query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
2
300
passage
stringlengths
78
8.98k
category
stringclasses
7 values
link
stringlengths
28
740
⌀
50fa46b1d4a2885f8baa9b59453f6beb
d1fe34b9f70628748e8924597e226dc2
ደብረብርሃን የሦስት ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት አቅዳ 17 ቢሊዮን ብር አገኘች
 አዲስ አበባ፡- የደብረብርሃን ከተማ ኢንቨስትመ ንት ፍሰት በ2011 በጀት ዓመት ከነበረበት 10 ቢሊዮን ብር ወደ 17 ቢሊዮን ብር ማደጉን የደብረብርሃን ከተማ ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ለዓመታት መሬት አጥረው ወደ ልማት ካልገቡ ባለሃብቶች 80 ሄክታር መሬት ተመላሽ በማድረግ ለአልሚዎች ተላልፏል።የደብረብርሃን ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃን ገብረሕይወት በተለይ ለጋዜጣው ሪፖርተር እንደገለፁት፤ የደብረብርሃን ከተማ በፈጠነ መልኩና አገራዊ ፋይዳቸው የጎላ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን ጠቁመው በአሁኑ ወቅት የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር ባለሃብቶች ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰሳቸው ለበርካታ ዜጎችም የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አብራርተዋል።  በ2011 ዓ.ም 11 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት መሳቡን ያስታወሱት አቶ ብርሃን፤ በ2012 በጀት ዓመት የሦስት ቢሊዮን ኢንቨስትመንት ለመሳብ ታቅዶ ሲሰራ ቢቆይም 17 ቢሊዮን ብር ፈሰስ ያደረጉ 270 ኢንቨስትመንት ፈቃድ  መሰጠቱን አረጋግጠዋል። በበጀት ዓመቱም 112 የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፤ ፍሰቱ ከፍተኛ ስለነበር ከእቅዱ በላቀ መልኩ 270 የኢንዱስትሪ ፈቃዶችን መሠጠቱንም ኃላፊው ገልፀዋል። ከኢንቨስተሮችም መካከል 85 ከመቶ የሚሆኑት የአገር ውስጥ ባለሃብቶች ናቸው ተብሏል።አቶ ብርሃን እንዳሉት፤ በአካባቢው 76 አዋጭና ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ የኢንቨስትመንት አማራጮች በጥናት ተለይተዋል። የመሬት አቅርቦቱ ደግሞ ለምግብና ምግብ ነክ፣ ለጋርመንትና ጨርቃጨርቅ፣ ኬሚካልና ኢንዱስትሪዎች ብሎም እንጨትና ብረታ ብረት በሚል አራት ክላስተሮች የተደራጀ ሲሆን፤ ይህም ባለሃብቶች ሥራቸውን በተቀላጠፈ መንገድ ለማከናወን ብሎም የሚመለከታቸው አካላትም ለቁጥጥር እንዲያመች ታስቦ የተደራጀ ነው።ኃላፊው እንዳብራሩት፤ በክላስተር የተደራጀ የመሬት አቅርቦት መኖሩ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ ለኢንቨስትመንትና ለኢንቨስተሮች ንብረት ጥበቃና ከለላ በመሆን ከመንግሥት ጋር ጠንካራ ትብብር መፍጠሩ፣ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት መገኘቷ፣ ምቹ የአየር ንብረትና ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸው፣ ቢሮክራሲ የበዛባቸውና የተንዛዙ አሠራሮች መቃለላቸው፣ በአካባቢው በየዓመቱ በአማካይ 10ሺ በላይ ሰዎች የሚመረቁ መሆናቸውና ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉትን የተማረ የሰው ኃይል ማግኘታቸው ለኢንቨስትመንቱ ማደግ ትልቅ አበርክቶ አድርገዋል።አንድ ባለሃብት የሚጠበቅበትን መስፈርት ካሟላ ከሦስት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መሬት ይሰጣል ያሉት አቶ ብርሃን፤ የኢንቨስትመንት መምሪያ ባለሙያዎች እሁድና ቅዳሜን ጨምሮ ሣምንቱን ሙሉ እንደሚሰሩና በተለይም እሁድና ቅዳሜ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለጉዳዮችና ባለሃብቶች እንደሚስተናገዱም ገልፀዋል። በሌላ በኩል ምንም እንኳን ከተማዋ ከፍተኛ የኢንቨስተሮች መዳረሻ ማዕከል እየሆነች ቢሆንም ፈተናዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል። በተለይም የከተማዋ አደረጃጀት በመካከለኛ ደረጃ ላይ ያለች ሲሆን ይህም ወደ ከፍተኛ ከተሞች እርከን በማስገባት በክፍለ ከተማ ደረጃ አለማዋቀርና መሠረተ ልማቶች አለመሟላታቸው እንዲሁም የክልሉን እና የፌዴራል መንግሥት ይሁንታ የሚጠብቀውና ይሻሻል ተብሎ ጥያቄ የቀረበበት የካሣ ክፍያ ሥርዓት አንድ ዓመት መዘግየቱ በአስፈላጊ ጊዜ ለአርሶ አደሮች ካሣ ለመክፈል እክል የፈጠረ ሲሆን በኢንቨስትመንቱ እንቅስቃሴ ላይ ጫና መፍጠሩንም አረጋግጠዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ምበ ክፍለዮሐንስ አንበርብር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36415
6cfe910765a4f209c3ba23b2f2cee306
92c3a45dee294a9594cc25d1970fdfbe
የእግር ኳስን ‹‹መዝገብ›› ያደበዘዙ ገፆች
 በዓለማችን ላይ ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል እግር ኳስ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ስፖርቱ ታዳሚዎችን ከማዝናናት ባለፈ በርካታ ክስተቶችንም ያስተናግዳል። በዚህ ተወዳጅ ውድድር ላይ የሚታዩ ክስተቶች አወንታዊ እና አሉታዊ ጎን ያላቸው ናቸው። በዛሬው ዝግጅታችን ላይ በእግር ካስ ላይ በአሉታዊ ጎን «ጥቁር ነጥብ» ጥለው ያለፉ ታሪካዊ ክስተቶችን እናነሳለን። ስፖርቱ ላይ መጥፎ አሻራቸውን ያኖሩ አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው። ከነዚህ መካከል ተጫዋቾች በአደገኛ ሁኔታ የመጎዳት እና ሞት፣ የሜዳ ላይ ግጭቶች፣ የደጋፊዎች ነውጥ፣ ያልተጠበቀ የዳኝነት ስህተቶች፣ የውጤት ማጭበርበር ወይም «ማች ፊክሲንግ» ይጠቀሳሉ። ታሪክ ደግሞ እነዚህን ትዝታዎች ከማይዘነጉ ተመሳሳይ ክስተቶች መካከል ሰንዶ ያስቀምጣቸዋል። ለዛሬ ወደ ኋላ መለስ ብለን ከላይ ካነሳናቸው «እግር ኳስን ካደበዘዙ ታሪኮች» መካከል የሚመደበውን ጉዳይ እናንሳ። ትኩረታችንንም የስፖርቱ ሞገስ የሆኑት ደጋፊዎች እና ስታዲዮሞች ላይ አድርገን የደረሰውን የማይዘነጋ አሳዛኝ አጋጣሚ እናስቃኛለን። የእግር ኳሱ ጨዋታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ በጣም በርካታ አሳዛኝ ክስተቶች በስቴዲዮሞች ተስተናግዷል። ይህም ምናልባት ስፖርቱ በጣም በብዙ ሚሊዮን ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ በመሆኑ የሚፈጠር ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የደጋፊዎች እና ሌሎች አካላት የአጥፊነት እና ጠብ አጫሪነት ባህሪ «Hooliganism» ከአፍ እስከ ገደፋቸው ስታዲየሞች በመሙላታቸው፣ ያረጁ እና ተገቢውን ጥገና ያላረጉ ስታዲዮሞች በመሆናቸው፣ እንዲሁም በሁለት ባላንጣ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ጨዋታዎች ከቁጥጥር  ውጪ በመውጣታቸው የሚከሰቱ አሳዛኝ አደጋዎች ዋናውን ድርሻ ይወስዳሉ። አሁን የምናነሳው ታሪክ የአርጀንቲና ከተማ ወደ ሆነችው ቦነስ አይረስ ይወስደናል፡፡ አሳዛኙ አጋጣሚ የተከሰተው እአአ በ1968 ነው፡፡ ቦታው ደግሞ ‹‹ስታዲዮ ሞኑምንታል››፡፡ በአርጀንቲና ክለቦች መካከል ከሚደረጉ የእግር ኳስ ፍጥጫዎች መካከል አቻ የማይገኝለት የደርቢ ጨዋታ በሪቨር ፕሌት እና በቦካ ጁኒየርስ እየተካሄደ ነበር። ሆኖም ግን ከጨዋታው በኋላ ያልተጠበቀ ክስተት ስታዲየሙን በድንገት አናወጠው። ወትሮውንም እነዚህ ሁለት ክለቦች ሲገናኙ በደጋፊዎቻቸው መካከል ግጭት የተለመደ ነው፡፡ እርስ በርስ ተሸናንፈው በከተማዋ ላይ መንገስን ከምንም ነገር በበለጠ የሚፈልጉት ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ሊጉን በበላይነት ከማጠናቀቅም የበለጠ ለሁለቱ ባላንጣዎች አስፈላጊ ነው። በዛች ቀን ግን ከምን ጊዜውም በበለጠ የአርጀንቲናን ህዝብ ብቻ ሳይሆን፤ የአለምን ትኩረት የሳበ እና የእግር ኳስን አስቀያሚ ገፅታ ያሳየ አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ ተመልካቾች ወደ መውጫው በር እያቀኑ ነበር፡፡ በድንገት ግርግር በመነሳቱ ሁሉም ወደ በሩ እግሬ አውጪኝ አሉ፡፡ በዚህ ግርግር ውስጥ አቅም ያልነበራቸው እና ማምለጥ ያልቻሉት ለከፍተኛ ጉዳት እና ሞት ተጋለጡ፡፡ በዚች የተረገመች ቀን ከ71 ሰዎች በላይ ለህልፈተ ህይወት ሲዳረጉ‹፤ 150 ደጋፊዎች ደግሞ ክፉኛ ቆሰሉ፡፡ እግር ኳስም አፍቃሪዋን በላች፡፡ ለዚህ አሳዛኝ ክስተት መነሻ እርግጠኛ የሆነ ምክንያት ግን ሊገኝ አልቻለም፡፡ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን፤ ግርግሩ የተነሳው የቦካ ጁኒየርስን ደጋፊዎች የሪቨር ፕሌትን ባንዲራ በእሳት አያይዘው በብዛት ህዝብ ወደ ነበረበት ስፍራ በመወርወራቸው ነው በማለት ሲዘግቡ፤ ሌሎች ደግሞ የሪቨር ፕሌት ደጋፊዎች የተቀናቃኛቸው የመቀመጫ ስፍራ በመሄዳቸው በዚህ ምክንያት በተፈጠረ ግርግር አደጋው ተከስቷል የሚል መላ ምት ይሰነዝራሉ፡፡ ፖሊስ ለሶስት ዓመት በጉዳዩ ላይ ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም ማንም ግለሰብም ሆነ ቡድን ወንጀለኛ እንዳልሆነ፤ ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጠረው በበሩ አካባቢ በተፈጠረ ፍፁም መጨናነቅ መሆኑን ሪፖርት አድርጓል፡፡ የሆነው ሆኖ የሁለቱ ተቀናቃኝ ቡድኖች ጨዋታ ዓለም በመጥፎ ጎኑ እንዲያስታውሰው ሆኖ ተጠናቋል፡፡ ሌላኛው እና በስታዲዮም ውስጥ ጥቁር ጠባሳውን ጥሎ ያለፈው ክስተት የ ‹‹ፖርትሴይድ ስታዲዮም ዲዛዝተር›› ነው፡፡ ወቅቱ እ.አ.አ በ2012 ሲሆን፤ ሁነቱ ደግሞ ግብፅ ውስጥ ነበር፡፡ በዚህ ስታዲዮም ውስጥ ይጫወቱ የነበሩት አል-ማስሪ እና አል-አህሊ ነበሩ፡፡ በወቅቱ አል-ማስሪ ተቀናቃኙን 3ለ1 ማሸነፍ ችሎ ነበር፡ ፡ ነገር ግን ፍፃሜው ማንም እንደሚወደው አይነት ሆኖ ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡ በግልባጩ ይህ ጥቁር ቀን ለ79 ደጋፊዎች ህይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ እንጂ፡፡ ለህይወት መጥፋት መነሻ የነበረው የአል- ማስሪ ደጋፊዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ በተቀናቃኛቸው የአል-አህሊ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ነበር፡፡ በሺ የሚቆጠሩት እነዚህ ደጋፊዎች ሜዳውን ስፖርታዊ ጨዋነት በጎደለው መልኩ በመውረር ተቀናቃኞቻቸውን አጠቁ፡፡ ወትሮ ሰላም የሚሰበክበትን እግር ኳስን በማጠልሸት ‹‹ጥቁር ታሪክ›› ፃፉ፡፡ ክስተቱ ለ79 ሰዎች ህይወት መጥፋት እና በሺ ለሚቆጠሩት የመቁሰል አደጋን አደረሰ፡፡ በጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር መጋቢት 12 ቀን 1988 ተመሳሳይ አሳዛኝ ክስተት ተስተናገደ፡፡ ወትሮውኑ ቀለምና ዘርን የማይለየው እግር ካስ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለብዙሀን ሞትን ለሌሎች ደግሞ ሀዘንን ይዞ ከተፍ አለ፡፡ አገሪቷ «ኔፓል» ስትሆን ቦታው ደግሞ ‹‹ካትማንዱ›› ብሄራዊ ስታዲዮም፡፡ ኔፓል እና ባንግላዲሽ በዚህ ቀን ጨዋታቸውን ያደርጉ ነበር፡ ፡ ሆኖም ነገሮች እንደተጠበቀው ሊሄዱ አልቻሉም ነበር፡፡ ከዚህ በተቃራኒው 30 ሺ ተመልካቾችን የሚይዘው የካትማንዱ ስታዲዮም ታሪክ የማይዘነጋው አጋጣሚን አስተናገደ፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን በሚያደርጉበት ወቅት በጣም ሀይለኛ ዝናብ መጣል ጀመረ፡፡ በረዶ ከተቀላቀለበት ዶፍ ዝናብ ለማምለጥ የሞከሩ ሰላሳ ሺ ደጋፊዎች ወደ በሩ መውጫዎች ሩጫቸውን ተያያዙት። ነገር ግን ከስምንቱ መውጫ በሮች አንዱ ብቻ ክፍት ነበር፡፡ በዚህ ግርግር በርካታ ሰዎች ተረጋገጡ፤ አቅም ያልነበራቸው ወጣቶች እና ህፃናት ለሞት ተዳረጉ፡፡ 93 ሰዎች በዚህ አደጋ ሲሞቱ በርካቶች ደግሞ ክፉኛ ቆሰሉ፡፡ ይሄኛው ጥቁር ጥላ ደግሞ ወደ ጋና ይዞን ይጓዛል፡፡ እአአ ግንቦት 9 በ2001 በአክራ ‹‹ስፖርት ስታዲዮም›› ወደ ተፈጠረ አሳዛኝ አጋጣሚ፡፡ ጨዋታው የሚካሄደው በጋና የእግር ካስ ሊግ ከፍተኛ ተፎካካሪዎች በሆኑት «በህርትስ ኦፍ ኦክ እና በአሳንቴ ኮቶኮ» መካከል ነበር፡ ፡ ከሁለቱም ክለቦች 70 ሺ የሚደርሱ ደጋፊዎች ይህን አጓጊ ጨዋታ ለመታደም በስታዲዮሙ ተገኝተዋል፡፡ አጋጣሚው ከመፈጠሩ በፊት ህርትስ ኦፍ ኦክ 2 ለ1 እየመራ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደ ጨዋታው ማብቂያ ላይ ፖሊስ በደጋፊዎች መካከል ተፈጥሯል ያለውን ብጥብጥ ለመበተን የአስለቃሽ ጭስ ይጠቀማል፡፡ ከዚህ አስለቃሽ ጭስ ለማምለጥ በሚደረግ ፍትጊያ ደግሞ በርካታ ሰዎች ለመረጋገጥ እና ለህልፈተ ህይወት ተዳረጉ፡ ፡ የሞቱት የደጋፊዎች ቁጥር 126 ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፖሊስ በሰራው ስህተት ደጋፊዎች ለሞት እና ለቁስለት መዳረጋቸውን ይናገራሉ፡፡ በወቅቱ አጋጣሚውን ሽፋን የሰጠው ቢቢሲም ይህንኑ ነበር በዘገባው ያነሳው፡፡ በዓለም እግር ኳስ ታሪክ ጥቁር ጥላቸውን ካሳረፉ አሳዛኝ አደጋዎች ውስጥ በአስከፊነቱ ወደር የማይገኝለት ተብሎ ተመዝግባል፡፡ ወቅቱ እ.አ.አ ግንቦት 24 1964 ነበር፡፡ በሊማ ብሄራዊ ስታዲዮም ጨዋታቸውን የሚደርጉት ደግሞ ፔሩ እና አርጀንቲና ነበሩ፡፡ ለኦሎምፒክ ውድድር ለማለፍ በሚደረገው በዚህ የማጣሪያ ጨዋታ ላይ አርጀንቲና ቀዳሚውን ጎል በማስቆጠር መምራት ጀመረች፡፡ በዚህ ጊዜ የፔሩ ደጋፊዎች ብስጭት ውስጥ በመግባታቸው ወደ ሜዳ ቁሳቁሶችን በመወርወር ተቃውማቸውን መግለፅ ጀመሩ፡ ፡ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ፔሩዎች አቻ የሚያደርጋቸውን ጎል በተመሳሳይ ማስቆጠር ቻሉ፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ግብ ዳኛው ሊያፀድቀው አልቻለም ነበር፡፡ ይህ ደግሞ እነዚህን ደጋፊዎች ክፉኛ አበሳጨ፡፡ ነገሩም ወደ ከፋ ብጥብጥ ተቀይሮ ለ318 ሰዎች ህልፈትና ከ500 ሰዎች በላይ ለሆኑት ደግሞ የመቁሰል ምክንያት ሆነ፡፡ ይህ አጋጣሚም በጥቁር ቀለም ተከትቦ የእግር ኳስ ታሪክ ላይ ሰፈረ። ከላይ ያነሳናቸው የእግር ኳስ መቅሰፍቶች በታሪክ ውስጥ ሰላማዊውን ስፖርት ወደ ጦር ሜዳነት የቀየሩ ክስተቶች ነበሩ፡፡ ከነዚህ አጋጣሚዎች በተጓዳኝ ግን፤ በተወዳጁ ስፖርት ፍቅር ይሰበካል፣ ሰላማዊ ፉክክር ይደረጋል፣ ሰብአዊነትን የሚያሳዩ ፍፁም አስደሳች ድርጊቶች፤ ዘርን እና ቀለምን መሰረት ሳያደርጉ ይካሄዳሉ፣ ባላንጣ ፖለቲከኞች በእግር ካስ ጨዋታ ይታረቃሉ፣ ለዓለም ህዝብ በጎው እንዲመጣና ጥላቻ እንዲጠፋ ሁለት ተቃራኒ ቡድኖች እጅ ለእጅ ተያይዘው ይፀልያሉ፡፡ ሆኖም ግን ይሄ ሁል ጊዜ አይሳካም፤ በተወዳጅነቱ ወደር የማይገኝለት የእግር ኳስ መዝገብ ላይ የደበዘዙ ታሪኮች የራሳቸው ገፅ ይኖራቸዋል፡፡አዲስ ዘመን  ሐምሌ 21/2011  ዳግም ከበደ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14917
e77b3495eb5903de8f5e7b7732f2c36d
7cde991eb4e3ca2b33fe419234c4cd6e
አልማዝ አያና ከጉዳቷ ለማገገም እየታገለች ነው
ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ አትሌት አልማዝ አያና ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ ለመመለስ ጥረት ማድረግ ከጀመረች ሰነባብታለች፡፡ ከጉዳት አገግማ ባለፈው ወር ዩጂን ዳይመንድ ሊግ ላይ በሦስት ሺ ሜትር ያደረገችው ተሳትፎ ውጤታማ አልነበረም። ይህም አልማዝ ከዘጠና ስድስት ቀናት በኋላ በኳታር ዶሃ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና አትደርስም የሚል ስጋት ፈጥሯል። ይሁን እንጂ አልማዝ ለዓለም ቻምፒዮናው ለመድረስ ልምምድ እያደረገች እንደምትገኝ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ድረ ገፅ ጋር ሰሞኑን ባደረገችው ቃለ ምልልስ ተናግራለች፡፡ የአልማዝ አያና አሰልጣኝና ባለቤት ሶሬሳ ፊዳ ከወራት በፊት ለአዲስ ዘመን እንደገለፀው አትሌቷ ጉልበቷ ላይ በደረሰባት ጉዳት ለአንድ ዓመት ያህል ከውድድር ርቃ የነበረ ሲሆን ከጉዳቷ ለማገገም የጅምናዚየም ልምምድ ስትሰራ ቆይታለች፡፡ አልማዝ በሁለቱም እግሮቿ ላይ በገጠማት ጉዳት የተለያዩ ቀዶ ጥገናዎችን ያከናወነች ሲሆን ቀስ በቀስ ወደ ልምምድ መመለስ እንዳለባት ዶክተሮቿ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ዝግጅቷን በተለመደው የአምስትና አስር ሺ ሜትር ርቀቶች ላይ በማድረግም በዓለም ቻምፒዮናው ኢትዮጵያን ወክላ ለመሮጥ ትልቅ ፍላጎት እንዳላት ተናግ ራለች፡፡ የዓለም የአስር ሺ ሜትር ክብረወሰን ባለቤት፤ የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮናዋ አልማዝ በ2017 የውድድር ዓመት ለአስራ አንድ ወራት ያህል ከውድድር ርቃ ብትቆይም የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ላይ በአስር ሺ ሜትር የወርቅ፤ በአምስት ሺ ሜትር ደግሞ የብር ሜዳሊያ ማጥለቋ ይታወሳል። በዚያ የውድድር ዓመት የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት አሸናፊ መሆን የቻለችው አልማዝ ምንም እንኳን በውድድር ዓመቱ ከለንደን ቻምፒዮና ሁለት ውድድሮች ውጪ መካፈል ባትችልም ከጉዳት ተመልሳ በአጭር ጊዜ ዝግጅት አስር ሺ ሜትሩን 30:16.32 በሆነ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ማሸነፏ አድናቆትን አስገኝቶላታል። በ2016 የውድድር ዓመት የአትሌቲክሱ ዓለም ከተመለከታቸው ድንቅ አትሌቶች መካከል አንዷ አልማዝ አያና ነበረች። በሪዮ ኦሊምፒክ በአስር ሺ ሜትር 29:17.45 የሆነ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀችው አልማዝ በአምስት ሺ ሜትርም የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ስትሆን የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊም ጭምር ነበረች። በዚያ የውድድር ዓመት በሮም ዳይመንድ ሊግ ላይ በአምስት ሺ ሜትር 14:12.59 የሆነ ሁለተኛው የዓለማችን ፈጣን ሰዓት ማስመዝገቧም በውድድር ዓመቱ የሚጠቀስ ታላቅ ስኬቷ ነበር። አልማዝ በሪዮ ኦሊምፒክ በተለይም በአስር ሺ ሜትር ስታሸንፍ ለሃያ ሦስት ዓመታት በቻይናዊቷ ዋንግ ጁአ ተይዞ የቆየውን የዓለም ክብረወሰን በአስራ አራት ሰከንዶች ማሻሻሏ ኢትዮጵያውያንን ብቻም ሳይሆን የዓለም አትሌቲክስ አፍቃሪን ጮቤ አስረግጧል። አልማዝ በወቅቱ አስር ሺ ሜትርን ለመጀመሪያ ጊዜ በሮጠችበት የሄንግሎ የመመዘኛ ውድድር ላይ ያስመዘገበችው 30:07 ሰዓት በርቀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሮጠች አትሌት የተመዘገበ ፈጣን ሰዓት ሆኖም ተይዟል። አልማዝ አያና በ2017 የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና በአስር ሺ ሜትር የወርቅና በአምስት ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ ካሸነፈች ወዲህ ግን ብቅ ያለችው በተለመደው የመም ውድድር ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የኒው ዴልሂ ግማሽ ማራቶን ውድድር ነው። አልማዝ የመም ውድድር ጉዞዋን ሳትቋጭ ወደ ግማሽ ማራቶን የመጣችበት ምክንያት ግልፅ ነው። አምስትና አስር ሺ ሜትር የመም ውድድሮች ከዓለም መጥፋታቸው አልማዝ ወደ ጎዳና ላይ ውድድሮች ፊቷን እንድታዞር ያደረጋት እውነታ እንደሆነ ይታመናል። ያም ሆኖ ግን ይህች ድንቅ ኢትዮጵያዊት አትሌት ለመጀመሪያ ጊዜ በግማሽ ማራቶን ራሷን ፈትሻ 1፡07፡11 በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆና ፈፅማለች። አልማዝ በለንደኑ የዓለም ቻምፒዮና በተለይ ደግሞ በሪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ካለ አንድ ወርቅ ከመሰናበት እንደታደገችው ሁሉ በ2017 ግማሽ ማራቶን ውድድሮች ወንዶች ያስመዘገቡት እዚህ ግባ የማይባል ውጤት በሴቶች እንዳይደገም አድርጋለች። ከዴልሂ ግማሽ ማራቶን ውድድሯ ወዲህም ካለፈው አንድ ዓመት በላይ በጉዳት የትኛውም ውድድር ላይ ሳትታይ ቀርታለች።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 22/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14953
636c3c7ab806804ef035fb10322b3598
53ab7d1a131bbe1c7665af3d0c05a93b
ኢትዮጵያ በሞተር ስፖርት የት ነች?
የሞተር ስፖርት ውድድሮች ከአፄ ሃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ይካሄድ ነበር። በወቅቱ ከአዲስ አበባ አስመራ ድረስ የሚዘጋጁ «የራሊ» የመኪና ፍልሚያዎች እንደነበሩ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ። ሆኖም በደርግ ዘመነ መንግስት ስፖርቱ «የቡርዥዋ» ስፖርት ነው በሚል እንዲቋረጥ አድርጎት ነበር። ይህ ስፖርት ረጅም ዓመታትን ይቆይ እንጂ ይህ ነው የሚባል አመርቂ ለውጥ ማምጣት አልቻለም። የደርግ ዘመን ማብቃቱን ተከትሎም ለስፖርቱ ፍቅር እና ቅርበት ያላቸው ሰዎች በማህበር ደረጃ በመሰባሰብ መሰረት ለመጣል ጥረት ከማድረጋቸው በዘለለ በኢትዮጵያ ውስጥ በልዩ ትኩረት እንዲታይ ማድረግ አልቻሉም። አቶ ኤርሚያስ አየለ የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት አሶሲዬሽን ቦርድ ፕሬዚዳንት ነው። ከሞተር ስፖርት አሶሴየሽን የቦርድ ፕሬዚዳንትነቱ በተጨማሪ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅም በመሆን አገልግሏል። ለአራት ዓመታት ማህበሩን ሲመራ በቆየበት ወቅት የኢትዮጵያ ስፖርት ላይ የጎላ ሚና እንዲኖረው ጥረት አድርጓል። በዚህ ማህበር ላይ ተሳታፊ እንዲሆንና ውድድሩ ላይ ልክ እንደ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ በሚል ነበር በአባላቱ ፍላጎት የመጣው። ሆኖም ግን ይህ ስፖርት ከሚጠይቀው ልዩ ትኩረት እና ኢንቨስትመንት አንፃር ውጤታማ ስራዎች ማከናወን እንዳልተቻለ ነው የነገረን። «ስፖርቱ በሚገባ ከተሰራበት ለአገር ኢኮኖሚ ያለው አበርክቶ ከፍተኛ ነው» የሚል እምነት ያለው አቶ ኤርሚያስ መንግስትም ሆነ የሚመለከተው አካል አስፈላጊ በሆነ መንገድ ድጋፍ ሊያደርግለት ይገባል። በተለይ የማስፋፊያ ቦታ ወሳኝነት አለው በማለት ይገልፃል። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ፈታኝ የሆኑ እንቅፋቶች የበዙበት እና በቀላሉ ውጤታማ መሆን ያልተቻለበት እንደሆነ ይናገራል። በመሆኑም የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሆኖ የመቀጠል ፍላጎት እንደሌለውም ይገልጻል። በተመረጥኩበት የስራ ዘመን ማህበሩ ዓለም አቀፍ ግንኙነቱ እንዲጠናከር ሆኗል። አፍሪካ የሞተር ስፖርት ማህበር ጉባኤ በኢትዮጵያ ተደርጓል። መንግስት ከቀረጥ ነፃ ድጋፍ እና የውድድር ማዘጋጃ ቦታዎችን ማመቻቸት ቢችል ወደፊት ስፖርቱን የሚመሩት አካላት ስኬታማ ውጤት ያስመዘግባሉ የሚል እምነቱን ገልጿል። አቶ እዮብ ገብረ ሚካኤል የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት አሶሲዬሽን የቴክኒክ ክፍል ሃላፊ እና የቦርድ አባል ነው። ስፖርቱ ከተጀመረ ረዘም ያሉ አመታትን ማስቆጠሩንና እድገት አለማሳየቱን ጠቅሰን ምክንያቱን እንዲያብራራልን ጠይቀነው ነበር። በጉዳዩ ላይ በሰጠው ምላሽ «ውድድሩ እስካሁንም ይህ ነው የሚባል ለውጥ እንዳያሳይ ያደረገው በባህሪው ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ስፖርት በመሆኑ ነው» በማለት ሃሳቡን ይሰነዝራል። ከላይ አቶ ኤርሚያስ ያነሳውንም ሃሳብ ይጋራል። አቶ እዮብ መንግስት የሞተር ስፖርትን ለማበረታታት ድጋፍ ያደርግ እንደነበር ይናገራል። ድጋፉም ከቀረጥ ነፃ የመወዳደሪያ መኪናዎች እንዲያስገባ ማህበሩ ይፈቅድ እንደነበርም ይገልፃሉ። ሆኖም ይህ ድጋፍ ግን አሁን ላይ ባልታወቀ ምክንያት ተቋርጧል። «በአገራችን ስፖርቱን ማስፋፋት ብንችል በከፍተኛ ደረጃ የቱሪስት ፍሰቱን መጨመር እንችላለን» የሚለው አቶ እዮብ በአፍሪካ ውስጥ በሚደረጉ ተመሳሳይ ውድድሮች ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን በምሳሌነት ያነሳል። መንግስት አሁንም ቢሆን ከቀረጥ ነፃ መኪኖች እንዳይገቡ መከልከሉ ግልፅ ሊሆንላቸው እንዳልቻለ ነው የሚናገረው። በዚህ ሂደት ውስጥ ሌሎች ችግሮች እንዳይከሰቱ የቁጥጥር ስልት በመንደፍ ቀድሞ የነበረውን ድጋፍ መቀጠል ይኖርበታል ይላል። «ድጋፍ ለማድረግ የሚችሉ አካላት ውድድሩ ቢካሄድ እና ስፖርቱ ቢያድግ ይዞት የሚመጣውን ጥቅም ሊረዱት የቻሉ አይመስለኝም» የሚለው አቶ እዮብ፤ የቀረጥ ነፃ ማበረታቻው ቢደረግ እና ስፖርቱ ቢያድግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንደሚኖሩት ይናገራል። በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪዎችን ለማፍራት፣ ቱሪስት ለመሳብ እና ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚቻል ይገልፃል። የስፖርት ማህበሩ ከዓለም አቀፉ የስፖርት ፌዴሬሽን ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለውና እገዛ እንደሚያደርግላቸውም ይገልፃል። መሳሪያዎችን በማቅረብ እና ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ እንደሚደግፋቸውም ይናገራል። ማህበሩ ለፌዴሬሽኑ የአባልነት ክፍያ ይፈፅማል። ለበርካታ ዓመታትም ሳያቋርጥ ከፍሏል። ስለዚህ ጉዳይ የቴክኒክ ሀላፊው ሲገልፁ «ለረጅም ዓመታት የፊያ አባል ሆነን ቆይተናል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን በገንዘብ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የአባልነት ክፍያ ለመፈፀም ተቸግረን ነበር» በማለት ዓለም አቀፍ ግንኙነታቸው በመልካም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይገልፃሉ። ፌዴሬሽኑ ለማህበሩ ወጣቶች እንዲያሰለጥንበት «ጎካርት» በመባል የሚታወቀውን የመወዳደሪያ መኪና እንደለገሳቸው ተናግረዋል። ማህበሩ በመላው ኢትዮጵያ የሞተር ስፖርት እንዲስፋፋ እየሰራሁ ነው ይላል። በኢትዮጵያ ስፖርት ላይ እንደሌሎቹ ሁሉ ፌዴሬሽን እንዲሆን ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑንም ይገልፃል። በባህርዳር ሃዋሳ እና ሌሎች ከተሞች ላይም የሞተር ስፖርት ማህበር በማቋቋም ወደ ፌዴሬሽን እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑንም ይፋ አድርጓል። ማህበሩ አሁን ላይ እንቅፋቶች ከሆኑበት መካከል የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ አለመኖር መሆኑን ይናገራሉ። ስፖርቱ በባህሪው ከሚፈልገው ሰፊ ማዘውተሪያ አንፃር አሁን ላይ ይህን ማሟላት አስቸጋሪ እንደሆነባቸውም አቶ እዮብ ይገልፃሉ። ሳንሱሲ አካባቢ ማህበሩ ማዘውተሪያ ስፍራ ቢኖረውም አሁን ላይ በተለያየ ምክንያት ከእጁ የመውጣት ስጋት እየተደቀነበት ነው። ይህንን ችግር መንግስት ከግምት አስገብቶ የማዘውተሪያ ስፍራ ለማህበሩ እንዲያመቻች ፍላጎታቸው ነው። በኢትጵያ ውስጥ በሚካሄዱ የሞተር ስፖርት ውድድሮች ላይ በብዛት ተሳታፊ የሚሆኑት የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ናቸው የሚለውን ትችት አቶ እዮብ ይቀበሉታል። ይህ ሊሆን የቻለው ስፖርቱ በባህሪው ከፍተኛ ወጪን ስለሚጠይቅ ነው በማለትም ምላሽ ይሰጣሉ። አሁን ላይ ግን የዓለም አቀፉ ፌዴሬሽን በሚያደርግላቸው ድጋፍ እና በማህበሩ ጥረት ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ይናገራሉ። የጣሊያኖች እና የግሪክ ተወዳዳሪዎችን የሚፎካከሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን እየተፈጠሩ መሆኑንም ያነሳሉ። አቶ እዮብ «አሁን በአገር ደረጃ ጥሩ መነቃቃት እየተፈጠረ ነው» ይላሉ። ይህንን እድል ማህበራቸው ለመጠቀም ተግቶ እንደሚሰራ ይገልፃሉ። «ፊያ» ከደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የሞተር ስፖርት ዳኝነት ባለሙያዎችን በመላክ ለአገር ውስጥ ዳኞች ስልጠና ሰጥቷል። ባለሙያዎቹ በውድድር ጊዜ ትክክለኛ ዳኝነት የሚሰጡበትን ቴክኖሎጂዎች እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና እንዲወስዱ አድርጓል። የከፍተኛ ዳኝነት ስልጠናውን በተግባር ታግዘው የወሰዱት ባለሙያዎቹ ከ20 በላይ ይሆናሉ። የቴክኒክ ሃላፊው ማህበሩ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚደረገውን ውድድር ለማዘጋጀት ማሰቡንና በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀውልናል። ፊያ ዳኞችን በማሰልጠን እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጁ መሳሪያዎችን በመደገፍ ስለተባበራቸው በቀጣይ የሚያዘጋጁት ውድድር ስኬታማ ይሆናል የሚል ተስፋ አላቸው። በአጠቃላይ የሞተር ስፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ ግን ከዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ባሻገር መንግስት በቀናነት ድጋፍ ያድርግልን የሚል ጥሪ ያስተላልፋሉ።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 21/2011  ዳግም ከበደ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14911
9952c0ab68e81babf14a9e8f9aa1f301
6bc23a29112d9da0d8dc053f4a118c82
የኬንያ አትሌቲክስ በዶፒንግ ቅሌት ቀውስ
 ሃይል ሰጪ ዕፅ መጠቀም ከስፖርት እኩል ረጅም ታሪክ ያስቆጠረ ነው። ጥንታውያኑ የግሪክ፤ የሮማ ስፖርተኞች በተለይም በሩጫ፤ በፈረስ ግልቢያና በትግል ስፖርተኞች አንዳቸውን ከሌላቸው ለመብለጥ ሃይል ሰጪ ቅጠላቅጠልና ስራስር ይወስዱ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ። ስፖርቱ ዓይነቱ እየበዛ፤ እየሰፋ፤ ውድድሩ እየረቀቀና እየጠነከረ በመጣ ቁጥር በእንክብል፤ በፈሳሽ፤ በምግብ መልክም እየተዘጋጀ አትሌቶች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ፤ ሃይል ሰጪ መድሃኒት በተደጋጋሚ እየወሰዱ አልፎ አልፎ ይጋለጡም ነበር።በተፈጥሯዊ አቅምና ብቃት ከመጠቀም ይልቅ አበረታች ንጥረ ነገርን ምርጫቸው በማድረግ ያገኙትን ሽልማት፤ ክብርና ማዕረግ እንዲሁም ሜዳልያ ተነጥቀውም አንገታቸውን የደፉ፤ በተግባ ራቸው አገራቸውን ጭምር ያዋረዱ በርካቶች ናቸው። አሜሪካዊቷ የሩጫ፤ የዝላይና የዱላ ቅብብል ስመ ጥር አትሌት ማሪዮን ሉዊስ ጆንሰን፤ እንዲሁም ብስክሌተኞች ስፖርት የቱር ደፍራንስ አሸናፊ ላንስ አርም ስትሮንግን ከአበረታች መድሃኒት (ዶፒንግ) ጋር ተያይዞ ክብራቸውን ከተገፈፉ ስፖርተኞች መካከል ይገኙበታል፡፡ እንደ አገር ሲታሰብም ሩሲያ ከሁሉ ቀድማ በቅሌቱ ስሟ ይነሳል፡፡ በመካከለኛና በረጅም ርቀት የአትሌቲክስ ውድድሮች ድንቅ ብቃት በማስመዝገብ የምትታ ወቀው ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዶፒንግ ቅሌት ጋር ስሟ በእጅጉ እየተዛመደ የመገናኛ ብዙሃንና የስፖርቱ ባለሙያዎች መነጋገሪያ እየሆነች ትገኛለች። ቅሌቱም አገሪቱ በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ መስክ የገነባቸውን የከፍታ ስም በእጅጉ እየናደው ይገኛል። ከቀናት በፊት መገናኛ ብዙሃኑ ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ከሃምሳ በላይ በዚህ ዓመት ደግሞ 12 የኬንያ አትሌቶች በአበረታች መድሃኒት/ዶፒንግ/ ቅሌት እግድ እንደተጣለባቸው አመላክተዋል። «ኬንያ በዶፒንግ ቅሌት ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከአፍሪካ አገራት ቀዳሚ ከዓለም ደግሞ ከሩሲያና ከህንድ ቀጥሎ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ሲል» የቻይናው የዜና አውታር ዥንዋ አስነብቧል መረጃዎች እንዳመላከቱት ከሆነም ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ስድስት የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር አትሌቶች ስማቸው ከቅሌቱ ጋር ተነስቷል።ከእነዚህ መካከል ደግሞ ሳሎሜ ጄሮኖ ቀድማ ትጠቀሳለች፡፡ አትሌቱ ባሳለፍነው ወር የተከለከለውን አበረታች ንጥረ ነገር መጠቀሟ በምርምር በመረጋገጡ ከአትልቲክሱ ስፖርት ስምንት አመት እግድ እንደተጣለባት ታውቃል። አትሌቷ መሰል ተግባር ፈፅማለች በሚል ክስ ሲቀርብባትም ከአራት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል፡፡ እኤአ በ2012 በናይሮቢ ማራቶን ቀዳሚ ሆና መግባቷን ተከትሎ በተደረገባት ምርመራ በዓለም አቀፉ ጸረ ዶፒንግ ኤጀንሲ (ዋዳ) የተከለከለ ንጥረ ነገር መውሰዷ በመታወቁ፤ እኤአ 2013 እስከ 2015 የሁለት ዓመት እግድ ተጥሎባት እንደነበርም ይታወሳል። የ36 ዓመቷ አትሌት ከቅጣት መልስ ጥቂት ወራት በኋላ፤ እኤአ 2016 በሃንኦቨር ማራቶን 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ከ47 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት የግሏን ምርጥ ሰዓት ያስመዘገበች ሲሆን፤ በዚህ ዓመትን በሳኦፖሎ ማራቶን 2 ሰዓት ከ 37 ደቂቃ ከ 33 ሴከንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃ ይዛለች። ከሳሎሜ ጄሮኖ በተጨማሪ የ2016, የሪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር የብር ሜዳሊያ ባሌቤቷ ዩኒስ ቺፕኪሩ ኪርዋ፤ ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የተሳተፈችው ሳይረስ ሩቶ፤ ከሦስት ዓመት በፊት በተካሄደው የሲንጋፖር ማራቶን ያሸነፈው ፊልክስ ኪርዋ እንዲሁም ባሳለፍነው ዓመት በስፔን ቫሌንሲያ የተካሄደውን የወንዶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን በመስበር ማሸነፍ የቻለው አብርሃም ኪፕቱም ከቅሌቱ ጋር ስማቸው ተነስቷል። እኤአ በ2014 የአፍሪካ 10 ሺ ሜትር ሻምፒየን ጆይስ ቼፕኪሩይ እና የረጅም ርቀት ሯጩ ጃኮብ ኪቤት በዶፒንግ ቅሌት ጋር በተያያዘ እግድ የተላለፋባቸው ሌሎች የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር አትሌቶች ሆነዋል፡፡ ጆይስ ቼፕኪሩይ እኤአ በ2011 በአፍሪካ ጨዋታ 1ሺ500 ሜትር የነሃስ ሜዳሊያ እንዲሁም እኤአ በ2015 የአምስተርዳምና ሆኖሎሉ ማራቶን ማሸነፍ የቻለች ሲሆን፣ በተመሳሳይ ዓመት በቦስተን ማራቶን አስረኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ሌላኛው የዶፒንግ ቅጣት ሰለባ ጃኩብ ኪቤት ካንዳጎር ነው፡፡ አትሌቱ ከሁለት ዓመት በፊት በሳዎል ማራቶን ስድስተኛ እንዲሁም፤ በሃንቡርግና በኢስታንቡል ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት በተካሄደው የኢስታንቡል ማራቶን አምስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ እነዚህን አትሌቶች ዋቢ በማድረግ የኬንያ አትሌቲክስ በዶፒንግ ቅሌት እየታመሰ ስለመሆኑ ያስነበበው የሮይተርሱ የአፍሪካ ስፖርት ጉዳዮች ተንታኝ አይዛክ ኦሙሎ፤ ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬኒያ በዶፒንግ ቅሌት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ከዓለም ደግሞ ሦስተኛ የመሆኗን ምክንያት አብራርቷል። እንደ ዘገባው ከሆነ፤ ሩሲያ በዶፒንግ ቅሌት ያስመዘገበቻቸው አትሌቶች ቁጥር 87 ደርሷል፤ ይህም ከዓለም ቀዳሚ አድርጓታል። 42 አትሌቶችን ያስመዘገበችው ህንድ ሁለተኛ ደረጃ ይዛለች። ምስራቅ አፍሪካዊቷ የሩጯ አገር ኬንያ ደግሞ 41 አትሌቶችን በስሟ አፅፋለች። ከእነዚህ መካከልም 24 የሚሆኑት ወንዶች ናቸው። ይህ የዶፒንግ ቅሌት ሪፖርት ኬንያ በዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ስፖርት መድረክ ለዓመታት የገነባችውን ገናና ስም በመናድ ረገድ የሚኖረው ጫና በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ ያመላከተው ዘገባው፤ ጉዳዩም አፋጣኝ መልስ የሚፈልግ ስለመሆኑ አፅንኦት ሰጥቶታል። የኬንያ ፀረ ዶፒንግ ኤጀንሲ የበላይ አለቃ ጃፕተር ራጌት፤«አትሌቶችን በመመርመር፤ ግንዛቤ በማስጨበጥ ተከታታይ የቁጥጥር ስራዎችን ሰርተናል፤ ይሁንና ሪፖርቱ ብዙ መስራት እንዳለብንያመላከተ ነው›› ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል። የዓለም አቀፉ ጸረ ዶፒንግ ኤጀንሲ ላብራቶሪ በአገሪቱ ዋና መዲና በናይሮቢ በመኖሩ በርካታ ምርመራዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ጠቁመው፤ በመጪው የዶሃው የዓለም ሻምፒየን ሺፕ ኬንያን እንዲወክሉ የሚመረጡ አትሌቶች እያንዳንዳቸው ቢያንስ አራት ጊዜ ምርመራው እንደሚካሄድላቸው ጨምረው አስታውቀዋል። የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጃክሰን ቱዊ በበኩላቸው፤አንዳንድ አትሌቶች ለመታመን ዝግጁ አይደሉም፤ ተግባሩ ኬንያ በዓለም አቀፉ መድረኮች የነበራትን ስም በእጅጉ የሚያጎድፍ ነው፤ ይህን ለማስወገድም ደግሞ የአገሪቱ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እረፍት አይኖረውም» ሲሉም ተደምጠዋል። የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒየኑ የኬንያው ስመጥር አትሌት ቺብቾጌ ኪኖ በበኩሉ፤ ከሁሉ ተግባራት ቀድሞ አትሌቶች ከዶፒንግ ጋር የመዛመዳቸው ዋነኛ ምክንያትና ስረ መሰረቱን ለይቶ ማወቅ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል። «ይህም ከመጋረጃው በስተጀርባ ሆነው የአገሪቱን ስፖርትና ባለተሰጥኦ አትሌቶችን እየገደሉ የሚገኙት ባለጭንብል ግለሰቦችስ እነማን ናቸው ከሚለው አንስቶ መስራት ይገባል፤ ግለሰቦቹ እኛ ለዓመታት የገነባነውን ሌጋሲ እንዲሁም ተተኪና ወጣቱን ትውልድ እየገደሉት ነው» የሚለው የ79 ዓመቱ አትሌት፤ግለሰቦቹን በማደን ጥፋተኛውን አካል ለህግ የማቅረቡ ስራ ሳይውል ሳያድር ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ነው ያስገነዘበው። የዚህን የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒየን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ የሚስማሙበት የኬንያ አትሌቲክስ ኮሚቴ አባል ባርናባ ኮሪር፤ተደጋጋሚ ቅሌት በኤትሌቲክሱ ላይ መከሰቱ የአገሬው አትሌቲክስ የበላይ አካላት የተከለከለውን ንጥረ ነገር ተጠቃሚዎች በማጋለጥ ረገድ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እንዳልሰሩ የሚያስገነዝብ መሆኑን አብራርተዋል። «የአትሌቲክሱ ስፖርት ከዶፒንግ እስኪነፃ ከመከላከሉ ባሻገር ተጠቃሚዎቹን አነፍንፎ ከማደንና ከማጋለጥ የተለየ ምንም አይነት ሌላ መፍትሄና አማራጭ አይኖርምም ነው ያሉት።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 22/2011ታምራት ተስፋዬ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14957
5fa0741338a43ef05e8e94a6eef65a89
6eb76ead2aabc5c1ffafe4dca4048da1
‹‹የልዩነትና የጠብን ችግኝ ነቅለን፣ የአንድነትና የፍቅርን ችግኝ ተክለናል›› – የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች
በሀገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉት የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ‹‹በእግር ኳሱ ሜዳ ያለንን የልዩነትና የጠብን ችግኝ ነቅለን የአንድነትና የፍቅር ችግኝ ተክለናል›› ሲሉ ተናገሩ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በተገኙበት የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች በመዲናዋ ልዩ ስሙ የሺ ደበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት ችግኝ ተክለዋል፡፡ በመርሃግብሩ ወቅት አዲስ ዘመን ካነጋገራቸው ተሳታፊዎች መካከል የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ የሆነው ሳሙኤል ለማ እንደተናገረው፤ ታሪካዊው የአረንጓዴ አሻራ ቀን ተፈጥሮን ከመታደግና አገሪቱን አረንጓዴ ከማድረግ በተጓዳኝ ሕብረተሰባዊ አብሮነትን በማጎልበት ለሀገራዊ ልማትና አንድነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በዚህ ቀን ተፈጥሮን ከመታደግና አገሪቱን አረንጓዴ ለማድረግ አሻራቸውን ከማስቀመጥ ባለፈ ወዳጅነትም ማጠናከር ችለዋል፡፡ ‹‹በሀገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ ቀን በእግር ኳሱ ሜዳ የሚያንፀባርቁትን የልዩነትና የጠብ ችግኝ ነቅለው የአንድነትንና የፍቅር ችግኝ ተክለዋል፡፡›› ያለው ሳሙኤል፣ ሁለቱ ክለቦች በዚህ ቀን በአንድነት አላማ በፍቅር መተሳሰራቸው ከአገሪቱ ስፖርት ባሻገር ለአገር ሰላም የሚኖረው ፋይዳ ብዙ መሆኑን አብራርቷል፡፡ ተግባሩ ለሌሎች የአገሪቱ ክለብ ደጋፊዎች ብቻም ሳይሆን ለአጠቃላይ ህዝብም ምሳሌ እንደሚሆን ያመላከተው ሳሙኤል፣ ‹‹ችግኝ መትከል ብቻም ሳይሆን አዕምሯችን ላይ የበቀለውን የዘርና ብሄር ችግኝ መነቃቀል ያስፈልጋል፡፡ ይህን በማድረግም የተሻለችና የበለፀገች ኢትዮጵያን መፍጠር እንችላለን፡፡›› ሲልም ተናግሯል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዋ እስከዳር ይፍሩ በበኩሏ፤ በሀገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብሩ ተፈጥሮን ከመታደግና አገሪቱን አረንጓዴ ከማድረግ በተጓዳኝ የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ልዩነታቸውን በመናድ አንድነታቸውን መገንባታቸውን ተናግራለች፡፡ ‹‹የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አገራዊ ጥሪ በመስማት ለአገራዊ አላማ በጋራ በመቆም የጠብን ችግኝ ነቅለው የፍቅር ችግኝ ተክለዋል፤ ለዚህም በመርሀ ግብሩ ላይ ከታየው አንድነትና ፍቅር በላይ ምስክር የለውም፡፡›› ብላለች፡፡ የኢትዮጵያ ቡናው እዮብ ስዩም እና የቅዱስ ጊዮርጊሱ ዳዊት ሽመልስ በየበኩላቸው፤ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በአረንጓዴ አሻራ ቀን ከችግኝ በተጨማሪ ፍቅርን ተክለው በፍቅር ማሳለፋቸውን ገልፀዋል፡፡ አንድነትና መተሳሰባቸውንም አሳይተዋል፡፡ ይህ ፍቅርና አንድነታቸውም ወቅታዊ ሳይሆን ዘላቂ ሆኖ እንዲቀጥልና በእግር ኳሱ ሜዳ ላይ ጎልቶ እንዲንፀባረቅ ሁሉም ደጋፊ የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ በአንድነት ተሳስረው የተከሉትን ችግኞች እንደሚንከባከቡ እና መፅደቃቸውንም በየጊዜው እንደሚከታተሉም አስታውቀዋል፡፡ አዲስ ዘመን ሀምሌ 23/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14991
f7042f436f53fc4ddcc11f962f50ee92
34c850ef118e02c9fcaf2661eeeae72e
ፋሲል ከነማ ለኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ሃዋሳ ከተማን በመለያ ምቶች በማሸነፍ የኢትዮጵያ ዋንጫን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ማሸነፉን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ኮን ፌዴሬሽን ውድድር ተሳታፊ ሆኗል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በ2009 ዓ.ም የውድድር ዓመት የተቀላቀለው ፋሲል በአጭር ጊዜ አህጉር አቀፍ መድረክ ላይ ተሳታፊ በመሆን ታሪክ ሠርቷል። ክለቡ በታሪካዊው የአፍሪካ ኮን ፌዴሬሽን ዋንጫ የተሳትፎ ምዕራፍ የታንዛኒያውን አዛም ክለብን ይገጥማል። የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ካፍ መርሐ ግብር መሰረት በቀጣዩ ወር ነሐሴ 5 ቀን 2011 ዓ.ም በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች ብዙም ርቀት በማይጓዙበት በአፍሪካ ኮን ፌዴሬሽን ዋንጫ የራሱን ታሪክ ለማጻፍ ክለቡ ከወዲሁ ዝግጅቱን መጀመሩን እየተናገረ ይገኛል። በተለይ ደግሞ በደጋፊ ፊት የሚያደርጉትን ጨዋታ በድል ለመወጣት ጠንካራ ልምምድ እያደረጉ መሆኑ ተሰምቷል። ለዚህም ቅድመ ዝግጅቱንም ከሐምሌ 21 ቀን ጀምሮ በውቢቷ በባህርዳር ከተማ እያደረገ ይገኛል። ቡድኑ በዝግጅቱ ውስጥ ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች በቀር ነባር እና አዳዲስ ፈራሚዎች ከቡድኑ ጋር በመቀላቀል ልምምዳቸውን እየሠሩ ይገኛሉ ተብሏል። ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው ያሬድ ባዬ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ሙጂብ ቃሲምም ከጅቡቲ ጨዋታ መልስ ቡድኑን የሚቀላቀሉ መሆኑን ከክለቡ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ምንም እንኳ ከቡድኑ ጋር ለመለያየት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡ ቢሆንም ይህን ኃላፊነት ለመወጣት ቡድኑን ለጨዋታው እያዘጋጁ መሆኑን በመረጃው ተካቷል። በክለቡ ነባር ውላቸውን ያጠናቀቁ ተጫዋቾችን በማነጋገር፤ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደክለቡ ለመቀላቀል አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከክለቡ ቦርዶች ጋር በመሆን ሥራቸውን በተገቢው መንገድ እያከናወኑ ይገኛሉ ተብሏል። ወደ ክለቡ የሚቀላቀሉ ተጫዋቾችን እና ተመሳሳይ አዳዲስ የክለቡ መረጃዎች በሙሉ በይፋዊ የክለቡ ድህረ ገፅ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። በ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመቐለ ሰባ እንደርታ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን መድረክ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ይኖረዋል የሚል ግምት ተሰጥቶታል። የታንዛኒያውን ክለብ ማሸነፍ ደግሞ የክለቡን በመድረኩ ወደፊት ላለው ግስጋሴ ወሳኝ መሆኑ ይታመናል። ተጋጣሚው ክለብ የታንዛኒያው አዛም ክለብ ከ12 ዓመታት በፊት የተመሰረተ ሲሆን በ2018/19 የውድድር ዓመት 3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡ ክለቡ በዚህ ጨዋታው ፋሲልን በሜዳው ለመገዳደር የሚያስችል አቅም ፈጥሮ እንደሚመጣም ተጠብቋል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ነሐሴ 5 ቀን በሚኖረው ጨዋታ ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል። ፋሲል ከነማ እና አዛም የመልስ ጨዋታቸውን በታንዛኒያ ከነሐሴ 17 እስከ 19 ባሉት ቀናት የሚያከናውን ሲሆን ይህን ዙር ካለፈም መስከረም ወር ከዛምቢያው ትሪያንግልስ እና ከብሩንዲው ቱኪንዞ ጋር ይጫወታል።አዲስ ዘመን ረቡዕ ሐምሌ 24/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=15099
bee22e098b855db293e0889e67b0eb6c
73a0a170fd88d02b9a41aa23ab8c274d
የትግራይ ክልል ሦስት ክለቦች ወደ ተባበሩት ዓረብ ኢሜሬትስ ያቀናሉ
የትግራይ ክልል ሦስት ክለቦች በተባበሩት ዓረብ ኢሜሬትስ በሚካሄዱ የቅድመ ውድድር የወዳጅነት ጨዋታዎች ሊያደርጉ ነው። የአልነጃሺ ኢትዮጵያ ቱር ኤንድ ትራቭል ፕሬዚዳንት መምህር ያሲን ራጁ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ መቐለ ሰብዓ እንደርታ፣ወልዋሎ ዓዲግራትና ስሑል ሸሬ በዱባይ በሚከናወኑ ጨዋታዎች ላይ ይሳተፋሉ። ክለቦቹ ግጥሚያቸውን የሚያደርጉት ከነሐሴ 20 እስከ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ሲሆን ግጥሚያዎቹን የሚያካሂዱት ከሦስት የአገሪቱ ክለቦች ጋር እንደሚሆነ ተናግረዋል።ጨዋታዎቹ የስፖርት ቱሪዝምን ለማስፋፋት፤ወጣቶች በስፖርት ታንፀው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራትና ልምድ ለመቅሰም ዓላማ እንዳላቸው አብራርተዋል። ጨዋታዎቹ “እግር ኳስ ለፍቅር፣ ለወዳጅትና ለጤንነት” በሚል መርህ የሁለቱ አገሮችን የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር እንደሚደረግ መምህር ያሲን አስረድተዋል። ክለቦቹ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ከባህልና  ቱሪዝም ሚኒስቴር የትብብር ደብዳቤ እንደተጻፈላቸውም አስታውቀዋል።የወልዋሎ ዓዲግራት ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አማረ በሰጡት አስተያየት ክለባቸው ከአገሪቱ ክለቦች ጋርም በሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ድጋፍ ለማግኘት እንደሚጥር ገልጸዋል። የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሸን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንገሶም ካሕሳይ ክለቦቹ አጋጣሚውን ዓለም አቀፍ ልምድ ለማግኘት፣ከባለሀብቶች ጋር ለመተዋወቅና የስፖርት አካዳሚ ለመክፈት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ የዘገበው ኢዜአ ነው።አዲስ ዘመን ረቡዕ ሐምሌ 24/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=15132
bead0b3d1301c3ad77482b2c212ed472
02b9f47004abfb732a05ece9249af780
በጉባ ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ኃይሎች በህውሓት የስልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት ያደረሰው ታጣቂ ኃይል በህውሓት ስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ የአማራ ክልል አስታወቀ። ዓላማው በብሄር ብህረሰቦች መካከል ግጭት በመፍጠር የአካባቢውን ሰላም ለማወክ መሆኑም ተመለከተ። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈትቤት ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር በጥቃቱ ዙሪያ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ጥቃቱን የፈጸመው ኃይል በአካባቢው የብሔር ግጭት የመቀስቀስ ዓላማ በመያዝ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራ ሲያደርግ የቆየ ነው። ታጣቂ ኃይሉ በህውሓት የስልጠናና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት አመልክተው፤ ህውሓት ሀገርን ለማተራመስ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ አካል መሆኑምን ጠቁመዋል። ድርጊቱ ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ አጥፊዎችን ፈልጎ ለመያዝና አስፈላጊውን ዕርምጃ ለመውሰድ የፀጥታ መዋቅሩ የተጠናከረ ጥረት እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል ።በአሁኑ ጊዜም አካባቢው ላይ ሰላም ሰፍኗል።አርሶአደሩም የእርሻ ሥራውን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል፡ ችግሩ የደረሰበት አካባቢ የአማራ ክልል አርሶአደሮች በስፋት የእርሻ ሥራ የሚያከናውኑበትና በቀን ሥራም ተቀጥረው የሚሠሩበት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ አገኘሁ፤ በአማራ እና በጉሙዝ ብሄረሰብ መካከል ምንም ዓይነት ግጭት እንደሌለና ለዘመናት አብሮ የኖረ ህዝብ መሆኑም አስረድተዋል፡፡ ድርጊቱ በሰላም አብሮ የኖረውን ህዝብ ለማለያየት ሆን ተብሎ የተፈጸመ መሆኑንም አመልክተዋል።ማን እንደፈጸመውም ይታወቃልም።አጥፊውን ታጣቂ ኃይል ህወሓት በገንዘብና በሥልጠና እንደሚያግዘውም አመልክተዋል፡፡ ጥቃቱ ህውሓት ለውጡን ወደቀውስ ለመለወጥ ምን ያህል አልሞ እየሠራ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ለህብረተሰቡ በችግሩ ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ የማድረግ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቁመዋል።በዚህም እስከአሁንም በአማራ ክልል የሽብር ተግባር ለማከናወን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ95 በላይ ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን መያዛቸውን አመልክተዋል፡፡ በአጥፊ ታጣቂ ኃይል ሕይወታቸው ያለፈ የአማራ ክልል አርሶአደሮች 12ቱ ከምዕራብ ጎጃም፣ ሁለቱ ደግሞ ከጎንደር መሆናቸውንና የሁሉም አስክሬን ለቤተሰብ ተሰጥቶ በክብር የቀብራቸው ሥነሥርዓት መፈጸሙን ገልጸዋል።አርሶአደሩ በተፈጸመው ነገር ሳይደናገጥ የወቅቱን የእርሻ ሥራ እንዲያከናውንም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱላዚዝ መሀመድ በመተከልዞን ጉባ ወረዳ ከሀገር ውጭና ከውስጥ ተልዕኮ የተሰጣቸው የጥፋት ኃይሎች ሐምሌ 20 ቀን 2012 ምሽት አካባቢ አቡጃር ቀበሌ ባደረሱት ጥቃት የ14 ንጹሐን ዜጎች ሕይወት ማለፉን ከትናንት በስቲያ ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱም የጥፋት ቡድኑ ተገቢ ስልጠናና ተልዕኮ በመያዝና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በተለይም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት የማስተጓጎል እና የብሔር ግጭት የመቀሳቀስ ዓላማ በመያዝ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡ የክልሉ የጸጥታ ኃይል ከመከላከያ ሠራዊትና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን ቀደም ብሎ በአካባቢው ሠላምን ለማረጋገጥ ዕርምጃ ሲወስድ መቆየቱን አመልክተዋል። በጥፋት ቡድኑ ላይ እየተወሰደ ካለው ዕርምጃ በተጨማሪ አራት ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል። ሕግን የማስከበር ዕርምጃዎች በአካባቢው ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቀዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 23/2012 በጋዜጣው ሪፖርተር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36302
34e0832758df4942cac42b41d4a5374a
0ccffb37ae03cdac122e86c9d7c32129
ድሬዳዋ ከነማ በመጨረሻ እጅ ሰጠ
ድሬዳዋ ከተማ አጥቂዎቹ ዮናታን ከበደ፣ ኃይሌ እሸቱ እንዲሁም ተከላካዩ ወሰኑ ማዜን በመጋቢት ወር መጀመሪያ አሰናብቷል። የክለቡን ውሳኔ በመቃወም ተጫዋቾቹ ለብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ቅሬታን አስገብተዋል። ተጫዋቾቹ ቀሪ የስድስት ወራት የውል ኮንትራት እያለን ያለ አግባብ ተሰናብተናል ሲሉም አቤት ብለዋል። ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን ከተመለከተ በኋላ ተጫዋቾቹ ያቀረቡት ቅሬታ ተገቢ ነው በማለት በ10 ቀን ውስጥ ለተጫዋቾቹ ደመወዛቸው እንዲከፈል የሚል የውሳኔ ደብዳቤን ለክለቡ ልኳል። ይሁንና ክለቡ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ውሳኔው አግባብነት እንደሌለው በመግለጽ የብሄራዊ ፌዴሬሽኑን ጣልቃ ገብነት መሰረተ ቢስ መሆኑን አመላክቶ ነበር። ሆኖም የክለቡ ጥያቄ በድጋሚ ውድቅ በመደረጉ ለሁለተኛ ጊዜ ፌዴሬሽኑ ለድሬዳዋ ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤን በድጋሚ ለመላክ ተገዶ ነበር። ክለቡ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተፈጻሚ ባለማድረጉ ምክንያት የዲሲፕሊን ኮሚቴ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳያገኝ አግዶ ቆይቷል፡፡ የክለቡ ቦርድ በስተመጨረሻም ተጫዋቾቹ የጠየቁትን ጥያቄ በመመለስ እጅ መስጠቱ ታውቋል። በጉዳዩ ላይ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንበስ አውግቸው ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት፤ ክለቡ ባሰናበታቸው ተጫዋቾች ዙርያ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ለሁለት ተጫዋቾች የሦስት ወር ደመወዝ፣ ለአንድ ተጫዋች ደግሞ የአንድ ወር ደሞዝ ለመክፈል መዘጋጀቱን ገልጸዋል። «እንዲከፈላቸውም ተወስኗል። በሊግ ኮሚቴው ውሳኔው መሠረት ዞሮ ዞሮ እልህ መጋባት ስለሌለብን በሚል ነው። ነገር ግን ውሳኔው ብዙ ክፍተቶች ነበሩበት። የህዝብ ክለብ እንደመሆኑ መጠን ክርክር አያስፈልግም፤ የተባልነውን ውሳኔ ተግባራዊ አድርገን እገዳው እንዲነሳ እንጠይቃለን» ብለዋል፡፡ በክለቡ በኩል ክፍተት ስለመኖሩ የተጠየቁት አቶ አንበስ በሰጡት ምላሽ፤ « ክፍተት በኛ በኩል ምንም የለም ብለን ነው የምናስበው። ለምሳሌ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በ25 ደብዳቤ ፅፎ በ26 ድረስ ምላሽ ስጡበት የሚልበት አግባብ ይህን ሁኔታ ይገልጸዋል፡፡ እንደዚያም አድርገን የእነሱ ደግሞ ውሳኔው ሁለት ወር ከሁለት ቀን በኋላ ዘግይቶ የመጣበት ሂደት ነው ያለው፤ ይሄ በራሱ የሚጋጭ ነው። ለምን በጊዜ አልተወሰነም? ብዙ ክፍተት አለ፤ የተጠየቅነው ሌላ የተፈረደብን ሌላ ነው» ሲሉ መልሰዋል። በክለቡ ላይ በሙሉ ክፍተት የለበትም ማለት እንዳልሆነ የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ የዲሲፕሊን ኮሚቴው አካሄድ ግን መልካም እንዳልነበር ተናግረዋል።አቶ አንበስ በመጨረሻም ‹‹በእርግጥ የተለያዩት ተጫዋቾች ውል ይቀራቸዋል፤ አቋማቸው ጥሩ ካልሆነ ግን ተሸክመን መጓዝ አንችልም በሚል ነው የተለያየነው፡፡ በመጨረሻ ቦርዱ ውሳኔም አሳልፏል። ክለቡ ታግዶ ይሄን ያህል መቆየት ስለሌለበት ደመወዛቸው ይከፈላቸው የሚል ውሳኔም ተላልፏል። ይህን ተፈፃሚ ለማድረግ ዝግጅት ጀምረናል። ደመወዛቸውን ከፍለን እገዳው እንዲነሳ ፌዴሬሽኑን እንጠይቃለን›› ብለዋል።አዲስ ዘመን ረቡዕ ሐምሌ 24/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=15156
6a1c7015febb272baa39bc0571e48b27
de07251d86b214335f95b310a78c4fbf
የሲሚንቶ ዘርፉን ተደጋጋሚ ችግሮች እየፈታተኑት እንደሆነ ተገለጸ
አዲስ አበባ፡- መንግሥት በሲሚንቶ ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት የምርት እጥረት እንዳይከሰት እየሠራ ቢሆንም ተደጋጋሚ ችግሮች ዘርፉን እየፈታተኑት እንደሆነ ተገለጸ። አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሀላላ እንደገለጹት፤ በሲሚንቶ ዘርፍ ላይ የተፈጠረውን የዋጋ ንረት መቆጣጠር የሚያስችል የተለያዩ ሥራዎች ተሠርተዋል። በዚህም ግንቦት መጨረሻ አካባቢና ሰኔ ወር ላይ ዘርፉ ውጤት ማሳየት ሲጀምር የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በየአካባቢው ተቀስቅሶ በነበረው ረብሻ ምክንያት የሲሚንቶ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተዘግተው እንደነበር አስታውሰዋል። ሲሚንቶ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ዝግ በሆኑበት ወቅትም ከፍተኛ የሆነ መበላሸትና የመቃጠል አደጋ አጋጥሟቸዋል። በዚህም ኢንዱስትሪዎቹ ወደ ሥራ ለመመለስ ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት ጊዜ ወስዶባቸዋል። ወደ ሥራ ሲመለሱም የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እጥረት የገጠማቸው እንዱስትሪዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል። ወቅቱ ክረምት በመሆኑም የሲሚንቶ ግብዓቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ በመያዛቸው ማሽኖች ላይ ተጨማሪ ችግር መፈጠሩን አመልክተዋል። እነዚህ ተደጋጋሚ ችግሮችም በታሰበው ልክ ዘርፉ ተስተካክሎ እንዳይጓዝ እንዳደረገው አስታውቀዋል። የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች በክረምት ወደ ጥገና መግባት እንጂ ማምረት አልነበረባቸውም ያሉት አቶ ሳሙኤል፤ ለዚህም ምክንያቱ ከሁሉም አካባቢ የሚመጣው የሲሚንቶ ግብዓት ከፍተኛ የሆነ የውሃ መጠን ይዞ ይመጣል። ይህም አንደኛ በሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ የሥራ ጫና ይፈጥራል። ማሽነሪዎቹ ላይም በውሃው መጠን ልክ ከፍተኛ ክብደት ያስከትላል። ስለዚህ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች በሐምሌና ነሐሴ ወራት ምርት አቁመው ጥገና የሚያደርጉበት ወቅት እንደሆነ አብራርተዋል። ይሁንና በተያዘው ዓመት ባጋጠመው የሲሚንቶ እጥረት ምክንያት ሁሉም የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች ጥገና ማድረግ አልቻሉም። የሲሚንቶ ግብዓቶቹ የሚይዙትን ከፍተኛ የውሃ መጠን ቀንሶ ለማምረት የሚደረገው ጥረት በኢንዱስትሪዎቹ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመምጣቱ ፋብሪካዎቹ የማምረት አቅማቸው ቀንሷል ። ፋብሪካዎቹ በቀን 343 ሺ ኩንታል ሲያመርቱ የነበሩ ቢሆንም አሁን ካለባቸው ጫና የተነሳ በቀን እስከ 260 ሺ ኩንታል ሲሚንቶ እያመረቱ ለገበያ ያቀርባሉ። ፋብሪካዎቹ የምርት መጠናቸው ቢቀንስም የዋጋ ጭማሪ አላደረጉም ያሉት አቶ ሳሙኤል፤ ፋብሪካዎቹ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ ታኅሣሥ ወር ላይ ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ 230 ብር እየሸጡ መሆኑን ተናግረዋል። ነገር ግን ነጋዴው የሲሚንቶ ምርት መጠን መቀነሱን ተከትሎ በ230 ብር የገዛውን አንድ ኩንታል ሲሚንቶ ከእጥፍ በላይ ጨምረው ከ500 ብር በላይ እየሸጡ መሆኑን አመልክተዋል። የኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ለፋብሪካዎቹ ተጨማሪ ተግዳሮት መሆኑን ያመለከቱት አቶ ሳሙኤል፣ ፋብሪካዎቹ ችግሩን ተቋቁመው በአሁን ወቅት በቀን እስከ 260 ሺ ኩንታል እያመረቱ ይገኛሉ። ምርትና ምርታማነቱን በማሻሻል ፋብሪካዎቹ በቀን ከ300 እስከ 340 ሺ ኩንታል ሲሚንቶ ማምረት እንዲችሉ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንም ጠቁመዋል። የተለያዩ የኮንስትራክሽን ግንባታዎች በክረምት ወቅት መቀነሳቸው ይታወቃል ያሉት አቶ ሳሙኤል፤ በዚህ ወቅት የሲሚንቶ ዋጋው በማይታመን መጠን መጨመሩ ከምን የመጣ እንደሆነ ማጥናት ያስፈልጋል። ነጋዴው ያለውንም ሲሚንቶ ደብቆ ክፍተት በመፍጠር በከፍተኛ ዋጋ መሸጥ ፈልጎ እንደሆነም የሚመለከታቸው አካላት ለይተው መፍትሔ ማስቀመጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 23/2012 ፍሬህይወት አወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36303
4c596ee23c7a285e362b9d6a9f502c90
f421aff3a0a63abf76d934d7aab1eae7
ግድቡ በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ሊለካ የሚችል ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ተገለጸ
አዲስ አበባ፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚያመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ሊለካ በሚችል መልኩ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ተገለጸ። አዲስ ዘመን ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዶክተር ጉቱ ቴሶ እንደገለጹት፤ ከትንሽ እስከ ትልቅ ላሉት የቢዝነስ እና የኢንቨስትመንት ሥራዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ወሳኝ እንደመሆኑ ለምጣኔ ሀብት ዕድገት የጀርባ አጥንት ነው። ኢትዮጵያ እጅግ በጣም አነስተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ከሚጠቀሙ አገራት መካከል አንዷ ናት ያሉት ዶክተር ጉቱ፤ የህዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ሲጀምር በገጠርና በገጠር ከተሞች እንዲሁም በትላልቅ ከተሞች በቂ የኃይል አቅርቦት እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዚህም ኢንቨስትመንቶች ይስፋፋሉ። በኃይል እጥረት ምክንያት በፈረቃ ይሠሩ የነበሩ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችም ቀጣይነት ባለው መልኩ ማምረት እንደሚችሉ ጠቁመዋል። በዚህም ምርትና ምርታማነት ያድጋል። ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጠራል። አምራች ኢንዱስትሪዎችም የተሻለ ምርት በማምረታቸው ለመንግሥት የተሻለ ግብር እንዲከፍሉ ያደርጋል ያሉት ዶክተር ጉቱ፤ በዚህም የአገሪቷ ምጣኔ ሀብት ሊለካ በሚችል መልኩ ለውጥ በማምጣት በአገሪቷ ብልጽግና ላይ በጎ ተፅዕኖ ማሳረፍ እንደሚቻል አብራርተዋል። የገጠሩን ክፍለ ኢኮኖሚ ለመቀየር በዋናነት የኤሌክትሪክ ኃይል አስፈላጊ ነው ያሉት ዶክተር ጉቱ፤ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠይቁ ሥራዎችን በማስፋፋት ኢትዮጵያ የምታስበውን የገጠር ምጣኔ ሀብት ዕድገት ለማሳካት ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል። በዚህም ከተማን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን ገጠሩንም ከተማ ማደረግ እንደሚቻል አመልክተዋል። እየተጠናቀቀ ያለው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንዱ ዓላማ ቀላል ኢንዱስትሪዎችን በመገንባት ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ መሻገር መሆኑን አስታውሰዋል። በመሆኑም በሀገር ደረጃ በርካታ የኢንዱስትሪያል ፓርኮችና ሼዶች ተገንብተው የተወሰኑትም ወደ ሥራ የገቡ መሆናቸውን ዶክተር ጉቱ ተናግረዋል። ነገር ግን ሁሉንም ኢንዱስትሪያል ፓርኮች አሁን ባለው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ ሥራ ማስገባት የማይቻል በመሆኑ ግድቡ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ለኢንዱስትሪዎች ትልቅ አቅም ይሆናል ብለዋል።ማንኛውም ባለሀብት ወደ አንድ አገር ሄዶ ማልማት የሚያስችለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ቀጣይነት ባለውና በበቂ መጠን እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እንደሚፈልግ አመልክተው፣ ባለሀብቱም ይህን ታሳቢ አድርጎ የሚመጣ በመሆኑ የውጭ ባለሀብቶችን በመሳብ እና የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን በማበረታታት አገሪቷ በታሰበው መጠን ወደ ኢንዱስትሪው መግባት እንድትችል ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን አብራርተዋል። በጥቅሉ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል በሀገር ውስጥ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ እምርታን ሊያመጣ፤ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፤ የኢትዮጵያውያንን የነፍስ ወከፍ ገቢ ማሻሻል የሚያስችል እንደሆነ አመልክተዋል። ከዚህም በላይ የመንግሥትን ገቢ በማሻሻል ለአገሪቷ ትልቅ አቅም ሆኖ በምጣኔ ሀብቷ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት የሚችል ፕሮጀክት ነው ብለዋል። ከዚህም ባለፈ ለጎረቤት አገራት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በመሸጥ በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ከሚገኘው ገቢ በበለጠ ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ ማግኘት እንደሚቻልም ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 23/2012 ፍሬህይወት አወቀ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36299
b76ef46b824927859a5ed209fd62e4e7
c32cb0c7e6127400fc69006e14273580
“በዚህ ፈታኝ ወቅት ለተቸገሩ ወገኖቻችን አለኝታቸው መሆናችንን እናሳይ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ
አዲስ አበባ፡- በዚህ ፈታኝ ወቅት ለተቸገሩ ወገኖቻችን አልኝታቸው መሆናችንን እናሳይ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ የኮሮና ቫይረስ የፈጠራቸውን ክፍተቶች ለመድፈን ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚኖርበት አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ1441 ኛው የታላቁ የዒድ አል-አድሐ በዓልን አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ በዚህ ፈታኝ ወቅት ለተቸገሩ ወገኖቻችን አለኝታቸው መሆናችንን እናሳይ ብለዋል፡፡ዒድ አል-አድሐ የመስዋዕትና የመዳን በዓል እንደመሆኑ መጠን ወደ ሐጅ የሚሄደው ሰው ብቻ ሳይሆን የማይሄደውም ጭምር ‹‹ኡድሒያ›› የማረድ ግዴታ እንዳለበት የእምነቱ አስተምሮ እንደሚያዝ አመልክተው፣ በአስተምህሮ መሰረት ለበዓሉ ከሚታረደው አንድ ሦስተኛውን ለድኾችና ለተቸገሩ ወገኖቻችን በማካፈል ይሄንን አስቸጋሪ ወቅት በስኬት እንደምንሻገረው አልጠራጠርም ብለዋል፡፡በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ፣ የሚታመሙና የሚሞቱ ወገኖቻችን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወረርሽኙን መከላከልን እንደ አንድ ሃይማኖታዊ ግዴታ ልንወስደው ይገባል ብለዋል። እንዲሁም ወረርሽኙ የፈጠራቸውን ክፍተቶች ለመድፈን ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚኖርበት አስታውቀዋል፡፡ አቅማቸው ደከም ያሉ ወገኖቻችንን እንድንደግፍ፤ ማዕዳችንን እንድናጋራ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ እንደ ኢብራሂም ያሉ መልካምና ቆራጥ ሰዎች፣ ለእምነታቸው ሲሉ አንድዬ ልጃቸውን መስዋዕት ለማድረግ ይዘጋጃሉ። እንደነዚህ ያሉ ለመልካም ዓላማ ሲሉ እጅግ ውድ የሆነ ሀብታቸውን፣ ልጃቸውን ሲሰጡ ቅር አይላቸውም፡፡ በተቃራኒው ክፉዎች ለእኩይ ዓላማቸው ወንድማቸው ላይ በትር ያነሳሉ:: እህታቸው ፣ ልጃቸው ፣ እናትና አባታቸው ላይ ሲጨክኑ ዐይናቸውን እንደማያሺ አመልክተዋል፡፡ ከእኛም መካከል አንዳንዶች ለተራ ቁሳዊ ሀብቶች፣ ለትንንሽ የፖለቲካ ድሎችና ለሥልጣን እኩይ ተግባራትን የሚፈጽሙ አሉ፡፡ ለሆዳቸው ሲሉ ቤተሰባቸውን፣ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ሀገርና ወገናቸውን ለመሸጥ ሲዘጋጁ እንደማየት የሚያሳዝን ነገር የለም፡፡እንዲህ የሚያደርጉ አካላት ከክፉ ሥራቸው እንደሚለሱ ሕዝበ ሙስሊሙ በጥበብ እንዲያስተምራቸው አደራ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡የዘንድሮው የዒድ አል-አድሐ (የዐረፋ) በዓል በተለያዩ ምክንያቶች ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ለየት ያለ ትርጉም አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዓመታት ግንባታና የዲፕሎማቲክ ትግል በኋላ የመጀመ ሪያውን የሕዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ባሳካንበት ጊዜ የሚከበር በመሆኑ በዓሉን በከፍተኛ ሐሴት ውስጥ ሆነን የምንቀበለው እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ ሙስሊሙ ወገናችን የሕዳሴ ግድባችን እውን እንዲሆንም ገንዘብ ከማዋጣትና ጠቃሚ ሐሳቦችን ከማበርከት ባለፈ በዲፕሎማሲያዊ ተጋድሎው ሂደት ግንባር ቀደም በመሆን የሁላችንም የሆነችው ሀገራችንን ለማኩራት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ሙስሊሞች መስዋዕትነት መክፈላችሁን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በክብር ያየዋል ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 24/2012በጋዜጣው ሪፖርተር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36353
73ac0f61c3a2d76ce56c368adb799d79
789255c0434c68e2b2d7443e44dc04e3
አብዛኛው የክልሉ አካባቢ ወደ መረጋጋት መመለሱ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፡- በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል አብዛኛው አካባቢዎች ባለፉት ጊዜያት ይስታዋልባቸው የነበሩ ግጭቶች በመርገብ ወደ መረጋጋት መመለሱን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ በክልሉ በበርካታ አካባቢዎች ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ይስታዋልባቸው እንደነበር አመልክተዋል። የግጭቶች መንስኤ የመሬት ወረራ እንደሆነም አስታውቀዋል።በቅርቡ በፌዴራልና በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ርብርብ በቁጥጥር ስር የዋለው በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት የዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነም ጠቁመዋል። በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች እና በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች የመሬት ወረራን እንደ ምክንያት በማድረግ ግጭቶች እንዲፈጠሩ፤ በዚህም ንብረት እንዲወድም፣ የሰው ህይወት እንዲጠፋ ያደረጉ እና ያስደረጉ አካላትን ለህግ የማቅረብ ሥራ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ግጭቶችን ለመፍታት የህዝቦች አብሮነት የማጠናከር ሥራ እየተሠራ ነው ያሉት አቶ አንድነት፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ዘላቂ ሰላም ግንባታና እርቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ አንድነት ማብራሪያ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ከክልል እንሁን ከሚለው እስከ ቀበሌ እንሁን የሚሉ የመዋቅር ጥያቄዎች የግጭት መንስኤ ሲሆኑ ነበር።በአንዳንድ አካባቢዎች ጥያቄዎቹ ምላሽ አግኝተው መረጋጋት ተፈጥሯል።በምለሾቹ ያልረካባቸውና ችግሮቹ በዘላቂነት ያልተፈቱባቸው አካባቢዎችም እንዳሉ አመልክተዋል። ከዚህ ቀደም ምላሽ ተሰጥቶባቸው ህዝቡ ባልረካባቸው እና ጥያቄው ያልተመለሰባቸው አካባቢዎች የክልሉ መንግሥት ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመሆን ጥያቄዎቹ የሚመልሱበት ማዕቀፍ አስቀምጦ እስከ ታች ድረስ በመውረድ ውይይት እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥትና ገዥ ፓርቲ ጥያቄዎቹ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የመዋቅር ጥያቄዎች በሰላማዊ፣ ህዝቦች በሚስማሙበት አግባብ ምላሽ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያብራሩት አቶ አንድነት፤ በአሁኑ ወቅት ከመዋቅር ጋር ተያይዘው የሚነሱ ግጭቶች እየረገቡ መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የመዋቅር ጥያቄዎች በግጭት፣ እርስ በእርስ በመጎዳዳት፣ በመፈነቃቀል የሚመለስ ጥያቄ አይደለም ያሉት አቶ አንድነት፤ ጥያቄዎቹ በመወያየትና በሰላማዊ መንገድ የሚመለስ ስለሆነ ህዝቡ እንዲረጋጋ የፖለቲካ አመራሩ ሰፊ ሥራ እየሠራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 23/2012መላኩ ኤሮሴ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36305
df7f1e94427d65ed749b0acc490cc9c1
184e843956f41f76fe489c376206bc43
“በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ አጋማሽ ላይ ሆነን ከ4 ነጥብ 1 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከላችን ውጤታማነት ነው” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
አዲስ አበባ፡- በዘንድሮው  የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አጋማሽ ላይ እያለን   ሊተከል ከታቀደው  5 ቢሊዮን ችግኝ   4 ነጥብ 1 ቢሊዮን መተከሉ ዕቅዱ፣ዝግጅቱና ተሳትፎው ውጤታማ እንደነበር ያሳያል ሲሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ የአረንጓዴ አሻራ  የቴክኒክ ኮሚቴ  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተገኝቶ ያቀረበውን   የስራ አፈጻጸም ሪፖሪት አዳምጠዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር በዚሁ ወቅት በሰጡት አስተያየት  በሶስት ወራት ሊተከል ከታቀደው 5 ቢሊዮን ችግኝ  4 ነጥብ አንድ ቢሊየኑን በአንድ ወር ተኩል መትክል መቻሉ የዝግጅቱንና የተሳትፎውን ውጤታማነት ያሳያል ብለዋል፡፡በመርሃግበሩ አጋማሽ የእቅዱን  83 በመቶ ማሳከት ከተቻለ በቀሪው ጊዜ የበለጠ ተግቶ በመስራት ከእቅዱ በላይ መስራት እንደሚቻልም ጠቅሰዋል፡፡  የአረንጓዴ አሻራው ልክ እንደ ህዳሴው ግድብ  ያቀድነውን  ማሳካት አንደምንችል ያሳየንበት አንዱ ፕሮጀክት ነውም ብለዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራን ጉዳይ እንደሁለተኛ ሳይሆን አንደዋነኛ ጉዳያችን መመልክት አለብን ያሉት  ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤  አሁንም  ከዚህ የበለጠ ትኩረት መስጠት እንደሚስፈልግ ጠቅሰዋል፡፡  እያንዳንዱ ተቋምም ቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ መንቀሳቀስ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ አረንጓዴ አሻራው ከምንተክለው ችግኝ ባሻገር የስራ እድል መፍጠርና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነትንም እያረጋገጠ መሄድ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡  አረንጓዴ አሻራ የቁጥሩ ጉዳይ ሳይሆን በየቀኑ እየተከልን የሚገኘውን ዘላቂ ጥቅም የምናረጋግጥበት ሂደት መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ክልሎች ባስመዘገቡት ውጤት ሳይዘናጉ የተሻለ ለመስራት መትጋት እንዳለባቸውና አስፍተው ማቀድ እንደሚገባቸውም  አሳስበዋል፡፡ በዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ ያሉ ክልሎችንም ማነቃቃትና መደገፍ  እንደሚስፈልግ ጠቅሰዋል።  በሚቀጥለው ዓመትም ሀገር በቀል ችግኞችንና   የተለያዩ የፍራፍሬ አይነቶችን ከወዲሁ በማዘጋጀት  በተለይም እንደ አፋርና ሶሜሌን በመሳሰሉ ቆላማ አካባቢዎች በመትክል  ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡  በቀጣይ በ2013 ዓ.ም በርካታ ችግኞችን ለመትከል ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚስፈልግና  ይህ ባህላችንም ከእኛ አልፎ ወደ ጁቡቲ ፣ኬኒያ፣ ኤርትራ እና ሌሎችም የጎረቤት ሀገራት መዳረስ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡ አካባቢው አረንጓዴ ካልሆነ የምንፈልገውን ዝናብ ማግኘት አንችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ የምንተክለው ችግኝ ለእነርሱ ፤እነርሱም የሚተክሉት ለእኛ ጠቃሚነው ብለዋል።በኢያሱ መሰለፎቶ በጸሀይ ንጉሤ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36328
6d1850c3e2912f50e3ccf008b54b48eb
b7fbcd803decf387029aef5d777cbf7c
ህዝበ ሙስሊሙ አረፋን እራሱን ከኮቪድ 19 በመከላከል፣ ሰላሙን በመጠበቅና ለሌላቸው በማካፈል እንዲያከብር ተጠየቀ
አዲስ አበባ፡- ህዝበ ሙስሊሙ ለአንድ ሺ 441ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ሲያከብር በተለያየ መንገድ አቅም ላነሳቸው ምስኪኖች በማካፈል፣ ሰላሙን በመጠበቅ እና ከኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ እራሱን በመከላከል መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አስታወቁ።ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር አንድ ሺ 441ኛውን የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የዘንድሮው የአረፋ በዓል መሰባሰብን የሚከለክል ቢሆንም ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ለበዓሉ ካዘጋጀው በተለያየ መንገድ አቅም ላነሳቸው ምስኪኖች በማካፈል እራሱንም ከኮቪድ በመከላከል እንዲሁም ከሁከትና ግርግር እራሱን ነፃ በማድረግ ሰላሙን ጠብቆ በደስታና በሰላም እንዲያከብር ጥሪ አስተላልፈዋል።ወረርሽኙን ለመከላከል ሲባል መንግሥት ያወጣው አስቸኳይ የጊዜ አዋጅ ያልተነሳ መሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት ያወሱት ፕሬዚዳንቱ፤ አደገኛ የሆነ ወረርሽኝ ባለበት በዚህ ወቅት እራስን ከመከላከል ባለፈ በፀፀትና በኀዘን በፀሎት መትጋት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ትጋቱ ከሌለ ችግሩ ሊባባስ እንደሚችልም አመልክተዋል።በሀገራዊ ጉዳይ ላይም ‹‹እርስበርስ መጣላት፣የንጹሐንን ደም ማፍሰስ፣ለዓመታት የተለፋበትን ሀብትና ንብረት በደቂቃ ማውደም›› በሃይማኖትም በሰብዓዊነትም ተገቢነት የሌለው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። መሪውም ተመሪውም በሰከነ መንፈስ ነገሮችን ማየትና ሀገርን  ከጥፋት መታደግ እንደሚገባ አስታውቀዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ምዕራፍ የውሃ ሙሌት መከናወኑ እንዳስደሰታቸውም ገልጸዋል። የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የእርድ በዓል መሆኑንና ዕርዱ ለኮቪድ በሚያጋልጥ መልኩ እንዳይከናወንም አስታውሰዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 24/2012 ለምለም መንግሥቱ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36351
85fb33f32d6a66d175f53a0384e78ff4
94c35ffe1f20c60433bca87db784d0ab
ዋልያዎቹ ጅቡቲን ለመግጠም ልምምድ ጀምረዋል
የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) በመጪው ዓመት ጥር ወር መጀመሪያ ላይ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ካሜሩን አስተናጋጅነት ይከናወናል። የአስተናጋጅነቱን ክብር ያጣችው ኢትዮጵያ የቅድመ ማጣሪያ ድልድል ውስጥ መካተት ግድ ብሏታል። በቅድመ ማጣሪያ ድልድሉ መሠረት ከጅቡቲ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ጅቡቲን በሜዳዋ ትገጥማለች። ከሳምንት ቆይታ በኋላ የመልሱን ጨዋታ በድሬዳዋ ከተማ የምታደርግ ይሆናል። በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሚመሩት ዋልያዎቹ ከቀናት በኋላ ጅቡቲን ለመግጠም ዝግጅታቸውን ትናንት ጀም ረዋል። ብሔራዊ ቡድኑ ከትናንት ጀምሮ በአዳማ ከተማ ልምምዱን ማድረግ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል። አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ እና ረዳቶቹ በቅርቡ 23 ተጫዋቾች ያሳወቁ ሲሆን፣ ግብ ጠባቂዎች መሳይ አያኖ ከሲዳማ ቡና፣ ተክለማርያም ሻንቆ ከሐዋሳ ከተማ፣ ምንተስኖት አሎ ከባህርዳር ከተማ ሲሆኑ፤ ተከላካዮች አስቻለው ታመነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ደስታ ደሙ ከወልዋሎ አዲግራት፣ ያሬድ ባየ ፋሲል ከተማ፣ ወንድሜነህ ደረጀ ከባህርዳር ከተማ፣ አህመድ ረሺድ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ጌቱ ኃይለማርያም ከሰበታ ከተማ፣ አምሳሉ ጥላሁን ፋሲል ከተማ፣ ረመዳን የሱፍ ስሁል ሽረ ናቸው። አማካዮች አማኑኤል ዮሐንስ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሙሉዓለም መስፍን ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሀይደር ሸረፋ ከመቐለ 70 እንደርታ፣ አፈወርቅ ኃይሉ ከወልዋሎ አዲግራት፣ ሱራፌል ዳኛቸው ፋሲል ከተማ፣ ታፈሰ ሰለሞንና ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ሐዋሳ ከተማ ሆነዋል። አጥቂዎች አቤል ያለው ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝና አዲስ ግደይ ከሲዳማ ቡና፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመቐለ 70 እንደርታ፣ አቡበክር ነስሩ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሙጅብ ቃሲም ከፋሲል ከተማ እና ፍቃዱ ተክለማርያም ከመከላከያ መሆናቸው ታውቋል። የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) በአገር ውስጥ ሊግ ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን የሚያሳትፍ የውድድር መድረክ ሲሆን፤ በሁለት ዓመት አንዴ ይደረጋል። እኤአ 2009 የተጀመረው ቻን የመጀመሪያዋ ዋንጫ ኮትዲቯር ስታዘጋጅ፤ 2ኛውና እኤአ በ2011 የተካሄደውን ደግሞ ሱዳን አዘጋጅታለች። እኤአ በ2014 ደቡብ አፍሪካ ሦስተኛውን ስታስተናግድ፤ እኤአ በ2016 ሩዋንዳ 4ኛውን አዘጋጅታለች። በ2018 በሞሮኮ አዘጋጅነት ለ5ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን፤ 6ኛውና እኤአ በ2020 የሚካሄደው የቻን ዋንጫ ደግሞ ወደ ምዕራብ አፍሪካ በመጓዝ ካሜሩን ቤት መግባቱ ተረጋግጧል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 11/2011ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14370
766608d2932245a6ab1e7f403326d2c5
1b24eeb1694de669112d93faae0c3f26
የስፖርት ስነ ልቦና ክህሎቶች
የስነ ልቦና መርሆዎች እና ፅንሰ ሃሳቦች በስፖርት አውድ ላይ ሲተገበር ‹‹ስፖርት ስነ ልቦና ››እየተባለ እንደሚጠራ የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ዛሬ ይህንኑ ዘርፍ በስፋት ለመዳሰስ በቅርቡ በኢትዮጵያን ምሁራን የተሰናዳ አንድ ጥናትን መሰረት እናደርጋለን።የስፖርት ስነ ልቦና መርሆዎችን በመከተል ‹‹አእምሮን እንዴት ማሰልጠን እና ብቃትን ማሻሻል ይቻላል?›› የሚለው ጉዳይ ላይ ሰፊ ጥናታዊ ዳሰሳ ከኢትዮጵያ የስፖርት አካዳሚ ጋር በትብብር ያካሄዱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር አቶ አእምሮ አስማማው እና የስነልቦና ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ተሾመ አጀበው ናቸው።ምሁራኑ በዘርፉ የሚታየውን ሳይንሳዊ የመፍትሄ አቅጣጫ የማሳየት ክፍተት ለመሙላት ይረዳል ያሉትን ጥናታዊ ፅሁፍ ባቀረቡበት ወቅት የሚከተለውን የመነሻ ሃሳብ አስፍረዋል።በስፖርቱ ዘርፍ ስኬታማነትን ለማግኘት የቴክኒክ፣ የታክቲክ፣ የአካል ብቃት እንዲሁም የአእምሮ ክህሎት አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ ይህንን ጉዳይ በጠንካራ መረጃ ለማስቀመጥ እንዲረዳቸው የአውስትራሊያ የክሪኬት ቡድን አሰልጣኝ የነበሩትን የጆን ቦቻናን ምክረ ሃሳብ ያሰፍራሉ፡፡ እርሳቸውም ስፖርተኞች በቋሚነት በችሎታቸው ልክ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ አእምሯዊ ክህሎቶችን በመረዳት በማሰልጠን በመጨረሻም ወደ ከፍተኛ ብቃት ለመድረስ በመጠቀም የስፖርት ስነ ልቦና ግዙፍ ድርሻ እንዳለው ይናገራሉ። እንደ ስፖርት ስነ ልቦና ባለሙያዎች አመለካከት በሁሉም ዘርፍ ላይ የሚገኙ ስፖርቶች በማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ ከሚያደርጓቸው ልምምዶች እና ዝግጅቶች እኩል አእምሯዊ ጥንካሬያቸውንም ማዳበር እና ማሰልጠን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የልምምድ ድርጊቱም በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎች ላይ በእቅድ ሊከናወኑ እንደሚገቡ ይናገራሉ፡፡ በዋናነት በስፖርት ውስጥ የብቃት ጫፍ ላይ ለመድረስ መካተት የሚገባቸው ግላዊ ምክንያቶች፣ ከመነቃቃት ጋር እንዲሁም ከአካባቢያዊ ጉዳዮች ጋር የሚያያዙ መሆናቸውን ባለሙያዎቹ ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህ ሶስት አስፈላጊ ነጥቦችን አቆራኝቶ ተግባራዊ ማድረግ ስፖርቱ አካላዊ፣አእምሯዊ እና የስሜት ዝግጅት እንዲኖረው ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ስፖርቶች ጥሩ የአእምሮ ዝግጅት ይዘው ወደ ውድድር እንዲገቡ የስነ ልቦና ስልጠና ስልቶች ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ የረጅም ርቀት የአትሌቲክስ ስፖርት ተወዳዳሪ ምንም ያህል እንኳን አካላዊ ብቃቱንም በልምምድ አዳብሮ ቢገባ እንኳን የስነ ልቦና ዝግጅት ማድረግ ካልቻለ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ በመሆኑን ስነ ልቦናዊ ዝግጅት ከምንም ነገር በላይ ወሳኝ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ እነዚህን የስነ ልቦና ክህሎቶች ግን በስልጠና እና በእለት ተዕለት ልምምድ ላይ ተግባራዊ በማድረግ ከአካል ብቃት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ነው የዘርፉ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ለመጠቆም የሚሞክሩት። እንደ ምሁራኑ የጥናት ውጤት ‹‹የስፖርት ስነ ልቦና መነቃቃት›› በሁለት መንገድ የሚመጣ ሲሆን እነርሱንም ‹‹ውጫዊ እና ውስጣዊ›› በማለት ያስቀምጧቸዋል፡፡ አንድ ስፖርተኛ ያለ ማንም አነሳሽነት ሁሉንም ነገር በራሱ የሚያከናውን ከሆነ ውስጣዊ መነቃቃት እንዳለው ይታመናል። ከዚህም ሌላ ከፍተኛ ብቃት ላይ መገኘቱን እና የአሸናፊነት ባህሪ መላበሱንም የሚያመላክት መሆኑን ይገልፃል። አንድ ስፖርተኛ ውስጣዊ የስነ ልቦና መነቃቃት ከሌለው ይህን የሚያዳብርበትን ዘዴዎችም ጥናት ያስቀምጣል። በዚህም ማበረታቻ፣ አድናቆት እንዲሁም ሽልማቶች ሳይጠብቁ የልምምድ ስነ ስርአትን በማክበር እና ተጨማሪ ሰዓት በመስራት ማምጣት እንደሚችል ይጠቁማል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ይህ አይነት ተነሳሽነት የሚከሰተው ተጫዋቹ ወይም ስፖርተኛው የሚሳተፍበትን ስፖርት ከውስጥ የማፍቀር እና ለስኬቱም በትጋት የመስራት ስሜት ሲኖረው ነው። በሌላ በኩል አንድ ስፖርተኛ ውጫዊ መነቃቃት አለው የሚባለው በሽልማት፣በማበረታቻ እና በአድናቆት ሲታገዝ እና እርሱን ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ በሚያመጣው ስኬት መሆኑን በጥናቱ ተጠቁሟል። ታዲያ ይህን አይነት ስነልቦናዊ የማነቃቂያ ዘዴ መጠቀሙ ለአንዳንድ ስፖርተኞች መልካም መሆኑን በምክረ ሃሳብ ደረጃ ያስቀምጣል። በጥቅሉ በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ የሚካሄደውን የልምምድ፣ የስልጠና ይዘትን፣ ቦታን፣ ብሎም ቅደም ተከተልን መቀየር፤ትኩረትን የመቆጣጠሪያ ልምምድ፤ስፖርተኞች አእምሯዊ ምስለ እይታ እንዲጠቀሙ ማድረግ ከማነቃቂያ ስነ ልቦናዊ ዘዴዎች መካከል መሆናቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ አእምሮ አስማማው እና የስነልቦና ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት አቶ ተሾመ አጀበው ይፋ ያደረጉት ሳይንሳዊ ጥናት ያመላክታል። የስነ ልቦና ጠቢባኑ ከሚያነሷቸው ሌሎች አንኳር ጥያቄዎች መካከል የስፖርተኞች ትኩረት ማጣትን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ በተለያየ ምክንያት በውድድር እና ልምምድ ሜዳዎች ጥሩ ብቃት ያላቸው እና ልዩነት መፍጠር የሚችሉ ስፖርተኞች ሳይቀሩ ትኩረታቸውን ሲያጡና ወቅታዊ ብቃታቸው ሲወርድ ይስተዋላል። ይህን ጉዳይ በዚህ መልክ ያስቀምጡታል። አንድን ስፖርተኛ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ትኩረቱን ይቀንሳሉ ተብለው የሚታሰቡት ጉዳዮች ውጫዊ እና ውስጣዊ ክስተቶች ናቸው፡፡ ውጫዊ ክስተት ሲሆን በቀጥታ ከአካባቢያዊ ክስተቶች ጋር የሚያያዝ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የግል ሃሳቦች፣ስሜቶች እና አካላዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ስፖርተኛው ትኩረቱን የሚነጠቅበትን ምክንያቶች ከዘረዘሩ በኋላ ይህን መሰል ሁኔታ በሚያጋጥምበት ወቅት በምን መንገድ መፍትሄ ማግኘት እና ወደ ተነቃቃ ሙሉ ትኩረት መመለስ እንደሚቻል ለማመላከት ይሞክራሉ፡፡ እነዚህ ዘዴዎች በስፖርቱ ዓለም ድል የመንሻ ቁልፎች መሆናቸውንም ይናገራሉ፡፡ ከነዚህ የትኩረት መሰብሰቢያ ዘዴዎች መካከል ‹‹የብቃት ግብ መጣል›› ወይም ውጤት ለማግኘት ከመጓጓት ይልቅ በድርጊቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ቀዳሚው መሆኑን ያስቀምጣሉ፡፡ በመቀጠል የዘወትር ልማዶችን ሳያጓድሉ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ያሳስባሉ። በልምምድ እና በውድድር ስፍራዎች ላይ ትኩረት ለመሰብሰብ በሚደረገው ሂደት ላይ አሰልጣኞች፣የቡድን መሪዎች፣የቡድን አጋሮች እንዲሁም ደጋፊዎች ተጫዋቹ ሙሉ አቅሙን እና ትኩረቱን እንዲያቀናጅ የማነቃቂያ ቀስቃሽ ቃላትን መጠቀምን ይመክራሉ፡፡ በህሊና ምስል ቀጣይ ለማግኘት የታሰቡ ስኬቶችን መሳል እና በአካላዊ ልምምድ እና ማፍታታት ላይ ማተኮር ከነዚህ የትኩረት መሰብሰቢያ ዘዴዎች መካከል የሚደባለቁ መሆናቸውን ነው የምሁራኑ የጥናት ውጤት የሚያሳየው። ጥናታዊ ፅሁፉ ከላይ ለመመልከት የሞከርናቸውን የስፖርት ስነ ልቦና ትርክቶች ለውጤት መሰረት ናቸው በማለት ይደመድማል፡ ፡ ስኬት እና ውድቀት ልክ እንድ አካላዊ ብቃቶች በአእምሯዊ ክህሎቶች ላይ እንደሚመረኮዝ ያሳየናል፡፡ የስፖርት ሳይኮሎጂስቶች ባደረጓቸው የተለያዩ ጥናቶች የስፖርተኞች የአእምሯዊ ሁኔታቸው በብቃታቸው ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ማወቃቸውንም ነው የሚናገሩት። ምሁራኑ ጉዳዩን ሲያጠቃልሉ ስፖርተኞች አእምሯቸውን ማሰልጠን ከእለት ተዕለት የአካል ብቃት ልምምዳቸው እኩል ሊተገብሩት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ያስገነዝባሉ። እያንዳንዱ ስፖርተኛ የላቁ ውጤቶችን የሚያስመዘግቡበት የሃይል ምንጭ እንዳላቸው በማሳየትም ይህንኑ ስጦታ በተለያዩ የስፖርት ስነ ልቦና መርሆ እና ዘዴዎች በይበልጥ ማዳበር እንደሚገባ ምክረ ሃሳባቸውን ይሰጣሉ። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር አእምሮ አስማማው እና የስነልቦና ትምህርት ክፍል መምህሩ አቶ ተሾመ አጀበው ብዙም ባልተለመደ መልኩ በአገራችን ያለውን የተዳከመ የስፖርት እድገት ምክንያት በቀጥታ ከስነ ልቦና ጋር በማገናኘት ሳይንሳዊ ትንታኔ እና መፍትሄ ለማመላከት ችለዋል። በስፖርቱ ዘርፍ ኢትዮጵያ የስኬት አናት ላይ እንድትደርስ ይህን መሰል አዳዲስ እይታዎች እና ስነ ዘዴዎች ማመላከት በእጅጉ ጠቃሚ መሆኑንም አሳይተውናል። አዲስ ዘመን ሀምሌ 14/2011ዳግም ከበደ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14539
46adfbb19426525bf6a464216cf02db2
ef46719f090fdff1a8afb7fbe0c9c9dd
የኢትዮጵያ ዝግጅት ለአፍሪካ ጨዋታዎች
የዓለም ትልቁ ስፖርታዊ ውድድር ኦሊምፒክ ከመካሄዱ አንድ ዓመት አስቀድሞ ይካሄዳል። በተለያዩ ክፍለ አህጉራት የሚካሄደው ይህ ውድድር እንደ ኦሊምፒክ የሚታይ ሲሆን፤ የአህጉሩን አገራት በተለያዩ ስፖርቶች ያወዳድራል። በአፍሪካም እ.ኤ.አ 1965 ለመጀመሪያ ጊዜ ሲካሄድ፤ በየአራት ዓመቱ እየተዘጋጀ አሁን 12ኛ ጊዜ ላይ ደርሷል። ውድድሩ እ.ኤ.አ እስከ 2012 የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በሚል ሲጠራ ቢቆይም፤ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው ጉባኤ የአፍሪካ ጨዋታዎች በሚል እንዲሻሻል ተደርጓል። በአፍሪካ ሕብረት፣ በአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበራት እንዲሁም በአፍሪካ ስፖርት ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አስተባባሪነት ይካሄዳል። የአፍሪካ ሕብረት የውድድሩ ባለቤት ሲሆን፤ የኦሊምፒክ ኮሚቴዎቹ ማህበር ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በመምራት እንዲሁም ኮንፌዴሬሽኑ ከገንዘብ እና ከስፖንሰሮች ጋር የተያያዘውን ጉዳይ በማስተባበር ተሳትፏቸውን ያደርጋሉ። በዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በበላይነት የሚመራው አህጉር አቀፉ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በኮንጎ ብራዛቪል ነበር የተካሄደው። በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሚሆኑት የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል አገራት ሲሆኑ፤ በአፍሪካ አቀፉ ውድድር ላይም 53ቱም አባል አገራት ተካፋይ ነበሩ። የኦሊምፒክን ጽንሰ ሐሳብ ተከትሎ የሚካሄደው ውድድሩ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትን ይቃወማል። ከዚህ ቀደም በደቡብ አፍሪካ በነበረው የአፖርታይድ ሥርዓት እንዲሁም በሞሮኮ ተከስቶ በነበረው ፖለቲካዊ ቀውስ ምክንያት አገራቱን ከተሳታፊነት አግልሎም ነበር። የዘንድሮው ውድድር በሞሮኮዋ ራባት የሚካሄድ ሲሆን፤ 53አገራት በ23 የስፖርት ዓይነቶች ብሔራዊ ቡድኖቻቸውን ያሳትፋሉ። በቀጣዩ ወር የሚጀመረው ውድድሩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱን በንጉሥ ሞሐመድ 6ኛ ስታዲየም እንደሚደረግ ይጠበቃል። አገሪቷ በአጠቃላይ ለውድድር እንዲሁም ለልምምድ የሚሆኑ 13 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችንም አዘጋጅታ ተሳታፊዎቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች። በዚህ ውድድር ተሳትፎ በርካታ ሜዳሊያዎችን በማስቆጠር በሰንጠረዡ አናት የተቀመጠችው ግብጽ 1ሺ362 ሜዳሊያዎችን ሰብስባለች። ሁለተኛዋ አገር ናይጄሪያ በበኩሏ 1ሺ199 ሜዳሊያዎች አሏት። ደቡብ አፍሪካ ደግሞ በ967 ሜዳሊያዎች ሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ስምንተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኢትዮጵያ 122 ሜዳሊያዎች ሲኖሯት፤ ከእነዚህ መካከል 39ኙ የወርቅ፣ 39ኙ የብር እንዲሁም 52 ቱ የነሐስ ሜዳሊያዎች ናቸው። ከአራት ዓመታት በፊት በኮንጎ ብራዛቪል በተካሄደው መላ አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ ኢትዮጵያ ኬንያን በመከተል ስምንተኛ ሆና ያጠናቀቀች ሲሆን፤ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 6 የነሐስ በጥቅሉ 17 ሜዳሊያዎችን ነበር ያስመዘገበችው። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ውድድር በ13 የስፖርት ዓይነቶች የምትሳተፍ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል። የተወሰኑ ስፖርቶች ዝግጅታቸውን ሲጀምሩ ሌሎች ደግሞ ተሳታፊ ስፖርተኞቻቸውን ለመምረጥ ሻምፒዮናዎችን እያካሄዱ ይገኛሉ። የስፖርት ዓይነቶቹም፤ አትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ቦክስ፣ ካራቴ፣ ወርልድ ቴኳንዶ፣ ቼስ፣ ክብደት ማንሳት፣ የውሃ ስፖርቶች፣ ጂምናስቲክ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ባድሜንተን፣ ጠረጴዛ ቴኒስ እና ሜዳ ቴኒስ ናቸው። ቀድመው ወደ ዝግጅት ከገቡት ስፖርቶች መካከል አንዱ ኢትዮጵያ የምትታወቅበትና ውጤታማ የሆነችበት የአትሌቲክስ ስፖርት አንዱ ነው። በዚህ ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶች በግንቦት ወር የተመረጡ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ሆቴል ተቀምጠው ዝግጅት በማድረግ ላይም ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከ100-10ሺ ሜትር ባሉት የሩጫ እና የሜዳ ተግባራት ስትካፈል፤ በጥቅሉ105 አትሌቶች ተመርጠዋል። አትሌቶቹ ሊመረጡ የቻሉትም ከወራት በፊት በተካሄደው 48ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቋል። ሌላኛው ዝግጅቱን አስቀድሞ የጀመረው ስፖርት ቦክስ ሲሆን፤ በ7 ወንድ እና 2 ሴት ቦክሰኞች ብሔራዊ ቡድኑ እንደሚወከል ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። በወንዶች ምድብ የተመረጡት ቦክሰኞች፤ በ49፣56፣ 60፣ 64፣ 69፣ 75 እና 81 ኪሎ ግራሞች በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ። በሴቶች በኩል ደግሞ በ48 እና 51 ኪሎ ግራሞች ተካፋይ ይሆናሉ። በየዓመቱ በአራት ዙሮች ከሚካሄደው የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የተመረጡት ቦክሰኞቹ በሦስቱ ዙር የተሻለ ብቃት በማሳየታቸው የተመረጡ መሆናቸውም ታውቋል። ሌላኛው ተሳትፎ የሚደረግበት ስፖርት ብስክሌት፤ በመቀሌ ከሰኔ 19- 22 በተካሄደው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ተመርጠዋል። እስከ ሐምሌ አንድ ቡድኑን የሚቀላቀሉት ብስክሌተኞች ታውቀው ወደ ዝግጅት የሚገቡ ሲሆን፤ በሁለቱም ፆታ በሚካሄዱት ሁሉም የውድድር ዓይነቶች ለመሳተፍ ማቀዱን ፌዴሬሽኑ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገልጿል። በክብደት ማንሳት ስፖርትም በተመሳሳይ ተካፋይ የሆኑ ስፖርተኞች የሚመረጡበት አገር አቀፍ ሻምፒዮና ተካሂዷል። በወንዶች ከ55-102 ኪሎ ግራም በሴቶች ደግሞ ከ45-71 ኪሎ ግራም በተካሄደው በዚህ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች አገርን የሚወክሉ ስፖርተኞች ይመረጡበታል። አዲስ ዘመን ሀምሌ 15/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14567
ee1d86b06e4a5a4b7bd0edafdeb4b6ed
52f89b24f4f0bb67a97cc080db22fd07
የ10ሺ ሜትር ዙፋን ተረካቢዎች እነማን ይሆናሉ?
የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ሲቃረብ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቻምፒዮናው ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን የሰዓት መስፈርት (ሚኒማ) ለማሟላት በኔዘርላንድ አገር ሄንግሎ ከተማ የሚያደርጉት የማጣሪያ ውድድር ተጠባቂ ነው። ውድድሩ በዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች የሚመረጡበት እንደመሆኑ የአንድ አገር አትሌቶች እርስበርስ የሚያደርጉት ፉክክር ተጠባቂ ነው። በተለይም በዓለም ላይ ውድድር እየጠፋበት በሚገኘው 10 ሺ ሜትር በሁለቱም ፆታ የሚደረጉ ፉክክሮች የሚጠበቁ ናቸው። ከሁለት ወራት በኋላ በኳታር ዶሃ በሚካሄደው የዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አገራቸውን ለመወከልና ሚኒማ ለማሟላት ባለፈው ረቡዕ ምሽት እንደተለመደው ሄንግሎ ላይ ተሰባስበዋል። ባለፉት ሦስት የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮናዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ10 ሺ ሜትር የነበራቸውን ክብር ለእንግሊዛዊው አትሌት ሞሐመድ ፋራህ አሳልፈው የሰጡ ሲሆን ፋራህ ካፈው የለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወዲህ ራሱን ከውድድር ማግለሉን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ዳግም ዙፋኑን ለመያዝ ተጠባቂ ናቸው። የትኛው አትሌት የዙፋኑ ተረካቢ ይሆናል? የሚለው ጥያቄ ግን የብዙዎች ጉጉት ነው። በሄንግሎው የማጣሪያ ውድድር ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ርቀቱን ከ27፡00 በታች በማጠናቀቅ የዓመቱን ፈጣን ሰዓቶች ከመቆጣጠራቸው ባሻገር ኢትዮጵያ በዶሃው ቻምፒዮና ጠንካራና ጥልቀት ያለው የቡድን ስብስብ እንደሚኖራት ፍንጭ የሰጠ ነው። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሄንግሎው ውድድር የመጀመሪያዎቹን ሦስት ደረጃዎች ይዘው ያጠናቀቁትን አትሌቶች በቀጥታ በዓለም ቻምፒዮና ኢትዮጵያን እንዲወክሉ ማድረግ አለማድረጉን ይፋ ባያደርግም መሬት ላይ ካሉ እውነታዎች ተነስቶ የትኛው አትሌት ሊመረጥ እንደሚችል ግምቶች እየተቀመጡ ይገኛሉ። ምናልባትም በሄንግሎው ውድድር ከአንድ እስከ ሦስት ያጠናቀቁት አትሌቶች በአምስት ሺ ሜትር ውድድርም ኢትዮጵያን እንደሚወክሉ እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚቻል መሆኑ እነዚህ አትሌቶች በ10 ሺ ሜትር ደርበው ሲሮጡ የውድድር ጫና እንዳይኖርባቸው ፌዴሬሽኑ ሽግሽግ በማድረግ ከሦስተኛ በላይ ያጠናቀቁ አትሌቶችን ምርጫው የሚያደርግበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል። ከሄንግሎው ውድድር ውጤት ባሻገር አትሌቶቹ ከዚህ ቀደም በቅርብ ጊዜያት በነበሯቸው ውጤቶችና ሰዓቶች መሰረት ምርጫ ሊደረግ እንደሚችልም ይጠበቃል። ያም ሆኖ በሄንግሎው ውድድር ቀዳሚ ሆነው ያጠናቀቁት አትሌቶች ብቃትና ከሦስተኛ በላይ ያጠናቀቁ አትሌቶች ለዓለም ቻምፒዮና የመመረጣቸውን ዕድልና ያላቸውን አቅም መመልከቱ አስፈላጊ ይሆናል። ከሦስት ሳምንታት በፊት በስቶክሆልም ዳይመንድ ሊግ ኬንያዊው ሮኔክስ ኪፕሩቶን ተከትሎ ሁለተኛ በመሆን ሲያጠናቅቅ 27፡01፡02 የሆነ ሰዓት ያስመዘገበው አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት ሄንግሎ ላይ 26፡48፡95 በሆነ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ቀዳሚ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል። ሐጎስ አሁን ካሉት አትሌቶች በተሻለ በኦሊምፒክና በዓለም ቻምፒዮና በአምስት ሺ ሜትር ብዙ ልምድና ሜዳሊያዎች ያሉት ሲሆን በዘንድሮው ዓመት አምስት ሺ ሜትር ላይ ወጣትና ድንቅ አቋም ያላቸው በርካታ አትሌቶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሊሆን ይችላል ትኩረቱን በ10 ሺ ሜትር ላይ አድርጓል። ሐጎስ እነዚህ ጠንካራ ተፎካካሪ ወጣቶች በመጡበት ወቅት ርቀቱን ጨምሮ 10 ሺ ሜትር ላይ ትኩረት ማድረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ከመሆኑ ባሻገር ውጤታማም እያደረገው እንደሚገኝ የዘንድሮው ዓመት ሁለት የ10 ሺ ሜትር ውድድሮቹን መመልከት በቂ ነው። በሁለቱ ውድድሮች ያስመዘገባቸው ሰዓቶችን በተለይም በሄንግሎ ውድድር ያስመዘገበውን ውጤት በውድድር ዓመቱ የትኛውም አትሌት አለማስመዝገቡ በዚህ ርቀት በየትኛውም መስፈርት ቀዳሚ ተመራጭ ሊያደርገው እንደሚችል መገመት ይቻላል። ሐጎስ በ10 ሺ ሜትር ስኬታማ ከመሆኑ ባሻገር በአምስት ሺ ሜትርም ያለው ስኬት ከሌሎች አትሌቶች የሚያንስ አይደለም። ምናልባት ግን ፌዴሬሽኑ ከ10 ሺ ሜትር በበለጠ አምስት ሺ ሜትር ላይ በርካታ አማራጮች ስላሉት ሐጎስ 10 ሺ ሜትር ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራ ማድረግ ከቻለ የብልህ ውሳኔ ወስኗል። ወጣቱ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይም በአምስት ሺ ሜትር በዓለም ቁንጮ ከሚባሉ አትሌቶች ተርታ ራሱን ማሰለፍ ችሏል። ሰለሞን በዘንድሮው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ10 ሺ ሜትር ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን በሄንግሎው ውድድር 26:49.46 በማስመዝገብ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። 10 ሺ ሜትር ከአምስት ሺ ሜትር የበለጠ ፅናትና ጥንካሬ የሚፈልግ ውድድር እንደመሆኑ ሰለሞን በሄንግሎው ፉክክር ፈጣን ሰዓት ቢያስመዘግብም በርቀቱ ብዙ ልምድ ካለማካበቱ ጋር በተያያዘ ትኩረቱን አምስት ሺ ሜትር ላይ ቢያደርግ የሚመረጥ መሆኑን የስፖርት ባለሙያዎች ይመክራሉ። እርግጥ ነው አንድ አትሌት አምስትም አስርም ሺ ሜትር ደርቦ ቢወዳደር ችግር ላይኖረው ይችላል። ይሁን እንጂ አንዱ ርቀት ላይ ወይም የበለጠ ውጤታማ የሆነበት ርቀት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ቢሠራ የበለጠ ውጤታማነቱ እንደሚጎላ እውን ነው። ከሰለሞን ባረጋ ጋር በተመሳሳይ መልኩ ዮሚፍ ቀጄልቻ በአምስት ሺ ሜትር ያለው አቅምና ስኬታ የሚያስቀና ነው። ዮሚፍ አስር ሺ ሜትርን ሲሮጥ የሄንግሎው ውድድር የመጀመሪያው ነው። ያም ሆኖ ድንቅ የሩጫ ተሰጥኦና ቁመና የታደለው ወጣት አትሌት ሐጎስና ሰለሞንን ተከትሎ እንደ መጀመሪያ ውድድር ያስመዘገበው 26:49.99 ሰዓት ሳይደነቅ የሚታለፍ አይደለም። እንደ ሰለሞን ሁሉ ዮሚፍ በርቀቱ ልምድና የተሻለ ችሎታ ይዘው በሄንግሎው ውድድር ላልቀናቸው አትሌቶች ቦታ ለቆ አምስት ሺ ሜትር ላይ ትኩረቱን ቢያደርግ የተሻለ እንደሚሆን ይታመናል። ይህም የአምስት ሺ ሜትር ስብስቡን በደንብ ከማጠናከር ባሻገር 10 ሺ ሜትሩን የበለጠ ልምድ ባላቸው አትሌቶች ስብስብ አስፈሪ እንዲሆን ዕድል ይሰጠዋል። ሐጎስ ገብረሕይወት 10 ሺ ሜትር ላይ መመረጡ አይቀሬ ከሆነ ፌዴሬሽኑ ሽግሽግ ሊያደርግ የሚችለው ወይንም በዚህ ርቀት ትክክለኛውን አትሌት ለመምረጥ የሚጨነቀው በቀሪዎቹ ሁለት ኮታዎች ላይ ይሆናል። ይህም ምርጫ ሰለሞንና ዮሚፍን ደርበው እንዲሮጡ ማድረግ ወይም 10 ሺ ሜትር ላይ ሌሎች አማራጮችን መፈለግ ነው። በዚህ አማራች ውስጥ ሁለት አትሌቶች ወደ 10 ሺ ሜትር የመምጣት ዕድል ሊኖራቸው ይችላል። አንደኛው አትሌት አንዱአምላክ በልሁ ሲሆን 10 ሺ ሜትር ላይ የተሻለ ልምድ አለው። በዚህ ዓመት የኒውዴልሂ ግማሽ ማራቶንን 59፡18 በሆነ ጥሩ ሰዓት ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በኢትዮጵያ ቻምፒዮና ሰለሞን ባረጋን ተከትሎ 28፡25 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። አንዱአምላክ በሄንግሎው ውድድርም 26፡53፡15 አራተኛ ሆኖ ያጠናቀቀበት ሰዓት በርቀቱ ካለው የተሻለ ልምድ አኳያ ቀድመውት ካጠናቀቁት አትሌቶች ያነሰ አያደርገውም። አንዱአምላክ ሄንግሎ ላይ ከአንድ እስከ ሦስት ያጠናቀቁት አትሌቶች በቀጥታ ቢመረጡ እንኳን ተጠባባቂ ሆኖ መያዙ አይቀርም። ስለዚህ ፌዴሬሽኑ ይህን አትሌት የመምረጥ ሰፊ ዕድል እንዳለው ይታመናል። በሌላ በኩል ሄንግሎ ላይ 26፡54፡39 በማስመዝገብ አምስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ጀማል ይመር ሐጎስ ስቶክሆልም ላይ ሁለተኛ ሆኖ ባጠናቀቀበት ውድድር ርቀቱን መፈፀም ባይችልም ጥሩ አቅም ያለው አትሌት እንደሆነ ይታወቃል። ጀማል ባለፈው የለንደን የዓለም ቻምፒዮናም በአስር ሺ ሜትር አምስተኛ ደረጃን ይዞ ነበር ያጠናቀቀው። በሴቶች መካከል ሄንግሎ የተደረገው ውድድር እንደ ወንዶቹ በርቀቱ አዳዲስና ወጣት አትሌቶች የታዩበት ሲሆን አስር ያህል አትሌቶች ርቀቱን ከ31፡00 በታች ማጠናቀቅ ችለዋል። በውድድር ዓመቱ በሴቶች 10 ሺ ሜትር ውድድሮች እምብዛም ካለመደረጋቸው ጋር ተያይዞ ፌዴሬሽኑ የሄንግሎው ውድድር ላይ ብቻ ተመስርቶ ለዓለም ቻምፒዮናው ምርጫ የሚያደርግበት ዕድል ሰፊ ይመስላል። ስለዚህ በሴቶች መካከል የሚደረገው የብሔራዊ ቡድን ምርጫ ከውዝግብ ሊያመልጥ ይችላል። በሄንግሎው ውድድር የሁለት ጊዜ የዓለም አገር አቋራጭ የወጣት ሴቶች አሸናፊዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ 30፡37፡89 በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ የዓለም ግማሽ ማራቶን ቻምፒዮንና የርቀቱ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ነፃነት ጉደታ 30:40.85 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆና ፈፅማለች። የ2015 የዓለም ቻምፒዮና የአምስት ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊዋ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ 30:45.14 በመግባት ሦስተኛ፣ ዘይነባ ይመር በ30:46.24 አራተኛ፣ዴራ ዲዳ በ30:51.86 ሰዓት አምስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።ከእነዚህ አትሌቶች መካከል ከአንድ እስከ ሦስት ባለው ደረጃ ውስጥ ያጠናቀቁት አትሌቶች አስር ሺ ሜትር ላይ በውድድር ዓመቱ ሌላ ሰዓት ማስመዝገባቸው ወይም መሮጣቸውን የሚያሳይ መረጃ የለም። ስለዚህ በሄንግሎው ውጤታቸው መሰረት በቀዳሚነት ተመራጭ የሚሆኑበት ዕድል ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል። ምናልባት እዚህ ጋር ፌዴሬሽኑ ከ10 ሺ ሜትር ጋር ተቀራራቢ የሆኑ እንደ ግማሽ ማራቶንና አስር ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ውድድሮች ውጤታቸውን ተመልክቶ በመምረጫ መስፈርቱ ውስጥ ሊያካትት የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችልም ማሰቡ አይከፋም። የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ የ10 ሺ ሜትር የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት አልማዝ አያና ከአንድ ዓመት በላይ በጉዳት ከውድድር ርቃ መቆየቷ ይታወቃል። አልማዝ ከጉዳት አገግማ ከወር በፊት ከምትታወቅበት ርቀት በተለየ ራባት ዳይመንድ ሊግ ላይ በሦስት ሺ ሜትር ተወዳድራ ስኬታማ መሆን አልቻለችም። ምናልባት አልማዝ ከጉዳቷ አገግማ ለዶሃው የዓለም ቻምፒዮና ትደርሳለች የሚለው የስፖርት ቤተሰቡ ስጋት ነው። አልማዝ ከጉዳቷ ማገገም ከቻለች በዓለም ቻምፒዮና ሚኒማ ሳታሟላና ሄንግሎ ላይ ከተወዳደሩት አትሌቶች ጋር ፉክክር ውስጥ ሳትገባ ያለፈው የዓለም ቻምፒዮና አሸናፊ በመሆኗ በቀጥታ የመወዳደር ዕድል ይኖራታል። ይህም ኢትዮጵያ በዶሃው ቻምፒዮና በ10 ሺ ሜትር ሴቶች በአራት አትሌቶች እንድትወከል ያስችላታል። አዲስ ዘመን ሀምሌ 13/2011 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14499
bb1c0611c09872f929ee0664ff223fb4
c54ed570f8da7c47852c657c6b48048e
የአገር አቀፍ የሠራተኞች ስፖርት ተጠባቂ ፉክክሮች
አገር አቀፍ የሠራተኞች ስፖርት በወንጂ ሁለገብ ስታድየም ከተጀመረ ዛሬ ዘጠነኛ ቀኑን አስቆጥሯል፡፡ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚደረጉ ፉክክሮች ሳምንቱን በሙሉ ሲከናወኑ የቆዩ ሲሆን ከትናንት ጀምሮ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግረዋል፡ ፡ በሁለት ዲቪዚዮን ተከፍሎ ጠንካራ ፉክክር በሚደረግበት እግር ኳስ ጨዋታ የሚሳተፉ ቡድኖች ከዛሬ ጀምሮ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የኢሠማኮ የስፖርት ክፍል ሃላፊ አቶ ዮሴፍ ካሳ ከስፍራው በስልክ ያደረሱን መረጃ ያመለክታል። በዚህም መሰረት በውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታ በሁለተኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርትን ገጥሞ ማራኪ ጨዋታ በማሳየት የተመልካቹን ቀልብ መግዛት የቻለው በበቃ ቡና ልማት ዛሬ በወንጂ ሸዋ ስቴድየም መተሃራ ስኳር ፋብሪካን ይገጥማል፡፡ በተመሳሳይ ሜዳ ከትግራይ ክልል የመጣው አዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርትን እንደሚገጥም ይጠበቃል፡፡ በዚሁ በሁለተኛ ዲቪዚዮን በከልቻ ትራንስፖርት ከአዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ በወንጂ ሁለገብ ስታድየም ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ የሚጠበቅ ሲሆን በተመሳሳይ ሜዳ ብርሸለቆ እርሻ ልማት ከደብረብርሃን ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይኖራል፡ ፡ በሁለተኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ውድድር የዛሬ ጨዋታዎች ውጤት ሳይካተት መተሃራ  ስኳር ፋብሪካ ከምድብ አንድ በነጥብ እየመራ ሲሆን ምድብ ሁለትን ኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ እየመራ ይገኛል። በስምንት ቡድኖች መካከል የሚካሄደው የአንደኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ውድድር ከነገ ጀምሮ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል፡፡ በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአንበሳ የከተማ አውቶብስ ወንጂ ሁለገብ ስቴድየም ነገ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ በተመሳሳይ ሜዳ ኢትዮ ፐልፕና ወረቀት ፋብሪካ ኢትዮ ቴሌኮምን ይገጥማል፡፡ ከሰም ስኳር ፋብሪካ ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የሚያደርጉት ጨዋታም ለነገ መርሃ ግብር ተይዞለታል፡፡ በአንደኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ኢትዮጵያ አየር መንገድና ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ምንም ጨዋታ ሳይሸነፉ በነጥብ እየመሩ እንደሚገኙ አቶ ዮሴፍ ተናግረዋል። በቮሊቦል ስፖርት ሙገር ሲሚንቶና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በነጥብ እየመሩ ይገኛሉ፡፡ በጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አንደኛ ሆኖ እየመራ የሚገኝ ሲሆን ሐረር ቢራ ፋብሪካና ኢትዮ ቴሌ ኮም ሁለተኛ ሆነው እየተከተሉ ናቸው። በአትሌቲክስና በቤት ውስጥ ስፖርቶች ማለትም ቼስ፣ ዳርት፣ ዳማ፣ ገበጣና ከረንቦላ ውድድሮች ከትናንት ጀምሮ ፉክክሮች የቀጠሉ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ፍፃሜ የሚያገኙ ይሆናል፡፡ በአጠቃላይም አገር አቀፍ የሠራተኞች ውድድር የፊታችን እሁድ በወንጂ ሁለገብ ስታድየም ፍፃሜውን  ያገኛል። የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) የማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊና የስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፍሰሃፂዮን ቢያድግልኝ በሠራተኛው መካከል በሚደረገው ውድድር ከሁሉም ክልል የተውጣጡ የሠራተኛ ስፖርት ማህበራት ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል፡ ፡ ውድድሩ ሠራተኛው በስፖርቱ ጤንነቱ የተጠበቀ አምራች ዜጋ እንዲሆን ከማስቻል ባሻገር በአሁኑ ወቅት አንገብጋቢ ከሆነው የሰላም ጉዳይ ጋር በተያያዘ ‹‹ስፖርት ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለጤንነትና ለምርታማነት›› በሚል መርህ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት የተለያዩ ማህበራትን እያሳተፈ የሚገኘው ይህ ውድድር የመገናኛ ብዙሃን ትኩረትን እየሳበ ይገኛል። ይህም አዳዲስ ተሳታፊ ማህበራትን ወደ ውድድር ከመሳብ በዘለለ ቀድሞ ዝነኛ ተፎካካሪ የነበሩና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከውድደሩ የራቁ ማህበራትን ወደ ውድድር እየመለሰ ይገኛል። ያም ሆኖ ለረጅም ዓመታት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን በርካታ ሠራተኞችን እያሳተፉ የነበሩ እንደ ንግድ ባንክ አይነት ማህበራት ዘንድሮ ከውድድሩ ቀርተዋል። ኢሠማኮ የሚካሄደው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ሦስት አይነት ገፅታን የተላበሰ ከፉክክርም በላይ በርካታ አላማዎችን የሰነቀ የስፖርት መድረክ ነው። ረጅም ወራትን ሠራተኛው በስፖርት አማካኝነት አብሮነቱን የሚያጠናክርበትና ልምድ የሚለዋወጥበት የበጋ ወራት የስፖርት ውድድር የበርካታ ድርጅትና ተቋማት ሠራተኞችን ማዕከል ያደረገ የውድድር መድረክ ሲሆን፤ የሠራተኛውን ዓመታዊ በዓል ታኮ የሚካሄደው የሜይ ዴይ ውድድር ሌላኛው አካል ነው። ክረምት ወራት ላይ በውቡ የወንጂ ሁለገብ ስቴድየም የሚካሄደው አገር አቀፍ የሠራተኞች ውድድርም በድምቀቱና አገር አቀፍ ሠራተኞችን በአንድ ላይ ለሁለት ሳምንታት በትንሿ ከተማ ይዞ የሚከርም ነው። ሦስቱም የውድድር ገፅታዎች ሠራተኛውን ከማቀራረብና ልምዱን እንዲለዋወጥ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር በሠራተኛው መካከል ቤተሰባዊ ስሜት እንዲጎለብት ሚናቸው ቀላል እንዳልሆነ አቶ ፍሰሃፂዮን ተናግረዋል። ሠራተኛው በስፖርት ጤንነቱ የተጠበቀ ምርታማ ዜጋ እንዲሆን ከማስቻል በተጨማሪ ሦስቱ የስፖርት መድረኮች ሠራተኛው «የእኔ ነው» የሚለው የመዝናኛ አማራጩ ጭምር መሆናቸውንም ሃላፊው አስረድተዋል። በውድድሩ የሚካፈሉ በርካታ ድርጅትና ተቋማት በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሠራተኞቻቸው ያላቸውን ክህሎት አውጥተው በመጠቀም ለአገር ስፖርት ዕድገት የበኩላቸውን ድርሻ ከመወጣት አልፈው ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ እንዳገኙም ባለፉት ዓመታት ውድድሮች ለመታዘብ እንደተቻለ ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 15/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14570
933377dd81c0bd28355a3810024ed7ec
e334b8b42825879e19ac39e257f70039
ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንደሚወክል አረጋገጠ
ፋሲል ከነማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊ በመሆን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንደሚወክል አርጋገጠ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ በቢሾፍቱ ከተማ ላይ ፍጻሜውን ባገኘው የ2011 የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ሐዋሳ ከተማን በማሸነፍ ባለድል ሆኗል፡፡ ሁለቱ ከለቦች ጨዋታውን በመደበኛ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ በማጠናቀቃቸው ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች ፋሲል ከነማ በመለያ ምቱ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ግብ ጠባቂ ሚካኤል ሳማኪ ሶስት የመለያ ምቶችን በማስቀረት የጨዋታው ኮከብ መሆን ችሏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ፋሲል ከነማ የተዘጋጀለትን ዋንጫ ከክብር እንግዳዳው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጂራ ተረክቧል።ከለቡ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊ መሆንን ተከትሎም በቀጣዩ አመት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚወክል መሆኑን አርጋግጧል፡፡፡ የ2019/20 የካፍ የክለብ ውድድሮች ድልድል ከትናንት በስቲያ ይፋ ሲሆን፣ የፋሲል ከነማ የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚም የታንዛኒያው አዛም መሆኑ ታውቃል፡፡ ከ12 ዓመታት በፊት የተመሰረተው የታንዛኒያው ክለብ በ2018/19 የውድድር ዓመት 3ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ክለብ ነው፡፡ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ልጆች፣የመጀመሪያው ጨዋታቸውን በነሃሴ ወር መጀመሪያ በባህርዳር አለምአቀፍ ስታዲየም የሚካሂዱ ይሆናል፡፡የመልሱን ጨዋታ ከሜዳው ውጪ ከነሐሴ ወር አጋማሽ የሚያከናውን ሲሆን ፣ይህን ዙር ካለፈም በመስከረም ወር ከዛምቢያው ትሪያንግልስና ከብሩንዲው ቱኪንዞ ጋር ይጫወታል። አጼው በውድድር ዓመቱ ጠንካራ የሚባል እንቅስቃሴ በማድረግ በተለይም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመጨረሻ ጨዋታ ከሠሁል ጋር አቻ መውጣቱን ተከትሎ ዋንጫ ማጣቱና መቐለ 70 እንደርታና ሲዳማ ቡናን ተክትሎ በሶስተኛነት ውድድሩን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ የሆነው መቐለ 70 እንደርታ በቅድመ ማጣርያው የኢኳቶርያል ጊኒው ካኖ ስፖርት አካዳሚን የሚገጥም ይሆናል፡። በ2014 የተመሰረተው ቡድኑ የሀገሪቱ የሊግ ውድድር አሸናፊ የሆነ ሲሆን እንደ መቐለ ሁሉ በውድድሩ ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው። መቐለ የመጀመሪያ ጨዋታውን ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ አምርቶ ከነሐሴ ወር መጀመሪያ ቀናት ሲያደርግ የመልሱን ጨዋታ በሜዳው ከነሐሴ አጋማች ባሉት ቀናት ያደርጋል። ይህን ዙር ካለፈ ደግሞ በአንደኛው ዙር ማጣሪያ መስከረም ወር ላይ ከደቡብ ሱዳኑ አትባራና የግብፅ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ከሚሆነው ቡድን ጋር የሚጫወት ይሆናል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ከለብ የመልሱን ጨዋታ ሊያደርግበት ያሰበው የትግራይ ስታዲየም የካፍ እውቅና እስካሁን ባለማግኘቱ በእድሳት ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባው አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል። ‹‹ጨዋታውን በሜዳችንና በደጋፊ ፊት ነው ለማድረግ ያሰብነው፣ ይህንን ለማድረግም ከዚህ ቀደም የካፍ ተወካዮች መጥተው የሰጡት አስተያየትና መሟላት ያለባቸውን ጉዳዮች በነገሩን መሰረት እያዘጋጀን ነው፣ በሚቀጥለው ሳምንት መሟላት ያለባቸውን ነገሮች አጠናቀን የካፍ ተወካዮችን በመጥራት እንዲመለከቱ፤ ፍቃድም እንዲሰጡን ጠንክረን እየሰራን ነው ››ሲሉ የመቐለ ሰባ እንዳርታ ምክትል ፕሬዚዳንት ልባርጋቸው ምህረቱ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አብዛኞቹ ጨዋታዎች አልተካሄዱም፡፡የግማሸ ፍፃሜን ጨምሮ ስምንት ጨዋታዎች በፎርፌ የተጠናቀቁ ሲሆን፣ የተካሄዱ ጨዋታዎች ብዛት ደግሞ ሰባት ብቻ ነው፡፡ከግምሽ በላይ የሚሆኑት የፕሪሚየር ሊጉ ከለቦች ከፋይናንስ ጋር በተያያዘ ጨዋታውን ለማካሄድ እንደተቸገሩ ሲገልፁ አንዳንዱቹ በአንፃሩ ያለመሳተፋቸውን ምክንያት በይፋ አላሳወቁም፡፡አዲስ ዘመን  ሐምሌ 16/2011 ታምራት ተስፋዬ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14609
e088ba20f562f7b45041f4c9c0685eec
c94b2031c96a2f14763c21297f51919f
ስፖርትና ፖለቲካ – አሳዛኙ አከራረማችን
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመቐለ ሰባእንደርታ ሻምፒዮናነት ነበር ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም የተጠናቀቀው። ሊጉ ከወርሃ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ቆይታን አድርጓል። ፕሪሚየር ሊጉ አዲስ የተቀላቀለውን ክለብ ሻምፒዮና አድርጎ ከመጠናቀቁ በተጓዳኝ በርካታ ትዕይንቶችን አስተናግዶ ነበር ያለፈው። ከበርካቶቹ ትዕይንቶች ጎልቶ የወጣውና ሊታረም የሚገባው ስፖርታዊ ጨዋነት የተመለከተው ሆኗል።ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈተና እየሆነ የመጣው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ ዘንድሮ ፈር በለቀቀ መልኩ በስፋት ታይቷል። የችግሩ ስፋትና ስጋት ምን መልክ እንደነበረው ለቀጣይ ማስተማሪያ ይሆን ዘንድ መለስ ብለን ለመቃኘት ወደድን። በዚህ መሰረትም በዛሬው የስፖርት ገጻችን «ነበር» በሚል ርዕስ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ተያይዞ የውድድር አመቱ የነበረው አነጋጋሪና አሳዛኝ ገጽታን እንዲህ ታዝበነዋል።የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በወርሃ ጥቅምት 17 በተለያዩ ክልል ከተሞች በተደረጉ ጨዋታዎች ነበር መጀመሩ የተበሰረው። የሊጉ መጀመር በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ሁለት አይነት ስሜትን ፈጠሮ ነበር ማለት ያስደፍራል። በአንድ ጎኑ ደስታን በሌላው ጎኑ ደግሞ ስጋትን። ስፖርቱ ቀዳሚ የመዝናኛ አማራጭ እንደመሆኑ ደስታን ሲፈጥር፤ ከጨዋነት ደንብ መራቁ ትዝ ሲለው ደግሞ ስጋት ፈጥሮበታል።የስፖርት ቤተሰቡ ለዚህም ማነጣጠሪያ ያደረገው የ2010 ዓ.ም የውድድር ዓመትን ነበር። አምና የሊጉ ስፖርታዊ ጨዋነት ገጽታው በእጅጉ አሳፋሪና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቸ ወደ ፀብ ማዘውተሪያነት የተለወጡበት ነበር። ደጋፊ በሜዳው ደብዳቢ፣ ከሜዳው ውጪ ተደብዳቢ የሆነበት ትዕይንትን ሲያስመለክት፣ ዳኞች በቡድን መሪ ሜዳላይ እየተሳደዱ ሲደባደቡ፣ በደጋፊ ስድብ፣ ዛቻና ድብደባን ሲቀበሉ በአደባባይ ያስመለከተ ነበር። በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ በተከናወነው ፕሪሚየር ሊጉ በችግሩ ሲቃ በጽኑ ሲቃትት ታዝበናል። በተለይ ደግሞ እግር ኳሱ ብሔር ተኮር መልክን የመያዙ ሁኔታ የውድድር ዓመቱን አስከፊ ገጽታን እንዲላበስ አድርገውታል። ከትናንት ጥፋት በተሻገረ ስጋት የተጀመረው ሊጉ የእግር ኳስ ባህሪ ከስታዲየም የተሳደደበት፣ ስፖርት ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለወንድማማችነት ………»ይሉት አለም ዓቀፍ እሳቤ ከየስታዲየሙ እየታደነ ተገድሎ የተቀበረበት ጊዜ ነበር። ክለቦች የማንነት ማግነኛ እና የራስ ኩራት መገለጫ መድረኮች በመሆን ክለብ ተኮር ሳይሆን ብሄር ተኮር ግጭቶችን በበርካታ ስታዲየሞች ተስተውለዋል። ከዳኝነት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር በዳኞች አንደበት «ኳስን ሳይሆን ብሄርን መዳኘት ነው ያቃተን» እስከመባል ተደርሷል። የብሄራዊ ፌዴሬሽን የሚወስዳቸው የዲሲፕሊን እርምጃዎች የሚቀበል ክለብ ጠፋ። «በብሔሬ ምክንያት ለቅጣት ተዳረኩ» ይሉት ምክንያት ሲቀርቡ ታዘብን። በሽንፈቱ የሚደፋው አንገት ማንነትን ይዞ ዝቅ ማለትን፣ መብሰልሰልን፣ መቆዘምን ያመጣ ነበር። በእግር ኳሱ ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰጡት አጉል ትንታኔዎች፣ ትችቶች፣ በጨዋታ ድልና ሽንፈት የሚንፀባረቁ ስሜቶች ከእግር ኳሱ የመነጩ ናቸው ለማለት አዳጋች ነበሩ። ጩኸቶች ያ አብዲ ኢሌ እንዳለው ‹‹ለቅሶው ከፍየሏ በላይ ነው ሲል በአንድ መድረክ ላይ የተናገራትን አባባል ትዝ የሚያስብል ነበር።ስፖርቱ ውስጥ ዘው ብሎ የገባው ፖለቲካው የእግር ኳስን ሽንፈት ሆነ ድል በእጅጉ አጋነነው። የደጋፊዎች መከፋትና መደሰት ወደር አልባነት ስንመለከት ይህ አይነቱ ጩኸት ከኳስ በላይ ነበር። አክቲቪስት ነን ባዮች ጭምር እግር ኳሱ ላይ ትንታኔ ሲሰጡ ስንመለከት ደግሞ ስፖርቱ ተጠልፏል ወደሚል ድምዳሜ ያደርሳል። ኳሱ በአየር ተሞልቶ እንደሚንከባለለው ሁሉ፤ ደጋፊው በፖለቲካ አጀንዳዎች ተሞልተው መነሁለላቸውን ለመታዘብ ያስቻለን ነበር። ስፖርቱ ላይ የሚሰነዘሩት አጉራ ዘለል ትችቶች እውነት ከስፖርቱ ስሜት በመነሳት? ወይስ እንደ አባባሉ ጩኸቶቹ ከፍየሏ በላይ ነበርን ? ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት እውነትን መጋፈጥ ያስፈልጋል።የእግር ኳሱን በሰሜን እና በደቡብ ክለቦች መካከል የነበሩትን በርካታ ሁነቶች ዘወር ብለን በማሳያነት መመልከቱ ሃሳብን ያጠናክራል። በመጀመሪያ ወደ ሰሜን በመጓዝ የአማራ ክልልና ትግራይ ክልል ክለቦች እርስ በእርስ በተገናኙባቸው አጋጣሚዎቸ የነበሩ ክስተቶችን እንደማሳያ ብናነሳ ይሄንኑ ምስል ይሰጡናል። በሊጉ 23ኛ ሳምንት በመቐለ ከተማ በሚገኘው ትግራይ አለም ዓቀፍ ስታዲየም በደደቢት እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ አካሂደዋል። በዚህ የጨዋታ ክዋኔ ወቅት የነበረው ሁኔታ በሁለቱ ክልል ክለቦች መካከል ያለውን ውጥረት በግልጽ ያስመለከተ ነበር። በተመሳሳይ በባህር ዳር ስታዲየም ስሁል ሽረ ከባሕር ዳር ከተማ በነበረው ጨዋታ የነበረውን ሁኔታ በእጅጉ የሚያስተዛዝብና እግር ኳሱ በብሄር ጥላ ውስጥ እየቧቸረ የመሆኑን እውነታ አመላክቶ አልፏል። ስፖርቱ በብሄርተኝነት ቀንበር ውስጥ የመውደቁን እሳቤ የሚያጠናክርልን ሌላው ክስተት በ30 ኛው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በፋሲል ከነማ እና ስዑል ሽረ ጨዋታ ነው። ለሻምፒዮናነት ከመቐለ ሰባ እንደርታ እኩል እድልን ይዘው ስዑል ሽሬን የገጠሙት ፋሲሎች በደጋፊዎች ከፍተኛ የሆነ ጫና ሲደርስባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። ከስዑል ሽረ ደጋፊዎች በኩል የነበረው ጥቃትና ጫና የሻምፒዮናነት እድልን እንዳሳጣቸው በቁጭት በክለቡ ማህበራዊ ገጽ አስታውቀዋል። ፋሲል ከነማ በዘንድሮውም ሆነ በቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ ትግራይ ክልል ሄዶ እንደማይጫወት እስከ ማስታወቅ ደርሷል። በማሳያነት የቀረቡት እነዚህ ክስተቶችን ስናሰላስል ስፖርቱ በሃገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ ተጠልፎ መውደቁንና ይሄንኑ ዳና እየተከተለ ስለመሄዱ ያረጋግጥልናል። በሁለቱ ክልሎች መካከል በተለይ ከባለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ያለው ውጥረት ስናስብ እውነታውን እናገኘዋለን።በሁለቱ ክልሎች መካከል በተለይ ከባለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ውጥረት መኖሩ ሃቅ ነው። በአመራሮች መካከል ያለው መፋጠጥ የወለደው ውጥረት በስፖርቱ ሳይቀር የተንጸባረቀ ነበር። በዚህም ምክንያት የሁለቱ ክልል ክለቦች ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በገለልተኛ ሜዳ ሲጫወቱ መቆየታቸው። የሁኔታው አሳሳቢነት በዘንድሮው የውድድር ዓመት የተሸጋገረ ሲሆን፤ ክለቦቹ እርስ በእርስ የሚያደረጉትን ጨዋታ በሜዳቸው ያደርጉ ዘንድ መግባባት ለመፍጠር ብዙ ርቀት አስፈልጓል። በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እና በመንግስት በኩል በተሰራው የማቀራረብ ስራ ፖለቲካዊ መፍትሄ በመስጠት በሜዳቸው ጨዋታዎች ማከናወን ችለዋል።ከሰሜን ወደ ደቡብ ክለቦች ስናቀና በውድድር ዓመቱ የእግር ኳሱ ጉዞ በእጅጉ አሳዛኝና ከስፖርት አውድ ውጪ መሆኑን ያመላክተናል። በክልሉ የሚገኙ የወላይታ ዲቻ፣ ሲዳማ ቡና፣ ሃዋሳና ደቡብ ፖሊስ ደጋፊዎች የስታዲየም ውሎን እናገኛለን። በወላይታ ዲቻ እና የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች መካከል የነበሩት መፋጠጦችና ከእግር ኳስ ስሜት በላይ የሆኑ ድርጊቶች በግልጽ ተስተውለዋል። በሃዋሳና ሲዳማ ቡና ደጋፊዎቸ መካከል፣ በደቡብ ፖሊስና በሲዳማ ቡና ደጋፊዎች መካከል የነበሩትን ውጥረቶች በሰሜን ብቻ ሳይሆን በደቡብ ሳይቀር ያለውን ውጥረት ያመላክተናል። ለዚህም በፕሪሚየር ሊጉ በ21ኛ ሳምንት የነበረውን ሁነት ማንሳቱ ለዚህ እንደ ማሳያ ይሆናል።ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ.ም በሐዋሳ ስታዲየም ወላይታ ድቻና ደቡብ ፖሊስ በነበራቸው በዚህ ጨዋታ የሁለቱ ክለብ ደጋፊች ወደ ጸብ ለማምራት የጨዋታውን መጀመር እራሱ አልጠበቁም ነበር። ስፖርታዊ መሰረት ባልነበረው መልኩ ግጭት መፈጠሩ ጨዋታውን ወደ ሌላ ጊዜና በዝግ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲካሄድ እስከመወሰን ነበር የተደረሰው። በደቡብም እግር ኳሱ መሰረቱን አጥቶ ፖለቲካዊ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ሲሆን ታዝበናል። የ2011 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ ጉዞ ከስፖርት አውድ ውጪ በሆነ መልኩ ፖለቲካን የማራመጃ ዋነኛ መሳሪያ ወደመሆን የተሸጋገረ ጭምር እንደነበር ወደ አዲስ አበባ መለስ ብለን እንመልከት። በኘሪምየር ሊጉ 27ኛ ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተከናወነው የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ ሰባ እንደርታ ጨዋታ የዚሁ ክስተት ባለቤት ነበር። ጨዋታው በብዙ ስጋት ታጅቦ የተጀመረው ስፖርታዊ ጨዋነት በነገሰበት መልኩ በአቻ ውጤት መጠናቀቅ ነበር የቻለው። ከጨዋታው በኃላ የነበረው ሁኔታ ግን በእጅጉ አንገት ያስደፋ ነበር። በተለይ ከመቐለ ሰባ እንደርታ በኩል የነበረው ድርጊት ብዙዎችን አሳዝኗል። ጨዋታው ሲጠናቀቅ የመቐለ ሰባ እንደርታ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ተጫዋቾቹን ሰብስቦ ፑሽ አፕ ያሰራበት ሁናቴ በእርግጥም ምን ይሉት ፌዝ ነው።በስፖርታዊ ጨዋነት ነግሶ ቢጠናቀቅም ድርጊቱን ተከትሎ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ድባብ ጭምር የረበሸ ሆኖ አልፏል።ከአሰልጣኙ ትዕዛዝ የተሻገረው የተጫዋቾቹ ተግባር በዕርግጥም ከንፈርን መጥጦ ከማለፍ ውጪ ምን ማለት የሚያስችል ነበር? እግር ኳስ ከፖለቲካ፣ ከኃይማኖትና ከዘር የፀዳ መሆን እንዳለበት የሚያስረዳው ዓለም አቀፍ መርኅ አለ። በኢትዮጵያ እግር ኳስ የዘንድሮው የውድድር ዓመት የነበረው ገጽታ ከዚህ ፍጹም የራቀ እንደመሆኑ የችግሩ ዳፋ ሃገሪቷን ሊያሳጣትና ሊያስቀጣት እንደሚችል የታሰበ አይመስልም ነበር። ምናልባትም «አላያችሁንም እንጂ ያላየነው የለም» እንዲሉ አበው መቼም በ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አላዩትም እንጂ ስፖርትና ፖለቲካ ፍቅር ሲሰሩ ቆይተዋል።ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበር ስፖርትና ፖለቲካ ለየቅል እንደሆኑና ፖለቲካው ስፖርቱ ውስጥ ገብቶ ቢገኝ ከባድ ቅጣት እንደሚጣል በህግ ደረጃ አስቀምጦታል። ታዲያ የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁኔታ «አላያችሁንም እንጂ ያላየነው የለም» በመሆኑ እንጂ ፊፋ ከባድ ቅጣት ሊያስተላልፍ እንደሚችል ማሰቡ አይከፋም። በ2011 ዓ.ም የውድድር ዘመን የነበረው ገጽታ አሳሳቢነቱ ቤተ መንግስት ድረስ አንኳኩቶ መግባቱ ልብ ይሏል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ የ2011 ዓ ም የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት «በአብዛኛው መንግሥት በሚበጅተው በጀት የሚተዳደሩ ክለቦች፣ ያውም ውጤት ሳይኖራቸውና በስፖርቱ ሌሎች አገሮች የሚያሳዩትን ሙያዊ እንቅስቃሴ ሳያሳዩ ለረብ የለሽ የዘር ፖለቲካ ማቀንቀኛነት ውለዋል። ስፖርቱ ዓለም አቀፋዊ የሆነ መርህና ሙያዊ ዲሲፕሊን ቢኖረውም ያንን ጠብቆ እየሄደ አይደለም፡፡ ስታዲዮሞች በኳስ ቴክኒክና ታክቲክ ያበዱ ታዳጊ ወጣቶች የሚስተዋልባቸው መሆን ተስኗቸዋል» ሲሉ የችግሩ አሳሳቢነት እርሳቸውን ጭምር ያሰጋ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡ ዶክተር አብይ ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አካል /ፊፋ/ ሳይቀር ዕርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል ጭምር በመግለጽ ነበር አካሄዱ አለም ዓቀፋዊ መዘዝን ይዞ እንደሚመጣ ያመላከቱት። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቁጭት ንግግር ሆነ በውድድር ዓመቱ የነበረው ገጽታ በብዙ መልኩ አክሳሪና አሳፋሪ የመሆኑን እውነታንም ጭምር በተጨባጭ ያስረዳል። የአምናው የፕሪምየር ሊግ «ዋንጫ» የት እንደሚገኝ ያውቃሉ? ሲል ሶከር ኢትዮጵያ ያወጣውን ዘገባ ሳስታውስ «ለዚህ ነበር በሬዬን ያረድኩት» የሚለው የሃገሬን ተረት አሰብኩት። የሶከር ዘገባ እንዲህ ይነበባል። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሀገሪቱ ከፍተኛው ውድድር ቢሆንም የጨዋታዎቹ እና በዙርያው የሚገኙት ነገሮች የወረደ የጥራት ደረጃ፣ ለአሸናፊው የሚበረከተው ሽልማት እና ቻምፒዮን በመሆኑ የሚያገኛቸው የፋይናንስ እና ሌሎች ጥቅሞች በውድድር ዓመቱ ከተጫዋቾች ዝውውር ለደመወዝ፣ አስተዳደራዊ ወጪዎች እና ለመሳሰሉት ከሚያፈሱት ገንዘብ ጋር በእጅጉ የማይመጣጠን ነው። የሚበረከተው ዋንጫም “ተራ” በሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ከስፖርት ሱቆች ተገዝቶ የሚሰጥ፣ የተለየ መለያ የሌለው እና በየዓመቱ የሚቀያየር በመሆኑ ዋንጫውን ትርጉም የለሽ ያደርገዋል። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ቡድኖች የሚያስመዘግቧቸው ስኬቶች ከዕለት ደስታ ያለፈ ትርጉም እንዳይሰጣቸው ሲያደርጋቸው እያስተዋልን እንገኛለን። ለዚህም እንደ ዓብነት የምንመለከተው የአምናው የፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ጅማ አባ ጅፋር የተበረከተለት ዋንጫን ነው። ዋንጫው በክለቡ ፅህፈት ቤት የሚገኝ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። ይልቁንም በሐምሌ ወር አጋማሽ ባዘጋጁት አንድ ዝግጅት ላይ በጅማ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል ተረስቶ እና አስታዋሽ አጥቶ በፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) ተቀምጦ ይገኛል። የሆቴሉ ሰራተኞች ሁኔታውን ተመልክተው ክለቡ ዋንጫውን እንዲወስድ ቢጠይቁም እስካሁን ወሳጅ አጥቶ በሆቴሉ እንደሚገኝ ታውቋል ሲል አስነብቧል። የዘንድሮው ሻምፒዮና መቐለ ሰባ እንደርታ ቢሆንም ሲያጠናቅቅ ከብሄራዊ ፌዴሬሽኑ የተበረከተለት ሽልማት ከ150 ሺህ ብር የማይበልጥ ሲሆን፤ የክለቡ ወጪ ደግሞ እስከ 40 ሚሊየን ብር ገደማ እንዲሚደርስ ይጠበቃል። ታዲያ አሁን ነው ‹‹ለዚህ ነው በሬዬን ያረድኩት?›› ማለት። ከየስፖርት ሜዳው ሳይጠፋ ድጋፉን የቸረው ደጋፊም የተፈነከትኩት፣ የተደበደብኩት፣ የወጣሁት፣ የወረድኩት …..ለዚሁ ነው እንዴ? ሲል መጠየቅ ቢችልም «ነበር» ሆኖ አልፏል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 17/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14698
08b74ceebf383d93188bbaf85f3032c1
5c9272056bcffabd716d07dfe233b8ad
በስፖርት ፖሊሲውና በሰራተኛው አዋጅ መካከል የተበጠሰው ሰንሰለት
ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የአንድ ህብረተሰብን አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጤንነትን በመጠበቅ ረገድ ፋይዳው ትልቅ ነው። ይህ ምርታማነትን የሚያጎለብት፥ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና ያለው የዜጎች መሰረታዊ መብት እየሆነም መጥቷል። ይህን ልብ ያለው የ1990 ዓ.ም የተቀረፀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስፖርት ፖሊሲ በየደረጃው መላውን ህብረተሰብ በስፖርት በማሳተፍ ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት ቀዳሚ አላማው አድርጎታል።ለዚህም መላው ህብረተሰብ በሚኖርበት፥ በሚሰራበት እና በሚማርበት አካባቢ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በየደረጃው ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጧል። የዚህን ፖሊሲ አቅጣጫ ስኬታማ በሆነ መልኩ ተፈፃሚ ለማድረግ የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን የመሳሰሉ ፅንሰ ሃሳቦች ለመጀመሪያ ጊዜ በ1996 ዓ.ም በወቅቱ በነበረው የኢፌዲሪ ስፖርት፤ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነበር የተጠነሰሰው።የኦሊምፒክና የመላ አፍሪካ ጨዋታዎችን መርህ መነሻ በማድረግ ህብረተሰቡን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በስፋት በማሳተፍ እና ተጠቃሚነቱን በማጎልበት የበርካታ ባህልና ትውፊቶች ባለቤት የሆኑ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በአንድ መድረክ ተገናኝተው የባህል እና ልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ታስቦ ፖሊሲው እንደተቀረፀ የመጀመሪያው የጥናት ሰነድ ላይ ተቀምጧል። ይህም አገሪቱ በምትከተለው የፌዴራሊዝም ስርዓት ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን በማጠናከር በጋራ መግባባት ላይ የተመሰረተ መተሳሰብ እና መቀራረብ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ታምኖበታል። ሆኖም እነዚህን መሰረታዊ አላማዎች መነሻ በማድረግ ከ1997 እስከ1998 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች እቅዱን መሬት ማውረድ አልተቻለም ነበር።ከ1998 ዓ.ም በፊት የነበረውን ጥናት መከለስ በማስፈለጉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም አገር አቀፍ የስፖርት ማህበራትን አስተያየቶች ባካተተ መልኩ የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን የመሳሰሉ የስፖርት መድረኮች 1999 ዓ.ም ተወለዱ። በወቅቱ በነበረው ጥናት መሰረትም ኢትዮጵያ በኦሊምፒክና መላ አፍሪካ ጨዋታዎች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች፤ እያንዳንዱ ስፖርት የሚገኝበት የእድገት ደረጃ እንዲሁም ክልሎች በእያንዳንዱ ስፖርት የመሳተፍ አቅማቸው ተፈትሾ መላ ኢትዮጵያ ጨዋታ በ17 የስፖርት አይነቶች እንዲካሄድ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ መረጃዎች ይጠቁማሉ።በኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አዘጋጅነት በርካታ ቁጥር ባለው ሰራተኛ መካከል የሚካሄዱት የበጋ ወራት፣የሜይ ዴይ መታሰቢያና አገር አቀፍ ውድድሮች ከመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ጋር ተመሳሳይነት ያለው ከመሆኑ በተጨማሪ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ማለት ይቻላል። ሠራተኛው በስፖርት ጤንነቱ የተጠበቀ ምርታማ ዜጋ እንዲሆን ከማስቻል በተጨማሪ ኢሠማኮ የሚያዘጋጃቸው የስፖርት መድረኮች ሠራተኛው «የእኔ ነው» የሚለው የመዝናኛ አማራጩ ጭምር ነው። በውድድሩ የሚካፈሉ በርካታ ድርጅትና ተቋማት በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሠራተኞቻቸው ያላቸውን ክህሎት አውጥተው በመጠቀም ለአገር ስፖርት እድገት የበኩላቸውን ድርሻ ከመውጣት አልፈው ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ የሚያገኙበትም ነው። ስፖርቱ ሠራተኛውን ከማቀራረብና ልምዱን እንዲለዋወጥ እድል ከመፍጠር ባሻገር በሠራተኛው መካከል ቤተሰባዊ ስሜት እንዲጎለብት የሚጫወተው ሚና ቀላል እንዳልሆነም ማየት ይቻላል።ኢሠማኮ በነዚህ ውድድሮች ‹‹መላው ህብረተሰብ በሚኖርበት፥ በሚሰራበት እና በሚማርበት አካባቢ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በየደረጃው ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር›› የሚለውን አገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲ ለማስፈፀም የሚያደርገው ጥረት በመልካም ጎኑ የሚነሳ ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ ከመሳተፍ አንስቶ ሰራተኛው በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማዘውተር ድርጅቶችና ተቋማት ለሰራተኛው ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል ማለት ግን አይቻልም። አገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲው ሰራተኛው በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እያከናወነ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን በግልፅ ቢያስቀምጥም በሰራተኛና አሰሪ አዋጁ የተደገፈ ባለመሆኑ ክፍተቶች ይታያሉ። ይህም ሰራተኛው በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ እንደ አንድ መብቱ ወስዶ ከመጠየቅ ይልቅ የአሰሪውን በጎ ፍቃድ ለመጠበቅ እያደረገው እንደሚገኝ መገንዘብ ይቻላል።በርካታ ተቋማት የመንግስትም ይሁኑ የግል ሰራተኛው በስፖርት እንዲደራጅ የማድረግ ባህል የላቸውም። ግፊት ሲያደርጉም አይታዩም። ከዚህ ይልቅ ሰራተኛው በስፖርታዊ ውድድሮች ተሳታፊ ለመሆንና እንቅስቃሴዎችን በሚሰሩበት አካባቢ ለማከናወን የሚያነሱት ጥያቄ ከበጀት ጋር በተያያዘ ወደ ጎን ሲገፋ ማስተዋል የተለመደ ነው። ኢሠማኮ በሚያዘጋጃቸው የተለያዩ ውድድሮች የሚሳተፉ ድርጅትና ተቋማትን ብንመለከት አብዛኞቹ ወጥ በሆነ መልኩ ተሳታፊ አይደሉም። በዚህኛው ዓመት ተሳታፊ የሆኑ ተቋማት በቀጣዩ ዓመት ተሳታፊ ስለመሆናቸው ምንም ማረጋገጫ የለም። ይህ ማለት ሰራተኛው አሰሪው ለስፖርት ባለው መልካም አመለካከት በስፖርቱ ይሳተፋል እንጂ መብቱን ተጠቅሞ ወደ ስፖርቱ አይመጣም። ለዚህም በአንዳንድ ተቋማት ለስፖርት መልካም አመለካከት ያላቸው አሰሪዎች ሲቀየሩና ለስፖርት መልካም አመለካከት በሌላቸው ሲተኩ ሰራተኛው ከውድድሮች የሚቀርበት በርካታ አጋጣሚዎች እንዳሉ መጥቀስ ይቻላል።ሰራተኛው በሰራተኞች ስፖርት ከመሳተፍ ባሻገር በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርግ ምንም አይነት ምቹ ሁኔታ እንዳልተፈጠረም ማየት ይቻላል። በሰራተኞች ስፖርት ዘወትር ተሳታፊ የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እንዲሁም የግል ተቋማትና ድርጅቶችን እንኳን ብንመለከት ስንቶቹ ናቸው በሚሰሩበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያዘወትሩ ምቹ ሁኔታ የተፈጠረላቸው? ብለን ብንጠይቅ ምቹ ሁኔታ እንዳለ ምሎ የሚናገር አይኖርም።በተለይም የመንግስት የልማት ድርጅት ያልሆኑ ተቋማት ሰራተኛውን ወደ ስፖርቱ በማምጣትም ይሁን በሚሰራበት አካባቢ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያዘወትር በማድረግ ረገድ ምንም አይነት ምቹ ሁኔታና ትኩረት እንዳልሰጡት ማስተዋል ይቻላል። ለዚህም በኢሠማኮ ውድድሮች ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ውጪ ያሉ ተቋማት ሲሳተፉ አለመታየታቸውን መገንዘብ ይቻላል።የኢሠማኮ ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊና የስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፍሰሃፂዮን ቢያድግልኝ፣ የመንግስት ሰራተኞች (civic servant) በኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ስር መጠቃለል እንደሚኖርበት ይናገራሉ። የመንግስት ሰራተኛው በኢሠማኮ ስር አለመተዳደሩ በሰራተኞች ስፖርት ላይ የመንግስት ሰራተኞች ላለመሳተፋቸው ዋነኛው ምክንያት መሆኑን የሚናገሩት አቶ ፍሰሃፂዮን ከስፖርቱ ባሻገርም የመንግስት ሰራተኞች መብትና ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ በኢሰማኮ ስር መታቀፍ አለባቸው የሚል አቋም አላቸው። ይህንንም ጥያቄ ኢሰማኮ ለቀድሞዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ለአቶ መለስ ዜናዊና ለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ማቅረቡን ያስታውሳሉ። ከሰራተኛ መብት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ህግና ደንቦች እንደ አገሪቱ ህገመንግስት እንደሚታዩ የሚጠቁሙት አቶ ፍሰሃፂዮን ሰራተኛው የመንግስትም ይሁን የግል መደራጀት ሰብዓዊ መብቱም ጭምር እንደሆነ ያብራራሉ። ሰራተኛውን በተመለከተ በአገራችን ሁለት አይነት አዋጆች አሉ፣ አንደኛው የመንግስት ሰራተኞችን የተመለከተው 164 አዋጅ ሲሆን ሌላኛው የመንግስት የልማት ድርጅቶችና የግል ድርጅቶች የሚተዳደሩበት 377/96 ነው። በኢሰማኮ ስር የሚተዳደረው በሁለተኛው አዋጅ ስር ያለው ሲሆን የመጀመሪያው ወይም የመንግስት ሰራተኛውን የሚመለከተውን አዋጅ ኢሰማኮ አያስተዳድረውም። ይህም የመንግስት ሰራተኛውን ኢሰማኮ ወደ ራሱ ስፖርታዊ መድረኮች ለማምጣት አዋጁ እንደሚገድበው ነው አቶ ፍሰሃፂዮን የሚናገሩት። ‹‹ሰራተኛ ሰራተኛ ነው፣ይሄ አዋጅ ተነስቶ በሌላ አዋጅ መተካት ይኖርበታል›› በማለትም ይናገራሉ። ኢሰማኮም ለዚህ ከመንግስት ጋር በቅርበት እየተወያየ እንደሚገኝ ያስቀምጣሉ። የአሰሪና ሰራተኛው አዋጅ ከብሔራዊ የስፖርት ፖሊሲው ጋር ተጣጥሞ እንዲጓዝ ለማድረግ አዋጁ መከለስ እንደሚኖርበት ሊሰመርበት ይገባል። የአሰሪና ሰራተኛው አዋጅ ሰራተኛው በሚሰራበት አካባቢ የስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርግ በሂደት አስገዳጅ ሁኔታዎችን ማስቀመጥ ካልቻለ የመንግስትም ይሁን የግል ተቋማት ሰራተኞች ወደ ስፖርቱ ለመምጣት ዘወትር የአሰሪውን በጎ ፍቃድ መጠበቃቸው የሚቀር አይሆንም። አዋጁ ሲከለስ እያንዳንዱ አሰሪ ለሰራተኛው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር ባሻገር ኢሰማኮ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች የራሱን የሆነ በጀት እንዲይዝ ማድረግም ይኖርበታል። ኢሰማኮም ሰራተኞች ወደ ስፖርቱ እንዲመጡና የተሳታፊዎቹን ቁጥር ለማሳደግ ከሚያደርገው ጥረት ጋር አያይዞ ይህን ጉዳይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሀምሌ 20/2011ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14820
6f6e91185143d92e7e4cffce88a8376e
19d42af9c79a7cd0f587a953ce23d4ac
አትሌት ሐጎስ በዳይመንድ ሊግ ውድድር አሸናፊ ሆነ
አስረኛው ዙር የ2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድር በሳምንቱ መጨረሻ በእንግሊዝ ለንደን በተለያዩ ርቀቶች ሲካሄድ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት በአምስት ሺህ ሜትር ውድድር አሸናፊ ሆኗል። አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት የአምስት ሺህ ሜትር ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀበት ሰዓትም 13 ደቂቃ ከ1 ሴኮንድ ከ86 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ አትሌት ሐጎስ በውድድሩ ከኖርዌያዊው አትሌት ጃኮብ ኢንብሪግስተን ብርቱ ፉክክር የገጠመው ሲሆን፣ በውድድሩ የመጨረሻ 250 ሜትሮች ላይ ፍጥነቱን በመጨመር ቀዳሚ ሊሆን መቻሉም ታውቃል፡፡ ሃጎስን ተከትሎ ኖርዌያዊው አትሌት ጃኮብ ኢንብሪግስተን 13 ደቂቃ ከ1 ሴኮንድ ከ86 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃን ሲገባ ኬኒያዊው አትሌት ኒኮላስ ክሚሊ 13 ደቂቃ ከ5 ሴኮንድ ከ45 ማይክሮ ሴኮንድ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡ አትሌት ሃጎስ ከሁለት ሳምንት በፊት በሲውዘርላንድ በተካሄደው የአምስት ሺ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር 4ሺ 600 ሜትሮችን እንደሮጠ የመጨረሻ መስመር የደረሰ መስሎት በድል አድራጊነት እጁን እያነሳ ሲጨፍር ተቀድሞ አስረኛ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ በሴቶች መካከል የተካሄደው የአምስት ሺ ሜትር ውድድር የኬንያውያን የበላይነት ታይቶበታል፡፡ ሄለን ኦኒሪ 14 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ36 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆናለች፡፡ አግኒስ ጂብት 14 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ68 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ ስትሆን ኢትዮጵያዊቷና ለኔዘርላድስ የምትሮጠው ሲፋን ሃሰን በሦስተኛነት ውድድሩን አጠናቃለች። አትሌቷ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም 14 ደቂቃ ከ22ሴኮንድ ከ12 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኖ ተመዝገቧልአትሌት ሐጎስ በዳይመንድ ሊግ ወድድር አሸናፊ ሆነ ኢትዮጰያዊዋ አትሌት ለተሰንበት ግደይ አስረኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች። በአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ሰሜን አሜሪካ በሚገኙ 14 ከተሞች የሚካሄደው የ2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለአስራ አንደኛ ጊዜ በነሐሴ ወር አጋማሸ በእንግሊዝ በርሚንገሃም ከተማ ይካሄዳል። ውድድሩ በቀጣዩ ጳጉሜን መጀመሪያ በቤልጂየም መዲና ብራሰልስ ላይ ይጠናቀቃል፡፡የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የዘንድሮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በአጠቃላይ የስምንት ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ማዘጋጀቱ ይታወሳል። በሁለቱም ጾታዎች በተመሳሳይ በ16 የተለያዩ የውድድር አይነቶች በእያንዳንዱ ርቀት የአጠቃላይ አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች የ50 ሺህ ዶላር እና የዳይመንድ ሽልማት ያገኛል። ከዚህም በተጓዳኝ በእያንዳንዱ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ የ100 ሺህ ዶላር ሽልማትም የተዘጋጀ ሲሆን በተጨማሪም በእያንዳንዱ ርቀት አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች ከመስከረም 17 እስከ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም በኳታር መዲና ዶሃ ለሚካሄደው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለማጣሪያ የሚያልፉ ይሆናል።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 16/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14615
d9142577955dbd3a29cc42e525abc457
38eee9aef4d5d06c24d2183da6dc556c
“የትግራይ ህዝብ በልጆቹ እና በልጅ ልጆቹ እምነት ሊኖረው ይገባል” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
አዲስ አበባ፦ የትግራይ ህዝብ በልጆቹና በልጅ ልጆቹ እምነት ሊኖረው እንደሚገባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። የትግራይን ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ ከሃምሳ እና ስድሳ ዓመት በፊት በነበረ ሃሳብ መምራት እንደማይቻልም አመልክተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፤የትግራይ ህዝብ በልጆቹና በልጅ ልጆቹ እምነት ሊኖረው እንደሚገባና ህዝቡ ለወቅቱ የሚመጥኑ የተማሩ ወጣት ልጆች እንዳሉት አስታውቀዋል ። የራስን ህዝብ በመደብ ከፋፍለህ ግማሹ የኔ ነው፤ ግማሹ ተከፋይ ነው ፣ሌላው ባንዳ ነው እያልክ መምራት የሚቻል አይመስለኝም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይሄ ከፋፋይ ሃሳብ ትላንት ሰርቶ ሊሆን ይችላል ዛሬ ግን ይሰራል ብዬ አላስብም ብለዋል። በልጆችዋ የማትተማመንና በአዲስ ትውልድ የማትመራ ትግራይ ልትቀየር፣ ልትለወጥ፣ ልትለማ ካሉባት ችግሮችዋ ልትወጣ እንደማትችል ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ሰው በሆነ ግዜ ሃሳብ ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ያቺ አቅም ሁሌ ቁጭ ብላ አትጠብቅም፤ አዲስ ትውልድ ሲመጣ በአዲሱ ትውልድ እምነት ከሌለ፣ እየታገዘ ካልበቃ በቀጣይነት ልማት ማምጣት እንደማይቻል አመልክተዋል ። የትናንቱን ትግል የመሩ ባቶችም በትላንት ችሎታቸው እና ማንነታቸው የዛሬ ፍላጎት መመለስ እንደማይቻል አውቀው፤ ትላንት የራሳቸውን ታሪክ እንደሰሩ ሁሉ፣ የዛሬ ትውልድ ወጣቱም የራሱን ታሪክ መስራት እንደሚፈልግ ተረድተው፣ ልጆቻቸው እና ልጅ ልጆቻቸው ከነሱ በተሻለ የተማሩና አቅም የፈጠሩ መሆናቸውን አምነው አዲሱን ምዕራፍ ለአዲሱ ትውልድ ሊሰጡት እንደሚገባ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ምሰረታ ጀምሮ ወሳኝ ቦታ የነበረው ትልቅ ህዝብ ነው፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ንቁ ተሳትፎ ያላደረገበት ግዜ የለም፤ ለወደፊትም አይኖርም የሚል እምነት አለኝ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ በለውጥ ግዜ ችግር መፈጠሩ የለውጥ ባህሪ ነው። እናት ምጥ ችላ ልጅ እንደምትወልደው ሁሉ እዚህም ትንሽ መታገስ ጥሩ ነው። በቅርቡ ችግሮቹ ሁሉ ቀስ በቀስ ይፈታሉ ብዬ አምናለሁ ብለዋል። “በህወሓት እና በብልፅግና ልዩነት እንዳለ ግልጽ ነው፤ ሁሉም ሰውም የሚያውቀው የአደባባይ ሃቅ ነው። በፌዴራል እና በክልል ያለው እሰጥ አገባ በትግራይ ተጨማሪ ችግር መፍጠሩ ግልጽ ነው፣ ምክንያቱም አብሮ ተነጋግሮ የማይሰራ ከሆነ ችግሮች እንደሚፈጠሩ ግልጽ ነው” ብለዋል። እንደብልጽግና ተፈጥረው ያሉ የሃሳብ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ፍላጎት አለን። በህወሓትም በኩል ነገሮች በውይይት እንዲፈታ የሚፈልጉ አመራሮች እንዳሉ እናውቃለን፤ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፣ጥቂቶች ከህወሓት ጋር ያሉ ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ ችግሩን መፍታት የሚፈልጉም ክፍተቱን ለማስፋት የሚሰሩ እንዳሉ ለሁሉም ግልጽ እንደሆነ አመልክተዋል። የትግራይ ህዝብ ወደ ጦርነት እንዲገባ እየገፋፉ ያሉ ሰዎች ተው ሊባሉና ሊመከሩ ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ይህን ለማድረግ የትግራይ ህዝብ የአቅም ችግር እንደሌለው አውቃለሁ፤ ሰላም የሚፈልጉት መሪዎችን መደገፍ አለበት ፤ ህዝቡ ይህን ካደረገ አብዛኛው ችግር ይፈታል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል ። በህወሓት እና በብልጽግና መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በማስፋት እና በዚህ ክፍተት የሚኖሩ ሃይሎችም እንዳሉ ጠቁመዋል ። ትግራይን ለመጉዳት የሚባል ሃሳብ በኔ በኩል በፍጹም የለም። በመንግሥት ውስጥ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ያለው ሰው ካለ ችግር ውስጥ ነው ያለው ማለት ነው፤ ሊታገዝ፣ ሊገመገም ራሱም ባህሪውም በአግባቡ ሊታይ ይገባዋል ብዬ አምናለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፤ ከዚህ ውጪ ያለውን የፖለቲካ ጫወታ ህዝብን ጨምሮ ማየት ልክ እንዳልሆነም አመልክተዋል። የምርጫ አስፈላጊነት እና ግዴታ መደረግ እንዳለበት ልዩነት ያለን አይመስለኝም። ምርጫ ለማድረግ ቀጠሮ ይዘን እየተዘጋጀን እያለ ድንገት ሳናስበው ኮቪድ 19 በሽታ መጣ፤ የፌዴሬሽን ምክርቤት ሁሉም ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች እንዲቀጥሉ ወስኗል። ይሄ ለብልጽግና ይሰራል፣ ለህወሓትም ይሰራል ብለዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ምርጫ የማይቀር ነገር ሁኖ እያለ የትግራይ ክልል መንግሥት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር በጀት መደቦ ምርጫ አደርጋለሁ ማለቱ የሚገርም ነው። በሌላ በኩል ኮቪድ 19 እያለ ምርጫ እናደርጋለን ማለት ኮቪድ19 ለትግራይ ስጋት አይደለም ማለት ነው፣ ትግራይ ላይ ሰው በኮረና አይያዝም ማለት ነው? ዘመናዊ ሆስፒታል መድሃኒት አለን ማለት ነው? ሎጂኩን ለመረዳት ከባድ ነው። እንደዚህ አይነት ጥያቄ እንድታነሳ ያደርግሃል፤ ኮረና አይደለም ለኢትዮጵያ ይቅርና አሜሪካንን እንዴት እያደረጋት እንዳለ እያየን በትግራይ ላይ ችግር አይፈጥርም ማለት እንደማይቻል ተናግረዋል። ‹‹የትግራይ መንግሥት ሚሊዮኖች አውጥቶ ምርጫ አደርጋለሁ ከሚል ትግራይ ላይ የውሃ ችግር እንዳለ ይታወቃል ፣ ሁለት ሦስት የውሃ ጉድጓድ ለምን አያስቆፍርም ? ለምን አንድ ሆስፒታል አያሰራም? ብለህ እንድትጠይቅ ያስገድዳል። ለልማት በጀት አጠረን፣ ፌዴራል መንግሥት በጀት ከለከለን እያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር አውጥቶ ምርጫ ማካሄድ አለብን ማለቱ ይገርመኛል›› ብለዋል። “ህወሓት ምርጫ ይደረግ የሚለው ሌላ አማራጭ ላላቸው ሰዎች ማስረከብ ፈልጎ ነው እንዳይባል የተለየ ሃሳብ የያዙ ሰዎች ታፍነው ነው ያሉት፣ ራሱ ተመልሶ ለመምጣት ከሆነ ደሞ የፌዴሬሽን ምክርቤት እኮ ምርጫ እስኪደረግ ስልጣን ላይ እንዲቆይ ፈቅዶለታል፣ ትንሽ ግዜ ታግሶ ባገር ደረጃ ምርጫ ማድረግ ሲገባ በጀቱን ደግሞ ለውሃ ማስቆፈሪያ፣ ለሆስፒታል ማሰሪያ ቢጠቀሙበት ይሻል ነበር ብዬ አስባለሁ” ብለዋል። የፌዴራል መንግሥት በክልል ጉዳይ ላይ እጁን አስገብቶ አያውቅም ለወደፊቱም አያስገባም። ያሄን ስል ግን የፌዴራል መንግሥት ኃላፊነቱን አሳልፎ አይሰጥም ። በህገ መንግስቱ የተሰጠን የስልጣን ክፍፍል መኖሩ ሊረሳ አይገባም ፤ የትግራይ መጠቀም ለኢትዮጵያ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም፤ ለይቶ ትግራይን ማጥቃት የሚባል ሃሳብ የፌዴራል መንግሥትም የብልጽግና ፓርቲም እንዳልሆነ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በኢትዮ ኤርትራ ያለው ግንኙነት በሁለት ሃገራት ያለ ግንኙነት ስለሆነ ይሄ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ስራ እና ሃላፊነት ነው። አሁን ተገኝቶ ያለው ሰላም ለትግራይ ህዝብ ብቻ አይደለም የሚጠቅመው ለሁላችንም ነው የሚጠቅመው። የተጀመረውን ግንኙነት አጠናክረን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታችንንም ለማጠናከር እየሰራን ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ‹‹ማን ለማን ነው የሚዋጋው? ለምንድነው የፌዴራል መንግሥት ትግራይ ክልልን የሚወጋው? ይሄ የእብደት ንግግር ነው። ከተናጋሪው የደገመው ይብሳል፤ የፌዴራል መንግሥት የትግራይ ህዝብን ሊወጋ ነው ብሎ ማሰብ ምን አይነት ሃሳብ እንደሆነ አይገባኝም። አይደለም ከህዝባችን ጋር ከጎረቤት አገሮች ጋር ውግያ አንፈልግም እያልን እኮ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል። ጦርነት የሚፈልጉ ሰዎች ጦርነት ጦርነት ይላሉ፤ እንደ ዘፈን ጠዋትና ማታ የጦርነት ንግግር ሲናገሩ ትሰማለህ እና ራሳቸው የሚያስቡትን ነው እየነገሩን ያሉት። በዚህ ዘመን ጦርነት የሚያስነሳ ምክንያት አለ ብዬ አላምንም። በሁሉም በኩል አንዳንድ ወጣ ያሉ የፖለቲካ ጫዋታዎች ሊታዩ ይችላሉ ነገር ግን ወደ ውጊያ ሊያስኬድ የሚችል አይደለም፣ አይገባምም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራን መንግሥት ኢትዮጵያን ውጋ ብሎ ይጠራል ብሎ ማሰብ ሃጢያት ነው። እንዴት ብሎ ነው ህዝብን ውጋልኝ ብሎ የሚጠራው ? ይሄ በታሪካችን እንዳልታየ፤ ለወደፊትም እንደማይኖር አስታውቀዋል ። የኤርትራ መንግሥት በዚህ ግዜ ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ጋር ያላትን ችግር ለመፍታት እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት አመራሮች ውስጥ እንደነ ዶ/ር ደብረጽዮን ያሉ ሰዎች ልማት እና ሰላም ስለሚፈልጉ ሊደግፋቸው ይገባል የሚል እምነት አለኝ። እነ ዶ/ር ደብረጽዮን ከመጀመሪያው ጀምሮ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን ችግር በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ነበሩ ብለዋል። የትግራይ ህዝብ በተለይ ዶ/ር ደብረጽዮንን ሊያግዙት ይገባል ፣በዚህም አብዛኞቹ ችግሮች ይፈታሉ ብዬ አስባለሁ፤ በሌላ ጎን ደሞ ሰላም ለማይፈልጉ ሰዎች ተው የጥፋት መንገድ ነው ሊላቸው እንደሚገባም አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 22, 2012 በጋዜጣው ሪፖርተር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36242
58d565496e27f09485cd36cd7411b8ef
28d9d595d352b6fa0edd70a530641d07
ክልሉበአንድ ጀንበር ከ300 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን እንደሚተክል አስታወቀ
አዲስ አበባ፡- በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ጀንበር በአገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር እንዲቀር የተወሰነ ቢሆንም፤ የኦሮሚያ ክልል አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ ለመተግበር የሚያስችል ሁኔታዎችን መፍጠር በመቻሉ ክልሉ ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 304 ሚሊዮን ችግኞችን እንደሚተክል አስታወቀ፡፡ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም የሚካሄደውን 304 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል መርሃ ግብር አስመልክቶ የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በመግለጫው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ እየተካሄደ ባለው አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደ ክልል ሶስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እስካሁን ሁለት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በተካሄደው አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በክልሉም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ችግኞች የተተከሉት በአንድ ጀንበር በተካሄደ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው፤ ዘንድሮ ግን በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ይህ እንዲቀር መወሰኑን ተናግረዋል፡፡ ሆኖም በአንድ ጀንበር በርካታ ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብሩ እንዲቀር የተወሰነው በአገር አቀፍ ደረጃ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው፤ “እኛ ግን እንደ ክልል አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ ለመተግበር እና ተከላውን ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታን መፍጠር በመቻላችን ዛሬ ማለትም ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም 304 ሚሊዮን ቸግኞችን በአንድ ጀንበር የምንተክል ይሆናል” ብለዋል፡፡ እርሳቸውም እዚህ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት የክልሉ መንግሥት ከአባ ገዳዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከአርሶ አደሮች፣ ከሴቶች፣ ከወጣቶች፣ ከምሁራንና ከመንግሥት ሰራተኞች በአጠቃላይ በገጠርና በከተማ ከሚገኙ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሰፊ ውይይት ማካሄዱንም አመላክተዋል፡፡ ኃላፊው ከሕዝቡ ጋር በተደረገው ውይይት ህብረተሰቡ በአንድ ቦታ ላይ በብዛት ሲሰባሰብ በከፍተኛ ደረጃ ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሚሆን እንደ አምናው በአንድ ቦታ ላይ በብዛት ሳይሰባሰብ ሁሉንም የጥንቃቄ እርምጃዎች በአግባቡ በመተግበር፤ ሕብረተሰቡ በየቀበሌው በተለዩ አነስተኛ የችግኝ መትከያ ስፍራዎች እርቀቱን ጠብቆ እንዲተክል መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ በሚከናወን የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 304 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉ ይሆናል ብለዋል አቶ ዳባ፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 22/2012ይበል ካሳ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36252
7d237f8214cdbb9985b2cebba225ac84
22c7405c692fc68bf60da01f42f15f0a
ኦብነግ ከሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ጋር በሰላም ዙሪያ በጋራ ለመስራት መፈራረሙ ለክልሉ ፀጥታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ
አዲስ አበባ፤ በኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አወጪ ግንባርና በክልሉ መንግሥት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ ለክልሉ ሰላምና ፀጥታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ በደል በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ በቀደሙት ዓመታት ያለመረጋጋትና ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እንደነበረ አመልክተው፤ አሁን ግን የተሻለ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል፤ በኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና በክልሉ መንግሥት መካከል የተደረሰው ስምምነት ይህንኑ አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችላል። የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ጫካ በነበረበት ወቅት በክልሉ የነበረው ያለመረጋጋት አሁን ሙሉ ለሙሉ መቀረፉን ያስታወሱት አቶ አሊ፤ በአሁኑ ወቅት አንድነትን በማጠናከር፣ ፀጥታን በማስከበርና ሰላምን በማስፈን ዙሪያ የተደረሱ ስምምነቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።ስምምነቱ የሶማሌ ክልል በኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ ላይ እንደመገኘቱ ፤ የሀገር ውስጥ ሰላምን በማስከበር ከውጭ የሚመጣውን ጫና መቀነስ እንደሚያስችል አስረድተው፤ ሰላምን ከማስከበር ባሻገር የፀጥታ ስጋት በማይኖርበት በእንደዚህ ዓይነቱ ወቅት ወጣቶች በስራ ፈጠራ ያለምንም መስተጓጎል እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱንም ተናግረዋል።ቀደም ሲል የህዝቡ እንቅስቃሴ የተገደበ፤ በኅብረተሰቡም ዘንድ የነበረው የፀጥታ ስጋት ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ላይ ያ ችግር ተቀርፎ ክልሉ የተሻለ ሰላም ባለቤት ሆኗል፤ የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠልም በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።አቶ አሊ ቀደም ሲል አሳሳቢ የነበረው የሰላም መደፍረስ ስለተቀረፈና ክልሉ ለግብርና የተመቸ መሬት፤ በርካታ ወንዞች የሚፈሱበት፤ ምርታማ አካባቢ በመሆኑ የክልሉ ወጣቶችን በግብርና ዘርፍ በስፋት ለማሰማራት ታቅዷል ብለዋል ። አቶ አሊ ክልሉ የድንበር አከባቢ እንደመሆኑ ሰላም በተጠበቀ ቁጥር ህገወጥ የነበረውን የንግድ እንቅስቃሴ ህጋዊ በማድረግ ሀገሪቱንም ሆነ ክልሉን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን አብራርተዋል።ተቃዋሚና ገዥው ፓርቲ ለሰላም ቁጭ ብሎ ሲወያይ ይህ የመጀመሪያው ነው ያሉት አቶ አሊ ፣ አሁን አንድም ቦታ የጥይት ድምፅ መሰማት ቆሟል ብለዋል። በክልሉም ከፍተኛ የመልማት አቅም ያለው መሬት በመኖሩ ወደ ክልሉ መጥቶ የልማቱ አካል ለመሆን የሚፈልግ ወደ ክልሉ መጥቶ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ለዚህም ቀልጣፋ መስተንግዶ እንደሚጠብቃቸውም አስታውቀዋል ።የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር በመንግሥት በኩል ለንግግርና ለሰላም እየተወሰዱ ያሉ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አዎንታዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ከሐምሌ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 22/2012አስመረት ብስራት
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36250
d5f04f5ef38ba90e937bc7395c23619b
54ad75c9d11034700508e0db91b2d827
ብዙዎች የታገሉለት ዓላማ በጥቂቶች መጠለፉን የፈንቅል አመራር ገለጹ
አዲስ አበባ፡- የትግራይ ህዝብ ህወሃትን የደገፈውና ወደበረሃ የገባው የህወሃት መሪዎችን እድሜ ልክ ስልጣን ላይ ለማቆየት አለመሆኑንና ብዙዎች የታገሉለት ዓላማ በጥቂት ሰዎች መጠለፉን የፈንቅል አመራር መምህር የማነ ንጉስ ገለጹ፡፡ መምህር የማነ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የትግራይ ህዝብ የዴሞክራሲ ስርዓት እንዲገነባ፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ ልማት እንዲረጋገጥ፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ቢታገልም፤ ግቡን እንዳልመታ ጠቁመዋል፡፡ ‹‹የወንድሞቻችን ደም በከንቱ ፈስሶ ነው የቀረው፡፡ የተሰዉት፣ አካላቸውንም ያጎደሉት ለጥቂቶች መፋነን አይደለም፤ አልነበረምም›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የትግራይ ህዝብ የታገለለት አላማ እና ህወኃት እየፈጸመች ያለው ተግባር መለያየታቸውን ፤ የትግራይ ህዝብ በትግራዋይነቱ፣ ኢትዮጵያዊነቱ እንዲከበርለት የሚፈልግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የትግራይ ሚዲያ ሁሉንም እንደማያስተናግድ፣ በአደባባይ ህወሃትን የማትደግፉ ከክልሉ ውጡ መባሉን እና የህወኃት አባል ያልሆነ ምንም አይነት ብድርም ሆነ እርዳታ እንደማያገኝም ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ህዝባችን አሁንም በመከራ ላይ ነው፡፡ ጤፍ ተወድዷል፡፡ አምራች በሚባለው ራያ እና ወጀራት አካባቢ አንድ ኪሎ ጤፍ 60 ብር እየተሸጠ›› ይገኛልብለዋል፡፡ የህወኃትን ካዝና የሚሞላው ማረት የሚባለው ድርጅት ህዝቡን 18 በመቶ ወለድ እያስከፈለ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡‹‹ህወሃቶች በተለይ አሁን እየሰሩት ያለው በኢትዮጵያ ትልቅ ቁጥር ያላቸውን አማራና ኦሮሞን ማጣላት ነው፡፡ እነዚህን ህዝቦች ማጣላት ማለት ኢትዮጵያ ተበታተነች ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከተበታተነች የሚፈልጉትን የፖለቲካ ትርፍ አገኙ ማለት ነው›› ብለዋል፡፡ ሰሞኑን የሐጫሉ ግድያ መነሻው ህወኃት መሆኑን በመግለጽ፤ ከሐጫሉ ሞት የሚያተርፍ ድርጅት ቢኖር ህወሃት ብቻ ነው፡፡ ኢትዮጵያን በማበጣበጥና ለውጥን በመቀልበስ ሊያተርፍ የሚችል ድርጅት ህወሃት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በስርዓት ነው የተለያዩት እንጂ ደርግና ህወኃት ምንም አይነት ልዩነት የላቸውም፡፡ ደርግ በአደባባይ እነርሱ ግን በሚስጥር ነው የሚያደርጉት፡፡ የትግራይ ህዝብ ብዙ መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡ ንብረቱን፣ ሃብቱን፣ ልጆቹን መስዋዕት አድርጓልም ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 22/2012 ዘላለም ግዛው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36245
77a9b89569ae2ff34789f992625b3164
58ef313e0057cd4a533b8cb12a1c09dc
መዘናጋት የከፋ ዋጋ እንዳያስከፍለን
በጃንሜዳ አትክልት ተራ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ነበር የተገኘነው፤ በቅጥር ግቢው ውስጥ ስንገባ የሰው ጎርፍ ከላይ ከታች ይራወጣል። ሰውና መኪናው ሁሉም ቅጥ በሌለው እንቅስቃሴ ይተረማመሳል። ወደ ውሰጥ ለመግባት ሙከራ ሳደርግ ጭቃው የቀለጠ ቅቤ መስሎ መቆሚያ መርገጫ ጠፍቷል። በጭቃው ላይ የተዘረጉ አትክልትና ፍራፍሬዎች፤ነጋዴዎች፤ የእለት ጉርሳቸውን ለማግኘት የሚሯሯጡ ወዛደሮች፤ ሻጩ ገዥው ሁሉም በየራሱ ጉዳይ ጠደፍ ጠደፍ እያለ ይታያል።ይህ ሁሉ ትእይንት በሚታይበት የገበያ ስፍራ የአፍ መሸፈኛ ጭንብል ያላደረጉ፤ ያደረጉትም ቢሆኑ አገጫቸው ላይ አውረደው ይታያሉ። እጅ ለመታጠብ የሚያስችል ቦታ ይኖር ይሆን ብዬ ለመመልከት የተወሰነ ርቀት ወደገበያው መሃል ተጓዝኩኝ። አንድም የእጅ መታጠቢያ ቦታ ለመመልከት አልቻልኩም። ህብረተሰቡም እርስ በእርስ እየተገፋፋ ከመተላለፍ በስተቀር በወቅቱ የተከሰተውን የኮሮና ወረርሽኝ ለአፍታ እንኳን ያስታወሰው አይመስልም። ከህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ መመሪያዎች በዚህ ስፍራ አይተገበሩም።የኮሮና ቫይረስን ሰርጭት ለመከላከል ታስቦ ከፒየሳ ተነስተው ወደ ጃንሜዳ አትክልት ገበያ የሄዱት ነጋዴዎች ዛሬም እንደትናንቱ በጥንቃቄ ዙሪያ ለውጥ አለመኖሩን ይናገራሉ። ከነጋዴዎቹ መካከል የፊት መሸፈኛ ጭንብላቸውን በአግባቡ ከመልበሳቸውም በተጨማሪ እጃቸውን በተገቢው ሁኔታ በእጅ ማፅጃ ሲያፀዱ ያገኘኋቸው አቶ ኡመር እድሪስ “ለራሴና እኔን ለሚጠብቁኝ ቤተሰቦቼ ስል እራሴን በአግባቡ እየጠበኩኝ ነው” ብለዋል።እንደ አቶ ኡመር ገለፃ፤ አሁን ያለው የአትክልት መሸጫ ስፈራ ቀደም ብሎ ለዚሁ አገልግሎት ባለመዘጋጀቱ ዝናብ ጠብ ባለ ቁጥር እየጨቀየ ለእንቅስቃሴ የማይመች ሆኗል። ከዚህም በሻገር ለሽያጭ ምቹ ባልሆነ ቦታ ጭቃና ቆሻሻ ላይ የሚሸጥ አትክልት ጤናው ስለመጠበቁ ምንም ዋስትና እንደማይኖረው አስረድተዋል። ህብረተሰቡም የእለት ጉርሱን ከማግኘት ባለፈ ስለጤናው ብዙም እንደማይጨነቅ የተናገሩት አቶ ኡመር፤ “እስካሁን ካጣናችው ሰዎች በላይ በርካቶችን አጥተን የበለጠ ዋጋ ከመክፈላችን በፊት የሚመለከተው አካል አንድ ነገር ቢያደርግ ይሻላል” ብለዋል።ሌላዋ በአትክልት ችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት ወይዘሮ ዘውዴ ሺሰማ እንደሚሉት፤ ሰው ሆኖ በሽታን ምርጫው ሊያደርግ የሚችል ባይኖርም ረሃብ ቀን አይሰጥምና የዛሬን በልቶ ለማደር ወደስራ ወጥተዋል ። ልጆቻቸውን ለማሳደግ ረዳት እንደሌላቸው ተናግረው የአፍ መሸፈኛ ጭንብል በመጠቀም እጃቸው ላይ ጓንት በማጥለቅ እራሳቸውን ከበሽታ ለመከላከል ጥረት እንደሚያደርጉ አስረድተዋል። “ይህ ሁሉ ቢደረግም” ይላሉ ወይዘሮ ዘውዴ፤ በየእለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ገብተው በሚወጡበት የገበያ ስፍራ መዋል በራሱ ከፍተኛ የጤና ስጋት ነው።በሸክም ስራ የሚተዳደረው ወጣት አያሌው ቢያዝን ከአፍንጫው በታች ያደረገውን የአፍ መሸፈኛ ጭንብል በጭቃ በተለወሰ እጁ እያስተካከለ ከረሃብ ሰርቶ ማደር የተሻለ በመሆኑ ለኮሮና ወረርሽኝ የተጋለጠ ቦታ ቢሆንም እንኳን የአለት ጉርሱን ለማግኘት እንደሚሰራ ተናግሯል። ወዛደር የሚፈልጉ ሸማቾች እንዳያመልጡት ከመሯሯጥ በስተቀር ከሰው መጠጋጋት ስለሚያመጣበት ቸግር ፈፅሞ የረሳው ወጣቱ የእለት ጉርሱን ለማግኘት ያለጥንቃቄ ሲሮጥ ህይወቱን ሊያሳጣው ስለሚችለውን ኮቪድ 19 ዘንግቷል።ወይዘሪት ትእግስት አለሙ ደግሞ በአትክልት ተራ ከሚገኙ ነጋዴዎች እቁብ በመሰብሰብና በሌሎች ተባራሪ ስራዎች የምትተዳደር ወጣት ናት። ኮሮና መጣ ሲባል ከነበረበት ጊዜ የነበረው የሰዎች ጥንቃቄ የተያዘው ሰው በዛ ሲባል ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ሲገባው መዘናጋቱን ትናገራለች።የህብረተሰቡ በዚህ ልክ መዘናጋቱ በርካታ የሰው ህይወት ሊያስከፍል እንደሚችል ስጋት እንዳላት ትናገራለች። እኔም በበኩሌ የህብረተሰቡ መዘናጋትም ሆነ የገበያ ቦታው አለመመቸት ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሊያበረክት እንደሚችል ታዝቤያለሁ። የጤና ባለሙያዎቹስ ምን ይላሉ ስል ወደ ኤካ ኮተቤ የኮቪድ ህከምና ማእከል ሀሎ ብያለሁ።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰርና የውስጥ ደዌ፤ የሳንባና የፅኑ ህመም ሀኪም ዶክተር ዳዊት ከበደ፤ ከሦስት ወራት በፊት በኤካ ኮተቤ የኮቪድ ህክምና ማእከል ተመድበው መስራት መጀመራቸውን ተናግረው እሳቸው ህክምና መስጠት የጀመሩ ጊዜ በላይ አሁን በበሽታው የተጠቃ ሰው በበዛበት ሰዓት ያለው የህብረተሰቡ መዘናጋት ግራ እያጋባቸው እንደሆነ አስረድተዋል።ኮቪድ 19 በራሱ ህክምና የለውም። የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን የማከምና ህመም የመቀነስ ሰራ ብቻ ነው የሚሰራው የሚሉት ዶክተሩ፤ በበሽታው ተጠቅቶ ወደር ከማይገኝለት ስቃይ ጋር ከመታገል ቅድመ ጥንቃቄ ላይ አተኩሮ መስራት አማራጭ እንደማይኖረው አስጠንቅቀዋል።̋በወረት የጥንቃቄ ሥራ እየተሰራ ከእለት ከእለት ኑሯችን ጋር አብሮ የተቆራኘውን በሽታ ለመከላከል የማይቻል ነው።” ያሉት ዶክተር ዳዊት፤ ህብረተሰቡ በሌሎች ሀገራት የተመለከትነውን አሰቃቂ የሟቾች ቁጥር ላለመድገም በተቻለው መጠን እጁን ቶሎ ቶሎ በመታጠብ፤ የፊት ጭንብል በማድረግና ርቀቱን በመጠበቅ በሽታው ከሚያመጣበት ጉዳት መከላከል ይችላል።በተለይ ወጣቱ የአውሮፓ ሻንፒዮንስ ሊግ ለመመልከት በሚል ሰበብ በዲኤስ ቲቪ መመልከቻ ቤቶች ውስጥ መታጨቅ መጀመሩን አመልክተው፤ ከቻለ ባይሄድ ካልቻለ ደግሞ አፉን መሸፈን እንደሚገባው ተናግረዋል። ወጣቱ በተቻለው መጠን ተጓዳኝ በሽታዎች ያሉባቸውን ሰዎች መጠበቅ እንደሚገባው አስረድተዋል።“የህብረተሰቡ መዘናጋት በቁጥሩ አነስተኛ በሆነው የህክምና ባለሙያ ላይ የሚፈጠረው ጫና ቀላል አይደለም፤” የሚሉት ዶክተሩ፤ ቀድሞ በኤካ ኮተቤ ብቻ የሚሰጠው ህክምና አሁን በጴጥሮስ፤ በጳውሎስና ሌሎች የግል ህክምና ተቋማት ላይ በከፍተኛ ርብርብ እየተሰጠ ነው። ይህ ሁሉ ቢሆንም እንኳን ፅኑ ህሙማንን ለማስተናገድ በጣም ከባድ መሆኑን ተናግረው ህመምተኞቹ የሚሰቃዩትን ሰቃይ በመመልከት በህክምና ባለሙያዎች ላይ ከሚከሰት የስነልቦና ጫና እንታደጋቸው ይላሉ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 22/2012አስመረት ብስራት
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36251
e83686d5eab4be8b880df9327ff41001
7f181b39c277108ec41c77f9587dedf4
ቅዱሳኖቹ ላስታ ላልይበላ በቶርናመንቱ ምን ያሳዩን ይሆን?
58 ክለቦች በስድስት ምድብ ተደልድለው ዓመቱን ሙሉ ሲፋለሙበት የነበረው የኢትዮጵያ የአንደኛ (ብሔራዊ) ሊግ የእግር ኳስ ውድድር መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ማጠቃለያው ውድድር ማለፋቸውን ያረጋገጡት 18 ቡድኖች በባቱ (ዝዋይ) ከተማ ከትመዋል። እነዚህ ክለቦች ከፍተኛ ሊጉን ለመቀላቀል በሚያደርጉት ትንቅንቅ ባቱ ከተማ ከሐምሌ 07 እስከ 28 ቀን 2011 ዓ.ም በዚህ ታላቅ የእግርኳስ ድግስ ደምቃ ትሰነብታለች። ክለቦችም ነገ በባቱ ከተማ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓታቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን፤ 18 ክለቦች በአራት ምድብ ይደለደላሉ። በሁለት ምድብ አምስት አምስት ክለቦች ሲደለደሉ፤ በተቀሩት አራት አራት ክለቦች ይደለደላሉ። ከየምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡ ስምንት ክለቦች ጥሎ ማለፉን የሚቀላቀሉ ሲሆን፤ እነዚህ ክለቦች በጥሎ ማለፉ እርስ በርስ በሚያደርጉት ጨዋታ አራት አሸናፊ ክለቦች ቀድመው ከፍተኛ ሊጉን መቀላቀላቸውን ያረጋግጣሉ። ቀሪ ሁለት ክለቦች ደግሞ በጥሎ ማለፉ የተሸነፉ አራት ክለቦች እርስ በርስ በሚያደርጉት ፍልሚያ ሁለቱ አሸናፊ ክለቦች ደግሞ ከፍተኛ ሊጉን ከሚቀላቀሉት ስድስት ክለቦች መካከል ለመሆን ይበቃሉ። በአጠቃላይ በማጠቃለያ ውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ ክለቦች የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል። ይሄን የማጠቃለያ ውድድር ከተቀላቀሉና ከፍተኛ ሊጉን ለመቀላቀል ከሚፋለሙ 18 ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ቅዱሳኖቹ ላስታ ላልይበላ የእግር ኳስ ክለብ ነው። ክለቡም በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአንደኛ ሊጉ 11 ክለቦች በተደለደሉበት ምድብ <<ሐ>> ተደልድሎ ዓመቱን ሙሉ እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ ማጠቃለያ ውድድሩን ለመቀላቀል በቅቷል። ክለቡ ለማጠቃለያ ውድድሩ ያደረገው ቅድመ ዝግጅትና የክለቡ ታሪካዊ አመጣጥ ምን እንደሚመስል ከክለቡ ዋና አሰልጣኝ አቶ ባየ ተፈሪ ጋር እንደሚከተለው ቆይታ አድርገናል። የክለቡን ታሪካዊ አመጣጥ የቅዱሳኖቹ አሰልጣኝ እንዳብራሩት፤ ላስታ ላልይበላ የእግር ኳስ ክለብ የተመሰረተው የላልይበላ ከተማ አስተዳደርን ወክሎ በተለያዩ የእግርኳስ ውድድሮች ላይ የሚሳተፍ ክለብ ለማቋቋም ባወጣው ዕቅድ መሰረት በ2004 ዓ.ም የላልይበላ ከነማ የእግር ኳስ ክለብን በከነማ ደረጃ ለማቋቋም በቅቷል። ክለቡም በተቋቋመበት ማግስት በ2004 ዓ.ም በክልሉ በተካሄደው የክለቦች ቻምፒዮና ላይ በመሳተፍ የዋንጫ ተፋላሚ በመሆን ድንቅ ብቃቱን ያስመሰከረ ሲሆን፤ በውድድሩም በ2005 ዓ.ም የአማራ ሊግን ለመቀላቀል የሚያስችለውን ውጤት አስመዘግቧል። የክለቡ ዝናና ውጤት ከዓመት ዓመት ከፍ እያለ የመጣ ሲሆን፤ በ2007 ዓ.ም የውድድር ዘመን በአማራ ሊግ አስደናቂ ተሳትፎ በማድረግ የክልሉ ቻምፒዮና ለመሆን በቅቷል። በዓመቱ መጨረሻ አንደኛ ሊጉን ለመቀላቀል ጂጂጋ ላይ በተካሄደው የማጠቃለያ ውድድር ላይ በንቃት በመሳተፍ አንደኛ ሊጉን ለመቀላቀል መቻሉን ይናገራሉ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አቶ ባየ። አሰልጣኙ ክለቡ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በአንደኛ ሊጉ ተፋላሚ ክልብ ከሆነ በኋላ ላስታ ላልይበላ የእግር ኳስ ክለብ የሚል ስያሜ እንደተሰጠው ይናገራሉ። አሰልጣኙም ምክንያቱን እንዳብራሩት፤ እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ለክለቡ ድጋፍ ሲያደርግ የነበረው የላልይበላ ከተማ አስተዳደርና በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት የከተማዋ ባለሀብት ነበሩ። ክለቡ አንደኛ ሊጉን ከተቀላቀለ በኋላ ግን የላስታ ወረዳ አስተዳደርና የላልይበላ ከተማ አስተዳደር በመተጋገዝ ድጋፍ እያደረጉ ክለቡ ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ ታሳቢ በማድረግ አሁን ያለውን ስያሜ አግኝቷል። እንዲሁም ክለቡ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው የሁለቱን ወረዳዎች ህዝብ ይወክላል በሚል የክለቡ አመራሮች በማመናቸውና በማህበረሰቡ ዘንድም ይህ ግንዛቤ ስላለ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ይሄን ስያሜ ሊያገኝ እንደቻለ ተናግረዋል። ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታማ የሚባል ስኬትን እያስመዘገበ የመጣው ቅዱሳኖቹ ላስታ ላልይበላ የእግር ኳስ ክለብ፤ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአንደኛ ሊጉ በመጀመሪያው የውድድር ዓመት ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች ምንም ጎል ሳይቆጠርበትና የሽንፈትን ጽዋ ሳይጎነጭ ታሪክ መስራት ችሏል። በውድድሩም 37 ነጥብ በመሰብሰብ ዳሞት ከተማን ተከትሎ የማጠቃለያ ውድድሩን መቀላቀል መቻሉን የሚናገሩት አሰልጣኙ፤ ለማጠቃለያ ውድድሩ ብለን ሳይሆን ዓመቱን ሙሉ ከጥቅምት 18/ 2011 ዓ.ም ጀምሮ የተሻለ ዝግጅት በማድረግ በምድባችን የተሻለ ውጤት በማምጣት ይሄን ቶርናመንት ተቀላቅለናል። በውድድር ዓመቱ በምድብ ባደረግናቸው ጨዋታዎች ደካማ ጎናችንንና ጠንካራ ጎናችንን የፈተሽንበት ነበር። ስለዚህ ያሉብንን ደካማ ጎን በመሙላትና ጠንካራ ጎኖቻችን ይበልጥ በማጠናከር በውድድሩ ላይ ተፎካካሪ ሁነን ውጤት ይዘን ወደቅድስቲቱ ከተማ እንደምንመለስ በተጫዋቾች ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል አሰልጣኙ። በታክቲክና በስነ ልቦና ጠንካራ የሆኑ በቂ የተጫዋቾች ስብስብ ይዘን የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ከፍተኛ ሊጉን ለመቀላቀል ታሳቢ በማድረግ ባቱ ላይ ከትመናል የሚሉት አሰልጣኙ፤ እግር ኳስ ነውና በውድድሩ የሚፈጠረውን ውጤት ቀድመን ለመገመት አዳጋች ቢሆንም በውድድሩ የተሻለ ተፎካካሪ የሚያደርገንን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቀን ባቱ ላይ ከትመናል ብለዋል። ‹‹አንድን ሥራ ፍላጎት ኖሮህ የምትሰራውና ፍላጎት ሳይኖርህ የምትሰራው ከሆነ ውጤታማ የመሆን እድሉ የተለያየ ነው›› የሚሉት አሰልጣኙ፤ የክለቡ ተጫዋቾቹ ዘንድሮ ከመቼውም ጊዜ ባላይ ከፍተኛ ሊጉን ለመቀላቀል ያላቸው ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ከፍተኛ ስለሆነ ተጫዋቾቹ የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡ ‹‹በውድድር ዓመቱ በአንደኛ ዙር በ10 ጨዋታዎች ላይ ጎል ሳይቆጠርብን ያደረግነው ያለመሸነፍ ጉዞ በዚህ በቶርናምንት ላይ የማንደግምበት ምንም ምክንያት የለም፡፡›› የሚሉት ወጣቱ አሰልጣኝ፤ በውድድር ዓመቱ በአንደኛው ዙር 10 ጨዋታዎችን ምንም ጎል ሳይቆጠርባቸው አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ የተጓዙት በአጋጣሚ ወይም በዕድል አለመሆኑንም ይናገራሉ። ‹‹ጠንክረን በመስራታችን እና በስነ ልቦና፣ በአካል ብቃት፣ በቴክኒክና በታክቲክ ከሌሎቹ ክለቦች የተሻልን ሆነን በመገኘታችን ነው።›› ብለዋል፡፡ ስለዚህ ይሄንን ለመድገም የሚያስችል የአሰልጣኞች፣ የአመራርና የተጫዋቾች ስብስብ ስላለ በቶርናምንቱ ከፍተኛ ሊጉን ለመቀላቀል የሚያስችላቸውን ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ምልክቶች መሆናቸውንም ነው የጠቆሙት። አሰልጣኙ የክለቡ 60 በመቶ የሚሆኑ ተጫዋቾች ተስፋ የሚጣልባቸው ታዳጊ ስፖርተኞች ናቸው። ክለቡ ሮጠው ባልጠገቡ ወጣት ተጫዋቾች የተገነባ ነው። በእንደዚህ አይነት ቶርናመንቶች ወጣት ተጫዋች የሚታዩበትና ጎልተው የሚወጡበት በመሆኑ፤ እነዚህ ወጣት ተጫዋቾች እራሳቸውን ለማሳየት በሚያደርጉት የተሻለ እንቅስቃሴ ክለቡ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያግዘዋል። እንዲሁም ተጫዋቾቹ በክለቡ ድንቅ ብቃታቸውን በማሳየት በተለያዩ ክለቦችና አሰልጣኞች እይታ ውስጥ በመግባት የተሻለ ደረጃ ላይ የሚደርሱበትን እድል የሚፈጥርላቸው ውድድር ነው ብለዋል። በዘንድሮው የውድድር ዓመት ክለቡ የላልይበላ ከተማ አስተዳደር በበጀተለት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ውድድሩን እያከናወነ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ባየ፤ ክለቡ ድርብ ድርብርብ ድሎችን ለማምጣት ቀን ከሌሊት እየሰራ ቢሆንም ከአካባቢው ማህበረሰብ የሚደረግለት ድጋፍ አናሳ መሆኑ፤ ነገ ላይ ክለቡ የተሻለ ውጤት ቢያስመዘግብ ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ለማድረግ እንደሚቸገር ይናገራሉ። አክለው፤ ክለቡ የተመሰረተበት አካባቢ የአገሪቱ ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻ በመሆኑ ትልልቅ ስምና ዝና ያላቸው ሆቴሎች አሉ። ነገርግን የተወሰኑ ጥቂት ግለሰቦች ካልሆኑ በስተቀር ባለሀብቱ ተንቀሳቅሶ የጎደለውን ነገር አይቶ ክለቡን ለማጠናከር የሚደረግ ድጋፍ የለም በሚባል ደረጃ ላይ ነው። ስለዚህ ማህበረሰቡ ክለቡ የኔነው ብሎ የሚያደርገው ድጋፍ አናሳ መሆኑን ያመለክታሉ። ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ የክለቡ ህልውና ያለው በከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ነው የሚሉት አሰልጣኙ፤ በውድድር ዓመቱ ክለቡ አብረውት ተደልድለው ከነበሩ 11 ክለቦች መካከል ክለቡ በሜዳው ጨዋታዎችን ሲያደርግ የሜዳ መግቢያ ክፍያ የማይፈፀምበትና ገቢ የማያገኝ፤ የደጋፊ ማህበር የሌለው፤ ክለቡን በተለያዩ ነገሮች ድጋፍ የሚያደርግለት ስፖንሰርም ሆነ ባለሀብት የሌለው ክለብ ነው ይላሉ። ነገርግን ክለቡ ይሄን ውጤት ያስመዘገበው በተጫዋቾቹ ጥረትና ከተማ አስተዳደሩ በሚያደርገው ድጋፍ ነው። የአካባቢው ማህበረሰብ ጨዋታ ሲኖር <<ሆ>> ብሎ ወጥቶ ከመደገፍ በዘለለ ክለቡ በተጠናከረ መንገድ እራሱን ችሎ እንዲቆምና የራሱን ሀብት መፍጠር እንዲችል የሚያስችል ድጋፍ እያደረገለት አይደለም ካሉ በኋላ፤ ስለዚህ የክለቡ ኃላፊነት ሙሉ ለሙሉ ከተማ አስተዳደሩ ላይ የወደቀ ስለሆነ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ ባለሀብት እና የላስታ ወረዳ አስተዳደር ተነቃቅቶ ክለቡን በተጠናከረ መልኩ እንዲደግፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። አቶ ባየ እንደሚሉት፤ ክለቡ የራሱን የደጋፊ ማህበር እንዲኖረው የከተማ አስተዳደሩ ስፖርት ጽህፈት ቤት የደጋፊ ማህበር ለማቋቋም ጥረት እያደረገ ይገኛል። ነገርግን ማህበረሰቡ የደጋፊ ማህበር ስር ለመታቀፍ ያለው ተነሳሽነትና ፍላጎት አናሳ በመሆኑ እንቅፋት እንደገጠመው ጠቁመዋል። ምናልባትም ክለቡ ወደ ከፍተኛ ሊግ የመቀላቀል ራዕዩ ከተሳካ ውጤቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነሳሳትን ስለሚፈጥር የክለቡን የደጋፊ ማህበር በተሳካ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚቋቋምበት ሁኔታ ይፈጠራል። ነገር ግን ውጤቱ ምንም ይሁን ምን የክለብ አመራር ጠንክሮ በመስራት በሚቀጥለው ዓመት የክለቡ የደጋፊ ማህበር ይቋቋማል ብለዋል። በአጠቃላይ የአሰልጣኝ ድካምና ልፋት ያለተጫዋቾች ጥረትና ቆራጥነት ዋጋ የለውም። በልምምድ ሜዳ ላይ የተሰጡትን ስልጠናዎች በተደረጉ ውድድሮች ላይ ወደ ተግባር በመቀየር ክለቡ ላስመዘገበው ውጤት የአንበሳውን ድርሻ ለተጫዋቾቹ የሚሰጥ ነው ያሉት የቅዱሳኖቹ አሰልጣኝ አቶ ባየ፤ <<በባቱ ከተማ ከፍተኛ ሊጉን ለመቀላቀል በሚደረገው ፍልሚያ ተፋላሚ የሆነውን የላስታ ላልይበላ የእግር ኳስ ክለብን ውድድሩ በሚካሄድበት አካባቢ ያሉ የአካባቢው ተወላጆች እና የባቱ ከተማ ሰፊው ህዝብ ድጋፍ እንድት ሰጡን>> ሲሉ አሰልጣኙ በክለቡና በተጫዋቾቹ ስም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 5/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13957
98c1def95f59233bb86183a36528a0d0
5b8e45165f6ae7640de83ac3fab2161b
ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድነትና የአትሌቲክሱ የቤት ሥራ
‘ኢጎ’ (Ego) የሚለው ቃል ከግሪክ የተወሰደና ትርጉሙም ‘እኔ’ ወይም ‘እኔነት’ ማለት ነው። ‘እኔ’ና ‘እኔነት’ ራስን ማወቅ፣ መሻትና አሻራ መተውን በማካተት ህልውናን የሚገልጽ የንቃተ ህሊና አካል መሆኑ በተለያዩ ድርሳናት ተቀምጧል። ይህ ስሜት መጠኑን ሲያልፍና ሌላውን አሳንሶ ራስን መሪ፣ አለቃ፣ ቀዳሚ፣ አዛዥ አድርጎ መቁጠር ሲጀመር ወደ (egoist, narcis­sist) ግለኝነት ወይም እኔ ብቻ ወደ ማለት እንደሚያድግ የስነ ልቦና ምሁራን ያስቀምጣሉ። ‘ኢጎ’ን በጥቅሉ መጥፎ ቅንፍ ውስጥ መጨመርም ስህተት ይሆናል የሚል ምልከታም አላቸው። ምክንያቱም እኔነትን ማለትም እራስን ማወቅ መሰረታዊና አስፈላጊ ጉዳይ በመሆኑ ነው። ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው ልክ-የለሽ እኔነት ወይም ራስ-ወዳድነት (egoism) በተለይም በስፖርት ውስጥ የሚኖረው ተፅዕኖ ላይ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ውጤታማ በሆነችበት የአትሌቲክስ ስፖ ርት በአትሌቶች መካከል የተለመደው አገርን አስቀድሞ የራስን ውጤት አሳልፎ የመስጠት ባህል መሸርሸርና ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድነት እያደገ መምጣቱ በውጤት ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ መመልከት ጠቃሚ ነው። ኢጎ ምንም እንኳን ከስነ ልቦና ጋር በተያያዘ በደንብ የሚታወቅ ቃል ቢሆንም በስፖርቱ ዓለም በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል። በስፖርት ዓለም ፉክክር ውስጥ አሸናፊና ተሸናፊ መኖሩን ተከ ትሎ በስፖርተኞች መካከል ኢጎ መኖሩ ተፈጥሯዊ ነው። የዓለማችን ከዋክብት ስፖርተኞች ከእኔ በላይ ላሳር በሚል ከልክ ባለፈ ራስ ወዳድነት ወይም ኢጎ የሚታሙትም ለዚህ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን አትሌቶች በተለይም በመካከለኛና ረጅም ርቀት ወንድ ሯጮች መካከል በሚካሄዱ የግል ውድድሮች ላይ የሚስተዋለው አላስፈላጊ ፉክክር ወደ ኢጎ እያደገ መምጣቱን ማስተዋል ይቻላል።ኢትዮጵያ በታላላቅ የስፖርት መድረኮች ውጤታማ ከሆነችባቸው የአት ሌቲክስ ውድድሮች መካከል የ5ሺ ሜትር ቀዳሚው ነው። በዚህ ርቀት ኢትዮጵያ ገናና ስም እንድታገኝ ካስቻሉት አትሌቶች ኃይሌ ገብረስላሴና ቀነኒሳ በቀለ ከውድድር መውጣት በኋላ እነሱን የሚተካ አትሌት በቀላሉ ማግኘት አልተቻለም። በዚህም ኢትዮጵያ በሁለት ኦሊምፒኮችና ሦስት የዓለም ቻምፒዮናዎች በ5ሺ ሜትር የነበራትን ክብር ለሌላ አገር ለመ ስጠት ተገዳለች። ካለፈው 2017 ዓ.ም የለንደን የዓለም ቻምፒዮና ወዲህ ግን ርቀቱ እየተዳከመ በሄደበት ወቅት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በውድድሩ ዳግም የበላይነትን የተቆጣጠሩበት አብዮት መፍጠር ችለዋል። በለንደኑ ቻምፒዮና አትሌት ሙክታር ኢድሪስ የርቀቱን ክብር ወደ ቤቱ ከመለሰ ወዲህ በተለያዩ የግል ውድድሮች በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሌሎች አገራት ተፎካካሪዎቻቸው ላይ የበላይነትን ተጎናፅፈዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የዓለም ቻምፒዮኑን ሙክታርን ጨምሮ ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሰለሞን ባረጋ፣ ሐጎስ ገብረሕይወት፣ ጥላሁን ኃይሌና ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች 5ሺ ሜትርን እየተፈራረቁ በበላይነት ተቆጣጥረውታል። እነዚህ አትሌቶች በሌሎች አገራት አትሌቶች ላይ የበላይነታቸውን ከማሳየት ባለፈ እጅግ ተቀራራቢ ብቃት ያላቸው መሆኑ ለኢትዮጵያውያን የወደፊት የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮና ውድድሮች ፍሰሃ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን ባለፉት ዓመታት ዳይመንድ ሊግን ጨምሮ በተለያዩ የግል ውድድሮች እነዚህ አትሌቶች እንደ አንድ አገር አትሌቶች ከዚህ ቀደም የሚስተዋሉ የመደጋገፍና የመዋደድ ባህሪ አይታይባቸውም። ከዚህ ይልቅ አንዱ አንዱን ለመብለጥ የሚያደርጉት አላስፈላጊ ፉክክር ጎልቶ ሲወጣ ይስተዋላል። በአጭሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በነዚህ አትሌቶች መካከል ኢጎ እየጎለበተ እንደመጣ በተግባር መታዘብ ይቻላል።ከዓመት በፊት በሉዛን ዳይመንድ ሊግ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻና ሰለሞን ባረጋ መካከል የተፈጠረው አንድ ማሳያ ነው። በዚያ ውድድር መጨረሻ ላይ ዮሚፍ ከፊት እየመራ በነበረበት አጋጣሚ ከኋላ ተጠልፎ ሊወድቅ በነበረበት ቅፅበት ሰለሞንን ጎትቶ ወደ ኋላ ለማስቀረት ሲሞክር በተፈጠረው ክፍተት ትውልደ ኢትዮጵያዊው የባህሬን አትሌት ብርሃኑ ባለው ከመሃል አፈትልኮ በመውጣት ማሸነፉ አይዘነጋም። ሁለቱ አትሌቶች ያልሆነ ፉክክርና እልህ ውስጥ በመግባታቸው ማሸነፍ የሚችሉትን ውድድር እንዲሸነፉ ሆኗል። ከዚህ ባሻገር በርካቶቹን ውድድሮች ማስተዋል ከተቻለ እነዚህ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከውድድር በኋላ አሸንፈውም ይሁን ተሸንፈው እንደተለመደው ተቃቅፈው እንኳን ደስ ያለህ ከመባባል ይልቅ የደስታ አገላለፃቸው የሌላ አገር አትሌት ያሸነፉ እየመሰለ መጥቷል። እርስ በርስ ተሸናንፈው የሚያሳዩት የደስታ አገላለፅ ያልተለመደና ከውጭ ሆኖ ለሚታዘብ የማይተዋወቁ ሊመስል ይችላል። እነዚህ አትሌቶች አላስፈላጊ ኢጎ እያዳበሩ እንደመጡ የግል ውድድሮች ላይ ነው መታዘብ የተቻለው። ምናልባት ስፖርት በባህሪው የፉክክር መድረክ እንደመሆኑ አንዱ አንዱን ለመብለጥ በግል ውድድሮች ኢጎ መፈጠሩ ተጠባቂ ሊሆን ይችላል። እነዚህ አትሌቶች ብቃታቸው ተቀራራቢ መሆኑም ኢጎ ቢፈጠር ላያስገርም ይችላል። ጥያቄው ግን በእንደዚህ አይነት የግል ውድድሮች አላስፈላጊ ኢጎ ያዳበሩ የአንድ አገር አትሌቶች ነገ ለብሔራዊ ቡድናቸው በአንድ ላይ ሲሮጡ እንዴት መቆጣጠር ይቻላል? የሚለው ነው። ከዚህ ቀደም የነበሩት ጀግኖች አትሌቶቻችን አገራቸውን ወክለው ሲሮጡ አንዱ አንዱን በማገዝና ራሱን በመሰዋት ወርቁ ከኢትዮጵያ እንዳያልፍ ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ። በዚህ መደጋገፍ ውስጥ የትኛው አትሌት መጨረሻ ላይ አሸናፊ እንደሚሆንና የቡድን ሥራውን ማን እንደሚሰራም ቀድሞ መገመት የሚቻ ልበት ሁኔታ ነበር። ስፖርቱ እየዘመነ ነገሮች እየተለወጡ በመጡበት በዚህ ዘመን ያሉት አትሌቶች ብቃታቸው እጅግ ተቀራራቢ ከመሆኑ የተነሳ በውድድሮች ላይ አሸናፊውን ቀድሞ መገመት አዳጋች ነው። በስፖርት ዓለም የትኛውም ተፎካካሪ ለመሸነፍ ብሎ ወደ ውድድር አይገባም። ተመጣጣኝ ብቃትና አቅም ይዞ በኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮና ለማሸነፍ የማያልም አትሌት አይኖርም። በአንድ አገር አትሌቶች መካከል እንዲህ አይነቱ ነገር ሲከሰት በግል ውድድሮች ላይ የምንታዘበው የአትሌቶች ኢጎ በብሔራዊ ቡድን ውድድሮች ላይ ላለመንፀባረቁ በምን እርግጠኛ መሆን ይቻላል? አትሌቶቹ ይህን ኢጎ ይዘው ወደ ብሔራዊ ቡድን ሲመጡ አላስፈላጊ ፉክክር ውስጥ ገብተው በግል ውድድሮች ላይ እንደታዘብነው ውጤታቸውን አሳልፈው የማይሰጡበት አጋጣሚ እንዳይፈጠር ምን ማድረግ ይቻላል? በፒፕል ዴቨሎፕመንት ኔትወርክ ድረ ገፅ ላይ ዴል ሮች የተባሉ የስነ ልቦና ምሁር ያሰፈሩት ፅሁፍ ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድነት የቡድን ሥራን እንደሚያበላሽ ያስቀምጣሉ። በአንድ የቡድን ሥራ ውስጥ ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድ ሰው ካለ የቡድን ሥራው እንደማይሳካ ያስቀምጣሉ። ይህ ከስፖርት ጋር ሲያያዝ ደግሞ ለመቆጣጠር ቀላል እንደማይሆን ያምናሉ። ያም ሆኖ በስፖርት ውስጥ የግለሰቦችን ከልክ ያለፈ ራስ ወዳድነት ለመቆጣጠር አሰልጣኞች ጉልህ ሚና እንዳላቸውና ችግሩን አስወግደው ወደ አዎንታዊ መንገድ የመውሰድ እድሉ እንዳላቸው ሌሎች ምሁራንም ይስማማሉ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን የረጅም ርቀት አሰልጣኝና የቀድ ሞው ኦሊምፒያን ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ በ5ሺ ሜትር ከዚህ ቀደም በወጣቶች የዓለም ቻምፒዮና አትሌት ሰለሞን ባረጋንና ጥላሁን ኃይሌን ይዘው ሄደው ሽንፈት እንደገጠማቸው ያስታውሳሉ። በቅድሚያ እነዚህ አትሌቶች ለሽን ፈታቸው ዋነኛው ምክንያት ደጋግመው ውድድሮችን በማድረግ አቅማቸውን ጨርሰው ወደ ብሔራዊ ቡድን ስለ ሚመጡ መሆኑን ይናገራሉ። ስለዚህ በመጀመሪያ አትሌቶች ገንዘብ የሚያ ገኙበትን የግል ውድድሮች ቀንሰው ለብሔራዊ ቡድን ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ያብራራሉ። ከልክ ካለፈ ራስ ወዳድነት የበለጠ የሚያሰጋቸውም አትሌቶች አቅማቸውን ጨርሰው ወደ ብሔራዊ ቡድን ሲመጡ ውጤታማ አለመሆናቸውን ይገልፃሉ። በግል ውድድሮች አትሌቶቹ ላይ ኢጎ ቢኖርም ወደ ብሔራዊ ቡድን ሲመጡ መቆጣጠር እንደሚቻል ሻምበል ቶሎሳ ያለፈውን የለንደን የዓለም ቻምፒዮና በምሳሌነት በማንሳት ያስረዳሉ። በዚያ ውድድር አስቸጋሪ የሆነውን ሞ ፋራህን ማሸነፍ የቻሉት አንዱ ለአንዱ መስዋት ሆነው እንደነበር በማስታወስ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሰለሞን ባረጋና ሙክታር ኢድሪስ በተሰጣቸው ታክቲክ መሰረት ተጋግዘው መሆኑን ያስረዳሉ። ‹‹ዮሚፍ ሞፋራህን እንዳያሳልፈው ተነግሮት ነበር፣ሙክታር ደግሞ ሁለት መቶ ሜትር ሲቀር እንዲወጣ ነግሬያቸው ታክቲኩን ተረድተው ነው ወደ ውድድር የገቡት›› በማለት ያስታወሱት ሻምበል ቶሎሳ በዚያ ውድድር ዮሚፍ ራሱን መስዋት ሊያደርግ በሚችል መልኩ አትሌቱ መቀረፁን ያነሳሉ። በቀጣይም እንደዚህ አይነት ሥራ መሰራት እንደሚገባው ያምናሉ። አትሌ ቶቹ የግል ውድድሮችን የሚያደርጉት በማኔጀሮቻቸው እንደመ ሆኑ መተጋገዝ ላይጠበቅባቸው እንደ ሚችል የጠቆሙት ሻምበል ቶሎሳ ብሔራዊ ቡድን የአገር ጉዳይ በመሆኑ ቅድሚያ ለአገር እንዲሰጡ በማድረግ ረገድ የአሰልጣኙ ሚና ትልቅ መሆኑን ያስቀምጣሉ። ከብሔራዊ ቡድን ውድድሮች ቀደም ብሎ እነዚህን አትሌ ቶች ሊያሸንፍ የሚችለው የሌላ አገር አትሌት ማነው? የሚለውን በማጤን አሰልጣኙ አትሌቶቹን ማዘጋጀት እንደ ሚኖርበት የሚናገሩት የቀድሞው ኦሊም ፒያን የቡድን ሥራ ሊያስፈልግም ላያስፈልግም የሚችልበት ሁኔታ ታይቶ ታክቲኮች እንደሚቀመሩ ያብራራሉ። የቡድን ሥራን በተመለከተ እንደቀድሞው ይሆናል ብለው እንደማይጠብቁም ያክ ላሉ። ስለዚህም ፌዴሬሽኑ ከወዲሁ በዚህ ጉዳይ ላይ ሥራዎችን ቀደም ብሎ መስራት እንደሚኖርበት ይመክራሉ። ከስነ ልቦና ምሁራንና ከብሔራዊ ቡድን አሰልጣኙ አስተያየት መረዳት እንደሚቻለው የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች የአትሌቶችን ኢጎ ለመቆ ጣጠርና በግል ውድድሮች የሚንፀባረቁ ችግሮች ወደ ብሔራዊ ቡድን እንዳ ይመጡ ለማድረግ ትልቅ ሥራ ይጠ ብቃቸዋል። በተለይም የአትሌቶችን ኢጎ ለመቆጣጠርና ሁሉም ተመሳሳይ የአሸናፊነት እድልና ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ አሰልጣኞች የተሻለ ታክቲክ መቅረፅ ይኖርባቸዋል። አትሌቶች በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ ለሚመጣ የብሔራዊ ቡድን ውድድር ካምፕ ገብተው ዝግጅት የሚያደርጉት ቢበዛ ለሁለት ወር ነው። የተቀረውን ጊዜ በየራሳቸው ማኔጀሮችና አሰልጣኞች በራሳቸው መንገድ ሲሰሩ ነው የሚቆዩት። ወደ ብሔራዊ ቡድን ሲመጡ በአካል ብቃትም ይሁን በስነ ልቦናው ረገድ አንድ የሚሆኑበትን አካሄድ መቅረፅ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች የቤት ሥራ ይሆናል። ከዚህ ቀደም አትሌቶች ወደ ብሔራዊ ቡድን ሲመጡ በራሳቸው አሰልጣኝ እንዲሰሩ የሚደረግበት አጋጣሚ አሁንም ካለ የኢጎ ጉዳይን መቆጣጠር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በስፖርቱ ውስጥ ባለፉ ሰዎች መመራት ከጀመረ ወዲህ እየተሸረሸረ የነበረው የቡድን ሥራ በመጠኑም ቢሆን መሻሻል ታይቶበታል። አሁንም ፌዴሬሽኑ ይህን ጅምር ከማጠናከር ባለፈ የብሔራዊ ቡድን አትሌቶች በብቃትም በስነ ልቦ ናም በደንብ የሚዋሃዱበትን አጋጣሚ ለመፍጠር የልምምድ ጊዜን መጨመር፣ አትሌቶች በግል ውድድር ያዳበሩትን ኢጎ እንዲያስቀሩ ማቀራረብና እንደ አገር እንዲያስቡ ማድረግ ይጠበቅበታል። ለዚህም የአገር ፍቅርን እንዲያጎለብቱ ለማድረግ ከስፖርታዊ ስልጠናዎች ባሻገር የስነ ልቦና ትምህርቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል። በውድድሮች ለአገር ወርቅ ያስመዘገበውም እንዲመዘገብ ምክንያት የሆነውም አትሌት እኩሉ ሽልማትና እውቅና እንዲያገኙ የማድረግ ጅምር በፌዴሬሽኑ በኩል እንዳለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተመልክተናል። ይህ አትሌቶች ኢጓቸውን ወደ ኋላ ትተው ለአገራቸው ቅድሚያ እንዲሰጡ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና ስለሚኖረው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሀምሌ 6/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14070
f94285a1e3b49bf4cb90021fe9907c8a
c2a3c78bdc4251ceb406effe0b33fc15
እንግዳዋ ክስተት
በአፍሪቃ የትልቋ ደሴት ማዳጋስካር በድንቅ እግር ኳሳዊ ጥበብ ችሎታ የተካኑ፣ ደጋፊዎችን ከመቀመጫቸው አስነስተው ማስጨብጨብ የቻሉና ከአህጉሪቱም ተሻግረው በታላላቅ ሊጎች ድንቅ ችሎታቸውን ያስመሰከሩ ጥበበኞች የላትም። በአህጉሪቱ እግር ኳስ እዚህ ግባ የሚባል ስምም ሆነ አበርክቶም የላትም፡፡ ፕሮፌሽናል የሆነ የሊግ ውድድርም አታካሂድም። የአገሬው እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮችም ቢሆኑ ለስፖርቱ እድገት ከመስራት ይልቅ የራሳቸው ኪስ በረብጣ ገንዘቦች ለመሙላት ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ናቸው በሚል ይታማሉ።ይህ የሙስና ውንጀላቸውም ፊፋን ሳይቀር ጣልቃ እንዲገባ አስግድዶት ታይቷል። የአገሬው ብሄራዊ ቡድን አስልጣኝ ኒኮላስ ዲፒየስም በፈረንሳይ አራተኛ ዲቪዚዮን የሚገኘው ፍሎሬ ክለብ ከማሰልጠን የዘለለ በታላላቅ ሊጎች ስራቸው ተፈትኖ ስማቸው ተሰምቶ አያውቅም።ይሁንና ደሴቲቱን አገር በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በግብፅ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ማብቃት ችለዋል። ከእግር ኳስ ጋር ብዙም ቀረቤታ የሌላት አገር የአህጉሪቱ ታላቅ የእግር ኳስ መድረክ ለመፋለም ወደ ካይሮ ከማቅናቷ ቀድሞ ታዲያ በርካታ የስፖርቱ አፍቃሪያንና ባለሙያዎች ከምድቧ እንኳን ማለፍ እንደማትችል ጥርጥር አልነበራቸውም።ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ዲፕየስ ብሄራዊ ቡድኑን ወደ አፍሪካው ዋንጫ ይዘው ሲጓዙ አንድ ቃል የገቡት ነገር ቢኖር መሰል የደሴቷን ቡድን በሚመለከት የተሰጡ አስተያየቶች ስህተት መሆናቸው ለማስመስክር ነበር። ፍልሚያ ሲጀመር በምድብ ድልድሉ ከጊኒ፤ ከብሩንዲና ናይጄሪያ ጋር የተደለደሉት የማዳጋስካር ተጫዋቾች ሜዳ ላይ ያሳዩትም ድንቅ ብቃትና የአልሸነፍ ባይነት ተጋድሎ የአሰልጣኙ ቃል የጠበቀና ብሄራዊ ቡድኑም በፈርኦኖቹ ሰማይ ስር ክስተት መሆኑን ያረጋገጠ ሆኗል። በውድድሩ ጅማሮ የናቢ ኬይታ አገር ጊኒ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በሁለት አቻ ውጤት ያጠናቀቁት የማዳካስካር ተጫዋች በመጀመሪያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፏቸው የመጀመሪያ ነጥብና ግብ ማስመዝገብ ችለዋል። ከሁሉ በላይ ግን በፈርኦኖቹ ሰማይ ስር በጨዋታው ያሳዩት ድንቅ ብቃትም የአልሸነፍ ባይነት ተጋድሎ ምናልባትም በርካቶች ስለ ቡድኑ የሰጡት ግምት ስህተት ስለመሆኑ ቆም ብለው እንዲያስቡ መልዕክት የሰጠ ነበር። በተለይ በሁለተኛው የምድብ ጨዋታዋ ከምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ብሩንዲ ጋር የተፋለመችው የዓለማችን አራተኛዋ ትልቅ ደሴት አገር፤ ጨዋታውን አንድ ለዜሮ በማሸነፍ በአፍሪካ ዋንጫው ታሪክ የመጀመሪያ ሦስት ነጥብ ማግኘትና አዲስ ታሪክ መፃፍ ችላለች። ውጤቱም 25 ሚሊየን ህዝብ እንዳላት የሚነገርላት አገር በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ቀልብን እንድትሰርቅ አስችሏታል። እንግዳዋ የአህጉሪቱ ታላቅ የእግር ኳስ መድረክ እንግዳ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋን ያደረገችው ደግሞ የአፍሪካ ዋንጫውን ምልክትና የመድረኩ ድምቀት የሆኑ በርካታ ስመጥር ተጫዋቾችን ከያዘችው ናይጄሪያ ጋር ነበር። በዚህ ጨዋታም የሦስት ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮናዋ ናይጄሪያ ከጠንካራነቷና በመድረኩ ካላት የካበተ ልምድ አንፃር ደሴቲቱ በፍልሚያው በቀላሉ እንደምትሸነፍ ቢገመትም ሜዳ ላይ የሆነው ግን ከዚህ ተቃራኒ ነው። ጨዋታውም በአፍሪካው ታላቅ የእግር ኳስ መድረክ እንግዳ ቡድን 2 ለ 0 አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል። ውጤቱንም ወደ አፍሪካው ዋንጫ ስትመጣ በርካቶች እርግጠኛ ሆነው ከምድቧ እንኳን እንዳማታልፍ የገመቷት አገር ግምቶቹን ሁሉ ማክሸፍ እንደቻለች ያስመሰከረ ሆኗል። በሰባት ነጥብ እና በአምስት ግቦች ከምድብ ሁለት ቀዳሚ ሆና ያጠናቀቀችው አገሪቱም ናይጄሪያን በማስከተል 16 ቱን መቀላቀሏም በአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ማንም የማይዘነጋው አዲስ ታሪክ ሆኖ ተመዝግቦላታል። እኤአ የ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮኗን ናይጄሪያን በድንቅ ብቃት ያሸነፉት ማዳካስካሮች በቀጣዩ መርሐ ግብር የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ከሌላኛዋ ጠንካራ የእግር ኳስ አገር ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ተጫውታለች።መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት አቻ በተጠናቀቀው ጨዋታ፤ በመጨረሻ በማዳጋስካር የ 4 ለ 2 አሸናፊነት መቋጫውን አግኝቷል። የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት አንደሪ ራጆሊናን ከጨዋታ ቀድሞ የመንግሥት ድጎማ በማድረግ አራት መቶ ሰማንያ ደጋፊዎችን ብሄራዊ ቡድኑን እንዲያበረታቱ ካይሮ የሚያደርሳቸውን የአውሮፕላን ወጪ ሸፍነው፤ ስታዲየም እንዲገኙ ማድረጋቸው ለውጤቱ መገኘት ወሳኝ ሆኖ ታይቷል። አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው 39ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጉባኤ ካሜሩናዊው ኢሳ ሃያቱ ለሦስት አስርታት ዓመታት የነገሱበትን በትረ ስልጣን በመረከብ ካፍን በፕሬዚዳንትነት መምራት የጀመሩት ማዳጋስካራዊው አህመድ አህመድ፤ ካይሮ በመገኘት ለቡድኑ ጥንካሬና አስደማሚ ጉዞ ከፍተኛውን አስተዋፆኦ አበርክተዋል። ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨዋታ በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫው አስደናቂና ተዓምራዊ ጉዟቸውን የቀጠሉት ማዳካስካሮች ውጤቱን ተከትሎ ወደ ሩብ ፍፃሜው ማለፍ ችለዋል።ይህ ውጤትም በመዲናዋ አንታናናሪቮና ሌሎች ከተሞች እንዲሁም በስታዲየም የተገኙ የአገሬው ደጋፊዎች በእጅጉ አስፈንጥዟል። ከሁሉ በላይ ግን በርካታ እግር ኳስ አፍቃሪያንና የዘርፉ ባለሙያዎች ከአስራ አምስት ዓመት ቀድሞ እኤአ በ2004 በተካሄደው የአውሮፓ ዋንጫ ላይ የግሪክ ብሄራዊ ቡድን ሳይጠበቅ የሰራውን የማይታመን ድንቅ ታሪክ ሊደግሙት እንደሚችሉ ሰፊ ግምት ሰጥቷቸዋል። ሩብ ፍፃሜው ፍልሚያም ለአፍሪካ ዋንጫው እንግዳ በሆነችውና በፊፋ የአገራት የእግር ኳስ ደረጃ 108 ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ማዳጋስካርን፤ በአፍሪካ ዋንጫው ብቻም ሳይሆን በዓለም ዋንጫ ሳይቀር መሳተፍ የቻለችውና በፊፋ የአገራት የእግር ኳስ ደረጃ 25ተኛ የሆነችው ቱኒዚያ አገናኝቷል። በጨዋታው ከሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ጋር የተፋጠጡት ማዳጋስካሮች ከአስደማሚ የመድረኩ ቆይታ በኋላ በመጨረሻ ለቱኒዚያን እጅ ሰጥተዋል። ከአስራ አምስት ዓመት በፊት የአፍሪካው ሻምፒዮን የነበረችው ቱኒዚያ፤ጨዋታውን ሶስት ለዜሮ አሸንፋለች። በርካቶችም ከሁለቱ አገራት ቡድን ጥራትና ደረጃ አንፃር የማዳጋስካር ሽንፈት ብዙም የሚያስገርም አለመሆኑን ተስማምተውበታል። በውጤቱ ምንም እንኳን ማዳጋስካር የግሪክን የአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ አፍሪካ ላይ ለመድገም ሳትታደል ብትቀርም፤ በፈርኦኖቹ ሰማይ ስር ደምቀው የታዩት የዴሴቷ ኮከብ ተጫዋቾች ግን አገራቸውንና ስማቸውን ከፍ አድርገው ማስጠራት ችለዋል። የሚገባቸውን ያህል ክብርና እውቅና ማግኘት አልተቸገሩም። የደሴቲቷ ተጫዋቾች በአፍሪካው ዋንጫ ያሳዩት ድንቅ ብቃትና ያልሸነፍ ባይነት ፅናት የበርካቶችን ጭብጨባ በማግኘት ብቻ አልተወሰነም።ይልቅስ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች እይታ ውስጥ እንዲገቡም አስችሏቸዋል። ከሁሉ በላይ ግን የአገሬው እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በቀጣይ ስፖርቱ ለማሳደግ በተለይ ወጣቶች ላይ ትኩረት መስጠት ከቻለ አገሪቱ ምርጥ ተጫዋቾች እንዳላት ማስመስከሩን በርካቶች ተስማምተውበታል። በአህጉሪቱ ታላቅ የእግር ኳስ መድረክ ሳይጠበቁ ክስተት መሆን የቻሉት የማዳጋስካር ኮከቦች አገራቸው ሲመለሱም የጀግና አቀባባል ቢደረግላቸውም የሚገርም አይሆንም። አዲስ ዘመን ሀምሌ 8/2011 ታምራት ተስፋዬ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14175
ad36a5a68f0fc293018217bdc315fad9
9be317def1613749b73235a75ec174e7
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ካንሰር ብሄር ተኮል “ስያሜ” ወይስ “እሳቤ”?
በኢትዮጵያ በተለይ እግር ኳሱ ስፖርት ለሰላም፣ለጤንነት የሚለው ዜማ ተገልብጦ ለጦርነት ከሆነ ሰንበት ብሏል። እግር ኳሱ ክፉኛ በሆነ መልኩ “ዘረኝነት” በሚባል ጊዜ አመጣሽ በሽታ ሽምድምድ ብሎ ከስታዲየም ውጪ ተኝቷል። የበሽታው ደረጃ በዚሁ ከቀጠለ እስከ ሞት ሊያደርሰው እንደሚችል በስፖርቱ አዋቂዎች በኩል በተደጋጋሚ የሚሰነዘር ምክረ ሃሳብ ሆኗል። በተለይ በ2011 ዓ.ም የውድድር ዓመት በእግር ኳስ ሜዳዎች ፈር የለቀቀ ስርዓት አልበኝነት፣ ግጭትና ሁከት በሰፊው ተንጸባርቋል። ከስፖርቱ አውድ ውጪ በሆነ መልኩ እግር ኳሱ ፖለቲካም ጭምር ሆኗል ታዝበናል። የስፖርቱ ባህሪ ባልሆነ መልኩም እነዚህ ተግባራት ስታዲየም ገብተው ተመልክተናል። ችግሩ ዓይን ባወጣ መልኩ የመፈጸሙ ሁኔታ እግር ኳሱን ከመዝናኛ አውዱ አውጥቶ የስጋት አውድማ አድርጎታል። በ2011 በዚህ ሂደት ውስጥ ያለፈው የኢትዮጵያ እግርኳስ የዓመቱ መርሐግብር ፍፃሜውን ቢያገኝም የችግሩ ዳፋ ወደ መጪው የውድድር ዓመት እንዳይሸጋገር ከወዲሁ የቤት ስራዎች በብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በኩል እየተሰሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ከ2012 ዓ.ም ስያሜያቸው ብሄር ተኮር የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦች ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ይደረጋል ሲል ከሰሞኑ ፌዴሬሽኑ ያስተላለፈው ውሳኔ አንዱ ማሳያ ነው። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እግር ኳሱ በተለየ መልኩ እየማቀቀ ካለው በሽታው እንዲፈወስ የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ ቢሆንም፤ ይህ አይነቱ ውሳኔ የተጠናና የሃገሪቱን ክለቦች ነባራዊ ሃቅን ያገናዘበ ስለመሆኑ ጥያቄን ያስነሳል። የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እንዲህ አይነት ውሳኔ ከማስተላለፍ ጀርባ «በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ቅኝቱን የቀየረው የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር የክለቦች ስያሜ ብሄር ተኮር ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ነው» የሚል አቋም እንዳለው ያመላክታል። በእግር ኳሱ ዘረኝነት ብሄርተኝነት የሚንጸባረቅ መሆኑን የአደባባይ ሚስጥር ቢሆንም፤ በሊጉ ብሄር ተኮር ስያሜ የያዙ ክለቦችን ከሁለትና ሦስት ክለቦች ውጪ አሉ ብሎ ለማስቀመጥ የሚቸግር ነው። ወደ ደቡብ ስንሻገር ወላይታ ዲቻ፣ ሲዳማ ቡና ብሄር ተኮር ስያሜን የያዙ ክለቦች እንደሆኑ መጥቀስ ይቻላል። በፕሪሚየር ሊጉ እየተንጸባረቀ ላለው ችግር በሁለቱ ክለቦች ደጋፊ መካከል ፍጥጫውን በተለያዩ ጊዜያት ታዝበናል። ሆኖም ይህ በችግሩ ላይ እንደ እርሾ ሊታይ የሚችል እንጂ ዋነኛ ተደርጎ ለማቅረብ የሚያዳግት ነው። ፋሲል ከነማ ፣መቐለ ሰባ እንደርታ ፣ባህርዳር ከነማ ፣ሃዋሳ ከነማ ፣ድሬዳዋ ከነማ ፣ስሁል ሽረ ፣ደደቢት ፣ጅማ አባ ጅፋር …ሌሎች ያልተጠቀሱት ክለቦች የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ መሆናቸው ይታወቃል። ብሄር ተኮር ስያሜን የያዙት ክለቦች የትኞቹ እንደሆኑ ግልጽ ማድረግ የሚገባውና አሻሚ ሃቅ መሆኑን ከስፖርቱ ቤተሰብ በኩል የሚነሱ ሃሳቦች ናቸው። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ከተጠቀሱት ክለቦች ውስጥ የትኞቹ ክለቦች ብሄር ተኮር ስያሜን እንዳልያዙ መናገር ይቻላል። የፌዴሬሽኑ ውሳኔ ቀጣይ ለሚመጡት ክለቦች? ወይስ አሁን ላሉት የሚለው ጉዳይ አሻሚ እንዲሆን ያደርጋል። ችግሩ የታየው ደግሞ ገና በሚመጡት ላይ ሳይሆን አሁን ባሉት እንደመሆኑ በምን አግባብ ይሆን ከሁለቱ ክለቦች ውጪ ያሉትን ክለቦች ብሄር ተኮር ስያሜን የያዙ መያዛቸውን መለየት የሚቻለው። እነዚህ ጉዳዮች ከብሄራዊ ፌዴሬሽኑ በኩል ማብራሪያን የሚፈልጉ ከመሆናቸው ባሻገር ፌዴሬሽኑ የችግሮቹን መሰረት በአግባቡ ተረድቷል ወደሚል እሳቤ አይወስዱም። ምክንያቱም በፕሪሚየር ሊግ የሚገኙ ክለቦች አብዛኛዎቹ ከተማ አቀፍና ተቋማዊ መሰረት ያደረጉ እንጂ ብሄርን መሰረት ያደረጉ አይደሉም። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ አካሄዱን ዘወር ብሎ መፈተሽ የሚገባው በከተማም ሆነ በተቋም ደረጃ የተደራጁት ክለቦች ደጋፊዎች የሚመነጩት ክልልን ፣ዘርን ፣ብሄርን ፣ማንነትን በለየ ሁኔታ መሆኑን ነው። ደጋፊዎች በክልላቸው እንዳለው ክለብ ብዛት አንድም ፣ሁለትም ፣ሦስትም ቡድንን በእኔነት ስሜት የመደገፍ ዝንባሌን አዳብረዋል። በደጋፊዎች በኩል መፋጠጦቹም ሆነ መቀራረቦቹ በክልል የተቧደኑ ነበሩ። የአንዱ ክለብ ደጋፊ ከሌላው ደጋፊ ሲጋጭና ሲቋሰል የነበረው ወቅታዊ የሃገሪቱን ፖለቲካ በተከተለ መልኩ እንደነበር ለመታዘብ ችለናል። ክለቦች ከቆሙበት ክልል አኳያ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችና የሚፈጠሩ መፋጠጦች፤ በተቃራኒው ደግሞ የወንድማዊነት፣ የወገንተኝነት አዝማሚያዎች በዚህ መልክ የተቃኙ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር። ለዚህም እንደማሳያ መጥቀስ ካስፈለገ ከሻምፒዮናው መቐለ ሰባ እንደርታ ፣ከስሁል ሽረ ፣ከደደቢት ብሎም ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለቦች እርስ በእርስ ሲገናኙ የሚስተዋለው የስታዲየም ድባብ የአንድነት ፣የወንድማማችነት አዝሎ ነው። በፋሲል ከነማ ፣ባህርዳር ከነማ ፣ወልዲያ ከነማ ደጋፊዎች መካከል ያለውን ስሜት በተመሳሳይ ስንቃኘው አብሮነት ፣ወንድማዊነቱ ጎልቶና ከፍ ብሎ ይስተዋላል። የስታዲየሙ ድባብም ሆነ የመዝሙሩ ሁናቴ ይቀየራል። ስፖርታዊ ጨዋነቱ ከፍ ብሎ ይስተዋላል። በዚህ መልክ በነበሩ ጨዋታዎች ላይ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግሮቸ ከሞላ ጎደል እንጂ ብዙም የጎላ አልነበሩም። የእግር ኳሱን ድባብ የሚቀይረውና ጸብና ስርዓት አልበኝነቱ የሚጎላው የአንዱ ክልል ክብ ከሌላ ክልል ክለብ ጋር በሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ ነው። በ2011 ዓ.ም የውድድር ዓመትን ዘወር ብለን በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል ክለቦች መካከል የነበረውን ሁኔታ ስንፈትሽ እውነታውን ያስረዳናል። ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ የስፖርታዊ ጨዋነት ምንጩ የክለቦች ብሄር ተኮር ስያሜ ከመያዛቸው መሆኑን ጠቅሶ «ብሄር ተኮር የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦች ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ይደረጋል »የሚለው ውሳኔ ዳግም ሊፈተሽ እንደሚገባ ያመላታል። ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ካንሰር የሆነው ብሄር ተኮር ስያሜ ሳይሆን ብሄር ተኮር እሳቤ መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል።ብሄር ተኮር ስያሜን የያዙ ክለቦች ያውም በሌሉበት ስያሜው ተቀይሮ አመለካከት ሳይቀየር ለውጥ ወዴት ይገኝ ይሆን ? ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ መሬት ያለውን እውነት ተቀብሎ አመለካከት ላይ መስራቱ አንዱና ዋነኛው መፍትሄ ሊሆን ይገባል። ሌላው በዘረኝነት በሽታ በሲቃ ውስጥ የሚገኘውን እግር ኳስ መድህን ለማግኘት በተለያዩ መድረኮች ሲነሱ የነበሩ የመፍትሄ ሃሳቦችን ዘወር ብሎ መመልከቱም መዘንጋት የለበትም። የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ የዘር ልዩነት እንዲጠፋ የኦሊምፒክና የዓለም አቀፍ የስፖርት ማኅበራት ደንብና መመሪያዎች እንዲከበሩ ማድረግ አንዱና ዋነኛው መፍትሄ ነው። የብሄራዊ ፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ህግ ዳግም መቃኘት ሌላው መፍትሄ ይሆናል። በእግር ኳሱ የሚስተዋለው የስፖርታዊ ጨዋነቱ ችግር ቀደም ሲል ከነበረው ፍጹም የተለየ ነው። በመሆኑም ኢትዮጵያ እግር ኳስ ወቅታዊና ነባራዊ እውነት መሰረት አድርጎ ማዘጋጀት ያስፈልጋል። የሕግ የበላይነት እንዲከበር የመንግሥት ቁርጠኝነትና ውሳኔ እንዲኖር ማድረግ ተያይዞ የሚነሳ መፍትሄ ነው፡፡ አዲስ ዘመን ሀምሌ 8/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14172
a4b7533fcb07dfd6e83316a63d98b750
e1b7442d800b9ee7d781bdfcb6823f6e
ከሄልሲንኪ እስከ ዶሃ
ከባድ በሆነውና ታላቅ ጽናትን በሚጠይቀው የአትሌቲክስ ዘርፍ ማራቶን ዓለም አቀፍ ተሳትፎዋን የጀመረችው ኢትዮጵያ፤ በበርካታ ገድሎች የአትሌቲክስ ታሪኳን አድምቃለች። ከኦሊምፒክ ቀጥሎ ታላቅ ስፍራ ባለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናም የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስመዘገበችው በማራቶን ነው። ሃገሪቷ ካስመዘገበቻቸው 77 ሜዳሊያዎች መካከልም 10 የሚሆኑት በማራቶን የተገኙ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ሁለቱ ወርቅ ሲሆኑ፤ አራት ብር እና አራት ነሃስ ናቸው። የኢትዮጵያ ተሳትፎ መነሻውን እአአ በ1983 በፊንላንዷ ሄልሲንኪ ካደረገው የዓለም ሻምፒዮና ሲጀመር በማራቶን የብር ሜዳሊያ ነው ሰንጠረዡ የተሟሸው። በወቅቱ ኢትዮጵያዊው አትሌት ከበደ ባልቻ በአውስትራሊያዊው ሮበርት ዴ ካስቴሌ ቢቀደምም ጀርመናዊውን ዋልዴማር ሴርፒኒስኪን በማስከተል የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን ነበር ውድድሩን ያጠናቀቀው። ይህ ሜዳሊያም ኢትዮጵያን በሻምፒዮናው በብቸኝነት ያስጠራ ሆኖ ነው የተጠናቀቀው። ከዚያ በኋላ በተካሄዱት ዓለም ሻምፒዮናዎች በዚህ ርቀት ተሳትፎ እንጂ ውጤት ሳታስመዘግብ ነበር የቆየችው። ድሉ ወደ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች እስከተመለሰበት እአአ 2001 የኤድመንተን ሻምፒዮና ድረስም ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ ቆይቷል። ኤድመንተን ላይ የ23 ዓመቱ ወጣት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ባልተጠበቀ መልኩ ሌሎቹን አስከትሎ በመግባት ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያውን ለሃገሩ ማስመዝገብም ችሏል። በወቅቱ የአትሌት ገዛኸኝ አበራ የማራቶን እና የአትሌት ደራርቱ ቱሉ የ10ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያዎች ከሌሎቹ ጋር ተደምረው ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ሁለተኛ ከዓለም ደግሞ ስድስተኛ ደረጃን እንድትይዝ አድርገዋት ነበር። ገዛኸኝ በዚህ ውድድር የወንዶች ተሳትፎ እስካሁንም ያልተደገመ ድል ሲያስመዘግብ፤ በዓለም ሻምፒዮና ታሪክ ከገዛኸኝ ባነሰ እድሜ ማራቶንን ያሸነፈ አትሌት ባለመታየቱ ባለ ድርብ ክብር አትሌት ያደርገዋል። እአአ በ2009 በበርሊን በተካሄደው ሻምፒዮና የበላይነቱ በኬንያዊያን አትሌቶች ቢያዝም ኢትዮጵያዊው አትሌት ጸጋዬ ከበደ ግን የነሃስ ሜዳሊያውን በማጥለቅ ለሃገሩ የርቀቱን ሦስተኛ ሜዳሊያ አጥልቋል። ይህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በማራቶን ሁለት ሜዳሊያ ያገኘችበት ሲሆን፤ በሻምፒዮናው ተሳትፎ ሴቶች የሜዳሊያ ሰንጠረዡን የተቀላቀሉበት የመጀመሪያው ዓለም ሻምፒዮናም ነው። በውድድሩ የቻይናና የጃፓን አትሌቶችን ተከትላ በመግባት የነሃስ ሜዳሊያውን ያጠለቀችው አትሌትም አሰለፈች መርጊያ ናት። በቀጣዩ የዴጉ የአትሌቲክስ ዓለም ሻምፒዮና ላይም ሌላኛው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በማራቶን የሜዳሊያ ሰንጠረዡን መቀላቀል ችሏል። አትሌቱ ሁለቱን ኬንያዊያን አትሌቶች ተከትሎ በመግባቱም ነበር የነሃስ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው። በ13ኛው የሞስኮ ዓለም ሻምፒዮና አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ታደሰ ቶላ ዩጋንዳዊውን አትሌት ተከትለው የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን አስመዝግበዋል። በሴቶች የታየው ውጤታማነት ግን ለሁለት ሻምፒዮናዎች ሳይደገም ነበር የቆየው። በቤጂንጉ ሻምፒዮና አትሌት የማነ ጸጋዬ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያውን ሲያገኝ፤ በሴቶች በኩል ሁለተኛው ሜዳሊያ የወርቅ ሆኖ ሊመዘገብ ችሏል። የጎዳና ላይ ሯጭ አትሌት ማሬ ዲባባ በሻምፒዮናው የኬንያ እና ባህሬን አትሌቶችን በማስከተልም ነው አሸናፊ ልትሆን የቻለችው። ከሁለት ዓመታት በፊት በለንደን በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮናም በአትሌት ታምራት ቶላ የብር ሜዳሊያ ተመዝግቧል። ኢትዮጵያ በማራቶን ካስመዘገበቻቸው 10 ሜዳሊያዎች መካከል ስምንቱ ሜዳሊያዎች በወንዶች የተመዘገቡ ናቸው። በዓለም ዓቀፍ ደረጃም ባስመዘገቧቸው ሜዳሊያዎች 4ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጡ ችለዋል። ከሦስት ወራት በኋላ በኳታሯ ዶሃ አስተናጋጅነት ትልቁ የአትሌቲክስ ውድድር የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለ17ኛ ጊዜ ይካሄዳል። በዚህ ሻምፒዮና ላይም ኢትዮጵያን አትሌቶች እንደተለመደው በርቀቱ የሚሳተፉ ሲሆን፤ ቡድኑን የሚወክሉት አትሌቶችም ታውቀዋል። በሻምፒዮናው ላይ በርካታ ሃገራትን ጨምሮ ማህበሩን የወከሉት የስደተኞችና በተለያዩ ምክንያቶች ለሃገራቸው የማይሮጡ በሺዎች የሚቆጠሩ አትሌቶችም ተሳታፊዎች ይሆናሉ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም በሁለቱም ጾታዎች የማራቶን ቡድኑን ከእነ ተጠባባቂዎቻቸው አስታውቋል። ምርጫውም አትሌቶቹ ባስመዘገቡት የተሻለ ሰዓት እንዲሁም በዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ዋና ዋና ውድድሮችና የወርቅ ደረጃ በተሰጣቸው ማራቶኖች ተሳትፏቸው የተመረጡ ናቸው። በውድድሮቹ ላይ እአአ ከሴፕቴምበር 2018- ኤፕሪል 2019 ድረስ ተወዳድረው ያስመዘገቡት የተሻለ ሰዓትም በሻምፒዮናው ሃገራቸውን እንዲወክሉ ያደርጋቸዋል። በወንዶች በኩል ስድስት አትሌቶች ቡድኑን ሲቀላቀሉ፤ በቅርቡ በተካሄደው የለንደን ማራቶን ተሳትፎው የኢትዮጵያን ክብረወሰን የሰበረው እና በዓለም ሦስተኛውን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበው አትሌት ሞስነት ገረመው በቅድሚያ የተመረጠ አትሌት ሊሆን ችሏል። ሞስነት ቀዳሚ ለመባል የቻለው ደግሞ ባስመዘገበው 2 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ የሆነ ምርጥ ሰዓት ነው። ባለፈው ዓመት በቺካጎ ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ሞስነት፤ እአአ በ2015ቱ የቤጂንግ ዓለም ሻምፒዮና 10ሺ ሜትር ሃገሩን እንደወከለ የሚታወስ ነው። በለንደኑ ማራቶን ከሞስነት ጋር በአንድ ደቂቃ ልዩነት የግሉን ፈጣን ሰዓት ማስመዘግብ የቻለው አትሌት ሙሌ ዋሲሁን ለቡድኑ በሁለተኛነት ተመርጧል። አትሌቱ ያለው ሰዓት 2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ ሲሆን፤ እአአ በ2016 የካርዲፍ ግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና፤ ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ ነበር ያጠናቀቀው። ሌላኛው አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳም ባስመዘገበው ሰዓት ቡድኑን የተቀላቀለ ሦስተኛው አትሌት ነው። እአአ በ2013ቱ የሞስኮ ዓለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ ለሃገሩ ያስመዘገበው አትሌቱ፤ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የኒውዮርክ ማራቶን የገባበት 2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ የሆነ ሰዓት ተመራጭ አድርጎታል። በማራቶን ዝነኛ ከሆኑ የዓለም አትሌቶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ሌሊሳ፤ ከኒውዮርክ ጎዳናዎች ባሻገር በቦስተን ማራቶንም ተደጋጋሚ ድሎችን አጣጥሟል። ዘንድሮ ባደረገው አራተኛ ተሳትፎውም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ነበር ያጠናቀቀው አትሌቱ። በሴቶች በኩልም በተመሳሳይ ሦስት አትሌቶች የተመረጡ ሲሆን፤ አትሌት ሩቲ አጋ ባላት ሰዓት ቡድኑን ትመራለች። አትሌቷ ቀዳሚ ምርጫ ልትሆን የቻለችው ባለፈው ዓመት በተካሄደውና የወርቅ ደረጃ ባለው የበርሊን ማራቶን ባስመዘገበችው 2 ሰዓት ከ18ደቂቃ ከ34 ሰከንድ የሆነ ምርጥ ሰዓቷ ነው። አትሌቷ ከወራት በፊት በተካሄደው የቶኪዮ ማራቶን 2:20:40 በሆነ ሰዓት አሸናፊ ነበረች። በዚህ ዓመቱ የዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 17ደቂቃ ከ41 ሰከንድ የገባችው አትሌት ወርቅነሽ ደገፉም በቡድኑ የተካተተች ሁለተኛዋ አትሌት ናት። በማራቶን ውድድሮች የተሻለ ውጤት ያላት አትሌቷ፤ ከዱባይ በኋላ በተካሄደው የቦስተን ማራቶን አሸንፋለች። በባለፈው ዓመቱ የዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት ከ19ደቂቃ ከ17ሰከንድ ያስመዘገበችው ሌላኛዋ አትሌት ሮዛ ደረጀም በሻምፒዮናው ሃገሯን እንደምትወክል አረጋግጣለች። በወንዶች በኩል በተጠባባቂነት ሦስት አትሌቶች የተያዙ ሲሆን፤ በቅርቡ በለንደኑ ማራቶን ተሳታፊ የነበረው ሹራ ኪጣታ ባለው ሰዓት ቀዳሚው ተጠባባቂ ሆኗል። ሹራ በዚህ ማራቶን 2ሰዓት ከ05ደቂቃ ከ01ሰከንድ የሆነ ሰዓት አስመዝግቧል። በተመሳሳይ በዚህ ዓመት በተካሄደው የቶኪዮ ማራቶን ተሳትፎው 2ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ48ሰከንድ በመግባት ያሸነፈው አትሌት ብርሃኑ ለገሰ ሁለተኛው ተጠባባቂ ነው። ባለፈው ዓመት የዱባይ ማራቶንን 2ሰዓት ከ04ደቂቃ ከ06 ሰከንድ የሮጠውና በለንደኑ የዓለም ሻምፒዮና በማራቶን ብቸኛውን ሜዳሊያ ያስመዘገበው አትሌት ታምራት ቶላም በተጠባባቂነት ከተያዙ አትሌቶች መካከል ይገኛል። በቶኪዮ ማራቶን በሰከንዶች ተበላልጠው ውድድራቸውን የፈጸሙት አትሌት ሹሬ ደምሴ እና ሄለን ቶላ ደግሞ በሴቶች በኩል በተጠባባቂነት የተያዙ አትሌቶች ናቸው። ከሄልሲንኪ የጀመረው የኢትዮጵያ የማራቶን ድል እስከ ዶሃ እንዲዘልቅም ዝግጅቱ ከወዲሁ ተጀምሯል። በውድድሩ ህግ መሰረት ለሻምፒዮናው የተመረጠ አትሌት ለሦስት ወራት የማገገሚያ ጊዜ የግድ ያስፈልገዋል። በዚህም መሰረት አሁን አትሌቶቹ ከውድድር ርቀው በአሰልጣኞቻቸው ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በመጪው ሐምሌ ወር በሻምፒዮናው ተሳታፊ የሚሆኑ አትሌቶችን ለመምረጥ በኔዘርላንድ ሄንግሎ ከሚካሄደው የሟሟያ ውድድር በኋላም ብሄራዊ ቡድኑ ወደ ካምፕ ገብቶ ልምምዱን እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 8/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14170
d2b5730b7ee1742564fa38eaf75afdc9
1235e334b4a67360d6c3c5da642d8a65
የኦሊምፒዝምን መርህለሳምንት ሳይሆን ለዓመት ማከበር ይገባል
አዲስ አበባ፡- ወንድማማችነት፣ አብሮነት፣ ፍቅር ሰላምና ክብር የሚሰብከውን የኦሊምፒዝም መርህን ለሳምንት ሳይሆን ለዓመት ማከበር እንደሚገባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው አስታወቁ። በአዲስ አበባ ከተማ ለአንድ ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲካሄድ የቆየው ዓመታዊው የኦሊምፒክ ሳምንት ከትናንት በስቲያ በካፒታል ሆቴል በተካሄደው የማጠቃለያ ውይይት ፍፃሜውን አግኝቷል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የኦሊምፒክ ሳምንት «ኦሊምፒዝም ለሰው ልጆች ክብር፣ ሰላምና አንድነት» በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 30 ጀምሮ ሲከበር ቆይቷል። በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው፤ «ወንድማማችነትን፣ አብሮነት፣ ፍቅር፣ ሰላምና ክብርን የሚሰብከው የኦሊምፒክ ሳምንት በተለይ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ሕዝቦች በመድኃኒትነት ለአንድ ሳምንት ሳይሆን ለዓመት መታዝዝ አለበት» ብለዋል። መድረኩ የኦሊምፒዝምን መርህ ይበልጥ ለማስረፅ የአስተሳሰብና እና የባህሪ ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው፤ የኦሊምፒዝም ፅንሰ ሃሳብ ከሁሉም ዘንድ እንዲሰርፅ የሚመለከታቸው አካላት ይበልጥ መስራት እንዳለባቸው አስታውቀዋል። የዘንድሮው የኦሊምፒክ ሳምንት በሀገሪቱ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ስድስት ሁነቶች ማለትም በእግር ኳስ፣ አትሌቲክስ፣ሲምፖዚየም፣ኮንሰርት፣ችግኝ ተከላና በኦሊምፒክ አባልነት ምዝገባ መከበሩን አብራርተዋል። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ በበኩላቸው፤ የመቻቻልና አብሮ የመኖር የብዝሃነት ተምሳሌት የሆነችው አዲስ አበባ የኦሊምፒክን መርህ ለማስተላለፍ ጥሩ ማሳያ መሆኗን ጠቁመው፤ በመዲናዋ የተካሄደው የኦሎምፒክ ሳምንትም የታለመለትን ዓላማ በማሳካት ረገድ ስኬታማ እንደነበር አስታውቀዋል። በዚህ ፕሮግራም ሚኒስትሮች፣ አንጋፋ አትሌቶች፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶችና አምባሳደሮች፣ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በሥነሥርዓቱ ላይ ከኦሊምፒክ ፅንሰ ሃሳብ ጋር የተገናኙ ጽሑፎች ለታዳሚ የቀረቡ ሲሆን፤ ለመርሃ ግብሩ ስኬታማነት የተሻለ ተግባር ለፈፀሙ አካላትም የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 9/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14235
c974bd3b216219a43372bb86032e3d95
118f9d0732266d99ba67fea07cfcf4a0
የማይታረሙ ስህተቶች
የጉዳት መጠናቸው ቢለያይም በስፖርቱ ዓለም ባለሙያዎቹ የሚፈፅሟቸው ስህተቶች በአብዛኛው የሁለት ምክንያቶች ውጤት መሆናቸው ይታመናል። አንዳንዶቹ በውጫዊ ተፅዕኖ ማለትም በደጋፊና በሌሎችም ጫናዎች ሲከሰቱ፤ አብዛኞቹ ደግሞ በስፖርተኞቹ ትኩረት ማጣት ሲከሰቱ ይስተዋላል። የስፖርት ሳይንስ ባለሙያዎች እንደ ሚገልፁት፤ በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር መጠናቀቁ እስካልተረጋገጠ ድረስ አሸናፊ ነኝ ብሎ ደስታውን ማጣጣም ስህተት ነው። ለአብነት እግር ኳስን ስንመለከት በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የሚፈጠረው አይታወቅምና የጨዋ ታውን መጠናቀቅ የሚያበስረው የዳኛ ፊሽካ እስካልተሰማ «አሸንፌአለሁ» ማለት ሞኝነት ነው። በሰፊ የግብ ልዩነት መምራትም ብቻውን ዋስትና አይሰጥም። ይልቅስ ጨዋታው ሊጠናቀቅ የቀሩ ደቂቃዎችን ታሳቢ ማድረግ የግድ ይላል። በአትሌቲክሱም ቢሆን አንድ አትሌት የመጨረሻዋን መስመር ማለፉን እስካላረጋገጠ ድረስ ማሸነፉን ማረጋገጥ አዳጋች ነው። አንድ አትሌትም አሸናፊ ለመሆን ብቃቱን ከመጠቀም በተጓዳኝ ሌሎች ተግባራትን መከወን ግድ ይለዋል። በተለይ መነሻን እንጂ መድረሻውን ማወቅ ካልቻለ እጅግ ከባድ ዋጋ መክፈሉ አይቀርም። ይህን ጠንቅቆ መረዳት ይኖርበታል። ፊት ያለ ሁሉ መሪ ሳይሆን ተደራቢ ሊሆን ይችላልና የትኛው አትሌት ቀዳሚ ሆኖ እየመራ እንደሚገኝና ጠንቅቆ ማወቅም ግድ ይለዋል። ከሁሉም በላይ ውድድሩ ሊጠናቀቅ የቀሩትን ዙሮች ጠንቅቆ ማወቅ የግድ ይላል። ምክንያቱም በርካታ አትሌቶች የመግቢያ መስመሩን ማለፋቸው እንደ አሸናፊነት በመውሰድ በደስታ ሲፈነጥዙ ከኋላ በነበሩ አትሌቶች ተቀድመው ወርቃማ ዕድላቸውን አሳልፈው ሰጥተዋልና ነው። ከሰሞኑ በኢትዮጵያዊው አትሌት ሃጎስ ገብረሕይወት ላይ የሆነውም ይህ ነው። አትሌቱ ከሳምንት በፊት በተካሄደ የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ብዙ ዙሮችን ሲመራ ቢቆይም በኋላ ለማመን በሚከብድ መልኩ «ዙሩ አልቋል» በሚል በድል አድራጊነት ውድድሩን ሲያቋርጥ ታይቷል። መነሻን እንጂ መድረሻውን ማወቅ ያልቻለው አትሌት ሐጎስ፤ በስዊዘርላንድ በተካሄደው የዳይ መንድ ሊግ ውድድር 4 ሺህ 600 ሜትሮችን እንደሮጠ የመጨረሻ መስመር የደረሰ ሲመስለው በድል አድራጊነት እጁን እያነሳ አሸናፊነቱን ሲገልፅ ሚሊዮኖች ተመልክተውታል። የ25 ዓመቱ አትሌት በጊዜያዊ ዝንፈትና ድክመት የፈፀመው ስህተትም የውድድሩን የአሸናፊነት አቅጣጫ ቀይሮቷል። ሐጎስ ዙሩን ሳይጨርስ ያሸነፈ መስሎት ውድድሩን ያቋረጠበትን ምክንያት ሲያስረዳም፤ «የዙሩ የመጨረሻ መግለጫ ደወል ሲደወል አልሰማሁም፤ ውድድሩን እየመራሁ በነበረበት ወቅት ከፊት ለፊቴ አንድ ካሜራማን ነበር፤ በዚያ ምክንያትም ውድድርን በመሪነት ጨርሻለሁ ብዬ አሰብኩና ቆምኩ፤ ተወዛግቤ ነበር፤ ሌሎች ተወዳዳሪዎች አልፈውኝ ሲሮጡ ሳይ እንደገና መሮጥ ጀመርኩ፤ ውድድሩን እንዴት እንደጨረስኩ ባላውቅም ክስተቱ መጥፎ አጋጣሚ ነበር» ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። በአትሌቲክሱ ዓለም መሰል ስህተቶችን በመስራት አሸናፊነቱን አሳልፈው የሰጠው አትሌት ሐጎስ ብቻ ግን አይደለም። ብዙም ባይሆን የኢትዮጵያዊውን ዓይነት የሚያስቆጩ ስህተቶች የሰሩ አትሌቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል ደግሞ እስራኤላዊቷ አትሌት ሎናህ ሳልፒተር ከሁሉ ቀድማ ትታወሳለች። አትሌቷ ባሳለፍነው ዓመት በአውሮፓ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ሺፕ ውድድር ላይ የመግቢያ መስመሩን ሁለተኛ ሆኗ ማለፏን እንደ አሸናፊነት በመውሰድ በደስታ ስትፈነጥዝ ከኋላዋ የነበሩ አትሌቶች ቀድመዋት በመሄድ ውጤቷን ነጥቅዋታል። አትሌቷ በወቅቱ የውድድሩ የመጨረሻ ዙር መሆኑን የሚጠቁመው የደውል ድምፅ ከማስተዋልና ማዳመጥ ይልቅ ደስታዋን ለማጣጣም በመቸኮሏ አራት መቶ ሜትር እየቀራት ሩጫዋን አቋርጣለች፡፡ ምንም እንኳን ካቋረጠችበት ብትቀጥለም በአንዳች ቅፅበት የሰራችው ስህተት ግን ወርቃማ ዕድሏን አሳልፋ እንድትሰጥና አራተኛ ሆና እንድታጠናቅቅ አስገድዷታል። መስል ሁነቶች በአትሌቲክሱ ላይ ብቻም ሳይሆን በሞተር ሳይክል ውድድር ላይም ሲከሰት ታይቷል። እኤአ በ2012 በተካሄደው በጣሊያን ሞተር ሳይክል ሻምፒዮን ሺፕ ሪካርዶ ሩሶ አንድ ዙር እየቀረው ለደስታ ጊዜውን ሲመድብ ተቀናቃኞቹ ቀድመውት አሸናፊነቱን በገዛ እጁ አሳልፎ ሰጥቷል። አንደኛ የነበረው ሞተረኛም አስራ አራተኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል። ምንም እንኳን እነዚህ ስፖርተኞች በአንዳች ቅፅበት በጥቃቅን ስህተት የፈፀሙት ተግባር ውድ ሽልማቶችና ክብሮችን ቢያሳጣቸውም፤ «የማይሳሳተው የሞተ ነው» እንደሚባለው፤ ተግባራቸው የሚያስተቻቸው አይሆንም። በስፖርቱ ዓለምም ስህተቶቹ ነገም መከሰታቸው አይቀሬ ነው። የስህተቶቹ የጉዳት መጠን ቢለያይም እንኳ፣ ዋናው ቁም ነገር እንዳይደገሙ ማስተካከል፣ነገ እንዳይለመዱም ማቅናትና ማፅናት ነው።አዲስ ዘመን  ሐምሌ 9/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14239
719711be17b399ae46c601553030a0c0
a66772bf71275c42b55e3694a7a4bf13
የፓራ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል
የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ ከሐምሌ 8 ቀን/2011 ዓ.ም ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየው አገር አቀፍ የፓራ አትሌቲክስ ቻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል። በቻምፒዮናው በመላ አፍሪካ ጨዋታና በኦሊምፒክ ፓራ አትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያን የሚወክሉ የብሔራዊ ቡድን አትሌቶች እንደሚመረጡ ታውቋል። በቻምፒዮናው አማራ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ተሳታፊ ሲሆኑ አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችም ተካፋይ ሆነዋል። የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚና ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚም ተወዳዳሪ ሆነዋል። ቻምፒዮናው ከተጀመረበት ቀን አንስቶ በተለያዩ ፉክክሮች የፍፃሜ ውድድሮችን እያስተናገደ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል ሙሉ በሙሉ አይነስውራን በሆኑ ወንዶች መካከል የተካሄደው የመቶ ሜትር የሩጫ ውድድር አንዱ ነው። በዚህ ውድድር ታደሰ በቀለ 00፡11፡40 በሆነ ሰዓት በመግባት ከኦሮሚያ ክልል አሸናፊ ሆኗል። በተመሳሳይ ከኦሮሚያ ክልል መሐመድ ከድር 00፡11፡74 ሰዓት በማጠናቀቅ ሁለተኛ ሆኗል። እዮብ ሌንዳሞ ከደቡብ ክልል 00፡12፡16 በመግባት ሦስተኛ ሆኖ ውድድሩን ፈፅሟል። ሙሉ በሙሉ አይነስውራን ባልሆኑ ሴቶች መካከል የተካሄደው የመቶ ሜትር የሩጫ ውድድር ሞሚና አቡ ከኦሮሚያ ክልል 00፡13፡34 በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ አበቡ ሞስየ ከአማራ ክልል 00፡ 14፡23 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። ያምሮት ካሳ 00፡14፡ 90 በመግባት ከአማራ ክልል ሦስተኛ ሆና ፈፅማለች። የእጅ ጉዳት ባለባቸው ሴቶች መካከል በተካሄደው የመቶ ሜትር የሩጫ ውድድር 00፡13፡54 በመግባት ጥሩነሽ ደሳለኝ ከአማራ ክልል ቀዳሚ መሆን ችላለች። ሳባ ተራማጅ ከደቡብ ክልል 00፡14፡02 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆና ስትፈፅም በተመሳሳይ ከደቡብ ክልል መሰረት ዮሐንስ 00፡14፡36 ገብታ በሦስተኛነት ውድድሩን ጨርሳለች። በወንዶች መካከል በተካሄደው ተመሳሳይ ውድድር ኤከር መቻል ከደቡብ ክልል በ00፡11፡29 ሰዓት አሸናፊ ሆኗል። ሮባ ደበሌ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ 00፡11፡ 52 በመግባት ሁለተኛ ሲሆን ቤዛ አለሙ ከአማራ ክልል 00፡11፡ 80 አስመዝግቦ በሦስተኛነት ጨርሷል። በወንድ ዊልቸር ተጠቃሚ 1ሺ500 ሜትር ውድድር ደምስ አበረ ከአዲስ አበባ 1ኛ ፣ ዮሴፍ ዓለሙ ከኦሮሚያ 2ኛ እንዲሁም ታከለ ፈለገህይወት ከአማራ 3ኛ በመሆን ጨርሰዋል። ቻምፒዮናው ዛሬ ሲጠናቀቅ በስምንት መቶ ሜትር በሁሉም የጉዳት ዓይነቶች ውድድሮች የሚከናወኑ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ በርዝመት ዝላይ ሙሉ በሙሉ አይነስውራንና ጭላንጭል አይነስውራን እንዲሁም በእጅ ጉዳተኞች መካከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ የውድድር ክፍል ኃላፊ አቶ ዮናስ ገብረማርያም በውድድሩ ወቅት ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፣ የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ስፖርት ውጤታማ ቢሆንም ካለው አካል ጉዳተኛ ቁጥር አኳያ በቂ አይደለም። ለዚህም ብዙ ምክንያቶችን ያስቀመጡ ሲሆን፣ በዋናነት የውድድሮች ማነስ፣ወጥ የሆነ የሥልጠና ሥርዓት አለመኖር፣የማዘውተሪያ ስፍራና ቁሳቁሶች አለመሟላት ስፖርቱን እንዳያድግ አድርገውታል። ያም ሆኖ ባለፉት ሁለት የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በተለያየ ጊዜ አራት የነሐስ ሜዳሊያና አልጄርስ ላይ ሁለት ብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያ ተመዝግቧል። ከነችግሮቻቸውም ቢሆን የፓራሊምፒክ አትሌቶች ውጤታማ እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ ዮናስ፤ ከዚህ በላይ ውጤታማ መሆን እየተቻለ በውድድርና በቁሳቁሶች እጥረት በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ መሆን እንዳልተቻለ አብራርተዋል። የውድድሩን ዓላማ አስመልክተው የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን ስጦታው እንደገለፁት፤ የፓራሊምክ ስፖርት በርካታ ስፖርቶችን ያቀፈ መሆኑ እና ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ፓራ አትሌቲክስ መሆኑን ጠቁመው፣ በፓራ አትሌቲክስ ኢትዮጵያ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ውጤታማ እየሆነች መምጣቷን ተናግረዋል። በመሆኑም የዚህ ውድድር ዓላማ በቀጣይ በሚካሄዱ የፓራሊምፒክ መላ አፍሪካ ጨዋታ፣ የዓለም ቻምፒዮና እና የቶኪዮ ፓራሊምፒክ ለመሳተፍ የማጣሪያ ውድድሮች ስለሚካሄዱ ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጀመሪያ ዙር ዕጩ የብሔራዊ ቡድን ለመምረጥ ታስቦ እንደተዘጋጀ አብራርተዋል። የብሔራዊ ቡድን ምርጫው በዚህ የሚያበቃ ሳይሆን በቀጣይ በሚካሄዱ የተለያዩ ውድድሮች ጥሩ ብቃት ያላቸው አትሌቶች እንደሚመረጡም አክለዋል ። ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14367
eef0249d82b9054a128f5552e9fa853b
d27d8530c76d096a5ddab0ac8e19594d
ስፖርት ለአንድነት ፤ ስፖርት ለልዩነት
ስፖርት አንድነት በማጠናከር ብሄራዊ ስሜትን በመገንባት ረገድ ትልቅ ሚና ያለው ማህበራዊ ክንውን እንደሆነ ይነገራል። በጥንቃቄና በተገቢው ሁኔታ መጠቀም ካልተቻለ ስፖርቱ የአንድነት ሳይሆን የልዩነት ምንጭ እንደሚሆን ብዙ ዓለም አቀፍ ልምዶች ያመላክታሉ። የስፖርቱን ሁለት አይነት ተቃርኗዊ ግብርን ከ«መድሃኒት» አጠቃቀም ጋር ተመስሎ ሊቀርብ ይችላል። መድሃኒት ለጤና ፈዋሽም ጠንቅም የመሆን ባህሪ አለው። በአግባቡና በጥንቃቄ መጠቀም ሲቻል ፈዋሽነቱ፤ አጠቃቀሙ ሲዛባና ክፍተት ሲኖረው ጠንቅ የመሆን ተቀያያሪ ባህሪን የሚላበስ መሆኑን የህክምና ሳይንሱ ይናገራል።የመድሃኒት አዳኝነት አጠቃቀሙን ተከትሎ እንደሚሰጠው ውጤት ሁሉ ፤በስፖርቱ አንድነትን ብሄራዊ ስሜትን መገንባትና ማምጣት አጠቃቀሙን መሰረት አድርጎ ነው። የስፖርቱን ይህ ሚና በሀገራችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ተከስተው አልፈዋል። በብሄራዊ ስሜት ግንባታ ውስጥ የስፖርቱን የተለያዩ ተቃራኒ ሚናዎችን ያሳዩ በርካታ አጋጣሚዎች ዘወር ብሎ መመልከቱ አካሄድን ለማስተካከል ይረዳልና ፤ለመመልከት ወደድን። በመጀመሪያ አንድነት በመፍጠር ረገድ ያለውን ሚና እኤአ በ2013 የደቡብ አፍሪካ ዋንጫ ትልቁ ማሳያ ይሆኗል የዋልያዎቹ ከ31 ዓመት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ በእግር ኳሱ ውስጥ ብሄራዊ ስሜት ሲገነፍል ለመታዘብ ተችሏል። ኢትዮጵያዊነት ስሜት ከገባበት ሰመመን በመቀስቀስ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት ያስፈነጠዘ ነበር። የልዩነት ነጋሪት ጉሰማውን ድምጽ የዋጠና ፤የአንድነቱን ድምጸት ያጎላም ጭምር ነበር። በአትሌቲክስ ስፖርት የተገነባው የዘመናት ብሄራዊ ስሜትን ዳግም እንዲያንሰራራ ያደረገ ትልቅ አጋጣሚ ከመሆን በተጓዳኝ ብሄራዊ መግባባት የፈጠረ ልዩ አጋጣሚ ተብሎ እንዲነገር ያስቻለም ነበር። እነዚህ ሁለት የተለያዩ አጋጣሚዎች ስፖርትን ይህን መስመር ይዞ የወንድማማችነት፣ የወዳጅነት፣ የአንድነት ማጠናከሪያ ገመድነቱን ይገልጣሉ። ስፖርትም እንደ መድሃኒት ሁሉ በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ውጤቱ የአንድነት ዋልታና ማገር ይሆናል። በተቃራኒው ደግሞ በአግባቡና በጥንቃቄ መጠቀም ካልተቻለ ስፖርት የልዩነት ምንጭ ፣ብሄራዊ ስሜትን የሚንድ ሆኖ እናገኘዋለን።የስፖርት ብሄራዊ ስሜትን የመናድ ግብሩ በዋነኛነት ስፖርቱ መሰረትን በሳተና ብሄርን መሰረት ባደረገ መልኩ ከመከወን የሚቀዳ እንደሆነ የዘርፉ አዋቂዎች ይናገራሉ። የስፖርት ሳይንስ ምሁሩ ፒተር አሊግ (Peter algi) እኤአ 2009 ባሳተመው ጆርናል የስፖርታዊ ክንውን እንዴት አንድነትን ሸርሽሮ የልዩነት ማዕከል እንደሚሆን አስፍሮታል። በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ብሄርተኛ ክለቦች መበራከት ብሄራዊ ስሜትን ወደ ፈተና የሚከቱ መሆናቸው ላይ አስፍሯል። ፒተር ስፖርትን የአንድነት ስሜት እንዲያደበዝዝ በተለየ መልኩ በቅኝ ገዢዎች ተግባራዊ መደረጉን በመግለጽ ፤ብሄርተኛ ክለቦች በአንድ ብሄር ፣ ብሄረሰብ፣ ጎሳ እና ዘር ተለይቶ እንዲታወቅ ብሎም እንዲደገፍ ተደርጎ የሚመሰረት የእግር ኳስ ክለብ ሲሆን በዘመነ ቅኝ ግዛት በተለይም በአፍሪካ ተስፋፍቶ የነበረ የክለብ አደረጃጀት ነው። ቅኝ ገዥዎች ስፖርትን በተለይም ደግሞ እግር ኳስን በመጠቀም የዘር እና የባህል ልዩነቶችን በአፍሪካውያን ላይ አንዲሰርጽ ለማስቻል በነገድ ላይ የሚያጠነጥኑ ቡድኖች በስራ ቦታዎች (በፋብሪካ፣በማዕድን ቁፋሮ) ላይ ያቋቁሙ ነበር። በዚህ መልኩ ክለቦችን በመመስረት የአንድ ሀገር ህዝቦችን በልዩነትና በብሄርተኝነት፣ በጎሰኝነት፣ በጎጠኝነተ ወዘተ… አስተሳሰብ እንዲወጠሩ በማድረግ ብሄራዊ ስሜታቸውን በመሸርሸር የሀብት ብዝበዛውን ያለጥያቄ ሲያከናውኑ መቆየታቸውን በዚሁ ጽሁፍ ገልጾታል። የስፖርት ሳይንስ ልሂቁ ፒተር አልጊ እንዳስቀመጠው ቅኝ ገዥዎች ስፖርትን በተለይም ደግሞ እግር ኳስን በመጠቀም የዘር እና የባህል ልዩነቶችን በአፍሪካውያን ላይ እንዲሰርጽ ለማስቻል በነገድ ላይ የሚያጠነጥኑ ቡድኖች እንዲስፋፉ በማድረግ ስፖርትን የአንድነት ጸር አድርገው መገልገላቸውን ጽፏል። በኢትዮጵያ በተለይ የእግር ኳስ ክለቦች በአብዛኛው ማለት ይቻላል ህልውናቸው ነገድንና ከተማን መሰረት ያደረጉ ናቸው። አገራችን በቀኝ ገዚዎች እጅ ላይ በታሪክ አለመውደቋ የሚነገር ቢሆንም ቅሉ የእነርሱን አስተሳሰብ በመቃኘት በእግር ኳሱ ልዩነትን በመፍጠር የሃሳብ ቅኝ ተገዢዎች በመሆን የስፖርት ሜዳዎች  የጦርነት አውድማ ሲሆኑ ታዝበናል። የብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በስፖርታዊ ጨዋነት ፣ የተመልካቾች ረብሻ፣ ሁከትና ብጥብጥ በኢትዮጵያ እግር ኳስ በሚል ባስጠናው ጥናት ይሄው ሃቅ መሆኑን ማረጋገጡ በስፖርት ልሂቁ ለቀረበው አመክንዮ ይደግፋል። ጥናቱ በማሳያነት እንዳቀረበው፤ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ስያሜ ቅጽል ስያሜ፣ አርማ፣ ዜማ ከተፈጥሯዊ አሰፋፈር ጋር ተዳብሎ በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ከብሄር/ፖለቲካ ጋር ተያያዥነት ኖሮት እንዲቀርብ መደረጉ ጠቅሷል። በስፖርት ውስጥ ልዩነት ለመፍጠር መንገድ የሆነውን እንዲህ አይነቱን አደረጃጀትን ተመልክቶ መፍትሄ መስጠት የሚገባ መሆኑን በጥናቱ ተካቷል። በእግር ኳሱ ውስጥ ያለው አደረጃጀት በሌሎች የስፖርት አይነቶች ላይ የሚታይም ጭምር ነው።በሀገር አቀፍ ውድድር መድረኮች ለምሳሌ እንደ መላው ኢትዮጵያ፣ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል በመሳሰሉት የውድድሮቹ ይዘት የአገሪቱን ህዝቦች በአንድ ጥላ ስር በማሰባሰብ የባህል፣ የቋንቋ፣ የልምድ፣ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ከስፖርቱ ባሻገር የሚያጠናክር እሳቤን ይዞ ቢጀመርም አተገባበሩ በተቃራኒው ውጤት ሲያመጣ ለመታዘብ እየተቻለ ነው። የመላውም ሆነ የባህል ፌስቲቫሎቹ በተደጋጋሚ የስፖርታዊ ጨዋነት ሰለባ ሲሆኑ ተመልክተናል። ይህም ብቻም ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ ከባለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ለማካሄድ አዳጋች የመሆኑም ሃቅ ከዚሁ የሚቀዳ መሆኑን መጥቀስ ያስፈልጋል። በተመሳሳይም በቅርቡ ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሊካሄድ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተነግሮለት የነበረው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል ለማካሄድ ምጥ የሆነ የውድድር አይነት ነው። የሁለቱ ውድድሮች ባለፉት ሶስትና ሁለት ዓመታት ላለመካሄድና መሰረዝ የነበረው ምክንያት ደግሞ ፤አገሪቱና ሰላም ባለፉት ሁለት ዓመታት ሆድና ናጫ መሆናቸውን ተከትሎ ነበር። በተለይ ደግሞ እንደ መላው የኢትዮጵያ ጨዋታዎች ፣የባህል ስፖርቶችና ፌስቲቫል ውድድር ደግሞ የነበረውን የጸጥታ ጉድለት የሚያባብሱ መሆኑን ከስጋት የመነጨ እንደሆነ እሙን ነው። ምክንያቱም የሁለቱ ስፖርታዊ ክንውኖች ያለፈ ታሪካቸው ተደጋጋሚ የሆነ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር ፤ያውም ከጀርባው ሌላ አጀንዳን ባነገበ መልኩ ይንጸባረቅባቸው ነበር። የውድድሮቹ በተደጋጋሚ መሰረዝ የጸጥታውን መናጋት ከማባባስ የሚታደግ መሆኑን ተከትሎ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑን አሳማኝ ነበር። በአገሪቱ የሰላም እጦት በነበረበት በዛን ወቅት የብሄር ፖለቲካን መሰረት ያደረጉ መገፋፋቶች በግልጽ ይንጸባረቁ ነበር። በሁለቱ የስፖርታዊ ክንውኖች በተደጋጋሚ ስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ጋር ተያይዞ የሚሰጡት አስተያየቶች እናንሳ። ውድድሮቹ የተቃኙበት መንገድ የብሄራዊ ስሜንት የሚያላላ እንጂ የሚያጠብቅ እንዳልሆነ ብዙዎች ቅሬታቸውን ያሰሙበት ጉዳይም ጭምር ነው። «መንግስት የዘረጋው ሥርዓት ኢትዮጵያዊነት ስሜት እያደበዘዘ ነው» የሚሉ ሙግቶች አይለዋል። ለዚህ ስሜት ጎልቶ ለመውጣቱ የነበሩት አስተዋጽኦዎች ተርታ የስፖርት ዘርፍ ትልቁን ድርሻ እንዳለው የፖለቲካ ምሁራን ፣የስፖርቱ ልሂቃን ፣ የኪነ ጥበብ ሙያተኞች፣ ደራሲያን ጭምር እንደየሙያቸው ባህሪ ይሄንኑ ሃሳብ አንጸባርቀዋል። የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲደበዝዝ የስፖርቱን ሚና ከገለጹት ደራሲያን መካከል ከአስር በላይ መጽሃፍትን ማሳተም የቻለው ዓለማየው ገላጋይ በ2010 ዓ.ም «መለያየት ሞት ነው «በሚለው መጽሃፍ የአገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ቁመናን በዳሰሰበት መጽሃፍ «ስፖርትና ጦርነት» በሚለው ጽሁፍ ስር በተለያዩ ሙያተኞች የተንጸባረቀውን ሃሳብ የሚሸከም ነበር። ስፖርታዊ ክንውኖች የተቃኙበት ሁኔታ ስፖርትን ለብሄራዊ ስሜት ከመጠን በላይ እንደተወሰደ መድሃኒት እንደሆነበት አስፍሮታል።አለማየው በመጽሃፉ እንዳተተው ፤ስፖርት ለጤንነት ለወዳጅነት ለሰላም የሚበጀው ስፖርቱን ማዕከል አድርጎ በክለቦች መካከል ሲካሄድ እንጂ ብሄርን መሰረት ሲያደርግ አይደለም። ብሄርን መሰረት ያደረገ ስፖርት የመለያየት ስሜትንና እኔነትን ማጎልበት መሆኑን ይኸው እያየን ነው። መቀሌዎች የአዲግራትን ንብረት ያወደሙት በስፖርት ነው። ባህርዳሮች መቀሌ ላይ የተደበደቡት በስፖርት ሰብብ ነው፤ መቀሌዎች ወልዲያ መጥተው በብጥበጥ ሳይጫወቱ የተመለሱት በስፖርት ነው፤ ፋሲል ከነማ ከመቀሌ ከተማ ጋር ጎንደር ላይ እንዳይጫወት የተሰጋው በስፖርት ሰብብ ነው። እናስ? መለያየት በስፖርት እውን አልሆነም? ስፖርት ለጦርነት አልዋለም? ብሄር ነክ ስፖርት ክብረነክ መሆኑን ለመረዳት ደግሞ የጨዋታ ዘገባ ምን እንደሚመስል ማየት ይበቃል። ኦሮሚያ ማንን አሸነፈ? ትግራይ ማንን ረመረመ ? ደቡብ ማን ላይ ሀትሪክ ሰራ? ቤኒሻንጉል ማንን በጨዋታ ሙሉ ለሙሉ በልጦ ተገኘ? አፋር ማንን ጥሎ ገባ? ሶማሌ ማንን አታለለ ሀረሪ ማን ላይ ‹‹ሎጩ›› ከተተ …ማን ላይ ምን ስሜት አሳደረ? ጊዮርጊስ ፣ ቡናን፣ ደደቢትን … እንደምንደግፈው እንዳልሆነም በመጥቀስ መጽሃፉ ይሞግታል። የባህል ስፖርትና ፌስቲቫል የውድድር ዘገባዎችም ከዚህ የራቀ አይደለም ፤በዚህ ስፖርት ውስጥ አካል የሆነው የትግል ስፖርትን ዘገባን እንመልከት፡፡ ኦሮሚያ ከ አማራ ይታገላሉ፤ደቡብ ከ ትግራይ ይታገላሉ፤ አፋር ከሶማሌ ይታገላሉ … ይህን አይነቱን ስሜት በሚይዘው ዘገባ የስፖርቱን ድባብ በራሱ የሚቀይርና ለአንድነት ሳይሆን ለልዩነት በር ከፋች መሆኑን አለማየው በትንታኔው ተመልክቶታል።የስፖርቱ ሚና ብሄራዊ ስሜትን እንዲያሸልብ ከማድረግ በተጓዳኝ ለራስ ብሄር ብቻ ማሰብን ያስከትላል፣ ዝቅ ሲል ደግሞ ወደ ጎሳ ይወርዳል፣ ወደ አካባቢያዊ እሳቤ እያለ ግለኝነት ትልቁን ቦታ ይዞ ይታያል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአትሌቲክስ ስፖርት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች የአትሌቶቹ የቡድን ስሜት ማንሳት የብሄራዊ ስሜቱ የቁልቁለት ጉዞ ወደ ግለኝነት መውረዱን ያመላክታል። በብሄራዊ ቡድን ደረጃ የሚገኙት አትሌቶች የመገኛ ምንጭ ከሆኑት ከእነዚህ የውድድር መድረኮች ነው። ብሄራዊ ስሜትን አንግቦ ሳይሮጥ የኖረን አትሌት በቡድን ስሜት የታጀበ ድልን እንዲያስመዘግብ መጠበቅ የሚያዋጣ አይሆንም። የኢትዮጵያን ክብርና ስም ትናንት በአትሌቲክስ ስፖርት ይመዘገብ የነበረው ድል ለመኮሰሱ ምክንያት ተደርገው ከሚነሱ ነጥቦች አንዱ የቡድን ስራ መጥፋት መሆኑን ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በተደጋጋሚ ሲናገር የመደመጡ ሃቅም ከዚህ እውነታ የራቀ አይደለም። በአትሌቲክስ ስፖርት ከእነ አበበ ቢቂላ፣ማሞ ወልዴ ፣ምሩጽ ይፍጠር ትውልድ፣ እስከ እን ኃይሌ ገብረስላሴ፣ አሰፋ መዝገቡ ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚ እስከነ ፤ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሰረት ደፋር ፣ቀነኒሳ በቀለ፣ስለሺ ስህን በነበረው የትውልድ ቅብብሎሽ አትሌቲክሱ በድል ተጉዟል። የአትሌቲክሱ የድል ውጤት በቡድን ስራ ድልን የማግኘቱ ልምድ እየወረደ መምጣቱ ይነገራል። በተለይ ከእነ ቀነኒሳ በቀለ ፣ስለሺ ስህን እግር የተተካው የእነ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሰለሞን ባረጋ ፣አልማዝ አያና፣ ገንዘቤ ዲባባ ትውልድ የድልን ጣዕም እንጂ የቡድንን ስራ ጣዕምን ያደበዘዘ ነበር። ለብሄራዊ ቡድን የሚመለመሉት ስፖርተኞች ከአገር ውስጥ ውድድር እንደመሆኑ፤ የብሄራዊ ስሜትን በመሸርሸር ግለኝነትን በስፋት የሚያንጸባርቅ እንደመሆኑ ይህ መሆኑ የሚያስገርም አይሆንም።በየቡድን ስራ ከመቅረት በተጓዳኝ የአትሌቶቻችን ፉክክር ከብሄራዊ ስሜት በመውረድ የእርስ በእርስ እስከመሆን መውረዱ አደጋውን ከፍ የሚያደርግ ይሆናል። እኤአ በ2018 የዳይመንድ ሊግ አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ መካከል የተፈጠረውን ክስተት ደግሞ የአትሌቶቻችን የቡድን ስራ እየተንኮታኮተ የመምጣቱን ሃቅ በግልጽ ያመላከተም ጭምር ነበር። አንዱ አንዱን ጠልፎ ጥሎ ለመሄድ ሲሞክርና፤ አጸፋው ደግሞ ቁምጣን ጎትቶ እስከማስቀረት የደረሰ የወንድማዊነት ፍቅር በዓለም ፊት የታየበት መሆኑ ወዴት እየተጓዝን ነው የሚለውን በሚገባ ያመላከተ ነበር። በአትሌቶቻችን ተረዳድቶና ተባብሮ በብሄራዊ ስሜት ባለድል የመሆንን ባህልን በግለኝነት መተካቱን የሚያንጸባርቅ ትልቅ አጋጣሚም ጭምር ነበር። ኢትዮጵያን አትሌቶች በትናንት ድላቸው ውስጥ በቡድን ስራ ድልን በመደጋገም አገራቸውን ማኩራት ችለዋል። ኢትዮጵያውያንን በደስታ እንባ አራጭተውታል፤በአገራቸው ልጆች ኩራት በማጎናጸፍ የብሄራዊ ስሜትን ከጫፍ እስከ ጫፍ እንዲቀጣጠል አድርገዋል። አሁን እየተመለከትን ያለነው ከዚህ ለየቅል መጓዙን ነው ። በመሆኑም በስፖርት መገንባት የተቻለው ብሄራዊ ስሜትን ፤በስፖርቱ በራሱ እየተናደ መሆኑን በተለያዩ የቀረቡት ማሳያዎችን ቆም ብሎ መመልከት ያስፈልጋል። በስፖርቱ ውስጥ እየጎላ የመጣውን ችግር ከወዲሁ መቅረፍ ካልተቻለ አደጋው አስከፊ እንደሚሆን ለቀረቡት አመክንዮች፤ ወደ የትኛው ማዕዘን መወሰድ እንደሚያስፈልግም በግልጽ ያስረዱም ጭምር ናቸው። በስፖርቱ ዘርፍ የብሄራዊ ስሜትን ማጠናከር እንዲቻል የስፖርት ኮሚሽን በሚገባ የውድደር ይዘቱን መቃኘቱ በስፖርቱ ብሄራዊ ስሜትን ማዳን ያስችላል። ኢትዮጵያዊነት ስሜትን በማጉላት በውድድሮቹ አንዱ ክልል የሌላውን ክልል ባህልና እሴት አክብሮ መጓዝ ከተቻለ አዎንታዊ ውጤት ማምጣት ይቻላል። በመጣንበት መንገድ ከተጓዝን ደግሞ የስፖርትን ብሄራዊ ስሜት ነጸብራቅነት በአሉታዊ እንዲሰርጽ ማድረጉ ይቀጥላል ማለት ነው።አዲስ ዘመን ረቡዕ ሐምሌ 10 / 2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14258
5a297740d87afec9625edb22ecd50b75
3172a2481a3080a9831dc56c58b9f726
የሞተር ስፖርት ከየት ወዴት?
«ሞተር ስፖርት» ዓለም አቀፍ መጠሪያ ነው። በሞተር ታግዘው የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በስፖርት ውድድር መሳተፋቸውን ተከትሎ የወጣለት ስም ነው። አራት እና ከዚያ በላይ ጎማ ያላቸው ተሽከርካሪዎችን በውድድር በማሳተፍ በበላይነት የሚመራው ዓለም አቀፉ የአውቶሞቢል ፌዴሬሽን «ፊያ» ሲሆን ሁለት ጎማ ያላቸውን የሞተር ስፖርት ደግሞ «ፌዴሬሽን ኢንተርናሽናል ሞተርሳይክሊዝም» የማስተዳደሩን ስራ ይሰራል። ስለ ሞተር ስፖርት ስናነሳ በውስጣችን «ስፖርቱ መቼ ተጠነሰሰ?» የሚለው ጥያቄ መከሰቱ የማይቀር ነው። የዛሬው የእሁድ ገፅ አምድ በዚህ ስፖርት ላይ ጠለቅ ያለ ታሪካዊ ዳሰሳ ባያደርግም ስለ ጉዳዩ በጥቂቱ እንዳስሳለን። ሞተር ስፖርት በ1894 በአንድ በፈረንሳይ ውስጥ ይታተም በነበረ «ሌ ፒቲ ጆርናል» ጋዜጣ አማካኝነት እንደተጀመረ የታሪክ መዛግብት ይጠቁሙናል። «ፓሪስ ቱራውን» በሚል ስያሜ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ የተጀመረው ይሄ ውድድር ቀስ እያለ ተወዳጅነትን እያተረፈ መጥቷል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1900 ደግሞ «የኒዮርክ ሄራልድ» ጋዜጣ ባለቤት እና የወቅቱ ቱባ ሀብታም ጄምስ ጎርደን «ጎርደን ቤኒት ካፕስ » በሚል ስፖርታዊ ውድድሮችን ማዘጋጀት ጀመረ። አንደኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ ግን አውሮፓውያኖች በግላቸው «ግራንድ ፕሪክስ» የሞተርስፖርት ውደድሮችን ማዘጋጀት ጀመሩ። በአሜሪካን አገር ደግሞ በተለምዶው «አቧራማ እና ጭቃማ» ቦታ ላይ የሚደረግ የሞተር ስፖርት ውድድር ተወዳጅነትን እያተረፈ መጣ። በአሁኑ ወቅት የሞተር ስፖርት ውድድር በዓለም ላይ እውቅናን ያተረፈ ተወዳጅ ስፖርት ነው። በመላው ዓለም የሚገኙ የስፖርት መገናኛ ብዙሀንም ሰፊ ሽፋን ይሰጡታል። በተለይ አሁን ላይ እየተካሄዱ ተወዳጅነትን ካተረፉ የሞተር ስፖርት ውድድሮች ውስጥ «ፎርሙላ ዋን» ይገኝበታል። ይህ ስፖርታዊ ውድድር በተሽከርካሪ ውስጥ አንድ ተወዳዳሪን ብቻ የሚያሳትፍ ሲሆን ጥብቅ ስፖርታዊ ህጎች አሉት። «ፊያ» ዓለም አቀፉ የሞተር ስፖርት ፌዴሬሽን ለበርካታ ዓመታት ውድድሩን በበላይነት ሲመራው ቆይቷል። አሁን ደግሞ የግል ካምፖኒ በሆነው «የፎርሙላ ዋን ግሩፕ» እየተዘጋጀ ይገኛል። ሌላው በዓለም ላይ ተወዳጅ የሆነው ውድድር «ፎርሙላ ኢ» የሚል ስያሜ ያለው ነው። ይህ ውድድር በኤሌክትሪክ ሃይል ብቻ የሚሰሩ መኪኖችን የሚያሳትፍ ሲሆን ሀሳቡ በ2012 ተጠንስሶ በ2014 በቻይናዋ ቤጂንግ የተጀመረ ነው። ለሌላው ተወዳጅ ውድድር «ኢንዲካር ሬስ» ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1909 የተጀመረ ነው። ኢንዲ ካር በፖርት ላንድ ኦሪጋን የሚካሄድ ስፖርታዊ የመኪና ውድድር ነው። ስፖርት ካር፣ ቱሪንግ፣ ስቶክ ካር እና ኦፍ ሮድ በዓለም ላይ ትልቅ ዝና አላቸው። የሞተር ስፖርት ውድድር ከዘመናት በፊት በአውሮፓውያን እና አሜሪካን የሚዘወተር ቢሆንም በአፍሪካ አህጉርም ቀላል የሚባል ታሪክ የለውም። በተለይ በደቡብ አፍሪካ፣ ጎረቤታችን ኬኒያ፣ ዙምባቡዌ እንዲሁም በኡጋንዳ ውስጥ ተወዳጅነቱ ከፍ ያለ ቦታ የደረሰ ነው። በአፍሪካ የሚካሄዱ የረጅም እርቀት የሞተር ስፖርት ውድድሮች በአህጉሩ እና በመላው ዓለም ይታወቃሉ። «ዘራግድ አፍሪካን ሮድ» እና «ኦፍ ሮድ» በአህጉሩ ከሚዘጋጁ ተወዳጅ የሞተር ስፖርት ውድድሮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በአህጉሩ የሚደረጉ ውድድሮችን የሚከታተሉ የስፖርቱ አፍቃሪዎች እየተበራከቱ መጥተዋል። ከተለያዩ አገራት ጭምር ይህን ስፖርት ለመመልከት በአፍሪካ ይከትማሉ። በተለይ በኬኒያ፣ ሴኔጋል እና ዙምባቡዌ የሞተር ስፖርት ለመመልከት እና በውድድሩ ተሳታፊ ለመሆን አያሌ ዜጎች ከመላው ዓለም ይተማሉ። ኬኒያ ውስጥ የሚካሄደው «ኬሲቢ ሳፋሪ» ከላይ ከጠቀስናቸው ዓመታዊ ዝግጅቶች በተለየ መንገድ በርካታ ቱሪስቶችን፣ የስፖርቱ አፍቃሪዎችን እና ተወዳዳሪዎችን የሚያሳትፍ ነው። የኬኒያ የንግድ ባንክ ስፖንሰር የሚያደርገው ይህ ውድድር በመላው ዓለም ላይ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረትን የሳበ ነው። እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1953 ጀምሮ መካሄድ የቻለው ይሄ የሞተር ስፖርት ውድድር በመላው የስፖርት አፍቃሪ ዘንድ ተወዳጅነትን እያገኘ መምጣቱን አስመስክሯል። በሴኔጋል ዳካር ከ1978 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው «ዘዳርክ ራሊ» ውድድርም በአፍሪካ ውስጥ እውቅና አግኝተው ተወዳጅነትን ካተረፉት መካከል የሚነሳ ነው። ይህ ውድድር ከዚህ ቀደም «ፓሪስ ዳርክ ራሊ» በሚል ስያሜ ይጠራ ነበር። በ2008 ላይ አዘጋጆቹ በደረሳቸው የደህንነት ማስጠንቀቂያ ምክንያት ውድድሩን ወደ ደቡብ አሜሪካ ለማዘዋወር ተገደዋል። ሆኖም ይህ ውድድር በአፍሪካ ውስጥ ለበርካታ ዓመት በስኬት የተዘጋጀ እና ተወዳጅነትም ያተረፈ ነው። «ዘኢስት አፍሪካን ሳፋሪ» ሌላኛው በአፍሪካ ውስጥ የሚዘጋጅ ተወዳጅ የሞተር ስፖርት ውድድር ነው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2003 ነው ውድድሩ መካሄድ የጀመረው። በዚህ ዝግጀት ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ መኪኖች «ክላሲክ ካር» ወይም ረዘም ያለ እድሜ ያላቸው መሆን አለባቸው። እነዚህን መኪኖች ሳይዝ ተሳታፊው በውድድሩ ላይ እውቅና አይሰጠውም። ይህ ተወዳጅ የመኪና ግልቢያ የሚዘጋጅባቸው ጎዳናዎች ደግሞ በኬኒያ እና ታንዛኒያ ይገኛሉ። ሁለቱ አገራት አፍሪካ ሳፋሪን በማሰናዳት በዓለም ላይ እውቅናን አግኝተዋል። በ1997 የተጀመረው ፒርል ኦፍ አፍሪካ ራሊ፣ በአፍሪካ ውስጥ ረጅም እድሜን ያስቆጠረ የሞተር ስፖርት ውድድር የዛምቢያው ኢንተርናሽናል ራሊ እና የኮት ዲቯር ራሊ በአህጉሩ የሚካሄዱ ተወዳጅ የመኪና ግልቢያ የስፖርት ውድድሮች ናቸው። እነዚህ ውድድሮች ግን ምንም እንቅፋት አያጋጥማቸውም ማለት አይቻልም። በተለይ ውድድሩን ለማሰናዳት በሚደረገው ሂደት ላይ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ስፖንሰር የሚያደርጉ ተቋማት ማጣት አንዱ ፈተና ነው። «ፊያ» ዓለም አቀፉ የሞተር ስፖርት ፌዴሬሽን በአፍሪካ የሚገኙ ውድድሮችን በመገምገም ለየ አገራቱ ደረጃ አውጥቷል። መረጃዎቹ እንደሚጠቁሙትም ኡጋንዳ 2ሺ754 ነጥብ በማምጣት በሞተር ስፖርት ውድድር ጥራት አንደኛ ላይ ተቀምጣለች፤ ከዓለም ደግሞ 27 ደረጃን ይዛለች። ሩዋንዳ ሁለተኛ ላይ ስትገኝ በዓለም ላይ 34ተኛ ደረጃን ይዛለች። ዙምባቤ ከአፍሪካ 3ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ ከዓለም ደግሞ የ38ተኛ ደረጃን ይዛ ትገኛለች። በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ስፖርቶች አሉ። ሆኖም እንደ እግር ኳስ እና የአትሌቲክስ ስፖርት ተወዳጅነት ማግኘት አልቻሉም። የሞተር ስፖርትም ከነዚህ ውስጥ የሚመደብ ነው። ቢሆንም በአገር ውስጥ የሞተር ስፖርትን መሰረት ለመጣል እንቅስቃሴ ከተጀመረ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል። ይህ ስፖርት «የሞተር ስፖርት አሶሲዬሽን» በሚል በማህበር ደረጃ ከተቋቋመ ረዘም ያለ ጊዜን አስቆጥሯል። ለዛሬ ስፖርቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለበትን ደረጃ እና እንቅስቃሴ ለመዳሰስ ባንሞክርም የሞተር ስፖርት “ከየት ወዴት” በሚል የገለጥነውን ዶሴ እንዘጋለን።አዲስ ዘመን ሀምሌ 7/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=14138
c187c403171a5549625e7d30d4b45aa1
396d4004013797c634e2aecc9c75c1be
የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተስፋና ተግዳሮት
በሰው ልጅ የታሪክ ጉዞ ዓለምን በአንድ ቋንቋ ያግባባ፤ የትኛውም ሀገር የኔ በሚለው ትምክህቱ ሊያቆመው ያልቻለ የታሪክ ክስተት ቢኖር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ነው ። ወረርሽኙ እያሳደረ ካለው የጤና አደጋ ባልተናነሰ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ መስክ እየፈጠረ ያለው ዝብርቅርቅ መላውን አለም አስጨንቋል። ከዚህ ጭንቀት ለመገላገል አለም የተለያዩ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማፍለቅ ላይ ቢገኝም እስካሁን ባለው ተጨባጭ እውነታ ቀደም ካሉት የጥንቃቄ መከላከያዎች የተሻለና የተለየ አማራጭ መፍትሄ አልተገኘም።ለበሽታው ክትባት ለማግኘት ሀገራትና የተለያዩ በህክምናው ዘርፍ አንቱ የተባሉ የምርምር ተቋም ቀን ከሌት እየተጉ ቢሆንም እስካሁን ያለቀለት ተስፋ የሚሆን ነገር አልተገኘም፤ የክትባት ፍለጋው እሩጫ ዳገት እንደመውጣት ከብዷል። ለዚህ ተግባር ይረዳ ዘንድ የዓለም ጤና ድርጅት በአብሮነትና በጋራ ወረርሽኙን ለመከላከል ክትባትን ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲሳተፍበት ጥሪ አቅርቧል ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ቫይረሱን ለመከላከል ብሎም እስከ ወዲያኛው ድረስ ደህና ሰንብት የሚያስብል ክትባቱን አገኘው ማለቱን የዓለም ጤና ድርጅት በሰጠው መግለጫ አብስሯል። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተገኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በአንድ ሺህ ሰዎች ላይ በተደረገ የሙከራ ክትባት፤ ክትባቱን የወሰዱት ሰዎች ቫይረሱን የመከላከል አቅማቸው አድጎ መገኘቱም ተመልክቷል ። የህንድ የዜና ወኪል ( Press Trust of India (PTI), እንደዘገበው በሰዎች ላይ የሚደረገው ክትባት በአንድ ሺህ 600 ሰዎች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል። በCOVID-19 ክትባት ላይ 1,600 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ ። የሙከራ ክትባቱም በመጪው ወር ይጀመራል። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ደግሞ በርካታ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች በጥሩ የሙከራ ደረጃ ላይ ቢሆኑም በዓለም ጤና ድርጅት የጤና ባለሞያዎች በቅርቡ አገልግሎት ላይ እንደማይውል መነገሩን አስታውቋል። በዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎችና ህክምና ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ማይክ ሪያን በቪዲዮ በታገዘ ውይይት ክትባቱ በሙከራ ደረጃ መልካም ውጤቶች ላይ መድረሱን ቢገልጹም ክትባቱ ሙሉ ለሙሉ ለሰዎች የሚደርሰው በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል። ለዚህም የክትባት ልማት ውስብስብ ሥራ መሆኑን አመልክተዋል ። የኦክስፎርድ ተመራማሪዎች እንደተናገሩት ደግሞ የመጀመሪያ ክትባት እስከ መስከረም መጀመሪያ ድረስ ዝግጁ ሊሆን ይችላል ብለዋል። ግን ሙከራዎች ከተጠበቀው ጊዜ በላይ ሊወስዱ ይችላል ማለታቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል። በዋነኝነት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 55 ዓመት የሆኑ ግለሰቦች ለክትባቱ የመጀመሪያ ሙከራ መሳተፋቸው ቫይረሱን ለመከላከል መልካም አጋጣሚ መሆኑን በንግግራቸው ጠቅሰው፣ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣና ለቀጣይ የምርምር ስራዎች ስኬት የሚያንደረድር መሆኑን ግን በዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋዎችና ህክምና ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ማይክ ሪያን ተናግረዋል። ክትባቱ ከፀደቀ በኋላ የመጀመሪያዎቹን መድኃኒቶች ማን መውሰድ እንዳለበት የሚወስነው የዓለም ጤና ድርጅት ቢሆንም ቫይረሱን ለመከላከል በኦክስፎር ዩኒቨርሲቲ የተገኘው ክትባት ከተሰማበት ቅጽበታዊ ሁኔታ አንስቶ የዓለም ኃያላን ሀገራት እኔ ልቅደም ውድድር ውስጥ ገብተዋል። ይሁን እንጂ የዓለም ጤና ድርጅት በዚህ አስከፊ ወረርሽኝ ወቅት የተገኘው ክትባት የሚሰጠው ለሀብታሞች አይደለም፤ ለድሆች አይደለም፤ ለሁሉም የሰው ልጅ ነው። ይህ ማለት ለህዝብ ጤና እንጂ አቅም ያላቸው ሀገራት የሚቀራመቱት ጉዳይ አለመሆኑ ነው የተነገረው። እነዚህ ክትባቶች ለህዝባቸው በሚመጥን መጠን ለሁሉም ተሳታፊ ሀገራት በእኩልነት ይላካሉ። ለጤና ባለሞያዎች፣ በእድሜ ወይም በሌላ በሽታ ምክንያት ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ፣ በእስር ቤቶችና በከፍተኛ የስርጭት ሁኔታ ውስጥ ለሚሰሩ ወይም ለሚኖሩ ባለሞያዎች ቅድሚያ ይሰጣልም እየተባለ ነው ። ይህንን ሃሳብ የሚያጠናከርልን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚለው ከሆነ ፣ በመጀመሪያ የጤና እንክብካቤ ሠራተኞች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። ከተሳተፉት ሀገራት ህዝብ 20 በመቶውን ይሸፍናል ። የዓለም ጤና ደርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከአውሮፓ ፓርላማ የጤና ኮሚቴ ተወካዮች ጋር ባደረጉት የቪዲዮ ኮንፈረንስ እንደዚህ ያለ ክትባት እውን ከሆነ የሁሉም ህዝብ ሀብት ሊሆን ይገባል ብለዋል። በመጀመሪያ ደረጃ የተደረጉት ሙከራዎች ውጤቱ በጣም ተስፋ ሰጭ ነው። በእነዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራዎች ደህንነትን የሚያመለክቱና ክትባቱ ጥሩ የበሽታ መከላከል አቅምን ወይም ሰውነታችን በሽታን የመቋቋም እድሉን እንዲጨምር አድርገዋል። በዚህ ዓመት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶዝዎችን የመፈለግ ምኞት ብሩህ ተስፋ እንዳለው ፣ በሚቀጥለው ዓመት እስከ ሁለት ቢሊዮን የሚደርስ ክትባት የመጠበቅ ተስፋ እንዳለም እየተገለጸ ነው። የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ለመስራት በታሪክ ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በፍጥነት እየተከናወነ ነው። ለምሳሌ ሞደርና የተባለው ኩባንያ ከጥቂት ቀናት በፊት የኮሮና ቫይረስ ክትባትን መስራት ችሏል። ባለፈው ሳምንት ኩባንያው ክትባቱ አስተማማኝ የሚመስል እና በሽታን የመከላከል አቅምን ሊያጎለብት የሚችል ንጥረ ነገር ያመነጫል በማለት የደረጃ አንድ የምርምር ውጤት እንደነበር ፋስት ካምፓኒ በድረ ገፁ አመላክቷል። ይህ ድረ ገፅ እንዳስነበበው ከሆነ በጆንስ ሆፕኪንስ ሜዲሲ የሕክምና ትምህርት ቤት የህፃናት ሐኪም እና ኦንኮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑት ራፋኤል ቪካዲዲ “ይህ በጣም ቀደም ያለ መረጃ ነው” ብለዋል። ፕሮፌሰሩ እንደሉት የቫይረሱ መከላከያ ክትባት የሙከራው ሂደት የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አሁን ካለው ምኞት በተለይም በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስክ ከሚደርሰው ቀውስ የመውጣት ፍላጎቱ የጊዜ ሰንሰለቶች የበለጠ ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆይ ይችላል ብለዋል። አዲስ ዘመን ሐመሌ 20/2020ወንድምአገኝ አሸብር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36150
6895e7c4534ceb04790825490c260229
ffcc87ec1d767802d54f5823835675c3
ከሊስትሮ እስከ ጉሊት ነጋዴ ማኅበረሰቡን ያስፈነደቀው የውሃ ሙሌት
አባይ ስበት አለው፤ የአገሪቱን ሕዝቦች በገመድ አስተሳስሯል፤ በፍቅር ልባቸውን አሸንፏል፤ ተስፋቸውን በእሱ ላይ እንዲጥሉ አድርጓል፣ የቤታቸው ኩራዝ እንዲለወጥ፣ የሥራቸው ዓይነት እንዲቀየር፣ አመራረታ ቸው በመስኖ በዓመት ሁለት ሦስቴ እንዲሆን፣ የገቢ አቅማቸው እንዲጎለብት በእሱ ምኞታቸውን ያሳደሩ ዜጎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ አሁን ተስፋቸው መፍካት ጀምሯል የጉባ ተራሮች ጎዝጉዘው የአባይን ውኃ በሥራቸው አስተኝተዋል። ከሕፃን እስከ አዋቂ፣ ከተማሪ እስከ ተመራማሪ የየድርሻቸውን በማበርከታቸው ኮርተዋል ከጉሊት እስከ ሱቅ በደረቴ፣ ከሊስትሮ እስከ ቆራሊዮ ድረስ ደስታቸውን ይገልጹ ይዘዋልሐሳባቸውንም ለአዲስ ዘመን ተንፍሰዋል። በጉሊት ሥራ የሚተዳደሩት የአዲስ አበባ ነዋሪ ወይዘሮ አዳነች አባተ እንደተናገሩት፤ የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ ደረጃ ውሃ ሙሌትን ዜና ስሰማ እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ ሲሉ ይናገራሉ፡፡ አያይዘውም የኮሮና ቫይረስ ባይኖር ኖሮ ከመሰሎቼ ጋር ወደ አስፋልት በመውጣት እልል ብዬ መንግሥትን እያመሰገንኩ የኢትዮ ጵያን ሕዝብ እንኳን ደስ አለን ማለት እፈለግ ነበር ይላሉ። ግድቡ ሲጀመር በጉሊት ገበያ ከማገኛት ገቢ በቤታችን ከሚገኘው ሕፃን ልጅ ጀምሮ ለግድቡ የበኩላችንን ስናደርግ ቆይተናል ብለውናል። ነገር ግን ግድቡ በአምስት ዓመት ያልቃል ተብሎ በተግባር በጊዜው ባለማለቁ ተከፍቼ ነበር ያሉት ወይዘሮ አዳነች፤ ቀኑ ቢረዝምም በአዲሱ መንግሥት በጥቂት ዓመታት ውስጥ የግድቡን መሞላት በመስማቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ ሲሉ ገልጸዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግሥት በክረምት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት አደርጋለሁ ብሎ የገባውን ቃል በመፈጸሙ መደሰታቸውን ወይዘሮ አዳነች አመላክተው፤ ይህን የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል ሲፈፅም ሳይ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንዲኖረኝ አድርጎኛል ሲሉ ይናገራሉ። የታላቁ የህዳሴ ግድብ ከፍጻሜ እስኪደርስ ድረስ እንደበፊቱ ትንሹም፤ ትልቁም ሁሉም የአቅሙን በማድረግ፤ መተባበር ይኖርበታል ሲሉ ወይዘሮ አዳነች የትብብር መንፈስን ይዘራሉ ሌላዋ በጉሊት ሥራ የሚተዳደሩት የአዲስ አበባ ነዋሪ ወይዘሮ የአብ ስራ አያልነህ ግድቡ ለኔም፣ ለልጄም፣ ለቤተሰቦቼም፣ ለሀገርም የተሻለ ነገር ይዞ እንደሚመጣ ተስፋ አደርግ ስለነበር ትናንት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የሙሌቱን ዜና ስሰማ ደስታዬ ወደር አልነበረውም ሲሉ ገልጸዋል፡፡መንግሥት በፓርላማ የተናገረውን ቃሉን ጠብቆ ግድቡ መሞላቱ በመንግሥት ላይ የሚኖረኝን አመኔታ ከፍ እንዲል አድርጎታል ሲሉ ወይዘሮ የአብ ስራ አመላክተዋል፤ ወደ ፊትም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ትን ሹም ትልቁም ተባብሮ የግድቡን ፈጻሜ ከዳር ማድረስ ይኖርበታል ሲሉ ተደምጠዋል። ሌላው በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆነው እና ጫማ በማፅዳት ሥራ የተሰማራው ወጣት አሰላ አበበ የመጀመሪያው ዙር ሙሌት መጠናቀቁን ስሰማ ደስታዬን በቃላት ለመግለጽ ከባድ ነበር ሲል መደሰቱን ተናግሯል፤ አሁንም የጀመርነውን ተባብረን የአቅማችንን በማድረግ እንጨርሰዋለን የሚለው ወጣት አሰላ አበበ፤ መገናኛ ብዙኃንም በርትተው በመስራት ማህበረሰቡን ማንቀሳቀስ ይገባቸዋል ሲል ጠቁሟል። አንዳንድ አካላት ስለግድቡ የተለያየ ነገር ሲያወሩ ይሰማል፤ እነዚህን አካላት መንግሥት ከሕዝቡ ጋር በመሆን ሊያስቆማቸው ይገባልም፡፡ ምክንያቱም እነኝህ አካላት የሰውን የመተባበር መንፈስ ስለሚሸረሽሩት የመተባበር መንፈስ ከተሸረሸረ ግድቡን በታቀደው ጊዜ አጠናቆ ለተፈለገለት አላማ ማዋል አይቻልም የሚለው ወጣት አሰላ አበበ ወጣቱም እነዚህን አካላት በንቃት መጠበቅ አለበት ሲል አሳስቧል። የአባይ ግድብ የእኛ የኢትዮጵያኖች ተስፋ ስለሆነ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍለን መጨረስ ይገባናል ነው ያለው ወጣቱ። ሌላው በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና ጫማ በማፅዳት ሥራ የተሰማሩት አቶ ሃይሉ ዘለቀ በራሳቸው እና በትምህርት ቤት ደግሞ በልጆቻቸው ስም ጭምር ጫማ ጠርገው ከሚያገኙት ገቢ ከዕለት ጉርሳቸው በመቀነስ ለአባይ ግድብ ያቅማቸውን ማበርከታቸውን ይገልጻሉ ግድቡም ከዚህ ደረጃ ደርሶ በማየቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ፤ ሀገሬ ስታድግ ሀገሬ ስትለማ ጥሩ ደረጃ ላይ ስትደርስ በጣም ደስታ ይሰማኛል የሚሉት አቶ ሃይሉ ዘለቀ የህዳሴው ግድብ ውሃ ሞልቶ ከማየት በላይ ለእኔ ደስታ ሊፈጥርልኝ የሚችል ነገር የለም ሲሉ ይናገራሉ፡፡ሀገራችን የጀመረችውን ግድብ ለመጨረስ ልክ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተጣጥሮ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ሲሉ አቶ ሃይሉ ተናግረዋል። አንዳንድ የኢትዮጵያን ማደግ የማይፈልጉ ኃይሎች ስላሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከመንግሥት ጎን በመቆም ሀገሩን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012አሸብር ሃይሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36134
e2f837953be2a121ebd16a3b36cfc9b5
330e2e3cb34a9212f9943c8fe4250580
ኮሮና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የመሳብ ፉክክሩን እያከበደው መምጣቱ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አገራት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሚያደርጉትን ፉክክር እያከበደው መምጣቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።የተቀናጀ ስራ መስራትና ተወዳዳሪነትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አመለከተ ። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ኮሮና ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰዎችን ጤና ከማቃወስና ለሞት ከመዳረግ ባለፈ በኢኮኖሚው በተለይ ደግሞ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል። የቫይረሱ ስርጭት መዋእለ ነዋያቸውን በዘርፉ ለማዋል ከጫፍ የደረሱ ኢንቨስተሮች ውሳኔዎቻቸውን እንደገና እንዲያዩ እያስገደዳቸው መሆኑን አመልክተው፣ ወደ ኢንቨስትመንቱ የመግባት ውሳኔያቸውን እንዲያዘገዩ ምክንያት መሆኑንም ጠቁመዋል ። ወረርሽኙ ዓለም አቀፉን የኢንቨስትመንት ፍሰት ከ30 እስከ 40 በመቶ እንዳቀዛቀዘው የጠቆሙት አቶ ተመስገን፣ይህም አገራት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሚያደርጉትን ፉክክር ከባድ እንደሚያደርገው አመልክተዋል። ፉክክሩ እየጠነከረ መምጣትም አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በጣም ጠንካራ ስራ መስራትን እንደሚጠይቅም አስታውቀው፣ ተወዳዳሪነትን ማጠናከር ካልተቻለ እንደ ሌሎች አገራት ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ስትስብ የነበረችውን ኢንቨስትመንትን ለማስቀጠል እንደምትቸገር አስገንዝበዋል። ኢንቨስትመንት በመሳብ ረገድ አሰራሮች በቀደመው መልኩ ይቀጥላሉ ብሎ መገመት ትልቅ ስህተት ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ፣አዳዲስ የፕሮሞሽን ስራዎች እንደሚፈጠሩ ተግባራቸውም በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንደሚሆን ጠቁመዋል ። በርካታ አገራትም ይህን አቅጣጫ መከተላቸውን ገልጸዋል። ‹‹ኢትዮጵያም ይህን ተግባር በከፍተኛ ቅንጅት በመተግበር ነባር የኢንቨስትመንት ተዋናዮችንም ሆነ አዳዲስ መዋእለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት ያላቸው ኢንቨስተሮችን በዲጂታል ቴክኖሎጂው አማራጮች በመድረስ ላይ ትገኛለች ››ብለዋል። ኮሚሽኑም የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅምና አማራጮች በዌብ ሳይቶች ላይ በተሻለ ሁኔታ የማሳየት ወደ ኢንቨስትመንቱ የሚመጡ ተዋናዮችም ከምዝገባ ጀምሮ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እስከመስጠት ድረስ በቀጥታ የመረጃ መረብ/ ኦን ላይን / ግልጋሎቶችን የማቅረብ ተግባራትን በትኩረት በመከወን ላይ መሆኗን አስታውቀዋል። ከባለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በዋነኝነት የኢንቨስትመንት ከባቢውን የማሻሻል ብሎም አናቂ የሆኑ ህግና አሰራሮችና ማነቆዎችን የማሻሻል ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ ተመስገን፣ በቅርቡ የሚፀድቀው አዲሱ የኢንቨስትመንት ደንብም የሀገሪቱን ኢንቨስትመንት ይበልጥ ሳቢ እና ተወዳዳሪ እንደሚያደርገው አብራርተዋል። ከዚህም ባሻገር የመንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ አቅጣጫ በተለይ ለግሉ ዘርፍ የተሻለ ትኩረት የሚሰጥና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረው፣እንደ አገር የተሻለ እድል የሚሰጥና ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችል ስለመሆኑም ጠቁመዋል። ከቀናት በፊት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በህገወጦች የተፈፀሙ ተግባራት ኢንቨስተሮች ነባር ኢንቨስትመንቶችን ለማስፋፋት ያላቸውን ተነሳሽነት፣አዳዲስ ኢንቨስተሮችም ወደ አገር ውስጥ ለመግባትና መዋእለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ያላቸውን ፍላጎት የሚገድብና ሊታረም የሚገባው መሆኑን አስገንዝበዋል። ህገወጥ ተግባሩ በእጅጉ ሊወገዝ እንደሚገባው ያስገነዘቡት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ ዜጎችም ከመሰል ህገ ወጥ ተግባር በመራቅ በአገሪቱ የመጣውን ታሪካዊ እና ሁለንተናዊ ለውጥ በአግባቡ በመጠቀም ኢትዮጵያን ከድህነት ለማውጣት የሚደረገውን ርብርብ ማገዝ እንደሚገባቸው አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 21/2012ታምራት ተስፋዬ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36168
74a970e024ef77fca93c4ff44d961173
5fd27ba0218ed849f64ad5dadbbeab18
‹‹ለእውነተኛ ትግል በረሀ የገቡ ብዙ የትግራይ ልጆች በህወሃት ሴረኛ ቡድን ተገድለዋል›› ሊላይ ሃይለማርያም ረዳ የቀዳማይ ወያነ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ልጅ
 አዲስ አበባ፦ ለእውነተኛ የህዝብ ትግል በረሀ የገቡ ብዙ የትግራይ ልጆች በህወሃት ሴረኛ ቡድን በበረሀ የትጥቅ ትግል ወቅት መገደላቸውን የቀዳማይ ወያነ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ልጅ ሊላይ ሃይለማርያም ረዳ አስታወቁ። ህዝባችንን ከዚህ ማፍያ ቡድን እንታደገው ሲሉም ጥሪ አቀረቡ፡፡አቶ ሊላይ ሃይለማርያም በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ የበረሀ ትግል ሲጀመር ትግሉን የተቀላቀሉ ኃይሎች ሁለት ባህሪ ነበራቸው፡፡ አንደኛው የህዝቡን እውነተኛ ጥያቄ ይዞ ለመታገል የገባ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከህዝብ ጥያቄ ይልቅ ስውር የሆነ ተልእኮ አንግቦ የተቀላቀለ ነው፡፡ 1968 ዓ.ም ጥቅምት ወር ሕወሃትን እንደተቀላቀሉ ያስታወሱት አቶ ሊላይ፣ ገሰሰ አየለ፣ ሙሴ ወደ በረሀ የገቡት ለእውነተኛ የህዝብ ትግል እንደነበር አመልክተዋል። እነዚህ የትግሉ መስራቾች ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እንደነበራቸውም አስታውቀዋል።ገሰሰ አየለ፣የትግራይ መገንጠል የሚባለውን እንደማይቀበልና ስህተት መሆኑንም ይናገር እንደነበር አመልክተው፤ የስብሓት ነጋ እና የአባይ ፀሃየ ቡድን ይህ ስላልጣመው የውጪ ግንኙነት እንዲሰራ በሚል በሱዳን በኩል እንዲወጣ ተደርጎ በመንገድ በነሱ አጃቢዎች ሆነ ተብሎ መገደሉን ጠቁመዋል፡፡ ገሰሰ፣ ደደቢት በረሀ ሲሄዱ የተሻለ ኢኮኖሚ፣ መሳሪያና የተሻለ ህዝባዊ ድጋፍ እንደነበረው ጠቅሰው፤ የገሰሰ ወደ በርሀ መግባት አብዛኞቹ የሽሬ ልጆች ለትግል እንዲነሳሱ የሞራል አቅም ፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል። በርካታ የሽሬ ልጆች ወደ ትግሉ መቀላቀላቸው ያስደነገጣቸው አቶ ስብሓት ነጋ፣ ‹‹ገሰሰ ፊውዳል ነው›› ብለው የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደጀመረቡትም ተናግረዋል። እየመጣ የአመራሩን ስፍራ በስፋት እንደተቆጣጠረው አመልክተው፤ ይህ ቡድን የሽሬ ልጆችን ‹‹ሰላይ ናችሁ›› በሚል ይገድል እንደነበር ተናግረዋል። በዚህ ሴራም ብዛት ያላቸው የሽሬ ልጆች መገደላቸውን አስታውቀዋል። በወቅቱ ከኢዲዩ ጋር በተደረገው አስከፊ ጦርነት ብዙ ታጋዮች መሰዋታቸውን ጠቁመው፤ ከኢዲዩ ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ምንም ምክንያት አልነበረም ብለዋል። ችግሩን በውይይት መፈታት ይቻል እንደነበር የገለጹና ውጊያው አያስፈልግም ብለው ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች በወቅቱ እንዲገደሉ ተደርጓል ብለዋል። ከ1967 እስከ 68 ዓ.ም የሽሬን ልጆች ካጸዱ በኋላ በ1969 ውጊያ የሚመሩ ሰዎች በአቶ ስብሓት ነጋ የቅርብ ዘመዶች መተካት መጀመራቸውን ገልጸዋል። ከዚያም ውጊያዎች መበላሸት መጀመራቸውን ያስተዋሉ ታጋዮች አቅም ያላቸው ሰዎች እያሉ ለምንድን ነው የማይመጥኑ ሰዎች እንዲመሩንና ውጊያ እንዲበላሽ የሚደረገው ሲሉ መጠየቅ መጀመራቸውንም ጠቅሰው፤ጉዳዩ በወቅቱ የመወያያ አጀንዳ ሆኖ እንደነበርም አስታውሰዋል።አጀንዳው ያሳሰባቸው በዘርኣይ አስገዶም በኩል ሁኔታውን ማሳወቃቸውን ገልጸው፤የነስብሀት ቡድን በታጋዮች መካከል ጠባብነት አለ በሚል ጥያቄውን ለማፈንም ብዙ ታጋዮች መገደላቸውን አስረድተዋል። በወቅቱ ግን በታጋዮች መካከል ይህ አይነት መከፋፈል እንዳልነበረ አስታውቀዋል።አቅም ያላቸው ለምን አይመሩንም ስላሉ ብቻ ብዙ ታጋዮች ከመገደላቸውም በተጨማሪ ያሉበት ሳይታወቅ እንደጠፉ ቀርተዋል ብለዋል።በአንድ ወቅት አባይ ፀሃዬ ከአጃቢዎቹ ጋር መጥተው ‹‹ቤታችሁ መሄድ የምትፈልጉ እጃችሁን አውጡ››ብለው በመጠየቃቸው ሰባት የተንቤን ልጆች እጃቸውን እንዳወጡ ያስታወሱት አቶ ሊላይ፣ሰባቱም ታጋዩ እያየ እዛው መረሸናቸውን ገልጸዋል። ከተረሸኑት ውስጥ 5ቱ ከዩኒቨርሲቲ የመጡ ወጣቶች እንደነበሩም አስታውሰዋል። የዓጋመ፣ክልተ ኣውላዕሎ፣ተንቤን እንደርታ ተወላጆች የሆኑ በርካታ ታጋዮች በነ ስብሀት ነጋ ሴረኛ ቡድን በተንኮል መገደላቸውንም አስታውሰዋል። በ1971ዓ.ም ማጽዳት በሚል ስትናገር” ኦኬ” ትላለህ ፤ይህም የኢምፔሪያሊስቶች ተፅእኖ እንዳለብህ ያመለክታል በሚል ብዙ ታጋይ መገደሉን ጠቁመዋል። በ1977 ዓ.ም ማሌሊት ሲመሰረት እነ ተኽለ ሃዋዝ፣ ሸዊት፣ ገብረ ህይወት እና ሌሎች ህወሓትን ደግፈው ይዘዋት የመጡ ሰዎች በዚህ ሴረኛ ቡድን መገደላቸውን አስታውቀዋል። እርሳቸው እንዳሉት፤ ገሰሰ እንዲገደል ካደረገው ምክንያት አንዱ የኤርትራ ጥያቄ ነው፤ በወቅቱ ሊቀ መንበር ነበር። እሱ ሳያውቅ የትግራይ ማኒፌስቶ ብለው እነ አባይ ፀሃየ በድብቅ አዘጋጅተው ያሳተሙትን ማኒፌስቶ ሊበትኑ ሲሉ ማኒፌስቶው በታጋዮች ፊት መቅደዱን አስታውሰዋል። አይደለም የትግራይ መገንጠል የኤርትራን መገንጠል አልቀበልም ብሎም በወቅቱ አቋሙን አሳውቆ ነበር። ከዛ ቀን ጀምሮ ገሰሰን ለመግደል እንቅስቃሴ ተጀምሯል።ህወሃት ፀረ ምሁር ነው፤ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ከዩኒቨርሲቲ የሄዱ ታጋዮች እንዲጠፉ ተደርገዋል ብለዋል። ሴረኛው ቡድን የተማረ ሰው አይወድም ያሉት አቶ ሊላይ፣ እነ ስብሓት ነጋ ፊውዳል ናችሁ እያሉ በግል ቂም ተነሳስተው የአባቱ ጠላት የነበሩ ትላልቅ ሰዎችን ጭምር መግደላቸውን ተናግረዋል። ስዩም መስፍንም ዓጋመ ላይ በተመሳሳይ መልኩ ይገድል ነበር ብለዋል።አቶ ሊላይ እንደገለጹት፤ይህ ሴረኛ ቡድን አሁንም በተደራጀ መልኩ በትግራይ ክልል ግፍ እየፈጸመ ይገኛል። በዚህ ቡድን የተነሳ የትግራይ ህዝብ ከሁሉ ጋር እንዲጣላ እየተደረገ ነው። በመሆኑም ትግራይ አገራችን በመሆኗ ህዝባችንን ከእነዚህ ማፍያዎች ልናድነው ይገባል። ለዚህ ደግሞ ተደራጅተን መታገል አለብን። ‹‹አሁን ጊዜው አይደለም አትናገሩ፤ አሁን እኮ ችግር ላይ ነን። በኋላ እንደርስበታለን›› የሚባለው ነገር አሁን አይሰራም ብለዋል። ከጠፋን በኋላ እንዴት ነው ወደ ውስጣችን የመምንመለሰው ሲሉም ጠይቀዋል። በትግራይ የሚገኙ ለም መሬቶችን ለዘመዶቻቸው አድለውታል። የእነሱ ልጆች በአቡዳቢ ደሴት ገዝተው እየኖሩ ነው ሲሉ አመልክተዋል። እኔ የየትኛውም ፖለቲካ አባል አይደለሁም ያሉት አቶ ሊላይ፣ ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት አውቃቸዋለሁ፤ የትግራይ ህዝብ ጠላት አይደሉም። ኢሳያስም ጠላታችን አይደለም፤ ጠላት እንዲሆኑ የሚያደርጓዋቸው እነዚህ ሀይሎች ናቸው ብለዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ይህንን ሀይል በተደራጀ መልኩ መታገል ያስፈልጋል፤አሁን ላይ አራት አምስት ፓርቲዎች በትግራይ ተፈጥረዋል፤ ጥሩ ነው። ግን የዚህን የህወሓት ቡድን ክፋት ያውቁታል ወይ? ትናንት በተንኮል የመጡ መሆናቸው አሁንም በተንኮል እየኖሩ መሆናቸውን ይረዱታል ወይ?ነው ጥያቄው። ተረድተውስ ህዝቡን ለማስተማር ሞራል አላቸው ወይ? ብለው ሁሌ ራሳቸውን ይጠይቃሉ። በዚህ በኩል ስጋት አላቸው።አዲስ ዘመን ሐምሌ 21/2012 በጋዜጣው ሪፖርተር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36166
5b8763cd630eef26f3e56d58445ced90
b3faf0308e0e8fb0e28ff1bb8d0beb24
ኤጀንሲው አዲስ የተሽከርካሪ መከላከያ ብረቶችን እየተከለ መሆኑን አስታወቀ
 አዲስ አበባ፡- በከተማዋ በተመረጡ ሃያ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ በ115 ሚሊዮን ብር ወጪ አዲስና የተሻሻሉ የተሽከርካሪ መከላከያዎችን /safety roller/ እየተከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂሬኛ ሂርጳ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤መከላከያ ብረቶቹ በከተማዋ በሚገኙና አደጋ በሚበዛባቸው መታጠፊያና ቁልቁለታማ ቦታዎች፣ አደባባዮችና የትራፊክ መጨናነቅ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እየተተከሉ ይገኛሉ። ብረቶቹ ተሽከርካሪዎች ከመንገድ አልፈው ጉዳት እንዳያደርሱ የሚከላከሉና በመሽከርከር ተሽከርካሪዎችን ወደትክክለኛ መንገድ የሚመልሱ አዲስና የተሻሻሉ የሲሊንደር ቅርፅ ያላቸው መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሰው፣1 ነጥብ 3 ኪሎሜትር የሚሸፍኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል። መከላከያ ብረቶቹ በቅድሚያ በከተማዋ በሚገኙና ግጭት በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው አምስት ቦታዎች በሙከራ ደረጃ የተተከሉ መሆናቸውንም ገልጸው፣በአሁኑ ወቅት ሃያ በሚሆኑ የከተማዋ አካባቢዎች ላይ እየተተከሉ መሆናቸውንም አስታው ቀዋል። እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ብረቶቹ የሚተከሉ ባቸው ቦታዎችም ሃይሌ ጋርመንት አደባባይ፣ ሰፈራ አደባባይ፣ መካኒሳ ቆሬ ድልድይ፣ ቀራንዮ ድልድይ፣ ቀራንዮ አካባቢ፣ ቫቲካን ኢምባሲ፣ የካ ሚሊኒየም ፓርክ፣ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን፣ ቀበና ደልድይ፣ ግንፍሌ ድልድይ፣ ራስ አምባ ሆቴል አካባቢ ናቸው። መገናኛ ኢንተርሴክሽን፣ ፔፕሲ ሰሚት ኢንተርሴክሽን፣ ሲኤም ሲ አደባባይ፣ ከአዲሱ ገበያ ወደ ሱሉልታ በሚወስደው መንገድ፣ ወሎ ሰፈር ኢንተርሴክሽን፣ ከዊንጌት ወደ አጠና ተራ በሚወስደው መንገድ፣ አፍንጮ በር ድልድይ፣ ጎላጎል ህንፃ፣ ሃኪም ማሞ ድልድይና ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢም ሌሎች ብረቶቹ የሚተከሉባቸው ቦታዎች ናቸው። የሚተከሉት ብረቶች በዋናነት ተሽከርካሪዎች በልዩ ልዩ ምክንያቶች ችግር አጋጥሟቸው ከመንገድ ወጥተው ሲገጯቸው ተሽከርክረው ተሽከርካሪዎቹን ወደመንገድ የሚመልሱ ናቸው። የመከላከያ ብረቶቹን የመትከል ስራው በአሁኑ ወቅት 50 ከመቶ መከናወኑም ጠቅሰው ፣ቀሪ ስራዎችን በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ በማከናወን ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም አመልክተዋል። የእግረኞችን ደህንነት ለመጠበቅና መንገድ ዘለው እንዳይሻገሩ ለመከላከል ኤጀንሲው በተለይ በቀለበት መንገድ አካባቢ የአጥር ስራዎችን በስፋት እየሰራ እንደሚገኝም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። የብረት መከለያ ፖሎቹ በመሀላቸው ሁለት ተሽከርካሪ ጎማዎችን የያዙና ከአስፓልት በታች 1 ነጥብ 001 ሜትር ከአስፓልት በላይ ደግሞ 1 ነጥብ 035 ሜትር ርዝመት አላቸው። አጠቃላይ ስራው በቻይናው /Ji­angxi changnan constractione co.ltd / እየተከናወነ መሆኑን ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያሳያል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 21/2012አስናቀ ፀጋዬ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36179
1b2abf9f979566d58091f2d9da1d9910
3a03790a95b5bd98812740fb4606a156
ሰላም ከሌለ ልማትን ማምጣትና የስራ ዕድል መፍጠር እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፡- “ሰላም ከሌለ የምንፈልገውን ልማት ማምጣትና የስራ ዕድል መፍጠር አንችልም”ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡ የአገር ሰላምና ደህንነትን ለማስከበር ፣ ኢንቨስትመንትን ለማሳለጥና ለዜጎች ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር ሁሉም ሰው የመንደሩን፣ከተማውን፣ወረዳውን፣ዞኑንና ክልሉን ሰላም መጠበቅ እንዳለበት አሳሰቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ የኢንቨስትመንትና የስራ ዕድል ፈጠራ መሪ ኮሚቴ ትናንት ውይይት ባካሄደበት ወቅት እንደገለጹት፤ለኢንቨስትመንትና ለስራ ዕድል ፈጠራ ትልቁ ማነቆ የስላም እጦት ነው፣ሰላምን ማስፈን የሚቻለው በመንግሥት ጸጥታ ኃይል ብቻ ሳይሆን የየአካባቢው ማህበረሰብ፣ቀበሌና እያንዳንዱ ኩባንያ የራሱን አካባቢ ሰላም ማረጋገጥ ሲችል ነው። ለወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ህዝብንና መንግሥትን አምነው ገንዘባቸውን በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ እንዲያውሉና ለልጆቻችን ስራ እንዲፈጥሩ እንደሚፈለግ አስታውቀዋል። ኢንቨስትመንትን የማቃጠልና የመጉዳት ነገር መቆም እንዳለበትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። ሰው የፈለገ ቢቸገርና ቢበሳጭ የሚበላበትን ገበታ መጣልና መስበር እንደሌለበት አስገንዝበዋል። የተለየ ውጫዊ ጠላት እስካልመጣ ድረስ በውስጥ የሚፈጠር መጠነኛ ግጭት የከፋ አደጋ እንዳያጋጥም ማህበረሰቡ አካባቢውንና አገሩን መጠበቅ እንዳለበት ገልጸው፤ የስራ ዕድል ፈጠራና ልማት በእያንዳንዱ ቤት ገብቶ ብዙዎችን መጠቀም የሚችለው ሰላም ሲኖር ነው ብለዋል። ከጸጥታ አኳያ አሁንም ተጨማሪ ስራ እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የአገር ሰላምና ደህንነት የማስከበር፣ ኢንቨስትመንትን የማሳለጥና ሰው ሳይቸገር ሰርቶ እንዲገባ የማድረጉ ጉዳይ በመንግሥት ብቻ ሊከወን እንደማይችልም አስታውቀዋል። እያንዳንዱ ክልል ከየአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት ሁሉም ሰው መንደሩን፣ ከተማውን፣ ወረዳውን፣ዞኑንና ክልሉን እንዲጠበቅ ማድረግ አለበት ሲሉ አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፤ክልሎች የጸጥታውን ዘርፍ ማጠናከርና ማህበረሰቡ ባለ ድርሻ አካል እንደ መሆኑ ሰላምን በማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማድረግ አለባቸው። ወጣቶች ኃይላቸውን ለበጎ ፈቃደኝነት ለማዋል የሚያስችላቸውን ጠንካራ አስተሳሰብ እና አቋም ማዳበር ላይ እንዲሠሩ፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በጎ ፈቃደኝነትን ከቅጥር ቅድመ ሁኔታዎች መካከል አንዱ እንዲያደርጉ፣በግል እና በመንግሥት ዘርፎች መካከል ያለው ትብብር እና መናበብ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ በልዩ ልዩ ኃላፊ ክስተቶች የተነሣ መቋረጥ እንደሌለበትም አስገንዝበዋል። የተገኙ ስኬቶችን እየመዘገቡ በዕድገት ጎዳና መገስገስ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ የሚቻለው የእያንዳንዱን ዜጋ ኑሮ ማሻሻል ስንችል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ክልሎች ለወጣቶች፣ ለአርሶ አደሮችና አነስተኛ ትርፍ በሚያስገኙ ሥራዎች ለተሠማሩ ዜጎች ድጋፍ በመስጠትና ተደራሽ በማድረግ የጀመሩትን የስራ አጥ ዜጎችን የመቀነስ ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። ክልሎች በበኩላቸው ወጣቶች ለጥፋት ዓላማ ማሳኪያ እንዳይውሉና ለስደት እንዳይዳረጉ ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በተለይ የቡድር ማነቆን በመፍታት፣ የንግድ አሰራሩን በማዘመንና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር ዝግጁ መሆናቸውን በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል። በእለቱም የሀዩንዳይ ኩባንያ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ተሽከርካሪ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በስጦታ አበርክቷል። ኩባንያው በኤሌክትሪክ የሚሰራ መኪና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ መገጣጠም መጀመሩም ታውቋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 21/2012ጌትነት ምህረቴ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36167
4dc0ea0008b1c696fcee61d40b691d9f
874c954e22d3021b2e9ccc277693bdc3
መንግስት ከመነካካት ባለፈ ሊያክማቸው የሚገቡ የእግር ኳስ ቁስሎች
የኢትዮጵያ እግር ኳስ በደጋፊዎች መካከል ለሚቀሰቀስ ግጭትና እሱን ተከትሎ ለሚፈጠር ጩኸት ባይተዋር ባይሆንም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚስተዋሉ ክስተቶች ከስፖርትም በዘለለ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ እያንፀባረቁ መጥተዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ሰኞ የ2011 በጀት ዓመትን አፈፃፀም ሪፖርት ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ የፖለቲካው ትኩሳት ስቴድየም ሰተት ብሎ መግባቱን መስክረዋል። ከዚህ ቀደም በመሪዎች ደረጃ የተለመደ አለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጠቃላይ በስፖርቱ ጉዳይ ማብራሪያ መስጠታቸው በራሱ የሚያስመሰግናቸው ነው። ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ እግር ኳስ ዙሪያ ያሉትን ቁስሎች ነካክተው አለፉ እንጂ ቁስሉን አፍረጥርጦ የሚድንበትን አቅጣጫ አላስቀመጡም። ከአገሪቱ እግር ኳስ ጋር በተያያዘ ከስቴድየም ግጭቶች በተጨማሪ ያሉትን አንገብጋቢ ችግሮች ጥልቀት በተለያዩ ማዕዘኖች መመልከት መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ማስቀመጥ እንደሚገባው ይረዳል ተብሎ ይታመናል። የአገራችን እግር ኳስ ውስብስብ ችግሮች የሞሉበት እንደመሆኑ መጠን ሁሉንም በስፋት ለመመልከት ከባድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጠኑም ቢሆን ጠቅሰው ያለፏቸው ሁለት አንኳር ነጥቦች የስቴድየም ግጭትና ክለቦች በመንግስት ላይ ያላቸውን የምጣኔ ሀብት ጥገኝነት እንዲህ በቀላሉ መታለፍ የሌለባቸውና አፋጣኝ ፈውስ የሚሹ ቁስሎች በመሆናቸው የችግሮቹን ስፋትና ጥልቀት መመልከት ተገቢ ነው። የስቴድየም ሁከትና ግጭትበ2009 ዓ.ም በርካታ ቁጥር ያለው የስቴዲየም ሁከት በተለይም በፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቢከሰቱም ከብጥብጦቹ ጀርባ እግር ኳስን የሚሻገሩ ገፊ ምክንያቶች እምብዛም እንዳልነበሩ ይጠቀሳል። ከዚያ ወዲህ ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚለኮሱ የስቴድየም ግጭቶችና ረብሻዎች ቁጥር አይሏል።በ2010 የውድድር ዓመት ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዲግራት፣ ጅማና ወልዲያ ከተሞች ውስጥ የስቴድየም ሁከትና ግጭቶች ተበራክተው እንደነበር ይታወሳል። በተለይም በውድድር ዓመቱ በወልዲያ ስፖርት ክለብና በመቐለ ሰብዓ እንደርታ መካከል ሊደረግ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት በሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወት የጠፋ ሲሆን፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት ተከስቷል። በዕለቱም ማገባደጃ ላይ በመቐለ ከተማ መንገዶች ላይ ክስተቱን ለመቃወም በርካታ ሰዎች ወጥተው እንደነበር አይዘነጋም። ጨዋታው ካለመካሄዱ በተጨማሪም የግጭቱ አሻራ እስከ ቀጣይ ቀናት ሲሻገርና ከእግር ኳሳዊ ምክንያት ይልቅ ፖለቲካዊ አንደምታው ሚዛን ሲደፋ ታይቷል። በወቅቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ጁነዲን ባሻ ክስተቱ ከእግር ኳስ የሚሻገር ገፅታ እንዳለው ተናግረው ነበር።የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ከረብሻዎች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ክለቦች ላይ የጣለው ቅጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር ገደማ መሰብሰብ መቻሉ ግጭቶች በምን ያህል ደረጃ እንደተበራከቱ ማሳያ ነው። በእንቁላሉ ጊዜ ያልተቀጣው እግር ኳስ ዛሬ ላይ ከፖለቲካም በላይ ጦዞ ለፀጥታ አስከባሪዎች ፈተና ከመሆን አልፎል እንደ አገርም ስጋት የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሰላም በራቃቸው የስፖርት ማዘውተሪያዎች መደበኛ የውድድር መርሐ ግብሮች መተማመኛ ማግኘት እየቻሉ አይደለም። በክልል የሚካሄዱ ጨዋታዎች በፖለቲካ ትኩሳት ሳቢያ ተጨማሪ ራስ ምታት እየሆኑ መምጣታቸውን በተለይም በዚሁ የውድድር ዓመት ለመታዘብ ተችሏል።በስፖርቱ ዓለም የተመልካቾች ነውጠኝነት ምክንያቶች ብዙ መሆናቸውን በስፖርቱ ጥልቅ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል። ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይንም ምጣኔ ሀብታዊ ብሶቶች ስቴዲየም ላይ ሊያጠሉ እንደሚችሉም ይታመናል። በኢትዮጵያ እግር ኳስን የታከከ ግጭትና ሁከት ሲከሰት የመጀመሪያው ባይሆንም አሁን ቀይ መስመር እያለፈ ይገኛል። የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ስናጤን ደግሞ ከእግር ኳስ ባሻገር ከነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ለስፖርት ጠንቅ የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ራሳቸው አስተውለውታል። እግር ኳስ ማኅበረሰባዊ መሰረት ከሌለው በስተቀር የጠነከረ የእኔነት ስሜት ሊፈጥር አይቻለውም የሚሉ ተንታኞች ፤ ክለቦች ከማኅበረሰባዊ መሰረታቸው በዘለለ ብሔር ተኮር መልክን እየተላበሱ የመምጣታቸው አዝማሚያ አደገኛ መሆኑ የበርካታ ስፖርት ቤተሰቦች እምነት ነው።ክለቦች ሲቋቋሙ ወይንም ሲዋቀሩ አካባቢያዊ መገለጫ ወይንም ከተማዊ ስያሜ ሊኖራቸው ቢችልም ከብሔር፣ ከዘር ወይንም ከሃይማኖት ጋር በተቆራኘ መልኩ መደራጀት ክልክል መሆኑን የስፖርት ኮሚሽን የስፖርት ማኅበራት ማደራጃ መመሪያ አንቀፅ 50 ቁጥር 2 ይገልፃል። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት ብቻ ፌዴሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ሊጎች የብሔር ስም የተቀጠላላቸው በርካታ ክለቦች ውድድር እያደረጉ ይገኛሉ። እግር ኳሱ ከአንዳንድ ሁከቶች አልፎ እጅግ ወደተደራጀ ነውጠኛነት እያመራ ስለመሆኑ ለማንም የተደበቀ አይደለም። ቀስ በቀስም የቡድናዊ መንፈስ እየተጓዘ ነው። ራሳችንን መከላከል እና ማዘጋጀት አለብን በሚል ደጋፊዎች ራሳቸውን ማደራጀት ከጀመሩ የሚያሰጋ ዓይነት እውነታ ሊፈጠር እንደሚችል ከወዲሁም እየተመለከትን ነው።በደጋፊዎች መካከል የእኔነቱ መንፈስ ከሮ ከኳስ ወዳጅነት አፈንግጦ በብሔርተኝነት ጎዳና መጓዝ ተጀምሯል። ከዚህ ቀደም ብጥብጡ ተጀምሮ የሚያልቀው ስቴዲየም ነው፤ ከዚያ አያልፍም። አሁን አሁን እየታየ ያለውን ግን ማብራሪያ የማይፈልግ የአደባባይ ሃቅ ነው። ክለቦች የማንነት ማግነኛና የራስ ኩራት መገለጫ መድረኮች እየሆኑ የመምጣታቸውን ሃቅ በየአካባቢው እየጎመራ ከመጣው ብሔርተኛነት ጋር የሚያስተሳስሩትም ጥቂት አይደሉም። ክለቦች መጠሪያው ባይኖራቸውም ከሚመጡበት ክልል ጋር ተያይዞ የእገሌ ብሔር ነው የሚል እምነት አሳድረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ክለቦች የተለያዩ የአገሪቱን ክልሎች እንደሚወክሉ መታሰቡ፤ ክልሎች ብሔርን መሰረት አድርገው እንደመዋቀራቸው ብሄርን እንደሚወክሉ ወደመታሰብ አድጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ፌዴሬሽኑ መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንደ ብሔራዊ ተቋም በሙሉ እግሩ ረግጦ መንቀሳቀስ እየቻለ እንዳልሆነ በግልፅ እየታየ ነው። ፌዴሬሽኑ ከውይይት የዘለለ ፋይዳ ያለው ነገር እየሰራ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ የስፖርት ቤተሰቦች ከዚህም በኋላ ችግሩን ይቀርፋል የሚል እምነት ማሳደር ተቸግረውበታል። መንግስት ይህን ስጋት ከተመለከተ ‹‹ጣልቃ የሚገባው ምን እስኪፈጠር ነው?›› የሚሉ ወገኖች መንግስት በእግር ኳሱ ጉዳይ ማሳሰቢያ ከመስጠት አልፎ ውሳኔ ማስተላለፊያ ትክክለኛው ወቅት ላይ እንደሆነ ፅኑ እምነት አላቸው። ቅጥ ያጣው የክለቦች የምጣኔ ሃብት ብክነትበማለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የአገራችን ክለቦች ምጣኔ ሀብት ምን ያህል በመንግስት ጫንቃ ላይ እንደተንጠለጠለ ተናግረዋል። እነዚህ ክለቦች የመንግስት የምጣኔ ሀብት ጥገኛ ከመሆናቸው ባሻገር ቅጥ ያጣው የገንዘብ ብክነታቸው በጥልቀት ታይቶ ርምጃ ሊወሰድበት እንደሚገባ መናገር አያስፈልግም። መንግሥት ለእግር ኳሱ የሚመድበው በጀትና የተጫዋቾች ክፍያ ነባራዊውን የአገር ኢኮኖሚ ያላገናዘበ፣ የክለቦች የፋይናንስ ሥርዓት የሌለበት፤ ዘመናዊ የእግር ኳስ አመራርና አደረጃጀት የሌለበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ሊጉ በተለመደው መንገድ እንዲቀጥል መፍቀድ የአገርና የሕዝብ ገንዘብ በከንቱ ሲባክን እንደመመልከት ይቆጠራል።ብዙዎቹ ክለቦች ቋሚ ገቢ የሌላቸው ሲሆኑ ከከተማ አስተዳደሮችና በመንግሥት ተቋማት በቀጥታ በጀት የሚመደብላቸው ናቸው። የተጫዋቾች ዝውውርና ሌሎች ክፍያዎቻቸውም ከዚሁ በጀት ላይ የሚታሰብ ሲሆን የሊጉ ተወዳዳሪዎች በየዓመቱ ከ30 እስከ 80 ሚሊዮን ብር የሚያንቀሳቅሱበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። የተጫዋቾች የዝውውር ገንዘብ በየዓመቱ እየናረና እያደገ መምጣቱን ተከትሎም በአማካኝ ከ50 እስከ 100 ሺ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ከአንዱ ክለብ ወደ ሌላኛው እየተዘዋወሩ ይገኛሉ። ዘንድሮ እንኳን በተጫዋቾች የዝውውር መስኮቱ አማካኝ ገንዘብ 100 ሺ ብር ሲሆን አነስተኛው 25 ሺ ብር ነው። አንድ ክለብ በዓመቱ በሚያስፈርማቸውና ውላቸውን የሚያድስላቸው የውጭና የአገር ውስጥ ተጫዋቾች ከአስር እስከ አስራ ሁለት ቢገመቱ፤ ሃያ ሚሊዮን ብር በተጫዋቾች ዝውውር ብቻ እንደሚያወጣ መገንዘብ ይቻላል። ክለቦች ከመንግስት በጀት ተላቀው የራሳቸውን ገቢ ማመንጨት አልቻሉም። የገቢ መንገዶች እየቀነሱ ወጪያቸውም ከዚህ በኋላ ይበልጥ እየተመነደገ እንደሚሄድ ከሁኔታዎች ተነስቶ ቢተነበይ ደግሞ ችግሩ ይበልጥ ጥርስ ያወጣ ይመስላል። የፕሪምየር ሊጉ ከከተማ ከተማ ተዟዙሮ የመጫወት መርሐግብር ከሊጉ ተሳታፊ ክለቦች መልክዓምድራዊ አቀማመጥ መራራቅ ጋር በተያያዘ ወጪያቸው በዚያው ደረጃ የሚደፈር ባይሆንም በድሃው ሕዝብ ገንዘብ እየተደፈረ ይገኛል።ከሁለት ዓመት በፊት አንድ የአዲስ አበባ ክለብ ለሊጉ ውድድር አንድም ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል አይጓዝም ነበር። ዘንድሮ ግን አራት ጊዜ መጓዝ ግድ ይለዋል። ባለፉት ሦስት የውድድር ዘመናት በየዓመቱ አንዳንድ የአዲስ አበባ ክለቦች ከሊጉ መውጣታቸውን ተከትሎ (አዲስ አበባ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ደደቢት) ከአምና እና ከካቻምና ይልቅ የአዲስ አበባ ክለቦች ለበለጠ ጊዜያት ወደ ክልሎች እየተጓዙ ለመጫወት ተገድደዋል። የክልሎችም ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።ክለቦቹ ብዙ በተጓዙ ቁጥር ወጪያቸው እየጨመረ መሄዱን ማስተዋል ይቻላል። በቀጣይ ዓመታትም ፕሪሚየር ሊጉን የሚቀላቀሉ ሦስት አዳዲስ ክለቦች ከአዲስ አበባ ውጪ መሆናቸው ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ለብዙሃኑ የመንግስት በጀት ላይ የተንጠለጠሉ የክልል ክለቦች ችግሩ ይበልጥ ብርቱ እንዲሆን ያደርገዋል።እነዚህ ክለቦች የህዝብ ሀብት የሚፈስባቸው እንደመሆናቸው «ሚሊዮኖችን ዘርተው ምን አጨዱ?» ብለን ብንጠይቅ መልሱ በቀላሉ ምንም ይሆናል። አሳዛኙ ነገር በእግር ኳሱ ይህን ያህል ገንዘብ እየተረጨ ከፋይናንስ ዕድገቱ ጋር ኳሱ አብሮ መራመድ ይቅርና በግማሽ መንገድ እንኳን ሊከተለው አቅሙ አለመፍቀዱ ነው። ከአስር ጨዋታ ዘጠኙ አንድ ለዜሮ በሆነ ውጤት በሚጠናቀቅበት አሰልቺ ሊግ፣ በሰላሙ ጊዜ እንኳን የስፖርት ቤተሰቡ ለመዝናናት ካምቦሎጆ ገብቶ ፀያፍ ስድብ ሰምቶ ከመመለስ የዘለለ ያገኘው ነገር የለም። ይህ ሁሉ የገንዘብ ክምር ብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ አገራት ከአስራ ስድስት ወደ ሃያ አራት አድጎ እንኳን ተወዳጁ መድረክ ጋር ሊያደርሰው የሚችል አቅም አልፈጠረለትም። የዘወትር ጩኸት ለሆነው የታዳጊ ወጣቶችና ተተኪዎች ላይ ገንዘቡ ባክኖ ቢሆን ኖር እሰየው ነበር። ኳስና መጫወቻ ጫማ አጥተው እግራቸው እየቆሰለ ለስፖርቱ ፍቅር ብቻ ድንቅ ብቃት ይዘው በየሰፈሩ የሚባክኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ታዳጊዎች ባላት አገር የነገ ተስፋቸው በደላላና በጥቅም ሰንሰለት በተሳሰሩ ግለሰቦች ጨልሟል። የሕዝብ ገንዘብ በገፍ የሚፈስባቸው ክለቦች ግን ከሌሎች አፍሪካ አገራት በወር ሦስት መቶ ሺ ብር ደመወዝ እየተከፈሉ ከኛ አገር ታዳጊዎች የማይሻል ተጫዋች ማስመጣትን ፋሽን አድርገውታል። ይህ ሁሉ ገንዘብ ባክኖ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል የእግር ኳስ ፍላጎት ተሳክቶ ቢሆን የስፖርት ቤተሰቡ አሜን ብሎ በተቀበለም ነበር። ምክረ ሃሳብክለቦች በክልሎች ተዟዙረው የሚያደርጉት ጨዋታ ከወጪውም አኳያ ቀድሞውንም ባይደግፉትም ፖለቲካው ባመጣው ጣጣ አንዳንዶቹ እየተዟዟሩ ለመጫወት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቆይተዋል። እግር ኳሱን ምክንያት በማድረግ የሚስተዋለውን አደገኛ አዝማሚያ መቀነስ የሚቻለው ውድድሮችን በዞን ማከናወን ሲቻል ብቻ እንደሆነ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ያምናሉ። ይህ የሚስተዋለውን አምባጓሮ ከመቀነሱም በላይ ተዟዙሮ በመጫወት ይባክን የነበረውን የክለቦች ፋይናንስ ይታደጋል የሚል ጠንካራ እምነትም በብዙዎች ዘንድ አለ። ፌዴሬሽኑ ግን የዚህን የውድድር ዓመት ቀሪ ሦስት ጨዋታዎች በጊዜው ማጠናቀቅ ተስኖት እንኳን በቀጣይ ዓመት የፕሪሚየር ሊጉን ፎርማት በተመሳሳይ መንገድ የመቀጠል እንጂ የመለወጥ አዝማሚያ አይታይበትም። መንግስት ከአደረጃጀትና ከክለቦች የፋይናንስ ሥርዓት ጋር በተያያዘ እግር ኳሱን ውስጥ ቢገባ ፊፋ ቅር እንደማይሰኝ ህጎቹን ጠንቅቀው የሚያውቁ ይመሰክራሉ። ፌዴሬሽኑ ቀጣዩን የውድድር ዓመት በተመሳሳይ መልኩ እንዳይጀምር መንግስት አንድ ጠንካራ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ካለበት ጊዜው አሁን ነው። የስቴድየም ሁከቶችን አደብ ማስያዝ ካለበትም ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻል እንኳን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ አደረጃጀቱን የቤት ስራው አድርጎ መያዝና አስፈላጊውን ማስተካከያ ማድረግ እንደሚኖርበት የበርካቶች ምክር ነው። ይህ ካልሆነ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ‹‹ወጣትም ገንዘብም እየከሰርን›› ላለመሄዳችን ማስተማመኛ የለም።አዲስ ዘመን ሰኔ 29/2011ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13621
2a354409f3b1f5880864256134aaf60e
abd6928923ba015baf15ced9547cbf3c
ጸብ አጫሪነትና መከላከያ ዘዴው
በስፖርት ውስጥ ሁከት ማለት ከአንድ የስፖርት ሕግና ደንብ በተፃራሪ የጠብ አጫሪነት ባህሪያት ማሳየት እና ድርጊቶችን መፈፀም ማለት እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ይህ ችግር በኢትዮጵያ ስፖርታዊ ሁነቶች ላይ መንፀባረቅ እና ችግር መፍጠር ከጀመረ ደግሞ ዘለግ ያሉ ዓመታትን በማስቆጠር ላይ ነው፡፡ ታዲያ የዚህ ችግር መንስኤዎች እና መከላከያ ዘዴዎች ምን ይሆኑ? በጉዳዩ ላይ ሳይንሳዊ ጥናት የሰሩ እና ምሁራዊ ምልከታቸውን ያስቀመጡ ባለሙያዎች ምላሽ አላቸው፡፡ አቶ ተሾመ አጀበው እና ዶክተር አእምሮ አስማማው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ትምህርት ክፍል መምህራኖች ናቸው፡፡ የስፖርት ሁከት ወይም ብጥብጥ በብዛትና በመጠን እየጨመረ መምጣቱን የተለያዩ መረጃዎች ጠቅሰው፣ በጥናታቸው ላይ አመላክተዋል። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በእግር ኳስ ቡድኖች መካከል በሚኖር ጨዋታ ወቅት ብጥብጥ እና ሁከት የተለመደ እስኪመስል ድረስ በብዛት መከሰቱን ያነሳሉ፡፡ በሚደረጉ ጨዋታዎች ዳኛን የመደብደብ ችግር በተለይ በደጋፊዎች፣ በተጫዋቾች፣ በአሰልጣኞች እንዲሁም በቡድን አመራሮች መፈፀሙን እንደመረጃ ያስቀምጣሉ። ለዚህ ችግር መፍትሄ ማምጣት እና በድጋሚ እንዳይከሰት አስቀድሞ ለመከላከል በስፖርት እንቅስቃሴ የሁከት መንስኤዎችን ለይቶ ማወቅ እንዲሁም ችግሩን በጥልቀት በመገንዘብ የተለያዩ ዘዴዎችን መተግበር መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ይህን ለማድረግ ለነገ የሚባል ሥራ መኖር እንደሌለበት ነው የሚያሳስቡት፡፡ ከችግሩ ምንጭ እና ስፋት አኳያ ከሁሉም የስፖርት ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግም አስፈላጊ መሆኑን በዚሁ ሳይንሳዊ ጥናታቸው ላይ ያመላክታሉ፡፡ እንደ ምሁራኑ ትንተና ሁከት ከስፖርት የውድድር ደንቦች ጋር በቀጥታ የማይገናኝ በደጋፊዎች፣ በአሰልጣኞች እንዲሁም በተለያዩ አካላት ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚፈፀም አካላዊ ጥቃት ነው፡፡ በብዛትም አካላዊ ንክኪ ባላቸው ስፖርቶች በእግር ኳስ ቅርጫት ኳስ እና ሌሎች መሰል ስፖርቶች ላይ የሚከሰት ነው። በአብዛኛው ጊዜ ይህን መሰል ድርጊት የሚነሳው በተጫዋቾች ሲሆን ነገር ግን ችግሩ እንዲባባስ ደጋፊዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ፣ አሰልጣኞች ፣ የቡድን መሪዎች እና ሌሎችም የበለጠ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ለስፖርት ጠብ አጫሪነት ወይም ሁከት አዲስ አይደለም፡፡ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በስፖርቱ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ የሆኑ አካላት የተለያዩ ጉዳቶችን ያስከተሉ ድርጊቶች ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በጥንታዊ ግሪክ እና የሮማ ስፖርቶች ደም አፋሳሽ ስፖርቶች ታዋቂ እንደነበሩ የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዱ ይጠቅሳሉ። በመካከለኛው እና በቅድመ ዘመናዊ የአውሮፓ ታሪኮችም ስፖርቶች ለጦርነት ሥልጠና ዝግጅቶች ያገለግሉ ስለነበር ልክ እንደ ጦርነት በርካታ መዘዞችን ያስከትል ነበር፡፡ ሁለቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ትምህርት ክፍል መምህራን ሁከትን በሦስት ዓይነት ሳይንሳዊ መንገድ በማስቀመጥ የችግሩን መንስኤ እና መፍትሄ ለማመላከት ሙከራ አድርገዋል፡፡ አጥኚዎቹ በቅድሚያ ለመመልከት የሞከሩት በስፖርቱ ላይ የሚከሰትን ተፈጥራዊ የጠብ አጫሪነት ባህሪ ወይም ሁከት ፈጣሪነት ላይ ነው፡፡ በተለይ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እና መምህራኖች እንደመሆናቸው መጠን የሰዎችን ባህሪያት ከዚህኛው አግባብ ለመረዳት መሞከራቸው ጉዳዩን በቀላሉ ለመገንዘብ ያግዛል፡፡ የሁከት መንስኤዎች የሰው ልጅ ተፈጥራዊ የጠብ አጫሪነት ባህሪ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይህን ባህሪ ከውስጥ ለማውጣት በተለይ ስፖርታዊ ውድድሮች እና እንቅስቃሴዎች ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥር ማህበራዊ መንገድ ተደርጎ እንደሚታሰብ ይናገራሉ። ለዚህም ነው አብድል ሃቂ የተባለ ታዋቂ ምሁርን በአስረጂነት በመጥቀስ ሰዎች ይህንን ተፈጥራዊ ባህሪያቸውን ለማውጣት ስፖርትን እንደ ሁነኛ የመተግበሪያ አጋጣሚ እንደሚጠቀሙበት የሚናገሩት። በአሰልጣኞች፣ተጫዋቾች፣ደጋፊዎች እና የስፖርቱ ተሳታፊ አካላት በሁከቱ ላይ ለመሳተፋቸው መነሻው ይኸው ተፈጥራዊ የጠብ አጫሪነት ባህሪያቸው መሆኑን ለማመልከት ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን የሰው ልጆች በዚህ ተግባር ላይ ሲሳተፉ ስፖርቶች የጠበኛ ደመ ነፍሶች ጤናማ በሆነ መንገድ ማንፀባረቂያ ቢሆኑም በዚህ ተግባር ላይ ያልተገባ ሁኔታ ከተፈጠረ ወደ አስከፊ ግጭት እና ሁከት ሊቀየር እንደሚችል ጥናት አቅራቢዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ ሌላኛው እና ሁለተኛው የጠብ አጫሪነት መንገድ የብስጭት የጠብ አጫሪነት እሳቤ መሆኑን በመግለፅ ሳይንሳዊ ትርጉሙን ለማስቀመጥ ይሞክራሉ፡፡ በዚህም የሁከት መንስኤ የብስጭት ጠበኝነት ቁርኝት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ በስፖርቶች ላይ የሚከሰተው ይህ ሁኔታ ምንም እንኳን በግልፅ የጠብ አጫሪነት ድርጊት ውጤት ባይሆንም ሁል ጊዜ ግን ክስተቱ ጋር የሚያያዝ የተወሰነ የብስጭት ሁኔታ ቀድሞ እንደሚኖር ከግምት ውስጥ ያስገባሉ፡፡ የብስጭት መኖር ደግሞ በዚህ ሁከት ውስጥ ተሳታፊ እንደሚያደርግ ይናገራሉ፡፡ ለዚህ ብስጭት መነሻ የሚሆኑት ደግሞ የጨዋታ እንቅስቃሴ፣ የብቃት ማነስ ወይም በተቃራኒ ቡድን የመበለጥ፣ ከአሰልጣኞች፣ከተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ወይም ደግሞ ከተለያዩ ሁኔታዎች አንፃር ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ሁከት ፈጣሪው አካል ጨዋታው የሚካሄድበት አግባብ አሊያም በዳኛው የሚሰጡት ውሳኔዎች የተገቢነት ጉድለት አላቸው በማለት አመኔታ ካሳደረ በዚህ ምክንያት ወደ ጠብ አጫሪነት ሊያመራ ይችላል፡፡ ወይም በጨዋታ ብልጫ ሲወሰድበት እንዲሁም ከተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ትንኮሳ ሲካሄድበት አሊያም ደግሞ በተቃራኒ ቡድን ተጫዋች አላግባብ ጥፋት ተፈፅሞብኛል ብሎ ሲያምን ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ተጫዋቹን በሥርዓት እና በሕግ እንዳይጫወት ሊያደርጉት ይችላሉ የሚል አመክንዮ በጥናት አቅራቢዎቹ ይሰነዘራል፡፡ ምሁራኑ በሦስተኝነት ለጠብ አጫሪነት እና ሁከት መንስኤ ያሉት የማህበራዊ ትምህርት ንድፈ ሃሳብ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በዚህም በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ የሚከሰቱ ችግሮች መንስኤ እነዚህን የሁከት ባህሪያት እና ድርጊቶች ከመማር የሚመጡ መሆናቸውን በመግለፅ በስፋት ለመተንተን ይሞክራሉ። በስፖርቱ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚሳተፉ አካላት ተገቢ ያልሆኑ ባህሪያትን ከአካባቢያቸው እና ከሁኔታዎች ለሚማሩበት አጋጣሚ ተጋላጭ ይሆናል የሚል አመክንዮ ያቀርባሉ፡፡ ሰዎች የሌሎችን አርአያ የሚሆኑ ሰዎችን ድርጊት እና ባህሪ በመመልከት የሚያስከትለውን ጉዳት እና መልካም ነገር በመገንዘብ ወደራሳቸው በማምጣት አዳዲስ ባህሪያትን ይማራሉ፡፡ ተምሳሌቶች በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ተፅዕኖ የማሳረፍ አቅም ስላላቸው እነዚህ አካላት አስፈላጊ የባህሪ ምሳሌዎችን እንዲያሳዩ ኃላፊነት እንደተሰጣቸው የሚያነሱት ጥናት አቅራቢዎች በተለይ አሰልጣኞች፣ የቡድን አጋሮች፣ ደጋፊዎች፣ መገናኛ ብዙሃን፣ እንዲሁም የስፖርት አስተዳዳሪ አካላት ጤናማ ተምሳሌቶች የመፍጠር ኃላፊነት ለሁሉም አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሦስቱ ዋና ዋና ምክንያት እና ባህሪዎች ባሻገር ምሁራኑ ለሁከት እና ጠብ አጫሪነት በዋነኝነት መንስኤ ይሆናል በማለት ያስቀመጡት ድርጊት በስፖርት ውስጥ የተጫዋቾች ግጭት ነው፡፡ ተጫዋቾች በእንቅስቃሴ ላይ ባሉበት ወቅት ከባላጋራ ጋር በሚያደርጉት ሰላማዊ ግብ ግብ ከሥርዓት እና ደንብ ውጪ አንደኛው አካል ጥፋት ሲሰራ ሌላኛው ደግሞ ለዚያ ጥፋት ተመሳሳይ ምላሽ መስጠቱን እንደ ችግር ያስቀምጣሉ፡፡ ይህ ደግሞ ለጠብ እና ግጭት መንስኤ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ለበለጠ ሁከት እና ብጥብጥ ሊዳርግ እና ሊያነሳሳ እንደሚችልም ነው የሚናገሩት፡፡ በሌላ መልኩ በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ውስጥ ለሁከት እና ለጠብ አጫሪነት ደጋፊዎች እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡ ምሁራኑ ይህን ጉዳይ በጽሑፋቸው ውስጥ በማካተት በአብዛኛው እነዚህ አካላት በዚህ ተግባር ላይ የሚሳተፉት ንክኪ እና ጉልበት የተቀላቀለበት እንቅስቃሴ በሚፈቅዱ ስፖርቶች ላይ መሆኑን ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ በሚደግፉት ቡድን እንቅስቃሴ ደስተኛ የሆኑ እና በተቃራኒ ቡድን ብልጫ የተወሰደባቸው ደጋፊዎች በእነዚህ ሁከት ውስጥ ለመሳተፍ ትልቅ ዕድል እንዳላቸው ይጠቁማሉ፡፡ ለዚህ ችግር መባባስ እንደ ተጨማሪ ምክንያት ሊወሰድ የሚገባው ደግሞ በማዘውተሪያ ስፍራዎች ላይ መጠጥ እና መሰል አደንዛዥ እፅ መጠቀም ሁከቱን ለማባባስ እና ተሳታፊ የመሆን ዕድላቸውን ያሰፋዋል የሚል አመክንዮ ያስቀምጣሉ፡፡አሰልጣኞች፣ተጫዋቾች እና የቡድን መሪዎች በመወዳደሪያ ስፍራዎች ላይ የሚያሳዩት ያልተገባ ባህሪም በነዚህ ሁከት ፈጣሪ ደጋፊዎች ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይናገራሉ፡፡ ጥናት አድራጊዎቹ ሰፋ ባለ መልኩ ስፖርታዊ ሁከቶች እና ጠብ አጫሪነት የሚከሰትባቸውን መንስኤዎች በመዘርዘር ብቻ አያበቁም ለነዚህ ችግሮች የሚሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሄዎችንም ያመላክታሉ፡፡ ከዚህ በታች በምሁራኑ የቀረቡ የመፍትሄ ሃሳቦች በተጨመቀ መንገድ ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ በነዚህ ምሁራን ከሚቀርቡት የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው ትምህርት እና ሥልጠና ነው፡፡ የስፖርት ተቋማት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ዜጎች ከሁከት እና ጠብ አጫሪነት ባህሪ እንዲርቁ እና ራሳቸውን መቆጣጠር እንዲችሉ በየጊዜው ትምህርት እና ሥልጠና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ነው በምክረ ሃሳባቸው የሚያስቀምጡት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የስፖርታዊ ጨዋነት ዘመቻዎች ማድረግ ችግሮችን ለማቃለል ከሚረዱ መፍትሄዎች መካከል መሆኑን ያመላክታሉ፡፡ ይህን ስኬታማ ለማድረግ ደግሞ የተቃራኒ ቡድንን የአቀባበል ሥርዓት እና መስተንግዶ፤ የድጋፍ ሥነ ምግባር ብሎም በተለያዩ የግንኙነት አግባቦች ይህንን በጎ ሥርዓት ማስተዋወቅ ተገቢ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡ ከስፖርታዊ ጨዋነት ባሻገር ለሁከት እና ብጥብጥ ዋነኛ መንስኤ ናቸው ተብለው ከሚታሰቡ ነገሮች መካከል የሆነውን የዳኝነት ብቃት በሥልጠና እና ቴክኖሎጂ ማሻሻል እንደሚገባ ይናገራሉ፡፡ ሕግ የማስከበር ሂደትን እና ተአማኒ እና ሚዛናዊ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ለስፖርት ማህበረሰቡ ማድረስ የመፍትሄው አካል መሆናቸውን ነው ምሁራኑ በጥናታቸው ላይ ለማመላከት የሞከሩት፡፡ በማጠቃለያቸው ላይም ስፖርታዊ ጨዋነትን በተግባር ማሳየት፣ መልካም ተምሳሌቶችን በተገቢው ማወደስ እና እውቅና መስጠት፤ አስተማሪ ቅጣቶችን እና የአሠራር ሥርዓቶችን መዘርጋት አስፈላጊ መሆናቸውን አስቀምጠዋል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 30/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13690
4274d76aabfc03f77432b9fbc68884f2
d84fb3bfd54e35c7558db07fd962b3ff
መቐለ 70 እንደርታ የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆነ
 በመቐለ 70 እንደርታ የበላይነት የተጠናቀቀው የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር፤ ከስፖርታዊ ውበቱና አዝናኝነቱ ይልቅ ውዝግቡና ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ የወጣበት እንደነበር ይታወቃል። በተለይ በአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ የተጠለፉት የእግርኳስ ክለቦቻችንና ደጋፊዎቻቸው በአካባቢና በማንነት ጭምር ሲወዛገቡ ሰንብተዋል። አብዛኞቹ የስፖርት ተንታኞች እንደሚሉት የአገራችን የእግር ኳስ ክለቦች አደረጃጀት በአካባቢና በክልል ላይ የተመሰረተ በመሆኑ እግርኳሱም አካባቢያዊ ይዘት ሊታይበት ችሏል። በዚህ የተነሳ ደጋፊዎች በነዚህ ማንነቶች ላይ በመመስረት በሚያደርጉት የድጋፍ ሁኔታ ግጭቶች ሲበራከቱ ተስተውሏል። ክለቦችም ከአንድ ቦታ ወደሌላው ቦታ ሄደው ለመጫወት ከፍተኛ ተግዳሮት ሲገጥማቸው ከርሟል። ይህ ብቻም አይደለም። በዚህ የተነሳ የዳኝነት ሥርዓቱም ትልቅ ፈተና ገጥሞት ሰንብቷል። በራሳቸው በእግርኳስ ዳኞች ላይ አልፎ አልፎ የሚታዩ የሥነምግባር ችግሮች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ደጋፊውና ክለቦች በሚያሳድሩባቸው ጫና ዳኞች ክለቦችን አናጫውትም እስከማለትም የደረሱበት ዓመት እንደነበር ይታወሳል። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑም ቢሆን በዓመቱ ውስጥ በርካታ ውዝግቦችን ሲያስተናግድ ሰንብቷል። በተለይ በምክንያቶች ግጭቶች ሲነሱና መከፋፈሉ ሲጠነክር ፌዴሬሽኑ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ማሳለፍ ተስኖት ሲንገዳገድ ተስተውሏል፡፡ በዚህም የተነሳ ፌዴሬሽኑ ስፖርቱን መምራት አልቻለም እስከመባል ደርሷል፡፡ ያም ሆኖ ግን በተለያዩ ወቅቶች ፌዴሬሽኑ በወሰዳቸው እርምጃዎችና ውሳኔዎች አብዛኛው የእግርኳሱ ቤተሰብ ደስተኛ ባይሆንም የዓመቱ ውድድር ቀጥሎ ትናንት ተጠናቋል፡፡ በውድድሩ እስከትናንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ድረስ ሦስት ክለቦች ለዋንጫው ዕድል ይዘው ወደሜዳ ገብተዋል። በዚህም መሠረት ቀደም ሲል ከተደረጉት 29 ጨዋታዎች 56 ነጥቦችን በመሰብሰብና 32 የግብ ክፍያ በመያዝ ሰፊ ዕድል ይዞ ወደሜዳ የገባው የፋሲል ከነማ ክለብ ነው፡፡ ፋሲል ከነማ ምንም እንኳን ከሜዳው ውጪ የሚጫወት ቢሆንም ተጋጣሚው የሽሬ እንዳስላሴ ክለብ በዓመቱ ውስጥ ከነበረው አጠቃላይ ብቃት አንጻር ፋሲልን የማሸነፍ አቅም እንደማይኖረውም አብዛኞቹ የእግር ኳስ ተንታኞች የመሰከሩበት ሁኔታ ነበር። በተለይ ከተከታዩ መቐለ 70 እንደርታ ክለብ 12 የጎል ብልጫ ይዞ መገኘቱ የተሻለ የአሸናፊነት ዕድል ይዞ ወደሜዳ እንዲገባ አድርጎታል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ዋንጫውን የመውሰድ ዕድል የነበረው ደግሞ ፋሲል እስኪረከበው ድረስ ለበርካታ ሳምንታት ሊጉን በበላይነት መምራት የቻለው የመቐለ 70 እንደርታ ክለብ ነው፡፡ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር እኩል 56 ነጥብ ቢኖረውም በጎል ክፍያ ተበልጦ ወደሜዳ መግባቱ ከፋሲል ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ዕድል እንዲኖረው አድርጓል። በአንጻሩ ግን መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታውን የሚያደርገው በሜዳው መሆኑ የተሻለ የማሸነፍ ዕድል እንዲይዝ አድርጎታል። በሦስተኛ ደረጃ ዋንጫውን የማንሳት ዕድል የነበረው ደግሞ የሲዳማ ቡና ክለብ ነው። ሲዳማ ቡና ለዋንጫው ፍልሚያ እንዲጠበቅ ያደረገው 55 ነጥቦችን በመሰብሰብ ከሁለቱ መሪ ክለቦች በአንድ ነጥብ ብቻ ዝቅ ብሎ መገኘቱ ሲሆን ፋሲል ከነማና መቐለ 70 እንደርታ ክለቦች ከተሸነፉ ወይም አቻ ከወጡና እሱ ተጋጣሚውን ማሸነፍ ከቻለ ዋንጫውን የማንሳት ዕድል ነበረው፡፡ ሆኖም ከሁለቱ መሪ ክለቦች አንጻር ሲታይ አነስተኛ ዕድል ይዞ ወደሜዳ ገብቷል፡፡ በመጨረሻም ተጠባቂው ጨዋታ በመቐለ 70 እንደርታ ክለብ የዋንጫ ባለቤትነት ተጠናቋል። አጓጊ በነበረው በዕለቱ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ገና ከ10ኛው ደቂቃ ጀምሮ ሽሬ እንዳስላሴን ሲመራ ቢቆይም ከእረፍት በኋላ በገባበት ጎል አቻ በመሆኑ ነጥብ ለመጣልና ዋንጫውንም ለመቐለ 70 እንደርታ አሳልፎ ለመስጠት ተገዷል። በአንጻሩ መቐለ 70 እንደርታ ድሬዳዋ ከነማን 2፡ 1 በማሸነፉ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል። በሌላ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራትን 3፡0 ቢያሸንፍም ዋንጫውን ማንሳት ሳይችል ቀርቷል። አዲስ ዘመን ሀምሌ 1/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13715
897142cdd4629f6c1e461cfeba803e37
98654feaa606f99a86204929cce852c1
የጠፋውን ስም ለማስመለስ
 እአአ የ2016ቱ የሪዮ ኦሊምፒክ ከመካሄዱ አስቀድሞ የስፖርት ቤተሰቡ ትኩረት አበረታች ቅመም በስፖርት ላይ ያሳደረው ተጽእኖ እና በዚህ ተጠቂ የሆኑ ሀገራት ላይ ያተኮረ ነበር። በአትሌቲክስ ስፖርት ከቀዳሚ ተጠቃሽ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያም ከተወቃሽነት ማምለጥ አልተቻላትም። በወቅቱ ሰባት የሚሆኑ አትሌቶች በዚሁ ሳቢያ ጥርጣሬ ውስጥ መግባታቸው ደግሞ በዓለም አቀፉ የፀረ- አበረታች መድኃኒቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ትኩረት ውስጥ ለመግባቷ ምክንያት ሆነ። በዓለም ላይ በአበረታች ቅመሞች ከሚጠረጠሩት ቀዳሚ አምስት ሀገራት መካከልም አንዷ ልትሆን ቻለች። ይህንን ተከትሎም ሀገሪቷ ለጉዳዩ የምትሰጠው ትኩረት ምን ድረስ እንደሆነ በግልጽ ለዓለም ይፋ በመሆኑ፤ በአበረታች መድኃኒቶች ላይ ያለው እንቅስቃሴም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰቢያ ተሰጠ። መንግሥትም ለጉዳዩ በሰጠው ትኩረት የኢፌዴሪ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት በአዲስ መልኩ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 400/2009 ተቋቁሟል። የአበረታች ቅመሞች ጉዳይ ሁሌም የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆን ያለበት እንደመሆኑ፤ ጽሕፈት ቤቱ የጠፋውን ስም ለማስመለስ በሚያደርጋቸው ተግባራት በየጊዜው የደረሰበትን እንዲህ ያሳውቃል። ቅድሚያ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በኢትዮጵያ የሁልጊዜም አርዕስት ያደረጉት የተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ናቸው። ሀገሪቷ የስጋት ቀጣና ውስጥ የገባችበት የመጀመሪያው መንስኤ፤ በስፖርቱ ስኬታማ ከሆኑ ሀገራት ተርታ መሰለፏ ነው። ሌላኛው ምክንያት ደግሞ በአትሌቶች ዘንድ የቅመሙ ተጠቃሚነት አዝማሚያ መታየቱ ነው። በወቅቱ አትሌቶች ከተጠቃሚነት ጋር ጥርጣሬ ውስጥ ገብተው በዓለም አቀፉ ኤጀንሲ ምርመራ መደረጉም በዚሁ ምክንያት ነው። ሀገሪቷ በስፖርቱ ታዋቂ እንዲሁም በአየር ንብረቷ እና የቦታ አቀማመጧ ተመራጭ እንደመሆኗ በርካታ የውጭ ሀገራት አትሌቶችና ሌሎች የስፖርት ባለሙያዎች መዳረሻ መሆኗም ሌላኛው ምክንያት ነው። ሰፊና ዓለም አቀፍ ሽፋን ያላቸው የመገናኛ ብዙኃን ተጠቃሚነቱን በተመለከተ በርካታ መረጃዎችን ማውጣታቸውም እንዲሁ። ይህንን የተመለከቱት የዓለም አቀፉ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ እንዲሁም በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበርም በሀገሪቷ ላይ ጫና ማሳደራቸው ጉዳዩ ይፋ ወጥቶ እንዲሰራበት አድርጓል። በመስፈርቱ መሠረትም ጽሕፈት ቤቱ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ፣ በመንግሥት በጀት ተመድቦለት እንዲሁም ከየትኛውም አካል ነፃ በሆነ መልኩ ሊቋቋም ችሏል። ተግባራት ቀዳሚው ሥራ የሕዝብ ንቅናቄን መፍጠር ነው። በየትኛውም ሥራ ቀዳሚው ተግባር ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደመሆኑ ጽሕፈት ቤቱ በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል፤ በማከናወን ላይም ይገኛል። ጉዳዩ ትኩረት ከተሰጠው ጊዜ አንስቶም የሥልጠና እና የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ለሁሉም ባለ ድርሻ አካላት መረጃው እንዲደርስ ተሰርቷል። ውድድር በሚካሄድበት ወቅትም ስፖርተኞችን እንዲሁም ሰልጣኞችን በተለያየ መንገድ ስለ ጉዳዩ እንዲረዱ እና በደንብ እንዲያውቁ የተለያዩ ሥራዎች በመከናወን ላይም ይገኛሉ። በየአካባቢውና ሕዝብ በብዛት የሚደርስባቸው አካባቢዎችም ስለ ጉዳዩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ትልልቅ ቢልቦርዶችን፣ ብሮሸሮችንና የተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ሕዝባዊ ንቅናቄውን ሲያጠናክር ቆይቷል። ከዚህ ባሻገርም ባለድርሻ አካላትን በሥራው በማካተትና ሰነዶችን በማዘጋጀት እየተሰራ ይገኛል። ከስፖርት ማህበራት ጋር በመሆን የትምህርትና ሥልጠና ማኑዋል ተዘጋጅቷል፣ የማሰልጠኛ ማዕከላትና ፕሮጀክቶች በሥልጠናቸው አካተውታል፣ ፎረሞች በመቋቋም ላይ ይገኛሉ (እስካሁን ሦስት ፎረሞች ተመስርተዋል) እንዲሁም በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም እንዲታቀፍ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ። ምርመራ እና ቁጥጥር በዚህ ሥራ ቀዳሚው ነገር ብቁ ባለሙያዎችን ማፍራት መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት 43 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎችን በማሰልጠን፤ በፌዴራል፣ ክልል እና ከተማ አስተዳደሮች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል። በሀገር ውስጥ በሚካሄዱ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ውድድሮች ከመካሄዳቸው አስቀድሞም የደምና ሽንት ናሙናዎች በባለሙያዎቹ የሚወሰዱ ሲሆን፤ እስካሁንም ከ1ሺ13 አትሌቶች ናሙና በመውሰድ በውጭ ሀገራት ወደሚገኙት ላቦራቶሪዎች ተልኳል። በየትኞቹ የስፖርት ዓይነቶች ተጋላጭነቱ ይጨምራል በሚለው ላይም ጽሕፈት ቤቱ ጥናት አዘጋጅቷል። በዚህም መሠረት ስፖርቶቹ የተለዩ ሲሆን፤ በርካታ ገፋፊ ምክንያቶች ያሉት አትሌቲክስ (በተለይ በማራቶን)፣ እግር ኳስ (በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች)፣ ብስክሌት፣ ቦክስ እና የፓራሊምፒክ ስፖርቶች በተለየ ተጠቃሚነቱ እንደሚጎላ ተረጋግጧል። የሕግ ጥሰትን በተመለከተ ከሚሰራው የመከላከልና የቁጥጥር ሥራ አፈንግጠው ቅመሙን እንደተጠቀሙ በተረጋገጠባቸው አካላት ላይም ሕጋዊ የእርምት እርምጃዎች ይወሰዳል። ጽሕፈት ቤቱ ከሕግ አካላት ጋር የሚሰራ ሲሆን፤ እስካሁንም ቅመሙን እንደተጠቀሙ የተረጋገጠባቸው አካላት ሕጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። በዚህም መሠረት ዘጠኝ የሚሆኑ አትሌቶች ከአራት እስከ ስምንት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ከውድድሮችም ሆነ ስፖርቱ እንዲገለሉ ተፈርዶባቸዋል። ዮሃና እና ግሸን የተባሉ የመድኃኒት መደብሮችም አበረታች ቅመሞችን ለአትሌቶች መሸጣቸው በመረጋገጡ ታሽገዋል። ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽሕፈት ቤቱ ከዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ እንዲሁም በየደረጃው ካሉት ቢሮዎች ጋር የሁለትዮሽና ሦስትዮሽ ግንኙነት ፈጥሮ እየሰራ ይገኛል። ዓለም አቀፉ ኤጀንሲ አመራሮችና ባለሙያዎች በየጊዜው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን፤ ጉባኤም ተካሂዷል። ከዚህ ባሻገር ጽሕፈት ቤቱ እስካሁን የሰራው ሥራ ተመዝኖ አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበ ስለታመነበት ተሞክሮውን ለሌላው ዓለም እንዲያካፍል መድረክ ተፈጥሮለታል። ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ትምህርትና ሥልጠናን በመስጠት ግንዛቤን የማስጨበጥ ሥራው በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። ከዚህ ባሻገር ታዳጊዎች ስለጉዳዩ ይበልጥ እንዲገነዘቡ በትምህርት ሥርዓቱም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተካቶ ተግባራዊ እንዲደረግ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። በምርመራና ቁጥጥር እንዲሁም ወንጀሎችን መርምሮ ይፋ በማውጣት ላይም ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል። ከባለድርሻ አካላት ይህ የጽሕፈት ቤቱ አፈጻጸም በቀረበበት መድረክ ላይ የተገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ባሏቸው ነጥቦች ላይ ሃሳብ ሰንዝረዋል። ችግሩ ጎልቶ የሚታየው በአትሌቲክስ ስፖርት ላይ ይሁን እንጂ በሌሎች ስፖርቶች ላይም የመጠቀም አዝማሚያ በመኖሩ የትኩረት አቅጣጫው ቢሰፋም ተብሏል። እስካሁን ተጠቃሚነታቸው ከተረጋገጠባቸው አትሌቶች የሚልቁት ሴቶች እንደመሆናቸው ግንዛቤ በማስጨበጡ በኩል ሴት አትሌቶች ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠቁሟል። በጽሕፈት ቤቱ እና በሚመለከታቸው አካላት መካከል ያለው የመረጃ ፍሰት እንዲጠናከርም ጥሪ ቀርቧል። ከዚህ ባሻገር አትሌቶች ሳያውቁ በአሰልጣኞቻቸውና ማናጀሮቻቸው በኩል በረቀቀና ስልታዊ በሆነ መንገድ ቅመሙ የሚሰጣቸው በመሆኑ ጽሕፈት ቤቱም አሠራሩን እንዲያዘምን ተጠይቋል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 1/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13719
8eb68fa15a752e5286084e933b2af24d
4c4d78e5ad8be6855a25b83661664340
ኢትዮጵያውያን በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ ይጠበቃሉ
 በተለያዩ የዓለም ከተሞች በመዘዋወር የሚካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር፤ ዘጠነኛውን ዙር በሞናኮ ያካሂዳል። በተያዘው ሳምንት መጨረሻ በዕለተ አርብ የሚካሄደው ይህ ውድድር፤ ዘንድሮ መታሰቢያነቱን ለአንድ አትሌት አድርጓል። በቅርቡ በሞት የተለየችውን በ1ሺ 500 ሜትር እና 5ሺ ሜትር ሩጫዎች ታዋቂዋን አሜሪካዊት አትሌት ጋብሬሌ ግሩንዋልድ። ባለፈው ወር በካንሰር ህመም ለህልፈት የተዳረገችው አትሌቷ፤ በተያዘው ወር 33ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ታከብር ነበር። ይህንን እና አትሌቷ እአአ በ2013 በ1ሺ500 ሜትር የግሏን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገቧን ምክንያት በማድረግ ሩጫው መታሰቢያ እንዲሆናት መደረጉን ዳይመንድ ሊግ በድረገጹ አስነብቧል። ከዚህ ባሻገር በሴቶች መካከል የሚካሄደው የማይል ውድድር የጋቤ ማይል በሚል ተሰይሟል። ይህ ውድድርም ሦስት ሴት የዓለም ክብረወሰን ባለቤት አትሌቶችን የሚያገናኝ ሲሆን፤ እአአ በ2015 የ1ሺ500 ሜትር ውድድር ክብረወሰን የሰበረችው ገንዘቤ ዲባባን፣ ያለፈው ዓመት የ3ሺ ሜትር መሰናክል ባለ ክብረወሰኗ ባትሬስ ቼፕኮች እንዲሁም በዚህ ዓመት የ5ኪሎ ሜትር ክብርን የተቀዳጀችው ሲፈን ሃሰን የሚያደርጉት ፍልሚያ ተጠባቂ ሆኗል። ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ደግሞ በርቀቱ የሴቶች ቁጥር አንድ አትሌት በመሆኗ ለአሸናፊነት ትጠበቃለች። ገንዘቤ እአአ በ2015 በሞናኮ ርቀቱን ያሸነፈችበት 3:50:07 የሆነ ሰዓት እስካሁንም ሊደፈር ያልቻለ የዓለም ፈጣኑ ሰዓት ሲሆን፤ አትሌቷ የዓለም ሻምፒዮናም ነበረች። በዓለም ሻምፒዮናው በ5ሺ ሜትርም ሜዳሊያ ያጠለቀችው አትሌቷ የዓመቱ ምርጥ ሴት አትሌት በሚል መመረጧም የሚታወስ ነው። በቤጂንጉ ዓለም ሻምፒዮና ሻምፒዮን ስትሆንም በሪዮ ኦሊምፒክ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ነበር ያጠናቀቀችው። ከዚህ ባሻገር በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የ1ሺ500 ሜትር ለንግስናዋ ተስተካካይ አልተገኘላትም። የርቀቱን ክብረወሰን የጨበጠችበት የዚህ ርቀት ሰዓት የተመዘገበው በሞናኮ መሆኑ እንዲሁም በርቀቱ ያላት ልምድ ደግሞ በዚህ ውድድር ላይም አግዟት እንደምታሸንፍ በአትሌቲክስ ቤተሰቡ ዘንድ ተስፋ ተጥሏል። በዚህ ርቀት ታዋቂ የሆነችውና በቤጂንግ እና የለንደን የአትሌቲክስ ዓለም ሻምፒዮናዎች ላይ ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎችን ማጥለቅ ችላለች። አትሌቷ በተለያዩ አህጉር አቀፍ ውድድሮችና ሌሎች ውድድሮች ላይም በ1ሺ 500ሜትር የተሻለ ውጤት ካስመዘገቡ አትሌቶች መካከል ትጠቀሳለች። አትሌቷ ከወራት በፊት በዚሁ በሞናኮ በተካሄደ የ5ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ14:44 የሆነ ክብረወሰን አስመዝግባለች። አትሌቷ የርቀቱን የመጨረሻ መስመር የረገጠችበት ሰዓት ክብረወሰን ሊባል የቻለው 15:48 የነበረውን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻሉ ነው። ይህም ሲፈንን ለባለ ክብረወሰኗ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ፈተና እንደሚሆንባት ይጠበቃል። ኬንያዊቷ አትሌት የመሰናክል ስፔሻሊስት የምትባል ሲሆን፤ በሪዮ ኦሊምፒክና በለንደኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ላይ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ነበር ያጠናቀቀችው። ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዜያት ግን በርቀቱ ወደ አሸናፊነት ከመምጣትም ባለፈ የክብረወሰን ባለቤት ልትሆን ችላለች። ርቀቱን 8:50 የነበረውን ሰዓት 8:45 በማሻሻል የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ናት። አትሌቷ ከመሰናክል ባሻገር በ1ሺ500 ሜትርም የምትሮጥ ሲሆን፤ እአአ በ2015 በተሳተፈችበት የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ነበረች። ባለፈው ዓመት በተካሄደው የኮመን ዌልዝ ጌምስ ርቀቱን ሁለተኛ በመውጣት ርቀቱን ሸፍናለች። በዚያው ዓመት በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ተሳትፎዋም ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። ይህ ውጤቷም አትሌቷን በዚህ ርቀት የተሻለ ውጤት ታመጣለች በሚል እንድትጠበቅ አድርጓታል። በወንዶች በኩል ደግሞ በቅርቡ ለረጅም ዓመታት ተይዞ የቆየውን ክብረወሰን መስበር የቻለው ወጣቱ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ተሳታፊ እንደሚሆን ታውቋል። በዚህ ውድድርም በተመሳሳይ ጠንካራ አትሌቶች የሚሳተፉበት እንደመሆኑ የአሸናፊነት ግምቱ አዳጋች ሆኗል። ኢትዮጵያዊው አትሌት በቅርቡ በበርሚንግሃም በተካሄደው የቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮና፤ 1ሺ500 ሜትሩን ለመሸፈን የፈጀበት ጊዜ 3:31.04 ነበር። ይህም በውድድሩ አሸናፊ ይሆናል በሚል እንዲጠበቅ ቢያደርገውም፤ የዓለም ሻምፒዮኑ ኤልጃህ ማናንጎይ እና የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ማቲው ሴንትሮዊትዝ ለውድድሩ ከባድ ፈተና እንደሚሆኑ ተገምቷል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 1/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13724
af35a750d109e8d629065d4043f8fe99
a610439e4a7c4a92a57b4b35f7b0d947
የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
ከታህሳስ 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ዋንጫ ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች እንደሚያደርጉ ታውቋል። በዛሬው እለት በተለያዩ ከተሞች የሚደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች አስቀድሞ በወጣው ድልድል መሰረት የሚደረጉ ሲሆን ፤ በዚህም በአንደኛው ዙር ያልተደረገው ብቸኛው ጨዋታ በአዳማ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ መካከል ሐሙስ ሐምሌ አራት በአዳማ አበበ ቢቂላ 10 ሰዓት የሚደረግ ሲሆን፣ ሁለት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎችም በዚሁ ዕለት ይደረጋሉ። በፎርፌ ራሱን ከውድድሩ ያገለለው ደቡብ ፖሊስን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜ ያለፈው የሊጉ ቻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ከመከላከያ በ9 ሰዓት ሲጫወት ጅማ እና ድሬዳዋን በፎርፌ አሸንፈው የመጡት ወላይታ ድቻ እና ሀዋሳ ከተማ አዳማ ላይ በ8 ሰዓት የሚጫወቱ ይሆናል ሲል ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ዋንጫ በተዘበራረቀ መልኩ እየተካሄደ የሚገኝ መሆኑን የጠቀሰው ዘገባው ፤በውድድሩ ከ16 ክለቦች አራቱ ራሳቸውን ማግለላቸው የተገለጸ ሲሆን ፤እስካሁን ባለው በተለያዩ ምክንያቶች ሦስት ጨዋታዎች ብቻ ተደርገዋል ተብሏል። በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተከታታይ ፎርፌዎች አግኝቶ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ሲያልፍ ቀሪ አንድ የመጀመሪያ ዙር እና ሦስት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተደርገው የመጨረሻ አራት ቡድኖች የሚለዩ መሆኑን ዘገባው አስረድቷል። በውድድሩ የመጀመሪያው ዙር በነበሩ ጨዋታዎች ስሑል ሽረ 2 ለ 2 ሲዳማ ቡና (ሽረ በመለያ ምት አሸንፏል)።መከላከያ 1 ለ 0 ቅዱስ ጊዮርጊስን ሲያሸነፍ፤ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 0 ለ 1 በፋሲል ከነማ ተረትቷል። በውድድሩ ለመሳተፍ ፍላጎት የሌላቸው ክለቦች መበርከታቸውን ተከትሎ አራት ጨዋታዎች ፎርፌ የተሰጣቸው ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ቡና ከደደቢት በነበረው ጨዋታ ደደቢት ለመጫወት ባለመቻሉ ቡናማዎቹ በፎርፌ 3 ለ 0 ደደቢት አሸንፈዋል። በተመሳሳይ ወላይታ ድቻ 3 ለ 0 ጅማ አባ ጅፋር፣ መቐለ 70 እንደርታ 3 ለ 0 ደቡብ ፖሊስ፣ ሀዋሳ ከተማ 3 ለ 0 ድሬዳዋ ከተማ በፎርፌ በማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ያለፉ ክለቦች ሆነዋል። በኢትዮጵያ ዋንጫ በአሸናፊነት የሚያጠናቅቅ ክለብ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክል ሲሆን፤ የሻምፒዮናነቱን ክብር መከላከያ የ2010 ዓ.ም ጨምሮ በተደጋጋሚ በመውሰድ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። በዘንድሮው የውድድር ዓመት ከፕሪሚየር ሊጉ የወረደው ክለቡ 14 ጊዜ የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድርን በሻምፒዮናነት አጠናቋል።   አዲስ ዘመን ሀምሌ 4/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13888
91d5075b8077ec9089007f4e821d83bd
77aab0cf038727e6a72e7b4df51302b5
ዕድሜ ከስፖርቱ ያላገለላቸው ብስክሌተኞች
በአገሪቱ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት ከሚዘወተሩ ስፖርቶች እግር ኳስ፣ አትሌቲክስ፣ ቦክስ፣ ቦሊቮልና ብስክሌት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ከእነዚህ አንዳንዶቹ ቀደም ባሉት ዓመታት ከአገር ውስጥም አልፎ የኦሎምፒክ ስፖርቶች ተብለው የሚወሰዱበት ወቅት እንደነበር ይታመናል። ከእነዚህ ውስጥ ቦክስና ብስክሌት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁንና ስፖርት ከመዝናኛነት አልፎ አዋጪ የቢዝነስ ማዕከል በሆነበት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ብዙዎቹ ስፖርቶች በ‹‹ነበር›› ታሪክ ብቻ ይገኛሉ፡፡ ቤን ጀማነህ የብስክሌት ስፖርትን የጀመሩት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ ነበር፡፡ በ1990 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የ‹‹ማውንቴን›› ብስክሌት ውድድር ላይ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የብስክሌት ፍቅራቸው እያደገ መጣ፡፡ በ1997 ዓ.ም በአገሪቷ በነበረው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ከአገራቸው ተሰድደው ከዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ላይ ብስክሌት ስፖርት የሚያዘወትሩ ጥቂት ልጆችን በመሰብሰብ ዛሬ ላይ ከ50 በላይ አባላት ያሉትን ቡድን መመስረት ችለዋል፡፡ ማውንቴን ባይክ ( ሮድ ባይክ ኢን ኢትዮጵያ) የሚል ስያሜ ያለው ቡድን በማቋቋም አገር ቤት ካሉት ነባር ስፖርተኞች በተጨማሪ የውጭ አገር ዜጎችን በማሳተፍ ዘወትር እሁድ ከአዲስ አበባ ከተማ ተነስተው ብዙ ኪሎሜትሮችን በማቋረጥ ከውድ እስከ መካከለኛ ወጭ የተደረገባቸውን ብስክሌት በመያዝ ወደ ተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ይጓዛሉ፡፡ እስካሁን በተደረጉት የብስክሌት ስፖርት እንቅስቃሴዎችም ሱሉልታ፣ ሰንዳፋ፣ ሆለታ፣ ደብረብርሀን፣ ወልቂጤ፣ አገና፣ ቡታጅራና የመሳሰሉት አካባቢዎች የስፖርተኞቹ መዳረሻዎች ሆነዋል፡፡ ይህን የሚያደርጉት እድሜያቸው ከ30ዎቹ እስከ 60ዎቹ የሚጠጉ የቤን ጓደኞች ናቸው፡፡ ስፖርቱ እንዳይረሳ ትልቅ ንቅናቄ መፍጠርና ጤንነትን መጠበቅ የስብስቡ ዓላማ ቢሆንም፤ ጎን ለጎን ትውልዱ ራሱን በስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲያሳልፍ ማስቻልም ሌላኛው ዓላማ ነበረ፡፡ ስፖርቱ እንዲያድግ ካላቸው ፍቅር የተነሳ ከቡድኑ ጋር ሆነው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በብስክሌት ለመጓዝ ተሳትፎ የሚያደርጉትን ስፖርተኞች በነጻ እንደሚያሳትፉና በየመንገዱ ያሉት ወጣቶችም እድሜ ከስፖርቱ ያላገለላቸውን በማየት እንዲሳቡ ለማድረግ አገዥ እንቅስቃሴ መሆኑን ነው ቤን የሚናገሩት፡፡ ቆየት ባሉት ዓመታት ኢትዮጵያ የብስክሌት ስፖርት ወርቃማ ዘመኖችን ማሳለፏን የሚነገሩት ቤን፤ አሁን ላይ ስፖርቱ መዳከሙንና በተለይም መንግሥት የቀደሙ ባለሙያዎችን ሰብስቦ ቢያማክርና ቀደምት ስመ ጥር ስፖርተኞች ልምዳቸውን ለአሁኑ ትውልድ ማስተላለፍ ቢችሉ ስፖርቱ ዳግም ሊያንሰራራ እንደሚችል ይጠቁማሉ፡፡ የብስክሌት መንገድ አሰራርን ጨምሮ ከውጭ የሚመጡ ብስክሌቶች ጥራት መጓደልን አካቶ ስፖርቱ በጥልቀት መዳሰስ እንደሚገባው በስደት በውጭ አገር በቆዩባቸው ወቅቶች ያስተዋሉትን በማስታወስ ተናግረዋል፡፡ ቤን፤ ‹‹የድሮ ትውልድ ከልጅነቱ ጀምሮ በስፖርቱ ንቃት ውስጥ ያለፈው ነው፡፡ በየቦታው ሩጫ፤ በየጫካውም የካራቴ ስፖርት በብዛት ይዘወተር ነበር፡፡ ይህ አሁን ላይ ያለው በውስን ደረጃ ላይ ነው::›› በማለትም አሁናዊውን የብስክሌት ስፖርት ገጽታ ይጠቁማሉ፡፡ የሩጫና የብስክሌት ስፖርት በልምምድ ረገድ ብዙ የሚራራቁ አይደለም በማለት፤ ኢትዮጵያውያን በተፈጥሮ ለሁለቱም ስፖርቶች የሚሆን አቋም እንዳላቸውና እንደ አትሌቲክሱ ብስክሌት ስፖርቱም ቢበረታታ የሚገኘው ውጤት ቀላል እንዳልሆነ ያብራራሉ፡፡ እንደ እርሳቸው ገለፃ፤ ሌሎች አገራት በተለይም እንደ አውሮፓና አሜሪካ ያሉት ለስፖርቱ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ስለሚንቀሳቀሱ በኦሎምፒክ መድረክም ሆነ ሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በምሳሌነታቸው ብቻ ሳይሆን በውጤትም መታጀብ ችለዋል፡፡ በመሆኑም ከውጭ የሚገቡ የአገር አቋራጭ ብስክሌቶች ላይ ቀረጥ ቅናሽ አስተያየት ቢደረግ፤ የቀድሞ ስፖርተኞችና የጤና ቡድኖችን ያሳተፈ ተደጋጋሚ ውድድሮች በሚመለከተው ፌዴሬሽን በኩል ቢካሄድ፣ ለስፖርቱ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ወደ ፌዴሬሽኑ ለመቅረብ ቢሞክሩም መንገዶች ጠባብ ሆነዋል፡፡ ተቀራርቦ መስራት ስፖርቱን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንዳለው በመገንዘብ መንግሥት በአብሮነት ቢሰራ ልምድን ጨምሮ በብዙ መልኩ መተጋገዝም ይቻላል፡፡ የረጅም ጊዜ ልምድን በመጠቀም ለአገሪቷ ብስክሌት ስፖርት እድገት ሙያዊ አበርክቶ እንዲኖር ወደ ፊት ውድድሮችን በማዘጋጀት ተተኪውን ወጣት ትውልድ ለማሳተፍ ጥረቶች ይደረጋሉም ብለዋል፡፡ ስፖርቱ በአንጻራዊነት ይሻል የነበረበትን ዘመን ዳግም ለማደስ ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን እንደሚሰሩና የታዳጊ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ከውጭ አገር ስፖርተኞች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የእዚህ ቡድን አባላት ቢያንስ ከ20 ዓመት በላይ በስፖርቱ የቆዩ ስፖርተኞች መሆናቸውንና ትልልቅ ሰዎች ስፖርቱን ቢያዘወትሩት ከጤና አኳያ በርካታ ጥቅሞችን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ እድሜያቸው 50ዎቹ ውስጥ የሚገኘው አቶ ተስፋሚካኤል ገረመው ሌላኛው የቀድሞ ብስክሌተኛ ሲሆኑ፤ በአሁኑ ወቅት ከቡድን አጋሮቹ ጋር በመሆን እድሜ ሳይበግራቸው ረጅም ርቀትን በብስክሌት በመጓዝ ላይ ከሚገኙት ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ስፖርቱን በ1970 ዓ.ም እንደተቀላቀሉት የሚናገሩት አቶ ተስፋሚካኤል፤ እስከ 1982 ዓ.ም ድረስ በብስክሌት ስፖርት ከታዳጊዎች እስከ ዋናው ብሄራዊ ቡድን ውስጥ በመሳተፍ የሻምፒዮንነት ድልን እስከመቀዳጀት የደረሱና ድንቅ ብቃትን ማሳየት የቻሉ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በግጭት ምክንያት ውድድሩ ሳይካፈሉ ይቅር እንጂ በ1976 ዓ.ም ለሎሳንጀለስ ኦሊምፒክ በዝግጅት ላይ የነበረውን የወርቃማ ትውልድ ዘመን አባልም ነበሩ፡፡ በውቀቱ ስፖርቱ ከደጋፊዎች ጀምሮ በጥሩ ቁመና ላይ እንደነበርና ከጊዜ በኋላ ግን እየመነመነ መምጣቱን አቶ ተስፋሚካኤል ይናገራሉ። ምንም እንኳን ብስክሌት ከአትሌቲክስ ጀምሮ የኢትዮጵያን ስም በአፍሪካ ሻምፒዮናና በኦሊምፒክ መድረክ ያስጠራ ቢሆንም ዛሬ ላይ ትኩረት በማጣቱ ስፖርት ክለቦችን እስከማፍረስ መደረሱንና ይህም የስፖርቱን መጻኢ እድል አዘቅት ውስጥ ሊከተው እንደሚችል ያሳስባሉ።የትኛውም ስፖርት በትውልድ ቅብብሎሽ ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል የሚሉት አቶ ተስፋሚካኤል፤ የእርሳቸው አጋሮች እድሜ ሳይገድባቸው እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ትውልዱ በማስተዋል እንዲቀበለውና በተራው አገር በዚህ የስፖርት ዘርፍ እንድትጠቀም ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ይመክራሉ፡፡ ስፖርቱን ለማስፋፋት ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸውን ውድድሮች ማዘጋጀት ከፌዴሬሽኑ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ ማንም ሰው ለራሱ የጤንነት ጥቅም ሲል ስፖርትን እንደሚያዘወትረው ሁሉ አቶ ተስፋሚካኤልና መሰል ጓደኞቻቸውም እርጅና ከስፖርቱ ሳይገድባቸው በየሳምንቱ ረጅም ኪሎሜትሮችን የመጓዛቸው ምክንያትም ለዚሁ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስፖርቱ እንዲበረታታና በህብረተሰቡ ዘንድ ስርጸት ለመፍጠር ታስቦ እንደሆነ ያብራራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ከአትሌቲክስ ቀጥሎ ከምትወከልባቸው ስፖርቶች ብስክሌት ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና ስፖርቱ በፋይናንስ በተለይም በመወዳደሪያ ብስክሌቶች እጥረት ምክንያት ህልውናው ፈተና ውስጥ መግባቱ ውጤቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ እንደተጠበቀ፣ በዲፕሎማሲው ረገድ የበኩሉን ድርሻ የሚወጣ ነው፡፡አዲስ ዘመን  ሐምሌ 5/2011አዲሱ ገረመው
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13954
c4573f3e479bb1669eecba41c55adf95
18bcf202a92ab7d78c323f4bd2a1e541
በኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ላይ ጥቃት የፈጸሙት ተቀጡ
የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ዲስፕሊን ኮሚቴ በኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ላይ ጥቃት የፈጸሙት የሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ተቀጡ። ፕሬዚዳንቱ በፈጸሙት ድርጊት ከእግር ኳሱ ለአንድ ዓመት እንዲገለሉ መወሰኑን ማህበሩ አስታውቋል። ካፍ በሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ፋውዚ ላካን ላይ ቅጣቱን ያስተላለፈው ባሳለፍነው ወር በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ በግብጹ ዛማሌክ እና ሞሮኮው ሬይኔሳንስ ቤርካን መካከል በነበረው ጨዋታ ወቅት በፈጸሙት ያልተገባ ተግባር እንደሆነ ገልጿል። ፕሬዚዳንቱ በሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ አድብተው ባምላክ ተሰማ ላይ በግንባር ጥቃት የፈፀሙት እና ለፀጥታ አካላት አስቸጋሪ የሆነ ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ስርዓት እንዳሳዩ በማስታወስ አብራርቷል። በወቅቱ የግብፅ ሰዎች እንደሚሉት ጥቃቱን የፈጸሙት የሞሮኮ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እና የሬይኔሳንስ ቤርካን ፕሬዝዳንት ፎክዚ ሌክጃ ናቸው። ክለቡ በደርሶ መልሱ ጨዋታ ዳኛ ባምላክ ተሰማ ፍጹም ቅጣት ምት መስጠታቸውን በመቃወም ክስ እንደሚመሰርትባቸው እስከ ማስታወቅ የደረሱ ቢሆንም ፤ድርጊቱ በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪና አሳዛኝ እንደሆነ የተገለጸም ጭምር ነበር። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የድርጊቱን መፈጸም ተከትሎ ጁን አምስት ባስገባው የክስ ደብዳቤ መሰረት የሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ፋውዚ ላካን ለመቅጣት ሲመርመር መቆየቱን ገልጾ ፤የካፍ ዲስፕሊን ኮሚቴ ፋውዚን የፈጸሙት ድርጊትን በማረጋገጥ ለአንድ ዓመት ከእግር ኳስ እንዲታገዱ ወስኗል። በ2018/19 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታ ዛማሌክ የሞሮኮው አር ኤስ በርካኔን አስተናግዶ በመለያ ምቶች በማሸነፍ ከ16 ዓመታት በኋላ የአህጉራዊ ዋንጫ ረሀቡን ማስታገሱ ይታወሳል። የሁለቱ ክለቦች የጨዋታው ሂደት በመጀመሪያው ዙር ሞሮኮ ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ በርካኔ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረ ጎል 1 ለ0 ማሸነፉ ተከትሎ የመልሱ ጨዋታ በበዓምላክ ተሰማ ዳኝነት የተከናወነው በአሌክሳንድሪያው ቦሮግ አል አረብ ስታድየም የተካሄደ ነበር። በጨዋታው የሞሮኮው አር ኤስ በርካኔን በ54ኛው ደቂቃ ላርቢ ናጂ ሳጥን ውስጥ ኳስ በእጁ በመንካቱ በቪአር ተረጋግጦ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት መሐመድ አላ አስቆጥሮ ዛማሌክ በድምር ውጤት አቻ እንዲሆን አድርጓል። ጨዋታው በዛማሌክ 1ለ0 አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትሎ በተሰጡ የመለያ ፍፁም ቅጣት ምቶች ዛማሌኮች ሁሉንም ሲያስቆጥሩ በበርካኔ በኩል ሐምዲ ላቸር አምክኖ ነጭ ለባሾቹ አሸናፊ መሆን ችለዋል። አምስት ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ፣ ሶስት ጊዜ የሱፐር ካፕ እንዲሁም የቀድሞው ካፕ ዊነርስ ካፕን አንድ ጊዜ ማሳካት የቻለው የግብፁ ታላቅ ክለብ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫን ሲያነሳ ይህ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የዋንጫው ባለቤት ዛማሌክ ነጥብ25 ሚሊዮን ዶላር ሲሸለም ተሸናፊው በርካኔ 625 ሺህ ዶላር ማግኘት ችሏል። አዲስ ዘመን ሀምሌ 4/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13891
4a8b5f08e6a8a58de638d33d3847d019
ba644e7e016339ea73e9273437db1b6e
በህዳሴ ግድቡ የተገኘው ድል ወደፊት የሚያስፈነጥር እንጂ የሚያዘናጋ ሊሆን እንደማይገባ ተገለፀ
 አዲስ አበባ፡- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት መሳካቱ አገሪቱ ላሰበችው የልማት እቅድ ከግብ መድረስ ወደፊት የሚያስፈነጥርና አቅም የሚፈጥር እንጂ የሚያዘናጋ ሊሆን እንደማይገባ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳሰቡ። ፓርቲዎቹ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ለዓመታት ርብርብና ብርቱ ትግል ሲያደርጉበት የቆዩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ትልቅ እምርታ ነው። ሆኖም የግንባታው ስራ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ስኬቱን ብቻ ከማጣጣም ባሻገር ለታቀደው የልማት ግብ ስኬት መስፈንጠሪያ መጠቀም ያስፈልጋል። የኢዜማ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፤ የግድቡ ውሃ ሙሌት እንደሚሳካ ከመጀመሪያው አንስቶ ሙሉ እምነት እንደነበራቸው ገልፀው፤ መንግሥት የውሃ ሙሌቱን ጉዳይ በብልሃት የሄደበት ርቀት እንዳስደነቃቸው አመልክተዋል። «ይህ ስኬት ግን በፌሽታና ፈንጠዝያ የሚያዘልለን ሳይሆን ድሉን አጣጥመን ለላቀ እድገት የምንስፈንጠርበት ነው» ብለዋል። በፈንጠዝያ ሊባክን የሚገባ ጊዜም መኖር እንደሌለበት ተናግረው፣በተለይም የውሃ ሙሌቱ ከታቀደው አንፃር ገና አምስት በመቶ ያህሉ ብቻ የተከናወነና ግንባታው ብዙ ስራ የሚጠይቅ እንደመሆኑ ግድቡ መቋጫ እስከሚያገኝ ድረስ ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። እንደ አቶ ግርማ ገለፃ፤ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንና መንግሥት እንደ አይጥና ድመት በባላንጣነት ከመተያየት ይልቅ እንደህዳሴ ግድብ ባሉ ትላልቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ ተሰልፈው እየሰሩ ይገኛሉ። አሁን ለተገኘው ስኬትም በውጭ ያለው ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ሲሆን በቀጣይም የውጭው ማህበረሰብ ድጋፍ በላቀ ሁኔታ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። በተለይም በግብፅና በአሜሪካ የሚደረገውን ውጫዊ ተፅዕኖ በማክሸፍ ረገድ ለአገራቸው ጥቅም በመቆም ወገንተኝነታቸውን ያለመታከት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። «ከዚህ ቀደም ግድቡ ውሃ መያዝ አይጀምርም እያሉ ሲያስወሩ የነበሩ ግለሰቦች አሁንም ቢሆን ግድቡ አይጠናቀቅም ሊሉ ይችላሉ» ያሉት አቶ ግርማ ፤ የድሉን ብሥራት ከማጣጣል ይልቅ ቢያጣጥሙ የተሻለ እንደሚሆንላቸው ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ምንም እንኳ የሃሳብ ልዩነት እንደወንጀል የሚታይ ባይሆንም የአገርና የህዝብን ጥቅም አሳልፈው የሚሰጡ ብለውም ከውጭ ኃይል ጋር የሚያብሩ ፖለቲከኞች ከህግ ተጠያቂነት ሊያመልጡ እንደማይችሉ አስገንዝበዋል። «በእንደዚህ አይነት ሸፍጥ ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞችን በምክር ሳይሆን ህግ በማስከበር ወደ ትክክለኛው መስመር ማስገባት ያስፈልጋል» ብለዋል። የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አብዱልቃድር አደም በበኩላቸው«ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ለሁላችንም ደስታ ፈጥሮልናል፤ ትልቅ ስኬትም ነው» ብለዋል። በተለይም የግድቡ ግንባታ የነበሩበትን የቴክኒክም ሆነ የአስተዳደር ችግሮችን አልፎ የስኬት ጅማሮ ላይ መድረሱ ትልቅ እመርታ መሆኑን አስገንዝበዋል። ፋይናንስ በማፈላለግም ሆነ በዲፕሎማሲረገድ ብዙ ዋጋ ያስከፈለው ይህ ፕሮጀክት ግንባታው የሚቀረው መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም በዲፕሎማሲው ረገድ የተገኘውን ድል በማስቀጠል በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የሁሉንም ርብርብ እንደሚጠይቅ አመልክተዋል። በተለይም በግድቡ ዙሪያ የሚነሱ አፍራሽ አስተሳሰቦችን በመከላከል ረገድ በውጭ የሚገኙ ዲፕሎማቶችና ዳያስፖራው ማህበረሰብ በንቃት ሊከታተሉ እንደሚገባ ተናግረዋል። « የእኛ ዋነኛ አላማ ሌሎች የተፋሰሱን አገራት መጉዳት አይደለም፤ የልማት አጀንዳ መሆኑን ለዓለም ህብረተሰብ ማድረሳችንን መቀጠል ይገባናል» ሲሉም አመልክተዋል። ፓርቲዎችም ትልቅ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን አስታውሰው፤ ያለምንም ልዩነት በጋራ መቆም እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። «የዚህ ግድብ መጠናቀቅ የአንድ ፓርቲ ወይም የአንድ መንግሥት ጉዳይ ሊሆን አይገባም» በማለት ተናግረዋል። በዚህ ረገድ የፕሮጀክቱን ሂደትና ግንባታ ሊያስተጓጉል በሚችል መልኩ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ ተቀባይነት ሊኖረው እንደማይችልም ጠቁመዋል። ለጊዜያዊ ጥቅም ብለው የአገር ሉዓላዊነትን የሚያስደፍሩ አካላት ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡና የታሪክም ተወቃሽ እንዳይሆኑ ሊጠነቀቁ እንደሚገባ አሳስበዋል። የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገሩት፤ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት ከታሰበው ጊዜ በፊት መጠናቀቁ በዚህ ሂደት ላይ ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ያለፉትም ሆነ በስራ ላይ ያሉት መሪዎች ያደረጉት ብርቱ ትግል የሚደነቅ ነው። በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አለምአቀፍና የአገር ውስጥ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ሳይበግራቸው የግድቡን ውሃ ሙሌት እዚህ ደረጃ በማድረሳቸው ከፍተኛ ምስጋና የሚያስቸራቸው ነው። ግድቡን እዚህ ለማድረስ በተደረገው ርብርብ መቀነት ፈታ ከሰጠች እናት ጀምሮ ባለሃብቱም ሆነ ፖለቲከኛው ያሳየው ድጋፍ የሚደነቅ ነው። «የመጀመሪያው ዙር ውሃ ሙሌት ተጠናቀቀ ማለት ስራ ሁሉ አለቀ ማለት አለመሆኑን ህዝባችን ተረድቶ ከዚህ በላቀ መነሳሳትና ተሳትፎ ማድረግ ይገባዋል» ያሉት አቶ ግርማ ፣ ግድቡ በውስጥ አቅም ብቻ የሚከናወንና ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ሕዝብ ያለአንዳች ልዩነትና መሰላቸት ያቅሙን ያህል በመደገፍ በበለጠ ትጋት እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል። «የህዳሴ ግድብን የሚቃወሙ በራሳቸውም ሆነ በውጭ ሃይል ግፊት የሚንቀሳቀሱ አካላት ጤናማ አይደሉም፤ ኢትዮጵያዊ ስለመሆናቸው አጠያያቂ ነው»ያሉት አቶ ግርማ ፤ «ይህ የአንድ መንግሥት ጉዳይ አይደለም፤ እናቶቻችን በማገዶ እንጨት ወገባቸው እየጎበጠና አይናቸው በጭስ እየተጨናበሰ ባሉበት ሁኔታ ለውጭ ኃይል መደገፍ ጤናማነት አይደለም» በማለት ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። ፕሮጀክቱ የዛሬው ትውልድ ብቻ ሳይሆን የመጪው ትውልድ ጭምር በመሆኑ እንደነዚህ ያሉ የፖለቲካ አስተሳሰቦችንም ሆነ በተለያየ ጥቅም የታወሩ ግለሰቦችና የተደራጁ ሃይሎችን ፓርቲያቸው አጥብቆ እንደሚቃወማቸው አመልክተዋል። በሌላ በኩልም ህዝቡ ለግድቡ ግንባታ ስኬት ያሳየውን አገራዊ አንድነት ለሌሎችም ፖለቲካዊ ችግሮች መፈታት በማዋል በአንድ ድምፅ በጋራ ሊሰለፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 21/2012 ማህሌት አብዱል
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36181
ec8682212f4e6b68e67b9c0891766c9c
5761e478e27945255390432c64b5000d
«የጀመርነውን ስኬት ማስቀጠል እንጂ ወደኋላ አንልም»- የአዲስ አበባ ወጣቶች
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቋል። ይህን ታላቅ የድል ጅማሮ በማስመልከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ የግልና የመንግስት ተቋማት፣ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ደስታቸውን ሲገልፁ ሰንብተዋል። በተለይ ይህ ታላቅ ስኬት ሊገኝ የቻለበት ምክንያት ኢትዮጵያ ለቆመችለት መርህ ታማኝነቷን በማሳየቷ እንደሆነና በቀጣይ ጊዜያትም በዚህ ጠንካራ መስመር ልትጓዝ እንደሚገባ፣የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና መላው የአገሪቷ ዜጎች በማሳሰብ ላይ ይገኛሉ።የዝግጅት ክፍላችን በአዲስ አበባ የተለያየ አካባቢ ወጣቶችን አነጋግሯል። በብሩህ ተስፋና ፈገግታ የተሞላበት፣ ትህትና የሚነበብባቸው ወጣቶች ግድቡ እንዲጠናቀቅ ደጋፊ እንጂ እንቅፋት መሆን አይጠበቅብንም የሚል አስተያየታቸውን ነበር የሰጡት። የጀመርነውን የስኬት ጉዞ ማስቀጠል እንጂ ወደኋላ አንልም ሲሉ ይናገራሉ።ወጣት በላይ ተሰማ በቴክኒክና ሙያ በኤሌክትሪሲቲ ሙያ ተመርቆ በግሉ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ኮንትራት እየወሰደ እንደሚሰራ ይናገራል። ስለህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት መጠናቀቅ እንደተሰማ በከፍተኛ የደስታ ስሜት ውስጥ እንደነበር ያስታውሳል። ይህን አጋጣሚ ለሁለተኛ ጊዜ ማስተናገዱን ተናግሮ፤ የመጀመሪያው የመሰረት ድንጋዩ የተጣለበት ጊዜ ተመሳሳይ ስሜት እንደተፈጠረበት ይገልፃል።‹‹ባለፉት ሳምንታት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃዘን ድባብና አለመረጋጋት ስለነበር ስሜቴ ተረብሾ ከርሟል›› የሚለው ወጣት በላይ ሁሌም ህይወት አንድ ጎን ስለሌላት የህዳሴው ግድብ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ሲሰማ ያ መጥፎ ስሜት በደስታ እንደተተካ ይናገራል። ይህ ድል ቀጣይነት እንዲኖረው የነገ አገር ተረካቢ ወጣቶች ቁርጠኝነትና ድጋፍ እንደሚፈልግ እንደተገነዘበም ያስረዳል። በዚህ ምክንያት ግድቡ ሙሉ ለሙሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ በሚችለው አቅሙ ለመደገፍና ሃላፊነት ለመውሰድ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ቃል እንደሚገባ ገልጿል።‹‹ወጣቶች ግድቡ ሙሉ ለሙሉ ተሞልቶ እንዲጠናቀቅ ደጋፊ እንጂ አደናቃፊ መሆን አይገባንም›› የምትለው ደግሞ የአብስራ ሰለሞን ነች። በካሳንችስ በተለምዶ መናህሪያ በሚባል አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወጣቷ በፅህፈት መሳሪያ ሽያጭ ውስጥ ትሰራለች። የመጀመሪያው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ ለተጨማሪ ስኬት የሚያነሳሳ መሆኑንም ትገልፃለች።ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ወጣቶች በአፍራሽ ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። በዚህ አይነት ድርጊት ላይ መሳተፋቸው ትልቁን የኢትዮጵያ የመበልፀግ ራዕይ ያደናቅፋል የምትለው ያብስራ፤ የህዳሴው ግድብ መሰል አይነት ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ለመስራት ወጣቱ በሃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ እንደሚገባው ትናገራለች። የኢትዮጵያን የመልማት ፍላጎት ማሳካት የሚችለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁ እንዳስደሰታት በመግለፅም፤ ይህን ተስፋ ተስፋ የሚያጨልም ተግባር ላይ ሁሉም ዜጋ እንዳይሳተፍ ይልቁኑ ደጋፊ ሆኖ እንዲቆም ጥሪዋን አቅርባለች።አብኤል ፉላሳ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት የባዮ ሜዲካል ተማሪ ነው። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በመገናኛ አካባቢ ይኖራል። የውሃ ሙሌቱ በአጭር ጊዜ ባልተጠበቀ ሰዓት መጠናቀቁን በመገናኛ ብዙኃን መስማቱ አስደንቆታል። ለኢትዮጵያውያን ታላቅ የምስራች መሆኑን ይናገራል። ‹‹ከ60 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን የኤሌክትሪክ ሃይል እንደማያገኙ አውቃለሁ፤ ይሄ ትልቅ ቁጭት የሚፈጥር ነው›› የሚለው አቤል፤ ግድቡ መጠናቀቁ የዜጎችን የሃይል ፍላጎት ከማሟላትም ባለፈ የድህነት ቀንበር የሚሰብር በመሆኑ እንደ አይናችን ብሌን ልንጠብቀው ይገባል ይላል። ከዚህ ባሻገር ሁሉም ዜጋ በተለይ ደግሞ አገር ተረካቢው ወጣት እራሱን ከኮሮና ወረርሽኝ ሊጠብቅ እንደሚገባም ያሳስባል። ዜጎች ይህን ማድረጋቸው በጥቅል የኢትዮጵያን እድገት የሚያረጋግጥ አስተዋጽኦ መሆኑን እንደሚያምን ተናግሯል።መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአባይ ወንዝ ዓመታዊ አማካይ የውሃ ፍሰት 49 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ነው። ከዚህ ውስጥ በመጀመሪያው ዓመት የውሃ ሙሌት ታላቁ የህዳሴ ግድብ 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዝ ችሏል። ይህም በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን እንድትሞከር ያስችላታል።በተጨማሪ በቀጣዩ የበጋ ወቅት ከግድቡ ጀርባ የተጠራቀመው ውሃ ስለሚቀንስ የግድቡን ቁመት መጠን ለመጨመር የሚደረገው ግንባታ እንዲቀጥል ዕድል ይሰጣል። ሥራውን በማከናወን በሁለተኛው ዓመት ደግሞ 13 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንዲይዝ ይደረጋል። በዚህ ጊዜም በግድቡ አማካይነት የሚታቀበው የውሃ መጠን በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተገነቡትን የኤሌክትሪክ ማመንጫ ተርባይኖች ጋር ይደርሳል። ይህ ደግሞ የውሃውን ፍሰት በበለጠ ለመቆጠጠር ያስችላል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም በጋዜጣው ሪፖርተር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36039
c5a1367f904bf4ade3131ef49f5054a4
a40d7b369b19d04b680043b3985eb91a
«የክልሉ መንግስትና ህዝብ የጥፋት ሃይሎችን ውጥን አስቀድሞ በመከላከል ሰላምና ጸጥታውን በዘላቂነት ያረጋግጣል» – አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር
አዳማ፡- የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ህዝብ የጥፋት ሃይሎችን ውጥን አስቀድሞ በመከላከል ሰላምና ጸጥታውን በዘላቂነት ያረጋግጣል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ።፣ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም ሰላምና ጸጥታውን እንዲያረጋግጥ ጥሪ አቀረቡ ። ጨፌ ኦሮሚያ በአምስተኛ የጨፌ ስራ ዘመን አምስተኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ስብሰባውን ትናንት በገልማ አባ ገዳ ባካሄደበት ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዳስታወቁት ፣የክልሉን ጸጥታ የሚያውኩ የጥፋት ሃይሎችን ውጥን አስቀድሞ በማወቅ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ በዘላቂነት ይረጋገጣል ። ባለፉት ሁለት ዓመታት በተሰሩት ስራዎች መልካም ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፣ ሰው ሰራሽ የሰላምና የጸጥታ ችግሮች ክልሉ በሚፈለገው ደረጃ እንዳይራመድ እንዳደረጉት አስታውቀዋል። መንግስት የዲሞክራሲን ምህዳር ለማስፋት ያሳየውን ትዕግስት እንደፍርሃትና አቅም ማነስ ቆጥረው ክልሉን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ ያሰቡት የጥፋት ሀይሎች ሁለት የተለያዩ መልኮች እንደነበሯቸው አመልክተው፤ በአንድ በኩል ከተማ ውስጥ ተቀምጠው ሰላማዊ ትግል የሚያደርጉ በመምሰል፤ በሌላ በኩል በደቡብና በምዕራብ ኦሮሚያ ታጥቀው በመንቀሳቀስ መስዋዕትነት አስከፍለውናል ብለዋል ።በተመሳሳይ ከስልጣን የተባረረው ሃይል በየጊዜው በሚፈጥረው የፖለቲካ ሴራና ከውጭና ከውስጥ በሚራገቡ የሚዲያ ዘመቻዎች ትልቅ ጥፋት ደርሷል ፤ በዚህም የለውጡ አቀጣጣይ የነበረውን አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል በክልሉ ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዲጠፋና በቢሊዮን የሚገመት ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። መንግስት የህግ የበላይትን ለማስጠበቅ እርምጃ በመውሰድ ላይ እንዳለ የገለጹት ርእሰ መስተዳድሩ ፣ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም ሰላምና ጸጥታውን እንዲያረጋገጥ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም ኮቪድ 19ን እየተከላከለ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል እንዳለበት፤ለዚህም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል። ክልሉ በ2012 ዓ.ም በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገባቸው መልካም ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ክፍተቶችም እንደሚሻሻሉ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የ2013 በጀት ዓመትን ዋና ዋና እቅዶች እና ትኩረት የተሰጣቸውን ዘርፎችም ዘርዝረው አሳውቀዋል ።በተለይም የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ፤ የተፋሰስና አካባቢ ጥበቃን አጠናክሮ ማስቀጠል ፤ የሥራ አጥነት ቁጥርን መቀነስ፤ መሰረተ ልማትን ማሳደግ፤ በትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ማሻሻል፤ ጤናማና አምራች ኃይልን ለመፍጠር የእናቶችና የህጻናትን ሞት መቀነስ ፤ የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ፣ ቅርስ ፣ባህልና ቋንቋ ማሳደግ፤ ኢንቨስትመንት በተለይም ኢንዱስትሪዎች ከማህበረሰቡ ጋር እንዲተሳሰሩ ማድረግ የሚሉት ዋነኛዎች ናቸው። የጨፌው አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ በበኩላቸው፤ ጉባኤው የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት በተጠናቀቀበት ወቅት በመደረጉና የጨፌው አባላትም የዚህ ታሪክ አካል በመሆናችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። የ2013 በጀት ዓመት እንደከዚህ ቀደሙ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠን ብቻ ያቀድነው ሳይሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ነው ብለዋል። ዕቅዱ የብልጽግና ጉዞን እውን ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ አመልክተዋል ። በ2013 በጀት ዓመት የታቀዱ ስራዎችን ለማስ ፈጸም 90 ቢሊዮን ብር በረቂቅ ደረጃ የቀረበ ሲሆን ጨፌው ከተወያየበት በኋላ ያጸድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል። የክልሉን ጠቅላይ ኦዲተር፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም በኢያሱ መሰለ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36036
13252a2fff8e1e3acf854c4a4bda9ea1
158a420e99406f5cc7b148cc3e62c38a
«ታላቁ የህዳሴ ግድብ ህይወታችንን ለመክፈልም የተዘጋጀንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው» – ጄኔራል አደም መሐመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
አዲስ አበባ ፦ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ህይወታችንን ለመክፈልም የተዘጋጀንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው ሲሉ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ አስታወቁ። የግድቡ ጉዳይ የልማታችን እና የህልውናችንም ጉዳይ እንደሆነም አመለከቱ ።ጄኔራል አደም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ህይወታችንን ለመክፈልም የተዘጋጀንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው ብለዋል። ለሰራዊቱ አንዱ የሉዓላዊነታችን መገለጫ እንደሆነም አመልክተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ሰራ ዊቱ የህዳሴውን ግድብ በዓይነ ቁራኛ የሚያየው እንደሆነ ገልጸዋል።መላው ህዝባችን የህዳሴ ግድብ ተገድቦ ለኢኮኖሚያችን የሚኖረውን አዎንታዊ አስተዋጽዖ በሚገባ ተረድቶ ፍጻሜውን በጉጉት እንደሚጠብቀው ሁሉ ሰራዊቱም የግድቡን ግንባታ ፍጻሜ በጉጉት እየጠበቀው መሆኑን ገልጸው በተለያዩ መንገዶች ለግንባታው ከአንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ማበርከቱንም አስታውቀዋል ።በህዳሴ ግድባችን ላይ ከውስጥም ከውጪም ሊቃጡ የሚችሉ ማንኛውንም ጥቃቶች ለመከላከል ከፍተኛ ጥረትና ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ያመለከቱት ጀነራሉ፣ እስካሁን ግንባታው ያለምንም እንከን እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።“የህዳሴ ግድቡን ጉዳይ እንደ ሰራዊት አንዱ የሉዓላዊነታችን መገለጫ አድርገን ስለምናየው፤ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ከፍተኛ የትኩረት አቅጣጫችን ነው። አመራሩም፤ አባሉም፤ በዛ አካባቢ ግዳጅ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስ ማንኛውም አካል ሌት ተቀን ግድቡን እየጠበቀ እስካሁን የመጣበት ሁኔታ አለ” ብለዋል ። ፕሮጀክቱ ሲታሰብ ጀምሮ ግብጾች ግንባታውን ለማደናቀፍ ያልሰሩት ስራ የለም ያሉት ጀነራል አደም፤ ፋይናንስ እንዳናገኝ አድርገዋል፤ ከዛ በላይ ህዳሴው ግድብ እንዲጓተት በተለያየ ምክንያት ሰርተዋል ብለዋል። ግብጾች እንኳን እንዲህ አይነት ግድብ መገደብ ይቅርና በተለያዩ ቦታዎች የምንሰራቸውን የውሃ ማቆር ስራዎች እስከመከታተል የሚደርሱ ከመሆናቸው አንጻር ስራቸው የሚጠበቅ እንደነበረ ገልጸዋል።በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለያየ መንገድ የውክልና ጦርነት፣ የውክልና ግጭት በማካሄድም አገር ውስጥ ባለ ቡድን ጭምር ከፍተኛ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አመልክተው፤ ከባቢ አገራትንም እንደ መነሻ በመጠቀም ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲዋን ለማዳከም ከጎረቤት አገሮች ጋር በጥርጣሬ እንድትተያይ በርካታ ስራዎች እየሰሩ የመጡበት ሁኔታ መኖሩንም አስታውቀዋል።ግብጾች አባይን ውሃ የህልውናችን ጉዳይ ነው እንደሚሉት፤ ለእኛም የልማታችንም፤ የህልውናችንም ጉዳይ መሆኑን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል ። ሰራዊታችንም እነዚህን ሁሉ ነገሮች በጥንቃቄ ያያቸዋል ያሉት ጀነራል አደም ፣ ከዚህ የተነሳም የግድቡን ግንባታ ሰራዊቱ በልዩ ሁኔታ የምንከታተለው፤ የምንጠብቀው፤ ከገንዘባችንም፣ ከጉልበታችንም በላይ ህይወትን እየከፈልንበት ያለ፤ ለመክፈልም የተዘጋጀንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው ብለዋል፡፡ ከጄኔራል አደም መሐመድ ጋር ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ሙሉ ቃል በ11ኛው ገጽ ይመልከቱ አዲስ ዘመን ሐምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም  በወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36038
e9bda6f772e2840ceec8ce940e5e6cb4
9bf3ae802b605878d936d3ee9c678220
በአደንዛዥ አስተሳሰብ የተመረዙ ወጣቶች ለአገሪቷ ሥጋት እንዳይሆኑ ሊሰራበት ይገባል
 አዲስ አበባ፡- በርካታ ወጣቶች በአደንዛዥ እና በተበላሸ አስተሳሰብ በመበረዛቸው ለአገር ተስፋ ሳይሆን ሥጋት እየሆኑ መምጣታቸውን የተለያዩ ምሁራን ገለጹ። በወጣቶች ስብዕና ዙሪያ የተጠናከረ ስራ መስራት ይገባል። የሱስና ሱሰኝነት ተጋላጭነት ቅነሳ ህክምናና መልሶ ማገገም ስልጠና ባለሙያው ወጣት ኤሊያስ ካልዕዩ እንደገለጸው፤ ወጣቱ በተበላሸ አስተሳሰብ መመረዙ አዳዲስ ሥራዎችን ከመሥራት ይልቅ በተሠራው ላይ አቃቂር ማውጣት፤ የሚሠራን አካል መተቸት፣ ራስን እንደ አዋቂ አድርጎ መቁጠር የሚታዩ ችግሮች ናቸው። ‹‹የእኔ ብሔር አንደኛ የሌላው ሁለተኛ›› የሚለው ሐሳብ መነሻው የአደንዛዥ አስተሳሰብ ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፤ የአስተሳሰቡ ስፋት ወጣቱን ገንዘብና ቁሳቁስ ከሰው አብልጦ እንዲወድ፣ የሰውን ክቡርነት እንዳይቀበል የሚያደርግ የአስተሳሰብ ዝንፈት ባለቤት እንዲሆን አድርጎታል። ይህ ደግሞ አገርን አደጋ ውስጥ እንድትገባ እያደረገ መሆኑን አስረድቷል።‹‹አደንዛዥ አስተሳሰብ ማለት ግለሰቦች ስለራሳቸው፣ ስለማህበረሰባቸው፣ ስለአገራቸው፣ ስለሚጠቀሙት ነገር ያላቸው አስተሳሰብ የተዛባ መሆን እና የተዛባ መረጃና እውቀትን እንደ እውነት አድርጎ መቀበል መጀመር ነው›› የሚለው ባለሙያው፤ ወጣቱ አሁን አፀያፊ ነገሮችን ማድረግ የጀመረው የአደንዛዥ አስተሳሰብ ሰለባ በመሆኑ ነው። ስለዚህ መንግሥት፣ ማህበረሰቡና ግለሰቦች በወጣቱ አዕምሮ ልማት ላይ ሊሠሩ ይገባል ሲል አሳስቧል። በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር መምህር ሃሳቡ ተስፋ እንደሚናገሩት፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በወጣቱ ዘንድ ነውር የሚባል ነገር ጠፍቷል። ለዚህም ዋና መንስኤው በጥላቻ የተሞላ አዕምሮ ባለቤት እንዲሆን በመደረጉ ነው። ወጣቱን የማያገናዝብ፣ አስቦና አሰላስሎ ነገሮችን የማይመለከት እንዲሁም ምክንያታዊ ባለመሆኑ ለአገር ተስፋ ሳይሆን አደጋ ፈጣሪ ሆኗል። ይህ ደግሞ ሀገር ተረካቢነቱን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። ወጣቱ ከሰውነት ተራ ወጥቶ በሪሞት እንደሚታዘዝ ማሽን እየሆነ መምጣቱን የሚያነሱት መምህሩ፤ አሁን በስሜት እና በተበላሸ አስተሳሰብ እየተመራ በመሆኑ ማወቅ የሚገባውን ያህል እየጠየቀና እያወቀ አይደለም ብለዋል። ወጣቱ መብትና ግዴታውን በሚገባ ስላልተገነዘበ በተነዳበት መንገድ እየሄደ ነው ያሉት መምህሩ መንግሥት መብትና ግዴታን ማሳወቅ፣ ጥፋት ሲያጋጥምም በሕግ አግባብ ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል። ለሚስተዋለው ችግር የመማር ማስተማሩ ዘዴና የልጆች የአስተዳደግ ሁኔታም ትልቅ አስተዋፅኦ ስላለው የትምህርት ሥርዓቱ መስተካከል እንዳለበት ጠቁመዋል። ‹‹ግዴታ ያለመብት ሊኖር ይችላል፤ መብት ግን ያለግዴታ አይኖርም›› የሚሉት የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር መምህሩ፤ ሞጋች ማህበረሰብ ባለመፈጠሩና መብቱን ብቻ በማየቱ አሁን ያለው ወጣት ከመሥራት ይልቅ የሌላውን ሀብት ሲያይ ዓይኑ የሚቀላ፤ ለእኔ ብቻ የሚል፤ የመንጠቅ መብት የተጠናወተው እየሆነ መምጣቱን አንስተዋል። በማያውቋቸው ሴረኞች በመንጋ አስተሳሰብ እየተመራ ንብረት ከማውደም አልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ ሰው ወደመግደሉ እየገባ ነው። በመሆኑም መንግሥት ወጣቱ ላይ መሥራት እንዳለበት ሲሉ መክረዋል። ማህበረሰቡ ልጆቹን ሲያሳድግ ሕግና ሥርዓት ባለው መልኩ ባለመሆኑ የሌላውን ዜጋ መብት ጭምር እየተጋፋ እንዲሄድ እንዳደረገው ጠቁመው፤ ይህም በማህበረሰቡ ዘንድ ሊሠራበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 19 ቀን 2012 ዓ.ም በ ጽጌረዳ ጫንያለው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36043
29f39ddb1ee2fac50575b44ef2c0c3ec
48e84f4f2b42e9e1cc0d21726bd83ef8
አዎን! ግድቡ የኔ ነው
የማያረጅ ውበት የማያልቅ ቁንጅናየማይደርቅ የማይነጥፍ ለዘመን የፀናከጥንት ከፅንሰ አዳም ገና ከፍጥረትየፈሰሰ ውሃ ፈልቆ ከገነት።ነበር ያለችው እጅጋየው ሽባባው አባይ በሚለው ዜማዋ። እውነት አባይን በቅርበት ለተመለከተው የሆነ ውስጥ የሚነካ የተለየ ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግ ውብ የተፈጥሮ ፀጋ ነው። አባይ ጣና ላይ ሲፈስ ጥቁር ቀለሙን ፅፎ ውሃው ሳይቀላቀል ሲያልፍ፤ ከጣናም ከወጣ በኋላ በዝምታ የባህር ዳር ከተማን አቋርጦ ሲወርድ ለተመለከተው እንደልብ ወዳጅ ሆድ እያባባ የሚሰናበት ያህል ልብ ይነካል። ከዚህ ቀጥሎ ጢስ አባይ ሲደርስ ደግሞ ከላይ ተወርውሮ ሲወርድ፤ ከዛ ተመልሶ ደግሞ ጭስ የመሰሉ ትናንሽ የውሃ ነጠብጣቦችን ይዞ ሲመለስ ለተመለከተው ልብን በሃሴት ጮቤ የሚያስረግጥ ውበት ያሳያል።እንኳን ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ሀገራችንን ሊጎበኙ ለመጡ ቱሪስቶች ይቅርና ከማህፀኗ ለፈለቅኩት ለኔ እንኳን ሳይቀር ሀገሬ ድንቅ ምድር እንደሆነች የፈጣሪ ውብ ስራ አንደሆነች ማመልከቻ ነው። ስለአባይ ማንሳት ከጀመርኩ ማቆሚያ የለኝም። አሁን ደግሞ ከሁሉ የሚልቀው ጉባ ላይ የከተመው ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሀገር ኩራት እውነተኛ የኢትዮጵያዊነት ወኔን የሚቀሰቅስ ነው።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ̋እንኳን ደስ አላችሁ የመጀመሪያው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት ስራ በስኬት ተጠናቋል” ብለው ለህዝቡ ሲያበስሩ ልቤን ፈንቅሎ የወጣው ስሜት ከልቤ የምወደውን አባይ ሳሞጋግስ አንድውል አድርጎኛል።ከቢሮዬ ወጣ ብዬ የህዝቡን ሁኔታ መመልከት ጀመርኩ። በእግሬ ትንሽ እርምጃዎችን ከተራመድኩኝ በኋላ ሰብሰብ ብለው የሚጨዋወቱ የእድሜ ባለፀጎች አጠገብ ደረስኩ። ፈቃዳቸውን ጠይቄ መቅረፀ ድምፄን ወደእነርሱ ጠጋ አደረግኩ።አቶ ታደሰ ሲሳይ ይባላሉ፤ የ63 ዓመት እድሜ ባለፀጋ ናቸው። ጡረተኛ መሆናቸውን የሚናገሩት አባት የአንድ ወር የጡረታ አበላቸውን አዋጥተው የግድቡን እድገት እንደ ህፃን ልጅ ከስር ከስር ሲከታተሉ መቆየታቸውን ይናገራሉ። “ከባልንጀሮቼ ጋር በተገናኘን ቁጥር ግድቡ እንዴት ሆነ? ምን ሰማችሁ? እንባባል ነበር” የሚሉት አቶ ታደሰ” ዛሬ ቀኑ ደርሶ የመጀመሪያውን ውሃ ለመያዝ መቻሉ ከአድዋ የማይተናነስ ድል ነው ብለዋል። እኔ እንኳን ባልደርስበት ለልጅ ልጆቼ የሚተላለፍ ግድብ ላይ አሻራዬን ስላኖርኩ ኩራት ይሰማኛል” ብለዋል። አቶ ጌታነህ አበባው በአንድ የግል ኮሌጅ ውስጥ በጥበቃ ስራ የሚተዳደሩ አባት ናቸው “ፈጣሪ እድሜ ሰጥቶኝ ይሄን ለማየት በመቻሌ እራሴን እንደ እድለኛ እቆጥረዋለሁ” ብለዋል። “ከኛ እኩል ካላቸው ላይ ቆጥበው ይሄን ቀን ለማየት ሲጓጉ የነበሩ ጓደኞቻችን ዛሬ በህይወት የሉም። እነርሱን ከጎናችን ብናጣቸውም ግን በነበራቸው አቅም ታሪክ ፅፈው እንዳለፉ እያሰብን እንጽናናለን ሲሉ ተናግረዋል። በውትድርና ሙያ ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የኖሩት አቶ ይደርሳል ብርሃኔ የሀገር ዳር ድንበርን በማስከበር ስራ ላይ ከኖሩበት ጊዜ በላይ የልማት አርበኛ ሆነው የቻሉትን ያህል ገንዘብ አዋጥተው የግድቡን መጠናቀቅ የድል ብስራት የሚጠባበቁበት ጊዜ እንደሚበልጥባቸው ገልፀው፤ በድሉም ወደር የሌለው ደስታ እንደተሰማቸው ይናገራሉ። ሌላዋ እናት ወይዘሮ ምህረት ልመንህ ይባላሉ፤ የ72 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው፤ በመንግስት ስራ ላይ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በጡረታ ጊዜያቸው ሀገርን በአንድ ድምፅ የሚያነጋግር ድል መገኘቱ የማይቆጣጠሩት ደስታ እንደሰጣቸው ተናግረዋል። ወይዘሮዋ እንደሚሉት ከሚመሩት እድር አባላቶቹን በማስተባበር የአስር ሺ ብር ቦንድ እንደገዙ አስረድተው፤ ህብረተሰቡ ከእለት ጉርሱ ቀንሶ ያዋጣው ገንዘብ ወደ ስራ ተቀይሮ ውጤት ላይ ሲደርስ ከማየት የበለጠ ደስታ የለም ብለዋል።የእድሜ ባለፀጎቹ በአንድ አይነት ሃሳብ ግድቡ የኛም የአረጋውያኑ መጦሪያ የልጆቻችን ሀብት ማፍሪያ በመሆኑ “ አዎ ግድቡ የኛም ነው” ብለን አስተዋጽኦችንን በህይወት እስካለን እንቀጥላለን ብለዋል።“አዎ ግድቡ የኔም ያንችም የእነሱም የሁላችንም ነው”።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012አስመረት ብስራት
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36098
71a28e2b89868a93b4cd4fd5a9c81423
bb1a45b513212f30ba42f2b4e35b6a58
የብልጽግና ጉዞውን ከዳር ለማድረስ አመራሩ ግንባር ቀደም ሚናውን መወጣት እንዳለበት ተጠቆመ
አዳማ ፡- የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ አመራሩ ግንባር ቀደም ሚናውን መወጣት እንዳለበት የክልሉ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ አመለከቱ ። ጨፌ ኦሮሚያ በአምስተኛው ዙር የስራ ዘመኑ አምስተኛ ዓመት ጉባኤ የባለስልጣናትን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል። የክልሉ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ ትናንትና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር፣ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር በማድረስ የክልሉንና የሀገሪቱ እድገት ማረጋገጥ የሚቻለው አመራሩ በትጋትና በቁርጠኝነት ሲሰራ እንደሆነ አመልክተዋል። በአሰራር ላይ እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮችን አስቀድሞ በመለየት አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት አፈ ጉባኤ፣ በተለይም የክልሉን ሰላምና ጸጥታ በማስከበር ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ አስታውቀዋል። ጨፌው በትናንትና ውሎው የክልሉን ጠቅላይ ኦዲት መስሪያ ቤት፣ ፍርድ ቤት እና የጨፌውን የ2012 ዓ.ም አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አድምጧል። የጨፌው አባላት በኦዲት የተገኙ ውጤቶች የክልሉን እንቅስቃሴና እድገት የጎዱ መሆናቸውን ጠቅሰው ይህን በተመለከተ የተወሰዱ ርምጃዎች አለመጠቀሳቸው ሪፖርቱ ሙሉዕ እንዳይሆን አድርጎታል ብለዋል። በወቅቱም ፍርድ ቤቶች የህግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ እና ፍትህን እንዲያረጋግጡ በርካታ ሀሳቦች ተንጸባርቀዋል። በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች፣ የፍትህ ስርዓቱን በጥቅም ለማዛባት የሚሞክሩ የውጭ ደላሎችና የውስጥ ጉዳይ አስፈጻሚዎችን አደብ ማስገዛት እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል። ጨፌው ለ2013 ዓ.ም በረቂቅ ደረጃ የቀረበውን የ 90 ቢሊዮን ብር በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ከዚህ ውስጥ 61 ነጥብ 2 ቢሊዮኑ ብር ከፌዴራል መንግስት የሚሰጥ ሲሆን 28 ነጥብ 8 ቢሊዮኑ ደግሞ ከክልሉ ገቢ የሚሰበሰብ መሆኑ ተገልጧል። በተጨማሪም ጨፌው የክልሉን የመጠጥ የውሃ ሃብት አጠቃቀም በተመለከተ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል እንዲሁም የ2012 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጁን በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል። ከቅዳሜ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ይህ ስብሰባ አስራ አንድ የሚደርሱ አጀንዳዎች የዳሰሰ ሲሆን፣ ትናንት ማምሻውን የባለስልጣናትን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል። በዚሁ መሰረት፤ ዶክተር መንግስቱ ሁሪሳ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ታረቀኝ ቡልቻ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ፤ ወይዘሮ መስከረም ደበበ የኦሮሚያ ገቢዎች ባልስልጣን ሃላፊ፣ አቶ አህመድ ሰይድ ኢብራሂም የህብረት ሥራ ኤጀንሲዎች ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ተሹመዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012በኢያሱ መሰለፎቶ በጸሀይ ንጉሤ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36097
18899017fbafa07d7201a1ede093d47e
b96ec47b8fd164aa94cfcfd109197b06
የግድቡን ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ለመጨረስ በዲፕሎማሲው መስክ በተጠናከረ መልኩ መንቀሳቀስ እንደሚገባ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፡- የህዳሴውን ግደብ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ በመጨረስ ወደስራ ለማስገባት በዲፕሎማሲው መስክ በተጠናከረ መልኩ መንቀሳ ቀስ እንደሚገባ ተጠቆመ። በመጀመሪያው ዙር የተያዘው ውሃ ለኢትዮጵያ የመደራደሪያ አቅም እንደ ሚፈጥር አስታወቁ።በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለምአቀፍ ትምህርት መምህር እና የትምህርት ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሞገስ ደምሴ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የህዳሴውን ግደብ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ አልቆ ወደስራ እንዲገባ በዲፕሎማሲው መስክ በተጠናከረ መንቀሳቀስ ይገባል።የዲፕሎማሲው ስራ እውቀቱ እና ክህሎቱ ባላቸው ሰዎች እንዲሳተፉ እና የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ ዲፕሎማሲው ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይጠይቃል ሲሉ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለምአቀፍ ትምህርት መምህሩ አስገነዘቡ።በግድቡ ዙሪያ የጀመርናቸውን ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ የዲፕሎማሲ ስራ በጣም ወሳኝ ነው የሚሉት መምህሩ ፤ ይፋዊም ይፋዊም ባልሆኑ የዲፕሎሚሲ ስራዎች አሁን ካለው ከፍ ባለ ደረጃ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ አመልክተዋል። በተለይም ይፋዊ ላልሆኑ የዲፕሎማሲ ስራዎች ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።ይፋዊ ያልሆነ ዲፕሎማሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ባህልን መሰረት ያደረገ እንደሆነ የሚያስረዱት መምህሩ ፤ ይህም ባንድ ወቅት ታይቶ የሚጠፋ ሳይሆን ተከታታይነት ባለው መንገድ በደንብ ተጠንቶ ሊተገበር እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡ በመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያ የተከተለችው መንገድ ብሄራዊ ጥቅም አስገኝቷል የሚሉት መምህሩ ፤ ወደፊትም ለሚኖረው ድርድር ግብፅ እና እና ሱዳንም በአንድ ልብ ወደ ድርድሩ እንዲመጡ ያስገድዳቸዋል ብለዋል። በመጀመሪው ዙር የተያዘው ውሃ ለኢትዮጵያ የመደራደሪያ አቅም የፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል። ከአሁን በኋላ ያለውን ድርድር በጥሩ ሁኔታ እንዲጠ ናቀቅ የማስፈንጠሪያ አቅም መሆኑንም ገልጸዋል። የህዳሴ ግድቡን ፕሮጀክት ከአድዋ ጦርነት ጋር የሚመሳሰል የህዝብ አንድነት የታየበት መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ አንድነት በዘላቂነት እንዲቀጥል መንግስት ተጠናክሮ መስራት እንደሚኖርበት መክረዋል። በሀገር ህልውና እና በዴሞክራሲ መካከል ያለውን ሚዛናዊነት የመጠበቅ አካሄድ መኖር አለበት የሚሉት ዶክተር ሞገስ፤ የሀገርን ህልውና ባገናዘበ መልኩ የዴሞክራሲው ምህዳሩን ማስፋት እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል። የውስጥ አለመግባባቶችና የውስጥ ሽኩቻዎች ለውጭ ሃይሎች ሀገራችንን እንዲያተራምሱ እድል የሚከፍት መሆኑን ገልጸው ፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት አንድነታችንን እያጠናከሩ መሄድ ይገባናል ብለዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 20/2012ሙሉቀን ታደገ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=36104
08cf01f676e42b201d96124a10e15570
f715a355a6ce4487a44d0eb0e6a93f45
በጸረ-አበረታች መድሃኒት ላይ የሚሰራ ፎረም ተቋቋመ
የኢፌዲሪ ብሄራዊ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት የሕዝብ ንቅናቄን ለመፍጠር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ። በዚህ ስራ ተሳታፊ የሚሆን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የጸረ አበረታች ቋሚ ፎረምም ተቋቁሟል። በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 400/2009 የተቋቋመው፤ የኢፌዲሪ ብሔራዊ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ከኃላፊነቶቹ መካከል አንዱ የስፖርቱ ስጋት የሆነውን ቅመም መከላከልና መቆጣጠር ነው። ይህንንም ለማከናወን የህዝብ ንቅናቄ መፍጠር አስፈላጊ ሲሆን፤ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆንም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል። ከእንቅስቃሴዎቹም መካከል፤ ከስፖርት ማህበራት ጋር አብሮ መስራት፣ በታዳጊ ፕሮጀክት ስልጠና እና በስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት የስልጠናው አንድ አካል እንዲሆን ማድረግ፣ በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ማካተት እንዲሁም የባለሙያ ፎረሞችን ማቋቋም ተጠቃሾቹ ናቸው። በዚህም መሰረት ከባለድርሻ አካላት መካከል አንዱና በተደራሽነት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት የታመነበት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ፎረም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተቋቁሟል። የፎረሙ ዓላማም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ትክክለኛ፣ በቂ እና ወቅታዊ መረጃ ለህብረተሰቡ ማድረስ ነው። ከዚህ ባሻገር ባለሙያዎቹ ከጽህፈት ቤቱ ጋር በቅንጅት፤ አጀንዳ በመያዝ፣ በማቀድና በመመካከር ለመስራት እንደሚያስችልም ተጠቅሷል። የመቋቋሙ አስፈላጊነት በሃገሪቷ የአበረታች መድሃኒቶች ተጠቃሚነት አዝማሚያ እያደገ መምጣቱ ሲሆን፤ ከዓለም አቀፉ የጸረ- አበረታች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ከፍተኛ ግፊት የተደረገ መሆኑም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል። ከዚህ ባሻገር አበረታች መድሃኒትን በመከላከልና በመቆጣጠር እንዲሁም በአሰራር ክፍተቶችንና በሚታዩ ጥርጣሬዎች ላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የድርሻቸውን መወጣት እንዲችሉ መሆኑም በማቋቋሚያ ደንቡ ላይ ተመልክቷል። ጽህፈት ቤቱ ከዚህ ቀደም የስፖርት ባለሙያዎች እንዲሁም የችግሩ ቅድሚያ ተጋላጭ የሚሆኑትን የአትሌቶች ፎረም በማቋቋም በጋራ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል። በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመአዲስ ዘመን ሰኔ 24/2011ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13373
983b0b0b72c2c587ffa212bcd1760b7e
2ba7283ba305ed5b50329e4cb74b87f3
«መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ሰው እንዲደባደብ መድረክ አያመቻችም»- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
 አዲስ አበባ፡- ‹‹በአገሪቱ የሚስተዋሉ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግሮች እልባት የማያገኙ ከሆነ መንግሥት ከፍተኛ በጀት እየመደበ ሰው የሚደባደብበት መድረክ አያመቻችም፤ አስፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳል» ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳሰቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2011 በጀት ዓመት የመንግሥት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በትላንትናው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። መንግሥት በአገሪቱ ለሚስተዋለው የስፖርታዊ የጨዋነት ችግር እልባት በመስጠት ረገድ በቀጣይ ምን ዓይነት አቅጣጫዎችን ሊከትል አስቧል የሚል ጥያቄም ከምክር ቤቱ አባላት ቀርቦላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጥያቄው በሰጡት ምላሽም «ስፖርት ባለባቸው አገራት የማይስተዋል ችግር፤ስፖርቱ በሌለበት በእኛ አገር እየተስተዋለ ነው፤ ስፖርት በባህሪው መንደር አይደለም፤የስፖርት ሜዳ ኳስ በጥበብና በዕውቀት ይንከባለልበታል እንጂ ፖለቲካ አይንከባለልበትም፤ይሁንና በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ፖለቲካ ስታዲየም ገብቷል» ብለዋል። በአገሪቱ አንድም ስታዲየም ያለው፤ማልያ ሸጦና በግሉ ስታዲየም ተጫውቶ ራሱን ችሎ የሚንቅሳቀስ ክለብ አለመኖሩን ጠቅሰው፣ እያንዳንዱ ከለብም መንግሥት እጁን ቢሰበስብ አንድ ወር መዝለቅ የማይችል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡ ክለቦች በመንግሥት ድጎማ እየተንቀሳቀሱ መልሰው መንግሥት ላይ ችግር ሲፈጥሩ እንደሚስተዋል አብራርተዋል። ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ አኳል /ፊፋ/ ሳይቀር ዕርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል ተናግረው፣ አስቀድሞ በርካታ ዕርምጃዎች እንደሚወሰዱ አመልክተዋል፡፡ በአህጉርም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረኮች ተስፋ እያሳየ ላልሆነ ስፖርት መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ ሰው እንዲደባደብ መድረክ  አያመቻችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ‹‹ገንዘብም ወጣትም አይከስርም፤ነገሮች በጊዜ የማይስተካከሉ ከሆነም መንግሥት እጁን ይይዛል» ብለዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ሰው ስታዲየም የሚገባው ድጋፍ ለመስጠት እንጂ የፖለቲካ አቋምና ብሄርን ለማንፀባረቅ ሲኮራረፍም ለመሰዳደብ አይደለም፡፡ ስፖርትን ከፖለቲካ አፅድቶ መጠቀም ያስፈልጋል። ስፖርትን ከብሄር፤ከፖለቲካ ነፃ ለማውጣትና ህግና ስርዓትን ተፈፃሚ በማድረግ ረገድም ፌዴሬሽኑ በርካታ ተግባራት ማከናወን ይጠበቅበታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ ስፖርት ላይ ከሚስተዋሉት የጨዋነት ችግሮች በተጓዳኝ በወር አንድ ቀን የሚካሄደው የማስ ስፖርት በተለይ ሰዎችን ከማቀራራብ፤ለጤና የሚወጣ በጀት በመቀነስና የተነቃቃ ትውልድ በመፍጠር ረገድ የሚያበረክተው ፋይዳ ጉልህ መሆኑን አመላክተዋል። በተመረጡ ቦታዎች ከመኪና ፍሰት በፀዳ ሁኔታ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄደው ስፖርታዊ ሁነትም፤በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብቻ መወሰን እንደሌለበት ጠቅሰው፣ በሌሎች አገራት እንደሚካሄደው ጎን ለጎን ጥበባዊ ትዕይንቶችን ማቅረብ እንዳለበትም አስረድተዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13411
162f13481563279e70af61e9a8d64858
aff080184d2729ee21ea6bedba8739ad
በዳይመንድ ሊጉ ኢትዮጵያውያን አልቀናቸውም
ሰባተኛ ዙር የዳይመንድ ሊግ ውድድር በሳምንቱ መጨረሻ በአሜሪካ ዩጂን ከተማ በተለያዩ ርቀቶች ሲካሄድ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም። በተለይ ተጠባቂ በነበረውና በርካታ ስመጥር አትሌቶችን ባሳተፈው የሴቶች ሦስት ሺ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሰፊ የማሸነፍ ዕድል ቢሰጣቸውም ውጤቱ ግን የተገላቢጦሽ ሆኗል። ያልተጠበቁ አትሌቶች ከፊት ሲሆኑ ተጠባቂዎቹ ወደኋላ በቀሩበት በሴቶች መካከል የተካሄደውን የሦስት ሺ ሜትር ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ለኔዘርላድ የምትሮጠው ሲፋን ሃሰን ቀዳሚ ሆና አጠናቃለች። አትሌቷ ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰዳባት ሰዓት 8 ደቂቃ ከ18 ሴኮንድ ከ49 ማይክሮ ሴኮንድ ሆኗል። ይህም የግሏና የውድድሩ የዓመቱ ምርጥ ሰዓት ሆኖ ተመዝገቧል። አትሌቷ ከቀናት በፊት በሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ርዕሰ መዲና ራባት በተካሄደው የዳይመንድ ሊጉ ስድስተኛው ዙር የ1ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር አሸናፊዋን ገንዘቤ ዲባባ ተከትላ በሁለተኝነት ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወሳል። የሦስት ሺ ሜትር ውድድሩን ሲፋንን ተከትላ ጀርመናዊቷ ኮንስታንዜ ሃልፈን ሁለተኛ ወጥታለች። 8 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ07 ማይክሮ ሴኮንድ ውድድሩን ጨርሳ የገባችበት ሰዓት ሆኗል። ኢትዮጰያዊቷ አትሌት ለተሰንበር ግደይ ሦስተኛ ሆና አጠናቃለች። ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓትም 8 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ27 ማይክሮ ሴኮንድ ነው፤ ይህም የሯሷ ምርጥ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦላታል። በውድድሩ ሰፊ የማሸነፍ ግምት አግኝታ የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ አራተኛ ስትሆን 8 ደቂቃ ከ21 ሴኮንድ ከ29 ማይክሮ ሴኮንድ የገባችበት ሰዓት ሆኗል። ገንዘቤ ከቀናት በፊት ሞሮኮ ርዕሰ መዲና ራባት በተካሄደው የዳይመንድ ሊጉ ስድስተኛው ዙር የ1ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር 3 ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ ከ47 ማይክሮ ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆና ማጠናቀቋ ይታወሳል። አትሌት ገንዘቤ እ.አ.አ በ2015 በፈረንሳይ ሞናኮ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር 3 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ከ8 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት በርቀቱ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት መሆኗም አይዘነጋም። በውድድር ዓመቱ የአምስት ሺ ሜትር ውድድርን በበላይነት ተቆጣጥራ የቆየችውንና በ8 ደቂቃ ከ23 ሴኮንድ ከ60 ማይክሮ ሴኮንድ የሦስት ሺ ሜትሩ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት የነበረችው ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ በዩጂን ስድስተኛ ሆና አጠናቃለች። ኢትዮጵያውያኑ ፋንቱ ወርቁ ዘጠነኛ፤ሰንበሬ ተፈሪ አስራ አንደኛ፤ ሃዊ ፈይሳ አስራ ሦስተኛ ሆነዋል። ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ውድድር ተመልሳ የመጀመሪያ ፉክክሯን ያደረገችውም የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ ዓለም የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ባለቤቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት አልማዝ አያና ውድድሩን 18ተኛ በመሆን አጠናቃለች። አልማዝ አያና ከሁለት ዓመት ቀድሞ በህንዱ ደልሂ ግማሽ ማራቶን ከተሳተፈች በኋላ በውድድሮች ላይ ሳትሳተፍ መቋየቷ ይታወሳል። ውጤቷ ባያምርም አትሌቷ ከረጅም ጊዜ የጉዳት ቆይታ በኋላ ተመልሳ ያሳየቸው አቋም ለቀጣይ ውድድር ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን በርካቶች ተስማምተውበታል። የሦስት ሺ ሜትር ፈጣን ሰዓት 8 ደቂቃ ከ06 ሴኮንድ ከ11ማይክሮ ሴኮንድ ሆኖ መመዝገቡ ይታወቃል። የሰዓቱ ባለቤትም ቻይናዊቷ ጁዋንግ ዋንግ ስትሆን ያስመዘገበችውም እኤአ 1993 ላይ በተካሄደ ውድድር ነው። ጠንከር ያለ ፉክክር የተስተዋለበትና በወንዶች መካከል የተካሄደው የሁለት ማይል ውድድር በዩጋንዳዊው አትሌት ጆሹዋ ቼፕቴጊ ቀዳሚነት መቋጫውን አግኝቷል። አሜሪካዊው ፖል ቺሊሞ ሁለተኛ ሲሆን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ደግሞ ሦስተኛ ሆኖ ገብቷል። ውድድሩን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ሰዓትም፤8ደቂቃ ከ08 ሴኮንድ ከ69 ማይክሮ ሴኮንድ የገባበት ሰዓት ሆኖ ተመዝገቧል። ሰባተኛ ዙር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ሌላኛው መርሐ ግብርም በሴቶች መካከል የተካሄደው የስምንት መቶ ሜትር ውድድር ነው። ውድድሩም፤ከፆታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (አይኤኤኤፍ) ጋር ውዝግብ ውስጥ የቆየችውና በመጨረሻ ወደ ውድድር የተመለሰችው ደቡብ አፍሪካዊቷ አትሌት ካስተር ሴሜኒያ አሸናፊነት መቋጫውን አግኝቷል። የሁለት ኦሎምፒክና ሦስት የዓለም ሻምፒዮና ባድል የሆነችው ሴሜኒያ፤ በስምምንት መቶ ሜትር ለአራተኛ ጊዜ ያለመሸነፍ ጉዞዋን በማስቀጠሏም አድናቆትን አግኝታለች። በዚህ ርቀት ጥሩ ብቃት በማሳየት ላይ የምትገኘው ሀብታም ዓለሙ አምስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና ሰሜን አሜሪካ በሚገኙ 14 ከተሞች የሚካሄደው የ2019 የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለስምንተኛ ጊዜ በስዊዘርላንድ ሉዛን የፊታችን ዓርብ ይካሄዳል። ውድድር በቀጣይም፤በሞናኮ፤ ለንደን፤በርሚንግሃም ኸፓሪስና ዙሪክ ቀጥሎ በጳጉሜ መጀመሪያ በቤልጂየም መዲና ብራሰልስ በሚካሄደው ውድድር የሚጠናቀቅ ይሆናል። የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በዘንድሮው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በአጠቃላይ የስምንት ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ማዘጋጀቱ ይታወሳል። በሁለቱም ጾታዎች በተመሳሳይ በ16 የተለያዩ የውድድር ዓይነቶች በእያንዳንዱ ርቀት የአጠቃላይ አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች የ50 ሺህ ዶላርና የዳይመንድ ሽልማት ያገኛሉ። ከዚህም በተጓዳኝ በእያንዳንዱ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ የ100 ሺህ ዶላር ሽልማትም ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም በእያንዳንዱ ርቀት አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶች ከመስከረም 17 እስከ 26 ቀን 2012 ዓ.ም በኳታር መዲና ዶሃ ለሚካሄደው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያለማጣሪያ የሚያልፉ ይሆናል። አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13413
b91e0ab75a612557fc064ad725e082ec
e5b6c5071d41efd8a45bc242365270c3
የክብደት ማንሳት ብሔራዊ ቡድኑ በመጪው ወር ወደ ልምምድ ይገባል
በሞሮኮ አዘጋጅነት 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ድምቀት ተደርገው ከሚቆጠሩ የስፖርት ዓይነቶች የክብደት ማንሳት ስፖርት ይጠቀሳል። ከፍተኛ ፉክክር በሚታይበት ስፖርት ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች ትሳተፋለች። የኢትዮጵያ ክብደት ማንሳት እና ሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን በመድረኩ ሀገሪቱን የሚወክሉ ተጫዋቾችን ለመምረጥ ከሰኔ 19 እስከ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በጃን ሜዳ ሀገር አቀፍ ሻምፒዮና አካሂዷል። ሻምፒዮናው ወንዶች ከ55 እስከ 102 ኪሎ ግራም በሴቶች ከ45 እስከ 71 ኪሎ ግራም ባሉት የክብደት ዘርፎች ተካሂዷል።በአህጉር አቀፍ ውድድሩ ሀገርን የሚወክሉ ተጫዋቾችን ለመመልመል በተካሄደው ሻምፒዮና ላይ የትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊ ሆነዋል። አጠቃላይ የተሳታፊ ቁጥሩም በወንድ 40 በሴት 25 በድምሩ 65 ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ሻምፒዮናው ለአራት ተከታታይ ቀናት በድምቀት ሲካሄድ ቆይቶ ባሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄዱ አራት የፍጻሜ ውድድሮች ተጠናቋል። በመዝጊያው ዕለት አራት የፍጻሜ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን፤ በወንዶች 102 ኪሎ ግራም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተወዳዳሪ ቢኒያም አክሊሉ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ተመስገን ቶማስ ከኦሮሚያ ክልል የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። በ96 ኪሎ ግራም ወንዶች የኦሮሚያ ክልሉ አዲሱ አለማየሁ የወርቅ ሜዳሊያ ሲያገኝ ምህረትአብ በቀለ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ ሃይልነት አወቀ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ያገኙ ተወዳዳሪዎች ናቸው።በተጨማሪም የ89 ኪሎ ግራም ወንዶች የሐረሪ ክልሉ ተወዳዳሪ ሳሙኤል በዛብህ፤ መስፍን ኃይሉ ከኦሮሚያ ክልል እምነት ደጉ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የብር እና የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል። በሴቶች ደግሞ በ71 ኪሎ ግራም የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ተወዳዳሪዋ ምንተአምር ታደሰ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። ከትግራይ ክልል የመጣችው ቤተልሄም መሳይ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታገኝ ፤ የአዲስ አበባዋ አበባ ማዳ ሦስተኛ በመሆን የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።በከፍተኛ ድምቀት ታጅቦ የተጀመረው ሻምፒዮና ድምቀቱን ጠብቆ በአጠቃላይ ውጤት በወንዶች የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በአራት ወርቅ ሜዳሊያ፣ በሴቶች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለት ወርቅ እና በአንድ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል። ድሬዳዋ ከተማ የስፖርታዊ ጨዋነት የጸባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።የኢትዮጵያ ክብደት ማንሳት እና ሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበበ አሽኔ እንደገለጹት፤ የሻምፒዮናው አላማ በነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም በሞሮኮ ርዕሰ ከተማ ራባት በሚካሄደው 12ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችን ለመምረጥ ነው። በመላው አፍሪካ ጨዋታ በሚኖረን ተሳትፎ ውጤትና ሜዳሊያዎችን ለማስመዝገብ ብቻም ሳይሆን፤ ውድድሩ ሀገራችን በስፖርቱ በምን ደረጃ ላይ እንዳለች የምንለካበት መልካም አጋጣሚም ጭምር መሆኑን አስረድተዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በነበረው ሻምፒዮናው ላይም ብሔራዊ ቡድኑን የሚወክሉ ጠንካራ ተወዳዳሪዎች የታዩበት መሆኑን ተናግረዋል።በሁለቱም ጾታዎች በሻምፒዮናው ጥሩ ተፎካካሪ የሆኑና በአፍሪካ ከሚገኙ ተወዳዳሪዎች ተቀራራቢ ውጤት ያስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ለመላው አፍሪካ ጨዋታ ይመረጣሉ። ፌዴሬሽኑ ያስቀመጠውን መስፈርት መሠረት በማድረግ በሻምፒዮናው ላይ በተመዘገበው ውጤት ተጫዋቾቹን በቅርብ ቀናት በመምረጥ ይፋ የሚደረግ ይሆናል። አስፈላጊውን መስፈርት እና መለኪያ ያሟሉ በወንድ አምስት፣ በሴት ሁለት ተወዳዳሪዎች ተመርጠው በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት ክልሎች እንዲያውቁት እንደሚደረግና ከሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ልምምድ እንደሚገቡም አስታውቀዋል።በሻምፒዮናው ተሳታፊ በኩል ደግሞ ከተሳትፎ አንጻር የተሻለና ጥሩ ፉክክር እንደታየበት መሆኑን ተናግረዋል። የሻምፒዮናው መዘጋጀት ተወዳዳሪዎች ያሉባቸውን ጉድለቶች ለመሙላት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ ስፖርቱን የሚመራው ፌዴሬሽን የውድድር አማራጮችን ከማስፋት አኳያ እንዲሁም ሥልጠናዎች ከማዘጋጀትና ክልሎች የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ ከማሟላት አንጻር ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቃል። ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች አንጻር ሲታይ ስፖርቱ ላይ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅና ለዚህም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት እንዳለባቸው አመልክተዋል።በሻምፒዮናው የትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የሐረሪ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉበት ነበር። በሌላ በኩል የአማራ፣ ሶማሌ፣ አፋር እና ጋምቤላ ክልሎች በበጀት እጥረት እና በዝግጅት ማነስ በሻምፒዮናው ሳይሳተፉ ቀርተዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 26/2011 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13491
e8c645a5af45d9eb2cab4794ce7cd548
3c7a29db0e8079a9638229cc8bcafacb
በዓለማችን ታላላቅ ሊጎች ጥቋቁር ኮከቦች
አፍሪካ የምርጥ ደጋፊዎች እንብርት የመሆኗን ያህል የድንቅ ተጫዎቾች ባለሀብትም ነች። ከልጅነት ጀምሮ በየመንደሩ ባዶ እግራቸውን እግር ኳስ የሚጫወቱ፤ ራሳቸውን ለኳስ ፍቅር አሳልፈው የሰጡና ለእግር ኳስ ፍቅር የሚታመኑ በርካታ ተጫዋቾችን ወልዳለች። በድንቅ የእግር ኳስ ጥበብ የተካኑ በሙያቸው ብዙዎችን ያስደመሙ፣ ከአህጉሪቱም ተሻገረው በታላላቅ ሊጎች ድንቅ ችሎታቸውን ያስመሰከሩ ጥበበኞችንም አፍርታለች። እኤአ1992/93 የውድድር ዓመት በፈረንሳዩ ኃያል ክለብ ማርሴይ ከነገሠው ጋናዊው አቢዲ ፔሌ፤ አንስቶ እ ኤ አ በ1995 በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ባሎንዶር ክብርን እስከተቀዳጀው ጆርጅ ዊሃ፤አፍሪካውያን የኳስ ጠቢባን በተለያዩ የአውሮፓ መድረኮች ችሎታቸውን አሳይተዋል። በአርሰናል ቤት አይረሴ ዘመን ያሳለፈው ናይጄሪያው ኑዋንኮ ካኑ፤ በእንግሊዝ ምድር በቦልተን ወንደረረስ የነገሠው ጄጄ ኦካቻ፤በጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየር ሙኒክ በርካቶችን ያስጨበጨበው ጋናዊው ሳሚ ኩፎር እንዲሁም በባርሴሎናና ኢንተር ሚላን ድንቅ የነበረው ካሜሮናዊው ሳሙኤል ኤቶና በቼልሲዎች መለያ ድንቅና ተአምራዊ ገድሎችን የሠራው አይቮሪኮስታዊው ዲዲየር ድሮግባ ተጠቃሾች ናቸው። የሚገባቸውን ያህል ክብርና እውቅና ማግኘት ባይችሉም በአሁኑ ወቅት የአህጉሪቱ እግር ኳስ ጥበበኞች በዓለማችን ሁሉም ማዕዘናት በተለያዩ ታላላቅ ሊጎች በመጫወት አገራቸውንና ስማቸውን ከፍ አድርገው እያስጠሩ ይገኛሉ። ብቃት ሲለካ የቆዳ ቀለም የልዩነት ተረኮች ስህተት ስለመሆናቸው በማስመስከር፤ የማንነት ሚዛንን አመጣጥነው የኃያልነት ትርጓሜ የቀየሩ፤በተለይ በፊት መስመር ተሰላፊነት ሚና የሚጫወቱ ውድ የአህጉሪቱ ኮከቦች፤ ክለቦችን ከሽንፈት መታደግና አሸናፊ ከማድረግ ባለፈ ሻምፒዮን እንዲሆኑ ማስቻላቸውን ቀጥለዋል። በተለይ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት የአህጉሪቱ ኮከቦች ከደመቁባቸው ታላላቅ የእግር ኳስ መድረኮች መካከል ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቀዳሚ ሆኖ ይጠቀሳል። የአርሰናሉ የፊት መስመር ተጫዋች ፔር-ኤሜሪክ ኦባሚያንግ፤የሊቨርፑሎቹ ሞህ ሳላህ እና ሳዲዮ ማኔ፤በውድድሩ የካበተ ልምድ ካላቸው ከማንችስተር ሲቲው ሰርጂዎ አጉዌሮና ከቶተንሃሙ ሃሪ ኬን በላይ ከፍተኛ ግብ በማስቆጠር የሊጉ የኮከብ ግብ አግቢነት ክብርን በጋራ ተቀዳጅተዋል። በተለይ በጀርመኑ ቦርሲያ ዶርቱመንድ ቆይታው ምርጥ የፊት መስመር ተጫዋች መሆኑን በሚገባ አሳምኖ ያረጋገጠው ጋቦናዊው አጥቂ ፔር-ኤሜሪክ ኦባሚያንግ፤ በ56 ሚሊየን ፓውንድ ከሁለት ዓመት በፊት መድፈኞቹን ከተቀላቀለ ወዲህ ድንቅ ችሎታውን እያሳየ ይገኛል። ተጫዋቹ በወቅቱ የጀርመን ቆይቷውን ለመቋጨት መወሰኑ ስህተትና እንደ ቡንደስሊጋው በፕሪሚየር ሊጉ ግብ ማስቆጠር ከባድ ሊሆንበት እንደሚችል በርካቶች ቢገምቱም ተጫዋቹ ግን ይህ እሳቤ የተሳሳተ ስለመሆኑ ለማረጋጋጥ ብዙም አልተቸገረም። አርሰናል ከኤቨርተን ጋር ባደረገው ጨዋታ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ የመድፈኞቹን መለያ መልበስ የቻለው ኦባሚያንግ፤ ክለቡ ጨዋታውን 5ለ1 ሲያሸንፍ በመጀመሪያ ጨዋታው የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል። በውድድር ዓመቱ አስር ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ አራት ለግብ ያለቀላቸው ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ማጋራት ችሏል። ተጫዋቹ በተለይ በ2018/19 የእንግሊዝ ፐሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ድንቅ ግብ የማግባት ችሎታ እንዳለው ይበልጥ ያስመሰከረ ሲሆን፤ለመድፈኞቹ በ36 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 22 ግቦችን አስቆጥሯል። አምስት ለግብ ያለቀላቸው ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ተጫዋቹ ያስቆጠራችው ግቦችም የሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት ክብር እንዲቀዳጅ አስችለውታል። በአሁኑ ወቅትም በዓለማችን ታላቁ ሊግ የአገሩንና የራሱን ስም ከፍ አድርጎ እያስጠራ ይገኛል። ሌላኛው በአሁኑ ወቅት በታላቁ ሊግ ድንቅ ችሎታቸውን በማስመሰከር ላይ የሚገኘው የአህጉሪቱ ፍሬ ጥበበኛው ሰይዲ ማኔ ነው። ከ2014/15 የውድድር ዓመት ጀምሮ በሊጉ ባለሁለት አሃዝ ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ የማይሳነው ሴኔጋላዊው ኮከብ ማኔ፤ በተለይ በ2016 ከሳውዝሃፕተን ሊቨርፖሎችን ከተቀላቀለ ወዲህ ስሙ እጅጉን ከፍ ብሎ መሰማት ጀምሯል። በሜዳ ላይ ታታሪነቱና የተቃራኒ ቡድን ተከላካዮች በማስጨነቅ የሚታወቀው ሴኔጋላዊው ኮከብ፣ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በማንሳት ማጣጣም የቻለ ሲሆን፣ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ግብ አግቢነት ክብርን በመቀዳጃት የወርቅ ጫማውንም ተሸልሟል።ብቃቱንና አስተዋፆኦውን በየጊዜው እያጎለበተ የሚጓዘው ሴኔጋላዊ ተጫዋች፤የብቃቱንና የአስተዋፅኦውን ያህል ባይዘመርለትም ሊጉን ከሚያደምቁት ድንቅ አፍሪካውያን ተጫዋቾች አንዱ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በድንቅ የእግር ኳስ ጥበብ ችሎታ ከተካኑ እና በሙያቸው ብዙዎችን ካስደነቁ አፍሪካውያን ኮከቦች መካከል በግንባር ቀደምትነት ስሙ ይነሳል። ግብፃዊው ሞሃመድ ሳላህ። የ26ዓመቱ ግብፃዊው ኮከብ በመጀመሪያ ዓመት የአንፊልድ ቆይታም በ38 ጨዋታዎች 32 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ይህም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሠላሳ ግቦች በላይ በማስቆጠር በታሪክ ብቸኛው ተጫዋች እንዲሆን አስችሎታል። ምትሐተኛው ግራ እግር ባሳልፈነው የውድድር ዓመት መጀመሪያ ደካማ የሚባል አቋም ማሳየቱን ተከትሎ «የአንድ ውድድር ዓመት አንበሳ» በሚል በበርካታ ወገኖች ትችት ቢሰነዘርበትም፣እያደር ብቃቱን በማረጋገጥ በብቃቱ የማይዋዝቅ ስለመሆኑ አስመስክሯል። በእግር ኳስ ጥበብ ልህቀቱ ዓለምን ያስደመመውና ሁልጊዜም ግብ ማስቆጠር የማይሳነው ሳላህ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ክለቡ ሊቨርፑል የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ከፍ አድርጎ እንዲስም የላቀ ሚና ተጫውቷል። በግሉም ፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ግብ አግቢነት ክብርን በመቀዳጃት የወርቅ ጫማውን አጥልቋል። በአሁኑ ወቅት በዘመናዊ እግር ኳስ ከሚጫወቱ ከፊት መስመር ተጫዋቾች ተመራጭ መሆኑ የሚመሰከርለት ሳላህ፤ የእግር ኳስ ጥብብ ችሎታውን ያህል ዓለም ስለእርሱ የምትዘምረው በጣም ዝቅ ባለ ድምፅ ስለመሆኑም ይገለጻል። ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውጪ በአሁኑ ወቅት በሌላ ማዕዘን በማንፀባረቅ ላይ ከሚገኙ ጥቁር ኮከቦች መካከል ስሙ ጎልቶ የሚነሳው ሌላኛው ተጫዋች ኒኮላስ ፔፔ ነው። በፈረንሳዩ ክለብ ሊል ድንቅ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ የሚገኘው አይቮሪኮስታዊው ኮከብ ፤ባሳለፍነው የውድድር ዓመት 19 ግቦችን ሲያስቆጥር፤11 ለግብ የተመቻቹ ኳስችን ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል ችሏል። «እርሱን በተቃራኒ መለያ መግጠም እጅግ አድካሚና ፈታኝ ስለመሆኑ ብዙዎች የሚመሰክሩለት የ23 ዓመቱ ፔፔ፤ክለቡ በፈረንሳይ አንደኛ ሊግ በሁለተኝነት እንዲጨርስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በፈረንሳይ ሊግ አንድም «ምርጡ የአፍሪካ ተጫዋች ነህ» የሚል ክብር ተቀዳጅቷል። የተጫዋቹ ወቅታዊ ብቃትም የበርካታ ወገኖችን አድናቆት እንዲያገኝ ከማስቻሉ በተጓዳኝ የታላላቅ የአውሮፓ ክለቦችን ቀልብም እንዲሰርቅ አርጎታል። ተጫዋቹም በቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ እንግሊዝ በማቅናት ሊቨርፖሎችን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል። ሞሮኮአዊው ሀኪም ዚያችም በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ምርጥ ተጫዋቾች ባለቤት ስለመሆኗ እያስመስከረ የሚገኝ ወጣት ኮከብ ነው። በሆላንዱ ክለብ አያክስ በሚያሳየው ድንቅና ውበት ያለው እግር ኳስ ችሎታው የበርካቶችን ቀልብ በቀላሉ ያገኘው ዚያች፡፡ ክለቡ የኤርዲቪዜዎን ዋንጫ እንዲያነሳ የላቀ ሚና ተጫውቷል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት 21 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ 24 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አመቻችቶ አጋርቷል።ይህም የክለቡ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርንም አስግኝቶለታል። አሁኑ ላይ በርካታ ክለቦች ተጫዋቹን በዓይነ ቁራኛ በመከታተል የተጠመዱ ሲሆን፤ ተጫዋቹም ስሙ ከአርሰናል ጋር በጥብቅ እየተዛመደ ይገኛል። ሴኔጋል ዳካር ውስጥ የተወለደው የ27 ዓመቱ ተጫዋች ምቤይ ዲያን በቱርክ ሊግ ገናና ስሙን እየገነባ ነው። በውድድር ዓመቱ 29 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 30 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ የቻለ ሲሆን፣ ይህ የግብ የማስቆጠር ብቃቱ ሲመዘንም በእያንዳንዱ 81 ደቂቃ አንድ ግብ ማስቆጠር እንደሚችል አረጋግጦለታል። በቱርክ ሱፐር ሊግ ለጋላታ ሰራይ የሚጫወተው ኮከብ፤ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ክለቡ ካስቆጠራቸው ግቦች መካከል 45 በመቶ የሚሆኑት ከእርሱ እግር ስር የወጡ ስለመሆናቸውም ተመላክቷል። ተጫዋቹ ለአራት ዓመት የሚያቆየው የውል ስምምነት ከኢስታንቡሉ ኃያል ክለብ ጋር ቢኖረውም፣ በርካታ አውሮፓውያን ኃያላን ክለቦችም ተጫዋቹን የግላቸው ለማድረግ አሰፍስፈዋል። በጀርመን ቡንደስሊጋ ለሆፈኒየም የሚጫወተው አልጄሪያዊው ኢሻክ ቤልፎዲልም፣ በአሁኑ ወቅት በድንቅ እግር ኳስ ችሎታቸው ዓለምን ማነጋጋር ከጀመሩ አፍሪካውያን ኮከቦች አንዱ ነው። ተጫዋቹ ባሳለፈነው የውድድር ዓመት ለክለቡ 28 ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ ዕድል አግኝቶ 16 ግቦችን ከመረብ አዋህዷል። አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለጓደኞቹ አመቻችቶ አቀብሏል። የተለያዩ የሜዳ ላይ ኃላፊነቶችን በብቃት የሚወጣውና «የትም ቦታ ተሰልፎ ቢጫወት ግብ ማስቆጠር አይከብደውም» የሚባልለት ኮከብ፤በቡንደስሊጋው ከፍተኛ ግብ ካስቆጠሩ ሦስት ተጫዋች መካካል ስሙን አፅፏል። በቤልጂየም ሊግ ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ የሚገኘው ሌላኛው አፍሪካዊ ኮከብ ማብዋና ሳማታ ነው። ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ውስጥ የተወለደው ተጫዋቹ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ለከለቡ 28 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 20 ግቦችን በስሙ አስመዝገቧል። የቀድሞው የአርሰናሎች ምልክት ቴሪ ዳንኤል ሄነሪ አድናቂ የሆነው ተጫዋቹ፣ በቅርቡ በቤልጂም ሊግ ከተከሰቱ አፍሪካውያን ተጫዋቾች መካከል ‹‹አንተ ምርጡ ነህ» በሚል የኮከብነት ክብር ማግኘት ችሏል። የሚገባቸውን ያህል ክብርና እውቅና ማግኘት ባይችሉና በምዕራባዊያኑ ተፅእኖ ስር ለመደበቅ ቢገደዱም በአሁኑ ወቅት እነዚህ የአህጉሪቱ እግር ኳስ ጥበበኞች በዓለማችን ታላላቅ ሊጎች አገራቸውንና ስማቸውን ከፍ አድርገው እያስጠሩ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሰኔ 25/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13415
0a32546d2dc29b98922abdf668579bd4
9a596f852833f52f5e8b5742265b6392
ጥንቃቄን የሚሹት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለቱ ሳምንታት
የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፍጻሜውን ሊያገኝ የሁለት ሳምንታት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል። ሊጉ ከወርሃ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ቆይታን አድርጓል። በብዙ ውጣ ውረዶች በመታጀብ ከፍጻሜ አፋፍ ላይ መድረስ ችሏል። በውድድር ዓመቱ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ተያይዞ የነበረው ውጥንቅጥ የስፖርቱን መልክ አጉድፈውት የተጓዙ ሳንካዎች ነበሩ። በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እየማቀቀ ያለው እግር ኳሱ በተለይ በዘንድሮው የውድድር መድረክ አውዱን ቀይሮ የፖለቲካ አጀንዳ ማራመጃ እስከመሆን የተጓዘም ነበር።በእግር ኳስ ጨዋታዎች የተዋጣለት ፉክክር ከመመልክት ይልቅ ወደ አምባጓሮና ወደ ግጭት የሚያመሩ ስሜቶች በስፋት ተንጸባርቆበታል። የስፖርቱን ህልውና ፈታኝ ምዕራፍ እስከ ማድረስ በተጓዘ ችግር ውስጥ በመሆን ለሻምፒዮናነት የሦስት ክለቦች እጆች ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎችን ይጠብቃሉ። እነርሱም የዘንድሮው የሊጉ አዳጊ ክለብ መቐለ ሰባ እንደርታ፣ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ናቸው።የመሪነቱን ጉዞ ፋሲል ከነማ እና መቐለ ሰባ እንደርታ በእኩል 53 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ ተበላልጠው መሪና ተመሪ ሲሆኑ፤ ሲዳማ ቡና በ52 ነጥብ ጥሩ ተከታይ ሆኗል። የውድድር ዓመቱን ሻምፒዮናነት ክብርን ለማግኘት በሚደረገው ግስጋሴ ላይ አዲስ መልክ እንዲኖር ያደረገው 28 ኛው ሳምንት፤ በተለይ ፋሲልና መቐለ ከነማን ፍጥጫ ከፍ እንዲል ያደረገው ነበር። በ28 ኛው ሳምንት ፋሲል ከነማ ነጥብ መጋራቱን መቐለ ደግሞ ማሸነፍን ተከትሎ ለሻምፒዮናነት የሚደረገው ፍጥጫ እንዲካረር ያደረገው አጋጣሚ ተፈጥሯል።ባሳለፍነው እሁድ ወደ አዳማ ያቀናው ፋሲል ከነማ ከባለሜዳው አዳማ ጋር 1 ለ 1 በመለያየት አንድ ነጥብ በመያዝ ተመልሷል። ፋሲል በጨዋታው ከእረፍት በፊት ሙጂብ ቃሲም በፍጹም ቅጣት ምት በማስቆጠር የሻምፒዮናነት ክብር ግስጋሴው ከፍ ያለ ተስፋ የታየበት ቢመስልም፤ባለሜዳዎቹ አዳማ ከነማ ከእረፍት መልስ ቡልቻ ሱራ በግንባሩ በመግጨት አቻ አድርጓቸዋል። ይሄንኑ ተከትሎ የተጠበቀው የፋሲል ከነማ ተስፋ ሊናድ ግድ ብሎታል።ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 53 ከፍ ማድረግ ቢችልም፤ የመቐለ ሰባ እንደርታ ደቡብ ፖሊስን መርታትን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ሻምፒዮናነቱን ቀድሞ ለማረጋገጥ የነበረው ግስጋሴ ተጨናግፎበታል። በ28 ኛው ሳምንት ደቡብ ፖሊስን በሜዳቸው ያስተናገዱት መለቐ ሰባ እንደርታዎች 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ ሦስት ነጥብ ማግኘት የቻለ ሲሆን፤ ከፋሲል ከነማ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት እኩል በማድረግ የሻምፒዮናነት ግስጋሴውን እጅግ አጓጊ መልክ እንዲኖረው አስችሏል። ክለቡ በጨዋታው ያስቆጠራቸውን አራት ግቦች ጋናዊው አጥቂ ኦሴይ ማውሊ ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤልና ያሬድ ብርሃኑ አንድ አንድ ግብ አስቆጥረዋል።ክለቡ ተጋጣሚው ላይ የወሰደው የግብና የጨዋታ የበላይነት ከፊት ለፊቱ ያሉትን ሁለት ጨዋታዎች በድል የመወጣት አቋም እንዳለው የፈተሸበት መሆኑን ተመላክቷል። ከፋሲል ከነማ በእኩል 53 ነጥብ ተቀምጦ በግፍ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። 52 ነጥብ በመሰብሰብ በአንድ ነጥብ ተበልጦ ሦስተኛ ደረጃን የያዘው ሲዳማ ቡና በ28 ኛው ሳምንት ድሬዳዋ ከተማን በመርታት ሦስት ነጥብ ከመሪዎቹ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 1 ዝቅ እንዲል ማድረግ ችሏል።የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሊግ ኮሚቴ ባስቀመጠው የውድድር መርሃ ግብር መሠረት 29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ የ30 ሳምንትና የመጨረሻው ጨዋታዎች ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሄዳል። በዚህ መሠረት አጼዎቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ስሁል ሽረ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የአጼዎቹን እግር የሚከተለው መቐለ ሰባ እንደርታ በበኩሉ ከድሬዳዋ፣ ከመከላከያ የሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታዎች ከፊት ለፊቱ የሚጠብቁት ይሆናል።መሪው ፋሲል ከነማ በ29 ኛው ሳምንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርገው ጨዋታ በእጅጉ ፈታኝ እንደሚሆን ተጠባቂ ሆኗል። በፕሪሚየር ሊጉ የሻምፒዮናነት ታሪክ ውስጥ ግዙፉን ድርሻ የያዘው ሳንጃው ለአጼዎቹ እጁን በቀላሉ እንደማይሰጥ ከወዲሁ መላምቶች ይሰማሉ። በሌላ ወገን ደግሞ የሻምፒዮናነት ፍላጎትንና ወኔን የታጠቁት አጼዎቹ ሳንጃውን በመርታት የተመኙት የሻምፒዮናነት ዘውድን ለመጫን የሚዋደቁ መሆኑን ተከትሎ የጨዋታው አሸናፊነት ግምት እንዲሰጣቸው አድርጓል። አጼዎቹ በ29 ኛው ሳምንት የሚኖራቸው ነጥብ ተከትሎ የመጨረሻው ምዕራፍ በሆነው 30ኛው ሳምንት ላይ ላለመውረድ ከሚታገለው ስሁል ሽረ ጋር ወሳኙን የሜዳ ላይ ቆይታ የሚያደርጉ ይሆናል።ከአጼዎቹ ጋር አንገት ለአንገት የተያያዘው መቐለ ሰባ እንደርታ በ29 ኛው ሳምንት ላለመውረድ ከሚጫወተው ከመከላከያ ጋር ይጋጠማል። መቐለ በዚህ ጨዋታ በቀላሉ ሙሉ ነጥብ ይዞ ለመውጣት ፈተና እንደሚገጥመው ይገመታል። መከላከያ ከሊጉ ላለመውረድ የሚያደርገው የሞት የሽረት ትግል የመቐለን የሻምፒዮናነት ግስጋሴን ሊገታ እንደሚችል በማስረጃነትም ቀርቧል። የመውጣትና የመውረድ ስሜትን በያዘው በዚህ ጨዋታ ውጤት ተንተርሶም በ30 ኛው ሳምንትን ከድሬዳዋ ጋር በሚኖረው ጨዋታ የሻምፒዮናነት ዕጣ ፈንታው የሚለይ ይሆናል። የሻምፒዮናነት ሚዛንን የተሸከመው ሲዳማ መውረዱን ካረጋገጠው ደደቢት ጋር 29 ኛ ሳምንት ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን፤ በጨዋታው ሙሉ ነጥብ ይዞ ለመመለስ ሰፊ ዕድል እንደሚኖረው ይገመታል። ምናልባትም በጨዋታው ካሸነፈ በ30ኛው ሳምንት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር በሚኖረው ጨዋታ አሸንፎ ሻምፒዮና የመሆን ወኔን እንዲይዝ የሚያደርገው አጋጣሚ ይሆናል።በአጠቃላይ የፋሲል ከነማና መቐለ ሰባ እንደርታ የነጥብ እኩልነትና የሻምፒዮናነት ግስጋሴ ትንቅንቅ ከወዲሁ አነጋጋሪና ጥንቃቄን የሚሻ መሆኑን የስፖርት ቤተሰቡ ስጋቱን እየገለጸ ይገኛል። እግር ኳሱ አውዱን ቀይሮ ፖለቲካዊና ብሔርን ወካይ ከሆነ የሰነበተ መሆኑን ተከትሎ፤ ጨዋታዎች ከዳኘነት ጋር ተያይዞ ጥንቃቄን የሚሹ እንደሆኑ ተገልጿል። ባለሜዳ ቡድኖች ዳኞች፣ ተጋጣሚ ተጫዋቾች እና ከእንግዳ ቡድን ደጋፊዎች ጋር የሚኖራቸው ሰላማዊ ግንኙነት አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅት ሊደረግ ይገባል። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ ክልሎችና የጸጥታ አካላት ቀሪዎቹን ጨዋታዎች በንቃትና ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት በሰፈነ መልኩ እንዲከናወኑ ከማድረግ አኳያ ከባድ ኃላፊነት እንዳለባቸው ቀድመው መረዳትና መዘጋጀት ሌላው መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ ይሁን። የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን ለሻምፒዮናነት በሚደረገው ግስጋሴ ውስጥ ደግሞ ደቡብ ፖሊስ በሃያ ስምንት ነጥቦች አስራ አራተኛ፤ ስሁል ሽረ በሃያ ሰባት ነጥቦች አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በአስራ ሦስት ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ በመያዝ፤ ለመውረድና ለመውጣት የሚያደርጉት እልህ አስጨራሽ ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል። በሌላ በኩል የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቀሌው አማኑኤል ገብረሚካኤልና የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ አምስት ግቦች አንደኛና ሁለተኛ ሲሆኑ፣ የፋሲሉ ሙጂብ ቃሲም በአስራ አራት ግቦች ሦስተኛ ደረጃን ይዟል።አዲስ ዘመን ሰኔ 26/2011 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13493
0ff83f6f42abe2c89a2c376babb8c052
5fa632e088eb300de7df74b39f53f8e4
አካዳሚውምርጥ ስፖርተኞችን የማፍራት ተልዕኮውን እያሳካ መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ ምርጥ ስፖርተኞች የማፍራት ተልዕኮውን እያሳካ መሆኑን ተገለጸ። ለአራት ዓመታት በ9ኝ የስፖርት ዓይነቶች በአሰላ ጥሩነሽ ዲባባ እና በአዲስ አበባ የማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን 105 ስፖርተኞችም በትናንትናው ዕለት አስመርቋል።የአካዳሚው ዋና ዳይሬክተር አቶ አንበሳው እንየው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ አካዳሚው ምርጥ ስፖርተኞች የማፍራት ተልዕኮውን እያሳካ ሲሆን ውጤታማነቱ ሰልጣኞች በሚያስመዘግቧቸው ውጤቶች የሚለካ ነው። አካዳሚው ፓራሊምክን ጨምሮ ሥልጠናውን በሚሰጥባቸው አስር የስፖርት ዓይነቶች ከአገር አቀፍ ውድድሮች ባሻገር፤ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተመልምለው በአህጉርና በዓለም አቀፍ መድረኮች መሳተፍ የቻሉ በርካታ ስፖርተኞች ማፍራት እንደተቻለው ገልጸዋል። በዘንድሮው ዓመት በነበሩ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች በመሳተፍ የነበራቸው ውጤታማነት ለዚህ እንደ ማሳያ የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል።እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ፤ በዚህም መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስት ሺ ሜትር መሰናክል በራባት ሞሮኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ አንደኛ የሆነው የኢትዮጵያ የርቀቱ ባለ ክብረ ወሰን ጌትነት ዋሌ፣ በሁለት ሺህ መሰናክል እና በ4 ኪሎ ሜትር ሀገር አቋራጭ ዘንድሮ ቦነስ አይረስ ላይ በተካሄደው የዓለም የታዳጊዎች ኦሎምፒክ የወርቅ ባለቤት የሆነው አብርሃም ስሜ፣ በማራካሽ ሞሮኮ በ4 ኛው ኢንተርናሽናል ፓራሊምፒክ አትሌቲክስ ውድድር የተሳተፈው ገመቹ አመኑ በ1 ሺ500 ሜትር ወርቅ፣ በ 800 ሜትር ነሐስ ማምጣት ችሏል። ዝናሽ አሰፋ በዚሁ መድረክ በ200 ሜትር እና በ400 ሜትር ወርቅ አስመዝግባለች።በዓለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ መድረኮች የአካዳሚው ፍሬ የሆኑ ስፖርተኞች እያስመዘገቡ የሚገኙት ውጤት አካዳሚው ከተቋቋመበት አላማና ራዕይ እኩል እየተጓዘ ስለመሆኑ ምስክር መሆኑን አመልክተዋል። አካዳሚው ባለፉት አራት ዓመታት በ9ኝ የስፖርት ዓይነቶች በአሰላ ጥሩነሽ ዲባባ እና በአዲስ አበባ የማሰልጠኛ ማዕከል ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን 105 ስፖርተኞችንም እንዳስመረቀ ተናግረዋል።ተመራቂዎቹ ሥልጠናቸውን ላለፉት አራት ዓመታት ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸው፤ ተመራቂዎቹ ለጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል 7ኛ ዙር 49 ሰልጣኞች ሲሆኑ ለአዲስ አበባ ካምፓስ ደግሞ የ 3 ኛ ዙር 56 ሰልጣኞችን መሆናቸውን አብራርተዋል። ሥልጠናውና ምርቃቱ በሀገሪቱ ቀጣይ የስፖርት ውጤታማነት ላይ ጉልህ ድርሻን እንደሚጫወቱ እምነታቸውን ገልጸዋል።የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ርስቱ ይርዳው በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአካዳሚው ላለፉት አራት ዓመታት ያገኛችሁትን እውቀት፣ ክህሎት እና ስፖርታዊ ሥነ ምግባር በምትቀላቀሏቸው ክለቦች እና ተቋማት ይበልጥ ልታጠናክሩ ይገባል። ተመረቃችሁ ማለት የነገ ተስፋ መሆናችሁ አመላከታችሁ እንጂ ምርጥ ስፖርተኞች የመሆን ጉዟችሁ አጠናቀቃችሁ ማለት አይደለም። የስፖርት ሥልጠና እና የመደበኛ ትምህርት ጉዞአችሁ በምትቀላቀሏቸው ክለቦ፣ የስፖርት እና ሌሎች ተቋማት ዘንድ ከፍ ወዳለ እርከን ልታደርሱት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ በ2006 ዓ.ም እንዲሁም የጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል በ2002 ዓ᎐ም ሥራ መጀመራቸው አይዘነጋም።አዲስ ዘመን ሰኔ 26/2011 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13496
d326c5d95769b7990da5b387ffa48af8
c19d28341ab07707ef2740c4af380372
‹‹ሙሌቱ ለነባርም ሆነ ለአዳዲስ ኢንቨስተሮች ከፍተኛ የሞራል ስንቅ ይሆናል››አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ
 አዲስ አበባ፦ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ፕሮጀክቶቻቸውን እንዲያስፋፉና አዳዲሶቹም ወደ አገሪቱ እንዲያማትሩ ከፍተኛ የሞራል ስንቅ እንደሚሆን ጀግናው አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረ ስላሴ ተናገረ፡፡ሙሌቱን አስመልክቶ የጋዜጣው ሪፖርተር ያነጋገረው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማራው ጀግናው ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ፣ ህዳሴ ግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት የታላቅ ድል መጀመሪያ ነው፣ በተግባሩም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል›› ብሏል፡፡የውሃ ሙሌቱ የኤሌክትሪክ ሃይል ማግኘት ፈተና በሆነበት አገር በተለይ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለቀጣይ ስራዎች ስንቅና ማበረታቻ እንደሚሆን ያመላከተው ሃይሌ፣ የሙሌቱ ብስራት ‹‹ነገ ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ የሃይል ችግር ፈተና ሆኖ እንዳይቀጥልና እኔ እና ሌሎችም በርካታ ኢንቨስተሮች ካለ ጭንቀት በልበ ሙሉነት ስራችንን እንድንቀጥል መተማመኛ የሚለግስ ነው›› ብሏል። አገሪቱም የውስጥ ፍላጎትን ከማርካት በተጓዳኝ በሽያጭ መልክ ለሌሎችም እንድትተርፍና ተጠቃሚነቷን እንድታጎለብት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝቧል፡፡‹‹እንደ አንድ የአትሌቲክስ ስፖርተኛ በጥሩ ብቃት ከአንድ ኦሎምፒክ ወደ ሌላ ኦሎምፒክ ከአንድ ድል ወደ ሌላ ድል፣ ከአንድ ክብረ ወሰን ወደ ሌላ ክብረ ወሰን መተላለፍ አለብን›፣ ህዳሴ ላይ የፈፀምነው ገድል መንደርደሪያችን እንጂ መቋጫችን ባለመሆኑ በተግባሩ ሳንኩራራ ሁለተኛውንም ሶስተኛውንም ሙሌት ማፋጠን እና እስከመጨረሻው በመዝለቅ በሙሉ አቅም ኤሌክትሪካችንን ማመንጨት ይገባናልም›› ብሏል፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በህገወጦች የሚፈፀሙ ተግባራት መሰል የደስታ ዜናዎችን እንደሚያደበዝዙ የጠቆመው ሃይሌ፤ የህገወጦቹ ተግባር የአገሪቱን ገፅታ የሚያበላሽ በተለይ ኢንቨስተሮችን ተስፋ የሚያስቆርጥ እንደመሆኑ ሊታረም እንደሚገባም አስገንዝቧል፡፡መንግስትም በህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩትን በቃችሁ በማለት ህግ የማስከበር ኃላፊነቱን በአግባቡ መፈፀም እንዳለበት አፅንኦት የሰጠው ሃይሌ፤ ይህ እስካልሆነም ግድቡን ጨምሮ ሌሎች ፕሮጀክቶች ኪሳራ እንደሚሆኑ መረዳት አግባብ መሆኑንም አመላክቷል፡፡በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚከሰት ሁከት ለጥፋት ከመነሳት ይልቅ ቆም ብሎ የሚያስብና “ለምን” የሚል የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚያወድም ሳይሆን የራሱ መሆኑን በመረዳት የሚጠብቅና የሚንከባከብ ትውልድ መፍጠር እንደሚያስፈልግም አፅንኦት ሰጥቶታል፡፡የህዳሴ ግድቡ ትሩፋት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ተጠቃሚ የሚያደርግና ጥቅሙም ለመቶና ለሁለት መቶ አመት የሚዘልቅ እንደመሆኑ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚሉ አንዳንድ አካላትም በዚሁ አቋማቸው ዙሪያ ቆም ብለው ማሰብ እንደሚገባቸውም አመላክቷል፡፡የኢትዮጵያውያን የጋራ አሻራ የሆነውን ታላቁ የህዳሴ ግድብ መደገፍ የምርጫ ሳይሆን የግዴታም ጉዳይ በመሆኑ ከቀደመው በበለጠ የሁሉም ተሳትፎ መጠናከር እንዳለበትና ህዝቡም ሆነ ባለሀብቶች የጀመሩትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸውም አትሌት ሃይሌ ጥሪ አቅርቧል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012ታምራት ተስፋዬ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35871
e694b2481e6f90cda55bc0a7c7837b6c
a1bd21ac55738d44ddaecd0f3c97d67b
አባይን በሀገሩ ያሳደሩ አርበኞች ድልና ተስፋ
 አዲስ አበባ፡- አባይን በሀገሩ ለማሳደር የዘመቱት አርበኞች የላባቸውን ዋጋ ፣ የእጆቻቸውን የስራ ውጤት ማየት በመጀመራቸው በጉባ ተራሮች ግርጌ ታላቅ ደስታና ፈንጠዝያ ፈጥሯል። ዓይናቸው የውሃ ሙሌቱ ከፈጠረው አዲስ መልክዓ ምድር ጋር እየተለማመደ ነው። ተራሮች ደሴት ፈጥረዋል። አባይ በተራሮች ግርጌ ተነጥፏል፤ አንዳንዴም ከወዲህ ወዲያ እየተንሸራሸረ የመኖሪያውን ጓዳ ጎድጓዳ ይጎበኛል። አንዳንዴም በግድቡ አናት ላይ ካልዘለልኩ ይላል። ግን አይዘልም፤ በሀጋሩ ልጆች ሙያና ፋይናንስ ትብብር አባይ በሀገሩ አድሯል ይላሉ በህዳሴው ግድብ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ አርበኞች። ኢንጂነር ታደሰ መልሰው ከወሎ ዩኒቨርሲቲ በመካኒካል ምህንድስና ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ለተከታታይ አራት ዓመታት በህዳሴው ግድብ ላይ ሲሰራ ነበር። ኢንጂነር ታደሰ ይህን በሚያክል ሜጋ ፕሮጀክት ላይ በተለይም በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ አሻራውን በማሳረፉና በሙያው አስተዋጽኦ ማበርከቱ ደስተኛ አድርጎታል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ግድቡ ውሃ ተሞልቶ ሲመለከት ደስታውን የሚገልጽበት ቃላት አጥሮታል። ተጨባጭ ውጤት ማየቱም ቀሪውን ስራ ለመስራት ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሆነው ይገልጻል። ልክ እንደ እርሱ ሰራተኛው በሙሉ በደስታ ማዕበል ውስጥ እየዋኘ መሆኑን የጠቀሰው ኢንጂነር ታደሰ፤ በተለይም የውጭ ሃይሎች የውሃ ሙሌቱን ለማደናቀፍ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉ ትልቅ ድል ነው ይላል። የህዳሴው ግድብ የኤሌክትሪክ ፣ የመስኖና የዓሳ እርባታ ፍላጎትን ከማርካት ባለፈ ካለው አቀማመጥ አንጻር የቱሪስት መስህብና ልዩ የመዝናኛ ቦታ መሆን እንደሚችል ያለውን ተስፋም አመላክቷል። ውሃ መያዝ ተጀመረ ማለት ተስፋችን እውን ሆነ ማለት እንደሆነም ጠቅሷል። ኢንጂነር አበባው ይሁን በኤሌክትሪካል ምህንድስና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተመርቆ በህዳሴው ግድብ መስራት ከጀመረ አራት ዓመታን አስቆጥሯል። በሃይድሮ ኤሌክትሪክ ስቲል ስትራክቸር ስራ ውስጥ ሴፍቲ ኦፊሰር ሆኖ በመስራትም ላይ ይገኛል። የህዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊም ሆነ አሻራውን በግድቡ ላይ እንዳሳረፈ ሙያተኛ ወደር የሌለው ደስታ እንደፈጠረበት ይገልጻል። ለዘመናት ብዙዎች ሲቆጩበት የነበረውን የአባይ ወንዝ እጅ ካሰጡ አርበኞች መካከል አንዱ መሆኑና ‹‹ አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል›› የሚለውን ምሳሌዊ አነጋገር ታሪክ ያደረገ ስራ መስራቱ እንደሚያኮራውም ይናገራል። የህዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌት በተለይም በግድቡ ስራ ላይ ለተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል እንደሆነ የገለጸው ኢንጂነሩ፤ የውሃው ሙሌቱን ለማደናቀፍ ሲሯሯጡ ለነበሩትም ተስፋ ያስቆረጠ ነው ብሏል። በበረሃው ሀሩር ላቡን እያንጠፈጠፈ ሲሰራ ለነበረው ሰራተኛ ሳምንቱ የተለየ ወቅት እንደነበር የጠቀሰው ኢንጂነር አበባው፤ የውሃው ሙሌቱ የአካባቢውን መልክዓ ምድር ወደ ገነት የቀየረና የመጪዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ ያሳየ ነው ይላል። ከምንም በላይ ፕሮጀክቱ በእቅዱ መሰረት ስራዎችን ማከናወኑ ለቀጣይ ስራዎች ሰራተኞችን የሚያነሳሳ መሆኑንም ይጠቅሳል። በጉጉት ለሚጠብቀው የኢትዮጵያ ህዝብም ትልቅ የምስራች እንደሆነ በማስረዳት። የውሃ ሙሌቱ የፈጠራቸው ደሴቶች ቀልብን የሚስቡ መሆናቸውና በረሃማው መልክዓ ምድርም ወደ ልምላሜና ነፋሻማነት የመቀየር እድሉ የሰፋ እንደሆነ የጠቀሰው ኢንጂነር አበባው፤ የተፈጠረው ሃይቅ ለበርካታ አገልግሎቶች የሚውል እንደሆነም ይጠቅሳል። ኢትዮጵያ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ወደ ጎን ትታ በመርሃ ግብሯ መሰረት ሙሌቱን ተፈጻሚ ማድረጓ ዛሬም እንደ ጥንቱ ሉአላዊነቷን፣ መብቷንና ክብሯን ያስጠበቀች ሀገር እንድትሆን አድርጓታል። የህዝቦቿንም ተስፋ አለምልሟል ይላል። ህዳሴው ግድብ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሰው ኢንጂነር አበባው፤ ህዝቡ ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠል ህልሙን እውን ማድረግ ይኖርበታልም ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 16/2012 ኢያሱ መሰለ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35855
93a01e131875cf2d54b99bec4ff9c805
dd5ad1e11cd0afe49e44af8f36a9ddb5
በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም እስካሁን ከ3ነጥብ5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል
አዲስ አበባ፡- ዘንድሮ በተጀመረው የአምስት ቢሊዮን ችግኞች ተከላ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም እስካሁን ከ3ነጥብ5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያትኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለጹ፡፡ኢትዮጵያውያን የጋራ ቤታቸውን በጋራ መገንባት ላይ በማተኮር የጀመሩትን ድል ለማስቀጠል እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡አቶ ንጉሱ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ሂደትን አስመልክተው ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ዘንድሮ በተጀመረው የአምስት ቢሊዮን ችግኞች ተከላ የአረንጓዴ አሻራ እስካሁን ከ3ነጥብ5 ቢሊዮን  በላይ ችግኞች መተከላቸውን ፤ ቀሪ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ገደማ ችግኞችም ካለው ምቹ ሁኔታ አኳያ በቀሪ ጊዜያት እንደሚተከሉ አስታውቀዋል ፡፡ መርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመነጩት ሀሳብና በባለቤትነትም የሚመሩት እንደመሆኑ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ተገኝተውም ተክለዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የተተከሉትንም አርአያ ለመሆን ሲንከባከቡ ቆይተዋል ብለዋል ። በዚህ ዓመት ደግሞ ይህ ስራ ሲሰራ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴን ግድብ ለመጀመሪያ ጊዜ ውሃ ሙሌት ማከናወን እንደተቻለም አስታውቀዋል ፡፡ በዚህ ወቅት የሚተከለው ችግኝ አንደኛ፣ የአየር ንብረቱን በማሻሻል በቂና ተመጣጣኝ ዝናብ እንዲገኝ የሚያስችል ሲሆን፤ ግድቡ በደለል እንዳይሞላ የሚያደርግ ነው፡፡ ችግኝ መትከል ደግሞ የአስር ዓመቱ የአረንጓዴ ልማት እቅዱ አንድ አካል የተደረገ እንደመሆኑ አረንጓዴ ልማቱን እውን ለማድረግ ይሄን ስራ አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡“አሁን የምንገኘው በደስታ ላይ ነው” ያሉት አቶ ንጉሱ፤ የደስታ ምንጩ ደግሞ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ውሃ በመያዝ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዓባይን ወደ አገሩ እንዲመለከት የሚያደርግ፤ ከአገር ውስጥ አልፎም ለታችኛው ተፋሰስ አገራት ለልማት የሚጠቅም እና  ኢትዮጵያ ዓባይን ተመልካች ብቻ ሳትሆን ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንድትሆን ያስቻለ ታሪክ የጻፍንበት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡ ወቅቱም ይሄ ታሪክ የተጻፈበት የደስታ ወቅት ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን ማለት እወዳለሁ፤ በማለት የደስታ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ አንደኛ፣ ግድቡን ማጠናቀቅ ይጠበቅብናል፡፡ ሁለተኛ፣ በዲፕሎማሲው መድረክም በትክክል ኢትዮጵያን ግብጽና ሱዳን ብቻ ሳይሆኑ ሌላውም ዓለም እንዲረዳት በማድረግ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት መብታችንን ማስከበር እና ይሄንን የማስገንዘብ ትልቅ ኃላፊነት አለብን፡፡ ሶስተኛም፣ የገነባነውን ግድብ በደለል እንዳይሞላ አረንጓዴ ልማቱን ማፋጠን ይኖርብናል፡፡ ለዚህ ደግሞ የእርከን ስራን ጨምሮ ችግኝ ተከላውን በማፋጠን ያስቀመጥነውንም ግብ ማሳካት ይኖርብናል ሲሉም አሳስበዋል፡፡ግድቡንም በገንዘብም በሞራልም፣ በእውቀትም ተደጋግፈን ማጠናቀቅ፤ ከዛም ባሻገር ምሑራን፣ የህግ ባለሙያዎች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎችና ሌሎችም የዲፕሎማሲ ስራው ላይ የሚያደርጉትን ተጋድሎ በአገር ውስጥም በውጪም የምንኖር ኢትዮጵያውያን መደገፍና የበኩላችንን አስተዋፅዖ ማበርከት ይጠበቅብናል፡፡ የኢትዮጵያን ጥቅም፣ ትክክለኛ ፍላጎትና መብት በመግለጽ፤ የማስረዳት፣ የመከራከርና የመሟገት እና ለፍትህ የመቆም ስራ መስራት አለባቸው፡፡ በችግኝ ተከላው ተሳትፎም ታሪክ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡እነዚህን ሁሉ ለማድረግ ግን የአገራችንን ሰላም መጠበቅ፤ አንድነታችንን ማስቀጠል እና በፍቅር በሰላምና በአንድነት ሊያጋጩን የሚችሉ ጥቃቅን ነገሮችን ወደጎን በመተው የጋራ ቤታችንን በጋራ መገንባት ይገባናል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012ወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35942
9bea146ff43d4e5799c75745abab8117
7e5c22c8201e68628b6d41e77587aa7b
‹‹ትህነግ የተለያዩ ማንነቶችን ጨፍልቆ አንድ ማንነት ለመገንባት እየጣረ ነው››አቶ አገዘው ህዳሩ የራያራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት
ህውሃት በትግራይ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማንነቶችን በመጨፍለቅ አንድ ማንነት ለመገንባት ጥረት እያደረገ መሆኑን የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አገዘው ህዳሩ አስታወቁ፡፡ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወት በኋላ የህወሃት አፈና መጠናከሩንም ገልጸዋል፡፡የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አገዘው ህዳሩ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት በትግራይ ውስጥ የተለያዩ ማንነቶች ያላቸው የራያ ፤የኩናማ ፤የሳሆ ፤የአገው እና የኢሮብ ሕዝቦች ቢኖሩም ሕውሓት እንደእርሳቸው አባባል ትህነግ ሁሉንም በአንድ ቅርጫት ውስጥ በመጨፍለቅ አንድ ማንነት ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡የራያ ህዝብ ከታሪክ አንጻር ትስስሩ ሰፊ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ራያ ከኦሮሞ ማህበረሰብ ፤ከአማራ፤ከአገው ጋር ውህድ ማንነት ያለው ሲሆን በታሪክ ሂደትም የራሱን ማንነትን የፈጠረ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ሆኖም ግን የራያንም ሆነ በትግራይ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ማንነቶችን ባለመቀበል ትህነግ በህዝቦች ላይ የተለያዩ በደሎችን በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡የራያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የራያ ማህበረሰብ የሚገኝበት አካባቢ በሙሉ እና በራያ ወረዳዎች የህዝቡን ማንነት እንዲገነባ ከምርጫ ቦርድ ፍቃድ የተሰጠው ቢሆንም ፓርቲው በራያ ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ በትህነግ በርካታ ማስፈራሪያዎችና ጥቃቶች እየደረሱበት መሆኑን አቶ አገዘው ያስረዳሉ፡፡ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲንና ሌሎች ትህነግን የሚቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ባንዳ የሚል ተቀጽላ በማውጣት የማሸማቀቅ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ አገዘው በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ 12 ከሚደርሱ ፓርቲዎች ውስጥም የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በግንባር ቀደምትነት ባንዳ ተብሎ መፈረጁንም ጠቁመዋል ፡፡የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በግንባር ቀደምትነት ባንዳ ተብሎ በህወሃት የተፈረጀበትንም ዋነኛ ምክንያትን አቶ አገዘው ሲስረዱ ‹‹ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠንክሮ ከወጣ ተመሳሳይ የማንነት ጥያቄ ያላቸው የአገው፤የኩናማ፤የሳሆ፤የውጅራትና የኢሮብ ማህበረሰቦች ትግላቸውን ማፋፋማቸው አይቀርም፡፡ስለዚህም የራያን የማንነት ጥያቄ ማፈን እና ጥያቄውንም የሚያነሱትንም እያሳደዱ ማጥፋት በዋነኝነት ትህነግ የሚከተለው ስልት ነው፡፡›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡በራያና አላማጣ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን የራያራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ደጋፊዎች ናችሁ በማለት የማንገላታትና በልዩ ልዩ የማሰቃያ መንገዶች ተማረው አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት የፓርቲው ፕሬዚዳንት የራያ ማንነትን የሚያቀነቅኑ ግለሰቦችን አድኖ ከመግደል አንስቶ የማህበረሰቡን ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦችን ስልታዊ በሆነ መንገድ የመግደልና የማጥፋት ስራዎችን ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሲከወን መቆየቱንም አብራርተዋል፡፡አቶ አገዘው አክለው እንደሚገልጹትም የራያ ማንነት ከዳር ለማድረስም ‹‹ስበር›› በሚል መጠሪያ ተደራጅቶ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርገውን ወጣት በገፍ በማሰርም ጥያቄውን ለማፈን ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ባለፉት ሁለት ዓመታት ስበር ባደረገው እንቅስቃሴም በመደናገጥ የተለያዩ የኃይል እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡ ከ17 በላይ ወጣቶች ተገድለዋል፡፡ከ2ሺ በላይ ወጣቶች አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡በአሁኑ ወቅትም ምርጫ እናካሂዳለን በሚል ቅስቀሳ ምርጫውን የሚያደናቅፍ ግለሰብም ሆነ ቡድን እርምጃ እንደሚወሰድበት በግልጽ እየዛቱ ነው፡፡በራያ ወረዳዎች ማለትም በጨርጨር፤በመሆኒ ፤አላማጣ፤ወፍላ ወረዳዎች በአንድ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ሰላሳ ሰዎችን በማዋቀር ህብረተሰቡን እንዲሰልሉ እየተደረገ ነው፡፡የተወሰኑት ተቃዋሚዎችን በእነሱ አጠራር ባንዳዎችን መንጥሮ የሚያወጣ ፤ሌላው ደግሞ ጸጉረ ልውጥ አሳሽ፤የተቀረው እነሱ እንጀምረዋለን ብለው የሚያስቡት ጦርነት ሲጀመር ምግብና ውሃ የሚያስተባብር ቀሪው ደግሞ ሙትና ቁስለኛ የሚያነሳ አድርገው አደራጅተውታል፡፡በተጨማሪም ትራንስፖርትና ሌሎች ሎጅስቲኮችን የሚያቀርብ ቡድንም የዚሁ አካል ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡በአጠቃላይ ትህነግ ተከበሃል በሚል ውዥንብር ወጣቱን ለጦርነት እየመለመለ ይገኛል፡፡በተለይም ከሃጫሉ ህልፈት በኋላ የትህነግ አፈና በእጅጉ መጨመሩንና በሃጫሉ ሞት የቀየሱት ሴራ ባለመሳካቱ ወደ ስልጣን እንመለሳለን ብለው ሲነዙት የነበረው ፕሮፖጋንዳ በመክሸፉ ሕዝቡም እንደታዘባቸውና ድጋፉንም እየነፈጋቸው መምጣቱን በመረዳታቸው ሙሉ ለሙሉ ከቁጥጥራቸው ሳይወጣ በአፈና እንዲገዛላቸው ለማድረግ እየሞከሩ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡አቶ አገዘው አክለውም ቀድሞውንም የሚቃወማቸውን አካባቢ እስከግድያ ድረስ የሚደርስ እርምጃ በመውሰድ ጸጥ ብሎ እንዲገዛና እንዲሸበርም ልዩ ኃይሎችንና ሚሊሺያዎችን በማዟዟር የጦር አቅማቸውን ለማሳየት እየሞከሩ ነው፡፡ይባስ ብሎም ለሚሊሺያው ቀለብ እንዲሰፍርና ለሚሊሺያው ደመወዝ ጭምር እስከ አምስት መቶ ብር ድረስ እንዲያዋጣ ግዴታ እየተጣለበት ይገኛል፡፡ገንዘብ የለኝም ያለ ጤፍና ስንዴ በመስፈር እንዲያስረክብ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡የቃለ መጠይቁን ሙሉ ሙሉ ሃሳብ በገጽ 6 ይከታተሉ፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012እስማኤል አረቦ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35937
ce2a207ff100b677034a44bdb9fb9a4a
9074ac2ef85731ee43a9d1352448665b
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የወደሙ ኢንቨስትመንቶች መልሰው እንደሚገነቡ አስታወቀ
አዳማ፡- የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ተከትሎ በተፈጸመ ሴራ የወደሙ ኢንቨስትመንቶች መልሰው እንደሚገነቡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ትናንት በአዳማ ከተማ ኦሮሚያ ሥራ አመራር አካዳሚ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ህልፈት ምክንያት በማድረግ በተፈጸመ ሴራ የወደሙ ኢንቨስትመንቶች መልሰው ይገነባሉ ብለዋል፡፡ መንግስት የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋትና ታፍኖ የኖረው ህዝብ እንዲተነፍስና ብሶቱን እንዲናገር የሰጠውን ነጻነትና ያሳየውን ትዕግስት ለዓላማቸው ማሳኪያ የተጠቀሙ ጸረ ሰላም ኃይሎች ጥፋት ማድረሳቸውን ጠቅሰዋል፡፡ እነዚህ ኃይሎች የኦሮሞን ህዝብ ስሜት ቀስቅሰው ክልሉን የጦርነት አውድማ ለማድረግ መሞከራቸውን የጠቀሱት ወይዘሮ ጫልቱ ያደረሱት ጥፋት ቀላል ነው ባይባልም ከውጥናቸው አንፃር ሲታይ ግን ጥቂት ነው ብለዋል፡፡ በተለይም ኢንቨስትመንት ለክልሉና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምን ያህል አስተዋጽኦ እያበረከተ እንዳለ የተረዱት እነዚህ ኃይሎች ሆን ብለው ባለሃብቱን ለማስበርገግና ዜጎችን ከስራ ለማፈናቀል አልመው መስራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በክልሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ የንግድና የኢንቨስትመንት ተቋማት እንደወደሙ የገለጹት ምክትል ፕሬዚዳንቷ እነዚህን የኢንቨስትመንት ተቋማት ለመገንባት የፌዴራል መንግስት ፣ የክልሉ መንግስትና ባለሃብቶች ተረባርበው ወደ ነበረቡት ይመልሷቸዋል ብለዋል፡፡ የክልሉ ህዝብ አቃፊ ፣ ስራ ወዳድና መልካም ሰብዕና እንዳለው የተናገሩት ፕሬዚዳንቷ የተፈጠረውን ክስተት እንደጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በሰዎች አዕምሮ ውስጥ መጥፎ ስዕል የሚስሉ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ባለሀብቱ ይህ ክስተት ለውጡን ለማደናቀፍና በአቋራጭ ወደ ስልጣን መምጣት በሚፈልጉ አካላት የተፈጸመ ድራማ መሆኑን ተረድቶ ያለምንም የስነ ልቦናና የጸጥታ ችግር ስራውን ማከናወን እንዳለበት አሳስበዋል:: በዘንድሮው ዓመትም በርካታ የኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች፣ መመሪያና ደንቦች ጸድቀው ወደ ስራ እንደተገባ የገለጹት ፕሬዚዳንቷ በመጪው ዓመትም በክልሉ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልግ ባለሃብት ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ክልሉ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ለነዋሪውና ለባለሃብቱ ዋስትና እንደሚሰጥና አሁን የተጀመረው ህግን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ፕሬዚዳንቷ ገልጸዋል፡፡ ኢንቨስትመንት ኢኮኖሚን ለማሳደግና የስራ እድልን በመፍጠር ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የጠቀሱት ወይዘሮ ጫልቱ አሁን የግል ባለሃብቱን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ ባለሃብቱም በሚሰራበት አካባቢ ካለው ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ መስራት እንዳለበትና ህዝቡ የፈሠሠው መዋዕለ ንዋይ የኔነው ብሎ እንዲያምን ማድረግ ይገባዋል ብለዋል፡፡ የሥራ ዕድል በመፍጠርም ይሁን ማህበራዊ አገልግሎት በመስጠት ህዝቡ የልማቱ ተጠቃሚ መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በክልሉ ለሚገኙ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች ልዩ ጥበቃ የማድረግ ስራ ለመተግበር እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውንም ፕሬዚዳንቷ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥፋት ላይ የተሰማሩ አካላትን እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አካላትን ተከታትሎ ለፍርድ በማቅረብ ህጋዊ እርምጃ የማስወሰዱ ስራ እንደተጀመረ ጠቅሰዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ በርካታ ባለሃብቶች የተሳተፉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ባንጸባረቁት ሃሳብም መንግስት የህግ የበላይነትን እንዲያስጠብቅና ላፈሰሱት መዋዕለ ንዋይም ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ በውይይቱ ላይ በክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የግብርና ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ እና የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ተመሳሳይ ሀሳቦችን አቅርበዋል፡፡ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሉ ጀልዴም የዓመቱን የኢንቨስትመንት ሥራ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎችን አሳይተዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012ኢያሱ መሰለ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35939
c18a3d5ca1607906c0f5b0687d5de9e2
86c4f1f2f3b4db38800229d82a7a1f4e
” ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ የላቸውም “ጄኔራል አደም መሐመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
 አዲስ አበባ፦ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ እንደሌላቸው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ አስታወቁ። የሰራዊቱ ወታደራዊ ቁመና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የሕዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ የሚያስችል እንደሆነም አመለከቱ። ጄኔራል አደም መሐመድ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከህግ ውጪ ሆኖ፤ በተለይ በሕዝቦች መካከል ቁርሾ በመፍጠር፤ ግጭት በመፍጠር፤ በሃይማኖትና በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች እየተፈረጁ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የሚደረጉ ሴራዎች ካሁን በኋላ ቦታ እንደማይኖራቸው አስታውቀዋል።ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ፤ ጎሳን ከጎሳ የሚያጋጩ ስራዎች ሆነ ተብለው የሚሰሩ ከሆነ፤ አድገው ወደ ዘር ማጥፋት፣ ወደ እልቂት የሚያመሩ በመሆኑ መንግስት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቀዋል ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ መንግስት እርምጃ መውሰድ ካልቻለ የመንግስትነት ተልዕኮው ምን ሊሆን ይችላል? እንደዚህ አይነት ጥፋቶች አድገው እንደ ሩዋንዳና ሌሎች አገሮች እንደሆኑት የሚጠብቅ ከሆነ ሕገመንግስታዊነቱ በምን ይገለጻል ሲሉም ጠይቀዋል ፡፡” ግልጽ መሆን ያለበት መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ እና አገርን የሚበትንና የሚያዳክም ማንኛውም ህገወጥ የሆኑ ተግባራትን እያየ ዝም አይልም ፡፡ ይህን ማስቆም በህገመንግስቱ የተሰጠው ኃላፊነት ነው ። የሰራዊቱም ተልዕኮ ይሄ ነው፡፡ መንግስትም ቢሆን የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ፤ ግዴታም አለበት” ብለዋል ፡፡ የመከላከያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያውያን ሰራዊት ነው ፤ተልእኮውም የሚመነጨው ከህገ መንግስቱ እንደሆነ ያመለከቱት ጄኔራል አደም ፣ ህገ መንግስቱ የሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ይወጣል ለዚህም ዝግጁ ነው ብለዋል ። የሰራዊቱ ተልእኮ የሚመነጨው ከህገ መንግስቱ በመሆኑም ተልእኮውን ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ጋር አይይዞ ማየት እንደማያስፈልግ ገልጸዋል ። ህዝቡም እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦችን ሊታገል እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያውያንን እኩል ሊያገለግል የሚችል ተቋም ሆኖ እየተገነባ መሆኑን አመልክተው፣ የጸጥታ ተቋማት የማንም ፓርቲ ዕሴት ወይም ሀብት ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ሀብት ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በአንድ ፓርቲ ፕሮግራም ሊቀረጽና ሊገነባ የማይገባው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያውያን ዕሴቶች፣ በአገር ሉዓላዊነት፣ ደህንነትና ብሔራዊ ጥቅም ተመስርቶ መገንባት ያለበት ተቋም ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በሰራዊቱ ውስጥ ለነበሩ በርካታ የሰራዊት የግንባታ ጥያቄዎች ብዙ ኪሳራዎች እንደነበሩ ጠቁመው፤ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የተቋም ግንባታ ላይ የተቀመጡ አስተሳሰቦችን በግለሰብ ደረጃ አለመቀበል እንደ ኃጢያት ይቆጠር ነበር፡፡ በዚህም የከሰርናቸው ኪሳራዎች አልነበሩም ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አንዱን ጠባብ ብለህ ታባርራለህ፤ ወይ ትከስሳለህ፡፡ ወይ አንዱን ትምክህተኛ ብለህ ትጠረጥራለህ፤ ታባርራለህ፤ ወይ ትከስሳለህ ነው ያሉት፡፡ የሰራዊቱም ጥንካሬ ከአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ጥንካሬ የሚነሳ መሆን የለበትም፡፡ ከአንድ ፓርቲ የፖለቲካ ጥንካሬ የሚነሳ ከሆነ፤ ፓርቲው ሲጠነክር አብሮ የሚጠነክር ይሆናል፡፡ ሌላውን እያዳከመ የሚኖርም ይሆናል፡፡ ያ ፓርቲ ሲደክም፣ ነገ በሌላ መንገድ ወደ ስልጣን የሚመጣ ኃይል ደግሞ የሚንደውና የሚያፈርሰው መሆን የለበትም:: ይሄ ተቋም የአገር እናየሕዝብ ተቋም ሆኖ በትውልዶች መገንባት መቻል አለበት ብለዋል፡፡ ፓርቲዎች በራሳቸው በሚያደርጉት ጭቅጭቅና ንትርክ ይሄንን ተቋም መጠቀሚያ የሚያደርጉበት ሁኔታ ከተፈጠረ የሆነ ፓርቲ ወደስልጣን በመጣ ቁጥር እየወደቀና እየፈረሰ እንደገና የሚገነባ ይሆናል፡፡ እየፈረሰ እየተገነባ የሚሄድ ተቋም ደግሞ ይህችን ታላቅ አገር አይመጥንም ብለዋል ጄኔራል አደም፡፡ የመከላከያ ሰራዊቱ ከለውጡ በፊትም ሆነ በኋላ የልማት እና የሰላም ጀግና ሆኖ እየተንቀሳቀሰ እንደነበር ያመለከቱት ጄኔራል አደም፤ በዚህ በኩል ትልቅ ዝናና ስም ያለው ሰራዊት ነው፡፡ አሁንም በውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ ማንኛውንም የሀገር እና የህዝብ ስጋቶችን በመከላከል ከፍተኛ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል። በአገር ውስጥ ሰላምና መረጋጋትን በማረጋገጥና በማስከበር ሚናው ከፍተኛ እንደሆነም አስታውቀዋል ፡፡ ህገ መንግስቱ ሰራዊቱ ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆን አለበት፤ በፖለቲካ ጉዳዮች እጁን አያስገባም ፣የፖለቲካ አዋላጅም መሆን እንደሌለበት በግልጽ ያስቀመጠ ቢሆንም ቀደም ባለው ጊዜ ሰራዊቱ የሚገነባበት የፖለቲካ ኢንዶክትሪኔሽን ህገ መንግስቱ ካስቀመጠው ከሰራዊቱ ዓላማና የግንባታ መርሆዎች አንጻር በተጻራሪው በአብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ፤ በአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ላይ የሚያተኩርና የሚያጠነጥን እንደነበር አመልክተዋል ። የተለያዩ ርዕዮተ ዓለም እና አመለካከቶች ያላቸው ፓርቲዎች ህገ መንግስታዊ እውቅና አግኝተው እየተንቀሳቀሱ ባሉበት አገር፤ ሰራዊቱን በአንድ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ፣ በአንድ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም ላይ መቅረጽና መገንባት ተገቢ እንዳልነበር ጠቁመዋል፡፡ በሪፎርሙ ከተከናወኑ ስራዎች አንዱ እና ትልቁ ሰራዊቱ የሰራዊት ግንባታ ዓላማ እና የሰራዊቱ ተልዕኮ ከየትኛውም የፓርቲ ፕሮግራም ወይም ርዕዮተ ዓለም በላይ እንዲሆን ማድረግ ነው ብለዋል ፡፡በሪፎርሙ ሰራዊቱ በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ተልእኮ በግልጽ አውቆ ለህገመንግስቱ ብቻ ታማኝ እንዲሆን በሚያስችል አስተሳሰብ እንዲገነባ ተደርጓል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፣ የሰራዊቱ ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ እጅጉን የገዘፈ ፤ከአንድ ፓርቲ ፕሮግራምና ዓላማ በላይ የሆነ ፣ የተከበረ፤ የአገርን ሉዓላዊነት፤ የሕዝብ ደህንነት ላይ መሰረት ያደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል። “ኢትዮጵያን እኔ ከሌለሁ ትፈርሳለች ወይም እኔ ካልተጠቀምኩ እናፍርሳት የሚለው አካል ሁል ጊዜ ቢናገርም፤ በእኔ በኩል ኢትዮጵያን የምትፈርሰው መጀመሪያ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ላይ የሚያምኑት ሕዝቦቿ እና መሪዎቿ ከሌሉና ከሌሉ ብቻ ነው ፡፡ ከዛ በላይ ኢትዮጵያ የምትፈርሰው የመከላከያ ኃይላችን፣ የፀጥታ ኃይላችን፣ የደህንነት ኃይላችን ሲፈርስ፤ ወይም እሱ መስዋዕት ሆኖ ሲሸነፍ ብቻ ነው:: ስለዚህ አሁን ያለን የሪፎርም ስራዎች የአገራችንን ገናናነትና ሉዓላዊነት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ስርዓት መፍጠር ላይ ያተኮረ ነው፤ የሰራዊት ግንባታውም እንዲሁ ፡፡ በአስተሳሰብም በተግባርም ኢትዮጵያን የበለጠ የሚያጠናክር ስራ ነው እየተሰራ ያለው” ብለዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012 ወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35947
7392ec68f61734b486515b3a602b4bf1
29a3ca6fe64130b8ae9da47b7bfb9a71
በኮሮና ምክንያት ችግር የደረሰባቸው 30 ሺ 87 ዜጎች ከስደት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል
አዲስ አበባ ፤ በተለያዩ ሀገራት በስደት ላይ የነበሩ እና በኮሮና በሽታ ምክንያት ችግር ውስጥ የወደቁ 30ሺህ 87 ኢትዮጵያውያን ወደሀገር ውስጥ መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ ዜጋ ተኮር የመንግስት ፖሊሲ ተግባራዊ በመደረጉ በኮሮና ምክንያት ለችግር የተጋለጡ እና በስደት የነበሩ 30ሺህ 87 ኢትዮጵያውያንን ወደሀገራቸው መመለስ ተችሏል። በፍቃደኝነት ወደሃገራቸው የተመለሱ ዜጎች በአብዛኛው ከገልፍ እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ ናቸው።አምባሳደር ዲና እንደገለጹት፤ በተለይ በአረብ ሀገራት እና በጎረቤት ሀገሮች በስደት የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በኮሮና በሽታ ወቅት ስራ በማጣት ጎዳና ላይ ሲወድቁ በየሀገራቱ የሚገኙ ቆንስላዎች ክትትል አድርገዋል። በተለይ በቤይሩት ከስራ ተባረው እና በመንገድ ላይ ተጥለው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን በቆንስላው አማካኝነት ድጋፍ በማድረግ በፍቃደኝነት መመለስ ተችሏል። በዚህ መሰረት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ከተደረጉ 30ሺ በላይ ዜጎች መካከል ከቤይሩት 656 ዜጎች፤ ከአቡዳቢ 72፤ ከሳዑዲ አረቢያ 3ሺህ 539፣ ከኩዌት ደግሞ 1 ሺህ 23 ዜጎች እንዲሁም በድንበር በኩል ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት 4ሺህ 792 ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።እንደ አምባሳደር ዲና ከሆነ፤ መንግስት በሚከተለው የዜጋ ተኮር ፖሊሲ መሰረት አሁንም በስደት ላይ ለእንግልት የተዳረጉ ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ለአብነት በየመን የቆየ ጦርነት በመኖሩ ምክንያት የት እንዳሉ እና ምን ያክል ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ከተባበሩት መንግስታት እና ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር ክትትል እየተደረገበት ይገኛል። በመሆኑም በቀጣይ ከተለያዩ ሀገራት የሚመለሱ ዜጎች ይኖራሉ። ወደሀገራቸው በፍቃደኝነት ከተመለሱ በኋላም እንዲቋቋሙ ይደረጋል። በዚህ ረገድ ቀጣይነት ባለው መልኩ የማቋቋም ስራው መሰራት እንዳለበት በመንግስት ደረጃ አቅጣጫ ተይዟል።በሌላ በኩል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በአባይ ግድብ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ የዘንድሮው የክረምት ዝናብ ውሃ ከፍተኛ መጠን ነበረው። በዚህም ምክንያት የግድቡን የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት ከታሰበው ጊዜ በፊት ማጠናቀቅ ተችሏል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 18/2012ጌትነት ተስፋማርያም
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35961
1a97dca69899baf790ae10472410f3b3
ab4fc98063f00d84a531264c456e54a1
ፌዴሬሽኑ ለሳይንሳዊ አትሌቲክስ አሰልጣኞች ስልጠና ትኩረት ሰጥቷል
አዲስ አበባ ፡- ኢትዮጵያውያን የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የ21ኛው ክፍለ ዘመን የአትሌቲክስ ስፖርት የሚጠይቀውን ሳይንሳዊ እውቀት ይበልጥ እንዲጨብጡ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት ገብረ እግዚአብሄር ገብረማርያም በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ስልጠና የውድድርና ውጤት መሰረት ነው።ፌዴሬሽኑ ከዓለም አቀፉ የአትሌቲክ ማህበርና የተለያዩ አገራት ጋር ባለው መልካም የሥራ ግንኙነትና ትብብር አሰልጣኞች ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እየሰራ ይገኛል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙያቸው ከበሬታን ያተረፉት ባለሙያዎችን ከውጭ በማስመጣት በሚሰጣቸው ስልጠናዎችም «ኢትዮጵያውያን የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የ21ኛው ክፍለ ዘመን የአትሌቲክስ ስፖርት የሚጠይቀውን ሳይንሳዊ እውቀት ይበልጥ እንዲያውቁ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው » ብለዋል። ከአሥርና አሥራ አምስት ዓመታት ቀድሞ ከነበሩ የፌዴሬሽኑ አመራሮች አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት ለአትሌቲክስ የአሰልጣኞች ስልጠናዎችን የማመቻቸት ተግባር ሲካሄድ መቆየቱን ያስታወሱት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤አሰልጣኞችን ወደ ውጭ አገራት በመላክ ስልጠና የሚያገኙበት እድል ሲመቻች መቆየታቸውን አብራርተዋል። በርካታ አሰልጣኞችን ወደ አገራት ልኮ ከማሰልጠን ሁለትና ሶስት አሰልጣኞችን ወደ አገር ውስጥ ማምጣቱ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ምክትል ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል፡፡በዚህ አይነት መንገድ በአገር ውስጥ የሚሰጡ ስልጠናዎች ወጪ ከማዳን ባሻገር በርካታ አሰልጣኞችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚችልም ጠቁመዋል። «ዘመናዊ አሰልጣኝ ካለ ዘመናዊ አትሌት ይኖረናል፤በዚህም ሰልጣኞቻችን የ21ኛው ክፍለ ዘመን የአትሌቲክስ ስፖርት ከሚፈልገውና ከሚጠይቅ ሳይንሳዊ እውቀት ጋር ተዋውቀዋል ብለን እናስባለን፤»ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፤ ስልጠናው አሰልጣኞች አዳዲስ ሳይንሳዊ ግኝቶችን የሚያስጭብጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል። ከተቋም ከክለብና ከክልል ተዉጣጥተው ስልጠና የወሰዱትንና በማሰልጠን ሙያ ላይ የሚገኙትን አሰልጣኞችም ወደ የመጡበት አካባቢ ሲመለሱ በቀሰሙት እውቀት ለአገሪቱ ስፖርት እድገት አይነተኛ ሚና ለመጫወት ብቃቱ ይኖራቸዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።ይህም አትሌቲክስ ለአገሪቱ ስፖርት እድገት ፋይዳው የጎላ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል። ከሙያ ብቃት ማሻሻያነቱ በተጓዳኝ በዓለም አቀፉ እትሌቲክስ ማህበር የሚወጡ  ህጎች ወደ አሰልጣኙ ወርደው አትሌቱ በትክክል እንዲያውቃቸው ለማድረግ ብቻ የአሰልጣኞች እውቀት በየጊዜው መጎልበት የግድ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡ሳይንሳዊ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ስልጠና ማመቻቸት የፌዴሬሽኑ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 18/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13107
3c50db21916d107f9fb0e935a0be6518
b5f986b5b52b76d607c3c37bb594f6e5
በአፍሪካው ዋንጫ የሚደምቁ አሥራ አንድ ኮከቦች
የወንድማማችነትን መንፈስ በአፍሪካውያን መካከል ማጠናከርና የፀረ-ቅኝ ግዛት ትግሉን ማበረታታት ዓላማው አድርጎ በኢትዮጵያ፣ሱዳን፣ግብፅና ደቡብ አፍሪካ መስራችነት እ ኤ አ በ1950 የተጀመረው የአፍሪካ ዋንጫ፤እያደገ እና ተወዳጅነቱ እየጨመረ ዛሬ በዓለማችን ከሚካሄዱ ምርጥ አህጉራዊ የእግር ኳስ መድረኮች አንዱ ለመሆን በቅቷል። መድረኩ በህብረ ቀለማት በደመቁ ደጋፊዎች ፤ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች ገልተው በሚሰሙ የድጋፍ ድምጾችና ማራኪ ጭፈራዎች ይደምቃል፤በድንቅ እግር ኳስ ጥበብ የተካኑ፣ በሙያቸው ብዙዎችን ያስደመሙ እና ከአህጉሪቱም ተሻግረው በታላላቅ የአውሮፓና የመሳሰሉት ሊጎች ድንቅ ችሎታቸውን ያስመሰከሩ ጥበበኞች ይሳተፉበታል። በአልሸነፍ ባይነት የዓላማ ፅናት የሚታጀበው አጓጊው የአፍሪካ ዋንጫ ዘንድሮ በግብፅ አስተናጋጅነት ባለፈው አርብ ምሽት ተጀምሯል።ትላላቅ ዝናና የእግር ኳስ ጥበብን የተካኑ እና በራሳቸው አቅም የአሸናፊነት ታሪክ መፍጠር የሚችል አቅም ያላቸው ተጫዋቾችም ለአሸናፊነት መፋለም ጀምረዋል። የተለያዩ አፍሪካ ተኮር የእግር ኳስ ትንታኔዎችን በማስነበብ የሚታወቀው ዘጠና ደቂቃ «90 min» በግብፅ ምድር በሚካሄደው የአፍሪካውያን ፍልሚያ ደምቀው የሚታዩ ናቸው ሲል ከግብ ጠባቂ እስከ ፊት መስመር ያሉ ተጫዋችን ይፋ አድርጓል። በዚህ 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አንድሬ ኦናና በግብ ጠባቂዎች ምድብ ተቀዳሚ ተመራጭ ሆኗል።ካሜሮናዊው የ23 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በድንቅ ብቃቱ በዚህ ዓመት ዓለም አቀፍ ትኩረት መሳብ ችሏል።ተጫዋቹ እኤአ በ2018 የካሜሮን እግር ኳስ ተጫዋቾች የዓመቱ ኮከብ ተብሎ የተመረጠ ሲሆን፣ በዚሁ ዓመትም የአፍሪካ ምርጥ ግብ ጠባቂ ክብርን ተቀዳጅቷል። በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ምድር የግብ ክልሉን በንቃት በመጠበቅ «ክእርሱ በላይ ማንንም ማግኘት አይቻልም» የሚባልለት አንድሬ ኦናና፣ በፈርኦኖቹ ሰማይ ስር በተሰናዳው ፍልሚያ የማይበገሩት አንበሶች የኋላ ደጀን ስለመሆኑ ታምኖበታል። በተከላካይ መስመር ከተመረጡት መካከል ደግሞ ካሊዱ ኩሊቫሊ ቀዳሚው ነው።ሴኔጋላዊው ግዙፉ የመሃል ተከላካዩ በጣሊያኑ ናፖሊ ድንቅ የውድድር ዓመት በማሳለፍ ላይ ይገኛል። በተለይ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ያሳየው ከሁሉ የላቀ ድንቅ ብቃት የሴሪአው የዓመቱ ምርጥ ተከላካይነት ክብርን እንዲቀዳጅ አስችሎታል። ይህ ብቃቱም በአውሮፓው እግር ኳስ መድረክ ሃያል ከሆኑ ክለቦች ሳይቀር ተጫዋቹን የግላቸው ለማድረግ ፅኑ መሻት እንዲያደርባቸው ማድረግ ችሏል። አድርጎታል። በተለይ የእንግሊዙ ማንቸስተር ዩናይትድም የተጫዋቹ ዋና ፈላጊ ከሆኑት ክለቦች ግንባር ቀደም ሆኗል። ናፖሊዎችም 90 ሚሊዮን ፓውንድ የሚከፍል ብቻ ተጫዋቹን የግሉ ማድረግ ይችላል በሚል አቋማቸው የፀኑ ሲሆን፤ተጫዋቹ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የሚያሳየው አቋምም ዋጋውን ከዚህም በላይ ሊያንረው እንደሚችል ተገምቷል። መሃዲ ቤናሺያ ሌላኛው በመሃል ተከላካይነት ጎልቶ እንደሚወጣ የተጠቆመ ተጫዋች ነው። የ31 ዓመቱ የሞሮኮው ኢንተርናሽናል ተጫዋች በመሃል ተከላካይነት ሚናው እጅግ የሚደነቅ ጠንካራ ስለመሆኑ ብዙዎች ይመሰክሩለታል።የክለቡን ውጤት አስጠብቆ ለመጓዝ ሁሌም የሜዳ ላይ ሚናውን ለመወጣት ተግቶ እንደሚሰራ ይነገርለታል። በተለይ ለዓመታት ያካበተው ልምድም የጥንካሬው ምንጭ ስለመሆኑ ይታመናል። የአርሰናሉ አለቃ ኡናይ ኤምሬ የክለባቸውን የመከላከል ክፍል ከደካማነት ለማውጣት ከሁሉም በላይ በዚህ ተጫዋች እምነት ቢኖራቸውም ተጫዋቹን ግን እስካሁን የግላቸው ማድረግ አልሆነላቸውም።ቁመተ መለሎው የመሃል ተከላካይም ካይሮ ምድር ላይ የአገሩን መረብ ላለማስደፈር ብርቱ ጥረት እንደሚያደርግ ተገምቷል። ሰርጄ አዩር ሌላኛው በተከላካይ ክልል ተመራጭ የሆነ ተጫዋች ነው።ሜዳውን እያካለለ አደገኛ ቦታዎችን በመሸፈን የሚታወቀው አይቮሪኮስታዊው ተጨዋች፤ በአሁኑ ወቅት ለእንግሊዙ ቶተንሃም ሆትስፐር በመጫወት ላይ ይገኛል። ምንም እንኳን 2018/19 የውድድር ዓመት 17ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሰልፎ ቢጫወትም፤የሰሜን ለንደኑን ክለብ የተከላካይ ክፍል በማገዝ ረገድ ድንቅ ሚና ተወጥቷል።አገሩ እኤአ በ2015 የተካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ ከፍ አድርጋ ስትስም የቡድኑ አባል የነበረው ይህ ተጫዋች፤ ዘንድሮም ለተጨማሪ ድል ለማስመዝገብ ያለውን ሁሉ ሜዳ ላይ እንደሚያሳይ ይጠበቃል። አክራፍ ሃኪም በመከላከሉ ሃላፊነት በግብፅ ምድር ብቃቱን ማሳያት እንደማይቸግረው የተገመተ ተጫዋች ነው።ሞሮኮአዊው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ተጫዋች ተወልዶ ያደገው በስፔን ማድሪድ ውስጥ ሲሆን፤በአሁኑ ወቅትም ለጀርመኑ ክለብ ቦሪሲያ ዶርትሙንድ እየተጫወተ ነው። የሃያ ዓመቱ ኮከብ በዚህ ክለብ ቆይታውም ስሙን በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ መንደር በላቀ ደረጃ ማስጠራት የሚያስችለውን ብቃት አሳይቷል።ተጫዋቹ በአፍሪካው ዋንጫ የሚያሳየው ብቃትም በቀጣይ በዓለም የእግር ኳስ መድረክ ላይ ጎልቶና ደመቆ ለመውጣት ብዙም የማይችግረው መሆኑን እንደሚያስመለክት ተገምቷል። የጀርመኑ ክለብ ተጫዋቹን ከሪያል ማድሪድ በውሰት የተረከበው ሲሆን፤ በአፍሪካ ዋንጫው የሚያሳየው ብቃትም ምናልባትም በቋሚነት ዝውውሩን እንዲጨርስ ሊጠቅመው እንደሚችል ተገምቷል።ምናልባትም የስፔኑ ሃያል ክለብ ተጫዋቹን ለመመለስ እንዲያስብ የሚያስገድደው ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል። ከምርጥ አራቱ ተከላካዮች ባሻገር የመሃል ሜዳውን ክፍል የሚሾሩበት ተጫዋቾችም ተለይተዋል። ከእነዚህ ተጫዋቾች ደግሞ ቶማስ ፓርቴይ ቀዳሚ ተመራጭ ሆኗል።ጋናዊው ቶማስ ፓርቴይ በኳስ ቁጥጥር ላይ የመሃል ሜዳን በሚገባ በማደራጀት ማጥቃትና መከላከልን አጣምሮ መተግበር ወሳኝ የሆነበት የዘመናዊ እግር ኳስ ፍልስፍና ተመራጭ ተጨዋች መሆኑ ይነገርለታል። በስፔን ላሊጋ ለአትሌቲኮ ማድሪድ የሚጫወተው ፓርቴይ፤በአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ የአጨዋወት ፍልስፍና ቀዳሚ ተመራጭና የቡድን ስብስብ ውስጥ ቁልፍ የመሃል ሜዳ ቴክኒሺያን የሚል ስያሜን እስከማግኘትም ደርሷል። ሜዳ ውስጥ እረፍት አልባና ታታሪ ሆኖ የሚስተዋለው ፓርቴይ፤በተከላካይ አማካኝነት ሚናው የክለቡን የመሃል ሜዳ ሚዛን አስጥብቆ የጨዋታ እንቅስቃሴ የሚያቀላጥፍ ሲሆን፣ ይህ ሚናውም የበርካቶችን አድናቆት አስገኝቶለታል።ከጥቋቁር ኮኮቦች መካከልም ግብፅ ላይ ከሚደምቁት መካከል ቀዳሚው ሆኖ ታጭቷል። ናቢ ኪዬታ ሌላኛው ምርጥ አስራ አንድ ውስጥ ስሙ የተቀመጠ ተጫዋች ነው። ተጫዋቹ ከጠንካራነቱ ና ጨዋታ የማንበብ ብቃቱ በተጓዳኝ ግብ ለማስቆጠር ወይም ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ለመስጠት የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾችን ለማለፍ የሚያስችለውን ብቃት ስለመካኑም የእግር ኳስ ሊህቃን ይመሰከሩለታል። ጊኒያዊውን አማካይ ከራሱ የግብ ክልል እስከተጋጣሚ የግብ ክልል የሚያደርገው አስገራሚ እንቅስቃሴ በተቃራኒ ቡድን ዘንድ እንደ «ሁለት ተጫዋች» እንዲታይ ያደርገዋል ሲሉም ይገልጹታል። በከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ ከሁለት ዓመት ቢፊት ሊቨርፑሎችን የተቀላቀለውና ጊኒ ኮናክሪ ላይ የተወለደው ኮከብ ምንም እንኳን አሁን በክለቡ የተጠበቀውን ያህል ግልጋሎት እየሰጠ ባይሆንም፤የቀዮቹ አለቃ ግን በተጫዋቹ አቅም ጥርጣሬ የላቸውም። በቀጣይም በአንፊልድ ቆይታው እንደማያሳፍራቸው እምነት አላቸው።በፈርኦኖቹ ሰማይ ስር የተደገሰውን የአፍሪካ ዋንጫም አገሩን ለተሻለ ውጤት ያበቃል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። በአፍሪካው ዋንጫ ከሚደምቁ አስራ አንድ ኮከቦች መካከል ከሁሉ ልቆ ስሙ የሚነሳው ሞሮኮአዊው ሃኪም ዚያች ነው። ሀኪም ዚያች በሆላንዱ ክለብ አያክስ በሚያሳየው ድንቅ አቋም የበርካቶችን ቅልብና አድናቆት በቀላሉ ማግኘት ችሏል።በታላቅ ተመስጦ የሚታይውና በብዙዎች ዘንድ የሚደነቅ ድንቅ ውበት ያለው እግር ኳስ መጫወት የሚችለው ዚያች፤ ክለቡ የኤርዲቪዜውን ዋንጫ እንዲያነሳ የላቀ ሚና ተጫውቷል። ባሳለፍነው የውድድር ዓመት 21 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ 24 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ አቋድሷል።ይህም የ26 ዓመቱ ኮከብ የክለቡ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርንም አስገኝቶለታል። አሁን በርካታ ክለቦች ተጫዋቹን በአይነ ቁራኛ በመከታተል ተጠምደዋል።ተጫዋቹ በአሁኑ ወቅት ስሙ ከአርሰናል ጋር እየተዛመደ ይገኛል። በ2016 ከሳውዝሃምፕተን ሊቨርፖሎችን የተቀላቀለው ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ በአንፊል ቆይታው ድንቅ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ ነው።ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ማጣጣም የቻለው ማኔ፤ከቡድን አጋሩ ሞህ ሳላህና ከአርሰናሉ ፔር ኤሜሪክ ኦባሚያንግ ጋር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ የወርቅ ጫማውን መቀበል ችሏል። እያንዳንዱን ጨዋታ አሸንፎ ለመውጣት ማድረግ የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ተጋጣሚውን ቡድን ተጭኖ በመጫወት በተከላካዮች ላይ ጫና መፍጠርና ግብ ማስቆጠር የማይከብደው ማኔ፤ወርቃማ ትውልድ የተባለለትን የወቅቱ የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን በአንበልነት በመምራት ለአዲስ ታሪክ ይፋለማል። ሁልጊዜም ግብ ማስቆጠር የማይሳነውና ግብ ለማስቆጠር የሚታትረው ግብፃዊው ሞሃመድ ሳላህም በአገሩ ምድር ደምቆ እንደሚታይ በበርካቶች የታመነበት ተጫዋች ነው።በእግር ካሳዊ የጥበብ ልህቀቱ ዓለምን የስደመመው ሳላህ፤ከሮማ በ34 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ሊቨርፑል ከተዘዋወረ በኋላ በአንፊልድ የሁለት ዓመት ቆይታው 71 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ክለቡ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ከፍ አድርጎ እንዲስም የእርሱ ሚና ከሁሉ የላቀ እንደነበር አስመስክሯል። በአስደማሚ ብቃቱ የሚማረኩ ወዳጆቹ ግብፃዊው ሜሲ ሲሉ የሚያሞካሹት ምትሃተኛው ግራ እግር ተጫዋች ፤ፈርኦኖቹን የሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤትነት ከፍ ለማድረግ በአገሩ ምድር በተሰናዳው ታላቁ የአህጉሪቱ ፍልሚያ ላይ ከባድ ሃላፊነት ተጥሎበታል።በርካታ ጨዋታ በማድረግና ከማንም ብሄራዊ ቡድን በላይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ሰባት ጊዜ ዋንጫውን በመሳም የሚስተካከላቸው ያላገኙት ፈርኦኖቹም በሌላ አዲስ ታሪክ የቁርጥ ቀን ልጃቸውን አቅም ተማምነዋል፡፡ በእዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ከሚደምቁ አስራ አንድ ኮከቦች መካከል የፊት መስመር ተሰላፊው ኒኮላስ ፔፔም ዋነኛው ነው። አይቮሪኮስታዊው ተጫዋች በአሁኑ ወቅት በፈረንሳዩ ክለብ ሊል እየተጫወተ ይገኛል። ተጫዋቹ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት የክለቡ ቆይታው 19 ግቦችን ሲያስቆጥር፤ 11 ለግብ የተመቻቹ ኳስችን ለቡድን አጋሮቹ ማቀበል ችሏል። ክለቡ በፈረንሳይ አንደኛ ሊግ በሁለተኝነት እንዲጨርስ ጉልህ ሚና የነበረው የዚህ ተጫዋች ወቅታዊ ብቃትም የበርካቶች ጭብጨባ ከማግኘት በተጓዳኝ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦችም ተጫዋቹን ለመውሰድ እንዲያሰፍስፉ አስገድዷቸዋል። አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎችም የ23 ዓመቱን ተጫዋቹ በቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ እንግሊዝ በማቅናት ሊቨርፖሎችን እንደሚቀላቀልና ከሞህ ሳላህና ሳዲዮ ማኔን ጋር እንደሚጣመር በማተት ላይ ይገኛሉ። አርሰናል፤ማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ኤቨርተን ተጫዋቹን የየግላቸው ለማድረግ ፍልሚያ የገጠሙ ሲሆን የተጫዋቹ ክለብ ሊልም ተጫዋቹን የሚፈልግ ካለ ካዝና ውስጥ 70 ሚሊዮን ፓውንድ ማስገባት ግድ እንደሚለው አሳውቋል። እርሱን በተቃራኒ መለያ መግጠም እጅግ አድካሚና ፈታኝ እንደሆነም ብዙዎች የሚናገሩለት ኒኮላስ ፔፓ፤ ሲሆን የመድረኩ ድምቀት እንደሚሆን ታምኖበታል።ተጫዋቹ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የሚያሳየው አቋምም የዝውውር ዋጋውን ሊያንረው እንደሚችል ተገምቷል።
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13110
afc158fa6d5c0f8ce12cc341aadb11ac
4445dba796870b36dd5a52fcd576a6cf
«የስፖርት ፖሊሲው መከለስ አለበት» – አቶ ባዘዘው ጫኔ የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽነር
እኔም አመሰግናለሁ። ክልላችን የበርካታ ስፖርቶች ጸጋ ያለው ሲሆን፤ ዘርፉም እንደየትኛውም የልማት ሥራ በስትራቴጂክ ዕቅድ ይመራል። በአንድ በኩል የክልሉ ህዝብ በስፖርቱ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በማድረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለሃገራዊ ዘርፉ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በሚያስችል አኳኋን እየተንቀሳቀስንም እንገኛለን። በአጠቃላይ 22 ስፖርቶች ሲዘወተሩ፤ ከዚህ መካከል ከክልሉ ልዩ ባህሪ፣ የአየር ንብረትና የቦታ አቀማመጥ አኳያ ምቹ የሆኑት ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን። እነዚሀም አትሌቲክስ፣ ውሃ ዋና እና ብስክሌት ሲሆኑ፤ የወጣቱ ተሳትፎም እየጨመረ ነው። እንደ ሃገርም ክልላችን ምርጥ ስፖርተኞችን በማበርከት ሲታወቅ፤ ከዓመት ዓመት ዕድገት በማሳየት ላይም ይገኛል። በስፖርት መሰረተ ልማትም በእያንዳንዱ ቀበሌ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ እንዲኖር፣ በወረዳና ዞኖች መካከለኛ ስታዲየሞች እንዲሁም በትልልቅ ከተሞች ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች እንዲገነቡ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል። ከትልልቆቹ መካከልም የክልሉ መንግሥት የሚያስገነባው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀውና 50ሺ ተመልካቾችን በመያዝ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የባህር ዳር ስታዲየም ይነሳል። በክቡር ዶክተር ሼህ መሃመድ አሊ አላሙዲ የተገነባውና ከሁለት ዓመት በፊት የተጠናቀቀው የወልዲያ ስታዲየምም እንዲሁ። የመጀመሪያው ነገር ፖሊሲውም የሚጠቁመው ስፖርቱን ህዝባዊ ማድረግ ነው። ከዚህ አንጻርም የተሳካልን ህዝቡ ስፖርቱን እንዲመራ እንዲሁም ሀብት በማሰባሰብና በስፖርቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው። ለምሳሌ መላው የክልላችን አርሶ አደር በክፍያ ለስፖርቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል። የመንግሥት ሠራተኛውም ከደሞዙ በፍቃደኝነት ይከፍላል፤ በእርግጥ አሁን መቀዛቀዝ አለ። እንደ አጠቃላይ ግን ከስፖርቱ ልማት ተጠቃሚ የሚሆነው ህዝቡ ራሱ በመሆኑ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደርጋል። ሌላው የሚያኮራው ተግባር የክልላችን ህዝብ በየትኛውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርገው ድጋፍ ነው። በዚህ ዓመት በስፖርታዊ ጨዋነት የተሻለ ነገር ታይቷል። በአማራና ትግራይ ክለቦች መካከል በነበረው ችግር በራሳቸው ሜዳ እንዳይጫወቱ መደረጉ የሚታወስ ነው። የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ስፖርት ኮሚሽን፣ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ስፖርት ቢሮዎች፣ ክለቦች እንዲሁም ደጋፊ ማህበራት በቅንጅት ባደረጉት እንቅስቃሴ የሁለቱ ክልል ክለቦች በየሜዳቸው በጨዋነት ሲጫወቱ ቆይተዋል። በክልላችን የተካሄዱት ጨዋታዎችም አስተማማኝ ጸጥታ ነበር። ይህም በዚህ ዓመት ውጤታማ ከሆንባቸው ሥራዎች መካከል ይጠቀሳል። ክልላችን ለአትሌቲክስ ስፖርት በጣም ምቹ ነው፤ ስለሆነም ልዩ ጸጋ ያላቸውን ስፍራዎች ለይተን ስምንት የሚሆኑ የአትሌቲክስ ማዕከላትን በመገንባት ላይ እንገኛለን። የደብረ ብርሃን፣ ቲሊሊ፣ ደጋ ዳሞት፣ ኮን፣ ጉና፣ ደባርቅ፣… ማዕከላት ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ ተስፋ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች ከፕሮጀክት ተመልምለው ይሠለጥኑበታል። ቀደም ብሎ የተቋቋመው የደብረብርሃን ማዕከል በየዓመቱ 40 ታዳጊዎችን በመቀበል የሚያሰለጥንና ብቃት ያላቸው አትሌቶችን እያፈራ ይገኛል፤ ሌሎቹም ወደዚሁ መስመር እየገቡ ነው። በውሃ ዋና ስፖርትም ጸጋው ባለባቸው አካባቢዎች፣ ለምሳሌ ባህርዳር ዙሪያ፣ ጎንደር እና ኮምቦልቻ አካባቢ ክለቦችን በማቋቋም ምርጥ ስፖርተኞችን የማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው። ሌላው በክልሉ ትልቅ አቅም ያለው የስፖርት ዓይነት ብስክሌት ነው። በባህር ዳር እንደሚታወቀው ብስክሌት ሳይዝ የሚንቀሳቀስ ወጣት የለም። ይህ ደግሞ ትልቅ ዕድል ነው፤ ከዚህ አኳያም ጥረት የሚባል አንድ ክለብ አለን። በቂ ባይሆንም ሌሎች ክለቦችን ለማቋቋም እሠራን እንገኛለን። ስፖርቱ እንዲዘወተርና የክልሉ መገለጫ እንዲሆንም ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ነን። እውነት ነው፤ በክልሉ ትልቅ ጸጋ አለ። ከክልሉም አልፎ ለሃገርም ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ስፖርተኞችን ማፍራት ይቻላል። በመሆኑም በቅድሚያ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እያከናወንን ነው። አሁን አሁን ከከተማ ባለፈ በገጠሩ አካባቢም ህበረተሰቡ ለመጓጓዣነት እየተጠቀመ መሆኑ መልካም ዕድል ነው። በመሆኑም ይህንን መለያው እንዲያደርግ ግንዛቤ እያስጨበጥን ነው። ሌላው ከዚህ ቀደም የተቋቋመውን የጥረት ክለብ የማጠናከር ሥራ ነው። በእርግጥ አሁን አሁን አንዳንድ ጥያቄዎች እየተነሱ በውይይት ላይ ነው ያለነው። ጥረት ከአቅም በላይ እንደሆነበትና ወደ ሌላ የልማት ሥራ መዞር ስላለበት ክለቡን ወደ ሌላ እንዲዞርለት አስታውቋል። እኛም ይህ መሆን እንደሌለበትና ክለቡ የህዝብ በመሆኑ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍሎ ይዞ እንዲቀጥል አሳስበናል። ሦስተኛው ሥራችን ደግሞ ቁሳቁስ የማሟላት ነው፤ ዘመናዊ ብስክሌቶች አስፈላጊ በመሆኑ ከዚህ ቀደም ገዝተን ነበር። አሁንም በድጋፍ ከፍተኛ ወጪ አውጥተን ከውጭ ዘመናዊ ብስክሌቶችን አስገብተናል። እነዚህ በቂ ናቸው ማለት አይደለም፤ በቀጣይም የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር ድጋፉን እንቀጥላለን። የውስጥ ውድድሮችን ለማዘጋጀት እንዲሁም ሃገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ለምናደርገው ተሳትፎ ትኩረት እንሰጣለን። በዚህ ሂደትም ምርጥ ስፖርተኞችን የማውጣትና የመለየት እንዲሁም ተሳትፎውን የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ነው። በዓመቱ በተካሄዱ ሃገር አቀፍ ተሳትፎዎች ያስመዘገብነው ውጤትም መልካም በመሆኑ ደረጃችንን እንዳሻሻልን ማንሳት ይቻላል። ሃገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ለመድረስ ከታች መጀመር አስፈላጊ ቢሆንም፤ በወረዳዎችና ዞኖች የገንዘብ እጥረት ስለሚያ ጋጥም የማይሳተፉባቸው አጋጣሚዎች አሉ። በመሆኑም ማስተካከያ ማድረግ እንደ ሚያስፈልግ ለይተናል። ሌላው በአንዳንድ ስፖርቶች ላይ በሚኖረን የውድድር ተሳትፎ በቂ ስፖርተኞችን አለማሳተፍ ይታያል ይህንንም ማስተካከል ይገባናል። እስከአሁን ያልተፈታውና መንግሥትም ትኩረት ቢሰጠው የምለው ስፖርት ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቅ እንደ መሆኑ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ብቻ ማሳደግ አይቻልም። በመሆኑም መንግሥት ዘለቄታዊ መፍትሔና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። የስፖርት ፖሊሲውም መከለስ አለበት። ከ20 ዓመት በላይ የቆየ በመሆኑ አሁን ከደረስንበት ደረጃ አኳያ መከለስ ይኖርበታል። ይዘቱ በዚያን ወቅት መልካም ቢሆንም፤ አሁን ስፖርቱ የደረሰበትን እንዲሁም ሃገሪቷ ያለችበትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የዕድገት ደረጃ ግምት ውስጥ አስገብቶ በድጋሚ መቀረጽ አለበት። ብዙ ጥረት የሚጠይቀው ሌላው ሥራ አደረጃጀትን የሚመለከት ነው። እኔ ወደዚህ ቦታ ከመጣሁ እንኳ ስፖርቱ አንዴ ራሱን ሲችል ሌላ ጊዜ ከሌላው ጋር ሲለጠፍ ቆይቷል፤ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም። በእርግጥ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ አደረጃጀት መታየት አለበት፤ ነገር ግን ለውጥ በመጣበት ጊዜ ሁሉ ይህንን ማድረግ ሴክተሩን የሚያሳድግ መስሎ አይሰማኝም። በመሆኑም ወጥበት ኖሮት እንዲቀጥል ማድረግና ትኩረት መስጠት ይገባል። የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በያሉበት ከልሎ ማልማትም ያስፈልጋል፤ ለዚህም አስገዳጅ የህግ ማዕቀፍ ያስፈልጋል። የፍቃደኝነት ሥራ ካደረግነው ረጅም ጊዜ ይወስድብናል፤ እንደ ውሃ እና መብራት ማዘውተሪያ ስፍራዎችም አስገዳጅ ማዕቀፍ ሊኖራቸው ይገባል። ይህንንም በፌዴራል ደረጃ እያነሳን እንገኛለን። የመጀመሪያውና ትኩረት ልንሰጠው ያቀድነው የህዝብ አደረጃጀትን ማጠናከር ነው። ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ ህዝባዊ አደረጃጀቶችን የማጠናከርና ባለቤት ሆነው እንዲመሩት ያስፈልጋል። የማዘውተሪያ ስፍራዎች በስታንዳርዱ መሰረት በሁሉም አካባቢ ህጋዊ ሆነው እንዲለሙና እንዲስፋፉ ማድረግም ሌላኛው ነው። የስፖርት ዘላቂነትን ካሰብን ተተኪዎች መኖር ይገባቸዋል። የፕሮጀክት ስልጠናን አጠናክሮ በመያዝና ውጤታማ በሆነ አኳኋን መምራት ስለሚያስፈልግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንሠራለን። ክለቦች ከሌሉ ስፖርተኛን በተናጥል አንቀሳቅሶ ውጤታማ መሆን ያስቸግራል። በመሆኑም በሁሉም ስፖርት ክለቦችን ለማቋቋም ተቋማትን፣ ባለሀብቶችን፣… ለማሳተፍ ጥረት ይደረጋል። የመጨረሻው ደግሞ ሀብት ማሰባሰብ ነው፤ እንደሚታወቀው ስፖርት ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግ ዘርፍ ነው። በመሆኑም ይህንን መሸከም የሚችል ሀብት ማሰባሰብ ትኩረት ሰጥተን የምንሠራው ነው።አዲስ ዘመን ሰኔ 17/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13143
e31020afdc079ae0710033d0dfcd0989
48e3deeca13a23c29b78b84459da045a
በአፍሪካ ዋንጫ የዛሬ ምድብ ጨዋታዎች
በውድድር ጊዜው እንዲሁም በተሳታፊ ሃገራቱ ብዛት ላይ ለውጥ በማድረግ እየተካሄደ ያለው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል። ዛሬ በሁለት ምድቦች ጨዋታዎች የሚከናወኑ ሲሆን፤ ምድብ አራት ኮትዲቯርን ከደቡብ አፍሪካ ያገናኛል። ከምድብ አምስት ደግሞ ቱኒዚያ ከአንጎላ እንዲሁም ማሊ ከሞሪታኒያ የሚጫወቱ ይሆናል። ከምድብ አራት ኮትዲቯርና ደቡብ አፍሪካን ለሚያገናኘውም ጨዋታ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷል። ይህንን ውድድር ለማዘጋጀት ፍላጎት አሳይታ ያልተሳካላት ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ ስኬትን ያስመዘገበችው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። እአአ በ1996 ባስተናገደችው ውድድር ዋንጫውን በሃገሯ ካስቀረች ወዲህም ሻምፒዮን ልትሆን አልቻለችም። ዝሆኖቹ በበኩላቸው እአአ በ1992ቱ የሴኔጋል እንዲሁም እአአ በ2015ቱ የኢኳቶሪያል ጊኒ የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ አሸናፊ በመሆን ከተጋጣሚያቸው የተሻለ ውጤት አላቸው። ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም የተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የበላይነት የተጠናቀቀ ቢሆንም፤ የዚህ ጨዋታ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ግን ወደ ዝሆኖቹ አድልቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በካይሮ በሚገኘውና 30ሺ ሰዎችን በሚይዘው አልሰላም ስታዲየም የሚከናወን ይሆናል። በአውሮፓ ክለቦች በሚጫወቱ ወጣቶች የተዋቀረው የኮትዲቯር ብሄራዊ ቡድን ዘንድሮ ለዋንጫ ይደርሳል የሚል ቅድመ ግምት ባያገኝም ጠንካራ ከሚባሉት ቡድኖች መካከል ይጠቀሳል። የመጨረሻ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ከዩጋንዳ ጋር ያደረገው ቡድኑ 1ለ0 በሆነ ውጤት ነበር የተረታው። ሆኖም በዛሬው ጨዋታ አሸናፊ ለመሆን የሚጫወቱት ዝሆኖቹ ዋንጫውን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ አቅደው ተሳትፏቸውን እያደረጉም ይገኛሉ። ባፋና ባፋናዎች እአአ 2015 እና 2017 የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ መሆኑን ተከትሎ በዚህ ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚጫወቱ መሆኑን የቡድኑ አባላት ይገልጻሉ። ሞሮኮ፣ ኮትዲቯርና ናሚቢያ ከተደለደሉበት ምድብ የሚገኘው ቡድኑ የረጅም ጊዜ የዋንጫ ረሃባቸውን ለማስታገስ ወደ ግብፅ እንደተጓዙም አስታውቀዋል። በቤልጂየም በሚገኘው ክለብ የሚጫወተው ፔርሲ ታኡ ከቢቢሲ ባደረገው ቆይታ፤ ምድቡ ጠንካራ የሚባል ቢሆንም ቡድናቸው ግን ከዚህ ቀደም ካስመዘገበው ውጤት የተሻለ ነገር ለማስመዝገብ የሚጫወት መሆኑን ጠቁሟል። አሰልጣኝ ስትዋርት ባክስተር ቡድኑን ከተቀላቀሉ በኋላም በቡድኑ የራስ መተማመን ስሜት እንደጎለበተም ተጫዋቹ ጠቅሷል። እኛም የአሰለጣጠኑን እንዲሁም አጨዋወቱን ተከትለን በመጫወት የተሻለ ውጤት እንደምናስመዘግብ እናምናለን። እርሱ ቡድኑን ከያዘ ጀምሮም ቡድኑ ለውጥ በማሳየት ላይ ይገኛል ሲልም አክሏል። በምድብ አምስት ሁለት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን፤ ቱኒዚያ ከአንጎላ እንዲሁም ማሊ ከሞሪታኒያ ይገናኛሉ። በዚህ ምድብ የተሻለ ግምት የሚሰጠው ብሄራዊ ቡድንም የቱኒዚያ ነው። የካርቴጅ ንስሮች በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ቡድኑ እአአ በ2004 ዋንጫውን በሃገሩ ማስቀረቱ የሚታወስ ነው። አንጎላ በመድረኩ የሚጠቀስ ውጤት የሌላት ከመሆኑ ባሻገር በምድቡ አስፈሪ ሊባል የሚችል ቡድን ባለመኖሩ ቱኒዚያ በቀላሉ ከምድቧ ማለፍ እንደምትችል ይጠበቃል። በፊፋ ማስጠንቀቂያ ሲሰነዘርባት የቆየችው ማሊም በመድረኩ አዲስ ገቢ የሆነችውን ሞሪታኒያን ታስተናግዳለች። እአአ 1972 ለፍጻሜ የደረሰችው እንዲሁም 2012 እና 2013 ሦስተኛ በመሆን ውድድሯን ያጠናቀቀችው ማሊ አዲሲቷን ሃገር በቀላሉ ልትረታ እንደምትችልም ይገመታል። በነገው ዕለትም የምድብ ስድስቶቹ ሻምፒዮናዋ ካሜሩን ከጊኒ-ቢሳዋ እና ጋና ከቤኒን የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።አዲስ ዘመን ሰኔ 17/2011 ብርሃን ፈይሳ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13146
c75fd5f862a25a28d05eb4ca761faaf0
186529f7b60d89b46b4ce0fea00acab4
የወርቃማዎቹ እንስቶች የዳይመንድ ሊግ ፍጥጫ
 ውድድር ዓመቱ የዳይመንድ ሊግ ፉክክሮች እየተጋመሱ መጥተው የአሜሪካዋ ዩጂን ከተማ ደርሰዋል፡፡ ዩጂን ዛሬ በተለያዩ ርቀቶች በርካታ ፉክክሮችን ስታስተናግድ በሴቶች መካከል የሚካሄደው የሦስት ሺ ሜትር ውድድር ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ሆኗል፡፡ የኦሊምፒክና የዓለም ቻምፒዮኗ ኢትዮጵያዊት አትሌት አልማዝ አያና ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ውድድር ተመልሳ የመጀመሪያ ፉክክሯን ዩጂን ላይ ታደርጋለች፡፡ አልማዝ ወደ ውድድር መመለሷ ለፉክክሩ ድምቀት የሰጠው ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ምድር በርካታ የዓለማችን ድንቅ አትሌቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡ ከነዚህም መካከል አልማዝን ጨምሮ ገንዘቤ ዲባባ፣ሔለን ኦቢሪ፣ሲፈን ሃሰን፣ካስተር ሲሜንያና ሌሎችም ድንቅ የመካከለኛና የረጅም ርቀት አትሌቶች ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። በውድድር ዓመቱ አምስት ሺ ሜትርን በበላይነት ተቆጣጥራ የያዘችው ኬንያዊቷ ኮከብ አትሌት ሔለን ኦቢሪ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ለመሆን የምታደርገውን ጉዞ በዩጂን አጠናክራ እንደምትቀጥል ይጠበቃል። የሃያ ዘጠኝ ዓመቷ ኦቢሪ የዓለም ቻምፒዮን ከመሆኗ ባሻገር በዘንድሮው ዓመት በአገር አቋራጭ ቻምፒዮና ወርቅ ማጥለቅ ችላለች፡፡ ባለፈው ሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ካጠለቀች ወዲህም በለንደን አትሌቲክስ ቻምፒዮና ወርቅ ማጥለቋ ይታወሳል። ከ1500 ሜትር ሯጭነት ተነስታ በረጅም ርቀት ኮከብ አትሌት መሆን የቻለችው ኦቢሪ እኤአ 2013 ላይ በዚሁ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ድንቅ ብቃት አሳይታለች፡፡ 2014 ላይም በአሜሪካ ምድር የምን ጊዜም ፈጣን ሰዓት የሆነውን 3፡57፡05 ማስመዝገቧ በዛሬው ውድድር ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት እንዲሰጣት አድርጓል፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኔዘርላንድስ አትሌት ሲፈን ሃሰን 2015 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳመንድ ሊግ ውድድር አሸናፊ መሆኗ የሚታወስ ሲሆን በ2016 አሜሪካ ፖርትላንድ የቤት ውስጥ የዓለም ቻምፒዮና ወርቅ ማጥለቅ ችላለች፡፡ ሲፈን ያለፈውን የ2017 ውድድር ዓመትን በተለያዩ ሦስት ርቀቶች ከምርጥ አምስት አትሌቶች ውስጥ መካተት ችላለች። ከ8 መቶ ሜትር እስከ 5 ኪሎ ሜትር ድንቅ ብቃት ማሳየት የቻለችው ሲፈን ባለፈው የውድድር ዓመት በ5ኪሎ ሜትር ሁለተኛና በ1500 ሜትር ሦስተኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች፡፡ ዘንድሮም ሲፈን በድንቅ አቋም ላይ የምትገኝ አትሌት መሆኗ በዩጂን ለአሸናፊነት ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡ ከፆታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ውስጥ የምትገኘው ደቡብ አፍሪካዊት ካስተር ሲሜንያ በዩጂን ዳይመንድ ሊግ መካተቷ ውድድሩን በተወሰነ ደረጃውን ከፍ እንዲል አድርጓታል፡፡ የሁለት ኦሊምፒክና ሦስት የዓለም ቻምፒዮና አሸናፊዋ ሲሜንያ በ8መቶ ሜትር ለሰላሳኛ ጊዜ ያለመሸነፍ ጉዞዋን ማስጠበቅ በመቻሏ አድናቆትን አትርፋለች። ከለመደችው የመወዳደሪያ ርቀት ከፍ ብላ በሦስት ሺ ሜትር የምታደርገውን ፉክክርም በተደጋጋሚ ማሸነፍ እንደምትችል ማሳየቷን ተከትሎ ለርቀቱ ኮከቦች ፈተና እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡ የ28 ዓመቷ ድንቅ የመካከለኛና ረጅም ርቀት አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከሰባት በላይ የዓለም ክብረወሰኖችን መያዝ የቻለች ሲሆን በዩጂን ባለፉት ሦስት የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች የተፎካከረችው በ5 ሺ ሜትር ነው፡፡ በተለይም 2015 ላይ በዚሁ በ5ሺ ሜትር 14:19.76 በመሮጥ በአሜሪካ ምድር የምንጊዜም ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ችላለች። ገንዘቤ ባለፈው ዓመት በዓለም የቤት ውስጥ ቻምፒዮና በ1500ና 3 ሺ ሜትር ጥምር ወርቅ በማጥለቅ የመጀመሪያዋ የዓለማችን አትሌት መሆን ችላለች። በዘንድሮው ዓመት 1500 ሜትርን 359፡08 አስመዝግባ ማሸነፍ የቻለች ሲሆን በ3 ሺ ሜትር ደግሞ በዶሃ ዳይመንድ ሊግ ኬንያዊቷ ኦቢሪን ተከትላ 8:26.20 ሰዓት ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ ከጉዳት ተመልሳ የመጀመሪያ ውድድሯን የምታደርገው አልማዝ በሪዮ ኦሊምፒክ 10ሺ ሜትርን 29፡17፡45 በሆነ የዓለም ክብረወሰን ሰዓት ማሸነፏ የሚታወስ ሲሆን 2016 ላይ የ5ሺ ሜትር የዳይመንድ ሊጉ አጠቃላይ አሸናፊ ነበረች። በ2015 የቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮና የውድድሩን ክብረወሰን በማሻሻል በ5ሺ ሜትር ስታሸንፍ በ2017 የዓለም ቻምፒዮና በ10ሺ ሜትር ወርቅ ማጥለቋ አይዘነጋም፡፡ ካለፈው አንድ ዓመት በላይ ግን አልማዝ በጉዳት ከውድድር ርቃ ቆይታለች። ይህም በክረምቱ መጨረሻ ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ቻምፒዮና አትደርስም የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር፡፡ አልማዝ አሁን ልምምዷን በተገቢ ሁኔታ እያከናወነች ሲሆን የዩጂን ዳይመንድ ሊግም ድንቅ ብቃቷን ታሳይበታለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በ2015 የቤጂንግ የዓለም ቻምፒዮና የ5ሺ ሜትር ውድድር በበርካቶች ዘንድ አሁንም ድረስ ይታወሳል፡፡ በዚያ ውድድር አልማዝ አያና ከሦስት ሺ ሜርት በኋላ አፈትልካ በመውጣት ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ በሁለተኛነት የማጠናቀቅ ሰፊ እድል የነበራት ገንዘቤ ዲባባ ነበረች፡፡ ይሁን እንጂ ገንዘቤ ውድድሩን ለመጨረስ ከሃምሳ ሜትር ያነሰ ርቀት በቀራት ወቅት ሰንበሬ ተፈሪ ከኋላ መጥታ የብር ሜዳሊያውን ማጥለቋ ይታወሳል፡፡ ሰንበሬ በዩጂኑ ውድድር እነዚሁን የአገሯን ልጆች ጨምሮ ሌሎች ኮከቦች በሚፎካከሩበት ዳይመንድ ሊግ ተካታለች፡፡ ለተሰንበት ግደይና ፋንቱ ወርቁ በዚህ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 23/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13329
fde580251c112687162bcf2696e3062e
02715ac18a6a7bee6707a6bc4b3d735e
አትሌቲክስና ጉዳት
ስፖርት ለጉዳት መንስኤ ነው ባይባልም፤ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ግን ለጉዳት አጋላጭ መሆናቸው ይታወቃል። በዓለም ላይ ከሚዘወተሩ በርካታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መካከልም እግር ኳስ፣ መረብ ኳስ እና ቤዝቦል በጉዳት አጋላጭነታቸው ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። ኢትዮጵያ ስሟን ያስጠራችበትና ከቀዳሚዎቹ ተወዳጅ ስፖርቶች መካከል አንዱ የሆነው አትሌቲክስ ከጉዳት ጋር ያለው ቁርኝት ምን ይመስላል? በዛሬው ዕትምም በአትሌቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ምክንያት፣ ህክምናው እንዲሁም በዚህ ዘርፍ በኢትዮጵያ ያለው ተሞክሮ ምን ይመስላል የሚለውን ይዳስሳል። በዚህ አርዕስት ላይ ሙያዊ ማብራሪያ የሰጡንም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ህክምና ከፍተኛ ባለሙያ እንዲሁም በጸረ- አበረታች ቅመሞች ጉዳይ ተጠሪዋ ቅድስት ታደሰ ናቸው። አትሌቲክስ ሰፊና በውስጡም በርካታ የውድድር ዓይነቶችን ያቀፈ ስፖርት እንደመሆኑ፤ የተለያዩ ጉዳቶች ይስተናገዳሉ። ከአጭር ርቀት ሩጫ እስከ ሜዳ ተግባራት ባሉት ስፖርቶች አትሌቶች በብዛት ከጡንቻ፣ ከህብለ ሰረሰር፣ ከጅማት፣ ከደም ቧንቧ፣ ከአጥንት … ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ያስተናግዳሉ። ኢትዮጵያ በተለይ የምትታወቀው በሩጫ ስፖርቶች እንደመሆኑ በእግር ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች የሚያመዝኑ ሲሆን፤ ዓይነቱም ከቀላልና መካከለኛ ከፍተኛ ህክምና እስከሚያ ስፈልጋቸው ጉዳቶች ይዘልቃሉ። አንዳንድ የጉዳት ዓይነቶች እረፍት በማድረግና በቀላል ህክምና ሲድኑ፤ ስር የሰደደ ጉዳት ደግሞ ረጅም ጊዜ ሊወስድና እስከ ቀዶ ጥገና ሊደርስም ይችላል። የጉዳት መንስኤዎች እንደ ጉዳት ዓይነቶቹ የተለያዩ ቢሆኑም፤ ከልምምድ ጋር በተያያዘ በደንብ ባለማሳሰብ፣ በቂ ውሃ ባለመውሰድ፣ በውድድር ላይ፣ በቂ እረፍት ባለማድረግ፣ እንደ ስፖርት ዓይነቱ ከሚጠቀሟቸው ቁሳቁሶች ጋር በተገናኘ፣ ከስነ-ምግብ አለመመጣጠን አሊያም አትሌቶቹ በዓመቱ መጀመሪያ ቅድመ ጤና ምርመራ ካለማድረግ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ ውጤታማ የሆነችበት የረጅም ርቀት ሩጫ እንደመሆኑ በዚህ ዘርፍ የሚታየው ጉዳት ከጫና ጋር በተያያዘ የሚደርስ ነው። በልምምድና ውድድር ጫና ምክንያትም አትሌቶች በተለይ ስብራትን ለመሰለ ጉዳት ተጋላጭ ይሆናሉ። በመካከለኛ እና አጭር ርቀት ሩጫዎች በአመዛኙ የሚስተዋለው ደግሞ ጡንቻ ላይ ጉዳት እንደሚደርስ ነው። በእርግጥ ከጉዳት በኃላ የሚኖረው የማገገሚያ ጊዜ እንደ አትሌቱ ጉዳት የሚወሰን እንደሚሆን ባለሙያዋ ያስረዳሉ። አትሌቱ የደረሰበት ጉዳት በህክምና ባለሙያዎች ከታየ በኃላ ከመንስኤው በመነሳት የማገገሚያ ጊዜው እንዲሁም የማገገሚያ ዓይነቱ ሊለያይ ይችላል። ከጉዳቱ ክብደት ባለፈም በሴት እና በወንድ አትሌቶች ላይ የሚደርሰው የጉዳት ዓይነት ልዩነት ሊኖረው ስለሚችልም ህክምናውም ሆነ የማገገሚያ ጊዜው ላይ ልዩነት ይኖራል። እንደሚታወቀው ስፖርት በኢትዮጵያ ከሳይንሳዊው መንገድ ይልቅ ወደ ተለምዶአዊ አሰለጣጠን ያደላል። አትሌቲክስ በዚህ ቅድሚያ ተጠቃሽ ሲሆን፤ ባህላዊ ሊባል በሚችል መልኩ አትሌቶች አሰልጥነው እስከ ብሔራዊ ቡድን መድረሳቸውም እሙን ነው። በዚህ መልክ መሰልጠናቸው ሙሉ ለሙሉ ስህተት ነው ሊባል ባይችልም ግን በሳይንሳዊ መንገድ ማሰልጠን ቢቻል የውጤታማነት መንገዱ ሊቀል እንዲሁም ሊደርሱ ከሚችሉ ጉዳቶችና ያለ ዕድሜ ከስፖርቱ የመራቅ ችግር ሊቀረፍ ይችላል። ጉዳትም በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ይገኛል፤ በተለይ በዚህ ወቅት ማሳጅ ቤቶችና ወጌሻዎች በየአካባቢው ተበራክተዋል። በብዛት እንደሚታየው ከሆነም አትሌቶች ጉዳት ሲያስተናግዱ ወደዚሁ መሄድን ምርጫቸው ያደርጋሉ። ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነም፤ አትሌቱ በልምምድ ወቅት ከሚሰራቸው እንቅስቃሴዎች በተጓዳኝ ፊዚዮቴራፒ እና ማሳጅቴራፒ በጉዳት ላይ የራሱ ድርሻ አለው። ከዚህም ባሻገር የስፖርት ህክምና ከስነ-ምግብ እና ስነ-ልቦና ጋርም ተመጋጋቢ ነው። አንዱን ከአንዱ መነጠል ከባድ ቢሆንም፤ አሁን ባለው አሰራር ግን እንደ ሃገር በርካታ የሚጠበቁ ነገሮች አሉ። ከማሳጅና ወጌሻ ጋር በተያያዘ በትምህርት ስርዓት ውስጥ ተካቶና የህክምና ባለሙያዎች ገብተውበት ከመስራት አኳያ በርካታ ክፍተቶች አሉ። ችግሩ በተለይ የሚስተዋለው ደግሞ በክለቦች እና በስልጠኛ ማዕከላት ላይ ነው። ለዚህ ምክንያት የሆነው የግንዛቤ ችግር፤ በስፖርቱ ባለድርሻ አካላትም ትኩረት ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ባለሙያዋ ያመለክታሉ። ቴራፒ ራሱን የቻለ ትልቅ ሙያ ሲሆን፤ በሌላው ዓለም ትምህርቱ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እሰከ ሶስተኛ ዲግሪ የሚሰጥ ነው። እዚህ የሚስተዋለው ባህላዊውን የህክምና ዘዴ በአንዴ ማውጣት ባይቻልም፤ በምን መልኩ መስተካከል ይገባዋል የሚለውም ቁልፍ ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ ባለሙያዋ ያስረዳሉ። ግንዛቤውም ለአትሌቶችና ከአትሌቶች ጋር አብረው ለሚሰሩ አካላት መስጠት አስፈላጊ ይሆናል። ፌዴሬሽኑ ከኃላፊነቶቹ መካከል ለባለ ሙያዎች ስልጠና እና ድጋፍ መስጠት አንዱ እንደሆነ ይታወቃል። በስፖርት ህክምና ላይ እንደ ሃገር ያለው እንቅስቃሴ እዚህ ግባ ባይባልም፤ የሙያ ማሻሻያ ከሚሰጥባቸው ዘርፎች መካከልም አንዱ የስፖርት ህክምና ነው። ከሳምንታት በፊትም በስፖርት ፊዚዮቴራፒና ተጓዳኝ ርዕሶች ላይ ለሶስት ቀናት በባህር ዳር ከተማ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው 69 ባለሙያዎችን በመያዝ በሁለት ተከፍሎ የተሰጠ ሲሆን፤ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች እንዲሁም በክለቦችና ማሰልጠኛ ማዕከላት የሚገኙ የማሳጅና ፊዚዮ ቴራፒ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ነበር። ከዚህ በተጓዳኝ ለጡንቻ እና በነርቭ ጉዳት ተጋላጭ የሆኑ አትሌቶችና ሰልጣኞች በባለሙያዎቹ ህክምና አግኝተዋል። ስልጠናውን የሰጠው በስፔን የሚገኝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ባለሙያዎች ቡድን በዓመታዊው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ላይ የመገኘት ልምድ እንዳለው ባለሙያዋ ይጠቁማሉ። ስልጠናውን የሰጡት 33 ባለሙያዎች ሲሆኑ፤ 27 የሚሆኑ በተለያዩ ክሊኒኮች የሚሰሩ ፊዚዮ ቴራፒስቶች እንዲሁም ስድስት የዘርፉ መምህራን ናቸው። የዚህን ዓመት ልዩ የሚያደርገውም ከስልጠናው ባሻገር ከፌዴሬሽኑ እንዲሁም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በአጭር እና ረጅም ጊዜ ስልጠናዎች ላይ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው። በሃገሪቷ ዘርፉ ያለው እንቅስቃሴ የጎላ አለመሆኑ ዋናው ክፍተት ሲሆን፤ ትምህርቱንም በተሻለ መልኩ በውጪ ሃገራት ነው ማግኘት የሚቻለው። በመሆኑም ልምድ ካላቸው የታወቁ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ትምህርቱ (ስልጠናው) ላይ መስራትና ራሱን የቻለ መስመር ቢዘረጋለት መልካም እንደሚሆን ባለሙያዋ ያመላክታሉ። ያሉትን ጅምሮችም አጠናክሮ በመቀጠል ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ እንዲቻል ባለድርሻ አካላት አጽንኦት መስጠት ተገቢ ነው። እንደሚታወቀው አትሌቲክስ ኢትዮጵያ የምትጠራበት ትልቁ ስፖርት ነው። በመሆኑም ሁሉም አካል ለስፖርት ህክምና አትኩሮት ኖሯቸው፤ ክለቦችና የማሰልጠኛ ማዕከላት በቂና በስርዓት የሰለጠኑ የስፖርት ህክምና ባለሙያዎች ቢኖሯቸው አትሌቶችን ከጉዳት ለመታደግ እንዲሁም የተሻለ ህክምና ለማግኘት ይቻላል። ይህንንም መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 24/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13360
b1d8f8ea0b21287c8d35dcb50a3267bd
077088a66213e3bade2344cea1c4e6d1
የአፍሪካ ወርቃማ እግሮች
በአፍሪካ አህጉር የእግር ኳስ ታላቁ ድግስ ከተጀመረ ሁለተኛ ሳምንቱን አስቆጥሯል። ግብጽ 32ኛውን አፍሪካ ዋንጫ ድግስ በካይሮ፣ አሌክሳንድሪያ፣ ኢስማኤሊያ እና ስዊዝ በተባሉት ከተሞቿ እያስተናገደችው ትገኛለች። በአውሮፓ ሊጎች ስመ ጥር የሆኑት፤ ሞሃመድ ሳላህ፣ ሳዲኦ ማኔ፣ ናቢ ኬታ፣ ሪያድ ማህሬዝ፣ ሃኪም ዚያክ፣ ኒኮላስ ፔፔ፣ ዊልፍሪድ ዛሃ፣ ሙሳ ማሬጋ፣ ካሊዱ ሉሊባሊ እና ቶማስ ፓርቴን የመሳሰሉ ተጫዋቾችም በውድድሩ በመፋለም ላይ ይገኛሉ። በርካታ አዳዲስ ነገሮች የታዩበትን የዘንድሮውን የአፍሪካ ዋንጫ፤ ለአሸናፊነት ከሚደረገው ፍልሚያ ባሻገር አህጉራቸውን ተሻግረው በሌላው ዓለምም ተጽእኖ መፍጠር የቻሉ አንጋፋ ተጫዋቾች እያደመቁት ይገኛሉ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ሰባት የአህጉሪቷን ባለ ወርቃማ እግር ተጫዋቾች በአምባሳደርነት ሰይሟል። በአፍሪካ የምንጊዜም ታላላቅ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ተርታ ከሚሰለፉት መካከል አንዱ የውድድር አዘጋጇ ሃገር ግብጽ የቀድሞ ተጫዋች ሞሃመድ አል ቃቲብ ነው። አንጋፋው ተጫዋች እአአ በ1983 ፈርኦኖቹ የመጀመሪያውን ዋንጫ ሲያነሱ ከቡድኑ አባላት መካከል ነበር። «ቢቦ» በሚል ቅጽል የሚጠራው ተጫዋቹ ሃገሩ አዘጋጅታ ሻምፒዮን የሆነችበትን እአአ የ1986 የአፍሪካ ዋንጫን አንስቷል። በአፍሪካ ዋንጫ ግብ በማስቆጠር ቀዳሚውን ስፍራ የተቆናጠጠው ካሜሩናዊው ሳሙኤል ኤቶም በዚህ ውድድር በአምባሳደርነት የተገኘ ተጫዋች ነው። በባርሴሎና እና ኢንተርሚላን የተሳካ ጊዜ ማሳለፍ የቻለው ኤቶ ለአራት ጊዜያት (እአአ በ2003፣ 2004፣ 2005 እና 2010) የካፍ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠ ታሪካዊ ተጫዋች ነው። ኤቶ ከካሜሩን ብሄራዊ ቡድን ጋር በመሆንም እአአ የ2000 እና 2002 የአፍሪካ ዋንጫዎችን አንስቷል። ኮትዲቯራዊያኑ ያያ ቱሬ እና ዲድየር ድሮግባም በውድድሩ በአምባሳደርነት ተሰይመዋል። በሌላው ዓለምና በሃገሩ ከምርጥ ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ያያ ቱሬ፤ ካፍ በተከታታይ ለአራት ዓመታት (እአአ ከ2011-2014) ምርጥ ተጫዋች ሲል መርጦታል። ሃገሩ እአአ በ2015 ሻምፒዮን ስትሆንም ተጫዋቹ ከቡድኑ ጋር ነበር። ሌላኛው የሃገሩ ልጅ ተወዳጁ ዲድየር ድሮግባ በአምስት የአፍሪካ ዋንጫዎች (እአአ 2006፣ 2008፣ 2010፣ 2012 እና 2013) ሃገሩን ወክሎ ለፍጻሜ በቅቷል። በታወቀበት የእንግሊዙ ክለብ ቼልሲ እንዲሁም ለሃገሩ ብሄራዊ ቡድን ባበረከታቸው አስተዋጽኦዎች ስሙ የሚወሳው ድሮግባ እአአ በ2006 እና 2009 የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች በሚል ተመርጧል። እአአ በ1990 አልጄሪያ የአፍሪካ ዋንጫን በምድሯ አሰናድታ ዋንጫውን ያስቀረችበት ቡድን አባል የሆነው ራቤህ ማጀር፤ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ ካፍ በአምባሳደርነት ከሾማቸው የወርቃማ እግር ባለቤቶች መካከል አንዱ ነው። ተጫዋቹ በተለይ በፖርቹጋሉ ክለብ ፖርቶ ያደርግ በነበረው እንቅስቃሴ ስሙ የሚነሳ ሲሆን፤ እአአ በ1987 ለአፍሪካ ክብር በቅቷል። ዋንኮ ካኑ ሌላኛው ከናይጄሪያ ተገኝቶ በአፍሪካ አህጉር ደምቀው ከታዩት ኮከቦች መካከል የሚገኝ ነው። እአአ ከ2000 – 2010 በተካሄዱት ስድስት የአፍሪካ ዋንጫዎች የተሳተፈው ይህ ተጫዋች እአአ 1996 እና 1999 የካፍ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ነው። በካሜሩን ብሄራዊ ቡድን ከፍተኛ ስፍራ ያለው አል ሃጂ ዲዩፍም ከአምባሳደሮቹ መካከል አንዱ ነው። እአአ በ2000 አካባቢ በዓለም ዙሪያ ስመጥር የሆነውና ወርቃማው ትውልድ በሚል የሚታወቀው ቡድን አባል የሆነው ዲዩፍ እአአ በ 2001 እና 2002 የአፍሪካን ክብር ሊቀዳጅ ችሏል። አዲስ ዘመን ሰኔ 24/2011
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13367
62c402752184cfad438c1784eab0de44
13d2c48a2cd4e4fa3592edecfcaae8c6
የስነ – ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት ለወጣቶች የህግ የበላይነትን የማስገንዘብ ክፍተት እንዳለበት ተገለጸ
አዲስ አበባ፡- የስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር ትምህርት በሃገራችን ለሚገኙ ወጣቶች የህግ የበላይነትን የማስገንዘብ ክፍተት እንደነበረበት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው ችግር ማሳያ እንደሆነ ተገለጸ። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለምአቀፍ ትምህርት መምህር እና የትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የስነምግባር መምህር የሆኑት ዶክተር ሞገስ ደምሴ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የስነ – ዜጋ እና የስነ-ምግባር ትምህርት በሀገራችን ለሚገኙ ወጣቶች የህግ የበላይነትን የማስገንዘብ ክፍተት ነበረበት። ተጨባጭ ማሳያውም ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው ችግር ነው።ስነ – ዜጋ እና ስነ – መግባር ትምህርት እንደሌሎች የትምህርት ዓይነቶች በንድፈ ሃሳብ ላይ ብቻ ያተኮረ ስለነበር፤ በተግባር የተማሪዎችን ባህሪይ ከመጀመሪያው ጀምሮ ኮትኩቶ በማሳደግ እና በመቅረጽ ውስንነቶች እንደነበሩበት ያመለከቱት ዶክተር ሞገስ፤ ወጣቶች ህግን ያለማክበር፣ ለስነምግባር ተገዥ ያለመሆን እና የማህበረሰቡ እሴት የኔ ናቸው ብሎ ያለማሰብ እና ከስነምግባር ያፈነገጡ ችግሮች በስፋት እየታየባቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ለክፍተቱ ማሳያ እንደሚሆን ተናግረዋል። በዋነኛነትም ስርዓተ ትምህርቱ ለገዥው ፓርቲ አስተሳሰብ ማስፈፀሚያ ነው ብሎ ህብረተሰቡና ተማሪዎች የማሰብ ዝንባሌ ስለነበር ወጣቶች ለትምህርቱ የሚሰጡት ቦታ ዝቅተኛ እንዲሆን አድርጎታል ያሉት ዶክተር ሞገስ፤ በቦታው በቂ ስልጠና የነበራቸው መምህራንም አለመኖር የታሰበውን ትምህርት መስጠት እናዳልተቻለ አስታውቀዋል። መምህራን በትክክል የዴሞክራሲን መርሆችን ሲያስተምሩ እና ወጣቱ ለህግ የበላይነት መታገል ሲጀምር መንግሥት እናንተ ያልሆነአጀንዳ እያሰረፃችሁ ነው በሚል መምህራኑን ስለሚከስ ትምህርቱን በልበ ሙሉነት እንዳያስተምሩ ማድረጉን አመልክተዋል።በእነዚህ እና ተያያዥ በሆኑ ሌሎች ችግሮች ቀደም ሲል ይሰጥ የነበረው የስነዜጋ እና የስነምግባር ትምህርቱ ለወጣቱ የህግ የበላይነትን ማስገንዘብ እንዳልቻለ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ወጣቱም ለህግ የበላነት ያለው አመለካከት ዝቅተኛ እንዲሆን ማድረጉን አመልክተዋል።ወጣቱ ለህግ የበላይነት ያለውን አመለካከት ለመቀየር የስነ ዜጋ እና ስነምግባር ትምህርት እንደ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች በንድፈ ሃሳብ ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑ ቀርቶ በተግባር የተደገፈ እና ስርዓተ ትምህርቱም መቀየር እንደሚኖርበት ጠቁመዋል። በዚህም ወጣቱ ሃገራዊ እሴቱን የተገነዘበና ዝም ብሎ የሚገፋ ሳይሆን መጠየቅ የሚችል ብሎም ለህግ የበላይነት መቆም የሚችል ዜጋ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የስነ ዜጋ እና ስነ ምግባር ትምህርት ጄኔራል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ለገሰ ነጋሻ በበኩላቸው የስነ ዜጋና ስነመግባር ትምህርት የነበሩበት ክፍተቶች በጥናት ተለይተው እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች መኖራቸውን አስታወቀዋል።የስነ ዜጋ እና ስነምግባር ትምህርት የሚለው ግብረገብ እና ዜግነት ትምህርት ወደሚል እንደተቀየረ የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በቀጣይ ተማሪዎች እራሳቸውን እና ህብረተሰባቸውን የሚገልጹበት፣ ሃገራዊ እሴቶቻቸውና መርሆዎች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሄድበት ሁኔታ ይኖራል ብለዋል። ግብረገብነት የሚባለው ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ ስድስተኛ ክፍል ለብቻው እራሱን ችሎ እንዲሰጥ፣ የዜግነት ትምህርቱ ደግሞ ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል እንዲሰጥ የሚያስችል ስርዓተ ትምህርት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል። በዚህም የወጣቱን ስነምግባር መቀየር እንደሚቻል አመልክተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012አሸብር ኃይሉ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35711
ddc2327d8eda5c38575908f5f0320f5f
38f48767cc66dc61e9c6ff1dae46b8ab
ስፖርትና ፖለቲካ ምን እና ምን ናቸው?
ስፖርት አንድ ትልቅ ማሕበራዊክንውን ነው።በተለይ በዚህ ዘመን ስፖርት ትልቅ የገቢ ምንጭም ነው፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን በተለይም በእግር ኳሱ መንደር እየተከሰቱ የመጡ ሁከቶችን ተከትሎ ስፖርትና ፖለቲካን ምን አገናኛቸው? በሚል በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ሙግት ሲገጥሙ ይታያል፡፡ በአንድ ወገን ስፖርትና ፖለቲካ አይገናኙም የሚሉ ሞጋቾች ፖለቲካና መንግሥት በስፖርቱ አካባቢ መድረስ የለባቸውም የሚል አቋም ሲያንፀባርቁ ይስተዋላል፡፡ በሌላ በኩል ስፖርት ብቻም ሳይሆን ሁሉም ነገር ፖለቲካ መሆኑን የሚያስቀምጡ ወገኖች ስፖርት ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሊሆን እንደማይችል ያስቀምጣሉ፡፡ከዚህ በተለየ መልኩ ስፖርት በመሰረታዊ ፅንሰ ሃሳቡ ከፖለቲካ ነፃ መሆን እንዳለበት ወይም ነፃ ቢሆን ይመረጣል፣ ነገር ግን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ እንደማይሆን በርካታ ማሳያዎችን የሚያስቀምጡ ምሁራን በርካታ ናቸው፡፡ስፖርት በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ሁነኛ የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ ማገልገል እንደቻለ ማስተዋል ይቻላል፡፡ስፖርት በጥሩ ከተጠቀምንበት ምላሹ ጥሩ እንደሚሆን ሁሉ ለመጥፎ ፖለቲካ አላማ ከተጠቀምንበት በተቃራኒው የሚያስከትለው ጉዳት በቀላል የሚታይ እንዳልሆነ ከታሪክ ማህደሮች መማር ይቻላል፡፡ ለዚህም በዓለማችን በሩቅና በቅርብ ዓመታት ስፖርት ከፖለቲካ ጋር እንዴት እየተሳሰረ እንደመጣ የተለያዩ አጋጣሚዎችንና የአገራትን ተሞክሮ በመዘርዘር መመልከት ይቻላል፡፡አሜሪካበሃያሏ አገር አሜሪካ እጅግ ተወዳጅና ሰፊ ተቀባይነት ባለው የአሜሪካን እግር ኳስ ውስጥ ስፖርት በበርካታ አጋጣሚዎች ከፖለቲካ ጋር ሲተሳሰር ማየት የተለመደ ነው፡፡ በአሜሪካ እግር ኳስ ውስጥ የሚሳተፉ ሃብታምና ዝነኛ ጥቁር ተጫዋቾች በአሜሪካዊያን ጥቁሮች ላይ የሚደረገውን የዘር መድልዎ በመቃወም ከጨዋታ በፊት የአሜሪካ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር መንበርከካቸው ዛሬ የመጣ ነገር አይደለም፡፡ በአሜሪካ እግር ኳስ ብቻም ሳይሆን በቅርጫት ኳስና ሌሎች ስፖርቶች ላይ የሚሳተፉ ታዋቂ ጥቁር ስፖርተኞች አሁንም ተመሳሳይ ነገር ሲያደርጉ ይታያል፡፡ ይህ የጥቁር ተጫዋቾች ተቃውሞ የዋይት ሃውስን በር እያንኳኳም ተፅዕኖ ማሳረፍ ሲችል በግልፅ ታይቷል፡፡ በቅርብ ሰሞን እንኳን የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ይህን የተጫዋቾችን ድርጊት በመቃወም ስቴድየም ጥለው ለመውጣት እስከ መገደድ የደረሱበት አጋጣሚ ይታወሳል፡፡ስፔንበስፔን ታላቁ ውድድር ላሊጋ የዓለማችን ሃያል የእግር ኳስ ክለቦች ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ በሚጫወቱበት ወቅት የሚፈጠረው ድባብ ከስፖርት ይልቅ ወደ ጦርነት የሚያደላ መሆኑን የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ያውቁታል፡፡ ጨዋታው በተገንጣዩ የካታላን ግዛት ወኪል ባርሴሎናና በማእከላዊያን ወኪል ሪያል ማድሪድ መካከል የሚደረግ መሆኑ እያንዳንዱ ጨዋታ ከፖለቲካ ትኩሳት ነፃ ሆኖ አያውቅም፡፡ የባርሴሎናው የተከላካይ መስመር ተጫዋች ጄራርድ ፒኬ በአንድ ወቅት ‹‹ከአሁን በኋላ ካታላን ለሚባል አገር እንጂ ስፔን ለሚባል አገር አልጫወትም›› ብሎ በአደባባይ ማወጁ ጨዋታው የሚካሄድበትን ድባብ ይገልጻል። ከስፔን ሳንወጣ በሁለቱ የማድሪድ ክለቦች ሪያል ማድሪድና አትሌቲኮ ማድሪድ መካከል የሚደረገው ጨዋታም ስፖርታዊ አይደለም። ፍጹም የፖለቲካ መንፈስ የሚንጸባረቅበት ነው። በአምባገነኑ ጀነራል ፍራንኮ ዘመን ከሪያል ማድሪድ ይልቅ አትሌቲኮ ማድሪድ መንግሥታዊ ድጋፍ ያገኝ ነበር ተብሎ ስለሚታመን የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ዘወትር ከፖለቲካ ተፅዕኖ ወጥቶ አያውቅም።ደቡብ አፍሪካኔልሰን ማንዴላ በአፓርታይድ ስርዓት ምክንያት የተቃቃረውን ደቡብ አፍሪካዊ ሁሉ አንድ ያደረጉት የራግቢን ስፖርት ተጠቅመው ነበር። ማዲባ ደቡብ አፍሪካ የዓለም ራግቢ ዋንጫን አዘጋጅ የነበረችበትን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የራሳቸውን የተለየ መርሐግብር በማውጣት ቡድናቸውን እያበረታቱ ደቡብ አፍሪካ ብታሸንፍም ባታሸንፍም በስፖርት አማካኝነት የአገሪቱ ህዝብ ወደ አንድ ሊመጣ እንደሚችል ቀድመው ተረድተዋል፡፡ የነፃነት ታጋዩ እድል ሲቀናቸው ቡድናቸው ዋንጫ ወሰደ፡፡ ይህም የተቃቃረው ህዝብ በደስታ ስሜት ቂሙን ረስቶ ተቃቅፎ በአንድ ላይ ይቅር የሚባባልበትን አጋጣሚ እንዲፈጠር አደረገ፡፡የነፃነት ታጋይና የሰላም አባት የሆኑት ማንዴላም በዓለም አቀፉ የስፖርት መድረክ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት ባደረጉት ትግል፣ ስፖርታዊ ውድድሮች በረጅሙ ዘመን የእርሳቸውና ሕዝባቸው እልህ አስጨራሽ የፀረ-አፓርታይድ የነፃነት ተጋድሏቸው ወቅት ‹‹ሰላማዊ የትግል ስልት›› መሆኑን ላሳዩበት ፖለቲካዊ ብቃታቸው በተሰጣቸው ዓለም አቀፍ ሽልማት ላይ ባደረጉት ንግግር ‹‹ ስፖርት ዓለምን ለመቀየርና ህዝቦችን አንድ ለማድረግ ትልቅ ሃይል አለው›› በማለት ገልፀውታል፡፡እንግሊዝና አርጀንቲናታላላቆቹ የእግር ኳስ አገራት እንግሊዝና አርጀንቲና በዓለም ዋንጫም ይሁን በሌሎች አጋጣሚዎች ሲጫወቱ ከኳስነቱ ይልቅ ፖለቲካነቱ እንደሚያመዝን በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡ እኤአ በ1982 ለአስር ያህል ሳምንታት በፎክላንድ ደሴቶች ምክንያት ሁለቱ አገራት የገጠሙት የውጊያ ታሪክ አሁንም ድረስ በሰላማዊው ጦርነት በኳስ ሜዳ ይከተላቸዋል፡፡ ከፍተኛ የሆነ ጦርነት ውስጥ ገብተው የነበሩት ሁለቱ አገራት ሲገናኙ ከኳሱ ውጤት ጀርባ የሚመነዘር ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ይራመዳል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኳሳዊ ሽንፈት የክብር፣የማንነት፣የሐገር፣የፖለቲካ ጉዳይ በመሆኑ ነው። በይበልጥ የሁለቱ አገራት የኳስ ፉክክር መክረር የጀመረውም ከጦርነቱ በኋላ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሴኔጋልና ፈረንሳይፈረንሳይ ባስተናገደችው የዓለም ዋንጫ በመክፈቻው ጨዋታ በሴኔጋል አንድ ለዜሮ መሸነፏ ከኳሱ ውጤት ይልቅ ፖለቲካዊ አንደምታው ትልቅ እንደነበር ይታወሳል፡፡ሴኔጋል ፈረንሳይን አሸነፈች፣ አፍሪካውያን ሁሉ በአንድ እግር ቆመው አጨበጨቡ፣ጨፈሩ፡፡ ምክንያቱም ሴኔጋል በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ውስጥ ወድቃ ነበር። ስለዚህ የሴኔጋል ፈረንሳይን ማሸነፍ ከኳስ በላይ ሊተረጎም የቻለ የመላውን አፍሪካውያን ስነልቦና የቀየረ ፖለቲካዊ አንድምታ ነበረው ማለት ነው፡፡ቻይናቻይና በ2050 አካባቢ የዓለምን እግር ኳስ መቆጣጠር እንደምትፈልግ ይታወቃል፡፡ለዚህም በመላው ቻይና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕጻናት እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የስፖርት አካዳሚዎች ተከፍቶላቸው ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ተመልምለው የኳስ ስልጠና እየወሰዱ ነው። የቻይና ክለቦች ልጆቻቸው ብቁ እስከሚሆኑ ድረስ የዓለምን ቀልብ ለመሳብ ከስፔን እና እንግሊዝ ተጫዎቾችን እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ እየገዙ የሚወስዱት ስፖርትን ብቻ አስበው እንዳልሆነ ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ አንድ አገር በዓለም ላይ የበላይነትን ለማሳየት ስፖርትም አንዱ አማራጭ መሆኑ ቻይናውያን ዘግይተውም ቢሆን ገብቷቸዋል፡፡ ጀርመንጀርመን ከሌላ አገር ጋር ገጥማ ስትሸነፍ በኳስ ብቻ የተሸነፈች አይመስልም፡፡ ይህም የሆነው ጀርመናውያን በኳስ የሚመጣ ሽንፈትን የክብር፣የፖለቲካና የስነልቦና ሽንፈት አድርገው ስለሚመለከቱት መሆኑ ይገለፃል፡፡ ይህንን የሚያደርጉት ኳስ የፖለቲካ ዋና መሳሪያ እንደሆነ በአግባቡ ስለሚረዱ መሆኑንም የሚናገሩ በርካታ ናቸው፡፡አሜሪካና ኢራንየ1998ቱ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ስፖርት ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለአንድነት … ወዘተ ያለው አዎንታዊ ፋይዳ በግልፅ የታየበት መድረክ ሆኖ ነበር ያለፈው። በአንድ ምድብ ተደልድለው የተገናኙት በጥንታዊ ስልጣኔዋ የምትታወቀው ኢራን ከዘመናችን ሃያሏ አገር አሜሪካ ጋር ነበር። እነዚህ ሁለት የፖለቲካ ባላንጣ አገሮች በአንድ ቡድን ተደልድለው የተገናኙበትን ጨዋታና ፉክክር ‹‹የጨዋታዎች ሁሉ እናት›› በማለት ነበር የአሜሪካው እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በአጭር ቃል የገለጹት፡፡ በወቅቱም ስለ ሁለቱ አገራት ጨዋታ የዘገቡ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሁለቱ አገራት ፖለቲከኞች፣ ዲፕሎማቶች፣ የእግር ኳስ ባለሙያዎችና ተንታኞች ጨዋታው ከስፖርታዊ ውድድር ባለፈ ጠንከር ያለ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው ሲዘግቡ ቆይተዋል፡፡ ከእግር ኳስ ፉክክሩ ባሻገር ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ በተነገረበት በዚህ የአሜሪካንና የኢራን ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ፣ ሁለቱ አገሮች በስፖርቱ መድረክ ለሰላምና ለመልካም ግንኙነት ያላቸውን አዎንታዊ ፍላጎትና ስሜት የገለጹበት መልካምና ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ይታወሳል፡፡በተጨማሪም የሁለቱ አገሮች ደጋፊዎች በውድድሩ ወቅት ያሳዩት ሰላማዊነትና ስፖርታዊ ጨዋነት ‹‹ስፖርት ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት፣ ለትብብር፣ ለወንድማማችነት›› የሚለውን የስፖርት መርህ ከፍ አድርጎ ለዓለም ሕዝብ ያሳየ ነበር። ጥቂት የማይባሉ የሁለቱ አገራት እግር ኳስ አፍቃሪያንና ደጋፊዎች አንድ ጉንጫቸውን በአሜሪካን አንድ ጉንጫቸውን ደግሞ በኢራን ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት በማስዋብ የእግር ኳስ ስፖርት በአገሮችና በሕዝቦች መካከል መቀራረብና ሰላም እንዲፈጠር የሚያስችል መድረክ መሆኑን በተግባር ለዓለም አሳይተውበታል። ይህን የወቅቱን እውነታ ያስተዋለው የኢራኑ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆነው አፍሺህን የእግር ኳስ ስፖርት አገራትን በሰላምና በፍቅር መንፈስ ለማስተሳሰር ያለውን ጉልበት እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው ‹‹ይህችን ዓለም በአንድ ላይ ለማምጣት ሁለት ነገሮች ብቻ ቁልፍ ናቸው፣ እነሱም እግር ኳስና ፍቅር ይባላሉ››፡፡ማጠቃለያየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ባንኪሙን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እ.ኤ.አ ግንቦት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ‹‹ስፖርት ለሰላምና ለልማት ያለው አስተዋጽዖ›› በሚል ባደረጉት ንግግራቸው እንዳረጋገጡት፤ ስፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገሮችን ድንበር ተሻግሮ የዘር፣ የጎሳና የኃይማኖት ልዩነቶች ሳይገድበው፣ የዓለም አቀፍ ቋንቋ መሆን እንደቻለና ስፖርታዊ ውድድሮች ለሰው ልጆች ሰላም፣ አንድነትና እድገት እየተጫወቱ ያለውን ቁልፍ ሚና መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ስፖርታዊ ውድድሮች የሰላም፣ የወንድማማችነትና የፍቅር መድረክ ናቸው ቢባሉም አልፎ አልፎም ቢሆን የዘረኝነት መንፈስ የሚንጸባረቅባቸው፣ የሌሎችን ክብርና ነፃነት የሚጋፋ ኃይማኖታዊ መልዕክቶች፣ ፖለቲካዊ ተቃውሞች፣ ጠብና ግጭት ድረስ የሚዘልቁ ክስተቶችን ማስተናገዳቸው አልቀረም።እንግሊዝና አርጀንቲና፣ የላቲን አሜሪካኖቹ የኤልሳልቫዶርና ሆንድራስ በእግር ኳስ ጨዋታ ምክንያት የተፋጠጡበትንና ጦር የተማዘዙበት አጋጣሚዎች ሲታሰቡ የስፖርቱ መድረክ አልፎ አልፎም ቢሆን የፖለቲካ አጀንዳዎች እንደማያጣው ያስገነዝበናል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 22/2011ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=13281
c06c62122ec53090b6e581b79a10858e
d15f30bcb6e72f469cccfb6b74adf3cd
«የኦሮሞ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው ኦነግ ሸኔ ነው»- አቶ ታዬ ደንደኣ፣ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
 አዲስ አበባ፦ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው ኦነግ ሸኔ መሆኑን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አስታወቁ። ህወሓት ኦነግ ሸኔን በአደባባይ እንደ ጠላት እየፈረጀ በተግባር ግን የኦሮሞን ትግል ለማክሰም እንደ መሣሪያ ይጠቀምበት እንደነበረም አመለከቱ።አቶ ታዬ ደንደኣ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ያካሄደው የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ፍሬያማ እንዳይሆን ኦነግ ሸኔ ከህወሃት ጋር የነበረው ከሕዝብ የተሰወረ ህብረት ዋንኛ ምክንያት ነው ብለዋል። ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ታጋዮች አንድ ወጥመድ ሆኖ ለህወሃት ሲያገለግል እንደነበርም አመልክተዋል።ብዙዎች ኦነግ ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ እያለው የዚህ ድርጅት ትግል ለምንድን ነው ወደፊት ገፍቶ የማይመጣው? የሚል ጥያቄ ነበራቸው። በርካታ ወጣቶች እና ምሁራን እንዲሁም መምህራንም ይሄንኑ ይጠይቁ እንደነበር አመልክተው፣ የኦነግ ትግል እውነተኛ የነፃነት ትግል ነው ብለን በማመን ትግሉን ከተቀላቀልን በኋላ ግን ኦነግ ሸኔ እና ህወሓት አብረው እንደሚሰሩ መገንዘብ ተችሏል። ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ መሆኑንም መረዳት ተችሏል ብለዋል። «የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት ይፈልጋል (ኦሮሞ ብቻም ሳይሆን ኢትዮጵያውያንም ነፃነት ፈልገው ዋጋ ሲከፍሉ ነበር)፤ ይሄን ነፃነት ማን ያመጣልኛል ብሎ ሲያስብ ደግሞ አንድ በነፃነት ስም የተደራጀ ድርጅት አለ ብሎ በማመን የትግሉ አካል ይሆን ነበር። ይሄ ድርጅት ግን ጭንቅላቱ በህወሓት በመያዙ እና ይህንን ሕዝቡ በሚገባ ባለማወቁ ብዙ ዋጋ ከፍሏል ሲሉ አስታውቀዋል። «ህወሓት ኦነግ ሸኔን ሆን ብሎ በዚያ ደረጃ የኦሮሞ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ወጣት፣ የኦሮሞ ምሑር የሌለ ነገር እንዲጠብቅ፤ በሴራ ያስቀመጠው ድርጅት ነው» ያሉት አቶ ታዬ፣ በዚህ መልኩም ለሃያ ዓመታት ያህል ተጠቅመውበታል፤ በተለይም አቶ ገላሳ ዲልቦ ከሥልጣን ወርደው የአሁኑ የሸኔ ሊቀመንበር ሥልጣን ከያዘ በኋላ በቀጥታ ትብብሩ ውስጥ እንደነበሩም አመልክተዋል። «ኦህዴድ ውስጥ ሆነህ ኦሮሞ ላይ ጉዳት ደርሷል ብለህ ካነሳህ ኦነግ ትባላለህ። የኦሮሞ ባለሀብት ሆነህ ሊዘርፉህ ከፈለጉ ኦነግ ይሉሃል። ይሄን የሚያደርጉት ደግሞ ኦነግ የሌለ ከሆነ የሚፈርጁበት ስለሌለ ስለሚቸገሩ ነው። ስለዚህ ኦነግ እንደሌለና በእነርሱ ስር እንዳለ ቢያውቁትም፤ በኦነግ ስም ተማሪን ለመደብደብም፣ መምህራንን ለማሰርም፣ ነገ ይገዳደረኛል ብሎ የሚያስቡትን ለመግደልም ይጠቀሙበታል፤ ህወሓት በዚያ ደረጃ በኦነግ ሸኔ ተጠቅሟል ሲሉም ተናግረዋል።ከዚያም በላይ ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ታጋዮች አንድ ወጥመድ ሆኖ አገልግሏል የሚሉት አቶ ታዬ ደንደኣ ፣ ለምሳሌ እኔ ሁለት ጊዜ ታስሬያለሁ። አስር ዓመት እስር ቤት ቆይቻለሁ። ሁለቱንም ጊዜ ያሳሰረኝ የኦነግ ሸኔ አባል ነው። ያሳሰረኝ ኦህዴድ አይደለም፤ ህወሓትም ራሱ ፈልጎ አላገኘኝም። ለህወሓት የሰጠኝ ኦነግ ሸኔ ነው። አብረው ስለሚሰሩ በገንዘብም ይሸጡሃል። እንዲያውም አንዳንዴ አደራጅተውና የኦነግን ባንዲራ አስይዘው አሳልፈው ለህወሃት ይሰጡሃልም ብለዋል። ለምሳሌ፣ ግርማ ጥሩነህ የሚባል የሸኔ ተወካይ 2008 አካባቢ ቦሌ ላይ 20 ሰዎችን ማህበር ብሎ በአንድ ጊዜ አደራጅቶና የኦነግ ሸኔ ባንዲራ አስቀምጦ ደህንነትን ጠርቶ አስይዟቸዋል ያሉት አቶ ታዬ፣ እናም በዚያ ደረጃ ነው በሰው የሚነግዱት ይላሉ። ከተያዝክና ከታሰርክ በኋላ ደግሞ ጀግና ታሰረ ብለው ውጪ ያሉት አባሎቻቸው በስደት እያሉ የሕዝቡን ነፃነት ከሚፈልጉ የዋሆች ላይ ገንዘብ እንደሚሰበስቡም አመልክተዋል። ከዚያ ባሻገር እነሱ የመሸጉበት ሶሎሎ የሚባል አካባቢ አለ። እዚህ መከራ ሲያይ፤ ሲታሰርና ሲገረፍ የተቸገረ ሰው በቃ ሄጄ ታጥቄ ልታገል ብሎ ወደዚያው ይሄዳል። እዚያም ይታይና ሃሳብ ያለው ከሆነና ጀግንነት ያለው ከሆነ እዚያው ይገደላል፤ ወይ ይቃጠላል። ይሄን የሚያደርጉት ደግሞ ይህ ሰው ነገ አብዮት ሊያመጣ ይችላል ብለው ስለሚሰጉ እንደሆነም ጠቁመዋል። እንደ አቶ ታዬ ማብራሪያ፤ ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ከዚህም ባለፈ መረጃም የሚለዋወጡ ናቸው። ለአብነት፣ ኅብረተሰቡ ሲያምጽ የወያኔ መልስ ጥይት ነው፤ ግድያ ነው። በተለያየ ጊዜ በተማሪ ደረጃ፣ በወጣት ደረጃ፣ በ2006 ዓ.ም ከዚያም በፊት በ1998፣ በ1996 እና በተለያየ ጊዜ የተለያዩ አመጾች በተለይ በኦሮሚያ ክልል ተደርገዋል። በጣም የሚያሳዝንህ ግን በዚህ ውስጥም የሴራ ፖለቲካ እንዲታይ ሆኗል። በሴራውም ህወሓት በአጠቃላይም የኢህአዴግ መንግሥት ንጹሃን ኦሮሞዎችን ገድሏል፤ ሰብዓዊ መብትም ተጥሷል በሚል በዓለምአቀፍ ደረጃ (በአምነስት ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስ ዎችና ሌሎችም) ክስ ይቀርብበታል። ይህ ክስ ሲቀርብ ህወሓት የሚያደርገው ነገር በእኔ ትዕዛዝ ነው ሕዝቡ ያመጸው በልና መግለጫ አውጣ ብሎ የሚያነበውን መግለጫ ጽፎ ለኦነግ ሸኔ ይልክለታል። ኦነግ ሸኔም አስመራ ላይ ሆኖ በህወሓት ተጽፎ የቀረበለትም መግለጫ ያነብባል።  የእኛ ትግል ነው ብሎ ያነበበውን የእርሱን መግለጫም እነ ቪኦኤና ዶቼቬሌ ጭምር ያስተላልፉታል። ህወሓት/ኢህአዴግ ደግሞ ይሄንን ተጠቅሞ እንቅስቃሴው የሕዝብ አልነበረም፤ የአሸባሪው ኦነግ ነው ብሎ ራሱን ለመከላከል መልስ ይሰጣል። እናም በዚህ ደረጃ በረቀቀ መልኩ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ አብረው ሲሰሩ እንደነበርም አስታውቀዋል። ይሄንን በደንብ ለመረዳት በኢሬቻ ጊዜ በርካታ ዜጎች ሕይወታቸው አልፏል። በተቃውሞ ጊዜም በተለይ «ግራንድ ራሊ» ተብሎ በተደረገው ትልቅ ሰልፍ የብዙ ወጣቶች ሕይወት አልፏል። የኦሮሞ ሕዝብ በአብዲ ኢሌ እና በህወሓት ሴራ በሚሊዮን የሚቆጠር ከሶማሌ ክልል ተፈናቅሏል፤ ሞቷልም። እንግዲህ ተኩስ ቢያስፈልግ ያን ጊዜ ጀግና ወጥቶ መተኮስ ነበረበት። ወጣቱ በሰላማዊ መንገድ ወጥቶ ባዶ እጁን መንገድ ላይ ሲረግፍ ኦነግ ሸኔ የሚባለው አንድ ጥይት አይደለም ወደጠላት ወደ ሰማይ አልተኮሰም ብለዋል። ይሁን እንጂ እነ ጌታቸው አሰፋ ከሥልጣን እንደወረዱ ጫካ ታይቶታል። ይህ ምን ማለት ነው? ትግሉ የነፃነት ነው ወይስ ፀረ ነፃነት ነው? ያኔ ሕዝቡ ለነፃነት ሲታገል የት ነበሩ? አዲስ አበባ፣ አማራ ክልል፣ ኦሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ክልል፣ ሶማሌ ክልል ሕዝቡ መከራ ሲያይ፣ ሲገረፍ፣ በግፍ ሲረግፍና ሲገደል አንድ ጥይት ለመተኮስ እንዳልሞከሩ አመልክተዋል። በወቅቱ ከእነርሱ ጋር የነበረ ኮሎኔል አበበ ገረሱ እንደምንም ለዚህ ሕዝብ እንድረስለትም ብለው ሲጠይቃቸው፣ አይ ኢትዮጵያን ሶሪያ አናደርጋትም፣ ተኩስ እዚያ ቢካሄድ ሶሪያ ነው የምትሆነው፤ ኅብረተሰቡ በራሱ ጊዜና በራሱ መንገድ በሰላማዊ መንገድ ቢታገል ነው የሚሻለው ነው ያሉት። ታዲያ ትጥቅ፣ ተኩስና ግድያ ከዚያ በኋላ ለምን አስፈለገ? የሚገድሉት ደግሞ እግር የቆረጠውን፤ ያኮላሸውን፤ ጥፍር የነቀለውናና ሌላም ግፍ ያደረሰውን አይደለም። ትናንት ይሄን ያደረገው ዛሬ የእነርሱ ወዳጅ ነው። አብረው ነው የሚሰሩት። እንዲያውም ሎጀስቲክስም ስትራቴጂም ከዚያ ነው የሚቀበሉት። ስለዚህ ግንኙነታቸው ከድሮም ጀምሮ ያለ እንደነበር አመልክተዋል። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ የሚገባው እና በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ሊነቃበት የሚገባው የኦነግ ሸኔ ፕሮፖጋንዳ የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ጭራቅና ገዳይ እንዲታይ፤ እንደ ሰይጣን እንዲፈራ እና እንዲጠረጠር የሚያደርግ ነው ያሉት አቶ ታዬ ደንደኣ፣ የኦሮሞ ሕዝብ የተለየ ጥያቄ እንዳለው እና ኦሮሞ ከኢትዮጵያ የተለየ እንደሆነ እንጂ፤ ከሌሎች ጋር ተስማምቶ ያለ እና ተመሳሳይ ጥያቄና ችግር ያለው፣ መፍትሄውም በጋራ ብንታገልና በጋራ ብንሰራ ነው የምናገኘው፤ የሚል አስተሳሰብ እንዲመጣ እንደማይፈልግም አስታውቀዋል። በዚህም በኦሮሞና ሶማሌ ነዋሪዎች መካከል ትንሽ እንኳን የግጦሽ ሳር ግጭት ብትፈጠር የፍረጃ ወሬን በማጋጋል ኦሮሞና ሶማሌን የሚያቃቅር፤ በተመሳሳይ በሲዳማና ኦሮሞ አዋሳኝ ላይ ትንሽ ግጭት ቢፈጠር እሱኑ አጋግሎ በኦሮሞና ሲዳማ መካከል ትልቅ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ማድረግ ትልቁ ሥራቸው እንደሆነ ጠቁመዋል። ራሳቸው በፈጠሩት ግርግር በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ አካባቢዎች ጉዳት በደረሰ ጊዜ የሚጠቀማቸው ቃላት ለሌሎች ማህበረሰቦች እጅግ ፀያፍ፤ የሚያበሳጩና ግጭትና ቁርሾን የሚያባብሱም እንደነበሩ አመልክተው፣ በዚህ ደረጃ ይሄን አቃፊ እና የኢትዮጵያ ትልቅ መሠረት የሆነውን ማህበረሰብ፤ ኢትዮጵያውያንን ወዶና አፍቅሮ አብሮ ኢትዮጵያን የመሠረተ እና አብሮም ለማሳደግና ለማሻገር የሚፈልገውን ማህበረሰብ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር እንዳይስማማ፤ እነርሱ በሚሰሩት የፕሮፖጋንዳ ሴራ ሌሎች እንዲጠራጠሩት እየሆነ ነው ብለዋል። ይሄን ማድረግ ደግሞ የህወሓት ባህሪ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ በራሱ የህወሓትና ኦነግ ሸኔ ግንኙነት የት ድረስ እንደሆነ የሚያሳይ እንደሆነም አስታውቀዋል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  ወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35769
69cc4e7669f5fc061c140913fe953f20
941a4214f109f29dab24df081714ddcb
በቀጣይ አስር ዓመት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች ይገነባሉ
አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ ከተሞች እየታየ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በቀጣይ አስር ዓመት ውስጥ በተያዘው የቤቶች ልማት መርሃግብር 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች እንደሚገነቡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ። ቤቶቹ የሚገነቡት በመንግሥት ብቻ እንዳልሆነ አመለከተ። በሚኒስቴሩ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ታደሰ ከበበ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ የቤቶች ልማት መርሃግብር ሪፎርም ያስፈልገዋል ተብሎ በጥናት ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉትአስር ዓመታት 4 ሚሊዮን 4 መቶ ሺ አንድ መቶ ቤቶች ለመገንባት እቅድ ተይዟል። ግንባታውም በአገሪቱ ሁሉም ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል። እርሳቸው እንዳሉት፤ ከሚገነቡ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች ውስጥ የመንግሥት ሚና 20 በመቶውን ብቻ ነው። በዚህ ውስጥ 10/90፣ 20/80 እንዲሁም 40/60 ግንባታቸው ይቀጥላሉ። 10/90 አዲስ አበባ ላይ ቆሞ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን በጥናት በመለየቱ የሚቀጥል ይሆናል። ቀሪዎቹ በፊትም ያሉና አሁንም የሚቀጥሉ ናቸው።እንደ አዲስ የተጨመረው የኪራይ ቤቶች በስፋት የሚገነቡ መሆናቸው መሆኑን ጠቅሰው፣ በተቻለ መጠን ሰዎች በገቢ ልካቸው ሊከራዩ የሚችሏቸውን ቤቶች መንግሥት እንዲገነባ ይደረጋል ብለዋል። በዚህም በመንግሥት የሚገነቡ ቤቶች ወደ አራት ደረጃ ከፍ እንደሚል አብራርተዋል። በሁለተኛ ደረጃ የተያዙት የማህበራት ቤቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ዜጎች በማህበር ተደራጅተው የሚገነቡት ቤት ይገነባል ተብሎ ከተያዘው ከ4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤት 35 በመቶ ያህሉን መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል። በግለሰቦች አሊያም በማህበራት ለሚገነባው ቤት መንግሥት የማደራጀት እና መሬት የማቅረብ ድጋፍ እንደሚያደርግም አመልክተዋል። አቶ ታደሰ እንደገለጹት፤ በሦስተኛ ደረጃ የግለሰቦች ቤት ሲሆን፣ ግለሰቦች በራሳቸው ነባር ይዞታ ላይ ወይም  መንግሥት በሚያወጣው የሊዝ ጨረታ ላይ ተሳትፈው ቤቶችን መገንባት እንዲችሉ አቅጣጫ ተቀምጧል። በእነሱ እንዲገነባ በእቅድ የተያዘው የቤት መጠን ደግሞ ወደ 15 በመቶ ያህል ነው። በአራተኛ ደረጃ የተቀመጠው አማራጭ በመንግሥትና በግል አጋርነት የሚገነባው ቤት ሲሆን፣ በዚህም 15 በመቶ ያህል የሚገነባ እንደሆነ ተናግረዋል። በአምስተኛው አማራጭነት የተቀመጠው ሪልስቴት ሲሆን፣ ባለሀብቶች በዚህ ዘርፍ በስፋት እንዲገነቡ መንግሥት ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም የሚገነባው 10 በመቶ ያህሉ ነው ብለዋል። ሪል ስቴትን ለመደገፍ አዋጅ እያዘጋጁ መሆኑንም ጠቁመዋል። እርሳቸው እንዳብራሩት፤ በመንግሥትና በግል ባለሀብቱ ብሎም በግሉ ዘርፍ የሚመደብ በሽርክና የሚሰራ የቤት ግንባታ እንደሚኖር ይታመናል። ስለዚህ በመንግሥት ብቻ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤት ሊመጣ አይችልም። ይህ በመሆኑ በስትራቴጂው የተቀመጠ ሲሆን፣ ስትራቴጂው በሚኒስቴሩ ደረጃ ውይይት ተካሂዶበት ጸድቋል፤ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲያጸድቁት ደግሞ ተልኳል። የተቀናጀ የቤቶች ልማት መርሃግብር የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ የሚባለው በ1996 ዓ.ም ተጀምሮ ወደየክልሎች እንዲሰፋ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ብቻ እስካሁን ባለው መረጃ ከ400 ሺህ ቤቶች በላይ መገንባቱ ይታወቃል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  በአስቴር ኤልያስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35764
12633cc79b5b02528ce2fe6aa79fdc41
813251c63b364137cca3c13626b1fc2c
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ሥራ ገብቶ ማየት የዘወትር ምኞታቸው መሆኑን ነዋሪዎች አመለከቱ
አዲስ አበባ፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁሉም የኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት እንደመሆኑ መጠን ወደ ሥራ ገብቶ ለማየት የዘወ ትር ምኞታቸው መሆኑን አመለከቱ። በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን አባተ እንደተናገሩት፡- የአባይ ግድብ የኛ ጉዳይ ነው። ከጎረቤት ሀገር ጋር ሰላማዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን ነው መወሰን ያለበት። አሁን ላይ መንግሥት የያዘው አቋም ትክክለኛና አግባብነት ያለው በመሆኑ የውሃ ሙሌትም ጊዜውን ጠብቆ መሞላት አለበት እንጂ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም ብለዋል። ኢትዮጵያ ህልውናዋን፤ ክብሯን፤ ነፃነቷን ለማስከበር በፍጹም አትደራደርም የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ የራሳችን የሆነውን አባይ ገድበን ለመጠቀም የማንንም ፈቃድ መጠየቅ የለብንም። እስከአሁን ግብፅ ብቻዋን ስትጠቀም የነበረውን አባይ በጋራ ለመጠቀም የጋራ የሆነ የሚያግባቡ ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው መደራደር የሚቻለው ካልሆነ በራሳችን ንብረት ወደኋላ የምንሸሽበት ምክንያት የለም። እኛ ኢትዮጵያውያን የሰውን ንብረት አንነ ካም የራሳችንን አሳልፈን አንሰጠም ሲሉ አቶ ሰለሞን ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጉን ጉዳዮች እስካሉ ድረስ ከጎረቤትና ከውጭ ሀገራት ጋር ተግባብቶ የመኖር ባህል መሆኑን ጠቁመው፤ የአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያ የልማትና የህልውና ጉዳይ ነው። ‹‹ግድቡ ሲጠናቀቅ ለልጅ ልጆቻችን ልማትና ተጠቃሚነትን በመስጠት ከድህነት የምንወጣበት አንዱ መንገዳችን ይሆናል›› ብለዋል። ለግድቡ መጠናቀቅ ከሌላው ጊዜ በይበልጥ አንድነታችንና አብሮነታችንን በማስጠበቅ የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ ከሀገራችን ጎን በመቆም የውስጥና የውጭ ሰላማችን እንዳይደፈርስ ጠብቀን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ አብረን በመጓዝ ውሃው ተሞልቶ ሥራ መጀመር እንዳለበት አመልክተዋል። ወይዘሮ መንበር መቋጫ በበኩላቸው፡- ግብፅ አባይ ብቻዋን ለዘመናት ስትጠቀም መቆየቷን የራሷን አድርጋ እንደትቆጥር ያደረጋት መሆኑን ጠቁመው፤ ግድቡ የኢትዮጵያውያን እንጂ የግብፅ ወይም የሌላ የውጭ ሀገር ንብረት አይደለም። የግድቡ ውሃ ሙሌት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ ሳይሆን በቶሎ ውሃው ተሞልቶ ከውሃ ሀብታችን ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዳለን መታወቅ አለበት ብለዋል። ‹‹ እኔ ባለኝ አቅም ከምንሠራው ትንሽ ሥራ አጠራቅሜ ቦንድ ገዝቻለሁ፤ የልጅ ልጄም ቦንድ እንዲገዛ አድርጌያለሁ›› የሚሉት ወይዘሮዋ፤ ከዚህም በላይ ለግድቡ ግንባታ የበኩላቸውን መወጣታቸውን ገልጸዋል። አባይ ህይወታችን መጦሪያ ቅርሳችን ነውም ብለዋል። እሳቸው የሚጦሩበት ልጆቻቸው የሚከብሩበት የአባይ ግድብ ተገድቦ ተጠቃሚ ለመሆን መጓጓታቸውን በመግለጽ፤ የግድቡ ሙሌት እውን እንዲሆን መንግሥት የያዘውን አቋም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ የሆነውን የግድቡን ውሃ መሌት ለማደናቀፍ በማሰብ በውጭ ገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚጥሩ የውስጥም ሆነ የውጭ ኃይሎች መኖራቸ ውን ገልጸው፤ የግድቡ የልማት ሥራዎች በእነሱ ድርጊት የማይቋረጥ መሆኑን አውቀው አርፈው በመቀመጥ ከእኩይ ድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ህዝቡ ሀገር ለማፍረስ የሚጥሩ ኃይሎች ምንም ጊዜ እንደማያንቀላፉ አውቆ ብልጥ በመሆን ለእነሱ ዕድሉን መስጠት የለብንም። ሁሉም ዜጋ ይህንን አውቆ የተሰማራበትን ሥራ ጠንክሮ በመሥራት ግድቡን ወደ ፊት ማስኬድ እንዳለበት አመልክተዋል። ከአባይ የምንጠብቀው ወጣቱ ትውልድ መስኖ እያለማ ሀገሩን በማበልጸግ የሥራ ዕድል የሚያገኝበት እንዲሆን ነውም ሲሉ ተናግረዋል። አባይ የሁላችንም አሻራ ያለበት ነው። ሁሉም ሰው የሚችለውን በማድረግ የተሳተፈበት በመሆኑ ግድቡን መድረስ ያለበት ቦታ ደርሶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ እያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅበትን መወጣት እንዳለበት ጠቁመዋል። ሁላችንም ተባብረን አባይን የእኛ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል። ‹‹ ግድቡ ተጠናቅቆ ለኔም ደርሶ ይረዳኛል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ›› የሚሉት አቶ ኋሊት ከሊል በበኩላቸው፤አባይ የህልውናችን መሠረት በመሆኑ ማንም እንዳንገድብ ሊያደርገን አይገባም። ግድቡ ድሮም ለግብፅ እየፈሰሰ እኛ የምንሞገስበት ሀብታችን ቢሆንም፤ አሁንም ደግሞ ተገድቦልን እኛም ከግድባችን ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባን አመልክተዋል። ምንም እንኳን አባይ ለረጅም ዘመናት ሳይገደብ በመኖሩ ቢቆጩም ዛሬ ላይ ተገድቦ ለማየት ተስፋ የጣሉበት በመሆኑ የግድብ የውሃ ሙሌት መጀመር እንዳለበት ጠቁመው፤ ህዳሴው ግድብ ተጠናቆ ሥራ እስኪጀምር ድረስ ሁሉም ያለውን አቅም ተጠቅሞ ግድቡን እውን ለማድረግ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  በወርቅነሽ ደምሰው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35765
79ebecdb99d97d8cc2109bada1afbbeb
36111acd5363a101c29ed1160bf1fdc3
ትከሻ አጉባጩ የዋጋ ንረት
ሸማቹ ማህበረሰብ ላይ በየቀኑ ዋጋ ካልጨመሩ ምድርና ሰማይ ይገለባበጣል የሚባልላቸውና በኢ-ሰላማዊ ወቅት ድሃውን ኅብረተሰብ የሚበዘብዙ አካላት ዛሬም የብዝበዛ ጦራቸውን ሰብቀዋል። በከተማ ደረጃም ሆነ በክልል በሚፈጠር ግጭት ምክንያት ድሃው የኅብረተሰብ ክፍል በግብይት ምክንያት እየተጎዳ ይገኛል። ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ድንገተኛ ግድያ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ አለመረጋጋት፣ እጥረት ተፈጥሮ ነው በሚል ሰበብ በሽንኩርት (ቀይና ነጭ)፣ ቲማቲም፣ ቃሪያ፣ ድንች፣ የጎመን ዓይነቶችና ሌሎች ፍራፍሬዎችም ላይ የተደረገው ጭማሪ ዜጎችን ለተጨማሪ ወጪ ከመዳረጉ ባሻገር፤ መደበኛ አኗኗራቸው ላይም ተጽእኖ መፍጠሩ ተሰምቷል። በአዲስ አበባ ያነጋገርናቸው አንዳንድ ነዋሪዎች ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ የአትክልት ዋጋ በእጅጉ ማደጉ ከሌሎች ወጪዎች ጋር ተዳምሮ ቤተሰብን ለማስተዳደር መቸገራቸውን ይናገራሉ። በአትክልት የዋጋ ንረት ሕይወታቸው ላይ ጫና ካሳረፈባቸው የአዲስ አበባ ኗሪዎች መካከል ወይዘሮ ትርንጉ ጉታ አንዷ ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚኖሩት ወይዘሮ ትርንጎ ለበርካታ ዓመታት የመስተንግዶ ሥራ በመስራት ቤተሰቦቻቸውን ሲያስተዳድሩ ከርመዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን «የኑሮ መወደድ ከአቅሜ በላይ ሆኖ እያንገዳገደኝ ነው» ይላሉ ሰሞነኛውን የአትክልት ዋጋ ንረት እንደ አብነት በማንሳት። ወይዘሮ ትርንጎ የሦስት ልጆች እናት ሲሆኑ ሁሉም ልጆቻቸው በትምህርት ላይ ናቸው። የሚያሳድጓቸውም ያለ አባት ነው። አሁን ላይ በየጊዜው የሚጨምረውን የኑሮ ውድነት መቋቋም ባለመቻላቸው መጪው ጊዜ ፈተና ሆኖባቸዋል። የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆኑት ወይዘሮ ትርንጎ፤«ኅብረተሰቡ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫው ከሚያደርጋቸውና ለምግብነት የሚጠቀማቸው የአትክልት ምርቶች ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ በተለይ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ላለነው የኅብረተሰብ ክፍሎች አትክልት ገዝቶ ለመብላት ፈተና ሆኖብናል» ይላሉ። አሁናዊው ሁኔታ መጪውን ጊዜ ይበልጥ እንዲፈሩት ያደረገው ወይዘሮ ትርንጎ፤ በኑሮ ውድነቱ ተስፋቸው ከዕለት ወደ ዕለት እንዲሟጠጥ ተጨማሪ ምክንያት የሆናቸው ደግሞ እርሳቸውን ለመሰሉ ከኑሮ ጋር እልህ አስጨራሽ ግብግብ ለገጠሙ ሰዎች በፖለቲካ ልሂቃን ዘንድ ብዙም ትኩረት እየተሰጠ አለመሆኑ ጭምር ነው። እንደ ወይዘሮ ትርንጎ ገለጻ፤ ጉዳዩ ከፍ ሲልም፤ የብሔር ጉዳይን እያራገቡ የራሳቸውን ሥልጣን ለማመቻቸት የድሃውን ጉዳይ ልብ ያላሉትንም ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል። በመሆኑም ፖለቲከኞች የራሳቸውን ጉዳይ ከማስፈፀም ወጥተው ውስጥን የሚነካና ስለኑሮ ጉዳይ ትኩረት የሚሰጥ አጀንዳ ቀርጸው ከመንግሥት ጋር መስራት ይጠበቅባቸዋል። ከወይዘሮ ትርንጎ ሀሳብ ጋር በሚስማማ መልኩ አስተያየት የሰጡት ሌላኛው የመዲናዋ ነዋሪ አቶ ተስፋዬ ጸጋዬ፤ አጠቃላይ የኑሮ ውድነት ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መምጣቱን በከፍተኛ ምሬት ይናገራሉ። ቀደም ሲል ከነበረው አመጋገብ በጥራትና በመጠን ባነሰ ሁኔታ ለመመገብ መገደዳቸውንና የኑሮ ውድነቱ ከመሻል ይልቅ በየጊዜው እየናረ መምጣቱን በመግለጽ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸውንም ገልጸዋል። በቅርቡ በአትክልት ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በአብዛኛው ከእጥፍ በላይ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ተስፋዬ፤ በጃንሜዳ አትክልት ተራ አንድ ኪሎ ከ20 ብር በታች ይሸጥ የነበረው ቀይ ሽንኩርት በአሁኑ ወቅት እስከ አርባ ብር እየተሸጠ መሆኑን፤ እስከ አስር ብር ይሸጥ የነበረው ቲማቲም አሁን ላይ ከ20 እስከ 25 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ለአብነት ጠቅሰዋል። ዋጋ መጨመሩ ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ምርቶችን ከአምስት ኪሎ በታች መግዛት ስለማይቻል ችግሩን አግዝፎታልም ይላሉ። በግብይቱ አቅም ያላቸው ያሻቸውን ቢገዙም ድሃው የኅብረተሰብ ክፍል ግን «በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ» ስለሆነበት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ከገበያው ተሰውሯል። » ይላሉ። በአትክልት ንግድ ላይ የተሰማሩት አቶ ተረፈ ሰለሞን በበኩላቸው፤ የዋጋ ግሽበትን ተከትሎ የተከሰተው የኑሮ ውድነቱ እንዳለ በማመን፤ በዚህም ሁሉም ባይሆኑም አንዳንድ ነጋዴዎች በአገሪቷ የተከሰተውን አለመረጋጋት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የማይፈታ ችግር እስከሚመስል ዋጋ በመጨመር ይበልጡንም በየጊዜው የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ ማድረጋቸውን ይናገራሉ። ቢሆንም በታማኝነት ያለዋጋ ጭማሪ የሚሰሩ ነጋዴዎች እንዳሉም ጠቁመዋል። አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች አላግባብ የዋጋ ጭማሪ ማድረግን እንዲያቆሙና መንግሥትም ጉዳዩን በትኩረት ሊመለከተው እንደሚገባም አስገንዝበዋል። አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአትክልትና ፍራፍሬ ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን አስመልክቶ «ምን እየተሰራ ነው?» የሚለውን ለማጣራት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጋር በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።አዲስ ዘመን ሀምሌ 14፣ 2012  በአዲሱ ገረመው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35767
b1a3501fdd8fd3d50121f7be2e154380
5e195906ff398d9e9986d06ce04419a1
ሶስቱ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀሉ ክለቦች
በሶስቱም ምድቦች ተከፍሎ በሚካሄደው የከፍተኛ ሊግ ውድድር በመጪው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የሚቀላቀሉ ሶስት ክለቦች ታውቀዋል። ሰበታ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕናም የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በከፍተኛ ሊጉ ምድብ «ሀ» የሚገኘው ሰበታ ከተማ ከተከታዩ በሳምንቱ መጨረሻ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ባደረገው ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ አንድ ጨዋታ እየቀረውም ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን ያረጋገጠ ክለብ ሆኗል። ለሊጉ አዲስ ያልሆነው ሰበታ በተሳትፎው ተፎካካሪ መሆን ቢችልም በኋላ ኋላ አቋሙ በመውረዱ በ2003 ዓ.ም ፕሪሚየር ሊጉን መሰናበቱ ይታወሳል። ዳግም ወደ ሊጉ ለመመለስም ስምንት የውድድር ዓመታትን መጠበቅ ግድ ያለው ሲሆን፣ በመጨረሻም ይህ ፍላጎቱ ሰምሮለታል። በምድብ «ለ» የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ሌላው በመጪው ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከምንመለከታቸው ክለቦች አንዱ መሆኑን ያረጋገጠ ክለብ ነው። ከሜዳቸው ውጪ ከነገሌ አርሲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ አቻ መውጣት አሊያም የመድንን ነጥብ መጣል ብቻ መጠባበቅ ግድ ያላቸው ወልቂጤዎች፤ ጨዋታውን በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል። ውጤቱን ተከትሎም እንደ ሰበታ ከተማ ሁሉ ወልቂጤም አንድ ጨዋታ እየቀራቸው በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ የሚያደርጋቸውን ትኬት ቆርጠዋል። በምድብ «ሐ» ሲወዳደሩ የቆዩት ሀዲያ ሆሳዕና ወይንም ነብሮቹ በቀጣዩ ዓመት ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፈው ሶስተኛው ክለብ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ሃዲያ ሆሳዕናዎች ይህን ማሳካት የቻሉትም በሜዳቸው ከከምባታ ሺንሺቾ ጋር ያደ ረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በማሸነፍ ሆኗል። ውጤቱም ሁለት ጨዋታ እየቀራቸው በቀጣዩ ዓመት የሊጉ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። እንደ ሰበታ ሁሉ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ ያልሆኑት ሀዲያ ሆሳዕናዎች በ2008 ዓ.ም የውድድር ዓመት በሊጉ ተፎካካሪ ክለብ ማስመልከታቸው አይዘነጋም። የዘንድሮው ከፍተኛ ሊግ እንደከዚህ ቀደሙ ለበርካታ ጊዜያት ሳይቆራረጥ በመካሄዱ ሶስቱ ክለቦች ከወዲሁ ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቅለዋል። በአሁኑ ወቅት ዋናው የሊግ ውድድርም በቀጣዩ ዓመት ከማይሳተፉ ክለቦች መካከል አንዱን በይፋ ተዋውቋል። በወቅታዊ የሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአስ ራሶስት ነጥብ የመጨረሻው ደረጃ ላይ የተቀመጠው ደደቢት በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የማይሳተፍ መሆኑን ቀድሞ ያረጋገጠ ክለብ ሲሆን፤ ከደደቢት ከፍ ብለው የተቀመጡት ደቡብ ፖሊስ እና ስሁል ሽረ የወራጅነት አደጋ ያንዣበበባቸው ሆነዋል። ከሁለቱ ከለቦች በተጓዷኝ በሂሳባዊ ስሌት መሰረት መከላከያ፤ ወላይታ ዲቻ ኢትዮጵያ ቡና ከሊጉ የመውረድ አደጋ ከተጋረጠባቸው ክለቦች ተርታ ስማቸው ተያይዟል። ቀሪ ሶስት የሊጉ ጨዋታዎችም ደደቢትን ተከትሎ በቀጣዩ ዓመት በሊጉ የማንመለከታቸውን ክለቦች ያሳውቃል። የከፍተኛ ሊግ አሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ድሬዳዋ ላይ እንደሚከናወን ታውቋል። ምድባቸውን በአንደኝነት የሚያጠናቅቁት ቡድኖች እርስ በእርስ ጨዋታ አድርገው ከፍተኛ ነጥብ የሰበሰበው ቡድን የከፍተኛ ሊጉ አጠቃላይ አሸናፊ መሆኑን ያረጋግጣል።አዲስ ዘመን ሰኔ 11/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12697
4551627357c58fd0e34a37bc38c30287
f2d60527383f226bdf97a80cd97fa6ac
ውጤት አልባው የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና
ስፖርቱን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ዋንኛ መሠረት እንደሆኑ ይታመናል። ለስፖርቱ መሠረታዊ ለውጥና ውጤታማነት የጀርባ አጥነት እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። በተለያዩ የዕድሜ ደረጃዎች አገርን የሚወክሉ ስፖርተኞችን በዘላቂነት ለማግኘት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ይነገራል፤ የታዳጊና ወጣት ሥልጠና ፕሮጀክቶች። ስፖርተኞች በሳይንሳዊ ሥልጠና ታግዘው በክለቦችና በብሔራዊ ቡድኖች ለመሳተፍ ብቁና ውጤታማ እንዲሆኑ የማሰልጠኛ ማዕከላት ወሳኝ ሚና አላቸው። የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ፕሮጀክቶች፣ ስፖርቱን ለማሳደግ ወሳኝ ናቸው። ችሎታ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች በሳይንሳዊ ሥልጠና ከታገዙ ክለቦችንና ብሔራዊ ቡድንን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል። የታዳጊ እና የወጣት ሥልጠና፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይ የታላላቅ የእግር ኳስ ክለቦች ብቃት ያላቸውን ተጫዋቾችን በማፍራት የስኬት መሠረት ናቸው። ለብሔራዊ ቡድኖች እና ለክለቦች ተተኪ የሚሆኑ ስፖርተኞችን ለማፍራት በታዳጊ ደረጃ ሳይንሳዊ ሥልጠና መስጠት ውጤታማ እንደሚያደርግ ይታወቃል። በኢትዮጵያም መሰል ሥልጠና የሚሰጡ ማዕከላት ወጣቶችን ለማፍራት እየሰሩ ነው። በአገር አቀፍ ደረጃ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመው የታዳጊ ወጣቶች የሥልጠና ልማት ፕሮግራም፣ በዋናነት ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ግብ በማድረግ እንቅስቃሴ ይደርጋል። ሆኖም በታዳጊ ስፖርት ፕሮጀክቶች አመርቂ ውጤት አለመምጣቱ በስፋት ይነገራል። በዘርፍ አዋቂዎች ሆነ ስፖርቱን በሚመራው አካል በኩል ጭምር ውጤታማ አለመሆናቸውን መተማመን መኖሩን ለማስተዋል ተችሏል። የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና ለስፖርቱ እድገት ዋስትና ተደርጎ ቢታመንም፤ የፕሮጀክቱ ውድቀት ለስፖርቱ ቁልቁለት ጉዞ ምክንያት መሆኑም አብሮ ይነሳል። የስፖርቱ መድህን እንደሚሆን የታመነበት የታዳጊዎች ሥልጠና ምዘና ራሱ ድጋፍን እንደሚሻም በዘርፉ አዋቂዎች በኩል በስፋት ይነሳል። ከዚህ በመነሳት የአዲስ አበባ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከሰሞኑ ባዘጋጀው መድረክ ውድቀት ያመዘነበት የታዳጊዎች ወጣቶች ምዘና የቁልቁለት ጉዞን የሚያሳዩ ምክንያቶች በዘርፍ አዋቂዎች በኩል በዝርዝር ቀርበዋል። የኮሚሽኑን ጥናት መሠረት አድርገው አስተያየታቸውን የሰጡት የስፖርት ባለሙያው ዶክተር ኤልያስ አቢሻክራህ እንደተናገሩት፤ በስፖርቱ ውስጥ የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና ላይ የተሰራው ሥራ ፍሬ አልባ የሆነው ከሰልጣኞቸ፣ ከአሰልጣኞች፣ ከስፖርቱ አደረጃጀትና አመራር ድክመቶች መሆናቸውን በጥናቱ ተለይቷል። በመጀመሪያ ደረጃ ከሰልጣኞች አኳያ ያለውን ለመመልከት ያህል፤ በሥልጠና ማዕከላቱ የሚመለመሉ ታዳጊዎች በፍላጎትና በጨዋታ ብቻ መሆኑ ስፖርቱን ጎድቶታል። ምክንያቱም ሰልጣኞቹ በሜዳ ላይ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ባሻገር ሌሎች ቴክኒካል መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ ወደ ሥልጠና ማዕከላት መግባት አለባቸው። ይህን ሳይንሳዊ መንገድ አለመከተሉ የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠናዎች ማምጣት የሚገባቸውን ውጤትም ሆነ ለውጥ ማምጣት እንዳይችሉ ማድረጉን ጥናቱ እንደሚያመላክት ይናገራሉ። ከአሰልጣኞች በኩል ደግሞ ሙያተኞቹ በሥልጠና ፕሮግራሞቻቸው ላይ ምንም ዓይነት ራዕይም ሆነ ግብ አስቀምጠው የመስራት ዝንባሌ የላቸውም። ሰልጣኝ ታዳጊዎቹ ከየት ተነስተው ወዴት ለማድረስ እየሰሩ ስለመሆኑም አያውቁትም። የሥልጠና ውድድሮች ጨርሶ እቅድ የላቸውም፡፡ እንዲሁም የሥልጠና የጊዜ ገደብ ከሁለት ዓመት ያልበለጠ መሆኑ ሰልጣኞቹ በቆይታቸው በቂ የሆነ አቅምና እውቅት ይዘው እንዳይወጡ አድርጓቸዋል። በተመሳሳይ የአንድ ሥልጠና ክፍለ ጊዜ በዕድሜ እርከን የተቀመጠ አይደለም፡፡ የሥልጠና ማዕከላቱ የሥልጠና ሥነ ዘዴዎች ሳያስቀምጡ መስራት፤ የሥልጠና ፕሮግራሙ ውጤታማነት የሚለካው በውድድርና በውድድር ብቻ መሆኑ የውድቀቱ መሠረታዊ ምክንያቶች መሆናቸውን ጥናቱን መሠረት በማድረግ ያስቀምጣሉ። ኢንስትራክተር አለማየሁ ሸዋታጠቅ ደግሞ የውጤት ማጣቱን ከአሰልጣኞች የሙያ ብቃት ችግር ጋር የተያያዘ ነው ይላሉ። ʿየታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና በስፖርት ሳይንስ ምሩቅ ባለሙያ አልያም የስፖርት መምህር ይሰጥʾ የሚል መመሪያ አለ። በስፖርት ሳይንስ ዲግሪ ያለው ወይም ያላት አሰልጣኝ መቅጠሩን እንጂ፤ ባለሙያው ስለ ቮሊ ቦል፣ እግር ኳስ፣ አትሌቲክስ ወዘተ የስፖርት ዓይነት ምን ያህል እውቀትና ቅርበት አለው የሚለው ከግንዛቤ የሚገባ አልነበረም። በስፖርት ሳይንስ ብቻ ዲግሪ ምሩቅ ከሆነ የትኛውንም የስፖርት ዓይነት ያሰለጥናል። ይህ ዓይነቱ አካሄድ በታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶች ውጤታማነት አሉታዊ ነገር ፈጥሯል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በስፖርቱ የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና ሚናው መኮሰሱን ይስማሙበታል። በስፖርቱ ውስጥ የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና ውጤት ለማጣቱ መሠረታዊ ችግሩ የሥልጠና ማንዋሉ መሠረት ያደረገው የዕድሜ እርከን ችግር ያለበት መሆኑ ነው ባይ ናቸው። እንደ አሰልጣኝ ሰውነት ማብራሪያ፤ ታዳጊዎችና ወጣቶች ሥልጠና አማካኝነት የስፖርት ሳይንስና ተግባራዊ ልምምድ ማግኘት አለባቸው ከተባለ ትክክለኛውን ዕድሜ መሠረት ባደረገ መልኩ ማሰልጠን ይገባል። ትክክለኛ ዕድሜ ከየት ይጀምራል የሚለውን ጥያቄን መመለስ ያስፈልጋል። አንዳንድ አገሮች ከሦስት እስከ አምስት ዕድሜ ባሉ ታዳጊዎች ሥልጠና መስጠት ይጀምራሉ፡፡ ከመሰረቱ ስፖርቱን እንዲያውቁት በማድረግ የተለያዩ የዕድሜ እርከኖችን በመከፋፈል ከታች ወደ ላይ በማብቃት ውጤታማ ይሆናሉ። ለምሳሌ እንደ እነ ስፔን ዓይነት አገሮች ከሁለትና ከሦስት ዓመት ጀምሮ ሥልጠና ይሰጣሉ። በተለይ በእግር ኳሱ ያላቸውን ውጤት መመልከት ስልታቸው ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ያሳያል። ከዚህ በመነሳት የአገራችንን ነባራዊ ሁኔታ እንዲህ ይታዘቡታል። «የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠናን በሌሎች አገሮች ከሦስት እስከ አምስት ዓመት ዕድሜ ባላቸው ሕፃናት ሲጀምር፤ በኢትዮጵያ በዚህ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆች የት እንዳሉም አይታወቅም። ከቤታቸውም አይወጡም። የታዳጊ ወጣቶች ሥልጠናን በእኛ ሀገር ከ13 ዓመት ጀምሮ ሥልጠናውን እንጀምራለን። ፕሮግራሙ ከሌሎች አገራት አኳያ እኛ ስምንት ዓመት ወደ ኋላ ቀርተናል። በትክክለኛው የዕድሜ እርከን ላይ ለመስራት እንሞክር ሲሉ ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።» አሰልጣኝ ሰውነት ለተነሱት ችግሮች በመፍትሄነት ባቀረቡት ሃሳብ፤ በታችኛው ዕድሜ ላይ የሚገኙ ታዳጊዎችን ልናወጣቸውና የሌሎቹን ሀገራት ተሞክሮ ልንከተል ይገባል። ትውልዱ የታዳጊዎች ጉዳይ ይመለከተኛል ካለ ትኩረት አድርጎ መስራት ይኖርበታል። ትክክለኛውን የዕድሜ እርከን በጠበቀ መልኩ ብቃትና አቅም ያላቸውን ስፖርተኞች በማፍራት ስፖርቱ ከገባበት ቁዘማና የቁልቁለት ጉዞው መንጥቆ ማውጣት ይቻላል። አሰልጣኝ ሰውነት ሥልጠናው ከየትኛው ዕድሜ እንደሚጀመር የስፖርት ምሁራን ጥናት ማድረግ ይገባቸዋል። በእርግጥም ከታዳጊ ወጣቶች ዕድሜ አጀማመር ጋር ተያይዞ እልፍ ጥናቶች ተደርገዋል። ነገር ግን የታዳጊ ሥልጠና ተግባር ተኮር በመሆኑ ቤት ለቤት ተዘዋውሮ ሕፃኑ ምን እንደሚሰራ መመልከት ያስፈልጋል። ምሁራኑ የሚያደርጉት ጥናትና ምርምር የሕፃናቱን አቅምና ፍላጎት አጤኖ ማሰልጠን ውጤት ሊያመጣ የሚችል መሆኑን መዘንጋት እንደማይገባ ነው ያሳሰቡት። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ለሥልጠና ማዕከላቱም በትክክለኛው መንገድ የሥልጠና ሜዳዎችን፣ ቁሳቁሶችና ሌሎች ድጋፎችን መስጠት ያስፈልጋል። በዚህ መልኩ መጓዙ የሚታየውን ጉድለት ይሞላል፡፡ «ስለ እግር ኳስ እየተነጋገርን ታዳጊዎች ላይ በመስራት ወደ ውጤት ያመጣል የምትሮጠው ለመሮጥ ሳይሆን ለአላማ ሊሆን ይገባል። ስለዚህ የሚሰራው ነገር ለውጤት መሆን ይኖርበታል። በመሆኑም የአላማው ግብ እንዲመታ አስፈላጊውን ድጋፍና ተግባር ተኮር ክትትል ያስፈልጋል። የሥልጠና ማዕከላት ሕፃናትን ሰብስበው መለማመጃ ሜዳ ከሌለ፤ሕፃናትን ሰብስበው ኳስ ካጡ የእግር ኳስ ሜዳ ያላቸው ቡድኖች ይተባበሩ ሲሉ ሃሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡ ዶክተር ኤልያስ አቢሻክራህ በበኩላቸው ፕሮጀክቶች የስፖርት መሠረተ ልማቶች እና የማሰልጠኛ ቁሳቁሶች አሟልተው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ አሰልጣኞች እና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎችን በመቅጠር ጭምር መሰራት አለባቸው፡፡ በወቅታዊ የሥልጠና ማኑዋሎች፤ ሳይንሳዊ ዘዴዎች የጋራ መመሪያ፣ ራዕይና ግብ በመንደፍ ቢንቀሳቀሱ ስኬታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡ ኢንስትራክተር ኤርሚያስ አሽኔ በሰጡት ምክረ ሃሳብ፤ አሰልጣኞቹ ያላቸው ችሎታ ወይም የሥልጠና ብቃት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው። ሳይንሳዊ ሥልጠና በተገቢው መንገድ እንዳይሰጥ እንቅፋት ሆኗል ብዬ አስባለሁ። የሀገራችን እግር ኳስ የይድረስ ይድረስ በመሆኑ ክፍተቱ ሰፊ ነው፡ ፡ ሳይንሳዊ ሥልጠናን ወደ ተግባር ለመተርጎም ከልጅነት ጀምሮ የሚከናወን ነው። እግር ኳስ ቴክኒክ፣ ታክቲክ፣ የአካል ብቃትና ሥነ ልቦና ዝግጅት ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ሁሉ በሥልጠናው ተካተው በተሟላ መልኩ ለወጣቶች መሰጠት አለባቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በዚህ ረገድ ምን ያህል ተሰራ የሚለው ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆንም ሥርዓቱን ተከትሎ እየሄደ ነው ለማለት አያስደፍርም። በመሆኑም ይሄንን አካሄድ በሚገባ ማስተካከል በመፍትሄነት የሚቀርብ ሃሳብ ነው ባይ ናቸው። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ በተነሱት ችግሮችና በተመላከቱት የመፍትሄዎች ሃሳቦች ላይ ተተርስው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ኮሚሽኑ የጥናቱን ውጤት ወደ መሬት በማውረድ በስፖርቱ መሠረታዊ የሆነ ለውጥና ውጤት ለማምጣት ጥረት የሚደረግ ይሆናል ሲሉ አመላክተዋል። የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በበቂ ሁኔታ ያለመኖር ለታዳጊ ወጣቶች ሥልጠና ፕሮጀክቶች የሚጠበቅባቸውን ውጤት ያለማምጣታቸው በሌላ ወገን እንደ ችግር ተነስቷል። ኮሚሽኑ ያለውን ችግር እንደሚረዳና መፍትሄ ለመስጠት ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ነው ያመላከተው። በተለይ በአሁኑ ወቅት በከተማ አስተዳደሩ በኩል ለዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ስፖርቱ ከገባበት ቁዘማ ለማውጣት ጥረት ይደረጋል ሲሉም ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ። አቶ ዮናስ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ የ2011 ዓ.ም የበጋ_በጎ_ፈቃድ መርሀ ግብር ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ለወጣቶች ዕውቅና በመስጠትና ወደ ክረምት_የበጎ_የፈቃድ ሥራ ለመግባት የቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም አያይዘው ገልጸዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 12/2011 ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12736
503d3348ba0eb478096501949fd92364
a0010468390f91ccc8a329efcb21ffdb
በሻምፒዮናነት ግስጋሴው – መቐለ ሰባ እንደርታ ሰከን ሲል- አጼዎቹ ለሻምፒዮናነት ተቃርበዋል
የኢትዮጵያ ቡና እና የመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተከናውኗል። ጨዋታው የተካሄደው በብዙ ውጥረትና አወዛጋቢ ውሳኔ በኋላ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም በሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በዘጠኝ ሰዓት መካሄድ እንዳለበት ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነበር ሊካሄድ የበቃው። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በፊት በ26ኛው ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ የነበረበት ቢሆንም «የፀጥታ ስጋት» በሚል ሳይካሄድ ቀርቷል። የጨዋታው አለመካሄዱን ተከትሎ በስፖርት ቤተሰቡ፣ በክለብ አመራሮችና ደጋፊዎች፣ በመገናኛ ብዙኃን በኩል ሰሞነኛ አብይ ጉዳይ በመሆን ብዙ ሲባልልት ቆይቷል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀናት የውጥረት ቆይታ በኋላ የተካሄደው ጨዋታ፤ ያለምንም ግብ በአቻ ተጠናቋል።በጨዋታው ነጥብ የተጋሩት መቐለ ሰባ እንደርታዎች ከሻምፒዮናነት ግስጋሴያቸው ሰከን ሲሉ አጼዎቹን ለሻምፒዮናነት አቅርቧቸዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በአስደማሚ ድባብ የተከናወነው የኢትዮጵያ ቡናና መቐለ ሰባ እንደርታ ጨዋታ በርካታ የግብ ሙከራዎች ታይተዋል። በሁለቱም ክለብ ተጫዋቾች በኩል ኳስን ከመረብ ለማገናኘት የቻለ ግን አልነበረም። ቡናማዎቹ በጨዋታ እንቅስቃሴ የበለጠ ጫና ፈጥረው ሲጫወቱ ፤ መቐለ ሰባ እንደርታ ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። በዚህ መሠረት የተስተካካይ ጨዋታው ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ለመጠናቀቅ ችሏል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2011 ዓ.ም ዋንጫ የሻምፒዮናነት ሚዛኑ ወደ ሦስት ክለቦች በማመዘን ሊጠናቀቅ የሦስት ሳምንታት ጨዋታዎች ብቻ ቀርተውታል። የሻምፒዮናነት ክብሩንም ለመጎናጸፍ አጼዎቹ በ52 ነጥብ አንደኛና ቀዳሚ ዕድል ይዘዋል። በዛሬው ጨዋታ ነጥብ ተጋርቶ ወሳኙን ሦስት ነጥብ ያጣው መቐለ ሰባ እንደርታ በ50 ነጥብ ሁለተኛ በመሆን የአጼዎቹን ሽንፈት ይጠባበቃል። ከመቐለ ሰባ እንደርታ በመቀጠል 49 ነጥብ በመሰብሰብ በአንድ ግብ ተበልጦ ሦስተኛ የሆነው ሲዳማ ቡና ሌላ የሻምፒዮናነት ፍርቱና ከተጎናጸፉት ቡድኖች ተርታ የሚመደብ ሆኗል። የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮናነት ክብር ለማግኘት ሚዛን ደፊ ዕድል የያዙት ሦስቱ ክለቦች፤ከፊት ለፊታቸው የሚጠብቋቸው ሦስት ጨዋታዎች ምላሽ ይሰጣሉ። ይሁንና ክለቦቹ ቀጣይ ከሚጫወቱት ክለቦች አቋምና የጥንካሬ ዳራ በመነሳት የሻምፒዮናነት አሸናፊው መገመት አስቸጋሪ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል። የሆነው ቢሆንም፤የሊጉ አናት ላይ የሰፈሩት አጼዎቹ የሚኖራቸው ጨዋታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አዳማ እና ስሁል ሽረ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የአጼዎቹን እግር የሚከተለው መቐለ ሰባ እንደርታ በበኩሉ ከድሬዳዋ፣ደቡብ ፖሊስ እንዲሁም ከመከላከያ ከፊት ለፊቱ የሚጠብቁት ወሳኝ ጨዋታዎች ናቸው። ሲዳማ ቡና ደግሞ ከድሬዳዋ፣ ከደደቢት እና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚጫወት ይሆናል። በእነዚህ ሦስት ጨዋታዎች የሻምፒዮናነት ክብር ወዴትኛው ክለብ እንደሚያርፍ የሚለይ ይሆናል። ለሻምፒዮናነት በሚደረገው ግስጋሴ ውስጥ ደግሞ ደቡብ ፖሊስ በሃያ ስምንት ነጥቦች አስራ አራተኛ፤ ስሁል ሽረ በሃያ ሰባት ነጥቦች አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በአስራ ሦስት ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ በመያዝ፤ ለመውረድና ለመውጣት የሚያደርጉት እልህ አስጨራሽ ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል። የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቀሌው አማኑኤል ገብረሚካኤልና የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ አምስት ግቦች አንደኛ ሁለተኛ ሲሆኑ፣ የፋሲሉ ሙጂብ ቃሲም በአስራ አራት ግቦች ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 12/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12738
343cd7cf047ced2d2bb12bd652c6d2a2
e4da8385218b54a4aa19deeb7c96aef8
የአፍሪካ ዋንጫ አይረሴ አጋጣሚዎች 
ተወዳጁ የአፍሪካ ዋንጫ ተወዳጅነቱ እየተሸረሸረ መጥቶ ለሰላሳ ሁለተኛ ጊዜ በፈርኦኖቹ መንደር ሊጀመር የሃያ አራት ሰዓታት እድሜ ይቀረዋል፡ ፡ ከዓለም ዋንጫ ቀጥሎ በብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚካሄድ ታላቅ የእግር ኳስ መድረክ የሆነው የአፍሪካ ዋንጫ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሚሰጠው ትኩረትና ተወዳጅነቱ አሁን ላይ አብሮት ነው ለማለት አይቻልም፡፡ እኤአ ከ1957 ጀምሮ በአራቱ መስራች አገራት (ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ግብፅና ደቡብ አፍሪካ) አማካኝነት ተጀምሮ ባለፉት ሃምሳ ስድስት ዓመታት የተሳታፊ አገራትን ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃያ አራት አገራት መካከል ይካሄዳል፡፡ በነዚህ ዓመታትም በርካታ አይረሴ አጋጣሚና ታሪኮችን በእግር ኳስ አፍቃሪው ዘንድ አኑሯል፡፡ ጥቂቶቹን እንመልከት፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ከተጀመረ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ቢሆነውም በቴሌቪዥን መስኮት ለተቀረው ዓለም መድረስ የቻለው ሰላሳ ዓመታትን ዘግይቶ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን የተላለፈው የአፍሪካ ዋንጫ በሱዳን አስተናጋጅነት የተካሄደው ሲሆን በበርካታ የስፖርት ቤተሰቦች ተወዳጅነትን ለማግኘት መሰረት ያገኘበት የተለየ አጋጣሚና ታሪክ ሆኖ ይታወሳል፡፡ አፍሪካ ዋንጫ በመጣ ቁጥር በበርካታ የመለያ ምት የተጠናቀቀውና ‹‹ማራቶን የመለያ ምት›› ተብሎ የተሰየመው የፍፃሜ ጨዋታ አይዘነጋም፡ ፡ እኤአ 1992 ሴኔጋል ባስተናገደችው የአፍሪካ ዋንጫ ጋና ለአራተኛ ጊዜ ቻምፒዮን ከሆነች አስር ዓመታት በኋላ ለአምስተኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማንሳት ከጎረቤቷ ኮትዲቯር ጋር ለፍፃሜ ደርሳለች፡፡ ኮትዲቯር በበኩሏ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ለመሳም ከጫፍ ደርሳለች፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመቶ ሃያ ደቂቃዎች የሜዳ ላይ ፍልሚያ ኳስና መረብን ማገናኘት አልቻሉም፡፡ አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት መሄድ የግድ ሆነ፡፡ ኮከባቸው አቢዲ ፔሌን ጥለው የገቡት ጋናዎች በእግር ኳስ ታሪክ ረጅም ከሆነው የመለያ ምት በኋላ 11ለ10 በመሸነፍ ለአዲሱ ቻምፒዮን ዋንጫውን አሳልፈው ሰጡ፡፡ እኤአ 1957 የመጀመሪያው አፍሪካ ዋንጫ ላይ በአፓርታይድ ሥርዓት ከውድድር ውጪ የሆኑት ደቡብ አፍሪካዎች በ1996 የአፍሪካ ዋንጫ የፖለቲካ ባህላቸው ተለውጦ እግር ኳስ ለውህደታቸው ቁልፍ ሚና የተጫወተበት አጋጣሚ በመሆኑ ብዙዎች አይረሱትም፡፡ አገሪቱ ከአፓርታይድ ሥርዓት ተላቃ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ ከሁለት ዓመት በኋላ ኬንያ ባሰናዳችው አፍሪካ ዋንጫ ቀርባለች፡፡ ለፍፃሜ የቀረበችው ቱኒዚያን ሁለት ለምንም በማሸነፍም እስካሁን የመጀመሪያዋ የሆነውን የአፍሪካ ዋንጫ አነሳች፡፡ ለዚህም ድል የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንትና የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ለባፋና ባፋናዎቹ አምበል ኔል ቶቬይ ከፍፃሜው ጨዋታ በኋላ ዋንጫውን በክብር አስረክበዋል፡፡ ናይጄሪያ የአፍሪካ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አስተናግዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ቻምፒዮን ከሆነች አስራ አራት ዓመታት በኋላ ወርቃማ የእግር ኳስ ትውልዷ ታሪክ የሰራበት አጋጣሚ እኤአ 1994 ላይ ተከሰተ፡፡ በእርግጥ ወርቃማው የእግር ኳስ ትውልድ የአህጉሪቱን እግር ኳስ በበላይነት መቆጣጠር የጀመረው ከሌጎሱ ድል በኋላ ቢሆንም በድል የታጀበ አልነበረም፡፡ 1988ና 1992 ላይ በአፍሪካ ዋንጫው ለፍፃሜ ደርሶ አልተሳካለትም፡ ፡ 1994 ላይ ግን በምንጊዜም ከዋክብቶቹ ራሺድ ያኪኒና ኢማኑኤል አሙኒኪ ምትሃተኛ ብቃት ታጅበው ዋንጫውን የሳሙበት አጋጣሚ አሁንም ድረስ በብዙዎች ይታወሳል፡፡ ሰባ ስድስት ሺ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው የአልጄሪያ ስቴድየም በ1990 የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ በማይታመን መልኩ ከመቶ ሺ በላይ ተመልካቾችን አምቆ መያዝ ችሏል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፍፃሜው ተፋላሚ አልጄሪያና የወቅቱ የአህጉሪቱ አስፈሪ ስብስብ ናይጄሪያ ናት፡፡ በዚህ ጨዋታ አልጄሪያ አንድ ለምንም በማሸነፍ ዋንጫውን ስታነሳ በስቴድየም የነበረው ድባብ በየትኛውም የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ያልታየና የማይረሳ ሆኖ ይታወሳል፡፡ በዘፋኝነት ጭምር ብዙዎች የሚያስታውሱት የደቡብ አፍሪካው ኮከብ ቤኒ ማካርቲ በየትኛውም የእግር ኳስ መድረክ በየትኛውም ኮከብ ለመፈፀም የማይቻል የሚመስለውን ታሪክ በ1998 የአፍሪካ ዋንጫ መፈፀም ችሏል፡፡ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ማካርቲ ናሚቢያ ላይ በአስራ ሦስት ደቂቃዎች ውስጥ አራት ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ አይረሴ ታሪክ ሰርቷል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 13/2011ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12832
3ff251d9576bacb395f85ed0000cb1dd
7d6f71976e9f5b884a8ae31256a3d801
የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ከ30 በላይ ሜዳዎች እየሠራ ነው 
አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ከማዘውተሪያ ስፍራ ጋር ተያይዞ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ ከሰላሳ በላይ ጥርጊያ ሜዳዎች እየሰራ መሆኑን ገለጸ። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዮናስ አረጋይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ በመዲናዋ በስፖርቱ ዘርፍ በስፋት ከሚነሱ ችግሮች የማዘውተሪያ ስፍራ ምልኡ አለመሆን በዋነኛነት ይጠቀሳል። በተለይ ደግሞ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠናው ላይ በስፋት ከሚስተዋሉት ችግሮች ዋነኛው የማዘውተሪያ ቦታ መሆኑን ኮሚሽኑ ያስጠናው ጥናት ውጤት አመልክቷል። ከጥናቱና ከተጨባጭ እውነታው በመነሳት ችግሩን ለመቅረፍ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ፤በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከ30 በላይ ጥርጊያ ሜዳዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ሜዳዎቹ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ክቡር ከንቲባው ባሉበት ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል። ኮሚሽኑ በተመሳሳይ የሚታዩትን ጉድለቶች ለመሙላት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ፤ስፖርቱ ከታች ጀምሮ በሙያተኛው አለመመራቱ ለዘርፍ ውጤት አልባ መሆንና ውጥረት እንዳያመጣ ቁልፍ ምክንያት እንደሆነ ሲነገር ነበር። ስፖርቱን የማያውቁት ሰዎች ናቸው የሚቀመጡት፣ ስፖርቱን ከመምራት ይልቅ ሌላ ስራ ነው የሚሰሩት የሚሉና መሰል ትችቶች የሚነሱ መሆኑን የገለጹት አቶ ዮናስ፤ ሃሳቡ በስፖርት አዋቂዎችና ቤተሰቡ በኩል በስፋት ሃሳብ ሲሰነዘርበትም ጭምር መቆየቱን አስታውሰዋል። በመሆም በስፖርት ኮሚሽኑም በኩል ይሄንኑ በመፈተሽ ስፖርቱ በባለሙያ መመራት አለበት የሚል አቅጣጫ አስቀምጧል። ስፖርቱ እታች ላይ በሹመት ተመድቦ ሲመራ የነበረውን የጽፈት ቤት ኃላፊነት መደብን በስፖርት ሙያተኞች እንዲመራ ተደርጓል። በስፖርት ሳይንስ የጨረሱ ሙያተኞች በማሰባሰብ ነባር ቀበሌዎችንና ቀጣናውን በማስተባበርና በመምራት ስፖርቱ መሰረታዊ ለውጥና ውጤት እንዲያመጣ ያስችላል የሚል እምነት መኖሩን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ እንዲህ አይነትና መሰል እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ በቀጣይ ውጥኖችን የያዘ መሆኑን ገልጸው ፤ ህብረተሰቡ በመኖሪያ አካባቢ የማስ ስፖርት እንዲያዳብር ፣ተማሪው በትምህርት ቤቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ፣ በወይኒ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ የሚያስችሉ ሰፊ ስራዎችን ለማድረግ ውጥን መያዙን ተናግረዋል።አዲስ ዘመን ሰኔ 13/2011ዳንኤል ዘነበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12835
e6c3da8d61cab711913f33ca7301eaaa
5fe4fbe76d67c5baf14c462789a0e8e1
ከባህር ማዶ የነገሠው የኢትዮጵያዊያን ድምፅ
ሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ምሽት በኢትዮጵያ ሰምይ ስር አንድ ክፉ ጥላ አጠላ። ሀገርን ወደ ትርምስ ለመክተት ባሰቡ ወንጀለኞች እኩይ ተግባር አዲስ አበባ ገላን አካባቢ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ። ስለ ህዝቦች መብት የሚሟገተው የኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ሀጫሉ ሁንዴሳ መሞት ኢትዮጵያዊያን በኀዘን ስሜት ተቀባበሉት። የዚህ ታላቅ አርቲስት በሴረኞች መገደል ሰምተው ልባቸው በኀዘን የተሰበረው አይናቸው በእንባ የራሱት ኢትዮጵያዊያን ሌላ አስደንጋጭ ድርጊት ባልጠበቁት መልኩ ገጠማቸው። በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች የህዝብን አብሮነት በሚንድ ለዘመናት ጠብቆ ያቆየውን እሴት በተቃረነ መልኩ የጥፋት ኃይሎች በህዝብ ላይ ባደረሱት ጥቃት የንፁሐን ህይወት ተቀጠፈ፤ ይህች ታዳጊ አገር ከሌላት ላይ ቆንጥራ የገነባቻቸው የልማት አውታሮች ወደሙ። ዜጎች ለፍተው ጥረው ያፈሩት ንብረት እንደ ዘበት ዶጋመድ ሆነ።ይሄኔ መንግሥት የሀገር ህልውና ከስጋት ወደቀ፤ ዜጎች የመኖር መብታቸው በሴረኞች ታወከ ብሎ ህግ የማስከበሩ ዕርምጃ መውሰድ ግድ አለው። በዚህም አገሪቱ እንድትበታተን፣ ዜጎች ሰላማቸው እንዲደፈርስ የተመኙና የሞከሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድና በአገር ላይ የተጋረጠውን አደጋ መቆጣጠር ቻለ። የመንግሥት ህግ የማስከበር ዕርምጃ በተፈጠረው ችግር የራሳቸውን ዓላማ ማሳካት የፈለጉ ኃይሎች ቢቃወሙትም የአገርን ህልውና የሚፈልጉ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት መንግሥት የጀመረውን አገር የማዳንና የህግ የማስከበር ሥራ አጠንክሮ እንዲቀጥል በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሚገኙ የዓለም ታላላቅ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ድጋፋቸውን ለመንግሥት በመግለጽ ላይ ናቸው። ሰሞኑን በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲስ፣ ላስ ቬጋስ፣ በእንግሊዝ ለንደን፣ በኖርዌይ ኦስሎ በሌሎችም የአውሮፓና የአሜሪካ ከተሞች ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈፀሙ ግድያዎችና የንብረት ውድመትን የተቃወሙ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁን የጀመረውን የህግ ማስከበር ዕርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በዋሽንግተን ዲሲ በጠሩት ህዝባዊ ትዕይንት ላይ ተገኝተዋል። አስተያየታቸውን የሰጡት የሰልፉ አስተባባሪና ተሳታፊ አቶ ቴድሮስ ካብትይመር እንዳሉት ኢትጵያዊያን በአንድ በመቆም በአገሪቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝና የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረውን ህግ የማስከበር ዕርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ለመጠየቅ ህዝባዊ ትዕይቱ ተዘጋጅቷል ብለዋል። ሰልፈኞቹ በዚሁ ወቅት በአገር ጉዳይ አንደራደርም፣ መንግሥት እየወሰደ ያለው የህግ ማስከበር ሥራ አጠናክሮ ይቀጥል፣ በኢትዮጵያ ላይ የመጣ ማንኛውም ኃይል እንቃወማለን፣ ወንጀለኞች ለህግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥል የሚል መፈክር ይዘው ሲያስተጋቡ መዋላቸውን የሰልፉ አስተባበሪዎች ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በላኩት መልዕክት ገልጸዋል። በአሜሪካ ቨርጂንያ ከተማ ሰልፍ የወጡት ደግሞ መንግሥት የወሰደውን ህግ የማስከበሩን እርምጃ እንሚደግፉትና ኢትጵያዊያን በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ የሆኑንት አቶ ሰለሞን ጀማነህ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በላኩት መልዕክት አስታውቀዋል። በእንግሊዝ ዋና ከተማ ሎንደን በተካሄደው ሰልፍ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን መንግሥት እያደረገ ያለውን ህግ ማስከበር እርምጃ እንደሚደግፍ የገለጹ ሲሆን፤ በአገሪቱ ላይ እንቅፋት ለመፍጠር የሚሞክሩ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠይቀዋል። በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የጥላቻ መልዕክት በማሰራጨት ላይ የሚገኙ አካላት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። በኖርዌይ ኢትዮጵያዊያን በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በርካታ ህዝብ መገኘቱን የገለጹት የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ጌታቸው በቀለ ኢትዮጵያዊያኑ የመግሥትን የህግ ማስከበር እርምጃ እንደሚደግፉና የጥፋት ኃይሎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸሙ ያሉት ግድያ አውግዘው ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የመንግሥንት ህግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ የድጋፍ ሰልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።አዲስ ዘመን ሐምሌ 12/2012ተገኝ ብሩ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35653
12b096e877b27fec85c73055f10ca6cc
0d69ccf7a74bc0214664a4891123265c
ኢንስቲትዩቱ ከውጭ ገበያ ከ37 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
አዲስ አበባ፡- የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በበጀት ዓመቱ ባለፉት 11 ወራት ወደ 30 ሀገራት የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ(ኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ) ምርቶችን ልኮ 37 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።የኢንስቲትዩት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፊጤ በቀለ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በዓለም አቀፉ ገበያ ውስጥ ተሳትፎ ካደረጉ 18 ኩባንያዎች የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ምርት በመላክ በአስራ አንድ ወራት 37 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። የምርቶቹ የገበያ መዳረሻ ከጎረቤት አገራት ጀምሮ እስከ አውሮፓና አሜሪካ በመዝለቅ በዕቅድ ዘመኑ 30 አገሮች የሀገራችንን ምርቶች ተቀባይ ለማድረግ ተችሏል። እንደ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ የ2012 በጀት ዓመት የአስራ አንድ ወራት ዕቅድ 55 ሚሊዮን 748 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ እንደ መኪና፣ ሞባይል፣ አልሙኒየም፣ ቆርቆሮ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ወደ ተለያዩ አገሮች ለመላክ ግብ በማስቀመጥ ወደ እንቅስቃሴ የገባ ሲሆን፤ ከተላከው ምርት ከ37 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ችሏል።በመሠረታዊ ብረታ ብረት በአገር ውስጥና በውጭ ባለሀብት 14 ሚሊዮን 500 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለመላክ ታቅዶ 3 ሚሊዮን 409 ሺህ ዶላር ተገኝቷል። በኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ 41 ሚሊዮን 247 ሺህ ታቅዶ በአፈፃፀም 33 ሚሊዮን 593 ሺህ በላይ መላክ ተችሏል። በአጠቃላይ ከሐምሌ 2011 እስከ ግንቦት 2012 ዓ.ም ባለው ወቅት በመሰረታዊ ብረታ ብረት ፣ በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ከ37 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ የሚያወጡ የተለያዩ ምርቶችን ወደ 30 ሀገራት መላክ ተችሏል። ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የኤክስፖርት ምርቱ ቀንሷል ያሉት ዳይሬክተሩ ቀደም ሲል የምንዛሬ እጥረት በመኖሩ ምክንያት ኢንዱስትሪዎቹ የአቅማቸውን ያህል አምርተው ለገበያ እያቀረቡ እንዳልነበረ አስታውሰዋል። የኩባንያዎቹ ግብአት ከውጭ የሚመጣ በመሆኑም በተለያየ ምክንያት የሚፈለገውን ያክል ምርት ማምረት አለመቻሉን ገልጸዋል። የጥሬ ዕቃና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኮሮና ቫይረስ ጋር ተደማምሮ ኢንዱስትሪዎቹ ከአቅም በታች ያመርቱ እንደነበር አስታውሰው ያም ሆኖ ግን ለውጭ ገበያ እና ለአገር ውስጥ ለግልና ለመንግሥት ምርት እያቀረቡ ናቸው።በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ንዑስ ዘርፍ በ2006 ዓ.ም እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የወጪ ንግድ አፈፃፀም የተጀመረ ቢሆንም በየዓመቱ በምርት ዓይነትና በተሳታፊ ኢንዱስትሪዎች ብዛት እንዲሁም በገበያ ተደራሽነት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች አሳይቷል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 12/2012ዳግም ከበደ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35684
a8824924086bf70241bf9d44830bd684
fc4d8d99328e028effe26b6a4c41d917
ኮሚሽኑ ማህበረሰብን የማደራጀትና የሆቴሎች ድንገተኛ ፍተሻ መጀመሩን አስታወቀ
 ማህበረሰቡ ለማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ተቀጣሪዎች በዓመት ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ ይከፍላልአዲስ አበባ፡- የከተማውን ደህንነትና ጸጥታ ለመጠበቅ በህጋዊ መንገድ ማህበረሰቡን የማደራጀትና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴል፣ ፔንሲዮንና መሰል ቤቶችን ድንገተኛ ፍተሻ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ። ማህበረሰቡ በከተማው ጸጥታና ደህንነት እንዲረጋገጥ በዓመት ለማህበረሰብ አቀፍ ተቀጣሪ ጠባቂዎች ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ ይከፍላል።በኮሚሽኑ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን ፋንታሁን በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ የሚታየውን ድንገተኛ ችግሮች ለመፍታት ፖሊስ ብቻውን የሚያደርገው እንቅስቃሴ አጥጋቢ ባለመሆኑ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎቱን ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ሥራ እየተሠራ ነው። በአሁን ወቅት ድንገተኛ ችግሮች ጠንከር እና ውስብስብ እየሆኑ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ሥራ ለማከናወን በየአካባቢው ራሳቸውንና አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ በአስሩም ክፍለ ከተሞች እውቅና ያለው ማህበረሰብን የማደራጀት ሥራ ተጀምሯል። ሆቴሎች ቀደም ሲል በየቀኑ የሚያድሩ ሰዎችን ማንነት በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ የገለጹት ኮማንደሩ፤ አሁን ላይ እየተፈጠሩ ካሉ ችግሮች ስፋትና ክብደት አንጻር ይህንን ማድረጉ ብቻ በቂ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም በከተማዋ የመኝታ አገልግሎት በሚሰጡ ሆቴሎች፣ ፔንሲዮንና መሰል ሥራ ውስጥ በተሰማሩት ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ይደረጋል። በተመሳሳይ በፈቃዳቸው የተደራጁ የአካባቢ ጠባቂዎችንም በቅርበት ክትትል እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ከከተማው ስፋትና ከወንጀሎች ውስብስብነት አንጻር በቀጠና ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ላይ አንድ ኦፊሰር እንደሚመደብ የተናገሩት ኮማንደር ሰለሞን፤ይሄ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥም ሆነ ለሚፈጠረው ችግር ለመድረስ እጅግ ፈታኝ ነው። ስለሆነም በየደረጃው የተለያዩ አደረጃጀቶች ተፈጥሮው እየተሠራ ይገኛሉ። ሆኖም ወቅታዊ ችግሮች ሲመጡ ከበድ ስለሚል ፈጣንና ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ በዋናነት በሁለት መልኩ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። ኮማንደር ሰለሞን እንዳሉት፣ ነዋሪው አካባቢውን እንዲጠበቅ ማድረጉ ችግር የሚፈጥረውን አካል ወዲያው አግኝቶ ዕርምጃ እንዲወሰድ ከማድረጉም በላይ የፖለቲካ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲሉ የተደራጁ አካላትን ለማስቆም ያግዛል። በተመሳሳይ ማህበረሰቡን ከአደጋ ለመጠበቅም ፍቱን መፍትሔ ነው። የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎቱን በዚህና መሰል መንገዶች የማጠናከርሥራው ይቀጥላል ብለዋል። በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማህበረሰቡ ተሳትፎውን በተለያየ መልኩ እያሳየ መሆኑን የጠቀሱት ኮማንደር ሰለሞን ፤ ከዚህ ውስጥ በዓመት በከተማው የጸጥታና ደህንነት እንዲረጋገጥ ለማድረግ ለጥበቃ ቅጥር ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ አድርጎ እንደሚሸፍን አስታውቀዋል። የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎቱ በከተማ ደረጃ በ2005 ዓ.ም ቢጀመርም ብዙ ተግዳሮት አለበት ያሉት ኮማንደሩ በውጤት የተደገፈ ነው ለማለት ያስቸግራል። ሆኖም በ2011 መጨረሻ ችግሮች ተለይተው በተሻለ ሁኔታ እየተሠራና ለውጦች እየታዩ ነው። ማህበረሰቡም ፖሊስን እያመነውና አብሮ ለመሥራት ፈቃደኝነቱን እያሳየ መጥቷል። በዘንድሮ ዓመት ብቻ ለአካባቢ ጥበቃ ቅጥር ከ25 ሚሊዬን ብር በላይ አውጥቶ ደመወዝ ከፍሏል። ማህበረሰቡ ከኮሮና ጋር እየተሟገተ ባለበት በዚህ ወቅት ሳይቀር ድጋፉን ከማድረግ ወደኋላ እንዳላለ የሚገልጹት ኮማንደሩ፤ ዘንድሮ ብቻ 33 ደረጃቸውን የጠበቁ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት መስጫ የቀጠና ማዕከላት ተገንብተው ሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፤ ለዚህም 11 ሚሊየን 711 ሺህ 611 ብር ወጪ መደረጉን ገልጸዋል። በዚህ ዓመት ብቻ 3 ሺ 472 የሚሆኑ ጥበቃዎች የተቀጠሩ ሲሆን፤ ነባር 8 ሺ122 አሉ። እስከአሁን ማህበረሰቡ 12 ሺ 494 የሚሆኑትን ቅጥር ጥበቃዎች ደሞዝ ይከፍላል። በከተማ አስተዳደሩ 60 ፖሊስ ጣቢያ፣ 121 ወረዳና 833 ቀጠና አለ፤ በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሲ አገልግሎት ይሰጣል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 12/2012ጽጌረዳ ጫንያለው
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35654
cbb6d556e6758607bf8aad3c366ff2e0
88bbd09339e9195dd63b91ce8632c840
ህዝብን ከህዝብ ለማባላት የታቀደው ሴራ በአዳባ
ወይዘሮ የዝና ጨርቆሴ፣ የአዳባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፤ ከሰሞኑ ተከስቶ በነበረው ሁከት ቤት ንብረታቸውን ብቻ ሳይሆን ባለቤታቸውን አቶ ዘውዱን እና የልጃቸውን ባል አቶ ሰለሞንን በሞት ተነጥቀዋል። ሌላው ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰብ አቶ ካሳሁን ተሾመ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ በዕለቱ ንጋት ላይ የጀመረው ሰልፍና ሁካታን ተከትሎ የሰው ንብረት ማውደም መጀመራቸውን የሰሙት ከቤት ሆነው ነበር። ችግሩ እየከፋ መሄዱን ሲገነዘቡም ሆቴላቸውን ሊመለከቱ ይወጣሉ። በስፍራው ሲደርሱ ግን ነገሮች ተቀይረዋል፤ ሆቴሎቻቸውም በእሳት ተያይዘው፣ ግርግሩም በዝቶ አገኙት። በወቅቱም እንኳን እየተቃጠለ ያለውን ንብረታቸውን ሊያድኑ ቀርቶ፤ራሳቸውንም ማዳን እንደማይችሉ በመገንዘባቸው የሚቃጠሉ ሆቴሎቻቸው ወደአመድነት እየተቀየሩ እያዩም ቢሆን አካባቢውን ትተው ይሄዳሉ።ይሄን መሰል ጥቃት ሲደርስባቸው ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ካሳሁን፤ በዚህኛው የሀጫሉን መገደል ምክንያት አድርገው ወጡ እንጂ አካሄዳቸው አንድም ብሔርን ካልሆነም ሃይማኖትን ተገን አድርገው ኅብረተሰቡን እርስ በእርስ ለማባላት የሚፈጸም የጽንፈኛ አመለካከት ባለቤቶች የሚከውኑት ተግባር መሆኑን አስረድተዋል። በዚህም አሁን ላይ አንድም ንብረታቸው በመውደሙ፤ ሁለተኛም ለህይወታቸው በመስጋታቸው በቤተክርስቲያን ተጠልለው እን ዳሉ በመጠቆምም፤ ይሄን ዓይነት ተደጋጋሚ ጥቃቶች በከተማዋ እየተበራከቱና እየተደጋገሙ በመምጣታቸው ህዝቡ በስጋትና ሰቀቀን እየኖረ እንደመሆኑ መንግሥት መኖሩን በተግባር ሊያሳየን ይገባል ይላሉ። ይህ አካባቢ በተደጋጋሚ የሰላም፣ የህግና ፍትህ ችግር የሚስተዋልበት እንደመሆኑ፤ አሁን በተፈጠረው ችግርም ያንን ማድረግ ባለመቻሉ ህዝቡ ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ውድ ህይወቱን በግፍ እያጣ ይገኛል። እናም እነዚህ ወገኖች ችግሮች ተደጋግመው የሚፈጸሙባቸው እንደመሆኑ ከምንም በላይ ድምፃቸውን የሚያሰሙበት የመገናኛ አውታር አብዝተው የሚናፍቁ ናቸው። ምክንያቱም ብዙዎች ተጎድተው የሚያነቡ እንደመሆኑ እንባቸውም ለህዝብና ለመንግሥት የሚያደርስላቸው ይሻሉ፤ ዘወትር በስጋትና በፍርሐት ውስጥ እንደመሆናቸውም ይሄን ጭንቀታቸውን ሰምቶ የሚደርስላቸው የመንግሥት አካል አብዝተው ይናፍቃሉ። በመሆኑም ህዝቦች እንባቸው እንዲታበስ፤ በሰላም ወጥተው እንዲገቡ፤ ሠርተው ንብረት እንዲያፈሩ ብቻ ሳይሆን የንብረታቸው ባለቤትም ተጠቃሚም እንዲሆኑ መንግሥት ጆሮ ሰጥቶ የሲቃ ጩኸታቸውን ሊያዳምጥና ምላሽ ሊሰጥ ይገባል።የአዳባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ ዑመር እንደሚሉት የተፈጠረው ችግር ከባድና ጠላት ተዘጋጅቶበት በቅንብር የተፈጸመ ነው። በወቅቱ ኀዘኑን ለመግለጽ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ የሚመስል ቢሆንም፤ በሂደቱ አቅጣጫውን ሲቀይር ችግሩን ለመከላከል በአገር ሽማግሌና የሃይማኖት አባቶች ጭምር በመታገዝ ጥረት ተደርጓል። ሆኖም ነገሮች ከአቅም በላይ ሆነው በሆቴሎች፣ በሱቆችና በመኖሪያ ቤቶች ጭምር በተፈጸመ ጥቃት ከባድ የንብረት ውድመትና ከአራት ያላነሱ ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል። ይህ ከሆነ በኋላ ግን አመራሩም፣ የጸጥታ ኃይሉም በጋራ ተሠርቶ ችግሩን ለመቀነስ የተሞከረ ሲሆን፤ በየቤቱ እየሄዱ በሰዎች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ እንደመሆኑ ችግሩን በሚፈለገው ፍጥነት መግታት አልተቻለም።እንደ አቶ ሙስጠፋ ገለጻ፤ ይህ ጥቃት አንድም ሃይማኖትን፣ ሁለተኛም ብሔርን ለይቶ ለማጥቃት የተፈጸመ ለማስመሰል ተሞክሯል። የተጎዱ ወገኖችን ባሉበት ሁኔታ ለመደገፍም ሆነ የጠፋባቸውን ንብረት ለመተካት የሚያስችሉ ሥራዎች በህብረተሰቡ በራሱ ተነሳሽነት እየተሠሩ ይገኛሉ። ከዚህ ባለፈም አሁን የሆነው ነገር ጠላት አቅዶበት ያደረገው እንደመሆኑ አስተዳደሩ ሳይዘጋጅ የተፈጠረና ውድመትም ሞትም ያስከተለ ነው፤ በዚህ ጥፋት ላይ ተሳታፊ ናቸው ተብሎ የተጠረጠሩ ከ102 ሰዎች በላይ ተይዘዋል። በቀጣይም ህብረተሰቡ ያለበትን ስጋት ለማስወገድና ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ለማድረግ መንግሥት ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ ይገኛል።የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቀደም ሲል እንደጠቀሱት በኦነግ ሸኔ፣ በህወሓት ጥገኛ ቡድንና በውጭ ኃይሎች ቅንጅት አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በሴራ በማስገደል በቀሰቀሱት ሁከት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ሲያልፍ ከፍተኛ ግምት ያለው ሀብትና ንብረትም ወድሟል። ከዚህም ጋር ተያይዞ አጥፊዎችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ የማድረግና የመንግሥት መዋቅሩንም በመፈተሽ የማጽዳት ሥራ እየተሠራ መሆኑን መገለጻቸው ይታወሳል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012ወንድወሰን ሽመልስ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35714
ee0f2c55059b18629be2aa76652a8dd9
3b230700ecd26f47779536d4ac20ef1f
ወጣት የቴክኖሎጂ የፈጠራ ባለሙያዎች ኢትዮጵያን ወደፊት እንደሚያሻግሯት ተገለጸ- የፈጠራ ባለሙያው ወጣት ናኦል ዳባ ሁለት ድሮኖችን አስተዋወቀ
 አዲስ አበባ፡- ወጣት ባለሙያዎች የሚፈጠሯቸው ችግር ፈች ቴክኖሎጂዎች ኢትዮጵያን ወደፊት እንደሚ ያሻግሯት የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የፈጠራ ባለሙያው ወጣት ናኦል ዳባ ሁለት ሰው አልባ በራሪዎች(ድሮች)ና አንድ የሙቀት መለኪያ ማሻን አስተዋውቋል፡፡የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ትናንት በሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተካሄደው የወጣቱ የፈጠራ ሥራዎች ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ እንደገለጹት፤ የኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠንና የሥራ ዕድልን ለመፍጠር ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ እንደ ወጣት ናኦል ዓይነት የፈጠራ ባለሙያዎች ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ወደፊት የሚያሻግሯት ይሆናሉ፡፡በኢትዮጵያ በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙትን 26 ሚሊዮን ተማሪዎች ሁሉ መንግሥትና የግሉ ዘርፍ ሥራ መፍጠር እንደማይችል የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ተማሪዎች እንደ ናኦል ዓይነቱን የብሩህ አዕምሮ ባለቤት ወጣት ተምሳሌት በማድረግ ለአገራቸውና ለራሳቸው በሚጠቅምና ሌሎች ሥራ የሚፈጥር የፈጠራ ሥራ ላይ መስማራት እንደሚኖርባቸው መክረዋል፡፡መንግሥት ወጣቶች በተለያዩ የሙያ መስኮች ክህሎትና እውቀት ይዘው እንዲወጡ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኘ አመልክተው፣ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት የወጣት የፈጠራ ባለሙያዎችን ሥራዎች በመግዛት ሊያበረታቷቸው እንደሚገባም አስገዝበዋል፡፡ወጣት የፈጠራ ባለሙያው ናኦል ዳባ ያስተዋወቃቸው የፈጠራ ሥራዎች የፀረ፣አረምና ፀረ ተባይ መርጫ ድሮን፣የህዝብ መልዕክት ማስተላፊያ ድሮንና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የሙቀት መለኪያ ማሽን ናቸው፡፡ ወጣት ናኦል የሙቀት መለኪያው አዳማ መመረት መጀመሩን ጠቁሞ፣ ሆቴሎችና ባንኮች ግዥ ፈጽመው እየተጠቀሙበት እንደሚገኘ አስታውቋል፡፡ ለድሮኖቹ ለማምረትና አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ፈቃድ እንዳገኘ ለገበያ እንደሚቀርቡ አመልክቷል፡፡ወደፊትም በድሮን ቴክኖሎጂና መሰል የፈጠራ ሥራዎችን በኢትዮጵያ በማምረት ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካና በዓለም ገበያ የማቅረብ ዕቅድ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ፤የተቀላጠፈ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የፈጠራ ሥራዎችን ማበረታታት ተገቢናአስፈላጊ እንደሆነ አስታውቀዋል።የትራንስፖርት ሚኒስቴር በስሩ በሚገኘው የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በኩል ለድሮን ቴክሎጂና በረራ ፍቃድ ለመስጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝም በቅርቡም ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።ለድሮን ቴክኖሎጂና በረራ ፍቃድ ለመስጠት እየተሠራ ያለው ሥራ ለናኦል ሆነ ሌሎች በዚህ የሙያ መስክ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ዜጎች ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን አመልክተዋል፡፡አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35718
5abcf8144ec79ac98c5ac27b6da47c26
36a666236ac8d51d151c3dda951b6b60
«አባይን በሚመለከት መንግሥት የመደራደሪያ ሳይሆን የመረጃና ማስረጃ ሕጋዊ ሰነድ ማዘጋጀት አለበት” -ዶክተር ብርሃኑ ግዛው ከፍተኛ የኢነርጂ ዘርፍ ባለሙያና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር አባል
አዲስ አበባ፡- መንግሥት በውጭ አገራት የሚኖሩ ዲፕሎማሲዎችና ዲያስፖራዎችን ጨምሮ ማንኛውም ዜጋ በቀላሉ አግኝቶ እውነተኛ መረጃ የሚሸምትበት የመደራደሪያ ሳይሆን የማስረጃ አንድ ወጥ የሆነ የአባይ ግድብ ሕጋዊ ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚገባው ተገለጸ። በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ የኢነርጂ ዘርፍ ኤክስፐርት የነበሩትና ለበርካታ ዓመታት በአውሮፓ ቆይተው የተመለሱት፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በተለያዩ ማህበራዊ መስኮች በአማካሪነት እየሠሩ ያሉት ዶክተር ብርሃኑ ግዛው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳሉት፤ መንግሥት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ዲፕሎማቶች፣ ዲያስፖራዎችና በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ተመሳሳይና ወጥ እውቀትና እውነተኛ መረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ የሚያስችል ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚገባው ተናግረዋል። ሰነዱ በተለያዩ የአገሪቱ ቋንቋዎች እና በውጭ አገር(እንግሊዝኛ ፣አረብኛና ሌሎች በርካታ ቋንቋዎች) እንዲተረጎም በማድረግ ማንኛውም ዜጋ በአገር ውስጥም ሆነ በየትኛውም ዓለም ሆኖ በቀላሉ ከድረ-ገጽ በማውረድ ስለሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ከትክክለኛው አካል እውነተኛ መረጃ በማግኘትና ግንዛቤውን በማስፋት ወጥ አቋም መያዝ እንደሚያስችለውም ገልጸዋል።አገሪቱ ለምን አባይን መገደብ እንዳስፈለጋት፣ የአባይን የውኃ አስተዋጽኦ ድርሻ በግልጽ የሚያመላክት፣ ከዓለም አቀፍ ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች የውኃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ፣ ከአገሪቱ ገጸ ምድር እና ከኃይል አጠቃቀም ጋር በተያያዘ፣ የሌሎቹን የተፋሰሱን አገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ እንጂ የሚጎዳ እንዳልሆነ የሚያሳይ፣ የድሕነት ደረጃን የሚገልጽ፣ይሄን ዘመናዊ የኃይል ምንጭ(ኢነርጂን) ማስፋፋት በተዘዋዋሪ ለስነምህዳሩ ያለውን አበርክቶ የሚገልጽ የሕዳሴ ግድብ ሰነድ መኖር እንዳለበት አብራርተዋል። ሁሉም የመሰለውን እና የተሰማውን ከሚያቀርብ ይልቅ አንድ ወጥ የሆነ ሕጋዊ የአባይ ሰነድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በመስኖ፣ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አማካኝነት ተዘጋጅቶ ለዜጎች መድረስ እንደሚገባውም ነው ዶክተር ብርሃኑ የጠቆሙት። በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ብዥታ ያለባቸው፣ ዓላማና ፋይዳውን ያልተረዱ፣ ለስብሰባም ሆነ ለስልጠና የሚፈልጉት ኢትዮጵያውንም ሆኑ ሌሎች የውጭ አገር ዜጎች እንዲህ አይነት መረጃዎችን በቀላሉ ከድረገፅ አውርደው ትክክለኛ መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ ሲሉም ተናግረዋል።መንግሥት የሕዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የሚያዘ ጋጀውን ወጥ ሕጋዊ ሰነድ ለተለያዩ አገር መንግሥታት በሚገባቸው ቋንቋ አስተርጉሞ ማቅረብ እንዳለበት የተናገሩት ዶክተር ብርሃኑ፤ በዚያ ሰነድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ግንዛቤ በመፍጠር ወጥ አቋም እና እውነታውን እንዲይዙ ያስችላል። እያንዳንዱ ምሁርና እያንዳንዱ ዜጋም በያለበት የሥራ ደረጃና በሚገኝበት የዓለም ጫፍ ሆኖ ይሄን ሕጋዊ የሕዳሴ ግድብ ሰነድ የማስተዋወቅና የማስረዳት ሃገራዊ ግዴታ እንዳለበት አስረድተዋል።ዜጎች የሕዳሴ ግድብን የተመለከቱ መረጃዎች ከተደራዳሪዎች ብቻ እንዲያገኙ መፍቀድ አይገባም የሚሉት ዶክተር ብርሃኑ፤ መንግሥት በዚህ ሰነድ አማካኝነት እውነተኛውን መረጃ፣ በቁጥሮች (ስታስቲክስ) አስደግፎ ካቀረበ ለሚፈልገው አካል ግልጽ ይሆንለታል። ሌሎች አገራት በራሳቸው ጉዳይ ስለሚወጠሩ፣ፍላጎታቸውም ያን ያህል ጉጉት ኖረም አልኖረም ለሚፈልገው አካል እውነተኛ መረጃ የሚሰጥ አገርን የሚወክል የመደራደሪያ ሳይሆን የማስረጃ ሰነድ አዘጋጅቶ ማቅረብ ያስፈልጋል ብለዋል። ይህ ሲሆን ለዘመናት በተንሻፈፉ አመለካከቶች እና እሳቤዎች የተጠለፉ አካላት መስመር ይይዛሉ፣ በእውነተኛ መረጃ ላይ ይቆማሉ፣ አቋም መያዝ ይችላሉ፣ ለመከራከር፣ ለማስረዳትና ለመሞገት አቅም ያገኛሉ የሚል እምነት እንዳላቸውም ዶክተር ብርሃኑ አብራርተዋል።አዲስ ዘመን ሐምሌ 13/2012ሙሐመድ ሁሴን
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=35706