልክት ከመሆን ባለፈ መላው ዓለምን አስደንግጧል። በሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች ከቱርክ ወደ ግሪክ ለመግባት ይጓዛሉ የእነአብዱላህ ዓላማ በቱርክ መኖር ሳይሆን ቫንኩቨር ካናዳ ወደምትገኘው እህቱ ዘንድ ማቅናት ነበር። ይህን ጉዞ ለማድረግ ብዙ ቀላል አማራጮች ነበሩ። በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ለሚያዘዋውሩ የከፈሉት 4460 ዶላር ፓስፖርት ቢኖራቸው ኖሮ ለመላ ቤተሰቡ የአውሮፕላን ትኬት መግዛት የሚያስችል ነበር። የሶሪያ መንግስት ለኩርዶች የዜግነት መብትን ስለነፈጋቸው ፓስፖርት ሊያገኙ አልቻሉም በዚህም ይህን እድል እንዳይሞክሩ አድርጓል። ቢሆንም ግን ሁሉም ፓስፖርት በሁሉም ቦታ ተመሳሳይ ተቀባይነት ስለሌለው የሶሪያ ፓስፖርት ቢኖራቸው እንኳን ወደ ካናዳ ማቅናት አይችሉም ነበር። ካናዳ ውስጥ የስዊዲን፣ ስሎቫኪያ፣ ሲንጋፖር ወይም የሳሞኣ ፓስፖርት የተሻለ ተቀባይነት አላቸው። የሶሪያን ፓስፖርት የያዘ ግለሰብ ፓስፖርትን መግዛት ፓስፖርትን ለመቀየር እጅግ አስቸጋሪ ቢሆንም ፈፅሞ ግን አይቻልም ለማለት ግን አያስደፍርም። 250 ሺህ ዶላር ያለው ሰው ከካሪቢያኗ ሴንት ኪትስ እና ኔቪስ ፓስፖርት መግዛት ይችላል። ሴንት ኪትስ እአአ ከ1984 ጀምሮ 'የዜግነት ኢንቨስትመንትን' ተግባራዊ አድርጋለች ፓስፖርት በአብዛኛው በወላጆቻችን ማንነትና በተወለድንበት ቦታ ይወሰናል። ይህ ደግሞ በምርጫ የሚወሰን አይደለም። ስለዚህም ሰዎች መመዘን ያለባቸው በባህሪያቸው እንጂ በፓስፖርታቸው መሆን የለበትም ቢባልም ይህ እንዳይሆን አጥብቀው የሚከራከሩ ሰዎች ብዙም አይደሉም። የበርሊን ግንብ ከፈረሰ ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ የስደተኞች ቁጥጥር ፋሽን በሚመስል መልኩ ተጧጡፏል። ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካና ሜክሲኮ መካከል አጥር እንዲገነባ እየጠየቁ ናቸው። ዶናልድ ትራምፕ ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስናቸው ድንበር ላይ አጥር ለመገንባት አቅደዋል በአውሮፓ ውስጥ ከሃገር ሃገር በቀላሉ ለመንቀሳቀስ የሚያስችለው የሸንገን ዞን አካሄድም በስደተኞች ምክንያት በተፅዕኖ ስር ወድቋል። የአውሮፓ አገራት መሪዎች የፖለቲካ ስደተኞችን ብቻ በመቀበል ለተሻለ ኑሮ የሚሰደዱትን ለመተው የሚያደርጉት እንቅስቃሴም ከፋፍሏቸዋል። ተጠቃሚዎችና ተጎጂዎች የምጣኔ ሃብት እሳቤ ግን ከፖለቲካው በተቃራኒ ይቆማል። በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ምርት የተጠቃሚን ፍላጎት እንዲከተል መንገዱ ሲመቻችለት የሚገኘው ምርት እየጨመረ ይሄዳል። በተግባር ስደተኞችን ተከትሎ የሚጠቀሙና የሚጎዱ እንዳሉ ቢታይም፤ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ግን የተጠቃሚዎች ቁጥር ያመዝናል። በበለጸጉት አገራት ከስድስት ዜጎች አምስቱ በስደተኞች መምጣት ህይወታቸው ተሻሽሏል። ስደተኞች ከአካባቢያቸው ጋር ቶሎ ካልተዋሃዱ ወይም አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎት በዚያው መጠን ካልተስፋፋ ችግር ይፈጠራል። በተጨማሪም ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱን የማየት ዝንባሌም አለ። ለምሳሌ የተወሰኑ ሜክሲኳዊያን ወደ አሜሪካ ተሰደው በፍራፍሬ ለቀማ ሥራ ላይ በአነስተኛ ክፍያ ተሰማሩ ይባል። በዚህ ምክንያትት በአነስተኛ ዋጋ የቀረበው የፍራፍሬ ዋጋ ሳይስተዋል ከሥራ ስለተፈናቀሉ ጥቂት አሜሪካዊያን በስፋት ይወራል። ተጎጂዎችን መንግሥታት ለህዝብ አገልግሎት በሚመድቡት ገንዘብና ከግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ መካስ ይቻላል። የደህንነት ስጋት አንዳንድ ባለሙያዎች ሰዎች የፈለጉት ቦታ ተንቀሳቅሰው ቢሰሩ የዓለም ምጣኔ ሃብት በእጥፍ ያድጋል ይላሉ። በዚህም መሰረት ፓስፖርት ጥቅም ላይ ባይውል ዓለም የበለጠ የበለጸገች ትሆን ነበር። ይህ ላለለመሆኑ ትንሹ ማሳያ አንደኛው የዓለም ጦርነት ነው። ፓስፖርት ባይኖርም ጦርነት ሃብቱን ስለሚያጠፋው ማለት ነው። የደህንነት ጉዳይ አሳሳቢ በመሆኑ መንግስታት በጉዞ ላይ የያዙት ጠንካራ አቋም በሰላም ወቅትም የሚላላ አይመስልም። የተለያዩ አገራት ፓስፖርቶች እአአ በ1920 የተቋቋመው ሊግ ኦፍ ኔሽን "ዓለም አቀፍ የፓስፖርት፣ ጉምሩክ ህግና ትኬት ኮንፈረንስ" በማዘጋጀት ፓስፖርትን አስተዋውቋል። በቀጣዩ ዓመት በነበረው ጉባኤው ላይ ፓስፖርቶች ባለ 32 ገጽ፣ ፎቶ ያላቸው፣ ባለጠንካራ ሽፋንና 15.5 ሴንቲ ሜትር በ10.5 ሴንቲ ሜትር እንዲሆኑ በወሰነው መሰረት አስካሁንም ድረስ በጥቂት ማሻሻያ ብቻ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛሉ።
news-47025493
https://www.bbc.com/amharic/news-47025493
ኬንያ ውስጥ ተማሪዎች አስተማሪያቸውን በመግደል ተጠርጥረው ተያዙ
ሦስት ተማሪዎች ሞባይል ተወስዶብናል በሚል ሰበብ በአስተማሪያቸው ላይ ከተፈጸመ ግድያ ጋር በተያያዘ ኬንያ ውስጥ ተይዘው ታሰሩ።
ናኩሩ በተባለው የኬንያ ግዛት ሆፕዌል በተሰኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፊዚክስ መምህር የሆኑት ፒተር ኦማሪ በተማሪዎቹ ጥቃት የተፈፀመበት ባለፈው ሳምንት መጠናቀቂያ ላይ ነበር። ተማሪዎቹ ቢያንስ አንድ ሞባይል በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዘው በመገኘታቸው በመምህሩ ተወስዶብናል በሚል ነው ድርጊቱን እንደፈፀሙ የተነገረው። • መስታወት መፃዒውን ጊዜ ለማየት እንደሚያስችል ያውቃሉ? ለሥነ ሥርዓትና የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ሲባል በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ሞባይል እንዳይዙ ይከለክላል። ባለስልጣናት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት መምህሩ በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ውስጥ የምሽት ትምህርትን እያስተባበሩ ነበር። የአካባቢው ምክትል አስተዳዳሪ ኤሊም ሻፊ እንደተናገሩት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 150 ኪሎ ሜትር ሰሜን ምዕራብ ርቃ በምትገኘው የናኩሩ ከተማ፤ መምህሩ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲሄዱ ነው ጭቅላታቸው ላይ ተመትተው ለሞት የበቁት። • በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ተቃጠሉ ኬንያ ውስጥ በመምህራንና በትምህርት ቤቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ በመሆናቸው የሃገሪቱን ባለስልጣናት በእጅጉ እያሳሰበ ነው። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በምዕራባዊ ኬንያ በምትገኘው ኪሱሙ ውስጥ አንድ መምህር ከተማሪዎቹ ጋር ጠንከር ያሉ ቃላትን ከተለዋወጠ በኋላ በተማሪዎቹ በገጀራ ተመትቶ ለሞት ተዳርጓል። • ጉግል ኢንተርኔትን በላስቲክ ከረጢት ይዞ ኬንያ ገብቷል ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ ኪሲ በተባለ ቦታ የሚገኝ የአንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የአውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን የቀጥታ ሥርጭት በቴሌቪዥን እንዳይከታተሉ በመከልከላቸው መኝታ ክፍላቸውን በእሳት አውድመውት ነበር።
43326885
https://www.bbc.com/amharic/43326885
የሩሲያው ሰላይ ነርቭን በሚጎዳ መርዝ የመግደል ሙከራ ደረሰበት
የቀድሞው የሩሲያ ሰላይ እና ልጁን ለመግደል ነርቭን የሚጎዳ መርዝ መጠቀማቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የ66 ዓመቱ የቀድሞ የሩሲያ ሰላይ እና ልጁ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት በሆስፒታል ክትትል እያደረጉ ነው እሁድ ዕለት ከሰዓት ሰርጌ እና ዩሊ ስክሪፓል እራሳቸውን ስተው የተገኙ ሲሆን አሁንም በፅኑ እንደታመሙ ናቸው። በስፍራው ቀድሞ የደረሰው የፖሊስ አባልም በጠና ታሞ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ እያገኘ መሆኑን ረዳት ኮሚሽነር ማርክ ሮውሊ ተናግረዋል። ነርቭን የሚጎዱ ኬሚካሎች የነርቭ ሥርዓትን በማስተጓጎል የአካል እንቅስቃሴ እንዲገታ ያደርጋሉ። ይህ መርዝ በአብዛኛው ወደ ሰውነት የሚገባው በአፍ ወይም በአፍንጫ ሲሆን በዓይን እና በቆዳም ሊገቡ ይችላሉ። የፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ኃላፊ የሆኑት ሮውሌ እንዳሉት የመንግሥት ተመራማሪዎች የመርዙን ዓይነት የለዩት ሲሆን በዚህ ደረጃ መረጃውን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አልፈለጉም። "ይህ እንደ ከባድ የመግደል ሙከራ ወንጀል ነው የተያዘው" ብለዋል። "የሕመማቸው ምልክት ነርቭን የሚጎዳ ኬሚካል መሆኑን ከለየን በኋላ ሁለቱ ሰዎች ብቻ ተነጥለው ጥቃት እንደደረሰባቸው ማረጋገጥ ችለናል" ሲሉም አክለዋል። ሌሎች የሕብረተሰቦችን ክፍል የሚያሰጋ የጤና አደጋ ግን አለመኖሩን አሳውቀዋል። ሌሎች በስፍራው የነበሩ ሁለት የፖሊስ አባላት ለቀላል ጉዳት ሕክምና መከታተላቸውንም ጨምረው አብራርተዋል።
news-49843560
https://www.bbc.com/amharic/news-49843560
የመጀመሪያ ዙር 75 ስደተኞች ሩዋንዳ ገቡ
ሩዋንዳና እና የዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም በገቡት ውል መሠረት 75 ስደተኞች ሊቢያን ለቀው ኪጋሊ ገብተዋል።
ሩዋንዳ ከገቡት ስደተኞች መካከል አብዛኛዎቹ ተንከባካቢ የሌላቸው ሕፃናት እና እርዳታ የሚሹ ናቸው ተብለዋል። የሩዋንዳ ስደተኞች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል-አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ስደተኞቹ ከኪጋሊ 30 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኘው ቡጌሴራ መንደር ወስጥ ይሰፍራሉ። ሩዋንዳ ከአፍሪቃ ሕብረት እና ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ወኪል ጋር በያዝነው ወር መባቻ አዲስ አበባ ላይ በገባችው ቃል መሠረት 500 ስደተኞች ትቀበላለች። በስምምነቱ መሠረት ስደተኞቹ ሩዋንዳ ውስጥ የመኖር መብት እንዲሰጣቸው ይደረጋል፤ ፈቃደኛ ከሆኑ ደግሞ ወደ ገዛ ሃገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ ይደረግላቸዋል። የሜዲትራኒያንን ባሕርን ቀዝፈው ወደ አውሮጳ ለመግባት በማሰብ የተሰደዱ 4500 ገደማ ስደተኞች ሊቢያ ውስጥ በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ይነገራል። አብዛኛዎቹ ከአፍሪቃ ቀንድ እንደመጡም ተዘግቧል። ሊቢያን ረግጠው አውሮጳ መድረስ ያልቻሉ አፍሪቃውያን ስደተኞች ትሪፖሊ ውስጥ በደላሎች ከፍተኛ ግፍ እየተፈፀመባቸው እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ። አንዳንድ ስደተኞች እንደ ባሪያ እየተሸጡ እንዳሉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቶ ዓለምን ጉድ እንዳሰኘ አይዘነጋም።
news-57283783
https://www.bbc.com/amharic/news-57283783
ናይኪ ከኔይማር ጋር የተለያየው ከወሲባዊ ጥቃት ምርመራ ጋር በተያያዘ ነው አለ
የስፖርት አልባሳት አምራቹ ናይኪ ከታዋቂው ብራዚላዊ እግር ኳስ ተጫዋች ኔይማር ጋር መስራት ያቆመው ተጫዋቹ በቀረበበት ወሲባዊ ጥቃት ምርመራ አልተባበበርም በማለቱ እንደሆነ አስታወቀ።
ኔይማር የናይኪ ሠራተኛ ላይ ወሲባዊ ጥቃት ፈፅሟል የተባለው በአውሮፓውያኑ 2016 ሲሆን ለኩባንያው ደግሞ ሪፖርት የተደረገ በ2018 ነው። ናይኪ ምርመራው እንዳልተጠናቀቀም ገልጿል። የኔይማር ቃለ አቀባይ በበኩላቸው ደንበኛቸው የተወነጀለበትን ወሲባዊ ጥቃት እንዳልፈፀመና ኔይማር ከናይኪ ጋር ባለፈው ዓመት መስራት ያቆመው ከንግድ ጋር በተገናኘ ምክንያት ነው ብለዋል። "ኔይማር እንደዚህ አይነት መሰረት ቢስ ውንጀላዎች ሲቀርቡ ራሱን እስከ መጨረሻው ድረስ ይከላከላል። ማስረጃዎች ካሉ ያቅርቡ እስካሁንም ድረስ ምንም አይነት ማስረጃ ማምጣት አልቻሉም" በማለት ቃለ አቀባይዋ ለዋል ስትሪት ጆርናል ተናግረዋል። ናይኪ ከፍተኛ ስፍራ ከተሰጠው ከኔይማር የስፖንሰር ስምምነት ያቋረጠው በነሐሴ 2020 ነው። በወቅቱ ኩባንያው ከኔይማር ጋር የነበረውን ስምምነት ለምን እንዳቋረጠ ምክንያት አልሰጠም። ኩባንያው ባለፈው ሐሙስ ባወጣው መግለጫ "ናይኪ ያለምንም ማስረጃ ዝም ብሎ ውንጀላዎችን ማቅረብ ተገቢ ነው ብሎ አያምንም" ካለ በኋላ አክሎም "ናይኪ ከኔይማር ጋር የነበረውን ግንኙነት ያቋረጠው ከአንድ ሠራተኛ የደረሰንን የሚታመን መረጃ በደረሰን መሰረት ምርመራ እንዲካሄድ ብንጠይቀው እምቢተኝነቱን ስላሳየ ነው" በማለት አስፍሯል። ጥቃት ተፈፅሞባታል የተባለችው የኩባንያው ሠራተኛ ሪፖርት ያደረገችው በ2018 ሲሆን በመጀመሪያ ላይ ምርመራ እንዲከፈት ፈቃደኛ አልነበረችም። በምስጢርም እንዲያዝ ፈልጋ ነበር። ከዓመት በኋላ ሠራተኛዋ ምርመራ እንዲደረግ በጠየቀችው መሰረት ኩባንያው ምርመራ መክፈቱን አስታውቋል። ጥቃቱ ደርሶባታል የተባለችው ግለሰብ ስም ያልተጠቀሰ ሲሆን ኩባንያውም በመግለጫው "የግለሰቧን ማንነት እንዲገለጽ ስለማትፈልግ እሱን እናከብራለን። ምን ያህል አስቸጋሪ ሁኔታም ውስጥ እንዳለች እንረዳለን" በማለት አትቷል። ኔይማር በአሁኑ ወቅት ፓሪስ ሴይንት ጀርሜይን ለተባለ የፈረንሳይ ክለብ ይጫወታል። ከሁለት ዓመት በፊት ውንጀላው ሲቀርብበት አልፈፀምኩም ብሎ የካደ ሲሆን ክሱም ወዲያው ውድቅ ተደርጓል።
57326607
https://www.bbc.com/amharic/57326607
በትግራይ የምግብ እጥረት እና የሕፃናት ጥቃት መባባሱ ተገለጸ
ዓለም አቀፍ ተቋማት በትግራይ ክልል በርካታ ነዋሪዎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እና ሕፃናት የጥቃት ሰለባ መሆናቸውቸውን ገለጹ።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና የተመድ የህጻናት አድን ድርጅቱ ዩኒሴፍ ባወጡት መግለጫ ነው በክልሉ የምግብ እርዳታ በአስቸኳይ እንዲደረግ እንዲሁም ሕፃናት ላይ የሚደርሰው ጥቃት እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆሙት። የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል 5.2 ሚሊዮን ሰዎች በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አስታውቋል። ከክልሉ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ነዋሪ በአፋጣኝ የምግብ እርዳታ እንዲያገኝ 203 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገውም ድርጅቱ አስታውቋል። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፤ ከመጋቢት ጀምሮ የምግብ እርዳታ ባከፋፈለባቸው ሁለት የክልሉ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ረድቷል። እነዚህ የምግብ እርዳታ ካገኙ ዜጎች ባሻገር አብዛኛው የክልሉ ነዋሪ በአፋጣኝ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ግንቦት 24፣ 2013 ዓ. ም. የወጣው የድርጅቱ መግለጫ ይጠቁማል። በያዝነው ሳምንት ሰኞ እለት ለ4,500 ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ መደረጉ ተገልጿል። እርዳታው የሚሰጠው በየስድስት ሳምንቱ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ 2.1 ሚሊዮን ሰዎችን ለመድረስ መታቀዱ ተጠቁሟል። የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለልጆች፣ ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ እናቶች የአደጋ ጊዜ የምግብ እርዳታ እያደረገ ቢሆንም "በተለይም በገጠር አካባቢዎች ነዋሪዎችን በቀላሉ መድረስ አልተቻለም" ብሏል። ድርጅቱ ለኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ ለሚገኙ አጋሮቹ 40,000 ሜትሪክ ቶን ምግብ እንደሰጠ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ 20,000 ሜትሪክ ቶን ምግብ ለትግራይ ክልል የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ቢሮ አስረክቧል። ስለ ሕፃናት ጥቃት በተባበሩት መንግሥታት ሥር የልጆችን ጉዳይ የሚከታተለው ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ "በትግራይ ሕፃናት ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት እየተባባሰ ነው" ብሏል። ግንቦት 24፣ 2013 ዓ. ም. በወጣው መግለጫ የዩኒሴፍ ዋና ኃላፊ ሄንሬታ ፎር እንዳሉት፤ እስካሁን ድረስ ከ6,000 በላይ ከወላጆቻቸው የተለዩ ወይም ጠባቂ የሌላቸው ልጆች ተመዝግበዋል። "በደኅንነት ስጋት ወይም የግጭቱ ተሳታፊዎች እገዳ ስላደረጉብን መድረስ ባልቻልንባቸው አካባቢዎች ከዚህ በላይ እርዳታ የሚሹ ልጆች አሉ ብለን እንሰጋለን" ብለዋል። በክልሉ የቴሌኮምንኬሽን መቆራረጥ ስላለ እንዲሁም የማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች ውስን ስለሆኑ ልጆችን ከወላጆቻቸው ለማገናኘት ከባድ መሆኑን ዋና ኃላፊዋ አክለዋል። በክልሉ ሴቶች አሁንም ድረስ "ለአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ተጋልጠዋል" ብለዋል ሄርኔታ። ዩኒሴፍ ከጥቅምት ጀምሮ 540 ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን መርዳት ቢችልም፤ በደኅንነት ስጋት እና ሴቶቹ በድጋሚ በበቀል የተነሳሳ ጥቃት ይሰነዘርባቸዋል በሚል ፍርሀት በርካቶች እርዳታ ሳያገኙ እንደቀሩ አስረድተዋል። "ታዳጊ ወንዶች እንመለመላለን ብለው ይሰጋሉ" ሲሉም ተናግረዋል። በህወሓት እና በመከላከያ ሠራዊቱ መካከል ጥቅምት ላይ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች እንደተፈናቀሉና ከእነዚህ መካከል 720,000 የሚሆኑት ታዳጊዎች እንደሆኑ የዩኒሴፍ መግለጫ ይጠቁማል። ዋና ኃላፊዋ ሄርኔታ እንዳሉት፤ መጠለያ ካምፖች በሰው ከመጨናነቃቸው ባሻገር ንጽህናቸው ያልተጠበቀ፣ ደኅንነታቸውም የማያስተማምን ናቸው። በተያያዘም "ከሚያዝያ ጀምሮ ዩኒሴፍ የሚደግፋቸው 31 የጤና፣ የምግብና ውሃ አቅራቢ ሚሽኖች እርዳታ እንዳያቀርቡ ታግደዋል። ለዚህም ምክንያቱ የደኅንነት ስጋት እና እርዳታ አቅራቢዎች ጥቃት ስለተሰነዘረባቸው ጭምር ነው" ብለዋል። ዩኒሴፍ ሁሉም ወገን ለሕፃናት ጥበቃ እንዲያደርግ አሳስቧል። ዋና ኃላፊዋ በመግለጫው "ሁሉም ወገን ልጆችን ከጥቃት፣ ከብዝበዛ እና ከቤተሰብ ከመነጠል እንዲጠብቅ እንጠይቃለን" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
news-42106117
https://www.bbc.com/amharic/news-42106117
ሩዋንዳ በሊቢያ 'በባርነት' የተያዙትን ስደተኞች እንደምትቀበል አሳወቀች
ሩዋንዳ በሊቢያ 'በባርነት'ተይዘው ከሚገኙ አፍሪካውያን ስደተኞች መካከል 30 ሺህ ለሚሆኑት መጠለያ እንደምታዘጋጅ አሳውቃለች።
ሲኤንኤን ባለፈው ሳምንት አፍሪካውያን ስደተኞች ለእርሻ ሥራ በጨረታ ሲሸጡ የሚያሳይ ምስል ከለቀቀ በኋላ ነው ሩዋንዳ ለስደተኞቹ መጠለያ ለማዘጋጀት መወሰኗን ያሳወቀችው። በሊቢያ እየተካሄደ ያለውን ''የባሪያ ንግድ'' የሚያሳይ ምስል ድንጋጤን ፈጥሯል "አንድም ያሳለፍነውን በማስታወስ ሌላም አፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን እንደ ከብት ለጨረታ ሲቀርቡ እያየን ዝም ማለት ስለማንችል ነው ይህን ለማድረግ የወሰንነው" ሲሉ የሩዋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሉዊ ሙሺኪዋቦ ተናግረዋል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች በየዓመቱ ሊቢያን አቋርጠው በሜድትራንያን ባሕር በኩል ጉዟቸውን ወደ አውሮፓ ያደርጋሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ግን ብዙ መከራና ስቃይ ያልፋሉ፤ እጅግ አነስተኛ በሆነ ዋጋ ለጉልበት ሥራ እስከመሸጥ ድረስ። "ሶስት ጊዜ ለተለያዩ ነጋዴዎች ተሽጫለሁ" "ሩዋንዳ እንደ ሌሎች ሃገራት ሁሉ እየሆነ ባለው ነገር እጅግ ተዳናግጣለች። አፍሪካውያን ሴቶች፣ ወንዶች፣ ሕፃናት ሃጋራቸውን ጥለው ተሰደው እንዲህ ዓይነት መከራ ሲደርስባቸው ማየት እጅግ ያስደንግጣል" ብለዋል ሚኒስትሯ። ሩዋንዳ ትንሽዬ ሃገር ብትሆንም ለችግር ጊዜ የሚሆን ቦታ ግን አታጣም በማለት አክለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ። "እኔ የማውቀው ሩዋንዳውያን ስደተኞቹን በደስታ እንደሚቀበሏቸው ነው። የሃገሬ ሕዝብ ሰው ወዳድና የተቸገረን የሚረዳ እንደሆነም አውቃለሁ" በማለት ነበር ሚኒስትሯ ኒው ታይምስ ለተሰኘው የሩዋንዳ ጋዜጣ ቃለቸውን የሰጡት። ሩዋንዳ ጉዳዩን ከዳር ለማድረስ እንዲሁም በሊቢያ ተይዘው ስላሉ አፍሪካውያን ስደተኞች ዕጣ ፈንታ ዙሪያ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ጋር እየመከረች እንደሆነም አሳውቀዋል። ባለፈው ሳምንት የአፍሪካ ሕብረት በሊቢያ እየተከናወነ ባለው የባርያ ሽያጭ እጅግ መደንገጡን አሳውቆ ነበር። በይነ-መረብ ላይ የተበተነው ምስል ከኒጅር ተሰደው የመጡ ሰዎች ለጉልበት ሥራ በ400 ዶላር (10 ሺህ ብር ገደማ) ለጨረታ ሲቀርቡ ያሳያል። ወርሃ ሚያዝያ ላይ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ቤት በሊቢያ ባርያ ንግድ እየተከናወነ እንደሆነ መረጃ አለኝ ሲል አስዋውቆ እንደነበር አይዘነጋም። በሊቢያ የአይኦኤም ተዋካይ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ስደተኞቹን ይዘው ገንዘብ ካላቸው እሱን ተቀብለው እንደሚለቋቸው ካልሆነ ደግሞ ለሌሎች አሳልፈው እንደሚሸጧቸው ተናግረው ነበር።
news-56076204
https://www.bbc.com/amharic/news-56076204
ናይጄሪያዊቷ የዓለም ንግድ ድርጅትን እንዲመሩ ተመረጡ
ናይጄሪያዊቷ ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢውያላ የመጀመሪያዋ ሴት እንዲሁም የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት የዓለም ንግድ ድርጅት ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።
ደብልዩ ቲ ኦ በተሰኘው ቅፅል ስሙ የሚታወቀው የዓለም ድርጅትን እንዲመሩ የተመረጡት ናይጄሪያዊት ከዚህ ቀደም የፋይናንስ ሚኒስትር ነበሩ። የድርጅቱ ጠቅላይ ምክር ቤት ባደረገው ልዩ ስብሰባ ነው ናይጄሪያዊቷ በዳይሬክተር ጄኔራልነት እንዲመሩ የመረጠው። የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ዶ/ር ኦኮንጆ የዓለም ባንክ 'ማኔጂንግ ዳይሬክተር' ሆነው አገልግለዋል። የዓለም ንግድ ድርጅት የተለያዩ ፈተናዎች የተጋረጡበት ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። ከእነዚህ መካከል የንግድ አለመግባባቶችን መፍታት፣ የገቢ ንግድ የማያበረታቱ ሃገራትን ማግባባትና በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተከሰተውን መላሸቅ መግታት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ተቺዎች ድርጅቱ በብዙ ችግር የተተበተበ ነው ሲሉ ይገልፁታል። ንጎዚ ማናቸው? የ66 ዓመቷ ናይጄሪያዊት የድርጅቱ ኃላፊ በመሆን የተመረጡ የመጀሪያዋ አፍሪካዊት ናቸው። ምንም እንኳ በቅርቡ የአሜሪካ ዜግነት ቢያገኙት ለሃገራቸው ናይጄሪያ ከፍተኛ ፍቅር እንዳለቸው ይናገራሉ። በናይጄሪያ ሕብረ ቀለማዊ ልብስ አጊጠው የሚታዩት ንጎዚ የአራት ልጆች እናት ሲሆኑ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ናቸው። ከቢቢሲ ሃርድ ቶክ ዝግጅት ጋር ባለፈው ሐምሌ ቆይታ የነበራቸው አዲሷ ኃላፊ ድርጅቱ ፈርሶ መሠራት ያለበት ነው ሲሉ ያምናሉ። በሥራ አጋሮቻቸው ዘንድ እጅግ ትጉህና ፀባየኛ ባሕሪ እንዳላቸው የሚመሰክርላቸው ንጎዚ በዓለም ባንክ ለ25 ዓመታት ሠርተዋል። በዓለም ባንክ ቆይታቸው አነስተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች በርካታ ፈንድ በማሰባሰብ ይታወቃሉ። በተለይ በፈረንጆቹ 2010 ከተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች 50 ቢሊዮን ዶላር ሰብስበው አነስተኛ ገቢ ላላቸው መለገሳቸው ሁሌም የሚወሳላቸው ተግባር ነው። ነገር ግን ወደ ሃገራቸው ናይጄሪያ ተመልሰው ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ያልቆፈሩት እንደሌላቸው ይነገርላቸዋል። እሳቸውም በዚህ ድርጊታቸው ይኮራሉ። በፕሬዝደንት ኦሌሴጉን ኦባሳንጆና በጉድላክ ጆናታን ዘመነ ሥልጣን የፋይናንስ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። በዚህ ሥልጣን ዘመናቸው ወቅት ሃገራቸውን ከ18 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ማስወጣት ችለዋል። በናይጄሪያ የነዳጅ ገበያ ያለውን ሥር የሰደደ ሙስና ለማስወገድ ባደረጉት ድርጊት ብዙዎች ያነሷቸዋል። ቀልድ የማያውቁት የማሕበረሰብ ትምህርት [ሶሲዮሎጂ] ፕሮፌሰር የሆኑት የሕክምና ዶክተር እናታቸው በፈረንጆቹ 2012 ታፍነው ተወስደው ነበር። ሰዎች እንደቀልድ ታፍነው በሚወሰዱባት ናይጄሪያ የሳቸውን እናት አፍነው የወሰዱ ሰዎች ገንዘብ ከመጠየቃቸው በፊት ንጎዚ ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀው ነበር። ነገር ግን የፈለገ ቢሆን አፋኞቹ የሚፈልጉትን ነገር ላለማድረግ ወስነው ነበር። እናታቸው ዝርዝሩ ባልታወቀ ሁኔታ ከአምስት ቀናት በኋላ ሊለቀቁ ችለዋል። ብዙዎች እናታቸው የተለቀቁት በሴትዬዋ ጠንካራ ስብዕናና 'ቀልድ የማያውቁ' በመሆናቸው ሊሆን ይችላል ሲሉ ይገምታሉ። ሴትዬዋ በአዲሱ የሥልጣን ዘመናቸው ለሴቶች ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚችሉ ብዙዎች ይገምታሉ።
news-50926125
https://www.bbc.com/amharic/news-50926125
አፕል ገንዘብ ካልከፈለኝ ብሎ ያስፈራራው ታሠረ
የአይክላውድ አካውንቶችን (iCloud) ሰብሬ ገብቻለሁ በማለት አፕል ገንዘብ ካልከፈለው መረጃ እንሚያወጣ ያስፈራራው ወጣት በቁጥጥር ሥር ዋለ።
ነዋሪነቱ ለንደን ከተማ የሆነው የ22 ዓመቱ ከሪም አልባይራክ ወንጀሉን መፈጸሙን አምኗል። አልባይራክ፤ አፕል 100 ሺህ ዶላር ዋጋ ያለው የአይቲዩንስ ስጦታ ካርድ የማይሰጠው ከሆነ 319 ሚሊዮን አካውንቶችን እንደሚሰርዝ ሲያስፈራራ ነበር። ይሁን እንጂ አፕል ባካሄደው ምረመራ ወጣቱ የአፕልን ሥርዓት አብሮ እንዳልገባ አረጋግጧል። ወጣቱ ለአፕል ሴኪዩሪቲ ቡድን ኤሜይል በመጻፍ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አካውንቶችን ሰብሮ መግባቱን አሳውቆ ነበር። በዩቲዩብ ገጹ ላይ ቪዲዮ በመጫን የአይክላውድ አካውንቶችን እንዴት ሰብሮ እንደሚገባ አሳይቷል። • አፕል ቲቪ ጀመረ • አፕል ስልኮች በዝግታ እንዲሰሩ በማድረጉ ይቅርታ ጠየቀ • ሴቶችን ከመንቀሳቀስ የሚያግደው መተግበሪያ ሊመረመር ነው የጠየቀው ገንዘብ የማይከፈለው ከሆነ የአካውንቶቹን የይለፍ ቃል እንደሚቀይር እና አካውንቶቹ የያዙትን መረጃ ይፋ እንደሚያወጣ አስፈራርቶ ነበር። ይህን ማስፈራሪያ ካደረሰ ከሁለት ቀናት በኋላ በቁጥጥር ሥር ውሏል። የዩናይትድ ኪንግደም የብሔራዊ ወንጀል መከላከል ኤጀንሲ እንዳለው ወጣቱ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካላት ተሰብረው ይፋ የተደረጉ የኢሜይል አድራሻዎችን እና የይለፍ ቃሎችን ከሰበሰበ በኋላ፤ የይለፍ ቃላቸውን ያልቀየሩ ተጠቃሚዎችን አካውንት ለመክፈት ሞከረ እንጂ የአፕልን ሥርዓት ሰብሮ ለመግባት አልሞከረም። ወጣቱ ለመርማሪዎች "በኢንተርኔት ላይ አቅም ሲኖርህ ዝነኛ ትሆናለች፤ ሁሉም ያከብርሃል" ብሏል። ወጣቱ ለፈጸመው ወንጀል በይርጋ የሚቆይ የሁለት ዓመት እስር ተፈርዶበታል። ወጣቱ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ምንም አይነት ወንጀል የማይፈጽም ከሆነ ነጻ ይሆናል። በወንጀል ተጠርጥሮ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ግን የሁለት ዓመት እስሩ ተፈጻሚ ይደረግበታል። ከዚህ በተጨማሪም አልባይራክ ለ300 ሰዓታት ያለ ክፍያ እንዲሠራ እና ለስድስት ወራት ደግሞ ከኤሌክትሮኒክስ ጋር ግነኙነት እንዳይኖረው ማዕቀብ ተጥሎበታል።
news-46131622
https://www.bbc.com/amharic/news-46131622
ደሴ፡ የሰባት ዓመት ህፃን ገድሏል በተባለው የእንጀራ አባት ምክንያት ቁጣ ተቀሰቀሰ
በደሴ ከተማ የሰባት ዓመት ልጅ ሬሳዋ በማዳበሪያ ተጠቅልሎ በመገኘቱ የአካባቢው ህዝብ በቁጣ እንደተነሳ የደሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተስፋየ ጫኔ ገልፀዋል። በትናንትናው ዕለት ተገድላ የተገኘችው ይህች ህፃን ለሰባት ቀናት ያህል ከቤተሰቦቿ ጠፍታ ነበር።
የልጅቷን አሟሟት "በጣም አሰቃቂና ሰይጣናዊ" ያሉት ምክትል ከንቲባው ፖሊስ የህፃኗን ገዳይ ማንነት ባጣራው መሰረት የእንጀራ አባቷ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያም ታስሮ ይገኛል። •ጀግኒት ከትናንት እስከ ዛሬ •የተነጠቀ ልጅነት የግለሰቡን መያዝ የሰሙ ወጣቶች አሰቃቂ ግድያውን በመቃወምና "ፍፁም ከባህላችን ውጭ" ነው በሚል ሰውየው በሞት እንዲቀጣና ተላልፎም እንዲሰጥ ጥያቄ እንዳቀረቡ አቶ ተስፋየ ተናግረዋል። ጥያቄው በመጀመሪያ የተነሳው በጥቂት ግለሰቦች ቢሆንም በኋላም እየሰፋ መጥቶ የአካባቢውን ማህበረሰብ በሰፊው ሊያካትት ችሏል ብለዋል። •ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? የአካባቢው ህዝብ የተቃውሞ ሰልፍ በመውጣትም "ግለሰቡ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለገደላት ተሰቅሎ ሊገደል ይገባል" የሚሉ መፈክሮችንና የልጅቷንም ፎቶ በመያዝ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። "እውነት ለመናገር በከተማችን እንደዚህ አይነት ነገር መፈጠሩ ብዙዎችን አሳዝኗል። ሆኖም ግን ግለሰቡ ተጠርጥሮ እስከተያዘ ድረስ ተጣርቶ በህግ አግባብ በሚጠይቀው መሰረት ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል" የሚሉት አቶ ተስፋየ ይህ ግን በአካባቢው ማህበረሰብ ተቀባይነት አላገኘም። ከህግ አግባብ ውጭ ሊሰቀል፣ ሊገደል ይገባል የሚለው ድምፅም በርትቶ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያንና አንዳንድ ሆቴሎች ላይ ድንጋይ ተወርውሮ መስታወት እንደተሰባበረም ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ ሱቆች ላይ ዝርፊያ የተቃጣ ሲሆን ለማረጋጋትም የፀጥታ ኃይሎች ተኩሰዋል። ቁጥሩን በትክክል ባይገልፁም በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች አሉ። ቀላል ጉዳት በአንድ የፀጥታ ኃይል ከመድረሱ ሌላ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልተከሰተና ሁኔታዎችም እንደተረጋጉ ምክትል ከንቲባው ጨምረው ገልፀዋል። ግርግሩ ሲፈጠር ፒያሳ አካባቢ የነበረ ኃይለየሱስ በቀለ የተባለ የዓይን እማኝ በበኩሉ የእንጀራ አባቷ ገድሎ፣ ፒያሳ አካባቢ ጥሏታል የሚለው መረጃ ሲሰማ ሰዎች እንደተጋጋሉና ፒያሳ እንዲሁም የሔደበት ፖሊስ ጣቢያ ሰኞ ገበያ አካባቢ ግርግሮች እንደነበሩ ተናግሯል። ግለሰቡ ከተያዘ በኋላ ሲሆን ወሬው የተሰማው " በአደባባይ እንግደለው" የሚሉ ድምፆች እንደተሰሙና ከእምነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችም እንደተነሱ ገልጿል። ፖሊሶች የአድማ ብተና እያደረጉ እንደሆነና ትንሽ እንደተረጋጋ ተናግሯል። ህፃኗ ከእናቷና ከእንጀራ አባቷ ጋር ትኖር የነበረ ሲሆን፤ ዝርዝር መረጃ ባይኖራቸውም ሰውየው ከልጅቷ እናት የወለዳቸው ሌሎች ልጆችም እንዳሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል። ከመሞቷ በፊት ተደፍራለች ለሚለው ጥያቄ መረጃ እንደሌላቸው አቶ ተስፋየ ገልፀዋል።
news-53609385
https://www.bbc.com/amharic/news-53609385
ሆንግ ኮንግ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርጫዋን ለአንድ ዓመት አራዘመች
የኮሮናቫይረስ በመስፋፋቱ ምክንያት የሆንግ ኮንግ መንግሥት በመጪው መስከረም ሊያካሂደው አቅዶት የነበረው የፓርላማ ምርጫን በአንድ ዓመት ማራዘሙን አስታወቀ።
የሆንግ ኮንግ አስተዳዳሪ ካሪ ላም ሆንግ ኮንግ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ሲሆን ዛሬ 121 በበሽታው የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል። የምርጫውን መራዘም ተከትሎ ተቃዋሚ ፓርቲ መንግሥት ወረርሽኙን እንደ ሰበብ በመጠቀም ሕዝቡ የሚፈልገውን እንዳይመርጥ እያደረገ ነው ሲል ከሷል። ትናንት የግዛቲቱ መንግሥት 12 የዴሞክራሲያዊ ለውጥ ጠያቂዎች በምርጫው እንዳይወዳደሩ አግዷቸው ነበር። ተቃዋሚው ፓርቲ ቻይና በግዛቲቱ የጣለችውን አወዛጋቢ የደኅንነት ሕግ ተከትሎ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ መሰረት በማድረግ በፓርላማው ውስጥ በርካታ መቀመጫዎችን ለማግኘት ተስፋ አድርጎ ነበር። እነዚህ የዴሞክራሲ ለውጥ አራማጆች ባለፈው ዓመት በተካሄደው አካባቢያዊ ምርጫ ላይ ከ18 ምከር ቤቶች 17ቱን ለማሸነፍ ችለው ነበር። የሆንግ ኮንግ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ካሪ ላም የምርጫውን ጊዜ ለማራዘም የአስቸኳይ ጊዜ የማወጅ ሥልጣናቸውን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስታውቀው፤ "ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ከሰጠሁት ውሳኔዎች ሁሉ ይህ እጅጉን አስቸጋሪ ውሳኔ ነው" ብለዋል። ሆንግ ኮንግ ውስጥ የወረርሽኙ ሁኔታ ከዕለት ዕለት እየተበራከተ ሲሆን ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ በተከታታይ በየዕለቱ ከ100 በላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎች እየተመዘገቡ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል። በሆንግ ኮንግ ውስጥ እየተመዘገበ ያለው የህሙማን ቁጥር ዝቅተኛ ቢሆንም ግዛቲቱ በሽታውን ተቆጣጥራው መቆየቷን ተከትሎ በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱ ስጋትን ፈጥሯል። በአሁኑ ጊዜ በግዛቲቱ የታየው የበሽታው መስፋፋት "ለሦስተኛ ጊዜ በሽታው ማገርሸቱን" የሚያመለክት ነው እየተባለ ሲሆን፤ ረቡዕ ዕለት አስተዳዳሪዋ ካሪ ላም የሆንግ ኮንግ ሆስፒታሎች ሊቋቋሙት በማይቸል "የወረርሽኙ ማዕበል ልትመታ" ከምትችልበት ጠርዘ ላይ እንደደረሰች አስጠንቅቀው ነበር። ሆንግ ኮንግ ከሁለት ሰዎች በላይ በአንድ ስፍራ ላይ መገኘትን የሚከለክለውን ደንብ ተግባራዊ ከማድረግ በተጨማሪ ጥብቅ የቫይረሱ መከላከያ መንገዶችን እንዲተገበሩ አዛለች።
45180743
https://www.bbc.com/amharic/45180743
ከፀሐይ ኃይል ለአፍሪካ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚጥሩ ወንድማማቾች
በዓለማችን ከአምስት ሰዎች አንዱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አያገኝም። ሁለት ቢሊየን የሚገመቱ ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይልን የሚያገኙት ከእንጨት፣ ከሰልና ከመሳሰሉት ነዉ።
መትከል ዘርአይ እና ኢንጅነር ግርማይ ዘርአይ በቂ የኤሌክትሪክ አቅርቦት አለመኖር የአየር ብክለት ምክንያት ሆኖዉ የሚነሱ ነገሮችን ሰዎች ኤሌክትሪክ ለማግኘት ከሚጠቀሙዋቸዉ አማራጮች የሚመነጩ እንደሆኑም ይታመናል። ኤርትራዊያኑ ወንድማማቾች፤ መትከል ዘርአይና ኢንጅነር ግርማይ ዘርአይ የአፕቴክ አፍሪካ መስራቾች ናቸዉ። በ2006 በኤርትራ የተመሰረተዉ አፕቴክ አፍሪካ ከፀሐይ በሚገኝ ኤሌክትሪክና በፀሐይ የሚሰሩ የውሃ ፓምፖች በመስራትና በማቅረብ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነዉ። • በፀሐይ የሚሰራው የሕዝብ ማመላለሻ ጀልባ • የምግብ ብክነትን ለማስወገድ አዲስ ፈጠራ ይህ ተቋም በ2012 በደቡብ ሱዳን የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመስራት እዉቅና እያገኘ መምጣቱን የሚናገረዉ መትከል ዘርኣይ፤ 2015 ላይ በኡጋንዳ አዲስ ቅርንጫት እንደከፈተ ይገልጻል። ይህ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል በማመንጨት ሥራ ላይ የተሰማራው ተቋም በሩዋንዳ፣ በሴራሊዮን፣ በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፐብሊክና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲሁም ላይቤሪያ ቅርንጫፎቹን በማስፋት እየሰራ ይገኛል። አፕቴክ አፍሪካ በአፍሪካ ቀንድ ትልቁ በፀሐይ ኃይል የሚንቀሳቀስ የውሃ መሳቢያ ፓምፕ የሰራ ተቋም ሲሆን፤ የፀሐይ ኃይልን በሚጠቀም 82 ኪሎ ዋት የሚያመነጭ ሞተር በደቡብ ሱዳን ተክሏል። "ባለን መረጃ መሰረት ከ345 ሺህ በላይ ሕዝብ ውሃ ያገኛል። 109 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኝ አድርገናል። እስከ አሁን 2.6 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጭ መሳሪያ ተክለናል" ይላል መትከል ዘርኣይ። አብዛኛው ፕሮጀክት በገጠር አካባቢዎች የሚሰራ መሆኑን የሚናገረው ይህ ባለሙያ የውሃ፣ የኤሌክትሪክና የመሰል አገልግሎቶች ችግር በእነዚህ አካባቢዎች መፍታት ችለናል ይላል። ደቡብ ሱዳን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ማዕከላዊ አፍሪካን በመሰሉ ይህ ፕሮጀክት የሚንቀሳቀስባቸዉ ሃገራት፤ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የሚፈትናቸዉ በመሆኑ ለብዙ ባለሀብቶች የሚመች ሁኔታ የላቸዉም ይላል። አፕቴክ ሰራተኞች ካምፓላ "የመፍትሄዉ አካል መሆንን መርጠናል" መትከል ዘርአይ ይህ ሥራ የተጀመረበትን ሁኔታ ሲገልጽ "ታላቅ ወንድሜ ኢንጅነር ግርማይ ለረጅም ዓመታት በዚሁ ዘርፍ ስለተማረና ስለሰራ ከፀሐይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማቅረብ ሥራን ልንጀምር ችለናል። በተለይ ደግሞ ዓለምን እየፈተናት ያለው የሙቀት መጨመር ሥራውን በሰፊው ወደዚህ ፕሮጀክት እንድንገባ ምክንያት ሆኗል" ይላል። "የመፍትሄው አካል በመሆን ህፃናት ንጹህ ውሃ ሲጠጡ፣ ኤሌክትሪክ አግኝተዉ ሲማሩ፣ ማየትና ስደተኞች በውሃ ችግር ከሚመጡ በሽታዎች ሲጠበቁ ማየት የሚፈጥረው ደስታ የተለየ ነዉ" ሲል ይገልጻል። ይህን ፕሮጀክት በስፋት ለማከናወን ትልቁ ችግር ገንዘብ እንደሆነ እነመትከል ይናገራሉ። ነገር ግን አፕቴክ አፍሪካ በ2020 ወደ አስር የአፍሪካ አገራት ሥራውን ለማስፋፋት ዕቅድ አለው ። "ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት የሚኖር 600 ሚሊዮን የሚደርስ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ያላገኘ ህዝብ አለ። እኛ እየሰራንበት ባለው ቀጠናም በድህነት ስር ሆኖ ሻማ የሚጠቀምው ህዝብ፤ ሻማ በሚገዛበት ዋጋ ትንሽ በፀሐይ ኃይል የሚያመነጭ መሳሪያ በመስራት መፍትሄ ማበጀት የረጅም ጊዜ እቅዳችን ነው" ይላል መትከል። ከዚህ ባሻገርም በገጠር በእርሻ የሚተዳደረው ማህበረሰብ በቂ የውሃ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ የውሃ መሳቢያ ሞተሮችን በማምረት ለግብርና እንዲጠቀሙ ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን አክሏል።
news-52683718
https://www.bbc.com/amharic/news-52683718
ኮሮናቫይረስ፡ ዝንጀሮዎች ላይ የተሞከረው ክትባት ተስፋ ሰጪ ነው ተብሏል
ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ክትባት በስድስት ሬሰስ ማኩዌ በተሰኙ የዝንጀሮ ዝርያዎች ላይ ተሞክሮ ተስፋ ሰጪ ውጤት አሳይቷል።
ክትባቱ በአሁኑ ወቅት በሰው ልጅ ላይ እየተሞከረ ይገኛል። ነገር ግን የሰው ልጅ ላይ ያለው ውጤታማነት ሙሉ በሙሉ አልተረጋገጠም። ስድስቱ ዝንጀሮዎቹ ሳርስ-ኮቭ-2 የተሰኘው ቫይረስ እንዲሰጣቸው ከተደረገ በኋላ ክትባቱን እንዲወጉ ተደርገዋል። ዝንጀሮዎቹ ክትባቱ ከተሰጣቸው በኋላ ሳንባቸውና በመተንፈሻ አካላቸው ውስጥ ያለው ቫይረስ እየቀነሰ መጥቷል። ከአሜሪካ መንግሥት ብሔራዊ የጤና ኢንስቲትዩት እና የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ባለሙያዎች ናቸው ዝንጀሮዎቹ ላይ ሙከራ እያደረጉ ያሉት። ክትባቱ እንስሳቱ የሳንባ ምች [ኒሞኒያ] በሽታ እንዳይዛቸው እንደተከላከለም ተዘግቧል። ሬሰስ ማኩዌ የተሰኙት የዝንጀሮ ዝርያዎች ከሰው ልጅ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም ያላቸው እንስሳት ናቸው። ተስፋ በሚሰጥ ሁኔታ እንስሳቱ በሽታን የመከላከል አቅማቸውን የሚያዳክም በሽታም አልያዛቸውም። ከዚህ በፊት በነበረው የሳርስ ወረርሽኝ ጊዜ መሰል ክትባት እንስሳት ላይ ተሞክሮ ጉዳት አምጭ ሆኖ ተገኝቶ ነበር። አሁን ግን ይህን ዓይነት ክስተት አልታየም ተብሏል። ጥናቱ በሌሎች ሳይንቲስቶች ታይቶ ገና መታተም ቢጠበቅበትም የለንደን ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ስቴፈን ኢቫንስ ግን "በጣም አበረታችና ጥራቱን የጠበቀ" ሲሉ ክትባቱን ገልፀውታል። በሌላ በኩል የዩናይት ኪንግደሙ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ ፈቃደኛ ሰዎች ላይ ክትባት እየሞከረ ነው። የለንደን ኪንግስ ኮሌጅ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ፔኒ ዋርድ ክትባቱ ጉዳት አምጭ አለመሆኑና ኒሞኒያን መከላከሉ እጅግ ተስፋ የሚሰጥ ነው ይላሉ። ክትባቱ የተሠራው ከኮሮናቫይረስ ቅንጣት ሲሆን፤ የሰው ልጅ ሰውነት ቫይረሱን እንዲያውቀውና በቫይረሱ በሚጠቃበት ጊዜ ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው። ክትባቱ ሰውነት በቫይረሱ ሲጠቃ በቂ የሆነ መከላከለያ እንዲያዘጋጅ ያግዛል። ዝንጀሮዎቹ ላይ የተሞከረው ክትባት ይህንን ማድረግ ችሏል። ማለትም ዝንጀሮዎቹ በቫይረሱ ሲጠቁ መከላከል የሚያስችል አቅምን አጎልብቷል። በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ከ100 በላይ ኮሮናቫይረስን ይከላከላሉ የተባሉ ክትባቶች ሙከራ እየተደረገባቸው ነው።
45002979
https://www.bbc.com/amharic/45002979
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ጉዞ ተጠናቀቀ
ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ''ግንቡን እናፍርስ፤ ደልድዩንም እንገንባ'' በሚል መሪ ቃል እያደረጉት ያለው የአሜሪካ ጉዞ ዛሬ በሚኒሶታ በሚያደርጉት ጉብኝት ይጠናቀቃል።
እስካሁን በነበራቸው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለዓመታት በአሜሪካና በኢትዮጵያ ተከፋፍለው የቆዩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሲኖዶሶች ጋር ተገናኝተዋል። ሁለቱ ሲኖዶሶች ተዋህደው ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል። • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ሁለት ፓትሪያርክ ይኖራታል • የመደመር ጉዞ ወደ አሜሪካ ባሳለፍነው ዓርብ በአሜሪካ ከሚገኙ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋርም ውይይት አድርገው ነበር። በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን በጠቅላይ ሚንስትሩ መልስ ተሰጥቶባቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በተሳታፊዎቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች መመለስ ከመጀመራቸው በፊት ''አንዳንዶቹ ጥያቄዎች ሰፋ ያለ ጊዜ ተወስዶባቸው ልንመክርባቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ናቸው። የእራሴን ምልከታ ብቻ የማሳይባቸውን ጥያቄዎች ግን እመልሳለሁ'' ብለው። ሁሉን አቀፍ የሆነ አገራዊ ጉባኤ ይዘጋጅ አገራዊ መግባባት ሊያመጣ የሚችል የፖለቲካ ምሁራንና የሚመለከታቸውን ተቋማት የሚያሳትፍ ጉባዬ እንዲዘጋጅ ጥያቄ ካቀረቡ ተወካዮች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር መስፍን አብዲ የሁሉን አቀፍ የአገራዊ መግባባት ኮሚቴን ተወካይ ናቸው። ከዶ/ር መስፍን በተጨማሪም ብሩህ የሚባል ድርጅትን ወክለው የተገኙት ዶ/ር አክሎግ ቢራራ ሁሉን አቀፍ አገራዊ ጉባዬ ማካሄድ አገራዊ ፍይዳው ላቅ ያለ ነው ብለዋል። ከእሳቸው በተጨማሪ የብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤትን ወክለው የተገኙት ግለሰብም ሀሉን አቀፍ ህዝባዊ የምክክር አገራዊ ጉባኤ ይካሄድ በማለት ተመሳሳይ ጥያቄ አቀርበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩም በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሲሰጡ ''በየቀኑ ሰው በሚሞትበት አገር ውስጥ እየኖርን ዕርቅ አያስፈልግም ማለት እንችልም። ነገር ግን እርቁን እንዴት ማድረግ እንችላለን የሚለው ላይ ትኩረት መሰጠት አለባት'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጨምረው እንደተናገሩት ''ኢትዮጵያ ውስጥ ከጠበኛው እኩል ሽማግሌው በዝቷል። ሽምግልና ንግድ እየሆነ መጥቷል። በዚህም ሽማግሌ ዋሽቶ አያጣላም እንጂ እያስታረቀ አይደለም'' ያሉ ሲሆን ''እኔ ይበጃል የምለው በቅድሚያ መሰረታዊ የሆኑ ልዩነቶቻችንን ማጥበብ አለብን ከዚያም የተቀሩ ልዩነቶቻችንን መፍታት እንችላለን'' ብለዋል። የፌደራል ሥርዓት አያስፈልግም ፌደራላዊውን የመንግሥት ሥርዓትን ከነቀፉ ተወካዮች መካከል አንዱ የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን ወክለው የተገኙት አቶ ተክሌ የሻው ናቸው። አቶ ተክሌ ኢትዮጵያን በዘር ከፋፍሎ መመራት አይበጃትም ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ ''የፌደራል ሥርዓቱን እንናደው ከማለታችን በፊት ለኢትዮጵያ ምን አይነት የፖለቲካ ሥርዓት ያስፈልጋታል የሚለውን ለይተን ማወቅ አለብን'' በለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የማንነት ጥያቄዎች ላለፉት 40 ዓመታት ሲነሱ መቆየታቸውን በማስታወስ አገሪቱ ያስፈልጋታል የሚባሉት የፖለቲካ ሥርዓት በጥናት መደገፍ እንዳለበት አሳስበዋል። የሽግግር መንግሥት ይቋቋም በርካታ የውይይቱ ተሳታፊዎች የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ጥያቄ አቅርበዋል። ከእነዚህም መካከል አንዱ የጋምቤላ ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄን ወክለው የተገኙት አቶ ኦማን ጎራ ናቸው። ፓርቲያቸው በትጥቅ ትግል ላይ አሥመራ እንደሚገኝ አስታውሰው፤ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ጥያቄ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ለሚሉት ጥያቄዎች መላሽ ሲሰጡ ''እኔ በሽግግር መንግሥት ሃሳብ አላምንም። ምክንያቱም ሁሉም መንግሥት የሽግግር መንግሥት ነው። ቆይታው አምስት ዓመት ብቻ ነው'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ ''የሽግግር መንግሥት ይቋቋም የሚልው ጥያቄያችሁ ከዚህ በፊት የነበሩት መሪዎች ከስልጣናቸው አልነሳ እያሉ ስላስቸገሯችሁ ስጋት ገብቷችሁ የምታነሱት ጥያቄ ነው'' ሲሉ ለውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ቢባል እንኳ ሽግግሩን ሊያቀላጥፍ የሚችል መንግሥታዊ መዋቅር እና ተቋማት እንደሌለም ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ያስፈልጋል አቶ ደጀኔ አያሌው መድህን የተባለን ድርጅትን ወክለው የተገኙ ሲሆን የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ እንዲኖር ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩም የፕሬስ፣ የምርጫ ቦርድ እና ፍርድ ቤቶች የተመለከቱ ሕጎችን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ካመኑ በኋላ መንግሥትም በጉዳዩ ላይ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሕጉን ማሻሻል ስለማስፈለጉ እያነሱ ባሉበት ወቅት ነበር ኢኤንኤን የተባለው የሚዲያ ተቋም የመንግሥት ንብረትን ለድርጅቱ ሥራ ማስፈጸሚያነት ይጠቀም እንደነበር የተናገሩት። ''ኢኤንኤን የግለሰቦች ልሳን ነበር። መንግሥት ለእንዲህ አይነት የሚዲያ ተቋም ድጋፍ አያደርግም'' ሲሉም ተደምጠዋል። ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ይረጋገጥ ከተሳታፊዎች ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል ሌላኛው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲረጋገጥ የሚጠይቀው ይገኘበታል። ጠቅላይ ሚንስትሩም ''እኔ የማረጋግጥላችሁ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይሰፍናል። ይህንንም በተግባር ትመለከቱታለችሁ'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች አንድ ሆነው ወደ አገር ተመልሰው ኢህአዴግን እንዲፈታተኑም ጋብዘዋል። ሌሎች ጥያቄዎች ኢሕአፓን ከመሰረቱት መካከል አንዱ ነኝ ያሉት አቶ በላይነህ ንጋቱ፤ ኢሕአፓ አገር ውስጥ ገብቶ መንቀሳቀስ እንደሚፈልግ ከተናገሩ በኋላ የፓርቲያቸው አባላት ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ እንደተሰወሩ እና እስከሁን ድርስ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ለአቶ በላይነህ ምላሻቸውን በሰጡበት ወቅት ኢሕአፓ እንደማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ወደ አገር ቤት ተመልሶ የፖለቲካ ምህዳሩን መቀላቀል እንደሚችል አሳውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ተሰውረዋል ስለተባሉት የፓርቲው አባላት ጉዳይ ምላሽ ሲሰጡ ''እነሱ የኢሃፓ አባላት ብቻ አይደሉም ኢትዮጵያዊያንም ጭምር ናቸው። ጉዳዩን እንመለከተዋለን'' ብለዋል። ከኢሮብ ብሔረሰብ እንደመጡ የተናገሩት የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር ተወካዩ፤ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የድንበር ጉዳይ ህዝብን ባሳተፈ መልኩ ይሰራ ብለው ጠይቀው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትሩም የደንበር ጉዳይ ሁለተኛ ነገር ነው። ከድንበሩ በፊት የህዝብ ለህዝብ ግነኙነት መቅደም አለበት ብለዋል። እስካሁን ስለደንበር ጉዳይ ከኤርትራ ጋር የተወሰነ ነገር የለም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ''ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን የሚመለከተው የፌደራል መንግሥቱን ነው። የፌደራል መንግሥቱን የሚመራው ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ይወክለኛል እስካሉ ደረስ ለእኔ ይተዉት'' ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ እያደረጉት ባለው ጉብኝት ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዝድነት ማይክ ፔንስ፣ ከዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ጂም ዮንግ ኪም እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ክርስቲያን ላጋርድ ጋርም ውይይት አካሂደዋል። ይህ ጉብኝት የተሳካ እንዲሆን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዋሽንግተን ከሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ እና ሎስ አንጀለስ ከሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ጋር ተባብረው እየሰሩ ነው ሲል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቢሮ አሳውቋል።
news-49902826
https://www.bbc.com/amharic/news-49902826
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ቀጣዩ ምርጫ ግልጽ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንደሚሆን ተናገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ቀጣዩ ምርጫ በማያጠራጥር ሁኔታ ግልጽ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንደሚሆን ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በተፈራረሙበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አክለውም "ሕዝቡ ከዚህ በኋላ የሚፈልገውን ሃሳብ ያቀረበለትንና የሚፈልገውን አካል የመምረጥ እድል አለው" ሲሉ የመጨረሻው ውሳኔ የሕዝቡ መሆኑን ገልጸዋል። • ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ? • "መንግሥት አይወክለኝም ለሚሉ ወገኖች ምርጫ ምላሽ ይሰጣል" ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፓርቲዎቹም ቀጣዩ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ነፃና ግልፅ እንዲሆን በትብብር ለመስራት እንዲሁም ከወራት በኋላ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ምርጫ በክልሉ ውስጥ መካሄድ ባለበት ሁኔታ ላይም በጋራ ተመካክሮ የሚያስማማ ውሳኔ ላይ ለመድረስም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። በጋራ ለመስራት ስምምነቱን የፈረሙት የኦዲፒ ሊቀ መንበር እና የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፣ የኦዲፒ ምክትል ሊቀ መንበርና የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ፣ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ የኦፌኮ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ የኦዴግ ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታን ጨምሮ ሌሎች ኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ናቸው። በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲዎች ፓለቲካውን ወቅቱን በሚጠይቅ መልኩ በማዘመን ከመጠፋፋትና ከመወጋገዝ በመውጣት "በሀሳቦች ላይ በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየት ሕጋዊ በሆነ መንገድ ፍላጎታችንን ከግብ ማድረስ እንችላለን" ሲሉ ተናግረዋል። በፖለቲካ ፉክክር ምክንያት በሕዝቡ ላይ ምንም ዓይነት ስቃይና ጉዳት መድረስ የለበትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "ሀሳባችንን በሰላማዊ መንገድ እየተወያየን መስራት እንችላለን የሚለው ትልቅ ሀሳብ ነው" ሲሉ እርምጃውን አድንቀዋል። ጨምረውም አሁን በኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት የተጀመረው የምክክር መድረክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች መስፋት እንዳለበት አመክልተው አብሮ በመስራት ሀገሪቱን ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚቻል በመወያየትና በመመካከር መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። • ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ከአስርት ዓመታት በፊት በሕዝቡ ዘንድ ሲነሱ የነበሩትን ጥያቄዎች በዚህ ዘመን ይዞ መቅረብ ከጊዜው ጋር እንደማይሄድ ጠቅሰው "እንደ ሀገር ትልቅ ኃላፊነት የወሰደውን ለተቀበለ ሕዝብ አዲስ ሀሳብ በማምጣት ሀገሪቱን ማሸጋገር እንደሚያስፈልግና ኢትዮጵያ በምትገኝበት ቀጠና ውስጥ ተገቢውን ሚና መጫወት ይጠበቃል" ብለዋል። ፓርቲዎቹ በደረሱት ስምምነት የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በቅንጅት ለመስራት የሚያስችልና አመራሮችን በአንድ የሚያሰባስብ አካል በመመስረት በመካከላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች በዚሁ አካል በኩል መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተገልጿል። በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት እየሆኑ ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ጥሪ ቀርቧል። ፓርቲዎቹም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በማስቆም ሰላምን ለማስፈን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
54546133
https://www.bbc.com/amharic/54546133
አማራ ክልል፡ ባለፉት ሦስት ወራት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ ተጠቅተዋል
አቶ ሃብታሙ ሃይሌ የምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደ ውሃ ከተማ ነዋሪ ናቸው። እንደ አቶ ሃብታሙ ከሆነ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በአካባቢው የወባ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ይገኛል።
የወባ ትንኝ "ቁጥሩ ጨምሯል። . . . ሁሌም በዚህ ወቅት የወባ በሽተኞች ቁጥር ይጨምራል። አሁን ግን ከበፊቱ እየጨመረ እያየን ነው" ሲሉ ይገልጻሉ። "ምንም የተለየ ምክንያት የለም። ዘንድሮ ኬሚካልም ሆነ የአጎበር ስርጭት ለህብረተሰቡ ተካሂዷል። የተለየ የሚያደርገው የዝናቡ መጠን ጨምሯል። ከፍተኛ ዝናብ ነበር። ይህ ደግሞ ለወባ መጨመር ምክንያት ነው" ሲሉ ምክንያት የሚሉትን ተናግረዋል። በአካባቢው በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ቢገልጹም በዚህ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ ሰው እንደሌለ ጠቁመዋል። በወባ የሚያያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ደጋግመው የተናገሩት አቶ ሃብታሙ በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። በህክምና ተቋማት ህክምና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው ስለ አጎበር አጠቃቀም ትምህርት መሰጠቱትንና በወባ ላይ የሚሠሩ የህክምና ባለሙያዎች በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ እየሠሩ እንደሆነ አስታውቀዋል። በአካባቢያቸው ከነሐሴ ወር ጀምሮ በወባ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን በመተማ ወረዳ ጤና ጥበቃ የወባ ኦፊሰር የሺሃረግ አያናው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ካለፉት አምስት ዓመታት አንጻር በአካባቢው ከፍተኛ የሚባል ለውጥ የለውም ያሉት ወይዘሮ የሺሃረግ ባለፉት ጥቂት ወራት ግን ቁጥሩ ማሻቀቡን ገልጸዋል። ከሳምንት ሳምንት ቁጥሩ እየጨመረ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም ከፍተኛ ቁትር መመዝገቡን ጠቁመዋል። በአካባቢው ያሉ የቀን ሠራተኞችን ጨምሮ ብዙዎቹ አዲስ በወባ የተጠቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የኬሚካል ርጭት በቂ ባይሆንም እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው ዘግይቶም ቢሆን አጎበር ባለፉት ጥቂት ሳምንታት እየተከፋፈለ ይገኛል ሲሉ አስረድተዋል። በተጨማሪም ችግሩን ለመቅረፍም ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን በማፋሰስ እና በማዳፈን እንዲሁም የተቃጠለ ዘይት በመጠቀም እየተከላከሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በክልሉ የወባ ስርጭት ከሳምንት ሳምንት እየጨመረ ይገኛል ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ ማስተዋል ወርቁ ናቸው። ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባሉት ወራት የወባ ስርጭት መጨመሩ የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸው ሆኖም የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ የክልሉ መልክዓ ምድር አቀማመጥ ለወባ መራቢያ ምቹ መሆን፣ የማህበረሰቡ ቁጥጥር እና መከላከል ሥራ መቀነስ እና የአልጋ አጎበር አጠቃቀም እና ትኩረት ለኮሮናቫይረስ በመደረጉ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ አንዲመዘገብ አድረጓል ብለዋል። እንደአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃ ከሆነ በ2012 በጀት ዓመት በክልሉ በወባ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በ2011 ዓመት ከነበረው 66 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ የ2012 በጀት ዓመትን የመጀመሪያ ሦስት ወራት ከሐምሌ 1/2012 ጀምሮ ካሉት ሦስት ወራት ጋር በማነጻጸር አራት በመቶ ጭማሪ እንዳለው ወይዘሮ ማስተዋል ገልጸዋል። በክልሉ ነፍሰጡር እናቶች እና ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ይበልጥ በወባ ተጠቂ መሆናቸውን እና ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ መጠቃታቸውን አስተባባሪዋ ገልጸዋል፡፡ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች የክልሉን 88% የወባ ስርጭት ይይዛሉ። የኬሚካል እና የአጎበር ስርጭት እጥረት መኖሩን ጠቁመው ኬሚካል መረጨት ያለባቸው አካባቢዎች ጭምር እንዳልተረጩ ገልጸዋል። ክልሉ ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ በ53 ወረዳዎች የኬሚካል ርጭት እንዲካሄድ ጥያቄ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ባለው እጥረት ምክንያት በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት ካለመከናወኑም በላይ በዘጠኝ ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ አለመረጨቱን ጠቁመዋል። ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካበቢዎች በየሦስት ዓመቱ አጎበር የሚቀየር ሲሆን ለ55 ወረዳዎች ቀደም ሲል የነበራቸው አጎበር ይተካላቸዋል ቢባልም እስካሁንየደረሳቸው መተማ፣ ገንደ ውሃ እና ፎገራ ወረዳዎች ብቻ ናቸው ተብሏል። ወቅቱ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ በመሆኑ እስከ ታህሳስ 30 ድረስ በንቃት መሳተፍ ያስፈልጋል ብለዋል። ወባን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ግንዛቤ የማጎልበት፤ የጤና ተቋማት ዝግጅትን ማሰደግ፤ የአጎበር ስርጭትን ማጠናከር እና የኬሚካል ርጭት በማከናወን ላይ በትኩረት ይሠራል ብለዋል። የጤና ተቋማት በ2012 ካጋጠማቸው የግብዓት መቆራረጥ ወጥተው በቁሳቁስም ሆነ በባለሙያ ዝግጁ ሆነዋል ብለዋል። ለዚህም ማንኛውም ትኩሳት ያለበትን ሰው ወደ ህክምና ተቋም ሲያመራ በመጀመሪያ የወባ ምርመራ እንዲደረግለት አቅጣጫ መቀመጡን አስተባባሪዋ ተናግረዋል።
news-46639619
https://www.bbc.com/amharic/news-46639619
"በግድ ደስተኛ መሆን አይቻልም" ተመራማሪዎች
ደስታ በግድ ማንቁርቱን ይዘህ የምታመጣው አውራ ዶሮ አይደለም። ደስተኛ ለመሆን ጥረት የሚያሳዩ ሰዎች ጥንቸል ላይ የከባድ መኪና ጡሩንባ እያንባረቁ ጥንቸሏ ከእቅፋቸው እንድትገባ የሚናፍቁ ናቸው።
ይህን የሚሉት ተመራማሪዎች ደስተኝነት እየራቃቸው የሚሄዱ ሰዎች ደስተኝነትን አብዝተው የሚያስቡቱ ናቸው ሲሉም ደምድመዋል። • 1550 ተማሪዎች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን ለውጠዋል ለመሆኑ ደስታን እንዴት አድርገን ነው የምናስባት? ማንን ነው የምትመስለው? ፈንጠዚያ ደስታ ናት? ያለማቋረጥ በሳቅ መንከትከት ደስተኝነት ነው? በምቾት መንገላታትስ? ምንድናት ደስታ? እንዴት ነው ጅራቷን መያዝ የሚቻለው? በሥነ ልቡና ሳይንስ መስክ ስለ ደስታ መሻትና ማግኘት አያሌ ጥናቶች ተደርገዋል። ተለዋዋጭ ድምዳሜዎች ላይ ተደርሶም ያውቃል። አንድ የማያወላዳ መቋጫ የሚባለው ታዲያ የሚከተለው ነው፤ ደስታን በእጅጉ መሻት ደስታን ማራቅ ነው። የደስታን ጅራት የጨበጠ እጁን ያውጣ ለብዙዎች ደስታ የምርጫ ጉዳይ ነው። በእነዚህ ሰዎች አስተሳሰብ ደስተኛነት የጥረት ፍሬ ናት። ደስተኛ ለመሆን የፈለገ ልክ በፈተና እጅግ በጣም ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚታትር ተማሪ ቀን ተሌት መልፋት መድከም አለበት። ጎበዟ ደራሲ ኤልዛቤት ጊልበርት ከዓመታት በፊት ዓለምን አነጋግሮ በነበረውና "Eat, Pray, Love" በተሰኘው የአንድ ወቅት መጽሐፏ ይህን ብላ ነበር፦ "ደስታ የጥረት ውጤት ነው። ትታገላለህ፣ ትሟሟታለህ፣ አንዳንዴም ተነስተህ ፍለጋ ትወጣለህ፤ አገር፣ አህጉር፣ ባሕር ታቋርጣለህ። በረከትህን ለመቀበል ቁጭ ብለህ አይሆንም፤ መቃረም አለብህ። ልክ የደስታን ጅራት ስትጨብጠው እንዳልትለቀው ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይኖርብሃል። በሐሴት የተነጠፈ የዋና ውሀ ላይ ለመንሳፈፍ የምትችለውን ሁሉ ማድረግ አለብህ፤ አለበለዚያ ትሰጥማለህ።" •አርበኞች ግንቦት ሰባት ፈርሶ አዲስ ፓርቲ ሊመሰረት ነው እንዲህ ዓይነቱን "ደስታን በባትሪ ፈልጋት" የሚለው ምክር የብዙዎች ቢሆንም አዳዲስ ጥናቶች ግን "ኧረ በፍጹም" ይላሉ። "ፍለጋ ከወጣህ ባዶ እጅህን ትገባለህ፤ እመኑን ደስታ በፍለጋ አትገኝም" ይላሉ። ከዚያም አልፈው ደስታ ፍለጋ የወጡ ሰዎች ለጭንቀት፣ ለብቸኝነት፣ ለድብታ እና ለውድቀት ነው የሚዳረጉት ብለዋል። ይህ ጥናት እግረ መንገዱን በየአውዳመቱ ድብታ ውስጥ ስለሚገቡ ሰዎች አዲስ ፍንጭም ሰጥቷል። በገና፣ በአዲስ ዓመት፣ በኢድ አንዳንዴም በገዛ የልደት ቀናቸው ከባድ የድብርት ቅርቃር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች ደስታን ካልጨበጥናት ሞተን እንገኛለን ስለሚሉ ነው። ደስታን በትግል፤ ቀን ጠብቀው ሊያገኟት... "ደስተኛ ሁን!" የሚሉ ብሽቅ መጻሕፍት በካሊፎርኒያ ባርክሌይ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆነችው አይሪስ ማውስ ስለ ደስታና ደስተኝነት ስታጠና እግረ መንገዷን አነቃቂ መጻሕፍትን ታዝባቸዋለች። ባለፉት ሁለት አሥርታት በአሜሪካ እነዚህ የንሸጣ መጻሕፍት አገሩን አጥለቅልቀውት ነበር። እነዚህ መጻሕፍት አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ስለደስታ ያላቸው ምልከታ ነው። በሕይወት ለመቆየት ደስታን መጎናጸፍ የግድ ነው ይላሉ። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ ሁሉንም ስትገልጣቸው "ደስተኛ ካልሆንክማ ለምን ትኖራለህ? እንዴትም ብለህ እራስህን ደስተኛ ማድረግ አለብህ እንጂ" እያሉ አንድ ሁለት ሲሉ አቋራጭ መንገዶችን ይዘረዝራሉ። በዚህ የተነሳ ጤነኛ ሰው በሰላም እየኖረ ሳለ ልክ እነዚህን መጻሕፍት ሲያነብ 'አሃ! ለካ ሁልጊዜ ደስተኛ መሆን አለብኝ...' ሲል ማሰብ ይጀምራል። እንደውም አሁን ደስተኛ አይደለሁም "በጣም ደስተኛ መሆን ነው ያለብኝ..." ሲል ከራሱ ጋር አዲስ የቅራኔ ውል ይፈራረማል። ተመራማሪዋ አይሪስ እንደምትለው አንድ ሰው ራሱን "ምን ያህል ደስተኛ ነኝ ግን?" ብሎ የጠየቀ 'ለታ ከደስታ ጋር ፍቺ ፈጽሟል። ማነው ታዲያ ደስተኛ? ይህ የነ አይሪስ ጥናት ብዙ ክፍሎች ነበሩት። ከመሪር ሃዘን በቅርብ የወጡ ሰዎችን ጭምር አካቶ ይዟል። ፊልም እንዲመለከቱ የተደረጉም ነበሩ። ደስተኛ ስለመሆን የሚያወሱ መጻሕፍትን አንብበው የጨረሱ ሰዎችም ዋንኛ የጥናቱ አካል ተደርገዋል። በሚገርም ሁኔታ ሌሎች ይዘት ያላቸውን ጽሑፎች ካነበቡት በተለየ አነቃቂ መጻሕፍትን ያነበቡት "ደስተኛማ መሆን አለብኝ" በሚል አዲስ መብሰልሰል ውስጥ ገብተው ተገኝተዋል። እነዚህ ሰዎች መጻሕፍቱን ካገባደዱ በኋላ ስለ ደስታ የነበራቸው ስሜት በመናሩ ያሉበትን ሁኔታና ሕይወታቸውን መንቀፍ ነበር የያዙት። ይህ ተመሳሳይ ስሜትና ከፍተኛ ደስታን መሻት ሙሽሮች ላይም ተስተውሏል። ለሰርጋቸው ከፍ ያለ ቦታን በመስጠታቸው፤ በሰርጋቸው ማግስት በደስታ ባሕር እንደሚቀዝፉ በማመናቸው ለበለጠ ድብርት ተዳርገው ተገኝተዋል። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ይህ ስሜት ብዙ ሰዎች ያጋጥማቸዋል፤ ውድ የሽርሽር ቦታ አቅደው የሄዱ ሰዎች በማግስቱ ባዶነት ይሰማቸዋል። ነገር ግን በድንገት ወይም ባልተጠበቀና ባልታቀደ ሁኔታ አንድ ቦታ ብትሄዱ ላቅ ያለ ደስታን ልታገኙ ይቻላችኋል። የባርክሌይ ዩኒቨርስቲ ጥናት ታዲያ "ይህ የሚነግረን ደስታ በቁፋሮ እንደማትገኝ ነው" ይላል። ለምን ከተባለ ደስታን ስለማግኘት ቀን ተሌት መጣር ስሜታችንን በአላስፈላጊ ደረጃ ማዳመጥን ያስከትልብናል። ስለራሳችን አብዝተን እንድንጠበብ ያደርገናል። አካባቢያችንን ይጋርድብናል። ተፈጥሮን መገንዘብና ማድነቅ እናቆማለን። ሳር ቅጠሉ ሁሉ ስለኛ መሆን እንዳለበት ያሳስበናል። ሌላው ተመራማሪ ማግሊዮ ከካናዳ አንድ ተጨማሪ ነጥብ አንስቷል። ፌስቡክን የመሰሉ የማኅበራዊ ትስስር ድረገጾች ላይ የተጠመዱ ሰዎች ደስተኝነታቸው የሚያሽቆለቁለው የሚያዩት ነገር ስለራሳቸው ስለሚነግራቸው ነው። እኔ እንደ እከሌ ደስተኛ መሆን አለብኝ እያሉ ለማሰብ ይገደዳሉ። ጥናቱ ረዥም ነው። የጥናቱን ውጤት ግን እንዲህ ብሎ መደምደም ይቻላል። ደስታን ማሳደድ ማለት ያለበረቱ የተገኘ ቀንዳም በሬን እንደማሳደድ ነው። ለበሬው ገለል በሉለት... ሰላም ይሆን ዘንዳ!
news-56121978
https://www.bbc.com/amharic/news-56121978
የአገረሰብ ሙዚቃ ንግሥት ዶሊ ፓርተን ሐውልት እንዳይቆምልኝ አለች
በአሜሪካ የአገረሰብ ሙዚቃ ታሪክ ንግሥት ተደርጋ የምትታየው ዶሊ ፓርተን የቴነሲ ግዛት ለእርሷ ክብር ሐውልት ሊያቆም የያዘውን ሐሳብ ለጊዜው ውድቅ እንዲያደርገው ጠየቀች፡፡
የቴነሲ ግዛት ሕግ አውጪዎች ለሷ በናሽቪል ስቴት ካፒቶል የመንግሥት ሕንጻ ቅጥር ውስጥ ሐውልት እንዲቆም ያቀረቡትን ረቂቅ ድጋሚ እንዲያጤኑት ጠይቃለች፡፡ ‹9 ቱ 5› ዘፈን ባለቤት ዶሊ በትዊተር ሰሌዳዋ እንደጻፈችው አሁን ለሷ ሐውልት የሚቆምበት ጊዜ አይደለም፡፡ ‹አሁን በዓለማችን ላይ እየሆነ ካለው ደስ የማይል ሁኔታ አንጻር ለኔ በዚህ ጊዜ ስለ ሐውልት ማቆም ማውራት ስሜት አይሰጥም›› ብላለች ዶሊ፡፡ የአገረ ሰብ ሙዚቃ ንግሥት ዶሊ አሁን 75 ዓመቷ ነው፡፡ ሐውልት ልታቆሙልኝ ስላሰባችሁ እጅግ ክብር ተሰምቶኛል ብላለች፡፡ ‹‹ነገር ግን ያ እንዲሆን የምመኘው ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ ወይም እኔ ከሞትኩ በኋላ፣ ይገባታል ብላችሁ ካሰባችሁ ብቻ ቢሆን ነው የምመርጠው፡፡ ያን ጊዜ በካፒቶል ሂል እንደ አንዲት የቴነሲ ተወላጅ ደስታዬ ወደር አይኖረውም›› ብላለች፡፡ ባለፈው ኅዳር የአገረ ሰብ ሙዚቃ ንግሥት ዶሊ ለኮቪድ 19 ምርምር የሚሆን 1 ሚሊዮን ዶላር ለግሳ ነበር፡፡ ልገሳው በናሽቪል ቫንደርቢለት ዩኒቨርስቲ ለሚደረገው ጥናትና ምርምር የሚውል ነው፡፡ ይህ ማዕከል የሞደርና ክትባት ከሚሞከርባቸው ተቋማት አንዱ ነው፡፡ ሞደርና የኮቪድ ክትባት 95 ከመቶ ያህል ፈዋሽነቱ መረጋገጡ ይታወሳል፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ ዶሊ ይፋ እንዳደረገችው በአሜሪካ ትልቁን የክብር ሽልማት እንድትቀበል በትራምፕ 2 ጊዜ ተጠይቃ ውድቅ አድርጋለች፡፡ ይህ ሽልማት ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትልቅ ተግባር ለፈጸሙ የሚበረከት ሲሆን የአሜሪካ ፕሬዝዳንሻል የነጻነት ሜዳሊያ ተብሎ ይጠራል፡፡ ሽልማቱን ለመቀበል ፍቃደኛ ያልሆነችው ባለቤቷ ታሞ ስለነበረ ወደ ዋሺንግተን ለመጓዝ ባለመፍቀዷ ነው፡፡ ዶሊ ለ5 አሥርታት በትዳር የጸናች ናት፡፡ ከሙዚቃ ባሻገር በሲኒማ ተሳትፎዋ የምትታወቅ ሲሆን 9 ቱ 5 ፊልም ተዋናይ ስትሆን በዚሁ ርዕስም ሙዚቃ ተጫውታለች፡፡ ዶሊ ፓርተን በሕይወት ዘመኗ ፖለቲካ ውስጥ ገብታ አታውቅም፡፡ ፖለቲካዊ አስተያየት መስጠትም አትወድም፡፡ ሆኖም ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ለጥቁሮች መብት እንቅስቃሴ (ብላክ ላይቭስ ማተር) ድጋፏን ሰጥታ አነጋጋሪ ሆና ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠይቃ ለቢልቦርድ መጋዚን ስትመልስ ‹‹የኛ የነጮች ሕይወት ብቻ ነው ዋጋ ያለው የሚመስልህ? ግድ የሚሰጥህ የነጮች ጉዳይ ሲሆን ከሆነ ትክክል አይደለም›› ብላ መልሳለች፡፡ ዶሊ ፓርተን ሕይወቷን በሙሉ ለጋስ በመሆን በአሜሪካዊያን ዘንድ ትታወቃለች፡፡ ዶሊውድ ፋውንዴሽን ለበርካታ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት ስመ ጥር ነው፡፡ በልጅነቷ በአስቸጋሪ ድህነት እንዳደገች ዶሊ ትናገራለች፡፡ ዶሊ ፓርተን ‹‹አይ ዊል ኦልዎይስ ላቭ ዩ› እና ‹ጆሊን› በሚለው ሙዚቃዎቿ በኛም አገር ይበልጥ ትታወቃለች፡፡ ዶሊ የ9 ግራሚ ሽልማቶች አሸናፊ ናት፡፡ ዶሊ ከሌላኛው የአገረሰብ ሙዚቃ አቀንቃኝ ኬኒ ሮጀርስ የተጫወተችው ሙዚቃ በታሪክ በጥምረት ተዘፍነው እጅግ ተወዳጅነት ካገኙ ሙዚቃዎች በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ ‹አይላንድስ ኢን ዘ ስትሪም› የተሰኘው የጥምረት ሙዚቃ በዶሊና በኬኒ ሮጀርስ የተቀነቀነ ዘመን አይሽሬ ሙዚቃ ተደርጎ ዛሬም ድረስ ይወደዳል፡፡
news-47986557
https://www.bbc.com/amharic/news-47986557
የሩሲያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዜና አቅራቢ ሮቦት ይፋ አደረገ
የሩሲያ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዜና የሚያቀርብ ሮቦት ይፋ አደረገ።
'አሌክስ' የተሰኘው ዜና አቅራቢ ሮቦት ገና ከአሁኑ በቴሌቪዥኑ ተመልካቾች ዘንድ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን፤ በርካቶች መልኩን አለመውደዳቸው እና ፕሮፖጋንዳ ይነዛል እያሉ እየወቀሱት ይገኛሉ። ሮቦቱ ፐርም በተባለች የሩሲያ ከተማ ውስጥ የተሰራ ሲሆን የፊቱ ቅርጽ ከቴሌቪዥን ጣቢያው መስራቾች መካከል አንዱ የሆነዉን አሌክሲ ዩዘሀኮቨን እንዲመስል ተደርጎ ተቀርጿል። • የሶፊያ ንብረት የሆነ አንድ ሻንጣ ጠፋ የሮቦቱ ግንባታ ከሁለት ዓመታት በፊት የተጀመረ ሲሆን አሁን ባለበት ደረጃ ሮቦቱ ፊቱን እና አንገቱን ብቻ ነው ማነቃነቅ የሚችለው። አሌክሲ ዩዘሀኮቨ (ግራ) እና አሌክስ ሮቦቱ (ቀኝ) ቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳለው የአሌክስ ውጫዊ አካል እና ውስጣዊ ስሪቱ (ሶፍትዌሩ) ሙሉ በሙሉ የተሰራው ሩሲያ ውስጥ ነው። በርካታ የዜና ሰዓቶችን የተቆጣጠረው አሌክስ በርካታ ትችቶችን እያስተናገደ ይገኛል። የፊቱ ገጽታዎች ያልተለመደ እና በርካቶች አስቂኝ ሆኖ ያገኙታል። ተመልካቾች "አሌክስ ሁሉንም ዜናዎች በተመሳሳይ ፍጥነት እና ስሜት ነው የሚያነበው" በማለት ከሰው ልጆች የሚለይበትን መንገድ ይዘረዝራሉ። • ታዋቂው ኩባንያ ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞችን ''ይበድላል'' ተባለ • ጾታዊ ትንኮሳን ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት ሮሲያ 24 የተሰኘው የቴሌቪዝን ጣቢያ ''ለመጀመሪያ ጊዜ ሮቦት የቴሌቪዥን ዜና አቅራቢ ሆነ ''ሲል በድረ-ገጹ አስፍሯል። ቴሌቪዥን ጣቢያው ጨምሮም ''ውሳኔው የተመልካቾች ነው፤ ሮቦቶች ጋዜጠኞችን መተካት ይችላሉ?'' በማለት ጠይቋል።
news-55198053
https://www.bbc.com/amharic/news-55198053
ሕክምና ፡ ቁመት ለመጨመር ምን አይነት ቀዶ ሕክምና ነው የሚደረገው?
ሳም ቤከር የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳለ የክፍሉ ረዥም ልጅ ነበር።
ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው እአአ 2015 ላይ ሲሆን፤ ከ162 ሴንቲ ሜትር ወደ 170 ሴንቲ ሜትር ከፍ እንዲል አስችሎታል። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆነው ጓደኞቹ ሁሉ ዘለግ ዘለግ ያሉ ሲሆኑ የእሱ ቁመት ግን አልጨመረም። "ኮሌጅ ስገባ ከሌሎች ወንዶችና ሴቶች ያጠርኩ መሆኔን አስተዋልኩ። ሴቶች ከእነሱ ከሚያጥር ሰው ጋር ፍቅር አይጀምሩም። እናም ሚስት አላገኝም ብዬ እሰጋ ነበር" ይላል። የ30 ዓመቱ የኒው ዮርክ ነዋሪ ሳም እረዝማለሁ ብሎ ቢጠብቅም ቁመቱ አልጨምር አለው። "ቁመትና ስኬትን አስተሳስሬ ነው የማየው" የሚለው ሳም ቁመት ለመጨመር አማራጮች ያስስ ጀመር። ከፍ ያለ ጫማ ማድረግ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወዘተ. . . የሚሉት አማራጮች አላሳመኑትም። እግር ስለሚያረዝም ቀዶ ሕክምና ሲያነብ ግን ትኩረቱን ሳበው። "ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ" በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁመታቸውን ለመጨመር ቀዶ ሕክምና ያደርጋሉ። ቀዶ ሕክምናው ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሳም ስለ ቀዶ ሕክምናው ከእናቱ ጋር ከተወያየ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ቢኖርም እንኳን ለማካሄድ ወሰነ። ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሲሆን፤ ይህም ከ162 ሴንቲ ሜትር ወደ 170 ሴንቲ ሜትር ከፍ እንዲል አስችሎታል። "ሐኪሙ መጀመሪያ ሲያገኘኝ ቀዶ ሕክምናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነግሮኛል። ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ።" ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሆስፒታል ውስጥ የማገገሚያ ሕክምና ተደርጎለታል። ለስድስት ወራት፣ በሳምንት ለአራት ቀን ሕክምና ይሰጠው እንደነበር ያስታውሳል። "እንደ አዲስ መራመድ መማር ነበረብኝ" ይላል። ብዙ አገሮች እግር ለማርዘም ቀዶ ሕክምና ይሰጣሉ። እስከ አምስት ኢንች ወይም 13 ሴንቲ ሜትር ድረስ ቁመት መጨመርም ይቻላል። አሜሪካ፣ ጀርመን እና ደቡብ ኮርያ የሚገኙ ሆስፒታሎች በዓመት ከ100 እስከ 200 ቀዶ ሕክምናዎችን ያደርጋሉ። ስፔን፣ ሕንድ፣ ቱርክ እና ጣልያን ውስጥ በዓመት ከ20 እስከ 40 የሚደርሱ ቀዶ ሕክምናዎች ይካሄዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ደግሞ በዓመት 15 ጊዜ ቀዶ ሕክምናው ይደረጋል። ቀዶ ሕክምናውን የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ቀዶ ሕክምናውን የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ቀዶ ሕክምናው እንዴት ይካሄዳል? ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቀዶ ሕክምናው እስከ 50 ሺህ ፓውንድ ያስከፍላል። አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ከ75 ሺህ እስከ 280 ሺህ ዶላር ያስወጣል። ቀዶ ሕክምናው ውድ ነው። ረዥም ሰዓታት ይወስዳል። ያማልም። በሕክምናው ፈር ቀዳጅ የሆኑት የሶቪየቱ ጋቪል ሊዝሮቭ ናቸው። ሕክምናውን የጀመሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉ ወታደሮችን ለማከም ነበር። ቀዶ ሕክምናው ባለፉት 70 ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ሕክምናው የሚካሄደው የእግር አጥንትን ቦርቡሮ ለሁለት ከከፈሉ በኋላ አነስተኛ ብረት በክፍተቱ በመክተት ነው። ግለሰቡ የሚፈለገው ርዝመት ላይ እስኪደርስ ብረቱ በየቀኑ አንድ ሚሊ ሜትር ከፍ እንዲል ይደረጋል። ታካሚው ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ለወራት የማገገሚያ ሕክምና ይሰጠዋል። ቀዶ ሕክምናው ነርቭ ሊጎዳ፣ የደም ዝውውር ሊገታም ይችላል። የእግር አጥንትን መልሶ ለመግጠም የሚያስቸግርበትም ጊዜ አለ። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር" ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከአምስት ዓመት በፊት ጣልያን ሲሆን፤ 3 ኢንች ጨምሯል። የእግር ቀዶ ሕክምና እንዲያደርግ የታዘዘው በሐኪሞች ምክር ነበር። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር። የእግሬ አጥንት መልሶ ሊገጥም አልቻለም። የሦስት ኢንች ክፍተት ተፈጥሮ ነበር" ይላል። ቀዶ ሕክምናው ምቾት ነስቶት እንደነበር ይናገራል። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር። የእግሬ አጥንት መልሶ ሊገጥም አልቻለም። የ3 ኢንች ክፍተት ተፈጥሮ ነበር" "እያንዳንዱ የእግሬ ነርቭ እንደተወጠረ ይሰማኝ ነበር። ህመሙ ቀላል አልነበረም።" የብሪትሽ የአጥንት ሕክምና [ኦርቶፒዲክ] ማኅበሩ ፕሮፌሰር ሀሚሽ ሲምሰን እንደሚሉት፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሕክምናው እየተሻሻለ መጥቷል። "ሂደቱ አስተማማኝ እየሆነ ቢመጣም ከአጥንት በተጨማሪ ጡንቻ፣ ነርቭ፣ የደም መዘዋወሪያ እና ቆዳን ማሳደግም ስለሚያስፈልግ ሂደቱ ውስስብ ነው" ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም የሚሠሩት ዶ/ር ዴቪድ ጎደር፤ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማዳን ብለው ደኅንነቱ በማያስተማምን ቦታ ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ይናገራሉ። ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ካካሄደ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው የመጨረሻውን የሕክምና ደረጃ ያጠናቀቀው። በስተመጨረሻ እግሩ ውስጥ የቀረው ብረት እንዲወጣ ተደርጓል። "የአንዳንዶች ቀዶ ሕክምና በስኬት ይጠናቀቃል። እኔ ግን ለማገገም ገና ጊዜ ይወስድብኛል። ሆኖም ቀዶ ሕክምናውን ማድረጌ አይጸጽተኝም። አጭር ሰዎች ከሚገጥማቸው መድልዎ ነጻ ሆኜ ሕይወቴን እንድገፋ እድል ሰጥቶኛል" ይላል።
57326605
https://www.bbc.com/amharic/57326605
በዩኬ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሰው ያልሞተባቸው ቀናት ተመዘገቡ
ዩናይትድ ኪንግደም ከመጋቢት ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፉት 28 ቀናት ውስጥ በተደረገ ምርመራ በኮቪድ ምክንያት ምንም ሰው አለመሞቱን አስታውቃለች።
በዚህም መሠረት ትናንት ማክሰኞ 3 ሺ 165 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ሰኞ ደግሞ 3 ሺ 383 ሰዎች ተይዘዋል ተብሎ ነበር። ባለፈው ሳምንት በአማካይ 2493 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ በሕንድ የታየው የኮሮናቫይረስ አይነት በዩናይትድ ኪንግደም መከሰቱን ተከትሎ በርካቶች ሲያዙ የነበረ ሲሆን በአገሪቱም ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሮ ነበር። በመንግሥት መረጃ መሠረት በሳምንቱ መጨረሻ እና መጀመሪያ አካባቢ የሚመዘገቡ የሟቾች ቁጥር አነስተኛ ነው። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የሚካሄደው ቆጠራ ስለሚቀንስና በርካታ ባለሙያዎች እረፍት ላይ ስለሚሆኑ ነው። የጤና ሚኒስትሩ ማት ሀንኮክ ከመጋቢት በኋላ ምንም ሞት ሳይመዘገብ ማደሩ ለመላው አገሪቱ ጥሩ ዜና እንደሆነና እሳቸውም ደስ እንዳላቸው ገልጸዋል። አክለውም "ክትባቶቹ በትክክል እየሠሩ ነው። ክትባቶቹ እናንተን፣ በዙሪያችሁ ያሉትን እና የምትወዷቸውን ሰዎች ከቫይረሱ እየተከላከሉ ነው''ብለዋል። "ነገር ግን ምንም እንኳን ይህ ጥሩ ዜና ቢሆንም ገና ቫይረሱን አላሸነፍነውም። አሁንም በየቀኑ የሚያዙ ሰዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት እባካችሁ እጃችሁን እና ፊታችሁን ታጠቡ፣ በቤት ውስጥ ስትሆኑ ንጹህ አየር እንዲገባ በርና መስኮት ክፈቱ፣ እድሉን የምታገኙ ከሆነ ደግሞ ሁለቱንም ዙር ክትባቶች ተከተቡ'' ሲሉ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል የእንግሊዝ የማኅበረሰብ ጤና ዳይሬክተሯ ዶክተር ይቮን ዶይል በበኩላቸው፤ ምንም ሞት አለመመዝገቡ የሚያበረታታ ነው ካሉ በኋላ አሁንም ቢሆን ሰዎች ክትባቱን ሄደው እንዲወስዱ ጥሪያቸውም አቅርበዋል። በዩናይትድ ኪንግደም በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች፣ በየቀኑ በቫይረሱ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች እና በየቀኑ ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ጥር ላይ ከነበረው አንጻር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። በተጨማሪም በዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ አዋቂዎች መካከል አንድ ሦስተኛዎቹ ሁለቱንም ዙር ክትባት ወስደዋል። በዚህም መሠረት ከ25 ሚሊየን በላይ ሰዎች ሁለት ዙር ክትባት የወሰዱ ሲሆን፤ ከ39 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የመጀመሪያ ዙር ክትባቱን አግኝተዋል።
news-41924883
https://www.bbc.com/amharic/news-41924883
የተባበሩት ምንግሥታት በየመን የዓለማችን አስከፊው ረሃብ ሊከሰት ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ
ለየመን የሚደረገው እርዳታ እደገና ካልተጀመረ ሚሊዮኖችን የሚጎዳ አስከፊው ረሃብ ሊከሰት ይችላል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣን አስጠነቀቁ።
ማርክ ሎወኮክ በሳውዲ የሚመራው ጥምር ኃይል የእርዳታ ቁሶች ወደ የመን እንዲገቡ መተባበር አለበት ብለዋል። ባለፈው ሰኞ የሁቲ አማጺያን ወደ ሳዑዲ ሚሳዬል ከተኮሱ በኋላ ጥምር ኃይሉ ወደ የመን የሚደረጉ የአየር፣ የየብስ እና የምድር መጓጓዣ ዘዴዎችን በሙሉ ዝግ አድርጓል። ሳውዲ አረቢያ ወደ የመን የሚደረጉ የመጓጓዣ ዘዴዎችን በሙሉ ዝግ ማድረጉ ያስፈለገው ኢራን የመን ውስጥ ለሚገኙ የሁቲ አማጺያን የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዳታደርግ ነው ብላለች። እአአ ከ2015 ጀርምሮ የሳውዲ መራሽ ኃይልን ስትዋጋ የቆየችው ኢራን፤ ለአማጺያኑ ምንም አይነት ድጋፍ አለደረኩም ትላለች። በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የተባበሩት ምንግሥታት እና የቀይ መስቀል ማህበር በየመን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚሹ ሚሊዮኖች እርዳታ ማቅረብ አለመቻሉን ተናግረዋል። በጦርነት እየታመሰች ያለቸው የመን የዜጎቿን ፍላጎት የምታሟለው ሁሉንም አይነት ሸቀጦች ከውጪ ሃገር በማስገባት አው። አሁን ላይ ግን ምግብም ሆነ፣ ነዳጅ አልያም መድሃኒት ወደ ሃገሪቱ ማስገባት አልተቻለም።
news-49093866
https://www.bbc.com/amharic/news-49093866
መገደል፣ መደፈር፣ መዘረፍ ማብቂያ የሌለው የኢትዮጵያውያን የስደት ጉዞ
"የሞተ ሰው ሲቀበር አይቻለሁ። ሴቶች ሲደፈሩም አይቻለሁ። ምንም ማድረግ ስለማንችል አልቅሰን ትተናቸው ነው የምናልፈው" የምትለው ዘምዘም ሃሰን ናት።
ኡመር ሰዒድ የ16 ዓመት ወጣት ሳለ ነበር ከሦስት ጓደኞቹ ጋር ወደ ሳዑዲ አረቢያ በሕገ ወጥ መንገድ የተሰደደው ይህ ዞን መዳረሻቸውን አረብ አገር ለሚያደርጉ ሰዎች የስቃይና ሰቆቃ ምናልባትም የሞትና መደፈር መነሻ ነው። ለሕገ ወጥ ደላሎች ደግሞ ይህ ዞን ኪሳቸውን የሚሞሉበት ሥፍራ ነው። ይህ ዞን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ነው። በሶማሊያ፣ በጅቡቲ እና በሱዳን በኩል አድርገው መዳረሻቸውን መካከለኛው ምሥራቅ የሚያደርጉ ስደተኞች ይህንን ዞን በየምሽቱ ይሰናበታሉ። • የትኞቹ ሃገራት ከፍተኛ ስደተኛ አላቸው? "ቀን የምንቀሳቀስ ከሆነ ልንያዝ ስለምንችል ሁልጊዜ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት እስከ ሱቢ ሶላት ድረስ ብቻ ነው የምንጓዘው" ትላለች ከአንድም ሁለቴ በሕገ ወጥ መንገድ ከአገር የተሰደደችው ዘምዘም።በስደት ላይ የሚደርስባቸው ስቃይ ያማረራቸው ወጣቶች በቃን ብለው ወደ ቀያቸው ሲመለሱ፤ ሌሎች ደግሞ የስደት ጉዞ ይጀምራሉ። ድህነትእና ሰቆቃ. . . ወጣት ኡመር ሰኢድ የ16 ዓመት ወጣት ሳለ ነበር ጂሌ ዱጉማ ከምትባል ወረዳ በመነሳት የስደት ጉዞ የጀመረው። "አንድ አረብ ማድረግ ያስጠለውን ነገር ቢያዝህ፤ እምቢ ማለት አትችልም፤ የተባልከውን ታደርጋለህ" ይላል። ከዓለም አቀፉ የስደተኖች ድርጅት (IOM) ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ድርጅቱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2018 እና 2019 ብቻ በሕገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ የተሰደዱ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 2500 ወጣቶችን ወደ ኢትዮጵያ መልሷል። ከሦስት ጓደኞቹ ጋር በሕገ ወጥ መንገድ ከአገር የተሰደደው ኡመር፤ በስደት ላይ የደረሰባቸውን በደል ሲያስብ እምባውን መቆጣጠር አይችልም። "እስከ ቦሳሶ ሱማሊያ ድረስ በእግር ነው የተጓዝነው። ቦሳሶ እስክንደርስ ከፍተኛ ስቃይ ነው የደረሰብን። በቢላዋ አስፈራርተው የለበስነው ልብስ እንኳ ሳይቀር ዘርፈውናል። የምንበላው እያጣን፤ ብዙ ጊዜ ሕይወታችንን ያተረፍነው ምግብ በመለመን ነው" ይላል። • የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ ኡመር ቤተሰቦቹ አቅመ ደካማ ስለሆኑ ትምህርቱን ከ8ኛ ክፍል ለማቋረጥ መገደዱንና የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ቢሰደድም ከየመን መመለሱን ይናገራል። ኡመር እንደሚለው ታናሽ ወንድሙም ለደላሎች 20ሺህ ብር ከከፍለ በኋላ ከስንት ውጣ ውረድ ሳዑዲ ቢደርስም ያለ ሥራ እንዲሁ ተቀምጦ ይገኛል። አቶ አንተነህ ፍቃዱ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ውስጥ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሠራተኛ ስምሪት፣ የአሠሪና ሠራተኛ አስተዳደር ክፍል ውስጥ ባለሙያ ናቸው። ከድህንነት በተጨማሪ በማህብረሰቡ ውስጥ ያለው የተሳሳተ አመለካከት፤ በዞኑ ውስጥ በስፋት ለሚታየው የሕገ ወጥ ስደት ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። ማኅበራዊ ቀውስ . . . አቶ አንተነህ በገጠርም ሆነ በከተማ ያለው ማኅበራዊ ቀውስ ወጣቶች ሕገ ወጥ ስደተን እንደ አማራጭ እንዲወስዱ ያስገድዳቸዋል ይላሉ። በዞኑ ሕጋዊ መንገድ ተከትለው ከአገር ከሚወጡት በሕገ ወጥ መንገድ ጉዞ የሚጀምሩ ወጣቶች ቁጥር ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። የተመዘገቡ አሃዞች እንደሚጠቁሙት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በሕገ ወጥ መንገድ ከዞኑ ተሰደው የነበሩ ከ11ሺህ በላይ ሰዎች ወደ ትውልድ ቀያቸው ተመልሰዋል። አቶ አንተነህ እንደሚናገሩት፤ ከተመላሾቹ መካከል ቀላል የማይባለውን ቁጥር የሚይዙት፤ የአካል ጉዳትና የአእምሮ ጤና ቀውስ አጋጥሟቸው የተመለሱ ናቸው። • "ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" አሊ ቢራ ሌላ ተስፋ . . . ዘምዘም ሃሰን ኡመር ሰኢድ ለሁለት ዓመታት የመን ቆይቶ ተመልሷል። ኡመር እንደሚለው አሁንም ቢሆን ወደዚያው ለመሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል። በአረብ አገር ያስፈልገኛል ብሎ ያሰበውን ክህሎት ለመቅሰም፤ በከሚሴ ከተማ በአንድ ተቋም ውስጥ ለህጻናትና እርዳታ ለሚሹ ሰዎች እንክብካቤ እንዴት እንደሚደረግ ስልጠና እየወሰደ ይገኛል። • "አሁን ያገኘነው ሰላም ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው"- ዘማሪ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል "በሕገ ወጥ መንገድ የስደት ጉዞ ማድረግ እጅግ አደገኛ ነው። እኔ በጣም ጠልቼዋለሁ። ሌሎች ሰዎችም የሕገ ወጥ ስደትን እንደ አማራጭ መምረጥ የለባቸውም" የምትለው ዘምዘም ሃሰን፤ 12 ዓመታትን በስደት አረብ ሃገር ቆይታ አሁን በከሚሴ ከተማ ኑሮዋን መስረታለች። "በሕገ ወጥ መንገድ እንዳይሄዱ ብዙዎችን እመክራለሁ። እነሱ ግን አይሰሙኝም" ትላለች ዘምዘም። በዞኑ የስደት ተመላሾችን ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት አስተኛ መሆኑን መታዘብ ችላናል። የዞኑ ሠረተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ ወደ አረብ አገራት ጉዞ ሚያደርጉ ወጣቶች ሕጋዊ መንገዶችን እንዲመርጡ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነ ይናገራል።
news-50025342
https://www.bbc.com/amharic/news-50025342
የዛምቢያ ፍርድ ቤት ከካናቢስ እፅ ኬክ የጋገረውን ተማሪ 'ደብዳቤ ፃፍ' በማለት ቀጣ
የዛምቢያ ፍርድ ቤት ከካናቢስ እፅ የተጋገሩ ኬኮችን ለመሸጥ እቅድ በነበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ላይ ዘለግ ያለ ደብዳቤ እንዲፅፍ ቅጣት አስተላልፏል።
ፖሊስ እንዳስታወቀው ቺክዋንዳ ችሴንደሌ 1 ኪሎግራም የሚመዝን የካናቢስ እፅ የተቀባ ኬክ ይዞ ተገኝቷል በኮፐርቤልት ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት የምህንድስና ተማሪ የሆነው ቸሂክዋንዳ ቺሴንደሌ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን 1 ኪሎግራም የሚመዝንና በካናቢስ እፅ የተቀባ ኬክ ይዞ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል። • የአሜሪካው ኩባንያ በኬንያ ካናቢስ ለማብቀል ፍቃድ አገኘ ተባለ • የስምንት ዓመት ልጁን በዕፅ አዘዋዋሪነት የመለመለው ግለሰብ ታሠረ ፍርድ ቤቱ በ21 ዓመቱ ተማሪ ላይ ከጣለው ቅጣት በተጨማሪ ለጥፋቱ በእፅ አጠቃቀም ዙሪያ 50 ገጽ ሃተታ እንዲፅፍ ፍርድ ቤቱ በይኖበታል። ፍርድ ቤቱ አክሎም ተማሪው ለዩኒቨርሲቲው፣ ለቤተሰቦችን እና ለዛምቢያ የእፅ ቁጥጥር ኮሚሽን ከሕዳር 15 በፊት የይቅርታ ደብዳቤ እንዲፅፍ አዞታል። ከዚህም ባሻገር ተማሪ ቺሴምቤል በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከምንም ዓይነት ወንጀል ራሱን እንዲያቅብ ካልሆነ ግን ለእስር እንደሚዳረግ ውሳኔ ተላልፎበታል። የእፅ ቁጥጥር ኮሚሽኑም "ሰዎችን በእፅ ለማደንዘዝ የካናቢስ ኬክ በመጋገር ያልተገባ ጥረት አድርጓል" ሲል ተማሪውን ኮንኖታል። ኮሚሽኑ ለዩኒቨርሲቲዎች ባስተላለፈው ማሳሰቢያ "በካናቢስና በሌሎች እፆች የተጋገሩ ኬኮች በተማሪዎች ዘንድ እየተዘዋወሩ ስለመሆን አለመሆኑ ዐይናቸውን ከፍተው በጥንቃቄ መከታታል አለባቸው" ብሏል። • በጀርመን ከፍተኛ መጠን ያለው ኮኬይን በቁጥጥር ሥር ዋለ በዛምቢያ ሕግ መሠረት ማሪዋና ከአደገኛ እፆች ተርታ የሚመደብ ሲሆን እፁን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው። በመሆኑም እንደ ካናቢስ ያሉ እፆችን ማዘዋወር፣ መጠቀም እና ይዞ መገኘት የገንዘብ ቅጣት አሊያም እስር ሊያስከትል ይችላል። ዛምቢያ፤ በተለይ በካናቢስ እና ሄሮይን እፅ አጠቃቀምና ዝውውር ስትፈተን ቆይታለች።
52831056
https://www.bbc.com/amharic/52831056
በሚኒሶታ የጥቁር አሜሪካዊውን ሞት ተከትሎ ቁጣ ገንፍሏል
በሚኒሶታ ክፍለ ግዛት ሚኒያፖሊስ ከተማ በነጭ ፖሊስ በግፍ የተገደለውን ጥቁር አሜሪካዊ ድርጊት ለመኮነን ሺዎች አደባባይ ወጥተዋል።
ትናንትናና ዛሬ በርካታ ሱቆች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ ቢሮዎች ተዘርፈዋል፤ ወድመዋል፤ አንዳንዶቹም እሳት ነዶባቸዋል። ለምን ንብረት ታወድማላችሁ በሚል የተጠየቀ አንድ ተቃዋሚ፣ ‹‹ምን እንድናደርግ ነው የምትፈልገው? እንዴት ነበር ድርጊቱን መቃወም የነበረብን? እየገደሉን እኮ ነው ያሉት፤ ነገሮች እስኪስተካከሉ ጊዜ ይወስዳሉ ይሉናል፤ ጊዜው አብቅቷል የሚለውን መልእክት ማስተላለፍ እንፈልጋለን›› ሲል ተናግሯል። ሰኞ ልብ የሚነካው የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በማኅበራዊ ገጾች ከተሰራጨ በኋላ ከማክሰኞ ጀምሮ የተቃውሞው መጠን እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ ባለመሄዱ የአሜሪካ ናሽናል ጋርድ (ልዩ ኃይል) ወደ ሚኒያፖሊስ ከተማ እንዲገባና ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ተቃውሞዎችን እንዲቆጣጠር ታዟል፡፡ የ46 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ጀርጅ ፍሎይድ ባለፈው ሰኞ ነበር አንድ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ተጭኖት እየተሰቃየ እንዲሞት ያደረገው፡፡ ይህ ለደቂቃዎች በመንገደኞች የተቀረጸ ተንቀሳቃሽ ምሥል እንዳስረዳው ጆርጅ ፍሎይድ ፖሊሱን ‹‹እባክህን መተንፈስ አቃተኝ፤ እባክህን አትግደለኝ›› እያለ ሲማጸነው ያሳያል፡፡ ጆርጅ ፍሎይድ በጊዜው የታጠቀው መሣሪያ አልነበረም፡፡ በአሜሪካ የጥቁር ነፍስ ዋጋ ስንት ነው? በሚል ተቃውሞዎች ሲደረጉ ረዥም ዓመታትን አስቆጥረዋል፡፡ በተለይም ነጭ ፖሊሶች በጥቁሮች ላይ ያለ በቂ ምክንያት የሚወስዱት ያልተመጣጠነ እርምጃ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በቅርብ ጊዜ እንኳ በተመሳሳይ በጠራራ ፀሐይ የተገደሉት አህመድ አርበሪ በጆርጂያ እንዲሁም ብሬኖና ቴይለር በኬንታኪ ይጠቀሳሉ፡፡ በሜኒያፖሊስ ተቃውሞው ከቁጥጥር ውጭ በመውጣቱ በከተማው ከንቲባ ጥያቄ መሰረት የሜኔሶታ ክፍለ ግዛት ገዥ ቲም ዋልትዝ ናሽናል ጋርድ (ልዩ ኃይል) ወደ ስፍራው እንዲንቀሳቀስ ፈቅዷል፡፡ የክፍለ ግዛቷ ገዥ ቲም እንደሚለው ተቃውሞን ተከትሎ በዛች ከተማ የተፋፋመው ዝርፍያና ውንብድና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች ንብረትም ለጉዳት የሰጠ ሆኗል፡፡ "የጆርጅ ፍሎይድ ሞት ወደ ውንብድናና ዝርፍያ ሊወስደን አይገባም፡፡ የፍትህ ሥርዓት እና አሠራር ለውጥን ነው መጠየቅ የሚኖርብን" ሲል ለከተማዋ ነዋሪዎች የሰላም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የሚኒያፖሊስ ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ የጥቁሩ ሞት እንዳሳዘናቸው ገልጸው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ መዝገብ እንዲከፍት ጠይቀዋል፡፡ ከጆርጅ ፍሎይድ ሞት ጋር ተያይዞ አንገቱ ላይ በጉልበቱ የቆመበትን ነጭ ፖሊስ ጨምሮ ሌሎች ሦስት ተባባሪ ፖሊሶች ከሥራቸው እንዲባረሩ ብቻ ተደርጓል፡፡ በጎርጎሳውያኑ 2014 በበኒውዮርክ ከተማ ኤሪክ ጋርነር የተባለ ጥቁር ወጣት በተመሳሳይ በነጭ ፖሊስ ማጅራቱን የፊጢኝ ተቆልፎ ትንፋሽ አጥሮት እንዲሞት መደረጉ በመላው አሜሪካ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር፡፡ ኤሪክ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ፖሊሱን ይማጸን ነበር፡፡ ይህ የኤሪክ ሞት "የጥቁሮች ነፍስ ዋጋ ስንት ነው?" (ብላክ ላይቭስ ማተር) የሚለውን አገር አቀፍ እንቅስቃሴ አቀጣጥሎት ቆይቷል፡፡ ከሜኔሶታ ሚኒያፖሊስ ባሻገር አሁን ተቃውሞ የበረታባቸው የአሜሪካ ከተሞች ኢሊኖይስ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርኒያና ቴኔሲ ናቸው፡፡ በሁሉም ከተሞች እየተስተጋባ የሚገኘው መፈክር ጆርጅ ፍሎይድ ከመሞቱ ከደቂቃዎች በፊት ይናገር የነበረው ቃል ነው፤ "መተንፈስ አልቻልኩም!"
news-50591231
https://www.bbc.com/amharic/news-50591231
የኤርትራ መንግሥት፡ ኳታር ባለስልጣኖቼን ለመግደል ዕቅድ አላት
ኳታር የተለያዩ ኃይሎችን በመጠቀም የአገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ለመግደል ዕቅድ እንዳላት እንደደረሰበት የኤርትራ መንግሥት ይፋ አደረገ።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የኤርትራ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው ኳታር የተለያዩ የሽብርና የተቃውሞ ተግባራት በኤርትራ ውስጥ እንዲፈጸሙ የማስተባበር ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን እንደደረሰበትም አስታወቀ። ለዚህም ተግባር ጎረቤት ሱዳንን እንደ ድልድይ በመጠቀም የአገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ የተለያዩ ተግባራት በኳታር ደጋፊነት እየተከናወኑ መሆናቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። • ኤርትራ፡ "ሲአይኤ መፈንቅለ መንግሥት አሲሮብኝ ነበር" • ኤርትራ በዶይቼ ቬለ ዘገባ ሳቢያ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀች 'ኳታርና ተላላኪዎቿ' እብደታቸው እያደገ ነው ብሎ የሚጀምረው መግለጫው "ኳታርና ሸሪኮቿ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎችና የፖለቲካ መሪዎች እንዲሁም ወጣቶችን በመቀስቀስ የጦር መሳሪያ እንዲታጠቁና ተቃውሞ እንዲያስነሱ ተዘጋጅታለች" ሲል ይከሳል። መግለጫው "ሙስሊም የኤርትራ ተቃዋሚዎችን ሃይማኖታዊ አስተምህሮቶችን በመስበክ በኤርትራ ሕዝብ መካከል የብሔር ጥላቻ በመዝራት፣ ሙስሊሞች በሌላው ሕዝብ ላይ እንዲነሱ የሐሰት ወሬ እያሰራጨች ነው" ይላል። በተጨማሪም በኤርትራ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳሉ የሚያሳዩ ቪድዮዎችን በማዘጋጀት ተቃውሞና አድማዎች እንዲካሄዱ በማበረታታትና የጦር መሳሪያዎችን በማቅረብ የኤርትራ መንግሥት ኳታርን ይከሳል። በዚህም የአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ተቋሞች ላይ ጥቃት እንዲፈጸምና ውድመት እንዲደርስ እንዲሁም አስፈላጊ እና ተጽእኖ ፈጣሪ የመንግሥት ባለስልጣናትን ለመግደል ስልጠና እየሰጠች ነው ይላል። • ኢትዮጵያና ኤርትራ የመጨረሻውን የሠላም ስምምነት ፈረሙ በምሥራቃዊ ሱዳን በብሔሮች መካከል ግጭት መፍጠርን በሚመለከትም 'አጃኢብ የሚያሰኝ ዕቅድ' ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን መግለጫው ያመለክታል። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ የኤርትራ መንግሥት ቱርክ እና ኳታር በኤርትራ ላይ አውዳሚ ተግባራት ለመፈጸም እየተዘጋጁ እንደሆነ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ገልጾ ነበር። ቱርክ በዚህ ዓመት 'የኤርትራ ዑላማ ምክር ቤት' በሚል የሚታወቀው ቡድን ጽህፈት ቤቱን እንዲከፍት መፍቀድዋን ጠቅሶ ይህም መግለጫው 'አውዳሚ' ላለው አላማ እንደሚውል ይገልጻል። የኤርትራ ዑላማ ምክር ቤት (መጅልስ ሹራ ራቢጣ ዑላማእ ኤሪትሪያ) በሱዳን ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንደሌለው የቡድኑ አባል የሆኑት መሓመድ ጁማ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። • የኤምሬትስና የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ፖለቲካ? የኤርትራ መንግሥት "ይህንን ከንቱ ተግባር በተለያየ መንገድ በመደገፍ በኩል ኳታርና ለእንደዚህ እኩይ አላማ ግዛቱን አሳልፎ በሰጠው የሱዳን ሥርዓት አማካይነት የሚፈጸሙ ናቸው" ሲል ከሶ ነበር። ኤርትራ ከኳታር ጋር የነበራት ጠንካራ ዝምድና በመሻከሩ በሳዑዲ አረቢያ ወደ ሚመራውን የመካከለኛው ምሥራቅ የፖለቲካ ጥምረት ፊቷን አዙራለች። ከአራት ዓመታት በፊት በየመን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ለፈጸመው በሳዑዲ የሚመራውን ኅብረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ኤርታራ አስታውቃ ነበር። ሳዑዲና አረብ ኤምሬቶች የሚገኙበት የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ጥምረት ኳታርን ካገለሉና የየብስና የባሕር መተላላፊያ ማእቀቦችን ከጣሉባት በኋላ ቱርክ የኳታር ሸሪክ መሆንዋን ይታወሳል።
news-55581626
https://www.bbc.com/amharic/news-55581626
ትግራይ፡ መከላከያ ተጨማሪ የህወሓት አመራሮችን መማረካቸውንና መገደላቸውን ገለጸ
በሕግ ከሚፈለጉ ከፍተኛ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አራቱ መገደላቸውንና ዘጠኙ ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንድ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባለስልጣን ትናንት፣ ሐሙስ ፣ማታ አስታወቁ።
ብርጋዲየር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው የስምሪት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ብርጋዲየር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ሠራዊቱ ከፍተኛ የህወሓት የፖለቲካና የወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ እያደርገ ባለው ዘመቻ ነው እርምጃው የተወሰደው። በእርምጃው ከተገደሉት መካከል ጥቅምት 24 /2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ውስጥ ለተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ምክንያት የሆነውን በሠሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት "እራስን ለመከላከል የተወሰደ ቀድሞ የማጥቃት መብረቃዊ እርምጃ" መሆኑን በቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የተናገሩት አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው ይገኙበታል ተብሏል። በተጨማሪም የህወሓት ቀደምት ታጋይና የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርዓይ አስገዶም፣ የህወሓት የመገናኛ ብዙሃን ተቋም የሆነው ድምጺ ወያኔ ኃላፊ አቶ አበበ ገብረመድኅን፣ የትግራይ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል አሰፋ ከተገደሉት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እንደሆኑ ተገልጿል። ከከፍተኛ አመራሮቹ በተጨማሪም አብረዋቸው ነበሩ የተባሉ የግለሰቦቹ ሹፌሮችና ጥበቃዎቻቸው ጭምር የመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል የጸጥታ ተቋማት ከሕዝቡ ጋር ባካሄዱት የተቀናጀ ዘመቻ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ብርጋዲየር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ገልጸዋል። በተወሰደባቸው እርምጃ ከተገደሉት አራት ሰዎች ባሻገር ሌሎች ዘጠኝ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጀነራሉ ተናግረዋል። የይፋ የሆነው የስም ዝርዝር እንደሚያሳየው የቀድሞ የትግራይ ክልል አፈጉባኤና የህወሓት መስራችና ከሚፈለጉት ግለሰቦች መካከል አንዷ የሆኑት የአቶ ስብሐት ነጋ እህት ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ፣ ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ተክለወይኒ አሰፋ በህወሓት ሥር የነበረው የእርዳታ ድርጅት (ማረት) ሥራ አስፈጻሚ፣ አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ይገኙበታል። በተጨማሪም አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር፣ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኤፈርት ቦርድ ኃላፊ ሰብሳቢ፣ ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የትግራይ ምክር ቤት ሕግ አማካሪና አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ሥራ ሂደት ኃላፊ የነበሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። ብርጋዲየር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደተናገሩት የተጠቀሱት ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች የተገደሉትና በቁጥጥር ስር የዋሉት በተለያዩ በክልሉ ውስጥ ባሉ ጫካዎችና ዋሻ ውስጥ በመከላከያ ሠራዊትና በፌደራል ፖሊስ በተደረገ ክትትልና አሰሳ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይም በተመሳሳይ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው አሰሳ የተገደሉና በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮች የስም ዝርዝር ይፋ መደረጉ ይታወሳል። እስካሁን ድረስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት ዶ/ር ደብረፂዮንም ሆኑ ሌሎች ከፍተኛ ሹማምንቶች ያሉበት ሁኔታ በዚህ መግለጫ ላይ አልተጠቀሰም። ከጥቂት ሳምንት በፊት የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል። በዚህ ምለጫም የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዓርብ ታኅሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ፣ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔርና በርካታ ወታደራዊ መኮንኖች መማረካቸውን፣ እንዲሁም በርካቶች መደምሰሳቸውን አስታወቆ ነበር። መንግሥት በቁጥጥር ስር ውለዋል ወይም ተገድለዋል ያላቸውን የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮችን በተመለከተ ከቡድኑም ሆነ ከሌላ ገለልተኛ ወገን የተሰማ ነገር የለም። የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ስትገባ የህወሓት አመራሮች ውጊያውን እንደሚቀጥሉ ከገለጹ በኋላ ስላሉበት ሁኔታና ወቅታዊ ጉዳዮች በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም። እስካሁን መገደላቸው እንዲሁም መያዛቸው ከተገለፁ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ሌላ የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማንና የቀድሞዋን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ኬርያ ኢብራሂም ጨምሮ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የቀድሞ ባለሥልጣናት ይገኛሉ። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ህወሓት ከሥልጣን መወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ አደረገው ነበር። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። በተጨማሪም የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮችም በአገር ክደትና በሠራዊት አባላት ላይ በተፈጸመ ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመንግሥት እየተፈለጉ ያሉትን የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ጠቁሞ በመንግሥት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ የሚያስችል መረጃዎችን ለሚሰጡ ሰዎች የአስር ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል መግባቱ ይታወሳል።
news-45225065
https://www.bbc.com/amharic/news-45225065
በታንዛንያ የአንድ ሰፈር ነዋሪዎች የውሃ መስመር አበላሸታችኋል በሚል በቁጥጥር ስር ዋሉ
በታንዛንያ ደቡባዊ ክፍል የምቤዬ ግዛት ፖሊስ የአንድ ሰፈር ሰዎችን በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል።
ፖሊስ ሰዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ለአካባቢው የውሃ አገልግሎት ለመስጠት የተዘረጋውን የቧንቧ መስመር ከጥቅም ውጪ አድርገውታል በማለት ነው። የእስር ትእዛዙን ያስተላለፉት የግዛቲቱ ፖሊስ ዋና ኃላፊ በበኩላቸው የሃገር ሃብት የፈሰሰበትን የውሃ መስመር በማበላሸታቸው ምክንያት በቁጥጥር እንደዋሉ ገልፀዋል። • በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው •በምስራቅ ጎጃም የመሬት መንሸራተት አደጋ የሰዎችን ህይወት ቀጠፈ •የመገንጠል መብት ለማን? መቼ? በአካባቢው ነዋሪዎች ጉዳት የደረሰበት የውሃ አገልግሎት መስጫ በብዙ ሺ ዶላሮች ወጪ የተሰራ ሲሆን፤ እስካሁን የአካባቢው ተመራጭን ጨምሮ ብዙ የአካባቢው ነዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ሁላችንም በጉዳዩ ስላልተሳተፍን የምርመራው ሂደት ንጹህ ሰዎችን እንዳያካትት እንሰጋለን እያሉ ነው። ፖሊስ በበኩሉ ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ መገልገያዎችን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ብሏል። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ይህንን ማድረግ ስላልቻሉ ለዚህ ውሳኔ እንደደረሰ ገልጿል።
news-54921441
https://www.bbc.com/amharic/news-54921441
የአሜሪካ የምርጫ ኃላፊዎች የትራምፕን ተጭበርብሯል ክስ ውድቅ አደረጉ
የአሜሪካ የምርጫ ኃላፊዎች የዘንድሮው የአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ "በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው" በማለት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ተጭበርብሯል ክስ ውድቅ አድርገዋል።
"በምርጫው ስርአት ውስጥ የተሰረዙ፣ የጠፉ እንዲሁም የተቀየሩ ድምፆች የሉም። በምንም መንገድ ምርጫው ክፍተት አልታየበትም" በማለት የምርጫው ኮሚቴው አስታውቋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለሳቸው የተሰጡ 2.7 ሚሊዮን ድምፆች ያለ ምንም ማስረጃ ጠፍተዋል መባሉን ተከትሎ ነው ኮሚቴው ይህንን የተናገረው። ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዘንድሮው ምርጫ ላሸነፉት ዲሞክራቱ ጆ ባይደንም ስልጣን ማስረከብ አለባቸው ተብሏል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተደረገውን የአሜሪካ ምርጫ ማን ሊያሸንፍ ይችላል የሚለውን ዋነኞቹ የአሜሪካ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቀድመው ተንብየው ነበር። ጆ ባይደን በአሪዞና አሸንፈዋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም የኤሌክቶራል ኮሌጅ ድምፃቸውን ወደ 290 ከፍ ያደርገዋል፤ ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ያገኙት የኤሌክቶራል ኮሌጅ አጠቃላይ ውጤት 217 ነው። አሪዞና ከጎሮጎሳውያኑ 1996 በኋላ ዲሞክራትን ስትመርጥ ለመጀመሪያ ጊዜም ነው ተብሏል። ውጤቱን በፀጋ አልቀበልም ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ቁልፍ በሚባሉ የአሜሪካ ግዛቶች ክስ ጀምረዋል። ተጨባጭ ማስረጃ የሌላቸው ሰፊ ማጭበርበር ተፈፅሟልም እያሉ ነው። ከምርጫው ሳንወጣ ዝም ብላ የነበረችው ቻይና ለተመራጮቹ ጆ ባይደንና ካማላ ሃሪስ እንኳን ደስ ያላችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፋለች። "የአሜሪካውያንን ምርጫ እናከብራለን" በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አስታውቋል። ሩሲያ በበኩሏ ኦፊሴላዊ ውጤትን እንደምትጠብቅ ተናግራለች።
news-55822135
https://www.bbc.com/amharic/news-55822135
ምዕራባውያኑ የትግራዩን ግጭት ተከትሎ ያላቸውን ስጋት ዳግም ገለጹ
የአሜሪካ ዲፕሎማቶች፣ የተባበሩት መንግሥታት እና አውሮፓ ሕብረት ተወካዮች በትግራይ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ስጋት ገለጹ፡፡
ከግራ ወደ ቀኝ፤ አምባሳደር ፓርቲሺያ ሃስላች፣ ዴቪድ ሺን፣ ኡሬሊያ ብራዜለ እና ቪኪ ሃድልስተን። ስጋታቸውን ከገለጹት መካከል አራት የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደሮች ይገኙበታል። አራቱ የቀድሞ አምባሳደሮች ጽኑ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ነው፡፡ አምባሳደሮቹ በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት እንዳሳሰባቸው ለሪፖርተር ጋዜጣ በላኩት ይፋ ደብዳቤ አስታውቀዋል። አራቱ የቀድሞ አምባሳደሮች በትግራይ የተከሰተውን ግጭት በአጽንኦት መከታተላቸውን እና ግጭቱን ተከትሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቅለው አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ጠባቂዎች መሆናቸው እጅጉን እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከ60ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ስለመሸሻቸው፣ ወደ 2.2 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በክልሉ ውስጥ መፈናቀሉን እና 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ ደግሞ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው የተባበሩት መንግሥት ድርጅት አሐዞች ይጠቁማሉ። የአገሪቱ መንግሥት በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር 2.5 ሚሊዮን ብቻ መሆኑን እና ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እንዲሁም መድኃኒት እያቀረበ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጿል። ደብዳቤውን የጻፉት አራቱ የቀድሞ አምባሳደሮች አምባሳደር ዴቪድ ሺን፣ ኡሬሊያ ብራዜለ፣ ቪኪ ሃድልስተን እና ፓርቲሺያ ሃስላች እንደ አውሮጳዊያን አቆጣጠር ከ1996 እስከ 2016 ባሉት ዓመታት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል። አራቱ የቀድሞ አምባሳደሮች ለጠቅላይ ሚንስትሩ በጻፉት ደብዳቤ፤ በአገሪቱ ዘርን መሠረት ያደረገ ውጥረት እያየለ መምጣቱ፣ የጥላቻ ንግግር መበራከቱ እንዲሁም ብሔርን እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረገ ግጭት እዛም እዚህም መስፋፋቱ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። በተመሳሳይ የአገልግሎት ጊዜያቸውን እያጠናቀቁ ያሉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር ትናንት በኤምባሲያቸው ጋዜጠኞችን ጠርተው አነጋግረዋል። አምባሳደሩ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ እየወጡ ባሉ ሪፖርቶች ዙሪያ በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ተሰናባቹ አምባሳደር ግጭቱን ተከትሎ ተፈጽመዋል ስለተባሉ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ ጠይቀዋል። የተባበሩት መንግሥት በትግራይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ሪፖርቶች እየደረሱት መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል። አምባሳደሩ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በበቂ ሁኔታ እርዳታ እየደረሳቸው ስላልሆነ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ በጎ አድራጊ ተቋማት ድጋፋቸውን በአስቸኳይ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች የአውሮፓ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮችን ተቀብለው አነጋግረዋል። የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በትግራይ ክልል እየተደረገ ስለሚገኘው የሰብዓዊ ድጋፍ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስተባባሪ ለሆኑትን ካትሪን ሶዚን (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል። ካትሪን ሶዚ (ዶ/ር)፤ ክስተቱን ተከትሎ መንግሥት እያደረገ ያለው ምላሽ የሚደነቅ እንደሆነ፤ ከሁኔታው ጋር ተያይዞ የተሰራጩትን የተዛቡ መረጃዎችን በድርጅታቸው በኩል ለማጣራት እንደሚንቀሳቀሱ ስለመናገራቸው የሰላም ሚንስቴር በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል። በተመሳሳይ መልኩ የፋይናንስ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት ተወካይን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በውይይቱ ላይ አህመድ ሺዴ በትግራይ ያለውን መልሶ ግንባታ እና የሰብዓዊ ድጋፍ በማስመልከት መንግሥት እያከናወነ ስላለው ተግባር ማስረዳታቸውን ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ኤሪክ ሃቤርስ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትን በተመለከተ ለነበራቸው ስጋት የፋይናንስ ሚንስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል ብሏል የፋይናንስ ሚኒስቴር። አህመድ ሺዴ በውይይቱ ወቅት በትግራይ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን እና ይህም የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል ተብሏል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በሚገኘው ሠራዊቱ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት ተሰንዝሯል በሚል ነበር ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ሠራዊቱ በክልሉ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበርና "ወንጀለኛውን ቡድን" ለሕግ ለማቅረብ የተወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ እንደሆነ ገልጸዋል። የፌደራሉ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ ከተቆጣጠረ በኋላ ውጊያውን እንደሚቀጥሉ ያሳወቁትን የህወሓት አመራሮችን ለመያዝ አሰሳ እያካሄደ ይገኛል። እስካሁንም በርካቶች መያዛቸውንና መገደላቸው የአገሪቱ ሠራዊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
news-54384869
https://www.bbc.com/amharic/news-54384869
ኢሬቻ ፡ በበዓል ላይ ጥብቅ የደኅንነት ቁጥጥር እንደሚደረግ ተጠቆመ
ነገ እና ከነገ ወዲያ በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች በሚከበረው ዓመታዊው የኢሬቻ በዓል ላይ ጥብቅ የደኅነነት ቁጥጥር እንደሚደረግ ተጠቆመ።
የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ በዓሉ ወደ ብጥብጥ ለመቀየር አቅደው እና ተዘጋጅተው በአራቱም አቅጣጫ የሚንቀሳቀሱ አካላት ስላሉ በዚህም ምክንያት አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ትናንት በቢሾፍቱና በአዲስ አበባ ከተሞች በርካታ ሕዝብ ታድሞበት ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ጥቃቶች ለመፈጸም፣ ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ሲያቅድ የነበረ ቡድን በቁጥጥር ሥር እንዲውል አድርጊያለሁ ማለቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ስላለ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የሚያስገቡ መንገዶች ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፉት ሁለት ቀናት ወደ አዲስ አበባ ከተማ የተጓዙ ሰዎች በመንገድ ላይ በርካታ ጊዜ ለፍተሻ መቆማቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለምሳሌ ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው 120 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው መንገድ ላይ 8 ጊዜ መፈታሻቸውን ተጓዦች ገልጸዋል። የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከምሥራቅ ሐረርጌ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ የተጓዘ አንድ ወጣት ደግሞ መንገድ ላይ ለበርካታ ጊዜ በተደጋጋሚ መንገድ ላይ እንዲቆሙ እተደረጉ መፈተሻቸውን ተናግሯል። ይህ ወጣት የክልሉ ጸጥታ አስከባሪዎች አንዳንድ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሲያውሉ መመልከቱንም ጨምሮ ተናግሯል። አቶ ጌታቸው ይህ ፍተሻ የበዓሉን ደኅንነት ለማረጋግጥ ታስቦ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰው፤ "ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ የተከለከለ ሰላማዊ ሰው ግን የለም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዛሬ ጀምሮም ዝግ የሚደረጉ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች መኖራቸው ተነግሯል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ትናንት የኢሬቻ በዓል ላይ ረብሻ ለመፍጠር ሲዘጋጁ ነበር ያሏቸውን ከ500 በላይ ሰዎችን መያዛቸውን አስታውቀዋል። ከተጠርጣሪዎቹ በተጨማሪ የጦር መሳሪያዎች እና በርካታ የእጅ ቦምቦች መያዛቸውን ፖሊስ ኮሚሽነሩ ጨምረው ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት በዓሉ ላይ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ከዚህ ቀደም ይታደሙ ከነበሩ ሰዎች ቁጥር አንጻር ሊቀንስ እንደሚችል ተጠቁሟል። መንግሥት እስካሁን በዚህ በዓል ላይ መታደም ያለበት ሰው ቁጥር ይህን ያክል ነው አለማለቱን የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። "መታደም ያለበት ሰው ቁጥር ይህን ያክል ነው ማለቱ የመንግሥት ድርሻ አይደለም። ይህን የሚወስኑት አባ ገዳዎች ናቸው" ብለዋል። አባ ገዳዎች ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ሰዎች ምስጋናቸውን የሚያቀርቡበትን ቦታ ይከፍታሉ ከዚያ በኋላ የፈለገ ወደ ውሃው ዳርቻው ሄዶ ምስጋናውን ማቅረብ ይችላል ብለዋል። አባ ገዳ ጎበና ሆላ "የጸጥታውን ጉዳይ የጸጥታ ሰዎች፤ የጤናውን ጉዳይ ደግሞ የጤና ሰዎች እንዲያስፈጽሙ ተስማምተናል" ብለው ነበር። የአርቲስት ሃጫሉን ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በርካታ ሰዎች በበርካታ ቁትር ተጠጋግተው አደባባይ የወጡባቸው ብዙ አጋጣሚዎች መከሰታቸውን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የቫይረሱ ስርጭት በ500 በመቶ መጨመሩን አቶ ጌታቸው ያስታውሳሉ። በዚህም ምክንያት የበዓሉ ተሳታፊዎች እራሳቸውን ከኮሮናቫይረስ ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ መልዕክት አስተላልፈዋል።
news-50944601
https://www.bbc.com/amharic/news-50944601
ኢትዮጵያ፡ በ2020 ግጭት ይበረታባቸዋል ከተባሉ ሥፍራዎች መካከል ትገኛለች
ክራይሲስ ግሩፕ የተሰኘው ተቋም ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት [2020] ግጭት ሊበረታባቸው ከሚችሉ አገራት መካከል አንዷ ልትሆን ትችላለች ሲል ይፋ አድረገ።
በተለያዩ የዓለማችን አገራት ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን የሚከታተለው ተቋሙ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት 2020 ዓ.ም ግጭት እጅግ ገዝፎ ሊታይባቸው ይችላል ያላቸውን 10 አገራት ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ሦስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። • የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደቤታቸው ለመላክ ለምን ወሰነ? • ህወሓት፡ ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች በተቋሙ ዝርዝር አናት ላይ የምትገኘው አፍጋኒስታን ስትሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ተባብሶ የቀጠለው ግጭት በሚመጣው ዓመትም [2020] የሚያባራ አይመስልም ይላል። በሁለተኛ ደረጃ ላይ ደግሞ የመን የምትገኝ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታትም የመን የዓለም አቀፉን ማሕበረሰብ ትኩረት የምትሻ ሃገር ሲል ማወጁ አይዘነጋም። የየመን ጦርነት ቢያንስ የ100 ሺህ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያም የአረቡ ዓለም ደሃ አገር የሆነችው የመን ረሃብ እያጠቃት ይገኛል። ኢትዮጵያ 2020 ለኢትዮጵያ ተስፋና ስጋት የደቀነ ዓመት ሲል 'ክራይሲስ ግሩፕ' ይገልፀዋል። በሕዝብ ብዛት ምሥራቅ አፍሪካን የምትመራው የቀጣናው 'ኃያል' አገር ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መምጣት በኋላ ብዙ ለውጦችን አይታለች። ሚያዝያ 2010 ዓ.ም ሥልጣን የጨበጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የፖለቲካ ምሕዳሩ እንዲከፈት ብዙ ተራምደዋል ይላል የተቋሙ ዘገባ። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች አልፎም ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ለዓመታት የዘለቀውን ጠላትነት ማስወገድ መቻላቸው፣ የፖለቲካ እሥረኞችን መፍታታቸው፣ ስደት ላይ የነበሩ ተቃዋሚ ኃይሎች በነፃነት አገር ቤት እንዲንቀሳቀሱ መፍቀዳቸው እና ተቋማዊ ለውጦችን ማካሄዳቸው መልካም እመርታ ነው ሲል ተቋሙ ይዘረዝራል። በአገር ቤት ከተሰጣቸው እውቅና ባለፈም በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ክብር ተሰጥቷቸዋል ሲል የኖቤል የሰላም ተሸላሚነታቸውን ያነሳል። ነገር ግን ከፊታቸው ከባድ ፈተና ተደቅኗል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መምጣት በፊት የነበሩ ተቃውሞዎች ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ መጎሳቆል የወለዳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብሔር ተኮር ይዘት ያላቸው ናቸው፤ በተለይ ደግሞ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ ከእሳቸው ቀደም ብሎ በነበረው ሥርዓት መዋቅር ላይ ለውጥ ያካሄዱበት መንገድ ብሔር ተኮር ፖለቲካ የበለጠ እንዲያብብ እና ማዕከላዊው መንግሥት እንዲዳከም ዕድል ፈጥሯል ሲል ተቋሙ ትዝብቱን ያስቀምጣል። • በሞጣ የተፈጠረው ምንድን ነው? የብሔር መልክ ያላቸው ግጭቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸው እንዲጠፋ ምክንያት ሲሆን ሚሊዮኖች እንዲፈናቀሉ አድርጓል። አልፎም በክልሎች መካከል መቃቃር እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል ብሏል ሪፖርቱ። ከጥቂት ወራት በኋላ እንደሚከናወን የሚጠበቀው አገራዊ ምርጫ ግጭት እንዲበረታ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተቋሙ ስጋቱን ገልጿል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ የሚጠቅሰው ዕጩዎች ድምፅ ለማግኘት በሚያደርጉት ግብግብ ብሔርን መሠረት ያደረገ ፉክክር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ የሚለው አስተሳሰብ ነው። አገሪቱ በይፋ የምትተዳደርበት ብሔርን የተንተራሰ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ሌላኛው ለግጭት መፋፋም እንደ ቤንዚን ሊሆን የሚችል ነው ባይ ነው ተቋሙ። ነገር ግን የሥርዓቱ ደጋፊዎች አሁን ያለው ፌደራላዊ አወቃቀር እንደ ኢትዮጵያ ላለ የብሔር ስብጥሩ ለገዘፈበት አገር አዋጭ ነው ሲሉ ይከራከራሉ። የሥርዓቱ አውጋዦች ደግሞ ፌዴራሊዝም አንድነት የሚባለውን ሃሳብ የሚያፈርስና ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ነው ሲሉ ይተቹታል። ኢሕአዴግን አክስመው አንድ ሃገራዊ ፓርቲ ያቋቋሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በሚቀጥለው ምርጫ ከብሔር ተኮር ፌዴራሊስቶች ከፍተኛ ፉክክር እንደሚገጥማቸው ይጠበቃል። • የትግራይና የፌደራል መንግሥቱ ግንኙነት በጣም አሳሳቢ ነው- ዶ/ር አብረሃም ተከስተ ኢትዮጵያ እያለፈችበት ያለው ለውጥ ትልቅ ተስፋ ያለውና ድጋፍ የሚሻ ቢሆንም ስጋት የተጫጫነው መሆኑ ሊካድ አይገባውም ይላል ተቋሙ በሪፖርቱ አክሎም አንዳንዶች አገሪቱ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደሆነች ስጋታቸውን እንደሚገልጹ አመልክቷል። ክሎም የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ ኃያል አገራት ኢትዮጵያዊያን ፖለቲከኞች ግጭት ቀሳቃሽ ንግግሮችን ከማሰማት እንዲቆጠቡ ግፊት ማድረግ አለባቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አገሪቱን ይታደጓት ዘንድም የገንዘብ እርዳታ ማድረግ ይገባቸዋል ሲል ክራይሲስ ግሩፕ አቋሙን ያንፀባርቋል። ሎሎች በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ሃገራትና ቀጣናዎች ቡርኪናፋሶ፣ ሊቢያ፣ አሜሪካ-እስራኤል-ኢራን እና የፋርስ ባሕረ-ሰላጤ በጋራ፣ አሜሪካ-ከሰሜን ኮሪያ፣ ካሽሚር፣ ቬንዝዌላና ዩክሬን ናቸው።
49055713
https://www.bbc.com/amharic/49055713
ምግብ ወሲብን የተሻለ ያደርጋል?
ወሲብና ምግብን ምን ያገናኛቸዋል? ብለው ይጠይቁ ይሆናል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት አመጋገባችን እና የወሲብ ሕይወታችን ቀጥተኛ ትስስር አላቸው።
ደስታ የሚፈጥር ንጥረ ነገር ያላቸው ምግቦች ጤናማ የወሲብ ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋሉ። ከነዚህ ምግቦች ጥቂቱን እናስተዋውቃችሁ። 1. ቃርያ፣ ሚጥሚጣ. . . ካፕሳይሲን የሚባለው ንጥረ ነገር ቃርያ፣ ሚጥሚጣ በመሰሉ የሚያቃጥሉ ምግቦች ውስጥ ይገኛል። ሰዎች ደስታ ሲሰማቸው የሚመነጨው ኢንዶርፊን ሆርሞን እንዲዘዋወር ቃርያና ሚጥሚጣ ያግዛሉ። በተጨማሪም የደም ዝውውርን ያፋጥናል። የሰውነት የሙቀት መጠንና የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨምርም ይረዳል። እነዚህ በወሲብ ወቅት ሰውነታችን ላይ የሚስተዋሉ ለውጦች ናቸው። • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? 2. ቸኮሌት ቸኮሌት ፊኒሌትያላሚን የሚባል ንጥረ ነገር አለው። ቸኮሌት መብላትና በፍቅር መክነፍ የሚያያዙትም በዚህ ንጥረ ነገር ምክንያት ነው። ንጥረ ነገሩ የፍቅር ግንኙነት ሲጀመር ደስ የሚል ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል። ቸኮሌት ውስጥ ትራይፕቶፋን የተባለ አሚኖ አሲድ ይገኛል። ይህም ሰውነት ውስጥ ደስታ የሚያመነጭ ሴሮቶይን የሚባል ንጥረ ነገር እንዲዘዋወር ይረዳል። ትራይፕቶፋን ከእንቁላል፣ ከለውዝ፣ ከሶያ ምርቶችም ሊገኝ ይችላል። • ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን? ቸኮሌትና የወሲብ ሕይወት መካከል ግንኙነት አለ መባል የጀመረው ከ16ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ ነው። 3. አልኮል ወሲብን የተሻለ ያደርጋል? አልኮል የወሲብ ተነሳሽነትን ቢጨምርም፤ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚደረግበት ወቅት ተጽዕኖ ሊያሳድርም ይችላል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ከመጠን በላይ መጠጣት የወሲብ ፍላጎትን ይቀንሳል። የአልኮል ሽታ ስለሚረብሽም የወሲብ ሕይወት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። • እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ''ደካማ ነው'' ተባለ 4. ፍራፍሬዎችስ? ጥናቶች እንደሚያሳዩት የብልት አለመቆም ችግር ያለባቸው ወንዶች ፍላቮኖይድ የተባለ ኬሚካል የያዙ ምግቦች እንዲመገቡ ይመከራል። ለምሳሌ ብሉቤሪ የተባለ የእንጆሪ ዝርያ፣ ብርቱካንና ሎሚም ችግሩን ይቀርፋሉ። የተለያዩ ፍራፍሬዎችን መመገብ የብልት አለመቆም ችግርን 14% ይቀንሳል። • የአለም የምግብ ቀን: አስገራሚ የአለማችን ምግቦች ከአትክልት፣ ፍራፍሬዎች፣ የወይራ ዘይትና ለውዝ በተጨማሪ የሜዲትራኒያን አካባቢ ምግቦች የብልት አለመቆም ችግርን እንደሚቀርፉም ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ቼሪ፣ ብላክቤሪ የተባለው የእንጆሪ አይነት፣ የወይን ፍሬ እና ቀይ ጥቅል ጎመን አንቶካይኒን የያዙ ምግቦች ናቸው። ሲጠቃለል. . . የወሲብ ሕይወትን እንደሚያሻሽሉ የሚነገርላቸው አፍሮዲሲያክ የተባሉ ምግቦችን በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል። አንደኛው የወሲብ ፍላጎት፣ ሁለተኛው ወሲብ የመፈጸም ብቃትና ሦስተኛው ከወሲብ የሚገኝ ሀሴት ናቸው። በእርግጥ ተመራማሪዎች እነዚህን ውጤቶች መለካት አልቻሉም። እንዲያውም እስካሁን በእርግጠኛነት መናገር የቻሉት አፍሮዲሲያክ የቆዩ ፍራፍሬዎችን ሽታ ነው። ዶ/ር ክሪችማን የተባሉ የተባሉ የሥነ ተዋልዶ ጤና ተመራማሪ እያንዳንዱ ሰው የተሻለ የወሲብ ሕይወት እንዲኖረኝ ረድቶኛል የሚለውን ምግብ እንዲያዘወትር ይመክራሉ። አብዛኞቹ አፍሮዲሲያክ የሚባሉ ምግቦች ጤናማ ምግቦች ናቸው። ወሲብ የተሻለ እንዲሆን ይረዳሉ የሚባሉ ነገር ግን ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን አለመጠቀም ይመከራል። አንዳንዴ የወሲብ ፍላጎት አናሳ ሲሆን ከጤና ችግር ጋር ሊያያዝ ስለሚችል ሀኪም ማማከር ያሻል።
news-53782014
https://www.bbc.com/amharic/news-53782014
ናይጄሪያ፡ ለአመታት በቤተሰቦቹ ጋራዥ ውስጥ ተቆልፎበት የነበረው ናይጄሪያዊ ነፃ ወጣ
ከወገቡ በታች እርቃኑን ሆኖ ያለ ድጋፍ መንቀሳቀስ የማይችል ሆኖ ነው ፖሊስ ያገኘው።
ናይጀሪያዊው ግለሰብ በቤተሰቦቹ ጋራዥ ውስጥ ለሶስት አመታት ያህል ተቆልፎበት ነበር ብሏል ፖሊስ። በሰሜናዊዋ ናይጄሪያ ካኖ ከተማ በሚገኝ ጋራዥ የቆለፉበት ቤተሰቦቹ ናቸው። የ32 አመቱ አህመድ አሚኑ የተገኘው ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ ነው። ጥርጣሬ ያደረባቸው ጎረቤቶቹ ሂውማን ራይትስ ኔትወርክ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅትን ስለ አህመድ ሁኔታ ያሳውቃሉ። አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለሰባት አመታትም ያህል ተቆልፎበት እንደነበር ነው። አህመድ ነፃ በወጣበት ወቅት የተቀረፀ ቪዲዮ እንደሚያሳየው በከፍተኛ ሁኔታ የገረጣ፣ አጥንቱ የገጠጠና የተጎሳቆለ ሲሆን መራመድ አቅቶትም በድርጅቱ ሰራተኞችም ድጋፍ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። ቪዲዮውም በማህበራዊ ሚዲያ የተጋራ ሲሆን አሰቃቂም ነው ተብሏል። አጥንት ብቻ የሆነው ሰውነቱም ብዙዎችን አስደንግጧል። "አህመድን ስናገኘው በተጎሳቆለ ሁኔታ ነው። ከተቆለፈበት ጋራዥም መውጣት ስለማይችል ባለበት ቦታም ነው የሚፀዳዳው። ምግብም የሚሰጠውም አይመስልም። ሞቱን እየተጠባበቀ ያለም ነው የሚመስለው። በጣም አሰቃቂ ነው" በማለት የሂውማን ራይትስ ኔትወርክ ኃላፊ ሃሩና አያጊ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአህመድ አባትና እንጀራ እናቱም በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ምርመራ እንደተከፈተባቸውም የፖሊስ ቃለ አቀባይ ሃሩና ኪያዋ በመግለጫቸው አትተዋል። አህመድ አደንዛዥ ዕፅ ይጠቀማል በሚል ጥርጣሬ ለአመታት እንደቆለፉበት፣ አየርም አግኝቶ እንደማያውቅ ተገልጿል። ምግብም በበቂ ሁኔታ እያገኘ ስላልነበር የጤናውም ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል። በናይጄሪያ በቤተሰቦቹ ተቆልፎበት እንዲህ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገኝ አህመድ በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለተኛው ነው። በዚህ ሳምንት ረቡዕ በሰሜናዊ ምዕራብ ናይጄሪያ ኬቢ ግዛት ለሁለት አመታት ያህል በእንስሳ በረት ተቆልፎበት የነበረ የአስር አመት ታዳጊ ነፃ ወጥቷል። የቆለፉበት ቤተሰቦቹ ናቸው የተባለ ሲሆን በፖሊስ እገዛም ነው የወጣው።
52289891
https://www.bbc.com/amharic/52289891
ኮሮናቫይረስ፡ ከኮቪድ-19 ያገገሙት የአዳማ ነዋሪ ምን ይላሉ?
"ወንድ ልጄን ኮሪደር ላይ ሳየው በጣም ደነገጥኩኝ፤ ጮኬ ወደቅኩ። ቤተሰቦቼ በአጠቃላይ እዚያ ያሉ ነው የመሰለኝ" ይህን ያሉት በአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና በኮቪድ-19 ተይዘው የነበሩት የፋርማሲ ባለሙያ ናቸው።
አቶ ዳግማይ በቀለ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው እንደታወቀ የተወሰዱት አዲስ አበባ ወደ ሚገኘው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሲሆን፤ እዚያ ተኝተው በሚታከሙበት ወቅት ልጃቸውን ማየታቸውን የፈጠረባቸውን ስሜት ነበር ለቢቢሲ ያጋሩት። አቶ ዳግማይ በቀለ የአዳማ ከተማ ነዋሪ ናቸው፤ ከሁለት ሳምንት በፊት መጋቢት 18/2012 ዓ.ም ነበር በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ጤና ጥበቃ ያስታወቀው። እኚህ የ61 ዓመት አዛውንት አዲስ አበባ በሚገኘው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሲታከሙ ቆይተው በአሁን ጊዜ ከቫይረሱ በማገገማቸው አዳማ ወደ ሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰዋል። የፋርማሲ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳግማይ፣ ቫይረሱ እንዴት ሊይዛቸው እንደቻለ እንደማያውቁ ይናገራሉ፤ ነገር ግን አንዳንድ ምልክቶችን በማየታቸው ራሳቸውን ለመለየት ስለፈለጉ ከቤተሰባቸው ርቀው ሆቴል ተከራይተው መቀመጣቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። "ራሴን ስለጠረጠርኩኝ ከዚህ እስከምወጣ ማንም ሰው እኔ ጋር እንዳይመጣ፤ ከመጣም የእጅ ጓንትና ጭምብል አድርጎ ይምጣ በማለት ለሆቴሉ ሠራተኞች ጭምር ተናግሬ ነበር" ብለውናል። የኮቪድ-19 ምልክቶች የተባሉትን ራሳቸው ላይ ማየት እንደጀመሩ አዳማ ከተማ ወዳሉ የጤና ተቋማት መሄዳቸውን ይናገራሉ። እንደ አቶ ዳግማይ ከሆነ ማንም ቫይረሱ አለብህ ሊላቸው አልቻለም። ከዚያም ይላሉ አቶ ዳግማይ "ወደ ጤና ጥበቃ ደውዬ ያመኛል ነገር ግን የሚመረምረኝ ሰው አላገኘሁም ብዬ ነገርኳቸው። ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወደ ኦሮሚያ ጤና ቢሮ ከዚያም ወደ አዳማ ከተማ ተደውለ" በማለት በወቅቱ እንዴት መመርመር እንደቻሉና ቫይረሱነም እንደተገኘባቸው ያስረዳሉ። አቶ ዳግማይ በቀለ የኮቪድ-19 በማስመልከት አዳማ ላይ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል ነበሩ። መጀመሪያ ደረቅ ሳል ያስለኝ ነበር የሚሉት አቶ ዳግማይ በመቀጠልም ጉሮሮዋቸው ውስጥ የመብላት የማሳከክ ስሜት እንደጀመራቸው ይናገራሉ። • ዴንማርክ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የዘጋችውን በሯን ለመክፈት ለምን ቸኮለች? • ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮሪያውያን ጭምብልና ክሊኒኮች በተዘጋጁበት ሁኔታ ምርጫ እያካሄዱ ነው "ኮሮና ይሆን ብዬ በቀልድ ሳወራ ሰዎች አይ አይደለም ሳይነስ ነው የተነሳብህ እንጂ ኮሮና አይደለም ይሉኝ ነበር።" በመቀጠልም ከባድ ራስ ምታት እንደጀመራቸውና ሰውነታቸውም መደካከም እንደጀመረ ያስታውሳሉ። "ትንሽ ያሳሳተኝ የሰውነቴ ሙቀት ረዘም ላለ ጊዜ ከ36 በልጦ አያውቅም፤ ሁልጊዜም ከሦስት እስከ አራት በሚሆን ሰዓት ልዩነት ውስጥ የሰውነቴን ሙቀት እለካ ነበር። ከዚያ በኋላ አንድ ቀን ማለዳ ስለካ ሙቀቴ 38 ሆኗል፤ በዚህ ጊዜ እርሱ ነው[ኮሮና] ብዬ መያዜን ተጠራጠርኩኝ።" ከዚህ በኋላ የድጋፍ አሰባሳቢው ኮሚቴ ስብሰባ መካፈል ማቆማቸውን ይገልፃሉ። የአዳማ ከተማ የኤካ ኮተቤ ቆይታና ድንጋጤ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች የሚቆዩበትና ህክምና የሚከታተሉበት ሆስፒታል ነው። በዚህ ሆስፒታል ውስጥ ከ20 ቀናት በላይ እንደቆዩ የሚናገሩት አቶ ዳግማይ በሆስፒታሉ ውስጥ ከ10 ቀን በላይ ከባድ ህመም ላይ እንደነበሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የህክምና ባለሙያዎችም የሜካኒካል ቬንትሌተር ገጥመውልኝ እና የተለያዩ መድኃኒቶች ሲሰጡኝ ነበር" በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ለሰባት ወይንም ለስምንት ቀናት ምግብና ውሃ እንዳልወሰዱ ከወሰዱም ደግሞ ያስመልሳቸው እንደነበር ያስረዳሉ። አቶ ዳግማይ በከባድ ህመም ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ባለቤታቸውና የ14 ዓመት ወንድ ልጃቸው በበሽታው ተይዘው ወደ ሆስፒታሉ መጡ። "ለሦስትና ለአራት ቀን ደብቀውኝ አልተገናኘንም ነበር" የሚሉት አቶ ዳግማይ "እኔም በወቅቱ ከባድ ህመም ላይ ነበርኩ" ብለዋል። እርሳቸው ወደ ሆስፒታል ከገቡ ከሦተኛው ቀን በኋላ ወደ ባለቤታቸው በመደወል መያዛቸውን መስማታቸውን ይገልፃሉ። በዚህ ወቅት ስለልጆቻቸው ጤንነት የጠየቁት አቶ ዳግማይ ሁሉም ደህና መሆናቸው እንደተነገራቸው ገልፀዋል። ነገር ግን ብዙም ሳይቆዩ ባለቤታቸው የተኙበት ክፍል ድረስ በመምጣት ሲያናግሯቸውና እርሳቸውም መያዛቸውን ሲግሯቸው አዘኑ። • ትራምፕ ለዓለም ጤና ድርጅት የሚሰጠው ገንዘብ እንዲቋረጥ አዘዙ ወንድ ልጃቸው በበሸታው እንደተያዘ ያልተነገራቸው አቶ ዳግማይ ልጃቸውን ሆስፒታል ውስጥ በማየታቸው ከባድ ስሜት እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ። "ከአምስት ቀን በኋላ ወደ ንጽህና መስጫ እየሄድኩኝ ልጄን ኮሪደር ላይ አየሁት በጣም ደንግጬ ጮህኩና ወደኩኝ፤ ከዚያ በኋላ ደብቀንህ ነው እንጂ እዚህ ከገባን አንድ ሳምንት ሆኖናል አሉኝ" ይላሉ። አቶ ዳግማዊ፣ ባለቤታቸውና ልጃቸው በአሁኑ ሰዓት አገግመው አዳማ ወደሚገኘው ቤታቸው ተመልሰዋል። በእርግጥ አቶ ዳግማይ አሁንም በመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ እንደሚተነፍሱ ነግረውናል። "እንደኔ ራሱን የሚጠብቅ ሰው የለም" የሚሉት አቶ ዳግማይ ሕዝቡ ስለኮሮናቫይረስ በደንብ ማወቅ አለበት ሲሉ ይመክራሉ። የዓለም ጤና ድርጅትና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር የሚሰጡትን ምክር መስማት ያስፈልጋል ሲሉም ያብራራሉ። እጅን ቶሎ ቶሎ መታጠብ፣ ሳኒታይዘር መጠቀም፣ ከተቻለ የአፍ መሸፈኛ ማድረግ አለብን በማለትም መጨባበጥን ማስወገድና ርቀትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባሉ። "ግዴታ የሌለባቸው ቤት መቆየት አለባቸው፤ ከቤት መውጣት አያስፈልግም፤ ቤት ሲሆኑም ደግሞ አልጋ ላይተኝቶ ቴሌቪዥን ማየት ብቻ ሳይሆን መጽሀፍ ማንበብ፤ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል። እኔ ራሴ አሁን ጠዋት ከ30 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ያህል ስፖርት ከልጄ ጋር እሰራ ነበር" ሲሉ ልምዳቸውን ያጋራሉ። በመጨረሻም "ለራስ የምናስብ ከሆነ፣ ለሕዝብም እናስባለን፤ ይህንንም መጥፎ ወቅት አብረን እንሻገራለን፤ አገራችንንም እንጠብቃለን" ብለዋል።
news-55610108
https://www.bbc.com/amharic/news-55610108
የአውሮፓ ሕብረት በትግራይ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች ጠየቀ
የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከተወያዩ በኋላ በሁሉም የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች ጠየቁ።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሱዳን ተሰደዋል የእርዳታ ድርጅቶች ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የክልሉን አንዳንድ አካባቢዎች አንዲጎበኙ የተፈቀደላቸው ቢሆንም ይህ ከህወሓት ጋር ውጊያዎች የተካሄዱባቸውን ሁሉንም የክልሉን አካባቢዎች የሚያካትት አይደለም ተብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በምግብ አቅርቦት እጥረትና በዘረፋ ሳቢያ አሳሳቢ ነው ሲል ገልጾታል። የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊው ጆሴፍ ቦሬል በትግራይ ክልል ውስጥ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር መመቻቸት አለበት ብለዋል። ኃላፊው ጨምረውም ይህ ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት መፈጸም ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉና ኤርትራዊያን ስደተኞችን የሚያስጠልሉ ሁለት የስደተኛ ካምፖችን ለመጎብኘት እንዳልቻለ ማመልከቱ ይታወሳል። የስደተኛ ካምፖቹን የሚያሳዩ የሳተላይት ምሰሎች የዓለም ምግብ ፕሮግራም ህንጻን ጨምሮ በካምፖቹ ውስጥ የሚገኙ ቤቶች መውደማቸውን አመልክተዋል ተብሏል። በቅርቡ አንድ ወታደራዊ አዛዥ የኤርትራ ወታደሮች ኢትዮጵያ ውስጥ መግባታቸውን ያመኑ ሲሆን የኤርትራ ሠራዊት አባላት የተለያዩ በደሎች ፈጽመዋል በሚል በርካታ ክሶች ሲሰነዘሩባቸው ቆይቷል። የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ከገባች በኋላ በነበረው ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ከተባበሩት መንግሥታት ጋር የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚያስችሉ መስመሮችን ለማመቻቸት ከስምምነት መድረሱ ይታወሳል። ነገር ግን አሁን ድረስ የእርዳታ ድርጅቶች በግጭቱ ሳቢያ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠው ለቆዩ የክልሉ ነዋሪዎችና በካምፖች ለሚገኙ ስደተኞች አስፈላጊውን የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላቸው ያልተገደበ ፈቃድ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ይገኛሉ። በህወሓት ኃይሎችና በፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት መካከል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የትራንስፖርትና ኮምዩኒኬሽን ግንኙነት መስመሮች በክልሉ ውስጥ ተቋርጠው የቆዩ ሲሆን፤ መቀለ ከተማ ከተያዘች በኋላ መንግሥት በጦርነቱ የተጎዱ መሰረተ ልማቶች ተጠግነው ክልሉን ክፍት እንደሚደረግ ገልጾ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታትና የተለያዩ የተራድኦ ድርጅቶች በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ስለሚገኙ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦት መስመሮችን እንዲያመቻች እየጠየቁ ነው። በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ጦርነቱን ሸሽተው ወደ ሱዳን መግባታቸው የተነገረ ሲሆን በክልሉ ውስጥ ያሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል። ይህ ቀውስ የተከሰተው የትግራይ ክልልን ያስተዳድር የነበረው የህወሓት ኃይሎች በአገሪቱ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በጥቅምት ወር መጨረሻ አካባቢ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ነው።
news-54876534
https://www.bbc.com/amharic/news-54876534
አሜሪካ፡ ጆ ባይደንን እንኳን ደስ አለዎት ያላሉት መሪዎች የትኞቹ ናቸው?
ጆ ባይደን የአሜሪካ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ በርካታ የዓለማችን መሪዎች እንኳን ደስ አለዎት ለማለት ፈጥነዋል።
ነገር ግን ሁሉም የዓለም አገር መሪዎች በአንድ ድምጽ የጆባይደን ፕሬዝዳንት ሆኖ መመረጥ ደስታ እንደፈጠረባቸውና አብረው ለመስራትም ዝግጁ መሆናቸውን አልገለፁም። በተመራጭ ፕሬዝዳንቱ መመረጥ የተሰማቸውን ካልገለፁ የዓለማችን መሪዎች መካከል የሩሲያው ፕሬዝዳንት አንዱ ናቸው። ከአራት ዓመት በፊት ፕሬዝዳንት ፑቲን ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ቀድመው እንኳን ደስ አለዎት ካሉ መሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ። አሁን ግን ምንም ዓይነት የትዊት፣ የቴሌግራም ወይንም የስልክ መልዕክት አልላኩም። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲምትሪ ፔስኮቭ እንኳን ደስ አለዎት ለማለት የዘገዩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የምርጫውን ውጤት በማስመልከት የመሰረቱት ክስ ነው ብለዋል። ''እኛ ትክክለኛው ነገር ብለን የምናስበው የምርጫው ውጤት በይፋ ሲገለጽ ነው'' ብለዋል ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቆይታ። ነገር ግን ሞስኮ የሚገኘው የቢቢሲው ዘጋቢ ስቲቭ ሮዝንበርግ ከሞስኮ በኩል የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አለመላኩ በውጤቱ ደስተኞች አለመሆናቸውን ያስጠረጥራል ይላል። ጆ ባይደን ቀንደኛ የሩሲያ ተቺ ሲሆኑ በቅርቡም የአሜሪካ ትልቋ ጠላት ሩሲያ ናት ብለው ነበር። ከ2016ቱ ምርጫ ጋር በተያያዘም ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች በማለት ይከሳሉ ባይደን። ሌላኛው ምንም አስተያየት ያልሰጡት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይብ ኤርዶጋን ናቸው። በ2016 በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ ማሸነፋቸው ከተነገረ ከአንድ ቀን በኋላ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ስልክ በመደወል የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን አስተላልፈው ነበር። በተመሳሳይ 2012 ላይ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሲያሸንፉ እንኳን ደስ አለዎት ብለው ነበር። ኤርዶጋን ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ጠበቅ ያለ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ባለፉት አራት ዓመታት አሜሪካ ቱርክ ላይ በሩሲያ በኩል ሊጣሉ የሚችሉ ማዕቀቦችን መከላከል ችላለች። አንዳንድ የአካባቢው ተንታኞች ኤርዶጋን እስካሁን ምንም ያላሉት ወዳጃቸው ዶናልድ ትራምፕን ላለማስከፋት እንደሆነ እየገለጹ ነው። ነገር ግን ከዚህ በኋላ ጆ ባይደንን እና ቱርክ የሚኖራቸው ግንኙነት ወደፊት የምናየው ነው።
news-55112959
https://www.bbc.com/amharic/news-55112959
እግር ኳስ ፡ ከማራዶና ሞት ጋር በተያያዘ ፖሊስ ሐኪሙ ላይ ምርመራ ጀመረ
የአርጀንቲና ፖሊስ በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ሞት ጋር ተያይዞ የዝነኛውን እግር ኳስ ተጫዋች ሐኪም እየመረመረ ይገኛል።
ዶ/ር ሊኦፖልዶ ሉኬ ፖሊስ በዋና ከተማዋ ቦነስ አይረስ የሚገኘውን የዶ/ር ሊዮፖልዶ ሉኮን መኖርያ ቤትና የግል ክሊኒክ በርብሯል። ምርመራው ሊጀመር የቻለው ማራዶና የተሳካ የተባለ ቀዶ ህክምና ማድረጉን ተከትሎ በድንገት መሞቱ ምናልባት የሕክምና ቸልተኝነት ተጫዋቹን ለሞት ዳርጎታል የሚል ጥርጣሬ በመፈጠሩ ነው። የ60 ዓመቱ የእግርኳስ ኮከብ የሞተው ከ4 ቀናት በፊት በልብ ድካም ነው። ማራዶና ከሕመሙ እያገገመ ሳለ ነበር በድንገት የሞተው። ዶ/ር ሊዮፖልዶ እስካሁን ክስ አልተመሰረተበትም። ሆኖም አንድም ጥፋት የለብኝ ሲል እንባ እየተናነቀው ለጋዜጠኞች ተናግሯል። ማራዶና ከመሞቱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የተሳካ የተባለ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና አድርጎ ነበር። ቀዶ ጥገናው ያስፈለገው በጭንቅላቱ ውስጥ የደም መርጋት ምልክቶች በመታየታቸው ነበር። በሚቀጥለው ወር ደግሞ ከአልኮል ሱስ ለመውጣት አዲስ ሕክምና ይጀምራል ተብሎ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር። የማራዶና ሴት ልጆች ስለ አባታቸው የሕክምና ሁኔታ ምርመራ እንዲደረግ ግፊት አድርገዋል ተብሏል። ትናንት እሑድ ወደ 30 የሚሆኑ ፖሊሶች የማራዶና የግል ሐኪም ወደ ሆነው የ39 ዓመቱ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ቤት በድንገት በመድረስ ብርበራ አድርገዋል። ሌሎች 20 የሚሆኑ ፖሊሶች ደግሞ ክሊኒኩን ፈትሸዋል። ፖሊስ የማራዶና የመጨረሻ ቀናት ሕክምና ምን ይመስል እንደነበር ለመፈተሽ ነው ፍላጎቱ። ኮምፒውተሮችን፣ ስልኮቹንና የሕክምና ማስታወሻዎችን ጭምር አንድ በአንድ እየመረመሩ ነው ተብሏል። ፖሊስ ጥርጣሬ አለኝ የሚለው የማራዶና ቀዶ ጥገናን ተከትሎ ምናልባት ሐኪሙ ሊያደርጋቸው ይገቡ የነበሩ ጥንቃቄዎችን ሳያደርግ ቀርቶ ከሆነ በሚል ነው። ማራዶና ቀዶ ጥገናውን አሳክቶ ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ እንዲያገግም የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ነበሩ ወይ? የሚለው በምርመራው ይካተታል። ለምሳሌ 24 ሰዓት በተጠንቀቅ የሚንከባከቡት ነርሶች መኖር፣ በአደገኛ እጽ ሱስ ለሚሰቃይ ሰው ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች መኖር፣ በአስቸኳይ ሊጠሩ የሚችሉ ሐኪሞች እና በተጠንቀቅ የሚቆም አምቡላንስ ነበረ ወይ? የሚለው ይፈተሻል። መርማሪ ፖሊስ ዶ/ር ሊዮፖልዶ እነዚህ ሁኔታዎች ለታማሚው አሟልቶ ነበር ወይ፣ የሐኪሙ የመጨረሻ ቀናትን ምን ይመስላሉ የሚለውን እየመረመረ ነው። የ39 ዓመቱ የማራዶና የግል ሐኪም ዶ/ር ሊዮፖልዶ ደንበኛው ከሞተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት ዝምታውን ሰብሯል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ ስሜታዊ ሆኖ በእንባ እየታጠበ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የማራዶናን ሕይወት ለማትረፍ የሚችለውን ሁሉ እንዳደረገለት ተናግሯል። ማራዶና በመጨረሻ ቀናት ከፍተኛ ሐዘን ይሰማው እንደነበረም ጠቅሷል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ በጋዜጠኞች በእንዝህላልነት ለደንበኛው መሞት ተጠያቂ ይሆን እንደሆነ ሲጠየቅ በቁጣ እንዲህ መልሷል፣ "እኔ ተጠያቂ የምሆነው በምን ምክንያት እንደሆነ ልናገር? ማራዶናን በጣም በመውደዴ፣ ለእሱ በጣም እንክብካቤ በማድረጌ፣ በአጭር ይቀጭ የነበረውን ሕይወቱን በማራዘሜ፣ እስከመጨረሻው ከእሱ ጋር በመሆኔ ነው መጠየቅ ካለብኝ" ሲል በድንገተኛ ቁጣ ገንፍሎ ምላሽ ሰጥቷል። ፖሊስ በበኩሉ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ለማራዶና ቀዶ ጥገና ካደረገለት በኋላ ክትትል ማድረግ ሲገባው አላደረገለትም ብሎ ጠርጥሮታል። በዚህ ረገድ ዶ/ር ሊዮፖልዶ ሲመልስ "የእኔ ሙያ የአንጎል ቀዶ ህክምና ነው። እኔ ህክምናውን ጨርሻለሁ" በማለት ማራዶና ከእሱ ክሊኒክ ከወጣ በኋላ ላለው ነገር ተጠያቂ እንዳልሆነ አስገንዝቧል። ዶ/ር ሊዮፖልዶ እንደሚለው ማራዶና ከቀዶ ህክምናው በኋላ መሄድ የነበረበት ወደ አደገኛ እጽ ማገገሚያ ማዕከል እንጂ ወደ ቤት አልነበረም። ማራዶና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሳለ ቤቱ የተዘጋጀና የሕክምና ቁሶች የተሟሉለት አምቡላንስ እንዴት ላይኖር ቻለ የሚለው እያነጋገረ ነው። ማራዶና በመጨረሻው ሰዓት ልጆቹንም፣ ቤተሰቡንም ማስጠጋት አልፈለገም፣ ከፍ ያለ ሐዘን ይሰማው ስለነበር ብቻውን መሆን ፈልጓል ሲል ሐኪሙ አብራርቷል። ማራዶና የድኅረ ዝና መስቅልቅልና የኮኬይን ሱሰኝነት ለሕይወቱ ማጠር ሚና እንደነበራቸው ይታመናል።
news-54725930
https://www.bbc.com/amharic/news-54725930
የአሜሪካ ምርጫ የሕዳሴ ግድብ ፖለቲካን እንዴት ሊቀይር ይችላል?
የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሊካሄድ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እና ዲሞክራቱ ጆ ባይደን የሚያደርጉትን የምረጡኝ ዘመቻቸውም እያጠናቀቁ ይገኛሉ። ወደ 70 ሚሊዮን የሚጠጉ አሜሪካውያንም ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ይህን የአሜሪካ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሜሪካውያን ብቻ ሳይሆኑ መላው ዓለም በአትኩሮት የሚመለከተው ጉዳይ ነው። የዚህ የምርጫ ውጤትም መጠን እና ስፋቱ ይለያይ እንጂ በሕዳሴ ግድብ ፖለቲካ ላይ ተጽእኖ ሊያመጣ እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ ወዳጅነት አላቸው። አሜሪካ "በሽብር" ላይ ከፍታ በነበረው ጦርነት በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ አንዷ ትልቋ አጋር ኢትዮጵያ ሆና ቆይታለች። ይሁን እንጂ በቅርቡ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ካለችው የኃይል ማመንጫ ግድብ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምታደርገው ድጋፍ 130 ሚሊዮን ዶላር መከልከሏ ይታወሳል። በግድቡ ጉዳይም አሜሪካ ለግብጽ ወግና ቆማለች። ይህንንም ፕሬዚደንት ትራምፕ በአደባባይ አንጸባርቀዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ግብጽ የሕዳሴ ግድቡን "ልታፈነዳው ትችላለች" ሲሉ ተደምጠዋል። ለመሆኑ የምርጫው ውጤት በሕዳሴ ግድብ ፖለቲካ ላይ የሚኖረው ለውጥ ምንድነው? 'አሜሪካ ግብጽን ትታ ለኢትዮጵያ አትወግንም' በዩናትድ ኪንግደም በሚገኘው ኪል ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አወል አሎ (ዶ/ር) ሪፐብሊካኖቹም ይሁኑ ዲሞክራቶች ምርጫውን ቢያሸንፉ የነበረውን የአሜሪካ የውጪ ፖሊስ የሚያስቀጥሉት ይላሉ። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊስ ሁልጊዜም ቢሆን በአገሪቱ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መሆኑን በማስታወስ የምርጫው ውጤት በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል የቆየውን ግነኙነት ያን ያህል ሊቀይር እንደማይችል ይናገራሉ። የተለየ የሚያደርገው "ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም አቀፍ ሕግ እና ስምምነቶች ተገዢ የሚሆኑ ሰው አይደሉም የሕዝቡን ትኩረት ለማግኘት ከእርሳቸው የማይጠበቅ ንግግር ይናገራሉ" ይላሉ። ትራምፕ አንዳንድ ጊዜ እንደ ፕሬዚዳንት ሳይሆን "ልክ እንደ ሰባት ዓመት ልጅ ይናገራሉ" ይላሉ። ስለ ሕዳሴ ግድብ በቅርቡ የተናገሩትም ለዚሁ ሁነኛ ማሳያ መሆኑን አወል አሎ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። ቀድሞውንም ቢሆን በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ አሜሪካ ግብጽን ገሸሽ አድርጋ ፊቷን ወደ ኢትዮጵያ ታዞራለች ብሎ ማሰቡ ስህተት መሆኑንም ጠቆም ያደርጋሉ። አሜሪካ በመካለኛው ምስራቅ አገራት ልዩ ፍላጎቶች እንዳላት የሚያስረዱት አዎል (ዶ/ር) ከእነዚህም መካከል ዋነኛው የእስራኤልን ፍላጎት ማስጠበቅ ነው ይላሉ። ለአሜሪካ ሁነኛ ወዳጅ ለሆነችው እስራኤል ደግሞ እውቅና እና ድጋፍ ስታደርግ የቆየችው ተጽእኖ ፈጣሪ የአረብ አገር ግብጽ መሆኗንም ያወሳሉ። ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ከደረሱ እና ለእስራኤል እውቅና ከሰጡ ጥቂት የአረብ አገራት መካከል አንዷ ግብጽ መሆኗ ይታወቃል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ፤ "ትራምፕ ፒስ ፕላን" በተባለው እቅዳቸው ለእስራኤል እና ፍልስጥኤም ግጭት መፍትሄ ያሉትን አማራጭ እየተገበሩ ይገኛሉ። በቅርቡም የተባበበሩት ዩናይትድ አረብ ኤምሬት እና ባህሬን ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ደርሰዋል። ጎረቤት አገር ሱዳንም ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ለመፈረም በዝግጅት ላይ ትገኛለች። አዎል አሎ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንት ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈው ለሁለተኛ ዙር የሰልጣን ዘመን በዋይት ሃውስ የሚቆዩ ከሆነ በዚሁ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲያቸው የሚቀጥሉ ይሆናል ይላሉ። ዲሞክራቶችም ቢሆኑ ይህን ምርጫ ቢያሸንፉ በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ውስጥ የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ቁልፍ ነገር ስለሆነ ለኢትዮጵያ ለውጥ ይዞ እንደማይመጣም ይገልፃሉ። ይሁን እንጂ ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ ጉዳዩን ትራምፕ እየሄዱበት ባለው መንገድ ሳይሆን የሚያስቀጥሉት ዓለም አቀፍ ሕግ እና ስምምነቶችን ተከትሎ እንደሚሆንም ያስረዳሉ። የትራምፕ አስተዳደር ያቋረጠውን የገንዘብ እርዳታም ጆ ባይደን ሊያስቀጥሉ እንደሚችሉ በመጠቆም ይሁን እንጂ የጆ ባይደን አስተዳደርም ግብጽን ትቶ ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ ያዞራል ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም ይላሉ። በሌሎች አገራት ላይ ግን የምርጫ ውጤት ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ ዲሞክራቶች ወይስ ሪፐብሊካን . . . ? ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ብርሃኔ ቤካ የዋሺንግተን ዲሲ ነዋሪ ሰትሆን ከዲሞክራት ፓርቲ ጋር አብራ እንደምትሰራ ትናገራለች። ብርሃኔ፤ "ሰልጣን መልሰን ለመያዝ ትልቅ ቅስቀሳ እያደረግን ነው" ትላለች። ብርሃኔ የመምረጥ መብት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዲሞክራት እጩዎች ድምጻቸውን እንዲሰጡ ቅስቀሳ እያደረጉ መሁኑን በመጥቀስ አብዛኛው የመምረጥ መብት ያለው ስደተኛ ድጋፉን እየገለጸ ያለው ለጆ ባይደን ፓርቲ ነው ትላለች። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዲሞክራቱ ባራክ ኦባማ ለሥራ ጉብኝነት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አስታውሳ ዲሞክራቶች ምርጫውን ቢያሸንፉ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የተሻለ ግንኙነት እንደሚኖራቸው ትናገራለች። ሌላኛው ትውልድ ኢትዮጵያዊት እና ከአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ጋር አብራ የምትሰራው ሴና ጂምጂሞ ይህ የአሜሪካ ምርጫ ለአሜሪካውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ወሳኝነት አለው ትላለች። ሴና ዲሞክራቶች በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ አሜሪካ ከአፍሪካ ጋርም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር የተሻለ ግነኙነት ነበራት ትላለች። የትራምፕ አስተዳደር ለሁለተኛ ዙር በስልጣን እንዲቆይ እድሉን የሚያገኝ ከሆነ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው ግድብ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ታስረዳለች። የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጥቅምት 24 ይካሄዳል።
news-56411412
https://www.bbc.com/amharic/news-56411412
ታንዛኒያ ስለጠፉት ፕሬዝዳንት አሉባልታ ያሰራጩ ዜጎቿን አሰረች
የታንዛኒያ ፖሊስ አራት ዜጎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊን በተመለከተ አሉባልታን አስወርተዋል በሚል ነው፡፡
የ61 ዓመቱ አወዛጋቢ ፕሬዝዳንት ከሁለት ሳምንታት በላይ ለሕዝባቸው በይፋ አልታዩም፡፡ ይህንን ተከትሎ የተለያዩ አሉባልታዎች በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች እየወጡ ነው፡፡ አንዳንዶች ፕሬዝዳንቱ ኮሮና ይዟቸው በሕንድ እየታከሙ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ ሰውየው ደህና ናቸው፤ በየቀኑ ለሕዝባቸው በቴሌቪዥን የመታየት ግዴታ የለባቸውም፤ ፕሬዝዳንት እንጂ ዜና አንባቢ አይደሉም ይላሉ፡፡ የአሉባልታውን መባዛት ተከትሎ የታንዛኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሲም ማጃሊዋ ባለፈው ሳምንት ማጉፉሊ በሰላምና በጤና ሥራቸውን ጠንክረው እየሰሩ ነው ብለው ተናግረው ነበር፡፡ ሆኖም ተቃዋሚዎች ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር በፍጹም አልተቀበሉትም፡፡ የተቃዋሚ መሪዎች እንደሚሉት ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ምናልባት በሚሳለቁበት በሽታ በኮቪድ ተይዘው ለሕክምና ከአገር ውጭ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ማጃሊዋ እንደሚሉት ግን እንዲህ ዓይነት አሉባልታ ማስወራት ከጥላቻ የሚመነጭ ነው፡፡ ‹ፕሬዝዳንቴን ማጉፉሊን በስልክ አግኝቼዋለሁ፤ ሕዝቤን ሰላም በልልኝ ብሎኛል› ብለዋል አርብ ዕለት፡፡ ትናንት ሰኞ ደግሞ የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሚአ ሱሉሁ ‹ታንዛናዊያን እባካችሁ ሐሜትና አሉባልታ አትስሙ› ሲሉ ሕዝባቸውን መክረዋል፡፡ ‹አንድ ሰው መታመሙ፣ ጉንፋን መያዙ፣ ትኩሳትም ቢኖረው ብርቅ አይደለም፤ አንድነታችን ላይ ማተኮር ያለብን ጊዜ ነው አሁን፤ በጸሎት አንድ መሆን አለብን› ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሚአ፡፡ ሆኖም ምክትል ፕሬዝዳንቷ ይህ አነጋገራቸው ስለ ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ይሁን አይሁን ግልጽ አላደረጉም፡፡ የቢቢሲዋ ዘጋቢያችን ሙኒራ ሁሴን ከዳሬሰላም እንደጻፈጻችው አሉባልታ አውርታችኋል ተብለው የታሰሩት አራቱ ሰዎች ከታንዛኒያ የተለያዩ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንት ማፉፉሊ በእርግጥ የት ነው ያሉት የሚለው ጉዳይ በየዕለቱ እያነጋገረ ሲሆን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ቱንዱ ሊሱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሁነኛ የወሬ ምንጭ ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ኮቪድ ተይዘው በናይሮቢ ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ ነግሯቸዋል፡፡ ተቃዋሚው ጨምረው እንዳሉት ጆን ማጉፉሊ አሁን በልብ ሕመም እየተሰቃዩ ሲሆን በሞትና በሕይወት መካከል ናቸው ሲሉም አብራርተዋል፡፡ ሌላ ስሙን ለደኅንነቱ ሲል የደበቀ የተቃዋሚ መሪም በተመሳሳይ ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ በጠና መታመማቸውን መስማቱን ለቢቢሲ ተናግሯል፡፡ ማጉፉሊ በኮቪድ ሲሳለቁ የኖሩ መሪ ሲሆኑ ዜጎቻቸው ስለ ኮቪድ እንዳይጨነቁና በጸሎታቸው እንዲበረቱ ይናገሩ ነበር፡፡ ማጉፉሊ በአንድ ወቅት ኮቪድ ውሃ በመታጠን እንዲሁም በባህላዊ መንገድ ቅጠላቅጠልና ሥራሥር በመጠቀም የሚፈወስ ተራ በሽታ ነው ሲሉም ተናግረው ያውቃሉ፡፡
news-55127127
https://www.bbc.com/amharic/news-55127127
ትግራይ ፡ የመቀለው አይደር ሆስፒታል የሕክምና መገልገያ እያለቀበት መሆኑ ተገለጸ
በመቀለ ከተማ የሚገኘው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል አስፈላጊ የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች እያለቁበት እንደሆነ ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል አስታወቀ።
በግጭቱ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሕክምና እየሰጠ ያለው ሆስፒታሉ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ተገልጿል። ያሳለፍነው ቅዳሜ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት መቀለን እንደተቆጣጠረ እና ሦስተኛው ምዕራፍ ዘመቻ ምዕራፍ እንደተጠናቀቀ መናገራቸው አይዘነጋም። የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ግን ትግሉን እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ቀይ መስቀል ምን አለ? ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር እንዳለው፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አምቡላንሶች በግጭቱ ሳቢያ የተጎዱና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል እያጓጓዙ ነው። ሆስፒታሉን የጎበኙ የድርጅቱ ባልደረቦች "80 በመቶው ታካሚዎች በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። ሌሎች ሕክምናዎች ቆመው ለድንገተኛ አደጋ ብቻ አገልግሎት እየተሰጠ ነው" ብለዋል። የማኅበሩ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ማሪያ ሶልዳድ "ቁስል ለመስፋት የሚውል መገልገያ፣ ጸረ ተህዋሰ መድኃኒት፣ የህመም ማስታገሻ እና ሌሎችም መድኃኒቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እያለቁ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የሞቱ ሰዎችን አስክሬን ማቆያ ፕላስቲክኮች እየጨረሱ መሆኑንም ኃላፊዋ ተናግረዋል። ማኅበሩ ምን ያህል ሰዎች እንደተጎዱና እንደሞቱ ምንም መረጃ አልሰጠም። ተጎጂዎቹ ወታደሮች ይሁኑ ሲቪሎች አልተገለጸም። ጠቅላይ ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው፤ "በትግራይ እየተካሄደ የነበረው ወታደራዊ ዘመቻ ተገባዷል" ብለዋል። በህወሓት ተይዘው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማስለቀቅ እንደተቻለ እንዲሁም መከላከያ ሠራዊቱ በከተማዋ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ ቁልፍ መሥሪያ ቤቶችን እንደተቆጣጠረም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህ የተካሄደው "ለንጹሀን ዜጎች ጥንቃቄ ተደርጎ ነው" ብለዋል። ለሮይተርስ በጽሑፍ መልዕክት ያስተላለፉትና አሁን የት እንደሚገኙ ያልታወቀው የህወሓት መሪ በደብረጽዮን "ጭካኔው በትግላችን እስከመጨረሻው ድረስ እንድንገፋ ያበረታታናል" ብለዋል። በክልሉ የቴሌቭዥን ጣቢያ የተላለፈ የህወሓት መግለጫ፤ "በደረሰው ድብደባ ንጹሀን ዜጎች ተገድለዋል፣ ተጎድተዋልም። እኛም ለጥቃቱ ምላሽ እንሰጣለን" ይላል። ተንታኞች እንደሚሉት፤ ህወሓት ወደ ሽምቅ ውጊያ አምርቶ ሊሆን ይችላል። የሰብአዊ ጉዳት ስጋቶች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መቀለ ላይ ጥቃት ካደረሰ የጦር ወንጀል ሊፈጸም ይችላል ሲል አስጠንቅቆ ነበር። የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች መተላለፊያ አለማግኘታቸው እንዳሰጋውም ድርጅቱ አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብአዊ እርዳታ መንገድ እንደሚመቻች መግለጹ ይታወሳል። መንግሥት ንጹሀን ዜጎችን ለመጠበቅ ከተባበሩት መንግሥታት እንደሚተባበርም ተገልጿል። ከትግራይ ክልል ወደ ሱዳን የገቡ ስደተኞች እንደተናገሩት፤ በክልሉ አዋሳኝ ድንበር ላይ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ስደተኞች ወደ ሱዳን እንዳያቋርጡ እያገዷቸው ነው። ግጭቱ ከተከሰተ ወዲህ ከ40 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ተናግሯል።
news-49380063
https://www.bbc.com/amharic/news-49380063
በባለቤታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ያልጠበቁት የገጠማቸው አሜሪካዊ አዛውንት
ከሳምንት በፊት ኤል ፓሶ ቴክሳስ ውስጥ በተፈጸመ የጅምላ ግድያ ሚስታቸውን ያጡት አዛውንት በሚስታቸው የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ ባልጠበቁት ሁኔታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመገኘታቸው ደንግጠው ነበር።
አዛውንቱ አንቶንዮ ባስኮ ዘመድ አዝማድ ስላልነበራቸው ለባለቤታቸው ቀብር ላይ በዙሪያቸው የሚኖሩ ሰዎችን ብቻ ነበር በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዲገኙ የጠሩት። • በቴክሳሱ ጅምላ ጥቃት 20 ሰዎች ሞተዋል አንቶንዮ ጥቂት ሰዎች በባዶው የቤተክርስቲያን አዳራሽ ወስጥ በመገኘት የሃዘናቸው ተካፋይ በመሆን ለባለቤታቸው የመጨረሻ ስንብት ያደርጋሉ ብለው ነበር የጠበቁት። ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አዳራሹ ለመግባት ተሰልፈው ሲመለከቱ በጣም ነበር የደነገጡት። ለቀብር ሥነ ሥርዓቱ የተገኘው ሕዝብ ቁጥር አዳራሹ ከሚችለው በላይ ስለነበረ ቀብሩን የሚያስፈጽመው ድርጅት ስንብቱ ሰፋ ባለ አዳራሽ እንዲካሄድ አድርጓል። ሚስታቸውን በታጣቂ ጥይት የተነጠቁት ሃዘንተኛው አዛውንትም ሊያጽናኗቸው በተሰበሰቡት ሰዎች ብዛት ተደንቀው "የማይታመን ነው!" በማለት ነበር መደነቃቸውን የገለጹት። • የኦሃዮው ታጣቂ እህቱንና ስምንት ሰዎችን ገደለ • አሜሪካ ውስጥ አንድ ታጣቂ ስድስት ፖሊሶችን አቆሰለ አንድ ታጣቂ በገበያ አዳራሽ ውስጥ በፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት 22 ሰዎች መካከል አንዷ ለሆኑት የ63 ዓመቷ ባልቴት የአንቶኒዮ ባለቤት ማጊ ሬካርድ የመጨረሻ ስንብት የተሰበሰበው ሰው 700 እንደሚደርስ ተነግሯል። ሰልፉም ረጅም የነበረ ሲሆን ለአዛውንቱ ሃዘናቸውን ለመግለጽ በርካታ ሰዎች ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች መጥተው ነበር። ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው ከ900 በላይ የአበባ ጉንጉኖች ከእስያ አህጉር ጭምር ለስንብት ሥነ ሥርዓቱ ተልኳል።
news-50206432
https://www.bbc.com/amharic/news-50206432
የአንበጣ መንጋው እስካሁን በሰብል ላይ ጉዳት አላደረሰም
ከሰሞኑ በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አላደረሰም ሲል የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የአማራ ክልል የግብረና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን አሰፋ (ዶ/ር) የአማራ ክልል የግብረና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን አሰፋ (ዶ/ር) ለቢቢሲ እንዳስታወቁት መንጋው የተከሰተው ክልሉን ከአፋር ጋር በሚያዋስኑ ወረዳዎች ነው። "በሰሜን ወሎ፤ በራያ ቆቦ እና ሃብሩ ወረዳዎች፤ በደቡብ ወሎ ደግሞ ወረባቦና አርጎባ እንዲሁም በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ደዌ ሃረዋ፣ ባቲ እና አርጡማ ፉርሲ" የአምበጣ መንጋው መከሰቱን አስረድተዋል። • የኢትዮጵያን በቆሎ እያጠቃ ያለው ተምች የአንበጣ መንጋው ወደ አማራ ክልል ከመዛመቱ በፊት በአፋር እና ሶማሌ ክልል የመከላከል ሥራዎች ቢሠሩም ከጥቅምት ወር ጀምሮ ወደ አማራ ክልል ገብቷል። አንበጣው ጉዳት እንዳያደርስ የተለያዩ የመከላከያ ዘዴዎች ተግባራዊ መደረጉን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አስታውቀዋል። "ያደገው አንበጣ ሰብል የማይበላ ቢሆንም ለእርባታ ምቹ ሁኔታን ካገኘ እንቁላሉ ሙሉ የዕድገት ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ አውዳሚ ስለሆነ ለበልግና መስኖ ስራ አስቸጋሪ ይፈጥራል ስለዚህም የመከላከል ስራ እየተሠራ ነው" ይላሉ አቶ ሰለሞን። "በመኪና፣ በሰው በአውሮፕላንን እንዲሁም በባህላዊ መንገድ እየተከላከልን ነው።" በአውሮፕላን የታገዘው የመድኃኒት ርጭት በትላንትናው ዕለት ደዌ ሃረዋ አካባቢ ሲሰራ ቆይቷል። እስካሁን የአንበጣ መንጋው ኢኮኖሚያዊ ጉዳት አላደረሰም ያሉት ኃላፊው ክልሎች እና ግብርና ሚኒስቴርን በማቀናጀት የህይወት ሂደቱን ካለቋረጥን በበልግ እና በመስኖ ሥራችን ላይ ችግር ስለሚፈጥር መረባረብ አለብን ብለዋል። • ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ክልል በትግራይ ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ዞኖች ተመሳሳይ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል። የአከባቢው ነዋሪዎች በባህላዊ መንገድ የአምበጣ መንጋውን ለማበረር ቢጥረም እየተደረገ ያለው ጥረት ግን እጅግ አድካሚ እና የተፈለገውን አይነት ውጤት እያስገኘ አለመሆኑ ተነግሯል። የአንበጣ መንጋው ባለፈው ዓመት ሰኔ መጀመሪያ ላይ ነበር ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የገባው።
49994237
https://www.bbc.com/amharic/49994237
ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች
በትናንትናው ዕለት መስከረም 28፣ 2012 የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚህ ሹኩሪ ፓርላማ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ላይ የውሃ ሙሌቱን መቀጠሏ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
"ኢትዮጵያ በኦፕሬሽኑ ቀጥላለች፤ የህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት መቀጠሏ ተቀባይነት የለውም። ይህ ተግባር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ እና በቀጠናው ላይ አለመረጋጋትን በመፍጠር አሉታዊ ተጽእኖ ያስከትላል" በማለት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። •ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን? የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም "ዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ሁሉንም አካላት የሚያስማማ መፍትሄ በማፍለቅ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን" ማለታቸው ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። • በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም፡ ግብጽ የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ መስከረም 23 እና 24 በህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ የተደረገውን የሦስትዮሽ ምክክር ተከትሎ ግብፅ ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ አቅርባ ነበር። ኢትዮጵያ በበኩሏ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት፤ በሦስቱ አገራት መካከል የተደረሱ አበረታች ስምምነቶችን የሚያፈርስ ከመሆኑ በተጨማሪ ሦስቱ አገራት በመጋቢት 2017 የፈረሟቸውን የመግለጫ ስምምነቶችም ይጥሳል በማለት የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል ገልፃለች። ግብፅ ማን አደራዳሪ ይሁን በሚለው ላይ ምንም ባትልም የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ፤ አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ላይ ያላት ሚና ከፍ ያለ እንዲሆን ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው። ግብፅ ዓለም ባንክ ሶስተኛ ወገን ሆኖ ልዩነቶችን በመፍታት እንዲያደራድር ግብፅ ምክረ ሃሳብ እንደምታቀርብ የግብፁ አሀራም ኦንላይን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በትናንትናው ዕለት ሳሚህ ሽኩሪ "ግብፅ ከናይል ወንዝ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም አሳልፋ አትሰጥም" ስለማለታቸው እንዲሁ አህራም ዘግቧል። "[ኢትዮጵያ] 630 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የዝናብ ውሃ ታገኛለች፤ 10 ወንዞቿን ሳንጠቅስ ማለት ነው። ግብጽ ግን በውሃ እጥረት አጣብቂኝ ውስጥ ወድቃለች። . . . የናይል ውሃ ጉዳይ ለግብጽ የህይወት እና የሞት ጉዳይ ነው።" በማለትም ተናግረዋል። • ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን እንደማትቀበል አሳወቀች አህራም እንዳስነበበው የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚህ ሹኩሪ ሱዳን ከግብጽ ጋር ትብብር እንድታደርግም ጥሪ ቀርቦላታል። "ወንድማማች ህዝቦች ብቻ ስለሆንን ሳይሆን፤ የህዳሴ ግድቡ ግብጽን ብቻ ሳይሆን ሱዳንንም ይጎዳል" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም የግብጽ ፓርላማ የህዳሴ ግድብ ግንባታን የሚከታተል ልዩ ጊዜያዊ ኮሚቴ ማቋቋም ተገልጿል። ኮሚቴው የግብጽን የናይል ውሃ የመጠቀም መብት ለማስከበር አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን እንደሚያጠናም አህራም አስነብቧል። የግብጽ ፓርላማ አባላት የሃገሪቷ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር፣ ኢትዮጵያ የምትገነባው የህዳሴ ግድብ ያስከተለውን ቀውስ ለመቅረፍ የወሰደው እርምጃ እጅግ ደካማ ነው ሲሉ ስለመተቸታቸው አህራም ዘገባው ላይ አስፍሯል። ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታንና የውሃ መሙላት ሂደትን በተመለከተ ለአራት ዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ውይይት ምንም ውጤት እንዳላመጣ ሳሚህ ሽኩሪ መናገራቸው ይታወሳል።
news-57340388
https://www.bbc.com/amharic/news-57340388
ናሳ ምርምር ለማድረግ ሁለት ልዑኮችን ወደ ቬኑስ እንደሚልክ ገለጸ
ናሳ የስነ ምድርና የከባቢ አየር ምርምር ለማድረግ ሁልት ልዑኮችን ወደ ቬኑስ እንደሚልክ አስታወቀ
እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር በ2028ና 2030 ወደ ቬኑስ ለሚደረጉት ተልዕኮዎች እያንዳንዳቸው 500 ሚሊዮን ዶላር እንደሚወጣባቸውም ተገልጿል። የናሳ አስተዳዳሪ ቢል ኔልሰን ተልዕኮዎቹ "ከ 30 ዓመታት በላይ ያልደረስንበትን ፕላኔት ለመመርመር እድል ይሰጡናል" ብለዋል፡፡ በፕላኔቷ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ምርምር የተደረገው እንደ አውሮፓውያኑ 1990 ነበር። ናሳ ተልዕኮዎቹን ለመፈጸም ከውሳኔ ላይ የደረሰው የተለያዩ ግምገማዎችን ካከናወነ፣ ያላቸውን ሳይንሳዊ አስፈላጊነትና አዋጭነት ካረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ታዲያ "እነዚህ ሁለት ጥምር ተልእኮዎች ቬኑስ እንዴት እርሳስ [lead] ማቅለጥ የሚችል የእሳትን ገጽታ የተላበሰ ዓለም ሊሆን እንደቻለ ለመረዳት ዓላማ ያደረጉ ናቸው ሲሉ አስተዳዳሪው ኔልሰን አስረድተዋል፡፡ ቬኑስ ከጸሀይ በመቀጠል ሁለተኛዋ ሞቃታማ ፕላኔት ስትሆን እስከ 500 ሴልሺየስ የምትሞቅና እራሳስን ማቅለጥ የሚችል የአየር ሁኔታ ላይ ያላት የምትገኝ ናት።
news-45974821
https://www.bbc.com/amharic/news-45974821
አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ-ኢትዮጵያ ሴት ርዕሰ ብሔር አገኘች
አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ 4ኛው የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር በመሆን በዛሬው ዕለት ተሹመዋል። አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት አምባሳደር ሳህለወርቅ የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናቸው።
አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በወርሃ የካቲት 1942 የተወለዱ ሲሆን ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛና አማርኛ አቀላጥፈው የይናገራሉ። • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ • አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው? አምባሳደር ሳህለወርቅ የፈረንሳዩ ሞንተፔለ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ምሩቅ ሲሆኑ እኤአ ከ1989-1993 ተቀማጭነታቸውን ሴነጋል በማድረግ የማሊ፣ የኬፕ ቨርድ፣ የጊኒ ቢሳዎ፣ የጋምቢያና የጊኒ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። ርዕሰ ብሔር ሳህለወርቅ ዘውዴ ቃለ መሀላ ሲፈፅሙ እኤአ ከ1993-2002 ደግሞ በጅቡቲ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን በወቅቱ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይም ነበሩ። ከዚያም በመቀጠል ከ2002-2006 በፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ተወካይ ሆነው ሰርተዋል። በኋላም በተባበሩት መንግሥታት ልዩ መልዕክተኛ ውስጥ የተቀናጀው የሰላም አስከባሪ ሃይል ተወካይ በመሆን በሴንትራል አፍሪካ(BINUCA) ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል። • ለእነ ባራክ ኦባማ የተላከው ጥቅል ቦምብ • ልዑሉ የኻሾግጂን ገዳዮች ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ዛቱ በአፍሪካ ሕብረት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥም የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ሳህለወርቅ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥም የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ሰርተዋል። እኤአ በ2011 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ የነበሩት ባን ኪሙንም በኬኒያ የተባበሩት መንግሥታት ዳይሬክተር ጄነራል አድርገው ሾመዋቸው አገልግለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተወካይ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል። አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የርዕሰ ብሔሯ የመጀመርያ ንግግር አዲሷ ርዕሰ ብሔር በሕዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክርቤት አባላት ፊት ቃለ መሀላ ከፈፀሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር ስለ ሰላም እና ስለ ሴት ልጆች እኩልነት አፅንኦት ሰጥትው ተናግረዋል። ርዕሰ ብሔር ሳህለወርቅ በንግግራቸው የቀድሞው ርዕሰ ብሔር በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣን በመልቀቃቸው አመስግነው ይህ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ያልተለመደ ነገር በሀገራችን እየተለመደ መምጣቱንና ለለውጥና ለተስፋ ዕድል መሰጠት መጀመሩን እንደሚያሳይ ተናግረዋል። ይህም አሉ ርዕሰ ብሔሯ ባደጉና በሰለጠኑ ሀገራት እንደተለመደው "ከያዝነው ሥልጣንና ኃላፊነት በፊትም ሆነ በኋላ ሕይወት የሚቀጥል መሆኑን መረዳታችንን ያሳያል" ብለዋል። ይህ ለሌሎች ዕድል የመስጠት አርአያነት በተለያዩ እርከኖችና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል። ርዕሰ ብሔሯ ጨምረውም ታላቅ ሀገር የመገንባት ህልማችንን እውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም በማለት ስለሰላም አበክረው ተናግረዋል። "በሰላም እጦት ዋነኛ ተጠቂዎች ሴቶች በመሆናችን በዚህ የኃላፊነት ቆይታዬ አብይ ትኩረቴ መላው የኢትዮጵያን ሴቶችንና... ሰላም ወዳድ ዜጎችን ከጎናቸው በማሰለፍ ሰላም ማስፈን እንደሚሆን ተናግረዋል። በዚህም መላው ሕዝብና የምክር ቤት አባላት ከጎናቸው እንደሚሆኑ ያላቸውን አምነት ተናግረዋል። ርዕሰ ብሔሯ በንግግራቸው ደጋግመው አፅንኦት የሰጡት ስለ ሴቶች እኩልነት ነው። ይህ ንግግራቸው በዛ ብለው የሚያስቡ ካሉ "ገና ምኑ ተነካና" በማለት የሕዝብ እንደራሴዎችን ፈገግ አሰኝተዋል። አባታቸው አራት ሴት ልጆች እንዳሏቸው የገለጹት ርዕሰ ብሔሯ ለዚህ እንድበቃ ረድተውኛል ያሏቸውን ወላጆቻቸውን ባሉበት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ብለዋቸዋል።
news-45339557
https://www.bbc.com/amharic/news-45339557
ተጭበርብራ የተሞሸረችው ሴት አፋቱኝ እያለች ነው
በሆንግ ኮንግ የምትኖረው የ21 ዓመቷ ሴት ለሥራ ቅጥር የተዘጋጀ ነው በተባለ የሰርግ ድግስ ላይ ሙሽራ ሆና እየተወነች እንደሆነ ነበር የምታውቀው። ጉዳዩ ሌላ ሆኖ የፈረመችው ፊርማ በቻይና ህጋዊ ሆኖ ባለትዳር ነሽ ተብላለች።
ሴትየዋ እነደምትለው የሰርግ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተሳተፈችው በአንድ ድርጅት ውስጥ የሰርግ አዘጋጅ ሆና ለመቀጠር የመጨረሻው ፈተና እንደ ሙሽራ መተወን እንዳለባት ከተነገራት በኋላ ነበር። በስነ-ስርዓቱ ላይም እሷና እንደ ባል ሆኖ ይተውን የነበረው ባለቤቷ ህጋዊ ፊርማ ተፈራርመዋል። የሆነውን ሁሉ ያወቀችውም ወደ ሆንግ ስትመለስ እንደሆነ ታውቋል። ወዲያው ለከተማው ፖሊስ ብታመለክትም ወንጀል መፈጸሙን እና ተገዳ የፈረመች መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ስላልቻለች ጉዳዩ መፍትሄ ሊያገኝ አልቻለም። • ትዳር ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገችው ሴት ከሁለት ወራት በፊት በፌስቡክ በወጣ የስራ ማስታወቂያ ላይ ተመዝግባ ነበር። ስራውም ረዳት የሜክአፕ ባለሙያ ቢሆንም፤ ድርጅቱ ለሰርግ አዘጋጅነት እንድትወዳደር እንዳሳመኗት ገልጻለች። ለስራው መመረጧ ከተነገራት በኋላም ለአንድ ሳምንት ስልጠና የወሰደች ሲሆን፤ በመጨረሻው ፈተናም በቻይናዋ ፉዞዉ ግዛት እንደ ሙሽራ ሆና አንድትተውን እንደተነገራት ትገልጻለች። በየዋህነት ወደ ግዛቲቱ የመንግስት መስሪያ ቤት ሄዳ የፈረመችው የጋብቻ ወረቀትም ህጋዊ ሆኖ ተገኝቷል። ጉዳዩ እስከሚጣራና ያገባችው ሰው ማንነት እስከሚታወቅ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ ባለትዳር ሆና እንደምትቆይም ተነግሯታል። • የደሞዙን 100 እጥፍ በስህተት የተከፈለው ሰው • ሽጉጥ ይዘው ለመንቀሳቀስ የተገደዱት ከንቲባ የሆንግ ኮንግ ፖሊስ እንደገለጸው በየዓመቱ ከ1000 በላይ ቻይናውያን ወደ ሆንግ ኮንግ የሚያስገባቸውን ህጋዊ ወረቀት ለማግኘት ከሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ጋር የውሸት ጋብቻ ይፈጽማሉ። የ21 ዓመቷ ወጣትም የዚህ ወንጀል ሰለባ ሳትሆን እንዳልቀረች ፖሊስ ገልጿል።
news-44418131
https://www.bbc.com/amharic/news-44418131
"መንግሥት እየተባባሰ ካለው ብሔርን መሰረት ካደረገ ጥቃት ዜጎቹን ይጠብቅ" አምነስቲ
የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል ብሔርን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች ሳቢያ ከመፈናቀል አፋፍ ላይ ያሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር አባላትን ለመጠበቅ ጣልቃ እንዲገባ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።
አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት እንደጠቀሰው በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ሰዮ ወረዳ በዚህ ሳምንት በቡድን የተሰባሰቡ የአካባቢው ወጣቶች የአማሮችን ቤት መክበብ፣ ድብደባና የንብረት ዝርፊያ ፈፅመዋል ሲል ይከሳል። በተጨማሪም ከጥቅምት ወር አንስቶ ቢያንስ 20 የሚደርሱ አማሮች በእንዲህ ያሉ ጥቃቶች መገደላቸውን ገልፆ፤ ባለስልጣናት ድርጊቱን ለማስቆም ምንም እንዳላደረጉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል ብሏል። "የኢትዮጵያ መንግሥት በብሔራቸው ምክንያት የጥቃት ኢላማ ሆነው ከመኖሪያቸው ሊፈናቀሉ በተቃረቡት የአማራ ማህበረሰብ አባላት ላይ የሚፈፀሙትን የጭካኔ ጥቃቶች ለመከላከል እርምጃ መውሰድ አለበት" ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የታላላቅ ሃይቆች ዳይሬክተር የሆኑት ጆዋን ኒያኑኪሰ ተናግረዋል። ሪፖርቱ ጨማሮም 1400 የሚደርሱ የአማራ ቤተሰቦች ጥቃት ይፈፀምባታል በተባለችው የሰዮ ወረዳ ውስጥ የቀሩ ሲሆን፤ ነዋሪዎቹ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደተናገሩት ቄሮና ፎሌ በተባሉት የኦሮሞ ወጣቶት ቡድኖች በተደጋጋሚ በሚፈፀሙ ጥቃቶች ሳቢያ ከሦስት አስርታት በላይ ከኖሩበት አካባቢ ተገደው ሊወጡ እንደሚችሉ ስጋት አድሮባቸዋል። "ለልጆቻችን ህይወት እንሰጋለን። መንግሥት ጣልቃ ካልገባ በስተቀር አካባቢውን ለቀን ለመውጣት ያለንን ንብረት አዘጋጅተናል" ሲሉ አንድ ነዋሪ ለአምነስቲ ተናግረዋል። ነዋሪው ጨምረውም ምንም እንኳን እየተፈፀሙ ስላሉት ጥቃቶች ማህበረሰቡ ተደጋጋሚ አቤቱታዎችን ለወረዳና ለዞን ባለስልጣናት ቢያቀርቡም ምንም መፍትሄ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል። ስለሪፖርቱ የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ተጠይቀው ለቢቢሲ እንደተናገሩት "በአሁኑ ጊዜ ያለውን እውነታ የማያሳይ መሰረተ-ቢስ ሪፖርት ነው'' ብለዋል። አሁን ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለናል የሚሉት ሰዎች በጥቅምት ወር በአካባቢው በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ስጋት ውስጥ ገብተው ከቦታው የሄዱ እንደነበሩና ከመካከላቸውም የተወሰኑት እንደተመለሱም ዶክተር ነገሪ ተናግረዋል። ''አምነስቲ ባወጣው ሪፖርት ላይ በተጠቀሰው አካባቢ እንዲህ ያለችግር መከሰቱን የሚገልፅ ምንም አይነት ነገር አልሰማሁም'' ያሉት ዶክተር ነገሪ በክልላቸው ከየትኛውም የሃገሪቱ አካባቢ የመጣን ሰው ኢላማ ያደረገ ጥቃት እንዲፈፀም የክልሉ መንግሥት እንደማይፈቅድ ተናግረዋል። የአምነስቲ ዘገባ እንዳመለከተው በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋና ኢሉ-አባቦራ ዞኖች ውስጥ በሚኖሩ አማሮች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት የጀመረው በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ነው። በተጨማሪም በቤኒሻንጉል ክልል ሺናሻ ዞን ውስጥ የሚኖሩ አማሮች ተመሳሳይ ጥቃት አጋጥሟቸዋል። በዚህም ቢያንስ 20 የሚደርሱ አማሮች በሚያዚያ ወር ውስጥ በተፈፀሙ ጥቃቶች ተገድለዋል ብሏል የአምነስቲ ሪፖርት።
news-53722440
https://www.bbc.com/amharic/news-53722440
በወላይታ ዞን በነበረው ግጭት በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ
በወላይታ ዞን ከተነሳው የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በነበረ እንቅስቃሴ የኮማንድ ፖስቱን መመሪያ ጥሰዋል የተባሉ ግለሰቦች ከተያዙ በኋላ በተከሰተ አለመረጋጋት በሰው ህይወትና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።
በትናንትናው ዕለት የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ አክቲቪስቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች ዞኑን በክልል ለማደራጀት ከተቋቋመው ሴክሬታሪያት ጋር ስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት በጸጥታ ኃይሎች መያዛቸውን ተከትሎ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል። በትናንትናው ዕለት በነበረው ግጭት ተጎድተው ወደ ሶዶ ክርስትያን ሆስፒታል ለሕክምና ከመጡ ሰዎች መካከል አንድ ሰው የሕክምና እርዳታ ቢደረግለትም መትረፍ እንዳልቻለ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሆስፒታሉ ባልደረባ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አምስት ሰዎች የተለያየ የጉዳት መጠን ደርሶባቸው በሆስፒታሉ ሕክምና ማግኘታቸውን እና በአሁኑ ሰዓትም ተኝተው እየታከሙ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። እኚሁ ግለሰብ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት እነዚህ ሰዎች ወደ ሆስፒታላችን የመጡ ይሁን እንጂ፣ በትናንትናው እለት ሊጋባ ትምህርት ቤት አካባቢ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አውቃለሁ ሲሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ለግጭቱ ምክንያት በሆነው የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በአጠቃላይ 26 መሆናቸውን የገለጸው የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች ከተለያዩ ቡድኖች ጋር በትብብር ይሰራሉ ሲል ከሷል። በመግለጫው ላይ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች የኮማንድ ፖስቱን ትዕዛዝ በመተላለፍ ሕገወጥ ስብሰባዎች እንዲሁም ሰልፎችን እንዳደረጉ ተገልጿል። የወላይታ ዞን ምክር ቤት ሰኔ 15/2012 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንዲቋቋም ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። የክልሉን መንግሥት ለማደራጀት የሚያስችል ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤትም እንዲቋቋም እና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንዲከናወኑም በዚሁ ወቅት ወስኖ ነበር። በዞኑ የተቋቋመው የክልል ምስረታ ሴክሬታሪያት ካውንስል አማካሪ ቦርድ አባላት፣ በሕግ ኮሚቴው የተዘጋጀውን የሕገ መንግሥት ረቂቅ ላይ እንዲወያዩ ስብሰባ መጠራቱን የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ማቲዎስ ባልቻ እና የወላይታ ወጣት (የለጋ) የሆነው ዳንኤል ታደነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቦርዱ የተቋቋመው ከመንግሥት አካላት፣ በግል ሥራ ላይ ከተሰማሩ፣ ከወጣቶች፣ ከንግድ ማኅበራት፣ ከተቃዋሚዎች፣ ከአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ምሁራን እንደሆነ የሚናገሩት ግለሰቦቹ በትናንትናው ዕለትም በአዳራሽ ስብሰባው የተካሄደው ለእነዚሁ የቦርድ አባላት የሕገ መንግሥት ረቂቁን አቅርቦ ውይይት ለማድረግ እነደነበር ለቢቢሲ አስረድተዋል። "ስብሰባው የተዘጋጀው በሕገመንግሥት ረቂቅ ላይ ለመወያየት ብቻ መሆኑን ነው የማውቀው" ሲሉ የሚያስረዱት አቶ ማቲዎስ በዕለቱ ሌላ አጀንዳ ስለመነሳቱ በስፍራው ስላልነበሩ አለመስማታቸውን ተናግረዋል። የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ማቲያስ የድርጅታቸው አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎበዜ አበራም በቁጥጥር ከዋሉት መካከል አንዱ መሆናውን በመግለጽ፣ ትናንት በነበረው አለመረጋጋት አንድ ሰው መሞቱንና የቆሰሉ መኖራውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የወላይታ የለጋ አባል የሆኑት አቶ ዳንኤል ታደነ በበኩላቸው ትናንትና የግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር መዋል ተከትሎ በከተማዋ አለመረጋጋት ተከስቶ እንደነበር ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አቶ ዳንኤል አክለውም በትናንትናው አለመረጋጋት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን አረጋግጠው ዛሬ ግን ያለውን ሁኔታ "ውጥረት የሚታይበት" ሲሉ ተናግረዋል። ትናንት ጉዳት የደረሰባው ሰዎች ምን ያህል እንደሆኑ በትክክል መረጃዎችን አለማጠናቀራቸውነ የሚገልፁት አቶ ማቲዎስ በበኩላው "ዛሬ እንቅስቃሴ እንደልብ ስለለሌለ" መረጃ ማደራጀት አለመቻላቸውን ተናግረዋል። አቶ ዳንኤል አክለውም ማለዳ ላይ እርሳቸው ከሚኖሩበት ስፍራ ራቅ ብሎ በሚገኝ አካባቢ ጎማ የሚያቃጥሉ ወጣቶች እንደነበሩ አሁን ግን ሰላም መሆኑን ገልፀዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወላይታ ሶዶ ነዋሪዎች ከከተማዋ መውጣትም ሆነ መግባት እንደማይቻል ተናግረዋል። አረካ አካባቢ ማለዳ ተቃዋሞ ለማድረግ ሙከራ ቢደረግም መበተኑንን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በሶዶ ከተማ አልፎ አልፎ ተኩስ እንደሚሰማ የተናገሩት ነዋሪዎች ዛሬም ከፀጥታ አካል በተተኮሰ ጥይት የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን እንደሰሙ ለቢቢሲ አስረድተዋል። የሶዶ ከተማ ነዋሪዎችም ሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ አባሉ ሶዶ ከተማ ዛሬ በብዛት እንቅስቃሴ እንደማይታይባት ተናግረው፣ በብዛት የመከላከያ አባላት ሲንቀሳቀሱ እንደሚታይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ዳንኤል ከዚህ ቀደም እርሳው በተገኙበት ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚነስትር ዐብይ "ጥያቄው የካድሬ ጥያቄ ካልሆነ፤ ሕገመንግሥታዊ ጥያቄ ነው። ጥያቄያችሁ ሕግን ተከትሎ ምላሽ እንዲያገኝ ጥረት አደርጋለሁ" ማለታቸውን በማስታወስ አሁንም በእነዚህ ሰዎች ቁጥጥር ስር መዋል የተነሳ ጥያቄው ተዳፍኖ እንደማይቀር ያላቸውን እምነት ይናገራሉ። አቶ ማቲዎስ በበኩላቸው ሕዝቡ መሪዎቹ በመታሰራቸው በተለያየ አካባቢ ተቃውሞውን ለማሰማት እየሞከረ ነው ሲሉ ያለውን ሁኔታ ለቢቢሲ አስረድተዋል። በዞኑ ስለተፈጠረውና ስለደረሰው ጉዳት ከደቡብ ፖሊስ ለማጣራት ብንደውልም የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባዎች የተጠናከረ መረጃ እንዳልደረሳቸው በመግለጽ መልሰን እንድንደውል ነግረውናል። የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ባውዲ ለደቡብ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ አገር ለማፍረስ ከሚን ቀሳቀሱ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመስራት ላይ ነበሩ ሲሉ በቁጥጥር ስር የዋሉትን ሰዎች ከሰዋል።
46464208
https://www.bbc.com/amharic/46464208
የሁዋዌ ባለቤት ልጅ ካናዳ ውስጥ ታሠረች
የቻይናው ቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ ባለቤት ሴት ልጅ ካናዳ ውስጥ ለእሥር ተዳርጋለች፤ ወደ አሜሪካ ልትላክ እንደምትችልም እየተነገረ ነው።
ከጥቂት ቀናት በፊት ነበረ ሜንግ ዋንዦ፤ የሁዋዌ ባለቤት ሴት ልጅ እና የሁዋዌ ምክትል ኃላፊ በካናዳዋ ቫንኮቨር ከተማ በቁጥጥር ሥር የዋለችው። ሜንግ የታሠረችበት ምክንያት ግልፅ ባይሆንም አሜሪካ ሁዋዌ የተሰኘውን ኩባንያ ከኢራን ጋር በተያያዘ ጉዳይ እየመረመረች እንደሆነ ተነግሯል። በካናዳ የቻይና ኤምባሲ እሥሩ ህጋዊ አይደለም በሚል ሜንግ ዋንዦ በፍጥነት እንድትፈታ ጠይቋል። • አይፎን አዲስ ስልኮችን ይዞ ብቅ ብሏል ኩባንያው ስለጉዳዩ ብዙም የሚያውቀው መረጃ እንደሌለ በመጠቆም ምክትል ኃላፊዋ ግን ምንም ዓይነት እኩይ ተግባር እንደሌለባቸው ጠቁሟል። ጉዳዩ አሜሪካ እና ቻይና ንግድ በተመለከተ ከገበቡት እሰጥ-አገባ አንፃር ውጥረት እንዲነግስ አድርጓል እየተባለ ነው። ምክትል ኃላፊዋ ለአሜሪካ ተላልፈው ሊሰጡ እንደሚችሉ ፍንጭ የሰጠው የካናዳ ፍትህ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በዋስትና ጉዳይ ብይን ለመስጠት ለዕለተ አርብ የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንደተሰጠ አሳውቋል። አሜሪካ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባለች። • ከኢትዮ- ቻይና ወዳጅነት ጀርባ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ሁዋዌ አሜሪካ ኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ሳይጥስ አልቀረምና ለዚህ ነው ምክትል ኃላፊዋ ለእሥር የተዳረጉት በማለት እየዘገቡ ይገኛሉ። ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኩባንያው አሜሪካ ኢራን ብቻ ላይ ሳይሆን ሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ሳይተላለፍ አልቀረም ሲል ዘግቧል። የአሜሪካ ሕግ አርቃቂዎችም ኩባንያው ለሃገራችን ደህንነት ስጋት ነው በማለት በተደጋጋሚ ሲከራከሩ ይደመጣሉ። የሁዋዌ ፈጣሪ ሬን ዤንገፌይ ሴት ልጅ ሜንግ ዋንዦ ካናዳ እንደመሸጋገሪያ ተጠቅማ ወደሶስተኛ ሃገር ለመብረር እየተዘጋጀች ሳለ ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለችው። አሜሪካ፤ ኢራን የኑክሊዬር ጦር መሣሪያ እያብላለቸው ነው በማለት ማዕቀብ መጣሏ የሚዘነጋ አይደለም፤ ከማዕቀቦቹ አንዱ ደግሞ ምጣኔ ሃብታዊ ነው። ሁዋዌ የተሰኘው ግዙፍ የቻይና ኩባንያ ይህንን በመተላለፍ በምስጢር ከኢራን ጋር ሳይሰራ አልቀረም። • በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል?
news-52152165
https://www.bbc.com/amharic/news-52152165
ኮሮናቫይረስ፡ ወሲብና ኮቪድ-19ን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች
'ወሲብ ብፈጽም ኮሮናቫይረስ ሊይዘኝ ይችላል?' በእርግጠኝነት ይህ ጥያቄ በብዙዎች አእምሮ ውስጥ ቢያቃጭልም ለመጠየቅ ግን እንሸማቀቃለን።
ሃቅንና ብዥታን ለመለየት ጥያቄዎን ለጤና ሙያዎች በማቅረብ ቢቢሲ ተገቢውን ምለሽ አግኝቷል። የቀድሞው የላቭ አይላንድ አወዳዳሪ ዶ/ር አሌክስ ጆርጅ እና የቢቢሲዋ ጋዜጠኛ አሊክስ ፎክስ በጉዳዩ ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል። በጥያቄዎቹ ዙሪያ ሁለቱም ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ወሲብ መፈጸም ችግር ያመጣል? ዶ/ር አሌክስ ጆርጅ፡ ግንኙነት ውስጥ ከሆናችሁ.… አብራችሁ የምትኖሩ ከሆነና ተመሳሳይ አካባቢ ውስጥ ካላችሁ የሚቀየር ነገር አይኖርም። ነገር ግን አንደኛችሁ ብቻ የኮሮናቫይረስ ምልክት ካሳያችሁ፤ ማኅበራዊ እርቀታችሁን መጠበቅና እራስን መለይት ያስፈልጋል። ኑሯችሁ አንድ ቤት ውስጥ ቢሆንም እንኳ ማለት ነው። እንደ ዓለም አቀፍ መስፈርት ቤት ውስጥ እንኳ ቢሆን ማንም ሰው ሁለት ሜትር መራራቅ እንዳለበት ይመከራል። በእርግጥ በአብዛኛው ይሄ ሲተገበር አይታይም። • ባለስልጣኑ ወደ ለይቶ ማቆያ አልገባም በማለታቸው ታሰሩ አሊክስ ፎክስ፡ አንዳንድ ጊዜም እርሰዎ የሚሰማዎት ቀላል የኮሮናቫይረስ ምልክት ከታያብዎት የፍቅር አጋርዎም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ብለው ማሰቡ መልካም ነው። በመሆኑም ምንም ዓይነት ምልክት ካሳዩ ምልክቱ ምንም ይሁን ምን እራስዎን ከፍቅረኛዎ መለየት አለብዎት። ከአዳዲስ ሰዎች ጋር የሚፈጸም ወሲብስ? ዶ/ር አሌክስ፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በእርግጠኝነት መምከር የምችለው ባለንበት አስቸጋሪ ወቅት ከአዳዲስ ሰዎች ጋር ምንም አይነት ወሲብ መፈጸም የለብዎትም ነው። ምክንያቱም መዘዙ ቫይረሱን ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ወይም ደግሞ መቀበል ነውና። አሊክስ ፎክስ፡ ደግሞም መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር፤ አንዳንድ ሰዎች ቫይረሱ ኖሮባቸው ነገር ግን ምንም የኮሮናቫይረስ ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። ስለዚህ ፍጹም ደኅንነት ቢሰማዎትም ወሲብ በሚፈጽሙበት ወቅት በሚፈጠረው መጠጋጋትና መሳሳም ምክንያት ቫይረሱ ከአንዱ ወደ ሌላው ይተላለፋል። የቢቢሲዋ ጋዜጠኛ አሊክስ ፎክስ እና ዶ/ር አሌክስ ጆርጅ በቅርቡ ተሳስሜያለሁ፤ ከቀናት በኋላ ያ ሰው የቫይረሱን ምልክት ማሳየት ጀምሯል። ምን ማድረግ አለብኝ? ዶ/ር አሌክስ፡ በቅርቡ የሳሙት ግለሰብ ቫይረሱ እንዳለበት ካወቁ በፍጥነት እራስዎን ለይተው ያቆዩ። ምልክቶቹን በደንብ ይከታተሉ። ምልክት ማሳየት ከጀመሩ ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን ያድርጉ። ህመሙ ከጠናብዎ ግን ለተጨማሪ ሕክምና ሐኪሞችን ማማከር ይኖርብዎታል። አሊክስ ፎክስ፡ በግንኙነታችን ወቅት አንዳችን ለሌላኛችን ኃላፊነት ሊሰማን ይገባል። ለምሳሌ ከተሳሳሙ በኋላ ምልክቶቹን ቀድመው ማሳየት የጀመሩት እርሰዎ ከሆኑ ምልክት ማሳየት መጀመርዎን ለፍቅር አጋርዎ ቶሎ መንገር ይኖርብዎታል። በዚህ ሂደት ከሁለታችሁ መካከል ምልክት ያላሳዩት እርሰዎ እንደሆኑ ካወቁም በፍጥነት እራስዎን ይለዩ። ኤች አይ ቪ አለብኝ፤ ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭነቴ የሰፋ ነውን? አሊክስ ፎክስ፡ በዚህ ጉዳይ ዶ/ር ሚካኤል ብራዲ ትልቅ ምክረ አስቀምጠዋል። በተከታታይ የኤችአይቪ መድኃኒት የሚወስዱ ከሆነና ጥሩ በሽታን የሚከላከሉ የነጭ ሕዋሳት ብዛት [የሲዲ4] ካለዎና በደምዎ ውስጥ ያለው የቫይረሱ መጠን ሊለይ በማይችል ደረጃ ከሆነ እርሰዎ በሽታውን የመቋቋም አቅምዎ ዝቅተኛ ነው ከሚባሉት መካከል አይደሉም። ይህ ማለት ኮሮናቫይረስ ቢይዝዎ ሕመምዎን የሚያፋፍም ተጨማሪ በሽታ የለብዎትም ማለት ነው። ነገር ግን ከኤችአይቪ ነጻ ነዎት ማለት ግን አይደለም። ስለዚህ የኤችአይቪ በደምዎ ውስጥ ካለ የተለመደ መድኃኒትዎን የመውሰድ ተግባርዎን ሳያስተጓጉሉ ይቀጥሉ። የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን ጨምሮ እራስን ለይቶ ማቆየትን የመሳሰሉ ትዕዛዞች ሲሰጡ ይፈጽሙ። ለሌሎች ሰዎች የሚሰጡ ማንኛቸውንም ትዕዛዞች ማክበርዎንም አይዘንጉ።
news-45481917
https://www.bbc.com/amharic/news-45481917
ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬና በዛላምበሳ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሁለቱን ሃገራት በሚያዋሰኑባቸው በቡሬ በዛላምበሳ አካባቢዎች ተገኝተው ከሕዝቡና ሠራዊታቸው ጋር አዲስ ዓመትን አከበሩ።
ይህ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረውን ግንኙነትን የማሻሻል እርምጃን ተከትሎ ተዘግተው የነበሩትን የሁለቱን ሃገራት የድንበር መተላለፊያዎች በመክፈት በኩል ትልቁ እርምጃ ነው ተብሏል። በትናንትናው ዕለት ከሃያ ዓመታት በፊት ሁለቱ የሃገራት የድንበር ጦርነት ሲቀሰቀስ ጀምሮ ተዘግቶ የነበረው ከዛላምበሳ ወደ ሰንዓፈ የሚወስደውን መንገድ ተከፍቷል። • ድንበር ላይ የነበረው የድንጋይ አጥር ፈረሰ • 'መቐለ' በምፅዋ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ከዚህ በተጨማሪ በስፍራው የነበረው የኤርትራ ጦር ምሽግም እንዲፈርስ ተደርጓል። ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኘው የድንበር መተላለፊያ አካባቢ ተቀብረው የነበሩ ፈንጂዎችን ማፅዳት ሥራ በሁለቱም ሠራዊት አባላት በጋራ ሲያከናውኑ ማየታቸውን የዓይን እማኞቹ ተናግረዋል። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በሌላኛው ሃገር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከማደሳቸው ባሻገር የአየር ትራንስፖርት ተጀምሯል። ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ከጂቡቲ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ለወጪና ለገቢ ቁሳቁሶች ማንቀሳቀሻ ሁለቱን የኤርትራ ወደቦችን እንድትጠቀም ማስቻል ቀጣዩ እርምጃ እንደሚሆን ተነግሯል።
news-55829610
https://www.bbc.com/amharic/news-55829610
የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ በአስቸኳይ እንዲወጡ የጆ ባይደን አስተዳደር ጠየቀ
የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲወጡ አሜሪካ ጠየቀች።
በትግራይ ካለው ግጭት ጋር ተያያዞ ዝርፊያዎች፣ መደፈሮችና በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ጥቃቶችና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየደረሱ መሆናቸውን የሚታመኑ ሪፖርቶች እንዳሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) አስታውቋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ በቃለ አቀባዩ በኩል በተለይ ለቢቢሲ በገለፀው መሰረት የተለያዩ ኃይሎች ብሎ የጠራቸው አካላት ጥሰቶቹን እየፈፀሙት ነው ብሏል። አገራቸው የኤርትራን ወታደሮች በተመለከተ ግልፅ አቋም እንዳላት ያስታወቀው መስሪያ ቤቱ የኤርትራ ወታደሮች በሙሉ ከክልሉ በአስቸኳይ እንዲወጡ በማለት አፅንኦት ሰጥቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በተደጋጋሚ በትግራዩ ግጭት የኤርትራ ጦር አለመሳተፉን አስታውቋል። ወታደሮቹ ዝርፊያ፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ላይ ጥቃትና ሌሎች ጥሰቶች እያደረሱ እንደሆነ የሚታመኑ ሪፖርቶች አግኝቻለሁ ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ ክልል የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን የኤርትራ ወታደሮች በግድ እየመለሷቸው እንደሆነ ማስረጃ እንዳገኘም ጠቁሟል። ምን ያህል የኤርትራ ወታደሮችና የት እንዳሉ ግልፅ አይደለም ያለው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ነገር ግን የኤርትራ ኃይሎች በከፍተኛ የጦር መሳሪያ የታገዘ ጥቃት እያደረሱ እንደሆነና ይህም በትግራይ በሚያዋስነው ድንበር በኩል ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ኤርትራና ትግራይን በሚያዋስነው ድንበር በኩል ወደ ትግራይ መግባታቸውን እንዲሁ ቃለ አቀባዩ አስፍረዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ ትግራይ ላይ በተደረገው ወታደራዊ ግጭት የኤርትራ ሰራዊት ተሳትፏል ስለመባሉ "ፕሮፓንዳና መሰረተ ቢስ ነው" ብለውታል። ከኤርትራም በተጨማሪ የሶማሊያ ሰራዊት ተሳትፏል መባሉን ሃሰት ነው ማለታቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአገሩን ዳር ድንበር ማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን በሶማሊያ፣ በሩዋንዳ፣ በብሩንዲና፣ ኮንጎ "ትልቅ ገድል የሰራ ኃይል ነው" በማለትም የሰራዊቱን ጥንካሬ አስረድተዋል። ቃለ አቀባዩ ጥር 12/2013 ዓ. ም በሰጡት መግለጫ "የውስጥ የህግ በላይነትን ለማስከበር ማንንም አገር የሚጠራ አይደለም፤ የሚጠራም አገር የለም፤ ሊጠራም አይችልም፤ አይገባም፤ አይፈልግምም፤ አስፈላጊም አልነበረም" በማለት አፅንኦት በመስጠትም ነው የተናገሩት። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ እየተፈፀሙ ናቸው የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ነፃና ገለልተኛ በሆነ አካል ምርመራዎች እንዲካሄድና ይህንን የፈፀሙ አካላት ተጠያቂ መሆን ሊኖርባቸው እንደሚገባ አሳስቧል። ከዚህም በተጨማሪ ውጊያዎች ሙሉ በሙሉ እንዲቆሙና በግጭቱ ለተጎዱ የክልሉ ነዋሪዎች ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ፣ ምንም አይነት እክል በሌለበት ሁኔታ የሰብዓዊ እርዳታዎች የሚደርሱበት መንገድ በአፋጣኝ ሊመቻች እንደሚገባ አሜሪካ ጥሪ አድርጋለች። "እነዚህን ተግባራት በአፋጣኝ ማከናወን ሰላምን ለመመለስና የእርቁን ሂደት ለማረጋገጥ ቁልፍ የመጀመሪያ ሂደቶች ናቸው። በመንግሥትና በተጋሩ መካከልም ውይይት አስፈላጊ ነው" ይላል። ከዚህም በተጨማሪ ከግጭቱ ጋር ተያይዞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ነዋሪዎች በረሃብ ሊሞቱ ይችላሉ የሚለው ሪፖርት "ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮብናል" ያለው መስሪያ ቤቱ የህይወት አድን እርዳታ አስፈላጊነትን አስምሮበታል። በትግራይ ክልል ውስጥ "በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ" አንድ የመንግሥት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ የሰፈረ ጽሁፍ ማመልከቱ የሚታወስ ነው። ከሰሞኑ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በግጭት ወቅት የሚከሰት ወሲባዊ ጥቃት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ቡድን በትግራይ ክልል እየደረሰ ያለው ወሲባዊ ጥቃት እንዲገታ ያሳሰበ ሲሆን ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ "በመቀለ ከተማ በርካታ ቁጥር ያለው ሰው የመደፈሩ ክስና በአጠቃላይ ከትግራይ ክልል የተሰሙት የወሲባዊ ጥቃት ክሶች እጅግ አሳስበውኛል" በማለት ገልጿል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በተመሳሳይ በከልሉ ውስጥ እንዲሁ ወሲባዊ ጥቃት እየደረሰ እንደሆነ የሚታመን ሪፖርት ማግኘቱን ያሳወቀ ሲሆን መስሪያ ቤቱ እንዲህ አይነት "አስነዋሪ ተግባርን መንግስታችን ያወግዛል" በማለት አትቷል። መደፈርን ጨምሮ ደርሰዋል የተባሉ ሌሎች ጥሰቶችን የኢትዮጵያ መንግሥት ነፃና ገለልተኛ በሆነ መልኩ አጣርቶ ወደ ፍርድ እንዲያቀርብ ጥሪ አድርጓል መስሪያ ቤቱ በቃለ አቀባዩ በኩል። በቅርቡም የአውሮፓ ሕብረት በከፍተኛ ዲፕሎማቱ ጆሴፕ ቦሬል በኩል ባወጣው መግለጫ "ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች፣ አስገድዶ የመድፈር ድርጊቶችና ስደተኞችን በግዴታ ወደ አገራቸው መመለስና የጦር ወንጀል ድርጊቶች ሊሆኑ የሚችሉ ክስተቶችን በተመለከተ በተከታታይ መረጃ ይደርሰናል" ማለቱ የሚታወስ ነው። በተደጋጋሚ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ የፈጠረበትን ስጋትም መንግሥታቸው እንደሚጋራ ገልፆ ስደተኞችን ጨምሮ በነፃ ዜጎች ላይ የሚፈጠረውን "የጭካኔ ተግባር እናወግዛለን" ብለዋል ቃለ አቀባዩ። ሁሉም ወገኖች ቢሆኑ አለም አቀፉን የሰብዓዊ መብት ህግጋት ማክበር እንዳለባቸው አስታውሰዋል በመልዕክታቸው። በክልሉ የተገደሉና ማስፈራራት የደረሰባቸውን የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች እንዲሁም የእርዳታ ቁሳቁሶች መዘረፍ፣ የዜጎች ልማት መውደምን አገራቸው "ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ታወግዘዋለች" የሚል መልእከትም የአሜሪካ መንግሥት አስተላልፏል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል። ነገር ግን አልፎ አልፎ ውጊያ እንደሚካሄድ የተነገረ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ "የከፋ" ሲል ገልጾታል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ውጊያው መቀጠሉን በጠቆመበት መግለጫ፤ የቀጠለው ውጊያ በቀጣይነት በክልሉ ረዘም ላለ ጊዜ የሽምቅ ውጊያ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቅሶ ይህም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አለመረጋጋት እንደሚፈጥርና በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የብሔር ውጥረት እንደሚያባብሰው ጠቁሟል። "ይህ ሁኔታ በአሜሪካ ተቀባይነት ባገኙት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተሰሩ የዲሞክራሲ እንዲሁም ሌሎች ማሻሻያዎችን ስጋት ውስጥ ከመክተት በተጨማሪ በሶማሊያ እንዲሁም በሽግግር መንግሥት ያለችውና በከባድ ችግሮች እየተናወጠች ያለችው ሱዳን ላይ አለመረጋጋት ይፈጥራል" በማለት አስምሯል። ቢሮው ኢትዮጵያ በሶማሊያ ያሏትን ሰላም አስከባሪዎች ማውጣቷን ጠቅሷል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል።
news-53314777
https://www.bbc.com/amharic/news-53314777
ዶናልድት ትራምፕ ስለ ሶማሊያ የተሳሳቱት ምንድነው?
ጋዜጠኛ ኢስማኢል ኢይናሼ ሶማሊያ በማያገባት የአሜሪካ ምርጫ እሰጥ-አገባ ውስጥ ገብታለች ይላል።
ለምን? እንዴት? - ኢስማኢል እንዲህ ያስረዳል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሶማሊ-ኤሜሪካዊቷ ፖለቲከኛ ኢልሃን ኦማር ላይ ጥርስ ከነከሱ ሰንበትበት ብለዋል። በተለይ ደግሞ የአሜሪካ ምርጫ መቃረቡን ተከትሎ ስለእሷ ክፉ ሲያወሩ ተደምጠዋል። ነገር ግን ትራምፕ በፖለቲካ ተቀናቃኛቸው የተገቱ አይመስሉም። የፖለቲከኛዋን የትውልድ አገርንም በነገር እየጎሸሙ ነው። በቅርቡ እንኳ በኦክላሆማ ግዛት ተልሳ ከተማ በነበራቸው የምርጫ ቅስቀሳ የ37 ዓመቷን ፖለቲከኛ አሜሪካ ልክ እንደ ሶማሊያ "እንደትረበሽ" ትፈልጋለች ሲሉ ወንጅለዋል። "አገራችንን ልክ እንደ መጣችበት አገር ሶማሊያ አስደተዳደር ማድረግ ትሻለች። መንግሥት የሌለበት፣ ደህንነት ያልተጠበቀበት፣ ፖሊስ የማይታይበት፤ ረብሻ ብቻ እንዲሆን ነው የምትፈልገው። እዚህ መጥታ አገር እንዴት እንደሚመራ ልታስተምረን ትፈልጋለች። ይቅርብን እናመሰግናለን።" በአውሮፓውያኑ 1995 ከሶማሊያ ተሰዳ በልጅነቷ አሜሪካ የገባችው ኢልሃን ኦማር የሚኒሶታ ግዛት የኮንግረስ ተወካይ ናት። ሚኒያፖሊስ ከሚኒሶታ ግዛት ከተሞች አንዷ ናት። ከተማዋ ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በኋላ ብላክ ላይቭስ ማተር [የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት] የተሰኘው እንቅስቃሴ እንደ አዲስ የተቀሰቀሰባት ናት። ነገር ግን ፕሬዝደንቱ ከገዛ አገራቸው ረብሻ ይልቅ የትውልደ ሶማሊያዊቷን ፖለቲከኛ አገር ቀውስ ላይ ማተኮር መርጠዋል። ፖለቲከኛዋ የፕሬዝደንቱ ንግግር 'ዘረኛ' እንደሆነ ጠቅሳ ምላሽ ሰጥታለች። ፕሬዝደንቱ ይህንን የተናገሩት በሚኒሶታ ግዛት የመጪው ምርጫ ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ከእሳቸው የተሻለ ተቀባይነት ስላላቸው ነው እንዲህ ዓይነት ንግግር ያሰሙትም ብላለች። ወጣም ወረደ ትራምፕና ደጋፊዎቻቸው ስለ ሶማሊያ ያላቸው አመለካከት፤ የአሜሪካ ወታደሮች በ1993 ዓ.ም ሞጋቃዲሾ ላይ ከፈፀሙት የከሸፈ ተልዕኮ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ኢልሃን ወደ አሜሪካ የሄደችው ገና ታዳጊ እያለች ነበር ፕሬዝደንቱ፤ ፖለቲከኛዋን 'በጥላቻ የተሞላችና አሜሪካን የምታጣጥል ሶሻሊስት' ሲሉ ይኮንናሉ። ትራምፕ፤ ኢልሃን የጆ ባይደን ደጋፊ ናት ይበሉ እንጂ ፖለቲከኛዋ ለበርኒ ሳንደርስ ግልፅ የሆነ ድጋፍ ታደርግ ነበር። ትራምፕ ባለፈው ዓመት በሰሜን ካሮላይና በነበራቸው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ደጋፊዎቻቸው "ወደ አገሯ ላካት" እያሉ ሲጮሁ እንደነበር አይዘነጋም። ኢልሃን፤ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ለእስራኤል ያግዛሉ ብላ በትዊተር ገጿ መፃፏን ተከትሎ ከዴሞክራቶች ጭምር ትችት ሲሰዘነርባት እንደነበር አይዘነጋም። ይህን ተከትሎ በይፋ ይቅርታ ጠይቃም ነበር። በወቅቱ ሪፐብሊካኑ ራንድ ፖል ፖለቲከኛዋ ወደ አገሯ የምትመለስ ከሆነ የጉዞ ወጪዋን እንደሚሸፍኑ መናገራቸው ይታወሳል። ትራምፕና ሶማሊያ ትራምፕ ለሶማሊያ ያላቸው አመለካከት ዚያድ ባሬ ከሥልጣን መውረድ በኋላ የተቃኘ ይመስላል። ባሬ በ1991 ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ሶማሊያ በዓለማችን ካሉ ቀውስ ያለባቸው አገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ሲጠቀስ መስማት አዲስ አይደለም። ምንም እንኳ ሶማሊያ የዚያን ጊዜ ከነበረችበት ሁኔታ አሁን ብትሻሻልም በወቅቱ የተሰጣት ስም አሁንም መለያዋ ሆኗል። ትራምፕ፤ ሶማሊያ ሕግ የሌለባት፣ ፖሊስ የማይታባት፣ መንግሥት የከሸፈባት ቢመስላቸውም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። ምንም እንኳ አል-ሻባብ አሁንም በሞቃዲሾ ጥቃቶችን ማድረስ ባያቆምም፤ ሶማሊያ ግን ትራምፕ የሳሏትን ዓይነት አይደለችም። አስደናቂው ብሔራዊ ትያትር ባለፈው ሳምንት ተመርቋል። ሶማሊያም ውድና ምቾት ያላቸው ሆቴሎች አሏት። ካፌዎች እና የባህር ዳርቻ ምግብ ቤቶች በሶማሊያ አሉ። የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ የሆነችው ሃርጌሳ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ በጣም ሰላማዊ ከሆኑ ከተሞች መካከል ናት። ሶማሊላንድ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና አታግኝ እንጂ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ታደርጋለች። ዳሃብሺል እና ዎርልድ ረሚት የተሰኙት በአፍሪካ ስመ ገናናዎቹ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች የተመሠረቱት በሶማሊያውያን ነው። የአገሪቱ ዜጎች የወረቀት ገንዘብን ወደሚያስቀር የንግድ እንቅስቃሴ ማምራት ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈው መንግሥት እስላማዊ ታጣቂዎችን ለመግታት እየጣረ ነው። ሞሐመድ አብዱላሂ ሞሐመድ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ የአሜሪካ ዜግነታቸውን ትተዋል በርካቶች ወደ አገራቸው እየተመለሱ ነው። ከእነዚህ መካከል የወቅቱ ፕሬዝደንት ሞሐመድ አብዱላሂ ሞሐመድ ወይም ፎርማጆ አንዱ ናቸው። ፎርማጆ አሜሪካ ውስጥ የተመዘገቡ ሪፐብሊካን ነበሩ። ነገር ግን አገራቸውን ለማገልገል የአሜሪካ ዜግነታቸውን ትተው መጥተዋል። እርግጥ ነው አሜሪካውያን ስለ ሶማሊያ ሲያስቡ ትዝ የሚላቸው የ1991 የከሸፈ ወታደራዊ ተልዕኮ ይሆናል። በወቅቱ አንድ የጦር አበጋዝን ለመያዝ የመጡት አሜሪካውያን ድል ተነስተው ተመልሰዋል። ሁለት 'ብላክ ሃውክ' ሄሊኮፕተሮች ተመትተው ተጥለዋል፤ 18 የአሜሪካ ወታደሮች እና 500 ሶማሊያዊያን ተገድለዋል። የአሜሪካውያኑ ወታደሮች ሬሳ በሞቃዲሾ መንገዶች ላይ ሲጎተት የሚያሳየው ምስል አሜሪካውያን አስደንግጧል፤ አሸማቋል። ነገር ግን የትራምፕ መንግሥት አል-አሸባብን ለማጥፋት ሶማሊያ ውስጥ አሁንም ተልዕኮ ይፈፅማል። ሰው አልባ አውሮፕላኖች ይበራሉ። ልዩ ኃይሎች ማንነታቸውን ሸፍነው ይንቀሳቀሳሉ። ይህንን የሚያውቁ ግን ጥቂት አሜሪካውያን ናቸው። ሶማሊያ ከሦስት አሥርት ዓመታት በፊት ምስቅልቅሏ ሲወጣ በርካቶች አገር ጥለው ተሰደዋል። ሶማሊያውያን ከአጥናፍ አጥናፍ ይገኛሉ። ከአርክቲክ እስከ ኒውዚላንድ ሶማሊያውያን የማይገኙበት የምድር ክፍል የለም ማለት ማጋነን አይሆንም። በርካታ ጥቁሮችና ሙስሊሞች የሚኖሩባት የአሜሪካዋ ሚኒያፖሊስ ግዛት ደግሞ በርካታ ሶማሊያውያን የይገኙባታል። ከመስከረም 1 [ወይንም 9/11] ክስተት በኋላ ሙስሊሞች አሜሪካ ውስጥ ጥርጣሬ እንደሚታዩ ማድረጉ ሳይታለም የተፈታ ነው። ፕሬዝደንት ትራምፕም ለሙስሊሞች ያለውን አመለካከት ከማላላት ይልቅ እያባባሱት ይመስላሉ። ኢልሃን ለትራምፕ 'መልካም ስደተኛ' አይደለችም። ሂጃብ በኩራት የምትለብሰው ወጣቷ ፖለቲከኛ በአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሂጃብ ለብሳ ለመቅረብ ተከራክራ መርታቷ አይዘነጋም። የአሜሪካ ምርጫ አምስት ወራት ቀርተውታል። በእነዚህ ወራት ኢልሃን በፖለቲካ አቋሟ ሳይሆን በባህሏና እምነቷ ስትተችና ስትዘለፍ መስማት አያስደንቅ ይሆናል።
55706106
https://www.bbc.com/amharic/55706106
በማዕድን ጉድጓድ ውስጥ የታፈኑ ቻይናውያን የላኩት ማስታወሻ ተስፋ ፈንጥቋል
ከሳምንት በፊት በቻይና የወርቅ ማዕድን ማውጫ ከደረሰ ፍንዳታ በኋላ ከምድር በታች ታፍነው የሚገኙት 12 ማዕድን አውጪዎች በሕይወት መኖራቸውን አስታወቁ።
የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ ሠራተኞቹ አደጋው ከደረሰ ከሰባት ቀናት በኋላ ለሕይወት አድን ሠራተኞች "እኛን ለማግኘት ሙከራችሁን አታቁሙ" የሚል ማስታወሻ መላክ ችለዋል። የሌሎች 10 ማዕድን አውጪዎች ዕጣ ፈንታ ግን እስካሁን አልታወቀም፡፡ በቻይና የማዕድን አደጋዎች የተለመዱ ሲሆኑ ብዙውን ጊዜ በደንብ ባልተተገበሩ የደህንነት ደንቦች ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው፡፡ 22ቱም ሠራተኞች በምስራቅ ቻይና ሻንዶንግ አውራጃ በያንታይ አቅራቢያ በሚገኘው ሁሻን የማዕድን ማውጫ ጣቢያ ላይ በደረሰው ፍንዳታ ነው የታፈኑት። ፍንዳታው የማዕድን ማውጫውን መውጫ እና የግንኙነት ሥርዓት የጎዳ ሲሆን ጉዳቱን ለማስተካከል እየተሠራ ነው፡፡ የመንግሥት ሚዲያዎች እንደዘገቡት የነፍስ አድን ሠራተኞች ከአንዳንድ ማዕድን አውጪዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ ችለዋል፡፡ ወደ ጉድጓዱ ያወረዱት ገመድ ሲጎትት ከተሰማቸው በኋላ ምግብ፣ መድሃኒት፣ ወረቀት እና እርሳሶች ልከዋል፡፡ ከጉድጓዱ በተሰጣቸው ማስታወሻ በጻፉት መሠረት፤ 12 ሰዎች በማዕድን ማውጫው መካከለኛ ክፍል ውስጥ በሕይወት እንዳሉ የገለጹ ሲሆን የተቀሩት አስር ሰዎች ሁኔታ ግን ግልጽ አይደለም፡፡ 12ቱ ማዕድን አውጪዎች የህመም ማስታገሻ እና ተጨማሪ መድሃኒቶች መጠየቃቸውም ተገልጻል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ የከርሰ ምድር ውሃ እንዳለ ተናግረዋል፡፡ እንደ ቻይና ሚዲያ ዘገባ ከሆነ ከመግቢያው ወደ 600 ሜትር ርቀው ይገኛሉ የተባሉት ሠራተኞችን ለማዳን ተጨማሪ ማውጫ መስመሮች እየተቆፈሩ ነው፡፡ መጀመሪያ ላይ አደጋው ሪፖርት እስኪደረግ ከአንድ ቀን በላይ በመፍጀቱ የነፍስ አድን ሠራተኞች የማዕድን ሠራተኞቹን ለመድረስ እንዲዘገዩ ተገደዋል ተብሏል፡፡ የአከባቢው የኮሚኒስት ፓርቲ ፀሐፊ እና ከንቲባ በዚህ የ30 ሰዓት የመረጃ ልውውጥ መዘግየት ምክንያት ከሥራ ታግደዋል፡፡ በቻይና የማዕድን አደጋዎች ብዙውን ጊዜ የሚከሰቱት የደህንነት ደንቦች በአግባቡ ካለመተግበር ጋር የተቆራኙ ናቸው፡፡ ባለፈው ዓመት ታህሳስ በድንጋይ ከሰል ማዕድን ማውጫ የካርቦን ሞኖክሳይድ አፈትልኮ 23 የማዕድን ሠራተኞች ሞተዋል፡፡ በመስከረም ወር በቾንግኪንግ ዳርቻ በሚገኝ ሌላ የማዕድን ማውጫ ስፍራ 16 ሠራተኞች ሕይወታቸው አልፏል፡፡ በጎርጎሮሳዊያኑ ታህሳስ 2019 በደቡብ ምዕራብ ቻይና በጊዡ ግዛት በከሰል ማዕድን ማውጫ ስፍራ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 14 ሰዎች ሞተዋል፡፡
news-43511595
https://www.bbc.com/amharic/news-43511595
እውን የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ለኢትዮጵያ ጠቀሜታ አለው?
በሩዋንዳዋ ዋና ከተማ ኪጋሊ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያን ጨምሮ 44 የአፍሪካ ሃገራት መሪዎችና የሃገራት ተወካዮች አህጉሪቱን በነፃ የንግድ ልውውጥ ሊያስተሳስር የሚችል ስምምነትን ፈርመዋል።
ስምምነቱ 1.2 ቢሊዮን አፍሪካውያንን ተጠቃሚ እንደሚያደርግና ለሃገራት ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ እንዳለው እየተነገረም ይገኛል። እንደ አውሮፓ ሕብረት ዓይነት ቅርፅ ይዞ ለመንቀሳቀስ እያሰበ ያለው ይህ ቀጣና በአፍሪካ ሃገራት መካከል ድንበር የማያግዳቸው የንግድ ልውውጦች እንዲካሄዱ እንደሚያዝ፤ አልፎም ግብር እና አስመጭዎች ላይ የሚጫነውን ቀረጥ በማስቀረት በአህጉሪቱ ሃገራት መካከል ያለውን ነፃ ዝውውር እንደሚያበረታታ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ምንም እንኳ ኢትዮጵያን ጨምሮ 44 የአፍሪካ ሃገራት ስምምነቱ ይጠቅመናል ብለው ቢፈርሙም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የአፍሪካ ሃገራት በእኩል የዕድገት ደረጃ ላይ አለመሆናቸው ለማዕቀፉ ተፈፃሚነት ትልቅ እንቅፋት ነው ሲሉ ይሞግታሉ። ከእነዚህም መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍና ንግድ፣ ግብር፣ ፋይናንስና ኢንቨስትመንት መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ፍሰሃ-ፅዮን መንግሥቱ አንዱ ሲሆኑ ከስምምነቱ ቀድሞ መምጣት ያለበት ነገር እንዳለ ለቢቢሲ ይናገራሉ። "በጠቅላላቅ የአፍሪካን ሆነ የኢትዮጵያን ገበያ ሳናሳድግ አንድ ማዕከላዊ ገበያ መመስረታችን ጥቅሙ ለማን ነው?" በማለት ይጠይቃሉ ምሁሩ። ስምምነቱ ላይ ምንም ዓይነት ተቃውሞ እንደሌላቸው የሚያስረግጡት ፕሮፌሰር ፍሰሃ ከማዕቀፉ በፊት ሊሰሩ የሚገቡ በርካታ የቤት ሥራዎች እንዳሉ ይጠቁማሉ። "ቪሳ እንኳን ለማግኘት ችግር በሆነበት አህጉር ይህ ስምምነት ላይ መድረስ ትንሽ ችኮላ የበዛበት ይመስለኛል። እንደእኔ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ መሪዎች የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብር ውሳኔ ነው መወሰን ያለባቸው። ለሃገራችን ተስማሚ ሆኖ ካልተገኘ አንቀበለም ማለት መቻል አለባቸው። ማንኛውም ስምምነት ሲደረግ መለኪያው መሆን ያለበት አሁን ላለው እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ያለው በጎ አስተዋፅኦ ነው" ባይ ናቸው ምሁሩ። ነፃ የንግድ ቀጣናው ለኢትዮጵያዊያን አምራቾች የሚሰጠው ጥቅም ምንድነው? ጉዳቱስ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ፕሮፌሰር ፍሰሃ ምላሽ ሲሰጡ "ለምሳሌ ኬንያን እንመልከት። በቴክኖሎጂ፣ ኢንዱስትሪና በሰለጠነ የሰው ኃይል ከኛ የተሻሉ ናቸው። ወደእኛ ሃገር መጥተው ንግድ የሚያከናውኑ ከሆነ በእርግጠኝነት የእነሱ ጥቅም እንጂ የእኛ ጥቅም አይከበርም። ለአምራቹም ጉዳቱ የሚያመዝ ነው የሚሆነው።" "መሆን ያለበት ለእኛ ከሚበጁ ጋር አብሮ መስራት እንጂ ሁሉንም እሺ ብለን የምንቀበል ከሆነ ዘላቂ የሆነ ጥቅም አናገኝም፤ የሃገራችን አምራቾችም አይጠቀሙም" ይላሉ። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የወቅቱ ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በበኩላቸው ስምምነቱን ''መልካም ፈተና" ሲሉ ቢጠሩትም "የስኬት ጥማት እንዲኖረንና ድፍረት እንድናዳብር ኃይል ይሰጠናል" ብለዋል። ለስምምነቱ መሳካት የአህጉሪቱ ሃገራት ''ፖለቲካዊ ልዩነቶቻቸውን ማጥበብ ይኖርባቸዋል'' ሲሉም አሳስበዋል። የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት ኮሚሽን ስምምነቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ ''በዚህ ስምምነት 80 በመቶ በሚሆነው የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት እንዲሁም 70 በመቶ መደበኛ ያልሆነ ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች እና ወጣቶች ዋነኛ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ይላል። ሆኖም ግን ናይጄሪያን ጨምሮ ሌሎች 10 የአፍሪካ ሃገራት ይህን ስምምነት ለመፈረም አልፈቀዱም። ስምምነቱ እውን እንዲሆንና ተፈፃሚነቱ እንዲረጋገጥ 54ቱም የአፍሪካ ሃገራት ፊርማቸውን ማሳረፍ ግድ ይላቸዋል።
news-42400647
https://www.bbc.com/amharic/news-42400647
ስልክዎ ጥሩ አሽከርካሪ ሊያደርግዎ እንደሚችል ያስባሉ?
ቱዶር ኮባላስ የተባለ ሮማኒያዊ ወጣት በአንድ ወቅት ስልክ እያናገረ ሲነዳ መኪና ተጋጭቶ ይተርፋል። ከዚያም ስልክ በአግባቡ ካልተጠቀሙበት የመሳሪያ ያህል አጥፊ መሆኑን በመረዳት ሌሎችም እያሽከረከሩ ስልክ እንዳይጠቀሙ የሚያበረታታ መንገድ ይዘይዳል።
ሴፍ ድራይቭ (ጥንቃቄ ያልተለየው ማሽከርከር) በሚል ኮባላር ይሆናል ያለውን እርምጃ ጀመረ። ሴፍ ድራይቭ የሞባይል መተግበሪያ (አፕ) ሲሆን አሽከርካሪዎች አስር ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ ስልካቸው የመቆለፍ ምልክት ያሳያል ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስልካቸውን ምንም ሳይመለከቱ ያሽከረከሩ ሾፌሮች ነጥብ ይመዘገባል። እነዚህ ነጥቦች ተጠራቅመው ደግሞ በራሱ በሴፍ ድራይቭ ሱፐርማርኬት ቅናሸ ያስገኛሉ። በተቃራኒው እያሽከረከሩ ስልካቸውን ለመመልከት የሞከሩ ግን ነጥብ ይቀነስባቸዋል። ይህ ቀላል አሰራር እስካሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ መቶ ሺህ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን መሳብ የቻለ ሲሆን፤ ሰላሳ የንግድ አጋሮችንም ማፍራት ችሏል። ከነዚህ የንግድ አጋሮች መካከልም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ይገኙባቸዋል። ኮባላስ ታዳጊ ሾፌሮች ላይ ያተኮረ ማይልዝ የተሰኘ ሌላ የሞባይል መተግበሪያ ፈጥሯል። "ልጆቻቸውንና ወጣቶችን ማስተማር በሚፈልጉ አሜሪካዊያንን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ነው ይህን መተግበሪያ የሰራሁት"ብሏል። በተመሳሳይ የዚህኛው መተግበሪያ አሰራርም ቀላል ነው። በጥንቃቄ የሚያሽከረክሩ ታዳጊዎች በማይልዝ አማካኝነት ከወላጆቻቸውና ከዘመዶቻቸው ሽልማት ያገኛሉ። የኮባላዝ አገር ሮማኒያ በመኪና አደጋ ስሟ በክፉ የሚጠራ ነው። በአጠቃላይ አውሮፓ ከሚሊዮኖች 51.1 የሚሆኑ ህይወታቸውን የሚያጡት በመኪና አደጋ ነው። በሮማኒያ ደግሞ ይህ ቁጥር እጥፍ ይሆናል። የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.25 ሚሊዮን ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ያጣሉ። ለዚህ ደግሞ ለአብዛኛው አደጋ ስልክ እያነጋገሩ ማሽከርከር አይነተኛ ምክንያት ነው። ስልክ እያናገሩ የሚያሽከረክሩ አራት እጥፍ ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውን የድረጅቱ መረጃ ያሳያል። ይህንን ታሳቢ በማድረግ በርካታ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ስልክ እያነጋገሩ የሚፈጠርን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ ነው። ስማርት ስልኮች ለአደጋ ምክንያት እየሆኑ ቢሆንም ጥንቃቄ ለተሞላበት ማሽከርከርም ያግዙ ዘንድ መዋል እንደሚችሉ ማሳየት ግባቸው መሆኑን መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ባላክሪሻናን ይናገራሉ። ይህ ኩባንያም ድራይቭ ዌል የተባለ ሞባይል መተግበሪያ ሰርቷል። በተመሳሳይ ይህ ዘዴም አሽከርካሪዎች ምን ያህል ጊዜ በስልካቸው ይረበሻሉ የሚለውን የሚመዘግብ ነው። በሚመዘገበው ነጥብ መሰረት አሽከርካሪዎች ከጓደኞቻቸውና ከዘመዶቻቸው ጋር ይወዳደራሉ። የስልኮች ችግር አሁንም አሁንም እየጮሁና የመልዕክት ድምፅ እያሰሙ አሽከርካሪዎችን መረበሻቸው ነው። ነገር ግን እነዚህኑ ስልኮች የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ መጠቀም ይቻላል። አካሄዱም ጥሩ ውጤት እያስገኘ እንደሆነ የእንግሊዝን ጨምሮ የተለዩ አገራት ትራፊክ አደጋዎች መከላከል ተቋማት ያስታውቃሉ። ለምሳሌ የሞባይል ስልኮችን ተፅእኖ ለመቀነስ የስልክ መልዕክቶችን በድምፅ የሚቀይር መተግበሪያ ተሰርቷል። በተመሳሳይ እያሽከረከሩ ያሉ ሰዎች መልስ መስጠት ቢፈልጉ ያን በድምፅ ማድረግ ይችላሉ። መተግበሪያው መልዕክቶችን፣ ኢሜሎችንና የማህበራዊ ድረ-ገፅ መልዕክቶችን ወደ ድምፅ መቀየር ይችላል። በተጨማሪም ማንኛውንም ቋንቋ ማንበብ የሚችል ሲሆን ምላሽ መስጠት የሚችልው ግን በተወሰኑ ቋንቋዎች ብቻ ነው። አዳዲስ መኪናዎች መልዕክትን በድምፅ የማንበብ እድል የሚሰጡ ቢሆንም ምላሽ መስጠትን ግን የሚፈቅዱ አይደሉም። ስለዚህ የሞባይል መተግበሪያዎቹ ዓይነተኛ መፍትሄ ናቸው። ይህ መልዕክትን ወደ ድምፅ የሚቀይር የሞባይል መተግበሪያ ሃያ ሁለት ሺህ ተጠቃሚዎች አሉት። አንድ ጥያቄ ግን እየተነሳ ነው። እጆች ነፃ መሆናቸው ከአደጋ ነፃ ያደርጋል ወይ? የሚል። ምክንያቱም አሽከርካሪዎች በድምፅ መልዕክት ሲቀበሉና ሲመልሱም ሃሳባቸው ሊሰረቅ ይችላልና። ከዚህ በመነሳት ጉዞ ከመጀመር በፊት የስልክ መልዕክት ማሳያን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት የተሻለው እርምጃ እንደሆነ እየተገለፀ ነው።
news-41410787
https://www.bbc.com/amharic/news-41410787
የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በተለይም በምርጫ ማግስት የብዙዎች ዓይን ያርፍባቸዋል።
ኮከብ ለሽልማቱ ከአምስት አፍሪካውያን ዲዛይነሮች ጋር ትወዳደራለች ከነዚህ ዳኞች ጀርባ ደግሞ አንዲት ኢትዮጵያዊት አለች- ዲዛይነር ኮከብ ዘመድ። በአውሮፓውያኑ 2013 በቅኝ ከተገዙባት ብሪታኒያ የመጣው አለባበስ የነጻይቱ ኬንያ ተምሳሌት በሆነ ልብስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀየረው ኮከብ በምትመራው ኮኪ ዲዛይንስ ነው። በዳኞቹ ልብስ ላይ አረንጓዴው ጨርቅ የኬንያን ህገ-መንግስት ሲወክል በዙሪያው ያለው ወርቃማ ቀለም ደግሞ የፍርድ ቤቱ ህንጻ ተምሳሌት ነው። ይህ ስራ ኮከብ ከስራዎቿ ሁሉ በጣም የምትደሰትበትና የምትኮራበት ነው። ከወራት በፊት ልብሱ በአዲስ መልክ ቢቀየርም ፈር ቀዳጅ በመሆኑ በፍርድ ቤቱ ሙዚየም ለእይታ ቀርቧል። የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ከነጻነት በኋላ ራሳቸውን የሚወክል ካባ መልበስ የጀመሩት በኢትዮጵያዊቷ ኮከብ በተሰራላቸው ልብስ ነው። ይህ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ልብስ ለአራት ዓመታት አገልግሏል ወደ ቤቷ ስንሄድ የተቀበለችንም ከስድሳ ዓመታት በፊት አያቷ ሲያጌጡበት በነበረው የሀገር ባህል ልብስ ላይ ባለፈው ዓመት ከሱፍ ጨርቅ ያዘጋጀችውን የአንገት ልብስ ያለውን ካባ ደረብ አድርጋ ነው። ፋሽንና ባህል ሊነጣጠሉ አይችሉም፤ ይልቅስ አንዱ ሌላውን ይደግፋል የምትለው የኮኪ ዲዛይንስ መስራችና ባለቤት ኮከብ ዘመድ ፋሽን ባህልን ወደፊት የማሻገር ሚና የ60 ዓመታት ልዩነትን ባስታረቀ አለባበሷ ትመሰክራለች። ናይሮቢ መኖር ከጀመረች 17 ዓመታት ቢያልፉም በመኖሪያዋም ሆነ በመስሪያ ቦታዋ ያሉት ቁሳቁሶ፣ የሃገር ባህል አልብሳትና ጥልፎች ዘወትር ከሚጎዘጎዘው ቡና ጋር ተዳምረው ከኢትዮጵያ ውጪ መሆኑን ያስረሳል። ኮከብ ከአውሮፓውያኑ 2009 ጀምሮ ባቋቋመችው ኮኪ ዲዛይንስ የኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አልባሳትን እያዋሃደች የአፍሪካን ባህል በማስተሳሷሯ በናይሮቢ እውቅናን እያገኘች ነው። "በእኛ ጨርቅ ላይ በመመስረት ኮትና ቀሚስ እሰራለሁ፤ ወይም ደግሞ በየቀኑ የሚለበስ ልብስ ላይ ጥለቱን ብቻ አድርጌ ከሌላ ጨርቅ ጋራ አዋህደዋለሁ፤ መጀመሪያ አልፈለግኩትም ነበር፤ ምክንያቱም ያለፈውን መሰባበር ወይም መቀየጥ ሆኖ ነበር የሚታየኝ ፤ አሁን ግን ሳስበው እንደውም ትንሽ ጥለት ኖሮት የኛንም ባህል ቢያስተዋውቅስ?" በሚል ትጠይቃለች። የኢትዮጵያ ጥለቶች ከሌሎች ጨርቆች ጋር በቅይጥ ይሰራሉ። ከደንበኞቿ አብዛኞቹ ኬንያውያን ናቸው፤ "የኢትዮጵያን ባህላዊ ጨርቆችና ጥለቶች በጣም ይወዷቸዋል" ትላለች ኮከብ። ከእነዚህና ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ልብስ በተጨማሪ ደግሞ ሌሎች አፍሪካውያን የሚቀምሙላትን ባህላዊና ዘመናዊ ልብሶች ታዘጋጃለች። ለሴቶች ፣ ለወንዶችና ለልጆች ለልዩ ዝግጅት፣ ለስራ ቦታና ለበዓላት የሚሆኑ ንድፎችን ቀርጻ በተለያዩ የፋሽን ትርዒቶች ላይ ታሳያለች፤ ለገበያም ታቀርበለች። አሁን ደግሞ ለ2017 ምርጥ የምስራቅ አፍሪካ ዲዛይነር ሽልማት እጩ ሆና ተመርጣለች። "እዚሁ ኬንያ የተመረቱ ጨርቆችን ተጠቅሜ አዳዲስ ዲዛይኖችን ሰርቻለሁ፤ የኢትዮጵያንም የሃገር ቤት ስሪት የሆኑ ልብሶችን ነው በአዲስ እይታና ዲዛይን የምሰራው፡ በዛ ላይ ደግሞ ከአውሮፓውያኑ 2009 እስካሁን በኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ ሆኜ መዝለቄም ለእጩነቴ መንገድ ከፍቶልኝ ይሆናል" ትላለች ውድድሩ ራሷን ወደ ዓለም ገበያ ለመቀላቀል ጥሩ አጋጣሚ እንደሚፈጥርላት የምትጠብቀው ኮከብ። የሽልማቱ አላማ በኢንዱስትሪው የራሳቸውን አዲስ እይታ ተጠቅመው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ዲዛይነሮች ክብር መስጠት እንደሆነ በአዘጋጆቹ ድረገጽ ላይ ሰፍሯል። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ ደግሞ አዳዲስ ፈጠራ ፣ ጥሩ የዲዛይን አጨራረስ፣ የግል ምልከታ የሚታይባቸውና ለሌሎች አርአያ መሆናቸውን ይጨምራል። ኮከብ ለዚህ ሽልማት ከኬንያ፣ ከሩዋንዳና ከታንዛኒያ እጩ ከሆኑ አምስት ሌሎች ዲዛይነሮች ጋር ትፎካከራለች። በ2017 በሰባት የፋሽን ትርዒቶች ላይ ተሳትፋለች የሽልማት ስነስርዓቱ በድረ ገጽ ከአድናቂዎች የሚሰጡ ድምጾች ከባለሙያዎች ዳኝነት ጋር ተዳምረው ውጤቱ መስከረም 27 ይካሄዳል።። ታዲያ ኮከብ ባለፉት ስምንት ዓመታት ሁሉ ነገር አልሰመረላትም ፤ በተለይም በጅማሬዋ አካባቢ በዙ ተማርኩባቸው የምትለውን ስህተቶች ሰርታለች። "መጀመሪያ የሰራሁት ልብስ አሁንም ድረስ አለ፤ በርካሽ ጨርቅ ናሙና ሰርቼ መሞከር ነበረብኝ። እኔ ግን ሳላውቅ በራሱ በሳባ ቀሚስ ሰራሁትና ጥሩ ስላልነበር ገዢ አጣ ፤ እኔም ከነኪሳራዬ ይሁን ብዬ ዝም አለኩ " በእርግጥ እናቷ ገና በልጅነቷ ጥልፍ አስተምረዋታል ፤ እርሷም ብትሆን የተለየ ልብስ መልበስና ለልጆቿም ልብስ መስፋትን ትወድ ነበር። ነገር ግን ይህንን እንደመዝናኛ እንጂ እንደስራ ለማሰብ ብዙ ዓመታትን ፈጅቶባታል፤ ይህም ዋጋ አስከፍሏታል። "በራስ መተማመኑን አሰራሩንም ሆነ ቴክኒኩን ከመጀመሪያው አዳብሬው ቢሆን ኖሮ ድሮ ነበር ዲዛይነር የምሆነው። ስጀምርም እውቀቱ ስላልነበረኝ ማን ነው የሚገዛኝ? ለማንስ ነው የምሰራው? የሚለው ነገር አላሳሰበኝም ነበር " ኮከብ በጅማሬዋ ለኬንያም ሆነ ለዘርፉ እንግዳ ነበረችና ሁኔታዎችን በአግባቡ ለመረዳት ጊዜ ወስዶባታል። ሂደቱን ግን ያቀለለልኝ የኬንያውያን አቀባበልና አዲስ ነገር ለመሞከር ያሳዩት ፍላጎት ነው ባይ ነች- ኮከብ ። በዚህ በመበረታታት ኮኪ ዲዛይንን ባቋቋመች በሶስተኛ ወሯ የመጀመሪያውን የፋሽን ትርዒት አቀረበች። ኮከብ እንደምትለው ያለፉት ስምንት ዓመታት ስኬቶች ሁሌም ጅማሬያቸው ሃሳብ ነው። "ብዙ ጊዜ ሃሳቡ ሲመጣልኝ ሌሊት ብድግ እላለሁ፤ አዲስ ነገር አስቤ ጠዋት እስክሰራው ድረስ ልቤ አትረጋም፤ ቶሎ ተነስቼ ንድፉን እስለዋለሁ።" "የዲዛይን ንድፎች ሁልጊዜም ስራዬን ያቀላጥፉልኛል" ሁልጊዜም የመጀመሪያ ስራዎቿን የምትሞክረው በራሷ ላይ ነው ። ምክንያቷ ደግሞ ደንበኞቼ ላይ የሚፈጥረውን ስሜት በትክክል እረዳበታለሁ የሚል ነው። " ውጥን ሃሳቤ በተግባር ምን እንደሚመስል ትክክለኛ ስሜቱን አገኘዋለሁ፤ የማይንቀሳቀሱና የተዋጣ ሰውነት የተሰራላቸው ግዑዝ አሻንጉሊቶች ውበቱን እንጂ ተግባራዊነቱን አያሳዩንም " ኮከብ ድርጅቷ ኮኪ ዲዛይንስ ከአምስት ዓመታት በኋላ ይበልጥ የተደራጀና ዘላቂ ሥራ ይዞ ምርቱን ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያደርስ ትልቅ የፋሽን ቤት እንዲሆን ወጥናለታለች። እስከዛው ግን እቅዶቿን በቶሎ ለማሳካት ተስፋ የጣለችበትን የ2017 የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ዲዛይነሮች ሽልማት በጉጉት ትጠብቃለች።
news-53075009
https://www.bbc.com/amharic/news-53075009
በአሜሪካ የደኅንነት ምስጢር ይዟል የተባለው መጽሐፍ እንዳይሰራጭ ክስ ተመሰረተ
የአሜሪካ የፍትህ ቢሮ በቀድሞው የዶናልድ ትራምፕ የደኅንነት ከፍተኛ አማካሪ ጆን ቦልተን ላይ ክስ ከፍቷል።
ጆን ቦልተን ክሱ ጆን ቦልተን የጻፉትና በኅትመት ላይ ያለ መጽሐፍ ታትሞ እንዳይሰራጭ ለማገድ የታሰበ ነው። ክሱ እንደሚያስረዳው ጆን ቦልተን መጽሐፋቸው ላይ ለሕዝብ ይፋ መደረግ የሌለበት ከፍተኛ የአገር ደኅንነት ምስጢርን ይዟል። ይህ ክስ የተከፈተው ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞው አማካሪያቸው ጆን ቦልተንን "በወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ይችላል" ብለው ካስጠነቀቁ በኋላ ነው። ይህ መጽሐፍ "ዘ ሩም ዌር ኢት ሃፕንድ" የሚል ርዕስ ሲኖረው በሰኔ 23 ሊመረቅ ቀጠሮ ተይዞለታል። መጽሐፉ ቦልተን ከእኔ ጋር ያደረገውን እያንዳንዱን የደኅንነት ጉዳይ የያዘ ነው፤ ይህ ማለት ይሄ ሰውዬ መጽሐፍ ከጻፈና ያን መጽሐፍ ካሳተመው በወንጀል መጠየቁ አይቀርለትም ብለዋል ዶናልድ ትራምፕ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች። የአሜሪካ ሲቪል ሊበርቲ ዩኒየን በበኩሉ የትራምፕ አስተዳደር ይህን መጽሐፍ ለማዳፈን የሚያደርገው ሙከራ ሁሉ ከንቱ ነው ሲል ተችቷል። የቦልተን ጠበቃ ቻርለስ ኩፐር ለተከፈተባቸው ክስ በቂ ምላሽ እያዘጋጁ እንደሆነ አረጋግጠዋል። ባለፈው ጥር ዋይት ሀውስ ጆን ቦልተን እየጻፉት ያለው መጽሐፍ ከፍተኛ የአገር ምስጢር ስለያዘ እንዳይታተም አስጠንቅቆ ነበር። ጆን ቦልተን ግን ማስጠንቀቂያውን ቸል ብለውታል። ይህ መጽሐፍ ይዟቸዋል ከተባሉ ምስጢሮች አንዱ ዶናልድ ትራምፕ ለዩክሬን ሊሰጥ የነበረውን ወታደራዊ የገንዘብ እርዳታ ለእራሳቸው ጥቅም ሲሉ አዘግይተዋል የሚል ነው። ይህም ጉዳይ ፕሬዝዳንቱን አስከስሷቸው እንደነበር አይዘነጋም። ፕሬዝዳንቱ የዩክሬን እርዳታ እንዲዘገይ ያደረጉት በምላሹ የዩክሬን መንግሥት የእርሳቸው ተፎካካሪ የሆኑት ጆ ባይደንና ልጃቸው ሀንተር በዩክሬን የሙስና ክስ ከፍቶ እንዲመረምራቸው ለማግባባት ነበር ተብሏል። የዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ የደኅንነት አማካሪ የነበሩት ጆን ቦልተን ወደ ዋይት ሃውስ የመጡት በሚያዚያ 2018 ሲሆን በቀጣዩ ዓመት መስከረም ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል። ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ቦልተን መቼ በገዛ ፈቃዱ ሥራ ለቀቀ፤ እኔ ነኝ ያባረርኩት ይላሉ።
49786244
https://www.bbc.com/amharic/49786244
ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዙት የአል ሸባብና የአይ ኤስ አባላት ማንነት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ሥፍራዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ላይ የነበሩ የተባሉ የአል-ሸባብና የአይ ኤስ ቡድን አባላት መያዛቸው ተገለጸ።
ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በቁጥጥር ስር ስለዋሉት ተጠርጣሪዎች ማንነት እና ስለተያዙበት ሁኔታ በዝርዝር ገልጿል። የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ቅዳሜ ምሽት ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው አልሸባብ እና አይ ኤስ ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃት በመፈፀም በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ በዝግጅት ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል። • የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ 'በአየር ጥቃት መገደሉ' ተነገረ • አልቃይዳ ከወዴት አለ? የአገር መከላከያ ሠራዊት፤ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በርካታ የጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን-አይኤስ አባላትን በቁጥጥር ሥር አዋልኩ ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል። የኢታማዦር ሹሙ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ኮለኔል ተስፋዬ አያሌው ከአንድ ሳምንት በፊት የጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሞያሌ እና ዶሎ ከተማዎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ውስጥ መያዛቸውን ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሶማሊያ፣ የሶሪያ እና የየመን ዜጎች እንደሚገኙበት ኮለኔል ተስፋዬ ተናግረዋል። "አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች አማርኛ ቋንቋ ተምረው የተላኩ ናቸው" ሲሉም አክለው ነበር። ህዝብ የሚበዛባቸውን ቦታዎች እንዲሁም የሀይማኖት ክብረ በዓል የሚካሄድባቸውንና የተለያዩ ሆቴሎችን የመለየትና የፎቶግራፍ መረጃዎችን የመሰብሰብ ጥናት ካደረገ በኋላ ጥቃት ለመፈጸም በጅቡቲ በኩል ወደ አዲስ አበባ የገባው አንደኛው የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባል ሙሐመድ አብዱላሂ ዱለት፤ ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ መያዙን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ገልጿል። ከግለሰቡ በተጨማሪ ሌሎች ተባባሪዎች ለተለያዩ የጥቃት ተልዕኮዎች ከጅቡቲና ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውንና ከሃገራቱ የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ስር እንደዋሉም ተነግሯል። ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በቁጥጥር ስር ስለዋሉት ተጠርጣሪዎች ማንነት እና ስለተያዙበት ሁኔታ በዝርዝር ገልጿል። ከአል-ሸባብ በተጨማሪ የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት ከቦሳሶ በሶማሌላንድ ሃርጌሳ በኩል ወደ አዲስ አበባ በመግባት የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በብሔሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በአዲስ አበባና በአዋሽ አካባቢ መያዛቸው ተገልጿል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት የቡድኖቹ አባላት በተጨማሪ የሚጠቀሙባቸው የግንኙነት መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች መያዙም ተጠቅሷል። • መከላከያ የሶሪያ እና የየመን ዜጋ የሆኑ የአይኤስ አባላትን በቁጥጥር ሥር አዋልኩ አለ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እነማን ናቸው? ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በቁጥጥር ስር የዋሉትን ግለሰቦች ማንነት እና የት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት፤ የአል-ሸባብ የሽብር ቡድንን የሚመራው ሙሐመድ አብዱላሂ ዱለት በሀሰተኛ ስሙ ያህያ አሊ ሃሰን በጅቡቲ በኩል ወደ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ቦሌ አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል። የሙሐመድ አብዱላሂ ዱለት ግብረ አበሮች የሆኑት አብደክ መሃመድ ሁሴን፣ ሬድዋን መሃመድ ሁሴን እና በቅፅል ስሙ ስመተር መሀመድ ኢማን ዩሱፍ በመባል የሚታወቀው ጅቡቲ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ከደቡባዊ ሶማሊያ በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩት ይሳቅ አሊ አደን እና አደን ሙሃሙድ መሃመድ በቅፅል ስሙ አደን ቦራይ ሱማሊላንድ ውስጥ ተይዘዋል። ይሳቅ አሊ አደን ከሶማሌ ክልል ቦህ ወረዳ ጨርቃን ቀበሌ የተሰጠ የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ የተገኘ ሲሆን፤ አደን ሙሃሙድ መሃመድ የሚባለው ተጠርጣሪ ደግሞ በስሙ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2.5 ሚሊዮን ተቀማጭ ብር ተገኝቷል። መካከል ዒድ መሃመድ ዓሊ የተባለ ተጠርጣሪ በሶማሌ ክልል ጨርጨር ዞን አራርሶ ወረዳ፣ በሽር ዑስማን አብዲ በሶማሌ ክልል ፊቅ አከባቢ እንዲሁም ዑስማን አሊ ሁሴን በኦሮሚያ ክልል በሞያሌ ከተማ በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአይ ኤስ አባል የሆነው ፋዕድ አብሽር የሱፍ ከቦሳሶ ሶማሊያ በሃርጌሳ ፑንትላንድ በኩል አድርጎ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ሙህመድ ጉሀድ ቡዲል የተባለው ተጠርጣሪ ደግሞ ሶማሌ ክልል በአፍዴር ዞን ምዕራብ ኢሚ ወረዳ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዉሏል። ሌላ የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባል የሆነ ሰይድ ዑመር ሸበሺ የተባለው ተጠርጣሪ በፀጥታ አካላት በአዋሽ አካባቢ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል። የሸብር ቡድኖችን በመከታተል በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለማድረግ በተካሄደው የኦፕሬሽን የጁቡቲ፣ የሶማሊላንድ፣ የፑንትላንድ፣ የአሜሪካ፤ የጣሊያን፣ የፈረንሳይና የስፔን የመረጃ ተቋማት እገዛ ማድረጋቸውን ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በመግለጫው አሳውቋል። ከዚህ ቀደም አይኤስ በአማርኛ ቋንቋ የጽሑፍ መልዕክቶችን በቴሌግራም አማካኝነት ማስተላለፍ እንደሚጀምር ማስታወቂያ አሰራጭቶ እንደነበረ ይታወሳል። የኢታማዦር ሹሙ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮለኔል ተስፋዬ "የአገራችን የደህንነት ጥበቃ ጠንካራ ስለሆነ ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው መግባት ባለመቻላቸው፤ ፕሮፖጋንዳ ብቻ ነው የሚነዙት። ድንበር አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረግን ነው" ብለው ነበር።
news-52279889
https://www.bbc.com/amharic/news-52279889
ኮሮናቫይረስ፡ ከሳኡዲ አረቢያ የሚመለሱት ስደተኞች በኮሮናቫይረስ ምክንያት አይደለም
የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ እየተደረጉ ያሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኮሮናቫይረስ ምክንያት አይደለም አለ።
ፎቶ ፋይል። እአአ 2013 ላይ ከሳዑዲ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ስደተኞች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ። በውጪ ጉዳይ ሚንስትር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ሾዴ፤ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከዚህ ቀደምም የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳኡዲ መንግሥት ጋር ባለው ዲፕሎማሲያዊ ግነኙነት ሲመለሱ ነበር ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ቫይረሱ ከተገነባቸው ሰዎች መካከል በርካታዎቹ ከውጪ አገራት በተለይ ደግሞ ከመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በዋናነት በዱባይ በኩል የመጡ መሆናቸው በስፋት ሲነገር ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሳኡዲ አረቢያ በአገሯ የሚገኙ 'ሕገ ወጥ' ያለቻቸውን ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እያደረገች መሆኑ ጥያቄ እያስነሳ ይገኛል። አገሪቱ በግዛቷ ውስጥ የሚታየውን የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደች ባለችበት በዚህ ወቅት ስደተኞችን መመለሱ እየተደረገው ባለው ጥረትና በጤና ሥርዓቷ ላይ ተጨማሪ ጫናን ሊፈጥር ይችላል የሚሉ ስጋቶች መነጋገሪያ ሆኗል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት በርካታ ስደተኞች ከሳኡዲ እና ከሌሎች አገራት መመለሳቸው የሚጠቅሱት አቶ ዮሐንስ ስደተኞቹ አሁን እተመለሱ ያሉት “ኮሮናቫይረስ ስለተከሰተ አይደለም” ብለዋል። አቶ ዮሐንስ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች መመለሳቸውንም ያስታወቁ ሲሆን፤ ከሳኡዲ መንግሥት ጋር በሚደረግ ግነኙነት መሠረት ስደተኞቹ ከሳኡዲ ከመነሳታቸው በፊት ለ14 ቀናት ተለይተው የሚቆዩበት ቦታ ዝግጁ ሲሆን እንደሚመጡ ተናግረዋል። የሰደተኞቹ ወደ አገር ቤት መመለስ የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ መከላከል አቅም ላይ ጫና አያሳድርም ወይ ተብለው የጠየቁት አቶ ዮሐንስ፤ ሰደተኞቹ የሚመለሱት ከሳኡዲ መንግሥት ጋር የሚደረግ ንግግርን ተከትሎ፤ ኢትዮጵያ ለስደተኞቹ ማረፊያ ቦታ ካዘጋጀች በኋላ እንደሚላኩ ጠቅሰዋል። አቶ ዮሐንስ ጨምረውም “የሳኡዲ መንግሥት በተቻለው አቅም እዚያ ለሚገኙት ድጋፍ እያደረገ ነው። ምርመራም እያደረገ ነው። ወደዚህ የሚመጡትም ተመርምረው ነው እየተላኩ ያሉት” ብለዋል። በዚህ ወቅት ስደተኞችን አንቀበልም ለማለት አስቸጋሪ መሆኑን የሚጠቅሱት አቶ ዮሐንስ “አንድ ሉዓላዊ አገር በሕገ-ወጥ መንገድ የሄደውን ዜጋህን ውሰድ ሲልህ ‘አይ አንቀበልም’ ማለት አንችልም” ብለዋል። ሰደተኞቹ በሳኡዲ መንግሥት ወጪ በልዩ በረራ እየተመለሱ መሆኑን ጠቁመው፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተቋቋመው ግብረ ኃይል ደግሞ ስደተኞቹ ወደተዘጋጁላቸው ስፍራዎች እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል። ተመሳሽ ስደተኞቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ጨምሮ በሆቴሎች እንዲያርፉ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በቅርቡ በቻናይ በሚገኙ አፍሪካውያን ላይ ከኮሮናቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ መገለል እና መድሎ እየደረሰ ነው የሚሉ ሪፖርቶች በስፋት ተሰምተዋል። የውጪ ጉዳይ ሚንሰቴር በቻይና በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰ መገለል ካለ የተጠየቁት አቶ ዮሐንስ፤ በቻይና ከ100-150 የሚገመቱ ተማሪዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ብዙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አለመኖሩን ተናግረዋል። “ገና መጀመሪያ ላይ የቫይረሱ ስርጭት ሲጀምር የቻይና መንግሥት ከዜጎቹ በላይ ለኢትዮጵያውን ተማሪዎች ቅድሚያ ሰጥቶ ጥበቃ ተደርጎላቸው አንድም ተማሪ በቫይረሱ አልተያዘም" ብለዋል። "በዚህም የቻይና መንግሥት ሊመሰገን ይገባል” ብለዋል።
news-46943494
https://www.bbc.com/amharic/news-46943494
ያሳደጋቸው ሦስት ልጆች የእራሱ አለመሆናቸውን ያወቀው እንግሊዛዊ ቱጃር
"በመዶሻ የተመታሁ የክል ነው የተሰማኝ።" በማለት ነበር የ54 ዓመቱ ቱጃር መውለድ እንደማይችል ሲነገረው የተሰማውን ስሜት የገለጸው።
ሪቻርድ ማሶን እውነቱን ሲገነዘብ የተሰማውን ለቢቢሲ ተናግሯል ባለጸጋው ሪቻርድ ሜሰን 'ሲስቲክ ፋይብሮሲስ' የተሰኝ የጤና ችግር እንዳለበት ከሁለት ዓመት በፊት ነበር የተነገረው። 'ሲስቲክ ፋይብሮሲስ' የሚጠቁ ከ97-98 በመቶ መውለድ አይችሉም። ሪቻርድን ለከፍተኛ ደንጋጤ የዳረገው ግን በዘር በሚተላለፈው በሽታ 'ሲስቲክ ፋይብሮሲስ' መያዙን ማወቁ አልነበረም። የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው? የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም የሶስት ልጆች አባት ነኝ ብሎ የሚያስበውን አባት ክፉኛ ያስደነገጠው ግን ከልጅነቱ ጀምሮ መሃን እንደሆነ ማወቁ ነበር። ሪቻርድ አንድ እውነታ ተገልጦለታል። ይህም ከቀድሞ ሚሰቱ ወልጃለሁ ብሎ ያሰባቸው ሦስቱ ልጆቹ የእርሱ አለመሆናቸውን። "'ሲስቲክ ፋይብሮሲስ' ያለባቸው ወንዶች በሙሉ መሃን መሆናቸውን እና የመውለድ እድላቸውም ዝቅተኛ መሆኑ ነው ሃኪሞች የነገሩኝ" በማለት ለቢቢሲ ሬድዮ ፋይቭ ላይቭ ተናግሯል። የዘረመል ምርመራ ሦስቱም ልጆች ከሪቻርድ አለመወለዳቸውን አረጋግጠዋል "ዶክተሮቹ ተሳስተው መስሎኝ ነበር። እነርሱ ግን እርግጠኛ መሆናቸውን እና የቅድሞ ባለቤቴን ማነጋገር እንደሚኖርብኝ መከሩኝ" ሪቻርድ ከአዲሷ ባለቤቱ ኤማ ጋር መውለድ ሲያቅታቸው ነበር ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ያቀኑት። ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ? ጎዳና ተዳዳሪዎችን በህክምና መታደግ ሪቻርድ ከቅድሞ ባለቤቱ ኬት ጋር ፍቺ የፈጸሙት ከ20 ዓመታት የጋብቻ ህይወት በኋላ ነበረ። በህክምና ውጤት ግራ የተጋባው ሪቻርድ የቀድሞ ባለቤቱን በጉዳዩ ላይ ያነጋግራታል። የቀድሞ የትዳር አጋሩም የ19 ዓመት መንታዮቹ ኤድ እና ጆኤል የ23ዓመቱ ታላቃቸው ዊሌም ጭምር ልጆቹ እንደሆኑ ተትነግረዋለች። የዘረመል ምርመራው ግን ይህ አለመሆኑን አረጋግጧል። "ይህ ሁሉ በሚፈጠርበት ጊዜ ጆሮዬ ውስጥ የሚደውልበኝ ነገር ነበር" ብሏል። በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሠረት የሪቻርድ የቀድሞ ባለቤት የልጆቹን አባት ትክክለኛ ማንነነት አለማሳወቅ ትችላለች በማለት ፈርዷል "ሁሉም ነገር ግራ አጋባኝ። የአባታቸው ማንነት እንቅልፍ ነሳኝ" የቀድሞ ባለቤቱ ከሪቻርድ ጋር ስትለያይ 5 ሚሊዮን ዶላር ወስዳ ነበረ። ሪቻርድ ለተፈጸመበት በደል የቀድሞ ባለቤቱን ፍርድ ቤት ገተራት። ለደረሰበት ጉዳትም 320 ሺህ ዶላር ካሳ እንድትከፍል ፍርድ ቤቱ የወሰነባት ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ጨምሮም የልጆቹን አባት ማንነት ያለመናገር መብት ፍቅዶላታል። "የቀድሞ ባለቤቱ የልጆቹን አባት ማንነነት ማሳወቅ አልፈለገችም። ይህ ለምን እንደሆነ አላወቅንም። ለዚህም ነው የገንዘብ ካሳ ለመክፈል የተስማማችው። ፍርድ ቤቱም ይህን መብት ሰጥቷል" በማለት የሪቻርድ የሕግ አማካሪ ሮጀር ቴሬል ለዴይሊ ቴሌግራፍ ተናግሯል ። ሪቻርድ ማሶን እና አሁኗ ባለቤቱ ጋር "ወደፊት ልጆቹ የአባታቸውን ማንነት ማወቅ መፈለጋቸው አይቀርም። ጊዜው ሲደርስ ደግሞ መረጃው ይኖረኛል። የሰውዬውን ማንነት ማወቅ አልቻልኩም። ከጓደኞቼ መካከል መሆኑን አላውቅም ግን የቅርብ ሰው ሊሆን ይችላል" ይላል ሪቻርድ። "ልጆቹ ኳስ ሲጫወቱ ከአጠገቤ ሆኖ ሲመለከት የኖረ ሰው ሊሆን ይችላል። ወይም በትምህርት ቤታቸው በሚደረጉ የወላጆች ጥሪዎችም ላይ ተሳታፊ ሆኖ ይሆናል" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል። አክሎም "እንደዚህ ዓይነት ምስጢር በሕይወት ውስጥ ሲያጋጥምና በተለይ ከባድ ተጽዕኖ ያደረሰ ሲሆን የበለጠ ለማወቅ ያጓጓል" ብሏል። ሪቻርድ ማሶን የልጆቹን ትክክለኛ አባት ማንነት ለሚነግረው ሰው 6400 ዶላር እንደሚከፍል ተናግሯል። • አዲስ የፀረ-ተህዋስ ዝርያ በአፈር ውስጥ ተገኘ ዴይሊ ሜል የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ የሪቻርድ የቀድሞ ባለቤት ትሠራበት በነበረው ባርክሌ ባንክ አብሯት ይሠራ ከነበረ ሰው ጋር በተለያዩ ጊዜያት የፍቅር ግንኙነት ጀምረዋል ብሎ የሚገመተው ግለሰብ የልጆቹ አባት ሊሆን እንደሚችል እንደሚጠረጥር ነግሮኛል ሲል ዘግቧል። ቢቢሲ ኬትን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። • በጀርባቸው የሚተኙ ነፍሰጡሮች ህይወት የሌለው ልጅ እየወለዱ ነው • የወባ ትንኝ አደገኛ የሆነችው በሂደት ነው የግንኙነት መቋረጥ በክሱ ምክንያት ሁለቱ ልጆች ከሪቻርድ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ አቋርጠዋል። "እንቅስቃሴያቸውን በሙሉ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እከታተላለሁ። ታላቁ ልጅ ከቀርብ ጊዜ በፊት ተመረቀ እኔ ግን አልተጠራሁም ነበር። ይህ ደግሞ በጣም ያሳዝነኛል" በማለት ለዴይሊ ሜል ተናግሯል። ኤድ የተሰኘው ከመንትዮቹ አንዱ ብቻ ነው ከሪቻርድ ጋር ግንኙነት ያለው። ጆኤል የተሰኘው ከመንትያዎቹ አንዱ ባሳለፍነው ሳምንት ለዴይሊ ሜል ሲናገር የሪቻርድን ውሳኔዎች ተችቷል። "ሰዎችን የሚጨቁን ሰው ነው። ከእርሱ ጋር ብዙ ጊዜ የማሳለፍ ፍላጎት አይፈጥርም። ከ15 ዓመቴ ጀምሮ ነው ይህ እየታወቀኝ የመጣው" ብሏል። አክሎም ወላጅ አባቱን የማግኘት ፍላጎት እንደሌለውም ተናግሯል።
news-52796482
https://www.bbc.com/amharic/news-52796482
ኮሮናቫይረስ፡' 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር "ዓለም ለ10 ዓመታት ትማቅቃለች" አሉ
ኖሪኤል ሮቢኒ ስመ ጥር የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰር ናቸው። መጪውን ዘመን በመተንበይ ይታወቃሉ። ሆኖም ሰውየው በጎ በጎው ስለማይታያቸው 'ጨለምተኛው ኢኮኖሚስት' የሚል ቅጽል ተበጅቶላቸዋል።
ፕሮፌሰር ኖሪኤል ሮቢኒ ትንቢታቸው ጠብ አይልም የሚባሉት ፕሮፌሰር ሮቢኒ ከዚህ በፊት ባንኮችና የቁጠባ ቤት ገዢዎች በፈጠሩት ሀሳዊ የቢዝነስ ሽርክና የዓለም ኢኮኖሚ ይናጋል ብለው ከማንም በፊት ተንብየው ነበር፤ እንዳሉትም ሰመረላቸው። ይህ የሆነው በፈረንጆች 2008 የዛሬ 12 ዓመት ነበር። ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ቀድመው ያዩት እኚህ ሰው ታዲያ ከሰሞኑ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኮቪድ-19 የፈጠረው ምስቅልቅል ቢያንስ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ዓለምን ያናጋታል፤ የዓለም ምጣኔ ሃብትም ለ10 ዓመታት ይማቅቃል ብለዋል። ሰውየው እንደሚሉት ይህ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር ውሎ በዓመት ውስጥ ምጣኔ ሃብቱ ማንሰራራት ቢጀምርም ነቀርሳው ግን ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ይቆያል። እንዲያውም አንዳንድ የሥራ ዘርፎች ጨርሶውኑ ላያንሰራሩ እንደሚችሉም ተንብየዋል። ወረርሽኙን ከ2008ቱ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ጋር ሲወዳደርም ሆነ በ1930ዎቹ ከተከሰተው የዓለም ክፉው የምጣኔ ሃብት ድቀት ጋር ሲተያይ የአሁኑ የከፋ እንደሆነ ሮቢኒ ያብራራሉ። ያን ጊዜ ምርት በዓለም ላይ እንዲቀንስ ወይም የቀውሱን ምልክቶች በተግባር ለማየት ከችግሩ በኋላ ዓመታትን ወስዶ ነበር። ኮሮናቫይረስ ግን ከእነዚህ ሁለቱ ቀውሶችም በላይ ነው። በባህሪው ይለያል። ያስከተለውን የምርት ማሽቆልቆልን በግላጭ ለማየት ዓመታት ወይም ወራት አልወሰደበትም። በሳምንታት ውስጥ በመላው ዓለም ምርት ተንኮታክቷል። ይህ የሚነግረን መጪው ዘመን ፍጹም ጭጋጋማ መሆኑን ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። "በዚያ ዘመን 3 ዓመት የወሰደው የምርት መንኮታኮት በዚህ ዘመን 3 ሳምንት ነው የወሰደበት።" "ዩ" እና "ኤል" ፕሮፌሰሩ ከምጣኔ ሃብት ቀውስ በኋላ የማገገሙን ሂደት ሲያስረዱ በሁለት የእንግሊዝኛ ሆሄያት ይመረኮዛሉ። ዩ እና ኤል ["U" እና "L"]። ዩ በእኛ ሀሌታው 'ሀ' ብለን ልንተረጉመው እንችላለን። የሀሌታው ሀ የማገገም ሂደት የሚያሳየው አንድ ምጣኔ ሀብት በአንዳች መጥፎ አጋጣሚ ሲንኮታኮት ቀስ በቀስ መሬት ይነካል። ከዚያ ወደነበረበት ለመመለስ የሀሌታው ሀ ቅርጽን ይዞ ሲንፏቀቅ ቆይቶ፣ በብዙ አዝጋሚ ሂደት ምጣኔ ሃብቱ ይመለሳል። ይህ ሂደት ዓመታትን የሚወስድ ነው። ከዚህ የተሻለው ደግሞ በቪ "V" ይወከላል። ቶሎ ወድቆ ቶሎ የሚያንሳራራ ምጣኔ ሃብት። አሁን የገጠመን ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ ኮቪድ-19 ያስከተለው የምጣኔ ሃብት ድቀት የሀሌታው ሀ ቅርጽን ሳይሆን የእንግሊዝኛው ሆሄ "L"ን ወይም በእኛ የ"ረ" ቅርጽ የያዘ ነው። ይህም ማለት በአንድ ጊዜ ዘጭ ያለው ምጣኔ ሃብት ጨርሱኑ አያንሰራራም ወይም ለማንሰራራት አሥር ዓመት ይወስድበታል። 'ጨለምተኛው' ፕሮፌሰር እንዲያውም የኮቪድ-19 ተጽእኖ የመጪውን ዘመን ምጣኔ ሃብት በአይ ሆሄ "I" የሚወከል እንዳይሆን ይሰጋሉ። እንደወደቀ የሚቀር ኢኮኖሚ። በፕሮፌሰሩ ትንቢት መሠረት በዚህ ወረርሽኝ ሥራ ያጡ ዜጎች ወደ ሥራቸው የመመለስ ዕድላቸው አነስተኛ ነው። ከተመለሱም በጊዝያዊ ሠራተኝነት እንጂ ቋሚ ሥራ የሚያገኙት በጣም ጥቂቶች ናቸው። ከደመወዝ ውጭ ያሉ ጥቅማጥቅሞች ከዚህ በኋላ የሚታሰቡ አይሆኑም። በዝቅተኛና መካከለኛ የቅጥር ሥራ ላይ ያሉ ሰዎችም ቢሆን የሥራ ዋስትና አይኖራቸውም። ይህ በብዙ የምርት ዘርፎች ላይ ይታያል ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ከዚህ በኋላ ምርት አይጨምርም፤ የአገራትም ሆነ የኩባንያዎች እድገት ባለበት እርገጥ ይሆናል፣ ሰዎች ገቢያቸው ይደቃል፤ ገበያ ይተናል፣ ፍላጎት ይከስማል። "ሰዎች ስለ ቢዝነስ መልሶ መከፈት ያወራሉ፤ ቢከፍቱስ ማን ይገዛቸዋል? ጀርመን ሱቆችን ከፈተች፤ ገዢ ግን የለም። ቻይና ትልልቅ የንግድ መደብሮቿ ክፍት ናቸው፤ ማን ይገዛቸዋል? ከፍተው ነው የሚዘጉት፤ በረራዎች ተስተጓጉለዋል…ይህ ሁኔታ ለዓመታት የሚቀጥል ነው የሚሆነው" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ፕሮፌሰር ሮቤኒን ከበለጸጉ አገራት ይልቅ ታዳጊ የእሲያ ምጣኔ ሃብት በሁለት እግሩ ለመቆም የተሻለ እድል እንዳለውም ተናግረዋል። "ዓለም ለሁለት ትከፈላለች" ፕሮፌሰር ኖሪኤል ሮቢኒ ሌላው ትንቢታቸው ዓለም ልክ እንደ ቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን በሁለት ግዙፍ እድሮች እንደሚሰባሰብ ነው። የእድሮቹ አባቶች የሚሆኑትም ቻይናና አሜሪካ ይሆናሉ ይላሉ። ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸው እየሻከረ እንደሚሄድና የራሳቸውን የምጣኔ ሃብት አጋሮች ማሰባሰብ እንደሚጀምሩ አስምረውበታል። አብዛኛዎቹ የእሲያና ታዳጊ አገራት ከእነዚህ ሁለት አገሮች ወደ አንዱ እድር እንዲገቡ የሚገደዱበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ፕሮፌሰሩ ተንብየዋል። "ሁለቱ የእድር አባቶች ወይ ከእኔ ጋር ነህ፣ ከእኔ ካልሆንክ ደግሞ ከጠላቴ ጋር ነህ ማለት ይጀምራሉ። ይህ ማለት ወይ የእኔን 5ጂ ትጠቀማለህ፣ አልያም የጠላቴን፤ ወይ የእኔን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትጠቀማለህ ወይም የጠላቴን…እየተባለ ሁለት ዓለም ይፈጠራል። ታዳጊ አገራትም በሁለት ቢላ መብላት አይፈቀድላቸውም" ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ከኒውዮርክ ቤታቸው ሆነው ቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት ፕሮፌሰር ሮቢኒ ጨለምተኛው ፕሮፌሰር ስለመባላቸው አስተያየት ሲጠየቁ "ከዚያ ይልቅ እቅጩን ነጋሪው ፕሮፌሰር የሚለው ስም ይመጥነኛል" ብለዋል።
54510330
https://www.bbc.com/amharic/54510330
ወሲባዊ ጥቃት፡ ባንግላዲሽ ደፋሪዎችን በሞት ልትቀጣ ነው
ባንግላዲሽ በመድፈር የተከሰሱ ሰዎችን በሞት ልትቀጣ ነው። በአገሪቱ የተባባሰውን ወሲባዊ ጥቃት በመቃወም ለቀናት ሰልፍ ከተካሄደ በኋላ ነው የሞት ቅጣት በሕጉ እንዲካተት የተወሰነው።
"ደፋሪዎች ይሰቀሉ"፣ "ደፋሪዎች ይቅር አይባሉም" የሚሉና ሌሎችም ተመሳሳይ ሐሳብ ያላቸው መፈክሮች በመዲናዋ ዳካ ተሰምተዋል የሕግ ሚንስትሩ አኒሹ ሐቅ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የፊታችን ማክሰኞ ፕሬዘዳንቱ ቅጣቱን በይፋ የሕጉ አካል ያደርጋሉ። በቡድን አንዲት ሴት ላይ ጥቃት ሲፈጸም የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መለቀቁን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ከፍተኛ ተቃውሞ ነበር። . ታንዛንያ ለሕፃናት ደፋሪዎች ይቅርታ አደረገች . የናይጄሪያዋ ግዛት ደፋሪዎች እንዲኮላሹ በህግ ፈቀደች አንድ የመብት ተሟጋች ቡድን ባለፈው ዓመት 5,400 ሴቶች መደፈራቸውን መዝግቧል። ሆኖም ግን ለፍርድ የሚቀርቡት ደፋሪዎች እምብዛም አይደሉም። ብዙ ሴቶች መገለል ይደርስብናል ብለው ስለሚሰጉ መደፈራቸውን ሪፖርት አያደርጉም። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨው ቪድዮ አስቆጥቷቸው ሰልፍ የወጡ ሰዎች፤ የፍትሕ ሥርዓቱ ጉዳዩን የሚያይበት መንገድ መለወጥ እንዳለበትና የፍርድ ሂደቱ ፈጣን መሆን እንደሚገባው አስረግጠዋል። የባንግላዲሽ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምርመራ እንደሚያሳየው፤ በቪድዮው ላይ የታየችው ሴት በተደጋጋሚ ተደፍራለች። ቪድዮው ከተሰራጨ በኋላ ስምንት ወንዶች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ባለፈው ሳምንት በባንግላዲሽ ደቡባዊ ግዛት ሲልሄት በሚገኝ ሆቴል ውስጥ አንድ ሴት በቡድን ተደፍራለች። ይህን ተከትሎም የገዢው ፓርቲ የተማሪዎች ክንድ በርካታ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል። . የስፔኑ ፍርድ ቤት ኃይል አልተጠቀሙም ያላቸውን 5 አስገድዶ ደፋሪዎች ነፃ አለ . ዓለምን ያስቆጣው የህንድ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተጠያቂዎች በስቅላት ተቀጡ በተለይም በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ባንግላዲሽ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል። "ደፋሪዎች ይሰቀሉ"፣ "ደፋሪዎች ይቅር አይባሉም" የሚሉና ሌሎችም ተመሳሳይ ሐሳብ ያላቸው መፈክሮች በመዲናዋ ዳካ ተሰምተዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ መንግሥት ሕጉ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ወስኗል።
news-54090728
https://www.bbc.com/amharic/news-54090728
የትግራይ ምርጫ፡ "ይህንን ምርጫ እንደ ሪፈረንደም ነው የምናየው" የትግራይ ተቃዋሚ ድርጅት
በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል ክልላዊ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን መራጮች ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን ሲሰጡ ውለዋል።
በክልላዊ ምርጫው ክልሉን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን ጨምሮ አምስት ፓርቲዎች እየተሳተፉም ይገኛሉ። ድርጅታቸውን በመወከል እየተፎካከሩ ያሉት የሳልሳይ ወያነ፣ ባይቶና እና ውናት (ውድብ ነፃነት ትግራይ) የተቃዋሚ አመራሮች በመቐለ ከተማ ድምፅ ሰጥተዋል። ትግራይ ነፃ አገር ሆና ልትመሰረት ይገባል በማለት የሚያቀነቅነው የውናት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳኦች ሃላፊ መሃሪ ዮሃንስ ምርጫው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውድድር ፉክክር በላይ ትርጉም ያለው እንደሆነም ለቢቢሲ ተናግሯል። "ይህች ቀን የትግራይ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ በተግባር ያረጋገጠበት ሰለሆነች የተለየች ናት" ብሏል። "እንደ ውናት ይህንን ምርጫ እንደ ሪፈረንደም ነው የምናየው። እንደ ሕዝብ ትልቅ ዋጋ የከፈለበት መብት አደጋ ላይ ወድቆ ነበር። ከእዚህም አደጋ ወጥቶ የሉአላዊነትና የግዛት ነፃነት የሚያረጋግጥበት ሁኔታ መፈጠር አለበት" በማለት "ማስፈራርያ ቢመጣም እሱን ተቋቁመን እዚሁ ደርሰናል" በማለት ተናግሯል። ሌላኛው በከተማዋ ድምፁን የሰጠው የባይቶና ሊቀመንበር ኪዳነ አመነ በምርጫው ሂደት በበኩሉ ደስተኛ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል:: መራጩ አካላዊ ርቀቱን ጠብቆ፣ የፀረ-ተህዋሲያን (ሳኒታይዘር) በርካቶች ይዘውና በመጠቀም በአግባቡ ሲመርጡ መታዘቡን ተናግሯል። የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ኃያሉ ጎድፋይም በደቡብ ትግራይ አላጀ ወረዳ ከሌሎች አራት የድርጅቱ አመራሮች ጋር ሆኖ ቦራ በተባለ የድምፅ መስጫ ጣቢያ ላይ ድምፅ መስጠቱን ተናገሯል። "በጣም ደስ ብሎኛል። ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ምርጫው እንዳይደናቀፍ የራሱ አስተዋፅኦ አድርጓል። ስለዚህ ይህቺ ቀን ለእኛ የተለየ ትርጉም ነው ያላት:: ምርጫው ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ ከተጠናቀቀ ድግሞ የበለጠ ሙሉ ትርጉም ይኖረዋል" ብሏል። ምንም እንኳን በምርጫው ከሞላ ጎደል ደስተኛ ቢሆኑም አንዳንድ ቅሬታ እንዳላቸውና አጠቃለው መግለጫ እንደሚሰጡበት ለቢቢሲ አስረድተዋል። በክልሉ 2 ሺህ 672 የምርጫ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን መቀለ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ከንጋት 10፡30 ጀምሮ ምርጫ ጣቢያዎች ፊት ለፊት ተሰልፈው መመልከቱን ገልጿል። በክልሉ 38 የምርጫ ክልሎች እንዳሉ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን መግለጹ ይታወሳል። በኢትዮጵያ በነሐሴ መጨረሻ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ፤ በትግራይ በተናጠል እየተካሄደ የሚገኘው ክልላዊ ምርጫ ሕገ-ወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት የፌደሬሽን ምክር ቤት መወሰኑ ይታወሳል።
news-46142396
https://www.bbc.com/amharic/news-46142396
በኢራቅ የካቢኔ አባላት በፌስቡክ ማስታወቂያ ተመረጡ
የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር አደል አብዱል ማህዲ በበይነ መረብ ከተወዳደሩ 15 ሺ ሰዎች መካከል የካቢኔያቸው አባል የሚሆኑ አምስት ሰዎችን መረጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ወር ነበር በበይነ መረብ የሚካሄደውን የቅጥር ሥነ ሥርዓት ለሕዝቡ ይፋ ያደረጉት። የካቢኔ አባል መሆን የሚፈልጉ የሃገሬው ተወላጆች ሲቪያቸውንና ብቃታቸውን የሚያሳዩ የተለያዩ ማስረጃዎችን አያይዘው እንዲልኩም ተጠይቀው ነበር። እስካሁን ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመረጡት አምስት የካቢኔ አባላት ስማቸው አልተገለጸም። ጠቅላይ ሚኒስትር አዲል አብዱል ማህዲ አዲስ መንግሥት በአጭር ጊዜ እንዲያቋቁሙ ጥቅምት ላይ የተጠየቁት ወራትን የፈጀ ያልተቋጨ ፖለቲካዊ ምርጫ ያስከተለውን ውጥንቅጥንና የፓርቲ ፍጥጫን ተከትሎ ነበር። • "የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው" ጄኔራል አሳምነው • "ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም" ብርቱካን ሚደቅሳ ይህ በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት ውስጥ ያልተለመደ የቅጥር መንገድ መጀመሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ማህዲ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተዋወቀ ሲሆን፤ ከሚያስፈልጉት 14 የካቢኔ አባላት መካከል አምስቱ በዚህ መንገድ ተመርጠዋል። ተወዳዳሪዎች ማመልከቻቸውን ሲያስገቡ የየትኛው የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆናቸውን እንዲናገሩና የትኛውን የሚኒስትር መሥሪያ ቤት መምራት እንደሚፈልጉ እንዲጠቅሱ ተጠይቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ያከናወኗቸውን ሥራዎች መጥቀስ ፣ ውጤታማ መሪ ምን መሆን እንዳለበት እንዲሁም በሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ያለውን ችግር እንዴት እንደሚፈቱ መልሳቸውን ማስቀመጥ አለባቸው። • ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት የሃገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው
news-44393961
https://www.bbc.com/amharic/news-44393961
ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ያሳፈረችው ጀልባ ሰጠመች
ከሶማሊያ ወደ የመን አገር እያቋረጡ የነበሩ 46 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መሞታቸው ተሰምቷል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃላፊዎች እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊያኑ ብቻ የተሳፈሩባት ጀልባ በመገልበጧ ነው አደጋው የደረሰው። ሌሎች 16 ኢትዯጵያዊያን ደግሞ የገቡበት አለመታወቁን የዓለማቀፉ የስደተኛ ጉዳዮች ማኅበር አይኦኤም አስታውቋል። ከሞት የተረፉ ዜጎች እንዳሉት ከሆነ ድንበር አሻጋሪዎቹ የሚሾፍሯት ጀልባ ቢያንስ አንድ መቶ ኢትዮጵያዊያንን አሳፍራ ነበር። ጀልባዋ መነሻዋን አድርጋ የነበረው ቦሳሶ ወደብን ነበር። ስደተኞቹ ኢትዮጵያዊያን በጦርነት በምትታመሰው የመንና በሌሎች የገልፍ አገሮች ሥራ ለማግኘት ያለሙ ነበሩ ተብሏል። ሁሉም ሰደተኞች ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ይህን አደጋ ልዩ አድርጎታል። ጀልባዋ የተገለበጠቸው ረቡዕ ማለዳ በገልፍ ኤደን ሲሆን ከሞቿቹ ውስጥ ዘጠኙ ሴቶች ናቸው። በዚህ የሶማሊያ-የመን መንገድ ቢያንስ 7 ሺህ ስደተኞች በየወሩ ለማቋረጥ እንደሚሞክሩ ጥናቶች ያሳያሉ። ባለፈው ዓመት ብቻ 100 ሺህ ስደተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ባሕር ለማቋረጥ ሞክረዋል። የዓለማቀፉ የስደተኛ ጉዳዮች ማኅበር ኃላፊ ሞሐመድ አብዲከር እንደሚሉት ከሆነ ጉዞው እጅግ አደገኛ ሲሆን ስደተኞቹም በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚያልፉት። መነሻቸውን ከምሥራቅ አፍሪካ ያደረጉ ስደተኞች ወደ የመን የሚያደርጉት ጉዞ ለዓመታት የቀጠለ ሲሆን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የአረብ አገራት ለመዝለቅ የሚሞክሩ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ የመን ምቹ ተደርጋ ትታሰባለች። ምንም እንኳ የመን ጭልጥ ባለ የእርስ በርስ ጦርነት የምትታመስ አገር ብትሆንም የኢኮኖሚ ስደተኞች አሁንም ወደዚያ ማቅናታቸውን እርግፍ አድርገው ለመተው አልፈቀዱም።
53840729
https://www.bbc.com/amharic/53840729
አሜሪካ፡ ባራክ ኦባማ "ትራምፕ አሜሪካን ላይ ቀልዶባታል" አሉ
ሦስተኛ ቀኑን በያዘው ታላቁ የዲሞክራት ፓርቲ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ተተኪያቸውን ዶናልድ ትራምፕን አብጠልጥለዋል፡፡
‹ሰውየው አሜሪካ ላይ ቀልዷል፤ አገሪቷም የመራትም የመዝናኛ የቴሌቪዥን ትእይንት (Reality show) እንደሚመራ አድርጎ ነው፡፡› ብለዋል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት በተለያዩ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ትእይንታዊ መርሐግብሮች ላይ በመሳተፍ፣ እንዲሁም በመዳኘት ይታወቃሉ፡፡ ‹ያሳዝናል፣ ተተኪዬ ከመዝናኛ ትእይንት መሪነት ከፍ ሊል አልቻለም፣ ምክንያቱም ስለማይችል፡፡› ብለዋል ኦባማ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ወዲያው በሰጡት ምላሽ ‹‹አንተ ያቦካኸውን ለማጽዳት እኮ ነው ሕዝብ የመረጠኝ›› የሚል መንፈስ ያለው ነገር ተናግረዋል፡፡ በሦስተኛ ቀን ምሽቱ የዲሞክራቶች ታላቅ ጉባኤ ካማላ ሐሪስ የምክትል ፕሬዝዳንትነት እጩነቷን በይፋ ተቀብላለች፡፡ ዛሬ ሐሙስ የጉባኤው መዝጊያ ሲሆን የዲሞክራቶች እጩና የትራምፕ ተገዳዳሪ ጆ ባይደን የማሳረጊያ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባይደንና ሐሪስ በመጪው ኅዳር የሚፋለሙት ከዶናልድ ትራምፕና ምክትላቸው ማይክ ፔንስ ጋር ይሆናል፡፡ በዛሬው ጉባኤ አምርረው የተናገሩት ባራክ ኦባማ ንግግራቸውን ያቀረቡት ከፊላደልፊያ ሆነው ነው፡፡ ‹‹ዶናልድ ትራምፕ በነጩ ቤተመንግሥት ውስጥ ስለራሱና ስለጓደኞቹ ሲጨነቅ ነው አራት ዓመታትን ያጠፋው፤ ለአሜሪካ ሕዝብ ምን ፈየደለት?››ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹…በዚህ ሰውዬ ፕሬዝዳንት መሆን የተነሳ በዓለም ስማችን ጎድፏል፣ አንጀታችን ቆስሏል፣ የዲሞክራሲ ተቋሞቻችን አደጋ ላይ ወድቀዋል›› ሲሉ ትራምፕን አውግዘዋል፡፡ ‹‹…አሜሪካዊያን ሆይ! ይህ ሰው ሲቀልድባችሁ ዝም ብላችሁ አትመልከቱት፣ ዲሞክራሲያችሁን ሲቀማችሁ፣ አገራችሁን ሲነጥቃችሁ ቆማችሁ አትዩት፤ ድምጻችሁን ተጠቀሙበት፤ ባይደንን ምረጡ›› ብለዋል፡፡ ባራክ ኦባማ ገና ከነጩ ቤተ መንግሥት ሳይወጡ ከአራት ዓመት በፊት ስለ ትራምፕ መመረጥ ተጠይቀው ‹‹አሜሪካዊያን ይህንን ሰው ከመረጡማ ለኔ ውርደት ነው፤ እኔ እንደ ስድብ ነው የምመለከተው›› ብለው ነበር፡፡ ያን ጊዜ ትራምፕ የሪፐብሊካን እጩና ‹‹ዘ አፓረንቲስ›› የሚሰኝ የቴሌቪዥን አዝናኝ ትእይንት አቅራቢ ነበሩ፡፡ 44ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የፈሩት ደርሶ ትራምፕ ሰተት ብለው ነጩ ቤት መንግሥት ገቡ፡፡ የኦባማን ውርሶችም አንድ በአንድ ማውደም ያዙ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ኦባማ ወደ ሚዲያ ወጥተው መናገር የጀመሩት፡፡ ሰኞ በተጀመረው ታላቁ የዲሞክራቶች ጉባኤ ሚሼል ኦባማ ባደረጉት ንግግር ‹‹ትራምፕ የጤና እርዳታ የሚሻ ሰው ነው፣ብቃት የሚባል ነገር አልፈጠረበትም›› ብለው ነበር፡፡ የሚሼል ኦባማ ንግግር አነጋጋሪ የሆነው በተለምዶ ቀዳማዊት እመቤቶች የሚያደርጓቸው ንግግሮች በተቻለ መጠን ከፖለቲካዊ መንፈሶች የጸዱ እንዲሆኑ ስለሚጠበቅ ነው፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ኦባማ ስለርሳቸው በተናገሩት ላይ ‹‹ምን የሚሉት ነገር አለ?›› ተብለው ተጠይቀው ነበር፡፡ ‹‹እሱ ትቶልን የሄደው ኮተት ነው ለዚህ የዳረገን›› ብለዋል፡፡ ‹‹ተመልከቱ እንዴት ቀሽም መሪ እንደነበረ፣ እንዴት ሥራ አይችል እንደነበረ፣ እንዴት ብቃት ያልፈጠረበት ከንቱ ሰው እንደነበረ›› ብለዋል ዶናልድ፣ ባራክ ኦባማን፡፡ ‹‹…እኔ ፕሬዝዳንት የሆንኩት እኮ የሱን ኮተት ለማጽዳት ነው፡፡ የሱና የጆ ባይደንን ቆሻሻ›› ብለዋል፡፡ ይህን ንግግራቸውን ተከትሎ በትዊተር ሰሌዳቸው ‹‹እንኳን በሰላም መጣችሁልኝ ባራክና ያቺ ቀጣፊዋ ሂላሪ፣ በትግል ሜዳው ያገናኘን› የሚል ዛቻ የሚመስል ነገር ጽፈዋል፡፡ ሒላሪ ክሊንተን በዚህ የዲሞክራቶች ጉባኤ ላይ ከኒውዮርክ ቤታቸው ሆነው ባደረጉት ንግግር ‹‹ትራምፕ የተሻለ መሪ ቢሆን ደስ የለኝ ነበር፡፡ ግን እሱ በቃ ይኸው ነው›› ብለዋል፡፡ ‹‹ሰዎች ሲያገኙኝ እንዲህ አሳፋሪ መሪ ይሆናል ብለን አልጠበቅንም ነበር፣ ምነው ድምጽ በሰጠንሽ፣ ምነው አንቺን መርጠን ቢሆን፣ ምናለ ያኔ አውቀን ቢሆን ይሉኛል፡፡ …አሁን እንዲህ ባረኩ ኖሮ፣ እንዲያ ባረኩ ኖሮ ማለት አያስፈልግም፡፡ ባይደንን ድምጽ ስጡት›› ብለዋል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በቀጣይ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዳግማዊ እጩ ተደርገው በይፋ በፓርቲያቸው ይሰየማሉ፤ ሥነ ሥርዓቱንም በዋይት ሐውስ አጸድ ላይ ይከወናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
news-53747874
https://www.bbc.com/amharic/news-53747874
ዶናልድ ትራምፕ ሻወር ቤት ውሃ ቀነሰብኝ ብለው አማረሩ
የአሜሪካ መንግሥት የገላ መታጠብያ ቧንቧ ጭንቅላት ምን ያህል ውሃ ማፍሰስ አለበት የሚለውን ደንብ ለመቀየር እያጤነ ነው፡፡
ይህን ደንብ ለማጤን የተገደደው ደግሞ ከሕዝብ በመጣ ቅሬታ ሳይሆን በዶናልድ ትራምፕ ጸጉር የተነሳ ነው፡፡ የ1992 የአሜሪካ በተደነገገ ሕግ የአሜሪካ የሻወር ቧንቧዎች ጭንቅላት በደቂቃ ከ2.5 ጋሎን በላይ እንዳያፈስ ያስገድዳል፡፡ ይህም ብክነትን ለመከላከል የወጣ ደንብ ነው፡፡ የትራምፕ አስተዳደር ይህንን መጠን ለመጨመር ይሻል፡፡ ምክንያቱም ትራምፕ ገላዬን ስታጠብ በቂ ውሃ እየፈሰሰልኝ አይደለም ሲሉ ቅሬታ በማቅረባቸው ነው፡፡ የሸማቾች እና የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች የሻወር ውሃ ግፊትን ከዚህ በላይ መጨመር አላስፈላጊ ከመሆኑም በላይ ለብክነት ይዳርጋል ብለዋል፡፡ ይህ የሻወር ቧንቧ ውሀ ደንብ ሊቀየር የታሰበው የአሜሪካ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለሥልጣን ባለፈው ወር በዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ቅሬታ ተንተርሶ ነው፡፡ ‹‹እነዚህ የሻወር ውሃ ማፍሰሻዎች ግን…›› አሉ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት፣ ‹‹…ለመሆኑ ውሃ በበቂ ይፈስላችኋል? ለኔ ግን ውሃ አይወርድልኝም፡፡ ልብስ አውልቃችሁ ለረዥም ሰዓትሻወር ቤት ገብታችሁ ትቆማላችሁ፣ ውሀው ግን ግፊት የለውም፡፡ ስለናንት ባላውቅም እኔ ግን በተለይ ፀጉሬን በደንብ በሚፈስ ውሃ መታጠብ እፈልጋለሁ፡፡›› የአሜሪካ የኃይል ጥበቃና የቁሳቁሶች ደረጃ መዳቢ ቡድን ኃላፊ አንድሩ ዴላስኪ ‹‹ትራምፕ ያቀረቡት ሀሳብ ‹የጅል ሐሳብ›› ብለውታል፡፡ በያንዳንዱ የሻወር ቧንቧ ቀዳዳ 2.5 ጋሎን ውሀ ይፍሰስ ማለት በጠቅላላው በደቂቃ ከ10 እስከ 15 ጋሎን ማለት ነው፡፡ ይህ የውሃ ግፊት ሻወር የሚወስደውን ሰውዬ ከሻወር ቤት ጠርጎ ሊያስወጣው ሁሉ ይችላል ብለዋል ለአሶሺየትድ ፕሬስ። በትራምፕ ምክንያት የሚቀየረው ደንብ ወደ ፍርድ ቤት ሊሄድ ይችላል ብሏል ሮይተርስ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ፀጉራቸው ሰው ሰራሽ ነው ወይስ የተፈጥሮ የሚለው አሁንም የመገናኛ ብዙኃንት መነጋገርያ ነው፡፡
news-44144426
https://www.bbc.com/amharic/news-44144426
ከረመዳን ጾም ጋር የተያያዙ የተሳሳቱ እሳቤዎች
ከቀናት በፊት በጀመረው የረመዳን የጾም ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙ ሁሉም የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች፤ ፀሐይ ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ ከማንኛውም አይነት ምግብ እና መጠጥ ይቆጠባሉ።
የጾሙ ዋና አላማ መንፈሳዊነትን መጨመር እና ሐይማኖታዊ ክብርን ማሳየት ሲሆን፤ ረጅም ጸሎቶችን በማድረግ እና ራስን በመቆጣጠር የሐይማኖቱ ተከታዮች የጾሙን ወቅት ያሳልፋሉ። ምንም እንኳ ይህን ማድረግ ቀላል መስሎ ቢታይም፤ የብዙ ሰዎችን አስተሳሰብ መከፋፈል የቻሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች እና አፈ ታሪኮች አሉ። ሙሉውን ቁርአን በቃሉ የሚያስታውሰው ሻቢር ሃሳን የእስላማዊ ሳይንስ እና ሸሪዓ ሕግ ተማሪ ነው። በረመዳን ጾም ወቅት በተለምዶ የምንሰራቸውን ስህተቶች እንዲህ ያስቃኘናል። 'ጥርስ መፋቅ' እንደ ዘርፉ ምሁራን ከሆነ ጥርስን መፋቅ ጾሙን መግደፍ ማለት አይደለም። አንዳንድ ሰዎች ጥርሳቸውን በሚፍቁበት ወቅት ወደ አፋቸው የሚገባው የጥርስ ሳሙና ጣእም ጾማቸውን እንዳስገድፍባቸው ይሰጋሉ። ነገር ግን ይህ ተቀባይነት የለውም ቢሉም ምሁራኑ፤ ለጥንቃቄ የሚረዱ አንዳንድ መፍትሄዎች አሉ ይላል ሃሳን። የመጀመሪያው ትንሽ የጥርስ ሳሙና መጠቀም ሲሆን፤ ቀለል ያለ ጣዕም ያላቸው ምርቶችን መጠቀምም እንደሚረዳ ይመክራል። በሌላ በኩል የዓለም ጤና ድርጅትን እውቅና ያገኙ ከተፈጥሮአዊ ተክሎች የሚሰሩ የጥርስ ሳሙናዎችን መጠቀምን ደግሞ ተጨማሪ አማራጭ ነው። 'ምራቅ መዋጥ' የራስን ምራቅ መዋጥ ምንም ችግር የለውም፤ እንደውም ይበረታታል። "ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ምንም መሰረት የለውም" ይላል ሃሳን። "ምራቅን መዋጥ ተፈጥሮአዊ ሂደት ነው። ስለዚህ ጾምን አያስገገድፍም።'' ጾሙን ሊያስገድፍ ሚችለው ግን የሌላን ሰው ማንኛውም አይነት ፈሳሽ ወደ ውስጥ ማስገባት ነው። የሌላ ሰውን ምራቅ ወደ ውስጥ ማስገባት በጾም ወቅት እጅግ ክልክል እና ሀጢያት ነው፤ ይላል የእስላማዊ ሳይንስ እና ሸሪዓ ህግ ተማሪው ሃሳን። "ከዚህ ጋር ተያይዞ የፍቅር ጓደኛም ሆነ የትዳር አጋርን መሳም አይፈደቀድም'' የሚለው ሃሳን፤ በዚህ ቅዱስ ወቅት ራስን ከእንደዚህ አይነት ስሜቶች መቆጣጠር እና ከምግብ እና ውሃ መራቅ ወደ አምላክ ያቀርባል ሲል ያክላል። በጾሙ ወቅት ከምግብ እና ውሃ ብቻ ሳይሆን፤ ከሃጥያት፣ ከክፉ ሃሳብ እና ሌሎችን ከማስቀየም መቆጠብ አለባቸው ሲል ሃሳን ያክላል። 'በስህተት መመገብ ወይም መጠጣት' "ጾም ላይ መሆኖን ረስተው በፍጹም ስህተት ከተመገቡ ወይም ውሃ ከጠጡ ጾሞን እንዳፈረሱ አይቆጠርም። ነገር ግን ባስታወሱባት ቅፅበት መመገብንም ሆነ መጠጣትን ማቆምዎን አይዘንጉ" ይላል ሃሳን። "ሰውነትዎን በሚታጠቡ ወቅት ግን ውሃ ወደ ሰውነትዎ ቢገባ ጾሙ እንደፈረሰ ይቆጠራል።'' እንደ ሃሳን ከሆነ ሐይማኖታዊ በሆነ መንገድ ሰውነታችንን በምናጸዳበት ጊዜ ውሃ ወደ አፋችን እንዳይገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ሲል ይመክራል። 'መድኃኒት መውሰድ' የእንግሊዝ እስላማዊ ምክር ቤት እና ዓለም አቀፉ የግላኮማ ማኅበር በረመዳን ጾም ወቅት እንደ አይን ጠብታ እና ክትባት ያሉ ጥቂት መድኃኒቶችን መጠቀም እንደሚቻል ያስቀምጣሉ። ነገር ግን የሚዋጡ መድኃኒቶችን ከጾም በፊተ አልያም በኋላ መወሰድ እንዳአለባቸው ይመከራል። እንደ ሃሳን ሃሳብ ከሆነ ህክምና ላይ ያለ ሰው በመጀመሪያ ጾሙን መጾም አለብኝ ውይ? ብሎ መጠየቅ አለበት። 'የጾም ግዴታ' በእስልምና ሐይማኖት ማንኛውም ከ15 ዓመት በላይ የሆነ ጤናማ ሰው ይህን ዓመታዊ ጾም መጾም ግዴታ ነው። ይሄ ማለት ህጻናት፣ ህመምተኞች፣ የአእምሮ ህሙማን፣ መንገደኞች፣ እርጉዞች እና የሚያጠቡ እናቶች የመጾም ግዴታ የለባቸውም። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከህመሞ እንደሚድኑ እርግጠኛ ከሆኑ ግን ጾሙን መጀመር ይቻላል ሲል ሃሳን ይናገራል። ከባድ ህመም ላይ ያሉ በሽተኞች ግን ካገገሙ በኋላ መጾም እንደሚችሉና አቅመ ደካማ ቤተሰቦችን በመመገብ ፊድያህ ተብሎ የሚጠራውን ሥርዓት መፈጸም እንደሚችሉ ሃሳን ጨምሮ ይገልፃል።
news-55026905
https://www.bbc.com/amharic/news-55026905
ኮሮናቫይረስ ፡ እሽቅድድም ለኮቪድ-19 ክትባት፡ የማይደርሳቸው አገሮች ይኖራሉ?
በዓለም ዙሪያ ከ57 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።
ይህንን ወረርሽኝ ለማስቆም መላው ዓለም እየተጠባበቀ ያለው ብቸኛ ተስፋው ክትባት ነው። ነገር ግን ድሃ አገሮች ክትባቱ ላይደርሳቸው ይችላል የሚል ስጋት ተስተጋብቷል። አሁን ላይ ሁለት ክትባቶች ውጤታማነታቸው ሲረጋገጥ፤ ሌሎች በርካታ ክትባቶች ደግሞ የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ክትባቶቹ እስካሁን ፍቃድ ባያገኙም አንዳንድ አገሮች ከወዲሁ እያዘዙ ነው። የአሜሪካው ዱክ ዩኒቨርስቲ በሠራው ጥናት መሠረት፤ እስካሁን ወደ ለ6.4 ቢሊዮን የክትባት ጠብታዎች ግዢ ተፈጽሟል። በተጨማሪም በድርድር ላይ ያሉ ወይም በተጠባባቂነት የተያዙ 3.2 ቢሊዮን ጠብታዎች አሉ። ቀድመው ክትባቱን ያዘዙ አገሮች በመድኃኒት ሽያጭ ዓለም ውስጥ መድኃኒቶችንና የክትባት ጠብታዎችን ቀድሞ ለመግዛት መስማማት የተለመደ ነው። በለንደን የምጣኔ ሀብት መምህርት ክሌር ዊንሀም እንደሚሉት ይህ ለግዢ ቀድሞ መዋዋል አምራቾቹን ያበረታታል ተብሎ ይታመናል። በሌላ በኩል ቀድሞ የከፈለ ቅድሚያ አገልግሎት ያገኛል ማለት ነው። የዱክ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ቀድመው ክትባት ለመግዛት የተስማሙት ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ናቸው። ማምረት የሚችሉ ጥቂት መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገሮች በከፍተኛ መጠን ክትባቱን ለማግኘት መደራደር ችለዋል። የክትባት ሙከራ ማስተናገድ የሚችሉ እንደ ብራዚል እና ሜክሲኮ ያሉ አገሮች መስተንግዷቸውን ክትባት ለማግኘት ይጠቀሙበታል። የሕንዱ ሰረም ተቋም አገር ውስጥ ከሚያመርተው ክትባት ግማሹን እዚያው ሕንድ ውስጥ እንደሚያስቀር ተናግሯል። ኢንዶኔዥያ ከቻይና ጋር ብራዚል ደግሞ ከኦክስፎርዱ መድኃኒት አምራች አስትራዜንካ ጋር ተጣምረዋል። ሕንድ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና የአውሮፓ ኅብረት የተለያየ የክትባት አማራጭ ያስቀመጡ አገሮች ናቸው። የዓለም ጤና ድርጅት ለቢቢሲ እንደገለጸው፤ "መሪዎች ዜጎቻቸውን እንደሚያስቀድሙ ጥያቄ የለውም። ነገር ግን ወረርሽኙን ለመግታት ዓለም አቀፍ ትብብር ያስፈልጋል"። ውስን ክትባትን ለዓለም ሕዝብ ማከፋፈል የዱክን ጥናት የመሩት አንድርያ ቴይለር እንደሚሉት፤ ቀድመው ክትባቱን የሚገዙ አገሮች መኖራቸው እና የክትባት መጠን ውስን መሆኑ ድሃ አገሮች ክትባቱን እንዳያገኙ እንቅፋት ይሆናል። ምን ያህል ክትባት፣ መቼ ገበያ ላይ እንደሚውል ገና አልታወቀም። ስርጭትን በተመለከ የሚነሱ ጥያቄዎችም ገና መልስ አላገኙም። ቻንድራካት ላህርያ እንደሚሉት፤ አቅመ ደካማ አገሮች ክትባት የማግኘት እድላቸው የሚወሰነው ምን ያህል ክትባት በምን ያህል ፍጥነት ይሠራል በሚለው ነው። "ሕንድ ውስጥ ባለው የማምረት አቅም ዋጋው እንደሚቀንስና ተደራሽነቱ እንደሚሰፋ እገምታለሁ። ስለዚህም ክትባቱን ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ያገኛሉ" ይላሉ። ተስፋ ሰጪዎቹ ክትባቶችን ለመግዛት እየተስማሙ ያሉት ሀብታም አገሮች ናቸው የሚሉት ፖሊሲ ተንታኟ ፌቸል ሲልቨርማን ናቸው። "ብዙ ውጤታማ ክትባቶች ካሉ ሀብታም አገሮች ብዙ አማራጭ ስለሚኖራቸው ክትባቶች ይተርፋሉ ማለት ነው" ይላሉ። ሆኖም ግን ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገሮች በቀጣዩ ዓመት መገባደጃ ላይ ክትባቱ በስፋት የመድረሱ እድሉ ውስን ነው። ፋይዘር በ2020 እስከ 50 ሚሊዮን ክትባት፤ እስከ 2021 ደግሞ 1.3 ቢሊዮን ክትባት እንደሚያመርት አስታውቋል። ይህ በመላው ዓለም ይዳረሳል ብሎ መጠበቅ እንደማይቻል ባለሙያዋ ያስረዳሉ። ምናልባትም እንደ ሞደርና ያሉ ተቋሞችም ተስፋ ሰጪ ክትባት ማግኘታቸው ተደራሽነቱን ያሰፋው ይሆናል ብለው ይጠብቃሉ። አዲስ የክትባትስርጭት እቅድ የዓለም የጤና ሥርዓት እኩል ደረጃ ላይ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። እአአ 2009 ላይ ለተከሰተው ወረርሽኝ ክትባት ሲገኝ በዋነኛነት የገዙት ሀብታም አገሮች ነበሩ። 90 በመቶው የዓለም መድኃኒት አምራቾች 10 በመቶውን ሕዝብ እንደሚያገለግሉ ባለሙያዋ ይናገራሉ። ኮቫክስ የክትባቶችን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ለማረጋገጥ በጋቪ ክትባት አቅራቢና የዓለም ጤና ድርጅት የተመሠረተ ጥምረት ነው። ጥምረቱ ለአባል አገሮቹ 20 በመቶ ዜጎች ክትባት የማዳረስ አቅድ አለው። ሀብታም አገሮች ክትባት ሲገዙ ለድሃ አገሮች የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግበት እቅድም አለ። 2 ቢሊዮን ዶላር አሰባስበው ለ92 አገሮች ክትባት ገዝተው ያከፋፍላሉ። ኮቫክስ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ጠብታዎች አስቀድሞ አዟል። ይህም ለአባል አገራት ይከፋፈላል። በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ክትባት የሚሠራው አስትራዜንካ የዚህ ጥምረት አንድ አካል ነው። ኃላፊው ፓስካል ሶሪት በሁሉም አገር ያሉ ዜጎች ክትባቱ እንዲደርሳቸው ለማድረግ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ፋይዘር እስካሁን በኮቫክስ ስምምነት ውስጥ አልገባም። ሆኖም ውይይት እየተደረገ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጿል። መድኃኒት አምራቹ ክትባቱን ለሁሉም ለማከፋፈል እንደሚፈልግም ገልጿል። በሌላ በኩል የኮቫክስ ስምምነት ውስጥ ካሉ አገሮች መካከል እንደ ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ ያሉት በቀጥታ ከመድኃኒት አምራቾች ጋር እየተደራደሩ መሆኑ መሰማቱ ስጋት ፈጥሯል። የዱክ ተመራማሪው እንደሚሉት፤ አገሮቹ ለኮቫክስ ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ ቢያደርጉም ጎን ለጎን ክትባቱን ቀድመው ለመግዛትም እየሞከሩ ነው። እምነስቲ፣ ኦክስፋም እና ሌሎችም ተቋሞችም ክትባቱ ለመላው ዓለም ተደራሽ እንዲሆን ከወዲሁ እያሳሰቡ ነው። መድኃኒት አምራቾች በዓለም ጤና ድርጅት አማካይነት መረጃ እንዲለዋወጡም ጠይቀዋል። የኦክስፋም የጤና ፖሊሲ አማካሪ አና ማርዮት "የትኛውም ድርጅት ብቻውን በቂ ክትባት ማምረት አይችልም። አቅርቦቱ ካልሰፋ ሀብታምና ድሃ አገሮች ፉክክር ውስጥ ይገባሉ። ሁሌ የሚያሸንፉት ሀብታም አገሮች ናቸው" ይላሉ። የዓለም ጤና ድርጅት ወረርሽኙን ማሸነፍ የሚቻለው ሁሉም አገሮች ክትባቱን ማግኘት ከቻሉ ብቻ መሆኑን አስታውቋል። "በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ ቫይረስ ነው። በተሳሰረች ዓለም ውስጥ ሁሉም አገር ከወረርሽኙ ነጻ ካልሆነ በስተቀር የትኛውም አገር ብቻውን ነጻ አይሆንም" ሲልም አሳስቧል።
news-56884284
https://www.bbc.com/amharic/news-56884284
በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ለመሳተፍ እየተፎካከሩ ያሉ ኩባንያዎች ታወቁ
በኢትዮጵያ በቴሌኮምዩኒኬሽን ዘርፍ ለመሳተፍ ስድስት የውጭ አገራት ኩባንያዎች በጥምረትና በተናጠል ለመሥራት ፍላጎታቸውን መግለጻቸው ተነገረ።
በመንግሥት በሚተዳደረው ኢትዮቴሌኮም በብቸኝነት ተይዞ የቆየውን የቴሌኮምዩኒኬሽን ዘርፍ የውጭ ድርጅቶች እንዲሳተፉበት ጥሪ መቅረቡን ተከትሎ በተለያዩ አገራት ውስጥ በዘርፉ የሚሰሩ ተቋማት በጨረታው ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ ከኢትዮቴሌኮም በተጨማሪ ለሁለት የዘርፉ ተቋማት ፈቃድ ለመስጠት እንደምትፈልግ ካሳወቀች በኋላ በአፍሪካና በሌሎች አህጉራት ውስጥ የሚሠሩ ድርጅቶች በወጣው ጨረታ ላይ ተሳትፈዋል። በዚህም መሰረት የኬንያው ሳፋሪኮም፣ የብሪታኒያው ቮዳፎን፣ ከደቡብ አፍሪካ ቮዳኮም እና ኤምቲኤን ግሩፕ፣ የብሪታኒያው ሲዲሲ ግሩፕ እና የጃፓኑ ሱሙቲሞ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ለመስራት የጨረታ ሰነዳቸውን አስገብተዋል። በዘርፉ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎታቸውን በጨረታው ካሳወቁ ኩባንያዎች መካል የተወሰኑት በጥምረት ለመስራት የሚፈልጉ ሲሆን ሁሉም በተለያዩ አገራት ውስጥ በቴሌኮም ዘርፍ የዳበረ ልምድ እንዳላቸው ተገልጿል። በተደጋጋሚ ሲራዘም የቆየው የጨረታው ሂደት ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 18/2013 ዓ.ም ተጠናቆ ሁለቱን የቴሌኮም ፈቃዶች ለማግኘት ሰነዶቻቸውን ያስገቡት ኩባንያዎችን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የጨረታ ጥሪ ያቀረበው ኅዳር 18/2013 ዓ.ም ነበረ። ሚኒስቴሩ ጨምሮም በቀጣይነት ሁለቱን ፈቃዶች የሚያገኙትን ኩባንያዎች በተመለከተ የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን በቀረቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ በሚያካሂዳቸው የተለያዩ ግምገማዎች መሠረት ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጿል። ከ110 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ያላት ኢትዮጵያን የቴሌኮም ገበያን በብቸኝነት እያገለገለ ያለው መንግሥታዊው ኢትዮቴሌኮም ሲሆን፤ በአህጉሪቱ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ላይ የምትገኘው አገር የቴሌኮም ዘርፍ ለውጪ ኩባንያዎች አጓጊ በመሆኑ የተለያዩ ተቋማት ፍላጎታቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለሚሳተፉ ኩባንያዎች ሁለት ፈቃዶችን ከማዘጋጀቷ በተጨማሪ በመንግሥት ቁጥጥር ስር የሚገኘውን የኢትዮቴሌኮም የተወሰነ ድርሻ ለመሸጥም ተዘጋጅታላች። በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የቴሌኮም አገልግሎትን በብቸኝነት እየሰጠ የሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ሲሆን በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር የሞባይል ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ ካላቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው። ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ተቋማት ክፍት እንደምታደርግ ያስታወቀችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች ነው።
news-50863099
https://www.bbc.com/amharic/news-50863099
"የጥላቻና የሐሰተኛ መረጃ ረቂቅ ሕጉ የመናገር ነጻነትን አደጋ ላይ ይጥላል" ሂይውመን ራይትስ ዎች
የኢትዮጵያ ሕግ አውጪዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የተመራውን የጥላቻና ሐሰተኛ መረጃን የሚመለከተው ረቂቅ ሕግ ዳግመኛ በሚገባ እንዲያጤኑት ሲል ሂይውመን ራይትስ ዎች አሳሰበ።
ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቆሪው ድርጅት ሕጉ ከጸደቀ የመናገር ነጻነትን ይገድባል ሲል ያለውን ስጋት አስቀምጧል። እኤአ ከ2018 አጋማሽ ጀምሮ ኢትዮጵያ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ በሚለቀቁ ሐሰተኛና የጥላቻ መልዕክቶች የተነሳ በርካታ የብሔር ውጥረቶችና ግጭቶች ተከስተዋል ያለው መግለጫው መንግሥት ይህንን ተከትሎ ሕጉን ማስተዋወቁን ጠቅሷል። ሂይውመን ራይትስ ዎች እኤአ በ2019 ሕዳር ወር በፌስ ቡክ ላይ በተለቀቀ መልዕክት የተነሳ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች በተደረገ ሰልፍና እርሱን ተከትሎ በተከሰተ ግጭት የ86 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ጠቅሶ መንግሥት ሕጉን ወደ ፓርላማ መርቶታል ብሏል። • ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃን የተመለከተ አዋጅን ልታጸድቅ ነው • "ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ማቋረጧን ማቆም አለባት" የተመድ ከፍተኛ ባለሙያ "የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የብሔር ግጭቶች፣ አንዳንዴ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን በሚሰራጩ የጥላቻ መልዕክቶች የተነሳ ለሚከሰቱት ግጭቶች ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ግፊት ላይ ነው" ያሉት የድርጅቱ የአፍሪካ ተመራማሪ ላቲቲያ ባደር "ነገር ግን ይህ በአግባቡ ባልተጠና ሁኔታ የተረቀቀ ሕግ የመንግሥት ኃላፊዎች የመናገር ነጻነት መብትን ለመገደብ ሊጠቀሙበት ይችላሉ" በማለት ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። እንደ ሂይውመን ራይትስ ዎች ከሆነ የጥላቻ ንግግር ሕግ ያላቸው የዓለማችን ሀገራት ባለስልጣናት ለፖለቲካዊ ጥቅማቸው ሲሉ አለአግባብ ሲጠቀሙበት ይታያሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ሕግ ይልቅ ግጭትን፣ አለመረጋጋትንና ማገለልን የሚቀሰሰቅሱ ጥላቻ ንግግሮችን የሚከላከሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ስልት መቀየስ አለበት ብሏል። ከእነዚህም መካከል በጠቅላይ ሚኒስትሩ በየወቅቱ በሚተላለፍ መልዕክቶች እንዲሁም ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ስለ ጥላቻ ንግግር አስከፊነት እንዲሁም ሌሎች የማህበረሰቡን እውቀት ከፍ የሚያደርጉ ሥራዎች መሰራት ይኖርባቸዋል ሲል ይመክራል። መግለጫው አክሎም በረቂቅ ሕጉ ላይ የጥላቻ ንግግር ብያኔ የተበየነበት መንገድ በዓለም አቀፍ ህግ ላይ እንደተቀመጠው አለመሆኑን በመጥቀስ ይህም ለትርጉም ሰፊ መሆኑን ይገልጻል። • “ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ • የጥላቻ ንግግርን የሚያሠራጩ ዳያስፖራዎች እንዴት በሕግ ሊጠየቁ ይችላሉ? ረቂቅ ህጉ አሻሚ አገላለጾችን፣ ብያኔዎችን እንዲሁም አንቀጾችን መያዙን በማንሳትም ኢትዮጵያውያንና ዓለም አቀፍ የንግግር ነፃነት መብት ተሟጋቾች ያላቸውን ስጋት በማንሳት መተቸታቸውን ያስረዳል። ለዚህም የተባበሩት መንግሥታት የንግግር ነጻነት ከፍተኛ ባለሙያ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት ያሉትን በማስታወስ ሕጉ የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የማያሟላ እና በጥላቻ ንግግር ላይ የተቀመጠው ብያኔ አሻሚ መሆኑን መጥቀሳቸውን ያስታውሳል። "የኢትዮጵያ መንግሥት የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል በሥራ ላይ ያሉ በርካታ ሕጎች አሉት" ያሉት ባደር "የብሔር ግጭትን የሚያነሳሱትን በመኮነን፣ የመንግሥት ኃላፊዎች መቻቻልን የሚያበረታታ ውይይት በማድረግ መጀመር ይቻላል" ብሏል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን የጥላቻ እና ሐሰተኛ መረጃ ረቂቅ ሕግ ከማጽደቁ በፊት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከሚገኘው ከሕግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ምክር ቤት ጋር፣ የኢትዯጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች እንዲሁም በንግግር ነጻነት ባለሙያ ከሆኑ አካላት ጋር አብሮ ቢሰራ መልካም ነው ሲል ይመክራል። በስተመጨረሻም "ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህ ረቂቅ ሕግ ተጨማሪ የጭቆና መሳሪያ እንዳይሆን ሚናውን ሊወጣ ይገባል" ብሏል።
news-56045022
https://www.bbc.com/amharic/news-56045022
ኮሮናቫይረስ፡ደቡብ አፍሪካ በኮሮና ምክንያት ዘግታቸው የነበሩ ድንበሮቿን ልትከፍት ነው
በኮሮና ክፉኛ ከተጠቁ የአፍሪካ አገራት መካከል ቀዳሚ ስፍራ የምትይዘው ደቡብ አፍሪካ ስርጭቱን ለመግታት ከወር በፊት ዘግታቸው የነበሩ ድንበሯቿን ልትከፍት መሆኑን አስታውቃለች።
በመጪው ሰኞም 20 የሚሆኑ የድንበር መስመሮቿን እንደምትከፍት ገልፃለች። ይህ ውሳኔ የተላለፈው በትናንትናው ዕለት፣ የካቲት 6/ 2013 ዓ.ም በነበረ የምክር ቤቱ ስብሰባ ነው። በዚህም መሰረት አገሪቷ ከዚምባብዌ፣ ቦትስዋና፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ሌሴቶና እስዋቲኒ የሚያዋስኗትን የድንበር መስመሮች ክፍት ታደርጋለች። ምንም እንኳን ድንበር ማቋረጥ የሚፈልጉ ሰዎች መስመሩ ክፍት እንደሆነ ቢነገራቸውም ነፃ የኮቪድ-19 ሰርቲፊኬት ማሳየት እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር አሮን ሞቶሳሌዲ ተናግረዋል። ምርመራውም በቅርብ የተደረገ መሆን አለበት ተብሏል። ሚኒስትሩ ራሳቸው እንቅስቃሴ የሚበዛባቸውን አራቱን መስመሮች እንደሚጎበኙና መንገደኞች እየተስተናገዱበት ያለውን ሂደት እከታተላለሁ ማለታቸው ተዘግቧል። ደቡብ አፍሪካ ድንበሮቿን ለመዝጋት የተገደደችው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ በርካታ አገራት የደቡብ አፍሪካ ጉዞዎችን አግደዋል። በደቡብ አፍሪካ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ሁለተኛ ዙር አገርሽቶ ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ተዛምቷል። በአገሪቷ እስካሁን ድረስ በወረርሽኙ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የ47 ሺህ ዜጎቿን ህይወት ደግሞ ተነጥቃለች። ይህም ከአፍሪካ በአንደኝነት ስፍራ ያስቀምጣታል። በአሜሪካው የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሰረት እስካሁን ድረስ በአለማችን 108 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 2.3 ሚሊዮኖች ደግሞ ሞተዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ
51004416
https://www.bbc.com/amharic/51004416
እውን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆን? እና ሌሎች ጥያቄዎች ሲመለሱ
አርብ ታኅሣሥ 24/2012 ዓ.ም. ኢራን አለኝ የምትላቸውን የጦር ጄኔራል አሜሪካ በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ገደለች።
ቴህራን አደባባይ የወጡ ኢራናውያን ቁጣቸውን የአሜሪካንን ባንዲራ በማቃጠል ገልፀዋል ጄኔራል ሶሌይማኒ መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የተለያዩ የጦርነት 'ኦፕሬሽኖችን' በማፋፋም ይታወቃሉ፤ ለዋሽንግተንና ቴህራን መፋጠጥም እንደ ምክንያት ይቆጠራሉ። የቢቢሲው መከላከያና ዲፕሎማሲ ተንታኝ ጆናታን ማርከስ ዓለማችን ወደ ሶስተኛው ዓለም ጦርነት እያመራች ይሆን ወይ የሚለውን ጥያቄ ምላሽ እንዲህ አሰናድቷል። ጉዞ ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት? ቃሲም ሶሌይማኒ የኢራን ኩድስ ኃይል መሪ ነበሩ የጄኔራል ቃሲም ሶሌይማኒን መገደል ብዙዎች የሶስተኛው ዓለም ጦርነት መባቻ ሲሉ ገልፀውታል። እርግጥ ነው ግድያው እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። የጀኔራሉ መገደል ግን ለሶስተኛው የዓለም ጦርነት መንስዔ አይሆንም። በጀኔራል መገደል ድራማ ውስጥ ያሉት አሜሪካ እና ኢራን ብቻ ናቸው። ምናልባት ሩስያ እና ቻይና በዚህ ግርግር ውስጥ እጃቸው ገብቶ ቢሆን ኖሮ ሁኔታው አስጊ ይሆን ነበር። ነገር ግን ሩስያም ቻይናም የጀኔራሉ መገደል አያገባቸውም። ነገር ግን የሶሌይማኒ መገደል መካከለኛው ምሥራቅን እንደሚንጥ ሳይታለም የተፈታ ነው። ኢራን የአፀፋ ምላሽ እንደምትሰጥም የታመነ ነው። ይህ ደግሞ ከአሜሪካ ሌላ ምላሽ ሊያመጣ ይችላል። ኢራን በምላሹ የአሜሪካ ጥቅም ያለበት አካባቢን ልታጠቃ ትችላለች። በዚህ መካከል የሚፈጠረው የጦርነት ሰርግና ምላሽ አስጊ ሊሆን ይችላል። የጀኔራሉ ግድያ ሕጋዊ ነውን? ሶሌይማኒ ኢራቅ ውስጥ ባግዳድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢ ነው የተገደሉት ዩናይትድ ስቴትስ ጀኔራሉን የገደልኩት ኢራቅ ውስጥ ለሞቱ አሜሪካውያን ወታደሮች ተጠያቂ ስለሆነ ነው ትላለች። አሜሪካ በኢራቅ መንግሥት ጥያቄ መሠረት ባግዳድ ውስጥ ወታደሮች እንዳሠፈረች አይዘነጋም። ሶሌይማኒ የበርካታ አሜሪካውያን ደም በእጁ አለ ብላ የምታምነው አሜሪካ ጄኔራሉ የሚመሩትን የኩድስ ጦር አሸባሪ ድርጅት ስትል ትወነጅላለች። ይህ ደግሞ የሰውየው መገደል በአሜሪካ ዘንድ ሕጋዊነት እንዲላበስ ያደርገዋል። የኖትር ዳም ሕግ ት/ት ፕሮፌሰሯ ኤለን ኦኮኔል መሰል ግድያ ሕጋዊ አግባብነት የለውም ይላሉ። «ግድያው ሕጋዊ ሊሆን የሚችለው የተባበሩት መንግሥታትን ቻርተር የተከተለና ግልፅ የሆነ ጥቃትን ለመከላከል ብቻ ሲሆን ነው።» «ኢራን የአሜሪካን ልዑላዊነት አጥቅታ አታውቅም። አሜሪካ ሶሌይማኒ ጥቃት ያደርስብኛል ብላ በሰው ምድር መግደሏ አግባብነት የለውም። ይህ ማለት አሜሪካ ሕጋዊ ያልሆነ ግድያ ከመፈፀም አልፋ፤ ኢራቅ ውስጥ ያልተገባ ጥቃት ፈፅማለች።» የጄኔራሉ ግድያ ትራምፕ ለፖለቲካ ጥቅማቸው ያደረጉት ይሆን? እርግጥ ነው ጊዜው ትራምፕ ግድያውን የፈፀሙት ሆን ብለው ነው ብሎ ለመውቀስ አመቺ ነው። ቀጣዩ ጊዜ የአሜሪካ ምርጫ የሚካሄድበት ነውና። ወጣም ወረደ ሁኔታው ለትራምፕ ዕድልም ፈተናም ነው። ፔንታገን ኢራቅ ውስጥ ያሉ የአሜሪካ ካምፖች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፤ ወደፊትም ሊደርስባቸው ይችላል ሲል ይወቅሳል። ትራምፕ በያዙት የምርጫ ዘመን ማስረገጥ የሚፈልጉት በመካከለኛው ምሥራቅ ምንም ዓይነት አሜሪካዊ ሕይወትም ሆነ ንብረት ላይ ጥፋት አለመድረሱን ነው። ምንም እንኳ ትራምፕ ወሬያቸው ላይ ኃይለኝነት ቢስተዋልባቸውም እንዲህ ዓይነት እርምጃ ይወስዳሉ ብሎ የገመተ ያለ አይመስልም። ኢራን የኒውክሌር መሣሪያዋን ለአፀፋ ምላሽ ትጠቀምበት ይሆን? አቅሙስ አላት? ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ አቅም የላትም። ነገር ግን ኒውክሌር የማብላላት አቅሙም ችሎታውም አላት። ኢራን ሁሌም ኒውክሌር የማብላላው ለቦምብ አይደለም እንዳለች ነው። ነገር ግን አሁን ኢራን በአውሮፓውያኑ 2015 ላይ ለተፈረመው ስምምነት አልገዛም ማለቷን ተከትሎ ምናልባትም ኒውክሌር እንደ አዲስ ማብላላት ትጀምራለች የሚል ስጋት አለ። 2015 ላይ ዩናይትድ ኪንገደም፣ ፈረንሳይ፣ ሩስያ፣ ቻይና፣ ጀርመን እና የአውሮጳ ሕብረት እንዲሁም አሜሪካ ሆነው የደረሱት ስምምነት ኢራን ኒውክሌር ማብላላቷን እንድትገታ ያስስባል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ስምምነቱ ከምርጫ ቅስቀሳቸው ጀምሮ ሲያጣጥሉት ከርመው ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ ከስምምነቱ ሃገራቸውን ማግለላቸው አይዘነጋም። ጄኔራል ሶሌይማኒ ኢራቅ ውስጥ ምን እያደረጉ ነበር? ቃሲም ሶሌይማኒ (በስተግራ) 2015 በተካሄደው የአይኤስን ማጥፋት ዘመቻ ላይ የተነሱት ፎቶ ሶሌይማኒ ኢራቅ ውስጥ ምን ሢሠሩ እንደነበር በውል አይታወቅም። ኢራን ጎረቤት ሃገር ኢራቅ ውስጥ ያሉ የሺያ ሚሊሻዎችን እንደምትደግፍ ይታወቃል። ከሶሌይማኒ ጋር የተገደሉት አቡ ማሕዲ አል-ሙሃንዲስ በአሜሪካ የጦር መንደሮች ላይ ለደረሱ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆነው ካታይብ ሂዝቦላህ መሪ ናቸው። በአሜሪካና ኢራን ጥል ውስጥ ኢራቅ መከራዋን እያየች ነው። የኢራቅ መንግሥት ከአሜሪካም ሆነ ከኢራን ድጋፍ ይቀበላል። ወታደሮቿ በምድሯ ጥቃት እየደረሰባት ያለው አሜሪካ ኢራቅን ትኮንናለች። የኢራቅ መንግሥት ግድያውን ኮንኖታል። አልፎም ሟቾቹን 'መስዋዕት' ሲል ገልጿቸዋል። ኢራንና አሜሪካ ኢራቅ ውስጥ ምን አጋጫቸው? ኢራን የሺያ ሙስሊሙ የኢራቅ መንግሥት ወዳጅ ናት። አልፋም በተዘዋዋሪ የኢራቅን ወታደራዊ ኃይል ትዘውራለች ተብላ ትታማለች። አሜሪካ ደግሞ ኢራቅ ውስጥ 5 ሺህ ገደማ የጦር ሠራዊት አላት። ዋነኛ ዓላማቸው ደግሞ አይኤስን መዋጋትና የኢራቅ ጦርን መደገፍ ነው። እነዚህ ሁለት የውጭ ኃይሎች ኢራቅ ውስጥ የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር መገፋፋት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። አሁን ዋነኛው ጥያቄ የሶሌይማኒ መገደል አሜሪካ በኢራቅ ያላትን ጥቅም የበለጠ እንድታስጠብቅ ያደርጋት ይሆን ወይ ነው።
news-47815940
https://www.bbc.com/amharic/news-47815940
ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ ምን ያህል ያውቃሉ?
እድሜያቸው ወደ 60 ዓመት የሚጠጋ ወይዘሮ ናቸው። ወደ ሃኪም ዘንድ የሄዱት ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ከማህጸናቸው መውጣት ከጀመረ ከዓመት በኋላ ነበር።
ወይዘሮዋ ቀደም ብሎ ከፍ ያለ ህክምና እንዲያገኙ በሃኪም ቢታዘዙም ባለቤታቸው ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤታቸው ቆይተዋል። ችግሩ ሲከፋ ወደ ሃኪም ዘንድ ቀርበው ለዶ/ር ቤርሳቤህ መናሻ "ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ ታምሜ ሪፈራል ተፅፎልኝ ባለቤቴ ስላልፈቀደ ችላ በማለት ሳልታከም ቀረሁ" ብለው ሲነግሯት በጣም እንዳዘነች ታስታውሳለች። "ማህበረሰባችን የበሽታውን ክብደት ብዙም ስለማይገነዘበው በርካታ ሴቶች ህመማቸውን ይዘው ከፍተኛ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ይቆያሉ" ትላለች ዶ/ር ቤርሳቤህ። ለወይዘሮዋ አስፈላጊውን ምርመራና ህክምና አድርጋ በድጋሚ ለተጨማሪ ህክምና ከፍ ወዳለ ሆስፒታል ስትልካቸው ባለቤትየው "እህል የምናበረይበት ወቅት ስለሆነ ሰው ያስፈልገኛል" ብለው ሞገቱኝ ትላለች። • አስጊነቱ እየጨመረ ያለው ካንሰር ይህ አጋጣሚ የእኚህ እናት ብቻ አይደለም። ብዙ ሴቶች ይህን አሳዛኝ ታሪክ እንደሚጋሩ ዶ/ር ዳግም ታደለም "ብዙዎቹ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርሱ ነው እኛ ጋር የሚመጡት" በማለት ያረጋግጣል። ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽ የካንሰር፣ የአባላዘር በሽታዎችና የሌሎች ኢንፌክሽኖች አንዱ ምልክት ሆኖ ሳለ ብዙዎች ስለጉዳዩ ዕውቀት አለማግኘታቸውና ለመነጋገር አለመቻላቸው ችግሩን አባብሶታል። እርሶስ ስለጉዳዩ ምን ያህል ያውቃሉ? ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ በማህበረሰቡ ውስጥ በቂ እውቀት እንዲኖር የሚያስችል አጋጣሚ የለም የሚሉት ባለሙያዎቹ የራሳቸውን ተሞክሮ ያስታውሳሉ። ዶ/ር ቤርሳቤህ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷ ውስጥ በግልፅ ከማህፀን ስለሚወጣ ፈሳሽ ባለመማሯ "የህክምና ሙያ ባላጠና ኖሮ ስለዚህ ጉዳይ አለላውቅም ነበር" ትላለች። • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? የጥቁር አንበሳ የህክምና ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ሃብቶም አለሙም ዩኒቨርሲቲ ከመግባቱ በፊት ስለዚህ ጉዳይ ለምን በትምህርት ቤት ሳለ እንዲያውቅ እንዳልተደረገ ጥያቄ እንደፈጠረበት ይናገራል። ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ምንድን ነው? በእንግሊዘኛው 'ቫጃይናል ዲስቻርጅ' የሚባለው ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ የአንድ ሴት የወር አበባ ኡደትን ተከትሎ በተለያየ መጠንና ዓይነት ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽ ነው። ማህፀንና ፅንስን የሚያጠኑት ዶ/ር ዳግም ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ጤናማ የሆነ ተፈጥሯዊ ነገር ሲሆን፤ በሽታ ሲይዝ ግን ጤናማ ያልሆነ ሽታ ሊያመጣና ቀለሙም ሊቀየር እንደሚችል ይናገራሉ። ይህ ከማህፀን የሚወጣ ተፈጥሯዊ ፈሳሽ ከሆርሞን የሚመነጭ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ዳግም "አንዲት ሴት ሁሌም ይህ ፈሳሽ ሊኖራት ይችላል። እንዲያውም በቀን ከ 1 እስከ 4 ሚሊሊትር ሽታ የሌለው ከማህፀን የሚወጣ ነጭ ፈሳሽ ጤናማ ተደርጎ ይወሰዳል" ይላሉ። • የወር አበባ ለምን በአንዳንድ ሴቶች ላይ ህመም ያስከትላል? ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ የፈሳሽ መጠን ግን ሴቷ ጤናማ ሁኔታ ላይ ሆናም በእርግዝናና በአንዳንድ እርግዝና መከላከያዎች ምክንያት መጠኑ ሊቀየር እንደሚችል ዶክተሩ ይናገራሉ። ከማህፀን የሚወጣው ፈሳሽ የማህፀን ካንሰርና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል። እነዚህ በሽታዎች በሚያጋጥሙ ጊዜም የፈሳሹ መጠን፣ ጠረንና ቀለም ሊለወጥ ይችላል። በግልጽ የማይነገር ጉዳይ በርካታ ሴቶች ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ በግልጽ በአስፈላጊው ጊዜ ለመናገር አይደፍሩም። ለሃኪሞችም ቢሆን የሚገልጹት ከብዙ ጉትጎታ በኋላ ነው። "ታካሚዎች ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ለውጥ እንዳለ የሚናገሩት ሌሎች ምልክቶችን ጠቅሰው ሲጨርሱ መጨረሻ ላይ ነው" የምትለው ዶ/ር ቤርሳቤህ ለማውራት ነፃነት እንዲያገኙም ባሎችን ወይም ሌሎች ሰዎችን አስወጥተን ነው የምናነጋርራቸው ትላለች። አንድ ታካሚዋ ከማህጸኗ የሚወጣው ፈሳሽ ደም ከመቀላቀል አልፎ ህመም ሲበረታባት እንደመጣች የምታስታውሰው ዶ/ር ቤርሳቤህ "በርካታ ሴቶች የማህፀን ፈሳሻቸው ከተለመደው የተለየ ሲሆን ህክምና ፈልገው አይመጡም፤ ሁሌም ከእሱ ጋር የተያያዘ ሌላ ህመም ሲኖራቸው ብቻ ነው የሚመጡት" ትላለች። በተለይ ከከተማ ውጪ የሚኖሩ ሴቶች ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ሲቀየር ህክምና ባለማድረጋቸው ምክንያት ችግሩ ከማህጸን ጫፍ ወደ ውስጥ በመግባት ኢንፌክሽን ፈጥሮ ሌላ ከባድ ችግር ሲያጋጥማቸው ወደህክምና እንደሚሄዱ ዶ/ር ዳግምም ይናገራሉ። • ጥበብን በወር-አበባና በአጽም ዶ/ር ቤርሳቤህ እንደምትለው ከማህጸን የሚወጣው ፈሳሽ የካንሰር፣ የአባላዘር በሽታዎችና የሌሎች ኢንፌክሽኖች ምልክት ሆኖ ሳለ በጉዳዩ ላይ በግልጽ መነጋገር ስለማይደፈር፤ ያለው የህክምና አገልግሎት እርዳታ እንዳያደርግ መሰናክል እንደሆነበት ትናገራለች። ከማህጸን በሚወጣ ፈሳሽ ላይ የሚታዩ ለውጦችን በመከታተል በጊዜ ወደ ህክምና መሄድ ከቻሉ ለካንሰርም ሆነ ለአባላዘር በሽታዎች የተሻለ ህክምና በማግኘት ጤናቸውን የማሻሻል ዕድል እንዳለ ባለሙያዎቹ ይመክራሉ። የህክምና ድጋፍ ለማግኘትም የሚከተሉትን ምልክቶች ትኩረት ሰጥቶ ማስተዋል ያስፈልጋል። ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽ ሽታ ወይም ቀለም መቀየር፣ ደም መቀላቀል፣ የመራቢያ አካላት መቅላትና በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት ካለ ባለሙያ ጋር በመሄድ ማማከር ያስፈልጋል። ትምህርት ቤቶችና የሥነ ተዋልዶ የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎቻቸው ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽና ስለሌሎች የሥነ ተዋልዶ ጉዳዮች በግልጽና በአግባቡ ማስተማር ከቻሉ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሀፍረትና የህክምና ድጋፍ ለማግኘት ያለመድፈር ጉዳይ ሊቀረፍ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳለች "ስለ ሥነ ተዋልዶና የተያያዠ ጉዳዮች ስንማር በአስተማሪው ተነሳሽነት ላይ ይወሰን ነበር" የምትለው ዶ/ር ቤርሳቤህ፤ ብዙም ጠለቅ ያለና ስለጉዳዩ በቂ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ትምህርት እንዳልሆነ ታስታውሳለች። አክላም በመጀመሪያና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷ ወቅት ስለ ሥነ ተዋልዶና ስለየወር አበባ ብትማርም ሴቶች ስለሚያጋጥማቸው ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ምንም ነገር ስላልተማረች በወቅቱ ምንም የምታውቀው ነገር እንዳልነበረ ትገልጻለች። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት አቶ ተሾመ መሳፍንት የባዮሎጂ መምህር ሲሆኑ፤ የሥነ ተዋልዶ ትምህርት 7 እና 8ተኛ ክፍል እንደሚሰጥ ነገር ግን በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል የባዮሎጂ ትምህርት ውስጥ እንደሌለ ይናገራሉ። ዶ/ር ቤርሳቤህ "ወንዶች ህክምና ካላጠኑ በስተቀር ከማህፀን ስለሚወጣ ፈሳሽ የማወቅ እድል የላቸውም" ስትል ከዚህ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ዶ/ር ዳግምም "ህክምና ስማር አንብቤ ነው ያወኩት" ብሏል። ከታች ባሉት የትምህርት ክፍሎች ውስጥ ከሥነ ተዋልዶ ትምህርት ጋር ተጣምሮ ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ ትምህርት ቢሰጥ መልካም እንደሆነ የሚገልጹት ሁለቱ የህክምና ባለሙያዎች እነሱም ስለፈሳሹ ያወቁት ህክምና በማጥናታቸው እንደሆነ ይመሰክራሉ።
news-57251173
https://www.bbc.com/amharic/news-57251173
ቻይና ለዩናይትድ ኪንግደም እቃዎችን በማቅረብ ጀርመንን በለጠች
ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በምትልካቸው ቁሳቁሶች ብዛት ጀርመንን በለጠች።
የንግድ ልውውጥ መመዝገብ ከጀመረ አንስቶ ባልታየ ሁኔታ ቻይና ለዩናይትድ ኪንግደም እቃ በመላክ ግንባር ቀደም አገር ሆናለች። የብሔራዊ ስታትስቲክስ መረጃ እንደሚያሳየው በዚህ ዓመት የመጀመሪያው ሦስት ወራት ከቻይና የተላኩ ቁሳቁሶች በ16.9 ቢሊዮን ዩሮ ይገመታሉ። ይህም እአአ በ2018 ከነበረው የ66 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በአንጻሩ ከጀርመን የሚላኩ እቃዎች ወደ 12.5 ቢሊዮን ዩሮ ወርደዋል። ይህ የንግድ አጋር ለውጥ የመጣው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ከአውሮፓ ሕብረት መውጣቷን ተከትሎ ነው። ከብሬግዚት ወዲህ የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት የንግድ ትስስር ላልቷል። ከዚህ ባሻገር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የቻይና ቁሳቁሶች ተፈላጊ እንዲሆኑ ግድ ብሏል። የብሔራዊ ስታትስቲክስ ተቋም ብሬግዚት እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዩኬ ንግድ ላይ ያሳደሩትን ተጽዕኖ ፈትሿል። የዩኬ እና የአውሮፓ ሕብረት አዲስ አይነት ግንኙነት የንግድ ትስስራቸውን እንዳላላው የሚጠቁም ማስረጃ ተገኝቷል። ከጀርመን ወደ ዩኬ የሚላኩ ቁሳቁሶች ቁጥር የቀነሰው እአአ ከሚያዚያ 2019 ወዲህ ነው። ይህ ወቅት ዩኬ ከአውሮፓ ሕብረት ስለምትወጣበት መንገድ ጥያቄዎች የነበሩበት ነው። በሌላ በኩል የጀርመን መኪና አምራቾች በወረርሽኙ ሳቢያ ገበያቸው ተቀዛቅዟል። በዩኬ የመኪና ማሳያ መደብሮች በወረርሽኙ ሳቢያ በመዘጋታቸው አዲስ መኪና ለመግዛት ያለው ፍላጎት አሽቆልቁሏል። ዩኬ ከአውሮፓ ሕብረት ከወጣች ወዲህ ከአየርላንድ ጋር የነበራት የንግድ ትስስርም እንቀድሞው አልሆነም። ቀድሞ ዩኬ መገልገያዎችን ትልክላቸው ከነበሩ አምስት ግንባር ቀደም አገራት አንዷ አየርላንድ ነበረች። በዘመናዊ መንገድ የንግድ ልውውጥ ምዝገባ የተጀመረው እአአ በ1997 ነው። ከዚያ ዘመን አንስቶ ጀርመን ለዩኬ እቃ በመላክ ቁጥር አንድ አገር ነበረች። በእርግጥ 2000 ላይ ለስድስት ወራት ያህል ይህንን የአንደኝነት ቦታ አሜሪካ ወስዳው ነበር። ዩኬ ከአጠቃላይ የአውሮፓ ሕብረት አገራት ጋር ታደርግ የነበረው ንግድ 23.1 በመቶ ቢቀንስም፤ አሁንም የዩኬ ዋነኛ የንግድ አጋሮች የሕብረቱ አባል አገራት ናቸው። ከቻይና ወደ ዩኬ ከሚገቡ መገልገያዎች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እና የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ናቸው። ባለፈው ዓመት፤ ቻይና ከዓለም አገራት ቀድማ ወረርሽኙን ማሸነፏን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ንግዷ ያደገ ቀዳሚዋ አገር ናት።
news-50120800
https://www.bbc.com/amharic/news-50120800
ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ሲካሄዱ የነበሩ ስብሰባዎች በቡድን በመጡ ወጣቶች መስተጓጎላቸው ተነግሯል
ትናንት የአማራ ወጣቶች ማህበር እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሥፍራዎች ሲያካሂዷቸው የነበሩ ስብሰባዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ወጣቶች መስተጓጎላቸው ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ትናንት ጥቅምት 9፣ 2012 ዓ.ም. በዓላማ እና ግቦች፣ የፖለቲካ አመለካከቶች እንዲሁም የምርጫ ዝግጅት ዙሪያ በአዲስ አበባ የተለያዩ ወረዳዎች ከአባላት ጋር ውይይት ማካሄዱን የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ይሁን እንጅ ስብሰባው ከተካሄደባቸው ሥፍራዎች መካከል ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 (በምርጫ ወረዳ አጠራር 'ምርጫ ወረዳ 19') የነበረው ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት የተወሰኑ ወጣቶች "ስብሰባው አይደረግም፤ ሰዎች ወደ አዳራሹ አይገቡም" የሚል ክልከላ አድርገው እንደነበር ይገልፃሉ። "በወቅቱ አባላቶቻችን ተረጋግተው፤ ሰዎችን ለማረጋጋት ሞክረዋል።" የሚሉት የህዝብ ግነኙነት ኃላፊው፤ ሁኔታውን መቆጣጠር እንደማይቻል ሲገነዘቡ ፖሊስ እንዲጠራ መደረጉን ተናግረዋል። • "ውስኪ ጠጪ ኢህአዴጎች እባካችሁ ውሃ የናፈቀው ሕዝብ እንዳለ አትርሱ" ጠ/ሚ ዐብይ • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት አቶ ናትናኤል ስብሰባውን ለማካሄድም ፍቃድ አግኝተው በወረዳ 06 ግቢ ውስጥ የሚገኝ አዳራሽ መጠቀማቸውን ይናገራሉ። "እኛ ማሳወቅ የነበረብንን ሰዎች አሳውቀን ነው አዳራሹን የተከራየነው፤ ለፖሊስም ቀደም ብለን አሳውቀን ነበር። ማድረግ ያለብንን አድርገናል" ይላሉ። ወጣቶቹ ስብሰባው አይካሄድም ያሉበትን ምክንያት ምን እንደሆነ የተጠየቁት የህዝብ ግነኙነት ኃላፊው፤ 'እንዲሁ በደፈናው እዚህ ስብሰባ አታደርጉም' የሚል ምክንያት እንጂ ዝርዝር ነገር አለመናገራቸውን ያስረዳሉ። ስብሰባው እንዳይካሄድ ያስተጓጎሉት ወጣቶች አዳራሹ ላይ የነበሩ ባነሮችን እና ሰንደቅ አላማዎችን እንዳወረዱ እና የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ በቦታው ደርሶ ወጣቶቹን ገለል ስላደረገ ስብሰበባው መካሄዱን ይገልፃሉ። ወጣቶቹ ቁጥራቸው 20 ይሆናል የሚሉት ኃላፊው፤ የፓርቲው አባል ያልሆኑ እና በአካባቢው የሚታወቁ ሰዎች እንዳልሆኑ በአካባቢው አባል የሆኑ ሰዎች እንዳረጋገጡላቸው ገልፀው፤ "ሌላውን ሥራ ለፖሊስ ትተናል" ብለዋል። በዕለቱ በሌሎች ወረዳዎች የተካሄዱት የኢዜማ ስብሰባዎች ችግር ሳያጋጥማቸው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በንፋስ ስልክ የነበረውም ውይይት መጀመሪያ ላይ ቢስተጓጎልም በመጨረሻ መካሄዱን የህዝብ ግነኙነት ኃላፊው አክለዋል። አቶ ናትናኤል በተፈጠረው ችግር በሰው አካል ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አስረድተዋል። በተያያዘ ትናንት በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 09 ልዩ ስሙ ኮዬ ፈጨ ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባላት ሲያደርጉት የነበረው ስብሰባ በሌሎች ወጣቶች እንዲበተን መደረጉ ተነግሯል። ከስብሰባው አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው በለጠ ተገኘ ለቢቢሲ ሲናገር፤ ስብሰባው የአማራ ወጣቶች ማህበር ሪፖርት መስማትና የጠቅላይ ሚንስትሩን የሰላም የኖቤል ሽልማት በማስመልከት ደስታ ለመግለጽ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ እንደነበር ይገልጻል። ስብሰባውን በማገባደድ ላይ እያሉ ከቀኑ 6፡30 አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ ወጣቶች መጥተው የግቢውን ዘበኛ ጥሰው በማለፍ "እኛ ወደ ተሰበሳብንበት አራተኛ ፎቅ መውጣት ጀመሩ" የሚለው ወጣት በለጠ፤ ደረጃው ላይ የስብሰባው ተሳታፊ ወጣቶች እንዲያግዷቸው መደረጉን ይገልጻል። በተሰብሳቢዎቹና ከውጭ በመጡት ሰዎች መካከል በተፈጠረ ፍጥጫ ለመውጣትም አስቸጋሪ በመሆኑ "ጠዋት አንድ ሰዓት እንደገባን ቁርስም ምሳም ሳንበላ እስከ ከሰዓት ድረስ እዚያው ታግተን ለመዋል ተገደናል" ይላል። ከታች ሆነው ድንጋይ ሲወረውሩባቸው እንደቆየ የገለጸው በለጠ፤ የሚወረወረው ድንጋይ የህንጻውን መስኮት መሰባበሩን ተናግሯል። ግቢው ውስጥ ህጻናት የያዙ እናቶችና በተሽከርካሪ ወንበር [ዊልቸር] የሚሄዱ ሰዎች ስለነበሩ እነሱ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በማሰብ ቀሪዎቹ ወጣቶች የሚደርስባቸውን ጥቃት መከላከላቸውን ተናግሯል። ፖሊስ ነገሮችን ካረጋጋ በኋላ 'ኤፍኤስአር' የጭነት መኪና እና ከኋላው ክፍት በሆነ ፒክ አፕ ተሽከርካሪዎች እየታገዘ ተሰብሳቢዎችን ከስፍራው ማስወጣቱን በለጠ ይናገራል። "ስብሰባው ሕጋዊ ነው፤ ለስብሰባውም ፍቃድ አለን"ሲል በለጠ ለቢቢሲ ተናግሯል። በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጠን የፌደራል ፖሊስ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ እና ችግር ተፈጥሮባቸዋል በተባሉ የክፍለ ከተማ ፖሊስ ጋር በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም። ዛሬም ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የጸጥታ መደፍረስ አጋጥሞ የጸጥታ አስከባሪዎች በቦታው ተሰማርተው እንደነበረ እና አምቡላንሶችም በሥፍራው በስፋት መታየታቸውን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ለመጠየቅ የምናደርገው ጥረት ይቀጥላል።
news-55998615
https://www.bbc.com/amharic/news-55998615
ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት እስከ 9 ሚሊዮን የኮሮና ክትባት እንደምታስገባ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ እስከ 9 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት ለማስገባት እየሰራች መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ።
ክትባት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ይህንን ያሉት ዛሬ፣ ማክሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ለክትባቱ በዋናነት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎች ተጋላጭ ይሆናሉ ተብለው የተለዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸው ብለዋል። በዚህ መሰረት የጤና ባለሙያዎች፣ የማህበራዊ ጤና ሰራተኞች፣ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ያሉ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ግብረ ሀይልም የተሳለጠ የክትባት አሰጣጥና ቁጥጥር እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል ዶ/ር ሊያ። ሚኒስትሯ አክለውም ኢትዮጵያና መሰል ሀገራት ከኮቫክስ የክትባት ትብብር ተቋም ጋር በመሆን እስከ ፈረንጆቹ 2021 መጨረሻ 20 በመቶ የሚሆነውን ህዝባቸውን ለመከተብ እየሰሩ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ክትባቱን ወደ ሃገር ውስጥ የምታስገባው ‹‹ኮቫክስ›› በተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ሸማች ማህበር በኩል ነው። ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ኢኒሼቲቭ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ኢኒሼቲቭ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል። አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ ተገልጿል። አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተው ነበር። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው።
50772861
https://www.bbc.com/amharic/50772861
ናይጄሪያ ለአፍሪካዊያን በሯን ክፍት ልታደርግ ነው
አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ዜጎች ናይጄሪያ ለመግባት ለቪዛ ቀደም ብለው ማመልከትና ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸው ነበር።
ከአዲስ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ግን ይህ ጣጣ ይቀራል። ዜጎችም በቀጥታ አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ቪዛ ይታደላቸዋል ተብሏል። ርዕሰ ብሔር መሐመድ ቡሃሪ እንደተናገሩት አፍሪካዊያን በአፍሪካ ውስጥ ነጻ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። የቡሃሪ ተቺዎች ግን ፕሬዝዳንቱ እንዲያውም ጸረ ፓን አፍሪካን ናቸው ይሏቸዋል። ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም ካለፈው ነሐሴ ጀምሮ የናይጄሪያን ድንበር ቁጥጥር ማጥበቃቸውንና ይህም ንግድ ከአጎራባች አገሮች ጋር ለማድረግ ፈታኝ ማድረጉን ያወሳሉ። ቡሃሪ በበኩላቸው ይህን ያደረኩት ሕገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ስል ነው ይላሉ። • አሜሪካ የቪዛ አመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ ዝርዝር ልትጠይቅ ነው • አፍሪካዊያን ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትን መጎብኘት ለምን ይከብዳቸዋል? ናይጄሪያ የመዳረሻ ቪዛን ተግባራዊ ስታደርግ ቪዛ አመልካቾች በአገራቸው ሳሉ የመግቢያ ቪዛ የማመልከት ሂደት ሙሉ በሙሉ ያስቀርላቸዋል። በአዲሱ ዓመት ማንኛውም ከአፍሪካ አገራት የሚመጣ ዜጋ ናይጄሪያን እንደረገጠ ቪዛ ያገኛል። ባለፈው ወር በአፍሪካ ባንክ በተደረገ አንድ ጥናት አፍሪካዊያን 49 ከመቶ በሚሆኑ የአፍሪካ አገራት ለመግባት ቪዛ የግድ ይላቸዋል። የመዳረሻ ቪዛን የሚያድሉ አገራት 26 ከመቶዎቹ ብቻ ናቸው። ምንም ቪዛ የማይጠይቁት ደግሞ 25 ከመቶዎቹ ብቻ ናቸው። ከ54ቱ የአፍሪካ አገራት አጅግ ቀላል የቪዛ ጣጣ ያለባቸው አገራት ሲሸልስ፣ ቤኒን፣ ሴኔጋል፣ ሩዋንዳና ጋና ናቸው። የቪዛ ሂደታቸው ፈታኝ የሚባሉት አገራት ደግሞ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሊቢያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ጎረቤት ኤርትራ ናቸው። ኢትዮጵያ የቪዛ ጣጣቸው ከበዙ አገራት ውስጥ ዋነኛ ተጠቃሽ እንደነበረች ሪፖርቱ ይጠቅሳል። ባለፈው ዓመት ግን የመዳረሻ ቪዛን ተግባራዊ በማድረጓ ቪዛን ካከበዱት አገራት ጎራ ተላቃለች።
50052266
https://www.bbc.com/amharic/50052266
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት የማግባታቸው ወሬ ቢነፍስም ቀዳማዊቷ እመቤት ወደ ሃገራቸው ተመለሱ
የናይጄሪያ ቀዳማዊት እመቤት አይሻ ቡሃሪ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ሁለተኛ ሚስት ሊያገቡ ነው እየተባለበት ባለበት ሁኔታ ከሁለት ወራት ከውጭ ቆይታቸው በኋላ ቅዳሜ ተመልሰዋል።
ቀዳማዊት እመቤት ለሃይማኖታዊ ጉዞ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው የነበረ ሲሆን በመቀጠልም ወደ እንግሊዝ አምርተው ነበር። ከተመለሱ በኋላም ሀሰተኛ ዜናዎችም ወደማይታሰብ ስቃይ እንደሚመራ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። •የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? •በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው ቀዳማዊቷ ከተመለሱ በኋላም ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ሁለተኛ ሚስት ለማግባት ማቀዳቸውንም የተነዛውንም ጭምጭምታ ተጠይቀውም በሽሙጥ መልሰዋል ሳዲያ ፋሩቅ የተባሉ ፖለቲከኛ ለማግባት ማቀዳቸው ተነግሯል። ሰርጉ ባለመከናወኑ፤ ፖለቲከኛዋ መበሳጨታቸውን ቀዳማዊቷ እመቤት ለቢቢሲ ሃውሳ በቅኔ መልኩ አስረድተዋል። "ሊያገባት ቃል የገባላት ሰው ሰርጉ እንደሚፈጠር አያውቅም። እሷም ሳዲያ ፋሩቅ ቀኑ እስከሚያልፍ ድረስም ጋብቻው እንደሚከናወን አልካደችም ነበር" ብለዋል። •"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የተወራ ሲሆን ባለፈው አርብ ዕለት ሰርጉ ሊከናወንም ነበር የሚሉ ወሬዎችም ተናፍሰዋል። ፕሬዚዳንት ቡሃሪም ሆነ ሳዲያ ፋሩቅ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ቀዳማዊቷ የፕሬዚዳንቱ እህት ልጅ ጋር ሲከራከሩ የሚያሳየውንም ቪዲዮ እውነትነት ቢያረጋግጥጡም ከጋብቻው ጋር ያልተገናኘና የቀድም እንደሆነ ነው። የፕሬዚዳንቱ እህት ልጅ ፋጢማ ማማን ዱራምም ቪዲዮው የቆየ መሆኑን አረጋግጣ አሁን የወጣበትም ምክንያት ሌላ ትርጉም እንዲሰጠው ነው ብላለች።
51030413
https://www.bbc.com/amharic/51030413
ኮንጎ፡ ከ6ሺህ ሰዎች በላይ የሞቱበት የኩፍን ወረርሽኝ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኩፍኝ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 6ሺህ ማለፉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የኩፍኝ ወረርሽኝ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በርካቶችን እየገደለ ይገኛል የዓለም ዓቀፍ ጤና ድርጅት ይህ ወረርሽኝ በስፋትና በፍጥነት የተዛመተ መሆኑን በመግለጽ ከዓለማችን ትልቁ ነው ብሎታል። እ.ኤ.አ. በ2019 ብቻ 310 ሺህ ሰዎች በኩፍኝ በሽታ የተጠረጠሩ ሰዎች መመዝገባቸውን ድርጅቱ ጨምሮ አስታውቋል። • በኩፍኝ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው • ኢትዮጵያዊያን ለክትባቶች ከፍተኛ የሆነ አውንታዊ አመለካከት አላቸው • ኢትዮጵያ አሁንም 'ኩፍኝ አልወጣላትም' የኮንጎ መንግሥት ባለፈው መስከረም ወር አስቸኳይ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት መርሀ ግብርን ይፋ አድርጓል። እንደ ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት መግለጫ ከሆነ በ2019 ብቻ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ከ18 ሚሊየን በላይ ሕፃናት ተከትበዋል። ነገር ግን ደካማ የሆነ መሰረተ ልማት፣ በጤና ተቋማት ላይ የሚደርስ ጥቃትና ተከታታይ የሆነ የጤና እንክብካቤ አለመኖሩ የበሽታውን በፍጥነት መዛመት ሊገታው እንዳልቻለ ተገልጿል። በኮንጎ የሚገኙ 26 ግዛቶች ውስጥ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በሽታው በወረርሽኝ ለመልክ መከሰቱ ከተነገረ ጊዜ ጀምሮ በርካታ በኩፍኝ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለው የኩፍኝ ወረርሽኝ በማዕከላዊ አፍሪካ ካለው የኢቦላ ወረርሽን በሁለት እጥፍ የሚልቁ ሰዎችን እየገደለ ነው። "ይህንን ወረርሽን ለመቆጣጠር የአቅማችንን ሁሉ እያደረግን ነው" ያሉት የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ማትሺድሶ ሞዬቲ ናቸው። "በትክክል ውጤታማ ለመሆን ግን ማንኛውም ሕጻን በቀላሉ በክትባት መከላከል በሚቻል በሽታ እንዳይሞት ማድረግ አለብን። አጋሮቻችን በፍጥነት ድጋፋቸውን እንዲያደርጉልን ጥሪ እናቀርባለን" ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እድሜያቸው ከ6 እስከ 14 የሆኑ ሕፃናትን በመከተብ መከላከሉን ለማጠናከር ተጨማሪ 40 ሚሊየን ዶላር ያስፈልገኛል ሲል ተናግሯል። በዓለም ላይ በየዓመቱ 110ሺህ ሰዎች በኩፍኝ በሸታ ተይዘው ይሞታሉ ሲል ድርጅቱ በመግለጫው ላይ አስታውቋል።
52106873
https://www.bbc.com/amharic/52106873
በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በትናንትናው ዕለት ባደረገው 66 ተጨማሪ ምርመራ ሁለቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ግለሰቦች በአማራ ክልል ነዋሪ መሆናቸውን አስታውቋል
ይህንንም ተከትሎ ከታማሚዎቹ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲሁም ንክኪ ይኖራቸዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎችን የመለየትና የክትትል ሂደት እየተከናወነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ ገልፀዋል። •በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች •በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው በቫይረሱ የተያዙት ግለሰቦች በአማራ ክልል ባሕር ዳር ነዋሪ የሆኑ የ37 ዓመት ሴትና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የአዲስ ቅዳም ነዋሪ የሆኑ የ32 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውም ተገልጿል። ግለሰቦቹ መንግሥት ያዘዘው የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ ዕለት አስቀድሞ ከዱባይ እና ከአሜሪካ የገቡ ሲሆን፤ የበሽታውን ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፤ በምርመራው መሰረትም መያዛቸው ተረጋግጧል ብሏል። •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ በተለይም ከአሜሪካ የመጣው ግለሰብ 'እንኳን ደህና መጣህ' በሚሉ በርካታ ሰዎች መጎብኘቱን ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲጋሩት ነበር የሚለውን ቢቢሲ ጠቅሶ ለዶ/ር ፋንታ ጥያቄ ሰንዝሮላቸዋል። በምላሻቸውም ግለሰቡ መጋቢት 12 ከአሜሪካ መጥቶ ወደ አዊ ዞን ደግሞ መጋቢት 15 መሄዱን ማረጋገጣቸውን ገልፀው፤ አቀባበል ነበር የሚለውን የዞኑ አስተዳደር ኃላፊነት ወስዶ ከጤና ባለሙያዎች ጋር እያጣራን ነው ብለዋል። "አቀባበል ከነበረ የሚደበቅ ነገር የለውም። በሽታው በንክኪ የሚተላለፍ ስለሆነ በሽተኛውም ቤተሰቦቹን የሚደብቅ አይመስለኝም። ጉዳዩ ሌሎችን የመርዳት ነው። የተጠቁ ካሉ ጥንቃቄ አድርገው ራሳቸውን ረድተው የሚሸጋገሩበትን ለማመቻቸት ስለሆነ እንደሚስጥር ይታፈናል ብዬ አላምንም። ተደርጎ ከሆነ እነዚህ ሰዎች መረዳት አለባቸው። ሌላውን ወገናቸውን እና ቤተሰባቸውን እንዳይበክሉ የመለየት ሥራ እየሠራን ነው" ብለዋል። ሁለቱም ታማሚዎች በአማራ ክልል የለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከል የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኝ ሲሆን እስከ ትላንት ምሽት ድረስ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተጫማሪ አስረድተዋል። •በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች በክልሉም እስከ ትላንት ድረስ 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን በምርመራው መሰረት ሁለቱ ቫይረሱ እንዳለባቸው ሲረጋገጥ ሌሎቹ ነፃ መሆናቸው መረጋገጡን ዶ/ር ፋንታ አስረድተዋል። የአለም ጤና ድርጅትም ሆነ የተለያዩ የጤና ሚኒስትሮችም ሆነ ባለሙያዎች አበክረው እንደሚናገሩት ዶ/ር ፋንታም ግለሰቦች አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንዲሁም ንክኪን ማስወገድ መፍትሄ እንደሆነና በተለይም ምልክቱ ስለማይታይ ከቫይረሱ ነፃ የመሆን ማረጋገጫ አይደለም ብለዋል። " ከቫይረሱ ነጻ ነን ለማለት በምርመራ ብቻ የምናረጋግጠው ነው" በማለት አስረድተዋል። በተለይም 27 ሰዎች ተጠርጥረው ምርመራ መደረጉና 25 ነፃ መሆናቸውና ሁለት ሰዎች መገኘታቸው ቫይረሱ ተዛምቷል ወይም አልተዛመተም የሚለውን ሳይሆን የሚያሳየው ዶ/ር ፋንታ እንደሚሉት ቁጥሩ ተጠርጥረው ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤታቸው የታወቁትን ብቻ የሚያሳይ መሆኑን አስታውቀዋል። "ከማህበረሰብ ስንቱ ተጠቅቷል ስንቱ አልተጠቃም የሚለውን እንዲሁም በክልሉ ያለው ሁለት ብቻ ነው ለማለት የክልሉን ህዝብ መመርምረን ነው ያንን መናገር የምንችለው።" ብለዋል። በቀጣዪም በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማካሄድ እየተሠራ መሆኑንም ዶ/ር ፋንታ ገልዋል "ከክልሉ ወደ ፌደራል ማዕከል ከመላክ እዚሁ ለመጀመር የሚያስችል አንድ ማሽን አግኝተን ሶፍት ዌር ኮንፊገሬሽን እየተሠራ ነው። እሱ እንዳለቀ ክልሉ እዚሁ ናሙና እየተወሰደ ውጤቱን በአጭር ከዚሁ የምንሰማበት ቀን በቅርብ ይኖራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን" በማለት አስረድተዋል። በቅርቡ ከውጭ ሃገራት የመጡ ግለሰቦች ሪፖርት እንዲያደርጉ ክልሉ ትላንት ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ምን ያህል ሰዎች ሪፖርት እንዳደረጉ ተጠይቀው እስካሁን ሪፖርቱ እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል።
54445178
https://www.bbc.com/amharic/54445178
ቻይና፡ ሐሰተኛ መረጃ ያጠላበት የሕንድና ቻይና የድንበር ግጭት
ሰኔ ላይ በሕንድ እና በቻይና ድንበር ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ አሁንም በአካባቢው ውጥረት ይስተዋላል። በግጭቱ ቢያንስ 20 የሕንድ ወታደሮች ተገድለዋል።
ቻይናውያን ወታደሮች ሁለቱ አገራት እርስ በእርስ ላለመጋጨት እየተወያዩ ነው። ሆኖም ግን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል። ከነዚህ ጥቂቱን እንመልከት። የሚያለቅሱት ቻይናውያን ወታደሮች የተወራው፡ ቻይናውያን ወታደሮች ወደ ድንበር ሲላኩ ያለቅሳሉ። እውነታው፡ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ከአውድ ውጪ ተወስዶ የተሰራጨ መረጃ ነው። ትዊተር ላይ የነበረ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል መስከረም ላይ በታይዋን ዜና ማሰራጫ ተላልፏል። ከዛም በሕንድ ተሰራጭቷል። ቻይናውያን ወታደሮች ወደ ድንበር ሲላኩ ያለቅሳሉ በሚል ብዙዎች ሲሳለቁ ነበር። ቪድዮው ከ300,000 ጊዜ በላይ ታይቷል። የሕንድ ሚዲያዎችም አስተላልፈውታል። በቪድዮው የሚታዩት ቻይናውያን ወታደሮች አውቶብስ ውስጥ ሆነው በማንደሪን ስለ አገር ናፍቆት የሚያወሳ ታዋቂ ወታደራዊ ዘፈን እያዜሙ ነበር። "በክብር የወታደር ኃይሉን ተቀላቀሉ" የሚል ጽሑፍም የደንብ ልብሳቸው ላይ ተለጥፏል። ሆኖም ግን እነዚህ ወታደሮች ወደ ሕንድና ቻይና ድንበር እየሄዱ ስለመሆኑ የሚጠቁም መረጃ ቢቢሲ አላገኘም። የቻይና መገናኛ ብዙሀን እንደሚሉት ወታደሮቹ አዲስ ምልምል ናቸው። ወደ አሁኒ ግዛት የተላኩት ወታደሮች፤ ቤተሰቦቻቸውን ተሰናብተው በሀዘን ተውጠው ነበር። በቻይናው ማኅበራዊ ሚዲያ ዊቻት ላይ የተሰራጨ መረጃ ከወታደሮቹ አምስቱ ቲቤት ውስጥ ለመሰማራት ፍቃደኛ ነን ብለዋል። ወደ ሕንድ ድንበር ስለመሄዳቸው ግን የተባለ ነገር የለም። መስከረም 22 አንድ የቻይና ሚዲያ ታይዋን ቪድዮውን ከቻይናና ሕንድ የድንበር ግጭት ጋር በማያያዟ "ውሸታም" ብሏታል። ሕንዳውያን ወታደሮች ከቻይና በተለቀቀ ሙዚቃ ሕንዳውያን ደንሰዋል የተወራው፡ ከቻይና ድምጽ ማጉያ በተለቀቀ ሙዚቃ ሕንዳውያን ወታደሮች ደንሰዋል። እውነታው፡ ቪድዮው የተቀረጸው ድንበር ላይ ድምጽ ማጉያ መኖሩ ከመገለጹ በፊት ነው። መስከረም 16 በሕንድ እና በቻይና ሚዲያ የቻይና ገዢ ፓርቲ ድንበር ላይ ያሉ ሕንዳውያን ወታደሮችን ለማዘናጋት የፑንጃቢ ሙዚቃ ለቋል የሚል መረጃ አውጥተዋል። የቻይና መንግሥት ድምጽ ማጉያ ድንበር አካባቢ መትከሉ ተዘግቧል። ቦታው 24 ሰዓት በሕንድ ወታደሮች የሚጠበቅ ነው። የሕንድና የቻይናም ሚዲያዎች የመከላከያ ምንጮቻቸውን ጠቅሰው መረጃውን ዘግበዋል። የሕንድ መከላከያ መረጃውን አላረጋገጠም። ዘገባው ሲቀርብ ፎቶም ይሁን ቪድዮም አልታየም። ሆኖም ግን የሕንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ወታደሮች በፑንጃቢ ሙዚቃ ሲደንሱ የሚያሳዩ የቆዩ ቪድዮዎች አሰራጭተዋል። ቢቢሲ እነዚህ ቪድዮዎች ድምጽ ማጉያ ከመተከሉ በፊት የተቀረጹ መሆናቸውን ደርሶበታል። አምስት ወታደሮች በፑንጃቢ ሙዚቃ ሲደንሱ የሚያሳይ አንድ ቪድዮ 88,000 ተመልካች አግኝቷል። ቪድዮው በሕንድና ቻይና ድንበር ላድካህ ነው የተቀረጸው ቢባልም እውነታው ግን ምስሉ ከሕንድና ፓኪስታን ድንበር የተገኘ መሆኑ ነው። የቻይና ሙዚቃ የሕንዳውያን ወታደሮችን ጆሮ አሳምሟል። የተባለው፡ ቻይና በትልቅ ድምጽ ማጉያ በምታጫውተው ሙዚቃ ሳቢያ የሕንድ ወታደሮች ጆሯቸውን ታመዋል። እውነታው፡ በተባለው መሣሪያ ድንበር ላይ ሙዚቃ ስለመከፈቱ ማስረጃ የለም። በቻይናዊ የትዊተር ተጠቃሚ የተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ቻይና ከመጠን በላይ የሚጮህ ሙዚቃ ከፍታ አንዳንድ የሕንድ ወታደሮች ጆሯቸውን መታመማቸውን ይጠቁማል። ከ200,000 ጊዜ በላይ ታይቷል። ቪድዮው በሕንድ ሚዲያም ታይቷል። . ቻይና 20 የሕንድ ወታደሮችን ድንበር ላይ ገደለች . 'ዋትስአፕ' በቻይና እክል ገጥሞታል ቪድዮው የተቀረጸው 2016 ላይ ነው። በቻይና የሚሠራ የተንቀሳቃሽ ስልክ ማስጠንቀቂያን ለማስተዋወቅ ነበር የተለቀቀው። በምስሉ 4.6 ቶን የሚመዝን የማስጠንቀቂያ ደውል መስጫ ሲሽከረከር ይታያል። መሣሪያው ተፈጥሯዊ አደጋ ሲከሰት ለሕዝብ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንደተባለው ሙዚቃ ለመልቀቅ የሚውል መሣሪያ አይደለም። የቻይና ወታደሮች ድንበር ላይ መሣሪያውን ስለመጠቀማቸውም እርግጠኛ መረጃ የለም። በተጨማሪም ድንበር አካባቢ ጆሮውን የተጎዳ ሕንዳዊ ስለመኖሩ ሪፖርት አልተደረገም። የመኪና አደጋው የመኪና አደጋው የተባለው፡ የመኪና አደጋ የገጠመው ሕንድ የጸጥታ አባል ጉዳይ ከድንበር ውጥረቱ ጋር ይያያዛል። እውነታው፡ አደጋው የተከሰተው ድንበር አካባቢ አይደለም። የቻይና የትዊተር ተጠቃሚ መስከረም 21 ላይ "ሕንድ ከቻይና ጋር ስምምነት ላይ ልትደርስ አትችልም። ምክንያቱም ወታደሮቿ ራሳቸውን እንዳይገሉ ለመታደግ እየሞከረች ነው" በማለት አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ለጥፎ ነበር። በቪድዮው በከፊል ወንዝ ውስት የሰጠመ የወታደር አውቶብስ በወታደሮች ተከቦ ይታያል። የሕንድ ወታደሮች በድንበር ላድከህ አካባቢ ራሳቸውን ሊያጠፉ እንደሞከሩም ይጠቁማል። ወደ 5,000 ጊዜ ገደማ ታይቷል። ቪድዮው እውነተኛ ቢሆንም የተቀረጸው በቻይና እና በሕንድ ድንበር አይደለም። አደጋው የተከሰተው በማዕከላዊ ሕንድ ነው። በወቅቱ የሕንድ መገናኛ ብዙሀን ዘግበውትም ነበር።
43708828
https://www.bbc.com/amharic/43708828
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የጅግጅጋ ጉብኝት ፋይዳ
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በመጀመሪያው ይፋዊ የሥራ ጉዟቸው ምክትላቸው ደመቀ መኮንን እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳን በማስከተል ወደ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ አቅንተው ነበር።
ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት መፍታት ያስችል ዘንድ ወደ ጅግጅጋ እንዳቀኑ የተነገረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቆይታቸው ከክልሉ ፐሬዚዳንት እና ከማሕበረሰቡ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል። እንደ አዲስ መሪነታቸው በክክልሎቹ መካከል ለተፈጠሩ ግጭቶች መፍትሄ ያመጡ ይሆን ሲል የሕብረተሰቡ አባላት ጥያቄ እንዳቀረቡላቸው ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል "እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ሕገ-መንግሥቱ ላይ የተቀመጡ መብቶቻችን እንዲከበሩልን ዘንድም አንጠይቃለን፤ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ድረስ" በማለት የሕብረተሰቡ አባላት ጥያቄ እንዳነሱም ተዘግቧል። አልፎም ነዋሪዎቹ ገዢውን ፓርቲ ኢህአዴግን የሚመሰርቱ አራቱ ፓርቲዎች ያላቸው የውሳኔ ሰጭነት ኃይል ለሶማሊ ክልልም ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በበኩላቸው በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸው ለማስመለስ ቃል ገብተዋል። "ለሰላምና ለአብሮነት በሚደረጉ ማንኛውም ዓይነት ሥራዎች ውስጥ በቀደምትነት እንደምሳተፍ ፊት ለፊታችሁ ቃል እገባለሁ። ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የሶማሌ ወንድሞቻችን በሰላም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱም የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን።" በማለት አቶ ለማ መገርሳ ገልፀዋል። ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችን አናግሮ የዘገበው ቢቢሲ ሶማልኛ ከሁለቱም ወገን ወደቀያቸው ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎች መኖራቸውን ጠቅሶ ተመሳሳይ ግጭቶች ዳግም እንዳይከሰቱ የሚሰጉ ሰዎች መመለሰ አንሻም እያሉም መሆኑን ጨምሮ ገልጿል። በጅግጅጋ ከተማ 01 ቀበሌ ነዋሪ የነበረው ኬረዲን ከድር በአሁኑ ወቅት በአማራሴ ተፋናቃዮች ጣቢያ ተጠልሎ ይገኛል። በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የጅግጅጋ ጉብኝት የተሰማውን ደስታ የሚገልፀው ኬረዲን "ሰላም ለአንድ ሃገር መሠረት ነው" ይላል። ሆኖም ግን "ያለው ነገር እስኪፈታ ድረስ ለመመለስ ስጋት አለኝ፤ ምክንያቱም በግጭቱ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ሳስብ በጣም አስፈሪ ነው።" በማለት ያለውን ስጋት ገልጿል። ከዚህ በፊት እንደሚታወሰው የሁለቱ ክልሎች በለሥልጣናት ግጭቱን ለመፍታት ቃል ገብተው ነበር። የአሁኑን ውይይት ግን ለየት እንደሚያደርገው የፖለቲካ ተንታኙ ገረሱ ቱፋ ይገልፃል። "በትክክልም ግጭቱ ተፈቷል በተባለ በሰዓታት ልዩነት ዳግም ሲያገረሽ አስተውለናል። ይህ ተፈጥሯዊ ግጭት አይደለም፤ ማለትም በግጦሽ ወይም በመሰል ምክንያቶች የተከሰተ ግጭት አይደለም። ይህ የተቀናበረ ግጭት ነው ብዬ ነው የማምነው። ስለዚህ እንዲፈታ የማይፈልግ ኃይል መኖሩ እሙን ነው" ሲል ገረሱ ያስረዳል። "ምናልባትም ይህን ጉብኝት ልዩ የሚያደርገው የኦሮሚያ አስተዳደሪ የነበረ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆኖ መሄዱ ነው። ሙሉ ሥልጣን አለው ወይ? ሌላ ጥያቄ ሆኖ ሳለ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚያመጡትን ለውጥ ማየት ግን አጓጊ ነው" በማለት ገረሱ ይገልፃል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቀጣይ ወደ አምቦ እንዲሁም መቀሌ በመጓዝ ከነዋሪዎችና እና አስተዳዳሮዎች ጋር ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ እንደያዙ እየተዘገበ ይገኛል።
news-55464176
https://www.bbc.com/amharic/news-55464176
በፈረንጆቹ 2020 ከባድ የአየር ሁኔታ ዓለምን ለኪሳራ ዳርጓታል ተባለ
ክርስቲያን ኤይድ የተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መሰረት ዓለማችን እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ ዓመት በከፋ የአየር ንብረት ለውጥ መመታቷን አስታወቀ።
ድርጅቱ በ2020 የተከሰቱ እና በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ያስከተሉ አስር ጉልህ ክስተቶችን መርጧል። ከእነዚህ መካከል ስድስቱ በእስያ የተከሰቱ ሲሆኑ በቻይናና በሕንድ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከ40 ቢሊዮን ዶላር በላይ ውድመት አስከትሏል ሲል ያትታል። በአሜሪካ የተከሰተው ከባድ አውሎ ንፋስ እና ሰደድ እሳት ደግሞ ወደ 60 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አድርሷል። ዓለም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እግር ተወርች ተይዞ መላወሻ ባጣበት ወቅት የአየር ንብረት ለውጥ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበት ነበር ይላል ሪፖርቱ። ክርስቲያን ኤይድ አስር ከባድ አውሎ ነፋሶችን፣ ሰደድ እሳቶችንና ጎርፎችን በመጥቀስ በአጠቃላይ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ውድመት አስከትለዋል ብሏል። አክሎም ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ 5 ቢሊዮን ዶላር ውድመት አድርሰዋል ሲል ያክላል። በሕንድ ለወራት በዘለቀው እና ከባድ ዝናብ ባስከተለው ከባድ ጎርፍ ከ2000 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ሚሊዮኖች ደግሞ ቀያቸውን ጥለው ተሰድደዋል። የመድን ዋስትና የተገባለት ንብረት ላይ የደረሰው ኪሳራ ብቻ ሲገመትም 10 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ተብሏል። ቻይና በጎርፍ አደጋ ብቻ ከፍተኛ የሆነ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ገጥሟታል። በእርግጥ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰው አደጋ ከሕንድ ጋር ሲነጣጸር አነስተኛ ቢሆንም፣ ከሰኔ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ 32 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራን ያስተናገደችው በጎርፍ የተነሳ ነው። እነዚህ አደጋዎች ቀስ በቀስ ተከስተው ውድመት ያደረሱ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በድንገት ተከስተው ከፍተኛ ጥፋት ያደረሱም ነበሩ። ለዚህ ተጠቃሹ በግንቦት ወር የቤንጋል የባሕር ዳርቻን የመታው ሳይክሎን አምፋን ሲሆን፣ በጥቂት ቀናት ብቻ 13 ቢሊየን ዶላር የተገመተ ንብረት አውድሟል። የአየር ንብረት ለውጥ በትሩን ካሳረፈባቸው አህጉራት መካከል አፍሪካ አንዷ ናት። በአህጉሪቷ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ 8.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሰብልን አውድሟል። የተባበሩት መንግሥታት የበረሃ አንበጣ ወረርሽኙን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ያያዘው ሲሆን፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰቱ ከባድ ዝናቦች ለበረሃ አንበጣው መከሰትና መስፋፋት ምክንያት ሆነዋል ብሏል። አውሮፓም በ2020 ሲያራ የተሰኘ አውሎ ነፋስ ክፉኛ ጎድቷታል። ይህ አውሎነፋስ አየርላንድ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እንዲሁም በርካታ አገራትን ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ አጥቅቷል። ይህ ከባድ አውሎ ነፋስ የ14 ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፍ 2.7 ቢሊዮን ዶላር የተገመተ ንብረት አውድሟል። ክርስቲያን ኤይድ በሪፖርቱ ላይ በገንዘብ ተገምተው የተቀመጡት ቁጥሮች የመድን ዋስትና በተገባላቸው ንብረቶች ላይ የደረሱ ኪሳራዎች ብቻ ዝቅ ተደርጎ ተሰልተው ነው ብሏል። ስለዚህ የጉዳቱ መጠን ከዚህ ከፍ ሊል የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። በሀብት የደረጁ አገራት ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጣ ንብረት ስላላቸው በተፈጥሮ አደጋዎቹም የሚደርስባቸው ጉዳት በዚያው ልክ ከፍ ያለ ይሆናል ሲል አስቀምጦታል። በእንደዚህ ዓይነት የተፈጥሮ አደጋዎች ወቅት የገንዘብ ኪሳራ ብቻ የጉዳቱን መጠን አያሳይም። ለምሳሌ በደቡብ ሱዳን የደረሰው የጎርፍ አደጋ የ138 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን፣ የዚህ ዓመት የምርት ዘመንን ሰብል ሙሉ በሙሉ አውድሞታል። ስለዚህ ኪሳራው በገንዘብ ተሰልቶ የሚቀመጥ አለመሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ የመጣ እና ቀጣይነት ያለውም ነው ብለዋል። ከቀናት በኋላ በሚጀምረው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመትም የአየር ንብረት ተጽዕኖው ይቀጥላል ተብሎ የተገመተ ሲሆን፤ ነገር ግን ከ2020 በተለየ የፖለቲካ መሪዎች የከባቢ አየር ሙቀት መጨመርን ለመዋጋት የተሻለ እርምጃ ይወስዳሉ ተብሎ ተስፋ ተደርጓል። የጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆኖ መመረጥ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት እና አረንጓዴ እጸዋት እንዲያገግሙ ያሳረፈው በጎ ተጽዕኖ እንዲሁም የመብት ተሟጋቾች ውትወታ አገራት የዓለማችንን ሙቀት ለመቀነስ እና ወደ ተሻለ ነገ ለሚደረገው ጉዞ የሚጠቅመውን ይወስናሉ ለሚለው ተስፋን ፈንጥቋል።
51338936
https://www.bbc.com/amharic/51338936
"የተማሪዎቹ ዕገታ እንደ አገር ከገጠሙን ችግሮች አንዱ ነው" ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን
ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግተው የሚገኙ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ዕገታ በአሁኑ ወቅት እንደ አገር ካገጠሙ ችግሮች ውስጥ አንዱ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
ይህንን የተማሪዎች ዕገታ ጉዳይ "በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ የተጨበጠ ውጤት ላይ ለማድረስ መንግሥት ሙሉ ኃይሉን አሰባስቦ እየተረባረበ" መሆኑንም አመልክተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በሰባት ቤት የአገው ፈረሰኞች ማኅበር 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በእንጅባራ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። • የታገቱት 17ቱ ተማሪዎች፡ "ከታገቱት መካከል አንዷ ነበርኩ፤ በሦስተኛ ቀኔ አምልጫለሁ" • የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀንና የመንግሥት ዝምታ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳሉት "መንግሥትን በማመን ከወላጆቻቸው ተነጥለው በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ዕገታ በወቅቱ እንደ አገር ከገጠሙን ፈተናዎች መካከል አንዱ ወቅታዊ ፈተና ነው" ብለዋል። ተማሪዎቹ ከታገቱበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች የተደረጉ መሆኑን የጠቀሱት ም/ጠ/ሚኒስትሩ ተጨባጭ ውጤት ላይ አለመደረሱና የተማሪዎቹ እገታ የወሰደው ረጅም ጊዜ የታጋች ተማሪዎች ቤተሰቦችንና ሕዝቡን ባልተቋጨ ጭንቀትና ባልተፈታ ሐዘን ውስጥ እንዲቆዩ አስገድዷቸዋል ብለዋል። ጨምረውም ችግሩ ውስብስብ መሆኑን አመልክተው በቅርቡ ከታጋች ቤተሰቦች ጋር ፊት ለፊት በተደረገ ውይይት በተለያዩ ወገኖች ያልተጣሩና ተለዋዋጭ መረጃዎች መሰራጨታቸው የታጋች ቤተሰቦችን ስጋትና ጭንቀት እጅግ መራር እንዳደረገው ለመረዳት እንደተቻለ ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተማሪዎቹና በወላጆቻቸው ላይ ባጋጠመው አሳዛኝ ክስተት እንደወላጅ "ከልባችን አዝነናል" ሲሉ ስሜታቸውን ገልጸዋል። ክስተቱም መንግሥት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅና ችግር ሲያጋጥምም ፈጥኖ የመፍታት አቅሙን ማጠናከር እንዲሁም ድክመቶችን ማረም እንዳለበት በእጅጉ የሚያስገነዝብ ሁኔታ መሆኑን ተናግረዋል። • ስለታገቱት ተማሪዎች መንግሥት ዝምታውን የሰበረበት መግለጫ • ተለቀዋል የተባሉት ታጋቾች የት ናቸው? ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ዕገታው ያጋጠመበት አካባቢ "የሰላምና የጸጥታ ችግር የሚስተዋልበት በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችም በተደጋጋሚ የችግሩ ሰለባ ሆነው ቆይተዋል" ሲሉ ድርጊቱ ቀደም ሲልም የነበረ መሆኑን አመልከተዋል። በተጨማሪም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ እንደተናገሩት በዩኒቨርስቲዎች የተረጋጋ ድባብ እንዳይሰፍን ፍላጎት ባላቸው አካላት ከዚህ በከፋ ደረጃ ጉዳት እንዳይደርስና አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ "በየደረጃው የምንገኝ አካላት በተግባር የመፍትሄው አካል ሆኖ መገኘት የሚጠይቀን ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን" ብለዋል። ከሰሞኑ ስለታገቱ ተማሪዎች ለመጠየቅ በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የተካሄዱትን ሰልፎችን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ሰልፎቹ በሰላማዊ ሁኔታ መካሄዳቸው የሚያስመሰግን ነው" ሲሉ ምስጋና አቅርበዋል። በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት አካላትን በተመለከተም "ስህተትን ላለመድገም በማረም፤ እንዲሁም ተጨባጭ ሁኔታ ያለፈቀደውን በግልጽ በማሳወቅ ሁሉም የመፍትሄ አካል መሆን ኃላፊነትም ግዴታችንም ነው" ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን።
news-53176032
https://www.bbc.com/amharic/news-53176032
ከእንቅስቃሴ ገደቡ ጋር ተያይዞ በኤርትራ የመሰረታዊ ሸቀጦች እጥረት አጋጠመ
በኤርትራ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በተወሰዱ እርምጃዎች ምክንያት የመሰረታዊ ሸቀጦች እጥረት ማጋጠሙን፣ ገበያ ላይ ባሉት ሸቀጦችም ላይ የዋጋ ንረት በመታየቱ ለከፋ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገለጹ።
አሥመራ የዛሬ ሁለት ዓመት በኤርትራ ቆላማ አካባቢዎች በተለይ በጋሽ ባርካ አካባቢ ሁኔታው የባሰ እንደሆነና በተለይም ሃይኮታ በሚባሉ የገጠር አካባቢዎች ህጻናት ለረሃብ እየተጋለጡ እንደሆነ የቢቢሲ ምንጮች ተናግረዋል። የሸቀጦች እጥረቱ ያጋጠመው በአብዛኛው የኤርትራ ከተሞች እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በአንድ ሺህ ናቅፋ ሲሸጥ የነበረው 'የማሽላ ወዲ ዓከር' ጥሬ በአሁኑ ወቅት ሁለት ሺህ ናቅፋ እየተሸጠ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል። በተጨማሪም በአገሪቱ ያለው የውሃ እጥረት አሳሳቢ እንደሆነ ሲገለጽ ቆይቷል፤ ይህንን እጥረት ለማቃለልም ከዚህ በፊት በውሃ ጫኝ መኪኖች ውሃ ይታደል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በወረርሽኙ ምክንያት ባጋጠመ የነዳጅ እጥረት ሳቢያ መኪኖቹ አገልግሎታቸውን እንደቀነሱ ተነግሯል። የኤርትራ መንግሥት ወረርሽኙን በተመለከተ ቀደም ብሎ በሰጠው መግለጫ "ድንበሮችን እና ቤታችንን ዘግተን ከመከላከሉ ውጪ አማራጭ የለንም" ማለቱ ይታወሳል። ስለሆነም ዜጎች ምግብ ለመግዛትና ለአስገዳጅ ነገሮች ካልሆነ በስተቀር ከቤታቸው እንዳይወጡ ሰለተነገረ ቤቶቻቸውን ዘግተው እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገልጸዋል። 'ሕድሪ' ከሚባሉት በመንግሥት ድጎማ ሸቀጦችን ከሚያከፋፍሉ ሱቆች እንደ ማሽላ፣ ዘይት፣ የሻይ ቅጠል እና ስኳርን የመሳሰሉ ሸቀጦችን ሲገዙ የነበሩ የአሥመራ ከተማ ነዋሪዎች እጥረት በማጋጠሙ ለችግር እንደተጋለጡ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዜጎች በቅርበት ምግብና ሌሎች ሸቀጦች ያስገቡባቸው የነበሩት የሱዳን እና የኢትዮጵያ ድንበሮችም ዝግ በመሆናቸው ችግሩ እንደተባባሰ ተጠቅሷል። ስማቸውን ሳይጠቅሱ ለቢቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ ነዋሪዎች እንዳሉት መንግሥት ለወረርሽኙ መከላከያ ከአገር ውስጥና ከውጭ ገንዘብ እያሰባሰበ በመሆኑ እርዳታ ያደርግልን ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። ከውጭ አገራት ገንዘብ የተላከላቸው ቤተሰቦች ከሃዋላ ድርጅቶች ተደውሎ "ገንዘባችሁ መጥቷል እንቅስቃሴ ሲፈቀድ መውሰድ ትችላላችሁ" መባላቸውን ገልጸው፤ የእንቅስቃሴ ገደቡ ዕለታዊ ፍላጎቶቻቸው ለማሟላት አዳጋች እንዳደረገው ይገልጻሉ። አንዳንድ የአካባቢ አስተዳደሮች በወረርሽኙ ምክንያት በጥብቅ የተጎዱትን ለመደገፍ የሚውል እህል ከአርሶ አደሮች እየሰበሰቡ እንደሆነም ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ኤርትራ በኮሮናቫይረስ ስጋት ድንበሮቿን ዘግታ ዜጎቹም በየቤታቸው እንዲቀመጡ ካደረገች ሦስት ወር ተቆጥሯል። በአገሪቱ ያለው የበሽታ መስፋፋትም እጅግ ዝቅተኛ ከሙባለው ደረጃ ላይ እንደሆነ ይፋዊ መረጃዎች ያመለክታሉ።
news-49712381
https://www.bbc.com/amharic/news-49712381
በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም፡ ግብጽ
ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታንና የውሃ መሙላት ሂደትን በተመለከተ ለአራት ዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ውይይት ምንም ውጤት እንዳላመጣ የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚህ ሹህሪ ተናገሩ።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካይሮ ውስጥ ከኬኒያዋ አቻቸው ሞኒካ ጁማ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው ይህንን የተናገሩት። ሳሚህ ሹህሪ እንዳሉት ሃገራቸው ከአባይ የምታገኘውን የውሃ ድርሻን በከፍተኛ ደረጃ እስካልቀነሰው ድረስ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ያላትን መብት ግብጽ እውቅና እንደምትሰጥ ገልጸዋል። • ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? • ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ? ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባው ግዙፍ ግድብ 6 ሺህ ሜጋዋት የሚደርስ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ እንደተጀመረ ይታወሳል። ግብጽም ከወንዙ የማገኘውን የውሃ መጠን ይቀንስብኛል በሚል የግድቡን ግንባታ በቅርብ ስትከታተል ቆይታለች። ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን መገንባት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ሱዳንና ግብጽ የሚሳተፉበት የሦስትዮሽ ውይይት በግድቡ ዙሪያ ሲካሄድ ቆይቷል። ባሳለፍነው ቅዳሜ ደግሞ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ በአባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባት የጀመረችው ሃገራቸው እ.አ.አ. በ2011 የገባችበትን ቀውስ ተከትሎ መሆኑን 'አህራም ኦንላየን' ከተባለው የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። ''ግብጽ በዛ ወቅት አለመረጋጋት ውስጥ ባትሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ መገንባት አትጀምርም ነበር'' ብለዋል። ''ከ2011 ግርግር ግብጻውያን ብዙ መማር ያለባቸው ነገሮች አሉ። ይህንን ትልቅ ሃገራዊ ስህተት ልንደግመው አይገባም'' ሲሉም ተደምጠዋል። የኢትዮጵያ ህዳሴ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በግብጽ የተከሰተውን ህዝባዊ አብዮት ተከትላ ግድቡን መገንባት ለአመጀመሯን ይናገራሉ። ኢንጅነር ክፍሌ እንደሚሉት ምንም እንኳ ይፋዊ የግድብ ግንባታው መጀመር ምርቃት የተደረገው እአአ 2011 ላይ ቢሆንም ግንባታው የተጀመረው የፈረንጆቹ 2010 ዓመት መጨረሻ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በተያያዘ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የግብጽ፣ የሱዳንና የኢትዮጵያ የውሃ ሚኒስትሮች የሚያድርጉት ውይይት ትናንት በካይሮ እንደተጀመረ አስታውቋል። ውይይቱ ባለፈው ዓመት መስከረም ላይ በአዲስ አበባ ተካሂዶ ከነበረው ስብሰባ የቀጠለ እንደሆነ ታውቋል። የውሃ፣ መስኖና ሃይል ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን መገንባት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በጥሩ መንፈስና እና በመተባበር ላይ መሰረት ያደረገ ስራ ስታከናውን እንደቆየች ገልጸዋል። በሶስቱ ሃገራት መካከል በጉዳዩ ላይ የሚደረሰው መግባባት የሁሉም ሀገራትን ጥቅም ለማስከበር ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል። • ''የሚፈርስ የግድቡ አካል የለም'' የግድቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ የካይሮው ውይይት ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገው ሀገራቱ በቀሪ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በባለሙያዎች የቀረበለትን ሪፖርት እና ምክረ-ሃሳቦች መርምሮ የወደፊት መመሪያዎችን ለማበጀት መሆኑ ተጠቁሟል። ሀገራቸውን ወክለው በውይይቱ የተገኙት የግብጹ የውሃ ሚኒስትር ዶክተር ሞሐመድ አብድል አቲ ደግሞ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየታየ ያለው የትብብር መንፈስ ለሌሎች ሀገራትም አርአያ ይሆናል ብለዋል። በግድቡ አሞላል እና የውሃ አለቃቀቅ ላይ የሚደረጉ ውይይቶች የሶስቱንም ሃገራት ጥቅም መሰረት ያደረጉ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል። የሱዳኑ የውሃ እና መስኖ ሚኒሰትር ፕሮፌሰር ያሲር ሞሐመድ አባስ ሃገራቱ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የጀመሩት ትብብር ስኬታማ ስራዎች የተከናወኑበት ስለመሆኑ ተናግረዋል።
55792460
https://www.bbc.com/amharic/55792460
በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ቻይና አሜሪካንን በልጣ ከዓለም 1ኛ ሆነች
ቻይና በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI) ለመጀመርያ ጊዜ አሜሪካንን በመብለጥ የምድራችን ቁጥር አንድ አገር ለመሆን በቃች።
ትናንት እሑድ ይፋ በተደረገ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት መሠረት ቻይና አዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተው በአጭር የጊዜ ሂደት አሜሪካንን ለመብለጥ ችላለች። ይህ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው መረጃ እንደሚያትተው ወደ ቻይና ድርጅቶች አዳዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ4 ከመቶ ተመንድጓል። በሌላ አነጋገር በፈረንጆቹ 2020 ወደ ቻይና የተመሙ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ወደ አሜሪካ ከተመሙት አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች በእጅጉ ያላቁ ናቸው። ይህ የሚያሳየው ቻይና በዓለም ዙርያ ያላት ተጽእኖ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነው ብሏል ሪፖርቱ። ከውጭ አገራት ወደ አሜሪካ የሚገቡ አዳዲስ የቀጥታ ኢንቨስትመንቶች ባለፈው ዓመት (2020) በግማሽ መቀነሳቸውን ዘገባው አትቷል። ሆኖም ወደ ቻይና የሚተሙ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንቶች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው የመጡት። በዚህም ምክንያት ነው ቻይና ከአሜሪካ ልቃ እንድትገኝ ያስቻላት። ቻይና ባለፈው ዓመት ብቻ 163 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገሯ አዲስ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈሶላታል። አሜሪካ ግን 134 ቢሊዮን ብቻ ነው ወደ አገሯ የቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ የቻለችው። ይህን አሐዛዊ ዘገባ ያወጣው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በንግድና በልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) ላይ ነው። በ እአአ 2019 አሜሪካ የ251 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ ችላ ነበር። በዚህ ጊዜ ቻይና የ140 ቢሊዮን የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ነበር ማግኘት የቻለችው። ምንም እንኳ ቻይና በተገባደደው የፈረንጆች ዓመት አዲስ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ አሜሪካንን ቀድማ አንደኛ ብትሆንም በጠቅላላ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት ግን አሁንም ዓለምን የምትመራው አሜሪካ ናት። ይህም የሚያሳየው ለዓመታት አሜሪካ የአዳዲስ የውጭ ኢንቨስትመንቶች መዳረሻ ተመራጭ አገር እንደነበረችና የውጭ ኢንቨስትምነት ምን ያህል የተከማቸባት አገር መሆኗን ነው ይላል ሪፖርቱ። የምጣኔ ሀብት አዋቂዎች ግን በአዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የታየው የአሰላለፍ ልዩነት አሁን ቻይና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ወሳኝ የሆነ ተጽእኖ ማሳረፍ መጀመሯን አመላካች ነው ይላሉ። በአሜሪካ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ2016 የትራምፕን መምጣት ተከትሎ ነበር ወደ 472 ቢሊዮን ዶላር የተመነደገው። ያን ጊዜ ቻይና 134 ቢሊዮን ዶላር ላይ ነበረች። ያን ጊዜ የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ኩባንያዎች ቶሎ ቻይናን እየለቀቁ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ከፍተኛ ማበረታቻ እየሰጠ ነበር። በተመሳሳይ የትራምፕ አስተዳደር የቻይና ኩባንያዎች ለደኅንነት ስጋት ስለሚሆኑ በየጊዜው ይመረመራሉ በሚል በአሜሪካ የነበራቸው ሚና ለማንኳሰስ ሞክሯል። ይህ የትራምፕ አስተዳደር በዚህ መንገድ ተጽእኖ ለመፍጠር በመቻሉ ሊሆን ይችላል ባለፉት ዓመታት የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የበላይነት በአሜሪካ ተይዞ የቆየው። ሆኖም ባለፈው ዓመት (2020) የአሜሪካ ኢኮኖሚ በኮቪድ ወረርሸኝ የተነሳ ሲቀዛቀዝ የቻይና ኢኮኖሚ ግን ቶሎ ማንሰራራት ችሏል። በ2020 የቻይና የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት መጠን (GDP) በ2.3% ማደጉን መረጃዎች ይጠቁማሉ።. ይህም ቻይናን በኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የኢኮኖሚ ድቀት ብዙም ያልተሰማት ብቸኛዋ የዓለም አገር አድርጓታል። ብዙ ኢኮኖሚስቶች በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የቻይና ኢኮኖሚ በፍጥነት ማንሰራራቱ አስገርሟቸዋል። በ2020 በዓለም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በጠቅላላው በ42% ወድቋል። ብዙውን ጊዜ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የሚባለው አንድ የውጭ ኩባንያ በሌላ አገር ውስጥ ያሉ ኩባንያዎችን በመግዛት ወይም ከራሱ ኩባንያ ጋር እንዲጣመሩ በማድረግ ወይም በአዲስ ኩባንያ አዲስ ሥራ ለመጀመር መዋእለ ነዋዩን ማፍሰስ ሲጀምር ነው።