id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-50052017
https://www.bbc.com/amharic/news-50052017
ተመራማሪዎች ለአንድ ታካሚ ብቻ መድሃኒት ሠሩ
የ8 አመቷ ጨቅላ ገዳይ የሆነ የጭንቅላት በሽታ ተጠቂ ነች፤ ይህን ያዩ ሐኪሞች ለእርሷ ብቻ የሚሆን መድኃኒት ሠሩ።
ሚላ ማኮቬች፤ የያዛት የጭንቅላት በሽታ እጅግ ክፉኛ ያሰቃያት ነበር። ይህን ያስተዋሉት የቦስተን ሕፃናት ሆስፒታል ተመራማሪዎች ለሚላ ብቻ የሚሆን መድኃኒት ለመሥራት ደፋ ቀና ይሉ ጀመር። ተመራማሪዎቹ የሠሩት መድኃኒት የሚላ ዘረ-መል ውስጥ ገብቶ የጤና እክሏን እንዲፈታ የተዘጋጀ ነው። • የአምስት ቤተሰብ አባላትን ሕይወት የቀጠፈው የመሬት ናዳ አሁን ሚላ ምንም እንኳ ከበሽታዋ ሙሉ በሙሉ ባታገግምም ከእንደ በፊቱ ዓይነት ስቃይ ተገላግላለች። 'ባተን' በእንግሊዝኛው 'የባተን በሽታ' ይባላል። ከሚሊዮን አንዴ የሚከሰት ነው፤ ከጊዜ ጊዜ አደጋው እየከፋ የሚመጣ በሽታ። ሚላ ገና የሶስት ዓመት ሕፃን ነበረች። ቀኝ እግሯ ወደ ውስጥ መታጠፍ ጀመረ። ከአንድ ዓመት በኋላ በቅርቧ ያለ ነገር ካልሆነ ማየት የማትችል ሆነች። አምስት ዓመት ሲሆናት ድንገት መውደቅ ጀመረች። አረማመዷም ያልተለመደ ዓይነት ሆነ። ሚላ ስድስት ስትደፍን የዓይን ብርሃኗን አጣች፤ መናገርም ይሳናት ያዘ። ድንገተኛ የጭንቅላት እንፍርፍሪትም [ሲዠር] በተደጋጋሚ ያጋጥማት ጀመር። ሚላን የያዛት በሽታ እየፀና ሲመጣ ጭንቅላቷ ውስጥ ያሉ ሕዋሳትን [ሴሎች] የመግደል አቅም አለው። • ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም" • ዕድሜያችን የማቱሳላን ሲሶ እንኳ መሄድ የተሳነው ለምን ይሆን? የሚላ ቤተሰቦች በሽታው በዘር የሚተላለፍ መሆኑን አላጣቱም። ኃኪሞቹም የሚላን የዘር-ቅንጣት በመውሰድ ምርምራቸውን ያጣድፉት ያዙ። ይሄኔ ነው እክሉ ምን እንደሆነ በውል የተገለጠላቸው። ሊታከም እንደሚችልም ፍንጭ አገኙ። ከዚያም ያዘጋጁትን መድኃኒት በሚላ ሕዋሳት ላይ ሞከሩት። አልፎም ቤተ-ሙከራ ውስጥ ባሉ እንስሳት ውጤቱን ካረጋገጡ በኋላ ከአሜሪካ ምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር ፈቃድ አገኙ። ሚላሰን የተሰኘ ስም የተሰጠው መድኃኒት በይፋ ለሚላ እንዲሰጣት ተደረገ። ይህ የሆነው በፈረንጆቹ 2018 የመጀመሪያ ወር ላይ ነበር። መሰል መድኃኒቶችን ቤተ-ሙከራ ውስጥ አብላልቶ ለተጠቃሚ ማድረስ ቢያንስ 15 ዓመታት ይፈጃል። የሚላን በሽታ ለማከም ቆርጠው የተነሱት ተመራመሪዎች ግን በአንድ ዓመት ተኩል ነው መድኃኒቱን መፈብረክ የቻሉት። ውጤቱስ? መድኃኒቱ ሚላ የደረሰባትን ሁሉ ሽሮ እንደ አዲስ የሚያስተካክላት አይደለም። ከተመራማሪዎቹ አንዱ የሆኑት ዶክተር ዩ የመጀመሪያው ዓመት ጥቂት ለውጦች ብቻ የሚታዩበት ነው ይላሉ። ከመድኃኒቱ በፊት ሚላ ቢያንስ በቀን ከ15-30 ጊዜ 'ሲዠር' [የጭንቅላት እንፍርፍሪት] ያጋጥማት ነበር። እንፍርፍሪቱ ለሁለት ደቂቃዎች ይቆይ ነበር። አሁን ግን ይህ እክል እየቀለላት ነው። አልፎም ቀጥ ብላ መቆም እና ምግብ በሥርዓቱ መመገብ መጀመሯን ቤተሰቦቿ ይናገራሉ። በሽታው መድኃኒቱን እንዳይላመድ ሐኪሞች በየጊዜው ክትትል ያደርጉላታል። መድኃኒቱ የሚላ አከርካሪ አጥንት ፈሳሽ ላይ እንዲወጋ ነው የተደረገው የዋጋው ነገርስ? ይህ ለሚላ ብቻ ተብሎ የተዘጋጀው መድኃኒት ሌሎች ቢሹት ሊገዙት ይችላሉ ወይ? የብዙዎች ጥያቄ ነው። ተመራማሪዎቹ መድኃኒቱን ለመፍበረክ ምን ያህል ገንዘብ እንዳወጡ ይፋ አላደረጉም። ነገር ግን ዶ/ር ዩ አዋጭ ባይሆን ኖሮ እናቋርጠው ነበር ሲሉ ተስፋ ያለው ምላሽ ይሰጣሉ።
44598630
https://www.bbc.com/amharic/44598630
ተዋናይቷ በ54 ዓመቷ ሴት ልጅ ተገላገለች
በሪጌት ኒልሰን ትባላለች። ዴንማርካዊት ስትሆን ዕውቅ ተዋናይት ናት። አምስተኛ ልጇን በ54 ዓመቷ ከሰሞኑ ተገላግላለች። አራቱ ልጆቿ ሁሉም ወንዶች ነበሩ።
ጣሊያናዊው ባለቤቷ የ39 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ባለቤቱ በ54 ዓመቷ ልጅ ስለወለደችለት "ደስታዬ ወሰን የለውም" ሲል ተናግሯል። ብሪጌት ኒልሰን ብዙ ሰው የሚያውቃት "Rocky IV" እና "Cobra" በተሰኙት በተለይም ከሁለተኛ ባሏ ሲልቨስተር ስታሎን ጋር መሪ ተዋናይት ሆና በተወነችባቸው ፊልሞች ነበር። ኒልሰን በፊልም ብቻም ሳይሆን በሞዴሊንግና በቴሌቪዥን ትዕይንቶች ዓለም አቀፍ ዝናን ተቀዳጅታለች። ሁለቱ ጥንዶች ለፒፕል መጽሔት እንደተናገሩት አዲስ ልጅ በማግኘታቸው ደስታቸው ወሰን አጥቷል። ኒልሰን የ39 ዓመቱን ዴሲን ያገባችው በ2006 ሲሆን አምስተኛ ባሏ ነው። ቀደም ያሉት አራት ልጆቿ ከ23 እስከ 34 ዕድሜ ያላቸው ሲሆን ሁሉም ወንዶች ነበሩ። ኒልሰን ነፍሰ ጡር ስለመሆኗ በማኀበራዊ መገናኛ ብዙኃን ስትገልጽ ሰፊ መነጋገሪያ ለመሆን ችላ ነበር። በ2008 የአደንዛዥ ዕጽ ሱሰኞች ማገገሚያ ውስጥ ገብታ እንደነበር ይታወሳል። በዚህም ብሪጌት ኒልሰን ዕድሜያቸው ከገፉ በኋላ የወለዱ ዕውቅ ሰዎችን ቡድን ተቀላቅላለች። ጃኔት ጃክሰን ባለፈው ዓመት በ50 ዓመቷ ልጅ ያገኘች ሲሆን ሬችል ዊዝ በተመሳሳይ በ48 ዓመቷ ልጅ እየጠበቀች ነው።
news-44720967
https://www.bbc.com/amharic/news-44720967
ጠ/ሚ ዐብይ አልበሽርን የድንበር ግጭቱን አብረን እንፍታ አሉ
በመተማ አካባቢ የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለኦማር አልበሽር መልዕክት እንደላኩ የኃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ከሱዳኑ ፕሬዚዳንትና ከሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልዳርዲሪ መሀመድ ጋር በነበረ ውይይት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) መልዕክቱን አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር በድንበር ላይ የተከሰተውን ግጭትም ሁለቱም ኃገራት በጋራ መፍታት አለብን የሚል መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በቀጠናው ስላለው የፀጥታ ጉዳዮችም እንደተወያዩ ተዘግቧል። ከሰባት መቶ ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያለውና በቅጡ ያልተሰመረውን የኢትዮጵያ እና የሱዳን ድንበር ታክከው የሚኖሩ የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ አርሶ አደሮች ለውጥረት ባይታዋር ያለመሆናቸውን ይገልፃሉ። ከትናንት በስቲያ ማለዳ ድንበር ተሻግረው በዘለቁ የሱዳን ወታደሮች ተፈፅሟል የሚሉት ጥቃት የውጥረቱ መገንፈል መገለጫ ነውም ይላሉ። የመሬት ይገባኛል ጥያቄ በድንበሩ አቅራቢያ ለሚፈጠሩ ግጭቶች እርሿቸው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ መሆኑ ሲዘገብ የቆየ ሲሆን ፤ አሁንም የጥቃቱ መንስዔ ከዚሁ እንደማይዘል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘላለም ልጃለም ለክልሉ የብዙኃን መገናኛ በሰጡት ቃል ገልፀዋል። ጥቃቱ ተፈፅሞበታል በተባለው ደለሎ አራት አካባቢ ማሣ እንደነበራቸው የነገሩን የአካባቢው ኗሪ፤ ቦታውን ሱዳን ይገባኛል እንደምትል ያስረዳሉ። "አሁን ቁጥር አራት የሚጣሉበት የኢትዮጵያ መሬት ነው። የእኔ የእርሻ መሬት ነበር" የሚሉት ነዋሪው ታፍነው የተወሰዱ እንዲሁም አራት ሰዎች እንደሞቱም እንደሰሙም ተናግረዋል። ሰባት ሰዎች እንደቆሰሉ የሚገልፁት እኚሁ የአይን እማኝ ሁለቱ የመከላከያ ኃይል አባላት ናቸው ብለዋል። የክልሉ ዋና አፈ ቀላጤ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከብሄራዊው የቴሌቭዥን ጣብያ ጋር ባደረጉት ውይይት የሱዳንን ታጣቂዎች የሰርክ የእርሻ ስራቸውን በሚያከናውኑ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን አረጋግጠው ፤ታጣቂዎቹ "መሬቱ የእኛ ነው" የሚል ተገቢ ያለሆነ ጥቃት አንስተዋል ብለዋል። አቶ ንጉሡ በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያዊን ሁለት መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል። ከመተማ አርባ ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ግንደ ውሃ ከተማ ቁስለኞችን ህክምና እንዲያገኙ በማስተባበር ላይ መጠመዱን የገለፀልን ሌላ የአካባቢው ኗሪ በዙሪያው ባሉ ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች ድጋፍ ለማድረግ ወደስፍራው ማቅናት መጀመራቸውን ይናገራል፤ ከዚህም ተጨማሪ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ስፍራው ማቅናቱን ሰምቻለሁ ይላል። "ግጭቱ ተባብሶ ነው ያለው። ትናንትና የኃገር መከላከያ ሰራዊት ከሰዓት በኋላ ከአዘዞ ተነስቶ ገብቷል" ይላሉ። በአካባቢው ሌላኛው ነዋሪ ግጭቱ ቀዝቀዝ እንዳለ ገልፆ የሟቾች ቀብርም ገንዳ ውሀ በሚባለው አካባቢም እየተከናወነ መሆኑን ይናገራል። ሁለት ሟቾችም ደለሎ የሚባለው አካባቢ የተቀበሩ ሲሆን ሌላኛው ሟች ወደ ትውልድ ቦታው እንደተመለሰ እኚሁ ነዋሪ ገልፀዋል። የሱዳን አርሶ አደሮችና የፀጥታ ኃይል እንደተገደሉ የዘገበው ሱዳን ትሪቢውን "እንዲህ አይነት ግጭቶች በየዓመቱ በክረምት ወቅት የሚከሰቱና የተጋነኑ ሊሆኑ እንደማይገባቸው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አልዳርዲሪ መሀመድን ጠቅሶ ዘግቧል።
news-50045019
https://www.bbc.com/amharic/news-50045019
"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ
ከሰሞኑ በህዳሴ ግድቡ ሊገጠሙ ከታቀዱት አስራ ስድስት ተርባይኖች መካከል ሶስቱ እንዲቀነሱ ምክረ ኃሳብ መቅረቡን የሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሃሮ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
የተርባይኖች መጠን መቀነሱ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጉዳዮች ምላሽ የሰጡት ኢንጅነሩ፤ አንድ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ትልቅነት የሚለካው ጄነሬተሮች ወይም ተርባይኖችን በመደርደር አይደለም ይላሉ። አክለውም ብዙ ተርባይኖችን መደርደር ሁልጊዜም አዋጭ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። • ግብጽ በአባይ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች • ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን? • ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ ኢንጅነሩ እንደሚሉት ከሆነ ለአንድ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ቁልፍ ከሆኑት ነገሮች መካከል የመጀመሪያው ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠንና ውሃው ከምን ያክል ከፍታ ተወርውሮ ተርባይኑን ይመታል የሚሉት ናቸው። ዋና ሥራ አስኪያጁ ከዝናብ መጠን ጋር ተያይዞ በየዓመቱ ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን እና የውሃው የከፍታ መጠን ሊለያይ እንደሚችል በማስገንዘብ፤ የህዳሴ ግድቡ ያመነጫል ተብሎ የተሰላው በዓመት በአማካይ 15760 ጊጋ ዋት (Gigawatt hours) ወይም አንድ ሚሊዮን ኪሎ ዋት ሃዎር እንደሆነ ይናገራሉ። "በዚህ የኢነርጂ (ኃይል) መጠን ላይ የተለወጠ ነገር የለም" የሚሉት ኢንጂነሩ፤ "አሁን ይህን ኢነርጂ (ኃይል) ለተጠቃሚው እንዴት ላድርስ? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ጄነሬተሮች ይመጣሉ'' ይላሉ። ጄነሬተሮች መካኒካል ኢነርጂን ወደ ኤሌክትሪካል ኢነርጂ እንደሚቀይሩ የሚያስረዱት ኢንጂነር ክፍሌ፤ "ጄነሬተር ወይም ተርባይን መደርደር በሚመነጨው የኢነርጂ (የኃይል) መጠን ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" በማለት ያስረዳሉ። የተርባይን እና ጄነሬተር ቁጥር የሚወሰነው፤ ግድቡ በሚይዘው የውሃ መጠን፣ ውሃው ከምን ያክል ከፍታ ላይ በምን ያክል ፍጥነት ተርባይኑን ይመታል፣ የኃይል ፍላጎት፣ ኢኮኖሚያዊ አዋጭነቱ እና የመሳሰሉት ላይ ነው ይላሉ። "10፣ 12፣ 20 ጄነሬተሮች ቢደረደሩ ተመሳሳይ የሆነ ኢነርጂ (ኃይል) ነው ማመንጨት የምንችለው" በማለትም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። "ተርባይን ተቀነሰ ብሎ ማውራቱ ትርጉም የለውም። ለአንድ የኃይድሮ ኃይል ማመንጫ ወሳኙ ኢነርጂ (ኃይል) ነው" የሚሉት ኢንጂነር ክፍሌ፤ ጥቅም ላይ ይውላሉ ከተባሉት ከ16ቱ ተርባይኖች መካከል ሶስቱን ለመቀነስ የታሰበው ከዋጋና አዋጭነት አንፃር እንደሆነ ያስረዳሉ። ኢንጂነር ክፍሌ ይህ ውሳኔ በምንም አይነት መልኩ ከግብጽ ፍላጎት ጋር የተገናኘ አይደለም ያሉ ሲሆን፤ ይህ ውሳኔ ኢኮኖሚያዊ እና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ ብቻ ያስገባ እንደሆነ ያስረዳሉ። "እንዳውም ብዙ ጀነሬተር ብንደርድር ብዙ ውሃ እንለቃለን ማለት ነው። ይህ ደግሞ የእነሱ ፍላጎት ነው" ብለዋል። • የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? • "ለእናንተ ደህንነት ነው በሚል እንዳሰሩን ተገልፆልናል" የባላደራ ምክር ቤት አስተባባሪ ዋና ሥራ አስኪያጁ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ 68.58 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል። "ይህ የሲቪል፣ የኤሌክትሮ መካኒካል፣ የኃይድሮሊክስ ስትራክቸርን ጨምሮ ነው" ሲሉም ይናገራሉ። "በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2013 ዓ.ም. ላይ ኃይል ማመንጨት እና 2015 ደግሞ ፕሮጀክቱን ማጠናቀቀ የተያዘ እቅድ ነው" ብለዋል። የህዳሴ ግድብ ግንባታ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ልዩነቶችን መፈጠሩ ይታወሳል። ከቀናት በፊት የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚህ ሹኩሪ ለግብጽ የህዝብ እንደራሴዎች ባሰሙት ንግግር ግብጽ ከአባይ ወንዝ የምታገኘው ጥቅም እና መብት አስከብራ ለማስቀጠል ቁርጠኝነቱ እንዳላት አጽንዖት ሰጥተው ተናግረው ነበር። የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ ያደረጉት የሦስትዮሽ ምክክር አለመሳካቱን ተከትሎ ግብፅ ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል። የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ አሜሪካ አደራዳሪ እንድትሆን ፍላጎታቸውን ቢያሳዩም፤ ኢትዮጵያ ግን የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት፤ በሦስቱ አገራት መካከል የተደረሱ አበረታች ስምምነቶችን የሚያፈርስ ከመሆኑ በተጨማሪ ሦስቱ አገራት በመጋቢት 2017 የፈረሟቸውን የመግለጫ ስምምነቶችም ይጥሳል በማለት የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል ገልጻለች። የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ጋር በሩሲያ ተገናኘተው በጉዳዩ ላይ ለመምከር መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን በሩሲያ መቼ እንደሚያገኙ ግልጽ ባያደርጉም ሩሲያ ጥቅምት 12 እና 13 ሩሲያ-አፍሪካ መድረክ ታዘጋጃለች።
55914754
https://www.bbc.com/amharic/55914754
ሩሲያ ሠራሹ 'ሰፑትኒክ' ክትባት 92% ፈዋሽነቱ ተረጋገጠ
ሩሲያ ሠራሹ 'ስፑትኒክ' ተብሎ የሚጠራው የኮሮናቫይረስ ክትባት ፈዋሽነቱ በ92% በመቶ አስተማማኝ እንደሆነ ተረጋገጠ።
ይህ የተረጋገጠው ክትባቱን በ3ኛ ምዕራፍ ሰፊ ጥናት የተሳተፉ ሰዎችን ሁኔታ በማየት በታተመ ሳይንሳዊ ትንታኔ ነው። የዚህ የሦስተኛ ምዕራፍ ውጤት በታዋቂው ላንሴት የጤና ጆርናል ላይ ታትሞ ወጥቷል። ክትባቱ በበርካታ ሰዎች ላይ ከተሞከረ በኋላ ክትባቱ የተሰጣቸው ሰዎች ከተለመዱት መለስተኛ የህመም ምልክቶች ሌላ ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላመጣባቸው ተስተውሏል። ስፑትኒክ ክትባት ጤንነትን የማይጎዳና ለተህዋሲው አስተማማኝ መከላከልን የሚሰጥ እንደሆነ ተረጋግጦለታል። ይህ ክትባት ከሌሎች ክትባቶች በተለየ ቀደም ብሎ በሩሲያ መሰጠት መጀመሩን ተከትሎ በቂ ጥናትና ምርምር ሳይደረግበት ነው ለሕዝብ የታደለው በሚል ጭቅጭቅ አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል። ብዙ የምዕራብ አገራትም ለሩሲያ ሠራሹ ክትባት ዕውቅና ነፍገውት ቆይተዋል። አሁን ግን ሳይንቲስቶቹ አስተማማኝነቱን አረጋግጠናል ብለዋል። ይህን ተከትሎም ሩሲያ ሠራሹ ስፑትኒክ ክትባት በዓለም እውቅና የተሰጣቸውን 4 ክትባቾን ተከትሎ 5ኛ ሆኖ ተመዝግቧል። አራቱ ዋንኛው የኮቪድ ክትባቶች ፋይዘር፣ ኦስክስፎርድ አስትራዜኒካ፥ ሞደርና እና ጃንሰን ናቸው። አሁን ሰፑትኒክ ይህንኑ ተርታ ተቀላቅሏል። ስፑትኒክ ክትባት የሚሰራበት መንገድ ልክ እንደ በታላቋ ብሪታኒያ ውስጥ እንደተመረተው ኦክስፎርድ አስትራዜኒካ እና በቤልጂየም እንደተሰራው ጃንሰን ነው። ይህም ማለት ክትባቱ የሚጠቀመው ደካማ ተህዋሲውን ሲሆን ይህ ተህዋሲ በቤተ ሙከራ ውስጥ በምህንድስና ይበልጥ እንዲዳከም ከተደረገ በኋላ ሰውነት ለዚህ ደካማ ተህዋሲ እንዲጋለጥ የማድረግ ዘዴ ነው። በጥንቃቄ ደካማውን የተህዋሲውን ዝርያ ለሰውነት በማጋለጥና ጄኔቲክ ኮዱን ሰውነት እንዲያውቀው በማድረግ ሰውነት በሽታውን አውቆ እንዲዋጋው የማድረግ ጥበብ ነው። ይህን ክትባት የወሰደ ሰው ሰውነቱ ወዲያውኑ አንቲቦዲ ተከላካዮችን ያመርታል። ይህ ስፑትኒክ ክትባት ከ2 እስከ 8 ዲግሪ ሴንትግሬድ ውስጥ ሊቀመጥ ስለሚችል ለማጓጓዝ የተሻለ ክትባት ሆኖ ተወስዷል። ይህም ክትባቱ እንደ ፋይዘር ለማጓጓዝም ሆነ ለማጠራቀም የተለየ ማቀዝቀዣ ስለማይፈልግ ነው። ስፑትኒክ ክትባትን ሌላ ልዩ የሚያደርገው 2 ጊዜ በ21 ቀናት የሚሰጡት ክትባቶች በተወሰነ ደረጃ መለያየታቸው ነው። ይህም ሰውነት ተህዋሲውን በደንብ እንዲለየው ለማድረግ ነው ተብሏል። ስፑትኒክ ክትባት ከሩሲያ ሌላ በአርጀንቲና፥ በፍልስጤም ግዛቶች፣ በቬንዝዌላ፥ በሐንጋሪ፥ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና በኢራን አገልግሎት ላይ እየዋለ ነው።
48302184
https://www.bbc.com/amharic/48302184
"ማህበሩ የማያልፈው ቀይ መስመር የስራ ማቆም አድማ ነው"-ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የጤና ህክምና ባለሙያዎች ለመንግሥት ያቀረቡት ጥያቄ በአግባቡ ሊመለስ ባለመቻሉ በስራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የስራ ማቆም አድማውን እንደማይደግፍ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የጤና ባለሙያዎቹ ያነሱት ጥያቄ የማህበሩም እንደሆነ የተናገሩት የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገመቺስ ጥያቄዎቹን በተለያዩ መድረኮች እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍ እስከ መውጣት ድረስ እንደሚወስዱት ቢናገሩም የስራ ማቆም አድማ ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀዋል። "እንደ ማህበር የማናልፈው ቀይ መስመር የስራ ማቆም አድማ ነው" ብለዋል። •"የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ የጤና ባለሙያዎቹ ጥያቄ ወቅታዊና በአመታት ሲንከባለሉ የመጡ መሆናቸውን የገለፁት ዶ/ር ገመቺስ በአካሄዱ ላይ ማህበሩ የተለየ መስመር እንደሚከተሉ ተናግረዋል። "አንድነት ቢኖረንና እንደ ሀኪም ማህበር አንድ አይነት ጥያቄ ብናነሳ ደስ ይለናል፤ ከእኛ ጋር እንዳይገጥሙ ያደረጋቸው ለእኛ ያላቸው ጥርጣሬና አመለካከት ነው። ይህንን ምንም ልናደርገው አንችልም፤ እኛ በስራ ከሐኪሙ ጎን መቆማችንን ማሳመን መቻል አለብን እንጂ ዛሬ ከኛ ጋር ካልሆናችሁ አንልም።" ብለዋል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል በሰላማዊ ሰልፎች ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው አይዘነጋም። ካቀረቧቸውም ጥያቄዎች መካከልም የደመወዝ ዝቅተኛ መሆን፣የጤና መድን ዋስትና፣ የኢንተርን ሃኪሞች የስራ ድርሻ ግልፅ አለመሆን፣ ሀኪሞች ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶች፣ የሆስፒታሎች ምቹ አለመሆን፣ የህክምና ስርአቱ አወቃቀር፣ የጤና ቁሳቁሶች አቅርቦት ችግር ይገኙበታል። •“ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ በችግሮቻቸውና በመፍትሄዎቹ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር ውይይት ቢያደርጉም ከመንግሥት በኩል ያገኙት ምላሽ አጥጋቢ እንዳልሆነም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። መንግሥት ጥያቄያቸውን ለመመለስ ዝግጁ አለመሆኑን ጠቅሰው እስኪመለስ ድረስም በስራ ገበታቸው እንደማይገኙም በተለያዩ መንገዶች እየገለፁ ነው። አራት ሺ አባላት ያሉት ማህበር በበኩሉ ከመንግሥት በኩል ማሻሻያና ሊቀረፉ ይገባቸዋል የሚላቸውን ጉዳዮችንም አትተዋል። ከነዚህም ውስጥ የሀገሪቱ የጤና ፖሊሲ የሚጠይቀውን ሪፎርም መሰረት በማድረግ እንዲከለስ፣ ሀገሪቱ ለጤና የምትመድበውን በጀት እንድታሻሽል፣ የታካሚና የህክምና ባለሙያ ግንኙነት እና የታካሚ መብትና ግዴታን የሚገዛ የህግ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ፣ ደመወዝ እንዲሻሻል፣ የትርፍ ሰአት ክፍያዎች ወጥ በሆነ መንገድ እንዲተገበሩ፣ የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግራቸው እንዲቀረፍ የሚሉት ይገኙበታል። •የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ? የህክምና ባለሙያዎቹ ጥያቄ የማህበሩ ጥያቄ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ገመቺስ በተለያዩ መድረኮችም እነዚህን ጥያቄዎች ለአመታት ማቅረባቸውን ገልፀዋል። "አርባ በመቶ መብራትና ውሃ የሌለውን ሆስፒታል ብላችሁ አትጥሩ፤ መድኃኒት በሌለበት አገር ውስጥ የተሟላ የጤና አገልግሎት አለን አትበሉ ስንል ቆይተናል" ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ በአጠቃላይ በህክምና ስርአቱ ላይ መፍትሄን አቅጣጫን ለመሚመለከታቸው አካላት እንዳቀረቡ የሚናገሩት ዶ/ር ገመቺስ ከዚህም ውስጥ የህክምና ባለሙያዎች ደመወዝ ሀገሪቱ በተራቆተችበት ሁኔታ ሳይሆን የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እርዳታን በመለገስ ክፍተቱን እንዲሞሉ የሚለው ይገኝበታል። እንደ ምሳሌነትም አንድ ሀኪም ሲመረቅ የሚያገኘው ደመወዝ 4700 ብር መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ገመቺስ ይህ በከፍተኛ ሁኔታ ሊሻሻል እንደሚገባም በመግለጫቸው አፀንኦት ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የህክምና ባለሙያዎቹ ጥያቄ ለግላቸው ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰቡ እንደሆነም ዶ/ር ገመቺስ ተናግረዋል። "የተነሱት ጥያቄዎች ከሰላሳ አመት በፊትም ይሁን አሁን ወቅታዊ ናቸው፤ የዛን ጊዜም ቢሆን ስናገለግል የነበረው ህብረተሰቡን ነበር። ከአመታትም በፊት ቢሆን ህብረተሰቡ እንዳይጎዳ ነበር የጠየቅነው ዛሬም ህብረተሰቡ እንዳይጎዳ ነው የምንጠይቀው" ብለዋል።
48715701
https://www.bbc.com/amharic/48715701
የአሜሪካ ሴኔት ለሳዑዲ የጦር መሳሪያ እንዳይሸጥ ወሰነ
አሜሪካ ለሳዑዲ አረቢያ በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት የጦር መሳሪያ ሽያጭ ለማድረግ ተስማምታ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ሴኔቱ ስምምነቱን አግዷል።
አሜሪካ ለሳዑዲ የምታደርጋቸውን ወታደራዊ ሽያጮች የሚያሳይ ቻርት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀንደኛ ተቀናቃኟ ኢራን ሳውዲን ስጋት ውስጥ ከታታለች በሚል ሰበብ የኮንግረሳቸውን አቋም ተላልፈው ከሳውዲ ጋር የስምንት ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነት ለማድግ ደፋ ቀና ሲሉ ነበር። በሪፐብሊካን የሚመራው ሴኔቱ ግን ትናንት ይህን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነት በሚያስቆምባቸው ሶስት የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ውሳኔ አሳልፏል። • ለ148 ህይወት መቀጠፍ ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ሦስት ግለሰቦች ተፈረደባቸው • በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረርሽኝ አሳሳቢ በመሆኑ ክትባት መሰጠት ተጀመረ • ኢትዮጵያ ለመድኃኒት ከዋጋው 30 እጥፍ ትከፍላለች ውሳኔው ለትራምፕ ትልቅ ኪሳራ ነው ተብሏል። ዲሞክራቶች የሚቆጣጠሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የስምምነቱን ተግባራዊነት ለመግታት ተመሳሳይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። ትራምፕ በስምምነቱ መሰረት የጦር መሳሪያ ለመሸጥ አቅደው የነበረው ለሳዑዲ አረብያ ብቻ ሳይሆን ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ዮርዳኖስም ጭምር ነበር። ትራምፕ ባለፈው ወር ስምምነቱን እውን ያደረጉት ብዙም ተግባራዊ ሆኖ የማያውቅ የአገሪቱን የፌደራል ህግ መሰረት በማድረግ ነበር። ትራምፕ ቦምብን ጨምሮ ለሳውዲ በአፋጣኝ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን መሸጥ ያስፈለገው ሳዑዲን ተቀናቃኟ ኢራን አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተተቻት ነው ቢሉም የምክር ቤቱ አባላት ግን የጦር መሳሪዎቹ በየመን ጦርነት ንፁሃን ዜጎችን ለማጥቃት ሊውሉ ይችላሉ የሚል ፍርሃት ስምምነቱን በጣም ተቃውመውታል።
news-51145403
https://www.bbc.com/amharic/news-51145403
በትግራይ የወረዳነት ጥያቄ ያነሱ ነዋሪዎች የመቀሌ- ሳምረን መንገድ ዘጉ
ከመቀሌ ከተማ ወደ ሳምረ የሚወስደው መንገድ "ወረዳችን ይመለስልን" በሚሉ የሕንጣሎ ነዋሪዎች ደንጎላት በሚባል አካባቢ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ እንደተዘጋ ተገለጸ።
'ሕንጣሎ ወጀራት' ተብሎ ይጠራ የነበረው ወረዳ ለሁለት ተከፍሎ፤ ወጀራት እራሱን የቻለ ወረዳ ሲሆን ሕንጣሎ ደግሞ ሒዋነ ከምትባል ሌላ ወረዳ ጋር እንዲካተት ተደርጓል። ሒዋነ ከምትባለው ወረዳ ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረጉት የሕንጣሎ ነዋሪች፤ እራሳችንን የቻለ ሕንጣሎ የተባለ ወረዳ ሊኖረን ይገባል እንጂ ከሒዋነ ወረዳ ጋር መቀላቀል የለብንም የሚል ቅሬታ ነው የሚያነሱት። ከነዋሪዎቹ እንደሰማነው አሁን በተጀመረው አዲስ የአስተዳደር መዋቅር፤ ወጀራት ከ1-9 ጣቢያዎች ያሉት ሲሆን ሕንጣሎ ግን ሒዋነ ወደሚባል ወረዳ እንዲቀላቀል ተደርጓል። ታዲያ ነዋሪዎቹ የራሳችን ወረዳ ይኑረን ሲሉ ነው እየጠየቁ ያሉት። የአካባቢው ነዋሪዎች ኮሚቴ ወኪል አቶ ደሱ ፀጋየ፤ "ጥያቄያችን ወረዳችን ይመለስልን የሚል ነው፤ ሕንጣሎ ወጀራት ወረዳ ነበረች። ወጀራት ተመለሰች ነገር ግን ሕንጣሎ ተሰጠች።" ይላሉ። አቶ ደሱ ይህንን ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩ ስድስት ወራት መቆጠራቸውን ይናገራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ቅሬታቸውን ለማቅረብ ያልሄዱበት፤ ያልደረሱበት ቦታ የለም። በወረዳ እና በዞን የሚገኙ የፍትሕም ሆነ የፀጥታ አካላትን አዳርሰዋል። ነገር ግን ያገኙት ምላሽ የለም። "እኛ መንግሥት በደነገገው ሕግ መሠረት ሁሉንም አሟልተናል። አንደኛ ከ115 ሺህ ሕዝብ በላይ ነን። ሁለተኛ መንግሥት 'ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዞ የወረዳ አገልግሎት ማግኘት የለበትም' ነው የሚለው እኛ ግን ከ30 በላይ ኪሎ ሜትር በላይ ሄደን ነው ይህንን አገልግሎት የምናገኘው፤ ስለዚህ የልማት ጥያቄያችን እንዲመለስልን ነው የምንፈልገው" ሲሉ ጥያቄያቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ነገር ግን ይህንን ጥያቄ ማንሳት ከጀመሩ መንፈቅ ቢሞላቸውም፤ የፖለቲካ አስተዳዳሪዎችን መልስ እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም ጆሮ የሰጣቸው የለም። አቶ ደሱ "በተቃራኒው በዞንና በወረዳ ፖሊስ አማካኝነት ያስፈራሩን ገቡ፤ ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎችም መንገድ በመዝጋታቸው ወደ ገበያ የሚሄዱ ከብቶች ሳይቀሩ መንገድ ላይ ነው የዋሉት፤ መንገድ ዝግ ነው፤ ይሄው እንዲህ ከሆነ ሦስት ቀን ሆኖታል" ብለዋል። ከአከባቢው ነዋሪዎች እንደሰማነው መንገዱ በመዘጋቱ ትናንት እስከ 150 የሚደርሱ መኪኖች መንገድ ላይ ሲጉላሉ ውለዋል። በሌላ በኩል "ወረዳችን ይመለስልን" የሚሉ የዓዲ ነብሪ ኢድ ነዋሪዎች መንገድ ዘግተው ነበር የሚሉ መረጃዎች ተሰምተዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸውን የሰሜን ምዕራብ ዞን ኃላፊዎችና የክልሉን አመራሮች ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
news-56425425
https://www.bbc.com/amharic/news-56425425
ፕሬዝዳንት ፑቲን የአሜሪካ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ እንዲደረግ አዝዘዋል ተባለ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የባለፈውን ዓመት የአሜሪካ ምርጫን ዶናልድ ትራምፕን በመደገፍ ተጽዕኖ እንዲደረግ ይሁንታቸውን ሳይሰጡ አልቀሩም ሲሉ የደኅንነት ባለሥልጣናት ተናገሩ።
ሞስኮ ስለ አሸናፊው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን "አሳሳች እና መሰረተ ቢስ ውንጀላዎችን" ስታሰራጭ ነበር ተብሏል። ነገር ግን የትኛውም የውጪ ኃይል የመጨረሻው ውጤት ላይ ተጽዕኖውን አላሳረፈም ሲል የአሜሪካ መንግሥት መረጃ ያስረዳል። ሩሲያ በተደጋጋሚ በአሜሪካ ምርጫ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ትሞክራለች የሚለውን ውንጀላ ስታታጥል ቆይታለች። በአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት መሥሪያ ቤት በኩል ማክሰኞ ዕለት ይፋ የተደረገው ባለ 15 ገጽ ሪፖርት በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት በሩሲያ እና በኢራን "ተጽዕኖ የማድረግ ዘመቻ" በሚል የተደረገ እንቅስቃሴ እንደነበር ያትታል። በሪፖርቱ ላይ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦች ከምርጫው በፊት ስለ ፕሬዝዳንት ባይደን መሰረተ ቢስ ወሬዎችን ሲያናፍሱ እንደነበር ተገልጿል። አክሎም በሰፊው የምርጫ ሂደት ላይ መተማመንን ለማሳጣት የሐሰተኛ መረጃ ዘመቻ ተከፍቶ ነበር ሲል ገልጿል። ከሩሲያ የደኅንነት ተቋም ጋር ግንኙነት ያላቸው አንዳንድ ግለሰቦች ለመገናኛ ብዙሃን፣ ለትራምፕ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና አጋሮቻቸው ፀረ ባይደን የሆኑ ትርክቶችን ሲያቀብሉ ነበር ሲል ሪፖርቱ ያስቀምጣል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዶናልድ ትራምፕን በማሸነፍ የአሜሪካ 46ኛው ፕሬዝዳንት ለመሆን በቅተዋል። ሪፖርቱ አክሎም ሩሲያ የትራምፕን የማሸነፍ እድል ለማስፋት ጥረት ስታደርግ ኢራን በሌላ ወገን የትራምፕን ድጋፍ ለማሳነስ ዘመቻ ላይ ነበረች ብሏል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ "ከፍተኛ ግፊት" የሚያደርግ ፖሊሲን ተከትለው የነበረ ሲሆን ማዕቀቦችን በመጣል በሁለቱ አገራት መካከል የቃላት ጦርነት እንዲጦፍ ምክንያት ሆነዋል። በሪፖርቱ ላይ በተደጋጋሚ የሳይበር ወንጀሎች በመፈፀም ስሟ የሚነሳው ቻይና ከምርጫው በፊት ምንም ዓይነት ዘመቻ ላለማድረግ ራሷን አቅባ እንደነበር ተጠቅሷል። "ቻይና ከአሜሪካ ጋር ባላት ግንኙነት መረጋጋትን አሳይታ ነበር፤ የምርጫው ውጤት ለቻይና ጥቅም ያደላ እንዲሆን ምንም ዓይነት እርምጃ አላሳየችም" ይላል። ሪፖርቱ የምርጫ ሂደቱም ሆነ የመጨረሻው ውጤት በውጪ ኃይሎች ጫና እንዳልተደረገበት አመልክቷል። የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ሪፖርት ይፋ የተደረገው በዚሁ ጉዳይ ላይ የአገር ውስጥ ደኅንነት እና ፍትህ ቢሮዎች በጋራ የሰሩት ጥናትን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው። የአነዚህ ሁለት መሥሪያ ቤቶች ሪፖርት እንደሚለው ከሆነ "በሩሲያና ኢራን መንግሥታት በወሳኝ ተቋማት ላይ የተከፈተው ዘመቻዎች ምርጫን በሚመለከት የሚሰሩ ኔትወርኮችን ማጥቃት ሳይችል ቀርቷል።" እነዚህ የተባሉ ጣልቃ ገብነቶች በሙሉ በተዘዋዋሪ የተፈፀሙ መሆናቸውንም ጥናቱ ጠቅሷል። ሩሲያና ኢራን በምርጫው ላይ ጣልቃ በመግባት ተጽዕኗቸውን ማሳረፍ የፈለጉት የምርጫ ሂደቱን ቴክኒካዊ ሂደት፣ ድምጽ ቆጣራ፣ ድምጽ አሳጣጥ እና ውጤት ይፋ አደራረግ ላይ መሆኑን ከቢሮዎቹ የወጣው ሰነድ ያሳያል። የአሜሪካ ደኅንነት ማኅበረሰብ ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ሩሲያ ዶናልድ ትራምፕ እንዲያሸንፉ ቻይናና ኢራን ደግሞ እንዲሸነፉ ዘመቻዎችን እያደረጉ ነው ሲሉ ይፋ አድርገው ነበር።
50900207
https://www.bbc.com/amharic/50900207
አሜሪካ አነፍናፊ ውሾዎቼ 'ነጡ፤ ገረጡብኝ' በሚል ወደ ግብጽና ዮርዳኖስ ላለመላክ ወሰነች
አሜሪካ ፈንጂ አነፍናፊ ውሾችን ወደ ዮርዳኖስና ግብጽ ላለመላክ ወሰነች። እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በቸልተንነት የተነሳ በርካታ ውሾች ከሞቱ በኋላ ነው ተብሏል።
አነፍናፊ ውሾች የጸረ ሽብር ተግባሩን ለማገዝ በተለያዩ ሀገራት ተሰማርተው ይገኛሉ "በተልዕኮ ላይ ያለ የየትኛውም ውሻ ሞት ልብ ይሰብራል" ያሉት የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ናቸው። በመስከረም ወር የወጣ አንድ ሪፖርት ይፋ እንዳደረገው በዮርዳኖስ፣ ግብጽና ሌሎች ስምንት አገራት ለግዳጅ ከተላኩ ከ100 በላይ አነፍናፊ ውሾች በቸልኝነትና እንክብካቤ ጉድለት የተነሳ መጎሳቆላቸወን አሳይቷል። • ለማነፍነፍ የሰነፈችው ጥሩ ውሻ • ሟች አሳዳጊውን የሚጠባበቀው ውሻ የአሜሪካ አነፍናፊ ውሾች የጸረ ሽብር ፕሮግራሙን ለመደገፍ የተሰማሩ ናቸው። ዮርዳኖስም ሆነች ግብጽ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ድረስ አስተያየታቸውን አልሰጡም። አሜሪካ ጊዜያዊ እገዳዋን ይፋ ያደረገችው ሰኞ እለት ሲሆን የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው እርምጃው የተወሰደው ተጨማሪ ሞትን ለመከላከል ነው። ውሾቹ "ከሌሎች አገራት ጋር በመሆን የምናደርገውን የጸረ ሽብር ተግባር በመደገፍና የአሜሪካዊያንን ሕይወት በመታደግ ረገድ ቁልፍ ሚና አላቸው" ብለዋል ባለስልጣኑ። ባለስልጣኑ አክለውም በዮርዳኖስና ግብጽ ያሉት ውሾች ለጊዜው በዚያው ይቆያሉ ብለዋል። በከፍተኛ ሁኔታ ክብደታቸው የቀነሰ ሁለት አነፍናፊ ውሾች በጆርዳን የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው እ.ኤ.አ. በ2017 አንድ ውሻ በዮርዳኖስ በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ህይወቱ አልፏል። ሌሎች ሁለት ውሾች ደግሞ "ክፉኛ ታመው ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል" ይላል ሰነዱ። • 'ሕዝቤ ሆይ! እባክህ ውሻ አትብላ'፡ ቪየትናም • "በዓይን የሚታይ የእምቦጭ አረም ወደ ሚቀጥለው ዓመት እንዳይተላለፍ እናደርጋለን" የአሜሪካ ባለሰልጣናት እንዳሉት ከሆነ ውሾቹ ተጎሳቁለውና ክብደታቸው ቀንሶ ስለነበር ጤንነታቸው እስኪመለስና እስኪያገግሙ ድረስ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው። በቅርቡ የወጣ ሌላ ሪፖርት እንደሚያሳየው ደግሞ ወደ ዮርዳኖስ ከተላኩ ውሾች ሁለቱ "ተፈጥሮአዊ ባልሆነ ምክንያት" ሞተዋል። የፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ አንዱ ውሻ በከፍተኛ ሙቀት ሌላኛው ደግሞ የፖሊስ አባል በረጨው የተባይ ማጥፋያ ምክንያት ሞተዋል። በርካታ አነፍናፊ ውሾች ከአሜሪካ ወደ ዮርዳኖስ የሚሄዱ ሲሆን 100 ያህሉ ደግሞ በመከከለኛው ምሥራቅ አገራት ተሰማርተው ይገኛሉ። የአሜሪካ ሪፖርት እንደሚያሳየው ወደ ግብጽ ለግዳጅ ከተላኩ ውሾች አስር ያህሉ በሳንባ ካንሰር፣ በከፍተኛ ሙቀት እንዲሁም በሽንት ፊኛ መቀደድ ምክንያት ተልዕኳቸውን መፈፀም አቅቷቸዋል።
news-43297762
https://www.bbc.com/amharic/news-43297762
የ2018ን ኦስካር ሽልማት ያገኘችውን ፍራንስስ ማክዶርማን ሽልማት የሰረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ላይ ዋለ
እሁድ ዕለት ከተካሄደው የኦስካር ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በኋላ ፍራንስስ ማክዶርማንድ የተቀበለችውን ሽልማት የሰረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ሽልማቷ በሃገረ ገዢው ግብዣ ላይ መጥፋቱ እንደታወቀ ቴሪ ብራያንት በከባድ ስርቆት በቁጥጥር ስር እንደዋለ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ አረጋግጧል። የ47 ዓመቱ ቴሪ ከታሰረ በኋላ የ20 000 ዶላር ዋስ ጠርቶ እንዲለቀቅ ተወስኗል። ፍርድ ቤት የሚቀርብበትም ቀን እንዳልተቆረጠ ተገልጿል። ሽልማቱም በምርጥ ተዋናይቷ እጅ ተመልሶ ገብቷል። የተዋናይቷ ተወካይ ለዩኤስ ኤ ቱዴይ ''ፍራን እና ኦስካር በሰላም ተገናኝተው አብረው ኢን ኤን አውት በርግር እያጣጣሙ ነው'' ብላለች። ፍራንስስ ሃውልቱ ከመሰረቁ በፊት ስሟን አስቀርፃበት ነበር። ተዋናይቷ 'ትሪ ቢልቦርድስ አውትሳይድ ኤቢንግ ሚዙሪ' በተሰኘው ፊልም ላይ ለነበራት ሚና ባገኘችው የምርጥ ተዋናይነት ሽልማትን እያከበረች ነበር። ፍራንስስ በሃገረ ገዢው ዝግጅት ላይ ከመጥፋቱ በፊት ሃውልቷ ላይ ስሟን ስታስቀርጽ ፍራንስስ ሽልማቱን ስትቀበል ባደረገችው ንግግር ላይ ሴት እጩዎችን በሙሉ አንዲቆሙ በመበጋበዟ የጋለ ተቀባይነት ነበር ያገኘችው። ንግግሯንም ''የዛሬን ምሽት በሁለት ቃላት ነው የምስናበታችሁ - 'ኢንክሉዥን ራይደር' '' ብላ ነበር። ኢንክሉዥን ራይደር ማለት ተዋናዮች ውላቸው ላይ ቢያንስ 50% ብዝሃነት ከተዋናዮች አንፃር ብቻ ሳይሆን ከፊልሙ ጀርባ ያሉትንም ጨምሮ እንዲካተት የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ማስተወሷ እንደነበር ከመድረክ ከወረደች በኋላ አስረድታለች። ፍራንስስን ለኦስካር ሽልማት ባበቃት ፊልም ላይ የተወነችው ልጇ ተደፍራ ከተገደለችባት በኋላ ባለሥልጣናት ምንም ስላላደረጉላት ለመበቀል የተነሳችን እናት ወክላ ነው። ተዋናይቷ ይህ ሁለተኛ የኦስካር ሽልማት ሲሆን የመጀመሪያ ኦስካሯን ያገኘችው ከ21 አመት በፊት 'ፋርጎ' በተሰኘ ፊልሟ ነው።
46381948
https://www.bbc.com/amharic/46381948
ቶጎዋዊያን ተመራማሪዎች የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻን ወደ ሮቦቶች ቀይረዋል
ቶጎ በየዓመቱ ወደ ሀገሯ ከምታስመጣቸው 500 ሺህ ሰልባጅ ኤልክትሮኒክሶች መካከል አንዳንዶቹ ለጤና ጠንቅ ቢሆኑም እንኳ የሀገሪቱን ወጣት ተመራማሪዎችን ግን ለአዳዲስ ፈጠራ አነሳስቷቸዋል።
ከተጣለ ማተሚያ ማሽን በሸረሪት ቅርፅ የተሰራ ሮቦት ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በመንግሥት ወይም በግለሰቦች ጥቅም ላይ ውለው ከተወገዱ በኋላ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቆሻሻ ይሆናሉ። የ29 ዓመቱ ቶጓዊ ሀገሩ የምታስገባቸው የኤሌክትሮኒክስ ውድቅዳቂዎችን በመሸጥ ይጠቀማል። አነስተኛ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ የሚያክል ስፍራ ላይ ያገለገሉ ቴሌቪዥኖችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተከምረው ይታያሉ። ከእነዚህ ውድቅዳቂና ያገለገሉ እቃዎች በቶጎ የመጀመሪያውን ስሪ ዲ ማተሚያ እንደሰራ የሚናገረው ጊንኮ አፋቴ ያገለገሉ እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ስለማዋል በርካታ ነገሮች እንደተማረ ይናገራል። የእርሱ ፈጠራ እውቅና አግኝቶ በ2015 በባርሴሎና የቴክኖሎጂ ምርቶች ጉባኤ ላይ ቅድሚያ አግኝቷል። ከዚህ በፊት የተጣሉ እቃዎችን እየሰበሰቡ የተለያዩ ነገሮች ከሚሰሩ ወዳጆቹ ጋር በህብረት ይሰራ የነበረው የ39 ዓመቱ የፈጠራ ባለሙያ ዛሩሬ የራሱን መስሪያ ቦታ ከፍቷል። "የቶጎ ጎዳናዎች ባገለገሉ እቃዎችና በበሰበሱ የኮምፒውተር አካላት ተሞልተው ነበር። ዛሬ ይህ ነገር አይታይም። አሁን የቆሻሻ ክምር ሳይሆን የወርቅ ጉድጓድ ነው የሚታየኝ" ይላል ለፈጠራ የሚያነሳሳውን የኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻ ሲያስታውስ። በዓለም ላይ 41 የአውሮፓ ሀገራት ብቻ ናቸው ስለሚያስወግዷቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መረጃ የሚይዙት። ከ1 ሰው 140 ፈጠራ ? • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ ያገለገሉ የሞባይል ቀፎዎች፣ ላፕቶፖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ ጄኔሬተሮች፣ በእቃ መጫኛ መኪናዎች ተጭነው ከሎሜ ወደብ ይመጣሉ። መኪኖቹ እቃዎቹን የሚያራግፉት ከወደቡ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ የገበያ ስፍራ ነው። ያኔ ሰልባጅ እቃዎችን ለመግዛት የሚረባረቡ ሰዎች ቁጥር አይን አይቶ አይሰፍረውም። ሸማቾች ለቴክኖሎጂ ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ ሰልባጅ እቃዎችን በድርድር ዋጋ መግዛት ጀምረዋል። ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፍላጎት መኖር ብቻ ሳይሆን ባደጉ ሀገራት ያገለገሉ እቃዎችን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ነገር በበቂ ሁኔታባለመኖሩ ቶጎን መጣያ አድርጓታል። እኤአ በ2016 በዓለማችን 44 ሚሊየን ቶን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቆሻሻ እንደተሰበሰበ ተገልጾ ነበር። ከዚህ ውስጥ 20 በመቶው ብቻ ተመልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል። • የታኘከ ማስቲካ ዳግም ነብስ ሲዘራ • ዘመናዊውን የመፀዳጃ መቀመጫ የፈጠረው ሰዓት ሠሪ በ2021 ይህ ወደ 52 ሚሊየን ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
news-53328675
https://www.bbc.com/amharic/news-53328675
እስካሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ፖለቲከኞች እነማን ናቸው?
ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ ጥቂት የማይባሉ ፖለቲከኞች ተይዘው መታሰራቸው ተሰምቷል።
በዚህም መሰረት ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አቶ ደጀኔ ጣፋ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ደግሞ ኮሎኔል ገመቹ አያና በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል። የኦፌኮ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ ማክሰኞ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊስ ተይዘው መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ አሰለፈች ሙላቱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለቤታቸው እንዳሉት ፖሊሶች አቶ ደጀኔ ጣፋን አሸዋ ሜዳ አካባቢ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዷቸውና ተመልሰው ይዘዋቸው በመምጣት ቤታቸውን ፈትሸው እንደሄዱ ገልጸዋል። በተጨማሪም የኦነግ ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ ቶሌራ አደባ የፓርቲያቸው አባል የሆኑት ኮሎኔል ገመቹ አያና በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ከዚህ ባሻገር ከሃጫሉ ሁንዴሳ መገደል በኋላ ባሉት ቀናት በመጀመሪያ የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው አባላት አቶ ጃዋር መሐመድ እንዲሁም ሐምዛ ቦረና በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። በተከታይነትም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ እስክንድር ነጋና የፓርቲው አመራር አባላት አቶ ስንታየሁ ቸኮልና ወ/ሮ አስቴር ስዩም ባለፈው ሳምንት በፖሊስ ተይዘው በእስር ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው አስታውቀወል። የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው የተነገረው ባለፈው ሳምንት ነው። የፓርቲው አባላት እንደተናገሩት ሊቀመንበራቸው ለእስር የተዳረጉበትን ምክንያት እንዳላወቁ ገልጸዋል። ኦነግ ትናንት ታስረውብኛል ካላቸው አባላቱ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንትም ሌሎች የግንባሩ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። እነሱም የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አቶ ሚካኤል ቦረን እና አቶ ኬነሳ አያና እንዲሁም የፓርቲው አማካሪ ዶክተር ሽጉጥ ገለታ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ባለፈው ሳምንት ለእስር ከተዳረጉ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት መካከል የተወሰኑት ፍርድ ቤት ቀርበው ቀጣይ ቀጠሮ የተሰጣቸው ሲሆን ቀሪዎቹም ዛሬ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦችና የፓርቲ አባላት ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-54039364
https://www.bbc.com/amharic/news-54039364
ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ
ትውልደ ሶማሊያዊው ሞ ፋራህ በኃይሌ ገብረስላሴ ለ13 ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ።
አትሌት ሞ ፋራህ ለግሬት ብሪቴን የሚሮጠው የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሞ ፋራህ የአንድ ሰዓት የዓለም ክብረ ወሰንን በዳይመንድ ሊግ ውድድር ነው ትናንት ምሽት ማሻሻል የቻለው። ፋራህ በአንድ ሰዓት ውስጥ 23.33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው የሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴን 21.285 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሻሻለው። “የዓለም ክብረ ወሰንን መስበር ቀላል ነገር አይደለም። ይህን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ይህ ክብረ ወሰን ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር ቆይቷል” ሲል ከውድድሩ በኋላ ሞ ፋራህ ተናግሯል። በዚህ ውድድር አትሌቶች በአንድ ሰዓት ውስጥ በተቻላቸው መጠን ረዥም ርቀትን ለመሸፈን ይወዳደራሉ። አትሌት ሲፈን ሃሰን ከዛ ቀደም ብሎ በተካሄደ ተመሳሳይ የሴቶች ውድድርም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን በተመሳሳይ የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችላለች። ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፈን ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ ተይዞ የነበረውን ነው። ሲፈን በአንድ ሰዓት ውስጥ 18.930 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ከ14 ዓመታት በፊት ድሬ ቱኔ አስመዝግባ የነበረውን 18.517 ኪሎ ሜትር ማሻሻል ችላለች።
news-57197222
https://www.bbc.com/amharic/news-57197222
የዩኬ መንግሥት ዕድሜያቸው የገፉ አርሶ አደሮችን ጡረታ እንዲወጡ ሊከፍል ነው
አዲስ ሀይል ወደ በእርሻው ዘርፍ እንዲሰማራ በማለም የዩኬ መንግስት እድሜያቸው የገፉ የእንግሊዝ አርሶ አደሮችን በጡረታ እንዲገለሉ ሊያደርግ ነው። የጡረታ ደመወዝም ይቆርጥላቸዋል።
በአማካኝ አንድ አርሶ አደር የጡረታ ጊዜውን ክፍያ ድምር 50 ሺህ ፓውንድ ሊያገኝ ይችላለ። ሰፋ ያለ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች ደግሞ ይህ ክፍያ በእጥፍ አድጎ በአማካኝ 100 ሺህ ፓውንድ ይከፈላቸዋል። ይህ የጡረታ ክፍያ በሰፋፊ እርሻዎች ላይ አርሶ አደሮች ከባቢያቸውን እንዲንከባከቡ የሚያበረታታው የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴ አካል ነው። ሆኖም ይህንን ሀሳብ አንቀበልም ያሉ በዕድሜ የገፉ አርሶ አደሮች አሉ። አሁን ላይ የእንግሊዝ አርሶ አደሮች በቀደመው የአውሮፓ ህበረት ስርዓት ባላቸው የእርሻ መሬት ልክ ድጋፋ የሚደረግላቸው ሲሆን በአማካኝ ወደ 21 ሺህ ፓውንድ ያገኛሉ። ምንም እንኳን እንደ ንግሰቲቱ ያሉ ሰዎች ባላቸው ግዙፍ የእርሻ መሬት ልክ በዓመት እስከ ግምማሽ ሚሊዮን ፓውንድ ቢከፈላቸውም። በዌልስ ያሉ አርሶ አደሮችም በአዲሱ የዩኬ መንግስት የጡረታ ክፍያ ውስጥ እንደሚካተቱ ይጠበቃል። ታዲያ እንደ አካባቢ ጠበቃ ባለሙያው ጆርጅ ኢውስተስ ገለጻ የአውሮፓ ህብረት የአርሶ አደሮች የድጋ ስርዓት አከባቢን ለመታደግና አርሶ አደሮችን ከስጋት ለማላቀቅ ያግዛል። አዲሱ የዩኬ መንግስት በጡረታ የማግለል ሀሳብ ደገሞ አርሶ አደሮቹን በሌሎች የስራ መስኮች እንዲሰማሩ ያበረታታል በለዋል። ከ 10 አርሶ አደሮች ወደ 4 የሚጠጉት ዕድሜያቸው ከ 65 በላይ ሲሆን አማካኙ ደግሞ 59 ነው።
news-53060107
https://www.bbc.com/amharic/news-53060107
"አባላቶቻችን በአካባቢው ይህን የደንብ ልብስ መልበስ ካቆሙ ስድስት ወራት አልፈዋል" የኦሮሚያ ፖሊስ
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከሰሞኑ በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ የክልሉን ፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው አንድ የሳር ክዳን ጎጆ ቤትን ሲያቃጥሉ የሚያሳያውን ተንቀሳቃሽ ምስል እያጣራ መሆኑን ገለጸ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጉዳዩ የት፣ መቼ እና በማን እንደተፈጸመ የሚያጣራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ጉጂ ዞን ተልኳል ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ግርማ ምንም እንኳ ጉዳዩን የሚያጣራ ግብረ ኃይል ወደ ስፍራው መላኩን ቢጠቁሙም፤ ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚታየውን አይነት የደንብ ልብስ የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ ኃይል አባላት እንደማይለብሱ ገልጸዋል። "የጸጥታ ችግር ባለባቸው በወለጋ፣ በጉጂ እና በቦረና ዞኖች ይህን አይነት (ሽሮ መልክ ያለው ቡራቡሬ የፖሊስ የደንብ ልብስ) እንዳለይለበስ ሲል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከስድስት ወራት በፊት መመሪያ አስተላልፏል" ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ። አቶ ግርማ ለዚህም ምክንያቱን ሲያስረዱ፤ "ይህን ዩኒፎርም በብዛት እየለበሱ ያሉት የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው። በተለይ ደግሞ በጉጂ ዞን ውስጥ ይህን እየለበሱ ያሉት የሸኔ አባላት ናቸው። የጸጥታ ኃይሎች በአካባቢው የሚለብሱት የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል" ብለዋል። አቶ ግርማ "ይህ ቪዲዮ የቆየ ከሆነ ብለን አጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው ልከናል። ውጤቱ ሲታወቅ ይፋ እናደርጋለን። እስከዚያው ግን እነዚህ ሰዎች የእኛ አባላት ናቸው ወይም አይደሉም ማለት እንችልም። ምክንያቱም ልክ እንደናንተው ነው ቪዲዮን የተመለከትነው" ብለዋል። የተንቀሳቃሽ ምስሉ ይዘት ምን ነበር? ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ በጉጂ ዞን ውስጥ ተፈጸመ በተባለው እርምጃ፤ 'የሸኔ አባል ቤት ነው' የተባለ የሳር ክዳን ቤት የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት የደንብ ልብስን በለበሱ እና የአካባቢው ሚሊሻ ናቸው በተባሉ ሰዎች ሲቃጠል ታይቷል። ቢቢሲ ምሰሉ የት እና መቼ እንደተቀረጸ እንዲሁም የሳር ክዳን ቤቱ እንዲቃጠል የተደረገው በየትኛው አካል እንደሆነ እና የቤቱ ባለቤት ማን እንደሆነ በገለልተኛነት አላረጋገጠም። ወደ ሰባት ደቂቃ ገደማ በሚረዝመው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ቁጥራቸው ከ10 በላይ የሚሆኑ ሽሮ መልክ ያለው ቡራቡሬ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ የሳር ክዳኑን ቤት ሲያቃጥሉ፤ እንዲሁም ቁጥራቸው ያነሰ ሙሉ በሙሉ አረንጓዴ ዩኒፎርም የለበሱ እና የታጠቁ ሰዎች ሰዎች ቆመው ያሳያል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ሽሮ መልክ ያለው ቡራቡሬ የደንብ ልብስ የለበሱት ሰዎች "ቤቱ የሸኔ ነው ይቃጠል"፣ "ፎቶ አንሳን" ሲሉ ይሰማል። አንድ የቡድኑ አባል በቤት ውስጥ "ሞፈር አለ" ሲል ሌላኛው ደግሞ "ተወው ማን አርሶ ሊበላ ነው ይቃጠል" ሲል ይሰማል። ከዚያም የታጠቁት ሰዎች ከጎጆው ፊት ለፊት ሆነው በድል አድራጊነት ሲጨፍሩ እና ፎቶግራፍ ሲነሱ ይታያሉ። ሁለተኛው ቪዲዮ ከዚህ ቪዲዮ በተጨማሪ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች አንድን ግለሰብ ከበው ሲያንገላቱ የሚያሳየው ምስል በስፋት ተሰራችቷል። ቢቢሲ ይህም ተንቀሳቃሽ ምስል የት እና መቼ እንደተቀረጸ እንዲሁም ጥቃት አድራሾቹን እና ጥቃት የደረሰበት ግለሰብን ማንነት በገለልተኛነት አላረጋገጠም። በምስሉ ላይ የሳር ክዳኑ ቤት ሲያቃጥሉ የነበሩ ሰዎች የለበሱትን አይነት የደንብ ልብስ የለበሰቡ ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የታጠቁ ሰዎችን አንድ ግለሰብን ሲያንገላቱ ይታያሉ። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ "የሸኔ አባል ነህ፤ መሳሪያውን የት ነው የደበቅከው አውጣ" ይላሉ ታጣቂዎቹ። ግለሰቡም "የአከባቢውን ሰው ጠይቁ እኔ ከምኑም የለሁበትም" ሲል ይሰማል። ከዚያም "በለው በጥይት" ይላለ ምስሉን የሚቀርጸው ግለሰብ፤ ከታጣቂዎቹ አንዱም መሳሪያውን አንስቶ ግለሰቡ ላይ ሲያነጣጠር ይታያል። ከዚያም ታጣቂዎቹ ግለሰቡን ተነስቶ እንዲቆም ይነግሩታል። በደብደባ ምክንያት በሚመስል መልኩ ግለሰቡ ተነስቶ በእግሩ ለመቆም ሲታገል ይታያል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ግርማ ገላን፤ ይህ ሁለተኛው ቪዲዮ ላይ የሚታየው ድርጊት እንደተባለው በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት አለተፈጸመም። "ይህ በእኛ አባላት አለመፈጸሙን አረጋግጠናል ብለዋል" ሲሉ ምክትል ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ገልጸው በጉዳዩ ላይ ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል።
44493134
https://www.bbc.com/amharic/44493134
አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት አዲስ አሰራር እንዲኖር ትፈልጋለች
ሞሮኮ የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ተወዳድራ አለማሸነፏን ተከትሎ አፍሪካዊያን ፊፋ ውድድሩን ለማስተናገድ የሚሰጠው ዕድል በዙር እንዲሆን እንደሚፈልጉ አሳወቁ።
የሰሜን አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሮኮ ከስምንት ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን የዓለም ዋንጫ ለማስተናገድ በጥምረት ከቀረቡት ከካናዳ፣ከሜክሲኮና ከአሜሪካ ጋር ተወዳድራ ረቡዕ እለት 134 ለ 64 በሆነ ድምፅ ተሸንፋለች። በዚህ ውጤት ያልተደሰቱት አፍሪካዊያን ውድድሩን ለማዘጋጀት ሌላ አማራጭ አቅርበዋል። "ውድድሩ በዙር እንዲዘጋጅ ማድረግ መፍትሄ ነው" ሲሉ የማላዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዋልተር ኒያሚላንዱ ተናግረዋል። ቀጣዮቹን የዓለም ዋንጫ ውድድሮችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከተደረጉት 23 ውድድሮች መካከል በአፍሪካ ውስጥ የተዘጋጀው አንድ ብቻ መሆኑ ጥያቄን አስነስቷል። ከስምንት ዓመታት በፊት ደቡብ አፍሪካ ያዘጋጀችው በአፍሪካ ምድር የተስተናገደው የዓለም ዋንጫ ዕድል የተገኘው ፊፋ በዙር ውድድሩን የማዘጋጀት አሰራርን ፈቅዶ ስለነበር ነው። ይህም ደቡብ አፍሪካ ውድድሩን ለማዘጋጀት ከጀርመን ጋር ተፎካክራ በጠባብ የድምፅ ልዩነት ከተሸነፈች በኋላ በወቅቱ የፊፋ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሴፕ ብላተር እድሉ በዙር እንዲሰጥ ካስወሰኑ በኋላ ነበር። ግፊቱ የሚቀጥል ከሆነ ፊፋ አስተናጋጅነቱን ለአህጉራት በዙር የመስጠቱን ጉዳይ መልሶ ሊያጤነውና ተግባራዊ ሊያደርገው እንደሚችል እየተነገረ ነው። "የዓለም ዋንጫ ማለት እግር ኳስን ወደ ህዝቡ መውሰድ ማለት እስከ ሆነ ድረስ ፊፋ ይህንን ሃሳብ ይቀበለዋል ብዬ አስባለሁ" ሲሉ አንድ የአፍሪካ እግር ኳስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ለቢቢሲ ስፖርት ተናገረዋል። "በዓለም ዙሪያ በሃገራት መካከል የደረጃ ልዩነት አለ፤ ስለዚህም ይህንን ውድድር በዙር እንዲዘጋጅ ለማድረግ የሚያስችል ህግ ማውጣት ያስፈልጋል። በምርጫው ወቅት ሞሮኮ ያገኘችው ድምፅም ይህንን ያሳያል" ሲሉም አክለዋል። ሞሮኮ በሦስቱ የሰሜን አሜሪካ ሃገራት ጥምረት በከፍተኛ ድምፅ ተበልጣ የዓለም ዋንጫን ከማስተናገድ ውጪ ከሆነች በኋላ፤ በድምፅ አሰጣጡ ሥነ-ሥርዓት ላይ የነበሩ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት ልኡካን በዚህ ሁኔታ አህጉሪቱ ውድድሩን የማዘጋጀት እድል ታገኝ ይሆን? የሚል ጥያቄ ተፈጥሮባቸዋል።
43593959
https://www.bbc.com/amharic/43593959
ታግተው የነበሩት የትሪፖሊ ከንቲባ ተለቀቁ
የሊቢያዋ መዲና ትሪፖሊ ከንቲባ ለሰዓታት በታጣቂዎች ታግተው ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው አሳወቁ።
አብደልራውፍ ቢይተልማል ከቤታቸው በታጣቂዎች የተወሰዱት ትናንት ሃሙስ ጠዋት ላይ ነበር። ቤተሰቦቻቸው እንዳረጋገጡት ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ነው የተለቀቁት። ለከንቲባው ቤተሰብ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ ወደመኖሪያቸው ሲመጡ ጥይት መተኮሳቸውንና የከንቲባውን ወንድ ልጅ እንደመቱት ተናግረዋል። ቢሆንም ግን በሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ-ሕግ መስሪያ ቤት ውስጥ የምርመራ ክፍል ሃላፊ የሆኑ ግለሰብ ከንቲባው ለጥያቄ ወደ እስር ቤት እንደተወሰዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነገር ግን ባለስልጣኑ ሳዲቅ አልሱር ከንቲባው በቁጥጥር ስር የዋሉት በሕጋዊ መንገድ ስለመሆኑ ምክንያት አልሰጡም። የትሪፖሊ ከተማ ከንቲባን ለመያዝ ከዕኩለ ሌሊት በኋላ ወደቤታቸው የሄዱት ታጣቂዎች ጥይት መተኮሳቸውን የከንቲባው ቤተሰብ ምንጮች ተናግረዋል። ሐሙስ ዕለት የከንቲባው በታጣቂዎች መያዝን በመቃወም የዋና ከተማዋ ምክር ቤት ሥራውን አቁሞ ነበር። በሊቢያ ያሉ ታጣቂ ቡድኖች በመንግሥት ባለስልጣናትና ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመፈፀምና በማስፈራራት ይታወቃሉ። በሊቢያ በታጣቂዎችና በመንግሥት ኃይሎች የሚፈፀሙ ሰዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ድርጊቶች የተደበላለቁ በመሆናቸው ሕጋዊውን ከሕገ-ወጡ ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ ይነገራል። ለአስርታት ሃገሪቱን የመሩት ሙአመር ጋዳፊ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ቀውስ ውስጥ በገባችው ሊቢያ፤ የመንግሥት ኃይሎችና ታጣቂዎች የሃገሪቱን ሥልጣን ለመቆጣጠር ፍልሚያ ከጀመሩ ሰባት ዓመት ሆኗቸዋል።
news-57173551
https://www.bbc.com/amharic/news-57173551
ኢትዮጵያ 1 ቢሊዮን ችግኞች ለጎረቤት አገራት ልታድል ነው
'ኢትዮጵያን እናልብሳት' በሚል መርሃ ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ 6 ቢሊየን ችግኝ የሚተከል ሲሆን አንድ ቢሊየን ችግኝ ደግሞ ለጎረቤት አገራት ይሰጣል ተባለ።
በመርሃ ግብሩ መሠረት ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ለመድረስ መታቀዱን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሃሰን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ከትናንት በስቲያ ይህን የችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ባስጀምሩበት ወቅት የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለመቅረፍ የወጣው የአራት ዓመት እቅድ አካል መሆኑን ገልጸው ነበር። "ለመላው ኢትዮጵያውያን "ኢትዮጵያን እናልብሳት" ብዬ ጥሪ አቀርባለሁ" ሲሉ በፌስቡክ ገጻቸው ጽፈው ነበር። የግብር ሚንስትሩ ዕቅዱ በኢትዮጵያ አነሳሽነት የሚተገበር መሆኑን ጠቅሰው "ኢትዮጵያ ናት ሃሳቡን ያነሳቸው እንጂ ሃገራቱ ይህ ይሰጠን ብለው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የጎረቤት አገራትን ማካተቱ የዲፕሎማሲ አካል መሆኑን አስታውሰው፤ "የባህል ዲሎማሲም ዓይነት ነው። ከሌላ ስጦታም በላይ ተመሳሳይ ሥራ አብሮ ቢሰራ ትልቅ መነቃቃት ይፈጥራል በሚል ነው" ሲሉ አስረድተዋል። መርሃ ግበሩ ከጅቡቲ በመጀመር ወደ ሌሎች አገራት እንደሚቀጥልም ተናግረዋል። ለጎረቤት አገራት ከሚሰጡት አንድ ቢሊየን ችግኞች መካከል ወደ 780 ሚሊዮን የሚሆኑት ችግኞች አይነታቸውም ሆነ የሚፈልጉት የአየር ጸባይ የተለየ መሆኑን እና በቅርብም ማከፋፈል እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የግብርና ሚንስትሩ ኡመር ሃሰን በአገር አቅፍ ደረጃ የሚተከሉት 6 ቢሊዮን ችግኞች በክልል ከተሞች እና በከተማ ዳርቻ አካባቢ ባሉት ቦታዎች እንደሚሆን ተናግረው፤ የክልሎች የችግኞች ድርሻ የሚወሰነው በዝግጅታቸው ልክ ይሆናል ብለዋል። ደን ለመፍጠር ከሚያስችሉ ችግኞች ጎን ለጎን በአጭር ጊዜ ጥቅም የሚሰጡ እንደ አቮካዶ እና ፓፓዬ ያሉትም ይተከላሉ ብለዋል። "ቁጥሩ ከፍ ሲል ሰዉ በደን መልክ ብቻ ስለሚያስብ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ለሌላ ጥቅም ሲያውለው የነበረውን እና ከ3-5 ዓመት እየተከለ የሚጠቀምበትን ማለት ነው። ፍሬውን ሸጦ የሚጠቀምበት ዓይነት ዝርያዎችንም እንዲኖሩ ተደርጎ ነው የተዘጋጀው" ሲሉ ገልጸዋል። እስካሁን በአገር አቀፍ ደረጃ ስለተደረጉ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ውጤታማነት አስመልክተውም "ቀደም ሲል በብሔራዊ ደረጃ ዕድገቱ በጣም የወረደ ነበር። ከ65-72 በመቶ አካባቢ ነበር። አሁን ግን ያሉትን ሁለት ዓመታት አማካይ ስናወጣ አምና ከተተከለው 5.9 ቢሊዮን ችግኞች ውስጥ 87 በመቶ ያህሉ አጸዳደቁ ጥሩ እንደሆነ ታይቷል" ሲሉ መልሰዋል።
42602950
https://www.bbc.com/amharic/42602950
ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት
ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተነሳው ተቃውሞ ከገዢው ፓርቲ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተቋማትን ምርቶችንና አገልግሎቶችን አለመጠቀም እንዲሁም የማጥቃት ሁኔታን አስተናግዷል።
በአገሪቷ መንግሥት በብቸኝነት በሚቆጣጠራቸው እንደ ኢትዮ-ቴሌኮም አይነት ተቋም ባሉበት ሁኔታ ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት ከፍተኛ ቀጣሪ በሆነበት ሀገር ምርትና አገልግሎትን ላለመጠቀም አድማ መምታት (ቦይኮት ማድረግ) የተወሳሰበ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። በተቃራኒውም መንግሥት ህዝቡን መፈናፈኛ በማሳጣቱና ለሚነሱ ተቃውሞዎችም አፀፋዊ ምላሹ ሀይል በመሆኑ ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞ እንደ አንድ ተፅእኖ መፍጠሪያ መንገድ እንደሆነ የሚናገሩም አሉ። ቀዳሚ ኢላማዎች በባለፈው ዓመት በባህርዳር ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ ብዙዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው የሚታወስ ነው። የክልሉ መንግሥት አፀፋዊ ምላሽን በመቃወም እንዲሁም ለሕይወት መጥፋቱ ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባቸዋል የሚሏቸው ድርጅቶችን ያለመገልገል አድማ ታይቷል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ በጥረት ኢንዶውመንት ፈንድና የእንግሊዙ ቫሳሪ ግሎባል ባለቤትነት የሚተዳደረው "ዳሽን ቢራ" አንዱ ነው። የባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆነው አበበ ሰጠኝ 'ዳሽን ቢራን' ከማይጠጡት መካከል አንዱ ነው። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚያነሳው በባህርዳር ከተማ ከነበረ ተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ነው። በአሁኑ ወቅት በባህር ዳር ከተማ በርካታ ሰው የዳሽን ቢራን ፈፅሞ እንደማይጠጣ የሚናገረው አበበ በአንዳንድ መጠጥ ቤቶችም ከራሳቸው አልፈው ሌሎች ሲጠጡ ቢታዩ ከቁጣ አልፎ ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል ይገልፃል። ለዳሽን ቢራ የገብስ አቅርቦት የሚሰጡትን ገበሬዎች ይህ አካሄድ ሊጎዳ እንደሚችል ቢያስብም "ለድሃ ህዝብ ምንም አማራጭ የለም፤ ባለው ነው የሚያምፀው፤ የዳሽን ቢራ ምርት በቀነሰ ቁጥር ገበሬው እንደሚጎዳ እናውቃለን ግን መንግሥትን ማስጠንቀቂያ መንገድ ነው" ይላል። ሌላኛው የዚህ አይነት እርምጃ ተጠቂ በትግራይ ልማት ማህበር መነሻ ካፒታል የተቋቋመው ሰላም የአውቶብስ አገልግሎት ማህበር አንዱ ነው። አሁን ከልማት ማህበሩ ወጥቶ እንደ አክሲዮን ማህበር በ1600 ባለድርሻዎች እንደተቋቋመ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሃጎስ አባይ ይናገራሉ። ምን ገጠማቸው? በቅርቡ ወደ ቁልቢ ገብርኤል በመጓዝ ላይ የነበሩ አራት የሰላም አውቶብሶች ተቃውሟቸውን በሚገልፁ ሰዎች መስታወቶቻቸው እንደተሰበረ አቶ ሃጎስ ያስታውሳሉ። ቀደም ባለው ጊዜም በተለያዩ ቦታዎች ጥቃትም ሁለት አውቶብሶች ተቃጥለዋል። አቶ ሃጎስ ጥቃቱ ሰላም ባስ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አይደለም ቢሉም የተለያዩ ሰዎች አስተያየት ግን ከዚህ ተቃራኒ ነው። በርካቶች በሰላም አውቶብስ ለመሄድ ፍራቻ ላይ ናቸው። "የሰላም ባስ አክሲዮን ማህበር ራሱን የቻለ ከመንግሥት ነፃ የሆነ የባለድርሻ አካላት ስብስብ ነው፤ በብዙዎች ዘንድ ግን የመንግሥት ተቋም እንደሆነ ተደርጎ መታየቱ የግንዛቤ እጥረት ነው" ይላሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘም ከ17 መሥመሮች ውስጥ አራት መሥመሮች በሀረር፣ በድሬዳዋ፣ ጂጂጋና አሶሳ ከሦስት ወራቶች በላይ አገልግሎት መስጠት አቁመዋል። "ከእነዚህ አራት መስመሮች ውጭ ከፍተኛ የሆነ ተፅእኖ አልገጠመንም። በማህበራዊ ድረ-ገፆች የሚወሩት እውነት ነው ከፍተኛ ተፅእኖ ያመጣሉ። ግን የባለፈው ዓመት ገቢ ጋር ስናስተያየው ከመቶ ሺ ብር በላይ ልዩነት የለውም'' አቶ ሃጎስ ይላሉ። የዳሽን ቢራ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሙሉጌታ ማሩ በበኩላቸው የዳሽን ግማሹ ንብረት የአማራ ክልል መንግሥት ኢንዶውመንት ፈንድ የሆነው ጥረት በመሆኑ ብዙዎች መንግሥትን ለመቃወም ቢራውን መጠጣት እንዳቆሙ ይናገራሉ። "በተደጋጋሚ ብዙዎች የሚያነሱት ይህ የጥይት መግዣ ነው የሚሉ አሉ። ግን የትኛው ድርጅት ነው ግብር የማይከፍለው? ይህ ድርጅት ከፖለቲካው ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም" የሚሉት አቶ ሙሉጌታ ለብዙ ወጣቶችም ሥራ እድል ፈጥሯል ይላሉ። በዚህም ምክንያት ባህርዳር ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ደርሶብናልም የሚሉት አቶ ሙሉጌታ፤ ኪሳራ ላይ እንዳልሆኑ ነገር ግን ከባለፉት ዓመታት ጋር ሲወዳደር ትርፋቸው በእንደቀነሰ ይናገራሉ። "በባህርዳር አንዳንድ መጠጥ ቤቶች በሌሎች መብት በመግባት የሚያስፈራሩም አሉ" በማለት ይናገራሉ። በተለይም ባህርዳር ላይ ከሞቱት ሰዎችም ጋር ተያይዞ ሁኔታዎች ቀውስ እንደፈጠሩ አቶ ሙሉጌታ ይናገራሉ። "በድሃ ሀገር ድርጅቶች ወይም ኢንቨስትመንቶች ቢከስሩ የበለጠ የሚጎዳው የሰራተኛው ክፍል ነው'' በማለት የሚናገሩት አቶ ሙሉጌታ ሥርዓቱን መቃወም መብት ቢሆንም የሰዎችን መብት የሚነካና ኢኮኖሚውን የሚያደናቅፍ መሆን ግን የለበትም። አድማ እንደ ፖለቲካዊ ስትራቴጂ? "አንድን የፖለቲካ ሁኔታ ለመቃወም ወይም ጫና ለመፍጠር የተቋማትን ምርትና አገልግሎት አለመጠቀም ሊሆን ይችላል፤ ሁለተኛው ደግሞ በሚገለገለው ማህበረሰብ ውስጥ ጥሩ ምስል እንዳይኖራቸውና ደህንነት እንዳይሰማቸው ማድረግ ነው" በማለት የፓለቲካ ሳይንስ ተንታኟ ህሊና አማረ ትናገራለች። የሚቃወመው ህዝብ ያለውን ሁኔታ በመገምገም ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው የምትለው ህሊና ትክክለኛ መሰረት አለው ወይስ የለውም ለሚለው ጥያቄ መልስ ላይኖረው ይችላል ወይም ከፍተኛ ጥናት ሊፈልግ ይችላል። "ተቃውሞ ከሰማይ አይወርድም። ማህበረሰቡ ፓለቲካውን የተረዳበትን ሁኔታና ለዚያ እየሰጠ ያለውን ምላሽ አድማው ያሳያል። የኢኮኖሚ ግብአቶች ከፖለቲካ ጋር ተሳስረው ላይታዩ ይችላሉ። ያለው የየዕለት ኑሮ ወደ ፖለቲካዊ ሁኔታ ሲያመራ እነዚህ ስፍራዎችም ሆኑ ሁኔታዎች የፖለቲካ ስፍራ ይሆናሉ" ትላለች። አንዳንዶች አድማውን ወይም ጥቃቱን ሃገሪቱ ላይ እንደተፈጠረ ቀውስ ወይም የሽብር ሁኔታ ቢያዩትም በተቃራኒው ለህሊና "ሰዎች አንድን ሥርዓት ልክ አይደለህም ለማለት የሚጠቀሙበት መሳሪያ ነው። የተቃውሞው ዋና መሰረት መንግሥት ራሱ ህብረተሰቡ እንደ የፖለቲካ መሳሪያነት እያያቸው ያሉትን አድማዎች ከማውገዝና ከማዳፈን ይልቅ ከህብረተሰቡ ጋር በጥልቅ ሊወያይ ይገባል" ትላለች። ሕዝቡ ቅሬታውን የሚሰማበት መድረክ ከሌለ እንደዚህ አይነት ተቃውሞዎች እንደሚያይሉም ትገልፃለች። "የኢኮኖሚ ውድቀት ያመጣል ከዚያም በተጨማሪ ባለሀብቶች መንግሥትንና ህብረሰተሰቡን እንደሚያገለግሉ ሳይሆን እንደ ጠላት እንዲታዩ ያደርጋል" ትላለች። እስካሁን ባለው ሁኔታ ለክስተቶች ከውግዘት ይልቅ ፓለቲካዊ መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል የምትለው ህሊና "ማውገዝ የቤተ-ክርስቲያን ሥራ እንጂ የፖለቲካ ሥራ አይደለም" ትላለች። እነዚህ ክስተቶች ዘላቂ የሆኑ ተቃውሞዎች ሳይሆኑ ''ህዝቡ ያለውን ጥያቄ፣ መሰላቸትና መናድድን የሚያሳዩ ናቸው። ንግግሮች፣ ፅሁፎች ያላመጡትን ለውጦችም ማምጣት ይችላሉ" በማለት ህሊና ትገልፃለች። መፍትሄውም መንግሥት ህዝቡ የሚሳተፍበትን ሁኔታ ፈጥሮ በየአካካባቢው ችግሮችን በመቅረፍ ማሳየት አለበት ትላለች። ይህ ካልሆነ ግን ግጭቶች፣ መጠላላት ወይም ጥቃት መድረሱ ሊቀጥል እንደሚችልም ብዙዎች ይናገራሉ።
news-49361985
https://www.bbc.com/amharic/news-49361985
እስራኤል ሁለቱን የኮንግረስ አባላት ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ አገደች
የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት የሆኑት ራሺድ ተሊብ እና ኢልሃን ኦማርን ወደ እስራኤል እንዳይገቡ እገዳ ተጣለባቸው።
ኮንግረስ አባላት የሆኑት ራሺድ ተሊብ እና ኢልሃን ኦማርን የእስራኤል ባለስልጣናት ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ሁለቱ የኮንግረስ አባላት ከዚህ ቀደም እስራኤል የፍልስጤማውያንን ጥያቄ የምታስተናግድበትን አግባብ በተደጋጋሚ በመኮነናቸው ነው ተብሏል። ፕሬዝደንት ትራምፕ የእስራኤል መንግሥት በእነዚህ ሙስሊም የኮንግረስ አባላት ላይ ይህን መሰል ውሳኔን እንዲያስተላልፍ ከፍተኛ ጫና ሲያሳድሩ ነበር። ፕሬዝደንት ትራምፕ ራሺድ ተሊብ እና ኢልሃን ኦማርን ጨምሮ ከሌሎች ሁለት የኮንግረስ አባላት ጋር የቃላት ጦርነት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል። ሁለቱ የኮንግረስ አባላት ከፊታችን እሁድ ጀምሮ በእስራኤል እና በፊልስጤም ግዛቶች ጉብኝት ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ ይዘው ነበር። ይህ የእስራኤል ውሳኔ ይፋ ከመደረጉ በፊት ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ላይ የኮንግረስ አባላቱ እስራኤልን እንዲጎበኙ የሚፈቀድ ከሆነ "ትልቅ ድክመትን ያሳያል። ራሺድ ተሊብ እና ኢልሃን ኦማር እስራኤልን እና አይሁድን ይጠላሉ። ምንም ነገር ቢደረግ ይህን አመለካከታቸውን መቀየር አይቻልም" ሲሉ አስፍረው ነበር። ከእስራሴሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ጋር የቅርብ ግነኙነት ያላቸው ትራምፕ፤ የምክር ቤቱ አባላት በእስራኤል ተቀባይነት የሌላቸው ሰዎች ለማድረግ ከፍተኛ ጥረትን ሲያደረጉ ቆይተዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከኮንግረስ አባላቱ ጋር የቃላት ጦርነት ውስጥ የገቡት ትራምፕ "ዘረኝነት የተሞላበት" በተባለው ነቀፋቸው የኮንግረስ አባላቱ "ወደ መጣችሁበት ወደ ወላጆቻችሁ አገር ተመለሱ" ሲሉ ነቅፈዋቸዋል። ከአንድ ወር በፊት በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር የኮንግረስ አባላቱ እስራኤል እንዲገቡ እንደሚፈቀድ አሳውቀው ነበር። በወቅቱ አምባሳደሩ "ለአሜሪካ ኮንግረስ ካለን አክብሮት እና የሁለቱን ሃገራት ጠንካራ ግነኙነት ከግምት ውስጥ በማስገባት" ሁለቱ ዲሞክራቶች እስራኤል እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል ብለው ነበር። ይሁን እንጂ የእስራኤል የሃገር ውስጥ ሚንስቴር "እስራኤልን ለመጉዳት የሚያስቡ ወደ ሃገሪቱ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል ብሎ ማሰብ አይቻልም" በማለት ሁለቱ የኮንግረስ አባላት ወደ እስራኤል መጓዝ እንደማይችሉ አስታውቋል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ የኮንግረስ አባላቱ ወደ እስራኤል ለመሄድ ያቀዱት የፊታችን እሁድ ነበር። በእስራኤል ቆይታቸውም ፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸውን መንፈሳዊ ቦታዎችን ለመጎብነት ቀጠሮ ይዘው ነበር። ራሺድ ተሊብ በፍልስጤም መንደር ውስጥ የሚኖሩትን ሴት አያታቸውን ለመጎብኘትም አቅደው ነበር። እስራኤል ከዚህ ውሳኔ ከመድረሷ በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከሃገር ውስጥ ሚንስቴር ሚንስትር፣ ከደህንነት አማካሪያቸው እና ከጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ሃሬትዝ የተሰኘው የእስራኤል ጋዜጣ ዘግቧል። ከዚህ ቀደም እስራኤል ከብሄራዊ ደህንነቷ፣ ከምጣኔ ሃብቷ፣ ከባህል እና ከትምህርት ፍላጎቷቸ ጋር የሚነጻጸር አድማ ያደረገ ወደ እስራኤል እንዳይገባ ትከለክላለች።
news-47961614
https://www.bbc.com/amharic/news-47961614
"ለውጡን ለማደናቀፍ ከተቻለም ለመቀልበስ የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ" ኢህአዴግ
የኢህአዴግ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያደርግ የነበረውን መደበኛ ስብሰባ ማጠናቀቁን ከድርጅቱ የወጣው መግለጫ አመለከተ።
መግለጫው እንዳመለከተው ምክር ቤቱ በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በተመለከተ ሰፊ ውይይት ማድረጉን አመልክቶ "ለውጡ ህዝባዊ መሰረት ይዞ እንዳይጓዝ፤ ከተቻለም እንዲቀለበስ የሚጥሩ ኃይሎች የተቀናጀ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን" ጠቅሷል። በተጨማሪም ከፅንፈኛ ብሔረተኝነት፣ ሥርዓት አልበኝነትና የሕግ የበላይነት የማረጋገጥ ፈተናዎች የሃገራዊ አንድነት ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሶ "ይህንን በተባበረ ክንድ በመፍታት ለውጡን ማስቀጠልና ማስፋት ለምርጫ የሚቀርብ ሳይሆን የሀገር ህልውና ጉዳይ ነው" ብሏል። • የምክር ቤቱ ስብሰባ ኢህአዴግን ወዴት ይመራው ይሆን? • "ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት ምክር ቤቱ ባለፉት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን የገመገመ ሲሆን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ያስቻሉ ተጨባጭ እርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውን ጠቅሶ በተለይ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተፈረመው የቃል ኪዳን ሰነድ በሃገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ጉልህ ቦታ ያለው እንደሆነ አመልክቷል። መግለጫው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል ካላቸው ጉዳዮች መካከል በድርጅቱ ውስጥ ስላለው ዴሞክራሲና የአመራር አንድነት፣በአባል ድርጅቶችና በአመራሩ መካከል ይታያል ያለውን መጠራጠር በመፍታት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየቱንና "ሃገርንና ህዝብን ማዕከል ያደረጉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ተፈጥሯል" ሲል ጠቅሷል። ምክር ቤቱ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን አንስቶ የተወያየ ሲሆን የተወሰዱ እርምጃዎች የኢኮኖሚ መቀዛቀዙን በማስተካከል ረገድ በጎ ሚና እንደነበራቸውና በተለይም የውጪ ምንዛሬ ክምችቱን በማሳደግ በኩል የተከናወነውን ተግባር ገምግሟል። በተጨማሪም ከፍተኛ ሥራ አጥነት፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት፣ የብድር ጫና ችግሮች ያልተቀረፉ መሆናቸውን ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ ምክር ቤቱ ተወያይቶ ወስኗል። የህግ የበላይነትን በማስከበር በኩል እየታዩ ያሉ ችግሮችን ለማስተካከል "ማንኛውም ለግጭት እና አለመረጋጋት የሚዳርጉ ሁኔታዎች በግልፅ ተለይተው በአስቸኳይ መታረም እንዳለባቸውና መንግሥትም ህግን የማስከበር ቁልፍ ሃላፊነቱን በጥብቅ መወጣት እንደሚገባው የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል" ሲል መግለጫው አመልክቷል። በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ምክር ቤቱ የተወያየበት ሲሆን ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬያቸው ለመመስለ አስፈላጊውን ጥረት እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል። የውጪ ግንኙነቱንም በተመለከተ ከሁሉም ጎረቤት ሃገራት ጋር መልካም ግንኙነት መመስረቱና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ትብብር እየተካሄደ መሆኑን የጠቆመው የኢህአዴግ ምክር ቤት መግለጫ "በተለይ ከኤርትራ መንግሥትና ህዝብ ጋር የተጀመረው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ወስኗል" ብሏል። የመገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ ለውጦች እንዳሉ ጠቅሶ ነገር ግን "የወደፊት ተልዕኳችንን ለማሳካት የሚያግዙ መልዕክቶችን ከመቅረፅ ይልቅ ባለፉት ጉድለቶች ላይ ብቻ በመንጠልጠል ብሶትን ማራገብ የሚታይበት በመሆኑ በቀጣይ መታረም እንደሚገባው" አሳስቧል። ማህበራዊ ሚዲያውን በተመለከተም አዎንታዊ ሚና እንዳለው ጠቅሶ "ዴሞክራሲውን የማቀጨጭ ሚናው እየጎላ መምጣቱን" ምክር ቤቱ መገምገሙን አንስቶ ከለውጡ ጋር በተዛመደ መልኩ የሚታረምበትን አካሄድ መከተል እንደሚገባና እንዲሁም የጥላቻ ንግግሮችን በሕግ አግባብ መከላከል አስፈላጊ እንደሆነ ምክር ቤቱ እንዳመነበት በመግለጫው አመላክቷል። • "የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ" መሐመድ አደሞ የኢህአዴግ ምክር ቤት ሰኞና ማክሰኞ ባደረገው ስብሰባ ላይ በቀረበው ሰነድና ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት አድርጎ ውሳኔውን በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁም ተመልክቷል።
news-50889366
https://www.bbc.com/amharic/news-50889366
ቱርክ ከዚህ በኋላ ከሶሪያ የሚመጡ ስደተኞችን አልቀበልም አለች
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከዚህ በኋላ ሀገራቸው አዲስ የሚመጡ የሶሪያ ስደተኞችን ማስተናገድ እንደማትችል ገለጹ።
ምንም እንኳን የቱርክ ድንበር አካባቢ ከበድ ያለ ጥበቃና በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በምታዋስነው ኢድሊብ ግዛት በኩል የአይኤስ ታጣቂዎች ቢኖሩም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሶሪያውያንን ወደ ቱርክ ከመሰደድ አላስቆማቸውም። ቱርክ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት 3.7 ሚሊዮን የሶሪያ ስደተኞችን የተቀበለች ሲሆን በዓለማችን ከፍተኛው ቁጥር ነው። • አሜሪካ በቱርክ ላይ ማዕቀብ ልትጥል እየተሰናዳች ነው • በጦርነት የተጎሳቆሉ ስደተኞች መዳረሻቸው የት ነው? ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን እንዳሉት አዲሱ የሶሪያውያን ስደተኞች እንቅስቃሴ ከሀገራቸው አልፎ መላው አውሮፓን የሚያቃውስ ነው። በአማጺያንና ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድን የሚቃወሙ አክራሪ ቡድኖች በሚንቀሳቀሱባት ኢድሊብ ግዛት እስከ ሶስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሶሪያውያን የሚኖሩ ሲሆን መጨረሻቸው እስካሁን አልታወቀም። '' ከ 80 ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከኢድሊብ አቅጣጫ ወደ ቱርክ ድንበር መጥተዋል። እነዚህ ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጭካኔ የማይቆም ከሆነ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ይጨምራል። ቱርክም ብትሆን ተጨማሪ ስደተኞችን የማስተናገድ አቅም የላትም'' ብለዋል ፕሬዝዳንቱ ። • 300 የሶሪያ ስደተኞችን የታደገው ካናዳዊ ቱርክ እንደ አማራጭ የምታቀርበው ደግሞ ሶሪያ ውስጥ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ከኩርድ ኃይሎች ባስለቀቀችው ነጻ ቀጠና ውስጥ ስደተኞቹ እንዲሰፍሩ ነው። ፕሬዝዳንቱ ይህ የማይሆነ ከሆነ እና የአውሮፓ ሀገራት አፋጣኝ መፍትሄ የማያቀርቡ ከሆነ ግን ቱርክ ሁሉም የሶሪያ ስደተኞች ወደ አውሮፓ አልፈው እንዲገቡ በሯን እንደምትከፍትላቸው አስጠንቅቀዋል።
news-54569305
https://www.bbc.com/amharic/news-54569305
ኮሮናቫይረስ፡ ቫይታሚን ዲ ከኮቪድ-19 ይከላከለን ይሆን?
ተመራማሪዎች ቫይታሚን ዲ ሰውነታችን የበሽታ መከላከል ስርዓት ብርታትን በመስጠት ከኮቪድ-19 ጋር ለሚያደርገው ፍልሚያ እገዛ ያደርጋል ወይ? የሚለውን ለማረጋገጥ የሚያስችላቸውን ሙከራ ለማድረግ በጎ ፈቃደኞችን እየፈለጉ መሆኑ ተገልጿል።
በጎ ፈቃደኞቹ ከጸሀይ ብርሀን የሚገኘው ቫይታሚን ዲ እጥረት ካለባቸው ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በፖስታ ቤት በኩል የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ወደቤታቸው ይላክላቸዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎችና ነዋሪዎች ደግሞ የብርዱ ወቅት እየመጣ መሆኑን ተከትሎ የቫይታሚን ዲ እጥረት በሰውነታችሁ ውስጥ ሊፈጠር ስለሚችል እንክብሎቹን ብትወስዱ ጥሩ ነው ተብለዋል። የቫይታሚን ዲ እንክብሎቹ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ለማድረግና ኢንፌክሽኖችን ለመቀነስም በእጅጉ ጠቃሚ ነው ተብሏል። የቫይታሚን ዲ እጥረት የሚታይባቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ እድሜያቸው የገፋና የአፍሪካ አልያም የእሲያ ዝርያ ያለባቸው ሰዎች ሲሆኑ እነዚህ ሰዎች ለኮቪድ-19 ተጋላጭ መሆናቸውም ሌላ አሳሳቢ ነገር ነው። በለንደን ኩዊን ሜሪ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እየተደረገ የሚገኘው ምርምር በባርትስ በጎ አድራጎት ድጋፍ ይደረግለታል። በምርምሩም የቫይታሚን ዲ እንክብሎች ለሰዎች ይታደላሉ። የምርምሩ መሪ የሆኑት ዴቪድ ጆሊፍ እንደሚሉት ''ሙከራው በዚህ ረገድ ጠንከር ያለ ምላሽ ይሰጠናል ብለን እናምናለን'' ብለዋል። አክለውም ''ቫይታሚን ዲ ኮቪድ-19ኝን የመከላከል አቅም ከፍ የሚያደርግ ከሆነ ትልቅ ዜና ይሆናል'' ብለዋል። ''የቫይታሚን ዲ እንክብሎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ የሚገኙ ናቸው፤ በተጨማሪም የጎንዮሽ ጉዳታቸው ዝቅተኛና በቀላሉ መገኘት የሚችሉ ናቸው። ወረርሽኙን ለመዋጋት እየተሰራ ያለው ዓለማ አቀፍ ሰራ በደንብ ሊያግዝ ይችላል'' ምንም እንኳን የቫይታሚን ዲ እንክብሎችን መውሰድ ለጤና ጠቃሚ ቢሆንም ከህክምና ባለሙያዎች ምክር ውጪ መውሰድ ግን የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።
news-54836625
https://www.bbc.com/amharic/news-54836625
የአሜሪካ ምርጫ፡ የትራምፕ ክስ እና የባይደን የሰላም ጥሪ
ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዴሞክራቶች ምርጫውን ለማጭበርበር እየሞከሩ ነው ብለው ከሰዋል።
ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን ደግሞ ቆጠራው እየተካሄደ ስለሆነ ሰከን ማለት ያዋጣል ይላሉ። ባይደን በኔቫዳ እና አሪዞና በጠባብ ውጤት እየመሩ ነው። በፔንስልቬንያ እና ጆርጅያ ደግሞ እየተከተሉ ነው። ባይደን እስካሁን የ73 ሚሊዮን መራጮችን ድምጽ አግኝተዋል። ይህም በአሜሪካ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ታሪክ ትልቁ ነው። ትራምፕ 70 ሚሊዮን የሚጠጋ ድምጽ መሰብሰብ ችለዋል። ትራምፕ ምን አሉ?“ ሕጋዊ ድምጾች ከተቆጠሩ አሸንፋለሁ” ብለዋል። ነገር ግን ዴሞክራቶች ምርጫውን ለማጭበርበር እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል። ትራምፕ ይህንን ክስ የሚሰነዝሩት ያለ ማስረጃ ነው። በቁልፍ የውድድር ግዛቶች በሰፊ ልዩነት እየመሩ እንደነበረና ከዛም “ሳይጠበቅ ቁጥሩ እንዳሽቆለቆለ” ይናገራሉ። የትራምፕ ተቺዎች እንደሚሉት፤ ቁጥሩ የቀነሰው ከባይደን ደጋፊዎች አብዛኞቹ ድምጻቸውን በፖስታ ስለላኩ ነው። ለወትሮው ትራምፕን የማይተቹ ሪፐብሊካኖች፤ የፕሬዘዳንቱን ንግግር ኮንነዋል። ሚት ሮምኒ “ድምጹ ይቆጠራል። ሕግ ከተጣሰ ይጣራል። በዴሞክራሲያችን፣ በሕገ መንግሥታችን እና በሕዝባችን እምነት እናሳድር” ብለዋል። የሜሪላንድ አገረ ገዢ ሌሪ ሆገን የፕሬዘዳንቱ ንግግር ዴሞክራሲን ያጣጣለ ነው ብለዋል። ባይደን ምን አሉ? ባይደን እንደሚያሸንፉ አምነው አገሪቱ እንድትረጋጋ ጥሪ አቅርበዋል። “ዴሞክራሲ አንዳንዴ ትዕግስት ይጠይቃል። ትዕግስተኛነት ለ240 ዓመታት ጠቅሞናል። ዓለም የሚቀናበት ሥርዓት አለን” ሲሉም ተደምጠዋል። ቆጠራው ሲጠናቀቅ ውጤቱ እንደሚታወቅ እና እስከዛ ግን ሕዝቡ መስከን እንደሚገባው ተናግረዋል። ዋና ዋና በሚባሉ ከተሞች የሁለቱም ተወዳዳሪዎች ደጋፊዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። በሌላ በኩል ድምጽ እየተቆጠረ ያለው ያለ ታዛቢ ነው የሚልና ሌላም ውንጀላ የሚሰነዝሩት ትራምፕ፤ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ደፍርድ ቤት እንደሚወስዱት ተናግረዋል። ውድድሩ ምን ላይ ደርሷል? የዊስኮንሰን፣ ፔንስልቬንያ፣ ኔቫዳ፣ አሪዞና፣ ጆርጅያ፣ ሚሺገን እና ኖርዝ ካሮላይና ውጤት ገና አልታወቀም። ሆኖም ባይደን ሚሺገን እንዳሸነፉና ዊስኮንሰንን የማሸነፍ ሰፊ እድል እንዳላቸው ተነግሯል። ባይደን እስካሁን 253 የኤሌክቶራል ኮሌጅ ድምጽ አግኝተዋል። ትራምፕ ደግሞ 214። ለማሸነፍ 270 ድምጽ ያስፈልጋል። ባይደን በፔንስልቬንያ ወይም በተቀሩት ሁለት ግዛቶች ካሸነፉ ሊመረጡ ይችላሉ።ትራምፕ ደግሞ ፔንስልቬንያን እንዲሁም ተጨማሪ ሦስት ግዛቶች ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል። የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ክስ ለመመስረት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያሰባሰቡ ነው። ድምጽ ቆጣሪዎች ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ታገሱ ብለዋል። ፕሬዘዳንቱ ምን ብለው ከሰሱ? ምርጫው ግልጽነት የለውም ያሉት ትራምፕ፤ የዊስኮንሰን ድምጽ በድጋሚ ይቆጠር ብለዋል። በዚህ ግዛት ትፈምፕ ባይደንን በ20,000 ድምጽ እየመሩ ነበር። ትራምፕ የሚሺገን እና ጆርጅያ ቆጠራ ላይም ቅሬታ አቅርበዋል። ጆርጅያ ውስጥ 53 ዘግይተው የደረሱ ድምጾች ተቆጥረዋል ብለው ቢከሱም፤ ፍርድ ቤት ማስረጃ አላገኘሁም ብሏል። ትራምፕ በፔንሰልቬንያ ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት አግኝቶ፤ የሪፐብሊካን ታዛቢዎች ቆጠራውን በቅርበት እንዲከታተሉ እንዲፈቀድ ተወስኗል። ዴሞክራቶች ይህንን ውሳኔ ጥሰው ሪፐብሊካን ታዛቢዎችን ከቆጠራው እንደተከላከሉ ተገልጿል። የኔቫዳ የሪፐብሊካን ፓርቲ ክንፍ፤ ቢያንስ 3,062 ድምጾች ተጭበርብረዋል ሲል ለፍትሕ ሚንስቴር ቅሬታ አሰምቷል። ግዛቱን የለቀቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ድምጽ እንደሰጡ ተነግሯል። የትራምፕ አጋርና የቀድሞ የነቫዳ ዓቃቤ ሕግ አዳም ላክሴት “የሞቱ ሰዎች ድምጽም ተቆጥሯል” ብለዋል። የባይደን የሕግ አማካሪዎች በበኩላቸው፤ ክሶቹ “መሠረተ ቢስ ናቸው” ብለዋል።
news-46970450
https://www.bbc.com/amharic/news-46970450
አቶ በረከት ስምኦንና እና አቶ ታደሰ ካሳ በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ባህር ዳር ተወሰዱ
አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።
የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽነር አቶ ዝግአለ ገበየሁ በሰጡት መግለጫ፤ ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈፀመው በክልሉ በመሆኑ ጉዳያቸው በክልሉ ፍርድ ቤት ስለሚታይ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ባህር ዳር መወሰዳቸውን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት በግለሰቦቹ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችለኝን ከበቂ በላይ ማስረጃ ሰብስቢያለሁም ብሏል።እንደ መግለጫው ከሆነ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ በቁጥጥር ስር የዋሉት በጥረት ኮርፖሬት የሃብት ብክነት ፈጽመዋል በመባል ተጥርጥረው ነው። በቀድሞ ስሙ ብአዴን እና በአሁኑ መጠሪያው የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መታገዳቸው ይታወሳል። የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦንን እና አቶ ታደሰ ካሳን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማገዱን ያስታወቀው ነሐሴ 18/2010 ዓ.ም ነበር። ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች አንዱ የነበሩት አቶ በረከት የቀድሞ የማስታወቂያ ሚንስቴር ሚንስትር በኋላም የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር እንዲሁም በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል። የአማራ ክልል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዝግአለ ገበየሁ በሰጡት መግለጫ "የአዋጭነት ጥናት ሳይከናወን ግዥ መፈፀሙ ጥረትን ለኪሳራ ዳርጎታል፤ ቀሪ ምርመራ የሚጠበቅ ሆኖ፤ እነዚህ እስካሁን የያዝናቸው ማስረጃዎች ክስ ለመመስረት የሚስችሉ ናቸው ብለን እናምናለን" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ምርመራውን የበለጠ ለማቀላጠፍ ሲሆን ሌሎች ተጠርጣሪዎችም እንደሚኖሩ አክለዋል። "የዳሸን ቢራ ፋብሪካ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የዳሸን ቢራ ሽያጭ የወሰኑት አቶ በረከት ብቻ ሊሆኑ አይችሉም። በቦርድ ስለሆነ የሚወሰነው ሌሎች ተጠያቂዎች ይኖራሉ'' ሲሉ ተደምጠዋል ኮሚሽነሩ። "ግለሰቦች በሕዝብ ሃብት፤ በጥረት ሃብት ያለአግባብ እንዲጠቀሙ ተደርጓል። ኃላፊዎቹ ሥራቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ምክንያት በጥረት ስር ባሉ በአምስቱም ኩባንያዎች ላይ ኪሳራና ዕዳ ነው የሚታየውም ብለዋል። ''ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሥራ ጊዜ የወሰደብን ደግሞ ለፍርድ ቤት በሚቀርብ መልኩ ኦዲቱ በአግባቡ መደራጀት ስለነበረበት ነው" በማለት ጉዳዩን አስረድተዋል ኮሚሽነር ዝግአለ። አቶ በረከት ከጥቂት ወራት በፊት ከቢቢሲ አማርኛ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ለመመልከት ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይከተሉ። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» በትግል ስማቸው 'ጥንቅሹ' ተብለው የሚታወቁት እና የጥረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ታደሰ ካሳም ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር ከብአዴን ማዕከላቂ ኮሚቴ መታገዳቸው ይታወሳል። ቢቢሲ አማርኛ አቶ ታደስ በጥረት ኮርፖሬሽን ውስጥ የነበራቸው ተሳትፎ ምን ይመስል እንደነበረ እና የብአዴንን ውሳኔውን እንዴት አገኙት ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር። ከአቶ ታደሰ ጋር የነበረንን ቆይታ ከዚህ በታች መመልከት ይችላሉ። • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው"
news-48908026
https://www.bbc.com/amharic/news-48908026
አትሌት ሃጎስ፡ ''ምን እንደተፈጠረ አልገባኝም። ይህ ግን የህይወቴ ትልቁ ገጠመኝ ነው"
ባለፈው አርብ በስዊዘርላንድ በተደረገው የዳይመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አንድ አስገራሚ ነገር ተከስቷል።
አትሌት ሃጎስ ገ/ሕይወት ውድድሩን በሰፊ ርቀት ሲመራ የነበረው ኢትዮጵያዊው አትሌት ሃጎስ ገብረሕይወት ገና አንድ ዙር ሲቀረው ጨርሶ ያሸነፈ መስሎት ሩጫውን በማቆም ደስታውን ሲገልጽ ከኋላ በነበረው ዮሚፍ ቀጄልቻ ተቀድሟል። አትሌት ሃጎስ ''የጨረስኩ ነው የመሰለኝ፤ ምን እንደተፈጠረ አልገባኝም። ይህ የህይወቴ ትልቁ ገጠመኝ ነው" ሲል ለቢቢሲ ስለ ነበረው ሁኔታ ተናግሯል። • "ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ የ25 ዓመቱ አትሌት ሃጎስ ገ/ሕይወት በአትሌቲክሱ ልምድ ካላቸው የወቅቱ አትሌቶች መካከል የሚጠቀስ ነው። በሪዮው ኦሎምፒክ በ5 ሺህ ሜትር የነሃስ ሜዳልያ ባለቤት ሲሆን በዓለም ሻምፒዮና በርካታ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል። ከዚህ በተጨማሪም ሃጎስ በሃገር አቋራጭ እና በዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ድልን ተጎናጽፏል፤ ዓርብ ዕለት ያጋጠመው ግን ለእርሱም ትንግርት ሆኖበታል። ሃጎስ ውድድሩን እንደማሸንፍ ''በራሴ ተማምኜ ነበር። ስሜት ውስጥ ገብቼ ነበር። የሆነው ነገር ለእኔም ግራ ገብቶኛል" በማለት የተፈጠረው ነገር ለእርሱም ጥያቄ እንደሆነበት ደጋግሞ ተናግሯል። "ሰው ሲደግፈኝና ሲያበረታታኝ፣ ጭብጨባውም ሲደምቅ ውድድሩን የጨረስኩ መሰለኝ። ከዚያ ሩጫውን አቋረጥኩት" ብሏል አትሌቱ። • "አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው የአለም ሪከርድን መስበር ነው" ዮሚፍ ቀጀልቻ ሃጎስ አንድ ዙር እየቀረው ያሸነፈ መስሎት ደስታውን እየገለጸ ሳለ የውድድሩን ዳኞች እና ከመሮጫ መሙ አቅራቢያ ያሉ ሰዎች ውድድሩ እንዳላለቀ ሲነግሩትና እሱም የተቀሩት ተወዳዳሪዎች ሩጫቸውን መቀጠላቸውን ሲመለከተ ነው እንደገና ወደ ሩጫው የተመለሰው። በዚህ ምክንያት በቅርብ ርቀት ሲከተለው የነበረው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አንደኛ ሆኖ ሲጨርስ ሃጎስ የአስረኛ ደረጃን ይዟል። ''ውድድሩን ያሸነፈውን ዮሚፍ ቀጄልቻን እንኳን ደስ ያለህ ብዬዋለሁ። አሰልጣኞቹም 'ሊፈጠር የሚችል አጋጣሚ ነው' በማለት አበረታተውኛል'' ብሏል ሃጎስ። • በዋግ ኸምራ አስተዳደር 7 የዳስ ት/ቤቶች አሉ "ቢሳካልኝ አሪፍ ነበር፤ አልተሳካም፤ በጸጋ መቀበል ነው" የሚለው ሃጎስ ከክስተቱ በኋላ በርካታ የስልክ ጥሪዎች እየደረሱት እንደሆነ እና አብኛዎቹም 'አይዞህ በርታ የሚያጋጥም ነው' የሚሉ ናቸው" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። በቀጣይ ሁለት የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ይቀሩኛል የሚለው ሃጎስ፤ ለእነዚህ ውድድሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ልምምድ እያደረገ መሆኑን ተናግሯል።
news-54039328
https://www.bbc.com/amharic/news-54039328
ትራምፕ በጦር ሜዳ የተገደሉ አሜሪካውያን ወታደሮችን "ተሸናፊዎች" እና "ልፍስፍሶች" አላልኩም አሉ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በግዳጅ ላይ ሳሉ የተገደሉ የአሜሪካ ወታደሮችን ''ተሸናፊዎች'' እና ''ልፍስፍሶች'' ሲሉ ተሳድበዋል መባሉን ተከትሎ በርካቶች በፕሬዝዳንቱ ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
ትራምፕ በግዳጅ ላይ ሳሉ የሞቱ የአሜሪካ ወታደሮችን ''ተሸናፊዎች'' እና ''ልፍስፍሶች' ብለው ጠርተዋል ብሎ የዘገበው 'ዘ አትላንቲክ' የተሰኘው መጽሄት ነበር። ከዚያም 'አሶሺየትድ ፕሬስ' እና 'ፎክስ ኒውስ' ይህን ዘገባ የሚያጠናክሩ ምልከታዎች ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ ፕሬዝደንቱ እና አስተዳደራቸው ይህን እንዳላሉ ተናግራዋል። • ጆ ባይደን ፕሬዝዳንት ከሆኑ የሚለወጡ 8 ጉዳዮች • ሰባት ጊዜ በጥይት የተመታው አሜሪካዊ አባት ትራምፕን ማግኘት አልፈልግም አሉ የአሜሪካ ፖለቲካ ተንታኞች፤ ትራምፕ ሰጡት የተባለው አስተያየት የአሜሪካ ጦር አባላት ቤተሰቦች በቀጣዩ ምርጫ ድጋፍ እንዳይሰጧቸው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ። ትራምፕ አሉ የተባለው ምንድነው? እንደ ዘ አትላንቲክ ዘገባ ከሆነ ትራምፕ እአአ 2018 ላይ በፈረንሳይ የሚገኘውን የአሜሪካ ወታደሮች መቃብር ስፍራ ለመጎብኘት የነበራቸው እቅድ የተሰረዘው የመቃብር ስፍራው "በተሸናፊዎች የተሞላ ነው" ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ዘ አትላንቲክ አራት ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው ከሆነ ትራምፕ ወደ ፈረንሳይ የመሄዱን ጉዞ ውድቅ ያደረጉት ዝናቡ ጸጉራቸውን ሊያበለሻሸው ስለሚችል እና በጦርነት የተገደሉ አሜሪካውያንን መዘከር አስፈላጊ ነው ብለው ስለማያምኑ ነው። በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከጀርመን ጋር ተዋግተው ፈረንሳይ ውስጥ የሞቱ 1800 አሜሪካውያንን ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ልፍስፍሶች" ሲሉ ጠርተዋቸዋል ብሏል ዘ አትላንቲክ በዘገባው። 'ቤሎው ውድ' በተሰኘው የጦር አውድማ የአሜሪካ ወታደሮች የጀርመን ጦር ፓሪስን እንዳይቆጣጠር በከፈሉት መሰዋእትነት ይወደሳሉ። በወቅቱ ዋይት ሃውስ ትራምፕ ወደ ፈረንሳይ ያልሄዱበት ምክንት የአየር ጸባዩ የፕሬዝደንቱን ሄሊኮፍተር ማንቀሳቀስ ስላላስቻለ ነው ብሎ ነበር። • ባይደን ከተመረጡ "የአሜሪካን ሕልም ይቀጫል" ፡ ትራምፕ ዘ አትላንቲክ በዚህ ዘገባው ላይ የምንጮቹን ማንነት አይጥቀስ እንጂ አሶሺየትድ ፕሬስ እና የፎክስ ኒውስ ዘጋቢዋ በዘገባው ከተጠቀሱት መካከል የተወሰኑ እውነታዎችን ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል። ከዘገባው በኋላ ምን ተባለ? በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ የትራምፕ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ጆ ባይደን፤ ትራምፕ አሜሪካንን ለመምራት "ብቁ" አይደሉም ሲሉ ተችተዋል። "ይህ ዘገባ እውነት ሆኖ የሚገኝ ከሆነ- ከዚህ ቀደም ካለው ነገር በመነሳት እውነት ሊሆን ይችላል- ይህ በጣም አዋራጅ ነው። አሳፋሪ ነው" ብለዋል ጆ ባይደን። በኢራቅ ግዳጃቸውን ሲወጡ ሁለት እግራቸውን ያጡት ዲሞክራቲኩ ሴናተር ታሚ ዳክዎርዝ፤ "ትራምፕ ለእራሱ ሲል የአሜሪካን ወታደሮች ለመጠቀም ይሞክራል" ብለዋል። ዘገባው ከወጣ በኋላ ዶናልድ ትራምፕን አጥብቀው ከኮነኑት መካከል የቀድሞ የአሜሪካ ጦር አባላት ይገኙበታል። 'ቮትቬትስ' የሚባለው የቀድሞ ዘማቾች ስብሰብ የሆነው ቡድን፤ ልጆቻቸው በግዳጅ ላይ ሳሉ የተገደሉባቸው ወላጆች ምስክርነትን የያዘ ተንቀሳቃሽ ምስል ይዞ ወጥቷል። በምስሉ ላይ የሚታዩት ወላጆች፤ "ልጄ ተሸናፊ አይደለም"፣ "ልጄ በኢራቅ የተገደለው አገሩን በኩራት ሲያገለግል ነው"፣ "ልጅን ማጣት ምን ማለት እንደሆነ ዶናልድ ትራምፕ ሊገባው አይችልም" ሲሉ ተደምጠዋል። • "ዶናልድ ትራምፕ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ያለፉት ሰው ተፈትኖላቸው ነው" ትራምፕ በጉዳዩ ላይ ምን አሉ? ፕሬዝደንት ትራምፕ ይህን ዘገባ "ሐሰተኛ ዜና" ነው ብለውታል። ትራምፕ "ማንም ያላደረገውን ለጦር አባላት የደሞዝ ጭማሪ አድርጊያለሁ። ይህን ሁሉ እያደረኩ መስዕዋት ስለሆኑ ጀግኖቻችን እንዲህ አይነት አሉታዊ አስተያየት ልሰጥ አልችልም። ይህ አጸያፊ ዘገባ ነው። አሳፋሪ በሆነ መጽሄት" ብለዋል። ትራምፕ ትናንት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ የዚህ ዘገባ ምንጭ የቀድሞ የዋይት ሐውስ ባልደረባ ጆን ኬሊ ሳይሆን እንደማይቀር ጠቁመዋል። ትራምፕ ጆን ኬሊ የሥራውን ጫና መቋቋም ተስኖት ነበር ብለዋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ፣ የመከላከያ ሚንስትሩ ማርክ ኤሰፐር እና የዋይት ሐውስ ባልደረባ ሚክ ሙለቫኔይ ትራምፕ ይህን መሰል አስተያየት እንዳልሰጡ ተከላክለው ተናግረዋል።
44920776
https://www.bbc.com/amharic/44920776
'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት
ሁሉም ጋዜጠኛ በሆነበትና ተጠያቂነት በሌለበት በማህበራዊ ድር አምባ ዘመን 'ፌክ ኒውስ' ወይም 'ሃሰተኛ ዜና' በከፍተኛ መጠን እየተሰራጨ ነው።
በተለይም የሃገራት የሚዲያ ሕጎች በዜጎች ላይ ተግባራዊም ስለማይደረጉባቸው ሃሰተኛ ዜናዎችን ለግልም ይሁን ለፖለቲካዊ ፍጆታ ማስፋፋት የተለመደ ሆኗል። 'ሃሰተኛ ዜና' ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት እየተፍጨረጨሩ ላሉም ሆነ 'ዴሞክራሲን ለእኛ ተዉት' ላሉ ሃገራት አደጋ እየጋረጠ ያለ ጉዳይ ሆኗል። ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አፍ ጠፍቶ የማያውቀው ይህ ቃል ፈረንጆቹ የ2017 አወዛጋቢው ቃል ሲሉ መርጠውታል። • በደሴ ከተማ የሸዋበር መስጂድ ላይ በደረሰ ጥቃት ሰዎች ተጎዱ • የኤምሬትስና የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ፖለቲካ? ወደ ሃገራችን ስንመጣም ሃሳዊ ዜናዎች ለበይነ መረባዊ ጥቃት (ሳይበር አታክ) ከመዳረግ አልፈው በየሥፋራው እየተስተዋሉ ላሉ ማንነትን መሠረት ላደረጉ ግጭቶች መንስኤ እስከመሆን ደርሰዋል። የፋይናንስና ኦዲቲንግ ባለሙያው አቶ ታምሩ ሁሊሶ በፌስቡክ ገፃቸው የሃሰተኛ ዜናዎችን በመንቀፍ ይታወቃሉ። «ለሃሰተኛ ዜና አሰራጭ ግለሰቦች የአሁኑን የመሰለ የተመቻቸ ጊዜ እና ሁኔታ የለም፤ በተለይ ደግሞ በማሕበራዊ ድረ-ገፆች ላይ» ይላሉ። አቶ ታምሩ 'የሰጠ ጊዜ' ብለው የሚያስቀምጡት ወቅቱ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች እዚህም እዚያም መነሳታቸውን ዋቢ በማድረግ ነው። «ሰዉ አሁን ስጋት ላይ ነው ያለው፤ በእዚህ ስጋት ላይ እዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ነገር ተፈጥሯል የሚል ሃሰተኛ ዜና ሲጨመርበት ከማመን ወደኋላ አይልም።» • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ • የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' እውነታ ጣል የተደረገበት ልብ-ወለድ ሃሰተኛ ዜና ሰው ጆሮ እውነት ያለው ዜና መስሎ ይደርስ ዘንድ መጀመሪያ የተፈጠረ ነገር አለ ማለት ነው በማለት የማሕበራዊ ድረ-ገፅ ተጠቃሚው አቶ ተስፋዬ ሰሙንጉሥ ይናገራሉ። በፌስቡክ ገፃቸው እውቀትን በማካፈል የሚታወቁት አቶ ተስፋዬ «ሃሰተኛ ዜና ከመሬት አይነሳም» ባይ ናቸው። «ለምሳሌ. . .» ይላሉ አቶ ተስፋዬ «ለምሳሌ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ አንድ ሃሰተኛ ዜና ቢሰራጭ ተቀባይነት የማግኘቱ ነገር ሰፋ ያለ ነው። ብጥብጥ ያለበት ቦታ እንዲህ ዓይነት ነገር ተፈጥሯል በማለት ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልዕክት ያስተላልፋሉ።» በእንግሊኛ አጠራሩ 'የሎ ጆርናሊዝም' በመባል የሚታወቀውን ሃሰተኛ ዜና የማሰራጨት ዘዴ አቶ ተስፋዬ «እውነታ ጣል የተደረገበት ልብ-ወለድ ሲሉ ይጠሩታል። «ሰዎች ሃሰተኛ ዜናዎችን የሚያሰራጩት ለዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ሊሆን ይችላል። በጎም ይሁን አሉታዊ ዓላማ ያዘለም ሆኖ ብናገኘው አይገርምም። ሰዎች ሃሰተኛ ዜና የሚያሰራጩት ማስታወቂያ ለመሥራት ሊሆን ይችላል፤ በጎ ሃሳብ ለማስተላለፍ አልያም ፕሮፓጋንዳቸውን ለማስፋፋትም ይሆናል።» ከደመናው በላይ ያለ አደጋ አቶ ተስፋዬም ሆነ አቶ ታምሩ የሚስማሙት ሃሰተኛ ዜናዎች ብዙ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል አደጋ እንዳላቸው ነው፤ በተለይ ደግሞ አሁን ባለው የሃገሪቱ ሁኔታ። «ጠንካራ ወገብ ያላቸው ዴሞክራሲያዊ ተቋማት በሌሉበት፣ ሁኔታዎች ባልተረጋጉበት፣ ያኮረፉ ኃይሎች ባሉበት፣ ብዙ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በሚታዩበት፣ ሰዎች ፍርሃት ተጭኗቸው እያየን ሃሰተኛ ዜና ማሰራጨት አደጋው ከፍ ያለ ነው» ሲሉ አቶ ታምሩ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። «ማዕከላዊ አፍሪካ በተከሰተ ግጭት ላይ የተነሳን ዘግናኝ ግድያ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ተለጥፎ የሚያምን ሰው ካለ ይህ የሚነግረን እንዲህ ዓይነት ድርጊት እኛ ሃገር ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት ያለበት ማሕረሰብ አለ ማለት ነው» ሲሉ ያክላሉ። አቶ ተስፋዬ አደጋውን በማሕበራዊ፣ ሐይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ አንደምታው ከፋፍለው ያዩታል «ፖለቲካዊ አደጋው አንድን ሃገር ሙሉ በሙሉ እስከማውደም የሚደርስ ተፅዕኖ አለው» ሲሉ ያስረዳሉ። «መሰል ዜናዎችን ለበጎ ዒላማ የሚጠቀሙባቸው ሰዎች ያሉትን ያህል በጎ ላልሆነ ዓላማ ጥቅም ላይ ሲውል የሚያመጣው አደጋ እጅጉን አስጊ ነው።» ማንን እንመን. . .? ታድያ ሃሰተኛ ዜናዎች በሚያሳምን መልኩ የሚመጡ ከሆነ ማንን እንመን? እንዴትስ ነው እውነታውን ከሃሰተኛው የምንለየው? ለአቶ ታምሩ በተለይ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ የሚሰራጩ ዜናዎችን ለይቶ «ይህ ሃሰት ነው ይህ እውነተኛ ነው» ለማለት የሰዎች የማገናዘብ እና የትምህርት ደረጃ ወሳኝ ነው። «ተረጋግቶ ማገናዘብ እንጂ እያንዳንዱ ሰው ቴክኖሎጂውን ተጠቅሞ የዜናውን እውነተኛነት ያራጋግጥ ማለት ከባድ ነው።» አቶ ተስፋዬም በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ፤ «የዜናው ምንጭ ማን ነው? ብሎ መጠየቅ እጅጉኑ ያሻል» ይላሉ። «ለምሳሌ እናንተ አንድ ዜና ስትሰሩ የድርጅታችሁን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ተከትላችሁ፣ መረጃ፣ ማስረጃ ሰብስባችሁ እማኝ አናግራችሁ ነው። ሌላውም ተዓማኒነት ያለው ተቋም የሚያደርገው ይህንኑ ነው። ታዳሚያን ይህንን ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ ያስፈልጋል።» «ዜናውን አይተን ወዲያውኑ ፍርድ ከምንሰጥ ይልቅ ማጣራት መልመድ ብንችል በጎ ነው፤ ዜናው ካጠራጠረን ቢያንስ ጉግል ብናደርግ የተሻለ ነው» ሲሉ አቶ ተስፋዬ ይመክራሉ። «ሃሰተኛ ዜናዎችን የሚያመጡትን አደጋ ለመዋጋት የማሕበረሰቡ ንቃተ ኅሊና ወሳኝ ነው፤ የትኛው ተቋም ነው ይህን ዜና ያሰራጨው? የትኛው ግለሰብ? ብሎ መጠየቅ አስፈላጊነቱ ላቅ ያለ ነው። ጊዜን እና ሁኔታን ከግምት ውስጥ ማስገባትም ያሻል» ይላሉ አቶ ተስፋየ። «መንግሥት ደግሞ. . .» ይላሉ አቶ ታምሩ «መንግሥት ደግሞ ሕብረተሰቡን የማረጋጋት ሥራ ጠዋት ማታ ሳይል ሊሠራ ይገባል፤ ዋናው ነገር እሱ ነው። ነገ መጥፎ ነገር ይከሰታል የሚለውን ጭንቀት ከሕብረተረሰቡ ውስጥ መንቀል አለበት» ባይ ናቸው። ከሃሰተኛ ዜና እንጠበቅ!!! ሃሰተኛ የሆነ ዜና አጋርተው ወይም ተጋርተው ያውቃሉ? እዚህ ቦታ ቦንብ ፈነዳ. . . እከሌ/እከሊት እኮ ሞተ/ሞተች. . .ብቻ ትኩስ ያሉትን ዜና ለወዳጅ ዘመድዎ አጋርተው/ተጋርተው ያውቁ ይሆን? ቆም ብለው ይህ ነገር እውነት ይሆን ወይስ የተፈበረከ ነው ብለው ራስዎን ጠይቀው ያውቃሉ? ባለሙያዎች ይህን እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ዜናውን ከማጋራትዎ በፊት ታማኝ ከሚሉት ምንጭ መምጣት አለመምጣቱን ያረጋግጡ፤ ጋዜጣ፣ ቴሌቪዥን፣ ራድዮ ወይም የበይነ መረብ ምንጭ ሊሆን ይችላል፤ ብቻ ማረጋገጥ የመጀመሪያ ሥራዎ መሆኑን አይዘንጉ። ዜናው ታማኝ ከሚሉት አንድ ምንጭ መጥቶም ሊሆን ይችላል፤ ሌሎችስ ስለዚህ ዜና ምን አሉ? ብለው ራስዎን ይጠይቁ። ተንቀሳቃሽ ምስል ሊሆን ይችላል ወይም ፎቶግራፍ ምን ያህል እውነት ያዘለ ነው? ብለው መመርመርዎንም አይዘንጉ። ሃሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች ተመሳሳይ ይዘት እና ቅርፅ ያላቸው ፎቶዎችም ይሁኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ከማዛመት ወደኋላ አይሉምና። በተለይ ፌስቡክ እንዲሁም ዩትዩብ የተሰኘው የተንቀሳቃሽ ምስል መጋሪያ መድረክ ላይ ከማስታወቂያ ገንዘብ ለማግኘት ብለው ሃሰተኛ ዜና የሚያሰራጩ የበረከቱበት ዘመን ነው።
news-48803469
https://www.bbc.com/amharic/news-48803469
ጄኔራል አደም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ
ጄኔራል አደም መሐመድ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ።
ጄኔራል አደም መሐመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከጄኔራል አደም ሞሐመድ በተጨማሪ ሌፍ/ ጄኔራል ሞላ ኃ/ማርያምን የምድር ኃይል አዛዥ፤ ደመላሽ ገ/ሚካኤልን ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በትዊተር ገፁ አስፍሯል። ጄነራል አደም መሐመድ የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ነበሩ። ጄነራል አደም የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት ኃላፊ ሳሉ ደመላሽ ገ/ሚካኤል ምክትላቸው ነበሩ። • የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ ከሥልጣናቸው ተነሱ ጄኔራል አደም መሐመድ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለአንድ ዓመት ያክል አገልግለዋል።
54798221
https://www.bbc.com/amharic/54798221
በትግራይ የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል
በትግራይ ክልል ከትናንት ሌሊት ጀምሮ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት መቋረጡ ተገልጿል።
በኢንተርኔት ነፃነት ላይ የሚሰራው ኔት ብሎክስ የተሰኘው ድርጅትም ከዛሬ ዕለት ጥዋት ጀምሮ ኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት መቋረጡንም አስታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ ከጥዋት ጀምሮ የመብራት አገልግሎት ተቋርጧል፤ ባንኮች ተዘግተዋል። መቀሌ የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ እንደገለፀው ኢትዮ-ቴሌኮም መስሪያ ቤት የተዘጋ ሲሆን ሰራተኞችም በሩ አካባቢው ይታያሉ ብሏል። በርካቶች በእግር እየተንቀሳቀሱ ሲሆን በህዝቡም ዘንድ ግራ የመጋባት ሁኔታ እንደሚታይና ዝርዝር መረጃዎች እየወጡ እንዳልሆነ በተጨማሪ ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ክልል ቴሌቪዥንም ሆነ ድምፂ ወያነ የሚሰሩ ሲሆን የተለመደ ፕሮግራማቸውን እያስተላለፉም ይገኛሉ። ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ኃይሎች ሲንቀሳቀሱ እየታየ የነበረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ክልሉን በሚያስተዳድረው ሕወሃት ላይ ጦርነት መከፈቱን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው የመከላከያ ሠራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ "ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል" ብለዋል። ትናንት ሌሊት (ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም) ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ በመቀሌና አስራ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኩዊሃ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር የቢቢሲ ዘጋቢ ከስፍራው አድርሷል። እስካሁን ድረስ ከትግራይ ክልል በኩል ምንም አይነት መረጃ ያልተገኘ ሲሆን የህወሃት ከፍተኛ አመራር ጌታቸው ረዳ ትናንት ሌሊት "ወንድምና እህቶች ተረጋጉ" በማለት በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረው ነበር።
news-55960667
https://www.bbc.com/amharic/news-55960667
በሚየንማር ተቃውሞ መበርታቱን ተከትሎ ኢንተርኔት ማቋረጡ ተገለፀ
የሚየንማር ጦር መሪዎች የአገሪቱን ኢንተርኔት መዝጋታቸውን የዓለም አቀፍ ኢንተርኔትን ፍሰት የሚከታተለው ቡድን አስታወቀ።
ሚያናማር ተቃዋሚዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚየንማር ወታደር ያካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም ሠልፍ እያካሄዱ ነው። ኔት ብሎክስ የተሰኘው የኢንተርኔትን ፍሰት የሚከታተለው ተቋም የአገሪቱ የኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ ሊባል ደረጃ መቋረጡን አስታውቋል። የቢቢሲ በርማ ቋንቋ አገልግሎትም የኢንተርኔት መቋረጡን አረጋግጧል። ወታደራዊ ኃይሉ ሰኞ ዕለት መፈንቅለ መንግሥት ካካሄደ ወዲህ ትልቁ ነው የተባለ የተቃውሞ ሠልፍ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። "ወታደራዊ አምባገነንነትይውደም፤ ዲሞክራሲ ይለምልም" የሚል መፈክሮች የያዙ ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ ያንጎን ጎዳናዎች ታይተዋል። የመከላከያ ቆብ ያደረጉና ጋሻ የያዙ ፖሊሶች ሰልፈኞቹን ወደ ማዕከላዊው የከተማ ክፍል እንዳይሄዱ አግደዋቸዋል። በሚየንማር በማሕበራዊ መገናኛ ብዙኀን ተቃውሞ ሰልፎች ጥሪ እንዳይደረግ በሚል ፌስቡክ ከተቋረጠ ከአንድ ቀን በኋላ ትዊተር እና ኢንስታግራምም ታግዷል። ወታደራዊ ኃይሉ በማህበራዊ ሚዲያዎቹ መታገድ ላይ አስተያየታቸውን አልሰጡም። ትዊተር እና ኢንስታግራምን በሚየንማር ቴሌኖር የተባለው የአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ተጠቃሚዎቹ ትዊተር እና ኢንስታግራምን እንዳይጠቀሙ እንዲያግድ መደረጉን ይፋ አድርጓል። ጦሩ ፌስቡክን ባሳለፍነው ሐሙስ ማገዱ ይታወሳል። በቀድሞዋ በርማ በአሁኗ ሚየንማር በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የአገሪቱ ጦር መፈንቅለ መንግሥት በማድረግ ሥልጣን መቆጣጠሩ ይታወሳል። ወታደሮቹ የሥልጣን መንበሩን መያዛቸውን ይፋ ያደረጉት የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚዋ ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ሌሎች የፖለቲካ መሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተከትሎ ነበር። በአገሪቱ የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ በጦሩ ላይ ተቃውሞ እየበረታ ይገኛል። በያንጎን ከተማ ተማሪዎች እና መምህራን አደባባይ በመውጣት ኦንግ ሳን ሱ ቺ እና ለሲቪል መሪዎቻቸው ያላቸውን ድጋፍ አሰምተዋል። እንደ ሳን ሱ ቺ ጠበቃ ከሆነ የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት በቁም እስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ፖሊስ በሕገ-ወጥ መንገድ የግንኙነት መሳሪያዎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት በመኖሪያ ቤታቸው ተጠቅመዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል። ማሐበራዊ ሚዲያዎች ለምን ተዘጉ? በሚየንማር ኢንተርኔት ፌስቡክ ነው ይባላል። የአገሪቱ ዜጎቹ ጦሩ መፈንቅለ መንግሥት ሲያደርግ በቀጥታ በፌስቡክ ተመልክተውታል። በርካታ ሲቪል መሪዎች በአገሪቱ ጦር አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ሲለቀሙ በፌስቡክ በቀጥታ ተሰራጭቷል። መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቀወሙ የተለያየ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች በፌስቡክ፣ ትዊተር እና ኢንስታግራም ተሰራጭቷል። በዚህም ጦሩ የሚነሳበትን ተቃውሞ ለማብረድ እና የመረጃ ስርጭትን ለመግታት ማህበራዊ ሚዲያውን ለመዝጋት መገደዱን የቀጠናው ተንታኞች ይናገራሉ። የትዊተር ቃል አባይ “ሰዎች ድምጻቸውን የማሰማት መብታቸው ተገፏል” ያሉ ሲሆን፤ የኢንስታግራም ባለቤት የሆነው ፌስቡክ ደግሞ፤ ለሚየንማር ባለስልጣናት “ግንኙነቱን ማስጀመር አለባቸው። ሰዎች ከቤተሰብ እና ጓደኞቻቸው ጋር እንዲገናኙ እና መረጃ እንዲኖራቸው መፍቀድ አለባቸው” ሲል መልዕክት አስተላልፏል። ለጦሩ መፈንቅለ መንግሥት የዜጎች ምላሽ ጦሩ ስልጣን በኃይል መቆጣጠሩን የሚቃወሙ በርካቶች ሲሆኑ በተለይም መምህራንና ተማሪዎች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው ተብሏል። በንግድ ከተማዋ ያንጎን በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ተቃዋሚዎች በኃይል የተገረሰሱትንና በእስር ላይ የሚገኙትን መሪ ኦንግ ሳን ሱ ቺ ስም እያነሱ መፈክር ሲያሰሙ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የፓርቲያቸውን ቀለም የሚወክል ቀይ ሪባን አድርገው ታይተዋል። መፈንቅለ መንግሥት ከተከሰተበት ከሰኞ እለት ጀምሮ ለህዝብ ያልታዩት ኦንግ ሳን ሱ ቺ በቤት ውስጥ እስር እንደሚገኙ አንድ የፓርቲያቸው ባለስልጣን አስታውቋል። የቀድሞዋ በርማ በመፈንቅለ መንግሥቱ ማግስት ፀጥታ ወሯት የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን አመፆች ተቀጣጥለዋል ተብሏል። "የኛ ትውልድ በእንደዚህ አይነት አምባገነን ስርአት እንዲሰቃይ አንፈቅድም" በማለት ሚን ስትሁ የተሰኘች ተማሪ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግራለች።
news-52883920
https://www.bbc.com/amharic/news-52883920
የምዕራብ ኦሮሚያ እሮሮ፡ በነጆ አራት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች ተገደሉ
በምዕራብ ኦሮሚያ በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ባለፈው ዓርብ አራት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች መገደላቸው ነገረ።
ከጥቃቱ ከተረፉት ሰዎች፣ ከሟች ቤተሰቦች እና ከነጆ ወረዳ አስዳዳሪ ቢቢሲ እንደተረዳው ዓርብ ዕለት የሸኔ አባላት ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች በ10 የመንግሥት ሠራተኞች ላይ በተፈጸመ ጥቃት አራቱ ሲገደሉ ሦስቱ የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሦስት ሰዎች ደግሞ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጥቃቱ ተርፈዋል። ግንቦት 21/2012 ዓ.ም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ለማከፋፈል ከተለያዩ ቢሮዎች የተወጣጣ ኮሚቴ አሞማ ዴገሮ ወደ ሚባል ቀበሌ ተጉዞ እንደነበነር የነጆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተፈራ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የመንግሥት ሠራተኞቹ ከሄዱበት ስፍራ በሰላም ሥራቸውን ጨርሰው እየተመለሱ ዋጋሪ ቡና ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲደርሱ ጸረ ሰላም በሆኑት የሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶበናቸዋል" ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። ለመስክ ሥራ ተሰማርተው የነበሩት ሰዎች በአጠቃላይ 10 እንደነበሩ የሚያስታውሱት አቶ ተሊላ በጥቃቱ ከመካከላቸው አራቱ ተገድለዋል። "አንደኛው ሟች አብዲ አበራ የሚባል ሹፌር ሲሆን ሁለተኛው የእንስሳት ሐኪም የነበረው ዳዊት ተርፋሳ ሲሆን፤ ባሕሩ አየለ እና እስራኤል መርዳሳ የሚባሉት ሟቾች ደግሞ የወረዳው ሚሊሻ አባላት ናቸው" ብለዋል። በታጣቂዎቹ በተሰነዘረባቸው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ ሦስቱ በጥቃቱ የቆሰሉት ሲሆን፤ ከጥቃቱ ጉዳት ሳይደርስባቸው ያመለጡት ደግሞ ሦስት ናቸው። የተፈጠረው ምን ነበር? በመንግሥት ሠራተኞቹ ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው ዓርብ ከሰዓት በኋላ ላይ ነበር። የአስሩ የመንግሥት ሠራተኞች መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት ድጋፍ የተገኘውን የምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ በጸጥታ ችግር ምክንያት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ለማከፋፈል ወደ አሞማ ዴገሮ ይጓዛሉ። እነዚህ የመንግሥት ሠራተኞች ከወረዳው የአደጋ ዝግጁነት እና ቁጥጥር ጽህፈት ቤት፣ ከእንስሳት ጤና፣ ከሚሊሻ የተወጣጡ ነበሩ። ለመስክ ሥራ የተሰማሩት ሠራተኞቹ የሄዱበትን ሥራ ፈጽመው ወደ ነጆ ከተማ እየተመለሱ ሳለ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ከ35 ገደማ ዋጋሪ ቡና ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሸኔ አባላት ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸዋል። "በቅድሚያ የመኪናውን ጎማ በጥይት መቱ" ያሉት አቶ ተሊላ፤ መኪናው ሲቆም በመኪናው ውስጥ በነበሩት ሠራተኞች ላይ ተኩስ መከፈቱን ይናገራሉ። "ከዓይን እማኞች መገንዘብ እንደቻልነው ጥቃቱን የሰነዘሩት ታጣቂዎች በቁጥር ስምንት ይሆናሉ" ብለዋል። "መኪናው በጥይት ተመትቶ እንደቆመ ሮጠው ማምለጥ የቻሉት ህይወታቸውን ማትረፍ ችለዋል። በመኪናው ውስጥ ከነበሩት መካከልም በጥይት ተመተው 'ሞተዋል' ብለው ያለፏቸውም አሉ" ይላሉ አቶ ተሊላ። በጥቃቱ የተገደሉት አራቱ ሰዎች ህይወታው ያለፈው ወዲያ ጥቃቱ ከተፈጸመበት ስፍራ መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ፈጽመው በመኪናው ውስጥ ያሉትን ሰዎች ከገደሉና ካቆሰሉ በኋላ የመንግሥት ሠራተኞቹ ይዘዋቸው የነበሩትን 4 የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶችን ዘረፍው መሄዳቸውን ገልጸዋል። ከጥቃቱ በኋላ በአካባቢው ተሰማርቶ የሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የአሮሚያ ልዩ ኃይል የጥቃቱን ፈጻሚዎች ለማግኘት አሰሳ እያካሄደ መሆኑን እና እስካሁን ግን ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋለ እንደሌላ አስረድተዋል። ሥራ በጀመረ በሦስተኛ ሳምንቱ የተገደለው ሹፌር በታጣቂዎቹ ከተገደሉት መካከል አንዱ የሆነውና መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው አብዲ አበራ ነው። የአብዲ ታላቅ ወንድም ቴዲ አበራ "ወንድሜን ድንጋይ ተሸክሜ ነው ያሳደኩት፤ ሥራ ከጀመረ እንኳ ገና ሦስተኛ ሳምንቱ ነው" ይላል። "ያለ አባት ነው ያደገው። ከተቀጠረ እንኳን ገና ሦስት ሳምንት አልሆነውም። የአንድ ወር ደሞዝ እንኳን አልበላም። የአንድ ዓመት ከሁለት ወር ወንድ ልጅ አለው። ይሄው ልጁም ልክ እንደሱ ያለ አባት ሊያድግ ነው" ሲል በመሪር ሐዘን ውስጥ ሆኖ ስለወንድሙ ለቢቢሲ ተናግሯል። ቴዲ "አስክሬኑን አመጥተው ነው የሰጡን። ማን ገደለው? ለምን ተገደለ? ብለን የምንጠይቀው እንኳን የለም። ሰው ቀና ብሎ የማያይ፤ ሰዎች የሚወዱት ገና የ21 ዓመት ልጅ ነበረ" ሲል ታናሽ ወንድሙን ያስታውሳል። ስለወንድሙ ሲናገር እምባ የሚቀድመው ቴዲ፤ ታናሽ ወንድሙ አብዲ ከሦስት ሳምንት በፊት ይህን የሹፍርና ሥራ በወረዳው ተቀጥሮ መስራት ከመጀመሩ በፊት በነጆ ከተማ የሰው ባጃጅ እየነዳ ይተዳደር እንደነበረ ገልጿል። በሐዘን ክፍኛ የተጎዳው ቴዲ በመረረ ስሜት የወንድሙን ሞት "ተስፋዬ ነበር። ተስፋዬን ቀበርኩ። በእኛ ላይ የደረሰው በጠላት ቤት እንኳን አይግባ" ሲል የደረሰበት መከራ ሌሎች ላይ እንዳይደርስ ተመኝቷል። የመንግሥት ሠራተኞች ስጋት ? የነጆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተፈራ እንደሚሉት፤ በተለይም የመንግሥት ሠራተኞችን ዒላማ ያደረገ መሰል ጥቃት በአካባቢው ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። "አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ነገር እነዚህ ቡድኖች የልማት ሥራዎች ሲሰሩ አይደሰቱም። ከዚህ ቀደም የመንግሥት ሠራተኞችን ኢላማ ሲያደርጉ ነበር" ይላሉ። ከዚህ በፊት የወረዳ፤ የቀበሌ አስተዳዳሪ ተገድሏል፣ ሚሊሻ ተገድሏል፣ ማዕድን አውጪ ባለሙያዎች መገደላቸውን የሚናገሩት አቶ ተሊላ "አሁን ጥቃት የተፈጸመባቸው ሠራተኞች በመንግሥት መኪና መንቀሳቀሳቸውንና ሚሊሻ ከእነሱ መሆኑ ሲያውቁ ነው ጥቃት የሰነዘሩባቸው" ይላሉ። ይህ በአካባቢው የሚፈጸመው ተደጋጋሚ ጥቃት በመንግሥት ሠራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩንም ተናግረዋል። "የመንግሥት ሠራተኞች ስጋት አላቸው። በጸጥታ ኃይል ካልታጀቡ በቀር ወደ ገጠር ለሥራ የሚሰማራ የመንግሥት ሠራተኛ የለም። ሥራ የሚሰራው በጸጥታ ኃይሎች ትብብር ብቻ ነው" ይላሉ። ማቆሚያ የሌለው የሚመስለው የምዕራብ ኦሮሚያ እሮሮ በምዕራብ ኦሮሚያ በታጣቂዎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተፈጽመዋል በሚባሉ ጥቃቶች በርካታ ንጹሃን ዜጎች ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸውን፣ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው በተለያዩ ጊዜያት ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። መንግሥት በአካባቢው በታጣቂዎች ለሚፈጸሙት ጥቃቶች የኦነግ ሸኔ አባላትን ተጠያቂ ያደርጋል። የኦሮሚያ አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ በምዕራብ ኦሮሚያ ባሉ ዞኖች በኦነግ ሸኔ በተፈጸሙ የተለያዩ ጥቃቶች ከ770 በላይ ሰዎች መገደላቸው እና 1300 በላይ የሚሆኑ ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል። ከዚህ ባሻገርም 72 ሰዎች ደግሞ ታፍነው የተወሰዱ እና የገቡበት ቦታ እስካሁን የማይታቅ መሆኑን ተገልጿል።
news-51315502
https://www.bbc.com/amharic/news-51315502
ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች የሚፈልጉትን ገንዘብ ለማውጣት ተቸገርን አሉ
ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ገንዘብ ማውጣት አለመቻላቸው ተናገሩ።
ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ደንበኞች ገንዘብ ማውጣት አለመቻላቸውን ለቢቢሲ ገለጸዋል። በአብዛኞቹ የኢዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ከአንድ ሺህና ከሁለት ሺህ ብር በላይ ማውጣት እንደማይችሉ ተነግሮናል ይላሉ። ለምሳሌ በዓድዋ ከተማ ሰሎዳ ዓዲኣቡን በተባለው ቅርንጫፍ ብር ለማውጣት የሄደችው ተጠቃሚ ወጣት፤ "ከሁለት ሺህ ብር በላይ ማውጣት አትችይም" መባሏን ለቢቢሲ ትናገራለች። • በስህተት የተሰጣቸውን 1 ሚሊየን ብር የመለሱት መምህር • በሴት ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የባንክ ቅርንጫፍ ተከፈተ በዚህ ከተማ የሚገኙ ሌሎች ቅርንጫፎች ደግሞ ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ ሲሰጥ እንደዋለ ከዚያ በላይ ግን ብር የለም በማለት አልስጥም መባላቸውን ተገልጋዮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተመሳሳይ በውቅሮ ክልተውላዕሎ የሚገኘው ቅርንጫፍ ከአንድ ሺህ ብር በላይ አልሰጥም ማለቱን የባንኩ ደንበኞ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አምስት ሺህ ለማውጣት ወደ ቅርንጫፉ ሂዳ፤ አንድ ሺህ ብር ብቻ የተሰጣት አንድ ነዋሪም በተመሳሳይ የገጠማትን ተናግራለች። • የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች ከዚህ መጠን በላይ ማውጣት አትችሉም ተብለው የተከለከሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ተጨንቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። እንዲሁም ደግሞ ደመወዛቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚከፈላቸው የክልሉ የመንግሥት ሠራተኛ በተመሳሳይ "ብር የለም ጠብቁ" መባላቸውን ምንጮች ይናገራሉ። በመቀለ የሚገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር ተዘዋወሮ እንተመለከተው፤ በመቀለ የሚገኙ ቅርንጫፎችም በወረፋ መጨናነቃቸውንና የጠየቁት ብር ሳይሰጣቸው ስለቀረ ሲበሳጩና በቁጣ ሲናገሩ ታዝቧል። • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው አንድ በመቀለ ቅርንጫፍ በኃላፊነት ላይ የሚገኝ የባንኩ ሠራተኛ፤ ባንኩ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመው ይናገራል። በተለይ በትግራይ የሚገኙ ቅርንጫፎች ምንም ብር እንደሌላቸው ተናግሯል። ለዚህ እንደምክንያት የተጠቀሰውም የተለያዩ ሰዎች ገንዘባቸው ከባንኩ እያወጡ እንደሆነ ነው። ችግሩ በሌሎች አከባቢዎችና በሌሎች የግል ባንኮችም፤ ሊከሰት እንደሚችል አመላክቷል። የባንኩ ሠራተኛ አክሎም በትግራይ ውስጥ፤ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የተሰጣቸው አራት ዋና ዋና አከፋፈይ ማዕከላት በመቀለ፣ በማይጨው፣ በዓድዋና ሽረ እንዳሥላሰ የሚገኙ ሲሆን፤ በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የብር እጥረት ስለአጋጠመ ነው ወደ ቅርንጫፎች ብር ያልተላከው ይላል። • "ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?" ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀው ይኸው ኃላፊ እንጋለው ብሔራዊ ባንክ ችግሩን በጥቂት ቀናት ለመፍታት እየሰራ እንደሆነ አክሎ ተናግሯል። ቢቢሲ ያናገራቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አልሰን አሰፋ ግን የገንዘብ ዕጥረት እንደሌለ ገልጸዋል። "የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ዕጥረት አልገጠመውም። ምናልባች የኔትወርክ ችግር ቢኖርበት ነው" በማለት የተባለው ውሸት እንደሆነ ጠቅሰዋል። ጨምረውም "ከ2 ሺህ ብር በላይ አታወጡም የሚል ህግም የለም" የሚሉት አቶ አልሰን፤ ያለው ችግር ከቴሌ ጋር የሚያያዝ እንደሆነም ይናገራሉ። ገንዘብ የማውጣት ገደቡንም በተመለከተ "ይሄ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም። የባንኩ አሰራርም አይደለም" ብለዋል። "ማንኛውም ሰው በባንኩ ያስቀመጠውን ብር በየትኛውም ቅርንጫፍ የማውጣት መብት አለው። ይህንን መብቱ የመከልከል መብት የለንም። የተባለው ችግር በትግራይ ካለ ለምን የእዚያ አከባቢ ቅርንጫፍ ኃላፊዎች አላነሱልንም? እንደሱ የሚባል መረጃ አልደረሰንም" ብለዋል።
news-55693638
https://www.bbc.com/amharic/news-55693638
ሙዚቃ፡ ታዋቂው አሜሪካዊ ራፐር ዶ/ር ድሬ አገግሞ ከሆስፒታል ወጥቷል ተባለ
ታዋቂው አሜሪካዊ ራፐርና ፕሮዲዩሰር ዶ/ር ድሬ በአንጎል የደም ቧንቧ ችግር ሆስፒታል ገብቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገግሞ ወደ ቤቱ ተመልሷል ተብሏል።
የ55ቱ አመት ራፐር ጠበቃ በትናንትናው ዕለት እንዳሳወቁት ሙዚቀኛው ወደ ቤቱ ተመልሷል ከማለት ውጭ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ከቀናት በፊትም ራፐርና ተዋናዩ አይስቲ ከዶ/ር ድሬ ጋር እንዳወራና " ደህና ነው" በማለት በተሻለ ሁኔታ እንደሚገኝ ተናግሮ ነበር። መረጃዎችን ፈልፍሎ በማውጣት የሚታወቀው ቲኤምዚ ራፐሩ ከሁለት ሳምንታት በፊት ራፐሩ ሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርኒያ በሚገኝ ሴዳርስ ሲናይ ሜዲካል ማዕከል ተወስዷል ብሎ ነበር። በዚያኑ ወቅትም የራፐሩ ተወካዮች ባወጡት መግለጫ በመድረክ ስሙ ዶ/ር ድሬ ተብሎ የሚታወቀው አንድሬ ሮሜል ያንግ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። "ለቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼና አድናቂዎቼ ለመልካም ምኞታቸው ምስጋና ይድረሳቸው። በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት። ከህክምና ቡድኑም ጥሩ እንክብካቤ እያገኘሁ ነው" በማለት ራፐሩ በኢንስታግራም ገፁ መልዕክቱን ማስተላለፉ የሚታወስ ነው። "በቅርቡ ከሆስፒታል ወጥቼ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ። በሴዳርስ ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች በሙሉ ከፍተኛ ምስጋና ይድረሳቸው። ፍቅር ለሁላችንም" የሚል መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ራፐሩ ታሞ ሆስፒታል መግባቱ ከተሰማ በኋላ ጓደኞቹ እንዲሁም ዝነኛ ሰዎች ከህመሙ እንዲያገግም መልካም ምኞቻውን ገልፀዋል። በ1980ዎቹ ኤንደብልዩኤ (NWA) ተብሎ በሚታወቀው ታዋቂው ባንድ ውስጥ ከዶ/ር ድሬ ጋር አብሮ የነበረው የባንዱ አባል አይስ ኪዩብ "ለጓደኛዬ ዶ/ር ድሬ ከህመሙ እንዲያገግም በፀሎትና በፍቅር እያሰብኩት ነው" በማለት በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሮ ነበር። ለሙዚቃ ህይወቱ ከፍተኛ ሚና የተጫወተለት ሌላኛው ታዋቂው ራፐር ስኑፕ ዶግ እንዲሁ "እንዲሻልህ እመኛለሁ፤ ታስፈልገናለህ ቤተሰባችን" ብሎ ነበር። ሌላኛዋ ታዋቂ ራፐር ሚሲ ኤሊየት እንዲሁ ራፐሩ በጥንካሬና በጤንነት እንዲመለስ ምኞታቸውን ከገለፁት መካከል አንዷ ናት። በሂፕሆፕ ሙዚቃ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ራፐሩ ኤንደብልዩኤ (NWA) በሚባለው የሂፕ ሆፕ ቡድን፣ በግሉም የነበረው የሙዚቃ ህይወቱ ዝናን አትርፏል። ከዚህም በተጨማሪ በፕሮዲውሰርነቱም ከፍተኛ ዝናን መጎናፀፍ የቻሉ እንደ 50 ሴንት፣ ኬንድሪክ ላማርና ኤሚኒየም የመሳሳሉ ሙዚቀኞች ጀርባ አሻራውን አሳርፏል።
news-46834098
https://www.bbc.com/amharic/news-46834098
በኔፓል እናትና ልጇቿ ለወር አበባ በተገለለ ጎጆ ህይወታቸው አለፈ
ኔፓላዊት እናትና ሁለት ልጆቿ ለወር አበባ በተከለለ ጎጆ ውስጥ ጭስ አፍኗቸው ህይወታቸው እንዳለፈ ተዘግቧል።
በኔፓል ሴት ልጅ የወር አበባ በምታይበት ወቅት ከሰው ተገልላ በተከለለ ጎጆ ውስጥ መቀመጥ አለባት። ይህንንም ተከትሎ አንዲት እናት ከሁለት ልጆቿ ጋር በተከለለ ጎጆ ውስጥ ሆነው የክረምቱን ቅዝቃዜ መቋቋም ስላልቻሉ እሳት አቀጣጠሉ። •'የወር አበባ ላይ ስለነበርኩ ለአያቴ ሐዘን መቀመጥ አልቻልኩም' •የወር አበባ ለምን በአንዳንድ ሴቶች ላይ ህመም ያስከትላል? በነጋታውም ሶስቱም ሞተው የተገኙ ሲሆን፤ በጭስ ታፍነው ሳይሞቱ እንዳልቀሩም የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ኔፓሊ ገልፀዋል። በባህሉ መሰረት ሴት የወር አበባ በምታይበት ወቅት በተገለለ ቦታ ማስቀመጥ በኔፓል የታገደ ቢሆንም አሁንም ቢሆን በገጠሪቷ ክልል መከናወኑ አልቀረም። ይህ አሳዛኝ ሁኔታ የመጀመሪያ አይደለም ከዚህ ቀደምም ታፍና እንዲሁም በእባብ ተነድፈው የሞቱ ሴቶችም ይገኙበታል። ይህንንም ተከትሎ ነበር ከሁለት አመት በፊት አግልሎ ማስቀመጥ ወንጀል እንዲሆን የተደረገው። በዚህም መሰረት የሶስት ወር እስራትና 810 ብር ቅጣትም ያስከትላል። በጥንታዊ ሂንዱይዝም እምነት መሰረት የወር አበባ እያዩ ያሉ ሴቶችና የወለዱ ሴቶች ቆሻሻ ተደርገው ከመታየት በተጨማሪ መጥፎ እድል ያመጣሉ ተብለው ስለሚታመኑ ለብቻቸው በተከለለ ጎጆ ወይም በእንስሳት በረት እንዲቆዩ ይገደዳሉ። ከብቶችንና ሰዎችን መንካት የማይፈቀድላቸው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የተወሰኑ ምግቦች ይከለከላሉ፤ በቤት ውስጥ የሚገኙ መታጠቢያ ቤትና ልብስ ማጠቢያ ቦታ ስለማይፈቀድላቸው ረዥም መንገድ መጓዝ አለባቸው። •ጥበብን በወር-አበባና በአጽም ሴት ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ቤት ከመሄድ ይታቀባሉ። ለከፍተኛ ቁር መጋለጥ፣ የወንጀለኞች ጥቃት ከሚደርሱባቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው። በቅርብ የሞቱት እናትና ልጆችን አሟሟት ምርመራ እየተደረገ ነው። እናቲቱ ለብሳው የነበረው ብርድ ልብስ በከፊል የተቃጠለ ሲሆን እግሯም ላይ ቃጠሎ እንደደረሰባትም ኤኤፍፒ ፖሊስን ጠቅሶ ዘግቧል። ልጆቹም የ12ና ዘጠኝ አመት ዕድሜ ያላቸው ሲሆን አስከሬናቸውም ለቤተሰቦቻቸው ተመልሷል።
45636166
https://www.bbc.com/amharic/45636166
ኬንያዊው ባለሥልጣን ነብሰ ጡር ጓደኛውን በማስገደል ወንጀል ተከሷል
ኦኮት ኦባዶ የተባሉት ኬንያዊ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከትዳራቸው ውጪ ግንኙነት የነበራቸውን ነብሰጡር ጓደኛቸውን በጭካኔ እንድትገደል አዘዋል እንዲሁም አስተባብረዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
ባለሥልጣኑ ይህን ድርጊት አልፈፀምኩም በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። የሻሮን ኦቲየኖ ሬሳ ጫካ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ነው ሁኔታው ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ከበርካቶች ጫና መበርታት የጀመረው። • ቻይናዊው በዘረኛ ንግግሩ ምክንያት ከሃገር ሊባረር ነው የአስከሬን ምርመራው እንዳረጋገጠው የ26 ዓመቷ ሻሮን ተደፍራ እና በስለት 8 ቦታ ተወግታ ነው የተገኘችው፤ ሽሉም በጥቃቱ ጊዜ ሕይወቱ እንዳለፈ ተረጋግጧል። ሚጎሪ የተሰኘው የኬንያ ግዛት አስተዳዳተሪ የሆኑት እኚህ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሲሆን ክሱ ወደ ፍርድ ቤት ተልኳል። የፍርድ ቤቱ ዳኛ ባልሥልጣኑ ብቻ ሳይሆኑ ሁለት አጋሮቻቸው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አዘዋል፤ አንዱ በግድያ ሌላኛው ደግሞ በማስተባበር ወንጀል ተጠርጥረው። አቃቤ ሕግ ሻሮን እና ሃገረ ገዢ ኦባዶ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው አረጋግጫለሁ ብሎ እርግዝናው ግን ያልተፈለገ ነው፤ በተለይ ደግሞ በተጠርጣሪ በኩል ሲል አክሏል። • ጉግል ኢንተርኔትን በላስቲክ ከረጢት ይዞ ኬንያ ገብቷል የሟች እና የተጠርጣሪው ኦባዶ ግንኙነት ሃገር ያወቀው፤ ፀሐይ የሞቀው ነው በተለይ ደግሞ ባለሥልጣኑ በሚያስተዳድሩት አካባቢ ሲል አቃቤ ሕግ ጉዳዩን አብራርቷል። የሃገር ገዢው ኦባዶ ባለቤት የባላቸውን ከትዳር ውጭ የተመሠረት ግንኙት እያወቁት ባለሥልጣኑ ይህን ድርጊት መፈፀማቸው ደግሞ ክሱን ያከብደዋል ይላል አቃቤ ሕግ። በርካታ ኬንያዊያንን ያስቆጣው ይህ ድርጊት በቅርብ ቀን ፍርድ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። • ኬንያ ሺሻን አገደች
news-50328129
https://www.bbc.com/amharic/news-50328129
ቻይና ጌም በሚያዘወትሩ ታዳጊዎች ላይ ሰዓት እላፊ ጣለች
ቻይና በይነ-መረብ ላይ ተተክለው 'የቪድዮ ጌም' ሲጫወቱ የሚውሉ ታዳጊዎች ላይ እግድ ጥላለች።
ከ18 ዓመት በታች ያሉ 'ኦንላይን ጌመኞች' ከዚህ በኋላ ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋት ሁለት ሰዓት ድረስ መጫወት አይችሉም ተብሏል። አልፎም በሥራ ቀናት 90 ደቂቃ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ ለ3 ሰዓታት ነው መጫወት የሚፈቀድላቸው። የቻይና ባለሥልጣናት፤ የበይነ-መረብ ቪድዮ ጌሞች ሱስ እየሆኑ ነው፤ ትውልዱንም ጤና እየነሱት ነው በሚል ነው ይህን ሕግ ያወጡት። • የወላጆች ራስ ምታት እየሆነ የመጣው የልጆች የጌም ሱስ ቻይና የበይነ-መረብ ጨዋታ (የኦንላይን ጌሚንግ) ገበያ የደራባት ሃገር ናት። በዚህ ገበያ ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ተብላም ትቆጠራለች። ቻይና ሕግ በማብዛቷ ነው እንጂ ከዓለም ከፍተኛውን ድርሻ ለመያዝ ትችል እንደነበር ይነገርላታል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ዕድሜያቸው ከ8 እስከ 16 የሆኑ ታዳጊዎች ለጨዋታ በወር ማውጣት የሚችሉት 200 ዩዋን ነው። 860 ብር ገደማ መሆኑ ነው። ከ16 እስከ 18 ያሉ ደግሞ 400 ዩዋን (1600 ብር በላይ) ማውጣት ይችላሉ። የቻይና መንግሥት የበይነ-መረብ ጨዋታን የሚቆጣጠር መሥሪያ ቤት ያቋቋመው አምና ነበር። ይህ ተቋም 'ስክሪን' ላይ ተሰክተው የሚውሉ ሕፃናትና ታዳጊዎችን ቁጥር የመቀነስ ኃላፊነት አለበት። • ለፌስቡክ ሱሰኞች የተገነባው አስፋልት ተመረቀ አልፎም ቻይና ውስጥ አዲስ የቪድዮ ጨዋታዎችን ማስተዋወቅ እጅግ የከበደ እየሆነ ነው። ባለፈው ዓመት የዓለም የጤና ድርጅት የቪድዮ ጨዋታዎች ሱስ እንደሚያስዙ ደርሼበታለሁ፤ የአዕምሮ ጤና ችግርም ሊያመጡ ይችላሉ ሲል ማወጁ አይዘነጋም። የአሜሪካ የሥነ አዕምሮ ህክምና ማህበር የቪድዮ ጨዋታዎች የአዕምሮ ጠና መቃወስ ያመጣሉ ባይልም ሰበብ ሊሆን ስለሚችል ጥናት ያስፈልገዋል ይላል። ይህንን ተከትሎ አንዳንድ ሃገራት 'ቪድዯ ጌም' ክትትል ያሻዋል እያሉ ነው።
news-55975691
https://www.bbc.com/amharic/news-55975691
በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን ያጡት የኖቤል ሎውሬት አን ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው?
በአንድ ወቅት የሰብአዊ መብትና የዲሞክራሲ ባንዲራ ሆነው ይታዩ ነበር፡፡ አሁን ግን በብዙ ተቋማት ዓይንዎትን ላፈር ተብለዋል፤ አን ሳን ሱ ቺ፡፡
ከሳምንት በፊት በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን አጥተዋል፡፡ አሁን በቁም እስር ላይ ናቸው፡፡ ከስማቸው አወዛጋቢነት እስከ አገሪቱ ትክክለኛ የስም አጠራር ድረስ የቀድሞዋ በርማ የአሁኗ ሚየንማር፣ የቀድሞዋ የሰብአዊ መብት እመቤት፣ የአሁኗ እስረኛ የሰሞኑ የሚዲያ ዐቢይ ጉዳይ ሆነዋል፡፡ በእርግጥ የሴትዮዋ ‹ሌጋሲ› በትክክል ምንድነው? በሚለው ጉዳይ ሚዲያዎችና ተቋማት ተስማምተው አያውቁም፡፡ ለመሆኑ ኦን ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው? አን ሳን ሱ ቺ አባታቸው የበርማ የነጻነት አባት የሚባሉት የጄኔራል ኦን ሳን ሴት ልጅ ናቸው፡፡ ታላቋ ብሪታኒያ በርማን (በአዲሱ ስሟ ሚየንማር) ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል ጊዜ በቅኝ ገዝታታለች፡፡ ጄኔራል ኦን ሰን ለበርማ ነጻነት ተዋድቀዋል፡፡ የተገደሉትም በ1947 በተቀናቃኞቻቸው ነበር፡፡ ያን ጊዜ ሳን ሱ ቺ ገና 2 ዓመቷ ነበር፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በሰኔ 19፣ 1945 ነበር የተወለዱት፡፡ ኦን ሳን ሱ ቺ በ1960ዎቹ መጀመርያ ከእናታቸው ዳው ኪን ኬዪ ጋር ወደ ሕንድ ሄዱ፡፡ እናታቸው በደልሂ የበርማ አምባሳደር ተደርገው በመሾማቸው ነበር ወደዚያ ያቀኑት፡፡ ሕንድ አራት ዓመት ከኖሩ በኋላ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ በማቅናት በሥመጥሩ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፍልስፍናን፣ ፖለቲካንና ምጣኔ ሀብትን አጥንተዋል፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሳሉ የወደፊት ባለቤታቸው ጋር ተገናኙ፡፡ እንግሊዛዊው ባለቤታቸው ማይክል አሪስ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ነበሩ፡፡ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ ኦን ሳን ሱ ቺ ከትምህርት በኋላ በቡታን እና በጃፓን በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ በመሄድ ጎጆ መሥርተው አሌክሳንደርና ኪም የሚባሉ ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በ1988 ከታላቋ ብሪታኒያ ወደ ሚየንማር ዋና ከተማ ያንጎን ሲመለሱ በጠና ታመው የነበሩትን እናታቸውን ለማስታመም ነበር፡፡ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ በበዚያ ወቅት በሚየንማር በርካታ የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን ያነሱ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ያስነሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹ ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ የቡድሀ መነኮሳት፣ የቢሮ ሰራተኞችና ተማሪዎችም ይገኙበት ነበር፡፡ ይህን ተቃውሞ ተከትሎ አን ሳን ሱ ቺ ጠቅልለው በሚየንማር መኖር ጀመሩ፡፡ አን ሳን ሱቺ ከቀድሞ ባለቤታቸው ጋር በለንደን ከ2 ዓመት በኋላ በ1990 አዲስ በተመሠረተው የናሽናል ሊግ ፓርቲ ውስጥ ገብተው ተቃውሞ ውስጥ በቀጥታ መሳተፍ ጀመሩ፡፡ በአካባቢ ምርጫ ተወዳድረውም አሸነፉ፡፡ በከፍተኛ ድምጽ የኦን ሳን ሱ ቺ በምርጫ ማሸነፍ ያስቆጣው ወታደራዊው መንግሥት ሴትዮዋን ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት በቁም እስር አስቀመጣቸው፡፡ በ1991 ኦን ሳን ሱ ቺ በቁም እስር ላይ ሳሉ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ፡፡ ይህም ወታደራዊውን መንግሥት በይበልጥ አስቆጣ፡፡ በ2010 ኦን ሳን ሱ ቺ ከቁም እስር ነጻ ተባሉ፡፡ በ2012 አን ሳን ሱ ቺና ፓርቲያቸው በአካባቢ ምርጫ እንዲሳተፉ ወታደራዊው መንግሥት ፈቀደ፡፡ በ2015 የብሔራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ (NLD) ፓርቲያቸው ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገ ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ምርጫ አሸነፈ፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በሚየንማር የሮሒንጋ ሙስሊሞች ላይ ወታደሩ ያደረሰውን ግፍና ጭፍጨፋ ለማውገዝ አለመፍቀዳቸው በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የሮሒንጋ ሙስሊሞች ከሚየንማር ሞትን ሽሽት ወደ ባንግላዴሽ ተሰደዋል፡፡ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ክብራቸው ዝቅ ይበል እንጂ አን ሳን ሱ ቺ በአገራቸው ቡድሀዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ናቸው፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በ2015 የተደረገውን ምርጫ አሸንፈው መንግሥት ቢመሠርቱም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት መሆን ግን አልተፈቀደላቸውም፡፡ ይፋዊ ሥልጣናቸው ‹የመንግሥት የበላይ ጠባቂ› ወይም ስቴት ካውንስለርነት ነው፡፡ ይህም የሆነው ያፈሯቸው ልጆች የውጭ ዜግነት ስላላቸው ነው፡፡ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚስተር ዊ ቢሆኑም አን ሳን ሱ ቺ ግን በውስጥ ታዋቂነት (de facto) የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሆነው ይወሰዳሉ፡፡ ስቴት ካውንስል የሚባለው ሹመት የተፈጠረው አን ሳን ሱ ቺ ሕጋዊ ፕሬዝዳንት መሆን ስለማይችሉ ነው፡፡ ሆኖም በፖለቲካ ሥልጣን ረገድ የጠቅላይ ሚኒስትር ያህል ቁልፍ ቦታ ነው፡፡ አን ሳን ሱ ቺ ይህን ሥልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት ለአጫጭር ጊዜም ቢሆን የኢነርጂ ሚኒስትር፣ የትምህርት ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ማለትም 2020 አን ሳን ሱ ቺ እና ፓርቲያቸው ምርጫ ማሸነፍ ችሎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉትም አዲሱን መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና በሚሉበት ሰዓት ነው፡፡ በ2021 የዛሬ ሳምንት አካባቢ የተወካዮች ምክር ቤት ሸንጎ አዲስ የሥራ ዘመን ስብሰባ በሚጀምርበት ቀን አን ሳን ሱ ቺ በድጋሚ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ አን ሳን ሱ ቺ አሁን የ76 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው፡፡
48605255
https://www.bbc.com/amharic/48605255
ኢቦላ ወደ ኡጋንዳ እየተዛመተ ነው
በኡጋንዳ አንድ የአምስት ዓመት ህፃን በኢቦላ በሽታ መሞቱ ተነገረ።
ይህ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውጪ ኢቦላ ቫይረስ ሲገኝ የመጀመሪያው ነው። ባለፉት አስር ወራት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ብቻ 2ሺህ ታማሚዎች የተመዘገቡ ሲሆን የበርካቶቹ ጤና በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው ተብሏል። አሁን በኡጋንዳ በኢቦላ የሞተው ሕፃን ቅዳሜ እለት ከቤተሰቡ ጋር በመሆን ከኮንጎ ወደ ኡጋንዳ በድንብር በኩል የተሻገረ ነው። እናቱ እና አያቱም በቫይረሱ መያዛቸው ተሰምቷል። • ሴት እግር ኳሰኞች እና ቡድኖች ስንት ይከፈላቸው ይሁን? • በአማራ ክልል በተከሰቱ ግጭቶች 224 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ የኡጋንዳ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ሕፃኑ ደም የቀላቀለ ማስመለስና ሌሎች ምልክቶችን እንዳሳየ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ነበር። በልጁ ደም ውስጥ የኢቦላ ቫይረስ መገኘቱ የታወቀው በኡጋንዳ የቫይረስ ምርመራ ተቋም ውስጥ ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ነው። ወዲያው የዓለም ጤና ድርጅትና የኡጋንዳ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የአስቸኳይ ጊዜ የሕክምና ቡድን ወደ ስፍራው የላኩ ሲሆን ቡድኑ ሌሎች ሰዎች በቫይረሱ መያዝ አለመያዛቸውን በመለየት አስፈላጊውን ሕክምናና ትምህርት ይሰጣል ብለዋል። የኡጋንዳ ጤና ሚኒስትር ለመገናኛ ብዙኀን እንደገለፁት የህፃኑ ቤተሰቦችና ሌሎች የኢቦላ ምልክት የሚመስል የታየባቸው ሁለት ሰዎች ክትትል እየተደረገላቸው ነው። ሚኒስትሯ በቲውተር መልእክታቸው ላይ እንዳስቀመጡት ኡጋንዳ በአሁኑ ሰአት የኢቦላን ወረርሽኝ ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ትገኛለች ብለዋል። • አፍሪካ ከቴክኖሎጂ ውጪ ለእድገት ምን አማራጭ አላት? ኡጋንዳ ከ4500 በላይ ጤና ባለሙያዎችን የኢቦላ መከላከያ ክትባት መስጠቷን የዓለም ጤና ድርጅትና የኡጋንዳ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። በኮንጎ የደረሰው የኢቦላ ወረርሽኝ በታሪክ ሁለተኛው ነው የተባለ ሲሆን በየሳምንቱ አዳዲስ በሽተኞች በከፍተኛ ቁጥር እየተመዘገቡ ነው ተብሏል። ከባለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ 1400 ሰዎች በኢቦላ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። ጉረቤት ሃገሮችም የኢቦላ መዛመት እጅጉን አሳስቧቸዋል። ኢቦላ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወደ ኡጋንዳ መዛመቱ ከተሰማ በኋላ ሩዋንዳ በድንበሮቿ ላይ የኢቦላ በሽታ ቁጥጥርን አጠናክራለች። ሩዋንዳ በምዕራብ በኩል ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፤ በሰሜን በኩል ደግሞ ከኡጋንዳ ጋር ትዋሰናለች። የሩዋንዳ የጤና ጥበቃ ሚንስትር ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ ''ሩዋንዳ በጎረቤት ሃገራት የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሸኝ አጽንኦት ሰጥታ ትከታተለዋለች'' ብለዋል። ሩዋንዳ ዜጎቿን የግል ንጽህናቸውን እንዲጠብቁ እና በኢቦላ ወደተጠቁ ስፍራዎች እንዳይጓዙ አሳስባለች።
news-47317092
https://www.bbc.com/amharic/news-47317092
"ከ[እኛ] የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም" መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ
በመንግሥትና በኦነግ መካከል፣ በሽማግሌዎች አማካይነት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ በርካታ የግንባሩ አባላት መሽገው ከነበሩባቸው ቦታዎች በሰላም እየተመለሱ ቢሆንም በምዕራብ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ኃይል አዛዥ ግን ይህንን ለመፈፀም ዝግጁ እንዳልሆነ ገልጿል።
በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተሰማርተው የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጦር አባላት የአባገዳዎችን ጥሪ ተከትለው ትጥቅ ፈትተው ወደ ጦር ካምፖች ከመግባታቸው በፊት ወደተዘጋጁላቸው ጊዜያዊ ማቆያ ስፍራዎች በዚህ ሳምንት እየገቡ እንደሆነ እየተዘገበ ነው። • በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል? • «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) ሽምግልናውን የመሩትና ስምምነቱ ከፍጻሜ እንዲደርስ ጥረት እያደረጉ ያሉት አባገዳዎች እና የየአካባቢዎቹ ባለስልጣናት ለውሳኔው ተገዢ በመሆን ወደተዘጋጁላቸው ስፍራዎች ከነትጥቃቸው ሲመጡ አቀባበል እያደረጉላቸው ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የአባገዳዎችን ጥሪ ተከትሎ ሁሉም የኦነግ ጦር አባላት እየተመለሱ እንዳልሆነ ወደተዘጋጁላቸው ጊዜያዊ ማቆያ ስፍራዎች ከገቡ የኦነግ ጦር አባላት ተሰምቷል። ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቀሰው የምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ የሆነው ኩምሳ ድሪባ ወይም በትግል ስሙ 'ጓድ መሮ' የአባገዳዎችን ጥሪ አለመቀበሉ ነው። • "የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ • በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኘው የኦነግ ጦር አዛዥ እንደሆነ በስፋት የሚነገርለት ኩምሳ ድሪባ (መሮ)ን ቢቢሲ ስለዚሁ ጉዳይ በስልክ አነጋግሮታል። እንደተባለውም መሮ ባለው ሁኔታ ስምምነቱን ተቀብሎ ለመግባት ዝግጁ እንዳልሆነ ገልጿል። የአባገዳዎችን ጥሪ ለመቀበል እና እርቅ ለማውረድ ዝግጁ ስለመሆኑ ሲጠየቅም "የእርቅ የተባለው ኮሚቴ እኔን በአካል አግኝተው ለማነጋገር ፍላጎት የላቸውም። ትኩረት ያደረጉት ጦሩን አንድ በአንድ እጁን እንዲሰጥ ማድረግ ላይ ነው" በማለት እሱም እነሱን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ይናገራል። እንዲያውም "ጦሩን የመበታተን ዓላማ ይዘው ነው እየተንቀሳቀሱ ያሉት" ሲል ይከሳል። የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ የእርቅ ኮሚቴውን በመደገፍ የኦነግ ጦር ጥሪውን ተቀብሎ ወደተዘጋጀለት ስፍራ እንዲሄድ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። የጦሩ መሪ መሮ የግንባሩ ሊቀመንበር ተገዢ መሆን አለመሆኑን ተጠይቆ ሲመልስ "ሊቀመንበሩ የእርቅ ኮሚቴውን ያሉት፤ 'የኦነግ ጦር የእናንተው ነው። ሂዱና አወያይታችሁ የሚሉትን ስሟቸው' ነው" ብሏል። ጨምሮም እንደተናገረው "እኔ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንወያይ ነው ያልኩት እንጂ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ጥቅም የለውም፤ የኦሮሞ ህዝብ መሰቃየት የለበትም ነው የምለው። እነሱ ግን የጦሩ አባላት የእጅ ስልክ ላይ እየደወሉ አንድ በአንድ ጦሩን የማፍረስ ሥራ ነው እየሰሩ የሚገኙት" ሲል ገልጿል። • በምዕራብ ኦሮሚያ ምን ተከሰተ? • በምዕራብ ኦሮሚያ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደሉ ያለው ችግር ከስር መሰረቱ መፍትሄ አላገኘም ብሎ የሚያምነው መሮ አሁን እየተደረገ ያለው "በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ሰዎችን አንድ በአንድ የማስኮብለል ሥራ ነው። ከዚህ የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም። 95 በመቶ አሁንም እንደታጠቀ ነው የሚገኘው" በማለት ተናግሯል። "ወደፊት መራራ ትግል ማድረጋችንን እንቀጥላለን" ያለው መሮ "ብቻዬን ብቀር እንኳ ትግል ማድረጌን እቀጥላለሁ እቅዴም ይሄው ነው" በማለት በትጥቅ ትግሉ እንደሚቀጥል ጠንከር በማለት ተናግሯል። የቀረበውን የእርቅ ጥሪ ተቀብለው ከገቡት የኦነግ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት የግንባሩ ጦር የሞራል እና ፖለቲካ መምህር የ57 ዓመቱ የዕድሜ ባለጸጋ አቶ ታፈሰ ኦላና በመሮ በኩል ያሉት ወታደሮች እየተመለሱ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል። • በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተገለፀ ጨምረውም "መሮ መመለስ አይፈልግም፤ ስልክ እየደወለ ጸያፍ ቃል እየተናገረን ነው። 'እጃችሁን ለአባገዳዎች እየሰጣችሁ ሰዎች ከትግላችን ዓላማ ውጪ የሆነ ተግባር እየፈጸማችሁ ነው። ታሪክ ይፋረዳችኋል' እያለ ያስጠነቅቀናል።" አቶ ታፈሰ እንደሚሉት አሁንም በምዕራብ ኦሮሚያ ትዕዛዝ የሚሰጠው መሮ መሆኑንና "የኦሮሞን ምድር የጦር አውድማ ማድረግ ነው የሚፈልገው። ህዝብ ሰላም እየፈለገ እሱ ግን አሁንም ደም ማፍሰስ የሚፈልግ ከሆነ ተሳስቷል" ብለዋል። የኦነግ የምዕራብ ኦሮሚያ ጦር አዛዥ መሮ በአባ ገዳዎች የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ የሄዱ የጦሩ አባላት ላይ ይሰነዝራል ስለተባለው ማስፈራሪያን በተመለከተ "የምን ማስፈራራት ነው። መሳሪያ ይዘን እያየናቸው እኮ ነው እየሄዱ ያሉት። ምርጫቸው ነው። ማንም ማንንም አላስፈራራም" ሲል ምላሽ ሰጥቷል። መሮ ችግሩን ለመፍታትም እንደቅድመ ሁኔታ የሚጠይቀው "በደቡብ ኢትዮጵያ እና በተለያዩ ዞኖች ከሚገኙ አባላቶቻችን ጋር በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ማድረግ አለብን" በማለት የሽምግልና ኮሚቴውም እንዲያወያያቸውና "አንድ በአንድ የጦሩን አባላት ማስኮብለል" ያለውን ድርጊት ማስቆም እንዳለባቸው ተናግሯል። የእርቅ ኮሚቴው ጸኃፊ የሆነውን ጀዋር መሐመድ በበኩሉ የኮሚቴው አባላት በተንቀሳቀሱባቸው ስፍራዎች ሁሉ የኦነግ የጦር አመራሮችን ለማግኘት ያደረጉት ጥረት የጦሩ አመራሮች ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ሳይሳካ እንደቀረ ይናገራል። ''ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ የተጓዙት አቶ በቀለ ገርባ እና አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካላቸውም። ወደ ደቡብ ኦሮሚያ የሄድኩት ደግሞ እኔ ነበርኩኝ። የኦነግ የምዕራብ ዞን የጦር ኃላፊ ሊያገኘን ፍቃደኛ አልነበረም።'' ሲል ተናግሯል።
news-46015070
https://www.bbc.com/amharic/news-46015070
ቀኝ ዘመሙ እና አክራሪው ቦልሶናሮ የብራዚል ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ
ቀኝ ዘመሙ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ጃይር ቦልሶናሮ በጉጉት የተጠበቀውን የብራዚል ምርጫ ማሸነፍ ችለዋል።
ቦልሶናሮ 55.2 በመቶ ድምፅ በማምጣት ነው ዋነኛ ተቀናቃኛቸው የነበሩት የሰራተኞች ፓርቲው ፈርናንዶ ሃዳድን መርታት የቻሉት። «ሙስናን ነቅዬ አጠፋለሁ፤ በሃገሩ የተስፋፋውን ወንጀልም እቀንሳለሁና ምረጡኝ» ሲሉ ነበር ቦልሶናሮ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ የሰነበቱት። የምርጫ ቅስቀሳ ሂደቱ በጣም ከፋፋይ እንደበር ብዙዎች የተስማሙበት ሲሆን ሁለቱም ወገኖች 'አጥፊ' እየተባባሉ ሲወቃቀሱ ከርመዋል። ወግ አጥባቂው ሚሼል ቴሜር በሙስና ምክንያት ከሥልጣን በወረዱት ዴልማ ሩሴፍ ምትክ ብራዚልን ላለፉት ሁለት ዓመታት ቢያስተዳድሩም ህዝቡ ዓይንዎትን ለአፈር ብሏቸዋል። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ ከጠቅላላ ህዝብ 2 በመቶ ብቻ ተወዳጅነት ያገኙት ቴሜር አሁን ሥልጣናቸውን በሰላማዊ መንገድ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል። ተቀናቃኛቸውን በ10 በመቶ ድምፅ የረቱት ቦልሶናሮ ለሃገራቸው ህዝብ ለውጥ ለማምጣት አማልክትን ጠርተው ምለዋል። «ዲሞክራሲን ጠብቄ አስጠብቃለሁ፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ የሃገራችንን ዕጣ ፈንታ አብረን እንቀይራለን» ሲሉም ቃላቸውን ሰጥዋል አዲሱ መሪ። የአዲሱ ተመራጭ ቦልሶናሮ ተቃዋሚዎች ግን ሰውየው ያለፈ ሕይወታቸው ከውትድርና ጋር የተያያዘ ስለሆነ ረግጥህ ግዛ እንጂ ዲሞክራሲ አያውቁም ሲሉ ይወርፏቸዋል። • “የኻሾግጂን ሬሳ ለማን እንደሰጣችሁት ንገሩን” ቦልሶናሮ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ያሰሟቸው የፆታ ምልክታን፣ ሴቶችን እንዲሁም ዘርን አስመልክተው የሰጧቸው አጫቃጫቂ አስተያየቶችም ያሳሰቧቸው አልጠፉም። ዋነኛው ተቀናቃኝ ፈርናንዶ ሃዳድ በበኩላቸው ድምፁን ለእኔ የሰጠው ሕዝብ አደራ አለብኝ ብለዋል፤ በተቃዋሚ ፖለቲከኛነት እንደሚቀጥሉ ፍንጭ በመስጠት። ብራዚል በፈረንጆቹ 2000-2013 ባሉት 13 ዓመታት ያክል በግራ ዘመም የሰራተኞች ፓርቲ ስትመራ ብትቆይም አሁን ግን ወደ ቀኝ ዘማለች። • «ዶ/ር ዐብይ ተገዳዳሪያቸውን ስልታዊ በሆነ መልኩ እያገለሉ ነው» ዶ/ር ደሣለኝ ጫኔ
news-56229305
https://www.bbc.com/amharic/news-56229305
መስፈርት ሳያሟሉ የኮቪድ-19 ምርመራ ለሚያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ የኮቪድ-19 ምርመራ የሚያደርጉ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ሰጠ።
ኢንስቲትዩቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ የኮቪድ-19 ምርመራ የሚያደርጉ ተቋማት መኖራቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል። “በቅርቡ ‘የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እናደርጋለን እስከ 6 ሰዓትም ውጤት እናሳውቃለን’ እያሉ ማስታወቂያ የሚያሰራጩ ተቋማት መኖራቸውን ደርሰንበታል” ብሏል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ባወጣው መግለጫ። ኢንስቲትዩቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሶ፤ የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። በምርምር ተቋማት፣ በክልል ላብራቶሪዎች፣ በዩኒቪርቲዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት ጋር በመተባበር የኮቪድ-19 ምርመራ ተቋማት ተስፋፍተዋል ብሏል። ኢንስቲቲዩቱ እስካሁን ተገቢውን መስፈርት ያሟሉ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ፍቃድ የተሰጣቸው የግል ተቋማት ብዛት 15 ናቸው ያለ ሲሆን የተቋማቱን ዝርዝር በፌስቡክ ገጹ ላይ አውጥቷል። ኢትዮጵያ እስካሁን ከ2 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርምራ አድርጋ 158ሺህ 053 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጣለች። ከጤና ሚንስቴር በሚሰጠው ዕለታዊ የኮቪድ-19 ወቅት መግለጫ መሠረት ቫይረሱ በኢትዮጵያ ሪፖርት ከተደረገ ወዲህ 134ሺህ 736 ሰዎች ከበሽታው ሲያገግሙ፤ 2ሺህ 354 ሰዎች ከበሽታው ጋር በተያያዙ ሕመሞች ህይወታቸው አልፏል።
44150425
https://www.bbc.com/amharic/44150425
ኢትዮ ቴሌኮም... ወዴት? ወዴት?
ከአንድ ሳምንት በፊት ኢትዮ ቴሌኮም ለመኖሪያ ቤቶችና ድርጅቶች የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሰጥ ለሃገር በቀል የግል ድርጅት ፍቃድ ሰጥቻለሁ ብሎ ካሳወቀ በኋላ ዜናው የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
በርካቶች የኢትዮ ቴሌኮም እርምጃ የተሻለ የኢንተርኔት አገልግሎትን ለማግኘት መልካም አጋጣሚ ነው በማለት ተስፋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ መንግሥት የግል ኩባንያዎች የቴሌኮም ዘርፉን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ አስቧል ይህም የመጀመሪያው እርምጃ ነው በማለት የሚከራከሩ የዘርፉ ባለሙያዎች አሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ ፍቃድ የተሰጠው ድርጅት ሃገር በቀል አይደለም፣ ባለቤቶቹም ከመንግሥት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚሉ ክሶችን ጭምሮ በርካታ አስተያየቶች በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ሲንሸራሸር ቆይቷል። ከኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎት ለማቅረብ ፍቃድ ከወሰዱት ድርጅቶች መካከል አንዱ አቶ ብሩክ ሞገስ የሚያስተዳድሩት ጂቱጂ (G2G) ግሩፕ ይገኝበታል። አቶ ብሩክ ጂቱጂ ግሩፕ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሴክተሩን በአራት ከፍሎ እየሰራ የሚገኘ ኩባንያ ነው ሲሉ ስለሚመሩት ድርጅት ያስረዳሉ። ከአራቱ ምድቦች መካከል አንዱ ጂቱጂ አይቲ ክላሪቲ አንዱ ሲሆን የኢትዮ ቴሌኮም አጋር እና በቅርቡ ለመኖሪያ ቤቶች እና መስሪያ ቤቶች የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀ ድርጅት መሆኑንን ያስረዳሉ። ጂቱጂ ከዚህ ቀደም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የአጭር የጽሁፍ መልዕክትን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎችን ሲሰራ እንደቆየ አቶ ብሩክ ያስታውሳሉ። የቴሌኮም ዘርፉን ወደ ግል የማዘዋወር የመጀመሪያ እርምጃ? የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ኢትዮ ቴሌኮም የተወሰኑ አገልግሎቶቹን የግል ኩባንያዎች በማሳተፍ እያስፋፋ ይገኛል ይላሉ። እንደምሳሌም ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢትዮ ቴሌኮም የሲም ካርድ ሽያጩን የግል አከፋፋዮችን በመጠቀም ወደ ገበያ ማቅረቡን የሚያስታውሱት አቶ ዘመዴነህ፤ ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ተሞክሮ የሲም ካርድ ሽያጩን በከፍተኛ ደረጃ ከፍ እንዳደረገለት ይናገራሉ። "አሁንም የግል ኩባንያዎችን በማሳተፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስፋፋት ይህን ፕሮግራም እንዳስጀመረ እንጂ በእኔ ግምት የቴሌኮም ዘርፉን ወደ ግል የማዘዋወር እርምጃ ሆኖ አይታየኝም" ይላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህር የሆኑት አቶ ጉታ ለገስ በበኩላቸው የቴሌኮም ዘርፉን ወደ ግል ለማዘዋወር ይህ የመጀመሪያው ትንሹ እርምጃ ነው ይላሉ። እንደ አቶ ጉታ ከሆነ የተለያዩ ዘርፎችን ወደ ግል ለማዘዋወር ብዙ ደረጃዎች መታለፍ አለባቸው። ከዚህ አንጻርም የግል ኩባንያዎች የኢንተርኔት አገልግሎቱ እንዲሰጡ ማስቻል የመጀመሪያዋ ትንሿ እርምጃ ነች ሲሉ ያስረዳሉ። የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሃላፊ የሆኑት አቶ አብዱራሂም አህመድ በበኩላቸው የቴሌኮም ዘርፉን ወደግል የማዘዋወር እርምጃ ነው የሚለው ''የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው። የሞባይል ካርድ እንዲሸጡ ፍቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች፤ የሞባይል ካርዶችን ከቴሌ በብዛት ገዝተው እንደሚቸረችሩት ሁሉ ይህም ድርጅት ከእኛ ይገዛና ለደንበኞቹ ያስተላልፋል እንጂ የፖሊሲ ለውጥ የለም'' ሲሉ ተናግረዋል። የአገልግሎት ጥራት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ተክሊት ሃይላይ የኢንተርኔት አገልግሎት በግል ኩባንያዎች አማካኝነት ለደንበኞች እንዲደርስ ማድረጉ ተደራሽነቱን ከፍ ያደርጋል እንዲሁም የተጠቃሚውን ቁጥር ይጨምራል ባይ ናቸው። እንደ አይሲቲ ባለሙያው ከሆነ የኢትዮ ቴሌኮም /ኮር ኔትዎርክስ/ ዋና ኔትዎርኮች ብዙ ወጪ የፈሰሰባቸው እና ጥራታቸው አስተማማኝ ነው። አቶ ተክሊት ''የኢትዮ ቴሌኮም የኔትዎርክ ችግር የሚከሰተው ከአክሰስ ኔትወርክ ነው። በየሰፈሩ የሚገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ማከፋፈያ ሳጥኖች እስከ ደንበኛው ድረስ ያለው መስመር በተደጋጋሚ ችግር ያጋጥመዋል ይህም በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ ችግር ያስከትላል'' በማለት ያስረዳሉ። የጂቱጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ በበኩላቸው በየሰፈሩ ከሚገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ማከፋፈያ ሳጥኖች እሰከ ደንበኛው ድረስ ያለው የመስመር ችግርን በመቅረፍ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ያስችለናል ይላሉ። እንደ አቶ ብሩክ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮ ቴሌኮም ከሚሰጠው የኢንተርኔት ዋጋ ለመኖሪያ ቤቶች ከ10 እሰከ 50 በመቶ እንዲሁም ለንግድ ድርጅቶች ከ5-20 በመቶ ቅናሽ እናደርጋለን ብለዋል። የድርጅቱ ባለቤትነት ከዓመታት በፊት ከመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስቴር በስድስት ዓይነት የኢትዮ ቴሌኮም ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍቃድ እንደተሰጣቸው፤ ከእነዚህም መካከል አንዱ አሁን የተጀመረው የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሆነ አቶ ብሩክ ይናገራሉ። የድርጅቱ ባለቤት የማን እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ብሩክ ሲመልሱ ''ድርጅቱ የአክሲዮን ማህበር ነው። የማህበሩን አባላትን ይፋ ማድረግ አልሻም፤ ይሁን እንጂ ከድርጅቱ ባለቤቶች መካከል መግለጫ የሰጠነው እኔ እና ባልደረባዬ ቴዎድሮስ መሃሪ እንገኝበታለን'' ብለዋል። ''ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቴ በፊት ኤ ኤንደ ዲ አይቲ ሶሉሽንስ የሚባል ድርጅት በአትላንታ አሜሪካ አቋቁሜ ነበር። ይህን ድርጅት በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የተለያዩ ሥራዎችን ለመስራት ስሞክር ተጨማሪ አጋሮች በማግኘቴ ጂቱጂ የሚባል በኢትዮጵያ የተመዘገበ ሃገር በቀል ድርጅት መሰረትን'' ሲሉ ይናገራሉ። የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ሃላፊው አቶ አብዱራሂም ስለ ጂቱጂ ግሩፕ ሲናገሩ ''ይህ ድርጅት ጎልቶ ወጣ እንጂ አጠቃላይ ይህን አገልግሎት እንዲሰጡ ለ8 ድርጅቶች ፍቃድ ሰጥተናል። ዋናው ነገር ከመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስቴር የሚሰጠውን ፍቃድ የሚያገኝ ድርጅት አገልግሎቱን ለመስጠት በዘርፉ ሊሰማራ ይችላል'' ብለዋል።
news-48488713
https://www.bbc.com/amharic/news-48488713
አሜሪካ የቪዛ አመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ እንደምትፈልግ አስታወቀች
ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ የሚያመለክቱ ሁሉ የሚጠቀሙትን የማህበራዊ ሚዲያ ዝርዝር መረጃ መስጠት የሚያስገድድ አዲሱ ሕግ ወጣ።
የቪዛ አመልካቾች የሚጠቀሙትን የማህበራዊ ሚዲያ ስም ማስገባት ይጠበቅባቸዋል ይህ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሕግ እንደሚለው ሁሉም ሰው የሚጠቀመውን የማህበራዊ ሚዲያ ስምና ላለፉት አምስት ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የኢሜይል አድራሻ እና የስልክ ቁጥር መስጠት ይጠበቅበታል። • እንግሊዝ አጭበርባሪ ባለሀብቶችን ቪዛ ልትከለክል ነው • የአይኤስ አባል የነበረችው አሜሪካ እንዳትገባ ተከለከለች ሕጉ ባለፈው ዓመት ለውይይት ሲቀርብ በዓመት 14.7 ሚሊየን ሰዎች ላይ ተፅእኖ ሊያሳድር እንደሚችል ባለሥልጣናቱ ግምታቸውን አስቀምጠው ነበረ። ይህ ሕግ በዲፕሎማሲያዊ መንገድና በመንግሥት ደረጃ ቪዛ የሚጠይቁ አመልካቾችን አይመለከታቸውም ተብሏል። ነገር ግን ለትምህርትም ሆነ ለሥራ ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቪዛ የሚያመለከት ማንኛውም ሰው የተጠየቀውን መረጃ አሳልፎ መስጠት የግድ ነው። "ሕጋዊ የሆኑ ሰዎች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ለማድረግ እና የአሜሪካ ዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የቪዛ አመልካቾችን አጣርተን የምንቀበልበት መላ ስናስስ ቆይተናል" ሲል ይህ አንደኛው መንገድ መሆኑን የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል። ቀደም ሲል ይህን መሰል ተጨማሪ መረጃ እንዲያቀርቡ ይገደዱ የነበሩት በሽብርተኛ ቡድኖች ቁጥጥር ሥር ከሚገኙ አገራት የሚመጡ እና ወደ እነዚህ ሃገራት የተጓዙ አመልካቾች ነበሩ። • አሜሪካ ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ አዲስ የጉዞ ዕገዳ አወጣች አሁን ግን ማንኛውም የቪዛ አመልካች የሚጠቀመውን የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት እንዲሁም በሌሎች ድረ ገፅም ላይ ያላቸውን ዝርዝር መረጃ በፈቃደኝነት እንዲያሳውቁ ይጠየቃሉ። ስለሚጠቀሙት ማህበራዊ ሚዲያ የሀሰት መረጃ የሚሰጡ ሰዎች ካሉም የማይወጡት ችግር ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ዘ ሂል ለተባለ ሚዲያ ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል። የዚህን ሕግ ሃሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀረቡት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሲሆኑ ያቀረቡትም ባለፈው ዓመት ነበር። በወቅቱ የአሜሪካ 'ሲቪል ሊበርቲስ ዩኒየን' የተሰኘ የሰብዓዊ መብት ቡድን እነዚህ ማህበራዊ ሚዲያዎች ውጤታማ ወይም ሚዛናዊ እንደሚሆኑ የሚያመላክት ምንም ማስረጃ የለም ሲሉ ተቃውመውት ነበር። ፕሬዝደንት ትራምፕ በአውሮፓውያኑ 2016 የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸው በሥልጣን ዘመናቸው ትኩረት ሰጥተው ከሚሰሩበት አንዱ የስደተኞች ጉዳይ መሆኑን ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ፕሬዝደንቱ ባለፈው አርብም ሜክሲኮ በደቡባዊ የአሜሪካ ድንበር ተሻግረው የሚገቡ ስደተኞችን መቆጣጠር ካልቻለች አሜሪካ ቀስ በቀስ የንግድ ታሪፍ ጭማሪ እንደምታደርግ ፕሬዝዳንቱ አስጠንቅቀዋል።
news-48500960
https://www.bbc.com/amharic/news-48500960
የስዊዝ ፍርድ ቤት ለካስተር ሰሜንያ ፍርድ ሰጠ
ካስተር ሰሜንያ የቴስቴስትሮን መጠኗን ለመቀነስ መድሃኒት መውሰድ አያስፈልጋትም ሲል የስዊዝ ፍርድ ቤት የዓለም አቀፉን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግን ላልተወሰነ ጊዜ አገደ።
ሰሜንያ የኦሎምፒክ 800 ሜትር ሁለት ጊዜ አሸናፊ ነች ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቴስቴስትሮን ለሴት ሯጮች ከፍተኛ ጉልበት ስለሚሆን እንደ ሰሜንያ ያሉ ይህ ሆርሞን በከፍተኛ መጠን ያላቸው ሴት ሯጮች በውድድር ፍትሃዊ ያልሆነ ብልጫ ያሳያሉ በሚል ነው የቴስቴስትሮን መጠን በመድሃኒት መገደብ አለበት የሚል ህግ ያወጣው። የ800 ሜትር ኦሎምፒክ ሻሚፒዮን የሆነችው የ28 ዓመቷ ደቡብ አፍሪካዊት ሯጭ ካስተር ሰሜንያ 'ቴስቶስትሮን' መጠንን ለመቀነስ መድሃኒት መውሰድ አለብሽ የሚለውን የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን ወደ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም (ካስ) ወስዳዋለች። • ፆታዋ ያከራከረው ሯጭ በፍርድ ቤት ተረታች • ደቡብ አፍሪካዊቷ ሯጭ ለፍርድ ቤት ይግባኝ አለች ጉዳዩን ሲመለከት የነበረው የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም (ካስ)ጥያቄዋን ውድቅ አድርጎባት ነበር። የካስን ውሳኔ ተከትሎ "ላለፉት አስርት ዓመታት ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከዓላማዬ ሊያደናቅፈኝ ሞክሯል፤ ይሁን እንጂ ይህ ጠንካራ እንድሆን አድርጎኛል፤ ተቋሙ ያስተላለፈው ውሳኔም ከዓላማዬ ሊያቆመኝ አይችልም።" ያለችው ሰሜንያ፤ ጉዳዩን ወደ ስዊዘርላንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ እንደምትል አስታውቃ ነበር። እንዳለችውም ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የስዊዚ ፍርድ ቤት ካስተር ሰሜንያ የቴስቴስትሮን መጠኗን ለመቀነስ መድሃኒት መውሰድ አያስፈልጋትም በማለት የዓለም አቀፉን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግን ላልተወሰነ ጊዜ አግዷል። ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ ''የፍርድ ቤቱን ዳኞች ማመስገን እፈልጋለሁ። ከአሁን በኋላ በነጻነት መወዳደር እችላለሁ።'' ብላላች ሰሜንያ።
news-55397489
https://www.bbc.com/amharic/news-55397489
ጁፒተር እና ሳተርን መንገድ ላይ ሊገናኙ ነው
ጁፒተር እና ሳተርን አንድ ላይ ገጥመው አንድ ፕላኔት መስለው እንደሚታዩ ሳይንቲስቶች ጠቁመዋል።
ይህ የጁፒተር እና ሳተርን ጥምረት የሚፈጥረው ብርሃን ዛሬ ምሽት ሊታይ እንደሚችልም ተነግሯል። ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ሰማይ ላይ እጅግ ደማቅ ብርሃን ታይቶ እንደነበር የሚናገሩት ሳይንቲስቶች ይህ ክስተት አሁን ሊፈጠር ይችላል ከተባለው ጋር ተመሳሳይነት ሳይኖረው አይቀርም ይላሉ። ይህ ክስተት 'ዘ ስታር ኦፍ ቤቴልሄም' ወይም የቤቴልሄም ኮከብ ተብሎ ይጠራል። ፕላኔቶቹ ከቀን ቀን እየተቀራረቡ መጥተው ዛሬ ምሽት ታኅሣሥ12/2013 ደማቅ ብርሃን ሊፈነጥቁ እንደሚችሉ ይጠበቃል። አውሮፓውያን አሁን ያሉበት የክረምት ወቅትና ደመና ተባብረው ይህን የብርሃን ትርዒት እንዳይከለክሏቸው ሰግተዋል። "እውነት ለመናገር የአየር ሁኔታው አስተማማኝ አይደለም" ይላሉ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የአስትሮኖሚ ተቋም ምሁሯ ዶክተር ካሮሊን ክራውፎርድ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ። ነገር ግን በደመና መካከል በተገኘ ቀዳዳ ሁለቱ ፕላኔቶች ገጥመው የሚፈጥሩት ብርሃን ሊታይ እንደሚችል ተነግሯል። ይህ ዳግማይ የቤቴልሄም ኮከብ መመለስ ይሆን? አንዳንድ የህዋ ጥናት ተመራማሪዎች 'አዎ' ሊሆን ይችላል ይላሉ። የቨርጀኒያ ኮሌጅ የኃይማኖት አጥኚው ፕሮፌሰሩ ኤሪክ ቫንዴን ሁለቱ ፕላኔቶች የሚገጥሙበት ሰዓት ሰዎችን ለሴራ ትንታኔ አጋልጧል ይላሉ። "ምናልባት ይህ ጊዜ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ካለው ክስተት ጋር ተመሳሳይነት አለው ወይ የሚለው አነጋጋሪ ሆኗል። ዮሴፍ፣ ማርያምና የክርስቶስ መወለድን የሚተርከው የመፅሐፍ ቅዱስ ክስተት የብርሃን መፈንጠቅን ያካተተ ነውና" ይላሉ ምሁሩ። በ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀርመናዊው አስትሮኖመር 'ዘ ስታር ኦፍ ዎንደር' በማለት ጁፒተርና ሳተርን በጣም ተቀራርበው ያመነጩትን ብርሃን ገልፆት ነበር። "ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ሰዎች ሰማይ ላይ ምን እንየተከናወነ እንዳለው በደንብ ያውቁ ነበር" የሚሉት ደግሞ ዶ/ር ክራውፎርድ ናቸው። ስለዚህ የቤቴልሄም ኮከብ የመሆኑ ነገር አጠራጣሪ ነው ባይ ናቸው። ይህ ክስተት በስንት ጊዜ ይከሰታል? ፕላኔቶች በፀሐይ ዙሪያ አንድ መስመር ላይ ሲገናኙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባይሆንም የአሁኑ ግን ለየት ይላል። እኒህ ክስተቶች ለእይታ መልካም ናቸው፤ አልፎ አልፎ ይከሰታሉ። ነገር ግን ሁለት ፕላኔቶች ይህን ያክል ሲቀራረቡ ማየት እጅግ አስደናቂ ነው የሚሉት የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ቲም ኦብራያን ናቸው። ሕዋ ላይ ሁለቱ ግዙፍ የሆኑት ፕላኔቶች ላለፉት 800 ዓመታት ሰማይ ላይ ይህን ያክል ተቀራርበው አያውቁም። ሁለቱ ፕላኔቶች በጥምረት የሚፈነጥቁት ብርሃን መሸትሸት ሲል ሊታይ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
news-56100771
https://www.bbc.com/amharic/news-56100771
ትግራይ ፡ በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመላው ትግራይ ዳግም ኃይል ተቋረጠ
በመላው የትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዳግም መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በክልሉ የኃይል መቋረጥ ያጋጠመው ማክሰኞ የካቲት 09/2013 ዓ. ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ነው። በመላው አገሪቱ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚያስተዳድረው ተቋሙ እንዳለው "የጁንታው ርዝራዦች" ያላቸው በክልሉ ባለ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በፈፀሙት ጥቃት በመላው ትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡን ገልጿል። የተጠቀሱት ኃይሎች አዲጉዶም ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከአላማጣ - መሆኒ - መቀለ በተዘረጋ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በፈጸሙት ጥቃት በክልሉ ኤሌክትሪክ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገልጿል። የትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከሚያገኝባቸው መስመሮች አንዱ የሆነውና ጥቃት የተፈጸመበት የአላማጣ - መሆኒ - መለለ መስመር ሲሆን ሌላኛው የተከዜ አክሱም መስመር ደግሞ የጥገና ሥራው እየተከናወነ እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል። "የተቆረጠው ማስተላለፊያ መስመር ነው። ይህ ነው ኃይል እንዲቋረጥ ያደረገው። ጉዳቱ ይሄ ብቻ ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያልቃል። ሌሎች ጉዳቶች ደርሰው ከሆነ ግን መስመሮቹን መፈተሽ ያስፈልጋል" ብለዋል አቶ ሞገስ። በደረሰበት ጥቃት ለኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት የሆነው ይህ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረ ሲሆን ለመጠገንም ረዘም ያለ ጊዜ እንደወሰደ ተቋሙ አመልክቷል። በጥቅምት ወር መጨራሻ ላይ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በደረሰ ጉዳት ለረዥም ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን በክልሉ ያሉ የተለያዩ አካባቢዎች ኃይል መልሰው ለማግኘት ረዘም ላለ ጊዜ ለመጠበቅ ተገደው ቆይተው ነበር። በትግራይ ክልል ውስጥ በተዘረጉ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መሠረተ ልማቶች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ሳቢያ ሕዝቡ ከኃይል አቅርቦት ውጪ ከመሆኑ ባሻገር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የወጣባቸው የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች መውደማቸው መገለጹ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በደረሰባቸው ጥቃት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑትን ለትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀርብባቸውን መሠረተ ልማቶች በመጠገን የክልሉ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲመለስ እየሠራ መሆኑን ገልጿል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት፣ ማክሰኞ፣ በትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ላይ ባስተላለፈው መግለጫ ክልሉ እንዳይረጋጋ ለማድረግ የሚሞክሩ "የተበተኑ የህወሓት ኃይሎች" እንዳሉና ሕዝቡም ለእነዚህ ኃይሎች መጠጊያ እንዳይሰጥ ማሳሰቡ ይታወቃል። ጊዜያዊው አስተዳደር በመግለጫው "የተበተኑ" ያላቸው የህወሓት ኃይሎች በሕዝቡ ውስጥ መሸሸጋቸውን አመልክቶ "የጥፋት ኃይሎች በመንደሮችና በከተሞች ውስጥ ተሰማርተው የሕዝቡን ሠላም በማናጋት ወደ ሌላ የከፋ ቀውስ እንዲገባ እየሠሩ ነው" ብሏል። ጨምሮም በእነዚህ ኃይሎች ላይ ሊወሰድ በሚችለው እርምጃ ሕዝቡ እንዳይጎዳ "የጥፋት ኃይሎቹን አሳልፎ እንዲሰጥ ወይም ለደኅንነቱ ሲል ራሱን ከእነዚህ ኃይሎች እንዲያርቅ" አሳስቧል። በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የፌደራል መንግሥት በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ የክልሉ አስተዳዳሪ የነበረው የህወሓት አመራሮች ከስልጣን በማስወገድ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መደረጉ ይታወሳል። ወታደራዊ ግጭቱን ተከትሎ በክልሉ የኤሌክትሪክ ኃይል በመቋረጡ ምክንያት የውሃ፣ የባንክ፣ የስልክ፣ የኢንተርኔትና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ለረዥም ጊዜ ተቋርጠው ቆይተው አብዛኛው የክልሉ አካባቢ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘው በቅርቡ ነበር።
news-49030115
https://www.bbc.com/amharic/news-49030115
ስጋት ያጠላበት የሲዳማ የክልልነት ጥያቄና የሀዋሳ ክራሞት
ሰኞ ሐምሌ 8/2011 ዓ.ም ጠዋት አራት ሰዓት አካባቢ የሞተር ሳይክል ጡሩንባ በከተማዋ መስተጋባት ጀመረ። በደስታ የሚጨፍሩ ወጣት ወንድና ሴቶች በቡድን ሆነው በመሃል ሐዋሳ ውስጥ በብዛት መታየት ጀመሩ።
በተለይ አቶቴ ተብሎ በሚታወቀውና በርካታ የሲዳማ ብሔር አባላት የሚኖሩበት የሐዋሳ ክፍል የፈንጠዝያው ማዕከል ነበር። በከባድ መኪኖች ላይ እየተጫኑ ወደ ስፍራው የሚያመጡ ሰዎች ቁጥሩ እየጨመረ እንዲመጣ አደረገው። በቡድን የተሰባሰቡ ሰዎች ደስታቸውን ለመግለጽ ከሐይማኖታዊ ዜማዎች ጋር የተቀላቀሉ የተለያዩ ዘፈኖችን ያሰሙ ነበር። በተሰበሰቡት ሰዎች በብዛት ሲዜሙ ከነበሩት መዝሙሮች መካከል በሲዳማ ቋንቋ የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያመለክቱ በሲዳምኛና በአማርኛ "አሁን ምን ይላል ጠላቴ" እንዲሁም "ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ" የሚሉት መዝሙሮች ደስታቸውን ለማድመቅ ሲያዜሙ ነበር። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው ? • በሲዳማ ክልልነት ጉዳይ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የምርጫ ቦርድ ወሰነ አንዳንዶች "የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት" የሚል ጽሁፍ የሰፈረባቸውን ከናቴራዎች ደስታቸውን ለሚገልጹት ሰዎች ሲሸጡ፤ ሌሎች ከደስታቸው ብዛት በመንገድ ላይ ያገኙትን ሁሉ እያቀፉ 'እንኳን ደስ አላችሁ' ሲሉ ነበር። ይህ የደስታ ስሜት በከተማዋ ውስጥ የተፈጠረው የክልሉ ገዢ ፓርቲ ደኢህዴን የሲዳማ ዞን ራሷን የቻለች ክልል እንድትሆን ከሚያስችል ውሳኔ ላይ ደርሷል የሚል ወሬ በመሰማቱ ነበር። ምንም እንኳን የዚህን ወሬ እውነተኛነት የሚያረጋግጥ ከሚመለከተው አካል የተገኘ ማረጋገጫ ባይኖርም ጥያቄው ክልል በመሆን ምላሽ እንደሚያገኝ እምነት ነበራቸው። ነገር ግን ምንም ሳይሰማ ቀኑ አለፈ። በቀጣዩ ቀን ሐዋሳ በእርግጠኝነትና ግራ በመጋባት ውስጥ ስትዋልል ዋለች። የሰኞ እለቱ የአደባባይ ፈንጠዝያ ማክሰኞ እለት ጉዱማሌ በሚባለው ቦታ ላይ በተደረጉ ስብሰባዎች ተተካ። ስብሰባዎቹም የሚጠበቀው ምላሽን የበለጠ እንዲጠበቅ አደረገው። ከዚያም በተከታታይ ከደኢህዴን፣ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ከሲዳማ ዞን አስተዳደር ጉዳዩን በተመለከተ የተሰጡት መግለጫዎች ከፍ ብሎ የነበረውን የደስታ ስሜት ቀዝቀዝ እንዲል አደረጉት። ስጋትና ውጥረት በእርግጥም የሲዳማ ክልል የመሆን ነገር ተቀባይነት አግኝቷል የተባለው ወሬ ከተሰማ በኋላ ባሉት ቀናት የተስተዋለው የደስታ ጭፈራና መዝሙር ብቻ አልነበረም። ቀይ ቆብ ያጠለቁ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በክፍት መኪኖች ላይ ሆነው የከተማዋን ዋና ዋና አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ይቃኙ ነበር። ይህም የሲዳማ ብሔር የመብት ተከራካሪዎች ሐምሌ 11 ያለማንም ፈቃድ ክልል የመሆን ጥያቄያቸውን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ካሳወቁ በኋላ በሕብረ ብሔሯ ከተማ ሐዋሳ ላይ ውጥረት መንገሱን የሚያመለክት ነው። የሲዳማ ብሔር አባል ያልሆነ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደተናገረው የወታደሮቹ በከተማዋ ውስጥ መሰማራት ደህንነት እንዲሰማኝ አድርጎኛል ይላል። "እውነቱን ለመናገር መጥፎ ነገር ቢከሰት በክልሉ ፖሊስ ላይ እምነት የለኝም" ሲል ያክላል። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች ለዚህም አባባሉ ከዓመት በፊት በከተማዋ ተከስቶ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን የብሔር ግጭት እንደ ምሳሌ ይጠቅሳል። ነገር ግን የሲዳማ ብሔር መብት አቀንቃኞች አንዳንዶች እንደሚሰጉት አዲስ ክልል ሲመሰረት ማንነትን መሰረት ያደረገ መድልኦ ወይም ጥቃት ሲዳማ ባልሆኑት ላይ ሊከሰት ይችላል የሚለውን ጥርጣሬ አጥብቀው ይቃወሙታል። "የሲዳማን ሕዝብ ትግል ለማጠልሸት የሚደረጉ ቅስቀሳዎች አሉ" ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ ረዳት ፕሮፌሰርና የመብት ተከራካሪ የሆኑት ተሰማ ኤሊያስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ከዚህም መካከል ሌሎች ብሔሮችን በተለየ ሁኔታ ሊታዩ ይችላሉ የሚለው አንዱ ነው።" አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት የሲዳማ ክልል ሲመሰረት ከሌሎች ማህበረሰቦች ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት፣ ስለሐዋሳ ከተማና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ እቅዶችን የሚያወጣና የሚመራ ግብረ ኃይል ታዋቂ ሰዎችን አካቶ እየሰራ መሆኑ ይነገራል። የደረሰበትንም ከሐምሌ 19 በፊት ለምርጫ ያቀርባል ተብሎም ይጠበቃል። እምነት ማጣት ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሲዳማ መብት ተከራካሪዎችና ኤጀቶ የተባለው የሲዳማ ወጣቶች ስብስብ አባል ነን የሚሉ ሰዎች በሁኔታው እንዳዘኑና በክልሉ ገዢ ፓርቲን ደኢህዴን ላይ እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል። አንዳንዶቹ እንዲያውም የሲዳማን ክልል የመሆን ጥያቄ ፓርቲው ሲያደናቅፍ ቆይቷል በሚል ጣታቸውን ይቀስራሉ። "ደኢህዴን የሲዳማን ጥያቄ ለማስተናገድ ቁርጠኛ አይደለም። ሕዝበ ውሳኔው እንዲካሄድ ጠንክረው አልገፉም" ስትል ለቢቢሲ የተናገረችው ለምለም ጸጋዬ ናት። "ለዚህም ነው እንዲህ አይነት ችግር ውስጥ የገባነው።" • ኢትዮጵያ ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር እንዴት ትውጣ? • "ነገ ክልል መሆናችንን እናውጃለን" የኤጀቶ አስተባባሪ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞችና ታዛቢዎች እንደሚሉት የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ ችግር ላይ ተጨማሪ ሸክም ነው ይላሉ። በዓለም ዙሪያ የሚያጋጥሙ ቀውሶችን የሚከታተለው የኢንትርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የኢትዮጵያ ተንታኝ የሆነው ዊሊያም ዳቪሰን እንደሚለው በርካታ ብሔሮች ክልል የመሆን ጥያቄ ባቀረቡበት የደቡብ ክልል ውስጥ ያለው ችግር እጅግ ስር የሰደደ ነው። "ይህም መንግሥት ለመወሰን እንዲቸገር ካደረጉት ነገሮች መካከል ዋነኛው ነው። የሲዳማን ክልል የመሆን ጥያቄ ቢቀበል ቀጥሎ ምን ይከሰታል?" ሲል ይጠይቃል ዳቪሰን ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ። "የቀሩትን የዘጠኝ ብሔሮች ጥያቄ ይቀበላሉ? ካልተቀበሉ ሌሎቹ ምን ይላሉ? ከተቀበሉትስ ቀጥሎ የሚመጡ ክልል የመሆን ጥያቄዎችን ይቀበላሉ?" የመብት ተከራካሪው ተሰማ ከሲዳማ ሌላ ክልል የመሆን ጥያቄ ያቀረቡትን ቡድኖች በሙሉ ይደግፋል። ነገር ግን አነዚህ ጥያቄዎች እንዲነሱ የተደረገው የሲዳማን ጥያቄ ለማፈን ነው ሲል ለዚህም የክልሉን ገዢ ፓርቲ ይከሳል። "ይህ ካልሆነ ታዲያ እነዚህ ጥያቄዎች እስካሁን የት ነበሩ?" ሲል ይጠይቃል። ከዚህ ሁሉ ደስታና ግራ መጋባት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ የሲዳማን ክልልነት ለመወሰን የሚያስችል ሕዝበ ውሳኔ በወራት ውስጥ እንደሚያካሂድ አስታወቋል። መግለጫውን ተከትሎ አንድ ወጣት ለቢቢሲ "ጥቂት ወራትን ለመታገስ ችግር የለብኝም" ካለ በኋላ ስጋቱን ይገልጻል። "ነገር ግን እኔ የምፈራው፤ ጥያቄያችን ከእጃችን ተነጥቆ ቢወሰድስ?"
news-48864603
https://www.bbc.com/amharic/news-48864603
"መንግሥት አይወክለኝም ለሚሉ ወገኖች ምርጫ ምላሽ ይሰጣል" ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
ከሁለት ሳምንት በፊት በባህር ዳርና በአዲስ አበባ ከፍተኛ አመራሮችና ጄነራሎች መገደላቸው "አገሪቷ ያለችበትን የፖለቲካ ችግር በግልጽ አሳይቷል" ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለቢቢሲ ተናገሩ።
ሕዝብ በመንግሥት ላይ ቅሬታ ካለው፣ መንግሥት እየበደለኝ ነው ወይም እያገለገለኝ አይደለም ብሎ ካመነ እንዲሁም በአገሪቱ ትልቅ ክፍተቶች ካሉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ለማድረግ የሚነሳሳ ኃይል ሊኖር ይችላል ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ያስረዳሉ። ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ተከትሎ በሀይል ለሕዝብ ምላሽ እሰጣለሁ የሚል ቡድን ካለ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሊያደርግ ይችላል በማለትም ያክላሉ። • አዴፓ እነ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን "የእናት ጡት ነካሾች" አለ የሕዝብን ጥያቄ በመፈንቅለ መንግሥት አንመልሳለን ብለው የሚነሱ ሀይሎች ለሚወስዱት እርምጃ በቂ ምክንያት አላቸው ወይስ የላቸውም? የሚለውን መመለስ የሚኖርባቸው ራሳቸው ኃይሎቹ ናቸው ይላሉ። "በአጠቃላይ የተፈጸመው ተግባር በአገሪቱ ውስጥ ችግር መኖሩን ነው ያሳየን" ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፤ መሰል ተግባር ከባድ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። ምርጫ እንደ አማራጭ መሰል ችግሮች መፍትሄ ከሚያገኙባቸው መንገዶች አንዱ ምርጫ ነው የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ፤ "ይህ መንግሥት አይወክለኝም ለሚሉ ወገኖችም ምርጫ ምላሽ ይሰጣል፤ ስለዚህ መፍትሄው ምርጫ ማካሄድ ነው" ይላሉ። በቀጣይ ዓመት እንዲካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት ምርጫ ይዘራም ወይስ ይካሄድ? የሚለው ሀሳብ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሀሳብ ልዩነት ፈጥሯል። ገሚሱ ምርጫው በተያዘለት ጊዜ መካሄድ ይኖርበታል ያሉ ሲሆን፤ ሌሎች ደግሞ በአገሪቱ የሰላምና የደህንነት ስጋቶች እያሉ ምርጫ ማካሄዱ ትክክል አይደለም ይላሉ። የደህንነት ስጋት እያለ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም የሚሉት አካላት፤ "ሕዝቡን ማን ያረጋጋ? ሥራዎችን ማን ያከናውን? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ የላቸውም" ይላሉ ፕሮፌሰር መረራ። • ኢትዮጵያ ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር እንዴት ትውጣ? "ሕዝቡን አረጋግቶ ወደ ምርጫ የምንሄድበትን መንገድ ስርዓት ማስያዝ ነው እንጂ ፕሮፖጋንዳ መንዛት ብቻ መፍትሄ አይሆንም" ብለዋል። "መሬት ላይ አለ የሚሉትን ችግር ማን እንዲያስተካክልላቸው ነው የሚጠብቁት?" ሲሉም ፕሮፌሰር መረራ ይጠይቃሉ። መንግሥት እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን መፈጸም መቻል እንዳለበትና የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሁለት ጫፍ ረግጠው እርስ በእርስ ከመባላት ይልቅ መፍትሔ የሚሆን አጀንዳ ይዘው መሥራት እንዳለባቸውም ያስረዳሉ። ፕሮፌስር መረራ፤ ከሁሉም በላይ መንግሥት አገራዊ መግባባት ለማምጣት ሕዝባዊ ድጋፍ ካላቸው ፓርቲዎች ጋር ተቀምጦ መወያየት አለበት ይላሉ። "ሕዝቡ የመረጠው መንግሥት ስልጣን ላይ ሲወጣ ብቻ 'አትወክሉንም' የሚለው ጥያቄ ምላሽ ያገኛል'' የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ፤ በአሁኑ ወቅት እየታዩ ላሉት ችግሮች መፍትሄው ምርጫ ማካሄድ እንደሆነ ይናገራሉ። ፕሮፌሰር መረራ በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ የማይካሄድ ከሆነ አገሪቱ የባሰ ሰላምና መረጋጋት ሊርቃት እንደሚችል ይናገራሉ። • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን በምርጫ ቦርድ ውስጥ እየታዩ ያሉ ለውጦች እንዲሁም ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ቁጭ ብለው መነጋገራቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ እንደሚመለከቱት የሚናገሩት ፕሮፌሰር መረራ፤ ከዚህ በላይ ግን ለሕዝቡ ተስፋ የሚሰንቁ ነገሮች መሬት ላይ መታየት አለባቸው ይላሉ። ፕሮፌሰር መረራ ጨምረውም "በኢህአዴግ ውስጥ ያሉት አራቱ ፓርቲዎች ከመደማመጥና አብሮ ከመሥራት ይቅል እርስ በእርሳቸው መጠላለፍ ነው የያዙት ይህም በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው" ይላሉ።
news-47785829
https://www.bbc.com/amharic/news-47785829
አንበሳዋ እናት፡ የልጃቸውን ደፋሪ የገደሉት እናት ነጻ ወጡ
ኖኩቦንጋ ኳምፒ በደቡብ አፍሪካ "አንበሳዋ እናት" በመባል የታወቁት ልጃቸውን ከደፈሩ ሦስት ወንዶች መካከል አንዱን ገድለው ሌሎቹን ካቆሰሉ በኋላ ነው። በግድያ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ቢሆንም በሕዝብ ድምፅ ምክንያት ክሱ ተነስቷል።
አንበሳዋ እናት ኖኩቦንጋ ኳምፒ ነገሩ የጀመረው እኩለ ሌሊት ላይ የስልክ ጥሪ ኖኩቦንጋን ከእንቅልፍ ሲቀሰቅሳቸው ነበር። የደወለችውም ሴት ኖኩቦንጋ ሲፎካዚ የተባለችው ሴት ልጃቸው በሚያውቋቸው ሦስት ወንዶች መደፈሯን በዚያ ሌሊት ነበር የነገረቻቸው። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? ኖኩቦንጋ የመጀመሪያ እርምጃቸው ፖሊስ መጥራት ነበር፤ ነገር ግን የፖሊሶቹ ስልክ አይመልስም። በጊዜው ልጃቸውን መርዳት የሚችሉት እራሳቸው ብቻ ነበሩ። "በጣም ፈርቼ ነበር ግን ልጄ ናት፤ መሄድ ነበረብኝ" ይላሉ እናት ኖኩቦንጋ። "እዚያ እስክደርስ ትሞታለች ብዬ አስቤ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ እኛን ስለሚያውቁን እንዳትናገር ፈርተው በሕይወት አይለቋትም ብዬ አስቤ ነው።" በጊዜው ሲፎካዚ ጓደኞችዋን ለማግኘት ነበር እግሯን ወደዛች መንደር የመራቸው። በቆይታዋም ጓደኞችዋ በተኛችበት ለብቻዋ ጥለዋት በወጡበት አጋጣሚ ነበር የጠጡት ወንዶች ከተኛችበት ገብተው ጥቃት ያደረሱባት። • "በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት "ቢላ ይዤ የሄድኩት እራሴን እዚያ እስክደርስ ባለው መንገድ ላይ ለመከላከል ብዬ ነበር" ሲሉ ኖኩቦንጋ ሁኔታውን ያስታውሳሉ። "ከቢላው ጋር ስልኬን ለብርሃን ብዬ ይዤ ነበር።" ልጃቸው ወደ ነበረችበት ቤት ሲደርሱ ስትጮህ ሰሟት፤ ቤት ውስጥ ሲገቡም አንዱ ወንድ ልጃቸውን ሲደፍራትና ሌሎቹ ሁለት ወንዶች ደግሞ ሱሪያቸው ወልቆ ተራቸውን ሲጠባበቁ እንዳኟቸው ይናገራሉ። "በጣም ስለፈራሁ በር ላይ ቆሜ ምን እያደረጉ እንደሆነ ጠየኳቸው። እኔ እንደሆንኩ ሲያውቁ በቁጣ ተንደርድረው ወደ እኔ መጡ፤ ያኔ ነው እራሴን መከላከል እንዳለብኝ የገባኝ።" ክሱን ሲከታተል የነበረው ዳኛ ኖኮቦንጋ ልጃቸው ስትደፍር በአይናቸው ማየታቸው "በጊዜው በጣም ስሜታዊ" አድርጓቸዋል ብለዋል። • ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች ኖኩቦንጋም በጊዜው ይዘውት የነበረውን ቢላ በመጠቀም አንዱን ደፋሪ ገድለው ሌሎቹን በቆሰሉበት ትተው ልጃቸውን በቅርብ ወደ ሚገኝ ጎረቤት ወሰዷት። ፖሊሶችም ከቦታው ደርሰው ቦኩቦንጋን በቁጥጥር ስር ካደረጓቸው በኋላ በአቅራቢያ ወደ ሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወሰደወቸው። "ስለ ልጄ እያሰብኩ ነበር፤ ካዳንኳት በኋላ ስለእሷ ምንም አልሰማሁም። በጣም አስጨናቂ ጊዜ ነበር" ይላሉ። ልጅና እናት እናትዋ ወደ እስር ቤት ሲወሰዱ ሲፎካዚ ሆስፒታል ሆና ስለእናትዋ እያሰበች ነበር። "በፍርድ ቤት ተወስኖባት ለዓመታት የምትታሰር ከሆነ እኔ ቅጣቷን እቀበልላታለሁ እያልኩኝ አስብ ነበር" ትላለች። ሲፎካዚ በጊዜው ስለተፈጠረው ነገር እናትዋ ከነገሯት ነገር ውጪ ምንም አታስታውስም ነበር። በጊዜውም እናትና ልጅ አንዳቸው የአንዳቸው ደጋፊ ነበሩ። ቡህሌ ቶኒስ የኖኩቦጋ ጠበቃ ስትሆን ከጥቃቱ አንድ ሳምንት በኋላ ስታገኛቸው እናትና ልጅ በጣም ተስፋ ቆርጠው እንደነበር ታስታውሳለች። "ኖኩቦንጋ በጭንቀት ውስጥ ነበረች" ትላለች። "በጣም ድሃ የሆኑ ሰዎችን ስታገኚ ገንዘብ ስለሌላቸው እናትየዋ ወደ እስር ቤት የምትሄድ ይመስላቸዋል። ይህ ደግሞ ጥብቅና የሚቆምላቸው ሰው አለ ብለው ሰለማያስቡ ነው።" ቡህሌ ኖኩቦነጋ ክሱን ማሸነፍ እንደምትችል እርግጠኛ ብትሆንም ቀላል እንደማይሆን ገምታለች። ሁለቱም ግን ያልጠበቁት ነገር ቢኖር የማህበራዊ ሚዲያ የሚያደርግላቸውን ድጋፍ ነበር። በደቡብ አፍሪካ የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች ብዙም የማህበራዊ ሚዲያ ሽፋን አይሰጣቸውም፤ ነገር ግን የኖኩቦንጋ ድርጊት እናት ልጇን ለመከላከል ያላትን አቋም ማሳያ ነው በማለት የማህበራዊ ሚዲያውን ቀልብ ሳበ። የልጃቸውን ማንነት ላለመግለፅ ሲባል የኖኩቦንጋን ስም መጥቀስ ባልተቻለበት ጊዜ አንድ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም "አንበሳዋ እናት" ብሎ ምስላቸውን ሴት አንበሳ ከልጆችዋ ጋር አድርጎ ይፋ አደረገው። ይህም ስም በመላ አገሪቷ አስተጋባ። "መጀመሪያ ስሙን ስሰማ አልወደድኩትም ነበር፤ ልክ ግን የጀግንነት ምሳሌ መሆኑን ሳውቅ በጣም ደስ አለኝ" ይላሉ እናት። የደቡብ አፍሪካ ሕዝብ የኖኩቦንጋን ክስ በመተቸት የህግ አማካሪ ጠበቃ እንዲኖራት ገንዘብ አሰባሰቡ። "ወደ ፍርድ ቤት ስሄድ ስለፈራሁ ጠዋት ተነስቼ ፀለይኩኝ" ይላሉ። ኖኩቦንጋ ፍርድ ቤት ሲደርሱ በሰዎች ተሞልቶ ነበር ያገኙት። "ከመላዋ ደቡብ አፍሪካ የተሰባሰቡ ሰዎች ነበሩ። ለሰዎቹ አመሰግናለሁ እያልኩኝ እነሱ ሊደግፉኝ በመምጣታቸው በተስፋ ተሞላሁ።" "ፍርድ ቤት ስደርስ ክሱ እንዲነሳ ተወሰነ። በጣም ደስ አለኝ፤ ያኔ ዳኛው እኔ ሰውን የመግደል ሃሳብ እንዳልነበረኝ እንደተረዳ ገባኝ።" ቡህሌ ቶኒስ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሲፎካዚ ላይ የፈጠረውን ስሜት ታስታውሳለች። "ፍርድ ቤቱ ክሱን እንዳነሳ ኖኩቦንጋ ወደ ልጇ ደወለች። ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ሲፎካዚ ስትስቅ የሰማኋት ያኔ ነበር። እሷም ለእናትዋ ወንዶቹ እንዲታሰሩ እንደምትፈልግም ነገረቻት" ትላለች። ይህ ፍላጎቷ እውን እንዲሆን ከዓመት በላይ መጠበቅ ነበረባቸው። ከዚያም ባለፈው የታህሳስ ወር ላይ ሁለቱ ወንጀለኞች የ30 ዓመት እስራት ተወሰነባቸው። ሲፎካዚ "በውሳኔው ደስተኛ ነኝ፤ አሁን ደህንነት ይሰማኛል ነገር ግን የእድሜ ልክ እስራት ይገባቸው ነበር" ትላለች። ልክ ክሱ ሲጠናቀቅ ሲፎካዚ ሌሎች የዚህ ዓይነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶችን ለመደገፍ በማለት ማንነትዋን ለህዝብ ይፋ አድርጋለች። ኖኩቦነጋ በበኩላቸው በሚያስገርም ሁኔታ ልጃቸውን የደፈሩት ሰዎች ወደፊት ከእስር ሲወጡ መልካም ነገር ያደርጋሉ፣ ምሳሌም ይሆናሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
news-56659418
https://www.bbc.com/amharic/news-56659418
በዱባይ እርቃናቸውን ፎቶ የተነሱት ሴቶች ወደ አገራቸው ሊባረሩ ነው
በዱባይ ባለፈው ሳምንት እርቃናቸውን ፎቶ ተነስተው በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት የውጭ አገር ዜጎች በአስቸኳይ ወደ አገራቸው ሊባረሩ ነው፡፡
በትንሹ 12 ዩክሬናዊያን እና አንድ ሩሲያዊ በዚህ ‹ከባሕል ያፈነገጠ› በተባለ ድርጊት ጠርጥሮ የዱባይ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በዱባይ ማሪና አካባቢ በሚገኝ በረንዳ 12ቱ ሴቶች እርቃናቸውን ፎቶ የተነሱበት ቪዲዮ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ከተጋራ በኋላ ነበር የዱባይ ፖሊስ የውጭ ዜጎቹን አድኖ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው፡፡ በዱባይ የጋራ ባሕልና እሴትን የሚሸረሽሩና ከባሕል ያፈነገጡ የሚባሉ እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች እስከ 6 ወራት እስርና እስከ 5ሺህ ዲርሃም የሚያስቀጡ ናቸው፡፡ ዱባይ ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ የጎብኚዎች መዳረሻ ብትሆንም የራሷ ጥብቅና ምዕራባዊ ጎብኚዎችን የማያፈናፍኑ ሕጎች አሏት፡፡ በዱባይ አገሬው የሚገዛባቸው ሕጎች ጎብኚዎችም እንዲከተሏቸው አስገዳጅ የሆኑ ናቸው፡፡ ይህ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች በመቶ ሺዎች ተቀባብለውታል የተባለው ቪዲዮ 12 ዩክሬናዊያንና አንድ ሩሲያዊ የፎቶ ጥበብ ባለሙያ የእርቃን ፎቶ መነሳት ሥነ ሥርዓት ሲያደርጉ የሚያሳይ ነበር፡፡ ከ12ቱ ዩክሬናዊያን ሴቶች በተጨማሪ የየት አገር ዜጎች በዚህ ሕግ መተላለፍ ውስጥ እጃቸው አለበት የሚለው ገና እየተጣራ ነው፡፡ ፖሊስ ይህ ገላን አጋልጦ ፎቶ የመነሳት ተግባር የኢምሬቶችን እሴት የሚጻረር ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩሉ ዱባይ የሚገኘው ቆንጽላው በእስር ላይ የሚገኙትን 12ቱን ሴቶች እንደጎበኘ ይፋ አድርጓል፡፡ የዱባይ ሚዲያዎች የሚመለከታቸውን ባለሥልጣናትን ጠቅሰው እንደተናገሩት ሁሉም በዚህ ወንጀል ተሳትፎ ያላቸው ወደ አገራቸው እንዲባረሩ ይደረጋል፡፡ በዱባይ የውጭ ዜጎች በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ከአገር ሲባረሩ ይህ የመጀመርያው አይደለም፡፡ በ2017 እንደ አውሮጳዊያኑ አንዲት የእንግሊዝ ዜጋ ከአንድ ማንነቱ ካልተጠቀሰ ወንድ ጋር በትዳር ሳትተሳሰሪ ወሲብ ፈጽመሻል በሚል የአንድ ዓመት እስር ተላልፎባት ነበር፡፡ ስለ ግንኙነታቸው የተደረሰበት እንግሊዛዊቷ አንሶላ የተጋፈፈችው ሰው ማስፈራሪያ መልእክቶችን እየላከ ሲያስቸግራት ይህንኑ ለዱባይ ፖሊስ ባሳወቀችበት ጊዜ ነበር፡፡
56228217
https://www.bbc.com/amharic/56228217
ትግራይ፡ አሜሪካ የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ኃይሎች ከትግራይ መውጣት አለባቸው አለች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በትግራይ ይገኛሉ ያላቸው የኤርትራ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ኃይል ከክልሉ መውጣት አለባቸው አለ።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንሰትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ይህን ያለችው በትግራይ ክልል ውስጥ ግድያዎች ስለመፈጸማቸውና በክልሉ ያለው አጠቃላይ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን የሚገልጹ ሪፖርቶች በእጅጉ አሳስበውኛል ባለችበት መግለጫ ላይ ነው። የኤርትራ እና የአማራ ክልል ኃይሎች ከትግራይ መውጣታቸው ወሳኝነት ያለወቅ ቀዳሚ እርምጃ ነው ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ፤ በዚህም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት እራሳቸውን ከኃይል እርምጃዎች ቆጥበው በትግራይ ክልል ውስጥ ድጋፍ የሚያሻቸው ሰዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርሳቸው መፍቀድ ይኖርባቸዋል ብሏል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትም ይሁን የኤርትራ መንግሥት በትግራዩ ጦርነት ኤርትራ ተሳትፎ የላትም ቢሉም፤ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከዚህ ቀደም የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል መግባቱን የሚገልጽ መረጃ ማውጣቱ ይታወሳል። በአገሪቱ ክልሎች ውስጥ ከሚገኙ የክልል ልዩ የፖሊስ ኃይሎች መካከል አንዱ የሆነው የአማራ ልዩ ኃይል የፈደራሉ ሠራዊት ከህወሓት ኃይሎች ጋር ወታደራዊ ግጭት ውስጥ መግባቱን ተከትሎ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሆን ተሳታፊ እንደነበር በወቅቱ ተገልጿል። የአሜሪካ ውች ጉዳይ ኃላፊ የአንቶኒ ቢልንከን መግለጫ የወጣው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከ200 በላይ ሰዎች በአክሱም ከተማ በኤርትራ ወታደሮች ተገድለዋል የሚል ሪፖርት ማውጣቱን ተከትሎ ነው። "በተለያዩ ወገኖች የሚፈጸሙት ግድያዎች፣ በኃይል ማፈናቀልን፣ ጾታዊ ጥቆቶች እንዲሁም ሌሎች አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጥብቀን እናወግዛለን" ብሏል ትናንት የወጣው መግለጫ። አምነስቲ ዓርብ ዕለት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም ከተማ የፈጸሙት ግድያ በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን ይችላል ብሏል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ይህ በአምነስቲ የወጣው ሪፖርት "ባልተሟላ መረጃና ውስን በሆነ የጥናት ዘዴ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው" ሲል ተችቷል። ሚኒስቴሩ ለሪፖርቱ ግብአትንት ጥቅም ላይ የዋሉት መረጃዎች በምሥራቃዊ ሱዳን ከሚገኙ ስደተኞችና አክሱም ውስጥ ካሉ ግለሰቦች በስልክ የተሰበሰበ ቁንጽል መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው ብሎ፤ ከስደተኞች መካከልም አንዳንዶቹ የህወሓት የቀድሞ ተዋጊዎች የነበሩ ናቸው ብሏል። በተመሳሳይ ኤርትራ የአምነስቲን ሪፖርት እንደማትቀበለው ገልጻለች። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው ላይ ሪፖርቱ በአብዛኛው መሠረት ያደረገው ሱዳን መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉ 31 ግለሰቦችን ነው ብለዋል። "በዚህ መጠለያ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን በተገደሉበት የማይካድራው ጭፍጨፋ ተሳታፊ ሆነው የሸሹ የህወሓት ሚሊሻዎች መሆናቸው ይታወቃል" በማለት በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንሰትር አንቶኒ ብሊንክን በትናንትናው መግለጫቸው በትግራይ ክልል የተከሰተውን ቀውስ ማስቆም አስፈላጊነት ላይ፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ፣ እንዲሁም ተፈጽመዋል የተባሉ ግፎችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር የተሟላ፤ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ መርማሪ ቡድን እንዲገባ መፍቀድን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በተደጋጋሚ መነጋገራቸውን ገልጸዋል። የትግራይ ክልልን ያስተዳድር የነበረው ህወሓት በማዕከላዊው መንግሥት ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከተሎ ከተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ጋር ተያይዞ የተለያዩ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች መውጣታቸው ይታወሳል። የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ "ገለልተኛና ዓለም አቀፍ ምርመራ እንዲደረግና ጠፋተኞች ተጠያቂ መሆን አለባቸው" ብሏል። ይህ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጫ፤ ዓርብ ዕለት የጠቅላይ ሚንሰትሩ ጽ/ቤት እና የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ተፈጽመዋል የተባሉ በደሎችን ለመመርመር ዓለም አቀፍ ድጋፍን ለመቀበልና ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለማመቻቸት እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የገቡትን ቃል በበጎ ጎኑ እንደሚቀበለው አመልክቷል። አሜሪካም ይህን ግብ ለማሳካት ከሌሎች የዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ አካላት ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጿል። ለዚህም የአሜሪካ መንግሥት የእርዳታ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) አንድ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ህይወት አድን የእርዳታ ሥራ ላይ እንደሚሰማራ ተገልጿል። መግለጫው የተባበሩት መንግሥታትና ሌሎች አጋሮችን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለይም የአፍሪካ ሕብረት እና የቀጠናው አጋሮች በትግራይ ያለውን ቀውስ ለመፍታት ከአሜሪካ ጋር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል። በመጨረሻም አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ዘላቂ የሆነ ወዳጅነት ለመገንባት አሁንም ቁርጠና መሆኗን ገልጸዋል። ከቀናት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ ስለተከሰተው ቀውስ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር መወያየታቸውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ማስታወቁ ይታወሳል። ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች በስልክ በነበራቸው ወይይት፤ "በትግራይ ክልል እየተባባሰ ስለመጣው የሰብዓዊ ቀውስና የሰብዓዊ መብት ጥሰት" መነጋገራቸውን ዋይት ሃውስ ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ አመላክቷል። መሪዎች መሪዎቹ በትግራይ "ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ መከላከልና የሰብዓዊ ድጋፍ መድረስ አስፈላጊነት ላይ" ተነጋግረዋል ሲል የዋይት ሐውስ መግለጫ አመልክቷል።
news-51499402
https://www.bbc.com/amharic/news-51499402
ፓኪስታናዊው ሙሽራው ሠርጉን እንዲታደሙለት በጠራቸው እንግዶች ተደበደበ
አንድ ሙሽራ በራሱ ሠርግ ላይ በተቆጡ እድምተኞች መደብደቡ ከወደ ፓኪስታን ተሰምቷል።
አሲፍ ራፊቅ ሲዲቂ በአዲሷ ሙሽራ ቤተሰቦች ተደብድቧል ታዳሚዎቹ የተቆጡት የሙሽራው የመጀመሪያ ሚስት፤ አዲሷ ሙሽራ ግለሰቡ አንድ ሚስት ብቻ ሳይሆን ሁለት ሚስት እንዳለው እንዲያውቅ በሚል ሠርጉ ላይ በመገኘቷ ነው። ሙሸራው ከአሳዳጆቹ ለማምለጥ አውቶቡስ ስር በደረቱ ተስቦ የገባ ሲሆን ጉዳዩን ያላወቁ ሰዎች ከጥቃት እንደታደጉት ለማወቅ ተችሏል። በፓኪስታን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በሕግ የተፈቀደ ነው። • በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አቃቤ ሕግ አስታወቀ • የህዳሴው ግድብ ድርድር ያለስምምነት ተበተነ አንድ ወንድ እስከ አራት ሚስት ድረስ ማግባት ቢፈቀድለትም ነገር ግን የቀደሙት ሚስቶቹን ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅበታል። አሲፍ ራፊቅ ሲዲቂ የተባለው ይህ ሙሽራ ግን ይህንን ሳያደርግ በመቅረቱ አዲሱ ሚስቱና ቤተሰቦቿ ሠርጉ ላይ ድንገት ከተከሰተችው የቀድሞ ሚስቱ ይህንን ሊረዱ ችለዋል። ሙሽራው ሠርጉን እያካሄደ የነበረው በካራቺ የባህር ዳርቻ በምትገኝ ከተማ ሲሆን የሙሽራው የቀድሞ ሚስት ድንገት በታዳሚዎች መካከል ስትገኝ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ታይቷል። በዚህ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ የሙሽራዋ ዘመድ የሆነ "ምን ፈልገሽ ነው?" ብሎ ሲጠይቃት ይሰማል። ትንሽ ወንድ ልጅ ከጎኗ ሻጥ ያደረገችው ይህች ሴት ጊዜ ማባከን አልፈለገችም። በቀጥታ ወደ ጉዳይዋ በመግባት "መዲሃ ሲዲቂ እባላለሁ" አለች። "ሙሽራው ባለቤቴ ነው፤ የዚህ ልጅም አባት ነው። ከቤት የወጣው ሃይደርባድ ለሦስት ቀናት እንደሚሄድ ነግሮን ነው" በማለት አስረዳች። የሙሽራዋ ዘመዶች ይህንን ሲሰሙ እያካለቡ ወደጎን በመውሰድ ጉዳዩን በደንብ ማጣራት ጀመሩ። እርሷም አስከትላ የመጣችውን የሙሽራውን እናትና እህቱን በማሳየት አማቾቿ መሆናቸውን ተናገረች። "ባልተቤቴ መሆኑን አታውቁም ነበር? ስለዚህ ምንም ስለማያውቅ ልጅ እንኳ አላሰበም" በማለትም ጉዳይዋን አስረዳች። የሙሽራውና የመጀመሪያ ባለቤቱ መዲሃና ሳዲቅ የተጋቡት እኤአ በ2016 ካራቺ ፌደራል ኡርዱ ዩኒቨርስቲ ከተገናኙ በኋላ መሆኑን ሁሉ አብጠርጥራ ተናገረች። አክላም በሚስጥር ዘህራ አሽራፍን በ2018 ማግባቱን አስረዳች። የዚህንም ሰርግ ልታውቅ የቻለችው ባሏ ስልክ ላይ የተላከ መልዕክት በማየቷ መሆኑን አብራራች። አቶ ባል አሲፍ ራፊቅ ሲዲቂ፤ በመጀመሪያ አይኑን በጨው አጥቦ፣ አይኔን ግንባር ያርገው ብሎ ምሎ ተገዝቶ፣ ሚስቱን እንደማያውቃት ቢክድም በኋላ ግን አምኗል። • ሥጋት ያጫረው የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ሕግ ጸደቀ ከዚህ በኋላ ምን እንደሆነ ግልጽ ባይሆንም ቢቢሲ ወደ ፖሊስ ደውሎ እንዳጣራው ግለሰቡ ልብሱ ተቀዳዶ መደብደቡን መረዳት ችሏል። ፖሊስ በአካባቢው ደርሶ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ቢወስደውም የሙሽራዋ ቤተሰቦች ከፖሊስ ጣቢያ እስኪወጣ ድረስ ይጠብቁት ነበር ተብሏል። ከፖሊስ ጣቢያም ከወጣ በኋላ ከተቆጡ እድምተኞች ሸሽቶ ከአውቶብስ ስር ተደብቆ እንዲወጣ ሲጠይቁት፤ አለበለዚያ ግን አውቶብሱን በእሳት እንደሚያያይዙት ሲናገሩ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ይደመጣል። "አንድ ደቂቃ ብቻ ስጡኝ" እያለ ከአውቶብሱ ስር ለመውጣት ሲሳብና ሌሎች ሰዎች ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስበት ሲከላከሉ ይታያል። ቢቢሲ ሙሽራውንና ሙሽሪትን በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም። የአካባቢው ፖሊስም እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ክስ የመሰረተ አካል እንደሌለ ገልጿል። "የቤተሰብ ጉዳይ ነው። ቅሬታ አቅራቢዎች ጉዳያቸውን ይዘው ወደ ቤተሰብ ችሎት መሄድ ይኖርባቸዋል" ያሉት የራኦ ናዚም የታይሙሪሃ ፖሊስ ጣቢየያ አዛዥ ናቸው።
55825417
https://www.bbc.com/amharic/55825417
ጀርመን አዛውንት ዜጎቼን አስትራዜኔካ የኮቪድ ክትባትን አልከትብም አለች
የጀርመን የክትባት ኮሚቴ አስትራዜኔካ ክትባት መሰጠት ያለበት ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በታች ለሆኑት ብቻ ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ።
ኮሚቴው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በአዛውንቶች ላይ ክትባቱ ያስገኘው ውጤትን በተመለከተ በቂና የማያወላዳ ሳይንሳዊ ማስረጃ ባለመገኘቱ ነው። የአውሮጳ መድኃኒት ኤጀንሲ ዛሬ አርብ አስትራዜኔካ ክትባት ዕድሜያቸው ለገፉ ሰዎች ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ታላቋ ብሪታኒያ ይህን ክትባት በሁሉም ዕድሜ ላይ ለሚገኙ ዜጎቿ እየሰጠች ትገኛለች። የጤና ባለሙያዎችም ደኀንነቱ የሚያሰጋ አይደለም፤ ከፍ ያለ መከላከል አቅምም አለው ሲሉ ይናገራሉ። ጀርመን ግን ይህን አሳማኝ ሆኖ አላገኘችውም። የአውሮጳ ኅብረትና አስትራዜኔካ ኩባንያ ከሰሞኑ በምርት አቅርቦት ማነስ ምክንያት ሲነታረኩ ነው የከረሙት። ይህ የጀርመን ዜና የመጣውም ይህ አለመግባባት ባልተቋጨበት ወቅት ነው። አስትራዜኔካ እንደሚለው በአውሮጳ ያሉ መድኃኒቱን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ያሉባቸው ችግሮች ካልተቀረፉ ክትባቱን ለአውሮጳ በተባለው ጊዜ ለማድረስ እንደሚቸገር ይናገራል። ነገር ግን የአውሮጳ ኅብረት አስትራዜኔካ ውል ገብቷል፤ ውሉን ማክበር አለበት፤ በታላቋ ብሪታኒያ ያለውን ክምችት ለአውሮጳ ኅብረት ሊሰጥ ይገባል ይላል። ይህን ማድረግ ካልቻለ ወደ ሕግ እንደሚሄድም ኅብረቱ አስታውቋል። አስትራዜኒካ ብቻም ሳይሆን ፋይዘር እና ባዮንቴክም በተመሳሳይ ለ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት አባል አገራት ክትባት በወቅቱ ማድረስ እንደማይችል አስታውቋል። የጀርመን መንግሥትን በክትባቶች ዙርያ የሚያማክረው የባለሙያዎች ኮሚቴ እንደወሰነው አስትራዜኔካ በአዛውንቶች ዘንድ የሚያመጣው የጎንዮሽ ጉዳትን በተመለከተ አስተማማኝ ሳይንሳዊ መረጃዎች እስኪገኙ ድረስ ጀርመን ክትባቱን መስጠት ያለባት ከ18 እስከ 64 ዓመት ለሆናቸው ዜጎች ብቻ ነው። ነገር ግን የታላቋ ብሪታኒያ የክትባት ዘመቻ መሪ ዶ/ር ሜሪ ራምሴይ በዚህ አይስማሙም። እሳቸው እንደሚሉት አስትራዜኔካም ሆነ ፋይዘር ዕድሜያቸው ለገፉ ሰዎች መስጠቱ ጉዳት አላሳየም። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የጀርመን ኮሚቴ ያስተላለፈው ውሳኔ እንደማይረብሻቸውና አስትራዜኒካን ለሁሉም ዜጎች በስፋት ማደላቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
49996607
https://www.bbc.com/amharic/49996607
በቤተ መንግሥት ግቢ የተገነባው አንድነት ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል?
በቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ የተሰራው አንድነት ፓርክ 5 ቢሊየን ብር ተመድቦለት የተገነባ ሲሆን ዛሬ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል።
ይህንን ፓርክ ለመገንባት የገንዘብ ድጋፍ የተገኘው ከዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለጋዜጠኞች ባስጎበኘበት ወቅት ተናግሯል። ቤተ መንግሥቱ በ40 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በውስጡ ሦስት ዋነኛ የቱሪስት መስህቦች ይገኙበታል። • በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ? • ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ምን ይላሉ? ይህ ቤት ከቤተ መንግሥቱ በምሥራቃዊ አቅጣጫ የሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ሲሆን፤ ከአጤ ሚኒሊክ ቤት ጋር በድልድይ የሚገናኘው የእቴጌ ጣይቱ ቤት ነው ታሪካዊ መስህብ ከ1880ዎቹ ጀምሮ የተገነቡ የነገሥታት መኖሪያና ጽህፈት ቤቶች በዋናኝነት እዚህ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን በዚህ ፕሮጀክት የነበሩበትን ይዞታ ሳይለቁ ዕድሳት እንደተደረገላቸው ተገልጿል። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው የሚኒሊክ የግብር አዳራሽ ሲሆን ንጉሡ በዚህ አዳራሽ እንግዶቻቸውን ያስተናግዱ እንደነበር ታውቋል። የአዲስ አበባ ወንዞችና ዳርቻዎቻቸውን የማልማት ሥራን ለመተግበር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ታቅዶ በነፍስ ወከፍ አምስት ሚሊዮን ብር በማበርከት የእራት ድግስ የተካሄደበት 'ገበታ ለሸገር' መርሃ ግብር የተደረገውም በዚሁ በታደሰው አዳራሽ ውስጥ መሆኑ ይታወሳል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ልጅ የተዳረችውም በዚሁ አዳራሽ እንደሆነ በጉብኝቱ ወቅት ተነግሯል። እኚህ የታሪክ ቅርሶች ሦስት ጊዜ እድሳት እንደተደረገላቸው በገለፃው ወቅት መረዳት ተችሏል። የመጀመሪያው በ1963 ዓ.ም በኃይለ ሥላሴ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደርግ 10ኛ ዓመቱን ሲያከብር፣ ሶስተኛው ደግሞ ቫርኔሮ በሚባል የኮንስትራክሽን ድርጅት ነው። በዚህ ሥፍራ መጀመሪያ የምናገኘው የፊት አውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴን (አባ መላ) መኖሪያ ነው። አባ መላ የአጤ ሚኒሊክ የጦር ሚንስትር የነበሩ ሲሆን ይኖሩበት የነበረ ትንሽ የእንጨት ቤት ከአጤ ምኒሊክ መኖሪያ ቤት ጎን ላይ ይገኛል። አጤ ሚኒሊክ ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላም እንደ መኖሪያና ቢሮ አድርገው ሲጠቀሙበት ነበር። ቤቱ ፈርሶ የነበረ ሲሆን አሁን ሙሉ በሙሉ ታድሷል። ወደ አጤ ሚኒሊክ ባለ አንድ ፎቅ መኖሪያና ጽ/ቤት በሮች በእንጨት የተሠሩ ሲሆን በሚያምር መልኩ የአበባና የሐረግ ጌጥ የተፈለፈለበት ነው። ይህ ቤት ከሁለት ሌሎች ቦታዎች ጋር በድልድይ ይገናኛል። አንደኛው በሰሜናዊ አቅጣጫ የአጤ ምኒሊክ የፀሎት ቤትና የሥዕል ቤት ሲሆን እንቁላል ቤት በመባል ይጠራል። አንዳንዴም እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበት ነበር። ወደ አጤ ሚኒሊክ ባለ አንድ ፎቅ መኖሪያና ጽ/ቤት በሮች በእንጨት የተሠሩ ሲሆን በሚያምር መልኩ የአበባና የሐረግ ጌጥ የተፈለፈለበት ነው። ይህ ቤት ከሁለት ሌሎች ቦታዎች ጋር በድልድይ ይገናኛል። አንደኛው በሰሜናዊ አቅጣጫ የአጤ ምኒሊክ የፀሎት ቤትና የሥዕል ቤት ሲሆን እንቁላል ቤት በመባል ይጠራል። አንዳንዴም እንደ ጽ/ቤት ይጠቀሙበት ነበር። በሌላ በኩል አጤ ምንሊክ ከጦር መኮንኖቻቸው ጋር የሚገናኙበት ክፍል ይገኛል። በወቅቱ የጦር ሚኒስትር የነበሩት ፊት አውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ እንደ ቢሮ ይጠቀሙበት ነበር። የዘውድ ቤት ሌላኛው የዘውድ ቤት ነው። ይህ ህንፃ በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ነገሥታትንና ዲፕሎማቶችን የተለያዩ ሀገራት ተቀብለው ያስተናግዱበት ነበር። በዚህ ህንፃ ከተስተናገዱ የውጪ ሀገራት እንግዶች መካከል በ1965 ንግሥት ኤልሳቤጥ 2ኛ፣ በ1966 የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ቻርልስ ደጎል እንዲሁም በ1956 የዩጎዝላቪያው ፕሬዝደንት ቲቶ ይገኙበታል። ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም፣ የዚህን ህንፃ ምድር ቤት የአጼ ኃይለሥላሴን ባለስልጣናት አስሮ ለማሰቃየት ተጠቅመውበት እንደነበር ታሪክ ሰነዶች ያስረዳሉ። የፀሎት ቤቱና የሥዕል ቤቱ ባለ ሁለት ፎቅ ነው። ሁለተኛው ፎቅ ላይ ከፍ ብላ የተሠራች በመስታወት የተሸፈነች ቤት አለች፤ ይህች ቤት 'ቴሌስኮፕ' ያላት ሲሆን አዲስ አበባን በሁሉም አቅጣጫ ማየት ታስችላለች። በዚች እንቁላል ቤት መገናኛው ድልድይ ጋ የመጀመሪያው ስልክ የገባበት ቤት ይገኛል። ቤቱ ከድንጋይና ከእንጨት የተገነባ ነው። አርክቴክት ዮሐንስ የኪነ ህንፃውን ጥበብ ሲገምቱ ከአርመኖችና ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ሕንዶች ሳይሳተፉበት እንደማይቀሩ ይገምታሉ። ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የውይይት ክበብ በመሆን አገልግሏል። • አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ሌላኛው ከአጤ ሚኒሊክ ቤት ጋር በድልድይ የሚገናኘው የእቴጌ ጣይቱ ቤት ነው። ይህ ቤት ከቤተ መንግሥቱ በምሥራቃዊ አቅጣጫ የሚገኝ ባለ አንድ ፎቅ ሕንፃ ነው። በምድር ቤት የዙፋን ግብር ቤት ይገኛል። የነገሥታቱ መመገቢያ አዳራሽ ሲሆን ንጉሣዊ ቤተሰቦች ምግብ የሚመገቡበት ክፍል ነበር፤ ይህ ቤት በደርግ ጊዜ የደርግ ምክር ቤት መሰብሰቢያ በመሆን አገልግሏል። የተፈጥሮ መስህቦች በፓርኩ ከተሰሩ መስህቦች መካከል የእንስሳት ማቆያና አኳሪየም (የውሃ አካል) አንደኛው ነው። በዚህም ውስጥ የጥቁር አንበሳ መኖሪያ፣ የዝንጀሮ መጠለያ፣ የአሳ ማርቢያ (አኳሪየም) ጨምሮ የ46 ዓይነት ዝርያ ያላቸው 300 ለሚሆኑ እንስሳት መጠለያ የሚሆን ስፍራ ይገኛል። ለእንስሳቱ ምግብ የሚዘጋጅበትና ሕክምና የሚሰጥበት ስፍራ በዚሁ አለ። ይህ የእንስሳት መጠለያ ሕዳር 2012 ስራ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል። ባህላዊ መስህብ በአንድነት ፓርክ ከተካተቱት አንዱ የብሔር ብሔረሰቦች ባህል የሚንፀባረቅበት ስፍራ ነው። ይህ ስፍራ የተገነባው በብሔር ብሔረሰቦች ቤት፣ ባህል፣ ምጣኔ ኃብትና የሕዝቦችን አኗኗር መሰረት በማድረግ ነው። በዚህ ሕንፃ ብሔር ብሔረሰቦች ባህላቸውን እንዲያንፀባርቁ እንደሚደረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ገልጿል። በፓርኩ የጓሮ አትክልት፣ የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያን መልክዓ ምድር አቀማመጥ በጠበቀ መልኩ ተሰርቷል። በዛሬው እለት የተመረቀው የአንድነት ፓርክ በነገው እለት የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት እንደሚጎበኙት ለማወቅ ተችሏል። ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ አዛውንቶች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ይጎበኛሉ ተብሏል። ከሰኞ ማለትም ከጥቅምት 3 2012 ጅምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር እንዲሁም በቪአይፒ (VIP) 1 ሺህ ብር በመክፈል ቤተ መንግስቱን መጎብኘት ይችላል የተባለ ሲሆን 1000 ብር የሚከፍሉ ጎብኝዎች ታሪካዊ ቁሳቁስ የሚገኙበትንና ሌሎች እንግዶች እንዲያዩ ያልተፈቀደላቸው ስፍራ መጎብኘት እንደሚችሉ ለመረዳት ችለናል።
news-51602797
https://www.bbc.com/amharic/news-51602797
ደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ፍራቻ የእግር ኳስ ቡድኗን ወደ ጃፖን አልክም አለች
ደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ፍራቻ የኦሎምፒክ እግር ኳስ ቡድኗን ወደ ጃፓን አልክም ማለቷ ተዘግቧል። ደቡብ አፍሪካና ጃፓን ከአራት ወራት በኋላ የሚካሄደው የቶክዮ ኦሎምፒክስ ከመድረሱ በፊት የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ እቅድ ይዘው ነበር።
ጨዋታው የታሰበው ከአንድ ወር በኋላ ቢሆንም ደቡብ አፍሪካ ባላት ስጋት ምክንያት ተሰርዟል። በጃፓን እስካሁን ባለው 85 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን አንድ ሰው መሞቱን ከዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት የተገኘው መረጃ ያሳያል። • ቻይና ዘረኝነት ተንፀባርቆበታል ባለችው ፅሁፍ ምክንያት ጋዜጠኞችን ከሃገሯ አባረረች • የጨለቆት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተዘረፈው ዘውድ ይመለስልኝ እያለች ነው የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ተጠባባቂ ስራ አስኪያጅ ጌይ ሞኮየና እንዳሉት የጃፓን እግር ኳስ ማህበር ውሳኔያቸውን ቀስ ብለው እንዲያጤኑት ቢነግራቸውም ውሳኔያቸውን እንደማይቀለብሱት አሳውቀዋል። "ጃፓን ውሳኔያችሁን ቀይሩ እያለችን ነው፤ እኛ ግን ምንም የምንቀይርበት ሁኔታ የለም። ለኛ ቅድሚያ የምንሰጠው የተጨዋቾቻችን ደህንነት ነው" ያሉት ጌይ ሞኬና አክለውም " የተጨዋቾቻችንን ህይወት አደጋ ውስጥ መክተት አንፈልግም፤ በየቀኑ የሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ነው፤ እንዲህ አይነት ስጋትን የመሸከም አቅሙ የለንም" ብለዋል። የአይቮሪ ኮስትም ቡድን ከወር በኋላ ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ጃፓን ለማምራት እቅድ የተያዘ ሲሆን እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም። • ኢትዮጵያውያን፡ የአስወጡን ድምጽ በጎሉባት የቻይናዋ ዉሃን • ኬንያዊውን ገርፈዋል የተባሉት ቻይናውያን አሰሪዎች ከሃገር እንዳይባረሩ ፍርድ ቤቱ አዘዘ በሐምሌ ወር ለሚጀምረው ኦሎምፒክ ስድስት ከተሞች የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ለማሰተናገድ ተመርጠዋል። ደቡብ አፍሪካና አይቮሪ ኮስት በወንዶች እግርኳስ ለመሳተፍ ከአፍሪካ ማጣሪያውን አልፈዋል። የመጪው ኦሎምፒክ ስራ አስፈፃሚ ቶሺሮ ሙቶ ከዚህ ቀደም እንዳሉት የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን መሰረዝም ሆነ ማስተላለፍ ግምት ውስጥ አለመግባቱን ነው።
46873759
https://www.bbc.com/amharic/46873759
የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው?
የአንድ ግሮሰሪ ኃላፊ ሆነው ሥራ አገኙ እንበል። ያው አዲስ ሥራ እንደመሆኑ መፍራትዎ አይቀርም። ሆኖም አንድ የበላይ አስተዳዳሪ የሥራ ቦታውንና የሥራውን ባህሪ ሊያሳይዎት ወይም ሊያስረዳዎት ፍቃደኝነት ያሳያል።
የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? መጀመሪያ 'እንዴት ያለ መልካም ሰው ነው?' ብለው ማሰብዎ አይቀርም። ሆኖም ግለሰቡ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት ቢሰጥዎስ? በየሰበቡ ሊዳብስዎ ቢሞክርስ? ምቾት በማይሰጥዎ ሁኔታ ሰውነትዎን ቢነካስ? • ሴቶች እንዲደፈሩ ያበረታታው ግብጻዊ የህግ ባለሙያ ተፈረደበት ነገሩን ችላ ብለው ሥራዎ ላይ አተኮሩ እንበል። 'ምናልባትም ችግሩ ከኔ ይሆን?' ሲሉ ራስዎን እስከመጠራጠር ይደርሳሉ። ቀናት ሲገፉ ግን 'ምንም አይደለም' ብለው ቸል ያሉት ነገር ገዝፎ ከቁጥጥርዎ ውጪ ይሆናል። ይህ ወሲባዊ ትንኮሳ ነው! ለመሆኑ ወሲባዊ ትንኮሳ ምን ማለት ነው? ምን አይነት ንግግር ወይም ምን አይነት ተግባርስ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ውስጥ ይካተታል? በሥራ ቦታ ላይ የሥራ ባልደረባን ጀርባ መንተራስ? ስለሥራ ባልደረባ አለባበስ አስተያየት መስጠት? መሳም? የትኛው መስመር ሲታለፍ ነው ይህ ወሲባዊ ትንኮሳ ነው የሚባለው? ቢቢሲ በተለይም በሥራ ቦታ ላይ የሚደርስ ወሲባዊ ትንኮሳ የቱ ነው? በሚል አንድ ማኅበራዊ ጥናት ሠርቶ ነበር። ጥናቱ ምን ያህል ሰዎች ወሲባዊ ትንኮሳ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? የሚል ጥያቄ አጭሯል። ኬሪ ዊዴት ባሪስታ ናት። "ወሲባዊ ትንኮሳ ምንድን ነው? በሚለው ላይ የግንዛቤ ክፍተት አለ" ትላለች። አብዛኞቹ ወጣት ሴቶችም ይሁን ወንዶች ወሲባዊ ትንኮሳ የሚባለው የትኛው መስመር ሲታለፍ እንደሆነ አያውቁም። • ካይሮ፡ ለሴቶች በጣም አደገኛ ከሆኑ ከተሞች አንዷ እንደ ሚቱ (#MeToo) እና ታይምስአፕ (#TimesUp) አይነት ንቅናቄዎች፤ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን የሚነቅፉ፣ አጥቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚያስችሉም ናቸው። ሆኖም ስንቶች ወሲባዊ ትንኮሳ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? ክብረ ነክ ወሲባዊ ትንኮሳ ማንኛውም አይነት፣ ያልተፈለገ ወሲብን ያማካለ ንግግር እንዲሁም እንቅስቃሴ ነው። ወሲባዊ ትንኮሳ ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ነው። በማንኛውም መንገድ ከክብር ዝቅ የሚያደርግ ነገር ሲከናወን ትንኮሳ ይባላል። ያልተፈለገ ወሲብ ነክ ድርጊት የደረሰበት ሰው ክብሬ ተነክቷል ወይም አካባቢዬ ምቹ ያልሆነ ስሜት ተፈጥሯል ሲል ወሲባዊ ትንኮሳ ደርሶበታል ማለት ነው። የሚያስጨንቅ አንድ ሰው ወሲባዊ ትንኮሳ ሲደርስበት አስጨናቂ ስሜት ይፈጠራል። አጥቂው ሰው ምን አይነት ስሜት ሊፈጥር አስቦ ተግባሩን ፈጸመ? ከሚለው ስሜት ጋር ፈጽሞ አይገናኝም። "አንድ ሰው ወሲባዊ ትንኮሳ ለማድረግ ማሰብ ወይም አለማሰቡ ትርጉም የለውም። ወሲባዊ ትንኮሳ ምንጊዜም ወሲባዊ ትንኮሳ ነው።" ስትል ኬሪ ትናገራለች። አስቀያሚ ስሜትና ድባብ ማንም ሰው ምቾት የማይሰጠው ቦታ መሥራት አይሻም። ወሲባዊ ትንኮሳ ደግሞ ምቾት ከሚነሱ አንዱ ነው። አንድ ሰው በወሲብ ነክ በእንቅስቃሴ ወይም በንግግር ደስ የማይል ድባብ ከፈጠረ ትንኮሳ ነው። አንድ እንቅስቃሴ ወይም ተግባር ወሲባዊ ትንኮሳ ነው ለማለት ከላይ የተዘረዘሩትን ባጠቃላይ መምሰል አያስፈልገውም። ከተጠቀሱት አንዱን እንኳ ከሆነ ወሲባዊ ትንኮሳ ይባላል። ከሁለት ዓመት በፊት እንግሊዝ ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት 53 በመቶ ሴቶች እና 20 በመቶ ወንዶች በሥራ ወይም በትምህርት ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ደርሶባቸዋል። • ሞርጋን ፍሪማን በፆታዊ ትንኮሳ ለቀረበባቸው ውንጀላ ይቅርታ ጠየቁ ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች 63 በመቶ የሚሆኑትና 79 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች ጥቃት እንደደረሰባቸው ሪፖርት አላደረጉም። ማንም ሰው ወሲባዊ ትንኮሳ ሊደርስበት ይችላል። ወንድም ሴትም። ወሲባዊ ትንኮሳ ከተቃራኒ ወይም ከተመሰሳሳይ ጾታም ሊሰነዘር ይችላል። በሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ሙከራ ሲደረግ፤ ተጠቂዋ ወይም ተጠቂው፤ ጥቃቱ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጠይቀው ላይቆም ይችላል። ሌሎች ሰዎች ጥቃቱን ቢያዩትም ባያዩትም ወሲባዊ ትንኮሳ ነው። ብዙ ጊዜ በሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲደርስ ሪፖርት ለማድረግ ተጠቂዎቹ እንደሚቸገሩ በተደጋጋሚ ተዘግቧል። ኬሬ እንደምትለው "ወሲባዊ ትንኮሳ የደረሰባቸው ሰዎች ለሚያምኑት ወይም ለሚቀርባቸው ሰው ከመናገር መጀመር አለባቸው።" ይህም በመደበኛ ሁኔታ ሪፖርት ለማድረግ ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ ነው። የሚሠሩበት ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳ ፖሊስ፤ ለማን ሪፖርት እንደሚደረግ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት። የሥራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳምን ያካትታል? • ወሲብ ነክ አስተያየት ወይም ቀልድ • ሳይፈቀድ መንካት ወይም የንክኪ ሙከራ ማድረግ • ወሲባዊ መልዕክት ያለው አስተያየት ወይም ዘለግ ላለ ጊዜ በአትኩሮ መመልከት • መስመር የዘለሉ፣ ወሲባዊ ይዘት ያላችውና የሰውን ግላዊ መረጃ የሚመለከቱ ጥያቄዎች • ወሲብ ነክ ሀሜቶች ማሰራጨት • ወሲባዊ ምስል፣ ቪድዮ ወይም ወሲባዊ ይዘት ያለው መረጃ መላክ
news-41896916
https://www.bbc.com/amharic/news-41896916
ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንታቸውን ምናንጋግዋ ታማኝ አይደሉም በማለት ከስልጣን አባረዋል
የዝምባብዌ መንግሥት የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከስልጣን መነሳታቸውን ይፋ አድርጓል።
ኤመርሰን ምናንጋግዋ ፕሬዝደንት ሙጋቤን በቀጣይ ይተካሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው መሪ ነበሩ። የ75 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ፤ ''ታማኝ'' አይደሉም ሲሉ የኢንፎርሜንሽን ሚኒስትሩ ሳይመን ካሃያ ሞዮ ተናግረዋል። የምክትል ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን በመነሳታቸው የሮበርት ሙጋቤ ባለቤት የሆኑት ግሬስ ሙጋቤ ባለቤታቸውን በመተካት ቀጣይ የዝምባብዌ መሪ ይሆናሉ ተብሏል። ከዚህ በፊት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንቱን ከስልጣናቸው እንዲያነሱ ሮበርት ሙጋቤን ሲወተውቱ ነበር። የቀድሞው የደህንነት ሹም የነበሩት ምናንጋግዋ ፕሬዝዳንት ሙጋቤን የመተካት ተስፋ የተጣለባቸው መሪ ነበሩ። ግሬስ ሙጋቤ እና ኤመርሰን ምናንጋግዋ ምናንጋግዋ ከምክትል ፕሬዝዳንትነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ በቀጣይ ወር ፓርቲው በሚያደርገው ስብሰባ ላይ የሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳናት ሆነው ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው እሁድ በዋና ከተማዋ ሃራሬ ግሬስ ሙጋቤ ባደረጉት ንግግር ''እባቡ በሃይል ጭንቅላቱን መመታት አለበት። በፓርቲው ውስጥ መከፋፈል እና አለመግባባትን የሚፈጥሩትን ማስወገድ አለብን። ወደ ቀጣዩ የፓርቲያችን ስብሰባ በአንድ መንፈስ ነው መሄድ ያለበን'' ሲሉ ተደምጠዋል።
news-54759332
https://www.bbc.com/amharic/news-54759332
ህንዳዊው ዶክተር 'የአላዲን ኩራዝ' በሚል 41 ሺህ 500 ዶላር ተጭበረበረ
በህንዷ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ሁለት ግለሰቦች ጤናና ሃብት ያመጣል ያሉትን የአላዲንን ኩራዝ በ41 ሺህ 500 ዶላር ለአንድ ዶክተር መሸጣቸውን ተከትሎ ከስ ተመስርቶባቸዋል።
ግለሰቦቹ ኩራዙን ከገዛህ "ሃብት ያትረፈፍርልሃል ጤናንም ይሰጥሃል" ብለው አጭበርብረዋል በሚልም ነው የተከሰሱት። በተረቶች ላይ የሚታወቀውን የአላዲንን ኩራዝ እውነተኛ በማስመሰል 'ጂኒ ለማስወጣትም መሞከራቸውንም የህንድ ሚዲያዎች ዘግበዋል። በመጀመሪያ ግለሰቦቹ ጠይቀውት የነበረው ብር 200 ሺህ ዶላር ሲሆን ዶክተሩ 41 ሺህ 500 ዶላር የመጀመሪያ ክፍያ በመስጠት ቀሪውን ሌላ ጊዜ እንደሚከፍልም ነግሯቸዋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ አንዲት ሴት ተሳትፋለች የተባለች ሲሆን ተጠርጣሪዋንም ፖሊስ በመፈለግ ላይ ነው። ዶክተሩ በዚህ ሳምንት ለፖሊስ ሪፖርት ባደረገው መሰረት ሁለቱን ግለሰቦች ያገኛቸው እናታቸውን ሲያክም መሆኑንም የህንዱ ኤንዲቲቪ ሚዲያ ዘግቧል። የግለሰቦቹን እናት ለአንድ ወር ያህልም በሚያክምበት ወቅት አንድ አዋቂ ግለሰብ ቤታቸው እየመጣ እንደሚጠይቃቸውና የተለያዩ ተአምራቶችንና ፈውሶችን እንደሚያከናውን በመንገርም ቀስ በቀስ እንዳሳመኑት ተገልጿል። ከዚያም በኋላ ይህንን አዋቂ የተባለውን ግለሰብም ጋር መገናኘቱን ተናግሯል። በአንድ ወቅትም "አላዲንን በአካል እንዳየውና ፊት ለፊቱም መቆሙን የሚናገረው ዶክተር በኋላ ግን አንደኛው ተጠርጣሪ ግለሰብ እንደ አላዲን ለብሶ መምጣቱን መረዳት ችሏል። ሌሎች የህንድ ሚዲያዎችም እንዲሁ ተጠርጣሪዎቹ ጅኒ ለማውጣት መሞከራቸውን ዘግበዋል። ሃብትና ንብረት ያመጣልሃል እንዲሁም ጤንነትህ የተሟላ ይሆናልም ብለው ቃል በመግባት 15 ሚሊዮን የህንድ ሩፒ (200 ሺህ የአሜሪካን ዶላር) ከጠየቁት በኋላ 41 ሺህ 500 ዶላር ክፍያ መስማማታቸውም ተገልጿል። በሜሩት የሚገኙ የፖሊስ ኃላፊ አሚት ራይ ሌሎች ግለሰቦችም እንዲሁ ሌሎች ቤተሰቦችን እያጭበረበሩ መሆናቸውንም ኤንዲቲቪ በዘገባው አሳይቷል።
news-53085388
https://www.bbc.com/amharic/news-53085388
8.9 ሚሊዮን ብር የተሸጠው ደብዳቤ
ቫን ጎ እና ጎውገን መሸታ ቤት የጎበኙበትን ምሽት ያሰፈሩበት አንድ ደብዳቤ በ210 ሺህ ዩሮ [በብር ሲሰላ 8.9 ሚሊዮን ገደማ] ተሽጧል።
ደብዳቤው አርቲስቶቹ ቪንሰንት ቫን ጎ እና ፖል ጎውገን አንድ መሸታ ቤት ገብተው በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን የጎበኙበትን ምሽት በምስል ከሳች ቃላት ያሰፈሩበት ነው። ዕለተ ማክሰኞ ፓሪስ በሚገኘው ድሩዎ የጨረታ ማዕከል ደብዳቤው 210 ሺህ ዩሮ አውጥቷል። ደብዳቤውን የገዛው የቫን ጎ ፋውንዴሽን [እርዳታ ድርጅት] ነው። አርቲስቶቹ በ1880 ደብዳቤውን የፃፉት ለፈረንሳዊው ጓደኛቸው ሰዓሊ ኤሚል በርናርድ ነው። ጓደኛሞቹ ሕይወት በፈረንይዋ አርለ ከተማ ምን እንደሚመስል ቁልጭ አድርገው አስፍረዋል። ጎ እና ጎውገን የተሰኙት ሰዓሊዎች ደብዳቤው ላይ 'የጥበብ አብርሆትን እየመራን' ሲሉ ፅፈዋል። ጓደኛሞቹ ሰዓሊዎች በአርለ ከተማ የጥበብ አሻራቸውን ማሳረፍ ችለዋል። የጓደኝነታቸው መጨረሻ ግን ያማረ አልነበረም። ለስምንት ወራት ያክል አርለ ከኖሩ በኋላ በመካከላቸው በተፈጠረ መቃቃር ጎውገን ከተማዋን ጥሎ መጥፋቱን ታሪክ ያትታል። ደብዳቤው ቫን ጎ የአእምሮ በሽታ አጋጥሞት ግራ ጆሮውን ቆርጦ ከመጣሉ ሳምንታት በፊት እንደተፃፈ ይነገራል። ኔዘርላንዳዊው ሰዓሊ በ1882 ራሱን ማጥፋቱ ይታወቃል። ውዱ ደብዳቤ አምስተርዳም በሚገኘው የቫን ጎ ሙዚዬም እንደሚሰቀልና ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆን ታውቋል። ጨረታ ማዕከሉ ቫን ጎ እና ጎውገን ከጊዜያቸው ቀድመው የተፈጠሩ አርቲስቶች ናቸው ሲል ይገልፃቸዋል። ሰዓሊዎቹ የምንሰራው ሥራ ወደፊት በሚመጣው ትውልድ አድናቆት ያገኛል ብለው ያስቡ እንደነበርም ጨምሮ ያትታል። ደብዳቤው ምን ይላል? አርቲስቶቹ በታሪካዊው ደብዳቤ ላይ በአርለ ከተማ የነበራቸውን የሌተ-ቀን ውሎ አስፍረዋል። የሎ ሐውስ በተሰኘ ስፍራ አንድ አፓርታማ ተከራይተው በጋራ እየኖሩ በጋራ እየሰሩ ጥበብን እንደቃኙ አስፍረውበታል። "አንድ የሚያስገርምህ ነገር ደግሞ እንንገርህ። አንድ ምሽት ወደ አንድ መጠጥ ቤት አምርተን በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን ጎበኘን። ከሥራ በኋላ ያንን ቤት ደጋግመን መጎበኝታችን የማይቀር ነው' ሲል ቫን ጎ ባለ አራት ገፁ ደብዳቤ ላይ የመሸታ ቤት ታሪኩን አስፍሯል። "ይሄን በምፅፍልህ ሰዓት ጎውገን አቡጀዲውን ዘርግቶ በዚያው ምሽት የጎበኘነውን አንድ ካፌ እየሳለ ነው። ይህንን ስዕል እኔም ስየዋለሁ። እሱ ግን መሸታ ቤት ያያቸውን እየጨመረበት ነው። ድንቅ ስዕል እንደሚወጣው አልጠራጠርም።" ምንም እንኳ ደብዳቤው ለጓደኛቸው በርናርድ የተፃፈ ይሁን እንጂ በሁለቱ ሰዓሊያን መካከል የነበረውን የቃላት ልውውጥንም የሚያስቃኝ ነው፤ በተለይ ደግሞ በጋራ መኖርና መሥራቱ ምን እንደሚመስል ይቃኛል። ደብዳቤው ላይ ጎ፤ ጎውገንን "ያልተጨማለቀ፤ የዱር እንሰሳ ደመ ነፍስ ያለው ፍጥረት" ሲል ይገልፀዋል። ደብዳቤው በሚቀጥለው በሚቀጥለው ጥቅምት በአምስተርዳሙ ቫን ጎ ሙዚዬም ለሕዝብ ዕይታ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
news-52410525
https://www.bbc.com/amharic/news-52410525
ኮሮናቫይረስ፡ በአለም ላይ በኮሮና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ አለፈ
በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ መሆኑን ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ ያወጣው መረጃ ያሳያል።
በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም ቁጥር ከ2.8 ሚሊዮን በላይ መሆኑንም ይኸው መረጃ ጠቁሟል። በቫይረሱ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ የሟቾች ቁጥር 50 ሺህ ያለፈ ሲሆን፤ ይህም አሃዝ ከአለም ቀዳሚ አድርጓታል። •በኒውዮርክ የመድኃኒት መደብሮች የኮሮና ምርመራ ሊጀመር ነው •በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበር መስራች አቶ መንግሥቴ አስረሴ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ የቻይና ሚዲያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የሞተው ግለሰብ በጥር ወር አጋማሽ ሪፖርት ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ፣ ቫይረሱ በተለያዩ ሃገራት ተዛምቶ በ120 አገራትም ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል። በአምስት አገራት ውስጥ የሟቾች ቁጥር ከ20 ሺህ በላይ የሆነ ሲሆን፤ በተለይም አሜሪካ፣ ስፔንና ጣልያን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዜጎቻቸውን ህይወት አጥተዋል። በእንግሊዝም የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ሲሆን፣ በትናንትናውም ዕለት በኮሮና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሃያ ሺህ መብለጡን የሃገሪቱ የጤና ዘርፍ አስታውቋል። ይህ ቁጥር የሚያሳየው በሆስፒታሎች ውስጥ ብቻ የሞቱትን መሆኑም ተገልጿል። በቤታቸው እንዲሁም በተለያዩ መጠለያዎች ውስጥ የሞቱ ሰዎች አሃዝም ባለመካተቱ ቁጥሩ ከዚህ በላይ ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል። •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት •በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? በፈረንሳይም የሟቾች ቁጥር 22 ሺህ 614 ሲሆን በሆስፒታሎች ውስጥ የሟቾች ቁጥር መቀነሱን እንዲሁም በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ህመምተኞች ቁጥርም እንዲሁ ለሰባተኛ ቀን መቀነሱን የሃገሪቱ የጤና ኃላፊዎች አሳውቀዋል። የአለም የጤና ድርጅት ከሰሞኑ እንዳሳወቀው ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሰዎች እንደገና አይያዙም ማለት እንዳልሆነ ገልጿል። የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአውሮፓ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑንና በሌሎች አገራት ግን ሊጨምር እንደሚችል አስታውቀዋል። •ከሚስታቸውና ከልጃቸው ጋር ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የአዳማ ነዋሪ ወደ ቤታቸው ተመለሱ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመግታት ከፍተኛ ስራ በመስራት ምስጋና በተቸራቸው እንደ ሲንጋፖር ባሉ እስያ ሃገራት ደግሞ ወረርሽኙ በፋብሪካዎች ውስጥ መከሰቱ ተዘግቧል። የቻይና ባለስልጣናት ባለፉት አስር ቀናት በቫይረሱ የሞተ ሰው እንደሌለ ያሳወቁ ሲሆን በደቡብ ኮሪያም እንዲሁ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሞት ከተከሰተ ቀናት ተቆጥረዋል።
43566055
https://www.bbc.com/amharic/43566055
ዶ/ር ዐብይ በግላቸው ለውጥ ያመጣሉ?
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ መረጋጋት እርቆት ከሰነበተ ቆይቷል። በዚህም የተነሳ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በአንዳንድ የደቡብ ክልሎች ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተስተውለዋል። ይህንን ተከትሎም ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ አድርጓል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።
ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀ-መንበር ሆነው ተመረጡ የቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ፈተናዎች ነገር ግን ሕዝባዊ ተቃውሞዎች፣ በመንግሥት ኃይሎች የሚወሰዱ የኃይል እርምጃዎች እና እስሮች ቀጠሉ። ይህ ደግሞ ግንባሩ በድጋሚ ለተሀድሶ እንዲቀመጥ አስገደደው። ያንንም ተከትሎ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ልልቀቅ ሲሉ ጠየቁ። በርካታ የፖለቲካ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪዎች ከእስር ተለቀቁ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሚ ተደነገገ። ከዚህ ሁሉ በኋላ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሦስተኛው የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ። በአሜሪካ ጆርጂያ ጉኔት ኮሌጅ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶ/ር ዮሐንስ ገዳሙ የዶ/ር አብይ ቀጠዩ የኢህአዴግ ሊቀ-መንበር ሆኖ መመረጥ ባለፉት ሳምንታት ኢህአዴግ ተከፋፍሏል እየተባለ ሲነገር ከነበረው አንፃር ካየነው፤ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አንድነቱን ጠብቆ የወጣበትና ወደ አንድነት የተመለሰበትን መንገድን ማሳያ ነው ይላሉ። ለዶ/ር ዮሐንስ ገዳሙ ኢህአዴግ ጠንካራ ድርጅታዊ ባህል አለው። ሁሌም የጋራ ችግሮቹን በጣም ረጃጅም ጊዜ ወስዶ በመነጋገር ወደ አንድነት የሚመጣበትን ባህል አለው። "ያንንም ያሳኩ ይመስለኛል። ስለዚህ የዶ/ር ዐብይ የፓርቲው ሊቀ-መንበር ሆኖ መመረጥ ትልቁ ድል ነው ብዬ የማስበው ለራሱ ለድርጅቱ ነው" ይላሉ። አቶ ክቡር ገና ደግሞ በበኩላቸው የዶ/ር ዐብይ መመረጥ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውስጥ ለውጥ ፈላጊው አካል የተሻለ ተደማጭነት አግኝቶ ማሸነፉን ያሳያል ባይ ናቸው። የኢትዮጵያዊያን ፍላጎት ዶ/ር ዮሐንስ ገዳሙ ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን የሚያጠናክር፣ በሕዝቦች መካከል ትስስርን የሚፈጥር፣ ለወጣቶች፣ ለሴቶች አዲስ ተሰፋን ሰንቆ ሀገሪቱን በተረጋጋ ሁኔታ መምራት የሚችል መሪ ይፈልጋሉ ስለዚህ ለዜጎች የዶ/ር ዐቢይ መመረጥ እንደ አንድ ተስፋ ሰጪ እድል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ለዶ/ር ዮሐንስ ይህ ተስፋ ሰጪ ብቻ ሳይሆን በራሱ ተግዳሮቶችንም ያዘለ ነው። የአራቱ የኢህአዴግ አባል ፓርቲ አመራሮች ለ17 ቀን ከዘለቀው ስብሰባቸው በኋላ በሰጡት መግለጫ ላይ ቃል የገቡትን ትልልቅ ማሻሻያዎች የተመረጠው አዲስ ሊቀመንበር እና ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊያሳካ ይችላል ወይ ብቃትስ አለው? ብቃቱስ ቢኖረው ኢህአዴግ ፈቃደኛ ሆኖ ያሰራዋል? የሚሉት ጉዳዮችን በጥያቄ መልክ ያነሳሉ። ዶ/ር ዮሐንስ የአዲሱ የኢህአዴግ ሊቀ-መንበር መመረጥ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ላለፉት ሦስት ዓመታት የነበረውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ሊያስቆመው ይችላል ይላሉ። ነገር ግን በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ከማንነት ጥያቄ ጋር የተነሳ በመሆኑ ህዝቡ የሚፈልገውን በመረዳት ወደታች ወርዶ በማነጋገር መልስ መስጠት እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ። በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ የፍትሃዊነት እና የእኩልነት ጥያቄ በመሆኑ እና ይህ ደግሞ የኢትዮጵያዊያን አጠቃላይ ጥያቄ ስለሆነ ለዶ/ር ዮሐንስ በአንዴ የሚመለስ አይደለም። ስለዚህ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ፍንጮችን በማሳየት የህዝቡን ትዕግስት መግዛት ያስፈልጋል ባይ ናቸው። ቀጣይ ኃላፊነቶች አቶ ክቡር ገና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀዳሚ ሥራዎች ፓርቲው የሚያስቀምጣቸው ቢሆኑም፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዘለቂ ሰላምን በማምጣት ረገድ ምን ያህል እንዳገዘ መመልከት እና ውሳኔ መስጠት ግን ያስፈልጋል ባይ ናቸው። ዶ/ር ዮሐንስም በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ። ኢህአዴግ በተደጋጋሚ የሚታወቀው ተሀድሶ በማካሄድ ነው። በቅርቡም ጥልቅ ተሃድሶ አካሄዷል። ወደ ተግባር ስንመጣ ግን ብዙ ጥያቄ የሚያስነሱ ነገሮችን ብዙ ጊዜ እናያለን ይላሉ ዶ/ር ዮሐንስ። በቅርቡ ታዋቂ ፖለቲከኞች ጋዜጠኞች ከእስር መለቀቃቸውን የሚያስታውሱት ዶ/ር ዮሐንስ፤ አሁንም በርካታ ኢትዮጵያዊያን በእስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ ሲሉ ይናገራሉ። በመቀጠልም በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጠቀም እነዚያን የተለቀቁ እስረኞችንና ሌሎችንም ወደ እስር ቤት የማስገባት ነገር በድጋሚ መታየቱን በማንሳት፤ የኢህአዴግን ጥልቅ ተሃድሶ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ያስገቡታል። ስለዚህ ዶ/ር ዮሐንስ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የሀገሪቱ ትልቅ ስልጣን ስለሆነ ይህንን ዶ/ር ዐቢይ በርካቶችን ወደ እስር ቤት መልሶ ያስገባውን የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ መቀልበስ የመጀመሪያ ሥራቸው መሆን ብለው ያስባሉ። አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ ኃላፊነት መሆን ይገባዋል በማለት ያነሱት ለወጣቶች ሥራ መፍጠርንና ሙስናን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እንደሆነ ይጠቁማሉ። ዶ/ር ዮሐንስ ደግሞ ይህንን ለማድረግ ተቋማዊም ሆነ ፖለቲካዊ ለውጦችን ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል ይላሉ። እንደ ዶ/ር ዮሐንስ ከሆነ ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እምነቱን በመከተል እስካሁን ድረስ ተጉዞ የትም ስላላደረሰው ዶ/ር ዐቢይ አዲስ የሆነ ሀገሪቱ የምትመራበት፣ ለህዝቡ ተስፋን የሚሰንቅ፣ አዲስ አመለካከት መቅረፅ ያስፈልጋቸዋል። "ዶ/ር ዐቢይ ከተማረው ወገን በመሆናቸው እነዚህን ጉዳዮች ያስቡበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ይላሉ። በተጨማሪም ሀገሪቱን ማረጋጋት፣ የምትመራበት ፌደራላዊ ሥርዓት ለብዙ ችግር የዳረጋት ከመሆኑ አንፃር እሱን ማስተካከልም ከሥራቸው መካከል እንደሚገኝበት ያስታውሳሉ። "ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ስደተኛ ሆነዋል። ይህ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በማዕከላዊ መንግሥቱ የተወሰዱ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች አይታዩም። እኚህ ጠቅላይ ሚኒስትር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ወይ?'' ሲሉም ይጠይቃሉ። በተጨማሪም ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችንና የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠናን የሚይዙበት መንገድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቃት መፈተኛዎች መሆናቸውንም ዶ/ር ዮሐንስ ያስረዳሉ። የኢህአዴግ የፓርቲ ባህል እንደ ዶ/ር ዮሐንስ አመለካከት ከሆነ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱበት ጊዜ አንስቶ በኢህአዴግ ውስጥ የቡድን አመራር የሚባል ነገር ገኖ ታይቷል። ይህ ደግሞ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትርም ጠፍንጎ ይዞ ብዙ ሥራ እንዳይሰሩ ሊያደርጋቸው ይችላል ሲሉ ይሰጋሉ። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትርነት በሀገሪቱ ውስጥ ያለ ትልቁ የመንግሥት ሃላፊነት ስለሆነ የሚኖረውን ተግዳሮት በአጠቃላይ ተቋቁሞ መስራት ያስፈልጋል ባይ ናቸው። በፖለቲካዊ ተሳትፎ ውስጥ የማይታወቁ ምሁራንን በካቢኔያቸው ውስጥ እና ከዚያም ውጭ በማሳተፍ በጋራ መስራት ያስፈልጋል። ይህንንም ይላሉ ዶ/ር ዮሐንስ አዲሱ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ሥራቸውን ሲጀምሩ በሚፈፅሙት ቃለ መሃላ እና በሚወስዷቸው እርምጃዎች የምናየው ይሆናል። ከገዢው ፓርቲ የቆየ አሰራር አንፃር አቶ ክቡር ገና አዲሱ ሊቀ-መንበር ከተለመደው የኢህአዴግ የቡድን አመራር ባህል ይወጣሉ ብለው አያስቡም። ይህንን ለማለት ያበቃቸው ደግሞ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን ወዴት አቅጣጫ እንደሚወስዷት የሚያሳይ ምንም የፃፉትም ሆነ የገለፁበት መድረክ ባለማየታቸው ነው።
49340953
https://www.bbc.com/amharic/49340953
እስራኤላዊው ቢሊየነርና ረዳቶቹ ለጊኒ ባለስልጣናት ሙስና በመስጠት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው
እስራኤላዊው ቢሊየነር ቤኒ ስቴይንሜትዝ እና ሁለት ረዳቶቹ በጊኒ የማእድን ማውጣት ፍቃድ ለማግኘት ለባለስልጣናቶቹ ጉቦ በመስጠት ተከስሰው ችሎት ፊት ሊቀርቡ መሆኑን የስዊዝ አቃቤ ሕግ አስታወቀ።
ሶስቱ ተጠርጣሪዎች 10 ሚሊየን ዶላር ለቀድሞ የጊኒ ፕሬዝዳንት ላንሳና ኮንቴ ሚስት መክፈላቸው ተገልጿል። ስቴይንሜትዝ እና የማእድን አምራች ኩባንያቸው እንዲህ አይነት ነገር አይነካካንም ሲሉ ክሱን አስተባብለው ነበር። አቃቤ ሕግ ሁለቱ ተከሳሾች በአስር ዓመት እስር እንዲቀጡለት ይፈልጋል። • የባቢሌ ዝሆኖች ህልውና አደጋ ላይ ነው • አንድም ሴት የፓርላማ አባል የሌላት ሃገር • ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት የአይጥ እርዳታ ያስፈልገን ይሆን? ከስድስት ዓመት በፊት አቃቤ ሕግ ስቴይንሜትዝ በጊኒ ደቡብ ምስራቅ በምትገኘው ሲማንዳኡ ክልል ለሚገኘው ሲማንዳኡ ማእድን ማምረቻ ፈቃድ ያገኘው ሙስና በመስጠት ነው ሲል ነበር ምርመራውን የጀመረው። ገንዘቡ በከፊል ለጊኒ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሚስት በስዊዝ በሚገኝ ባንክ በኩል ገቢ መደረጉ ተገልጿል። በዚህ አመት የካቲት ወር ላይ የጊኒ መንግስት በስቴይንሜትዝ እና ቢኤስጂአር ላይ ከፍተውት የነበረውን የሙስና ክስ በመተው በምላሹ በሲማንዳኡ ማእድን ማውጫ ላይ ያላቸውን መብት አግኝተዋል። የጊኒ መንግስት በስዊስ ምርመራ ላይ አለመሳተፉን ገልጾ ከቢኤስጂአር ጋር "አላስፈላጊ ውዝግብ" ውስጥ መግባት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። በ2016 ስቴይንሜትዝ ከማእድን ማውጣት ስራቸው ጋር በተያያዘ በእስራኤል መንግሥት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ የተደረገባቸው ሲሆን በወቅቱ ምንም አይነት ጥፋት አለመስራታቸውን ተናግረው ነበር። ሲማንዳኡ በአለማችን ከፍተኛ የሆነ የብረት ማእድን ክምችት የሚገኝበት ስፍራ ነው። ጊኒ በማእድን ኃብት ከበለፀጉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ዜጎቿ ግን በቀን ከ27 ብር በታች ገቢ የሚያገኙ ምንዱባን ናቸው።
news-55547008
https://www.bbc.com/amharic/news-55547008
ኮሮናቫይረስ፡ በአፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮቪድ ወረርሽኝ "በጣም ፈጣን ነው" ተባለ
አፍሪካን በሁለተኛ ዙር እያጠቃ ያለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከመጀመሪያው ይልቅ "እጅግ ፈጣን" መሆኑን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ገለፀ።
የድርጅቱ ኃላፊው፣ ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት አፍሪካ በአሁን ሰዓት በቀን 30 ሺህ በቫይረሱ የሚያዙ አዳዲስ ሰዎችን እያስመዘገበች መሆኑን ገልፀው፣ ይህ ግን በሐምሌ ወር አጋማሽ በቀን 18 ሺህ ሰው ብቻ እንደነበር በማነጻጸር ቫይረሱ በፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑን እንደሚያሳይ አብራርተዋል። አፍሪካ በአሁኑ ሰዓት ወደ ሦስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ስታረጋግጥ ከእነዚህም መካከል 68,755 ያህሉ ደግሞ መሞታቸውን ይፋ ተደርጓል። ሩዋንዳ፣ ናሚቢያ፣ ዚምብብዌ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት አዲስ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥለዋል። ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ባለበት ለማቆምና ለመግታት የአህጉሪቷ ብቸኛ ተስፋ የአፍና አፍንጫ መሸፈናን በአገገግባቡ ማድረግ ብቻ ነው ካሉ በኋላ መንግሥታት ድጎማ በማድረግ ለሕዝባቸው እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል። በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ አህጉር በሚገኙ የተለያዩ አገራት የሚኖሩ ሕዝቦች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሁልጊዜ አልያም ፈጽሞውኑ እንደማያደርጉ የገለጹት ዶክተሩ፣ የአካላዊ ርቀቱም ቢሆን እጅግ በጣም የተጠጋጋ መሆኑን ማስተዋላቸውን ገልጸዋል። "ይህ አሳሳቢ ነው" ካሉ በኋላም፣ "ሁለተኛው ዙር እጅግ ፈጣን ነው" ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
news-55134082
https://www.bbc.com/amharic/news-55134082
ትግራይ ፡ አክሱም ተያዘና አውሮፕላን ተመታ መባሉን መንግሥት ሐሰት ነው አለ
የህወሓት ኃይሎች ትላንት [እሁድ] ምሽት አክሱም ከተማ መልሰው እንደያዙና የፌዴራል መንግሥት ንብረት የሆነ ተዋጊ ጄት መትተው መጣላቸውን ገልጸው ነበር።
ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በህወሓት በኩል ተባሉት ነገሮችን "ነጭ ውሸት" ሲሉ አጣጥለውታል። ሚኒስትር ዛዲግ ጨምረውም "የህወሓት የመጨረሻ ይዞታ የነበረችው መቀሌ ናት፤ ይህንን ሊያደርጉ አይችሉም" ሲሉ ተናግረዋል። ከሦስት ሳምንት በላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ውስጥ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ዋና ከተማዋን መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መከላከያ "ሕግ የማስከበሩ ዘመቻ" መጠናቀቁን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከመቀለ መያዝ በኋላ ለሮይተርስ ዜና ወኪል በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እንደገለጹት በውጊያው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። በተጨማሪም የቡድኑ ኃይል መቀለ ከተማ አቅራቢያ ውጊያ እያካሄደ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን በተመለከተ ህወሓት የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ እንደሆነ በቢቢሲ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ዛዲግ አብረሃ ሲመልሱ "የህወሓት አመራሮች በአሁኑ ጊዜ ሕይወታቸውን ለማዳንና በሕግ ከመጠየቅ ለማምለጥ እየሸሹ ነው እንጂ ውጊያ ላይ አይደሉም" ሲሉ መልሰዋል። ትናንት ምሽት ከየት ቦታ እንደሆነ ካልታወቀ ስፍራ ከህወሓት በኩል ወጣ በተባለ መግለጫ ላይ የቡድኑ ተዋጊዎች ከሳምንት በፊት በፌደራሉ ኃይሎች የተያዘችውን የአክሱም ከተማን መልሰው እንደተቆጣጠሩና አንድ ተዋጊ አውሮፕላን መትተው መጣላቸውን ገልጸዋል። አቶ ዛዲግ አብርሃ ግን ተመትቶ የወደቀ የጦር አውሮፕላን እንደሌለና የአክሱም ከተማ "መያዝም በፍፁም ከእውነት የራቀ ነው" ብለው፤ "ህወሓት በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት ወታደራዊ አቅም የለውም፤ ሚሊሻውም ሆነ ልዩ ኃይሉ እጅ እየሰጠ ነው" ሲሉ ከቢቢሲ ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ አክለው በክልሉ ያለውን ሁኔታ ለጋዜጠኞች ክፍት ለማድረግ በትግራይ የተለያዩ ቦታዎች በርካታ መሠረተ ልማቶች በህወሓት ኃይል በመውደማቸው እነሱ ከተጠገኑ በኋላ ጋዜጠኞች ወደ ሥፍራው ሄደው ሁኔታውን ማጣራት ይችላሉ ሲሉ የመገናኛ መስመሮች አለመኖራቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ዛዲግ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር ስለዋሉ ሰዎች ትክክለኛው አሃዝ እንደሌላቸው አመልክተው፤ የቀሩት የህወሓት አመራሮች ሲያዙ ለሕግ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል። በትግራይ ክልል ያሉ የስልክና የኢንተርኔት መገናኛ መንገዶች የማይሰሩ በመሆናቸው ቢቢሲ ከክልሉ የሚወጡ መረጃዎችን በራሱ ማጣራት አልቻለም። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው ህወሓት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው አለመግባባት ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ መካረሩ ይታወሳል። ተከትሎም የፌደራል መንግሥቱን ውሳኔ ባለመቀበል ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተካሄደው የተናጠል ምርጫ የፌደራል መንግሥቱን ተቀባይነት ካለማግኘቱ በተጨማሪ በአገሪቱ ምክር ቤቶች ሕገ ወጥ ተብሎ ውድቅ ተደርጓል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የክልሉን አስተዳዳሪዎች ሕገ መንግሥቱን በመጣስና ከሕግ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በማለት የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ክልል ክልል አስተዳደር ጋር የነበረውን የቀጥታ ግንኙነት አቋርጦ የበጀት ዕቀባ ጥሎ ነበር። አለመግባባቱና መካሰሱ ያለማቋረጥ በቀጠለበት ሁኔታ ጥቅም 24/2013 ዓ.ም ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ክልል በነበረው የፌደራሉ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት በትግራይ ክልል ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመሩ ይታወሳል። መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ባለውና ከሦሰት ሳምንታት በላይ በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል። ባለፈው ቅዳሜ የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ሰር ከዋለች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳውቀዋል።
49897069
https://www.bbc.com/amharic/49897069
"የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ
የኢትዮጵያ የማራቶን ውድድር ሯጮች ላይ ምንም አይነት የእገዳ ውሳኔ እንዳልተላለፈ ከአትሌቶቹ ጋር ካታር የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክትር ዱቤ ጂሎ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ፣ ሰለሞን ባረጋና ዱቤ ጂሎ በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌቶች ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት እረፍት አድርገው እንዲያገግሙ እንጂ እገዳ አለመሆኑን ገልጸዋል። • ቀነኒሳ 'ከሞት እንደመነሳት' ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ • በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ ውሳኔው ከ42 ኪሎሜትሮች በላይ በሚሮጥበት ከባድ በሚባለው የማራቶን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሯጮችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰድ ተቀባይነት ያለው እረፍት ነው ብለዋል ዱቤ ጅሎ። አትሌቶች የሦስት ወራት የማገገሚያ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ በዓለም አቀፍ የውድድር ሕግና ደንብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውና በሌሎችም ሃገራት የሚሰራበት እንደሆነ አመልክተዋል። ለሦስት ወራት ከውድድር እርቆ የሚወሰደው እረፍት ሁሉንም በማራቶን ውድድር የተሳተፉ አትሌቶችን የሚመለከት መሆኑን የጠቀሱት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ፤ በተለይ በዶሃ ያለው ከባድ ሙቀት ላይ ለተወዳደሩ አትሌቶች እረፍቱ በጣም አስፈላጊያቸው ነው ብለዋል ለቢቢሲ። ባለፈው አርብ ሌሊት በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ሯጮች በነበረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ውድድሩን አቋርጠው መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ በርካቶችም ለማቋረጥ ተገደው ነበር። • ''በኳታር የኢትዮጵያ ቡድን በሙቀቱ ተቸግሯል'' የቡድኑ መሪ • የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ከአትሌቲክስ ታገዱ ስለዚህም የማራቶን ሯጮቹ ከነበሩበት ከባድ ሁኔታ እንዲያገግሙ በፌዴሬሽኑ ደንብ መሰረት ለሦስት ወራት ልምምድ እየሰሩ እረፍት እንዲያደርጉና ከውድድር እንዲርቁ መደረጉን አመልክተዋል። በሴቶቹ የማራቶን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩትና አቋርጠው ለመውጣት የተገደዱት ሯጮች የጤንነት ሁኔታን በተመለከተ በስፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ዱቤ ጅሎን ጠይቆ ባገኘው መረጃ መሰረት አንዷ ከገጠማት ቀላል ችግር በስተቀር ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋዋል። በዶሃ ባለው ከባድ ሙቀት ምክንያት በእኩለ ሌሊት ጎዳና ላይ በሚደረጉት የማራቶንና የእርምጃ ውድድሮች ተሳታፊዎች ላይ ከባድ ጫናን የሚያሳድር እንደሆነ የተናገሩት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ስታዲየም ውስጥ የሚደረገው ግን ብዙም አስቸጋሪ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
news-56755836
https://www.bbc.com/amharic/news-56755836
አሜሪካ ከሳይበር ጥቃት ጋር በተያያዘ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ልትጥል ነው
የአሜሪካ መንግሥት በሩሲያ ላይ መጠነ ሰፊ ማዕቀብ ሊጥል እንደሆነ የተለያዩ ሪፖርቶች ቢቢሲ አግኝቷል።
አሜሪካ ይህንን ሰፊ ማዕቀብ የምትጥለው ሩሲያ ባደረገችው የሳይበር ጥቃት አፀፋዊ ምላሽ እንደሆነ አስታውቃለች። ከዚህም በተጨማሪ አሜሪካ በባለፈው አመት ባደረገችው ምርጫ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች በማለትም ትወነጅላለች። ማዕቀቡ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ይጀምራል ተብሎ የሚታመን ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 30 የሩሲያ ተቋማትን ጨምሮ 10 ሩሲያውያን እንደሚባረሩ ተገልጿል። ኢላማ ከሆኑት መካከል ዲፕሎማቶችም አሉበት ተብሏል። የጆ ባይደን አስተዳደር በተጨማሪ የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት ከሰኔ ጀምሮ የሩሲያ ቦንድ ከመግዛት እንደሚታገዱም ምንጮችን ጠቅሶ የቢቢሲ የሚዲያ አጋር ሲቢኤስ ዘግቧል። የአሜሪካና የሩሲያ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሻከረ መጥቶ ወደ ባላንጣነት ሊሸጋገሩ ይችላል በሚባልበት ወቅት ነው ይህ ማዕቀብ የሚጣለው። ጆ ባይደንና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ማክሰኞ እለት ባደረጉት የስልክ ልውውጥ ባይደን አገራቸው ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር "ቆፍጠን ያለ እርምጃ ትወስዳለች" ብለዋል። ባይደን ከዚህ በተጨማሪ ከፑቲን ጋር "ሶስተኛ አገር እንገናኝ" የሚል እቅድ ያቀረቡ ሲሆን ሁለቱም መሪዎች አብረው የሚሰሩባቸውን ዘርፎችም ለማየት ያስችላቸዋል ተብሏል። በባለፈው ወር ጆ ባይደን ከአንድ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ "ፑቲን ነፍሰ ገዳይ ነው ብለው ያስባሉ ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸው "አዎ" የሚል ነበር። አክለውም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለሩሲያ ፕሬዚዳንት "የሚያደግዱበት ወቅት አብቅቷል" ብለዋል። ውስብስብ በተባለው ሩሲያን ጥፋተኛ ባደረገው የሳይበር ጥቃት ዒላማ ከሆኑት የአሜሪካ ኢነርጂ ቢሮ እና ፌደራል መሥሪያ ቤቶች በተጨማሪ የመከላከያ ፣ የአገር ውስጥ ደኅንነት (ሆምላንድ ሴኩሪቲ)፣ የአሜሪካ ግምጃ ቤትና ንግድ ሚኒስቴር ዳታዎች ዒላማ ተደርገዋል።
news-51440260
https://www.bbc.com/amharic/news-51440260
ቻይና ውስጥ በኮሮና ቫይረስ 97 ሰዎች በአንድ ቀን ሞቱ
በቻይና በትናንትናው ዕለት በኮሮና ቫይረስ ብቻ በአንድ ቀን 97 ሰዎች ሞቱ፤ ይህም ቁጥር እስካሁን በቀን ውስጥ ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው ተብሏል።
በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር 908 የደረሰ ቢሆንም በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ግን ለውጥ አላሳየም እንዲያውም መረጋጋት አሳይቷል እየተባለ ነው። በአጠቃላይ በቻይና በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 40 ሺ 171 የደረሰ ሲሆን፣ 187 ሺ 518 ግለሰቦች ደግሞ በቅርብ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው። • በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ቁጥር ከሳርስ እንደበለጠ ተገለፀ • ኢትዮጵያውያን፡ የአስወጡን ድምጽ በጎሉባት የቻይናዋ ዉሃን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ቫይረሱ ያለበትን ሁኔታ የበለጠ ለመመርመር በቅርቡ የህክምና ባለሙያዎችንና ተመራማሪዎችን የያዘ ቡድን ልኳል። ከቻይና መንግሥት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እስካሁን ድረስ በቫይረሱ የተያዙ 3 ሺ 281 ግለሰቦች ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። የቻይና አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግና በተጨማሪም ቫይረሱ እንዳይዛመት ተብሎ ስራ እንዲቋረጥ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፤ በዛሬው ዕለት ሚሊዮኖች ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል። ነገር ግን የስራ ቦታ እንደ ቀድሞው አይሆንም፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት፣ እንዲሁም የስራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት እንደ አስፈላጊነቱም የሚቀያየር ይሆናል፤ አንዳንድ የስራ አይነቶችም ለተወሰነ ጊዜ ተዘግተው ይቆያሉ። • 29 የኮሮናቫይረስ ጥቆማዎች እንደደረሱት ጤና ጥበቃ አስታወቀ • በሽታውን ለመደበቅ ባለስልጣናት ዶክተሮችን ያስፈራሩ ነበር በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር በጎርጎሳውያኑ 2003 የተነሳው የሳርስ ወረርሽኝ ከቀጠፈው ህይወት እንደበለጠ ተገልጿል። የቫይረሱ መነሻ በሆነችው ሁቤ ግዛት የሟቾች ቁጥር 780 እንደደረሰና፤ ቅዳሜ ዕለትም በግዛቷ 81 ሰዎች እንደሞቱ የጤና ባለሙያዎች አስታውቀዋል። የዓለም የጤና ድርጅት በቫይረሱ የሚያዙ አዲስ ሰዎች ቁጥር ለውጥ እንደሌለው ከሰሞኑ ገልጿል። በትናንትናው ዕለት ድርጅቱ ዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጪዎችንም ወደ ቻይና ልኳል። ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በሁቤዋ ግዛት ውሃን ከተማ ሲሆን፤ የአስራ አንድ ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያ የሆነችው ውሃን ለሳምንታትም የጉዞ፣ የመውጣትና የመግባት እግድ ተጥሎባታል። ከሳምንት በፊት ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስን የአለም የጤና ስጋት ነው ብሎታል። • አፍሪካ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል አቅሙ አላት? ቫይረሱ ከቻይና ወደ 27 ሃገራት የተዛመተ ቢሆንም ከቻይና ውጭ ያለው የሟቾች ቁጥር ሁለት ነው፤ አንደኛው በሆንግኮንግ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በፊሊፒንስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ወደ ሆንግ ኮንግ የገባች መርከብ መንገደኞችና ሰራተኞቹ በጥርጣሬ ምክንያት በለይቶ ማቆያ ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆዩ ቢደረግም ከምርመራ በኋላ እንዲወርዱ ተፈቅዶላቸዋል። ይህቺ መርከብ እንድትለይ የተደረገችው ከዚህ ቀደም በአንዲት የጃፓን መርከብ ላይ ስምንት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በመገኘታቸው ነው። በጃፓን በመርከቡ ውስጥ ካሉ መንገደኞች መካከል በቫይረሱ የተያዙ መኖራቸው መረጋገጡን ተከትሎ መርከቧ ተለይታ እንድትቆይና መንገደኞችም እንዳይወርዱ ተደርገዋል። ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ ቫይረሱ ይዛመታል በሚል ፍራቻ ማንኛውም መርከብ ሃገሯ እንዳይገባ እግድ ጥላለች።
news-55420996
https://www.bbc.com/amharic/news-55420996
ትራምፕ ለአሜሪካውያን 600 ሳይሆን 2 ሺህ ዶላር ነው የሚገባቸው አሉ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በወረርሽኙ ምክንያት ገቢያቸው ለተዳከመ ዜጎቻቸው የተዘጋጀውን ድጎማ ውድቅ አደረጉ።
ፕሬዝደንቱ፤ አሜሪካዊያን በነብስ ወከፍ 2 ሺህ ዶላር እንዲከፈላቸው ኮንግረሱን ጠይቀዋል። በትዊተር ገፃቸው ላይ በለጠፉት የቪድዮ መልዕክት ነው ትራምፕ "ይህን ብኩን እና አላስፈላጊ ኮተት" የሞላውን ድጎማ ወዲያ በሉልኝ ያሉት። ሰኞ ዕለት የአሜሪካ ኮንግረስ ያፀደቀውን ድጎማ ትራምፕ "እጅግ አሳፋሪ" ሲሉ ዘልፈውታል። "ለስሙ የኮቪድ ድጎማ ብላችሁታል፤ ነገር ግን ስለ ኮቪድ አንዳች ነገር የለውም" ሲሉ ተደምጠዋል ተሰናባቹ ፕሬዝደንት። በሚቀጥለው ጥር ሥልጣናቸውን ለጆ ባይደን አሳልፈው የሚሰጡት ትራምፕ ሰኞ ዕለት የቀረበላቸውን የድጎማ ጥያቄ ሰነድ ፊርማ በማሳረፍ ያፀድቁታል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ነገር ግን ከዋይት ሐውስ ሆነው ባስተላለፉት መልዕክት "ገንዘቡ ችግር ላሉ አሜሪካዊያን የሚበቃ አይደለም" ብለዋል። "ድጎማው 85.5 ሚሊዮን ዶላር ለካምቦዲያ፣ 134 ሚሊዮን ዶላር ለበርማ፣ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ለግበጽና የግብፅ መከላከያ ኃይል [በእርግጠኝነት በዚህ ገንዘብ የሩስያ መሣሪያ ነው የሚገዙበት]፣ 25 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ለፓኪስታን ዴሞክራሲና የፆታ እኩልነት እንዲሁም ለሌሎች አገራት የያዘ ነው" ብለዋል ትራምፕ። ትርምፕ "ለምንድነው ዲሲ የሚገኘው የኬኔዲ አርት ማዕከል ሳይከፈት 40 ሚሊዮን ዶላር ድጎማ የተመደበለት" ሲሉ ጠይቀዋል። አልፎም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለአሜሪካ መንግሥት ማዕከል ለሆነችው ዲሲ ሙዚየሞች መመደቡ ትክክል አይደለም ሲሉ ወርፈዋል። "ኮንግረሱ ለውጭ አገራት በርካታ ገንዘብ ካገኘ በጣም ለሚያስፈልጋቸው አሜሪካዊያን እንዴት ይህን ማድረግ ተሳነው። ይህ የእነሱ ጥፋት አይደለም፤ የቻይና እንጂ" ብለዋል ትራምፕ በቪድዮ መልዕክታቸው። "ኮንግረሱ ለአሜሪካዊያን በነብስ ወከፍ 600 ዶላር ሲል የመደበውን አስቂኝ ድጎማ ወደ 2 ሺህ [ለጥንዶች 4 ሺህ] ከፍ እንዲያደርግ እጠይቃለሁ። "በተጨማሪም አላስፈላጊ የሆኑ ድጎማዎችን አስወግዶ የመጨረሻ ፊርማ እንዳሳርፍ ያቅርብልኝ። አለበለዚያ ቀጣዩ መንግሥት ነው የኮቪድ ድጎማ የሚያፀድቀው።" የትራምፕ አስተያየት በርካታ ፖለቲከኞችን አስደንግጧል። ለወራት ሲያከራክር የቆየው የኮቪድ-19 ድጎማ ድጋሚ ሌላ ውጥንቅጥ አግኝቶታል። ዴሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች በዚህ ጉዳይ ከባለፈው ሐምሌ ጀምሮ ሲሟገቱ ቆይተዋል። ነገር ግን ድጎማው በርካታ አጠርጣሪና ከኮቪድ-19 ጋር ግንኙነት የሌላቸው አንቀፆች አዝሏል ሲሉ የአሜሪካ መገናኝ ብዙሃን ተችተውት ነበር። ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ይህ ድጎማ ቅድመ ክፍያ ነው እንጂ በቀጣይ መንግሥት ዳጎስ ያለ ድጎሞ ያዘጋጃል ብለው ነበር። የትራምፕ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆኑት የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ ጉባዔዋ ናንሲ ፔሎሲ "ፕሬዝደንቱ ትክክል ናቸው፤ ክፍያው 2 ሺህ ዶላር ሊሆን ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል። ባፈለው ሰኞ ከሰዓታት ክርክር በኋላ የፀደቀውን ድጎማ በርካታ ሕግ አውጭዎች በውል አላነበብነውም ሲሉ አማረው ነበር። ድጎማው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ችግር ላሉ በርካታ ሚሊዮን አሜሪካዊያን በነብስ ወከፍ ይደርሳል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ባለፈው መጋቢት የአሜሪካ መንግሥት ለተቸገሩ አሜሪካዊያን የሚሆን 2.4 ትሪሊዮን ዶላር መድቦ ነበር። አሁን ለአሜሪካዊያን የተመደበው 600 ዶላር ካለፈው ጋር ሲነፃፀር ግማሽ ያህል ነው።
news-54726762
https://www.bbc.com/amharic/news-54726762
ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ
በእንግሊዝ ውስጥ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በየቀኑ በኮሮናቫይረስ እንደሚያዙ አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡
እንደለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ ጥናት ከሆነ ወረርሽኙ በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን በየዘጠኝ ቀናትም በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል፡፡ አጥኚዎቹ "ወሳኝ ደረጃ ላይ በመሆናችን አንድ ነገር መደረግ አለበት" እያሉ ነው፡፡ ፈረንሳይ እና ጀርመን ቫይረሱን ለመቆጣጠር የተለያየ ደረጃ ያለው ገደብ ጥለዋል፡፡ በፀደይ ወራት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወደ ነበረበት ደረጃ በፍጥነት እየተቃረብን ነው በማለት ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ፡፡ ጥናቱ ወቅታዊ የሆነው የኮቪድ -19 ጥናት በመሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው ተብሎለታል፤ 86 ሺህ የሚጠጉ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት እና የመጨረሻዎቹ ምርመራዎች እሁድ የተካሄደበት ጥናት መሆኑን በመጠቆም፡፡ ጥናቱ እንዳሳየው ቫይረሱ በሁሉም የእድሜ ክልል እና በእያንዳንዱ የእንግሊዝ ግዛት እየጨመረ መሆኑን ያሳያል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ስርጭቱ ከፍተኛ ቢሆንም በደቡብ በኩል ቢሆን በፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ከአጥኚዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቨን ሪሌይ መረጃው መገኘት ሲጀምር እንዳዘኑ ገልፀው "አሁን ያሉት እርምጃዎች በቂ አይደሉም" ብለዋል ፡፡ "ለውጥ መኖር አለበት። ፍጥነት በእውነቱ በጣም ፈጣን በመሆኑ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከገና በፊት ለውጥ ሊኖር ይገባል" ብለዋል ፡፡ ህዝቡ በደንብ ህጎችን ማክበር አለበት ወይም መንግሥት ከባድ ገደቦችን መጣል አለበት ሲሉም ተከራክረዋል ፡፡ "መረጃዎቹ በፍጥነት መወሰንን የሚሹ ናቸው" ብለው ገልጸዋል።
news-54723540
https://www.bbc.com/amharic/news-54723540
ቱርክ ፕሬዚዳንቷን አዋርዷል ያለችውን የፈረንሳይ መፅሄት ልትከስ ነው
የፈረንሳዩ መፅሄት ቻርሊ ሄብዶ የቱርክን ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋንን ክብር በሚነካ መልኩ የካርቱን ምስል አትሟል በሚል ቱርክ ህጋዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎችን እንደምትወስድ ቃል ገብታለች።
በካርቱኑ ምስል ላይ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የጠመጠመችን ሴት ቀሚስ ሲገልቡ ያሳያል። የቱርክ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ከሆነ የአገሪቱ አቃቤያነ ህግ በቧልተኛው መፅሄት ላይ ይፋዊ የሆነ የምርመራ ፋይል መክፈታቸውን ነው። በቱርክ መንግሥት ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ ቁጣም ቀስቅሷል። የፕሬዚዳንቱ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ፋህረቲን አልቱን"ቻርሊ ሄብዶ ፕሬዚንዳንቱ ላይ ያነጣጠረ አፀያፊ የካርቱን ምስሎችን አትሟል። መፅሄቱ እነዚህን አፀያፊ ምስሎች በማተም የሚያደርገውን የባህል ዘረኝነትና ጥላቻ ማስፋፋት እናወግዛለን" ብለዋል። የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንትም እንዲሁ ይህንን ክብር የሚያዋርድ ምስልን በመቃወም ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አቅርበዋል። "የማሰብና የመናገር ነፃነት በሚል ሽፋን ስም በመደበቅ የሚሰራው ስራ ማንንም አያታልልም" ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንቱ በትዊተር ገፃቸው የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "ፅንፈኛ ሙስሊሞች" ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ እወስዳለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በፈረንሳይና በቱርክ መካከል ውጥረት ነግሷል። በኔዘርላንድ ባለ ፀረ እስላም የፓርላማ አባልም ከካርቱን ጋር በተገናኘ ክስ የመመስረት ሂደት ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የፈረንሳይ ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ፕሬዚዳንት ማክሮንንም "የአእምሮ ምርመራ ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል። ውጥረቱ በቱርክና በፈረንሳይ መካከል ብቻ ሳይሆን በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ባሉዋቸው ባንግላዴሽ፣ ኩዌት፣ ዮርዳኖስና ሊቢያ በመሳሰሉት አገራትም የፈረንሳይ ምርቶችን አንገዛም በሚል የማእቀብ ጥሪ ተደርጓል። ውዝግቡ በተለይ የተጧጧፈው የነብዩ መሃመድን ካርቱን በክፍል ውስጥ በማሳየቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀልቶ የተገደለው ፈረንሳያዊው መምህርን ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ ባደረጓቸው ንግግር ነው። ፕሬዚዳንት ማክሮን መምህር ሳሙኤል ፓቲ "የተገደለበት ምክንያት የእስልምና እምነት ተከታዮች የወደፊቱ እጣ ፈንታችንን መቆጣጠር ስለሚፈልጉ ነው። ፈረንሳይ ካርቱኗንም ቢሆን አሳልፋ አትሰጥም" ብለዋል። የነብዩ መሃመድን ምስል በየትኛውም ሁኔታ ማሳየት በእስልምና እምነት ነውርና አፀያፊ ተደርጎም ይቆጠራል። ሆኖም ፈረንሳይ ከእምነት ውጭ ያለ አገዛዝን እንደመከተሏ መጠን የመናገር ነፃነትን የሚቀለብስ ነው ነው በማለትም ትከራከራለች።
43722154
https://www.bbc.com/amharic/43722154
"ድርጅቴ ከሩስያ ጋር ጦርነት ገጥሟል" የፌስቡክ አለቃ ዙከርበርግ
የፌስቡክ መሥራች እና አለቃ የሆነው ማርክ ዙከርበርግ ትላንት በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ፊት ቀርቦ ባሰማው ንግግር "ድርጅቴን በዝብዘው መረጃ ለመውሰድ ከሚፈልጉ ሩስያውያን ጋር ጦርነት ገጥሜያለሁ" ሲል ተደምጧል።
"ይህ የለየለት ጦርነት ነው። እነሱ መረጃ መበርበር ላይ እጅጉን እየበረቱ መጥተዋል" ሲል ነው ዙከርበርግ ስሞታውን ያሰማው። ዙከርበርግ ትላንት በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ፊት ሊቀርብ የተገደደበት ምክንያት "አንድ ድርጅት የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን መረጃ በርብሯልና ጉዳዩን አብራራልን" ተብሎ በመጠየቁ ነው። አልፎም ሮበርት ሙለር የተባሉቱ ሩስያ በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች ወይስ አልገባችም የሚለውን አጀንዳ የሚያጣሩ ግለሰብ ፌስቡክ ላይ ምርመራ እንዳከናወኑ ዙከርበርግ አሳውቋል። በአውሮፓውያኑ 2016 መባቻ ላይ ነበር የአቶ ሙለር ቢሮ ሩስያ በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ሳትገባ አትቀርም የሚለውን ጉዳይ ለማጣራት ሥራውን የጀመረው። ይህ ልዩ አጣሪ ኃይል ሩስያ በይነ-መረብን ተጠቅማ ምርጫው ላይ ጫና አሳድራ እንደሆነ የሚያጣራ ክንፍ ያለው ሲሆን ፌስቡክ ደግሞ አንዱ ምርመራ የሚካሄድበት ድር ሆኖ ተገኝቷል። ቢሆንም ዙከርበርግ ከህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥበት ባመሸበት ምሽት ድርጅቱ መረጃ ሾልኮ እንዳይወጣ የታቸለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ተናግሯል። ከምክር ቤቱ አባላት አንዱ የሆኑት ጆን ኬኔዲ "ፌስቡክ ቁጥጥር ይደረግበት ብዬ ማለት አልፈልግም፤ አስፈላጊ ከሆነ ግን ከማድረግ ወደኋላ አልልም። ሲቀጥል ተጠቃሚዎች ከድርጅቱ ጋር የሚያደርጉት ስምምነት ችግር አለበት" ሲሉ ሃሳባቸውን ለዙከርበርግ ነግረውታል። በምላሹ ዙከርበርግ "የሰዎችን መረጃ ለመጠበቅ ፍፁም የሆነ ተግባር እንዳልፈፀምን እሙን ነው። ፖለቲካዊ ሃሳቦች ድርጅታችን ላይ ተፅዕኖ እንዳያመጡም ጠንክሬ አሠራለሁ" ሲል ቃል ገብቷል። የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ሾልኮ ወጥቷል የሚለው ዜና በተሰማ ጊዜ ወርዶ የነበረው የድርጅቱ ድርሻ የዙከርበርግ ምላሽ ከተሰማ በኋላ በ5 በመቶ ጨምሮ ታይቷል።
news-48167002
https://www.bbc.com/amharic/news-48167002
የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ሱዳን አቀኑ
በውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ሱዳን አቀና።
የውጨ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳስታወቀው ልዑኩ ትናንት ቅዳሜ ምሽት ካርቱም የደረሰ ሲሆን፤ ዛሬ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ከሱዳኑ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጋር ውይይት አድርገዋል። አቶ ገዱ ኢትዮጵያ የሱዳንን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ ለሱዳን ህዝብ ያላሰለሰ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ለወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሊውተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን አሳውቀዋል። • የሱዳን ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወታደሩ ያስቀመጠውን ሰዓት እላፊ ጣሱ • በሱዳን የኦማር አል-በሽር ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተዋል ሚንስትሩ ጨምረውም ኢትዮጵያ የኢጋድ ሊቀመንበር እንደመሆኗ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከተቀረው ዓለም አቀፍ ማህብረሰብ ጋር በመሆን በሱዳን ሰላማዊ እና ሁሉን አቀፍ ሽግግር እንዲኖር ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል። ሊውተናንት ጀነራል አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን በበኩላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የሰጡትን ድጋፍ እና የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት አዲስ አበባ ባቀናበት ወቅት ለተደረገለት አቀባበል አመስግነዋል። ሊውተኔት ጀነራል አብዱል ምንም እንኳ በሱዳን የመንግሥት ለውጥ ቢኖርም ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያለት መልካም ግነኙነት አይቀየርም ማለታቸውን የውጪ ጉዳይ ሚንሰቴር አስታውቋል።
45731011
https://www.bbc.com/amharic/45731011
"ማንም ቢሆን ኢትዮጵያን ለብቻዬ ሰራኋት ሊል አይችልም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
'ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና' በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የኢህአዴግ ጉባዔ ላይ የግንባሩ አባል ድርጅቶች አመራሮችና አባላት፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ የወዳጅ ሀገራት ልዑካን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔና የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ንቅናቄ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል የጉባኤውን ታዳሚዎች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ጉባዔውን በንግግር አስጀምረዋል። በመቀጠልም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጋብዘዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም በንግግራቸው ጉባዔው የኢትዮጵያን የወደፊት ዕድል የሚወስን እንደሚሆን ተናግረዋል። • አቶ መላኩና ጄነራል አሳምነው ለማዕከላዊ ኮሚቴ ተመረጡ • የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ • "ለወጣቶች አስፈሪ ጊዜ ነው" ትራምፕ ኢህአዴግ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች ፊት ለፊት ተጋፍጦ ሳይንሳዊ መፍትሄ በመስጠት እንደፈታ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ወቅታዊ ለውጥ የምናካሄደው የህዝቡን ደጀንነት በመያዝ በኢህአዴግ መሪነት ነው" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የወጣት ሀገር ናት፤ ኢትዮጵያ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አብሪ ኮከብ ለመሆን እየተጋች ነች በማለት ተናግረዋል። በንግግራቸው ሀገር የምታድገው በቅብብሎሽ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲሱ ትውልድ ከማማረር ይልቅ ያለፈውን ትውልድ በማመስገን ከቀደመው ትውልድ በጎ በጎውን በመውሰድ መማር ያስፈልገዋል ብለዋል። "የአዲሱ ትውልድ ተተኪ መሪዎችም ያለፈውን ነገር ሁሉ ማማረርና ባለፈው ትውልድ ላይ ማሳበብ አይገባቸውም። ይልቅም ያለትናንት ዛሬ አልተገኘምና ያለፈውን ትውልድ ማመስገን ያስፈልጋል" ሲሉ ተደምጠዋል። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚደረገው ሽግግር በመመሰጋገን እና በመተራረም ላይ የሚያደርግ የፖለቲካ ባህል መትከል ያስፈልጋል። መተካካት የታቀደ የፖለቲካ ባህል እንጂ ድንገተኛ የመበላላት ክስተት እንዳይሆን ስርዓት መትከል ያስፈልጋል ሲሉ በአፅንኦት ተናግረዋል። ተተኪ የማያፈራ መሪ እንደማይባል ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ትውልዱ ቀድሞ የነበረውን በማፍረስ ላይ መጠመድ እንደማያስፈልግ "እጅና እጅ ሆነን ከፍታችንን መውጣት ይገባናል" ሲሉ አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ አምባገነን መሪዎች እንደነበሯት ሁሉ ለሀገር አንድነት የሰሩ መኖራቸውን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ "በአሁኑ ወቅት ያሉት አመራሮችስ? ኢትዮጵያን የዓለም ራስ እናደርጋታለን ወይስ ጭራ?" በማለት ለተሰብሳቢው ጥያቄ አቅርበዋል። መሪነትን በፖለቲካ እና በመንግሥት ስልጣን ላይ ፊጥ ማለት አድርጎ ማሰብ ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው ህዝብን የሉዓላዊ ስልጣን ምንጭ አድርጎ ማሰብ ተገቢ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በንግግራቸው ሀገር የተሳካ ጉዞ መጓዝ የምትችለው ሕዝብ የሚያዳምጣቸውና የሚከተላቸው የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሞራልና የግብረገብ መሪዎች በብዛት ሲገኙ፤ የማህበረሰብን የአስተሳሰብ ደርዝ የሚያሰፉ፣ በሀሳብ ልዕልና የሚያምኑ፣ ትውልድን የሚቀርፁ የእውቀትና የፍልስፍና ልሂቃን ሲበራከቱ ነው ብለዋል። በስራና ሀብት ፈጠራ የተካኑ፣ ዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪ የብልፅግና ቁመና ያላቸው፣ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን የሚወጡ የምጣኔ ሀብት አንቀሳቃሾች ካሉና ጎልተው ከወጡ፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምርና ጥናት ዓለም ከደረሰበት የእድገት ማማ ላይ በፈጣን ግስጋሴ የሚያደርሱ ታላላቅ ተመራማሪዎችና መምህራን በየዩኒቨርስቲዎቹ ከተገኙ እንደሆነም ተናግረዋል። በተጨማሪም ግጭትና ሽብር በበዛበት ዓለም ላይ ለልዑላዊነታችን መከበርና ለሰላማችን መረጋገጥ በሰለጠነ መልኩ ስልጡን የጦር መሪዎች ቦታቸውን ከያዙ፣ በሙያዊ ክህሎታቸውና በአመለካከታቸው የበሰሉ የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሱ በተለያዩ የስራ መስኮች ከተሰማሩ እንደሆነም በዝርዝር አስረድተዋል። "የተረከብናትን ኢትዮጵያ አለመውደድ መብታችን ነው፤ የምናስረክባትን ኢትዮጵያ ግን አስውበን ማስረከብ ግዴታችን ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እኛን ልትመስል የተዘጋጀች ነች ብለዋል። የ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ አርማ • በቤንሻንጉል ጉምዝ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ • ኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት ታሥመዘግባለች፡ አይ.ኤም.ኤፍ. "ማንም ቢሆን ኢትዮጵያን ለብቻዬ ሰራኋት ሊል አይቻለውም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ በሁላችንም ላብና ደም የተሰራች በመሆኗ የጋራችን ናት ብለዋል። በመሆኑም ኢህአዴግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጎች ድርጅት እንዲሆን ጉባዔው የተለየ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም በንግግራቸው ገልፀዋል። አክለውም "በዋናነት ፉክክራችን ከዓለም ጋር እንጂ እርስ በእርሳችን ሊሆን አይገባም፤ ከዓለምም ጋር ስንፎካከር በመጠፋፋት መንፈስ ሳይሆን ለሁላችንም የምትሆን የተሻለች ዓለምን በመገንባት መንፈስ ላይ መሆን ይኖርበታል" ብለዋል። የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ለሶስት ቀናት በተለያየ ጉዳይ ላይ በመምከር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
news-53297108
https://www.bbc.com/amharic/news-53297108
ታዋቂው ራፐር ካንዬ ዌስት ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደር አስታወቀ
ታዋቂው ራፐር ካንዬ ዌስት ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደር በትናነትናው ዕለት አስታውቋል።
ይህም ማለቱ ሙዚቀኛው ከሚያደንቃቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይፎካከራል ማለት ነው። "በአሁኑ ወቅት ለአሜሪካ ቃል የገባነውን አምላክን በማመን የምንፈፅመበት ወቅት ነው። ራዕያችንን በአንድነት እንዲሁም የወደፊቱን የምንገነባበት ወቅት ነው" በማለት በትዊተር ገፁ ላይ ያሰፈረው ራፐሩ "ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ወስኛለሁ" ብሏል ባለቤቱ ኪም ካርዳሺያንና ቢሊዮነሩ ኤሎን መስክ ለራፐሩ ያላቸውንም ድጋፍ ገልፀዋል። ነገር ግን ካንዬ በርግጥ ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደር ግልፅ አይደለም። በህዳር ወር ለሚደረገውም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫም ስሙ በፌደራል ምርጫ ኮሚሽንም በተወዳዳሪነት አልተመዘገበም። ከምርጫ ኮሚሽኑ ቋት በተገኘው መረጃ መሰረት ከካንዬ ጋር የሚመሳሰል ስም ያለው ካንዬ ዲዝ ነትስ ዌስት የሚባል ስም በግሪን ፓርቲ ስም በጎርጎሳውያኑ 2015 በተወዳዳሪነት ተመዝግቦ ነበር። ራፐሩ ለፕሬዚዳንትነት እወዳደራለሁ ሲልም የመጀመሪያው አይደለም። በጎርጎሳውያኑ 2015 በነበረው የኤምቲቪ የቪዲዮ ሙዚቃ ሽልማትም በ2020 እንደሚወዳደር አሳውቆ ነበር። ነገር ግን በዚህ አመት ህዳር ወር ላይ የሚወዳደርበትን ጊዜ እንደገፋውና ከአራት አመት በኋላም በውድድሩ እንደሚሳታፍ ገልፆ ነበር። በወቅቱም ስሙን "ክርስቲያን ጂኒየስ ቢሊዮነር ካንዬ ዌስት" እንደሚለውም ተናግሯል። የአርባ ሶስት አመቱ ራፐር በትናንትናው ዕለት በትዊተር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት የፖለቲካ ፓርቲን ተቀላቅሎ ይወዳደር የሚለውን ነገር አላሳፈረም። ሆኖም ግን አራት ወራት ብቻ በቀሩት ምርጫ ያሉትን ፓርቲዎች ወክሎ መወዳደር የሚታሰብ አይደለም። ሙዚቀኛው በግል መወዳደር ከፈለገ ደግሞ ፊርማ አሰባስቦ ከቀነ ገደቡ በፊት በአንድ ግዛት መመዝገብ ይኖርበታል። በታላላቅ ግዛቶች በግል ተወዳዳሪነት ለመመዝገብ ያለው ቀነ ገደብ ያለፈ ሲሆን ነገር ግን በትንንሽ ግዛቶች አሁንም መመዝገብ ይችላል። በቀጣዩ ምርጫ ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት የሚፋለሙት ዶናልድ ትራምፕና የዲሞክራት እጩ የሆኑት ጆ ባይደን ናቸው። ከሁለት አመታት በፊት ራፐሩ በትራምፕ ደጋፊዎች ዘንድ የሚዘወተረውን "አሜሪካን ታላቅ እናድርግ" የሚል ባርኔጣ አድርጎ በዋይት ሃውስ ከፕሬዚዳንቱ ጋር የተገናኘ ሲሆን፤ ለብዙዎችም ያልገባቸውን ንግግርም አድርጓል። ትራምፕን በጣም እንደሚወዳቸው ተናግሮ ሊያቅፋቸውም ሲጠጋ ፕሬዚዳንቱም በበኩላቸው "በጣም የሚያስደስት ነው" ብለዋል። ራፐሩ ከዚህ በተጨማሪ ጥቁር አሜሪካውያን የዲሞክራት ደጋፊ መሆን አለባቸው የሚለውን እሳቤ በመቃወም ተናግሯል። ባለቤቱ ኪም ካርዳሺያን የካንዬን የፕሬዚዳንትነት መወዳደር ውሳኔ ከአሜሪካ ሰንደቅ አላማ ጋር በማድረግ በትዊተር ገጿ አስፍራለች። በአሁኑ ሰዓት የፍትህ ስርአቱ እንዲሻሻል ዘመቻ እያደረገች ያለችው ኪም ፕሬዚዳንቱም በርካታ እስረኞችን እንዲለቁ ተፅእኖንም መፍጠር ችላለች።
news-51131074
https://www.bbc.com/amharic/news-51131074
ሴት በመምሰል ጋብቻ የፈፀመው ግለሰብ 'ከተፈጥሮ ጋር በሚቃረን ድርጊት' ተከሰሰ
ሴት በመምሰል ከኢማሙ ጋር ጋብቻ የፈፀመው ግለሰብ 'ከተፈጥሮ ጋር በሚቃረን ድርጊቱ' ክስ እንደተመሠረተበት ዘ ዴይሊ ሞኒተር ጋዜጣ ዘገበ።
የግለሰቡ፣ ሪቻርድ ቱሙሻቤ እውነተኛ ማንነት የተገለጠው የጎረቤቱን ቴሌቪዥንና ልብሶች በመስረቅ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ነበር። "ግለሰቡ ያለሁበት ሁኔታ ድርጊቱን እንድፈፅም አስገድዶኛል" ሲልም የኢማሙ ሀሰተኛ ሙሽራ ድርጊቱን ስለመፈፀሙ አምኗል። ሼህ ሞሃመድ ሙቱምባ ሂጃብ ለባሿ 'ሚስታቸው'፣ ሰዋቡላህ ናቡኬራ ወንድ መሆኑን ባወቁ ጊዜ ክፉኛ ነበር የደነገጡት። ከአገሪቷ ዋና መዲና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ክያምፒሲ በተባለች መንደር በሚገኝ መስጊድ ኢማም የሆኑት ሼህ ሙቱምባ፤ በነበሩት የጫጉላ ጊዜያት 'ከሙሽራቸው' ጋር ወሲባዊ ግንኙነት አልነበራቸውም። ከሙሽራቸው ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ያልፈፀሙትም ሙሽሪት "የወር አበባ ላይ ነኝ" በማለቱ ነበር። ቱሙሻቤ ባለፈው ማክሰኞ በማጂስትሬት ፍርድ ቤት ሲቀርብ ይቅርታ እንዲጠይቅ አልተጠየቀም። እስከ ቀጣዩ ቀጠሮ የፈረንጆቹ ጥር 24 ድረስ በቁጥጥር ሥር ውለው እንዲቆዩ ታዟል። የፍርድ ቤቱ ዳኛ አለን አኬቶ፤ ለቱሙሻቤ የዋስትና መብት የመጠየቅ እድል እንዳላው እና ጉዳዩ ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚላክ ነግረውታል። በእምነት ተቋሙ ካላቸው ኃላፊነት የታገዱት ሼህ ሙቱምባ ግን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። የአካባቢው ካዲ [የእስልምና ዳኛ] ሼህ አብዱል ኑር ካካንዴ በበኩላቸው፤ አጋጣሚው ያልተጠበቀ መሆኑን ገልፀው በኢማሙ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል። ጋዜጣው ሼህ ሙቱምባ በሚያስተምሩበት መስጊድ ዋና ኢማም የሆኑትን ሼህ ኢሳ ቡሱልዋን ጠቅሶ እንደዘገበው የእስልምና ኃይማኖትን ላይ ያለውን እምነት ለመጠበቅ ሲባል ኢማሙ ከኃላፊነታቸው ታግደዋል።
news-55909544
https://www.bbc.com/amharic/news-55909544
ግብጽ ከወርቅ የተሠራ ምላስ የተገጠመላቸው 2ሺህ ዓመታት ያስቆጠሩ አፅሞችን አገኘች
የግብጽ በመሬት ውስጥ የተቀበሩ ቅርሶች ጥናት ተመራማሪዎች 2ሺ ዓመት ያስቆጠሩ አፅሞችን አገኙ፡፡
አፅሞቹ ወደ አፈርነት እንዳይቀየሩ በመድኃኒት አድርቆ የማቆየት ጥበብ የተጠበቁ ሲሆን ልዩ የሚያደርጋቸው ግን ምላሳቸው በወርቅ መተካቱ ነው፡፡ የግብጽና የዶሚኒካን ቡድን በአሌክሳንድሪያ ከተማ፣ በታፖሲሪስ ማግና ቤተ መቅደስ አካባቢ 16 በማድረቂያ የተጠበቁ አፅሞችን ከአለት በተሰሩ የመቃብር ቤቶች ውስጥ እንዳሉ ነው ያገኙት፡፡ ከፍ ባለ እርከን ላይ የሚገኙ ሰዎችን በዚህ መንገድ አንዳንድ የሰውነት ክፍላቸውን በወርቅ ተክቶ መቅበር በግሪክና ሮማዊያን ሥልጣኔ ዘመን የተለመደ ነበር፡፡ ምናልባት አፅሞቹ ምላሳቸው በወርቅ የተሰራላቸው ከሞት በኋላ ይኖራል ብለው በሚያምኑት ሕይወት የፍርድ ቀን ላይ ጣኦት ኦሲሪስን አቀላጥፈው እንዲያናግሩት ያግዛቸዋል በሚል እንደሆነ ተገምቷል፡፡ የጥንታዊ ግብጻዊን እምነት ጣኦት ኦሲሪስ ከመሬት በታች ያለውን ዓለም የሚመራ ጌታና የሙታን ፈራጅ እንደሆነ ይታመን ነበር፡፡ ወርቁ የተለበጠባቸው ምላሶች ጫፎቻቸው የአክሊል ምልክት ተደርጎባቸው ተገኝተዋል፡፡ ከዚህም ሌላ የኮብራ እባብ ምልክት ተገኝቷል፡፡ የአሌክሳንድሪያ የከርሰ ምድር ቅርሶች ጥናት ኃላፊ ካሊድ አቦ ኤል ሐምድ በዚህ ፍለጋ የመቃብር ውስጥ የአፅሞች ጭምብሎችም መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ እነዚህ የፊት ጭምብሎች የ2ሺህ ዘመን ዕድሜ ያላቸው ናቸው፡፡ ሚስተር ካሊድ ጨምረው እንደገለጹት በዚሁ መቅደስ ስፍራ ከዚህ ቀደም የዝነኛዋ ንግሥት ክሊዮፓትራ 7ኛ ምሥል ያለባቸው ሳንቲሞች መገኘታቸውን አስታውሰዋል፡፡ ክሊዮፓትራ 7ኛ የግሪክ ተናጋሪው ቶሌማቲክ ሥርወ መንግሥት የመጨረሻዋ ንግሥት እንደሆነች ይታወቃል፡፡ የግዛት ዘመኗም ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ51 እስከ 30 ዓመተ ዓለም ነበር፡፡ ንግሥት ኪሊዮፓትራ መሞቷን ተከትሎ ነው ጥንታዊት ግብጽ በሮማዎች እጅ የወደቀችው፡፡
53161077
https://www.bbc.com/amharic/53161077
«የሕዳሴው ግድብ ለግብፅና ሱዳንም ይጠቅማል» ጥቁር አሜሪካውያን ፖለቲከኞች
ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ስምምነት ላይ ያልደረሰቡትን የአባይ ወንዝ ውሃ አጠቃቀም በተመለከ ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት መግለጫ አውጥተዋል።
በቅፅል ስሙ ሲቢኤስ የሚል መጠሪያ ያለው የጥቁር አሜሪካውያን የኮንግረስ አባላት ኮውከስ ሶስቱ ሃገራት በመሃላቸው ያለውን ጡዘት እንዲያረግቡት ጥያቄ አቅርቧል። መግለጫው፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ትብብራቸውን እንዲቀጥሉበትና ችግራቸውን በድርድር እንዲፈቱ አሳስቧል። ሃገራቱ በጋራ ተጠቃሚነት ተማምነው በዓለም አቀፍ ሕጎች መሠረት በመጓዝ ከመፍትሔ እንዲደርሱ አባላቱ አሳስበዋል። በፈረንጆቹ 2011 ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከቀጣናው አልፎ በአፍሪካ ትልቁ ኤሌክትሪክ አመንጪ ግድብ እንደሚሆን ይጠበቃል። • የህዳሴው ግድብ ድርድር ወደ ማይታረቅ ቅራኔ ደረጃ ደርሶ ይሆን? • ሰኔ 15 ያጎደለው የአምባቸው ቤተሰብ • ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ በአሜሪካ ኮሮና በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊያንሰራራ እንደሚችል አስጠነቀቁ ፕሮጀክቱ እስከ 6 ሺህ ሜጋዋት ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሃገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈል እንድትችል አቅም ይሰጣታል። የጥቁር አሜሪካውያን ኮንግረስ አባላት ኮውከስ ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች ዓለም አቀፍ አካላት በ2015 ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የገቡትን የስምምነት ሰነድ እንዲያከብሩ ጠይቋል። አልፎም እኒህ አካላት ጉዳዩን ከአፍሪካ ሕብረትና በቀጣናው ከሚገኙ ዲፕሎማቶች ጋር በመተባበር ለመፍታት እንዲሞክሩ አሳስቧል። በተለይ ደግሞ ይላል መግለጫው፤ በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ሕብረት በሶስቱ ሃገራት መካከል የሚደረገው ሰላማዊ ስምምነት ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ እንጂ አንድ ወገንን ብቻ የሚጠቅም አለመሆኑን ማረጋገጥ ይገባዋል። 'የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት የአባይ ወንዝ ፍሰት፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የምግብ አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ አለው። የግብፅ ሕዝብ ቁጥር 100 ሚሊዮን እየተጠጋ በመሆኑ የሕዳሴው ግድብ በናይል ወንዝ ላይ ያለውን ጫና በመቀነስ ለግብፅ ሕዝብ የተሻለ የውኃ አቅርቦት ሊያመጣ ይችላል። ኢትዮጵያ ደግሞ 20 በመቶ ሕዝቧን ሊጎዳ ይችላል ተብሎ የተገመተ የድርቅ አደጋ ተደግኖባታል። አልፎም በቅርቡ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ 80 ሺህ አክር [ከ32 ሺህ ሄክታር በላይ] መሬት ላይ የሰፈረ ሰብል ጎድቷል። በሌላ በኩል ሱዳን ከሕዳሴው ግድብ ልትጠቀም ትችላለች። ግድቡ የውሃ ፍሰትን ይመጥናል፣ ደለል ያስቀራል፣ የግብርና ፕሮጀክቶቹን ያስፋፋል፣ እንዲሁም ከውሃ የሚመነጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ይሰጣታል።' • የሕዳሴ ግድብ ድርድር የት ደረሰ? መግለጫው በመጨረሻም፤ የሕዳሴው ግድብ በሁሉም ሃገራት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያለው፤ የምግብ አቅርቦትን የሚያሻሽል፣ ኃይል የሚያመነጭ፣ ንፁህ ውሃ የሚያቀርብና የቀጣናውን ምጣኔ ኃብት የሚያጎለብት ነው ብሏል። 'የጥቁር አሜሪካውያን ኮንግረስ አባላት ኮውከስ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሰላማዊ ውይይቶችን ይደግፋል፤ ለአፍሪካ ሕብረትና ሌሎች አካላት አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ሁሉም ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስምምነት ጠረጴዛ ላይ እንዲቀርብ ይጥራል' የመግለጫው መቋጫ ነው። የኮውከሱ አባል የሆኑት የአሜሪካ ሕዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት አባሉ ስቲቨን ሆርስፈርድ ከጥቂት ወራት በፊት አሜሪካ ሚዛናዊ የሆነ ሚና እንድትጫወት ማሳሰባቸው አይዘነጋም። እንደራሴ ስቲቨን የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስቲቨን ሚኑቺንን በጥያቄ ባፋጠጡበት ወቅት ነው ይህን ያሉት።
news-54292908
https://www.bbc.com/amharic/news-54292908
“አልማዝ በአማርኛም በእንግሊዘኛም ታስቀን ነበር” አልማዝ ኃይሌ ስትታወስ
በትወና እንዲሁም በማስታወቂያም አንጋፋ ከሆኑ ባለሙያዎች ማሚ በሚለው ቅጽል ስሟ የምትታወቀው አልማዝ ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።
አልማዝ ኃይሌ ለሳምንታት ታማ የነበረችው አልማዝ ዛሬ ማለዳ እንዳረፈችና ሥርዓተ ቀብሯ ነገ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው ዘግቧል። በቴአትር፣ በፊልም፣ በተከታታይ የቴሌቭዥን እና ሬዲዮ ድራማዎች እንዲሁም በማስታወቂያ ዘርፍም ለዓመታት የሠራችው አልማዝ ስመ ጥር ከሆኑ የኪነ ጥበብ ሰዎች አንዷ ናት። የሙያ አጋሯን እና በማስታወቂያ ሥራ አብሯት የሰሩ ሰዎችን አነጋግረናል። በቅርብ ከሚያውቋት መካከል በጽሑፍ፣ በዝግጅት፣ በትወናና ሌሎችም የጥበብ ሙያዎች የሚታወቀው ተስፋዬ አበበን ስለ አልማዝ የሚከተለውን ብሎናል። “በቅርቡ ባልና ሚስት ሆነን ተውነን ነበር” ተስፋዬ አልማዝን የሚያስታውሳት ብሔራዊ ቴአትር (የቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴአትር) በተወዛዋዥነት ስትቀጠር ነው። ከአራት ዓሠርታት በፊት ከነአልጋነሽ ታሪኩ ጋር ዘመናዊና ባህላዊ ውዝዋዜ ያቀርቡ ነበር። ከዛም ወደ ትወናው ገባች። “አልማዝ ኮሜድያን ነች። በጣም ታስቀናለች” ሲል ተስፋዬ ያስታውሳታል። ከብሔራዊ ቴአትር ጡረታ ከወጣች በኋላ “በፊልሙ ዘርፍ ይሻሟታል” ሲል ከሷ ጋር ለመሥራት በርካቶች እንደሚጓጉም ይናገራል። “አልማዝ ቁምነገረኛም ናት። ለአገሯ ልዩ ፍቅር አላት” የሚለው ተስፋዬ በቅርቡ ባልና ሚስት ሆነው በተከታታይ ድራማ ላይ መተወናቸውን ነግሮናል። ድራማው ላይ ተስፋዬ የደን ልማት ሠራተኛ ሲሆን ከባለቤቱ ጋር አዘውትርው ሲጋጩ ይታያል። ከዛም ልጆቻቸው ጣልቃ ይገቡና እርቅ ይወርዳል። ተስፋዬ ከድራማው የማይረሳው ክፍል አልማዝ የምትጫወታት ገጸ ባህሪ መርዶ ተነግሯት ስታለቅስ ነው። “እውነተኛ እንባ እያፈሰሰች ነበር። የማስመሰል ብቃቷ የሚገርም ነው። 'facial expression' የምንለው የተዋጣላት ናት።” ለሻይ እረፍት ሲያደርጉ አልማዝ በጣም ታስቃቸው እንደነበርም ያስታውሳል። “በአማርኛም በእንግሊዘኛም ታስቀን ነበር” ይላል። አልማዝ ብሔራዊ ቴአትር ሳለች ከአልጋነሽ ታሪኩ፣ አሰለፈች በቀለ፣ ጠለላ ከበደ፣ አስናቀች ወርቁና ከሌሎችም በርካታ እውቅ ባለሙያዎች ጋር ሠርታለች። በአንድ ቴአትር መነኩሴ ሆና የተወነችውን ተስፋዬ አይረሳውም። አልማዝ “ትራጀዲም ኮሜዲም ይዋጣላታል” የሚለውም ለዚህ ነው። በማስታወቂያው ዘርፍ የሸኖ ለጋ ቂቤ ማስታወቂያን በርካቶች አይዘነጉትም። ተስፋዬም “ሸኖ ለጋ ቂቤን ያስተዋወቀችው ግሩም አርጋ ነው። ምስሏ በየቢልቦርዱ ተሰቅሎ እንደነበር ትዝ ይለኛል” ይላል። አልማዝ ያልተጫወተችው አይነት ገጸ ባህሪ አለ ለማለት ይከብዳል። ተስፋዬ የሚገልጻትም “ትወና የተፈጥሮ ጸጋዋ ነው። ማንም ሳያስተምራት ራሷን በራሷ ያስተማረች ባለሙያ ናት” በማለት ነው። " 'ቅቤው የጾም መሆኑን እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ?' ብላን ነበር" አልማዝ በርካታ ማስታወቂያዎች ብትሠራም በርካቶች ሸኖ ለጋን ያስታውሳሉ። ያኔ የኃይል ሰዒድ ግሩፕ ኦፍ ካምፓኒ የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር የነበረው ሪያድ አብዱልራዛቅ አሕመድ ነበር። በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያና ጅቡቲ የነበረውን የድርጅቱን እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ሆኖ ይቆጣጠር ነበር። ለሸኖ ለጋ ቂቤ ማስታወቂያ አልማዝ ከተመረጠች በኋላ " 'ቅቤው የጾም መሆኑን እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ? እኔ ክርስቲያን ነኝ። እንዴት ጾም እንደሌለው ሳላምን ማስታወቂያውን እሠራለሁ?' " ብላ እንደነበረ ሪያድ ያስታውሳል። ማስታወቂያ ሠሪዎች አምቢ ካሉ በሌላ መለወጥ የተለመደ ቢሆንም አልማዝን ከመቀየር ግን ቅቤው የሚመረትበትን የየመን ፋብሪካ ለማስጎብኘት እንደወሰነ ይናገራል። የመን በሚገኘው ፋብሪካ ቂቤው ሙሉ በሙሉ ከአትክልት እንደሚመረት ከተመለከተች በኋላ ማስታወቂያውን ለመሥራት ተስማማች። ማስታወቂያው ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል በቴሌቭዥን ተላልፏል። በተለያዩ አካባቢዎች ግዙፍ ቢልቦርዶች ተሰቅለውም ነበር። የሸኖ ለጋ ቂቤ የኢትዮጵያ ቃና እንዲኖረው ለማድረግ በርካታ ገንዘብ እንደፈሰሰ የሚያስታውሰው ሪያድ፤ ማስታወቂያው ስኬታማ ለመሆኑና ምርቱም ለመሸጡ "የአልማዝ አሻራ አለበት" ይላል። ድርጅቱ ከአቡወለድ ብስኩት ቀጥሎ ለዓመታዊ የማስታወቂያ ወጪ ከፍተኛ ገንዘብ የመደበው ለሸኖ ለጋ ቂቤ ነበር። የሸኖ ለጋ ቂቤ ሽያጭ ውጤታማነት ሪያድ ወደ ድርጅቱ የዱባይ ዋና መሥሪያ ቤት እንዲዘዋወር ምክንያትም ሆኗል። "አልማዝ የስኬት ታሪኬ ውስጥ አለች" ሲልም ይገልጻታል። ድርጅቱ ምርቱ በስፋት ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ ለአልማዝ ሽልማት አበርክቶም ነበር። በሐረርጌ ክፍል አገር አሰበ ተፈሪ ውስጥ በ1938 ዓ.ም የተወለደችው የአርቲስት አልማዝ ኃይሌ የአራት ልጆች እናት የነበረች ሲሆን፤ ያጋጠማትን ህመም ተከትሎ ህክምና ስትከታተል ቆይታ መስከረም 15/2013 ዓ.ም ነበር ከዚህ ዓለም በሞቶ የተለየችው። የታዋቂዋ ሁለገብ አርቲስት የቀብር ሥነ ሥርዓት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መስከረም 16/2013 ዓ.ም ተፈፅሟል።
news-54226170
https://www.bbc.com/amharic/news-54226170
ካሜሮን፡ ሴቶችና ህፃናትን የገደሉ ወታደሮች በእስራት ተቀጡ
በካሜሮን ሁለት ሴቶችና ሁለት ህፃናትን የገደሉ ወታደሮች የአስር አመት እስር ተፈርዶባቸዋል። ግድያው የተፈፀመው ከአምስት አመታት በፊት ነው።
ከሁለት አመታት በፊት ግድያው ሲፈፀም የሚያሳይ ቪዲዮም ወጥቶም ብዙዎችን አስደንግጦ ነበር። ቪዲዮውም ላይ ፊታቸው ሴቶቹ ጭንቅላታቸው ሲሸፈንና ሲተኮስባቸው ያሳያል። መጀመሪያ ላይ "ሃሰተኛ መረጃ" በሚል የካሜሮን መንግሥት ለማጣጣል ቢሞክርም በኋላ ግን ሰባት ወታደሮችን በቁጥጥር ስር አውሏል። የቢቢሲው ምርመራ ዘጋቢ ፕሮግራም አፍሪካ አይ ባደረገውም ምርምር ጥቃቱ የደረሰው በሰሜናዊ ካሜሮን በምትገኝ መንደር መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል። የሶስቱን ተኳሽ ወታደሮችም ማንነት ማወቅም ተችሏል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ (ቪዲዮው) ላይ እንደሚታየው ወታደሮቹ ሴቶቹን ቦኮ ሃራም ትደግፋላችሁ በማለት ሲወነጅሏቸው ይታያል። ቦኮ ሃራም በናይጄሪያ የሚንቀሳቀስ ፅንፈኛ ታጣቂ ቡድን ሲሆን ናይጄሪያን በሚያዋስኗት ድንበር ከተሞችም ተስፋፍቷል ይባላል። አንደኛዋ እናት ልጅ አዝላ የነበረ ሲሆን ወደ መገደያቸው ቦታም ወታደሮቹ ሲመሯቸው ያሳያል። በአቧራ በተሸፈነው መንገድ ከወሰዷቸው በኋላም ወደ ሆነ ስፍራ ወስደው አይናቸውን ሸፍነው 22 ጊዜም ተኩሰባቸዋል። ከሰባቱ ወታደሮች አንደኛው በካሜሮና መዲና ያውንዴ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ሲሆን ነፃ ወጥቷል ተብሏል። ከሱ በተጨማሪ አንደኛው ወታደርም ነፃ የወጣ ሲሆን አራቱ ወታደሮች ግን በግድያው በነበራቸው ሚና እያንዳንዳቸው አስር አመት ተፈርዶባቸዋል። ሌላኛው ወታደርም ሲገደሉ ቪዲዮ በመቅረፁና ለተለያዩ ሚዲያዎች በማጋራቱ የሁለት አመት እስር ተበይኖበታል። የቢቢሲ ምርመራ ዘገባ ሁኔታውን ማጋለጡ ተከትሎ በርካታ ሚሊዮኖች ያዩት ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃም ሁኔታው እንዲጋለጥ አድርጎታል።
news-57239419
https://www.bbc.com/amharic/news-57239419
ሱዳን በሰሜን ምሥራቅ ግዛቷ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደነገገች
በሱዳን ሰሜን ምሥራቅ ግዛት ውስጥ በተከሰተ የጎሳ ግጭት ሳቢያ የደረሰ ጉዳትን ተከትሎ በአካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።
የአገሪቱ መንግሥት ዜና ወኪል የሆነው ሱና እንደዘገበው በፖርት ሱዳን ግዛት ውስጥ በተከሰተው ግጭት አምስት ሰዎች ሲገደሉ 13 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ችግሩ የተከሰተበት የሬድ ሲ ግዛት አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ስለደረሰው ጉዳት ምንም አይነት ዝርዝር መግለጫ አስካሁን አልሰጠም። በዚህም ሳቢያ የአገሪቱ የቀይ ባሕር ተዋሳኝ ግዛት በሆነችው በፖርት ሱዳን ከተማ የተከሰተውን ግጭት ለመቆጣጠር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተደነገገ ሲሆን የምሽት የሰዓት እላፊ ገደብም ተጥሏል። የአካባቢው የደኅንነት ኮሚቴ ስላጋጠሙት ሁኔታዎች እንደመረመረና የዜጎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ያላቸውን አስፈላጊ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን የሱና ዘገባ አመልክቷል። ሱና በዘገባው ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት ስለሆነው ግጭት መንስኤ የሰጠው ዝርዝር የለም። ነገር ግን የአካባቢውን ጸጥታ የሚከታተለው ኮሚቴ ነዋሪዎች የሚናፈሱ አሉባልታዎችን እንዳይሰሙና ማኅበራዊ ትስስሩንና ሰላሙን እንዲጠብቁ ጥሪ ማቅረቡን ገልጿል። ሱዳን ከቀይ ባሕር ጋር የምትዋሰንበት ግዛት በሆነው ምሥራቃዊ ክፍሏ ውስጥ በምትኘው የወደብ ከተማዋ ፖርት ሱዳን ውስጥ ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን ግጭት ለመቆጣጠር እርምጃ እየወሰደች መሆኑ ተነግሯል። ሬድ ሲ ለተባለው የሱዳን ሰሜን ምሥራቅ ግዛት በጎሳዎች መካከል የሚከሰት ደም አፋሳሽ ግጭት አዲስ ክስተት አይደለም። ከዚህ ቀደም በአካባቢው ባሉ የቤኒ አሚርና ኑባ ማኅበረሰቦች መካከል ተደጋጋሚ ከባድ ግጭቶች ማጋጠማቸው የተነገረ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት ጎሳዎቹ አለመግባታቸውን በዘላቂነት ለመፍታት በመሪዎቻቸው አማካይነት ስምምነት ላይ ቢደርሱም ግጭቱ ቀጥሏል።
news-55156381
https://www.bbc.com/amharic/news-55156381
ሎተሪ በአንድ ጀንበር ሚሊዬነር ያደረጋቸው ሰዎች ምን አሉ?
ይበለውና ዛሬ ድንገት ዝሆን ሎተሪ ቢደርስዎ ምን ያደርጉበታል? የሀብታሞች አገሮቹ ዝሆን ሎቶሪ።
የ71 ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ የደረሰው አዴ ምናልባት እንደ ዝሆን ጎምለል እያሉ ዓለምን ይዞሩ ይሆናል። ምናልባት ቀሪ ሕይወትዎን በተድላ ይመሩ ይሆናል። ምናልባት ከዚያ በኋላ በደስታ ሕንድ ውቅያኖስ ጠልቀው በሐሴት ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ብቅ የሚሉ ይመስልዎት ይሆናል። ነገሩ እንደዚያ ላይሆን ይችላል ብለው አስበው ያውቃሉ? በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ መናጢ ጋዜጠኛ ከሚዘባርቅ የደረሳቸው ቢናገሩት ሳይሻል አይቀርም። አዲ ጉድቻይልድ ባለፈው ዓመት የ71 ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ አሸነፈ። ዩሮ ሚሊዮንስ የሚባለውን ዝሆን ሎቶሪ ነበር ያሸነፈው። ከዚህ በኋላ ጡረታ ወጥቼ ቁጭ ብዬ እበላለሁ ብሎ ነበር። ቁጭ ብሎ መብላት ደስታን የሚያመጣ ነገር እንዳልሆነ የተረዳው ግን ዘግይቶ ነው። አዲ ብቻውን አይደለም። ጄን አለች። "ሎተሪ ማሸነፌ ሕይወቴን አተራማምሶታል" በ17 ዓመቷ የ1 ሚሊዮን ፓወንድ ሎተሪ የደረሳት ጄን ጄን ሬስቶሪክ ሎተሪ ሳይደርሳት በፊት ጄን ፓርክ ነበር ስሟ። ስሟን እንድትቀይር ብቻም ሳይሆን ሕይወቷም እንዲቀየር ያደረጋትን ሎተሪ ያሸነፈችው የዛሬ 4 ዓመት ግድም ነበር። በብሪታኒያ ታሪክ ሎተሪን በማሸነፍ ልጅ አግሯ እሷ ናት፤ ጄን። ሎተሪው ሲደርሳት የሆነ አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ትንሽዬ ሥራ ነበረቻት። በኤደንብራ በትንሽዬ አፓርታማ ውስጥ ከእናቷ ጋር ትኖር ነበር። ጄን አንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪው እንደደረሳት በፌስቡክ አወጀች። ከዜናው ጋር የመደነቅ ኢሞጂ የሚሉትን (እኛ ለዚህ የሎቶሪ አዝናኝ ታሪክ ደቂቀ ገጽታ ብለን የምንጠራውን የማኅበራዊ ሚዲያ አሻንጉሊት ሳቅ) አስከተለች። መጀመሪያ ያደረገችው ውድ የቺኋሄ ቡችላ ዝርያን (Chihuahua dog) የሳሎን ውሻ መግዛት ነበር። ፕሪንሰስ ብላ ጠራቻት። ከዚያ ውድ የንግድ ስም ያለውን አንድ ቦርሳ መግዛት ህልሟ ነበር። እንዳሰበችውም የሉዊ ቪቶ (Louis Vuitton) ቅንጡ ፋሽን የእጅ ቦርሳ ገዛች። በእነዚህ ሁለት ወጪዎች ብቻ 10 ሺህ ፓውንዶች እልም ብለው ሄዱ። ከዚያ በኋላ ግን ግራ ገባት። ሕይወቴ እላዬ ላይ ሲፈርስ ነበር የሚታየኝ ብላለች ከሦሰት ዓመት በፊት በሰጠችው አንድ ቃለ ምልልስ። በየቀኑ ስነሳ የማስበው ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነገር ነበር። ያ ስሜት ደስ አይልም ትላለች። ይህን ሐሳቧን ከአእምሮዋ ማውጣት ግን አልቻለችም። "ምነው ይሄ ሎተሪ ጭራሽ ባልደረሰኝ" ብላ እስከመመኘት ደርሳም ነበር። የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ ለ17 ዓመት ልጅ አደገኛ ነገር ነው። ይሄ ምንም አጠራጣሪ አይደለም። "ምን ማድረግ ነው ትክክል የሚለውን ነገር የሚመራኝ ሰው አልነበረም" ትላለች። ሎተሪው ከደረሳት በኋላ ወዳጅ ዘመዶቿ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ዓይን ዓይኗን ማየት ጀመሩ። ይቺ ልጅ "የገንዘብ ችግራችንን የምትቀርፍልን" በሚል መነጽር ብቻ ያይዋት ጀመረ። "ሰዎች እኔን የሚፈልጉኝ ከሎተሪ ገንዘቡ ጋር በተያያዘ ብቻ መሆኑን ስረዳ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ" ትላለች። የሎተሪው ድርጅት ኃላፊ ካሜሎት በበኩላቸው "ለልጅቷ የሥነ ልቦና ደጋፍ ብቻም ሳይሆን ገንዘቧን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባት የሚያማክራት ሰው በነጻ አቅርበንላት ነበር" ሲሉ ጥፋቱ ከእነሱ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። "ሚሊየነር ብሆንም ሥራዬን እወደዋለሁ" የ3 ሚሊዮን ፓወንድ ሎተሪ የደረሳት ሱ ሪቻርድስ ሱ ሪቻርድስ በ2016 ወደ ቤት እየሄደች ነበር። እግረ መንገዷን ሱፐር ማርኬት ገብታ ፈጣን ሎተሪ ገዛች። ነገሩን ከቁብም አልቆጠረችውም ነበር። እንደጨዋታ ነበር የገዛችው። ቤት ገብታ ፋቀችው። 3 ሚሊዮን ፓውንድ አሸናፊ አደረጋት። ደስታዋ ወደር አልነበረምው። ከባሏ ጋር ወደ ኢሴክስ ከተማ ሄደው ቤት ገዙ። አራት መኪኖችን እላዩ ላይ መረቁበት። ከዚያ በኋላ ደግሞ ዓለምን ዞር ዞር ብለው ማየት ጀመሩ። ለልጆቻቸውም የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አሟሉ። ባለፈው ዓመት ሚስ ሪቻርድ ከባለቤቷ ጋር ሆና ሎተሪ ያሸነፉበትን አራተኛ ዓመት አከበሩ። የቤታቸው ግቢ አፀድ ውስጥ በርከት ያለ ብር አውጥተው በሻምፓኝ ነበር ያከበሩት። ሚስ ሪቻርድስ ሚሊየነር ብትሆንም ቅሉ በሳምንት 90 ሰዓት አዛውንት ተንከባካቢ ሆና ትሰራለች። ምን በወጣሽ ትለፊያለሽ? ስትባል "ሥራዬን እወደዋለሁ" ነው መልሷ። ምናልባት ከሚሊዮን ዶላሩ ባሻገር የደስታዋ ምንጭ ሥራዋ ሳይሆን አልቀረም። "ሚሊየነር መሆን ያን ያህልም አልደነቀኝም" የ5 ሚሊዮን ፓወንድ ሎተሪ የደረሳት ሜሊሳ ከጓደኛዋ ጋር በታኅሣስ 2017 ሜሊሳ ኤድ ወደ ሐል ነዳጅ ማደያ ገባች። እሷም እንዲሁ የሚፋቅ ሎተሪ ገዛች። ፈጣኑን። በሦስተኛው ቀን ባንክ ደብተሯ አብጦ ሊፈነዳ ደርሶ አገኘችው። 5 ሚሊዮን ፓውንድ ገብቶበታል። "በአንድ ጀንበር የባንክ ደበተሬ ከአንደ ፓውንድ ወደ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ተመነደገ" ብላ ነበር ለቢቢሲ። ሜሊሳ ሚሊየነር ከመሆኗ በፊት ማታ ማታ የታክሲ ሾፌር ነበረች። ቤሳ ቤስቲን አልነበራትም። "ሕይወት በጣም ፈተና ሆናብኝ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ገንዘብ ስለማይኖረኝ እራት እንኳን የማልበላበት ጊዜ ነበር" ትለላች። ካሸነፈች በኋላ 3 ሚሊዮን ፓውንዱን ኢንቨስት አደረገችው። ቤት ገዛች። የቤተሰቧንና የጓደኞቿን እዳቸውን ከፋፈለች። ሕይወታቸውን ለወጠች። ይህን ሁሉ አሳክታም እንዲህ ትላለች። "ሰዎች ሎተሪ ሁሉን ነገር የሚቀይር ይመስላቸዋል። ያን ያህልም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም። ከጊዜ በኋላ ሁሉም ነገር ወደነበረበት ይመለሳል" ትላለች። "ብዙ ሰዎቸ ገንዘብ ሁሉንም ችግር የሚቀርፍ ይመስላቸዋል። ውሸት ነው። ሚሊየነር መሆን ደስተኛ መሆን ማለት እንዳልሆነ እኔ ህያው ምስክር ነኝ" ብላ ነበር ለቢቢሲ። "በኬክ ላይ የተንሸራተትኩ ያህል ተሰማኝ" የ6 ሚሊዮን ፓወንድ ሎተሪ የደረሳቸው ካቲ እና ሪቻርድ ብራውን ሪቻርድና ካቲ ብራውን ጋዜጠኞች ነበሩ። ሳያስቡት 6 ሚሊዮን ፓውንድ አሸነፉ። ለነገሩ ሎተሪ ማን አስቦት አሸንፎ ያውቃል። እነ ሪቻርድ ወዲያውኑ ዓለምን መዞር ጀመሩ። በበረዶ ወደተሸፈነው የአንታርክታካ አህጉር ሄደው በረዶ ሸርተቴ ተጫውተዋል። ህልማቸውም እሱ ነበር። "በኬክ ላይ የመንሸራተት ያህል ነው" ይላሉ የሕይወታቸውን መቃናት ሲያሰምሩበት። ባልና ሚስቱ አሁን ጡረታ ወጥተዋል። በሰሜን ዋልታ በባህር ቀዘፋ እየተጫወቱ ዓመቱን ሙሉ ሽር ብትን እያሉ ለማሳለፍ ነው ያቀዱት። "በሎተሪ ያገኘነው ገንዘብ በሕይወታችን ከሚያስፈልገን የገንዘብ መጠን እጅግ የበዛ ነው። ስለዚህ በተቻለ መጠን ቤተሰባችን ከእኛ መልካም ዕድል ተጋሪ ማድረግ ነው የምንሻው" ብለዋል ለቢቢሲ። ሚሊየነር መሆን የገንዘብ ችግርን ይቀርፍ ይሆናል እንጂ በራሱ የደስታ ምንጭ እንዳልሆነ ግን ያሰምሩበታል። ባልና ሚስቱ።
news-45518226
https://www.bbc.com/amharic/news-45518226
ናይጄሪያዊው ስደተኛ ሚሊዮን ዶላሮችን ሲያጭበረብር ነበር ተብሏል
የአውስትራሊያ ፖሊስ ሲድኒ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ሆኖ ሚሊዮን ዶላር እያጭበረበ ነው ያለውን ናይጄሪያዊ በቁጥጥር ሥር አውሏል።
የ43 ዓመቱ ናይጄሪያዊ የኢሜይል ማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም በርካቶች ገንዘብ እንዲልኩለት አድርጓል በሚል ነው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው። ሌሎች ሦስት አጋሮቹም በፖሊስ እጅ ሥር እንዳሉ ታውቋል። ግለሰቦቹ ታማኝ ኩባንያ በመምሰል የኢሜይል መልዕክት በመላክ ወደ 3 ሚሊዮን ዶላር ገደማ አጭበርብረዋል ተብሏል። • ኮዴይን፦ ገዳዩ 'ሽሮፕ' • ናይጄሪያ በሊቢያ ያሉ ዜጎቿን ለመለስ ማቀዷን ገለፀች ገንዘቡ ናይጄሪያ ውስጥ አድራሻው ወዳልታወቀ ተቀባይ እንደተላከ እና የመመለሱ ነገር አስቸጋሪ እንደሆነም እየተነገረ ነው። ግለሰቦቹ 16 ስልኮችና እና 17 ሲም ካርዶች በመጠቀም ነው ከስደተኞች ጣቢያ የማጭበርበር ሂደታቸውን ሲያጧጡፉት የነበረው። አንድ የ20 ዓመት ግለሰብ እና ሌሎች ሁለት ሴቶች ናቸው በአጋርነት በመሥራት የተጠረጠሩት። የአውስትራሊያ ፖሊስ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን ገንዘቡን ለማስመለስ እንደሚጥር አስታውቋል። ኩባንያዎች በስሞቻቸው የሚፈፀሙ መሰል ማጭበርበሪያ ዘዴዎችን እንዲቆጣጠሩም መክረዋል። በከፍተኛ ቁጥጥር ሥር የሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣብያ ለ600 ገደማ ስደተኞች ዞሮ መግቢያቸው ነው። ከ60 ሃገራት ያክል የመጡ ግለሰቦች በመጠለያ ሥፍራው እንደሚገኙ ባለፈው ታህሳስ ተዘግቦ ነበር።
news-48701187
https://www.bbc.com/amharic/news-48701187
በጦርነት የተጎሳቆሉ ስደተኞች መዳረሻቸው የት ነው?
መኖሪያ ሃገራቸው በጦርነትና በግጭት ሲናጡ፤ ግለሰቦች መንግሥታት ሲያሳድዷቸውና መተንፈሻ ሲያጡ ህይወታቸውን ለማቆየት ወደየት ይሄዱ ይሆን?
መረጃዎች እንደሚያሳዩት የትኛውም ሃገር ላይ 80% የሚሆኑት ነዋሪዎች እዛው በችግር እየተቆራመቱ የሚቆዩ ሲሆን፤ አማራጭ አጥተው ከሚሰደዱት ደግሞ 80%ቱ ጎረቤት ሃገራት ይቆያሉ። የስደተኞችን ቀን በምንዘክርበት በዛሬው እለት በጎርጎሳውያኑ ያለፈው አመት የስደተኞች መሸጋገሪያ የሆኑ ስድስት ሃገራትን እንመለከታለን። •አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ •የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን፡ ኢትዮጵያን መጠጊያ ያደረጉ የስደተኞች ታሪክ ቱርክ ከየትኛውም አገር በበለጠ ቱርክ ስደተኞችን ትቀበላለች። በተለይም ከስምንት አመታት በፊት በተነሳው የጎረቤቷ ሶሪያ የርስበርስ ብጥብጥን ተከትሎ የስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። ከዚህም በተጫማሪ ራቅ ካለችው አፍጋኒስታንም ብዙ ስደተኞች የሚተሙ ሲሆን፤ በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጂያ ድርጅት (ዩኤንኤችሲአር) መረጃ እንደሚያሳየው ከአለም ስደተኞች ውስጥ 1/5ኛውን ስደተኞች የምትቀበለው ቱርክ ናት። ፔሩ ፔሩ ስደተኞችን በመቀበል ሁለተኛ ስትሆን ይህም የጎረቤቷ ቬንዙዌላ የኢኮኖሚ ቀውስን ተከትሎ ነው። በጎርጎሳውያኑ 2015 ጀምሮ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ጎረቤት ኃገራት እንደተሰደዱ የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያሳያል። ይህንንም ተከትሎ የስደተኞችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ፔሩ ጠበቅ ያለ አዲስ ህግ አስተዋውቃለች። •ሕይወትን ከዜሮ መጀመር ሱዳን አብዛኛውን ወደ ሱዳን የሚገቡት ስደተኞች በርስ በርስ ጦርነት ከምትበጣበጠው ደቡብ ሱዳን ነው። ከዚህም በተጨማሪ ከመካከለኛው ምስራቅ ካሉት አገራት ውጭ የሶሪያ ስደተኞችን በመቀበል ከአለም ሶስተኛ ናት። ነገር ግን ሱዳን የራሷ 724ሺ 800 ስደተኞች በባለፈው አመት አገሪቷን ለቀው ወጥተዋል። ኡጋንዳ ኡጋንዳ እርስ በርስ ግጭት እየተናጡ ካሉት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎና ደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ተቀብላለች። ከኮንጎ የተቀበለቻቸው ስደተኞች ወደ 120ሺ የሚጠጉ ሲሆን፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ህፃናት በመቀበልም ከአለም አንደኛ ናት። በባለፈው አመትም 83 ሺ 600 ስደተኞች ወደ ደቡብ ሱዳን ተመልሰዋል። አሜሪካ ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ስደተኞችን የመቀበል አዝማሚያ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም፤ አሁንም በአለም የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር አለምን ትመራለች። ስደተኞቹ ከ166 አገራት የተውጣጡ ቢሆንም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ግን ከመካከለኛው አሜሪካ አራት ሃገራት በተለይም ከሜክሲኮ ነው። ከቀደሙት ሃገራት ጋር ሲወዳደር የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሽቆለቆለ እየተነገረም ነው። ጀርመን ጀርመን ከሚሊዮን ለሚበልጡ ስደተኞች ቤት ስትሆን፤ 532ሺዎቹ የመጡት በጦርነት እየወደመች ካለችው ሶሪያ ነው። ከሶሪያ በተጨማሪ ከኢራቅም የሚመጡ ስደተኞች ቁጥር ከፍተኛ ነው። በአዲስ ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር ከአለም ሶስተኛ ብትሆንም ከ2016 በኋላ ቁጥሩ ያሽቆለቆለ ሲሆን፤ በባለፈው አመት ብቻ በ14% እንደወረደ ተገልጿል። ሁሉም መረጃዎች የተገኙት ከተባበበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት ነው
news-47908210
https://www.bbc.com/amharic/news-47908210
የስዊዘርላንድ መንግሥት ቡና ለህይወት አስፈላጊ እንዳልሆነ ገለፀ
የስዊዘርላንድ መንግሥት ችግሮች በሚያጋጥሙ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለት የሚያከማቸውን ቡና ሊያቆም ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ቡና ለሰው ልጅ ህልውና የግድ አስፈላጊ አይደለም በሚል ነው።
ስዊዘርላንድ በመጀመሪያውና ሁለተኛው የአለም ጦርነት የቡና ምርት ይቋረጥብኛል በሚል ስጋት መጠባበቂያ ቡና ታከማች ነበር። ከዚያም በኋላ ለበርካታ አመታት ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ችግሮች ሲፈጠሩ "የምጠቀምበት" በማለት ቡናን ማከማቸቷን ቀጥላበት ነበር። • እውን ቡና መጠጣት እድሜ ይጨምራል? ይህ አይነቱ ሃገራዊ አሰራር ግን ከጎርጎሳውያኑ 2022 በኋላ እንደማይቀጥል መንግሥት አስታውቋል። መንግሥት ይህንን ቢልም በርግጥ መሆን የለበትም በማለት ተቃዋሚዎች ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። በአሁኑ ወቅት ስዊዘርላንድ 15 ሺ 300 ቶን የቡና ክምችት አላት። ይህም ለሶስት ወራት በቂ ነው። ለምን ማቆም አስፈለገ? መንግሥት እንዳስታወቀው ቡና ለህይወት አስፈላጊ ባለመሆኑ ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ከሚያስፈልጋቸው የምርት ዝርዝሮች ውስጥ መውጣት እንዳለበት አስረድቷል። "ቡና ምንም በሚባል ደረጃ ኃይል የሚሰጥ ንጥረ ነገር ያለው ባለመሆኑ ለሥነ ምግብ አስተዋጽኦ የለውም።" ብሏል የፌደራል ጽ/ቤት የምጣኔ ሃብት አቅርቦት። ውሳኔው ሊጸና ይችል ይሆን? እቅዱ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ የተደረገ ሲሆን የመጨረሻው ውሳኔም በሚቀጥለው ህዳር ይሰጣል። ነገር ግን በጉዳዩ ላይ አብዛኛው ስዊዘርላንዳውያን ደስተኛ የሆኑ አይመስሉም። • የቡና ምርትና ጣዕም አደጋ ላይ ነው የቡና መጠባበቂያውን ከሚያዘጋጁ 15 ኩባንያዎች መካከል 12 የሚሆኑት መጠባበቂያ የማከማቸት ሂደቱ መቀጠል አለበት ብለዋል። ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ይዞት የወጣው ደብዳቤ ደግሞ እንደሚያሳየው የካሎሪ መጠንን ለቡና መስፈርትነት መጠቀም ፍትሃዊ አይደለም፤ ሊሆንም አይገባም ይላል። ለመሆኑ ስዊዘርላንዳዊያን ምን ያክል ቡና ይጠጣሉ? በአለም አቀፉ የቡና ድርጅት መረጃ መሰረት ስዊዘርላንዳዉያን የቡና አፍቃሪዎች ናቸው። በአመትም በነፍስ ወከፍ 9 ኪሎ ግራም ቡና ይጠጣሉ። ይህም በነፍስ ወከፍ 3.3 ኪሎ ግራም ቡና በአመት ከሚጠጡት እንግሊዛውያን ጋር ሲነጻጸር ሶስት እጥፍ እንደማለት ነው።
news-57167978
https://www.bbc.com/amharic/news-57167978
ማላዊ በሺዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ-19 ክትባቶችን አስወገደች
የማላዊ የጤና ባለሥልጣናት 19,610 የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የአስትራዜኔካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን አስወገዱ።
የጤና ባለስልጣናት ጊዜያቸው የለፈ ክትባቶች መወገዳቸው ሕዝቡ በክትባቱ ላይ ያለውን መተማመን ከፍያደርገዋል ይላሉ እርምጃው ሕብረተሰቡ የሚያገኘው ክትባት ለአደጋ የማያጋልጥ ስለመሆኑ ያረጋግጣል ተብሏል። ማላዊ ይህንን በይፋ ያከናወነች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት አገር ነች። የዓለም ጤና ድርጅት ቀደም ሲል አራት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶች እንዳያስወግዱ አጥብቆ ቢያሳስብም በኋላ ላይ ሃሳቡን ቀይሯል። በማላዊ ክትባቱን የሚውሰዱ ሰዎች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ የነበረ ሲሆን እርምጃው የሕዝቡን እምነት እንደሚያሳድገው የጤና ባለሙያዎች ተስፋ አድርገዋል። ወደ 18 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት አገሪቱ 34,232 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሲያዙባት የ1153 ሰዎችን ህይወት በወረርሽኙ ተነጥቃለች። ማላዊ ከአፍሪካ ሕብረት 102,000 ብልቃጥ የአስትራዜኔካ ክትባት ተቀብላ 80 በመቶ የሚሆነውን ተጠቅማለች። የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን ክትባቶች በመለየትም ከስርጭት እንዲወጡ ተደርገዋል። የማላዊ የጤና ዋና ኃላፊ ለቢቢሲ እንደገለፁት ክትባቶቹን ማውደማቸው አሳዛኝ ቢሆንም ጥቅሙ ከሚያስከትላቸው ጉዳቶች ይበልጣል። ዶ/ር ቻርለስ ምዋንሳምቦ በበኩላቸው "ጊዜ ያለፈበት ክትባት ስለመያዛችን መረጃው ሲሰራጭ ሰዎች ወደ ክሊኒካችን ከመምጣት እንደተቆጠቡ አስተውለናል" ብለዋል። "ካላስወገድናቸው በእኛ ተቋማት ውስጥ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ክትባቶችን እንደምንጠቀም ካሰቡ ሰዎች ስለሚቀሩ በኮቪድ-19 በጣም ይጎዳሉ።" የማላዊ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ኩምቢዜ ቺፒንዳ ረቡዕ እለት ጊዜ ያለፈባቸው ክትባቶች የማቃጠያ ክፍሉን ሲዘጉ ፎቶግራፍ ተነስተዋል። በዋና ከተማው ሊሎንዌ የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎች የክትባቱ ደኅንነት ጉዳይ አስጨንቋቸዋል። "መከተብ ብፈልግም ወደ ሆስፒታል ከሄድኩ ጊዜው ያለፈበት ክትባት እንዳልተሰጠኝ ምን ያህል እርግጠኛ እሆናለሁ?" ሲል በመንግሥት ሥራ የተሰማራው ጃክ ቺቴቴ ለቢቢሲ ተናግሯል። "ሰዎች የደም መርጋት እንዳጋጠማቸው እና አንዳንዶችም ከተከተቡ በኋላ ስለሚሞታቸው ሰምቻለሁ። እነዚያ ሰዎች ውሸትን እየናገሩ ነውን? እውነት ከሆነ ለምን ተመሳሳይ ክትባቶች ይሰጡናል?" በማለት ሌላኛው ነጋዴ ምፋሶ ቺፔንዳ ጠይቋል። በአስትራዛኔካ ክትባት እና አልፎ አልፎ በሚያጋጥመው የደም መርጋት መካከል ያለው ትስስር ያልተረጋገጠ ሲሆን የመከሰት እድሉም ኮቪድ -19 ካለው ስጋት አንጻር አነስተኛ በመሆኑ ሰዎች ከቻሉ ክትባት እንዲወስዱ የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ። በአፍሪካ ውስጥ ጊዜው ያለፈባቸው ክትባቶችን የያዘችው ማላዊ ብቻ አይደለችም። የዓለም ጤና ድርጅት መጀመሪያ ላይ በድጋሚ ጥቅም ላይ መዋል አለመቻላቸውን እስኪያረጋግጥ ድረስ ክትባቱን እንዲይዙ ጠየቆ ነበር። አሁን ግን በአምራቹ መጠቀሚያ ጊዜ ተጽፎባቸው ተመርተው ጊዜው ያለፈባቸው ክትባቶች መወገድ አለባቸው ብሏል። "ክትባቶችን ሳይጠቀሙ ማስወገድ ከክትባት መርሃ ግብር አንፃር የሚያሳዝን ቢሆንም፣ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ክትባቶች ከስርጭት ሰንሰለቱ ወጥተው በጥንቃቄ ይወገዱ" ሲል የዓለም የጤና ድርጅት መክሯል። በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት ላይ እየዋሉ የሚገኙ ሌሎች ክትባቶች እስከ 36 ወር ድረስ ጥቅም ላይ የመዋያ ጊዜ አላቸው። የኮቪድ-19 ክትባቶች አገልግሎት ላይ መዋል ከጀመሩ ከአንድ ዓመት በታች የሆነ ጊዜ ብቻ ስለሆናቸው ከረጅም ጊዜ በኋላ ስለሚኖራቸው ውጤታማነት ተጨባጭ መረጃ አለመኖሩ ዋነኛው ተግዳሮት ነው ተብሏል። የተወገዱ ክትባቶች
news-54709925
https://www.bbc.com/amharic/news-54709925
ከአሜሪካ ተባሮ ቻይና መንኩራኩር እንድታመጥቅ የረዳው ተመራማሪ
ቻይናዊው ሳይንቲስት ሁለቱ የዓለማችን ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤቶች ወደ ጨረቃ እንዲጓዙ ከፍተኛ አስተዋጽኦን አበርክቷል።
ሺያን ሺንሰን ነገር ግን የዚህ ሳይንቲስት ስም በአግባቡ ተመዝግቦ የሚገኘው በአንድ አገር ብቻ ነው። በቻይናዋ ሻንግሃይ ውስጥ 70 ሺ ቅርሶችን የያዘ አንድ ሙዝየም በሙሉ ለእሱ ማስታወሻ እንዲሆን ተደርጓል። ''የህዝብ ተመራማሪ'' በመባልም ነው የሚጠራው፤ ሺያን ሺንሰን ። ተመራማሪው ሺያን የቻይና ሚሳኤል እና የሕዋ ምርምር ፕሮግራም አባት ነው ይባላል። የእርሱ የምርምር ስራዎች ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ መንኩራኩሮችን ወደ ህዋ ስታመጥቅ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የአሜሪካ ምርጫ የሕዳሴ ግድብ ፖለቲካን እንዴት ሊቀይር ይችላል? "በሶማሌና በአፋር ክልሎች መካከል ያለው ንግግር ይቀጥላል" በኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ እና በቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የነበረው የዕርቅ ሂደት መጠናቀቁ ተገለጸ በፈረንሳይ ሦስት ሰዎች በስለት ተወግተው ተገደሉ በተጨማሪም የቻይና የኒዩክሌር ፕሮግራም አካል የሆነው ሚሳኤልም የእርሱ የምርምር እጅ አለበት። ለዚህም ነው ይህ ሰው በቻይናውያን ዘንድ እንደ ብሄራዊ ጀግና የሚቆጠረው። ነገር ግን የመጀመሪያ ትምህርቱን የተከታተለባትና ከአስር ዓመታት በላይ በስራ ያሳለፈባት ሌላኛዋ ታላቅ አገር ግን ስራዎቹን እምብዛም አታስታውሳቸውም። ከነጭራሹም የተረሳ ይመስላል። ሺያን ሺንሰን የተወለደው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1911 ላይ ሲሆን በወቅቱ ቻይና ከንጉሳዊ አገዛዝ ወደ ሪፐብሊክ ልትሸጋገር የመጨረሻዎቹ ዓመታት ላይ ነበረች። ሁለቱም ወላጆቹ ቀለም ቀመስ ሲሆኑ ጃፓን ውስጥ ይሰሩ ነበር። የቻይናን የትምህርት ስርአትምን መስመር ያሲያዙት የሺያን ወላጆች እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ገና ከልጅነቱ ኪያን ብሩህ አእምሮን የታደለ ልጅ ነበር። በሻንግሃይ ጂያኦ ቶንግ ዩኒቨርሲቲም ከክፍሉ ከፍተኛውን ነጥብ በማምጣት አሜሪካ በሚገኘው ማሳቹሴትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ የትምህርት ዕድል ማግኘት ችሏል። በዚሁ ማዕከል ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በወቅቱ ትልቅ ቦታ ከነበራቸው ቴዎዶር ቮን ካርማን ስር ለማጥናት ወደ ካሊፎርኒያ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ተዘዋወረ። በዚሁም 'ሱውሳይድ ስኳድ' የሚል ቅጽል ስም የተሰጠውን የተመራማሪዎች ቡድን ለመቀላቀል ቻለ። ይህ የተመራማሪዎች ቡድን ቀስ በቀስ እውቅናን እየታረፈና በርካታ የምርመር ስራዎችን መስራቱን ቀጠለበት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ቡድኑ የሮኬት ማስወንጨፊያ ሞተሮች ላይ ምርም በማድረግና ሙከራ መስራት ጀመረ። በወቅቱ ሮኬት ሳይንስ ብዙ ተመራማሪዎች የማይደፍሩትና በቁምነገር የማይከታተሉት ዘርፍ ነበር። ነገር ግን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጀመር በኋላ የሮኬት ሳይንስ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መጣ። በዚህም ምክንያት ሺያን ሺንሰን አባል የሆነበት የተመራማሪዎች ቡድን የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋምን ትኩረት መሳብ ቻለ። በርካታ ምርምሮቻቸውም በተቋሙ በኩል የገንዘብ ድጋፍና ትብብር ይደረግላቸው ጀመር። 1943 ላይም ሺያን እና ጓደኞቹ የጀት ማስወንጨፊያ ቤተ ሙከራን ማቋቋም ቻሉ። ምንም እንኳን ኪያን ዜግነቱ ቻይናዊ በሆንም በወቅቱ አሜሪካና ቻይና ወዳጆች ስለነበሩ ማንም ግድ የሰጠው አልነበረም። እንደውም በርካታ የሕዋ ምርምሮችን እንዲያካሂድና እንዲመራ ከፍተኛ የደህንነት ፍቃድ ተሰጠው። የአሜሪካ ሳይንስ አማካሪ ቦርድ ውስጥም አባል ሆኖ አገልግሏል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቅ በኋላ ደግሞ ኪያን በዘርፉ አሉ ከሚባሉ ተመራማሪዎች መካከል አንዱ መሆን ቻለ። ከእውቁ ማሃንዲስ ቴዎዶር ቮን ካርማን ጋር በመሆን ለአንድ ግዳጅ ወደ ጀርመን ተልከውም ነበር። ዋና ዓላማቸው የጀርመን ኤንጂነሮችን ማነጋገርና ጀርምን በዘርፉ ምን ያክል እውቀት እንዳላት ማወቅ ነበር። በዚህ ስራቸውም ሁለቱ ተመራማሪዎች ትልቅ እውቅናና ክብር ማግኘት ችለዋል። ነገር ግን ኪያን አስር ዓመታትን በአሜሪካ በዚህ መልኩ ካሳለፈ በኋላ ከሙያው ጋር ያልተያያዙ ጋሬጣዎች መከሰት ጀመሩ። 1949 ላይ ዋና ጸሀፊው ማኦ የቻይና ህዝቦች ኮሚዩኒስት ሪፐብሊክ መመስረትን አወጁ። ወዲያውም ቻይና አሜሪካን በእርኩስ ጠላትነት አወጀች። አሜሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት ውስጥ በነበረችበት ወቅት የአሜሪካው ፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ሺያን ሺንሰን እና ፍራንክ ማሊናን ኮሚዩኒስት እንደሆኑ እና ለብሄራዊ ደህንነት ስጋት እንደሆኑ አወጀ። በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ዡዮ ዋንግ እንደሚሉት ሺያን የኮሚዩኒስት ፓርቲ አባል ስለመሆኑና ለቻይና ስለመሰለሉ ምንም አይነት መረጃ በወቅቱ ማቅረብ አልተቻለም ነበር። ነገር ግን ተሰጥቶት የነበረው ከፍተኛ የደህንነት ፈቃድ ከተነጠቀ በኋላ ከአምስት ዓመታት የቤት ውስጥ እስር አሳልፎ በፕሬዝደንት ኤይሰንሆወር ትዕዛዝ ወደ ቻይና እንዲመለስ ተደረገ። በጀልባ ተጭኖ ከባለቤቱና ሁለት አሜሪካ ከተወለዱ ልጆቹ ጋር ሆኖ ለጋዜጠኞች ሲናገር ከዚህ በኋላ በድጋሚ የአሜሪካን አፈር እንደማይረግጥ ገልጾ ነበር። እንዳለውም አድርጎታል። አሜሪካ ድርሽ አላለም። ሺያን ሺንሰን ቻይና ሲደርስ የጀግና አቀባበል ነበር የጠበቀው። ነገር ግን ወዲያውኑ የቻይና ኮሚዩንስት ፓርቲን አልተቀላቀለም። በወቅቱ ቻይና ውስጥ ስለ ሮኬት ሳይንስ የነበረው እውቀት ዝቅተኛ ነበር። ነገር ግን ከ15 ዓመታት ልፋትና ምርምር በኋላ ቻይና የመጀመሪያውን መንኩራኩር ወደ ሕዋ ማምጠቅ ቻለች። በነበሩት አስርት ዓመታትም በርካታ ተማሪዎችን ያሰለጠነ ሲሆን ቻይና ጨረቃ ላይ ላደረገችው ምርምር የመሰረት ድንጋዩን እንደጣለም ጭምር ይነገርለታል፤ ሺያን ሺንሰን። በሚያስገርም ሁኔታ በሺያን ልፋት ቻይና ውስጥ የተሰሩት ሮኬቶች በጦርነት ወቅት አሜሪካ ላይ ተተኩሰው ነበር። በ1991ዱ የገልፍ ጦርነት ላይ ቻይና ሰራሽ ሮኬቶች አሜሪካ ላይ ተተኩሰው ነበር። በአሁኑ ሰአት የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት ከምን ጊዜውም በበለጠ የተካረረበት ወቅት ነው። ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ አሜሪካውያን ስለ ሺያን ሺንሰን ያላቸው እውቀት ውሰን ቢሆንም አሜሪካውያን ትውልደ ቻይናውያን ግን አሁንም እንደ ጀግና ነው የሚቆጥሩት።
news-47275533
https://www.bbc.com/amharic/news-47275533
በደቡብ አፍሪካ መብራት ለምን በፈረቃ ሆነ?
ሀብታም አገር ናት። በኢንዱስትሪ ብዙ ርቀት ተራምዳለች። 'በአፍሪካ አህጉር የምትገኝ አውሮፓ' እየተባለች ትንቆለጳጰሳለች። ለዜጎቿ ግን መብራት ማዳረስ ተስኗት፣ ወደ ፈረቃ ሥርዓት ገብታለች፤ የማንዴላ አገር ደቡብ አፍሪካ። ለምን?
የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መብራት ኃይል 'ኢስኮም' ተብሎ ይጠራል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በኃይል አቅርቦት ስመ ገናና ነው። በዚህ ተቋም የተፈጠረው ቀውስ ግንቦት ላይ ምርጫ ለሚጠብቃቸው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ በመንበራቸው የመቆመር ያህል ነው። ሆኖም ምንም ማድረግ አልቻሉም። ኢስኮም እስከ አፍንጫው ዕዳ ውስጥ ተነክሯል። ድርጅቱ ራሱ አፍ አውጥቶ 'ነገሮች ካልተሻሻሉ በታኅሣሥ ወር ቤሳቤስቲን ላይኖረኝ ይችላል' ብሏል። ኢስኮም በዋናነት በማስተላለፊያዎች መጠነ ሰፊ ጥገና እያካሄድኩ ነው መብራት በፈረቃ ለማድረግ የተገደድኩት ቢልም ይህ ከፊል እውነት ብቻ ነው የሚሆነው። • በርካታ ኢትዮጵያዊያን በታንዛኒያ እስር ቤቶች ይገኛሉ • ጤፍ ሃገሩ የት ነው? ደቡብ አፍሪካ? አውስትራሊያ? . . . • በአትላንታ አየር ማረፊያ መብራት በመቋረጡ በረራዎች ተሰናከሉ ደቡብ አፍሪካ መብራት በፈረቃ ስታድል አሁን የመጀመርያዋ አይደለም። እንደ ጎርጎሮሲያውያኑ በ2008 እና በ2015 መብራት በፈረቃ ታድል እንደነበር። አሁን በመብራት ኃይሉ ለተፈጠረው ቀውስ ሙስና፣ የሥልጣን መባለግ፣ የገቢ ማሽቆልቆል፣ የዕዳ መናር፣ የመሠረተ ልማት መፍረክረክ ሁሉም በእኩል ድርሻ አላቸው። ኢስኮም መብራት የሚያመነጨው ሙሉ በሙሉ ከከሰል ነው። ከሰል በደቡብ አፍሪካ በሽበሽ ነው። ይህ ከከሰል ኤሌክትሪክን የማመንጨት ነገር በአፓርታይድ ዘመን ለአገሪቱ በበቂ ሁኔታ መብራት ያዳርስ ነበር። አሁን ግን ላሽቋል። አንዱ ምክንያት ያን ጊዜ ጥቁሮች የሚኖሩባቸው ሰፈሮች መብራት አይቀርብላቸው ስለነበረ ነው። ሌላው ደግሞ በአጭር ዓመታት ውስጥ የኃይል ፍላጎት በእጥፍ ማደጉ ነው። ይህ ደግሞ የኢኮኖሚው መመንደግ ያመጣው 'በባርኮት ውስጥ ያለ መርገም' ነው። • የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ዙማ በሙስና እንዲከሰሱ ፍርድ ቤት ወሰነ። • ሩሲያ ኢንተርኔትን ለማቋረጥ እያሰበች ነው ከዓመታት በፊት ይህ የኃይል አቅርቦት ችግር ሊከሰት እንደሚችል ታሳቢ ተደርጎ ሁለት አዳዲስ የኃይል ማመንጫ ግንባታ ተጀምሮ ነበር፤ ኩሲሊና ሜዱፒ የሚባሉ ፕሮጀክቶች። እነዚህ ሁለት ፕሮጀክቶች በ2015 ሥራ ይጀምራሉ ተብለው ነበር የተወጠኑት። ነገር ግን ግንባታቸው በግንባታ እቃዎች መናርና ለከት ባጣ የሙስና ቅሌት ተሽመድምዷል። ባለፉት 10 ዓመታት ለደቡብ አፍሪካ መብራት ኃይል ከተሾሙ ስድስት ሥራ አስፈጻሚዎች በሪያን ሞሌፍ ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር። ኾኖም ጸረ ሙስና ጠርጥሯቸዋል፤ የባለጸጎቹን የጉብታ ቤተሰብና የጃኮብ ዙማን ልጅ ለመጥቀም አሲረሃል በሚል። ዛሬ ሀብታም የደቡብ አፍሪካ ሰፈሮች በታዳሽ ኃይል መብራት ቢያገኙም አብዛኞቹ ለመብራት ፈረቃ ተዳርገዋል። መብራት ኃይል በበኩሉ 'እኔንስ ለምን አትረዱኝም፤ ፈረቃው ገቢዬ እንዲያሽቆለቁል አድርጎታል። በመብራት ታሪፍ ማሻሻያ ካልተደረገ በቁሜ መፍረሴ ነው' እያለ ነው። አሁን የመሥሪያ ቤቱ የዕዳ ቁልል እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ኢስኮም ደቡብ አፍሪካን መቀመቅ ሊከታት የሚችል የአገሪቱ ዋና ስጋት ነው ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።
news-57303945
https://www.bbc.com/amharic/news-57303945
በናይጄሪያ ታጣቂዎች ተማሪዎችን አግተው ወሰዱ
በናይጄሪያ ሰሜናዊ ክፍል ከሚገኝ አንድ እስላማዊ ትምህርት ቤት ታጣቂዎች ተማሪዎችን አግተው መውሰዳቸውን ባለስልጣናት ተናገሩ።
ታጣቂዎቹ ቴጊና ተብላ በምትጠራው ከተማ ከሚገኘው ትምህርት ቤት ትናንት እሁድ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቀ ተማሪዎች መውሰዳቸውን ባለስልጣናቱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አንድ መምህር 150 ተማሪዎች መወሰዳቸውን ሲናገር ሌሎች ደግሞ ታፍነው የተወሰዱት ተማሪዎች ቁጥር ከ200 በላይ ነው ይላሉ። ከጥቂት ወራት በፊት 300 ሴት ተማሪዎች በታጣቂዎች ታግተው ተወስደው ነበር። በወቅቱ ታግተው ከተወሰዱ ተማሪዎች መካከል እስካሁን ያልተለቀቁ ተማሪዎች አሉ። ዚስ ደይ የተባለ ድረ-ገጽ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው ታጣዊዎቹ በበርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ ተኩስ ከፍተዋል። ታዳጊዎቹ ታፍነው የተወሰዱበት ትምህርት ቤት እድሜያቸው ከ6-18 ያሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር ነው ተብሏል። የአከባቢው ባለስልጣናት ታጣቂዎቹ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ሰዎች በጥይት ከተመቱ በኋላ የአንዱ ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል። የቢቢሲዋ ዘጋቢ ማዬኒ ጆነስ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሰሜናዊ የአገሪቷ ክፍል በሚገኙ ግዛቶች ውስጥ ተማሪዎችን አግቶ ገንዘብ የመጠየቅ ወንጀል እየተበራከተ ነው ትላለች። እነዚህ ተማሪዎች የታገቱት በሰሜናዊ ናይጄሪያ በምትገኘው ካዱና ግዛት ዩኒቨርሲቲ 14 ሰዎች ታግተው ቆይተው የመለቀቃቸው ዜና ከተሰማ በኋላ ነው። ባለፉት ስድስት ወራት በሰሜናዊ ናይጄሪያ ክፍል ቢያንስ ስድስት ጊዜ ያህል የእገታ ወንጀሎች ተፈጽመዋል። የትምህርት ተቋማት ላይ ባነጣጠሩ እገታዎች ከ800 በላይ ተማሪዎች እና ሠራተኞች ታግተዋል። እአአ 2014 ቺቦክ ተብላ ከምትጠራው ከተማ 276 ሴት ተማሪዎች በቦኮ ሃራም ቡድን ታፍነው የመወሰዳቸው ዜና በርካቶችን ያነጋገር ክስተት ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተፈጸሙ ያሉ እገታዎች ግን በአደጋኛ የወንጀለኛ ቡድኖች አማካኝነት የሚፈጸም ሳይሆን አይቀርም ይባላል።
news-57099026
https://www.bbc.com/amharic/news-57099026
በሞዛምቢክ ጥቃት ነፍስ አድን ሰራተኞች ለነጮችና ለውሾች ቅድሚያ ሰጥተዋል ተባለ
መጋቢት ወር ላይ ጂሃዲስቶች አደረሱት በተባለ ጥቃት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ለነጮች ቅድሚያ መስጠታቸውን አለም አቀፉ የመብት ተሟጋቾች ድርጅት አምነስቲ አስታውቋል።
አምነስቲ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ሪፖርት ከነጮች በተጨማሪ ሁለት ውሾችንም ከጥቃቱ ለማዳን በሄሊኮፕተር እንደተወሰዱ ነው። ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች ከጥቃቱ ለመዳን በሆቴል ጀርባ እንደተሸሸጉም ተናግረዋል። "የነፍስ አድን ሂደቱ በዚህ መንገድ ዘርን መድልዎ አድርጎ መታቀዱ ከፍተኛ ስጋትን አጭሮብናል። በዚህም ሂደት ለነጭ ሰራተኞች ቀድሚያ መሰጠቱንም መረጃዎች ደርሰውናል" በማለት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የቀጠናው ዳይሬክተር ዴፕሮስ ሙቼና ተናግረዋል። አምነስቲ ጥቃቱን ለማምለጥ በሆቴሉ ውስጥ ተደብቀው ከነበሩ 220 ሞዛምቢካውያን መካከል 11ዱን ያናገረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አምስቱ ጥቃት ደርሶባቸው የተረፉ ናቸው ብሏል። "ከጥቃቱ ለማምለጥ በሚል በሆቴሉ ተደብቀን የነበርነው 220 ሰዎች ነበርን። ነጮቹ 20 ብቻ ነበሩ። በአብዛኛው ጥቁርና የአካባቢው ሰዎች ነበርን። ነጮቹን በሄሊኮፕተር መጥተው የወሰዷቸው ሲሆን እኛን ግን እዛው ትተውን ሄዱ" በማለት ከጥቃቱ የተረፈ ግለሰብ ለአምነስቲ ተናግሯል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተዋቸው ግለሰቦችም በእግራቸው ከሆቴሉ በእግራቸው ለማምለጥ ሲሞክሩ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። ይሄም ሁኔታ ምርመራ እንዲደረግበት ድርጅቱ አሳስቧል። "በእንዲህ አይነት ጥቃት ላይ ግለሰቦችን በቆዳቸው ቀለም ምክንያት ትቶ መሄድ ዘረኝነት ነው። የሰላማዊ ሰዎችን ጥበቃ ጋር የሚጣረስም ነው። ይሄ ሁኔታ ሳይመለስ መቅረት የለበትም" በማለት ዴፕሮስ ሙቼና ገልፀዋል። የነፍስ አድን ስራውን እያከናወነ ነበር የተባለው የግል ኩባንያው ድያክ አድቫይዘሪ ግሩፕ በበኩሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገረው የተባለው ነገር "ሁሉም ትክክለኛ እንዳልሆነና" በቅርቡም መግለጫ እንደሚያወጣ አስታውቋል።
52829808
https://www.bbc.com/amharic/52829808
ትራምፕ 'ቀላል ጉንፋን ነው' ያሉት ቫይረስ የ100ሺህ ዜጎቻቸውን ህይወት ነጠቀ
አሜሪካ በኮሮናቫይረስ የሞቱባት ዜጎች ቁጥር በቬትናም፣ በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታንና በኮሪያ ጦርነቶች በድምሩ ከሞቱትም በላይ ሆኗል፡፡
በጥር 21 የመጀመርያው በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው በአሜሪካ ተገኘ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ለነገሩ ፊትም አልሰጡትም ነበር፡፡ ‹‹ቀላል ጉንፋን ነው›› ሲሉት ነበር፡፡ ቀጥለው ደግሞ ‹‹ሥራ ፈት ዲሞክራቶች እኔን ለማሳጣት የፈጠሩት አሉባልታ ነው›› እያሉ አጣጣሉት፡፡ ትንሽ ቆይተው ‹‹ተራ ነገር ነው፤ ሰሞኑን ብን ብሎ ይጠፋል›› አሉ፡፡ በኋላ ላይ ነገር ዓለሙ ሲምታታባቸው ከልብስ ማጽጃ ኬሚካል እስከ ወባ መድኃኒት ውሰዱበት ማለት ጀመሩ፡፡ እውነት ለመናገር ትራምፕም ሆነ ሌሎች ፖለቲከኞች ወረርሽኙ በዚህ አጭር ጊዜ እንዲህ አሜሪካንን የሚያህል አገር በእምብርክክ ያስኬዳል ያለ አልነበረም፡፡ የሆነው ማንም ከገመተው በላይ ነው፡፡ በተለይ በሕክምናም ሆነ በኅብረተሰብ ጤና እጅግ መጥቃለች የምትባለው ኃያል አሜሪካን በዚህ ደረጃ የሚዳፈር ወረርሽኝ ይኖራል ያለ ነበር ለማለት ይከብዳል፡፡ እነሆ ኮቪድ በአራት ወራት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ዜጎቿን ሰቅዞ ይዞ፣ አንድ መቶ ሺዎቹን ደግሞ ከዚህ ዓለም በሞት አሰናብቷል፡፡ በሌላ ቋንቋ በዓለም ላይ በዚህ ክፉ ደዌ ከተያዘው ሰው 30 እጁ አሜሪካዊ ነው እንደማለት ነው፡፡ በሟቾችም ሆነ በተያዦች ቁጥር አሜሪካ የዓለም ቁንጮ ትሁን እንጂ ከሕዝቧ ስፋት አንጻር የሟቾች አሀዝ ሲሰራ አሜሪካ በዓለም 9ኛዋ ተጠቂ አገር ነው የምትሆነው፡፡ አሁን በመላው ዓለም የተያዦች ቁጥር አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺ አልፏል፡፡ በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር መቶ ሺ ሲዘል ጠቅላላው የዓለም የሟቾች ቁጥር ደግሞ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ 354 ሺህ 984 ደርሷል፡፡ አሐዞችን እየተከታተለ ይፋ የሚያደርገው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የመረጃ ቋት እንደሚያስረዳው አሁን በትክክል በአሜሪካ ምድር የተመዘገው የሟቾች ቁጥር 100ሺህ 276 ነው፡፡ የቢቢሲው የሰሜን አሜሪካ የፖለቲካ አርታኢ ባልደረባችን ጆን ሶፔል ይህንን ቁጥር በተሸለ ሲገልጸው አሜሪካ አሁን በኮቪድ-19 ያጣቻቸው ዜጎቿ ቁጥር በታላቁ የቬትናም ጦርነት፣ በኢራቅ፣ በኮሪያ፣ በአፍጋኒስታን ባለፉት 44 ዓመታት የሞቱባት ዜጎች ተደምረው እንኳ የሚበልጥ ነው፡፡
news-49264235
https://www.bbc.com/amharic/news-49264235
የሶማሊያ ባለስልጣናት ከአልሸባብ ጋር በተያያዘ የጎሳ መሪዎችን አስጠነቀቁ
የሶማሊያ ግዛት በሆነችው ጁባላንድ የአስተዳደር ክልል ውስጥ ታጣቂው እስላማዊ ቡድን አልሸባብ የሚያወጣቸውን መመሪያዎች ተግባራዊ በሚያደርጉ የጎሳ መሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።
አስተዳደሩ ባወጣው ማስጠንቀቂያ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የጎሳ መሪዎች አልሸባብ ይካሄዳል የተባለው የምርጫ ሂደትን እንዲያወግዙና ለታጣቂ ቡድኑ ታማኝነታቸውን እንዲገልጹ ያቀረበውን ጥሪ ተከትለው የተባለውን ድርጊት ከፈጸሙ አስፈላጊውን የቅጣት እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። • አል ሻባብ የጎሳ መሪዎችን አስጠነቀቀ • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ለምን ተስተጓጎለ? አልሸባብ በቅርቡ ባወጣው ትዕዛዝ የፓርላማ አባላትን በመምረጥ ሂደት ውስጥ የተሳተፉ የጎሳ መሪዎች ድርጊታቸውን በማውገዝ "ንሰሐ" እንዲገቡ አለዚያም ሞት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቆ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጎሳ መሪዎች እስላማዊው ቡድን ሊወስድ በሚችለው እርምጃ ለሕይወታቸው በመስጋት ቡድኑ ላቀረበው ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል።. በዚህም የጁባላንድ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ለአልሸባብ ጥሪ ተገዢ በመሆን ምላሽ የሚሰጡ የጎሳ መሪዎች የስድስት ወራት እስራትና የሽምግልና ቦታቸውን እንዲያጡ ከመደረጉም በላይ እያንዳንዳቸው ሁለት መትረየሶችን በቅጣት መልክ ለአስተዳደሩ እንዲሰጡ ይገደዳሉ። አልሸባብ በበኩሉ በምርጫው ሂደት የተሳተፉ የጎሳ መሪዎች "የንሰሐ ቅጣት" በሚል እያንዳንዳቸው አንድ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ከአራት ካርታ ጥይቶች ጋር እንዲያስረክቡ አዞ ነበር። • "የወ/ሮ መዓዛ ንግግር ሌሎችንም [ክልሎች] የተመለከተ ነበር" የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትናንት ማክሰኞ በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በምትገኘው ቡላይ ፉላይ መንደርና በጁባላንድ አንድ መቶ የሚደርሱ የጎሳ መሪዎች "ንስሐ" በመግባታቸው ይቅርታ አድርጎላቸዋል ተብሏል። ከጁባላንድ በተጨማሪ ጋልሙዱግ በተባለውና በሌሎች የደቡብ ምዕራብ የሶማሊያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ከአልሻባብ ጋር ግንኙነት የሚፈጽሙ የጎሳ መሪዎችን አስጠንቅቀዋል። አልሻባብ በሶማሊያ ውስጥ እስላማዊ አስተዳደር ለመመስረት የሚፈልግ ቡድን ሲሆን አሁን ያለው የሶማሊያ መንግሥትን እውቅና በመንፈግ በኃይል ለማስወገድ የተለያዩ ጥቃቶችን እየፈጸመ የሚገኝ ቡድን ነው።
48392892
https://www.bbc.com/amharic/48392892
የዊኪሊክስ መስራች ጁልያን አሳንጅ ተጨማሪ 17 ክስ ቀረበበት
የአሜሪካ የፍትሕ ሚንስቴር፤ የዊኪሊክስ መስራች ጁልያን አሳንጅ ላይ 17 ተጨማሪ ክሶች አቅርቧል። አሁን በእስር ከሚገኝበት እንግሊዝ ወደ አሜሪካ እንደሚወሰድም ይጠበቃል።
አሜሪካ አሳንጅ ላይ ያቀረበችው ክስ በሕገ ወጥ መንገድ የመረጃ ምንጮችን ማውጣት ይገኝበታል። ክሱ የአሜሪካን ሕግ በመጣስ 2010 ላይ ሚስጥራዊ የሆኑ ወታደራዊና የዲፕሎማሲ መረጃዎችን ማሾለክንም ያካትታል። • ኢኳዶር የጁሊያን አሳንጅን እቃዎች ለአሜሪካ ማስረከብ ጀመረች የፔንታጎንን መረጃ ለማግኘት ቸልሲ ማኒንግ ከተባለች የቀድሞ ሰላይ ጋር በመመሳጠር ባለፈው ወር ተከሶ እንደነበር ይታወሳል። እንግሊዝ ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ በነበረበት ቀን ባለመቅረቡ የ50 ሳምንት እስር ተፈርዶበት ሚያዝያ ላይ በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር። አሳንጅ ከመታሰሩ በፊት ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ በጥገኝነት ይኖር የነበረ ሲሆን፤ ኢኳዶር ጥገኝቱትን ከነጠቀችው በኋላ ዘብጥያ መውረዱም ይታወሳል። ስዊደን ውስጥ ወሲባዊ ጥቃት በማድረስ መከሰሱን ተከትሎ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2012 ላይ በኢኳዶር ኤምባሲ ጥገኝነት ጠይቆ ነበር። በወቅቱ የ47 ዓመቱ አሳንጅ ክሱን ማጣጣሉም ተዘግቦ ነበር። • የኤርትራ 28ኛ ዓመት ነፃነት ከየት ወደየት? አሳንጅ ምንጮቹ ሚስጥራዊ መረጃ በማውጣት ለዊኪሊክስ እንዲሰጡ ያበረታታ እንደነበር በክሱ ተመልክቷል። የቀድሞዋ ሰላይ ቸልሲ ማኒንግ ሚስጥራዊ መረጃ እንድትሰርቅ ይደግፍ እንደነበርና የወታደራዊ ኮምፒውተር ይለፍ ቃልን ጥሶ ለመግባት እንደተስማማም ተገልጿል። የቀድሞዋ ሰላይ ወታደራዊ መረጃ በማሾለክ የ35 ዓመት እስር ተፈርዶባት ነበር። ፍርዱን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ቢቀንሱላትም፤ ዊኪሊክስ ላይ ለመመስከር ፍቃደኛ ስላልሆነች በእስር ላይ ትገኛለች። በአፍጋኒስታን፣ በቻይና፣ በኢራን፣ በኢራቅና በሌሎችም ሀገሮች የሚኖሩ ምንጮችን ይፋ በማድረግ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ በመጣል የተከሰሰው አሳንጅ፤ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የዓመታት እስር ይጠብቀዋል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ በሚያውቋቸው አንደበት ዊኪሊክስ በበኩሉ፤ ክሱ ጋዜጠኞች ላይ የተቃጣና የመናገር ነጻነትን የሚጋፋ ነው ሲል በትዊተር ገጹ አስፍሯል። ተባባሪ አቃቤ ሐወግ ጆን ደርሜስ መሥሪያ ቤታቸው የጋዜጠኞችን መብት እንደማይገፍ ተናግረው "ደግሞም አሳንጅ ጋዜጠኛ አልነበረም" ብለዋል። ጋዜጠኞች በጦር ሜዳ ያሉ ምንጮችን ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ ማንነታቸውን ይፋ እንደማይደርጉም አክለዋል።
48361912
https://www.bbc.com/amharic/48361912
ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ለምንስ ግድ ይሰጠናል?
ምድራችን ላይ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሕልውናው የአንዱ ከሌላኛው ጋር የተሳሰረ ነው።
በዓለም ላይ የተለያዩ ፍጥረታት አንዳቸው ከሌላቸው ጋር በሰመረ ጥምረት ይኖራሉ። አንዳቸው ከሌላቸው ጋር ያላቸው መስተጋብር እንዲሁም ከሚኖሩበት አካባቢ ጋር ያላቸው ግንኙነትም የተጣጣመ ነው። የሰው ልጅም በዚህ የሕይወት ዑደት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ ሕይወቱም በዓለማችን ላይ ከሚገኙ ፍጥረታት መኖር ጋር የተሳሰረ ነው። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርበት የተከታተሉት የእራት ግብዣ • ህወሀት እና ህግደፍ ይታረቁ ይሆን? ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ሕይወት ያለው ሁሉ፣ እኛን ጨምሮ፣ በሚኖርበት ፕላኔት ላይ በዙሪያው የተለያዩ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሊኖሩ ይገባል። ይህንን ነው ብዝኀ ሕይወት የምንለው። ተክሎች የምንተነፍሰውን አየር ያመርቱልናል፤ ንቦች ደግሞ ሰብሎች እንዲራቡ በማድረግ ውስጥ አይተኬ ሚና አላቸው። ፈንገስ ደግሞ አፈር ለምነቱን ጠብቆ አንዲቆይ ያደርጋል። ስለዚህ ካልተበረዘው የተፈጥሮ ዓለም፣ የምንጠጣውን ኩልል ያለ ንፁህ ውሃ፣ ባመመን ጊዜ የምንፈወስበትን መድኀኒት እንዲሁም መንፈሳችንን የሚያድስ እይታ እናገኛለን። ከምድር ገፅ ላይ የአንድ ተክል ወይም እንስሳ ዝርያ መጥፋት ቀላል ሊመስል ይችል ይሆናል። ነገር ግን አንዳችን ከሌላችን ጋር በማይበጠስ ገመድ ስለተሳሰርን የአንድ ዝርያ መጥፋት ትልቅ ጉዳት ነው። ስለምን ግድ ይሰጠናል? አንድ ቤትን አስቡ። እናም አንድ ሰው ቤቱ ከተገነባበት ጡብ አንዱን መዞ ቢያወጣው ቤቱ ውበቱ እየደበዘዘ ጥንካሬውም እየደከመ ይሄዳል። በርካታ ጡቦች ሲወጡ ደግሞ በአጠቃላይ ቤቱ ይፈርሳል። በምድርም ከአጠቃላይ የሕይወት ማዕቀፉ ውስጥ አንድ ዝርያ ሲጎድል፤ ብዝኀ ሕይወቱ ደካማ እየሆነ ይሄዳል፤ ያ ደግሞ በምድር ላይ ሕብር ሠርተው እየኖሩ ያሉ ፍጥረታትንም ያያደክማል። በአሁኑ ወቅት ዓለማችንን ስንመለከት መፃዒ ተስፋችን ጭጋግ የለበሰ ነው። ተፈጥሮ ሚዛኗ ተዛብቷል። ምን እየሆነ ነው? ለምን? ተመራማሪዎች በምድራችን ላይ የተለያዩ ዝርያዎች በሚሊየን ዓመታት አይተን በማናውቀው ፍጥነት እየጠፉና እየተመናመኑ ነው ይላሉ። ይህንን እያደረገ ያለው ደግሞ የሰው ልጅ ነው። የደን መጨፍጨፍ፣ ለእርሻ፣ ለቤት ግንባታና ኢንደስትሪን ለማስፋፋት ተብለው የሚካሄድ ምንጣሮና ቃጠሎ ምድራችንን አደጋ ላይ ጥለዋታል። አየሩን፣ አፈሩን እና ውሀውን እየበከልን በእነዚህ ላይ ኑሯቸውን ያደረጉ ፍጥረታትን አደጋ ላይ ጥለናል። ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድና አደን፣ ከተገቢው በላይ አሳ ማስገር እንስሳት በከፍተኛ ቁጥር እንዲሞቱና እንዲጠፉ እያደረገ ነው። የሰው ልጅ እፅዋትንና እንስሳትን ከዚህ ቀደም ወደማይገኙበት የዓለማችን ክፍል እያጓጓዘ፤ በስፍራው ቋሚ ነዋሪ የነበሩት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳረፈባቸው ይገኛል። • ለወሲብ ባርነት ወደ ቻይና የሚወሰዱት ሴቶች በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የአየር ጠባይ ለውጥ ምድራችንን እያናወጣት ነው። ይህ ሁሉ ጥፋት ተስፋችን የተመናመነ ሊያስመስለው ይችላል። ግን ተስፋ አለን። እያንዳንዱ ግለሰብም ሆነ አገራትን የሚመሩ ባለስልጣናት ማድረግ የሚችሉት ነገር አለ። መንግሥታት ሕገ ወጥ አደንንና የዱር እንስሳት ንግድን ቢከላከሉና ዝርያቸው ለመጥፋት ለተቃረቡ እንስሳት ልዩ ጥበቃ ቢያደርጉ ተፈጥሮን መታደግ እንደሚቻል ባለሙያዎች ይመክራሉ። ምን እናድርግ? ማድረግ የምንችለው ነገር አለ። የምንጠቀመውን ኃይል መቀነስ፣ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ በመጠቀም፣ አየርንና ምድሪቱን ከብክለት መታደግ፣ ነዳጅ በመቀነስ ሌሎች የኃይል አማራጮችን መጠቀም። ከባቢ አየሩን የማይጎዱ ምርቶችን መጠቀምም ልናደርጋቸው ከምንችላቸው ነገሮች መካከል ይገኝበታል። በሚኖሩበት አካባቢ አበባ በመትከል ንቦች ለሰብሎች መራባት ያላቸውን አስተዋፅኦ ማስቀጠል ይችላሉ። አሁን ያለንበት ወቅት የተፈጥሮ አደጋ ጊዜ ይሰኛል። ስለዚህ ተፈጥሮ ላይ የሚደርስ ማንኛውም ነገር እኛንም ይጎዳናል።
news-54752422
https://www.bbc.com/amharic/news-54752422
ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ በአንድ ቀን ብቻ 94 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ተያዙ
በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 94 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማካሄድ ቀናት በቀሯት አሜሪካ በተለያዩ ግዛቶችም በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሻቅቧል ተብሏል። በዚህ ሳምንት ሃሙስ 91 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ከፍተኛ ቁጥር ነው በማለት ሪፖርት አድርጋ የነበረቸው አሜሪካ በተከታታይ ባሉት ቀናትም እንዲሁ ከዚህ በላይ ያለው ቁጥር በየቀኑ ተመዝግቧል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮም እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ሚሊዮን መድረሱን ከጆንስ ሆፕኪንስ የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ፕሬዚዳንታዊ ስልጣኑን ለመጨበጥ ዶናልድ ትራምፕና ጆ ባይደን እየተፋለሙ ባሉባት አሜሪካ ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም አሸናፊው የሚታወቅ ይሆናል። አሁን ባለውም ሁኔታ 21 የአሜሪካ ግዛቶች በወረርሽኙ ክፉኛ የተመቱ ሲሆን አንዳንድ ግዛቶችም በዚህ ምርጫ ላይ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ተብሏል። በምርጫው ወሳኝ ከሆነችው ግዛት አንዷ ዊስኮንሰን የሚገኙ ሆስፒታሎች አርብ እለት የነበረውን የዶናልድ ትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ወረርሸኙን ያባብሰዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "በአሁኑ ወቅት በተቻለ መጠን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ባይሰበሰቡ ይመረጣል። በተለይም በዊስኮንሰን ግዛት ግሪን ቤይ አካባቢ በአገሪቱ ካሉ ቦታዎች በከፍተኛ ፍጥነት ወረርሽኙ እየተዛመተ መሆኑን እያየን ነው" በማለት የግዛቲቱ ሆስፒታሎች በጥምረት መግለጫ አውጥተዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ አርብ ከነበረው የምርጫ ቅስቀሳቸው በፊትም "ከፍኛ ምርመራ ከፍተኛ ቁጥርን እያስመዘገበ ነው። ምርጥ የሆነ ምርመራ አለን። ሞት እየቀነሰ ነው" በማለት በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በቅርቡ የነበረው የትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ ተሳታፊው ሙቀት ሲለካ ነበር እንዲሁም ጭምብልም እየታደለ ነበር። በወረርሽኙ ምክንያት ትልልቅ ዝግጅቶችም ከአዳራሽ ውጭ እየተደረጉ ነው። ሆኖም በነዚህ ስፍራዎች አካላዊ ርቀት ሲጠበቅ አይታይም እንዲሁም አንዳንድ ደጋፊዎች ጭምብል አናጠልቅም የሚል እምቢተኝነት አሳይተዋል። ጆ ባይደንም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን እያካሄዱ ሲሆን ዲሞክራቶቹ አካላዊ ርቀትን እያስጠበቁ ነው ተብሏል። ለምሳሌም ያህል ደጋፊዎች በየመኪኖቻቸው ሆነው እንዲከታተሉ አድርገዋል።
news-54157962
https://www.bbc.com/amharic/news-54157962
ዩቲዩብ ቲክቶክ መሰል መተግበሪያ ሕንድ ውስጥ ሊጀምር ነው
ዩቲዩብ የተሰኘው ግዙፍ ማሕበራዊ ድር አምባ ሕንድ ውስጥ ቲክቶክን ይቀናቀናል የተባለ መተግበሪያ ይፋ ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል።
ዩቲዩብ ሾርትስ የተሰኘ ስም የተሰጠው መተግበሪያ ተንቀሳቃሽ ምስሎች መጋሪያ ነው። ተጠቃሚዎች ከ15 ሰኮንድ የረዘመ ምስል እንዲጭኑ አይፈቀድላቸውም። መተግበሪያ ከቻይናው ቲክቶክ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀምም ታውቋል። ሕንድ ባለፈው ሰኔ ከቻይና ጋር ድንበር ላይ መጋጨቷን ተከትሎ ቲክቶክ የተሰኘው አነጋጋሪ የተንቀሳቃሽ ምስል መጋሪያ ድር አምባን ጨምሮ ሌሎች 58 መተበግሪያዎችን ማገዷ አይዘነጋም። በወቅቱ ቲክቶክ ሕንድ ውስጥ በዓለም ትለቁ የተባለ ገበያ ነበረው። የተጠቃሚዎች ቁጥርም 120 ሚሊዮን ገደማ ነበር። ዩቲዩብ ሕንድ ውስጥ የቲክቶክን ክፍተት ለመሙላት ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ ሃገር በቀል ድርጅቶችም ፉክክር ይጠብቀዋል። የዩቲዩብ ምርቶች ቁጥጥር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ክሪስ ጄፍ እንዳሉት ሾርትስ የተሰኘው አዲስ ቴክኖሎጂ ዋና ዓላማው ተጠቃሚዎች ሞባይል ስልካቸውን ብቻ ተጠቅመው አጠር ያሉ ማራኪ ቪድዮዎችን እንዲሠሩ ማመቻቸት ነው። አዲሱ ቴክኖሎጂ የተለያዩ ካሜራዎችን ተጠቅሞ ቪድዮዎችን መሥራት ያስችላል። አልፎም ተጠቃሚዎች ከሙዚቃ ቤተ መዘክር የፈለጉትን ሙዚቃ ተጠቅመው መጠቀም እንዲችሉ ያደርጋል። ምክትል ፕሬዝደንቱ ሾርትስ በደንብ እየተሻሻለ ሲመጣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ተገጥመውለት ወደ ሌሎች ገበያዎች እንደሚሠራጭ ተናግረዋል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና ሠራሹ ቲክቶክ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዳይሠራ አደርጋለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በርካታ አማራጮች ወደ ገበያ መምጣት ጀምረዋል። ፕሬዝደንቱ የተጠቃሚዎች ግላዊ መረጃ በቲክቶክ አማይነት ለቻይና መንግሥት ተላልፎ እየተሰጠ ነው ይላሉ። የሕንድ መንግሥትም ተመሳሳይ ቅሬታ በማቅረብ ነው ቲክቶክን ከጥቅም ውጭ ያደረገው።
41276892
https://www.bbc.com/amharic/41276892
ሰሜን ኮሪያ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን የባለስቲክ ሚሳኤል ወደ ጃፓን አስወነጨፈች
የመጀመሪያውን ሙከራ ካደረግች ጥቂት ሳምንታት የሆናት ሰሜን ኮሪያ ሁለተኛውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ወደ ጃፓን ውቅያኖስ አቅጣጫ አስወንጭፋለች።
የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ሀይል እንዳስታወቀው ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈችው የባለስቲክ ሚሳኤል 3700 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዞ ሆካይዶ በተባለችው የጃፓን ደሴት አቅራቢያ አርፏል። የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ሀገራቸው የሰሜን ኮሪያን ትንኮሳ እና አደገኛ እንቅስቃሴ እንደማትታገስ አስታውቀዋል። አቤ በሰጡት መግለጫ "ሰሜን ኮሪያ መሰል ድርጊቷን የምትቀጥል ከሆነ የወደፊት ተስፋ የሚባል ነገር የላትም" ብለዋል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቴይለርሰንም እንዲሁ የሚሳኤል ሙከራውን ወቅሰው ሰሜን ኮሪያ በተባበሩት መንግስታት የተጣለባትን ማዕቀብ እየጣሰች ትገኛለች ብለዋል። በተጨማሪም ቴይለርሰን ለዚህ ተጠያቂው የሰሜን ኮሪያ አጋር የሆኑት ቻይና እና ሩስያ ናቸው በማለት ይወቅሳሉ። አክለውም "ቻይና ለሰሜን ኮሪያ ነዳጅ ትሸጣለች ሩስያ ደግሞ ሰሜን ኮሪያውያንን በጉልበት ሰራተኛነት እያሰራች ነው" ይላሉ። "ቻይና እና ሩስያ የራሳቸውን ቀጥተኛ እርምጃ በመውሰድ ለሰሜን ኮሪያ ምላሽ መስጠት አለባቸው" ብለዋል። ሰሜን ኮሪያ ሙከራውን ባካሄደች በደቂቃዎች ልዩነት ደቡብ ኮሪያም ሁለት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ውቅያኖስ እንዳስወነጨፈች ዮንሃፕ የተሰኘው የደቡብ ኮሪያው ዜና ወኪል ዘግቧል። ደቡብ ኮሪያም በምላሹ የሚሳኤል ሙከራ አድርጋለች የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚደንት ጃየ-ኢን ከሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ጋር የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ አድርገዋል። ፕሬዚደንቱ "የሰሜን ኮሪያ መሰል የሚሳኤል ሙከራዎች በሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት ላይ ትልቅ አደጋ የሚጥሉ ናቸው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በሆካይዶ ደሴት ለሚኖሩ ጃፓናውያን በፅሁፍ መልዕክት ማስጠንቀቂያ ሲደርሳቸው፤ በአካባቢው የተሰቀሉ የማስጠንቀቂያ ደወሎችም ሚሳኤሉ በተተኮሰበት ጊዜ ጩኸታቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ታውቋል። የአሁኑ ሙከራ ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ጊዜ ከሞከረችው የባለስቲክ ሚሳኤል ከፍተኛ አቅም ያለው እንደሆነም ተገምቷል። የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራዎች ዋነኛ ትኩረት አሜሪካን መምታት የሚችል ረጅም ርቀት ተጓዥ ሚሳኤል መስራት እንደሆነ እየተዘገበ ይገኛል።
news-51306279
https://www.bbc.com/amharic/news-51306279
ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና
ቻይና ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሮናቫይረስ በርካታ ሰዎችን መግደሉንና በሺህዎች የሚቆጠሩት በበሽታው መያዛቸውን ተከትሎ በተለይ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ስጋት ነግሷል።
ወረርሽኙ ከአንዲት የቻይና ግዛት ተነስቶ በመላዋ ቻይና መስፋፋቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በዚህም ሳቢያ የበሽታው መስፋፋት ስጋት ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢ ያሉ ሰዎች ካሉባቸው ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገባቸው መሆንኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ባለፉት ዓመታት ከቻይና ጋር ጠንካራ ግንኙነት የገነባችው ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለንግድ፣ ለሥራና ለትምህርት ወደተለያዩ ግዛቶች ይሄዳሉ። • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ በተለይ ደግሞ ከቻይና ከፍተኛ ቁጥር ያለው የትምህርት ዕድል ከሚያገኙ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በርካታ ተማሪዎች በተለያዩ የቻይና ግዛቶች በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ አሏት። በቅርቡ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ የቻይና መንግሥት ከ800 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ቻይና ውስጥ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጣና እንዲያገኙ እድል ሰጥቷል። ከቻይና የንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው በጎርጎሳውያኑ 2018 ከ7 ሺህ 600 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ቻይና ውስጥ ስልጠና አግኝተዋል። • ኮሮናቫይረስ አሜሪካ፣ ታይዋን፣ ጃፓን፣ ቬትናም ጨምሮ በሌሎች አገራት ተሰራጭቷል በአሁኑ ጊዜ ቻይና ውስጥ በትምህርት ምክንያት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ትክክለኛ ቁጥር ማግኘት ባይቻልም ከዚህ በፊት ከነበረው ቁጥር አንጻር ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች በቻይና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ይገኛሉ። ታዲያ ዓለምን በከፍተኛ ደረጃ ያሳሰበው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት በዚህ ወቅት ቻይና ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሁኔታ ምን ይመስላል? ስንል ሁለት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎችን ጠይቀናል። ባዩ አቦኃይ በቻይና ቶንጂ ዩኒቨርስቲ በአካባቢ ምህንድስና ሁለተኛ ዲግሪውን እያጠና ነው። ከበሽታው መከሰት ጋር በተያያዘ የእለት ከዕለት እንቅስቃሴው እንደተስተጓጎለ ይናገራል። አሁን ወቅቱ የቻይና አዲስ ዓመት በመሆኑ በርካታ ተማሪዎች ወደየመጡባቸው አካባቢዎች በመሄዳቸው፤ በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚገኙት እሱን የመሰሉ ከሌሎች አገራት የመጡ ተማሪዎች ብቻ ናቸው። የዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ስለበሽታውና ማድረግ ስላለባቸው የመከላከያ ጥንቃቄዎች በየዕለቱ ተከታታይ መረጃዎች እንደሚያገኙ የሚናገረው ባዩ እስካሁን የሚያሰጋ ነገር የለም ይላል። • በቻይና የተከሰተው አዲስ ቫይረስ ምን ያህል አስጊ ነው? በመላዋ ቻይና ስለተከሰተውና በርካታ ሰዎችን ስለገደለው በሽታ በስፋት መወራቱና በባለስልጣናት የሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር እስካሁን ምንም ስጋት እንዳልፈጠረበት የሚገልጸው ባዩ ዋነኛው ስጋት ነው የሚለው በጥቂት ቀናት ውስጥ እረፍት ላይ ያሉ ተማሪዎች የሚመለሱ ከሆነ ነው። "ለበዓል ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሄዱ ተማሪዎች ተመልሰው ዩኒቨርስቲው ውስጥ ካሉት ጋር ያለምንም ጥንቃቄ እንዲቀላቀሉ የሚደረጉ ከሆነ ግን የበሽታውን ስጋት ይጨምረዋል" ይላል ባዩ። • ቻይና በ 6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ ነው አሁን እንደተነገራቸው ግን በሽታው በፍጥነት በመስፋፋቱና በተለያዩ የቻይና ግዛቶች ውስጥ ያለው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር በመደረጉ ቀጣዩ ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ እንዲራዘም በመደረጉ ያለውን ስጋት በተወሰነ ደረጃ ቀንሶታል። የዩኒቨርስቲው ኃላፊዎች ላሉት ተማሪዎች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ ተከታታይ ምክር ከመስጠት ባሻገር ከግቢው እንዳይወጡ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉባቸው የሚገልጸው ባዩ፤ ምግብ ለመመገብ ወደ ካፍቴሪያ ከመሄድ ውጪ አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በመኝታ ክፍሎቻቸው ውስጥ ነው። መንግሥት ምናለ በሾንጂ የኒቨርስቲ በአካባቢ ሳይንስ የዶክትሬት ትምህርቱን እየተከታተለ ነው። በከተማዋ ያሉ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል እንቅስቃሴዎች በከፍተኛ ደረጃ በመቀዛቀዛቸው ምክንያት "ያለው ሁኔታ ከባድና አስፈሪ ነው" ይላል መንግሥት። በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተወሰኑ የሌሎች አገራት ተማሪዎች መኖራቸውን የሚናገረው መንግሥት በሚወጡና በሚገቡ ቁጥር እንደሚመዘገቡና ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው እንዲሁም ከግቢው መውጣት እንደማይቻል ይህም ያሉበትን ሁኔታ "አስቸጋሪ አድርጎብናል" ይላል። • የኮሮናቫይረስ እየተዛመተ ነው፤ የሟቾች ቁጥርም ጨምሯ መንግሥት እንደሚለው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቻይናዊያን ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ስለሌሉ ምግብ በሽያጭ የሚቀርብበት ካፍቴሪያ ውስን ምግቦችን ስለሚያዘጋጅ ሊያልቅ እንደሚችል በዚህም እየተቸገሩ መሆኑን አመልክቷል። ከግቢው መውጣት ባለመቻላቸው "በተለይ ምግብ ማግኘት ላይ ችግር እየገጠመን ነው" በማለት የእንቅስቃሴ ቁጥጥሩ በግቢው ውስጥም ጥብቅ በመሆኑ ለመንቀሳቀስ እንደተቸገሩና በቀጣይም አገልግሎቱ የበለጠ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለው። ከበሽታው መከሰት ጋር ተያይዞ በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚገኙት መደብሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መዘጋታቸው እንዲሁም ውጪ ያለው እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በመቆሙ ተማሪዎቹ ባሉበት ቦታ ብቻ ተወስነው ይገኛሉ። • አንድ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ኬንያ ውስጥ ተገኘ መንግሥት እንደሚለው የሚደረገው ቁጥጥር ጥብቅ ነው "ከመኝታ ክፍሎቻችን ወጥተን በዩኒቨርስቲው ውስጥ ወደሚገኘው ካፍቴሪያ ለመሄድ እንኳን የምንመለስበትን ጊዜ የሚጠቅስ ፎርም መሙላት ይጠበቅብናል" ይላል። ስለጤንነታቸውና ስላሉበት ሁኔታ በኢንተርኔት አማካይነት በቀን ሦስት ጊዜ ሪፖርት እንሚያደርጉና፤ በግቢው ውስጥ ባሉ ህንጻዎች ውስጥ ከሚኖሩ ተማሪዎች ጋርም ለመገናኘት አስቸጋሪ መሆኑን መንግሥት ለቢቢሲ ተናግሯል። በቻይና ውስጥ በተለይ የበሽታው ዋነኛ ማዕከል እንደሆነች በሚነገረው የሁቤይ ግዛት ዋና ከተማ ዉሃን ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለማግኘት እንዲሁም በቻይና ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአገሪቱ ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የኮሮናቫይረስ በቻይና ውስጥ እየተስፋፋ በመሄዱ የተለያዩ አገራት ዜጎቻቸውን ከዉሃን ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ ነው። አንዳንድ አየር መንገዶች ደግሞ በረራዎችን ሰርዘዋል።
news-49475827
https://www.bbc.com/amharic/news-49475827
የተጠለፈው ልዑል አለማየሁ አፅምና የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት እንግሊዝ እመልሳለሁ አለች
በእንግሊዝ መንግሥትና በኢትዮጵያው ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ የተደረገውን የመቅደላ ውጊያ ተከትሎ እልፍ ቁጥር የሌለው ቅርስ፣ ሃብት፣ ንብረት ተዘርፏል።
መቅደላ ውጊያ ላይ የተመዘበሩት ቅርሶችና ንብረት ብቻ አልነበረም ከዚህም በላይ የሰባት ዓመት እድሜ ያለውን የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁ ተጠልፎ ተወስዷል። ለዘመናትም ከኢትዮጵያ የተመዘበሩ ቅርሶች እንዲመለሱ የተለያዩ ምሁራንም ሆነ ግለሰቦች እንዲህም በሃገር ደረጃ ሲጥሩ ነበር። በቅርቡ የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ የተመለሰ ሲሆን ተጠልፎ የተወሰደውን የልጃቸውን አፅም ለማስመለስም ያለሰለሰ ጥረቱ እንደቀጠለ ነው። •የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት መመለሳቸውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ምላሽ ምንድን ነው? •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ልዑል አለማየሁ እናትና አባቱን ሲያጣ ለቅርብ ቤተሰቡ መሰጠት ሲገባው ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ወደ እንግሊዝ እንደሄደ ገልፀው በወቅቱም ደስተኛ አልነበረም ብለዋል። ሚኒስትሯ ለዚህ ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱት ደግሞ ንግስት ቪክቶሪያ "በሰው ሃገር ባይተዋር ሆነህ ደስተኛ ሳትሆን በመሞትህ አዝናለሁ" በማለት ለልዑሉ ጸጸታቸውን የገለጹበትን የሃዘን መግለጫ ነው። "የንግስቲቷን ጽሁፍ ስናነብ ልባችን ይደማል፤ እናዝናለንም። ልዑሉ ወደ ሃገሩ አለመመለሱም ሌላኛው ፀጸት ነው" የሚሉት ሚንስትሯ የልዑሉን አጽም እንግሊዞች እንደሚመልሱላቸው እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል ይህንንም ለማሳካት "የሁለቱም ሃገራት ድልድይ በመሆናቸው በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያግዙናል ብለን እናስባለን" ብለዋል። ልዑሉ በብቸኝነት ሲሰቃይ ቆይቶም በ18 ዓመቱ እንደሞተ የታሪክ መዛግብቶች ያወሳሉ። የመጨረሻ ጊዜውን አስመልክቶ ከልዑል አለማየሁ አንደበት የተወሰደውን አሉላ ፓንክረስት በፅሁፉ አስቀምጦታል ይህም " ተመርዣለሁ" የሚል ነው። ተጠልፎ ተወስዶ ህይወቱ ያለፈው የልጅ ልዑል አለማየሁ ህይወት አሳዛኝ እንደሆነ ህይወቱ ላይ የወጡ ፅሁፎች ያሳያሉ። ከሞተ በኋላ እንኳን አፅሙ ኃገሩ ይረፍ ተብሎም ለእንግሊዝ መንግሥት በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም እስካሁን ምላሽ የለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የልዑል አለማየሁ አጽም መመለስ አስፈላጊ መሆኑን ለማወቅ የዓጼ ቴዎድርስ ቁንዳላ ሲመለስ ሕዝቡ ያሳየውን ስሜት መረዳት በቂ ነው ብለዋል ሚንስትሯ። በተለይም ከቁንዳላው መመለስ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያውያን የአንድነት ስሜት ከፍ ያደረገ መሆኑን እንደ ትልቅ እመርታ ጠቅሰው ሕዝቡ ቅርሶቻችን ተወስዷል የሚለው ስሜት ተቀይሮ ማስመለስ ይቻላል የሚል ጥሩ ስሜትና ተስፋ እንዲፈጠርበት እንዳደረገ ሚኒስትሯ አስረድተዋል። የንጉሰ ነገስቱም ቁንዳላ፣ የልዑሉ አፅምና ታቦታቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ክብርና ቦታ የሚሰጣቸውና ከአለማዊ ትርጉማቸው በዘለቀ ትርጉም አላቸው የሚሉት ሚኒስትሯ በተለይም ታቦታቱ ለእምነቱ ተከታዮች መንፈሳዊ ጠቀሜታ አላቸው። "ለእነሱ ምንም ትርጉም የላቸውም፤ ለእኛ ግን መንፈሳዊ ሕይዎትም ናቸው። ስለዚህ እነዚህን በመመለሷ አንደኛ ሰብኣዊ መብትን ታከብራለች፣ ሁለተኛው ደግሞ ትልቋ ወዳጃችን እንግሊዝ ቅርሶቹን በመመለሷ ግንኙነታችንን ከወዳጅነት አልፎ ወደ ቤተሰብነት ያሳድገዋል። በሌሎች ሃገራት ዘንድም ትልቅ ተቀባይነት እንዲኖራት አስተዋጽኦ ያደርግላታል" ብለዋል ዶ/ር ሂሩት እንግሊዝም ሆነ የተለያዩ ቅርሶችን የዘረፉ የአውሮፓ ሃገራት እንደሚመልሱ ሲጠየቁ ኢትዮጵያውያንም ሆነ አፍሪካውያን ቅርሶቹን የሚያስጠብቁበት አሰራር የላቸውም የሚሉ ምላሾችን ይሰጣሉ። ኢትዮጵያ የሁሉም ነገር መገኛ የሆነችና በዓለም ላይ የሚገኙ ሁሉም የአየር ንብረት አይነቶችና ዝርያዎች ያሉባትና ብዙ ጥበቦችና የራሷ ፊደል ያላት ሃገር መሆኗን የሚናገሩት ሚኒስትረወ "የዓለም ሙዚየም ነች ብለን ስለምናምን ቅርስ ከኢትዮጵያ መወሰድ ሳይሆን ወደ ኢትዮጵያ ነው መምጣት ያለባቸው እንላለን" ብለዋል። በመሆኑም የዓለም ሙዚየም በመሆኗ ዓለም ሊጠብቃት ይገባል፤ ከዚህ አንጻር የቅርጹ መመለስ ተገቢ ነው ይላሉ ሚንስትሯ። •በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ ቅርሶቹም ሆነ የልዑሉ አፅም ቢመለስ የሚቀመጥበት ቦታ መዘጋጀቱንና ለዚህም ታላቁ ቤተ መንግሥትም እንደተመረጠ ዶ/ር ሂሩት ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪ አንዳንዶቹን ቅርሶች በሙዚየማቸው ለህዝብ እንዲጎበኙ ቢያደርጉም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው የተዘረፉት ታቦታት አንድ ቤት ተቆልፎባቸው ነው የሚገኙት። ሚኒስትሯም ስለ ታቦታቱ ጉዳይ አንስተው የእንግሊዝ መንግሥት ለመመለስ ቃል እንደገባላቸው ጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ "እኛም የምናደርገውን አድርገናን" ብለዋል ሚንስትሯ። ምንም እንኳን በሁለቱ መንግሥታት መካከል ቅርሶቹን ለማስመለስ ውይይቶች ቢጀመሩም አንዳንድ እክሎች አጋጥመዋል። እንደ ዋነኛ ችግር የሚያነሱት በእንግሊዝ ህግ መሰረት አንድ ወደ ሙዚየም የገባ ቅርስ ተመልሶ አይወጣም። ከዚያም ጋር ተያይዞ በውሰት ውሰዱ የሚል አማራጭ እንዳቀረቡላቸው ሚኒስትሯ በአግራሞት ገልፀዋል። "እንዴት የራሳችንን ኃብት እንዋሳል? ሰጥተናቸው ሳይሆን ተዘርፎ ነው የተወሰደው። ስለዚህ በህጋዊ መንገድ ነው መመለስ ያለበት" ብለዋል። •''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" ውሰቱም የመመለሻው ጊዘው ሳይገለፅ ላልተወሰነ ጊዜ ውሰዱ የሚል አማራጭ ያቀረቡ መሆቸውን ሚኒስትሯ ተናግረው ምን ማለትም እንደሆነ ያስረዳሉ። "በዚህ አረዳድ እነሱ እንደሚሉት 'ላልተወሰነ ጊዜ' የሚለው ሕጋቸውን ላለመጣስ እንጅ 'ጊዜው ስላልተገለጸ ላትመልሱ ውሰዱ' ማለት እንደሆነ ነግረውናል" ይላሉ ዶ/ር ሂሩት። ይህም ሆኖ ግን ችግሮች እንዳሉት ሚኒስትሯ አልደበቁም ቅርሶቹን በውሰት ለመስጠትም ኢንሹራን መግባትን እንደ መስፈርት ይጠይቃሉ። •ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን "ግን እሱን ማድረግ አልቻልንም፤ ምክንያቱም የተጠየቀው ከፍተኛ ገንዘብ ነው እነሱም 'ለእናንተ መውሰድ ለእኛ ግን ውሰት የሆነ ቃል አምጡና ህጋችንን አክብረን እንስጣችሁ' ብለውናል" የሚሉት ሚንስትሯ ይህንን ስምምነት የሚያሟላ ቃል ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሕጋቸውን ማስተካከል ካለባቸው እንዲያስተካክሉ ግፊት ለማድረግ እንደሚሞክሩ ሚኒስተሯ ተናግረው በበለጠ ግን እንግሊዝ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሊረዷቸው እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።