context
stringclasses
367 values
question
stringlengths
10
114
answer
stringlengths
1
90
answer_start
int64
0
3.22k
ሮማንሽ ሮማንሽ ወይም ሩማንች (Rumantsch) ከስዊስ አገር 4 ብሔራዊ ቋንቋዎች 1ዱ ሆኖ ሌሎቹ 3 ጀርመንኛ ጣልኛና ፈረንሳይኛ ናቸው። ከሮማይስጥ የታደገ ቋንቋ በመሆኑ የሮማንስ ቋንቋ ቤተሠብ አባል ነውና በተለይ የሚመስለው ፈረንሳይኛ ወይም እጣልኛ ነው። የሚናገረው በግራውብውንደን (ግሪዞን) ካንቶን ስዊስ በሚኖሩ 60,000 ሰዎች ነው። ይህ ከስዊስ አገር ሕዝብ ብዛት 1% ብቻ ሲሆን ከስዊስ አገር ብሔራዊ ቋንቋዎች ሁሉ ትንሹ ነው። እንኳን በስዊስ አገር ከሚኖሩት ስርቦ-ክሮዌሽኛ ተናጋሪዎች ቁጥር ብዛት (111,000) በግማሽ ያንሳል። በስሜን እጣልያ አገር ዛሬ ለሚናገሩ ቋንቋዎች ለፍሪዩልያንና ለላዲን ቅርብ ዘመድ ነው።
የሮማንሽ ቋንቋ በሰሜን ጣልያን ከሚነገሩት ቋንቋዎች ለየትኞቹ ቅርብ ነው?
ለፍሪዩልያንና ለላዲን
373
አንኮበር በ፲፯፻፳ ዓ/ም በሸዋው ነጋሲ በመርድ አዝማች አብዬ የተመሠረተችና በአልጋ ወሪሹ መርድ አዝማች አምኀ ኢየሱስ የተስፋፋች የሸዋ ከተማ ስትሆን ከደብረ ብርሃን ምስራቃዊ አቅጣጫ ፵፫ ኪሎ ሜትር ርቀት የስምጥ ሸለቆው አፋፍ ላይ ትገኛለች። አንኮበር ከዓፄ ይኵኖ አምላክ (፲፪፻፸-፲፪፻፹፭ ዓ/ም) ዘመን ጀምሮ ለኢትዮጰያ ነገሥታት በማረፊያነት አገልግላለች። ዓፄ አምደ ጽዮን ፲፫፻፲፬-፲፫፻፵፬ ዓ/ም የድንኳን ከተማቸውን እንደተከሉባት ይነገራል። አስቲት ኪዳነ ምሕረት የርሳቸው ትክል ናት። ጦረኛዉ ዓፄ አምደ ጽዮን በ፲፫፻፴፭ ዓ/ም አዳልን ለማስገበር የዐማራን፣ የዳሞትን፣ የጐዣምን ሠራዊት ይዘው አንኮበር ሠፈሩ።ለ፬ ወራት ያህል እስከ ዘይላና በርበራ ድረስ በመዝለቅ ድል አድርገው አስገብረውታል። ዓፄ ልብነ ድንግል (፲፭፻፰-፲፭፻፵ ዓ/ም) ደግሞ በተሻለ ሁኔታ በቦለድ የባለወልድን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ጀምረው እንደነበር የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ። የከተማነት ታሪኳ የጐላው ግን ከግራኝ ወረራ በኋላ ተበታትኖ የቆየውን የጥንታዊ ሸዋን ግዛት አንድ ለማድረግ የሸዋ ስርወ-መንግሥት በአቤቶ ነጋሲ በመንዝ አጋንቻ ላይ በ፲፮፻፷፭ ዓ/ም ተጀምሮ በተከታታይ እስከ ፲፰፻፹፩ ዓ.ም የጥንት ኢትዮጶያ ግዛትን ለማስመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ ነው። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ወደ ፲፫ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሥር መሠረቱ የረር | እንጦጦ እስከዞረበትና በኋላም አዲስ አበባ እስከተቆረቆረችበት ጊዜ ድረስ በቀዝቃዛ አየሯ የምትታወቀው አንኮበር ለአምስት የሸዋ ነገሥታት በማእከልነት አገልግላለች።
አንኮበር ከተማ ከደብረ ብርሃን በምን ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች ?
፵፫ ኪሎ ሜትር
116
መንግስቱ ለማ መንግሥቱ ለማ (1924-1988) በጣሊያን ወረራ ዋዜማ በሀረር ሀደሬ ጢቆ መካነ ሥላሴ ተወልዶ ከቆሎ ተማሪነት ተነስቶ የለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ደቀመዝሙርነት እስከመሆን በቅቶ የቅኔ ቤት ሊቅነት ሳይበቃው የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ቀደምቶች መሃከል ለመደብለቅ የበቃ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ድንቅ ገጣምያን/ፀሃፌ ተውኔቶች አንዱ ነው። አባቱ አለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ-ታሪክ (ታሪክ የእናታቸው ስም ነው - ምናልባት በኢትዮጵያ ታሪክ የእናታቸውን ስም ከስማቸው አስተባብረው በመጻፍ የመጀመሪያው ሳይሆኑ አይቀሩም) ታዋቂ የቤተክርስቲያን ሊቅ የነበሩ ሲሆን በመጀመሪያ ላይ የመንግስቱን የአስኳላ (በወቅቱ ዘመናዊ ትምህርት የሚጠራው እንዲህ ነበር) ትምህርት ባይወዱለትም ጣሊያኖቹ ልጁን የማያስተምር ሰው ሁሉ ይቀጡ ስለነበር ለማስተማር ተገደዋል። ሁዋላ ላይ ግን እሳቸው አዲስ አበባ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ ተቀይረው መጥተው እሱ የኮተቤ ተማሪ ከሆነና የትምህርት ውጤቱም እስደሳች ሲሆን የቀድሞ ቅዋሜያቸውን ሳያላሉት አልቀሩም። መንግስቱ በእንግሊዝ አገር ወደ ስድስት አመት ቢቆይም ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ነው በ1956 ዓ.ም ወደ አገሩ ለመመለስ የበቃው። ይሁን እና በቆይታው ከብዙ የእንግሊዝ ደራስያን ጋር ለመተዋወቅ በቅቷል። በተለይም ከጆርጅ በርናርድ ሾው ጋር ወዳጆች እንደነበሩ ይነገራል። መንግሥቱ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በሁዋላ የተሰማራው ወደ መንግስት ሥራ ሲሆን በህንድ አገር ዲፕሎማት ሆኖ ከሄደ በሁዋላ ምናልባትም በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ዘመናዊ ኮሜድ ተውኔት «ጠልፎ በኪሴ"ን ደርሷል ከዚያ በሁዋላ የደረሳቸው እነ «ያላቻ ጋብቻ»፣ «ጸረ-ኮሎኒያሊስት»፣ «ባለካባና ባለዳባ» የመንግስቱን ስም በኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ካደረጉት ስራዎቹ መካከል ናቸው። በተጨማሪም «The bear» የተሰኘውን እና የታዋቂው የሩሲያ ደራሲ አንቷን ቼኾቭ ተውኔት የሆነውን «ዳንዴዎ ጨቡዴ» በሚል የተረጎመ ሲሆን የጄ.ቢ. ፕሪስትሊን «The Inspector Calls»ን ተርጉሞ ለመድረክ አብቅቷል። መንግስቱ ከተውኔቱ በተጨማሪም በስነ-ግጥም የተዋጣለት እንደነበር ስራዎቹ ይመሰክራሉ። «የግጥም ጉባኤ» የተሰኘው ስብስብ መንግስቱ የግጥም መክሊት የተቸረው ደራሲ እንደነበር ይመሰክራል። መንግሥቱ ደራሲም ብቻ አልነበረም፤ በተማሪዎቹ የተወደደ መምህር በሳል ተመራማሪ ለባህሉ እና ለቋንቋው ሙት የነበረ ከኢትዮጵያ ብርቅዬዎች አንዱ ነው።
መንግስቱ ለማ መቼ ተወለደ?
1924
19
ሚያዝያ ፲፰ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፳፰ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፯ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኙት ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው አንድ አገር መሠረቱ። ይሄም የተዋሕዶ አገር ከሁለቱም ስም በተውጣጣው አዲሱ ስም ታንዛኒያ ተብሎ ተሰየመ። ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - የኡዝቤኪስታን ርዕሰ ከተማ ታሽኬንት በትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ክስተት ስትወድም ሰብ ስምንት ሺ መኖሪያ ቤቶች በመጥፋታቸው ከሦስት መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎቿ መኖሪያ ቢስ ሆነዋል። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በሼክ ሞሀመድ ማህሙድ ኤል ሳዋ የተመራ የሳዑዲ አረቢያ ልዑካን ቡድን ለአጭር ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ከደርግ በተላለፈ ትእዛዝ መሠረት፣ የፖሊስ አለቆች፤ የቀድሞ ሚኒስትሮችና ባለ ሥልጣናት ታሠሩ። ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ የቸርኖቢል የኑክሊዬር መብራት ኃይል ማምረቻ ክፉ አደጋ ተከሰተ። የዚህን አደጋ ክስተት የስካንዲናቪያ አገሮች ይፋ እስካደረጉት ድረስ የሶቪዬት ሕብረት ባለ ሥልጣናት ደፋፍነውት ነበር።
በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ የቸርኖቢል የኑክሊዬር መብራት ኃይል ማምረቻ አደጋ የተከሰተው በስንት ዓመተ ምህረት ነው?
፲፱፻፸፰ ዓ/ም
587
መጋቢት ፳፮ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት የመጀመሪያው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፱ ቀናት ይቀራሉ። ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፺፯ ዓ/ም - ‘የካንግራ ሸለቆ’ በሚባለው የሕንድ ግዛት ውስጥ የተከሰተው እሳተ ገሞራ የ ፳ ሺ ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ የአካባቢውን ከተማዎችና ሠፈሮች አውድሟል። ፲፱፻፵፩ ዓ/ም - አሥራ ሁለት ምዕራባውያን አገሮች፤ የአሜሪካ ኅብረት፣ ታላቋ ብሪታንያ፣ ፈረንሲስ፣ ቤልጂግ፣ ሆላንድ፣ ዴንማርክ፣ ኢጣልያ፣ ሉክሳምቡርግ፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ፣ ካናዳ እና ብርቱጋል በስምምነት የሰሜን አትለንቲክ የውል ድርጅት መሠረቱ። ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ሴኔጋል ከ ፈረንሳይ ነጻነቷን ተቀዳጀች። ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የጥቁር አሜሪካውያን መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄምስ ኧርል ሬይ በተባል ነፍሰ ገዳይ እጅ በሜምፊስ ከተማ ተገደለ። የኪንግ ሞት ዜና ሲሰማ በ መቶ የአሜሪካ ከተሞች ከፍ ያለ የሕዝብ ሽብር ተከተለ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኒው ዮርክ መንታ ሰማይ-ጠቀስ ፎቆች (የዓለም የንግድ ማዕከል) ሕንፃ ግንባታ ተጠናቀቀ። እነዚህ መንታ ፎቆች መስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ/ም በአመጽ የአየር ዠበብ ግጭት ወድመዋል። ፲፱፻፷ ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ በሜምፊስ ከተማ በነፍሰ-ገዳይ እጅ ተገደለ።
አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የጥቁር አሜሪካውያን መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ በማን ተገደለ?
ጄምስ ኧርል ሬይ
566
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ተፈሪ መኰንን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺ እመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ፲፰፻፺፱ የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. የሐረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ። የሐረርጌ አገረ ገዥ ሲሆኑ ፣ በጣም ብዙ ሺህ ተከታዮች ነበሩዋቸውና ልጅ እያሱን ከእንደራሴነት በኅይል እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ተፈሪን ከሐረር አገረ ገዥነት እንዳይሽሯቸው የሚል ስምምነት ተዋዋሉ። ዳሩ ግን እያሱ ሃይማኖታቸውን ከክርስትና ወደ እስልምና እንደቀየሩ የሚል ማስረጃ ቀረበና ብዙ መኳንንትና ቀሳውስት ስለዚህ ኢያሱን አልወደዱዋቸውም ነበር። ከዚህም በላይ እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት ስምምነታቸው እንግዲህ ተሠርዞ ተፈሪ ደግሞ ለወገናቸው ከስምምነቱ ተለቅቀው በዚያን ጊዜ እሳቸው እያሱን ከእንደራሴነት አስወጡ። እንግዲህ በ፲፱፻፱ ዓ.ም. መኳንንቱ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ሆነው አድርገዋቸው ተፈሪ ደግሞ እንደራሴ ሆኑ። ከዚህ ወቅት ጀምሮ ተፈሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙሉ ሥልጣን ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. የንጉሥነት ማዕረግ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ አርፈው ንጉሠ ነገሥት ሆኑና ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ብዙ የውጭ ልዑካን በተገኙበት ታላቅ ሥነ-ሥርዓት ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው እሳቸውና ሚስታቸው እቴጌ መነን ዘውድ ጫኑ። በንግሥ በዓሉ ዋዜማ ጥቅምት ፳፪ ቀን የትልቁ ንጉሠ-ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለዘውድ በዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት ፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ። ለንግሥ ስርዐቱ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገር ልኡካን ከየአገራቸው ጋዜጠኞች ጋር ከጥቅምት ፰ ቀን ጀምሮ በየተራ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ስለነበር ሥርዓቱ በዓለም ዜና ማሰራጫ በየአገሩ ታይቶ ነበር። በተለይም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት በጃማይካ አንዳንድ ድሀ ጥቁር ሕዝቦች ስለ ማዕረጋቸው ተረድተው የተመለሰ መሢህ ነው ብለው ይሰብኩ ጀመር። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ፊተኛው ስማቸው «ራስ ተፈሪ» ትዝታ ራሳቸውን «ራስታፋራይ» (ራሰተፈሪያውያን) ብለዋል።
ራስ ተፈሪ መኮንን የሐረርጌ አውራጃ አስተዳዳሪ የሆኑት መቼ ነበር?
በ፲፱፻፫ ዓ.ም.
242
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ስብሐት (ስብሐት ለአብ) ገብረ እግዚአብሔር (ሚያዝያ 27 [1928]ዓ.ም. - ሰኞ፣ ቀን ትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደ ፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው። ስብሐት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ በመነን መጽሄት የዝግጅት ክፍል ውስጥ ሰርቷል። በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲቋቋም በአርታኢነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በመንግሥት ትእዛዝም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን የካርል ማርክስ ሥራ የሆነውን ካፒታልን ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመመለስ ሥራ ላይ ተሳትፏል። ብዙዎቹ የስብሐት ሥራዎች በተጻፉበት ጊዜ ለመታተም ባይታደሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የህትመትን ብርሃን ለማየት በቅተዋል። ጽሁፎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይታተሙ ለመቆየታቸው ዋነኛው ምክንያቱ ስብሐት በመጽሐፉ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ባህል ያደገ አንባቢን አይን የሚያስፈጥጡ፣ ጆሮ የሚያስይዙ በመሆናቸው ነው። በገበያ ላይ በቅርብ የወጡት ድርሰቶቹ ከመጀመሪያ ቅጂያቸው ብዙ ለውጥ እና የአርትኦት ሥራ የተደረገባቸው እንደሆኑ ይነገራል። ስለዚሁ ጉዳይ ለአዲስ ላይቭ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገር «በጨለማ ያልተደረገውን ነገር አንድም የጻፍኩት የለም... ያለውን እንዳለ ነው የምጽፈው» ብሏል። ይህንኑም ከኤሚል ዞላ የአጻጻፍ ዘይቤ የወሰደው እንደሆነ ይናገራል። ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ደራሲ፣ አርታኢ፣ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም - የልብ-ወለድ ድርሰት ገጸባህርይም ነው። ደራሲው የተሰኘው የበአሉ ግርማ ልብ-ወለድ በስብሐት ህይወት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው። ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች አባት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነው።
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የት ተወለደ?
አድዋ
89
በ628 ዓክልበ.፣ ድራኮ የሚባል ጸሃፊ የአቴና ከተማ ሕግጋት ጻፈ፤ ይህም ሕግ እጅግ ጨካኝ ሆኖ ይሙት በቃ ለማንኛውም ጥፋት ወሰነ። በ600 ዓክልበ.፣ የአቴና አለቃ ሶሎን አዲስ ሕገ መንግሥት ፈጠረ። የሰራተኞች ሸክም አቀለለ፣ ነገር ግን ባላባትነት በልደት ሳይሆን በንብረት ብዛት እንዲቈጠር አስደረገ። ክሊስቴኔስ እንደገና በ516 ዓክልበ. በዴሞክራሲያዊ መሠረት የተሻሸለ ለአቴና ሕገ መንግሥት አወጣ። የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ በ350 ዓክልበ. ግድም የሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ዐወቀ። በጽሑፎቹ የአቴና፣ የስፓርታና የካርታግና ሕገ መንግሥቶች ያነጻጽራል። በመደምደሚያው የተሻለው ሕገ መንግሥት ከንጉሣዊ፣ ከመኳንንታዊና ከሕዝባዊ ወገኖች የተደባለቀ መሆኑን ገመተ። በሀሣቡ በመንግሥት የሚከፋፈሉ ዜጎች ከማይከፋፈሉ ከባርዮችና ዜጎች ካልሆኑ ሰዎች ልዩነት አደረገ። ሮማውያን መጀመርያ «12ቱ ሰንተረዦች» የተባለውን ሕገ መንግሥት ያወጡ በ457 ዓክልበ. ነበር። ከዚያ በኋላ አንዳንዴ የተለያዩ ሕጎችና ትእዛዛት ይጨምሩበት ነበር እንጂ እስከ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስ ድረስ (430 ዓ.ም.) ሌላ ክምቹ ሕገ መንግሥት አልኖረም ነበር። በኋላም በምሥራቁ መንግሥት (ቢዛንታይን) በኩል መጽሐፈ ዩስጢኒያኖስ (526 ዓ.ም.) ለአውሮፓ ከፍ ያለ ተጽእኖ ነበረው። ይህም በምስራቁ ነገሥታት 3ኛ ሌዎን ኢሳውራዊ «ኤክሎጋ» (732 ዓ.ም.) እና በ1ኛ ባሲሌዎስ «ባሲሊካ» (870 ዓ.ም.) በተባሉት ሕገ ፍትሐን ተከተለ።
ከመጀመሪያው ሕግ ቀጥሎ የአቴናው አለቃ ሶሎን አዲሱን ሕገ መንግሥት መች ፈጠረ?
በ600 ዓክልበ.
85
67ኛው ግጥም በጃዝ ምሽት የፊታችን ረቡዕ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በራስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ አንጋፎቹ ገጣሚያን ነቢይ መኮንን፣ ተፈሪ አለሙ፣ ዶ/ር ሙሉአለም ተገኝወርቅ፣ መርድ ተስፋዬና ቤዛ ትዕዛዙ የግጥም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን አርቲስት ሽመልስ አበራና እታፈራሁ መብራቱ አጭር ተውኔት ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር የሆኑት አቶ አበባው አያሌው ዲስኩር እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡
በ67ኛው ግጥም በጃዝ ምሽት ላይ አርቲስት ሽመልስ አበራና እታፈራሁ መብራቱ ምን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል?
አጭር ተውኔት
177
አንኮበር የሸዋ ነገሥታት ቋሚ መናኸሪያ ለመሆን የበቃችው ከመርድ አዝማች አምኀየሱስ ዘመነ መንግሥት ሲሆን በ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላዶ ሥልጣን በያዙት በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በይበልጥ ተስፋፍታ ነበር። ንጉሡ የእጅ ባለሙያዎችን በከፍተኛ ደረጃ ያበረታቱ ስለነበር፣ በርካታ የእደ ጥበብ ሥራዎች ይከናወኑባት ነበር። በቤተ መንግሥት የሚተዳደሩ ከሺ በላይ አናጺዎችና ግንበኞች በተለይም ባሩድ ቀማሚዎች፣ የጦር መሣሪያ ሠራተኞችና አንጥረኞች በወቅቱ ነበሩባት። የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ዐልጋ ወራሽ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ተተክተው ፰ ዓሙታት ያህል እንደገዙ ሸዋ በዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት ተወረረ። የቴዎድሮስ ሠራዊት አንኮበር ከተማ ግቢው ቅጥሩ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሹማምንቱ የግቢውን ቤተ መንግሥቱን አቃጥለውታል። ዓፄ ቴዎድሮስም በቦታው ድንኳን ጥለው ጥቂት ቀናት ቆይተው የራሳቸውን ወኪል ሾመው ተመልሰዋል። ጥቂት ቆይቶ የሸዋ መኳንንት በአቤቶ ሰይፉ ሣህለ ሥላሴ መሪነት የዓፄ ቴዎድሮስን ተወካይ በዛብህን አባረው ግቢዉን ሲይዙ ዓፄ ቴዎድሮስ ለሁተኛ ጊዜ ወደ ሸዋ ዘምተዉ በተካሄደው ከፍተኛ ጦርነት አንኮበር ክፉኛ መጐዳቷን መረጃዎች ይገልፃሉ። ተዘርፋለች፥ተቃጥላለች። የ፲፩ ዓመቱ ምኒልክና የሸዋ መኳንንት በግዞት ወደ ጎንደር ተወስደዋል። ምንይሊክ በዓፄ ቴዎድሮስ እጅ በእስራት ከነበሩበት መቅደላ አምልጠው ሲመለሱ አንኮበር እንደገና ተቋቁማ የጥንት ማዕረጓ ተመልሷል።
በአንኮበር ምን ዓይነት ስራዎች በብዛት ይሰሩ ነበር?
የእደ ጥበብ ሥራዎች
187
የሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች ከአገልግሎት ጋር ተያይዞ ለተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃቶች የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው። የኮምፒውተሮችን አጠቃላይ ባህሪ መረዳት፣ በየጊዜው ማሻሻልና መቀየር ያለባቸውን ስርዓቶች በማወቅ መረጃዎች እንዳይጠፉ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ከዚህ አንጻር የኮምፒውተሮችን ደህንነት ለመጠበቅ .ጠቃሚ ፋይሎችን መጠባበቂያ ወይም ባክአፕ መያዝ . የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ሥርዓት ለደህንነት ሥጋት እንዳይጋለጡ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ክፍተት መሙላት . ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም፣ በየጊዜው መተግበሪያዎችን ማዘመን . ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ አጠቃላይ የኮምፒውተር ስርዓት ስካን ማድረግ .አጥፊ ሶፍትዌሮችን የሚከላከሉ ፀረ አጥፊ ሶፍትዌሮችን መጠቀም እና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ስካን ማድረግ እንዲሁም . የተመጠነ የፋይል አስተዳደር መተግበር እና ዲስኮችን በየጊዜው ማፅዳት መረጃው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ነው
የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ሥርዓት ለደህንነት ሥጋት እንዳይጋለጡ በምን ያህል ጊዜ ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም አለብን?
ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ
345
እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው የአውስትራሊያ የእንቁራሪት ዝርያ (ጋስትሪክ ብሩዲንግ ፍሮግ) ያልተለመደ ዓይነት የመራቢያ ሥርዓት አላት፤ የዚህች እንቁራሪት ዝርያ ከ2002 ጀምሮ እንደጠፋ ይታሰባል የሚለው ጄደብሊው ዶት ኦርግ ድረ ገጽ ነው።
እንቁላሏን በሆዷ የምትታቀፈው የአውስትራሊያ እንቁራሪት ዝርያ ከ2002 ጀምሮ እንደጠፋች የገለጸው ድረ ገጽ ስያሜው ምን ይባላል?
ጄደብሊው
133
ቀጭኔ ከዝሆን በስተቀር ማንኛውም ሌላ እንስሳ ሊደርስ በማይችልበት ከፍታ ላይ የሚገኙ ረዣዥም ቀንበጠቦችን ለመብላት የሚያስችል አስደናቂ አፈጣጠር አላት። ልዩ የሆነ የመቆንጠጥ ችሎታ ያለው የላይኛው ከንፈሯና እንደተፈገለው የሚተጣጠፍ ችሎታ ያለው ምላሷ ሹል በሆኑ እሾሆች የታጠሩ ቅጠሎችን ለመቀንጠብ ያስችሏታል። ቀጭኔዎች በቀን እስከ 34 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕፅዋት መመገብ ይችላሉ። የተለያዩ ዕፅዋትን የሚበሉ ቢሆኑም ይበልጥ የሚመርጡት በአፍሪካ ሜዳዎች የሚገኙትን እሾሃማ ግራሮች ነው። አንድ ወንድ ቀጭኔ ምግብ ለመፈለግ ምላሱን እስከ 42 ሳንቲ ሜትር መዘርጋት ይችላል። የቀጭኔ አንገት በጣም አስደናቂ የሆነ የመተጣጠፍ ችሎታ አለው። ይህም ላይኛዎቹን የዛፍ ቅርንጫፎች ለመቀንጠብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ረዥሙን ራሷን እንደ ልቧ ለማዘንበልና ለማዟዟር ያስችላታል። ለቀጭኔ ወደ ላይ መንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት ግን ይከብዳታል። ወደ ውኃ ጉድጓድ በምትቀርብበት ጊዜ የፊት እግሮቿን ቀስ በቀስ ከፍታ ካራራቀቻቸው በኋላ ወደ ውኃው ለመድረስ እንድትችል ሁለት ጉልበቶቿን አጠፍ ታደርጋለች። ቀጭኔዋ እንዲህ ባለው አመቺ ባልሆነ ሁኔታ እያለች ረዥም አንገቷን እስከ መጨረሻ ትዘረጋለች። ደግነቱ ግን ከምትመገባቸው ቅጠላ ቅጠሎች በቂ እርጥበት ስለምታገኝ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አያስፈልጋትም። የቀጭኔ አንገትና ትከሻ የቅጠል ቅርፅ ባላቸውና ቀጫጭን በሆኑ ነጭ መስመሮች ያጌጠ ነው። ቀለማቸው የተለያየ ሲሆን ከወርቃማ ዳለቻ አንስቶ እስከ ቡናማ እንዲያውም ጠቆር እስካለ ቀለም ይደርሳል። የቀጭኔ ዕድሜ እየገፋ በሄደ መጠን ቀለሟም እየጠቆረ ይሄዳል። ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው። አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ ልጅዋን ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት ከተሸከመች በኋላ ሁለት ሜትር ቁመት ያለው ግልገል ትወልዳለች። ግልገሏ በምትወለድበት ጊዜ ራስዋን ታስቀድምና ከሁለት ሜትር ከፍታ ላይ ወደ መሬት ትወረወራለች። ይሁን እንጂ በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባት እየተውተረተረች ትነሳና ጡት ለመጥባት ዝግጁ ትሆናለች። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ በደመ ነፍስ ተመርታ የግራር ቀንበጦችን መለቃቀም ስለምትጀምር ብዙም ሳትቆይ ረዥም እርምጃ ያላትን እናትዋን ተከትላ ለመሄድ የሚያስችል ጉልበት ታገኛለች። አንዲት የቀጭኔ ግልገል በጣም ውብ መልክ ሲኖራት የወላጆችዋ አነስተኛ ግልባጭ ነች። ቁመቷ ከቀጭኔ ርዝመት ጋር ሲወዳደር አጭር ብትሆንም ከብዙ ሰዎች ቁመት ግን ትበልጣለች። በእናቷ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ተማምና አላንዳች መሸበር አካባቢዋን የምትማትረው ግልገል ላያት ሁሉ ልዩ መስህብ አላት። ግልገል ቀጭኔዎች በተወለዱበት ወራት በግልገል መዋያ ተሰባስበው ሙሉውን ቀን ዕረፍት በማድረግ፣ በመጫወትና በአካባቢያቸው የሚሆነውን ነገር በመመልከት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የቀጭኔ ግልገል ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት ያድ⁠ጋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሜትር የሚያክል ቁመት ሲጨምር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል። በአንድ ሳምንት ብቻ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ሊያድግ ይችላል! እናትዬው ለልጅዋ ከፍተኛ ጥበቃ የምታደርግ ሲሆን ልጅዋ የተወሰነ ርቀት እንድትዘዋወር ብትፈቅድላትም ሩቅ የማየት ችሎታ ስላላት በዓይኗ ትከታተላታለች። ቀጭኔ ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ስላላት ከአንበሳ በቀር የሚያጠቃት ጠላት የለም። ቢሆንም ይህችን የምታምር ፍጥረት የሰውን ያህል በብዛት አድኖ የገደለ የለም። ቀጭኔ በሚያምር ቆዳዋ፣ በሚጣፍጥ ሥጋዋና አንዳንዶች ምትሐታዊ ኃይል አለው በሚሉት ረዥምና ጥቁር ጭራዋ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ ስለሆነች በአሁኑ ጊዜ የዚህች ሰላማዊ ፍጡር የወደፊት ሕልውና ስጋት ላይ ወድቋል። በአንድ ወቅት በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች እንደ ልብ ትታይ የነበረችው ቀጭኔ በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው በቂ ጥበቃ በሚደረግላት ፓርኮች ብቻ ሆኗል። የቀጭኔ አካላዊ ቅርጽና ግዝፈት ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል። በጣም ትልቅ ቁመትና ረዥም አንገት ስላላት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖራትና ወደ ሁሉም የአካሏ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ማድረግ የማይቻል ነገር ሊመስል ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀጭኔ አንገቷን ወደ መሬት ስታጎነብስ በስበት ኃይል ምክንያት ብዙ ደም ወደ ጭንቅላቷ ፈስሶ አንጎሏን ማጥለቅለቅ ነበረበት። ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ደሟ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ልቧ ተመልሶ ራሷን እስከ መሳት ሊያደርሳት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ነገር አይደርስም። ለምን? የቀጭኔ የደም ዝውውር ሥርዓት በዓይነቱ ልዩ ለሆነው ለዚህች እንስሳ ቅርጽና መጠን እንዲያገለግል ሆኖ በታላቅ ጥበብ የተሠራ ነው። ልቧ ራሱ በጣም ትልቅ ሲሆን ደሙን ሦስት ሜትር ተኩል ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ አንጎላ ለመግፋት የሚያስችል አቅም አለው። በደቂቃ እስከ 170 ጊዜ የሚመታውና 7 ሳንቲ ሜትር ያህል ውፍረት ባለው ጡንቻ የተገነባው የቀጭኔ ልብ ከሰው የደም ግፊት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ግፊት ያመነጫል። ወደ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው ካሮቲድ የተባለው የደም ቧንቧና ከአንጎል ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም የሚሸከመው ጀጉላር የተባለው የደም ቧንቧ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚያስችል መጠን ሊኖራቸው ይገባል። በእርግጥም እነዚህ የደም ቧንቧዎች ከ2.5 ሳንቲ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው ከመሆኑም በላይ ጠንካራና የመለጠጥ ችሎታ ባላቸው ሕዋሳት የተገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንካሬና የመለመጥ ችሎታ አላቸው። ቀጭኔ ከጭንቅላቷ ጎንበስ በምትልበት ጊዜ ወደ አንጎሏ የሚሄደውን የደም ፍሰት የሚቆጣጠሩ ልዩ መቆጣጠሪያዎች አሏት። አንጎልና አንገት በሚገናኙበት ቦታ ላይ ትልቁ ካሮቲድ የደም ቧንቧ ሬቴ ሚራቢሌ ተብሎ ከሚጠራ አስደናቂ የሆነ መረብ መሰል አካል ይገናኛል። በከፍተኛ ኃይል ተገፍትሮ የመጣው ደም እዚህ ጋር ሲደርስ በጣም በርካታ ወደሆኑ ትናንሽ የደም ሥሮች እንዲገባ ስለሚደረግ የደሙ ግፊት ተስተካክሎ በአንጎል ላይ ጉዳት የማያስከትል ይሆናል። ቀጭኔዋ ራስዋን ጎንበስ በምታደርግበት ጊዜ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው መረብ ይለጠጣል፤ ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ይኮማተራል። ይህም የስበት ኃይል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና የደም ግፊቷ በእጅጉ ቀንሶ ራሷን የምትስትበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳታል። የሳይንስ ሊቃውንት በጣም አስደናቂ ርዝመት ያለው የቀጭኔ አንገት ያሉት አከርካሪዎች ቁጥር ከአይጥ ወይም ከብዙዎቹ አጥቢ እንስሳ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቁ በጣም ተደንቀዋል! ይሁን እንጂ የቀጭኔ አከርካሪዎች በጣም ረዣዥሞችና እርስ በርሳቸው ልዩ በሆነ ሁኔታ የተሰካኩ በመሆናቸው እንደ ልብ ሊተጣጠፉ ይችላሉ። ቀጭኔ አንገቷን መጠምዘዝና ማጠፍ ስለምትችል ሁሉንም የአካሏን ክፍሎች ለመላስም ሆነ ረዣዥም የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ለመድረስ ትችላለች።
ለቀጭኔ ወደ ላይ በመንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ከባዱ ነገር ምንድነው?
ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት
519
በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ። ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ። በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች። አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው። ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።
በሴኔጋል አብዱ ዲዮፍ ከመቼ ጀምሮ ነው ወደ ፕሬዝዳንትነት ስልጣን የመጡት?
ከ1981
863
ሊንጋላ ሊንጋላ (Lingala) ከባንቱ ቋንቋዎች ቤተሠብ አንድ ነው። የሚናገርበት በተለይ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ስሜን-ምዕራብ ክፍል፣ በኮንጎ ሪፑብሊክም፣ እንዲሁም በአንጎላና በመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ነው። ተናጋሪዎቹ 10 ሚልዮን ናቸው። የሊንጋላ መነሻ ቦባንጊ በተባለ ቋንቋ ነበር። ከኮንጎ ነጻ መንግሥት አስቀድሞ ቦባንጊ የአከባቢው መደበኛ ቋንቋ ይሆን ነበር። የቤልጅክ ንጉስ አገሩን ከያዙ በኋላ የቀኝ አገሩ መንግሥት ለማስተዳደርና ለመሰበክ ቋንቋውን ጠቃሚ ሆኖ አገኙት። ካለፈው ቦባንጊ እንዲለይ የአዲሱን ቋንቋ ስም ባንጋላ ብለው ጠሩት። ሚስዮናዊዎቹ ወዲያ (1900 አ.ም.) ባንጋላን ዳግመኛ ሲያሻሽሉ "ሊንጋላ" እንዲህ ተፈጠረ። ሊንጋላ ከፈረንሳይኛ ብዙ ቃሎች ተበድሮ ደግሞ ከፖርቱጊዝ ተጽእኖ አለ (ለምሳሌ "ማንቴካ" = ቅቤ፤ "ሜሳ" = ጠረጴዛ፤ "ሳፓቱ" = ጫማ) ከእንግሊዝኛም ተጽእኖ አለ ("ሚሊኪ" = ወተት፤ "ቡኩ" = መጽሐፍ)።
የሊንጋላ ምንጭ ምን ቋንቋ ነበር?
ቦባንጊ
168
ደስታ ተክለወልድ አለቃ ደስታ ተክለወልድ የኢትዮጵያ ዕውቅ የቤተክርስቲያን ሊቅ፣ የመዝገበ ቃላት አዘጋጅና ደራሲ ነበሩ። ሐምሌ 19 ቀን 1893 ዓ.ም. በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ላይ ወግዳ ጎሽ ውኃ ቀበሌ የተወለዱት አለቃ ደስታ፣ ያረፉት ጳጉሜን 2 ቀን 1977 ዓ.ም. ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ከአጥቢያቸው ጀምሮ እስከ ደብረ ሊባኖስ የቅኔና የዜማ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡ ቀለምን ፈጥኖ በመቀበልና በማስተዋል ችሎታቸው የተመሰከረላቸው አለቃ ደስታ የመጻሕፍት አንድምታ ትርጓሜን አደላድለዋል፡፡ በብርሃንና ሰላም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት ቅዱሳት መጻሕፍትን በማረምና በማስተካከል ከ1916 እስከ 1920 ዓ.ም. ድረስ የሠሩ ሲሆን፣ በእርሳቸው አረጋጋጭነት በርካታ መጸሕፍት ለሕትመት በቅተዋል፡፡ በሀገረ ጀርመን በታተመው ኢንሳይክሎፔዲያ ኢትዮፒካ እንደተዘገበው፣ ወደ ድሬዳዋ በመሄድ በአልዓዛር ማተሚያ ቤት ሥራቸውን የቀጠሉበት አጋጣሚ የተፈጠረው ከሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መተዋወቃቸው ነበር፡፡ ከ30 ዓመት በፊት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ምን እየሠሩ ዐምድ አጋጣሚውን እንዲህ ያስታውሰዋል፡፡
አለቃ ደስታ ተክለወልድ በብርሃንና ሰላም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ማተሚያ ቤት ከመቼ እስከ መቼ ሰሩ?
ከ1916 እስከ 1920 ዓ.ም.
399
ኃይሌ ገብረሥላሴ ኃይሌ ገብረሥላሴ በ ሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፷፭ (1965) ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ፣ አርሲ ክፍለ ሀገር የተወለደ አቻ ያልተገኘለት ድንቅ የረጅም ርቀት ኢትዮጵያዊ ሯጭ ነው። ኃይሌ በሩጫ ዘመኑ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ፣ በግማሽ ማራቶን፣ በማራቶንና እንዲሁም በሌሎቹ የሩጫ ዓይነቶች ከ ፲፩ በላይ የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብሯል። ኃይሌ በሩጫ ችሎታው ጠንካራ የሆነበት ምናልባትም ከመንደሩ ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ነው ተብሎ ቢታመንም የተፈጥሮ ጥንካሬው ዓለምን ያስደነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ኃይሌ ሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከመሆኑም በላይ በ፴፫ ዓመት ዕድሜው ፪ ሰዓት ከ፬ ደቂቃ በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለምን ማራቶን ክብረ-ወሰን ሊሰብር ችሏል። ኃይሌ ገብረሥላሴ እስካሁን ድረስ ፳፮ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን ሰብሯል። ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ በሲድኒ እና በአትላንታ ኦሊምፒኮች በ፲ ሺህ ሜትር ሩጫዎች ወርቅ አስመዝግቧል። በ ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. ኤንዱራንስ (Endurance) የተባለ ስለ እራሱ የእሩጫ ድል ፊልም ተሠርቷል።
ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ የሩጫ ሕይወቱን በተመለከተ የተሰራው ፊልም ርእሱ ምን ይባላል?
ኤንዱራንስ
560
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፯ ዓ/ም በአንዲት “ብርሃንና ሰላም” በተሰኘች አነስተኛ ጋዜጣ ሕትመት ሥራውን ጀመረ። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መጻሕፍት ፣ ጋዜጦች ፣ መጽሔቶችና የምስጢራዊ ሕትመት ሥራዎች በተለያዩ ቋንቋዎች እያተመ ይገኛል። ማተሚያ ቤቱ በርካታ የመንግሥት እና የግል ጋዜጦችን የሚያትም ሲሆን ፥ በተጨማሪም በየዓመቱ በርካታ የፈተና ሥራዎችን በማተም ይታወቃል። ጥንታዊ ኢትዮጰያውያን ሊቃውንት የሚጽፏቸው መጻሕፍት ለሕዝብ የሚቀርቡት ብራና ተፍቆ ፣ ቀለም ተቀምሞ በእጅ ተፅፎ ነበር። በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ-መንግሥት የተጀመረው የዘመናዊ ሕትመት ሥራ በሀገሪቱ ቁጥራቸውና መጠናቸው በርከት ያሉ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች፣ መጻሕፍት፣ እንዲሁም ሌሎች የሕትመት ውጤቶች መታተም በመጀመራቸው የትምህርትና የሥልጣኔ መሰፋፋት ላይ የበኩሉን ሚና መጫወት ጀመረ። የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤትም ምሥረታ ዋና ዓላማ የአገሪቱን መንፈሳዊ መጻሕፍት በብዛት እና በዘመናዊ መልክ ከእጅ ጽሑፍ ወደ ሕትመት ለማሸጋገር ሲሆን፤ ምሑሩ ተክለጻድቅ መኩሪያ (፲፱፻፷፩ ዓ/ም)፣ ማተሚያ ቤቱ መስከረም ፫ ቀን ፲፱፻፲፬ ዓ/ም መቋቋሙን እና ብዙ ሥጋዊና የመንፈሳዊ መጻሕፍት እንዲሁም ምክርና ተግሣጽ፣ የለት ወሬ፣ የሹም-ሽር አዋጆችን ያትም እንደነበር ዘግበዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ረዳት መምህር መኩሪያ መካሻ፤ “የፕሬስ ታሪክ” በተሰኘ ጽሑፋቸው ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ፣ ራስ ተፈሪ መኮንን በ፲፱፻፲፫ ዓ/ም የማተሚያ መሣሪያ አስመጥተው “ትንሹ ግቢ” (በኋላ ገነተ ልዑል — አሁን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ) ይባል በነበረው መኖሪያቸው ውስጥ አስተክለው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የተባለውን እንደመሠረቱ ዘግበዋል። ከሁለት ዓመት በኋላ በ፲፱፻፲፭ ዓ/ም አራት ተጨማሪ ማተሚያዎች ተገዝተው ከተተከሉ ከአንድ ዓመት በኋላ ሣምንታዊው ‘ብርሃንና ሰላም’ የተሰኘው ጋዜጣ እየታተመ፣ አስቀድሞ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ከተጀመረችው ‘አዕምሮ’ ጋዜጣ ጋር እስከ ጠላት ወረራ ዘመን ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ይሠራጩ ነበር። የወቅቱ ማተሚያ መሣሪያዎች በእግር እየተረገጡ የሚንቀሳቀሱ መሣሪያዎች ሲሆኑ የሠራተኞቹ ቁጥር ከሰባት እስከ አሥራ-ሁለት እንደነበር ተዘግቧል። ራስ ተፈሪም አልፎ-አልፎ በብርሃን እና ሰላም ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት ይረዱ እንደነበረና ጽሑፎቻቸውንም ለሕትመት ያበቁ እንደነበር ተምዝግቧል።
ጥንታዊ ኢትዮጰያውያን ሊቃውንት መጻሕፍት የሚጻፈው እንዴት ነበር?
ብራና ተፍቆ ፣ ቀለም ተቀምሞ በእጅ ተፅፎ ነበር።
324
መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጅሩ ቆላ ውስጥ እምባጮ መግደላዊት በሚባል ሥፍራ መጋቢት ፲፯ ቀን በ፲፰፻፺፩ ዓ/ም ተወለዱ። በቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያ ትምህርታቸውን እስከ ዳዊት ድረስ ካጠናቀቁ በኋላ የዜማ ትምህርት ተከታትለው ጾመ ድጓ እና ድጓን ዘልቀዋል። ቀጥሎም የቅኔ ትምህርታችውን አጠናቀው በ ፲፱፻፭ ዓ/ም በአሥራ አራት ዓመት ዕድሜያቸው በወንበር ፀሐፊነት የመጀመሪያ ሥራቸውን ጀመሩ። የመጻሕፍተ ሐዲሳትን ትርጓሜ፤ የዮሐንስ አፈወርቅን ትርጓሜ፤ እንዲሁም የመቅድመ ወንጌልን ትርጓሜ ትምህርት ያጠናቀቁት እኝህ ታላቅ ሰው ብርሃንና ሰላም (ጋዜጣ) የተሰኘው ጋዜጣ ሲመሠረት የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ በመሆን፣ ቀጥለውም በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የግዕዝና የአማርኛ አስተማሪ በመሆን አገልግለዋል። ከፋሺስት ወረራ በኋላ ከ፲፱፻፴፫ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፷፫ ዓ/ም ድረስ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በኃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ሥነ ጽሑፍንና ታሪክን በተመለከተ፣ አሥራ ሦስት መጻሕፍትን የደረሱ ሲሆን፣ ሰባት መጻሕፍት ደግሞ ተርጉመው አቅርበዋል። እንዲሁም የተለያዩ ጽሑፎችን አሰባስበው ከማዘጋጀታቸው ባሻገር፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ሥራዎችም ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በትብብር አዘጋጅተዋል።
ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ መቼ ተወለዱ?
መጋቢት ፲፯ ቀን በ፲፰፻፺፩ ዓ/ም
84
ከ1881 እስከ 1905 ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በአፍሪካ ይዞታቸውን እያሰፉ የነበሩትን የአውሮፖ ሀይሎችን ጥቃት በመከላከል ኢትዮጵያን በስርዓት አስተዳድረዋል፡፡ በዚያን ጊዜ ጣልያን ኤርትራን በከፊል ቅኝ ገዝታ የነበረችበትና በ1880ዎቹ አጋማሽ ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ቅኝ ገዝታት የነበረችበት ጊዜ ስለነበር ከሌሎች አውሮፖ አገራት በበለጠ ለኢትዮጵያ አስጊ ነበረች፡፡ በ1880 ግን እስከዛሬ ድረስ ዝነኛ በሆነው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ጣልያንን ድል በማድረግ በአፍሪካ የባእዳን ገዥ ሀይሎችን ያሸነፈች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የቅኝ ገዥዎችን ወረራና መስፋፋት በመመከትና ድልን በመቀዳጀት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በባርነት ቀንበር ተጠምደዉ ለሚማቅቁ የመላዉ ዓለም ህዝቦች ከፍተኛ ክብርና ተስፋን አጎናጥፈዋል በ1908 የዳግማዊ ሚኒሊክ ልጅ የሆኑትን እቴጌ ዘውዲቱ ስልጣን ያዙ ፡፡ የሳቸው የቅርብ የስጋ ዘመድ የነበሩት ራስ ተፈሪ መኮንንም ሞግዚት አስተዳደርና ወራሽ ሆነው ተሹመዋል፡፡ እቴጌ ዘውዲቱ በ1922 ሲሞቱ ተተኪያቸው ዐጼ ሀይለስላሴ ስልጣን ያዙ ፡፡ ነገር ግን በ1928 ዓ.ም የጣልያን ሀይሎች ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ ወረው ሲቆጣጠሩ ግዛታቸው ተቋርጦ ነበር፡፡
ዳግማዊ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን በሚያስተዳድሩበት ወቅት ከሰሩት አንዱ ተግባር ምን ነበር?
የአውሮፖ ሀይሎችን ጥቃት በመከላከል
53
ኢትዮጵያ ከ ፹ (80) በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የቻለች ሀገር ነች። ትልልቆቹ ብሄረሰቦች ፣ የአማራ ፣ እና የኦሮሞ የትግራይ እንደሁም የሶማሌ ሲሆኑ እነዚሁ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የሀገሪቷ ሕዝብ ቁጥር ከ 3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ። በሃይማኖት በኩልም ሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖቶች ክርስትና እና እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። የክርስትና እምነት ተከታዮች ከ 55%-60 % ፣ እስልምና ከ35% እሰከ 40% እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ 5%-8% የሚሆነውን ይይዛሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ከ ፹ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች አፍሮ-ኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ በሚባሉ ሁለት ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥም ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ የሚባሉ ንዑስ ክፍሎች አሉ። ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ ፣ ኩናማኛ ፣ ጉሙዝኛ ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው።
ኩሻዊ የቋንቋ መደብ ውስጥ የሚጠቃለሉ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ዘርዝር?
አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ
738
ሄርበርት ሁቨር (1866 - 1957 ዓ.ም.) ከ1921 እስከ 1925 ዓ.ም. ድረስ 31ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። የሁቨር ቤተሠብ ከስዊስና ጀርመን ትውልድ ሲሆን ሃይማኖቱ የክዌከር ('የሚንቀጠቀጡ' ማለት ነው) ቤተ ክርስቲያን ነበረ። ወላጆቹ በልጅነቱ ጊዜ ካረፉ አንስቶ ድሃ አደግ ሆነና ከአጎቱ ጋር አደገ። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቴ መጀመርያ ክፍል በመሆኑ ትምህርቱ በነጻ ተቀበለ። ከዚያ በላይ የዩኒቬርሲቴው የቤስባልና የፉትቦል ቡድኖች አለቃ ሆነ። በ1887 ዓ.ም. የጂዮሎጂ ዲግሪ ይዘው ተመረቁ። ለ20 ዓመት የማዕደን ሊቅ ሲሆኑ እንኳን በአውስትራልያና በእንግሊዝ በማዕደን ዘርፍ የሠሩት ሥራ ስመ ጥሩ ሆነ። መጀመርያው ታላቅ አለማዊ ጦርነት በ1906 ዓ.ም. በጀመረበት ወቅት ሁቨር ከራሳቸው ኪስ ለጋሥነት አውጥተው 120,000 አሜሪካውያን ቱሪስቶችና ሠራተኞችን ከአውሮፓ ወደ አገራቸው አስመለሷቸው። ከዚያ በጀርመኖች በተወረረው በቤልጅግ ውስጥ የኖሩት ረሃብተኞች ምግብ እንዲደርሳቸው ብዙ አደረጉ። በዚህ አይነት ሥራ በጦርነት ጊዜ የሁቨር ስም ጀግና እንዳለው ሁኔታ በመገኘት ላይ ሄዶ ነበር። ጦርነቱም ከተጨረሰ በኋላ ለምሥራቅ አውሮጳ ድሃ ሕዝብ እስከ ሩስያም ድረስ በረሃብ ላሉት ሰዎች ምግብ አደረሷቸው።
ሄርበርት ሁቨር ወላጆች ከሞቱ በኃላ ማን ነው ያሳደገው?
ከአጎቱ
185
ጁፒተር እና ሳተርን ጁፒተር እና ሳተርን ከ4 መቶ አመት በሆላ ትላንት ምሽት በአንድ ላይ ገጥመው አንድ ፕላኔት መስለው ታይተዋል፡፡ ፕላኔቶቹ ከቀን ቀን እየተቀራረቡ መጥተው ትላንት ምሽት በአንድ ላይ በመግጠም ደማቅ ብርሃን ፈንጥቀዋል፡፡ የሁለቱ ግዙፍ ፕላኔቶች ምህዋር  በየ20 ዓመቱ የሚገናኙ ሲሆን ክስተቱ በብዛት በቀን ውስጥ ስለሚሆን በዓይን ለማየት ከባድ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ‘ዘ ስታር ኦፍ ቤቴልሄም’ ወይም የቤቴልሄም ኮከብ ተብሎ በሚጠራው በዚህ ክስተት ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ሰማይ ላይ እጅግ ደማቅ ብርሃን ታይቶ እንደነበር ሳይንቲስቶች መናገራቸውን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡
በየ20 አመቱ በመግጠም አንድ የሚሆኑ ፕላኔቶች እነማ ናቸው?
ጁፒተር እና ሳተርን
13
አፄ ዘርአ ያዕቆብ አጼ ዘርአ ያዕቆብ በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስት ክብረ እግዚእ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮውፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ(ከቀኝ ያለውን ካርታ ይመልከቱ) ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው። የዘርዓ ያዕቆብ አባት ቀዳማዊ ዳዊት ባረፉ ጊዜ፣ እንደ ጥንቱ የኢትዮጵያ ባህል ወግ መሰረት፣ ታላቅ ወንድማቸው የነበሩት ቀዳማዊ ቴወድሮስ በ1414 ሲነግሱ ታናሽ ወንድማቸውን በግዞት ወደ አምባ ግሽን እንዲሄድ አደረጉ። አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሀፈ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው መሰረት እስከ ነገሱበት ሰኔ 20 ፣ 1434 ዓ.ም. ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ (አምባ ግሸን) ላይ ለሚቀጥሉት 20 አመታት በእስር ኖሩ። ሆኖም ግን በግዞት እያሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊያቸው መጠን እየበዛ ሄደ። በነዚህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዓመት ወደ ዓመት እይተበላሸ ሂዶ በመጨረሻ ከአምባው ላይ ለሹመት ሲወርዱ አገሪቱ በእርስበርስ ሽኩቻ እየታመሰች፣ በሃይማኖት በኩልም መከፋፈል ተፈጥሮ የውጭ ሀይሎችም ከነገ ዛሬ አጠቁን እየተባለ ይሚፈራበት ሁኔታ ገጠመው። የወደፊቱ ንጉስ ብዙ እድሜውን ያሳለፈው ከሰው ተለይቶ አምባ ላይ ስለነበር፣ የዲፕሎማሲ ጥቅሙ አልተረዳውም ነበር። ይልቁኑ ፊት ለፊት የተጋረጡትን የሃገሪቱን ችግሮች በሚያስፈራ ድፍረት እና ምንም በማያወላዳ ጽናት ተጋፈጠው። ዓፄ ዘርአ ያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ንግስት እሌኒን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ። በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤተክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን ቆይቱ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳተ በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል ። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቀ እስጢፋ ወገኖች እምነት ነው። እነዚህ እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴ ባስተማራቸው መሰረት ለመስቀል መስገድና ለስእል አድኅኖ ለድንግል ማርያም መስገድ አይገባም የሚሉ ነበሩ።ተከራክረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ አሸንፈዋል። በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀው ግዛታቸውን ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር። በ1456 ዓ.ም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ በነበሩበት ቦታ ታላቅ ብርሃን ስለታየ የነበሩበትን ቦታ ደብረ ብርሃን በማለት የሃገሪቱ ዋና ከተማ አድርገው ቆርቁረዋል። እስከ እለት ህልፈታቸውም ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበረች።ኢትዮጵያዊ መንፈሳዊ ፈላስፋ። አጼ ዘርአ ያዕቆብ በጦር ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን የሚታወቁት፣ ከ 20 በላይ መጻህፍትንም በመድረስና ለትውልድ በማቅረብ ጭምርም ነው።
አጼ ዘርአ ያዕቆብ የነገሱበት ዘመን ከመቼ እስከ መቼ ነበር?
1434 - 1468 እ.ኤ.አ.
196
የመደመር መንገድ መጽሐፍ ሁለት ዓላማ ያነገበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ ይህም በአንድ በኩል ሐሳብ ማስተላለፍ በሌላ በኩል በገቢው ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ የመጽሐፉ የነጠላ መሸጫ ዋጋ 350 ብር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አንባቢዎች ሊዳረስ የሚችል በቂ ቅጅ ስላለ ከዚህ በላይ ከሚሸጡት እንዳይገዙም አሳስበዋል፡፡
የመደመር መጽሐፍ ጸሐፊ ማነው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
34
ዳምጠው አየለ ዳምጠው አየለ (23.11. 1944 አ/ም – 27.10. 2006 አ/ም) ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፋኝ ነበር። በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል። ዳምጠው ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል። ዳምጠው መራቤቴ እያለ በየባእላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። ባጋጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል። ዳምጠው አየለ ኖርዌይ ሃገር በስደት ለ 8 አመት ያክል ኖሯል። ኢትዮጵያም ከገባ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብራኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ 62 አመቱ ሰኔ 27 2006 አ/ም ቀን ህይወቱ አልፏል። የቀብር ስነስርአቱም ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።
ዳምጠው አየለ ወደ አዲስ አበባ ይዘውት የመጡት ክፍሌ ሞገስ ምኑ ነበሩ?
መምህሩ
493
ኃይሌ ገብረሥላሴ ኃይሌ ገብረሥላሴ በ ሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፷፭ (1965) ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ፣ አርሲ ክፍለ ሀገር የተወለደ አቻ ያልተገኘለት ድንቅ የረጅም ርቀት ኢትዮጵያዊ ሯጭ ነው። ኃይሌ በሩጫ ዘመኑ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ፣ በግማሽ ማራቶን፣ በማራቶንና እንዲሁም በሌሎቹ የሩጫ ዓይነቶች ከ ፲፩ በላይ የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብሯል። ኃይሌ በሩጫ ችሎታው ጠንካራ የሆነበት ምናልባትም ከመንደሩ ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ነው ተብሎ ቢታመንም የተፈጥሮ ጥንካሬው ዓለምን ያስደነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ኃይሌ ሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከመሆኑም በላይ በ፴፫ ዓመት ዕድሜው ፪ ሰዓት ከ፬ ደቂቃ በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለምን ማራቶን ክብረ-ወሰን ሊሰብር ችሏል። ኃይሌ ገብረሥላሴ እስካሁን ድረስ ፳፮ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን ሰብሯል። ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ በሲድኒ እና በአትላንታ ኦሊምፒኮች በ፲ ሺህ ሜትር ሩጫዎች ወርቅ አስመዝግቧል። በ ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. ኤንዱራንስ (Endurance) የተባለ ስለ እራሱ የእሩጫ ድል ፊልም ተሠርቷል።
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የምን ሀገር ሰው ነው?
ኢትዮጵያዊ
105
ኢትዮጵያ በመሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ላስመዘገበችው ውጤት ሩዋንዳ በተዘጋጀው የአፍሪካ የጤና ኮንፍራስ ላይ እውቅናን አግኝታለች :: በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያ የሆነችው ወ/ሮ ሰናይት 40,000 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን በመወከል ሽልማቱን ተቀብላለች::
ኢትዮጵያ በመሠረታዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ላስመዘገበችው ውጤት የት ሀገር ነው እውቅና የተሰጣት?
ሩዋንዳ
47
ባሕር-ዳር ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች። ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎሜትር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት። ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ "ከባሕሩ-ዳር" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል። ባሕር-ዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕር-ዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር-ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር-ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር-ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ።
ባሕር ዳር ከተማ ከአዲስ አበባ በምን ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች?
565 ኪ.ሜ
315
አንድ ወጣት ተማሪ ከወዳደቁ ቁሳቁሶች በውሃ ላይ የሚነዳ የብስክሌት ጀልባ መስራቱ ተገለጸ፡፡ ጌታባለው መኩሪያው የተባለው ወጣት በባህርዳር ዩኒቨርስቲ 3ኛ ዓመት የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወጣቱ የወዳደቁ ፒፒሲ ትቦዎች፣ የላሜራ ብረቶችና ፌሮዎች እንዲሁም አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የብስክሌት አካላትን ተጠቅሞ ነው የብስክሌት ጀልባ (Pedal-Boat) መስራት የቻለው፡፡ ጌታባለው መኩሪያው ከወዳደቁ ቁሳቁሶች የሰራውን የብስክሌት ጀልባ በውሃ ላይ በመንዳት ሙከራ ማድረጉም ተገልጿል፡፡
ጌታባለው መኩሪያ የፈጠራ ስራውን ከምን ከምን ሊሰራው ቻለ?
የወዳደቁ ፒፒሲ ትቦዎች፣ የላሜራ ብረቶችና ፌሮዎች
129
ጣና ሐይቅ ጣና ሐይቅ ቅዱሱ ሐይቅም ይባላል። ከኢትዮጵያ አንደኛ እና ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል። በቁጥር ከ35 በላይ ደሴቶች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥም 22ቱ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት ናቸው። ባንዳንዶቹ ላይም (ለምሳሌ በዳጋ ደሴት) የድሮ የኢትዮጵያ መሪዎች መቃብሮች ሲገኙ ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ለመጀመሪያ ያስተዋወቀው አቡነ ሰላማ መቃብርም በዚሁ ሃይቅ ይገኛሉ። የጣና ሃይቅን የሚመግቡ 3ቱ ዋና ወንዞች ርብ፣ ጉማራ ወንዝ ና ትንሹ አባይ በመባል ይታወቃሉ። አሁን ባለው ይዞታ የጣና ሃይቅ 1,454 ቶን አሳ በአመት ይመረታል። ነገር ግን ይሄ የምርት ሃይቁ ያለምንም ችግር ሊያስተናግድው ከሚችለው 15 በመቶው ያህል ብቻ ነው።
ከጣና ሐይቅ በዓመት ምን ያል የዓሳ ምርት ይገኛል?
1,454 ቶን
374
ሺስቶሶሚሲስ ሺስሰቶሶሚያሲስ (ቢልሃርዚያ እና ካታያማ ትኩሳት በመባል ይታወቃል፡፡) በሽታው የሚተላለፈው ጥገኛ ትላትሎች በሆነው የ ሺስቶሶማ የህዋስ አይነት ነው፡፡ የ ሽንት መተላለፊያ ወይም አንጀት ሊያጠቃ ይችላል። የህመሙ ምልክት የሆድ ህመም፣ ተቅማጥ፣ ደም የተቀላቀለበት ሰገራ ወይም በሽንት ላይ ደም መታየትን ያጠቃልላል። ለረጅም ጊዜ ህመሙ የቆየበት ሰው የጉበት ህመም፣ የኩላሊት ስራ ማቆም፣ መሃንነት ፣ ወይም የፊኛ ካንሰር ሊያስከትብ ይችላል፡፡ በልጆች ላይ ዝቅተኛ እድገትና የመማር ችግር ሊያስከትል ይችላል። ቢልሃርዝያ በሽታው የሚሰራጨው ትላትሎቹ ያሉበት ውሀ ላይ በሚፈጠር የቆዳ ንክኪ ነው። እነዚህ ትላትሎች የሚመነጩት ከተበከሉ ቀንድ አውጣዎች ነው፡፡ ይህ በሽታ በታዳጊ ሀገራት በሚነኙ ታዳጊዎች ላይ የተለመደ ሲሆን ምክንያቱም ልጆቹ በተበከለ ውሃ የመጫወታቸው አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በእለት ከእለት ስራ አማካኝነት ማለትም ገበሬዎች፣ አሳ አጥማጆችና ሌሎች የተበከለውን ውሀ የሚጠቀሙ ሰዎች የበሽታው ስጋት የሚያጠቃልላቸው ቡድኖች ናቸው። ሄልመንት በሽታዎች በሚባለው ቡድን ውስጥ ይጠቃለላሉ። ምርመመራው የሚደረገው የትሉን እንቁላሎች በሽንት ወይም ሰገራ ላይ በመመርመር ነው፡፡ በደም ላይ ፀረ እንግዳ አካል በመፈለግ ማረጋገጥም ይቻላል። በሽታውን የመከላከያ መንገድ ንፁህ ውህ አቅርቦትን ማሻሻልና የቀንድኣውጣ ቊጥርን መቀነስ ነው፡፡ ሲስቶሶሚያሲስ በዓለም ላይ ወደ 210 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ያጠቃል፣ እንዲሁም የሚገመተው ከ 12 000 እስከ 200,000 የሚሆነው ሕዝብ በአመት ውስጥ ይሞታል ተብሎ ይገመታል፡፡ በሽታው በስፋት የሚታየው በ አፍሪካ ፣ እንዲሁም በ እስያ ና ደቡም አሜሪካ ነው። ወደ 700 ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ፣ ከ70 በላይ ሃገራት፣ በሽታው በስፋት በተሰራጨበት አካባቢ ይኖራል፡፡ ሲስቶሶሚሲሰ ከወባ ወይም ማላሪያ ቀፅሎ በሁለተኛነት ያለ፣ እንደ ትላትል ትልቅ የኢኮኖሚ ተፅእኖ ያለው በሽታ ነው። ከጥንት ጀምሮ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ፣ ሲስቶሶሚሲሰ የ በሽንት ውስጥ ያለ ደም ምልክት የሚታየው በስሕተት እንደ የወንድ አይነት ወር አበባ እየተባለ በ ግብፅ እናም ለወንዶች ልጆች እንደ rite of የአምልኮ መተላለፊያ ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ የሚመደበው ችላ ከተባሉት የትሮፒካል በሽታ ስር ነው።
የቪስቶሶቶሚሲስ በሽታ ሲቆይ በልጆች ላይ ምን ሊያስከትል ይችላል?
ዝቅተኛ እድገትና የመማር ችግር
298
ከአድዋ ሽንፈት በኋላ ጣሊያኖች ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራርመው አዲስ ገዢ፣ ፈርዲናንዶ ማርቲኒ፣ 1897 ላይ በመሾም ግዛታቸውን ማጽናት ጀመሩ። በዚህ ወቅት የቀደመው ወታደራዊ ስርዓት እንዲቋረጥ ተደርጎ አገሪቱ የብሔር ልዩነትን "በሚያከበር" አስተዳደር ተከፍሎ እንዲቋቋም ተደረገ። ዳህላክ፣ አፋር እና ሰምሃር አንድ ላይ "ምስራቃዊ ክፍል" ተብለው ከምጽዋ እንዲተዳደሩ ተደረገ። "ምዕራባዊ ክፍል" ከአቆርዳት እንዲተዳደር ሲደረግ ቤኒ አሚርን፣ ናራንና ኩናማ ምድርን ያጠቃልል ነበር። ከከረን ሆኖ የሚተዳደረው ደግሞ ሰሜናዊ ሐማሴን (የእስልምና ተከታይ የሆነ)፣ ቤት አሰገደና ዓድ ሼኽ ነበሩ። ቀሪው ሐማሴን ከአስመራ፣ ሰራየ ከመንደፈራ(አዲ ወግሪ) እንዲተዳደር ሲደረግ አካለ ጉዛይ ከሳሆ ጋር ተዋህዶ ከአዲ ቀይሕ ይገዛ ጀመር። ከላይ ወደታች በተዘርጋ መዋቅር የጣሊያን ባለስልጣኖች እያንዳንዱን ክፍል ያስተዳድሩ ጀመር። የአገሪቱ ዋና ከተማ ከምጽዋ ወደ አስመራ የተዛወረው በዚህ ወቅት፣ በ1898 ነበር። ከ1898 እስከ 1908 በተደረጉ ውሎች (ከኢትዮጵያ፣ ከአንግሎ-ግብጻዊ ሱዳንና ከጅቡቲ ጋር) መሰረት የቅኝ ግዛቱ ድንበር ታወቀ። ኢትዮጵያን ስለ ድንበሩ ለማሳመን 3 አመትና 5ሚሊዮን ሊሬ ፈጅቶባቸው ግንቦት 1900 ላይ ያሰቡት ሊሳካላቸው ቻለ። ድንበሩ ከሞላ ጎደል የመረብ፣ በለሳና ሙና ወንዞችን የታከከ ነበር።
በ1898 የኤርትራ ዋና ከተማ ወደ አስመራ የተዛወረው ከየት ነበር?
ከምጽዋ
527
የኢትዮጵያ ሙዚቃ የመጀመሪያውን ግራማፎን ወይም የሸክላ ማጫወቻ በ፲፰፻፹፱ ዓ.ም. ሄንሪ ደ አርሊንስ እና ኒኮላስ ሊዋንቲቭ ለዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ አመጡላቸው። ይኸውም ማጫወት ብቻ እንጂ ድምጽ አይቀዳም ነበር። በኋላ ግን በዓመቱ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. ከንግሥት ቪክቶሪያ የተላኩ የእንግሊዝ መልዕክተኞች በመጡ ጊዜ ግራማፎኑንና ድምፅ መቅጃውን ይዘውላቸው መጡ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸው በዲስክ የተቀረፁት ዓፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ናቸው። ዛሬ በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ ብሪቲሽ ኢንስቲቲውት ኦፍ ሪኮርድ ሳውንድ በተባለው ሙዚየም ውስጥ ይገኛል። በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በሸክላ የተቀረፀው የመጀመሪያው ዜማ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ስራዎች ሲሆኑ ዘመኑም በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ነበር። ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በጀርመን ቆይታቸው ወቅት የጀርመን የሙዚቃ ድርጅት ጠይቋቸው የኢትዮጵያ መዲናና ዘለሰኛ ዜማዎች በ፲፯ አይነት ስልት እየተጫወቱ ተቀርፀዋል። ኩባንያው የተሰማ እሸቴን ዜማዎች በ፲፯ ሸክላዎች የቀረፀው ሲሆን ለዜማው ባለቤት የድካም ዋጋ እንዲሆን በወቅቱ ፲፯ ሺህ የጀርመን ማርክ ከፍሏቸዋል። በዘመኑ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያም አሁንም እነዚህ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ብርቅዬ ሸክላዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ውስጥ ተሰብስበው ይገኛሉ። እነዚህ በተቋሙ እጅ ያሉት ፲፮ ሸክላዎች እያንዳንዳቸው ሁለት ዜማዎችን የያዙ ሲሆኑ ባጠቃላይ ፴፪ ዜማዎች ተቀርፀውባቸዋል። እያንዳንዱ የሸክላው ገፅ ላይ A ወይም B ተብሎ ተሰይሟል፣ የዜማው ስም ተፅፎበታል፣ የዜማው ባለቤት ተሰማ እሸቴ ስም አለ፣ ሸክላው ጀርመን ሀገር መሰራቱ እንዲሁም የሸክላው ቁጥር ተጠቅሷል። በ፲፱፻፳፭-፳፮ ዓ.ም. አካባቢ የእነ ፈረደ ጎላ፣ ንጋቷ ከልካይና ተሻለ መንግሥቱ የዜማ ሸክላዎች ብቅ እስከሚሉ ድረስ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ሸክላዎች ከ፳ ዓመታት በላይ አቅም ባላቸው ቤተሰቦች ዘንድ በብቸኝነት በግራማፎን ሲደመጡ ቆይተዋል።
የመጀመሪያውን የሸክላ ማጫዋች ሄንሪ ደ አርሊንስ እና ኒኮላስ ሊዋንቲቭ ለአፄ ሚኒልክ ያመጡላቸው መቼ ነበር?
በ፲፰፻፹፱ ዓ.ም.
40
ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የወይዘሮ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ ነበር። በ1860 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ጦርነት ልጃቸው ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ሀገር ተወስዶ ነበር፡፡ ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡ በልዑሉ ውልደት የተደሰቱት አፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500 ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ በኋላ ከእድሜው ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴን ስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እና አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች እና አጫዋቾች ተመረጡለት፡፡ አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብ ተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡ በመርከቢቱ ላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀ ወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉ አለማየሁን ማስከተል ያዘወትር ነበር፡፡ ይህንን የሁለቱን ፍቅር ያየው ጀነራል ናፒየርም ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይልቁንም የአለማየሁን ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ካፕቴን ስፒዲ እንዲረከብ ስለወሰነ ሁለቱ ሞግዚቶች ጉዞው ተጠናቆ እንግሊዝ ሀገር ሳይደርሱ ከስዊዝ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡ ከሶስት ወራት የመርከብ ላይ ጉዞ በኃላ አለማየሁ እንግሊዝ ሀገር ደረሰ፡፡
ልዑል አለማየሁ ሲወለድ በደስታ አጼ ቴዎድሮስ ስንት እስረኞች ፈቱ?
500
254
ዶናልድ ጆን ትራምፕ ዶናልድ ጆን ትራምፕ (ጁን 14 ቀን 1946 እ.ኤ.አ. ተወለደ) አሜሪካዊ ነጋዴ ፣ ፖለቲከኛ ፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቹ ታዋቂ እና 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፕሬዚደንት ነው። ሥልጣኑንም እ.ኤ.አ. በጃኑዌሪ 20 ቀን 2017 ተረክቧል። በክዊንስ ኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው አቶ ትራምፕ በሪል እስቴት ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የፍሬድ ትራምፕ ልጅ ነው። በኮሌጅ እያለም ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ በተባለው ድርጅት ይሠራ ነበር። በእ.ኤ.አ. 1968 ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ ያንን ድርጅት ተቀላቀለ። በእ.ኤ.አ. 1971 ደግሞ ሙሉ ሥልጣን ከተሠጠው በኋላ የድርጅቱን ስም ወደ "ዘ ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን" ለወጠው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ካሲኖዎችን ፣ የጎልፍ ሜዳዎችን ፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች በእርሱ ስም የሚጠሩ ንብረቶችን አፍርቷል። እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2015 ድረስ ዘ አፕሬንቲስ የተባለ ፕሮግራምን በኤን ቢ ሲ ላይ ያቀርብ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የሪፎርም ፓርቲ እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ ቴድ ክሩዝ እና ጆን ካሲች ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታወጀ። በእ.ኤ.አ. ኖቬምበር 8 ቀን 2016 ላይ የፕሬዚደንትነት ምርጫውን አሸነፈ። ማሸነፉንም ተከትሎ ብዙ የተቃውሞ ሠልፎች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በ70 ዓመቱም ሥልጣን ላይ በመውጣቱ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ፕሬዚደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ያደርገዋል።
ዘኦፕሬንተስ የተባለው ፕሮግራም በኤን ቢ ሲ ላይ መቼ ቀረበ?
በእ.ኤ.አ. 1971
338
ጎንደር ከተማ ፋሲለደስ የጎንደር ከተማን በ1636 የኢትዮጵያም ዋና ከተማ አድርጎ እንደቆረቆራት ይታመናል። ከሱ በፊት በአካባቢው ከተማ እንደነበር ወይም እንዳልነበር በታሪክ የተገኘ ማስርጃ እስካሁን የለም። አከታትሎም የፋሲል ግቢንና 44ቱ ታቦታት ተብለው የሚታወቁትን የጎንደር ከተማ አብያተ ክርስቲያናት መሰረት ጣለ። በአፄ ፋሲል ከተመሰረቱት ታዋቂወቹ 44 አብያተ ክርስቲያናት፣ ታዋቂወቹ አደባባይ እየሱስ፣ አደባባይ ተክለ ሃይማኖት፣ አጣጣሚ ሚካኤል፣ ግምጃቤት ማራያም፣ ፊት ሚካኤል፣ እና ፊት አቦ ይገኙበታል። ያለመታከትም 7 የድንጋይ ድልድዮችን በማሰራት እስካሁን ድረስ ስሙ ሲጠራ ይኖራል። አልፎም በግራኝ አህመድ ዘመን በእሳት ጋይቶ የነበረችውን አክሱም ፂዮን በአዲስ መሰረት እንደገና ማሰራት ችሎአል። ፋሲለደስ በዘመኑ እጅግ ተወዳጅ ንጉስ ቢሆንም አመጽ መነሳቱ አልቀረም። በላስታ ለምሳሌ በ1637 መልክዓ ክርስቶስ በተባለ ሰው መሪነት ጦርነት ተነስቶ አፄ ፋሲልን ስጋት ላይ ቢጥልም በሚቀጥለው አመት በተደረገው ጦርነት አመፁ ሊገታ ችሎአል። ፋሲለደስ ፖርቱጋሎችን ቢያባርርም ከውጭው አለም ጋር ብዙ ግንኙነት ያደርግ ነበር። ለምሳሌ በ1664-5 የህንድ ንጉስ አውራንግዘብ ሲነግስ መልካም ምኞትን በመልክተኞቹ ለሙግሃሉ መሪ ልኮ ነበር። በ1666 ልጁ ዳዊት ሲያምጽ፣ ወህኒ ተብሎ ወደሚታወቀው አገር በግዞት ልኮት ነበር። ይህም ከጥንቶቹ የኢትዮጵያውን ነገሥት ተፎካካሪያቸውን ወደ አምባ ግሽን በግዞት እንደሚልኩት ስርዓት ነበር።
አፄ ፋሲል በ1664-5 ማን የተባለው የህንድ ንጉስ ሲነግስ መልካም ምኞታቸውን ገለጹ?
አውራንግዘብ
682
ቺኑዋ አቼቤ በሙሉ ስሙ ሲጠራ አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ ይሰኛል። ምናልባትም ናይጄሪያ ካሉዋት ምርጥ ፀሃፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ የሚሰለፍ ሳይሆን አይቀርም። በ1930 እ.ኤ.አ. ኦጊዲ በተባለች የናይጄሪያ ግዛት ከአዜያህ ኦካፎ እና ከጃኔት አቼቤ ተወለድ። በ1953 እ.ኤ.አ. ከለንደን ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። ለአቼቤ ድንቅ ሥራ የተባለለት "Things Fall Apart" 50 ወደሚሆኑ የአለም ቁዋንቁዋዎች የተተርጎመ ሲሆን ወደ 10,000,000 ቅጂዎች እንደተሸጡለት ይነገራል። አቼቤ ከአፍሪካ ፀሃፍት ሁሉ ሥራው በበዙ ቁዋንቁዋዎች በመተርጎም ክብረ ወሰኑን እንደያዘ ነው። ብዙዎችም ይኸው ድርሰቱ በአለም እስከዛሬ ከተደረሱ ምርጥ ልበ-ወለዶች መካከል እንደሆነ ይስማማሉ። አቼቤ ከ30 ከሚበልጡ ዩኒበርስቲዎች የክብር ዶክትሬት የተቀበለ ሲሆን ብዙ ሽልማቶችንም ከተለያዩ ድርጅቶች አግኝቷል። ይሁንና እስከ አሁን ድረስ የኖቤል ሽልማት ለማግኘት አልታደለም። ይኸውም በብዙው ጽሁፉ የመራቡን አለም ዘረኛነት የሚተች በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል። በ1990 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ምክንያት ከወገቡ በታች መንቀሳቀስ የተሳነው ሲሆን ኒው ዮርክ ውስጥ በሚገኘው የባርድ ኮሌጅ የቋንቋና ሥነ-ፅሁፍ ፕሮፌሰር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
ቺኑዋ አቼቤ ሙሉ ስሙ ማን ይባላል?
አልበርት ቺኑዋሉሞጉ አቼቤ
19
አኩሪ አተር አኩሪ አተር የአባዝርት አትክልት ዝርያ ነው። በየጊዜው አኩሪ አተርን መመገብ ለሴቶች ጉዳት ባያደርግም፣ ለወንዶች ጤናማ እንደማይሆን በሰፊ ቢታወቅም በአንዳንድ አገር ባሕል አመጋገብ በብዛት ይጨመራል። ከ20ኛዉ ክፍለ ዘመን አንስቶ በተለይ አሜሪካን ዉስጥ ወርቃማዉ ወይም ተዓምረኛዉ እህል የሚል ስያሜ አግኝቷል። አኩሪ አተር በፕሮቲን እና ቅባት ምንጭነቱ የሚወዳደረዉ የእህል ዘር የለም። ባለሙያ ካገኘም ለመጠጣትም ለመበላትም የሚችል የእህል ዘር ነዉ። ስለአኩሪ አተር ሲወሳ ብዙዎች የሚያስታዉሱት ለሕፃናት አካል ግንባታ ጠቃሚ መሆኑ ብዙ ጊዜ የተነገረለትን የአኩሪ አተር ወተት ሊሆን ይችላል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በኢትዮጵያዉያን የምግብ ጣዕም ለዛ ተላብሶ በተለያየ ምግብነት መቅረብ እንደሚችል እየታየ ነዉ። አኩሪ አተር ወደኢትዮጵያ የገባዉ በ1950ዎቹ መሆኑን ነዉ በእህሉ ላይ ምርምር የሚያደርጉት ባለሙያዎች የሚያስረዱት። በአኩሪ አተር ላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደረገዉ ዝርያ የማዉጣት ምርምርም 22 ዓይነት ዘሮች እስካሁን ተገኝተዋል። አኩሪ አተርን በሀገር ዉስጥ በ12 የምርምር ማዕከላት ላይ ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚያገኙ፤ መካከለኛ የዝናብ መጠን በሚያገኙ እና ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች ምርምሩ ይካሄዳል። አኩሪ አተር ሀገር ዉስጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚመረተዉ በቤንሻንጉል ጉምዝ እና በኦሮሚያ ክልል ነዉ። አኩሪ አተርን በብዛት ከሚያመርቱ ሃገራት ዩናትድ ስቴትስ፤ ብራዚል እና አርጀንቲና ቀዳሚዎቹ ናቸዉ። ከአኩሪ አተር ወተት ለማዘጋጀት ሲታሰብ እህሉን ከአንድ ቀን በፊት ለቅሞና አጥቦ ለ15 ደቂቃ ያህል መቀቀል ያስፈልጋል። ከዚያም አዉጥቶ ተዘፍዝፎ ያድራል። ከዚያም የራሰዉን አኩሪ አተር ልጣጩን በሚገባ በዉኃ አስለቅቆ በትንሽ በትንሹ እየቆነጠሩ ፈጭቶ እንደእህሉ መጠን ዉኃ ጨምሮ መቀቀልና መጭመቅ ነዉ። እንደባለሙያዉ ከሆነም ለአንድ ኪሎ አኩሪ አተር ስምንት ሊትር ዉኃ ያስፈልጋል። ተፈጥሮን ተከትሎ የማይበቅል እህልም ሆነ በተፈጥሮ ሥርዓት ያላደጉ እንስሳትን መመገብ ለጤና አደገኛ መሆኑን በተግባር የተረዳዉ ምዕራቡ ዓለም በአሁኑ ጊዜ ፊቱን ከእንስሳት ተዋፅኦ ወደተክሎችና ሰብሎች አዙሯል። በዚህ ምክንያትም ከአኩሪ አተር የሚገኙ የምግብ ተዋፅኦዎች ተመራጭነትን እያገኙ ነዉ። ከአኩሪ አተር ወተት እና አይቡ እንደሚገኝ ሁሉ የአኩሪ አተር ሥጋም አለዉ።
አኩሪ አተር በአለም ላይ በብዛት የት ይመረታል?
ዩናትድ ስቴትስ፤ ብራዚል እና አርጀንቲና
806
ሳዑዲ አረቢያ የሣውዲ አረቢያ ግዛት 28.7 ሚሊዬን የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡ ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ ኤዥያ ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡ የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡ ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡ የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡ አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡ የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በ1932 እ.ኤ.አ. በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡ ኢብን ሣኡድ ቀድሞ በ1894 ዓም (1902 እ.ኤ.አ.) ከብሪታንያ ግዛት ከኩወይት ዘምቶ ሪያድን ያዘ። ኢብን ሳኡድ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስልምና ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ የነዳጅ አምራች ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ሀይድሮ ካርቦን ክምችት ካላቸው አገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሀገሪቱ ባለው የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛ ክምችት ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ እና የህዝብ ቁጥር እድገት ከያዙ ሀገራት ጋር ትመደባለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ G-2ዐ ተብለው ከሚታወቁት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የሀገራት ቡድን ውስጥ ብቸኛዋ የአረቡ ዓለም አገር ናት፡፡ ይህም ቢሆን የሣውዲ ኢኮኖሚ በአብዛኛው በአንድ ቡድን የተያዘ ነው፡፡ የሣውዲ አረብያን ፈላጭ ቆራጭ በሆነ የመንግስት ስርዓት በመመራት “ነጻነት የለም” በሚል “ነጻነት ቤት” በሚል በሚታወቀው ድርጅት ተሰይማለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ለጦር ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያወጡ አገሮች ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2ዐ1ዐ-2ዐ14 በስኘሪ ተብሎ በሚታወቅ ድርጅት በተደረገው ጥናት ሣውዲ አረቢያ ዓለም ላይ ከሚገኙ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ደረጃ በማስገባት ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡ ሣውዲ አረቢያ በአካባቢው ካሉ ሀገሮች በዓለም ላይ ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማድረግ ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የኦፔክ፣ ጂሲስ እና የእስላም ግሩፕ አባል ናት፡፡
በሳውዲ አረቢያ ከሚኖሩት ምን ያህሉ የሳውዲ ዜጎች ይኖራሉ?
2ዐ ሚሊዬኑ
55
አዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።
አዲስ አበባ ከተማ ከባህር ጠለል በምን ያህል ከፍታ ትገኛለች?
በ2500 ሜትር
426
ሳህሌ ደጋጎ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል። በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ መሆኑን የሕይወት ታሪኩ ላይ ተጠቅሷል። ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ (በተቋቋመ ጊዜ ) በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁር ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር። ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ፣ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል።
ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከወላጆቻቸው ከእነማን ተወለዱ?
ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ
28
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል። በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። የገብላዊ ልጆች የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል። ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው። ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው። ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
ናጊብ ማህፉዝ በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ ላይ ምን ያህል አጫጭር ታሪኮችን ለዓለም አበርክቷል?
ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች
255
ሱዳን ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ (አረብኛ السودان) ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ከሊቢያ ጋር ድንበር ትካለላለች። የአባይ ወንዝ (ናይል) ሀገሪቱዋን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ይከፍላል። የአረብ ባህል ደንበኛ ሲሆን አብዛኛው ሕብዝ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው። ሱዳን ከግብፅ የተጣመረ ረዥም ታሪክ አላት። የመጀመሪያው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1955 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ከዚያም ሁለተኛው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1983 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ተከስቷል። በ1989 እ.ኤ.አ. በሰላማዊ መፈንቅለ መንግሥት ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር ሥልጣን ላይ የወጡ ሲሆን እራሳቸውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ብለው ሾመዋል። የእርስ በርስ ጦርነቱ በሰላም ውል የቆመ ሲሆን ይህ ውል ያኔ የሀገሪቱዋ ደቡባዊ ክፍል ለነበረው ቦታ ራስን የመምራት መብት ሰጥቷል። በጃኑዋሪ 2011 እ.ኤ.አ. በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት በሱዳን ፈቃድ ደቡብ ሱዳን ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ሉዓላዊ ሀገር ሆነች። ዋና ከተማዋ ካርቱም የሱዳን የፖለቲካ፣ ባህል እና ንግድ ማዕከል ናት። የሀገሪቱዋ መንግሥት በይፋ ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ቢሆንም ስልጣን ላይ ያለው ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (National Congress Party) በሁሉም የመንግሥት አካላት ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት በብዙ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ዘንድ መንግሥቱ አምባገነናዊ ተብሎ ይቆጠራል።
ደቡብ ሱዳን ነጻ ሀገር የሆነች መቼ ነው?
ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም.
674
ዳምጠው አየለ ዳምጠው አየለ (23.11. 1944 አ/ም – 27.10. 2006 አ/ም) ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፋኝ ነበር። በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል። ዳምጠው ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል። ዳምጠው መራቤቴ እያለ በየባእላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። ባጋጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል። ዳምጠው አየለ ኖርዌይ ሃገር በስደት ለ 8 አመት ያክል ኖሯል። ኢትዮጵያም ከገባ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብራኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ 62 አመቱ ሰኔ 27 2006 አ/ም ቀን ህይወቱ አልፏል። የቀብር ስነስርአቱም ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።
ዳምጠው አየለ መነሻ የሆነው ዘፋኝ ማነው?
አበበ ተሰማ
661
ፕሮፌሰር ሙሃመድ ዩኑስ ትውልድ በ28 ጁን 1940 እ.ኤ.አ. የባንግላዴሽ የባንክ ባለሞያና ኤኮኖሚስት ናችው። ማይክሮክሬዲት ተብሎ የሚታወቀውን የአነስተኛ የብድር አገልግሎት በችግር ለሚኖሩ ወገኖች የመስጠትን ስራ የጀመሩትና የስፋፉት ሰው ናችው። ፕሮፌሰሩ እንነኝህ ባንክ አላስተናግድ ብሎ የተዋቸውን ድሆች የሚያገለግለውን ግራሚን ባንክን አቋቁመዋል። በጥቅምት 1999 ፕሮፈሠሩና ባንኩ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለመሆነ በቅተዋል ይህም ሽልማት የልማት እድገትና ማህበረሰባዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በማስመስከራቸውና ይህ ደግሞ ለሰላም ወሳኝነት ያለው መሆኑን ሽልማት ሰጭው ኮሚቴ ስላመነበት ነው። ፕሮፌሰር የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት ሲሆኑ ከነዚህም የአለም የምግብ ሽልማት ይገኝበታል። የድሆች አበዳሪ በሚል ርዕስ አንድ የስራሳቸውንና የስራቸውን ታሪክ የሚያትት መጽሐፍ ደርሰዋል።
የባንግላዴሽ የባንክ ባለሞያና ኤኮኖሚስት የሆኑት ፕሮፌሰር ሙሃመድ ዩኑስ መቼ ተወለዱ?
በ28 ጁን 1940 እ.ኤ.አ
20
ሆ ቺ ሚን ሆ ቺ ሚን ከ1890-1969 እ.ኤ.አ. የኖረ የቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ መሥራችና መሪ ነበር። ሆ ቺ ሚን ከወጣትነት ጊዜው ጀምሮ ለአብዮታዊ ተግባራት የቆመ ነበር። ሆ ቺ ሚን በሥራ ምክንያት ፈረንሳይ ውስጥ በነበረበት ወቅት የካፒታሊስት ሥርዓት ምን ያህል ሠርቶአድሩን ሕዝብ ለሥቃይና ለመከራ እንደዳረገውና የዓለም ወዛደሮች በቀለም በቋንቋና በባህል ቢለያዩም ብሶታቸው አንድ መሆኑን በቅርብ ተገነዘበ። በአፍሪካና በእስያ የኢምፔሪያሊስቶች መምጣት ምን ያህል ሥቃይና ውርደት በእነዚህ ሕዝቦች ላይ እንዳደረሰ ተረዳ። በዚህም ምክንያት ሆ ቺ ሚን የቬትናም ሕዝብ ጠላት የፈረንሳይ ኢምፔሪያሊዝም እንጂ የፈረንሳይ መላው ሕዝብ አለመሆኑን ደጋግሞ ገልጿል። ሆ ቺ ሚን በ1917 እ.ኤ.አ. በፈረንሳይ ወዝአደሮች ትግል ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊ በመሆን የፈረንሳይ ሶሻሊስት ፓርቲ አባል ሆነ። ከዚህም በላይ በፈረንሳይ የቬትናም አርበኞችን ማኅበር በማቋቋም በፈረንሳይ ይኖሩ የነበሩትን ቬትናማውያን በማንቃትና በማስተማር ለሀገራቸው ነፃነትና ክብር እንዲታገሉ ያነሣሣ ነበር። የጥቅምቱ የሩሲያ አብዮት ለአያሌ ዓመታት በዓለም ሰፍኖ የነበረውን የኢምፔሪያሊዝም ብቸኛ የበላይነት ሰባብሮ አዲስ ዘመን በማብሰሩ ሆ ቺ ሚን የጀመረውን ትግል ከግብ ለማድረስ የቦልሼቪኮችን ፈለግ መከተል እንዳለበት አመነ። በሆ ቺ ሚን አስተሳሰብ የቬትናም ብቻ ሳይሆን የሌሎች ቅኝ ተገዥ የሆኑ ሀገሮች ነፃነት የሚገኘው የወዝአደሩን የአብዮት ጎዳና በመከተል ብቻ እንደሆነ አጥብቆ ያምን ነበር። የነዚህ ሀገሮች ብሔራዊ ነፃነት ከማኅበራዊ ነፃነት ጋር መያያዙንና ይህም ነፃነት ከሶሻሊዝምና ከኮሚኒዝም ጋር በጥብቅ የተሳሰረ መሆኑን አስገንዝቧል። ሆ ቺ ሚን ከ1924 እስከ 1930 እ.ኤ.አ. በቻይናና በቬትናም በመዘዋወር ለዚህ ውስብስብ ትግል ግንባር ቀደም አመራር ሊሰጥ የሚችለውን ማርክሳዊ ሌኒናዊ ፓርቲ ለማቋቋም ከፍተኛ ትግል አደረገ። በመጀመሪያም የቬትናም አብዮታዊ ወጣቶች ማኅበር የተባለውን በማቋቋም «ወጣት» በተባለው ጋዜጣ ወጣቱን ለትግል ቀሰቀሰ። በዚህ ዓይነት ከብዙ ጥረትና ትግል በኋላም በ1930 እ.ኤ.አ. የኢንዶቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን (ኋላ የቬትናም ሠራተኞች ፓርቲ፤ ዛሬ ደግሞ የቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ) መሠረተ። በ1935 እ.ኤ.አ. ሞስኮ ውስጥ የተካሄደው የኮሚኒስቶች ስብሰባ አንድ ሰፊ ፀረ ኢምፔሪያሊስት የሆነ ዲሞክራሲያዊ ግንባር እንዲቋቋም በወሰነው መሠረት ሆ ቺ ሚን ቬትሚን የተሰኘውን ሰፊ ፀረ ኢምፔሪያሊስት ግንባር በማቋቋም መላውን ሕዝብ በትግሉ ለማሳተፍ ችሏል። ዲየን ቢየን ፉ በተባለው ታሪካዊ ስፍራ የቬትናም አርበኞች የፈረንሳይን ጦር በማሸነፋቸው ፈረንሳይ በጀኔቩ ስምምነት መሠረት የቬትናምን አንድነት በማወቅ የሰላም ውል ፈረመች። ነገር ግን ከ1955 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም በፈረንሳይ እግር በመተካት የደቡቡን ክፍል ለመቁረስ የጦር ሰፈር በመሥራትና በውስጥ አርበኞች በመጠቀም ጦርነት ከፈተ። ነገር ግን አሜሪካ ከግማሽ ሚሊዮን ወታደሮች በላይና በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ቢያፈስም ቬትናምን ሊያሸንፍ አልቻለም።
ሆ ቺ ሚን ትግሉን ለማሸነፍ ምን አይነት መንገድ ተጠቀመ?
የቦልሼቪኮችን
722
አፋር (ክልል) አፋር ክልል (ክልል 2) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ዋና ከተማው ሰመራ ሲሆን የቀድሞዋ ከተማ ግን አሳይታ ነበረች። 96,707 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሸፍን በ1999 እ.ኤ.አ. የሕዝብ ብዛቱ 1,188,000 ነው። የድንቅ ነሽ ወይም ሉሲ አጽም በአፋር ክልል ውስጥ በ, 1967 (Nov. 24, 1974 እ.ኤ.አ.) ነው የተገኘው። በማርች 5, 2005 ደግሞ ሌላ 3.8 ሚሊዮን ዓመት የሚገመት አጽምም በዚሁ ክልል ተገኝቷል።
ሉሲ በአፋር ክልል የተገኘችው መቼ ነበር?
1967 (Nov. 24, 1974 እ.ኤ.አ.)
199
አሸናፊ ከበደ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አዲስ አበባ ግንቦት ፰ ቀን ፲፱፻፴ ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ግራዝማች ከበደ አድነው ሲሆኑ ክልጅነታቸው ጀምሮ የሙዚቃ ስሜትንና ፍቅር ያሳደሩባቸው እናታቸው ወይዘሮ ፋንታዬ ነከሬ ነበሩ። አያታቸው ሊቀመኳስ አድነው ጎሹ ደግሞ የአድዋ አርበኛ እናየንግሥት ዘውዲቱም ታማኝ አማካሪ እንደነበሩ ይነገራል። የሙዚቃ ፍቅርን ገና በልጅነታቸው ያሳደሩባቸው እናታቸው ሲሆኑ ታዳጊው አሸናፊ ገና የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሳሉ እኒህ የሚያፈቅሯቸውና ዕድሜ ልካቸውን በኀዘን የሚስታውሷቸው እናታቸው ሞተውባቸዋል። መሠረታዊ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኮከበ ጽባሕ) ካጠናቀቁ በኋላ በሐረር የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኒው ዮርክ ክፍለ-ሀገር ከሚገኘው የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ፣ “ኢስትማን የሙዚቃ ትምህርት ቤት” በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፤ የያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤትን መሠረቱ። የዚሁ ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው ዳይሬክቶር ከመሆናቸውም ባሻገር በአዲስ አበባው የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር (ወ.ወ.ክ.ማ Y.M.C.A.)፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርሓ-ዕውራን ትምህርት ቤት እና በመሳሰሉ የወጣቶች ማኅበራት እየተገኙ የሙዚቃ ትምህርት ይሰጡ ነበር።
የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያው ዳይሬክተር ማን ነበሩ?
ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ
9
ጉጃራቲ ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው። የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር። አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።
ጉጃራቲ ቋንቋ በታንዛንያ ምን ያህል ተናጋሪዎች አሉት?
250,000
108
የፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ምርምሮች በቫይረስ ጥቃት በእንስሳትና በሰው ላይ ለሚከሰቱ በሽታዎች በዘረመል ምህንድስና ጥበብ ክትባት ወይም መከላከያ መድሃኒት ግኝቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው። በዚህም የበርካታ በሽታዎች ክትባትና መድሃኒት ግኝቶች ባለቤት ሲሆኑ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ያደረጋቸው ደስታ በተሰኘውና ከ100 ዓመት በፊት በአውሮጳና በአፍሪካ ከፍተኛ ዕልቂት ላደረሰው የከብቶች መቅሰፍት በሽታ ክትባት መፈልሰፋቸው ነው። ይህን ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በርካታ የምርምር ተቋማት ደክመው ያላሳኩትን የደስታ በሽታ ክትባት ማግኘታቸው በህክምና ግኝቶች መስፈርት አንቱ አስብሏቸዋል፤ ዓለምንም በደስታ በሽታ ከሚደርሰው እልቂት ታድገዋል። በእንግሊዝና በጣሊያን ወታደሮች ሴራ ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ከብቶች በተዛመተው የደስታ በሽታ እ.አ.አ ከ1888-1892 ለአራት ዓመታት በኢትዮጵያ በደረሰው እልቂት ከፍተኛ ረሀብ መከሰቱን ያስታወሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን የምርምራቸው መነሻ ከወላጆቻቸው ስለ ከብት መቅሰፍት ሲሰሙ ማደጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሰውና በእንስሳት ህክምና ዕውቀት በሁለቱም ሰይፍ የተካኑት አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ ለኤች አይ ቪ/ኤዲስ ቫይረስ ክትባት ለማግኘትም ደክመዋል። ከ124 በላይ የሚሆኑ የምርምር ግኝቶች በስመ ጥር ዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔቶች የታተሙላቸው ሲሆን በአሜሪካና በቻይና በሚገኙ በርካታ ተቋማትም የአካዳሚ አባልነት ተመርጠዋል፤ በአማካሪነትም እየሰሩ ይገኛል። በተማሩበት ብሎም ባስተማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጨምሮ በአሜሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ዕውቅናና ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን ለአብነትም የዩኒቨርሲቲዎች የምርጥ አስተማሪነትና ተመራማሪነት ሽልማት፣ የእንስሳት ህክምና ዘርፍ ከፍተኛውን ዓለም አቀፍ ሽልማት፣ የልዩ አገልግሎት ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል። እርሳቸው ባቋቋሙትና በዳይሬክተርነት በሚመሩት የዓለም አቀፉ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የምርምር ማዕከል ከተለያዩ ታዳጊ አገራት በርካታ ሳይንቲስቶችንም አፍርተዋል። በትምህርትና ምርምር ዘመናቸው የነጮችን የዘረኝነት ጫና በመቋቋም ከስኬት ማማ ላይ የደረሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ አሁን ላይ በማደግ ላይ በሚገኙ አገራት ወጣት ሳይንቲስቶችን በማስተማርና በማበረታት ላይ ትኩረት አድርገው በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ የምን ክትባት ፈለሰፉ?
የደስታ በሽታ ክትባት
326
ቴሌቪዥን ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው። በ1873 እ.ኤ.አ. (1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ። በ1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም። ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ... ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በ 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ። በ1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።
በ1927 እ.ኤ.አ. 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ የላከው ሰው ኸርበርት አይቭስ የማን ድርጅት ሰራተኛ ነበር?
የቤል ላብራቷር
1,209
ፌስቡክ የሰዎችን ምስል ለማጣራት እና ለመለየት የሚጠቀምበት መሳሪያ ጋር ተያይዞ ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የህግ ክርክር እልባት መስጠቱ ተገልጿል። ፌስቡክ በፈረንጆቹ 2010 የሰዎችን የፊት ገጽታ መለያዎች መሣሪያን መጠቀም በፈረንጆቹ 2010 ላይ  የጀመረ ሲሆን፥ መሣሪያው የተጠቃሚውን ፊት ገጽታ በመቃኘት ስለ ደንበኛው ማንነት ሃሳቦችን የሚያቀርብ መሆኑ ተገልጿል። ምንም እንኳን ተጠቃሚዎች እሱን የማጥፋት አማራጭ ቢኖራቸውም፣ በወቅቱ ቴክኖሎጂው አወዛጋቢ ሆኖ መገኘቱ ተጠቁሟል። ተቃዋሚዎቹ የፊት ገጽታ መለያ መሣሪያው በኢሊኖስ ግዛትከወጣው የግላዊነት ህጎችን ይጥሳል ብለው የተከራከሩ ሲሆን ÷በግዛቱ ለሚገኙ ቡድኖችም 550 ሚሊየን ዶላር ይከፍላልም ተብሏል። ጉዳዩ በፈረንጆቹ ከ2015 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ፥ስምምነቱም በየሩብ ዓመቱ ከሚገኝ ገቢ  መሆኑም ተመላክቷል። ይህ የፊት ገጽታ እውቅናው  በፖሊስ እና በአደባባይ ቦታዎችጥቅም ላይ ሲውል  በጥልቀት ክትትል እንደሚደረግበትም ተገልጿል። በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር 2017ተጠቃሚዎች ይበልጥ በቀላሉ ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ እንዲችሉ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን ÷በ 2019 ፌስቡክ ይበልጥ በግላዊነት ላይ ያተኮረ እንዲሆን አድርጎ  አዲሱ የመቆጣጠሪያ አካል አድርጎ መስራቱም ነው የተገለጸው። የማህበራዊ አውታር መረቡ  ይህንን ጉዳይ ለማህበረሰባችን እና ለባለአክሲዮኖቻችን ጥቅም ስንል  ለመፍታት ወስነናል ሲል አስታውቋል፡፡ ይህ ማስተካከያ የሰዎችን መረጃ እና ግላዊነትን ለመጠበቅ  በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን ትልቁ  መሆኑን የኢንቨስትመንት ባንክ  ጃንስትር የሆኑት  ክርስቶፎር ሮዝባች ተናግረዋል። ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ
ፌስቡክ የሰዎችን የፊት ገጽታ መለያዎች መሣሪያን መጠቀም የጀመረው መቼ ነው?
በፈረንጆቹ 2010
98
መስከረም 23/12 ዓ ም ሽሬ ኢዜአ  የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ይሁንታ ያገኘው የ35 ዓመት ወጣት ሔሊኮፕተር ሰርቶ ለሙከራ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ ። ወጣት ዕበ ለገሰ ይባላል ። በመደበኛ ትምህርት ብዙ ገፍቶ ባይሔድም በፈጣራ ብቃቱ ግን በርካታ ስራዎች ለህዝብ እንዲያደርስ አድርጎታል ። የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ ምጣድ ጥገና ሥራ የጀመረው ወጣት አሁን ላይ ትልቅ ራእይ አንግቦ የራሱ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን በማቅረብ ውጤታማነቱን በተጠቃሚዎች ዘንድ እየተመሰከረለት መጥቷል ። የምጣድ ጥገና ስራው ለታናሽ ወንድሙ በመልቀቅ የወርቅ መአድን መፈለጊያ መሳሪያ ወደ ማሻሻል መሸጋገሩን ይገልፃል ። በራሱ ፈጠራ ያሻሻለው የወርቅ መፈለጊያ መሳሪያ በባህላዊ መንገድ ወርቅ ለሚያመርቱ ሰዎች በሽያጭ በማቅረብ የፍለጋ ሥራቸውን እንዲቃለል እንዳስቻላቸው ተጠቃሚዎቹ ይናገራሉ ። ቀደም ሲል የነበረው ‘’ጂ አር ዜድ’’ የተባለው የወርቅ መፈለጊያ መሳሪያ ከ70 እስከ 80 ሳንቲ ሜትር ጥልቀት ባለው መሬት ውስጥ የሚገኝ የደለል ወርቅ የሚጠቁም ነበር ። ወጣቱ ያሻሸለው ግን በአንድ ሜትር ጥልቀት የሚገኘውን የደለል ወርቅ በቀላሉ መለየት የሚያስችል መሳርያ ሆኖ ተገኝቷል ። እንዲሁም ከድንጋይ ጋር ተደባልቆ የሚገኝ ወርቅ በቀላሉ መለየት የሚያስችል የድንጋይ ወፍጮ በመፍጠር ለተጠቃሚዎቹ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም ወጣት  ለገሰ ይናገራል ። ባለፉት አምስት ዓመታት አምስት የድንጋይ ወፍጮዎችን በመስራት ለተጣቀሚዎቹ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቧል ። በተጠናቀቀው ዓመት በራሱ ፈጠራ ሶስት ሰዎች የማሳፈር አቅም ያለት ሔሊኮፕተር ሰርቶ በሙከራ ደረጃ ለህዝብ እይታ አቅርቦ የነበረው ወጣቱ ዘንድሮ ለማብረር እየተዘጋጀ መሆኑንም ተናግሯል ። የፈጠራ ሥራዬ ስኬትና ሚስጥር “ይቻላል” የሚል ጽኑ እምነት ስላለኝ ነው የሚለው ወጣቱ ከኢንተርኔት የሚያገኛቸው የፈጠራ ሥራዎችም እገዛ እንዳደረጉለት ጠቁሟል። ሥራ ፈጣሪ ወጣቱ ወደ ገበያ በሚያቀርባቸው የፈጠራ ውጤቱ ጥሩ ገቢ ከማግኘቱም ባሻገር ለሌሎች 10 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግሯል። የወጣቱ የፈጠራ ወጤት ተጠቃሚ ከሆኑትና በባህላዊ መንገድ በደለል ወርቅ ምርት ፍለጋ ከተሰማሩ ማህበራት መካከል የ“ስምረት” ማህበር አንዱ ነው። የማህበሩ አባል የሆነው ወጣት በላይ ተክለሃይማኖት በሰጠው አስተያየት ” ከወጣቱ የገዛነው የደለል ወርቅ ጠቋሚ መሳርያ ሥራችንን ከማቃለል በተጨማሪ በወርቅ ፍለጋው ስኬታማ እንድንሆን አግዞናል” ብሏል። ሌላው የማህበሩ አባል ወጣት ተስፋይ በላይ በበኩሉ ” ከድንጋይ ጋር ተደባልቆ የሚገኝ ወርቅ ለመለየት እጅግ አድካሚ የነበረው ሥራ ወጣቱ ባቀረበልን አነስተኛ የድንጋይ ወፍጮ በመጠቀም የድካማችንን ዋጋ ማግኘት አስችሎናል ” በማለት አድናቆቱን ገልፆለታል ። የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ጎይቶኦም ይሰማ እንዳሉትም ደግሞ የወጣቱን የፈጠራ ክህሎት እንዲሰፋና ሄሊኮፕተሯ ለህዝብ እይታ እንድትበቃ አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረግለታል ። የሽሬ እንደስላሴ ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋይ ገብረሚካኤል በበኩላቸው የፈጠራ ባለቤት የሆነው ወጣት እበ ለገሰ የፈጠራ ስራዎች የሚያተኩሩት በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ በሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች ዙሪያ በመሆናቸው ተቀባይነታቸው የጎላ ነው ብለዋል ። ወጣቱ የሚያሳየው ትጋት የተሞላበት የፈጠራ ስራ ለሌሎች ወጣቶችም አርአያ በመሆን መነቃቃት መፍጠሩን የኮሌጁ ዲን መስክረውለታል ።
በሽሬ ከተማ ለሙከራ ሔሊኮፕተር ሰርቶ ያቀረበው ወጣት ማን ይባላል?
ወጣት ዕበ ለገሰ
113
አቡነ ጴጥሮስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን በአደራነት የሰጠቻቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ሕዝበ ክርስቲያኑን በጸሎታቸው እየደገፉ በትምህርታቸው እያበረቱ በማስተዳደር ላይ እንዳሉ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. አረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ ሀገራችንን ለመውረር ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት በማለት ባሕርን አቋርጦ መጣ፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀገር በመጣ ወራሪ ቀጥተኛ ተጠቂናትና ሊቃውንቷ፣ ገዳማትና አድባራቷ እንዲሁም ንዋያተ ቅድሳቷ በወራሪው የኢጣልያ ኃይል ይጨፈጨፉና ይቃጠሉ ገቡ ፡፡ ይህ ግፍ በዕውቀት ኮትኩታ ባሳደገቻቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ሲፈጸም ያዩት ብፁዕነታቸው ወራሪውን ኃይል ከኢትዮጵያውያኑ አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎት ሊዋጉት ወሰኑ፡፡ ይሁን እንጂ ጠላት በመላ ከተማዋ ባሰማራቸው በርካታ ባንዳዎች መካከል ብፁዕነታቸው እንዳሰቡት ሊንቀሳቀሱ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ እዚሁ ከተማ ተሰውሬ መኖር አልፈልግም፤ ወደ ገጠር ፊቴን አልመልስም በማለት ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በወቅቱ የኢጣሊያ እንደራሴ ለነበሩት ራስ ኃይሉ እጃቸውን ሰጡ፡፡ እራስ ኃይሉም ወዲያውኑ ለግራዚያኒ አሳልፈው ሰጧቸው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን 1928 አቡነ ጴጥሮስ ተይዘው ወደ ግራዚያኒ ቀረቡ ፡፡ ጠላት ድል ተደርጎ ሀገራችን ነፃነቷን ከተቀዳጀት በኋላ የብፁዕነታቸውን አኩሪ ታሪክ ትውልድ ሲያዘክርላቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት ሐውልት ቆሞላቸዋል፡፡ ከድል በኋላ የብፁዕነታቸ ሐውልት ተመርቆ የቤተ መንግሥቱም ሆኑ የቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት አበባ ጉንጉን ከሐውልቱ ሥር ሲያስቀምጡ ከቤተ ክህነት ካስቀመጡት አባቶች አንዱ በ1921 ዓ.ም አብረዋቸው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ነበሩ፡፡ ትውልድ ሁሉ ለሀገር ክብርና ለነጻነት በተከፈለው፡፡ የብዕፁነታቸው ሕይወት እንዲማርበትና ሕያው ምስክር ሆኖ እንዲኖር የቆመላቸውን ሐውልት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በክብር ይጠብቁታል ፡፡ የእኝህን ታላቅና ቅዱስ ሰማዕት አባት ክብርና ተጋድሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከአምስት ዓመት በፊት ቅዱስ /ሰማዕት/ ብሎ በማጽደቅ በስማቸው በቅድስና ማዕረግን ሰጥቶ በስማቸው ታቦት ተቀርጾ ቤተክርስቲያን እንዲሰራላቸው ወስኗል ፡፡ ይህም በተወለዱበት በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሃገረሰብከት በፍቼ ከተማ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ አርበኛ፣ ጀግና፣ ጳጳስ፣ ሰማዕት ቅዱስም የሆኑ አባት ናቸው ፡፡
አቡነ ጴጥሮስ መቼ ለግራዚያኒ ቀረቡ?
ሐምሌ 22 ቀን 1928
638
ቲቪ በ1950ዎቹ እንደ ብርቅ በሚታይበት ዘመን በ1957 አ.ም ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተከፈተ፡፡ ታዲያ የመጀመሪያዋ የቲቪ ሴት አንባቢ የነበሩት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ ነበሩ፡፡ ይህ ለወይዘሮ እሌኒ ትልቅ የታሪክ አጋጣሚ ነበር፡፡ በወቅቱ ሳሙኤል ፈረንጅ አንዱ ወንድ ተናጋሪ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ሬድዮ በጋዜጠኝነቱና በህዝብ ግንኙነት ሙያ ያገለገሉት ወይዘሮ እሌኒ ከሰው ጋር በቀላሉ የሚግባቡ ተወዳጅ ደግ እናት ነበሩ፡፡ በበጎ አድራጎት ምግባራቸው በስፋት የሚታወቁት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማህበር ውስጥ በንቃት በመሳተፍ ማህበሩን ረድተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንሚ ሬድዮ ከ20 አመት በፊት ያገለገሉት ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ወልደስላሴ ከአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ጋር የጠበቀ ቁርኝት ነበራቸው፡፡ ከዚህም ባሻገር አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ወደ ሀገራችን በሚመጡበት ጊዜ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ስራ ላይ ትልቅ ሚና አበርክተዋል፡፡ ቤታቸው ሲኬድ ሁልጊዜም ከአረንጓዴ ተክል ጋር የማይታጡት ወይዘሮ እሌኒ ነፋሻማ ቦታ ልዩ ትርጉም ይሰጣቸዋል፡፡ አንድ ከዛፍ ጋር በተያያዘ በፎቶግራፍ የታገዘ መጽሀፍም ለህትመት አብቅተዋል፡፡ በዚህም መጽሀፍ አማካይነት ስለ ሀገራችን ዛፎች በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ የተለያዩ ሀገሮችን ቴምብሮችን ያሰባስባሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ለታሪክ ልዩ ፍቅር ያላቸው ወይዘሮ እሌኒ የጡረታ ጊዜያቸውን በማንበብ እና በምርምር ያሳልፉ ነበር፡፡ ወይዘሮ እሌኒ በ1959 አመተ ምህረት ከኢንጂነር ሰይፉ ለማ ጋር ጋብቻን መስርተው 3 ሴት ልጆችን ወልደው አንድ ልጅ ደግሞ አሳድገዋል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ በተወለዱ በ79 አመታቸው ሮብ ሀምሌ 14 2013 ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን የቀብር ስነስርአታቸውም ሀሙስ ሀምሌ 15 2013 ከቀኑ በ6 ሰአት በየካ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
ወ/ሮ እሌኒ ጡረታ ከወጡ በኋላ ምን በማድረግ ጊዜቸውን ያሳልፉ ነበር?
በማንበብ እና በምርምር
837
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ሰባት ወራት 169 ቢሊየን 501 ሚሊየን 789 ሺህ 893 ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ አፈፃጸሙ ከዕቅድም ሆነ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ የታየበት መሆኑን ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው አስታውቀዋል፡፡ ሚኒስቴሩ 169 ቢሊየን ብር 408 ሚሊየን 889 ሺህ 4 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የእቅዱን 100 ነጥብ 5 በመቶ ማሳካት መቻሉንም ገልጸዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ሰባት ወራት ምን ያህል ገንዘብ ሰበሰበ?
169 ቢሊየን 501 ሚሊየን 789 ሺህ 893 ብር
25
ነሐሴ ፲፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፩ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፭ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፬ ቀናት ይቀራሉ። ፲፰፻፶ ዓ/ም - በብሪታኒያ ንጉዛት እና በአሜሪካ ኅብረት መኻል በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የተዘረጋውን አዲሱን የቴሌግራፍ መስመር በመመረቅ ንግሥት ቪክቶሪያ እና የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጄምስ ቡካነን የሰላምታ መልእክት ተለዋወጡ። ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአገሪቱን የመጀመሪያ አየር-ዠበብ (አውሮፕላን) በዚህ ዕለት ተረከበ። ሁለተኛው አየር-ዠበብ ከጂቡቲ ወደብ እስከ ድሬዳዋ በባቡር ተጭኖ፤ ከድሬ ዳዋ ደግሞ እስከ አዲስ አበባ አሥራ ስምንት የአውሮፓ የፖስታ ቦርሳዎችን ጭኖ እየበረረ ነሐሴ ፴ ቀን ገባ። ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ዋና መላክተኛ አምባሳደር ዳግላስ ራይት በኢትዮጵያ እና በኬንያ መኻል ያለውን ድንበር ለመስማማት የተዘጋጀውን የውል ረቂቅ ለኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ አስረከበ። ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከ ፲፰፻፸፯ ዓ/ም ጀምሮ በፈረንሳይ ሥር በቅኝ ግዛትነት ትተዳደር የነበረችው ጋቦን በዚህ ዕለት ነፃ ወጣች። ሊዮን ምባ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ሽግግር የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የክብር ዘበኛ ሠራዊት አዛዥ የነበሩት ማዮር ጄነራል ታፈሰ ለማ በደርግ ተይዘው ታሠሩ። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነብሩት አቡነ ቴዎፍሎስ አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ ሕገ-መንግሥት ውስጥ በተካተቱ አንዳንድ አንቀጾች ላይ ቅዋሜ እንዳላቸው አስታወቁ። ፳፻፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ከገዛቸው አሥር ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አየር-ዠበቦች የመጀመሪያውና በሰሌዳ ቁጥር ET-AOQ የተመዘገበው አየር-ዠበብ በዚህ ዕለት ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስቶ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ልጅ ልዕልት ፀሐይ በተወለዱ በ፳፫ ዓመታቸው በዚህ ዕለት አረፉ።
ብሪታኒያ ዋና መላክተኛ አምባሳደር ዳግላስ ራይት በ ፲፱፻፶፪ ዓ/ም በኢትዮጵያ እና በኬንያ መኻል ያለውን ድንበር ለማስማማት የውል ረቂቅ የተረከቡት ማን ይባላሉ?
አክሊሉ ሀብተ-ወልድ
668
ኢትዮጵያ በመሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ላስመዘገበችው ውጤት ሩዋንዳ በተዘጋጀው የአፍሪካ የጤና ኮንፍራስ ላይ እውቅናን አግኝታለች :: በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያ የሆነችው ወ/ሮ ሰናይት 40,000 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን በመወከል ሽልማቱን ተቀብላለች::
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ የሆነችው ወ/ሮ ሠናይት ስንት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ወክላ ነው በአፍሪካ የጤና ኮንፈረንስ ላይ የተቀበለችው?
40,000
143
ሊቢያ ኦይል ከኢትዮጵያ የተሰናበተውን ሼል ኢትዮጵያ ሊሚትድ በመግዛት የኢትዮጵያን የነዳጅ ገበያ የተቀላቀለው በ2000 ዓ.ም. ነበር፡፡ ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ 143 የነዳጅ ማደያዎች ሲኖሩት፣ 24 በመቶ የገበያ ድርሻ አለው፡፡ ኩባንያው በየዓመቱ ዘጠኝ ማደያዎች በመክፈት እ.ኤ.አ. በ2020 የነዳጅ ማደያዎቹን ቁጥር 185 ለማድረስ፣ የገበያ ድርሻውን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ አቅዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኩባንያው ዓመታዊ ሽያጭ 13 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡ ሊቢያ ኦይል 50 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የአቪዬሽን ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያና በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የነዳጅ ዲፖ የኤታኖል ማደባለቂያ ገንብቷል፡፡ ኩባንያው እስከዛሬ እንደ አዲስ የገነባቸው ስምንት የነዳጅ ኩባንያዎችን ብቻ ነው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ለግንባታ የሚሆን ቦታ የማግኘት ችግር በመኖሩ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዘካሪያስ፣ ከሼል ኩባንያ ግዢ ጋር የተፈጠረው የታክስ ክርክር የኩባንያውን ዕድገት እንደጎተተው ያስረዳሉ፡፡ የታክስ ክርክሩ እልባት ያገኘ በመሆኑ ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ቆርጦ መነሳቱን አስታውቋል፡፡ ሊቢያ ኦይል ባለፈው ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ አዳዲስ የሞተር ዘይትና ቅባቶችን አስተዋውቋል፡፡ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ የሊቢያ ኦይል የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፣ የሊቢያ ኦይል ምርቶች አከፋፋዮችና የትራንስፖርት ኩባንያዎች የሊቢያ ኦይል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሙስባሕ ኤልቤሽቲ ሽልማቶች አበርክተዋል፡፡
ሊቢያ ኦይል ሼል ኩባንያን ከገዛ በኋላ ያጋጠመው አለመግባባት ምን ነበር?
የታክስ ክርክር
536
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ተፈሪ መኰንን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺ እመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ፲፰፻፺፱ የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. የሐረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ። የሐረርጌ አገረ ገዥ ሲሆኑ ፣ በጣም ብዙ ሺህ ተከታዮች ነበሩዋቸውና ልጅ እያሱን ከእንደራሴነት በኅይል እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ተፈሪን ከሐረር አገረ ገዥነት እንዳይሽሯቸው የሚል ስምምነት ተዋዋሉ። ዳሩ ግን እያሱ ሃይማኖታቸውን ከክርስትና ወደ እስልምና እንደቀየሩ የሚል ማስረጃ ቀረበና ብዙ መኳንንትና ቀሳውስት ስለዚህ ኢያሱን አልወደዱዋቸውም ነበር። ከዚህም በላይ እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት ስምምነታቸው እንግዲህ ተሠርዞ ተፈሪ ደግሞ ለወገናቸው ከስምምነቱ ተለቅቀው በዚያን ጊዜ እሳቸው እያሱን ከእንደራሴነት አስወጡ። እንግዲህ በ፲፱፻፱ ዓ.ም. መኳንንቱ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ሆነው አድርገዋቸው ተፈሪ ደግሞ እንደራሴ ሆኑ። ከዚህ ወቅት ጀምሮ ተፈሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙሉ ሥልጣን ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. የንጉሥነት ማዕረግ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ አርፈው ንጉሠ ነገሥት ሆኑና ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ብዙ የውጭ ልዑካን በተገኙበት ታላቅ ሥነ-ሥርዓት ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው እሳቸውና ሚስታቸው እቴጌ መነን ዘውድ ጫኑ። በንግሥ በዓሉ ዋዜማ ጥቅምት ፳፪ ቀን የትልቁ ንጉሠ-ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለዘውድ በዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት ፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ። ለንግሥ ስርዐቱ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገር ልኡካን ከየአገራቸው ጋዜጠኞች ጋር ከጥቅምት ፰ ቀን ጀምሮ በየተራ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ስለነበር ሥርዓቱ በዓለም ዜና ማሰራጫ በየአገሩ ታይቶ ነበር። በተለይም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት በጃማይካ አንዳንድ ድሀ ጥቁር ሕዝቦች ስለ ማዕረጋቸው ተረድተው የተመለሰ መሢህ ነው ብለው ይሰብኩ ጀመር። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ፊተኛው ስማቸው «ራስ ተፈሪ» ትዝታ ራሳቸውን «ራስታፋራይ» (ራሰተፈሪያውያን) ብለዋል።
ንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለሥላሴ ወደዚህ ዓለም የመጡበት ዕለት መቼ ነው?
ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም.
112
አሪዞና አሪዞና (Arizona) በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ክፍላገር ነው። ኒው ሜክሲኮ ፣ ዩታህ ፣ ኔቫዳ ፣ ካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ያዋስኑታል። የአሪዞና ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ የ30 ሰው ሴኔት እና የ60 ሰው ምክር-ቤት አለው። የሪፑብሊካን ፓርቲ በስቴቱ ዋነኛው ፓርቲ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. የአሪዞና ስቴት ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ በጀት 14.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በጀት ደግሞ 13.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። የስቴቱ ሴኔተሮች እና ምክር-ቤት ተወካዮች ለሁለት-ዓመት ጊዜ ላልተወሰነ ብዛት ይመረጣሉ። ከ4 ጊዜ በላይ በተካካይ መመረጥ ግን አይችሉም። የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በአስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን ለ4 ዓመት ሥልጣን ላይ ይቆያል። ያልተወሰነ ጊዜ መወዳደር ሲቻል ከሁለት ጊዜ በላይ ግን በተካካይ መመረጥ አይፈቀድም።
አሪዞና ስቴት የት ሀገር ይገኛል?
ዩናይትድ ስቴትስ
27
መልከአ-ምድር አንጎላ፣ በ1,246,620 ካሬ ኪ.ሜ. ከኒጄር ቀጥላ ከዓለም 23ኛው ትልቅ አገር ናት። በስፋት ከማሊ ጋር ትነጻጸራለች። የአሜሪካ የቴክሳስ ክፍላገርን ሁለት ዕጥፍ ታክላለች። አንጎላ ከደቡብ በናሚቢያ፣ ከምሥራቅ በዛምቢያ፣ ከሰሜን-ምሥራቅ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። የአንጎላ አማካይ የባህድ ዳር የአየር ሁኔታ በክረምት 16° ሴንቲግሬድና በበጋ 21° ሴንቲግሬድ ነው። አንጎላ ሁለት ወቅቶች አሏት። እነዚህም ደረቅና ዝናባማ ናቸው። መጓጓዣ በአንድ ላይ ርዝመታቸው 2,761 ኪ.ሜ. የሆኑ ሦስት የባቡር መንገዶች፤ 76,626 ኪ.ሜ. አውራ ጎዳና ከዚህም ውስጥ 19,156 ኪ.ሜ. አስፋልት፤ 1,295 ኪ.ሜ. የውሃ መንገድስምንት ትልቅ ወደቦች፤ 243 የአውሮፕላን ማረፊያዎች ከነዚህም 32ቱ የአስፋልት መንደርደሪያ ያላቸው፤ አንጎላ የሰፋ የመጓጓዛ አውታር ቢኖራትም በጊዜ ማለፍና ጦርነት ምክንያት መንገዶች አስፈላጊ ጥገኛ አልተደረገባቸውም። በአንዳንድ ቦታዎች አሽከርካሪዎች መጥፎ ቦታዎችን ለማለፍ ሲሉ ከመንገድ ውጭ ይነዳሉ። እንደዚህ ከማድረግ በፊት ግን በመንገድ ዳር ያሉ በመሬት ውስጥ ስለተቀበሩ ፈንጂዎች የሚያስጠነቅቁ ምልክቶችን ማስተዋል ያስፈልጋል። ኢኮኖሚ የአንጎላ ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ አሳይቷል። የሩብ ምእተ ዓመት ጦርነት ያሳደረበት ተጽእኖን አልፎ ዛሬ በዓለም ውስጥ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። በ2004 እ.ኤ.አ. የቻይና ኤክሲምባንክ ፪ ቢሊዮን ብር ለአንጎላ አበድሯል። ይህ ገንዘብ እንደ መንገዶች ያሉትን የአንጎላ መሠረታዊ ተቋሞች ለማሻሻል የሚውል ነው። ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት በ2008 እ.ኤ.አ. እንደዘገበው ነዳጅና ዕንቁ የአንጎላ ዋና ኤክስፖርቶችና የገቢ ምንጮች ናቸው።
አንጎላ በናሚቢያ ከየት አቅጣጫ ትዋሰናለች?
ከደቡብ
125
ኢትዮጵያ በዓለም ዉስጥ ክሚገኙ ጥንታዊ አገሮች ኢትዮጵያ ቀዳሚ በመሆን ከሁሉም የበለጠ ረጅም እድሜ አስቆጥራለች፡፡ በግእዝ/ዓማርኛ እና በመጽሀፍ ቅዱስ ከተመዘገቡት ተጨባጭ መረጃዎች በተጨማሪ አምስት ሚሊዮን አመት የሚሆነውና በጣም ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የሰው ቅሪት የተገኘው በኢትዮጵያ አዋሽ ሸለቆ አካባቢ ሲሆን ይህም፣ 3.2 ሚሊዮን አመት የሆነውን እዛው አካባቢ የተገኘውን የሉሲን (ድንቅነሽን) አጽም በእድሜ ይበልጣል፡፡ ግብጽን ሲገዛ የነበረው ሄሮደስ የሚባለው ንጉስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ታሪክ ፀሀፊ የጥንቷን ኢትዮጵያ በጽሁፎቹ ላይ ይገልፃታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይም ብዙ ግዜ የምትወሳ ስትሖን በተለይም ብሉይ ኪዳን ላይም የንግስት ሳባ (መከዳ) ኢየሩሳሌም መሄድና ለንጉስ ሰለሞን ከባድ የሆኑ ጥያቄዎች ማንሳቷ ተጽፏል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ያላትን መልክ እንድትይዝ ያደረጋት ንጉስ ሚኒሊክ የንግስት ሳባና የንጉስ ሰለሞን ዘር ናቸው፡፡ የንግስት ሳባ ቤተ መንግስት ፍርስራሽ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በአክሱም አካባቢ ይገኛል፡፡ ክርስትናን ኢትዮጵያዉያን ከመቀበላቸዉ በፊት (ኣስቅድመዉ)  የኦሪትን ህግ ሰለሚያዉቁ ኣመተ ዓለምን ወደታች እየቆጠሩ የጌታን መወለድ ይጠብቁ ሰለነበረ ክርስትናን ለመቀበል ኣላስቸገራቸዉም፡፡ ነገር ግን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በእስልምና መስፋፋት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአውሮፖውያኑ ክርስትያን ርቃ ቆይታለች፡፡
ንግስት ሳባ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ሄዳ ጥያቄ ስለማቅረቧ የሚያወሳው ታሪክ በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ይገኛል?
ብሉይ ኪዳን
411
ዐምደ ጽዮን ቀዳማዊ አጼ ዐምደ ጽዮን (የዙፋን ስም ገብረ መስቀል) ከ1314 እስከ 1344 ዓ.ም. የነገሡ ሲሆን በጥንቱ ዘመን ከተነሱ ነገሥታት ውስጥ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሰፋ ያለ አሻራ ትተው ካለፉት (ለምሳሌ፦ ዘርአ ያዕቆብ) ጎን ወይም በላይ ስማቸው ይጠቀሳል። አጼ ዐምደ ጽዮን የአጼ ይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅና የአጼ ወድም አራድ ልጅ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ይኩኖ አምላክ አዲሱን የሰሎሞን ስርወ መንግስት ቢመሰርቱም፣ በልጅ ልጆቻቸው የነበረው ፉክክርና አዲስ ከሚስፋፋው የእስልምና ሃይማኖት የሚሰነዘረው ጥቃት ስርዓቱን ስጋት ላይ የጣለ ነበር። አጼ አምደ ጽዮን ይህን ፉክክር በማስቆምና በዘመናት በማይደበዝዘው ጀግንነታቸው የኢትዮጵያን ድንበር ከሞላ ጎደል አሁን በሚታወቀው መልኩ በማስቀመጥ፣ የአዲሱን ስርወ መንግስት መሰረት በማጽናት እንዲሁም በማረጋጋት ዝናቸው በጥንቱ አለም ክአፍሪቃ ቀንድ እስከ አውሮጳ የተንሰራፋ ነበር።
የአጼ ዐምደ ጽዮን የዙፋን ስም ማን ይባላል?
ገብረ መስቀል
34
ኢትዮጵያ ከ ፹ (80) በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የቻለች ሀገር ነች። ትልልቆቹ ብሄረሰቦች ፣ የአማራ ፣ እና የኦሮሞ የትግራይ እንደሁም የሶማሌ ሲሆኑ እነዚሁ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የሀገሪቷ ሕዝብ ቁጥር ከ 3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ። በሃይማኖት በኩልም ሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖቶች ክርስትና እና እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። የክርስትና እምነት ተከታዮች ከ 55%-60 % ፣ እስልምና ከ35% እሰከ 40% እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ 5%-8% የሚሆነውን ይይዛሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ከ ፹ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች አፍሮ-ኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ በሚባሉ ሁለት ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥም ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ የሚባሉ ንዑስ ክፍሎች አሉ። ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ ፣ ኩናማኛ ፣ ጉሙዝኛ ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው።
ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ መደብ የሚካተቱ ቋንቋዎች እነማን ናቸው?
በርታኛ ፣ ኩናማኛ ፣ ጉሙዝኛ ፣ ሙርሲኛ
813
ሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው። ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ የእንግሊዝን አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ። ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በሩሲያኖች የተገነባው የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ እራሳቸውን ከሥልጣናቸው አስወገዱ። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - አቶ ለገሰ ዜናዊ አስረስ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አድዋ ላይ ተወለዱ።
የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ መቼ ተጣለ?
፲፱፻፶፯ ዓ/ም
737
አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ በሃገራችን ኢትዮጵያ ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅ እና ቅድስት እድና ይባላሉ ። የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው ። ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረአምላክ ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ። በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል። "የት ልሒድ?" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለስምንት ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየኋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከስምንቱ ጋር ከቃልኬዶን ጉባዔ በኋላ በ፬፻፶፩ ዓም ወደ ኢትዮጵያ መጡ ። ከዘጠኙ ቅዳሳን ወደ ኢትዮጵያ ከሮምና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከፈለሱት አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው ። በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል ። አቡነ አረጋዊ ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል ። በመጨረሻም ደብረ ዳሞ ማረካቸዋለች ። ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል ፡፡
አቡነ አረጋዊ በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የማን ደቀመዝሙር ነበሩ?
የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ
326
ቀጭኔ ከዝሆን በስተቀር ማንኛውም ሌላ እንስሳ ሊደርስ በማይችልበት ከፍታ ላይ የሚገኙ ረዣዥም ቀንበጠቦችን ለመብላት የሚያስችል አስደናቂ አፈጣጠር አላት። ልዩ የሆነ የመቆንጠጥ ችሎታ ያለው የላይኛው ከንፈሯና እንደተፈገለው የሚተጣጠፍ ችሎታ ያለው ምላሷ ሹል በሆኑ እሾሆች የታጠሩ ቅጠሎችን ለመቀንጠብ ያስችሏታል። ቀጭኔዎች በቀን እስከ 34 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕፅዋት መመገብ ይችላሉ። የተለያዩ ዕፅዋትን የሚበሉ ቢሆኑም ይበልጥ የሚመርጡት በአፍሪካ ሜዳዎች የሚገኙትን እሾሃማ ግራሮች ነው። አንድ ወንድ ቀጭኔ ምግብ ለመፈለግ ምላሱን እስከ 42 ሳንቲ ሜትር መዘርጋት ይችላል። የቀጭኔ አንገት በጣም አስደናቂ የሆነ የመተጣጠፍ ችሎታ አለው። ይህም ላይኛዎቹን የዛፍ ቅርንጫፎች ለመቀንጠብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ረዥሙን ራሷን እንደ ልቧ ለማዘንበልና ለማዟዟር ያስችላታል። ለቀጭኔ ወደ ላይ መንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት ግን ይከብዳታል። ወደ ውኃ ጉድጓድ በምትቀርብበት ጊዜ የፊት እግሮቿን ቀስ በቀስ ከፍታ ካራራቀቻቸው በኋላ ወደ ውኃው ለመድረስ እንድትችል ሁለት ጉልበቶቿን አጠፍ ታደርጋለች። ቀጭኔዋ እንዲህ ባለው አመቺ ባልሆነ ሁኔታ እያለች ረዥም አንገቷን እስከ መጨረሻ ትዘረጋለች። ደግነቱ ግን ከምትመገባቸው ቅጠላ ቅጠሎች በቂ እርጥበት ስለምታገኝ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አያስፈልጋትም። የቀጭኔ አንገትና ትከሻ የቅጠል ቅርፅ ባላቸውና ቀጫጭን በሆኑ ነጭ መስመሮች ያጌጠ ነው። ቀለማቸው የተለያየ ሲሆን ከወርቃማ ዳለቻ አንስቶ እስከ ቡናማ እንዲያውም ጠቆር እስካለ ቀለም ይደርሳል። የቀጭኔ ዕድሜ እየገፋ በሄደ መጠን ቀለሟም እየጠቆረ ይሄዳል። ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው። አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ ልጅዋን ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት ከተሸከመች በኋላ ሁለት ሜትር ቁመት ያለው ግልገል ትወልዳለች። ግልገሏ በምትወለድበት ጊዜ ራስዋን ታስቀድምና ከሁለት ሜትር ከፍታ ላይ ወደ መሬት ትወረወራለች። ይሁን እንጂ በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባት እየተውተረተረች ትነሳና ጡት ለመጥባት ዝግጁ ትሆናለች። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ በደመ ነፍስ ተመርታ የግራር ቀንበጦችን መለቃቀም ስለምትጀምር ብዙም ሳትቆይ ረዥም እርምጃ ያላትን እናትዋን ተከትላ ለመሄድ የሚያስችል ጉልበት ታገኛለች። አንዲት የቀጭኔ ግልገል በጣም ውብ መልክ ሲኖራት የወላጆችዋ አነስተኛ ግልባጭ ነች። ቁመቷ ከቀጭኔ ርዝመት ጋር ሲወዳደር አጭር ብትሆንም ከብዙ ሰዎች ቁመት ግን ትበልጣለች። በእናቷ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ተማምና አላንዳች መሸበር አካባቢዋን የምትማትረው ግልገል ላያት ሁሉ ልዩ መስህብ አላት። ግልገል ቀጭኔዎች በተወለዱበት ወራት በግልገል መዋያ ተሰባስበው ሙሉውን ቀን ዕረፍት በማድረግ፣ በመጫወትና በአካባቢያቸው የሚሆነውን ነገር በመመልከት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የቀጭኔ ግልገል ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት ያድ⁠ጋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሜትር የሚያክል ቁመት ሲጨምር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል። በአንድ ሳምንት ብቻ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ሊያድግ ይችላል! እናትዬው ለልጅዋ ከፍተኛ ጥበቃ የምታደርግ ሲሆን ልጅዋ የተወሰነ ርቀት እንድትዘዋወር ብትፈቅድላትም ሩቅ የማየት ችሎታ ስላላት በዓይኗ ትከታተላታለች። ቀጭኔ ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ስላላት ከአንበሳ በቀር የሚያጠቃት ጠላት የለም። ቢሆንም ይህችን የምታምር ፍጥረት የሰውን ያህል በብዛት አድኖ የገደለ የለም። ቀጭኔ በሚያምር ቆዳዋ፣ በሚጣፍጥ ሥጋዋና አንዳንዶች ምትሐታዊ ኃይል አለው በሚሉት ረዥምና ጥቁር ጭራዋ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ ስለሆነች በአሁኑ ጊዜ የዚህች ሰላማዊ ፍጡር የወደፊት ሕልውና ስጋት ላይ ወድቋል። በአንድ ወቅት በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች እንደ ልብ ትታይ የነበረችው ቀጭኔ በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው በቂ ጥበቃ በሚደረግላት ፓርኮች ብቻ ሆኗል። የቀጭኔ አካላዊ ቅርጽና ግዝፈት ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል። በጣም ትልቅ ቁመትና ረዥም አንገት ስላላት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖራትና ወደ ሁሉም የአካሏ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ማድረግ የማይቻል ነገር ሊመስል ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀጭኔ አንገቷን ወደ መሬት ስታጎነብስ በስበት ኃይል ምክንያት ብዙ ደም ወደ ጭንቅላቷ ፈስሶ አንጎሏን ማጥለቅለቅ ነበረበት። ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ደሟ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ልቧ ተመልሶ ራሷን እስከ መሳት ሊያደርሳት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ነገር አይደርስም። ለምን? የቀጭኔ የደም ዝውውር ሥርዓት በዓይነቱ ልዩ ለሆነው ለዚህች እንስሳ ቅርጽና መጠን እንዲያገለግል ሆኖ በታላቅ ጥበብ የተሠራ ነው። ልቧ ራሱ በጣም ትልቅ ሲሆን ደሙን ሦስት ሜትር ተኩል ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ አንጎላ ለመግፋት የሚያስችል አቅም አለው። በደቂቃ እስከ 170 ጊዜ የሚመታውና 7 ሳንቲ ሜትር ያህል ውፍረት ባለው ጡንቻ የተገነባው የቀጭኔ ልብ ከሰው የደም ግፊት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ግፊት ያመነጫል። ወደ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው ካሮቲድ የተባለው የደም ቧንቧና ከአንጎል ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም የሚሸከመው ጀጉላር የተባለው የደም ቧንቧ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚያስችል መጠን ሊኖራቸው ይገባል። በእርግጥም እነዚህ የደም ቧንቧዎች ከ2.5 ሳንቲ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው ከመሆኑም በላይ ጠንካራና የመለጠጥ ችሎታ ባላቸው ሕዋሳት የተገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንካሬና የመለመጥ ችሎታ አላቸው። ቀጭኔ ከጭንቅላቷ ጎንበስ በምትልበት ጊዜ ወደ አንጎሏ የሚሄደውን የደም ፍሰት የሚቆጣጠሩ ልዩ መቆጣጠሪያዎች አሏት። አንጎልና አንገት በሚገናኙበት ቦታ ላይ ትልቁ ካሮቲድ የደም ቧንቧ ሬቴ ሚራቢሌ ተብሎ ከሚጠራ አስደናቂ የሆነ መረብ መሰል አካል ይገናኛል። በከፍተኛ ኃይል ተገፍትሮ የመጣው ደም እዚህ ጋር ሲደርስ በጣም በርካታ ወደሆኑ ትናንሽ የደም ሥሮች እንዲገባ ስለሚደረግ የደሙ ግፊት ተስተካክሎ በአንጎል ላይ ጉዳት የማያስከትል ይሆናል። ቀጭኔዋ ራስዋን ጎንበስ በምታደርግበት ጊዜ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው መረብ ይለጠጣል፤ ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ይኮማተራል። ይህም የስበት ኃይል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና የደም ግፊቷ በእጅጉ ቀንሶ ራሷን የምትስትበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳታል። የሳይንስ ሊቃውንት በጣም አስደናቂ ርዝመት ያለው የቀጭኔ አንገት ያሉት አከርካሪዎች ቁጥር ከአይጥ ወይም ከብዙዎቹ አጥቢ እንስሳ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቁ በጣም ተደንቀዋል! ይሁን እንጂ የቀጭኔ አከርካሪዎች በጣም ረዣዥሞችና እርስ በርሳቸው ልዩ በሆነ ሁኔታ የተሰካኩ በመሆናቸው እንደ ልብ ሊተጣጠፉ ይችላሉ። ቀጭኔ አንገቷን መጠምዘዝና ማጠፍ ስለምትችል ሁሉንም የአካሏን ክፍሎች ለመላስም ሆነ ረዣዥም የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ለመድረስ ትችላለች።
ቀጭኔ የእርግዝና ጊዜዋን አጠናቃ ልጅ በምትወልድበት ጊዜ የልጇ ቁመት ምን ያህል ነው?
ሁለት ሜትር
1,061
ስዋሂሊ ስዋሂሊ ፡ (ወይም ፡ ኪሷሂሊ Kiswahili) ፡ በምሥራቅ ፡ አፍሪቃ ፡ የሚናገር ፡ የባንቱ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የስዋሂሊ ፡ ሕዝብ (፭ ፡ ሚሊዮን ፡ ተናጋሪዎች) ፡ ልደት ፡ ቋንቋ ፡ ከመሆኑ ፡ በላይ ፡ ለ ፴ ፡ እስከ ፡ ፶ ፡ ሚሊዮን ፡ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ሁለተኛ ፡ ቋንቋ ፡ ሆኗል። የስዋሂሊ ፡ ስም ፡ መነሻ ፡ ከዓረብኛ ፡ ቃል ፡ «ሰዋሂል» ፡ ነበር ፤ ይህም ፡ የ«ሳኸል» ፡ (ማለት ፡ ዳር) ፡ ብዙ ፡ ቁጥር ፡ ነው። ስለዚህ ፡ የ«ስዋሂሊ» ፡ ትርጉም ፡ የ(ባሕር) ፡ ዳረኞች ፡ ቋንቋ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል። የቋንቋው ፡ ቤተሰብ ፡ ባንቱ ፡ ሲሆን ፡ ተናጋሪዎቹ ፡ መርከበኞችና ፡ ነጋዴዎች ፡ በመሆናቸው ፡ መጠን ፡ ከዓረብኛ ፣ ከፋርስ ፣ ከህንዲ ፣ እና ፡ ከቻይንኛ ፡ ቢሆንም ፡ ብዙ ፡ ቃሎች ፡ ተበድረዋል።
ስዋሂሊ በየት አካባቢ የሚነገር ቋንቋ ነው?
በምሥራቅ ፡ አፍሪቃ
37
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ስብሐት (ስብሐት ለአብ) ገብረ እግዚአብሔር (ሚያዝያ 27 [1928]ዓ.ም. - ሰኞ፣ ቀን ትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደ ፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው። ስብሐት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ በመነን መጽሄት የዝግጅት ክፍል ውስጥ ሰርቷል። በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲቋቋም በአርታኢነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በመንግሥት ትእዛዝም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን የካርል ማርክስ ሥራ የሆነውን ካፒታልን ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመመለስ ሥራ ላይ ተሳትፏል። ብዙዎቹ የስብሐት ሥራዎች በተጻፉበት ጊዜ ለመታተም ባይታደሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የህትመትን ብርሃን ለማየት በቅተዋል። ጽሁፎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይታተሙ ለመቆየታቸው ዋነኛው ምክንያቱ ስብሐት በመጽሐፉ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ባህል ያደገ አንባቢን አይን የሚያስፈጥጡ፣ ጆሮ የሚያስይዙ በመሆናቸው ነው። በገበያ ላይ በቅርብ የወጡት ድርሰቶቹ ከመጀመሪያ ቅጂያቸው ብዙ ለውጥ እና የአርትኦት ሥራ የተደረገባቸው እንደሆኑ ይነገራል። ስለዚሁ ጉዳይ ለአዲስ ላይቭ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገር «በጨለማ ያልተደረገውን ነገር አንድም የጻፍኩት የለም... ያለውን እንዳለ ነው የምጽፈው» ብሏል። ይህንኑም ከኤሚል ዞላ የአጻጻፍ ዘይቤ የወሰደው እንደሆነ ይናገራል። ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ደራሲ፣ አርታኢ፣ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም - የልብ-ወለድ ድርሰት ገጸባህርይም ነው። ደራሲው የተሰኘው የበአሉ ግርማ ልብ-ወለድ በስብሐት ህይወት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው። ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች አባት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነው።
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመው የልብ-ወለድ ድርስቱ ምን ይባላል?
ሌቱም አይነጋልኝ
588
ገብረሃና ገብረማሪያም አለቃ ገብረሃና ገብረማሪያም (፲፯፻፺፯ - ፲፰፻፺፬ ዓ.ም.) ዕውቅ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። አባታቸው መምህር ገብረ ማርያም ምጥኑ ሲባሉ እናታቸው ወይዘሮ ሳህሊቱ ተክሌ ይባሉ ነበር። ገብረሃና ገብረማሪያም በቤገምድር ጠቅላይ ግዛት በደብረታቦር አውራጃ በፎገራ ወረዳ ልዩ ስሟ ናበጋ ጊዮርጊስ በምትባል ቦታ በ፲፯፻፺፯ ዓ.ም. ተወለዱ። ገብረሃና እቴጌ መነንን መዝሙርን፣ ውዳሴ ማርያምንና ሌሎችንም አስተምረው ከጨረሱ በኋላ ለከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በእቴጌይቱ ትዕዛዝ ወደ ጎንደር ተላኩ። ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላም በእቴጌይቱ ትዕዛዝ የአለቃነት ማዕረግ ተሰጣቸው። ከዚያም ገብረሃና በጎንደር አካባቢ የሚገኙትን ቤተ ክርስቲያናት ብቃት በተሞላበት ሁኔታ ያስተዳድሩ ጀመር። እንደ ትልቅ ምሁር ይታዩ ጀመር። በተለይ ፍትሐ ነገስትን በመተርጎም የሚወዳደራቸው ወይም የሚስተካከላቸው አልነበረም። አለቃ ገብረሃና አቶ ሙንሮዝ በተባለ አውሮጳዊ በ1890 ዓ.ም. ፎት እንደተነሱ ሞላቨር ይገልጻል። ዓፄ ቴዎድሮስ ስልጣን ከያዙና እራሳቸውንም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ብለው ዙፋናቸውን በጫኑበት ጊዜ በሀገሪቱ ከፍትሐ ነገስት ሌላ የተፃፈ ሕግ ባለመኖሩ አለቃ ገብረሃና በተለይ ፍትሐ ነገስትን መሠረት በማድረግ ንጉሡ ሀገርን እንዲያስተዳድሩ ይረዱዋቸው ነበር። በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ቤተክርስቲያን ብሉይ ኪዳንንና አዲስ ኪዳንን በመተርጎም ትልቅ አገልግሉት ቢያደርጉም ትልቁን አስተዋጽዖ ያደረጉት በሕግና በቤተ ክርስቲያን ዜማና አቋቋም ነበር። እንደዚሁም የፈጠሩት አዲስ ዓይነት የቤተክርስቲያን አቋቋም ከደብረታቦር ወደ ሸዋ እና ትግራይ ተሰራጭቷል። ይህንንም አቋቋም ከብቸኛው ልጃቸው በኋላ ተክለ ብለው ሰየሙት። ይህም አቋቋም አስደሳችና ማራኪ የአቋቋም ዘዴ ነው።
አለቃ ገብረሃና ገብረማሪያም የት ተወለዱ?
በቤገምድር ጠቅላይ ግዛት በደብረታቦር አውራጃ በፎገራ ወረዳ ልዩ ስሟ ናበጋ ጊዮርጊስ በምትባል ቦታ
144
ሄርበርት ሁቨር (1866 - 1957 ዓ.ም.) ከ1921 እስከ 1925 ዓ.ም. ድረስ 31ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። የሁቨር ቤተሠብ ከስዊስና ጀርመን ትውልድ ሲሆን ሃይማኖቱ የክዌከር ('የሚንቀጠቀጡ' ማለት ነው) ቤተ ክርስቲያን ነበረ። ወላጆቹ በልጅነቱ ጊዜ ካረፉ አንስቶ ድሃ አደግ ሆነና ከአጎቱ ጋር አደገ። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቴ መጀመርያ ክፍል በመሆኑ ትምህርቱ በነጻ ተቀበለ። ከዚያ በላይ የዩኒቬርሲቴው የቤስባልና የፉትቦል ቡድኖች አለቃ ሆነ። በ1887 ዓ.ም. የጂዮሎጂ ዲግሪ ይዘው ተመረቁ። ለ20 ዓመት የማዕደን ሊቅ ሲሆኑ እንኳን በአውስትራልያና በእንግሊዝ በማዕደን ዘርፍ የሠሩት ሥራ ስመ ጥሩ ሆነ። መጀመርያው ታላቅ አለማዊ ጦርነት በ1906 ዓ.ም. በጀመረበት ወቅት ሁቨር ከራሳቸው ኪስ ለጋሥነት አውጥተው 120,000 አሜሪካውያን ቱሪስቶችና ሠራተኞችን ከአውሮፓ ወደ አገራቸው አስመለሷቸው። ከዚያ በጀርመኖች በተወረረው በቤልጅግ ውስጥ የኖሩት ረሃብተኞች ምግብ እንዲደርሳቸው ብዙ አደረጉ። በዚህ አይነት ሥራ በጦርነት ጊዜ የሁቨር ስም ጀግና እንዳለው ሁኔታ በመገኘት ላይ ሄዶ ነበር። ጦርነቱም ከተጨረሰ በኋላ ለምሥራቅ አውሮጳ ድሃ ሕዝብ እስከ ሩስያም ድረስ በረሃብ ላሉት ሰዎች ምግብ አደረሷቸው።
ሄርበርት ሁቨር ከመቼ እስከ መቼ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ነበሩ?
ከ1921 እስከ 1925 ዓ.ም.
29
ጎንደር ከተማ ፋሲለደስ የጎንደር ከተማን በ1636 የኢትዮጵያም ዋና ከተማ አድርጎ እንደቆረቆራት ይታመናል። ከሱ በፊት በአካባቢው ከተማ እንደነበር ወይም እንዳልነበር በታሪክ የተገኘ ማስርጃ እስካሁን የለም። አከታትሎም የፋሲል ግቢንና 44ቱ ታቦታት ተብለው የሚታወቁትን የጎንደር ከተማ አብያተ ክርስቲያናት መሰረት ጣለ። በአፄ ፋሲል ከተመሰረቱት ታዋቂወቹ 44 አብያተ ክርስቲያናት፣ ታዋቂወቹ አደባባይ እየሱስ፣ አደባባይ ተክለ ሃይማኖት፣ አጣጣሚ ሚካኤል፣ ግምጃቤት ማራያም፣ ፊት ሚካኤል፣ እና ፊት አቦ ይገኙበታል። ያለመታከትም 7 የድንጋይ ድልድዮችን በማሰራት እስካሁን ድረስ ስሙ ሲጠራ ይኖራል። አልፎም በግራኝ አህመድ ዘመን በእሳት ጋይቶ የነበረችውን አክሱም ፂዮን በአዲስ መሰረት እንደገና ማሰራት ችሎአል። ፋሲለደስ በዘመኑ እጅግ ተወዳጅ ንጉስ ቢሆንም አመጽ መነሳቱ አልቀረም። በላስታ ለምሳሌ በ1637 መልክዓ ክርስቶስ በተባለ ሰው መሪነት ጦርነት ተነስቶ አፄ ፋሲልን ስጋት ላይ ቢጥልም በሚቀጥለው አመት በተደረገው ጦርነት አመፁ ሊገታ ችሎአል። ፋሲለደስ ፖርቱጋሎችን ቢያባርርም ከውጭው አለም ጋር ብዙ ግንኙነት ያደርግ ነበር። ለምሳሌ በ1664-5 የህንድ ንጉስ አውራንግዘብ ሲነግስ መልካም ምኞትን በመልክተኞቹ ለሙግሃሉ መሪ ልኮ ነበር። በ1666 ልጁ ዳዊት ሲያምጽ፣ ወህኒ ተብሎ ወደሚታወቀው አገር በግዞት ልኮት ነበር። ይህም ከጥንቶቹ የኢትዮጵያውን ነገሥት ተፎካካሪያቸውን ወደ አምባ ግሽን በግዞት እንደሚልኩት ስርዓት ነበር።
አፄ ፋሲል ልጃቸውን ዳዊትን መቼ ወደ ግዞት ቤት ወሰዱት?
በ1666
731
ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት ቀረቡ። በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ  ኢትዮጵያን በመወከል  ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ነው የተነገረው። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋና የቋንቋ ጥናት ክፍል ለረጅም ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።
ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የጠቅላይ ሚንሰትሩ የምን አማካሪ ሆነው ሰርተዋል?
የማህበራዊ ጉዳዮች
99
ፍቅር እስከ መቃብር ፍቅር እስከ መቃብር በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያትን ፍቅር ይተርካል። ይህ ድርሰት ከሌሎች ልብወለድ ሥራዎች ለየት የሚያደርገው ደራሲው ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በፊደል አጠቃቀም ላይ ለውጥ አድርገው በማቅረባቸው ነው። ይኸውም ለምሳሌ ያህል ሦስት «ሀ»ዎች፣ ሁለት «ሰ»ዎች፣ ሁለት «ኣ»ዎች የመሳሰሉትን እንደ አንድ ወይም የመጀመሪያውን ብቻ በመያዝ ነው። በተጨማሪም ጠብቀው በሚነገሩ ቃላት ላይ ከላይ አንድ ነጥብ በማስቀመጥ ይታወቃሉ።ሀዲስ ኣለማየሁ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሑፍ የራሳቸው ትልቅ አሻራ አኑረው ያለፉ አንጋፋ ደራሲ ናቸው። የታሪኩ ማጠቃለያ በዛብህ‌ ‌ጎጃም‌ ‌ማንኩሳ‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከእናቱ‌ ‌ከውድነሽ‌ ‌በጣሙና‌ ‌ከአባቱን‌ ‌ከቦጋለ‌ ‌መብራት‌ ‌ይወለዳል።‌ ‌በሽታ‌ ‌ይበዛበትና‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይባላል።‌ ‌እናቱ‌ ‌ከበሽታው‌ ‌እንዲድን‌ ‌ስእለት‌ ‌ይሳላሉ።‌ ‌ዕድል‌ ‌ሆኖ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይተርፋል፤‌ ‌አድጎ‌ ‌ጎበዝ‌ ‌ልጅ‌ ‌ይሆናል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌በሽታ፣‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ዕውቀትና‌ ‌ፍቅር‌ ‌(የሰው‌ ‌መውደድ)‌ ‌ይበዛበታል።‌ ‌በወጣትነቱ‌ ‌ይቀድስና‌ ‌ለቤተሰቡ‌ ‌ገንዘብ‌ ‌ማምጣት‌ ‌ይጀምራል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌የስእለት‌ ‌ልጅ‌ ‌መባልን‌ ‌አይጠላም‌ ‌ነበር።‌ ‌ሲያድግ‌ ‌ግን‌ ‌ትርጉሙን‌ ‌በመረዳቱ‌ ‌ነጻነቱን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌ዲማን‌ ‌ጥሎ‌ ‌ወደደብረ‌ ‌ወርቅ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌እዚያም‌ ‌ከእመት‌ ‌ጠጂቱ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይጠጋል።‌ ‌ትንሽ‌ ‌ዜማና‌ ‌ቅኔም‌ ‌ይማራል።‌ ‌ደብተራ‌ ‌በየነ‌ ‌መጥቶ‌ ‌የወላጆቹን‌ ‌ሞት‌ ‌ሲያረዳው‌ ‌ወደዲማ‌ ‌ይወርዳል።‌ ‌በተክለ‌ ‌አልፍአው‌ ‌በዓል‌ ‌በመልካም‌ ‌ድምጹ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻንና‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትን‌ ‌ያወድሳል።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻም‌ ‌የሰብለ‌ ‌መምህር‌ ‌አድርገው‌ ‌ይቀጥሩታል።‌ ‌ሰብለና‌ ‌በዛብህ‌ ‌የሕይወት‌ ‌ገጠመኞቻቸው‌ ‌በመጠኑ‌ ‌ስለሚመሳሰል‌ ‌ይግባባሉ።‌ ‌በመሃል‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌አሰጋኸኝ‌ ‌ሰብለን‌ ‌በፈት‌ ‌ወግ‌ ‌አገባለሁ‌ ‌በማለቱ‌ ‌በርሱና‌ ‌በፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌መካከል‌ ‌ጥል‌ ‌ተፈጠረ፤‌ ‌ሆኖም‌ ‌በሃይማኖት‌ ‌ጣልቃገብነት‌ ‌ሳይዋጉ‌ ‌ቀሩ።‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከባላገሮች‌ ‌ጋራ‌ ‌በግብር‌ ‌ጉዳይ‌ ‌ተጣሉ።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ተማርከው‌ ‌ሳለ‌ ‌የበዛብህንና‌ ‌የሰብለወንጌልን‌ ‌የፍቅር‌ ‌ዜና‌ ‌ይሰማሉ።‌ ‌ወዲያውም‌ ‌መጥተው‌ ‌ሰብለን‌ ‌በሌሊት‌ ‌ያስሯታል።‌ ‌የሰብለ‌‌አጎት‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ሁለቱን‌ ‌ለማስመለጥ‌ ‌ወጣ፣‌ ‌ወረደ።‌ ‌የዕጣ‌ ‌ነገር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ግን‌ ‌ሳይሳካ‌ ‌ቀረ።‌ ‌በዛብህ‌ ‌ግን‌ ‌በግራጌታ‌ ‌ቀለመወርቅና‌ ‌በጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጥረት‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌በራጉኤል‌ ‌ቤተክርስቲያንም‌ ‌የቅኔ‌ ‌መምህር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ይቀጠራል።‌ ‌ባደረጉላቸው‌ ‌ውለታ‌ ‌ምክንያት‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌ሰብለን‌ ‌ለፊታውራሪ‌ ‌ታፈሰ‌ ‌ሊድሯት‌ ‌ይሞክራሉ።‌ ‌የሰብለን‌ ‌አቋም‌ ‌አውቀው‌ ‌አባ‌ ‌ተክለሃይማኖት‌ ‌በተባሉ‌ ‌መነኩሴ‌ ‌ያስጠብቋቷል።‌ ‌መነኩሴው‌ ‌ግን‌ ‌ሰክረው‌ ‌ሰብለ‌ ‌ታመልጣለች።‌ ‌ፍለጋ‌ ‌ሲሄዱ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከፈረስ‌ ‌ላይ‌ ‌ተወርውረው፣‌ ‌ተንኮታክተው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትም‌ ‌ቤተክርስቲያን‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከደረጃ‌ ‌ላይ‌ ‌ተንሸራትተው‌ ‌ወድቀው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ሰብለ‌ ‌ደግሞ‌ ‌በዛብህን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌መነኩሴ‌ ‌መስላ‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ትሄዳለች።‌ ‌ደርሳም‌ ‌በዛብህ‌ ‌አለመኖሩን‌ ‌ትሰማና‌ ‌ጎሃጽዮን‌ ‌ትወርዳለች።‌ ‌በዚያም‌ ‌በዛብህ‌ ‌ተደብድቦ፣‌ ‌ነፍስ‌ ‌ውጪ‌ ነፍስ‌ ‌ግቢ‌ ‌አይነት‌ ‌ሁኔታ‌ ‌ላይ‌ ‌ሳለ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌እንደምንም‌ ‌ብለው‌ ‌ሥጋ‌ ‌ወደሙን‌ ‌ይቀበላሉ።‌ ‌ጥቂት‌ ‌ቆይቶ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይሞታል።‌ ‌ሰብለም‌ ‌መንኩሳ፣‌ ‌የበዛብህን‌ ‌አስከሬን‌ ‌ባጠገቧ‌ ‌አድርጋ‌ ‌ስትኖር‌ ‌ከጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጋራ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌ጉዱ‌ ‌የተሰኘው‌ ‌ካሳ‌ ‌ዳምጤም‌ ‌እርሷ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይቀመጣል።‌ ‌አስራ‌ ‌አምስት‌ ‌ቀናት‌ ‌አንድ‌ ‌ላይ‌ ‌ይኖሩና‌ ‌ሰብለ‌ ‌የልብ‌ ‌በሽታዋ‌ ‌ተነሥቶባት‌ ‌ትሞታለች፣‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ከበዛብህ‌ ‌አጠገብ‌ ‌ያስተኛታል።‌ ‌በሦስተኛው‌ ‌አመት‌ ‌ጉዱም‌ ‌አረፍተ‌ ‌ዘመን‌ ‌ይገታዋል።‌
በዛብህ ዜማና ቅኔ የት ተማረ?
ደብረ‌ ‌ወርቅ‌
828
ሮማንሽ ሮማንሽ ወይም ሩማንች (Rumantsch) ከስዊስ አገር 4 ብሔራዊ ቋንቋዎች 1ዱ ሆኖ ሌሎቹ 3 ጀርመንኛ ጣልኛና ፈረንሳይኛ ናቸው። ከሮማይስጥ የታደገ ቋንቋ በመሆኑ የሮማንስ ቋንቋ ቤተሠብ አባል ነውና በተለይ የሚመስለው ፈረንሳይኛ ወይም እጣልኛ ነው። የሚናገረው በግራውብውንደን (ግሪዞን) ካንቶን ስዊስ በሚኖሩ 60,000 ሰዎች ነው። ይህ ከስዊስ አገር ሕዝብ ብዛት 1% ብቻ ሲሆን ከስዊስ አገር ብሔራዊ ቋንቋዎች ሁሉ ትንሹ ነው። እንኳን በስዊስ አገር ከሚኖሩት ስርቦ-ክሮዌሽኛ ተናጋሪዎች ቁጥር ብዛት (111,000) በግማሽ ያንሳል። በስሜን እጣልያ አገር ዛሬ ለሚናገሩ ቋንቋዎች ለፍሪዩልያንና ለላዲን ቅርብ ዘመድ ነው።
በስዊስ ሀገር የሮማንሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች በመቶኛ ምን ያህል ይሆናሉ?
1%
237
ሃይማኖት ሃይማኖት አንድ ሕብረተሠብ የሚያምንባቸው ጽኑ እምነቶች መሠረት ነው። በዓለም ውስጥ በርካታ ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች አሉ። ዋና ዓለማዊ ሃይማናቶች ክርስትና፣ እስልምና፣ አይሁድና፣ የሕንዱ ሃይማኖት እና ቡዲስም ናቸው። እነዚህ ሃይማኖቶች በአንዳንድ አገር በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ሁኔታ አላቸው። ከነዚህ መጀመርያ ሦስቱ. ክርስትና፣ እስልምናና አይሁድና፣ ሁላቸው ከአብርሐም ስለ ተነሡ፣ «አብርሃማዊ ሃይማኖቶች» ተብለዋል። ሒንዱኢዝምና ቡዲስም ግን ከሕንድ ተነሡና «ሕንዳዊ» ወይም «ዳርማዊ ሃይማኖቶች» ተብለዋል። ሌሎች ሃይማኖቶች በአሁኑ ሰዓት በየትም አገር የመንግሥት ሃይማኖት ባይሆኑም፣ ባለፉት ዘመናት በታሪክ መንግሥታት ይኖራቸው ነበር፦ በተለይ ዛርጡሽና፣ ጃይኒስም፣ ሲኪስም፣ ዳዊስም፣ የኮንግ-ፉጸ ትምህርት፣ ሺንቶና የተለያዩ ኗሪ ወይም አረመኔ ሃይማኖቶች የቀድሞ መንግሥታት ነበሯቸው፤ የጠፉት ሃይማኖቶች ማኒኪስም እና አሪያኒስም ደግሞ የቀድሞ መንግስታት ነበሯቸው። በተጨማሪ መቸም መንግስት ያልነበረላቸው በርካታ ሌሎች አነስተኛ ሃይማኖቶች ወይም እምነቶች አሉ ወይም በታሪክ ተገኝተዋል።
ከሕንድ የተነሱ ሃይማኖት ምን በመባል ይታወቃሉ?
ሒንዱኢዝም
272
ከዛሬ ፶00 ዓመት በፊት የሶሎሞን ስረወ መንግስት ሸዋ (መንዝንና ተጉለት) ላይ  ሆኖ ለረጅም ዘመን ኢትዮጵያን ካስተዳደረ በሁዋል  የግራኝ መሃመድ ወረራ በአጼ ልብነድንግል ዘመን ተካሄደ።  ኢትዮጵውያን በግራኝ መሃመድ ወረራ የተነሳ ከፖርቱጋሎች ጋር ግንኙነትን መሰረቱ፡ በ፩፮፴ ተጀምሮ ለረጅም ጊዜ የተካሄደው ግጭት ከውጪ የመጡትን ሚሲዮናዊያን በሙሉ ከኢትዮጵያ በማባረር ሰላም ተመልሷል፡፡ ይህ የከፋ የግጭት ጊዜ ኢትዮጵያ የውጭ ክርስትያኖች ላይ እና አውሮፖውያኖች ላይ እስከ ሀያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ፊቷን እንድታዞር አስተዋጾ ከማድረጉም በተጨማሪ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ ከመላው አለም ተገልላ እንድትቆይ አድርጓታል፡፡ ከ1700 ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አገዛዝ ሳይኖሯት ቆይታለች፡፡ ይህም “ዘመነ መሳፍንት”  ሲሆን በ1869 አፄ ቴዎድሮስ መሳፍንቶቹን ሁሉ አስገብረው ኢትዮጵያን አንድ አድርገዋል
በኢትዮጵያ ዘመነ መሳፍንት ለምን ያህል ጊዜ ቆየ?
ከ1700 ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት
410
ኃይሌ ገብረሥላሴ ኃይሌ ገብረሥላሴ በ ሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፷፭ (1965) ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ፣ አርሲ ክፍለ ሀገር የተወለደ አቻ ያልተገኘለት ድንቅ የረጅም ርቀት ኢትዮጵያዊ ሯጭ ነው። ኃይሌ በሩጫ ዘመኑ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ፣ በግማሽ ማራቶን፣ በማራቶንና እንዲሁም በሌሎቹ የሩጫ ዓይነቶች ከ ፲፩ በላይ የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብሯል። ኃይሌ በሩጫ ችሎታው ጠንካራ የሆነበት ምናልባትም ከመንደሩ ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ነው ተብሎ ቢታመንም የተፈጥሮ ጥንካሬው ዓለምን ያስደነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ኃይሌ ሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከመሆኑም በላይ በ፴፫ ዓመት ዕድሜው ፪ ሰዓት ከ፬ ደቂቃ በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለምን ማራቶን ክብረ-ወሰን ሊሰብር ችሏል። ኃይሌ ገብረሥላሴ እስካሁን ድረስ ፳፮ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን ሰብሯል። ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ በሲድኒ እና በአትላንታ ኦሊምፒኮች በ፲ ሺህ ሜትር ሩጫዎች ወርቅ አስመዝግቧል። በ ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. ኤንዱራንስ (Endurance) የተባለ ስለ እራሱ የእሩጫ ድል ፊልም ተሠርቷል።
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ስንት ክብረ ወሰኖችን ሰበረ?
፳፮
452
ፍሬምናጦስ የተወለዱት ታይር በምትባል ቦታ በምሥራቃዊ የሮማ ነገሥት በ፬ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያዎቹ ሲሆን ማንም መርምሮ ሊደርስበት በማይችለው በእግዚአብሔር ሀሳብ ወደ ኢትዮጵያ መተው ክርስትናን ከመሠረቱት ዋነኛው አባት ሆኖ በመቆጠር ፣ አገራችንን ከሌሎች ክርስቲያን አገሮች ጋር ያስተዋወቁ ፣ ያስተካከሉ ፣ በአክሱም ዘመነ መንግሥትና መንግሥት የተወደዱና የተከበሩ ፣ በመላው ኢትዮጵያ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የተከበሩ ታላቅ አባት ናቸው ። አባታችን ፍሬምናጦስ የ፲፪ ዓመት ልጅ እያለ ሜሮጵዮስ የተባለ ነጋዴ ፈላስፋም የነበረ መርከበኛ ይዞት ወደ አገራችን መጣ ። ከእርሱም ጋር ወንድሙ ኤድስዮስ የተባለም አብሮት እንደነበረ ይታወቃል ። እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ የመጣው ሜሮጵዮስ በቀይ ባሕር አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በጣሉለት አደጋ በዚሁ እንደ ሞተ ታሪክ ይነግረናል ። ይህም በንጉሥ ዒዛና ዘመነ መንግሥት ሆነ ። ፍሬምናጦስና ኤድስዮስ ግን በወቅቱ የአክሱም ንጉሥ የነበረው ንጉሥ ታዜር ጋር አድገዋል ። ንጉሡ በአእምሮ መብሰላቸውን ተመልክቶ ፍሬምናጦስ በጅሮንድ ኤድስዮስም ጋሻ ጃግሬው አድርጎ ሾማቸው ። ከዚያ በኋላ ንጉሥ ታዜር ሲያርፍ ወደ ፈለጉበት እንድሄዱ ነፃ ስለተለቀቁ ኤድስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ሄዷል ። አባታችን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ግን ወንድሙን ሸኝቶ "በጨለማ የሚኖረውን ሕዝብ ትቼ ወደ አገሬ አልመለስም" በማለት የኢትዮጵያን ሕዝብ በማፍቀር እንደቀረ ታሪክ ያስረዳናል ። የቅዱሳን ፍቅራቸው እውነትም ልብ ይነካል ። በዚያን ዘመን በአገራችን ኢትዮጵያ ክርስትና ነገሥታቱ የታወቀ ቢሆንምኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ስርዓተ ንስሐ ፣ ስርዓተ ጥምቀት ፣ ስርዓተ ቅዳሴ ፣ ስርዓተ ቅዱስ ቁርባን የሚያከናውን ጳጳስ ስላልነበረ ይህን የተመለከቱ ነገስታት ኢዛናና ሳይዛና ጵጵስና እንዲያመጣ አባታችን አቡነ ሰላማን ወደ ግብጽ ላኩት ። አባታችንም ወደ ግብጽ በመሄድ ስርዓቶቹን በመማር በቅዱስ አትናትዮስ አንብሮተ እድ "ኤጲስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ" ተብሎ ጵጵስና ተቀበለ።
አባ ፍሬምናጦስ በሮማ የት አካባቢ ተወለዱ?
ታይር
14
አዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አሁን ምን በመባል ይጠራል?
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
683
ፌስቡክ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እያበለፀገ መሆኑን ከሰሞኑ የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። ኩባንያው የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚሰራውም ከጎግል አንድርይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ከአይፎን አይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ አንደሆነም ታውቋል። አዲሱ የፌስቡክ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሙሉ በሙሉ ከዜሮ ተነስቶ በራሱ መንገድ እየበለፀገ መሆኑንም ኩባንያው አስታውቋል። ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ በምን መልኩ ይሰራል የሚለው ነገር በግልፅ ባይታወቀም የፌስቡክ የቪዲዮ የስልክ ጥሪን ጨምሮ ሌሎች የኩባንያው አገልግሎቶች ግን ተጠቃሚ ይሆናሉ ነው የተባለው። ፌስቡክ አሁን በሚያመርታቸው መገልገያዎች ላይ በብዛት የጎግል አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተመን የሚጠቀም ሲሆን፥ ይህም ጎግል በአብዛኛው የፌስቡክ አገልግሎቶች ላይ በበላይነት እንዲቆጣጠር እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። ፌስቡክ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም መስራቱም ከጎግል አንድሮይድ ጥገኝነት የሚያላቅቀው መሆኑን እና በሚያመርታቸው መገልገያዎችን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ስልጣን እንዲኖረው እንደሚያደርገውም ተገልጿል። ምንጭ፦ www.techworm.net
በኡበር የታክሲ አገልግሎት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በቦርድ አባልነት ያገለገሉት ትራቪስ ካላኒክ መቼ በተስተዋለው የሙስና ችግር ምክንያት ነው ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ያሰቡት?
ከጎግል አንድርይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ከአይፎን አይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ
89
ዝናሽ ማሞ በኢትዮጵያ ሬድዮ በእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ከ1979 ጀምሮ በመስራት ትታወቃለች፡፡ በኢትዮጵያ ሬድዮ ለ 16 አመት ያገለገለችው ዝናሽ ከእነ ታደሰ ሙሉነህ ፤ ታምራት አሰፋ ጋር በትጋት የሰራች ሲሆን ከ20 አመት በፊት ከእነ ቤተሰቦችዋ ወደ ምድረ አሜሪካ አቅንታለች፡፡ እምብዛም ልደት መከበር ባልተለመደበት በዚያን ዘመን ከተወለደች ከአንድ አመቷ ጀምሮ እስከ 16 አመቷ ድረስ ቤተሰቦቿ የልደት በዐልዋን እያከበሩላት ያደገችው ዝናሽ ማሞ አብዲበአዲስ አበባ ከተማ ግንቦት 21 ቀን 1954 አ.ም መወለድዋን ለማስታወስ አልተቸገረችም:: ትውልዷም እድገቷም ጠብመንጃ ያዥ ወይም በቅሎ ቤትበሚባለው አካባቢ ነበርእናትና አባቷ ወ/ሮ ሽብሬ ወ/ሃናና አቶ ማሞ አብዲ ይባላሉ:: ዝናሽ ማሞ መጀመሪያ በቄስ ትምህርት ቤት ከፊደል እስከ መልእክተ ዮሀንስ ተምራ ፊደላትን ከለየች በኋላ በበቅሎ ቤት አካባቢ በነበረው አስቀድሞ ኤስ አይ ኤም የልጃገረዶች ክርስቲያን አካዳሚ ተብሎ ይታወቅ በነበረው ጂሲኤ የልጃገረዶች ት/ቤት ከ አንደኛ እስከ ስድስተኛቀጥሎም ይኸው ት/ቤት የፀጋ ክርስቲያን አካዳሚ በመባል ስሙ ተቀይሮ ወንዶችም አብረው መማር በጀመሩበት ት/ቤት ከሰባተኛ እስከ አስረኛበመጨረሻም በጊዜው የነበረው የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ት/ቤቱን ወደ መንግስት ንብረትነት በማዘዋወር የአብዬት ቅርስ ተብሎ ከሰየመው በኋላ አስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛ ክፍልን እዚያው ተምራለች::
የዝናሽ ማሞ እድገቱዋ የት ነው?
ጠብመንጃ ያዥ ወይም በቅሎ ቤትበሚባለው አካባቢ
359
አዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዕውቁና አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ በውጭ አገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች ወጣቶችን በሳይንስ በማነጽ ተግባር እንዲሰማሩ፤ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር ጥላሁን በቻይና ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የአፍሪካ ሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል ሊያቋቁሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚዘጋጀው ወርኃዊ የሳይንስ ገለጻ መድረክ ወጣቱን ትውልድ ማስተማርና ማነጽ ለኢትዮጵያ ተስፋ፤ የቻይና ተምሳሌትነት በሚል ትናንት ምሽት ገለጻ አድርገዋል። በአውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 1943 በኢትዮጵያ የተወለዱት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች አጠናቀው በቀድሞው የአለማያ እርሻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት በኮሌጅ ቆይታቸው ባሳዩት የላቀ ውጤትም አሜሪካን አገር በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህር ቤት ተልከው ትምህርታቸውን በማጥናት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት አስተምረዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላም ወደ ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በደቂቀ ሥነ ሕይወት መስክ በማጥናት በአውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1980-2006 በተማሩበት ካሊፎርኒያ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አስተምረዋል፤ ተመራምረዋል። እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ደግሞ የዲስቲንጉሽድ ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.አ.አ ከ1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል በማቋቋም በዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በየት ሀገር ተወለዱ?
በኢትዮጵያ
461
በ1240 አካባቢ በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ፍትሐ ነገሥት በአረብኛ ጻፉ። እብን አል-አሣል ሕጎቹን የወሰዱት በከፊል ከሃዋርያት ጽህፈቶችና ከሕገ ሙሴ፤ በከፊልም ከድሮ ቢዛንታይን ነገስታት ሕጎች ነበር። መጽሐፉ በግዕዝ ተተርጉሞ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ወቅት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በ1450 አከባቢ እንደነበር የሚል ታሪካዊ መዝገብ አለ። ቢሆንም መጀመርያ እንደ ሕገ ምንግሥት መጠቀሙን የተመዘገበው በዓፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን (ከ1555 ጀምሮ) ነው። ፍትሐ ነገስት እስከ 1923 ዓ.ም. የብሄሩን ዋና ሕግ ሆኖ ቆየ። በ1904 ዓ.ም. ዐጼ 2 ምኒልክ የዘመናዊ ሕገ መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ ተረድተው በጸሀፊው መምሬ ብስራት አንድ ሕገ መንግሥት የሚመስል ሰነድ ታተመ፤ ይህ ግን በውነት ሕገ መንግሥት አይባልም። «በምኒሊክ ስለተቋቋሙት ሚኒስቴሮች በምሳሌ የቀረበ ጽሑፍ» በምሳሌና በትርጓሜ የእያንዳንዱን ሚኒስቴር ሥራ እንደ ሰውነት አካላት አስመሰለ። ለምሳሌ፦ ኢትዮጵያ መጀመርያ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት የተቀበለችው በ1923 አመተ ምኅረት በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የታወጀ ሲሆን የሕግ አማካሪ ቤቶች በሁለት ያስከፈለ ነው። ይህ የመንግሥታቸው ዋና መሠረት ሆኖ እስከ 1948 አ.ም. አገለገለ፤ በዚያ አመት ተሻሽሎ በወጣ ሕገ መንግሥት ሕዝቦች በመንግሥት ሥራ የሚጫወቱት ሚና እንደገና ተስፋፋ። ይህ ብቻ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሆኖ እስከ 1967 አ.ም. ቆየ፤ የዛኔ በደርግ (በሕገ መንግስት እራሱ ባልሆነ ሂደት) ተሰረዘ።
በ1240 በግብጽ ሀገር በአረብኛ ፍትሐ ነገሥት ያዘጋጀው ማን ነበር?
አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል
24
ፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ "The Nation"፣ "The Chinese Recorder"፣ "Asia" እና "The Atlantic Monthly" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል።
ፐርል በክ የመቃብር ስፍራ ስሙ ምን በመባል ይታወቃል?
ፔንሲልቬንያ
1,174
የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። ውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ። ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል።
ዶ/ር ውለታ ለማ ያሸነፉበት አዲስ የሥራ ፈጠራ ውድድር በምን ዘርፍ ነው?
በጤና ቴክኖሎጂ
314
ደቡብ አፍሪካ በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ። ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውን፣ ብሉምፎንቴንና ፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው። ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው። የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ። የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካ የአፍሪካንስ ቋንቋ በተናጋሪ ብዛት ስንተኛው ነው?
3ኛው
154
አልጄሪያ አልጄሪያ (አረብኛ፦ الجزائر‎ አል ጃዝኤር; በርበርኛ፦ ድዜየር) በይፋ የአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሰሜን አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከቆሳ ስፋት አኳያ በሜዲቴራንያን ባህር ዙሪያ ትልቋ ስትሆን፣ ከአፍሪካ ደግሞ ከሱዳን በኋላ ሁለተኛ ናት። አልጄሪያ ከሰሜን ምሥራቅ በቱኒዚያ፣ ከምሥራቅ በሊቢያ፣ ከምዕራብ በሞሮኮ፣ ከደቡብ ምዕራብ በምዕራባዊ ሣህራ፣ ሞሪታኒያና ማሊ፣ ከደቡብ ምሥራቅ በኒጄር፣ ከሰሜን በሜዲቴራንያን ባህር ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ አልጂርዝ ሲሆን የ፳፻፫ ዓ.ም. ሕዝብ ብዛቷ ወደ 35.7 ሚሊዮን ይገመታል። አልጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ ኦፔክ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ሀገር ናት። የሀገሯ ስም የመጣው ከአልጂርዝ ከተማ ሲሆን በድሮ ጊዜ ከዛሬዎቹ ምዕራብ ቱኒዚያና ምሥራቅ ሞርኮ አብራ ኑሚዲያ ትባል ነበር። በጥንት ጊዜ አልጄሪያ የኑሚዲያ መንግሥት ትባል የነበረ ሲሆን ነዋሪዎቿ ደግሞ ኑሚዲያውያን ይባሉ ነበር። የኑሚዲያ መንግሥት ከካርታጎ፣ ሮማና ጥንታዊ ግሪክ ጋር ግንኙነት ነበራት። አካባቢው ለምለም እንደነበረ ሲነገር ኑሚዲያውያን ደግሞ ለኃይለኛ ፈረሰኛ ጦራቸው ይታወቁ ነበር።
የአልጄርያ የጥንት መንግሥት ስያሜ ምን ይባል ነበር?
የኑሚዲያ መንግሥት
513
ፍቅር እስከ መቃብር ፍቅር እስከ መቃብር በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያትን ፍቅር ይተርካል። ይህ ድርሰት ከሌሎች ልብወለድ ሥራዎች ለየት የሚያደርገው ደራሲው ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በፊደል አጠቃቀም ላይ ለውጥ አድርገው በማቅረባቸው ነው። ይኸውም ለምሳሌ ያህል ሦስት «ሀ»ዎች፣ ሁለት «ሰ»ዎች፣ ሁለት «ኣ»ዎች የመሳሰሉትን እንደ አንድ ወይም የመጀመሪያውን ብቻ በመያዝ ነው። በተጨማሪም ጠብቀው በሚነገሩ ቃላት ላይ ከላይ አንድ ነጥብ በማስቀመጥ ይታወቃሉ።ሀዲስ ኣለማየሁ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሑፍ የራሳቸው ትልቅ አሻራ አኑረው ያለፉ አንጋፋ ደራሲ ናቸው። የታሪኩ ማጠቃለያ በዛብህ‌ ‌ጎጃም‌ ‌ማንኩሳ‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከእናቱ‌ ‌ከውድነሽ‌ ‌በጣሙና‌ ‌ከአባቱን‌ ‌ከቦጋለ‌ ‌መብራት‌ ‌ይወለዳል።‌ ‌በሽታ‌ ‌ይበዛበትና‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይባላል።‌ ‌እናቱ‌ ‌ከበሽታው‌ ‌እንዲድን‌ ‌ስእለት‌ ‌ይሳላሉ።‌ ‌ዕድል‌ ‌ሆኖ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይተርፋል፤‌ ‌አድጎ‌ ‌ጎበዝ‌ ‌ልጅ‌ ‌ይሆናል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌በሽታ፣‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ዕውቀትና‌ ‌ፍቅር‌ ‌(የሰው‌ ‌መውደድ)‌ ‌ይበዛበታል።‌ ‌በወጣትነቱ‌ ‌ይቀድስና‌ ‌ለቤተሰቡ‌ ‌ገንዘብ‌ ‌ማምጣት‌ ‌ይጀምራል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌የስእለት‌ ‌ልጅ‌ ‌መባልን‌ ‌አይጠላም‌ ‌ነበር።‌ ‌ሲያድግ‌ ‌ግን‌ ‌ትርጉሙን‌ ‌በመረዳቱ‌ ‌ነጻነቱን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌ዲማን‌ ‌ጥሎ‌ ‌ወደደብረ‌ ‌ወርቅ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌እዚያም‌ ‌ከእመት‌ ‌ጠጂቱ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይጠጋል።‌ ‌ትንሽ‌ ‌ዜማና‌ ‌ቅኔም‌ ‌ይማራል።‌ ‌ደብተራ‌ ‌በየነ‌ ‌መጥቶ‌ ‌የወላጆቹን‌ ‌ሞት‌ ‌ሲያረዳው‌ ‌ወደዲማ‌ ‌ይወርዳል።‌ ‌በተክለ‌ ‌አልፍአው‌ ‌በዓል‌ ‌በመልካም‌ ‌ድምጹ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻንና‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትን‌ ‌ያወድሳል።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻም‌ ‌የሰብለ‌ ‌መምህር‌ ‌አድርገው‌ ‌ይቀጥሩታል።‌ ‌ሰብለና‌ ‌በዛብህ‌ ‌የሕይወት‌ ‌ገጠመኞቻቸው‌ ‌በመጠኑ‌ ‌ስለሚመሳሰል‌ ‌ይግባባሉ።‌ ‌በመሃል‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌አሰጋኸኝ‌ ‌ሰብለን‌ ‌በፈት‌ ‌ወግ‌ ‌አገባለሁ‌ ‌በማለቱ‌ ‌በርሱና‌ ‌በፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌መካከል‌ ‌ጥል‌ ‌ተፈጠረ፤‌ ‌ሆኖም‌ ‌በሃይማኖት‌ ‌ጣልቃገብነት‌ ‌ሳይዋጉ‌ ‌ቀሩ።‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከባላገሮች‌ ‌ጋራ‌ ‌በግብር‌ ‌ጉዳይ‌ ‌ተጣሉ።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ተማርከው‌ ‌ሳለ‌ ‌የበዛብህንና‌ ‌የሰብለወንጌልን‌ ‌የፍቅር‌ ‌ዜና‌ ‌ይሰማሉ።‌ ‌ወዲያውም‌ ‌መጥተው‌ ‌ሰብለን‌ ‌በሌሊት‌ ‌ያስሯታል።‌ ‌የሰብለ‌‌አጎት‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ሁለቱን‌ ‌ለማስመለጥ‌ ‌ወጣ፣‌ ‌ወረደ።‌ ‌የዕጣ‌ ‌ነገር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ግን‌ ‌ሳይሳካ‌ ‌ቀረ።‌ ‌በዛብህ‌ ‌ግን‌ ‌በግራጌታ‌ ‌ቀለመወርቅና‌ ‌በጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጥረት‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌በራጉኤል‌ ‌ቤተክርስቲያንም‌ ‌የቅኔ‌ ‌መምህር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ይቀጠራል።‌ ‌ባደረጉላቸው‌ ‌ውለታ‌ ‌ምክንያት‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌ሰብለን‌ ‌ለፊታውራሪ‌ ‌ታፈሰ‌ ‌ሊድሯት‌ ‌ይሞክራሉ።‌ ‌የሰብለን‌ ‌አቋም‌ ‌አውቀው‌ ‌አባ‌ ‌ተክለሃይማኖት‌ ‌በተባሉ‌ ‌መነኩሴ‌ ‌ያስጠብቋቷል።‌ ‌መነኩሴው‌ ‌ግን‌ ‌ሰክረው‌ ‌ሰብለ‌ ‌ታመልጣለች።‌ ‌ፍለጋ‌ ‌ሲሄዱ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከፈረስ‌ ‌ላይ‌ ‌ተወርውረው፣‌ ‌ተንኮታክተው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትም‌ ‌ቤተክርስቲያን‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከደረጃ‌ ‌ላይ‌ ‌ተንሸራትተው‌ ‌ወድቀው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ሰብለ‌ ‌ደግሞ‌ ‌በዛብህን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌መነኩሴ‌ ‌መስላ‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ትሄዳለች።‌ ‌ደርሳም‌ ‌በዛብህ‌ ‌አለመኖሩን‌ ‌ትሰማና‌ ‌ጎሃጽዮን‌ ‌ትወርዳለች።‌ ‌በዚያም‌ ‌በዛብህ‌ ‌ተደብድቦ፣‌ ‌ነፍስ‌ ‌ውጪ‌ ነፍስ‌ ‌ግቢ‌ ‌አይነት‌ ‌ሁኔታ‌ ‌ላይ‌ ‌ሳለ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌እንደምንም‌ ‌ብለው‌ ‌ሥጋ‌ ‌ወደሙን‌ ‌ይቀበላሉ።‌ ‌ጥቂት‌ ‌ቆይቶ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይሞታል።‌ ‌ሰብለም‌ ‌መንኩሳ፣‌ ‌የበዛብህን‌ ‌አስከሬን‌ ‌ባጠገቧ‌ ‌አድርጋ‌ ‌ስትኖር‌ ‌ከጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጋራ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌ጉዱ‌ ‌የተሰኘው‌ ‌ካሳ‌ ‌ዳምጤም‌ ‌እርሷ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይቀመጣል።‌ ‌አስራ‌ ‌አምስት‌ ‌ቀናት‌ ‌አንድ‌ ‌ላይ‌ ‌ይኖሩና‌ ‌ሰብለ‌ ‌የልብ‌ ‌በሽታዋ‌ ‌ተነሥቶባት‌ ‌ትሞታለች፣‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ከበዛብህ‌ ‌አጠገብ‌ ‌ያስተኛታል።‌ ‌በሦስተኛው‌ ‌አመት‌ ‌ጉዱም‌ ‌አረፍተ‌ ‌ዘመን‌ ‌ይገታዋል።‌
በዛብህ የትውልድ ቦታው የት ነው?
ጎጃም‌ ‌ማንኩሳ‌
426
ቴሌቪዥን ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው። በ1873 እ.ኤ.አ. (1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ። በ1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም። ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ... ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በ 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ። በ1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።
ጆን ሎጂ ቤርድ በ1926 እ.ኤ.አ. በቴሌቪዥን ምን ዓይነት ምስሎችን ነበር ማስተላለፍ የቻለው?
ጥቁርና ነጭ
989
ቀጭኔ ከዝሆን በስተቀር ማንኛውም ሌላ እንስሳ ሊደርስ በማይችልበት ከፍታ ላይ የሚገኙ ረዣዥም ቀንበጠቦችን ለመብላት የሚያስችል አስደናቂ አፈጣጠር አላት። ልዩ የሆነ የመቆንጠጥ ችሎታ ያለው የላይኛው ከንፈሯና እንደተፈገለው የሚተጣጠፍ ችሎታ ያለው ምላሷ ሹል በሆኑ እሾሆች የታጠሩ ቅጠሎችን ለመቀንጠብ ያስችሏታል። ቀጭኔዎች በቀን እስከ 34 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕፅዋት መመገብ ይችላሉ። የተለያዩ ዕፅዋትን የሚበሉ ቢሆኑም ይበልጥ የሚመርጡት በአፍሪካ ሜዳዎች የሚገኙትን እሾሃማ ግራሮች ነው። አንድ ወንድ ቀጭኔ ምግብ ለመፈለግ ምላሱን እስከ 42 ሳንቲ ሜትር መዘርጋት ይችላል። የቀጭኔ አንገት በጣም አስደናቂ የሆነ የመተጣጠፍ ችሎታ አለው። ይህም ላይኛዎቹን የዛፍ ቅርንጫፎች ለመቀንጠብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ረዥሙን ራሷን እንደ ልቧ ለማዘንበልና ለማዟዟር ያስችላታል። ለቀጭኔ ወደ ላይ መንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት ግን ይከብዳታል። ወደ ውኃ ጉድጓድ በምትቀርብበት ጊዜ የፊት እግሮቿን ቀስ በቀስ ከፍታ ካራራቀቻቸው በኋላ ወደ ውኃው ለመድረስ እንድትችል ሁለት ጉልበቶቿን አጠፍ ታደርጋለች። ቀጭኔዋ እንዲህ ባለው አመቺ ባልሆነ ሁኔታ እያለች ረዥም አንገቷን እስከ መጨረሻ ትዘረጋለች። ደግነቱ ግን ከምትመገባቸው ቅጠላ ቅጠሎች በቂ እርጥበት ስለምታገኝ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አያስፈልጋትም። የቀጭኔ አንገትና ትከሻ የቅጠል ቅርፅ ባላቸውና ቀጫጭን በሆኑ ነጭ መስመሮች ያጌጠ ነው። ቀለማቸው የተለያየ ሲሆን ከወርቃማ ዳለቻ አንስቶ እስከ ቡናማ እንዲያውም ጠቆር እስካለ ቀለም ይደርሳል። የቀጭኔ ዕድሜ እየገፋ በሄደ መጠን ቀለሟም እየጠቆረ ይሄዳል። ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው። አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ ልጅዋን ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት ከተሸከመች በኋላ ሁለት ሜትር ቁመት ያለው ግልገል ትወልዳለች። ግልገሏ በምትወለድበት ጊዜ ራስዋን ታስቀድምና ከሁለት ሜትር ከፍታ ላይ ወደ መሬት ትወረወራለች። ይሁን እንጂ በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባት እየተውተረተረች ትነሳና ጡት ለመጥባት ዝግጁ ትሆናለች። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ በደመ ነፍስ ተመርታ የግራር ቀንበጦችን መለቃቀም ስለምትጀምር ብዙም ሳትቆይ ረዥም እርምጃ ያላትን እናትዋን ተከትላ ለመሄድ የሚያስችል ጉልበት ታገኛለች። አንዲት የቀጭኔ ግልገል በጣም ውብ መልክ ሲኖራት የወላጆችዋ አነስተኛ ግልባጭ ነች። ቁመቷ ከቀጭኔ ርዝመት ጋር ሲወዳደር አጭር ብትሆንም ከብዙ ሰዎች ቁመት ግን ትበልጣለች። በእናቷ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ተማምና አላንዳች መሸበር አካባቢዋን የምትማትረው ግልገል ላያት ሁሉ ልዩ መስህብ አላት። ግልገል ቀጭኔዎች በተወለዱበት ወራት በግልገል መዋያ ተሰባስበው ሙሉውን ቀን ዕረፍት በማድረግ፣ በመጫወትና በአካባቢያቸው የሚሆነውን ነገር በመመልከት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የቀጭኔ ግልገል ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት ያድ⁠ጋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሜትር የሚያክል ቁመት ሲጨምር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል። በአንድ ሳምንት ብቻ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ሊያድግ ይችላል! እናትዬው ለልጅዋ ከፍተኛ ጥበቃ የምታደርግ ሲሆን ልጅዋ የተወሰነ ርቀት እንድትዘዋወር ብትፈቅድላትም ሩቅ የማየት ችሎታ ስላላት በዓይኗ ትከታተላታለች። ቀጭኔ ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ስላላት ከአንበሳ በቀር የሚያጠቃት ጠላት የለም። ቢሆንም ይህችን የምታምር ፍጥረት የሰውን ያህል በብዛት አድኖ የገደለ የለም። ቀጭኔ በሚያምር ቆዳዋ፣ በሚጣፍጥ ሥጋዋና አንዳንዶች ምትሐታዊ ኃይል አለው በሚሉት ረዥምና ጥቁር ጭራዋ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ ስለሆነች በአሁኑ ጊዜ የዚህች ሰላማዊ ፍጡር የወደፊት ሕልውና ስጋት ላይ ወድቋል። በአንድ ወቅት በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች እንደ ልብ ትታይ የነበረችው ቀጭኔ በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው በቂ ጥበቃ በሚደረግላት ፓርኮች ብቻ ሆኗል። የቀጭኔ አካላዊ ቅርጽና ግዝፈት ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል። በጣም ትልቅ ቁመትና ረዥም አንገት ስላላት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖራትና ወደ ሁሉም የአካሏ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ማድረግ የማይቻል ነገር ሊመስል ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀጭኔ አንገቷን ወደ መሬት ስታጎነብስ በስበት ኃይል ምክንያት ብዙ ደም ወደ ጭንቅላቷ ፈስሶ አንጎሏን ማጥለቅለቅ ነበረበት። ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ደሟ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ልቧ ተመልሶ ራሷን እስከ መሳት ሊያደርሳት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ነገር አይደርስም። ለምን? የቀጭኔ የደም ዝውውር ሥርዓት በዓይነቱ ልዩ ለሆነው ለዚህች እንስሳ ቅርጽና መጠን እንዲያገለግል ሆኖ በታላቅ ጥበብ የተሠራ ነው። ልቧ ራሱ በጣም ትልቅ ሲሆን ደሙን ሦስት ሜትር ተኩል ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ አንጎላ ለመግፋት የሚያስችል አቅም አለው። በደቂቃ እስከ 170 ጊዜ የሚመታውና 7 ሳንቲ ሜትር ያህል ውፍረት ባለው ጡንቻ የተገነባው የቀጭኔ ልብ ከሰው የደም ግፊት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ግፊት ያመነጫል። ወደ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው ካሮቲድ የተባለው የደም ቧንቧና ከአንጎል ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም የሚሸከመው ጀጉላር የተባለው የደም ቧንቧ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚያስችል መጠን ሊኖራቸው ይገባል። በእርግጥም እነዚህ የደም ቧንቧዎች ከ2.5 ሳንቲ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው ከመሆኑም በላይ ጠንካራና የመለጠጥ ችሎታ ባላቸው ሕዋሳት የተገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንካሬና የመለመጥ ችሎታ አላቸው። ቀጭኔ ከጭንቅላቷ ጎንበስ በምትልበት ጊዜ ወደ አንጎሏ የሚሄደውን የደም ፍሰት የሚቆጣጠሩ ልዩ መቆጣጠሪያዎች አሏት። አንጎልና አንገት በሚገናኙበት ቦታ ላይ ትልቁ ካሮቲድ የደም ቧንቧ ሬቴ ሚራቢሌ ተብሎ ከሚጠራ አስደናቂ የሆነ መረብ መሰል አካል ይገናኛል። በከፍተኛ ኃይል ተገፍትሮ የመጣው ደም እዚህ ጋር ሲደርስ በጣም በርካታ ወደሆኑ ትናንሽ የደም ሥሮች እንዲገባ ስለሚደረግ የደሙ ግፊት ተስተካክሎ በአንጎል ላይ ጉዳት የማያስከትል ይሆናል። ቀጭኔዋ ራስዋን ጎንበስ በምታደርግበት ጊዜ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው መረብ ይለጠጣል፤ ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ይኮማተራል። ይህም የስበት ኃይል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና የደም ግፊቷ በእጅጉ ቀንሶ ራሷን የምትስትበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳታል። የሳይንስ ሊቃውንት በጣም አስደናቂ ርዝመት ያለው የቀጭኔ አንገት ያሉት አከርካሪዎች ቁጥር ከአይጥ ወይም ከብዙዎቹ አጥቢ እንስሳ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቁ በጣም ተደንቀዋል! ይሁን እንጂ የቀጭኔ አከርካሪዎች በጣም ረዣዥሞችና እርስ በርሳቸው ልዩ በሆነ ሁኔታ የተሰካኩ በመሆናቸው እንደ ልብ ሊተጣጠፉ ይችላሉ። ቀጭኔ አንገቷን መጠምዘዝና ማጠፍ ስለምትችል ሁሉንም የአካሏን ክፍሎች ለመላስም ሆነ ረዣዥም የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ለመድረስ ትችላለች።
ቀጭኔዎች በመንጋ ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ሲሆኑ በአነድ መንጋ ምን ያህል ይኖራሉ?
ከ2 እስከ 50
933
ዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘውድ እንደጫኑ የአገሪቱን የመጀመሪያ ሕገ-መንግሥት እንዲዘጋጅ አዝዘው በዘውዱ አንደኛ ዓመት በዓል ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. በአዲሱ ምክር ቤት (ፓርላማ) ለሕዝብ ቀረበ። ከዚህም በላይ ብዙ የቴክኖዎሎጂ ስራዎችና መሻሻያዎች ወደ ኢትዮጵያ ከውጭ አገር አስገቡ። በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. የሙሶሊኒ ፋሺስት ሠራዊት ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ጃንሆይ ሕዝባቸውን ወራሪውን በሙሉ ለመቃወም እንዳስነሡና የከተት ዐዋጆቻቸው በታሪክ ገጾች ይዘገባሉ። በዐዋጅ መሠረት የዘመቻው ጊዜ እስቲያልቅ ድረስ ለሚታግሉ ነጋዶች ከቀረጥ አስተስርየት ሰጣቸው። እራሳቸው በቆራጥነት ከታገሉ በኋላ የጠላቱ ጦር ኅይል ግን በመጨረሻ ወደ እንግሊዝ አገር ለጊዜው አሰደዳቸው። ወደ ጄኔቭ ስዊስ ወደ ዓለም መንግሥታት ማኅበር ሄደው ስለ ጣልያኖች የዓለምን እርዳታ በመጠየቅ ተናገሩ። የዓለም መንግሥታት ግን ብዙ አላደረጉም። በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ግን አውሮፓ ሁሉ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተያዘ። የእንግሊዝ ሠራዊቶች ለኢትዮጵያ አርበኞች እርዳታ በመስጠት ጣልያኖች ተሸንፈው በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ኢትዮጵያን ተዉ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ አዲስ አበባን እንደገና የገቡበት ቀን ከወጡበት ቀን በልኩ ዕለት አምስት ዓመት በኋላ ነበረ። ከዚህ በኋላ በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የሕዝቦችን መብቶችና ተከፋይነት በመንግሥት አስፋፍቶ ሁለቱ ምክር ቤቶች እንደመረጡ አደረገ። በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ግርማዊነታቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአዲስ አበባ እንዲመሠረት ብዙ ድጋፍ ሰጡ። በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ወደ ካሪቢያን ጉብኝት አድርገው የጃማይካ ራስታዎች ተገኛኙ። በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. በማርክሲስት አብዮት ደርግ ሥልጣን ያዙና እሳቸው በእሥር ቤት ታሰሩ። በሚከተለው ዓመት ከተፈጥሮ ጠንቅ እንደ አረፉ አሉ ፤ ሆኖም ለምን እንደ ሞቱ ስለሚለው ጥያቄ ትንሽ ክርክር አለ። ብዙ ራስታዎች ደግሞ አሁን እንደሚኖሩ ይላሉ። የዓፄ ኃይለ ሥላሴ የትውልድ ስም ልጅ ተፈሪ መኮንን ነው። ስመ-መንግሥታቸው ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነበር። ሞዓ አንበሣ ዘእምነገደ ይሁዳ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የሚለው የሰሎሞናዊ ሥረወ-መንግሥት ነገሥታት መጠሪያም በንጉሠ-ነገሥቱ አርማ እና ሌሎች ይፋዊ ጽሑፎች ላይ ከመደበኛው ማዕረግ ጋር ይጠቀስ ነበር። ጃንሆይ ፣ ታላቁ መሪ እና አባ ጠቅል በመባልም ይታወቁ ነበር።
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በማን ታሰሩ?
በማርክሲስት አብዮት ደርግ
926
ጋሊልዮ ጋሊልዮ ጋሊሊ ታህሳስ 15, 1564 – ጥር 8, 1642 የነበረ የጣሊያን ሥነ-ፈለክ አጥኝና ተመራማሪ ነበር። ጋሊልዩ በዘመኑ የራሱን አጉሊ መነጽር በመስራት ጨረቃ ተራራ እንዳላት፣ ጁፒተር የተባለው ፈለክ ልክ እንደ መሬት የራሱ የሆኑ 4 ጨረቃወች እንዳሉት፣ ረጨቶች ከከዋክብት ስብስብ እንደተሰሩ፣ ፀሐይ ጥቁር ነጠብጣቦች እንዳሏት፣ ቬነስ ልክ እንደ ጨረቃ የተለያየ ቅርጽ በጥልቁ እንደምትይዝ የመሰከረና በኋላም መጽሃፍ ጽፎ ያሳተመ ሳይንቲስት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ጋሊልዮ የተፈጥሮ ህጎችን/ጉልበቶችን አጥንቷል። በትውፊት እንደሚነገር ጣልያን ውስጥ ባለው የተንጋደደው የፒሳ ግንብ ላይ በመውጣት፣ የተለያዩ ክብደት ያላቸውን የብረት ኳሶች ወደመሬት በመልቀቅ፣ ሁሉም በዕኩል ሰዓት መሬትን እንደሚመቱ አረጋግጧል። ከዚህ በመነሳት እስከሱ ዘመን ይሰራበት የነበረውን የአሪስቶትል አስተሳሰብ (ከባድ ነገሮች ከቀላል ነገሮች በበለጠ ፍጥነት ወደመሬት ይወድቃሉ) ፉርሽ አድርጓል። ሆኖም ግን በጊዜው የአሪስቶትል አስተሳሰብ በህብረተሰቡ ህሊና ውስጥ በጥብቅ ስለሰረጸ ቆይቶ ኢሳቅ ኒውተን የጋሊልዮን አስተሳሰብ ልክ መሆኑን በግስበት ጥናቱ እስካረጋገጠበት ድረስ የአሪስቶትል አስተሳሰብ ተቀባይነት ነበረው። ጋሊልዩ ከሱ ቀድሞ የተነሳውን የኮፐርኒከስን ሃሳብ (መሬት ሳትሆን ፀሓይ የአለም መካከለኛ ናት) በመደገፉ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለእስር ተዳርጎ ነበር። ይህም በዚያ ዘመን የነበሩ የቤ/ክርስቲያኒቱ አዋቂወች ያምኑት እንደነበረው መሬት ቆማ ሌላው አለም ሁሉ በመሬት ዙሪያ ይሽከረከራሉ የሚለውን ስለተቃወመ ነበር። ከዚህ በኋላ እስከ አረፈበት 1642 ድረስ የቤት እስረኛ ሆኖ ዘልቋል። በቅርቡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የሮማው ፓፓ ጆን ፓውል 2ኛ ጋሊልዮን "የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት] አባት" በማለት የካቶሊክ ቤ/ክርስቲያ ከ400 አመት በፊት በጋሊልዮ ላይ ለፈጸመችው ግፍ ይቅርታ ጠይቀዋል።
የሮማው ፓፓ ጆን ፓውል 2ኛ የጋሊልዮ ጥናት ትክክለኛ እንደነበር በማመን የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ወክለው ስለደረሰበት ግፍ ይቅርታ የጠየቁት ከስንት ዓመት በኋላ ነበር?
ከ400
1,023
የሕገ መንግሥት ታሪክ የሱመር ከተማ ላጋሽ አለቃ ኡሩካጊና በ2093 ዓክልበ. ያሕል ያዋጀ ሕገ ፍትሕ በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያ የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይታወቃል። ከዚህ በኋላ ብዙ መንግሥታት በተጻፈ ሕግ እንዲገዙ ልዩ ስርዓት ነበራቸው። ከተገኙት ሕግጋት ሁሉ ጥንታዊ የሆነው በ1983 ዓክልበ. የገዙ የኡር ንጉሥ የኡር-ናሙ ሕግጋት ነው። በተለይ ዕውቅ የሆኑ የጥንት መንግሥት ሕጎች የኢሲን ንጉሥ ሊፒት-እሽታር ሕግጋት (1832 ዓክልበ.) ፤ የኤሽኑና ሕግጋት (ምናልባት 1775 ዓክልበ. ግድም)፤ የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ሕግጋት (1704 ዓክልበ.) እና፤ ሕገ ሙሴ ለእስራኤል (1661 ዓክልበ.) ናቸው። ሕገ ሙሴ በተለይ በኦሪት ዘጸአት 21 እና 22 ያህዌ አስተካክሎ ከነዚህ ሁሉ የተሻሸሉት ብያኔዎች ይጠቅልላል። በኋላ ኬጢያውያን (1488 ዓክልበ. ግድም) እና አሦር (1080 ዓክልበ. ግድም) በበኩላቸው ለራሳቸው ሕግጋት አወጡ።
በ1704 ዓክልበ. በባቢሎኑ ሕዝቡን ለማስተዳደር ሕግ አውጥቶ የነበረው ንጉሥ ማን ይባላል?
ንጉሥ ሃሙራቢ
457
አሸናፊ ከበደ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አዲስ አበባ ግንቦት ፰ ቀን ፲፱፻፴ ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ግራዝማች ከበደ አድነው ሲሆኑ ክልጅነታቸው ጀምሮ የሙዚቃ ስሜትንና ፍቅር ያሳደሩባቸው እናታቸው ወይዘሮ ፋንታዬ ነከሬ ነበሩ። አያታቸው ሊቀመኳስ አድነው ጎሹ ደግሞ የአድዋ አርበኛ እናየንግሥት ዘውዲቱም ታማኝ አማካሪ እንደነበሩ ይነገራል። የሙዚቃ ፍቅርን ገና በልጅነታቸው ያሳደሩባቸው እናታቸው ሲሆኑ ታዳጊው አሸናፊ ገና የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሳሉ እኒህ የሚያፈቅሯቸውና ዕድሜ ልካቸውን በኀዘን የሚስታውሷቸው እናታቸው ሞተውባቸዋል። መሠረታዊ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኮከበ ጽባሕ) ካጠናቀቁ በኋላ በሐረር የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኒው ዮርክ ክፍለ-ሀገር ከሚገኘው የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ፣ “ኢስትማን የሙዚቃ ትምህርት ቤት” በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፤ የያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤትን መሠረቱ። የዚሁ ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው ዳይሬክቶር ከመሆናቸውም ባሻገር በአዲስ አበባው የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር (ወ.ወ.ክ.ማ Y.M.C.A.)፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርሓ-ዕውራን ትምህርት ቤት እና በመሳሰሉ የወጣቶች ማኅበራት እየተገኙ የሙዚቃ ትምህርት ይሰጡ ነበር።
ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ በየት የመምህራን ማሰልጠኛ ተመረቁ?
በሐረር
423
አዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዕውቁና አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ በውጭ አገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች ወጣቶችን በሳይንስ በማነጽ ተግባር እንዲሰማሩ፤ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር ጥላሁን በቻይና ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የአፍሪካ ሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል ሊያቋቁሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚዘጋጀው ወርኃዊ የሳይንስ ገለጻ መድረክ ወጣቱን ትውልድ ማስተማርና ማነጽ ለኢትዮጵያ ተስፋ፤ የቻይና ተምሳሌትነት በሚል ትናንት ምሽት ገለጻ አድርገዋል። በአውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 1943 በኢትዮጵያ የተወለዱት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች አጠናቀው በቀድሞው የአለማያ እርሻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት በኮሌጅ ቆይታቸው ባሳዩት የላቀ ውጤትም አሜሪካን አገር በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህር ቤት ተልከው ትምህርታቸውን በማጥናት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት አስተምረዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላም ወደ ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በደቂቀ ሥነ ሕይወት መስክ በማጥናት በአውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1980-2006 በተማሩበት ካሊፎርኒያ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አስተምረዋል፤ ተመራምረዋል። እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ደግሞ የዲስቲንጉሽድ ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.አ.አ ከ1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል በማቋቋም በዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ የእንስሳት ህክምና ትምህርት የት ሀገር በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ተማሩ?
አሜሪካን
653
ጨኖ ጨኖ ግራጫ ቢጤ የሆነ፣ ፈርጠም ያለ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ አፍሪቃ፣ በተጨማሪም በኮንጎ ደኖች የሚገኝ ዝንጀሮ ነው። በኢትዮጵያ የሚገኘው ዓይነት ጨኖ የፀጉሩ ቀለም ግራጫና ጥቁር የሆነ፣ ፊቱ የጠቆረ ሰማያዊ የሆነ፣ አገጭና አንገቱ ነጭ ነው። የወንዶቹ ክብደት እስከ 12 ኪ.ግ. ሲሆን፤ አማካዩ 4.5 ኪ.ግ ይመዝናሉ። ጨኖ የደን ዝንጀሮ ነው። የደን ዝንጀሮች ብዙ ጊዜ ከዝናባማ ሥፍራዎች ደኖች ውጪ አይገኙም። ጨኖ ግን ከነዚህ ደኖች ውጪም በሚገኙ ደኖች ውስጥ ይኖራል። በኢትዮጵያ፣ በጎደሬ ደን ውስጥ፣ ቴፒ አጠገብ ሜጢ አካባቢ ይገኛሉ። በተራራማ ሥፍራዎች ደኖችም እስከ 3000 ሜትር ከፍታ ድረስ ይገኛሉ። እጅጉን በዛፍ ላይ የሚገኝ ዝንጀሮ ነው። የሚገኘው በደን ዛፎች ግማሽ ላይ ነው። በተለያዩ ዓይነት ተግባሮች መገለጫ የሚሆኑ ሰባት ዓይነት ድምፆች አሏቸው። በቡድናቸው ውስጥ የሚታየው አብዛኛው ፀብ፣ በዋናው ወንድና ለአካለ መጠን ባልደረሱና ጎረምሳ ወንዶች መሃል የሚታየው ነው። በሴቶቹና ሕፃናትን በሚገድሉ ወንዶች መኻከል ከባድ ግጭት ያድጋል። በቡድኖች መኻከል የሚደረግ ግጭት የሚሆነው አልፎ አልፎ ነው። እንዲህ ያለ ግጭት የሚነሳው በድንበር አካባቢ በምግብ ሽኩቻ የተነሳ ነው። የእርግዝና ጊዜአቸውን 140 ቀን ነው። የልጆቻቸውን እድገትም ቀስ ያለ ነው። ከወለዱ ወዲያ ለሚቀጥለው እርግዝና 15 ወራት መቆየት አለባቸው።
የጨኖ አማካይ ክብደት ስንት ነው?
4.5 ኪ.ግ
199
መዓዛ ብሩ በእሁድ የሬዲዮ ፕሮግራም ታቀርባቸው የነበሩት ሥራዎች ይዘት ማህበራዊ ሕይወት እንዲሠምር በመጣር ላይ ያተኮሩ ሆነው ግልጽ፣ ቀላልና ለዛ ያልተለያቸው ስለነበሩ ከሶስት አሥርት ዓመታት በኋላም ትውስታቸው ከአድማጭ ህሊና አልጠፉም፡፡ በዚሁ ፕሮግራም ላይ መዓዛ ካበረከተቻቸው የፈጠራ ሥራዎቿ ውስጥ ጎልቶ የሚታወሰው “የአዲሱ ቤተሰብ” የተሰኘ ባለ ሰማንያ ስድስት ክፍል ድራማ ሲሆን በዘመኑ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉም የሚያደምጠው ተወዳጅ የቤተሰብ ድራማ ነበር፡፡ መዓዛ በ “መርሀ ስፖርት” እና በሬዲዮ መካከል ሆና ከአራት ዓመት በላይ ከቆየች በኋላ በ1979 ዓ.ም የባህል ሚኒስቴርን ለቃ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጠረች፡፡ አዲሱን መስሪያ ቤቷን ከተቀላቀለችበት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከሬዲዮ እየራቀች መጣች፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የቆየችው ለሶስት ዓመታት ያህል ሲሆን ከዚያ በኋላ የግሏን የማስታወቂያ ሥራ ድርጅት መሥርታ የራስዋ ተቀጣሪ ሆናለች፡፡ ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1992 ዓ.ም ባሉት የአስራ ሶስት ዓመታት ጊዜ ግን መዓዛና ሬዲዮ ተራራቁ፡፡ መዓዛና ሬዲዮ ዳግም የተዋደዱት ከላይ እንደተገለጸው በ1992 ዓ.ም ሳምንታዊውን የ “ጨዋታ” ፕሮግራም በኤፍ ኤም 97.1 ከተፈሪ ዓለሙ ጋር በጋራ ማቅረብ ሲጀምሩ ነበር፡፡ የ “ጨዋታ” ፕሮግራም እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ በአድማጮቹ እንደተወደደ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ መንግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ፈቃዶችን ለግሉ ዘርፍ ለመስጠት ሲዘጋጅ፣ ዝርዝር የሥራ እቅድ አቅርባ ባመለከተችው መሠረት፤ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ከአስር አመልካቾች መካከል አንዷ ሆና የመጀመሪያ የግል የኤፍ ኤም ሬዲዮ ባለቤት ያደረጋትን ፈቃድ ተቀበለች፡፡ መዓዛ የሬዲዮ ማሰራጫ መሳሪያዎችን ውድነት፣ የማሰራጫ ቦታ እና የባለሙያ እጦትን ተቋቁማ ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮን በታህሳስ 1999 ዓ.ም አበረከተችልን፡፡ ባለትዳርና የሶስት ልጆች እናት የሆነችው መዓዛ እንደ ባለቤት፣ ሥራ አስኪያጅና ጋዜጠኛ በመሆን በኢትዮጵያ ተወዳጁንና የመጀመሪያውን የግል የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ትመራለች፡ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!”እያለች::
መዓዛ ብሩ የየትኛው ኤፍ ኤም ራድ ጣቢያ ባለቤት ነች?
ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮ
1,027