context
stringclasses
367 values
question
stringlengths
10
114
answer
stringlengths
1
90
answer_start
int64
0
3.22k
ማርክ ትዌይን ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ ወይም በብእር ስሙ ማርክ ትዌይን አሜሪካ ካፈራቻቸው ድንቅ ጸሃፍት መካካል የሚመደብ ደራሲ ነው። ትዌይን በኖቬምበር 1835 ዓ.ም. ሚዙሪ በተባለችው የአሜሪካ ግዛት ተወለደ። 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር የኖረው ሃኒባል በተባለች እና ሚሲሲፒ ላይ በተቆረቆረች ትንሽ ከተማ-አከል ቦታ ነው። አባቱ በ1847 ሲሞት ትዌይን ትምህርቱን በማቋረጥ በማተሚያ ቤት ውስጥ በሰልጣኝነት ተቀጠረ። ይህን ስራውን በ1857 በመተው የእንፋሎት ጀልባ ነጂ በመሆን መስራት ጀመረ። በዚሁ ስራ በቆየባቸው አመታት ነው ኋላ ላይ አድናቆትን ላተረፉለት የስነ-ጽሁፍ ስራዎቹ የሚሆኑትን እውቀቶች ለማሰባሰብ የበቃው። እሱ ራሱም እንዳለው በዚሁ ስራ ላይ ነው "ማንኛውንም በልብ-ወለድ፣ በግለ-ታሪክም ሆነ በታሪክ ላይ ሊገኙ የሚችሉ የሰው ባህርያትን" ሊያጠና የበቃው። በ1861 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የእርስ-በርስ ጦርነት በመቀስቀሱ ምክንያት ማንኛውም አይነት የመርከብ ላይ ጉዞ ሲስተጓጎል ትዌይንም ስራውን ለመልቀቅ ተገዷል። ከዚህ በኋላም በውትድርና ወዶ-ገብነት፣ በወርቅ ማእድን ፈላጊነት፣ በጋዜጠኝነት ወዘተ ስረቷል። በ1869 ዓ.ም የመጀመሪያ ዋነኛ ስራው የሆነውን "The Innocents Abroad" ለማሳተም በቃ። ይኽ ድርሰት ክሌመንስ ራሱ በአውሮፓ እና በእየሩሳሌም ባካሄዳቸው ጉብኝቶች ላይ የተመሰረተ ነው። በ1870 ዓ.ም ኦሊቭያ ላንግዶንን በማግባት ኑሮውን ኮኔቲከት በተባለችው ግዛት አድርጓ በዛው ለ17 ዓመታት ኖሯል። በነዚህ 17 ዓመታት ነው አድናቆት ያተረፉለት ስራዎቹን ማለትም "Roughing It"፣ "The Adventures of Tom Sawyer"፣ Life on the Mississippi"፣ እና ከሁኡ የላቀ የተባለለት ድርሰቱን "The Adventures of Huckleberry Finn"ን ያሳተመው። ትዌይን በ1910 ዓ.ም አርፎ ሬዲንግ፣ ኮኔቲከት ውስጥ በድኑ አርፏል።
ማርክ ትዌይን ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ የመጀመሪያ ስራው የሆነው የመጽሐፍ ርዕሱ ምን ይባላል?
The Innocents Abroad
694
አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ በሃገራችን ኢትዮጵያ ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅ እና ቅድስት እድና ይባላሉ ። የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው ። ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረአምላክ ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ። በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል። "የት ልሒድ?" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለስምንት ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየኋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከስምንቱ ጋር ከቃልኬዶን ጉባዔ በኋላ በ፬፻፶፩ ዓም ወደ ኢትዮጵያ መጡ ። ከዘጠኙ ቅዳሳን ወደ ኢትዮጵያ ከሮምና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከፈለሱት አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው ። በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል ። አቡነ አረጋዊ ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል ። በመጨረሻም ደብረ ዳሞ ማረካቸዋለች ። ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል ፡፡
አቡነ አረጋዊ መቼ ተሰወሩ?
ጥቅምት አሥራ አራት
1,192
ልዑል ራስ መኮንን የንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክ ተወካይ ሆነው ሁለት ጊዜ የአውሮፓን አገሮች ጎብኝተዋል። በዚህ ጊዜ እሳቸው ኢጣሊያን ሲጎበኙ በነበረ ጊዜ የኢጣሊያ ጋዘጦች የውጫሌ ውልን በተመለከተ፤ «...በውጫሌ ውል ላይ ኢትዮጵያ የኢጣሊያን ጥገኝነት ተቀብላ ውል ከፈረመች በኋላ የጀርመን ንጉሠ ነገሥት ከኢትዮጵያ የሚላከውን ማንኛውንም ደብዳቤም ሆን ጉዳይ በኢጣሊያ መንግሥት በኩል መቀበል ሲገባቸው በቀጥታ ከምኒልክ የተጻፈውን ደብዳቤ ተቀብለዋል...» እያሉ የጻፉትን ራስ መኮንን ተቃውሞአቸውን ለኢጣሊያ መንግሥት ከነገሩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የውሉን መበላሸት ለአጤ ምኒልክ አሳወቁ። ከኢጣሊያንም ጋር በተደረገውም ጦርነት ራስ መኮንን ፲፭ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ይዘው ከምኒልክ እና ታላላቅ ጦር አዛዦች ጋር ዘምተዋል። በ፲፰፻፺፰ ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለኅክምና ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ጥር ፬ ቀን ከከተማቸው ከሐረር ተነሱ። ጥር ፱ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የጥምቀትን በዓል አክብረው ከዋሉ በኋላ ሕመሙ ስለጸናባቸው ወደ ኋላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር። እዚሁም ሲታመሙ ከቆዩ በኋላ መጋቢት ፲፫ ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም ቁልቢ ላይ አርፈው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ። ዐፄ ምኒልክም የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው አዲስ አበባ እንዲሆን ባዘዙት መሠረት፤ ሰኞ ሚያዝያ ፳፪ ቀን በአዲስ አበባና በዙሪያው ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የክርስቲያን የፍታት ጸሎት ተድርጎ በማግስቱም ማክሰኞ የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ ፳፫ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ፤ መኳንንቱና ሠራዊቱ ተሰብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውና የራስ ወርቃቸው፤ ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸው ተይዞ ፈረስና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊቱ መካከል እየተመላለሱ ታላቅ ልቅሶ ተለቀሰላቸው።
የራስ መኮንን አርባ በአዲስ አበባ የተደረገበት ዕለቱ ምን ነበር?
የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ ፳፫ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም
869
ሁዋዌ የተሰኘው ግዙፍ የቻይና ቴሌኮም ኩባንያ በብሪታኒያ የ5ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑ ተሰምቷል። የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሀገራቸው ከሁዋዌ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በቅንጅት ለመስራት ፍላጎት ያላት መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ መሰረትም ኩባንያው በቀጣይ በብሪታኒያ የ5ጂ ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጹት። ሁዋዌ ቻይና ከአሜሪካ ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ በዩናይትድ ስቴትስ አገልግሎት እንዳይሰጥ ክልከላ የተደረገበት መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ባለፈም ኩባንያው አገልግሎት በሚሰጥባቸው ሀገራት በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ይገባል በሚል ካናዳ እና አውስትራሊያን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት ጋር ያለው ግንኙነት መሻከሩ ይታወቃል። ብሪታኒያ ከኩባንያው ጋር በቅንጀት ለመስራት እና አገልግሎቱን ለመጠቀም መፈለጓም ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ሊያሻክረው እንደሚችል ተሰግቷል። ምንጭ፦ሲ ጂ ቲኤ ን
ሁዋዌ በአሜሪካ አገልግሎቱን ያቋረጠው ቻይናና አሜሪካ ወደ ምን በመሄዳቸው ምክንያት ነው?
የንግድ ጦርነት
265
ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ 10 የመተግበሪያ ስርዓት አጋጥሞ የነበረውን ችግር መፍታቱን አስታወቀ። በርካታ ተጠቃሚዎች መተግበሪያው ከትናንት ጀምሮ መስራት ማቆሙን ገልጸው ነበር። ተጠቃሚዎች እንደገለጹት በዴስክቶፕ መረጃ መፈለጊያ ትዕዛዝ ሲጠይቁ የሚፈልጉትን ነገር ከማግኘት ይልቅ ባዶ ሳጥን ያገኙ ነበር። ኩባንያውም የተጠቃሚዎችን ሪፖርት ካገኘ ከሰዓታት በኋላ የብዙ ተጠቃሚዎችን ችግር መቅረፍ መቻሉን አስታውቋል። ይሁን እንጅ አሁንም አንዳንድ ተጠቃሚዎች ኮምፒተሮቻቸውን እንደገና ማስጀመር ወይም ሪስታርት ማድረግ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ብሏል። ኩባንያው ምን ያህል ሰዎች ይህ ችግር እንዳጋጠማቸው ግን ያለው ነገር የለም፡፡ ዊንዶውስ 10 መተግበሪያ ሥርዓት በዓለም ዙሪያ 800 ሚሊየን የሚሆኑ ተጠቃሚዎች አሉት።
ዊንዶውስ 10 በዓለም ላይ ምን ያህል ሰዎች ይጠቀሙታል?
800 ሚሊየን
422
ካሣ አያሌው ገና የአራት ዓመት ህፃን ልጅ ሳለ በወቅቱ የትምህርት ገበታን መቋደስ የሚጀመርበት የቄስ ትምህርት ቤት ተልኮ ፊደል መቁጠር ጀምሯል። በዚህ ቆይታው ከፊደል ቆጠራ እስከ ዳዊት ንባብ በአግባቡ ለመማር በቅቷል። በኋላም በጊዜው እንጦጦ አምባ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተብሎ ይጠራ የነበረው ት/ቤት በመዝለቅ ዘመናዊ ትምህርቱን አንድ ብሎ ጀምሯል። ካሣ በዚህ ት/ቤት ሳለ ነበር ውስጡ ከነበረው የህይወት መክሊቱ ጋር የተገናኘው። የሦስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ በት/ቤታችን የሚገኘውን ሚኒ ሚዲያ የምቀላቀልበት ዕድል ተፈጠረ። ይህ ዕድል የተገኘው በክፍሌ ውስጥ ተማሪዎች ፊት ቆሜ ጋዜጣ ሳነብ ድንገት ክፍላችን በተገኙት የት/ቤታችን ም/ርዕሰ መምህር አማካኝነት ነው። ስማቸው መምህር ግርማ ይገዙ ይባላል። አነባበቤን አይተው ስለወደዱት እርሳቸው ይመሩት የነበረውን የሚኒ ሚዲያ ክበብ እንድቀላቀል አደረጉ። በዚህ ክበብ ውስጥ ሆኜ በትምህርት ቤቱ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩ ዜናዎችን እየዘገብኩ ዘወትር ማለዳ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር እየተዘመረ ሰንደቅ ዓላማ በሚሰቀልበት የተማሪዎች ሰልፍ ላይ ማንበብ ጀመርኩ» በማለት ካሣ የጋዜጠኝነት ህይወት መስመሩ አንድ ብሎ የተጀመረበትን ሁኔታ ያስታውሳል። ካሣ አያሌው ካሣ የዘጠነኛ ክፍል ትምህርቱን በእንጦጦ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት /ቲ ኤም ኤስ/ ከጀመረ አንስቶ ሙሉ ትኩረቱን የቀለም ትምህርቱ ላይ አድርጎ ቆይቷል። በዚህ ቆይታው ከማህበራዊ ሳይንስ ይልቅ የተፈጥሮ ሳይንስን ምርጫው አድርጎ ትምህርቱን ተከታትሏል። የአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ አገር ዓቀፍ ፈተና ሲወስድም እንደ ተለመደው ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ከፍተኛ ትምህርት የሚሸጋገርበት ዕድል አግኝቷል። በወቅቱ የከፍተኛ ትምህርት ምደባ የሚሰጠው በዕጣ ስለነበር ካሣ በዚህ አመዳደብ መሰረት የኢንጂነሪንግ ትምህርት እንዲማር የአዳማ ቴክኒክ ኮሌጅን እንዲቀላቀል ምደባ ወጥቶለታል። ምደባውን ተከትሎ ወደ አዳማ በማቅናት የቴክኖሎጂ ትምህርቱን መከታተል ቢጀምርም ቅሉ ሁኔታው ምቾት እንዳሳጣውና እንዳሎደደው ካሣ ይናገራል። ካሣ በ2005ዓ.ም ላይ ከፍቅረኛው ሊና ኑር አሕመድ ጋር በጋብቻ የተሳሰረ ሲሆን ቀዳማዊትና ለዕልና የተባሉ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዷል። በትዳር ህይወቱ እጅግ የተሳካለት እንደሆነ በቅርበት የሚያውቁት ጓደኞቹ ይመሰክራሉ። ከስራ ውጪ ያለ ሰዓቱን ሁሉ ከቤተሰቦቹ ጋር ማሳለፍ እንደሚያስደስተው ሁሉም ይመሰክሩለታል።
ካሳ በትምህርት ቤቱ ሚኒ ሚዲያ ክለብ ውስጥ አንቢገባ ያደረጉት ማን ናቸው?
መምህር ግርማ ይገዙ
439
በኢትዮጵያ የሚገኙ በርካታ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች መንግሥት ተገቢውን ክትትል እያደረገ ባለመሆኑና ኩባንያዎች በክህሎት የበቁ ኢትዮጵያዊያን በሥልጠና ዕገዛ ባለማድረጋቸው ምክንያት፣ አብዛኛዎቹ በሲሚንቶ ፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሠሩት ሠራተኞች የውጭ ዜጎች መሆናቸው ተገለጸ፡፡ በኢትዮጵያ ምርት በማምረትና በግንባታ ላይ የሚገኙትን ጨምሮ 17 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚገኙ ሲሆን፣ 12ቱ በተለያየ የማምረት መጠን ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በበርካታ ፋብሪካዎች በተለይም ግዙፍ በሚባሉት ዳንጎት፣ ሙገርና ደርባ ኩባንያዎች ውስጥ የውጭ ዜጎች የማኔጅመንቱንና ቴክኒካል ሥራውን በበላይነት እንደሚይዙ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ስምረት ግርማ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም በሥራ ላይ በሚገኙት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች እንዳሉ የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሯ፣ ኢትዮጵያውያን እየሠሩባቸው ያሉ ዘርፎችም ቢሆን በዝቅተኛ ዕርከንና በጉልበት ሥራ ላይ የሚገኙ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በዳንጎት፣ ሙገርና ደርባ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የውጪ ሀገር ዜጎች ሠራተኞች በብዛት የሚሳተፉት በምንድን ነው?
የማኔጅመንቱንና ቴክኒካል ሥራውን
336
መለጋሲ መለጋሲ (Malagasy) ከአውስትሮኔዚያን የቋንቋ ቤተሠብ ቋንቋዎች ሁሉ ምእራበኛው ሲሆን የማዳጋስካር መደበኛ ቋንቋ ነው። 1500-2000 አመታት ከዛሬ በፊት ከእንዶኔዚያ የመጡ የማዳጋስካር ኗሪዎች ቋንቋ በመሆኑ፣ ከቃላቱ መዝገብ 90% ከመቶ በቦርኔዮ እንዶኔዚያ ከተገኘው ቋንቋ ከማአንያን ጋራ ተመሳሳይ ነው። የቀሩትም 10% ቃላት በተለይ ከአፍሪቃ ቋንቋዎች (ከባንቱ) እና ከአረብኛ ተበድረዋል። በአረፍተ ነገር ውስጥ ግሡ ከሁሉ ይቀድማል። ይህ ተራ እንደ ዕብራይስጥ ይመስላል እንጂ ለብዙዎች ቋንቋዎች የተለመደ አይደለም። በየቃሉ ውስጥ ከመጨረሻው ክፍለ-ቃል በፊት የሆነው ክፍለ-ቃል አናባቢ ይጠበቃል፤ ሌሎቹ አናባቢዎችም ይነበነባሉ (በሙሉ አይስሙም)፤ ስለዚህ "Malagasy" እንደ ፈረንሳይኛ አጻጻፉ "Malgache" (መልጋሽ) ይመስላል።
በመለጋሲኛ ቋንቋ የሚናገሩ የማዳጋስካር ነዋሪዎች ከየት አካባቢ የመጡ ናቸው?
ከእንዶኔዚያ
106
ጋሞጐፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ከ1955 እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ የጋሞ ጐፋ ጠቅላይ ግዛት፣ የሰሜን ኦሞ አስተዳደር አካባቢና ከዚያም የሰሜን ኦሞ ርዕሰ ከተማ በመሆን ለቀድሞዎቹ የጋሞ፣ የጐፋ፣ የጋርዱላና ሐመር ባኮ አውራጃዎች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ማዕከል ሆና ያገለገለች ስትሆን ከ1993 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ዓመታት ደግሞ አስራ አምስት ወረዳዎችንና ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን አቅፎ ለያዘው ጋሞ ጐፋ ዞን ዋና ከተማ በመሆን እያገለገለች የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የዘይሴ ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሄረሰቦችን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ ሌሎች የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ተወላጆች ተከባብረውና ተቻችለው በፍቅርና በሰላም የሚኖሩባት አርባ ምንጭ ከተማ በቀለማት አደራደሩ ትኩረትና ተወዳጅነት የማይለየው የጋሞ ብሔረሰብ የክብርና የማዕረግ ልብስ እንዲሁም መታወቂያው የሆነውንና ዱንጉዛ በመባል የሚታወቀው ባህላዊ ልብስ ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ የሸማ ጥበብ አልባሳት ሥራዎች መፍለቅያ አካባቢዎች እምብርት ከመሆኗም በተጨማሪ በባህላዊ ቤት አሰራራቸው በለቅሶና ሠርግ ስርዓታቸው በባህላዊ የማምረቻና የመገልገያ ቁሳቁሶቻቸው የብዙዎችን አድናቆትና አግራሞትን ላስጫሩት የጋሞ፣ የጐፋ፣ የዘይሴ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሔረስብ ህዝቦች መዲና ነች፡፡    ከባህር ወለል በላይ ከ1,300 እስከ 1,500 ሜትር ከፍታ ላይ ስትገኝ  የአርባ ምንጭ ከተማ አየር ንብረት በተለምዶ ቆላማ የሚሉት አይነት ሲሆን፤ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠኗ 240c ነው፡፡ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኗ 900 ሚሊ ሜትር ሆኖ ግንቦት፣ ሰኔ፣ መስከረምና ጥቅምት ወራት ከፍተኛ የዝናብ መጠን በዓመቱ ውስጥ የሚመዘግብባቸው ወራት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡  በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ስፍራ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን መንትያዎቹ የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ፤በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን   የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያ  እና የተፈጥሮ ደኖችን  ሌሎች ከህሊና ጓዳ የማይፋቅ ትዝታን ጥለው የሚያልፉ ሃብቶች ባለቤት ናት በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ከተማ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን ፤ የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያን በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት እና የተፈጥሮ ደኖችን ይገኛሉ፡፡ የዞኑን አስደናቂ የቱሪስት መስህቦች እንግዶቻችንን በማስጎብኘት ከታዋቂ የዓሳ ምርታችን ፣ ከማንጎ ፤ ከሙዝ እና በአፕል ማሳችን እየተንሸራሸርን የማይረሱ ትዝታዎችን ጥለው ያልፋሉ፡፡
የከተማዋ የሙቀት መጠን ምን ያህል ነው?
240c
862
አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። አፈወርቅ ተክሌ በእንግሊዝ አገር የአዳሪ ተማሪ ቤትን ኑሮ ሲያስታውሱ የባዕድ ባህላት፣ የአየር ለውጥ እና የተለመደው የተማሪ ቤት ዝንጠላ እንዳስቸገራቸው ያወሳሉ። ቢሆንም ትምሕርታቸውን በትጋት ሲከታተሉ ቆዩ። በተለይም በሒሣብ፣ በኬሚስትሪ እና በታሪክ ትምሕርቶች ጥሩ ውጤት በማምጣት ሰለጠኑ። ነገር ግን አስተማሪዎቻቸው የተፈጥሮ ስጦታቸው ኪነ ጥበብ እንደሆነ ለመገንዘብ ብዙ ጊዜም አልወሰደባቸውም። በነሱም አበረታችነት በእዚህ ስጦታቸው ላይ የበለጠ ለማተኮር ወስነው በሎንዶን የኪነ ጥበብ ማእከላዊ ትምሕርት ቤት ተመዝግበው ገቡ እዚህ ትምህርት ቤት ጥምሕርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለከፍተኛ ጥናት በስመ ጥሩው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ የስሌድ ኪነ ጥበብ ማዕከል የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ተማሪ (ከተከተሏቸው አፍሪቃውያን አንዱ የሱዳን ተወላጁ ኢብራሂም ኤል ሳላሂ ናቸው) በመሆን ገቡ። እዚህ በስዕል፣ ቅርጽ እና በአርክቴክቸር ጥናቶች ላይ አተኩረው ተመረቁ። ትምሕርታቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ፣ በየጥቅላይ ግዛቶቹ እየተዘዋወሩ፣ በየቦታው እስከ ሦስት ወራት በመቀመጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እና የብሔረሰቦቿን ባህልና ወግ በሚገባ አጥንተዋል።
አፈወርቅ ተክሌ መች ተወለዱ?
ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም
135
መዓዛ ብሩ መዓዛ የተወለደችው እዚህ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን ዘመኑም 1951 ዓ.ም ነበር፡፡ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ክፍል በሐረርጌ ክፍለ ሀገር በሒርና ከተማ ተምራ፣ ከአራተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርቷን ደግሞ በቅድስት ማርያም ትምህርት ቤት ተከታትላ ፈጽማለች፡፡ መዓዛ በትምህርት ቤቷ በክፍል ውስጥ አጫጭር ታሪኮችን ለተማሪዎች በማንበብ ከመታወቋም ሌላ ከፍ ያለ የሥነ - ጽሑፍ ዝንባሌ እንደነበራት የሚያስታውሱት መምህራኗ “አንድ ቀን ታላቅ የጥበብ ሰው እንደሚወጣት እናውቅ ነበር” ይላሉ፡፡ መዓዛ በ1971 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ - ቋንቋ ጥናት ተቋም ውስጥ በሥነ-ልሣን ትምህርት ክፍል ተመደበች፡፡ ሥነ-ልሣን መዓዛ የምትፈልገው ጥናት ባለመሆኑ በምደባው ቅር ብትሰኝም፤ በንዑስ ትምህርት ደረጃ የምትወስደው የውጭ ቋንቋና ሥነ - ጽሑፍ በመሆኑ ለነበራት ቅሬታ እንደማካካሻ ሆኖላታል፡፡ በዚህ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ሳለች የተፈጠረ አንድ አጋጣሚ ደግሞ መዓዛንና ሬዲዮንን የሚያስተሳስር ይሆናል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ ሬዲዮ የፕሮግራሞች ኃላፊ የነበረው አቶ ታደሰ ሙሉነህ ለሚያዘጋጀው የእሁድ የሬዲዮ ፕሮግራም ድራማ የሚጫወቱ ሸጋ ድምጽ ያላቸው ወጣቶችን ሲያፈላልግ ከመዓዛ ጋር ይተዋወቃል፡፡ ድራማው አስታጥቃቸው ይሁን ያሰናዳው ሲሆን የመዓዛ ድምጽ ለሙከራ በስቱዲዮ ተቀርጾ ሲሰማው፣ ታደሰ ሙሉነህ የሚፈልገውና የሚወደው ድምጽ ሆኖ ስላገኘው ይደሰታል፡፡ ከዚህ በኋላም ለእሁድ ፕሮግራም የሚሆኑ ጽሑፎችን በየሳምንቱ እንድታነብለት ያግባባትና የመዓዛና የሬዲዮ ፍቅር በኢትዮጵያ ሬዲዮ ይወለዳል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የመዓዛ ድምጽ በእሁድ የሬዲዮ ፕሮግራም አድማጮች ዘንድ የተለመደና የተወደደ ሆነ፡፡ መዓዛም የሌሎችን ጽሑፎች በማንበብ ብቻ ሳትወሰን የራሷን ጽሁፎች እያዘጋጀች የምታቀርብ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ከሬዲዮ ፕሮግራሙ ቤተሰቦች እንደ አንዱ ሆነች፡፡ በ1974 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲ ተመርቃ ትምህርቷ ፍጻሜውን እስካገኘ ድረስም መዓዛ ሬዲዮና ትምህርትን ጎን ለጎን ስታስኬድ ቆይታለች፡፡ የመዓዛ የሥራ ዓለም የተጀመረው ግን በምትወደውና በምትፈልገው በኢትዮጵያ ሬዲዮ ውስጥ ሳይሆን መንግስት በመደባት በባህል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ ስራዋም ባህልና ስፖርት የተባለው የመስሪያ ቤቱ መምሪያ በሚያሳትመው “መርሐ ስፖርት” የተሰኘ ወርሃዊ የስፖርት መጽሔት (በኋላ ጋዜጣ) ላይ ሆነ፡፡ ምንም እንኳ አዲሱ ስራዋ ከራዲዮ የሚያርቃት ቢሆንም መዓዛ ግን ሳትሸነፍ ሬዲዮን በትርፍ ጊዜ ሥራነት ተያያዘችው፡፡ ሬዲዮ ጣቢያው የሚሠጣትን አነስተኛ ክፍያ እየተቀበለችም ልዩ ልዩ ጭውውቶችን እና መጣጥፎችን በግልና በጋራ በማቅረብ ተወዳጅ ሥራዎቿን ለሕዝብ አበርክታለች፡፡
መዓዛ ብሩ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ክፍል ድረስ የት ተማረች?
በሐረርጌ ክፍለ ሀገር በሒርና ከተማ
82

መዓዛ ብሩ በስንት ዓመተ ምህረት ተወለደች?
1951 ዓ.ም
48
ፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ "The Nation"፣ "The Chinese Recorder"፣ "Asia" እና "The Atlantic Monthly" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል።
ፐርል በክ የመጀመሪያ ድርሰቷ የት ኩባንያ ውስጥ ታተመላት?
በጆን ዴይ ኩባንያ
675
አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ በሃገራችን ኢትዮጵያ ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅ እና ቅድስት እድና ይባላሉ ። የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው ። ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረአምላክ ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ። በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል። "የት ልሒድ?" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለስምንት ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየኋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከስምንቱ ጋር ከቃልኬዶን ጉባዔ በኋላ በ፬፻፶፩ ዓም ወደ ኢትዮጵያ መጡ ። ከዘጠኙ ቅዳሳን ወደ ኢትዮጵያ ከሮምና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከፈለሱት አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው ። በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል ። አቡነ አረጋዊ ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል ። በመጨረሻም ደብረ ዳሞ ማረካቸዋለች ። ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል ፡፡
አቡነ አረጋዊ በየት መጽሐፍትን ተረጎሙ?
በቤተ ቀጢን (አክሱም)
810
የትነበርሽ ንጉሴ የትነበርሽ ንጉሴ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ እና የአካል ጉዳተኛ መብትቶች ተሟጋች ናት ፡ እ.ኤ.አ በ 2017 "የአካል ጉዳተኞችን መብቶችን እና ማካተቶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም  በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉየአእምሮ ውቅርን መለወጥ የሚያበረታታ ሥራዋ"  ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድን ተሸልማለች። የትነበርሽ ንጉሴ የአይን ብርሃኗን ያጣችው በ 5 ዓመቷ ነበር ። ይህ አጋጣሚ በተወለድችበት በአማራ ክልል በስፋት ይተገበር ከነበረው ያለ አድሜ ጋብቻ  አንድታመልጥ እድሉን እንደፈጠረላት ትናገራለች። ፡፡የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሻሸመኔ ካቶሊክ የዓይነ ስውራን  ት/ቤት ተከታትላ ወደ ዳግማዊ  ምኒልክ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (አካታች ትምህርት ቤት) ገብታ እስከ 12 ኛ ክፍል እዚያ ተማረች። በትምህርት ቤቱ ካላት አካዳሚክ ተሳትፎ በተጨማሪ የተማሪዎችን አማካሪ ጨምሮ ከ 6 በላይ የክለቦችን ክበባት መርታለች ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በመቀላቀል የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ በማኅበራዊ ሥራ አግኝ ታለች፡፡ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ  በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በተከታታይ  ትሳተፋለች በዚህም  የመኢአድ የፀረ ኤድስ እንቅስቃሴን ከ2004 - 05 በመምራት በ 2006 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (አአዩ) ሴት ተማሪዎች ማህበርን በመመስረት እንዲሁም የማህበሩ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት በመሆን  አገልግላለች ፡፡
በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ እና የአካል ጉዳተኛ መብትቶች ተሟጋች ማን ትባላለች?
የትነበርሽ ንጉሴ
0
ዕዝራ ዕዝራ ወይም ሱቱኤል በብሉይ ኪዳን ዘንድ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ የአይሁድ ካህን ነበረ። የሠራያ ልጅ ሲሆን በፋርስ ንጉስ አርጤክስስ 7ኛው አመት (464 ክ.በ.) ከ5000 ከወገኖቹ ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ፈቃድ ተቀበለ። ከዚህ 13 አመት በኋላ ነህምያ የከተማውን ቅጥር ሲጠግነው ዕዝራ ኦሪት በሙሉ ለሕዝብ አነበበ (መጽሐፈ ነህምያ ምዕ. 8)። በአይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ በዮሴፉስ ዘንድ ይህ የፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ሳይሆን አሕሻዊሮስ ነበረ። አርጤክስስ የአሕሻዊሮስ ልጅ ሲሆን እነዚህ 2 ነገስታት ስሞች ብዙ ጊዜ በተለያዩ ቅጂዎች ተደናገሩ። ዮሴፉስ ደግሞ ዕዝራ የሞተበት ወራት ኤልያሴብ ታላቁ ካህን በሆኑበት ወቅት ገደማ እንደ ነበር ይመሰክራል። የአሕሻዊሮስ ዘመን ከሆነ 7ኛው አመት 486 ክ.በ. ነበር። ዕዝራ መጽሐፈ ዕዝራንና መጽሐፈ ነህምያ ከመጻፉ በላይ በዲዩትሮካኖኒካል መጽሐፍት ክፍል የሚገኙት መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤልና መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ እንደ ጻፈ ይባላል። መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ ለመጽሐፈ ዕዝራ በጣም ተመሳሳይ በመሆኑ በዕዝራ ካልዕ 81 ግን ሠራያ ሳይል በግድፈት የአዛርያስ ልጅ ይለዋል። ዕዝራ ሱቱኤል በሚባለው ትንቢት ደግሞ በ11 የጻፈው ኢየሩሳሌም ከጠፋች 30 አመት በባቢሎን መሆኑን ይላል። ይህም 565 ክ.በ. ማለት ነው። በዚህ መጽሐፍ 1344 መሠረት 24 መጻሕፍት በ40 ቀን ውስጥ ጻፈ ቢለን፥ በሌሎች ልሣናት ሕትመት ግን ስለ 94 መጻሕፍት እየተናገረ ከነዚህ መሀል ተጨማሪው 70 መጻሕፍት በምስጢር እንዲቆዩ ነበረባቸው ይላል።
የሠራያው ልጅ በፋርስ ንጉስ አርጤክስስ ከ5000 ከወገኖቹ ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ፈቃድ የተቀበለው መቼ ነው?
7ኛው አመት (464 ክ.በ.
86
ናሚቢያ ናሚቢያ በደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ፣ በስሜን በአንጎላና በዛምቢያ፣ በምስራቅ በቦትስዋና፣ በደቡብም በደቡብ አፍሪቃ ትካለላለች። በ1982 አመተ ምኅረት ነጻነትዋን ከደቡብ አፍሪቃ ስላገኘች በጣም አዲስ አገር ነች። ዋና ከተማዋ ዊንድሁክ ነው። የናሚቢያ በረኅ አውራጃ ከጥንት ጀምሮ በሳን (ቡሽማን)፣ በዳማራና በናማቋ ሕዝቦች ተሰፈረ። በ14ኛው መቶ ዘመን፣ የባንቱ ወገኖች ባስፋፉ ጊዜ አገሩን ሠፈሩ። ክልሉ ግን ከ19ኛው መቶ ዘመን በፊት በአውሮጳውያን አልተዘለቀም። በዚያን ጊዜ ጀርመን ደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ ተብላ አገሪቱ የጀርመን ቅኝ ግዛት ሆነች። ዳሩ ግን ዋልቪስ በይ የተባለው ትንሽ ወደብ ብቻ የእንግሊዝ ግዛት ነበር።
ናሚቢያ ከደቡብ አፍሪካ ነጻነቷን ያገኘችው መቼ ነው?
በ1982
117
ኒሺ ፍሬደሪክ ዊልሄልም ኒትሸ (ኦክቶበር 15, 1844 - ኦገስት 25, 1900) ጀርመናዊ ጻህፊና ፈላስፋ ሲሆን አለምን ይቀይራሉ ብሎ ያመነባቸውን ብዙ መጻህፍት በመድረስ ይታወቃል። እርግጥ ኒሺ፣ በነበረበትም ሆነ በኋላ ዘመኑ ብዙ ተቃዋሚወች ቢነሱበትም በዚያው ልክ ብዙ ሰወች ስራወቹን እንደ ታላቅ የፍልስፍና እና ስነ ጽሁፍ ስራ ይወስዷቸዋል። ኒትሸ አብዛኛው ጽሁፉ የሚያተኩረው ሰወች እንዴት ሊኖሩ ይገባቸዋል? በሚለው ጥያቄ ነው። በዚህ ምክንያት እሱ ይኖርበት የነበረውን ዘመን የጀርመን ሥነ ምግባር (ኤቲክስ) በመንቀፍ ብዙ ጽፎአል። ሠናይ እና እኩይ (ጥሩና መጥፎ) ተብለው ተለይተው ይሰራባቸው የነበሩትን የጊዜውን ሥነ ምግባር ዋጋወች በመተቸት ሰወች አዲስ ሥነ ምግባር ፈጥረው ለሁሉም ምግባር አዲስ የሠናይነትና እኩይነት (ጥሩ እና መጥፎ) ዋጋ እንዲሰጡ በጽሑፎቹ ብዙ ሞክሯል።በዚህ መሰረት፣ ለምሳሌ፣ በክርስቲያኖች ዘንድ የሚሰራበትን ለደካሞች ማዘንን ሠናይነት ተቃውሟል። በሱ አስተያየት ደካሞች ሲታዘንላቸው የበለጠ ይዳከማሉ የሚል ነው ምክንያቱም በሱ አስተያየት ደካሞቹ በጠንካሮቹ ላይ የበለጠ ጥገኛ በመሆን መላው ህብረተሰብ ይዳከማል የሚል ነው። በተጨማሪም፣ የሰው ልጅ የሚኖርበትን ተጨባጩን አለም መገንዘብ እና ክሁሉ በላይ ስለዚሁ ዓለም ማተኮር አለበት ብሏል። ሰማይና ሌሎች አለማትን በማጣጣል፣ የሰው ልጅ እነዚህን አይነት አለሞች የሚፈጥረው አሁን ያለበትን ተጨባጩ የውኑ አለም ችግሮች መፍታት ሲያቅተው ለመፈርጠጥ ነው በማለት የሰው ልጅ ስለዚህ ምድር ብቻ እንዲያስብ ይወተውታል። ኒሽ የሰው ልጅ እራሱን በራሱ ማሸነፍ እንዲችል አጥብቆ ያምናል። በኒሺ ፍልስፍና፣ አንድ እራሱን ያሽነፈ ሰው በጣም የተለወጠ እና የተሻለ ስለሚሆን "ሱፐር ማን" ወይም "የበላይ ሰው" እንዲባል ሰይሟል። የበላይ ሰው እንግዴህ ጠንካራና በሌሎች ሰወች "ሠናይ" እና "እኩይ" ወይም ደግሞ "ጥሩ" ና "መጥፎ" ዋጋወች የማይመራ፣ ይልቁኑ የራሱን ሥነ ምግባር የሚፈጥር ነው።
የኒሽ አቁዋም ምን ነበር?
የሰው ልጅ እራሱን በራሱ ማሸነፍ እንዲችል
886
በማደግ ላይ ባሉ አገራት የሚኖሩ ህዝቦች ግንባር ቀደም ገዳይ ከሚባሉት በሽታዎች አንዱ የሆነውን የቲቢ በሽታ ለማስቆም የሚያስችል ”EndTB” የተሰኘ ንቅናቄ ተካሄደ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባለፈው ረቡዕ በሒልተን ሆቴል በይፋ ያስጀመረው ቲቢን እናስቁም ንቅናቄ እ.ኤ.አ በ2032 በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ100 ሺህ አስር ብቻ ለማድረስ የታለመ ነው፡፡ ከአዳሱ የፈረንጆች ዓመት እስከ 2032 ዓ.ም ይደረጋል በተባለው በዚሁ “ቲቢን እናስቁም” ንቅናቄ፤ አገራት ሁሉ፤ ተሳታፊ በመሆን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለውን የቲቢ በሽታ ለመግታትና በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በትጋት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የግሎባል ቲቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ማርዮ ራቨግሊዮን እንደገለፁት፤ በሽታው በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ስርጭት 133 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች ሲሆን በኢትዮጵያ ቁጥሩ 200 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች ይደርሳል ብለዋል፡፡ በሽታውን ለማስቆም በተያዘው ዕቅድ መሰረትም፤ እ.ኤ.አ ከ2016-2032 ዓ.ም ድረስ በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ100ሺ አስር ለማድረስ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡ ዕቅዱ እንዲሳካም አገራት ከፍተኛ ሥራ እንደሚጠበቅባቸውና ለተግባራዊነቱም የመንግስታቱን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት በቲቢ በሽታ የሚያዙ ሰዎችን በ2032 ወደ ስንት ለመቀነስ አስቧል?
ከ100 ሺህ አስር ብቻ
203
ገብረሃና ገብረማሪያም አለቃ ገብረሃና ገብረማሪያም (፲፯፻፺፯ - ፲፰፻፺፬ ዓ.ም.) ዕውቅ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። አባታቸው መምህር ገብረ ማርያም ምጥኑ ሲባሉ እናታቸው ወይዘሮ ሳህሊቱ ተክሌ ይባሉ ነበር። ገብረሃና ገብረማሪያም በቤገምድር ጠቅላይ ግዛት በደብረታቦር አውራጃ በፎገራ ወረዳ ልዩ ስሟ ናበጋ ጊዮርጊስ በምትባል ቦታ በ፲፯፻፺፯ ዓ.ም. ተወለዱ። ገብረሃና እቴጌ መነንን መዝሙርን፣ ውዳሴ ማርያምንና ሌሎችንም አስተምረው ከጨረሱ በኋላ ለከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በእቴጌይቱ ትዕዛዝ ወደ ጎንደር ተላኩ። ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላም በእቴጌይቱ ትዕዛዝ የአለቃነት ማዕረግ ተሰጣቸው። ከዚያም ገብረሃና በጎንደር አካባቢ የሚገኙትን ቤተ ክርስቲያናት ብቃት በተሞላበት ሁኔታ ያስተዳድሩ ጀመር። እንደ ትልቅ ምሁር ይታዩ ጀመር። በተለይ ፍትሐ ነገስትን በመተርጎም የሚወዳደራቸው ወይም የሚስተካከላቸው አልነበረም። አለቃ ገብረሃና አቶ ሙንሮዝ በተባለ አውሮጳዊ በ1890 ዓ.ም. ፎት እንደተነሱ ሞላቨር ይገልጻል። ዓፄ ቴዎድሮስ ስልጣን ከያዙና እራሳቸውንም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ብለው ዙፋናቸውን በጫኑበት ጊዜ በሀገሪቱ ከፍትሐ ነገስት ሌላ የተፃፈ ሕግ ባለመኖሩ አለቃ ገብረሃና በተለይ ፍትሐ ነገስትን መሠረት በማድረግ ንጉሡ ሀገርን እንዲያስተዳድሩ ይረዱዋቸው ነበር። በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ቤተክርስቲያን ብሉይ ኪዳንንና አዲስ ኪዳንን በመተርጎም ትልቅ አገልግሉት ቢያደርጉም ትልቁን አስተዋጽዖ ያደረጉት በሕግና በቤተ ክርስቲያን ዜማና አቋቋም ነበር። እንደዚሁም የፈጠሩት አዲስ ዓይነት የቤተክርስቲያን አቋቋም ከደብረታቦር ወደ ሸዋ እና ትግራይ ተሰራጭቷል። ይህንንም አቋቋም ከብቸኛው ልጃቸው በኋላ ተክለ ብለው ሰየሙት። ይህም አቋቋም አስደሳችና ማራኪ የአቋቋም ዘዴ ነው።
አለቃ ገብረሃና ገብረማሪያም የሕይወት ዘመናቸው ከመቼ እስከ መቼ ነው?
፲፯፻፺፯ - ፲፰፻፺፬ ዓ.ም.
33
የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች አሉ። እነዚህም መሣሪያዎች የጅማት፣ የትንፋሽና የምት ተብለው ወደ ሶስት ይከፈላሉ። የክር ሙዚቃ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በንዝረት ነው፤ ክራር መሰንቆ ከዚህ የሙዚቃ መሳርያዎች ወገን ይመደባሉ፡፡ የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በትንፋሽ ኃይል ነው ምሳሌ ዋሽንት። የምት የሙዚቃ መሣርያ እንደ ከበሮ ሲመቱ ድምጽ የሚያወጡ ናቸው።
የክር ሙዚቃ መሳሪያዎች ድምፅ የሚሰጡት እንዴት ነው?
በንዝረት
133
ጣይቱ ብጡል «ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ዓ/ም በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ በ ፹ ቀናቸው ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፴፫ ዓ/ም በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ። እናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ከባለቤታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ከሞቱ በኋላ በጅሮንድ መዩ የተባሉትን የዓፄ ቴዎድሮስን ባለሟል አግብተው ነበር። እሳቸውም ጣይቱ ብጡል ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ ልዩ መምህር ቀጥረውላቸው እንደነበር ይታወቃል። እቴጌ ጣይቱ በማኅደረ ማርያም ሆነው ሲማሩና መፃሕፍትን ይቀጽሉ በነበሩበት ጊዜ ለቤተክርስቲያን መጋረጃ መሥሪያ በትርፍ ጊዜያቸው ፈትል እየፈተሉ ያቀርቡ ነበር። በበገና ቅኝትና ድርደራም በኩል የታወቁ ባለሙያ እንደነበሩ ይተረክላቸዋል። የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የዓፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ/ም በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገብተው በነሐሴ ፳፬ ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከተጫጩ ከሁለት ዓመት በኋላ ወይዘሮ ጣይቱን ለማስመጣት በቤተ መንግሥቱ በተደረገው ምክር መሠረት አለቃ ተክለማርያም ወልደ ሚካኤል ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ተላኩ። በዚያም አስፈላጊው ሁሉ በተፋጠነ ሁኔታ ተሟልቶ በጐጃም በኩል ደንገጡሮችና አሽከሮች አስከትለው ጉዞውን ጀመሩ። ደብረ ብርሃንም በገቡ ጊዜ ንጉሡ /ምኒልክ/ ታላቅ አቀባበል አደረጉላቸው። ከዚያም ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌ ብጡል ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የጋብቻቸው ስነ-ሥርዓት የፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ/ም በአንኮበር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ተጋቡ።
እቴጌ ጣይቱ በየት ተወለዱ?
ደብረ ታቦር ከተማ
126
ቺኑዋ አቼቤ በሙሉ ስሙ ሲጠራ አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ይሰኛል። ምናልባትም ናይጄሪያ ካሉዋት ምርጥ ፀሃፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የሚሰለፍ ሳይሆን አይቀርም። በ1930 እ.ኤ.አ. ኦጊዲ በተባለች የናይጄሪያ ግዛት ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ ተወለድ። በ1953 እ.ኤ.አ. ከለንደን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ለአቼቤ ድንቅ ሥራ የተባለለት "Things Fall Apart" 50 ወደሚሆኑ የአለም ቁዋንቁዋዎች የተተርጎመ ሲሆን ወደ 10,000,000 ቅጂዎች እንደተሸጡለት ይነገራል። አቼቤ ከአፍሪካ ፀሃፍት ሁሉ ሥራው በበዙ ቁዋንቁዋዎች በመተርጎም ክብረ ወሰኑን እንደያዘ ነው። ብዙዎችም ይኸው ድርሰቱ በአለም እስከዛሬ ከተደረሱ ምርጥ ልበ-ወለዶች መካከል እንደሆነ ይስማማሉ። አቼቤ ከ30 ከሚበልጡ ዩኒበርስቲዎች የክብር ዶክትሬት የተቀበለ ሲሆን ብዙ ሽልማቶችንም ከተለያዩ ድርጅቶች አግኝቷል። ይሁንና እስከ አሁን ድረስ የኖቤል ሽልማት ለማግኘት አልታደለም። ይኸውም በብዙው ጽሁፉ የመራቡን አለም ዘረኛነት የሚተች በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል። በ1990 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ከወገቡ በታች መንቀሳቀስ የተሳነው ሲሆን ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኘው የባርድ ኮሌጅ የቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ፕሮፌሰር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
ለአቼቤ 50 ወደሚሆኑ የአለም ቋንቋ የተተርጎመ እና 10,000,000 ቅጂዎች የተሸጡለት ድንቅ የስነፅሑፍ ስራው ምን በመባል ይታወቃል?
Things Fall Apart
234
አፖሎ 11 አፖሎ 11 ለመጀመሪያ ጊዜ ሰወችን ከመሬት ወደ ጨረቃ ለማጓጓዝ የተዘጋጀ የመንኮራኩር ሚስዮን ነው። ይህ ጉዞ የተቀናበረው በአሜሪካው የጠፈር አጥኝ ተቋም ናሳ ነበር። መንኮራኩሩ ሐምሌ16 1961ዓ.ም ከመሬት ሲመጥቅ፣ በውስጡ ሶስት ጠፈርተኞችን፣ ማለትም ኔል አርምስትሮንግ፣ በዝ አልድሪንና ማይክል ኮሊንስን የያዘ ነበር። መጓጓዣ መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ ከ4 ቀን በኋላ ሐምሌ 20 ሲደረስ፣ በዚሁ ቀን አርምስትሮንግና አልድሪን የጨረቃን ምድር በእግራቸው በመርገጥ የመጀመሪያወቹ ሰዎች ሆኑ። ኮሊንስ ባንጻሩ በጨረቃ ከባቢ በመብረር ከላይ ይጠብቃቸው ስለነበር ጨረቃን አልረገጠም። ይህ ድርጊት በፕሬዘደንት ኬኔዲ "የሰወች ልጅን ጨረቃ ላይ አሳርፎ በሰላም መመለስ" አላማ ያሳካ ነበር። የአፖሎ 11 ሚሲዮን ወደ ጠፈር ሲመነጠቅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰወች በአለም ዙሪያ በቴለቪዥናቸው ተመልክተውታል። ይህን ሚሲዮን ይዞ የተጓዘው ሮኬት ሳተርን ፬ ሲባል ችቦው እየተንቀለቀለ ወደ ሰማይ ጉዞ የጀመረው ኬኔዲ ጠፈር ማዕከል፣ 1961 ዓ.ም. ነበር። መሬትን ከለቀቀ ከ2 ሰዓት በኋላ የጨረቃ ትዕዛዝ ማዕከልና ማረፊያ ሞጅሎቹ ዋናውን ሮኬት ለቀው በጠፈር ጉዞ ቀጠሉ። ከ3 ቀን በኋላ ትዕዛዝ ማዕከሉና ማረፊያው ሞዱል የጨረቃን ምህዋር ተከትለው ጨረቃን መዞር ጀመሩ። ከአንድ ቀን በኋላ ማረፊያው ሞዱል ከትዕዛዝ ማዕከሉ ተላቆ ጨረቃ ላይ አረፈ። በዚህ የማረፍ ተግባር ወቅት የኮምፒውተር ስህተት ስለገጠመ ማረፊያው ሞዱል በኔል አርምስትሮንግ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር ነበር። የሆኖ ሆኖ ለ25 ሰኮንዶች በቂ የሆነ ነዳጅ ሲቀር ማረፊያው መንኮራኩር ኔል አርምስትሮንግንና አልድሪንን ይዞ ጨረቃ ላይ በሰላም አረፈ። ጨረቃ ላይ ስራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሁለቱ ጠፈርተኞች ወደ ማረፊያ መንኮራኩራቸው በመመለስ ለ7 ሰዓት ጨረቃ ላይ ከተኙ በኋላ ከላይ በኮሊንስ ወደ ሚበረው የትዕዛዝ ማዕከል ለመብረር ዝግጅት ጀመሩ። እነ አርምስትሮንግ በጨረቃ ላይ በነበሩበት ጊዜ ብዙ ቁሶችን ትተው ተመልሰዋል። ለምሳሌ ከ73 የአለም መሪወች የተላለፉ መልዕክቶችን፣ የሰላምታ መልክዕት በሁሉ የመሬት ላይ ቋንቋወችና የሁለት ሰው ልጆች ስዕሎችን ትተው ተመልሰዋል። የአሜሪካንንም ባንዲራ በጨረቃ ተክለዋል። ሓምሌ 24 የትዕዛዝ ማዕከሉ መሬት ላይ ሲደርስ ምናልባትም ጠፈርተኞቹ ያልታወቀ አደገኛ ቫይረስ ጨረቃ ላይ አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል በሚል በኳረንታይን ለ3 ሳምንት ከሰው ልጆች ተለይተው ተቀመጡ። ከኳረንታይን ሲወጡ፣ በርግጥም እንደ ታላላቅ ጀግኖች በተለያዩ የአለም ክፍሎች ስማቸው ተጠራ በዋሽንግተን ዲሲና በሜክሲኮ ሲቲ ለጠፈርተኞቹ ትልቅ ሰልፍ ሆነ።
ሀምሌ 16/1961 አፓሎ 11 ከመሬት ሲመነጠቅ በውስጡ የያዛቸው ጠፈርተኞችን እነማን ነበሩ?
ኔል አርምስትሮንግ፣ በዝ አልድሪንና ማይክል ኮሊንስ
167
ደቡብ አፍሪካ በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ። ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውን፣ ብሉምፎንቴንና ፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው። ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው። የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ። የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካ ተወዳጅ ስፖርቶች ምን ምን ናቸው?
እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ
695
አማራ (ክልል) አማራ (ክልል 3) ከዘጠኙ የኢትዮጵያ ክልሎች አንዱ ሲሆን ከ 1994 በፊት አራት የሀገሪቱን ዋና ወና ክፍለ ሀገራት የ ካትት ነበር እነሱም በጌምድር ጐጃም ወሎና ሸዋ ነበሩ ።የአማራ ብሔራዊ ክልል ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ በ8° 45 እስከ 13° 45 ሰሜን የኬንትሮስ እና በ35° 46 እስከ 40° 25 ምስራቅ የኬንትሮስ መስመር ውስጥ ይገኛል። በምስራቅ የአፋርና የኦሮሚያ ክልሎች፣ በምዕራብ ሱዳን እና ቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል፣ በሰሜን የትግራይ ክልልና በደቡብ የኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል። የቆዳ ስፋቱ ፻፶፯ሺ፸፮ ካሬ ሜትር ሲሆን ከአገሪቱ አሥራ አምስት በመቶ ድርሻ ይይዛል። የክልሉ ሕዝብ ብዛት ደግሞ በ፳፻፪ ዓ/ም 20,875,456 እንደነበር የተገመተ ሲሆን ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ 33.9% አካባቢ ድርሻ ይይዛል ተብሎ ይገመታል። ክልሉ በ፲ ዞኖችና በ፻፷፮ የገጠርና የከተማ ወረዳ አስተዳደሮች የተከፋፈለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ፴፰ የሚሆኑት የከተማ አስተዳደሮች ናቸው። የአማራ፣ የአገው፣ የኦሮሞና የሌሎች ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት ክልል ነው። እንዲሁም የአማራ ክልል አሁን ላይ የክልል ከተማው ባህር ዳር ነው። በክልሉ አልፎ አልፎ ከሚታዩ የመንግሥትና የማኅበራት ደኖች፣ በደሴቶች፣ በአብያተ ክርስቲያናት፣ በወንዞች ዳርቻና ሰው ሊደርስባቸው በማይችሉ ገደላማና ተራራማ ስፍራዎች ከሚገኙ ጥቂት ደኖች በስተቀር ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የደን ሀብት ጋር በቅርብ የተያያዘ ነው። በዚህ ረገድ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ እንደ ቀይ ቀበሮ፣ ዋልያ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እንዲሁም በምዕራባዊው የክልሉ አካባቢ ዝሆን አንበሳና ነብር፣ ሰጐንና የተለያዩ አዕዋፋት በስተቀር ከፍተኛ የዱር እንስሳት ክምችት ካለመኖሩም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጥቂት የደን ቅሪቶችና ዋሻዎች የነበሩት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አራዊቶችም ለዘመናት በደረሰው የደን መጨፍጨፍና መራቆት ምክንያት ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ እንደተሰደዱ ይታወቃል። ክልሉን የማዕድን ሀብት አስመልክቶ በሚገባ የተጠናከረ ጥናት ባይኖርም ከክልሉ ስነ-ምድራዊ ሁኔታዎችና ከተካሄዱ አንዳንድ ጠቋሚ ጥናቶች መረዳት እንደሚቻለው በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ማዕድናት እንደአሉ ይገመታል። በዚህም መሠረት በሰሜን ሸዋ የኦፓል ማዕድን፣ በሰሜን ጐንደር፣ በጭልጋና በደቡብ ወሎ በአምባሰል ወረዳ የድንጋይ ከሰል ክምችት እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ለግንባታ ሥራ የሚውል በቂ የድንጋይ፣ የኖራ ድንጋይ፣የሸክላ አፈር፣ ጅኘሲየም፣ የጌጣጌጥ ማዕድናት እንዲሁም በዓባይ ሸለቆ የዕብነ በረድ ሐብቶች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይሁን እንጅ በውል የሚታወቀው ሐብትም ቢሆን በበቂ ሁኔታ አልለማም።
የአማራ ክልል የቆዳ ስፋት ምን ያህል ነው?
፻፶፯ሺ፸፮ ካሬ ሜትር
327
ታኅሣሥ ፳፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፲፫ተኛው እና የመፀው ወቅት ፹፰ተኛው ቀን ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየወሩ ፳፫ኛ ቀን የሰማዕታትን ዓለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስንን ታስታውሳለች። ፲፯፻፷፰ ዓ/ም - የእንግሊዝ ሠራዊት የክዌቤክ ከተማን ከአሜሪካ አስመለሰ። ፲፯፻፺፮ ዓ/ም - በሀይቲ ደሴት የፈረንሳይ ሉዐላዊነት ሲያከትም ደሴቷ በሰሜን አሜሪካ አኅጉር ከአሜሪካ ኅብረት ተከትላ ሁለተኛዋ ነፃ ሪፑብሊክ ሆነች። ፲፰፻ ዓ/ም - በባርነት የተገዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ ኅብረት እንዳይገቡ የሚከለክል ሕግ ተደነገገ። ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ተመሰረተ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ፩ሚሊዮን ፱መቶ ሺ ኪሎ የመዳብ ሽያጭ ወደጃፓን ላከች። መዳቡ በኤርትራ ውስጥ ከሚገኘው የድባሮ መዳብ ማዕድን ቁፋሮ የተገኘ ነው። ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ባንኮችንና የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን የብሔራዊ ንብረት አድርጎ ወረሰ። ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - ጋናዊው ዲፕሎማት ኮፊ አናን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፯ተኛው ዋና ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ።
ጋናዊው ዲፕሎማት ኮፊ አናን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስንተኛው ዋና ጸሐፊ ሆነው ናቸው?
፯ተኛው
622
ኮንታ የኮንታ ብሔረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ኮንቲኛ ሲሆን፣ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ከንግግር ቋንቋነት ባሻገር የትምህርትና የሥራ ቋንቋ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ ዳውሮኛ፣ ጋሞኛ፣ ወላይትኛና አማርኛ ይናገራሉ። የኮንታ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር መዋቅር ተዋረዳዊ ኃላፊነትና ተግባር ባላቸው የተለያዩ ክፍሎች የተደራጀ ነው፡፡ በእዚህ መዋቅር የሁሉም የበላይ ካዎ ወይም ንጉስ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከማላ ጎሳ ይመረጣል፡፡ በኮንታ ብሔረሰብ ስድስት ባህላዊ የጋብቻ ዓይነቶች ያሉ ሲሆን፣ እነዚህም በቤተሰብ ስምምነት የሚፈጸም ጋብቻ (ቦሣ) የለፋ ጋብቻ (ላታ) በተጋቢዎች ስምምነት የሚፈጸም ጋብቻ (ማቆ) የቃል ጋብቻ (ያኤኤኩዎ) እና ሚሽቶ (የምትክ ጋብቻ) በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህ የጋብቻ ዓይነቶች በብዛት ሲከናወን የሚስተዋለው በቤተሰብ ስምምነት የሚፈጸመው የቦሣ ጋብቻ ነው፡፡ ከብሔረሰቡ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ፂፄ፣ ጫቻ፣ ዛይ፣ዲንኬ እና ኡልዱዶ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ የትንፋሽና የምት የሙዚቃ መሣሪያዎች ለለቅሶና ለደስታ ጊዜ ያገለግላሉ፡፡ በተለይ ኡላዱዶ የተሰኘው የትንፋሽ መሣሪያ ከድኩላ ቀንድ ተበስቶ የሚሠራ ሲሆን ከብቶቻቸው ሆራ (ጨውነት ያለው ውሃ) ሊያጠጡ የሚወስዱ እረኞች ይነፉታል፡፡ የኮንታ ባህላዊ የቤት አሠራር ከፍልጥ እንጨት፣ ከቀርከሀ ከሰንበሌጥና ከሣር የሚዘጋጅ ሲሆን በደጋውና በቆላው አካባቢ ልዩነት አለው፡፡ ሱልሶ፣ ሲሊሶ፣ ኡስታ፣ ጨዲያ፣ ኩበዋ፣ ቦሩዋ (ዱቢያ) እና ባጨራ የኮንታ ብሔረሰብ ዋነኛ ባህላዊ ምግቦች ናቸው፡፡ ሲልሶ ለአብነት ከምን እንደሚሠራ እንይ፡፡ ሲልሶ ከጥሬ ሥጋ፣ ከቅቤ፣ ከደም፣ ከሀሞት እና ከተለያዩ የማጣፈጫ ቅመሞች ከተዘጋጀ በኋላ ከተለበለበና በክብ በተቆረጠ የእንሰት ቅጠል ላይ ለቤተሰቡ አባላት ይቀርብና በቡላ ወይም በቆጮ ይበላል፡፡ በብሔረሰቡ ወንዶች ከአቡጀዲ በእጅ የተሰፋ እጀ ጠባብ ሸሚዝና ሱሪ እንዲሁም ሀሲያ የተባለ በእጅ የተፈተለ ልብስ ሲለብሱ ሴቶች በኋላ በኩል ባለወጥ ጥለት የሆነውን ማዳ የተባለ የእጅ ፈትል ይለብሳሉ፡፡
የኮንታ ብሔረሰብ የሙዚቃ መሣሪያዎች ለምን አገልግሎት ይውላሉ?
ለለቅሶና ለደስታ
624
መጋቢት ፪ ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን ያዘ። ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት (በኋላ ፕሬዚዳንት) ሪቻርድ ኒክሰን ኢትዮጵያን ጎበኙ ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ሊትዌኒያ እራሷን ከሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ውጭ ነጻ መሆኗን አወጀች። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ በልብ ምታት አረፈ።
፲፰፻፷፰ ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ ሰው ማን ይባላል?
አሌክሳንደር ግራሃም ቤል
19
ነሐሴ ፳፯ ነሐሴ ፳፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፰ ዕለታት ይቀራሉ። ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ። ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አረፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ነጻነትን አስከትሎ በጃዋሃርላል ኔህሩ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ የሕንድ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት።
መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ የት ቤተክርስቲያን ተቀበረ?
ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
500
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ተፈሪ መኰንን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺ እመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ፲፰፻፺፱ የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. የሐረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ። የሐረርጌ አገረ ገዥ ሲሆኑ ፣ በጣም ብዙ ሺህ ተከታዮች ነበሩዋቸውና ልጅ እያሱን ከእንደራሴነት በኅይል እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ተፈሪን ከሐረር አገረ ገዥነት እንዳይሽሯቸው የሚል ስምምነት ተዋዋሉ። ዳሩ ግን እያሱ ሃይማኖታቸውን ከክርስትና ወደ እስልምና እንደቀየሩ የሚል ማስረጃ ቀረበና ብዙ መኳንንትና ቀሳውስት ስለዚህ ኢያሱን አልወደዱዋቸውም ነበር። ከዚህም በላይ እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት ስምምነታቸው እንግዲህ ተሠርዞ ተፈሪ ደግሞ ለወገናቸው ከስምምነቱ ተለቅቀው በዚያን ጊዜ እሳቸው እያሱን ከእንደራሴነት አስወጡ። እንግዲህ በ፲፱፻፱ ዓ.ም. መኳንንቱ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ሆነው አድርገዋቸው ተፈሪ ደግሞ እንደራሴ ሆኑ። ከዚህ ወቅት ጀምሮ ተፈሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙሉ ሥልጣን ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. የንጉሥነት ማዕረግ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ አርፈው ንጉሠ ነገሥት ሆኑና ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ብዙ የውጭ ልዑካን በተገኙበት ታላቅ ሥነ-ሥርዓት ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው እሳቸውና ሚስታቸው እቴጌ መነን ዘውድ ጫኑ። በንግሥ በዓሉ ዋዜማ ጥቅምት ፳፪ ቀን የትልቁ ንጉሠ-ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለዘውድ በዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት ፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ። ለንግሥ ስርዐቱ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገር ልኡካን ከየአገራቸው ጋዜጠኞች ጋር ከጥቅምት ፰ ቀን ጀምሮ በየተራ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ስለነበር ሥርዓቱ በዓለም ዜና ማሰራጫ በየአገሩ ታይቶ ነበር። በተለይም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት በጃማይካ አንዳንድ ድሀ ጥቁር ሕዝቦች ስለ ማዕረጋቸው ተረድተው የተመለሰ መሢህ ነው ብለው ይሰብኩ ጀመር። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ፊተኛው ስማቸው «ራስ ተፈሪ» ትዝታ ራሳቸውን «ራስታፋራይ» (ራሰተፈሪያውያን) ብለዋል።
በልጅ ኢያሱና በራስ ተፈሪ መካከል ተደርጎ የነበረው ስምምነት የተሻረው በምን ምክንያት ነው?
እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት
500
ቴሌቪዥን ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው። በ1873 እ.ኤ.አ. (1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ። በ1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም። ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ... ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በ 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ። በ1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።
ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል የሚያስችል መሳሪያ የፈጠረው ምን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ነው?
የሲርቲን ቴክኖሎጂ
755
ቀጭኔ ቀጭኔ በአፍሪካ የሚኖር ባለሙሉ ጣት ሸሆኔ ጡት አጥቢ አራዊት ሲሆን በምድር ከሚገኙ እንሰሳት በርዝማኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። ወንዱ ከ 4.4 እስከ 5.5 ሜትር ርዝማኔና 1,360 ኪሎግራም ክብደት ያስመዘግባል። እስካሁን በሪኮርድ የተያዘው የ 5.87ሜና የ2000ኪ.ግ ቀጭኔ ነው። ሴቶቹ በጥቁቱ አነስ ብለው ይታያሉ። እነዚህን ፍጥረታት በአራዊት ማቆያ ቦታዎች አንገታቸውን ከታጠሩበት አጥር በላይ ወጣ አድርገው የተመለከተ ሰው በአፍሪካ ቁጥቋጦዎች ነፃ ሆነው ሲሮጡ ያላቸውን ውበትና ግርማ መገመት ያስቸግራል። የቀጭኔ እንቅስቃሴ ትልቅ ግርማ ያለውና እንደ ውኃ ሙላት የሚፈስ ነው። በገላጣው የግጦሽ መስክ ላይ በሚጋልቡበት ጊዜ ቁመናቸው ትንሽ እንቅፋት ቢነካቸው ወድቀው የሚሰባበሩ ያስመስላቸዋል። ይሁን እንጂ እስከ 1, 300 ኪሎ ግራም የሚደርስ ክብደት ያላቸው ወንድ ቀጭኔዎች ቀልጣፋና ምንም የማያደናቅፋቸው ሯጭ ከመሆናቸውም በላይ በሰዓት እስከ 60 ኪሎ ሜትር ሊሮጡ ይችላሉ። ይህች አስደናቂ ፍጡር የምትገኘው በአፍሪካ ብቻ ነው። እርጋታዋና ሰላማዊ ተፈጥሮዋ ዓይን ይስባል። የቀጭኔ ፊት በዓይነቱ ልዩ የሆነና ቆንጆ ሊባል የሚችል ሲሆን ረዥምና ጠባብ ጆሮዎች፣ ሁለት ትናንሽ ቀንዶች እንዲሁም ጠቆር ያለ ለስላሳ ጠጉር አላት። ዓይኖቿ በጣም ትላልቅና ጥቁር ሲሆኑ ረዣዥም በሆኑ ቅንድቦች ይጠበቃሉ። ቀጭኔ ያን በመሰለ ከፍታ ላይ ሆና ሩቅ ስትመለከት ፊቷ ላይ የየዋህነት ገጽታ ይታይባታል። በጥንት ዘመናት ቀጭኔ ባላት አስደሳች ቁመና እንዲሁም ጨዋ፣ ዓይነ አፋርና ሰላማዊ ባሕርይ ያላት በመሆኑ በጣም ተወዳጅና ትልቅ ግምት የሚሰጣት ነበረች። በብሔራት መካከል ሰላምና በጎ ፈቃድ መኖሩን ለማመልከት የቀጭኔ ግልገሎች ለነገሥታትና ለገዥዎች በገጸ በረከትነት ይሰጡ ነበር። ጥንታዊ በሆኑት የአፍሪካ አለቶች ላይ ቀለማቸው የደበዘዘ የቀጭኔ ሥዕሎች እስከ ዛሬ ይታያል። ከእንስሳት ሁሉ ቀጭኔን በቁመት የሚወዳደር የለም። ሙሉ ዕድሜ ላይ የደረሱ ወንድ ቀጭኔዎች ከእግራቸው ኮቴ አንስቶ እስከ ቀንዳቸው ድረስ ከ5.5 ሜትር የሚበልጥ ርዝመት አላቸው። በግብፃውያን ጥንታዊ ሥዕላዊ የአጻጻፍ ዘዴ ቀጭኔ በረዥም ቁመቷና አርቆ በመመልከት ችሎታዋ ምክንያት “መተንበይ” የሚለውን ግሥ ትወክል ነበር። ቀጭኔ በአፍሪካ መስኮች በሚሰማሩት የሜዳ አህዮች፣ ሰጎኖች፣ አጋዘኖችና ሌሎች እንስሳት መካከል ስትቆም እንደ ማማ ሆና ትታያለች። ቁመቷና አርቆ የማየት ችሎታዋ ማንኛውንም አደጋ ገና ከሩቅ ለማወቅ ያስችላታል። ስለዚህ የቀጭኔ መኖር ለሌሎች እንስሳት የመረጋጋት ስሜት እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም።
በብሔራት መካከል ሰላምና በጎ ፈቃድ መኖሩን ለማመልከት ለነገሥታትና ለገዥዎች ምን ዓይነት ገጸ በረከትነት ይሰጥ ነበር?
የቀጭኔ ግልገሎች
957
መዓዛ ብሩ በእሁድ የሬዲዮ ፕሮግራም ታቀርባቸው የነበሩት ሥራዎች ይዘት ማህበራዊ ሕይወት እንዲሠምር በመጣር ላይ ያተኮሩ ሆነው ግልጽ፣ ቀላልና ለዛ ያልተለያቸው ስለነበሩ ከሶስት አሥርት ዓመታት በኋላም ትውስታቸው ከአድማጭ ህሊና አልጠፉም፡፡ በዚሁ ፕሮግራም ላይ መዓዛ ካበረከተቻቸው የፈጠራ ሥራዎቿ ውስጥ ጎልቶ የሚታወሰው “የአዲሱ ቤተሰብ” የተሰኘ ባለ ሰማንያ ስድስት ክፍል ድራማ ሲሆን በዘመኑ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉም የሚያደምጠው ተወዳጅ የቤተሰብ ድራማ ነበር፡፡ መዓዛ በ “መርሀ ስፖርት” እና በሬዲዮ መካከል ሆና ከአራት ዓመት በላይ ከቆየች በኋላ በ1979 ዓ.ም የባህል ሚኒስቴርን ለቃ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጠረች፡፡ አዲሱን መስሪያ ቤቷን ከተቀላቀለችበት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከሬዲዮ እየራቀች መጣች፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የቆየችው ለሶስት ዓመታት ያህል ሲሆን ከዚያ በኋላ የግሏን የማስታወቂያ ሥራ ድርጅት መሥርታ የራስዋ ተቀጣሪ ሆናለች፡፡ ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1992 ዓ.ም ባሉት የአስራ ሶስት ዓመታት ጊዜ ግን መዓዛና ሬዲዮ ተራራቁ፡፡ መዓዛና ሬዲዮ ዳግም የተዋደዱት ከላይ እንደተገለጸው በ1992 ዓ.ም ሳምንታዊውን የ “ጨዋታ” ፕሮግራም በኤፍ ኤም 97.1 ከተፈሪ ዓለሙ ጋር በጋራ ማቅረብ ሲጀምሩ ነበር፡፡ የ “ጨዋታ” ፕሮግራም እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ በአድማጮቹ እንደተወደደ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ መንግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ፈቃዶችን ለግሉ ዘርፍ ለመስጠት ሲዘጋጅ፣ ዝርዝር የሥራ እቅድ አቅርባ ባመለከተችው መሠረት፤ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ከአስር አመልካቾች መካከል አንዷ ሆና የመጀመሪያ የግል የኤፍ ኤም ሬዲዮ ባለቤት ያደረጋትን ፈቃድ ተቀበለች፡፡ መዓዛ የሬዲዮ ማሰራጫ መሳሪያዎችን ውድነት፣ የማሰራጫ ቦታ እና የባለሙያ እጦትን ተቋቁማ ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮን በታህሳስ 1999 ዓ.ም አበረከተችልን፡፡ ባለትዳርና የሶስት ልጆች እናት የሆነችው መዓዛ እንደ ባለቤት፣ ሥራ አስኪያጅና ጋዜጠኛ በመሆን በኢትዮጵያ ተወዳጁንና የመጀመሪያውን የግል የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ትመራለች፡ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!”እያለች::
መኣዛ ብሩ በኢትዮጵያ ሬድዮ ካበረከተቻቸው አንጋፋ ስራዎች አንዱ የትኛው ነው?
“የአዲሱ ቤተሰብ” የተሰኘ ባለ ሰማንያ ስድስት ክፍል ድራማ
204
አክሱም አክሱም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክ/ሃገር ከአድዋ ተራራዎች አጠገብ የምትገኝ ከተማ ነች። በክርስቶስ ልደት በፊት ተመስርቶ የነበረው የአክሱም ስርወ መንግስት ማእከል ነበረች የአክሱም ስርወ መንግስት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እየተዳከመ ሲመጣ የማእከላዊው መንግስት ወደ ደቡብ ተንቀሳቀሰ። ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የከተማው ነዋሪ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ነው። የተቀሩት ነዋሪዎች የሱኒ እስልምና ተከታዮች ናቸው። ባላቸው ታሪካዊ ተፈላጊነት ከተማ ውስጥ የሚገኙት የአክሱም ስርወ መንግስት ቅሪቶች UNESCO በ1980 የአለም ቅርስ ቦታ ተብለው ተሰይመዋል ። አክሱም በኢትዮጵያ የ ትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በማዕከላዊ ዞንና በላዕላይ ማይጨው ወረዳ ይገኛል።
አክሱም በኢትዮጵያ በየት አቅጣጫ ትገኛለች?
በሰሜን
10
ባለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል። በዚህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ተደርሶ የነበረው ስምምነት ወደ ትግበራ ገብቷል። ባለፉት ስደስት ወራት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች መረጣ እና ተመሳሳይነት ልየታም ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህ መሰረት 25 የህንድ የቴክኖሎጂ ባላሙያዎችና ድርጅቶች ከ57 የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መመስረታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በቅንጅት በመስራት ታምናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር፥ የሁለቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጥምርታ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የቴክኖሎጂው ዘርፍ የእውቀት ሽግግር እንዲያመጣ፣ ሃብት እና የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ ኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራንግ ስትራቫስታቫ በበኩላቸው፥ኢትዮጵያ እና ህንድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመሩት ስራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን ተናግረዋ። በኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ፕሮግራም በሚቀጥሉት አምስት አመታት 50 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ለመፍጠር እቅድ መያዙ ተመላክቷል። ባለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል። በዚህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ተደርሶ የነበረው ስምምነት ወደ ትግበራ ገብቷል። ባለፉት ስደስት ወራት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች መረጣ እና ተመሳሳይነት ልየታም ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህ መሰረት 25 የህንድ የቴክኖሎጂ ባላሙያዎችና ድርጅቶች ከ57 የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መመስረታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በቅንጅት በመስራት ታምናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር፥ የሁለቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጥምርታ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የቴክኖሎጂው ዘርፍ የእውቀት ሽግግር እንዲያመጣ፣ ሃብት እና የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ ኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራንግ ስትራቫስታቫ በበኩላቸው፥ኢትዮጵያ እና ህንድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመሩት ስራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን ተናግረዋ። በኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ፕሮግራም በሚቀጥሉት አምስት አመታት 50 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ለመፍጠር እቅድ መያዙ ተመላክቷል።
በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ማናቸው?
አኑራንግ ስትራቫስታቫ
633
ዶናልድ ጆን ትራምፕ ዶናልድ ጆን ትራምፕ (ጁን 14 ቀን 1946 እ.ኤ.አ. ተወለደ) አሜሪካዊ ነጋዴ ፣ ፖለቲከኛ ፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቹ ታዋቂ እና 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፕሬዚደንት ነው። ሥልጣኑንም እ.ኤ.አ. በጃኑዌሪ 20 ቀን 2017 ተረክቧል። በክዊንስ ኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው አቶ ትራምፕ በሪል እስቴት ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የፍሬድ ትራምፕ ልጅ ነው። በኮሌጅ እያለም ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ በተባለው ድርጅት ይሠራ ነበር። በእ.ኤ.አ. 1968 ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ ያንን ድርጅት ተቀላቀለ። በእ.ኤ.አ. 1971 ደግሞ ሙሉ ሥልጣን ከተሠጠው በኋላ የድርጅቱን ስም ወደ "ዘ ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን" ለወጠው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ካሲኖዎችን ፣ የጎልፍ ሜዳዎችን ፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች በእርሱ ስም የሚጠሩ ንብረቶችን አፍርቷል። እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2015 ድረስ ዘ አፕሬንቲስ የተባለ ፕሮግራምን በኤን ቢ ሲ ላይ ያቀርብ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የሪፎርም ፓርቲ እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ ቴድ ክሩዝ እና ጆን ካሲች ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታወጀ። በእ.ኤ.አ. ኖቬምበር 8 ቀን 2016 ላይ የፕሬዚደንትነት ምርጫውን አሸነፈ። ማሸነፉንም ተከትሎ ብዙ የተቃውሞ ሠልፎች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በ70 ዓመቱም ሥልጣን ላይ በመውጣቱ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ፕሬዚደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ያደርገዋል።
ትራምፕ የፕሬዝደንትነት ስልጣን ላይ መቼ ወጣ?
እ.ኤ.አ. በጃኑዌሪ 20 ቀን 2017
138
አንጎላ አንጎላ፣ በይፋ የአንጎላ ሪፑብሊክ በደቡብ-ምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከናሚቢያ ፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ እና ከዛምቢያ ጋር ድንበር ትጋራላች። በምዕራብ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ትገናኛለች። የፖርቹጋል ቅኝ-ተገዥ ነበረች። ነዳጅ እና አልማዝ ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የሚመደቡ ናቸው። የአንጎላ የሕግ-አስፈጻሚ ፕሬዝዳንቱን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የሚኒስትሮች ካውንስሉን ያጠቃልላል። ሁሉም ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የሚኒስተሮች ካውንስሉን ሲሰሩ በየጊዜው እየተሰበሰቡ ስለተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣሉ። የአስራ ስምንቱ ክልሎች መሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚመረጡት። በ1992 እ.ኤ.ኣ. የወጣ ሕገ-መንግስት የመንግስቱን አወቃቀር እና የዜጎችን መብትና ግዴታ ይዘረዝራል። ፕሬዝዳንቱ መንግሥቱ በ2006 እ.ኤ.ኣ. ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ እነዳለው ገልጸዋል። ይህ ምርጫ ከ1992 አ.ኤ.ኣ. በኋላ የመጀመሪያው ምርጫ ነው የሚሆነው። አንጎላ ውስጥ ሶስት ዋና ብሔረሰቦች ይገኛሉ። ኦቪምቡንዱ 37% ፣ ኪምቡንዱ 25% ፣ እና ባኮንጎ 13%። ሌሎች ብሔረሰቦች ቾክዌ (ሉንዳ)፣ ጋንጉዌላ፣ ንሀኔካ-ሁምቤ፣ አምቦ፣ ሄሬሮ፣ እና ዢንዱንጋን ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም ክልሶች (አውሮፓና አፍሪካዊ) 2% ይሆናሉ። ፖርቱጋሎች አንጎላዊ ካልሆኑ ሰዎች ብዙዎቹ ናቸው። ታሪክ በአንጎላ መጀመሪያ የሠፈሩት የኮይሳን ሰዎች ነበሩ። በባንቱ ፍልሰቶች ጊዜ እነዚህ ሰዎች ወደ ደቡብ አንጎላ ሄዱ። በ1483 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋሎች በኮንጎ ወንዝ አጠገብ ሠፈሩ። በ1575 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋል ካቢንዳ ጋር በባሪያ ንግድ ላይ ያቶከረ ግዛት መሠረተች። በ16ኛው ክፍለ ዘመን፣ ፖርቱጋል የአንጎላ የባህር ጠረፍን ተቆጣጠረች። በተለያዩ ውሎችና ጦርነቶች የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት አንጎላ ተስፋፋ። የፖርቱጋል መመለሻ ጦርነትን ምክኒያት በማድረግ የደች ሪፐብሊክ ሏንዳን ከ1641 እስከ 1648 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ተቆጣጠረች።
አንጎላ በአፍሪካ በየትኛው አቅጣጫ ትገኛለች?
በደቡብ-ምዕራብ
27
ጾመ ነቢያት በአራቱም ዘመናት ምን ጊዜም ኅዳር ዐሥራ አምስት እንዲጾም ተወስኗል፡፡ ጾመ ገሀድ የምትክ ጾም ነው፡፡ ይህ ጾም ዓርብንና ሮብን የሚያሽር በዓል በዓርብና በሮብ ሲውል በምትኩ በዋዜማው የሚጾም ጾም ነው፡፡ ለምሳሌ ጥምቀት ዓርብ ቢውል ሐሙስ ጾመ ገሀድ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አበው ለጾም ማድላት አለብን በማለት ጾመ ገሀድ ምንጊዜም ጥምቀት በጾም ቀን ዋለም አልዋለም በዋዜማው እንዲጾም ወስነዋል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያት የእመቤታችንን ትንሣኤ ለማየት ይበቁ ዘንድ ሱባኤ ገብተው የጾሙት ጾም ሲሆን ምንጊዜም ነሐሴ አንድ ቀን ገብቶ ከሁለት ሱባኤ በኋላ የእመቤታችን ዕርገት ይፈጸማል፡፡
በአራቱም ዘመናት ኅዳር አስራ አምስት የሚጀምረው ጾም ምን ይባላል?
ጾመ ነቢያት
0
በ628 ዓክልበ.፣ ድራኮ የሚባል ጸሃፊ የአቴና ከተማ ሕግጋት ጻፈ፤ ይህም ሕግ እጅግ ጨካኝ ሆኖ ይሙት በቃ ለማንኛውም ጥፋት ወሰነ። በ600 ዓክልበ.፣ የአቴና አለቃ ሶሎን አዲስ ሕገ መንግሥት ፈጠረ። የሰራተኞች ሸክም አቀለለ፣ ነገር ግን ባላባትነት በልደት ሳይሆን በንብረት ብዛት እንዲቈጠር አስደረገ። ክሊስቴኔስ እንደገና በ516 ዓክልበ. በዴሞክራሲያዊ መሠረት የተሻሸለ ለአቴና ሕገ መንግሥት አወጣ። የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ በ350 ዓክልበ. ግድም የሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ዐወቀ። በጽሑፎቹ የአቴና፣ የስፓርታና የካርታግና ሕገ መንግሥቶች ያነጻጽራል። በመደምደሚያው የተሻለው ሕገ መንግሥት ከንጉሣዊ፣ ከመኳንንታዊና ከሕዝባዊ ወገኖች የተደባለቀ መሆኑን ገመተ። በሀሣቡ በመንግሥት የሚከፋፈሉ ዜጎች ከማይከፋፈሉ ከባርዮችና ዜጎች ካልሆኑ ሰዎች ልዩነት አደረገ። ሮማውያን መጀመርያ «12ቱ ሰንተረዦች» የተባለውን ሕገ መንግሥት ያወጡ በ457 ዓክልበ. ነበር። ከዚያ በኋላ አንዳንዴ የተለያዩ ሕጎችና ትእዛዛት ይጨምሩበት ነበር እንጂ እስከ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስ ድረስ (430 ዓ.ም.) ሌላ ክምቹ ሕገ መንግሥት አልኖረም ነበር። በኋላም በምሥራቁ መንግሥት (ቢዛንታይን) በኩል መጽሐፈ ዩስጢኒያኖስ (526 ዓ.ም.) ለአውሮፓ ከፍ ያለ ተጽእኖ ነበረው። ይህም በምስራቁ ነገሥታት 3ኛ ሌዎን ኢሳውራዊ «ኤክሎጋ» (732 ዓ.ም.) እና በ1ኛ ባሲሌዎስ «ባሲሊካ» (870 ዓ.ም.) በተባሉት ሕገ ፍትሐን ተከተለ።
የግሪኩ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ መች ነበር ስለሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ያወቀው?
በ350 ዓክልበ.
276
አዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መስራች ማናቸው?
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
738
መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር በቢትወደድ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ተጽፎ በ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. የታተመ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ ከመስራት የተነሳ የሰው ልጅ እንዴት ከተፈጥሮ ጥገኝነት ተላቅቆ ከኋላ ቀር አኗኗር ወደ ተሻለ ሕይወት እንደሚለወጥ የሚያስረዳ ሲሆን የዓለም ሕዝቦች የዕውቀታቸውና የሀብታቸው ደረጃ ከፍና ዝቅ ያለ መሆኑ ምክንያቱ ከጦርነት የተነሳ ነው ይላል። ጦርነቱንም የሚነሱ ነገሥታትና አለቆቹ ሁሉ ልባቸው ሀብት እንደፈለጉ አይገልፅም። ነገር ግን ስም ለመፈለግና ለማግኘት ወይም ሀይማኖቱን ለማስፋፋት ወይም የተጠቃውን ለመርዳት አስመስለው ይነሳሉ። የጦርነት ሁሉ ፍፃሜ ምኞት ግን መዝረፍና ማስገበር ነው። ይህንንም ሲሉ ዕውቀታቸው የሰፋ ነገሥታትም ቢሆኑ መዝረፍን አይተዉም። አዘራረፋቸው ግን የዕውቀት አዘራረፍ ነው እያለ በሰፊው ያወሳል። በአክሱም ዘመነ መንግሥት የእስራኤልና የአህዛብ ወገን ተብሎ የሁለት ዓመት ጦርነት በመፍጀቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍ ወዳለው ደረጃ እንዳይደርስ ዋና መሰናክል ሆኗል። ዋጋ ማለት የስራ መለኪያ ነው። ዕውቀት ከጉልበት ይከበራል። ዕውቀት የሌለው ሕዝብ ሁሉ ለብቻው መንግሥት ቢኖረውም ባይኖረውም ዕውቀት ያላቸው ሕዝቦች ይገዙታል። ሰው ሲፈጠር ጌታና ድሀ ሆኖ አልተፈጠረም። ድህነትና ጌትነት የተለየው በሰው ዕውቀት ነው። የሀብት መለኪያ ሥራ ነው። ስለዚህ ሀብት ማለት የተከማቸ ሥራ ማለት ነው።
መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር የተሰኘው መጽሐፍ በማን ተጻፈ?
በቢትወደድ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ
38
ሶቪዬት ሕብረት ሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ ሪፐብሊክ በ፲፱፻፲ ዓ.ም. የተከሰተውን የሩሲያ አብዮት ፍንዳታ፤ እንዲሁም ያንን ተከትሎ ለሦስት ዓመታት የተከናወነውን የሩሲያ «ውስጣዊ ሕዝባዊ የርስ በርስ ግጭት» ተከትሎ በኅብረተስብአዊ ሕገ መንግሥት (socialist constitution) በአራት ሪፑብሊኮች ቅንብርነት የተመሠረተ አገር ነበር። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ከቀድሞው የናዚ ጀርመን እጅ የተወሰዱ አገሮችን በማቀላቀል እንዲሁም በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም በጉልበት ሌሎች የምሥራቅ አውሮፓ አገሮችን በመቀላቀል ኅብረቱ ዓሥራ ስድስት ሪፑብሊኮችን ያካተተ ነበር። በዘመን ቆይታና በጥንካሬም የጎለበተ ሕዝባዊ አብዮታዊ የኅብረት ሪፑብሊክ በመሆኑም በተለይ በ«ቀዝቃዛ ጦርነት» በሚባለው በ«ምዕራብና በምሥራቅ» ዓለም ተከስቶ በነበረው ፍጥጫ ጊዜ፣ በዓለም ላይ ለሚመሠረቱ ሕዝባዊ መንግሥታት ዋና የሽከታ አርአያ የነበረ መንግሥት ነበር። በ ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጀምሮ ይሄ ኅብረት እስከፈረሰበት እስከ ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የ«ቀዝቃዛ ጦርነት» ዘመን የሶቪየት ኅብረት በዓለም ከነበሩት ሁለቱ ተቃራኒ ኃያላን መንግሥታት አንዱ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ላይ በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም የተመሠረተውን የአብዮት ወታደራዊ የደርግ መንግሥት በጦር መሣሪያ፤ በአማካሪነት፤ በገንዘብ፤ ወዘተረፈ፤ ዋነኛ ደጋፊና ታላቅ ተዋናይ አገር ነበር። የቀድሞው የሶቪዬት ኅብረት መጨረሻ ላይ ታኅሣሥ ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ተደምስሶ በዓለም መንግሥታት እውቀትና ስምምነት ሕጋዊ ወራሽነት የሩሲያ መንግሥት እንደሆነ ታወጀ። ሩሲያም በዚህ መሠረት የቀድሞውን የሶቪዬት ሕብረት የውጭ ዕዳዎች እንዲሁም የውጭ ንብረቶች በፈቃዱ ተቀበለ። በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ተፈርመው የነበሩም ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንም ሩሲያ መቀበሏን አስታውቃለች።
የሶቭየት ሕብረት መቼ ፈረሰ?
ታኅሣሥ ፲፮ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም
811
ኋንግ ዲ ኋንግ ዲ (ቢጫው ንጉሥ) በቻይና ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ የቻይና ሕዝብ አባትና ንጉሥ ነበረ። የቤተሠቡ ስም «ጎንግሱን» የተሰጠው ስም «ሽወንዩወን» ነበር ይባላል። አባቱ ሻውድየን ተባለ። የተወለደው ሾው ጪው በተባለ ሥፍራ በጩፉ ሲሆን በኋላ ነገዱን ወደ ዥዎሉ ወሰደው፤ በዚያ ገበሬ ሆኖ ድብ፣ ነብርና ባለክንፍ አንበሣ የመሰለ ፍጡር አንዳስለመደ የሚል ትውፊት አለ። ያንጊዜ የኋንግ ዲ ወገን እና የያንዲ (ዩዋንግ) ወገን ለቢጫው ወንዝ ሸለቆ ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ሦስተኛ ወገን - የሊ ሕዝብና ንጉሣቸው ቺ ዮው - ደግሞ ጠላቶቻቸው ሆኑ። ሦስት ውግያዎች ተከተሉ። በመጀመርያው የቺ ዮው ሥራዊት ያንዲውን አሸነፈው። ከዚያ ያንዲው ተሸንፎ ወደ ኋንግ ዲ ሸሸ። በሁለተኛው የዥዎሉ ውግያ ኋንግ ዲ እና ቺ ዮው ተጋጠሙ። በዚህ ውግያ ቺ ዮው ጉምን በጥንቆላ ፈጥሮ ኋንግ ዲ እንደገና በተነው፣ ብዙም ሌሎች ጉድ ሥራዎች እንደ ተከሠቱ የሚል ትውፊት አለ። ቺ ዮው በዚህ ውግያ ቢሸነፍም፣ የኮርያ ሕዝብና የህሞንግ ሕዝብ ዛሬውንም እንደ ቅድማያታቸው ይቆጥሩታል። በሦስተኛው የባንጯን ውግያ፣ ኋንግ ዲ በያንዲው ላይ ድል አደረገ። ከዚያ በኋላ ወገኖቻቸው ተባብረው የኋሥያ ብሔር (የቻይና ሕዝብ ቅድማያቶች) ፈጠሩ። ኋንግ ዲ በይፋ የቻይና ንጉሥነት ማዕረግ ወሰደ፤ የዘውድና ቤተ መንግሥት ሥርዓት ጀመረ። ከዚህ በተረፈ ኋንግ ዲ ጋሪና መርከብ እንደ ፈጠረ ይጻፋል። ደግሞ ምኒስትሩ ጻንግችየ መጀመርያ የቻይና ጽሕፈት ፈጠረ፤ የኋንግ ዲ ሚስት ሌዙም ልብስ ከሃር ትል እንዴት እንደሚሠራ አሳየች። የህክምና መጽሓፍ ኋንግዲ ኔጂንግ ሌሎችንም መጻሕፍት እንደ ጻፈ ይታመናል። ከዚህ በላይ የቻይና ስነ ፈለክና የቻይና ዘመን አቆጣጠር ፈጠረ። ስለ ኋንግ ዲ ብዙ ሌሎች ትውፊቶች አሉ። መጀመርያ ሚስቱ ሌዙ ተከታዩን ሻውሃውን ወለደች። 3 ሌሎች ሚስቶች እነርሱም ፋንግሌ፣ ቶንግዩ እና ሞሙ ነበሩት። በተለመደው ታሪክ ዘንድ ለ99 አመት ነገሠ። ታላቅ መቃብሩ በያንአን ከተማ ሲገኝ እስከ ዛሬ ድረስ በየአመቱ በሥነ ስርአት ይከብራል።
ኋንግ ዲ ከዋና ሚስቱ በተጨማሪ የነበሩት 3 ሚስቶች እነማን ናቸው?
ፋንግሌ፣ ቶንግዩ እና ሞሙ
1,039
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ በመሳተፍ በ58 ኪ.ግ ምድብ 7ኛ በመያዝ ዲፕሎማ አግኝታለች፡፡ ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ የወከለው አትሌት ሰለሞን ቱፋ እየተካሄደ ባለው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ58 ኪ .ግ ምድብ ባደረገው ውድድር 7ኛ ደረጃ በመያዝ ዲፕሎማ መገኘቱን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ በወርልድ ቴኳንዶ የተሳተፈችው ለስንተኛ ጊዜ ነው?
ለመጀመሪያ ጊዜ
17
የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። ውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ። ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል።
የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት አንዷ መስራችና ዋና ኃላፊ ስማቸው ማን ይባላል?
ውለታ ለማ (ዶ/ር)
58
አባይ ሀገሬው አባይ ብሎ ይጠራዋል፣ አባይ ማለት ታላቅ ማለት ነው። ከወንዞች ሁሉ አብይ ነው። የበኩር ልጅን አባይነህ ይሉታል ታላቅ ነህ ማለታቸው ነው። አባይ ከወንዞች ሁሉ ታላቁ ነው። የቀዬው ሰው አባይ ብሎ በአክብሮት ይጥራው እንጂ፣ ስሙ ግዮን ነው። ግዮን በመፅሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት ምዕራፍ ሁለት ቁጥር 10 እና 13 ላይ ከኤደን ገነት ከሚወጡት አራት ወንዞች አንዱ ሆኖ ተፅፏል። ይህ ወንዝ የኢትዮጵያን ምድር ይከብባል ሲልም ይናገራል። ግዮን የሚለው ቃል የግዕዝ ሲሆን በዕብራይስጥ ጊሖን፣በፅርዕ (ግብፅ) ጌዖን ይባላል። ትርጓሜውም “ዘየሐውር፡ በኃይል፡ ወይርም በድምፀ ማዩ ዐቢይ ወግሩም ማለት ነው።” ወደ አማርኛ ሲገለበጥ “ የውሃውን ብዛት፣ የመልካውን(የወንዙን) ስፋት፣ያካሄዱን ኅይል፣ የጩኸቱን ግርማ፣ ፏፏቴውንና ተመማውን(አፈሳሰሱ)፣ ድምፁ እንደ ነጎድጓድ መሆኑን ያሳያል”። ባለፉት 6 ሚሊዮን ዓመታት በተለያዩ የመሬት ነውጦች ምክንያት የአባይ ሸለቆ ብዙ ጊዜ ተቀያይሯል። Eonile የተፈጠረው ከ5.4 ሚሊዮን ዓመት ገደማ የሜዲትራኒያን ባሕር ተኖ ኃይለኛ ዝናብ በመከሰቱ ምክንያት በወረደው ዝናብ ነው። ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ይፈስ የነበረው አባይንኳ ከ 5 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በተከሰተ የመሬት መናድ ምክንያት አቅጣጫውን ቀይሮ ወደሰሜን መፍሰስ ጀምሯል። የጣና ሐይቅን የፈጠረው እሳተ ገሞራም የዛሬ 2.6 ሚሊዮን ዓመት የተከሰተ ነበር። ከሕንድ ውቅያኖስ የሚነሳው እርጥበታማ አየር በኢትዮጵያ ተራራማ ክፍል ሲያልፍ የሙቀት መጠኑ እየቀዘቀዘ ይመጣል። ጉም ምድርን እንደሚያጠጣ፣ ያም ከሕንድ ውቅያኖስ የነፈሰው እርጥበት አዘል አየር፣ ሳይዘንብ የግሸንን ተራራን ያጠጣል። ከግሸን ተራራ ስር፣ ከሰቀላ ወረዳ የፈለቀው ምንጭ በግሸን ሜዳ ላይ ግልገል አባይን ሆኖ ይፈሳል። ግልገል አባይ, በግሸን ሜዳ ላይ ሮጦ ከጣና ሐይቅ ሲስርግ በጣና ተውጦ አይቀርም። በጣና ላይ ተንሳፎ፣ ወደ አባይ ሸጥ ይንደረደራል። አባይ ከጣና ወጥቶ አርባ ኪሎ ሜትር ከተጓዘ በኋላ የአባይ ፏፏቴጋ ሲደርስ 37 ሜትር ቁልቁል ቋጥኝ ላይ ይፈጠፈጥና ሽቅብ አየሩ ላይ ተበትኖ ዳግም ቁልቁል ይወርድና ጥልቀቱ 1200 ሜትር፣ ስፋቱ 24ኪ.ሜ ወደሆነው የአባይ ሸለቆ ውስጥ ይገባና በታላቁ የአባይ ገደላማ ሸለቆ፣ በእናቱ በኢትዮጵያ ሆድ ውስጥ 800 ኪሎ ሜትር ይጓዛል። ይህ ዑደት ላለፉት 5000 ዓመታት አልተለወጠም። በ460 ታሪክ ፀሐፊው ሔረዶቱስ አባይ ከሁለት ትላልቅ ተራሮች እንደሚፈልቅ ያምን ነበር። በኋላም ንጉሠ ነገሥት ኔሮ፣ አሽከሮቹ የአባይን ወንዝ እንዲከተሉ ትዕዛዝ ሰጥቷቸው መልዕክተኞቹ የሱዳን ከተማ የሆነችው ሲናር ሲቲ ከሚገኘው የሱድ ማጥ ደርሰው አባይ ከዛ ነው የሚመነጨው የሚል መልስ ይዘው ተመለሱ። ከአራተኛው እስከ አሥራ ሰባተኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የኢትዮጵያ ተራሮች የአባይ መፍልቂያ መሆናቸውን የገመተ የውጭ ዜጋ አልነበረም።
የአባይ ፏፏቴ ላይ ውሃው ወደ ታች ምን ያህል ርቀት ይወረወራል?
37 ሜትር
1,136
በ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ (400) ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር። የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ኛው እና በ ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ. ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ። ከዚያም ለብዙ ዘመናት የሰለሞናዊው መንግስት ከጠለ።
በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ በ800 ዓመተ-ዓለም የተቋቋመው መንግስት ምን ይባል ነበር?
ደአማት
24
አንበሳ አንበሳ ጡት አጥቢ የእንስሶች መደብ ውስጥ ሲሆን ግዙፍ ድመቶች ከሚባሉት 4 አራዊት አንዱ ነው። ከነዚህም መካከል ነብር ከሚባለው ግሥላ መሳይ አውሬ ቀጥሎ በቁመቱና ክብደቱ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አንበሳ ዛሬ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በህንድ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በታሪክ እስያና በደቡብ አውሮፓ እንደነበርና እንደጠፋ ይታወቃል። አንበሶች በጣም ቁጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሙጭሊትን ያህል ገራምና ተጫዋች ይሆናሉ። ሲጠግቡ በዝግታ የሚያንኮራፉ ቢሆንም እንኳ እስከ ስምንት ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሰማ በሚችል ኃይለኛ ድምፅ ሊያገሡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰነፎችና ልፍስፍሶች ይመስሉ ይሆናል፤ ሆኖም በሚያስገርም ፍጥነት የመንቀሳቀስ ችሎታ አላቸው። የሰው ልጅ፣ አንበሳ ባለው ድፍረት ለዘላለም ሲወሳ እንዲኖር አድርጓል፤ በመሆኑም ደፋር ሰው አንበሳ ተብሎ ይጠራል። አንበሶች በማኅበር ከሚኖሩት የድመት ወገን የሆኑ እንስሶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በትልልቅ መንጋ ተከፋፍለው የሚኖሩ ሲሆን እያንዳንዱ መንጋ ከጥቂት አባሎች አንስቶ ከ30 በላይ ሊደርስ ይችላል። አንድ መንጋ የጠበቀ ዝምድና ያላቸው በርከት ያሉ ሴት አንበሶች ይኖሩታል። አንድ ላይ ይኖራሉ፣ ያድናሉ እንዲሁም ይወልዳሉ። ዕድሜ ልካቸውን ሊዘልቅ የሚችለው ይህ የጠበቀ ትስስር ለመንጋው ጠንካራ መሠረት የሚጥል ከመሆኑም በላይ ለመንጋው ሕልውና ጥሩ ዋስትና ይሆናል። እያንዳንዱ መንጋ እየተዘዋወሩ የሚጠብቁና የመንጋውን የክልል ወሰን የሚያወጡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ለአካለ መጠን የደረሱ ወንድ አንበሶች ይኖሩታል። እነዚህ ዕጹብ ድንቅ የሆኑ አውሬዎች ከጥቁሩ የአፍንጫቸው ጫፍ አንስቶ እስከ ጭራቸው ጫፍ ድረስ ከሦስት ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን ከ225 ኪሎ ግራም በላይ ሊመዝኑ ይችላሉ። ቤተሰቡን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ወንዶቹ ቢሆኑም አመራር የሚሰጡት ግን ሴቶቹ ናቸው። ወደ ጥላ ሥፍራ መሄድን ወይም አደን መጀመርን በመሳሰሉት ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ መንጋውን ለአንድ ዓይነት እንቅስቃሴ የሚያነሳሱት ሴቶቹ አንበሶች ናቸው። ሴት አንበሶች በአብዛኛው በየሁለት ዓመቱ ይወልዳሉ። ግልገሎቹ በሚወለዱበት ጊዜ ምንም ዓይነት አቅም አይኖራቸውም። ግልገሎችን ማሳደግ የሁሉም የጋራ ሥራ ነው፤ በመሆኑም ሴቶቹ አንበሶች በሙሉ በመንጋው ውስጥ ያሉትን ግልገሎች ይጠብቃሉ እንዲሁም ያጠባሉ። የግልገሎቹ ዕድገት ፈጣን ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ መሮጥና መቦረቅ ይጀምራሉ። ልክ እንደ ሙጭሊቶች እየተንደባለሉ ይጫወታሉ፤ ከሚያጫውቷቸው ጋር ይታገላሉ፤ እንዲሁም በረጃጅሙ ሣር ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይዘላሉ። እያንዳንዱ የሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ ስሜታቸውን ይማርከዋል፤ ቢራቢሮዎችን ለመያዝ ይዘላሉ፣ ትናንሽ ነፍሳትን ያሳድዳሉ፣ ከየጭራሮና ከየሐረጉ ጋር ይታገላሉ። ይበልጥ ስሜታቸውን የሚማርከው ግን እነርሱን ለማጫወት እናታቸው ወዲያና ወዲህ የምታወናጭፈው ጭራዋ ነው። እያንዳንዱ መንጋ የሚኖርበት በደንብ የተከለለ ቦታ ያለው ሲሆን ይህ መኖሪያ ብዙ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ሊኖረው ይችላል። አንበሶች ውኃ እንደ ልብ ባለበትና ከቀትር ሐሩር የሚከላከል ጥላ በሚያገኙበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ መኖር ይመርጣሉ። በእንዲህ ዓይነቱ ሥፍራ ከዝሆኖች፣ ከቀጭኔዎች፣ ከጎሽና ከሌሎች ሜዳማ በሆኑ ሥፍራዎች ከሚኖሩ እንስሶች ጋር በአንድነት ይኖራሉ። አንበሳ አብዛኛውን ጊዜውን በእንቅልፍ ጥቂቱን ጊዜ ደግሞ በአደንና በተዋስቦ ያሳልፋል። እንዲያውም አንበሶች በቀን ውስጥ ወደ 20 የሚጠጋውን ሰዓት የሚያሳልፉት በዕረፍት፣ በመተኛት ወይም በመቀመጥ ነው። ከባድ እንቅልፍ ተኝተው ሲታዩ ሰላማዊና ለማዳ ይመስላሉ። ይሁን እንጂ በዚህ መታለል የለብህም፤ አንበሳ እጅግ ቁጡ ከሆኑት አራዊት መካከል አንዱ ነው!
አንበሶች በማኅበር ከሚኖሩት ሲሆን ወገናቸው ከእንስሳት መካከል የትኛው ወገን ነው?
የድመት ወገን
513
ቦትስዋና ቦትስዋና ወይም በይፋ የቦትስዋና ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ Republic of Botswana ሰጿና፡ Lefatshe la Botswana) በደቡባዊ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ አገር ናት። ቦትስዋና የቀድሞ የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ስትሆን ነፃነቷን በመስከረም ፳ ቀን ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. ከተቀዳጀች በኋላ መሪዎቿ በነፃ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ተመርጠዋል። ቦትስዋና ሜዳማ ስትሆን ከሰባ ከመቶ በላይ በካለሃሪ በርሃ የተሸፈነች ናት። በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ከደቡብ አፍሪካ፣ በምዕራብና ሰሜን ከናሚቢያ እና በሰሜን ምሥራቅ ከዚምባብዌ ጋር ትዋሰናለች። ከዛምቢያም ጋር በደንብ ያልተወሰነ ቢበዛ በመቶ ሜትር የሚቆጠር ወሰን አላት።
ቦትስዋና በሰሜን ምሥራቅ የምትዋሰነው ከማን ጋር ነው?
ከዚምባብዌ
327
አማራ (ክልል) አማራ (ክልል 3) ከዘጠኙ የኢትዮጵያ ክልሎች አንዱ ሲሆን ከ 1994 በፊት አራት የሀገሪቱን ዋና ወና ክፍለ ሀገራት የ ካትት ነበር እነሱም በጌምድር ጐጃም ወሎና ሸዋ ነበሩ ።የአማራ ብሔራዊ ክልል ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ በ8° 45 እስከ 13° 45 ሰሜን የኬንትሮስ እና በ35° 46 እስከ 40° 25 ምስራቅ የኬንትሮስ መስመር ውስጥ ይገኛል። በምስራቅ የአፋርና የኦሮሚያ ክልሎች፣ በምዕራብ ሱዳን እና ቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል፣ በሰሜን የትግራይ ክልልና በደቡብ የኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል። የቆዳ ስፋቱ ፻፶፯ሺ፸፮ ካሬ ሜትር ሲሆን ከአገሪቱ አሥራ አምስት በመቶ ድርሻ ይይዛል። የክልሉ ሕዝብ ብዛት ደግሞ በ፳፻፪ ዓ/ም 20,875,456 እንደነበር የተገመተ ሲሆን ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ 33.9% አካባቢ ድርሻ ይይዛል ተብሎ ይገመታል። ክልሉ በ፲ ዞኖችና በ፻፷፮ የገጠርና የከተማ ወረዳ አስተዳደሮች የተከፋፈለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ፴፰ የሚሆኑት የከተማ አስተዳደሮች ናቸው። የአማራ፣ የአገው፣ የኦሮሞና የሌሎች ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት ክልል ነው። እንዲሁም የአማራ ክልል አሁን ላይ የክልል ከተማው ባህር ዳር ነው። በክልሉ አልፎ አልፎ ከሚታዩ የመንግሥትና የማኅበራት ደኖች፣ በደሴቶች፣ በአብያተ ክርስቲያናት፣ በወንዞች ዳርቻና ሰው ሊደርስባቸው በማይችሉ ገደላማና ተራራማ ስፍራዎች ከሚገኙ ጥቂት ደኖች በስተቀር ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የደን ሀብት ጋር በቅርብ የተያያዘ ነው። በዚህ ረገድ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ እንደ ቀይ ቀበሮ፣ ዋልያ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እንዲሁም በምዕራባዊው የክልሉ አካባቢ ዝሆን አንበሳና ነብር፣ ሰጐንና የተለያዩ አዕዋፋት በስተቀር ከፍተኛ የዱር እንስሳት ክምችት ካለመኖሩም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጥቂት የደን ቅሪቶችና ዋሻዎች የነበሩት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አራዊቶችም ለዘመናት በደረሰው የደን መጨፍጨፍና መራቆት ምክንያት ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ እንደተሰደዱ ይታወቃል። ክልሉን የማዕድን ሀብት አስመልክቶ በሚገባ የተጠናከረ ጥናት ባይኖርም ከክልሉ ስነ-ምድራዊ ሁኔታዎችና ከተካሄዱ አንዳንድ ጠቋሚ ጥናቶች መረዳት እንደሚቻለው በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ማዕድናት እንደአሉ ይገመታል። በዚህም መሠረት በሰሜን ሸዋ የኦፓል ማዕድን፣ በሰሜን ጐንደር፣ በጭልጋና በደቡብ ወሎ በአምባሰል ወረዳ የድንጋይ ከሰል ክምችት እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ለግንባታ ሥራ የሚውል በቂ የድንጋይ፣ የኖራ ድንጋይ፣የሸክላ አፈር፣ ጅኘሲየም፣ የጌጣጌጥ ማዕድናት እንዲሁም በዓባይ ሸለቆ የዕብነ በረድ ሐብቶች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይሁን እንጅ በውል የሚታወቀው ሐብትም ቢሆን በበቂ ሁኔታ አልለማም።
የአማራ ክልል በስንት ዞኖች የተከፈለ ነው?
በ፲
478
አዲስ ዘመን (ጋዜጣ) አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥር የምተዳደር ነዉ ፣ በየዕለቱ የሚታተም ብሔራዊ ጋዜጣ ነው። አዲስ ዘመን በአሁኑ ጊዜ ከ ፵ በላይ ጋዜጠኞች ያሉት ሲሆን የጋዜጣው መጠን ‘መካከለኛ’ /በርሊነር/ (31.5 cm × 47 cm (12.4 in × 18.5 in) ) ሆኖ የፊትና ጀርባ ገፆችን በሙሉ ቀለም ያቀርባል። ይህ ጋዜጣ የአገሪቱ ብቸኛው ዕለታዊ ጋዜጣ ሲሆን የመንግሥትን አቋም የሚያንፀባርቅ እና በየዕለቱ የተለያዩ ልማታዊ ዜናዎችን ይዞ ይወጣል። ከአምሥት ዓመት የኢጣልያ ወረራ በኋላ የኢትዮጵያ ነፃነት መመለሱን ተከትሎ ንጉሠ ነገሥቱ ዙፋናቸው እንደ ተረከቡ ካከናወኗቸው ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ተግባራት አንዱ የመገናኛ ብዙኀን በማደራጀትና በማቋቋም ላይ ያተኮረ ነበር። በዚህም መሠረት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ቅዳሜ፣ ግንቦት ፴ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በይፋ ሥራ ጀመረ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከጠላት ወረራ በኋላ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ሲገቡ ባደረጉት ንግግር የመግቢያው አንቀጽ፦ «የሰማይ መላእክት የምድር ሠራዊት ሊያስቡትና ሊያውቁት ይቻላቸው ባልነበረ በዚህ በዛሬው ቀን ቸር እግዚአብሔር በመካከላችሁ ለመገኘት ስላበቃኝ በሰው አፍ የሚነገር ምስጋና የሚበቃ አይደለም። ከማናቸውም አስቀድሞ ለሁላችሁ ልነግራችሁና ልትረዱት የምፈልገው፣ ይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የአዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ መሆኑን ነው። በዚሁ በአዲሱ ዘመን ሁላችንም መፈጸም ያለብን አዲስ ሥራ ይጀመራል።» የሚል ነበር የጋዜጣውም ሥያሜ «ይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የአዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ ነው» ማለታቸውን መሠረት ያደርጋል። የጋዜጣው ድረ-ገጽ ስለጋዜጣው ታሪክ ሲዘግብ፤«የመጀመሪያ ዕትም ባለሁለት ገፅ፣ አርበ ጠባብ /ታብሎይድ/» (43.2 cm X 27.9 cm (17 in X 11 in)) እንደነበረና ስርጭቱም ፲ሺ ቅጂ እንደነበር ይገልጽና፤በዚሁ የመጀመሪያ ዕትም ርዕሰ አንቀጽ «"የአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጀመር" በሚል ርዕስ ባስነበበው ጽሑፍ ‹ይህ አዲስ ዘመን ተብሎ የተሰየመው ጋዜጣ ከዛሬ ጀምሮ ወደፊት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱን ሥራ ይሠራ ዘንድ ተመሠረተ› በማለት የተቋቋመበትን ዓላማ ያስረዳል» ይለናል። ቀጥሎም ያንኑ የመጀመሪያውን ርዕሰ አንቀጽ በመጥቀስ፤ «‹ይህ ጋዜጣ የፕሮፖጋንዳ ጋዜጣ ሳይሆን እውነትን፣ አገልግሎትን፣ ረዳትነትን መሰረት አድርጐ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ በአዲስ ሥራ ተመርቶ እንዲረዳ የቆመ ነው› ቢልም ‹አገልግሎት ስንል የኢትዮጵያን ነፃነት ሲመሰስ ራሳቸውን መስዋዕት አድርገው፤ የነበራቸውን ጥቅም ሁሉ አስወግደው፤ ለሕዝባቸውና ለአገራቸው ሲሉ የሰው አቅም ሊሸከመው የማይችለውን ድካም ተቀብለው፤ ማናቸውም ሰው ሊያደርገው ያልቻለውን በኢትዮጵያ ሕይወት ውስጥ እስከ ዛሬ ያልታየውን ሥራ ከፍፃሜ ላደረሱ ለንጉሠ ነገሥታችንና ላቆሙት መንግሥት የሚያገለግል እንዲሆነ ነው።› በማለትም በዋነኝነት የተቋቋመበትን ዓላማ በግልፅ ይተነትናል።» የሚል ዘገባ እንደነበር የጋዜጣው ድረ-ገጽ አስቀምጦታል። አዲስ ዘመን ከተጀመረበት ጊዜ እስከ ታኅሣሥ ወር ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ድረስ በየሳምንቱ፤በአርበ-ጠባብ፣ በመካከለኛና በአርበ-ሰፊ /ብሮድሺት/ (74.9cm X 59.7cm (291⁄2 in X 231⁄2 in)) መጠን ሲታተም ከቆየ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ፲፱፻፶ ዓ/ም ያቋቋመው የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ ጽሕፈት ቤቱን አዲስ አበባ ላይ ማድረጉን ምክንያት በማድረግ የጋዜጣው ዕትመት በሳምንት ወደ ስድስት ቀን ተሸጋግሯል። ከመስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ ጋዜጣው ከሰኞ እስከ እሑድ በሳምንት ሰባት ቀናት ወደመታተምከተሸጋገር በኋላ የጋዜጣው መጠን ከታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ጀምሮ ወደ መካከለኛ ጋዜጣነት /በርሊነር/ ዝቅ ብሏል።
አዲስ ዘመን ከተጀመረበት ጊዜ እስከ ታኅሣሥ ወር ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ድረስየሚታተመው መቼ መቼ ነበር?
በየሳምንቱ
1,747
ጣና ሐይቅ ጣና ሐይቅ ቅዱሱ ሐይቅም ይባላል። ከኢትዮጵያ አንደኛ እና ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል። በቁጥር ከ35 በላይ ደሴቶች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥም 22ቱ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት ናቸው። ባንዳንዶቹ ላይም (ለምሳሌ በዳጋ ደሴት) የድሮ የኢትዮጵያ መሪዎች መቃብሮች ሲገኙ ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ለመጀመሪያ ያስተዋወቀው አቡነ ሰላማ መቃብርም በዚሁ ሃይቅ ይገኛሉ። የጣና ሃይቅን የሚመግቡ 3ቱ ዋና ወንዞች ርብ፣ ጉማራ ወንዝ ና ትንሹ አባይ በመባል ይታወቃሉ። አሁን ባለው ይዞታ የጣና ሃይቅ 1,454 ቶን አሳ በአመት ይመረታል። ነገር ግን ይሄ የምርት ሃይቁ ያለምንም ችግር ሊያስተናግድው ከሚችለው 15 በመቶው ያህል ብቻ ነው።
በጣና ሐይቅ ከሚገኙ ደሴቶች 22ቱ ምንድን ናቸው?
ገዳማትና አብያተክርስቲያናት
159
የጥምቀት በዓል በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዓ/ም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ በዓል ነው። መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው። በአገራችን፣ ጥር ፲ ቀን፣ በከተራ፣ በገጠር ወራጅ ውሃ የሚከተርበት፣ ታቦታት ከየአቢያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በምዕመናን ታጅበው እየዘመሩ ይሄዳሉ። እዚያም በየተዘጋጀው ድንኳን እንዲያርፉ ተደርጎ ሌሊቱን እዛው ያሳልፋሉ።በከተሞች ግን ሰው ሰራሽ ግድብ ይሰራል። ጥር ፲፩ ቀን የጥምቀት ዕለት፤ በገጠር፣ ጎኅ ሲቀድ ምእመናን እዚያው በድንኳኑ ዙሪያ አስቀድሰው ሲጨርሱ በካህናት መሪነት ሁሉም ወደከተራው ያመራና ውሃውም ተባርኮ ሕዝቡ ይረጫል። «ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ፤ ሰማያዊው በመሬታዊው እጅ ተጠመቀ» የሚለው የዕለቱ ቀለም በሊቃውንቱ አንደበት በያሬዳዊ ዜማ ጎልቶ ይሰማል። ከዚህ ሥነ ሥርዓት በኋላ በመቋሚያ፣ በከበሮና በጽናፅል በሚታጀብ ኃይማኖታዊ ዝማሬ፣ ወንዱ በሆታ፤ ሴቱ በእልልታ፤ ካህኑ በሃሌታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየ ቤተክርሲያናቸው ይመለሳሉ። በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየጥምቀተ ባሕሩ የሚከበሩ በመኾናቸው፣ ሀገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብ በመፍጠሩ፣ ቱሪስቶችን መሳቡ አልቀረም። ጥቁርና ነጭ፣ ቀይና ብጫ ያለም ዘር፣ ከአዲስ አበባ እስከ ላሊበላ፣ ከአክሱም እስከ ጎንደር በሁሉም ሥፍራዎች በዚሁ ዓይነት ደምቆ ይከበራል። የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ ፍፁም በሚማርክ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁል ጊዜ አዲስ ነው። ሊቃውንቱ እንደሚናገሩት፣ ዘመነ አስተርእዮ የሚባለው፣ ከጥር ፲፩ ቀን ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አምላክ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር መታወቁ፣ በቃና ዘገሊላ በተደረገው ሠርግ ላይ የመጀመሪያው ተዐምር በመፈጸሙ፣ አምላካዊ ኃይሉ መገለጡ፣ እየታሰበ ምስጋና ይቀርባል። ይህ ሁነት ኢትዮጵያ ብሂልን ከባህል ጋር አዛምዳ ከሌላው የክርስቲያን ዓለም በተለየ አከባበር በዓሉን ማክበሯ፣ አያሌ ቱሪስቶችን ለመሳብ አስችሏታል።
ኤጲፋንያ ምን ማለት ነዉ?
መገለጥ፣ መታየት
174
የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። ውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ። ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ውለታ ለማ ባሸነፉበት አዲስ የሥራ ፈጠራ ውድድር በመጀመሪያው ዙር ምን ያህል ተወዳዳሪዎች ነበሩ?
2500
217
ናዋትል ናዋትል (nāhuatl, mexìcatlàtōlli, Nawatl) በኡቶ-አዝቴካዊ የቋንቋ ቤተሠብ የሚከተት በሜክሲኮ ኗሪዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። በተለይ እስፓንያውያን በ16ኛው መቶ ዘመን ከወረሩ አስቅደሞ በጣም ትልቅና መደበኛ ቋንቋ ሆኖ ነበር። እስከ ዛሬ ግን በ1.5 ሚሊዮን ኗሪዎች በሜክሲኮ እየተናገረ ነው። የዛሬውኑ ናዋትል ከስፓንኛ ታላቅ ተጽኖ ተቀብሏል። ኣብዛኛው ተናጋሪዎቹ ስፓንኛ ደግሞ የሚችሉ ናቸውና። ስፓንያውያን በደረሡ ጊዜ ናዋትል የራሱ ጽሕፈት ነበረው። ይህ ጽሕፈት እንደ ጥንታዊ ግብጽ ስዕል ጽሕፈት ይመስል ነበር። ነገር ግን እነዚህ ጽሑፎች በአብዛኛው በካቶሊኮች ስለ ተቃጠሉ፣ ዛሬ ቋንቋው የሚጻፈው በላቲን ፊደል (አልፋቤት) ሆኗል። በናዋትል ሰዋስው አያሌ ባዕድ መነሻዎችና መድረሻዎች አንድላይ ሊቀጣጥሉ ይችላሉ። ስለዚህ አንድ ቃል እጅጉን እንዲረዝም ተችሏል።
የናዋትል ቋንቋ በሌላ በምን ቋንቋ ተጽእኖ ስር ነው?
ስፓንኛ
246
የአሜሪካ ታላቅ ማኅተም የአሜሪካ ብሔራዊ ምልክት የአሜሪካ ታላቅ ማኅተም ይባላል። መጀመርያው የተገለጸው በ1774 ዓ.ም. ነበር። እንዲያውም በይፋ 'አርማ' ሳይሆን 'ማኅተም' ነው። ነገር ግን ይፋዊ አርማ ስለማይኖር በዘልማድ ይህ ማኅተም እንደ አርማ ይጠቀማል። በአሜሪካ ዶላር ላይ (ከ1927 ዓ.ም. ጀምሮ) እንዲሁም በአሜሪካ ፓስፖርት ላይ ይታያል። በማኅተሙ ፊት ላይ ክንፎቹን የሚዘረጋ የመላጣ ንሥር ስዕል እሱም የአሜሪካ ምልክት ይታያል። በግራው ጥፍሩ (ከንሥሩ አንጻር) ውስጥ አሥራ ሦስት ፍላጻ ይዟል። እነርሱም ከእንግሊዝ ያመጹ የመጀመርያ 13 ክፍላገሮች ያመልክታሉ። በቀኙም ጥፍር የወይራ ቅርንጫፍ ይይዛል። ይህ 13 ቅጠልና 13 ፍሬዎች አሉበት። ፍላጻ የጦር ምልክትና ወይራ የሰላም ምልክት በመሆኑ የንሥሩ ራስ ወደሱ ቀኝ ሲዞር ስላምን ይመርጣል እንደ ማለት ነው። በመንቁራው ውስጥ ደግሞ E PLURIBUS UNUM የሚለውን መፈክር ይይዛል። ይህም በሮማይስጥ ማለት 'አንድ ከብዙ' ነው። ከራሱ በላይ 13 ከዋክብት በሰማያዊ በስተኋላ መደብ አለ። እኚህ ከዋክብት የዳዊት ኮከብ ይሠራሉ። በፍርምባው ላይ የሚሸክመው ጋሻ እንደ አሜሪካ ሰንደቅ አለማ ዝንጉርጉር ነው። በማኅተሙ ጀርባ ላይ ያልተጨረሰ ሀረም (ፒራሚድ) ይታያል። ይህ 13 ደረጃዎች ሲኖሩት በመሠረቱ ላይ MDCCLXXVI ይላል። ይህ በሮማይስጥ ቁጥሮች ማለት '፼፯፻፸፮' ወይም 1776 ሲሆን በአውሮጳውያን አቆጣጠር የአሜሪካ ነጻነት አዋጅ የተፈረመበት አመት (1768 ዓ.ም.) ለማመልከት ነው። በሀረሙ ጫፍ ፈንታ 'የእግዚአብሔር ጥበቃ ዓይን' የሚባል ምልክት ይታያል። በዚሁ ዙሪያ «ANNUIT CŒPTIS» የሚለው መፈክር አለ፤ ይህም በሮማይስጥ 'የተጀመረው ተስማምቶታል' ለማለት ነው። በግርጌው ደግሞ «NOVUS ORDO SECLORUM» የሚል መፈክር እያለ ይህ ትርጉም 'የዘመናት አዲስ ሥርዓት' ነው።
የአሜሪካ ብሔራዊ ምልክት ያለው ወይራ የምን ምልክት ነው?
የሰላም ምልክት
434
ዩናይትድ ኪንግደም ዩናይትድ ኪንግደም ማለት የተባበረው ግዛት በተለመደው እንግሊዝ አገር ሲባል፣ እንዲያውም እንግሊዝ አገር ወይም ደግሞ «ኢንግላንድ» ከዩናይትድ ኪንግደም ዋና ክፍላገሮች አንዱ ብቻ ነው። ሌሎቹም፦ ስኮትላንድ ዌልስ ሰሜን አይርላንድ ናቸው። ከነዚህም እንግሊዝ፣ ስኮትላንድና ዌልስ አብረው «ታላቋ ብሪታንያ» የምትባል ደሴት ናቸው። ከ1699 ዓ.ም. (1707 እ.ኤ.አ.) አስቀድሞ፣ እንግሊዝና ስኮትላንድ የተለያዩ ንጉዛት ነበሩ። ከ1595 ዓ.ም. ጀምሮ ግን 2ቱ አገራት አንድ ንጉሥ ነበራቸውና በ1699 በመዋሐዳቸው አንድ ላይ «ዩናይትድ ኪንግደም» ሆነዋል።
ዓ.ም. (1707 እ.ኤ.አ.) አስቀድሞ፣ እንግሊዝና ስኮትላንድ ከተለያዩ ንጉሳት አስተዳደር ወጥተው በአንድ መተዳደር የጀመሩት በስንት ዓመተ ምህረት ነው?
ከ1595 ዓ.ም
281
በ1240 አካባቢ በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ፍትሐ ነገሥት በአረብኛ ጻፉ። እብን አል-አሣል ሕጎቹን የወሰዱት በከፊል ከሃዋርያት ጽህፈቶችና ከሕገ ሙሴ፤ በከፊልም ከድሮ ቢዛንታይን ነገስታት ሕጎች ነበር። መጽሐፉ በግዕዝ ተተርጉሞ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ወቅት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በ1450 አከባቢ እንደነበር የሚል ታሪካዊ መዝገብ አለ። ቢሆንም መጀመርያ እንደ ሕገ ምንግሥት መጠቀሙን የተመዘገበው በዓፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን (ከ1555 ጀምሮ) ነው። ፍትሐ ነገስት እስከ 1923 ዓ.ም. የብሄሩን ዋና ሕግ ሆኖ ቆየ። በ1904 ዓ.ም. ዐጼ 2 ምኒልክ የዘመናዊ ሕገ መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ ተረድተው በጸሀፊው መምሬ ብስራት አንድ ሕገ መንግሥት የሚመስል ሰነድ ታተመ፤ ይህ ግን በውነት ሕገ መንግሥት አይባልም። «በምኒሊክ ስለተቋቋሙት ሚኒስቴሮች በምሳሌ የቀረበ ጽሑፍ» በምሳሌና በትርጓሜ የእያንዳንዱን ሚኒስቴር ሥራ እንደ ሰውነት አካላት አስመሰለ። ለምሳሌ፦ ኢትዮጵያ መጀመርያ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት የተቀበለችው በ1923 አመተ ምኅረት በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የታወጀ ሲሆን የሕግ አማካሪ ቤቶች በሁለት ያስከፈለ ነው። ይህ የመንግሥታቸው ዋና መሠረት ሆኖ እስከ 1948 አ.ም. አገለገለ፤ በዚያ አመት ተሻሽሎ በወጣ ሕገ መንግሥት ሕዝቦች በመንግሥት ሥራ የሚጫወቱት ሚና እንደገና ተስፋፋ። ይህ ብቻ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሆኖ እስከ 1967 አ.ም. ቆየ፤ የዛኔ በደርግ (በሕገ መንግስት እራሱ ባልሆነ ሂደት) ተሰረዘ።
በግብጽ ሀገር አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ያዘጋጀው ፍትሐ ነገሥት በምን ቋንቋ ተጻፈ?
በአረብኛ
53
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ላሉት መጻሕፍት አርእስት የሰጡት ሠለስቱ ምዕት ናቸው፡፡ በምን ምክንያት ቢሉ ድዮቅልጥያኖስ መክስምያኖስ የሚባለ ሁለት ዓላውያን ነገስታት ተነስተው "አብያተ ጣዖታት ይትረኃዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትዓፀዋ" ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትና ቅዱሳት መፃህፍት ተዘረፉ፤ ተቃጠሉ፡፡ ከምዕመናን ወገን ብዘዎች ሞቱ የተረፉትም ተሰደዱ፡፡ እጅግ ከፍተኛ እልቂትና ስደት በቤተክርስቲያን ላይ ሆነ፡፡ ከመከራው ጽናት የተነሳ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ተባለ (ከ285 - 395)፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መፍቀሬ ሃይማኖት የሆነውን ቆስጠንጢኖስን አነገሰው፡፡ የቆስጠንጢኖስ አባቱ ኮስታንዲዮስ(ቁንስጣ) ሲሆን እናቱ ደግሞ እላኒ ትባላለች፡፡ ቆስጠንጢኖስም የድዮቅልጥያኖስን አዋጅ በአዋጅ ሽሮ "አብያተ ክርስቲያናት ይትረኃዋ አብያተ ጣዖታት ይትዓፀዋ" ብሎ አወጀ፡፡ በዘመኑ አርዮስ የተባለ መናፍቅ ወልድ ፍጡር በመለኮቱ ብሎ ተነሳ፡፡ በዚህ ጊዜ ጉባኤ በኒቂያ ተደረገ፡፡ ሶስት መቶ ዓሥራ ስምንት የቤተክርስቲያን ሉቃውንት ተሰብስበው አርዮስን በማውገዝ ሃይማኖትን አጽንተው በሚለያዩበት ጊዜ ለመጻህፍት ሁሉ አርእስት ሰጥተዋል፡፡
የእላኒና የቁንስጣ ልጅ ማን ይባላል?
ቆስጠንጢኖስ
350
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓ/ም በአንዲት “ብርሃንና ሰላም” በተሰኘች አነስተኛ ጋዜጣ ሕትመት ሥራውን ጀመረ። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መጻሕፍት ፣ ጋዜጦች ፣ መጽሔቶችና የምስጢራዊ ሕትመት ሥራዎች በተለያዩ ቋንቋዎች እያተመ ይገኛል። ማተሚያ ቤቱ በርካታ የመንግሥት እና የግል ጋዜጦችን የሚያትም ሲሆን ፥ በተጨማሪም በየዓመቱ በርካታ የፈተና ሥራዎችን በማተም ይታወቃል። ጥንታዊ ኢትዮጰያውያን ሊቃውንት የሚጽፏቸው መጻሕፍት ለሕዝብ የሚቀርቡት ብራና ተፍቆ ፣ ቀለም ተቀምሞ በእጅ ተፅፎ ነበር። በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ-መንግሥት የተጀመረው የዘመናዊ ሕትመት ሥራ በሀገሪቱ ቁጥራቸውና መጠናቸው በርከት ያሉ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች፣ መጻሕፍት፣ እንዲሁም ሌሎች የሕትመት ውጤቶች መታተም በመጀመራቸው የትምህርትና የሥልጣኔ መሰፋፋት ላይ የበኩሉን ሚና መጫወት ጀመረ። የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትም ምሥረታ ዋና ዓላማ የአገሪቱን መንፈሳዊ መጻሕፍት በብዛት እና በዘመናዊ መልክ ከእጅ ጽሑፍ ወደ ሕትመት ለማሸጋገር ሲሆን፤ ምሑሩ ተክለጻድቅ መኩሪያ (፲፱፻፷፩ ዓ/ም)፣ ማተሚያ ቤቱ መስከረም ፫ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓ/ም መቋቋሙን እና ብዙ ሥጋዊና የመንፈሳዊ መጻሕፍት እንዲሁም ምክርና ተግሣጽ፣ የለት ወሬ፣ የሹም-ሽር አዋጆችን ያትም እንደነበር ዘግበዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ረዳት መምህር መኩሪያ መካሻ፤ “የፕሬስ ታሪክ” በተሰኘ ጽሑፋቸው ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ፣ ራስ ተፈሪ መኮንን በ፲፱፻፲፫ ዓ/ም የማተሚያ መሣሪያ አስመጥተው “ትንሹ ግቢ” (በኋላ ገነተ ልዑል — አሁን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ) ይባል በነበረው መኖሪያቸው ውስጥ አስተክለው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የተባለውን እንደመሠረቱ ዘግበዋል። ከሁለት ዓመት በኋላ በ፲፱፻፲፭ ዓ/ም አራት ተጨማሪ ማተሚያዎች ተገዝተው ከተተከሉ ከአንድ ዓመት በኋላ ሣምንታዊው ‘ብርሃንና ሰላም’ የተሰኘው ጋዜጣ እየታተመ፣ አስቀድሞ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ከተጀመረችው ‘አዕምሮ’ ጋዜጣ ጋር እስከ ጠላት ወረራ ዘመን ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ይሠራጩ ነበር። የወቅቱ ማተሚያ መሣሪያዎች በእግር እየተረገጡ የሚንቀሳቀሱ መሣሪያዎች ሲሆኑ የሠራተኞቹ ቁጥር ከሰባት እስከ አሥራ-ሁለት እንደነበር ተዘግቧል። ራስ ተፈሪም አልፎ-አልፎ በብርሃን እና ሰላም ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ይረዱ እንደነበረና ጽሑፎቻቸውንም ለሕትመት ያበቁ እንደነበር ተምዝግቧል።
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት መቼ ስራ ጀመረ?
ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓ/ም
36
የትነበርሽ ንጉሴ የትነበርሽ ንጉሴ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ እና የአካል ጉዳተኛ መብትቶች ተሟጋች ናት ፡ እ.ኤ.አ በ 2017 "የአካል ጉዳተኞችን መብቶችን እና ማካተቶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም  በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉየአእምሮ ውቅርን መለወጥ የሚያበረታታ ሥራዋ"  ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድን ተሸልማለች። የትነበርሽ ንጉሴ የአይን ብርሃኗን ያጣችው በ 5 ዓመቷ ነበር ። ይህ አጋጣሚ በተወለድችበት በአማራ ክልል በስፋት ይተገበር ከነበረው ያለ አድሜ ጋብቻ  አንድታመልጥ እድሉን እንደፈጠረላት ትናገራለች። ፡፡የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሻሸመኔ ካቶሊክ የዓይነ ስውራን  ት/ቤት ተከታትላ ወደ ዳግማዊ  ምኒልክ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (አካታች ትምህርት ቤት) ገብታ እስከ 12 ኛ ክፍል እዚያ ተማረች። በትምህርት ቤቱ ካላት አካዳሚክ ተሳትፎ በተጨማሪ የተማሪዎችን አማካሪ ጨምሮ ከ 6 በላይ የክለቦችን ክበባት መርታለች ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በመቀላቀል የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ በማኅበራዊ ሥራ አግኝ ታለች፡፡ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ  በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በተከታታይ  ትሳተፋለች በዚህም  የመኢአድ የፀረ ኤድስ እንቅስቃሴን ከ2004 - 05 በመምራት በ 2006 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (አአዩ) ሴት ተማሪዎች ማህበርን በመመስረት እንዲሁም የማህበሩ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት በመሆን  አገልግላለች ፡፡
የትነበርሽ ንጉሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን የት ተከታተለች?
ዳግማዊ  ምኒልክ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
375
ሊቢያ ኦይል ከኢትዮጵያ የተሰናበተውን ሼል ኢትዮጵያ ሊሚትድ በመግዛት የኢትዮጵያን የነዳጅ ገበያ የተቀላቀለው በ2000 ዓ.ም. ነበር፡፡ ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ 143 የነዳጅ ማደያዎች ሲኖሩት፣ 24 በመቶ የገበያ ድርሻ አለው፡፡ ኩባንያው በየዓመቱ ዘጠኝ ማደያዎች በመክፈት እ.ኤ.አ. በ2020 የነዳጅ ማደያዎቹን ቁጥር 185 ለማድረስ፣ የገበያ ድርሻውን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ አቅዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኩባንያው ዓመታዊ ሽያጭ 13 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡ ሊቢያ ኦይል 50 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የአቪዬሽን ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያና በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የነዳጅ ዲፖ የኤታኖል ማደባለቂያ ገንብቷል፡፡ ኩባንያው እስከዛሬ እንደ አዲስ የገነባቸው ስምንት የነዳጅ ኩባንያዎችን ብቻ ነው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ለግንባታ የሚሆን ቦታ የማግኘት ችግር በመኖሩ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዘካሪያስ፣ ከሼል ኩባንያ ግዢ ጋር የተፈጠረው የታክስ ክርክር የኩባንያውን ዕድገት እንደጎተተው ያስረዳሉ፡፡ የታክስ ክርክሩ እልባት ያገኘ በመሆኑ ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ቆርጦ መነሳቱን አስታውቋል፡፡ ሊቢያ ኦይል ባለፈው ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ አዳዲስ የሞተር ዘይትና ቅባቶችን አስተዋውቋል፡፡ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ የሊቢያ ኦይል የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፣ የሊቢያ ኦይል ምርቶች አከፋፋዮችና የትራንስፖርት ኩባንያዎች የሊቢያ ኦይል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሙስባሕ ኤልቤሽቲ ሽልማቶች አበርክተዋል፡፡
ሊቢያ ኦይል በኢትዮጵያ በ2007 ዓ.ም በ50 ሚልየን ብር ያስገነባው ምንድን ነው?
የአቪዬሽን ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያና በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የነዳጅ ዲፖ የኤታኖል ማደባለቂያ
323
ስዋሂሊ ስዋሂሊ ፡ (ወይም ፡ ኪሷሂሊ Kiswahili) ፡ በምሥራቅ ፡ አፍሪቃ ፡ የሚናገር ፡ የባንቱ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የስዋሂሊ ፡ ሕዝብ (፭ ፡ ሚሊዮን ፡ ተናጋሪዎች) ፡ ልደት ፡ ቋንቋ ፡ ከመሆኑ ፡ በላይ ፡ ለ ፴ ፡ እስከ ፡ ፶ ፡ ሚሊዮን ፡ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ሁለተኛ ፡ ቋንቋ ፡ ሆኗል። የስዋሂሊ ፡ ስም ፡ መነሻ ፡ ከዓረብኛ ፡ ቃል ፡ «ሰዋሂል» ፡ ነበር ፤ ይህም ፡ የ«ሳኸል» ፡ (ማለት ፡ ዳር) ፡ ብዙ ፡ ቁጥር ፡ ነው። ስለዚህ ፡ የ«ስዋሂሊ» ፡ ትርጉም ፡ የ(ባሕር) ፡ ዳረኞች ፡ ቋንቋ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል። የቋንቋው ፡ ቤተሰብ ፡ ባንቱ ፡ ሲሆን ፡ ተናጋሪዎቹ ፡ መርከበኞችና ፡ ነጋዴዎች ፡ በመሆናቸው ፡ መጠን ፡ ከዓረብኛ ፣ ከፋርስ ፣ ከህንዲ ፣ እና ፡ ከቻይንኛ ፡ ቢሆንም ፡ ብዙ ፡ ቃሎች ፡ ተበድረዋል።
ስዋሂሊ የምን ቋንቋ ቤተሰብ ነው?
የባንቱ
60
ዋዝንቢት ዋዝንቢት የሦስት አጽቄ አይነት ነው። የፌንጣና የአንበጣ ዘመድ ነው። ሁለንተናው ትንሽ ለጥ ይላል፤ ረጃጅም አንቴኖችም አሉት። ዋዝንቢት የሚታወቀው በሚያሰማው ድምጽ ነው። ድምጽ ማውጣትና ማሰማት የሚችለው አውራው ዋዝንቢት ብቻ ነው። የተባዕቱ ዋዝንቢት ክንፍ እንደ "ሚዶና ሞረድ" የሚመስል ፍርግርግ ነው። ክንፎቹን በማፋተግ ድምጽ ይፈጥራል፤ የድምጹ ቅላፄ እንደየ ዋዝንቢቱ ወገን ይለያያል። ሁለት ዓይነት የዋዝንቢት ዘፈኖች አሉ፤ የጥሪ ዘፈንና የመርቢያ ዘፈን ናቸው። የጥሪ ዘፈን ዓላማ አንስት ዋዝንቢ ለመሳብ ሲሆን ረጅምና ከፍተኛ ድምፅ ነው። ለመራባት ሲባል የሚዘፈነው ድምፅ አንስቲቱ እንስቲቱን ለማቅረብ ስለሆነ ቀስ ያለና ለስላሳ ነው። አንስት ዋዝንቢት መርፌ የሚመስል ረጅም የዕንቁላል መጣያ አላት። በምድር ላይ 900 የሚያሕሉ የዋዝንቢት ዝርያዎች ይገኛሉ። አንዳንድ ዝርያ ሣርና ተክል ብቻ ሲበላ፣ ሌሎች ዝርዮች ደግሞ ነፍሳት ያድናሉ። ዋዝንቢት ሌሊት የሚነቃ ፍጥረት ነው። ብዙ ጊዜ ከፌንጣ ጋር ይመሳሰላል፣ በተለይ የመዝለያ እግሮቹ ከፊንጣ እግሮች አይለዩም። በ1963 ዓ.ም. ዶ/ር ዊሊያም ከይድ ምርመራ አድርጎ አንዲት ተባይ ዝንብ ደግሞ በተባዕቱ ዘፈን እንደምትሳብ፤ ዕጯንም እንድታስቀምጥበት ቦታውን ለማወቅ እንደሚጠቅማት አገኘ። የመርባትን ድምጽ በመጠቀም የአስተናጋጇን ቦታ ለምታገኝ የተፈጥሮ ጠላት ይህች መጀመርያ ምሳሌ ሆነች። ከዚያ በኋላ ብዙ የዋዝንቢት ወገኖች ይህችን ተባይ ዝንብ ሲሸክሙ በምድር ላይ ተገኝተዋል። በእስያ በተላይም በቻይና ዋዝንቢት ዝነኛ ለማዳ እንስሳ ሆኖ መያዙ እንደ መልካም እድል ይቈጠራል። የተያዘ ዋዝንቢት ሁሉ ማናቸውም አትክልት ወይም ሥጋ ቢሰጥ ይበላል። በአንዳንድ ባሕል ደግሞ ዋዝንቢት እንደ ምግብ ሊበላ ይችላል።
ዋዝንቢት ባለ ስንት አጽቄ ነፍሳት ነው?
የሦስት
12
ዐምደ ጽዮን ቀዳማዊ አጼ ዐምደ ጽዮን (የዙፋን ስም ገብረ መስቀል) ከ1314 እስከ 1344 ዓ.ም. የነገሡ ሲሆን በጥንቱ ዘመን ከተነሱ ነገሥታት ውስጥ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሰፋ ያለ አሻራ ትተው ካለፉት (ለምሳሌ፦ ዘርአ ያዕቆብ) ጎን ወይም በላይ ስማቸው ይጠቀሳል። አጼ ዐምደ ጽዮን የአጼ ይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅና የአጼ ወድም አራድ ልጅ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ይኩኖ አምላክ አዲሱን የሰሎሞን ስርወ መንግስት ቢመሰርቱም፣ በልጅ ልጆቻቸው የነበረው ፉክክርና አዲስ ከሚስፋፋው የእስልምና ሃይማኖት የሚሰነዘረው ጥቃት ስርዓቱን ስጋት ላይ የጣለ ነበር። አጼ አምደ ጽዮን ይህን ፉክክር በማስቆምና በዘመናት በማይደበዝዘው ጀግንነታቸው የኢትዮጵያን ድንበር ከሞላ ጎደል አሁን በሚታወቀው መልኩ በማስቀመጥ፣ የአዲሱን ስርወ መንግስት መሰረት በማጽናት እንዲሁም በማረጋጋት ዝናቸው በጥንቱ አለም ክአፍሪቃ ቀንድ እስከ አውሮጳ የተንሰራፋ ነበር።
የአጼ ዐምደ ጽዮን አባት ማን ናቸው?
የአጼ ይኩኖ አምላክ
184
መስከረም 22/2012 በአገሪቷ ወጥ የምርምር ስርአት ለመዘርጋት ብሄራዊ የሳይንስና ምርምር ካውንስል ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አስታወቀ። በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ የሳይንስና ምርምር አውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። በአውደ ጥናቱ ላይ ከከፍተኛ ትምህርት ፣ ከምርምር ተቋማትና ከሞያ ማህበራት የተውጣጡ ተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል። የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረ ማርያም እንደተናገሩት በአገሪቷ በሳይንስ ዘርፉ ብቃትና አቅም ያላቸው ተማራማሪዎች ቢኖሩም ምርምሮች ወጥ ባልሆነና ቅንጅት በጎደለው መልኩ እየተከናወኑ ይገኛል። በመሆኑም በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርትና የምርምር ተቋማት የሚከናወኑ ምርምሮችን በተቀናጀ መልኩ ለማከናወንና ምርምሮች ላይ ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ ብሄራዊ የሳይንስና ምርምር ካውንስል ማቋቋም ያስፈልጋል ብለዋል። የካውንስሉ መቋቋም በአገሪቷ ወጥ የሆነ የምርምር አሰራር ስርአት ለመዘርጋት፣ በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል፣ በጀትና የምርምር መሰረተ ልማቶችን በአግባቡ ለመጠቀም እንደሚያስችል ጠቁመዋል። በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር የሳይንስና የምርምር ዘርፍ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን ቢኖር በበኩላቸው ካውንስል ቢቋቋም የሳይንስ ዘርፍ ለአገሪቷ ዕድገትና ልማት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በሳይንስ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አገራት ተሞክሮም የካውንስሉን መቋቋም ጠቀሜታ ያረጋግጣል ብለዋል። የሚንስቴሩን አደረጃጀት የመፈተሽና በተገቢው መልኩ የማዋቀር ምርምሮችን ለመከታተል የሚያስችል የመረጃ ስርዓት የመዘርጋት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል። በአገር ወስጥ የሚታተሙ የምርምር ጆርናሎችን ጥራት ለማሳደግ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት የመዘርጋት እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል። የዩንቨርስቲ ኢንደሰትሪ ትስስር ያለመጎልበት፣ የምርምር ተቋማት ቅንጅት ክፍተት፣ በሳይንስ ፖሊሲና አገራዊ ልማት አጀንዳ ላይ የምሁራን ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆን በዘርፉ ከሚጠቀሱ ችግሮች መሆናቸውንም ዶክተር ሰለሞን አብራርተዋለ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም እንዳሉትም የሳይንስና ምርምር አውደ ጥናቱ ዋነኛ ትኩረት በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ ምርምሮች ጥራት፣ በጀት፣ ስርጭትና ውጤቶችን ለመዳሰስ ነው። በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን መለየትና በተለያዩ ተቋማት የሚከናወኑ ምርምሮች ተግባራዊነትን መዳሰስም የአውደ ጥናቱ ትኩረት መሆኑን አንስተዋል። ከአውደ ጥናቱ በሳይንስ ዘርፉ ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው ዘርፉን ለማሳደግ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረ ማርያም ያሉበት ኃላፊነት ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት
260
ቶማስ ጄፈርሰን ቶማስ ጄፈርሰን (ሚያዝያ 7 ቀን 1735 ~ ሰኔ 28 ቀን 1818 ዓ.ም.) ከየካቲት 26 ቀን 1793 እስከ የካቲት 25 ቀን 1801 ዓ.ም. ድረስ የአሜሪካ 3ኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኚያን ያቋቋሙት ጄፈርሰንም ነበሩ። ቶማስ ጄፈርሰን ከአባቱ ከፒተር ጄፈርስን እና ከእናቱ ጄን ራንዶልፍ ተወለዱ። ቶማስ በአሜሪካ አብዮት ጊዜ በ1768 ዓ.ም. ከእንግሊዝ ንጉሥ የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ ጻፉ። በኋላ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመርከብ ሃያላት ወደ አልጀርስ ላኩ፣ ከናፖሌዎን ደግሞ ሰፊ መሬት በሚሲሲፒ ወንዝ አቅራቢያ (የሉዊዚያና አቅራቢያ የተባለው) ገዝተው ነበር። ይህ ድርጊት የአሜሪካ ስፋት በሁለት እጅ አስፋፋ።
ቶማስ ጄፈርሰን ከመቼ እስከ መቼ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ሰሩ?
ከየካቲት 26 ቀን 1793 እስከ የካቲት 25 ቀን 1801 ዓ.ም.
58
ዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
ዩጋንዳ ከመቼ ጀምሮ ነበር በታላቁ ብሪታን ስትገዛ የነበረው?
ከ1894 እ.ኤ.አ.
340
ፋሽስት ቅዲስቲቱዋን ኢትዮጵያን ለማዋረድ ለመዝረፍና ለመግዛት ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ዝግጅቱን አጠናቆ በ1928 ዓም 300, 000 ሰራዊት 160 ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች 450 ታንኮች 2000 የመጉዋጉዋዣ መኪናዎችን በማሰማራት ድንበር አልፎ ጦርነት በመክፈት ከገጠር እስከ ከተማ ህዝቡን ያለ እርህራሄ ጨፈጨፈ። በዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ላይ የመጀመሪያውን ህይወት ያለዉን ነገር ሁሉ የሚያጠፋውን “ማስተርድ ጋዝ” የሚባል ኬሚካል መሳሪያ በመጠቀም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ፈጸመ። በዚያን ክፉ ቀን የነጻነትና የሀገር ትርጉም የገባቸው የቁርጥ ቀን ልጆች በየአካባቢያቸው ፋኖዎችን በመምራት የእብሪተኛዉን የፋሽ ስት ጦር መግቢያ መዉጫ በማሳጣት ኢትዮጵያ ዉስጥ በሰላም መኖር እንደማይችል ተስፋ አስቆርጠዉታል። ከነዚህ ነበልባል የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች መካከል ጠላትን በተከታታይ ዝርክርኩን አዉጥተው ከደቡብ ያሳደዱትና በመጨረሻው ዉጊያ ላይ ኢትዮጵያዊ በሚመስሉ የተሀሬ ስርጎ ገብ ባንዶች ቆሰለው የተያዙትና በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ዉዱ የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ልጅ ራስ ደስታ ዳምጠው ነበሩ።
ጣልያን ኢትዮጵያን ለመውረር ድጋሚ ሲመጣ ስንት ጦር ሠራዊት ነበረው?
300, 000
73
ውትድርና የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት ሀገሯን የመከላከል፣ የሀገሯን ፍላጎት የማስጠበቅ እና ፀጥታ አስጠባቂ ጥረቶችን የመደገፍ ግዴታ አለበት። ሠራዊቱ የምድር፣ የባህርና የአየር ኃይል አለው። ሠራዊቱ ከነፃነት ጀምሮ በሀገሯ ታሪክ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በተለያዩ ጊዜያት የውትድርና ጁንታዎች ሥልጣን በመያዝ አገሯን አስተዳድረዋል። የናይጄራያ ሠራዊት በፀጥታ ጠባቂነት ደረጃ ከ1995 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በላይቤሪያ (1997 እ.ኤ.አ.)፣ አይቮሪ ኮስት (ከ1997 እስከ 1999 እ.ኤ.አ. ) እና ሲየራ ሊዮን (ከ1997 እ.ኤ.አ. 1999 እ.ኤ.አ.) ተሰማርቷል። ምጣኔ ሀብት በግብርና ናይጄሪያ በዋናነት ለአለም የምታቀርበው ምርቶች በተለይ ካካውና ጎማ ናቸው። እንዲሁም ፔትሮሊየም ከሚያቀርቡት አገራት 12ኛ ነች። በተጨማሪ፣ የመኪና ሥራ ድርጅት (ኢኖሶን ተሽከርካሪ መፈብረክ) ይኖራል። መልከዓ ምድር ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ በጊኒ ባሕረ ሰላጤ ላይ ትገኛለች። የቆዳ ስፋቷ 923,768 ካሬ ኪ.ሚ. ሲሆን ከዓለም ፴፪ኛዋ ትልቅ ሀገር ናት። ድንበሯ 4,047 ኪ.ሜ. ርዝመት ሲኖረው ከቤኒን 773 ኪ.ሜ.፣ ኒጄር 1,497 ኪ.ሜ.፣ ቻድ 87 ኪ.ሜ.፣ ካሜሩን 1,690 ኪ.ሜ. ትዋሰናለች። በተጨማሪም 853 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ጠረፍ አላት። በናይጄሪያ ውስጥ ከፍተኛው ቦታ ቻፓል ዋዲ ተራራ ሲሆን ከፍታው 2,419 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ነው። የአገሯ ዋና ወንዞች ኒጄር እና ቤንዌ ሲሆን ወደ ኒጄር ደለል ይፈሳሉ።
ናይጄሪያ ለዓለም ከምታቀርባቸው ምርቶች ዋነኞቹ የትኞቹ ናቸው?
ካካውና ጎማ
404
ቅዱስ ላሊበላ ቅዱስ ላሊበላ በ 1101 አ.ም ትህሳስ 29 ቀን ከ እናቱ ከኬርዮርና ከአባቱ ዛንስዮም ላሰታ ቡግና ወረዳ ሮሃ ከተባለች ቦታ ከፍልፍል ቤተ መቅደስ ውስጥ ተወለደ በዚህ ፍልፍል ቤተ-መቅደስ ውስጥ እድገቱን አደረገ ስድስት አመት ሲሞላው ቤተ-መንግስት አባ ዳንእል የተባሉ መምህር ተቀጥረውለት ከ ፊደል እስከ ዳዊት አጠናቆ ከዚያም የተማረውን የዕሁፍ ጥበብ በቤተ ጎሎጎታ ደብረ ሲና በሚገኘው ከ ኪዳነ ምህረት መንበር ታቦት ዙሪያ ላይ እራሱ የተዓፋቸው የሚዐለይበት ዕሁፎቸች ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ላሊበላ 12 አመት ሲሞላው አባቱ ዘንሳዮም 40 አመት ነግሶ በተወለደ በ 76 አመቱ ከዚህ አለም በ ሞት ተለየ ወድያው ብዙም ሳይቖይ እናቱ ኬርዮርና በሞት ተለየች፡፡ ቅዱስ ላሊበላ በ እናቱ ና አባቱ ህልፈተ ህይወተ በደረሰበት ሀዘን የተነሳ ሁሉን ነገር ለመርሳት ና የትምህርት ፍላጎት ለሞሞላት ጉዞውን ወደ ጎጃም በማድረገ አለም ስላሴ ከተባለው ደብር ከመምህር ኬፋ ሃዲሳቱን አጠናቖ በመመረቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ በወቅቱም በኤትዮጵያ ላይ ነግሶ የነበረው ታላቅ ወንድሙ ቅዱሰ ገብረ ማሪያም ነበር ይህ እንዲህ እያለ በእህቱ ላይ እሱ ሊነግስ መሆኑ ቅናት አሳደረባት ቅዱስ ላሊበላ ሁሌም እሚጠጣው ባህላዊ መድሃኒት ውስጥ መርዝ በመጨመር ታስቀምጥለታለች አትሙት ያላት ነፍስ ግን የሃገሬውን በሃል ምክንያት አድርጎ ሳይቀመስ አይሰጥምና አብሮት የነበረው ዲያቖን የተቀመጠውን መድሃኒት ቀምሶ ወደ ነበረበት ጠረቤዛ ላይ አንዳሰቀመጠው ወድያውኑ ህይወቱ ታልፋለች ቅዱስ ላሊበላ ይህን ባየ ጊዚ እኔን ለማጥፋት የመጣው መድሃኒት የሌላውን ነፍስ አጠፋች በማለት የቀረውን መድሃኒት በመጠጣት ለሶሰት ለሊት እንደ ወደቀ ቀረ ከዚያም ነዋሪው ገንዞ ለመቅበር ሲዘጋጁ የሰውነቱ ሙቀት አልተለየውም ነበር ይሄን ጊዜ ወድያው ቅዱስ ላሊበላ ነቃ የተመለከቱት ሰዎች ተደናገጡ ከዚያም ይህ ሁሉ ነገር በእህቱ መደረጉ ያሳዘነው ቅዱስ ላሊበላ በመነሳት ጉዞውን ወደ ጫካ አደረገ ኑሮውንም ለረጅም አመት እዚያው አደረገ ይህ እንዲ እንዳለ ሚስት እምትሆነውን ሴት አገኝ ቤተሰቧን በማስጠየቅ በቤተክርስትያን ስርአት ተጋብተው ጥቂት አመት እንደቆዩ ጉዞውን እየሩሳሌም አደረገ ለተከታታይ 13 አመታትም ቆይታ በኋላ ወደ ባለቤቱ ተመልሶ ከወንድሙ ከ ቅዱስ ገብረ ማሪያም ጋር እርቅ በማውረድ ቅዱስ ገብረ ማሪያም ንግስናውን ለቅዱስ ላሊበላ በተወለደ በ57 አመቱ በማስረከብ ኑሮውን በገዳም አደረገ፡፡
የቅዱስ ላሊበላ ወላጆች እነማን ናቸው?
ከ እናቱ ከኬርዮርና ከአባቱ ዛንስዮም
40
ታሊየም የተሰኘው የሰሜን ኮሪያ መረጃ መዝባሪዎች ቡድን ሚስጢራዊ መረጃዎችን ሲመዘብር እንደተቆጣጠረው ማይክሮ ሶፍት አስታወቀ፡፡ መቀመጫው ሰሜን ኮሪያ እንደሆነ የታመነው ይህ መረጃ መዝባሪ ቡድን የመንግስት ሰራተኞችን ፣ የዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችን ፣ የኒውክሌር ሙያተኞችን እና የጥናት ተቋማንን ኢላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡ የመረጃ መዝባሪ ቡድኑ በዋነኝነት ኢላማ ያደረገው በአሜሪካ የሚገኙ ተቋማትን ሲሆን በጃፓንና ደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ተቋማንንም ኢላማ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡ ታሊየም በመጀመሪያ እይታ ትክክለኛ ሆነው የሚታዩ የኢሜል አድራሻዎችን  በመጠቀም   መረጃ ሲመዘብር ነበር ተብሏል፡፡ ማይክሮሶፍትም በአሁን ወቅት መረጃ መዝባሪ ቡድኑ የሚጠቀምባቸውን 50 የድር ጎራዎች መቆጣጠሩን የገለፀ ሲሆን በምሥራቃዊ ቨርጂኒያ አውራጃ በሚገኝ ፍርድ ቤት በጠለፋ ቡድን ላይ  ክስ መመስረቱን ገልጿል፡፡ ምንጭ፡-ሮይተርስ
ማይክሮሶፍት ታሊየም የመዘበራቸውን ስንት የድር መደቦችን ተቆጣጠረ?
50
414
ጎፋ የጎፋ ብሔረሰብ ቋንቋ ‹ጎፍኛ› ሲሆን፣ ቋንቋው ከማዕከላዊ ኦማዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ይመደባል። በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 363ሺ9 ነው፡፡ የጎፋ ብሔረሰብ በጋሞጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ብሔረሰቡ በዋናነነት በጎፋ ዙሪያ፣ ዛላ፣ ዑባ፣ ደብረፀሐይ እና መሎካዛ በሚባሉ ወረዳዎች ይገኛል፡፡ የብሔረሰቡ ዋና የሀብት መሠረት ጥምር ግብርና ሲሆን፤ የገቢ ምንጭ በሚያስገኙ ምርቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የጎፋ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ነባር ባህላዊ አስተዳደር አለው፡፡ ጥንት በጎፋ ግዛት ክልል ሥር የነበሩ አካባቢዎች በሰባት የካዎ (ነጉሥ) ግዛቶች ተከፋፍለው የተደራደሩ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ከአዎ የአስተዳደር ማዕከል ቤተ-መንግሥት(ጋዶ) ነበረው፡፡ ማዕከላዊ አስተዳደሩ የተለየ ሥልጣንና የሥራ ድርሻ ያላቸውን አስፈፃሚ አካላትን የያዘ ነበር፡፡ ካዎ (ንጉሥ)- የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮና ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሲሆን፤ ከእርሱ ቀጥሎ የሚገኙትን የሥልጣን አካላትንና አማካሪዎችን የመሾምና የመሻር ሥልጣን ነበረው። ጠንከር ያለ ውሳኔን የሚሹ ጉዳዮች የመጨረሻ ብይን የሚያገኙትም በካዎ ነበር፡፡ ብሔረሰቡ ጋብቻ የማፈጸመው የጎሣ አቻነትን፣ የሀብት ደረጃ በማስተያየትና የሥጋ ዝምድና አለመኖርን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ወንዶች ከ17-25፤ ሴቶች ደግሞ ከ14-19 ባለው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ይፈጽማሉ፡፡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ይገረዛሉ፡፡ ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ሴቷ ጥጥ ፈትላ አልባሳት ስታዘጋጅ ወንድም በፊናው የመኖሪያ ቤትና የራሱን የእርሻ ቦታ ያደራጃል፡፡ በብሔረሰቡ የተለያዩ የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች አሉት፡፡ በቤተሰብ ስምምነት፣ በጠለፋ የሚፈጸሙ ጋብቻዎች ኣሉት። በተጋቢዎችም ሆነ በቤተሰብ መካከል ያለመግባባት ሲከሰት ወይም የአግቢው ገቢ ሀብት አቅም ውሱንነት ሲከሰት ተጋቢዎቹ ሳይተዋወቁ የወንዱ አባት ሽማግሌ ይዞ የልጅቷን ቤተሰብ ከ1-2 ቀን ደጅ በመጥናት የሚፈጸም የሽምግልና ጋብቻም ኣለው። የምትክ ጋብቻ የሚባለው ደግሞ፤ ሚስት ከሞተች እህቷ ወይም የቅርብ ዘመዷ በምትክ ሚስትነት የምትሰጥበት የጋብቻ ኣይነት ነው፡፡ ወዶ ገብ ጋብቻ ደሞ ሌላው በብሔረሰቡ የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ ይኸውም፤ ሳታገባ የቆየች ሴት የራሷን ንብረት በመያዝ ወደ ወንዱ ቤት በፈቃዷ ሄዳ በመግባት የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ በብሔረሰቡ በበዓላት ቀናት ከሚዘጋጁት ምግቦች መካከል ሸንዴራ ይገኝበታል፡፡ ከበቆሎና ከገብስ ዱቄት የሚሠራ ሆኖ ቅመማቅመምና ቅቤ በማጣፈጫነት ገብቶበት የሚበላ ጥሩ ምግባቸው ነው፡፡ ቡላ በአይብ ጎመንና ቅቤ ገብቶበት የማሠራው ባጭራ የተባለው ምግባቸውና ቅንጬ በበዓላት ቀን ከሚያዘጋጇቸው ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የጎፋ ብሔረሰብ ህዝብ በ1999ዓ.ም በተደረገው የቤት ቆጠራ ምን ያህል ነበሩ?
363ሺ9
112
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል። በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። የገብላዊ ልጆች የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል። ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው። ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው። ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
ናጊብ ማህፉዝ መጠሪያ ስሙን ያገኘው ከየት ነው?
አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ
146
አዳማ /ኢዜአ/መስከረም 23/2012 የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ስምንት የምርምርና የልህቀት ማእከላት እያደራጀ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሾመ አብዶ ለኢዜአ እንደገለጹት ግንባታቸው ከ90 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው የምርምር ፓርኮችንና የልህቀት ማዕከላትን በመሳሪያ ለማደራጀት 86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት ተመድቦ እየተሰራ ነው ብለዋል። በዚህም ሁለት ሊትል ስታር የተባሉ ሳተላይቶች በደቡብ ኮሪያና ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች በመገጣጠም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የፋርማቲካል የልህቀት ማእከሉ የባህል መድኋኒቶችን በመቀመምና በምርምር በማዘጋጀት ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ምርት እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ተሾመ በተለይም በባህላዊ መድኋኒቶች ዙሪያ በትኩረት የምርምር ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል። የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በ19 የትምህርት ፕሮግራሞች ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በኤክስቴሽን ፕሮግራም ተቀብሎ ማስተማር ላይ ይገኛል።
የአዳማ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በስንት ትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እያስተማረ ነው?
በ19 
549
ቶክ ፒሲን ቶክ ፒሲን (Tok Pisin) በስሜን ፓፑዋ ኒው ግኒ የሚናገር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲቃላ ነው። ከእንግሊዝኛ ስዋሰው በጣም ተለውጧልና ዛሬ እንደ ራሱ ቋንቋ ይቆጠራል። የፓፑዋ ኒው ግኒ መደበኛ ቋንቋ ሆኖ በ120,000 ያሕል ተናጋሪዎችና በ4 ሚሊዮን እንደ 2ኛ ቋንቋ ይነገራል። የቶክ ፒሲን አጀማመር በፓሲፊክ ውቅያኖስ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ የተላያዩም ልሣናት የሚችሉ ሰራተኞች አንድላይ ለአትክልት ስፍራዎች ሲሰሩ ነበር። ብዙ ጊዜ የእነዚህ ሰራተኞች የጋራ ቋንቋ ጥቂት ቀላል እንግሊዝኛ ቃሎች ብቻ ነበር። ስለዚህ አዲስ "የቋንቋ ዲቃላ" ተወለደ። ከእንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከደሴተኞቹ ቋንቋዎች፣ ከጀርመንኛ፣ ወይም ከፖርቱጊዝ ነበር። ይህ ቋንቋ "ፕጅን" ተብሎ አሁን ሶስት ተወላጆች አሉት፣ እነሱም ቢስላማ (በቫኑዋቱ) ፒጂን (በሰሎሞን ደሴቶች) እና ቶክ ፒሲን ይባላሉ። ቶክ ፒሲን በአንዳንድ ትምህርት ቤት የትምህርት ቋንቋ ነው።
ቶክ ፒሲን በሁለተኛ ቋንቋነት በምን ያህል ሰዎች ይነገራል?
በ4 ሚሊዮን
156
አዳም ረታ አዳም ረታ ልቦለድና ግጥም በአማርኛ የሚጽፍ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነው። አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በትምህርት አለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው ልቦለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት። ከተደራሲው ጋር የተዋወቀበት እና በኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ተከታታዮችና አንባቢዎች ልብ ውስጥ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠበት “አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት የታተመው በ1977 ዓ.ም ነው። (በዚህ መድብል ውስጥ አራት ስራዎችን አዋጥቷል፡ “ድብድብ”፣ “ዕብዱ ሺበሺ”፣ “ሲሮኮ” እና “ሲፊንክስ”) ሜጋ አሳታሚ ድርጅት በ1990 ዓ.ም ባሳተመው “ጭጋግና ጠል” የአጭር ታሪኮች ስብስብ “ዘላን” የተባለው ልቦለዱ ታትሟል። እነዚህ ሁለቱ ከሌሎች ደራሲዎች ስራዎች ጋር የታተሙለት ስለሆነ እንደ ወጥ ሳይቆጠሩ ነው ከላይ የሰፈረው የተባለው። በ1981 ዓ.ም በኩራዝ አሳታሚ የታተመው “ማህሌት” የደራሲው የመጀመሪያ ወጥ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መፅሀፍ ነው። በሻማ ቡክስ በ1997 ዓ.ም የታተመው “ግራጫ ቃጭሎች” እንደ ብሉይ (classic) ሥራ ሊታይ የሚችልና የደራሲው ልዩ ብቃት የታየበት ወጥ ረጅም ልብወለድ ነው። በ2001 ዓ.ም ሁለት ልዩ ስራዎች ይዞ የቀረበው አዳም፡ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነው “አለንጋና ምስር” እና እርስ በርሳቸው በቀጭን የታሪክ ክር የሚገናኙ ልብወለዶች (ኖቬላዎች) ያካተተው “እቴሜቴ ሎሚ ሽታ” ለአንባቢያን አበርክቷል። ይህ የአጻጻፍ ስልቱ ሕጽናዊነት የሚባል ሲሆን ደራሲው በሌሎቹ መጻሕፍቱም ውስጥ በስፋት ተጠቅሞበታል፡፡ በቀጠሉት ሦስት ዓመታት በየዓመቱ አንዳንድ መፅሐፍ ለአንባቢያ ያደረሰ ሲሆን በ2002 ዓ.ም “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር”፣ በ2003 ዓ.ም “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” እና በ2004 ዓ.ም “ሕማማት እና በገና” ታትመው ለንባብ በቅተዋል። “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር” በተሰኘው መፅሀፉ ድንቅ የፋንታሲ (“ፈንጠዚያ”) ሥራዎች የተካተቱ ሲሆን በ”ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” ለመጀመሪያ ጊዜ መቼቱን ከሀገር ውጭ በማድረግ የውጭውን ሕይወት በስሱ የዳሰሰ ሲሆን ከሌሎቹ ስራዎቹ በተለየ መልኩ ስለሀገራችን ፖለቲካ ወጣ-ገባ መንገድ በታዛቢ አይን ምልከታው፣ ትውስታውን … አስፍሯል፡፡ ሕማማትና በገና የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ ሲሆን ለየት ያለ ቅርፅ ያላቸው አንዳንድ ልቦለዶች ተካተውበታል። ፍልስፍናውና ስልቱ ሕፅናዊነት በሚል ስያሜው ይፋ ሆኗል።
“እቴሜቴ ሎሚ ሽታ” በተሰኘው መፅሀፍ ላይ ምን አይነት ያጻጻፍ ስልት ተጠቅሟል?
ሕጽናዊነት
974
ከተጠመቀ በኋላ ባስሊዮስ በ፫፻፵፱ ዓ ም ወደ ፍልስጤም ፣ ግብፅ ፣ ሶርያ እንዲሁም ሜዞፖታሚያ የመመንኮስንና የገዳማዊነት ትምህርት ለማጥናት ሄደ ። ያለውን ሐብት በሙሉ ለድሆች አድሎ እንደጨረሰ ወደ ምነና በፖንተስ ኒዎሢዛርያ (በዘመኑ አጠራር ኒክሳር ቱርክ) ቤተክርስቲያን ገባ ። ባስልዮስ ይህን የገዳማዊ ኑሮ ቢያከብረውም ለሱ እንዳልተጠራ ተረዳ ። የሴባስቴው እዩስታቴየስ እጅግ የታወቀ መኖክሴ በፖንተስ አካባቢ ባስሊዮስን ያስተምረው ነበር ። በዶግማ ላይ ግን ይለያዩ ነበር ። ይልቁን ባስሊዮስ በመንፈሳዊ ማኅበራዊ ኑሮ ተሳበና በ፫፻፶ በአስተሳሰብ ከእሱ ጋር የሚመሳሰሉትን የክርስትና ደቀመዝሙሮች ወንድሙን ጴጥሮስን ጨምሮ ማሰባሰብ ጀመረ ። አንድላይ ሆነው በቤተሰቡ ርስት ላይ አኔዚ አጠገብ ገዳም መሠረቱ ። በጣም ግልፅ ለማረግ (በዘመኑ አጠራር ሶኑዛ ወይም ኡሉኮይ የዬሲሊርማክ ባሕርና የኬልኪት ባሕር የሚገናኙበት ቦታ ላይ ማለት ነው ።). ባልተቤትዋ እናቱ ኤሚልያ ፣ እህቱ ማክሪናና ሌሎች ሴቶችም ራሳቸውን ለቅዱስ ተግባር መጽዋት በማድረግ ከባስሊዮስ ጋር ተባበሩ ። (ይህን ማኅበረሰብ የመሠረተችው እህቱ ማክሪና ናት የሚሉም አሉ) ። ቅዱስ ባስሊዮስ እዚህ ባታ ላይ ስለ ገዳማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ጽፎ ነበር ። ጽሁፉ ግን ለምሥራቃዊ ክርስትና ዕድገት ከፍተኛ ምክኒያት ሆንዋል. በ፫፻፶ዓ ም ባስሊዮስ ጉዋደኛውን ጎርጎሪ (ግሬጎሪ) የናዚያነስን በአኔዚ እዲቀላቀል ጋበዘው። ጎርጎሪዮም (ግሬጎሪ) እንደመጣ በኦሪጄን ፊሎካሊያ የኦሪጄን ሥራዎች ስብስብ ላይ ጥናት ማድረግ ጀመሩ ። ከዚህም በኋላ ግሬጎሪ ወደ ናዚያነስ ወደ ቤተሰቦቹ ለመመለስ ወሰነ ። ባስሊዮስ የቁንስጥጢናውን የሊቃውንት ጉባዔን ፫፻፶፪ ዓ ም ተሳተፈ ። በመጀመሪ ከኤዩስታቲየስና ከሆሞወሲያንስ ወገነ ፣ ግማሽ አራዊያን የሆነ የመናፍቅ ቡድን ፣ ወልድ ከአብ ጋር ተመሳሳይ እንጂ አንድ ባሕርዪ ወይም አካል አይደለም ብለው ከሚያስተምሩ ጋር ማለት ነው። ሆሞወሲየንስ የአውኖሚየስን አርያኒዝም ይቃወማሉ ግን ደግሞ ከኒቂያ ጉባዔ ተከታዮች ጋር የሥላሴን አንድነት "ሆሞወሲዮስ" ከሚያስተምሩት ጋር መተባበር አይፈቅዱም ። በዚህም ቢሆን በዚያ የባስሊዮስ ጳጳስ ዲያኒየስ የቄሣሪያው የሚከተሉት የቀድሞውን ንቂያ ስምምነት ነበረ ። ባስሊዮስም ወዲያውኑ ሆሞወሲያንስን ጥሎ እንዲየውም ጠንካራ የኒቂያ ጉባዔ ውሳኔን ተከታይ ሆነ።
ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ የምንኩስናን ትምህርት ለመማር ወደ የትኞቹ ሀገራት ሄደዋል?
ወደ ፍልስጤም ፣ ግብፅ ፣ ሶርያ እንዲሁም ሜዞፖታሚያ
26
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት ኡጋንዳ ገብተዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በፕሬዝዳንት ዮዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ኡጋንዳ መግባታቸውን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለከተው፡፡ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ባለፈው ጥር ወር ላይ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ለ6ኛ ዙር ሀገሪቱን ለመምራት ዛሬ ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኡጋንዳ የተገኙበት ምክንያት ምንድንነው?
በፕሬዝዳንት ዮዌሪ ካጉታ ሙሴቪኒ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት
60
አሸናፊ ከበደ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አዲስ አበባ ግንቦት ፰ ቀን ፲፱፻፴ ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ግራዝማች ከበደ አድነው ሲሆኑ ክልጅነታቸው ጀምሮ የሙዚቃ ስሜትንና ፍቅር ያሳደሩባቸው እናታቸው ወይዘሮ ፋንታዬ ነከሬ ነበሩ። አያታቸው ሊቀመኳስ አድነው ጎሹ ደግሞ የአድዋ አርበኛ እናየንግሥት ዘውዲቱም ታማኝ አማካሪ እንደነበሩ ይነገራል። የሙዚቃ ፍቅርን ገና በልጅነታቸው ያሳደሩባቸው እናታቸው ሲሆኑ ታዳጊው አሸናፊ ገና የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሳሉ እኒህ የሚያፈቅሯቸውና ዕድሜ ልካቸውን በኀዘን የሚስታውሷቸው እናታቸው ሞተውባቸዋል። መሠረታዊ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኮከበ ጽባሕ) ካጠናቀቁ በኋላ በሐረር የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኒው ዮርክ ክፍለ-ሀገር ከሚገኘው የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ፣ “ኢስትማን የሙዚቃ ትምህርት ቤት” በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፤ የያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤትን መሠረቱ። የዚሁ ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው ዳይሬክቶር ከመሆናቸውም ባሻገር በአዲስ አበባው የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር (ወ.ወ.ክ.ማ Y.M.C.A.)፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርሓ-ዕውራን ትምህርት ቤት እና በመሳሰሉ የወጣቶች ማኅበራት እየተገኙ የሙዚቃ ትምህርት ይሰጡ ነበር።
የፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አያት ማን ይባላሉ?
ሊቀመኳስ አድነው ጎሹ
148
ዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
በዩጋንዳ የአቴሶ ቋንቋ በተናጋሪዎች ብዛት በስንተኛነት ይገኛል?
በሁለተኛነት
1,464
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል። በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። የገብላዊ ልጆች የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል። ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው። ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው። ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ማን ይባላል?
ናጊብ ማህፉዝ
168
የቅኝ ግዛት ጊዜ በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠረች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ. ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ፳ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተቆጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር። ነፃነትና የእርስ በርስ ጦርነት አንጎላ ነጻነቷን በኅዳር ፲፱፻፷፰ ከተቀዳጀች በኋላ ግን ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሚቀጥል የእርስ በርስ ጦርነት ገጠማት። ይህ ውጊያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞትና ስደት አብቅቷል። ከአልቮር ስምምነት በኋላ ሶስቱ ትልቅ የትግል ግንባሮች የሽግግር መንግሥትን ለማቋቋም በጃኑዋሪ 1975 እ.ኤ.አ. ተስማሙ። ነገር ግን በሁለት ወራት ውስጥ እነዚህ ግንባሮች ወደ ውጊያ ተመልሰው አገሯ ወደ ክፍፍል እያመራች ነበር። በዚህ ወቅት የቀዝቃዛው ጦርነት ኃያል አገራት የነበሩት የሶቭየት ሕብረትና አሜሪካ አንዱን ወይም ሌላውን ወገን ደግፈው ወደ ጦርነቱ ገብተዋል። ሌሎችም እንደ ፖርቱጋል፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካና ኩባ የመሳሰሉት ሀገራትም ከማገዝ ወደ ኋላ አላሉም። ፖለቲካ የአንጎላ የሕግ አስፈፃሚ አካል ፕሬዝዳንቱን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱንና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱን ያጠቃልላል። ለብዙ ዓመታት አብዛኛው ሥልጣን በፕሬዝዳንቱ እጅ ነው ያተኮረው። የ፲፰ቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። የ1992 እ.ኤ.አ. ሕገ መንግሥት የመንግሥቱን አወቃቀርና የዜጎችን መብቶችና ግዴታዎች ይዘረዝራል። የሀገሩ ሕግ ተርጓሚ አካል የፖርቱጋል ሥርዓትን ይከተላል። ጦር ኃይል የአንጎላ ጦር ኃይሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ሲሆኑ በሦስት ይከፈላሉ። እነዚህም ምድር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና አየር ኃይል ናቸው። የሀገሩ ጠቅላላ ሠራዊት ፻፲ ሺህ ይሆናል። የጦር ኃይሉ ንብረቶች መካከል በሩሲያ የተሰሩ ተዋጊ፣ ቦምብ ጣይና አጓጓዥ አውሮፕላኖች ይገኛሉ። አንዳንድ የጦር ኃይሉ ክፍሎች በኮንጎ ኪንሻሳና ኮንጎ ብራዛቪል ተመድበዋል።
የአንጎላ ጦር ሰራዊት ብዛት ምን ያህል ይሆናል?
፻፲ ሺህ
1,327
በጀት በጀት ማለት ለወደፊቱ የሚመጣን ገቢና ወጪ የሚተነብይ የንዋይ/ገንዘብ እቅድ ነው። በዚህ እቅድ ውስጥ ቁጠባ፣ ብድር እና ወጪ ይካተታሉ ። ግለሰቦች ወይንም ቢዝነሶች ገቢና ወጪያቸው ሲመረመር ከሞላ ጎደል ቋሚ ሆኖ ስለሚገኝ የበጀት ጥቅም ከዚህ ይመነጫል። ማለት፣ ቋሚ ገቢ ወጪ፣ ለወደፊት ይሚሆነን ለመተንበይ አመቺ ነው። ተንብዮ በበጀት መመራት ግለሰቦብ በገንዘባቸው/ንዋያቸው ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ያደርጋል። አላስፈላጊ ወጭወችን ለመለየት እና በአቅም መኖርን ለማወቅ ይረዳል። የበጀት ዋናው ጥቅም አንድ ግለሰብ በራሱ ገቢና ወጪ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖረው ማስቻሉ ነው። ስለሆነም ግለሰቦች ዕዳ ውስጥ መግባት ሲጀምሩ በቶሎ እንዲያውቁ ይሆናሉ። ስለሆነም ችግሩ ከመባባሱ በፊት አስቀድመው እርምጃ ለመውሰድ ይችላሉ። አንድ ግለሰብ ዕዳ ውስጥ እየገባ መሆኑን መረዳት ሲጀመር መጀመሪያውኑ የዕዳውን አይነት መለየት አስፈላጊ ነው። ቅድሚያ ትኩረት አግኝተው መከፈል ያለባቸው እማይለወጡ ዕዳወች (ምሳሌ ሞርጌጅ፣ የቤት ኪራይ ..) እና ቀስ ብለው ሊከፍሉ የሚችሉ ተለዋዋጭ ዕዳዎች (ምግብ፣ የኤሌክትሪክ፣ ውሃ ና ሌሎች በጥንቃቄ ሊቀነሱ የሚችሉ ቢሎች) ተለየተው ሊታወቁ ይገባል። ዕዳዎቹ ከተለዩ በሗላ፣ ዕዳዎቹን ለማስወገድ መንገድ ማበጀት ተገቢ ነው። ለዚህ ተግባር እንዲረዳ «በደህና ጊዜ» በትንሽ በትንሹ ማጠራቀም ጥሩ ነው። ነገር ግን ይህ ተደርጎ ካልሆነ፣ ቀሪ እዳን ቀስ በቀስ ለመክፍል የሚያስችል ስምምነት ከዕዳ-ሰጪው ጋር መግባት ጥሩ ነው። ባንኮች የአንድ ግለሰብ ዕዳ ባለቤት ከሆኑ፣ ግለሰቡን ለመርዳት ፍላጎት ይኖራቸዋል፣ ምክንያቱም ከርሱ ነውና ገንዘብ የሚያገኙት። ለዚህ ተግባር እንዲረዳ ኮንሶሊዴሽን (ሁሉን ዕዳን በአንድ ላይ መሰብሰብ) እና ሪፋይናንሲንግ (ብድርን፣ በተራዘመ ጊዜ እንዲከፍሉ ማስቻል) የሚባሉ ሁለት መሳሪያወችን ባንኮች ይጠቀማሉ። እኒህን ማግኘት እዳ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ ይረዳሉ። ሆኖም እኒህ እድሎች ካልተገኙ ዴቢት ስፔሻሊስት የተሰኙ መካሪዎችን ማነጋገር ይቻላል።
አንድ ግለሰብ ዕዳ ውስጥ እየገባ መሆኑን መረዳት ሲጀመር መጀመሪያ ምን ማረግ አለበት?
የዕዳውን አይነት መለየት
504
ቺኑዋ አቼቤ በሙሉ ስሙ ሲጠራ አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ይሰኛል። ምናልባትም ናይጄሪያ ካሉዋት ምርጥ ፀሃፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የሚሰለፍ ሳይሆን አይቀርም። በ1930 እ.ኤ.አ. ኦጊዲ በተባለች የናይጄሪያ ግዛት ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ ተወለድ። በ1953 እ.ኤ.አ. ከለንደን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ለአቼቤ ድንቅ ሥራ የተባለለት "Things Fall Apart" 50 ወደሚሆኑ የአለም ቁዋንቁዋዎች የተተርጎመ ሲሆን ወደ 10,000,000 ቅጂዎች እንደተሸጡለት ይነገራል። አቼቤ ከአፍሪካ ፀሃፍት ሁሉ ሥራው በበዙ ቁዋንቁዋዎች በመተርጎም ክብረ ወሰኑን እንደያዘ ነው። ብዙዎችም ይኸው ድርሰቱ በአለም እስከዛሬ ከተደረሱ ምርጥ ልበ-ወለዶች መካከል እንደሆነ ይስማማሉ። አቼቤ ከ30 ከሚበልጡ ዩኒበርስቲዎች የክብር ዶክትሬት የተቀበለ ሲሆን ብዙ ሽልማቶችንም ከተለያዩ ድርጅቶች አግኝቷል። ይሁንና እስከ አሁን ድረስ የኖቤል ሽልማት ለማግኘት አልታደለም። ይኸውም በብዙው ጽሁፉ የመራቡን አለም ዘረኛነት የሚተች በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል። በ1990 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ከወገቡ በታች መንቀሳቀስ የተሳነው ሲሆን ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኘው የባርድ ኮሌጅ የቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ፕሮፌሰር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ከስንት ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተቀበለ ሲሆን ብዙ ሽልማቶችንአግኝቷል?
ከ30 ከሚበልጡ ዩኒበርስቲዎች
447
አፋር (ክልል) አፋር ክልል (ክልል 2) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ዋና ከተማው ሰመራ ሲሆን የቀድሞዋ ከተማ ግን አሳይታ ነበረች። 96,707 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሸፍን በ1999 እ.ኤ.አ. የሕዝብ ብዛቱ 1,188,000 ነው። የድንቅ ነሽ ወይም ሉሲ አጽም በአፋር ክልል ውስጥ በ, 1967 (Nov. 24, 1974 እ.ኤ.አ.) ነው የተገኘው። በማርች 5, 2005 ደግሞ ሌላ 3.8 ሚሊዮን ዓመት የሚገመት አጽምም በዚሁ ክልል ተገኝቷል።
የአፋር ክልል የበፊቷ ዋና መዲና ማን ነበረች?
አሳይታ
97
ሰቆጣ ሰቆጣ ከ1956 ጀምሮ የዋግ አውራጃ ማዕከል እና የሰቆጣ ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከሰቆጣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የውቅሮ መስቀል ክርስቶስ አለት ውቅር ቤ.ክ. ይገኛል። በዚሁ ቤተ ክርስቲያን ላስታን ከሰቆጣ ሆነው ያስተዳደሩ ዋግሹሞች ደረቅ ቅሪቶች ይገኛሉ። ከአክሱም መዳከም በኋላ በአረብ ጸሐፊዎች ዘንድ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማነት ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰውኩባር የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ገናና ማዕከል ሰቆጣ እንደነበር በታሪክ ግንዛቤ አለ። ስለሆነም ይመስላል፣ ላስታን በዋግ ሹም ማዕረግ ያስተዳደሩ ገዢዎች መቀመጫቸው ሰቆጣ ነበር። ከጥፋት በተረፉ መዝገቦች ዘንድ ሰቆጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅሶ የምናገኘው በ1738ዓ.ም. ሲሆን፣ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ወደ ላስታ ባደረጉት ዘመቻ ሰቆጣ ውስጥ በዋግ ሹም ነዓኩቶ ለአብ (የዋግ ሹም ቴዎድሮስ አባት) ቤት ለ5ቀን እንዳረፉ ዜና መዋዕላቸው በማተቱ ነው ። ከዚያም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ የአውሮጳ ተጓዦች ሰቆጣን ሲጎበኙ፣ ዋልተር ፕላውዴን ለምሳሌ በኢትዮጵያ ከሚገኙ 5 ብቻ ነጋድራሶች አንዱ በሰቆጣ ይገኝ እንደነበር መዝግቧል። ከዚያም በ1800ዎቹ መጨረሻ ሰቆጣን የጎበኘው ኤ.ቢ.ዋይልድ ሰቆጣን የላስታ ዋና ከተማ አድርጎ ሲጠቅስ፣ የሰቆጣ ቤተ መንግስት ባለ ሶስት ፎቅና በ1650ዎቹ የተገነባ እንደነበር ያትታል። ቤተ መንግስቱን የሰሩት የፋሲል ግቢን አናጺዎ እደሆኑም መላምት ያቀርባል። ይሄው የአውሮጳ ተጓዝ፣ በ1880ዎቹ የሰቆጣ ገበያ ከአካባቢው ካሉት ሁሉ ግዙፉ እንደነበር ፣ የዝሆን ጥርስ እና በቅሎ ገበያው የደራ እንደነበር፣ እንዲሁም 21፣000 በሬዎች፣ 2፣900 ላሞች፣ 10ሺህ ፍየሎች፣ 1፣500 በጎች በየአመቱ ለግብይት ይቀርቡበት እንደነበር ሳይጠቅስ አላለፈም። ጥር 2፣ 1929 ጣሊያኖች በሰቆጣ ላይ የመርዝ ጋዝ ቦምብ እንደጣሉ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
ከ1956 ጀምሮ የዋግ አውራጃ ማዕከል እና የሰቆጣ ወረዳ ዋና ከተማ ማን ናት?
ሰቆጣ
0
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ተፈሪ መኰንን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺ እመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ፲፰፻፺፱ የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. የሐረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ። የሐረርጌ አገረ ገዥ ሲሆኑ ፣ በጣም ብዙ ሺህ ተከታዮች ነበሩዋቸውና ልጅ እያሱን ከእንደራሴነት በኅይል እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ተፈሪን ከሐረር አገረ ገዥነት እንዳይሽሯቸው የሚል ስምምነት ተዋዋሉ። ዳሩ ግን እያሱ ሃይማኖታቸውን ከክርስትና ወደ እስልምና እንደቀየሩ የሚል ማስረጃ ቀረበና ብዙ መኳንንትና ቀሳውስት ስለዚህ ኢያሱን አልወደዱዋቸውም ነበር። ከዚህም በላይ እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት ስምምነታቸው እንግዲህ ተሠርዞ ተፈሪ ደግሞ ለወገናቸው ከስምምነቱ ተለቅቀው በዚያን ጊዜ እሳቸው እያሱን ከእንደራሴነት አስወጡ። እንግዲህ በ፲፱፻፱ ዓ.ም. መኳንንቱ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ሆነው አድርገዋቸው ተፈሪ ደግሞ እንደራሴ ሆኑ። ከዚህ ወቅት ጀምሮ ተፈሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙሉ ሥልጣን ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. የንጉሥነት ማዕረግ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ አርፈው ንጉሠ ነገሥት ሆኑና ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ብዙ የውጭ ልዑካን በተገኙበት ታላቅ ሥነ-ሥርዓት ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው እሳቸውና ሚስታቸው እቴጌ መነን ዘውድ ጫኑ። በንግሥ በዓሉ ዋዜማ ጥቅምት ፳፪ ቀን የትልቁ ንጉሠ-ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለዘውድ በዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት ፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ። ለንግሥ ስርዐቱ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገር ልኡካን ከየአገራቸው ጋዜጠኞች ጋር ከጥቅምት ፰ ቀን ጀምሮ በየተራ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ስለነበር ሥርዓቱ በዓለም ዜና ማሰራጫ በየአገሩ ታይቶ ነበር። በተለይም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት በጃማይካ አንዳንድ ድሀ ጥቁር ሕዝቦች ስለ ማዕረጋቸው ተረድተው የተመለሰ መሢህ ነው ብለው ይሰብኩ ጀመር። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ፊተኛው ስማቸው «ራስ ተፈሪ» ትዝታ ራሳቸውን «ራስታፋራይ» (ራሰተፈሪያውያን) ብለዋል።
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መቼ ተወለዱ?
ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም.
112
ሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡ ከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው። ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው። ሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው። የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮም፣ ዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ። የአገር ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከብዙ ኗሪ ቋንቋዎች 11ዱ በተለይም ዎሎፍኛ አገራዊ ዕውቅና አላቸው። ሌሎቹ ባላንታኛ፣ ማንዲንክኛ፣ ፑላርኛ (ፉላኒኛ)፣ ሰረርኛ፣ ሶኒንክኛ፣ ኖንኛ፣ ማንካኛኛ፣ ማንጃክኛ፣ ጆላኛ እና ሀሣኒያ አረብኛ ናቸው። ፖርቱጊዝኛም በትምህርት ቤት ይማራል፣ የካቦ ቨርዴ እና የጊኔ-ቢሳው ኅብረተሠቦችም ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል ይናገራሉ። ከሴኔጋል ሕዝብ 94% የእስልምና አማኞች፣ 5% ክርስትና (ባብዛኛው ካቶሊክ)፣ 1% የኗሪ አርመኔነት ተከታዮች ናቸው። የመንግሥት ሃይማኖት የለውም። በሴኔጋል ልማዳዊ ባሕል ግሪዮት የተባሉ ሽማግሎች ታሪኮቻቸውን በአፍ ቃል ይደግማሉ። ሴኔጋል ለሙዚቃዊ ስልቶቹ ይታወቃል፤ በተለይ የሚወድደው ዘመናዊው ስልት ምባላክስ ተብሏል። በሴኔጋል አበሳሰል በተለይ አሣ፣ ዶሮ፣ በግ፣ አተር፣ ዕንቁላል፣ በሬ ይጠቀማሉ፤ እስላም አገር እንደ ሆነው መጠን ግን አሳማ አይበላም። ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ስኳር ድንች፣ ምስር፣ ጥቁር-ዐይን አተር ደግሞ በሴኔጋል አበሳሰል በሰፊ ይገኛሉ። በእስፖርት በኩል፣ ከሁሉ የሚወደደው ባህላዊው የሴኔጋል ትግል ግጥሚያ ሲሆን፣ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ ደግሞ እጅግ ይወደዳሉ።
በሴኔጋል ዳኞች የሚሾሙት በማን ነው?
በፕሬዝዳንቱ
184
በ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ (400) ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር። የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ኛው እና በ ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ. ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ። ከዚያም ለብዙ ዘመናት የሰለሞናዊው መንግስት ከጠለ።
በደአማት መንግስት ላይ ተጽእኖ የነበራቸው እነማን ናቸው?
በየመን የሚኖሩት ሳባውያን
103
ታሊየም የተሰኘው የሰሜን ኮሪያ መረጃ መዝባሪዎች ቡድን ሚስጢራዊ መረጃዎችን ሲመዘብር እንደተቆጣጠረው ማይክሮ ሶፍት አስታወቀ፡፡ መቀመጫው ሰሜን ኮሪያ እንደሆነ የታመነው ይህ መረጃ መዝባሪ ቡድን የመንግስት ሰራተኞችን ፣ የዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችን ፣ የኒውክሌር ሙያተኞችን እና የጥናት ተቋማንን ኢላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡ የመረጃ መዝባሪ ቡድኑ በዋነኝነት ኢላማ ያደረገው በአሜሪካ የሚገኙ ተቋማትን ሲሆን በጃፓንና ደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ተቋማንንም ኢላማ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡ ታሊየም በመጀመሪያ እይታ ትክክለኛ ሆነው የሚታዩ የኢሜል አድራሻዎችን  በመጠቀም   መረጃ ሲመዘብር ነበር ተብሏል፡፡ ማይክሮሶፍትም በአሁን ወቅት መረጃ መዝባሪ ቡድኑ የሚጠቀምባቸውን 50 የድር ጎራዎች መቆጣጠሩን የገለፀ ሲሆን በምሥራቃዊ ቨርጂኒያ አውራጃ በሚገኝ ፍርድ ቤት በጠለፋ ቡድን ላይ  ክስ መመስረቱን ገልጿል፡፡ ምንጭ፡-ሮይተርስ
ታሊየም የተባለው የሰሜን ኮሪያ ቡድን ምስጢራዊ መረጃዎችን ሲመዘብር የያዘው ማን ነው?
ማይክሮ ሶፍት
65
ዋዝንቢት ዋዝንቢት የሦስት አጽቄ አይነት ነው። የፌንጣና የአንበጣ ዘመድ ነው። ሁለንተናው ትንሽ ለጥ ይላል፤ ረጃጅም አንቴኖችም አሉት። ዋዝንቢት የሚታወቀው በሚያሰማው ድምጽ ነው። ድምጽ ማውጣትና ማሰማት የሚችለው አውራው ዋዝንቢት ብቻ ነው። የተባዕቱ ዋዝንቢት ክንፍ እንደ "ሚዶና ሞረድ" የሚመስል ፍርግርግ ነው። ክንፎቹን በማፋተግ ድምጽ ይፈጥራል፤ የድምጹ ቅላፄ እንደየ ዋዝንቢቱ ወገን ይለያያል። ሁለት ዓይነት የዋዝንቢት ዘፈኖች አሉ፤ የጥሪ ዘፈንና የመርቢያ ዘፈን ናቸው። የጥሪ ዘፈን ዓላማ አንስት ዋዝንቢ ለመሳብ ሲሆን ረጅምና ከፍተኛ ድምፅ ነው። ለመራባት ሲባል የሚዘፈነው ድምፅ አንስቲቱ እንስቲቱን ለማቅረብ ስለሆነ ቀስ ያለና ለስላሳ ነው። አንስት ዋዝንቢት መርፌ የሚመስል ረጅም የዕንቁላል መጣያ አላት። በምድር ላይ 900 የሚያሕሉ የዋዝንቢት ዝርያዎች ይገኛሉ። አንዳንድ ዝርያ ሣርና ተክል ብቻ ሲበላ፣ ሌሎች ዝርዮች ደግሞ ነፍሳት ያድናሉ። ዋዝንቢት ሌሊት የሚነቃ ፍጥረት ነው። ብዙ ጊዜ ከፌንጣ ጋር ይመሳሰላል፣ በተለይ የመዝለያ እግሮቹ ከፊንጣ እግሮች አይለዩም። በ1963 ዓ.ም. ዶ/ር ዊሊያም ከይድ ምርመራ አድርጎ አንዲት ተባይ ዝንብ ደግሞ በተባዕቱ ዘፈን እንደምትሳብ፤ ዕጯንም እንድታስቀምጥበት ቦታውን ለማወቅ እንደሚጠቅማት አገኘ። የመርባትን ድምጽ በመጠቀም የአስተናጋጇን ቦታ ለምታገኝ የተፈጥሮ ጠላት ይህች መጀመርያ ምሳሌ ሆነች። ከዚያ በኋላ ብዙ የዋዝንቢት ወገኖች ይህችን ተባይ ዝንብ ሲሸክሙ በምድር ላይ ተገኝተዋል። በእስያ በተላይም በቻይና ዋዝንቢት ዝነኛ ለማዳ እንስሳ ሆኖ መያዙ እንደ መልካም እድል ይቈጠራል። የተያዘ ዋዝንቢት ሁሉ ማናቸውም አትክልት ወይም ሥጋ ቢሰጥ ይበላል። በአንዳንድ ባሕል ደግሞ ዋዝንቢት እንደ ምግብ ሊበላ ይችላል።
በዓለማችን ምን ያህል የዋዝንቢት ዝርያዎች አሉ?
900
463
ኢትዮጵያ  በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የዓለም አቀፍ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዚየም ልታካሂድ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ። ዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዚየምና የአፍሪካ አስትሮኖሚ ማኅበር የምክክር መድረክ ከመስከረም 26-30 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ እንደተብራራው በሁለቱ መድረኮች ከ30 አገራት ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶች፣ ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎችና ባለድርሻ ተቋማት ሾለ አስትሮኖሚና ስፔስ ሳይንስ ይመክራሉ። በኢንስቲትዩቱ የአስትሮኖሚና አስትሮፊዚክስ ምርምር ክፍል ኃላፊ ዶክተር ማሪያና ፖቪች እንዳሉት በዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት በተለያዩ አገራት በየዓመቱ የሚዘጋጁ ሲምፖዚየሞች አሉ። ኅብረቱ መቶኛ ዓመቱን እያከበረ ይህንንም ክብረ በዓል ያከናወናቸውን ስራዎችና ስኬቶች እየገመገመ በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ ነው። እስካሁን 355 ሲምፖዚየሞች የተካሄዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሲምፖዚየሙን የምታካሂድ ሶስተኛዋ የአፍሪካ አገር ስትሆን በደቡብ አፍሪካና ቡርኪናፋሶ መሰል ሲምፖዚየም ተካሂዷል። ሲምፖዚየሙ በዘርፉ ልምድና እውቀት ያካበቱ ተመራማሪዎች ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በሳይንስ ዘርፍ እየከወኗቸው ያሉ ተግባራትን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስገንዘብ የሚያስችል ነው ብለዋል። የምስራቅ አፍሪካ አስትሮኖሚ ለልማት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ አለምዬ ማሞ በበኩላቸው እንደገለጹት የአፍሪካ አስትሮኖሚ ማኅበር የሚያዘጋጀው የአፍሪካ አስትሮኖሚ የሳይንስ ምክክር መድረክ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል። መድረኩ በአፍሪካ አስትሮኖሚ ምን አይነት አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚችል የሚያመላክት ራዕይና ስትራቴጂ ሰነድ የሚነደፍበት ይሆናል ነው ያሉት። የማኅበሩን እንቅስቃሴ ለሳይንስና ለጠቅላላ ማኅበረሰቡ ማስተዋወቅ፣ የአህጉሪቱ ወጣት ተመራማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማስቻል፣ በአፍሪካ በአስትሮኖሚና ስፔስ ሳይንስ ዘርፍ የሚሰሩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ማጎልበት የመድረኩ ዓላማዎች መሆናቸውን አንስተዋል። መድረኩ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብርና ትስስር መፍጠር ያስችላልም ነው ያሉት። ነገና ከነገ በስቲያ አራት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ በዘርፉ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪያቸውን እየሰሩ ላሉ ተማሪዎች የእውቀትና ክህሎት ስልጠናም ይሰጣል። ከሁለቱ መድረኮች ጎን ለጎን በተመረጡ 10 የህዝብ ትምህርት ቤቶች በተግባር የታገዘ አስትሮኖሚን የማስገንዘብ ሾል እንደሚሰራም ተገልጿል። ለበርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሾለ አስትሮኖሚ ሳይንስ ግንዛቤ የመፍጠር እንዲሁም ለሁለተኛ ደረጃ መምህራን የሚሰጥ ስልጠና መኖሩም ተጠቁሟል።    
በኢትዮጵያ ከመስከረም 26-30 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚካሄደው የአስትሮኖሚካል ሲምፖዚየም ላይ ከስንት ሀገራት ተሳታፊዎች ይመጣሉ ተብሎ ይታመናል?
ከ30
252
ማርክ ትዌይን ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ ወይም በብእር ስሙ ማርክ ትዌይን አሜሪካ ካፈራቻቸው ድንቅ ጸሃፍት መካካል የሚመደብ ደራሲ ነው። ትዌይን በኖቬምበር 1835 ዓ.ም. ሚዙሪ በተባለችው የአሜሪካ ግዛት ተወለደ። 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር የኖረው ሃኒባል በተባለች እና ሚሲሲፒ ላይ በተቆረቆረች ትንሽ ከተማ-አከል ቦታ ነው። አባቱ በ1847 ሲሞት ትዌይን ትምህርቱን በማቋረጥ በማተሚያ ቤት ውስጥ በሰልጣኝነት ተቀጠረ። ይህን ስራውን በ1857 በመተው የእንፋሎት ጀልባ ነጂ በመሆን መስራት ጀመረ። በዚሁ ስራ በቆየባቸው አመታት ነው ኋላ ላይ አድናቆትን ላተረፉለት የስነ-ጽሁፍ ስራዎቹ የሚሆኑትን እውቀቶች ለማሰባሰብ የበቃው። እሱ ራሱም እንዳለው በዚሁ ስራ ላይ ነው "ማንኛውንም በልብ-ወለድ፣ በግለ-ታሪክም ሆነ በታሪክ ላይ ሊገኙ የሚችሉ የሰው ባህርያትን" ሊያጠና የበቃው። በ1861 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የእርስ-በርስ ጦርነት በመቀስቀሱ ምክንያት ማንኛውም አይነት የመርከብ ላይ ጉዞ ሲስተጓጎል ትዌይንም ስራውን ለመልቀቅ ተገዷል። ከዚህ በኋላም በውትድርና ወዶ-ገብነት፣ በወርቅ ማእድን ፈላጊነት፣ በጋዜጠኝነት ወዘተ ስረቷል። በ1869 ዓ.ም የመጀመሪያ ዋነኛ ስራው የሆነውን "The Innocents Abroad" ለማሳተም በቃ። ይኽ ድርሰት ክሌመንስ ራሱ በአውሮፓ እና በእየሩሳሌም ባካሄዳቸው ጉብኝቶች ላይ የተመሰረተ ነው። በ1870 ዓ.ም ኦሊቭያ ላንግዶንን በማግባት ኑሮውን ኮኔቲከት በተባለችው ግዛት አድርጓ በዛው ለ17 ዓመታት ኖሯል። በነዚህ 17 ዓመታት ነው አድናቆት ያተረፉለት ስራዎቹን ማለትም "Roughing It"፣ "The Adventures of Tom Sawyer"፣ Life on the Mississippi"፣ እና ከሁኡ የላቀ የተባለለት ድርሰቱን "The Adventures of Huckleberry Finn"ን ያሳተመው። ትዌይን በ1910 ዓ.ም አርፎ ሬዲንግ፣ ኮኔቲከት ውስጥ በድኑ አርፏል።
ማርክ ትዌይን ሳሙኤል ላንግሆርን ክሌመንስ የተወለደባት የአሜሪካ ግዛት ማን ትባላለች?
ሚዙሪ
110
መስከረም ፩ መስከረም ፩ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ የመጀመሪያው ዕለት ነው። በመሆኑም ቀኑ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በዓል ወይም ዕንቁጣጣሽ በመባል ይታወቃል። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፷፭ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ፤ ማቴዎስ፤ እና ማርቆስ ደግሞ ፫፻፷፬ ቀናት ይቀራሉ። ==ታሪካዊ ማስታወሻዎች== ፲፭፻፯ ዓ/ም - የፖሎኝ ሠራዊት በኦርሻ ውግያ በሩስያ ላይ አሸነፈ። ፲፮፻፺፮ ዓ/ም - በጎንደር ትልቅ አውሎ ነፋስ ተነስቶ ብዙ የሕዝብ እና የንጉሥ ቤቶችን ሲያወድም፣ የሸዋው ታላቅ መኮንን አቤቶ ወልደ ብርሃን እና ፵ ሰዎች ሞተዋል። ፲፰፻፮ ዓ/ም - የአሜሪካ መርከቦች በኤሪ ሐይቅ በእንግሊዝ አሸነፉ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በላቲመር ፔንሲልቬኒያ ፖሊሶች 19 የማዕደን ሰራተኞች በእልቂት ገደሉ። ፲፱፻፲፭ዓ/ም - የእንግሊዝ አስተዳደር በፍልስጤም ጀመረ። ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - የጀርመን ሃያላት ሙሶሊኒን ከእስር በት እንዲያመልጥ ነጻ አወጡት። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ የቀድሞው የምሥራቅ ጀርመን ዜጋዎች ወደ ምዕራብ ፈለሱ። ፲፱፻፺፬ ዓ/ም - አራት አውሮፕላኖች በአረብ ተዋጊዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ።
በኢትዮጵያ መስከረም ፩ የሚከበረው በዓል ምን ይባላል?
አዲስ ዓመት በዓል ወይም ዕንቁጣጣሽ
71
መጋቢት ፪ ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን ያዘ። ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት (በኋላ ፕሬዚዳንት) ሪቻርድ ኒክሰን ኢትዮጵያን ጎበኙ ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ሊትዌኒያ እራሷን ከሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ውጭ ነጻ መሆኗን አወጀች። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ በልብ ምታት አረፈ።
በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ የተጀመረው መቼ ነው?
፲፱፻፷፮ ዓ/ም
466
ኢትዮጵያ  በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የዓለም አቀፍ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዚየም ልታካሂድ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ። ዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዚየምና የአፍሪካ አስትሮኖሚ ማኅበር የምክክር መድረክ ከመስከረም 26-30 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ እንደተብራራው በሁለቱ መድረኮች ከ30 አገራት ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶች፣ ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎችና ባለድርሻ ተቋማት ሾለ አስትሮኖሚና ስፔስ ሳይንስ ይመክራሉ። በኢንስቲትዩቱ የአስትሮኖሚና አስትሮፊዚክስ ምርምር ክፍል ኃላፊ ዶክተር ማሪያና ፖቪች እንዳሉት በዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት በተለያዩ አገራት በየዓመቱ የሚዘጋጁ ሲምፖዚየሞች አሉ። ኅብረቱ መቶኛ ዓመቱን እያከበረ ይህንንም ክብረ በዓል ያከናወናቸውን ስራዎችና ስኬቶች እየገመገመ በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ ነው። እስካሁን 355 ሲምፖዚየሞች የተካሄዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሲምፖዚየሙን የምታካሂድ ሶስተኛዋ የአፍሪካ አገር ስትሆን በደቡብ አፍሪካና ቡርኪናፋሶ መሰል ሲምፖዚየም ተካሂዷል። ሲምፖዚየሙ በዘርፉ ልምድና እውቀት ያካበቱ ተመራማሪዎች ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በሳይንስ ዘርፍ እየከወኗቸው ያሉ ተግባራትን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስገንዘብ የሚያስችል ነው ብለዋል። የምስራቅ አፍሪካ አስትሮኖሚ ለልማት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ አለምዬ ማሞ በበኩላቸው እንደገለጹት የአፍሪካ አስትሮኖሚ ማኅበር የሚያዘጋጀው የአፍሪካ አስትሮኖሚ የሳይንስ ምክክር መድረክ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል። መድረኩ በአፍሪካ አስትሮኖሚ ምን አይነት አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚችል የሚያመላክት ራዕይና ስትራቴጂ ሰነድ የሚነደፍበት ይሆናል ነው ያሉት። የማኅበሩን እንቅስቃሴ ለሳይንስና ለጠቅላላ ማኅበረሰቡ ማስተዋወቅ፣ የአህጉሪቱ ወጣት ተመራማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማስቻል፣ በአፍሪካ በአስትሮኖሚና ስፔስ ሳይንስ ዘርፍ የሚሰሩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ማጎልበት የመድረኩ ዓላማዎች መሆናቸውን አንስተዋል። መድረኩ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብርና ትስስር መፍጠር ያስችላልም ነው ያሉት። ነገና ከነገ በስቲያ አራት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ በዘርፉ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪያቸውን እየሰሩ ላሉ ተማሪዎች የእውቀትና ክህሎት ስልጠናም ይሰጣል። ከሁለቱ መድረኮች ጎን ለጎን በተመረጡ 10 የህዝብ ትምህርት ቤቶች በተግባር የታገዘ አስትሮኖሚን የማስገንዘብ ሾል እንደሚሰራም ተገልጿል። ለበርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሾለ አስትሮኖሚ ሳይንስ ግንዛቤ የመፍጠር እንዲሁም ለሁለተኛ ደረጃ መምህራን የሚሰጥ ስልጠና መኖሩም ተጠቁሟል።    
በዓለም ላይ እስካሁን ምን ያክል የአስትሮኖሚካል ሲምፖዚየም ተከናውነዋል?
355
550

የአስትኖሚካል ሲምፖዚየም መድረክ ምን አይነት ትስስር ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል?
ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ
1,255
አዋሽ ብሔራዊ የመዝናኛ እና የዱር አራዊት ጥበቃ ክልል የአዋሽ ብሔራዊ መዝናኛ እና የዱር አራዊት ጥበቃ ክልል በ፲፱፻፶፰ ዓ/ም የተመሠረተ ክልል ሲሆን ከአዲስ አበባ በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በ፪መቶ ፲፩ ኪሎሜትር ርቀት ፤ በአፋርና በኦሮሚያ አዋሳኝ ክልሎች ሥር ይገኛል። ይህ ክልል ሲመሠረት በ ፱፻፮ ካሬ ኪሎሜትር የቆዳ ስፋት (ቦልቶን ፲፱፻፷፰) የነበረው ቢሆንም፤ ባሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ማስረጃ እንዳስቀመጠው የክልሉ የቆዳ ስፋት ፯መቶ ፶፮ ካሬ ኪሎ-ሜትር ነው። የክልሉ ደቡባዊ ድንበር የአዋሽ ወንዝ ሲሆን፣ የተሠየመውም በዚሁ ታላቅ ወንዝ ስም ነው። ክልሉ የብዙ ዓይነት አራዊት እና አዕዋፍ መጠለያ ከመሆኑም ባሻገር ፍል-ውሓ እና የፋንታሌ ተራራ ይገኙበታል። የአገሪቱ የዱር አራዊት ጥበቃ ባለ-ሥልጣን ሲመሠረት ለንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በአማካሪነት የተመደበው እንግሊዛዊ ባቀረበው ኃሣብ መሠረት የመጀመሪያው ብሔራዊ የዱር አራዊት ጥበቃ ባለ-ሥጣን ከተመሠረተ በኋላ የቅድሚያ ሥራ የተደረገው፤ በታቀዱት ክልሎች የሚገኙትን የአገሪቱን የዱር አራዊት ኃብት መጠን ማረጋገጥ ነበር። ለዚህም ሥራ ከብሪታኒያ ተመልምሎ የተቀጠረው ባለ-ሙያ እንግሊዛዊው የሥነ-ሕይወት ባለሙያ ሜልቪን ቦልቶን ነበር። የአዋሽ ብሔራዊ መዝናኛ እና የዱር አራዊት ጥበቃ ክልል የበርካታ የዱር አራዊት፤ አዕዋፋት እና የውሐ አራዊት መኖሪያ ነው። በደቡብ አዋሳኙ በሆነው የአዋሽ ወንዝ አዞ እና ጉማሬ ሲገኝበት፤ በሰሜን ክፍሉ ደግሞ ጦጣና ዝንጀሮ፤ እንዲሁም ጅብ እና አጋዘን ይገኙበታል። በክልሉ ከሚገኙት የዱር አራዊት በከፊሉ፦ ጉሬዛ፤ ተራ ዝንጀሮ፤ ነጭ ዝንጀሮ፤ ጦጣ፤ ሳላ፤ የሜዳ ፍየል፤ ሚዳቋ፤ ትልቁ የቆላ አጋዘን ፤ አምባራይሌ፤ ከርከሮ፤ ቆርኪ በብዛት የሚገኙ ሲሆን አንበሣ፤ ነብር፤ ጀርባ-ጥቁር እና ተራ ቀበሮ፤ዳልጋ አንበሣ፤ አነር እና የዱር ድመት ደግም አልፎ-አልፎ ይታያሉ። ባለፉት አሥር ዓመታት ጊዜ ውስጥ በተካሄደ ምዝገባ እንደተረጋገጠው፣ በክልሉ ውስጥ ፬መቶ ፷፪ ዓይነት የወፍ ዝርያዎች ተመዝግበዋል። ከነዚህም መኻል ስድስቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ናቸው። እነዚህም መንቆረ-ጥቁር ጋርደም፤ ግንደ-ቆርቁር፤ ክንፈ-ነጭ የገደል-ቻት፤ ጅራተ-ረጅም ወማይ፤ ቁራ እና ጋጋኖ ናቸው።
የአገሪቱን የዱር አራዊት ኃብት መጠን ለማረጋገጥ የተመረጠው ሰው የምን ሃገር ዜጋ ነበር?
እንግሊዛዊው
680