doc_no
int64
1
12.6k
doc_text
stringlengths
81
395k
relevant_topic_nos
sequencelengths
0
1
relevant_topic_titles
sequencelengths
0
1
relevant_topic_descriptions
sequencelengths
0
1
relevant_topic_narratives
sequencelengths
0
1
12,301
8  ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ ቀደም ሲል ከተገለጠልኝ ራእይ በኋላ ለእኔ፣ ለዳንኤል ሌላ ራእይ ተገለጠልኝ። 2  እኔም ራእዩን ተመለከትኩ፤ በራእዩም ላይ ራሴን፣ በኤላም አውራጃ በሚገኘው በሹሻን ግንብ አየሁት፤ ደግሞም ራእዩን ተመለከትኩ፤ እኔም በኡላይ የውኃ መውረጃ አጠገብ ነበርኩ። 3  ዓይኔን አንስቼ ስመለከት፣ እነሆ በውኃ መውረጃው አጠገብ ሁለት ቀንዶች ያሉት አንድ አውራ በግ ቆሞ ነበር። ሁለቱ ቀንዶች ረጃጅም ነበሩ፤ ይሁንና አንደኛው ከሌላው ይረዝማል፤ ይበልጥ ረጅም የሆነው ቀንድ የበቀለው በኋላ ነው። 4  አውራ በጉ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ በቀንዱ ሲወጋ ተመለከትኩ፤ አንድም አውሬ ሊቋቋመው አልቻለም፤ ከእጁም መታደግ የሚችል ማንም አልነበረም። የፈለገውን ያደርግ ነበር፤ ራሱንም ከፍ ከፍ አደረገ። 5  እየተመለከትኩ ሳለ፣ እነሆ አንድ አውራ ፍየል ከምዕራብ ተነስቶ መሬት ሳይነካ መላዋን ምድር እያቋረጠ መጣ። አውራውም ፍየል በዓይኖቹ መካከል ጎልቶ የሚታይ ቀንድ ነበረው። 6  እሱም በውኃ መውረጃው አጠገብ ቆሞ ወዳየሁት ሁለት ቀንድ ወዳለው አውራ በግ አመራ፤ በታላቅ ቁጣም ተንደርድሮ መጣበት። 7  ወደ አውራው በግ ሲቀርብ አየሁት፤ በበጉም እጅግ ተመርሮ ነበር። በጉን መትቶ ሁለቱንም ቀንዶቹን ሰባበራቸው፤ አውራውም በግ ሊቋቋመው የሚችልበት አቅም አልነበረውም። በጉን መሬት ላይ ጥሎ ረጋገጠው፤ አውራ በጉንም ከእጁ የሚያስጥለው አልነበረም። 8  ከዚያም አውራው ፍየል እጅግ ታበየ፤ ሆኖም ኃያል በሆነ ጊዜ ትልቁ ቀንድ ተሰበረ፤ በምትኩም ጎልተው የሚታዩ አራት ቀንዶች ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በቀሉ። 9  ከእነሱ መካከል ከአንደኛው፣ አንድ ሌላ ትንሽ ቀንድ በቀለ፤ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ውብ ወደሆነችው ምድር በጣም እያደገ ሄደ። 10  ወደ ሰማይ ሠራዊት እስከሚደርስ ድረስ እያደገ ሄደ፤ ከሠራዊቱና ከከዋክብቱ መካከልም የተወሰኑትን ወደ ምድር ጣለ፤ ረጋገጣቸውም። 11  በሠራዊቱ አለቃ ላይ እንኳ ሳይቀር ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፤ የዘወትሩም መሥዋዕት ከአለቃው ተወሰደ፤ ጽኑ የሆነው የመቅደሱ ስፍራም ፈረሰ። 12  ከተፈጸመው በደል የተነሳ ሠራዊቱ ከዘወትሩ መሥዋዕት ጋር ለቀንዱ አልፎ ተሰጠ፤ እውነትን ወደ ምድር ጣለ፤ እንደ ፈቃዱ አደረገ፤ ደግሞም ተሳካለት። 13  ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላውም ቅዱስ እየተናገረ ለነበረው ቅዱስ እንዲህ አለው፦ “ስለ ዘወትሩ መሥዋዕትና ጥፋት ስለሚያመጣው በደል እንዲሁም ቅዱሱ ስፍራና ሠራዊቱ እንዲረገጡ ስለመተዋቸው በሚገልጸው ራእይ ላይ የታየው ነገር የሚቆየው እስከ መቼ ነው?” 14  እሱም “2,300 ምሽቶችና ንጋቶች እስኪያልፉ ድረስ ነው፤ ቅዱሱም ስፍራ ወደ ትክክለኛው ሁኔታ በእርግጥ ይመለሳል” አለኝ። 15  እኔ ዳንኤል ራእዩን እየተመለከትኩና ለመረዳት እየጣርኩ ሳለ፣ ሰው የሚመስል ድንገት ከፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁ። 16  ከዚያም ከኡላይ መካከል የሰው ድምፅ ሰማሁ፤ እሱም ጮክ ብሎ “ገብርኤል፣ ለዚህ ሰው ያየውን ነገር አስረዳው” አለ። 17  በመሆኑም እኔ ወደቆምኩበት ስፍራ ቀረበ፤ ሆኖም ወደ እኔ ሲመጣ፣ በጣም ከመደንገጤ የተነሳ በግንባሬ ተደፋሁ። እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ራእዩ የሚፈጸመው በዘመኑ ፍጻሜ መሆኑን ተረዳ” አለኝ። 18  እኔ ግን እያናገረኝ ሳለ መሬት ላይ በግንባሬ ተደፋሁ፤ ከባድ እንቅልፍም ወሰደኝ። ስለዚህ ዳሰሰኝና ቆሜበት በነበረው ቦታ እንድቆም አደረገኝ። 19  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ በቁጣው ዘመን ማብቂያ ላይ የሚሆነውን ነገር አሳውቅሃለሁ፤ ምክንያቱም ራእዩ በተወሰነው የፍጻሜ ዘመን ይፈጸማል። 20  “ያየኸው ሁለት ቀንዶች ያሉት አውራ በግ የሜዶንንና የፋርስን ነገሥታት ያመለክታል። 21  ፀጉራሙ አውራ ፍየል የግሪክን ንጉሥ ያመለክታል፤ በዓይኖቹ መካከል ያለው ትልቁ ቀንድ የመጀመሪያውን ንጉሥ ያመለክታል። 22  ቀንዱ ተሰብሮ በምትኩ አራት ቀንዶች እንደወጡ ሁሉ ከእሱ ብሔር የሚነሱ አራት መንግሥታት ይኖራሉ፤ ሆኖም የእሱን ያህል ኃይል አይኖራቸውም። 23  “በዘመነ መንግሥታቸውም መገባደጃ ላይ በደለኞቹ እስከ መጨረሻ በደል ሲፈጽሙ፣ ግራ የሚያጋቡ አባባሎችን የሚረዳ አስፈሪ መልክ ያለው ንጉሥ ይነሳል። 24  ኃይሉ እጅግ ታላቅ ይሆናል፤ በገዛ ኃይሉ ግን አይደለም። ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጥፋት ያደርሳል፤ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለታል። በኃያላን ሰዎችና በቅዱሳኑ ሕዝብ ላይ ጥፋት ያደርሳል። 25  መሠሪ ዘዴ ተጠቅሞ ብዙዎችን በማታለል ረገድ ይሳካለታል፤ በልቡም ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ሰዎች ተረጋግተው በሚኖሩበት ጊዜም በብዙዎች ላይ ጥፋት ያደርሳል። አልፎ ተርፎም የልዑላን ልዑል በሆነው ላይ ይነሳል፤ ሆኖም የሰው እጅ ሳይነካው ይሰበራል። 26  “ምሽቶቹንና ንጋቶቹን በተመለከተ በራእይ የተነገረው ነገር እውነት ነው፤ አንተ ግን ራእዩን በሚስጥር ያዝ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ የሚሆነውን ነገር የሚያመለክት ነውና።” 27  እኔም ዳንኤል ኃይሌ ተሟጠጠ፤ ለተወሰኑ ቀናትም ታመምኩ። ከዚያም ተነስቼ ለንጉሡ የማከናውነውን ሥራ መሥራት ጀመርኩ፤ ሆኖም ባየሁት ነገር የተነሳ ደንዝዤ ነበር፤ ራእዩንም ማንም ሰው ሊረዳው አልቻለም።
[]
[]
[]
[]
12,302
9  በከለዳውያን መንግሥት ላይ ንጉሥ ሆኖ የተሾመውና የሜዶናውያን ተወላጅ የሆነው የአሐሽዌሮስ ልጅ ዳርዮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት፣ 2  አዎ፣ በዘመነ መንግሥቱ የመጀመሪያ ዓመት እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ኤርምያስ በተነገረው የይሖዋ ቃል ላይ በተጠቀሰው መሠረት ኢየሩሳሌም ፈራርሳ የምትቆየው ለ70 ዓመት እንደሆነ ከመጻሕፍቱ አስተዋልኩ። 3  በመሆኑም ወደ እውነተኛው አምላክ ወደ ይሖዋ ፊቴን አዞርኩ፤ ማቅ ለብሼና በራሴ ላይ አመድ ነስንሼ በጸሎትና በጾም ተማጸንኩት። 4  ወደ አምላኬ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ፤ ደግሞም ተናዘዝኩ፤ እንዲህም አልኩ፦ “እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ለሚወዱህ፣ ትእዛዛትህንም ለሚያከብሩ ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅና ታማኝ ፍቅር የምታሳይ ታላቅና የምትፈራ አምላክ ነህ፤ 5  እኛ ኃጢአት ሠርተናል፤ በደል ፈጽመናል፤ ክፋት ሠርተናል እንዲሁም ዓምፀናል፤ ከትእዛዛትህና ከድንጋጌዎችህ ዞር ብለናል። 6  ለነገሥታታችን፣ ለመኳንንታችን፣ ለአባቶቻችንና ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በስምህ የተናገሩትን አገልጋዮችህን ነቢያትን አልሰማንም። 7  ይሖዋ ሆይ፣ ጽድቅ የአንተ ነው፤ እኛ ግን ይኸውም የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲሁም በቅርብም ይሁን በሩቅ ባሉ አገራት ሁሉ የበተንካቸው የእስራኤል ቤት ሰዎች በሙሉ ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ኀፍረት ተከናንበናል፤ ምክንያቱም እነሱ ለአንተ ታማኝ ሳይሆኑ ቀርተዋል። 8  “ይሖዋ ሆይ፣ እኛ፣ ነገሥታታችን፣ መኳንንታችንና አባቶቻችን በአንተ ላይ ኃጢአት በመሥራታችን ኀፍረት ተከናንበናል። 9  ምሕረትና ይቅር ባይነት የአምላካችን የይሖዋ ነው፤ እኛ በእሱ ላይ ዓምፀናልና። 10  የአምላካችንን የይሖዋን ቃል አልታዘዝንም፤ አገልጋዮቹ በሆኑት በነቢያት አማካኝነት የሰጠንን ሕጎችም አላከበርንም። 11  የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ሕግህን ተላልፈዋል፤ ቃልህን ባለመታዘዝም ለአንተ ጀርባቸውን ሰጥተዋል፤ በዚህም የተነሳ የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ በሆነው በሙሴ ሕግ የተጻፈውን እርግማንና መሐላ በእኛ ላይ አወረድክ፤ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና። 12  በእኛ ላይ ታላቅ ጥፋት በማምጣት በእኛ ላይና እኛን በገዙት ገዢዎቻችን ላይ የተናገረውን ቃል ፈጸመብን፤ በኢየሩሳሌም ላይ እንደተፈጸመው ያለ ነገር ከሰማይ በታች ታይቶ አያውቅም። 13  በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው ይህ ሁሉ ጥፋት ደረሰብን፤ ያም ሆኖ ከበደላችን በመመለስና ለእውነትህ ትኩረት በመስጠት የአምላካችንን የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት አልተማጸንም። 14  “በመሆኑም ይሖዋ በትኩረት ሲከታተል ቆይቶ ጥፋት አመጣብን፤ አምላካችን ይሖዋ በሥራው ሁሉ ጻድቅ ነውና፤ እኛ ግን ቃሉን አልታዘዝንም። 15  “አሁንም ሕዝብህን ከግብፅ ምድር በኃያል እጅ ያወጣህና እስከዚህ ቀን ድረስ ስምህ እንዲታወቅ ያደረግክ አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ እኛ ኃጢአት ሠርተናል፤ ክፉ ድርጊትም ፈጽመናል። 16  ይሖዋ ሆይ፣ እንደ ጽድቅ ሥራህ መጠን፣ እባክህ ቁጣህንና ንዴትህን ከከተማህ ከኢየሩሳሌም ይኸውም ከቅዱስ ተራራህ መልስ፤ ምክንያቱም በኃጢአታችንና አባቶቻችን በፈጸሙት በደል የተነሳ ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ባሉት ሁሉ ዘንድ መሳለቂያ ሆነዋል። 17  አሁንም አምላካችን ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ፤ ይሖዋ ሆይ፣ ለራስህ ስትል ለፈረሰው መቅደስህ ሞገስ አሳይ። 18  አምላኬ ሆይ፣ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ! ዓይንህን ገልጠህ በስምህ በተጠራችው ከተማችን ላይ የደረሰውን ጥፋት ተመልከት፤ ልመናችንን በፊትህ የምናቀርበው ከእኛ ጽድቅ የተነሳ ሳይሆን ከታላቅ ምሕረትህ የተነሳ ነው። 19  ይሖዋ ሆይ፣ ስማ። ይሖዋ ሆይ፣ ይቅር በል። ይሖዋ ሆይ፣ ትኩረት ስጥ፤ እርምጃም ውሰድ! አምላኬ ሆይ፣ ለራስህ ስትል አትዘግይ፤ ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቷልና።” 20  እኔም ገና እየተናገርኩና እየጸለይኩ፣ የራሴንና የሕዝቤን የእስራኤልን ኃጢአት እየተናዘዝኩ እንዲሁም በአምላኬ ቅዱስ ተራራ ላይ ሞገሱን እንዲያደርግ አምላኬን ይሖዋን እየለመንኩ፣ 21  አዎ፣ እየጸለይኩ ሳለ፣ ቀደም ሲል በራእዩ ላይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል፣ በጣም ተዳክሜ ሳለ የምሽቱ የስጦታ መባ በሚቀርብበት ጊዜ ወደ እኔ መጣ። 22  እሱም እንዲህ በማለት እንዳስተውል ረዳኝ፦ “ዳንኤል ሆይ፣ አሁን ጥልቅ ማስተዋልና የመረዳት ችሎታ ልሰጥህ መጥቻለሁ። 23  ልመናህን ገና ማቅረብ ስትጀምር ትእዛዝ ተሰጥቷል፤ እኔም ልነግርህ መጥቻለሁ፤ ምክንያቱም አንተ እጅግ የተወደድክ ነህ። ስለዚህ ለጉዳዩ ትኩረት ስጥ፤ ራእዩንም አስተውል። 24  “መተላለፍን ለማስቆም፣ ኃጢአትን ለመደምሰስ፣ በደልን ለማስተሰረይ፣ የዘላለም ጽድቅ ለማምጣት፣ ራእዩንና ትንቢቱን ለማተም እንዲሁም ቅድስተ ቅዱሳኑን ለመቀባት ለሕዝብህና ለቅድስቲቱ ከተማህ 70 ሳምንታት ተወስኗል። 25  ኢየሩሳሌምን ለማደስና መልሶ ለመገንባት ትእዛዝ ከሚወጣበት ጊዜ አንስቶ መሪ የሆነው መሲሕ እስከሚገለጥበት ጊዜ ድረስ 7 ሳምንታትና 62 ሳምንታት እንደሚሆን እወቅ፤ አስተውልም። ኢየሩሳሌም ትታደሳለች፤ ዳግመኛም ትገነባለች፤ አደባባይዋና የመከላከያ ቦይዋ እንደገና ይሠራል፤ ይህ የሚሆነው ግን በአስጨናቂ ወቅት ነው። 26  “ከ62ቱ ሳምንታት በኋላ መሲሑ ይቆረጣል፤ ትቶት የሚያልፈው ምንም ነገር አይኖርም። “የሚመጣውም መሪ ሠራዊት፣ ከተማዋንና ቅዱሱን ስፍራ ያጠፋል። ፍጻሜው በጎርፍ ይሆናል። እስከ ፍጻሜውም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተወስኗል። 27  “እሱም ለብዙዎች ቃል ኪዳኑን ለአንድ ሳምንት ያጸናል፤ በሳምንቱም አጋማሽ ላይ መሥዋዕትንና የስጦታ መባን ያስቀራል። “ጥፋት የሚያመጣውም በአስጸያፊ ነገሮች ክንፍ ላይ ሆኖ ይመጣል፤ ጥፋት እስኪመጣም ድረስ የተወሰነው ነገር በወደመው ነገር ላይ ይፈስሳል።”
[]
[]
[]
[]
12,303
1  የይሖዋ ቃል ወደ አሚታይ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2  “ተነስተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድና በእሷ ላይ የፍርድ መልእክት አውጅ፤ ክፋታቸውን አስተውያለሁና።” 3  ዮናስ ግን ከይሖዋ ፊት ኮብልሎ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሳ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፤ ከዚያም ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብ አገኘ። ከይሖዋም ፊት ሸሽቶ፣ በመርከቡ ውስጥ ከነበሩት ጋር ወደ ተርሴስ ለመሄድ የጉዞውን ዋጋ ከፍሎ ተሳፈረ። 4  ከዚያም ይሖዋ በባሕሩ ላይ ኃይለኛ ነፋስ አመጣ፤ ከባድ ማዕበል ስለተነሳ መርከቧ ልትሰበር ተቃረበች። 5  መርከበኞቹ እጅግ ከመፍራታቸው የተነሳ እርዳታ ለማግኘት እያንዳንዳቸው ወደየአምላካቸው ይጮኹ ጀመር። የመርከቧንም ክብደት ለመቀነስ በውስጧ የነበሩትን ዕቃዎች ወደ ባሕሩ መጣል ጀመሩ። ዮናስ ግን ወደ መርከቧ ውስጠኛ ክፍል ወርዶ ተኝቶ ነበር፤ ጭልጥ ያለ እንቅልፍም ወስዶት ነበር። 6  የመርከቧ አዛዥ ወደ እሱ ቀርቦ እንዲህ አለው፦ “እንዴት ትተኛለህ? ተነስተህ ወደ አምላክህ ጩኽ! ምናልባት እውነተኛው አምላክ ለእኛ አስቦ ከጥፋት ያድነን ይሆናል።” 7  ከዚያም እርስ በርሳቸው “ይህ መከራ የደረሰብን በማን ምክንያት እንደሆነ ማወቅ እንድንችል፣ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። በመሆኑም ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ። 8  እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ይህ መከራ የደረሰብን በማን ምክንያት እንደሆነ እባክህ ንገረን። ሥራህ ምንድን ነው? የመጣኸው ከየት ነው? አገርህስ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?” 9  እሱም መልሶ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማያትን አምላክ ይሖዋን የምፈራ ሰው ነኝ” አላቸው። 10  በዚህ ጊዜ ሰዎቹ የባሰ ፈሩ፤ “ያደረግከው ነገር ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። (ሰዎቹ ዮናስ ነግሯቸው ስለነበር ከይሖዋ ፊት እየሸሸ እንዳለ አወቁ።) 11  የባሕሩ ማዕበል እያየለ በመሄዱ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት። 12  እሱም “አንስታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል፤ ይህ ከባድ ማዕበል የመጣባችሁ በእኔ የተነሳ መሆኑን አውቃለሁና” በማለት መለሰላቸው። 13  ሰዎቹ ግን መርከቧን ወደ የብስ ለመመለስ በኃይል ቀዘፉ፤ ይሁንና ማዕበሉ ይበልጥ እያየለባቸው ስለሄደ ሊሳካላቸው አልቻለም። 14  ከዚያም ወደ ይሖዋ በመጮኽ እንዲህ አሉ፦ “እንግዲህ ይሖዋ ሆይ፣ በዚህ ሰው ምክንያት እንዳንጠፋ እንለምንሃለን! ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ደስ እንዳሰኘህ ስላደረግክ ለንጹሕ ሰው ደም ተጠያቂ አታድርገን!” 15  ከዚያም ዮናስን አንስተው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም መናወጡን አቆመ። 16  በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ይሖዋን እጅግ ፈሩ፤ ለይሖዋም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ስእለትም ተሳሉ። 17  ይሖዋም ዮናስን እንዲውጠው አንድ ትልቅ ዓሣ ላከ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ቆየ።
[]
[]
[]
[]
12,304
2  ከዚያም ዮናስ በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ ይሖዋ ጸለየ፤ 2  እንዲህም አለ፦ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ይሖዋ ተጣራሁ፤ እሱም መለሰልኝ። በመቃብር ጥልቅ ውስጥ ሆኜ እርዳታ ለማግኘት ጮኽኩ። አንተም ድምፄን ሰማህ። 3  ወደ ጥልቁ፣ ወደ ታችኛው የባሕሩ ወለል በጣልከኝ ጊዜፈሳሹ ውኃ ዋጠኝ። ማዕበሎችህና ሞገዶችህ ሁሉ በላዬ አለፉ። 4  እኔም ‘ከፊትህ አባረርከኝ! ቅዱስ የሆነውን ቤተ መቅደስህን ዳግመኛ እንዴት መመልከት እችላለሁ?’ አልኩ። 5  ውኃው ዋጠኝ፤ ሕይወቴንም አደጋ ላይ ጣለው፤ጥልቁ ውኃ ከበበኝ። የባሕር አረም ራሴ ላይ ተጠመጠመ። 6  ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥኩ። የምድር መቀርቀሪያዎች ለዘላለም ተዘጉብኝ። ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓዱ ውስጥ አወጣህ። 7  ሕይወቴ እየተዳከመች ስትሄድ ይሖዋን አስታወስኩ። ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ቅዱስ ወደሆነው ቤተ መቅደስህ ገባ። 8  ለማይረቡ ጣዖቶች ያደሩ ሰዎች ታማኝ ፍቅር የሚያሳያቸውን ይተዋሉ። 9  እኔ ግን በምስጋና ድምፅ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ። የተሳልኩትን እከፍላለሁ። መዳን ከይሖዋ ነው።” 10  በኋላም ይሖዋ ዓሣውን አዘዘው፤ ዓሣውም ዮናስን በደረቅ ምድር ላይ ተፋው።
[]
[]
[]
[]
12,305
3  ከዚያም የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ዮናስ መጣ፦ 2  “ተነስተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የምነግርህንም መልእክት በመካከሏ አውጅ።” 3  ዮናስም የይሖዋን ቃል በመታዘዝ ተነስቶ ወደ ነነዌ ሄደ። ነነዌ እጅግ ታላቅ ከተማ የነበረች ስትሆን በእግር የሦስት ቀን ያህል መንገድ ታስኬድ ነበር። 4  ዮናስም ወደ ከተማዋ ገብቶ የአንድ ቀን መንገድ ከተጓዘ በኋላ “ነነዌ በ40 ቀን ውስጥ ትደመሰሳለች” ብሎ አወጀ። 5  የነነዌም ሰዎች በአምላክ አመኑ፤ ከትልቁም አንስቶ እስከ ትንሹ ድረስ ጾም አወጁ፤ ማቅም ለበሱ። 6  የነነዌ ንጉሥ መልእክቱን በሰማ ጊዜ ከዙፋኑ ተነስቶ ልብሰ መንግሥቱን አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ አመድ ላይ ተቀመጠ። 7  በተጨማሪም በመላው ነነዌ አዋጅ አስነገረ፤“ንጉሡና መኳንንቱ ያወጡት ድንጋጌ፦ ሰውም ሆነ እንስሳ፣ ከብትም ሆነ መንጋ ምንም ነገር አይቅመስ። ምግብ አይብሉ፤ ውኃም አይጠጡ። 8  ሰውም ሆነ እንስሳ ማቅ ይልበስ፤ ሁሉም አጥብቆ ወደ አምላክ ይጩኽ፤ ክፉ መንገዳቸውንና የሚፈጽሙትን ግፍ ይተዉ። 9  እኛ እንዳንጠፋ፣ እውነተኛው አምላክ ሊያመጣው ያሰበውን ነገር እንደገና በማጤን ከሚነደው ቁጣው ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?” 10  እውነተኛው አምላክ ያደረጉትን ነገር ይኸውም ከክፉ መንገዳቸው እንዴት እንደተመለሱ አየ፤ በእነሱም ላይ አመጣዋለሁ ያለውን ነገር መልሶ በማጤን ጥፋቱን ከማምጣት ተቆጠበ።
[]
[]
[]
[]
12,306
4  ሆኖም ይህ ጉዳይ ዮናስን ፈጽሞ አላስደሰተውም፤ በመሆኑም እጅግ ተቆጣ። 2  ወደ ይሖዋም እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በገዛ አገሬ ሳለሁ ያሳሰበኝ ጉዳይ ይህ አልነበረም? መጀመሪያውኑም ወደ ተርሴስ ለመሸሽ የሞከርኩት ለዚህ ነበር፤ አንተ ሩኅሩኅና መሐሪ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየህና ታማኝ ፍቅርህ የበዛ፣ አዝነህም ጥፋት ከማምጣት የምትቆጠብ እንደሆንክ አውቃለሁና። 3  አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ በሕይወት ከመኖር ይልቅ መሞት ስለሚሻለኝ እባክህ ግደለኝ።” 4  ይሖዋም “እንዲህ መቆጣትህ ተገቢ ነው?” ብሎ ጠየቀው። 5  ከዚያም ዮናስ ከከተማዋ ወጥቶ በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ። በዚያም ለራሱ መጠለያ ሠርቶ በከተማዋ ላይ የሚደርሰውን ነገር ለማየት በጥላው ሥር ተቀመጠ። 6  በዚህ ጊዜ ይሖዋ አምላክ፣ ዮናስ ራሱን እንዲያስጠልልባትና ከሥቃዩ እንዲያርፍ ሲል አንዲት የቅል ተክል ከበላዩ እንድታድግ አደረገ። ዮናስም በቅል ተክሏ እጅግ ተደሰተ። 7  ይሁን እንጂ እውነተኛው አምላክ በሚቀጥለው ቀን፣ ማለዳ ላይ አንድ ትል ላከ፤ ትሉም የቅል ተክሏን በላት፤ ተክሏም ደረቀች። 8  ፀሐይ መውጣት ስትጀምር አምላክ የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አመጣ፤ ፀሐይዋም የዮናስን አናት አቃጠለችው፤ እሱም ተዝለፈለፈ። እንዲሞትም ለመነ፤ ደግሞ ደጋግሞም “በሕይወት ከምኖር ብሞት ይሻለኛል” አለ። 9  አምላክም ዮናስን “ስለ ቅል ተክሏ እንዲህ መቆጣትህ ተገቢ ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም “መቆጣት ሲያንሰኝ ነው፤ እንዲያውም ብሞት ይሻለኛል” አለ። 10  ይሖዋ ግን እንዲህ አለው፦ “አንተ በአንድ ሌሊት አድጋ በአንድ ሌሊት ለጠፋችው፣ ላልደከምክባት ወይም ላላሳደግካት የቅል ተክል አዝነሃል። 11  ታዲያ እኔ ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር ለይተው የማያውቁ ከ120,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎችና በርካታ እንስሶቻቸው ለሚኖሩባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ ላዝን አይገባም?”
[]
[]
[]
[]
12,307
1  በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከአምላክ ጋር ነበር፤ ቃልም አምላክ ነበር። 2  እሱም በመጀመሪያ ከአምላክ ጋር ነበር። 3  ሁሉም ነገሮች ወደ ሕልውና የመጡት በእሱ በኩል ነው፤ ያለእሱ ወደ ሕልውና የመጣ አንድም ነገር የለም። 4  በእሱ አማካኝነት ሕይወት ወደ ሕልውና መጥቷል፤ ይህ ሕይወት ደግሞ የሰው ብርሃን ነበር። 5  ብርሃኑም በጨለማ እየበራ ነው፤ ጨለማውም አላሸነፈውም። 6  ከአምላክ የተላከ አንድ ሰው ነበር፤ እሱም ዮሐንስ ይባላል። 7  ይህ ሰው ስለ ብርሃኑ ይመሠክር ዘንድ ምሥክር ሆኖ መጣ፤ ይህን ያደረገው ሁሉም ዓይነት ሰዎች በእሱ በኩል እንዲያምኑ ነው። 8  ያ ብርሃን እሱ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ እሱ የመጣው ስለ ብርሃኑ ሊመሠክር ነው። 9  ለሁሉም ዓይነት ሰው ብርሃን የሚሰጠው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም የሚመጣበት ጊዜ ደርሶ ነበር። 10  እሱም በዓለም ነበረ፤ ዓለምም ወደ ሕልውና የመጣው በእሱ በኩል ነው፤ ሆኖም ዓለም አላወቀውም። 11  ወደ ገዛ አገሩ መጣ፤ ነገር ግን የገዛ ወገኖቹ አልተቀበሉትም። 12  ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ስላመኑ የአምላክ ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። 13  እነሱም የተወለዱት ከአምላክ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አይደለም። 14  ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ኖረ፤ አንድያ ልጅ ከአባቱ እንደሚያገኘው ክብር ያለ ክብሩን አየን፤ እሱም መለኮታዊ ሞገስንና እውነትን ተሞልቶ ነበር። 15  (ዮሐንስ ስለ እሱ መሥክሯል፤ እንዲያውም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “‘ከእኔ ኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለነበረ ከእኔ ይበልጣል’ ብዬ የተናገርኩት ስለ እሱ ነው።”) 16  ከእሱ የጸጋ ሙላት የተነሳ ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀብለናል። 17  ምክንያቱም ሕጉ የተሰጠው በሙሴ በኩል ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን የመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው። 18  በየትኛውም ጊዜ ቢሆን አምላክን ያየው አንድም ሰው የለም፤ ስለ እሱ የገለጸልን ከአብ ጎን ያለውና አምላክ የሆነው አንድያ ልጁ ነው። 19  አይሁዳውያን “አንተ ማን ነህ?” ብለው እንዲጠይቁት ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩ ጊዜ ዮሐንስ የሰጠው ምሥክርነት ይህ ነው፤ 20  “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም” ብሎ በግልጽ ተናገረ እንጂ ጥያቄውን ከመመለስ ወደኋላ አላለም። 21  እነሱም “ታዲያ ማን ነህ? ኤልያስ ነህ?” ሲሉ ጠየቁት። እሱም መልሶ “አይደለሁም” አለ። “ነቢዩ ነህ?” አሉት። እሱም “አይደለሁም!” ሲል መለሰ። 22  በዚህ ጊዜ “ለላኩን ሰዎች መልስ መስጠት እንድንችል ታዲያ አንተ ማን ነህ? ስለ ራስህስ ምን ትላለህ?” አሉት። 23  እሱም “ነቢዩ ኢሳይያስ እንደተናገረው ‘የይሖዋን መንገድ አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኸው ሰው እኔ ነኝ” አለ። 24  ሰዎቹን የላኳቸውም ፈሪሳውያን ነበሩ። 25  በመሆኑም “ታዲያ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካልሆንክ ለምን ታጠምቃለህ?” ሲሉ ጠየቁት። 26  ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውኃ አጠምቃለሁ። እናንተ የማታውቁት ግን በመካከላችሁ ቆሟል፤ 27  እሱም ከኋላዬ ይመጣል፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ እንኳ ለመፍታት አልበቃም።” 28  ይህ የሆነው ዮሐንስ ሲያጠምቅ ከነበረበት ከዮርዳኖስ ማዶ በሚገኘው በቢታንያ ነበር። 29  በማግስቱ ኢየሱስ ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የአምላክ በግ ይኸውላችሁ! 30  ‘ከኋላዬ አንድ ሰው ይመጣል፤ ከእኔ በፊት ስለነበረ ከእኔ ይበልጣል’ ያልኳችሁ እሱ ነው። 31  እኔም እንኳ አላውቀውም ነበር፤ እኔ በውኃ እያጠመቅኩ የመጣሁበት ምክንያት ግን እሱ ለእስራኤል እንዲገለጥ ነው።” 32  በተጨማሪም ዮሐንስ እንዲህ ሲል ምሥክርነት ሰጥቷል፦ “መንፈስ ከሰማይ ወጥቶ እንደ ርግብ ሲወርድ አይቻለሁ፤ በእሱም ላይ አረፈ። 33  እኔም እንኳ አላውቀውም ነበር፤ ሆኖም በውኃ እንዳጠምቅ የላከኝ ራሱ ‘በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው፣ መንፈስ ሲወርድበትና ሲያርፍበት የምታየው ያ ሰው ነው’ አለኝ። 34  እኔም አይቻለሁ፤ እሱም የአምላክ ልጅ መሆኑን መሥክሬአለሁ።” 35  በማግስቱም ዮሐንስ ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደገና በዚያ ቆሞ ነበር፤ 36  ኢየሱስ ሲያልፍ አይቶም “የአምላክ በግ ይኸውላችሁ!” አለ። 37  ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ይህን ሲናገር በሰሙ ጊዜ ኢየሱስን ተከተሉት። 38  ከዚያም ኢየሱስ ዞር ብሎ ሲከተሉት አየና “ምን ፈልጋችሁ ነው?” አላቸው። እነሱም “ረቢ፣ የት ነው የምትኖረው?” አሉት (ረቢ ማለት “መምህር” ማለት ነው)፤ 39  እሱም “ኑና እዩ” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የት እንደሚኖር አዩ፤ ጊዜውም አሥር ሰዓት ገደማ ነበር፤ በዚያም ዕለት አብረውት ዋሉ። 40  ዮሐንስ የተናገረውን ከሰሙትና ኢየሱስን ከተከተሉት ሁለት ሰዎች አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበር። 41  እንድርያስ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና “መሲሑን አገኘነው” አለው (መሲሕ ማለት “ክርስቶስ” ማለት ነው)፤ 42  ወደ ኢየሱስም ወሰደው። ኢየሱስም ባየው ጊዜ “አንተ የዮሐንስ ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ተብለህ ትጠራለህ” አለው (ኬፋ ማለት “ጴጥሮስ” ማለት ነው)። 43  በማግስቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ። ከዚያም ፊልጶስን አግኝቶ “ተከታዬ ሁን” አለው። 44  ፊልጶስም እንደ እንድርያስና እንደ ጴጥሮስ የቤተሳይዳ ከተማ ሰው ነበረ። 45  ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ “ሙሴ በሕጉ፣ ነቢያት ደግሞ በመጻሕፍት የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው” አለው። 46  ናትናኤል ግን “ደግሞ ከናዝሬት ጥሩ ነገር ሊገኝ ይችላል?” አለው። ፊልጶስም “መጥተህ እይ” አለው። 47  ኢየሱስም ናትናኤል ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እሱ “ተንኮል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይኸውላችሁ!” አለ። 48  ናትናኤልም “እንዴት ልታውቀኝ ቻልክ?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይቼሃለሁ” አለው። 49  ናትናኤልም “ረቢ፣ አንተ የአምላክ ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” ሲል መለሰለት። 50  ኢየሱስም መልሶ “ያመንከው ከበለስ ዛፍ ሥር አየሁህ ስላልኩህ ነው? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ገና ታያለህ” አለው። 51  ከዚያም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማይ ተከፍቶ የአምላክ መላእክት ወደዚያ ሲወጡና የሰው ልጅ ወዳለበት ሲወርዱ ታያላችሁ” አለው።
[]
[]
[]
[]
12,308
10  “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በበሩ ሳይሆን በሌላ በኩል ዘሎ ወደ በጎቹ ጉረኖ የሚገባ ሌባና ዘራፊ ነው። 2  በበሩ በኩል የሚገባ ግን የበጎቹ እረኛ ነው። 3  በር ጠባቂውም ለእሱ ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ። የራሱን በጎች በየስማቸው ጠርቶ እየመራ ያወጣቸዋል። 4  የራሱ የሆኑትን ሁሉ ካወጣ በኋላ ከፊት ከፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምፁን ስለሚያውቁ ይከተሉታል። 5  እንግዳ የሆነውን ግን ይሸሹታል እንጂ በምንም ዓይነት አይከተሉትም፤ ምክንያቱም የእንግዳ ሰዎችን ድምፅ አያውቁም።” 6  ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነሱ ግን ምን እያላቸው እንዳለ አልገባቸውም። 7  ስለዚህ ኢየሱስ እንደገና እንዲህ አለ፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በጎቹ የሚገቡበት በር እኔ ነኝ። 8  አስመሳይ ሆነው በእኔ ስም የመጡ ሁሉ ሌቦችና ዘራፊዎች ናቸው፤ በጎቹ ግን አልሰሟቸውም። 9  በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል የሚገባ ሁሉ ይድናል፤ ይገባል፤ ይወጣል፤ መሰማሪያም ያገኛል። 10  ሌባው ለመስረቅ፣ ለመግደልና ለማጥፋት ካልሆነ በቀር ለሌላ አይመጣም። እኔ የመጣሁት ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው ነው። 11  እኔ ጥሩ እረኛ ነኝ፤ ጥሩ እረኛ ሕይወቱን ለበጎቹ ሲል አሳልፎ ይሰጣል። 12  እረኛ ያልሆነና በጎቹ የራሱ ያልሆኑ ተቀጣሪ ሠራተኛ ተኩላ ሲመጣ ሲያይ በጎቹን ጥሎ ይሸሻል (ተኩላውም በጎቹን ይነጥቃል እንዲሁም ይበታትናል)፤ 13  ሠራተኛው እንዲህ የሚያደርገው ተቀጣሪ ስለሆነና ለበጎቹ ደንታ ስለሌለው ነው። 14  እኔ ጥሩ እረኛ ነኝ። በጎቼን አውቃቸዋለሁ፤ በጎቼም ያውቁኛል፤ 15  ይህም አብ እኔን እንደሚያውቀኝና እኔም አብን እንደማውቀው ነው፤ ሕይወቴንም ለበጎቹ ስል አሳልፌ እሰጣለሁ። 16  “ከዚህ ጉረኖ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነሱንም ማምጣት አለብኝ፤ ድምፄንም ይሰማሉ፤ ሁሉም አንድ መንጋ ይሆናሉ፤ አንድ እረኛም ይኖራቸዋል። 17  ሕይወቴን መልሼ አገኛት ዘንድ አሳልፌ ስለምሰጣት አብ ይወደኛል። 18  በራሴ ተነሳስቼ አሳልፌ እሰጣታለሁ እንጂ ማንም ሰው ከእኔ አይወስዳትም። ሕይወቴን አሳልፌ ለመስጠት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ ለመቀበልም ሥልጣን አለኝ። ይህን ትእዛዝ የተቀበልኩት ከአባቴ ነው።” 19  ከዚህ ንግግር የተነሳ በአይሁዳውያኑ መካከል እንደገና ክፍፍል ተፈጠረ። 20  ብዙዎቹም “ይህ ሰው ጋኔን አለበት፤ አእምሮውን ስቷል። ለምን ትሰሙታላችሁ?” አሉ። 21  ሌሎቹ ደግሞ “ጋኔን የያዘው ሰው እንዲህ አይናገርም። ጋኔን የዓይነ ስውራንን ዓይን ሊከፍት ይችላል እንዴ?” አሉ። 22  በዚያ ጊዜ በኢየሩሳሌም የመታደስ በዓል ይከበር ነበር። ወቅቱም ክረምት ነበር፤ 23  ኢየሱስም በቤተ መቅደሱ በሚገኘውና መጠለያ ባለው የሰለሞን መተላለፊያ ውስጥ እያለፈ ነበር። 24  በዚህ ጊዜ አይሁዳውያን ከበውት “እስከ መቼ ድረስ ልባችንን ታንጠለጥላለህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንክ በግልጽ ንገረን” አሉት። 25  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ ነግሬአችኋለሁ፤ እናንተ ግን አታምኑም። በአባቴ ስም እየሠራኋቸው ያሉት ሥራዎች ስለ እኔ ይመሠክራሉ። 26  ሆኖም እናንተ በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም። 27  በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ እነሱም ይከተሉኛል። 28  የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ መቼም ቢሆን ጥፋት አይደርስባቸውም፤ ከእጄ የሚነጥቃቸውም የለም። 29  አባቴ የሰጠኝ በጎች ከሌሎች ነገሮች ሁሉ ይበልጣሉ፤ እነሱንም ከአባቴ እጅ ሊነጥቃቸው የሚችል የለም። 30  እኔና አብ አንድ ነን።” 31  በዚህ ጊዜም አይሁዳውያኑ ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ። 32  ኢየሱስም መልሶ “ከአብ ዘንድ ብዙ መልካም ሥራዎች አሳየኋችሁ። ታዲያ የምትወግሩኝ ከእነዚህ ሥራዎች መካከል በየትኛው የተነሳ ነው?” አላቸው። 33  አይሁዳውያኑም “እኛ የምንወግርህ ስለ መልካም ሥራህ ሳይሆን አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ ራስህን አምላክ በማድረግ አምላክን ስለተዳፈርክ ነው” ሲሉ መለሱለት። 34  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በሕጋችሁ ላይ ‘“እናንተ አማልክት ናችሁ” አልኩ’ ተብሎ ተጽፎ የለም? 35  የአምላክ ቃል ያወገዛቸውን እሱ ‘አማልክት’ ብሎ ከጠራቸውና ቅዱስ መጽሐፉ ሊሻር የማይችል ከሆነ 36  አብ የቀደሰኝንና ወደ ዓለም የላከኝን እኔን፣ ‘የአምላክ ልጅ ነኝ’ ስላልኩ ‘አምላክን ትዳፈራለህ’ ትሉኛላችሁ? 37  እኔ የአባቴን ሥራ እየሠራሁ ካልሆነ አትመኑኝ። 38  የአባቴን ሥራ እየሠራሁ ከሆነ ግን እኔን ባታምኑኝ እንኳ ሥራዬን እመኑ፤ ይህም አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው እንዲሁም እኔም ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝ እንድታውቁና ይህን ይበልጥ እያወቃችሁ እንድትሄዱ ነው።” 39  ስለዚህ እንደገና ሊይዙት ሞከሩ፤ እሱ ግን አመለጣቸው። 40  ከዚያም ዮሐንስ ቀደም ሲል ያጠምቅ ወደነበረበት ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳለው ቦታ ዳግመኛ ሄደ፤ በዚያም ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። 41  ብዙ ሰዎችም ወደ እሱ መጥተው እርስ በርሳቸው “ዮሐንስ አንድም ተአምራዊ ምልክት አላደረገም፤ ሆኖም ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ነገር ሁሉ እውነት ነበር” ተባባሉ። 42  በዚያም ብዙዎች በእሱ አመኑ።
[]
[]
[]
[]
12,309
11  ማርያምና እህቷ ማርታ በሚኖሩበት መንደር በቢታንያ አልዓዛር የተባለ ሰው ታሞ ነበር። 2  ማርያም በጌታ ላይ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ያፈሰሰችውና በፀጉሯ እግሩን ያበሰችው ሴት ስትሆን የታመመውም፣ ወንድሟ አልዓዛር ነበር። 3  ስለዚህ እህቶቹ “ጌታ ሆይ፣ የምትወደው ሰው ታሟል” ሲሉ መልእክት ላኩበት። 4  ኢየሱስ ግን ይህን በሰማ ጊዜ “ይህ ሕመም ለአምላክ ክብር የሚያመጣ ነው እንጂ በሞት የሚያበቃ አይደለም፤ ይህም የአምላክ ልጅ በዚህ አማካኝነት ክብር ይጎናጸፍ ዘንድ ነው” አለ። 5  ኢየሱስ ማርታንና እህቷን እንዲሁም አልዓዛርን ይወዳቸው ነበር። 6  ይሁን እንጂ አልዓዛር መታመሙን ከሰማ በኋላ በዚያው በነበረበት ቦታ ሁለት ቀን ቆየ። 7  ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን “ተመልሰን ወደ ይሁዳ እንሂድ” አላቸው። 8  ደቀ መዛሙርቱ ግን “ረቢ፣ በቅርቡ እኮ የይሁዳ ሰዎች በድንጋይ ሊወግሩህ ፈልገው ነበር፤ ታዲያ ወደዚያ ተመልሰህ ልትሄድ ነው?” አሉት። 9  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በቀን ውስጥ ብርሃን የሚሆንበት 12 ሰዓት አለ አይደል? ማንም ሰው በቀን ብርሃን የሚሄድ ከሆነ የዚህን ዓለም ብርሃን ስለሚያይ ምንም ነገር አያደናቅፈውም። 10  ሆኖም በሌሊት የሚሄድ ሰው በእሱ ዘንድ ብርሃን ስለሌለ ይደናቀፋል።” 11  ይህን ከነገራቸው በኋላም “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤ እኔም ልቀሰቅሰው ወደዚያ እሄዳለሁ” አላቸው። 12  በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ጌታ ሆይ፣ ተኝቶ ከሆነ ይሻለዋል” አሉት። 13  ይሁንና ኢየሱስ የተናገረው ስለመሞቱ ነበር። እነሱ ግን ለማረፍ ብሎ እንቅልፍ ስለመተኛቱ የተናገረ መሰላቸው። 14  በዚህ ጊዜ ኢየሱስ በግልጽ እንዲህ አላቸው፦ “አልዓዛር ሞቷል፤ 15  ታምኑ ዘንድ በዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል። ያም ሆነ ይህ ወደ እሱ እንሂድ።” 16  በዚህ ጊዜ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ለተቀሩት ደቀ መዛሙርት “ከእሱ ጋር እንድንሞት አብረነው እንሂድ” አላቸው። 17  ኢየሱስ እዚያ በደረሰ ጊዜ አልዓዛር በመቃብር ውስጥ አራት ቀን እንደሆነው አወቀ። 18  ቢታንያ ለኢየሩሳሌም ቅርብ የነበረች ሲሆን ሦስት ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ ትገኝ ነበር። 19  ወንድማቸውን በሞት ያጡትን ማርታንና ማርያምን ለማጽናናት ብዙ አይሁዳውያን መጥተው ነበር። 20  ማርታ፣ ኢየሱስ እየመጣ መሆኑን ስትሰማ ልትቀበለው ወጣች፤ ማርያም ግን እዚያው ቤት ቀረች። 21  ማርታም ኢየሱስን እንዲህ አለችው፦ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር። 22  አሁንም ቢሆን አምላክ የጠየቅከውን ነገር ሁሉ እንደሚሰጥህ አምናለሁ።” 23  ኢየሱስም “ወንድምሽ ይነሳል” አላት። 24  ማርታም “በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንደሚነሳ አውቃለሁ” አለችው። 25  ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ። በእኔ የሚያምን ሁሉ ቢሞት እንኳ እንደገና ሕያው ይሆናል፤ 26  በሕይወት ያለና በእኔ የሚያምን ሁሉ ደግሞ ፈጽሞ አይሞትም። ይህን ታምኛለሽ?” 27  እሷም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው የአምላክ ልጅ ክርስቶስ መሆንህን አምናለሁ” አለችው። 28  ይህን ካለች በኋላም ሄዳ እህቷን ማርያምን ለብቻዋ ጠርታት “መምህሩ መጥቷል፤ እየጠራሽ ነው” አለቻት። 29  ማርያምም ይህን ስትሰማ በፍጥነት ተነስታ ወደ እሱ ሄደች። 30  ይሁንና ኢየሱስ እዚያው ማርታ ያገኘችው ቦታ ነበር እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር። 31  እሷን እያጽናኑ በቤት አብረዋት የነበሩ አይሁዳውያንም ማርያም ፈጥና ተነስታ ስትወጣ ሲያዩ ወደ መቃብሩ ሄዳ ልታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት። 32  ማርያምም ኢየሱስ የነበረበት ቦታ ደርሳ ባየችው ጊዜ እግሩ ላይ ተደፋች፤ ከዚያም “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው። 33  ኢየሱስ እሷ ስታለቅስና አብረዋት የመጡት አይሁዳውያን ሲያለቅሱ ሲያይ እጅግ አዘነ፤ ተረበሸም። 34  እሱም “የት ነው ያኖራችሁት?” አለ። እነሱም “ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት። 35  ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ። 36  በዚህ ጊዜ አይሁዳውያኑ “እንዴት ይወደው እንደነበር ተመልከቱ!” አሉ። 37  ሆኖም ከእነሱ መካከል አንዳንዶች “የዓይነ ስውሩን ዓይን ያበራው ይህ ሰው ይሄኛውንም እንዳይሞት ማድረግ አይችልም ነበር?” አሉ። 38  ከዚያም ኢየሱስ ልቡ ዳግመኛ በሐዘን ታውኮ ወደ መቃብሩ መጣ። መቃብሩ ዋሻ ሲሆን በድንጋይም ተዘግቶ ነበር። 39  ኢየሱስ “ድንጋዩን አንሱት” አለ። የሟቹ እህት ማርታም “ጌታ ሆይ፣ አራት ቀን ስለሆነው አሁን ይሸታል” አለችው። 40  ኢየሱስም “ካመንሽ የአምላክን ክብር ታያለሽ ብዬ አልነገርኩሽም?” አላት። 41  ስለዚህ ድንጋዩን አነሱት። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመልክቶ እንዲህ አለ፦ “አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። 42  እውነት ነው፣ ሁልጊዜ እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ይህን ያልኩት ግን እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ ነው።” 43  ይህን ከተናገረ በኋላ በታላቅ ድምፅ “አልዓዛር፣ ና ውጣ!” አለ። 44  የሞተው ሰው እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደተገነዙ ወጣ፤ ፊቱም በጨርቅ ተጠምጥሞ ነበር። ኢየሱስም “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው። 45  በመሆኑም ወደ ማርያም መጥተው ከነበሩትና ያደረገውን ነገር ካዩት አይሁዳውያን መካከል ብዙዎቹ በእሱ አመኑ፤ 46  አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገር ነገሯቸው። 47  ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሳንሄድሪንን ሸንጎ ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራዊ ምልክቶች እያደረገ ስለሆነ ምን ብናደርግ ይሻላል? 48  እንዲሁ ብንተወው ሁሉም በእሱ ያምናሉ፤ ሮማውያንም መጥተው ቦታችንንና ሕዝባችንን ይወስዱብናል።” 49  ሆኖም ከመካከላቸው አንዱ፣ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ምንም አታውቁም፤ 50  ደግሞም ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ፣ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት እንደሚሻል ማሰብ ተስኗችኋል።” 51  ይሁንና ይህን የተናገረው ከራሱ አመንጭቶ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት ስለነበረ ኢየሱስ ለሕዝቡ እንደሚሞት ትንቢት መናገሩ ነበር፤ 52  የሚሞተውም ለሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ተበታትነው ያሉትን የአምላክ ልጆችም አንድ ላይ መሰብሰብ ይችል ዘንድ ነው። 53   ስለዚህ ከዚያን ቀን አንስቶ ሊገድሉት አሴሩ። 54  በመሆኑም ኢየሱስ ከዚያን ጊዜ አንስቶ በአይሁዳውያን መካከል በይፋ መንቀሳቀስ አቆመ፤ ከዚህ ይልቅ በምድረ በዳ አቅራቢያ ወዳለ ስፍራ ሄደ፤ በዚያም ኤፍሬም ተብላ በምትጠራ ከተማ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ። 55  በዚህ ወቅት የአይሁዳውያን ፋሲካ ቀርቦ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም ከፋሲካ በፊት የመንጻት ሥርዓት ለመፈጸም ከገጠር ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ። 56  ኢየሱስንም ይፈልጉት ጀመር፤ በቤተ መቅደሱም ቆመው እርስ በርሳቸው “ምን ይመስላችኋል? ጭራሽ ወደ በዓሉ አይመጣ ይሆን?” ይባባሉ ነበር። 57   የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ግን ኢየሱስን መያዝ እንዲችሉ እሱ ያለበትን ቦታ የሚያውቅ ሁሉ እንዲጠቁማቸው አዘው ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,310
12  የፋሲካ በዓል ከመድረሱ ከስድስት ቀን በፊት ኢየሱስ፣ ከሞት ያስነሳው አልዓዛር ወደሚኖርባት ወደ ቢታንያ መጣ። 2  በዚያም የራት ግብዣ አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግላቸው የነበረ ሲሆን አልዓዛር ግን ከእሱ ጋር ከሚበሉት አንዱ ነበር። 3  ከዚያም ማርያም ግማሽ ሊትር ገደማ የሚሆን እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ አምጥታ በኢየሱስ እግር ላይ አፈሰሰች፤ እግሩንም በፀጉሯ አብሳ አደረቀች። ቤቱም በዘይቱ መዓዛ ታወደ። 4  ሆኖም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነውና አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንዲህ አለ፦ 5  “ይህ ዘይት በ300 ዲናር ተሸጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምንድን ነው?” 6  እንዲህ ያለው ግን ለድሆች አስቦ ሳይሆን ሌባ ስለነበረ ነው፤ የገንዘብ ሣጥኑን ይይዝ የነበረው እሱ በመሆኑ ወደ ሣጥኑ ከሚገባው ገንዘብ የመስረቅ ልማድ ነበረው። 7  በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ለቀብሬ ቀን ለማዘጋጀት ብላ ያደረገችው ስለሆነ ይህን ልማድ እንዳትፈጽም አትከልክሏት። 8  ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።” 9  በዚህ ጊዜ ብዙ አይሁዳውያን ኢየሱስ እዚያ መኖሩን አውቀው መጡ፤ የመጡትም ኢየሱስን ለማየት ብቻ ሳይሆን እሱ ከሞት ያስነሳውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር። 10  በመሆኑም የካህናት አለቆቹ አልዓዛርንም ለመግደል አሴሩ፤ 11  ምክንያቱም በእሱ የተነሳ ብዙ አይሁዳውያን ወደዚያ እየሄዱ በኢየሱስ ያምኑ ነበር። 12  በማግስቱም ወደ በዓሉ የመጡ እጅግ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየመጣ መሆኑን ሰሙ። 13  በመሆኑም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ። እንዲህ እያሉም ይጮኹ ጀመር፦ “እንድታድነው እንለምንሃለን! በይሖዋ ስም የሚመጣው የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው!” 14  ኢየሱስ የአህያ ውርንጭላ አግኝቶ ተቀመጠበት፤ ይህም የሆነው እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው፦ 15  “የጽዮን ልጅ ሆይ፣ አትፍሪ። እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል።” 16  ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ እነዚህን ነገሮች አላስተዋሉም ነበር፤ ኢየሱስ ክብር በተጎናጸፈ ጊዜ ግን እነዚህ ነገሮች የተጻፉት ስለ እሱ እንደሆነና እነዚህን ነገሮች ለእሱ እንዳደረጉለት ትዝ አላቸው። 17  ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር ጠርቶ ከሞት ባስነሳበት ጊዜ አብረውት የነበሩት ሰዎች ስላዩት ነገር ይመሠክሩ ነበር። 18  ከዚህም የተነሳ ይህን ተአምራዊ ምልክት መፈጸሙን የሰማው ሕዝብ ሊቀበለው ወጣ። 19  ስለዚህ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው “ምንም ማድረግ እንዳልቻልን አያችሁ! ተመልከቱ፣ ዓለሙ ሁሉ ግልብጥ ብሎ ተከትሎታል” ተባባሉ። 20  ለአምልኮ ወደ በዓሉ ከመጡት ሰዎች መካከል አንዳንድ ግሪካውያን ነበሩ። 21  እነሱም በገሊላ የምትገኘው የቤተሳይዳ ሰው ወደሆነው ወደ ፊልጶስ ቀርበው “ጌታ ሆይ፣ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” ብለው ጠየቁት። 22  ፊልጶስ መጥቶ ለእንድርያስ ነገረው። ከዚያም እንድርያስና ፊልጶስ መጥተው ለኢየሱስ ነገሩት። 23  ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የሰው ልጅ ክብር የሚያገኝበት ሰዓት ደርሷል። 24  እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አንዲት የስንዴ ዘር መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች አንድ ዘር ብቻ ሆና ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። 25  ሕይወቱን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን የሚጠላ ሁሉ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። 26  እኔን ሊያገለግል የሚፈልግ ቢኖር ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል። የሚያገለግለኝንም ሁሉ አብ ያከብረዋል። 27  አሁን ተጨንቄአለሁ፤ እንግዲህ ምን ማለት እችላለሁ? አባት ሆይ፣ ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ይሁንና የመጣሁት ለዚህ ሰዓት ነው። 28  አባት ሆይ፣ ስምህን አክብረው።” በዚህ ጊዜ “ስሜን አክብሬዋለሁ፤ ደግሞም አከብረዋለሁ” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። 29  በዚያ ቆመው የነበሩት ብዙ ሰዎች ድምፁን በሰሙ ጊዜ ‘ነጎድጓድ ነው’ አሉ። ሌሎች ደግሞ “መልአክ አናገረው” አሉ። 30  ኢየሱስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ድምፅ የተሰማው ለእኔ ሳይሆን ለእናንተ ሲባል ነው። 31  ይህ ዓለም የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ የዚህ ዓለም ገዢ አሁን ይባረራል። 32  እኔ ግን ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከተደረግኩ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች ወደ ራሴ እስባለሁ።” 33  ይህን የተናገረው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምን ዓይነት አሟሟት እንደሚሞት ለማመልከት ነው። 34  በዚህ ጊዜ ሕዝቡ “ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕጉ ሰምተናል። ታዲያ አንተ የሰው ልጅ ከፍ ማለት አለበት እንዴት ትላለህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው?” ብለው መለሱለት። 35  ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ብርሃኑ ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ይቆያል። ጨለማ እንዳይውጣችሁ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃን ሂዱ፤ በጨለማ የሚሄድ ሁሉ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም። 36  የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃኑ እመኑ።” ኢየሱስ ይህን ተናግሮ እንደጨረሰ ሄደ፤ ከእነሱም ተሰወረ። 37  በፊታቸው ብዙ ተአምራዊ ምልክቶች ቢፈጽምም በእሱ አላመኑም፤ 38  ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ከእኛ የሰማውን ነገር ያመነ ማን ነው? የይሖዋስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” 39  ደግሞም ኢሳይያስ ሊያምኑ ያልቻሉበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ 40  “በዓይናቸው አይተውና በልባቸው አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳይፈውሳቸው ዓይናቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል።” 41  ኢሳይያስ ይህን የተናገረው የክርስቶስን ክብር ስላየ ነው፤ ስለ እሱም ተናገረ። 42  ያም ሆኖ ከገዢዎችም እንኳ ሳይቀር ብዙዎች በእሱ አመኑ፤ ይሁንና ፈሪሳውያን ከምኩራብ እንዳያባርሯቸው ስለፈሩ በእሱ ማመናቸውን በግልጽ አይናገሩም ነበር፤ 43  ይህም የሆነው ከሰው የሚገኘውን ክብር ከአምላክ ከሚገኘው ክብር አስበልጠው ስለወደዱ ነው። 44  ይሁን እንጂ ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “በእኔ የሚያምን ሁሉ በእኔ ብቻ ሳይሆን በላከኝም ጭምር ያምናል፤ 45  እኔን የሚያይ ሁሉ የላከኝንም ያያል። 46  በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ። 47  ይሁንና ማንም ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቅ ከሆነ የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ እኔ የመጣሁት ዓለምን ለማዳን እንጂ በዓለም ላይ ለመፍረድ አይደለምና። 48  እኔን የሚንቀውንና ቃሌን የማይቀበለውን ሁሉ የሚፈርድበት አለ። በመጨረሻው ቀን የሚፈርድበት የተናገርኩት ቃል ነው። 49  እኔ የተናገርኩት በራሴ ተነሳስቼ አይደለምና፤ ከዚህ ይልቅ ምን እንደምልና ምን እንደምናገር ያዘዘኝ የላከኝ አብ ራሱ ነው። 50  ደግሞም የእሱ ትእዛዝ የዘላለም ሕይወት እንደሚያስገኝ አውቃለሁ። ስለዚህ ምንጊዜም የምናገረው ልክ አባቴ በነገረኝ መሠረት ነው።”
[]
[]
[]
[]
12,311
13  የፋሲካ በዓል ተቃርቦ በነበረበት ወቅት ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደደረሰ ስላወቀ በዓለም የነበሩትንና የወደዳቸውን ተከታዮቹን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው። 2  በዚህ ጊዜ ራት እየበሉ ነበር። ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ውስጥ ኢየሱስን አሳልፎ የመስጠት ሐሳብ አሳድሮ ነበር። 3  ኢየሱስ፣ አብ ሁሉን ነገር በእጁ እንደሰጠው እንዲሁም ከአምላክ እንደመጣና ወደ አምላክ እንደሚሄድ ያውቅ ስለነበር 4  ከራት ተነስቶ መደረቢያውን አስቀመጠ። ፎጣ ወስዶም ወገቡ ላይ አሸረጠ። 5  ከዚያም በመታጠቢያ ዕቃ ውስጥ ውኃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና ባሸረጠው ፎጣ ማድረቅ ጀመረ። 6  ከዚያም ወደ ስምዖን ጴጥሮስ መጣ። ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ እግሬን ልታጥብ ነው?” አለው። 7  ኢየሱስም መልሶ “እያደረግኩት ያለውን ነገር አሁን አትረዳውም፤ በኋላ ግን ትረዳዋለህ” አለው። 8  ጴጥሮስም “በፍጹም እግሬን አታጥብም” አለው። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ምንም ድርሻ አይኖርህም” ሲል መለሰለት። 9  ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንና ራሴንም እጠበኝ” አለው። 10  ኢየሱስም “ገላውን የታጠበ ሁለመናው ንጹሕ በመሆኑ ከእግሩ በስተቀር መታጠብ አያስፈልገውም። እናንተ ንጹሐን ናችሁ፤ ሁላችሁም ግን አይደላችሁም” አለው። 11  ምክንያቱም አሳልፎ የሚሰጠው ሰው ማን እንደሆነ ያውቅ ነበር። “ሁላችሁም ንጹሐን አይደላችሁም” ያለው ለዚህ ነው። 12  እግራቸውን አጥቦ ካበቃና መደረቢያውን ለብሶ ዳግመኛ በማዕድ ከተቀመጠ በኋላ እንዲህ አላቸው፦ “ምን እንዳደረግኩላችሁ አስተዋላችሁ? 13  እናንተ ‘መምህር’ እና ‘ጌታ’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ እንደዚያ ስለሆንኩም እንዲህ ብላችሁ መጥራታችሁ ትክክል ነው። 14  ስለዚህ እኔ ጌታና መምህር ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብኩ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል። 15  እኔ እንዳደረግኩላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ አርዓያ ሆኜላችኋለሁ። 16  እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፤ የተላከም ከላከው አይበልጥም። 17  እነዚህን ነገሮች ስለምታውቁ ብትፈጽሟቸው ደስተኞች ናችሁ። 18  ይህን ስል ስለ ሁላችሁም መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኳቸውን አውቃለሁ። ይሁንና ‘ከማዕዴ ይበላ የነበረ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሳ’ የሚለው የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። 19  ገና ሳይፈጸም በፊት አሁን የምነግራችሁ፣ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ እሱ መሆኔን እንድታምኑ ነው። 20  እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ የምልከውን የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ሁሉ ደግሞ የላከኝንም ይቀበላል።” 21  ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ መንፈሱ ተረብሾ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” ሲል በግልጽ ተናገረ። 22  ደቀ መዛሙርቱም ስለ ማን እየተናገረ እንዳለ ግራ ገብቷቸው እርስ በርሳቸው ይተያዩ ጀመር። 23  ከእነሱ አንዱ ይኸውም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ኢየሱስ አጠገብ ጋደም ብሎ ነበር። 24  ስምዖን ጴጥሮስም ለዚህ ደቀ መዝሙር ምልክት በመስጠት “ስለ ማን እየተናገረ እንዳለ ንገረን” አለው። 25  እሱም ወደ ኢየሱስ ደረት ጠጋ ብሎ “ጌታ ሆይ፣ ማን ነው?” አለው። 26  ኢየሱስም “ይህን የማጠቅሰውን ቁራሽ ዳቦ የምሰጠው ሰው ነው” ሲል መለሰ። ከዚያም ዳቦውን አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ስምዖን ልጅ ለይሁዳ ሰጠው። 27  ይሁዳም ቁራሹን ከተቀበለ በኋላ ሰይጣን ገባበት። ስለዚህ ኢየሱስ “እያደረግከው ያለኸውን ነገር ቶሎ አድርገው” አለው። 28  ይሁን እንጂ በማዕድ ከተቀመጡት መካከል አንዳቸውም ለምን እንዲህ እንዳለው አልገባቸውም። 29  እንዲያውም አንዳንዶቹ ይሁዳ የገንዘብ ሣጥኑን ይይዝ ስለነበር ለበዓሉ የሚያስፈልጉትን ነገሮች እንዲገዛ ወይም ለድሆች የሆነ ነገር እንዲሰጥ ኢየሱስ ያዘዘው መስሏቸው ነበር። 30  ስለዚህ ይሁዳ ቁራሹን ዳቦ ከተቀበለ በኋላ ወዲያውኑ ወጣ። ጊዜውም ሌሊት ነበር። 31  ይሁዳ ከሄደ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ክብር ተጎናጸፈ፤ አምላክም በእሱ አማካኝነት ከበረ። 32  አምላክ ራሱም ያከብረዋል፤ ደግሞም ወዲያውኑ ያከብረዋል። 33  ልጆቼ ሆይ፣ ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ። እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁዳውያን ‘ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ እንዳልኳቸው ሁሉ አሁን ደግሞ ለእናንተ ይህንኑ እላችኋለሁ። 34  እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። 35  እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ሰዎች ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።” 36  ስምዖን ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ ወዴት ልትሄድ ነው?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፤ በኋላ ግን ትከተለኛለህ” ሲል መለሰ። 37  ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ አሁን ልከተልህ የማልችለው ለምንድን ነው? ሕይወቴን ስለ አንተ አሳልፌ ለመስጠት ፈቃደኛ ነኝ” አለው። 38  ኢየሱስም “ሕይወትህን ስለ እኔ አሳልፈህ ትሰጣለህ? እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል መለሰ።
[]
[]
[]
[]
12,312
14  “ልባችሁ አይረበሽ። በአምላክ እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ። 2  በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ ቦታ አለ። ይህ ባይሆን ኖሮ በግልጽ እነግራችሁ ነበር፤ ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት እሄዳለሁና። 3  ደግሞም ሄጄ ቦታ ባዘጋጀሁላችሁ ጊዜ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ እንደገና መጥቼ እኔ ወዳለሁበት እወስዳችኋለሁ። 4  እኔ ወደምሄድበትም ቦታ የሚወስደውን መንገድ ታውቃላችሁ።” 5  ቶማስም “ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም። ታዲያ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው። 6  ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። 7  እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ታውቁት ነበር፤ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ታውቁታላችሁ፤ ደግሞም አይታችሁታል።” 8  ፊልጶስም “ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። 9  ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ፊልጶስ፣ ከእናንተ ጋር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ ኖሬም እንኳ አላወቅከኝም? እኔን ያየ ሁሉ አብንም አይቷል። ታዲያ እንዴት ‘አብን አሳየን’ ትላለህ? 10  እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝና አብ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው አታምንም? የምነግራችሁን ነገር የምናገረው ከራሴ አመንጭቼ አይደለም፤ ሆኖም ሥራውን እየሠራ ያለው ከእኔ ጋር አንድነት ያለው አብ ነው። 11  እኔ ከአብ ጋር አንድነት እንዳለኝ አብም ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለው እመኑኝ፤ ካልሆነ ደግሞ ከተሠሩት ሥራዎች የተነሳ እመኑ። 12  እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያምን ሁሉ እኔ የምሠራቸውን ሥራዎች ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ እሱ ከእነዚህ የበለጡ ሥራዎች ይሠራል። 13  በተጨማሪም አብ በወልድ አማካኝነት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። 14  ማንኛውንም ነገር በስሜ ከለመናችሁ እኔ አደርገዋለሁ። 15  “የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዛቴን ትጠብቃላችሁ። 16  እኔም አብን እጠይቃለሁ፤ እሱም ለዘላለም ከእናንተ ጋር የሚሆን ሌላ ረዳት ይሰጣችኋል፤ 17  እሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን አብሯችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስላለ ታውቁታላችሁ። 18  ሐዘን ላይ ትቻችሁ አልሄድም። ወደ እናንተ እመጣለሁ። 19  ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም ከቶ አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ ምክንያቱም እኔ እኖራለሁ፤ እናንተም ትኖራላችሁ። 20  እኔ ከአባቴ ጋር አንድነት እንዳለኝ፣ እናንተ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳላችሁና እኔም ከእናንተ ጋር አንድነት እንዳለኝ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ። 21  እኔን የሚወደኝ ትእዛዛቴን የሚቀበልና የሚጠብቅ ነው። እኔን የሚወደኝን ሁሉ ደግሞ አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።” 22  የአስቆሮቱ ሳይሆን ሌላው ይሁዳ “ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን ለመግለጥ ያሰብከው ለምንድን ነው?” አለው። 23  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ማንም ሰው እኔን የሚወደኝ ከሆነ ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል፣ እኛም ወደ እሱ መጥተን መኖሪያችንን ከእሱ ጋር እናደርጋለን። 24  እኔን የማይወደኝ ሁሉ ቃሌን አይጠብቅም። ይህ እየሰማችሁት ያለው ቃል ደግሞ የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም። 25  “አሁን ከእናንተ ጋር እያለሁ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ። 26  ሆኖም አብ በስሜ የሚልከው ረዳት ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል እንዲሁም የነገርኳችሁን ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያደርጋችኋል። 27  ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ። እኔ ሰላም የምሰጣችሁ ዓለም በሚሰጥበት መንገድ አይደለም። ልባችሁ አይረበሽ፤ በፍርሃትም አይዋጥ። 28  ‘እሄዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ’ እንዳልኳችሁ ሰምታችኋል። ብትወዱኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ ከእኔ አብ ይበልጣልና። 29  በመሆኑም በሚፈጸምበት ጊዜ እንድታምኑ ከመፈጸሙ በፊት አሁን ነግሬአችኋለሁ። 30  የዚህ ዓለም ገዢ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር ብዙ አልነጋገርም፤ እሱም በእኔ ላይ ምንም ኃይል የለውም። 31  ይሁን እንጂ እኔ አብን እንደምወድ ዓለም እንዲያውቅ አብ ባዘዘኝ መሠረት እየሠራሁ ነው። ተነሱ ከዚህ እንሂድ።
[]
[]
[]
[]
12,313
15  “እኔ እውነተኛው የወይን ተክል ነኝ፤ አትክልተኛው ደግሞ አባቴ ነው። 2  በእኔ ላይ ያለውን፣ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቆርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ደግሞ ይበልጥ እንዲያፈራ ያጠራዋል። 3  እናንተ ከነገርኳችሁ ቃል የተነሳ አሁን ንጹሐን ናችሁ። 4  ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ኑሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ያለኝን አንድነት ጠብቄ እኖራለሁ። ቅርንጫፉ ከወይኑ ተክል ጋር ተጣብቆ ካልኖረ በራሱ ፍሬ ማፍራት አይችልም፤ እናንተም ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ጠብቃችሁ ካልኖራችሁ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም። 5  እኔ የወይኑ ተክል ነኝ፤ እናንተ ደግሞ ቅርንጫፎቹ ናችሁ። ማንኛውም ሰው ከእኔ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ከኖረና እኔም ከእሱ ጋር አንድ ሆኜ ከኖርኩ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ እናንተ ከእኔ ተለይታችሁ ምንም ነገር ልታደርጉ አትችሉምና። 6  አንድ ሰው ከእኔ ጋር ያለውን አንድነት ጠብቆ ካልኖረ እንደ ቅርንጫፍ ይጣልና ይደርቃል። ሰዎችም እንዲህ ያሉትን ቅርንጫፎች ሰብስበው እሳት ውስጥ በመጣል ያቃጥሏቸዋል። 7  እናንተ ከእኔ ጋር ያላችሁን አንድነት ከጠበቃችሁና ቃሌ በልባችሁ ከኖረ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ብትጠይቁ ይፈጸምላችኋል። 8  ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ መሆናችሁን ብታሳዩ በዚህ አባቴ ይከበራል። 9  አብ እኔን እንደወደደኝ፣ እኔም እናንተን እንዲሁ ወድጃችኋለሁ። እናንተም በፍቅሬ ኑሩ። 10  እኔ የአብን ትእዛዛት ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም ትእዛዛቴን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ። 11  “እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ እኔ ያገኘሁትን ደስታ እንድታገኙና የእናንተም ደስታ የተሟላ እንዲሆን ነው። 12  ትእዛዜ ይህ ነው፤ እኔ እንደወደድኳችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። 13  ሕይወቱን ለወዳጆቹ ሲል አሳልፎ ከሚሰጥ ሰው የበለጠ ፍቅር ያለው ማንም የለም። 14  የማዛችሁን ነገር የምትፈጽሙ ከሆነ ወዳጆቼ ናችሁ። 15  ከእንግዲህ ባሪያዎች ብዬ አልጠራችሁም፤ ምክንያቱም ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን ነገር አያውቅም። እኔ ግን ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ ስላሳወቅኳችሁ ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ። 16  እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩና ፍሬያችሁ ጸንቶ እንዲኖር ሾሜያችኋለሁ፤ የመረጥኳችሁ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ ነው። 17  “እነዚህን ነገሮች የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው። 18  ዓለም ቢጠላችሁ፣ እናንተን ከመጥላቱ በፊት እኔን እንደጠላኝ ታውቃላችሁ። 19  የዓለም ክፍል ብትሆኑ ኖሮ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር። አሁን ግን እኔ ከዓለም መረጥኳችሁ እንጂ የዓለም ክፍል ስላልሆናችሁ ከዚህ የተነሳ ዓለም ይጠላችኋል። 20  ባሪያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን ስደት አድርሰውብኝ ከሆነ እናንተንም ስደት ያደርሱባችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ ደግሞ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ። 21  ሆኖም የላከኝን ስለማያውቁት በስሜ ምክንያት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያደርጉባችኋል። 22  መጥቼ ባልነግራቸው ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር። አሁን ግን ለኃጢአታቸው የሚያቀርቡት ሰበብ የለም። 23  እኔን የሚጠላ ሁሉ አባቴንም ይጠላል። 24  ሌላ ማንም ያላደረገውን ነገር በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እኔን አይተዋል እንዲሁም እኔንም ሆነ አባቴን ጠልተዋል። 25  ይሁን እንጂ ይህ የሆነው ‘ያለምክንያት ጠሉኝ’ ተብሎ በሕጋቸው የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው። 26  ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ከአብ የሚወጣው ረዳት ይኸውም የእውነት መንፈስ ሲመጣ እሱ ስለ እኔ ይመሠክራል፤ 27  እናንተም ደግሞ ትመሠክራላችሁ፤ ምክንያቱም ከመጀመሪያ አንስቶ ከእኔ ጋር ነበራችሁ።
[]
[]
[]
[]
12,314
16  “ይህን ሁሉ የነገርኳችሁ እንዳትሰናከሉ ብዬ ነው። 2  ሰዎች ከምኩራብ ያባርሯችኋል። እንዲያውም እናንተን የሚገድል ሁሉ ለአምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንዳቀረበ አድርጎ የሚያስብበት ሰዓት ይመጣል። 3  ሆኖም እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ስላላወቁ ነው። 4  ይሁንና እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ የሚፈጸሙበት ሰዓት ሲደርስ አስቀድሜ ነግሬአችሁ እንደነበረ እንድታስታውሱ ነው። “ከእናንተ ጋር ስለነበርኩ እነዚህን ነገሮች በመጀመሪያ አልነገርኳችሁም። 5  አሁን ግን ወደ ላከኝ ልሄድ ነው፤ ሆኖም ከመካከላችሁ ‘ወዴት ነው የምትሄደው?’ ብሎ የጠየቀኝ የለም። 6  እነዚህን ነገሮች ስለነገርኳችሁ ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል። 7  ይሁንና እውነቱን ለመናገር እኔ የምሄደው ለእናንተው ጥቅም ነው። ምክንያቱም እኔ ካልሄድኩ ረዳቱ በምንም ዓይነት ወደ እናንተ አይመጣም፤ ከሄድኩ ግን እሱን ወደ እናንተ እልከዋለሁ። 8  እሱ ሲመጣ ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ለዓለም አሳማኝ ማስረጃ ያቀርባል፦ 9  በመጀመሪያ ደረጃ ስለ ኃጢአት የተባለው፣ ሰዎች በእኔ ስላላመኑ ነው፤ 10  ከዚያም ስለ ጽድቅ የተባለው፣ እኔ ወደ አብ ስለምሄድና እናንተ ከእንግዲህ ስለማታዩኝ ነው፤ 11  ስለ ፍርድ የተባለው ደግሞ የዚህ ዓለም ገዢ ስለተፈረደበት ነው። 12  “ገና ብዙ የምነግራችሁ ነገር አለኝ፤ አሁን ግን ልትሸከሙት አትችሉም። 13  ይሁን እንጂ እሱ ይኸውም የእውነት መንፈስ ሲመጣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ምክንያቱም የሚናገረው ከራሱ አመንጭቶ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የሰማውን ይናገራል፤ እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ያሳውቃችኋል። 14  የሚያሳውቃችሁ የእኔ ከሆነው ወስዶ ስለሆነ እሱ እኔን ያከብረኛል። 15  አብ ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ነው። የእኔ ከሆነው ወስዶ ያሳውቃችኋል ያልኳችሁ ለዚህ ነው። 16  ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ።” 17  በዚህ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው “‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ እንዲሁም ‘ወደ አብ ልሄድ ነውና’ ሲለን ምን ማለቱ ነው?” ተባባሉ። 18  ስለዚህ “‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ’ ሲል ምን ማለቱ ነው? ስለ ምን ነገር እየተናገረ እንደሆነ አልገባንም” አሉ። 19  ኢየሱስ ሊጠይቁት እንደፈለጉ ተረድቶ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ ስለዚህ ጉዳይ የምትጠያየቁት ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ ስላልኩ ነው? 20  እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ ታለቅሳላችሁ እንዲሁም ዋይ ዋይ ትላላችሁ፤ ዓለም ግን ይደሰታል፤ እናንተ ታዝናላችሁ፤ ሆኖም ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል። 21  አንዲት ሴት የመውለጃዋ ሰዓት ደርሶ ስታምጥ ትጨነቃለች፤ ሕፃኑን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሰው ወደ ዓለም በመምጣቱ ከደስታዋ የተነሳ ሥቃይዋን ሁሉ ትረሳለች። 22  ስለዚህ እናንተም አሁን አዝናችኋል፤ ሆኖም እንደገና ስለማያችሁ ልባችሁ በደስታ ይሞላል፤ ደስታችሁን ደግሞ ማንም አይነጥቃችሁም። 23  በዚያን ጊዜ እኔን ምንም ጥያቄ አትጠይቁኝም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብን ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትጠይቁት ይሰጣችኋል። 24  እስካሁን ድረስ በስሜ አንድም ነገር አልጠየቃችሁም። ደስታችሁ የተሟላ እንዲሆን ጠይቁ፤ ትቀበላላችሁ። 25  “እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ በምሳሌ ነው። ይሁንና ለእናንተ በምሳሌ የማልናገርበት ሰዓት ይመጣል፤ ከዚህ ይልቅ ስለ አብ በግልጽ እነግራችኋለሁ። 26  በዚያ ቀን አብን በስሜ ትለምናላችሁ፤ ይህን ስል ስለ እናንተ አብን እጠይቃለሁ ማለቴ አይደለም። 27  ምክንያቱም እናንተ እኔን ስለወደዳችሁኝና የአምላክ ተወካይ ሆኜ እንደመጣሁ ስላመናችሁ አብ ራሱ ይወዳችኋል። 28  እኔ የአብ ተወካይ ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ። አሁን ደግሞ ዓለምን ትቼ ወደ አብ ልሄድ ነው።” 29  ደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አሉ፦ “አሁን እኮ በግልጽ እየተናገርክ ነው፤ በምሳሌም አልተናገርክም። 30  አሁን ሁሉን ነገር እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ እስኪጠይቅህ ድረስ መጠበቅ እንደማያስፈልግህ ተረዳን። ስለሆነም ከአምላክ ዘንድ እንደመጣህ እናምናለን።” 31  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አሁን አመናችሁ? 32  እነሆ፣ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን ትታችሁ የምትሄዱበት ሰዓት ቀርቧል፤ እንዲያውም ደርሷል። ይሁንና አብ ከእኔ ጋር ስላለ ብቻዬን አይደለሁም። 33  እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ በእኔ አማካኝነት ሰላም እንዲኖራችሁ ነው። በዓለም ሳላችሁ መከራ ይደርስባችኋል፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,315
17  ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ እንዲህ ሲል ጸለየ፦ “አባት ሆይ፣ ሰዓቱ ደርሷል። ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤ 2  ይህም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደሰጠኸው ሁሉ እሱም አንተ ለሰጠኸው ሰው ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲሰጥ ነው። 3  የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ የሆንከውን አንተንና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ አለባቸው። 4  እንድሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርኩህ። 5  ስለዚህ አባት ሆይ፣ ዓለም ከመመሥረቱ በፊት በጎንህ ሆኜ ክብር እንደነበረኝ ሁሉ አሁንም በጎንህ አድርገህ አክብረኝ። 6  “ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገልጬላቸዋለሁ። እነሱ የአንተ ነበሩ፤ አንተም ለእኔ ሰጠኸኝ፤ ደግሞም ቃልህን ጠብቀዋል። 7  የሰጠኸኝ ነገር ሁሉ ከአንተ የተገኘ መሆኑን አሁን አውቀዋል፤ 8  ምክንያቱም የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ፤ እነሱም ተቀብለውታል፤ እንዲሁም የአንተ ተወካይ ሆኜ መምጣቴን በእርግጥ አውቀዋል፤ አንተ እንደላክኸኝም አምነዋል። 9  ስለ እነሱ እለምንሃለሁ፤ የምለምንህ ስለ ዓለም ሳይሆን አንተ ስለሰጠኸኝ ሰዎች ነው፤ ምክንያቱም እነሱ የአንተ ናቸው፤ 10  ደግሞም የእኔ የሆነው ነገር ሁሉ የአንተ ነው፤ የአንተ የሆነውም ሁሉ የእኔ ነው፤ እኔም በእነሱ መካከል ከብሬአለሁ። 11  “ከእንግዲህ እኔ በዓለም ውስጥ አልኖርም፤ እነሱ ግን በዓለም ውስጥ ናቸው፤ እኔ ወደ አንተ መምጣቴ ነው። ቅዱስ አባት ሆይ፣ እኛ አንድ እንደሆንን ሁሉ እነሱም አንድ እንዲሆኑ፣ ስለሰጠኸኝ ስለ ራስህ ስም ስትል ጠብቃቸው። 12  እኔ ከእነሱ ጋር ሳለሁ፣ ስለሰጠኸኝ ስለ ራስህ ስም ስል ስጠብቃቸው ቆይቻለሁ፤ ደግሞም ጠብቄአቸዋለሁ፤ የቅዱስ መጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ከጥፋት ልጅ በቀር አንዳቸውም አልጠፉም። 13  አሁን ግን ወደ አንተ መምጣቴ ነው፤ ደስታዬ በውስጣቸው ሙሉ እንዲሆን አሁን በዓለም ላይ እያለሁ እነዚህን ነገሮች እናገራለሁ። 14  ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ ሆኖም እኔ የዓለም ክፍል እንዳልሆንኩ ሁሉ እነሱም የዓለም ክፍል ስላልሆኑ ዓለም ጠላቸው። 15  “የምለምንህ ከዓለም እንድታወጣቸው ሳይሆን ከክፉው እንድትጠብቃቸው ነው። 16  እኔ የዓለም ክፍል እንዳልሆንኩ ሁሉ እነሱም የዓለም ክፍል አይደሉም። 17  በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። 18  አንተ ወደ ዓለም እንደላክኸኝ ሁሉ እኔም ወደ ዓለም ልኬአቸዋለሁ። 19  እነሱም በእውነት እንዲቀደሱ እኔ ራሴም ስለ እነሱ ስል ቅድስናዬን እጠብቃለሁ። 20  “የምለምንህ ስለ እነዚህ ብቻ ሳይሆን በእነሱ ቃል አማካኝነት በእኔ ለሚያምኑ ጭምር ነው፤ 21  ይህን ልመና የማቀርበውም ሁሉም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ ይኸውም ዓለም አንተ እንደላክኸኝ ያምን ዘንድ አባት ሆይ፣ አንተ ከእኔ ጋር አንድነት እንዳለህና እኔም ከአንተ ጋር አንድነት እንዳለኝ ሁሉ እነሱም ከእኛ ጋር አንድነት እንዲኖራቸው ነው። 22  እኛ አንድ እንደሆንን ሁሉ እነሱም አንድ እንዲሆኑ ለእኔ የሰጠኸኝን ክብር ሰጥቻቸዋለሁ። 23  እኔ ከእነሱ ጋር አንድነት አለኝ፤ አንተም ከእኔ ጋር አንድነት አለህ፤ ይህ ደግሞ እነሱም ፍጹም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ በተጨማሪም ዓለም አንተ እንደላክኸኝ እንዲሁም እኔን እንደወደድከኝ ሁሉ እነሱንም እንደወደድካቸው ያውቅ ዘንድ ነው። 24  አባት ሆይ፣ እነዚህ የሰጠኸኝ፣ እኔ ባለሁበት እነሱም ከእኔ ጋር እንዲሆኑ እፈልጋለሁ፤ ይህም ዓለም ከመመሥረቱ በፊት ስለወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብር እንዲያዩ ነው። 25  ጻድቅ አባት ሆይ፣ በእርግጥ ዓለም አላወቀህም፤ እኔ ግን አውቅሃለሁ፤ እነዚህ ደግሞ አንተ እንደላክኸኝ አውቀዋል። 26  እኔን የወደድክበት ፍቅር እነሱም እንዲኖራቸው እንዲሁም እኔ ከእነሱ ጋር አንድነት እንዲኖረኝ ስምህን አሳውቄአቸዋለሁ፤ ደግሞም አሳውቃለሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,316
18  ኢየሱስ ስለ እነዚህ ነገሮች ከጸለየ በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የቄድሮንን ሸለቆ ተሻግሮ ወደ አንድ የአትክልት ስፍራ ሄደ፤ እሱና ደቀ መዛሙርቱም ወደ አትክልት ስፍራው ገቡ። 2  ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብዙ ጊዜ በዚህ ስፍራ ይገናኝ ስለነበር አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም ቦታውን ያውቅ ነበር። 3  ስለዚህ ይሁዳ አንድ የወታደሮች ቡድን እንዲሁም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን የተላኩ የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች አስከትሎ መጣ፤ እነሱም ችቦና መብራት እንዲሁም መሣሪያ ይዘው ነበር። 4  በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የሚደርስበትን ነገር ሁሉ ስላወቀ ወደ ፊት ራመድ ብሎ “ማንን ነው የምትፈልጉት?” አላቸው። 5  እነሱም “የናዝሬቱን ኢየሱስ” ሲሉ መለሱለት። እሱም “እኔ ነኝ” አላቸው። አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም ከእነሱ ጋር ቆሞ ነበር። 6  ይሁን እንጂ ኢየሱስ “እኔ ነኝ” ሲላቸው ወደ ኋላ አፈግፍገው መሬት ላይ ወደቁ። 7  ዳግመኛም “ማንን ነው የምትፈልጉት?” ሲል ጠየቃቸው። እነሱም “የናዝሬቱን ኢየሱስ” አሉት። 8  ኢየሱስም መልሶ “እኔ ነኝ አልኳችሁ እኮ። የምትፈልጉት እኔን ከሆነ እነዚህን ተዉአቸው ይሂዱ” አለ። 9  ይህም የሆነው “ከሰጠኸኝ ከእነዚህ መካከል አንዱም እንኳ አልጠፋብኝም” ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። 10  በዚህ ጊዜ ሰይፍ ይዞ የነበረው ስምዖን ጴጥሮስ ሰይፉን በመምዘዝ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው። የባሪያውም ስም ማልኮስ ነበር። 11  ይሁን እንጂ ኢየሱስ ጴጥሮስን “ሰይፉን ወደ ሰገባው መልስ። አብ የሰጠኝን ጽዋ መጠጣት አይኖርብኝም?” አለው። 12  ከዚያም ወታደሮቹና የጦር አዛዡ እንዲሁም ከአይሁዳውያን የተላኩት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት። 13  በመጀመሪያም ወደ ሐና ወሰዱት፤ ምክንያቱም ሐና በዚያ ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው የቀያፋ አማት ነበር። 14  ቀያፋ ደግሞ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት ለእነሱ የተሻለ እንደሚሆን ለአይሁዳውያን ምክር የሰጠው ሰው ነው። 15  ስምዖን ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን እየተከተሉ ነበር። ይህን ደቀ መዝሙር ሊቀ ካህናቱ ያውቀው ስለነበር ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ገባ፤ 16  ጴጥሮስ ግን ውጭ በር ላይ ቆሞ ነበር። ስለሆነም ሊቀ ካህናቱ የሚያውቀው ይህ ደቀ መዝሙር ወጥቶ በር ጠባቂዋን አነጋገራትና ጴጥሮስን አስገባው። 17  በር ጠባቂ የነበረችውም አገልጋይ ጴጥሮስን “አንተም ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ አይደል?” አለችው። እሱም “አይደለሁም” አለ። 18  ብርድ ስለነበር ባሪያዎቹና የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ባቀጣጠሉት ከሰል ዙሪያ ቆመው እየሞቁ ነበር። ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። 19  በዚህ ጊዜ የካህናት አለቃው ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው። 20  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ። አይሁዳውያን ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኩራብና በቤተ መቅደሱ ሁልጊዜ አስተምር ነበር፤ በስውር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም። 21  እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? እኔ የነገርኳቸውን ነገር የሰሙትን ሰዎች ጠይቃቸው። እነዚህ የተናገርኩትን ያውቃሉ።” 22  ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ አጠገቡ ቆመው ከነበሩት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች አንዱ በጥፊ መታውና “ለካህናት አለቃው የምትመልሰው እንዲህ ነው?” አለው። 23  ኢየሱስም “የተሳሳተ ነገር ተናግሬ ከሆነ ስህተቴ ምን እንደሆነ ንገረኝ፤ የተናገርኩት ነገር ትክክል ከሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ?” ሲል መለሰለት። 24  ከዚያም ሐና ኢየሱስን እንደታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው። 25  ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት እየሞቀ ነበር። በዚህ ጊዜ ሰዎቹ “አንተም ከእሱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነህ አይደል?” አሉት። እሱም “አይደለሁም” ሲል ካደ። 26  ከሊቀ ካህናቱ ባሪያዎች አንዱ ይኸውም ጴጥሮስ ጆሮውን የቆረጠው ሰው ዘመድ “በአትክልቱ ስፍራ ከእሱ ጋር አይቼህ አልነበረም?” አለው። 27  ይሁን እንጂ ጴጥሮስ እንደገና ካደ፤ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ። 28  ከዚያም ኢየሱስን ከቀያፋ ቤት ወደ ገዢው መኖሪያ ወሰዱት። ጊዜውም ማለዳ ነበር። ሆኖም እነሱ ፋሲካን መብላት ይችሉ ዘንድ እንዳይረክሱ ወደ ገዢው መኖሪያ አልገቡም። 29  ስለዚህ ጲላጦስ እነሱ ወዳሉበት ወጥቶ “በዚህ ሰው ላይ የምታቀርቡት ክስ ምንድን ነው?” አላቸው። 30  እነሱም መልሰው “ይህ ሰው ጥፋተኛ ባይሆን ኖሮ ለአንተ አሳልፈን አንሰጠውም ነበር” አሉት። 31  ስለዚህ ጲላጦስ “እናንተ ራሳችሁ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት” አላቸው። አይሁዳውያኑም “እኛ ማንንም ሰው ለመግደል ሕግ አይፈቅድልንም” አሉት። 32  ይህ የሆነው ኢየሱስ በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚሞት ለማመልከት የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። 33  ስለሆነም ጲላጦስ ወደ ገዢው መኖሪያ ተመልሶ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” አለው። 34  ኢየሱስም መልሶ “ይህ የራስህ ጥያቄ ነው ወይስ ሌሎች ስለ እኔ ነግረውህ ነው?” አለው። 35  ጲላጦስም “እኔ አይሁዳዊ ነኝ እንዴ? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ የራስህ ሕዝብና የካህናት አለቆች ናቸው። ያደረግከው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። 36  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል አይደለም። መንግሥቴ የዚህ ዓለም ክፍል ቢሆን ኖሮ በአይሁዳውያን እጅ እንዳልወድቅ አገልጋዮቼ ይዋጉልኝ ነበር። አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለም።” 37  በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “እንግዲያው አንተ ንጉሥ ነህ?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ እየተናገርክ ነው። እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመሥከር ነው። ከእውነት ጎን የቆመ ሁሉ ቃሌን ይሰማል።” 38  ጲላጦስም “እውነት ምንድን ነው?” አለው። ይህን ከተናገረ በኋላ እንደገና አይሁዳውያኑ ወዳሉበት ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም። 39  ከዚህም በላይ በልማዳችሁ መሠረት በፋሲካ አንድ ሰው ለእናንተ መፍታቴ አይቀርም። ስለዚህ የአይሁዳውያንን ንጉሥ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” 40  እነሱም እንደገና በመጮኽ “ይህን ሰው አንፈልግም፤ በርባንን ፍታልን!” አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,317
19  ከዚያም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ ገረፈው። 2  ወታደሮቹም የእሾህ አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ ደፉበት፤ እንዲሁም ሐምራዊ ልብስ አለበሱት፤ 3  ወደ እሱ እየቀረቡም “የአይሁዳውያን ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” ይሉት ነበር። ደግሞም በጥፊ ይመቱት ነበር። 4  ጲላጦስም ዳግመኛ ወደ ውጭ ወጥቶ “ምንም ጥፋት እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እነሆ ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ” አላቸው። 5  በመሆኑም ኢየሱስ የእሾህ አክሊል እንደደፋና ሐምራዊ ልብስ እንደለበሰ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም “እነሆ፣ ሰውየው!” አላቸው። 6  ይሁን እንጂ የካህናት አለቆቹና የቤተ መቅደስ ጠባቂዎቹ ባዩት ጊዜ “ይሰቀል! ይሰቀል!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “እኔ ምንም ጥፋት ስላላገኘሁበት ራሳችሁ ወስዳችሁ ግደሉት” አላቸው። 7  አይሁዳውያኑም “እኛ ሕግ አለን፤ ይህ ሰው ደግሞ ራሱን የአምላክ ልጅ ስላደረገ በሕጉ መሠረት መሞት አለበት” ሲሉ መለሱለት። 8  ጲላጦስ ያሉትን ነገር ሲሰማ ይበልጥ ፍርሃት አደረበት፤ 9  ዳግመኛም ወደ ገዢው መኖሪያ ገብቶ ኢየሱስን “ለመሆኑ ከየት ነው የመጣኸው?” አለው። ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም። 10  ስለሆነም ጲላጦስ “መልስ አትሰጠኝም? ልፈታህም ሆነ ልገድልህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም?” አለው። 11  ኢየሱስም “ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን አይኖርህም ነበር። ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው የባሰ ኃጢአት ያለበት ለዚህ ነው” ሲል መለሰለት። 12  ከዚህ የተነሳ ጲላጦስ ኢየሱስን መፍታት የሚችልበትን መንገድ ያስብ ጀመር፤ አይሁዳውያኑ ግን “ይህን ሰው ከፈታኸው አንተ የቄሳር ወዳጅ አይደለህም። ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሰው ሁሉ የቄሳር ተቃዋሚ ነው” እያሉ ጮኹ። 13  ጲላጦስ ይህን ከሰማ በኋላ ኢየሱስን ወደ ውጭ አውጥቶ የድንጋይ ንጣፍ በተባለ ቦታ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ፤ ይህ ቦታ በዕብራይስጥ ጋባታ ይባላል። 14  ጊዜው የፋሲካ የዝግጅት ቀን ነበር፤ ሰዓቱ ደግሞ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር። ጲላጦስም አይሁዳውያኑን “እነሆ፣ ንጉሣችሁ!” አላቸው። 15  እነሱ ግን “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “ንጉሣችሁን ልግደለው?” አላቸው። የካህናት አለቆቹም “ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ሲሉ መለሱ። 16  በዚህ ጊዜ እንጨት ላይ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው። እነሱም ኢየሱስን ይዘው ወሰዱት። 17  ኢየሱስም የመከራውን እንጨት ራሱ ተሸክሞ የራስ ቅል ቦታ ወደተባለ ስፍራ ወጣ፤ ይህ ቦታ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ይባላል። 18  በዚያም በእንጨት ላይ ቸነከሩት፤ ከእሱም ጋር ሁለት ሰዎችን የሰቀሉ ሲሆን ኢየሱስን በመካከል አድርገው አንዱን በዚህ ሌላውን በዚያ ጎን ሰቀሉ። 19  በተጨማሪም ጲላጦስ ጽሑፍ ጽፎ በመከራው እንጨት ላይ አንጠለጠለው። ጽሑፉም “የአይሁዳውያን ንጉሥ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ነበር። 20  ኢየሱስ በእንጨት ላይ የተቸነከረበት ቦታ በከተማዋ አቅራቢያ የሚገኝ በመሆኑ ብዙ አይሁዳውያን ይህን ጽሑፍ አነበቡት፤ ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፣ በላቲንና በግሪክኛ ነበር። 21  ይሁን እንጂ የአይሁድ የካህናት አለቆች ጲላጦስን “እሱ ‘የአይሁዳውያን ንጉሥ ነኝ’ እንዳለ ጻፍ እንጂ ‘የአይሁዳውያን ንጉሥ’ ብለህ አትጻፍ” አሉት። 22  ጲላጦስም “እንግዲህ የጻፍኩትን ጽፌአለሁ” ሲል መለሰ። 23  ወታደሮቹ ኢየሱስን በእንጨት ላይ ከቸነከሩት በኋላ መደረቢያዎቹን ወስደው እያንዳንዱ ወታደር አንድ አንድ ቁራጭ እንዲደርሰው አራት ቦታ ቆራረጧቸው፤ ከውስጥ ለብሶት የነበረውንም ልብስ ወሰዱ። ሆኖም ልብሱ ከላይ እስከ ታች አንድ ወጥ ሆኖ ያለስፌት የተሠራ ነበር። 24  ስለዚህ እርስ በርሳቸው “ከምንቀደው ዕጣ ተጣጥለን ለማን እንደሚደርስ እንወስን” ተባባሉ። ይህም የሆነው “መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤ በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” የሚለው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። ወታደሮቹም ያደረጉት ይህንኑ ነበር። 25  ይሁንና ኢየሱስ በተሰቀለበት የመከራ እንጨት አጠገብ እናቱ፣ የእናቱ እህት፣ የቀልዮጳ ሚስት ማርያምና መግደላዊቷ ማርያም ቆመው ነበር። 26  ስለዚህ ኢየሱስ እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙር በአቅራቢያው ቆመው ሲያያቸው እናቱን “ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት። 27  ከዚያም ደቀ መዝሙሩን “እናትህ ይህችውልህ!” አለው። ደቀ መዝሙሩም ከዚያ ሰዓት አንስቶ ወደ ራሱ ቤት ወሰዳት። 28  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሁሉም ነገር እንደተፈጸመ አውቆ የቅዱስ መጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም “ተጠማሁ” አለ። 29  በዚያም የኮመጠጠ ወይን ጠጅ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር። በመሆኑም ወይን ጠጁ ውስጥ የተነከረ ሰፍነግ፣ በሂሶጵ አገዳ ላይ አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት። 30  ኢየሱስ የኮመጠጠውን ወይን ጠጅ ከቀመሰ በኋላ “ተፈጸመ!” አለ፤ ራሱንም ዘንበል አድርጎ መንፈሱን ሰጠ። 31  ዕለቱ የዝግጅት ቀን ስለነበር አይሁዳውያን በሰንበት (ያ ሰንበት ታላቅ ሰንበት ስለነበር) አስከሬኖቹ በመከራ እንጨቶቹ ላይ ተሰቅለው እንዳይቆዩ ሲሉ እግራቸው ተሰብሮ እንዲወርዱ ጲላጦስን ጠየቁት። 32  ስለዚህ ወታደሮቹ መጥተው ከእሱ ጋር የተሰቀሉትን የመጀመሪያውን ሰውና የሌላኛውን ሰው እግሮች ሰበሩ። 33  ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ቀደም ብሎ መሞቱን ስላዩ እግሮቹን አልሰበሩም። 34  ሆኖም ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ፈሰሰ። 35  ይህን ያየው ሰውም ምሥክርነት ሰጥቷል፤ ምሥክርነቱም እውነት ነው፤ እናንተም እንድታምኑ ይህ ሰው የሚናገራቸው ነገሮች እውነት እንደሆኑ ያውቃል። 36  ይህም የሆነው “ከእሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም” የሚለው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። 37  ደግሞም ሌላ የቅዱስ መጽሐፉ ቃል “የወጉትን ያዩታል” ይላል። 38  ይህ ከሆነ በኋላ፣ የአርማትያሱ ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ጠየቀ፤ ዮሴፍ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር። ሆኖም አይሁዳውያንን ይፈራ ስለነበር ይህን ለማንም አልተናገረም። ጲላጦስ ከፈቀደለት በኋላ መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን ወሰደ። 39  ቀደም ሲል በማታ ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስም 30 ኪሎ ግራም ገደማ የሚሆን የከርቤና የእሬት ድብልቅ ይዞ መጣ። 40  የኢየሱስንም አስከሬን ወስደው በአይሁዳውያን የአገናነዝ ልማድ መሠረት ጥሩ መዓዛ ባላቸው በእነዚህ ቅመሞች ተጠቅመው በበፍታ ጨርቅ ገነዙት። 41  እሱ በተገደለበት ቦታ አቅራቢያ አንድ የአትክልት ስፍራ ነበር፤ በአትክልት ስፍራው ውስጥ ደግሞ ገና ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር። 42  ዕለቱ አይሁዳውያን ለበዓሉ የሚዘጋጁበት ቀን ስለነበርና መቃብሩም በአቅራቢያው ይገኝ ስለነበር ኢየሱስን በዚያ አኖሩት።
[]
[]
[]
[]
12,318
2  በሦስተኛውም ቀን በገሊላ በምትገኘው በቃና የሠርግ ድግስ ነበር፤ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች። 2  ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሠርጉ ተጠርተው ነበር። 3  የወይን ጠጁ እያለቀ ሲሄድ የኢየሱስ እናት “የወይን ጠጅ አልቆባቸዋል” አለችው። 4  ኢየሱስ ግን “አንቺ ሴት፣ ይህ ጉዳይ እኔንና አንቺን ምን ይመለከተናል? ሰዓቴ ገና አልደረሰም” አላት። 5  እናቱም በዚያ የሚያገለግሉትን ሰዎች “የሚላችሁን ነገር ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው። 6  የአይሁዳውያን የመንጻት ሥርዓት በሚያዘው መሠረት እያንዳንዳቸው ሁለት ወይም ሦስት የፈሳሽ መለኪያዎች የሚይዙ ከድንጋይ የተሠሩ ስድስት የውኃ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር። 7  ኢየሱስም “ጋኖቹን ውኃ ሙሏቸው” አላቸው። እነሱም እስከ አፋቸው ድረስ ሞሏቸው። 8  ከዚያም “አሁን ቀድታችሁ ለድግሱ አሳዳሪ ስጡት” አላቸው። እነሱም ወስደው ሰጡት። 9  የድግሱ አሳዳሪም ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውኃ ቀመሰ፤ ሆኖም ከየት እንደመጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ 10  እንዲህ አለው፦ “ሰው ሁሉ በቅድሚያ ጥሩውን የወይን ጠጅ ያቀርብና ሰዎቹ ከሰከሩ በኋላ መናኛውን ያቀርባል። አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስካሁን ድረስ አስቀምጠሃል።” 11  ኢየሱስ ከምልክቶቹ የመጀመሪያ የሆነውን ይህን ተአምር በገሊላ በምትገኘው በቃና ፈጸመ፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእሱ አመኑ። 12  ከዚህ በኋላ እሱና እናቱ እንዲሁም ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤ ሆኖም በዚያ ብዙ ቀን አልቆዩም። 13  በዚህ ጊዜ የአይሁዳውያን ፋሲካ ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። 14  በቤተ መቅደሱ ውስጥ ከብት፣ በግና ርግብ የሚሸጡ ሰዎችን እንዲሁም በዚያ የተቀመጡ ገንዘብ መንዛሪዎችን አገኘ። 15  በዚህ ጊዜ የገመድ ጅራፍ ሠርቶ ሁሉንም ከበጎቻቸውና ከከብቶቻቸው ጋር አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ሳንቲሞች በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ። 16  ርግብ ሻጮቹንም “እነዚህን ከዚህ አስወጡ! የአባቴን ቤት የንግድ ቤት ማድረጋችሁ ይብቃ!” አላቸው። 17  ደቀ መዛሙርቱም “ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት ይበላኛል” ተብሎ የተጻፈው ትዝ አላቸው። 18  በዚህ ጊዜ አይሁዳውያን መልሰው “እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ የሚያረጋግጥ ምን ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት። 19  ኢየሱስም መልሶ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ እኔም በሦስት ቀን ውስጥ አነሳዋለሁ” አላቸው። 20  አይሁዳውያኑም “ቤተ መቅደሱን ለመገንባት 46 ዓመት ፈጅቷል፤ ታዲያ አንተ በሦስት ቀን ታነሳዋለህ?” አሉት። 21  እሱ ግን ቤተ መቅደስ ሲል ስለ ራሱ ሰውነት መናገሩ ነበር። 22  ከሙታን በተነሳ ጊዜም፣ ደቀ መዛሙርቱ ይህን ደጋግሞ ይናገር እንደነበር አስታወሱ፤ ቅዱሳን መጻሕፍትንና ኢየሱስ የተናገረውንም ቃል አመኑ። 23  ይሁንና በፋሲካ በዓል፣ በኢየሩሳሌም በነበረበት ጊዜ ብዙ ሰዎች የሚያከናውናቸውን ተአምራዊ ምልክቶች ሲያዩ በስሙ አመኑ። 24  ኢየሱስ ግን ሁሉንም ያውቃቸው ስለነበር አይተማመንባቸውም ነበር፤ 25  እንዲሁም በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ስለነበር ማንም ስለ ሰው እንዲመሠክርለት አላስፈለገውም።
[]
[]
[]
[]
12,319
20  በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን መግደላዊቷ ማርያም በማለዳ፣ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብሩ መጣች፤ መቃብሩ የተዘጋበትም ድንጋይ ተንከባሎ አየች። 2  ስለዚህ ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር እየሮጠች መጥታ “ጌታን ከመቃብሩ ውስጥ ወስደውታል፤ የት እንዳኖሩትም አናውቅም” አለቻቸው። 3  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብሩ አመሩ። 4  ሁለቱም አብረው ይሮጡ ጀመር፤ ሆኖም ሌላው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞ በመሮጥ መቃብሩ ጋ ደረሰ። 5  ጎንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት የበፍታ ጨርቆቹ እዚያ ተቀምጠው አየ፤ ወደ ውስጥ ግን አልገባም። 6  ከዚያም ስምዖን ጴጥሮስ ተከትሎት መጥቶ መቃብሩ ውስጥ ገባ። የበፍታ ጨርቆቹም በዚያ ተቀምጠው አየ። 7  በራሱ ላይ የነበረው ጨርቅ፣ ከመግነዝ ጨርቆቹ ጋር ሳይሆን ለብቻው ተጠቅልሎ አንድ ቦታ ላይ ተቀምጦ አየ። 8  ከዚያም ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደርሶ የነበረው ሌላው ደቀ መዝሙርም ወደ ውስጥ ገባ፤ እሱም አይቶ አመነ። 9  ከሞት መነሳት እንዳለበት የሚናገረውን የቅዱስ መጽሐፉን ቃል ገና አልተረዱም ነበር። 10  ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ። 11  ይሁን እንጂ ማርያም እዚያው መቃብሩ አጠገብ ቆማ ታለቅስ ነበር። እያለቀሰችም ወደ መቃብሩ ውስጥ ለማየት ጎንበስ አለች፤ 12  ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክትም የኢየሱስ አስከሬን አርፎበት በነበረው ቦታ አንዱ በራስጌው ሌላው በግርጌው ተቀምጠው አየች። 13  እነሱም “አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ?” አሏት። እሷም “ጌታዬን ወስደውታል፤ የት እንዳደረጉትም አላውቅም” አለቻቸው። 14  ይህን ካለች በኋላ ዞር ስትል ኢየሱስን በዚያ ቆሞ አየችው፤ ነገር ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቀችም። 15  ኢየሱስም “አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ? የምትፈልጊው ማንን ነው?” አላት። እሷም አትክልተኛው ስለመሰላት “ጌታዬ፣ አንተ ከዚህ ወስደኸው ከሆነ የት እንዳደረግከው ንገረኝ፤ እኔም እወስደዋለሁ” አለችው። 16  ኢየሱስም “ማርያም!” አላት። እሷም ዞር ብላ በዕብራይስጥ “ራቦኒ!” አለችው (ትርጉሙም “መምህር!” ማለት ነው)። 17  ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “ጥብቅ አድርገሽ አትያዥኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግኩምና። ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ‘ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ላርግ ነው’ ብለሽ ንገሪያቸው።” 18  መግደላዊቷ ማርያም መጥታ “ጌታን አየሁት!” ብላ ለደቀ መዛሙርቱ አበሰረቻቸው፤ እሱ ያላትንም ነገረቻቸው። 19  የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በነበረው በዚያው ቀን ምሽት ላይ ደቀ መዛሙርቱ አይሁዳውያኑን በመፍራታቸው በሮቹን ቆልፈው ተቀምጠው ሳለ ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። 20  ይህን ካለ በኋላ እጆቹንና ጎኑን አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን በማየታቸው እጅግ ተደሰቱ። 21  ኢየሱስም ዳግመኛ “ሰላም ለእናንተ ይሁን። አብ እኔን እንደላከኝ፣ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው። 22  ይህን ካለ በኋላ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፦ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። 23  የማንንም ሰው ኃጢአት ይቅር ብትሉ ኃጢአቱ ይቅር ይባላል፤ ይቅር የማትሉት ሰው ሁሉ ደግሞ ኃጢአቱ እንዳለ ይጸናል።” 24  ይሁን እንጂ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ኢየሱስ በመጣበት ጊዜ አብሯቸው አልነበረም። 25  ስለዚህ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት “ጌታን አየነው!” አሉት። እሱ ግን “በእጆቹ ላይ ምስማሮቹ የተቸነከሩበትን ምልክት ካላየሁ እንዲሁም ጣቴን ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ካላስገባሁና እጄን በጎኑ ካላስገባሁ ፈጽሞ አላምንም” አላቸው። 26  እንደገናም ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነሱ ጋር ነበር። በሮቹ ተቆልፈው የነበሩ ቢሆንም ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አለ። 27  ከዚያም ቶማስን “ጣትህን እዚህ ክተት፤ እጆቼንም ተመልከት፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አስገባ። መጠራጠርህን ተውና እመን” አለው። 28  ቶማስም መልሶ “ጌታዬ፣ አምላኬ!” አለው። 29  ኢየሱስ “ስላየኸኝ አመንክ? ሳያዩ የሚያምኑ ደስተኞች ናቸው” አለው። 30  እርግጥ ኢየሱስ በዚህ ጥቅልል ውስጥ ያልተጻፉ ሌሎች ብዙ ተአምራዊ ምልክቶችም በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል። 31  ሆኖም እነዚህ የተጻፉት ኢየሱስ በእርግጥ ክርስቶስ እንዲሁም የአምላክ ልጅ እንደሆነ እንድታምኑና በማመናችሁም በስሙ አማካኝነት ሕይወት እንዲኖራችሁ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,320
21  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር እንደገና ለደቀ መዛሙርቱ ተገለጠ። የተገለጠውም በዚህ መንገድ ነበር፤ 2  ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ፣ የገሊላ ቃና ሰው የሆነው ናትናኤል፣ የዘብዴዎስ ልጆችና ሌሎች ሁለት ደቀ መዛሙርቱ አብረው ነበሩ። 3  ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ላጠምድ መሄዴ ነው” አላቸው። እነሱም “እኛም አብረንህ እንሄዳለን” አሉት። ወጥተው ሄዱና ጀልባ ላይ ተሳፈሩ፤ በዚያ ሌሊት ግን አንድም ዓሣ አልያዙም። 4  ይሁን እንጂ ጎህ ሲቀድ ኢየሱስ መጥቶ በባሕሩ ዳርቻ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም ነበር። 5  ከዚያም ኢየሱስ “ልጆቼ፣ የሚበላ ነገር አላችሁ?” አላቸው። እነሱም “የለንም!” ብለው መለሱለት። 6  እሱም “መረቡን ከጀልባዋ በስተ ቀኝ ጣሉት፤ ዓሣ ታገኛላችሁ” አላቸው። እነሱም መረቡን ጣሉ፤ ከዓሣውም ብዛት የተነሳ መረቡን መጎተት አቃታቸው። 7  በዚህ ጊዜ፣ ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን “ጌታ እኮ ነው!” አለው። ስምዖን ጴጥሮስም ጌታ መሆኑን ሲሰማ ከወገቡ በላይ ራቁቱን ስለነበር መደረቢያውን ለበሰና ዘሎ ባሕሩ ውስጥ ገባ። 8  ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከባሕሩ ዳርቻ ብዙም ሳይርቁ 90 ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ስለነበሩ በዓሣዎች የተሞላውን መረብ እየጎተቱ በትንሿ ጀልባ መጡ። 9  ወደ ባሕሩ ዳርቻ በደረሱ ጊዜ በከሰል ፍም ላይ የተቀመጠ ዓሣ እንዲሁም ዳቦ አዩ። 10  ኢየሱስ “አሁን ከያዛችሁት ዓሣ የተወሰነ አምጡ” አላቸው። 11  ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጀልባዋ ላይ ወጥቶ በትላልቅ ዓሣዎች የተሞላውን መረብ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ጎተተው፤ የዓሣዎቹም ብዛት 153 ነበር። መረቡ ይህን ያህል ብዙ ዓሣ ቢይዝም አልተቀደደም። 12  ኢየሱስ “ኑ፣ ቁርሳችሁን ብሉ” አላቸው። ጌታ መሆኑን አውቀው ስለነበር ከደቀ መዛሙርቱ መካከል “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም። 13  ኢየሱስም መጥቶ ዳቦውን አነሳና ሰጣቸው፤ ዓሣውንም አንስቶ እንዲሁ አደረገ። 14  ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር። 15  ቁርስ በልተው ከጨረሱም በኋላ ኢየሱስ፣ ስምዖን ጴጥሮስን “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ ከእነዚህ አስበልጠህ ትወደኛለህ?” አለው። እሱም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም “ጠቦቶቼን መግብ” አለው። 16  ደግሞም ለሁለተኛ ጊዜ “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ ትወደኛለህ?” አለው። እሱም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ሲል መለሰለት። ኢየሱስም “ግልገሎቼን ጠብቅ” አለው። 17  ለሦስተኛ ጊዜም “የዮሐንስ ልጅ ስምዖን፣ በጣም ትወደኛለህ?” አለው። ጴጥሮስ ለሦስተኛ ጊዜ “በጣም ትወደኛለህ?” ብሎ ስለጠየቀው አዘነ። በመሆኑም “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ግልገሎቼን መግብ። 18  እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ወጣት ሳለህ ራስህ ለብሰህ ወደፈለግክበት ቦታ ትሄድ ነበር። ስታረጅ ግን እጅህን ትዘረጋለህ፤ ሌላ ሰውም ያለብስሃል፤ ወደማትፈልግበትም ቦታ ይወስድሃል።” 19  ይህን የተናገረው፣ ጴጥሮስ በምን ዓይነት አሟሟት አምላክን እንደሚያከብር ለማመልከት ነበር። ይህን ካለ በኋላ “እኔን መከተልህን ቀጥል” አለው። 20  ጴጥሮስ ዞር ሲል ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ሲከተላቸው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር ራት በበሉ ጊዜ ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ “ጌታ ሆይ፣ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው። 21  ጴጥሮስም ባየው ጊዜ ኢየሱስን “ጌታ ሆይ፣ ይህስ ሰው ምን ይሆናል?” አለው። 22  ኢየሱስም “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲቆይ ብፈቅድ አንተ ምን ቸገረህ? አንተ እኔን መከተልህን ቀጥል” አለው። 23  በመሆኑም ይህ ደቀ መዝሙር አይሞትም የሚል ወሬ በወንድሞች መካከል ተሰራጨ። ይሁንና ኢየሱስ “እኔ እስክመጣ ድረስ እንዲቆይ ብፈቅድ አንተ ምን ቸገረህ?” አለው እንጂ አይሞትም አላለውም። 24  ስለ እነዚህ ነገሮች የሚመሠክረውና እነዚህን ነገሮች የጻፈው ይህ ደቀ መዝሙር ነው፤ እሱ የሚሰጠው ምሥክርነትም እውነት እንደሆነ እናውቃለን። 25  እርግጥ ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮችም አሉ፤ እነዚህ ሁሉ በዝርዝር ቢጻፉ ዓለም ራሱ የተጻፉትን ጥቅልሎች ለማስቀመጥ የሚበቃ ቦታ የሚኖረው አይመስለኝም።
[]
[]
[]
[]
12,321
3  ከፈሪሳውያን ወገን፣ የአይሁዳውያን ገዢ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል ሰው ነበር። 2  ይህ ሰው በማታ ወደ ኢየሱስ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ረቢ፣ አንተ ከአምላክ ዘንድ የመጣህ አስተማሪ እንደሆንክ እናውቃለን፤ ምክንያቱም አምላክ ከእሱ ጋር ካልሆነ በቀር አንተ የምትፈጽማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች መፈጸም የሚችል አንድም ሰው የለም።” 3  ኢየሱስም መልሶ “እውነት እውነት እልሃለሁ፣ አንድ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የአምላክን መንግሥት ሊያይ አይችልም” አለው። 4  ኒቆዲሞስም “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግም ወደ እናቱ ማህፀን ገብቶ ሊወለድ ይችላል?” አለው። 5  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ አምላክ መንግሥት ሊገባ አይችልም። 6  ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስ የተወለደ ደግሞ መንፈስ ነው። 7  ‘ዳግመኛ መወለድ አለባችሁ’ ስላልኩህ አትገረም። 8  ነፋስ ወደፈለገው አቅጣጫ ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ሆኖም ከየት እንደሚመጣና ወዴት እንደሚሄድ አታውቅም። ከመንፈስ የተወለደም ሁሉ እንደዚሁ ነው።” 9  ኒቆዲሞስም መልሶ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለው። 10  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “አንተ የእስራኤል አስተማሪ ሆነህ ሳለህ እነዚህን ነገሮች አታውቅም? 11  እውነት እውነት እልሃለሁ፣ እኛ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሠክራለን፤ እናንተ ግን እኛ የምንሰጠውን ምሥክርነት አትቀበሉም። 12  ስለ ምድራዊ ነገሮች ነግሬአችሁ የማታምኑ ከሆነ ስለ ሰማያዊ ነገሮች ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? 13  ደግሞም ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም። 14  ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደሰቀለ፣ የሰው ልጅም እንዲሁ ሊሰቀል ይገባዋል፤ 15  ይኸውም በእሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው። 16  “አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል። 17  ምክንያቱም አምላክ ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ላይ እንዲፈርድ ሳይሆን ዓለም በእሱ አማካኝነት እንዲድን ነው። 18  በእሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም። በእሱ የማያምን ሁሉ ግን በአምላክ አንድያ ልጅ ስም ስለማያምን ቀድሞውኑም ተፈርዶበታል። 19  እንግዲህ የሚፈረድባቸው በዚህ መሠረት ነው፦ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለነበረ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ። 20  መጥፎ ነገር የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ እንዲሁም ሥራው እንዳይጋለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም። 21  ትክክል የሆነውን የሚያደርግ ሁሉ ግን ያደረገው ነገር ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ የተከናወነ መሆኑ እንዲታይ ወደ ብርሃን ይመጣል።” 22  ከዚህ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ ገጠራማ ክልል ሄዱ፤ በዚያም ከእነሱ ጋር ለተወሰነ ጊዜ ቆየ፤ ያጠምቅም ነበር። 23  ይሁንና ዮሐንስም በሳሊም አቅራቢያ በሄኖን ብዙ ውኃ በመኖሩ በዚያ እያጠመቀ ነበር፤ ሰዎችም እየመጡ ይጠመቁ ነበር፤ 24  በዚህ ጊዜ ዮሐንስ ገና እስር ቤት አልገባም ነበር። 25  የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት የመንጻት ሥርዓትን በተመለከተ ከአንድ አይሁዳዊ ጋር ተከራከሩ። 26  ከዚያ በኋላ ወደ ዮሐንስ መጥተው “ረቢ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረውና ስለ እሱ የመሠከርክለት ሰው እያጠመቀ ነው፤ ሰዉም ሁሉ ወደ እሱ እየሄደ ነው” አሉት። 27  ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በቀር አንዳች ነገር ሊያገኝ አይችልም። 28  ‘እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤ ከዚህ ይልቅ ከእሱ በፊት የተላክሁ ነኝ’ እንዳልኩ እናንተ ራሳችሁ ትመሠክራላችሁ። 29  ሙሽራይቱ የሙሽራው ናት። ይሁን እንጂ የሙሽራው ጓደኛ በዚያ ቆሞ ሲሰማው በሙሽራው ድምፅ የተነሳ እጅግ ደስ ይለዋል። በመሆኑም የእኔ ደስታ ተፈጽሟል። 30  እሱ እየጨመረ መሄድ አለበት፤ እኔ ግን እየቀነስኩ መሄድ አለብኝ።” 31  ከላይ የሚመጣው ከሌሎች ሁሉ በላይ ነው። ከምድር የሆነው ምድራዊ ነው፤ የሚናገረውም ስለ ምድራዊ ነገሮች ነው። ከሰማይ የሚመጣው ከሌሎች ሁሉ በላይ ነው። 32  ስላየውና ስለሰማው ነገር ይመሠክራል፤ ነገር ግን ምሥክርነቱን የሚቀበል ሰው የለም። 33  ምሥክርነቱን የተቀበለ ሰው ሁሉ አምላክ እውነተኛ መሆኑን አረጋግጧል። 34  ምክንያቱም አምላክ የላከው የአምላክን ቃል ይናገራል፤ አምላክ መንፈሱን ቆጥቦ አይሰጥምና። 35  አብ ወልድን ይወዳል፤ ደግሞም ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል። 36  በወልድ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ወልድን የማይታዘዝ ግን የአምላክ ቁጣ በላዩ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
[]
[]
[]
[]
12,322
4  ጌታ፣ ከዮሐንስ ይበልጥ ብዙ ደቀ መዛሙርት እያፈራና እያጠመቀ መሆኑን ፈሪሳውያን እንደሰሙ ባወቀ ጊዜ፣ 2  (እርግጥ ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም) 3  ይሁዳን ለቆ እንደገና ወደ ገሊላ ሄደ። 4  ሆኖም በሰማርያ በኩል ማለፍ ነበረበት። 5  ስለሆነም ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው መሬት አጠገብ ወዳለችው ሲካር ወደተባለች የሰማርያ ከተማ መጣ። 6  ደግሞም በዚያ የያዕቆብ የውኃ ጉድጓድ ነበረ። ኢየሱስም ከጉዞው የተነሳ ደክሞት ስለነበር በውኃ ጉድጓዱ አጠገብ ተቀመጠ። ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር። 7  አንዲት የሰማርያ ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም “እባክሽ፣ የምጠጣው ውኃ ስጪኝ” አላት። 8  (ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማዋ ሄደው ነበር።) 9  ሳምራዊቷም “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለ እኔን ሳምራዊቷን እንዴት የምጠጣው ውኃ ስጪኝ ትለኛለህ?” አለችው። (ይህን ያለችው አይሁዳውያን ከሳምራውያን ጋር ምንም ግንኙነት ስላልነበራቸው ነው።) 10  ኢየሱስም መልሶ “የአምላክን ነፃ ስጦታ ብታውቂና ‘የምጠጣው ውኃ ስጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብትረጂ ኖሮ አንቺ ራስሽ ትጠይቂው ነበር፤ እሱም የሕይወት ውኃ ይሰጥሽ ነበር” አላት። 11  እሷም እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ፣ አንተ ውኃ መቅጃ እንኳ የለህም፤ ጉድጓዱ ደግሞ ጥልቅ ነው። ታዲያ ይህን የሕይወት ውኃ ከየት ታገኛለህ? 12  አንተ ይህን የውኃ ጉድጓድ ከሰጠን እንዲሁም ከልጆቹና ከከብቶቹ ጋር ከዚህ ጉድጓድ ከጠጣው ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህ?” 13  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል። 14  እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ፈጽሞ አይጠማም፤ ከዚህ ይልቅ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት የሚያስገኝ የውኃ ምንጭ ይሆናል።” 15  ሴትየዋም “ጌታዬ፣ እንዳልጠማም ሆነ ውኃ ለመቅዳት ወደዚህ ቦታ እንዳልመላለስ ይህን ውኃ ስጠኝ” አለችው። 16  እሱም “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ተመልሰሽ ነይ” አላት። 17  ሴትየዋም “ባል የለኝም” ብላ መለሰችለት። ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “‘ባል የለኝም’ ማለትሽ ትክክል ነው። 18  ምክንያቱም አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁን አብሮሽ ያለው ሰው ደግሞ ባልሽ አይደለም። ስለዚህ የተናገርሽው እውነት ነው።” 19  ሴትየዋም እንዲህ አለችው፦ “ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደሆንክ አሁን ተረዳሁ። 20  አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ አምልኳቸውን ያካሂዱ ነበር፤ እናንተ አይሁዳውያን ግን ሰዎች ማምለክ ያለባቸው በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ።” 21  ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “አንቺ ሴት፣ እመኚኝ፤ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም አብን የማታመልኩበት ሰዓት ይመጣል። 22  እናንተ የማታውቁትን ታመልካላችሁ፤ እኛ ግን መዳን የሚጀምረው ከአይሁዳውያን ስለሆነ የምናውቀውን እናመልካለን። 23  ይሁንና እውነተኛ አምላኪዎች አብን በመንፈስና በእውነት የሚያመልኩበት ሰዓት ይመጣል፤ ያም ሰዓት አሁን ነው፤ ምክንያቱም አብ እንዲያመልኩት የሚፈልገው እንዲህ ያሉ ሰዎችን ነው። 24  አምላክ መንፈስ ነው፤ የሚያመልኩትም በመንፈስና በእውነት ሊያመልኩት ይገባል።” 25  ሴትየዋም “ክርስቶስ የተባለ መሲሕ እንደሚመጣ አውቃለሁ። እሱ ሲመጣ ሁሉንም ነገር ግልጥልጥ አድርጎ ይነግረናል” አለችው። 26  ኢየሱስም “እያነጋገርኩሽ ያለሁት እኔ፣ እሱ ነኝ” አላት። 27  በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡ፤ ከሴት ጋር ሲነጋገር አይተውም ተደነቁ። ይሁን እንጂ “ምን ፈልገህ ነው?” ወይም “ከእሷ ጋር የምትነጋገረው ለምንድን ነው?” ያለው ማንም አልነበረም። 28  ሴትየዋም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማዋ በመሄድ ሰዎቹን እንዲህ አለቻቸው፦ 29  “ያደረግኩትን ሁሉ የነገረኝን ሰው መጥታችሁ እዩ። ይህ ሰው ክርስቶስ ይሆን እንዴ?” 30  እነሱም ከከተማዋ ወጥተው ወደ እሱ መጡ። 31  በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ረቢ፣ ብላ እንጂ” እያሉ ጎተጎቱት። 32  እሱ ግን “እናንተ የማታውቁት የምበላው ምግብ አለኝ” አላቸው። 33  ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው “ምግብ ያመጣለት ይኖር ይሆን እንዴ?” ተባባሉ። 34  ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና እንዳከናውነው የሰጠኝን ሥራ መፈጸም ነው። 35  እናንተ መከር ሊገባ ገና አራት ወር ይቀረዋል ትሉ የለም? እነሆ እላችኋለሁ፣ ዓይናችሁን ወደ ማሳው አቅንታችሁ አዝመራው እንደነጣ ተመልከቱ። 36  አሁንም እንኳ አጫጁ ደሞዙን እየተቀበለና ለዘላለም ሕይወት ፍሬ እየሰበሰበ ነው፤ ስለዚህ ዘሪውም ሆነ አጫጁ በአንድነት ደስ ይላቸዋል። 37  ከዚህም የተነሳ ‘አንዱ ይዘራል፤ ሌላኛውም ያጭዳል’ የሚለው አባባል እውነት ነው። 38  እኔም ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ። ሌሎች በደከሙበት እናንተ የድካማቸው ፍሬ ተካፋዮች ሆናችሁ።” 39  ሴትየዋ “ያደረግኩትን ሁሉ ነገረኝ” ብላ ስለመሠከረች ከዚያች ከተማ ብዙ ሳምራውያን በእሱ አመኑ። 40  ሳምራውያኑም ወደ እሱ በመጡ ጊዜ አብሯቸው እንዲቆይ ለመኑት፤ እሱም በዚያ ሁለት ቀን ቆየ። 41  በመሆኑም ሌሎች ብዙ ሰዎች ከተናገረው ቃል የተነሳ አመኑ፤ 42  ሴትየዋንም “ከእንግዲህ የምናምነው አንቺ ስለነገርሽን ብቻ አይደለም፤ ምክንያቱም እኛ ራሳችን ሰምተናል፤ እንዲሁም ይህ ሰው በእርግጥ የዓለም አዳኝ እንደሆነ አውቀናል” አሏት። 43  ከሁለት ቀናት በኋላ ከዚያ ተነስቶ ወደ ገሊላ ሄደ። 44  ይሁንና ኢየሱስ ራሱ፣ ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር ተናግሮ ነበር። 45  ገሊላ በደረሰ ጊዜም የገሊላ ሰዎች በጥሩ ሁኔታ ተቀበሉት፤ ምክንያቱም በኢየሩሳሌም በበዓሉ ላይ ተገኝተው በዚያ ያከናወናቸውን ነገሮች ሁሉ አይተው ነበር። 46  ከዚያም ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ ወደለወጠባት በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ቃና በድጋሚ መጣ። በዚህ ጊዜ በቅፍርናሆም፣ ልጁ የታመመበት የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን የሆነ አንድ ሰው ነበር። 47  ይህ ሰው ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መምጣቱን ሲሰማ ወደ እሱ ሄደና ወደ ቅፍርናሆም ወርዶ በሞት አፋፍ ላይ ያለውን ልጁን እንዲፈውስለት ለመነው። 48  ኢየሱስ ግን “መቼም እናንተ ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ካላያችሁ ፈጽሞ አታምኑም” አለው። 49  የቤተ መንግሥት ባለሥልጣኑም “ጌታዬ፣ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ በቶሎ ድረስ” አለው። 50  ኢየሱስም “ሂድ፤ ልጅህ ድኗል” አለው። ሰውየውም ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ሄደ። 51  ሆኖም ሰውየው ወደዚያ እየወረደ ሳለ ባሪያዎቹ አገኙትና ልጁ በሕይወት እንዳለ ነገሩት። 52  እሱም ልጁ ስንት ሰዓት ላይ እንደተሻለው ጠየቃቸው። እነሱም “ትናንት ሰባት ሰዓት ላይ ትኩሳቱ ለቀቀው” ብለው መለሱለት። 53   በዚህ ጊዜ አባትየው ልጁ የዳነው ልክ ኢየሱስ “ልጅህ ድኗል” ባለው ሰዓት ላይ መሆኑን አወቀ። እሱና መላው ቤተሰቡም አማኞች ሆኑ። 54  ይህም ደግሞ ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ ሲመጣ ያከናወነው ሁለተኛው ተአምራዊ ምልክት ነው።
[]
[]
[]
[]
12,323
5  ከዚህ በኋላ የአይሁዳውያን በዓል ስለነበረ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። 2  በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ አምስት ባለ መጠለያ መተላለፊያዎች ያሉት በዕብራይስጥ ቤተዛታ ተብሎ የሚጠራ አንድ የውኃ ገንዳ ነበር። 3  በእነዚህ መተላለፊያዎች ውስጥ ብዙ ሕመምተኞች፣ ዓይነ ስውሮች፣ አንካሶችና ሽባዎች ይተኙ ነበር። 4  —— 5  በዚያም ለ38 ዓመት ሕመምተኛ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበር። 6  ኢየሱስ ይህን ሰው በዚያ ተኝቶ አየውና ለረጅም ጊዜ ሕመምተኛ ሆኖ እንደኖረ አውቆ “መዳን ትፈልጋለህ?” አለው። 7  ሕመምተኛውም “ጌታዬ፣ ውኃው በሚናወጥበት ጊዜ ገንዳው ውስጥ የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፤ ወደ ገንዳው ስሄድ ደግሞ ሌላው ቀድሞኝ ይገባል” ሲል መለሰለት። 8  ኢየሱስም “ተነስ! ምንጣፍህን ተሸክመህ ሂድ” አለው። 9  ሰውየውም ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ ምንጣፉንም አንስቶ መሄድ ጀመረ። ቀኑም ሰንበት ነበር። 10  በመሆኑም አይሁዳውያን የተፈወሰውን ሰው “ሰንበት እኮ ነው፤ ምንጣፍህን እንድትሸከም ሕጉ አይፈቅድልህም” አሉት። 11  እሱ ግን “የፈወሰኝ ሰው ራሱ ‘ምንጣፍህን ተሸክመህ ሂድ’ ብሎኛል” ሲል መለሰላቸው። 12  እነሱም “‘ምንጣፍህን ተሸክመህ ሂድ’ ያለህ ሰው ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት። 13  ሆኖም ኢየሱስ ከቦታው ዞር ብሎ ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅሎ ስለነበር ሰውየው የፈወሰውን ሰው ማንነት ማወቅ አልቻለም። 14  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሰውየውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘውና “አሁን ደህና ሆነሃል። የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ኃጢአት አትሥራ” አለው። 15  ሰውየውም ሄዶ የፈወሰው ኢየሱስ መሆኑን ለአይሁዳውያኑ ነገራቸው። 16  ከዚህም የተነሳ አይሁዳውያኑ በኢየሱስ ላይ ስደት ያደርሱበት ጀመር፤ ይህን ያደረጉት በሰንበት ቀን እነዚህን ነገሮች ይፈጽም ስለነበረ ነው። 17  እሱ ግን “አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም እሠራለሁ” ሲል መለሰላቸው። 18  ከዚህም የተነሳ አይሁዳውያኑ ሰንበትን ስለጣሰ ብቻ ሳይሆን አምላክን የገዛ አባቱ እንደሆነ አድርጎ በመጥራት ራሱን ከአምላክ ጋር እኩል ስላደረገ እሱን ለመግደል ይበልጥ ተነሳሱ። 19  ስለሆነም ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ወልድ፣ አብ ሲያደርግ ያየውን ብቻ እንጂ በራሱ ተነሳስቶ አንድም ነገር ሊያደርግ አይችልም። አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድም በተመሳሳይ መንገድ ያንኑ ያደርጋል። 20  ምክንያቱም አብ ወልድን ይወደዋል፤ እንዲሁም እሱ ራሱ የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከእነዚህም የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል። 21  አብ ሙታንን እንደሚያስነሳቸውና ሕያው እንደሚያደርጋቸው ሁሉ ወልድም እንዲሁ የፈለገውን ሰው ሕያው ያደርጋል። 22  አብ በማንም ላይ አይፈርድምና፤ ከዚህ ይልቅ የመፍረዱን ሥልጣን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶታል፤ 23  ይህን ያደረገውም ሁሉም አብን እንደሚያከብሩ ሁሉ ወልድንም እንዲያከብሩ ነው። ወልድን የማያከብር ሁሉ እሱን የላከውን አብንም አያከብርም። 24  እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን የሚሰማና የላከኝን የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ ወደ ፍርድም አይመጣም፤ ከዚህ ይልቅ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግሯል። 25  “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ሙታን የአምላክን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ ያም ሰዓት አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ። 26  አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና። 27  እሱ የሰው ልጅ ስለሆነ የመፍረድ ሥልጣን ሰጥቶታል። 28  በዚህ አትደነቁ፤ በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣልና፤ 29  መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ ደግሞ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ። 30  በራሴ ተነሳስቼ አንድም ነገር ማድረግ አልችልም። እንደሰማሁ እፈርዳለሁ፤ የራሴን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ መፈጸም ስለምፈልግ የምፈርደው የጽድቅ ፍርድ ነው። 31  “እኔ ብቻ ስለ ራሴ ብመሠክር ምሥክርነቴ እውነት አይደለም። 32  ስለ እኔ የሚመሠክር ሌላ አለ፤ ደግሞም እሱ ስለ እኔ የሚሰጠው ምሥክርነት እውነት እንደሆነ አውቃለሁ። 33  ወደ ዮሐንስ ሰዎች ልካችሁ ነበር፤ እሱም ለእውነት መሥክሯል። 34  ይሁን እንጂ እኔ የሰው ምሥክርነት አያስፈልገኝም፤ ይህን የምናገረው ግን እናንተ እንድትድኑ ነው። 35  ያ ሰው የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበር፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በእሱ ብርሃን እጅግ ለመደሰት ፈቃደኞች ነበራችሁ። 36  እኔ ግን ከዮሐንስ የበለጠ ምሥክር አለኝ፤ ምክንያቱም አባቴ እንዳከናውነው የሰጠኝ ሥራ ማለትም እየሠራሁት ያለው ይህ ሥራ አብ እንደላከኝ ይመሠክራል። 37  የላከኝ አብም ራሱ ስለ እኔ መሥክሯል። እናንተ መቼም ቢሆን ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤ 38  እሱ የላከውንም ስለማታምኑ ቃሉ በልባችሁ ውስጥ አይኖርም። 39  “እናንተ በቅዱሳን መጻሕፍት የዘላለም ሕይወት የምታገኙ ስለሚመስላችሁ እነሱን ትመረምራላችሁ፤ እነዚሁ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሠክሩ ናቸው። 40  ሆኖም ሕይወት እንድታገኙ ወደ እኔ መምጣት አትፈልጉም። 41  እኔ ከሰው ክብር መቀበል አልፈልግም፤ 42  ይሁንና እናንተ የአምላክ ፍቅር በውስጣችሁ እንደሌለ በሚገባ አውቃለሁ። 43  እኔ በአባቴ ስም መጣሁ፤ እናንተ ግን አልተቀበላችሁኝም። ሌላው ግን በራሱ ስም ቢመጣ ትቀበሉታላችሁ። 44  እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትሰጣጡና ከአንዱ አምላክ የሚገኘውን ክብር የማትፈልጉ ሆናችሁ ሳላችሁ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? 45  እኔ በአብ ፊት የምከሳችሁ አይምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ ሌላ አለ፤ እሱም ተስፋ የጣላችሁበት ሙሴ ነው። 46  ደግሞም ሙሴን ብታምኑት ኖሮ እኔንም ታምኑኝ ነበር፤ እሱ ስለ እኔ ጽፏልና። 47  ሆኖም እሱ የጻፈውን ካላመናችሁ እኔ የምናገረውን እንዴት ታምናላችሁ?”
[]
[]
[]
[]
12,324
6  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የገሊላን ማለትም የጥብርያዶስን ባሕር አቋርጦ ወደ ማዶ ተሻገረ። 2  ብዙ ሰዎችም ኢየሱስ የታመሙትን በመፈወስ የፈጸማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች ስላዩ ተከተሉት። 3  ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚያ ተቀመጠ። 4  በዚያን ጊዜ የአይሁዳውያን በዓል የሆነው ፋሲካ ተቃርቦ ነበር። 5  ኢየሱስም ቀና ብሎ ብዙ ሕዝብ ወደ እሱ እየመጣ እንዳለ ሲመለከት ፊልጶስን “እነዚህ ሰዎች የሚበሉት ዳቦ ከየት ብንገዛ ይሻላል?” አለው። 6  ሆኖም ይህን ያለው ሊፈትነው ብሎ እንጂ ለማድረግ ያሰበውን ያውቅ ነበር። 7  ፊልጶስም “እያንዳንዱ ሰው ትንሽ ትንሽ እንዲደርሰው ለማድረግ እንኳ የ200 ዲናር ዳቦ አይበቃም” ሲል መለሰለት። 8  ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነው የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ እንዲህ አለው፦ 9  “አምስት የገብስ ዳቦና ሁለት ትናንሽ ዓሣ የያዘ አንድ ትንሽ ልጅ እዚህ አለ። ይህ ግን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ እንዴት ይበቃል?” 10  ኢየሱስም “ሰዎቹ እንዲቀመጡ አድርጉ” አለ። በስፍራው ብዙ ሣር ስለነበር ሰዎቹ በዚያ ተቀመጡ፤ ወንዶቹም 5,000 ያህል ነበሩ። 11  ኢየሱስ ዳቦዎቹን ወስዶ ካመሰገነ በኋላ በዚያ ለተቀመጡት ሰዎች አከፋፈለ፤ ትናንሾቹን ዓሣዎችም ልክ እንደዚሁ አደለ፤ እነሱም የሚፈልጉትን ያህል ወሰዱ። 12  በልተው ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “ምንም እንዳይባክን የተረፈውን ቁርስራሽ ሁሉ ሰብስቡ” አላቸው። 13  ስለዚህ ከአምስቱ የገብስ ዳቦ ሰዎቹ በልተው የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ። 14  ሰዎቹም ኢየሱስ የፈጸመውን ተአምራዊ ምልክት ባዩ ጊዜ “ወደ ዓለም እንደሚመጣ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ በእርግጥ ይህ ነው” አሉ። 15  ከዚያም ኢየሱስ ሰዎቹ መጥተው ሊይዙትና ሊያነግሡት እንዳሰቡ ስላወቀ ብቻውን ዳግመኛ ወደ ተራራ ገለል አለ። 16  በመሸ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ወረዱ፤ 17  በጀልባም ተሳፍረው ባሕሩን በማቋረጥ ወደ ቅፍርናሆም ለመሻገር ተነሱ። በዚያን ሰዓት ጨልሞ የነበረ ቢሆንም ኢየሱስ ገና ወደ እነሱ አልመጣም ነበር። 18  በተጨማሪም ኃይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለነበረ ባሕሩ ይናወጥ ጀመር። 19  ይሁን እንጂ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ገደማ እንደቀዘፉ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቃረብ ተመልክተው ፈሩ። 20  እሱ ግን “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ!” አላቸው። 21  ከዚያም ወዲያው ጀልባዋ ላይ አሳፈሩት፤ ጀልባዋም ሊሄዱ ወዳሰቡበት ቦታ በፍጥነት ደረሰች። 22  በማግስቱም፣ በባሕሩ ማዶ የቀሩት ሰዎች ባሕሩ ላይ ከአንዲት ትንሽ ጀልባ በስተቀር ሌላ ጀልባ እንዳልነበረና ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን በጀልባዋ እንደሄዱ፣ ኢየሱስ ግን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንዳልተሳፈረ ተረዱ። 23  ሆኖም ከጥብርያዶስ የተነሱ ጀልባዎች፣ ሕዝቡ ጌታ የባረከውን ዳቦ ወደበሉበት አካባቢ መጡ። 24  ሕዝቡ ኢየሱስም ሆነ ደቀ መዛሙርቱ በዚያ አለመኖራቸውን ባወቁ ጊዜ በጀልባዎቻቸው ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። 25  ከባሕሩ ማዶ ባገኙትም ጊዜ “ረቢ፣ መቼ ወደዚህ መጣህ?” አሉት። 26  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የምትፈልጉኝ ተአምራዊ ምልክት ስላያችሁ ሳይሆን ዳቦ ስለበላችሁና ስለጠገባችሁ ነው። 27  ለሚጠፋ ምግብ ሳይሆን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ዘላቂ ለሆነውና የዘላለም ሕይወት ለሚያስገኘው ምግብ ሥሩ፤ ምክንያቱም አብ ይኸውም አምላክ ራሱ እሱን እንደተቀበለው አሳይቷል።” 28  እነሱም “ታዲያ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን ሥራ ለመሥራት ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት። 29  ኢየሱስም መልሶ “አምላክ የሚቀበለው ሥራማ እሱ በላከው ሰው ማመን ነው” አላቸው። 30  በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉት፦ “ታዲያ አይተን እንድናምንብህ ምን ተአምራዊ ምልክት ትፈጽማለህ? ምን ነገርስ ትሠራለህ? 31  ‘ይበሉ ዘንድ ከሰማይ ምግብ ሰጣቸው’ ተብሎ በተጻፈው መሠረት አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ።” 32  ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከሰማይ የወረደውን ምግብ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ አባቴ ግን እውነተኛውን ምግብ ከሰማይ ይሰጣችኋል። 33  ምክንያቱም አምላክ የሚሰጠው ምግብ ከሰማይ የሚወርድና ለዓለም ሕይወት የሚያስገኝ ነው።” 34  እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ይህን ምግብ ሁልጊዜ ስጠን” አሉት። 35  ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሕይወት የሚያስገኘው ምግብ እኔ ነኝ። ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ ፈጽሞ አይራብም፤ እንዲሁም በእኔ የሚያምን ሁሉ ፈጽሞ አይጠማም። 36  ነገር ግን “አይታችሁኝም እንኳ አታምኑም” ብያችሁ ነበር። 37  አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔ የሚመጣውንም ፈጽሞ አላባርረውም፤ 38  ከሰማይ የመጣሁት የራሴን ፈቃድ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ነውና። 39  የላከኝም ፈቃድ፣ ከሰጠኝ ሁሉ አንዱም እንኳ እንዳይጠፋብኝና በመጨረሻው ቀን ሁሉንም ከሞት እንዳስነሳቸው ነው። 40  ምክንያቱም የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያውቅና በእሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ።” 41  ከዚያም አይሁዳውያን “ከሰማይ የወረደው ምግብ እኔ ነኝ” በማለቱ በኢየሱስ ላይ ያጉረመርሙ ጀመር። 42  ደግሞም “ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለም? አባቱንና እናቱንስ እናውቃቸው የለም እንዴ? ታዲያ እንዴት ‘ከሰማይ ወረድኩ’ ይላል?” አሉ። 43  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ። 44  የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል ሰው የለም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሳዋለሁ። 45  ነቢያት በጻፏቸው ጽሑፎች ላይ ‘ሁሉም ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ’ ተብሎ ተጽፏል። ከአብ የሰማና የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል። 46  ከአምላክ ዘንድ ከመጣው በስተቀር አብን ያየ አንድም ሰው የለም፤ እሱ አብን አይቶታል። 47  እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው። 48  “ሕይወት የሚያስገኘው ምግብ እኔ ነኝ። 49  አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ፤ ይሁን እንጂ ሞቱ። 50  ከሰማይ የወረደውን ምግብ የሚበላ ሁሉ ግን አይሞትም። 51  ከሰማይ የወረደው ሕያው ምግብ እኔ ነኝ። ከዚህ ምግብ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል፤ ምግቡ ደግሞ ለዓለም ሕይወት ስል የምሰጠው ሥጋዬ ነው።” 52  አይሁዳውያንም “ይህ ሰው እንዴት ሥጋውን እንድንበላ ሊሰጠን ይችላል?” በማለት እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ጀመር። 53   በመሆኑም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁና ደሙን ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። 54  ሥጋዬን የሚበላና ደሜን የሚጠጣ ሁሉ የዘላለም ሕይወት አለው፤ በመጨረሻውም ቀን ከሞት አስነሳዋለሁ፤ 55  ሥጋዬ እውነተኛ ምግብ፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። 56  ሥጋዬን የሚበላና ደሜን የሚጠጣ ሁሉ ከእኔ ጋር አንድነት ይኖረዋል፤ እኔም ከእሱ ጋር አንድነት ይኖረኛል። 57   ሕያው የሆነው አብ እንደላከኝና እኔም ከእሱ የተነሳ በሕይወት እንደምኖር ሁሉ የእኔን ሥጋ የሚበላም ከእኔ የተነሳ በሕይወት ይኖራል። 58  ከሰማይ የወረደው ምግብ ይህ ነው። ይህም አባቶቻችሁ በበሉበት ጊዜ እንደነበረው አይደለም፤ እነሱ ቢበሉም እንኳ ሞተዋል። ይህን ምግብ የሚበላ ሁሉ ግን ለዘላለም ይኖራል።” 59  ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም በምኩራብ እያስተማረ ሳለ ነበር። 60  ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ይህን ሲሰሙ “ይህ የሚሰቀጥጥ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል?” አሉ። 61  ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ጉዳይ እያጉረመረሙ እንዳሉ ስለገባው እንዲህ አላቸው፦ “ይህ ያሰናክላችኋል? 62  ታዲያ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደነበረበት ሲወጣ ብታዩ ምን ልትሉ ነው? 63  ሕይወትን የሚሰጠው መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም። እኔ የነገርኳችሁ ቃል መንፈስም ሕይወትም ነው። 64  ነገር ግን ከእናንተ መካከል የማያምኑ አንዳንዶች አሉ።” ኢየሱስ ይህን ያለው የማያምኑት እነማን እንደሆኑና ማን አሳልፎ እንደሚሰጠው ከመጀመሪያው ያውቅ ስለነበረ ነው። 65  ከዚያም “አብ ካልፈቀደለት በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም ያልኳችሁ ለዚህ ነው” አላቸው። 66  ከዚህም የተነሳ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ትተውት ወደነበረው ነገር ተመለሱ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም እሱን መከተላቸውን አቆሙ። 67  በዚህ ጊዜ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን “እናንተም መሄድ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። 68  ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ። 69  አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ እንደሆንክ አምነናል፤ ደግሞም አውቀናል።” 70  ኢየሱስም መልሶ “አሥራ ሁለታችሁንም የመረጥኳችሁ እኔ አይደለሁም? ይሁንና ከመካከላችሁ አንዱ ስም አጥፊ ነው” አላቸው። 71  ይህን ሲል የአስቆሮቱ ስምዖን ልጅ ስለሆነው ስለ ይሁዳ መናገሩ ነበር፤ ምክንያቱም ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ቢሆንም አሳልፎ የሚሰጠው እሱ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,325
7  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በገሊላ መዘዋወሩን ቀጠለ፤ ምክንያቱም አይሁዳውያን ሊገድሉት ይፈልጉ ስለነበር በይሁዳ ምድር መዘዋወር አልፈለገም። 2  ይሁን እንጂ የአይሁዳውያን በዓል የሆነው የዳስ በዓል ተቃርቦ ነበር። 3  ስለዚህ ወንድሞቹ እንዲህ አሉት፦ “ደቀ መዛሙርትህም የምታከናውነውን ሥራ ማየት እንዲችሉ ከዚህ ተነስተህ ወደ ይሁዳ ሂድ። 4  በይፋ እንዲታወቅ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ሰው የለምና። እነዚህን ነገሮች የምትሠራ ከሆነ ራስህን ለዓለም ግለጥ።” 5  ወንድሞቹም ቢሆኑ አላመኑበትም ነበር። 6  ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ጊዜዬ ገና አልደረሰም፤ ለእናንተ ግን ማንኛውም ጊዜ ተስማሚ ነው። 7  ዓለም እናንተን የሚጠላበት ምንም ምክንያት የለውም፤ እኔ ግን ሥራው ክፉ እንደሆነ ስለምመሠክርበት ይጠላኛል። 8  እናንተ ወደ በዓሉ ሂዱ፤ እኔ ግን ገና ጊዜዬ ስላልደረሰ ወደ በዓሉ አልሄድም።” 9  ይህን ከነገራቸው በኋላ በገሊላ ቆየ። 10  ሆኖም ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ እሱም በግልጽ ሳይሆን በስውር ወደዚያው ሄደ። 11  በበዓሉም ላይ አይሁዳውያን “ያ ሰው የት አለ?” እያሉ ይፈልጉት ጀመር። 12  በሕዝቡም መካከል ስለ እሱ ብዙ ጉምጉምታ ነበር። አንዳንዶች “እሱ ጥሩ ሰው ነው” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “አይደለም። እሱ ሕዝቡን ያሳስታል” ይሉ ነበር። 13  እርግጥ አይሁዳውያንን ይፈሩ ስለነበረ ስለ እሱ በግልጽ የሚናገር ሰው አልነበረም። 14  በበዓሉም አጋማሽ ላይ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሄዶ ያስተምር ጀመር። 15  አይሁዳውያንም በጣም ተገርመው “ይህ ሰው ትምህርት ቤት ገብቶ ሳይማር ቅዱሳን መጻሕፍትን እንዴት እንዲህ ሊያውቅ ቻለ?” አሉ። 16  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “የማስተምረው ትምህርት የራሴ ሳይሆን ከላከኝ የመጣ ነው። 17  ማንም የእሱን ፈቃድ ማድረግ የሚፈልግ ከሆነ ይህ ትምህርት ከአምላክ የመጣ ይሁን ከራሴ ለይቶ ያውቃል። 18  ከራሱ አመንጭቶ የሚናገር ሁሉ ራሱ እንዲከበር ይፈልጋል፤ የላከው እንዲከበር የሚፈልግ ሁሉ ግን እሱ እውነተኛ ነው፤ በእሱም ዘንድ ዓመፅ የለም። 19  ሕጉን የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም? ሆኖም አንዳችሁም ሕጉን አትታዘዙም። እኔን ለመግደል የምትፈልጉት ለምንድን ነው?” 20  ሕዝቡም “አንተ ጋኔን አለብህ። ሊገድልህ የፈለገው ደግሞ ማን ነው?” ብለው መለሱለት። 21  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ነገር ስለሠራሁ ሁላችሁም ተደነቃችሁ። 22  እስቲ ይህን ልብ በሉ፦ ሙሴ የግርዘትን ሕግ ሰጣችሁ (ይህ ሕግ የተሰጠው ከአባቶች ነው እንጂ ከሙሴ አይደለም)፤ እናንተም በሰንበት ሰው ትገርዛላችሁ። 23  የሙሴ ሕግ እንዳይጣስ ሲባል በሰንበት ቀን ሰው የሚገረዝ ከሆነ እኔ በሰንበት አንድን ሰው መፈወሴ ይህን ያህል ሊያስቆጣችሁ ይገባል? 24  የሰውን ውጫዊ ገጽታ በማየት አትፍረዱ፤ ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ፍረዱ።” 25  በዚህ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መካከል አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፦ “ሊገድሉት የሚፈልጉት ሰው ይህ አይደለም እንዴ? 26  እሱ ግን ይኸው በአደባባይ እየተናገረ ነው፤ እነሱም ምንም አላሉትም። ገዢዎቹ ይህ ሰው በእርግጥ ክርስቶስ እንደሆነ አስበው ይሆን? 27  ሆኖም እኛ ይህ ሰው ከየት እንደመጣ እናውቃለን፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከየት እንደመጣ ማንም አያውቅም።” 28  ከዚያም ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እያስተማረ ሳለ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “እኔ ማን እንደሆንኩም ሆነ ከየት እንደመጣሁ ታውቃላችሁ። የመጣሁትም በራሴ ተነሳስቼ አይደለም፤ ሆኖም የላከኝ በእውን ያለ ነው፤ እናንተም አታውቁትም። 29  እኔ ግን የእሱ ተወካይ ሆኜ የመጣሁ ስለሆንኩ አውቀዋለሁ፤ የላከኝም እሱ ነው።” 30  በመሆኑም ሊይዙት ፈለጉ፤ ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም። 31  ይሁንና ከሕዝቡ መካከል ብዙዎች በእሱ አምነው “ክርስቶስስ በሚመጣበት ጊዜ ይህ ሰው ካደረገው የበለጠ ብዙ ተአምራዊ ምልክት ያደርጋል እንዴ?” ይሉ ነበር። 32  ፈሪሳውያን ሕዝቡ በጉምጉምታ ስለ እሱ የሚያወራውን ነገር ሰሙ፤ የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያኑም ይይዙት ዘንድ የቤተ መቅደስ ጠባቂዎችን ላኩ። 33  በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ከእናንተ ጋር የምቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ። 34  እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ ወደምሄድበትም ልትመጡ አትችሉም።” 35  በዚህ ጊዜ አይሁዳውያን እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ሰው ልናገኘው የማንችለው ወዴት ሊሄድ ቢያስብ ነው? በግሪካውያን መካከል ተበታትነው ወደሚገኙት አይሁዳውያን ሄዶ ግሪካውያንን ሊያስተምር አስቦ ይሆን እንዴ? 36  ‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ ወደምሄድበትም ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ይሆን?” 37  የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፦ “የተጠማ ካለ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። 38  በእኔ የሚያምን ሁሉ ቅዱስ መጽሐፉ እንደሚለው ‘ሕይወት የሚሰጥ የውኃ ጅረት ከውስጡ ይፈስሳል።’” 39  ይሁን እንጂ ይህን ሲል በእሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ መናገሩ ነበር፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ክብሩን ገና ስላልተጎናጸፈ መንፈስ አልተሰጠም ነበር። 40  ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶች ይህን ቃል ሲሰሙ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢዩ ነው” ይሉ ጀመር። 41  ሌሎችም “ይህ ክርስቶስ ነው” ይሉ ነበር። አንዳንዶች ግን እንዲህ አሉ፦ “ክርስቶስ የሚመጣው ከገሊላ ነው እንዴ? 42  ቅዱስ መጽሐፉ ክርስቶስ ከዳዊት ዘርና ዳዊት ከኖረበት መንደር ከቤተልሔም እንደሚመጣ ይናገር የለም?” 43  ስለዚህ እሱን በተመለከተ በሕዝቡ መካከል ክፍፍል ተፈጠረ። 44  ይሁንና አንዳንዶቹ ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አልያዘውም። 45  ከዚያም የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ወደ ካህናት አለቆቹና ወደ ፈሪሳውያኑ ተመልሰው ሄዱ፤ እነሱም ጠባቂዎቹን “ለምን ይዛችሁት አልመጣችሁም?” አሏቸው። 46  ጠባቂዎቹም “ማንም ሰው እንደዚህ ተናግሮ አያውቅም” ብለው መለሱ። 47  ፈሪሳውያኑ ግን እንዲህ አሏቸው፦ “እናንተም ተታለላችሁ? 48  ከገዢዎች ወይም ከፈሪሳውያን መካከል በእሱ ያመነ አለ? 49  ሕጉን የማያውቀው ይህ ሕዝብ ግን የተረገመ ነው።” 50  ቀደም ሲል ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረውና ከእነሱ አንዱ የሆነው ኒቆዲሞስ እንዲህ አላቸው፦ 51  “ሕጋችን በመጀመሪያ ግለሰቡ የሚለውን ሳይሰማና ምን እያደረገ እንዳለ ሳያውቅ ይፈርድበታል?” 52  እነሱም “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህ? ከገሊላ አንድም ነቢይ እንደማይነሳ ቅዱሳን መጻሕፍትን መርምረህ ተረዳ” አሉት።
[]
[]
[]
[]
12,326
8  12  ደግሞም ኢየሱስ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ። እኔን የሚከተል ሁሉ በምንም ዓይነት በጨለማ አይሄድም፤ ከዚህ ይልቅ የሕይወት ብርሃን ያገኛል።” 13  ፈሪሳውያንም “አንተ ስለ ራስህ ትመሠክራለህ፤ ምሥክርነትህም እውነት አይደለም” አሉት። 14  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ስለ ራሴ ብመሠክር እንኳ ከየት እንደመጣሁና ወዴት እንደምሄድ ስለማውቅ ምሥክርነቴ እውነት ነው። እናንተ ግን ከየት እንደመጣሁና ወዴት እንደምሄድ አታውቁም። 15  እናንተ በሥጋዊ አስተሳሰብ ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም ላይ አልፈርድም። 16  እኔ ብፈርድ እንኳ ፍርዴ እውነተኛ ነው፤ ምክንያቱም የምፈርደው ብቻዬን አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው። 17  በሕጋችሁም ላይ ‘የሁለት ሰዎች ምሥክርነት እውነት ነው’ ተብሎ ተጽፏል። 18  ስለ ራሴ የምመሠክር አንዱ እኔ ነኝ፤ ደግሞም የላከኝ አብ ስለ እኔ ይመሠክራል።” 19  በዚህ ጊዜ “አባትህ የት ነው?” አሉት። ኢየሱስም “እናንተ እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁም። እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር” ሲል መለሰላቸው። 20  ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቤተ መቅደስ፣ ግምጃ ቤቱ አካባቢ ሆኖ ሲያስተምር ነበር። ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም። 21  ኢየሱስም እንደገና “እኔ እሄዳለሁ፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ይሁንና ኃጢአተኛ እንደሆናችሁ ትሞታላችሁ። እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም” አላቸው። 22  አይሁዳውያኑም “‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ የሚለው ራሱን ሊገድል አስቦ ይሆን እንዴ?” አሉ። 23  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ከምድር ናችሁ፤ እኔ ከላይ ነኝ። እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም። 24  በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኳችሁ ለዚህ ነው። እኔ እሱ እንደሆንኩ ካላመናችሁ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ።” 25  እነሱም “ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ድሮውንም እኔ ከእናንተ ጋር የምነጋገረው እንዲያው በከንቱ ነው። 26  ስለ እናንተ ብዙ የምናገረው ነገር አለኝ፤ ፍርድ የምሰጥበትም ብዙ ነገር አለኝ። በመሠረቱ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእሱ የሰማሁትን ያንኑ ነገር ለዓለም እየተናገርኩ ነው።” 27  እነሱ ግን ስለ አብ እየነገራቸው እንደሆነ አልተረዱም ነበር። 28  ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰውን ልጅ ከሰቀላችሁት በኋላ እኔ እሱ እንደሆንኩና በራሴ ተነሳስቼ አንዳች ነገር እንደማላደርግ ከዚህ ይልቅ እነዚህን ነገሮች የምናገረው ልክ አብ እንዳስተማረኝ መሆኑን ታውቃላችሁ። 29  እኔን የላከኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ሁልጊዜ እሱን ደስ የሚያሰኘውን ስለማደርግ ብቻዬን አልተወኝም።” 30  ይህን በተናገረ ጊዜ ብዙዎች በእሱ አመኑ። 31  ከዚያም ኢየሱስ በእሱ ላመኑት አይሁዳውያን እንዲህ አለ፦ “ቃሌን ጠብቃችሁ ብትኖሩ በእርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ 32  እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል።” 33  እነሱም መልሰው “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ለማንም ባሪያዎች ሆነን አናውቅም። ታዲያ አንተ ‘ነፃ ትወጣላችሁ’ እንዴት ትለናለህ?” አሉት። 34  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው። 35  ደግሞም ባሪያ በጌታው ቤት ለዘለቄታው አይኖርም፤ ልጅ ከሆነ ግን ሁልጊዜ ይኖራል። 36  ስለዚህ ወልድ ነፃ ካወጣችሁ፣ በእርግጥ ነፃ ትሆናላችሁ። 37  የአብርሃም ዘር እንደሆናችሁ አውቃለሁ። ሆኖም ቃሌ በእናንተ ውስጥ ሥር ስለማይሰድ ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። 38  እኔ ከአባቴ ጋር ሳለሁ ያየሁትን ነገር እናገራለሁ፤ እናንተ ግን ከአባታችሁ የሰማችሁትን ነገር ታደርጋላችሁ።” 39  እነሱም መልሰው “አባታችን አብርሃም ነው” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የአብርሃም ልጆች ብትሆኑ ኖሮ አብርሃም የሠራውን ትሠሩ ነበር። 40  እናንተ ግን ከአምላክ የሰማሁትን እውነት የነገርኳችሁን እኔን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። አብርሃም እንዲህ አላደረገም። 41  እናንተ እየሠራችሁ ያላችሁት የአባታችሁን ሥራ ነው።” እነሱም “እኛስ በዝሙት የተወለድን አይደለንም፤ እኛ አንድ አባት አለን፤ እሱም አምላክ ነው” አሉት። 42  ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አምላክ አባታችሁ ቢሆን ኖሮ እኔ ወደዚህ የመጣሁት ከእሱ ዘንድ ስለሆነ በወደዳችሁኝ ነበር። እሱ ላከኝ እንጂ እኔ በራሴ ተነሳስቼ አልመጣሁም። 43  እየተናገርኩት ያለው ነገር የማይገባችሁ ለምንድን ነው? ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። 44  እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት መፈጸም ትሻላችሁ። እሱ በራሱ መንገድ መሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ በእሱ ዘንድ እውነት ስለሌለ በእውነት ውስጥ ጸንቶ አልቆመም። ውሸታምና የውሸት አባት ስለሆነ ውሸት ሲናገር ከራሱ አመንጭቶ ይናገራል። 45  በሌላ በኩል ግን እኔ እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም። 46  ከመካከላችሁ እኔን ኃጢአት ሠርተሃል ብሎ በማስረጃ ሊወነጅለኝ የሚችል ማን ነው? የምናገረው እውነት ከሆነ ደግሞ የማታምኑኝ ለምንድን ነው? 47  ከአምላክ የሆነ የአምላክን ቃል ይሰማል። እናንተ ግን ከአምላክ ስላልሆናችሁ አትሰሙም።” 48  አይሁዳውያኑም መልሰው “‘አንተ ሳምራዊ ነህ፤ ደግሞም ጋኔን አድሮብሃል’ ማለታችን ትክክል አይደለም?” አሉት። 49  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ አባቴን አከብራለሁ እንጂ ጋኔን የለብኝም፤ እናንተ ግን ታቃልሉኛላችሁ። 50  እኔ ለራሴ ክብር እየፈለግኩ አይደለም፤ ይሁንና ይህን የሚፈልግና የሚፈርድ አለ። 51  እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ቃሌን የሚጠብቅ ከሆነ ፈጽሞ ሞትን አያይም።” 52  አይሁዳውያኑም እንዲህ አሉት፦ “አሁን በእርግጥ ጋኔን እንዳለብህ ተረዳን። አብርሃም ሞቷል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ማንም ሰው ቃሌን የሚጠብቅ ከሆነ ፈጽሞ ሞትን አይቀምስም’ ትላለህ። 53   አንተ ከሞተው ከአባታችን ከአብርሃም ትበልጣለህ እንዴ? ነቢያትም ሞተዋል። ለመሆኑ አንተ ማን ነኝ ልትል ነው?” 54  ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ራሴን የማከብር ከሆነ ክብሬ ከንቱ ነው። እኔን የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን ነው የምትሉት አባቴ ነው። 55  ሆኖም እናንተ አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን አውቀዋለሁ። አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ውሸታም መሆኔ ነው። ይሁንና እኔ አውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። 56  አባታችሁ አብርሃም ቀኔን እንደሚያይ ተስፋ በማድረግ እጅግ ተደሰተ፤ አይቶትም ደስ ተሰኘ።” 57   አይሁዳውያኑም “አንተ ገና 50 ዓመት እንኳ ያልሞላህ፣ አብርሃምን አይቼዋለሁ ትላለህ?” አሉት። 58  ኢየሱስም “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ” አላቸው። 59  በዚህ ጊዜ ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወረና ከቤተ መቅደሱ ወጥቶ ሄደ።
[]
[]
[]
[]
12,327
9  በመንገድ እያለፈ ሳለም ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነ አንድ ሰው አየ። 2  ደቀ መዛሙርቱም “ረቢ፣ ይህ ሰው ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደው ማን በሠራው ኃጢአት ነው? በራሱ ኃጢአት ነው ወይስ በወላጆቹ?” ሲሉ ጠየቁት። 3  ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እሱም ሆነ ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም፤ ሆኖም ይህ የሆነው የአምላክ ሥራ በእሱ እንዲገለጥ ነው። 4  ቀን ሳለ፣ የላከኝን የእሱን ሥራ መሥራት አለብን፤ ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት ይመጣል። 5  በዓለም እስካለሁ ድረስ የዓለም ብርሃን ነኝ።” 6  ይህን ካለ በኋላ መሬት ላይ እንትፍ በማለት በምራቁ ጭቃ ለወሰ፤ ጭቃውንም በሰውየው ዓይኖች ላይ ቀባ፤ 7  ሰውየውንም “ሄደህ በሰሊሆም ገንዳ ታጠብ” አለው (ሰሊሆም ማለት “ተላከ” ማለት ነው)። ሰውየውም ሄዶ ታጠበ፤ ዓይኑም በርቶለት መጣ። 8  ከዚያም ጎረቤቶቹና ቀደም ሲል ሲለምን ያዩት የነበሩ ሰዎች “ይህ ሰው ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለም እንዴ?” አሉ። 9  አንዳንዶች “አዎ፣ እሱ ነው” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “አይ፣ እሱን ይመስላል እንጂ እሱ አይደለም” ይሉ ነበር። ሰውየው ግን “እኔው ነኝ” ይል ነበር። 10  በመሆኑም “ታዲያ ዓይኖችህ እንዴት ተከፈቱ?” ሲሉ ጠየቁት። 11  እሱም “ኢየሱስ የተባለው ሰው ጭቃ ለውሶ ዓይኖቼን ቀባና ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ። እኔም ሄጄ ታጠብኩ፤ ዓይኔም በራልኝ” ሲል መለሰ። 12  በዚህ ጊዜ “ሰውየው የት አለ?” አሉት። እሱም “እኔ አላውቅም” አለ። 13  እነሱም ዓይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት። 14  እንደ አጋጣሚ ሆኖ ኢየሱስ ጭቃውን የለወሰበትና የሰውየውን ዓይኖች ያበራበት ቀን ሰንበት ነበር። 15  በዚህ ጊዜ ፈሪሳውያኑም እንዴት ማየት እንደቻለ ጠየቁት። እሱም “ሰውየው ዓይኖቼን ጭቃ ቀባ፤ እኔም ታጠብኩ፤ ከዚያም ማየት ቻልኩ” አላቸው። 16  ከፈሪሳውያንም መካከል አንዳንዶቹ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከአምላክ የመጣ አይደለም” አሉ። ሌሎቹ ደግሞ “ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እንዲህ ያሉ ተአምራዊ ምልክቶችን እንዴት ሊፈጽም ይችላል?” አሉ። በመሆኑም በመካከላቸው ክፍፍል ተፈጠረ። 17  በድጋሚም ዓይነ ስውሩን “ይህ ሰው ዓይኖችህን ስላበራልህ ስለ እሱ ምን ትላለህ?” አሉት። ሰውየውም “እሱ ነቢይ ነው” አለ። 18  ይሁን እንጂ አይሁዳውያኑ ማየት የቻለውን ሰው ወላጆች እስከጠሩበት ጊዜ ድረስ ሰውየው ዓይነ ስውር እንደነበረና በኋላ ዓይኑ እንደበራለት አላመኑም ነበር። 19  ወላጆቹንም “ዓይነ ስውር ሆኖ ተወልዷል የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነው? ታዲያ አሁን እንዴት ሊያይ ቻለ?” ሲሉ ጠየቋቸው። 20  ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ይህ ልጃችን እንደሆነና ዓይነ ስውር ሆኖ እንደተወለደ እናውቃለን። 21  አሁን ግን እንዴት ሊያይ እንደቻለ የምናውቀው ነገር የለም፤ ዓይኖቹን ማን እንዳበራለትም አናውቅም። እሱን ጠይቁት፤ ሙሉ ሰው ነው። ስለ ራሱ መናገር ያለበት እሱ ነው።” 22  ወላጆቹ ይህን ያሉት አይሁዳውያኑን ስለፈሩ ነው፤ ምክንያቱም አይሁዳውያን ኢየሱስን፣ ‘ክርስቶስ ነው’ ብሎ የተቀበለ ማንኛውም ሰው ከምኩራብ እንዲባረር አስቀድመው ወስነው ነበር። 23  ወላጆቹ “ሙሉ ሰው ነው። እሱን ጠይቁት” ያሉት ለዚህ ነበር። 24  ስለዚህ ዓይነ ስውር የነበረውን ሰው ለሁለተኛ ጊዜ ጠርተው “እውነቱን በመናገር ለአምላክ ክብር ስጥ፤ እኛ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እናውቃለን” አሉት። 25  እሱም መልሶ “ኃጢአተኛ ይሁን አይሁን የማውቀው ነገር የለም። እኔ የማውቀው ዓይነ ስውር እንደነበርኩና አሁን ግን ማየት እንደቻልኩ ነው” አለ። 26  በዚህ ጊዜ “ምንድን ነው ያደረገልህ? ዓይንህን ያበራልህስ እንዴት ነው?” አሉት። 27  እሱም “ነገርኳችሁ እኮ፤ እናንተ ግን አትሰሙም። እንደገና መስማት የፈለጋችሁት ለምንድን ነው? እናንተም የእሱ ደቀ መዝሙር መሆን ፈለጋችሁ እንዴ?” ሲል መለሰላቸው። 28  እነሱም ሰውየውን በንቀት እንዲህ አሉት፦ “የዚያ ሰው ደቀ መዝሙር አንተ ነህ፤ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን። 29  አምላክ ሙሴን እንዳነጋገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደመጣ አናውቅም።” 30  ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ከየት እንደመጣ አለማወቃችሁ በጣም የሚያስገርም ነገር ነው፤ ያም ሆነ ይህ ዓይኖቼን አብርቶልኛል። 31  አምላክ ኃጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤ ፈሪሃ አምላክ ያለውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን ሁሉ ግን ይሰማዋል። 32  ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደን ሰው ዓይኖች የከፈተ አለ ሲባል ከጥንት ዘመን ጀምሮ ተሰምቶ አይታወቅም። 33  ይህ ሰው ከአምላክ ባይሆን ኖሮ ምንም ነገር ሊያደርግ አይችልም ነበር።” 34  እነሱም መልሰው “አንተ ሁለመናህ በኃጢአት ተበክሎ የተወለድክ! እኛን ልታስተምር ትፈልጋለህ?” አሉት። ከዚያም አባረሩት! 35  ኢየሱስም ሰውየውን እንዳባረሩት ሰማ፤ ባገኘውም ጊዜ “በሰው ልጅ ላይ እምነት አለህ?” አለው። 36  ሰውየውም “ጌታዬ፣ አምንበት ዘንድ እሱ ማን ነው?” ሲል መለሰ። 37  ኢየሱስም “አይተኸዋል፤ ደግሞም እያነጋገረህ ያለው እሱ ነው” አለው። 38  እሱም “ጌታ ሆይ፣ በእሱ አምናለሁ” አለ። ከዚያም ሰገደለት። 39  ኢየሱስም “የማያዩ ማየት እንዲችሉ፣ የሚያዩም እንዲታወሩ፣ ለዚህ ፍርድ ወደዚህ ዓለም መጥቻለሁ” አለ። 40  በዚያ የነበሩ ፈሪሳውያንም ይህን ሰምተው “እናንተም ዕውሮች ናችሁ እያልከን ነው?” አሉት። 41  ኢየሱስም “ዕውሮች ብትሆኑማ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባችሁ ነበር። አሁን ግን ‘እናያለን’ ትላላችሁ። ስለዚህ ኃጢአታችሁ እንዳለ ይኖራል” አላቸው።
[]
[]
[]
[]
12,328
1  የአምላክና የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የሆነው ያዕቆብ፣ በየቦታው ለተበተኑት ለ12ቱ ነገዶች፦ ሰላምታ ይድረሳችሁ! 2  ወንድሞቼ ሆይ፣ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፤ 3  ይህን ስታደርጉ ተፈትኖ የተረጋገጠው እምነታችሁ ጽናት እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ። 4  ይሁንና በሁሉም ረገድ ምንም የማይጎድላችሁ ፍጹማንና እንከን የለሽ እንድትሆኑ ጽናት ሥራውን ሙሉ በሙሉ ይፈጽም። 5  እንግዲህ ከእናንተ መካከል ጥበብ የጎደለው ሰው ካለ አምላክን ያለማሰለስ ይለምን፤ አምላክ ማንንም ሳይነቅፍ ለሁሉም በልግስና ይሰጣልና፤ ይህም ሰው ይሰጠዋል። 6  ሆኖም ምንም ሳይጠራጠር በእምነት መለመኑን ይቀጥል፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ እንደሚገፋና እንደሚናወጥ የባሕር ማዕበል ነውና። 7  እንዲያውም እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከይሖዋ አንዳች ነገር አገኛለሁ ብሎ መጠበቅ የለበትም፤ 8  ይህ ሰው በሁለት ሐሳብ የሚዋልልና በመንገዱ ሁሉ የሚወላውል ነው። 9  ይሁንና ዝቅ ያለው ወንድም ከፍ በመደረጉ ደስ ይበለው፤ 10  እንዲሁም ባለጸጋ የሆነው ዝቅ በመደረጉ ደስ ይበለው፤ ምክንያቱም ባለጸጋ ሰው እንደ ሜዳ አበባ ይረግፋል። 11  ፀሐይ ወጥታ በኃይለኛ ሙቀቷ ተክሉን ታጠወልጋለች፤ አበባውም ይረግፋል፤ ውበቱም ይጠፋል፤ ባለጸጋ ሰውም ልክ እንደዚሁ በዕለት ተዕለት ተግባሩ ሲዋትት ከስሞ ይጠፋል። 12  ፈተናን በጽናት ተቋቁሞ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ሰው በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት በሚያገኝበት ጊዜ፣ ይሖዋ እሱን ለሚወዱት ቃል የገባውን የሕይወት አክሊል ይቀበላል። 13  ማንም ሰው ፈተና ሲደርስበት “አምላክ እየፈተነኝ ነው” አይበል። አምላክ በክፉ ነገር ሊፈተን አይችልምና፤ እሱ ራሱም ማንንም በክፉ ነገር አይፈትንም። 14  ሆኖም እያንዳንዱ ሰው በራሱ ምኞት ሲማረክና ሲታለል ይፈተናል። 15  ከዚያም ምኞት ከፀነሰች በኋላ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአት ሲፈጸም ደግሞ ሞት ያስከትላል። 16  የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ አትታለሉ። 17  መልካም ስጦታ ሁሉና ፍጹም ገጸ በረከት ሁሉ ከላይ ነው፤ ይህ የሚወርደው ከሰማይ ብርሃናት አባት ሲሆን እሱ ደግሞ ቦታውን እንደሚቀያይር ጥላ አይለዋወጥም። 18  ፈቃዱ ስለሆነም ከፍጥረታቱ መካከል እኛ እንደ በኩራት እንድንሆን በእውነት ቃል አማካኝነት ወለደን። 19  የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን እወቁ፦ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየና ለቁጣ የዘገየ መሆን አለበት፤ 20  የሰው ቁጣ የአምላክ ጽድቅ እንዲፈጸም አያደርግምና። 21  ስለዚህ ጸያፍ የሆነውን ነገር ሁሉና ክፋትን ሁሉ አስወግዳችሁ እናንተን ሊያድን የሚችለውን በውስጣችሁ የሚተከለውን ቃል በገርነት ተቀበሉ። 22  ሆኖም ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ የውሸት ምክንያት እያቀረባችሁ ራሳችሁን በማታለል ሰሚዎች ብቻ አትሁኑ። 23  ማንም ሰው ቃሉን የሚሰማ እንጂ የማያደርገው ከሆነ የገዛ ፊቱን በመስተዋት እያየ ካለ ሰው ጋር ይመሳሰላል። 24  ይህ ሰው ራሱን ካየ በኋላ ይሄዳል፤ ወዲያውም ምን እንደሚመስል ይረሳል። 25  ሆኖም ነፃ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ በትኩረት የሚመለከትና በዚያ የሚጸና ሰው ሰምቶ የሚረሳ ሳይሆን በሥራ ላይ የሚያውል ሰው ነው፤ በሚያደርገውም ነገር ደስተኛ ይሆናል። 26  አንድ ሰው አምላክን እያመለከ እንዳለ ቢያስብም እንኳ አንደበቱን የማይገታ ከሆነ ይህ ሰው የገዛ ልቡን ያታልላል፤ አምልኮውም ከንቱ ነው። 27  በአምላካችንና በአባታችን ዓይን ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ ‘ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና መበለቶችን በመከራቸው መርዳት እንዲሁም ከዓለም እድፍ ራስን መጠበቅ’ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,329
2  ወንድሞቼ ሆይ፣ በአንድ በኩል ክብር በተጎናጸፈው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ ሆናችሁ በሌላ በኩል ደግሞ አድልዎ ታደርጋላችሁ? 2  በጣቶቹ ላይ የወርቅ ቀለበቶች ያደረገና ያማረ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ስብሰባችሁ ቢመጣና ያደፈ ልብስ የለበሰ ድሃ ሰውም እንደዚሁ ወደ ስብሰባው ቢገባ 3  ያማረ ልብስ ለለበሰው ሰው አክብሮት በማሳየት “እዚህ የተሻለው ቦታ ላይ ተቀመጥ” ድሃውን ደግሞ “አንተ እዚያ ቁም” ወይም “እዚህ ከእግሬ ማሳረፊያ በታች ተቀመጥ” ትሉታላችሁ? 4  እንዲህ የምትሉ ከሆነ በመካከላችሁ የመደብ ልዩነት እንዲኖር ማድረጋችሁ አይደለም? ደግሞስ ክፉ ፍርድ የምትፈርዱ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለም? 5  የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ስሙ። አምላክ በእምነት ባለጸጋ እንዲሆኑና እሱን ለሚወዱ ቃል የገባውን መንግሥት እንዲወርሱ ከዓለም አመለካከት አንጻር ድሆች የሆኑትን አልመረጠም? 6  እናንተ ግን ድሃውን ሰው አዋረዳችሁ። እናንተን የሚጨቁኗችሁና ጎትተው ፍርድ ቤት የሚያቀርቧችሁ ሀብታሞች አይደሉም? 7  እናንተ የተጠራችሁበትን መልካም ስም የሚሳደቡት እነሱ አይደሉም? 8  እንግዲያው በቅዱስ መጽሐፉ መሠረት “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለውን ንጉሣዊ ሕግ ተግባራዊ የምታደርጉ ከሆነ መልካም እያደረጋችሁ ነው። 9  ማዳላታችሁን የማትተዉ ከሆነ ግን ኃጢአት እየሠራችሁ ነው፤ ሕጉም ሕግ ተላላፊዎች ናችሁ ብሎ ይፈርድባችኋል። 10  አንድ ሰው ሕጉን ሁሉ የሚጠብቅ ሆኖ ሳለ አንዱን ትእዛዝ ሳይጠብቅ ቢቀር ሁሉንም እንደጣሰ ይቆጠራል። 11  “አታመንዝር” ያለው እሱ “አትግደል” የሚል ትእዛዝም ሰጥቷልና። እንግዲህ ምንዝር ባትፈጽምም እንኳ ከገደልክ ሕግ ተላላፊ ሆነሃል። 12  ነፃ በሆኑ ግለሰቦች ሕግ የሚዳኙ ሰዎች በሚናገሩበት መንገድ መናገራችሁንና እነሱ እንደሚያደርጉት ማድረጋችሁን ቀጥሉ። 13  ምሕረት የማያደርግ ሰው ያለምሕረት ይፈረድበታልና። ምሕረት በፍርድ ላይ ድል ይቀዳጃል። 14  ወንድሞቼ ሆይ፣ አንድ ሰው እምነት አለኝ ቢል ነገር ግን እምነቱ በሥራ የተደገፈ ባይሆን ምን ጥቅም ይኖረዋል? እምነቱ ሊያድነው ይችላል? 15  አንድ ወንድም ወይም አንዲት እህት የሚለብሱት ቢያጡና ለዕለት የሚያስፈልጋቸውን በቂ ምግብ ባያገኙ 16  ሆኖም ከመካከላችሁ አንዱ “በሰላም ሂዱ፤ ይሙቃችሁ፤ ጥገቡም” ቢላቸው ለሰውነታቸው የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግን ባይሰጣቸው ምን ይጠቅማቸዋል? 17  ስለዚህ በሥራ ያልተደገፈ እምነትም በራሱ የሞተ ነው። 18  ይሁን እንጂ አንድ ሰው እንዲህ ይላል፦ “አንተ እምነት አለህ፤ እኔ ደግሞ ሥራ አለኝ። እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔ ደግሞ እምነቴን በሥራ አሳይሃለሁ።” 19  አንድ አምላክ እንዳለ ታምናለህ አይደል? ማመንህ መልካም ነው። ይሁንና አጋንንትም ያምናሉ፤ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ። 20  አንተ ከንቱ ሰው፣ እምነት ያለሥራ እንደማይጠቅም ማረጋገጥ ትፈልጋለህ? 21  አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ ካቀረበ በኋላ የጸደቀው በሥራ አይደለም? 22  እምነቱ ከሥራው ጋር አብሮ ይሠራ እንደነበረና ሥራው እምነቱን ፍጹም እንዳደረገው ትገነዘባለህ፤ 23  ደግሞም “አብርሃም በይሖዋ አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፤ እሱም የይሖዋ ወዳጅ ለመባል በቃ። 24  እንግዲህ ሰው የሚጸድቀው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም ጭምር እንደሆነ ትገነዘባላችሁ። 25  ዝሙት አዳሪዋ ረዓብም መልእክተኞቹን በጥሩ ሁኔታ ተቀብላ ካስተናገደቻቸውና በሌላ መንገድ ከላከቻቸው በኋላ በሥራ አልጸደቀችም? 26  በእርግጥም አካል ያለመንፈስ የሞተ እንደሆነ ሁሉ እምነትም ያለሥራ የሞተ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,330
3  ወንድሞቼ ሆይ፣ ከእናንተ መካከል ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ፤ ምክንያቱም እኛ የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁ። 2  ሁላችንም ብዙ ጊዜ እንሰናከላለንና። በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር ይህ ሰው መላ ሰውነቱንም መቆጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው። 3  ፈረሶች እንዲታዘዙልን አፋቸው ውስጥ ልጓም ካስገባን መላ ሰውነታቸውንም መምራት እንችላለን። 4  መርከቦችንም ተመልከቱ፦ በጣም ትልቅና በኃይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም የመርከቡ ነጂ በትንሽ መሪ ወደሚፈልገው አቅጣጫ ሁሉ ይመራቸዋል። 5  ልክ እንደዚሁም ምላስ ትንሽ የአካል ክፍል ሆና ሳለ ጉራዋን ትነዛለች። በጣም ሰፊ የሆነን ጫካ በእሳት ለማያያዝ ትንሽ እሳት ብቻ ይበቃል! 6  ምላስም እሳት ናት። ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የክፋትን ዓለም ትወክላለች፤ መላ ሰውነትን ታረክሳለችና፤ እንዲሁም መላውን የሕይወት ጎዳና ታቃጥላለች፤ እሷም በገሃነም ትቃጠላለች። 7  ማንኛውም ዓይነት የዱር እንስሳ፣ ወፍ፣ በምድር ላይ የሚሳብ ፍጥረትና በባሕር ውስጥ የሚኖር ፍጥረት በሰዎች ሊገራ ይችላል፤ ደግሞም ተገርቷል። 8  ምላስን ግን ሊገራ የሚችል አንድም ሰው የለም። ምላስ ገዳይ መርዝ የሞላባት፣ ለመቆጣጠር የምታስቸግር ጎጂ ነገር ናት። 9  በምላሳችን አባት የሆነውን ይሖዋን እናወድሳለን፤ ይሁንና በዚህችው ምላሳችን “በአምላክ አምሳል” የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። 10  ከአንድ አፍ በረከትና እርግማን ይወጣሉ። ወንድሞቼ፣ ይህ መሆኑ ተገቢ አይደለም። 11  አንድ ምንጭ ከዚያው ጉድጓድ ጣፋጭና መራራ ውኃ ያፈልቃል? 12  ወንድሞቼ፣ የበለስ ዛፍ ወይራን ወይም ደግሞ የወይን ተክል በለስን ሊያፈራ ይችላል? ከጨዋማ ውኃም ጣፋጭ ውኃ ሊገኝ አይችልም። 13  ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ሰው ማን ነው? ሥራውን የሚያከናውነው ከጥበብ በመነጨ ገርነት መሆኑን በመልካም ምግባሩ ያሳይ። 14  ሆኖም በልባችሁ ውስጥ መራራ ቅናትና ጠበኝነት ካለ አትኩራሩ፤ እንዲሁም በእውነት ላይ አትዋሹ። 15  ይህ ከሰማይ የሚመጣ ጥበብ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ምድራዊ፣ እንስሳዊና አጋንንታዊ ነው። 16  ቅናትና ጠበኝነት ባለበት ሁሉ ብጥብጥና መጥፎ ነገሮችም ይኖራሉ። 17  ከሰማይ የሆነው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላማዊ፣ ምክንያታዊ፣ ለመታዘዝ ዝግጁ የሆነ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬዎች የሞሉበት እንዲሁም አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው። 18  ከዚህም በላይ የጽድቅ ፍሬ ሰላም ፈጣሪ ለሆኑ ሰዎች ሰላማዊ በሆኑ ሁኔታዎች ይዘራል።
[]
[]
[]
[]
12,331
4  በእናንተ መካከል ያለው ጦርነትና ጠብ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ከሚዋጉት ሥጋዊ ፍላጎቶቻችሁ የመነጨ አይደለም? 2  ትመኛላችሁ ሆኖም አታገኙም። ትገድላላችሁ እንዲሁም ትጎመጃላችሁ፤ ይሁንና ማግኘት አትችሉም። ትጣላላችሁ እንዲሁም ትዋጋላችሁ። ስለማትጠይቁም አታገኙም። 3  በምትጠይቁበት ጊዜም አታገኙም፤ ምክንያቱም የምትጠይቁት ለተሳሳተ ዓላማ ይኸውም ሥጋዊ ፍላጎታችሁን ለማርካት ነው። 4  አመንዝሮች ሆይ፣ ከዓለም ጋር መወዳጀት ከአምላክ ጋር ጠላትነት መፍጠር እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ራሱን የአምላክ ጠላት ያደርጋል። 5  ወይስ ቅዱስ መጽሐፉ “በውስጣችን ያደረው መንፈስ በቅናት ሁልጊዜ ይመኛል” ያለው ያለምክንያት ይመስላችኋል? 6  ይሁን እንጂ አምላክ የሚሰጠው ጸጋ እንዲህ ካለው መንፈስ የላቀ ነው። በመሆኑም ቅዱስ መጽሐፉ “አምላክ ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላል። 7  ስለዚህ ራሳችሁን ለአምላክ አስገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙት፤ እሱም ከእናንተ ይሸሻል። 8  ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤ እናንተ ወላዋዮች ልባችሁን አጥሩ። 9  ተጨነቁ፣ እዘኑ፣ አልቅሱ። ሳቃችሁ ወደ ሐዘን፣ ደስታችሁም ወደ ተስፋ መቁረጥ ይለወጥ። 10  በይሖዋ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል። 11  ወንድሞች፣ አንዳችሁ ሌላውን መንቀፋችሁን ተዉ። ወንድሙን የሚነቅፍ ወይም በወንድሙ ላይ የሚፈርድ ሁሉ ሕግን ይነቅፋል እንዲሁም በሕግ ላይ ይፈርዳል። በሕግ ላይ የምትፈርድ ከሆነ ደግሞ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም። 12  ሕግ የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ብቻ ነው፤ እሱ ማዳንም ሆነ ማጥፋት ይችላል። ታዲያ በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? 13  እንግዲህ እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ከተማ እንሄዳለን፤ እዚያም ዓመት እንቆያለን፤ እንነግዳለን እንዲሁም እናተርፋለን” የምትሉ ስሙ፤ 14  ሕይወታችሁ ነገ ምን እንደሚሆን እንኳ አታውቁም። ለጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁና። 15  ከዚህ ይልቅ “ይሖዋ ከፈቀደ በሕይወት እንኖራለን፤ ደግሞም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ማለት ይገባችኋል። 16  አሁን ግን እናንተ ከልክ በላይ ጉራ በመንዛት ትኩራራላችሁ። እንዲህ ያለው ጉራ ሁሉ ክፉ ነው። 17  ስለዚህ አንድ ሰው ትክክል የሆነውን ነገር እንዴት ማድረግ እንዳለበት እያወቀ ሳያደርገው ቢቀር ኃጢአት ይሆንበታል።
[]
[]
[]
[]
12,332
5  እናንተ ሀብታሞች እንግዲህ ስሙ፤ እየመጣባችሁ ባለው መከራ አልቅሱ እንዲሁም ዋይ ዋይ በሉ። 2  ሀብታችሁ በስብሷል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል። 3  ወርቃችሁና ብራችሁ ሙሉ በሙሉ ዝጓል፤ ዝገቱም በእናንተ ላይ ይመሠክራል፤ ሥጋችሁንም ይበላል። ያከማቻችሁት ነገር በመጨረሻዎቹ ቀናት እንደ እሳት ይሆናል። 4  እነሆ፣ በእርሻችሁ ላይ ያለውን ሰብል ለሰበሰቡት ሠራተኞች ሳትከፍሏቸው የቀራችሁት ደሞዝ ይጮኻል፤ አጫጆቹም ለእርዳታ የሚያሰሙት ጥሪ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ ይሖዋ ጆሮ ደርሷል። 5  በምድር ላይ በቅንጦት ኖራችኋል፤ የራሳችሁንም ፍላጎት ለማርካት ትጥሩ ነበር። በእርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል። 6  ጻድቁን ኮነናችሁት፤ ደግሞም ገደላችሁት። እሱ እየተቃወማችሁ አይደለም? 7  እንግዲህ ወንድሞች፣ ጌታ እስከሚገኝበት ጊዜ ድረስ በትዕግሥት ጠብቁ። እነሆ፣ ገበሬ የመጀመሪያውና የኋለኛው ዝናብ እስኪመጣ ድረስ በመታገሥ የምድርን መልካም ፍሬ ይጠባበቃል። 8  እናንተም በትዕግሥት ጠብቁ፤ ጌታ የሚገኝበት ጊዜ ስለተቃረበ ልባችሁን አጽኑ። 9  ወንድሞች፣ እንዳይፈረድባችሁ አንዳችሁ በሌላው ላይ አታጉረምርሙ። እነሆ፣ ፈራጁ ደጃፍ ላይ ቆሟል። 10  ወንድሞች፣ በይሖዋ ስም የተናገሩትን ነቢያት መከራ በመቀበልና ትዕግሥት በማሳየት ረገድ አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው። 11  እነሆ፣ የጸኑትን ደስተኞች እንደሆኑ አድርገን እንቆጥራቸዋለን። ስለ ኢዮብ ጽናት ሰምታችኋል፤ በውጤቱም ይሖዋ ያደረገለትን አይታችኋል፤ በዚህም ይሖዋ እጅግ አፍቃሪና መሐሪ እንደሆነ ተመልክታችኋል። 12  ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ፣ በሰማይም ሆነ በምድር ወይም በሌላ መሐላ መማላችሁን ተዉ። ከዚህ ይልቅ “አዎ” ካላችሁ አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ካላችሁ አይደለም ይሁን፤ አለዚያ ለፍርድ ትዳረጋላችሁ። 13  ከእናንተ መካከል መከራ እየደረሰበት ያለ ሰው አለ? መጸለዩን ይቀጥል። ደስ የተሰኘ አለ? የምስጋና መዝሙር ይዘምር። 14  ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የጉባኤ ሽማግሌዎችን ወደ እሱ ይጥራ፤ እነሱም በይሖዋ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። 15  በእምነት የቀረበ ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሰዋል፤ ይሖዋም ያስነሳዋል። በተጨማሪም ኃጢአት ሠርቶ ከሆነ ይቅር ይባላል። 16  ስለዚህ ፈውስ ማግኘት እንድትችሉ አንዳችሁ ለሌላው ኃጢአታችሁን በግልጽ ተናዘዙ፤ እንዲሁም አንዳችሁ ለሌላው ጸልዩ። ጻድቅ ሰው የሚያቀርበው ምልጃ ታላቅ ኃይል አለው። 17  ኤልያስ እንደ እኛው ዓይነት ስሜት ያለው ሰው ነበር፤ ያም ሆኖ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ በጸለየ ጊዜ በምድሩ ላይ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር ዝናብ አልዘነበም። 18  ከዚያም እንደገና ጸለየ፤ ሰማዩም ዝናብ ሰጠ፤ ምድሩም ፍሬ አፈራ። 19  ወንድሞቼ፣ ከእናንተ መካከል አንድ ሰው ከእውነት መንገድ ስቶ ቢወጣና ሌላ ሰው ቢመልሰው፣ 20  ኃጢአተኛን ከስህተት ጎዳናው የሚመልስ ማንኛውም ሰው ኃጢአተኛውን ከሞት እንደሚያድንና ብዙ ኃጢአትን እንደሚሸፍን እወቁ።
[]
[]
[]
[]
12,333
1  ቴዎፍሎስ ሆይ፣ ኢየሱስ ስላደረገውና ስላስተማረው ነገር ሁሉ በመጀመሪያው መጽሐፍ ላይ ጽፌልሃለሁ፤ 2  ታሪኩም አምላክ እስከወሰደው ቀን ድረስ ያለውን ያካትታል። ለመረጣቸው ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት መመሪያዎች ከሰጣቸው በኋላ አረገ። 3  መከራ ከተቀበለ በኋላ ሕያው መሆኑን በብዙ አሳማኝ ማስረጃዎች አሳያቸው። እነሱም ለ40 ቀናት ያዩት ሲሆን እሱም ስለ አምላክ መንግሥት ይነግራቸው ነበር። 4  ከእነሱ ጋር ተሰብስቦ ሳለ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ከኢየሩሳሌም አትውጡ፤ ከዚህ ይልቅ አብ ቃል የገባውንና እኔም ስለዚሁ ጉዳይ ስናገር የሰማችሁትን ቃል ፍጻሜ ተጠባበቁ፤ 5  ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፤ እናንተ ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።” 6  እንደገና ተሰብስበው ሳሉ “ጌታ ሆይ፣ ለእስራኤል መንግሥትን መልሰህ የምታቋቁመው በዚህ ጊዜ ነው?” ሲሉ ጠየቁት። 7  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጊዜያትንና ወቅቶችን የመወሰን ሥልጣን ያለው አብ ብቻ ስለሆነ እናንተ ይህን ማወቅ አያስፈልጋችሁም። 8  ሆኖም መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኃይል ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በመላው ይሁዳና በሰማርያ እንዲሁም እስከ ምድር ዳር ድረስ ምሥክሮቼ ትሆናላችሁ።” 9  ይህን ከተናገረ በኋላም እያዩት ወደ ላይ ወጣ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰወረው። 10  እሱ ወደ ላይ እየወጣ ሳለ ትኩር ብለው ወደ ሰማይ ሲመለከቱ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ፤ 11  እንዲህም አሏቸው፦ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ የቆማችሁት ለምንድን ነው? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የተወሰደው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁት በዚሁ ሁኔታ ይመጣል።” 12  ከዚያም ደብረ ዘይት ከተባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ይህ ተራራ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን ርቀቱ የሰንበት መንገድ ያህል ብቻ ነበር። 13  እዚያ በደረሱ ጊዜ ያርፉበት ወደነበረው ደርብ ወጡ። እነሱም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብና እንድርያስ፣ ፊልጶስና ቶማስ፣ በርቶሎሜዎስና ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ቀናተኛው ስምዖን እንዲሁም የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ። 14  እነዚህ ሁሉ ከአንዳንድ ሴቶችና ከኢየሱስ እናት ከማርያም እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋር በአንድ ልብ ተግተው ይጸልዩ ነበር። 15  በዚያው ሰሞን 120 የሚያህሉ ሰዎች አንድ ላይ ተሰብስበው ሳለ ጴጥሮስ በወንድሞች መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፦ 16  “ወንድሞች፣ ኢየሱስን የያዙትን ሰዎች እየመራ ስላመጣው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ በዳዊት በኩል በትንቢት የተናገረው የቅዱስ መጽሐፉ ቃል መፈጸሙ የግድ ነበር። 17  ምክንያቱም እሱ ከእኛ እንደ አንዱ ተቆጥሮ የነበረ ከመሆኑም በላይ በዚህ አገልግሎት የመካፈል አጋጣሚ አግኝቶ ነበር። 18  (ይኸው ሰው ለዓመፅ ሥራው በተከፈለው ደሞዝ መሬት ገዛ፤ በአናቱም ወድቆ ሰውነቱ ፈነዳ፤ ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ። 19  ይህም በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ በመሆኑም መሬቱ በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፤ ትርጉሙም “የደም መሬት” ማለት ነው።) 20  በመዝሙር መጽሐፍ ላይ ‘መኖሪያው ወና ይሁን፤ በውስጡም ማንም ሰው አይኑርበት’ እንዲሁም ‘የበላይ ተመልካችነት ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፏልና። 21  ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል ሆኖ ሥራውን ያከናውን በነበረበት ጊዜ ሁሉ ከእኛ ጋር ከነበሩት ወንዶች መካከል በአንዱ እሱን መተካት ያስፈልጋል፤ 22  የሚተካው ሰው ኢየሱስ በዮሐንስ ከተጠመቀበት ጊዜ አንስቶ ከእኛ እስከተወሰደበት ጊዜ ድረስ አብሮን የነበረ መሆን ይኖርበታል። በተጨማሪም ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምሥክር መሆን ያስፈልገዋል።” 23  ስለዚህ ሁለት ሰዎችን ዕጩ አድርገው አቀረቡ፤ እነሱም በርስያን ተብሎ የሚጠራው ዮሴፍ (ኢዮስጦስ ተብሎም ይጠራል) እና ማትያስ ነበሩ። 24  ከዚያም እንዲህ ብለው ጸለዩ፦ “የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቀው ይሖዋ ሆይ፣ ከእነዚህ ሁለት ሰዎች መካከል የመረጥከውን አመልክተን፤ 25  ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ለመሄድ ሲል የተወውን ይህን የአገልግሎትና የሐዋርያነት ቦታ የሚወስደውን ሰው ግለጥልን።” 26  ከዚያም በሁለቱ ሰዎች ላይ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣውም ለማትያስ ወጣና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቆጠረ።
[]
[]
[]
[]
12,334
10  በቂሳርያ “የጣሊያን ክፍለ ጦር” ተብሎ በሚጠራ ሠራዊት ውስጥ ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ የጦር መኮንን ነበር። 2  እሱም ከመላው ቤተሰቡ ጋር ለአምላክ ያደረና ፈሪሃ አምላክ የነበረው ሰው ሲሆን ለሰዎች ምጽዋት የሚሰጥና ዘወትር ወደ አምላክ የሚማልድ ሰው ነበር። 3  ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ አንድ የአምላክ መልአክ ወደ እሱ ሲመጣ በራእይ በግልጽ አየ፤ መልአኩም “ቆርኔሌዎስ!” አለው። 4  ቆርኔሌዎስም በድንጋጤ ትኩር ብሎ እያየው “ጌታ ሆይ፣ ምንድን ነው?” በማለት ጠየቀው። እሱም እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህና ምጽዋትህ በአምላክ ፊት መታሰቢያ እንዲሆን አርጓል። 5  ስለዚህ አሁን ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን አስጠራው። 6  ይህ ሰው፣ ቤቱ በባሕሩ አጠገብ በሚገኘው በቆዳ ፋቂው በስምዖን ቤት በእንግድነት አርፏል።” 7  ያነጋገረው መልአክ ተለይቶት እንደሄደ ከአገልጋዮቹ ሁለቱን እንዲሁም እሱን በቅርብ ከሚያገለግሉት ወታደሮች መካከል ለአምላክ ያደረ አንድ ወታደር ጠራ፤ 8  የሆነውንም ነገር ሁሉ ከነገራቸው በኋላ ወደ ኢዮጴ ላካቸው። 9  በማግስቱም የተላኩት ሰዎች ተጉዘው ወደ ከተማዋ ሲቃረቡ ጴጥሮስ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ገደማ ሊጸልይ ወደ ሰገነት ወጣ። 10  ይሁን እንጂ በጣም ከመራቡ የተነሳ መብላት ፈለገ። ምግብ እየተዘጋጀ ሳለም ሰመመን ውስጥ ገባ፤ 11  ሰማይም ተከፍቶ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራቱም ጫፍ ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድ አየ፤ 12  በላዩም የተለያዩ በምድር ላይ የሚኖሩ አራት እግር ያላቸው እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታት እንዲሁም የሰማይ ወፎች ነበሩ። 13  ከዚያም አንድ ድምፅ “ጴጥሮስ፣ ተነሳና አርደህ ብላ!” አለው። 14  ጴጥሮስ ግን “ጌታ ሆይ፣ በጭራሽ፤ ምክንያቱም እኔ ንጹሕ ያልሆነና የረከሰ ነገር በልቼ አላውቅም” አለ። 15  ያም ድምፅ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ “አምላክ ንጹሕ ያደረገውን ነገር ርኩስ ነው ማለትህን ተው” አለው። 16  ይህም ለሦስተኛ ጊዜ ተደገመ፤ ወዲያውኑም ጨርቅ የሚመስለው ነገር ወደ ሰማይ ተወሰደ። 17  ጴጥሮስ ‘የራእዩ ትርጉም ምን ይሆን’ በማለት በጣም ግራ ተጋብቶ እያለ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች የስምዖንን ቤት አጠያይቀው መጡና የውጭው በር ላይ ቆሙ። 18  ከዚያም ተጣርተው ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራው ስምዖን በዚያ በእንግድነት አርፎ እንደሆነ ጠየቁ። 19  ጴጥሮስ ያየውን ራእይ በሐሳቡ እያወጣና እያወረደ ሳለ መንፈስ እንዲህ አለው፦ “እነሆ፣ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል። 20  ስለዚህ ተነስተህ ወደ ታች ውረድ፤ የላክኋቸው እኔ ስለሆንኩ ምንም ሳትጠራጠር አብረሃቸው ሂድ።” 21  ጴጥሮስም ሰዎቹ ወዳሉበት ወርዶ “የምትፈልጉት ሰው እኔ ነኝ። ወደዚህ የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው። 22  እነሱም እንዲህ አሉ፦ “በአይሁዳውያን ሁሉ የተመሠከረለት ቆርኔሌዎስ የተባለ ጻድቅና አምላክን የሚፈራ አንድ የጦር መኮንን፣ ወደ አንተ መልእክተኞች ልኮ ወደ ቤቱ እንዲያስመጣህና የምትለውን ነገር እንዲሰማ አንድ ቅዱስ መልአክ መለኮታዊ መመሪያ ሰጥቶታል።” 23  እሱም ወደ ቤት አስገብቶ አስተናገዳቸው። በማግስቱም ተነስቶ ከእነሱ ጋር ሄደ፤ በኢዮጴ ያሉ አንዳንድ ወንድሞችም አብረውት ሄዱ። 24  በሚቀጥለው ቀንም ወደ ቂሳርያ ገባ። ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን ሰብስቦ እየጠበቃቸው ነበር። 25  ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተቀበለውና እግሩ ላይ ወድቆ ሰገደለት። 26  ጴጥሮስ ግን “ተነስ፣ እኔም እንደ አንተው ሰው ነኝ” ብሎ አስነሳው። 27  ከእሱ ጋር እየተነጋገረ ወደ ውስጥ ሲገባም ብዙ ሰዎች ተሰብስበው አገኘ። 28  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ አይሁዳዊ ከሌላ ዘር ጋር ይወዳጅ ወይም ይቀራረብ ዘንድ ሕጉ እንደማይፈቅድ በሚገባ ታውቃላችሁ፤ ሆኖም አምላክ ማንንም ሰው ንጹሕ ያልሆነ ወይም ርኩስ ማለት እንደማይገባኝ ገልጦልኛል። 29  በመሆኑም በተጠራሁ ጊዜ ምንም ሳላንገራግር መጣሁ። ስለዚህ ለምን እንዳስጠራችሁኝ ማወቅ እፈልጋለሁ።” 30  ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለ፦ “ከአራት ቀን በፊት በዚሁ ሰዓት ይኸውም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በቤቴ ሆኜ እየጸለይኩ ሳለ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው ድንገት ፊቴ ቆሞ 31  እንዲህ አለኝ፦ ‘ቆርኔሌዎስ፣ ጸሎትህ ተሰምቶልሃል፤ ምጽዋትህም በአምላክ ፊት ታስቦልሃል። 32  ስለዚህ ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን አስጠራው። ይህ ሰው፣ ቤቱ በባሕሩ አጠገብ በሚገኘው በቆዳ ፋቂው በስምዖን ቤት በእንግድነት አርፏል።’ 33  እኔም ወዲያውኑ ሰዎች ላክሁብህ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። ስለዚህ አሁን እኛ ይሖዋ እንድትናገር ያዘዘህን ነገር ሁሉ ለመስማት ይኸው ሁላችንም በአምላክ ፊት ተገኝተናል።” 34  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፦ “እነሆ፣ አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤ 35  ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው። 36  አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለእስራኤል ልጆች የሰላም ምሥራች ለማወጅ ቃሉን ላከላቸው፤ ይህም ምሥራች ኢየሱስ የሁሉ ጌታ እንደሆነ የሚገልጽ ነው። 37  ዮሐንስ ስለ ጥምቀት ከሰበከ በኋላ ከገሊላ አንስቶ በመላው ይሁዳ ይወራ ስለነበረው ጉዳይ ታውቃላችሁ፤ 38  የተወራውም ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ቀባው፤ ደግሞም ኃይል ሰጠው፤ ኢየሱስም አምላክ ከእሱ ጋር ስለነበር መልካም ነገር እያደረገና በዲያብሎስ ቁጥጥር ሥር የወደቁትን እየፈወሰ በዚያ አገር ሁሉ ተዘዋወረ። 39  እሱ በአይሁዳውያን አገርም ሆነ በኢየሩሳሌም ላደረጋቸው ነገሮች ሁሉ እኛ ምሥክሮች ነን፤ እነሱ ግን በእንጨት ላይ ሰቅለው ገደሉት። 40  አምላክ እሱን በሦስተኛው ቀን አስነሳው፤ ከዚያም ለሰዎች እንዲገለጥ አደረገው፤ 41  የተገለጠው ግን ለሁሉም ሰው ሳይሆን አምላክ አስቀድሞ ለመረጣቸው ምሥክሮች ይኸውም ከሞት ከተነሳ በኋላ አብረነው ለበላንና ለጠጣን ለእኛ ነው። 42  በተጨማሪም አምላክ እሱን በሕያዋንና በሙታን ላይ ፈራጅ አድርጎ እንደሾመው ለሰዎች እንድንሰብክና በተሟላ ሁኔታ እንድንመሠክር አዘዘን። 43  በእሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአት ይቅርታ እንደሚያገኝ ነቢያት ሁሉ ስለ እሱ ይመሠክራሉ።” 44  ጴጥሮስ ስለዚህ ጉዳይ ገና እየተናገረ ሳለ ቃሉን እየሰሙ በነበሩት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። 45  ከጴጥሮስ ጋር የመጡት የተገረዙ አማኞች የመንፈስ ቅዱስ ነፃ ስጦታ ከአሕዛብ ወገን በሆኑ ሰዎችም ላይ በመፍሰሱ ተገረሙ። 46  ምክንያቱም በባዕድ ቋንቋዎች ሲናገሩና አምላክን ሲያወድሱ ይሰሟቸው ነበር። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ አለ፦ 47  “እንደ እኛው መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉትን እነዚህን ሰዎች በውኃ እንዳይጠመቁ ሊከለክላቸው የሚችል አለ?” 48  ይህን ካለ በኋላ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ አዘዛቸው። ከዚያም የተወሰነ ቀን አብሯቸው እንዲቆይ ለመኑት።
[]
[]
[]
[]
12,335
11  በይሁዳ የነበሩት ሐዋርያትና ወንድሞች፣ አሕዛብም የአምላክን ቃል እንደተቀበሉ ሰሙ። 2  ስለዚህ ጴጥሮስ ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ግርዘትን የሚደግፉ ሰዎች ይተቹት ጀመር፤ 3  “ወዳልተገረዙ ሰዎች ቤት ሄደህ ከእነሱ ጋር በልተሃል” አሉት። 4  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ጉዳዩን በዝርዝር አብራራላቸው፦ 5  “በኢዮጴ ከተማ እየጸለይኩ ሳለ ሰመመን ውስጥ ሆኜ ራእይ አየሁ፤ አንድ ትልቅ ጨርቅ የሚመስል ነገር በአራቱም ጫፍ ተይዞ ከሰማይ ወረደና ወደ እኔ መጣ። 6  ይህን ነገር ትኩር ብዬ ስመለከት አራት እግር ያላቸው የምድር እንስሳት፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች አየሁ። 7  በተጨማሪም አንድ ድምፅ ‘ጴጥሮስ፣ ተነሳና አርደህ ብላ!’ ሲለኝ ሰማሁ። 8  እኔ ግን ‘ጌታ ሆይ፣ በጭራሽ፤ ምክንያቱም ንጹሕ ያልሆነ ወይም የረከሰ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም’ አልኩ። 9  ለሁለተኛ ጊዜ ከሰማይ የመጣው ድምፅ ‘አምላክ ንጹሕ ያደረገውን ነገር ርኩስ ነው ማለትህን ተው’ ሲል መለሰልኝ። 10  ይህም ለሦስተኛ ጊዜ ተደገመ፤ ከዚያም ሁሉም ነገር እንደገና ወደ ሰማይ ተወሰደ። 11  ልክ በዚያው ሰዓት ደግሞ ከቂሳርያ ወደ እኔ የተላኩ ሦስት ሰዎች እኛ ወደነበርንበት ቤት ደረሱ። 12  በዚህ ጊዜ መንፈስ፣ ምንም ሳልጠራጠር አብሬያቸው እንድሄድ ነገረኝ። እነዚህ ስድስት ወንድሞችም አብረውኝ ሄዱ፤ ወደ ሰውየውም ቤት ገባን። 13  “እሱም በቤቱ ውስጥ መልአክ ቆሞ እንዳየና እንዲህ እንዳለው ነገረን፦ ‘ወደ ኢዮጴ ሰዎች ልከህ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራውን ስምዖንን አስጠራ፤ 14  እሱም አንተና መላው ቤተሰብህ መዳን ልታገኙ የምትችሉበትን ነገር ሁሉ ይነግርሃል።’ 15  እኔም መናገር ስጀምር መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደወረደው ሁሉ በእነሱም ላይ ወረደ። 16  በዚህ ጊዜ፣ ‘ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ፤ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ’ እያለ ጌታ ይናገር የነበረውን ቃል አስታወስኩ። 17  እንግዲህ አምላክ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላመንነው ለእኛ የሰጠውን ያንኑ ነፃ ስጦታ ለእነሱም ከሰጠ፣ ታዲያ አምላክን መከልከል የምችል እኔ ማን ነኝ?” 18  እነሱም ይህን በሰሙ ጊዜ መቃወማቸውን ተዉ፤ ደግሞም “እንዲህ ከሆነማ አምላክ አሕዛብም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ንስሐ የሚገቡበት አጋጣሚ ሰጥቷቸዋል ማለት ነው” እያሉ አምላክን አከበሩ። 19  ከእስጢፋኖስ ሞት በኋላ በተቀሰቀሰው ስደት የተነሳ የተበተኑት ደቀ መዛሙርት እስከ ፊንቄ፣ ቆጵሮስና አንጾኪያ ድረስ ሄዱ፤ ቃሉን ይናገሩ የነበረው ግን ለአይሁዳውያን ብቻ ነበር። 20  ይሁን እንጂ ከእነሱ መካከል የቆጵሮስና የቀሬና ሰዎች የሆኑ አንዳንዶች ወደ አንጾኪያ መጥተው ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎችን በማነጋገር የጌታ ኢየሱስን ምሥራች ይሰብኩላቸው ጀመር። 21  የይሖዋም እጅ ከእነሱ ጋር ነበር፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም አማኝ በመሆን ጌታን መከተል ጀመሩ። 22  በኢየሩሳሌም የሚገኘው ጉባኤ ስለ እነሱ የሚገልጸው ወሬ ደረሰው፤ በዚህ ጊዜ በርናባስን ወደ አንጾኪያ ላኩት። 23  እሱም እዚያ ደርሶ አምላክ ለደቀ መዛሙርቱ ያሳየውን ጸጋ ባስተዋለ ጊዜ በጣም ተደሰተ፤ ሁሉም በጽኑ ልብ ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲቀጥሉም አበረታታቸው፤ 24  በርናባስ መንፈስ ቅዱስ የሞላበትና ጠንካራ እምነት ያለው ጥሩ ሰው ነበር። ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም በጌታ አመኑ። 25  በመሆኑም ሳኦልን ፈልጎ ለማግኘት ወደ ጠርሴስ ሄደ። 26  ካገኘውም በኋላ ወደ አንጾኪያ አመጣው። ከዚያም አንድ ዓመት ሙሉ ከእነሱ ጋር በጉባኤ አብረው እየተሰበሰቡ ብዙ ሕዝብ አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርቱም በመለኮታዊ አመራር ለመጀመሪያ ጊዜ ‘ክርስቲያኖች’ ተብለው የተጠሩት በአንጾኪያ ነበር። 27  በዚያን ጊዜ ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ። 28  ከእነሱም መካከል አጋቦስ የተባለው ተነስቶ በምድሪቱ ሁሉ ታላቅ ረሃብ እንደሚከሰት መንፈስ አነሳስቶት ትንቢት ተናገረ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ዘመን ተፈጸመ። 29  ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ እያንዳንዳቸው አቅማቸው በፈቀደ መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩ ወንድሞች እርዳታ ለመላክ ወሰኑ፤ 30  እርዳታውንም በበርናባስና በሳኦል እጅ ለሽማግሌዎቹ ላኩ።
[]
[]
[]
[]
12,336
12  በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሄሮድስ በአንዳንድ የጉባኤው አባላት ላይ ስደት ማድረስ ጀመረ። 2  የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። 3  ይህ ድርጊቱ አይሁዳውያንን እንዳስደሰተ ባየ ጊዜ ጴጥሮስን ደግሞ በቁጥጥር ሥር አዋለው። (ይህም የሆነው በቂጣ በዓል ሰሞን ነበር።) 4  ከያዘውና እስር ቤት ካስገባው በኋላ በአራት ፈረቃ፣ አራት አራት ሆነው እንዲጠብቁት ለተመደቡ ወታደሮች አስረከበው፤ ይህን ያደረገው ከፋሲካ በኋላ ሕዝቡ ፊት ሊያቀርበው አስቦ ነው። 5  ስለዚህ ጴጥሮስ እስር ቤት እንዲቆይ ተደረገ፤ ሆኖም ጉባኤው ስለ እሱ ወደ አምላክ አጥብቆ ይጸልይ ነበር። 6  ሄሮድስ ጴጥሮስን ሕዝቡ ፊት ሊያቀርበው ካሰበበት ቀን በፊት በነበረው ሌሊት፣ ጴጥሮስ በሁለት ወታደሮች መካከል በሁለት ሰንሰለቶች ታስሮ ተኝቶ ነበር፤ በር ላይ ያሉ ጠባቂዎችም እስር ቤቱን እየጠበቁ ነበር። 7  ይሁንና የይሖዋ መልአክ ድንገት መጥቶ ቆመ፤ በክፍሉም ውስጥ ብርሃን በራ። ጴጥሮስን ጎኑን መታ አድርጎ ከእንቅልፉ ቀሰቀሰውና “ቶሎ ብለህ ተነሳ!” አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጆቹ ላይ ወደቁ። 8  መልአኩም “በል ልብስህን ልበስ፤ ጫማህንም አድርግ” አለው። እሱም እንደተባለው አደረገ። ከዚያም “መደረቢያህን ልበስና ተከተለኝ” አለው። 9  እሱም ወጥቶ ይከተለው ጀመር፤ ይሁንና መልአኩ እያደረገ ያለው ነገር በእውን እየተከናወነ ያለ አልመሰለውም። እንዲያውም ራእይ የሚያይ መስሎት ነበር። 10  የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ አልፈው ከእስር ቤቱ ወደ ከተማዋ ወደሚያስወጣው የብረት መዝጊያ ደረሱ፤ መዝጊያውም በራሱ ተከፈተላቸው። ከወጡ በኋላ በአንድ ጎዳና አብረው ተጓዙ፤ ወዲያውም መልአኩ ተለይቶት ሄደ። 11  ጴጥሮስም የሆነውን ነገር ሲረዳ “ይሖዋ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና አይሁዳውያን በእኔ ላይ ይደርሳል ብለው ካሰቡት ነገር ሁሉ እንደታደገኝ አሁን በእርግጥ አወቅኩ” አለ። 12  ይህን ከተገነዘበ በኋላ ማርቆስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት ሄደ፤ በዚያም በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ይጸልዩ ነበር። 13  የውጭውን በር ሲያንኳኳ ሮዳ የተባለች አንዲት አገልጋይ በሩን ለመክፈት መጣች። 14  የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑን ባወቀች ጊዜ በጣም ከመደሰቷ የተነሳ በሩን ሳትከፍት ሮጣ ወደ ውስጥ በመግባት ጴጥሮስ በር ላይ መቆሙን ተናገረች። 15  እነሱም “አብደሻል እንዴ!” አሏት። እሷ ግን ያንኑ አስረግጣ መናገሯን ቀጠለች። እነሱም “ከሆነም የእሱ መልአክ ይሆናል” አሉ። 16  ጴጥሮስ ግን እዚያው ቆሞ ማንኳኳቱን ቀጠለ። በሩን ከከፈቱም በኋላ ሲያዩት በጣም ተገረሙ። 17  እሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ምልክት ከሰጣቸው በኋላ ይሖዋ ከእስር ቤት እንዴት እንዳወጣው በዝርዝር ነገራቸው፤ ከዚያም “ይህን ነገር ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሯቸው” አላቸው። ይህን ካለም በኋላ ወጥቶ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ። 18  በነጋም ጊዜ ወታደሮቹ ጴጥሮስ የት እንደደረሰ ግራ ስለተጋቡ በመካከላቸው ከፍተኛ ትርምስ ተፈጠረ። 19  ሄሮድስም ፈልጎ አፈላልጎ ባጣው ጊዜ ጠባቂዎቹን ከመረመረ በኋላ እርምጃ እንዲወሰድባቸው አዘዘ፤ ከዚያም ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ወርዶ በዚያ የተወሰነ ጊዜ ተቀመጠ። 20  ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቆጥቶ ነበር። እነሱም በአንድ ልብ ሆነው ወደ እሱ በመምጣት የንጉሡ ባለሟል የሆነውን ብላስጦስን ካግባቡ በኋላ ንጉሡን እርቅ ጠየቁ፤ ይህን ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለነበረ ነው። 21  አንድ ልዩ ዝግጅት በተደረገበት ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ለሕዝቡ ንግግር መስጠት ጀመረ። 22  የተሰበሰበውም ሕዝብ “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ የሰው አይደለም!” እያለ ይጮኽ ጀመር። 23  በዚህ ጊዜ፣ ለአምላክ ክብር ባለመስጠቱ ወዲያውኑ የይሖዋ መልአክ ቀሰፈው፤ በትል ተበልቶም ሞተ። 24  የይሖዋ ቃል ግን እየተስፋፋ ሄደ፤ ብዙ ሰዎችም አማኞች ሆኑ። 25  በርናባስና ሳኦልም በኢየሩሳሌም እርዳታ ከሰጡ በኋላ ተመለሱ፤ ማርቆስ ተብሎ የሚጠራውን ዮሐንስንም ይዘውት መጡ።
[]
[]
[]
[]
12,337
13  በአንጾኪያ ባለው ጉባኤ ውስጥ ነቢያትና አስተማሪዎች ነበሩ፤ እነሱም፦ በርናባስ፣ ኒጌር ማለትም ጥቁር ተብሎ የሚጠራው ሲምዖን፣ የቀሬናው ሉክዮስ፣ የአውራጃ ገዢ ከሆነው ከሄሮድስ ጋር የተማረው ምናሔና ሳኦል ናቸው። 2  እነዚህ ይሖዋን እያገለገሉና እየጾሙ ሳሉ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳኦልን አንድ ሥራ እንዲሠሩ ስለመረጥኳቸው ለዩልኝ” አለ። 3  እነሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ ከዚያም አሰናበቷቸው። 4  ሰዎቹም በመንፈስ ቅዱስ ተልከው ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዙ። 5  ስልማና በደረሱ ጊዜም የአምላክን ቃል በአይሁዳውያን ምኩራቦች ማወጅ ጀመሩ። ዮሐንስም እንደ አገልጋይ ሆኖ ይረዳቸው ነበር። 6  ደሴቲቱን ከዳር እስከ ዳር አዳርሰው እስከ ጳፎስ ተጓዙ፤ በዚህ ጊዜ በርያሱስ የተባለ ጠንቋይና ሐሰተኛ ነቢይ የነበረ አንድ አይሁዳዊ አገኙ። 7  እሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አስተዋይ የሮም አገረ ገዢ ጋር ነበር። ይህ አገረ ገዢ የአምላክን ቃል ለመስማት ስለጓጓ በርናባስንና ሳኦልን ጠራቸው። 8  ይሁን እንጂ ጠንቋዩ ኤልማስ አገረ ገዢው ይህን እምነት እንዳይቀበል ለማከላከል ፈልጎ ይቃወማቸው ጀመር። (ኤልማስ የተባለው ስም ትርጉም ጠንቋይ ማለት ነው።) 9  በዚህ ጊዜ፣ ጳውሎስ ተብሎ የሚጠራው ሳኦል በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትኩር ብሎ ተመለከተው፤ 10  ከዚያም እንዲህ አለው፦ “አንተ ተንኮልና ክፋት ሁሉ የሞላብህ፣ የዲያብሎስ ልጅ፣ የጽድቅም ሁሉ ጠላት! ቀና የሆነውን የይሖዋን መንገድ ማጣመምህን አትተውም? 11  እነሆ፣ የይሖዋ እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዓይነ ስውር ትሆናለህ፤ ለተወሰነ ጊዜም የፀሐይ ብርሃን አታይም።” ወዲያውኑም ጭጋግና ጨለማ ዓይኑን ጋረደው፤ እጁን ይዞ የሚመራው ሰው ለማግኘትም ዙሪያውን መፈለግ ጀመረ። 12  አገረ ገዢውም ስለ ይሖዋ በተማረው ነገር ተደንቆ ስለነበር ይህን ባየ ጊዜ አማኝ ሆነ። 13  ጳውሎስና ባልደረቦቹ ከጳፎስ ተነስተው በባሕር ላይ በመጓዝ ጵንፍልያ ውስጥ ወዳለችው ወደ ጴርጌ ሄዱ። ዮሐንስ ግን ከእነሱ ተለይቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። 14  እነሱ ግን ጉዟቸውን በመቀጠል ከጴርጌ ተነስተው በጵስድያ ወደምትገኘው ወደ አንጾኪያ መጡ። በሰንበት ቀንም ወደ ምኩራብ ገብተው ተቀመጡ። 15  የሕጉና የነቢያት መጻሕፍት በሕዝቡ ፊት ከተነበበ በኋላ የምኩራቡ አለቆች “ወንድሞች ሆይ፣ ሕዝቡን የሚያበረታታ የምትናገሩት ቃል ካላችሁ ተናገሩ” የሚል መልእክት ላኩባቸው። 16  ስለዚህ ጳውሎስ ተነስቶ በእጁ ምልክት በመስጠት እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሰዎችም ሆናችሁ አምላክን የምትፈሩ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ስሙ። 17  የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መረጠ፤ በግብፅ ምድር ባዕዳን ሆነው ይኖሩ በነበረበት ጊዜም ሕዝቡን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ በኃያል ክንዱም ከዚያ አወጣቸው። 18  ለ40 ዓመት ያህልም በምድረ በዳ ታገሣቸው። 19  በከነአን ምድር የነበሩትን ሰባት ብሔራት ካጠፋ በኋላ ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሰጣቸው። 20  ይህ ሁሉ የሆነው በ450 ዓመት ያህል ጊዜ ውስጥ ነው። “ይህ ከሆነ በኋላ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ዘመን ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው። 21  ከዚያ በኋላ ግን ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ጠየቁ፤ አምላክም ከቢንያም ነገድ የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለ40 ዓመት አነገሠላቸው። 22  እሱን ከሻረው በኋላ ‘እንደ ልቤ የሆነውን የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤ እሱ የምፈልገውን ነገር ሁሉ ያደርጋል’ ሲል የመሠከረለትን ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ አስነሳላቸው። 23  አምላክ በገባው ቃል መሠረት ከዚህ ሰው ዘር ለእስራኤል አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን አመጣ። 24  ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት በይፋ ሰብኮ ነበር። 25  ይሁንና ዮሐንስ ተልእኮውን በማጠናቀቅ ላይ ሳለ ‘እኔ ማን እመስላችኋለሁ? እኔ እኮ እሱ አይደለሁም። ይሁን እንጂ ከእኔ በኋላ ሌላ ይመጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ ለመፍታት እንኳ አልበቃም’ ይል ነበር። 26  “ወንድሞች፣ እናንተ ከአብርሃም ዘር የተወለዳችሁ እንዲሁም በመካከላችሁ ያሉ አምላክን የሚፈሩ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ይህ የመዳን ቃል ለእኛ ተልኳል። 27  የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና የሃይማኖት መሪዎቻቸው የእሱን ማንነት አልተገነዘቡም፤ በእሱ ላይ በፈረዱበት ጊዜ ግን በየሰንበቱ ከፍ ባለ ድምፅ የሚነበበውን ነቢያት የተናገሩትን ቃል ፈጸሙ። 28  ለሞት የሚያበቃ አንድም ምክንያት ባያገኙበትም እንኳ ያስገድለው ዘንድ ጲላጦስን ወተወቱት። 29  ስለ እሱ የተጻፈውን ነገር ሁሉ ከፈጸሙ በኋላም ከእንጨት ላይ አውርደው መቃብር ውስጥ አኖሩት። 30  ሆኖም አምላክ ከሞት አስነሳው፤ 31  እሱም ከገሊላ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ አብረውት ለሄዱት ሰዎች ለብዙ ቀናት ታያቸው። እነሱም አሁን ስለ እሱ ለሕዝቡ እየመሠከሩ ነው። 32  “ስለሆነም እኛ ለአባቶቻችን ስለተገባው ቃል የሚገልጸውን ምሥራች እያወጅንላችሁ ነው። 33  አምላክ ኢየሱስን ከሞት በማስነሳት ለእነሱ የገባውን ቃል ለእኛ ለልጆቻቸው ሙሉ በሙሉ ፈጽሞታል፤ ይህም የሆነው በሁለተኛው መዝሙር ላይ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ’ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው። 34  አምላክ ኢየሱስን የማይበሰብስ አካል ሰጥቶ ከሞት አስነስቶታል፤ ይህን አስቀድሞ በትንቢት ሲናገር ‘ለዳዊት ቃል የተገባውን የማይከስም ታማኝ ፍቅር አሳያችኋለሁ’ ብሏል። 35  ስለዚህ በሌላም መዝሙር ላይ ‘ታማኝ አገልጋይህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ብሏል። 36  በአንድ በኩል፣ ዳዊት በሕይወት ዘመኑ አምላክን ካገለገለ በኋላ በሞት አንቀላፍቷል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮ መበስበስን አይቷል። 37  በሌላ በኩል ግን አምላክ ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ መበስበስን አላየም። 38  “ስለዚህ ወንድሞች፣ በእሱ በኩል የሚገኘው የኃጢአት ይቅርታ አሁን እየታወጀላችሁ እንዳለ እወቁ፤ 39  በኢየሱስ የሚያምን ማንኛውም ሰው፣ በእሱ አማካኝነት ‘ከበደል ነፃ ነህ’ ሊባል ይችላል፤ የሙሴ ሕግ ግን እናንተን ከበደል ነፃ ሊያደርጋችሁ አልቻለም። 40  ስለዚህ በነቢያት መጻሕፍት እንዲህ ተብሎ የተነገረው ነገር በእናንተ ላይ እንዳይደርስ ተጠንቀቁ፦ 41  ‘እናንተ ፌዘኞች፣ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፤ ጥፉም፤ ማንም በዝርዝር ቢነግራችሁ እንኳ ፈጽሞ የማታምኑትን ሥራ በእናንተ ዘመን እያከናወንኩ ነውና።’” 42  እየወጡ ሳሉም ሰዎቹ ስለዚሁ ጉዳይ በሚቀጥለው ሰንበትም እንዲነግሯቸው ለመኗቸው። 43  በምኩራቡ የተደረገው ስብሰባ ከተበተነ በኋላ ከአይሁዳውያንና ወደ ይሁዲነት ተለውጠው አምላክን ከሚያመልኩት መካከል ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሏቸው፤ እነሱም ሰዎቹን በማነጋገር የአምላክን ጸጋ አጥብቀው እንደያዙ እንዲቀጥሉ አሳሰቧቸው። 44  በቀጣዩ ሰንበት የከተማዋ ሕዝብ ሁሉ ማለት ይቻላል፣ የይሖዋን ቃል ለመስማት አንድ ላይ ተሰበሰበ። 45  አይሁዳውያንም ሕዝቡን ባዩ ጊዜ በቅናት ተሞልተው ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በመቃወም ይሳደቡ ጀመር። 46  በዚህ ጊዜ ጳውሎስና በርናባስ በድፍረት እንዲህ አሏቸው፦ “የአምላክ ቃል በመጀመሪያ ለእናንተ መነገሩ አስፈላጊ ነበር። እናንተ ግን ወደ ጎን ገሸሽ እያደረጋችሁትና የዘላለም ሕይወት እንደማይገባችሁ በራሳችሁ ላይ እየፈረዳችሁ ስለሆነ እኛም ለአሕዛብ እንሰብካለን። 47  ይሖዋ ‘እስከ ምድር ዳር ድረስ መዳንን እንድታመጣ ለብሔራት ብርሃን አድርጌ ሾሜሃለሁ’ በማለት ትእዛዝ ሰጥቶናልና።” 48  ከአሕዛብ ወገን የሆኑት ይህን ሲሰሙ እጅግ በመደሰት የይሖዋን ቃል አከበሩ፤ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ያላቸው ሁሉ አማኞች ሆኑ። 49  ከዚህም በተጨማሪ የይሖዋ ቃል በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ እየተስፋፋ ሄደ። 50  ይሁንና አይሁዳውያን ፈሪሃ አምላክ ያላቸውን የተከበሩ ሴቶችና በከተማዋ የሚኖሩትን ታላላቅ ወንዶች በመቀስቀስ በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደት አስነሱ፤ ከክልላቸውም አስወጧቸው። 51  እነሱም የእግራቸውን አቧራ አራግፈው ወደ ኢቆንዮን ሄዱ። 52  ደቀ መዛሙርቱም በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።
[]
[]
[]
[]
12,338
14  በኢቆንዮን ጳውሎስና በርናባስ አብረው ወደ አይሁዳውያን ምኩራብ ገቡ፤ በዚያም ጥሩ ንግግር ስለሰጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አይሁዳውያንና ግሪካውያን አማኞች ሆኑ። 2  ሆኖም ያላመኑት አይሁዳውያን ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን ሰዎች በማነሳሳት በወንድሞች ላይ ጥላቻ እንዲያድርባቸው አደረጉ። 3  በመሆኑም ከይሖዋ ባገኙት ሥልጣን በድፍረት እየተናገሩ በኢቆንዮን ረዘም ላለ ጊዜ ቆዩ፤ እሱም ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች በእነሱ አማካኝነት እንዲከናወኑ በማድረግ ስለ ጸጋው የሚነገረው መልእክት ትክክል መሆኑን ያረጋግጥላቸው ነበር። 4  ይሁንና የከተማዋ ሕዝብ ተከፋፈለ፤ አንዳንዶቹ ከአይሁዳውያን ጎን ሲቆሙ ሌሎቹ ደግሞ ከሐዋርያት ጎን ቆሙ። 5  አሕዛብና አይሁዳውያን ከገዢዎቻቸው ጋር ሆነው ሊያንገላቷቸውና በድንጋይ ሊወግሯቸው በሞከሩ ጊዜ 6  ጳውሎስና በርናባስ ይህን ስላወቁ ልስጥራና ደርቤ ወደሚባሉት የሊቃኦንያ ከተሞች እንዲሁም በዙሪያቸው ወዳሉት መንደሮች ሸሹ። 7  በዚያም ምሥራቹን ማወጃቸውን ቀጠሉ። 8  በልስጥራም አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር። እሱም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ሽባ የነበረ ሲሆን ፈጽሞ በእግሩ ሄዶ አያውቅም። 9  ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ያዳምጥ ነበር። ጳውሎስም ትኩር ብሎ አየውና ለመዳን የሚያበቃ እምነት እንዳለው ተመልክቶ 10  ከፍ ባለ ድምፅ “ተነስና በእግርህ ቁም” አለው። ሰውየውም ዘሎ ተነሳና መራመድ ጀመረ። 11  ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ በሊቃኦንያ ቋንቋ “አማልክት በሰው አምሳል ሆነው ወደ እኛ ወርደዋል!” በማለት ጮኹ። 12  በርናባስን ዙስ፣ ጳውሎስን ደግሞ ዋና ተናጋሪ ስለነበር ሄርሜስ ብለው ይጠሯቸው ጀመር። 13  በከተማዋ መግቢያ ላይ ይገኝ የነበረው የዙስ ቤተ መቅደስ ካህን፣ ኮርማዎችና የአበባ ጉንጉን ወደ ከተማዋ መግቢያ በማምጣት ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መሥዋዕት ሊሠዋላቸው ፈለገ። 14  ይሁን እንጂ ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ ይህን ሲሰሙ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ሮጠውም ሕዝቡ መሃል በመግባት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፦ 15  “እናንተ ሰዎች፣ እንዲህ የምታደርጉት ለምንድን ነው? እኛም እንደ እናንተው ድክመት ያለብን ሰዎች ነን። ምሥራቹን እያወጅንላችሁ ያለነውም እነዚህን ከንቱ ነገሮች ትታችሁ ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠረውን ሕያው አምላክ እንድታመልኩ ነው። 16  ባለፉት ትውልዶች፣ ሕዝቦች ሁሉ በራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ ፈቀደላቸው፤ 17  ይሁንና ለራሱ ምሥክር ከማቅረብ ወደኋላ አላለም፤ ከሰማይ ዝናብ በማዝነብና ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠት እንዲሁም የተትረፈረፈ ምግብ በማቅረብና ልባችሁን በደስታ በመሙላት መልካም ነገር አድርጓል።” 18  ይህን ሁሉ ተናግረው እንኳ ሕዝቡ እንዳይሠዋላቸው ያስጣሉት በብዙ ችግር ነበር። 19  ሆኖም አይሁዳውያን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጥተው ሕዝቡን አግባቡ፤ ጳውሎስንም በድንጋይ ከወገሩት በኋላ የሞተ መስሏቸው ጎትተው ከከተማዋ አወጡት። 20  ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በከበቡት ጊዜ ግን ተነስቶ ወደ ከተማዋ ገባ። በማግስቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤ ሄደ። 21  በዚያች ከተማ ምሥራቹን ሰብከው በርካታ ደቀ መዛሙርት ካፈሩ በኋላ ወደ ልስጥራ፣ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ። 22  በዚያም “በብዙ መከራ አልፈን ወደ አምላክ መንግሥት መግባት አለብን” እያሉ በእምነት ጸንተው እንዲኖሩ በማበረታታት ደቀ መዛሙርቱን አጠናከሩ። 23  ከዚህም በተጨማሪ በየጉባኤው ሽማግሌዎችን ሾሙላቸው፤ ከጾሙና ከጸለዩም በኋላ ላመኑበት ለይሖዋ አደራ ሰጧቸው። 24  ከዚያም በጵስድያ በኩል አልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፤ 25  በጴርጌ ቃሉን ካወጁ በኋላ ወደ አታሊያ ወረዱ። 26  ከዚያም ተነስተው በመርከብ ወደ አንጾኪያ ሄዱ፤ ጳውሎስና በርናባስ አሁን ያጠናቀቁትን ሥራ እንዲያከናውኑ ለአምላክ ጸጋ በአደራ የተሰጡት በአንጾኪያ ነበር። 27  እዚያም ደርሰው ጉባኤውን ከሰበሰቡ በኋላ አምላክ በእነሱ አማካኝነት ያከናወናቸውን በርካታ ነገሮች እንዲሁም ለአሕዛብ የእምነትን በር እንደከፈተላቸው ተረኩላቸው። 28  በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ረዘም ያለ ጊዜ አሳለፉ።
[]
[]
[]
[]
12,339
15  አንዳንድ ሰዎች ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ወርደው “በሙሴ ሥርዓት መሠረት ካልተገረዛችሁ በቀር ልትድኑ አትችሉም” እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ጀመር። 2  በዚህ የተነሳ ጳውሎስና በርናባስ ከሰዎቹ ጋር የጦፈ ክርክርና ጭቅጭቅ ውስጥ ገቡ። በመሆኑም ጳውሎስና በርናባስ እንዲሁም አንዳንድ ወንድሞች ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ጉዳዩን በዚያ ለሚገኙት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች እንዲያቀርቡ ተወሰነ። 3  በዚህም መሠረት ጉባኤው የተወሰነ መንገድ ከሸኛቸው በኋላ በፊንቄና በሰማርያ በኩል በማለፍ ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰዎች ተለውጠው አምላክን ማምለክ እንደጀመሩ በዝርዝር ተናገሩ፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኟቸው። 4  ኢየሩሳሌም ሲደርሱም በዚያ የሚገኘው ጉባኤ እንዲሁም ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ጥሩ አቀባበል አደረጉላቸው፤ የተላኩትም ወንድሞች አምላክ በእነሱ አማካኝነት ያከናወናቸውን በርካታ ነገሮች ተረኩላቸው። 5  ይሁንና ከፈሪሳውያን ሃይማኖታዊ ቡድን መካከል አማኞች የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ከመቀመጫቸው ተነስተው “እነዚህን ሰዎች መግረዝና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ማዘዝ አስፈላጊ ነው” ሲሉ ተናገሩ። 6  ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ይህን ጉዳይ ለመመርመር ተሰበሰቡ። 7  ከብዙ ክርክር በኋላ ጴጥሮስ ተነስቶ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ አሕዛብ የምሥራቹን ቃል ከእኔ አፍ ሰምተው እንዲያምኑ አምላክ ገና ከመጀመሪያው ከእናንተ መካከል እኔን እንደመረጠኝ በሚገባ ታውቃላችሁ። 8  ልብን የሚያውቀው አምላክ ለእኛ እንዳደረገው ሁሉ ለእነሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሠከረላቸው። 9  ደግሞም በእኛና በእነሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም፤ ከዚህ ይልቅ በእምነታቸው የተነሳ ልባቸውን አነጻ። 10  ታዲያ አባቶቻችንም ሆኑ እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርቱ ጫንቃ ላይ በመጫን አሁን አምላክን ለምን ትፈታተናላችሁ? 11  በአንጻሩ ግን እኛ የምንድነው በጌታ ኢየሱስ ጸጋ አማካኝነት እንደሆነ እናምናለን፤ እነሱም ቢሆኑ ይህንኑ ያምናሉ።” 12  በዚህ ጊዜ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ጸጥ አለ፤ በርናባስና ጳውሎስ፣ አምላክ በእነሱ አማካኝነት በአሕዛብ መካከል ያከናወናቸውን በርካታ ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ሲናገሩም ያዳምጥ ጀመር። 13  እነሱ ተናግረው ካበቁ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞች፣ ስሙኝ። 14  አምላክ ከአሕዛብ መካከል ለስሙ የሚሆኑ ሰዎችን ለመውሰድ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ለእነሱ ትኩረት እንደሰጠ ሲምዖን በሚገባ ተርኳል። 15  እንዲህ ተብሎ የተጻፈው የነቢያት ቃልም ከዚህ ጋር ይስማማል፦ 16  ‘ከዚህ በኋላ ተመልሼ የፈረሰውን የዳዊትን ድንኳን ዳግመኛ አቆማለሁ፤ ፍርስራሹንም አድሼ ዳግም እገነባዋለሁ፤ 17  ይህን የማደርገው የቀሩት ሰዎች፣ ከብሔራት ከመጡት በስሜ የተጠሩ ሰዎች ጋር አንድ ላይ ሆነው ይሖዋን ከልብ እንዲፈልጉ ነው በማለት እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው ይሖዋ ተናግሯል፤ 18  እነዚህም ነገሮች ከጥንት ዘመን ጀምሮ ይታወቃሉ።’ 19  ስለዚህ እንደ እኔ ሐሳብ ከሆነ፣ ተለውጠው አምላክን ማምለክ የጀመሩትን አሕዛብ ባናስቸግራቸው ይሻላል፤ 20  ከዚህ ይልቅ በጣዖት ከረከሱ ነገሮች፣ ከፆታ ብልግና፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከደም እንዲርቁ እንጻፍላቸው። 21  ምክንያቱም ከጥንት ዘመን ጀምሮ በየከተማው በሰንበት ቀናት ሁሉ በምኩራቦች ውስጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ከሙሴ መጻሕፍት በማንበብ በውስጡ የሰፈረውን ቃል የሚሰብኩ ሰዎች ነበሩ።” 22  ከዚያም ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከመላው ጉባኤ ጋር ሆነው ከመካከላቸው የተመረጡ ሰዎችን ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ በወንድሞች መካከል ግንባር ቀደም የሆኑትን በርስያን የሚባለውን ይሁዳንና ሲላስን ላኩ። 23  ደግሞም የሚከተለውን ደብዳቤ ጽፈው በእነሱ እጅ ላኩላቸው፦ “ከወንድሞቻችሁ ከሐዋርያትና ከሽማግሌዎች፣ በአንጾኪያ፣ በሶርያና በኪልቅያ ለምትኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁ ወንድሞች፤ ሰላምታችን ይድረሳችሁ! 24  ከእኛ መካከል አንዳንዶች ወጥተው እኛ ምንም ሳናዛቸው በሚናገሩት ነገር እንዳስቸገሯችሁና ሊያውኳችሁ እንደሞከሩ ስለሰማን 25  ሰዎች መርጠን ከተወደዱት ወንድሞቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ለመላክ በአንድ ልብ ወሰንን፤ 26  በርናባስና ጳውሎስ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ናቸው። 27  ስለዚህ ይህንኑ ነገር በቃልም እንዲነግሯችሁ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። 28  ከሚከተሉት አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር፣ ሌላ ተጨማሪ ሸክም እንዳንጭንባችሁ መንፈስ ቅዱስና እኛ ወስነናል፦ 29  ለጣዖት ከተሠዉ ነገሮች፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋና ከፆታ ብልግና ራቁ። ከእነዚህ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ከራቃችሁ መልካም ይሆንላችኋል። ጤና ይስጣችሁ!” 30  የተላኩትም ሰዎች ከተሰናበቱ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ እዚያ የሚገኙትንም ደቀ መዛሙርት በአንድነት ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጧቸው። 31  እነሱም ካነበቡት በኋላ ባገኙት ማበረታቻ እጅግ ተደሰቱ። 32  ይሁዳና ሲላስም ራሳቸው ነቢያት ስለነበሩ ብዙ ቃል በመናገር ወንድሞችን አበረታቷቸው፤ እንዲሁም አጠናከሯቸው። 33  በዚያም የተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ወደላኳቸው ሰዎች እንዲመለሱ ወንድሞች በሰላም አሰናበቷቸው። 34  —— 35  ይሁን እንጂ ጳውሎስና በርናባስ እያስተማሩና ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር ሆነው ምሥራቹን ይኸውም የይሖዋን ቃል እየሰበኩ በአንጾኪያ ቆዩ። 36  ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “የይሖዋን ቃል ባወጅንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉት ወንድሞች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተመልሰን እንጠይቃቸው” አለው። 37  በርናባስ፣ ማርቆስ ተብሎ የሚጠራው ዮሐንስ አብሯቸው እንዲሄድ ወስኖ ነበር። 38  ጳውሎስ ግን ማርቆስ በጵንፍልያ ተለይቷቸው ስለነበረና ያከናውኑት ወደነበረው ሥራ ከእነሱ ጋር ስላልሄደ አሁን አብሯቸው እንዲሄድ አልፈለገም። 39  በዚህ ምክንያት በመካከላቸው ኃይለኛ ጭቅጭቅ ስለተፈጠረ ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። 40  ጳውሎስ ደግሞ ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለይሖዋ ጸጋ በአደራ ከሰጡት በኋላ ከዚያ ተነስቶ ሄደ። 41  ጉባኤዎችንም እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ በኩል አለፈ።
[]
[]
[]
[]
12,340
16  ከዚያም ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ ሄደ። በዚያም አማኝ የሆነች አይሁዳዊት እናትና ግሪካዊ አባት ያለው ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ 2  እሱም በልስጥራና በኢቆንዮን ባሉ ወንድሞች፣ በመልካም ምግባሩ የተመሠከረለት ነበር። 3  ጳውሎስ፣ ጢሞቴዎስ አብሮት እንዲሄድ እንደሚፈልግ ገለጸ፤ አባቱ ግሪካዊ መሆኑን ሁሉም ሰው ያውቅ ስለነበረም በእነዚያ አካባቢዎች ስላሉት አይሁዳውያን ሲል ወስዶ ገረዘው። 4  በየከተሞቹ ሲያልፉም በዚያ ለሚያገኟቸው ሁሉ በኢየሩሳሌም ያሉት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ያስተላለፏቸውን ውሳኔዎች እንዲጠብቁ ጉዳዩን ያሳውቋቸው ነበር። 5  ጉባኤዎቹም በእምነት እየጠነከሩና ከዕለት ወደ ዕለት በቁጥር እየጨመሩ ሄዱ። 6  ከዚህም ሌላ መንፈስ ቅዱስ ቃሉን በእስያ አውራጃ እንዳይናገሩ ስለከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አድርገው አለፉ። 7  ደግሞም ወደ ሚስያ በወረዱ ጊዜ ወደ ቢቲኒያ ሊገቡ ሞከሩ፤ ሆኖም የኢየሱስ መንፈስ አልፈቀደላቸውም። 8  ስለዚህ በሚስያ በኩል አልፈው ወደ ጥሮአስ ወረዱ። 9  ጳውሎስም ሌሊት በራእይ አንድ የመቄዶንያ ሰው በዚያ ቆሞ “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን” ብሎ ሲለምነው አየ። 10  ጳውሎስ ይህን ራእይ እንዳየም ‘አምላክ ምሥራቹን እንድንሰብክላቸው ጠርቶናል’ የሚል መደምደሚያ ላይ ስለደረስን ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ሞከርን። 11  ስለዚህ ከጥሮአስ መርከብ ተሳፍረን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ ሄድን፤ በማግስቱ ደግሞ ወደ ኔያጶሊስ ተጓዝን፤ 12  ከዚያም ተነስተን የሮማውያን ቅኝ ግዛትና የመቄዶንያ አውራጃ ቁልፍ ከተማ ወደሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ መጣን። በዚህች ከተማም ለተወሰኑ ቀናት ቆየን። 13  በሰንበት ቀን የጸሎት ስፍራ ይገኝበታል ብለን ወዳሰብነው ከከተማው በር ውጭ ወዳለ አንድ ወንዝ ዳር ሄድን፤ በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩት ሴቶች መናገር ጀመርን። 14  ከትያጥሮን ከተማ የመጣች፣ ሐምራዊ ጨርቅ የምትሸጥና አምላክን የምታመልክ ሊዲያ የተባለች አንዲት ሴት እያዳመጠች ነበር፤ ይሖዋም ጳውሎስ የሚናገረውን በማስተዋል እንድትሰማ ልቧን በደንብ ከፈተላት። 15  እሷና በቤቷ የሚኖሩ ሰዎች ከተጠመቁ በኋላ “ለይሖዋ ታማኝ እንደሆንኩ አድርጋችሁ ከቆጠራችሁኝ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እረፉ” ብላ ተማጸነችን። እንድንገባም አስገደደችን። 16  አንድ ቀን ወደ ጸሎት ስፍራ እየሄድን ሳለ መንፈስ ይኸውም የጥንቆላ ጋኔን ያደረባት አንዲት አገልጋይ አገኘችን። እሷም በጥንቆላ ሥራዋ ለጌቶቿ ብዙ ትርፍ ታስገኝላቸው ነበር። 17  ይህች ሴት ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች “እነዚህ ሰዎች የመዳንን መንገድ የሚያውጁላችሁ የልዑሉ አምላክ ባሪያዎች ናቸው” በማለት ትጮኽ ነበር። 18  ለብዙ ቀናት እየደጋገመች ይህንኑ ትናገር ነበር። በመጨረሻም ጳውሎስ በዚህ ነገር በመሰላቸቱ ዞር ብሎ ያን መንፈስ “ከእሷ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው። መንፈሱም በዚያው ቅጽበት ወጣ። 19  ጌቶቿ የገቢ ምንጫቸው መቋረጡን ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው እየጎተቱ ገዢዎቹ ወደሚገኙበት ወደ ገበያ ስፍራው ወሰዷቸው። 20  ከዚያም የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ፊት አቅርበዋቸው እንዲህ አሉ፦ “እነዚህ ሰዎች ከተማችንን ክፉኛ እያወኩ ነው። እነሱ አይሁዳውያን ናቸው፤ 21  ደግሞም እኛ ሮማውያን ልንቀበለውም ሆነ ልንፈጽመው የማይገባንን ልማድ እያስፋፉ ነው።” 22  ሕዝቡም በአንድነት በእነሱ ላይ ተነሳ፤ የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎችም ልብሳቸውን ከገፈፏቸው በኋላ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ። 23  በጣም ከደበደቧቸው በኋላ እስር ቤት አስገቧቸው፤ የእስር ቤቱንም ጠባቂ በደንብ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። 24  እሱም እንዲህ ያለ ትእዛዝ ስለተሰጠው ወደ እስር ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን በእግር ግንድ አሰረው። 25  ይሁንና እኩለ ሌሊት ገደማ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና አምላክን በመዝሙር እያወደሱ ነበር፤ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር። 26  ድንገት ከባድ የምድር ነውጥ በመከሰቱ የእስር ቤቱ መሠረት ተናጋ። በተጨማሪም በሮቹ ወዲያውኑ የተከፈቱ ሲሆን ሁሉም የታሰሩበት ማሰሪያ ተፈታ። 27  የእስር ቤቱ ጠባቂም ከእንቅልፉ ነቅቶ የእስር ቤቱ በሮች መከፈታቸውን ሲያይ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ለመግደል ሰይፉን መዘዘ። 28  ጳውሎስ ግን ድምፁን ከፍ አድርጎ “በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ! ሁላችንም እዚህ አለን” ሲል ተናገረ። 29  በዚህ ጊዜ የእስር ቤቱ ጠባቂ መብራት እንዲያመጡለት ጠይቆ ወደ ውስጥ ዘሎ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ ፊት ተደፋ። 30  ወደ ውጭ ካወጣቸውም በኋላ “ጌቶቼ፣ ለመዳን ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” አለ። 31  እነሱም “በጌታ ኢየሱስ እመን፤ አንተም ሆንክ ቤተሰብህ ትድናላችሁ” አሉት። 32  ከዚያም ለእሱና በቤቱ ላሉት ሰዎች ሁሉ የይሖዋን ቃል ነገሯቸው። 33  ጠባቂውም ሌሊት በዚያው ሰዓት ይዟቸው ሄዶ ቁስላቸውን አጠበላቸው። ከዚያም እሱና መላው ቤተሰቡ ወዲያውኑ ተጠመቁ። 34  ወደ ቤቱም ወስዶ ማዕድ አቀረበላቸው፤ በአምላክ በማመኑም ከመላው ቤተሰቡ ጋር እጅግ ተደሰተ። 35  ሲነጋም የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች “እነዚያን ሰዎች ልቀቃቸው” ብለው እንዲነግሩት መኮንኖቹን ላኩበት። 36  የእስር ቤቱ ጠባቂ የላኩትን መልእክት እንዲህ ሲል ለጳውሎስ ነገረው፦ “የከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ሁለታችሁ እንድትፈቱ ሰዎች ልከዋል። ስለዚህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ።” 37  ጳውሎስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እኛ የሮም ዜጎች ሆነን ሳለ ያለፍርድ በሕዝብ ፊት ገርፈው እስር ቤት ወረወሩን። ታዲያ አሁን በድብቅ አስወጥተው ሊጥሉን ይፈልጋሉ? እንዲህማ አይሆንም! እነሱ ራሳቸው መጥተው ይዘውን ይውጡ።” 38  መኮንኖቹም ይህን ነገር ለከተማዋ ሕግ አስከባሪዎች ነገሯቸው። እነሱም ሰዎቹ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ፍርሃት አደረባቸው። 39  በመሆኑም መጥተው ለመኗቸው፤ ከእስር ቤቱም ይዘዋቸው ከወጡ በኋላ ከተማዋን ለቀው እንዲሄዱ ጠየቋቸው። 40  እነሱ ግን ከእስር ቤቱ ወጥተው ወደ ሊዲያ ቤት አመሩ፤ እዚያም ወንድሞችን አግኝተው ካበረታቷቸው በኋላ ከተማዋን ለቀው ሄዱ።
[]
[]
[]
[]
12,341
17  ከዚያም በአምፊጶሊስና በአጶሎንያ በኩል ተጉዘው የአይሁዳውያን ምኩራብ ወዳለበት ወደ ተሰሎንቄ መጡ። 2  ጳውሎስም እንደ ልማዱ ወደ ምኩራብ ገባ፤ ለሦስት ሰንበትም ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነሱ ጋር ተወያየ፤ 3  ክርስቶስ መከራ መቀበሉና ከሞት መነሳቱ አስፈላጊ እንደነበር ማስረጃ እየጠቀሰ በማብራራትና በማስረዳት “ይህ እኔ የማውጅላችሁ ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ ነው” አላቸው። 4  ከዚህም የተነሳ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹ አማኞች በመሆን ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤ ከግሪካውያንም መካከል አምላክን የሚያመልኩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እንዲሁም ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የታወቁ ሴቶች እንዲሁ አደረጉ። 5  ሆኖም አይሁዳውያን ቅናት ስላደረባቸው በገበያ ስፍራ የሚያውደለድሉ አንዳንድ ክፉ ሰዎችን አሰባስበው አሳደሙ፤ ከተማዋንም በሁከት አመሷት። ጳውሎስንና ሲላስንም አምጥተው ለረብሻ የተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ለማቅረብ የያሶንን ቤት ሰብረው ገቡ። 6  ባጧቸው ጊዜም ያሶንንና አንዳንድ ወንድሞችን እየጎተቱ ወስደው የከተማዋ ገዢዎች ፊት በማቅረብ እንዲህ እያሉ ጮኹ፦ “ዓለምን ሁሉ ያናወጡት እነዚያ ሰዎች እዚህም መጥተዋል፤ 7  ያሶንም በእንግድነት ተቀብሏቸዋል። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሳርን ሕግ የሚቃረን ነገር ያደርጋሉ።” 8  ሕዝቡና የከተማዋ ገዢዎች ይህን ሲሰሙ ተሸበሩ፤ 9  ያሶንን እና ሌሎቹን የዋስትና ገንዘብ እንዲያስይዙ ካደረጓቸው በኋላ ለቀቋቸው። 10  ወንድሞችም እንደመሸ ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ቤርያ ላኳቸው። እነሱም እዚያ እንደደረሱ ወደ አይሁዳውያን ምኩራብ ገቡ። 11  በቤርያ የነበሩት አይሁዳውያን በተሰሎንቄ ከነበሩት ይልቅ ቀና አስተሳሰብ ስለነበራቸው የሰሙት ነገር ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ በየዕለቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጉጉት ተቀበሉ። 12  ስለዚህ ከእነሱ መካከል ብዙዎቹ እንዲሁም ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የተከበሩ ግሪካውያን ሴቶችና የተወሰኑ ወንዶች አማኞች ሆኑ። 13  ሆኖም በተሰሎንቄ ያሉት አይሁዳውያን ጳውሎስ የአምላክን ቃል በቤርያም እንዳወጀ ባወቁ ጊዜ ሕዝቡን ለማነሳሳትና ለማወክ ወደዚያ መጡ። 14  በዚህ ጊዜ ወንድሞች ወዲያውኑ ጳውሎስን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ላኩት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቀሩ። 15  ጳውሎስን የሸኙት ሰዎችም እስከ አቴንስ አደረሱት፤ ከዚያም ጳውሎስ ‘ሲላስና ጢሞቴዎስ በተቻለ ፍጥነት ወደ እኔ እንዲመጡ ንገሯቸው’ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፤ ሰዎቹም ተመልሰው ሄዱ። 16  ጳውሎስ በአቴንስ እየጠበቃቸው ሳለ ከተማዋ በጣዖት የተሞላች መሆኗን አይቶ መንፈሱ ተረበሸ። 17  ስለዚህ በምኩራብ ከአይሁዳውያንና አምላክን ከሚያመልኩ ሌሎች ሰዎች ጋር እንዲሁም በየዕለቱ በገበያ ስፍራ ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይወያይ ጀመር። 18  ሆኖም ከኤፊቆሮስና ከኢስጦይክ ፈላስፎች መካከል አንዳንዶቹ ይከራከሩት ጀመር፤ ሌሎቹ ደግሞ “ይህ ለፍላፊ ምን ሊያወራ ፈልጎ ነው?” ይሉ ነበር። “ስለ ባዕዳን አማልክት የሚያውጅ ይመስላል” የሚሉም ነበሩ። ይህን ያሉት ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤ የሚገልጸውን ምሥራች ያውጅ ስለነበር ነው። 19  ስለዚህ ይዘው ወደ አርዮስፋጎስ ከወሰዱት በኋላ እንዲህ አሉት፦ “ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ ልታስረዳን ትችላለህ? 20  ምክንያቱም ለጆሯችን እንግዳ የሆነ ነገር እያሰማኸን ነው፤ ይህ ነገር ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን።” 21  የአቴንስ ሰዎችና በዚያ የሚገኙ የባዕድ አገር ሰዎች ትርፍ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ስለ አዳዲስ ነገሮች በማውራትና በመስማት ብቻ ነበር። 22  በዚህ ጊዜ ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፦ “የአቴንስ ሰዎች ሆይ፣ በሁሉም ነገር ከሌሎች ሰዎች ይበልጥ እናንተ አማልክትን እንደምትፈሩ ማየት ችያለሁ። 23  ለአብነት ያህል፣ እየተዘዋወርኩ ሳለሁ የምታመልኳቸውን ነገሮች በትኩረት ስመለከት ‘ለማይታወቅ አምላክ’ የሚል ጽሑፍ የተቀረጸበት አንድ መሠዊያ አይቻለሁ። ስለዚህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ አሳውቃችኋለሁ። 24  ዓለምንና በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ የፈጠረው አምላክ፣ እሱ የሰማይና የምድር ጌታ ስለሆነ በእጅ በተሠሩ ቤተ መቅደሶች ውስጥ አይኖርም፤ 25  በተጨማሪም ሕይወትንና እስትንፋስንም ሆነ ማንኛውንም ነገር ለሰው ሁሉ የሚሰጠው እሱ ስለሆነ የሚጎድለው ነገር ያለ ይመስል በሰው እጅ አይገለገልም። 26  በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም የሰውን ወገኖች በሙሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ የተወሰኑትን ዘመናትና የሰው ልጆች የሚኖሩበትንም ድንበር ደነገገ፤ 27  ይህን ያደረገው ሰዎች አምላክን እንዲፈልጉትና አጥብቀው በመሻት እንዲያገኙት ብሎ ነው፤ እንዲህ ሲባል ግን እሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ ነው ማለት አይደለም። 28  ምክንያቱም ከእናንተ ባለቅኔዎች አንዳንዶቹ ‘እኛም የእሱ ልጆች ነንና’ ብለው እንደተናገሩት ሁሉ ሕይወት ያገኘነው፣ የምንንቀሳቀሰውና የምንኖረው በእሱ ነው። 29  “እንግዲህ እኛ የአምላክ ልጆች ከሆንን አምላክ በሰው ጥበብና ንድፍ ከወርቅ፣ ከብር ወይም ከድንጋይ የተቀረጸን ነገር ይመስላል ብለን ልናስብ አይገባም። 30  እርግጥ አምላክ ሰዎች ባለማወቅ የኖሩበትን ጊዜ ችላ ብሎ አልፎታል፤ አሁን ግን በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ እያሳሰበ ነው። 31  ምክንያቱም በሾመው ሰው አማካኝነት በዓለም ሁሉ ላይ በጽድቅ ለመፍረድ ዓላማ ያለው ሲሆን ይህን ለማድረግም ቀን ወስኗል፤ እሱንም ከሞት በማስነሳት ለሰዎች ሁሉ ዋስትና ሰጥቷል።” 32  እነሱም ስለ ሙታን ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ አንዳንዶቹ ያሾፉበት ጀመር፤ ሌሎቹ ግን “ስለዚሁ ጉዳይ በድጋሚ መስማት እንፈልጋለን” አሉት። 33  በዚህ ጊዜ ጳውሎስ ትቷቸው ሄደ፤ 34  አንዳንድ ሰዎች ግን ከእሱ ጋር በመተባበር አማኞች ሆኑ። ከእነሱም መካከል የአርዮስፋጎስ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆነው ዲዮናስዮስና ደማሪስ የተባለች ሴት እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ይገኙበታል።
[]
[]
[]
[]
12,342
18  ከዚህ በኋላ ከአቴንስ ተነስቶ ወደ ቆሮንቶስ መጣ። 2  በዚያም የጳንጦስ ተወላጅ የሆነ አቂላ የተባለ አይሁዳዊ አገኘ፤ ይህ ሰው ቀላውዴዎስ አይሁዳውያን ሁሉ ከሮም እንዲወጡ ባዘዘው መሠረት ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር በቅርቡ ከጣሊያን የመጣ ነበር። ጳውሎስም ወደ እነሱ ሄደ፤ 3  ሙያቸው አንድ ዓይነት በመሆኑ እነሱ ቤት ተቀምጦ አብሯቸው ይሠራ ነበር፤ ሙያቸውም ድንኳን መሥራት ነበር። 4  በየሰንበቱ በምኩራብ ንግግር እየሰጠ አይሁዳውያንንና ግሪካውያንን ያሳምን ነበር። 5  ሲላስና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ፣ ጳውሎስ ቃሉን በመስበኩ ሥራ በእጅጉ ተጠመደ፤ ኢየሱስ በእርግጥ ክርስቶስ መሆኑን እያስረዳ ለአይሁዳውያን ይመሠክር ነበር። 6  አይሁዳውያኑ እሱን መቃወማቸውንና መሳደባቸውን በቀጠሉ ጊዜ ግን ልብሱን አራግፎ “ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ይሁን። እኔ ንጹሕ ነኝ። ከአሁን ጀምሮ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ” አላቸው። 7  ከዚያም ተነስቶ ቲቶስ ኢዮስጦስ ወደሚባል አምላክን ወደሚያመልክ ሰው ቤት ሄደ፤ የዚህ ሰው ቤት ምኩራቡ አጠገብ ነበር። 8  የምኩራብ አለቃው ቀርስጶስ ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር በጌታ አመነ። መልእክቱን የሰሙ በርካታ የቆሮንቶስ ሰዎችም አምነው ይጠመቁ ጀመር። 9  ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን እንዲህ አለው፦ “አትፍራ፣ መናገርህን ቀጥል፤ ደግሞም ተስፋ አትቁረጥ፤ 10  እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ ማንም አንተን ሊያጠቃና ሊጎዳህ አይችልም፤ በዚህች ከተማ ብዙ ሰዎች አሉኝና።” 11  ስለዚህ በመካከላቸው የአምላክን ቃል እያስተማረ ለአንድ ዓመት ተኩል እዚያ ቆየ። 12  የሮም አገረ ገዢ የሆነው ጋልዮስ አካይያን ያስተዳድር በነበረበት ጊዜ አይሁዳውያን ግንባር ፈጥረው በጳውሎስ ላይ ተነሱበት፤ በፍርድ ወንበር ፊት አቅርበውትም 13  እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ሕጉን በሚጻረር መንገድ ሰዎች አምላክን እንዲያመልኩ እያሳመነ ነው።” 14  ይሁንና ጳውሎስ ሊናገር ሲል ጋልዮስ አይሁዳውያንን እንዲህ አላቸው፦ “አይሁዳውያን ሆይ፣ አንድ ዓይነት በደል ወይም ከባድ ወንጀል ተፈጽሞ ቢሆን ኖሮ በትዕግሥት ላዳምጣችሁ በተገባኝ ነበር። 15  ነገር ግን ክርክራችሁ ስለ ቃላትና ስለ ስሞች እንዲሁም ስለ ሕጋችሁ ከሆነ እናንተው ጨርሱት። እኔ እንዲህ ላለ ነገር ፈራጅ መሆን አልፈልግም።” 16  ከዚያም ከፍርድ ወንበሩ ፊት አስወጣቸው። 17  በዚህ ጊዜ የምኩራብ አለቃ የሆነውን ሶስቴንስን ይዘው በፍርድ ወንበሩ ፊት ይደበድቡት ጀመር። ጋልዮስ ግን እንዲህ ባሉ ጉዳዮች እጁን አያስገባም ነበር። 18  ይሁንና ጳውሎስ በዚያ ለተወሰኑ ቀናት ከቆየ በኋላ ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋር በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለት ስለነበረበትም ክንክራኦስ በተባለ ቦታ ፀጉሩን በአጭሩ ተቆረጠ። 19  ኤፌሶን በደረሱም ጊዜ እነሱን እዚያው ተዋቸው፤ እሱ ግን ወደ ምኩራብ ገብቶ ከአይሁዳውያን ጋር ይወያይ ነበር። 20  ምንም እንኳ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲሰነብት አጥብቀው ቢለምኑትም ፈቃደኛ አልሆነም፤ 21  ከዚህ ይልቅ “ይሖዋ ከፈቀደ ተመልሼ እመጣለሁ” ብሎ ተሰናበታቸው። ከዚያም ከኤፌሶን መርከብ ተሳፍሮ 22  ወደ ቂሳርያ ወረደ። ወጥቶም ለጉባኤው ሰላምታ ካቀረበ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረደ። 23  በዚያም የተወሰነ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ከዚያ ወጥቶ በገላትያና በፍርግያ አገሮች ከቦታ ወደ ቦታ እየተዘዋወረ ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ አበረታታ። 24  በዚህ ጊዜ የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እሱም ጥሩ የመናገር ተሰጥኦ ያለውና ቅዱሳን መጻሕፍትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነበር። 25  ይህ ሰው የይሖዋን መንገድ የተማረ ሲሆን በመንፈስ እየተቃጠለ ኢየሱስን ስለሚመለከቱ ጉዳዮች በትክክል ይናገርና ያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ እሱ የሚያውቀው ዮሐንስ ይሰብከው ስለነበረው ጥምቀት ብቻ ነበር። 26  እሱም በምኩራብ ውስጥ በድፍረት መናገር ጀመረ፤ ጵርስቅላና አቂላም በሰሙት ጊዜ ይዘውት በመሄድ የአምላክን መንገድ ይበልጥ በትክክል አብራሩለት። 27  በተጨማሪም ወደ አካይያ መሄድ ፈልጎ ስለነበር ወንድሞች በዚያ የሚገኙት ደቀ መዛሙርት ጥሩ አቀባበል እንዲያደርጉለት የሚያሳስብ ደብዳቤ ጻፉለት። እዚያ በደረሰ ጊዜም በአምላክ ጸጋ አማኞች የሆኑትን ሰዎች በእጅጉ ረዳቸው፤ 28  ከአይሁዳውያን ጋር በይፋ በመወያየት ከቅዱሳን መጻሕፍት ላይ እያሳያቸው ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ እንደሆነ በመግለጽ ትክክል እንዳልሆኑ በጋለ ስሜት ያስረዳቸው ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,343
19  ከጊዜ በኋላ፣ አጵሎስ በቆሮንቶስ በነበረበት ጊዜ ጳውሎስ በመሃል አገር አቋርጦ ወደ ኤፌሶን ወረደ። በዚያም አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን አገኘ፤ 2  እነሱንም “አማኞች በሆናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ተቀብላችሁ ነበር?” አላቸው። እነሱም “ኧረ እኛ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰማነው ነገር የለም” ሲሉ መለሱለት። 3  እሱም “ታዲያ ምን ዓይነት ጥምቀት ነው የተጠመቃችሁት?” አላቸው። እነሱም “የዮሐንስን ጥምቀት” አሉት። 4  ጳውሎስም እንዲህ አላቸው፦ “ዮሐንስ ያጠምቅ የነበረው የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት ነበር፤ ሰዎች ከእሱ በኋላ በሚመጣው ይኸውም በኢየሱስ እንዲያምኑ ይነግራቸው ነበር።” 5  እነሱም ይህን ሲሰሙ በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ። 6  ጳውሎስም እጁን በላያቸው በጫነ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤ እነሱም በባዕድ ቋንቋዎች መናገርና መተንበይ ጀመሩ። 7  ሰዎቹም በአጠቃላይ 12 ገደማ ነበሩ። 8  ጳውሎስም ወደ ምኩራብ እየገባ ንግግር በመስጠትና ስለ አምላክ መንግሥት አሳማኝ በሆነ መንገድ በማስረዳት ለሦስት ወራት ያህል በድፍረት ሲናገር ቆየ። 9  ሆኖም አንዳንዶቹ ግትሮች ስለነበሩ ለማመን ፈቃደኞች አልሆኑም፤ የጌታን መንገድ በሕዝቡ ፊት ባጥላሉ ጊዜ ከእነሱ በመራቅ ደቀ መዛሙርቱን ለይቶ ወሰዳቸው፤ በጢራኖስ የትምህርት ቤት አዳራሽም በየዕለቱ ንግግር ይሰጥ ነበር። 10  ይህም ለሁለት ዓመት ያህል ቀጠለ፤ ከዚህም የተነሳ በእስያ አውራጃ የሚኖሩ አይሁዳውያንና ግሪካውያን ሁሉ የጌታን ቃል ሰሙ። 11  አምላክም በጳውሎስ እጅ በጣም አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን መፈጸሙን ቀጠለ፤ 12  ሰዎችም የጳውሎስን ሰውነት የነኩ ጨርቆችንና ሽርጦችን ወደታመሙት ሰዎች ሲወስዱ ሰዎቹ በሽታቸው ይለቃቸው ነበር፤ ርኩሳን መናፍስትም ይወጡ ነበር። 13  ይሁንና እየዞሩ አጋንንትን ያስወጡ ከነበሩት አይሁዳውያን አንዳንዶቹም “ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ ስም እንድትወጣ አጥብቄ አዝሃለሁ” እያሉ ክፉ መናፍስት በያዟቸው ሰዎች ላይ የጌታ ኢየሱስን ስም ለመጥራት ሞከሩ። 14  አስቄዋ የተባለ የአንድ አይሁዳዊ የካህናት አለቃ ሰባት ወንዶች ልጆችም ይህን ያደርጉ ነበር። 15  ክፉው መንፈስ ግን መልሶ “ኢየሱስን አውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተ ደግሞ ማን ናችሁ?” አላቸው። 16  ከዚያም ክፉው መንፈስ ያደረበት ሰው ዘሎ ጉብ አለባቸው፤ አሸነፋቸውም፤ ስለዚህ ራቁታቸውን ሆነውና ቆስለው ከዚያ ቤት ሸሹ። 17  በኤፌሶን የሚኖሩት አይሁዳውያንና ግሪካውያን ሁሉ ይህን ሰሙ፤ በመሆኑም ሁሉም ፍርሃት አደረባቸው፤ የጌታ ኢየሱስ ስምም ይበልጥ እየገነነ ሄደ። 18  አማኞች ከሆኑት መካከል ብዙዎቹም እየመጡ ያደረጉትን ይናዘዙና በግልጽ ይናገሩ ነበር። 19  ደግሞም አስማት ይሠሩ ከነበሩት መካከል ብዙዎች መጽሐፎቻቸውን አንድ ላይ ሰብስበው በማምጣት በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉ። የመጽሐፎቹንም ዋጋ ሲያሰሉ 50,000 የብር ሳንቲሞች ሆኖ አገኙት። 20  በዚህ መንገድ የይሖዋ ቃል በኃይል እየተስፋፋና እያሸነፈ ሄደ። 21  ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ወሰነ። “እዚያ ከሄድኩ በኋላ ደግሞ ወደ ሮም ማቅናት አለብኝ” አለ። 22  ስለዚህ ከሚያገለግሉት መካከል ሁለቱን ማለትም ጢሞቴዎስንና ኤርስጦስን ወደ መቄዶንያ ላካቸው፤ እሱ ግን በእስያ አውራጃ ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። 23  በዚህ ወቅት የጌታን መንገድ በተመለከተ ታላቅ ሁከት ተፈጠረ። 24  ምክንያቱም ድሜጥሮስ የተባለ አንድ የብር አንጥረኛ የአርጤምስን ቤተ መቅደስ የብር ምስሎች እየቀረጸ ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትርፍ ያስገኝ ነበር። 25  ድሜጥሮስ እነሱንና በተመሳሳይ ሙያ የተሰማሩ ሰዎችን ሰብስቦ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሰዎች፣ መቼም ብልጽግናችን የተመካው በዚህ ሥራ ላይ እንደሆነ ታውቃላችሁ። 26  አሁን ግን ይህ ጳውሎስ የተባለ ሰው በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን በመላው የእስያ አውራጃ ማለት ይቻላል፣ በእጅ የተሠሩ አማልክት ሁሉ በፍጹም አማልክት አይደሉም እያለ ብዙ ሰዎችን አሳምኖ አመለካከታቸውን እንዳስለወጠ ያያችሁትና የሰማችሁት ጉዳይ ነው። 27  ከዚህም በላይ አሳሳቢ የሆነው ነገር የእኛ ሥራ መናቁ ብቻ ሳይሆን የታላቋ አምላክ የአርጤምስ ቤተ መቅደስ ዋጋ ቢስ ሆኖ ሊቀርና መላው የእስያ አውራጃም ሆነ ዓለም በሙሉ የሚያመልካት አርጤምስ ገናና ክብሯ ሊገፈፍ መሆኑ ጭምር ነው።” 28  ሰዎቹ ይህን ሲሰሙ በቁጣ ተሞልተው “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ይጮኹ ጀመር። 29  በመሆኑም ከተማዋ በረብሻ ታመሰች፤ ሕዝቡም የመቄዶንያ ሰዎች የሆኑትን የጳውሎስን የጉዞ ጓደኞች ይኸውም ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን እየጎተቱ ግር ብለው ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ ገቡ። 30  ጳውሎስም ሕዝቡ ወዳለበት ሊገባ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ከለከሉት። 31  የጳውሎስ ወዳጆች የነበሩ አንዳንድ የበዓላትና የውድድር አዘጋጆች እንኳ ሳይቀሩ ወደ ጨዋታ ማሳያው ስፍራ በመግባት ራሱን ለአደጋ እንዳያጋልጥ መልእክት በመላክ ለመኑት። 32  በተሰበሰበው ሕዝብ መካከል ከፍተኛ ትርምስ ተፈጥሮ ስለነበር አንዳንዶቹ አንድ ነገር ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ነገር እየተናገሩ ይጯጯኹ ነበር፤ አብዛኛው ሰው ለምን እዚያ እንደተገኘ እንኳ አያውቅም ነበር። 33  አንዳንዶች እስክንድርን ከሕዝቡ መካከል ባወጡት ጊዜ አይሁዳውያን ወደ ፊት ገፉት፤ እስክንድርም የመከላከያ ሐሳቡን ለሕዝቡ ሊያቀርብ ፈልጎ በእጁ ምልክት ሰጣቸው። 34  ሆኖም አይሁዳዊ መሆኑን ባወቁ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ለሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። 35  በመጨረሻ የከተማዋ ዋና ጸሐፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ፦ “የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፣ የታላቋ አርጤምስ ቤተ መቅደስና ከሰማይ የወረደው ምስሏ ጠባቂ የኤፌሶናውያን ከተማ እንደሆነች የማያውቅ ማን አለ? 36  ይህ ፈጽሞ የማይታበል ሐቅ ስለሆነ ልትረጋጉና የችኮላ እርምጃ ከመውሰድ ልትቆጠቡ ይገባል። 37  ምክንያቱም እነዚህ ያመጣችኋቸው ሰዎች ቤተ መቅደስ የዘረፉ ወይም የምናመልካትን አምላክ የሰደቡ አይደሉም። 38  ስለዚህ ድሜጥሮስና አብረውት ያሉት የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች የሚከሱት ሰው ካለ ችሎት የሚሰየምባቸው ቀናት ያሉ ከመሆኑም ሌላ የሮም አገረ ገዢዎች አሉ፤ እዚያ መሟገት ይችላሉ። 39  ከዚህ ያለፈ ልታቀርቡት የምትፈልጉት ክስ ካለ ግን በመደበኛ ጉባኤ መዳኘት ይኖርበታል። 40  አለዚያ ዛሬ በተፈጸመው ነገር የተነሳ ሕዝብ አሳድማችኋል ተብለን እንዳንከሰስ ያሰጋል፤ ለዚህ ሁሉ ሁከት መንስኤው ምን እንደሆነ ብንጠየቅ የምንሰጠው አጥጋቢ መልስ የለም።” 41  ይህን ከተናገረ በኋላ የተሰበሰበው ሕዝብ እንዲበተን አደረገ።
[]
[]
[]
[]
12,344
2  በጴንጤቆስጤ በዓል ቀን ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ነበር። 2  ድንገትም እንደ ኃይለኛ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ ተቀምጠውበት የነበረውንም ቤት ሞላው። 3  የእሳት ምላሶች የሚመስሉም ታዩአቸው፤ ተከፋፍለውም በእያንዳንዳቸው ላይ አረፉ፤ 4  ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስም እንዲናገሩ ባስቻላቸው መሠረት በተለያዩ ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር። 5  በዚያን ጊዜ በምድር ዙሪያ ካለ አገር ሁሉ የመጡ ለአምላክ ያደሩ አይሁዳውያን በኢየሩሳሌም ነበሩ። 6  ስለዚህ ይህ ድምፅ በተሰማ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ፤ እያንዳንዱም ሰው ደቀ መዛሙርቱ በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ በመስማቱ ግራ ተጋባ። 7  ደግሞም ሕዝቡ እጅግ ተደንቀው እንዲህ አሉ፦ “እንዴ፣ እነዚህ እየተናገሩ ያሉት የገሊላ ሰዎች አይደሉም? 8  ታዲያ እያንዳንዳችን በአገራችን ቋንቋ ሲናገሩ የምንሰማው እንዴት ነው? 9  እኛ ከጳርቴና፣ ከሜዶን፣ ከኤላም፣ ከሜሶጶጣሚያ፣ ከይሁዳ፣ ከቀጰዶቅያ፣ ከጳንጦስ፣ ከእስያ አውራጃ፣ 10  ከፍርግያ፣ ከጵንፍልያ፣ ከግብፅ፣ በቀሬና አቅራቢያ ካሉት የሊቢያ አውራጃዎችና ከሮም የመጣን አይሁዶችና ወደ ይሁዲነት የተለወጥን ሰዎች፣ 11  የቀርጤስና የዓረብ ሰዎች ሁላችን ስለ አምላክ ታላቅ ሥራ በየቋንቋችን ሲናገሩ እየሰማናቸው ነው።” 12  ስለዚህ ሁሉም ተገርመውና ግራ ተጋብተው እርስ በርሳቸው “ይህ ነገር ምን ይሆን?” ይባባሉ ነበር። 13  ይሁን እንጂ ሌሎች “ያልፈላ የወይን ጠጅ ተግተው ነው” በማለት አፌዙባቸው። 14  ጴጥሮስ ግን ከአሥራ አንዱ ጋር ተነስቶ በመቆም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ተናገረ፦ “እናንተ የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ፣ አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ስላለ ንግግሬን በጥሞና አዳምጡ። 15  ጊዜው ገና ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ስለሆነ እነዚህ ሰዎች እናንተ እንዳሰባችሁት አልሰከሩም። 16  ከዚህ ይልቅ ይህ የሆነው በነቢዩ ኢዩኤል በኩል እንዲህ ተብሎ በተነገረው መሠረት ነው፦ 17  ‘አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በመጨረሻው ቀን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ ወጣቶቻችሁ ራእዮችን ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤ 18  በዚያ ቀን በወንዶች ባሪያዎቼና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ሳይቀር ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ እነሱም ትንቢት ይናገራሉ። 19  በላይ በሰማይ ድንቅ ነገሮች፣ በታች በምድር ደግሞ ተአምራዊ ምልክቶች አሳያለሁ፤ ደም፣ እሳትና የጭስ ደመናም ይታያል። 20  ታላቁና ክብራማው የይሖዋ ቀን ከመምጣቱ በፊት ፀሐይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። 21  የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”’ 22  “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ይህን ቃል ስሙ፦ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት፣ አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት በመካከላችሁ የፈጸማቸው ተአምራት፣ ድንቅ ነገሮችና ምልክቶች የናዝሬቱ ኢየሱስ በአምላክ የተላከ ሰው እንደሆነ የሚያሳዩ ማስረጃዎች ናቸው። 23  ይህ ሰው ለሞት አልፎ ተሰጠ። ይህም አምላክ አስቀድሞ የወሰነው ፈቃዱና የሚያውቀው ነገር ነበር። እናንተም በክፉ ሰዎች እጅ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ ገደላችሁት። 24  አምላክ ግን ከሞት ጣር አላቆ አስነሳው፤ ምክንያቱም ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለም። 25  ዳዊትም ስለ እሱ እንዲህ ይላል፦ ‘ይሖዋን ሁልጊዜ በፊቴ አደርገዋለሁ፤ እሱ በቀኜ ስለሆነ ፈጽሞ አልናወጥም። 26  ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሴት አደረገ። እኔም በተስፋ እኖራለሁ፤ 27  ምክንያቱም በመቃብር አትተወኝም፤ ታማኝ አገልጋይህም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም። 28  የሕይወትን መንገድ አሳውቀኸኛል፤ በፊትህ በታላቅ ደስታ እንድሞላ ታደርገኛለህ።’ 29  “ወንድሞች፣ ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደሞተና እንደተቀበረ እንዲሁም መቃብሩ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደሚገኝ ለእናንተ በግልጽ እንድናገር ፍቀዱልኝ። 30  እሱ ነቢይ ስለነበረና አምላክ ከዘሮቹ አንዱን በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል እንደገባለት ስላወቀ 31  አምላክ ክርስቶስን በመቃብር እንደማይተወውና ሥጋውም እንደማይበሰብስ አስቀድሞ ተረድቶ ስለ ትንሣኤው ተናገረ። 32  ይህን ኢየሱስን አምላክ ከሞት አስነሳው፤ እኛ ሁላችንም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን። 33  ስለዚህ ወደ አምላክ ቀኝ ከፍ ከፍ ስለተደረገና ቃል የተገባውን ቅዱስ መንፈስ ከአብ ስለተቀበለ ይህን የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው። 34  ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፤ ሆኖም እሱ ራሱ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ ‘ይሖዋ ጌታዬን እንዲህ ብሎታል፦ “በቀኜ ተቀመጥ፤ 35  ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ሁን።”’ 36  ስለዚህ ይህን እናንተ በእንጨት ላይ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን አምላክ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ቤት ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።” 37  ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ልባቸው እጅግ ተነክቶ ጴጥሮስንና የቀሩትን ሐዋርያት “ወንድሞች፣ ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሏቸው። 38  ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፦ “ንስሐ ግቡ፤ እያንዳንዳችሁም ለኃጢአታችሁ ይቅርታ እንድታገኙ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ነፃ ስጦታ ትቀበላላችሁ። 39  ምክንያቱም የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ እንዲሁም ይሖዋ አምላካችን ወደ ራሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነው።” 40  በሌላ ብዙ ቃልም በሚገባ መሠከረላቸው፤ “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ” እያለም አጥብቆ አሳሰባቸው። 41  ስለዚህ ቃሉን በደስታ የተቀበሉ ተጠመቁ፤ በዚያም ቀን 3,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ተጨመሩ። 42  የሐዋርያቱንም ትምህርት በትኩረት መከታተላቸውን ቀጠሉ፤ አንድ ላይ ይሰበሰቡ፣ ምግባቸውንም አብረው ይበሉ እንዲሁም በጸሎት ይተጉ ነበር። 43  ሰው ሁሉ ፍርሃት አደረበት፤ ሐዋርያቱም ብዙ ድንቅ ነገሮችና ተአምራዊ ምልክቶች ያደርጉ ጀመር። 44  ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውም ነገር ሁሉ የጋራ ነበር፤ 45  በተጨማሪም ያላቸውን ሀብትና ንብረት በመሸጥ ገንዘቡን ለሁሉም አከፋፈሉ። ለእያንዳንዱም ሰው የሚያስፈልገውን ያህል ሰጡ። 46  በየዕለቱም በአንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅደሱ አዘውትረው ይገኙ ነበር፤ ምግባቸውንም በተለያዩ ቤቶች ይበሉ የነበረ ሲሆን የሚመገቡትም በታላቅ ደስታና በንጹሕ ልብ ነበር፤ 47  አምላክንም ያወድሱ የነበረ ከመሆኑም በላይ በሰው ሁሉ ፊት ሞገስ አግኝተው ነበር። ይሖዋም የሚድኑ ሰዎችን በየዕለቱ በእነሱ ላይ ይጨምር ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,345
20  ሁከቱ ሲበርድ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስጠራቸው፤ ካበረታታቸውና ከተሰናበታቸው በኋላ ወደ መቄዶንያ ጉዞ ጀመረ። 2  በሚያልፍባቸው ስፍራዎች የሚያገኛቸውን ደቀ መዛሙርት በብዙ ቃል እያበረታታ ወደ ግሪክ መጣ። 3  በዚያ ሦስት ወር ቆየ፤ ይሁንና ወደ ሶርያ በመርከብ ለመሄድ ተነስቶ ሳለ አይሁዳውያን ሴራ ስለጠነሰሱበት ሐሳቡን ቀይሮ በመቄዶንያ አድርጎ ለመመለስ ወሰነ። 4  የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሶጳጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤው ጋይዮስ፣ ጢሞቴዎስ እንዲሁም ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና ጢሮፊሞስ አብረውት ነበሩ። 5  እነዚህም ወደ ጥሮአስ ቀድመውን በመሄድ እዚያ ጠበቁን፤ 6  እኛ ግን የቂጣ በዓል ካለፈ በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሳን፤ በአምስት ቀን ጊዜ ውስጥም እነሱ ወዳሉበት ወደ ጥሮአስ ደረስን፤ በዚያም ሰባት ቀን ቆየን። 7  በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ምግብ ልንበላ አንድ ላይ ተሰብስበን ሳለን ጳውሎስ በማግስቱ ይሄድ ስለነበር ንግግር ይሰጣቸው ጀመር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አስረዘመ። 8  በመሆኑም ተሰብስበንበት በነበረው ፎቅ ላይ ባለው ክፍል ውስጥ ብዙ መብራት ነበር። 9  ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ መስኮት ላይ ተቀምጦ የነበረ አውጤኪስ የሚባል አንድ ወጣት ከባድ እንቅልፍ ያዘው፤ እንቅልፍ ስለጣለውም ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ወደቀ፤ ሲያነሱትም ሞቶ ነበር። 10  ጳውሎስም ከፎቅ ላይ ወርዶ በላዩ ላይ ተኝቶ አቀፈውና “በሕይወት ስላለ አትንጫጩ” አላቸው። 11  ከዚያም ወደ ፎቅ ወጥቶ ማዕዱን ካስጀመረ በኋላ በላ። እስከ ንጋትም ድረስ ሲነጋገር ቆየ፤ በኋላም ተነስቶ ሄደ። 12  ሰዎቹም ወጣቱን ወሰዱት፤ ሕያው በመሆኑም እጅግ ተጽናኑ። 13  እኛም ጳውሎስ በሰጠን መመሪያ መሠረት በመርከብ ተሳፍረን በቅድሚያ ወደ አሶስ ተጓዝን፤ ምክንያቱም ጳውሎስ በእግሩ ተጉዞ በዚያ ለመሳፈር አስቦ ነበር። 14  ስለዚህ አሶስ ላይ ከተገናኘን በኋላ አሳፍረነው ወደ ሚጢሊኒ ሄድን። 15  በነጋታውም ጉዟችንን በመቀጠል ከኪዮስ ትይዩ ወዳለው ስፍራ ደረስን፤ በሚቀጥለው ቀን ደግሞ ሳሞስ ላይ አጭር ቆይታ አደረግን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን። 16  ጳውሎስ በእስያ አውራጃ ምንም መቆየት ስላልፈለገ ኤፌሶንን አልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ምክንያቱም ቢችል በጴንጤቆስጤ በዓል ቀን ኢየሩሳሌም ለመድረስ ቸኩሎ ነበር። 17  ይሁን እንጂ ከሚሊጢን ወደ ኤፌሶን መልእክት ልኮ የጉባኤውን ሽማግሌዎች አስጠራ። 18  ወደ እሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “በእስያ አውራጃ እግሬ ከረገጠበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ በመካከላችሁ እንዴት እንደተመላለስኩ ታውቃላችሁ፤ 19  በአይሁዳውያን ሴራ ምክንያት ብዙ መከራ ቢደርስብኝም እንኳ በታላቅ ትሕትናና በእንባ ጌታን አገለግል ነበር፤ 20  ደግሞም የሚጠቅማችሁን ማንኛውንም ነገር ከመንገርም ሆነ በአደባባይና ከቤት ወደ ቤት ከማስተማር ወደኋላ ብዬ አላውቅም። 21  ከዚህ ይልቅ አይሁዳውያንም ሆኑ ግሪካውያን ንስሐ እንዲገቡና ወደ አምላክ እንዲመለሱ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ በተሟላ ሁኔታ መሥክሬላቸዋለሁ። 22  አሁን ደግሞ እዚያ ምን እንደሚደርስብኝ ባላውቅም መንፈስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው፤ 23  እርግጥ ነው፣ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ በደረስኩበት ከተማ ሁሉ በተደጋጋሚ ያሳስበኛል። 24  ይሁንና ሩጫዬን እስካጠናቀቅኩ እንዲሁም ስለ አምላክ ጸጋ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ በመመሥከር ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልኩትን አገልግሎት እስከፈጸምኩ ድረስ ሕይወቴ ምንም አያሳሳኝም። 25  “አሁንም እነሆ፣ የአምላክን መንግሥት የሰበክሁላችሁ እናንተ ሁላችሁ ዳግመኛ ፊቴን እንደማታዩ አውቃለሁ። 26  ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን ለማሳየት በዚህች ቀን እናንተን ምሥክር አድርጌ መጥራት እችላለሁ፤ 27  ምክንያቱም የአምላክን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመንገር ወደኋላ አላልኩም። 28  ለራሳችሁም ሆነ አምላክ በገዛ ልጁ ደም የዋጀውን ጉባኤውን እረኛ ሆናችሁ እንድትጠብቁ መንፈስ ቅዱስ የበላይ ተመልካቾች አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ትኩረት ስጡ። 29  እኔ ከሄድኩ በኋላ ጨካኝ ተኩላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡና መንጋውን በርኅራኄ እንደማይዙ አውቃለሁ፤ 30  ከእናንተ መካከል እንኳ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሳቸው ለመሳብ ጠማማ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ይነሳሉ። 31  “ስለዚህ ነቅታችሁ ጠብቁ፤ ሦስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን እያንዳንዳችሁን በእንባ ከማሳሰብ ወደኋላ እንዳላልኩ አስታውሱ። 32  አሁንም ለአምላክ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው፣ ስለ እሱ ጸጋ ለሚገልጸው ቃል አደራ እሰጣችኋለሁ። 33  የማንንም ብር፣ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም። 34  እነዚህ እጆቼ ለእኔም ሆነ ከእኔ ጋር ለነበሩት የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለማሟላት እንዳገለገሉ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 35  እናንተም እንዲሁ እየሠራችሁ ደካማ የሆኑትን መርዳት እንዳለባችሁ በሁሉም ነገር አሳይቻችኋለሁ፤ እንዲሁም ‘ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል’ በማለት ጌታ ኢየሱስ ራሱ የተናገረውን ቃል ማስታወስ ይኖርባችኋል።” 36  ይህን ተናግሮ ከጨረሰም በኋላ ከሁሉም ጋር ተንበርክኮ ጸለየ። 37  ከዚያም ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም እቅፍ አድርገው ሳሙት፤ 38  ከሁሉ ይበልጥ ያሳዘናቸው ከዚህ በኋላ ፊቱን እንደማያዩ የተናገረው ቃል ነው። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።
[]
[]
[]
[]
12,346
21  ከእነሱ በግድ ከተለያየን በኋላ በመርከብ ተሳፍረን በቀጥታ በመጓዝ ቆስ ደረስን፤ በማግስቱ ደግሞ ወደ ሮድስ አመራን፤ ከዚያም ወደ ጳጥራ ሄድን። 2  ወደ ፊንቄ የሚሻገር መርከብ ባገኘን ጊዜ ተሳፍረን ጉዟችንን ቀጠልን። 3  የቆጵሮስ ደሴት በታየችን ጊዜ በስተ ግራ ትተናት ወደ ሶርያ አመራን፤ መርከቡ ጭነቱን በጢሮስ ማራገፍ ስለነበረበት እኛም እዚያ ወረድን። 4  ደቀ መዛሙርቱን ፈልገን ካገኘን በኋላ በዚያ ሰባት ቀን ቆየን። እነሱም በመንፈስ ተመርተው ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ደጋግመው ነገሩት። 5  የቆይታ ጊዜያችን ባለቀ ጊዜ ከዚያ ተነስተን ጉዟችንን ጀመርን፤ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ከከተማዋ እስክንወጣ ድረስ ሸኙን። ከዚያም በባሕሩ ዳርቻ ተንበርክከን ጸለይን፤ 6  በኋላም ተሰነባበትን። ከዚያም እኛ ወደ መርከቡ ገባን፤ እነሱ ደግሞ ወደ ቤታቸው ተመለሱ። 7  ከጢሮስ ተነስተን በመርከብ በመጓዝ ጴጤሌማይስ ደረስን፤ እዚያም ለወንድሞች ሰላምታ ካቀረብን በኋላ አብረናቸው አንድ ቀን ቆየን። 8  በማግስቱ ከዚያ ተነስተን ቂሳርያ ደረስን፤ በዚያም ከሰባቱ ወንዶች አንዱ ወደሆነው ወደ ወንጌላዊው ፊልጶስ ቤት ገብተን እሱ ጋ አረፍን። 9  ይህ ሰው ትንቢት የሚናገሩ አራት ያላገቡ ሴቶች ልጆች ነበሩት። 10  ለብዙ ቀናት እዚያ ከተቀመጥን በኋላ አጋቦስ የሚባል አንድ ነቢይ ከይሁዳ ወረደ። 11  ወደ እኛም መጥቶ የጳውሎስን ቀበቶ በመውሰድ የራሱን እግርና እጅ ካሰረ በኋላ እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ‘አይሁዳውያን የዚህን ቀበቶ ባለቤት በኢየሩሳሌም እንዲህ አድርገው ያስሩታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።’” 12  ይህን ስንሰማ እኛም ሆንን በዚያ የነበሩት ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ እንለምነው ጀመር። 13  በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “እያለቀሳችሁ ልቤን ለምን ታባባላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም እንኳ ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ። 14  እሱን ለማሳመን ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ “እንግዲህ የይሖዋ ፈቃድ ይሁን” ብለን ዝም አልን። 15  ከዚህ በኋላ ለጉዞው ተዘጋጅተን ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ ጀመርን። 16  በቂሳርያ ከሚኖሩት ደቀ መዛሙርት አንዳንዶቹ ወደምናርፍበት ሰው ቤት እኛን ለመውሰድ አብረውን ሄዱ፤ ይህ ሰው ምናሶን የተባለ የቆጵሮስ ሰው ሲሆን ከቀድሞዎቹ ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበር። 17  ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን። 18  በማግስቱም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ሄደ፤ ሽማግሌዎቹም ሁሉ በዚያ ነበሩ። 19  ሰላምታ ካቀረበላቸውም በኋላ፣ እሱ ባከናወነው አገልግሎት አማካኝነት አምላክ በአሕዛብ መካከል የፈጸማቸውን ነገሮች በዝርዝር ይተርክላቸው ጀመር። 20  እነሱም ይህን ከሰሙ በኋላ አምላክን አመሰገኑ፤ እሱን ግን እንዲህ አሉት፦ “ወንድም፣ ከአይሁዳውያን መካከል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማኞች እንዳሉ ታውቃለህ፤ ደግሞም ሁሉም ለሕጉ ቀናተኞች ናቸው። 21  እነሱም አንተ በአሕዛብ መካከል ያሉት አይሁዳውያን ሁሉ ልጆቻቸውን እንዳይገርዙም ሆነ የቆየውን ልማድ እንዳይከተሉ በመንገር የሙሴን ሕግ እንዲተዉ ስታስተምር እንደቆየህ ስለ አንተ የሚወራውን ወሬ ሰምተዋል። 22  እንግዲህ ምን ማድረግ ይሻላል? መምጣትህን እንደሆነ መስማታቸው አይቀርም። 23  ስለዚህ አሁን የምንነግርህን ነገር አድርግ፦ ስእለት ያለባቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ። 24  እነዚህን ሰዎች ይዘህ በመሄድ ከእነሱ ጋር የመንጻት ሥርዓት ፈጽም፤ ራሳቸውንም እንዲላጩ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ክፈልላቸው። ይህን ካደረግክ በአንተ ላይ የተወራው ሁሉ ከንቱ መሆኑንና አንተም ሕጉን እያከበርክ በሥርዓት እንደምትኖር ሁሉም ሰው ያውቃል። 25  ከአሕዛብ የመጡትን አማኞች በተመለከተ ግን ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋና ከፆታ ብልግና እንዲርቁ ወስነን ደብዳቤ ጽፈንላቸዋል።” 26  ከዚያም ጳውሎስ በማግስቱ ሰዎቹን ይዞ በመሄድ አብሯቸው የመንጻት ሥርዓቱን ፈጸመ፤ የመንጻት ሥርዓቱ የሚያበቃበትን ቀንና ለእያንዳንዳቸው መባ የሚቀርብበትን ጊዜ ለማሳወቅም ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ። 27  ሰባቱ ቀናት ሊጠናቀቁ በተቃረቡበት ጊዜ ከእስያ የመጡ አይሁዳውያን ጳውሎስን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያዩት ሕዝቡን ሁሉ ለሁከት በማነሳሳት ያዙት፤ 28  እንዲህ እያሉም ጮኹ፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እርዱን! በሄደበት ቦታ ሁሉ ለሚያገኛቸው ሰዎች ሕዝባችንን፣ ሕጋችንንና ይህን ስፍራ የሚቃወም ትምህርት የሚያስተምረው ይህ ሰው ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የግሪክ ሰዎችን ወደ ቤተ መቅደሱ ይዞ በመምጣት ይህን ቅዱስ ስፍራ አርክሷል።” 29  ይህን ያሉት ቀደም ሲል የኤፌሶኑን ሰው ጢሮፊሞስን ከእሱ ጋር ከተማው ውስጥ አይተውት ስለነበር ነው፤ ደግሞም ጳውሎስ ይህን ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ ይዞት የገባ መስሏቸው ነበር። 30  በመሆኑም ከተማዋ በሙሉ ታወከች፤ ሕዝቡም ግር ብለው እየሮጡ በመምጣት ጳውሎስን ያዙት፤ እየጎተቱም ከቤተ መቅደሱ አወጡት፤ በሮቹም ወዲያው ተዘጉ። 31  ሊገድሉትም እየሞከሩ ሳለ መላዋ ኢየሩሳሌም እንደታወከች የሚገልጽ ወሬ ለሠራዊቱ ሻለቃ ደረሰው፤ 32  እሱም ወዲያውኑ ወታደሮችንና የጦር መኮንኖችን ይዞ እየሮጠ ወደ እነሱ ወረደ። እነሱም ሻለቃውንና ወታደሮቹን ሲያዩ ጳውሎስን መደብደባቸውን ተዉ። 33  በዚህ ጊዜ የሠራዊቱ ሻለቃ ቀርቦ በቁጥጥር ሥር አዋለውና በሁለት ሰንሰለት እንዲታሰር አዘዘ፤ ከዚያም ማን እንደሆነና ምን እንዳደረገ ጠየቀ። 34  ከሕዝቡም መካከል አንዳንዶች አንድ ነገር ሲናገሩ ሌሎቹ ደግሞ ሌላ ነገር ይናገሩ ነበር። ስለዚህ ሻለቃው ከጫጫታው የተነሳ ምንም የተጨበጠ ነገር ማግኘት ስላልቻለ ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲወሰድ አዘዘ። 35  ሆኖም ጳውሎስ ወደ ደረጃው በደረሰ ጊዜ ከሕዝቡ ዓመፅ የተነሳ ወታደሮቹ ተሸክመውት ለመሄድ ተገደዱ፤ 36  ብዙ ሕዝብም እየተከተለ “ግደለው!” እያለ ይጮኽ ነበር። 37  ጳውሎስ ወደ ጦር ሰፈሩ ሊያስገቡት በተቃረቡ ጊዜ ሻለቃውን “አንዴ ላናግርህ?” አለው። ሻለቃውም እንዲህ አለው፦ “ግሪክኛ መናገር ትችላለህ እንዴ? 38  አንተ ከዚህ ቀደም ዓመፅ አነሳስተህ 4,000 ነፍሰ ገዳዮችን ወደ ምድረ በዳ ያሸፈትከው ግብፃዊ አይደለህም?” 39  በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “እኔ እንኳ በኪልቅያ የምትገኘው የታወቀችው የጠርሴስ ከተማ ነዋሪ የሆንኩ አይሁዳዊ ነኝ። ስለዚህ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ” አለ። 40  ከፈቀደለት በኋላ ጳውሎስ ደረጃው ላይ ቆሞ ለሕዝቡ በእጁ ምልክት ሰጠ። ታላቅ ጸጥታ በሰፈነ ጊዜ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፦
[]
[]
[]
[]
12,347
22  “ወንድሞችና አባቶች፣ አሁን ለእናንተ የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ።” 2  እነሱም በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ ይበልጥ ጸጥ አሉ፤ እሱም እንዲህ አለ፦ 3  “እኔ ኪልቅያ ውስጥ በምትገኘው በጠርሴስ የተወለድኩ አይሁዳዊ ነኝ፤ ሆኖም የተማርኩት በዚህችው ከተማ በገማልያል እግር ሥር ተቀምጬ ሲሆን የአባቶችን ሕግ በጥብቅ እንድከተል የሚያስችል ትምህርት ቀስሜአለሁ፤ ዛሬ እናንተ ሁላችሁ እንዲህ እንደምትቀኑ ሁሉ እኔም ለአምላክ እቀና ነበር። 4  ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን በማሰርና ለወህኒ ቤት አሳልፌ በመስጠት የጌታን መንገድ የሚከተሉትን እስከ ሞት ድረስ ስደት አደርስባቸው ነበር፤ 5  ይህን በተመለከተም ሊቀ ካህናቱና መላው የሽማግሌዎች ጉባኤ ሊመሠክሩ ይችላሉ። ከእነሱም በደማስቆ ላሉ ወንድሞቻችን የተጻፈ ደብዳቤ ተቀብዬ በዚያ ያሉትን አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም በማምጣት ለማስቀጣት በጉዞ ላይ ነበርኩ። 6  “ሆኖም በጉዞ ላይ ሳለሁ ወደ ደማስቆ ስቃረብ፣ እኩለ ቀን ገደማ ላይ ድንገት ከሰማይ የመጣ ኃይለኛ ብርሃን በዙሪያዬ አንጸባረቀ፤ 7  እኔም መሬት ላይ ወደቅኩ፤ ከዚያም ‘ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ?’ የሚል ድምፅ ሰማሁ። 8  እኔም መልሼ ‘ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?’ አልኩት። እሱም ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ’ አለኝ። 9  ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች ብርሃኑን አይተዋል፤ ሆኖም እሱ ሲያነጋግረኝ ድምፁን አልሰሙም። 10  በዚህ ጊዜ ‘ጌታ ሆይ፣ ምን ባደርግ ይሻላል?’ አልኩት። ጌታም ‘ተነስተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ እዚያም ልታደርገው የሚገባህ ነገር ሁሉ ይነገርሃል’ አለኝ። 11  ይሁንና ከብርሃኑ ድምቀት የተነሳ ዓይኔ ማየት ስለተሳነው አብረውኝ የነበሩት ሰዎች እጄን ይዘው እየመሩ ደማስቆ አደረሱኝ። 12  “ከዚያም ሕጉን በሚገባ በመጠበቅ ለአምላክ ያደረ እንዲሁም እዚያ በሚኖሩት አይሁዳውያን ሁሉ የተመሠከረለት ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው 13  ወደ እኔ መጣ። አጠገቤም ቆሞ ‘ወንድሜ ሳኦል፣ ዓይኖችህ ይብሩልህ!’ አለኝ። እኔም በዚያው ቅጽበት ቀና ብዬ አየሁት። 14  እሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ፣ ጻድቁን እንድታይና ድምፁን እንድትሰማ መርጦሃል፤ 15  ይህን ያደረገው ስላየኸውና ስለሰማኸው ነገር በሰው ሁሉ ፊት ለእሱ ምሥክር እንድትሆን ነው። 16  ታዲያ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነስና ተጠመቅ፤ ስሙንም እየጠራህ ኃጢአትህን ታጠብ።’ 17  “ሆኖም ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለስኩ በኋላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እየጸለይኩ ሳለ ሰመመን ውስጥ ገባሁ፤ 18  ጌታም ‘ስለ እኔ የምትሰጠውን ምሥክርነት ስለማይቀበሉ ፍጠን፤ ከኢየሩሳሌም ቶሎ ብለህ ውጣ’ ሲለኝ አየሁት። 19  እኔም እንዲህ አልኩት፦ ‘ጌታ ሆይ፣ በየምኩራቡ እየዞርኩ በአንተ የሚያምኑትን አስርና እገርፍ እንደነበረ እነሱ ራሳቸው በሚገባ ያውቃሉ፤ 20  ደግሞም የአንተ ምሥክር የነበረው የእስጢፋኖስ ደም ሲፈስ እኔ በድርጊቱ በመስማማት እዚያ ቆሜ የገዳዮቹን ልብስ ስጠብቅ ነበር።’ 21  እሱ ግን ‘በሩቅ ወዳሉ አሕዛብ ስለምልክህ ተነስተህ ሂድ’ አለኝ።” 22  ሕዝቡ ይህን እስኪናገር ድረስ ጸጥ ብለው ሲያዳምጡት ቆዩ። ከዚያም “ይህ ሰው መኖር የማይገባው ስለሆነ ከምድር ገጽ ይወገድ!” ብለው ጮኹ። 23  ደግሞም እየጮኹ መደረቢያቸውን ይወረውሩና አፈር ወደ ላይ ይበትኑ ስለነበር 24  የሠራዊቱ ሻለቃ ጳውሎስን ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲያስገቡት ትእዛዝ ሰጠ፤ ደግሞም በጳውሎስ ላይ እንዲህ የሚጮኹት ለምን እንደሆነ በትክክል ማወቅ ስለፈለገ እየተገረፈ እንዲመረመር አዘዘ። 25  ሆኖም ሊገርፉት ወጥረው ባሰሩት ጊዜ ጳውሎስ አጠገቡ የቆመውን መኮንን “አንድን ሮማዊ ሳይፈረድበት ለመግረፍ ሕግ ይፈቅድላችኋል?” አለው። 26  መኮንኑ ይህን ሲሰማ ወደ ሠራዊቱ ሻለቃ ሄዶ “ምን ለማድረግ ነው ያሰብከው? ይህ ሰው እኮ ሮማዊ ነው” አለው። 27  ሻለቃውም ወደ ጳውሎስ ቀርቦ “ሮማዊ ነህ እንዴ?” አለው። እሱም “አዎ” አለው። 28  ሻለቃውም መልሶ “እኔ ይህን የዜግነት መብት የገዛሁት ብዙ ገንዘብ አውጥቼ ነው” አለው። ጳውሎስ ደግሞ “እኔ ግን በመወለድ አገኘሁት” አለ። 29  ስለዚህ እያሠቃዩ ሊመረምሩት የነበሩት ሰዎች ወዲያውኑ ከእሱ ራቁ፤ የሠራዊቱ ሻለቃም በሰንሰለት አስሮት ስለነበር ሮማዊ መሆኑን ሲገነዘብ ፈራ። 30  በመሆኑም በማግስቱ አይሁዳውያን የከሰሱት ለምን እንደሆነ በትክክል ማወቅ ስለፈለገ ፈታውና የካህናት አለቆቹ እንዲሁም መላው የሳንሄድሪን ሸንጎ እንዲሰበሰቡ አዘዘ። ከዚያም ጳውሎስን አውርዶ በመካከላቸው አቆመው።
[]
[]
[]
[]
12,348
23  ጳውሎስ የሳንሄድሪንን ሸንጎ ትኩር ብሎ እየተመለከተ “ወንድሞች፣ እኔ እስከዚህ ቀን ድረስ በአምላክ ፊት ሙሉ በሙሉ ንጹሕ ሕሊና ይዤ ተመላልሻለሁ” አለ። 2  በዚህ ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ ጳውሎስ አጠገብ የቆሙት ሰዎች አፉን እንዲመቱት አዘዘ። 3  ጳውሎስም “አንተ በኖራ የተለሰንክ ግድግዳ! አምላክ አንተን ይመታሃል። በሕጉ መሠረት በእኔ ላይ ለመፍረድ ተቀምጠህ ሳለ አንተ ራስህ ሕጉን በመጣስ እንድመታ ታዛለህ?” አለው። 4  አጠገቡ የቆሙትም “የአምላክን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህ?” አሉት። 5  ጳውሎስም “ወንድሞች፣ እኔ እኮ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላወቅኩም። ምክንያቱም ‘በሕዝብህ ገዢ ላይ ክፉ ቃል አትናገር’ ተብሎ ተጽፏል” አላቸው። 6  ጳውሎስ ግማሾቹ ሰዱቃውያን ግማሾቹ ደግሞ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ስላወቀ በሳንሄድሪን ሸንጎ ውስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ወንድሞች፣ እኔ ከፈሪሳውያን የተወለድኩ ፈሪሳዊ ነኝ። ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ ተስፋ በማመኔ ነው” ሲል ተናገረ። 7  ይህን በመናገሩ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ግጭት ተፈጥሮ ጉባኤው ለሁለት ተከፈለ። 8  ምክንያቱም ሰዱቃውያን ትንሣኤም፣ መልአክም፣ መንፈሳዊ ፍጥረታትም የሉም ይሉ የነበረ ሲሆን ፈሪሳውያን ግን በእነዚህ ነገሮች ያምኑ ነበር። 9  ስለዚህ ከፍተኛ ሁከት ተፈጠረ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ ጸሐፍት ተነስተው እንዲህ ሲሉ አጥብቀው ተከራከሩ፦ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘንም፤ መንፈስ ወይም መልአክ አናግሮት ከሆነ ግን . . . ።” 10  በመካከላቸው የተፈጠረው ግጭት እየከረረ ሲሄድ የሠራዊቱ ሻለቃ ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ወታደሮቹ ወርደው ከመካከላቸው ነጥቀው እንዲያመጡትና ወደ ጦር ሰፈሩ እንዲያስገቡት አዘዘ። 11  ሆኖም በዚያኑ ዕለት ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ እንዲህ አለው፦ “አይዞህ፣ አትፍራ! ምክንያቱም በኢየሩሳሌም ስለ እኔ በሚገባ እንደመሠከርክ ሁሉ በሮምም ልትመሠክርልኝ ይገባል።” 12  በነጋም ጊዜ አይሁዳውያን በጳውሎስ ላይ በማሴር እሱን እስኪገድሉ ድረስ እህል ውኃ ላለመቅመስ ተማማሉ። 13  ይህን ሴራ ለመፈጸም የተማማሉት ሰዎች ቁጥራቸው ከ40 በላይ ነበር። 14  እነሱም ወደ ካህናት አለቆቹና ወደ ሽማግሌዎቹ ሄደው እንዲህ አሉ፦ “ጳውሎስን እስክንገድል ድረስ አንዳች እህል ላለመቅመስ ጽኑ መሐላ ተማምለናል። 15  ስለዚህ እናንተ ከሳንሄድሪን ሸንጎ ጋር ሆናችሁ የጳውሎስን ጉዳይ ይበልጥ ማጣራት የምትፈልጉ በማስመሰል እሱን ወደ እናንተ እንዲያመጣው ለሠራዊቱ ሻለቃ ንገሩት። ይሁንና እኛ እዚህ ከመድረሱ በፊት እሱን ለመግደል ተዘጋጅተን እንጠብቃለን።” 16  ይሁን እንጂ የጳውሎስ የእህቱ ልጅ አድብተው ጥቃት ለመሰንዘር እንዳሰቡ በመስማቱ ወደ ጦር ሰፈሩ ገብቶ ጉዳዩን ለጳውሎስ ነገረው። 17  ጳውሎስም ከመኮንኖቹ አንዱን ጠርቶ “ይህ ወጣት ለሠራዊቱ ሻለቃ የሚነግረው ነገር ስላለው ወደ እሱ ውሰደው” አለው። 18  እሱም ወደ ሻለቃው ይዞት ሄደና “እስረኛው ጳውሎስ ጠርቶኝ ይህ ወጣት የሚነግርህ ነገር ስላለው ወደ አንተ እንዳቀርበው ጠየቀኝ” አለው። 19  ሻለቃውም እጁን ይዞ ለብቻው ገለል ካደረገው በኋላ “ልትነግረኝ የፈለግከው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። 20  እሱም እንዲህ አለ፦ “አይሁዳውያን ስለ ጳውሎስ ጉዳይ በዝርዝር ማወቅ የፈለጉ በማስመሰል ነገ ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ እንድታመጣው ሊጠይቁህ ተስማምተዋል። 21  አንተ ግን በዚህ እንዳትታለል፤ ምክንያቱም ከመካከላቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች አድብተው በእሱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየጠበቁ ነው፤ ደግሞም እሱን እስኪገድሉ ድረስ እህልም ሆነ ውኃ ላለመቅመስ ተማምለዋል፤ አሁንም ተዘጋጅተው የአንተን ፈቃድ እየተጠባበቁ ነው።” 22  በዚህ ጊዜ የሠራዊቱ ሻለቃ “ይህን ነገር ለእኔ መንገርህን ለማንም እንዳታወራ” ብሎ ካዘዘው በኋላ ወጣቱን አሰናበተው። 23  ከዚያም ከመኮንኖቹ መካከል ሁለቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ወደ ቂሳርያ የሚሄዱ 200 ወታደሮች እንዲሁም 70 ፈረሰኞችና ጦር የያዙ 200 ሰዎች አዘጋጁ። 24  በተጨማሪም ጳውሎስን ወደ አገረ ገዢው ወደ ፊሊክስ በደህና ለማድረስ የሚጓዝባቸው ፈረሶች አዘጋጁ።” 25  እንዲህ የሚል ደብዳቤም ጻፈ፦ 26  “ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ፤ ለክቡር አገረ ገዢ ለፊሊክስ፦ ሰላም ለአንተ ይሁን። 27  አይሁዳውያን ይህን ሰው ይዘው ሊገድሉት ነበር፤ ሆኖም የሮም ዜጋ መሆኑን ስላወቅኩ ወዲያውኑ ከወታደሮቼ ጋር ደርሼ አዳንኩት። 28  እሱን የከሰሱት ለምን እንደሆነ ለማወቅ ስለፈለግኩም ወደ ሳንሄድሪን ሸንጓቸው አቀረብኩት። 29  የተከሰሰውም ከሕጋቸው ጋር በተያያዘ በተነሳ ውዝግብ እንደሆነ ተረድቻለሁ፤ ሆኖም ለሞት ወይም ለእስር የሚያበቃ አንድም ክስ አላገኘሁም። 30  ይሁንና በዚህ ሰው ላይ የተሸረበ ሴራ እንዳለ ስለተነገረኝ ወዲያውኑ ወደ አንተ ልኬዋለሁ፤ ከሳሾቹም ክሳቸውን በአንተ ፊት እንዲያቀርቡ አዝዤአቸዋለሁ።” 31  ስለዚህ ወታደሮቹ በታዘዙት መሠረት ጳውሎስን ይዘው በሌሊት ወደ አንቲጳጥሪስ ወሰዱት። 32  በማግስቱም ፈረሰኞቹ ከጳውሎስ ጋር ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ በማድረግ እነሱ ወደ ጦር ሰፈሩ ተመለሱ። 33  ፈረሰኞቹም ቂሳርያ በደረሱ ጊዜ ደብዳቤውን ለአገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳውሎስንም አስረከቡት። 34  እሱም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ የየትኛው አውራጃ ሰው እንደሆነ ጠየቀ፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑንም ተረዳ። 35  ከዚያም “ከሳሾችህ ሲመጡ ጉዳይህን በደንብ አየዋለሁ” አለው። በሄሮድስም ቤተ መንግሥት ውስጥ በጥበቃ ሥር ሆኖ እንዲቆይ አዘዘ።
[]
[]
[]
[]
12,349
24  ከአምስት ቀን በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከተወሰኑ ሽማግሌዎችና ጠርጡለስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ እነሱም በጳውሎስ ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዢው አቀረቡ። 2  በተጠራም ጊዜ ጠርጡለስ እንዲህ ሲል ይከሰው ጀመር፦ “ክቡር ፊሊክስ ሆይ፣ በአንተ አማካኝነት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ አስተዋይነትህም ለዚህ ሕዝብ መሻሻል አስገኝቷል፤ 3  በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ለእነዚህ ነገሮች ሁሉ ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን። 4  ይሁንና አሁን ጊዜህን እንዳልወስድብህ በአጭሩ የምንነግርህን ጉዳይ መልካም ፈቃድህ ሆኖ እንድትሰማን እለምንሃለሁ። 5  ይህ ሰው መቅሰፍት ሆኖብናል፤ በዓለም ባሉት አይሁዳውያን ሁሉ መካከል ዓመፅ ያነሳሳል፤ ከዚህም ሌላ የናዝሬታውያን ኑፋቄ ቀንደኛ መሪ ነው። 6  በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ መቅደሱን ለማርከስ ሲሞክር ስላገኘነው ያዝነው። 7  —— 8  አንተ ራስህ ስትመረምረው በእሱ ላይ ያቀረብነው ክስ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ ትችላለህ።” 9  አይሁዳውያኑም የተባለው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን በመግለጽ በክሱ ተባበሩ። 10  አገረ ገዢውም እንዲናገር በጭንቅላቱ ምልክት በሰጠው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ ሆነህ ስታገለግል መቆየትህን አውቃለሁ፤ በመሆኑም ስለ ራሴ የመከላከያ መልስ የማቀርበው በደስታ ነው። 11  ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከ12 ቀን እንደማይበልጥ አንተው ራስህ ማረጋገጥ ትችላለህ፤ 12  እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ከማንም ጋር ስከራከርም ሆነ በምኩራቦች ወይም በከተማው ውስጥ ሕዝቡን ለዓመፅ ሳነሳሳ አላገኙኝም። 13  በተጨማሪም አሁን ላቀረቡብኝ ክስ ሁሉ ምንም ማስረጃ ሊያቀርቡልህ አይችሉም። 14  ይሁን እንጂ በሕጉና በነቢያት የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ ስለማምን እነሱ ኑፋቄ ብለው የሚጠሩትን የሕይወት መንገድ እንደምከተልና በዚህም መንገድ ለአባቶቼ አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንደማቀርብ አልክድም። 15  ደግሞም እነዚህ ሰዎች ራሳቸው ተስፋ እንደሚያደርጉት ጻድቃንም ሆኑ ዓመፀኞች ከሞት እንደሚነሱ በአምላክ ተስፋ አደርጋለሁ። 16  በዚህ የተነሳ በአምላክም ሆነ በሰው ፊት ንጹሕ ሕሊና ይዤ ለመኖር ሁልጊዜ ጥረት አደርጋለሁ። 17  ከብዙ ዓመታት በኋላም ለወገኖቼ ምጽዋት ለመስጠትና ለአምላክ መባ ለማቅረብ መጣሁ። 18  በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያገኙኝ የመንጻት ሥርዓት ፈጽሜ ይህንኑ ሳደርግ እንጂ ከብዙ ሕዝብ ጋር ሆኜ ሁከት ሳነሳሳ አልነበረም። ሆኖም ከእስያ አውራጃ የመጡ አንዳንድ አይሁዳውያን ነበሩ፤ 19  እነሱ እኔን የሚከሱበት ነገር ካላቸው እዚህ ፊትህ ተገኝተው ሊከሱኝ ይገባ ነበር። 20  ወይም እዚህ ያሉት ሰዎች በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት በቀረብኩበት ጊዜ ያገኙብኝ ጥፋት ካለ እነሱ ራሳቸው ይናገሩ፤ 21  በመካከላቸው ቆሜ በነበረበት ጊዜ ድምፄን ከፍ አድርጌ ‘ዛሬ በፊታችሁ ለፍርድ የቀረብኩት በሙታን ትንሣኤ በማመኔ ነው!’ ብዬ ከመናገር በቀር ያደረግኩት ነገር የለም።” 22  ይሁን እንጂ ፊሊክስ ስለ ጌታ መንገድ በሚገባ ያውቅ ስለነበረ “የሠራዊቱ ሻለቃ ሉስዮስ ሲመጣ ለጉዳያችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ” በማለት ያቀረቡትን ክስ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈው። 23  ከዚያም ጳውሎስ በቁጥጥር ሥር እንዲቆይ፣ ይሁንና መጠነኛ ነፃነት እንዲሰጠው መኮንኑን አዘዘው፤ ደግሞም ወዳጆቹ የሚያስፈልገውን ነገር ለማድረግ ሲመጡ እንዲፈቅድላቸው መመሪያ ሰጠው። 24  ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ፊሊክስ አይሁዳዊት ከሆነችው ሚስቱ ከድሩሲላ ጋር መጣ፤ ጳውሎስንም አስጠርቶ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ማመን ሲናገር አዳመጠው። 25  ጳውሎስ ስለ ጽድቅ፣ ራስን ስለ መግዛትና ስለሚመጣው ፍርድ ሲናገር ግን ፊሊክስ ፈርቶ “ለአሁኑ ይበቃል፤ አጋጣሚ ሳገኝ ግን እንደገና አስጠራሃለሁ” አለው። 26  በዚሁ አጋጣሚ ጳውሎስ ጉቦ ይሰጠኛል ብሎ ተስፋ ያደርግ ስለነበር ብዙ ጊዜ እያስጠራ ያነጋግረው ነበር። 27  ይሁንና ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፊሊክስ በጶርቅዮስ ፊስጦስ ተተካ፤ በዚህ ጊዜ ፊሊክስ በአይሁዳውያን ዘንድ ተወዳጅነት ማትረፍ ስለፈለገ ጳውሎስን እንደታሰረ ተወው።
[]
[]
[]
[]
12,350
25  ፊስጦስም ወደ አውራጃው ከመጣና ኃላፊነቱን ከተረከበ ከሦስት ቀን በኋላ ከቂሳርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። 2  የካህናት አለቆችና አንዳንድ የታወቁ አይሁዳውያንም በጳውሎስ ላይ ያላቸውን ክስ ለእሱ አቀረቡ። ከዚያም ፊስጦስን ይለምኑት ጀመር፤ 3  ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም በማስመጣት እንዲተባበራቸው ጠየቁት። ይህን ያሉት ግን መንገድ ላይ አድፍጠው ጳውሎስን ሊገድሉት አስበው ስለነበር ነው። 4  ይሁን እንጂ ፊስጦስ፣ ጳውሎስ እዚያው ቂሳርያ ታስሮ እንደሚቆይና እሱ ራሱም በቅርቡ ወደዚያ እንደሚመለስ ነገራቸው። 5  “በመሆኑም ከእናንተ መካከል ሥልጣን ያላቸው ከእኔ ጋር ይውረዱና ሰውየው ያጠፋው ነገር ካለ ይክሰሱት” አላቸው። 6  ስለዚህ ፊስጦስ ከስምንት ወይም ከአሥር ቀን ያልበለጠ ጊዜ ከእነሱ ጋር ካሳለፈ በኋላ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በማግስቱም በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ። 7  ጳውሎስ በቀረበ ጊዜ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁዳውያን በዙሪያው ቆመው በማስረጃ ያልተደገፉ በርካታ ከባድ ክሶች አቀረቡበት። 8  ጳውሎስ ግን “እኔ በአይሁዳውያን ሕግ ላይም ሆነ በቤተ መቅደሱ ወይም በቄሳር ላይ ምንም የፈጸምኩት በደል የለም” ሲል የመከላከያ መልሱን ሰጠ። 9  ፊስጦስም በአይሁዳውያን ዘንድ ተወዳጅነት ማትረፍ ስለፈለገ ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ እኔ ባለሁበት መዳኘት ትፈልጋለህ?” ሲል ጠየቀው። 10  ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ “እኔ ልዳኝበት በሚገባኝ በቄሳር የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተ ራስህ በሚገባ እንደተገነዘብከው በአይሁዳውያን ላይ የፈጸምኩት ምንም በደል የለም። 11  በእርግጥ ጥፋተኛ ሆኜ ከተገኘሁና ለሞት የሚያበቃ ነገር ፈጽሜ ከሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ ሰዎች ያቀረቡብኝ ክስ ሁሉ መሠረተ ቢስ ከሆነ ግን እነሱን ለማስደሰት ብሎ ማንም ሰው እኔን ለእነሱ አሳልፎ የመስጠት መብት የለውም። ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!” 12  በዚህ ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ከተመካከረ በኋላ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ስላልክ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ” ሲል መለሰለት። 13  የተወሰኑ ቀናት ካለፉ በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ለፊስጦስ ክብር ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ቂሳርያ መጡ። 14  በዚያም ብዙ ቀናት ስለቆዩ ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለንጉሡ በማቅረብ እንዲህ አለው፦ “ፊሊክስ እስር ቤት የተወው አንድ ሰው አለ፤ 15  ኢየሩሳሌም በነበርኩበት ጊዜ የካህናት አለቆቹና የአይሁዳውያን ሽማግሌዎች ይህን ሰው በመክሰስ እንዲፈረድበት ጥያቄ አቅርበው ነበር። 16  እኔ ግን ክስ የቀረበበት ሰው ከከሳሾቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ ለቀረበበት ክስ የመከላከያ መልስ መስጠት የሚችልበት አጋጣሚ ሳያገኝ እንዲሁ ሰውን ለማስደሰት ተብሎ ብቻ አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት እንዳልሆነ ገለጽኩላቸው። 17  ስለዚህ ከሳሾቹ ወደዚህ በመጡ ጊዜ ምንም ሳልዘገይ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጬ ሰውየውን እንዲያመጡት አዘዝኩ። 18  ከሳሾቹም ቆመው በተናገሩ ጊዜ እኔ የጠበቅኩትን ያህል ከባድ በደል እንደፈጸመ የሚያሳይ ክስ አላቀረቡበትም። 19  ከዚህ ይልቅ ከእሱ ጋር ይከራከሩ የነበረው ስለ ገዛ አምልኳቸውና ስለሞተው፣ ጳውሎስ ግን ሕያው ነው ስለሚለው ኢየሱስ ስለተባለ ሰው ነው። 20  እኔም ይህን ክርክር እንዴት እንደምፈታው ግራ ስለገባኝ ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ መፋረድ ይፈልግ እንደሆነ ጠየቅኩት። 21  ጳውሎስ ግን አውግስጦስ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ታስሮ እንዲቆይ ይግባኝ ጠየቀ፤ በመሆኑም ወደ ቄሳር እስከምልከው ድረስ በእስር ቤት እንዲቆይ አዘዝኩ።” 22  በዚህ ጊዜ አግሪጳ ፊስጦስን “እኔም ይህ ሰው ሲናገር ብሰማው ደስ ይለኝ ነበር” አለው። እሱም “እንግዲያውስ ነገ ትሰማዋለህ” አለው። 23  ስለዚህ በማግስቱ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ክብር ደምቀው እንዲሁም በሻለቃዎችና በከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ታጅበው ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ ገቡ፤ ፊስጦስም ትእዛዝ በሰጠ ጊዜ ጳውሎስ እንዲቀርብ ተደረገ። 24  ፊስጦስም እንዲህ አለ፦ “ንጉሥ አግሪጳና ከእኛ ጋር እዚህ የተሰበሰባችሁ ሁሉ፣ ይህ የምታዩት ሰው በኢየሩሳሌምም ሆነ እዚህ፣ አይሁዳውያን ሁሉ ከእንግዲህ በሕይወት ሊኖር አይገባውም እያሉ በመጮኽ ለእኔ አቤቱታ ያቀረቡበት ሰው ነው። 25  እኔ ግን ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር እንዳልፈጸመ ተረድቻለሁ። በመሆኑም እሱ ራሱ ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ ልልከው ወስኛለሁ። 26  ይሁንና ስለ እሱ ወደ ጌታዬ የምጽፈው ምንም የተረጋገጠ ነገር አላገኘሁም። ስለዚህ አሁን በችሎቱ ፊት ከተመረመረ በኋላ ልጽፈው የምችለው ነገር አገኝ ዘንድ በእናንተ ሁሉ ፊት በተለይ ደግሞ በአንተ በንጉሥ አግሪጳ ፊት አቀረብኩት። 27  ምክንያቱም አንድን እስረኛ የተከሰሰበትን ምክንያት ሳይገልጹ መላክ ተገቢ አልመሰለኝም።”
[]
[]
[]
[]
12,351
26  አግሪጳ ጳውሎስን “ስለ ራስህ እንድትናገር ተፈቅዶልሃል” አለው። በዚህ ጊዜ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ እንዲህ ሲል የመከላከያ መልሱን ይሰጥ ጀመር፦ 2  “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ አይሁዳውያን በእኔ ላይ ያቀረቡትን ክስ ሁሉ በተመለከተ ዛሬ በአንተ ፊት የመከላከያ መልስ መስጠት በመቻሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ፤ 3  በተለይ ደግሞ አንተ የአይሁዳውያንን ልማዶችና በመካከላቸው ያሉትን ክርክሮች ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ስለዚህ በትዕግሥት እንድታዳምጠኝ እለምንሃለሁ። 4  “ገና ከልጅነቴ በሕዝቤ መካከልም ሆነ በኢየሩሳሌም እንዴት እንደኖርኩ አይሁዳውያን ሁሉ በሚገባ ያውቃሉ፤ 5  ከድሮ ጀምሮ የሚያውቁኝ ሰዎች ሊመሠክሩ ፈቃደኞች ቢሆኑ ኖሮ በሃይማኖታችን ውስጥ ወግ አጥባቂ የሆነውን ቡድን በመከተል ፈሪሳዊ ሆኜ እንደኖርኩ ያውቃሉ። 6  አሁን ግን እዚህ ለፍርድ የቀረብኩት አምላክ ለአባቶቻችን የገባውን ቃል ተስፋ በማድረጌ ነው፤ 7  ደግሞም 12ቱ ነገዶቻችን ለአምላክ ቀንና ሌሊት በትጋት ቅዱስ አገልግሎት በማቅረብ እየተጠባበቁ ያሉት የዚህኑ ተስፋ ፍጻሜ ነው። ንጉሥ ሆይ፣ አይሁዶች የከሰሱኝ በዚህ ተስፋ ምክንያት ነው። 8  “አምላክ ሙታንን የሚያስነሳ መሆኑ ሊታመን የማይችል ነገር እንደሆነ አድርጋችሁ የምታስቡት ለምንድን ነው? 9  እኔ ራሴ የናዝሬቱ ኢየሱስን ስም በተቻለኝ መጠን መቃወም እንዳለብኝ አምን ነበር። 10  ደግሞም በኢየሩሳሌም ያደረግኩት ይህንኑ ነው፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ ብዙ ቅዱሳንን ወህኒ ቤት አስገብቻለሁ፤ እንዲገደሉም የድጋፍ ድምፅ ሰጥቻለሁ። 11  ብዙ ጊዜም በየምኩራቡ እነሱን እየቀጣሁ እምነታቸውን በይፋ እንዲክዱ ለማስገደድ ሞክሬአለሁ፤ በእነሱ ላይ እጅግ ተቆጥቼ በሌሎች ከተሞች ያሉትን እንኳ ሳይቀር እስከ ማሳደድ ደርሻለሁ። 12  “ይህን እያከናወንኩ በነበረበት ወቅት ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ተልእኮ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ እየተጓዝኩ ሳለ 13  ንጉሥ ሆይ፣ እኩለ ቀን ሲሆን በመንገድ ላይ ከፀሐይ ብርሃን የበለጠ ድምቀት ያለው ከሰማይ የመጣ ብርሃን በእኔና አብረውኝ በሚጓዙት ሰዎች ዙሪያ ሲያበራ አየሁ። 14  ሁላችንም መሬት ላይ በወደቅን ጊዜ አንድ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ‘ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ? መውጊያውን መቃወምህን ከቀጠልክ ለአንተው የባሰ ይሆንብሃል’ ሲለኝ ሰማሁ። 15  እኔም ‘ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?’ አልኩ። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ‘እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። 16  ይሁንና አሁን ተነስተህ በእግርህ ቁም። የተገለጥኩልህ እኔን በተመለከተ ስላየኸው ነገርና ወደፊት ስለማሳይህ ነገር አገልጋይና ምሥክር እንድትሆን አንተን ለመምረጥ ነው። 17  ወደ እነሱ ከምልክህ ከዚህ ሕዝብና ከአሕዛብ እታደግሃለሁ፤ 18  የምልክህም የኃጢአት ይቅርታ ያገኙና በእኔ ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት በተቀደሱት መካከል ርስት ይቀበሉ ዘንድ ዓይናቸውን እንድትገልጥ እንዲሁም ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣን ሥልጣንም ወደ አምላክ እንድትመልሳቸው ነው።’ 19  “በመሆኑም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ከሰማይ ለተገለጠልኝ ራእይ አልታዘዝም አላልኩም፤ 20  ከዚህ ይልቅ በመጀመሪያ በደማስቆ ላሉ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በመላው የይሁዳ አገር ሁሉ ለሚገኙ ከዚያም ለአሕዛብ ንስሐ እንዲገቡና ለንስሐ የሚገባ ሥራ በመሥራት ወደ አምላክ እንዲመለሱ የሚያሳስበውን መልእክት ማዳረሴን ቀጠልኩ። 21  አይሁዳውያኑ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የያዙኝና ሊገድሉኝ የሞከሩት በዚህ የተነሳ ነው። 22  ይሁን እንጂ ከአምላክ እርዳታ በማግኘቴ እስከዚህ ቀን ድረስ ለትንሹም ሆነ ለትልቁ መመሥከሬን ቀጥያለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ ይፈጸማል ብለው ከተናገሩት በስተቀር ምንም የተናገርኩት ነገር የለም፤ 23  እነሱም የተናገሩት ክርስቶስ መከራ እንደሚቀበልና ከሙታን የመጀመሪያ ሆኖ በመነሳት ለዚህ ሕዝብም ሆነ ለአሕዛብ ስለ ብርሃን እንደሚያውጅ ነው።” 24  ጳውሎስ የመከላከያ መልሱን እየሰጠ ሳለ ፊስጦስ ጮክ ብሎ “ጳውሎስ አሁንስ አእምሮህን ልትስት ነው! ብዙ መማር አእምሮህን እያሳተህ ነው!” አለ። 25  ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ “ክቡር ፊስጦስ ሆይ፣ አእምሮዬን እየሳትኩ አይደለም፤ እኔ እየተናገርኩ ያለሁት እውነተኛ እንዲሁም ከጤናማ አእምሮ የሚመነጭ ቃል ነው። 26  እንደ እውነቱ ከሆነ በነፃነት እያናገርኩት ያለሁት ንጉሥ ስለ እነዚህ ነገሮች በሚገባ ያውቃል፤ እነዚህ ነገሮች በድብቅ የተፈጸሙ ባለመሆናቸው አንዳቸውም ቢሆኑ ከእሱ የተሰወሩ እንዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ። 27  ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ በነቢያት ታምናለህ? እንደምታምን አውቃለሁ።” 28  አግሪጳም ጳውሎስን “በአጭር ጊዜ ውስጥ አሳምነህ ክርስቲያን ልታደርገኝ እኮ ምንም አልቀረህም” አለው። 29  በዚህ ጊዜ ጳውሎስ “በአጭርም ሆነ በረጅም ጊዜ አንተ ብቻ ሳትሆን ዛሬ እየሰሙኝ ያሉት ሁሉ ከእስራቴ በስተቀር እንደ እኔ እንዲሆኑ አምላክን እለምናለሁ” አለ። 30  ከዚያም ንጉሡ ተነሳ፤ አገረ ገዢው፣ በርኒቄና አብረዋቸው ተቀምጠው የነበሩት ሰዎችም ተነሱ። 31  እየወጡ ሳሉም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃ ምንም ነገር አላደረገም” ተባባሉ። 32  ከዚያም አግሪጳ ፊስጦስን “ይህ ሰው ወደ ቄሳር ይግባኝ ባይል ኖሮ ሊፈታ ይችል ነበር” አለው።
[]
[]
[]
[]
12,352
27  እኛም በመርከብ ወደ ጣሊያን እንድንሄድ ስለተወሰነ ጳውሎስንና የተወሰኑ እስረኞችን የአውግስጦስ ክፍለ ጦር አባል ለሆነ ዩልዮስ ለሚባል አንድ የጦር መኮንን አስረከቧቸው። 2  ከአድራሚጢስ ተነስቶ በእስያ አውራጃ የባሕር ዳርቻ ላይ ወደሚገኙት ወደቦች ሊሄድ በተዘጋጀ መርከብ ተሳፍረን ጉዞ ጀመርን፤ በተሰሎንቄ የሚኖረው የመቄዶንያው አርስጥሮኮስም አብሮን ነበር። 3  በማግስቱ ሲዶና ደረስን፤ ዩልዮስም ለጳውሎስ ደግነት በማሳየት ወደ ወዳጆቹ እንዲሄድና እንክብካቤ እንዲያደርጉለት ፈቀደለት። 4  ከዚያም ተነስተን በባሕር ላይ ጉዟችንን ቀጠልን፤ ነፋሱ ከፊት ለፊታችን ይነፍስ ስለነበር ቆጵሮስን ተገን አድርገን አለፍን። 5  ከዚያም በኪልቅያና በጵንፍልያ ዳርቻ በኩል ያለውን ባሕር አቋርጠን በሊቂያ ወደሚገኘው የሚራ ወደብ ደረስን። 6  በዚያም መኮንኑ ወደ ጣሊያን የሚሄድ ከእስክንድርያ የመጣ መርከብ አግኝቶ አሳፈረን። 7  ከዚያም ለብዙ ቀናት በዝግታ ተጉዘን በስንት ችግር ቀኒዶስ ደረስን። ነፋሱ እንደ ልብ እንድንጓዝ ስላልፈቀደልን በስልሞና በኩል ቀርጤስን ተገን አድርገን አለፍን። 8  የባሕሩን ዳርቻ ይዘን በብዙ ችግር በመጓዝ በላሲያ ከተማ አቅራቢያ ወዳለው “መልካም ወደብ” ወደተባለ ስፍራ ደረስን። 9  ረጅም ጊዜ በመቆየታችንና የስርየት ቀን ጾም እንኳ ሳይቀር በማለፉ፣ ወቅቱ በባሕር ላይ ለመጓዝ አደገኛ ነበር፤ በመሆኑም ጳውሎስ አንድ ሐሳብ አቀረበ፤ 10  እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ሰዎች፣ ይህ ጉዞ በጭነቱና በመርከቡ ላይ ብቻ ሳይሆን በሕይወታችንም ላይ እንኳ ሳይቀር ከፍተኛ ጉዳትና ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል ይታየኛል።” 11  ይሁን እንጂ መኮንኑ ጳውሎስ የተናገረውን ከመቀበል ይልቅ የመርከቡ መሪና የመርከቡ ባለቤት የተናገሩትን ሰማ። 12  ወደቡ የክረምቱን ጊዜ በዚያ ለማሳለፍ አመቺ ስላልነበረ አብዛኞቹ ከዚያ ተነስተው ጉዟቸውን በመቀጠል እንደ ምንም ፊንቄ ወደተባለው የቀርጤስ ወደብ ደርሰው ክረምቱን እዚያ ለማሳለፍ ሐሳብ አቀረቡ፤ ይህ ወደብ ወደ ሰሜን ምሥራቅም ሆነ ወደ ደቡብ ምሥራቅ ለመሄድ የሚያስችል ነበር። 13  የደቡብ ነፋስ በቀስታ እየነፈሰ እንዳለ ባዩ ጊዜ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሏቸው መልሕቁን ነቅለው የቀርጤስን የባሕር ዳርቻ ይዘው መጓዝ ጀመሩ። 14  ይሁንና ብዙም ሳይቆይ አውራቂስ የሚባል ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ከደሴቲቱ ቁልቁል ነፈሰ። 15  መርከቡ እንቅስቃሴው ስለተገታና ነፋሱን ሰንጥቆ መሄድ ስላልቻለ ዝም ብለን በነፋሱ እየተነዳን ሄድን። 16  ከዚያም ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተገን አድርገን በፍጥነት ተጓዝን፤ ሆኖም በመርከቡ ኋለኛ ክፍል የነበረችውን ትንሿን ጀልባ መቆጣጠር የቻልነው በብዙ ችግር ነበር። 17  ጀልባዋ ወደ ላይ ተጎትታ ከተጫነች በኋላ መርከቡን ዙሪያውን በማሰር አጠናከሩት፤ ከስርቲስ አሸዋማ ደለል ጋር እንዳይላተሙ ስለፈሩም የሸራውን ገመዶች በመፍታት ሸራውን ዝቅ ካደረጉ በኋላ በነፋስ እየተነዱ ሄዱ። 18  አውሎ ነፋሱ ክፉኛ እያንገላታን ስለነበር በማግስቱ የመርከቡን ጭነት ያቃልሉ ጀመር። 19  በሦስተኛውም ቀን ለመርከቡ የሚያገለግሉትን ቁሳቁሶች በገዛ እጃቸው ወደ ባሕሩ ወረወሩ። 20  ለብዙ ቀናት ፀሐይንም ሆነ ከዋክብትን ማየት ስላልቻልንና ውሽንፍሩ ስለበረታብን በመጨረሻ በሕይወት የመትረፍ ተስፋችን እየተሟጠጠ ሄደ። 21  ሰዎቹ እህል ሳይቀምሱ ብዙ ቀን ከቆዩ በኋላ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሰዎች፣ ምክሬን ሰምታችሁ ቢሆን ኖሮ ከቀርጤስ ባልተነሳችሁና ይህ ጉዳትና ኪሳራ ባልደረሰ ነበር። 22  አሁንም ቢሆን አይዟችሁ! ምክንያቱም መርከቡ ብቻ እንጂ ከእናንተ አንድም ሰው አይጠፋም። 23  ቅዱስ አገልግሎት የማቀርብለትና ንብረቱ የሆንኩለት አምላክ የላከው መልአክ ትናንት ሌሊት አጠገቤ ቆሞ 24  ‘ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ። ቄሳር ፊት መቅረብ ይገባሃል፤ አምላክ ለአንተ ሲል ከአንተ ጋር የሚጓዙት ሰዎች ሁሉ እንዲተርፉ ያደርጋል’ ብሎኛል። 25  ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ አይዟችሁ! ምክንያቱም ይህ የተነገረኝ ነገር በትክክል እንደሚፈጸም በአምላክ ላይ እምነት አለኝ። 26  ይሁን እንጂ ከአንዲት ደሴት ዳርቻ ጋር መላተማችን የግድ ነው።” 27  በ14ኛው ሌሊት በአድርያ ባሕር ላይ ወዲያና ወዲህ እየተንገላታን ሳለ እኩለ ሌሊት ላይ መርከበኞቹ ወደ አንድ የብስ የተቃረቡ መሰላቸው። 28  ጥልቀቱንም ሲለኩ 36 ሜትር ገደማ ሆኖ አገኙት፤ ጥቂት ርቀት ከተጓዙም በኋላ በድጋሚ ሲለኩ 27 ሜትር ገደማ ሆኖ አገኙት። 29  ከዓለት ጋር እንላተማለን ብለው ስለፈሩ ከመርከቡ የኋለኛ ክፍል አራት መልሕቆች ጥለው የሚነጋበትን ጊዜ በጉጉት መጠባበቅ ጀመሩ። 30  ሆኖም መርከበኞቹ ከመርከቡ የፊተኛ ክፍል መልሕቅ የሚጥሉ አስመስለው ትንሿን ጀልባ ወደ ባሕር በማውረድ ከመርከቡ ለማምለጥ ሲሞክሩ 31  ጳውሎስ መኮንኑንና ወታደሮቹን “እነዚህ ሰዎች መርከቡን ጥለው ከሄዱ ልትድኑ አትችሉም” አላቸው። 32  በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ የትንሿን ጀልባ ገመዶች ቆርጠው ብቻዋን ተንሳፋ እንድትቀር አደረጓት። 33  ሊነጋ ሲል ጳውሎስ እንዲህ በማለት ምግብ እንዲቀምሱ ሁሉንም አበረታታቸው፦ “እህል የሚባል ነገር ሳትቀምሱ እንዲሁ ልባችሁ ተንጠልጥሎ ስትጠባበቁ ይኸው ዛሬ 14ኛ ቀናችሁ ነው። 34  ስለዚህ ለራሳችሁ ደህንነት ስለሚበጅ እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋለሁ፤ ምክንያቱም ከእናንተ መካከል ከራስ ፀጉሩ አንድ እንኳ የሚጠፋበት የለም።” 35  ይህን ካለ በኋላ ዳቦ ወስዶ በሁሉ ፊት አምላክን አመሰገነ፤ ቆርሶም ይበላ ጀመር። 36  በዚህ ጊዜ ሁሉም ተበረታተው ምግብ እየወሰዱ ይበሉ ጀመር። 37  መርከቡ ላይ በአጠቃላይ 276 ሰዎች ነበርን። 38  በልተው ከጠገቡ በኋላ ስንዴውን ወደ ባሕሩ በመጣል የመርከቡን ጭነት አቃለሉ። 39  ሲነጋም የደረሱበትን አገር ለይተው ማወቅ አልቻሉም፤ ሆኖም አሸዋማ የሆነ የባሕር ወሽመጥ ተመለከቱ፤ ስለዚህ እንደ ምንም ብለው መርከቡን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለማድረስ ወሰኑ። 40  በመሆኑም መልሕቆቹን ቆርጠው ባሕሩ ውስጥ ጣሉ፤ በዚያው ጊዜም የመቅዘፊያዎቹን ገመዶች ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ነፋስ እንዲያገኘው ከፍ ካደረጉ በኋላ ወደ ባሕሩ ዳርቻ አመሩ። 41  ሆኖም ድንገት በባሕር ውስጥ ካለ የአሸዋ ቁልል ጋር ተላተሙ፤ በዚህ ጊዜ መርከቡ መሬት ስለነካ የፊተኛው ክፍሉ ሊንቀሳቀስ በማይችል ሁኔታ አሸዋው ውስጥ ተቀረቀረ፤ የመርከቡ የኋለኛ ክፍል ግን በማዕበል እየተመታ ይሰባበር ጀመር። 42  በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ ከእስረኞቹ አንዳቸውም እንኳ ዋኝተው እንዳያመልጡ ሊገድሏቸው ወሰኑ። 43  መኮንኑ ግን ጳውሎስን ለማዳን ቆርጦ ስለነበር ያሰቡትን እንዳይፈጽሙ ከለከላቸው። ከዚያም መዋኘት የሚችሉ ወደ ባሕሩ እየዘለሉ እንዲገቡና ቀድመው ወደ የብስ እንዲደርሱ አዘዘ፤ 44  የቀሩትም ሰዎች አንዳንዶቹ በሳንቃዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ በመርከቡ ስብርባሪዎች ላይ እየተንጠላጠሉ እንዲወጡ አዘዘ። በዚህ መንገድ ሁሉም በደህና ወደ የብስ ደረሱ።
[]
[]
[]
[]
12,353
28  እኛም በደህና ወደ የብስ ደረስን፤ ደሴቲቱም ማልታ ተብላ እንደምትጠራ አወቅን። 2  የአካባቢው ነዋሪዎችም የተለየ ደግነት አሳዩን። ዝናብ መዝነብ ጀምሮ ስለነበረና ብርድ ስለነበር እሳት በማቀጣጠል ሁላችንንም በደግነት አስተናገዱን። 3  ይሁን እንጂ ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ እሳቱ ውስጥ ሲጨምር ከሙቀቱ የተነሳ እፉኝት ወጥታ እጁ ላይ ተጣበቀች። 4  ባዕድ ቋንቋ የሚናገሩትም ሰዎች እፉኝቷ እጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ መሆን አለበት፤ ከባሕሩ ተርፎ በደህና ቢወጣም እንኳ ፍትሕ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ይባባሉ ጀመር። 5  እሱ ግን እፉኝቷን እሳቱ ላይ አራገፋት፤ አንዳችም ጉዳት አልደረሰበትም። 6  ሆኖም ሰዎቹ ከአሁን አሁን ሰውነቱ ያብጣል ወይም ድንገት ወድቆ ይሞታል ብለው ይጠባበቁ ነበር። ብዙ ጠብቀው ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት ባዩ ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ይህ ሰው አምላክ ነው ይሉ ጀመር። 7  በዚያ አካባቢ፣ ፑፕልዮስ የተባለ የደሴቲቱ አስተዳዳሪ ርስት ነበረው፤ እሱም በእንግድነት ተቀብሎን ሦስት ቀን በደግነት አስተናገደን። 8  የፑፕልዮስ አባት ትኩሳትና ተቅማጥ ይዞት ተኝቶ ነበር፤ ጳውሎስም ወደ እሱ ገብቶ ጸለየለት፤ እጁንም ጫነበትና ፈወሰው። 9  ይህ ከሆነ በኋላ በደሴቲቱ የሚኖሩ የታመሙ ሌሎች ሰዎችም ወደ እሱ እየመጡ ይፈወሱ ጀመር። 10  በተጨማሪም ብዙ ስጦታ በመስጠት አክብሮታቸውን ገለጹልን፤ በመርከብ ለመሄድ በተዘጋጀን ጊዜም የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሁሉ ጫኑልን። 11  ከሦስት ወር በኋላም “የዙስ ልጆች” የሚል ዓርማ ባለው መርከብ ጉዞ ጀመርን። ይህ መርከብ ከእስክንድርያ የመጣ ሲሆን ክረምቱን ያሳለፈው በዚህች ደሴት ነበር። 12  በስራኩስ ወደሚገኘው ወደብ ከደረስን በኋላ በዚያ ሦስት ቀን ቆየን፤ 13  ከዚያም ተነስተን በመጓዝ ሬጊዩም ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላም የደቡብ ነፋስ ስለተነሳ በሁለተኛው ቀን ፑቲዮሉስ ደረስን። 14  በዚያም ወንድሞችን አገኘን፤ እነሱም ሰባት ቀን አብረናቸው እንድንቆይ ለመኑን፤ እነሱ ጋር ከቆየን በኋላ ወደ ሮም አመራን። 15  በዚያ የነበሩ ወንድሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ እስከ አፍዩስ የገበያ ስፍራና ሦስት ማደሪያ እስከሚባለው ቦታ ድረስ ሊቀበሉን መጡ። ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ አምላክን አመሰገነ፤ እንዲሁም ተበረታታ። 16  በመጨረሻም ሮም በደረስን ጊዜ ጳውሎስ አንድ ወታደር እየጠበቀው ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት። 17  ይሁን እንጂ ከሦስት ቀን በኋላ የአይሁዳውያንን ታላላቅ ሰዎች አንድ ላይ ጠራ። ሰዎቹም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ ምንም እንኳ ሕዝቡን ወይም የአባቶቻችንን ልማድ የሚጻረር ነገር ያልፈጸምኩ ቢሆንም በኢየሩሳሌም አስረው ለሮማውያን አሳልፈው ሰጥተውኛል። 18  እነሱም ከመረመሩኝ በኋላ ለሞት የሚያበቃ ምንም ጥፋት ስላላገኙብኝ ሊፈቱኝ ፈልገው ነበር። 19  ሆኖም አይሁዳውያን ይህን በተቃወሙ ጊዜ ለቄሳር ይግባኝ ለማለት ተገደድኩ፤ ይህን ያደረግኩት ግን ሕዝቤን የምከስበት ነገር ኖሮኝ አይደለም። 20  እናንተንም ለማየትና ለማነጋገር ጥያቄ ያቀረብኩት ለዚህ ነው፤ በዚህ ሰንሰለት የታሰርኩትም ለእስራኤል በተሰጠው ተስፋ ምክንያት ነው።” 21  እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ስለ አንተ የተጻፈ ከይሁዳ የመጣ ምንም ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከዚያ ከመጡት ወንድሞች መካከልም ስለ አንተ ክፉ ነገር የተናገረ ወይም ያወራ አንድም ሰው የለም። 22  ሆኖም ስለዚህ ኑፋቄ በየቦታው መጥፎ ነገር እንደሚወራ ስለምናውቅ የአንተን ሐሳብ ደግሞ መስማት ተገቢ ይመስለናል።” 23  በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ከእሱ ጋር ቀን ከወሰኑ በኋላ ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያ ስፍራው መጡ። እሱም በኢየሱስ እንዲያምኑ ለማድረግ ከሙሴ ሕግና ከነቢያት እየጠቀሰ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ በመመሥከር ጉዳዩን አብራራላቸው። 24  አንዳንዶቹ የተናገረውን ነገር ሲያምኑ ሌሎቹ ግን አላመኑም። 25  እርስ በርስ ሊስማሙ ስላልቻሉም ለመሄድ ተነሱ፤ በዚህ ጊዜ ጳውሎስ የሚከተለውን የመጨረሻ ሐሳብ ተናገረ፦ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ለአባቶቻችሁ እንዲህ ሲል የተናገረው ቃል ትክክል ነበር፦ 26  ‘ወደዚህ ሕዝብ ሄደህ እንዲህ በላቸው፦ “መስማቱን ትሰማላችሁ፤ ግን በፍጹም አታስተውሉም፤ ማየቱን ታያላችሁ፤ ግን በፍጹም ልብ አትሉም። 27  ምክንያቱም በዓይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው እንዲሁም በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል፤ በጆሯቸው ሰምተው ምላሽ አልሰጡም፤ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል።”’ 28  ስለዚህ አምላክ ሰዎችን ስለሚያድንበት መንገድ የሚናገረው ይህ መልእክት ለአሕዛብ እንደተላከ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤ እነሱም በእርግጥ ይሰሙታል።” 29  —— 30  ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ኖረ፤ ወደ እሱ የሚመጡትንም ሁሉ በደግነት ያስተናግዳቸው ነበር፤ 31  ያለምንም እንቅፋት በታላቅ የመናገር ነፃነት ስለ አምላክ መንግሥት ይሰብክላቸው የነበረ ከመሆኑም በላይ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተምራቸው ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,354
3  አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ሰዓት ይኸውም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደሱ እየወጡ ነበር፤ 2  ሰዎችም ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ተሸክመው በማምጣት ወደ ቤተ መቅደሱ ከሚገባው ሰው ምጽዋት እንዲለምን “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደሱ በር አጠገብ በየዕለቱ ያስቀምጡት ነበር። 3  ይህ ሰው ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሊገቡ ሲሉ አያቸውና ምጽዋት እንዲሰጡት ይለምናቸው ጀመር። 4  ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን ትኩር ብለው አዩት፤ ከዚያም ጴጥሮስ “ወደ እኛ ተመልከት” አለው። 5  ሰውየውም የሆነ ነገር ሊሰጡኝ ነው ብሎ በማሰብ ትኩር ብሎ ተመለከታቸው። 6  ይሁንና ጴጥሮስ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ። በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነስና ተራመድ!” አለው። 7  ከዚያም ቀኝ እጁን ይዞ አስነሳው። ወዲያውም እግሩና ቁርጭምጭሚቱ ጠነከረ፤ 8  ዘሎም ተነሳ፤ መራመድም ጀመረ፤ ደግሞም እየተራመደና እየዘለለ እንዲሁም አምላክን እያወደሰ ከእነሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ። 9  ሰዎቹም ሁሉ ሲራመድና አምላክን ሲያወድስ አዩት። 10  ይህ ሰው “ውብ በር” በተባለው የቤተ መቅደሱ መግቢያ አጠገብ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው ሰው መሆኑን ስላወቁ በእሱ ላይ በተፈጸመው ሁኔታ እጅግ ተገረሙ፤ በአድናቆትም ተዋጡ። 11  ሰውየው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዟቸው ሳለ በዚያ የነበሩት ሰዎች ሁሉ እጅግ ተደንቀው እነሱ ወዳሉበት “የሰለሞን መተላለፊያ” ወደሚባለው ስፍራ ግር ብለው እየሮጡ መጡ። 12  ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ ሰዎቹን እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በዚህ ለምን ትደነቃላችሁ? ደግሞስ በእኛ ኃይል ወይም እኛ ለአምላክ ያደርን በመሆናችን የተነሳ ይህን ሰው እንዲራመድ ያስቻልነው ይመስል ለምን ትኩር ብላችሁ ታዩናላችሁ? 13  የአባቶቻችን አምላክ ይኸውም የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ጲላጦስ ሊፈታው ወስኖ የነበረ ቢሆንም በእሱ ፊት የካዳችሁትን አገልጋዩን ኢየሱስን አከበረው። 14  አዎ፣ እናንተ ይህን ቅዱስና ጻድቅ ሰው ክዳችሁ ነፍሰ ገዳይ የሆነን ሰው እንዲፈታላችሁ ጠየቃችሁ፤ 15  በአንጻሩ ግን የሕይወትን “ዋና ወኪል” ገደላችሁት። አምላክ ግን ከሞት አስነሳው፤ እኛም ለዚህ ነገር ምሥክሮች ነን። 16  የኢየሱስ ስምና እኛ በስሙ ላይ ያለን እምነት ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን ሰው አጠነከረው። በኢየሱስ አማካኝነት ያገኘነው እምነት ይህ ሰው በሁላችሁም ፊት ፍጹም ጤናማ እንዲሆን አደረገው። 17  አሁንም ወንድሞች፣ ገዢዎቻችሁ እንዳደረጉት ሁሉ እናንተም ይህን ያደረጋችሁት ባለማወቅ እንደሆነ አውቃለሁ። 18  ይሁንና አምላክ፣ ክርስቶስ መከራ እንደሚቀበል በነቢያት ሁሉ አፍ አስቀድሞ ያሳወቀው ነገር በዚህ መንገድ እንዲፈጸም አድርጓል። 19  “ስለዚህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሐ ግቡ፣ ተመለሱም፤ ከይሖዋም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ 20  እንዲሁም ለእናንተ የሾመውን ክርስቶስን ይኸውም ኢየሱስን ይልክላችኋል። 21  እሱም አምላክ በጥንቶቹ ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገራቸው ነገሮች ሁሉ የሚታደሱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ በሰማይ መቆየት ይገባዋል። 22  ደግሞም ሙሴ እንዲህ ብሏል፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል። እሱ የሚነግራችሁንም ነገር ሁሉ ስሙ። 23  ያንን ነቢይ የማይሰማ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።’ 24  ከሳሙኤል ጀምሮ በተከታታይ የተነሱት ነቢያት ሁሉ ስለ እነዚህ ቀናት በግልጽ ተናግረዋል። 25  እናንተ የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እንዲሁም አምላክ ለአብርሃም ‘የምድር ቤተሰቦች ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ይባረካሉ’ ብሎ ከአባቶቻችሁ ጋር የገባው ቃል ኪዳን ወራሾች ናችሁ። 26  አምላክ አገልጋዩን ካስነሳ በኋላ እያንዳንዳችሁን ከክፉ ሥራችሁ በመመለስ ይባርካችሁ ዘንድ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው።”
[]
[]
[]
[]
12,355
4  ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ እየተናገሩ ሳሉ ካህናቱ፣ የቤተ መቅደሱ ሹምና ሰዱቃውያን ድንገት ወደ እነሱ መጡ። 2  እነሱም ሐዋርያቱ ሕዝቡን እያስተማሩና ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ በግልጽ እየተናገሩ ስለነበር እጅግ ተቆጡ። 3  በመሆኑም ያዟቸው፤ መሽቶም ስለነበር እስከ ማግስቱ ድረስ እስር ቤት አቆዩአቸው። 4  ይሁን እንጂ ንግግሩን ሰምተው ከነበሩት መካከል ብዙዎቹ አመኑ፤ የወንዶቹም ቁጥር 5,000 ገደማ ሆነ። 5  በማግስቱም የሕዝቡ ገዢዎች፣ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ 6  የካህናት አለቃው ሐና፣ ቀያፋ፣ ዮሐንስ፣ እስክንድርና የካህናት አለቃው ዘመዶችም ሁሉ ከእነሱ ጋር ነበሩ። 7  ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከላቸው አቁመው “ይህን ያደረጋችሁት በምን ሥልጣን ወይም በማን ስም ነው?” ብለው ጠየቋቸው። 8  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሕዝቡ ገዢዎችና ሽማግሌዎች፣ 9  ዛሬ በእኛ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ያለው ለአንድ ሽባ ሰው በተደረገ መልካም ሥራ የተነሳ ከሆነና ይህን ሰው ያዳነው ማን እንደሆነ ማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ፣ 10  ይህ ሰው ጤናማ ሆኖ እዚህ ፊታችሁ የቆመው፣ እናንተ በእንጨት ላይ በሰቀላችሁት ሆኖም አምላክ ከሞት ባስነሳው በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ይኸውም በኢየሱስ አማካኝነት እንደሆነ እናንተም ሆናችሁ መላው የእስራኤል ሕዝብ ይወቅ። 11  ‘እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፣ የማዕዘን ራስ የሆነው ድንጋይ’ እሱ ነው። 12  ደግሞም መዳን በሌላ በማንም አይገኝም፤ ምክንያቱም ልንድንበት የምንችል ከሰማይ በታች ለሰዎች የተሰጠ ሌላ ስም የለም።” 13  ሰዎቹ ጴጥሮስና ዮሐንስ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ ያልተማሩና ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ። ከኢየሱስ ጋር እንደነበሩም ተገነዘቡ። 14  የተፈወሰውንም ሰው ከእነሱ ጋር ቆሞ ሲያዩት ምንም መልስ መስጠት አልቻሉም። 15  ስለዚህ ከሳንሄድሪን ሸንጎ አዳራሽ እንዲወጡ አዘዟቸው፤ ከዚያም እርስ በርሳቸው ይማከሩ ጀመር፤ 16  እንዲህም ተባባሉ፦ “እነዚህን ሰዎች ምን ብናደርጋቸው ይሻላል? ምክንያቱም በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ የታወቀ አስደናቂ ነገር እንደፈጸሙ የማይታበል ሐቅ ነው፤ ይህን ደግሞ ልንክድ አንችልም። 17  ይሁንና ይህ ነገር በሕዝቡ መካከል ይበልጥ እንዳይስፋፋ ከዚህ በኋላ በዚህ ስም ለማንም ሰው እንዳይናገሩ በማሳሰብ እናስፈራራቸው።” 18  ከዚያም ጠርተዋቸው በኢየሱስ ስም ፈጽሞ እንዳይናገሩ ወይም እንዳያስተምሩ አዘዟቸው። 19  ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው እንዲህ አሏቸው፦ “አምላክን ከመስማት ይልቅ እናንተን መስማት በአምላክ ፊት ተገቢ እንደሆነና እንዳልሆነ እስቲ እናንተው ፍረዱ። 20  እኛ ግን ስላየነውና ስለሰማነው ነገር ከመናገር ወደኋላ ማለት አንችልም።” 21  በመሆኑም እንደገና ካስፈራሯቸው በኋላ ለቀቋቸው፤ ይህን ያደረጉት እነሱን ለመቅጣት የሚያስችል ምንም ተጨባጭ ነገር ስላላገኙና ሕዝቡን ስለፈሩ ነው፤ ምክንያቱም ሕዝቡ ሁሉ በተፈጸመው ሁኔታ አምላክን እያከበረ ነበር። 22  በዚህ ተአምር የተፈወሰውም ሰው ዕድሜው ከ40 ዓመት በላይ ነበር። 23  ከተለቀቁ በኋላ ወደ ወንድሞቻቸው ሄደው የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ ያሏቸውን ሁሉ ነገሯቸው። 24  እነሱም ይህን በሰሙ ጊዜ በአንድ ልብ ሆነው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እንዲህ ሲሉ ወደ አምላክ ጸለዩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ሆይ፣ ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ የፈጠርክ አንተ ነህ፤ 25  በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለሃል፦ ‘ብሔራት ለምን ታወኩ? ሕዝቦችስ ለምን ከንቱ ነገር ያውጠነጥናሉ? 26  የምድር ነገሥታት ተሰለፉ፤ ገዢዎችም በአንድነት ተሰብስበው በይሖዋና እሱ በቀባው ላይ ተነሱ።’ 27  በእርግጥም ሄሮድስና ጳንጥዮስ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው አንተ በቀባኸው በቅዱስ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሱ፤ 28  ይህም የሆነው እጅህና ፈቃድህ አስቀድመው የወሰኑት እንዲፈጸም ነው። 29  አሁንም ይሖዋ ሆይ፣ ዛቻቸውን ተመልከት፤ ባሪያዎችህም ቃልህን በፍጹም ድፍረት መናገራቸውን እንዲቀጥሉ እርዳቸው፤ 30  ለመፈወስም የዘረጋኸውን እጅህን አትጠፍ፤ በቅዱስ አገልጋይህ በኢየሱስ ስም ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ማድረግህንም ቀጥል።” 31  ምልጃ ካቀረቡም በኋላ ተሰብስበውበት የነበረው ቦታ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው የአምላክን ቃል በድፍረት መናገር ጀመሩ። 32  በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር የነበራቸው ያመኑት ሰዎች አንድ ልብና ነፍስ ነበራቸው፤ አንዳቸውም ቢሆኑ ያላቸው ማንኛውም ንብረት የግላቸው እንደሆነ አድርገው አይቆጥሩም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ያላቸው ነገር ሁሉ የጋራ ነበር። 33  ደግሞም ሐዋርያቱ ስለ ጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ በታላቅ ኃይል መመሥከራቸውን ቀጠሉ፤ ሁሉም የአምላክን ታላቅ ጸጋ አግኝተው ነበር። 34  ከመካከላቸውም አንድም ችግረኛ አልነበረም፤ ምክንያቱም መሬት ወይም ቤት የነበራቸው ሁሉ እየሸጡ ገንዘቡን በማምጣት 35  ለሐዋርያት ያስረክቡ ነበር። ከዚያም ለእያንዳንዱ ሰው በሚያስፈልገው መጠን ይከፋፈል ነበር። 36  የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበር፤ ሐዋርያት በርናባስ ብለውም ይጠሩት የነበረ ሲሆን ትርጉሙም “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው፤ 37  እሱም መሬት ስለነበረው መሬቱን ሸጦ ገንዘቡን በማምጣት ለሐዋርያት አስረከበ።
[]
[]
[]
[]
12,356
5  ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው ከሚስቱ ከሰጲራ ጋር መሬት ሸጠ። 2  ይሁንና ከገንዘቡ የተወሰነውን ደብቆ አስቀረ፤ ሚስቱም ይህን ታውቅ ነበር፤ የቀረውንም አምጥቶ ለሐዋርያት አስረከበ። 3  ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለ፦ “ሐናንያ፣ ሰይጣን መንፈስ ቅዱስን እንድትዋሽና ከመሬቱ ሽያጭ የተወሰነውን ደብቀህ እንድታስቀር ያደፋፈረህ ለምንድን ነው? 4  ሳትሸጠው በፊት ያንተው አልነበረም? ከሸጥከውስ በኋላ ገንዘቡን የፈለግከውን ልታደርግበት ትችል አልነበረም? እንዲህ ያለ ድርጊት ለመፈጸም በልብህ ለምን አሰብክ? የዋሸኸው ሰውን ሳይሆን አምላክን ነው።” 5  ሐናንያ ይህን ቃል ሲሰማ ወደቀና ሞተ። ይህን የሰሙ ሁሉ እጅግ ፈሩ። 6  ወጣት ወንዶችም ተነስተው በጨርቅ ከጠቀለሉት በኋላ ተሸክመው አውጥተው ቀበሩት። 7  ይህ ከሆነ ከሦስት ሰዓት ገደማ በኋላ ደግሞ የተፈጸመውን ነገር ያላወቀችው ሚስቱ መጣች። 8  ጴጥሮስም “እስቲ ንገሪኝ፣ መሬቱን የሸጣችሁት በዚህ ዋጋ ነው?” አላት። እሷም “አዎ፣ በዚሁ ዋጋ ነው” አለች። 9  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ሁለታችሁ የይሖዋን መንፈስ ለመፈተን የተስማማችሁት ለምንድን ነው? እነሆ፣ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር ደጃፍ ላይ ነው፤ እነሱም ተሸክመው ያወጡሻል” አላት። 10  ወዲያውም እግሩ ሥር ወድቃ ሞተች። ወጣቶቹ ሲገቡም ሞታ አገኟት፤ ተሸክመው አውጥተውም ከባሏ አጠገብ ቀበሯት። 11  በመሆኑም መላው ጉባኤ እንዲሁም ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ በከፍተኛ ፍርሃት ተዋጡ። 12  በተጨማሪም ሐዋርያት በሕዝቡ መካከል ብዙ ተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች መፈጸማቸውን ቀጥለው ነበር፤ ሁሉም አንድ ላይ ሆነው መጠለያ ባለው “የሰለሞን መተላለፊያ” ይሰበሰቡ ነበር። 13  እርግጥ ከሌሎቹ መካከል ከእነሱ ጋር ሊቀላቀል የደፈረ አንድም ሰው አልነበረም፤ ሆኖም ሕዝቡ ያሞግሳቸው ነበር። 14  ከዚህም በላይ በጌታ ያመኑ እጅግ በርካታ ወንዶችና ሴቶች በየጊዜው በእነሱ ላይ ይጨመሩ ነበር። 15  ደግሞም ጴጥሮስ በዚያ ሲያልፍ በአንዳንዶቹ ላይ ቢያንስ ጥላው ቢያርፍባቸው በማለት ሕመምተኞችን አውራ ጎዳናዎች ላይ አውጥተው በትናንሽ አልጋዎችና በምንጣፎች ላይ ያስተኟቸው ነበር። 16  በተጨማሪም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ ከተሞች ብዙ ሰዎች ሕመምተኞችንና በርኩሳን መናፍስት የሚሠቃዩ ሰዎችን ተሸክመው መምጣታቸውን ቀጠሉ፤ የመጡትም ሁሉ ይፈወሱ ነበር። 17  ይሁንና ሊቀ ካህናቱና አብረውት የነበሩት የሰዱቃውያን ሃይማኖታዊ ቡድን አባላት ሁሉ በቅናት ተሞልተው ተነሱ። 18  ሐዋርያትንም ይዘው እስር ቤት ከተቷቸው። 19  ይሁን እንጂ ሌሊት የይሖዋ መልአክ የእስር ቤቱን በሮች ከፍቶ አወጣቸውና እንዲህ አላቸው፦ 20  “ሂዱና በቤተ መቅደሱ ቆማችሁ ስለዚህ ሕይወት የሚገልጸውን ቃል ሁሉ ለሕዝቡ መናገራችሁን ቀጥሉ።” 21  እነሱም በተነገራቸው መሠረት ንጋት ላይ ወደ ቤተ መቅደሱ ገብተው ያስተምሩ ጀመር። ሊቀ ካህናቱና ከእሱ ጋር የነበሩት በመጡ ጊዜም የሳንሄድሪንን ሸንጎና መላውን የእስራኤል ልጆች ሽማግሌዎች ጉባኤ በአንድነት ሰበሰቡ፤ ሐዋርያቱንም ወደ እነሱ እንዲያመጧቸው ሰዎችን ወደ እስር ቤቱ ላኩ። 22  የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች እዚያ በደረሱ ጊዜ ግን እስር ቤቱ ውስጥ አላገኟቸውም። ስለዚህ ተመልሰው መጥተው ነገሯቸው፤ 23  እንዲህም አሏቸው፦ “እስር ቤቱ በሚገባ ተቆልፎ ጠባቂዎቹም በሮቹ ላይ ቆመው አገኘናቸው፤ በሮቹን ስንከፍት ግን ውስጥ ማንንም አላገኘንም።” 24  የቤተ መቅደሱ ሹምና የካህናት አለቆቹም ይህን ሲሰሙ ‘የዚህ ነገር መጨረሻ ምን ይሆን?’ በማለት በነገሩ ግራ ተጋቡ። 25  በዚህ ጊዜ አንድ ሰው መጥቶ “እስር ቤት ያስገባችኋቸው ሰዎች በቤተ መቅደሱ ቆመው ሕዝቡን እያስተማሩ ነው” ብሎ ነገራቸው። 26  ከዚያም የቤተ መቅደሱ ሹም ከጠባቂዎቹ ጋር ሄዶ አመጣቸው፤ ሆኖም ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግራቸው ስለፈሩ ያመጧቸው በኃይል አስገድደው አልነበረም። 27  አምጥተውም በሳንሄድሪን ሸንጎ ፊት አቆሟቸው። ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ይጠይቃቸው ጀመር፤ 28  እንዲህም አለ፦ “በዚህ ስም ማስተማራችሁን እንድታቆሙ በጥብቅ አዘናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋታል፤ የዚህንም ሰው ደም በእኛ ላይ ለማምጣት ቆርጣችሁ ተነስታችኋል።” 29  ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዢያችን አድርገን ልንታዘዝ ይገባል። 30  እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሳው። 31  እስራኤል ንስሐ እንዲገባና የኃጢአት ይቅርታ እንዲያገኝ አምላክ እሱን “ዋና ወኪል” እና “አዳኝ” አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው። 32  ለዚህም ጉዳይ እኛ ምሥክሮች ነን፤ እንዲሁም አምላክ እሱን እንደ ገዢያቸው አድርገው ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምሥክር ነው።” 33  እነሱም ይህን ሲሰሙ እጅግ ተቆጡ፤ ሊገድሏቸውም ፈለጉ። 34  ሆኖም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የተከበረ፣ የሕግ አስተማሪ የሆነ ገማልያል የሚባል አንድ ፈሪሳዊ በሳንሄድሪኑ ሸንጎ መካከል ተነስቶ ሰዎቹን ለጊዜው ወደ ውጭ እንዲያስወጧቸው አዘዘ። 35  ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በእነዚህ ሰዎች ላይ ልታደርጉ ያሰባችሁትን ነገር በተመለከተ ልትጠነቀቁ ይገባል። 36  ለምሳሌ ያህል፣ ከዚህ ቀደም ቴዎዳስ ራሱን እንደ ታላቅ ሰው በመቁጠር ተነስቶ ነበር፤ ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎችም ከእሱ ጋር ተባብረው ነበር። ነገር ግን እሱም ተገደለ፤ ተከታዮቹም ሁሉ ተበታትነው እንዳልነበሩ ሆኑ። 37  ከእሱ በኋላ ደግሞ የሕዝብ ቆጠራ በተካሄደበት ወቅት የገሊላው ይሁዳ ተነስቶ ተከታዮች አፍርቶ ነበር። ይሁንና እሱም ጠፋ፤ ተከታዮቹም ሁሉ ተበታተኑ። 38  ስለዚህ አሁን የምላችሁ፣ እነዚህን ሰዎች አትንኳቸው፤ ተዉአቸው። ይህ ውጥን ወይም ይህ ሥራ ከሰው ከሆነ ይጠፋል፤ 39  ከአምላክ ከሆነ ግን ልታጠፏቸው አትችሉም። እንዲያውም ከአምላክ ጋር ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።” 40  እነሱም ምክሩን ተቀበሉ፤ ሐዋርያትንም ጠርተው ገረፏቸው፤ ከዚያም በኢየሱስ ስም መናገራቸውን እንዲያቆሙ አዘው ለቀቋቸው። 41  እነሱም ስለ ስሙ ውርደት ለመቀበል ብቁ ሆነው በመቆጠራቸው ደስ እያላቸው ከሳንሄድሪን ሸንጎ ወጡ። 42  ከዚያም በየቀኑ በቤተ መቅደስም ሆነ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ስለ ክርስቶስ ይኸውም ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን ምሥራች ያለማሰለስ ማስተማራቸውንና ማወጃቸውን ቀጠሉ።
[]
[]
[]
[]
12,357
6  በዚያን ወቅት የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ አይሁዳውያን በየዕለቱ በሚከናወነው ምግብ የማከፋፈል ሥራ መበለቶቻቸው ቸል ስለተባሉባቸው ዕብራይስጥ ተናጋሪ በሆኑት አይሁዳውያን ላይ ቅሬታ ማሰማት ጀመሩ። 2  ስለዚህ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ደቀ መዛሙርቱን በሙሉ ጠርተው እንዲህ አሏቸው፦ “በማዕድ ምግብ ለማከፋፈል ስንል የአምላክን ቃል የማስተማር ሥራችንን ብንተው ተገቢ አይሆንም። 3  ስለዚህ ወንድሞች፣ ለዚህ አስፈላጊ ጉዳይ እንድንሾማቸው ከእናንተ መካከል መልካም ስም ያተረፉ፣ በመንፈስና በጥበብ የተሞሉ ሰባት ወንዶች ምረጡ፤ 4  እኛ ግን በጸሎትና ቃሉን በማስተማሩ ሥራ ላይ ሙሉ በሙሉ እናተኩራለን።” 5  የተናገሩት ነገር ሁሉንም ደስ አሰኛቸው፤ ስለሆነም ጠንካራ እምነት የነበረውንና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን እንዲሁም ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞንን፣ ፓርሜናስንና ወደ ይሁዲነት ተለውጦ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ። 6  ሐዋርያትም ፊት አቀረቧቸው፤ እነሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው። 7  ከዚህም የተነሳ የአምላክ ቃል መስፋፋቱን ቀጠለ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርቱ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ሄደ፤ በጣም ብዙ ካህናትም ይህን እምነት ተቀበሉ። 8  እስጢፋኖስም ጸጋና ኃይል ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ድንቅ ነገሮችና ተአምራዊ ምልክቶች ይፈጽም ነበር። 9  ይሁን እንጂ ‘ነፃ የወጡ ሰዎች ምኩራብ’ ተብሎ የሚጠራው ቡድን አባላት የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ከተወሰኑ የቀሬና፣ የእስክንድርያ፣ የኪልቅያና የእስያ ሰዎች ጋር መጥተው እስጢፋኖስን ተከራከሩት። 10  ይሁንና ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም። 11  ስለዚህ “ይህ ሰው በሙሴና በአምላክ ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተነዋል” ብለው እንዲናገሩ አንዳንድ ሰዎችን በድብቅ አግባቡ። 12  በተጨማሪም ሕዝቡንና ሽማግሌዎችን እንዲሁም ጸሐፍትን ቀሰቀሱ፤ ከዚያም ድንገት መጡና በኃይል ይዘው ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ ወሰዱት። 13  የሐሰት ምሥክሮችም አቀረቡ፤ እነሱም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን የሚቃወም ነገር ከመናገር ሊቆጠብ አልቻለም። 14  ለምሳሌ ያህል፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ እንደሚያፈርሰውና ሙሴ ያስተላለፈልንን ወግ እንደሚለውጥ ሲናገር ሰምተነዋል።” 15  በሳንሄድሪን ሸንጎ ተቀምጠው የነበሩትም ሁሉ ትኩር ብለው ሲያዩት ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው።
[]
[]
[]
[]
12,358
7  ሊቀ ካህናቱም “ይህ የተባለው ነገር ልክ ነው?” አለው። 2  እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ ስሙ። አባታችን አብርሃም በካራን መኖር ከመጀመሩ በፊት በሜሶጶጣሚያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለት፤ 3  እንዲህም አለው፦ ‘ከአገርህ ወጥተህ፣ ከዘመዶችህም ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።’ 4  እሱም ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን መኖር ጀመረ። አባቱ ከሞተ በኋላ ደግሞ አምላክ ከዚያ ተነስቶ አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት ወደዚህ ምድር እንዲዛወር አደረገው። 5  ሆኖም በወቅቱ በዚህ ምድር ምንም ርስት፣ ሌላው ቀርቶ እግሩን ሊያሳርፍ የሚችልበት መሬት እንኳ አልሰጠውም፤ ይሁንና ገና ልጅ ሳይኖረው ለእሱም ሆነ ከእሱ በኋላ ለዘሮቹ ምድሪቱን ርስት አድርጎ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባለት። 6  ከዚህም በላይ አምላክ፣ ዘሮቹ በሰው አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም የአገሩ ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው ነገረው። 7  ደግሞም አምላክ ‘በባርነት የሚገዛቸውን ብሔር እፈርድበታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከነበሩበት አገር ወጥተው በዚህ ስፍራ ቅዱስ አገልግሎት ያቀርቡልኛል’ ሲል ተናግሯል። 8  “በተጨማሪም አምላክ ከእሱ ጋር የግርዘት ቃል ኪዳን አደረገ፤ አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው። ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም 12ቱን የቤተሰብ ራሶች ወለደ። 9  የቤተሰብ ራሶቹም በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብፅ ሸጡት። ሆኖም አምላክ ከእሱ ጋር ነበር፤ 10  ከመከራውም ሁሉ ታደገው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስና ጥበብ አጎናጸፈው። ፈርዖንም በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ገዢ አድርጎ ሾመው። 11  ይሁንና በግብፅና በከነአን አገር ሁሉ ታላቅ መከራ ያስከተለ ረሃብ ተከሰተ፤ አባቶቻችንም የሚበሉት ነገር አጡ። 12  ሆኖም ያዕቆብ በግብፅ እህል መኖሩን ሲሰማ አባቶቻችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚያ ላካቸው። 13  ለሁለተኛ ጊዜ ሲሄዱ ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ ነገራቸው፤ ፈርዖንም ስለ ዮሴፍ ቤተሰብ ሰማ። 14  ስለዚህ ዮሴፍ መልእክት ልኮ አባቱን ያዕቆብንና ዘመዶቹን ሁሉ ከዚያ አገር አስጠራ፤ እነሱም በአጠቃላይ 75 ሰዎች ነበሩ። 15  ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም ሞተ፤ አባቶቻችንም በዚያ ሞቱ። 16  አፅማቸውም ወደ ሴኬም ተወስዶ አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በብር ገንዘብ በገዛው መቃብር ውስጥ ተቀበረ። 17  “አምላክ ለአብርሃም የተናገረው የተስፋ ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብ ሕዝባችን በግብፅ እየበዛና እየተበራከተ ሄደ፤ 18  ይህም የሆነው ዮሴፍን የማያውቅ ሌላ ንጉሥ በግብፅ እስከተነሳበት ጊዜ ድረስ ነው። 19  ይህ ንጉሥ በወገኖቻችን ላይ ተንኮል በመሸረብ ሕፃናት ልጆቻቸውን ለሞት አሳልፈው እንዲሰጡ አባቶቻችንን አስገደዳቸው። 20  በዚህ ወቅት በአምላክ ፊት እንኳ ሳይቀር እጅግ ውብ የነበረው ሙሴ ተወለደ። በአባቱም ቤት ሦስት ወር በእንክብካቤ ኖረ። 21  በተጣለ ጊዜ ግን የፈርዖን ልጅ ወስዳ እንደ ራሷ ልጅ አድርጋ አሳደገችው። 22  ሙሴም የግብፃውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ። በንግግሩና በተግባሩም ብርቱ ሆነ። 23  “ሙሴ 40 ዓመት በሞላው ጊዜ ወንድሞቹ የሆኑት የእስራኤል ልጆች ያሉበትን ሁኔታ ለማየት በልቡ አሰበ። 24  እሱም አንድ ግብፃዊ በአንድ እስራኤላዊ ላይ በደል ሲፈጽም አየ፤ ለእስራኤላዊውም አግዞ ግብፃዊውን በመግደል ተበቀለለት። 25  ወንድሞቹ አምላክ በእሱ አማካኝነት እንደሚያድናቸው የሚያስተውሉ መስሎት ነበር፤ እነሱ ግን ይህን አላስተዋሉም። 26  በማግስቱም እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኛቸው፤ እሱም ‘ሰዎች፣ እናንተ እኮ ወንድማማቾች ናችሁ። ለምን እርስ በርሳችሁ ትጣላላችሁ?’ በማለት ሊያስታርቃቸው ሞከረ። 27  ይሁንና በባልንጀራው ላይ ጥቃት እየፈጸመ የነበረው ሰው ገፈተረውና እንዲህ አለው፦ ‘አንተን በእኛ ላይ ማን ገዢና ፈራጅ አደረገህ? 28  ትናንት ግብፃዊውን እንደገደልከው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋለህ እንዴ?’ 29  ሙሴ ይህን ሲሰማ ሸሽቶ በምድያም አገር ባዕድ ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ። 30  “ከ40 ዓመትም በኋላ በሲና ተራራ አቅራቢያ በሚገኝ ምድረ በዳ፣ በሚነድ ቁጥቋጦ ነበልባል ውስጥ አንድ መልአክ ተገለጠለት። 31  ሙሴም ባየው ነገር ተደነቀ። ሆኖም ሁኔታውን ለማጣራት ወደዚያ ሲቀርብ የይሖዋ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማ፦ 32  ‘እኔ የአባቶችህ አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ።’ በዚህ ጊዜ ሙሴ ይንቀጠቀጥ ጀመር፤ ሁኔታውን ይበልጥ ለማጣራትም አልደፈረም። 33  ይሖዋም እንዲህ አለው፦ ‘የቆምክበት ስፍራ ቅዱስ መሬት ስለሆነ ጫማህን አውልቅ። 34  በግብፅ ባለው ሕዝቤ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና በእርግጥ አይቻለሁ፤ የጭንቅ ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ልታደጋቸውም ወርጃለሁ። አሁንም ና፣ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ።’ 35  ‘አንተን ማን ገዢና ፈራጅ አደረገህ?’ ብለው የተቃወሙትን ይህንኑ ሙሴን አምላክ በቁጥቋጦው ውስጥ በተገለጠለት መልአክ አማካኝነት ገዢና ነፃ አውጪ አድርጎ ላከው። 36  ይህ ሰው በግብፅ፣ በቀይ ባሕርና በምድረ በዳ ለ40 ዓመት ድንቅ ነገሮችንና ተአምራዊ ምልክቶችን በመፈጸም ከግብፅ እየመራ አወጣቸው። 37  “‘አምላክ ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳላችኋል’ ብሎ ለእስራኤል ልጆች የተናገረው ይኸው ሙሴ ነው። 38  በሲና ተራራ ካነጋገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ በጉባኤው መካከል የነበረው እሱ ነው፤ ደግሞም ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ሕያው የሆነውን ቅዱስ ቃል ተቀበለ። 39  አባቶቻችን ለእሱ ለመታዘዝ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ከዚህ ይልቅ እሱን በመቃወም በልባቸው ወደ ግብፅ ተመለሱ፤ 40  አሮንንም ‘ፊት ፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን። ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት አናውቅምና’ አሉት። 41  ስለሆነም በዚያን ጊዜ ጥጃ ሠርተው ለጣዖቱ መሥዋዕት አቀረቡ፤ በእጃቸውም ሥራ ይደሰቱ ጀመር። 42  በዚህ ጊዜ አምላክ ፊቱን ከእነሱ አዞረ፤ በነቢያትም መጻሕፍት እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት የሰማይ ሠራዊትን እንዲያመልኩ ተዋቸው፦ ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ መባና መሥዋዕት ያቀረባችሁት ለእኔ ነበር? 43  ይልቁንም ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን ምስሎች ይኸውም የሞሎክን ድንኳንና ሮምፋ የሚባለውን አምላክ ኮከብ ተሸክማችሁ ተጓዛችሁ። ስለዚህ ከባቢሎን ወዲያ እንድትሰደዱ አደርጋችኋለሁ።’ 44  “አባቶቻችን በምድረ በዳ የምሥክሩ ድንኳን ነበራቸው፤ ይህ ድንኳን የተሠራው አምላክ ሙሴን ባነጋገረው ወቅት በሰጠው ትእዛዝና ባሳየው ንድፍ መሠረት ነበር። 45  አባቶቻችንም ይህን ድንኳን በመረከብ ከኢያሱ ጋር ሆነው አምላክ ከአባቶቻችን ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይኖሩበት ወደነበረው ምድር ይዘውት ገቡ። እስከ ዳዊት ዘመን ድረስም በዚህ ምድር ቆየ። 46  ዳዊትም በአምላክ ፊት ሞገስ አገኘ፤ ለያዕቆብ አምላክም መኖሪያ ስፍራ የማዘጋጀት መብት እንዲሰጠው ጠየቀ። 47  ይሁን እንጂ ቤት የሠራለት ሰለሞን ነበር። 48  ሆኖም ልዑሉ አምላክ የሰው እጅ በሠራው ቤት አይኖርም፤ ይህም ነቢዩ እንዲህ ሲል በተናገረው መሠረት ነው፦ 49  ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድር ደግሞ የእግሬ ማሳረፊያ ናት። ለእኔ የምትሠሩልኝ ምን ዓይነት ቤት ነው? ይላል ይሖዋ። ወይስ የማርፍበት ቦታ የት ነው? 50  እነዚህን ነገሮች ሁሉ የሠራው እጄ አይደለም?’ 51  “እናንተ ግትሮች፣ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ፣ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን እንደተቃወማችሁ ነው፤ አባቶቻችሁ እንዳደረጉት እናንተም እንዲሁ ታደርጋላችሁ። 52  ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ስደት ያላደረሱበት ማን አለ? አዎ፣ እነሱ የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገድለዋቸዋል፤ እናንተም አሁን ይህን ጻድቁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ደግሞም ገደላችሁት፤ 53   በመላእክት አማካኝነት የተላለፈውን ሕግ ተቀበላችሁ፤ ነገር ግን አልጠበቃችሁትም።” 54  እነሱም ይህን ሲሰሙ ልባቸው በንዴት በገነ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጩበት ጀመር። 55  እሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ትኩር ብሎ ወደ ሰማይ ሲመለከት የአምላክን ክብር እንዲሁም ኢየሱስ በአምላክ ቀኝ ቆሞ አየ፤ 56  ከዚያም “እነሆ፣ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በአምላክ ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ። 57   በዚህ ጊዜ በኃይል እየጮኹ ጆሯቸውን በእጃቸው ደፍነው በአንድነት ወደ እሱ ሮጡ። 58  ይዘውት ከከተማው ውጭ ካስወጡት በኋላ በድንጋይ ይወግሩት ጀመር። ምሥክሮቹም መደረቢያቸውን ሳኦል በተባለ ወጣት እግር አጠገብ አስቀመጡ። 59  እስጢፋኖስም እየወገሩት ሳለ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ መንፈሴን ተቀበል” ብሎ ተማጸነ። 60  ከዚያም ተንበርክኮ በታላቅ ድምፅ “ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው” ብሎ ጮኸ። ይህን ከተናገረም በኋላ በሞት አንቀላፋ።
[]
[]
[]
[]
12,359
8  ሳኦልም በእሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም በሚገኘው ጉባኤ ላይ ከባድ ስደት ተነሳ፤ ከሐዋርያት በስተቀር ደቀ መዛሙርቱ በሙሉ በይሁዳና በሰማርያ ክልሎች ሁሉ ተበተኑ። 2  ሆኖም ለአምላክ ያደሩ ሰዎች እስጢፋኖስን ወስደው ቀበሩት፤ ታላቅ ለቅሶም አለቀሱለት። 3  ሳኦልም በጉባኤው ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረስ ጀመረ። በየቤቱ እየገባ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን ጎትቶ በማውጣት ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር። 4  ይሁን እንጂ የተበተኑት ደቀ መዛሙርት በሄዱበት ቦታ ሁሉ የአምላክን ቃል ምሥራች ሰበኩ። 5  በዚህ ጊዜ ፊልጶስ ወደ ሰማርያ ከተማ ሄዶ ስለ ክርስቶስ ይሰብክላቸው ጀመር። 6  ሕዝቡ ፊልጶስ የሚናገረውን ሲሰሙና የፈጸማቸውን ተአምራዊ ምልክቶች ሲመለከቱ ሁሉም በአንድ ልብ በትኩረት ይከታተሉት ጀመር። 7  ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸው ብዙ ሰዎችም ነበሩ፤ ርኩሳን መናፍስቱም በከፍተኛ ድምፅ እየጮኹ ይወጡ ነበር። በተጨማሪም ሽባና አንካሳ የነበሩ በርካታ ሰዎች ተፈወሱ። 8  ከዚህም የተነሳ በዚያች ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። 9  በዚያች ከተማ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ከዚህ ቀደም አስማት እየሠራ የሰማርያን ሕዝብ ያስደምም የነበረ ሲሆን ታላቅ ሰው እንደሆነ አድርጎም ይናገር ነበር። 10  ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ፣ ሰዎች ሁሉ “ይህ ሰው ታላቅ ተብሎ የሚጠራ ‘የአምላክ ኃይል’ ነው” በማለት ትልቅ ቦታ ይሰጡት ነበር። 11  ረዘም ላለ ጊዜ በአስማት ሥራው ሲያስደንቃቸው ስለቆየ የሚለውን ሁሉ ይቀበሉ ነበር። 12  ይሁንና ስለ አምላክ መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምሥራች እያወጀ የነበረውን ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ ወንዶችም ሴቶችም ይጠመቁ ጀመር። 13  ስምዖን ራሱም አማኝ ሆነ፤ ከተጠመቀም በኋላ ከፊልጶስ አይለይም ነበር፤ ምልክቶችና ታላላቅ ተአምራት ሲፈጸሙ በማየት ይደነቅ ነበር። 14  በኢየሩሳሌም ያሉ ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የአምላክን ቃል እንደተቀበሉ ሲሰሙ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው፤ 15  እነሱም ወደዚያ ወርደው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጸለዩላቸው። 16  ምክንያቱም በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ እንጂ መንፈስ ቅዱስ ገና በአንዳቸውም ላይ አልወረደም ነበር። 17  ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ እነሱም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። 18  ስምዖንም ሐዋርያት እጃቸውን የጫኑበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እንደሚቀበል አይቶ ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ቃል በመግባት 19  “እጄን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል ይህን ሥልጣን ለእኔም ስጡኝ” አላቸው። 20  ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “የአምላክን ነፃ ስጦታ በገንዘብ ማግኘት እንደምትችል ስላሰብክ የብር ገንዘብህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። 21  ልብህ በአምላክ ፊት ቀና ስላልሆነ በዚህ አገልግሎት ምንም ዓይነት ድርሻም ሆነ ዕድል ፋንታ የለህም። 22  ስለዚህ ከዚህ ክፋትህ ንስሐ ግባ፤ ምናልባት የልብህ ክፉ ሐሳብ ይቅር ይባልልህ እንደሆነ ይሖዋን ተማጸን፤ 23  መራራ መርዝና የክፋት ባሪያ እንደሆንክ አያለሁና።” 24  ስምዖንም መልሶ “ከተናገራችሁት ነገር አንዱም እንዳይደርስብኝ እባካችሁ ይሖዋን ማልዱልኝ” አላቸው። 25  ጴጥሮስና ዮሐንስ የተሟላ ምሥክርነት ከሰጡና የይሖዋን ቃል ከተናገሩ በኋላ የሰማርያ ሰዎች በሚኖሩባቸው በርካታ መንደሮች ምሥራቹን እያወጁ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። 26  ይሁንና የይሖዋ መልአክ ፊልጶስን “ተነስተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ሂድ” አለው። (ይህ መንገድ የበረሃ መንገድ ነው።) 27  እሱም ተነስቶ ሄደ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሥልጣንና የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባም አገኘ። ይህ ሰው ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ 28  እየተመለሰም ሳለ በሠረገላው ውስጥ ተቀምጦ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያነብ ነበር። 29  መንፈስም ፊልጶስን “ሂድና ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው። 30  ፊልጶስ ከሠረገላው ጎን እየሮጠ ጃንደረባው የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ ጮክ ብሎ ሲያነብ ሰማና “ለመሆኑ የምታነበውን ትረዳዋለህ?” አለው። 31  እሱም “የሚመራኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ልረዳው እችላለሁ?” አለው። ፊልጶስንም ሠረገላው ላይ ወጥቶ አብሮት እንዲቀመጥ ለመነው። 32  ያነበው የነበረው የቅዱስ መጽሐፉ ክፍል የሚከተለው ነበር፦ “እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል ጠቦት እሱም አፉን አልከፈተም። 33  ውርደት በደረሰበት ወቅት ፍትሕ ተነፈገ። ስለ ትውልዱ ማን በዝርዝር ሊናገር ይችላል? ምክንያቱም ሕይወቱ ከምድር ላይ ተወግዷል።” 34  ጃንደረባውም ፊልጶስን “እባክህ ንገረኝ፣ ነቢዩ ይህን የተናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነው ወይስ ስለ ሌላ ሰው?” አለው። 35  ፊልጶስም መናገር ጀመረ፤ ከዚህ ቅዱስ መጽሐፍ አንስቶም ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች ነገረው። 36  እየተጓዙም ሳሉ ውኃ ወዳለበት ቦታ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “ውኃ ይኸውና፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?” አለው። 37  —— 38  ከዚያም ሠረገላው እንዲቆም አዘዘ፤ ሁለቱም ወርደው ውኃው ውስጥ ገቡ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው። 39  ከውኃውም በወጡ ጊዜ፣ የይሖዋ መንፈስ ወዲያውኑ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ፊልጶስን ከዚያ በኋላ አላየውም፤ ይሁንና ደስ ብሎት ጉዞውን ቀጠለ። 40  በኋላ ግን ፊልጶስ በአሽዶድ ታየ፤ ቂሳርያም እስኪደርስ ድረስ በሚያልፍበት ክልል በሚገኙ ከተሞች ሁሉ ምሥራቹን ያውጅ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,360
9  ሳኦል ግን አሁንም በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ በመዛትና እነሱን ለመግደል ቆርጦ በመነሳት ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤ 2  የጌታን መንገድ የሚከተሉትን በዚያ የሚያገኛቸውን ወንዶችና ሴቶች ሁሉ አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደማስቆ ለሚገኙ ምኩራቦች ደብዳቤ እንዲጽፍለት ጠየቀው። 3  እየተጓዘም ሳለ ወደ ደማስቆ ሲቃረብ ድንገት ከሰማይ የመጣ ብርሃን በዙሪያው አንጸባረቀ፤ 4  እሱም መሬት ላይ ወደቀ፤ ከዚያም “ሳኦል፣ ሳኦል ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ። 5  ሳኦልም “ጌታዬ፣ አንተ ማን ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። 6  አሁን ተነስተህ ወደ ከተማዋ ግባ፤ ምን ማድረግ እንዳለብህም ይነገርሃል።” 7  አብረው እየተጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፅ የሰሙ ቢሆንም ማንንም ባለማየታቸው የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም ብለው ቆሙ። 8  ሳኦልም ከወደቀበት ተነሳ፤ ዓይኖቹ ቢገለጡም ምንም ነገር ማየት አልቻለም። በመሆኑም እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ ወሰዱት። 9  ለሦስት ቀንም ምንም ሳያይ እንዲሁም ሳይበላና ሳይጠጣ ቆየ። 10  በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታም በራእይ “ሐናንያ!” አለው። እሱም “ጌታ ሆይ፣ እነሆኝ” አለ። 11  ጌታም እንዲህ አለው፦ “ተነስተህ ‘ቀጥተኛ’ ወደተባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳም ቤት ሳኦል የሚባለውን የጠርሴስ ሰው ፈልግ። እሱም አሁን እየጸለየ ነው፤ 12  ሐናንያ የሚባል ሰው እንደሚመጣና ዓይኑ ይበራለት ዘንድ እጁን እንደሚጭንበት በራእይ አይቷል።” 13  ሐናንያ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ፣ ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳን አገልጋዮችህ ላይ ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰ ከብዙዎች ሰምቻለሁ። 14  ወደዚህ ስፍራ የመጣው ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተሰጥቶት ነው።” 15  ጌታ ግን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሰው በአሕዛብ እንዲሁም በነገሥታትና በእስራኤል ልጆች ፊት ስሜን እንዲሸከምለእኔ የተመረጠ ዕቃ ስለሆነ ወደ እሱ ሂድ። 16  እኔም ስለ ስሜ ሲል ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበት በግልጽ አሳየዋለሁ።” 17  ስለዚህ ሐናንያ ሄደ፤ ወደተባለውም ቤት ገባ፤ እጁንም በላዩ ጭኖ እንዲህ አለው፦ “ወንድሜ ሳኦል፣ ወደዚህ ስትመጣ መንገድ ላይ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ የዓይንህ ብርሃን እንዲመለስልህና በመንፈስ ቅዱስ እንድትሞላ እኔን ልኮኛል።” 18  ወዲያውም ከዓይኖቹ ላይ ቅርፊት የሚመስሉ ነገሮች ወደቁ፤ እሱም እንደገና ማየት ቻለ። ከዚያም ተነስቶ ተጠመቀ፤ 19  እንዲሁም ምግብ በልቶ ብርታት አገኘ። በደማስቆ ካሉ ደቀ መዛሙርት ጋር የተወሰኑ ቀናት ቆየ፤ 20  ወዲያውም ስለ ኢየሱስ እሱ የአምላክ ልጅ እንደሆነ በምኩራቦቹ ውስጥ መስበክ ጀመረ። 21  የሰሙት ሁሉ ግን እጅግ በመደነቅ እንዲህ ይሉ ነበር፦ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሲያጠፋ የነበረው አይደለም? ወደዚህስ የመጣው እነሱን እያሰረ ለካህናት አለቆች ለማስረከብ አልነበረም?” 22  ሳኦል ግን ይበልጥ እየበረታ ሄደ፤ በደማስቆ የሚኖሩ አይሁዶችን ኢየሱስ እሱ ክርስቶስ እንደሆነ አሳማኝ ማስረጃ እያቀረበ አፋቸውን ያስይዛቸው ነበር። 23  በርካታ ቀናት ካለፉ በኋላ አይሁዳውያን እሱን ለመግደል አሴሩ። 24  ይሁን እንጂ ሳኦል ሴራቸውን አወቀ። እነሱም ሊገድሉት ስለፈለጉ ቀን ከሌት የከተማዋን በሮች ነቅተው ይጠብቁ ነበር። 25  ስለዚህ የእሱ ደቀ መዛሙርት ሳኦልን ወስደው በሌሊት በከተማዋ ቅጥር ላይ ባለ መስኮት በማሾለክ በቅርጫት አወረዱት። 26  ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመቀላቀል ጥረት አደረገ፤ እነሱ ግን ደቀ መዝሙር መሆኑን ስላላመኑ ሁሉም ፈሩት። 27  ስለዚህ በርናባስ ረዳው፤ ሳኦልንም ወደ ሐዋርያት ወስዶ በመንገድ ላይ ጌታን እንዴት እንዳየውና እሱም እንዴት እንዳናገረው እንዲሁም በደማስቆ በኢየሱስ ስም እንዴት በድፍረት እንደተናገረ በዝርዝር ነገራቸው። 28  እሱም በኢየሩሳሌም በነፃነት እየተንቀሳቀሰና በጌታ ስም በድፍረት እየተናገረ አብሯቸው ቆየ። 29  ግሪክኛ ተናጋሪ ከሆኑ አይሁዳውያን ጋር ይነጋገርና ይከራከር ነበር፤ እነሱ ግን ሊገድሉት ሞከሩ። 30  ወንድሞች ይህን ሲያውቁ ወደ ቂሳርያ ይዘውት ወረዱ፤ ከዚያም ወደ ጠርሴስ ላኩት። 31  በዚያ ወቅት በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ ያለው ጉባኤ ሁሉ ሰላም አገኘ፤ በእምነትም እየጠነከረ ሄደ፤ መላው ጉባኤ ይሖዋን በመፍራትና መንፈስ ቅዱስ ከሚሰጠው ማጽናኛ ጋር በመስማማት ይኖር ስለነበር በቁጥር እየበዛ ሄደ። 32  ጴጥሮስም በየቦታው እየተዘዋወረ በነበረበት ወቅት በልዳ ወደሚኖሩት ቅዱሳን ደግሞ ወረደ። 33  በዚያም ሽባ በመሆኑ የተነሳ ለስምንት ዓመት የአልጋ ቁራኛ የሆነ ኤንያስ የተባለ አንድ ሰው አገኘ። 34  ጴጥሮስም “ኤንያስ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል። ተነሳና አልጋህን አንጥፍ” አለው። እሱም ወዲያውኑ ተነሳ። 35  በልዳ እና በሳሮን ሜዳ የሚኖሩ ሁሉ እሱን አይተው በጌታ አመኑ። 36  በኢዮጴ ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟም ትርጉም “ዶርቃ” ማለት ነው። እሷም መልካም በማድረግና ምጽዋት በመስጠት የምትታወቅ ነበረች። 37  በዚያን ጊዜም ታማ ሞተች። ሰዎችም አጠቧትና በደርብ ላይ በሚገኘው ክፍል ውስጥ አስቀመጧት። 38  ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለነበረች ደቀ መዛሙርቱ ጴጥሮስ በዚያች ከተማ እንዳለ ሲሰሙ “እባክህ ፈጥነህ ወደ እኛ ና” ብለው እንዲለምኑት ሁለት ሰዎች ወደ እሱ ላኩ። 39  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ተነስቶ አብሯቸው ሄደ። እዚያም ሲደርስ ደርብ ላይ ወደሚገኘው ክፍል ይዘውት ወጡ፤ መበለቶቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው እያለቀሱ ዶርቃ ከእነሱ ጋር በነበረችበት ጊዜ የሠራቻቸውን በርካታ ልብሶችና ቀሚሶች ያሳዩት ነበር። 40  ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች። 41  እሱም እጇን ይዞ አስነሳት፤ ቅዱሳኑንና መበለቶቹንም ጠርቶ ሕያው መሆኗን አሳያቸው። 42  ይህ ነገር በመላው ኢዮጴ ታወቀ፤ ብዙዎችም በጌታ አመኑ። 43  ጴጥሮስም በኢዮጴ ስምዖን በተባለ አንድ ቆዳ ፋቂ ቤት ለበርካታ ቀናት ተቀመጠ።
[]
[]
[]
[]
12,361
1  ነቢዩ ዕንባቆም በራእይ የተቀበለው መልእክት፦ 2  ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ከግፍ እንድታስጥለኝ ስለምን ጣልቃ የማትገባው እስከ መቼ ነው? 3  ለምን በደል ሲፈጸም እንዳይ ታደርገኛለህ? ጭቆናንስ ለምን ዝም ብለህ ታያለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ የሚፈጸመው ለምንድን ነው? ጠብና ግጭትስ ለምን በዛ? 4  ስለዚህ ሕግ ላልቷል፤ፍትሕም ጨርሶ የለም። ክፉው ጻድቁን ከቦታልና፤ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ተጣሟል። 5  “ብሔራትን እዩ፣ ደግሞም ልብ በሉ! በመገረም ተመልከቱ፤ ተደነቁም፤እናንተ ቢነገራችሁም እንኳ የማታምኑት አንድ ነገርበዘመናችሁ ይከናወናልና። 6  እነሆ፣ ጨካኝና ፈጣን የሆነውን ብሔር ይኸውምከለዳውያንን አስነሳለሁና። የእነሱ ያልሆኑ ቤቶችን ለመውረስ፣ሰፋፊ የምድር ክፍሎችን ይወራሉ። 7  እነሱ አስደንጋጭና አስፈሪ ናቸው። የገዛ ራሳቸውን ፍትሕና ሥልጣን ያቋቁማሉ። 8  ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፤ከሌሊት ተኩላዎችም ይልቅ ጨካኞች ናቸው። የጦር ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ፈረሶቻቸው ከሩቅ ስፍራ ይመጣሉ። ለመብላት እንደሚጣደፍ ንስር ተምዘግዝገው ይወርዳሉ። 9  ሁሉም ዓመፅ ለመፈጸም ቆርጠው ይመጣሉ። እንደ ምሥራቅ ነፋስ ፊታቸውን ያቀናሉ፤ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ያፍሳሉ። 10  በነገሥታት ይሳለቃሉ፤በከፍተኛ ባለሥልጣናትም ላይ ይስቃሉ። በተመሸገ ስፍራ ሁሉ ላይ ይስቃሉ፤የአፈር ቁልልም ሠርተው ይይዙታል። 11  ከዚያም እንደ ነፋስ ወደ ፊት እየገሰገሱ በምድሪቱ ላይ ያልፋሉ፤ይሁንና በደለኛ ይሆናሉ፤ምክንያቱም የኃይላቸው ምንጭ አምላካቸው እንደሆነ ይናገራሉ።” 12  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከዘላለም አንስቶ ያለህ አይደለህም? ቅዱስ የሆንከው አምላኬ ሆይ፣ አንተ አትሞትም። ይሖዋ ሆይ፣ እነሱን ፍርድ ለማስፈጸም ሾመሃቸዋል፤ዓለቴ ሆይ፣ እንዲቀጡ አቋቁመሃቸዋል። 13  ዓይኖችህ ክፉ የሆነውን ነገር እንዳያዩ እጅግ ንጹሐን ናቸው፤ክፋትንም ዝም ብለህ ማየት አትችልም። ታዲያ ከዳተኛውን ዝም ብለህ የምትመለከተው ለምንድን ነው?ደግሞስ ክፉ ሰው ከእሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጥ ለምን ዝም ትላለህ? 14  ሰው እንደ ባሕር ዓሣ፣ገዢም እንደሌላቸው መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታት እንዲሆን ለምን ትፈቅዳለህ? 15  እሱ እነዚህን ሁሉ በመንጠቆ ጎትቶ ያወጣል። በመረቡ ይይዛቸዋል፤በዓሣ ማጥመጃ መረቡም ይሰበስባቸዋል። በዚህም እጅግ ሐሴት ያደርጋል። 16  በመሆኑም ለመረቡ መሥዋዕት ይሠዋል፤ለዓሣ ማጥመጃ መረቡም መሥዋዕት ያቀርባል፤በእነሱ የተነሳ ድርሻው በቅባት ተሞልቷል፤ምግቡም ምርጥ ነው። 17  ታዲያ መረቡን ሁልጊዜ ያራግፋል? ብሔራትንስ ያለርኅራኄ መፍጀቱን ይቀጥላል?
[]
[]
[]
[]
12,362
2  በጥበቃ ቦታዬ ላይ እሰየማለሁ፤በመከላከያ ግንቧም ላይ እቆማለሁ። በእኔ አማካኝነት ምን መናገር እንደሚፈልግ ለማየትናበምወቀስበት ጊዜ ምን መልስ እንደምሰጥ ለማወቅ በንቃት እጠባበቃለሁ። 2  ይሖዋም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነበው ሰው በቀላሉ እንዲያነበውራእዩን ጻፈው፤ በጽላትም ላይ ግልጽ በሆነ መንገድ ቅረጸው። 3  ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ገና ይጠብቃልና፤ወደ ፍጻሜውም ይቸኩላል፤ ደግሞም አይዋሽም። ቢዘገይ እንኳ በተስፋ ጠብቀው! ያላንዳች ጥርጥር ይፈጸማልና። ራእዩ አይዘገይም! 4  ኩሩ የሆነውን ተመልከት፤ውስጡ ቀና አይደለም። ጻድቅ ግን በታማኝነቱ በሕይወት ይኖራል። 5  በእርግጥም የወይን ጠጅ አታላይ ስለሆነእብሪተኛው ሰው ግቡን አይመታም። ፍላጎቱን እንደ መቃብር ያሰፋል፤እሱ እንደ ሞት ነው፤ ደግሞም ሊጠግብ አይችልም። ብሔራትን ሁሉ ወደ ራሱ መሰብሰቡን ይቀጥላል፤ሕዝቦችንም ሁሉ ለራሱ ያከማቻል። 6  እነዚህ ሁሉ ሰዎች በእሱ ላይ አይተርቱም? ደግሞስ አሽሙርና ግራ የሚያጋባ ቃል አይሰነዝሩም? እንዲህ ይላሉ፦‘የራሱ ያልሆነውን የሚያጋብስ፣ዕዳውንም የሚያበዛ ወዮለት! ይህን የሚያደርገው እስከ መቼ ነው? 7  አበዳሪዎችህ በድንገት አይነሱም? ተነስተው በኃይል ይነቀንቁሃል፤በእነሱም እጅ ለብዝበዛ ትዳረጋለህ። 8  ብዙ ብሔራትን ስለዘረፍክከሕዝቦቹ መካከል የቀሩት ሁሉ ይዘርፉሃል፤ምክንያቱም አንተ የሰው ልጆችን ደም አፍስሰሃል፤በምድሪቱ፣ በከተሞችናበዚያ በሚኖሩት ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል። 9  ከጥፋት እጅ ያመልጥ ዘንድጎጆውን ከፍ ባለ ቦታ ላይ ለመሥራትለቤቱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም የሚሰበስብ ወዮለት! 10  በቤትህ ላይ አሳፋሪ ነገር አሲረሃል። ብዙ ሕዝቦችን ጠራርገህ በማጥፋት በራስህ ላይ ኃጢአት ሠርተሃል። 11  ድንጋይ ከግንቡ ውስጥ ይጮኻል፤ከጣሪያው እንጨቶችም መካከል አንድ ወራጅ ይመልስለታል። 12  ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚገነባናበዓመፅ ለሚመሠርታት ወዮለት! 13  እነሆ፣ ሰዎች እሳት ለሚበላው ነገር እንዲደክሙ፣ብሔራትም ከንቱ ለሆነ ነገር እንዲለፉ የሚያደርገው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አይደለም? 14  ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣ምድርም የይሖዋን ክብር በማወቅ ትሞላለችና። 15  እርቃናቸውን ለማየት ሲልታላቅ ቁጣውንና ንዴቱን ቀላቅሎለባልንጀሮቹ መጠጥ በመስጠት እንዲሰክሩ ለሚያደርግ ሰው ወዮለት! 16  በክብር ፋንታ ውርደት ትሞላለህ። አንተ ራስህም ጠጣ፤ ያልተገረዝክ መሆንህንም አሳይ። በይሖዋ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ወደ አንተ ይዞራል፤ክብርህም በውርደት ይሸፈናል፤ 17  በሊባኖስ ላይ የተፈጸመው ግፍ ይሸፍንሃል፤አራዊትንም ያሸበረው ጥፋት በአንተ ላይ ይደርሳል፤ምክንያቱም አንተ የሰዎችን ደም አፍስሰሃል፤በምድር፣ በከተሞቿናበውስጧ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ግፍ ፈጽመሃል። 18  የተቀረጸ ምስል፣ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳከብረት የተሠራ ሐውልትና ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው? 19  እንጨቱን “ንቃ!” መናገር የማይችለውንም ድንጋይ “ተነስ! አስተምረን!” ለሚል ወዮለት! እነሆ፣ በወርቅና በብር ተለብጧል፤በውስጡም እስትንፋስ የለም። 20  ይሖዋ ግን በቅዱስ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው። ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ በይ!’”
[]
[]
[]
[]
12,363
3  ነቢዩ ዕንባቆም በሙሾ ያቀረበው ጸሎት፦ 2  ይሖዋ ሆይ፣ ስለ አንተ የተወራውን ሰምቻለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ፍርሃት አሳደረብኝ። በዓመታት መካከል ሥራህን ሕያው አድርግ! በዓመታትም መካከል ሥራህን አሳውቅ። መዓት በሚወርድበት ጊዜ ምሕረትን አስታውስ። 3  አምላክ ከቴማን፣ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ። (ሴላ) ግርማው ሰማያትን ሸፈነ፤ምድርም በውዳሴው ተሞላች። 4  ጸዳሉ እንደ ፀሐይ ብርሃን ነው። ከእጁ ሁለት ጨረሮች ፈነጠቁ፤ብርታቱም በዚያ ተሰውሯል። 5  ቸነፈር ከፊቱ ሄደ፤የሚያቃጥል ትኩሳትም እግር በእግር ተከተለው። 6  ቆመ፤ ምድርንም አንቀጠቀጠ። ባየም ጊዜ ብሔራትን አብረከረካቸው። ዘላለማዊ የሆኑት ተራሮች ተፈረካከሱ፤የጥንቶቹ ኮረብቶች ተደፉ። የጥንቶቹ መንገዶች የእሱ ናቸው። 7  በኩሻን ድንኳኖች ውስጥ ችግር አየሁ። የምድያም የድንኳን ሸራዎች ተንቀጠቀጡ። 8  ይሖዋ ሆይ፣ ቁጣህ የነደደው በወንዞች ላይ ነው?በእርግጥ በወንዞች ላይ ነው? ወይስ ታላቅ ቁጣህን የገለጽከው በባሕሩ ላይ ነው? በፈረሶችህ ላይ ተቀምጠህ ጋልበሃልና፤ሠረገሎችህ ድል ተቀዳጅተዋል። 9  የቀስትህ ሽፋን ተነስቷል፤ ቀስትህም ተዘጋጅቷል። ዘንጎቹ በመሐላ ተመድበዋል። (ሴላ) ምድሪቱን በወንዞች ከፈልክ። 10  ተራሮች አንተን ሲያዩ በሥቃይ ተንፈራገጡ። ዶፍ ዝናብ ጠራርጎ ሄደ። ጥልቁ በኃይል ጮኸ። እጁን ወደ ላይ አነሳ። 11  ፀሐይና ጨረቃ ከፍ ባለው መኖሪያ ስፍራቸው ቆሙ። ፍላጾችህ እንደ ብርሃን ተወረወሩ። ጦርህ እንደ መብረቅ አብረቀረቀ። 12  በምድር ላይ በቁጣ ዘመትክ። ብሔራትን በቁጣ ረገጥካቸው። 13  ሕዝብህን ለመታደግ፣ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ። የክፉውን ቤት መሪ አደቀቅክ። ቤቱ ከመሠረቱ አንስቶ እስከ አናቱ ድረስ ተጋለጠ። (ሴላ) 14  እኔን ለመበታተን በቁጣ በተነሱ ጊዜበገዛ ራሱ መሣሪያዎች የተዋጊዎቹን ራስ ወጋህ። እነሱ ጎስቋላውን ሰው በስውር በመዋጥ ሐሴት አድርገዋል። 15  በባሕር ውስጥ፣ በሚናወጠው ብዙ ውኃ መካከልበፈረሶችህ እየጋለብክ አለፍክ። 16  እኔ ሰማሁ፤ ሆዴም ታወከ፤ከድምፁ የተነሳ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ። አጥንቶቼም ነቀዙ፤ከታች ያሉት እግሮቼ ተብረከረኩ። ሆኖም የጭንቀትን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ፤ይህ ቀን ጥቃት በሚሰነዝርብን ሕዝብ ላይ ይመጣልና። 17  የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣የወይን ተክልም ፍሬ ባይሰጥ፣የወይራ ዛፍም ባያፈራ፣እርሻዎቹም እህል ባይሰጡ፣መንጋው ከጉረኖው ቢጠፋ፣ከብቶቹም ሁሉ በረት ውስጥ ባይገኙ፣ 18  እኔ ግን በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ፤አዳኜ በሆነውም አምላክ እደሰታለሁ። 19  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ብርታቴ ነው፤እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤በከፍታ ስፍራዎችም ላይ ያስኬደኛል።
[]
[]
[]
[]
12,364
1  በጥንት ዘመን አምላክ በተለያዩ ጊዜያትና በብዙ መንገዶች በነቢያት አማካኝነት ለአባቶቻችን ተናግሯል። 2  አሁን ደግሞ በእነዚህ ቀናት መጨረሻ የሁሉም ነገር ወራሽ አድርጎ በሾመውና የተለያዩ ሥርዓቶችን በፈጠረበት በልጁ አማካኝነት ለእኛ ተናገረ። 3  እሱ የአምላክ ክብር ነጸብራቅና የማንነቱ ትክክለኛ አምሳያ ነው፤ እሱም በኃያል ቃሉ ሁሉንም ነገር ደግፎ ያኖራል። እኛን ከኃጢአታችን ካነጻ በኋላም በሰማይ በግርማዊው ቀኝ ተቀምጧል። 4  ስለዚህ ከመላእክት ስም እጅግ የላቀ ስም የወረሰ በመሆኑ ከእነሱ የተሻለ ሆኗል። 5  ለምሳሌ፣ አምላክ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ” ደግሞም “አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል” ብሎ ከመላእክት መካከል ስለ የትኛው መልአክ ተናግሮ ያውቃል? 6  ሆኖም የበኩር ልጁን እንደገና ወደ ዓለም የሚያመጣበትን ጊዜ በተመለከተ “የአምላክ መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ይላል። 7  በተጨማሪም ስለ መላእክት ሲናገር “መላእክቱን መናፍስት፣ አገልጋዮቹን ደግሞ የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል። 8  ስለ ልጁ ሲናገር ግን እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤ የመንግሥትህ በትርም የቅንነት በትረ መንግሥት ነው። 9  ጽድቅን ወደድክ፤ ዓመፅን ጠላህ። ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት ቀባህ።” 10  ደግሞም እንዲህ ይላል፦ “ጌታ ሆይ፣ አንተ በመጀመሪያ የምድርን መሠረት ጣልክ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። 11  እነሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ 12  እንደ ካባ፣ እንደ ልብስም ትጠቀልላቸዋለህ፤ ደግሞም እንደ ልብስ ትለውጣቸዋለህ። አንተ ግን ያው ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።” 13  ይሁንና “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ብሎ ከመላእክት መካከል ስለ የትኛው መልአክ ተናግሮ ያውቃል? 14  ሁሉም መዳን የሚወርሱትን እንዲያገለግሉ የሚላኩ ቅዱስ አገልግሎት የሚያከናውኑ መናፍስት አይደሉም?
[]
[]
[]
[]
12,365
10  ሕጉ ወደፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ ነው እንጂ የእነዚህ ነገሮች እውነተኛ አካል አይደለም፤ ስለዚህ ሕጉ ከዓመት ዓመት እነዚያኑ መሥዋዕቶች በማቅረብ አምላክን የሚያመልኩትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም። 2  ቢችልማ ኖሮ መሥዋዕት ማቅረቡን ይተዉት አልነበረም? ምክንያቱም ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርቡት ሰዎች አንዴ ከነጹ በኋላ ሕሊናቸው በጥፋተኝነት ስሜት አይወቅሳቸውም ነበር። 3  ይሁንና እነዚህ መሥዋዕቶች ከዓመት ዓመት ኃጢአት እንዲታወስ ያደርጋሉ፤ 4  የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ አይችልምና። 5  ስለዚህ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለ፦ “‘መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤ ከዚህ ይልቅ አካል አዘጋጀህልኝ። 6  ሙሉ በሙሉ በሚቃጠል መባና ለኃጢአት በሚቀርብ መባ ደስ አልተሰኘህም።’ 7  በዚህ ጊዜ ‘እነሆ፣ አምላክ ሆይ፣ (ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል እንደተጻፈ) ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ’ አልኩ።” 8  በመጀመሪያ እንዲህ አለ፦ “መሥዋዕትን፣ መባን፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባንና ለኃጢአት የሚቀርብ መባን አልፈለግክም፤ እንዲሁም ደስ አልተሰኘህበትም።” እነዚህ መሥዋዕቶች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የሚቀርቡ ናቸው። 9  ከዚያም “እነሆ፣ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ። ሁለተኛውን ለማቋቋም የመጀመሪያውን ያስወግዳል። 10  በዚህ “ፈቃድ” መሠረት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖ በቀረበው የኢየሱስ ክርስቶስ አካል አማካኝነት ተቀድሰናል። 11  በተጨማሪም እያንዳንዱ ካህን ቅዱስ አገልግሎት ለማቅረብና ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የማይችሉትን እነዚያኑ መሥዋዕቶች በየጊዜው ለማቅረብ ዕለት ዕለት በቦታው ይገኛል። 12  ይህ ሰው ግን ስለ ኃጢአት ለሁልጊዜ የሚሆን አንድ መሥዋዕት አቅርቦ በአምላክ ቀኝ ተቀምጧል፤ 13  ከዚያን ጊዜ አንስቶ ጠላቶቹ የእግሩ መርገጫ እስኪደረጉ ድረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። 14  እነዚያን የሚቀደሱትን ለሁልጊዜ ፍጹማን ያደረጋቸው አንድ መሥዋዕት በማቅረብ ነውና። 15  ከዚህ በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስም ስለ እኛ ይመሠክራል፤ በመጀመሪያ እንዲህ ይላልና፦ 16  “‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው’ ይላል ይሖዋ። ‘ሕግጋቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በአእምሯቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ።’” 17  በመቀጠልም “ኃጢአታቸውንና የዓመፅ ድርጊታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም” ይላል። 18  እንግዲህ እነዚህ ይቅር ከተባሉ፣ ከዚህ በኋላ ለኃጢአት መባ ማቅረብ አያስፈልግም። 19  ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅዱሱ ስፍራ በሚወስደው መንገድ ለመግባት የሚያስችል ድፍረት አግኝተናል፤ 20  እሱ የከፈተልን ይህ መንገድ ወደ ሕይወት የሚመራ አዲስ መንገድ ነው። ይህን ያደረገው በመጋረጃው ማለትም በሥጋው በኩል በማለፍ ነው፤ 21  በተጨማሪም በአምላክ ቤት ላይ የተሾመ ታላቅ ሊቀ ካህናት ስላለን 22  ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን እንዲሁም ሰውነታችንን በንጹሕ ውኃ ታጥበን በቅን ልቦና እና በሙሉ እምነት ወደ አምላክ እንቅረብ። 23  የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ስለሆነ ተስፋችንን በይፋ ለማወጅ የሚያስችለንን አጋጣሚ ያላንዳች ማወላወል አጥብቀን እንያዝ። 24  እንዲሁም እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤ 25  አንዳንዶች ልማድ እንዳደረጉት መሰብሰባችንን ቸል አንበል፤ ከዚህ ይልቅ እርስ በርስ እንበረታታ፤ ደግሞም ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስናይ ከበፊቱ ይበልጥ ይህን እናድርግ። 26  የእውነትን ትክክለኛ እውቀት ካገኘን በኋላ ሆን ብለን በኃጢአት ጎዳና ብንመላለስ ለኃጢአታችን የሚቀርብ ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤ 27  ከዚህ ይልቅ አስፈሪ ፍርድ ይጠብቀናል፤ አምላክን የሚቃወሙትን የሚበላ የሚነድ ቁጣም ይኖራል። 28  የሙሴን ሕግ የጣሰ ማንኛውም ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሠከሩበት ያለርኅራኄ ይገደል ነበር። 29  ታዲያ የአምላክን ልጅ የረገጠ፣ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳኑን ደም እንደ ተራ ነገር የቆጠረና የጸጋን መንፈስ በንቀት ያጥላላ ሰው ምን ያህል የከፋ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? 30  “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና። ደግሞም “ይሖዋ ሕዝቡን ይዳኛል።” 31  በሕያው አምላክ እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነገር ነው። 32  ይሁን እንጂ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ በመከራ ውስጥ በከፍተኛ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀድሞውን ጊዜ ዘወትር አስታውሱ። 33  በአደባባይ ለነቀፋና ለመከራ የተጋለጣችሁባቸው ጊዜያት ነበሩ፤ ደግሞም እንዲህ ዓይነት ሁኔታ የደረሰባቸውን ሰዎች መከራ የተጋራችሁባቸው ጊዜያት ነበሩ። 34  እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ዘላቂ የሆነ ንብረት እንዳላችሁ ስለምታውቁ በእስር ላይ ላሉት ራራችሁላቸው፤ እንዲሁም ንብረታችሁ ሲዘረፍ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ። 35  እንግዲህ ትልቅ ወሮታ የሚያስገኘውን በድፍረት የመናገር ነፃነታችሁን አሽቀንጥራችሁ አትጣሉት። 36  የአምላክን ፈቃድ ከፈጸማችሁ በኋላ የተስፋው ቃል ሲፈጸም ማየት እንድትችሉ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። 37  ምክንያቱም “ለጥቂት ጊዜ ነው” እንጂ “የሚመጣው እሱ ይመጣል፤ ደግሞም አይዘገይም።” 38  “ሆኖም ጻድቅ አገልጋዬ በእምነት ይኖራል”፤ ደግሞም “ወደኋላ ቢያፈገፍግ በእሱ ደስ አልሰኝም።” 39  እንግዲህ እኛ በሕይወት የሚያኖር እምነት እንዳላቸው ሰዎች ነን እንጂ ወደ ጥፋት እንደሚያፈገፍጉ ሰዎች አይደለንም።
[]
[]
[]
[]
12,366
11  እምነት ተስፋ የተደረጉትን ነገሮች በእርግጠኝነት መጠበቅ ማለት ነው፤ በተጨማሪም የምናምንበት ነገር በዓይን የሚታይ ባይሆንም እውን መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። 2  በጥንት ዘመን የኖሩት ሰዎች የተመሠከረላቸው በዚህ አማካኝነት ነው። 3  ሥርዓቶቹ የተቋቋሙት በአምላክ ቃል መሆኑን የምንረዳው በእምነት ነው፤ በመሆኑም የሚታየው ነገር ወደ ሕልውና የመጣው ከማይታዩ ነገሮች ነው። 4  አቤል፣ ቃየን ካቀረበው የበለጠ ዋጋ ያለው መሥዋዕት ለአምላክ በእምነት አቀረበ፤ አምላክ ስጦታውን ስለተቀበለ በዚህ እምነቱ የተነሳ ጻድቅ እንደሆነ ተመሥክሮለታል፤ ቢሞትም እንኳ በእምነቱ አማካኝነት አሁንም ይናገራል። 5  ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ወደ ሌላ ቦታ ተወሰደ፤ አምላክ ወደ ሌላ ቦታ ስለወሰደውም የትም ቦታ ሊገኝ አልቻለም፤ ከመወሰዱ በፊት አምላክን በሚገባ ደስ እንዳሰኘ ተመሥክሮለት ነበርና። 6  በተጨማሪም ያለእምነት አምላክን በሚገባ ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ አምላክ የሚቀርብ ሁሉ እሱ መኖሩንና ከልብ ለሚፈልጉትም ወሮታ ከፋይ መሆኑን ማመን ይኖርበታልና። 7  ኖኅ ገና ስላልታዩት ነገሮች መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ከተቀበለ በኋላ አምላካዊ ፍርሃት ያሳየውና ቤተሰቡን ለማዳን መርከብ የሠራው በእምነት ነበር፤ በዚህ እምነት አማካኝነትም ዓለምን ኮንኗል፤ እንዲሁም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ለመውረስ በቅቷል። 8  አብርሃም በተጠራ ጊዜ ወደፊት ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ በመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ይኖርበት የነበረውን ስፍራ ለቆ ወጣ። 9  በባዕድ አገር እንደሚኖር እንግዳ በተስፋይቱ ምድር በእምነት ኖረ፤ ደግሞም አብረውት የዚሁ ተስፋ ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በድንኳን ኖረ። 10  አምላክ ንድፍ ያወጣላትንና የገነባትን፣ እውነተኛ መሠረት ያላትን ከተማ ይጠባበቅ ነበርና። 11  ሣራም የተስፋን ቃል የሰጠው እሱ ታማኝ እንደሆነ አድርጋ ስላሰበች ዕድሜዋ ካለፈ በኋላም እንኳ ዘር ለመፀነስ በእምነት ኃይል አገኘች። 12  ከዚህም የተነሳ እንደሞተ ያህል ከሚቆጠረው ከአንድ ሰው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዙና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የማይቆጠሩ ልጆች ተወለዱ። 13  እነዚህ ሁሉ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ ባያዩም እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከሩቅ አይተው በደስታ ተቀበሉት፤ በምድሩም ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች መሆናቸውን በይፋ ተናገሩ። 14  እንዲህ ብለው የሚናገሩት ሰዎች የራሳቸው የሆነ ቦታ ለማግኘት ከልብ እንደሚሹ ያሳያሉ። 15  ይሁንና ትተውት የወጡትን ቦታ ሁልጊዜ ቢያስቡ ኖሮ መመለስ የሚችሉበት አጋጣሚ በኖራቸው ነበር። 16  አሁን ግን የተሻለውን ይኸውም ከሰማይ የሆነውን ስፍራ ለማግኘት ይጣጣራሉ። ስለዚህ አምላክ፣ እሱን አምላካችን ብለው ቢጠሩት አያፍርባቸውም፤ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። 17  አብርሃም በተፈተነ ጊዜ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ እስከ ማቅረብ ድረስ እምነት አሳይቷል፤ የተስፋን ቃል በደስታ የተቀበለው ይህ ሰው አንድያ ልጁን መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ተዘጋጅቶ ነበር፤ 18  ይህን ያደረገው “ዘርህ የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ይሆናል” ተብሎ ተነግሮት እያለ ነው። 19  ይሁንና አምላክ ከሞት እንኳ ሳይቀር ሊያስነሳው እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር፤ ልጁንም ከሞት አፋፍ መልሶ አገኘው፤ ይህም እንደ ምሳሌ ሆኖ አገልግሏል። 20  ይስሐቅም ወደፊት ከሚሆኑት ነገሮች ጋር በተያያዘ ያዕቆብንና ኤሳውን በእምነት ባረካቸው። 21  ያዕቆብ መሞቻው በተቃረበ ጊዜ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን የባረካቸውና የበትሩን ጫፍ ተመርኩዞ ለአምላክ የሰገደው በእምነት ነበር። 22  ዮሴፍ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ ስለ እስራኤል ልጆች ከግብፅ መውጣት በእምነት ተናገረ፤ ስለ አፅሙም መመሪያ ሰጣቸው። 23  ሙሴ ከተወለደ በኋላ ወላጆቹ መልኩ የሚያምር ሕፃን መሆኑን ስላዩ የንጉሡን ትእዛዝ ሳይፈሩ ለሦስት ወር የሸሸጉት በእምነት ነበር። 24  ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ ተብሎ ለመጠራት በእምነት እንቢ አለ፤ 25  በኃጢአት ከሚገኝ ጊዜያዊ ደስታ ይልቅ ከአምላክ ሕዝብ ጋር መንገላታትን መረጠ፤ 26  ምክንያቱም ቅቡዕ ሆኖ የሚደርስበት ነቀፋ በግብፅ ከሚገኝ ውድ ሀብት የላቀ እንደሆነ አስቧል፤ የሚከፈለውን ወሮታ በትኩረት ተመልክቷልና። 27  ደግሞም በእምነት ግብፅን ለቆ ወጣ፤ ሆኖም ይህን ያደረገው የንጉሡን ቁጣ ፈርቶ አይደለም፤ የማይታየውን አምላክ እንደሚያየው አድርጎ በጽናት ቀጥሏልና። 28  አጥፊው የበኩር ልጆቻቸውን እንዳይገድል ሙሴ ፋሲካን ያከበረውና መቃኖቹ ላይ ደም የረጨው በእምነት ነው። 29  እስራኤላውያን በደረቅ ምድር የሚሄዱ ያህል ቀይ ባሕርን በእምነት ተሻገሩ፤ ይሁንና ግብፃውያን እንዲህ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሰመጡ። 30  እስራኤላውያን የኢያሪኮን ግንብ ሰባት ቀን ከዞሩት በኋላ በእምነት ወደቀ። 31  ዝሙት አዳሪዋ ረዓብ ታዛዥ ሳይሆኑ ከቀሩት ሰዎች ጋር ከመጥፋት የዳነችው በእምነት ነው፤ ምክንያቱም ሰላዮቹን በሰላም ተቀብላለች። 32  እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን እላለሁ? ስለ ጌድዮን፣ ስለ ባርቅ፣ ስለ ሳምሶን፣ ስለ ዮፍታሔ፣ ስለ ዳዊት እንዲሁም ስለ ሳሙኤልና ስለ ሌሎቹ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ ያጥረኛል። 33  እነዚህ ሰዎች በእምነት መንግሥታትን ድል አድርገዋል፤ ጽድቅን አስፍነዋል፤ የተስፋን ቃል ተቀብለዋል፤ የአንበሶችን አፍ ዘግተዋል፤ 34  የእሳትን ኃይል አጥፍተዋል፤ ከሰይፍ ስለት አምልጠዋል፤ ደካማ የነበሩት ብርታት አግኝተዋል፤ በጦርነት ኃያላን ሆነዋል፤ ወራሪ ሠራዊትን አባረዋል። 35  ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀብለዋል፤ ሌሎች ወንዶች ግን ቤዛ ተከፍሎላቸው ነፃ መሆን ስላልፈለጉ ከባድ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፤ ይህን ያደረጉት የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ ነው። 36  አዎ፣ ሌሎች ደግሞ መዘባበቻ በመሆንና በመገረፍ ይባስ ብሎም በመታሰርና ወህኒ ቤት በመጣል ፈተና ደርሶባቸዋል። 37  በድንጋይ ተወግረዋል፤ ተፈትነዋል፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰንጥቀዋል፤ በሰይፍ ተቀልተዋል፤ እየተቸገሩ፣ መከራ እየተቀበሉና እየተንገላቱ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ተንከራተዋል፤ 38  ዓለም እንዲህ ዓይነት ሰዎች የሚገቡት ሆኖ አልተገኘም። በየበረሃው፣ በየተራራው፣ በየዋሻውና በምድር ውስጥ ባሉ ጉድጓዶች ተቅበዝብዘዋል። 39  ይሁንና እነዚህ ሁሉ በእምነታቸው ምክንያት በመልካም የተመሠከረላቸው ቢሆኑም እንኳ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ አላዩም፤ 40  ምክንያቱም አምላክ ያለእኛ ወደ ፍጽምና እንዲደርሱ ዓላማው ስላልነበረ ለእኛ የተሻለ ነገር ለመስጠት አስቀድሞ አስቧል።
[]
[]
[]
[]
12,367
12  እንግዲያው እንዲህ ያለ ታላቅ የምሥክሮች ደመና በዙሪያችን ስላለልን እኛም ማንኛውንም ሸክምና በቀላሉ ተብትቦ የሚይዘንን ኃጢአት ከላያችን አንስተን እንጣል፤ ከፊታችን የሚጠብቀንን ሩጫም በጽናት እንሩጥ፤ 2  የምንሮጠውም የእምነታችን “ዋና ወኪል” እና “ፍጹም አድራጊ” የሆነውን ኢየሱስን በትኩረት በመመልከት ነው። እሱ ከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲል፣ የሚደርስበትን ውርደት ከምንም ሳይቆጥር በመከራ እንጨት ላይ እስከ መሞት ድረስ ጸንቷል፤ እንዲሁም በአምላክ ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል። 3  እንግዲህ እንዳትደክሙና ተስፋ እንዳትቆርጡ ኃጢአተኞች የራሳቸውን ጥቅም በመጻረር የሚያሰሙትን እንዲህ ዓይነቱን የተቃውሞ ንግግር በጽናት የተቋቋመውን እሱን በጥሞና አስቡ። 4  እናንተ ከዚህ ኃጢአት ጋር እያደረጋችሁ ባላችሁት ትግል ደማችሁ እስኪፈስ ድረስ ገና አልታገላችሁም። 5  ደግሞም ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን የተሰጣችሁን የሚከተለውን ማሳሰቢያ ሙሉ በሙሉ ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ የሚሰጥህን ተግሣጽ አቅልለህ አትመልከት፤ በሚያርምህም ጊዜ ተስፋ አትቁረጥ፤ 6  ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻልና፤ እንዲያውም እንደ ልጁ አድርጎ የሚቀበለውን ሁሉ ይቀጣል።” 7  ተግሣጽ የምትቀበሉበት አንዱ መንገድ ይህ ስለሆነ መከራ ሲደርስባችሁ መጽናት ያስፈልጋችኋል። አምላክ የያዛችሁ እንደ ልጆቹ አድርጎ ነው። ለመሆኑ አባቱ የማይገሥጸው ልጅ ማን ነው? 8  ሆኖም ሁላችሁም ይህን ተግሣጽ ካልተቀበላችሁ ዲቃላዎች ናችሁ እንጂ ልጆች አይደላችሁም። 9  ከዚህም በላይ ሰብዓዊ አባቶቻችን ይገሥጹን ነበር፤ እኛም እናከብራቸው ነበር። ታዲያ የመንፈሳዊ ሕይወታችን አባት ለሆነው ይበልጥ በፈቃደኝነት በመገዛት በሕይወት ልንኖር አይገባም? 10  እነሱ መልካም መስሎ በታያቸው መንገድ ለጥቂት ጊዜ ገሥጸውናል፤ እሱ ግን ከቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለጥቅማችን ሲል ይገሥጸናል። 11  እርግጥ ነው፣ ማንኛውም ተግሣጽ ለጊዜው የሚያስደስት አይመስልም፤ ይልቁንም ያስከፋል፤ በኋላ ግን በተግሣጽ ሥልጠና ላገኙ ሰዎች የጽድቅን ሰላማዊ ፍሬ ያፈራላቸዋል። 12  ስለዚህ የዛሉትን እጆችና የተብረከረኩትን ጉልበቶች አበርቱ፤ 13  የተጎዳው የአካል ክፍል እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ እግራችሁ ዘወትር ቀና በሆነ መንገድ እንዲጓዝ አድርጉ። 14  ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፤ ቅድስናንም ፈልጉ፤ ያለቅድስና ማንም ሰው ጌታን ማየት አይችልም። 15  ማንም የአምላክን ጸጋ እንዳያጣ ብሎም መርዛማ ሥር በቅሎ ችግር እንዳይፈጥርና ብዙዎችን እንዳይበክል ተጠንቀቁ፤ 16  በተጨማሪም በመካከላችሁ ሴሰኛ ሰውም ሆነ ለአንድ ጊዜ መብል ሲል የብኩርና መብቱን አሳልፎ እንደሰጠው እንደ ኤሳው ቅዱስ ነገሮችን የማያደንቅ ሰው እንዳይገኝ ተጠንቀቁ። 17  ኤሳው የኋላ ኋላ በረከቱን ለመውረስ በፈለገ ጊዜ እንደተከለከለ ታውቃላችሁና፤ ሐሳብ ለማስቀየር እያለቀሰ ብርቱ ጥረት ቢያደርግም እንኳ አልተሳካለትም። 18  እናንተ እኮ የቀረባችሁት ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደተያያዘው ተራራ፣ ወደ ጥቁሩ ደመና፣ ወደ ድቅድቁ ጨለማ፣ ወደ አውሎ ነፋሱ፣ 19  ወደ መለከት ድምፁና ቃል ያሰማ ወደነበረው ድምፅ አይደለም፤ ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይነገራቸው ለምነው ነበር። 20  “እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት” የሚለው ትእዛዝ በጣም አስፈርቷቸው ነበርና። 21  በተጨማሪም በዚያ ይታይ የነበረው ነገር በጣም አስፈሪ ስለነበረ ሙሴ “ፈራሁ፤ ተንቀጠቀጥኩም” ሲል ተናግሯል። 22  እናንተ ግን የቀረባችሁት ወደ ጽዮን ተራራና የሕያው አምላክ ከተማ ወደሆነችው ወደ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም፣ አንድ ላይ ወደተሰበሰቡ አእላፋት መላእክት፣ 23  በሰማያት ወደተመዘገበው የበኩራት ጉባኤ፣ የሁሉ ፈራጅ ወደሆነው አምላክ፣ ፍጽምና እንዲያገኙ ወደተደረጉት ጻድቃን መንፈሳዊ ሕይወት፣ 24  የአዲስ ቃል ኪዳን መካከለኛ ወደሆነው ወደ ኢየሱስና ከአቤል ደም በተሻለ ሁኔታ ወደሚናገረው ወደተረጨው ደም ነው። 25  እየተናገረ ያለውን እሱን ከመስማት ወደኋላ እንዳትሉ ተጠንቀቁ። በምድር ላይ መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸው የነበረውን ከመስማት ወደኋላ ያሉት ሰዎች ከቅጣት ካላመለጡ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረውን እሱን ከመስማት ዞር ብንል እንዴት እናመልጣለን? 26  በዚያን ጊዜ ድምፁ ምድርን አናውጦ ነበር፤ አሁን ግን “ምድርን ብቻ ሳይሆን ሰማይን ጭምር እንደገና አናውጣለሁ” ሲል ቃል ገብቷል። 27  እንግዲህ “እንደገና” የሚለው አባባል የማይናወጡት ነገሮች ጸንተው ይኖሩ ዘንድ የሚናወጡት ይኸውም የተሠሩት ነገሮች የሚወገዱ መሆናቸውን ያመለክታል። 28  ስለዚህ እኛ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ልንቀበል እንደሆነ ስለምናውቅ ጸጋውን መቀበላችንን እንቀጥል፤ ይህም በጸጋው አማካኝነት በአምላካዊ ፍርሃትና በጥልቅ አክብሮት፣ ተቀባይነት ባለው መንገድ ለአምላክ ቅዱስ አገልግሎት ማቅረብ እንችል ዘንድ ነው። 29  አምላካችን የሚባላ እሳት ነውና።
[]
[]
[]
[]
12,368
13  እርስ በርሳችሁ እንደ ወንድማማች መዋደዳችሁን ቀጥሉ። 2  እንግዳ መቀበልን አትርሱ፤ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋልና። 3  በእስር ላይ ያሉትን ከእነሱ ጋር ታስራችሁ እንዳላችሁ አድርጋችሁ በማሰብ ሁልጊዜ አስታውሷቸው፤ እናንተም ራሳችሁ ገና በሥጋ ያላችሁ በመሆናችሁ እንግልት እየደረሰባቸው ያሉትን አስቡ። 4  ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፣ መኝታውም ከርኩሰት የጸዳ ይሁን፤ አምላክ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ይፈርድባቸዋልና። 5  አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን፤ ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ። እሱ “ፈጽሞ አልተውህም፤ በምንም ዓይነት አልጥልህም” ብሏልና። 6  ስለዚህ በሙሉ ልብ “ይሖዋ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን። 7  የአምላክን ቃል የነገሯችሁን በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ፤ ደግሞም ምግባራቸው ያስገኘውን ውጤት በሚገባ በማጤን በእምነታቸው ምሰሏቸው። 8  ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ለዘላለምም ያው ነው። 9  በልዩ ልዩና እንግዳ በሆኑ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን በምግብ ሳይሆን በአምላክ ጸጋ ቢጠናከር መልካም ነውና፤ በዚህ የተጠመዱ ምንም አልተጠቀሙም። 10  እኛ መሠዊያ ያለን ሲሆን በድንኳኑ ውስጥ ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርቡት ከመሠዊያው ላይ ወስደው መብላት አይፈቀድላቸውም። 11  ምክንያቱም ሊቀ ካህናቱ የእንስሳቱን ደም የኃጢአት መባ አድርጎ ወደ ቅዱሱ ስፍራ የሚወስደው ሲሆን ሥጋው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል። 12  ስለዚህ ኢየሱስም ሕዝቡን በገዛ ራሱ ደም ለመቀደስ ከከተማው በር ውጭ መከራ ተቀበለ። 13  እንግዲህ እኛም እሱ የተሸከመውን ነቀፋ ተሸክመን ከሰፈር ውጭ እሱ ወዳለበት እንሂድ፤ 14  በዚህ ቋሚ ከተማ የለንምና፤ ከዚህ ይልቅ ወደፊት የምትመጣዋን ከተማ በጉጉት እንጠባበቃለን። 15  ስለዚህ በኢየሱስ አማካኝነት የውዳሴ መሥዋዕት ዘወትር ለአምላክ እናቅርብ፤ ይህም ስሙን በይፋ የምናውጅበት የከንፈራችን ፍሬ ነው። 16  በተጨማሪም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤ አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታልና። 17  ተግተው ስለሚጠብቋችሁና ይህን በተመለከተ ስሌት ስለሚያቀርቡ በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ታዘዙ እንዲሁም ተገዙ፤ ይህን የምታደርጉት ሥራቸውን በደስታ እንጂ በሐዘን እንዳያከናውኑ ነው፤ አለዚያ ሥራቸውን የሚያከናውኑት በሐዘን ይሆናል፤ ይህ ደግሞ እናንተን ይጎዳችኋል። 18  ለእኛ መጸለያችሁን ቀጥሉ፤ ምክንያቱም ሐቀኛ ሕሊና እንዳለን እናምናለን፤ ደግሞም በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን። 19  በተለይ ደግሞ ወደ እናንተ በፍጥነት ተመልሼ እንድመጣ ትጸልዩልኝ ዘንድ አሳስባችኋለሁ። 20  እንግዲያው ታላቅ የበጎች እረኛ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ የዘላለማዊውን ቃል ኪዳን ደም ይዞ ከሞት እንዲነሳ ያደረገው የሰላም አምላክ 21  ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ እሱ በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን ነገር እንድናደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ያነሳሳናል። ለእሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። 22  እንግዲህ ወንድሞች፣ የጻፍኩላችሁ ደብዳቤ አጭር ስለሆነ ይህን የማበረታቻ ቃል በትዕግሥት እንድታዳምጡ አሳስባችኋለሁ። 23  ወንድማችን ጢሞቴዎስ መፈታቱን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። ቶሎ ከመጣ አብረን መጥተን እናያችኋለን። 24  በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ሁሉና ለቀሩት ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጣሊያን ያሉት ሰላምታ ልከውላችኋል። 25  የአምላክ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
[]
[]
[]
[]
12,369
2  ቀስ በቀስ እንዳንወሰድ ለሰማናቸው ነገሮች ከወትሮው የበለጠ ትኩረት መስጠታችን አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው። 2  በመላእክት አማካኝነት የተነገረው ቃል የጸና መሆኑ ከተረጋገጠ እንዲሁም ማንኛውም አለመታዘዝና መተላለፍ ከፍትሕ ጋር የሚስማማ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ 3  እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንል እንዴት ከቅጣት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ መዳን መጀመሪያ ጌታችን የተናገረው ሲሆን እሱን የሰሙት ሰዎችም ለእኛ አረጋግጠውልናል፤ 4  አምላክም በምልክቶች፣ በድንቅ ነገሮች፣ በተለያዩ ተአምራትና ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በማደል መሥክሯል። 5  ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለምያስገዛው ለመላእክት አይደለምና። 6  ነገር ግን አንድ ምሥክር፣ አንድ ቦታ ላይ እንዲህ ብሏል፦ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ወይስ ትንከባከበው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? 7  ከመላእክት ጥቂት አሳነስከው፤ የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፋህለት፤ እንዲሁም በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምከው። 8  ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዛህለት።” አምላክ ሁሉንም ነገር ለእሱ ስላስገዛ፣ ያላስገዛለት ምንም ነገር የለም። ይሁንና በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም። 9  ነገር ግን ከመላእክት በጥቂቱ እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ መከራ በመቀበሉ አሁን የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፍቶ እናየዋለን፤ እሱ በአምላክ ጸጋ ለሰው ሁሉ ሲል ሞትን ቀምሷል። 10  ሁሉ ነገር የሚኖረው ለአምላክ ነው፤ የሚኖረውም በእሱ አማካኝነት ነው። ስለዚህ አምላክ ብዙ ልጆችን ክብር ለማጎናጸፍ ሲል ለመዳን የሚያበቃቸውን “ዋና ወኪል” በመከራ አማካኝነት ፍጹም ማድረጉ የተገባ ነበር። 11  የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሰዎች፣ ሁሉም ከአንድ አባት የመጡ ናቸውና፤ ከዚህም የተነሳ እነሱን ወንድሞች ብሎ ለመጥራት አያፍርም፤ 12  ምክንያቱም “ስምህን ለወንድሞቼ አሳውቃለሁ፤ በጉባኤ መካከልም በመዝሙር አወድስሃለሁ” ይላል። 13  ደግሞም “እኔ እምነቴን በእሱ ላይ እጥላለሁ” ይላል። እንደገናም “እነሆ! እኔና ይሖዋ የሰጠኝ ልጆች” ይላል። 14  ስለዚህ እነዚህ “ልጆች” ሥጋና ደም ስለሆኑ እሱም ሥጋና ደም ሆነ፤ ይህም የሆነው ለሞት የመዳረግ አቅም ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ አማካኝነት እንዳልነበረ ያደርገው ዘንድ ነው፤ 15  እንዲሁም ሞትን በመፍራታቸው በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ በባርነት ቀንበር የተያዙትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ ነው። 16  እሱ እየረዳ ያለው መላእክትን እንዳልሆነ የታወቀ ነውና፤ ከዚህ ይልቅ እየረዳ ያለው የአብርሃምን ዘር ነው። 17  ስለሆነም ለሕዝቡ ኃጢአት የማስተሰረያ መሥዋዕት ለማቅረብ በአምላክ አገልግሎት መሐሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ በሁሉ ረገድ እንደ “ወንድሞቹ” መሆን አስፈለገው። 18  በተፈተነ ጊዜ እሱ ራሱ መከራ ስለደረሰበት በፈተና ላይ ላሉት ሊደርስላቸው ይችላል።
[]
[]
[]
[]
12,370
3  ስለሆነም የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች፣ በእሱ እንደምናምን በይፋ የምንናገርለትን፣ ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ። 2  ሙሴ በመላው የአምላክ ቤት ላይ ታማኝ እንደነበረ ሁሉ እሱም ለሾመው ታማኝ ነበር። 3  ቤቱን የሠራው፣ ከቤቱ የበለጠ ክብር ስላለው እሱ ከሙሴ የበለጠ ክብር ይገባዋል። 4  እያንዳንዱ ቤት ሠሪ እንዳለው የታወቀ ነው፤ ሁሉን ነገር የሠራው ግን አምላክ ነው። 5  ሙሴም በመላው የአምላክ ቤት ላይ ታማኝ አገልጋይ ነበር። አገልግሎቱም ከጊዜ በኋላ ለሚነገሩ ነገሮች ምሥክር ነው። 6  ክርስቶስ ግን በአምላክ ቤት ላይ የተሾመ ታማኝ ልጅ ነበር። እኛም አፋችንን ሞልተን የመናገር ነፃነታችንንና የምንደሰትበትን ተስፋችንን እስከ መጨረሻው አጥብቀን ከያዝን የአምላክ ቤት ነን። 7  ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ 8  በምድረ በዳ እጅግ የሚያስቆጣ ድርጊት በተፈጸመበት በፈተና ቀን እንደሆነው ልባችሁን አታደንድኑ፤ 9  በዚያ፣ አባቶቻችሁ ያደረግኩትን ሁሉ ለ40 ዓመት ቢያዩም እኔን በመፈተን ተገዳደሩኝ። 10  በዚህም ምክንያት በዚያ ትውልድ በጣም ተንገሸገሽኩ፤ እንዲህም አልኩ፦ ‘ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፤ መንገዴንም ሊያውቁ አልቻሉም።’ 11  በመሆኑም ‘ወደ እረፍቴ አይገቡም’ ብዬ በቁጣዬ ማልኩ።” 12  ወንድሞች፣ ሕያው ከሆነው አምላክ በመራቅ እምነት የለሽ የሆነ ክፉ ልብ ከእናንተ መካከል በማናችሁም ውስጥ እንዳያቆጠቁጥ ተጠንቀቁ፤ 13  ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል አንዳችሁም ኃጢአት ባለው የማታለል ኃይል እንዳትደነድኑ “ዛሬ” ተብሎ የሚጠራ ጊዜ እስካለ ድረስ በየዕለቱ እርስ በርሳችሁ ተበረታቱ። 14  የክርስቶስ ተካፋዮች የምንሆነው በመጀመሪያ የነበረንን ትምክህት እስከ መጨረሻው አጽንተን ከያዝን ብቻ ነውና። 15  ይህም “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ እጅግ የሚያስቆጣ ድርጊት በተፈጸመበት ጊዜ እንደሆነው ልባችሁን አታደንድኑ” እንደተባለው ነው። 16  ድምፁን ቢሰሙም እንኳ እጅግ ያስቆጡት እነማን ነበሩ? ይህን ያደረጉት ሙሴ እየመራቸው ከግብፅ የወጡት ሁሉ አይደሉም? 17  ከዚህም ሌላ ለ40 ዓመት አምላክ በእነሱ እንዲንገሸገሽ ያደረጉት እነማን ናቸው? እነዚያ ኃጢአት የሠሩትና ሬሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረው አይደሉም? 18  ደግሞስ ወደ እረፍቴ አይገቡም ብሎ የማለው ስለ እነማን ነው? እነዚያን ያልታዘዙትን በተመለከተ አይደለም? 19  ስለዚህ ሊገቡ ያልቻሉት እምነት በማጣታቸው የተነሳ እንደሆነ እንረዳለን።
[]
[]
[]
[]
12,371
4  ስለዚህ ወደ እረፍቱ የመግባት ተስፋ አሁንም ስላለ ከእናንተ መካከል ማንም ለዚያ የማይበቃ ሆኖ እንዳይገኝ እንጠንቀቅ። 2  ለአባቶቻችን ተሰብኮ እንደነበረው ሁሉ ምሥራቹ ለእኛም ተሰብኳልና፤ እነሱ ግን ሰምተው የታዘዙት ሰዎች የነበራቸው ዓይነት እምነት ስላልነበራቸው የሰሙት ቃል አልጠቀማቸውም። 3  እኛ ግን እምነት በማሳየታችን ወደዚህ እረፍት እንገባለን። ምንም እንኳ የእሱ ሥራ ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም “‘ወደ እረፍቴ አይገቡም’ ብዬ በቁጣዬ ማልኩ” ብሏል። 4  በአንድ ቦታ ላይ ሰባተኛውን ቀን አስመልክቶ “አምላክም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ አረፈ” ብሏልና፤ 5  እንደገና እዚህ ላይ “ወደ እረፍቴ አይገቡም” ብሏል። 6  ስለዚህ ገና ወደ እረፍቱ የሚገቡ ስላሉና መጀመሪያ ምሥራቹ የተሰበከላቸው ባለመታዘዛቸው ምክንያት ሳይገቡ ስለቀሩ 7  ከረጅም ጊዜ በኋላ በዳዊት መዝሙር ላይ “ዛሬ” በማለት እንደገና አንድን ቀን መደበ፤ ይህም ቀደም ሲል “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ ልባችሁን አታደንድኑ” እንደተባለው ነው። 8  ኢያሱ ወደ እረፍት ቦታ እየመራ አስገብቷቸው ቢሆን ኖሮ አምላክ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር። 9  ስለዚህ የአምላክ ሕዝብ የሰንበት እረፍት ገና ይቀረዋል። 10  ወደ አምላክ እረፍት የገባ ሰው አምላክ ከሥራው እንዳረፈ ሁሉ እሱም ከሥራው አርፏልና። 11  ስለዚህ ማንም የእነዚያን ያለመታዘዝ ምሳሌ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደዚያ እረፍት ለመግባት የተቻለንን ሁሉ እናድርግ። 12  የአምላክ ቃል ሕያውና ኃይለኛ ነው፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ከየትኛውም ሰይፍ የበለጠ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን እንዲሁም መገጣጠሚያንና መቅኒን እስኪለያይ ድረስ ሰንጥቆ ይገባል፤ የልብንም ሐሳብና ዓላማ መረዳት ይችላል። 13  ደግሞም ከአምላክ እይታ የተሰወረ አንድም ፍጥረት የለም፤ ይልቁንም ተጠያቂዎች በሆንበት በእሱ ዓይኖች ፊት ሁሉም ነገር የተራቆተና ገሃድ የወጣ ነው። 14  እንግዲህ ወደ ሰማያት የገባ ታላቅ ሊቀ ካህናት ይኸውም የአምላክ ልጅ ኢየሱስ እንዳለን ስለምናውቅ በእሱ ላይ እምነት እንዳለን ምንጊዜም በይፋ እንናገር። 15  ያለን ሊቀ ካህናት በድካማችን ሊራራልን የማይችል አይደለምና፤ ከዚህ ይልቅ እንደ እኛው በሁሉም ረገድ የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁንና እሱ ኃጢአት የለበትም። 16  እንግዲህ እርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትና ጸጋ እናገኝ ዘንድ ያለምንም ፍርሃት ወደ ጸጋው ዙፋን እንቅረብ።
[]
[]
[]
[]
12,372
5  ከሰዎች መካከል የተመረጠ እያንዳንዱ ሊቀ ካህናት ለኃጢአት መባና መሥዋዕት ያቀርብ ዘንድ እነሱን በመወከል የአምላክን አገልግሎት ለማከናወን ይሾማል። 2  እሱ ራሱ ድክመት ስላለበት አላዋቂ የሆኑትንና የሚሳሳቱትን በርኅራኄ ሊይዛቸው ይችላል፤ 3  በዚህም የተነሳ ለሕዝቡ የኃጢአት መባ እንደሚያቀርብ ሁሉ ለራሱም ለማቅረብ ይገደዳል። 4  አንድ ሰው ይህን የክብር ቦታ የሚያገኘው እንደ አሮን፣ አምላክ ሲጠራው ብቻ ነው እንጂ በራሱ ፈቃድ አይደለም። 5  ክርስቶስም ሊቀ ካህናት በመሆን ራሱን ከፍ ከፍ አላደረገም፤ ከዚህ ይልቅ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ” ብሎ ስለ እሱ የተናገረው፣ ከፍ ከፍ አደረገው። 6  ደግሞም በሌላ ቦታ ላይ “እንደ መልከጼዴቅ፣ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሏል። 7  ክርስቶስ በምድር ላይ በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ለሚችለው በከፍተኛ ለቅሶና እንባ ምልጃና ልመና አቀረበ፤ አምላካዊ ፍርሃት ስለነበረውም ጸሎቱ ተሰማለት። 8  ልጅ ቢሆንም እንኳ ከደረሰበት መከራ መታዘዝን ተማረ። 9  በዚህም ፍጹም ከሆነ በኋላ የሚታዘዙት ሁሉ ዘላለማዊ መዳን እንዲያገኙ ምክንያት ሆነላቸው፤ 10  ምክንያቱም ከመልከጼዴቅ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ አምላክ ሊቀ ካህናት አድርጎ ሾሞታል። 11  እሱን በተመለከተ ብዙ የምንናገረው ነገር አለን፤ ይሁንና ጆሯችሁ ስለደነዘዘ ለማስረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው። 12  በአሁኑ ጊዜ አስተማሪዎች ልትሆኑ ይገባችሁ የነበረ ቢሆንም የአምላክን ቅዱስ መልእክት መሠረታዊ ነገሮች እንደገና ከመጀመሪያ ጀምሮ የሚያስተምራችሁ ሰው ትፈልጋላችሁ፤ ደግሞም ጠንካራ ምግብ ከመመገብ ይልቅ እንደገና ወተት መፈለግ ጀምራችኋል። 13  ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለሆነ ከጽድቅ ቃል ጋር ትውውቅ የለውም። 14  ጠንካራ ምግብ ግን ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታቸውን በማሠራት ላሠለጠኑ ጎልማሳ ሰዎች ነው።
[]
[]
[]
[]
12,373
6  ስለዚህ ስለ ክርስቶስ ከተማርነው መሠረታዊ ትምህርት አልፈን ስለሄድን ወደ ጉልምስና ለመድረስ እንጣጣር፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፤ ይኸውም ከሞቱ ሥራዎች ንስሐ ስለ መግባት፣ በአምላክ ስለ ማመን፣ 2  እንዲሁም ስለ ጥምቀቶች፣ እጆችን ስለ መጫን፣ ስለ ሙታን ትንሣኤና ስለ ዘላለማዊ ፍርድ የሚገልጹ ትምህርቶችን ደግመን አንማር። 3  አምላክ ከፈቀደ ይህን እናደርጋለን። 4  ቀደም ሲል ብርሃን በርቶላቸው የነበሩትን፣ ሰማያዊውን ነፃ ስጦታ የቀመሱትን፣ መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉትን፣ 5  መልካም የሆነውን የአምላክ ቃልና በሚመጣው ሥርዓት የሚገኙትን በረከቶች የቀመሱትን፣ 6  በኋላ ግን ከእምነት ጎዳና የራቁትን እንደገና ወደ ንስሐ መመለስ አይቻልም፤ ምክንያቱም የአምላክን ልጅ ለራሳቸው እንደገና በእንጨት ላይ ይቸነክሩታል፤ እንዲሁም በአደባባይ ያዋርዱታል። 7  በየጊዜው በላዩ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የሚጠጣና ለአራሾቹ መብል የሚሆን አትክልት የሚያፈራ መሬት ከአምላክ በረከትን ያገኛልና። 8  እሾህና አሜኬላ የሚያበቅል ከሆነ ግን የተተወና ለመረገም የተቃረበ ይሆናል፤ በመጨረሻም በእሳት ይቃጠላል። 9  ይሁን እንጂ የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ምንም እንኳ እንደዚህ ብለን ብንናገርም እናንተ በተሻለ ሁኔታ ላይ ይኸውም ወደ መዳን በሚያደርስ ሁኔታ ላይ እንደምትገኙ እርግጠኞች ነን። 10  አምላክ ቅዱሳንን በማገልገልም ሆነ ወደፊትም ማገልገላችሁን በመቀጠል የምታከናውኑትን ሥራ እንዲሁም ለስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር በመርሳት ፍትሕ አያዛባም። 11  ይሁንና ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ የሆነውን ተስፋ እስከ መጨረሻው መያዝ እንድትችሉ እያንዳንዳችሁ ያንኑ ትጋት እንድታሳዩ እንመኛለን፤ 12  ይህም አምላክ ቃል የገባቸውን ነገሮች በእምነትና በትዕግሥት የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ነው። 13  አምላክ ለአብርሃም ቃል በገባለት ጊዜ ሊምልበት የሚችል ከእሱ የሚበልጥ ሌላ ማንም ስለሌለ በራሱ ስም ማለ፤ 14  እንዲህም አለ፦ “በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በእርግጥ አበዛዋለሁ።” 15  በመሆኑም አብርሃም በትዕግሥት ከጠበቀ በኋላ ይህን የተስፋ ቃል አገኘ። 16  ሰዎች ከእነሱ በሚበልጥ ይምላሉ፤ መሐላቸውም እንደ ሕጋዊ ዋስትና ስለሆነ ማንኛውም ሙግት በመሐላው ይቋጫል። 17  በተመሳሳይም አምላክ ዓላማው ፈጽሞ የማይለወጥ መሆኑን ለተስፋው ቃል ወራሾች ይበልጥ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ለማሳየት በወሰነ ጊዜ የተስፋውን ቃል በመሐላ አረጋገጠ። 18  ይህን ያደረገው መጠጊያ ለማግኘት ወደ እሱ የሸሸን እኛ፣ አምላክ ሊዋሽ በማይችልባቸው፣ ፈጽሞ በማይለወጡት በእነዚህ ሁለት ነገሮች አማካኝነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን እንድንይዝ የሚረዳንን ከፍተኛ ማበረታቻ እንድናገኝ ነው። 19  እኛ ለነፍሳችን እንደ መልሕቅ አስተማማኝና ጽኑ የሆነ ይህ ተስፋ አለን፤ ተስፋውም መጋረጃውን አልፈን ወደ ውስጥ እንድንገባ ያስችለናል፤ 20  ከመልከጼዴቅ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው ኢየሱስ ፈር ቀዳጅ ሆኖ ስለ እኛ ወደዚያ ገብቷል።
[]
[]
[]
[]
12,374
7  አብርሃም ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሳሌም ንጉሥና የልዑሉ አምላክ ካህን የሆነው ይህ መልከጼዴቅ አግኝቶት ባረከው፤ 2  አብርሃም ደግሞ ከሁሉ ነገር አንድ አሥረኛ ሰጠው። በመጀመሪያ ስሙ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ ደግሞም የሳሌም ንጉሥ ማለትም “የሰላም ንጉሥ” ነው። 3  አባትና እናትም ሆነ የዘር ሐረግ እንዲሁም ለዘመኑ መጀመሪያ፣ ለሕይወቱም መጨረሻ የለውም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክን ልጅ እንዲመስል በመደረጉ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል። 4  እንግዲህ የቤተሰብ ራስ የሆነው አብርሃም ምርጥ ከሆነው ምርኮ ላይ አንድ አሥረኛውን የሰጠው ይህ ሰው ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ ተመልከቱ። 5  እርግጥ የክህነት ኃላፊነት የሚቀበሉ ከሌዊ ልጆች ወገን የሆኑት ሰዎች ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከገዛ ወንድሞቻቸው አሥራት እንዲሰበስቡ ሕጉ ያዛል። 6  ሆኖም ከእነሱ የትውልድ ሐረግ ያልመጣው ይህ ሰው ከአብርሃም አሥራት የተቀበለ ሲሆን የተስፋ ቃል የተሰጠውን ሰው ባርኮታል። 7  እንግዲህ አነስተኛ የሆነው ከእሱ በሚበልጠው እንደተባረከ ምንም ጥርጥር የለውም። 8  በአንድ በኩል አሥራት የሚቀበሉት ሟች የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በሌላ በኩል ግን አሥራት የሚቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሠከረለት ሰው ነው። 9  እንግዲህ አሥራት የሚቀበለው ሌዊ እንኳ በአብርሃም በኩል አሥራት ከፍሏል ማለት ይቻላል፤ 10  መልከጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ ሌዊ ገና በአባቱ በአብርሃም አብራክ ውስጥ ነበርና። 11  እንግዲህ ፍጽምና ሊገኝ የሚችለው በሌዊ ክህነት አማካኝነት ቢሆን ኖሮ (ክህነቱ ለሕዝቡ የተሰጠው ሕግ አንዱ ገጽታ ስለሆነ)፣ እንደ አሮን ሥርዓት ሳይሆን እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት ያለ ተብሎ የተነገረለት ሌላ ካህን መነሳቱ ምን ያስፈልግ ነበር? 12  ክህነቱ ስለሚለወጥ ሕጉም የግድ መለወጥ ያስፈልገዋልና። 13  ይህ ሁሉ ነገር የተነገረለት ሰው ከሌላ ነገድ የመጣ ነውና፤ ከዚህ ነገድ ማንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ያገለገለ የለም። 14  ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የታወቀ ነውና፤ ይሁንና ሙሴ ከዚህ ነገድ ካህናት እንደሚገኙ የተናገረው ነገር የለም። 15  ደግሞም እንደ መልከጼዴቅ ያለ ሌላ ካህን ሲነሳ ይህ ጉዳይ ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፤ 16  እሱ ካህን የሆነው በሥጋዊ ትውልድ ላይ በተመካውና ሕጉ በያዘው መሥፈርት ሳይሆን የማይጠፋ ሕይወት እንዲኖረው ባስቻለው ኃይል ነው። 17  “እንደ መልከጼዴቅ፣ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ተብሎ ተመሥክሮለታልና። 18  እንግዲህ የቀድሞው ትእዛዝ ደካማና ፍሬ ቢስ በመሆኑ ተሽሯል። 19  ሕጉ የትኛውንም ነገር ወደ ፍጽምና አላደረሰምና፤ ወደ አምላክ የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ መሰጠቱ ግን ይህን ማድረግ ችሏል። 20  በተጨማሪም ይህ ያለመሐላ እንዳልሆነ ሁሉ 21  (ያለመሐላ ካህናት የሆኑ ሰዎች አሉና፤ እሱ ግን በመሐላ ካህን ሆኗል፤ ይህም የሆነው “ይሖዋ ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ’ ብሎ ምሏል፤ ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም” በማለት ስለ እሱ የተናገረው አምላክ በማለው መሐላ መሠረት ነው፤) 22  እንደዚሁም ኢየሱስ ለተሻለ ቃል ኪዳን ዋስትና ሆኗል። 23  ከዚህም በተጨማሪ ካህናት አገልግሎታቸውን እንዳይቀጥሉ ሞት ስለሚያግዳቸው አንዱ ሌላውን እየተካ እንዲያገለግል ብዙዎች ካህናት መሆን ነበረባቸው፤ 24  እሱ ግን ለዘላለም ሕያው ሆኖ ስለሚኖር ክህነቱ ተተኪ የለውም። 25  ስለሆነም ለእነሱ ለመማለድ ሁልጊዜ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእሱ አማካኝነት ወደ አምላክ የሚቀርቡትን ፈጽሞ ሊያድናቸውም ይችላል። 26  እኛ የሚያስፈልገን ታማኝ፣ ቅን የሆነ፣ ያልረከሰ፣ ከኃጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው። 27  እነዚያ ሊቃነ ካህናት ያደርጉ እንደነበረው፣ በመጀመሪያ ለራሱ ኃጢአት ከዚያም ለሕዝቡ ኃጢአት በየዕለቱ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ምክንያቱም ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ ይህን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፈጽሞታል። 28  ሕጉ ድክመት ያለባቸውን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕጉ በኋላ የመጣው የመሐላ ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የተደረገውን ልጅ ይሾማል።
[]
[]
[]
[]
12,375
8  እንግዲህ የምንናገረው ነገር ዋና ነጥብ ይህ ነው፦ በሰማያት በግርማዊው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤ 2  እሱም የቅዱሱ ስፍራና የእውነተኛው ድንኳን አገልጋይ ነው፤ ይህም ድንኳን በሰው ሳይሆን በይሖዋ የተተከለ ነው። 3  እያንዳንዱ ሊቀ ካህናት የሚሾመው ስጦታና መሥዋዕት ለማቅረብ ነውና፤ በመሆኑም ይሄኛው ሊቀ ካህናትም የሚያቀርበው ነገር ያስፈልገዋል። 4  እሱ ምድር ላይ ቢሆን ኖሮ ካህን ባልሆነ ነበር፤ ምክንያቱም ሕጉ በሚያዘው መሠረት ስጦታ የሚያቀርቡ ሰዎች አሉ። 5  እነዚህ ሰዎች ለሰማያዊ ነገሮች ዓይነተኛ አምሳያና ጥላ የሆነ ቅዱስ አገልግሎት ያቀርባሉ፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኑን ለመሥራት በተዘጋጀ ጊዜ “በተራራው ላይ ተገልጦልህ ባየኸው ንድፍ መሠረት ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ ሥራ” ተብሎ ከተሰጠው መለኮታዊ ትእዛዝ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ነው። 6  ይሁንና ኢየሱስ እጅግ የላቀ አገልግሎት ተቀብሏል፤ ልክ እንደዚሁም ለተሻለ ቃል ኪዳን መካከለኛ ሆኗል፤ ይህም ቃል ኪዳን በተሻሉ ተስፋዎች ላይ በሕግ የጸና ነው። 7  የመጀመሪያው ቃል ኪዳን ምንም ጉድለት ባይኖረው ኖሮ ሁለተኛ ቃል ኪዳን ባላስፈለገ ነበር። 8  አምላክ በሕዝቡ ላይ ጉድለት ስላገኘ እንዲህ ብሎ ተናግሯልና፦ “‘እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። 9  ‘ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤ ምክንያቱም እነሱ በቃል ኪዳኔ አልጸኑም፤ በመሆኑም ችላ አልኳቸው’ ይላል ይሖዋ። 10  “‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና’ ይላል ይሖዋ። ‘ሕግጋቴን በአእምሯቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በልባቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ። እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። 11  “‘እነሱም እያንዳንዳቸው የአገራቸውን ሰው፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን “ይሖዋን እወቅ!” ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም። ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና። 12  ለክፉ ሥራቸው ምሕረት አደርግላቸዋለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም።’” 13  “አዲስ ቃል ኪዳን” ሲል የቀድሞውን ቃል ኪዳን ጊዜ ያለፈበት አድርጎታል። ስለዚህ ጊዜ ያለፈበትና እያረጀ ያለው ቃል ኪዳን ሊጠፋ ተቃርቧል።
[]
[]
[]
[]
12,376
9  የቀድሞው ቃል ኪዳን በበኩሉ ቅዱስ አገልግሎት የሚከናወንባቸው ደንቦችና በምድር ላይ የራሱ ቅዱስ ስፍራ ነበረው። 2  መቅረዙ፣ ጠረጴዛውና በአምላክ ፊት የቀረበው ኅብስት የሚገኙበት የድንኳኑ የመጀመሪያው ክፍል ተሠርቶ ነበር፤ ይህም ቅድስት ይባላል። 3  ከሁለተኛው መጋረጃ በስተ ኋላ ግን ቅድስተ ቅዱሳን የሚባለው የድንኳኑ ክፍል ይገኝ ነበር። 4  በዚህ ክፍል ውስጥ የወርቅ ጥና እና ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠው የቃል ኪዳኑ ታቦት ይገኙ ነበር፤ በታቦቱ ውስጥም መና የያዘው የወርቅ ማሰሮ፣ ያቆጠቆጠችው የአሮን በትርና የቃል ኪዳኑ ጽላቶች ነበሩ፤ 5  በላዩ ላይ ደግሞ የስርየት መክደኛውን የሚጋርዱ ክብራማ ኪሩቦች ነበሩ። ይሁንና ስለ እነዚህ ነገሮች በዝርዝር ለመናገር አሁን ጊዜው አይደለም። 6  እነዚህ ነገሮች በዚህ መንገድ ከተሠሩ በኋላ ካህናቱ ቅዱስ አገልግሎቶችን ለማከናወን ወደ ድንኳኑ የመጀመሪያ ክፍል ሁልጊዜ ይገባሉ፤ 7  ወደ ሁለተኛው ክፍል የሚገባው ግን ሊቀ ካህናቱ ብቻ ነበር፤ የሚገባውም በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ ደግሞም ለራሱና ሕዝቡ ባለማወቅ ለፈጸመው ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም። 8  በዚህ መንገድ፣ የመጀመሪያው ድንኳን ተተክሎ ሳለ ወደ ቅዱሱ ስፍራ የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ግልጽ አድርጓል። 9  ይህ ድንኳን ለአሁኑ ዘመን ምሳሌ ሲሆን ከዚህ ዝግጅት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ስጦታዎችና መሥዋዕቶች ይቀርባሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሮች ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርበው ሰው ፍጹም በሆነ መንገድ ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረው ሊያደርጉ አይችሉም። 10  እነዚህ ነገሮች ከምግብ፣ ከመጠጥና ከተለያዩ የመንጻት ሥርዓቶች ጋር ብቻ የተያያዙ ናቸው። ደግሞም አካልን የሚመለከቱ ደንቦች ሲሆኑ በሥራ ላይ የዋሉትም፣ ሁኔታዎች የሚስተካከሉበት የተወሰነው ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ነበር። 11  ይሁን እንጂ ክርስቶስ አሁን ላሉት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ በሰው እጅ ወዳልተሠራው ይኸውም ከዚህ ፍጥረት ወዳልሆነው ይበልጥ ታላቅና ፍጹም ወደሆነው ድንኳን ገብቷል። 12  ወደ ቅዱሱ ስፍራ የገባው የፍየሎችንና የወይፈኖችን ደም ይዞ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የገዛ ራሱን ደም ይዞ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገባ፤ ደግሞም ለእኛ ዘላለማዊ መዳን አስገኘልን። 13  የፍየሎችና የኮርማዎች ደም እንዲሁም በረከሱ ሰዎች ላይ የሚረጭ የጊደር አመድ ሥጋን በማንጻት የሚቀድስ ከሆነ 14  በዘላለማዊ መንፈስ አማካኝነት ራሱን ያላንዳች እንከን ለአምላክ ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው ለሆነው አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንድናቀርብ ሕሊናችንን ከሞቱ ሥራዎች እንዴት አብልጦ አያነጻም? 15  የአዲስ ቃል ኪዳን መካከለኛ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው። መካከለኛ የሆነውም የተጠሩት የዘላለማዊውን ውርሻ ተስፋ ይቀበሉ ዘንድ ነው። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በሞቱ የተነሳ ሲሆን በእሱ ሞት አማካኝነት በቀድሞው ቃል ኪዳን ሥር ሆነው ሕግ በመተላለፍ ከፈጸሟቸው ድርጊቶች በቤዛ ነፃ ወጥተዋል። 16  ቃል ኪዳን ሲኖር ቃል ኪዳኑን የፈጸመው ሰው መሞቱ መረጋገጥ አለበት፤ 17  ምክንያቱም ቃል ኪዳኑን የፈጸመው ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ቃል ኪዳኑ መቼም ተፈጻሚ ሊሆን ስለማይችል ቃል ኪዳን የሚጸናው ሞትን መሠረት በማድረግ ነው። 18  ከዚህም የተነሳ የቀድሞው ቃል ኪዳንም ያለደም ሥራ ላይ መዋል አልጀመረም። 19  ሙሴ በሕጉ ላይ የሰፈረውን እያንዳንዱን ትእዛዝ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ የወይፈኖችንና የፍየሎችን ደም ከውኃ፣ ከቀይ ሱፍና ከሂሶጵ ጋር ወስዶ መጽሐፉንና ሕዝቡን ሁሉ ረጭቷል፤ 20  የረጨውም “አምላክ እንድትጠብቁት ያዘዛችሁ የቃል ኪዳኑ ደም ይህ ነው” ብሎ ነው። 21  በተመሳሳይም በድንኳኑና ቅዱስ አገልግሎት በሚቀርብባቸው ዕቃዎች ሁሉ ላይ ደም ረጭቷል። 22  አዎ፣ በሕጉ መሠረት ሁሉም ነገር ማለት ይቻላል በደም ይነጻል፤ ደም ካልፈሰሰ በስተቀር ይቅርታ ማግኘት አይቻልም። 23  ስለዚህ በሰማያት ላሉት ነገሮች ዓይነተኛ አምሳያ የሆኑት ሁሉ በዚህ መንገድ መንጻታቸው የግድ አስፈላጊ ነበር፤ በሰማያት ያሉት ነገሮች ግን የተሻሉ መሥዋዕቶች ያስፈልጓቸዋል። 24  ክርስቶስ የገባው በሰው እጅ ወደተሠራውና የእውነተኛው ቅዱስ ስፍራ አምሳያ ወደሆነው ስፍራ አይደለምና፤ ከዚህ ይልቅ አሁን ስለ እኛ በአምላክ ፊት ይታይ ዘንድ ወደ ሰማይ ገብቷል። 25  የገባው ግን ሊቀ ካህናቱ የራሱን ሳይሆን የእንስሳ ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይገባ እንደነበረው ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ አይደለም። 26  አለዚያማ ዓለም ከተመሠረተ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ኃጢአትን ለማስወገድ በሥርዓቶቹ መደምደሚያ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ራሱን ገልጧል። 27  ሰው ሁሉ አንድ ጊዜ መሞቱ አይቀርም፤ ከዚያ በኋላ ግን ፍርድ ይቀበላል፤ 28  በተመሳሳይም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለመሸከም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል፤ ለሁለተኛ ጊዜ የሚገለጠውም ኃጢአትን ለማስወገድ አይደለም፤ መዳን ለማግኘት እሱን በጉጉት የሚጠባበቁትም ያዩታል።
[]
[]
[]
[]
12,377
1  በኤርምያስ በኩል የተነገረው የይሖዋ ቃል ይፈጸም ዘንድ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት የሚከተለውን አዋጅ በመላ ግዛቱ እንዲያውጅ ይሖዋ የፋርሱን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሳሳ፤ እሱም ይህ በጽሑፍ እንዲሰፍር አደረገ፦ 2  “የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማይ አምላክ ይሖዋ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳ በምትገኘው በኢየሩሳሌምም ቤት እንድሠራለት አዞኛል። 3  ከእሱ ሕዝብ መካከል የሆነ አብሯችሁ የሚኖር ማንኛውም ሰው አምላኩ ከእሱ ጋር ይሁን፤ እሱም በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፤ ቤቱ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ቤትም መልሶ ይገንባ፤ እሱ እውነተኛ አምላክ ነው። 4  በየትኛውም ስፍራ የባዕድ አገር ሰው ሆኖ የሚኖረውን ማንኛውንም ሰው፣ ጎረቤቶቹ በኢየሩሳሌም ለነበረው ለእውነተኛው አምላክ ቤት ከሚቀርበው የፈቃደኝነት መባ በተጨማሪ ብር፣ ወርቅ፣ የተለያዩ ዕቃዎችና የቤት እንስሳት በመስጠት ይርዱት።’” 5  ከዚያም የይሁዳና የቢንያም የአባቶች ቤት መሪዎች፣ ካህናቱና ሌዋውያኑ፣ እውነተኛው አምላክ መንፈሳቸውን ያነሳሳው ሰዎች ሁሉ ወጥተው በኢየሩሳሌም የነበረውን የይሖዋን ቤት መልሰው ለመገንባት ተዘጋጁ። 6  በዙሪያቸው ያሉትም ሁሉ በፈቃደኝነት ከተሰጠው መባ በተጨማሪ የብርና የወርቅ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ ዕቃዎችን፣ የቤት እንስሳትን እንዲሁም ውድ የሆኑ ነገሮችን በመስጠት ረዷቸው። 7  በተጨማሪም ንጉሥ ቂሮስ፣ ናቡከደነጾር ከኢየሩሳሌም ወስዶ በአምላኩ ቤት ያስቀመጣቸውን የይሖዋን ቤት ዕቃዎች አወጣ። 8  የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ በግምጃ ቤቱ ኃላፊ በሚትረዳት ተቆጣጣሪነት ዕቃዎቹ እንዲወጡ አደረገ፤ ሚትረዳትም ለይሁዳው አለቃ ለሸሽባጻር ቆጥሮ አስረከበው። 9  የተቆጠሩት ዕቃዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ በቅርጫት ቅርጽ የተሠሩ 30 የወርቅ ዕቃዎች፣ በቅርጫት ቅርጽ የተሠሩ 1,000 የብር ዕቃዎችና 29 ምትክ ዕቃዎች 10  እንዲሁም 30 ትናንሽ ጎድጓዳ የወርቅ ሳህኖች፣ 410 አነስተኛ ጎድጓዳ የብር ሳህኖችና 1,000 ሌሎች ዕቃዎች። 11  የወርቅና የብር ዕቃዎቹ በአጠቃላይ 5,400 ነበሩ። ሸሽባጻርም ግዞተኞቹ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ይዞ ወጣ።
[]
[]
[]
[]
12,378
10  ዕዝራ በእውነተኛው አምላክ ቤት ፊት ተደፍቶ እያለቀሰ፣ እየጸለየና እየተናዘዘ ሳለ በርካታ ቁጥር ያላቸው እስራኤላውያን ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ ሕዝቡም ምርር ብሎ ያለቅስ ነበር። 2  ከዚያም ከኤላም ልጆች መካከል የየሂኤል ልጅ ሸካንያህ ዕዝራን እንዲህ አለው፦ “በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦች መካከል ባዕዳን ሴቶችን በማግባት በአምላካችን ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጽመናል። ያም ሆኖ እስራኤል አሁንም ተስፋ አለው። 3  እንግዲህ ይሖዋም ሆነ ለአምላካችን ትእዛዝ አክብሮት ያላቸው ሰዎች በሰጡት መመሪያ መሠረት ሚስቶቻችንን በሙሉና ከእነሱ የተወለዱትን ልጆች ለማሰናበት ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እንጋባ። ሕጉንም ተግባራዊ እናድርግ። 4  ይህ የአንተ ኃላፊነት ስለሆነ ተነስ፤ እኛም ከጎንህ ነን። አይዞህ፣ እርምጃ ውሰድ።” 5  በዚህ ጊዜ ዕዝራ ተነስቶ የቀረበውን ሐሳብ ተግባራዊ እንዲያደርጉ የካህናቱን፣ የሌዋውያኑንና የመላው እስራኤልን አለቆች አስማላቸው፤ እነሱም ማሉ። 6  ከዚያም ዕዝራ ከእውነተኛው አምላክ ቤት ፊት ተነስቶ የኤልያሺብ ልጅ ወደሆነው ወደ የሆሃናን ክፍል ሄደ። ሆኖም በግዞት የተወሰደው ሕዝብ በፈጸመው ታማኝነት የጎደለው ድርጊት አዝኖ ስለነበር ወደዚያ ቢሄድም እንኳ እህል አልቀመሰም፤ ውኃም አልጠጣም። 7  ከዚያም በግዞት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የሚያዝዝ አዋጅ በይሁዳና በኢየሩሳሌም አወጁ፤ 8  መኳንንቱና ሽማግሌዎቹ ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ማንኛውም ሰው ንብረቱ በሙሉ እንዲወረስና በግዞት ከተወሰደው ሕዝብ ጉባኤ እንዲባረር ይደረጋል። 9  በመሆኑም ከይሁዳና ከቢንያም ነገድ የሆኑ ወንዶች ሁሉ በሦስት ቀን ውስጥ ማለትም በዘጠነኛው ወር ከወሩም በ20ኛው ቀን በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ በእውነተኛው አምላክ ቤት ግቢ ውስጥ ተቀምጠው ነበር፤ ከጉዳዩ ክብደትና ከሚዘንበው ኃይለኛ ዝናብ የተነሳም ይንቀጠቀጡ ነበር። 10  ከዚያም ካህኑ ዕዝራ ተነስቶ እንዲህ አላቸው፦ “ባዕዳን ሚስቶችን በማግባት ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጽማችኋል፤ በዚህም የተነሳ የእስራኤል በደል እንዲበዛ አድርጋችኋል። 11  እንግዲህ አሁን ለአባቶቻችሁ አምላክ ለይሖዋ ተናዘዙ፤ ፈቃዱንም ፈጽሙ። በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦችና ከባዕዳን ሚስቶቻችሁ ራሳችሁን ለዩ።” 12  በዚህ ጊዜ መላው ጉባኤ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ልክ እንደተናገርከው ማድረግ ግዴታችን ነው። 13  ይሁንና ሕዝቡ ብዙ ነው፤ የዝናብ ወቅት ስለሆነ ውጭ መቆም አስቸጋሪ ነው። ደግሞም ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የፈጸምነው ዓመፅ እጅግ ከባድ በመሆኑ ጉዳዩ በአንድ ወይም በሁለት ቀን የሚቋጭ አይደለም። 14  ስለዚህ እባክህ መኳንንታችን ለመላው ጉባኤ ተወካይ ሆነው ያገልግሉ፤ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ በከተሞቻችን በሙሉ የሚገኙ ሰዎችም ከእያንዳንዱ ከተማ ሽማግሌዎችና ፈራጆች ጋር በተወሰነው ጊዜ ይምጡ፤ በዚህ ጉዳይ የተነሳ የመጣብን የአምላካችን የሚነድ ቁጣ እስኪመለስ ድረስ እንዲህ ብናደርግ የተሻለ ነው።” 15  ይሁን እንጂ የአሳሄል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ያህዘያህ ይህን ሐሳብ ተቃወሙ፤ ሌዋውያኑ መሹላምና ሻበታይም ተባበሯቸው። 16  ሆኖም በግዞት የነበሩት ሰዎች በስምምነቱ መሠረት እርምጃ ወሰዱ፤ ከዚያም በአሥረኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ካህኑ ዕዝራና በየስማቸው የተመዘገቡት የአባቶቻቸው ቤት የቤተሰብ መሪዎች ሁሉ ጉዳዩን ለመመርመር ብቻቸውን ተሰበሰቡ። 17  እነሱም ባዕዳን ሴቶችን ያገቡትን ሰዎች ጉዳይ በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ መርምረው ጨረሱ። 18  ባዕዳን ሴቶችን ካገቡት ሰዎችም መካከል አንዳንድ የካህናት ልጆች መኖራቸው ታወቀ፤ እነሱም የየሆጼዴቅ ልጅ የየሆሹዋ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች የሆኑት ማአሴያህ፣ ኤሊዔዘር፣ ያሪብ እና ጎዶልያስ ናቸው። 19  እነዚህ ሰዎች ሚስቶቻቸውን ለማሰናበት ቃል ገቡ፤ በደለኞች ስለሆኑም ለበደላቸው ከመንጋው መካከል አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ። 20  ከኢሜር ወንዶች ልጆች ሃናኒ እና ዘባድያህ፤ 21  ከሃሪም ወንዶች ልጆች ማአሴያህ፣ ኤልያስ፣ ሸማያህ፣ የሂኤል እና ዖዝያ፤ 22  ከጳስኮር ወንዶች ልጆች ኤሊዮዔናይ፣ ማአሴያህ፣ እስማኤል፣ ናትናኤል፣ ዮዛባድ እና ኤልዓሳ። 23  ከሌዋውያኑ መካከል ዮዛባድ፣ ሺምአይ፣ ቄላያህ (ማለትም ቀሊጣ)፣ ፐታያህ፣ ይሁዳ እና ኤሊዔዘር፤ 24  ከዘማሪዎቹ መካከል ኤልያሺብ፤ ከበር ጠባቂዎቹ መካከል ሻሉም፣ ተሌም እና ዖሪ። 25  ከእስራኤል መካከል የፓሮሽ ወንዶች ልጆች የሆኑት ራምያህ፣ ይዝዚያህ፣ ማልኪያህ፣ ሚያሚን፣ አልዓዛር፣ ማልኪያህ እና በናያህ ነበሩ፤ 26  ከኤላም ወንዶች ልጆች ማታንያህ፣ ዘካርያስ፣ የሂኤል፣ አብዲ፣ የሬሞት እና ኤልያስ፤ 27  ከዛቱ ወንዶች ልጆች ኤሊዮዔናይ፣ ኤልያሺብ፣ ማታንያህ፣ የሬሞት፣ ዛባድ እና አዚዛ፤ 28  ከቤባይ ወንዶች ልጆች የሆሃናን፣ ሃናንያህ፣ ዛባይ እና አትላይ፤ 29  ከባኒ ወንዶች ልጆች መሹላም፣ ማሉክ፣ አዳያህ፣ ያሹብ፣ ሸአል እና የሬሞት፤ 30  ከፓሃትሞአብ ወንዶች ልጆች አድና፣ ከላል፣ በናያህ፣ ማአሴያህ፣ ማታንያህ፣ ባስልኤል፣ ቢኑይ እና ምናሴ፤ 31  ከሃሪም ወንዶች ልጆች ኤሊዔዘር፣ ይሽሺያህ፣ ማልኪያህ፣ ሸማያህ፣ ሺምኦን፣ 32  ቢንያም፣ ማሉክ እና ሸማርያህ፤ 33  ከሃሹም ወንዶች ልጆች ማቴናይ፣ ማታታ፣ ዛባድ፣ ኤሊፌሌት፣ የሬማይ፣ ምናሴ እና ሺምአይ፤ 34  ከባኒ ወንዶች ልጆች ማአዳይ፣ አምራም፣ ዑኤል፣ 35  በናያህ፣ ቤድያህ፣ ከሉሂ፣ 36  ዋንያህ፣ መሬሞት፣ ኤልያሺብ፣ 37  ማታንያህ፣ ማቴናይ እና ያአሱ፤ 38  ከቢኑይ ወንዶች ልጆች ሺምአይ፣ 39  ሸሌምያህ፣ ናታን፣ አዳያህ፣ 40  ማክናደባይ፣ ሻሻይ፣ ሻራይ፣ 41  አዛርዔል፣ ሸሌምያህ፣ ሸማርያህ፣ 42  ሻሉም፣ አማርያህ እና ዮሴፍ፤ 43  ከነቦ ወንዶች ልጆች የኢዔል፣ ማቲትያህ፣ ዛባድ፣ ዘቢና፣ ያዳይ፣ ኢዩኤል እና በናያህ። 44  እነዚህ ሁሉ ባዕዳን ሚስቶችን ያገቡ ናቸው፤ እነሱም ሚስቶቻቸውን ከነልጆቻቸው አሰናበቱ።
[]
[]
[]
[]
12,379
2  የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ባቢሎን በግዞት ወስዷቸው የነበሩትና ተማርከው በግዞት ከተወሰዱት መካከል ወጥተው በኋላ ላይ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ይኸውም ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት የአውራጃው ነዋሪዎች እነዚህ ናቸው፤ 2  ከዘሩባቤል፣ ከየሆሹዋ፣ ከነህምያ፣ ከሰራያህ፣ ከረኤላያህ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከቢልሻን፣ ከሚስጳር፣ ከቢግዋይ፣ ከረሁምና ከባአናህ ጋር የመጡት እነዚህ ናቸው። የእስራኤላውያን ወንዶች ቁጥር የሚከተሉትንም ይጨምራል፦ 3  የፓሮሽ ወንዶች ልጆች 2,172፣ 4  የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች 372፣ 5  የኤራ ወንዶች ልጆች 775፣ 6  የየሹዋና የኢዮዓብ ወንዶች ልጆች የሆኑት የፓሃትሞአብ ወንዶች ልጆች 2,812፣ 7  የኤላም ወንዶች ልጆች 1,254፣ 8  የዛቱ ወንዶች ልጆች 945፣ 9  የዛካይ ወንዶች ልጆች 760፣ 10  የባኒ ወንዶች ልጆች 642፣ 11  የቤባይ ወንዶች ልጆች 623፣ 12  የአዝጋድ ወንዶች ልጆች 1,222፣ 13  የአዶኒቃም ወንዶች ልጆች 666፣ 14  የቢግዋይ ወንዶች ልጆች 2,056፣ 15  የአዲን ወንዶች ልጆች 454፣ 16  የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ወንዶች ልጆች 98፣ 17  የቤጻይ ወንዶች ልጆች 323፣ 18  የዮራ ወንዶች ልጆች 112፣ 19  የሃሹም ወንዶች ልጆች 223፣ 20  የጊባር ወንዶች ልጆች 95፣ 21  የቤተልሔም ወንዶች ልጆች 123፣ 22  የነጦፋ ወንዶች ልጆች 56፣ 23  የአናቶት ሰዎች 128፣ 24  የአዝማዌት ወንዶች ልጆች 42፣ 25  የቂርያትየአሪም፣ የከፊራና የበኤሮት ወንዶች ልጆች 743፣ 26  የራማና የጌባ ወንዶች ልጆች 621፣ 27  የሚክማስ ሰዎች 122፣ 28  የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223፣ 29  የነቦ ወንዶች ልጆች 52፣ 30  የማግቢሽ ወንዶች ልጆች 156፣ 31  የሌላኛው ኤላም ወንዶች ልጆች 1,254፣ 32  የሃሪም ወንዶች ልጆች 320፣ 33  የሎድ፣ የሃዲድና የኦኖ ወንዶች ልጆች 725፣ 34  የኢያሪኮ ወንዶች ልጆች 345፣ 35  የሰናአ ወንዶች ልጆች 3,630። 36  ካህናቱ የሚከተሉት ናቸው፦ ከየሹዋ ቤተሰብ የሆነው የየዳያህ ወንዶች ልጆች 973፣ 37  የኢሜር ወንዶች ልጆች 1,052፣ 38  የጳስኮር ወንዶች ልጆች 1,247፣ 39  የሃሪም ወንዶች ልጆች 1,017። 40  ሌዋውያኑ የሚከተሉት ናቸው፦ የሆዳውያህ ወንዶች ልጆች የሆኑት የየሹዋና የቃድሚኤል ወንዶች ልጆች 74። 41  ዘማሪዎቹ የአሳፍ ወንዶች ልጆች 128። 42  የበር ጠባቂዎቹ ወንዶች ልጆች የሆኑት የሻሉም ወንዶች ልጆች፣ የአጤር ወንዶች ልጆች፣ የታልሞን ወንዶች ልጆች፣ የአቁብ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢጣ ወንዶች ልጆችና የሾባይ ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 139። 43  የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የሚከተሉት ናቸው፦ የጺሃ ወንዶች ልጆች፣ የሃሱፋ ወንዶች ልጆች፣ የታባኦት ወንዶች ልጆች፣ 44  የቀሮስ ወንዶች ልጆች፣ የሲአ ወንዶች ልጆች፣ የፓዶን ወንዶች ልጆች፣ 45  የለባና ወንዶች ልጆች፣ የሃጋባ ወንዶች ልጆች፣ የአቁብ ወንዶች ልጆች፣ 46  የሃጋብ ወንዶች ልጆች፣ የሳልማይ ወንዶች ልጆች፣ የሃናን ወንዶች ልጆች፣ 47  የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ የጋሃር ወንዶች ልጆች፣ የረአያህ ወንዶች ልጆች፣ 48  የረጺን ወንዶች ልጆች፣ የነቆዳ ወንዶች ልጆች፣ የጋዛም ወንዶች ልጆች፣ 49  የዑዛ ወንዶች ልጆች፣ የፓሰአህ ወንዶች ልጆች፣ የቤሳይ ወንዶች ልጆች፣ 50  የአስና ወንዶች ልጆች፣ የመኡኒም ወንዶች ልጆች፣ የነፉሲም ወንዶች ልጆች፣ 51  የባቅቡቅ ወንዶች ልጆች፣ የሃቁፋ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሑር ወንዶች ልጆች፣ 52  የባጽሉት ወንዶች ልጆች፣ የመሂዳ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሻ ወንዶች ልጆች፣ 53   የባርቆስ ወንዶች ልጆች፣ የሲሳራ ወንዶች ልጆች፣ የተማ ወንዶች ልጆች፣ 54  የነጺሃ ወንዶች ልጆችና የሃጢፋ ወንዶች ልጆች። 55  የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የሶጣይ ወንዶች ልጆች፣ የሶፈረት ወንዶች ልጆች፣ የፐሩዳ ወንዶች ልጆች፣ 56  የያላ ወንዶች ልጆች፣ የዳርቆን ወንዶች ልጆች፣ የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ 57   የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢል ወንዶች ልጆች፣ የፖክሄሬትሃጸባይም ወንዶች ልጆችና የአሚ ወንዶች ልጆች። 58  የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 392 ነበሩ። 59  ከቴልመላ፣ ከቴልሃርሻ፣ ከከሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የወጡት ሆኖም ከየትኛው የአባቶች ቤትና የዘር ሐረግ እንደመጡ በውል መለየትም ሆነ እስራኤላዊ መሆን አለመሆናቸውን በትክክል ማረጋገጥ ያልቻሉት የሚከተሉት ናቸው፦ 60  የደላያህ ወንዶች ልጆች፣ የጦብያ ወንዶች ልጆችና የነቆዳ ወንዶች ልጆች 652። 61  ከካህናቱ ወንዶች ልጆች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃባያ ወንዶች ልጆች፣ የሃቆጽ ወንዶች ልጆች እንዲሁም ከጊልያዳዊው ከቤርዜሊ ሴቶች ልጆች መካከል አንዷን ያገባውና በስማቸው የተጠራው የቤርዜሊ ወንዶች ልጆች። 62  እነዚህ የዘር ሐረጋቸውን ለማረጋገጥ በመዝገቡ ላይ የቤተሰባቸውን ስም ለማግኘት ቢጥሩም ሊያገኙት አልቻሉም፤ በመሆኑም ከክህነት አገልግሎቱ ታገዱ። 63  ገዢውም በኡሪምና ቱሚም አማካኝነት ምክር የሚጠይቅ ካህን እስኪገኝ ድረስ እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት እንደማይችሉ ነገራቸው። 64  መላው ጉባኤ በአጠቃላይ 42,360 ነበር፤ 65  ይህ 7,337 ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን አይጨምርም፤ በተጨማሪም 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎች ነበሯቸው። 66  ከዚህም ሌላ 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች 67  እንዲሁም 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው። 68  ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ኢየሩሳሌም ወደነበረው ወደ ይሖዋ ቤት ሲደርሱ ቤቱን በቀድሞ ቦታው ላይ መልሶ ለመገንባት ለእውነተኛው አምላክ ቤት የፈቃደኝነት መባዎችን አቀረቡ። 69  እነሱም ለሥራው ማስኬጃ እንዲሆን እንደየአቅማቸው 61,000 የወርቅ ድራክማ፣ 5,000 የብር ምናን እና 100 የካህናት ቀሚስ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። 70  ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ፣ ዘማሪዎቹ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ፤ የቀሩትም እስራኤላውያን በሙሉ በየከተሞቻቸው መኖር ጀመሩ።
[]
[]
[]
[]
12,380
3  በሰባተኛው ወር እስራኤላውያን በከተሞቻቸው ውስጥ ነበሩ፤ እነሱም ልክ እንደ አንድ ሰው ሆነው በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። 2  የየሆጼዴቅ ልጅ የሹዋና አብረውት የሚያገለግሉት ካህናት እንዲሁም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ወንድሞቹ በእውነተኛው አምላክ ሰው በሙሴ ሕግ ውስጥ በተጻፈው መሠረት በላዩ ላይ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን ለማቅረብ የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ። 3  በዙሪያቸው ባሉት አገሮች በሚኖሩት ሕዝቦች የተነሳ ፍርሃት አድሮባቸው የነበረ ቢሆንም መሠዊያውን በቀድሞ ቦታው ላይ ሠሩት፤ በላዩም ላይ ለይሖዋ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን ይኸውም ጠዋትና ማታ የሚቀርቡትን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ማቅረብ ጀመሩ። 4  ከዚያም በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት የዳስ በዓልን አከበሩ፤ እንዲሁም በእያንዳንዱ ቀን እንዲቀርብ በታዘዘው መጠን መሠረት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን አቀረቡ። 5  ከዚያም የተለመደውን የሚቃጠል መባ፣ ለአዲስ ጨረቃና ለተቀደሱት የይሖዋ በዓላት የሚቀርቡትን መባዎች እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው ለይሖዋ የሚያቀርበውን የፈቃደኝነት መባ አቀረቡ። 6  የይሖዋ ቤተ መቅደስ መሠረት ገና ያልተጣለ ቢሆንም ከሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለይሖዋ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን ማቅረብ ጀመሩ። 7  ለድንጋይ ጠራቢዎቹና ለእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹም ገንዘብ ሰጡ፤ በተጨማሪም የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ በሰጣቸው ፈቃድ መሠረት የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎችን ከሊባኖስ ወደ ኢዮጴ ወደብ ለሚያመጡ ለሲዶና እና ለጢሮስ ሰዎች የሚበላና የሚጠጣ ነገር እንዲሁም ዘይት ሰጡ። 8  በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እውነተኛው አምላክ ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የየሆጼዴቅ ልጅ የሹዋ እንዲሁም ካህናቱን፣ ሌዋውያኑንና ከምርኮ ወጥተው ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትን በሙሉ ጨምሮ የቀሩት ወንድሞቻቸው ሥራውን ጀመሩ፤ የይሖዋን ቤት ሥራ በበላይነት እንዲቆጣጠሩም ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሌዋውያንን ሾሙ። 9  በመሆኑም የሹዋ፣ ወንዶች ልጆቹና ወንድሞቹ፣ ቃድሚኤልና ወንዶች ልጆቹ እንዲሁም የይሁዳ ወንዶች ልጆች ሌዋውያን ከሆኑት የሄናዳድ ወንዶች ልጆች፣ ከእነሱ ወንዶች ልጆችና ከወንድሞቻቸው ጋር ሆነው በእውነተኛው አምላክ ቤት ውስጥ ሥራውን የሚሠሩትን ሰዎች በበላይነት ለመቆጣጠር ተባበሩ። 10  የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚገነቡት ሰዎች መሠረቱን ሲጥሉ የክህነት ልብሳቸውን የለበሱት ካህናት በመለከት፣ ሌዋውያኑ የአሳፍ ወንዶች ልጆች ደግሞ በሲምባል የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት ይሖዋን ለማወደስ ተነሱ። 11  “እሱ ጥሩ ነውና፤ ለእስራኤል የሚያሳየውም ታማኝ ፍቅር ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና” በማለት እየተቀባበሉ ይሖዋን ማወደስና ማመስገን ጀመሩ። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ የይሖዋ ቤት መሠረት በመጣሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይሖዋን አወደሰ። 12  የቀድሞውን ቤት ያዩ ሽማግሌዎች ይኸውም ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑና ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አብዛኞቹ የዚህ ቤት መሠረት ሲጣል ሲያዩ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ብዙዎቹ ግን በደስታ እልልታቸውን አቀለጡት። 13  ሕዝቡ ድምፁ ከሩቅ እስኪሰማ ድረስ ከፍ ባለ ድምፅ ይጮኽ ስለነበር ሰዎቹ የደስታውን እልልታ ከለቅሶው ጩኸት መለየት አልቻሉም ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,381
4  የይሁዳና የቢንያም ጠላቶች፣ ከግዞት የተመለሱት ሰዎች ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ቤተ መቅደስ እየገነቡ መሆናቸውን ሲሰሙ 2  ወዲያውኑ ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤት መሪዎች ቀርበው እንዲህ አሏቸው፦ “ከእናንተ ጋር እንገንባ፤ ልክ እንደ እናንተ እኛም አምላካችሁን እናመልካለን፤ ደግሞም ወደዚህ ካመጣን ከአሦር ንጉሥ ከኤሳርሃደን ዘመን ጀምሮ ለእሱ መሥዋዕት ስናቀርብ ኖረናል።” 3  ይሁንና ዘሩባቤል፣ የሆሹዋና የቀሩት የእስራኤል አባቶች ቤት መሪዎች እንዲህ አሏቸው፦ “የአምላካችንን ቤት በመገንባቱ ሥራ ከእኛ ጋር ተካፋይ መሆን አትችሉም፤ ምክንያቱም የፋርሱ ንጉሥ፣ ንጉሥ ቂሮስ ባዘዘን መሠረት እኛው ራሳችን የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ቤት እንገነባለን።” 4  የምድሪቱም ነዋሪዎች የይሁዳን ሕዝቦች ተስፋ ለማስቆረጥና ወኔ ከድቷቸው የግንባታ ሥራውን እንዲያቆሙ ለማድረግ ዘወትር ይጥሩ ነበር። 5  ከፋርሱ ንጉሥ ከቂሮስ ዘመን አንስቶ እስከ ፋርሱ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ የግዛት ዘመን ድረስ እቅዶቻቸውን ለማጨናገፍ አማካሪዎችን ቀጠሩባቸው። 6  በተጨማሪም በአሐሽዌሮስ የግዛት ዘመን መጀመሪያ ላይ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ በጽሑፍ ክስ መሠረቱባቸው። 7  ከዚህም ሌላ በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፣ ሚትረዳት፣ ታብኤልና የቀሩት ግብረ አበሮቹ ለንጉሥ አርጤክስስ ደብዳቤ ጻፉ፤ ደብዳቤውንም ወደ አረማይክ ቋንቋ ተርጉመው በአረማይክ ፊደል ጻፉት። 8   ዋናው የመንግሥት ባለሥልጣን ረሁም እና ጸሐፊው ሺምሻይ ኢየሩሳሌምን በመክሰስ ለንጉሥ አርጤክስስ የሚከተለውን ደብዳቤ ጻፉ፦ 9  (ደብዳቤውን የላኩት ዋናው የመንግሥት ባለሥልጣን ረሁም፣ ጸሐፊው ሺምሻይና የቀሩት ግብረ አበሮቻቸው እንዲሁም ዳኞቹ፣ የበታች ገዢዎቹ፣ ጸሐፊዎቹ፣ የኤሬክ ሕዝቦች፣ ባቢሎናውያን፣ የሱሳ ነዋሪዎች ማለትም ኤላማውያን፣ 10  ታላቁና የተከበረው አስናፈር በግዞት ወስዶ በሰማርያ ከተሞች ያሰፈራቸው የቀሩት ብሔራትና ከወንዙ ባሻገር ባለው ክልል የሚኖሩት የቀሩት ሰዎች ነበሩ፤ እንግዲህ 11  የላኩለት ደብዳቤ ቅጂ ይህ ነው።) “ለንጉሥ አርጤክስስ፣ ከወንዙ ባሻገር ባለው ክልል ከሚኖሩት አገልጋዮችህ፦ እንግዲህ 12  ከአንተ ዘንድ ወደዚህ ወደ እኛ የመጡት አይሁዳውያን ኢየሩሳሌም መድረሳቸውን ንጉሡ ይወቅ። እነዚህ ሰዎች ዓመፀኛና ክፉ የሆነችውን ከተማ መልሰው እየገነቡ ነው፤ ቅጥሮቿን ሠርተው እየጨረሱ ሲሆን መሠረቶቿንም እየጠገኑ ነው። 13  ከተማዋ ተመልሳ ከተገነባችና ቅጥሮቿም ተሠርተው ከተጠናቀቁ እነዚህ ሰዎች ቀረጥም ሆነ ግብር ወይም የኬላ ቀረጥ እንደማይከፍሉ፣ በዚህም የተነሳ ወደ ነገሥታቱ ግምጃ ቤት የሚገባው ገቢ እንደሚቀንስ ንጉሡ ይወቅ። 14  እኛ ደግሞ የቤተ መንግሥቱን ጨው እየበላን የንጉሡ ጥቅም ሲነካ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ መስሎ አልታየንም፤ በመሆኑም ንጉሡ ጉዳዩን እንዲያውቀው ለማድረግ ይህን ደብዳቤ ልከናል፤ 15  ስለዚህ የቀድሞ አባቶችህ መዝገብ ይመርመር። ይህች ከተማ ዓመፀኛና ነገሥታትንም ሆነ አውራጃዎችን ጉዳት ላይ የምትጥል፣ ከጥንት ጀምሮም ዓመፅ ቆስቋሾችን ሸሽጋ የምታኖር መሆኗን ከእነዚህ መዛግብት መረዳት ትችላለህ። ከተማዋም የተደመሰሰችው በዚህ የተነሳ ነው። 16  ይህች ከተማ ተመልሳ ከተገነባችና ቅጥሮቿም ተሠርተው ከተጠናቀቁ ከወንዙ ባሻገር ያለውን ክልል መቆጣጠር እንደማትችል ልናሳውቅህ እንፈልጋለን።” 17  ንጉሡም ለዋናው የመንግሥት ባለሥልጣን ለረሁም፣ ለጸሐፊው ለሺምሻይ፣ በሰማርያ ለሚኖሩት ለቀሩት ግብረ አበሮቻቸውና ከወንዙ ባሻገር ላለው ለቀረው ክልል እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ “ሰላምታዬ ይድረሳችሁ! እንግዲህ 18  የላካችሁልን ደብዳቤ በፊቴ ግልጽ ሆኖ ተነቧል። 19  በሰጠሁትም ትእዛዝ መሠረት ምርመራ ተደርጎ ከተማዋ ከጥንት ጀምሮ በነገሥታት ላይ ረብሻ የምትቀሰቅስ እንዲሁም የዓመፅና የወንጀል መፍለቂያ እንደነበረች ተረጋግጧል። 20  ኢየሩሳሌም ከወንዙ ባሻገር ያሉትን አካባቢዎች በሙሉ የሚገዙ ኃያላን ነገሥታት ነበሯት፤ እነሱም ቀረጥ፣ ግብርና የኬላ ቀረጥ ይቀበሉ ነበር። 21  እንግዲህ እኔ ትእዛዝ እስከምሰጥ ድረስ ከተማዋ ተመልሳ እንዳትገነባ እነዚህ ሰዎች ሥራውን እንዲያቆሙ ትእዛዝ አስተላልፉ። 22  የነገሥታቱን ጥቅም ይበልጥ የሚጎዳ ነገር እንዳይከሰት ይህን ጉዳይ በተመለከተ እርምጃ ከመውሰድ ቸል እንዳትሉ ተጠንቀቁ።” 23  ንጉሥ አርጤክስስ የላከው ደብዳቤ በረሁም፣ በጸሐፊው በሺምሻይና በተባባሪዎቻቸው ፊት ከተነበበ በኋላ ወዲያውኑ በኢየሩሳሌም ወዳሉት አይሁዳውያን በመሄድ አስገድደው ሥራውን አስቆሟቸው። 24  በኢየሩሳሌም የነበረውን የአምላክን ቤት የመገንባቱ ሥራ የተቋረጠው በዚህ ጊዜ ነበር፤ እስከ ፋርሱ ንጉሥ እስከ ዳርዮስ የንግሥና ዘመን ሁለተኛ ዓመት ድረስም ሥራው ባለበት ቆመ።
[]
[]
[]
[]
12,382
5  ከዚያም ነቢዩ ሐጌና የኢዶ የልጅ ልጅ የሆነው ነቢዩ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁዳውያን፣ ይመራቸው በነበረው በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩ። 2  በዚህ ጊዜ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የየሆጼዴቅ ልጅ የሆሹዋ በኢየሩሳሌም የነበረውን የአምላክን ቤት መልሰው መገንባት ጀመሩ፤ አብረዋቸው የነበሩት የአምላክ ነቢያትም ያግዟቸው ነበር። 3  በወቅቱ፣ ከወንዙ ባሻገር የነበረው ክልል ገዢ የሆነው ታተናይ እና ሸታርቦዘናይ እንዲሁም ግብረ አበሮቻቸው ወደ እነሱ መጥተው “ይህን ቤት እንድትገነቡና እንድታዋቅሩ ማን ትእዛዝ ሰጣችሁ?” ሲሉ ጠየቋቸው። 4  ከዚያም “ይህን ሕንፃ እየገነቡ ያሉት ሰዎች ስም ማን ነው?” አሏቸው። 5  ሆኖም አምላክ ለአይሁዳውያን ሽማግሌዎች ጥበቃ ያደርግላቸው ስለነበር መልእክቱ ለዳርዮስ ተልኮ ጉዳዩን የሚመለከት ደብዳቤ ከዚያ እስኪመጣ ድረስ ሥራውን ሊያስቆሟቸው አልቻሉም። 6  ከወንዙ ባሻገር ያለው ክልል ገዢ የሆነው ታተናይ፣ ሸታርቦዘናይና ከወንዙ ባሻገር ያለው ክልል የበታች ገዢዎች የሆኑት ግብረ አበሮቹ ለንጉሥ ዳርዮስ የላኩት ደብዳቤ ቅጂ ይህ ነው፤ 7  እንዲህ የሚል መልእክት ጽፈው ላኩለት፦ “ለንጉሥ ዳርዮስ፦ “ሰላም ለአንተ ይሁን! 8  በይሁዳ አውራጃ ወደሚገኘው ወደ ታላቁ አምላክ ቤት እንደሄድንና ቤቱ በትላልቅ ድንጋዮች እየተገነባ፣ በግንቡም ላይ ሳንቃዎች እየተነጠፉ መሆናቸውን ንጉሡ ይወቅ። ሕዝቡ ሥራውን በትጋት እያከናወነ ሲሆን ሥራውም በእነሱ ጥረት እየተፋጠነ ነው። 9  ሽማግሌዎቹንም ‘ይህን ቤት እንድትገነቡና እንድታዋቅሩ ማን ትእዛዝ ሰጣችሁ?’ አልናቸው። 10  በተጨማሪም ግንባር ቀደም ሆነው የሚመሩትን ሰዎች ስም ጽፈን ለአንተ ለማሳወቅ የሰዎቹን ስም እንዲነግሩን ጠየቅናቸው። 11  “እነሱም የሚከተለውን ምላሽ ሰጡን፦ ‘እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፤ አሁን መልሰን የምንገነባው ከበርካታ ዓመታት በፊት ተገንብቶ የነበረውን ይኸውም ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ ገንብቶ ያጠናቀቀውን ቤት ነው። 12  ሆኖም አባቶቻችን የሰማይን አምላክ ስላስቆጡት ለከለዳዊው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር አሳልፎ ሰጣቸው፤ እሱም ይህን ቤት አፈራርሶ ሕዝቡን በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰደ። 13  ይሁንና በባቢሎን ንጉሥ በቂሮስ የግዛት ዘመን የመጀመሪያ ዓመት ንጉሥ ቂሮስ ይህ የአምላክ ቤት ተመልሶ እንዲገነባ ትእዛዝ ሰጠ። 14  በተጨማሪም ንጉሥ ቂሮስ፣ ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ አውጥቶ ወደ ባቢሎን ቤተ መቅደስ የወሰዳቸውን የአምላክን ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች ከባቢሎን ቤተ መቅደስ አወጣ። እነዚህም ዕቃዎች ቂሮስ ገዢ አድርጎ ለሾመው ሸሽባጻር ለተባለ ሰው ተሰጡ። 15  ቂሮስም እንዲህ አለው፦ “እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ። ሄደህም በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ውስጥ አስቀምጣቸው፤ የአምላክም ቤት ቀድሞ በነበረበት ቦታ ላይ ተመልሶ ይገንባ።” 16  ከዚያም ሸሽባጻር መጥቶ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የአምላክን ቤት መሠረት ጣለ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ቤቱ በመገንባት ላይ ነው፤ ሆኖም ገና አላለቀም።’ 17  “እንግዲህ አሁን፣ ንጉሡ መልካም መስሎ ከታየው ንጉሥ ቂሮስ በኢየሩሳሌም የነበረው ያ የአምላክ ቤት ተመልሶ እንዲገነባ ትእዛዝ ሰጥቶ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማረጋገጥ በባቢሎን በሚገኘው የንጉሡ ግምጃ ቤት ምርመራ ይካሄድ፤ ይህን በተመለከተም ንጉሡ ያስተላለፈው ውሳኔ ይላክልን።”
[]
[]
[]
[]
12,383
6  በዚያን ጊዜ ንጉሥ ዳርዮስ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነሱም በባቢሎን የሚገኘውን ውድ ነገሮች የሚቀመጡበትን ግምጃ ቤት መረመሩ። 2  በሜዶን አውራጃ፣ በኤክባታና ውስጥ በሚገኘው የተመሸገ ስፍራ አንድ ጥቅልል ተገኘ፤ በላዩም ላይ የሚከተለው መልእክት ተጽፎ ነበር፦ 3  “ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት፣ ንጉሥ ቂሮስ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የአምላክ ቤት አስመልክቶ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠ፦ ‘መሥዋዕቶችን በዚያ ማቅረብ እንዲችሉ ቤቱ ተመልሶ ይገንባ፤ መሠረቶቹም ይጣሉ፤ ቁመቱ 60 ክንድ፣ ወርዱ 60 ክንድ ሆኖ 4  ትላልቅ ድንጋዮችን በሦስት ዙር በመደራረብና በላዩ ላይ አንድ ዙር ሳንቃ በማድረግ ይሠራ፤ ወጪውም ከንጉሡ ቤት ይከፈል። 5  በተጨማሪም ናቡከደነጾር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ አውጥቶ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸው የወርቅና የብር ዕቃዎች ይመለሱ፤ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ተወስደው በቀድሞ ቦታቸው ላይ ይደረጉ፤ በአምላክም ቤት ውስጥ ይቀመጡ።’ 6  “አሁንም ከወንዙ ባሻገር ያለው ክልል ገዢ የሆንከው ታተናይ፣ ሸታርቦዘናይና ከወንዙ ባሻገር የሚገኙ የበታች ገዢዎች የሆኑት ግብረ አበሮቻችሁ ከዚያ ራቁ። 7  በአምላክ ቤት ሥራ ጣልቃ አትግቡ። የአይሁዳውያን ገዢዎችና የአይሁዳውያን ሽማግሌዎች ያንን የአምላክ ቤት በቀድሞ ቦታው ላይ መልሰው ይገንቡት። 8  በተጨማሪም እነዚህ የአይሁዳውያን ሽማግሌዎች ያን የአምላክ ቤት መልሰው ሲገነቡ ልታደርጉላቸው የሚገባውን ነገር በተመለከተ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፦ ሥራው እንዳይስተጓጎል ከንጉሡ ግምጃ ቤት ይኸውም ከወንዙ ባሻገር ካለው ክልል ከተሰበሰበው ቀረጥ ላይ ተወስዶ የእነዚህ ሰዎች ወጪ በአፋጣኝ ይሸፈንላቸው። 9  ለሰማይ አምላክ ለሚቀርቡት የሚቃጠሉ መባዎች የሚያስፈልጉት ነገሮች ሁሉ ይኸውም ወይፈኖች፣ አውራ በጎች፣ የበግ ጠቦቶች፣ ስንዴ፣ ጨው፣ የወይን ጠጅና ዘይት በኢየሩሳሌም የሚገኙት ካህናት በሚጠይቁት መሠረት በየቀኑ ያለማቋረጥ ይሰጣቸው፤ 10  ይህም የሚደረገው የሰማይ አምላክን ደስ የሚያሰኙ መባዎችን ዘወትር እንዲያቀርቡ እንዲሁም ለንጉሡና ለልጆቹ ደህንነት እንዲጸልዩ ነው። 11  ከዚህ በተጨማሪ ይህን አዋጅ የጣሰ ማንኛውም ሰው ለዚህ ጥፋቱ ከቤቱ ምሰሶ እንዲነቀልና ወደ ላይ ከፍ ተደርጎ ላዩ ላይ እንዲቸነከር እንዲሁም ቤቱ የሕዝብ መጸዳጃ ቤት እንዲሆን አዝዣለሁ። 12  ስሙ በዚያ እንዲኖር ያደረገው አምላክ ይህን ትእዛዝ ለመቃወምና በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ያንን የአምላክ ቤት ለማጥፋት እጁን የሚያነሳን ማንኛውንም ንጉሥም ሆነ ሕዝብ ያጥፋው። እኔ ዳርዮስ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ። ይህም በአስቸኳይ ተግባራዊ ይደረግ።” 13  ከዚያም ከወንዙ ባሻገር ያለው ክልል ገዢ የሆነው ታተናይ፣ ሸታርቦዘናይና ግብረ አበሮቻቸው ንጉሥ ዳርዮስ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ወዲያውኑ ተግባራዊ አደረጉ። 14  የአይሁዳውያን ሽማግሌዎችም ነቢዩ ሐጌና የኢዶ የልጅ ልጅ ዘካርያስ በተናገሩት ትንቢት ተበረታተው ግንባታውን ማከናወናቸውንና ሥራውን ማፋጠናቸውን ቀጠሉ፤ በእስራኤል አምላክ ትእዛዝ መሠረት እንዲሁም በቂሮስ፣ በዳርዮስና በፋርሱ ንጉሥ በአርጤክስስ ትእዛዝ መሠረት ቤቱን ገንብተው አጠናቀቁ። 15  ቤቱንም በአዳር ወር በሦስተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት ሠርተው አጠናቀቁ። 16  ከዚያም እስራኤላውያን፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና በግዞት ተወስደው የነበሩት የቀሩት ሰዎች የአምላክን ቤት ምርቃት በደስታ አከበሩ። 17  ለአምላክ ቤት ምርቃትም 100 በሬዎችን፣ 200 አውራ በጎችንና 400 የበግ ጠቦቶችን እንዲሁም ለመላው እስራኤል የኃጢአት መባ እንዲሆኑ በእስራኤል ነገዶች ቁጥር ልክ 12 አውራ ፍየሎችን አቀረቡ። 18  እንዲሁም በሙሴ መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ለሚቀርበው የአምላክ አገልግሎት ካህናቱን በየክፍላቸው፣ ሌዋውያኑንም በየምድባቸው ሾሙ። 19  በግዞት ተወስደው የነበሩት ሰዎች በመጀመሪያው ወር በ14ኛው ቀን ላይ ፋሲካን አከበሩ። 20  ካህናቱና ሌዋውያኑ በሙሉ ራሳቸውን ስላነጹ ሁሉም ንጹሕ ሆነው ነበር፤ እነሱም በግዞት ተወስደው ለነበሩት ሰዎች በሙሉ፣ አብረዋቸው ለሚያገለግሉት ካህናትና ለራሳቸው የፋሲካውን እርድ አረዱ። 21  ከዚያም ከግዞት የተመለሱት እስራኤላውያን በምድሪቱ ከነበሩት ብሔራት ርኩሰት ራሳቸውን በመለየት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ለማምለክ ከእነሱ ጋር ከተቀላቀሉት ሁሉ ጋር ሆነው በሉት። 22  በተጨማሪም ይሖዋ እንዲደሰቱ ስላደረጋቸውና የእስራኤል አምላክ የሆነውን የእውነተኛውን አምላክ ቤት ይሠሩ ዘንድ እንዲረዳቸው የአሦርን ንጉሥ ልብ ስላራራላቸው የቂጣን በዓል ለሰባት ቀን በደስታ አከበሩ።
[]
[]
[]
[]
12,384
7  ከእነዚህ ነገሮች በኋላ በፋርሱ ንጉሥ በአርጤክስስ የግዛት ዘመን ዕዝራ ከባቢሎን ተመለሰ። ዕዝራ የሰራያህ ልጅ፣ ሰራያህ የአዛርያስ ልጅ፣ አዛርያስ የኬልቅያስ ልጅ፣ 2  ኬልቅያስ የሻሉም ልጅ፣ ሻሉም የሳዶቅ ልጅ፣ ሳዶቅ የአኪጡብ ልጅ፣ 3  አኪጡብ የአማርያህ ልጅ፣ አማርያህ የአዛርያስ ልጅ፣ አዛርያስ የመራዮት ልጅ፣ 4  መራዮት የዘራህያህ ልጅ፣ ዘራህያህ የዑዚ ልጅ፣ ዑዚ የቡቂ ልጅ፣ 5  ቡቂ የአቢሹዓ ልጅ፣ አቢሹዓ የፊንሃስ ልጅ፣ ፊንሃስ የአልዓዛር ልጅ፣ አልዓዛር የካህናት አለቃ የሆነው የአሮን ልጅ ነበር። 6  ይህ ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ። እሱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ የሰጠውን የሙሴን ሕግ ጠንቅቆ የሚያውቅ ገልባጭ ነበር። የአምላኩ የይሖዋ እጅ በእሱ ላይ ስለነበር ንጉሡ የጠየቀውን ሁሉ ሰጠው። 7  ንጉሥ አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ከእስራኤላውያን፣ ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ፣ ከዘማሪዎቹ፣ ከበር ጠባቂዎቹና ከቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ መካከል የተወሰኑት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ። 8  ዕዝራም ንጉሡ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ኢየሩሳሌም ደረሰ። 9  በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከባቢሎን ተነስቶ ጉዞ ጀመረ፤ መልካም የሆነው የአምላኩ እጅ በእሱ ላይ ስለነበር በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ኢየሩሳሌም ደረሰ። 10  ዕዝራ የይሖዋን ሕግ ለመመርመርና ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም ሥርዓቱንና ፍርዱን በእስራኤል ውስጥ ለማስተማር ልቡን አዘጋጅቶ ነበር። 11  ንጉሥ አርጤክስስ የይሖዋን ትእዛዛትና ለእስራኤላውያን ያወጣቸውን ሥርዓቶች በማጥናት ለተካነውና ገልባጭ ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ የሰጠው ደብዳቤ ቅጂ ይህ ነው፦ 12   “ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፣ የሰማይ አምላክ ሕግ ገልባጭ ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ፦ ሰላም ለአንተ ይሁን። እንግዲህ 13  በግዛቴ ውስጥ ካሉ የእስራኤል ሕዝቦች እንዲሁም ከእነሱ ካህናትና ሌዋውያን መካከል ከአንተ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ እንዲሄድ ትእዛዝ ሰጥቻለሁ። 14  ንጉሡና ሰባቱ አማካሪዎቹ በእጅህ የሚገኘው የአምላክህ ሕግ በይሁዳና በኢየሩሳሌም በተግባር ላይ እየዋለ እንደሆነና እንዳልሆነ እንድትመረምር ልከውሃል፤ 15  እንዲሁም ንጉሡና አማካሪዎቹ በኢየሩሳሌም ለሚኖረው ለእስራኤል አምላክ በፈቃደኝነት የሰጡትን ብርና ወርቅ፣ 16  ከመላው የባቢሎን አውራጃ ከተቀበልከው ብርና ወርቅ እንዲሁም ሕዝቡና ካህናቱ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው ለአምላካቸው ቤት በፈቃደኝነት ከሰጡት ስጦታ ጋር ይዘህ እንድትሄድ አዘዋል። 17  በዚህም ገንዘብ ሳትዘገይ በሬዎችን፣ አውራ በጎችንና የበግ ጠቦቶችን ከእህል መባዎቻቸውና ከመጠጥ መባዎቻቸው ጋር ግዛ፤ እነዚህንም በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው። 18  “በተረፈው ብርና ወርቅ እንደ አምላካችሁ ፈቃድ አንተም ሆንክ ወንድሞችህ መልካም መስሎ የታያችሁን አድርጉበት። 19  በአምላክህ ቤት ለሚቀርበው አገልግሎት እንዲሆኑ የተሰጡህን ዕቃዎች በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ወስደህ በአምላክ ፊት ታስቀምጣቸዋለህ። 20  ለአምላክህ ቤት መስጠት የሚጠበቅብህን ሌሎች አስፈላጊ ነገሮች ከንጉሡ ግምጃ ቤት አውጥተህ ትሰጣለህ። 21  “እኔ ንጉሥ አርጤክስስ ከወንዙ ባሻገር ባለው ክልል የምትገኙትን የግምጃ ቤት ኃላፊዎች በሙሉ የሰማይ አምላክ ሕግ ገልባጭ የሆነው ካህኑ ዕዝራ የጠየቃችሁን ነገር ሁሉ በአስቸኳይ እንድትፈጽሙለት ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤ 22  እንዲሁም እስከ 100 ታላንት ብር፣ እስከ 100 የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፣ እስከ 100 የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅና እስከ 100 የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ድረስ ስጡት፤ እንዲሁም የፈለገውን ያህል ጨው ስጡት። 23  በንጉሡ ግዛትና በልጆቹ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ የሰማይ አምላክ፣ የሰማይን አምላክ ቤት አስመልክቶ ያዘዘው ሁሉ በትጋት ይፈጸም። 24  በተጨማሪም ከካህናቱ፣ ከሌዋውያኑ፣ ከሙዚቀኞቹ፣ ከበር ጠባቂዎቹ፣ ከቤተ መቅደስ አገልጋዮቹም ሆነ ይህን የአምላክ ቤት ከሚሠሩት ሰዎች መካከል በአንዳቸውም ላይ ምንም ዓይነት ቀረጥ፣ ግብር ወይም የኬላ ቀረጥ መጣል እንደማትችሉ እወቁ። 25  “አንተም ዕዝራ፣ አምላክህ የሰጠህን ጥበብ ተጠቅመህ ከወንዙ ባሻገር ባለው ክልል ለሚኖሩት ሕዝቦች በሙሉ፣ የአምላክህን ሕጎች ለሚያውቁ ሁሉ ፍርድ የሚሰጡ ሕግ አስከባሪዎችንና ዳኞችን ሹም፤ ሕጎቹን የማያውቅ ሰው ካለም አስተምሩት። 26  እንዲሁም የአምላክህን ሕግና የንጉሡን ሕግ የማያከብር ማንኛውም ሰው ቅጣቱ ሞትም ይሁን ከአገር መባረር ወይም ገንዘብ አሊያም እስራት አፋጣኝ የፍርድ እርምጃ ይወሰድበት።” 27  እንዲህ ያለውን ነገር ይኸውም በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የይሖዋን ቤት የማስዋቡን ሐሳብ በንጉሡ ልብ ውስጥ ያኖረው የአባቶቻችን አምላክ ይሖዋ ይወደስ! 28  በንጉሡና በአማካሪዎቹ እንዲሁም ኃያላን በሆኑት የንጉሡ መኳንንት ሁሉ ፊት ታማኝ ፍቅር አሳይቶኛል። በመሆኑም የአምላኬ የይሖዋ እጅ በላዬ ስለነበር ድፍረት አገኘሁ፤ ከእኔም ጋር አብረው እንዲሄዱ ከእስራኤል መካከል መሪ የሆኑትን ሰበሰብኩ።
[]
[]
[]
[]
12,385
8  በንጉሥ አርጤክስስ የግዛት ዘመን ከባቢሎን አብረውኝ የወጡት የአባቶች ቤት መሪዎች የዘር ሐረግ ዝርዝር ይህ ነው፦ 2  ከፊንሃስ ልጆች ጌርሳም፣ ከኢታምር ልጆች ዳንኤል፣ ከዳዊት ልጆች ሃጡሽ፣ 3  ከሸካንያህ ልጆች፣ ከፓሮሽ ልጆች ዘካርያስ እንዲሁም ከእሱ ጋር የተመዘገቡ 150 ወንዶች ነበሩ፤ 4  ከፓሃትሞአብ ልጆች የዘራህያህ ልጅ የሆነው ኤሊየሆዔናይ እንዲሁም ከእሱ ጋር 200 ወንዶች፣ 5  ከዛቱ ልጆች የያሃዚኤል ልጅ የሆነው ሸካንያህ እንዲሁም ከእሱ ጋር 300 ወንዶች፣ 6  ከአዲን ልጆች የዮናታን ልጅ የሆነው ኤቤድ እንዲሁም ከእሱ ጋር 50 ወንዶች፣ 7  ከኤላም ልጆች የጎቶልያ ልጅ የሆነው የሻያህ እንዲሁም ከእሱ ጋር 70 ወንዶች፣ 8  ከሰፋጥያህ ልጆች የሚካኤል ልጅ የሆነው ዘባድያህ እንዲሁም ከእሱ ጋር 80 ወንዶች፣ 9  ከኢዮዓብ ልጆች የየሂኤል ልጅ የሆነው አብድዩ እንዲሁም ከእሱ ጋር 218 ወንዶች፣ 10  ከባኒ ልጆች የዮሲፍያህ ልጅ የሆነው ሸሎሚት እንዲሁም ከእሱ ጋር 160 ወንዶች፣ 11  ከቤባይ ልጆች የቤባይ ልጅ የሆነው ዘካርያስ እንዲሁም ከእሱ ጋር 28 ወንዶች፣ 12  ከአዝጋድ ልጆች የሃቃጣን ልጅ የሆነው ዮሃናን እንዲሁም ከእሱ ጋር 110 ወንዶች፣ 13  ከአዶኒቃም ልጆች የመጨረሻዎቹ የሆኑት ስማቸው ኤሊፌሌት፣ የኢዔልና ሸማያህ ሲሆን ከእነሱም ጋር 60 ወንዶች፤ 14  ከቢግዋይ ልጆች ዑታይና ዛቡድ እንዲሁም ከእነሱ ጋር 70 ወንዶች። 15  እኔም ወደ አሃዋ በሚፈሰው ወንዝ አጠገብ ሰበሰብኳቸው፤ በዚያም ለሦስት ቀን ሰፈርን። ሆኖም ሕዝቡንና ካህናቱን ልብ ብዬ ስመለከት ከሌዋውያን መካከል ማንንም በዚያ አላገኘሁም። 16  በመሆኑም መሪዎች ለሆኑት ለኤሊዔዘር፣ ለአርዔል፣ ለሸማያህ፣ ለኤልናታን፣ ለያሪብ፣ ለኤልናታን፣ ለናታን፣ ለዘካርያስና ለመሹላም እንዲሁም ለአስተማሪዎቹ ለዮያሪብና ለኤልናታን መልእክት ላክሁባቸው። 17  ከዚያም ካሲፍያ በተባለው ቦታ መሪ ወደሆነው ወደ ኢዶ እንዲሄዱ አዘዝኳቸው። ኢዶንና በካሲፍያ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች የሆኑትን ወንድሞቹን በአምላካችን ቤት የሚያገለግሉ ሰዎችን ያመጡልን ዘንድ እንዲጠይቋቸው ነገርኳቸው። 18  መልካም የሆነው የአምላካችን እጅ በእኛ ላይ ስለነበር የእስራኤል ልጅ የሌዊ የልጅ ልጅ ከሆነው ከማህሊ ልጆች መካከል አስተዋይ የሆነውን ሸረበያህን፣ ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን በአጠቃላይ 18 ሰዎችን አመጡልን፤ 19  እንዲሁም ሃሻብያህንና ከእሱም ጋር ከሜራራውያን መካከል የሻያህን፣ ወንድሞቹንና ወንዶች ልጆቻቸውን በአጠቃላይ 20 ሰዎችን አመጡልን። 20  በተጨማሪም ከቤተ መቅደሱ አገልጋዮች መካከል ዳዊትና መኳንንቱ ሌዋውያኑ ለሚያቀርቡት አገልግሎት የሰጧቸው 220 ሰዎች ነበሩ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዝግበው ነበር። 21  ከዚያም ራሳችንን በአምላካችን ፊት ለማዋረድ እንዲሁም በጉዟችን ወቅት ለእኛም ሆነ ለልጆቻችንና ለንብረቶቻችን በሙሉ የሚሆን መመሪያ ከእሱ ለማግኘት እዚያው በአሃዋ ወንዝ ጾም አወጅኩ። 22  “መልካም የሆነው የአምላካችን እጅ እሱን በሚሹት ሁሉ ላይ ነው፤ እሱን በሚተዉት ሁሉ ላይ ግን ኃይሉንና ቁጣውን ይገልጣል” በማለት ለንጉሡ ነግረነው ስለነበር በጉዟችን ላይ ከሚያጋጥሙን ጠላቶች የሚጠብቁን ወታደሮችና ፈረሰኞች እንዲሰጠን ንጉሡን መጠየቅ አፈርኩ። 23  ስለሆነም ጾምን፤ ይህን በተመለከተም ለአምላካችን ልመና አቀረብን፤ እሱም ልመናችንን ሰማ። 24  እኔም ከዋነኞቹ ካህናት መካከል 12ቱን ይኸውም ሸረበያህንና ሃሻብያህን እንዲሁም አሥር ወንድሞቻቸውን ለየሁ። 25  ከዚያም ንጉሡ፣ አማካሪዎቹና መኳንንቱ እንዲሁም በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ለአምላካችን ቤት የሰጡትን መዋጮ ማለትም ብሩን፣ ወርቁንና ዕቃዎቹን መዘንኩላቸው። 26  የሚከተሉትንም ዕቃዎች መዝኜ ሰጠኋቸው፦ 650 ታላንት ብር፣ 2 ታላንት የሚመዝኑ 100 የብር ዕቃዎች፣ 100 ታላንት ወርቅ 27  እንዲሁም 1,000 ዳሪክ የሚመዝኑ 20 ትናንሽ ጎድጓዳ የወርቅ ሳህኖችና የወርቅ ያህል ተፈላጊ የሆኑ ከሚያብረቀርቅ ጥሩ መዳብ የተሠሩ 2 ዕቃዎች። 28  ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ “እናንተ ለይሖዋ የተቀደሳችሁ ናችሁ፤ ዕቃዎቹም የተቀደሱ ናቸው፤ ብሩና ወርቁ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለይሖዋ የቀረበ የፈቃደኝነት መባ ነው። 29  በኢየሩሳሌም በሚገኙት በይሖዋ ቤት ክፍሎች ውስጥ በዋነኞቹ ካህናትና ሌዋውያን እንዲሁም በእስራኤል የአባቶች ቤት መኳንንት ፊት እስክትመዝኗቸው ድረስ በጥንቃቄ ጠብቋቸው።” 30  ካህናቱና ሌዋውያኑም የተመዘነላቸውን ብር፣ ወርቅና ዕቃ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ አምላካችን ቤት ለመውሰድ ተረከቡ። 31  በኋላም በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ12ኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከአሃዋ ወንዝ ተነሳን፤ የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበር፤ እሱም በመንገድ ላይ ከጠላት እጅና ከሽምቅ ጥቃት ታደገን። 32  ወደ ኢየሩሳሌም መጥተን በዚያ ለሦስት ቀን ተቀመጥን። 33  በአራተኛውም ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ዕቃዎቹን በአምላካችን ቤት መዝነን ለዑሪያህ ልጅ ለካህኑ ለመሬሞት አስረከብነው፤ ከእሱም ጋር የፊንሃስ ልጅ አልዓዛር እንዲሁም ሌዋውያን የሆኑት የየሹዋ ልጅ ዮዛባድና የቢኑይ ልጅ ኖአድያህ ነበሩ። 34  እያንዳንዱም ነገር ተቆጥሮ ተመዘነ፤ ክብደቱም ሁሉ ተመዘገበ። 35  በግዞት ተወስደው የነበሩት ከምርኮ ነፃ የወጡ ሰዎች ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን አቀረቡ፤ ለመላው እስራኤል 12 በሬዎችን፣ 96 አውራ በጎችን፣ 77 ተባዕት የበግ ጠቦቶችንና 12 ተባዕት ፍየሎችን የኃጢአት መባ አድርገው አቀረቡ፤ ይህ ሁሉ ለይሖዋ የቀረበ የሚቃጠል መባ ነበር። 36  ከዚያም ንጉሡ ያወጣቸውን ድንጋጌዎች ለንጉሡ የአውራጃ ገዢዎችና ከወንዙ ባሻገር ባለው ክልል ለሚገኙት ገዢዎች ሰጠናቸው፤ እነሱም ለሕዝቡና ለእውነተኛው አምላክ ቤት ድጋፍ ሰጡ።
[]
[]
[]
[]
12,386
9  እነዚህ ነገሮች እንደተጠናቀቁ መኳንንቱ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፦ “የእስራኤል ሕዝብ፣ ካህናቱና ሌዋውያኑ በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦች ይኸውም ከከነአናውያን፣ ከሂታውያን፣ ከፈሪዛውያን፣ ከኢያቡሳውያን፣ ከአሞናውያን፣ ከሞዓባውያን፣ ከግብፃውያንና ከአሞራውያን እንዲሁም አስጸያፊ ከሆኑት ልማዶቻቸው ራሳቸውን አልለዩም። 2  ከእነሱም ሴቶች ልጆች መካከል ለራሳቸውና ለወንዶች ልጆቻቸው ሚስቶች ወስደዋል። በመሆኑም ቅዱስ ዘር የሆኑት እነዚህ ሰዎች በምድሪቱ ከሚኖሩት ሕዝቦች ጋር ተቀላቅለዋል። ይህን ታማኝነት የጎደለው ድርጊት በመፈጸም ግንባር ቀደም የሆኑት መኳንንቱና የበታች ገዢዎቹ ናቸው።” 3  እኔም ይህን ስሰማ እጀ ጠባቤንና መደረቢያዬን ቀደድኩ፤ ፀጉሬንና ጺሜን ነጨሁ፤ በጣም ከመደንገጤም የተነሳ በተቀመጥኩበት ደርቄ ቀረሁ። 4  ምሽት ላይ እስከሚቀርበው የእህል መባ ድረስ እንደደነገጥኩ በዚያ ተቀምጬ ሳለሁ ለእስራኤል አምላክ ቃል አክብሮታዊ ፍርሃት ያላቸው ሰዎች ሁሉ፣ በግዞት ተወስደው የነበሩት ሰዎች በፈጸሙት ታማኝነት የጎደለው ድርጊት የተነሳ በዙሪያዬ ተሰበሰቡ። 5  ከዚያም ምሽት ላይ የእህል መባው በሚቀርብበት ጊዜ እጀ ጠባቤና መደረቢያዬ እንደተቀደደ ራሴን አዋርጄ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ፤ በጉልበቴም ተንበርክኬ እጆቼን ወደ አምላኬ ወደ ይሖዋ ዘረጋሁ። 6  እንዲህም አልኩ፦ “አቤቱ አምላኬ ሆይ፣ ፊቴን ወደ አንተ ቀና ማድረግ አሳፈረኝ፤ አሸማቀቀኝ፤ ምክንያቱም አምላኬ ሆይ፣ የፈጸምናቸው ስህተቶች በአናታችን ላይ ተቆልለዋል፤ በደላችንም ከመብዛቱ የተነሳ እስከ ሰማይ ደርሷል። 7  ከአባቶቻችን ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ የፈጸምነው በደል ታላቅ ነው፤ በሠራናቸውም ስህተቶች የተነሳ ይኸው ዛሬ እንደሚታየው እኛም ሆንን ነገሥታታችንና ካህናታችን በሌሎች አገሮች ነገሥታት እጅ ወድቀን ለሰይፍ፣ ለምርኮ፣ ለብዝበዛና ለውርደት ተዳርገናል። 8  አሁን ግን አምላካችን ይሖዋ ቀሪዎች እንዲተርፉና በቅዱስ ስፍራው አስተማማኝ ቦታ እንድናገኝ በማድረግ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ሞገስ አሳይቶናል፤ አምላካችን ሆይ፣ ይህን ያደረግከው ዓይኖቻችን እንዲበሩና ከተጫነብን የባርነት ቀንበር ትንሽ እንድናገግም ነው። 9  ባሪያዎች ብንሆንም እንኳ አምላካችን ባሪያዎች ሆነን እንድንቀር አልተወንም፤ ከዚህ ይልቅ በፋርስ ነገሥታት ፊት ታማኝ ፍቅሩን አሳየን፤ ይህን ያደረገውም ዳግም አገግመን የአምላካችንን ቤት ከወደቀበት እንድናነሳና የፈራረሱትን ቦታዎች መልሰን እንድንገነባ እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የድንጋይ ቅጥር እንድናገኝ ሲል ነው። 10  “አሁን ግን አምላካችን ሆይ፣ ከዚህ በኋላ ምን ማለት እንችላለን? ምክንያቱም ትእዛዛትህን ተላልፈናል፤ 11  በአገልጋዮችህ በነቢያት አማካኝነት የሰጠኸንን የሚከተለውን ትእዛዝ አላከበርንም፦ ‘ትወርሷት ዘንድ የምትገቡባት ምድር በነዋሪዎቿ ርኩሰት የተነሳ የረከሰች ናት፤ ምክንያቱም በምድሪቱ የሚኖሩት ሰዎች በአስጸያፊ ድርጊቶቻቸው ምድሪቱን ከዳር እሰከ ዳር በርኩሰታቸው ሞልተዋታል። 12  ስለሆነም ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ፤ እንዲሁም ይበልጥ እየበረታችሁ እንድትሄዱ፣ የምድሪቱን መልካም ነገር እንድትበሉና ምድሪቱን የልጆቻችሁ ዘላለማዊ ርስት ማድረግ እንድትችሉ ፈጽሞ የእነሱን ሰላምና ብልጽግና አትፈልጉ።’ 13  በተጨማሪም በመጥፎ ሥራዎቻችንና በፈጸምነው ታላቅ በደል ምክንያት ይህ ሁሉ ደረሰብን፤ አንተ ግን አምላካችን ሆይ፣ እንደ ጥፋታችን መጠን አልቀጣኸንም፤ ከዚህ ይልቅ እኛ እዚህ ያለነው እንድንተርፍ ፈቀድክ። 14  ታዲያ ትእዛዛትህን እንደገና መተላለፍና እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ከሚፈጽሙ ሕዝቦች ጋር በጋብቻ መዛመድ ይገባናል? አንተስ አንድም ሰው ሳታስቀር ወይም ሳታስተርፍ ፈጽሞ እስክታጠፋን ድረስ ልትቆጣ አይገባህም? 15  የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ምክንያቱም እኛ ከጥፋት ተርፈን እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በሕይወት አለን። እንዲህ ያለ ነገር አድርጎ በፊትህ መቆም የማይቻል ቢሆንም ይኸው ከነበደላችን በፊትህ ቀርበናል።”
[]
[]
[]
[]
12,387
1  ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስምንተኛው ወር የይሖዋ ቃል ወደ ኢዶ ልጅ፣ ወደ ቤራክያህ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2  “ይሖዋ በአባቶቻችሁ ላይ እጅግ ተቆጥቶ ነበር። 3  “እንዲህ በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ወደ እኔ ተመለሱ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።”’ 4  “‘የቀደሙት ነቢያት “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ‘እባካችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ራቁ’ ይላል በማለት የነገሯቸውን አባቶቻችሁን አትምሰሉ።”’ “‘እነሱ ግን አልሰሙም፤ ለእኔም ትኩረት አልሰጡም’ ይላል ይሖዋ። 5  “‘አባቶቻችሁ አሁን የት አሉ? ነቢያቱስ ለዘላለም መኖር ችለዋል? 6  ይሁን እንጂ አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያትን ያዘዝኳቸው ቃልና ድንጋጌ በአባቶቻችሁ ላይ ደርሶ የለም?’ በመሆኑም ወደ እኔ ተመልሰው እንዲህ አሉ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በወሰነው መሠረት እንደ መንገዳችንና እንደ ሥራችን አደረገብን።’” 7  ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ ሺባት በተባለው በ11ኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ኢዶ ልጅ፣ ወደ ቤራክያህ ልጅ፣ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ 8  “በሌሊት ራእይ አየሁ። አንድ ሰው ቀይ ፈረስ እየጋለበ ነበር፤ እሱም በሸለቆው ውስጥ በሚገኙት የአደስ ዛፎች መካከል ቆመ፤ ከበስተ ኋላውም ቀይ፣ ቀይ ቡኒና ነጭ ፈረሶች ነበሩ።” 9  እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ እነማን ናቸው?” አልኩ። ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ “እነዚህ እነማን እንደሆኑ አሳይሃለሁ” ሲል መለሰልኝ። 10  ከዚያም በአደስ ዛፎቹ መካከል ቆሞ የነበረው ሰው “እነዚህ በምድር ላይ እንዲመላለሱ ይሖዋ የላካቸው ናቸው” አለ። 11  እነሱም በአደስ ዛፎቹ መካከል ቆሞ ለነበረው የይሖዋ መልአክ “በምድር ላይ ተመላለስን፤ እነሆም መላዋ ምድር ጸጥታና እርጋታ ሰፍኖባታል” አሉት። 12  የይሖዋም መልአክ እንዲህ አለ፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ በእነዚህ 70 ዓመታት የተቆጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ምሕረትህን የምትነፍጋቸው እስከ መቼ ነው?” 13  ይሖዋም ሲያነጋግረኝ ለነበረው መልአክ ደግነት በተሞላባቸውና በሚያጽናኑ ቃላት መለሰለት። 14  ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፦ “እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለኢየሩሳሌምና ለጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ። 15  ዘና ብለው በተቀመጡት ብሔራት ላይ እጅግ ተቆጥቻለሁ፤ ምክንያቱም በመጠኑ ብቻ ተቆጥቼ እያለ እነሱ ግን ከልክ ያለፈ እርምጃ ወሰዱ።”’ 16  “ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት እመለሳለሁ፤ የገዛ ቤቴም በውስጧ ይገነባል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “በኢየሩሳሌምም ላይ የመለኪያ ገመድ ይዘረጋል።”’ 17  “በድጋሚ እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከተሞቼ እንደገና መልካም ነገር ይትረፈረፍባቸዋል፤ ይሖዋም እንደገና ጽዮንን ያጽናናል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣል።”’” 18  ከዚያም ቀና ብዬ ስመለከት አራት ቀንዶች አየሁ። 19  በመሆኑም ሲያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልኩት። እሱም “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው” ሲል መለሰልኝ። 20  ከዚያም ይሖዋ አራት የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች አሳየኝ። 21  እኔም “እነዚህ የመጡት ምን ሊያደርጉ ነው?” ስል ጠየቅኩ። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ፣ ማንም ራሱን ቀና ማድረግ እስኪሳነው ድረስ ይሁዳን የበታተኑ ቀንዶች ናቸው። እነዚህ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ደግሞ እነሱን ለማሸበር፣ ይሁዳን ይበታትኗት ዘንድ በምድሯ ላይ ቀንዶቻቸውን ያነሱትን የብሔራቱን ቀንዶች ለመጣል ይመጣሉ።”
[]
[]
[]
[]
12,388
10  “በበልግ ዝናብ ወቅት ይሖዋ ዝናብ እንዲያዘንብላችሁ ጠይቁ። ነጎድጓድ የቀላቀለ ደመና የሚያመጣው፣ለሰዎች ዝናብ የሚያዘንበው፣ለእያንዳንዱም በሜዳ ላይ የሚበቅለውን ተክል የሚሰጠው ይሖዋ ነው። 2  የተራፊም ምስሎች አታላይ ነገር ተናግረዋልና፤ሟርተኞችም የሐሰት ራእይ አይተዋል። ከንቱ ስለሆኑ ሕልሞች ይናገራሉ፤በከንቱም ሊያጽናኑ ይሞክራሉ። ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ እንደ በግ ይቅበዘበዛል። እረኛ ስለሌለ ይሠቃያል። 3  በእረኞቹ ላይ ቁጣዬ ይነዳል፤ጨቋኞቹንም መሪዎች ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ትኩረቱን ወደ መንጋው፣ ወደ ይሁዳ ቤት አዙሯልና፤ግርማ ሞገስ እንደተላበሰው የጦር ፈረሱ እነሱንም ግርማ ሞገስ አላብሷቸዋል። 4  ከእሱ ቁልፍ የሆነ ሰው፣ድጋፍ የሚሰጥ ገዢናየጦርነት ቀስት ይወጣል፤ተቆጣጣሪዎች ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው ከእሱ ይወጣሉ። 5  እነሱም በጦርነት ጊዜ፣በመንገድ ላይ ያለን ጭቃ እንደሚረግጡ ተዋጊዎች ይሆናሉ። ይሖዋ ከእነሱ ጋር ስለሆነ ይዋጋሉ፤የጠላት ፈረሰኞችም ኀፍረት ይከናነባሉ። 6  የይሁዳን ቤት ከሁሉ የላቀ አደርጋለሁ፤የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ። ምሕረት ስለማሳያቸውቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እመልሳቸዋለሁ፤እነሱም ፈጽሞ እንዳልጣልኳቸው ሰዎች ይሆናሉ፤እኔ ይሖዋ አምላካቸው ነኝና፤ ደግሞም እመልስላቸዋለሁ። 7  የኤፍሬም ሰዎች እንደ ኃያል ተዋጊ ይሆናሉ፤ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደጠጣ ሰው ሐሴት ያደርጋል። ልጆቻቸው ይህን አይተው ሐሴት ያደርጋሉ፤ልባቸውም በይሖዋ ደስ ይለዋል። 8  ‘አፏጭቼ አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤እዋጃቸዋለሁና፣ ብዙ ይሆናሉ፤መባዛታቸውንም ይቀጥላሉ። 9  በሕዝቦች መካከል እንደ ዘር ብበትናቸውም፣በሩቅ ስፍራዎች ሆነው ያስታውሱኛል፤ከልጆቻቸው ጋር ሆነው ያንሰራራሉ፤ ደግሞም ይመለሳሉ። 10  ከግብፅ ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ከአሦርም አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ወደ ጊልያድ ምድርና ወደ ሊባኖስ አመጣቸዋለሁ፤በቂ ስፍራም አይገኝላቸውም። 11  እሱም ባሕሩን አስጨንቆ ያልፋል፤በባሕሩም ውስጥ ሞገዱን ይመታል፤የአባይ ጥልቆች በሙሉ ይደርቃሉ። የአሦር ኩራት ይዋረዳል፤የግብፅም በትረ መንግሥት ይወገዳል። 12  በይሖዋ ብርቱ አደርጋቸዋለሁ፤በስሙም ይሄዳሉ’ ይላል ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,389
11  “ሊባኖስ ሆይ፣ እሳት አርዘ ሊባኖሶችህን እንድትበላበሮችህን ክፈት። 2  የጥድ ዛፍ ሆይ፣ አርዘ ሊባኖሱ ስለወደቀ ዋይ ዋይ በል፤ታላላቆቹ ዛፎች ወድመዋል! እናንተ የባሳን የባሉጥ ዛፎች፣ጥቅጥቅ ያለው ጫካ ስለጠፋ ዋይ ዋይ በሉ! 3  ስሙ! እረኞች ግርማ ሞገሳቸው ስለተገፈፈዋይ ዋይ ይላሉ። አዳምጡ! በዮርዳኖስ አጠገብ ያሉት ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ስለወደሙደቦል አንበሶች ያገሳሉ። 4  “አምላኬ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለእርድ የተዘጋጀውን መንጋ ጠብቅ፤ 5  የገዟቸው አርደዋቸዋል፤ ሆኖም ተጠያቂ አይሆኑም። የሚሸጧቸውም “ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን፤ ባለጸጋ እሆናለሁና” ይላሉ። እረኞቻቸውም ምንም ዓይነት ርኅራኄ አያሳዩአቸውም።’ 6  “‘ከእንግዲህ ለምድሪቱ ነዋሪዎች አልራራላቸውም’ ይላል ይሖዋ። ‘በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው በባልንጀራው እጅና በንጉሡ እጅ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ እነሱም ምድሪቱን ያደቋታል፤ እኔም እነሱን ከእጃቸው አልታደግም።’” 7  እናንተ ጉስቁልና የደረሰባችሁ የመንጋው አባላት፣ ለመታረድ የተዘጋጀውን መንጋ መጠበቅ ጀምሬአለሁ፤ ይህን ያደረግኩትም ለእናንተ ስል ነው። ስለዚህ ሁለት በትሮችን ወስጄ አንደኛውን በትር “ደስታ፣” ሌላኛውን ደግሞ “ኅብረት” ብዬ ጠራሁት፤ እኔም መንጋውን መጠበቅ ጀመርኩ። 8  ደግሞም በአንድ ወር ውስጥ ሦስት እረኞችን አባረርኩ፤ ይህን ያደረግኩት እነሱን መታገሥ ስላልቻልኩና እነሱም እኔን ስለተጸየፉኝ ነው። 9  እንዲህም አልኩ፦ “ከእንግዲህ እረኛችሁ አልሆንም። የምትሞተው ትሙት፤ የምትጠፋውም ትጥፋ። የቀሩት ደግሞ አንዳቸው የሌላውን ሥጋ ይብሉ።” 10  ስለዚህ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን በማፍረስ “ደስታ” የተባለውን በትሬን ወስጄ ሰበርኩት። 11  በመሆኑም በዚያን ቀን ቃል ኪዳኑ ፈረሰ፤ ይመለከቱኝ የነበሩት የተጎሳቆሉት የመንጋው አባላትም ይህ የይሖዋ ቃል መሆኑን አወቁ። 12  ከዚያም “መልካም መስሎ ከታያችሁ ደሞዜን ስጡኝ፤ ካልሆነ ግን ተዉት” አልኳቸው። እነሱም ደሞዜን፣ 30 የብር ሰቅል ከፈሉኝ። 13  ከዚያም ይሖዋ “እኔን የገመቱበትን የከበረ ዋጋ ይኸውም ብሩን ግምጃ ቤት ውስጥ ጣለው” አለኝ። እኔም 30ውን የብር ሰቅል ወስጄ በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤት ውስጥ ጣልኩት። 14  ከዚያም በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውን ወንድማማችነት በማፍረስ “ኅብረት” የተባለውን ሁለተኛውን በትሬን ሰበርኩት። 15  ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “እንግዲህ የሰነፍ እረኛ መሣሪያዎችን ውሰድ። 16  በምድሪቱ ላይ እረኛ አስነሳለሁና። እያለቁ ያሉትን በጎች አይንከባከብም፤ ግልገሎቹን አይፈልግም ወይም የተጎዳውን አይፈውስም አሊያም መቆም የሚችሉትን አይቀልብም። ከዚህ ይልቅ የሰባውን በግ ሥጋ ይበላል፤ የበጎቹንም ሰኮና ቆርጦ ይጥላል። 17  መንጋውን ለሚተው የማይረባ እረኛዬ ወዮለት! ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዓይኑን ይመታዋል። ክንዱ ሙሉ በሙሉ ይሰልላል፤ቀኝ ዓይኑም ሙሉ በሙሉ ይታወራል።”
[]
[]
[]
[]
12,390
12  የፍርድ መልእክት፦ “ስለ እስራኤል የተነገረው የይሖዋ ቃል።”ሰማያትን የዘረጋው፣የምድርን መሠረት የጣለውናየሰውን መንፈስ በውስጡ የሠራው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ 2  “እነሆ፣ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ የምታንገዳግድ ጽዋ አደርጋታለሁ፤ ጠላት ይሁዳንም ሆነ ኢየሩሳሌምን ይከባል። 3  በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን ለሕዝቦች ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ። ድንጋዩን የሚያነሱት ሁሉ ክፉኛ መጎዳታቸው የማይቀር ነው፤ የምድር ብሔራትም ሁሉ በእሷ ላይ ይሰበሰባሉ። 4  በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣ “እያንዳንዱን ፈረስ በድንጋጤ፣ ጋላቢውንም በእብደት እመታለሁ። ዓይኖቼን በይሁዳ ቤት ላይ አደርጋለሁ፤ የሕዝቦቹን ፈረሶች ሁሉ ግን አሳውራለሁ። 5  የይሁዳም አለቆች በልባቸው ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ አምላካቸው ስለሆነ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ብርታታችን ናቸው’ ይላሉ። 6  በዚያን ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ የሚነድ ምድጃና በታጨደ እህል መካከል እንዳለ የሚነድ ችቦ አደርጋቸዋለሁ፤ እነሱም በስተ ቀኝም ሆነ በስተ ግራ፣ በዙሪያቸው ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌምም በገዛ ስፍራዋ ይኸውም በኢየሩሳሌም ዳግመኛ የሰዎች መኖሪያ ትሆናለች። 7  “የዳዊት ቤት ውበትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ውበት ከይሁዳ እጅግ የበለጠ እንዳይሆን ይሖዋ በመጀመሪያ የይሁዳን ድንኳኖች ያድናል። 8  በዚያ ቀን ይሖዋ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ዙሪያ መከታ ይሆናል፤ በዚያም ቀን ከእነሱ መካከል የሚሰናከለው እንደ ዳዊት ይሆናል፤ የዳዊትም ቤት እንደ አምላክ፣ በፊታቸውም እንደሚሄደው የይሖዋ መልአክ ይሆናል። 9  ደግሞም በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን ብሔራት ሁሉ ለማጥፋት ቆርጬ እነሳለሁ። 10  “በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የሞገስንና የምልጃን መንፈስ አፈሳለሁ፤ እነሱም የወጉትን ያዩታል፤ ለአንድያ ልጅም እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኩር ልጅ እንደሚለቀሰው ያለ መራራ ለቅሶም ያለቅሱለታል። 11  በዚያን ቀን በኢየሩሳሌም የሚለቀሰው ለቅሶ በመጊዶ ሜዳ፣ በሃዳድሪሞን እንደተለቀሰው ለቅሶ ታላቅ ይሆናል። 12  ምድሪቱም ታለቅሳለች፤ እያንዳንዱም ቤተሰብ ለየብቻው ያለቅሳል፤ የዳዊት ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የናታን ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ 13  የሌዊ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የሺምአይ ቤት ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ 14  የቀሩትም ቤተሰቦች በሙሉ፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ ለብቻው፣ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው ያለቅሳሉ።
[]
[]
[]
[]
12,391
13  “በዚያ ቀን፣ ኃጢአታቸውንና ርኩሰታቸውን ለማንጻት ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የውኃ ጉድጓድ ይቆፈራል። 2  “በዚያ ቀን” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “የጣዖቶቹን ስም ከምድሪቱ ላይ እደመስሳለሁ፤ እነሱም ዳግመኛ አይታወሱም፤ ደግሞም ነቢያቱንና የርኩሰት መንፈሱን ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ። 3  አንድ ሰው ዳግመኛ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባትና እናቱ ‘በይሖዋ ስም ሐሰት ስለተናገርክ በሕይወት አትኖርም’ ይሉታል። ደግሞም የወለዱት አባትና እናቱ ትንቢት በመናገሩ ይወጉታል። 4  “በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ትንቢት በሚናገርበት ጊዜ ሁሉ በገዛ ራእዩ ያፍራል፤ ሰዎችንም ለማታለል የነቢያት ዓይነት ፀጉራም ልብስ አይለብስም። 5  ደግሞም እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ነቢይ አይደለሁም። ይልቁንም አራሽ ነኝ፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ልጅ ሳለሁ ባሪያ አድርጎ ገዝቶኛል።’ 6  አንድ ሰውም ‘በትከሻዎችህ መካከል ያሉት ቁስሎች ምንድን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቀው ‘በወዳጆቼ ቤት ሳለሁ የቆሰልኩት ነው’ ይላል።” 7  “ሰይፍ ሆይ፣ በእረኛዬ ይኸውምበወዳጄ ላይ ንቃ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “እረኛውን ምታ፤ መንጋውም ይበተን፤እኔም እጄን ታናናሽ በሆኑት ላይ አዞራለሁ።” 8  “በምድሪቱም ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣“በእሷ ላይ ካለው ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤አንድ ሦስተኛው ግን በውስጧ ይቀራል። 9  ደግሞም አንድ ሦስተኛው በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ብር እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ። እነሱ ስሜን ይጠራሉ፤እኔም እመልስላቸዋለሁ። ‘እነሱ ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነሱ ደግሞ ‘ይሖዋ አምላካችን ነው’ ይላሉ።”
[]
[]
[]
[]
12,392
14  “እነሆ፣ የይሖዋ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ከአንቺ የተማረከው በመካከልሽ ይከፋፈላል። 2  ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ ብሔራትን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዋም ትያዛለች፤ ቤቶቹ ይዘረፋሉ፤ ሴቶቹም ይደፈራሉ። የከተማዋም እኩሌታ ለግዞት ይዳረጋል፤ ከሕዝቡ መካከል የሚቀሩት ሰዎች ግን ከከተማዋ አይወገዱም። 3  “ይሖዋ ይወጣል፤ በጦርነት ቀን እንደሚዋጋው እነዚያን ብሔራት ይዋጋል። 4  በዚያ ቀን እግሮቹ በስተ ምሥራቅ በኢየሩሳሌም ትይዩ በሚገኘው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም ከምሥራቅ አንስቶ እስከ ምዕራብ ድረስ ለሁለት ይከፈላል፤ እጅግ ትልቅ ሸለቆም ይፈጠራል፤ የተራራው አንዱ ግማሽ ወደ ሰሜን፣ ሌላው ግማሽ ደግሞ ወደ ደቡብ ፈቀቅ ይላል። 5  እናንተ በተራሮቼ መካከል ወዳለው ሸለቆ ትሸሻላችሁ፤ በተራሮቹ መካከል ያለው ሸለቆ እስከ አዜል ድረስ ይደርሳልና። በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የተነሳ ሸሽታችሁ እንደነበረ ሁሉ አሁንም ትሸሻላችሁ። አምላኬ ይሖዋም ይመጣል፤ ቅዱሳኑም ሁሉ ከእሱ ጋር ይሆናሉ። 6  “በዚያ ቀን ደማቅ ብርሃን አይኖርም፤ ነገሮች ሁሉ ባሉበት ይረጋሉ። 7  ያም ቀን የይሖዋ ቀን ተብሎ የሚታወቅ ልዩ ቀን ይሆናል። ቀንም ሆነ ሌሊት አይሆንም፤ በመሸም ጊዜ ብርሃን ይኖራል። 8  በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ሕያው ውኃዎች ይወጣሉ፤ ግማሾቹ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ባሕር፣ ግማሾቹ ደግሞ በስተ ምዕራብ ወዳለው ባሕር ይፈስሳሉ። ይህም በበጋና በክረምት ይሆናል። 9  ይሖዋም በመላው ምድር ላይ ይነግሣል። በዚያ ቀን ይሖዋ አንድ፣ ስሙም አንድ ይሆናል። 10  “ከጌባ አንስቶ ከኢየሩሳሌም በስተ ደቡብ እስካለችው እስከ ሪሞን ድረስ መላው ምድር እንደ አረባ ይሆናል፤ ኢየሩሳሌም በቀድሞ ስፍራዋ ላይ ትነሳለች፤ የሰዎችም መኖሪያ ትሆናለች፤ ደግሞም ከቢንያም በር አንስቶ እስከ መጀመሪያው በርና እስከ ማዕዘን በር ድረስ ያለው ስፍራ ሁሉ እንዲሁም ከሃናንኤል ማማ አንስቶ እስከ ንጉሡ የወይን መጭመቂያዎች ድረስ ያለው ስፍራ ሁሉ ሰው ይኖርበታል። 11  በከተማዋም ውስጥ ሰዎች ይኖራሉ፤ ከእንግዲህም ጥፋት እንዲደርስባት አትረገምም፤ ደግሞም ኢየሩሳሌም ሰዎች ያለስጋት የሚኖሩባት ቦታ ትሆናለች። 12  “ይሖዋ ኢየሩሳሌምን የሚወጉ ሕዝቦችን ሁሉ የሚቀስፍበት መቅሰፍት ይህ ነው፦ በእግራቸው ቆመው እያለ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዓይኖቻቸውም በጉድጓዶቻቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። 13  “በዚያ ቀን ከይሖዋ ዘንድ የመጣ ሽብር በመካከላቸው ይሰራጫል፤ እያንዳንዱም ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ እጁንም በባልንጀራው እጅ ላይ ያነሳል። 14  ይሁዳም ራሱ በኢየሩሳሌም በሚደረገው ውጊያ ይካፈላል፤ በዙሪያዋም ያሉ ብሔራት ሁሉ ሀብት ይኸውም ወርቅ፣ ብርና ልብስ በብዛት ይሰበሰባል። 15  “በየሰፈሩ ባሉት ፈረሶች፣ በቅሎዎች፣ ግመሎች፣ አህዮችና መንጎች ሁሉ ላይ ተመሳሳይ መቅሰፍት ይወርዳል። 16  “በኢየሩሳሌም ላይ ከተነሱት ብሔራት ሁሉ የሚተርፉት ሰዎች በሙሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ለመስገድና የዳስ በዓልን ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ። 17  ይሁንና ከምድር ብሔራት መካከል ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጡ ቢኖሩ ዝናብ አይዘንብላቸውም። 18  የግብፅ ሰዎች ባይወጡና ወደ ከተማዋ ባይገቡ ዝናብ አይዘንብላቸውም። እንዲያውም ይሖዋ የዳስ በዓልን ለማክበር ባልመጡት ብሔራት ላይ በሚያመጣቸው መቅሰፍቶች ይቀሰፋሉ። 19  ግብፅ ለፈጸመችው ኃጢአትና የዳስ በዓልን ለማክበር ያልወጡት ብሔራት ሁሉ ለሠሩት ኃጢአት ይህ ቅጣት ይደርስባቸዋል። 20  “በዚያ ቀን በፈረሶቹ ቃጭል ላይ ‘ቅድስና የይሖዋ ነው!’ ተብሎ ይጻፋል። በይሖዋ ቤት ያሉት ድስቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉት ሳህኖች ይሆናሉ። 21  በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ድስቶች በሙሉ ቅዱስና ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ የተወሰኑ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት የሚያቀርቡትም ሁሉ ገብተው የተወሰኑትን ድስቶች ለመቀቀያ ይጠቀሙባቸዋል። በዚያ ቀን በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ቤት ዳግመኛ ከነአናዊ አይገኝም።”
[]
[]
[]
[]
12,393
2  እኔም ቀና ብዬ ስመለከት በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰው አየሁ። 2  ከዚያም “ወዴት እየሄድክ ነው?” ብዬ ጠየቅኩት። እሱም “ወርዷና ርዝመቷ ምን ያህል እንደሆነ አውቅ ዘንድ ኢየሩሳሌምን ለመለካት እየሄድኩ ነው” ሲል መለሰልኝ። 3  እነሆም፣ ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረው መልአክ ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ። 4  ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ወደዚያ ሮጠህ ሂድና ያንን ወጣት እንዲህ በለው፦ ‘“በመካከሏ ካሉት ሰዎችና መንጎች ሁሉ የተነሳ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች በነዋሪዎች ትሞላለች። 5  እኔም በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “ክብሬም በመካከሏ ይሆናል።”’” 6  “ኑ! ኑ! ከሰሜን ምድር ሽሹ” ይላል ይሖዋ። “ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና” ይላል ይሖዋ። 7  “ጽዮን ሆይ፣ ነይ! ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፣ አምልጪ። 8  ክብር ከተጎናጸፈ በኋላ፣ እናንተን ወደዘረፏችሁ ብሔራት የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን ይነካል። 9  አሁን በእነሱ ላይ እጄን በዛቻ አወዛውዛለሁ፤ የገዛ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል።’ እናንተም እኔን የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። 10  “የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ፤ እኔ እመጣለሁና፤ በመካከልሽም እኖራለሁ” ይላል ይሖዋ። 11  “በዚያን ቀን ብዙ ብሔራት ከይሖዋ ጋር ይተባበራሉ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በመካከልሽ እኖራለሁ።” ደግሞም እኔን ወደ አንቺ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቂያለሽ። 12  ይሖዋ ይሁዳን በተቀደሰው ምድር ላይ ድርሻው አድርጎ ይወርሰዋል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣል። 13  የሰው ልጆች ሁሉ፣ በይሖዋ ፊት ጸጥ በሉ፤ በቅዱስ መኖሪያው ሆኖ እርምጃ እየወሰደ ነውና።
[]
[]
[]
[]
12,394
3  እሱም ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን በይሖዋ መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፤ ሰይጣንም እሱን ለመቃወም በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር። 2  ከዚያም የይሖዋ መልአክ ሰይጣንን እንዲህ አለው፦ “ሰይጣን፣ ይሖዋ ይገሥጽህ፤ አዎ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠው ይሖዋ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት መካከል የተነጠቀ የእንጨት ጉማጅ አይደለም?” 3  ኢያሱም ያደፈ ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። 4  መልአኩ በፊቱ ቆመው የነበሩትን “ያደፈውን ልብሱን አውልቁለት” አላቸው። ከዚያም እሱን “እነሆ፣ ጥፋትህን አስወግጄልሃለሁ፤ ደግሞም ጥሩ ልብስ ትለብሳለህ” አለው። 5  እኔም “በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም ይደረግለት” አልኩ። እነሱም ንጹሑን ጥምጥም በራሱ ላይ አደረጉለት፤ ልብስም አለበሱት፤ የይሖዋም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር። 6  ከዚያም የይሖዋ መልአክ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ 7  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመንገዶቼ ብትመላለስና በፊቴ ኃላፊነቶችህን ብትወጣ፣ በቤቴ ፈራጅ ሆነህ ታገለግላለህ፤ ቅጥር ግቢዎቼንም ትንከባከባለህ፤ እኔም እዚህ በቆሙት መካከል በነፃነት የመቅረብ መብት እሰጥሃለሁ።’ 8  “‘ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ ሆይ፣ አንተም ሆንክ በፊትህ የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ እባካችሁ ስሙ፤ እነዚህ ሰዎች ምልክት ሆነው ያገለግላሉና፤ እነሆ፣ ቀንበጥ የሚል ስም ያለውን አገልጋዬን አመጣለሁ! 9  በኢያሱ ፊት ያስቀመጥኩትን ድንጋይ እዩ! በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዓይኖች አሉ፤ እኔም በላዩ ላይ ጽሑፍ እቀርጻለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ።’ 10  “‘በዚያ ቀን’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘እያንዳንዳችሁ ጎረቤታችሁን ከወይናችሁና ከበለስ ዛፋችሁ ሥር እንዲቀመጥ ትጋብዛላችሁ።’”
[]
[]
[]
[]
12,395
4  ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ተመልሶ መጥቶ አንድን ሰው ከእንቅልፉ እንደሚቀሰቅስ ቀሰቀሰኝ። 2  ከዚያም “የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም እንዲህ አልኩት፦ “እነሆ፣ ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተሠራና ላዩ ላይ ሳህን ያለበት መቅረዝ ይታየኛል። በላዩ ላይ ሰባት መብራቶች፣ አዎ ሰባት መብራቶች አሉበት፤ አናቱ ላይ ያሉት ሰባት መብራቶችም ሰባት ቱቦዎች አሏቸው። 3  ከጎኑም አንዱ ከሳህኑ በስተ ቀኝ፣ አንዱ ደግሞ በስተ ግራ የቆሙ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።” 4  ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “ጌታዬ ሆይ፣ የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኩት። 5  ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረውም መልአክ “የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቅም?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” ብዬ መለስኩለት። 6  በዚህ ጊዜ እንዲህ አለኝ፦ “ይሖዋ ለዘሩባቤል የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘“በመንፈሴ እንጂ፣ በወታደራዊ ኃይል ወይም በጉልበት አይደለም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 7  ታላቅ ተራራ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ መሬት ትሆናለህ። “እንዴት ያምራል! እንዴት ያምራል!” እያሉ በሚጮኹበት ጊዜ እሱ የመደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።’” 8  የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ 9  “የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤት መሠረት ጥለዋል፤ የገዛ እጆቹም ያጠናቅቁታል። እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። 10  ሥራው በትንሹ የተጀመረበትን ቀን የናቀ ማን ነው? እነሱ ሐሴት ያደርጋሉና፤ በዘሩባቤልም እጅ ላይ ቱምቢውን ያያሉ። እነዚህ ሰባቱ በመላው ምድር የሚዘዋወሩ የይሖዋ ዓይኖች ናቸው።” 11  ከዚያም “ከመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉት የእነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ትርጉም ምንድን ነው?” በማለት ጠየቅኩት። 12  ለሁለተኛም ጊዜ እንዲህ ስል ጠየቅኩት፦ “በሁለቱ የወርቅ ቱቦዎች አማካኝነት ወርቃማ ፈሳሽ የሚያፈሱት የሁለቱ የወይራ ዛፎች ቅርንጫፎች ትርጉም ምንድን ነው?” 13  እሱም “የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አታውቅም?” አለኝ። እኔም “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” ብዬ መለስኩለት። 14  እሱም “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ ቅቡዓን ናቸው” አለ።
[]
[]
[]
[]
12,396
5  ዳግመኛ ቀና ብዬ ስመለከት የሚበር ጥቅልል አየሁ። 2  እሱም “የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም “ርዝመቱ 20 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10 ክንድ የሆነ የሚበር ጥቅልል አያለሁ” ስል መለስኩለት። 3  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በመላው ምድር ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፤ ምክንያቱም የሚሰርቁ ሁሉ በአንደኛው በኩል በተጻፈው መሠረት አልተቀጡም፤ ደግሞም በሐሰት የሚምሉ ሁሉ በሌላኛው በኩል በተጻፈው መሠረት አልተቀጡም። 4  ‘እኔ ልኬዋለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ ‘ወደ ሌባውም ቤት ይገባል፤ በስሜ በሐሰት ወደሚምለውም ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ቤት ውስጥ ይቀመጣል፤ እንጨቱንና ድንጋዩን ጨምሮ ቤቱን ይበላዋል።’” 5  ከዚያም ሲያነጋግረኝ የነበረው መልአክ ወደ እኔ ቀርቦ “እባክህ ቀና ብለህ የምትወጣውን ነገር ተመልከት” አለኝ። 6  እኔም “ምንድን ነች?” አልኩ። እሱም መልሶ “ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት” አለ። አክሎም “በምድሪቱ ሁሉ የሰዎቹ መልክ ይህ ነው” አለ። 7  እኔም ከእርሳስ የተሠራው ክቡ መክደኛ ሲነሳ አየሁ፤ በመስፈሪያዋም ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር። 8  እሱም “ይህች ሴት ክፋትን ታመለክታለች” አለኝ። ከዚያም የኢፍ መስፈሪያዋ ውስጥ መልሶ ጣላት፤ ቀጥሎም ከእርሳስ የተሠራውን ከባዱን መክደኛ መስፈሪያዋ አፍ ላይ ገጠመው። 9  ከዚያም ቀና ብዬ ስመለከት ሁለት ሴቶች ወደ ፊት ሲመጡ አየሁ፤ በነፋስም መካከል ወደ ላይ ተወነጨፉ። ክንፎቻቸው የራዛ ዓይነት ክንፎች ነበሩ። እነሱም መስፈሪያዋን በምድርና በሰማይ መካከል አነሷት። 10  እኔም ያነጋግረኝ የነበረውን መልአክ “የኢፍ መስፈሪያዋን ወዴት እየወሰዷት ነው?” ስል ጠየቅኩት። 11  እሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ቤት ሊሠሩላት ወደ ሰናኦር ምድር እየወሰዷት ነው፤ ቤቱም በተዘጋጀ ጊዜ በዚያ በተገቢው ቦታዋ ላይ ያስቀምጧታል።”
[]
[]
[]
[]
12,397
6  ዳግመኛም ቀና ብዬ ስመለከት አራት ሠረገሎች ከሁለት ተራሮች መካከል ሲመጡ አየሁ፤ ተራሮቹም የመዳብ ተራሮች ነበሩ። 2  የመጀመሪያውን ሠረገላ የሚጎትቱት ቀይ ፈረሶች፣ ሁለተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ደግሞ ጥቁር ፈረሶች ነበሩ። 3  ሦስተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ነጭ ፈረሶች፣ አራተኛውን ሠረገላ የሚጎትቱት ደግሞ ነጠብጣብ ያለባቸውና ዥጉርጉር ፈረሶች ነበሩ። 4  ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” ብዬ ጠየቅኩት። 5  መልአኩ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙ በኋላ፣ ከዚያ የሚወጡት አራቱ የሰማያት መናፍስት ናቸው። 6  በጥቁር ፈረሶች የሚጎተተው ሠረገላ ወደ ሰሜን ምድር ይወጣል፤ ነጮቹ ፈረሶች ከባሕሩ ባሻገር ወዳለው ምድር ይወጣሉ፤ ነጠብጣብ ያለባቸው ፈረሶች ደግሞ ወደ ደቡብ ምድር ይወጣሉ። 7  ዥጉርጉሮቹ ፈረሶችም ወጥተው በምድር መካከል ለመመላለስ አቆብቁበው ነበር።” እሱም “ሂዱ፤ በምድር መካከል ተመላለሱ” አለ። እነሱም በምድር መካከል ይመላለሱ ጀመር። 8  ከዚያም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ ወደ ሰሜን ምድር የሚወጡት፣ የይሖዋ መንፈስ በሰሜን ምድር እንዲያርፍ አድርገዋል።” 9  የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ 10  “በግዞት ከተወሰደው ሕዝብ ያመጡትን ነገር ከሄልዳይ፣ ከጦቢያህና ከየዳያህ ውሰድ፤ በዚያም ቀን፣ ከባቢሎን ከመጡት ከእነዚህ ሰዎች ጋር ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ። 11  ብርና ወርቅ ወስደህ አክሊል ሥራ፤ ከዚያም በየሆጼዴቅ ልጅ በሊቀ ካህናቱ በኢያሱ ራስ ላይ አድርገው። 12  እንዲህም በለው፦ “‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ቀንበጥ ተብሎ የሚጠራው ሰው ይህ ነው። እሱ በገዛ ቦታው ላይ ያቆጠቁጣል፤ የይሖዋንም ቤተ መቅደስ ይሠራል። 13  የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚገነባው እሱ ነው፤ ግርማ የሚጎናጸፈውም እሱ ነው። በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ ደግሞም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ካህን ሆኖ ያገለግላል፤ በሁለቱም መካከል ሰላማዊ ስምምነት ይኖራል። 14  አክሊሉም ለሄሌም፣ ለጦቢያህ፣ ለየዳያህና ለሶፎንያስ ልጅ ለሄን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ መታሰቢያ ሆኖ ያገለግላል። 15  በሩቅ ያሉትም ይመጣሉ፤ በይሖዋ ቤተ መቅደስ የግንባታ ሥራም ይካፈላሉ።” እኔን ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ብትሰሙ ይህ ይሆናል።’”
[]
[]
[]
[]
12,398
7  ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ኪስሌው በተባለው በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በአራተኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ። 2  የቤቴል ሰዎች ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳያቸው ለመለመን ሳሬጸርንና ረጌምሜሌክን ከሰዎቹ ጋር ላኩ፤ 3  እነሱም የሠራዊት ጌታን የይሖዋን ቤት ካህናትና ነቢያቱን “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግኩት በአምስተኛው ወር ማልቀስና መጾም ይኖርብኛል?” ብለው ጠየቁ። 4  የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ 5  “ለምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ ‘ለ70 ዓመታት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ዋይ ዋይ ስትሉ፣ ትጾሙ የነበረው በእርግጥ ለእኔ ነበር? 6  ትበሉና ትጠጡ በነበረበት ጊዜስ ትበሉና ትጠጡ የነበረው ለራሳችሁ አልነበረም? 7  ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉት ከተሞቿ በሰዎች ተሞልተውና ሰላም ሰፍኖባቸው በነበረበት ጊዜ እንዲሁም ሰዎች በኔጌብና በሸፌላ ይኖሩ በነበረበት ወቅት ይሖዋ በቀድሞዎቹ ነቢያት አማካኝነት ያወጀውን ቃል መታዘዝ አልነበረባችሁም?’” 8  የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ ዘካርያስ መጣ፦ 9  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነተኛ ፍትሕ ላይ ተመሥርታችሁ ፍረዱ፤ አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ፍቅርና ምሕረት አሳዩ። 10  መበለቲቱንም ሆነ አባት የሌለውን ልጅ፣ ከባዕድ አገር የመጣውን ሰውም ሆነ ድሃውን አታታሉ፤ ደግሞም አንዳችሁ በሌላው ላይ ክፉ ለማድረግ በልባችሁ አታሲሩ።’ 11  እነሱ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም፤ በግትርነትም ጀርባቸውን ሰጡ፤ ላለመስማትም ሲሉ ጆሯቸውን ደፈኑ። 12  ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ እንዲሁም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በመንፈሱ አማካኝነት፣ በቀድሞዎቹ ነቢያት በኩል የላከውን ሕግና ቃል አልታዘዙም። ከዚህም የተነሳ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እጅግ ተቆጣ።” 13  “‘እኔ ስጠራቸው እንዳልሰሙኝ ሁሉ እነሱ ሲጣሩም አልሰማቸውም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 14  ‘ደግሞም ወደማያውቋቸው ብሔራት ሁሉ በአውሎ ነፋስ በተንኳቸው፤ ምድሪቱም ትተዋት ከሄዱ በኋላ ባድማ ሆነች፤ በእሷ የሚያልፍ ወይም ወደ እሷ የሚመለስ ማንም የለም፤ የተወደደችውን ምድር አስፈሪ ቦታ አድርገዋታልና።’”
[]
[]
[]
[]
12,399
8  የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ መጣ፦ 2  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለጽዮን በታላቅ ቅንዓት እቀናለሁ፤ ደግሞም በታላቅ ቁጣ ለእሷ እቀናለሁ።’” 3  “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤ በኢየሩሳሌምም እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ተብላ ትጠራለች፤ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ተራራም ቅዱስ ተራራ ተብሎ ይጠራል።’” 4  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሽማግሌዎችና አሮጊቶች በኢየሩሳሌም አደባባዮች እንደገና ይቀመጣሉ፤ እያንዳንዳቸውም ከዕድሜያቸው ርዝመት የተነሳ በእጃቸው ምርኩዝ ይይዛሉ። 5  የከተማዋም አደባባዮች በዚያ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።’” 6  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ይህ ነገር ለዚህ ሕዝብ ቀሪዎች የማይቻል ነገር መስሎ ቢታይ እንኳ ለእኔ የማይቻል ነገር ሊመስል ይገባል?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።” 7  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ሕዝቤን ከምሥራቅና ከምዕራብ አገሮች አድናለሁ። 8  እኔም አመጣቸዋለሁ፤ እነሱም በኢየሩሳሌም ይኖራሉ፤ ሕዝቤም ይሆናሉ፤ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላካቸው እሆናለሁ።’” 9  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በእነዚህ ቀናት በነቢያት አፍ የተነገሩትን እነዚህን ቃላት የምትሰሙ ሁሉ እጃችሁን አበርቱ፤ እነዚህ ቃላት፣ ቤተ መቅደሱን ለመገንባት፣ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቤት መሠረት በተጣለበት ጊዜ ነቢያት የተናገሯቸው ናቸው። 10  ከእነዚያ ቀናት በፊት ለሰውም ሆነ ለእንስሳ የሚከፈል ደሞዝ አልነበረምና፤ ደግሞም ከጠላት የተነሳ በሰላም መግባትና መውጣት አይቻልም ነበር፤ ሰው ሁሉ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ አድርጌ ነበርና።’ 11  “‘አሁን ግን በዚህ ሕዝብ ቀሪዎች ላይ እንደቀድሞው ዘመን አላደርግም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 12  ‘የሰላም ዘር ይዘራልና፤ የወይን ተክሉ ፍሬ ያፈራል፤ ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች፤ ሰማያትም ጠል ያዘንባሉ፤ እኔም የዚህ ሕዝብ ቀሪዎች እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንዲወርሱ አደርጋለሁ። 13  የይሁዳና የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በብሔራት መካከል እርግማን ነበራችሁ፤ አሁን ግን አድናችኋለሁ፤ እናንተም በረከት ትሆናላችሁ። አትፍሩ! እጃችሁን አበርቱ።’ 14  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘“አባቶቻችሁ ስላስቆጡኝ በእናንተ ላይ ጥፋት ላመጣባችሁ ቆርጬ እንደነበርና በዚያም እንዳልተጸጸትኩ ሁሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ 15  “አሁንም ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት መልካም ለማድረግ ቆርጫለሁ። አትፍሩ!”’ 16  “‘እናንተ እነዚህን ነገሮች ልታደርጉ ይገባል፦ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በከተማዋም በሮች የምትፈርዱት ፍርድ እውነትን የሚያጠናክርና ሰላምን የሚያሰፍን ይሁን። 17  አንዳችሁ በሌላው ላይ ክፉ ነገር ለማድረግ በልባችሁ አታሲሩ፤ ማንኛውንም የሐሰት መሐላ አትውደዱ፤ እነዚህን ነገሮች ሁሉ እጠላለሁና’ ይላል ይሖዋ።” 18  የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ 19  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የአራተኛው ወር፣ የአምስተኛው ወር፣ የሰባተኛው ወርና የአሥረኛው ወር ጾም ለይሁዳ ቤት የፍስሐና የደስታ ይኸውም የሐሴት በዓል ይሆናል። በመሆኑም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።’ 20  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሕዝቦችና የብዙ ከተማ ነዋሪዎች በእርግጥ ይመጣሉ፤ 21  በአንዲት ከተማ የሚኖሩ ሰዎችም በሌላ ከተማ ወደሚኖሩ ሰዎች ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳየን ለመለመንና የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግ ተነሱ፤ እንሂድ። እኔም እሄዳለሁ።” 22  ደግሞም ብዙ ሕዝቦችና ኃያላን ብሔራት የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ለመፈለግና ይሖዋ ሞገሱን እንዲያሳያቸው ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።’ 23  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቀው በመያዝ “አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን” ይላሉ።’”
[]
[]
[]
[]
12,400
9  የፍርድ መልእክት፦ “የይሖዋ ቃል በሃድራክ ምድር ላይ ነው፤ደማስቆንም ዒላማው አድርጓል፤የይሖዋ ዓይን በሰው ዘርናበእስራኤል ነገዶች ሁሉ ላይ ነውና፤ 2  አዋሳኟ የሆነችውን ሃማትንም ዒላማው አድርጓል፤ደግሞም እጅግ ጥበበኛ ቢሆኑም እንኳ ጢሮስንና ሲዶናን ዒላማው አድርጓል። 3  ጢሮስ የመከላከያ ግንብ ገንብታለች። ብርን እንደ አቧራ፣ወርቅንም በመንገድ ላይ እንዳለ አፈር ቆልላለች። 4  እነሆ፣ ይሖዋ ንብረቷን ይወስዳል፤ሠራዊቷንም ባሕሩ ውስጥ ይደመስሳል፤እሷም በእሳት ትበላለች። 5  አስቀሎን ይህን አይታ ትፈራለች፤ጋዛ በጣም ትጨነቃለች፤ኤቅሮንም እንዲሁ ትሆናለች፤ ምክንያቱም ተስፋ የምታደርግባት ለኀፍረት ትዳረጋለች። ከጋዛ ንጉሥ ይጠፋል፤አስቀሎንም ሰው አልባ ትሆናለች። 6  ዲቃላም በአሽዶድ ይቀመጣል፤እኔም የፍልስጤምን ኩራት አስወግዳለሁ። 7  በደም የተበከሉትን ነገሮች ከአፉ፣አስጸያፊ የሆኑትንም ነገሮች ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፤ከእሱም የሚተርፈው ማንኛውም ሰው የአምላካችን ይሆናል፤እሱም በይሁዳ እንደ አለቃ፣ኤቅሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል። 8  የሚገባም ሆነ የሚወጣ እንዳይኖር፣ቤቴን ለመጠበቅ በውጭ በኩል ድንኳን እተክላለሁ፤ከእንግዲህም ወዲህ በመካከላቸው የሚያልፍ አሠሪ አይኖርም፤አሁን በገዛ ዓይኔ አይቼዋለሁና። 9  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እጅግ ሐሴት አድርጊ። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ። እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል። እሱ ጻድቅ ነው፤ መዳንንም ያመጣል፤ትሑት ነው፤ ደግሞም በአህያ፣በአህያዪቱ ልጅ፣ በውርንጭላ ላይ ይቀመጣል። 10  የጦር ሠረገላውን ከኤፍሬም፣ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ። የጦርነቱ ቀስት ይወሰዳል። እሱም ለብሔራት ሰላምን ያውጃል፤ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርእንዲሁም ከወንዙ እስከ ምድር ዳርቻ ይሆናል። 11  አንቺ ሴት፣ በእኔና በአንቺ መካከል ካለው የደም ቃል ኪዳን የተነሳእስረኞችሽን ውኃ ከሌለበት ጉድጓድ አውጥቼ እልካቸዋለሁ። 12  እናንተ ተስፋ ያላችሁ እስረኞች ወደ ምሽጉ ተመለሱ። ዛሬ እንዲህ እልሻለሁ፦‘ድርሻሽን እጥፍ አድርጌ እከፍልሻለሁ። 13  ይሁዳን በእጄ እንዳለ ደጋን እወጥረዋለሁና። ደጋኑን በኤፍሬም እሞላዋለሁ፤ጽዮን ሆይ፣ ወንዶች ልጆችሽን እቀሰቅሳለሁ፤ግሪክ ሆይ፣ በወንዶች ልጆችሽ ላይ ይነሳሉ፤ጽዮን ሆይ፣ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።’ 14  ይሖዋ በእነሱ ላይ ይገለጣል፤ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወነጨፋል። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ቀንደ መለከት ይነፋል፤እሱም ከደቡብ አውሎ ነፋሳት ጋር ይሄዳል። 15  የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ይከላከልላቸዋል፤እነሱም የሚወነጨፍባቸውን ድንጋይ ውጠው ያስቀራሉ፤ ደግሞም ያመክናሉ። ይጠጣሉ፤ የወይን ጠጅ እንደጠጣም ሰው ይንጫጫሉ፤እንዲሁም እንደ ሳህኖቹናእንደ መሠዊያው ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ። 16  በዚያ ቀን አምላካቸው ይሖዋ፣እንደ ሕዝቡ መንጋ ያድናቸዋል፤በአክሊል ላይ እንዳሉ ፈርጦች በምድሩ ላይ ያብረቀርቃሉና። 17  ጥሩነቱ ምንኛ ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ያማረ ነው! እህል ወጣት ወንዶችን፣አዲስ የወይን ጠጅም ደናግሉን ያለመልማል።”
[]
[]
[]
[]