id
stringlengths 8
13
| url
stringlengths 36
41
| title
stringlengths 14
73
| summary
stringlengths 6
277
| text
stringlengths 318
10.6k
|
---|---|---|---|---|
48946713 | https://www.bbc.com/amharic/48946713 | የቀደመው ዘመናዊ ሰው ከአፍሪካ ውጪ ተገኘ | ተመራማሪዎች ከዘመናዊ ሰው ጋር ተቀራራቢ የሆነ ዝርያ ከአፍሪካ ውጪ አገኙ። | በግሪክ የተገኘው የራስ ቅል አውሮጳ በኒያንደርታሎች በተወረረችበት ወቅት 210 ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ነው ተብሏል። ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው፤ የሰው ልጅ ከአፍሪካ ወደ አውሮጳ ቅድመ ፍልሰት ስለማድረጉ ታሪክ ምንም አይነት የዘረመል ማስረጃ የለውም ለሚለው ሌላ አስረጅ ሆኖ ቀርቧል። ይህ ግኝት የታተመው 'ኔቸር' በተሰኘው ጆርናል ላይ ነው። ተመራማሪዎች በ1970ዎቹ በግሪክ አፒዲማ ዋሻ ውስጥ ሁለት ጠቃሚ ቅሪተ አካል አግኝተው ነበር። • ለባለስልጣናቱ ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ • "የለውጥ አመራሩን ሳይረፍድ ከጥፋት መመለስ ይቻላል" እስክንድር ነጋ አንዱ በጣም የተዛባ ሌላኛው ደግሞ ያልተሟላ ነበር። ቢሆንም ተመራማሪዎች የተለያዩ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የቅሪተ አካሉን ምስጢር ሊደርሱበት ችለዋል። ይህም ተመራማሪዎቹ በግሪክ ከዛሬ 210 ሺህ ዓመት በፊት ጥንታዊ ሰው በርከት ብሎ ይኖር ነበር እንዲሉ አስችሏቸዋል። ከአፍሪካ ውጪ የሚገኘው የዓለማችን ሕዝብ ከየት መጣሁ? ብሎ ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ ከአፍሪካ መፍለሱን ይናገራል። መቼ? ለሚለው ደግሞ ከ60 ሺህ ዓመት በፊት የተመራማሪዎች መልስ ነው። ይህ ዘመናዊ ሰው ወደ አውሮጳና እስያ ሲሄድ በመንገዱ ላይ ያገኛቸውን እነ ኒያንደርታልና ዴኒሶቫንስን እየተኩ መሄዳቸው ይታመናል። ነገር ግን ዘመኑ ጥንታዊ ሰው (ሆሞሳፒያንስ) ከአፍሪካ ወደ ሌሎች የዓለማችን ክፍል መፍለስ የጀመረበት የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም። የሆሞሳፒያንስ ቅሪተ አካል በ1990ዎቹ በእስራኤል ከስኩሁል እና ቃፍዜህ የተገኘ ሲሆን፤ እድሜውም ከ90 ሺህ እስከ 125 ሺህ ድረስ ተገምቷል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጥንታዊ ሰው ከአፍሪካ ወደ አውሮጳና ወደ እስያ ያደረገውን ፍልሰት በሚመለከት የሚደረጉ ጥናቶች ላይ አንዳንድ ፍንጮች እየተገኙ መሆናቸውን ተመራማሪዎች ያስረዳሉ። • የታገዱት ሞተረኞች እሮሮ እያሰሙ ነው ቻይና ውስት በዳኦክሲያንና ዝሂሬዶንግ የተገኘው ቅሪተ አካል እድሜው በ80 ሺህና በ120 ሺህ መካከል ተገምቷል። የዘረመል ጥናቶች ላይ ምርምር የሚያደርጉ ሰዎች፤ ከአፍሪካ የሄዱና ኒያንደርታሎች ተዳቅለው አግኝተናል ብለዋል። በጀርመኖቹ የኒያንደርታሎች መዳቀል የተፈጠረው 219 ሺህ እና በ460 ሺህ ዓመታት መካከል ነው። ነገር ግን አሁንም ሆሞሳፒያንስ መዳቀሉ ላይ ተሳትፈውበታል ወይስ ሌላ ጥንታዊ የአፍሪካ ቡድን አለ ለሚለው መልስ አልተገኘለትም። |
news-45022403 | https://www.bbc.com/amharic/news-45022403 | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በአሜሪካ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሰጡት ምላሽ | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት የሚገኙ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን በትልቅ መሰብሰቢያ ውስጥ አግኝተው ከነጋገሩ በኋላ በተዘጋጀ የእራትና የውይይት መረሃ ግብር ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ባለፉት አራት ዓመታት እንቅልፍ ተኝተው እንደማያውቁ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለፉ አስታውሰው በተለይ ከአራት ወራት በፊት የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው እንደነበርም ተናግረዋል። የእስር ማዘዣው ከየትኛው ወገን እንደመጣ በግልፅ ባይናገሩም ከሀገር እንዲወጡ የሚያስገድዱ ጫናዎች እንደነበሩም ጠቁመዋል። "እኛም አንወጣም ብለን እዚያው የሚመጠውን ሁሉ ለመጋፈጥ ቆርጠን ቆይተናል ምክንያቱም ከሃገር የወጡ አልተመለሱም። ለዚህም ነው እዚህ ቦታ ላይ ልንደርስ የቻለው" ብለዋል። • ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መቼ አገር ቤት ይገባሉ? • 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ጉዞ ተጠናቀቀ በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከታዳሚው ለቀረቡላቸው የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሌ ክልልን በተመለከተ በኢትዮጵያ ያሉት ሶማሌዎች ብቻ ሳይሆን ሞቃዲሾ ያለውም ጭምር ዴሞክራሲን እንዲተገብርና ከኢትዮጵያዊያንና በተለይ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ተሳስሮ መኖር አለበት ብለን በጽኑ እናምናለን በማለት ጀምረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ክልሉ መሪ ያስፈልገዋል፤ ክልሉ የልብ አንድነት ያስፈልዋል። ብዙዎቻችሁ ላታስተውሉት ትችላላችሁ ግን አፍሪካ በብዙ ጅብ መንግሥታት የተያዘች አህጉር ናት። እነዚህን መንግሥታት ከጎረቤት አስቀምጠን ኢትዮጵያ ላይ ዴሞክራሲ፤ ኢትዮጵያ ላይ ሰላም ማምጣት አይቻልም። አፍሪካ የሚገባትን ክብር እንድታገኝ በጋራ መስራት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በቂ ጭንቅላት አላት፤ 100 ሚሊዮን ምርጥ ጭንቅላት። ይህንን በማውጣት መስራት ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የሶማሌ ክልልን በተመለከተ በመንግስት በኩል ሪፎርም እየሰራ እንደሆነና ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል። ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? • ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ በኦሮሞና በሶማሌ መካከል የተነሳውን ግጭት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ "ኦሮሞና ሶማሌ አንድ ቤተሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ማንም ምንም አለ አብሮ ተጋግዞ መስራት ብቻ ነው የሚያዋጣው ብለዋል።" በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ ''በመጀመሪያ ትኩረተ የሰጠነው ዋነኛው ነገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ላይ ነው። ለዚህም ነው በፍጥነት የአውሮፕላን ጉዞ ያስጀመርነው፤ የሚያገናኙንን መንገዶች እየጠገንን ያለነው። ስለዚህ ህዝቡ ተገናኝቶ ሰላሙን መመስረት ከቻለ መንግሥት ደግሞ ይከተላል ማለት ነው።'' ''እንኳን ለመታረቅ ለመዋጋትም ከዚህ በፊት ውክልና አልሰጠንም። ስንዋጋም ሃገር የሚመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ተዋጉ ሲል ተዋጋን እንጂ በውክልና አልተዋጋንም። የትግራይን ህዝብ ሳናካትት ምንም አይነት ለውጥም ሆነ እድገት ማሳካት አንችልም፤ አንፈልግምም።" "ከትግራይ ህዝብ ውጪ ኢትዮጵያን የመቀየር ሃሳብ የለንም። ህዝቡ ያሳዝነናል፤ ህዝቡ ይቆረቁረናል። የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ጉዳይ ግድ አይሰጠውም ማለት አንችልም ምክንያቱም በባድመ ጦርነት ከማንም በላይ የሞቱት የኦሮሚያ ልጆች ናቸው።" የሰላሙ ጉዳይ ለህዝባችን ስለሚጠቅም፣ የኤርትራ ህዝብ የሰላም ህዝብ ስለሆነ፣ የትግራይ ህዝብ ደግሞ የሚጠቀመው ከዚህ ሰላም ስለሆነ ሌላውን ትተን አንድ ሆነን እንስራ የሚለውን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ፀጉረ ልውጦች እነማን ናቸው? "ፀጉረ ልውጦች የተወሰኑ የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው ብሎ ማሰብ በመሰረቱ የተሳሳተ ነው" በማለት የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የትግራይ ህዝብ ኦሮሚያ ወይም አማራ ክልል ውስጥ ፀጉረ ልውጥ ሊሆን አይችልም።" ብለዋል። "ኦሮሚያ ውስጥ ትግሬም ይሁን አማራ፤ ወላይታም ይሁን ጉራጌ፤ ህዝቡ ማንንም አቅፎ ለማኖር ፈቃደኛ ነው። እንደውም እኔና የወከልኩት ኦህዴድ ብዙ ችግር አለብን። የኦሮሞ ህዝብ ግን አቃፊ ነው። በእኛ መነጽር፤ በእኛ ልክ ህዝቡን አትለኩት። ህዝቡ እንደእኛ አይደለም፤ ህዝቡ ከእኛ የላቀ ብስለት ያለው ነው።" "ፀጉረ ልውጥ ያልኩት በፍጹም አንድን ቡድን በሚገልጽ መልኩ ሳይሆን፤ የሚሰማሩ ሃይሎች ስለነበሩ መረጃው ስላለኝ ነው እንጂ የሆነ ቡድን ፀጉረ ልውጥ ሌላኛው ደግሞ ንጹህ ለማለት አይደለም። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ውጥረት ማንኛውም ነገር ለፖለቲካዊ ጥቅም ሊውል ይችላል።" ባለፉት 27 ዓመታት የተሰራው ጥፋት ወይስ ልማት? ''ያለፉት 27 ዓመታ ብዙ ቆሻሻ ነገር የተሰራበት ዘመን ነው። ልማት ማለት አስፓልት፤ ልማት ማለት ኮንዶሚኒየም የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። መሰረተ ልማት ያለ ውስጣዊ ሥርዓት ምንም ጥቅም የለውም። ምክንያቱም እርስ በእርሱ የማይነጋገር ህዝብ፤ እርስ በእርሱ የማይግባባ ህዝብ ፈጥረን ስናበቃ አስፓልት ሰርተንልሃል የምንል ከሆነ ተገቢ አይደለም'' ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኘው ልማት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተገኘው ሰላም ባለቤቱ ህዝብ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ለጠፋው ጥፋት ግን ተጠያቂው መንግሥት ነው። ጥሩ ነገር ሲሰራ ሃላፊነት የምንወስድ፤ ጥፋት ሲጠፋ ደግሞ የምንሸሽ አክራሪዎች አይደለንም እኛ፤ መንግሥት ነን። እስከ ዛሬ ለጠፉ ጥፋቶች በሙሉ ኢህአዴግ እንደ መንግሥት ሃላፊነቱን ወስዶ ህዝቡንም ይቅርታ ጠይቋል። ይሄ ሁሉ ግን በይቅርታ ብቻ የሚያልፍ አይደለም። ባለፉት 27 ዓመታት ለገረፍናችሁ፣ ላባረርናችሁ፣ ላስቸገርናችሁ ሰዎች እኔ እንደ ኢህአዴግ ከልብ ይቅርታ እጠይቃችኋለው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። |
news-56304723 | https://www.bbc.com/amharic/news-56304723 | ዩኬ ለየመን የምትሰጠውን እርዳታ መቀነሷን የረድኤት ድርጅቶች አወገዙ | የረድዔት ድርጅቶች የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በየመን ላይ ያደረገውን የእርዳታ ቅነሳ አወገዙ። | በመቶ የሚቆጠሩ የረድዔት ድርጅቶች ተቀባይነት የለውም በሚልም ነው ያወገዙት። በዘንድሮው ዓመት ለመካከለኛ ምስራቋ አገር፣ የመን 87 ሚሊዮን ፓውንድ እርዳታ እንደሚሰጥ እንግሊዝ ቃል ገብታለች። ከአመት በፊት የነበረው ዕጥፍ ፣ 164 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ በበኩላቸው መንግሥታቸው የየመንን ህዝብ ለመርዳት የገባውን ቃል አያጥፍም ብለዋል። ነገር ግን የመን ከመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ አገራት መካከል የዩኬ እርዳታ ሊያሽቆለቁልባት ይችላል ከተባሉት ዋነኛዋ እንደሆነች ሾልኮ የወጣ ኢ-ሜይል አስታውቋል። በመጀመሪያ ጉዳዩን ሪፖርት ያደረገው ኦፕን ዲሞክራሲ እንዳስታወቀው በባለፈው ወር ከመንግሥት ባለስልጣናት ሾልኮ የወጣ መረጃን መሰረት አድርጌያለሁ በማለት በሶሪያ 67 በመቶና በሊባኖስ 88 በመቶ እርዳታ ይቀንሳል ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በናይጄሪያ 58 በመቶ፣ በሶማሊያ 60 በመቶ፣ በደቡብ ሱዳን 59 በመቶና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 60 በመቶ እርዳታ እንደሚቀንስ አስነብቧል። እነዚህ የረድዔት ድርጅቶች ለመሪው ቦሪስ ጆንሰን በፃፉት ደብዳቤ ህዝቡ በድህነት፣ በበሽታና በጦርነት የተጠቁ አገራትን ፊቱን ገሸሽ ያደርጋል ብሎ መንግሥት ማሰቡ ስህተት ነው ብለዋል። "የዩኬ መንግሥት በዚህ ወቅት የየመንን ህዝብ ችላ ብሎ የማይረዳ ከሆነ ታሪክ በጥሩ መልኩ አይዳኘውም። ከዚህ በተጨማሪ ለተቸገሩ አገራት አለሁ በማለት የምትረዳውን የዩናይትድ ኪንግደም አለም አቀፍ ስም የሚያጠለሽ ነው" ይላል ደብዳቤው ኦክስፋም፣ ክርስቲያን ኤይድ፣ ሴቭ ዘ ችልድረን፣ ኬር ኢንተርናሽናልን ጨምሮ 101 ድርጅቶች ናቸው ተቃውሟቸውን ያስገቡት። የእንግሊዙ ኦክስፋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዳኒ ስሪስካንዳራጅ እንዳሉት "ምጣኔ ኃብታችን ተጎድቷል በሚል የሚደረግና የበርካታ ሚሊዮናውያንን የመኖችን ህይወት የሚነጥቅ የእርዳታ ቅነሳ ሃሰተኛ ኢኮኖሚ ነው። በርካቶች ቤተሰቦቻቸውን መመገብ አልቻሉም፤ ቤታቸውን አጥተዋል፤ በኮሮናቫይረስና በግጭት ምክንያትም ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ እንዲህ በጦርነት በምትበጠበጥ አገር ላይ የጦር መሳሪያ በመሸጥ "'ኢ-ሞራላዊ' ተግባር እንዲታቀብ አስጠንቅቀዋል። |
news-47851138 | https://www.bbc.com/amharic/news-47851138 | በሰሜን ሸዋ በተከሰተ ግጭት ህይወት ጠፍቷል ንብረት ወድሟል | ቅዳሜና እሁድ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመ ግጭት ሰዎች መሞታቸውንና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ። | በባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ተከስቶ ውጥረት ቅዳሜ እለት ተቀሰቅሶ እሁድም በቀጠለው ግጭት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት መጥፋቱንና በርካቶች መቁሰላቸውን የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸው በቀለ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። • አወዛጋቢው ግጭት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከንቲባው ጨምረውም በግጭቱ የታጠቁ ኃይሎች መሳተፋቸውንና የዘረፋ ድርጊትም ተከስቶ እንደነበር ተናግረው ክስተቱ ከክልሉ ልዩ ኃይል አቅም በላይ በመሆኑ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እንዲገባ መደረጉንም አመልክተዋል። ግጭቱ ከአጣዬ ባሻገር በካራቆሬ፣ በማጀቴና በዙሪያቸው ባሉ አካባቢዎች መከሰቱን የተናገሩት ነዋሪዎች በቡድን የተደራጁ ታጣቂዎች በድርጊቱ ተሳታፊ እነደሆኑም ተናግረዋል። በጥቃቱ በሰው ህይወት ላይ ከደረሰው ጉዳት ባሻገር "በቤተ እምነቶች፣ በግለሰብ መኖሪያና በንግድ ተቋማት ላይ" ጥቃት መፈጸሙን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። • በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የሰው ህይወት መጥፋቱ ተሰማ የአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ምክትል ኅላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ እንደተናገሩት ከእሁድ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢዎቹ በመግባታቸው ሁኔታዎች መረጋጋታቸውን ተናግረዋል። ኅላፊው የፀጥታ ጨምረውም በተደራጀ ሁኔታ በመታጠቅ የሕዝብን ሰላም እያደፈረሰ ያለውን ቡድን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የተቀናጀ ሥራ እንደሚከናወንም ገልጸዋል። በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በየአካባቢው በሚገኙ የጤና ተቋማት ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን ከፍተኛ ህክምና የሚያስፈልጋቸውንም ወደሌሎች አካባቢዎች እንደተወሰዱ ተገልጿል። • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) እሁድ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ባጋጠሙ ግጭቶች በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የግጭቱን ምክንያት እና ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በተመለከተ በማጣራት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል። የአካባቢውን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ አመራሮች ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየሠሩ መሆኑን አመልክተው፤ በቀጣይም ከፌደራልና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር እንደሚሠራ ገልጸዋል። |
news-54187347 | https://www.bbc.com/amharic/news-54187347 | የናይጄሪያዋ ግዛት ደፋሪዎች እንዲኮላሹ በህግ ፈቀደች | የናይጄሪያዋ ካዱና ግዛት ደፋሪዎች በህክምና እንዲኮላሹ ህግ አፅድቃለች። | የግዛቷ አስተዳዳሪ ናስር አህመድ ኤል ሩፋይ ባለፈው ሳምንት የቀረበላቸውን ረቂቅ ህግ በትናንትናው እለት በመፈረም አፅድቀውታል። ህጉ ከአስራ አራት አመት በታች ያሉ ህፃናትን የደፈሩ እንዲኮላሹ ብቻ ሳይሆን የሞት ፍርድንም አካቷል። የተደፈሩት ደግሞ ከአስራ አራት አመት በላይ ከሆኑ በህክምና እንዲኮላሹ እንዲሁም የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ህፃናትን የሚደፍሩ ሴቶችም ቢሆኑ የማህፀን ቱቧቸው እንዲወገድ የሚደረግ ሲሆን የሞት ቅጣትም በተጨማሪ ተካቶበታል። የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸው ከአስራ አራት አመት በታች ያሉ ህፃናት በአባሪነት የህክምና ሪፖርት ማምጣት ይኖርባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ህፃናትን የሚደፍሩ ሰዎች ዝርዝርም በሚዲያ እንደሚወጣና ለህዝቡም ይፋ ይሆናል ተብሏል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ በትናንትናው ዕለት ረቂቅ ህጉ ላይ መፈረማቸውንና ህግ ሆኖም እንደፀደቀ ያስታወቁት በትዊተር ገፃቸው ነው። በናይጄሪያ ካሉ ግዛቶች መካከል እንዲህ አይነት ህግ በማፅደቅ ካዱና ቀዳሚ ሆናለች። የናይጀሪያ ፌደራል መንግሥት ደፋሪዎችን ከአስራ አራት አመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ቢቀጣም ግዛቶች ግን የራሳቸውን ህግ ማውጣት ይችላሉ። የተደፈሩ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በማህበረሰቡ ካለው ተጠቂዎችን ጥፋተኛ ከማድረግ እሳቤ አንፃር ብዙዎች ደፍረው ወደ ህግ ቦታ አይሄዱም። ደፍረው ሪፖርት ያደረጉትም ቢሆን ክስ ተመሰርቶ የሚፈረድባቸውም ጥቂቶች ናቸው። በሰኔ ወር ላይ በርካታ የናይጄሪያ ግዛት አስተዳዳሪዎች እየጨመረ የመጣውን የሴቶች መደፈርና ጥቃት አስመልክቶ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተላልፈው ነበር። በናይጄሪያ ከጎርጎሳውያኑ 2015 ጀምሮ የተፈረደባቸው 40 ደፋሪዎች ብቻ እንደሆኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል። አገሪቷም ህጓን አሻሽላለች። የመድፈር ክስን አስቸጋሪ የሚያደርገው አቃቤ ህግ ማስረጃ ማምጣት ስለሚኖርበት አድካሚና ቴክኒካል ጉዳዪ የተወሳሰበ እንደሚያደርገው ይነገራል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የተጣለው የእንቅስቃሴ መገደብም የሚደፈሩ ሴቶችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል። በሃምሌ ወር የ22 አመት እድሜ ያላት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ተደፍራ መገደሏ ከፍተኛ ቁጣን ፈጥሯል። ይህንንም ተከትሎ ናይጄሪያውያን ንዴታቸውን ለመግለፅ ጎዳና ላይ ወጥተዋል፤ 'ዊ አር ታየርድ' (ደክሞናል) በሚልም በትዊተር ላይ ዘመቻ ተጀምሮም ነበር። በርካቶችም የሞት ቅጣትን ጨምሮ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲወጣም ጠይቀዋል። በህክምና የማኮላሸት ቅጣት በአንዳንድ አገራት ተግባራዊ ቢሆንም አወዛጋቢ ነው። |
48701205 | https://www.bbc.com/amharic/48701205 | በጋሪሳ ዩኒቨርስቲ ጥቃት ለ148 ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የተባሉ ሶስት ሰዎች ተፈረደባቸው | ሶስት ግለሰቦች የዛሬ አራት ዓመት በኬንያ ጋሪሳ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ ተከሰው ፍርድ ተበይኖባቸዋል። | ራሺድ ቻርልስ ምቤሬሶ፣ ሞሐመድ ዓሊ አቢካር እና ሃሳን ኤዲን ሃሳን የተሰኙት እኒህ ግለሰቦች የጋሪሳውን ጥቃት ካቀነባበሩ መካከል ናቸው ተብለው ነው ፍርድ የተሰጠባቸው። አራት የታጠቁ ሰዎች ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ገብተው 148 ተማሪዎችንና ሠራተኞች ነፍስ ያጠፉት በጎርጎሳውያኑ 2007 ላይ ነበር። • ኬንያ ሺሻን አገደች ግለሰቦቹ የአል-ሸባብ አባል ናቸው በሚልም ነው ፍርድ የተሰጠባቸው። አራተኛው ተከሳሽ ግን ነፃ ሆኖ በመገኘቱ ሊለቀቅ እንደቻለ ታውቋል። ነፃ የወጣውን ግለሰብ ጨምሮ ሶስቱ ግለሰቦቹ ኬንያውያን ሲሆኑ ራሺድ ቻርልስ የተባለው ግለሰብ ታንዛኒያዊ እንደሆነ ታውቋል። ራሱን የአል-ቃይዳ ክንፍ አድርጎ የሚቆጥረው አል-ሸባብ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2007 ላይ ለተከሰተው የጋሪሳው ጥቃት ኃላፊነት መውሰዱ አይዘነጋም። በጎርጎርሳውያኑ አቆጣጠር 1998 ላይ አል-ቃይዳ የአሜሪካን ኤምባሲ አጋይቶ 200 ሰዎች ካለቁበት ክስተት በኋላ ሁለተኛው አሰቃቂ ጥቃት ነው የጋሪሳው እልቂት። • ኬንያ ሜሪ ስቶፕስን አገደች የቢቢሲው ኢማኑዔል ኢጉንዛ ፍርዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ነው ይላል፤ ከጥቃቱ ለተረፉ ትልቅ ትርጉም እንዳለው በመጠቆም። ለአራት ዓመታት ያክል የቆየው የፍርድ ሂደት የኬንያውያንን በተለይ ደግሞ ከጥቃቱ የተረፉትን ልብ አንጠልጥሎ የቆዬ እንደነበር ነው ኢጉንዛ የሚያስረዳው። መጋቢት 24/2007 ላይ በጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገር አማን ብለው ሳለ የደረሰው ጥቃት ጥበቃዎችን፣ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ሠራተኞችን ጨምሮ የ148 ሰዎችን ነፍስ ቀጥፏል። 500 ገደማ ተማሪዎች ደግሞ ጥቃቱን በመሸሽ ማምለጥ ችለዋል። 97 ግለሰቦች ደግሞ ክፉኛ አደጋ ደርሶባቸዋል። • 22 ኢትዮጵያዊያን ናይሮቢ ውስጥ ተያዙ |
45675456 | https://www.bbc.com/amharic/45675456 | የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ብሬት ካቭና የፍርድ ቤት ውሎ | በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃለቃነት ከወራት በፊት የታጩት ዳኛ ብሬት ካቭና በወሲባዊ ጥቃት ተጠርጥረዋል። | ጉዳዩ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን አፍ ማሟሻ ከሆነ ቢሰነባብትም በስተመጨረሻ ወደ ሃገሪቱ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት ደርሷል። ጥቃቱን አድርሰዋል የተተባሉት ዕጩ ብሬት እና ወሲባዊ ጥቃት ደርሶብኛል ያሉት ዶ/ር ክርስቲን ብላሲ ፎርድ በሴናቶሮች ፊት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ዳኛ ብሬት ካቭና ወሲባዊ ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲሉ ስሜታዊነት በተሞላበት መልኩ ክሱን አጣጥለዋል። •የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች ከሳሽ ዶ/ር ክርስቲን ፎርድ በበኩላቸው ሰውየው ከ30 ዓመታት በፊት ያደረሱባቸው ወሲባዊ ጥቃት ሕይወታቸውን ክፉኛ እንዳመሳቀለው አስረድተዋል። • የጎንደር ሙስሊሞች እና የመስቀል በዓል ፕሬዝደንት ትራምፕ ብሬት 'ሃቀኛ' ናቸው ሲሉ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት በዕጩነት ያቀረቧቸውን ሰው ደግፈው ታይተዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተሮች 'አጥፊ' የሆነ ዕቅድ የኮነኑ ሲሆን የተከሳሽን መልካም ስም እያጎደፉ ነው ሲሉም ወቀሳ ሰንዝረዋል። የሴናተሮች ሕግ ተርጓሚ ኮሚቴ በብሬት ካቭና ዕጩነት ዙሪያ ድምፅ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ይዟል፤ ምንም እንኳ ሪፐብሊካኑ ሙሉ በሙሉ ለሰውየው ድምፃቸውን መስጠታቸው ቢያጠራጥርም። ጠቅላላ ሴናተሮች በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ተሰባስበው በሰውየው ዕጣ ፈንታ ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል። የ51 ዓመቷ ዶ/ር ክርስቲን ፎርድ እንባ እየተናነቃቸው ነበር ቃላቸውን ለምክር ቤቱ አባላት ያሰሙት። • በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ ደርሷል ተባለ «እዚህ የተገኘሁት ወድጄ አይደለም» ሲሉ የተደመጡት ዶ/ር ክርስቲን «ፍራቻ ውስጥ ነኝ፤ እዚህ የተገኘሁት የዜግነት ግዴታዬን ለመወጣት ነው፤ ብሬት እና እኔ ትምህርት ቤት እያለን የገጠመኝን ለሁሉም ለማሳወቅ ነው» ሰሉ አክለዋል። ከሳሽ የ15 ዓመት ታዳጊ ሳሉ የ17 ዓመቱ ብሬት እና ጓደኛው መኝታ ቤት ውስጥ ቆልፈውባት ልብሷን በማወላለቅ ሊደፍሯት እንደሞከሩ እና እንደተሳለቁባት ቃላቸው ሰጥተዋል። ጉዳዩ ከበርካታ ዓመታት በፊት ስለሆነ ምናልባት ተሳስተው ከሆነ ተብለው ሲጠየቁ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሲሉ ተናግረዋል። ተከሳሽ በበኩላቸው «እኔ ዶ/ር ክርስቲንንም ይሁን ሌላ ሰው ላይ ወሲባዊ ጥቃት አላደርስኩም» ሲሉ ክሱን ክደዋል። ከሳሽ ባስቀመጡት ቦታ ላይ አለመገኘታቸውን ነው ለሴናተሮቹ ያሳወቁት። • ቢል ኮዝቢ ወደ ዘብጥያ ወረዱ |
news-46601907 | https://www.bbc.com/amharic/news-46601907 | ለፖለቲካ ፍላጎት የተጋጋለ ግጭት ነው፡ ሙስጠፋ ኡመር | የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ኡመር የግጭቱን መንስዔ ሲያስረዱ፤ በግጦሽ መሬት ሰበብ ከኃይለስላሴ መንግሥት ጀምሮ በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰቱ እንደነበረ አስታውሰው፤ ''ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ግን ሆነ ተብሎ የፖለቲካ ፍላጎት ተጨምሮበት የተጋጋለ ግጭት ነው'' ይላሉ። | ከጥቂት ዓመታት በፊት ተቀስቅሶ የነበረውን የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ለማዳከም በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች የሶማሌ ፖሊስን አንቀሳቅሰው በኦሮሚያ እና ሶማሌ ደንበር አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድረሰዋል ይላሉ አቶ ሙስጠፋ ኡመር። • ፓርቲዎች የምርጫ ቦርድን በሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከሩ ነው ከዚህ በፊት የነበረው ግጭት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነበረ። በግጭቱ የተጎዱ በሁለቱም በኩል ያሉት ኃይሎች ቁጭት እና ንዴት ስላለባቸው ግጭት እንዲቀጥል እያደረጉ ነው። አሁንም ግጭቱ እንዲቀጥል የሚያደርጉት እነርሱ ናቸው ይላሉ ሙስጠፋ ኡመር። ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር በሚያዋስነው አካባቢ ዋነኛዋ ከተማ በሆነችው ሞያሌ፤ የግጭት፣ የሞት እና የመፈናቀል ዜና መስማት እየተለመደ የመጣ ይመስላል። ነዋሪዎቿም በፍርሃት እና በሽብር መኖር ከጀመሩ ወራትን አስቆጥረዋል። መንግሥት ''በስህተት የተፈጸመ ነው'' ብሎ ከ10 በላይ ንጹሃን ነዋሪዎቿ ህይወታቸውን ያጡባት፤ በከተማዋ የሚኖሩ የኦሮሞ እና ሶማሌ ወጣቶች በሞያሌ ከተማ አስተዳደር ባለቤትነት ጥያቄ በድንጋይ የሚወጋገሩባት፤ ከፍ ሲልም በይዞታ ይገባኛል ምክንያት በጦር መሳሪያ የታገዙ ኃይሎች የሚፋለሙባት ግጭት፣ ሞት እና መፈናቀል የማያጣት ከተማ ሆናለች። እንደ አዲስ ከሁለት ሳምንታት በፊት በተቀሰቀሱ ግጭቶችም በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቆስለዋል፣ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። • "በምን ማስተማመኛ ነው የምንመለሰው" የሞያሌ ተፈናቃዮች ከዓይን እማኞች፣ ከጎሳ መሪዎች እና ከአካባቢው ባለስልጣናት እንደሰማነው ከሆነ ቢያንስ እንደ አዲስ ባገረሹት ግጭቶች እስካሁን ከ20 ሰዎች በላይ ተገድለዋል። የሰሞኑ ግጭት የተቀሰቀሰው ኦሮሚኛ ቋንቋ ተናገሪ በሆኑት ገሪ ተብለው በሚታወቁት የሶማሌ ጎሳ አባላትና በኦሮሞዎች መካከል በይዞታ ይገባኛል ምክንያት ነው። በኦሮሞ በኩል ያሉት የሞያሌ ወረዳ ኃላፊዎች ድንበር ተሻግረው በከባድ መሳሪያ ህዝቡ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙት የሶማሌ ታጣቂዎች ናቸው ይላሉ። በሶማሌ ወገን ያሉት በበኩላቸው ለግጭቱ፣ ለሞትና መፈናቀሉ የኦሮሞ ታጣቂዎች ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ኡመር የግጭቱን መንስዔ ሲያስረዱ፤ በግጦሽ መሬት ሰበብ ከኃይለስላሴ መንግሥት ጀምሮ በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰቱ እንደነበረ አስታውሰው፤ ''ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ግን ሆነ ተብሎ የፖለቲካ ፍላጎት ተጨምሮበት የተጋጋለ ግጭት ነው'' ይላሉ። • በሞያሌ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ የሰው ህይወት ጠፋ ከጥቂት ዓመታት በፊት ተቀስቅሶ የነበረውን የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ለማዳከም በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች የሶማሌ ፖሊስን አንቀሳቅሰው በኦሮሚያ እና ሶማሌ ደንበር አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድረሰዋል ይላሉ አቶ ሙስጠፋ ኡመር። ከዚህ በፊት የነበረው ግጭት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነበረ። በግጭቱ የተጎዱ በሁለቱም በኩል ያሉት ኃይሎች ቁጭት እና ንዴት ስላለባቸው ግጭት እንዲቀጥል እያደረጉ ነው። አሁንም ግጭቱ እንዲቀጥል የሚያደርጉት እነርሱ ናቸው ይላሉ ሙስጠፋ ኡመር። ''ሞያሌን እንደ ሞቃዲሾ'' አቶ አሊ ጠቼ የሞያሌ ወረዳ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ ናቸው። አቶ አሊ ሞያሌ ከተማ ከዘርፈ ብዙ ችግሮቿ ጋር ብዙ ዓመት ተሻግራለች ይላሉ። አቶ አሊ ከሳምንታት በፊት ለተቀሰቀሰው ግጭት ጽንፈኛውን ቡድንን አልሸባብን ጭምረው ተጠያቂ ያደርጋሉ። ''አልሸባብ እንዲሁም ከሶማሌ ልዩ ፖሊስ እና ከሃገር መከላከያ ያፈነገጠ ኃይል ከባድ የጦር መሳሪያ በመጠቀም ሞያሌን እንደ ሞቃዲሾ አደረጓት'' ይላሉ። • በርካታ ሰዎች ከሞያሌ በመሸሽ ወደ ኬንያ ገብተዋል ጉዳዩን ለክልል እና ፌደራል መንግሥት ቢያሳውቁም በቂ ምላሽ አለማግኘታቸውን እና በሞያሌ ሰፍሮ የሚገኘውም የሃገር መከላከያ ሠራዊት ግጭቱን ማስቆም እንዳልቻለም ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከአምስት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ግጭቱ እንዲከሰት የሚያደርጉት የሁለቱን ክልሎች መረጋጋት የማይሹ ኃይሎች ናቸው፤ ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብሏል። መግለጫው አክሎም በግጭቱ ለተጎዱ ሰዎች አስፈላጊው እርዳታ እየተሰጠ መሆኑን አመልክቷል። ''የፖለቲካ ጦርነት'' የሶማሌ ገሪ ጎሳ መሪ የሆኑት ሱልጣን ሞሐመድ ሃሰን በበኩላቸው ''ሁለቱ ህዝቦች [ገሪ እና ኦሮሞ] ከዚህ ቀደምም በይዞታ ይገባኛል ይጋጩ ነበረ። ይህ አዲስ አይደለም። ይህ ግጭት ግን የይዞታ ይገባኛል ሳይሆን የፖለቲካ ጦርነት ነው'' ይላሉ። ሱልጣን ሞሐመድ እየደረሰ ላለው ጥፋት የኦሮሞ ታጣቂዎችን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ''ድንበር ተሻግረው እየወጉን ያሉት እነሱ [የቦረና ኦሮሞ] ናቸው። እኛ እራሳችንን መከላከል ነው የያዝነው። መብታችንን እየተጋፉ ነው። በትልልቅ ጦር መሳሪያዎች የሚወጉን፣ ቤታችንን የሚያቃጥሉት እነሱ ናቸው።'' ይላሉ። • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች ሱልጣን ሞሐመድ እንደሚሉት ከሆነ፤ የፌደራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት ግጭቱን በውይይት ለመፍታት ሞያሌ ላይ ስብሰባ ቢጠሩንም በስብሰባው ላይ የኦሮሞ ተወካዮች በእምቢተኝነት ሳይገኙ ቀርተዋል ይላሉ። ''ምንም እንኳ እነሱ ስበሰባው ላይ ባይገኙም፤ እኛ ሰላም ነው የምንፈልገው ስንል ተናግረናል። ከዚያ በኋላም አዲስ አበባ ላይ ለስብሰባ ተጠርተን አባ ገዳው [የቦረና አባ ገዳ] ሳይገኝ ቀረ። የመጡትም ተወካዮች [የኦሮሞ ተወካዮች] ሰላም አንቀበልም ብለው ሄዱ'' ይላሉ። የቦረና አባ ገዳ ምን ይላሉ? ''የቦረና መሬትን የሸጠው መንግሥት ነው። የግጭቱ መንስዔ መንግሥት ነው። ችግሩን መፍታት ያለበትም መንግሥት ነው'' የሚሉት የቦረና አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ናቸው። ''ሞያሌ ውስጥ ሁለት ባንዲራዎች [የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል ባንዲራዎች] እስከተውለበለቡ ድረስ በከተማዋ ሰላም ሊሰፍን አይችልም።'' አባ ገዳ ኩራ፤ ሶማሌዎች ዳዋ የሚባል ወረዳ መስርተው ሞያሌን የወረዳው ከተማ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት ማቆም አለባቸው ይላሉ። "በ1997 ዓ.ም ላይ ተካሂዶ የነበረው ህዝበ ውሳኔ ሳይሆን የመሬት ዘረፋ ነበረ" የሚሉት አባ ገዳ ኩራ መንግሥት ታሪክ ተመልክቶ ውሳኔዎችን ያስተላልፍ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በግጭቱ በመኖሪያ ቤቶች፣ በመንግሥት ቢሮዎች እና ባንኮችን ጨምሮ በንግድ ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱንም የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። |
news-49982797 | https://www.bbc.com/amharic/news-49982797 | በአፍሪካ የመጀመሪያው ስማርት ስልክ ማምረቻ ፋብሪካ በሩዋንዳ ተከፈተ | ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያውን ስማርት ስልክ ማምረቻ ከፈተች። ፋብሪካው በዋና ከተማዋ ኪጋሊ የሚገኝ ሲሆን በምረቃው ላይ ፕሬዚደንት ፓል ካጋሜ ተገኝተዋል። | በማራ ግሩፕ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ማራ ኤክስና ማራ ዜድ ስማርት ስልኮችን የሚያመረተው ይህ ፋብሪካ ስልኮቹ የጎግልን አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንደሚጠቀሙ ተናግሯል። ስልኮቹ 5500 ብርና 3700 ብር አካባቢ ዋጋ ተተምኖላቸዋል። • እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት • ራስዎን ካላስፈላጊ የስልክ ጥሪ እንዴት ይታደጋሉ? ሰኞ ዕለት ፋብሪካውን ጋዜጠኞች ተዟዙረው እንዲጎበኙ ከተደረገ በኋላ "ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያው ስማርት ስልክ ማምረቻ ነው" ብለዋል የማራ ግሩፕ የበላይ ኃላፊ አሺሽ ታካር ለሮይተርስ። ታካር አክለውም ፋብሪካው ዒላማው ያደረገው ጥራት ላይ መሠረት አድርገው ለመክፈል የተዘጋጁ ግለሰቦችን ነው። በአፍሪካ ውስጥ ከሚሸጡ በርካታ ስልኮች መካከል አብዛኞቹ የሚመጡት ከቻይና ነው። እነዚህ ስልኮች ሁለት ሲም የሚወስዱ እንዲሁም ማራ ግሩፕ ከተመነው ዋጋ ባነሰ ለቀበያ የሚቀርቡ ናቸው። በኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ አልጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የተለያዩ መለዋወጫዎችን ከቻይና በማስመጣት የሚገጣጠሙ ስማርት ስልኮች እንዳሉ ሚስተር ታከር ይናገራሉ። "እኛ በማምረት ደረጃ የመጀመሪያዎቹ ነን። ማዘር ቦርዱን፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ንዑሳን ክፍሎቹን የምናመርተው እዚሁ ነው። በእያንዳንዱ ስልክ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን ነገሮች አሉ" ሲሉ ተናግረዋል። በቀን 1200 ስልኮችን ያመርታል የተባለው ይህ ፋብሪካን ለማቋቋም 24 ሚሊየን ዶላር እንደወጣበት ተነግሯል። ፕሬዝዳንት ካጋሜ ፋብሪካው የሩዋንዳውያንን ስማርት ስልክ ተጠቃሚነት እንደሚጨምር ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል። በአሁኑ ሰዓት በሩዋንዳ ከሚገኙ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች 15 በመቶው ብቻ ስማርት ስልክ ይጠቀማሉ። |
news-55905197 | https://www.bbc.com/amharic/news-55905197 | ጃክ ፓላዲኖ፡ የቢል ክሊንተን የትዳር መማገጥ ዜናን ያድበሰበሰው ሰው አስገራሚ አሟሟት | ዕውቁ የዝነኞች የግል መርማሪ በካሜራው ምክንያት ገዳዮቹን አጋለጠ። | ጃክ ፓላዲኖ ይባላል፡፡ ትናንትና 76 ዓመቱ ነበር፡፡ ዛሬ እንኳ የለም፡፡ በአሜሪካ ዕውቅ የግል ወንጀል መርማሪና ጉዳይ አስፈጻሚ ነበር፡፡ ባለፈው ሐሙስ ለታ ወንበዴዎች ድንገት ያዙት፡፡ ሳንፍራንሲስኮ በሚገኘው ቤቱ ደጅ ላይ ነው ማጅራቱን የቆለፉት፡፡ ታገላቸው፡፡ ጣሉት፡፡ ድንገት ግን አንዲት የድሮ ካሜራውን ይዟት ነበር፡፡ እነሱ ሊቀሙት ይታገሉት ነበር፡፡ ካሜራዋን። እንደምንም ብሎ ተጫናት፡፡ ፎቶ አነሳች፡፡ ወንደበዴዎቹ ጭንቅላቱ ላይ ባደረሱበት ጉዳት ኋላ ላይ ነፍሱ ከሥጋው ብትለይም ፖሊስ ጥፋተኞቹን ደርሶባቸዋል፡፡ ገዳዮቹ ሊደረስባቸው የቻለው ደግሞ ፓላዲኖ ከመሞቱ በፊት ፎቶ ስላነሳቸው ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ከ2 ሳምንታት በፊት ነው፡፡ ፓላዲኖ ሥመ ጥር የግል ወንጀል መርማሪ ሲሆን ከዋና ዋና ደንበኞቹ መሀል የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች እና ዕውቅ የሆሊውድ ተዋናዮች፣ ሙዚቀኞችና ጸሐፊ ተውኔቶች እና ሌሎች ገናናዎች ይገኙበታል፡፡ የፓላዲኖ ካሜራ የወንበዴዎቹን ምሥል በማስቀረቱ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን አድኖ ቢይዝም በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ሆስፒታል የነበረው ፓላዲኖ ግን ትናንትና ሰኞ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ዝነኛው ፓላዲኖ ዘመናትን ባስቆጠረው የግል መርማሪነት ሥራው አነጋጋሪ የነበሩ ጉዳዮችን በመያዝ ገናና ነበር፡፡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን፣ ሞዛቂና ተዋናይት ከርትኒ ላቭ፣ በቅሌት ማጥ ውስጥ የሚገኘው ዝነኛው ፕሮዲዩሰር ሐርቬይ ዊኒስተን የፓላዲኖ ደንበኞች ነበሩ፡፡ ባለፈው ሐሙስ ፓላዲኖ ጥቃት ሲደርስበት ሳንፍራንሲስኮ ከሚገኘው ቤቱ ደጅ ላይ የነበረ ሲሆን 2 አደገና ቦዘኔዎች ናቸው የተባሉ ወጣቶች ናቸው በእጁ ይዞት የነበረውን ካሜራ ሊቀሙት የታገሉት፡፡ ይህን ተከትሎ ፓላዲኖ ወደኋላ ወድቆ ጭንቅላቱ ስለመታው ራሱን ወዲያውኑ ሳተ፡፡ በሚደንቅ ሁኔታ ታዲያ አጥቂዎቹ ከመሸሻቸውና እሱ ራሱን ከመሳቱ በፊት በነበረች ቅጽበት ፓላዲኖ የካሜራውን ጉጠት ተጭኖት ነበር፡፡ ፓላዲኖ ቢሞትም ፖሊስ ግን ያን ምሥል ተጠቅሞ ነው ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው፡፡ የፓላዲኖ ባለቤት ሳንድራ ሱተርላንድ የወንጀለኞቹን መያዝ ስትሰማ፣ ‹‹ምነው የሰራው ሥራ ወንበዴዎቹ እንዲያዙ ማድረጉን መርማሪ ሆኖ የኖረው ባለቤቴ ባወቀ›› ብላ ተናግራለች፣ ለአሶሲየትድ ፕሬስ፡፡ ሕይወቱን ሙሉ የወንጀል መርማሪ ሆኖ የኖረ ሰው ገዳዮቹ በዚህ መልክ መያዛቸው የሕይወት ግጥምጥሞሽ በሚል ብዙዎቹን አስደንቋል፡፡ ፓላዲኖ ሕግ የተማረ ሲሆን የግል መርማሪ ሆኖ መሥራት የጀመረው በ1970ዎቹ ነበር፡፡ ያን ዘመን የግል መርማሪ በፊልሞች ውስጥ ገዝፎ ይሳል ስለነበር ሥራውም ገናና ያደርግ ነበር፡፡ በ1977 ፓላዲኖ በአንድ የግል የወንጀል ምርመራ ቡድን ውስጥ ከባለቤቱ ጋር ተቀጠረ፡፡ እሱና ባለቤቱ ለዓመታት ወንጀል ምርመራ ውስጥ አብረው ሰርተዋል፡፡ እነ ፓላዲኖ በተለይም ለሆሊውድ ዝነኞች ስማቸው እንዳይጎድፍ የሚዲያ ዘመቻ በመክፈት፣ ወይም የሚዲያ አፍ በማዘጋት ሥራ ይሰማሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ ሙዛቂዋ ከርተኔይ ባሏ ከሞተ በኋለ በሱ ዙርያ ይወሩ የነበሩ የሚዲያ ሐሜቶችን እንዲያከስምላት ፓላዲኖን ቀጥራው ነበር፡፡ ፓላዲኖ በተለይ ቢል ክሊንተን ከትዳራቸው ውጭ ወጣ ይሉ ነበር የሚለውን ሐሜት እንዲቀብርላቸው ክሊንተን ቀጥረውት ውጤታማ ሥራ ሰርቶላቸዋል፡፡ በ1999 ዓ/ም ሳንፍራንሲስኮ ኤክዛሚነር ጋዜጣ ፓላዲኖን ሲገልጸው፣ ‹አስጨናቂ መርማሪ፣ የጎደፈ ስም ወልዋይ፣ ለሙያው ሟች› ብሎት ነበር፡፡ |
news-55876977 | https://www.bbc.com/amharic/news-55876977 | ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ የኮቪድ ክትባትን የሚቃወሙ ሰልፈኞች ከፖሊስ ተጋጩ | በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት፣ ሎስ አንጀለስ ከተማ የኮቪድ ክትባት ውሸት ነው የሚሉ ቀኝ አክራሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡ | ከፖሊስ ጋር የተጋጩት ክትባት እየተሰጠበት የሚገኘውን የዶገር ስታዲየም በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ ይህን የክትባት መስጠቱ ሂደት ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡ ቁጥራቸው 50 የሚሆኑ የጸረ ክትባት አቀንቃኞች ስታዲየሙን ለማዘጋት የቻሉት መግቢያውን በመዝጋት ጭምር ነው፡፡ ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ላይ የነበሩ በርካታ መኪኖች በነዚህ የክትባት ተቃዋሚዎች ምክንያት አገልግሎት ሳያገኙ ተመልሰዋል፡፡ ሰልፈኞቹ የኮቪድ ክትባት የተጭበረበረ ስለመሆኑ የሚያወሱ መፈክሮችን የያዙ ሲሆን ኅብረተሰቡን ‹አትከተቡ፤ እናንተ የቤተ ሙከራ አይጥ አይደላችሁም› እያሉ ሲቀሰቅሱ ታይተዋል፡፡ የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ቀኝ አክራሪ ሰልፈኞቹ ለክትባት የተሰለፉ ሰዎችን ‹ ነፍሳችሁን አድኑ፣ የውሸት ሳይንስ መጫወቻ አትሁኑ እያሉ እየጮኹ ሲቀሰቅሱ ነበር፡፡ የክትባት መስጫውን ሰልፈኞቹ የተቆጣጠሩትም በአገሬው አቆጣጠር ከቀኑ 8 ሰዓመት ጀምሮ ነው፡፡ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ በትዊተር እንዳስታወቀው ስታዲየሙ አልተዘጋም፤ ክትባቱ ቀጥሏል ብሏል፡፡ የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሰን በስታዲየሙ እየተሰጠ የነበረው የክትባት ዘመቻ በሰልፈኞች ለጊዜው ቢስተጓጎልም ወደ ሥራ ተመልሷል ብለዋል፡፡ ጀርማን ጃኩዝ የተባለና ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ሲጠባበቅ የነበረ ዜጋ ለሎስ አንጀለስ ታይምስ ቁጣውን የገለጸ ሲሆን ‹‹ይህ የቀኝ አክራሪዎች ድርጊት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው› ብሏል፡፡ ‹‹ለሳምንታት ክትባት ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፡፡ እኔ የጥርስ ሐኪም ነኝ፡፡ በሽተኞቼን ሳክም በጣም ተጠግቻቸው ነው፡፡ ከኮቪድ መጠበቅ እሻለሁ፡፡ ክትባቱ ያስፈልገኛል፡፡ ተህዋሲውን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ክትባት ነው›› ሲል ሐሳቡን አጋርቷል፡፡ በአመዛኙ የትራምፕ ደጋፊ የነበሩ እንደሆኑ የሚገመቱና ቀኝ አክራሪ የሆኑት ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች አንዱ ‹‹ሲኤንኤን እያታለላችሁ ነው›› ይላል፡፡ ሌሎች መፈክሮች፣ ‹‹ጭምብላችሁን ቀዳዳችሁ ጣሉት››፣ ‹‹የሰው አይጥ አትሁኑ›› የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከአሜሪካ ግዛቶች ካሊፎርኒያ በተህዋሲው ክፉኛ ከተጠቁት ተርታ ትመደባለች፡፡ 40ሺ የግዛቲቱ ነዋሪዎች በኮቪድ ሞተዋል፡፡ 3 ሚሊዮኑ ተህዋሲው አለባቸው፡፡ በመላው አሜሪካ በኮቪድ ተህዋሲ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች በሚቀጥለው ወር ግማሽ ሚሊዮን እንደሚያልፍ ይጠበቃል፡፡ |
news-52932155 | https://www.bbc.com/amharic/news-52932155 | ለሥራ ቢሮ መሄድ ብሎ ነገር ከናካቴው ሊቀር ይሆን? | ለብዙዎቻችን ቤታችን ቢሯችን ሆኖ ሰንብቷል፤ በኮሮናቫይረስ ተህዋስ ምክንያት። ይህ ጽሑፍ እየተሰናዳ ያለውም በአንድ ከቤቱ እየሰራ በሚገኝ የቢቢሲ ሠራተኛ ነው። | እንቅስቃሴዎች ውስን ይሆናሉ መኝታን ቢሮ ማድረግ ይቀጥል ይሆን? እርግጥ ነው ከቤት ሆኖ መሥራት በድኅረ ኮሮናቫይረስ ዘመን ደንብ የሚሆንባቸው መሥሪያ ቤቶች እንደሚኖሩ ከወዲሁ እየተነገረ ነው። ይህ ሀቅ ከኩባንያ ኩባንያ ቢለያይም ቅሉ፤ ቀጣሪዎች በዚህ አጋጣሚ ሠራተኞቻቸው ከቤት ሲሰሩ ኩባንያቸው ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ እንደሚሆን በትንሹም ቢሆን ተረድተዋል። በዚህ ሀሳብ ገፍተውበት ቢሮ ድርሽ እንዳትሉ ቢሉንስ? ይህ የማይመስል የነበረ ነገር በብዙ ኩባንያዎች ዘንድ እየተጤነ ነው። "ለምን ቢሮ እንከራያለን?"፣ "ለምን በአንድ ቢሮ ሕንጻ ሺህ ሠራተኞች ይርመሰመሳሉ?" ያሉ የሥራ አስፈጻሚዎችና ቀጣሪዎች ቀስ በቀስ ቢሮዎቻችንን ወደ ሠራተኞቻቸው ሳሎን ሊያመጡት ሽር ጉድ ይዘዋል። ይህ ነገር የከተማን ሕይወት በጠቅላላ ሌላ መልክ ሊያሲዘው ይችላል። ማኅበራዊ ሕይወትና ትዳርም መልኩን ይቀይር ይሆናል። በዚህ ጉዳይ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉን ሦስት ባለሞያዎችን መርጠናል። ጭር ያሉ መሐል መሀል ከተማዎች ጭር ይሉ ይሆን? ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ሰዎች ማኅበራዊ እንሰሳ ናቸው። ውጤታማ ለመሆን የግድ ፊት ለፊት ከባለጉዳይ ጋር መገናኘት ያሻቸዋል። ለ20 ዓመታት የተደረገ ጥናት ያንን ነው የሚያስረዳው። አንዳንድ ነገሮች አሉ፤ የግድ ከሰው ጋር ስንገናኝ የምናደርጋቸው። ከእነዚያ መካከል አንዱ ዕለታዊ ሥራ ነው። ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) አዲስ ነገር ልንጀምር ጫፍ ላይ ያለን ይመስለኛል። የሰው፣ የቦታና የጊዜ መስተጋብር ሌላ መልክ በመያዝ እየመጡ ይመስለኛል። ከዚህ ወዲያ አንዳንድ ነገሮች በነበሩበት ይቀጥላሉ ለማለት እቸገራለሁ። ኦዲ ቢኮሌት (የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ) አንዳንድ ግዙፍ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እያበረታቱ መሆኑ ግልጽ ነው። ትዊተር ይህን ወስኗል። ፌስቡክም እንዲሁ። የባርክሌይ ባንክ ሥራ አስፈጻሚም "7 ሺህ ሠራተኛ ቢሮ ጠርቶ ማርመስመስ ከዚህ በኋላ ያረጀ ያፈጀ ጉዳይ" እንደሚሆን ጠቁመዋል። ቢሮ ሄዶ የመስራቱ ነገር ጨርሶውኑ ይጠፋል ባይባልም የቢሮ መሄድ ልማድ እየከሰመ ሲሄድ አነስተኛ፣ መካከለኛና ዋነኛ የከተማ አካባቢዎች እንደየደረጃው መልካቸው መለወጡ የማይቀር ጉዳይ ነው። ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) አንዳንድ ኩባንያዎች "ለምንድነው ሚሊዮን ዶላር ለቢሮ የምንከሰክሰው" ማለታቸው አይቀርም።፡ ከወዲሁ እንደዚያ ማሰብ የጀመሩ አሉ። ይሄ ማለት በትንሹ ሦስት ነገሮችን ጨርሶውኑ ይቀይራል። አንዱ የከተሞችን ማዕከላት፣ ሁለተኛው የልጅ አስተዳደግ፣ ሦስተኛው ደግሞ የትዳር ግንኙነት ናቸው። ይህ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። ኦዲ ቢኮሌት (የፖሊሲ ጥናት ተመራማሪ) እኔ እንደሚመስለኝ በየሰፈራችን፣ ወደ ቢሮ ርቀን ሳንሄድ ሬስቶራንቶች፣ መዝናኛዎች እና ሌሎች የምንፈልጋቸው ነገሮች ወደኛ እየቀረቡ ይሄዱ ይሆናል። ሰዎች በአቅራቢያቸው መገናኘት መጀመር ይፈልጉ ይሆናል። ሌላው ደግሞ ከቤታችሁ ስሩ ስንባል ቦታ ስንሻ በዚያው በሰፈራችን የተሸለ ስፍራ መፈለጋችን አይቀርም። ይህ ሀቅ ሰፈሮች እንዲያብቡ ሊያደርጋቸው ይችላል። ቢሮዎች በስፋት በሚገኙባቸው የከተማ ማዕከላትም ለውጦች መኖራቸው አይቀርም። እነዚያ ሰፋፊ የቢሮ ሕንጻዎች ቆመው አይቀሩም መቼስ። የዲዛይን ለውጥ እየተደረገባቸው ወደ መኖርያ አፓርትመን ይቀየሩ ይሆናል። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ የኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ከቤት ሥሩ ከተባልን ሁሉም የቤተሰብ አባል ቤት መዋሉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በቤታችን ውስጥ ሰፋፊ ቦታ መሻትን ያስከትላል። ካልሆነም በአቅራቢያችን የተመቻቸ ቦታ እንፈልግ ይሆናል። ለስብሰባ በሳምንት አንድ ሁለት ጊዜ ወደ ዋና ጽሕፈት ቤት መሄድ ሊኖር ይችላል። በሳምንት አንድ ጊዜ መሄድ ብቻ ግዴታ ሲሆን ደግሞ ሰዎች ከዋና ከተማ አቅራቢያ መስፈራቸው ጥቅሙ እየቀነሰ ይመጣል። ሰዎች ከከተማ ማዕከል ወደ ገጠር እየሄዱ መስፈር ይጀምሩ ይሆናል። በርሚንግሃም ውስጥ የሚገኝ ጭር ያለ የባቡር ጣቢያ ትራንስፖርትና የሰዎች እንቅስቃሴን በተመለከተ ምን ይፈጠራል? ማርገሬት ቤል በኒውካስል ዩኒቨርስቲ የትራንስፖርትና ኢንቫይሮንመንት ፕሮፌሰር ሰዎች መኪና መግዛት ይጀምራሉ። ይህም የሚሆነው ሰፋፊ ቦታ ፍለጋ ወደ ገጠር ስለሚያቀኑ ነው። በራቁ ቁጥር መኪና የግድ ይላቸዋል። ይህ ደግሞ የካርቦን ልቀትን ይጨምራል እንጂ አይቀንስም። ማድረግ የሚኖርብን ሰዎች ምንም ይሁን ምን ከሥራ ቦታቸው አቅራቢያ እንዲሰፈሩ ማድረግና ብስክሌት እንዲነዱ ማበረታት ነው። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል የኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ብዙ ሰዎች ቤት ሲቀመጡ ቤት ማብሰል ግድ እየሆነ ይመጣል። ይህ የኢነርጂ [ኃይል] አጠቃቀማችን ላይ ለውጥ ያመጣል። ከቤት ባለመውጣት ከምናድነው ኢነርጂ የበለጠ ቤት ውስጥ እንጠቀማለን። ጥናቶች ይህንን ነው የሚመሰክሩት። በከተሞቻችን ዙርያ ስለሚኖር ለውጥ ሌስ ባክ (የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር) ብዙ ጊዜ ስለዚህ ጉዳይ ስናወራ ከፍ ያለ የቢሮ ሥራ ስለሚሰሩ ሰዎች እያሰብን ነው፤ ለምሳሌ በፋይናንስ፣ በአይቲ ወዘተ። ከተሞች የተሞሉት ግን በእነዚህ ሠራተኞች አይደለም። ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና አገልግሎች ሰጪ ተቋማት ይቀጥላሉ። ደግሞም ከተሞች የመገናኛ ማዕከል መሆናችውን አንርሳ። አገልግሎት ብቻ አይደለም የምንፈልገው። ሰዎች ሌሎችን ማግኘት መተዋወቅ ወዳጅነት መመስረት ይፈልጋሉ። ይህ እነሱን ከማይመስሉ ሰዎች ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ይጨምራል። በባህል እኛን የማይመስሉ ሰዎችን በሰፈራችን ስለማናገኛቸው ርቀን ወደ ከተማ ማዕከላት መሄዳችን አይርም። ፖል ቼሽየር (በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር) ሌላው ጉዳይ መጠየቅ ያለብን ሰዎች ወደ ከተማ ወጥተው ለመቀላቀል ከዚህ በኋላ የኮሮናቫይረስ ፍርሃታቸው ብን ብሎ ይጠፋል ወይ? ሰዎች ወደ ድሮ ባህሪያቸው ለመመለስ ቢያንስ በሽታው በቁጥጥር ሥር ስለመዋሉን እርግጠኞች መሆን ይፈልጋሉ። ቢያንስ ክትባት ሊገኝ ይገባል። ይህ እስኪሆን ደግሞ ረዥም ጊዜ መፈለጉ አይርም። ረዥም ጊዜ! |
news-53018870 | https://www.bbc.com/amharic/news-53018870 | ፊልም ለመቅረጽ ሲል የጎዳና ተዳዳሪዎችን መርዝ ያበላው ሰው በቁጥጥር ሥር ዋለ | በአሜሪካ ካሊፎርኒያ አንድ ግለሰብ ስምንት የጎዳና ተዳዳሪዎችን አፍዝ አድንግዝ እጽ በምግብ ለውሶ ሰጥቷቸዋል፡፡ | ዊሊያም ሮበርት ኬብል የ38 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን ይህን አደንዛዥ መርዝ ለጎዳና ተዳዳሪዎቹ ከሰጣቸው በኋላ ሲሰቃዩ እርሱ ይቀርጻቸው ነበር ተብሏል፡፡የጎዳና ተዳዳሪዎቹ በተመገቡት የተመረዘ ምግብ የተነሳ ሆስፒታል ነው የሚገኙት፡፡ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ 19 ዓመት ዘብጥያ ይወርዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የኦሬንጅ ወረዳ የሕግ ጠበቃ ቶድ ስፒዘር እንደተናገሩት ተከሳሹ እነዚህን ሰዎች የመረጣቸው ድህነታቸውን ተጠቅሞ ነው፡፡ የነርሱን ስቃይ በካሜራ ቀርጾ እርሱ ለመዝናኛነት ሊያውለው ነው ያሰበው፤ ይህ ጭካኔ ነው ብለዋል ቶድ፡፡በካሊፎርኒያ የኦሬንጅ ወረዳ አቃቢ ሕግ እንዳብራራው ተከሳሹ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ያገኛቸው በሀንቲግተን የባሕር ዳርቻ ሲሆን ምግብ እንደሚፈልጉ ከጠየቃቸው በኋላ አዎ ሲሉት የተመረዘ ምግብ አቀብሏቸዋል። አንዳንዶቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች ተከሳሹ የሚያቃጥል ምግብ ውድድር እያደረኩ ነው፣ ቶሎ የጨረሰ ይሸለማል በሚል አታልሎ እንደቀረጻቸው ተናግረዋል፡፡ ያቀረበላቸው የተመረዘ ምግብ በአደገኛ በርበሬና ቃሪያ የተሰነገና እጅግ የሚያቃጥል ነው ተብሏል፡፡ምግቡን ከቀመሱ በኋላ የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ግማሾቹ ራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ቀሪዎቹ ለመተንፈስ ተቸግረው ታይተዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ሲያስመልሳቸው ነበር፡፡ ተከሳሹ አሁን በግማሽ ሚሊዮን ዶላር ዋስ የተለቀቀ ሲሆን ባፈለው ወር ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው፡፡አቃቢ ሕግ በሰውየው ላይ 8 ክሶችን አቅርቦበታል፡፡ ከጎዳና ተዳዳሪዎቹ አንዱ ሽማግሌ ሲሆኑ ትንንሽ ልጆችም ይገኙበታል፡፡ ይህም ክሱን ያጠናክርበታል፡፡ ባለፈው ዓመት አንድ ስፔናዊ የዩቲዩብ አሰናጅ በተመሳሳይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን አትታሎ ኦሪዮ ብስኩት እያስበላ ቀርጻ ሲያደርግ ነበር፡፡ ብስኩቱ ተለውሶ የነበረው ደግሞ በጥርስ ሳሙና ፈሳሽ ነበር፡፡ይህ ሰው 15 ወራት ተፈርዶበት ዘብጥያ ወርዷል፡፡ |
news-46176341 | https://www.bbc.com/amharic/news-46176341 | በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያገረሸው የኢቦላ ወረርሽኝ በታሪኳ ታይቶ አይታወቅም | በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በቅርቡ ያገረሸው ኢቦላ ወረርሽኝ በአገሪቷ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና አሰከፊ ነው ሲሉ የአገሪቷ ጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታውቀዋል። | የህክምና ባለሙያዎች የኢቦላ ሥርጭትን ለመግታት ክትባት እየሰጡ ነው። ከባለፉት አራት ወራት ጀምሮ ቢያንስ 200 ሰዎች በወረርሽኙ ሕይወታቸው ሲያልፍ ወደ 300 የሚሆኑ የተጠረጠሩ ህመምተኞች ተገኝተዋል። ወረርሽኙን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረገ ሲሆን እስካሁን 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ክትባት ተሰጥቷል። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና የጤና ባለሙያዎች ላይ በተለያየ ጊዜ ጥቃት በመድረሱ ለዓመታት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ተፈታትኖታል። • ኢቦላ በኮንጎ እየተዛመተ ነው • ኢቦላ ለምን አገረሸ? • "ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ የጤና ጥበቃው ሚንስትር ኦሊ ኢሉንጋ በዚህ ሰዓት 319 በበሽታው የተያዙና 198 ሞት መመዝገቡን ገልፀዋል። "ቤተሰቦቻቸውን ላጡ፣ ያለ አሳዳጊ ለቀሩ ሕፃናትና ለተበተኑ የቤተሰብ አባላት የተሰማኝን ሀዘን እገልፃለሁ ፤ መፅናናትን እመኛለሁ፤ በፀሎትም አስባቸዋለሁ" ሲሉም ተናግረዋል። ባለስልጣኑ እንደተናገሩት ግማሽ ያህሉ ተጎጂዎች 800 ሺህ ህዝብ ከሚኖርባት የሰሜናዊ ኪቩ ግዛት ቤኒ ነዋሪዎች ናቸው። አገሪቱ በአውሮፓውያኑ 1976 ካጋጠማት ስሙ በውል ካልታወቀው ወረርሽኝ በኋላ የአሁኑ በጣም አሰቃቂውና አስፈሪው ነው። ኢቦላ ከሰውነት ከሚወጣ ፈሻሽ እና ሌሎች ኢንፌክሽኖች አማካኝነት ይተላለፋል፤ ምልክቱም ጉንፋን መሳይ ህመም፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ ውስጣዊና ውጫዊ መድማት ናቸው። |
news-56318086 | https://www.bbc.com/amharic/news-56318086 | ትግራይ፡ በእስር ላይ የሚገኙት የህወሓት አመራር አባላት 'ክሳችን ፖለቲካዊ ነው' ማለታቸው ተነገረ | አዲስ አበባ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙት የቀደወሞው ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የቀረበባቸው ክስ ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናገሩ። | እስረኞቹ ይህንን የተናገሩት ስለእስር አያያዛቸው ሁኔታ ለመመልከት ለጎበኟቸው ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ለዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) እና ለኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች ነው። ኮሚሽኑ ባለፈው ቅዳሜ የካቲት 27/2013 ዓ.ም የጎበኟቸው አብረሀም ተከስተ (ዶ/ር)፣ አምባሳደር አባይ ወልዱ፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አምባሳደር አባዲ ዘሙ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር)፣ አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር)፣ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋን ጨምሮ 21 እስረኞችን ነው። ከታሰሩት ግለሰቦችና ከፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን የገለጸው ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ላይ "አብዛኞቹ ታሳሪዎች የቀረበባቸው ክስ ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ፣ የተጠረጠሩበት ጉዳይ በተናጠል አለመቅረቡና የምርመራ ሂደቱ በአፋጣኝ አለመታየቱን ገልጸው አቤቱታ አቅርበዋል" ብሏል። ኮሚሽኑ እንዳለው ታሳሪዎቹ በጥሩ አካላዊ ደኅንነት የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት አጠቃላይ ሁኔታ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ተመልክቶ፤ የተጠቀሱት ታሳሪዎች ወደ ፌዴራል ፖሊስ እስር ቤት ከመጡ ወዲህ "ተገቢ ያልሆነ የእስር አያያዝ አለመኖሩንና ፖሊሶች በተገቢው የሙያ ሥነ ምግባር የሚሰሩ መሆኑን" ገልጸዋል ብሏል። በተጨማሪም የህክምና አገልግሎት ባለው አቅም እያገኙ እንደሆነ፣ ከቤተሰባቸው ጋር ተገናኝተው አቅርቦት እንደሚቀበሉና ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት መቻላቸውን እንደተናገሩ ኮሚሽኑ በመግለጫው ላይ አመልክቷል። ታሳሪዎቹ ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ከጠበቆች ጋር የሚገናኙበት ጊዜ ማጠሩን እንዳነሱና የተወሰኑ ታሳሪዎች የራሳቸውና የቤተሰቦቻቸው የባንክ ሒሳብ በመታገዱ ቤተሰቦቻቸው መቸገራቸውን እንደተናገሩ ገልጸዋል ብሏል። አስረኞቹ አሁን ካሉበት ሁኔታ ባሻገር ገጠሙን በሚሏቸው ጉዳዮች ላይ ቅሬታቸውንም ለኮሚሽኑ አባለት መግለጻቸውን አመልክቷል። ከዚህም ውስጥ "ከተያዙ በኋላ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸውን፣ በትግራይ ክልል ከመቀለ ከተማ ሸሽተው ሲሄዱ በተያዙበት ጊዜ ስድብ፣ ድብደባ፣ ማስፈራራትና ተኩስ እንደነበረ እንዲሁም የአካል መቁሰል እንደደረሰባቸው" ገልጸዋል ብሏል። በተጨማሪም ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ "ነፃ ሆኖ የመገመት መብታቸውን በሚጋፋ መልኩ በሚዲያ አሰልፎ የማቅረብና የማንኳሰስ ሁኔታ እንደነበረ" በማንሳት ቅሬታቸውን ያቀረቡ እስረኞች እንደነበሩ ኢሰመኮ ገልጿል። ኮሚሽኑ ታሳሪዎቹ አሁን በእስር የተያዙበት ሁኔታ በተገቢው ደረጃ መሆኑን ማረጋገጡንና በታሳሪዎች የተነሱ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከእስር ቤቱ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አመልክቷል። የቀድሞ የህወሓት አመራሮች አዲስ አበባ ውስጥ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በሚገኘው እስር ቤት ያሉበትን ሁኔታ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ከተመለከቱ በኋላ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚደረገውን "ምርመራ በተቻለ ፍጥነት በማጠናቀቅ፤ የሕግ አግባብ በሚፈቅደው መልኩ በዋስትና ሊለቀቁ የሚገባቸውን ታሳሪዎች መለየት አስፈላጊ ነው" በማለት ማሳሰባቸው ተገልጿል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ህወሓት ከሥልጣን መወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ አድርገው ነበር። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው መሆኑ መገለጹ ይታወሳል። |
52627587 | https://www.bbc.com/amharic/52627587 | ኮሮናቫይረስ፡ በሊባኖስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ችግር ውስጥ ናቸው- የኢትዮጵያ ቆንስላ | በሊባኖስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። የተጣለው የሰዓት እላፊ ከነገ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እስከ ሰኞ ማለዳ ድረስ ይቆያል ተብሏል። | ከዚህ ቀደም የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ ለአንድ ወር ያህል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ዜጎች " ቤታቸው መቀመጥ አለባቸው አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠማቸው በስተቀር ወደ የትም መሄድ የለባቸውም" ያሉት የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ማናል አብደል ሳማድ ናቸው። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ከሆነ በአገሪቱ 870 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 26 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የኛ ሰው በሊባኖስ በሊባኖስ በርካታ ኢትዮጵያውያን በዝቅተኛ ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያኖች ይናገራሉ። ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁን በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን "ችግራችን የጀመረው ባለፈው ጥቅምት ወር የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት በተጎዳበትና የዶላር መወደድ ሲጀምር ነው" ብለውናል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየሰዉ ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ የተባረሩበት፣ ደሞዛቸውን በግማሽ ቀንሰው መስራት የጀመሩበት እስካሁን ድረስም ሳይከፈላቸው የሚሰሩ መኖራቸውን ይገልፃሉ። "ያለ ክፍያ ለመስራት የመረጡት ቢያንስ የተገኘውን እየበሉ በሕይወት መቆየት ይሻላል ያሉ ናቸው" በማለትም ይህንን ተቋቁመን አልፈነው ነበር ብለዋል። የዓለምን ሕዝብ ያስጨነቀው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት "ሕይወታችንን ከድጡ ወደ ማጡ ከቶብናል" የሚሉት ኢትዮጵውያኑ፣ ልጅ ኣላቸው ልጃቸውን መመገብ፣ ቤት ኪራይ መክፈል ፈተና እነደሆነባቸው ይገልፃሉ። ሊባኖስ የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል ጥላው የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ ማንሳቷን ተከትሎ ያገኙትን ሰርቶ ለማደር ተስፋ ሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም ዳግም በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ተከትሎ መንግሥት ለተከታታይ አምስት ቀናት ከቤት መውጣትም መከልከሉን በመናገሩ ሌላ ስጋት እንደተደቀነባቸው ለቢቢሲ ያስረዳሉ። እገዳው ለአምስት ቀናት የተጣለ ሲሆን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኞ ማለዳ ድረስ የሚቆይ ነው በማለትም "ሳይሰራ እንዴት ቤት ኪራይ ይከፈላል?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብ ፣ ባለፉት አራት ቀናት ብቻ 100 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልፀው ነው የአምስት ቀኑ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን የተናገሩት። መንግሥት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ላይ ያወጣውን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ሰዎችንም " ግዴለሽና ሃላፊነት የጎደላቸው" በማለት ወርፈዋቸዋል። በሊባኖስ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ የአካላዊ ርቀት መጠበቅ ተግባራዊ እንዲሆን በማሳሰብ ሱቆችና የአምልኮ ስፍራዎች ተከፍተዋል። ይህ የሆነው ከሁለት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። በቫይረሱ የተያዙ አዳዲስ ሰዎች የተገኙት በአብዛኛው ከአገር ውጪ የነበሩ ሊባኖሳውያን በመመለሳቸው መሆኑ ተገልጿል። ከአምስት ቀናት በፊት ከናይጄሪያ፣ ሌጎስ የመጡ ሁሉም ተሳፋሪዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር አስታውቆ ነበር። የእንቅስቃሴ ገደቡ ከተነሳ በኋላ ዜጎች በመገበያያ ስፍራዎች አካላዊ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ሲገበያዩ የታዩ ሲሆን፣ በአውራ ጎዳናዎችም ላይ ከተጠበቀው በላይ በርካታ ሰዎች ወጥተዋል። በሊባኖስ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ እየወደቀ የነበረው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብትን ይበልጥ አባብሶታል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ቢቢሲ ያነጋገራትና ሊባኖስ ውስጥ ለ12 ዓመታት መኖሯን የምትናገረው ኢትዮጵያዊት በበኩሏ "እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ ፓስፖርትም ሆነ የመኖሪያ ፈቃድ የለንም" ስትል የስጋታቸውን መደራረብ ታስረዳለች። ከዚህ በፊትም ቢሆን የተለያዩ ችግሮችን አልፌያለሁ ያለችን ይህች ሴት የአሁኑ ግን ከምንጊዜውነም የከፋ ነው ትላለች። የኮሮናቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ጀምሮ በሰዓት የሚከፈላት በግማሽ ተቀንሶ እየሰራች እንደነበር የተናገረችው ይህች ስደተኛ፣ የኮሮናቫይረስ ከመጣ በኋላም እጅጉን መታመሟን ታስታውሳለች። "ምናልባትም ኮሮና ይሆናል፤ እንደ ጉንፋን ያለ ነው" ትላለች በወቅቱ የነበራትን ሕመም ስታስታውስ። ለመመርመርም ሆነ ወደ ሆስፒታል ለመሄድና አገልግሎት ለማግኘት ፓስፖርትና የመኖሪያ ፈቃድ እንደምትጠየቅ በዚህም የተነሳ መታከም እንዳልቻለች ገልፃለች። ለተከታታይ 11 ቀናት ሳል እንደነበራት የምትናገረው ይህች በሊባኖስ የምትገኝ ስደተኛ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ስምንት ልጆች ሆነው እንደሚኖሩና እርሷ በቫይረሱ ብትያዝ ወደ ሌሎቹ የመተላለፍ እድሉ ሰፊ እንደነበር ታስረዳለች። "እኔ ብቻ ሳልሆን ሌሎችም ኢትዮጵያኖች አሉ ለአራትና ለአምስት በአንድ ክፍል የሚኖሩ" በማለትም ሕገወጥ ሆነው ሲኖሩ ኣለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጫና ታስረዳለች። ታምማ በነበረበት ሰዓት ከስራዋ ገበታ መቅረቷን የምታስታውሰው ይህች ሴት፣ እርሷና ጓደኞቿ ሕገወጥ ሆነው በመስራታቸው ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸውን ትናገራለች። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሥራ በመፍታታቸው ያላቸውን እየተጠቀሙ፣ መስራት ባለመቻላቸው የቤት ኪራይ የሚከፍሉት እንደሚቸግራቸው ወደ ጎዳና እንወጣለን የሚል ስጋት እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ልጅ ያላቸው ሴቶች መኖራቸውን በመጥቀስም ያለስራ፣ የቤት ኪራይ ሳይከፍሉ መኖር ሕይወታቸውን ማክበዱንና ነገን በተስፋ ለማየት መቸገራቸውን ይገልፃሉ። በሊባኖስ ቤሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ የሚናገሩት እነዚህ ስደተኞች በእስር ቤት፣ በሆስፒታል፣ ሞተው አስከሬናቸው ማቆያ ውስጥ ያለ በርካቶች መኖራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን የሊባኖስ የምጣኔ ሃብት ሁኔታ ወድቋል፣ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ሕገወጥ ሆኖ ለመስራትም ስላላስቻለ ወደ አገራችን ብንመለስ ፈቃደኛ ነን ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቆንስላ ምን ይላል? በቤሩት ሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ቆንስል የሆኑት አቶ አክሊሉ ታጠረ ውቤ ለቢቢሲ እንደገለፁት በቤይሩት ሊባኖስ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከአራት መቶ ሺህ በላይ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ "በሕገወጥ መልኩ" እንደሚኖሩ ተናግረዋል። በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኞቹ በሕጋዊ መንገድ ከመጡ በኋላ ከአሠሪዎቻቸው ጋር በተለያየ መንገድ ሳይግባቡ ሲቀሩ በመውጣት ቤት ተከራይተው "በሕገወጥ መልኩ" እንደሚኖሩ ይናገራሉ። ከእነዚህ መካከል ሰማንያ በመቶ ያህሉ ሕጋዊ ፓስፖርት፣ የመኖሪያም ሆነ የሥራ ፈቃድ የሌላቸው መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ ሊሆን የቻለው ከአሰሪዎቻቸው ጋር ሲጋጩ እዚያው ጥለው በመውጣታቸው መሆኑን ያስረዳሉ። በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያነሷቸው ችግሮች እውነት መሆናቸውን የተናገሩት አቶ አከሊሉ ኤምባሲው በተለያዩ ማህበረሰብ ቡድኖችና በኃይማኖት ተቋማት በኩል ስለወረርሽኙ ግንዛቤ ለመፍጠር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም ዜጎች ችግር ላይ እንዳይወድቁና እርስ በእርሳቸው እንዲረዳዱ ድጋፍ የመስጠት ሥራ መስራታቸውን ይገልፃሉ። በተጨማሪም ወደ አገር ቤት መመለስ ያለባቸው እስር ቤት፣ በተለያዩ መጠለያዎች ውስጥ የነበሩት ከአሁን በፊት ተመዝግበው የነበሩ 905 ዜጎችን ከሊባኖስ ለማስወጣት ከመንግሥት ጋር የመነጋገር፣ በረራ እና ለይቶ ማቆያ የማዘጋጀት ሥራዎች እየሰሩ መሆናቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ነገር ግን ይላሉ አቶ አክሊሉ "ከእነዚህ መካከል ስማቸው ተላልፎ የጉዞ ሰነድ ተዘጋጅቶ፣ ፎቶ ኑና ተነሱ ሲባል፣ 54 ሰዎች ስራ አግኝተናል መሄድ አንፈልግም በማለት የመጣውን እድል ሌሎች እንዳይጠቀሙበትም አስቀርተዋል።" ብለዋል ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ የሚገጥማቸውን የምግብ ችግር፣ የቤት ኪራይ መክፈል አለመቻልን በተመለከተ የተለያዩ ኃይማኖት ማህበራትና ተወካዮች የሚሰሩትን ስራ እንደሚደግፉ ገልፀዋል። ኤምባሲው የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ሳያሳድሱ ቀርተው ቅጣት ለሚጠብቃቸው ዜጎች ከሊባኖስ መንግሥት ጋር ተነጋግሮ ምንም ያህል ዓመት ሳያሳድሱ ቢቆዩ የአንድ አመት ብቻ እንዲከፍሉ ስምምነት ላይ መደረሱንም አክለው ተናግረዋል። አሁን ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ይህ የቅጣት ክፍያ እንዲቀ ርእየተነጋገሩ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። በቫይረሱ የሚያዙ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩ ቀይ መስቀልና የአገሪቱ መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ እንደሚያሳክም የገለፁት አቶ አክሊሉ፣ ምንም ዓይነት ሰነድ ለሌላቸውና የተለያዩ የጤና ችግር ለሚገጥማቸውም ኤምባሲው ደብዳቤ እንደሚጽፍላቸውና በዚያ መታከም እንደሚችሉ ጨምረው አስረድተዋል። በሊባኖስ እስካሁን ድረስ በኮሮናቫይረስ የታመመ አንድም ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን አቶ አክሊሉ ጨምረው ተናግረዋል። |
news-56674360 | https://www.bbc.com/amharic/news-56674360 | ትግራይ፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ትግራይ ውስጥ ግድያ ፈጽሟል መባሉን ሐሰት ነው አለ | በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተፈጸሙ የተባሉት የመብት ጥሰቶች ሐሰት ናቸው ሲል ሠራዊቱ ምላሽ ሰጠ። | የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት "ትግራይ ውስጥ ሠራዊቱ ንጹሃንን ፈጅቷል በሚል የሚናፈሰው ሐሰተኛ ወሬ በህወሓት ተላላኪዎች የተቀነባበረ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ጨምረውም የመከላከያ ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ "የህወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መደመሰሱን" ተናግረው፤ ይሁን እንጂ የቀሩ የቡድኑ አንዳንድ አባላት "የሸፍታነትን ባህሪ ተላበሰው፤ አካባቢዎች በአሳቻ ስፍራ ላይ በሕዝቡ ላይ ዘረፋ፣ እንግልትና ግድያ እየፈፀሙ ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ እነዚህ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን በመጨፍጨፍ አገርና ሕዝብን ድርጊቱ በመከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈፀመ ለማስመሰል የተለያዩ ተግባራትን እየፈጸሙ ነው ብለዋል። የቢቢሲ 'አፍሪካ አይ' ፕሮግራም ባደረገው ምርመራ በትግራይ ውስጥ ማኅበረ ዴጎ በሚባል ስፍራ በኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ጭፍጨፋ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች ማግኘቱን ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ቢያንስ 15 ወንዶች የተገደሉበትን ትክክለኛውን ቦታ ለመለየት ችሏል። የታጠቁና የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ያልታጠቁ ወንዶችን ከአንድ የገደል አፋፍ ላይ በመውሰድ አንዳንዶቹን ላይ በቅርብ ርቀት በመተኮስ አስከሬኖችን ወደ ገደል ገፍተው ሲጨምሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣቱን ተከትሎ ነበር 'አፍሪካ አይ' ምርመራውን ያደረገው። ቢቢሲ ይህ ድርጊት የተፈጸመው የኢትዮጵያ ሠራዊት የህወሓት ኃይሎችን እየተዋጋ ባለበት ትግራይ ክልል ውስጥ ማኅበረ ዴጎ ከተባለች ከተማ አቅራቢያ መሆኑን አረጋግጧል። በወቅቱ ቢቢሲ ያገኛቸውን ማስረጃዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት በማቅረብ ምላሽ የጠየቀ ሲሆን መንግሥት "በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ነገሮችና ክሶች እንደ ማስረጃ ሊወሰዱ አይችሉም" በማለት "ገለልተኛ ምርመራዎችን ለማካሄድ የትግራይ ክልል ክፍት ነው" ሲል መልስ ሰጥቶ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፌደራል ፖሊስ፣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምርመራ ለማድረግ ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ገልፆ መግለጫ አውጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው እንደተናገሩት፣ ትግራይ ውስጥ በኢትዮጵያ ሠራዊት ተፈጸሙ ስለተባሉት ጥፋቶች አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች በሕግ እንደሚጠየቁ መናገራቸው ይታወሳል። ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ምን አለ? ረቡዕ ዕለት በተሰጠው መግለጫ ህወሓት ግድያዎቹን በመፈፀም፣ የቪዲዮ ምስል በማቀናበር የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት የፈፀመው አስመስለው በማሰራጨት ስም ለማጥፋት እንደሞከሩ ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተናግረዋል። በተጨማሪም የመከላከያ የሚዲያ ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ብርጋዲየር ጀነራል ኩማ ሚደክሳ በቪዲዮው ላይ ዝርዝር ማብራሪያን ሰጥተዋል። በዚህም መሠረት በቪዲዮው ላይ የሚታዩት የሠራዊቱን የደንብ ልብስ ቢለብሱም አባላት እንዳልሆኑ ገልጸው፤ የደንብ ልብሱ በህወሓት ኃይሎች መዘረፉን ተናግረዋል። ለዚህም ለሠራዊቱ የሚሰጠው ልብስ ለእያንዳንዱ በልኩ የቀረበ ሲሆን በቪዲዮው ላይ የሚታዩት ግን ከልካቸው በላይ የሆነ የደንብ ልብስ በመልበሳቸው እጃቸው ላይ እንደሚያስታውቅ እንዲሁም በወገብ ላይ የያዙት ትጥቅ የሠራዊቱ አባላት እንዳልሆነ ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ "ቪዲዮው ሦስት የተለያዩ ምስሎችንና ቦታዎችን በማቀናበር የቀረበ ሐሰተኛ ምሰል ነው" በማለት ቪዲዮዎቹ በካሜራና በሞባይል ተቀርጾ የተለያዩ ቦታዎችን እንደሚያመለክት ገልጸዋል። የመጀመሪያው ቪዲዮ በካሜራ የተቀረጸ ሲሆን የሚታየው ስፍራ ከሁለተኛው ቪዲዮ የተለየ ነው በማለት ልዩነቱ ሜዳማና ገደላማ መሆናቸውን ጠቁመው ሦስተኛው ቪዲዮ አስከሬን የሚታይበት እንደሆነና ይህ ቪዲዮ በሞባይል የተቀረጸ መሆኑን ገልጸዋል። ብርጋዲየር ጀነራል ኩማ በቪዲዮዎቹ ላይ የሚታዩ ዝርዝሮችን በማንሳት የተሰራጩት ምስሎት በተለያዩ መሳሪያዎችና ቦታዎች ሆን ተብለው ተዘጋጅተው የተቀረጹና ሐሰተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ጨምረውም የአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ጥብቅ የዕዝ ሰንሰለት ያለውና ቁጥጥር የሚደረግበት በመሆኑ እያንዳንዱ ክስተት ስለሚታወቅ እንዲህ አይነቱን ወንጀል አይፈጽምም ሲሉ አስተባብለዋል። ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማም እነዚህ የተቀናበሩ ቪዲዮዎች "በህወሓት ተላላኪዎች በውሸት ተቀናብሮ ሕዝብን ለማደናገር የተሰሩ ናቸው" በማለት ሠራዊቱ ድርጊቱን እንዳልፈጸመ ተናግረዋል። አክለውም የአገር መከላከያ ሠራዊት በሥነ ምግባር የተገነባ ሕዝባዊ መሰረት ያለው በመሆኑ እንዲህ አይነቱን ሕዝብን የሚጎዳ ተግባር አይፈጽምም ብለዋል። ትግራይ ውስጥ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በመንግሥት ጦር ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ ነበር። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልከተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ከቪዲዮዎቹ ከአንዱ ላይ የተወሰደ ምስል |
news-52211338 | https://www.bbc.com/amharic/news-52211338 | ኮሮናቫይረስ፡ የአሜሪካዋ ግዛት ዊስኮንሰን አስገዳጁን ቤት የመቀመጥ ሕግ ተላልፋ ምርጫ አካሄደች | በኮሮናቫይረስ በርካታ ዜጎቿን እያጣች ባለችው አሜሪካ በበርካታ ግዛቶች ቤት የመቀመጥ አስገዳጅ ሕግ ቢወሰንም የዊስኮንሰን ግዛት ይህንን ተላልፋ በትናንትናው እለት ምርጫ አካሂዳለች። | ጥቂት ቁጥር ባላቸው የምርጫ ጣቢያዎችም በርካታ ሰዎች ተሰልፈው ታይተዋል። የምርጫ ጣቢያ ሰራተኞችም ኦክስጅን መተላለፊያ ያለው ከእግር እስከ ጭንቅላት የሚሸፍን አልባሳት ለብሰው ታይተዋል። የዊስኮንሰን አስተዳዳሪ ምርጫውን ወደ ሰኔ ለማስተላለፍ አቅደው የነበረ ቢሆንም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንን ውሳኔ ሽሮ ምርጫው መካሄድ አለበት ብሏል። •በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው •"ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?" ቀጣዩ የዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለመወዳዳር እየተፋለሙ ያሉት ጆ ባይደንና በርኒ ሳንደርስን አሸናፊ ለመለየት ከተደረጉ የመጀመሪያ ዙር ምርጫዎችም አንዱ ነው። የዚህ ምርጫ አሸናፊም በፈረንጆቹ ህዳር ለተያዘው ምርጫ ከሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የሚወዳደር ይሆናል። የአካባቢው ምርጫ አስፈፃሚዎችም በምርጫው ወቅት እንዲሁም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ ተገኝተዋል። •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች •በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው አሜሪካ ለሦስት ሳምንታት ያህል ቤት መቀመጥ እንዲሁም እንቅስቃሴ የሚገድብ መመሪያ ብታወጣም ዊስኮንሰን ይህንን ሕግ ተላልፋ ምርጫ ስታካሂድ የመጀመሪያዋ ግዛት ሆናለች። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በመጠቃት አለምን እየመራች ባለችው አሜሪካ አራት መቶ ሺህ የሚጠጋ ሰው በቫይረሱ ተይዟል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። አገሪቷ እንዲህ ባለ የጤና ቀውስ ባለችበት ሰዓት ምርጫ መካሄዱ ተተችቷል። ሌሎች ግዛቶች ምርጫውን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመውታል። እስካሁን ባለው መረጃ በዊስኮንሰን ግዛት 2 ሺህ 500 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 92 ግለሰቦች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል። |
news-51016945 | https://www.bbc.com/amharic/news-51016945 | በጀነራል ሶሌይማኒ ቀብር ላይ ከ35 በላይ ሰዎች ተረጋግጠው ሞቱ | በጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ በተፈጠረ መረጋገጥ ቢያንስ 35 ሰዎች መሞታቸውን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። | እንደ መገናኛ ብዙሃኑ ዘገባ ከሆነ፤ ተጨማሪ 48 ሰዎች በጀነራሉ የትውልድ ከተማ ኬርማን ተረጋግጠው ጉዳት ደርሶባቸዋል። በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ የተገደሉት ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ በትውልድ ከተማቸው ግብዓተ መሬታቸው እየተፈጸመ ይገኛል። በኢራቅ ባግዳድ ባሳለፍነው ዓርብ የተገደሉት ጀነራሉ፤ አስክሬናቸው ከኢራቅ ወደ ኢራን ሲጓዝ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃውያን አደባባይ ወጥተው ሸኝተዋል። ኢራቃዊያን የጀነራሉን አስክሬን ሲሸኙ ''ሞት ለአሜሪካ'' ሲሉ ተደምጠዋል። ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ። ፕሬዝደንት ትራምፕ ጀነራሉ መገደላቸው ከተሰማ በኋላ ''የሶሌይማኒ የዓመታት የሽብር አገዛዝ አብቅቶለታል" ብለዋል። "ሱሊማኒ በማንኛውም ሰዓት ሊቃጣ የሚችል የሽብር ሴራ በአሜሪካ ዲፕሎማቶች እና የጦር መኮንኖች ላይ ሲያሴር ነበር። ይህንን ሲፈጽም ያዝነው፤ አስወገድነው" ሲሉም ተደምጠዋል። በተያያዘ ዜና ቃሲም ሱሊማኒ ማን ነበሩ? ከእ.አ.አ. 1998 ጀምሮ ሜጀር ጀነራል ሱሊማኒ የኢራን ኩድስ ኃይልን ሲመሩ ቆይተዋል። ይህ ኃይል ከሃገር ውጪ የሚፈጸሙ ሚስጥራዊ ኦፕሬሽኖችን የሚያከናውን ነው። ጀነራሉ በኢራቅ ውስጥ አይኤስ እና አል-ቃይዳን በመዋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ ነበራቸው። ከዚህ በተጨማሪም፤ እኚህ የሽብር ቡድኖች እግራቸውን በኢራን እንዳይተክሉ ተከታትለው ድባቅ የመቷቸው ጀነራል ሱሊማኒ ነበሩ ተብሏል። ጀነራሉ የሚመሩት ኃይል በሶሪያ ግጭት ውስጥ ተሳትፎ እንዳለው አምኗል። ለፕሬዝደንት በሽር አል-አሳድ ታማኝ ለሆኑ ወታደሮች የጦር ምክር ይሰጣል። እንዲሁም ለባሽር አል-አሳድ ታማኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሺያ ሙስሊሞችን አስታጥቋል። በኢራቅ ደግሞ አይኤስን እየታገሉ ለሚገኙ ለሺያ ሙስሊም ሚሊሻዎች ድጋፍ ያደርጋል። በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የተከሰቱት ግጭቶች ጀነራሉ ኢራን ውስጥ እጅግ ዝነኛ ሰው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ጀነራል ሱሊማኒ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት የኢራን ከፍተኛ የጦር ሽልማት ተቀብለዋል። አሜሪካ በበኩሏ ጀነራሉ የሚመሩት የኩድስ ኃይል በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አሜሪካን በጠላትነት በመፈረጅ በሽብር መናጥ ለሚፈልጉ ኃይሎች ፈንድ፣ ሥልጠና እና የጦር መሳሪያን ጨምሮ የቁስ ድጋፍ ያደርጋል ስትል ትወነጅላለች። አሜሪካ እንደምትለው ከሆነ ይህ የኩድስ ኃይል ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ኃይሎች መካከል፤ የሌባኖሱ ሄዝቦላ እንዲሁም የፍልስጤሙ እስላማዊ ጅሃድ ተጠቃሽ ናቸው። የቀድሞ የሲአይኤ አለቃ የአሁኑ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ የኢራንን አብዮታዊ ጥበቃ እና ኩድስ ኃይሉን "የሽብር ቡድን" ሲሉ ከወራት በፊት ፈርጀውት ነበር። |
news-56391279 | https://www.bbc.com/amharic/news-56391279 | ተቃዋሚዎች የአርጀንቲናው ፕሬዝደንት ያሉበትን መኪና መስታወት ሰባበሩ | በርካታ ተቃዋሚዎች የአርጀንቲው ፕሬዝደንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝን የያዘችውን መኪና ማጥቃታቸው ተሰማ። | ይህ የሆነው ፓታጎኒያ በተሰኘችው ግዛት ሲሆን ፕሬዝደንቱ 'ሚኒባስ' ውስጥ ነበሩ ተብሏል። በደቡባዊቷ የአርጀንቲና ክፍለ ግዛት ቹቡት በሚገኝ አንድ የሕብረተሰብ ማዕከል ውስጥ የነበሩት ፕሬዝደንቱ በተቃዋሚዎች ተከበው ድንጋይ ተወርውሮባቸዋል። ተቀዋሚዎቹ የፕሬዝደንቱ መኪና በመክበብ ተሽከርካሪዋ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ፕሬዝደንቱ ወደ ሥፍራው ያቀኑት በአካባቢው የተነሳውን ሰደድ እሣት ተከትሎ አንድ ሰው መሞቱን በርካቶች መጎዳታቸውን በማስመልከት ነው። ነገር ግን ተቃውሞው በቹቡት ግዛት ሊካሄድ ነው የተባለውን የማዕድን ቁፋሮ የተመለከተ ነው። ተቃዋሚዎቹ መንግሥት ለትላልቅ ማዕድን ቆፋሪ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠት ረቂቅ ማውጣቱን በመቃወም ድምፃቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። አካባቢው ወርቅ፣ ብርና ዩራኒየምን በመሳሰሉ ማዕድናት የበለፀገ ነው ሲል ክላሪን ጋዜጣ ዘግቧል። በሥፍራው የነበረውን ግርግር የሚያሳዩ ተንቃሳቃሽ ምስሎች ላይ ፕሬዝደንቱ ከማሕበረሰብ ማዕከሉ ወጥተው ወደ መኪናቸው ሲሄዱ ተቃዋሚዎች የማዕከሉ በር ላይ ተኮልኩለው ይታያሉ። ከዚያ ተቃዋሚዎቹ ፕሬዝደንቱን ተከትለው የተሳፉበትን ሚኒባስ ሲደበድቡና እንዳይንቀሳቀስ ሲያግዱት ተስተውሏል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች የመኪናዋ መስታወት ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ነበር። ምንም እንኳ ፕሬዝደንቱ የነበሩባት መኪና ሕዝቡን ተሻግራ ማለፈው ብትችልም በርካታ መስኮቶች ተሰባብረዋል። በአርጀንቲናዋ ፓታጎኒያ ግዛት የተነሳው ሰደድ እሣት በርካቶች ቀያቸውን ጥለው እንዲወጡ አስገድዷል። በሰደዱ እሣቱ ምክንያት እስካሁን ድረስ ቢያንስ 200 ቤቶች ተቃጥለዋል። የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውና የውሃ አቅርቦት ማግኘት ያልቻሉ በርካቶች ናቸውም ተብሏል። ምንም እንኳ የሰደድ እሣቱ መንስዔ ባይታወቅም የሃገር ውስጥ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ይላል። |
news-56276139 | https://www.bbc.com/amharic/news-56276139 | ትግራይ፡ የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ ግጭት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል አለ | በትግራይ ግጭት የተሳተፉ አካላት "የጦር እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ፈጽመው ሊሆን እንደሚችል" የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባሽሌት ገለጹ። | ኮሚሽነሯ ዛሬ [ሐሙስ] ከትግራይ የሚወጡ ተያያዢነት ያላቸውና ተአማኒ ሪፖርቶች በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ የተለያዩ ወገኖች የተፈፀሙ ከባድ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊ እርዳታ ሕጎች ጥሰት ማመልከታቸውን ተናግረዋል። በዚህም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉትንና እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ሪፖርት የተደረጉ የጅምላ ግድያዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ወሲባዊ ጥቃቶችን ለመመርመር እንዲችል ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ሚሸል ባሽሌት የተፈፀሙት የመብት ጥሰቶች እንደ ጦር እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ሊቆጠሩ እንደሚችሉ ገልፀው በዚህም ውስጥ የተለያዩ አካላት ተሳታፊ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ጠቁመዋል። በተጠቀሱት ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ያሏቸውን አካላት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ህወሓት፣ የኤርትራ ወታደሮች፣ የአማራ ክልል ኃይሎችና ግንኙነት ያላቸው ታጣቂ ሚሊሻዎች ናቸው ብለዋል። "በግጭቱ ላይ በርካታ አካላት መሳተፋቸውን ጨምሮ፤ ጥሰቶቹን መካድ እንዲሁም ጣት መጠቆም ይታያል። የጥሰቶቹን ሪፖርት በተመለከተ ግልፅ፣ ነፃ የሆነ ግምገማና ምርመራ ያስፈልጋል። የጥቃቱ ሰለባና ተራፊዎች የእውነትና የፍትህ ጥያቄያቸው ሊካድ አይገባም" ብለዋል ኮሚሽነሯ። አክለውም "የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ቢሮና ሌሎች ነፃ መርማሪዎች ወደ ትግራይ ገብተው ያለውን ሁኔታ እንዲገመግሙና እንዲመረምሩ ፍቃድ እንዲሰጠን እንጠይቃለን። የትኛውም አካል ይፈፅመው እውነታው መታወቅ አለበት፤ ፈጻሚዎቹም ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል" በማለት ጥሪ አቅርበዋል። ኮሚሽነሯ ሚሸል ባሽሌት በአሁኑ ወቅት "የሚረብሹ" ያሏቸው የመደፈር፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየደረሳቸው መሆኑን አስታውቀዋል። "በክልሉ ተዓማኒ የሚባሉ ዓለም አቀፉን የሰብዓዊ መብት የሚጥሱ ሪፖርቶች በግጭቱ ተሳታፊ በሆኑ አካላት በሙሉ መፈፀማቸውን የሚገልጽ መረጃ ደርሶናል" ብለዋል። አክለውም "ግልጽና ነፃ ምርመራ ካልተካሄደና ጥሰቱን የፈፀሙትን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ካልተቻለ እነዚህ ጥቃቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እፈራለሁ። ሁኔታውም ባልተረጋጋ መልኩ ለዓመታት ሊቀጥል ይችላል" ብለዋል። ኮሚሽነሯ ከአስተማማኝ ምንጭ ነው ያገኘሁት ባሉት መረጃ መሰረት በአዲግራት፣ በመቀለ፣ በሽረና በውቅሮ በተነሳው ተቃውሞ ስምንት ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል ብለዋል። በተጨማሪም በትግራይ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት በመቀለ፣ በአይደር፣ በአዲግራትና በውቅሮ በአንድ ወር ብቻ 136 ወሲባዊ ጥቃቶች ሪፖርት መደረጋቸውን ገልፀው፣ ይህም ከዚህ በላይ በርካታ ጥቃቶች መድረሳቸውን ማሳያ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቅርቡ እነዚህ ጥቃቶች መድረሳቸውን አረጋግጦ ምርመራ ከፍቻለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው። በተጨማሪም በቅርቡ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ በትግራይ ከተሞች በኅዳር ወር በዘፈቀደ የከባድ መሣሪያ ድብደባ ደርሷል ያለውን መረጃ እንዳገኙና ማረጋገጥ መቻላቸውን ጠቁመዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአክሱም፣ ደንገላትና በማዕከላዊ ትግራይ በኤርትራ ጦር የተፈፀሙ ግድያዎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም እንዲሁ ማረጋገጣቸውን አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በቅርቡ ታስረው የተፈቱትን የቢቢሲ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሌሎች ዘጋቢዎችና ተርጓሚዎችን በተመለከተ ያላቸውን ስጋትም ገልጸዋል። ምንም እንኳን ጋዜጠኞቹ በአሁኑ ሰዓት ያለ ክስ ቢለቀቁም አንድ የመንግሥት ባለስልጣን "ዓለም አቀፉን ሚዲያ የሚያሳስቱ ግለሰቦችን ተጠያቂ ይሆናሉ" ማለታቸው እንዳሳሰባቸውም ገልፀዋል። "የሰብዓዊ መብት ጥቃት ሰለባዎችና የዓይን እማኞች ጉዳት ሊደርስብን ይችላል በሚል ፍራቻ ሊገደቡ አይገባም" ብለዋል ከፍተኛ ኮሚሽነሯ። ባሽሌት በዛሬው መግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ ረድዔት ድርጅቶች የሰጠውን ፈቃድ እንዲሁም አንዳንድ እርምጃዎቹን በመልካም ጎን አነንስተዋል። በተጨማሪም ባለስልጣናቱ የገቡትን ቃል ወደ ተግባር እንዲለወጡ ጠይቀዋል። የእራሳቸው ቢሮም በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚደረጉ ምርመራዎችን ይደግፋል ብለዋል። በትናንትናው ዕለትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከትግራይ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ የተነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ግድያዎችን በተመለከተም መንግሥት ከፌደራል ፖሊስ፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመጣመር ይመረምራል ብለዋል። ጨምረውም የእነዚህን አካላት ምርመራ መሰረት በማድረግም መንግሥታቸው በድረጊቱ ውስጥ እጃቸው ያለበትን አካላት ወደ ፍትህ እንደሚያቀርብ አፅንኦት ሰጥተው፤ በምርመራው ላይ ተጨማሪ እርዳታ ካስፈለገ መንግሥት የውጭ አካል ሊጋብዝ እንደሚችል ጠቆም አድርገዋል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሚያደርጉት ምርመራ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያም ሆነ ለዓለም ሕዝብ በወቅቱ እንደሚያሳውቁ ጨምረው ቃለ አቀባዩ ገልፀዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት በመፈፀሙ መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ወታደራዊ ዘመቻን ማካሄዱን ገልጿል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን ቢገልጽም በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከፍተኛ ኮሚሽነሯም በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ትግራይ ጦርነቱ መቀጠሉንም መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል። |
news-56343932 | https://www.bbc.com/amharic/news-56343932 | ትግራይ፡ ከ130 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገለጸ | ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ባደረገው ቅኝት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከ131 ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዳሉ አመለከተ። | ድርጅቱ እንዳለው ተፈናቃዮቹ በትግራይና ተጎራባች በሆኑት የአፋር እንዲሁም የአማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 39 በሚሆኑ ተደራሽ ስፍራዎች ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ይህ የተፈናቃዮች መረጃ የተሰበሰበው አዲስ በሆነው 'ዲስፕሌስመንት ትራኪን ማትሪከስ' በተባለ ዘዴ ሲሆን በዚህም የሕዝብ ቁጥርን በተመለከተ መረጃ በመሰብሰብና የሰዎችን ተጋላጭነት እንዲሁም የተፈናቃዮችን ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ መረጃን በመሰብሰብ የሚተነትን ነው። አይኦኤም እንዳለው በዚህ የቅኝት ተግባሩ 30,383 ተፈናቀሉ ቤተሰቦችን መለየት ችሏል። ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያ፣ ምግብና ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቶችን እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እናዳለው "ይህ መረጃ በተከሰተው ቀውስ ምክንያት የተፈናቀሉትን አጠቃላይ ሰዎች የሚያመለክት አይደለም። ከዚያ ይልቅ መረጃውን ለማሰባሰብ አመቺ በሆኑ ስፍራዎች በአገር ውስጥ የተፈናቀሉትን ሰዎች ብቻ የሚወክል ነው።" በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ላይ የቀድሞው የክልሉ አስተዳዳሪ በነበረው በህወሓት ኃይሎች የተሰነዘረበትን ጥቃት ተከትሎ ወታደራዊ ግጭት መጀመሩ አይዘነጋም። በዚህም ሳቢያ ጦርነቱን በመሸሽ ከ60 ሺህ የሚልቁ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ሲሰደዱ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በእዚያው በክልሉ የተለያዩ ስፍራዎች እንደሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በግጭቱ ሳቢያ የተፈናቀሉትን ለመርዳትና መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ የሰብአዊ እርዳታዎችን እያቀረበ መሆኑን ገለጸ ሲሆን፤ ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት እርዳታ ለማቅረብ ፈቃድ አግኝተው ተሳትፎ እያደረጉ ነው። |
news-51749412 | https://www.bbc.com/amharic/news-51749412 | የኦጋዴን ጦርነት፡ የሲያድ ባሬ ወረራ ሲታወስ | ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ - በወቅቱ ዕድሜው 20 ነበር። ካርሎስ ኦርላንዶ ጥር 1970 ዓ.ም. የሶማሊያ ወታደሮች እጅ ላይ ወደቀ። | ከቀኝ ወደግራ - መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ ፊደል ካስትሮ እና ራውል ካስትሮ የዓለም መገናኛ ብዙሃን በተሰበሰቡበት የኢትዮጵያንና ኩባን ወታደራዊ ምስጢር እንዲያወጣ ተደረገ። የኦጋዴን ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው በኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የተደረገው ጦርነት የዛሬ 42 ዓመት የካቲት 26/1970 ዓ.ም. ነበር የተጠናቀቀው። በ1966 ዓ.ም ሶማሊያ የአረብ ሊግን ተቀላቀለች። በወቅቱ የሶማሊያ መሪ የነበረው ሜጀር ጄኔራል ሲያድ ባሬ ኢትዮጵያን ወረረ። ጦርነቱ የተጀመረ ሰሞን የሲያድ ባሬ [ዚያድ ባሬ] ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከዩናይትስ ስቴትስ ጋር ወዳጅነት አለው። በወቅቱ በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ የነበሩት ሶቪዬት ኅብረትና አሜሪካ ምሥራቅ አፍሪካ ገቡ። ፕሬዝደንት አብዲራሺድ አሊ ሸርማርኬን በመንፈቅለ-መንግሥት ፈንግሎ ሥልጣን የጨበጠው የዚያድ ባሬ መንግሥት ድንበር ማስፋፋት ዋነኛ ዓላማው አደረገ። ወሳኟ ቦታ ደግሞ - ኦጋዴን። ኦጋዴን ሠፍሮ የሽምቅ ውጊያ ያካሂድ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ግንባር የኢትዮጵያ ጦር ላይ ጥቃት ሠነዘረ። የጦርነቱ መባቻ ተደርጎ የሚቆጠረውም ይህ ጥቃት ነበር። በመቀጠል የዚያድ ባሬ ጦር በሶቪዬት ኅብረት የጦር መሣሪያ ታግዞ ወደ አጋዴን ገሰገሰ። በወቅቱ ከንጉሡ አገዛዝ ወደ ወታደራዊው ደርግ የተሻጋገረችው ኢትዮጵያ በይፋ ራሷን ማርክሲስት ስትል አወጀች፤ ወዳጅነቷም ከሶቪዬት ኅብረት ጋር ሆነ። አሜሪካ ደግሞ ድጋፏን ለሶማሊያ አደረገች። ሁለቱ አገራት ወደ ቀለጠ ጦርነት ገቡ። በወቅቱ የሲያድ ባሬ መንግሥት ኩባውያን የኢትዮጵያውን ጦር ደግፈው እየተዋጉ ነው ሲል ወቀሰ። ይህንንም ለማሳመን ሲሉ የኩባ ወታደሮች መያዝ ጀመሩ። የዚያኔ ነው ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ ተይዞ ለጋዜጠኞች መግለጫ እንዲሰጥ የተገደደው። ኩባዊው ወታደር ካርሎስ ኦርላንዶ [በስተቀኝ] የዚያድ ባሬ መንግሥት ወራራውን አጠናክሮ በጅግጅጋ በኩል ደንበር አልፎ ገብቶ ብዙ ጥፋት አደረሰ። የንፁሃን ዜጎች ሕይወት ተቀጠፈ። አልፎም ወደ ሐረር ገሰገሰ። ይሄኔ ነው የኢትዮጵያ ክተት የታወጀው። ሐረር ላይ 40 ሺህ ገደማ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ጠበቀው። ተጨማሪ 10 ሺህ የኩባ ጦረኞች ከኢትዮጵያ ጎን ነበሩ። የኢትዮጵያ ጦር የዚያድ ባሬን ጦር አሳዶ ከመሬቱ አስወጣ። የመጨረሻው ውጊያ የነበረው ካራማራ ላይ ነበር። በወቅቱ በዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታገዘው የኢትጵያ ጦር በሰማይ በምድር ጥቃቱን በማጠናከር የሶማሊያ ጦርን ድባቅ መታ። ጦርነቱ ሲጀመር ኢትዮጵያ 10 በመቶ ብቻ የኦጋዴን መሬት በእጇ ነበር። ጦርነቱ ካራማራ ተራራ ላይ ሲያበቃ ኦጋዴን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ተያዘች። በካራማራ ጦርነት በርካቶች ተሰውተዋል። በቀጣናው ያለውን ድርሻ ለማስፋት ኢትዮጵያን የወረረው ሜጀር ጄነራል ሲያድ ባሬ ከሽንፈቱ በኋላ ተቀባይነቱ እየሟሸሸ መጣ። ታላቋ የሚል ቅጥያ የነበራት ሶማሊያም ከኦጋዴን ጦርነት በኋላ በእርስ በርስ ጦርነት መታመስ ጀመረች። ሲያድ ባሬ 1983 ዓ.ም ከሥልጣን ተወግዶ ወደ ናይጄሪያ ሸሸ። ሕልፈተ ሕይወቱም ለአራት ዓመታት በስደት በቆየባት ናይጄሪያ ሆነ። በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል። ከ16ሺህ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። የኢትዮ-ሶማሊያ የኦጋዴን ጦርነት የብዙሃን ሰላማዊ ዜጎችን ቢቀጥፍም፤ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ጅግንነታቸውን ያሳዩበት እንደሆነ በታሪክ ይወሳል። |
news-49520710 | https://www.bbc.com/amharic/news-49520710 | በጃፓን የሴቶችን መቀመጫ የሚጎነትሉ ወንዶችን ለመከላከል ሥውር ማኅተም ተዘጋጀ | ሁነኛ ጸረ-ለከፋ መሣሪያ በጃፓን ተመርቷል። ዋና ዓለማው በአውቶቡስና በባቡር እንዲሁም ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች የሴቶችን ዳሌና መቀመጫ "ቸብ" የሚያደርጉ አጉራ ዘለል ወንዶችን ለመቆጣጠር ነው። | ዲጂታል ሥውር ማኀተሙ የመዳፍ ቅርጽ ያለው ሆኖ የተሠራ ሲሆን ሴቶች ጥቃት አድራሹ ላይ ፈጥነው ምልክት እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል ተብሏል። • "ወፍራም ሴቶች ለአገርም ለቤተሰብም ሸክም ናቸው" የግብፅ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ • "አትግደሉን!"፡ የቱርክ ሴቶች ስለዚህ ሌሎች ሰዎች ወይም የሕግ አካላት ጥቃት አድራሹን በቀላሉ በተለደፈበት ማኅተም ምክንያት ዳናውን ተከትለው ነቅሰው ያወጡታል። ይህንን ሥውር ማኅተም የፈበረከው ኩባንያ ዓላማዬ የሴቶችን ጥቃት መከላከል ነው ብሏል። ሆኖም በሴቶች መብት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ሐሳቡን ሙሉ በሙሉ ወደውታል ማለት አያስደፍርም። "መሣሪያው ተጠቂዋ ላይ ሥራ የሚያበዛ ነው" ይላሉ። ኩባንያው ግን የፈበረኩት መሣሪያ የሴት ዳሌን ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ «ቸብ» ማድረግ የለመዱ 'ቅሌታሞችን' ለማደን እንዲረዳ ነው ይላል። ኩባንያው ረቂቅ ማኀተሙን ለመሥራት ያነሳሳው ባለፈው ግንቦት ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ በብዛት የታየውን ሁለት ሴት ተማሪዎች ጥቃት አድራሽ የሆነን ግለሰብ በቪዲዮ እየቀረጹ ሲያሳድዱት የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምሥል ተከትሎ ነው። በእንግሊዝና ዌልስ የጾታ ጥቃቶች ላይ የሚሠራ አንድ ቡድን ቃለ አቀባይ ለቢቢሲ ስለ ረቂቁ ማኀተም በሰጠችው አስተያየት « የሴቶች ጥቃት ላይ ንግድ ነው የተያዘው» ብላለች። በሰዎች ጥቃትና ፍርሃት መነገድ መልካም ነገር አይደለም ስትል አክላለች። የቶኪዮ ከተማ ዙርያ ፖሊስ ባወጣው አሐዝ በ2017 ብቻ ወደ 3ሺ የሚጠጉ ሴቶች "ወንዶች በባቡር ውስጥ አላስፈላጊ ንክኪ አድርገውብናል" ሲሉ መክሰሳቸውን ተናግረዋል። ይህ ተላካፊ ወንዶችን የሚያድነው መሣሪያ ለገበያ በቀረበ በግማሽ ሰዓት ውስጥ 500 ቅጂ ተሸጧል። የአንዱ ዋጋ 20 ፓውንድ ይደርሳል። • መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው ከዚህ ቀደም በየባቡር ጣቢያው የሴቶችን መቀመጫ የሚነካኩ ጋጠወጦችን ለመቆጣጠር በርካታ ካሜራዎች ባቡር ውስጥ ጭምር መተከላቸው ይታወሳል። ካሜራውን መሠረት በማድረግም 6ሺህ ወንዶች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። የሴቶችን መቀመጫ ከመጎንተልም አልፎ በሞባይል መቅረጽ በጃፓን የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል። ጃፓን የጾታ እኩልነትን በማስከበር ረገድ በዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ሰንጠረዥ ከ149 አገራት 110ኛ ደረጃ ነው ያላት። |
news-47391380 | https://www.bbc.com/amharic/news-47391380 | የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል? | ብዙ ጊዜ ከምግብ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ነገር የቤተሰብ አባላት ስለ ምግብ ያላቸው አስተሳሰብ ነው። በዚሁ ዙሪያ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት አብዛኞቹ አሜሪካዊያን ቤተሰቦች ስለሚመገቡት ምግብ ጤናማነት አብዝተው ይጨነቃሉ። | በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ ቤተሰቦች ደግሞ ምግቡ ምንም ይሁን ምን ዋናው ነገር መጣፈጡ ነው ብለው ያስባሉ። እርስዎ ጥሩ ምሳ በላሁ የሚሉት ምን ሲመገቡ ነው? ምናልባት አንዳንዶች አትክልት የበዛበት ነገር ሊመርጡ ይችላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሥጋ ነክ የሆኑ ምግቦችን ሊያስቀድሙ ይችላሉ፤ በርገር አልያም ፒዛ የሚሉም አይጠፉም። • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የምግቡ አይነት ብቻ ሳይሆን ስለምግቡ የምናወራበት መንገድና ባህላችን ጥሩ ወይም መጥፎ ብለን ለመለየት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ባለሙያዎቹ እንዲያውም ምግብና ስለምግብ የሚደረጉ ውይይቶች የአንድን ማህበረሰብ ባህል፣ ማንነትና ፖለቲካዊ አቋም እስከመግለጽ ይደርሳሉ ይላሉ። ተመራማሪዋ ማርታ ሲፍ ካረባይክ፣ ዴንማርክ ውስጥ ስላጋጠማት ነገር ስታወራ ተማሪዎች 'ሪይ' የተባለውን የዳቦ አይነት ለምሳ ይዘው እንዲመጡ ይመከራሉ ትላለች። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ግን ምግባቸው ጤናማ እንዳልሆነ በአስተማሪዎቻቸው ተነግሯቸው ለቤተሰቦቻቸው ማስጠነቀቂያ ይላካል ስትል ባህል በምግብ ላይ ያለውን ተጽእኖ ታስረዳለች። ''ይህ የሆነው 'ሪይ' የተባለው የዳቦ አይነት የተለየ ጤናማ ንጥረ ነገር በውስጡ ስለያዘ ሳይሆን ባህልና ማንነትን ለመግለጽ ስለሚጠቀሙበት ነው።'' ሌላዋ ተመራማሪ ካትሊን ራይሊ ደግሞ በፈረንሳይ በነበራት ቆይታ አስገራሚ ነገር እንደታዘበች ትናገራለች። የአንድ ማህበረሰብ አባላት ምግባቸው የማይጣፍጥ አልያም መጥፎ እንደሆነ ከተነገራቸው፣ ሰዎቹ ራሳቸው መጥፎ እንደተባሉና ባህላቸውም እንደተሰደበ ይቆጥሩታል። እነዚህ ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ከፍ ያለ ቦታ ከሌሎች ለመለየትና አስጠብቆ ለማስቀጠል ከሚጠቀሟቸው መንገዶች መካከል የሚበሉት የምግብ አይነት በዋነኛነት ይጠቀሳል። ምግቦቻችን ለዓለም ያለንን አመለካከት የሚቀርጹት እንዴት ነው? ማርታ ሲፍ ካረባይክ እንደምትለው ባለፉት አስር ዓመታት አሳማና የአሳማ ተዋጽኦዎችን አብዝቶ መጠቀም የዴንማርኮች መገለጫ እየሆነ መጥቷል። • አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች ዴንማርክ ውስጥ በአንድ ወቅት ትምህርት ቤቶች የአሳማ ስጋን ከምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ አስወጥተው ነበር። ይህ ደግሞ ከዓለም አቀፋዊነትና ስልጣኔ ጋር ተያይዞ እንደመጣ ይታሰባል። ጉዳዩ ያሳሰበው የአንድ ግዛት ምክር ቤት ትምህርት ቤቶች የአሳማ ስጋን በምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዲያካትቱ የሚያስገድድ ሕግ አውጥቶም ነበር። በሕጉ መሰረት ማንኛውም ተማሪ የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ቢሆን የዴንማርክ መገለጫ የሆኑ ምግቦች የመመገብ ግዴታ አለበት። የአሳማ ስጋ ደግሞ ዋነኛው ምግባቸው ነው። ስለዚህ ዴንማርካዊያን 'ሪይ' የተባለውን ዳቦ ሲመገቡ ስለጤናቸው በማሰብ ሲሆን የአሳማ ስጋን ሲበሉ ደግሞ ባህላቸውንና ማህበረሰባዊ እሴቶቻቸውን ከማስቀጠል አንጻር ነው። • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች ካትሊን ራይሊ እንደምትለው ድሮ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ምግብ ሳይሆን የተሻለ ሥራ ነበር። ዛሬ ዛሬ ግን ሰዎች የሚበሉትን ምግብ በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ቦታ እንደማሳያ ይጠቀሙታል። |
48014334 | https://www.bbc.com/amharic/48014334 | የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም | ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን ትባላለች። የጡት ካንሰር የቀዶ ጥገና ሀኪም ነበረች። የጡት ካንሰር ይዟት ሥራዋን ለማቆም እስከተገደደችበት ጊዜ ድረስ በሙያዋ ብዙ ሴቶችን አገልግላለች። | ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን ስለ ህመሟ ስትናገር፦ "እንደ አብዛኞቹ ሴቶች ጡቴን አልተመረመርኩም ነበር። የጡት ካንሰር ሀኪም ስለሆንኩ የጡት ካንሰር ይይዘኛል ብዬ አስቤ አላውቅም" • አስጊነቱ እየጨመረ ያለው ካንሰር ህክምና ስትማር ቢያንስ ለ20 ዓመት የጡት ካንሰር ሀኪም እሆናለሁ ብላ ነበር። ነገር ግን በሙያዋ መሥራት የቻለችው ሁለት ዓመት ብቻ ነበር። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 ጡቷ ላይ ቀዶ ጥገና ተደርጎ ነበር። ባለፈው ወር ካንሰር ዳግም አገርሽቶባታል። ዶ/ር ሊዝ ኦሪዮርዳን "ከሀኪምነት ወደ ታማሚነት ልሸጋገር ነው?" የጡት ካንሰር እንዳለባት ከማወቋ በፊት ጡቷ ላይ አንዳች ምልክት ታይቷት ነበር። ጡት በሚመረመርበት ኤክስሬይ 'ማሞግራም' ስትታይ ጡቷ ላይ ችግር እንደሌለ ተነገራት። ቢሆንም ምልክቱን በድጋሚ ስታይ እናቷ ካንሰር እንድትመረመር አደረጓት። በምርመራውም ካንሰር እንዳለባትም ታወቀ። የጡት ካንሰር ሀኪም በመሆኗ ምን እንደሚያስፈልጋት ለማወቅ አማካሪ አላስፈለጋትም። "ከሀኪምነት ወደ ታማሚነት ልሸጋገር ነው?" ብላ ትካዜ ቢገባትም፤ ኬሞቴራፒ እንደሚያስፈልጋት እንዲሁም ምን ያህል ጊዜ በሕይወት መቆየት እንደምትችል ታውቃለች። • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ዶ/ር ሊዝ አሁን 43 ዓመቷ ነው። ብዙ ዶክተሮች ህክምና በሚሰጡበት በሽታ አንደማይያዙ ትናገራለች። ዶክተሯ 'ሬድዮቴራፒ' (የጨረር ህክምና) ካደረገች በኋላ የክንዷ እንቅስቃሴ ተገደበ። ቀዶ ጥገና ማድረግም አልቻለችም። ህመሙ አካል ላይ የሚያደረሰውን ጉዳት እንጂ ሥነ ልቦናዊ ተጽዕኖው እስከሚደርስባት ድረስ አታውቅም ነበር። "የጡት ካንሰር ላለበትን ሰው መንገር እንጂ በበሽታው መያዝ ምን ማለት እንደሆነ አላውቅም ነበር።" ሀኪሟ ከቀዶ ጥገና በኋላ ትከሻዋን እንደቀድሞው ማዘዝ አልቻለችም "የራሴን ህመም ደጋግሞ ማስታወስ ነው የሆነብኝ" ካንሰር እንደያዛት ካወቀች በኋላ የቀዶ ጥገና አማካሪ ከሆነ ባለቤቷ ጋር ተመካክራ የትዊተር ገጿ ላይ ስለመታመሟ ጻፈች። ትዊተር ላይ 1,500 ተከታዮች ያሏት ሲሆን፤ እንደሷው የጡት ካንሰር ያለባቸው ሴቶች ማኀበራዊ ሚድያ ላይ ድጋፍ ይቸሯት ጀመረ። • "ወንዶች በጡት ካንሠር እንደሚያዙ አላውቅም ነበር" እንደሷው ሀኪም ሆነው የጡት ካንሰር ከያዛቸው ሴቶች ጋር የተገናኘችውም በማኀበራዊ ሚዲያ ነበር። የዋትስአፕ ቡድን ፈጥረው ተሞክሯቸውን ይጋራሉ። የጡት ካንሰር ከያዛት በኋላ ህመሙ ያለባቸውን ሰዎች በተሻለ ሁኔታ መርዳት እንደምትችል ገምታ ነበር። ሆኖም እንዳሰበችው ቀላል ሆኖ አላገኘችውም ። "ለእያንዳንዷ ሴት የጡት ካንሰር እንዳለባት መንገር ከባድ ነው። የራሴን ህመም ደጋግሞ ማስታወስ ነው የሆነብኝ" ትላለች ዶ/ር ሊዝ። ቀዶ ጥገና ከተደረገላት በኋላ ታካሚዎቿ ላይ ቀዶ ጥገና ማድረግ ተቸግራ ነበር "እኔና እሷ አንድ ነን" ትሠራበት በነበረው ሆስፒታል አንድ በሷ ዕድሜ ያለችና እንደሷው አይነት የጡት ካንሰር ያለባት ሴት ህክምና ትከታተል ነበር። ሰለታማሚዋ ከሌሎች ሀኪሞች ጋር እየተነጋገረች ሳለ "ያለችበት ሁኔታ እጅግ የከፋ ነው" ሲባል ልክ ስለሷ እንደሚወራ እንደተሰማት ትናገራለች፤ "እኔና እሷ አንድ ነን" ስትልም የተሰማትን ስብራት ትገልጻለች። • የካንሰር የደም ምርመራ "አሰደናቂ ውጤት" አስገኘ ዶ/ር ሊዝ ሰዎች ካንሰር ከያዛቸው በኋላ ወደሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ትመክራለች። በርካታ መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞቻቸው ካንሰር ከያዛቸው በኋላ ወደሥራ የሚመለሱበትን መንገድ እንደማያመቻቹም ትናገራለች። አሁን የጡት ካንሰር ላለባቸው ሴቶች እገዛ ማድረግ በምትችልባቸው ማህበሮች ውስጥ ትሳተፋለች፤ ታማክራለችም። "አማካሪ ሆኜ በዓመት ቢያንስ ከ70 እስከ 100 ሴቶች እረዳለሁ። በመጽሐፌ ደግሞ መቶ ሺዎችን አግዛለሁ" ትላለች ዶክተሯ። |
news-57077652 | https://www.bbc.com/amharic/news-57077652 | የኢትዮጵያ ምርጫ፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ሕብረት ምርጫው ታዛቢ ይልካል አለ | የአውሮፓ ሕብረት ቀጣዩን 6ኛ አገራዊ ምርጫ እንዲታዘቡ ባለሙያዎቹን ይልካል ሲሉ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። | ከአውሮፓ ሕብረት በተጨማሪ ከአሜሪካ እና ሩሲያ የተውጣጡ የባለሙያዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንደሚመጡ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባዩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ ባለመቻሉ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ አስቦ የነበረውን የምርጫ ታዛቢ እንዲቀር መወሰኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት የቀደመ ውሳኔውን ሰርዞ ምርጫውን ለመታዘብ ስለመወሰኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም። ሕብረቱ የሚልካቸው የምርጫ ታዛቢ ቡድን የሚሰማራበት ቁልፍ መለኪያዎች /ፓራሜትርስ/ ላይ ከመንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ አልተቻለም ብሎ ነበር። የአውሮፓ ሕብረት ይህን ካለ በኋላ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ከአንድ ሳምንት በፊት በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ ካቀደው የአውሮፓ ሕብረት ጋር ያልተስማማቸው ሕብረቱ ሉዓላዊነትን የሚጻረር ጥያቄን በማቅረቡ ነው ብለው ተናግረው ነበር። ቃል አቀባዩ በወቅቱ የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩን ላለመላክ የወሰነው በሁለት ምክንያት ነው ብለዋል። ይህም ሕብረቱ አገሪቱ የሌላትን የኮሚኒኬሽን ስርዓት ማስገባትን አስገዳጅ ማድረጉ እንዲሁም የምርጫውን ውጤት ይፋ የማደርገው እኔ ነኝ ማለቱን ተናግረው ነበር። ይህም የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና ደህንነት የሚጻረር ስለሆነ ከስምምነት ሳይደረስ ቀርቷል ሲሉ አስረድተው ነበር። ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ዛሬ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ ሕብረት ምርጫ ታዛቢ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥት የያዘው አቋም እንዳልተቀየረ ተናግረው፤ ከአውሮፓ ህብረት ስድስት አባላትን የያዘ ቡድን፣ ከአሜሪካ ሁለት ተቋማት የተውጣጣ እንዲሁም ከሩሲያና የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን የሚታዘቡ ባለሙያዎች ይመጣሉ ብለዋል። |
news-51764786 | https://www.bbc.com/amharic/news-51764786 | የኮሮናቫይረስ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ላይ ያጠላው ስጋት | የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ስጋት ምክንያት በአዲስ አበባ ሊካሄዱ ታቅደው የነበሩ ስብሰባዎች በመሰረዛቸው በአዲስ አበባ በሚገኙ ሆቴሎች ገቢ ላይ ተጽእኖ እንደሚያስከትል ተነገረ። | የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ብስራት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ባይከሰትም በሌሎች አገራት ውስጥ ባለው ሁኔታ ሳቢያ ተጓዦች ቀደም ሲል የያዙትን እቅድ እየሰረዙ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ባይኖራቸውም የሚሰረዙት ከፍተኛ የቋማትና የግለሰብ መረሃግብሮች በአገሪቱና በሆቴሎች ገቢ ላይ የእራሳቸው የሆነ ተጽእኖ እንደሚኖራቸው አመለክተዋል። አቶ ቢኒያም እንደ አብነትም አዲስ አባባ ውስጥ ሚያዚያ ወር ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውና አንድ ሺህ ሰው እንደሚሳተፍበት የሚጠበቀው የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ዓመታዊ ጉባኤ ተሰርዟል። በዚህም እያንዳንዱ ተሳታፊ አራት ምሽቶችን አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚያሰልፍ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን አንድ ሰው በአማካይ በአንድ ምሽት 100 ዶላር የሚከፍል ቢሆን የ400 ሺህ ዶላር ገቢ ሳይገኝ እንደሚቀር ተናግረዋል። ከእነዚህ መካከል በተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አማካይነት ከመጋቢት 9 እስከ 15 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ በከፍተኛ ሚኒስትሮች ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ጉባኤ አንዱ ነው። ይህም በገንዘብ፣ በዕቅድና በምጣኔ ሃብታዊ ልማት ሚኒስትሮች አማካይነት የሚደረግና የ53ኛው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጉባኤ አካል ነበር። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንን ጨምሮም በኮሮናቫይረስ መስፋፋት ሳቢያ እየጨመረ በመጣው ስጋት ከአጋሮቹ ጋር በመመካከር ለጥንቃቄ ሲባል ተጨማሪያ ማስታወቂያ እስኪያወጣ ድረስ "ሁሉም ሕዝባዊ ስብሰባዎች ለሌላ ጊዜ መተላላፋቸውን" ገልጿል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ አገራት ውስጥ በመስፋፋቱ ለሥራም ሆነ ለእረፍት ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች በሽታው ባስከተለው ስጋት ሳቢያ ዕቅዳቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል። በዚህም የሆቴል ዘርፉ ላይ የገቢ መቀነስ እንደሚያስከትል አቶ ቢያኒያም አመልክተዋል። የበሽታው መስፋፋትና ስጋት በዚሁ ከቀጠለ ግንቦትና ሠኔ አካባቢ ፊፋ የሚያዘጋጀው ትልቅ መሰናዶ እንዲሁም የዓለም ኢኮኖሚ መድረክ ለመስከረም ወር የያዟቸው ትልልቅ ስብሰባዎችንም የመካሄድ ጉዳይን ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባው እንደሚችል ጠቅሰዋል። እስካሁን በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ባይከሰትም ከሚያሳጣው ገቢ በላይ አሳሳቢው ነገር የጤና ጉዳይ በመሆኑ ማኅበሩ በሆቴሎች የሚገኙ ሠራተኞች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ ስልጠናዎችንና የጥንቃቄ መመሪያዎችን እየሰጡ ነው ብለዋል። ይህ በዓለም ዙሪያ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በገደለው የኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት የታላላቅ ጉባኤዎች መሰረዝ እያጋጠመ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የአፍረካ አገራት ውስጥ ጭምር ነው። ከእነዚህም መካከል በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በመጪው ሳምንት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው 'ዘ ኔክስት አይንስታይን ፎረም' የተባለው ስብሰባ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል። መድረኩ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለአምስት ቀናት ከ79 አገራት በላይ በመጡና ከሁለት ሺህ የሚበልጡ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት እንደነበር ተገልጿል። ሌላው ደግሞ የአፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ፎረም የተባለውና በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን ውስጥ በሚቀጥለው ሳምንት ለሁለት ቀናት ሊካሄድ የነበረው ስብሰባም እንደዚሁ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር ተደርጓል። |
47743552 | https://www.bbc.com/amharic/47743552 | ዓለም ለሴቶች እንዳልተሰራች የሚያሳዩ ነገሮች | ካሮላይን ክሪያዶ ፔሬዝ ነገሮች ሁሌም ከወንዶች አንፃር ብቻ መቃኘታቸውንና ይህች ዓለም እንዴት ለወንድ ብቻ እንድትሆን ተደርጋ እየተቀረፀች እንዳለ ጥናት መስራት የጀመረችው በአንድ ወቅት የልብ ህመምን በሚመለከት የተሰበሰቡ መረጃዎች ሁሉ በወንዶች የህመሙ ምልክት ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆናቸውን ካስተዋለች በኋላ ነው። | ጡትን ከግንዛቤ ካልከተቱት የፖሊስ ጥይት መከላከያ ልብሶችና ጫማዎች ጀምሮ በርካታ ነገሮች ወንድን ብቻ ታሳቢ በማድረግ የተሰሩ እንደሆኑ ትናገራለች። የህዋ ልብሶች በአንድ ወቅት ናሳ ሴቶች ብቻ ወደ ህዋ የሚያደርጉትን ጉዞ በመሰረዙ በትዊተር ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበት ነበር። ጉዞው የተሰረዘው ጠፈርተኛዋ አኒ ማክሌን ከዚህ በፊት ትለብስ የነበረው የህዋ ጉዞ ልብስ ትልቅ የነበረ ቢሆንም ሙሉ የሴት ቡድን በሚያደርገው ጉዞ ላይ ግን መካከለኛ መጠን ያለው ልብስ የበለጠ ልኳ ስለሆነ እሱን እለብሳለሁ በማለቷ ነበር። • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? የህዋ ልብሶቹ ወንዶችን ብቻ ታሳቢ አድርገው የሚሰሩ በመሆናቸው ትልቅ፣ በጣም ትልቅና ምናልባትም መካከለኛ መጠን ብቻ እንዲኖራቸው ተደርገው ነው የተሰሩት፤ ትንሽ ሚባል ነገር የለም። በወቅቱ በናሳ ሁለት መካከለኛ መጠን ያላቸው የህዋ ልብሶች የነበሩ ቢሆንም ለጉዞ ዝግጁ ተደርጎ የነበረው ግን አንዱ ብቻ ነበር። የጦር መሳሪያዎች እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 አሜሪካ ቀደም ሲል ወንዶችን ብቻ ትመለምልበት ለነበረው የምድርና ባህር ኃይል ክፍል ሴቶችን መመልመል ብትጀምርም በእነዚህ ክፍሎች ያሉ የጦር መሳሪያዎች ሁሉ ግን ለወንድ ብቻ እንዲመቹ ሆነው የተሰሩ ናቸው። የዲሞክራቲክ ፓርቲዋ የኮንግረስ አባል ኒኪ ሶንጋስ ይህ የአገሪቱ ጦር ኃይል ምን ያክል ለሴት አባላቱ ፍላጎቶች ምላሽ እንደማይሰጥ ማሳያ መሆኑን ተናግረው ነበር። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና በዚህ ምክንያት ሴት ወታደሮች መሳሪያ ለመተኮስና የጥይት መከላከያ ልብሶችን መልበስ እንኳ እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት የጦር ኃይሉ ለሴቶች ምቹ የሆኑ መሳሪያዎችን እንደሚያቀርብ አስታውቆ ነበር። በሴቶች የወታደራዊ አገልግሎት ላይ ጥናት የሰሩት አሌክስ ኤሊያስ "ሴቶች እስከ 2018 ለወንዶች በተሰሩ መሳሪያዎች በኢራቅና በአፍጋኒስታን ተሰማርተው ነበር" ብለዋል። ስማርት ስልኮች የስማርት ስልክ መተግበሪያዎችና የስልኮቹ መጠን ራሱ ለወንዶች እንዲሆኑ ተደርገው ተሰርተዋል ብለው የሚያስቡ ብዙ ሴቶች ናቸው። በአማካይ የሴቶች እጅ ከወንዶች በአንድ ኢንች የሚያንስ ሲሆን የስማርት ስልክ አምራች ኩባንያዎች ደግሞ የስልኮቹን መጠን እያሳደጉ መምጣታቸው ችግር ነው ይላሉ። 12 ሴ.ሜ በሆነ ወይም በትልቅ አይፎን በአንድ እጅ ስልክን ይዞ መልዕክት መላክ ለበርካታ ሴቶችና ትንሽ እጅ ላላቸው ወንዶች ከባድ ወይም የማይቻል ነው። የስፖርት ልብሶች ታዋቂው የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ስቴፈን ከሪ አዲስ የህፃናት የስፖርት ጫማ ንድፍ ሲያወጣ የሰራው ለወንዶች ብቻ የነበረ ሲሆን፤ አንዲት የዘጠኝ ዓመት ህፃን ለምን የወንዶች ብቻ የሚል ደብዳቤ ፅፋለት ነበር። "የሴቶችን የሩጫ ስፖርት እንደምትደግፍ አውቃለሁ ምክንያቱም ሁለት ሴቶች ልጆች አሉህ" በማለት ስህተቱን እንደሚያርም ተስፋ እንደምታደርግ ገልፃ ነበር። • ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ እሱም ህፃኗን ስለደብዳቤዋ አመስግኖ ስለተፈጠረው ነገር ማብራሪያ ሰጥቷል። ሳይንሳዊ መሳሪያዎች በካንሳስ አልያንስ የባይሎጂ ተመራማሪ የሆኑት ጀሲካ ማውንትስ በቤተ ሙከራ የሚጠቀሟቸው የምርምር መሳሪያዎች በሙሉ ለወንድ ተብለው የተሰሩ እንደሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ ይህ መሆኑ ደግሞ የሚረብሽ ብቻ ሳይሆን ለአደጋ ስጋት እንደሚሆንም ይናገራሉ። ሰፋፊ ገዋኖች እንቅስቃሴ ላይ በቁሳቁሶች ሲያዙ ትልልቅ ቡትስ ጫማዎች ደግሞ ለመውደቅ ይዳርጋል። የሥራ ቦታዎች የታሪክና ሌሎችም ምሁራን ወንበሮችና ሌሎችም የቢሮ እቃዎች ለወንዶች ምቹ እንዲሆኑ ተደርገው መሰራታቸውን የሚመለከቱ ጥናቶችን አድርገዋል። ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆኑት የታሪክ ምሁሯ ዋጅዳ ሺርሊ በኩባንያዎች ውስጥ ሁሌም ስለ ቡድን ሥራ ውጤታማነት እንደሚወራ፤ ነገር ግን ይህ ትርጉም እንደማይሰጥ "ምቹ በሆነ አካባቢ ሳይቀመጥ ማን ስለ ቡድን ስራ ሊጨነቅ ይችላል?" በማለት ያስረዳሉ። |
news-55950981 | https://www.bbc.com/amharic/news-55950981 | የዘር ቅንጣት የሚያክል እስስት ተገኘ | ተመራማሪዎች በምድራችን ላይ ትንሽ ነው የተባለ እስስት በማዳጋስካር ማግኘታቸውን ተናገሩ። | እስስቱ ከማነሱ የተነሳ የዘር ቅንጣት ያክላል ተብሏል። የማዳጋስካር እና ጀርመን ተመራማሪዎች በተጨማሪም ሁለት ትንንሽ እንሽላሊቶች ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል። ወንዱ እስስት፣ ብረኬዢያ ናና የሚባል ሲሆን አካሉ 13.5 ሚሊሜትር እንደሆነ ተገልጿል። በሙኒክ እንደሚገኘው ባቫሪያን የእንስሳት ሙዚየም ከሆነ ይህ እስስት በዓለም ላይ ከታወቁት 11 ሺህ 500 ተሳቢ እንስሳት መካከል በጣም ትንሹ ነው። ይህ በዓለማችን ላይ ትንሽ ነው የተባለው እስስት፣ ከጭራው ጫፍ እስከ አፍንጫው ድረስ ርዝመቱ 22 ሚሜትር ርዝመት አለው። ሴቷ ግን ከወንዱ በጥቂት ሚሊ ሜትሮች ረዘም ትላለች ያሉት ተመራማሪዎች 29 ሚሜትር እንደምትረዝም አሳውቀዋል። ተመራማሪዎቹ ሌላ ዝርያ ይገኛል በሚል ተስፋ ጥረታቸውን ቀጥለዋል። አዲሱ እስስት የተገኘው በሰሜን ማዳጋስካር ሞንታኔ በሚባል ጫካ ውስጥ ሲሆን የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተብሏል። በሃምቡርግ በሚገኘው የተፈጥሮ ታሪክ ማዕከል ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ኦሊቨር ሃውልቲሼክ ይህ የፍሬ ያክል ትንሽ የሆነ እስስት በደን ጭፍጨፋ ምክንያት ለመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል። ነገር ግን አካባቢው በቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥበቃ እየተደረገለት ሲሆን ይህም ዝርያው ሊተርፍ ይችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል። ተመራማሪዎች ይህንን የእስስት ዝርያ ምስጥ አድኖ እንደሚበላ እና በምሽት በሳሮች መካከል እንደሚደበቅ ደርሰውበታል። ተመራማሪዎች ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ይህ የእስስት ዝርያ በዓለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ ሕብረት ዘንድ ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል እጅግ በጣም ለአደጋ የተጋለጡ ዝርያዎች ዝርዝር ውስጥ እንዲመዘገብ ጠይቀዋል። |
news-55089960 | https://www.bbc.com/amharic/news-55089960 | ለጭቁኖች ተቆርቋሪው የክፍለ ዘመኑ ታላቅ የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ ማራዶና | አንፀባራቂ ስብዕና፣ ድንቅ ችሎታ፣ የላቀ አእምሮ፣ ተናዳጅ፣ ቁጡ፣ ለተጨቋኞች አዛኝ፣ እብሪተኛ ሌላም ሌላም. . . | በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የእግር ኳሱ ሊቅ ዲያጎ ማራዶና በህይወት እያለ ይሰጠው የነበሩ ስሞች ናቸው - የዓለማችን የእግር ኳስ ጀግና። ለእግር ኳስ የተፈጠረ ነው የሚባልለት አርጀንቲናዊው ማራዶና ለየት ያለ ድንቅ ችሎታን፣ ራዕይና ፍጥነትን ቀልብ ከመሳብ ጋር በማጣመር በርካታ አድናቂዎቹን አስደምሟል። "የአምላክ እጅ" ተብሎ በሚጠራው አወዛጋቢ ጎል፣ በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ መዘፈቁና ሌሎች ከግል ህይወቱ ጋር በተያያዘም ደጋፊዎቹ የተመሳቀለ እይታ እንዲኖራቸው አድርጓል። በአሁኑ ወቅት ጣልያንን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያሉ አድናቂዎቹ እየዘከሩት ሲሆን በተለይም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ ታላቅ ቦታ አለው። በርካታ ጊዜያትም "ልቤም ሆነ ውስጤ ፍልስጥኤማዊ ነው" ሲል የተሰማው ማራዶና "ጭቆናን እናውቃለን" በማለትም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ለፍልስጥኤም ያለውን ድጋፍ አሳይቷል። አጭርና ጣፋጭ ህይወት- የእግር ኳሱ ሊቅ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና የተወለደው በአርጀንቲናዋ፣ ቦነስ አይረስ የድሆች መንደር ውስጥ ከዛሬ 60 ዓመት በፊት ነበር። የእግር ኳስ ፍላጎቱም የተጠነሰሰው ገና በታዳጊነቱ ሲሆን፤ በእግር ኳስ ታሪክ ታላቅ ቦታ ላይ መድረስ ችሏል። አንዳንዶችም ከታላቁ የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች ፔሌ ያስበልጡታል። ማራዶና በ491 ጨዋታዎች 259 ጎሎችን በማስቆጠል የደቡብ አሜሪካ ተቀናቃኙን ፔሌን በመብለጥ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ ተጫዋች መሆን ቢችልም፤ ወደ በኋላ እግር ኳስን በበላይነት የሚያስተዳድረው ፊፋ የምርጫ ሕጉን በመቀየሩ ሁለቱም የክፍለ ዘመኑ ምርጥ በመሆን ተሰይመዋል። በእናቱ ማህፀን እግር ኳስን የለመደ ይመስል ማራዶና ገና በህፃንነቱ ነበር የላቀ ችሎታውን ማሳየት የጀመረው። ሎስ ሴቦሊታስ የተባለ የታዳጊዎች ቡድንን በመምራት በ136 ጨዋታዎች ባለመሸነፍ አይበገሬነቱን አሳይቷል። የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ህይወቱንም የጀመረው በ16 ዓመቱ አካባቢ ነው። አጠር ብሎ ደንደን ያለ ሰውነት ያለው ማራዶና ቁመቱም 1.65 ሜትር ነው። ሲታይ የተለመደው አይነት የስፖርተኛ ሰውነት የለውም። ነገር ግን ቀልጣፋነቱ፣ ነገሮችን ቀድሞ የመረዳት ችሎታው፣ የኳስ ቁጥጥሩ፣ ኳስ ማንቀርቀብና ቶሎ ማሳለፍ መቻሉ ላለመረጋጋቱና ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመውን የክብደት ችግሩን አካክሶለታል። ምንም እንኳን የተቀናቃኝ ቡድንን ተከላካዮች በቀላሉ ማለፍ ቢችልም ማራዶና በግል ህይወቱ ራሱን በርካታ ጊዜ ችግር ውስጥ ተዘፍቆ አግኘቶታል። የአምላክ እጅና የክፍለ ዘመኑ ጎል ማራዶ ለአገሩ በተሰለፈባቸው 91 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ 34 ጎል አስቆጥሯል። ነገር ግን ይህ ምናልባት ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ጨዋታ ታሪኩ ውስጥ ከወንዝ ውሃን በማንኪያ እንደ መጨለፍ የሚቆጠር ነው። በጎሮጎሳውያኑ በ1986 ሜክሲኮ ላይ በተደረገው የዓለም ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑን የመራው ማራዶና ከአራት ዓመታት በኋላም አገሩን ለመጨረሻ ዙር አደረሳት። በተለይም በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የተከሰተው ውዝግብ የማራዶና መታወቂያ ሆነ። በወቅቱ አርጀንቲናና እንግሊዝ ያደርጉት ጨዋታ እግር ኳስ ብቻ አልነበረም፤ ፖለቲካም የተቀላቀለበት ነበር። ከውድድሩ ከዓመታት በፊት ለአስር ሳምንታት ያህል ፎክላንድስ ተብላ በምትጠራው ደሴት ምክንያት አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ጦርነት ገጥማ ነበር። በጨዋታው ላይ ሁለቱም የውጊያው መንፈስ ሳይለቃቸው ወደ ሜዳ ገብተው በእግር ኳሱም ላይ ይሄው የፀበኝነት ስሜት ነበር የተንፀባረቀው። ለ51 ደቂቃዎችም ያህል ያለ ምንም ጎል ጨዋታው ሲካሄድ ቆይቶ በድንገት ማራዶና ከግብ ጠባቂው ፒተር ሺልተን ጋር ዘሎ የተሻማትን ኳሷን በተቃራኒው መረብ አስቆጠረ። ማራዶና ከጨዋታው በኋላም ግቧ እንዴት እንደተቆጠችረ በተናገረበት ወቅት በጎሉ ውስጥ "ማራዶና ትንሽ ነበረበት፤ የአምላክም እጅ በትንሹ ነበረበት" በማለት ተናገረ። በዚሁ ጨዋታ ላይ ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ብዙዎች 'የክፍለ ዘመኑ ጎል' ብለው የጠሩትን ግብ አስቆጠረ። የተቀናቃኙን ቡድን አባላት እጥፍጥፍ አድርጎ፤ ሜዳው ላይ ብቻውን ያለ ሰው ይመስል፤ ጎሏን አስቆጠረ። "ድንቅ ጎል ነበረች። የእግር ኳስ እልቅና የታየበት፤ የሚገርም ነው" በማለት የቢቢሲው ዘጋቢ ቤሪ ዴቪስ ተናግሯል። በጨዋታው እንግሊዝ አንድ ጎል ብታስቆጥርም፤ አርጀንቲና 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች። ለማራዶና ማሸነፉ ከጨዋታው፤ ከእግር ኳስም በላይ ነበር "እንግሊዞችን መዘረር" ፖለቲካዊ ድልም ነበረው። የናፖሊው ጀግና- በአደንዛዥ እፅ መዘፈቅ የዓለም አቀፍ የዝውውር ክብረ ወሰንን ማራዶና ሁለት ጊዜ መስበር ችሏል። በአገሩ ሲጫወትበት ከነበረው ቦካ ጁኒየርስ ወደ ስፔኑ ባርሴሎና በጎሮጎሳውያኑ 1982 ሲዛወር በ3 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ ወደ ጣልያኑ ክለብ ናፖሊም በ5 ሚሊዮን ፓውንድ ተዛወረ። በጣልያኗ ሳን ፓውሎ ስታዲየም በሄሊኮፕተር ሲያርፍም 80 ሺህ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ ተገኝተው ነበር- አዲሱን ጀግና ለመቀበል። ይህም በእግር ኳስ ታሪኩ ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገበት ወቅት ነው። ክለቡ በ1987 እና በ1990 የሊጉ አሸናፊ እንዲሆን እንዲሁም የአውሮፓ ሊግ ዋንጫን በ1989 እንዲያነሳም ቀዳሚውን ሚና የተጫወተው ማራዶና ነው። የመጀመሪያውን ድል በማስመልከት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በጎዳናዎች ላይ በመውጣት ለአምስት ቀናት ያህል ደስታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ወቅት ማራዶና የሁሉንም ትኩረት ሳበ የሚጠበቅበትም ኃላፊነት ከፍተኛ ሆነ። ይህ ደግሞ ጫናንና መጨናነቅን አስከተለ። "ታላቅ ከተማ ናት ግን መተንፈስ እንኳን አልቻልኩም። ነፃ ሆኜ በመንገዶች ላይ መረማመድ እፈልጋለሁ። እኔም እንደ ሌላው ሰው ነኝ" ብሏል በወቅቱ። ከጣልያኑ የካሞራ ማፊያ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት አለው በሚል፣ የኮኬይን አደንዛዥ እፅ ሱስ ውስጥ መዘፈቅና ከልጅ ማደጎ ጋር በተፈጠረ እሰጣገባም ጋር ስሙ በተደጋጋሚ መነሳት ጀመረ። በጎርጎሳውያኑ በ1990 ጣልያን ላይ በተዘጋጀው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በጀርመን 1 ለ 0 አገሩ አርጀንቲና መሸነፏን ተከትሎ እንዲሁም በቀጣዩ ዓመትም በተደረገለት ምርመራ አደንዛዥ እፅ መጠቀሙ በመታወቁ ለ15 ወራት እንዲታገድ ምክንያት ሆነ ። ከዚህ ሁሉ አገግሞና ራሱን አድሶ በጎሮጎሳውያኑ 1994 አሜሪካ ላይ ወደ ተካሄደው የዓለም ዋንጫ ቢመለስም ጎል አስቆጥሮ ደስታውን የገለፀበት መንገድ ያልተለመደና በርካቶችንም ያስደነገጠ ነበር። ማራዶና የታገደውን ኤፊድሪን የተባለ የተከለከለ አበረታች መድኃኒት ወስዶ በመገኘቱ ከውድድሩ እንዲወጣ ተደረገ። ህይወት ከጡረታ በኋላ ለሦስተኛ ጊዜ አበረታች እፅ በደሙ ውስጥ ከሦስት ዓመት በኋላ መገኘቱን ተከትሎ በ37 ዓመቱ ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ራሱን አገለለ። ነገር ግን ተጫዋቹን ችግሮች አልለቀቁትም። በጋዜጠኞች ላይ ተኩሷል በሚልም ሁለት ዓመት ከአስር ወራት እስር ቢፈረድበትም በማስጠንቀቂያ ታልፏል። የኮኬይንና የአልኮል መጠጡም የጤና እክል አስከትሎበታል ተብሏል። በከፍተኛ ሁኔታም ኪሎው የጨመረ ሲሆን፤ በአንድ ወቅት 128 ኪሎ ግራምም ይመዝን ነበር። በጎሮጎሳውያኑ 2004 በልብ ህመም ምክንያት ፅኑ የህሙማን ክፍል ውስጥ ገብቶም ነበር። ማራዶና ክብደቱን ለመቀነስ ቀዶ ህክምና ያደረገ ሲሆን ከአደንዛዥ ዕፅ ሱስም ለመላቀቅ ኩባ መኖር ጀመረ፤ የቀድሞውን የኩባ መሪና ሶሻሊስትና የነፃነት ታጋይ ፊደል ካስትሮንም አግኝቷቸው ነበር። ከዚህ ሁሉ በኋላ በጎሮጎሳውያኑ 2008 የአርጀንቲና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣን ሆነ። በዚያው ዓመትም በነበረው የዓለም ዋንጫ አገሩ ለሩብ ፍፃሜ የበቃች ቢሆንም በጀርመን 4 ለ 0 ከተሸነፈ በኋላ ከቡድኑ ጋር የነበረው የሁለት ዓመት ቆይታ ተቋጫ። ውሻው ሻሪ ፔይ ከንፈሩን ነክሳው ቀዶ ህክምና ማድረጉ፣ ከትዳሩ ውጭ ለወለደው ለዲያጎ አርማንዶ ጁኒየር እውቅና መስጠቱም ስሙ ከየመድረኩ እንዳይጠፋ አደረገው። ከሁለት ዓመት በፊት ሩሲያ በተደረገው የዓለም ዋንጫ አርጀንቲናና ናይጄሪያ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተገኝቶ የነበረው ማራዶና የብዙዎች መነጋገሪያነት ሆኖ ነበር። ከናይጄሪያ ደጋፊ ጋር አብሮ መደነሱ፣ ከጨዋታው በፊት ወደ ሰማይ አንጋጦ ያደረገው ፀሎት፣ ሊዮነል ሜሲ ጎል ሲያስቆጥር በከፍተኛ ሁኔታ መደሰቱ፣ መሃል ላይ መተኛቱ እንዲሁም አርጀንቲና ሁለተኛ ጎል ስታስቆጥር የመሃል ጣቱን ሁለት ጊዜ ማሳየቱ ለሚዲያዎች ትኩስ ወሬ ነበር። ማራዶና ባለ ብዙ ስሙ፣ ለተጨቋኞች አዛኝ፣ አዝናኝ፣ ታላቅ፣ ቁጡ፣ የሚያዋርድና ሌሎች የተባለው ታላቁ እግር ኳሰ ተጨዋች ይህችን ዓለም ቢሰናበትም ህይወቱን የኖረበት መንገድ ለወደፊት ትውልድ የሚዘከረው፣ በእግር ኳስ ችሎታው የማይሞት ስምና አሻራ ትቶ አልፏል። |
news-51353306 | https://www.bbc.com/amharic/news-51353306 | ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን የገነባችውን ሆስፒታል ልትከፍት ነው | የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት መዛመትን ተከትሎ ቻይና ለኮሮና ቫይረስ በብቸኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ገንብታ ጨርሳለች። | ሆስፒታሉን የገነባችው የቫይረሱ መነሻ በሆነችው ዉሃን ከተማ ሲሆን የግንባታው ስራን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ስምንት ቀናት ብቻ ነው ያስፈለጉት። ሆዎሸንሻን የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሆስፒታል አንድ ሺ የህሙማን አልጋዎች አሉት። ቻይና ከዚህ ሆስፒታል በተጨማሪ ለኮሮናቫይረስ ህሙማንን ብቻ የሚያክሙ ሆስፒታሎችን በመገንባት ላይ ናት። በመላው ቻይና በተስፋፋው ኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እስካሁን 17 ሺ የደረሰ ሲሆን ለ361 ህይወት መቀጠፍም ምክንያት ሆኗል። ኮሮናቫይረስ ለቻይና ብቻ ሳይሆን ለዓለም ስጋት መሆኑ ቀጥሎ ፊሊፒንስ ውስጥ አንድ ግለሰብ በቫይረሱ ህይወቱ ማለፏ ተረጋግጧል። ከቻይና ውጪ በቫይረሱ ሰው ሲሞት ይህ የመጀመሪያው ነው። የ44 ዓመቱ ቻይናዊ ግለሰብ ከዉሃን የመጣ ሲሆን፤ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው ግለሰቡ ፊሊፒንስ ከመድረሱ በፊት በቫይረሱ ተይዞ ነበር። ይህንንም ተከተሎ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች በርካታ አገራት ከቻይና የሚመጡ በረራዎችን አግደዋል። ነገር ግን የአለም ጤና ድርጅት በረራዎችን ማገድ ከሚጠቅመው በላይ ሊጎዳ እንደሚችል ምክሮችን እየለገሰ ነው። መረጃዎች እንዳይተላለፉ እንቅፋት ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የህክምና ቁሳቀሱሶች በቀላሉ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፤ እንዲሁን አጠቃላይ የአገራትን ኢኮኖሚ ይጎዳል። ከዚህ በተጨማሪም ተጓዦች በህገወጥ መንገድ ድንበሮችን እንዲያቋርጡ በር ስለሚከፍት የቫይረሱን በፍጥነት የመዛመቱን ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻቅበው ይችላል ይላል ከአለም ጤና ድርጅት የተገኘው መረጃ። አለም አቀፍ በረራ እግዶችን ተከትሎ ቻይና የአለም ጤና ድርጅትን ምክር የተላለፈ ነው በማለት ተችታዋለች። ከቻይና የጤና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እንዲሁም ከቻይና ውጭም 150 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውም ተረጋግጧል። በሁቤ ግዛት በምትገኘው ዉሃን ከተማም ሆስፒታሎች በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ የመጣውን የህሙማንን ቁጥር ለማከም ከአቅማቸው በላይ ነውም ተብሏል። ከሰሞኑም የሆንግ ኮንግ ዶክተሮች ቻይናን የሚያገናኘው ድንበር ሊዘጋ ይገባልም በሚል አድማ መትተዋል። የቻይና ባለስልጣናት ግን በአለም ጤና ድርጅት ምክር መሰረት ድንበሩ እንደማይዘጋና መመርመሪያ ቦታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ነገር ግን የቻይና ባለስልጣናትን ምላሽ አጥጋቢ አይደለም ያሉት እነዚህ ዶክተሮች ቻይና የጠየቁትን የማታደርግ ከሆነ ከነገ ጀምሮ ዶክተሮችም ሆነ ነርሶች የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በቦታቸው ላይ እንደማይገኙ ነው። ከሰሞኑም የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ የወቅቱ አሳሳቢ የምድራችን የጤና ስጋት ነው ሲል አውጇል። • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ •ኤርትራ አሜሪካ የጣለችው የቪዛ እገዳ አግባብነት የለውም አለች የድርጅቱ ዋና ዳይሬክትር ዶክትር ቴድሮስ አድሃኖም ይፋ እንዳደረጉት ለዚህ ውሳኔ ዋነኛው ምክንያት "በቻይና የተከሰተው ነገር ሳይሆን በሌሎች አገሮች እየሆነ ያለው ነው" ብለዋል። የዓለም የጤና ድርጅት የበሽታ ወረርሽኝ ተከስቶ ከዚህ አይነት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ይህ ስድስተኛው ሲሆን ከዚህ ቀደም ኤችዋን ኤን ዋን የተባለው ኢንፍሉዌንዛ፣ ኢቦላ፣ ፖሊዮ፣ ዚካና በድጋሚ የተከሰተው ኢቦላ ምክንያት ነበሩ። በሽታው ሲጀምር በትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ተከትሎት ይከሰታል፤ ከዚያም ከሳምንት በኋላ የትንፋሽ ማጠርን በማስከተል አንዳንድ ህሙማንን የሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያስፈልጋቸው ሊያደርግ ይችላል። በአራት ሰዎች ላይ ከሚከሰተው ይህ በሽታ አንዱ እጅግ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ። በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ማስነጠስና የአፍንጫ ፈሳሽ ላይታይበት ይችላል። የኮሮናቫይረስ ቀለል ካለ የጉንፋን ምልክቶች አንስቶ እየከፋ ሲሄድ እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። በሽታው የተያዙ ሰዎችን ለሞት እስከሚዳርጋቸው የተወሰነ ጊዜን ስለሚወስድ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል የተወሰኑት እስካሁንም ሊሞቱ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል። በተጨማሪም ምን ያህል እስካሁን ያልተመዘገቡ በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል። |
news-50709909 | https://www.bbc.com/amharic/news-50709909 | የቀድሞ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ መደፈሯን እንዳትናገር አባቷ እንደተጫኗት አሳወቀች | የቀድሞ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦብ ሃውኬ ልጅ እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1980ዎቹ ላይ ብትደፈርም የፖለቲካ ህይወታቸውን እንዳትጎዳ በሚል በምስጢርነት እንድትይዘው መገደዷን ከሰሞኑ ይፋ አድርጋለች። | ሮዝሊን ዲለን ውንጀላዋን ያቀረበችው ፍርድ ቤት መሆኑን የአውስትራሊያ ሚዲያ ዘ ኒው ደይሊ ዘግቧል። • ታዳጊዋ አንድን ግለሰብ ከጎርፍ ለማዳን ስትጥር ህይወቷ አለፈ • አምስቱ ተስፋ የተጣለባቸው አፍሪካውያን ሙዚቀኞች ደፋሪዋ ሌበር ፓርቲን ወክሎ የፓርላማ አባል የነበረው ቢል ላንደርዩ መሆኑንም ተናግራለች። አባቷም ሆነ ፖለቲከኛው ቢል ላንደርዩ በህይወት የሉም። የ59 አመቷ ሮዝሊን በአባቷ ንብረት ላይ የአራት ሚሊዮን ዶላር ይገባኛል ጥያቄም አንስታለች። በሰጠችው ምስክርነት ፖለቲከኛው የደፈራት ቢሮው ውስጥ ትሰራ በነበረበት ወቅት ነው። ሌሎች ሚዲያዎች እንደዘገቡት በተለያዩ ሶስት ጊዜያት መደፈሯን ነው። በሶስተኛው ጊዜ መደፈሯን ለአባቷ የተናገረች ሲሆን ለፖሊስ ልትከስ መሆኗን ብታሳውቀውም በወቅቱ የአባቷ ምላሽ " ወደ ፖሊስ መሄድ አትችይም። በአሁኑ ሰዓት ውዝግብ ውስጥ መግባት አልችልም። የሌበር ፓርቲን አመራር ለመቆጣጠር የስልጣን ፍትጊያዎች አሉ" እንዳላት የፍርድ ቤት መረጃዎች ያሳያሉ። እህቷም ሱ ፒተርስ ሃውክ ለኒውደይሊ እንደተናገረችው መደፈሯን ታውቅ እንደነበር ነው። • ለዓመቱ ምርጥ የታጨችው ኢትዮጵያዊት "በወቅቱ ለተለያዩ ሰዎች ተናግራ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ድጋፍ ሰጥተዋታል፤ ነገር ግን የትኛውንም የፍትህ ስርዓት ያሳተፈ አልነበረም" በማለት ቃሏን ሰጥታለች። ሌሎች የቤተሰቡ አካላት ምንም ከማለት ተቆጥበዋል። ቢል ላንደርዩ በፓርላማ አባልነት እንደ ጎርጎሳውያኑ ከ 1976-1992 አገልግሏል። ከአባቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦብ ሃውኬም ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸው ተብሏል። በአውስትራሊያ ፖለቲካ ትልቅ ስፍራ የነበራቸውም ቦብ ሃውኬም አራት ጊዜ ምርጫዎችን ማሸነፍ ችለዋል ። በሃገሪቱም የኢኮኖሚ እንዲሁም የማህበረሰቡ ለውጦች ላይ ትልቅ ስፍራ ተጫውቷል ይባላል። |
news-53216682 | https://www.bbc.com/amharic/news-53216682 | ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የሙከራ በረራ ሊያደርግ ነው | ቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላን በዚህ ሳምንት ወሳኝ የፍተሻ በረራ ያደርጋል። | በዓለም ዙሪያ ያሉ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች እንዲቆሙ ተደርገዋል ምናልባትም ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆየው የማክስ 737 የበረራ ሙከራ የፋይናንስና የመልካም ስም እጦት ለገጠመው ቦይንግ አንድ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል። ሆኖም የዚህ የሙከራ በረራ ስኬታማነት ማክስ 737 ወደ ገበያ የመመለስ ዋስትናን አይሰጠውም። አውሮፕላኑ ወደ ገበያ ለመመለስ ገና በርካታ ሌሎች ፈተናዎችን ማለፍ ይጠበቅበታል። በቦይንግ ታሪክ ከፍተኛ ገበያ የነበረው ይህ የአውሮፕላን ሞዴል ሁለት ተከታታይ አደጋዎች ከደረሱበትና ተሳፋሪዎችም ከሞቱ በኋላ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። በኢንዶኒዢያና በኢትዮጵያ አየር መንገዶች አውሮፕላኖች ላይ የደረሱ አደጋዎችን ተከትሎ የዚህ የማክስ 737 አውሮፕላን ግዢን የፈጸሙ፣ አውሮፕላኑን ሲጠቀሙ የነበሩ፣ አውሮፕላኑን ለመረከብ ሲጠባበቁ የነበሩና አዲስ ግዥ ለማድረግ ቀብድ የከፈሉ ጭምር ምርቱ ላይ ጥያቄ በማንሳታቸው ቦይንግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቶ ቆይቷል። ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚደረጉ በበራዎች ስኬታማ ቢሆኑ እንኳ ማክስ 737 ወደ ሰማይ ለመመለስ ገና በርካታ የደኅንነትና የምህድስና ፍተሻዎችን ማድረግ ይጠበቅበታል። ይህም ሂደት ከዚህ በኋላ በርካታ ወራትን ሊወስድ ይችላል ተብሏል። የአቪየሽን ተቆጣጣሪዎች ማክስ 737 ቦይንግ አውሮፕላንን ከበረራ ያገዱት የዛሬ 15 ወር ገደማ ሲሆን ይህም የላየን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ በአምስት ወራት ልዩነት የደረሰውን እጅግ አሰቃቂ አደጋን ተከትሎ ነበር። በሁለቱ አደጋዎች በድምሩ 346 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የበረራ እግዱን ተከትሎ የ103 ዓመቱ አንጋፋው የቦይንግ ኩባንያ ላይ የካሳና የደኅንነት ጥያቄዎች አንዲነሱበት አድርጓል። በዚህም ሳቢያ ኩባንያው የከፋ ችግር ውስጥ ገብቶ እንደቆየ ይታወሳል። በተለይም የአሜሪካ የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር የአውሮፕላኖችን የበረራ ደኅንነት የሚፈትሽበት መንገድ ላይ በአጠቃላይ ጥያቄ እንዲነሳ ማድረጉ አይዘነጋም። ቦይንግ መጀመርያ አካባቢ የአደጋዎቹን ችግሮች ከራሱ ለማራቅ ከፍተኛ ሙከራ ሲያደርግ ቆይቶ ነበር። አደጋውን ተከትሎ የተደረጉ ጥብቅ ምርመራዎች ግን የማክስ 737 አውሮፕላኖች ስሪት ላይ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓታቸው አንዳች ግድፈት እንዳለበት የጠቆሙ ነበሩ። አሁን ማክስ 737 እነዚህ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓቶቹ ላይ ያደረገውን የምህንድስና ማሻሻያ ተከትሎ ማሻሻያው ምን ያህል ስኬታማ እንደሆነ ለማረጋገጥ መለስተኛ የበረራ ሙከራዎችን በዚያው በቦይንግ ማምረቻ ሲያትል አካባቢ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በዚህ የሙከራ በረራ አብራሪዎች ሆን ብለው የማክስ 737 ግድፈት ነበረበት የተባለውን የኤምካስ ሶፍትዌር ቁልፍን በመጫን አውሮፕላኑ ራሱን በራሱ መቆጣጠር ይችል እንደሆን ይመለከታሉ ተብሏል። የአሜሪካ የበረራ ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት ለአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ ዛሬ ለሚጀመረው የሙከራ በረራው ይሁንታ መስጠቱን አስታውቋል። በዚህ ደብዳቤ ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቱ እንደገለጸው የማክስ አውሮፕላኖች ወደ ሥራ እንዲመለሱ ገና ፈቃድ አልሰጠም። ይህ እንዲሆን ገና ብዙ የሙከራ ሂደቶች መታለፍ አለባቸው ብሏል። ይህ የሙከራ በረራ ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ባለፈው ዓመት ሲሆን በመሀሉ በአውሮፕላኑ ላይ አንዳች ሌላ ያልተጠበቀ ግድፈት በመገኘቱ ነበር በድጋሚ ሙከራው እንዲዘገይ የተደረገው። ይህ የሙከራ መለስተኛ በረራ ከተደረገ በኋላ በበራው ሂደት የተገኙ ቴክኒካዊ ነጥቦች አንድ በአንድ ይተነተናሉ፣ ይጠናሉ ተብሏል። ሙከራው እንከን አልባ ሆኖ ቢጠናቀቅ እንኳ ይህ አውሮፕላን በቀጥታ ወደ ሥራ ይመለሳል ማለት አይደለም። አብራሪዎችን ከአውሮፕላኑ ጋር እንዲዋሀዱ ለማድረግ የስልጠና መርሀ ግብር ይዘረጋል፣ የአውሮፓና የካናዳ የበረራ ተቆጣጣሪዎች ደግሞ ለዚህ አውሮፕላን እውቅናና ይሁንታ መስጠት ይኖርባቸዋል። የአውሮፓ አቪየሽን ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ማክስ 737 ከአሜሪካ የአቪየሽን አስተዳደር የጤናማነት እውቅና ተሰጥቶት ወደ ሥራ መመለስ ይችላል የሚል ሰርተፍኬት ቢሰጠው እንኳ ይህ አውሮፕላን በአውሮፓ ሰማይ ላይ ለመብረር ያስችለዋል ማለት አይደለም ብሏል። ከአውሮፓ የኖርዌይ አየር መንገድ፣ ቲዩአይ እና አይስላንድ አየር መንገድ ይህን የቦይንግ ምርት የሆነውን ማክስ 737 አውሮፕላን ይጠቀሙ የነበሩ ሲሆን ሌሎች አገሮች ደግሞ አውሮፕላኑ እንዲመረትላቸው አዘው ሲጠባበቁ የነበሩ ናቸው። |
53864758 | https://www.bbc.com/amharic/53864758 | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መጠሪያውን እና የብሮድካስት መብቱን ሊሸጥ ነው | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ እንዲችሉ ጨረታ ማውጣቱን ገለፀ። | ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፤ ማህበሩ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን ለመሸጥ አቅዶ ጨረታ ማውጣቱን ተናግረዋል። አንደኛው፤ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በቴሌቪዥን ለማሰራጨት የብሮድካስቲንግ መብቱን ለመሸጥ በማሰብ የዓለም አቀፍ እንዲሁም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኖች እንዲወዳደሩ ጨረታ ማውጣቱን ገልፀዋል። ሁለተኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ኩባንያ የሚጠራበትን ስም ለመሸጥ ጨረታ ማውጣታቸውን አቶ ክፍሌ ሰይፈ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 16 ቡድኖች በጋራ ያቋቋሙትና በንግድ ድርጅትነት የተመዘገበ ማህበር መሆኑን ሥራ አስኪያጁ አቶ ክፍሌ ጨምረው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምከንያት በዝግ ስታድየም የሚታይ ከሆነ፣ እንዲሁም ምርመራ እንዲደረግ ግዴታ የሚቀመጥ ከሆነ ተጨማሪ ወጪ ስለሚጠይቅ እነዚህን ነገሮች ለመሸፈን በማሰብ የተለየ አማራጭ ማሰባቸውን ጨምረው ተናግረዋል። ከሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ የአክሲዮን ማህበሩ አባል ቡድኖች ከመንግሥት ድጎማ ተላቅቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሁም በአፍሪካም ሆነ በአውሮፓ ደረጃ ያሉ የስፖርት ቡድኖች እንደሚያደርጉት የስፖርት ኢንቨስትመንት ውስጥ እንዲገቡ መነሻ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ከጨረታው የሚገኘው አብዛኛው ገቢ የሚሰጠው ለእግርኳስ ቡድኖቹ መሆኑን የተናገሩት አቶ ክፍሌ፣ ቀሪው የድርጅቱ ሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል ብለዋል። ማሕበሩ የተቋቋመው የእግር ኳስ ቡድኖቹ ከመንግሥት ድጎማ ነፃ እንዲወጡ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚሳተፉ 16 ክለቦች መካከል ሁለቱ ቡድኖች ብቻ የራሳቸውን ወጪ በመሸፈን የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ደጋፊ አካላት (ስፖንሰርሺፕ) እንዳላቸው ገልፀዋል። ቀሪዎቹ 14 የእግር ኳስ ቡድኖች የከተማ ክለቦች ወይም ስፖንሰር የሌላቸው መሆናቸውን በመጥቀስ እነዚህን ቡድኖች በገቢ ራስን ማስቻል የዚህ ማህበር ቀዳሚ ዓላማ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ችግሮች እንዳለባቸው የሚጠቅሱት ኃላፊው፣ በአመራር ችግር ደሞዝ የማይከፈላቸው በመኖራቸው ከጨረታው የሚገኘው ገንዘብ አብዛኛው ለክለቦች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህንን የገቢ ክፍፍልን በሚመለከት የማስፈፀሚያ ሰነድ ተዘጋጅቶ 16ቱም ክለቦች መስከረም ወር ላይ ውይይት ካደረጉበት በኋላ የሚፀድቅ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ማህበሩ በርካታ ተጫራቾች እናገኛለን ብሎ ያሰበው ከዓለም አቀፍ ተጫራጮች መሆኑንም ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጨረታው ላይ የአገር ውስጥ ድርጅቶችም እንደሚሳተፉ የገለፁት አቶ ክፍሌ በሚወዳደሩበት ወቅት ምክረ ሃሳብ አዘጋጅተው ገቢ የሚያገኙበትን መልክ እና የድርሻ ክፍፍሉ ምን እንደሚመስል ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፟። በኢትዮጵያ እግርኳስ ረዥም ታሪክ ቢኖረውም፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ከማይሸጥባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። |
47770243 | https://www.bbc.com/amharic/47770243 | በወሲብ ፊልሞች ሱሰኛ የሆኑ ወጣት ሴቶች | ኔላም ቴለር የወሲብ ፊልሞችን ማየት የጀመረችው በ12 ዓመቷ ነበር። ገና አንድ ፍሬ ልጅ በምትባልበት ጊዜ። በመኝታ ክፍሏ ተደብቃ አጠር ያለ የአስር ደቂቃ የወሲብ ፊልም ማየት የጀመረችው በለጋ እድሜዋ ነው። | ኋላ ላይ እስከ አንድ ሰዓት ርዝማኔ ያላቸው ምስሎችን ማየት ጀመረች። በጊዜው ከቤተሰቦቿ ተደብቃ ታይ እንደነበር የምትናገረው ኔላም ለመጀመሪያ ጊዜ የወሲብ ፊልም ስታይ "የፍቅር ፊልሞች ወሲብን የተቀደሰና በፍቅር የተሞላ አድርገው ነበር አዕምሮዬ ላይ የሳሉት፤ ልክ በወንዶች ሃያልነት የተሞላና አካላዊ ተራክቦው የጎላበትን ምስል ማየት በጣም ነው ያስደነገጠኝ" ትላለች። የወሲብ ምስሎችን ማየት የጀመረችበትን ሰበብ ስታስታውስ ጉዳዩን ለማወቅ ከነበራት ፍላጎት ወይም ለአቅመ-ሔዋን እየደረሰች ስለነበረ የአፍላ ጉርምስና ግፊት ይሆናል በማለት ትናገራለች። ከጊዜ በኋላም የተለያዩ የወሲብ ምስሎችን ከማየቷ የተነሳ የራሷ ምርጫዎች እያዳበረች መጣች። • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት • የወንድ የእርግዝና መከላከያ፤ ለምን እስካሁን ዘገየ? "ወጣት ሴቶች በዕድሜ ገፋ ካሉ ወንዶች ጋር ሆነው ለሚሰሩ የወሲብ ምስሎች ልዩ ስሜት አደረብኝ። ሴቶቹ ታዛዥ ሆነው ወንዶቹ የበላይ የሆኑባቸውን ምስሎች በ13 ዓመቴ መፈለግ ጀመርኩ" የምትለው ኔላም ይህ ፍላጎቷ ብዙ የወሲብ ምስል ከማየቷ የተነሳ ይሁን ወይም ተፈጥሯዊ የሆነ ስሜት መለየት ይከብዳታል። የ25 ዓመቷ ሳራም ከኔላ የተለየ ልምድ የላትም። የወሲብ ምስሎችን ማየት የጀመረችው በ13 ዓመቷ ነበር፤ ለዚያውም በሳምንት ሁለት ጊዜ። "10 ወንዶችና 1 ሴት፤ በውስጡም ብዙ የወንዱን የበላይነት የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎች የተካተቱበትን ምስሎች ያየሁት የሩካቤስጋ መፈፀም ከመጀመሬ በፊት ነው " የምትለው ሳራ አሁን በ25 አመቷ ወደ ወሲብ ስሜት ለመግባት በጣም እንደሚከብዳት ትናገራለች። እስካሁን የወሲብ ምስል ሱስ በወንዶች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ በደንብ የተጠና ሲሆን፤ በሴቶች ላይ ያለው ጫና ግን በውል አልተጠናም። ብዙ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ሴቶች የወሲብ ምስልን እንደሱስ እንደማይጠቀሙትና በእነርሱ ላይ ብዙም ተፅዕኖ እንደሌለው ይናገራሉ። በዚህ የሕይወት መንገድ ላይ ያለፉ ሴቶች ግን ተመሳሳይ መልስ አይሰጡም። ዶ/ር ለይላ ፈሮድሻ የፅንስና የማህፀን አማካሪ ስትሆን በ20 ዓመት የስራ ልምዷ "አንድም የማያቸው የወሲብ ምስሎች ችግር እየፈጠሩብኝ ነው" ብላ የመጣች ሴት አጋጥማት እንደማታውቅ ትናገራለች። በጉዳዩም በደንብ ጥናት እንዳልተደረገበት የምትናገረው ለይላ "ሴቶች አካላዊና ስለ ልቦናዊ ጥቃት እየደረሰባቸው ነገርግን የሐኪም እርዳታ እየጠየቁ ስላልሆነ ነው? ወይስ ስለደረሰባቸው ችግር ለመናገር አፍረው? ወይስ ምንም ችግር እየፈጠረባቸው አይደለም?" በማለት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ታቀርባለች። ኔላም 16 ዓመቷ ሲሆን የወሲብ ምስሎችን ማየት አቆመች፤ ለዚህ ደግሞ ሰበብ የሆናትን ስትጠቅስ ምስሎቹ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ስለሚከቱ ነው ትላለች። ከእውነታው እያራቀች እንደነበር የምትገልፀው ኔላም "የወሲብ ምስል አይቼ የማገኘው የስሜት እርካታና ከጓደኛዬ ጋር ከወሲብ በኋላ ያለኝ ስሜት ያላቸው ልዩነት ያስፈራኝ ነበር።" አሜሪካዊቷ ፀሃፊ ኤሪካ ጋርዛ የወሲብ ምስል ማየት የጀመረችው በ12 ዓመቷ እንደሆነ ስትናገር "ትምህርት ቤት ያላግጡብኛል፤ ብዙ ጊዜም ብቸኛ ነበርኩ። ስለዚህም የወሲብ ምስሎችን ችግሬን የምረሳበትና እራሴን የማስደስትበት ነገር ነበር" ትላለች። ኤሪካ የወሲብ ምስሎችን ማየቷ በጣም ጫና እንዳደረሰባትና ለአንዳንድ የተለዩ የወሲብ መንገዶች የተለየ ስሜት እንዲኖራት እንዳደረገ ትናገራለች። በወሲብ ጊዜ ወንዱ ጉልበተኛና እኔን እንደፈለገ ማድረግ እንደሚችል ዓይነት ስሜቶችን እንድቀበል አድርጎኛል የምትለው ኤሪካ "ወንዶቹ ከሴቶቹ በዕድሜ ትልቅ የሆኑባቸውን ምስሎች ማየቴም ወንዶች በወሲብ ጊዜ ጉልበተኛ እንዲሆኑ እንድፈልግ አድርጎኛል" ስትል ታስረዳለች። ኔላምም በተመሳሳይ መልኩ የወሲብ ምስሎችን በለጋ ዕድሜዎ ማየቷ ወሲብን የምታይበትን መንገድ እንደቀየረው ትናገራለች። " 17 ወይም 19 እድሜዬ ላይ ስደርስ ታላቆቼ ከሆኑ ጋር ግንኙነት መፍጠር ጀመርኩ። ይህ ሁኔታዬ የተፈጥሮ ባህሪዬ ይሁን የወሲብ ምስል ማየቴ የፈጠረው ለማወቅ አልችልም" ትላለች። እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገ የ300 የወሲብ ምስሎች ግምገማ 88 በመቶ የሚሆኑት አንዱ ፆታ በወሲብ ላይ ያለውን የበላይነትን የሚያመላክቱ ሲሆን ብዙዎቹም የወንዶች የበላይነት ናቸው። በምስሎቹም ሴቶቹ በወንዶቹ ባህሪ በደስታ ወይም ከስሜት ነፃ በሆነ መልኩ እንደሚመልሱ ያሳያሉ። |
End of preview. Expand
in Dataset Viewer.
README.md exists but content is empty.
- Downloads last month
- 52