topic
stringlengths
16
333
news
stringlengths
16
46.2k
አባይን ለልጄ እንቅስቃሴ በፈረንሳይ ፓሪስ ተጀምሯል ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኅዳር ቀን፣ ዓ ም የዓለም ዜና ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ትኩረት በአፍሪካ እና የጋዜጦች አምድ መሰናዶዎች ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ትኩረት በአፍሪካ እና የጋዜጦች አምድ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሐምሌ ቀን ዓ ም የስፖርት መሰናዶ
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኢታሎ ቫሳሎ ሐምሌ ቀን ዓ ም በሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በጃፓን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በ ሺሕ ሜትር በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ብታገኝም በልዑካን ቡድኑ መካከል ተፈጠረ የተባለው አለመግባባት ለስፖርት አፍቃሪዎች አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኢታሎ ቫሳሎ ሐምሌ ቀን ዓ ም በሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኢታሎ ጉሮሯቸው ላይ በገጠማቸው ሕመም የቀዶ ሕክምና አድርገው መናገር ከማይችሉበት ደረጃ ደርሰው እንደነበር ለዶይቼ ቬለ የተናገሩት በቅርብ የሚያውቋቸው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ከሚኖሩባት አስመራ ለሕክምና በተጓዙባት የጣልያኗ ሮም ማረፋቸውን አስረድተዋል። ኢታሎ እና ታላቅ ወንድማቸው ሉቺያኖ ቫሳሎ አራት ብሔራዊ ቡድኖች በተሳተፉበት ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፈው ከተጫወቱ መካከል ይገኙበታል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ግብጽን ለ በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ሆናለች። በጃፓን በመካሔድ ላይ በሚገኘው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ በ ሺሕ ሜትር በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ብታገኝም በልዑካን ቡድኑ መካከል ተፈጠረ የተባለው አለመግባባት ለስፖርት አፍቃሪዎች አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። የሞሮኮው ኤል ባካሊ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በሆነበት የ መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት ለአገሩ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል። የዛሬው የስፖርት መሰናዶ ከሚያተኩርባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የኢታሎ ቫሳሎ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት እና የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ይገኝበታል። ሃይማኖት ጥሩነህ
ስፖርት፤ ጳጉሜ ቀን፣ ዓ ም
በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር ስታልፍ፤ በአውሮጳ ዋንጫ ማጣሪያ ደግሞ ጀርመን ዛሬ ከባድ ግጥሚያ ይጠብቃታል። የዐርቡን ከባድ ሽንፈት ለመካስ የጀርመን ቡድን ኳስ ይዞ በማጥቃት ላይ መመስረት ይኖርበታል። ባሕር ዳር ላይ ያለምንም ግብ የተለያየየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በመልሱ ግጥሚያ ከሌሶቶ ጋር አቻ ተለያይቶ ለቀጣዩ ዙር ማለፉ ከሳምንቱ ማሳረጊያ ዐበይት የስፖርት ክንውኖች ቀዳሚው ነው። ዋልያዎቹ አሁን ለቀጣዩ ማጣሪያ ከሚሳተፉት ሃገራት አንዱ መኾን ችለዋል። የጀርመን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለአውሮጳ ዋንጫ ማጣሪያ ዛሬ የምድቡ ቀዳሚን ይገጥማል። የዐርብ ዕለቱን ከባድ ሽንፈት ለመካስ የጀርመን ቡድን ኳስ ይዞ በማጥቃት ላይ መመስረት ይኖርበታል። በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ጀርመንን ወክሎ ለመሮጥ ከተዘጋጀ ትውልደ ኤርትራዊ ጀርመናዊ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገናል። ራፋኤል ናዳል ለ ኛ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስ የሜዳ ቴኒስ ፍጻሜ ባለድል ሲኾን፤ ብርቱዋ አሜሪካዊት ሴሬና ዊሊያምስ በፍጻሜው ለ ዓመቷ አዲስ አትሌት እጅ ሰጥታለች። ካታር ከሦስት ዓመት በኋላ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ በምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ፍልሚያው ተጧጡፏል። ኢትዮጵያ ሌሶቶን ጥላ ወደቀጣዩ ዙር ስታልፍ ያልተጠበቁ ውጤቶችም ተመዝግበዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ሌሶቶ ውስጥ የመልስ ጨዋታውን አንድ እኩል በመለያየት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል። ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በተደረገው የመጀመሪያው ዙር የማጣሪያ ግጥሚያ የኢትዮጵያ ቡድን ግብ ሳይቆጠርበት መውጣቱ ዕድሉን አስፍቶለታል። እናም ከአገር ውጪ ግብ ባስቆጠረ በሚለው ሕግ፦ ምንም እንኳን ጨዋታው አቻ ቢጠናቀቅም የኢትዮጵያ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል። በርካቶችን እጅግ ያስደመመው ግጥሚያ የተከናወነው ባለፈው ሐሙስ ነበር። ለሦስት ዐሥርተ ዓመት በእርስ በእርስ ጦርነት እና አለመረጋጋት ከስፖርቱ ዓለም ርቃ የቆየችው ጎረቤት ሶማሊያ በምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪቃ እግር ኳስ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣትን ዚምባብዌን ጉድ አድርጋለች። የዚምባብዌ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በሶማሊያ ቡድን ለ መሸነፉ በርካቶችን አስደንቋል። በፊፋ ደረጃ ዚምባብዌ ኛ ላይ ስትገኝ ሶማሊያ ልክ እንደ ኤርትራ ደረጃዋ ኛ ነው። እጅግ ያስደመመውም ሶማሊያ በደረጃ የምትርቃት ዚምባብዌን በድንቅ ግብ ማሸነፏ ነው። የሶማሊያ ቡድን በጸጥታ ችግር የተነሳ ጎረቤት ጅቡቲ ውስጥ ባደረገው ግጥሚያ ብቸናዋን ግብ ያስቆጠረው የመሀል ተመላላሹ አህመድ ዓሊ ብሪታንያ ማንቸስተር ሲቲ ውስጥ የአሽከርካሪዎች አሰልጣኝ ነው። በጣም ልብ የሚነካ ነው፤ በመላው ዓለም የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጨዋታውን እንደሚመለከቱት ስታውቅ እጅግ በጣም ልዩ ስሜት ይፈጥራል ብሏል ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው አህመድ። ሳይድ ዓሊ በ ኛው ደቂቃ ላይ አህመድ ኳሷን እንዲያቀብለው በእጁ ምልክት ሲሰጠው በድንቅ ኹኔታ አሻግሮለታል። አህመድም ተረጋግቶ እና አልሞ ኳሷን በጭንቅላቱ በመግጨት ከመረብ አሳርፏታል። ሶማሊያ ባለፈው ሐሙስ በአህመድ ዓሊ ማሃሙድ ባስቆጠረችው ብቸኛ ግብ ሰፊ ዕድል ይዛ ነው ነገ ዚምባብዌን በመልሱ ግጥሚያ የምትፋለመው። ታንዛንያ እና ቡሩንዲ ትናንት ያደረጉት ጨዋታ እኩል በመጠናቀቁ በተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት መለያ፦ ታንዛኒያ ለ አሸንፋለች። ኢኳቶሪያል ጊኒ ደቡብ ሱዳንን ለምንም ስታሸንፍ፤ ሴራሊዮን ላይቤሪያን አንድ ለባዶ ረትታለች። በመጀመሪያው ዙር ላይቤሪያ ለ ድል በማድረጓ በድምር ውጤት ለ አሸንፋ ወደቀጣዩ ዙር አልፋለች። ጅቡቲ ባለፈው ረቡዕ ለ ያሸነፈቻት ኢስዋቲኒን በነገው ዕለት ትገጥማለች፤ ሞዛምቢክ ከሞሪሺየስ እንዲሁም ሶማሊያ ከዚምባብዌ ጋር የመልስ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። ሞዛምቢክም ሶማሊያም በተመሳሳይ ለ ስላሸነፉ ሰፊ ዕድል ይዘው ነው ወደ ሜዳ የሚገቡት። በመጀመሪያው ዙር ለ የተሸነፈችው ኤርትራ ነገ ማታ ናሚቢያን ትገጥማለች። ሱዳን ከቻድ፤ ሩዋንዳ ከሲሼልስ፤ ጊኒ ቢሳዎ ከሳዎቶሜና ፕሪንሲፔ፤ ቶጎ ከኮሞሬን፤ አንጎላ ከጋምቢያ፤ እንዲሁም ማላዊ ከቦትስዋና በነገው ዕለት ይጫወታሉ። የአውሮጳ ዋንጫ ማጣሪያ ከማጣሪያ ጨዋታዎች ሳንወጣ የአውሮጳ ዋንጫ ማጣሪያም አውሮጳ ውስጥ እየተከናወነ ይገኛል። ባለፈው ረቡዕ በሜዳው በኔዘርላንድ ከባድ ሽንፈት የገጠመው የጀርመን ቡድን ዛሬ ከምድቡ መሪ ሰሜን አየርላንድ ጋር ይፋለማል። ጀርመን ካለፉት ዓመታት ወዲህ በሜዳዋ እንዲህ ከባድ ሽንፈት ስታስተናግድ የዐርብ ዕለቱ የመጀመሪያው ነው። ከረፍት መልስ አይለው ወደሜዳ የገቡት ኔዘርላንዶች ለ ድል ማድረግ ችለዋል። ጀርመን ለአውሮጳ ዋንጫ ማጣሪያ በሜዳው ሐምቡርግ ውስጥ መሸነፉን በተመለከተ የጀርመን እግር ኳስ የዓመቱ ኮከብ ማዕረግን የተቀዳጀው ማርኮ ሮይስ ለዶይቸ ቬለ አስተያየቱን ሰጥቷል። ኔዘርላንዶች ባሳዩት አቋም ማሸነፋቸው ተገቢ ቢኾንም፤ ቡድኑ በተለይ በተከላካይ መስመር በኩል ድክመት ማሳየቱ ለሽንፈታቸው ሰበብ መኾኑን ተናግሯል። በዛሬው ጨዋታም በዚህም አለ በዚያ ሰሜን አይርላንድን ማሸነፍ እንደሚጠበቅባቸው ገልጧል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮኣሒም ሎይቭም በተመሳሳይ ከማሸነፍ ውጪ ምንም አማራጭ እንደሌለ አስረግጠው ተናግረዋል። ሰሜን አየርላንዶች የደረጃ ሰንጠረዡ መሪዎች ናቸው። ያም በመኾኑ ብቸኛው ግባችን ጨዋታውን ለማሸነፍ የቻልነውን ኹሉ ማድረግ ነው። ያ በእርግጥ ማስቸገሩ አይቀርም፤ ምክንያቱም ሰሜን አየርላንዶች የሚጫወቱት በሜዳቸው የሰውነት ጥንካሬያቸውን ተጠቅመው ነው፤ እናም ያን ማድረግ ምንግዜም አስቸጋሪ ነው። ኾኖም ግባችን ነጥብ ማግኘት ነው። የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ምናልባትም ዛሬ የአጨዋወት ስልት ለውጥ አድርጎ ኳስን በብዛት በቁጥጥር ስር በማዋል በማጥቃት ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ለዚህም ይረዳው ዘንድ በጉዳት ዛሬ በማይሰለፈው ኢካይ ጎንዶዋን ምትክ የ ዓመቱ ወጣት ኬይ ሀቨርትስን ሊያሰልፉ ይችላሉ። ኬይ ለሌቨርኩሰን ባለፈው የቡንደስሊጋ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግቦችን ከመረብ ያሳረፈ በበርካቶች ዘንድ የሚጠበቅ ወጣት ነው። አሰልጣኝ ዮአሂም ሎይቭ ምናልባትም ዛሬ ወደተለመደው የ አሰላለፍ ሊመለሱም ይችሉ ይኾናል። ሰሜን አየርላንዶች በአንድ የመሀል አጥቂ ነው የሚጫወቱት ስለዚህ ሁለት የመሀል ተከላካይ ብቻ ነው የሚያስፈልጉን ሲሉም ተደምጠዋል ወደ ቀድሞ አሰላለፋቸው ሊመለሱ እንደኾን ሲጠቁሙ። ዛሬ ማታ ከጀርመን እና ሰሜን አየርላንድ በተጨማሪ አምስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ። አትሌቲክስ የተወለደው አሰብ፤ ኤርትራ ሲኾን በልጅነቱ አዲስ አበባ ከተማ እና ትግራይ ውስጥ ኖሯል። እዚህ ጀርመን ሀገር በስደት መጥቶ መኖር ከጀመረ ዓመታት ተቆጥሯል። አትሌት አማንአል ጴጥሮስ ይባል። ዘንድሮ ከጀርመን የአትሌቲክስ ቡድን ጋር በዶሃው የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር ይሳተፋል። በስልክ አነጋግረነዋል። ወደ ጀርመን ከመምጣቱ በፊትም በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ ነበር፤ በተለይ ደግሞ በእግር ኳስ። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ ወደ ጀርመን ሀገር ከመጣ ወዲህ በተለያዩ ውድድሮች ተሳታፊ ኾኗል። በ የጀርመን ዜግነት ከያዘ በኋላ ደግሞ ለጀርመን ቡድን ተሰልፎ በአውሮጳ ሃገራት ውጤት አስመዝግቧል። በዘንድሮው የዶሃ የዓለም አትሌቲክስ እና በቀጣዩ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ተፎካካሪ ለመኾን ጠንክሮ በመሥራት ላይ ይገኛል። የሜዳ ቴኒስ በዩናይትድ ስቴትስ የሜዳ ቴኒስ የፍጻሜ ግጥሚያ ስፔናዊው ራፋኤል ናዳል ለ ኛ ጊዜ ባለድል በመኾን፤ የ ሚሊዮን ዶላር ሽልማቱን ተቀብሏል። ለ ሰአታት ከ ደቂቃ በዘለቀው ግጥሚያ ራፋኤል ናዳል ያሸነፈው የሩስያው ተፎካካሪው ዳኒል ሜድቬዴቭን ነው። ከባድ ፉክክር የታየበት ግጥሚያ የተጠናቀቀው በ ፤ ፤ ፤ ፤ እና ነው። ያለፉትን የፍጻሜ ግጥሚያዎች ከአንዱ በስተቀር በተከታታይ ያሸነፉት ራፋኤል ናዳል፤ ሮጀር ፌዴሬር እና ኖቫክ ጄኮቪች ናቸው። በሴቶች ተመሳሳይ ውድድር የ ዓመቷ አሜሪካዊት በ ዋና ዋና ግጥሚያዎች ድልን ብትቀዳጅም በፍጻሜው ለ ዓመቷ ወጣት እጅ ሰጥታለች። ካናዳዊቷ ወጣት ቢያንካ አንድሪስኩ ቅዳሜ ዕለት የመጀመሪያዋ በኾነው የዩናይትድ ስቴትስ የሜዳ ቴኒስ ፍጻሜ እና ድል አድርጋ በሚሊዮናት ዶላር ተንበሽብሻለች። ማንተጋፍቶት ስለሺ
ስፖርት፤ ጳጉሜ ቀን፣ ዓ ም ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የእንግሊዙ የእግር ኳስ ቡድን አዲስ ታሪክን መፃፍ አልቻለም ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ስፖርት፤ ጥር ቀን፣ ዓ ም
ዕድሜያቸው ከ ዓመት በታች የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ድንቅ ጨዋታ አከናውነው ውጤት ግን አልቀናቸውም። ከ ዓመት በታች የሴቶች ቡድን ሳምንት ከቡሩንዲ ጋር ይጋጠማል። አጠር ያለ ዘገባ ይኖረናል። ብቸኛዋ ኢራናዊት የኦሎምፒክ ባለድልድ ከእንግዲህ ኑሮ በኢራን በቃኝ ብላለች። ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ድንቅ ጨዋታ አከናውነው ውጤት ግን ስላልቀናቸው ዕድሜያቸው ከ ዓመት በታች የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አጠር ያለ ዘገባ ይኖረናል። ብቸኛዋ ኢራናዊት የኦሎምፒክ ባለድልድ ከእንግዲህ ኑሮ በኢራን በቃኝ ብላለች። በሴትነቷ ከኢራን ባለለሥልጣናት ከፍተኛ በደል እንደደረሰባት የተናገረችው አትሌት ኔዘርላንድ ትገኛለች። የጫካ ሰደድ እሳት በሚለበልባት አውስትራሊያ ታዋቂው የአውስትራሊያ የሜዳ ቴኒስ ፍጻሜ ውድድር ነገ ይጀመራል። የአየሩ ኹኔታ እጅግ አሰሳሳቢ ነው ተብሏል። ጀርመናዊው የቦሩስያ ዶርትሙንድ ተጨዋች ማሪዮ ጎይትሰ የእግር ኳስ ቀጣይ እጣ ፈንታው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ምናልባት ማሪዮን ሊፈልጉት ይችላሉ የተባሉ ሁለት ቡድኖች በቡንደስሊጋው እና በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቢኖሩም የዶርትሙንድ ቆይታው ግን ያበቃ ይመስላል። ፕሬሚየር ሊግ በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል በተለመደ ግስጋሴው ቀጥሏል። አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው የፕሬሚየር ሊጉን ነጥብ ይዞ እየመራ ነው። ሊቨርፑል ቅዳሜ ዕለት ቶትንሀም ሆትስፐርን ለ ያሸነፈ ሲኾን፤ ትናንት አስቶን ቪላን የጎል ጎተራ ያደረገው ተከታዩ ማንቸስተር ሲቲን በ ነጥብ እየመራ ይገኛል። ሊቨርፑል ቀጣዩን ጨዋታ ካሸነፈ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ልዩነቱ ይኾናል ማለት ነው። ማንቸስተር ሲቲ አስቶን ቪላ ለ ነው የጎል ጎተራ ያደረገው። ቸልሲ በርንሌይን ለ ፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ኖርዊች ሲቲን ለ አሸንፈዋል። ኒውካስትል ከዎልቭስ አንድ እኩል ተለያይቷል። ዋትፎርድ ቦርሞስን ትናንት ለ ድል አድርጓል። ላይስተር ሲቲ በሳውዝሀምፕተን ለ ሲሸነፍ፤ ኤቨርተን ብራይተንን፤ ሼፊልድ ዩናይትድ ዌስትሀምን ለ አሸንፈዋል። በ ኛው ደቂቃ ላይ ማክስ ማየር ላይ በፈጸመው ከባድ ጥፋት ፒየር ኤሜሪክ አውባሜያንግን በቀይ ካርድ ያጣው አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ ጋር ቅዳሜ ዕለት አንድ እኩል ተለያይቶ ነጥብ ጥሏል። አርሰናል ነጥብ ይዞ ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በደረጃ ሰንጠረዡ ላይስተር ሲቲ ኛ፣ ቸልሲ ኛ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ኛ ናቸው። የሴቶች እግር ኳስ በኢትዮጵያ ህንድ በምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ አድርጋለች። ዕድሜያቸው ከ ዓመት በታች ተጨዋቾች በሚሳተፉበት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከኡጋንዳ አቻው ጋር ቅዳሜ ጥር ተጫውቶ ለ ተሸንፏል። ቡድኑ በቂ ልምምድ እና ዝግጅት እንዳላደረገ ቢነገርም ኡጋንዳ ውስጥ ያከናወነው ጨዋታ ግን ድንቅ እንደነበር የኡጋንዳ ቡድን አሰልጣኝ አዩብ ካሊፋ አልሸሸጉም። አዩብ ቡድናቸው የኢታዮጵያ አቻው ላይ ጨዋታው በተጀመረ ኛ ደቂቃ ላይ የመጀመሪያዋን ግብ በዡሊየት ናሉኬንጌ ቢያስቆጥርም ተፎካካሪው ጠንካራ እንደነበር መስክረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በበኩላቸው ቡድናቸውን የዝግጅት ጊዜ ማነስ እንደጎዳው ተነግሯል፡፡ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሳሙኤል አበራ ለሁለት ሳምንታት ብቻ ተዘጋጅቶ ወደ ውድድር የገባውን ብሔራዊ ቡድን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለወደፊት በቂ የዝግጅት ጊዜ አንዲሰጥ ከጨዋታው አስቀድመው አሳስበው ነበር። ከሽንፈቱ መልስ አሰልጣኝ ሳሙኤል የሚከተለውን ብለዋል፡፡ በዙር ግጥሚያው ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ አሸናፊ የሚኾነው ቡድን በማጣሪያው ከታንዛኒያ እና ቡሩንዲ አሸናፊ ከአንዱ ጋር ይገጥማል። የኢትዮጵያ ከ ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድንም በመጪው ቅዳሜ ከሜዳው ውጪ የማጣሪያ ጨዋታውን ከብሩንዲ ጋር ያደርጋል። ብሔራዊ ቡድኑ ተመሳሳይ የዝግጅት ጊዜ ማጠር ችግሮች እንደገጠመው ለማወቅ ተችሏል። በአጠቃላይ የሴቶች እግር ኳስ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገቢው ድጋፍ እየተደረገለት አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች በተደጋጋሚ ይሰማሉ። በሌላ ዜና የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ስብሰባ ያደረገ ሲኾን፤ የወንዶች ቡድን ቁጥር መጨመሩን እና የሴቶች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ገልጧል። ፌዴሬሽኑን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት በፕሬዝደንትነት አንዲመሩ አዲስ አበባ ውስጥ እሁድ ጥር በተደረገ ጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡት አቶ ፍትኅ ወልደሰንበት በስፖርቱ ያለውን የደከመ የሴቶች ተሳትፎ ለማሳደግ በጥረት ላይ አንደሚገኙ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ የበጀት ችግር በስፋት በሚታይበት የእጅ ኳስ ስፖርት የወንድ ክለቦች ቁጥር ባለፉት አራት ዓመታት ከነበረበት ወደ ቢያድግም የሴት ቡድኖች አለመቋቋማቸውን እንደድክመት አንስተዋል፡፡ የሴት ቡድኖች የሚቋቋሙ ከሆነም የውስጥ ሊግ ውድድር በፍጥነት ለመጀመር መታሰቡን አቶ ፍትኅ አስረድተዋል፡፡ በሌሎች ስፖርቶች በተለይም በእግር ኳስ ላይ ለሴቶች የሚሰጠው ትኩረት በቅርብ ጊዜያት እያነሰ ቢመጣም በእጅ ኳስ ፌዴሬሽን በኩል ተገቢውን ክትትል ለማድረግ መታቀዱን ፕሬዝደንቱ ጨምረው ጠቅሰዋል። ለሁለቱም ዘገባዎች መረጃዎቹን የላከልን የእግር ኳስ ስፖርት ጋዜጠኛው ኦምና ታደለ ነው። የእግር ኳስ ተጨዋቾች የዝውውር ዜና በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የተጨዋቾች ዝውውር ጎላ ብሎ አልታየም። በስፔን ላሊጋ ግን ባርሴሎና የቶትንሀም አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ለማስመጣት ንግግር እያደረገ ነው ተብሏል። ባርሴሎና ሉዊስ ሱዋሬዝን የሚተካ ተጨዋችም ያስፈልገዋል። የባርሴሎናው አጥቂ የ ዓመቱ ሉዊስ ሱዋሬዝ በደረሰበት የቀኝ ጉልበት ጉዳት ለሚቀጥሉት አራት ወራት መሰለፍ እንደማይችል ተገልጧል። የፊታችን እሁድ ባርሴሎና ከግራናዳ ጋር በሚያደርገው የሴሪኣው ግጥሚያ እና የሻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ የሱዋሬዝ አለመኖር ቡድኑን ይጎዳዋል ተብሏል። ሱዋሬዝ በላሊጋው ባስቆጠራቸው ግቦች እስካሁን ሦስተኛ ኮከብ ግብ አግቢ ነው። በተጨዋቾች የዝውውር መስኮቱ ከ ቀናት በኋላ ከመዘጋቱ በፊት ባርሴሎና ሉዊስ ሱዋሬዝን የሚተካ ተጨዋች ካላስፈረመ ምናልባት ፈረንሳዊው አጥቂ አንቷን ግሪዝማን ተክቶት ሊጫወት ይችላል። ማንቸስተር ዩናይትድ የስፖርቲንግ ሲፒ አማካይ ፖርቹጋላዊው ብሩኖ ፌርናንዴስን ለማስመጣት ሚሊዮን ፓውንድ መመደቡ ተገልጧል። የቤኔፊካው አማካይ ጌድሶን ፈርናንዴስ ደግሞ የህክምና ምርመራ አድርጎ ቶትንሀም ሆትስፐርን እስከ ነገ ድረስ ሊቀላቀል ይችላል ሲል ስካይ ስፖርት ዘግቧል። ለዲስ ስፖርት እንደዘገበው ደግሞ አርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ የዋትፎርዱ ተከላካይ ክርስቲያን ካባሴሌ ላይ ዐይናቸውን ከጣሉ አራት የፕሬሚየር ሊጉ ቡድኖች ሁለቱ ናቸው። ዌስትሀም ዩናይትድ እና ኒውካስልም ተከላካዩን ወደ ቡድናቸው ማስመጣት ይፈልጋሉ። የቶትንሀሙ አማካይ ክርስቲኢን ኤሪክሰን ደግሞ ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ጋር የአራት ዓመት ተኩል ውል ለመፈረም መስማማቱን የጣሊያን መገናኛ አውታሮች ዘግበዋል። ዴንማርካዊው አማካይን ለመልቀቅ ቶትንሀሞች ሚሊዮን ፓውንድ መጠየቃቸው ተዘግቧል። የጀርመን ብሔራዊ ቡድን እና የቦሩስያ ዶርትሙንድ አማካይ የ ዓመቱ ማሪዮ ጎይትሰ በቡድኑ ውሉ ባለመራዘሙ ወደፊት ለየትኛው ቡድን ተሰልፎ እንደሚጫወት ጥያቄ አጭሯል። የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት ምናልባት በአፍላ ወጣትነቱ ወቅት አሰልጣኙ የነበሩት ጀርመናዊው ዬርገን ክሎፕ ወደ ሊቨርፑል ሊያመጡት ይችሉ ይኾናል ተብሏል። ማሪዮ በቡንደስሊጋው ሔርታ ቤርሊንም ሊሄድ ይችላል እየተባለ ነው። እንደ ማሪዮ ሁሉ ሔርታ ቤርሊን ዡሊያን ድራክስለር፤ ኤሚር ቻን እና ሞሐመድ ዳውድ ላይ ዐይኑን ጥሏል። ማርዮ ጎይትሰ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ የማሸነፊያዋን ግብ በማስቆጠሩ ምንጊዜም ይታወሳል። አትሌቲክስ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር የቀድሞ ኃላፊ ላሚን ዲያክ የሩስያ ስፖርተኞች የአደንዛዥ ዕጽ ቅሌትን ለመሸሸግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ተቀብለዋል በሚል ዛሬ ፓሪስ ፈረንሳይ ውስጥ ክስ ተከፈተባቸው። የ ዓመቱ ሴኔጋላዊው ምንም ጥፋት የለብኝም ብለዋል። ላለፉት ሦስት ዓመታት በቤት ውስጥ እስረኛ ኾነው ምርመራ ሲደረግባቸው የቆየው ላሚን ዲያክ ጥፋተኛ ኾነው ከተገኙ የ ዓመት እስር ይጠብቃቸዋል። የፍርድ ሒደቱ ከዐሥር ቀናት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሏል። በሪዮ ኦሎምፒክ ለሀገሯ ብቸኛውን ሜዳሊያ ያስገኘችው የ ዓመቷ ወጣት ኢራናዊት አትሌት ኪሚያ ዓሊዛዴኅ ደረሰብኝ ባለችው ጾታዊ በደል እና እንክብካቤ ማጣት የተነሳ ኢራንን እስከወዲያናው ተሰናብታ ኔዘርላንድ መግባቷን ዐስታውቃለች። ኢራን ውስጥ ተንሰራፍቷል ያለችው ግብዝነት፣ ውሸት፣ ፍትኅ ዕጦት እና ቅጥ አልባ አጉል ሙገሳ ሀገሯን ጥላ እንድትሰደድ እንዳስገደዳት ገልጣለች። ልበሺ ያሉኝን ስለብስ አድርጊ ያሉኝን ሳደርግ ቆይቻለሁ ያለችው ኢራናዊት በይ ያሉኝን ሳስተጋባ ነበር በማለት እያንዳንዱን ዐረፍተ ነገር ሳይቀር ባለሥልጣናቱ ካሉዋት ውጪ መናገር አትችል እንደነበረም አክላለች። እንደ እቃ ነው የምንታየው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢራናውያን በተመሳሳይ ጭቆና ውስጥ ናቸውም ብላለች። ኪሚያ በሪዮ ኦሎምፒክ የቴክዋንዶ ፍልሚያ ለሀገሯ የነሐስ ሜዳሊያ በማስገኘት ታሪክ አስመዝግባለች። ወደፊት ለኢራን ፈጽሞ እንደማትሰለፍ የተናገረችው ኢራናዊት አትሌት በቀጣዩ የቶክዮ ኦሎምፒክ የመወዳደር ዕቅድ አላት። በምን መልኩ እንደምትሰለፍ ግን አልተገለጠም። የጫካ ሰደድ እሳት ከፍተኛ ጥፋት ባደረሰባት አውስትራሊያ እጅግ የሚጠበቀው የአውስትራሊያ የሜዳ ቴኒስ ፍጻሜ ነገ ይጀምራል። በእሳት ቃጠሎው የተነሳ ዐየሩ በመበከሉ ውድድሮች በዝግ አዳራሾች ውስጥ ይከናወናሉ ተብሏል። የፎርሙላ አንድ ባለድሉ ሌዊስ ሐሚልተን በዚህ የጫካ ሰደድ እሳት ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚውል ግማሽ ሚዮን ዶላር ርዳታ ለማበርከት ቃል መግባቱ ተዘግቧል። ማንተጋፍቶት ስለሺ ማንተጋፍቶት ስለሺ ሥዩም
የአርብ ሐምሌ ቀን ዓ ም ሙሉ ስርጭት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የነሐሴ ቀን ዓ ም ሙሉ ስርጭት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሰኞ ነሐሴ ቀን ዓ ም ሙሉ ስርጭት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሐረሪዎች የፍርድ ቤት ድል
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ሰሚ ችሎት ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሠረት ከክልሉ ውጭ ያሉ የብሔረሰቡ ተወላጆች የሐረሪ ጉባዔ አባላትን መምረጥ ይችላሉ። ከሐረሪ ክልል ውጭ የሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጆች የምርጫ ተሳትፎን በሚመለከት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረበውን ይግባኝ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውድቅ አደረገው፡፡ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ሰሚ ችሎት ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሠረት ከክልሉ ውጭ ያሉ የብሔረሰቡ ተወላጆች የሐረሪ ጉባዔ አባላትን መምረጥ ይችላሉ።ድሬደዋ የሚኖሩ የሐረሪ ማህበረሰብ አባላት ተጠሪ አቶ ዘይዳን በክሪ የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ ለሐረሪ ብሔረሰብ አባላት አስደሳች ብለዉታል፡፡ መሳይ ተክሉ
የእነ አቶ ጃዋር ክስ የምስክሮች ቃል ሂደት እና የመዝገብ እግድ
ዛሬ በአዲስ አበባ ያስቻለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከዛሬ ሚያዚያ ቀን ዓ ም ጀምሮ ሊሰማ የነበረው የአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃል፤ ከሳሽ ይግባኝ በመጠየቁ መዝገቡ መታገዱን አሳውቋል፡፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ ያስቻለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከዛሬ ሚያዚያ ቀን ዓ ም ጀምሮ ሊሰማ የነበረው የአቃቤ ህግ ምስክሮች ቃል፤ ከሳሽ ይግባኝ በመጠየቁ መዝገቡ መታገዱን አሳውቋል፡፡፡ የአቃቤ ህግ የምስክሮች ቃል እንዲሰማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዛሬ ጀምሮ ያሉትን ተከታታይ ሶስት ቀናት ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም አቃቤ ህግ ምስክሮቼ ለደህንነታቸው ሲባል ከመጋረጃ ጀርባ እንዲደመጡ ያለው አቤቱታ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤት ብሏል፡፡ ይህንኑን በዛሬ ችሎት ይፋ ያደረገው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነገው እለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሂደቱ ላይ ተከሳሾች በፕላዝማ ቀጥታ ከማረሚያ ቤት ገብተው የቃል ክርክር እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መተላለፉን አሳውቋል፡፡ በሌላ በኩል አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ችሎት የኮቪድ ክትባት እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲያስተላልፍላቸው ጠይቀዋል፡፡ ስዩም ጌቱ
የሐረሪ ጉባኤ ከምርጫ ቦርድ ጋር የገጠመዉን የፍርድ ቤት ሙግት አሸነፈ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የተጠረጠሩ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበዋል ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ገዳማት ይዞታ በእስራኤል
ከሰሃራ በታች ከሚገኙት አፍሪቃ ሃገራት በእስራኤል ገዳም እና ሌላም ይዞታ ያላት ብቸኛ ጥቁር አፍሪቃዊት አገር ኢትዮጵያ መሆንዋ ይታወቃል። የዴር ሱልጣን ገዳም ጥሪ በሚል ርዕስ፤ ባለፈዉ ሳምንት ባቀረብነዉ መሰናዶአችን ፤በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እና በግብፅ ኮፕት ቤተክርስትያን መካከል በይዞታ ይገባናል ጥያቄ ምክንያት ገዳሙ መጠገን ባለመቻሉ በመፈራስ ላይ መሆኑን፤ ስለጉዳዩ ጥናታዊ ፊልም የሰሩ ጀርመናዊ የፊልም ስራ አዋቂ እና አካባቢዉ ላይ የሚገኙትን የሃይማኖት አባቶችን አነጋግረን ዘገባ አስደምጠናል።ይህ ለዘመናት የቆየ ችግር መፍትሄዉ ምን ይሆን በእስራኤል የኢትዮጵያ ሌሎች ይዞታዎችስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ከሰሃራ በታች ከሚገኙት አፍሪቃ ሃራት በእስራኤል ገዳም እና ሌላም ይዞታ ያላት ብቸኛ ጥቁር አፍሪቃዊት አገር ኢትዮጵያ መሆንዋ ይታወቃል። በስድስት ሀገራት አብያተ ክርስትያ የተያዘዉ የጎልጎታዉ ዴር ሱልጣን ገዳም ዉዝግብ ከጀመረ ከ ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን ባለፈዉ ሳምንት በቅድስት ሀገር እየሩሳሌም የኢትዮጳያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ገዳማት ሊቃነ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ መናገራቸዉ ይታወሳል። መፍትሄዉ ምን ይሆን በእስራኤል የኢትዮጵያ ገዳማትና ታሪካዊ ቦታዎችን ለማስጠበቅ የተቋቋመዉ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ ተስፋዪ፤ ድርጅታቸዉ የኢትዮጳያን ይዞታዎች ለማስጠበቅ በርካታ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል። በተለይ የዴር ሱልጣንን ይዞታ በተመለከተ በፍርድ ቤት ሳይሆን በሚኒስትሮች ደረጃ የተቋቋመ ኮሚቴ ጉዳዩን እየተከታተለዉ መሆኑን ገልጸዋል። በርግጥ ይህን ችግር በተመለከተ መፍትሄ ለማፈላለግ በእስራኤል የኮፕት ቤተክርስትያንን እና በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤንባሲን ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም። በይፋ እንደሚታየዉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እና በግብፅ ኮፕት ቤተ ክርስትያ መካከል ጠንካራ የሆነ ጥሩ መግባባት ያላቸዉ መሆኑ ነዉ። ለዚህ በምሳሌ ተጠቃሹ የግብፅ ኮፕት ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ከዚህ ዓለም ሲለዪ ፍትሃቱን የመሩት የቀድሞዉ የኢትጵያዉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትርያርቅ አቡነ ጳዉሉስ ነበሩ። እየሩሳሌም የሚታየዉ የሁለቱ አብያተ ክርስትያን ግንኙነት ግን ከዚህ ገጽታ እጅግ የራቀ ሆኖ ነዉ ፤ እና ይህን እንዴት ይጣጣማል ለሚለዉ፤ በቅድስት ሀገር እየሩሳሌም የኢትዮጳያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ገዳማት ተጠሪ ሊቃነ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጉዳዩ መልስ የሌለዉ ነዉ ብለዉናል። በሃይማኖት በሀገር ፍቅር ጸንተዉ በእየሩሳሌም ዴር ሱልጣን ገዳምን ይዞታ ለማስጠበቅ እና ለልጅ ልጅ ለማቆየት ትግል ላይ ያሉት መነኮሳት ህዝብ ሊደግፈን የሀገር ቅርስ በመሆኑም መንግስት መፍትሄ ሊያገኝልን ይገባል ሲሉ ጥሪአቸዉን ያሰማሉ። በእየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማትን ይዞታ በተመለከተ በሁለት ተከታታይ ክፍል ቃለ ምልልስ በመስጠት የተባበሩንን ሁሉ በዝግጅት ክፍላችን ስም እናመሰግናለን። ሙሉዉን እንብር ያድምጡ አዜብ ታደሰ
የኅዳር ቀን፣ ዓ ም መጽሔተ ዜና ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ቁርቁስ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ደሜን ለኢትዮጵያዬ የደም ማሰባሰብ ዘመቻ በሐዋሳ
በኢትዮጲያ በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል እየተካሄደ የሚገኘው ግጭት ወትሮም ውስንነት ይታይበታል በሚባለው የደም አቅርቦት መጠን ላይ የራሱን ተፅእኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ይነገራል ። የአቅቦት እጥረቱን ለመቅረፍ በሀዋሳ ከተማ ደሜ ለኢትዮጲያዬ በሚል በከተማይቱ ጎዳናዎች ላይ የደም ማሰባሰብ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል ። በኢትዮጲያ በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል እየተካሄደ የሚገኘው ግጭት ወትሮም ውስንነት ይታይበታል በሚባለው የደም አቅርቦት መጠን ላይ የራሱን ተፅእኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ይነገራል ። የአቅቦት እጥረቱን ለመቅረፍ በሀዋሳ ከተማ ደሜ ለኢትዮጲያዬ በሚል በከተማይቱ ጎዳናዎች ላይ የደም ማሰባሰብ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል ። በዘመቻው ላይ የተገኙት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የደም ልገሳ ዘመቻው የከተማይቱ ነዋሪዎች ለአገራቸው የሚያደርጉት አንዱ የድጋፍ አካል ነው ብለዋል ። ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
በሐዋሳ ከተማ የተካሄደው የደም ማሰባሰብ ዘመቻ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በስልጤኛ ቋንቋ የወጣዉ የታሪክና የግጥም መድብል
የ ዓመቱ ሸምሱ ሱልጣን በሳዉዲ ዓረብያ ሲኖር ከአራት ዓመት በላይ ሆነዉ። በልጅነቱ የሃይማኖት ትምህርት ቀስሟል። ጅማ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በፋርማሲ ተመርቋል።ሃሳቡን በድምፅም ሆነ በጽሁፍ የመግለጽ አቅሙ ከፍተኛ ነው። ለመድረክ የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ መድረክ የመቆጣጠር ችሎታው ከፍተኛ እንደሆነ ብዙዎች ይናገሩለታል። አዜብ ታደሰ
ስለምርጫው በጀርመን የኢትዮጵያውያን አስተያየት
በአገር ውስጥ እና በውጭ ኃይላት ግጭትና ፖለቲካዊ ቀውስ በገጠማት ኢትዮጵያ ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለ ሁከትና የጸጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው በጀርመን ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ገለጹ። በአገር ውስጥ እና በውጭ ኃይላት ግጭትና ፖለቲካዊ ቀውስ በገጠማት ኢትዮጵያ ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለ ሁከትና የጸጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው በጀርመን ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ገለጹ። የምርጫው አጠቃላይ ሂደትና የመወዳደሪያው ሜዳ ለገዢው መንግሥትም ሆነ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች እኩል እንዳልነበረ ለዶይቼ ቨለ የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዎቹ ያም ቢሆን ሕዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ የሕዝብ ውክልና ያለው መንግስትን ለመምረጥ ያሳየው ትዕግስትና ጨዋነት ምርጫውን ለማደናቀፍ ጥረት ሲያደርጉ ለቆዩ አካላት ትምህርት የሰጠና የሚደነቅ ነው ብለዋል። በሌላ በኩል ዓለማቀፍ መስፈርትን ያሟላ ቅቡልነት ያለው ምርጫ ለማካሄድ በቅድሚያ የሕዝቦችን ደህንነት የመኖር ህጋዊ ዋስትናንና ሰላምን ማረጋገጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለውን አሰራር ማስፈን በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ በሰበብ አስባቡ እስርና ማዋከብን ማቆም እንዲሁም የዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል። በጀርመን እና አውሮጳ የሚገኙ አንዳንድ የተፎካካሪ ፓርቲ ድጋፍ ሰጪ አመራሮችም በትላንቱ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት የታዩት የተፎካካሪ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎችን ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እንዳይገቡ መከልከል የምርጫ ቁሳቁሶች እጥረትና የሎጂስቲክስ ችግሮች የፊታችን ጳጉሜ ዓ ም በሀረሪ በሶማሌና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚካሄዱ ቀጣይ ምርጫዎች እንዳይደገሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል መንግሥትም ሆነ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫውን ውጤት በሰላም እንዲቀበሉም ጥሪ አቅርበዋል። እንዳልካቸው ፈቃደ
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት በትግራይ የተፈጸሙ ግድያዎችን የሚያሳዩ ናቸው የተባሉ ቪዲዮዎች ሐዘን እና ቁጭት ካዘሉ አስተያየቶች ጋር በማኅበራዊ ድረገፆች እየተዘዋወሩ ነው። በሆሮ ጉዱሩ በታጣቂዎች የተፈጸመው ግድያም ሌላ ቁጣ ጭሯል። የአቶ ልደቱ አያሌው ከፖለቲካ ገለል ለማለት ያሳለፉት ውሳኔ እና ተክለ ስብዕናቸው ለአድናቂዎቻቸውም ሆነ ተቺዎቻቸው መነጋገሪያ ሆነዋል። አውዲዮውን ያዳምጡ። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን በሳምንቱ መገባደጃ ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት ለበርካታ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ተጠቃሚዎች ሐዘን፣ ቁጭት እና ቁጣን ፈጥሯል። የአካባቢው ነዋሪዎች ዶይቼ ቬለን ጨምሮ ለተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች እንደተናገሩት ጥቃቱ ያነጣጠረው በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ብሔር አባላት ላይ ነው። የአይን እማኞች እንደሚሉት በአበደንጎሮ ወረዳ ደቢስ በተባለ ቦታ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ባመሩበት ታጣቂዎች ከገደሏቸው ሰዎች መካከል ሕፃናት እና ሽማግሌዎች ጭምር ይገኙበታል። በማኅበራዊ ድረ ገፆች በጨርቅ ተጠቅልለው ለቀብር የተዘጋጁ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች አስከሬኖች ናቸው የተባሉ ፎቶግራፎች ተሰራጭተዋል። ገበያው መንግሥት የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደቡብ ሱዳናውያን እና ሶሪያውያን ተከብረው በሚኖሩባት ኢትዮጵያ አማራ እየታደነ ይታረዳል፤ በሞቱ የሚያዝንለት እንኳ የለም፤ የአማራ ሞት ለዜና እንኳ አይበቃም ሲሉ ጽፈዋል። ጥላሁን መልኬ የተባሉ የትዊተር ተጠቃሚ ትግራይ፣ ወለጋ እና መተከልን ጠቅሰው እስከመቼ ከንፈራችንን መጠን ዝም እንዲህ እየተጫረሰን እያለቅን እንዲህ እየሆንን ስቃይ ቆጠራ አንዳችን በሌላችን ሃዘን እየተሳለቅን መፍትሄ አጥተን ዝም የሚል መልዕክት አስፍረዋል። ዮሐንስ ቲ ደጉ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ወለጋ ላይ ሰዎች የጥይት መለማመጃ እየሆኑ ነው። ሞታቸው የአዘቦት ዜና ሆኗል። ዜናው ማንንም አይጎረብጥም። ማንም በጉዳዩ አይሞቀውም፥ አይበርደውም። ሞታቸው የብሔር ካባ ለብሷል። በሞታቸው የሚደነግጥ የለም። ወለጋ ላይ የሚረግፉ ሰዎች ለሞት እጅ መንሻ የተሰጡ ሆነዋል። እነሱን እንደፍጥርጥርህ አድርጋቸው፥ እኛ ጋር አትድረስ ይመስላል። በአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያን የሚለበልባት የዕልቂት እሳት ቤታችን ይደርሳል። ያኔ ማንም ለማንም አይደርስም በማለት ጽፈዋል። በጥቃቱ የብልጽግና ፓርቲ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከፍተኛ ፖለቲከኞች ወቀሳ እና ክስ ቀርቦባቸዋል። ይታያል ዋለልኝ የኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን ግድያዎች አሁንም አላባሩም። የተጠና እና ቅንጅት እንዳለው ለማወቅ አይከብድም። ነዋሪዎች ተደራጅተው ራሳቸውን ነቅተው እየጠበቁ ቆይተው ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ተደርገው ይሄው በግላጭ ተገደሉ ብለዋል። ወቀሳ እና ትችቱ የአማራ ብሔርን ወክለው የብልጽግና ፓርቲ አባል የሆኑ ፖለቲከኞችም አልቀረላቸውም። ሐመሩ ሐ ዋሸራ የሚል የፌስቡክ ስም የሚጠቀሙ አንድ ሰው አማራ ብልፅግና ሌላው ቢቀር ዘር ጭፍጨፋውን ለማውገዝ መሽኮርመም ነበረበት ሲሉ ጠይቀዋል። ከወደ ትግራይ ወጣ የተባለው ቪዲዮ በትግራይ ተፈጽመዋል የተባሉ ግድያዎችን ያሳያሉ የተባሉ ቪዲዮዎች በማኅበራዊ ድረ ገፆች እየተዘዋወሩ ነው። ከተንቀሳቃሽ ምስሎቹ መካከል በአንዱ አስከሬኖች ወደ ገደል ሲወረወሩ ይታያል። ይኸ ሰከንዶች ገደማ የሚረዝም ቪዲዮ ከአክሱም ከተማ በስተ ምስራቅ ማሕበረ ደጎ አዴት በተባለ ቦታ የተፈጸመ ኩነትን ያሳያል ሲሉ ምስሉን ያሰራጩ የማኅበራዊ ድረ ገፆች ተጠቃሚዎች ጽፈዋል። በምስሉ አንድ ሰው ግደለው የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ ይደመጣል። ትዕዛዙን ተከትሉ በምስሉ የሚታይ የወታደር መለዮ የለበሰ ግለሰብ ጥይት ይተኩሳል። አስከሬኖችም ወደ ገደል እየተገፉ ሲጣሉ ይታያል። ዶይቼ ቬለ የቪዲዮውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አልቻለም። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች ግን እንደየአሰላለፋቸው ምስሉን መሠረት አድርገው ሐሳባቸውን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። ፍሰሐ ታደሰ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ይኸ የኢትዮጵያ ጦር መለዮ የለበሱ ወታደሮች ወጣቶችን እየገደሉ ወደ ገደል ሲወረውሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በጣም ይረብሻል ብለዋል። ኃይለ ስላሴ አምሐ መተኛት አልቻልኩም። ላለፉት አራት ወራት በትግራይ የጅምላ ግድያ እየተፈጸመ እንደሆነ አውቃለሁ። እንዲህ አይነት ኩነቶችን በቪዲዮ መመልከት ግን የተለየ ነው። የተወሰኑ የኢትዮጵያ ጦር ወታደሮች ጥቂት ቀጫጭን ወጣቶችን ከበቡ፤ ከመኃላቸው መካከለኛ ወታደራዊ አዛዦች ይመስላሉ። ሴት ወታደሮችም አሉበት። የተረጋጉ ናቸው። ይሳሳቃሉ፤ የቀላለዳሉ። ምንም ሥጋት አይሰማቸውም። አንዳንዶቹ ይቀርፃሉ። እነዚህን ልጆች በርካታ ነገር ማድረግ ይችላሉ። ሊያስሯቸው ይችላሉ። ሊመቷቸው ይችላሉ። ነገር ግን ወደ ገደል አፋፍ ወስደው ገደሏቸው። ሬሳቸውን ወደ ገደል ጣሉ ሲሉ ጽፈዋል። ያሬድ ከበደ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ የሞተን ሰው ወደ ገደል መወርወር የጭካኔ ጣርያ ሲሉ ጽፈዋል። ያሬድ አሁንም ከትግራይ ክልል የሚለቀቁ ቪዲዮዎች አላለቁም። ሰው ሆኖ መፈጠር ያስፈራል፤ አብሶ ሴቶች ላይ የተፈፀመው የእንስሳት ተግባር ይዘገንናል በማለት አክለዋል። የትኛውም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወሩ ፎቶና ቪዲዮ ትክክለኛነታቸውን ሳናረጋግጥ መደምደሚያ ላይ ከመድረስ ብንቆጠብ ጥሩ ይመስለኛል። እኔ እንደተረዳሁት ጉዳዩ እውነቱን የማውጣት ሳይሆን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ውድድር በመንግስትም ጭምር ነው የተያዘው። ለምሳሌ የዛሬው ቪዲዮ በጣም አንገት ያሚስደፋ፣ ኢትዮጵያዊ መሆንን ያስረግማል ያሉት ደግሞ በፌስቡክ ሞገስ ዘውዱ ናቸው። ሞገስ ነገር ግን ቪድዮውን በትኩረት የተመለከተ ሰው አንድ ነገር ያስተውላል።የሚያወራው ልጅ በቦታው ሳይኖር ቪዲዮው ላይ ድምፁን እያስገባ የሚተርክ ነው። ይሄ ለጥርጣሬ አንድ በር ይከፍታል። ሲቀጥል እንዲህ ዓይነት ቪዲዮ የቀረፀ ሰው ጉዳዩ ከባድ ወንጀል መሆኑን እያወቀ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያጋራበት ምንም ምክንያት የለውም። ምናልባት ምስሉን የቀረፀው ሌላ ሰው ቢሆን እንኳን፤ በዚያ ሁኔታ ከሰዎቹ ጋር እየተነጋገረ ቪዲዮ የሚቀርፅበት አጋጣሚ አይኖርም በማለት ጥርጣሪያቸውን አስፍረዋል። ሙክታሮቪች ኦስማኖቫ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደግሞ የመከላከያ ስምን እንዲያጠፋ የታሰበ አሰቃቂ ቪዲዮ ብለውታል። ሙክታሮቪች የህወሓትን ታሪካዊ ሸፍጥ የምናቅ፤ ህይወቱን ለማትረፍ የሚያደርገውን የምናቅ፤ ጁንታው በሀገር መከላከያ ዩኒፎርም ትልቅ ድራማ ሰርቶ ለቆልናል። የማናቸውም መልክ እንዳይታይ አድርጎ፣ መልዕክቱ ደጋፊ ለማብዛት የተደረገ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ነው። ሀውዜንም እንዲህ ነው የተደረገው። ይህ የጦርነት ነገር የለበትም። ይህ ዜጎችን ጁንታው ገድሎ የሰራው ነው። የሰውን አዕምሮ እንዲረብሽ አድርገው ያቀናበሩት ነው ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ያለው ነገር የለም። የልደቱ አያሌው መንገድ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ መሥራች እና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ልደቱ አያሌው በልብ ሕመም ሳቢያ ከፖለቲካ ገለል ማለታቸውን ያስታወቁትም በዚሁ በመገባደድ ላይ በሚገኘው ሳምንት ነው። የልብ ሕመም እንዳለባቸው የገለጹት ልደቱ ከሐኪም ጋር ባደረግሁት ምክክር ለሕመሜ አስተማማኝ ሕክምና እስካገኝ ድረስ በአካሌም ሆነ በአዕምሮዬ ላይ ምንም ዓይነት ጫናና ውጥረት የሚፈጥር ሥራ እንዳልሠራና በቂ ረፍት እንዲኖረኝ ከባድ ማስጠንቀቂያና ምክር ተሰጥቶኛል ብለዋል። ሕክምና እንዳያገኙ በመንግሥት መከልከላቸውን የገለጹት ልደቱ በማኅበራዊ ድረ ገፆች በስፋት በተሰራጨ መሰናበቻቸው ተገቢውን የሕክምና ዕርዳታ አግኝቼ ጤናዬ እስኪመለስ ድረስ በሕይወት የመሰንበት ዕድሌን ለመሞከር ስል ከማንኛውም ዓይነት የትግል እንቅስቃሴ ገንዘብ ወይም ምክር ከማዋጣት ባለፈ ራሴን ለጊዜው ለማቀብ የተገደድኩ ስለመሆኑ በከፍተኛ ቁጭትና ሐዘን እገልጻለሁ ሲሉ ውሳኔያቸውን ይፋ አድርገዋል። በዚሁ ጽሁፋቸው አሳሳቢ ያሏቸውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሮች ዘርዘር አድርገው አቅርበዋል። መንግሥት እና የብልጽግና ፓርቲን ሸንቁጠዋል። ውሳኔያቸው እና ተክለ ስብዕናቸው ለአድናቂዎቻቸውም ሆነ ተቺዎቻቸው መነጋገሪያ ሆነዋል። አንዳርጌ ጫኔ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ውጭ ሆኖ ተናግሬ ነበር ለማለት ከሆነ፦ የምትነግረንን ባትነግረን ይሻለኛል። ሰው ማለት ሃገሩን የሚወድና የፓለቲካ ልዩነት ቢኖረውም እንኳ ሃሳቡን ለሃገሩ መፃዒ ዕጣ ሲል ከእልህና ከንዴት ራሱን በመቆጣጠር የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ሲገባ ከበር ውጭ ቁሞ ብየ ነበር ተናግሬ ነበር ለማለት መዘጋጀት ነውር ነው ብለዋል። ወንድማለም ያንተ ትልቁ ችግር ከሰው አይምሮ በላይ መፍጠንህና ትክክለኛ ለኢትዮጵያ ሀሳቢ መሆኑ ነው። አንተን የሚረዳህ ይህ መንጋ ዛሬ አይደለም እንደ ግሪክ ፈላስፋዎች ካለፍክ በኋላ ነው።አዝናለሁ እግዚአብሔር ጤናህን ይስጥህ ያሉት ደግሞ ናትናኤል ሞላ ናቸው። በአማን ቄርሎስ ደግሞ እኛ ኢትዮጵያውያን ዋና ችግራችን በጅምላ የምንፈርድ እና ምክንያታዊ አለመሆናችን እንጂ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ አንተ ከወሳኝ ሚዛናዊ ሰዎች መካከል አንዱ ነህ። ነገር ግን በ ምርጫ በተፈጠረ ሴራ የተወሰነ ህዝብ እምነት ነስቷል። ሆኖም ግን በዋና ዋና ሀገራዊ እና መንግስታዊ ጉዳዮች ዙርያ ብዙ ጠቃሚ ሀሳቦችን እያቀረብክና ተፅእኖ እየፈጠርክ እንደመጣህ ደግሞ የምናምን ሰዎች አለን። አሁን የወሰንከው ውሳኔ እንደ ግል ትክክል ቢሆንም እንደ ሀገር ግን በፖለቲካው ዙርያ ትልቅ ክፍተት እንደሚፈጥር የግል እምነቴ ነው የሚል አስተያየት አስፍረዋል። እሸቴ በቀለ
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት
በትግራይ የተፈጸሙ ግድያዎችን የሚያሳዩ ናቸው የተባሉ ቪዲዮዎች ሐዘን እና ቁጭት ካዘሉ አስተያየቶች ጋር በማኅበራዊ ድረገፆች እየተዘዋወሩ ነው። በሆሮ ጉዱሩ በታጣቂዎች የተፈጸመው ግድያም ሌላ ቁጣ ጭሯል። የአቶ ልደቱ አያሌው ከፖለቲካ ገለል ለማለት ያሳለፉት ውሳኔ እና ተክለ ስብዕናቸው ለአድናቂዎቻቸውም ሆነ ተቺዎቻቸው መነጋገሪያ ሆነዋል። በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን በሳምንቱ መገባደጃ ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት ለበርካታ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ተጠቃሚዎች ሐዘን፣ ቁጭት እና ቁጣን ፈጥሯል። የአካባቢው ነዋሪዎች ዶይቼ ቬለን ጨምሮ ለተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች እንደተናገሩት ጥቃቱ ያነጣጠረው በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ብሔር አባላት ላይ ነው። የአይን እማኞች እንደሚሉት በአበደንጎሮ ወረዳ ደቢስ በተባለ ቦታ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ባመሩበት ታጣቂዎች ከገደሏቸው ሰዎች መካከል ሕፃናት እና ሽማግሌዎች ጭምር ይገኙበታል። በማኅበራዊ ድረ ገፆች በጨርቅ ተጠቅልለው ለቀብር የተዘጋጁ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች አስከሬኖች ናቸው የተባሉ ፎቶግራፎች ተሰራጭተዋል። ገበያው መንግሥት የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደቡብ ሱዳናውያን እና ሶሪያውያን ተከብረው በሚኖሩባት ኢትዮጵያ አማራ እየታደነ ይታረዳል፤ በሞቱ የሚያዝንለት እንኳ የለም፤ የአማራ ሞት ለዜና እንኳ አይበቃም ሲሉ ጽፈዋል። ጥላሁን መልኬ የተባሉ የትዊተር ተጠቃሚ ትግራይ፣ ወለጋ እና መተከልን ጠቅሰው እስከመቼ ከንፈራችንን መጠን ዝም እንዲህ እየተጫረሰን እያለቅን እንዲህ እየሆንን ስቃይ ቆጠራ አንዳችን በሌላችን ሃዘን እየተሳለቅን መፍትሄ አጥተን ዝም የሚል መልዕክት አስፍረዋል። ዮሐንስ ቲ ደጉ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ወለጋ ላይ ሰዎች የጥይት መለማመጃ እየሆኑ ነው። ሞታቸው የአዘቦት ዜና ሆኗል። ዜናው ማንንም አይጎረብጥም። ማንም በጉዳዩ አይሞቀውም፥ አይበርደውም። ሞታቸው የብሔር ካባ ለብሷል። በሞታቸው የሚደነግጥ የለም። ወለጋ ላይ የሚረግፉ ሰዎች ለሞት እጅ መንሻ የተሰጡ ሆነዋል። እነሱን እንደፍጥርጥርህ አድርጋቸው፥ እኛ ጋር አትድረስ ይመስላል። በአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያን የሚለበልባት የዕልቂት እሳት ቤታችን ይደርሳል። ያኔ ማንም ለማንም አይደርስም በማለት ጽፈዋል። በጥቃቱ የብልጽግና ፓርቲ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከፍተኛ ፖለቲከኞች ወቀሳ እና ክስ ቀርቦባቸዋል። ይታያል ዋለልኝ የኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን ግድያዎች አሁንም አላባሩም። የተጠና እና ቅንጅት እንዳለው ለማወቅ አይከብድም። ነዋሪዎች ተደራጅተው ራሳቸውን ነቅተው እየጠበቁ ቆይተው ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ተደርገው ይሄው በግላጭ ተገደሉ ብለዋል። ወቀሳ እና ትችቱ የአማራ ብሔርን ወክለው የብልጽግና ፓርቲ አባል የሆኑ ፖለቲከኞችም አልቀረላቸውም። ሐመሩ ሐ ዋሸራ የሚል የፌስቡክ ስም የሚጠቀሙ አንድ ሰው አማራ ብልፅግና ሌላው ቢቀር ዘር ጭፍጨፋውን ለማውገዝ መሽኮርመም ነበረበት ሲሉ ጠይቀዋል። ከወደ ትግራይ ወጣ የተባለው ቪዲዮ በትግራይ ተፈጽመዋል የተባሉ ግድያዎችን ያሳያሉ የተባሉ ቪዲዮዎች በማኅበራዊ ድረ ገፆች እየተዘዋወሩ ነው። ከተንቀሳቃሽ ምስሎቹ መካከል በአንዱ አስከሬኖች ወደ ገደል ሲወረወሩ ይታያል። ይኸ ሰከንዶች ገደማ የሚረዝም ቪዲዮ ከአክሱም ከተማ በስተ ምስራቅ ማሕበረ ደጎ አዴት በተባለ ቦታ የተፈጸመ ኩነትን ያሳያል ሲሉ ምስሉን ያሰራጩ የማኅበራዊ ድረ ገፆች ተጠቃሚዎች ጽፈዋል። በምስሉ አንድ ሰው ግደለው የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ ይደመጣል። ትዕዛዙን ተከትሉ በምስሉ የሚታይ የወታደር መለዮ የለበሰ ግለሰብ ጥይት ይተኩሳል። አስከሬኖችም ወደ ገደል እየተገፉ ሲጣሉ ይታያል። ዶይቼ ቬለ የቪዲዮውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አልቻለም። የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች ግን እንደየአሰላለፋቸው ምስሉን መሠረት አድርገው ሐሳባቸውን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። ፍሰሐ ታደሰ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ይኸ የኢትዮጵያ ጦር መለዮ የለበሱ ወታደሮች ወጣቶችን እየገደሉ ወደ ገደል ሲወረውሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በጣም ይረብሻል ብለዋል። ኃይለ ስላሴ አምሐ መተኛት አልቻልኩም። ላለፉት አራት ወራት በትግራይ የጅምላ ግድያ እየተፈጸመ እንደሆነ አውቃለሁ። እንዲህ አይነት ኩነቶችን በቪዲዮ መመልከት ግን የተለየ ነው። የተወሰኑ የኢትዮጵያ ጦር ወታደሮች ጥቂት ቀጫጭን ወጣቶችን ከበቡ፤ ከመኃላቸው መካከለኛ ወታደራዊ አዛዦች ይመስላሉ። ሴት ወታደሮችም አሉበት። የተረጋጉ ናቸው። ይሳሳቃሉ፤ የቀላለዳሉ። ምንም ሥጋት አይሰማቸውም። አንዳንዶቹ ይቀርፃሉ። እነዚህን ልጆች በርካታ ነገር ማድረግ ይችላሉ። ሊያስሯቸው ይችላሉ። ሊመቷቸው ይችላሉ። ነገር ግን ወደ ገደል አፋፍ ወስደው ገደሏቸው። ሬሳቸውን ወደ ገደል ጣሉ ሲሉ ጽፈዋል። ያሬድ ከበደ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ የሞተን ሰው ወደ ገደል መወርወር የጭካኔ ጣርያ ሲሉ ጽፈዋል። ያሬድ አሁንም ከትግራይ ክልል የሚለቀቁ ቪዲዮዎች አላለቁም። ሰው ሆኖ መፈጠር ያስፈራል፤ አብሶ ሴቶች ላይ የተፈፀመው የእንስሳት ተግባር ይዘገንናል በማለት አክለዋል። የትኛውም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወሩ ፎቶና ቪዲዮ ትክክለኛነታቸውን ሳናረጋግጥ መደምደሚያ ላይ ከመድረስ ብንቆጠብ ጥሩ ይመስለኛል። እኔ እንደተረዳሁት ጉዳዩ እውነቱን የማውጣት ሳይሆን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ውድድር በመንግስትም ጭምር ነው የተያዘው። ለምሳሌ የዛሬው ቪዲዮ በጣም አንገት ያሚስደፋ፣ ኢትዮጵያዊ መሆንን ያስረግማል ያሉት ደግሞ በፌስቡክ ሞገስ ዘውዱ ናቸው። ሞገስ ነገር ግን ቪድዮውን በትኩረት የተመለከተ ሰው አንድ ነገር ያስተውላል።የሚያወራው ልጅ በቦታው ሳይኖር ቪዲዮው ላይ ድምፁን እያስገባ የሚተርክ ነው። ይሄ ለጥርጣሬ አንድ በር ይከፍታል። ሲቀጥል እንዲህ ዓይነት ቪዲዮ የቀረፀ ሰው ጉዳዩ ከባድ ወንጀል መሆኑን እያወቀ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያጋራበት ምንም ምክንያት የለውም። ምናልባት ምስሉን የቀረፀው ሌላ ሰው ቢሆን እንኳን፤ በዚያ ሁኔታ ከሰዎቹ ጋር እየተነጋገረ ቪዲዮ የሚቀርፅበት አጋጣሚ አይኖርም በማለት ጥርጣሪያቸውን አስፍረዋል። ሙክታሮቪች ኦስማኖቫ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደግሞ የመከላከያ ስምን እንዲያጠፋ የታሰበ አሰቃቂ ቪዲዮ ብለውታል። ሙክታሮቪች የህወሓትን ታሪካዊ ሸፍጥ የምናቅ፤ ህይወቱን ለማትረፍ የሚያደርገውን የምናቅ፤ ጁንታው በሀገር መከላከያ ዩኒፎርም ትልቅ ድራማ ሰርቶ ለቆልናል። የማናቸውም መልክ እንዳይታይ አድርጎ፣ መልዕክቱ ደጋፊ ለማብዛት የተደረገ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ነው። ሀውዜንም እንዲህ ነው የተደረገው። ይህ የጦርነት ነገር የለበትም። ይህ ዜጎችን ጁንታው ገድሎ የሰራው ነው። የሰውን አዕምሮ እንዲረብሽ አድርገው ያቀናበሩት ነው ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ያለው ነገር የለም። የልደቱ አያሌው መንገድ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ መሥራች እና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ልደቱ አያሌው በልብ ሕመም ሳቢያ ከፖለቲካ ገለል ማለታቸውን ያስታወቁትም በዚሁ በመገባደድ ላይ በሚገኘው ሳምንት ነው። የልብ ሕመም እንዳለባቸው የገለጹት ልደቱ ከሐኪም ጋር ባደረግሁት ምክክር ለሕመሜ አስተማማኝ ሕክምና እስካገኝ ድረስ በአካሌም ሆነ በአዕምሮዬ ላይ ምንም ዓይነት ጫናና ውጥረት የሚፈጥር ሥራ እንዳልሠራና በቂ ረፍት እንዲኖረኝ ከባድ ማስጠንቀቂያና ምክር ተሰጥቶኛል ብለዋል። ሕክምና እንዳያገኙ በመንግሥት መከልከላቸውን የገለጹት ልደቱ በማኅበራዊ ድረ ገፆች በስፋት በተሰራጨ መሰናበቻቸው ተገቢውን የሕክምና ዕርዳታ አግኝቼ ጤናዬ እስኪመለስ ድረስ በሕይወት የመሰንበት ዕድሌን ለመሞከር ስል ከማንኛውም ዓይነት የትግል እንቅስቃሴ ገንዘብ ወይም ምክር ከማዋጣት ባለፈ ራሴን ለጊዜው ለማቀብ የተገደድኩ ስለመሆኑ በከፍተኛ ቁጭትና ሐዘን እገልጻለሁ ሲሉ ውሳኔያቸውን ይፋ አድርገዋል። በዚሁ ጽሁፋቸው አሳሳቢ ያሏቸውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሮች ዘርዘር አድርገው አቅርበዋል። መንግሥት እና የብልጽግና ፓርቲን ሸንቁጠዋል። ውሳኔያቸው እና ተክለ ስብዕናቸው ለአድናቂዎቻቸውም ሆነ ተቺዎቻቸው መነጋገሪያ ሆነዋል። አንዳርጌ ጫኔ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ውጭ ሆኖ ተናግሬ ነበር ለማለት ከሆነ፦ የምትነግረንን ባትነግረን ይሻለኛል። ሰው ማለት ሃገሩን የሚወድና የፓለቲካ ልዩነት ቢኖረውም እንኳ ሃሳቡን ለሃገሩ መፃዒ ዕጣ ሲል ከእልህና ከንዴት ራሱን በመቆጣጠር የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ሲገባ ከበር ውጭ ቁሞ ብየ ነበር ተናግሬ ነበር ለማለት መዘጋጀት ነውር ነው ብለዋል። ወንድማለም ያንተ ትልቁ ችግር ከሰው አይምሮ በላይ መፍጠንህና ትክክለኛ ለኢትዮጵያ ሀሳቢ መሆኑ ነው። አንተን የሚረዳህ ይህ መንጋ ዛሬ አይደለም እንደ ግሪክ ፈላስፋዎች ካለፍክ በኋላ ነው።አዝናለሁ እግዚአብሔር ጤናህን ይስጥህ ያሉት ደግሞ ናትናኤል ሞላ ናቸው። በአማን ቄርሎስ ደግሞ እኛ ኢትዮጵያውያን ዋና ችግራችን በጅምላ የምንፈርድ እና ምክንያታዊ አለመሆናችን እንጂ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ አንተ ከወሳኝ ሚዛናዊ ሰዎች መካከል አንዱ ነህ። ነገር ግን በ ምርጫ በተፈጠረ ሴራ የተወሰነ ህዝብ እምነት ነስቷል። ሆኖም ግን በዋና ዋና ሀገራዊ እና መንግስታዊ ጉዳዮች ዙርያ ብዙ ጠቃሚ ሀሳቦችን እያቀረብክና ተፅእኖ እየፈጠርክ እንደመጣህ ደግሞ የምናምን ሰዎች አለን። አሁን የወሰንከው ውሳኔ እንደ ግል ትክክል ቢሆንም እንደ ሀገር ግን በፖለቲካው ዙርያ ትልቅ ክፍተት እንደሚፈጥር የግል እምነቴ ነው የሚል አስተያየት አስፍረዋል። እሸቴ በቀለ
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የቸገራቸው ተፈናቃዮች በሸዋሮቢት እና በሰንበቴ
ከሶስት ወራት ገደማ በፊት በተቀሰቀሰ ብርቱ ግጭት ተፈናቅለው በሸዋሮቢት የወጣቶች ማዕከል እና በሰንበቴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በርካታ የተጠለሉ በርካታ ሰዎች ለለት ጉርስ የሚሆን በቂ ዕርዳታ እስከማጣት መድረሳቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የፍትኃዊነት ችግር መኖሩን ያረጋገጡ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ዕርዳታ እየተሰጠ ነው ብለዋል ግድግዳዎቻቸው ተፋፍቀው በቆሸሹ የሰንበቴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች ወደ አንድ ጎን ተሰብስበው ለመኝታ የሚያገለግሉ ፕላስቲኮች ተነጥፈዋል። ፍራሾችም በመማሪያ ክፍሎቹ ውስጥ ይታያሉ። በየጥጋጥጉ ጀሪካኖች፣ ብረት ምጣድ እና ማብሰያዎች፣ የተለያዩ አልባሳት፣ በማዳበሪያ ቋጠሮዎች ተደርድረዋል። ቀኑ እሁድ ሰኔ ቀን ዓ ም የኢትዮጵያ ስድስተኛ አጠቃላይ ምርጫ ዋዜማ ነው። ከ አመታት በፊት የተቋቋመው ትምህርት ቤት በሩን በተማሪዎቹ ላይ ዘግቶ ላለፉት ሶስት ገደማ ወራት የተፈናቃዮች መጠለያ ሆኗል። የታጠቡ አልባሳት በቅጥር ግቢ ግቢው በተዘረጋ ሽቦ ላይ ተሰቅለው ይታያሉ። ትካዜ የተጫናቸው ጎልማሶች በየትምህርት ክፍሎቹ ዳጃፎች ቁጭ ብለዋል። እናቶች መሬት ይጭራሉ። አቀማመጣቸው፣ ፊታቸው እና አጠቃላይ ሁኔታቸው ባለፉት ሶስት ወራት ኑሮ እንደጨከነባቸው ይመሰክራሉ። ከሶስት ወራት ገደማ በፊት በአካባቢው በተቀሰቀሰ ግጭት ከአጣዬ ከተማ ተፈናቅሎ በሰንበቴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጠለለው ጀማል ዲሲር ኑሮ ከከፋባቸው አንዱ ነው። ውኃ እዚህ ግቢ አንዲት ቧንቧ አለች። ያቺ በሳምንት አንዳንዴ ትመጣለች። አለ አይባልም። አልባሳት ምንም ነገር የለንም። መኝታም ያው ካርቶን ነው። ካርቶን የሌለውም ሽርጡንም ምኑንም አንጥፎ ነው የሚተኛው። ሕክምና የሚባል ነገር ምንም ነገር የለም ይላል ጀማል ያሉበትን ሁኔታ ለዶይቼ ቬለ ሲያስረዳ። እንደ ጀማል ከሆነ ብርቱው ፈተና ግን በቀዝቃዛው የስሜንቶ ወለል ላይ መተኛት አይደለም። የሚበላ ምግብ እጦት እንጂ። ዛሬ ዛሬ በአሁኑ ሰዓት የምንበላው ያስፈልገናል። መኝታው ምኑ ምኑ ችግር የለውም። ዋናው ለሰው ልጅ አስፈላጊው ምግብ ነው። የመኝታውን ችግር መላመድ ይቻላል። እዚህም አፈሩ ላይ መተኛት እችላለሁ። የምግብ እና የውኃ እጦትን ግን መላመድ አይቻልም ይላል ጀማል። በሩን በተማሪዎቹ ላይ ዘግቶ የተፈናቃዮች መጠለያ የሆነው የሰንበቴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ ገደማ አባወራዎች በዚሁ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠልለው የነበረ ቢሆንም ቀስ በቀስ ቁጥራቸው መቀነሱን ዕርዳታ በማቅረብ ከተሰማሩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለመረዳት ተችሏል። እንደ ወጣቶቹ ከሆነ በአሁኑ ወቅት በቅጥር ግቢው አባወራዎች ወይም ከ ሺሕ በላይ ሰዎች ይገኛሉ። ጀማል እና ሌሎች ተፈናቃዮች እንደሚሉት በረመዳን የፆም ወቅት የሰንበቴ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች እገዛ ሲያደርጉላቸው ቆይተዋል። ይሁንና የፆሙ ወቅት ሲያበቃ እርዳታው እንዳልቀጠለ ከተፈናቃዮቹ አንዱ የሆነው መሐመድ አማን ያስረዳል። ረመዳን ከወጣ ወር ሆኗል። በዚህ ወር ውስጥ ማንም ሰው የሚበላው ነገር የለም። ግማሹ እየለመነ እየበላ ነው። ያን አጥቶ ደግሞ በባዶ ሆዱ የሚተኛ አለ የሚለው መሐመድ በቂ እርዳታ አለማግኘታቸውን ገልጿል። በአጣዬ በኩል እኛን የሚረዳ አንድ ኃላፊ አለ። እሱ ሔዶ አስተዳዳሪውን ጠየቀልን። እዚህ ይግቡ፣ እንሰጣቸዋለን፣ እርዳታ መጥተው ይውሰዱ ምናምን ተባለ። ስንሔድ እርዳታ ዛሬ ይገባል ነገ ተሰርቋል። ከዚህ የምንሔደው እንዲያውም እንደ አጣዬ ዜጋ አልሆንም። እሱ ግቡ ያለበት ቦታ ሕዝቡ ለመግባት ለነፍሳችን እንፈራለን ብሎ እምቢ አለ። በዚህ ምክንያት አልሰጣችሁም የለም ብሎ ዘጋበት። ከዛ መጥቶ እኛን ወንድሞቼ ከዚህ ወረዳም ከዚያ ወረዳም አጥቼላችኋለሁ። ምንም ነገር የለም። ተስፋችሁን ቆርጣችሁ ከለመናችሁ ለምናችሁ ኑሩ እኔ ምንም የማደርግላችሁ ነገር የለም ብሎ አቆመው ይላል መሐመድ። ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ ገደማ አባወራዎች በዚሁ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠልለው የነበረ ቢሆንም ቀስ በቀስ ቁጥራቸው መቀነሱን ዕርዳታ በማቅረብ ከተሰማሩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለመረዳት ተችሏል። መሐመድ አማን እና ጀማል ዲሲርን ጨምሮ በሰንበቴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተጠለሉ ተፈናቃዮች ዘንድ ሊሰጠን ይገባ የነበረ ዕርዳታ ተዘርፏል የሚል ተደጋጋሚ ክስ ይደመጣል። ዶይቼ ቬለ በእርግጥ ለተፈናቃዮች የተመደበ እርዳታ ለሌላ መሰጠቱን አሊያም መዘረፉን አላረጋገጠም። የዕርዳታ እጦት የሚፈትናቸው ግን በሰንበቴ የሚገኙትን ብቻ አይደለም። በሸዋሮቢት ከተማ በሚገኝ የወጣቶች ማዕከል የተጠለሉ ተፈናቃዮች ተመሳሳይ ፈተና ውስጥ ናቸው። እንደ ሰንበቴ ሁሉ ዕድሜያቸው የገፋ፣ ህመም የተጫናቸው ለወጣቶች መዝናኛ ተብሎ በተዘጋጀ ሰፊ አዳራሽ ውስጥ ተጠልለዋል። ሕፃናት ውር ውር ይላሉ። በአዳራሹ የቆሸሹ ፍራሾች በብዛት ይታያሉ። ሞፈር አገላብጠው ያርሱ የነበሩ ገበሬዎች ቀለስ ባደረጓቸው መጠለያዎች ዕቃ ያጣጥባሉ። ጀውሃ ከተባለችው አነስተኛ ከተማ የተፈናቀሉት የ አመቷ ወይዘሮ ዓለም አድማሱ አንዷ ናቸው። ወይዘሮ ዓለም ከእኛ የተሻሉ ሰዎች ከሕዝቡም መታፈግ ሁኔታ፣ ከበሽታውም ሁኔታ ትንሽ እኛ እንኳ እንውጣ ብለው ወደ ውጪ ተከራይተው የወጡ አሉ። ከጀውሃ የተፈናቀለው ወደ ሰው ነው። ለተጠየቀው ወደ ኋላ የማይል አርሶ አደር፣ በዚህ ቦታ ና ቶሎ ቢሉት ፊቱን የማያጠቁር ሕዝብ ነበር። የጀውሃ ሕዝብ ዕርዳታም ከመንግሥት የማይፈልግ ነበረ። የሰላም ሁኔታ ግን ንብረቱንም እሱንም አሳጥቶ ራቁቱን አስወጥቶታል ሲሉ ግጭቱ የአካባቢውን ሕዝብ አኗኗር ማናጋቱን ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። አብዱ ዳውድ አዲስ ዓለም ነጌሶ ከተባለ ቦታ በግጭቱ ሳቢያ ተፈናቅሎ ሸዋሮቢት ከተማ በሚገኘው መጠለያ ያለፉትን ሶስት ወራት የተጠለለ የ አመት ወጣት ነው። እስከ ዛሬ የሸዋሮቢት ከተማ መስተዳድር ዕርዳታ እያሰባሰበ ነው እየመገበን ያለው። አንድ ጊዜ ብቻ መንግሥት ዕርዳታ ሰጥቶናል። የሰጠን ዱቄት ብቻ ስለነበረ በሶ አይደለም በጥብጠን አንጠጣውም፣ በሶም ልጠጣ ብትል ስኳር ያስፈልገዋል። ተጓዳኝ ምግቦች የሉም። ያንን ሸጠን ሩዝ እየገዛን፣ ዘይት እና አሸቦ ጨው እያቻቻልን ተጠቅመንበታል። የከተማ መስተዳድሩ እስከ ዛሬ እየለመነ አብልቶናል። አሁን ግን ወደ መሰላቸቱ ላይ ደርሷል። መንግሥትም ዞር ብሎ ሊያየን አልቻለም ሲል ችግር እንደገጠማቸው አብዱ ያብራራል። ራሳቸው ተፈናቃይ ሆነው ተፈናቃዮችን የመመገብ ኃላፊነት የተጣለባቸው ወይዘሮ ዓለም ይኸንን ሶስት ሺሕ ምናምን ሕዝብ ስንመግበው የከተማ አስተዳደሩ የሚያመጣልንን ነገር ጠዋት ቁርስ ካበላን ምሳ እየዋለ፤ ምሳ ካበላን እራት እየዋለ ነው። እንጨት ይቸግራል፤ ዘይት ይቸግራል፤ ብዙ እዚህ የሚጎድሉ ነገሮች አሉ። አሁን የከተማ አስተዳደሩ በመሸነፍ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። ከሚገባው በላይ ታገለ። አሁን ከአቅሙ በላይ ነው። መንግሥት ተደራሽነቱን ለሕዝቡ ማሳየት አለበት ሲሉ ይወተውታሉ። ወይዘሮ ዓለም ከተማ የምታብበው ገበሬ ሲኖር ነው፤ ደሞዝተኛ የሚከፈለው ገበሬ ሲኖር ነው። እኛ በአመት ሶስት ጊዜ ማምረት የለመድን ሰዎች ነን። አሁን ግን እጃችን ታስሮ፤ ገበሬው አንገቱን ቀልሶ መሬት እየጫረ ነው ሲሉ የሚገኙበትን ሁኔታ አስረድተዋል። ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ላለፉት ሶስት ወራት ኑሯቸውን በሸዋሮቢት ከተማ ለወጣቶች መዝናኛ በተዘጋጀ አዳራሽ ያደረጉ ወይም በሰንበቴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጠለሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚያመሳስሏቸው ጉዳዮች ብዙ ናቸው። ሁሉም ተፈናቃይ ለመሆን የተገደዱት በተመሳሳይ ደም አፋሳሽ ግጭት ነው። ቤተሰባቸውን፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን አሊያም ጎረቤቶቻቸውን ተነጥቀዋል፤ ያፈሩት ጥሪት ወድሟል፤ በተጠለሉበት እርዳታ ቢቀርብላቸውም በቂ ሳይሆን ቀርቶ እየተራቡ ነው። ራሳቸው ተፈናቃይ ሆነው ተፈናቃዮችን የመመገብ ኃላፊነት የተጣለባቸው ወይዘሮ ዓለም እኛ በአመት ሶስት ጊዜ ማምረት የለመድን ሰዎች ነን። አሁን ግን እጃችን ታስሮ፤ ገበሬው አንገቱን ቀልሶ መሬት እየጫረ ነው ሲሉ የሚገኙበትን ሁኔታ አስረድተዋል። የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ግን በአካባቢው ሺሕ አካባቢ ተፈናቃዮች አሉ። ለእነሱ የሚሆን ድጋፍ ካሁን በፊት ልከናል። አሁንም እየተጓጓዘላቸው ነው የሚገኘው። የአሁኑ ወር እንደ አገርም የተፈጠረ ችግር ስላለ፤ የእኛም ሰፊ ቁጥር ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም ቦታ ትንሽ መዘግየት አለ። ከዚያ ውጪ ግን ባለፈው ወር ግጭቱ እንደተፈጠረ በሰሜን ሸዋ እና አካባቢው ለግንቦት ወር የሚሆን ሺሕ ኩንታል እህል አሰራጭተናል። አሁንም የሰኔ ወር እየተጓጓዘላቸው ነው። ምን ያህል በቂ ነው እንደ ቤት ሊሆን አይችልም። እኛ በዓለም የምግብ ድርጅት መስፈርት መሰረት ለአንድ ግለሰብ ኪሎ ግራም ለወር ይሰጣል ብለዋል። ኮሚሽነሩ በዕርዳታ ሥርጭት ረገድ ችግር መኖሩ ወደ አካባቢው ከተላከ ቡድን የክልሉ መንግሥት መረጃ እንዳገኘ ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። እነዚህን ነገሮች ማስተካከል እንዳለብን ተነጋግረናል የሚሉት ኮሚሽነር ዘላለም ከተፈናቃዮቹ ከሚቀርቡ ቅሬታዎች የማይቀበሏቸው አሉ። የተሰጠው ሐብት በትክክል ጥቅም ላይ ውሏል አልዋለም የሚለውን የሚያጣራ አንድ ቡድን ልከን እዛ የፍትኃዊነት ችግር አለ፤ የተላከው ድጋፍ በአግባቡ እየደረሰ አይደለም የሚል ምላሽ አምጥቷል። ግጭቱ የተፈጠረው መጋቢት መጨረሻ አካባቢ ስለሆነ የመጀመሪያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚያዝያ ወር ላይ እንዲህ አይነት ነገር ሊፈጠር ይችላል። እነዚህን ነገሮች ማስተካከል እንዳለብን ተነጋግረናል። እኛ የምንልከው ለዞን እና ለወረዳ ነው። እዚያ አካባቢ የሚስተዋሉ ችግሮች አሉ ተብሏል። ነገር ግን የግንቦትን ወር ሺሕ ኩንታል እህል ልከናል። የአሁኑ ትንሽ ዘግይቶባቸዋል። ይኸ ከመንግሥት የሚላከውን ነው እንጂ የምናነሳ ህብረተሰቡ እየደገፈ ነው ያለው። ይኸን ያህል ተርበን በጣም ጠቅላላ ረሐብ ውስጥ ነው ያለንው የሚለውን ግን ለመቀበል እቸገራለሁ ሲሉ ተናግረዋል። ወይዘሮ ዓለም፣ መሐመድ፣ ጀማል እና ዳውድን የመሳሰሉ ተፈናቃዮች የሚሉት ግን ከኃላፊው አስተያየት የተቃረነ ነው። በሸዋሮቢት የወጣቶች ማዕከል ከቀኑ ሰዓት ገደማ ደካክመው የተኙ ተፈናቃዮችን እያሳየ አብዱ ይኸ የምታየው ሰው ቁርስ ሳይበላ ቀርቶ የተኛ ነው። ምክንያቱም የከተማ አስተዳደሩም በጣም ደከመው በማለት ችግሩ ብርቱ መሆኑን አስረድቷል። ጥያቄው አንገብጋቢው የለት ጉርስ ጉዳይ ብቻ አይደለም። በአካባቢው ከተካሔደው እርቅ በኋላ ወደ ቀደመ ቀያቸው እንዲመለሱ ግፊት እየተደረገ ነው። ባለ ቆርቆሮ የመኖሪያ ቤቱ የተቃጠለበት አብዱ ዳውድ ብመለስ የት እወድቃለሁ የሚል ሥጋት አለው። በሸዋሮቢት ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃይ ጀማል ዲሲር ወደ ቀየው ተመልሶ ኑሮውን ማስተካከልን ቢመኝም እንዴት እና መቼ ለሚሉ ጥያቄዎች ግን መልስ ማግኘት ይቸግረዋል። የአካባቢው የጸጥታ ሁኔታ፣ ማረፊያ እና መቋቋሚያን የመሳሰሉ ሳንካዎች ጀማል እና መሐመድ አማንን ከመሳሰሉ ተፈናቃዮች ፊት የተጋረጡ ፈተናዎች ናቸው። ከዚህ ውጡ ከተባለ የት ነው የምንሔደው ኪስ የለም ምን የለም። ቤት ነው ኪራይ ላይ ነበርን ቤቱ ተቃጥሏል። መከራያስ ቤት ኪራይ ካገኘን በምን እንከራያለን እያለ የሚጠይቀው ጀማል መንግሥት ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ተናግሯል። በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት በተቀሰቀሰበት ወቅት በሁለቱም ወገን ተፈጽመዋል የሚባሉ ወንጀሎች ዘግናኝ ናቸው። የማምለኪያ ሥፍራዎች፣ የሕክምና እና የትምህርት አገልግሎት መስጪያ ተቋማት ወድመዋል። ግጭቱን ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፌድራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው በስፋት ተሰማርተው ይታያሉ። የጸጥታ አስከባሪዎቹ ቁጥጥር በተለይ ከሸዋሮቢት እስከ ሰንበቴ ባለው መንገድ ላይ ጥብቅ ነው። ለደም አፋሳሹ ግጭት መፍትሔ ለማበጀት በአካባቢው ዕርቅ እየተካሔደ ቢሆንም በእርግጥ ቀውሱ ዳግም ላለመቀስቀሱ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ማረጋገጫ የላቸውም። ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በአካባቢው ባለሥልጣናት የቀረበላቸውን ጥሪ የተቀበሉ የመኖራቸውን ያክል በጥርጣሬ የሚመለከቱት ጥቂት አይደሉም። የክልሉ መንግሥት ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ ኑሯቸው ለመመለስ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተካተቱበት ኮሚቴ አቋቁሞ እንቅስቃሴ ጀምሯል። በግጭቱ የፈረሱ ቤቶች እና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ወደ ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። እሸቴ በቀለ
ልውጥ የኮሮና ተዋህሲያንና ባህርያቸው
የኮሮና ተዋህሲ ራሱን እየቀየረ በመምጣቱ በአሁኑ ወቅት በቻይና ከተገኘው ከመጀመሪያው ተዋህሲ ጋር ተመሳሳይ አይደለም።ለዘርፉ ሊቃውንት የኮሮና ተዋህሲ ራሱን መለወጡ የሚጠበቅ ነው።ነገር ግን የተዋህሲያኑ የመተላለፍ ፍጥነት ከፈተኛ መሆኑና በክትባቶች ውጤታማነት ላይ ሊያሳድሩ የሚችሉት ተጽእኖ አሳሳቢ ነው። የኮሮና ተዋህሲ ከዓመት ከመንፈቅ በፊት በቻይና ውሃን ከተማ ሲገኝ ከነበረው ባህሪ በእጅጉ እየተለወጠ መምጣቱን ተመራማሪዎች በመግለፅ ላይ ናቸው።የዘርፉ ሊቃውንት እንደሚሉት የኮሮና ተዋህሲ እንደሌሎቹ ተዋህሲያን ራሱን መለወጡ የሚጠበቅ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ተዋህሲያን ለምን ራሳቸውን ይለወጣሉ የተለወጠው ተዋህሲስ የበለጠ አደገኛ ነውን የመሰራጨት ፍጥነቱስ ይህ እየተለወጠ የመጣ ተዋህሲ በክትባቶች ውጤታማነት ላይ ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን የሚሉት ጥያቄዎች ተደጋግመው ይነሳሉ።የዛሬው የሳይንስና ቴክኖሎጅ ዝግጅትም በነዚሁ ጥያቄዎች ላይ ያተኩራል። የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዋና ሳይኒቲስት ዶክተር ሶማያ ስዋሚናታን እንደሚሉት ሁሉም ተዋህሲያን ራሳቸውን ይለወጣሉ።ልክ እንደሌሎቹ ተዋህሲያን የኮሮና ተዋህሲም ራሱን በመለወጥ ላይ ይገኛል።በዚህ የተነሳ የኮሮና ተዋህሲ በአሁኑ ወቅት በቻይና ከተገኘው የመጀመሪያው ተዋህሲ ጋር በአብዛኛው ተመሳሳይ አይደለም።ይህንን ተከትሎ የሳይንስ ሊቃውንት የኮሮና ተዋህሲን የለውጥ ጉዞ በዓለም ዙሪያ በመከታተል ላይ ናቸው።ከኦስትሪያ የሳይንስ አካዳሚ ሞለኪውላዊ ሕክምና ምርምር ማዕከል ዶክተር አንድሪያስ ቤክ ታይለር የተለያዩ የተዋህሲያን ለውጦች መኖራቸውን ያስረዳሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የተዋህሲያን ለውጦች አሉ።ይህ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ሙሉ ተፈጥሯዊና የተለመደ ሂደት ነው። ምክንያቱም በራሳቸው ዘረ መል ውስጥ ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ የተባዙ ተዋህሲያን አሉ።ስለዚህ የተለወጠ ተዋህሲ ተገኜ ማለት መጥፎ ወይም ጥሩ ነው ማለት ሳይሆን ፤ ተፈጥሯዊ አሰራር ነው። ተመራማሪዎች እንደሚሉት የኮሮና ተዋህሲ በየጊዜው ራሱን እየለወጠ የመጣው በሰዎች ሰውነት ውስጥ በመባዛት ሲሆን፤ሂደቱም ተዋህሲው የራሱን የዘረ መል መረጃ ወደ ሰዎች ህዋሳት በማሰራጨት ራሱን ለማባዛት ይጠቀምበታል። ከዚያም የሰውነት ህዋሳት ለተዋህሲው መዳበር የሚረዱ የዘረ መል ቁሳቁሶችን በጅምላ የሚያመርቱ የፋብሪካዎች ይሆናሉ ማለት ነው። ይህ ማለት የዘረ መል ለውጥ ተዋህሲው ራሱን እንዲለውጥ ያደርጉታል ማለት ነው ።ይህ ለውጥ ከመነሻው ከነበረው ተዋህሲ የበለጠ አደገኛና ተላላፊ ሊሆን ይችላልን የተዋህሲያን ተመራማሪዋ ሜላኒ ቢሪንክማን ለዚህ መሰሉ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ጠለቅ ያለ ጥናት ያስፈልጋል ባይ ናቸው። ያ በቤተ ሙከራ ውስጥ በጣም የተወሳሰበ ሙከራን ይጠይቃል።ማለትም የበለጠ ለተላላፊ ነው የበሽታ መከላከል ስርዓትስ በተሻለ ሁኔታ ሊቋቋመው ይችላል ለሚሉት ለጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሙከራው በትክክል መከናወን አለበት።እንደዚህ ያሉ ጥናቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይወስዳሉ። የመጀመሪያው የተለወጠው የኮሮና ተዋህሲ በብሪታንያ የተገኘውና በመባል የሚጠራው ዝርያ ሲሆን፣ቆይቶም በደቡብ አፍሪቃ የተባለ ሌላ ዝርያ ተገኝቷል። በቤልጅየም የሊጅ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ባለፈው ሳምንት የተባለ አዲስ የኮሮና ተዋህሲ ዝርያ ማግኘታቸውን ገልፀዋል።ይህ ዝርያ በፈረንሳይ ፣ በእንግሊዝ ፣ በጀርመን ፣ በአየርላንድ ፣ በፖርቹጋል ፣ በአሜሪካ ፣ በሴኔጋል ፣ በኔዘርላንድስ እና በቡልጋሪያ ተለይቷል። በዚህ ሳምንትም በብራዚል ከደቡብ አፍሪካው ዝርያ ጋር የሚመሳሰል አዲስ የኮሮና ተዋህሲ መገኘቱን የሀገሪቱ የጤና ባለስልጣናት እየገለፁ ነው።ባለሙያዎች እንደሚሉት በእነዚህ ዝርያዎች የተያዙ ህሙማን በሰውነታቸው ውስጥ የተዋህሲ ቁጥር በርከት ያለ ነው። እንደማስበው በዚህ ወቅት የመተላለፍ ሂደቱ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በጣም ጥቂት ማስረጃዎች አሉ። ልገምተው የምችለው ብቸኛው ነገር ፤በተለወጠው ተዋህሲ የተያዙ ህሙማን ከፍ ያለ የተዋህሲ ቁጥር በሰውነታቸው ይኖራል።ይህም ለከፍተኛ የመተላለፍ አደጋ ሊዳርግ እንደሚችል ይብዛም ይነስም ማስረጃዎች ያሉ ይመስለኛል። ነገር ግን ለዚህ ትክክለኛ ማረጋገጫ አሁንም ቢሆን አልተገኜም። በቤተ ሙከራ ደረጃ የተደረጉ ምርምሮች እንደሚያሳዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለወጠው የኮሮና ተዋህሲ ስሪት ከመጀመሪያው ይልቅ ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።ያ ማለት ግን የተለወጠው የኮሮና ተዋህሲ የበለጠ አደገኛ ነው ማለት እንዳልሆነ ተመራማሪው ይገልፃሉ። የበለጠ አደገኛ ነው ማለት አይደለም።በእርግጥ ከወራት በፊት ተመራማሪዎች የለዩት ዲ የተባለው የዘረ መል ለውጥ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በየትኛውም ቦታ ይገኛል። በተጨማሪም ወደ ከፍተኛ ስርጭት ሊያመራ እንደሚችልም ተመራማሪዎች በቤተ ሙከራ ማስረጃ አግኝተዋል።ይህ ተዋህሲ ከሰው ወደ ሰው የመተላለፉ ሁኔታ ላይ ግን ተመራማሪዎች ሊሰሩበት የሚገባ ነገር ነው ፡፡ እንደ ዶክተር አንድሪያስ ቤክ ታይለር በአሁኑ ወቅት ራሱን በመለወጥ ላይ ያለው የኮሮና ተዋህሲ በክትባት ማበልፀግ ሂደትና በክትባቱ ውጤታማነት ላይ በመጠኑም ቢሆን ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል። በእርግጥ ክትባቱ ብዙውን ጊዜ የሚሰራው በፀረ በሽታ አካላት ወይም ቲ ሴል በተባለ ሌላ የበሽታ ተከላካይ ሕዋስ አማካኝነት መሆኑን ግልፅ ማድረግ ያስፈልጋል።እናም እነዚህ የበሽታ ተከላካይ ህዋሳት በተዋህሲው ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ የፕሮቲን ክፍሎችን ለይተው ያውቃሉ።እነዚህ ፕሮቲኖች ከተወገዱ ግን ዓላማው ግቡን አይመታም።ክትባቱም ሊሰራ አይችልም። ሆኖም ግን የክትባቱ ዒላማ አንድ ብቻ አይደለም።ከዚህ አኳያ በአስር ወይም በመቶዎች የሚቆጠሩ ብዙ ዒላማዎች ሊኖሩት ይችላሉ።ነገር ግን ጥቂት የተለውጡ ተዋህሲያን የክትባቱን ውጤታማነት ሊፈታተኑ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ። በሌላ በኩል በህንድ ሁለት ጊዜ የተቀየረ በእንግሊዥኛው አጠራር የተባለ ሌላ የኮሮና ተዋህሲ ዝርያ መታየቱን የሀገሪቱ ብሔራዊ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል በቅርቡ አስታውቋል። ይህ ዝርያ ሁለት የተለወጡ የኮሮና ተዋህሲ ዝርያዎች በአንድ ላይ በመሆን ሶስተኛ አይነት የኮሮና ተዋህሲ ዝርያ ሲፈጥሩ የሚከሰት ሲሆን፤የህንድ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት በቅርቡ በሀገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች ከ በላይ ሰዎች በዚሁ ተዋህሲ ተይዘዋል።ይህም ከመጀመሪያው የበለጠ አደገኛ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል። ሻሂድ ጀማል የተባሉ የህክምና ባለሙያ በበኩላቸው ምንም እንኳ ተጨማሪ ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ለሚታየው የኮቪድ ህሙማን መጨመር ይህ ዝርያ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ገልፀዋል። በአጠቃላይ የተለወጡ የኮሮና ተዋህሲዎች ለሰው ልጆች የበለጠ አደገኛና ተላላፊ መሆኑናቸው ወይም ለክትባቶች ያላቸው ምላሽ በጥናት ተረጋገጠም አልተረጋገጠ፤ ከምንም በላይ የጥንቃቄ መርሆዎችን በመከተል ከተዋህሲው ራስን መጠበቅ ጥናት የማያሻው መፍትሄ ነው። ፀሐይ ጫኔ
የቶክዮ ኦሎምፒክ እና የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውጤት
ሲካሄድ የሰነበተው የቶክዮ ኦሎምፒክ ሊጠናቀቅ አንንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና ዛሬ በተደረገው የሴቶች የ ሜትር የሩጫ ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ኔዘርላንዳዊት ሲፈን ሀሰን አሸናፊ ሆናለች ። ለውድድሩ ትልቅ ግምት የተሰጣት ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ኛ በመሆን የነሐስ ተሸላሚ ሆናለች። ሲካሄድ የሰነበተው የቶክዮ ኦሎምፒክ ሊጠናቀቅ አንንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው እና ዛሬ በተደረገው የሴቶች የ ሜትር የሩጫ ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ኔዘርላንዳዊት ሲፈን ሀሰን አሸናፊ ሆናለች ። ለውድድሩ ትልቅ ግምት የተሰጣት ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ኛ በመሆን የነሐስ ተሸላሚ ሆናለች። ሌላዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት እና ለባሕሬን የምትሮጠው ቃልኪዳን ገዛኸኝ የብር ሜዳልያ አሸናፊ ሆናለች። ዛሬ ለነገ አጥብያ እኩለ ሌሊት ላይ የወንዶች ማራቶን ይጠበቃል። በዘንድሮው የቶክዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያውያኑ የተጠበቁትን ያህል ውጥታማ አለመሆናቸው እየተነገረ ነው። የፓርሷ ወኪላችን ኃይማኖት ጥሩነህ በዛሬው ውድድር እና በ ቀጣይ የሚጠበ ቀውን የማራቶን ውድድር በተመለከተ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ አናግራ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች። ኃይማኖት ጥሩነህ
አንጋፋዋ ጋዜጠኛ እሌኒ መኩሪያ
ጋዜጠኛዋ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በ ዓ ም ሲቋቋምና ሲመረቅ የወቅቱን የጣቢያውን ሥራ አሥኪያጅ አቶ ሳሙኤል ፈረንጅን ንግግር እንዲያደርጉ የጋበዘች እና እንደ መጀመሪያ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናጋሪ የምትቆጠር መሆኗን የቀድሞ ባልደረቦቿ ይናገራሉ። ከጋዜጠኝነቱ በተጨማሪም የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን በመሥራትም አገልግላለች። በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት እድገት ታሪክ ቀዳሚ ከነበሩት አንጋፋ ጋዜጠኞች አንዷ እሌኒ መኩሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። የኢትዮጵያ ቴሌቪዝን በ ዓ ም ሲመሠረት የመጀመሪያ አንባቢ መሆኗ የሚነገርላት ጋዜጠኛ እሌኒ ለኢትዮጵያ ራዲዮ እንዲሁም ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለረዥም ዓመታት አገልግላለች። ጋዜጠኛ እሌኒ የኢትዮጵያ ሴት የመገናኛ ብዙሃን ማሕበርን ከመሠረቱና ካጠናከሩ አባላትም አንዷ በመሆን ትታወሳለች። ባደረባት ህመም ምክንያት ለረዥም ጊዜያት በሀገር ውስጥ እና በውጭም ህክምና ስትከታተል የቆየችው ታዋቂዋ ጋዜጠኛ ኢሌኒ መኩሪያ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም መለየቷን ሰምተናል። ሰሎሞን ሙጬ
ከኤኮኖሚው ዓለም፦ የቸገራቸው ተፈናቃዮች በሸዋሮቢት እና በሰንበቴ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የክስ ሂደት
የኢትዮጵያ መንግስት ሊቢያ ዉስጥ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያንን ለመዘከር የጠራዉን የአደባባይ ሠልፍ በማወክ ከተከሰሱ የሰማዊ ፓርቲ አባላት መካካል ሶስቱ ዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸዉ። ራሱን የኢራቅና የሶሪያ እስካማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራዉ ቡድን ኢትዮጵያዉን ስደተኞችን መግደሉን በመቃወም የተጠራዉን ሠልፍ አዉካችኋል ተብለዉ የታሰሩት አስራ አምስት ነበሩ። ከነዚሕ መካከል የተወሰኑት ሲፈረድባቸዉ፤ ሌሎቹ እየተሟገቱ ነዉ። በሊቢያ ራሱን አይ ኤስ በማለት የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የወሰደውን እርምጃ ለማውገዝ የኢትዮጵያ መንግሥት ሚያዝያ ቀን ዓ ም በመስቀል አደባባይ በጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ረብሻ በመፍጠር፣ በመሳደብና ድንጋይ በመወርወር የተከሰሱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የአንድ ወር ቀጠሮ ተሰጣቸው። በተመሳሳይ ክስ ማረሚያ ቤት የከረሙትና ባለፈው ሳምንት በዋስትና የተፈቱት ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ ማቲያስ መኩሪያ፤ብሌን መስፍን እና ተዋቸው ዳምጤ የተባሉት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በተመሳሳይ የህግ አንቀጽ መከሰሳቸውን ተናግረዋል። የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ ሚያዝያ ቀን ከተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ከታሰሩ የፓርቲው አባላት መካከል ከስድስት ወር እስከ ሶስት አመት እስር የተበነባቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል። በአባላት ደረጃ የታሰሩት ከ አያንሱም። የተወሰኑት ተፈተዋል። የሶስት አመት ተኩል ፍርድ የተፈረደበትና ሸዋሮቢት የሄደ ወጣት ናትናኤል አለምዘውድ የሚባል ልጅ አለ። የስምንት ወር እስራት የተፈረደባት የሁለት ልጆች እናት የሆነች ወይዘሮ ንግስት ወንድ ይፍራው የምትባል የፓርቲያችን ንቁ አባልም አለች። በ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው በእጩነት ተመዝግበው በእጣ ከውድድሩ ሳይገቡ የቀሩት ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ የእስልምና እምነት ተከታዮች በአንዋር መስጊድ አቅራቢያ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በተፈጠረ ግጭት ተሳትፎ አድርገዋል በሚል ለእስር ተዳርገው ነበር። ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ ከአሁኑ ክስ በአምስት ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ቢለቀቁም ሐምሌ ቀን ዓ ም ተመልሰው ከችሎት ይቆማሉ። ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ፣ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ዳንኤል ተስፋዬና ቤተልሔም አካለወርቅ በየፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምብድ ችሎት ሰኔ ቀን የተበየነባቸውን የሁለት ወር ቅጣት ካጠናቀቁ በኋላ ከማረሚያ ቤት ሲወጡ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን አስቆጥቶ ነበር። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ክስተቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የህግ የበላይነትን እየሸረሸረ ነው ሲል መተቸቱ አይዘነጋም። እሸቴ በቀለ
ምርጫ በአምቦ እና አካባቢው
ዛሬ በምዕራብ ሸዋ ዋና ከተማዋ በአምቦ ሲካሄድ በዋለው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ምንም እንኳ ብቸኛ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ቢሆንም ምርጫውን ቁጥራቸው የማይናቅ ነዋሪዎች ከማለዳው ጀምሮ ወጥተው የመራጭነት ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ዛሬ በምዕራብ ሸዋ ዋና ከተማዋ በአምቦ ሲካሄድ በዋለው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ምንም እንኳ ብቸኛ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ቢሆንም ምርጫውን ቁጥራቸው የማይናቅ ነዋሪዎች ከማለዳው ጀምሮ ወጥተው የመራጭነት ድምጻቸውን ሰጥተዋል። አምቦን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ላይ ቅኝት ያደረገው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ ከፍተኛ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴን በአከባቢው ማስተዋሉን ገልጿል፡፡ ዛሬ መራጮች በየምርጫ ጣቢያው ወጥተው ሲመርጡም ከተማዋ በእጅጉኑ ፀጥታ ተጭኗት እንቅስቃሴ አልባ ሆና ነው ያረፈደችው፡፡ በአምቦም ሆነ በዙሪያዋ ባሉ እንደ ጉደርና ጊንጪ እንዲሁም ሌሎች ከተሞች ላይ ምንም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴም አልተስተዋለም፡፡ ከሰዓቱን ግን በመንገድ ላይ የሚታዩ ሰዎች ቁጥር የተሻለ ሆኖ ተስተውሏል፡፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩዎች ለክልል ምክር ቤት ደግሞ እጩዎች ናቸው የተመዘገቡት፡፡ በዚህ ዞን በቡራዩ አንድ የህ ተ ም ቤት እጩ ካስመዘገበው አንድነትና እኩልነት እንዲሁም ለህ ተ ም ቤት አንድ እጩ እና ለክልል ምክር ቡት አንድ እጩ ካስመዘገበው የኦሮሞ እኩልነትና ነጻነት ፓርቲ ውጩ በሁሉም የምርጫ ክልሎች ብልጽግና ፓርቲ ብቸኛ ተወዳዳሪ መሆኑን ከዞኑ ምርጫ አስተባባሪ ተረድተናል፡፡ ስዩም ጌቱ
የአገው ብሔራዊ ሸንጎና የቅማንንት ዴሞካራሲ ፓርቲ የምርጫ ዝግጅት
የአገው ብሔራዊ ሸንጎ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ቢያሸንፍ የአገው ህዝብ በራሱ የሚተዳደርበትን ክልል እንደሚመሰርት አስታወቀ። የአገው ብሔራዊ ሸንጎ በአማራ ክልል ሦስት አካባቢዎች ይወዳደራል ተብሎአል። የቅማንንት ዴሞክራሲ ፓርቲ በበኩሉ በቀድሞው ሰሜን ጎንድር እጩዎችን ለፌደራል እና ክልል ምክር ቤቶች እንደሚያወዳድር አመልክቷል። የአገው ብሔራዊ ሸንጎ በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ቢያሸንፍ የአገው ህዝብ በራሱ የሚተዳደርበትን ክልል እንደሚመሰርት አስታወቀ። የአገው ብሔራዊ ሸንጎ በአማራ ክልል ሦስት አካባቢዎች ይወዳደራል ተብሎአል። የቅማንንት ዴሞክራሲ ፓርቲ በበኩሉ በቀድሞው ሰሜን ጎንድር እጩዎችን ለፌደራል እና ክልል ምክር ቤቶች እንደሚያወዳድር አመልክቷል። ሁለቱም ፓርቲዎች በምርጫው የሚወዳደሩት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና ሌሎች ምክንያቶች የተፈለገውን ያህል መራጭ እንዳልተመዘገበ ሁለቱም ፓርቲዎች ገልፀዋል፡፡ የአገው ብሔራዊ ሸንጎና የቅማንንት ዴሞካራሲ ፓርቲ በምርጫው ሲሳተፉ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ አቶ አላምረው ይርዳው በስልክ እንደገለፁለን ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሳተፉበት ኛው አገራዊ ምርጫ በ የምርጫ ክልሎች እጩዎችን ለክልልና ለፌደራል የተወካዮች ምክር ቤቶች እንዲወዳደሩ አቅርቧል፤ ዎቹ ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ ናቸው፡፡ የቅማንንት ዴሞክራሲ ፓርቲም ምክትል ሊቀመንበር አቶ አውግቸው ማለደ እንዳሉት ደግሞ ፓርቲያቸው በማዕከላዊ ጎንድር ዞን በ ፣ በጭልጋ በ ፣ እንዲሁም በላይ አርማጭሆ፣ በደንቢያ፣ በቋራ፣ በመተማና በወገራ በእያንዳንዳቸው አንድ አንድ በአጠቃላይ በ የምርጫ ጣቢያዎች እጩዎችን ለሁለቱም ምክር ቤቶች እንዲወዳደሩ አቅርቧል፣ ቱ ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ ናቸው፡፡ በመራጮች ምዝገባ ወቅት ከፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘና በሌሎችም ምክንያቶች በተለይ በዋግኽምራና ቅማንት አንዳንድ አካባቢዎች የተፈለገውን ያህል መራጭ እንዳልተመዘገበ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ ሊቀመንበር አቶ አላምረው ይርዳው ገልፀዋ ፡፡ የቅማንንት ዴሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አውግቸው፣ የፀጥታ ችግር ምክንያት በላይ አርማጭሆና በጭልጋ ቁጥር አንድና ቁጥር ሁለት የምርጫ ክልሎች የመጀመሪያ ዙር ምርጫ አይካሄድም ብለዋል፡፡ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ በምርጫ ቢያሸንፍ የአገው ህዝብ በራሱ የሚተዳደርበትን ክልል እንደሚመሰረትም ፓርቲው አመልክቷል፡፡ ሆኖም ፓርቲው እወዳደራለሁ የሚልባቸው አካባቢዎች የጋራ ወሰን የሌላቸው፣ በመልከዓ ምድር የተለያዩና የተራራቁ ሆነው ሳለ እንዴት በአንድ ክልል ሊረተዳደሩ ይችላሉ የሚል ጥቄ ከዶይቼ ቬለ የቀረበላቸው የፓርቲው ሊቀመንበር፣ አሁን በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰጡት አስተያየት እንደሌለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የጋራ ምክር ቤት ከተመሰረተ ጀምሮ በፓርቲዎች መካከል የተሻለ መግባባትና በተግባር የተደገፉ ስራዎችም መሰራታቸውን አቶ አላምረው አመልክተዋል፡፡ ዓለምነው መኮንን
የቶክዮ ኦሎምፒክ እና የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውጤት ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ሁለቱም ፓርቲዎች በምርጫው የሚወዳደሩት ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የደቡብ ክልል የምርጫ ሂደት ግምገማ
በሀዋሳ ከተማ ትናንት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ምርጫው እንደ አገር ኢትዮጲያ ያሸነፈችበት ነው ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች ህዝቡ የሚፈልገውን እንዳይመርጥ ተፅኖዎች ተስተውለዋል ሲሉ ተደምጠዋል ። በደቡብ ክልል በ ኛው አገራዊ ምርጫ የተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን ሂደት ለመገምገም ያስችለናል ያሉትን ውይይት አካሂዱ። በሀዋሳ ከተማ ትናንት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ምርጫው እንደ አገር ኢትዮጲያ ያሸነፈችበት ነው ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች ህዝቡ የሚፈልገውን እንዳይመርጥ ተፅኖዎች ተስተውለዋል ሲሉ ተደምጠዋል ። ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ስፖርት መስከረም ፣ ዓ ም መግቢያ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የጀርመን ክለቦች ድልና የአዉሮጳ ሊግ
ካራቱ ሐይለኞች፥የሐይለኞች ሐይለኛ የሚሆነዉ ማን ነዉ ነዉ የከእንግዲሁ ጥያቄ።የባየር አሰልጣኝ ዩፕ ሔይንከስ ያሻዉ አይጣ አይነት ይላሉ። ጥሩ እንጫወታለን፥ የተዋጣለት እግር ኳስ።ከማን ጋር እንደምንገጥም ግን ወደፊት እናያለን።በአየነ ቁራኛ የምንጠብቀዉ፥ ሪል ማድሪድን ይሁን ባርሴሎናን ወይም ዶርትሙንድን አናዉቅም። የዘንድሮዉ የአዉሮጳ የእግር ኳስ ክለቦች ግጥሚያ ሻምፒዮንስ ሊግ በሊጉ የእስካሁን ታሪክ ያልታዩ አዳዲስ ክስተቶች እየታዩበት ነዉ።ለረጅም ዘመን የሻምዮን ሊጉን ግጥሚያ የሚመሩት የኢንግላንድ፥ የፈረንሳይና የኢጣሊያ ክለቦች እየተንጠባጠቡ የስጳኝና የጀርመን ክለቦች ጥንካሬያቸዉን እያሳስመሰከሩ ነዉ።የስጳኞቹ ሪል ማድሪድ እና የጀርመኖቹ ባየር ሙዉኒክ እና ቦሪያሲያ ዶርትሙድ ተጋጣሚዎቻቸዉን እያሰናበቱ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሰዋል።ጀርመን በአዉሮጳ ሻምፒዮን ሊግ ሁለት ቡድናት ሥታሰልፍ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ። እግር ኳስ አገሩ ገባ ፉት ቦል ካም ሆም ብሎ ቡረቃ ዘንድሮ ኢንግላንድ ላይ የለም።በአዉሮጳ ሻምፒዮን የእስከ ዘንድሮ ኮኮቦች የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቡድናት እዚያዉ እንግሊዝ ናቸዉ።ፈረንሳዮች ፓሪስ ላይ ጮቤ ለመርገጥ የቀራቸዉ አንድ ተስፋ ነበር።ፓሪስ ሳ ዠርሜ። ካታላኖች አሰናበቱት። የማላጋዎች ተስፋ በዶርትሙንዶች ቢመክን ስጳኞች ከአንድም ሁለት አማራጭ አላቸዉ።የካታላኖቹ ባርሴሎና፥ ወይም ሪል ማድሪድ።ኢጣሊያዎችም፥ ጆቬንቱስ ቱሪኖን ተመኝተዉ ነበር።ባየር ሙኒኮች ትናንት በምኞት አስቀሩባቸዉ።የባየር ሙዉኒኩ ፕሬዝዳት ኡሊ ሆነስ እንዳሉት የአዉሮጳ አንደኞች እንግሊዞች፥ ኢጣሊያዎች፥ ወይም ፈረንሳዮች አይደሉም።ስጳኝ ወይም ጀርመኖች እንጂ። ዶርትሙንድ ክማላጋ ባሁኑ ጊዜ የጀርመን እና የስጳኝ እግር ኳስ ክለቦች ከአዉሮጳ አንደኛ መሆናቸዉ ምንም ጥር ጥር የለዉም። ከሪል ማድሪድ ይልቅ ባርሴሎና፥ ከባየር ሙዉኒክ ይበልጥ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ለግማሽ ፍፃሜ ያለፉበት መንገድ ከእግር ኳስ ጥበብ፥ ጥንካሬ፥ ከየተጋጣሚዎቻቸዉ ድክመት እኩል እድል የተቀየጠበት ነበር።ባርሴሎና ለግማሽ ፍፃሜ የደረሰዉ ከፓሪስ ሳ ዠርሜ ጋር በደርሶ መልስ ግጥሚያ የጎል ብዛት ቆጥሮ፥ ቦሪሲያ ዶርትሙንድ ደግሞ የማላጋን ክለብ በባከነ ሠዓት ባስቆጠረዉ ግብ በልጦ ነዉ።ለኡሊ ሆነስ ግን፥ድሉ እንዴትም ተገኘ እንዴት የጥንካሬ ዉጤት እንጂ የአጋጣሚ ግኝት አይደለም። አራቱ ቡድናት ለግማሽ ፍፃሜ መድረሳቸዉ አጋጣሚ አይደለም የጀርመን ብሔራዊ ቡድን እና የባየሩ ተጫዋች ቶማስ ሙለርም የራሱ ክለብም ሆነ የዶርት ሙንዶችን ድል የጥረታችን ዉጤት፥ የገባነዉ ቃል ገቢራዊነት እማኝ ይለዋል። ባይርና ጁቬንቱስ ለግማሽ ፍፃሜ በማለፋችን ደስተኞች ነን።አሁን የምንጫወተዉ ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ሳይሆን ለባየር ሙዉኒክ ቢሆንም ያገኘነዉ ዉጤት የጀርመን እግር ኳስን ለማሳደግ ባለፉት ዓመታት በገባነዉ ቃል መሠረት የተገኘ ነዉ። የሙለር ቡድን ትናንት ሁለት ለዜሮ የቀጣዉ የኢጣሊያዉ ጁቬንትስ ቱሪን በተለይ በመጀሪያዉ አጋማሽ ጥሩ ተጫዎቶ ነበር።ዴሎ ስፖርቶ የተሰኘዉ የኢጣሊያ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበዉ ግን ከአዉሮጳ ደረጃ ለመድረስ ብዙ ይቀረዋል። የደረጃዉ መለኪያ፥አሁን አራቱ ክሎቦች ናቸዉ። ሪል ማድሪድ እና ጋላታሳራይ ካራቱ ሐይለኞች፥የሐይለኞች ሐይለኛ የሚሆነዉ ማን ነዉ ነዉ የከእንግዲሁ ጥያቄ።የባየር አሰልጣኝ ዩፕ ሔይንከስ ያሻዉ አይጣ አይነት ይላሉ። ጥሩ እንጫወታለን፥ የተዋጣለት እግር ኳስ።ከማን ጋር እንደምንገጥም ግን ወደፊት እናያለን።በአየነ ቁራኛ የምንጠብቀዉ፥ ሪል ማድሪድን ይሁን ባርሴሎናን ወይም ዶርትሙንድን አናዉቅም። ከአራቱ ቡድናት ማን ከማን ጋር እንደሚጋጠም ነገ ንዮን ሲዊዘርላንድ በሚወጣዉ ዕጣ ይበየናል። ነጋሽ መሐመድ
የጎሳ ፖለቲካ የጎላበት የኬንያ ምርጫ
በኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታና በተቃዋሚው እጩ ራይላ ኦዲንጋ መካከል የተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውዝግብ አሁንም እንዳወዛገበ ይገኛል። የተቃዋሚው ቡድን እጩ ራይላ ኦዲንጋ የመራጭ ድምፅ ከሚከማችበት ዋና ከኬንያ አስመራጭ እና ድንበር ማካለል ኮሚሽን፣ ከ አይኢቢሲ ኮምፒውተር ድምፅ ተሰርቋል በሚል ውጤቱን እንደማይቀበሉ መግለጻቸው ይታወቃል። የኬንያ ተቃዋሚ ብሔራዊ ከፍተኛ ህብረት፣ በምህፃሩ የ ናሳ መሪ ሙሳሊያ ሙዳቫዲም ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በአስመራጩ ኮሚሽን ያሉ ታማኝ ያሏቸውን ምንጮች ጠቅሰው እንዳመለከቱት፣ ራይላ ኦዲንጋ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታን በ ድምፆች አሸንፈዋል። ይህን መሰረት በማድረግ፣ የ አይቢሲ ሊቀ መንበር የተከበሩ ራይላ አሞሎ ኦዲንጋን እና ስቴፈን ካሎንዞ ሙስዮካን የኬንያ ፕሬዚደንት እና ምክትል ፕሬዚደንት ብለው እንዲያሳውቁ እንጠይቃለን። አስመራጩ ኮሚሽን ኦዲንጋ ያቀረቡትን ወቀሳ አጣርቶ፣ ኮምፒውተሩን ለመጥለፍ በርግጥ ሙከራ ተደርጎ እንደነበረ ፣ ግን ጥረቱ እንደከሸፈ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ዋፉላ ቼኩባቲ ማረጋገጣቸው ይታወሳል። የተቃዋሚው ቡድን ኦዲንጋ አሸንፈዋል በሚል ያወጣውን ውጤት የተሳሰተ ነው በሚል አጣጥሎታል። የምርጫውን ውጤት መግለጽ የሚችለው አስመራጩ ኮሚሽን ብቻ መሆኑንም ኮሚሽነር ሮዝሊን አኮምቤም አስታውቀዋል። የኬንያ ሕገ መንግሥት ግልጽ ነው። ምርጫ የማዘጋጀት፣ የመቁጠር እና ውጤቱን የማሳወቅ ስልጣን ያለው ብቸኛው አካል ገለልተኛው የኬንያ አስመራጭ እና ድንበር ማካለል ኮሚሽን፣ በምህጻሩ አይኢቢሲ ነው። ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ወቀሳ ቢያሰሙም፣ ምርጫውን የታዘቡ ዓለም አቀፍ ቡድኖች ምርጫው ነፃ እና ትክክል ነበር በማለት አሞግሰዋል። ምርጫውን ከታዘቡት መካከል አንዱ የሆነው የካርተር ማዕከል ቡድን መሪ ኬንያዊቷ አሚናታ ቱሬ ስለምርጫው ሂደት ግልጽነት ተናግረዋል። በምርጫው ዕለት ሁኔታዉን ተከታትለናል፣ በዴሞክራሲያዊ ፖለቲካዊ መብታቸው ለመጠቀም ቆርጠው የተነሱ በብዛት ተሰልፈው ሲጠባበቁ የነበሩ ሰዎችን አይተናል። በምርጫ ጣቢያያዎችም ውስጥ ነበርን፣ሁኔታው የተረጋጋ ነበር። በኋላም ለድምፅ ቆጠራው ወደምርጫ ጣቢያዎች ተመልሰናል። ቆጠራው ግልጽ ነበር። እና የእያንዳንዱ ፓርቲ ተወካይ የተቆጠረው ድምፅ የተመዘገበበት ወረቀት ቅጂ ደርሶታል፣ ይኸው ሂደትም ግልጽ ነበር። የአውሮጳ ህብረት ቡድን መሪ ማሪየትየ ሻከም ተመሳሳይ አስተያየት ከሰጡ እና አስመራጩ ኮሚሽን የሚቀርቡ ወቀሳዎች በትክክል ሊያጣራ እንደሚገባ አስታውቀው፣ የምርጫ ተፎካካሪዎች ደጋፊዎቻቸውን እንዲያረጋጉ ሀሳብ አቅርበዋል። በምርጫው የተወዳደሩት ዋነኞቹ እጩዎች በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ትልቅ ተሰሚነት ያላቸው ይመስለኛል፣ እና ህዝቡ እንዲረጋጋ፣ ከኃይል ተግባር እንዲቆጠብ እና የምርጫውን ውጤት እንዲጠባበቅ የማድረግ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል። ከዚያ በምርጫው ታይቷል የሚሉት ያልተስተካካለ አሰራር ካለ ያለውን ሕግ በመከተል እንዲጠይቁ እና የሕግ የበላይነትን እንዲያከብሩ እናሳስባለን። ውጥረቱ በተካረረበት ባሁኑ ጊዜ ግን ብዙዎቹ የኬንያ ወጣቶች የሀገራቸው ፖለቲከኞች በሚከተሉት የጎሳ አሰራር እንደተሰላቹ ይናገራሉ። እንደሚታወሰው፣ በመዲናዋ ናይሮቢ እና በሌሎች አካባቢዎች ባሉት የተቃዋሚው ጠንካራ ሰፈሮች አልፎ አልፎ በኦዲንጋ ደጋፊዎች እና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት አራት ሰዎች ተገድለዋል። ይሁንና፣ የነሀሴ ስምንት ዓም ምርጫ ውጤት የሀገሪቱን ሰላም እንደማይናጋ ተስፋቸውን ሲገልጹ ነበር የተሰሙት። እርግጥ ምርጫ ነው። ሁሉም ሰው በውጤቱ ሊደሰት አይችልም። ቅር የሚሰኙ ወገኖች ይኖራሉ። ይህንን ቅሬታቸውን በሚገልጹበት ሁኔታ ላይ ግን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ይወጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የወቅቱ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ወይም የተቃዋሚው እጩ ራይላ ኦዲንጋ የምርጫው አሸናፊ ሆኑ አልሆኑ፣ የኬንያ ህዝብ ሰላሙን እንዲጠብቅ እፈልጋለሁ። በምሥራቅ አፍሪቃዊት ሀገር መራጩ ህዝብ፣ በተለይ፣ በዕድሜ ጠና ያሉት ድምፃቸውን የሚሰጡት በፖለቲካ ሳይሆን በጎሳ መስመር መሆኑን እና ፖለቲከኞቹም ይህን ለራሳቸው ጥቅም ማዋላቸውን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። እስከዛሬ እንደታየው ኬንያ ውስጥ በምርጫ ወቅት ትልቅ ሚና የሚጫወቱት ትልቆቹ አምስት ጎሳዎች ናቸው፣ በኬንያ ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት መዘርዝር መሰረት፣ ከ ሚልዮን የሀገሪቱ ህዝብ መካከል የኪኩዩ ጎሳ ሚልዮኑን፣ የሉህያ ጎሳ ሚልዮኑን የካሌንዢን ጎሳ ሚልዮኑ ን፣ የሉዎ ጎሳ አራት ሚልዮኑ ን እና የካምባ ጎሳ ሚልዮኑን ይሸፍናሉ። በዚህ ዓመቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ በናይሮቢ ከኪኩዩ ጎሳ የሚወለዱት ኡሁሩ ኬንያታ እና በምዕራብ ኬንያ ካሉት የሉዎ ጎሳ የመጡት ራይላ ኦዲንጋ የተፎካከሩ ሲሆን፣ ያቋቋሟቸው የፓርቲዎች ህብረትም በጎሳው መስመር ነው የተቀናጁት። የፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ምክትላቸው ዊልያም ሩቶ የጁብሊ ጥምረት የኪኩዩ እና የካሌንዢን ጎሳዎች፣ የተቃዋሚው የኬንያ ብሔራዊ ከፍተኛ ህብረት፣ በምህፃሩ የ ናሳ ህብረት እጩ ራይላ ኦዲንጋ፣ ሞዘስ ዌታንጉላ እና ካሎንዞ ሙሶይካ ደግሞ የሉዎ፣ ሉህያ እና የካምባ ጎሳዎች ድጋፍ አላቸው። በኬንያ ፖለቲካ ውስጥ የጎሳ ተፅዕኖ ስር የሰደደ በመሆኑ ይህን የመቀየሩ ሁኔታ አዳጋች እንደሚሆን ዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው ኬንያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ማርቲን ኦሎ ጠቁመው፣ ይህ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ማብቃቱን እንደሚጠራጠሩት ገልጸዋል። ይህ ቀላል ተግባር ይሆናል ብዬ አላስብም፣ እኛ ፖለቲካችንን ከጉዳዮ ክብደት ወይም ከፖለቲከኞች ችሎታ አኳያ መመልከት እስክንጀምር ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል ባይ ነኝ። በአሁኑ ጊዜ ነገሮችን የምናደራጀው እና በምርጫ ወቅትም ድምፃችን የምንሰጠው በጎሳ መስመር ነው። ይህም እኛን ለመከፋፈል እያገለገለ ነው። በዚህም የተነሳ ከዚህ ዓይነቱ ጎጂ አሰራር ማላቀቅ የሚችሉ የተለያዩ ፖለቲከኞች ያስፈልጉናል። እንደ ፖለቲካ ተንታኙ ኦሎ ፣ ብዙዎች ተስፋቸውን በወጣቱ የኬንያ ትውልድ ላይ አሳድረዋል። በነሀሴ ስምንቱ፣ ዓም ምርጫ ላይ ድምፅን ለመስጠት ከተመዘገበው ሚልዮን ኬንያዊ መካከል አምስት ሚልዮኑ አዳዲስ ወጣት መራጮች በመሆናቸው ፣ ተስፋቸው ምናልባት እውን ሊሆን እንደሚችል ኦሎ ገምተዋል። ከአምስት ዓመታት በኋላ ፣ ማን ያውቃል፣ ብዙዎቹ መራጮች ወጣቶች ሊሆኑ ይችላሉ፣ እና እነዚህ ወጣቶች በጎሳ ላይ የተመሰረተ አስተሳሰባቸውን ጋር ተጣብቀው ከሚገኙት በዕድሜ የገፉት መራጮች በመጠኑ የተሻለ አመለካከት አላቸው። በተለይ በጎርጎሪዮሳዊው እና ዓም ከተካሄደው ምርጫ በኋላ ተጠናክሮ የታየው ጎሳ ነክ ውጥረት በዘንድሮው ምርጫ እንዳይደገም ስጋት ቢኖርም፣ መንግሥት አስቀድሞ የወሰዳቸው ርምጃዎች ሁከት እንዳይነሳ ሊያግዙ እንደሚችሉ ማርቲን ኦሎ ጠቁመዋል። መንግሥት ባሁኑ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ተዘጋጅቷል። በስምጥ ሸለቆ በ እና ለተፈጠረው ግጭት መነሻ የሆኑትዋነኞቹ ምክንያቶች አሁን የሉም፣ ምክንያቱም በዚሁ አካባቢ ተቀናቃኝ የነበሩት ማህበረሰቦች አሁን አንድነት ፈጥረዋል። ስለዚህ ያ አካባቢ ሰላማዊ ነው። ይህ ቢባልም ግን በምርጫው የሚሸነፈው እጩ ማንም ሆነ ማን፣ ተሸናፊው እጩ በይፋ ሽንፈቱን መቀበል ይኖርበታል። አሁን እንደሚታየው ተሸናፊው የ ናሳ እጩ ነው። ይህ ኬንያን ካለፉት ምርጫዎች በኋላ ከታየው ዓይነት ግጭት ሊጠብቃት እንደሚችል ተንታኙ ማርቲን ኦሎ አስታውቀዋል። አርያም ተክሌ
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ሳይንስ ተንታኞች አስተያየት
በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ክራይስስ ተንታኝ ዊልያም ዴቪሰን የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልላዊ መስተዳድር የገቡበትን ውጥረት በሚመለከት ለዶይቸ ቬለ እንደሚሉት ከሆነ፤ ሁለቱ አካላት አሁኑኑ ተኩስ አቁም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በትግራይ ክልላዊ አስተዳደር እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሚመሩት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት መካከል የነበረው የቃላት ጦርነት አብቅቶ ከትናንት ሌሊት አንስቶ ውጊያ ውስጥ መገባቱን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አብይ አህመድ የተሰጠው መግለጫ ያመላክታል። ይህ ከመከሰቱ አስቀድሞ የውጭ ኃይል ጣልቃ እንዲገባበት ሲያሳስቡ ከነበሩ የፖለቲካ ተንታኞች መካከል በኢትዮጵያ የኢንተርናሽናል ክራይስስ ተንታኝ ዊልያም ዴቪሰን አንዱ ናቸው። አሁን በትግራይ ክልላዊ አስተዳደር እና በፌደራል መንግሥት መካከል የተፈጠረው የከረረ ግጭት ሀገሪቱ ወሳኝ ጊዜ ላይ ባለችበት ወቅት ነው ይላሉ። ይህ የሆነው ሀገሪቱ በተከፋፈለችበት ወቅት ነው። በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ግጭቶች ተከስተዋል። በተደጋጋሚ የጎሳ ግጭቶች ነበሩ፤ የምርጫው መዘግየት እንዲሁም የተቃዋሚ መሪዎች መታሰር፤ ከዚህም ሌላ ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የፖለቲካ ችግሮች አሉ ይሁንና የትግራይ ክልል ላይ አሁን በግልፅ የተጀመረው ግጭት ዋንኛው ነው። ይህም ሀገሪቷን ወደ ያልተረጋጋ ሁኔታ ሊከታት ይችላል የሚሉት ዴቬሰን ግጭቱን ያባባሰው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ብቻውን ያካሄደው ምርጫ ሊሆን እንደሚችል በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰዱት ርምጃስ አግባብ ነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ለግጭቱ በምክንያትነት ያቀረቡት ህውሐት ትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል የሚል ነው። የፌደራል መንግሥቱ የሚለው ይህንን ነው። ከትግራይ በኩል ደግሞ ሌላ አይነት ታሪክ ይሰማ ይሆናል። ዴቪሰን እንደሚሉት ከሆነ መፍትሔው ግጭቱ እንዳይባባስ ማድረግ ነው። ይህም ሁለቱ አካላት ተኩስ አቁም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ከዚህም ሌላ እንደ ዴቪሰን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት ማድረግ ይኖርበታል። ሌላው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ተንታኝ ፕሮፌሰር ሼል ትሮንፎል ናቸው። የግጭት እና ሰላም ጥናት ተመራማሪና በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚሰራው የኦስሎ አናሊስቲካ መሥሪያ ቤት ዳሬክተር የሆኑት ትሮንፎን እንደሚሉት ይህ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኃይላቸውን ለማሳየት የወሰዱት ርምጃ ሳይሆን ጉዳዩ ውስብስብ ነው። ርምጃው ኃይልን ከማሳየት ያለፈ እና ውስብስብ ነው። አብይ አህመድ ከሚመሩት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት አኳያ ካየነው አስፈላጊ ነበር። የፌደራል መከላከያ ሠራዊቱን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱት የኖርዌይ ተንታኝ ኢትዮጵያ ውስጥ በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል መካከል ካለው ግጭት ባሻገር ሰርጎ ገብ እንቅስቃሴዎች በምዕራብ ወለጋ እና በመላው በሀገሪቷ መንግስትን ፈታኝ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ ይላሉ። የትግራዩ ግጭት የሰሜን ዕዝን እና ንብረቶቹን ለመቆጣጠር የሚደረግ ነው። የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነት ከመቋረጡ በፊት ከህወሓት የተሰጠው መግለጫ የሰሜን ዕዝ ወታደሮች እና አዛዦች ዐቢይን ለመዋጋት ወደ እነሱ መክዳታቸውን ገልጿል። ይሁንና ይኸ ትክክል መሆኑ አልተረጋገጠም ስለሆነም የአብይ አህመድ ትልቁ ፈተና የመከላከያ ሠራዊቱን ተዓማኒ አድርጎ ማቆየቱ ይሆናል ይላሉ ትሮንፎል። የኢፌድሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ጠዋት በትግራይ ክልል ላይ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁም አስፈላጊ ነበር ሲሉ ትሮንፎል ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። የፖለቲካ ተንታኙም ከትግራይ ክልል ጋር የነበረው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ግንኙነት በመቋረጡ በክልሉ ስላለው ነገር ከሌላ አካል መረጃ ማግኘት መቸገራቸውን ተናግረዋል። አሁን ያላቸው መረጃ ሁለቱ አካላት ውጊያ ላይ እንዳሉ ቢሆንም የተባባሰ ጦርነት ውስጥ ሳይገቡ አሁንም ለማስቆም ይቻላል ይላሉ ትሮንፎል። ልደት አበበ
ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በድሬደዋ
ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በድሬደዋ አስተዳደር እና በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ስር ባሉ አካባቢዎች በጥሩ ሁኔታ ሲካሄድ ውሏል፡፡ዐሥር የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሁለት የግል እጩ ተወዳዳሪዎች በተሳፉበት የድሬደዋ ምርጫ ላይ በመራጭነት የተሳተፉ የድሬደዋ ነዋሪዎች ምርጫው ጥሩ መሆኑን ለዶይአ ቬለ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡ ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በድሬደዋ አስተዳደር እና በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ስር ባሉ አካባቢዎች በጥሩ ሁኔታ ሲካሄድ ውሏል፡፡ ዐሥር የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሁለት የግል እጩ ተወዳዳሪዎች በተሳፉበት የድሬደዋ ምርጫ ላይ በመራጭነት የተሳተፉ የድሬደዋ ነዋሪዎች ምርጫው ጥሩ መሆኑን ለዶይአ ቬለ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ከታየው መዘግየት ባለፈ በብዙ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በምርጫው ተፎከካሪ ፓርቲ የሆነው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ድሬደዋ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ዮናስ በትሩ ናቸው፡፡ የእናት ፓርቲ ድሬደዋ ተወካይ አቶ ናትናኤል ስናማው በበኩላቸው ህዝቡ በነፃነት መምረጥ መቻሉን መመልከታቸውን አስረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል ምርጫው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ስር ባሉ አካባቢዎች በተዘጋጁ ከሁለት ሺህ በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መካሄዱን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ሚጀና ለዶይቸ ቬለ በስልክ ተናግረዋል፡፡ መሳይ ተክሉ
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በድሬደዋ
በመጪው ኛው ሀገራዊ ምርጫ በድሬደዋ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መስርተዋል። በስምምነቱ ላይ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢዘገይም የጋራ ምክር ቤቱ መመስረት እና ሰነዱ መፈረሙ በከተማዋ የሚካሄደው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል። በመጪው ኛው ሀገራዊ ምርጫ በድሬደዋ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መስርተዋል። በስምምነቱ ላይ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢዘገይም የጋራ ምክር ቤቱ መመስረት እና ሰነዱ መፈረሙ በከተማዋ የሚካሄደው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል። ገዢው ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ በመጪው ኛው ሀገራዊ ምርጫ በድሬደዋ አስታዳደር ከሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘጠኙ ተገኝተው በመሰረቱት የጋራ ምክር ቤት ምስረታ መድረክ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ ቤት ኃላፊ አቶ ዚያድ ያሲን ፖለቲካ ፓርቲዎች ለመደማመጥ እና ለመከባበር ትኩረት መስጠት እናዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ የቅርንጫፍ ጽ ቤቱ ኃላፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች እስከታችኛው አደረጃጀታቸው አውርደው ለተግባራዊነቱ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ ቤት የክልል ምክር ቤት እጩ የሆኑት አቶ ዮናስ በትሩ ቢዘገይም ስምምነቱ መፈረሙ ጠቃሚ እና በከተማዋ የሚካሄደው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል፡፡ የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ተወካይ አቶ ጀማል ዑመር በበኩላቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የበለጠ ተቻችለን ከመተነኳኮል እና ከመወቃቀስ ይልቅ ያሉትን ችግሮች እየፈታን እንድንሄድ ያግዛል የሚል አስተያየት ሰተዋል፡፡ በድሬደዋ ለፌደራልና እና ለከተማዋ ምክር ቤት ህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሁለት የግል እጩ ተወዳዳሪዎች በምርጫው ይሳተፋሉ፡፡ መሳይ ተክሉ
የጅቡቲ ድሬዳዋ መስመር ተከፈተ
መስመሩን የዘጉት በአፋርና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰዉን ግጭት መንግሥት እንዲያስቆም የሚጠይቁ የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ነበሩ።በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን እንዳስታወቀዉ የመኪናና የባቡር መንገዶቹ ከትናንት ጀምረዉ ተከፍተዋል ለሁለት ቀናት ተዘግቶ የነበረዉ የድሬዳዋ ጅቡቲ የመኪናና የባቡር መስመር ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመረ።መስመሩን የዘጉት በአፋርና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰዉን ግጭት መንግሥት እንዲያስቆም የሚጠይቁ የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ነበሩ።በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን እንዳስታወቀዉ የመኪናና የባቡር መንገዶቹ ከትናንት ጀምረዉ ተከፍተዋል።ይሁንና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማበር፣ አንዳድ ቦታዎች የየአካባቢዉ ነዋሪዎች መንገድ እየዘጉ ለማለፍ የሚፈልጉ ሾፌሮችን ገንዘብ እንዲከፍሉ እያስገደዷቸዉ መሆኑን አስታዉቋል። መሳይ ተክሉ
ሾፌሮች ግን ገንዘብ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ ማሕበር ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ልጆቻቸው ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ወላጆች ድምጽ
ልጆቻቸው ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ወላጆች እና ቤተሰቦች ዛሬ ጠዋት በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ቢሮ በር ደጃፍ ጥያቄያቸውን አቀረቡ። ልጆቻቸው ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ በርከት ያሉ ወላጆች እና ቤተሰቦች ዛሬ ጠዋት በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ቢሮ በር ላይ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ወላጆቹ ልጆቻችን እስክሪብቶ እና ደብተር ብቻ ይዘው ለመማር ነው የሄዱት፣ አስመልሱልን የሚሉ ጥያቄዎችን በለቅሶ እና እንባ በታጀበ ድምፅ አሰምተዋል። ጥያቄ አቅራቢዎቹ ትግራይ ውስጥ የሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቹን ለመመለስ የነዳጅ ፍጆታ እንደሌላቸው መናገራቸውን የተባበሩት መንግሥታት ተነግሮናል ብለዋል። ከዚህ መነሻ የነዳጅ ፍጆታውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለመሸፈን ተስማምቶ ሚኒስቴሩ በተባበሩት መንግሥታት በኩል ሁለት ቦቴ ነዳጅ ማቅረቡን እና አውቶቡሶች ማዘጋጀቱን እንደገለፀላቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል። ሆኖም ከእሁድ እስከ ማክሰኞ ይመለሳሉ የተባሉት ተማሪዎች መውጣት ስላልቻሉ ለጥያቄ ዛሬ መውጣታቸውንም ወላጆች ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው ሁሉ መረጃ ለማግኘት ያደረግኩት ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ሰሎሞን ሙጬ
የኮሮና ተሕዋሲን የመከላከል አገልግሎትና ጥንቃቄ ቀስበቀስ እያንሰራራ መሆኑን የክልሉ የጤና ባለሙያዎች አስታወቁ።
አውዲዮውን ያዳምጡ። አብዛኛዉ ክትባት አስትራ ዜኒካ ነዉ ትግራይ ክልል ዉስጥ በሚደረገዉ ዉጊያና ግጭት ምክንያት ተዘንግቶ የነበረዉ የኮሮና ተሕዋሲን የመከላከል አገልግሎትና ጥንቃቄ ቀስበቀስ እያንሰራራ መሆኑን የክልሉ የጤና ባለሙያዎች አስታወቁ።ሐኪሞችና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ ክትባትም ለተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች እየተሰጠ ነዉ።ሕዝቡ ተሕዋሲዉን ለመከላከል የሚያደርገዉ ጥንቃቄ በመላላቱ ተሕዋሲዉ በተለይ በየመጠለያ ጣቢዎች በፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑን ተፈናቃዮች አስታዉቀዋል። ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ከተመድ ጽሕፈት ቤት ደጃፍ ተሰልፈዋል ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት
የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ተከታታዮችን በብዛት ያሳተፉ ሶስት ርዕሶች መርጠናል።የኤርትራ ፕሬዝደንት እና የትግራይ ምክርትል ርዕሠ መስተዳድር መግለጫዎች፣ የታገቱ ተማሪዎች፣ ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ዘገባና ወላጆች፣እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ናቸዉ። ጤና ይስጥልኝ እንደምን ሰነበታችሁ።ሳምንቱን የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ተከታታዮችን በብዛት ያሳተፉ ሶስት ርዕሶች መርጠናል።የኤርትራ ፕሬዝደንት እና የትግራይ ምክርትል ርዕሠ መስተዳድር መግለጫዎች፣ የታገቱ ተማሪዎች፣ ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ዘገባና ወላጆች፣እንዲሁም የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ናቸዉ።አብራችሁን ቆዩ የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባለፈዉ ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮ ኤርትራን ሥምምነት የድንበር ዉዝግቡ ያለበትን ደረጃ ጠቃቅሰዋል።የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሕወሓት ሊቀመንበርና የትግራይ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ለፕሬዝደንት ኢሳያስ አስተያየት አፀፋ የመሰለ መልዕክት ባለፈዉ ሮብ አስተላልፈዋል።ጉዳዩ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አስተያየት ሰጪዎችን የሳበ መስሏል። ብዙዎቹ አስተያየቶች ነቀፋ፤ ተራ ስድብ እና ርግማን የተፀባረቀባቸዉ ናቸዉ።ሰከን ያሉትን ለመምረጥ መክረናል። ተስፉ በርሄ በፌስ ቡክ በጣም የሚገርመው ጉዳይ የዚሕ ሰዉዬ ንግግር ነዉ። ብለዉ ይጀምራሉ የፕሬዝደንት ኢሳያስን ማለታቸዉ ነዉ። የራስዋ ኣሮባት የሰው ታማስላለች እንደሚባለው የኣገሩ ህዝብ ሰላምና ደህንነት ምንም ሳይመስለው ኣሁን ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ ሰላምና የምርጫ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ኣፉን ሞልቶ መናገሩ፣ ምን ያኽል ወዴታቸዉ የጠነከረና በኢትዮጵያ ጉዳይ እጁን ያስገባ መሆኑን በግላጭ ነግሮናል። እያሉ ይቀጥላሉ።ረጅም መልዕክታቸዉን በትግሪኛ ቋንቋ ባሰፈሩት መልዕክት ነዉ የዘጉት። አባ ኮስትር ጎድፌይ የተባሉት ደግሞ፤ ፕሬዝደንት ኢሳያስ የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ሁኔታ በከፋ ሁኔታ ላይ ነዉ ማለታቸዉ ሳያስቆጣቸዉ አልቀረም። አኛ እንዲህ እንድንናቆር ማን አደረገንና ነው አሁን አዛኝ መስሎ በከፋ ሁኔታ ላይ ነው የሚለው አባ ኮስትር ይሳደባሉም።አንደግመዉም። ስልጣኑን በቃኝ በልና ለአዲሱ ትውልድ አስተላልፍ ። ጨረሱ አባ ኮስትር። ሲራክ ባሕልቢ በቲዊተር ገፃቸዉ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ መግለጫ በኤኮኖሚ ላይ ያተኮረዉን መርጠዉ አስተያየት አስፍረዋል። ፕሬዝደንቱ ስለ ኤኮኖሚ ያስተላለፉት መልዕክት ግልፅና የማያሻማ ነበር ይላሉ ሲራክ በእንግሊዝኛ ባሰፈሩት ፅሁፍ፣ ዘላቂና የማይቀለበስ ምጣኔ ሐብት ስለመገንባት ነዉ እያሉ ይቀጥላሉ። የዳግም ባንቺ፣ አስተያየት የሕወሓት ሊቀመንበርና የትግራይ ምክርትል ርዕሠ መስተዳድር በሰጡት መግለጫ ላይ ያነጣጠረ ነዉ።ያዉ ትችት ነዉ። ህወሃት ፈርታለች ማለት ነው። አቅራራች ህውሃት። በ አቅጣጫ ድምጥማጧ ሊጠፋ ነው በዚሕ አላበቁም።እኛ ግን ሌላዉን አንጠቅስም። ባለፈዉ ሮብ ላሰራጨነዉ ዘገባ የኤርትራና የትግራይ እሰጥ አገባ የሚል ርዕሥ ነዉ የሰጠነዉ።ምክንያቱ የቃላት እሰጥ አገባ የገጠሙት የኤርትራና የትግራይ መሪዎች በመሆናቸዉ ነዉ።አንደለኝ አካሉ የተባሉ የፌስ ቡክ አስተያየት ሰጪ በጣም ያሳሰባቸዉ የዘገባዉ ይዘት፤ምክንያቱና መዘዙ ሳይሆን ርዕሳችን ነዉ። ዉዝግብ ካለ እንኳ የኢትዮጵያና የኤርትራ ተብሎ ነዉ የሚገለፀዉ ይላሉ የጋዜጠኞች አርታኢነት የሚዳዳቸዉ አስተያየት ሰጪ።ግን ስሕተት ነዉ።አስተያየት ሰጪ ሆይ። ተናጋሪዎቹ ኢትዮጵያን የሚወክሉ ሲሆኑ እርስዎ እንዳሉት እንላለን። ታዘባቸዉ ተስፉ ግን ባለስልጣን እንጅ ህዝብ ተጣልቶ አያውቅም ይላሉ ከሳቸዉ በፊት አስየያት የሰጠዉን ሲወቅሱ።አሚ መሐመድ ግን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ተባለ ወይም የኤርትራና የትግራይ ዉዝግቡን ለማስወገድ አለም አቀፉ ፍርድ ቤት የበየነውን መፈፀም ብቻ ነው መፍህቴው ባይ ናቸዉ። ባርኔጣ መለዮ የሚል የፌስ ቡክ ስም የደፉ አስተያየት ሰጪ ለየት ያለ ሐሳብ አላቸዉ። የኤርትራ ህዝብ አንድነቱ ፈራርሶ የትግሬ መጫዎቻና እግር ዓጣቢ ከመሆኑ በፊት በጉዳዩ ዓሥቦበት ከኢሣያሥ ጋር በመሆን እንደሃገር መኖር ካልሆነ ደግሞ የበለጠ መከራና ሥቃይ ሥደትና ዉርደት እየከፋ እንዳይሄድ ያለዉ ዓማረጭ ከኢትዮጵዮጵያ ህዝብ ጋር እንደቀድሞዉ ባይሆን እንኳን በፌዴሬሽን መተሣሠሩ በኢኮኖሚዉም በፖለቲካዉም የተሻለ ሥለሚሆን ቢያሥቡበት ይሻላል። አስተያየታቸዉ አለበቃም።በዚሕ ርዕስ ላይ እኛ አበቃን። ባለፈዉ ታሕሳስ ማንነታቸዉ ባልታወቁ ሰዎች የታገቱት የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉዳይ መንግሥትን እንዳስወቀሰ፣ ባለስልጣናትን እንዳስወገዘ፣ ሕዝብን ባደባባይ እንዳሰለፈ እነሆ ሶስተኛ ወሩን ያዘ።ልጆቹ ያሉበት ሥፍራ፣ሁኔታና የአጋቾቹ ማንነትም በገልፅ አልታወቀም።ጊዜ በጊዜ ሲተካ የይሆናል ግምቶች፣ የሴራ ትንታኔዎች፣ ከሁሉም በላይ የሐሰት ዘገቦች እየተሰራጩ ነዉ።በአብዛኛዉ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ የሐሰት መረጃዎች የተማሪዎቹ ወላጆችን ልብ እያደማዉ መሆኑን ባለፈዉ ሮብ ያነጋገርናቸዉ የሁለቱ ታጋቾች ወላጆች አስታዉቀዋል። የሚል ሐሽ ታግ የለጠፈ አንድ ዘለግ ያለ ፅሑፍ የተማሪዎቹ አጋቾች መንግሥት ነዉ ይላል።እገታዉን ከብሔር ጋር ያቆራኘዋልም።እንዲሕ ይነበባል አጋቹ መንግስታችን ሆይ ያለ ወንጀላቸው በማንነታቸው ምክንያት የታገቱ እህቶቻችንን ልቀቅልን አልን እንጅ ተማሪዎች አዘጋጅተህ በአብን እና በአንዳንድ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ትብብር የተፈፀመ የአጋች ታጋች ዶክመንተሪ ድራማ አዘጋጅልን አላልንህም ። የአብይ አስተዳደር እየሄደበት ያለው መንገድ ፍፁም ከመሳሳቱም በላይ ለታላቁ የአማራ ህዝብ ያለውን ከፍተኛ ጥላቻ እና ንቀት በግልፅ የሚያሳይ ነው ። በሚል ስም የሚጠሩ አስተያየት ሰጪ ደግሞ በፌስ ቡክ የአማራ ህዝብ ምንም ባልተረጋገጠ ሁኔታ ይህን ያህል ስሜታዊ ሆኖ በነቂስ በመትመም ሌሎችን በመዝለፉ፣ዝቅ በማለት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለበት። የሮ ጋሪ ናቸዉ ይሕን ያሉት። ተክለ፣ በበኩላቸዉ ድራማ ተሠራ ግን በሚፈለገው ደረጃ አላለቀም፡፡ በደንብ ሲዘጋጅ ይቀርባል፡ ጠብቁ፡፡ ቀጠሮ ይሰጣሉ የድራማዉ አዘጋጅ ይመስል።ከበደ ዳኜ የአማራ መስተዳድር ተቃዋሚ ፓርቲን ይወቅሳሉ። የአብን የፖለቲካ ጫወታ እንደ ነበረ ይታወቃል ብለዉ። አዲያ ኡስማን፤ የኛን ዘገባ ነዉ የወቀሱት። እናንተ ታዲያ የተጣራ መረጃ ከመንግስት አካል አጣርታችሁ አታቀርቡም፤ የፌስ ቡክ ወሬ ለቃቅማችሁ ከምታቀርቡ ይላሉ።አዲያ ዑስማን ዘገባችንን መስማታቸዉ ያጠራጥራል።እኛ የዘገብነዉ የሁለቱን ታጋቾች ወላጆች አነጋግረን ነዉ።የሚመለከታቸዉን የመንግስት ባለስልጣናት አስተያየት ለማካተት ያደረግነዉ ሙከራ አለመሳካቱንም ጠቅሰናል።የፌስ ቡክ ወሬ ከለቃቀምን የለቅመዉ በዚሕ ዝግጅት ነዉ።የዝግጅቱ ዓላማ ስለሆነ።እንጂ አቶ ወይም ወይዘሮ አዲ አስተያየት በሰጡበት ዘገባ አንድም የፌስ ቡክ ገፅ አልጠቀስንም።ተግባባን ወደ ሰሶስተኛዉ ርዕሥ እንለፍ።ሥለ አፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ፣ ዕቅድና ዉሳኔ የተሰጡ አስተያየቶች ናችዉ።የመረጥናቸዉን እናሰማችሁ። ስንታየው ገብረ ክርስቶስ፣ የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የአዲስ አበባ ነዋሪዋችን መንገድ እየዘጉ ከማሰቃየት ውጪ ምንም ፋይዳ የለውም። አንድም ፍሬ ነገር ጠብ አይልም። ከመሪዎቹ ጉባኤ ዋናዉ ርዕስ በአፍሪቃ ሕብረት አባል ሐገራት የሚደረጉ ግጭትችንና ጦርነቶችን ማስቆም የሚል ነበር። የጠመንጃዉን ላንቃ ለመዝጋት ወይም ጠመንጃዉን ዝም ለማሰኘት የሚል አማላይ ርዕስ ሰጥተዉታል። አብዱል መሊክ ናስር፣ ጥይት እንደ ሙዚቃ በሚሰማባት አፍሪካ ይሄ ቅዠት ነው በማለት ያጣጥሉታል።በፌስ ቡክ በሰጡት አስተያየት። ማሕደር ክፍሌ ደግሞ፣ መሪዎቹን እንዲሕ አሏቸዉ ምንም መፍትሄ ኣያመጡም። ኣበል ከመብላት ና ከመዝናናት በስተቀር። አልበርት ግርማ ግን፣ በፌስ ቡክ ለለጠፉት የጠመንጃና የብዕር ምስል በጠመንጃ ሳይሆን በዕዉቀት እናሸንፋለን የሚል ርዕስ ሰጥተዉታል።አንዋር አሕመድ የአልበርትን አስተያየት አልተቀበሉትም። ውውውይ ህልማችው ጥሩ ነበር ግን ቀን ላይ ሰው ሳይተኛ ህልም ያያል እንዴ ይጠይቃሉ። እንጃ ነጋሽ መሐመድ
የጆ ባይደን የአውሮጳ ጉብኝት ና ፋይዳው
ባይደን በአውሮጳ ቆይታቸው ብሪታንያ ባስተናገደችው ቡድን ሰባት በሚባሉት ባለፀጋ ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ፣ በሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ስብሰባ ላይ ተካፍለዋል። ከአውሮጳ ኅብረት ባለሥልጣናትም ጋር ተወያይተዋል። ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋርም ትናንት ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ውስጥ ውጤታማ የተባለ አካሂደዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአንድ ሳምንት የአውሮጳ ጉብኝታቸው አጠናቀው ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። ባይደን በአውሮጳ ቆይታቸው ብሪታንያ ባስተናገደችው ቡድን ሰባት በሚባሉት ባለፀጋ ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ፣ በሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ስብሰባ ላይ ተካፍለዋል። ከአውሮጳ ኅብረት ባለሥልጣናትም ጋር ተወያይተዋል። ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋርም ትናንት ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ውስጥ ውጤታማ የተባለ አካሂደዋል። ስለ ባይደን የአውሮጳ ጉዞ ውጤትና አንድምታው የብራሰልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ። ገበያው ንጉሴ
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ልዑክ በኢትዮጵያ ዉይይት
ዩናይትድስቴትስ በፅኑ አስግቶኛል ባለችው የትግራይ ክልል ቀውስ ላይ እንዲመክር ወደ አዲስ አበባ የላከችው ልዑክ ከኢትዬጵያ መንግስት መሪዎች ጋር ውይይት መጀመሩ ተገለፀ። በሴናተር ክሪስ ኩንስ የተመራው ልዑካኑ በኢትዬጵያ መንግስት ላይ ጫና የመፍጠር ተልዕኮ እንደሚኖረው ተመልክቶአል። ዩናይትድስቴትስ በፅኑ አስግቶኛል ባለችው የትግራይ ክልል ቀውስ ላይ እንዲመክር ወደ አዲስ አበባ የላከችው ልዑክ ከኢትዬጵያ መንግስት መሪዎች ጋር ውይይት መጀመሩ ተገለፀ። በአሜሪካ የኢትዬጵያ ኤምባሲ የቀድሞ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን ምክትል አምባሳደር ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሴናተር ክሪስ ኩንስ የተመራው ልዑካኑ በኢትዬጵያ መንግስት ላይ ጫና የመፍጠር ተልዕኮ እንደሚኖረው አመልክተዋል። በትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ኹኔታ ምክንያት በአሜሪካና በኢትዬጵያ መካከል በአሁኑ ወቅት ያለው ግንኙነት በውጥረት የታጀበ መሆኑን ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። ዘጋቢያችን ታሪኩ ኃይሉ ከአትላንታ ጆርጂያ ተጨማሪ ዘገባ አድርሶናል
የጆ ባይደን የአውሮጳ ጉብኝት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ተልዕኮዉ ጫና የመፍጠር ነዉ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የአፋርና ኢሳ የግዛት ዉዝግብ
በአፋርና ኢሳ ብሔረሰቦች መካከል በተለያዩ ጊዜያት አለመግባባትና ግጭት ሲከሰት ኖሯል። በምሥራቅ ኢትዮጵያ በአብዛኛዉ በከብት ርባታ ላይ ኑሯቸዉ የተመሰረተ ወገኖች የግጦሽ መሬትና ዉኃ ሲያጋጫቸዉ መኖሩ ግልፅ ቢሆንም ጠንካራ በሆነዉ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስልታቸዉም በሀገሪቱ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸዉ። እንዲያም ሆኖ ግን አሁንም ዉዝግቡ እልባት አላገኘም። ከሳምንታት በፊት ኢሳዎች የወሰን አከላለል ጉዳይ በሚመለከት ለፌደራል መንግስት አቤቱታ አቅርበዋል፤ የአፋር ተወላጆች በበኩላቸዉ ቦታዉ የማን እንደሆነ ለመረዳት ከመንግሥት ዶሴዎች በተጨማሪ ስያሜያቸዉን ማየት ነዉ ይላሉ። አፋርና ኢሳ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢ ተጎራብተዉ የሚኖሩ ብሔረሰቦች ናቸዉ። ከቋንቋ በቀር ሃይማኖትን ጨምሮ በአኗኗር ዘይቤያቸዉ ማለትም በባህል፤ በኤኮኖሚ ምንጭና በመሳሰሉት አንዱን ከሌላዉ ለመለየት ያዳግታል። በመካከላቸዉ በግጦሽ ቦታና ዉሃ ምክንያት ግጭቶች ይነሱ ነበር ዛሬም አልጠፋም። ወትሮ የነበረዉን ባህላዊ ግጭት የሚሉት የዚያዉ አካባቢ ተወላጆች ማለት ነዉ የተለመደና እያደርም ሲሰክን የታየ ጉዳይ ነዉ። ከጣሊያን ወረራ ወዲህ ግን ይላሉ ከአፋር ተወላጆች አንዱ የሆኑት አቶ ዑመር አሊ ይዘቱ ተለዉጧል፤ እነዚህ ወገኖች ከመሠረተ ልማት አንፃር አኗኗራቸዉ ያልተሻሻለ፤ የኑሯቸዉ መሠረት የሆኑት ከብቶቻቸዉ እንኳ በቂ ግጦሽ እና ዉሃ የሚያገኙበት ሁኔታ ዉሱን መሆኑን ያመለከቱት አቶ ዑመር እኩል ችግር የሚያዩ ቢሆኑም አንዱ የሌላዉን ወሰን ሳይገፋ ለመኖር አለመቻላቸዉን ነዉ የገለጹት። አፋርና ኢሳ በሚገኙበት እያንዳንዳቸዉ የራሴ የሚሉት የታወቀ አካባቢ አላቸዉ። አካባቢዉን በሚገባ እንደሚያዉቁ የሚናገሩት አቶ ዑመር የቦታዎቹ ስም አሰያየምም ራሱ የትኛዉ አካባቢ የአፋር ወይም የኢሳ መሆኑን ይናገራል። በእነዚህ ማስረጃነትም የሁለቱ የክልል መንግሥታት አለመግባባቱን መፍታት ይችላሉ ሲሉም ይገልጻሉ። አዳዲስ የወሰን አከላለል እና የቦታዎች ይገባኛል ጥያቄዎች ከጀርባቸዉ የያዙት ነገር አለ ሲሉም አቶ ኡመር አሊ እንዲህ ያስረዳሉ። የኢሳ ብሄር አባላት በቅርቡ ለፌደራል መንግሥት ያቀረቡት ደብዳቤ የወሰን አከላለልን ይመለከታል። በወቅቱም በጉዳዩ ላይ ተሰባስበዉ መወያየታቸዉን መዘገባችን ይታወሳል። አፋርና ኢሳ አንድ ከሚያደርጓቸዉ ነገሮች መካከል ባህላዊ የግጭት አፈታት ስልታቸዉን መጥቀስ ይቻላል። በብዙ መንገድ የተሳሰሩት እነዚህ ወገኖች መቋጫ ያጣ የሚመስለዉን ዉዝግብ ይህን ስልት ተጠቅመዉ ለመፍታት አልሞከሩ ይሆን ሸዋዬ ለገሠ
የቀይ ባህር አፋር ድርጅት መግለጫ
የድርጅቱ አመራር አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ የኤርትራ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሚወስዳቸው እርምጃዎች የቀይ ባህር አፋሮችን እንደሚገድል እንደሚያስርና ከቀያቸው እንዲሰደዱ እንደሚያደርግ ተናግረዋል ። የኤርትራ መንግሥት ባለፈው ሐምሌ አጋማሽ ላይ ወደ የመን በመጓዝ ላይ የነበረች አንዲት አነስተኛ መርከብ በሚሳይል መጥቶ በውስጧ የነበሩትን የቀይ ባህር አፋር ወጣቶችን ገድሏል ሲል የቀይ ባህር አፋር ተራድኦ ድርጅት አስታወቀ ። የድርጅቱ አመራር አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ የኤርትራ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት በሚወስዳቸው እርምጃዎች የቀይ ባህር አፋሮችን እንደሚገድል እንደሚያስርና ከቀያቸው እንዲሰደዱ እንደሚያደርግ ተናግረዋል ። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኘው የአዲስ አባባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ። የቀይ ባህር አፋር ተራድኦ ድርጅት ስላወጣው መግለጫ የኤርትራን መልስ ለማግኘት ለኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ ደውለን ወደ ኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መርተውን ነበር ። ሆኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናትን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
የጀርመን የልማት ድጋፍ በአፋር
ከሚከናወኑት የልማት ሥራዎች መካከል በአፋር ክልል የሰመራ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በሎግያ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታ ይገኙበታል ። ኢትዮጵያ ውስጥ በጀርመን መንግሥት ድጋፍ ከሚከናወኑት የልማት ሥራዎች መካከል በአፋር ክልል የሰመራ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በሎግያ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታ ይገኙበታል ። እነዚህኑ የልማት ተግባራት በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ሊዘሎረ ሲሩስና ባልደረቦቻቸው ሰሞኑን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው ። ከቡድኑ ጋር አብሮ የተጓዘው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ስለ ፕሮጀክቶቹ ውጤት ሥራው የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ። ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
በጀርመን ለሥራ ፈጠራዋ የተሸለመችዉ ኢትዮጵያዊ
በመላ ቡና በአሁን ሰዓት አምስት አባላት አሉት። የሚጠቀመው የኢትዮጵያን ቡና ሲሆን፤ ወደፊት የኮሎምቢያ እና የቬትናምንም ቡና የማስመጣት እቅድ አለው። የ ዓመቷ ኤልዳና ኑሮዋን በጀርመን ካደረገች ስምንት አመታት ተቆጥረዋል። በዚህ መሀል ለአንድ አመት ወደ ታይላንድ በመሄድ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና የሥዕል ትምህርት የማስተማር ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጥታለች። ወደ ጀርመን ተመልሳም የሁለተኛ ዲግሪዋን በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስተዳደር ማለትም ማኔጅመንት አጠናቃለች። ከዚህም በተጨማሪ ኤልዳና ከውጭ ሀገር አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር በመሆን ወደ ኢትዮጵያ እና ታይላንድ የሚጓዙ አገር ጎብኚዎችን በመላክ ዘርፍም እንደሠራች ትገልፃለች። በመጨረሻ ግን በቡና ንግዱ ለመፅናት ወስናለች። ልምዱን የቀሰመችው ደግሞ በተለያየ መንገድ ነው።
በሲዳማ ክልል የኮሮና ወረርሽኝ ተባብሷል
በሲዳማ ክልል አየተስፋፋ የመጣው የኮቪድ ወረርሽኝ የህክምና ተቋማት አልጋዎች በበሽታው ታማሚዎች እንዲሞሉ ፣ የመተንፈሻ ኦክስጅን አጥረት እንዲባባስ ምክንያት እየሆነ ይገኛል ሲሉ የክልሉ ባለስልጣናት አስታወቁ። በሲዳማ ክልል አየተስፋፋ የመጣው የኮቪድ ወረርሽኝ የህክምና ተቋማት አልጋዎች በበሽታው ታማሚዎች እንዲሞሉ ፣ የመተንፈሻ ኦክስጅን አጥረት እንዲባባስ ምክንያት እየሆነ ይገኛል ሲሉ የክልሉ ባለስልጣናት አስታወቁ ። በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና መምህራን ዛሬ የጎዳና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ቅስቀሳ ባደረጉበት ወቅት የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ በየነ በራሳ መሰረታዊ የጥንቃቄ መርሆችን ባለማክበራችን በአሁኑ ወቅት በሽታው ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል ብለዋል። ሸዋንግዛው ወጋየሁ
አዳዲሶቹ መተግበሪያዎች የኢትዮጵያን የሙዚቃ ገበያ ይታደጉታል
የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የገባበትን የግብይት ችግር በመፍታት የፈጠራ ባለሙያዎች የሚገባቸውን ክፍያ እንዲያገኙ የታቀዱ ሁለት መተግበሪያዎች ሥራ ላይ ውለዋል። ገደማ ድምፃውያን ሥራዎቻቸው በመተግበሪያ ለሽያጭ እንዲቀርብ ውል መግባታቸውን የተናገረው የአውታር መልቲሚዲያ ሥራ አስኪያጅ ጆኒ ራጋ ደንበኞቻቸው ሺሕ መድረሳቸውን አስረድቷል አውታር መተግበሪያ ከሁለት አመታት ገደማ በፊት በአራት ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ሙዚቃ ለመሸጥ ሥራ ሲጀምር በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ ነበር። ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ኤልያስ መልካ፤ ዮሐንስ በቀለ ጆኒ ራጋ ኃይለሚካኤል ጌትነት ኃይሌ ሩትስ እና ዳዊት ንጉሴ የተባሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች በጥምረት ያቋቋሙት አውታር መልቲ ሚዲያ የተባለ ኩባንያ በታላቅ ተስፋ መተግበሪያውን ቅንጡ የእጅ ስልኮች ለሚጠቀሙ ኢትዮጵያውያን ይፋ ቢያደርግም ሥራው እንደታሰበው አልሰመረም። በግንቦት ብንጀምርም ከዚያ በኋላ የመጀመሪያው መተግበሪያ ብዙ ቴክኒካዊ ፈተናዎች ነበሩት። እሱን አስተካክለን ከእንደገና ሌላ መተግበሪያ አዘጋጅተን አሁን ያለፈው መስከረም ነው በትክክል የጀመርንው ሲል የአውታር መልቲ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ ዮሐንስ በቀለ በመድረክ ስሙ ጆኒ ራጋ ሒደቱን ለዶይቼ ቬለ አስረድቷል። ይኸ መንገራገጭ ግን የአውታር መልቲ ሚዲያ ሰዎችን የሚያቆም አልሆነም። የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ዮሐንስ በቀለ ጆኒ ራጋ እንደሚለው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሙያ የሚገባውን ፍትሐዊ ክፍያ እንዲያገኝ ማድረገ ከተፈለገ ሌላ አማራጭ መንገድ አልነበረም። በሲዲ በኩል የመጣው የገበያ ሥርዓት ራሱን አጥፍቶ፤ ፕሮዲውሰሮች ከኢትዮጵያ ምድር ጠፍተው ከኋላ ደግሞ የብዙ ባለሙያዎች መብቶች ተዘርፈው፤ ባለ መብት ነን የሚሉ ሰዎች ከሰሩት ሥራ የሚያተርፉበት መንገድ ተዘግቶ አጭበርባሪ ነጋዴዎች ብቻ የሚያተርፉበት ሥርዓት ይዞ ነው የመጣው የሚለው ጆኒ ራጋ በቴክኖሎጂው ረገድ በአመታት የታየው ለውጥም በኢንዱስትሪው ተፅዕኖ እንዳሳረፈ ያምናል። ጆኒ በጣም ብዙ ሥራዎችን የሰሩ ትላልቅ የሙዚቃ ሰዎች በታመሙ ቁጥር ብር እየሰበሰብን ፤እየረዳን እና እየተረዳን የቆየንበት፤ ሙዚቃ ራሱን ያልቻለበት፤ አንድ ሰው የሰራውን ሙዚቃ ሸጦ የማያተርፍበት፣ ብዙ ሰው ከሙዚቃ ገበያ የወጣበት ቦታ ላይ ነው ያለንው። አገሪቷ በሙዚቃው ዙሪያ ከዚህ በላይ ልትወድቅ አትችልም። የባለሙያዎች መብት የማይከበርበት፣ የሚጣስበት፤ ሙዚቃው አለ የማይባልበት ደረጃ ላይ ነው የቆየንው። እኔን ጨምሮ ብዙ የሙዚቃ ሰዎች ከሙዚቃ የራቁት በዚያ ምክንያት ነው ሲል ውስብስብ የዘርፉን ችግሮች እየነቀሰ የግብይት ሥርዓቱን ከመቀየር ውጪ አማራጭ እንዳልነበር ይሞግታል። የኃይሉ መርጊያ ተወዳጅ የሙዚቃ ሥራዎች ዩቲዩብን ጨምሮ በተለያዩ የኢንተርኔት ገፆች በሕገ ወጥ መንገድ ተሰራጭተው ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ከገጠሟቸው ፈተናዎች አንዱ ይኸን መሰሉን ስርጭት ማስቆም ይሆናል። የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ እንዲህ አይነት ውስብስብ የግብይት ማጥ ውስጥ የገባው ቀደም ብሎ ነው። የሙዚቃ ገበያው ንቁ በነበረባቸው አመታት የዜማ እና ግጥም ደራሲዎችን አሰባብስቦ፣ ድምፃዊ እና ባንድ ለይቶ፣ ገንዘብ መድቦ ሙዚቃ የመሥራቱ ሚና በአሳታሚዎች የሚከወን ነበር። የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማሕበራት ኅብረትን በፕሬዝዳንትነት የሚመሩት አቶ ዳዊት ይፍሩ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ገበያው ይከተል የነበረው አሰራር ከሙዚቃ ባለሙያዎች ይልቅ ለአሳታሚዎች ያደላ ነበር። አሳታሚው ነጋዴ ነው። ነጋዴ ሁል ጊዜ ከትርፉ ጋር ነው የሚሔደው። ያዋጣኛል፣ ያተርፈኛል የሚለውን ዜማ እና ግጥም በራሱም ይሁን ከሰው ጋር ተማክሮ ያገኛል። ከዚያ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ተደማጭነት አለው ብሎ ያመነበትን ድምፃዊ ካገኘ የዛን ጊዜ ገንዘቡን ወደ ማውጣት ይሔዳል። ገንዘቡን አውጥቶ በአግባቡ ተቀርፆ ለሰው ጆሮ ተደማጭ እንዲሆን ለማድረግ በዘመኑ ተደማጭነት ካለው ባንድ ጋር መነጋገር አለበት። ከዚያ ባንድ ጋር ተነጋግሮ ከፍሎ ያሰራል። ያ ሥራ ከተሰራ በኋላ ማንኛቸውም ከዚያ በኋላ የሚከፈላቸው ነገር የለም። ለዚያች ሥራ ብቻ ይከፈላል። ሁሉም የየድርሻቸውን ይወስዳሉ። ከዚያ በኋላ ያለው ያሳታሚው ሥራ ነው። እንደ ዕድል ሆኖ በጣም የተወደደ ከሆነ ይኸንን ያሳተመው ሰውዬ በጊዜውም ተጠቃሚ ይሆናል። ለሚቀጥሉትም አመታት በሙሉ እያሳተመ የመሸጥ መብት አለው ሲሉ የቀደመው የሙዚቃ ገበያ ይከወን የነበረበትን አካሔድ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች የሚገባቸውን ጥቅም ለመጠየቅ ገፋ አድርገው አደባባይ የወጡት በ ዎቹ ነበር። በወቅቱ የሙዚቃ ሲዲዎች በሕገ ወጥ መንገድ እየተባዙ ገበያውን ማጥለቅለቃቸው ለተቃውሞው አንደኛው ምክንያት ነበር። አቶ ዳዊት ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ጊዜው የቀደመው ሥርዓት አግባብ አለመሆኑን ባለሙያዎቹ የተረዱበት ስለ ቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ጽንሰ ሐሳብም ግንዛቤ ያገኙበት ነበር። አቶ ዳዊት ብዙዎቹ ሥራ ይሰራሉ፤ ይሸጣል። አምስት ሺህ ብር የሚከፈለውም ይከፈላል፤ አስር ሺሕም የሚከፈለው ይከፈላል። ያቺን ከጨረሰ በኋላ ሁለተኛ ሥራ ካልሰራ ጾሙን ማደሩ ነው። የኮፒ ራይት መብት የሚባለው ጽንሰ ሐሳቡንም ያወቅንው የዛን ጊዜ ነው። በ ዎቹ አካባቢ ብዙ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ። ብዙዎቹ በሥራችን ተጠቃሚ አይደለንም የሚል የመብት ጥያቄ አነሱ። የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች አዋጅ ወጣ ይላሉ። የፈጠራ ባለቤትነትን ያስከብራል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የቅጅ እና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ሕግ የወጣው ከሙዚቃ ባለሙያዎቹ ግፊት በኋላ በ ዓ ም ነው። እንደተጠበቀው ግን ሕጉ በተጨባጭ የቀየረው ነገር እንዳልነበረ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። ጆኒ ራጋ በተለይ ከአዋጁ መውጣት በፊት በተደረጉት ሰልፎች የቀረበው ጥያቄ ከባለሙያዎች ይልቅ ለሙዚቃ አሳታሚዎች ጥቅም መከበር ያዘነበለ ነበር ሲል ይተቻል። በሰልፉ መባል የነበረበት የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ይከበሩ ነበር የሚለው ጆኒ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየው ኤልያስ መልካ ጋር በመተባበር የሙዚቃ ሥራዎች በየገበያ ማዕከሉ የሚሸጡበት አገር ኦሪጅናል የተባለ የግብይት ሥርዓት ለመጀመር ሙከራ አድርጎ ነበር። የባለሙያዎቹ ሙከራ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ ቀርቷል። ባለሙያዎቹን የወተወቱት እና የሮያሊቲ ክፍያ እንዲፈጸም የሚያስገድደው ማሻሻያ አዋጅ የወጣው ግን ዘግየት ብሎ በ ዓ ም ነው። ጥቅማቸውን ለማስከበር ባለሙያዎቹ የሙያ ማኅበራት ጭምር አቋቁመዋል። ተራው ግብይቱን መቀየር ነው። የሞተ ገበያ ላይ ያለን ብቸኛ አማራጭ አዲስ ነገር መፍጠር ነው የሚለው ጆኒ ራጋ አውታርን በመሳሰሉ መተግበሪያዎች ሙዚቃን ለሽያጭ በማቅረብ ግብይቱን ለመቀየር መቁረጣቸውን አስረድቷል። ቴዲ አፍሮ በሚለው የመድረክ ስሙ ይበልጥ የሚታወቀው ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ አልበም በአውታር አንድ ነጠላ ሙዚቃ በሶስት ብር፤ በሲዲ ብር የሚከፈልበት ሙሉ አልበም ደግሞ በ ብር ይሸጣሉ። ጆኒ እንደሚለው ሙሉ አልበም ከሥራው ክብደት አኳያ የአውታር መተግበሪያ የግዴታ አልበም እንዲገዛ የሚያበረታታ መሆን ነበረበት። አርቲስት፣ የፈጠራ ሥራ አመንጪ፣ ሙዚቀኛ የምንለው አካል በቀላሉ የሰራውን ሥራ ኪሱ ሳይጎዳ ለገበያ የሚያቀርብበት፣ ተጠቃሚውም በፈለገው ጊዜ፣ በፍጥነት፣ በቀላል እና በርካሽ የፈለገውን ሙዚቃ የሚያገኝበት፣ ያም ሲሸጥ አርቲስቱ ብዙ ትርፍ የሚያገኝበት፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አመት እና አመት ወደ ኋላ እየተመለሰ ይኸን ሙዚቃ የሰራው ሰው ማነው ተብሎ ለሰራው ሰው፤ እሱ ባይኖርም ለወራሾቹ መብት የሚተላለፍበትን መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው አውታር ያመጣው ይላል ጆኒ መተግበሪያው ያመጣውን ለውጥ ሲያስረዳ። ኢትዮጵያውያን ደንበኞች መተግበሪያውን ወደ እጅ ስልኮቻቸው ጭነው ከተመዘገቡ በኋላ በኢትዮ ቴሌኮም በሚገዙት ካርድ ወይም ከቴሌኮም አቅራቢው ባላቸው አገልግሎት በኩል ሙዚቃዎች መሸመት ይችላሉ። ከዚያ ባሻገር አሞሌ እና ሔሎ ካሽን በመሳሰሉ የባንኮች የክፍያ ሥርዓቶችም ከአውታር ሙዚቃ መግዛት ይቻላል። ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚኖሩ ደንበኞች ማስተር ካርድ እና ቪዛን በመሳሰሉ የክፍያ ሥርዓቶች ደንበኞች ለሚገዟቸው ሙዚቃዎች ክፍያ እንዲፈጽሙ የተመቻቸ ቢሆንም ጆኒ መተግበሪያው ሊስተካከሉ የሚገቡ እንከኖች እንዳሉት አስረድቷል። እንደ ጆኒ አባባል ከሆነ የገበያውም አቀባበል መልካም ነው። ገበያው በጣም ክፍት ነበር። እኛ ስንጀምር በ ቀናት ነው ወደ ሺሕ ደንበኛ ያገኘንው። ከዚያ በኋላ መተግበሪያው ቴክኒካዊ ችግሮች ገጥመውት ቆመ። አሁን ወደ ሺሕ አካባቢ ደንበኞች አሉን። በ ዓ ም አንድ ሚሊዮን ደንበኛ እንዲኖረን አቅደን እየሰራን ነው። አውታር ደንበኞቹን አንድ ሚሊዮን ለማድረስ በርካታ ፈተናዎች ይጠብቁታል። በተለይ መተግበሪያው ይታዩበታል የተባሉ ቴክኒካዊ ችግሮችን በዘላቂነት መቅረፍ እና ለአጠቃቀም ቀላል ማድረግ ቀዳሚ ሊሆኑ እንደሚገባ የተጠቀሙበት ሁለት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለዶይቼ ቬለ ጥቆማ ሰጥተዋል። ኩባንያው ከ በላይ ሥመ ጥር እና ወጣት ሙዚቀኞች በመፈራረም ሥራዎቻቸው በመተግበሪያው ለሽያጭ እንዲቀርብ ማድረግ እንደቻለ የገለጸው ጆኒ በምንም አይነት ሌብነትን የማያበረታታ መተግበሪያ ነው። ለአንድ ሰው መላክ ስትፈልግ ኢንክሪፕትድ ነው። በተዓምር አይልክልህም። ከፍለህ ነው የምትገዛው። ግብይቱ በጣም ግልጽ ነው። ሰዉ ቤቱ ቁጭ ብሎ በስልኩ ምን ያክል እንደሸጠ የሚቆጣጠርበት መንገድ አለው ይላል። አፕል እና ስፖቲፋይን የመሳሰሉ ኩባንያዎች ይፋ ያደረጓቸው መተግበሪያዎች ባደጉት አገሮች ሰዎች ሙዚቃ የሚሸምቱበትንም ሆነ የሚያደምጡበትን መንገድ ቀይረውታል። እንደ አውታር ተመሳሳይ ግልጋሎት ለመስጠት በቅርቡ ይፋ የሆነው ባና የሙዚቃ መተግበሪያም በገበያው ይገኛል። ማድ ቴክኖሎጂስ የተባለ ጀማሪ ኩባንያ ከካዛና ግሩፕ በመተባበር ያዘጋጀው መተግበሪያ ሥራ የጀመረው ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ከ አመታት ገደማ በኋላ ለአድማጭ የቀረበውን የሙዚቃ አልበም ለሽያጭ በማቅረብ ነበር። የባና ሙዚቃ የሽያጭ ኃላፊ ብሌን መኮንን ባለሙያዎች ሥራዎቻቸውን በቀላሉ ለገበያ አቅርበው ግልጽ በሆነ የሽያጭ ሥርዓት ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ ማስቻል ዋና ዓላማቸው መሆኑን ለዶይቼ ቬለ ተናግራለች። ብሌን መኮንን አሁን ከአርቲስቶች ጋር ሥምምነት በመፈራረም ላይ ነን። ስለዚህ የተጨማሪ አርቲስቶች ሥራዎች በመተግበሪያው ወደ ፊት ይቀርባሉ። በክፍያ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ነው ሥምምነት ያለን። አሁን ለምሳሌ የጥላሁን አልበም ብር ነው። ስለዚህ ስልክህ ላይ መጀመሪያ ብር መኖር አለበት። ከዚያ በኋላ ዳውንሎድ በተኑን ሲጫኑ ብር ይቆርጣል። ከዚያ በኋላ ኦፍላይንም ሆነ ኦንላየን ለማድመጥ ይቻላል ስትል የባና ደንበኞች እንዴት ከሙዚቃ መተግበሪያው እንደሚሸምቱ አብራርታለች። በባና መተግበሪያ ሸማቾች የገዙትን ሙዚቃ በስልኮቻቸው የኢንተርኔት ግልጋሎት ሳይኖር ጭምር ማድመጥ ይችላሉ። ይሁንና የሙዚቃ ሰነዱን እንደ አውታር ሁሉ ሰዎች አንዱ ለሌላው መላክ አይችልም። ይኸ የባለሙያዎቹን መብት ለማስጠበቅ እና ሕገ ወጡን ዝውውር ለመግታት ያለመ እርምጃ ነው። እሷ ራሷ ድምፃዊት የሆነችው ብሌን ባና እና አውታርን የመሳሰሉ መተግበሪያዎች ለባለሙያዎቹ ሊሰጡ ስለሚችሉት ጥቅም ጥርጣሬ ባይኖራትም ገበያውን በማለማመድ ረገድ ግን ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ ግን ተናግራለች። እውነት ለመናገር በጣም ብዙ የሚሰራ ሥራ አለ ብዬ አስባለሁ። ለእነደዚህ አይነት ነገር ሰው አዲስ ነው። የዩቲዩብ ገበያ የኢትዮጵያን ሰው ዘልቆ እስኪገባ በጣም ቆይቷል። አሁን ግን ሰው ሁሉ ዩቲዩብ ላይ ገብቶ ሙዚቃ መስማት ጀምሯል። ይኸ ግን ረዥም ጊዜ ወስዷል። በተመሳሳይ ይኸ የሙዚቃ መተግበሪያዎች በደንብ ሰው እስኪለምደው በደንብ ሥራ መሰራት እንዳለበት ነው የተረዳንው። የኢትዮጵያን ሙዚቃ በተለያዩ ዘመናት ጠንቅቀው የሚያውቁት የሮሐ ባንዱ አቶ ዳዊት ግብይቱ ለገባበት ቅርቃር መፍትሔ ለማበጀት ባለሙያው ሊታገል እንደሚገባ በአፅንዖት ያስረዳሉ። ተበደልኩ እያለ የሚያለቅሰው ባለሙያ ችግሩን ለመቅረፍ በጋራ እንስራ ሲባል ብቅ አይልም እያሉ የሚሸነቁጡት አቶ ዳዊት በተለይ ከወጣቶች ብዙ ይጠብቃሉ። እሸቴ በቀለ
ከኤኮኖሚው ዓለም፦ አዳዲሶቹ መተግበሪያዎች የኢትዮጵያን የሙዚቃ ገበያ ይታደጉታል ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የጨረቃ መንደርና የሳተላይቶቹ መጻኤ
በኅዋው ሳይንስ ከፍተኛ እመርታ ካስመዘገቡ የለማችን ተቋማት መካከል ግንባር ቀደሙ የአውሮጳ የኅዋ ምርምር ማዕከል የጨረቃ መንደር ምስረታ እና ሳተላይቶች ላይ የተጋረጡ ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል መክሯል። የአውሮጳ የኅዋ ምርምር ማዕከል ረቡዕ፤ ጥር ቀን ዓ ም ዓመታዊ ፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ውስጥ ዓመታዊ ጋዜጣዊ መግለጫውን ሰጥቶ ነበር። በኅዋው ሳይንስ ዘርፍ የማዕከሉ ያለፉ ሥራዎች እና የወደፊት ዕቅዶችን የዳሰሰ ነበር መግለጫው። የተቋሙ የወደፊት ዕቅዶቹንም አስቃኝቷል። የጨረቃ መንደር ምስረታ እና ሳተላይቶች ላይ የተጋረጡ ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚቻልም የምርምር ማዕከሉ መክሯል። ከኅዋ ላይ ሆኖ ከርሰ ምድርን በሺህ ኪሎ ሜትሮች ጥልቀት ግሉ ብረቷን ከሚዳስሰው ሳተላይት አንስቶ በጥልቊ ኅዋ ድምጽ አጥፍቶ እስከሚከንፈው ሳተላይት ድረስ ብዙ ተብሏል። ከሳተላይቶች የወደፊት ዕጣ አንስቶም ጣሊያንን የመታው ብርቱ ርእደ መሬትን እስከተነተነው ሳተላይት ማብራሪያ ተሰጥቷል። ነሐሴ ቀን ዓም ጣሊያን ውስጥ የተከሰተው ብርቱ የመሬት መንቀጥቀጥ የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል። ከጣሊያን እንብርት የአፔኒነስ ተራሮች የተነሳው በሬክተር ስኬል የተመዘገበው ርእደ መሬት የ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ ይታወሳል። ርእደ መሬቱ በትክክል የተቀሰቀሰበት ቦታ እና ያደረሰውን ጥፋት ሴንቲኔል አንድ ኤ በተሰኘችው ሳተላይ በመታገዝ የአውሮጳ የኅዋ ማዕከል ዝርዝር መረጃዎችን ሰጥቷል። ሴንቲኔል አንድ ኤ ወደ ኅዋ የተወነጨፈችው እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ ነው። ሳተላይቷ ኅዋ ላይ የምትንቀሳቀስበት ኃይል ከፀሐይ እንድታገኝ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ሳህን ተዘርግቶላታል። ይህ የኃይል ማመንጫ ሳህን ግን ከሁለት ዓመት በኋላ የሚያመነጨው ኃይል መቀነሱን ሳይንቲስቱ ደርሰውበታል። ምንም እንኳን የኃይል ማመንጫው ከፊል ብልሽት ሳተላይቱ ሥራውን ባያስተጓጉለውም ኅዋ ላይ በሚወረወሩ በርካታ ስብርባሪዎች ዳግም ጉዳት እንዳያደርስበት ሊጤን እንደሚገባም በመግለጫው ወቅት ተገልጧል። ፒ ቹሪዩሞቭ ጌራሲሜንኮ የተሰኘው የኮከብ ስባሪ ግዛትን ለማሰስ ከ ዓመታት በፊት ወደ ኅዋ የተወነጨፈችው የሮዜታ ተልዕኮም መስከረም ቀን ዓመት ከረፋዱ ሰአት ከ ደቂቃ ላይ ተግባሯ አክትሟል። ኮከብ ስባሪ ላይ ተወርውራ በመላተምም እዛው ከስማለች። ሮዜታ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ጥር ላይ እንድትነቃ ከመደረጉ አስቀድሞ በጥልቊ ኅዋ ውስጥ ለ ወራት ሁሉ ነገሯን አጥፍታ ከተግባር ውጪ ኾና ነበር። ሮዜታ የከዋክብት ስባሪዎች ምኅዋርን ቀርባ በማጥናት የመጀመሪያዋ ሳተላይት ናት። ሳተላይቶች የመጨረሻ ግባቸውን ሲመቱ እዛው ኅዋ ላይ እንዲከስሙ ነው የሚደረገው። ሮዜታ ሳተላይት ተላትማ ራሷን በራሷ ከማክሰሟ በፊት የነበረውን ምስል መስከረም ቀን ዓ ም ማለዳ ላይ ልካለች። ይህም በመግለጫው ተጠቅሷል። የአውሮጳ ኅዋ ተቋም በዋና ኃላፊው ያን ቮርነር በኩል ስለ ጨረቃ መንደር ምሥረታ ምን እየተደረገ እንደሆነም ይፋ አድርጓል። የጨረቃ መንደር በጽንሠ ሐሳብ ደረጃ ያለ ነው። ያ ማለት እኛ እንደ አውሮጳ የኅዋ ተቋም ጥሪ ያስተላለፍነው በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች አካላት ወደ ጨረቃ ተጉዘው እዚያ ከእኛ ጋር በጋራ እንዲሠሩ ነው። ያን ስንል እያንዳንዱ ነገር በዝርዝር አለን ማለት አይደለም። ግን ጨረቃን እንደ ማዕድን ቁፋሮ፣ ቱሪዝም፣ ሣይንስ እና የጨረቃ ሣይንስ ላሉ ለተለያዩ እንቅስቃሴዎች ለመጠቀም ነው። ከዚያም ባሻገር ወደ እኛ ሥርዓተ ፀሐይ ዘልቆ ለመግባት እንደመንደርደሪያም ለመጠቀም ነው። ኤክሶማርስ ሳተላይትን በተመለከተም መግለጫ ተሰጥቷል። ኤክሶማርስ ወደ ኅዋ የተወነጨፈች እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠርበ ዓመት ነው። በ ግን ኤክሶማርስ ተሸክማው የምትዘው በሮቦት እገዛ ማርስ ላይ ቁፋሮ የሚያከናው ሮቨር በዝግታ እና በተረጋጋ መልኩ እዛው ማርስ ላይ ማረፍ ይጠበቅበታል። ኤክሶማርስ የማርስ ንፍቀ ክበብ ውስጥ ስትገባ የጫነችው ሳተላይት እውስጡ የተገጠመው ኮምፒውተር ሞተሩ ለሦስት ሰከንድ ብቻ ከሠራ በኋላ እንዲጠፋ በማድረጉ ሳተላይቱ የማርስ ንጣፍን የረገጠችው በከባድ ምት ነበር። እንደ ዕቅዱ ቢሆን ኖሮ ሳተላይቱን የጫነችው መንኲራኲር መጀመሪያ የማርስ ንፍቀ ክበብ ውስጥ እየከነፈች ጥሳ ትገባለች። በከፍተኛ ፍጥነት ስትከንፍም ነበልባላዊ ግለት ይፈጠራል። ግለቱን መከላከያውም ከሳተላይቱ ተነጥሎ ይወድቃል። ሳተላይቱ ፍጥነቱን ለማረጋጋት ግዙፍ ዣንጥላ ትዘረጋለች። ከዚያም ፍጥነቱ መቀነስ ሲጀምር እና የተፈለገው ርቀት ላይ ሲደረስ የተገጠመለት ሞተር ተነስቶ ሥራ ይጀምራል። ሞተሩ መነሳት እስኪጀምር ድረስ ሁሉም ነገር በታቀደለት መሠረት ነበር የተከናወነው። ከ ሰከንድ በኋላ ሞተር መጥፋቱ የተከሰተው ሳተላይቱ ላይ የተገጠመው ኮምፒውተር የማርስ ዝቅተኛው ከባቢ አየር ውስጥ የገባ ስለመሰለው ነበር ተብሏል። ከሦስት ዓመት በኋላ ማርስ ላይ ቁፋሮ የሚያከናውነው ሮቨር መሰል ችግር እንዳይገጥመው ሳይንቲስቶች ከወዲሁ ጥልቅ ምርምር እያከናወኑ ነው። ከ ሰከንድ በኋላ ሞተር መጥፋቱ በዓለም የኅዋ ጠቢባን በጥልቀት ጥናት ይከናወንበታል ተብሏል። ሆኖም በኤክሶማርስ ተጭና የሄደችው የማርስ ከባቢ አየር ቃኚ ሳተላይት ግን በታቀደላት መሰረት ሜታን እና ሌሎች ጋዞችን የማሠሥ ተግባሯን እየፈጸመች መኾኗ ተገልጧል። ጋዞቹን ማጥናቱ ጠቀሜታው የጎላ ነው። በአውሮጳ የኅዋ ምርምር ማዕከል የ ኤክሶማርስ ተልዕኮ ሣይንቲስት ዮርጌ ቫጎ ቀደም ሲል እንዲህ ብለው ነበር። ከማርስ ኤክስፕረስ እና ከሌሎች ተልዕኮዎች ባገኘነው መረጃ መሠረት ሜቴይን ዋነኛ መነጋገሪያ ነጥብ ሆኗል። ስለዚህ የሜቴይን ምንጭን በማርስ የትኛው ክፍል መቼ እንደተመረተ እንዲሁም እንዴትስ ሊጠፋ እንደሚችል ለመረዳት መሞከር እጅግ በጣም ጠቃሚ ጉዳይ ነው። የኤክሶማርስ ተልዕኮ ምድር ላይ ቅራኔ የገቡ ሃገራትን ጭምር በአንድ ላይ ያሰባሰበ ነው። ለአብነት ያህል፦ምንም እንኳን የአውሮጳ ኅብረት በዩክሬን ቀውስ ከሩስያ ጋር እሰጥ አገባ ቢገጥምም፤ በኤክሶማርስ ተልዕኮ ግን ሩስያውያን ከአውሮጳ ኅብረት ጋር ተባብረው ሠርተዋል። በአውሮጳ የኅዋ ምርምር ማዕከል የኤክሶማርስ ተልዕኮ የጀርመን፣ የፈረንሳይ፣ የጣሊያን፣ የሩስያ እና የታላቋ ብሪታንያ የኅዋ ማዕከላት ተሳታፊ ናቸው። ሃገራቱ በጋራ የላኳቸው ሳተላይቶች የሰአት ችግር እንደገጠማቸውም በመግለጫው ተጠቅሷል። ሳተላይቶች ወደ ኅዋ ሲወነጨፉ ከምድር ውጪ ጊዜን የሚቆጥሩበት ልዩ ሰአት ተገጥሞላቸው ነው። የሰአት ችግር የተፈጠረባቸው የጋሊሊዮ ሳተላይቶች እንደሆኑም ተገልጧል። ሆኖም የአውሮጳ የኅዋ ምርምር ማዕከል ዋና ኃላፊ ያን ቮርነር ሰአቶቹ ብልሽት ቢገጥማቸውም ሳተላይቶቹን ከመሥራት አላገዱም ብለዋል። የሳተላይት አሠሣ በዋናነት እላዩ ላይ በተገጠሙለት ሰአቶች ጥገኛ ነው። ይኽን ሁሉም ሊረዳው ይገባል። እናም በበርካታ ሳተላይቶቻችን ላይ የሰአት ችግር መፈጠሩን አሳውቄያለሁ። በእያንዳንዱ ሳተላይት አራት ሰአቶችን ገጥመናል። የዕድል ጉዳይ ሆኖ ሳተላይቶቹ ላይ የተገጠሙት አንዳንዶቹ ሰአቶች መሥራት አቁመዋል። ግን ጨዋታው እዚህ ጋር ነው። ማለቴ፤ በእያንዳንዱ ሳተላይት አራት ሰአቶችን የገጠምነው ለዚሁ ነው። አንዱ ሲበላሽ በሌላኛው ለመጠቀም። ስለዚህ ዛሬ መግለጥ የምሻው አንድም ሥራ ያቆመ ሳተላይት እንደሌለ ነው። ሁሉም ይሠራሉ። ሳተላይቶቹ ላይ የተገጠሙት ሰአቶች ሩቢዲዩም እና ሀይድሮጂን ሜዘር ይሰኛሉ። ሁለቱም የሰአት አይነቶች ብልሽት ስለገጠማቸው ለወደፊቱ ችግሩን ለመፍታት የምርምር ማዕከል ጥረት እንደሚያደርግ ገልጧል። ሰአቶቹ በድጋሚ እንዲሠሩ ማድረግ ይቻል አይቻል ግን ለጊዜው የሚታወቅ ነገር የለም። የሰአት ችግር በመፈጠሩ እስካሁን ሥራ ያቆመ አንድም ሳተላይት አለመኖሩ ግን እርግጥ ነው። የሩቢዲዩም እና የሀይድሮጂን ሜዘር ሰአቶች ሥራ ማቆማቸውን የአውሮጳ የኅዋ ተቋም ይፋ አድርጓል። የሚሠሩ ሰአቶች በቁጥር ከሁለት በታች ያላቸው ሳተላይቶች የሉም። ሌሎቹም እንዲሠሩ ለማድረግ መላ እየሻትን ነው። ጋሊሊዮ በእርግጥም ለረዥም ጊዜ ያለእንከን መሥራት የምትችልበትን ዘዴ እያፈላለግን ነው። እስካሁን የአውሮጳ የኅዋ ምርምር ማዕከል ንብረት የሆኑ ጋሊሊዮ ሳተላይቶች ኅዋው ላይ ይሳንፈፋሉ። አንዳቸውም ተግባራቸው አልተቋረጠም። የአውሮጳ የኅዋ ምርምር ማዕከል አሠሣም በጥልቀት ሳይቋረጥ መቀጠሉ አይቀርም። ማንተጋፍቶት ስለሺ
የዓባይ ግድብ ውይይት በዋሽንግተን ዛሬ ይጠናቀቃል
ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የ ሕዳሴው ግድብ ን በተመለከተ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የሚያደርጉት ንግግር ዛሬ ይጠናቀቃል። የመፍትኄ ሐሳብም የሚጠበቀው ዛሬ ነው። ሦስቱ ሃገራት በአራት ዙር በሦስቱ ሃገራት መዲናዎች ውስጥ ተገናኝተው በተከታታይ ያደረጉት ንግግር ያለስምምነት ነው የተጠናቀቀው። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የ ሕዳሴው ግድብ ን በተመለከተ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የሚያደርጉት ንግግር ዛሬ ይጠናቀቃል። የመፍትኄ ሐሳብም የሚጠበቀው ዛሬ ነው። ሦስቱ ሃገራት በአራት ዙር በሦስቱ ሃገራት መዲናዎች ውስጥ ተገናኝተው በተከታታይ ያደረጉት ንግግር ያለስምምነት ነው የተጠናቀቀው። ዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ በተገኙበት ዋሽንግተን ውስጥ የሚከናወነው ስብሰባ የሦስቱ ሃገራት ውጭ ጉዳይ ሚንሥትሮች የተገኙበት ነው። ሦስቱ ሃገራትን ስለሚያወዛግበው የአባይ ግድብ የሚተነትኑ የውኃ እና ውኃ ነክ መሐንዲስ እንዲሁም የማኅበራዊ ሣይንስ ባለሞያን በማነጋገር መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። መክብብ ሸዋ
ስደት የነፍሳቸዉን ጥሪ ቀምቶ ለእንጀራ ብቻ እያኖራቻዉ ያሉ ብዙ የጥበብ ሰዎች አሉ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ከ ዓመት በኋላ የፈረንሳይና የቀድሞ ቅኝ ግዛቶቿ ግንኙነት
በ ዓ ም ነው በፈረንሳይ የቅኝ ግዛትነት ሥር ለ ዓመታት የቆዩት የአፍሪቃ ሃገራት ነጻነታቸውን ያገኙት። ሆኖም የየሃገራቱን ይዞታ በቅርበት የሚያስተውሉ ወገኖች እንደሚሉት ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎቹ የአፍሪቃ ሃገራት እውነተኛ የሆነ ነፃነት ገና አላገኙም። በ ዓ ም ነው በፈረንሳይ የቅኝ ግዛትነት ሥር ለ ዓመታት የቆዩት የአፍሪቃ ሃገራት ነጻነታቸውን ያገኙት። ቤኒን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ጊኒቢሳው፣ ኮትዴቯር፣ ማሊ፣ ኒዠር፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ ካሜሩን፣ ቻድ፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋቦን እና ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ ከቅኝ ተገዢነት ሲላቀቁ፤ በሚሊየኖች የሚቆጠሩት የእነዚህ ሃገራት ዜጎች ነጻነት፣ እፎይታና ተስፋ ሊሰማቸው እንደሚገባ ይታመናል። ሆኖም በኮትዴቩዋር ሪፑብሊክ የነጻነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ አማካሪ የሆኑት ናታሊ ያምቢ እንደሚሉት ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎቹ የአፍሪቃ ሃገራት እውነተኛ የሆነ ነፃነት ገና አላገኙም። ነጻ ወጡ ከተባለበት ከ ዓመት በኋላ ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎቹ የአፍሪቃ ሃገራት እውነተኛ ነጻነትና ነፃ ግዛታቸውን ከፈተንሳይ ገና አላገኙም። እነዚህ የቀድሞ ቅኝ ግዛቶቿ የሆኑት ሃገራት ነጻነታቸውን ከማግኘታቸው አስቀድሞ ፈረንሳይ የአንዳንዶቹን ሕገ መንግሥት ለውጣለች። በዚህም ፓርላሜንታዊ የነበረውን አገዛዝ ለመለወጥ ወስናለች፤ ለምሳሌ ኮትዴቩዋር እስከ ድረስ ፓርላሜንታዊ አገዛዝ ነበራት። ከዚያም ፕሬዝደንታዊ አገዛዝ በየሕገ መንግሥቱ ደነገጉ፤ ይህም በየሀገሩና ግዛቱ ያለው ሥልጣን በአንድ ሰው እጅ ማለትም በሀገር መሪው እጅ እንዲጠቀለል አደረጉ። እናም ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረውን አንድ ግለሰብ ተጠቅመው በዚያች ሀገር ላይ ይዞታቸውን ለማስቀጠል ችለዋል። በእነዚህ ሃገራትም የመማሪያ መጻሕፍት ከሚያካትቱት ይዘት አንስቶ የሚወሰነው በፈረንሳይ ነው። በዚያም ላይ የእነዚህ ሃገራት አብዛኞቹ ሥርዓቶች የሚመሠረቱት በፈንሳይ ቅጂ መሆኑንም ያነሳሉ። የፈረንሳይ ተፅዕኖም በእነዚህ ሃገራት በተለይ በወጣቶች ዘንድ በቀድሞ የቅኝ ገዢዎች ላይ ያሳደረው የቁጣ ስሜት መባባሱ ታይቷል። በዚህም ምክንያት ላለፉት ዓመታት ለፕሬዝደንታዊ እጩነት የቀረቡ ተፎካካሪዎች ፍራንኮ አፍሪኬ ከሚሉት የፈረንሳይ ተፅዕኖ ለመላቀቅ ቃል ሲገቡ ቆይተዋል። እንዲያም ሆኖ ይህ ሁሉ ቃል ኪዳን ከተለመደ ንግግር አልፎ አልታየም ይላሉ በስኮትላንድ ሴንት አንድሪው ዩኒቨርሲቲ የአፍሪቃ ፖለቲካ ፕሮፌሰር ኢያን ቴለር። ለመለወጥ እንደሚፈልጉ እንዲህ ያለውን ነገር ይናገራሉ ግን ደግሞ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ የንግድ እንዲሁም የፖለቲካ ፍላጎቶቹ አሁንም በጣም ጠንካሮች መሆናቸው ስለሚረዱ ከሁለቱም ወገን እውነተኛ የሆነ ግንኙቱ ላይ መሠረታዊ ማስተካከያ ሲያመጡ አልታየም። ለመሆኑ የአፍሪቃ ምሁራንም ሆኑ የፈረንሳይ የፍራንኮ አፍሪኬ መላቀቅ እንዴት ተሳናቸው በጎርጎሪዩዮሳዊው ዓ ም ነው የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ቻርልስ ደ ጎል በአማካሪያቸው ዣክ ፎካርት አማካኝነት ፍራንኮ አፍሪኬን ያቋቋሙት ፍራንኮ አፍሪኬ ዓላማው በፈረንሳይና የቅኝ ግዛቶቿ በነበሩት ሃገራት ምሁራን መካከል የግንኙነት ሰልሰለት መገንባት ነው። ዶቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ ካነጋገራቸው አንዱ በብሪታኒያው ቻተም ሀውስ የአፍሪቃ ፕሮግራም አማካሪ ፖል ሜሊ እንደሚሉት ይህ ከስኬት እንዳይደርስ ትልቁን ሚና የሚጫወተው የምሁራኑ የግል ፍላጎት ነው። ፎካርት ይህን ትስስር የመሰረቱት በግለሰቦች አማካኝነት በመሆኑም ግንኙነቱ ግላዊ፣ ግልፅነት የጎደለውና በጣም ቁጥጥር የታከተለበት ነውም ይላሉ። በዚህም የየሃገራቱ መሪዎች መፈንቅለ መንግሥትን ለመከላከል ከፈረንሳይ ለሚያገኙት ወታደራዊ ከለላ የፈረንሳይ ኩባንያዎች ስልታዊ በሆነ መንገድ የተፈጥሮ ሃብቶችን ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ ተመቻችቷል። እናም ዛሬ ፈረንሳይ አፍሪቃ ውስጥ ያላት ሕልውና ጠንካራ ነው፤ ይህም ከዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ ቀጥላ በሦስተኝነት ደረጃ ያስቀምጣታል። በወታደራዊውም ቢሆን የፈረንሳይ ወታደሮች በምዕራብ አፍሪቃ ተሰማርተዋል። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱትም በጎርጎሪዮሳዊው ዓ ም ሺህ የፈረንሳይ ወታደሮች አፍሪቃ ውስጥ በተለያየ ተልዕኮ ሥር ተሰማርተዋል። ባሉበት ሀገርም ከወታደራዊ አገልግሎት በተጨማሪ የማማከር ሙያ ያላቸው ሲሆኑ ለአገዛዞቹ ድጋፍና የማረጋጋት ሥራ ያከናውናሉ። ናታሊ ያምቢ ይህ ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ ነው ይላሉ። ከሥርአቱ በተጨማሪ የየሪፐብሊኩ ፕሬዝደንቶች ይህ እንዲቀየር አይሹም። የሕዝባቸውን ፍላጎት ከማስጠበቅ ይልቅ የፈረንሳይን መንግሥት ማገልገሉ እንዲቀጥል ይፈልጋሉ። ነገር ግን ሕዝቡም ሆነ ወጣቱ እውነተኛ ነጻነትና ቅጥ ያጣ ወዳጅነት እንዲሁም ጤናማ ባልሆነ መንገድ ከፈረንሳይ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲቆም በግልፅ ይጠይቃል። በፈረንሳዩ የዓለም አቀፍና ስልታዊ ግንኙነት ተቋም ረዳት ተመራማሪ ካሮሊን ሮውዚ ግን በዚህ አይስማሙም። ፈረንሳይ የቅኝ ግዛቶቿ በነበሩት የአፍሪቃ ሃገራት ላይ ያላት ተፅዕኖ በፕሬዝደንት ኢማኑዌል ማክሮ አስተዳደር ለመለወጥ እየተሞከረ ነው ሲሉም ይሞግታሉ። ራስ የመቻሉ ነገር ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሆኗል ማለት ባይቻልም ከ ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር የሚነጻጸር አይደለም። ፈረንሳይም ሆነች ፕሬዝደንት ማክሮ ይህን ለመለወጥ እየሞከሩ ነው። በዚህ ለውጥ አማካኝነትም በፈረንሳይና አፍሪቃ መካከል አዲስ ታሪክ ሊጀመር ነው። ለዚህ ማሳያም በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ለሌላ ጊዜ የተገፋውን አፍሪኬ ፍራንስ የተሰኘው የፈረንሳይና የአፍሪቃ መንግሥታት ጉባኤ ይጠቅሳሉ። በዚህ ጉባኤም ሁለቱም በጋራ አፍሪቃ ውስጥ በመጪዎቹ አስርት ዓመታት ለማከናወን የታቀደውም ከተሞች የማስፋፊያ ፕሮጀክት በመንደፍ መፍትሄውንም በጋራ ለመፈለግ ታቅዷል። ለናታሊ ያምቢ ግን ይህም ቢሆን የቃላት ጨዋታ ነው። ፍራንክ አፍሪኬም ሆነ አፍሪኬ ፍራንስ ለውጥ የለውም። እንደውም ግንኙነቱን ይበልጥ የከፋ ሊያደርገው ይችላልም ባይ ናቸው። ፈረንሳይ በአፍሪቃ ያላትን ሚና ካጣች ዋጋም አይኖራትምም ነው የሚሉት። ይህ እንዳይሆን ይሻሉ ያሏቸው ማክሮ አፍሪቃ የማትሻውን ነገር ለመጫን እየሞከሩ እንደሆነም የሚናገሩት ያምቢ የምዕራብ አፍሪቃ የጋራ መገበያያ ሃሳብን በምሳሌነት ያነሳሉ። ኤኮ ፕሮጀክት በጣም የቆየ ነው። የኤኮዋስ የድሮ ፕሮጀክት ነው። ፈረንሳይ ታዲያ ስሙን ብቻ እንቀይረው ብላ ወሰነች። የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ትብብር ፕሮጀክትን ወስዳ ስሙን ለወጠች። እናም ስሙን ብቻ በመለወጥ ስልቱ የተቀየረ የሚመስል ጨዋታ መሆኑ ነው። ይህ የአፍሪቃ ሃገራት ተነሳሽነት ሊሆን ይገባው ነበር። በፈረንሳይ ሊቀረጽ ወይም ይፋ ሊደረግ ወይም ሊታቀድ አይገባውም ነበር። ፈረንሳይ ኤኮን በሲኤፍ ኤ ነው የለወጠችው፤ ሲኤፍኤ በፈረንሳይ ምህጻሩ የአፍሪቃ የፋይናንስ ማኅበረሰብ እንደማለት ነው። በዚህ የጋራ መገበያያ የሚጠቀሙት የአፍሪቃ ሃገራት ለሚከናወነው የውጭ ገንዘብ ልውውጥ በመቶ የሚሆነውን በፈረንሳይ የገንዘብ ሚኒስቴር ማጠራቀም ይጠበቅባቸዋል። ከዩሮ ሊተካከል ይቃጣዋል የተባለው ይህ የጋራ ሸርፍ ሃሳቡ ድንቅ ቢሆንም ችግሩ ግን እያንዳንዱ የአፍሪቃ መንግሥት ምን ያህል ገንዘብ በፈረንሳይ ግምጃ ቤት እንዳለው አለማወቁ መሆኑን ፕሮፌሰር ኢያን ቴይለር ጠቁመዋል። በዚያም ላይ ቴይለር በዚህ መልኩ የሚሰባሰበውን ገንዘብ ፈረንሳይ የልማት ርዳታ የሚል መለያ መስጠቷ አይገባም ሲልም ይወቅሳሉ። ከቅኝ ተገዢነት የተላቀቁት የአፍሪቃ ሃገራት አሁን ከ ዓመታት በኋላ ወደ እውነተኛ ነጻነት መሻገር የሚችሉት ይህን በፈረንሳይ የተቀየሰላቸውን የጋራ ሸርፍ ወደመቃብር ሲልኩ ነው። ለዚህ የሚፈልጉት ደግሞ አፍሪቃን ማስቀደም የሚችሉ የአፍሪቃ ምሁራን ዝግጁነት እንደሚሆንም አጽንኦት ሰጥተዋል። ማሊን በአንድ ወገን በአካባቢው የተጠናከረው የፅንፈኛ ሙስሊሞች በሌላ ወገን የሀገር ውስጥ ፖለቲካ ውዝግብ ከመንታ መንገድ ጥሏታል። ከትናንት በስተያ ሐሙስ ዕለት ባማኮ ላይ አምስት የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት መሪዎች እንዲሁም የማሊ መንግሥትና ተቃዋሚ ኃይሎች በተገኙበት የተካሄደው ውይይት ያለውጤት ተጠናቋል። ውይይቱ ለማሊ ቀውስ የፈየደው ባለመኖሩም የፊታችን ሰኞ ሐምሌ ቀን ዓ ም የ ቱ የምዕራብ አፍሪቃ የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ ኤኮዋስ አባል ሃገራት በጉዳዩ ላይ አስቸኳ ጉባኤ በቪዲዮ ያካሂዳሊ። የሰኔጋል፤ የኮትዴቩዋር፣ የናይጀሪያ፣ ኒዠርና የጋና መሪዎች አስቀድመው ከፕሬዝደንት ኬይታ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነበር ተቃዋሚዎችን አክለው የተነጋገሩት። ሆኖም ተቀናቃኞቹ ሊግባቡ አልቻሉም። የወቅቱ የኤኮዋስ ሊቀመንበር የኒዠር ፕሬዝደንት ማሀማዱ ዩሱፉ ከስብሰባው በኋላ በሰጡት መግለጫ ተቋሙ ይህን ቀውስ ለመፍታት ጠንካራ ርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ተናግረዋል። በሙስና፣ በአካባቢ የምርጫ ውጤት እንዲሁም የሀገሪቱ ሠራዊት በጅሃዲስቶች በመሸነፉ በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በቁጣ ጎዳና ላይ በመውጣት ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል። በዚህም የተመድ እንደሚለው የተቃውሞው ሰልፈኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የድርጅቱ የሰብያዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽንም ማሊ ውስጥ ውጥረቱ በተባባሰበት በዚህ ወቅት አሁንም የፀጥታ ኃይሎች ከሚወስዷቸው የኃይል ርምጃዎች እንዲቆጠቡ አሳስቧል። በምህጻሩ በመባል የሚታወቀውን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ የሚመሩት ሳውድ አረቢያ የሰለጠኑት የሙስሊም ሃይማኖታዊ መምህር ማህሙድ ዲኮ የጀመሩትን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ባቡከር ኬይታ ሥልጣን ካለቀቁ በቀር አላቆምም ማለታቸው ቀውሱ ይዛመትብናል በሚል የማሊን ጎረቤት ሃገራት እያሰጋ ነው። የትናንት በስተያው ስብሰባ እንዳበቃም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እስካሁን ላቀረቡት ጥያቄ መፍትሄ ሊሆን የሚችል ምላሽ እንዳልተገኘ ተናግረዋል። ከጥያቄዎቻቸው መካከልም በሲቪሎች ላይ የተካሄደውን ግድያ የሚያጣራ ኮሚቴ ይቋቋም፤ እንዲሁም የሽግግር መንግሥት ይመስረት የሚሉት ይገኙበታል። የኒዠር ፕሬዝደንት ግን ፕሬዝደንቱ ሥልጣን ይልቀቁ የሚለውን በተመለከተ ኤኮዋስ ቀይ መስመር አስምሯል ብለዋል። አክለውም በኤኮዋስ አባል ሃገራት ውስጥ ኢሕገ መንግሥታዊ የሥልጣን ለውጥ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ቁጥሩን ተናግረዋል። ፕሬዝደንት ባቡከር ኬይታ ማሊ ውስጥ ለዓመታት የዘለቀውን ከፅንፈኞች ጋር የሚካሄድ ውጊያ ማጠናቀቅ አልቻሉም የሚለው ከፍተኛ ጫና አስከትሎባቸዋል። ሚሊየን ሕዝብ ያላት ድሀይቱ አፍሪቃዊት ሀገር ከጎርጎሪዮሳዊው ዓ ም አንስቶ በምታካሂደው ውጊያ ምንም እንኳን የውጭ ሃገር ወታደሮች በስፍራው ቢኖሩም በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ከመኖሪያቸው ይፈናቀሉባታል። ከሚያዝያ ወዲህ በማሊ ቀውሱን ያባባሰው በተካሄደው ምክር ቤታዊ ምርጫ ላወዛገበው ውጤት ሕገ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን ለገዢው ፓርቲ አድልቷል የሚለው ነው። በዚህ ምክንያት የተካረረው የፓለቲካ ውዝግብ በተቃዋሚዎችና የፀጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት አስከትሎ ሲገደሉ መጎዳታቸው ይበልጥ ቀውሱን አናረው። ለማደራደር የገባው ኤኮዋስ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተካተቱበት የአንድነት መንግሥት እንዲመሠረት ሃሳብ ከማቅረብ አልፎ ለውዝግቡ መንስኤ የሆነው የምርጫ ውጤት ላይ ብይን ያሳለፉት የሕገ መንግሥታዊው ፍርድ ቤት ዳኞች ያንን ውጤት ሊመረምሩ በሚችሉ ሌሎች ዳኞች እንዲተኩ ቢጠይቅም፤ ተቃዋሚዎቹ ፕሬዝደንቱ ከሥልጣን ይነሱ የሚለው ካልተካተተበት አንቀበልም ማለታቸው ድርድሩ ፍሬ እንዳያስገኝ እንዳደናቀፈ ታይቷል። ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ባማኮ የሚገኙ አንድ አውሮጳዊ ዲፕሎማት ግን ተቃዋሚዎቹ የፕሬዝደንት ኬይታ ስንብት ላይ ትኩረት መስጠታቸው ያለውን ችግር ያለማገናዘብ እንደሆነ ነው የጠቆሙት። እሳቸው እንደሚሉትም ለሳህል አካባቢ የፀጥታ ይዞታ አደገኛ መንገድ ሊሆን የሚችል ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ማንም አይፈልግም። የኤኮዋስም አቋም ከዚህ የሚለይ አይመስልም። ለሁሉም ከሰኞው ስብሰባ በኋላ የሚያሳልፈው ውሳኔውና የሚወስደው ጠንካራ ርምጃ የማሊን ዕጣ ፈንታ ወሳኝ መስሏል። ሸዋዬ ለገሠ
ከ ዓመት በኋላ የፈረንሳይና የቀድሞ ቅኝ ግዛቶቿ ግንኙነት ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ሩሲያ የአሮጌዉ ፕሬዝዳት አዲስ ፕሬዝዳትነትና ተቃዉሞዉ
ሚኻኤል ጎርቫቾቭ የለኮሱት የሩሲያ ሁለተኛ አብዮት ለፕሬዝዳትነት ያበቃቸዉ ቦሪስ የልትሲን አምነዉ ክሬምሊንን ሲያወርሷቸዉ ጎሮቫቾቭ ብቃታቸዉን ጠርጥረዉ ነበር።ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ሲያወድሷቸዉ፣ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትራቸዉ ኮሊን ፓዌል ጠልተዉቸዉ ነበር። የሩሲያ ፌደሬሽን ፕሬዝዳትን ሙሉ ሐላፊነት ገቢር ለማድረግ ቃል እገባለሁ።የሕዝቡን የዜጎችን መብትና ነፃነት ለማክበርና ለማስከበር፥ የሩሲያ ፌደሬሽንን ለማስጠበቅና ለመደገፍ፥ የሐገሪቱን ልዓላዊነት፥ ነፃነት፥ ደሕንነትና አንድነትን ለማስከበርና ዜጎችን በቅንነት ለማገልገል ቃል እገባለሁ። ቭላድሚር ቭላድሚሮቪች ፑቲን፥።በዉርስም፥ በምርጫም ብለዉ ከስምንት ዓመት በላይ የኖሩበትን የፕሬዝዳትነት ሥልጣን እንደገና ያዙ።ዛሬ።ተወገዙም።የአሮጌዉ ፕሬዝዳት አዲስ ፕሬዝዳትነት መነሻ፥ ፖለቲካዊ ስብናቸዉ ማጣቀሻ፣ የሩሲያ እዉነታ መድረሻችን ነዉ።ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።ሚኻኤል ጎርቫቾቭ የለኮሱት የሩሲያ ሁለተኛ አብዮት ለፕሬዝዳትነት ያበቃቸዉ ቦሪስ የልትሲን አምነዉ ክሬምሊንን ሲያወርሷቸዉ ጎሮቫቾቭ አብዮቱን ግብ የማድረስ ብቃታቸዉን ጠርጥረዉ አጠያይቀዉ ነበር።ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ሲያደንቁ፥ ሲያወድሷቸዉ፣ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትራቸዉ ኮሊን ፓዌል ጠልተዉ አናንቀዋቸዉ ነበር።ሩሲያን ከጥፋት፣ሁለተኛ አብዮቷን ከዉድቀት በማዳናቸዉ የመደነቃቸዉን ያክል በአምባገነንነት ይወገዛሉ።ቭላድሚር ፑቲን የተቃርኖ ዉሁድ። የዛሬዉ የሩሲያ የመካከለኛ መደብ ሕብረተሰብ የደረጀዉ በሳቸዉ ዘመነ ሥልጣን መሆኑ አላነጋገረም።ያ ሕብረተሰብ ግን ዋነኛ ተቃዋሚያቸዉ ነዉ።እሱ አንዱ ነዉ። ባለፈዉ መጋቢት አራት ማታ ፑቲን አደባባይ ወጥተዉ ባደረጉት ንግግር በምርጫ ማሸነፋቸዉ ማሸነፋቸዉን አስታዉቀዋል።ያዉቃሉ ነገሩ እንዲሕ ነዉ።አዎ እሳቸዉ በየትኛዉም መንገድ ለማግኘት የተፋለሙለትን ቁጥር ጦርነት በርግጥ አሸንፈዋል።እና እሳቸዉ የቁጥር ፕሬዝዳንት ናቸዉ።የሕዝቡ ፕሬዝዳት ግን አይደሉም። ማክሲም ቪቶርጋን።የፊልም ተዋኝ ነዉ። አዲሱ መንግሥት ምናልባት ሐገሪቱ ሥለምትለማበትና ሕዝቡ ሥለሚበለፅግበት መርሕ ከተቃዋሚዎች ጋር ገንቢ ዉይይት ያደርግ ይሆናል አለ ሚኻኤል ሹኮቭ።የሰላሳ አራት አመት ወጣት ነዉ።ገለልተኛ ነኝ ይላል። ደጋፊያቸዉ ሹኮቭ ያኔም ዛሬም እንደ ወጣት ሩሲያዊ ለራሱ ጥሩ ትምሕርት፥ ሥራ ለማግኘት ከመጣር፥ ለሐገር፣ ለወገኑ እድገት ደሕንነት ከመመኘት ባለፍ ሥለ ፖለቲካዉ ጡቃንጡቅ ብዙም አያዉቅም። የሱና የብጤዎቹ ኑሮ ከያኔ ዛሬ ብዙ እንደሚሻል ግን ጠንቅቆ ያዉቀዋል።ያኔ የሃያ አንድ አመት ተማሪ ነበር። ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ የወላጆቹ ገቢ ከዕለት ወደ ዕለት እያሽቆለቆለ፥ ድሕነት እያፈጠጠ መምጣቱን፣ የኑሮ ዉድነቱን፣ ከማላሰል ባለፍ ሰበብ ምክንያቱን ለማስተንተን እዉቀቱም ብስለቱ ፍላጎቱም አልነበረዉም። ቼችንያ የዘመተዉ ጦር ድል እያደረገ መሆኑን አለማወቅ ግን አችልም ነበር።ትንሽ ትንሽ የሚያዉቀዉ የኮፒዉተር መርሐ ግብር ከጥቂት ቀናት በሕዋላ በሚለወጠዉ አዲስ ዘመን ምክንያት ይሳከራል የሚለዉን አስተያየትም አለመስማት አይችልም ነበር።የሞስኮ ቴሌቪዥን ልዩ ቃለ መጠየቁን ያሰራጨዉ የዚያ ወጣት ዓዕምሮ ብዙ በሚያቀዉ ችግር፣ ብዙ በሰማዉ የቼችንያ ድል፥ ብዙ በማያዉቀዉ የኮፒዉተር መሳከር መሐል በተቃረጠበት ሰሞን ነበር። ታሕሳስ አጋማሽ ፕሬዝዳንቱ እርስዎን እንደተተኪያቸዉ ነዉ የሚያዎት። ጠየቀች ጋዜጠኛዋ አዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር፥ ፕሬዝዳንቱ እንደዚያ ካሉ፣ ባሉት አለመስመስማማት ከንቀት ይቆጠራል መለሱ።ከፕሬዝዳንት ቦሪስ የልሲን ምናልባት ከጥቂት ታማኞቻቸዉ በስተቀር፣ እኛ በሞስኮ ፖለቲካ ብዙም የማይታወቁት መጣጣ፣ መላጣ፣ አይነ ቅብዝብዝ ሰዉዬ የተመሰቃቀለችዉን ሐገር በቅጡ ይመራሉ፥ የነሹኮቭን ኑሮ ከቁልቁሊት ሩጫ ይገታሉ ብሎ የገመተ፥ ተስፋ ያደረገ መኖሩ ሲበዛ አጠራጣሪ ነዉ። ሰዉዬዉ ግን በሳምንቱ ያረጁ የፋጁትን፥ በጤና እጦት፥ በመጠጥ ብዛት የተዳከሙትን ፕሬዝዳት ቦሪስ የልትሲንን ተክተዉ ተጠባባቂ ፕሬዝዳት ሆኑ።ታሕሳስ ሰላሳ አንድ ።ቭላድሚር ፑቲን።ለሩሲያ የዘመን መለወጫ ስጦታ ብጤ ነበር። ኦሌግ ኖይማይቫኪን የሃያ ስድስት አመት ወጣት እና የኮሚዉተር ባለሙያ ነዉ። ከዚሕ ሥርዓት ምጣኔ ሐብታዊም ሆነ ማሕበራዊ ዕድገት ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም አለ በቀደም።ፑቲን የሚመሩት መንግሥት ለወደፊቱ በጎ መጥፎ መስራት አለመስራቱ በርግጥ ሲሆን የሚታይ ነዉ። ኖይማይቫኪን የአስራ ሰወስት አመት ልጅ በነበረበት ዘመን የፕሬዝዳትነቱን ሥልጣን የተረከቡት ፑቲን ግን ያኔ ብዙዎች የገመቱትን ኋላ በግምት አስቀርተዉታል።ፑቲን መጀመሪያ እንደ ጠቅላይ ሚንስትር ኋላ እንደ ፕሬዝዳት ወደ ቼቺንያ ያዘመቱት የሩሲያ ጦር በዚያች ትንሽ ግዛት ጉስቁል ሕዝብ ላይ ያደረሰዉ ግፍ በደል በርግጥ መንግሥታቸዉን በሰብአዊ መብት ረጋጭነት፥ ጦራቸዉን በገዳይነት ማስወቀስ ማስተቸቱ አልቀርም።ከሶቬት ሕብረት መፈረካከስ በሕዋላ ለሩሲያ ፌደረሽን መበታተን ትልቅ ስጋት የነበረዉን ጦርነት በድል አድራጊነት ማጠናቀቃቸዉ ግን በርግጥ አላከራከረም። ፑቲን የፕሬዝዳትነት ሥልጣኑን ሲረከቡ በቆዳ ሥፋት ከዓለም ተወዳዳሪ የማይገኝላት፥ በተፈጥሮ ሐብት የተንበሸበሸችዉ፥ በጦር ሐይል ቴክኖሎጂ፥ በጠፈር ሳይንስ የረቀቀች የመጠቀችዉ ሩሲያ ከልዕለ ሐይልነት ወደ ምዱባን መኖሪያነት፥ ከጠንካራ የሕግ ሥርዓት ተገዢነት ወደ ማጅራት መቺ፥ አጭበርባሪ ማፍያዎች መፍለቂያነት፥ ከእዉቀት ሐብት መፍለቂያነት ወደ ተበዳሪ ለማኝነት የዘቀጠች ሐገር ነበረች። የቀድሞዉ እዉቅ የስላላ ባለሙያ ሁለተኛ የፕሬዝዳትነት ዘመነ ሥልጣናቸዉን በሁለት ሺሕ ስድስት ሲያጋምሱ ግን የዚያች ሐገር አጠቃላይ የሐገር ዉስጥ ገቢ በሰባ ሁለት ከመቶ ተንቻሮ ነበር።በየቆመበት የዛገ የወላለቀዉ፥ ዘመናይ የጦር መሳሪያና መርከብ ታድሶ፥ ወይም ባዳዲስ ተተክቶ የቆመዉ የጦር እንዱስትሪ አንሰራርቶ ፥ደሞዝና ቀለብ አጥቶ የተጎሳቆለዉ ወታደር የታላቅ ሐገር ወታደርነት ክብር ማዕረግ አግኝቶ የትልቂቱን ሐገር ትልቅነት አስከባሪነቱን አረጋግጦ ነበር። በ ከሩሲያ ሕዝብ ከሰላሳ ከመቶ የሚበልጠዉ ከድሕነት ጠገግ በታች ይኖር ነበር።በሁለት ሺሕ ስምንት የደኸዉ ሩሲያ ቁጥር ወደ አስራ አራት ከመቶ አሽቆልቁሎ ነበር።ወደ ተመፅዋችነት ዘቅጣ የነበረችዉ ሩሲያ ከዓለም ሰባተኛ ባለ ኢኮኖሚ ሐገር ሆናለች። የሩሲያዊዉ ሠራተኛ አማካይ የወር ደሞዝ ከሰማንያ ዶላር ወደ ስድስት መቶ አርባ ዶላር ተንቻሯል። በዚሕም ሰበብ ሰዉዬዉን ዛሬም የትልቁ አባት ሐገር አዳኝ፥ የታላቁ ሕዝብ ታላቅ መሪ እያሉ የሚያንቆለጳጵሷቸዉ ሚሊዮኖች አሉ።ባለፈዉ መጋቢት በተደረገዉ ምርጫ የማሸነፋቸዉ ዜና ሲሰማ ሞስኮን የቀድሞ ቀይ አደባባይ ያጥለቀለቀዉ ደጋፊያቸዉ ቁጥርም ቀላል አይደለም። ተቃዉሞ ፑቲን፥ ለፈጠሯት ለዲሲቱ ሩሲያ ግን ብዙዎች እንደሚሉት መርሕ አስተሳሰባቸዉ አሁን በርግጥ አርጅተዉበታል።በፕሬዝዳትነትም በጠቅላይ ሚንስትርነትም ብለዉ ሩሲያን ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት የመሩት ፑቲን ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ በመቆየታቸዉ፥ መሠልቸታቸዉ አልበቃ ብሎ የመጋቢቱን ምርጫ አጭበርብረዋል መባሉ ነዉ እስከ ዛሬ ያልበረደዉ የተቃዋሚዎቻቸዉ ቁጣ ሰበብ። ምርጫ ነበር ንገሩኝ፥ ይሕ ምርጫ ነበር ያንን ያዞ እንባ ያነቡትን ሰዉዬ የኛ ፕሬዝዳንት ማለት እንችላለን።ዛሬ እንድንሰለፍ የተሰጠን ፍቃድ ሲያበቃ ሌላ የሆነ ቦታ መሔድ አለብን።ለመበተን መጣደፍ የለብንም።ነገሩ ቀላል ነዉ።አድም እነሱ እንደገና ስድስት አመት ይገዙናል አለበለዚያ እኛ እነሱን እናስወግዳለን ።እታገላለሁ።እናንተም። የግራ ፖለቲካ የሚያቀነቅነዉ ንቅናቄ መሪ ሰርጌይ ኡዳልሶቭ።ፑቲን ማሸነፋቸዉን ከተቃወሙት የሞስኮ ሠልፈኞች አንዱ ነበሩ።ፑቲን ዛሬ ቃለ መሐላ ሲፈፅሙም ተቃዋሚዎቻቸዉ በአደባባይ ሠልፍ እንዳወገዟቸዉ ነዉ። የፑቲን መርሕ ከሐገር ዉስጥ ደጋፊ ተቃዋቂዎቹን እንዳራራቀ ሁሉ የዉጪ መርሐቸዉም የድጋፍ ተቃዉሞ ስብጥር ነዉ።ተቃሮኖ።ሰኔ ሁለት ሺሕ ላይ ከያኔዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ ቡሽ የልባቸዉን ስሜት ካይናቸዉ ዉስጥ አነበብኩ በማለት አወድሰዉ አድንቀዋቸዉ ነበር። ፑቲንን ከቡሽ እኩል ያዩት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኮሊን ፓወል ግን የአለቃቸዉን እምነት አልተጋሩም ነበር።እንዲያዉም እኔ ከፑቲን አይን ያነበብኩት ኬጂቢን ነዉ አሉ። እሳቸዉም ጡረተኛ ጄኔራል እንጂ ዲፕሎማት አልነበሩም።ያም ሆኖ ፑቲን የአፍቃኒስታኑን ጦርነት ሲደግፉ፥ በአለም አቀፍ ፀረ ሽብር ዘመቻ ሲሳተፉ ለምዕራባዉያኑ ጥሩ ወዳጅ፥ ደሕና መሪ ነበሩ። የኢራቅ ወረራን ሲተቹ፥ የአሜሪካን የፀረ ሚሳዬል ሚሳዬል መርሐ ግብር ሲያወግዙ፥ በተለይ አሁን የሶሪያን መንግሥት መቀጣቱን ሲቃወሙ መጥፎ ፖለቲከኛ እና መሪ ናቸዉ። ዛሬ ቃላ መሐላ ከመፈፀማቸዉ በፊት በሰጡት መግለጫ ሐገራቸዉንና ከምዕራባዉያን በጣሙን ከዩናትድ ስቴትስ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል አስፈላጊዉን ርቀት እጓዛለሁ ብለዋል።ፑቲን ከዉድቀት ያዳኑት የሩሲያ ሁለተኛ አብዮት የሚደገፍ፥ የሚወደድበት ከምጣኔ ሐብቱ እድገት፥ ከወታደራዊ አቅሙ ብርታት እኩል የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማጎንቆሉ ነዉ።ጀርመናዊዉ የሩሲያ ጉዳይ አዋቂ የንስ ሲገርት የሩሲያ የዲሞክራሲዉ ሥርዓት ጅምር መጠንከሩን ይጠራጠራሉ። ተቃዉሞ ሰልፍ የዲሞክራሲያዊ አስተዳድርን በተመለከተ እኔ በጥቅስ ምልክት ዉስጥ ነዉ የማስቀምጠዉ።ምክንያቱም እኔ እንደሚመስለኝ ዲሞክራሲን የሚመሰክሩ ሁኔታዎች አይታዩም።ሩሲያ ዛሬ የአምባገነን ሐገር ናት።ዲሞክራሲያዊት ናት ማለት አይቻልም። ፕሬዝዳት ፑቲን በተሻሻለዉ ሕግ መንግሥት መሠረት ዛሬ ሉዓላዊነቷን እና አድነቷን ሊያስከብሩ ቃል የገቡላትን ትልቅ ሐገር እስከ ሁለት ሺሕ አስራ ስምንት ይመራሉ።ከዚያ በሕዋላ በሚደረገዉ ምርጫ እወዳደራለሁ ቢሉም ላንድ ዙር ሕጉም ይፈቅድላቸዋል፥ ሥልጣኑም በጃቸዉ ነዉ።ለዛሬዉ ይብቃን።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን። ነጋሽ መሐመድ
ቱኒዚያ ከመረጋጋት ይልቅ ለሌላ ቀውስ
የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካኢስ ሳኤድ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የሀገሪቱን ፓርላማ ማገዳቸው ተረጋግታ በቆየችው ቱኒዚያ ላይ ሌላ የፖለቲካ ትኩሳት ይዞባት መጥቷል። የፕሬዚዳንቱን እርምጃ የሚቃወሙ የሀገሪቱ ዜጎች ብርቱ ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን ከፖሊስ ጋር እስከመጋጨት ደርሰዋል። የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካኢስ ሳኤድ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የሀገሪቱን ፓርላማ ማገዳቸው ተረጋግታ በቆየችው ቱኒዚያ ላይ ሌላ የፖለቲካ ትኩሳት ይዞባት መጥቷል። የፕሬዚዳንቱን እርምጃ የሚቃወሙ የሀገሪቱ ዜጎች ብርቱ ተ ቃውሞ እያሰሙ ሲሆን ከፖሊስ ጋር እስከመጋጨት ደርሰዋል። ከ ዓመታት በፊት በዓረቡ ዓለም ዓብዮት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የነበረችው ቱኒዚያ በወቅቱ የተሳካ አብዮት ስለማካሄዷ ይነገርላታል። አሁን በፕሬዚዳንቱ የተወሰደው እርምጃ የሀገሪቱን ዜጎች ከማ ስቆጣት ኣልፎ ምዕራባውያን ሃገራትም ፕሬዚዳንቱ ለዴሞክራሲ ተገዢ እንዲሆኑ እና እርምጃቸውን እንዲቀለብሱ ጥሪ እያቀረቡ ነው። በሌላ በኩል ምዕራብ አፍራካዊቷ ሀገር ሴራሊዮን የሞት ቅጣትን ያስቀረች ከህገመንግስቷ በማስወገድ ኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች። የትኩረት በአፍሪካ የዕለቱ መሰናዶ በሁለቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። ለዝግጅቱ ገበያው ንጉሴ ታምራት ዲንሳ
ኢትዮጵያ፣ የሠላም ዋጋዉ ምንድነዉ ስንትስ ነዉ
የተወዳጁ ድምፃዊ መገደልና መዘዙ ጋጠወጦችን ለፌስ ቡክ ስድብ ዉግዘት እርግማን ሻምፒዮንነት ሲያሽቀዳድም፣ አዉሮጳና አሜሪካ ተሻግሮ ለንደን፣ ፍራንክፈርት፣ ዋሽግተንና ሚኒያፖሊስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን እያጋጨ፣ በአደባባይ ሲያስጮኽ፣ሳምንቱ ሔዶ ሌላ ሳምንት፣ ምናልባትም የሌላ ግድያ፣ ሁከት፣ ዉዝግብ ሳምንት መጣ። ሐጫሉ ሁንዴሳ ተገደለ።ሰኞ።እንደ ሐጫሉ ሁሉ ለኦሮሞ ሕዝብ መብት ሲታገሉ በአሸባሪነት ተከሰዉ የታሰሩ፣ በአሸባሪነት ተወንጅለዉ በሌሉበት ተፈርዶባቸዉ የነበሩም ፖለቲከኞችም እንደገና ታሰሩ።አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ እንደ ብዙዉ የቅርብ ዘመን ታሪኩ ሁሉ ሟቹን ቀብሮ፣ ቁስለኛዉን አክሞ፣ የጠፋ ሐብት ንብረቱን አስልቶ ከሐዘን፣ትካዜዉ ሳይላቀቅ የሐጫሉ አጎትን ጨምሮ በትንሽ ግምት ሰዎች ተገደሉ።ብዙ መቶዎች ቆሰሉ።ታሰሩም።ኢትዮጵያ ሰላም እየተዘመረባት ጦርነት ሲወርድባት፣ ምርጫ እያስተናገደች ሁከት ሲያናጥርባት፣ ለዉጥ እየታወጀባት ሽብር ሲነዉጣት፣ዘመን ሸኝታ ዘመን ተቀበለች።የሰላም ግብሩ ምድነዉ ስንትስ ነዉ ላፍታ አብረን እንጠይቅ። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ምስቅልቅል፣ የዜጎችዋ መገደል፣መፈናቀል፣ መራብ፣ መቸገር ዉድመት ጥፋቷ የዓመት ዑደት መርገምት የመሰላቸዉ አንድ አድማጭ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ሲባል እስማለሁ አሉ ሰሞኑን ። መቼ ነዉ የምትዘረጋዉ ዘርግታ ከሆነስ እያሉ ጠየቁም። እኔም አልገባኝም።የኢትዮጵያ እዉነታ ከአብዛኛ ዜጎችዋ ተስፋ፣ የአብዛኛ ፖለቲከኞችዋ እርምጃ እንመራሐለን ከሚሉት ሕዝብ ፍላጎትና ምኞት መቃረኑን ለማወቅ ግን ጠያቂም መላሽም ተንታኝም አያስፈልግም። ግራ የገባቸዉ አድማጭ መልስ አልባ ጥያቄ በደረሰን ሳምንት ድምፃዊ ሐጫሉ በሰዉ እጅ ተገደለ።ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣የፖለቲካ ቀንቃኞች፣ ጋዜጠኞች ታሰሩ።ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ መንገዶች፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ሁሉም ተዘጋ።ከአንቦ እስከ ሮቤ፣ ከድሬዳዋ እስከ ነገሌ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር፣ ከጭሮ እስከ ጊምቢ ሰዎች ይገደሉ፣ ሐብት ንብረታቸዉ ይዘረፍ፣ ይጋይ ገባ።የሰብአዊ መብት አጥኚዉ ያሬድ ኃይለ ማርያም እንደሚሉት አንዳድ ስፍራ የተፈፀመዉ ግድያ የተጠና የሚመስል ነዉ። የተወዳጁ ድምፃዊ መገደልና መዘዙ ጋጠወጦችን ለፌስ ቡክ ስድብ ዉግዘት እርግማን ሻምፒዮንነት ሲያሽቀዳድም፣ አዉሮጳና አሜሪካ ተሻግሮ ለንደን፣ ፍራንክፈርት፣ ዋሽግተንና ሚኒያፖሊስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን እያጋጨ፣ በአደባባይ ሲያስጮኽ፣ሳምንቱ ሔዶ ሌላ ሳምንት፣ ምናልባትም የሌላ ግድያ፣ ሁከት፣ ዉዝግብ ሳምንት መጣ። ኢትዮጵያ ባጠቃላይ ሰሞኑን ደግሞ ኦሮሚያ በተለይ ከጠብ፣ ግድያ፣ግጭት፣ እስራት ስደት ሌላ ሌላ እንዳያዉቁ የመገደዳቸዉ ሰበብ ምክንያት በርካታ ወቅታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባሕላዊ፣ ምጣኔ ሐብታዊ ከሁሉም በላይ ፖለቲካዊ እዉነታዎችን የሚያማዝዝ፣ ብዙ አነጋጋሪም ነዉ።ዶክተር ሐዩ ቱለማ በየነ ሰንበቱ ሮሚ ግን አንድ ነገር ይላሉ ሰሚ ጠፋ ዝነኛዉ ደቡብ አፍሪቃዊዉ የጥቁሮች መብት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ሰላም ማንኛዉም ሰዉ ሊኖረዉ የሚገባዉ የዕድገት ወይም የልማት መሳሪያ ነዉ ማለታቸዉን የሚያዉቋቸዉ ደጋግመዉ ይጠቅሱታል። ማንዴላ ለሕዝባቸዉ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዉ መብት መከበር ያደረጉትን ትግልና አስተምሕሮቱን ለመዘከር የዓለም መሪዎች ከጎርጎሪያኑ እስከ ያለዉን ዓመት የኔልሰን ማንዴላ የሰላም አስርት ብለዉ ሰይመዉታል። ማንዴላና የአስተምሕሮታቸዉ እንዲዘከር የወሰኑት እንደ ጎርጎርጎሪያኑ አቆጣጠር መስከረም በተሰየመዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ጉባኤ ላይ የተካፈሉ ከአንድ መቶ የሚበልጡ ሐገራት መሪዎችና ተወካዮች ናቸዉ። ማንዴላ ለሰላምና ለሰብአዊነት ያበረከቱት አስተዋፅዖ ኒዮርክ ላይ ከመዘከሩ ከአራት ወር በፊት የአዲስ አበባና ያካባቢዉ ሕዝብ አዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር ለማመስገን አደባባይ ወጥቶ ነበር።ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ አመስጋኝ ሕዝባቸዉን ለማመስገን አደባባይ ሲወጡ የማንዴላ ምስል የተለጠፈበት ቲ ሸርት ለብሰዉ ነበር። የጠቅላይ ሚንስትሩ የቲ ሸርት መልዕክት፣ ዓለም ማንዴላን በሚወነጅልበት በዚያ በሩቁ የመከራ ዘመን፣ ማንዴላን የረዳችና ያስተማረችዉ ኢትዮጵያ፣የማንዴላን የሰላም፣የሰብአዊነትና የእኩልነት ተጋድሎ ለመዘከርም ዓለም አቀፉ ድርጅት እስኪወስን አለመጠበቋን የሚያረጋግጥ በሆነ ነበር።ለኢትዮጵያዉያን ታሪካዊ ኩራት።የአዲስ አበባና አካባቢዉ ሕዝብ ምናልባት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈቃዱና ፍላጎቱ መሪዉን ባደባባይ ሰልፍ አመስግኖ፣ አድንቆ፣ አወድሶ ሳያበቃ ግን ሕዝቡም መሪዉም በቦምብ ፍንዳታ መሸበራቸዉ ነዉ አሳዛኙ ቁጭት ቅጭት። ዶክተር ሐዩ ቱለማ በየነ ሰንበቱ ሮሚ እንደ ሐገር ሽማግሌ ዛሬም ይመክራሉ። ባለፉት ና ሐምሳ ዓመታት የተፈራረቁት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች፣ የፖለቲካ አቀንቃኞች እና ደጋፊዎቻቸዉ ሰላም፣ አንድነት፣ብልፅግናና ዕድገትን የሚሰብኩትን ያክል ተከታያቸዉን ለማገዳደል፣ ለማነጣጠል፣ ለማቂያቂያም፣ የሚያጣድፉበት፣ እንዲደመጡ የሚሽቱን ያክል ሌሎችን የማያደምጡበት ምክንያት በርግጥ ሊጠና ሊተነተን ሊከለስ ይገባዋል። በ የኤርትራን ሕዝበ ዉሳኔ ለመታዘብ ከፈለጋችሁ ለማስፈፀም በሉት አስመራ የነበሩ አንድ የኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናንን የኤርትራን መገንጠል በግላቸዉ የሚደግፉበትን ምክንያት ጠይቄያቸዉ ነበር። የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግስት ደርግ ባጭሩ ቀይ ኮኮብ ያለዉን ዘመቻ በከፈተበት በ ግድም የሕወሓትን ጦር ይዘዉ ኤርትራ ዘምተዉ እንደነበር ነገሩኝ። ተራራ ስንወጣ ከታች አስከሬን እየረገጥን ካላይ አስከሬን ላይ እየተንጠላጠልል ሲተኮስብን በአስከሬን እየተከለልን እያሉ ቀጠሉ፣ ዘግናኛ ትዝታቸዉን ይከፍልላቸዉ ይመስል ሲጋራቸዉን በላይ በላዩ እየለኮሱ የኤርትራን ነፃነት ከፓርቲያቸዉ አቋም እኩል በግላቸዉ የደገፉት የጦርነትን ዘግናኝ እልቂት ስለተሳተፉበት፣እልቂቱን ለማስቀረት ነዉ።ሰዉዬዉ እንዳሉት።ዛሬም በሕይወት አሉ። ኤርትራ ለሰላም ሲባል በይፋ ነፃ በወጣች በ ኛ ዓመቱ ሁለቱ ሐገራት በገጠሙት ጦርነት መቶ ሺ ወጣቶች መርገፋቸዉ እንጂ የሰላም ቃል፣ተስፋ፣የእምነት ስብከታቸዉ ከንቱነት። በ የተደረገዉ ምርጫ ከኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በኋላ ለኢትዮጵያ የአስተማማኝ ሰላም መሠረት፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ጅምርም መስሎ ነበር።ሌላ ተስፋ። የዉጤቱ ዉዝግብ የመቶዎችን ሕይወት አጥፍቶ፣ የሺዎችን ደም አራጭቶ፣ ሺዎችን ወሕኒ ሲያስዶል ግን ተስፋዉ በንኖ ስቃይ ሰቆቃዉ ነገሰ። ከ ጀምሮ የስቃይ፣ ሰቆቃ፣ አፈና ጭቆናዉን ልክ እያሰላ የደረሰዉ ሕዝብ ካመፅ ሌላ ምርጫ አልነበረዉ።አመፁ መጋቢት በ በተስፋ ሰጪ ለዉጥ እስኪያሳርግ ድረስ ሺዎች፣ የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኞች እንደሚሉት ደግሞ፣ አምስት ሺሕ ወጣቶች ሕይወታቸዉን ገብረዋል። በተስፋ ሰጪዉ ለዉጥ ስልጣን በያዙት በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ላይ በተቃጣ የግድያ ሙከራ የመጀመሪያዎቹ የለዉጥ ማግስት ሰለቦች አብዮት አደባባይ ወደቁ። የዓለም መሪዎች፣ የማንዴላን ትግል ለመዝከር ኒዮርክ ላይ ጉባኤ በተቀመጡበት ዕለት መስከረም ፣ ከብዙዎች ቀድማ ማንዴላን የደገፈችዉ፣ ከብዙዎች በላይ ሰላም የተጠማችዉ ኢትዮጵያ ቡራዩ ላይ በደም አበላ ትለቃለቅ ነበር። ከቡራዩ ጭፍጫ፣ ሐጫሉ እስከተገደለበት ድረስ ለጎሰኞች፣ ለፅንፈኞች፣ ለጥቅም አጋባሾች፣ ለፖለቲከኞች የበላይነት ጥማት ርካታ፣ ከቅማንት እስከ ነገሌ ቦረና፣ ከጂጂጋ እስከ ራያ፣ ከናዝሬት እስከ ጌዲኦ፣ ከሐዋሳ እስከ ደምቢ ዶሎ፣ ከጉሙዝ እስከ አዲስ አበባ ብዙ ሺዎች ረግፋዋል።ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል።በቢሊዮን የሚቆጠር ሐብት ንብረት ወድሟል። ከአንድድ ሥፍራ የሚዘገበዉ ግድያ፣ዘረፋ፣ ቃጠሎ ዉድመት በርግጥ የሰዉ ልጅ በሰዉ ልጅ ላይ ይፈፅመዋል ብሎ ለማሰብ የሚዘግነነን ነዉ።እንደገና ያሬድ ኃይለማርያም። ለኢትጵያዉን የሰላም ዋጋዉ ምን ይሆን ግዛት ሕይወት ንብረት ስደት አመፅ የሥርዓት ለዉጥ ኖቤል ሐብት ንብረት ደግሞስ ስንትና እስከ መቼስ ይሆን ኢትዮጵያዉያን ከ ዓመት ጦርነት በኋላ ትልቅ ግዛት ሰጥተዉ፣ በትንሽ ቀበሌ ሰበብ ከ ሺ የሚበልጡ ወጣቶቻቸዉን ሕይወት ገብረዋል።እንደ ዲሞክራሲዉ ወግ በሰላም መርጠዉ፣ ለዉጤቱ ዉዝግብ መቶዎችን ሰዉተዋል። ከጆርጂያ እስከ ቱኒዚያ፣ ከግብፅ እስከ ዩክሬን እንደሆነዉ ለሥርዓት ለዉጥ ሲታገሉ ብዙ ሺዎች ወሕኒ ተወርዉረዉ፣ የሺዎችን ሕይወት ሰጥተዉ ከሚሹት ደርሰዋል።ከሚሽት በመድረሳቸዉ ሐሴት ፈንድቀዉ ሳያበቁ፣ ከጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እስከ ተራ ወታደር፣ ከብርጌድየር ጄኔራል እስከ ሚሊሺያ፣ ከርዕሰ መስተዳድር እስከ ወረዳ አስተዳዳሪ፣ ከታላቅ መሐንዲስ እስከ ዩኒቨርስቲ ተማሪ፣ ከገበሬ እስከ ከብት አርቢ ብዙ ሺዎችን ጭዳ አርገዋል።ሴቶ ወጣቶ ታግተዋል። መሳጂዶች፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ ፋብሪካዎች፣ ሱቆች፣ ትምሕርት ቤቶች፣ መኪኖች አግይተዋል። ሐዉልቶች፣ ድልድዮች፣ መንገዶች ፈርሰዋል።የዚያኑ ያሕል መሪያቸዉን ለሰላም ኖቤል አብቅተዋልም።ኢትዮጵያ ግን ሰላም የለም። ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድሕን በ በተዘጋጀ አንድ የሐዘን ሥርዓት ላይ ኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ሰዉ ትወልዳለች፣ ግን አታሳዳግም ታቀጭጫለች።ትቀጫለች። ብለዉም ነበር። ኢትዮጵያ በዘር ፖለቲካ ቀዉስ ስትዳክር ወጣቱ ድምፃዊ ሐጫሉ ሑንዴሳ ዘፍኖ፣ ጨፍሮ፣ ተናግሮ ሳይጠግብ ሳይጠግብ ተቀጨ። ሁለት መቶ ያክል ሰዎችም ተገደሉ።ፖለቲከኞች ታሰሩ።መገናኛ ዘዴዎች ተዘጉ።እና የሰላም ዋጋዉ ስንት ይቀረዉ ይሆን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ያሬድ ኃብተማርያም ደግሞ እንዲሕ ይላሉ።
የሐምሌ ዓ ም የትኩረት በአፍሪካ ዝግጅት ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የልዕልት ዙሪያሽ ወርቅ የቀብር ሥርዓት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ትኩረት በአፍሪካ እና የጋዜጦች አምድ መሰናዶዎች ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ትኩረት በአፍሪካ እና የጋዜጦች አምድ መሰናዶዎች ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ትኩረት በአፍሪካ እና የጋዜጦች አምድ መሰናዶዎች ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ትኩረት በአፍሪካ እና የጋዜጦች አምድ መሰናዶዎች ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ትኩረት በአፍሪካ እና የጋዜጦች አምድ መሰናዶዎች ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የ ዎቹ ፓርቲዎች የረሐብ አድማ ውጥንና የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት
ወደ ገደማ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቤቱታችንን ካልሰማ የረሐብ አድማ እናደርጋለን ማለታቸው በማኅበራዊ ድረ ገፅ ተጠቃሚዎች ዘንድ መወያያ ሆኗል። የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች አዲስ ስምምነት ሌላው ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ነበር። አዲሱ የምርጫና እና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ የሕልውናችን አደጋ ሆኗል የሚሉ ፓርቲዎች የረሐብ አድማ ልናደርግ ነው እያሉ ነው። ፓርቲዎቹ እንዳሉት ወደ ረሐብ አድማ ከመሔድ የሚያግዳቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዓመቱ የመጀመሪያ ስብሰባ በጉዳያቸው ላይ ከመከረ ብቻ ነው። ጉዳዩ በማኅበራዊ ድረ ገፆች ነቀፌታ በርትቶበታል። ፍሬው አበበ አባል እና ደጋፊ ያለው ፓርቲ ሲከፋው ሰልፍ ጠርቶ እንኳንስ ገዢውን ምድሩን ያንቀጠቅጣል። የኛዎቹ አባል አልባ ፓርቲዎች የሚጠሩት ቢያጡ በረሀብ አድማ ጮማቸውን እያቀለጡ ያለቅሳሉ ሲል ነቅፈዋቸዋል። ገረመው አያሌው ወትሮም ፓርቲ ያቋቋሙት ለርሀብ ማስታገሻ ነው ወዳጄ አለማፈራቸው የምርጫ ሕግ ካልተሻሻለ የርሀብ አድማ እናደርጋለን አሉ ሲሉ ለፍሬው አበበ በሰጡት መልስ ጠይቀዋል። በዚህ ጉዳይ ባልፅፍ ደስ ባለኝ ሲሉ የጀመሩት ተክሌ በቀለ እኔ በግሌ ሰው ተሁኖም ፖርቲ መመስረት መቻል አለበት ባይ ነኝ። የሀብት ክፍፍል ጥያቄን ሲያስከትል ግን አከፋፋዩ መንግስት በምርጫ ቦርድ በኩል የራሱን መመዘኛዎች ማውጣቱ ተገቢ ነው።ተቃዋሚዎቻችን የርሃብ አድማ ሊያረጉ ነው ሲባል ስሰማ ግን ለውድቀታቸው ማንን ተጠያቂ ሊያደርጉ እንደፈለጉ እየገረመኝ ነው ብለዋል። ግዛቸው አበበ ደግሞ የዐብይ አሕመድ ቡድን በሚሰጠውን መመሪያም ሆነ መሰሪ ምክርን በመጠቀም የፓርቲዎችን ቁጥር መወሰን ተገቢ አይደለም። የዐብይ ቡድን ማድረግ የሚችለው በገንዘብ የሚደጉማቸውንና የማይደጉማቸውን፣ ጽሕፈት ቤት የሚሰጣቸውንና የሚነፍጋቸውን ፓርቲዎች የሚለይበት መመሪያና ደንብ ማውጣት ብቻ ነው። የአገሪቱ አቅም ፓርቲ ነኝ የሚለውን ሁሉ መሸከም ስለማይችል። ነገር ግን አሜሪካ ውስጥ ሁለት ፓርቲዎች ብቻ ነው ያሉት በሚል ተረት የኢትዮጵያን ፓርቲዎች ቁጥር ለመወሰን ተጽዕኖ ማድረጉ አምባገነናዊ አካሄድ ነው። ምርጫ ቦርድ ይህን በዐብይ አሕመድ ጉትጎታ የመጣን ውሰና መተው አለበት። ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት አገር እንዴት ሺሕ በዛ ይባላል የሚለው ምክንያትም ውኃ አያነሳም ሲሉ ከተክሌ በቀለ ጋር በፌስቡክ ባደረጉት ውይይት ላይ ፅፈዋል። ለመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ውጥን ምንድነው በማኅበራዊ ድረ ገፆች መወያያ ሆነው የሰነበቱት ገደማ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታቸውን ማቅረብ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። ዋንኛ ቅራኒያቸው የሚመነጨው በቅርቡ ከጸደቀው አዲሱ የምርጫና እና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ነው። ፓርቲዎቹ ከዚህ ቀደም በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ለመወያየት ተሰብስበው የሕልውናችን ሥጋት በሚሉት በዚሁ የምርጫና እና የፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ሲወዛገቡ ታይተዋል። ፓርቲዎቹ በአዲሱ አዋጅ እንደገና ተመዝገቡ ተብለናል የሚል ቅሬታ አላቸው። የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ሊቀ መንበር አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ እና ዓመታት ሲንገላቱ እና ሲታገሉ የቆዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ አዲስ እንደገና ፓርቲያቸውን አፍርሰው በዚህ ህግ መመስረት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። ፓርቲዎቹ ሕልውናቸውን አጥተዋል የሚሉት አቶ ቶሎሳ አዋጁ አሳሪ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ በበኩላቸው አዋጁ የእያንዳንዳችንን ሕልውና አፍርሶታል ባይ ናቸው። ፓርቲዎቹ ባለፈው ረቡዕ በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ ዓ ም የመጀመሪያው ስብሰባ ጉዳያቸውን እንዲመለከት ጠይቀዋል። አለበለዚያ ከጥቅምት እስከ የረሐብ አድማ እናደርጋለን ሲሉ አስጠቅቀዋል። ለፖለቲካ ፓርቲዎቹ እስካሁን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠ ምላሽ የለም። ፌስቡክ እና ትዊተርን የመሳሰሉ የማኅበራዊ ድረ ገፆች ተጠቃሚዎች ግን በጉዳዩ መነጋገራቸውን ቀጥለዋል። ሐና ጫላ በትዊተር ኢትዮጵያዬ ከኮሜድያኖችሽ የተሻለ የሚያስቁኝ እኮ ፖለቲከኞችሽ ናቸው። የረሀብ አድማ ሲሉ በጉዳዩ መገረማቸውን ገልጸዋል። ታጋይ ህጻናት አሻንጉሊት ካልገዛሽልኝ ምሳዬን አልበላም ይላሉ ከሚል ማነፃጸሪያ የጀመሩት ካሳሁን መሰለ ደግሞ መድረክ አዘጋጅተው መወያየት እና መከራከር ያቃታቸው ታጋይ ፓርቲዎች አዋጁ ካልተሻረ የረሀብ አድማ እንመታለን ማለታቸውን ጠቅሰው ነቅፈዋል። ኤርሚያስ ሙሉጌታ ደግሞ በፖለቲካ ፓርቲዎች የታወጀውን የረሀብ አድማ ተከትሎ የምግብ ዋጋ ይወርዳል ተብሎ ይጠበቃል። ግን አድማ ባይደረግስ ምግብ እኮ የለንም ሲሉ ተሳልቀዋል። ደያሞ ዳሌ ደግሞ በትዊተር ስንት ሕዝብ እየተራበ በአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ሕይወቱን የሚያቆይባትን አገር ለመምራት፤ በምርጫ እንወዳደራለን የሚሉ ፓርቲዎች የሕዝብ ድጋፍ የፓርቲነት መስፈርት መሆኑን በመቃወም የረሀብ አድማ ሲመቱ ከማየት የበለጠ ቀልድ የለም ብለዋል። ኑረዲን ሰዒድ የረሀብ አድማውን እድሜ ልክ ቢያደርጉት ለኛ የኑሮ ውድነቱ ይቀንስልን ነበር። ምክንያቱም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመብዛታቸው የተነሳ ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጿቸው ከፍተኛ ነው ሲሉ ፌስቡክ ላይ ፅፈዋል። ሽመልስ ቶሎሳ ደግሞ ኸረ እባካችሁ እፈሩ። ሺሕ ደጋፊ ማስፈረም ካልቻላችሁ ማንን ልትወክሉ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ እንደበፊቱ በተለጣፊ አይሸወድም ነቄ ሆኗል ብለዋል። ደርቤ ቢሰጥ በበኩላቸው የፓርቲ ጋጋታ ለሀገራችን አይጠቅማትም፤ ሰብሰብ ብላችሁ አቋም ይኑራችሁ። በፓርቲ ስም ገንዘብ ለመሰብሰብና ህዝብን ለማጋጨት ማነሳሳት ይቅርባችሁ ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል። የኦሮሞ ፓርቲዎች ስምምነት በሳምንቱ ዋና ዋናዎቹ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸውን አሳውቀዋል። ፓርቲዎቹ ሰባት ናቸው። ስምምነት በተፈረመበት ዕለት በኦሮሞ ፖለቲካ ከፍተኛ ሚና ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና የለውጥ አራማጆች ተገኝተዋል። እጅግ ደስ የሚል ዜና ነው፣ ኢትዮጵያችን የምትፈልገው በጋራ አንድ ሆኖ ለሕዝቡ መሥራት ነው፣ ባሁኑ ጊዜ የሚያስፈልገው ሌሎችም ፓርቲዎች ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ወስደው መሥራትና መተባበር አለባቸው ያሉት ጀማል አብደላ የፓርቲዎቹን ስምምነት እንደ በጎ እርምጃ ተቀብለውታል። ታደሰ ጌታቸው ይህ ነዉ አንድነት፤ ኦሮሚያም ኢትዮጵያም ተስፋ አላት፣ ፈርጣማ አንድነት ነዉ፤ በዲሞክራሲ ባህል እንዲህ አብሮ መሥራት እንጂ በጠላትነት መፈራረጅ ማብቃቱ ያስደስታል። መባላት ሲቀር ማደግ ይመጣል በማለት እንደ ጀማል አብደላ ሁሉ ደስታቸውን ገልጸዋል። ጂቲ አሬዶ ይሄ ትልቅ ብስለት ነው፤ ሕዝቡም የሚፈልገው ይሄንን ነው፤ በውይይት በጠረጴዛ ዙሪያ መጨረሱም ምን ያህል ወደ ፊት እንደሄዳችሁ የሚያስይ ነው። ሕዝቡም እፎይታን ያገኛል። ጫካ ያሉትምን ለቤታቸው ያብቃቸው ሲሉ ምኞታቸውን ገልጸዋል። ኤርሚ ለ የኦሮሚያ ፓለቲከኞች የተለያየ ሀሳብ ቢኖራቸውም ልዩነታቸውን ወደ ጎን ትተው በሚስማሙበት መልኩ በአንድነት ለሚወክሉት ህዝብ መቆማቸው ከምንም አንፃር ስታየው ትልቅ ውሳኔ ነው። ለክልሉ ሰላም መሰረት ነው፤ ለውጭ ኃይሎች ደግሞ የማይናጋ፤ የማይነቃነቅ ግድግዳ ነው፤ አሁን የጃዋር፣ የኦነግ፣ የአብይ ደጋፊ ብሎ ምንም አይነት ሰላምን የሚያደፈርስ እንቅስቃሴ አይኖርም። ለኦሮሚያ ትልቅ ስራ ነው ሲሉ አተያያቸውን ጽፈዋል። የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲህ አይነት ስምምነት ሲፈፅሙ የመጀመሪያቸው አይደለም። ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ስምምነት ከፈረሙት መካከል የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድና፣ ምክትል ሊቀ መንበርና የመከላከያ ምኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታ እና በኦሮሞ ፖለቲካ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው አቶ ጃዋር መሐመድ ተገኝተዋል። በርካቶች በፌስቡክ እና በትዊተር አሁን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የተፈራረሙት ስምምነት ከከዚህ ቀደሙ በምን ይለያል ሲሉ ጠይቀዋል። ከዚያስ ወደየት የሚል ጥያቄም ያቀረቡም አሉ። ስለ ስምምነቱ በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም የኦሮሞ የፖለቲካ መሪዎችን በአንድ ላይ ያሰባስባል ያሉትን ጋዲሰ ሆጋንሳ ኦሮሞ ለመመስረት መስማማታቸውን በጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። አቶ ለማ መገርሳ የሚመሩት እና አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ መቋቋሙም ተገልጿል። እሸቴ በቀለ
የኦብነግ በምርጫዉ እንደሚሳተፍ አስታወቀ
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ኦብነግ ሃገራዊ ግንባር ሆኖ እንደሚሰራ አስታወቀ። ድርጅቱ ከሰሞኑ ለአንድ ሳምንት ጎዴ ከተማ ላይ ባካሄደው ጠቅላላ ስብሰባውም የቀድሞ ሊቀመንበሩ ሽሮ አዲስ መሪ መርጧል። የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ኦብነግ ሃገራዊ ግንባር ሆኖ እንደሚሰራ አስታወቀ። የትናቱን ዜናችንን ያደመጣችሁ እንደምታስታዉሱት ኦብነግ አንጋፋዉን የግንባሩን ሊቀመንበር ሽሮ አዲስ ሾሟል፤ ዓርማዉን ለወጧልም። ላንድ ሳምንት ያክል ጎዴ ሶማሌ መስተዳድር የመከረዉ ጉባኤ ለ ዓመት ግንባሩን በመሩት በአድሚራል መሐመድ ዑመር ዑስማን ምትክ የቀድሞዉን የግንባሩን ዋና ፀሐፊ አብዱረሕማን ሼሕ ማሪንን ሊቀመንበሩ አድርጎ መርጧል። የግንባሩ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀሰን ሙዓሊን ለድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ በስልክ አንደነገሩት ግንባሩ እስካሁን በሚጠቀምበት አርማ ላይ የነበረዉ የክላሺንኮቭ ምስል በእስኪሪብቶና ንስር እንዲለወጥ ጉባኤዉ ወስኗል። የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ የግንባሩን ቃል አቀባይ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። መሳይ ተክሉ
አዲስ ሊቀመንበርም መረጠ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
አንበጣ በድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ያደረሰው ጉዳት
የድሬደዋ አስተዳደር ግብርና ፣ ውሀ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለ በስልክ እንደተናገሩት በሃያ ስድስት ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው አንበጣ በአስራ ሰባቱ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። መንግስት ችግሩን ለመከላከል አንበጣ በድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ያደረሰው ጉዳት ከቀናት በፊት በድሬደዋ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሃያ ስድስት የገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በአርሶ እና አርብቶ አደሩ ኅብረተሰብ የደረሱ ሰብሎች ላይ መጠነኛ እና ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ መንግሥት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመደገፍ እና ችግሩን ለመከላከል እየሠራሁ ነው ብሏል፡፡ በድሬደዋ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች መካከል በሁሉል ሞጆ እና ዋሂል ገጠር ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ለ እንደገለፁት በአካባቢያቸው የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የድሬደዋ አስተዳደር ግብርና ፣ ውሀ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለ በስልክ እንደተናገሩት በሃያ ስድስት ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው አንበጣ በአስራ ሰባቱ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው መንግሥት ችግሩን ለመከላከል ምን እየሰራ እንደሆነ አስረድተዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ አርሶ አደሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሀመድ ዑስማን በሰጡት አስተያየት መንግሥት ቀድሞ የመከላከል ሠራ ሊሠራ ይገባ እንደነበር ጠቅሰው አሁንም ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል። የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአካባቢዎቹ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የመስክ ምልከታ ማደረጋቸውን ተከትሎ ምክትል ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ በአርሶና አርብቶ አደሩ ዘንድ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ በመግለፅ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡ ትናንት በተዘዋወርኩባቸው የዋሂል ክላስተር ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በደረሱ ሰብሎች ላይ ደረሰው ጉዳት ወትሮውኑ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ምርት በማምረት አብዛኛውን ግዜ በምግብ እህል ድጋፍ ላይ ባተኮረው የሴፍትኔት መርሀ ግብር ይደገፍ ለነበረው አርሶ እና አርብቶ አደር መጪው ጊዜ ከባድ መሆኑን አመላካች ነው፡፡ መሳይ ተክሉ
አንበጣ በድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ያደረሰው ጉዳት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ወጣቶች ማኅበር አመራርና ደጋፊዎች መታሰር
የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባሎቼና ደጋፊዎቼ በፖሊስ እየታሰሩብኝ ነው አለ። ፖሊስ በበኩሉ ሰሞኑን በክልሉ የተደረጉ ሰልፎች ችግር የነበረባቸው ባይሆኑም፤ በባሕር ዳር ከተማ ለሦስተኛ ጊዜ የተደረገውን ስልፍ ወደ አልተገባ አቅጣጫ እንዲሄድ አደረጉ ያላቸውን ተጠርጣሪዎች መያዙን ግን ገልጧል። የአማራ ወጣቶች ማኅበር አባሎቼና ደጋፊዎቼ በፖሊስ እየታሰሩብኝ ነው አለ። ፖሊስ በበኩሉ ሰሞኑን በክልሉ የተደረጉ ሰልፎች ችግር የነበረባቸው ባይሆኑም፤ በባሕር ዳር ከተማ ለሦስተኛ ጊዜ የተደረገውን ስልፍ ወደ አልተገባ አቅጣጫ እንዲሄድ አደረጉ ያላቸውን ተጠርጣሪዎች መያዙን ግን ገልጧል። ሰሞኑን በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች መንግሥትን በብርቱ የሚቃወሙ እና የሚነቅፉ ሰልፎች በተከታታይ ቀናት ተካኺደው ነበር። የተቃውሞ ሰልፈኞቹ የአማራ ተወላጆች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በማንነታቸው ምክንያት እየተገደሉ፤ እየተፈናቀሉና እየተሳደዱ ባለበት ወቅት የክልሉና የፌደራሉ መንግስት ርምጃ አልወሰዱም በሚል ነበር ተቃውሞዋቸውን ያስተጋቡት። የአማራ ተወላጆች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በማንነታቸው ምክንያት እየሞቱ፣ እየተፈናቀሉና እየተሳደዱ ባለበት ወቅት የክለሉና የፌደራሉ መንግስት እርምጃ አልወሰዱም በሚል ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች መንግስትን የሚነቅፉ ሰልፎች ተካሂደዋል። በአብዛኘዎቹ ከተሞች ሰልፎች በሰላም የተጠናቀቁ ሲሆን የአማራ ክልል መንግስት በይፋ የሰልፉን አስተባባሪዎችና ሰልፈኞችን አመስግኗል፡፡ ይሁን እንጂ በባሕር ዳር ለሦስተኛ ቀን በተካሄደውና በፍኖተ ሰላም ሰልፎች ወደግጭት አምርተው በፍኖተ ሰላም አንድ የፀጥታ አባል፣ በባሕር ዳር ደግሞ የአንድ ሰልፈኛ ሕይወታቸው አልፏል፣ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ ንብረትም ወድሟል፡፡ በተለይ በባሕር ዳር ከተማ ሚያዝያ ቀን፣ ዓ ም በባሕር ዳር የተደረገውን ሰልፍ ተከትሎ አመራሮቼና ደጋፊዎቼ እየታሰሩ ነው ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ ቤት አመልክቷል፡፡ የቅርንጫፍ ማኅበሩ ሊቀመንበር ወጣት ቴዎድሮስ ጌታቸው ለዶይቼ ቬለ እንደተናገረው በእለቱ ከነበረው ሰልፍ ጋር በተያያዘ የማኅበሩ ጸሐፊ ትህትና በላይ ቲና እስረኛ ለማስፈታትና የሴቶችን ሰልፍ አስተባብረሻል በሚል ታስራለች ብለዋል፡፡ ከጸሐፊዋ በተጨማሪ አንድ የልዩ ኃይል አባልንና ሌላ የሕግ ባለሞያን ደጋፊዎች ጨምሮ ሌሎች ሰዎች መታሰራቸውን ወጣት ቴዎድሮስ ተናግሯል፡፡ እንደ ወጣት ቴዎድሮስ እርሱን ጨምሮ ሌሎች የማህበሩ አመራሮች የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ገልጧል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ትህትና በላይንና አስረስ ማረን በ ሺህ ብርና ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በ ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ፣ አንዱን ደግሞ በነፃ እንዲሰናበት መወሰኑን የአማራ ወጣቶች ማኅበር የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስፈፃሚ አባል ኃይለሚካኤል ባየህ ለዶይቼ ቬለ በስልክ ተናግረዋል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ከፋለ አንዷለም ግን ሚያዝያ ዓ ም በከተማዋ የተካሄደውን ሰልፍ ወደአልተፈለገ አቅጣጫ ለመምራት የሞከሩ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ሰልፉን አስፈላጊ ወዳልሆነ አቅጣጫ ለመምራት ሰልፈኞች መንገድ ዘግተዋል፣ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆም አድርገዋል፣ ተቋማትን ለመስበር ሞክረዋል፣ በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ነው ሉት ረዳት ኮሚሽነሩ፡፡ ሰልፈኞች እስረኛ ለማስፈታት መሞከራቸውን የተናገሩት ኃላፊው በእለቱይነበረውን ህገወጥ እንቅስቃሴ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉንም ተናግረዋል፡፡ ሚያዝያ ቀን፣ ዓ ም በባሕር ዳር ከተማ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ የፀጥታ ኃይሎችና ሰልፈኞች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ ዶ ር ድረስ ሳህሉ ሰሞኑን ለዶይቼ ቬይሌ መናገራቸው ይታወሳል። ዓለምነው መኮንን
የተፈናቃዮች አቤቱታ በአማራ ክልል
ከኢትዮ ሱዳን የድንበር ግጭት ጋር ተያይዞ በሱዳን የተለያዩ ግዛቶች ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች እንዲወጡ እየተደረጉ መሆኑን አመለከቱ። ከኢትዮ ሱዳን የድንበር ግጭት ጋር ተያይዞ በሱዳን የተለያዩ ግዛቶች ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች እንዲወጡ እየተደረጉ መሆኑን አመለከቱ። ከተለያዩ የሱዳን ግዛቶች ወደ መተማ የገቡት እነዚህ ወገኖች አስፈላጊው ድጋፍ እንዳልተደረገላቸውም እየተናገሩ ነው፡፡ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ከተማ አስተዳደር ቅሬታው ትክክል መሆኑን ሲያረጋግጥ፤ የዞኑ አደጋ መከላከል መሥሪያ ቤት በበኩሉ ድጋፍ ለማድረግ ተዘጋቻለሁ እያለ ነው። ዓለምነው መኮንን
የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮብናል ይላሉ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በኢትዮ ሱዳን የድንበር ግጭት የተፈናቀሉ ናቸው ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በደቡብ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች ታሰሩ
በደቡብ ክልል ከምርጫ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ እንደገለጸው ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ሕጉን የሚፃረሩ ተግባራት ሲያከናወኑ በመገኘታቸው ነው ። በደቡብ ክልል ከምርጫ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ እንደገለጸው ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ሕጉን የሚፃረሩ ተግባራት ሲያከናወኑ በመገኘታቸው ነው ። በሕግ ጥላ ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል ሀሰተኛ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን በፎቶ ኮፒ ማሽን በማባዛት ድምፅ ለመስጠት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ይገኙበታል ተብሏል። ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
የአዲስ አበባ ፖሊስ የጸጥታ ስጋት ያላቸውን እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ ንጥቂያ የሚፈጽሙ፣ ከአሽከርካሪ ወይም ከተሳፋሪ ላይ የእጅ ስልክ፣ የአንገት ሃብል፣ ቦርሳ እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን ቀምተው የሚሰወሩ እንደሚገኙበት ለዶቼቬለ አስታውቋል።ተጠርጣሪዎች የኢትዮጵያን ሰላምና መረጋጋት የማይሹ ካላቸው አካላት ጋር ትስስር ያላቸው መሆኑንም አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት ሆነዋል ያላቸውን ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ባዩ ሽጉጤ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ ንጥቂያ የሚፈጽሙ፣ ከአሽከርካሪ ወይም ከተሳፋሪ ላይ የእጅ ስልክ፣ የአንገት ሃብል፣ ቦርሳ እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን ቀምተው የሚሰወሩ እንደሚገኙበት ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ኃላፊው በተያዙት ግለሰቦች ላይ በተካሄደው ምርመራ ቀጣዩ ኛ ብሔራዊ ምርጫ እና የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን ግንባታን የማደናቀፍ ዓላማን ያነገቡ ያሏቸው ስለመኖራቸው ፍንጭ መገኘቱንም ተናግረዋል።በብዙ ምክንያት የአገሪቱን ሰላምና ፀጥታ በማደፍረስ የአገር ገጽታን ለማጠልሸት መዲናዋ አሸባሪ ላሏቸው አካላት ዋነኛ ትኩረት በመሆኗ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ከፌዴራልና ከኦሮሚያ የፀጥታ መዋቅሮች ጋር እየተሰራ ነውም ብለዋል ሃላፊው። ምርመራ ላይ ያሉት ተጠርጣሪዎች የኢትዮጵያን ሰላምና መረጋጋት የማይሹ ካሏቸው አካላት ጋር ትስስር ያላቸው መሆኑንም አረጋግጠናል ሲሉም አስታውቀዋል፡፡ ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ዘገባ አጠናቅሯል። ስዩም ጌቱ
በአማራ ክልል ም ቤቶች አዳዲስ ድምፆች
በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ የጊዜያዊ ምርጫ ውጤቶች አዲስ በሚመሰረተው የክልልም ሆነ የተወካዮች ም ቤቶች አዳዲስ ድምፅ የሚሰማባቸው ሁኔታዎች እንዲሚኖር ጠቋሚ መሆናቸው ተባለ። ምክር ቤቶች የተለያዩ ፓርቲዎች ድምጾችን ካስተናገዱ ጠንካራ አገራዊ መመሪያ እና ስልታዊ በውይይት ዳብሮ እንዲወጣ ያደርጋል ሲሉ የፖለቲካ ምሁር ተናግረዋል። ኛው አገራዊ ምርጫ በብዙ ሂደቶች አልፎ ፣ የተቆረጠለት የምርጫ ቀን ሁለት ጊዜ ተራዝሞና በአንዳንድ አካባቢዎች በተለያዩ ምክንያቶች አሁንም የምርጫ ጊዜው ሌላ ጊዜ ተቀጥሮለት ባለፈው ሰኞ ምርጫ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ተካሂዶ በአብዛኛው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል። ብዙዎቹ እንደሚያምኑት ምርጫው ከዚህ በፊት ከተደረጉ ምርጫዎች አንፃር ሲታይ በሁሉም መልኩ ሰላማዊና ነፃ ነበር፣ በዚህ ምክንትም ያልተገመቱ ውጤቶችም በጊዜያዊነት እየወጡ እንደሆነ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ ምርጫው ከተካሄደ በኋላ የወጡ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች በክልልና በፌደራል ተወካዮች ምክር ቤቶች የተለያዩ ድምፆች የሚሰሙበት ሁኔታ እንደሚኖርም ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ቻላቸው ታረቀኝም የሚመሰረቱ ምክር ቤቶች ብዝሐ ድምፅ ሊስተናግዱ የሚችሉበት አዝማሚያ እንደሚታይ አስረድተዋል፡፡ አዳዲስ ድምፆች ወደ ክልልም ሆነ ተወካዮች ምክር ቤቶች መግባት ከቻሉ በክርክርና በውይይት የዳበሩ ጠንካራና ገንቢ ፖሊሲዎችንና ህጎችን ለማውጣት ጠቃሚ ሆናልም ብለዋል፡፡ አቶ ቻላቸው እንደሚሉት በምክር ቤቶች የብዝሐ ድምፅ መኖር አዳዲስ ፖሊሲዎችን አጠንክሮ ከማውጣት ባለፈም ቀደም ሲል እንከን የነበረባቸውን ለመከለስም እድል ይፈጠራል፡፡ ከ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለባት ኢትዮጵያ፣ ከ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በመራጭነት ተመዝግቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ዓለምነው መኮንን
የጤና ባለሙያዎችና የህክምና ቁሳቁስ እጥረት የባሕር ዳር
በባሕር ዳር ከተማ ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነው ሀን ጤና ጣቢያ ከፍተኛ የቦታ፣ የቤተሙከራ ቁሳቁስና የባለሙያ እጥረት እንዳለበት የጤና ጣቢያው ሠራተኞች ይገልፃሉ። በባሕር ዳር ከተማ ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነው ሀን ጤና ጣቢያ ከፍተኛ የቦታ፣ የቤተሙከራ ቁሳቁስና የባለሙያ እጥረት እንዳለበት የጤና ጣቢያው ሠራተኞች ይገልፃሉ። በጤና ጣቢያው የቀዶ ጥገናና የማህፀንና ጽንስ ህክምና ባለሙያ አቶ መንግሥት ከበደ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ባሉ ችግሮች ምክንያት ተገልጋዮችን ባግባቡ መርዳት አልተቻለም። የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አስማማው ሞገስ የቦታ እጥረት ችግርን ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ፣ የባለሙያ ቅጥር ለማካሄድም በጀት መመደቡንና ከክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር እየተነጋገርንበት ነው ይላሉ። የቤተሙከራ ቁሳቁሶችን በተመለከተም በሂደት የሚፈቱ እንደሚሆኑ ነው የተናገሩት። ወላዶችን በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ የባለሙያ፣ የቦታ ጥበትና እንዲሁም የህክምና ግብዓቶች እንዳሉባቸው አንዳንድ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች ቅሬታ ያቀርባሉ። ባለሥልጣናቱ ደግሞ ለአንዳንዶቹ መፍትሔ እየተፈለገ እንደሆነ ሲናገሩ፣ አንዳንድ ችግሮችን ደግሞ አንዱ ወደ ሌላው ሲገፋቸው እንደሚታይ ነው የሚጠቀሰቀው፣ ተገልጋይ እናቶችም በተለይ የክፍልና የመገልገያ ቁሳቁሶች እጥረት አጋጥሞናል ብለዋል፡፡ የሀን ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች በተለይ ወላዶችን ለማስተናገድ የክፍል እጥረትና በቂ ባለሙያ አለመኖር ፈተና እንደሆነባቸው ነው ያመለከቱተ። የአገልግሎት ፈላጊ እናቶች ከቀን ቀን እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የባለሙያ፣ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረትና የቦታ ጥበት ከፍተኛ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሆነ ለዶቼ ቬለ አስረድተዋል፡፡ በሀን ጤና ጣቢያ የቀዶ ህክምና ከተደረገላቸው እናቶች መካከል የወ ሮ አዝመራ አበዛውና የወ ሮ ሙሉዬ ቢክስ በሰጡት አስተያት ባለሙያዎቹ ነብስ ለማዳን የሚያደርጉት ጥረት የሚመሰገን መሆኑን ጠቁመው የኦፕሬሽንና የማዋለጃ ክፍሎች ጥበት ግን በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ባለው የክፍል ጥበት ምክንትም እስከ እናቶች በጋራ ህክምና ስለሚወስዱ የግል ሚስጢራቸውን ለግላቸው ማድረግ አልቻሉም፡፡ ዓለምነው መኮንን
ትኩረት የሚሻው የእናቶች ጤና
እናትነት ወልዶ ልጅን ማቀፍ ብቻ ሳይሆን ወደዚያ የሚያደርሰው የምጥ ስቃይም የሚታሰብበት ነው። የሕክምና ርዳታ እንደልብ በማይገኝባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ነፍሰጡሮች ልጅን በመውለድ ሂደት ለተለያዩ ችግሮች እንደሚዳረጉ የሚታይ የሚሰማ ጉዳይ ነው። በተመድ ከተቀረጸው ዘላቂነት ያለው የልማት ግቦች በወሊድ ወቅት ሕይወታቸውን የሚያጡ እናቶችን ቁጥር መቀነስ አንዱ ነው። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ይህን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት ከሚያደርጉ አዳጊ ሃገራት ተርታ ብትሆንም፤ አብዛኛዉ ሕዝቧ በከተማ አካባቢ የሚኖር ባለመሆኑ ሀኪም ቤት ውስጥ በዘርፉ በሰለጠኑ ሃኪሞች እጅ የመውለድ ዕድሉ ያላቸው ዛሬም ብዙ የሚባሉ አይደሉም። የሃኪም ቤቶች ርቀት አንድ ነገር ሆኖ የተለያዩ መረጃዎችን በሚያራጩት እንደፌስ ቡክ ያሉ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አሳዛዥና አስደንጋጭ የመውለድ ሂደት ገጠመኞችም አልፎ አልፎ ይነበባሉ። ኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት እየሻሻለ እና እየተስፋፋ ካለባቸው አዳጊ ሃገራት ተርታ የምትጠቀስ ሀገር ሆናለች። በተለይ የስነተዋልዶ ጤናን በተመለከተ ኅብረተሰቡ በአሁኑ ጊዜ ሀኪምቤት መውለድ ያልተጠበቁ አስደንጋጭ አጋጣሚዎችን ስጋት ሊቀንስለት እንደሚችል እየተገነዘበ መምጣሉት ለዶቼ ቬለ ኃትስአፕ መስመራችን ከደረሱን አስተያየቶች መረዳት ይቻላል። ግን ደግሞ ይላሉ አስተያየት ሰጪዎቹ በሀኪም እጅ የመገላገሉ ፍላጎት ቢኖርም የቦታው ርቀት የአገልግሎቱ ደረጃ ዝቅ ማለት ብዙ ነፍሰጡሮች በቤት ውስጥ እንዲገላለገሉ አስገድዷቸዋል የሚሉና የመንገድ ርቀትን የባለሙያ እጥረትን የሚያሳዩ በርከት ያሉ አስተያየቶች ናቸው የደረሱን። ከአስተያየቶቹ አብዛኞቹ ከእናቶች የጤና አገልግሎት አኳያ አማራ ክልል ውስጥ ይታያል ያሉትን ጉድለት የሚጠቆሙ በመሆናቸው ወደክልሉ የጤና ቢሮ ደወልን። በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የፈውስ ሕክምና እና ተሐድሶ አገልግሎት የሥራ ሂደት ባለቤት የሆኑት አቶ አበበ ዳኘውን አገኘን። ከእሳቸው እንደተረዳነው በክልሉ እስከ ሚሊየን የሚደርስ ሕዝብ አለ ተብሎ ይገመታል፤ ለዚህ ሕዝብም በተለይ ለእናቶች እና ሕጻናት የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ጤና ጣቢያዎች እና የመጀመሪያ ደረጃ ሃኪም ቤቶች አሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጤና ኬላዎችም እንዲሁ። እስከኅብረተሰቡ በወረደው የጤና ኤክስቴንሽን ስልትም ለነፍሰጡር እናቶች ተገቢዉ ትምህርት እና ክትትል እንደሚደረግ ይናገራሉ ኃላፊው። ለመውለድ የደረሱ ነፍሰጡሮችን በአቅራቢያቸው በሚገኙ የጤና ኬላዎች ማዋለድ የማይቻል ሲሆን ደግሞ በቅብብሎሽ ስርዓቱ መሠረት ለከፍተኛ የህክምና ርዳታ ወደሃኪም ቤቶች የሚሻገሩበት መስመርም ተዘርግቶ እየተሰራበት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። ለዚህ አገልግሎትም ከ የሚበልጡ አምቡላንሶች ክልሉ እንዳሉትም አቶ አበበ ዘርዝረዋል። ኅብረተሰቡ ስለሚያገኘው የሕክምና ሆነ የአምቡላንስ አገልግሎት ሁኔታ በኋትስአፕ የተላኩልንን አስተያየቶች አንስተን እንዴት ይመዝኑታል አልናቸው አቶ አበበን። ዝርዝሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤ ሸዋዬ ለገሠ
አንበጣ እና ተምች በክረምት
የዓለም የምግብ ድርጅት ከሰሞኑ በመካከለኛው ምሥራቅ እና ከሩቅ ምሥራቅ አካባቢ የአንበጣ መንጋ ቀንሶ ሲታይ፤ በተቃራኒው እድገታቸውን የጨረሱ አንበጣዎች የመን ውስጥ ተስፋፍተው መታየታቸውን አመልክቷል። ከመን ድንበር ተሻግሮ አንበጣ ወደ ሰሜን ሶማሊያ፤ ደቡባዊ ኤርትራ እና ወደ ምሥራቃቂ ኢትዮጵያ ግዛቶች መግባቱንም አሳስቧል። የዓለም የምግብ ድርጅት በእንግሊዝኛው ምህጻሩ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ይፋ ያደረገው ማሳሰቢያ፤ በኢራን፤ በሳውድ አረቢያ እና ፓኪስታን ተንሰራፍቶ የከረመው የአንበጣ መንጋ በዚህ ወር መቀነሱን ያመለክታል። እንደሚለው በተጠቀሱት ሃገራት ሺህ ሄክታር መሬትን አስግቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ሊቀንስ የቻለው በአየር ጠባዩ መድረቅ እና ሙቀት በመጨመሩ እንዲሁም በተደረገው ጠንካራ ቁጥጥር እና ክትትል አማካኝነት ነው። በዚህ አካባቢ ቀነሰ የተባለው የአንበጣ መንጋ የመን ላይ ተጠናክሮ መታየቱን፤ ከዚያም አልፎ ባሕር ተሻግሮ ወደ ሰሜን ሶማሊያ፣ ብሎም ደቡባዊ ኤርትራ እና ምሥራቅ ኢትዮጵያም መዝለቁንም ያሳያል። በእነዚህ ሃገራት በዚህ ወቅት ዝናብ የመኖሩ አጋጣሚ እድገቱን የጨረሰው አንበጣ እንቁላል በመጣል መስፋፋቱን ለማፋጠን እንደሚሞክር በማመልከትም ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እንዲሁም ሳውድ አረቢያ ከወዲሁ እንዲጠነቀቁም አሳስቧል። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለውን እንዲገልፁን የጠየቅናቸው በግብርና ሚኒስቴር የእጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘብዲዮስ ሰላቶ፤ በተለያዩ አካባቢዎች የተበታተነ አንበጣ ቢታይም በመንጋ መልኩ እንዳልተከሰተ እና የመቆጣጠሩ ሥራ እየተሠራ ነው ይላሉ። መንጋ እኮ አይደለም ይሄ ምንድነው ኖርማሊ ኢትዮጵያ የአንበጣ መራቢያ ወይም ይሄ ብሪዲንግ ሲዝን የሚባል አላት። ያው በዝናብ ወራት ከጎረቤት ሃገራት በተለይ ከየመን ወደ ሶማሌላንድ ሲመጣ ከሶማሌላንድ ወደ ኢትዮጵያ አንበጣ የሚገባባቸው፤ አንዳንዴ ደግሞ የራሳችንም በተናጠል የሚኖር አንበጣ ምቹ የአየር ጠባይ አግኝቶ ቁጥሩ የሚጨምርበት ወራት አሉ። ስለዚህ አሁን ይሄ በጣም ትልቅ ክሰት አይደለም፤ መንጋ የምንለውም አይነት አይደለም። የእጸዋት ጠር የሆኑት አንበጣዎች ለመራባት የሚፈልጉት ምቹ የአፈር አይነት እና አካባቢ መኖሩን የሚናገሩት ባለሙያው ይህንንም ኅብረተሰቡ ስለሚያውቅ አስቀድሞ ክትትል ለማድረግ እንደሚረዳም ገልጸዋል። በ አማካኝነት አንበጣ ሊመጣባቸው ያሉ አካባቢዎች ሃገራት ማስጠንቀቂያ እንደሚሰጣቸው፤ ያንን መሠረት በማድረግም እያንዳንዴ ሀገር የየራሱን ዝግጅት ማለትም አሰሳ እንዲሁም የመከላከል ሥራ እንደሚሠራም አስረድተዋል። ችግሩ ሲሰፋ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሲያስፈልግ ደግሞ፤ አህጉራዊም ዓለም አቀፋዊም ትብብር እንደሚደረግም ዘርዝረዋል። አቶ ዘብዲዎስ እንደገለፁት ባለፈው ሳምንት ማሳሰቢያውን አውጥቷል። በዚህ ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያም ተጠቅሳለች። እና በቂ ዝግጅት ተደርጎ ይሆን አዎ በቂ ዝግጅት፤ አሁን ምንድነው ሎጂስቲክ ማዘጋጀት ነው፤ ያው ምንድነው አንበጣ ቁጥሩ እየጨመረ ከመጣ በጸረ ተባይ ነው ሌላ ምርጫ የለም። ኢትዮጵያ ያላት የግብርና ኤክስቴንሽን ስርዓት ጠንካራ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዘብዲዮስ ሰላቶ፤ ተገቢው ስልጠና በቀበሌዎች ደረጃ እየተሰጠ ዝግጅቱ መጠናከሩን ገልጸውልናል። በክረምቱ ከወዲሁ የዝናቡ ሁኔታ ጥሩ መሆኑን ከብሔራዊ ሜቲሪዎሎጂ የሚደርሳቸው መረጃ እንደሚያስረዳ የሚናገሩት የግብርና ሚኒስቴር የእጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፤ በቆላማ አካባቢዎች ከሚታየው በቀር በቂ ዝናብ እንደሚኖር ያላቸውን ተስፋም አጋርተውናል። ዝናቡ መኖሩ ለአዝርዕቱም ሆነ ለኅብረተሰቡ ጤና መልካም ቢሆንም አጋጣሚውም ለአንበጣው መራባት ምቹ መሆኑ ይነገራል። ምን ያህል ያሰጋ ይሆን አሁንም አቶ ዘብዴዎስ፤ ትክክል ነው አሁን ምንድነው ለአንበጣ መራቢያ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ ተብለው ከሚታሰቡ የአየር ጠባይ ሁኔታዎች አንዱ ዝናብ ነው። መድኃኒት በሚረጭበት ጊዜም ሰብሎች እንዲሁም ጠቃሚ የሆኑ እንደንብ ያሉት ፍጠረታት ችግር እንዳይደርስባቸው የሚደረግ ጥንቃቄ ይኖር ይሆን አቶ ዘብዲዎስ ርጭሩ ሰብል ላይ እንደማይደረግ፣ የአንበጣው ማደሪያ እና ማረፊ የታወቀ በመሆኑ ሰዓቱን ጠብቁ በተወሰነ አካባቢ ብቻ እንደሚረጭ ነው ያስረዱት። የንብ ቀፎ በስፍራው ካለም ወደሌላ ቦታ ለተወሰኑ ቀናት እንዲዛወር እንደሚደረግም ዘርዝረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የታየው አንበጣም ቀድሞ ዝግጅት በመደረጉ ያን ያህል ጉዳት ያደርሳል የሚል ስጋት እንደሌለም ተናግረዋል። አንበጣ በተፈጥሮ የሚከሰት ድንበር የማያግደው ከቦታ ወደቦታ ምቹ ስፍራ እና ወቅትን እየመረጠ የሚገኝ ጸረ ሰብል ፍጥረት ነው። አንበጣን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቢጠናከርም ቁጥሩን በመቀነስ የሚያደርሰውን ጉዳት ለማሳነስ ከሚደረገው በዘለለ ጨርሶ ማጥፋቱ አዳጋች መሆኑን አቶ ዘብዲዎስ ገልጸዋል። ከዚህም ሌላ ባለሙያው እንደሚሉት በአሁኑ ጊዜ ከአንበጣ በበለጠ በመላው ሀገሪቱ ተስፋፍቶ የሚገኙ ሌላው የእህል ጠር አርሚዎርም የሚባለው የተምች አይነት ነው። ምንም እንኳን ይህ የተምች አይነት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ቢገኝም ተበራክቶ ከተከሰተ አንበጣ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ነው የገለፁት። ለምን ቢባል የሚመርጠው የእህል ዘር ስለሌለው እንደሆነ ባለሙያው ገልጸዋል። የዓለም የምግብ ድርጅት በዘንድሮው የኢትዮጵያ የክረምት ወቅት የአንበጣዎች መራባት ደረጃ ወትሮ ከነበረው ሊበረክት እንደሚችል፤ ሌሎች ትናንሽ ትሎችም ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰሜን ሶማሊያ፤ በሱዳን፤ የመን፤ እንዲሁም በሕንድ እና ፓኪስታን የድንበር አካባቢ ተበራክቶ ሊከሰቱ እንደሚችሉም አሳስቧል። ሸዋዬ ለገሠ
የሐዘን መግለጫ ስነ ስርዓት ለሟች የበረራ ሰራተኞች
የኢትዮጵያ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማኅበር ትናንት ቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ህይወታቸውን ያጡ ስምንት የበረራ ሰራተኞችን እና ሰዎችን አስበው ውለዋል። በመርሐ ግብሩ የታደሙ አውሮፕላኑን ያበረው የነበሩት ካፒቴን ያሬድ ትሁት እና ሰው አክባሪ እንደነበሩ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር አባላት ትናንት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ሲበር በተከሰከሰው አውሮፕላን ህይወታቸውን ላጡ ባልደረቦቻቸው እና ተጓዦች ሃዘናቸውን ሲገልጹ ውለዋል፡፡ ሐዘን በተጫነው እና በርካቶች በታደሙበት በዚህ መርሐ ግብር የማህበሩ አባላት የበረራ ሰራተኞችን ሻማ በማብራት አስበዋቸዋል። በጋራ ለሃዘን የተቀመጡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ሁሉንም ሟች ባልደረቦቻቸውን እየጠቀሱ፣ ትጋታቸውን እና ስነምግባራቸውን እያስታወሱ፣ ጥቁር ለብሰው፣ በሃዘን እንባ ሲራጩ ውለዋል። አደጋው እጅግ እንዳሳዛናቸው የተናገሩት እነዚህ የስራ ባልደረቦች ህይወታቸውን ያጡት የበረራ ሰራተኞች ታታሪዎችና ምስጉን ከመሆናቸው የተነሳ መልካም እና ጠንካራዎቹ ተሰባስበው ሄዱብን እንዲሉም አድርጓቸዋል፡፡ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ካፒቴን የሽዋስ ጌታሁን በተለይ ዋና አብራሪ የነበረው ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው የቅርብ ጓደኛቸው እንደነበሩ እና ዘወትር ማክሰኞና ሐሙስ አብረው ኳስ ይጫወቱ እንደነበር ለ ተናግረዋል፡፡ አስደንጋጩ አደጋ ባይከሰት ለሀዘን ሳይሆን እንደወትሮው ለኳስ ነበር የምንገናኘው ብለዋል። በሀዘን መግለጫ ስነ ስርዓቱ ላይ የታደመውን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰለሞን ሙጬን ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። ሰለሞን ሙጬ
የሐዘን መግለጫ ስነ ስርዓት ለሟች የበረራ ሰራተኞች መግቢያ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሰሞኑ ኹከትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስሞታዎች
ከሃጫሉ ግድያ ጋር የሚያገናኛቸው ጉዳይ ያልታወቀ ንጹሀን ዜጎች ላይ ለተፈጸመው ግድያና ለደረሰው የንብረት ውድመት ተገቢው ፍትህ እንዲሰጥ የሚጠይቁ ጥቂት አይደሉም ።በግድያው ሰበብ የደረሱ አሰቃቂ የደቦ ግድያዎች ፣ከባድ የንብረት ውድመት የሰዎች መፈናቀል እንዲሁም እስር ብዙ ጥያቄዎችን እያስነሱ ነው ። ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በአዲስ አበባና በኦሮምያ የተለያዩ ከተሞች በጥፋት አድራሾችና እነርሱን ለመከላከል በተሰማሩ ኃይሎች ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን በሃገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ዘግበዋል በግድያው ሰበብ የደረሱ አሰቃቂ የደቦ ግድያዎች ፣ከባድ የንብረት ውድመት የሰዎች መፈናቀል እንዲሁም እስር ብዙ መልስ የሚያሻቸው ጥያቄዎች እያስነሱ ነው ። መንግሥት በግድያውና በከግድያው በኋላ በተነሱ ሁከቶች ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሰዎች የእስር ይዞታም በሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ተተችቷል።የአንዳንድ እስረኞች ጠበቆችም ደንበኞቻቸው የተያዙባቸው ስፍራዎች ለዘመኑ የጤና ችግር ለኮቪድ የሚያጋልጡ ናቸው ሲሉ አቤት እያሉ ነው።ፍርድ ቤት የቀረቡ እስረኞችም ይህንኑ ችግር ማንሳታቸው አልቀረም።ሲያዙ መደብደባቸውን የተናገሩም አሉ።ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባለፈው ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ደግሞ መንግሥት የያዛቸው በርካታ ያላቸው ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ያሉበትን ቦታ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል።ከሃጫሉ ግድያ በኋላ ደረሱ የተባሉ የመብት ጥሰቶች፣ ምክንያታቸውና ችግሩን በዘላቂነት መከላከያ መፍትሄው የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው። በዚህ ውይይት ላይ የተሳተፉት አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ አማካሪ፣ እንዲሁም አቶ ፍስሀ ተክሌ በዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ናቸው። ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ። ኂሩት መለሰ
በኦሮሚያ ክልል ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ የኢ ሰ መ ኮ መግለጫና የክልሉ መንግስት ምላሽ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል አሳሳቢ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት መፈፀምን የተመለከተ መግለጫ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወቅቱን ያልጠበቀና የተሳሳተ ሲል አጣጣለ፡፡ መግለጫው ባንድ ወቅት የወጣና የእርምት እርምጃ ተወስዶበት የታለፈ ቢሆንም የኢ ሰ መ ኮ ለምን እንደ አዲስ እንዳወጣ አይታወቅም ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል አሳሳቢ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት መፈፀም ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ያወጣውን መግለጫ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ወቅቱን ያልጠበቀውና የተሳሳተ ሲል አጣጣለ፡፡ የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት መግለጫው ባንድ ወቅት የወጣና የእርምት እርምጃ ተወስዶበት የታለፈ ቢሆንም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለምን እንደ አዲስ እንዳወጣ አይታወቅም ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ምርመራ አድርጎ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ በክልሉ ከህግ አግባብ ውጭ የሚታሰሩ ሰዎች መበራከታቸውን እና ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ ስዩም ጌቱ
የፕላስቲክ ብክለት መዘዞች
አሁን የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎችን ያሳሰበው የፕላስቲክ ውዳቂዎች ክምችት ብቻ ሳይሆን በለውጥ ሂደቱ በአፈርም ሆነ በውኃ አካላት ላይ የሚያስከትሉት ብክለት ነው። በቅርቡ በደቡብ ኢትዮጵያ ቦረና ዞን ውስጥ ከብቶች የሚጣሉ ላስቲኮችን ከምግብ ጋር አብረው እየበሉ ለጤና እክልና ለሞት መዳረጋቸውን ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በየቦታው የሚጣሉ ያገለገሉ ፕላስቲኮች የመላው ዓለም ችግር ከሆኑ ውለው አደሩ። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የእነዚህ ፕላስቲኮች በምን ያህል ጊዜ ተበጣጥሰው በመበስበስ ወደአፈርነት ይቀየራሉ የሚለው ዛሬም ትልቅ ጥያቄ ነው። ምክንያቱም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ሂደቱ በመቶዎችና በሺህዎች በሚገመቱ ዓመታት ሊወስድ ይችላል። አሁን የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎችን ያሳሰበው የእነዚህ ፕላስቲኮች ክምችት ብቻ ሳይሆን በለውጥ ሂደቱ በአፈርም ሆነ በውኃ አካላት ላይ የሚያስከትሉት ብክለት ነው። በቅርቡ በደቡብ ኢትዮጵያ ቦረና ዞን ውስጥ ከብቶች የሚጣሉ ላስቲኮችን ከምግብ ጋር አብረው እየበሉ ለጤና እክልና ለሞት መዳረጋቸውን ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ዶክተር ፍራኦል ዋቆ በቦረና ዞን ዳስ ወረዳ የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ባልደረባ ናቸው። ከሙያ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በሰኔ ወር ከአንዲት ጊደር ሆድ ኪሎ የሚመዝን ፌስታል ያወጡ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ኪሎ የሚመዝን ፕላስቲክ ከከብት ሆድ በቀዶ ጥገና አውጥተዋል። የእንስሳት ህክምና ባለሙያው ለዚህ ዋናው ችግር ደግሞ ሰዎች ፕላስቲክ ቆሻሻን የሚያስወግዱበት ግዴለሽነት የተሞላው በመሆኑ ነው ይላሉ። የፕላስቲክ ቆሻሻ አወጋገድ በእንስሳት ብቻ ሳይሆን በሰው ጤናም ሆነ በአፈር ላይ የከፋ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑም መንግሥት አጠቃቀምና አወጋገድን የሚመለከት ደንብ ቢያወጣ እንደሚበጅም መክረዋል። በዚህ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ የማይቻል ከሆነ ግን እንደሌሎች ሃገራት ፕላስቲክ ወደሀገር እንዳይገባ ማገዱ ይበጃልም ባይ ናቸው። ኢትዮጵያ የከብት ሃብት አላቸው ከሚባሉ ግንባር ቀደም ሃገራት ተርታ የምትሰለፍ መሆኗ ይታወቃል። ግን ደግሞ የእንስሳቱን ጤና በተመለከተ ያን ያህል ትኩረት እንዳልተሰጠ ከባለሙያው ለመረዳት ችለናል። አቶ አሬሮ ተሪ ከብቶቻቸውን በፕላስቲክ መዘዝ አጥተዋል፤ በቀዶ ህክምናም ከሆዳቸው ፕላስቲክ የወጣላቸውም አሉ። ከወራት በፊት ነበር ከብቶቻቸው ውኃ ለመጠጣት ከሄዱበት አካባቢ መመለስ ሳይችሉ ቀርተው በዚያው የሞቱት። ሲታረዱም ከሆድ ዕቃቸው ውስጥ በርካታ ላስቲክ መከማቸቱ ታወቀ። በዚህ ጊዜ ወደእንስሳት ሃኪሞች ዘንድ ለመውሰድ ወሰኑ። የእሳቸው ጊደር በቀዶ ህክምናው መዳኗን በማረጋገጣቸውም ሌሎች የአካባቢው አርብቶ አደሮች ይህን ርዳታ መፈለጋቸው የማይቀር ነው። ዶክተር ፍራኦል በቦረና ዞን አንድም እንኳ የረባ የእንስሳት ህክምና መስጫ እንደሌለ ነው የገለፁት። ለሁለቱ ከብቶች ቀዶ ህክምናውን ከሰው የጤና ባለሙያዎች በተገኘ ማደንዘዣ መሥራታቸውን ነግረውናል። ኢትዮጵያ እንዳላት የከብት ብዛት ለዘርፉ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባም አሳስበዋል። ሸዋዬ ለገሠ
የሐዋሳ ሐይቅ የተጋረጠበት አደጋና መፍትሔዉ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የጣና ሐይቅ እና የተደቀኑበት ችግሮች
በደለል መሞላትና በፍሳሽ ቆሻሻ መመረዝ ሌላኛው በጣና ሐይቅ ላይ የህልውና ሥጋት መሆኑን ነዋሪዎችና ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነው፣ ጉዳቱን ባፋጣኝ መከላከል ካልተቻለ በአካባቢና በጤና ላይ የደቀነው አደጋ የከፋ መሆኑም እየተነገረ ነው፡፡ የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃ ስራና የፍሳሽ ማስወገድ ተግባራት ያለማቋረጥ ሊሰራ እነደሚገባ ደግሞ የአማራ ክልል የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን አሳስቧል፡፡ የፌደራል መንግስት ባለድርሻ አካላትም ከሐይቁ ከመጠቀም ውጪ ለሐይቁ ህልውና የሚያደርጉት ድጋፍ የለም ተብሏል፡፡ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ተንሳፋፊ የእምቦጭ አረም የጣና ሐይቅን በስፋ በመውረሩ የሐይቁ ህልውና ጥያቄ ላይ ወድቋል፡፡ አረሙን ለማጥፋት እየተሰራ ነው ቢባልም የቅንጅትና የቁርጠኝነት እጦት በሐይቁ ላይ የደቀነው ሁሉ አቀፍ ችግር ከጊዜ ወደጊዜ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ የሐይቁን ህልውና የሚፈታተኑ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች እተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በስነምህዳርና ብዝሓይወት ዙሪያ ተመራማሪ የሆኑት እና በጣና ሐይቅ ህልውና ዙሪያም በርካታ የምርምር ሥራዎች ያካሄዱት ዶ ር ዓለማየሁ ዋሴ ደለልና የፍሳሽ ቆሻሻ ተፈጥሯዊ የሆነውን የጣና ሐይቅ እየበከለ፣ እንዲሁም፣ ወንዞች ከእርሻ ማሳ ይዘውት የሚመጡት ማዳበሪያ አዘል ደለል በሐይቄ ላይ ሄቪ ሜታል ስለሚፈጥሩ በሰዎች ላይ የጤና ችግር፤ አጠቃላይ በሀይቁ ብዛ ሕይወት ላይ ደግሞ ጥፋት እየፈጠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የጣና ሐይቅ ስነ ምህዳር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መዝገቡ ዳኘው ተቋማቸው የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች የአካባቢ ችግርን በሚፈታ መልኩ መሰራታቸውን መቆጣጠር መሆኑን ጠቁመው በዚህ ረገድ ከፍተኛ ክፍተቶች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ ፍሳሽ ወደ ሐይቁ በሚለቁ አካላት ላይ ደግሞ ርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ገልጸዋል። ጣናን ለማዳን የአንድ ወገን ጥረት ውጤት አያመጣም ያሉት አቶ መዝገቡ በተላይ የሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት አካላት ተሳትፎ የለም ነው ያሉት፡፡ ዓለምነው መኮንን
አዉሮጳና ጀርመን የኮሮና ስርጭትና መከላከያዉ በአዉሮጳ
አዉሮጳ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርሺኝ መጠኑን እየለዋወጠ፣ ወረርሺኙን ለመከላከል በየሐገሩ የሚወሰደዉ እርምጃም ጠንከርና ላላ እያለ እንደቀጠለ ነዉ።የወረርሺኙ መከላከያ ክትባት በተፈለገዉ ፍጥነት ለሕዝቡ አልተዳረሰም።የክትባቱ አሰጣጥ አዝጋሚነት የአዉሮጳ ሕብረትን ለጠንካራ ትችት አጋልጦታል። የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት እዚህ ብራስልስ ባደረጉት ስብሰባ በተለያዩ አገሮች የሰባዊ መብት ጥሰትን ይፈጽማሉ፣ ያስፈጽማሉ ባሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የማዕቀብ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ማዕቀቡ የጉዞ ዕገዳ የሚያደርግና የንብረት ማንቀሳቀስን የሚከለክል ሲሆን፣ ውሳኔ የተላለፈባቸውም ከቻይና ስሜን ኮሪያ፣ ሊቢያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢርትራና ሩሲያ የተመረጡ አስራ አንድ ግልሰቦችና አራት ተቋማት መሆናቸው ተገልጿል። የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦሪየል በሰጡት መግለጫ፣ እርምጃው በሰባዊ መብት ጥሰቶች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፣ እርምጃው ኢላማ ያደረገው የትም ይሁን የት ግን ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች ላይ ነው። ሁሉም የአውሮፓ ህብረት የማዕቀብ እርምጃዎች የዓለማቀፍ ህግን ተከትለው ተግባራዊ ይሆናሉ በማለትም አፈጻጸማቸው አብራርተዋል። የማዕቀቡ እርምጃ ከተወሰደባቸው አራቱ ግለሰቦች፣ በቻይና ዚንጂያንግ ግዛት በሙስሊሞች ላይ በሚፈጸሙ ከፍተኛ የሰብዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂዎች መሆናቸው ተገልጿል። አሜርካ ብርታኒያና ካናዳ በቻይና ላይ ተመሳሳይ የማእቀብ እርማጃዎችን በመውሰድ፣ የአውሮፓ ህብረትን እንደተቀላቀሉ የታወቀ ሲሆን፣ እ እ እ በ ዓም በቲአናንመን አደባባይ ግድያ ምክኒያት ህብረቱ አሳልፎት ከነበረው ማዕቀብ ወዲህ፣ የአውሮፓ ህብረት በቻያና የማዕቀብ ውስኔ ሲያሳልፍ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል ቻይና ህብረቱ ያሳለፈውን የማዕቀብ ውሳኔ ተከትሎ፣ በ አውሮፓውያን ግለስቦችና ተቋማት ላይ የአጸፋ እርምጃ የወሰደች መሆኑን አስታውቃለች። ሚስተር ቦርየል ይህ የቻይና እርምጃ፣ ህብረቱ እየወሰዳቸው ካሉት ህጋዊ እርምጃዎች አያስቆመውም በማለት ፣ ቻይና እንደዚህ አይነት የአጸፋ እርምጃዎች ውስጥ ከምትገባ፣ ወደ ውይይት እንድትመጣ ጥሪ አቅርበዋል። የማዕቀቡ እርምጃ ኢላማ ካደረጋቸው ሶስት የአፍርካ አገሮች አንዷ በሆነችው ኤርትራ ላይ ማቀቡ የተጣለው፣ በሚፈጸሙ የሰባዊ መብት ጥሰቶች፣ ግድያዎችና የሰዎች መሰወር ወንጀሎች ምክኒያት መሆኑ ተገልጿል። ማዕቀቡ ኢላማ ያደረገውም በተለይ የኢርትራ ብሄራዊ ደህንነት ቢሮና ሀላፊው ጀነራል አብርሀ ካሳ ላይ ነው። በውሳኔው ላይ የኢርትራን መንግስት አስተያየት ለማካተት ያደርግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም ግን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን፣ በኢርትራ መንግስትና ህዝብ ላይ ያነጣጠረና መሰረት በሌለው ክስ ላይ የተመሰረተ ሲል አጣጥሎታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ላይም የተወያዩ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ህላፊው በጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል። በትግራይ ክልል ከተፈጠረው ችግር ወዲህ በየእለቱ በርካታ የሰባዊ መብት ጥሰት ዘገባዎች የሚደርሷቸው መሆኑን የገለጹት ሚስተር ቦሪየል፣ ይህ ሁኒታ መቀጠል የሌለበት በመሆኑ አሁንም ግፊታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። የስባዊ እርዳታ ያለገደብ በሁሉም ቦት እንዶደርስ፣ የተፈጸሙ ሰባዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ቡድን እንዲጣሩና የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ግፊታችንን እንቀጥላለን በማለት በሰባዊ መብት ጥሰት ተጠያቄ በሆኑ ላይ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች እያጤኑ መሆኑንም አስታውቀዋል። ሀላፊው አክለውም የፊንላድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሚስተር ፔካ ሃቪስቶ ለተመሳሳይ ተለእኮ በድጋሜ ወደ ኢትዮጵያ የሚሂዱ መሆኑንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሚስተር ሃቪስቶ በአንድ ፖሎቲኮስ በተሰኘ ጋዜጣ በሰጡት ስተያየት፣ በኢትያጵያ ሰሜናዊ ክፍል ባለው ሁኒታ ሶስት መሰርታዊ ችግሮችና ያዩ መሆኑን አውስተው፤ እነሱም የሰብዊ እርዳታ ጉዳይ፣ የሰባዊ መብት ጥሰቶችና የጦርነቱ መቆምና የሰላም መከበር ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል ። በሁለቱ ማለት የሰባዊ እርዳታ መድረስና የሰባዊ መብት ጥሰቶች ምርመራ ላይ፣ አንዳንድ መሻሻሎች እየታዩ ቤሆንም፣ በሶስተኛውና በማዕከላዊው መንግስትና የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ውይይት እንዲያካሂዱ የማድረጉ ጉዳይ ግን አስቸጋሪ እንደሆነ አስታውቀዋል ፣ መንግስት አማጽያኑ መሳሪያቸውን አውርደው እጃቸውነ እንዲሰጡ እየጠየቀ ቢሆንም፣ ይህ ግን በቀላሉ እውን ይሆናል ብለው እንደማይምኑና ለተሻለ ውጤትም የአውሮፓ ህብረት ከአሜርካ ጋር በህብረት ቢሰራ ጥሩ እንደሚሆን ለጋዜጣው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል። የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅት አዉሮጳ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርኝ ያደረሰዉን ጉዳትና ወረርሺኙን ለመከላከል የአዉሮጳ ሕብረት የሚያደርገዉን ጥረት ይቃኛል። ገበያዉ ንጉሴ
በደቡብ አፍሪቃ የቀጠለው የውጭ ዜጎች ጥቃት እና የሽብር ስጋት በሶማሊያ
ደቡብ አፍሪቃ በስደተኞች ጥላቻ እና የኃይል ጥቃቶች ጋር ስትታገል ዓመታትን አስቆጥራለች። ባለፈው ዓመት መስከረም በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያን ስደተኞችን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ወቅትም በሀገሪቱ ለሚታየው ሥራ አጥነትና ወንጀል ስደተኞችን ተጠያቂ አድርገዋል። በደቡብ አፍሪቃ ተባብሶ የቀጠለው የውጭ ዜጎች ጥቃት እንዲሁም አልሸባብ ከመጭዉ የሶማሊያ ሀገራዊ ምርጫ በፊት የሽብር ጥቃቶችን ሊፈፅም ይችላል መባሉ።የዛሬው የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅት የሚዳስሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው። ደቡብ አፍሪቃ በስደተኞች ጥላቻ እና የኃይል ጥቃቶች ጋር ስትታገል ዓመታትን አስቆጥራለች። ባለፈው ዓመት መስከረም በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያን ስደተኞችን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ወቅትም በሀገሪቱ ለሚታየው ሥራ አጥነትና ወንጀል ስደተኞችን ተጠያቂ አድርገዋል። በዚህ ተቃውሞ ንብረትነታቸው የውጭ ዜጎች የሆኑ መደብሮች የተዘረፉ ሲሆን በሁከቱም የሰው ህይወት ጠፍቷል የአካል ጉዳትም እንዲሁ። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች በቅርቡ ባወጣዉ ዘገባ በደቡብ አፍሪቃ የውጭ ዜጎች ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን አመልክቷል። በጥቃቶቹ በርካታ በሀገሪቱ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ሰለባ ቢሆኑም ፤ጥቃት ያደረሱ ከባድ ወንጀለኞችን ከአጭር ጊዜ እስር በኋላ መልቀቅ ወይም በጭራሽ ክስ አለመመስረት እንዲሁም ለህጋዊ ስደተኞች የመታወቂያ ወረቀቶች መከልከልና ያለበቂ ምክንያት በእስር ማንገላታትን የመሳሰሉ አድሎአዊ አሰራሮች በደቡብ አፍሪቃ በውጭ ዜጎች ላይ ይፈፀማል ፡፡ በዚህም በርካታ የውጭ ዜጎችና ቤተሰቦቻቸው የደህንነት ስጋት አንዣቦባቸዋል።የዕለት ተዕለት ህይወታቸውንም በአግባቡ ማከናወን አይችሉም።ኮንጓዊቷ ዶኔት ኒጎኒፊም ያጋጠማት ይሄው ነው።ዶኔት በዚህ ወቅት ትምህርት ቤት መሄድ የነበረባት ቢሆንም፤ በደህንነት ስጋት ከቤተሰቦቿ ጋር ቤት ውስጥ መቆየትን መርጣለች። በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት አልሄድም ፡፡ ትምህርቴ ላይም ማተኮር አልችልም። ህይወቴ ተመሰቃቅሏል። ምርጫ ቢኖረኝ ኖሮ እዚህ አልኖርም።ይህንን ሀገር ለዘላዓለም ለቅቄ እወጣ ነበር። ከ ዓመታት በፊት ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በስደተኝነት ወደ ኬፕታውን የመጡት የዶኔት ወላጆች የተሻለ ሕይወት ተስፋ አድርገው ነበር። ዶኔት በትምህርቷ ጥሩ ውጤት ያላት ተማሪ ነች። ይህንን የተመለከቱ አስተማሪዎቿም የክፍል አለቃ አድርገው መርጠዋታል።በክፍል ጓደኞቿ ዘንድ ግን ተቀባይነት አላገኘም። ምክንያቱም እነሱ የሚፈልጉት ሌላ ተማሪ የክፍል አለቃ እንዲሆን ነው። ደቡብ አፍሪቃዊ የሆነ ሌላ ሰው።ሁል ጊዜ አንቺ ደቡብ አፍሪቃዊ አይደለሽም።አንቺ የውጭ ዜጋ ነሽ። እኛ የምንሰራውን ስራ ለመንጠቅ ወደ ሀገራችን መምጣት አትችይም።ሁል ጊዜ ይህንን ነው የሚሉኝ። ከአንድ ዓመት በፊትም ከክፍል ጓደኞቿ በደረሰባት ድብደባ ሆስፒታል ገብታ ነበር። ደበደቡኝ የተወሰኑት ሆዴ ላይ ረጋገጡኝ። አንዲት ጓደኛዬ ልትረዳኝ ፈልጋ ነበር ፤ግን ምንም ማድረግ አልቻለችም። ምክንያቱም ወለል ላይ ወድቄ መላው የክፍል ተማሪ እየደበደበኝ ነበር። አስተማሪው እንኳ ምንም ማድረግ አልቻለም።ዝም ብዬ አለቀስኩ። ምክንያቱም ማንም ሊረዳኝ አልቻለም ነበር። ብላለች እንባ እየተናነቃት። ከጆሃንስበርግ የአፍሪካ ዲያስፖራ ፎረም አሚር ሸክ እንደሚሉት፤ እንደ ዶኔት ባሉ የውጭ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት የተለመደ ነው። በየዕለቱ እንዲህ አይነት ነገር ያጋጥመናል። ከሶማሌ ማኅበረሰብ ብቻ በአማካኝ በየቀኑ አንድ ሰው እናጣለን።በተመሳሳይ ሁኔታም ባንግላዲሽ እና ኢትዮጵያውያንም ይገደላሉ። በቅርብ ጊዜ ውስጥ በቶኮዛ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች መደብሮች ተዘርፈዋል ሰዎችም ተፈናቅለዋል።ይህ በየቀኑ ይከሰታል ።ነገር ግን በመገናኛ ብዙሃን የሚቀርቡት የጅምላ ጥቃቶች ብቻ ናቸው። ብለዋል። የከተማ ንግድ በውጭ ዜጎች ጥላቻ ለሚፈፀም ጥቃት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን የሚገልፁት ሶማሊያዊው አሚር ሸክ፤ የደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ችግሮች ውጥረቱን የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል ባይ ናቸው።ምክንያቱም በኮሮና ወረርሽኙ ሳቢያ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በደቡብ አፍሪቃ ሥራቸውን አጥተዋልና።የሳቸው ድርጅት በሳምንት አንድ ጊዜ የምግብ ስርጭቶችን ያስተባብራል። አድልኦ ስለተፈፀመብህና ስለተገለልክ አድሎ መፈፀም የለብህም። በሚል መሪ ቃልም በችግር ላይ ላሉና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ደቡብ አፍሪቃውያን የምግብ ልገሳ ያደርጋሉ። ሸኪ እንደሚሉት በደቡብ አፍሪካ እየጨመረ የመጣውን ውጥረት ለማርገብ የዘረኝነትን አስከፊነት በተመለከተ ሰዎችን ማስተማር አስፈላጊ ነው። በሌላ በኩል የደቡብ አፍሪቃ መንግስት በወረርሽኙ የተከሰተውን ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማቃለል የ ቢሊዮን ዩሮ የእርዳታ መርሀ ግብር አቋቁሟል። ነገር ግን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተገን ጠያቂዎች ፣ ስደተኞች እና ሰነድ አልባ ስደተኞችን ተጠቃሚ አይደሉም። ምንም እንኳ በሀገሪቱ የውጭ ዜጎች ጥላቻ ቢኖርም አንዳንድ ደቡብ አፍሪቃውያን በዚህ ጉዳይ መንግስታቸውን ይተቻሉ። እዚህ ስላልተወለዱ ብቻ የውጭ ዜጎችን መተው ፍትሃዊ አይደለም። እዚህ የመጡት ኢኮኖሚያችንን ለማገዝ ነው። ስለሆነም እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ልንረዳቸው ይገባል። ወደ ኬፕታወን ስንመለስ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጣችው ዶኔት ኒጎፊኒ የዘረኝነትና የመድሎ ሰለባ የሆኑ ሌሎች ህፃናትን ለመርዳት አንድ ቀን የህግ ባለሙያ የመሆን ህልም አላት፡፡ለጊዜው ግን እሷን የደበደቧት የክፍል ጓደኞቿ በፈፀሙት ድርጊት አልተቀጡም። የሽብር ስጋት በሶማሊያ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት የአልሻባብ ታጣቂ ቡድን በቅርቡ የሶማሊያ ብሔራዊ ጦርን ፣ በደቡባዊ ሶማሊያ የሚገኙ የመንግስት የጦር ሰፈሮችንና ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ያደረጉ በርካታ ጥቃቶችን ፈፅሟል።በዚህ ጥቃት ወታደራዊ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፡፡አልሸባብ በዋናነት ከአሜሪካ ጦር የአየር ድብደባ እየደረሰበት ቢሆንም ፣ ታጣቂው ቡድኑ በመንግስትና በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል።ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ በመላው የአፍሪካ ቀንድ ወደ የሚጠጉ በታጣቂ ቡድኑ የተፈፀሙ የሽብር ጥቃቶችም ተመዝግበዋል ። ጥቃቱ እየጨመረ የመጣው ደግሞ ሀገሪቱ በዚህ ዓመት መጨረሻ ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ባለችበት ወቅት ነው።ያ በመሆኑ አልሸባብ ከመጭዉ የሶማሊያ ሀገራዊ ምርጫ በፊትም በርካታ የሽብር ጥቃቶችን ሊፈፅም ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል። የቀድሞው የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ እና በአሁኑ ወቅት ሂራል የተባለው የሞቃዲሾ የደኅንነት ጥናት ተቋም መስራችና ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሁሴን ሸኪ አሊ ለተባባሰው የፀጥታ ችግርና ለአልሸባብ ጥቃት መባባስ ምክንያት ናቸው ከሚባሉት በርካታ ጉዳዮች ውስጥ ሶስቱን ይጠቅሳሉ። የመጀመሪያው በአጋሮች ውጤታማ የሆኑ የአፀፋ ርምጃዎች ካልተወሰዱ፤ ማለትም የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግሥት፣የክልል ግዛቶች፣በአፍሪካ ህብረት ኃይሎች ና በአሜሪካ አየር ሀይል ድጋፍ ካላደረጉ ፣ በሁለተኛ ደረጃ በአየር ሁኔታ በዝናብ ወቅት የጎርፍ አደጋ ተልዕኮውን የሚጎዳ ከሆነ ፣ሶስተኛው ጦርነት ለማካሄድ የሚስፈልጉ ቁሳቁሶች በቂና የተመጣጠኑ ካልሆኑ፤ በቅርቡ አልሸባብ በመላ ሀገሪቱ ተልዕኮውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይችላል። በሌላ በኩል በቀጣይ በሚካሄደው የምርጫ መመሪያ ላይ በክልል አመራሮች እና በፌዴራል መንግስቱ መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባት ለሀገሪቱ ሌላው ስጋት ሲሆን፤ ሁለቱ ወገኖች በሞቃዲሾ ለቀናት ባካሄዱት ውይይት ውዝግቡ መፍትሄ ያገኘ ይመስላል። መሪዎቹ ከ የምርጫ ሂደት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቀጥተኛ ያልሆነ ምርጫ ህዳር ቀን ለመጀመር ተስማምተዋል ። ከዚያ በኋላ የምርጫ ልዑካን ፕሬዚዳንቱን የሚሰይሙ የፓርላማ አባላትን ይመርጣሉ።ይህ ስምምነት በሀገሪቱ ምርጫውን ተከትሎ የታዩ ስጋቶችን የሚቀርፍ ቢሆንም፤ በፀጥታ ተግዳሮቶች እና በፖለቲካ ፉክክር ሳቢያ ሂደቱ በጉዞው ላይ መሰናክሎች ያጋጥሙት ይሆናል የሚሉ አሉ። በምርጫ ሂደት ላይ አለመግባባትን በተመለከተ የደህንነት ተንታኙ ሁሴን በመሪዎቹ መካከል ትብብር አለመኖር የበለጠ የፀጥታ ችግር ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው ፡፡ ሀገሪቱ እርግጠኛ ባልሆነ የምርጫ ሰሌዳ ውስጥ እየገባች ነው።ምክንያቱም እስካሁን ስምምነት የለም።ይህም አልሸባብ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው ስቃይና የደህንነት ስጋት የበለጠ እንዲጨምር ያደርጋል። ይሁን እንጅ ከፌዴራል መንግስት እና ከክልል መንግስታት የተውጣጡ አመራሮች በመጪው ምርጫ ላይ ሰሞኑን ስምምነት ሲያደርጉ፤ የሶማሊያ የፓርላማ አባላት በሂደቱ ውስጥ ለመሳተፍ በተወካዮች ደህንነት ላይ ስጋት ነበራቸው።ምክንያቱም ከዚህ ቀደም አልሸባብ የቀድሞ የምርጫ ልዑካንን ዒላማ ያደረገ ጥቃት በመፈፀም በርካታ ሰዎች በተለያዩ ከተሞች ገድሏልና። የቀድሞው የሶማሊያ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ጄኔራል አብዲራሂም ሙሐመድ ቱርየር በበኩላቸው የአልሸባብ ታጣቂዎች የመንግስት ተቋማን በማውደም የመንግሥት ባለሥልጣናትን ለማስፈራራትና በምርጫው ተስፋ ለማስቆረጥ እየሰራ ነው ብለው ያምናሉ። የጨመረው የአልሸባብ ጥቃት የመንግስት ባለስልጣናትን ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮችና የአፍሪቃ ህብረት ተልኮ በሶማሊያ ሀይሎች ላይም ተፅዕኖ ማሳደሩ አልቀረም። ያም ሆኖ የአሜሪካ ጦር በአየር ላይ በሚሰነዘሩ ጥቃቶች ቁልፍ የአልሸባብ ታጣቂዎችን እና የጦር ሰፈሮችን በማጥቃት ላይ ይገኛል።በዚህ መሰሉ የአየር ጥቃት የአሜሪካ ጦር በጎርጎሪያኑ ነሐሴ ቀን አብዱልቃድር ኮማንዶ የተባለ አንድ ከፍተኛ የአልሸባብ ታጣቂን ገደልኩ ማለቱ ይታወሳል። በአጠቃላይ የሽግግር ጊዜ የሽብር ቡድኑ የመንግስትን የአገልግሎት መስጫዎችን ለማውደም ከሚሞክሩባቸው የምርጫ ወቅቶች ውስጥ አንዱ በመሆኑ የስጋት ድባብ ቢነግስም፤ በአሁኑ ወቅት ከሰላሳ ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ፣ የባህር ላይ ወንብድና እንዲሁም ከፅንፈኝነት አስተሳሰቦች የማገገም የተስፋ ምልክት በሀገሪቱ መኖሩን ተንታኞች ይገልፃሉ።