topic
stringlengths
16
333
news
stringlengths
16
46.2k
የኮሮና ወረርሺኝ በአዉሮጳ
አዉሮጳ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርሺኝ መጠኑን እየለዋወጠ፣ ወረርሺኙን ለመከላከል በየሐገሩ የሚወሰደዉ እርምጃም ጠንከርና ላላ እያለ እንደቀጠለ ነዉ።የወረርሺኙ መከላከያ ክትባት በተፈለገዉ ፍጥነት ለሕዝቡ አልተዳረሰም አዉሮጳ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርሺኝ መጠኑን እየለዋወጠ፣ ወረርሺኙን ለመከላከል በየሐገሩ የሚወሰደዉ እርምጃም ጠንከርና ላላ እያለ እንደቀጠለ ነዉ።የወረርሺኙ መከላከያ ክትባት በተፈለገዉ ፍጥነት ለሕዝቡ አልተዳረሰም።የክትባቱ አሰጣጥ አዝጋሚነት የአዉሮጳ ሕብረትን ለጠንካራ ትችት አጋልጦታል። የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት እዚህ ብራስልስ ባደረጉት ስብሰባ በተለያዩ አገሮች የሰባዊ መብት ጥሰትን ይፈጽማሉ፣ ያስፈጽማሉ ባሏቸው ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የማዕቀብ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ማዕቀቡ የጉዞ ዕገዳ የሚያደርግና የንብረት ማንቀሳቀስን የሚከለክል ሲሆን፣ ውሳኔ የተላለፈባቸውም ከቻይና ስሜን ኮሪያ፣ ሊቢያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢርትራና ሩሲያ የተመረጡ አስራ አንድ ግልሰቦችና አራት ተቋማት መሆናቸው ተገልጿል። የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦሪየል በሰጡት መግለጫ፣ እርምጃው በሰባዊ መብት ጥሰቶች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፣ እርምጃው ኢላማ ያደረገው የትም ይሁን የት ግን ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች ላይ ነው። ሁሉም የአውሮፓ ህብረት የማዕቀብ እርምጃዎች የዓለማቀፍ ህግን ተከትለው ተግባራዊ ይሆናሉ በማለትም አፈጻጸማቸው አብራርተዋል። የማዕቀቡ እርምጃ ከተወሰደባቸው አራቱ ግለሰቦች፣ በቻይና ዚንጂያንግ ግዛት በሙስሊሞች ላይ በሚፈጸሙ ከፍተኛ የሰብዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂዎች መሆናቸው ተገልጿል። አሜርካ ብርታኒያና ካናዳ በቻይና ላይ ተመሳሳይ የማእቀብ እርማጃዎችን በመውሰድ፣ የአውሮፓ ህብረትን እንደተቀላቀሉ የታወቀ ሲሆን፣ እ እ እ በ ዓም በቲአናንመን አደባባይ ግድያ ምክኒያት ህብረቱ አሳልፎት ከነበረው ማዕቀብ ወዲህ፣ የአውሮፓ ህብረት በቻያና የማዕቀብ ውስኔ ሲያሳልፍ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል ቻይና ህብረቱ ያሳለፈውን የማዕቀብ ውሳኔ ተከትሎ፣ በ አውሮፓውያን ግለስቦችና ተቋማት ላይ የአጸፋ እርምጃ የወሰደች መሆኑን አስታውቃለች። ሚስተር ቦርየል ይህ የቻይና እርምጃ፣ ህብረቱ እየወሰዳቸው ካሉት ህጋዊ እርምጃዎች አያስቆመውም በማለት ፣ ቻይና እንደዚህ አይነት የአጸፋ እርምጃዎች ውስጥ ከምትገባ፣ ወደ ውይይት እንድትመጣ ጥሪ አቅርበዋል። የማዕቀቡ እርምጃ ኢላማ ካደረጋቸው ሶስት የአፍርካ አገሮች አንዷ በሆነችው ኤርትራ ላይ ማቀቡ የተጣለው፣ በሚፈጸሙ የሰባዊ መብት ጥሰቶች፣ ግድያዎችና የሰዎች መሰወር ወንጀሎች ምክኒያት መሆኑ ተገልጿል። ማዕቀቡ ኢላማ ያደረገውም በተለይ የኢርትራ ብሄራዊ ደህንነት ቢሮና ሀላፊው ጀነራል አብርሀ ካሳ ላይ ነው። በውሳኔው ላይ የኢርትራን መንግስት አስተያየት ለማካተት ያደርግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም ግን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን፣ በኢርትራ መንግስትና ህዝብ ላይ ያነጣጠረና መሰረት በሌለው ክስ ላይ የተመሰረተ ሲል አጣጥሎታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ላይም የተወያዩ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ህላፊው በጋዜጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል። በትግራይ ክልል ከተፈጠረው ችግር ወዲህ በየእለቱ በርካታ የሰባዊ መብት ጥሰት ዘገባዎች የሚደርሷቸው መሆኑን የገለጹት ሚስተር ቦሪየል፣ ይህ ሁኒታ መቀጠል የሌለበት በመሆኑ አሁንም ግፊታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። የስባዊ እርዳታ ያለገደብ በሁሉም ቦት እንዶደርስ፣ የተፈጸሙ ሰባዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ቡድን እንዲጣሩና የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ግፊታችንን እንቀጥላለን በማለት በሰባዊ መብት ጥሰት ተጠያቄ በሆኑ ላይ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች እያጤኑ መሆኑንም አስታውቀዋል። ሀላፊው አክለውም የፊንላድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሚስተር ፔካ ሃቪስቶ ለተመሳሳይ ተለእኮ በድጋሜ ወደ ኢትዮጵያ የሚሂዱ መሆኑንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሚስተር ሃቪስቶ በአንድ ፖሎቲኮስ በተሰኘ ጋዜጣ በሰጡት ስተያየት፣ በኢትያጵያ ሰሜናዊ ክፍል ባለው ሁኒታ ሶስት መሰርታዊ ችግሮችና ያዩ መሆኑን አውስተው፤ እነሱም የሰብዊ እርዳታ ጉዳይ፣ የሰባዊ መብት ጥሰቶችና የጦርነቱ መቆምና የሰላም መከበር ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል ። በሁለቱ ማለት የሰባዊ እርዳታ መድረስና የሰባዊ መብት ጥሰቶች ምርመራ ላይ፣ አንዳንድ መሻሻሎች እየታዩ ቤሆንም፣ በሶስተኛውና በማዕከላዊው መንግስትና የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ውይይት እንዲያካሂዱ የማድረጉ ጉዳይ ግን አስቸጋሪ እንደሆነ አስታውቀዋል ፣ መንግስት አማጽያኑ መሳሪያቸውን አውርደው እጃቸውነ እንዲሰጡ እየጠየቀ ቢሆንም፣ ይህ ግን በቀላሉ እውን ይሆናል ብለው እንደማይምኑና ለተሻለ ውጤትም የአውሮፓ ህብረት ከአሜርካ ጋር በህብረት ቢሰራ ጥሩ እንደሚሆን ለጋዜጣው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል። የዛሬዉ አዉሮጳና ጀርመን ዝግጅት አዉሮጳ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ወረርኝ ያደረሰዉን ጉዳትና ወረርሺኙን ለመከላከል የአዉሮጳ ሕብረት የሚያደርገዉን ጥረት ይቃኛል። ገበያዉ ንጉሴ
ትኩረት በአፍሪካ መስከረም ዓ ም ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
አዉሮጳና ጀርመን የኮሮና ስርጭትና መከላከያዉ በአዉሮጳ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ቢብሎኪ ልጆችን በጨዋታ የሚያስተምረው ኢትዮጵያዊ መተግበሪያ
ቴክኖሎጂ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዘርፎች ላይ ተፅዕኖ የሚያደርግ አስፈላጊ ክህሎት ነው። በዚህ የቴክኖሎጅ ዓለም ልጆች ገና በለጋ ዕድሜያቸው ከዚህ ክህሎት ጋር ማስተዋወቅ ወሳኝ መሆኑ ይነገራል። ቢቤሎኪ የተባለ ኢትዮጵያዊ ትምህርት ነክ መተግበሪያ ልጆችን በጨዋታ መልክ በማስተማር ለዚህ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው። ቴክኖሎጂ በአሁኑ ወቅት የዓለምን እድገትና እያንዳንዱን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚዘውር ሞተር ሆኗል።በዚህ የተነሳ የዲጅታል ቴክኖሎጂ ዕውቀት ከምን ጊዜውም በላይ አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል። በዚህ ለቴክኖሎጂ ጥገኛ በሆነ ዓለም ውስጥ ታዲያ የልጆች አስተዳደግና ትምህርትም ከዓመታት በፊት ከነበረው በዕጅጉ የተለዬ ሆኗል። ያ በመሆኑ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ፣ ታብሌቶች እና ዲጂታል ጨዋታዎች በልጆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ እየተካተቱ ነው።ስለሆነም ልጆች እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በሚጠቀሙ ጊዜ ከእነዚህ ቴክኖሎጅዎች ጀርባ ያለውን አመክንዮ በመረዳት የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩና አዳዲስ ነገሮችን እንዲማሩ ማድረግም ወሳኝ ነው። ይህንን በመገንዘብ ይመስላል ቢብሎኪ የተባለ ኢትዮጵያዊ መተግበሪያ ልጆችን በጨዋታ መልክ በማስተማር ዕውቀት እንዲጨብጡ በማበረታታት ላይ ይገኛል።ሰላም ጤና ይስጥልን አድማጮቻችን የዛሬው የሳይንስና ቴክኖሎጅ ዝግጅትም በዚሁ መተግበሪያ ላይ ያተኩራል አብራችሁን ቆዩ። ቢብሎኪ ናታን ዳምጠው በተባለ ኢትዮጵያዊ ወጣት የተሰራ መተግበሪያ ሲሆን፤ ዓላማውም ልጆች መሰረታዊ የኮምፒተር ፕሮግራም ዕውቀት እንዲኖራቸው ለማድረግ በጨዋታ መልክ ትምህርት መስጠት ነው። መተግበሪያው ኮድ ወይም የመለያ ስም አሰጣጥን ልጆች ሊገነዘቡት በሚችሉት ሁኔታ በቀላሉ ለመማር የሚረዳ ሲሆን፤ የመማር ሂደቱን ለልጆች አስደሳች እና ሳቢ ለማድረግም ስዕላዊ መግለጫዎችን ይጠቀማል። የ ቢብሎኪ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ወጣት ናታን ዳምጠው ይህንን መተግበሪያ የሰራው የኮሚፒዩተር ሳይንስ የመጨረሻ ዓመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ እያለ በ ዓ ም ሲሆን፤ መነሻውም በዩንቨርሲቲ ቆይታው ያጋጠመው ችግር ነበር። ይህ ትምህርት ነክ ቴክኖሎጅ ከ እስከ ዓመት ዕድሜ ላላቸው ልጆች የተዘጋጀ ሲሆን ምንም አይነት የኮምፒዩተር እውቀት የማይጠይቅ በመሆኑ ለጀማሪ ልጆችም ተስማሚ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አፍሪቃዊ መተግበሪያው እንደመሆኑ መጠን የአህጉሪቱን ተግዳሮቶች በመረዳት በተንቀሳቃሽ ስልክ ያለ በይነመረብ ግንኙነት የሚሰራም ነው። መተግበሪያውን የበለጠ አሳታፊና እና አስደሳች ለማድረግ የጨዋታውን አጠቃላይ ሁኔታ ወደ እውነተኛው ዓለም ለማምጣት ገፀ ባህሪያትን ይጠቀማል።በዚህም ልጆች እንደ ፐዝል ያሉ ምርምርና ብዙ ማሰብ የሚጠይቁ ጨዋታቸውን ሲጫወቱ የጨዋታውን እንቆቅልሽ ለመፍታት በሚጥሩበት ጊዜ አዲስና የተሻለ የመማሪያ መንገድን መለማመድ ይችላሉ ፡፡ በመተግበሪያው ልጆች በቅደም ተከተል መስቀመጥን፣ ቀለበት መስራትን በመሳሰሉ ጨዋታዎች መሰረታዊ የኮምፒዩተር ፕሮግራሞችን የሚማሩ ሲሆን፤ለዚህ የሚያግዙ ፈታኝ ደረጃዎች አሉት። ልጆች እያንዳንዱን ደረጃ ሲጨርሱ እንደ አፈፃፀም ውጤታቸው አዲስ ብሎኪ ዎች ለመግዛት የሚጠቀሙት ምዕናባዊ ሳንቲሞችን ይሸለማሉ። ብሎኪዎች የጨዋታው ገፀ ባህሪያት ሲሆኑ ትልልቅ ጭንቅላትና ዓይኖች እንዲሁም ያልተመጣጠነ ትናንሽ አካላት ያላቸው የጨዋታ ገፀ ባህሪያት ናቸው። የእነዚህ አሻንጉሊት መሰል ገፀ ባህሪያት ቅርፅ ጨዋታውን ለልጆች አስደሳች ያደርገዋል።ከዚህ በተጨማሪ ገፀ ባህሪያቱ በቀለምም ሆነ በአለባበስ ራሳቸው ልጆቹን የሚመስሉና እንዲሁም ከዚህ ቀደም በአካባቢያቸው የሚያውቋቸው በመሆናቸው ለልጆቹ እንግዳ አይደሉም። ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ አድዋን የሚመለከቱ ገፀባህሪያትን ማካተታቸውን የሚናገረው ናታን፤ ይህንን ማድረግ የፈለጉበት ዋናዉ ምክንያትም አብዛኛዎቹ ዲጅታል የልጆች ጨዋታዎች ከአፍሪቃዉያን ነባራዊ ሁኔታ ጋር ብዙም ቀረቤታ የሌላቸውና አካባቢውን የማይመስሉ በመሆናቸው ያንን ክፍተት ለመሙላት ነው። ናታን እንደሚለው ቢብሎኪ በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ መተግበሪያ ሲሆን በቅርቡም የተሻሉ ፅንሰ ሀሳቦችንና ተጨማሪ ተግባራትን ያካተተ ቢብሎኪ በሚል መጠሪያ መተግበሪያውን አሻሽሏል። በዚህም የውስጠ መተግበሪያ መማሪያ ፣ የወላጅ ቁጥጥር እና ሌሎች ማሻሻያዎች ተደርገውበታል። መተግበሪያው በአሁኑ ጊዜ ላይ በነፃ የሚጫን ሲሆን ፤እስካሁን ድረስ በዓለም ዙሪያ ከ በላይ የሆኑ ሰዎች እየተጠቀሙበት መሆኑን ናታን ገልጿል፡፡በሚቀጥሉት ከ እስከ ባሉት ዓመታት ደግሞ ለ ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ቢብሎኪ ን ተደራሽ ለማድረግና በተለይም ለአፍሪካቃውያን መሠረታዊ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ችሎታዎችን የማስጨበጥ ዕቅድ አለው። ይህንን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግም መተግበሪያው የተለያዩ የአፍሪቃ ቋንቋዎችንና ታዋቂ አፍሪቃዉያንን በገፀ ባህሪነት እንደሚያካትት ይናገራል። ልጆች በወደፊት ህይወታቸው በየትኛውም የሙያ መስክ ቢሰማሩ አዳዲስ ነገሮችን ፈጣሪዎች እንዲሆኑ የዲጂታል ክህሎት በጣም አስፈላጊ ነው።ይሁን እንጅ ድሃ ሀገራት ከዚህ በጣም የራቁ ናቸው።በመሆኑም የዲጂታል ዕውቀት የእኩልነት ጥያቄ በመሆኑ የቴክኖሎጅ ዕውቀትን መቅሰም ዕድለኛ እና ልዩ መብት ላላቸው ጥቂት ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም መዳረስ እንዳለበት አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያች ይከራከራሉ ። በዚህ ረገድ ቢብሎኪን የመሳሰሉ ሀገር በቀልና አካባቢያቸውን ችግር የተገነዘቡ የቴክኖሎጅ ፈጠራዎች የሚጫወቱት ሚና ቀላል አይደለም። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው እንዲያደምጡ እንጋብዛለን። ፀሐይ ጫኔ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን አስታወቀ
ዓለምም የኢትዮጵያ ህዝብም ያተኮረበት ከሁለት ቀናት በኋላ የሚካሂደው ስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን አስታወቀ። ዓለምም የኢትዮጵያ ህዝብም ያተኮረበት ከሁለት ቀናት በኋላ የሚካሂደው ስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን አስታወቀ።የኢዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር የከተማይቱን ጸጥታ ለማስጠበቅ በደንብ ተዘጋጅቷል። ኮማንደር ፋሲካ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣የወቅቱን የፀጥታ ሁኔታና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ ያስገባ ያሉትን እቅድ ማውጣቱን ፣ እያንዳንዱ የፖሊስ አባልም ስለ እቅዱ ግንዛቤ እንዲጨብጥ መደረጉን ተናግረዋል።ፀጥታ አስከባሪዎች መከተል ያለባቸው፣ የአሰራር ስርዓትና የስነ ምግባር መመሪያም ተዘጋጅቷል ብለዋል ኮማንደር ፋሲካ ፣ፖሊስ ድምጽ ለመስጠት የሚመጣውን ህዝብ ትኩረት የሚስብና የስነ ልቡና ጫና ሊፈጥር የሚችል ካሉት የተለየ እንቅስቃሴ መቆጠብ እንዳለበት ፣ለምርጫ አስፈጻሚዎችም መመሪያ ወይም ምክር መስጠት እንደማይችልም ገልጸዋል። ነጋሽ መሐመድ
አሳሳቢው የውኃና የምግብ ጥራት
የታሸጉ ውኃና ምግቦች አመራረት እና አያያዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ መሄዱን አንዳንድ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይናገራሉ። የምግብ እና ውኃ አምራቾች ችግሩ የምርቱ አቀማመጥ ነው ይላሉ። የምግብ እና መድሐኒት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ደግሞ ተገቢውን ቁጥጥር ለማድረግ የባለሞያዎች እጥረት እንዳለ ይገልጻል። የታሸገ ውኃና የምግብ ምርቶች በህብረተሰቡ ዘንድ በየጊዜው ቅሬታ እያስነሱ፤ ስጋትም እየፈጠሩ ነው። በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው እንደሚሉት ጥራቱ ባልተጠበቀ የታሽገ ምግብና ውኃ ምርት ምክንያት አሳሳቢ የጤና ችግር እያጋጠመ ነው። አስተያየት ሰጭዎቹ ችግሩ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው አመራረት እና አያያዛቸውን በሚመለከት መካሄድ ያለበት ቁጥጥር እየላላ በመሄዱ ነው ብለው ያምናሉ። የታሸገ ውኃና ምግብ አመራረት እና የጥራት ምዘና ምን ይመስላል ስንል የምግብና የውኃ ፋብሪካዎችን ጠይቀን ነበር። በምርት ሂደት ችግር መኖሩን የሚያሳይ መሳሪያ በመኖሩ የምርት ጥራቱ ላይ ችግር እንደሌለ የድሬደዋ የምግብ አምራች ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ደበበ ይናገራሉ። ሆኖም ከተመረቱ በኋላ የሚቀመጥበት ቦታ የምርቱ ጥራት ላይ ወሳኝነት እንዳለው ይገልጻሉ። ፋብሪካቸው ከእጅ ንክኪ ነጻ በሆነ መንገድ ውሃ እንደሚያመረት የፋም ውኃ ስራ አስኪያጅ አቶ ከማል በጅጋ ይገልጻሉ። ችግሩ የአመራረት ጥራት ችግር ሳይሆን በዋነኛነት በአቀማመጥ ወቅት የሚያመጣው ችግር እንደሆነ ገልጸው፤ ለዚህም በምርቱ ማሽጊያው ላይ እንዴት መቀመጥ እንዳለበት እንጽፋለን ብለዋል። ሆኖም ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንደማያደርግ ይናገራሉ አቶ ከማል። በአዲስ አበባ አንድ ተቋም በዓመት አራት ጊዜ ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ ተደንግጓል። ሆኖም በታሰበው መልክ ለመስራት ውሱን ባለሙያ በመኖሩ እንደማይከናወን አቶ ታደሰ ወርዶፋ የአዲስ አበባ የምግብ መድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን ምግብ መጠጥ ጤና ነክ ተቋማትና ኢንደስትሪዎች ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ለ ገልጸዋል። ከጤና ጋር የሚገናኙ የምግብና የመጠጥ ቁጥጥር ይደረጋል። አንድ ተቋም በዓመት አራት ጊዜ ቁጥጥር ቢደረግበት የሚል ስሌት አለ። ነገር ግን ጠብቆ መሄድ ያስቸግራል። ምክንያቱም ውስን ባለሙያ ነው ያለው። ያሉት ተቋማት እጅግ በርካታ ናቸው። ማምረቻዎቹ ከዚህ ችግር እርቀናል ሊሉ ይችላሉ። ምርታቸው በአግባቡ ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ ኃላፊነት አለባቸው። ሰዎች ለየት ያሉ ስሜቶች ሲኖሯቸው ወደ ጤና ተቋም መሄድ እንዳለባቸው ዶ ር አሚን መሐመድ የኢትዮ ጠቢብ ጠቅላላ ሀኪም ይመክራሉ። ለምሳሌ የምግብ መመረዝ ያጋጠመው በአስቸኳይ ህክምና ካልተደረገለት እስከሞት እንደሚያደርስ ዶ ር አሚን ይገልጻሉ። በተለይ ህጻናት በሽታ የመቋቋም አቅም ስለሌላቸው ለህይወታቸው አስጊ ሊሆን እንደሚችልም ዶክተሩ ጠቁመዋል።
የኑሮ ዉድነት፣ ሐዋሳ እንደማሳያ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ካፒታል ረቂቅ አዋጅ
ሐብታቸዉን በአክሲዎን ገበያ ላይ የሚያዉሉ ባለሀብቶችን መብትና ጥቅም ያስጠብቃል ፣ ቀልጣፋ የሠነድ መዋዕለ ንዋይ ሥርዓትንም ይፈጥራል ባዮችም ናቸዉ። የኢዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ በተዘጋጀዉ የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የተለያዩ መሥሪያ ቤት ባለሙያዎችን ምክር ዛሬ አድምጧል። አርቃቂዎቹ እንደሚሉት አዋጁ ከዓለም አቀፍና ከሐገር ዉስጥ ተመሳሳይና ሌሎች ሕጎች ጋር ተጣጥሞ እንዲሠራ ታቅዶ የተረቀቀ ነዉ። ሐብታቸዉን በአክሲዎን ገበያ ላይ የሚያዉሉ ባለሀብቶችን መብትና ጥቅም ያስጠብቃል ፣ ቀልጣፋ የሠነድ መዋዕለ ንዋይ ሥርዓትንም ይፈጥራል ባዮችም ናቸዉ።አስተያየት የሰጡት የፋይናንስ ሙሕራን አዋጁ ከፀደቀ ጠንካራ የሒሳብ ያዢ ተቋም ፣ የፋይናንስ ጉዳይ ዘጋቢዎች መገናኛ ዘዴዎችና የዘርፉ ትንታኔ ሰጭዎች ተቋማዊ በሆነ መልኩ ሊደራጁ ይገባል ብለዋል። ሰሎሞን ሙጬ
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅና አስተያየት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት
ጥቅምት ቀን ዕኩለ ለሊት ገደማ በትግራይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ልዩ ኃይል ጥቃት እንደደረሰበት ከተገለጸ በኋላ የተፋፋመው ውጊያ በማኅበራዊ ድረ ገፆችም በርትቷል። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል ደጋፊዎች አንዳቸው በሌላቸው የበላይነት ለማግኘት በማኅበራዊ ድረ ገፆች ይተጋተሉ። ሬሳ በሬሳ እየተከመረ ህዝቤ ተጠያቂው ማን ነው ይልልኛል እኔስ የጨነቀኝ የሟችን ቤተሰብ ማን ያረዳልኛል ይኸ ትዕግስት ሸዋረጋ የተባሉ ኢትዮጵያዊት በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በትግራይ መስተዳድር መካከል የተቀሰቀሰው ውጊያ የሚያስከትለው ዳፋ፣ በዜጎች ዘንድ የፈጠረውን ሥጋት ለማሳየት በትዊተር ያጋሩት ግጥም ነው። ልቤ ለብዙ ደስተኛ ዓመታት ለኖርኩባት ለኢትዮጵያ እና ለትግራይ እየተሰበረ ነው። እባካችሁ ጦር በሚሰብቁ የትዊተር መልዕክቶቻችሁ ከፍ ብለው እንዲሰሙ በመፈለግ ጎትታችሁ አታስገቡኝ። አላደርገውም። ውይይት እና ሰላም ነው የሚያስፈልገው የሚል መልዕክት በትዊተር ያሰፈሩት ደግሞ ፕሮፌሰር ላውራ ሐሞንድ ናቸው። የለንደን ዓለም አቀፍ የልማት ማዕከልን በኃላፊነት የሚመሩት ላውራ ያስተላለፉት መልዕክት ትዊተር እና ፌስቡክን በመሳሰሉ ማሕበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች የበረታው ውዝግብ በግለሰቦች ላይ የፈጠረውን ስሜት ለማሳየት ኹነኛ ምሳሌ ነው። ፌስቡክ እና ትዊተር እንደ ጦር አውድማ ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል የሚለው መረጃ ጥቅምት ቀን መጀመሪያ የተሰማው በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፌስቡክ ገጽ በኩል ነበር። ጠቅላይ ምኒስትሩ በማለዳ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ከ ዓመታት በላይ በክልሉ የሠፈረውን ጦር ሕወሐት እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል ብለዋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ በሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጽሟል ያሉት ጥቃት በርካታ ሰዎችን አስቆጥቷል። ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ክህደት እጅግ ዘግናኝ ሰቅጣጭ፣ ጆሮን ጪው የሚያደርግ የአረመኔ አረመኔነት ጥግ የታየበት አሳፋሪ ድርጊት ነው። ሲሉ ዳንኤል ዲሳሳ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ጽፈዋል። ጌታሁን ሔራሞ በበኩላቸው ቃታው የተሳበው በሰሜን ዕዝ ላይ ብቻ አይደለም፣ በመላ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ላይ እንጂ የአንድን ፓርቲ ሳይሆን የሀገር ውክልናን ባነገበውና በሀገራዊ ግዳጅ ላይ በተሰማራው የሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰው ጥቃት ዝርዝሩ ይፋ ሲደረግ በኢትዮጵያ ታሪክ በጥቁር ነጥብነት ዝንተዓለም ሲታወስ ይኖራል። ይህ እኩይ ተግባር የሕወሓት ተስፋ መቁረጥ ጎልቶ የወጣበት የአጥፍቶ መጥፋት አረመኔያዊ እርምጃ ነው፣ ዋጋ ይከፈልበታል ብለዋል። የትግራይ ክልላዊ መንግሥት እስካሁን የክልሉ ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ፈጸሙት የተባለውን ጥቃት በይፋ አላስተባበለም። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህወሓት ጥቅምት በፌስቡክ ገጹ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የፌደራሉ ኃይል በሰሜን ዕዝ ወረራ ተፈፀመ ሲል ተሰምቷል። የሰሜን ዕዝ በሁሉም ጉዳዮች ከትግራይ ህዝብ ጋር በመተባበር ሲሰራ የቆየ ኃይል ነው። ማለታቸውን አስፍሯል። በዚሁ የህወሓት ጽሁፍ ደብረጽዮን ከሰሜን ዕዝ ጋር በሰራነው ሥራ ራሳችንን ለመከላከል እንድንጠቀምበት የሚያስችል ሁኔታ ፈጥሯል። በአሁኑ ሰዓት በትግራይ ያለ የጦር መሣርያ ለትግራይ ህዝብ ደህንነት እንዲውል፣ ለራሱ እንዲከላከልበትና እንዲጠቀምበት መጠቀም ጀምረናል። ወደፊትም እንጠቀምበታለን ማለታቸው ሰፍሯል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ትጥቅ እንዴት በክልሉ መንግሥት እጅ እንደገባ ግን የተገለጸ ነገር የለም። በቅርቡ ወደ ጦሩ ተመልሰው ሥራ የጀመሩት ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ በኢትዮጵያ ጦር አባላት ላይ ተፈጽሟል ያሉት ጥቃት በተመለከተ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ውዝግቡ ተካሯል። ሌተናል ጀነራል ባጫ የጦሩ አዛዦች መታገታቸውን ወታደሮችም የራዲዮ ግንኙነት እንዲቋረጥ ተደርጎ በትግራይ ኃይሎች የእኛ መንግሥት የተመረጠ መንግሥት ነው። ያዲስ አበባ መንግሥት የተመረጠ መንግሥት ስላልሆነ ፈርሷል መባላቸውን አስረድተዋል። ከሰሜን ዕዝ የተለያዩ ክፍለ ጦሮች መካከል አንዱ የሆነው አራተኛ ድጋፍ ሰጪ ብርጌድ አባላት በትግራይ ኃይሎች ተከበው ከተታኮሱ በኋላ በርካቶች መገደላቸውን፤ አስከሬናቸው ሳይቀበር ሜዳ ላይ መጣሉንም ተናግረዋል። አሉላ ሰለሞን በፌስቡክ ባሰፈሩት ጽሑፍ የሌተናል ጀነራል ባጫ ማብራሪያ ከተሰማ በኋላ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል መከላከያ አሰማርተህ እምቢ ለመብቴ ያለን ህዝብ ስትጨፈጭፍ ከርመህ ስታበቃ አሁን ከውጭ ኃይል ጭምር በመተባበር በህዝብ ላይ የከፈትከውን ወረራ እና ያወጅከውን ጦርነት ምክንያታዊ ለማድረግ ሠራዊቱ ታረደ እራቁቱ ወጣ የሚል የለማጆች አስቂኝ ፕሮፖጋንዳ በማለት ተችተዋል። ማይካድራ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሱዳን እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ማይካድራ የተባለች አነስተኛ ከተማ ከ በላይ ሰዎች በትግራይ ልዩ ኃይል ተገድለዋል መባሉ ሌላ ሐዘንም ንዴትም የፈጠረ ጉዳይ ነው። እጅግ በርካታ የተገደሉ ሰዎች አስከሬኖች ቅጠልን ጨምሮ የተለያየ መሸፈኛ ጣል ተደርጎባቸው ለቀብር ሲጓዙ የሚያሳዩ ምስሎች በፌስቡክ እና በትዊተር ተዘዋውረዋል። ጌትነት ቢ የተባሉ ሰው የሟቾች አስከሬኖች የተሰበሰቡበትን ምስል አስደግፈው ትህነግ ማይካድራ ላይ ምንም የማያውቁ ነዋሪዎችና የቀን ሠራተኞችን ገድሏል። የሟቾቹ ቁጥር ከ በላይ ነው። በጦርነት የተሸነፈው ትህነግ ንጹህንን ወደ መግደል ተሸጋግሯል ሲሉ ጽፈዋል። ሰናይት ሰናይ በትዊተር ማይካድራ ያሳብዳል የሚፈልጉት በቀልን ነው። ኢትዮጵያ ላይ ሁሉ እርስ በእርስ ጦርነት እንዲሆን ይፈልጋሉ። አደራ በቀል ህውሃትን ይጠቀማል እንጂ አይጎዳውም። በግፍ የሞቱትን ነፍስ ይማርልን። የትግራይን ህዝብ አትንኩ፤ ህውሃት ግን ያለቀ ጉዳይ ነው ብለዋል። በጦርነቱ የተገደሉ እና የቆሰሉ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር እስካሁን በግልጽ አይታወቅም። በሺሕዎች የሚቆጠሩ ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት አስታውቋል። የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በመቆራረጣቸው ከትግራይ ውጪ የሚኖሩ የቤተሰቦቻቸውን ኹኔታ ለማወቅ መቸገራቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ፊልሞና የተባሉ የትዊተር ተጠቃሚ እናቴን እና ዕድሜዋ እየገፋ የሔደውን አያቴን ሳላናግር የቆየሁበት ረዥም ጊዜ ይኸ ሳይሆን አይቀርም። መቼ እንደማናግራቸው፣ እስከዚያ ጊዜ አያቴ በሕይወት ለመቆየቷ ምንም አላውቅም። በሕይወቷ በርካታ ጦርነቶች ተመልክታለች። መጠጊያ ፍለጋ በኤርትራ እና በትግራይ በርካታ ኪሎ ሜትሮች ተጉዛለች። የሚል መልዕክት አስፍረዋል። ፊልሞና እንዳሉት ይኸ ሊደገም አይገባም። እንደ ፊልሞና ሁሉ በርካቶች የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና የትግራይ ክልል የገቡበት ውጊያ በፍጹም አስፈላጊ አይደለም እያሉ ይሞግታሉ። ጦርነት አንሻም ፕሮፌሰር ሰናይት ፍሰሐ በትዊተር ባሰፈሩት መልዕክት በኢትዮጵያ እየተፈጠረ ያለው ነገር እጅግ አሳዛኝ ነው። ሁለቱም ወገኖች ያለ ርሕራሔ ከሚያቀርቧቸው ቁጥሮች ጀርባ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ይገኛሉ። ሰብዓዊው ቀውስ እየበረታ ነው። በማኅበራዊ ድረ ገፆች የሚታየው ጥላቻ እና ጀብደኝነት ሕመም እና ክፍፍሉን ይበልጥ እያባባሰው ነው። ጦርነት አሸናፊ የለውም ተራፊ እንጂ። ብለዋል። ሰልማን አል ፋሪስ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ደግሞ በሃገራችን አሁን የሚታየው ጦርነት ሰፊ የርዕዮተ ዓለም ልዩነት ባላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች መሃል እየተደረገ ያለ ጦርነት እየሆነ መጥቷል። የርዕዮተ ዓለም ልዩነት በፖለቲካዊ ሃሳብ የበላይነት እንጂ በጦር ሜዳ አይፈታም። ጠቅላይ ሚኒስትራችንም ግፋ በለው ከሚሉ ፖለቲከኞች፣ በደርግ ግዜ ምርኮኛ ከነበሩ ወታደሮች እና ፖለቲካውን ወደ ሐይማኖት ተቋማት ለመውሰድ ከሚዳዱ አማካሪዎቹ እጅ ወጥቶ ፖለቲካውን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ቢያመጣው ሀገሪቷን ከመበታተን የድናታል። ሲሉ ጽፈዋል። ኢብራሒም ዋዚር ጦርነቱ ማለቁ አይቀርም ያልቃል። መሪዎቹም ደግሞ በመጨረሻ ሰላም ይባባላሉ። እናት ደግሞ የሞተው ልጇ ይመጣል ብላ ትጠብቃለች። ሚስት ደግሞ የምትወደው ባሏ ይመጣል ብላ ትጠብቃለች። ልጆቹም የሚወዱት አባታቸው ይመጣል ብለው ይጠብቁታል። ጦርነት ክቡር የሰው ልጅ ህይወት ነው ሚወስደው ። ለመሪዎች አሪፍ እና ቀለል ያለ ጨዋታ ነው፤ ለህዝቦች ግን ትልቅ ጠባሳ ነው ሲሉ ዳፋው በማን ላይ እንደሚበረታ በፌስቡክ ባሰፈሩት ጽሑፍ ጠቆም አድርገዋል። አቡ ሲትራ ደግሞ ብቻዬን እስክቀር ጦርነት እቃወማለሁ። ጦርነት አልደግፍም። በተለይ የእርስ በርስ ጦርነትን፦ ምክንያቱም በጦርነት የሚጎዳው ምንም የማያውቅ ምስኪን ሕዝብ ስለሆነ። ይህን በማድረግ ሕሊናዬ ሰላም ያገኛል ብለዋል። አማኑኤል ገብረ መድሕን የዛሬዋን ቀን ትረግማታለህ የሚል ርዕስ ያለው ጽሁፍ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል። አማኑኤል ዛሬ ቁጭ ብለህ በማኅበራዊ ድረገፆች ላይ ፃፍ፣ ተሳደብ፣ ቀስቅስ፣ ሰዎችን አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው፤ በረባው ባልረባው ተባላ ነገ ያለህበት ስፍራ ሲተራመስ ኔትዎርኩ ሲዘጋ፤ መብራቱ ሲጠፋ፤ ውሀው ሲቋረጥ፤ የምትበላው ስታጣ፤ ገንዘብ በኪስህ ሞልቶ ለሻይ እንኳን ከቤትህ ለመውጣት ሲያቅትህ የት እንደምትገባ ግራ ይገባሀል። ዛሬ ያቀለልካት ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም። ዛሬማ ሰላም ነው ፎክር እንጂ የቤትህ አናት ላይ ሲተኮስ፤ የቦንብ ናዳው ሲወርድ፤ ሰው ወጥቶ ሲቀር ስትሰማ፤ ሕጻናት ሲረግፉ ስታይ፤ ህዝብ እየተሰደደ የበረሀ ሲሳይ ሲሆን፥ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ ሲቀር ስታይ የዛሬዋን ቀን ትረግማታለህ። ምነው ጌታ ባልፈጠርከኝ ትላለህ። ብቻህን ያለወንድም፤ ያለእናት አባት፤ ያለዘመድ ስትቀር መፈጠርህን ትጠላለህ። ዛሬ ያቀለልካትን ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም። ዛሬማ ሰላም ነው ፎክር አቅራራ ህዝብ ቀስቅስ ተነሳ በለው፣ ግደለው በል የለኮስከው እሳት አመድ ሲያደርግህ የሰላምን ዋጋ ያን ጊዜ ትረዳዋለህ ሲሉ እየተሳለቁ ያስጠነቅቃሉ። እሸቴ በቀለ
የሱዳን መንግስት እና አማጽያን የሰላም ስምምነቱን ፊርማ አኖሩ
የሱዳን የሽግግር መንግስት እና ተቃዋሚዎች አስርት አመታት ላስቆጠረው የእርስ በእርስ ደም አፋሳሽ ግጭት መቋጫ ያስገኝለታል የተባለለትን የሰላም ስምምነት ዛሬ ደቡብ ሱዳን ጁባ ውስጥ ተፈራረሙ። የሁለቱ ወገኖች የሰላም ስምምነቱን የተፈራረሙት ውይይቱን ከጀመሩ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው። የሱዳን የሽግግር መንግስት እና አማጽያን አስርት አመታት ላስቆጠረው የእርስ በእርስ ደም አፋሳሽ ግጭት መቋጫ ያስገኝለታል የተባለለትን የሰላም ስምምነት ዛሬ ደቡብ ሱዳን ጁባ ውስጥ ተፈራረሙ። የሱዳን የሽግግር መንግሥት እና የተቃዋሚ ቡድኖች ታሪካዊ የተባለለትን ይህንኑ የሰላም ስምምነት የተፈራረሙት የሰላም ውይይቱን ከጀመሩ ከአንድ ዓመት በኋላ መሆኑ ተመልክቷል። የቀድሞው አምባገነን ሀሰን ኦማር አልበሽር በህዝባዊ አብዮት ከስልጣናቸው ከተገረሰሱ ወዲህ በሀገሪቱ የተቋቋመው የሽግግር መንግሥት የሀገሪቱን የውስጥ ግጭት እልባት እንዲያገኝ ቅድሚያ ሰጥቶ ሲሰራ ነበር ተብሏል። የሽግግር መንግስቱን ከአማጽያኑ የማሸማገሉን ሂደት ሲያስተባብሩ የነበሩት የደቡብ ሱዳኑ ቱት ጋትሉክ የሰላም ስምምነቱ በስኬት ተጠናቋል፤ ደስ ተሰኝተናልም ብለዋል።የሰላም ስምምነቱን የሱዳን መንግስትን በመወከል የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ምክትል ሊቀ መንበር ሉቴናንት ጄኔራል ሞሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ሲፈርሙ ከአማጽያኑ ወገንም በሰላም ሂደቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የምዕራብ ዳርፉር ግዛት አማጽያን ፣ የደቡባዊ ብሉ ናይል እና የደቡባዊ ኮርዶፋን አንጃዎች በየፊናቸው ፊርማቸውን አኑረዋል። በፊርማ ስነስረዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ የአውሮጳ ህብረት ፣ ግብጽ ፣ቻድ እና እና ኳታር ተወካዮች ተገኝተዋል።በሰላም ስምምነቱ የመሬት ባለቤትነት የሃብት እና የስልጣን ክፍፍልን ጨምሮ በጦርነቱ ለተጎዱት ካሳ በሚከፈልበት እና በዚሁ ምክንያት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ተሰደው የቆዩ ሱዳናውያን ወደ መኖርያቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ እልባት እንደሚያገኙ ተጠቁሟል። ። ታምራት ዲንሳ
የቤኒሻንጉል ክልል መስተዳድር ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው ስምምነት
በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ያስችላል የተባለ የሰላም ስምምነት የክልሉ መንግስት እና ታጣቂ ሀይሎች መፈራማቸውን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል፡፡ ስምምነቱን ከታጣቂዎች በኩል የሚቀርቡ ጥቄዎችን በሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ተሀድሶ ስልጠና እየወሰዱ ከሚገኙት ጋር መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ያስችላል የተባለ የሰላም ስምምነት የክልሉ መንግስት እና ታጣቂ ሀይሎች መፈራማቸውን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል፡፡ የክልሉ መንግስት የሰላም ስምምነቱን የተፈራረመው ከታጣቂዎች በኩል የሚቀርቡ ጥቄዎችን በሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ተሀድሶ ስልጠና እየወሰዱ ከሚገኙት ጋር መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ የመተከል ዞን የጸጥታ ጉዳይን በበላይነት ከሚመሩት የዞኑ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ወይም ኮማንድ ፖስት የስራ ኀላፊዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልካቸውን ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡ ነጋሳ ደሳለኝ
የመኑ የስድስት ዓመታት ጦርነት ትልቁ ምስል ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳድር እና የታጣቂዎች ስምምነት ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የምርጫ ስልጠና ለሲቪክ ማኅበራት
ምርጫው ሁሉንም ኅብረተሰብ ማሳተፍ እንዳለበት ያመለከቱት አቶ ዳን ሲቪክ ማህበራት በዚህ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፣ በተለይም ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በምርጫው እንዲሳተፉ መትጋት እንደሚያስፈልግ አቶ ዳን አብራርተዋል፡።አንዳንድ የሲቪክ ማህበራት የበጀት እጥረት አጋጥሞናል የሚል ቅሬታ እያቀረቡ ነው፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ ኢሰመጉ መጪው ምርጫ ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሲቪክ ማህበራት በምርጫው ሂደት በስፋት መሳተፍ እንደሚገባቸው አስታወቀ።ምርጫው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማካተት እንደሚኖርበትም አመልክቷል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ ኢሰመጉ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ጽ ቤት፣ ከኢትዮጰያ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ህብረትና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሲቪክ ማህበራት በመጪው ምርጫ ስለሚኖራቸው ሚና ሰሞኑን በባህር ዳር ትምህርት ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባዔ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳን ይርጋ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት የስልጠናው ዓላማ ሲቪክ ማህበራት በምርጫው ሂደት ሲለሚከናወኑ ተግባራት፣ ስፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ማዘጋጀት ፣ ስከሰብአዊ መብቶች እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ትምህርት መስጠት ነው፡፡ በስልጠናው የሚሳተፉትም በአማራ ክልል የሚገኙ የሲቪክ ማህበራት አካላት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ምርጫው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ መካሄድ እንዳለበት ያመለከቱት አቶ ዳን ሲቪክ ማህበራት በዚህ ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፣ በተለይም ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በምርጫው እንዲሳተፉ መትጋት እንደሚያስፈልግ አቶ ዳን አብራርተዋል፡፡ አንዳንድ የሲቪክ ማህበራት ስለምርጫ ለማስተማር የበጀት እጥረት አጋጥሞናል የሚል ቅሬታ እያቀረቡ ነው፣ ችግራቸው እንዴት ሊፈታላቸው ይችላል ተብለው የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሲቪክ ማህበራት ወደስራው ሲገቡ የሚያቀርቡት እቅድና በጀት በሚመለከተው አካል ታይቶና ተፈቅዶ መሆኑን ጠቁመው የሚያግዝ አካል ከተገኘ ማህበራቱን በገንዘብ፣ በስልጠናና በሰው ኃይል መደገፍና ማጠናከር ግን ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምርጫው ለኢትዮጵያውያን ትርጉም ያለው በመሆኑ በተገቢው መንገድ እንዲካሄድ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ጽ ቤት ተወካይ አቶ ኪነጥበብ አረጋ በበኩላቸው ማንም ሰው በአስተሳሰቡ የአካል ጉዳትም ሆነ ሌላ አደጋ ሊደርስበት እንደማይገባ አስረድተዋል፡፡ ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሴት ተማሪዎች ፌደሬሽን የተገኘችው ፌቨን ሃይሉ ስልጠናውን በተመለከተ ጠይቀናት ምርጫን እንዴት መታዘብ እንደሚገባና ችግሮች ቢፈጠሩ እንኳ እንዴት መፈታት እንዳለባቸው ከስልጠናው ትምህርት አግኝተናል ብላለች፡፡ ተመሳሳይ ስልጠና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሀዋሳ መደረጉንና በቀጣይ አዳማን ጨምሮ በሌሎች ከተሞችም እንደሚሰጥ የሰብዓዊ መብት ጉባዔ አስታዉቋል፡፡ ዓለምነው መኮንን
ስልጠና ለሲቪክ ማኅበራት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ምርጫና የሕዝብ ተሳትፎን የተመለከተ አዉደጥናት
ቪዥን ኢትዮጵያን ኮንግረስ ፎር ዴሞክራሲ የተባለ አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከመጪዉ ምርጫ ጋ በተያያዘ ዴሞክራሲና የሕዝብ ተሳትፎን በሚመለከት የአንድ ቀን አዉደጥናት አካሄደ። ዛሬ በተካሄደዉ አዉደጥናት ከተለያዩ ሲቪክ ማኅበራት እና መንግሥታዊ አካላት የተዉጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ፤ ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
የተሻሻለው የጸረ ሽብር አዋጅ
የተሻሻለው የጸረ ሽብር አዋጅ ለጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሊቀርብ ነው። ሰላማዊ ሰልፍ እና የሥራ ማቆም አድማ በሽብር የማያስከስሱ ተግባራት መሆናቸውን በማሻሻያው አካትቷል። የሕጉ አጠቃላይ ይዘት ሰፊ ችግር የነበረበትና አተገባበሩም ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ ያተኮሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ጋዜጠኞችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችንና መንግሥትን ይተቹ የነበሩ አካላትን ለማፈን ጥቅም ላይ ውሏል ያለው ግብረ ኃይሉ አዲሱ የለውጥ ኃይል ይሻሻሉ ብሎ ካስቀመጣቸው የሲቪክ ማኅበራት ማደራጃ እና የሚዲያ ሕጎች በመቀጠል እንዱ የሆነው የጸረ ሽብር ሕግ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ ተሸሽሏል ብሏል። ከግንቦት ወዲህ ሰፊ ጊዜ ወስዶ የተሸሻለው ይህ ሕግ የአዋጁ መንፈስም ይሁን ድንጋጌዎች፤ ከዓለም አቀፍ ሕጎች ጋር እንዲጣጣሙ፤ ሰላማዊ ሰልፍ እና የሥራ ማቆም አድማ በሽብር የማያስከስሱ ተግባራት መሆናቸውን በማሻሻያው አካትቷል። ከዚህ በፊት አስፈጻሚው አካል እና ምክር ቤት ብቻቸውን ከተስማሙ አንድን ድርጅት አሸባሪ ብለው ይፈርጁ የነበረበትን ድንጋጌም በማሻሻያው እንዲነሳ አድርጓል። በተመሳሳይ የፍትህ አካላት ማንኛውንም በሽብር የጠረጠሩትን ግለሰብ ስልክ መጥለፍ እና ልዩ ክትትል ማድረግ የሚፈቅደውን አንቀጽ በማንሳት አስገዳጅ ከሆነም በፍርድ ቤት ትእዛዝ ብቻ እንዲከናወን የሚል የማሻሻያ ሃሳብ አስፍሯል። ረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ በቀጣይ ከፍትህ እና ጸጥታ አስከባሪ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወደ ሚኒስትሮች ምክርቤት ከዚያም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡። ሕጉ የሚጸድቅ ከሆነም እንደቀደመው ጊዜ አተገባበሩ እና አፈጻጸሙ ባልተገባ አኳኋን እንዳይሆን የአስፈጻሚ አካላትና ተቋማት አቅም እንዲጠናከር፤ ሲቪክ ማህበረሰቡም ሕጉን በንቃት እዲከታተለው ተጠይቋል። ሰለሞን ሙጬ
ካለፈው ግንቦት ወዲህ ማሻሻያው ሲሠራ ነበር ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የፀረ ሽብር ሕግ አጠቃቀም ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የአውሮጳ ህብረት አዲሱ የልማት መርህ መመሪያ
የአውሮጳ ህብረት የእርዳታ አሰጣጥ መስፈርት እና አተገባበሩ አሁንም አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥሏል ።የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተቋሙንም ሆነ አባል ሀገራቱን ሰብዓዊ መብት በመጣስ ለሚወቀሱ አንዳንድ የአፍሪቃ አገራት የልማት እርዳታ በመስጠት አጥብቀው ይተቿቸዋል ። የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት የልማት ሚኒስትሮች ከአስር ቀናት በፊት ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ በህብረቱ የልማት መርህ አዲስ መመሪያ ላይ ተስማምተዋል። አዲሱን የልማት መርህ መመሪያ የህብረቱ ፓርላማ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። የአውሮጳ ህብረት በአሁኑ ጊዜ ከዓለማችን በልማት እርዳታ አቅርቦት የመሪነቱን ቦታ ይዟል። ከዚህ ቀደም በልማት እርዳታ ለጋሽነት ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ዩናይትድ ስቴትስ ነበረች ህብረቱ ከዓመት ወደ ዓመት በልማት ወደ ኋላ ለቀሩ ሀገራት የሚሰጠውን የገንዘብ እርዳታም እያሳደገ ነው ። ባለፈው ሚያዚያ ይፋ እንደተደረገው ህብረቱ እና አባል ሀገራት በጎርጎሮሳዊው ለልማት እርዳታ የለገሱት ገንዘብ ቢሊዮን ዩሮ ደርሷል። ይህም በጎርጎሮሳዊው ከሰጠው ጋር ሲነፃፀር በ በመቶ ከፍ ያለ መሆኑ ነው የተገለፀው። የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት የልማት ሚኒስትሮች ከ ቀናት በፊት ባካሄዱት ስብሰባ ለህብረቱ የልማት መርህ በተዘጋጀው አዲስ መመሪያ ተስማምተዋል። አዲሱ የአውሮጳ ህብረት የልማት መርህ መመሪያ ትኩረት ዘላቂነትን እና አጋርነትን ይበልጥ ማጠናከር ነው። ህብረቱ ከጊዜያዊ እርዳታ ይልቅ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ፣ የሥራ እድል የሚፈጥሩ እና አስተማማኝ ድጋፍ የሚሰጡ ዘላቂ የልማት መርሃ ግብሮችን ነው የሚመርጠው። የህብረቱ ባለስልጣናት እንደሚሉት ህብረቱም ሆነ አባል ሀገራቱ ይህን የሚያደርጉት በሰብዓዊነት ብቻ አይደለም። የራሳቸውንም ጥቅም ለማስጠበቅ ጭምር እንጂ ። የተሻሻለው የህብረቱ የልማት ፖሊሲ መመሪያ ይፋ በተደረገበት ወቅት የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን የውጭ እና የፀጥታ መርህ ጉዳዮች ከፈተኛ ተጠሪ ፌደሪካ ሞጎሮኒ ይህንኑ የህብረቱን ግብ ግልጽ አድርገዋል። በኛ እምነት ለልማት ፣ ለሰላም ማስከበር ለሰብዓዊ ተግባራት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ የደህንነታችን እና የውጭ ፖሊሲያችን እጅግ አስፈላጊ አካል ነው። እኛ ይህን ለራሳችን ደህንነት እና ብልጽግና መዋዕለ ንዋይ እንደማፍሰስ ነው የምናየው። ለዚህም ነው የተመ ሁል ጊዜ የአውሮጳ ህብረትን ከጎኑ የማያጣው ። የአውሮጳ ህብረት አሁን አዲስ የልማት መመሪያ ማውጣት ያስፈለገው መመሪያውን ከወቅቱ የዓለማችን ፈተናዎች እና አጀንዳ ከተባለው የተመድ የዘላቂ ልማት ግቦች ጋር ለማጣጣም መሆኑ ተነግሯል። የዶቼቬለ የብራሰልስ ዘጋቢ ገበያው ንጉሴ እንደሚለው አዲሱን መመሪያ ከቀድሞው ከሚለዩት አንዱ የተቋሙ እና የአባል ሀገራቱ እርዳታ ትኩረት እና አቅጣጫ ወጥ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑ ነው ። መመሪያው ከበፊቱ ጋር ሲተያይ ብዙም አዲስ ሊባል የሚችል እንዳልሆነ ተነግሯል ። ዓለም ዓቀፉ የፀጥታ ጥናት ተቋም ስለ መመሪያው ባወጣው ዘገባ ከአዲሱ መመሪያ ከማንም በላይ ተጠቃሚዋ አፍሪቃ ናት። ህብረቱ ከዓለም እጅግ ድሀ የሚባሉ ሀገራት ለሚገኙባት ለአፍሪቃ እርዳታ ትኩረት እንደሚሰጥ በልማት ፖሊሲ መመሪያው ላይ ጠቅሷል። የልማት እርዳታው ትኩረት በልማት ወደ ኋላ ለቀሩ የአፍሪቃ ሀገራት መሆኑ በበጎ ቢታይም ትችት ግን አልተለየውም። እደንደገና ገበያው ጀርመንን የመሳሰሉ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት አዲሱ የልማት መርህ መመሪያ ላይ ስምምነት ላይ ሲደረስ ለእርዳታ ተቀባዮች ማሳሰቢያ መስጠታቸው አልቀረም። ተቀባይ ብቻ ከመሆን ችግሮችን ለመከላከል የበኩላችሁን ጥረትም አድርጉ የሚል። በብራሰልሱ ስብሰባ ላይ የተገኙት የጀርመን ተወካይ ከእስካሁኑ በተለየ አፍሪቃውያን የበኩላቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል ። የጀርመን የኤኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ ቶማስ ዚልበርሆርን በተፈጥሮ ሀብት በበለጸጉ የአፍሪቃ ሀገራት የሚከሰተውን ረሀብ እንደምሳሌ በማንሳት ሀገራቱ ችግሩን አስቀድመው ለመከላከል በዚዘጋጁ እንደሚበጅ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረው ነበር ። ረሀብ የተከሰተባቸው ሀገራት መንግሥታት የችግሩ ዋነኛ ተጠያቂዎች ናቸው። ለምሳሌ ናይጀሪያን ወይም ደቡብ ሱዳንን ተመልከቱ ፤ ሀብታም ሀገራት ናቸው። ስለዚህ በችግሩ የተጠቁ ሀገራት ለችግሩ መከላከያ ላይ ይበልጥ ወጪ እንዲያደርጉ መገፋፋት አለብን ። ለቀጣዮቹ ዓመታት ሥራ መሠረቱ ይህ መሆን አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ውጊያ በሚካሄድባቸው የአፍሪቃ ሀገራት ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርስ በመከልከል ረሀብን እንደ መሣሪያ መጠቀምም ተቀባይነት እንደሌለውም ተናግረዋል። ለእርዳታ ተቀባዮች ይህን መሰሉን መልዕክት የሚያስተላልፉት የህብረቱ አባል ሀገራትም ሆኑ የአውሮፓ ህብረት የእርዳታ አሰጣጥ መስፈርት እና አተገባበሩ አሁንም አነጋጋሪ ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ነው።የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተቋሙንም ሆነ አባል ሀገራቱን ሰብዓዊ መብት በመጣስ ለሚወቀሱ አንዳንድ የአፍሪቃ አገራት የልማት እርዳታ በመስጠት አጥብቀው ይተቿቸዋል ። የአውሮጳ ህብረት በጎርጎሮሳዊው ዓም ያስቀመጣቸውን እስካሁን ሲሰራባቸው የቆዩትን ግቦች ለዘላቂ ልማት ትኩረት ከሚሰጠው አጀንዳ ከሚባለው የዘላቂ ልማት ግብ ጋር እንዲጣጣም አድርጎ አዘጋጀው የተባለው መመሪያ ታዲያ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ትችት በሚሰነዘርበት የህብረቱ የልማት እርዳታ አሰጣጥ ላይ ያደረገው ለውጥ ይኖር ይሆን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉውን ዝግጅት ማዳመጥ ይቻላል ። ኂሩት መለሰ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ ዓ ም ስለተፈጸመው የአቃቤ ሕግ መግለጫ
ባለፈው ዓመት ሰኔ ቀን በባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ የተፈፀመው ግድያ በብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ የተመራ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደነበር የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጸ። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዛሬ ከቀትር በኋላ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባሕር ዳር ላይ በአማራ ክልል መስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም አዲስ አበባ በጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ላይ የተፈፀመው ግድያ በመፈንቅለ መንግሥቱ አደራጅ የተቀናበረ ነው ብሏል። ጉዳዩንም በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ማረጋገጥ መቻሉን ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ብርሃኑ ፀጋዬ ተናግረዋል። ድርጊቱን ለመፈፀም ከተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች መመልመላቸውን፤ ስልጠና እና ስምሪትም ተሰጥቷቸው መሳተፋቸውንም አመልክተዋል። በዚህ ድርጊት ተሳትፈዋል በሚል በባሕር ዳር በአዲስ አበባ ደግሞ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበርም ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ገልጸዋል። ከእነዚህ መካከል በዋስትና የተፈቱ መኖራቸውንም አክለዋል። በተጨማሪም እንዲያዙ ማዘዣ ከወጣባቸው ግለሰቦች፤ ዱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የሰነድ እና የሰው ማስረጃ የተጠናቀቀባቸው ያሏቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ለመመስረት ዝግጅቱ ማለቁንም ዐስታውቀዋል። ሸዋዬ ለገሠ
የ ክልሎች ውይይት በባሕር ዳር ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የአውሮጳና የአፍሪቃ ኅብረት ሥልታዊ ትብብር
ለአውሮጳ ኅብረት ይህ የአውሮጳውያን ዓመት የአፍርካ አመት እንዲሆን ነበር የታሰበው። ባለፈው ጥቅምት ወር የአውሮጳ ህብረት አባል አገሮችና የአፍርካ ህብረት መንግስታት መሪዎች ኢዚህ ብራስልስ ተገናኝተው አዲስ ያአፍርካና አውሮጳ ኅብረት አጋርነት ስምምነት ሊያበስሩ ነበር ዕቅዱ። ለአውሮፓ ህብረት ይህ የአውሮፓውያን አመት የአፍርካ አመት እንዲሆን ነበር የታሰበው። ባለፈው ጥቅምት ወር የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮችና የአፍርካ ህብረት መንግስታት መሪዎች ኢዚህ ብራስልስ ተገናኝተው አዲስ ያአፍርካና አውሮፓ ህብረት አጋርነት ስምምነት ሊያበስሩ ነበር ዕቅዱ። የአውሮፓ ህብረት ቀድሞ የህብረቱ አባል አገሮች ቅኝ ተገዥ ክነበሩት የአፍርካ፤ ካሪቢያን እና ፓስፊክ አገሮች ጋር አዲስ የንግድ ስምምነት የማድረግ ፍላጎትም ነበራቸው። ይሁንና ምንም ያህል ውጤት ላይ ሳይደረስ አመቱ ሊያልቅ ነው፡፤ዛሬ የአውሮፓውያኑ አመት አስራአንደኛው የህዳር ወር ላይ ነን። በዚህም ምክኒያት አንዳንዶች አመቱን የአውሮፓ ህብረትና አፍርካ ግንኙነትን በሚመለክት የባክነ ዓመት ይሉታል። አዲሱ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግኙነት ሀላፊ ሚስተር ጆሴፕ ቦሬል ባለፈው መጋቢት ወር ወደ ስልጣን ሲመጡ የተለየ አመት መጀመሪያ ተደርጎ ነበር የተወሰደው። በጋዜጣዊ መግለጫቸው፤ አዲስ የአፍርካ ስትርቴጂ አዘጋጅተው አቀረቡ፤ በሁለቱ አህጉሮች መካከል ጠንከራ ግንኙነትነ ለመመስረትም ቃል ገቡ ድምጽ የአውሮፓ ህብረት በሁሉም ማለት በንግድ፤ ኢንቭስትሜንት፤ ልማት፤ ትብብርና ደህንነት፤ ከአፍሪካ ጋር ያለው ትብብር በአንደኛ ደረጃ የሚጠቀስ መሆኑን መዘንጋት አይገባም ። ይህ ሁለንተናዊ ግንኙነት እንዲቀጥል፤ እንዲያድግና የበለጠ ውጤማ እንዲሆን እንፈልጋለን በማለት አዲሱን እቅድቅቸውን አስታውቀው ነበር። ይሁን እንጂ በሁለቱም ወገኖች በኩል ግንኙነትን እንደ አዲስ ለማሳደግ የነበረው ተነሳሽነት ብዙም አልነበረም። የአውሮፓ ህብረት መንግስታት አዲሱን የግንኑነት ስትራቴጂ ገና ማጽደቅ ነበረባቸው፡፤ በዚህም ምክኒያት አዲሱ የአውሮፓ ህብረትና አፍርካ አጋርነት ስምምነት ብስራት፤ ለሚቀጥለው አመት ሊተላልፈ ግድ ሁኗል ። ባለፈው ጥቅምት ወር ሊካሄድ የነበረው ከፍተኛ የአፍርካና ያውሮፓ ህብረት መሪዎች ጉባኤም ተሰርዟል። ቬንትሮ የተባለው የጀርመን የልማት ድርጅት ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ማቲያስ ሞጌ የዚህ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የሁለቱ አህጉሮች ግንኙነት ትኩረት ያላገኘበትን ምክኒያት ሲያብራሩ፤ ድምስ ። የአውሮፓ ህብረት በኮሮና ወረርሺኝ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የራሱ ጉዳዮች ተጠምዷል። ብዙ ሚሊዮን ኢሮ የሚጠይቁ ወጭዎች አሉ። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከፍርካ ጋር አዲስ የአጋርነት ስምምነት ማድረጉ ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም ብለዋል፤ ይህ ማለት ግን ወይዘሮ ሜርከል ፋላጎት አልነበራቸውም ማለት እንዳልሆነ በመግለጽ ጭምር። ሆኖም ግን ችግሩ ከአውሮፓ ህብረት ብቻ ልነበረም ። የአፍርካ ህብረት አገሮችም ለስምምነቱ መዘገግየት የራሳቸው አሉታዊ አስተዋጾ አለበት። የኮሮና ወረርሺን አንዱ ምክኒያት ነው። ይሁን እንጂ ለብዙዎቹ የአፍርካ አገሮች ከአውሮፓ ጋር የሚደረገው ግንኑነት ጠቀሜታም ከዚህ በፊት የነበረውን ያህል አይደለም፡፤ ይህ የሆነበት ምክኒያትም እንደ ቻይና ያሉ ሌሎች የውጭ ሀይሎችም በመነሳታቸው ወይም በመምጣታቸው ነው። ጀርመናዊው የኢኮኖሚ ባለሙያ ሮበርት ካፔል በአፍሪካና ቻይና ግንኙነ ላይ ባካሄዱት ጥናትና ባወጡት ጽሁፍ ፤ ድምጽ ቻይና በአፍሪካ ያላትን ተሰሚነት አሳድጋለች።። ለጂኦ ፖልቲካም ይሁን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ምክኒያት አውሮፓ ቻይና በአህጉሩ ያላትን ወታደራዊና ኢኮንሚያዊ ተሳትፎ ለመቋቋም የሚያስችል አጀንዳ ያስፈልጋታል በማለት አውሮፓ የአፍርካን ልባዊ አጋርነትና ወዳጅነትና ለማገኘት የበለጠ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ያስገነዝባሉ። ይህ ግን ቀላል እንዳልሆነ ነው የሚታመነው። ብዙዎቹ የአፍርካ አገሮች ከአውሮፓ ጋር ባለቸው ግንኙነት ደስተኖች አይደሉም። ቬንቶ የተባለው የጀርመን የልማት ድርጅቶች ህብረት ያካሄደው ጥናት ያረጋገጠው ይህንን ነው፡፤ ድርጅቱ በአፍርክና አውሮፓ ካሉ የሺቪል ድርጅቶች ተወካዮች ባሰባሰበው መረጀና ባካሄደው ጥናት፤ ካእፍርካ፤ ከግማሺ በላይ ከሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ያገኘው መልስ የአፍርካና አውሮፓ ግንኑነት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንዳልሆነ ወይም ጤናማ እንዳልሆነ የሚገልጽ ነው። በተጨማሪም ብዙዎቹ ግንኙነቱ ሊሻሻል ይችላል ብለው የሚያስቡ አይድሉም እንደጥናቱ ውጤት ። በጀርመን የአፍርካ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ናይጀራዊቷ ዶክተር ልይንዳ ኢሮሎም የአፍርካና አውሮፓ ግንኙነት ክመሰረቱ ችግር ያለበት ዕንደሆነ ነው የሚናገሩት፤ ድምስ የአፍርካና አውሮፓ ግንኑነት በእኩልነት ላይ የተመረተ ሆኖ አይውቅም፡ ። አለማቀፋዊ ትብብር ይባላል ግን የአፍርካና አውሮፓ ግኙነት አሁንም የተዛባ ነው። አውሮፓ አዋቂ አፍርካ ተማሪ የሆነበትም የባላይና የበታች ግንኙነት የሚንጸባረቅበት ነው። ለምሳሌ የንግዱን ግንኙነት ማየት ይችላል። አፍርካ የአውሮፓ ዋና አጋር ነው። አፍርካ ወደ ውጭ ከሚልከው ጥሬ ዕቃ አንድ ሶስተኛው ወደ አውሮፓ ነው የሚላከው። ወደ ውስጥ ከሚያስገባው ሸቀጥም አንድ ሶስተኛው ከአውሮፓ ነው የሚገባው። ይሁን እንጂ ግንኙነታቸው የእኩያሞች ግንኑነት ሆኖ አያውቅም። አፍርካ በአብዛኛው ወደ ወስጥ የሚያስገባው የእንዱስትሪ ውጤቶችን ሲሆን፤ ወደ ውጭ የሚልከው ደግሞ የማዕድን ጥሬ ዕቃዎችን እና የግብርና ውጤቶችን ነው። ይህ ደግሞ አፍርካ እንዱስትሪን እንዲያያስፋፋና ስራ እንዲፈጥር አያስችለውም። እንደ ጀርመናዊው የኢኮኖሚ ባለሙያ ሮበርት ካፐል እምነት ይኸ አይነቱ ግንኙነትም አፍርካ በአሁኑ ወቅት የተጋረጣበትን ችግር አይፈታም። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስራ አጥ ያለበትና ኢኮኖሚውም በአብዛናው ኢመደበኛ በመሆኑ አውሮፓ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ፋላጎት እንዲኖረው ያስፈልጋል ። የፍልሰተኖችና ስደተኖች ጉዳይ ሌላው የአውሮፓና አፍርካ ግንኑነ ትኩረት ነው፡፤ አውሮፓ በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ የአፍርካ መንግስታት ወደ አውሮፓ በህገወጥ መንገድ የሚገቡትን ስደተኖች እንዲያስቆም ከፍተኛ ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል። ይህን ለማድረግ የሚተባበሩ የአፍሪካ መንግስታትም የገንዘብና ቲክኒክ ድጋፍ ሲያገኙ ቆይተዋል። ከዚሁ ጋርም አውሮፓ በህጋዊ መንገድ ወደ አውሮፓ መግባት ለሚፈልጉ አፍርካውያን ሁኒታዎችን እንደሚያመቻች ቃል ተገብቶም ነበር። ይሁን እና ባለመያዎች እንደሚሉት ይህ የተገባ ቃል ተግባራዊ አልሆነም።ይልቁንም በአውሮፓ ለመስራትም ሆነ ለመማር ለሚፈልጉ አፍርካውያን ከሌሎቹ የበለጠ አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የሚታመነው። ዶክተር ልይንዳ ኢሮሎ እንድሚሉት የአውሮፓ የስደተኖች ፓሊሲ የስፍርካ ስደተኖችን የሚያገል ነው፡ እንደእሳቸው እምነት ፖሊሲው የመዋቅርና የአተገባበር ችግሮች ያሉበት መሆኑን በብዙ ማሳያዎች ማረጋገጥ ይቻላል። እራሳቸው ኢመደበኛ፤ ህገወጥ፤ ፈላሲ የሚሉት ቃላት አሉታዊ ትርጉም የሚሰጡ ናቸው። የዓውሮፓ ህብረት ያፍርካ ስትራቴጅ ሌሎች ጉድለቶች እንዳሉትም ነው የሚነገረው። ብራስልስ አምስት ከአፍርካ ጋር የሚተባበርባቸውን ዘርፎች ለይቷል፤ የአረንጓዴ ልማት፤ የዲጂታል ሽግግር ዘላቂ ልማት ደህንነትና የስደተች ጉዳይ። ነገር ግን ስትራቴጂው በተዘጋጀበት አግባብ ላይ ከሁለቱም ወገን ቅሬታ አለ። ሚስተር ሞጌ እንደሚሉት እንደዚህ አይነት ስትራቴጂ መዘጋጀት የነበርበት ከአፍርካ ህብረት ጋር በመመካከርና በጋራ ነበር ። እንደዚያ ቢሆን ለተግባራዊነቱ የበለጠ እድል የሚኖረው ቢሆንም፤ የአሁኑ ግን አውሮፓ አዘጋጅቶ አፍርካ በስራ ላይ እንዲያውለው ያቀረበው ዓይነት ነው በመሆኑም የአውሮፓና አፍርካ አዲስ ግኙነትን በሚመለከት አሁን ሁሉም ን ነው የሚጠብቀው። በዙ የተጠበቀው የአፍሪክና አውሮፓ ህብረት አዲስ የአጋርነት ስትራቴጂ ስምምነ በሚቀጥለው አመት ይበሰራል ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ የሁለቱ አህጉሮች ግንኙነት ጥልቅ ሊሆን እና ሊሰምርም የሚችለው የሁለቱ አህጉሮች መሪዎች በዕኩልነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለማድረግ ሲስማሙና ሲተገብሩም እንደሆነ የሚታመን ሲሆን ፤ይህ የመሆኑ አለመሆኑ ሁኒታ ግን ወደፊት የሚታይ ነው የሚሆነው። ገበያው ንጉሴ ዳንኤል ፔልስ
የአፍሪቃ አውሮጳ ሥልታዊ ትብብር ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ጎርፍ ያፈናቀላቸው በጋምቤላ
በጋምቤላ ክልል በጎርፍ የተጎዱ አካባቢ ነዋሪዎች እ የተሰጠን ያለው እርዳታ በቂ አይደለም ሲሉ ተናገሩ፣ የክልሉ መንግሥት ለዕለት እርዳታ የሚውል ሚሊዮን ብር መመደቡን የጋምቤላ ክልል መንግሥት አስታውቋል። በጋምቤላ ክልል በጎርፍ የተጎዱ አካባቢ ነዋሪዎች እ የተሰጠን ያለው እርዳታ በቂ አይደለም ሲሉ ተናገሩ፣ የክልሉ መንግሥት ለዕለት እርዳታ የሚውል ሚሊዮን ብር መመደቡን የጋምቤላ ክልል መንግሥት አስታውቋል። በክልሉ ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት እየተረባረቡ እንደሆነ ደግሞ የክልሉ አደጋ መከላከል መሥሪያ ቤት አመልክቷል። በክልሉ ሺህ ያህል ህዝብ በጎርፍ ምክንያት መፈናቀልና ጉዳት ደርሶባቸዋል። የጋምቤላ ክልል መንግሥት በአፋር በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች አንድ ሚሊዮን ሺህ ብር እርዳታ አድርጓል። ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ወንዞች ሞልተው ባስከተሉት ጎርፍ በርካታ ህዝብ ከመኖሪያ ቤቱ የተፈናቀለ ሲሆን ለከፍተኛ የምግብ እርዳታ መጋለጡን የጋምቤላ ክልል አደጋ መከላከል መሥሪያ ቤት አስታውቋል። መሥሪያ ቤቱ ጉዳቱን ከገመገመ በኋላ ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው እርዳታ እየሰጠ እንደሆነ ገልጧል። ከባሕር ዳር ዓለምነው መኮንን ዝርዝር ዘገባ አለው። ዓለምነው መኮንን
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የስነ ምግባር አዋጅን አፅድቋል። ምክር ቤቱ በአራተኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ ሶስተኛ አስቸኳይ ስብሰባው የቀረበለትን የአዋጅ ረቂቅ በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል። ለዕረፍት የተዘጋው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የስነ ምግባር አዋጅን አጸደቀ። ምክር ቤቱ በርካታ አከራካሪ ጥያቄዎችን ያስነሳውን አዋጅ ያጸደቀው በሙሉ ድምጽ ነው። በአዋጁ ረቂቅ ላይ በምርጫ ወቅት ሴት እና ወንድ ተወዳዳሪዎች እኩል ድምጽ ቢያገኙ ሴቷ እንደምታሸነፍ መደንገጉ በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባ ተቃውሞ ቀርቦበታል። ተቃውሟቸውን ካቀረቡ የምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሐመድ ሀሰን ውሳኔው ህገ መንግስቱን የሚጻረር ነው ብለዋል። ለጥያቄው በምክር ቤቱ የህግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኩል በተሰጠ ምላሽ ይህ ድንጋጌ የተካተተው በህገ መንግስቱም ከተፈቀደው ለሴቶች ከሚሰጥ ልዩ ድጋፍ አንጻር ታሳቢ ተደርጎ ነው። ሆኖም የምክር ቤቱ አባላት ካካሄዱት ክርክር በኋላ ድንጋጌው ውድቅ ተደርጓል። በረቂቅ አዋጁ ውይይት ወቅት አወዛግቦ የነበረው በምርጫ የሚወዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ እንዲለቅቁ ያስገድድ የነበረው አንቀጽም እንዲሻሻል ተደርጓል። በጸደቀው አዋጅ መሰረት ዕጩ ተወዳዳሪዎች በምርጫ ወቅት ያለ ደሞዝ የዓመት ፍቃድ መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል። ተወዳዳሪዎቹ በምርጫ ጊዜ የመንግስትን ንብረት እንዳይገለገሉም አዋጁ ከልክሏል። በአዋጁ ላይ አዲስ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመመስረት ሺህ፣ ለክልል ፓርቲ ደግሞ አራት ሺህ መስራች አባላትን የሚጠይቀው ክፍል በተቃዋሚ ፓርቲዎች ተደጋጋሚ ቅሬታ ቢቀርብበትም ተቃውሞው ተቀባይነት አላገኘም። የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአዋጁ አንቀጾች ላይ በአጠቃላይ ቅሬታ ማቅረባቸውን የህግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል። ዛሬ የጸደቀው አዋጅ በረቂቅ ደረጃ ከነበረው የቃላት እና ሌሎችም ማሻሻያዎች እንደተደረጉበት ተገልጿል። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። ዮሃንስ ገብረ እግዚያብሔር ተስፋለም ወልደየስ ልደት አበበ
የመልካሳ የምርምር ማዕከል የ ዓመት ጉዞ
በኢትዮጵያ በግብርና ምርምር ላይ ከተሰማሩ ተቋማት አንዱ የሆነው የመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓሉን ከማክሰኞ ጀምሮ በማክበር ላይ ይገኛል። ማዕከሉ ለህብረተሰቡ ጉልህ የምርምር ውጤቶች ማበርከቱን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከማዕከሉ የወጡት የቦሎቄ እና ማሽላ ዝርያዎች ለብዙ ተጠቃሚዎች መዳረሳቸውንም ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ስር ካሉ የምርምር ማዕከላት መካከል አንደኛው የተመሰረተው የአዋሽ ወንዝን ተንተርሶ ነው። ይህ የምርምር ማዕከል የዛሬ ዓመት ስራውን አሀዱ ያለው አምስት ሄክታር በማይበልጥ ቦታ ላይ ነበር። የአካባቢውን መጠሪያ ተውሶ መልካሳ የሚል ስያሜን የያዘው ማዕከሉ ቀድመውት ከተመሰረቱ አምስት የግብርና ምርምር ማዕከላት በተለየ ዘርፍ ላይ እንዲያተኩር ተደረገ። በአጼ ኃይለስላሴ የስልጣን ዘመን የተመሰረቱት እኒያ የምርምር ማዕከላት በወረር፣ ባኮ፣ ሆለታ፣ ደብረዘይት እና ጅማ ላይ የተቋቋሙ ነበሩ። የወረሩ በጥጥ እና በቆላ ቅባት እህሎች፣ የባኮው በተትረፈረፈ የበቆሎ ምርት፣ የሆለታው ደግሞ ለደጋማው የሀገሪቱ ክፍል የሚሆኑ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎች በማውጣት የታወቁ ናቸው። በዚያን ጊዜ የግብርና ኮሌጅ ከነበረው ከዓለማያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ጋር የተቆራኘው የደብረዘይቱ የምርምር ማዕከል በጤፍ፣ በዳቦ ስንዴ፣ በሽንብራ እና ምስር ዝርያዎች ስሙ የገነነ ነው። የጅማ ግብርና ኮሌጅ አካል የነበረው የጅማ የግብርና ምርምር ማዕከልም በቡና ምርምር ስሙን ተክሏል። ከአዳማ ከተማ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለው መልካሳ የግብርና ምርምር ማዕከል ሲቋቋም ምንን ታሳቢ አድርጎ ነበር በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት የዕውቀት ማኔጅመንት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አበበ ቅሩብ ምላሽ አላቸው። ከመዲናይቱ አዲስ አበባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአነስተኛ ስፍራ ስራውን የጀመረው የመልካሳ የግብርና ምርምር ማዕከል አሁን በ ሄክታር ላይ ተሰንራፍቷል። በአምስት ሰራተኞች ስራውን የጀመረው የምርምር ማዕከሉ አሁን በውስጡ የያዘው የሰለጠነ የሰው ኃይል ብቻ ደርሷል። ማዕከሉ ሲጠነሰስ የጀመረውን የአትክልት ልማት ምርምር አሁንም ቀጥሎበታል። የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ ር በድሩ በሺር በቅርብ ዓመታትም በዚህ ዘርፍ ለህብረተሰቡ ያደረሳቸው የምርምር ውጤቶች እንዳሉ ይናገራሉ። የመልካሳ የግብርና ምርምር ማዕከል በተለያዩ የሰብል እና ጥርጣሬ ዝርያዎች ላይም ምርምሮች ሲያከናውን ቆይቷል። ለቆላማ እና ዝናብ አጥር ለሚባሉ አካባቢዎች የሚስማሙ በምርምር ያወጣቸው ዝርያዎቹ በአርሶ አደሮች ዘንድ ተወዳጅ መሆናቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከማዕከሉ የወጡ የማሽላ የምርምር ውጤቶች በቆላማ እና ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች ነባር ዝርያዎችን ሁሉ እስከመተካት መድረሳቸውን በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት አቶ አበበ ይገልጻሉ። የምርምር ማዕከሉ በቦሎቄ ዝርያዎቹም ላቅ ያለ ውጤት ማስመዝገቡን ባለሙያው ያስረዳሉ። የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ ር በድሩ ይህንኑ ያረጋግጣሉ። በዚህ ሳምንት የወርቅ ኢዬቤልዩን እያከበረ ያለው የመልካሳ የግብርና ምርምር ማዕከል ከጥቂት ዓመታት በፊት በቦሎቄ እና ማሽላ የምርምር ውጤቶቹ ከቀድሞው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የወርቅ ሽልማት ተበርክቶለታል። የጥራጥሬ እና ሰብል ዝርያዎቹ ሽልማት ያገኙት በአርሶ አደሮች ምርት ላይ ምን ያህል በጎ ተጽዕኖ አምጥተዋል የሚለው በባለሙያዎች ተፈትሾ እንደሆነ ዶ ር በድሩ ያብራራሉ። አንድን አዲስ የአትክልት፣ የሰብል አሊያም የጥርጣሬ ዝርያ ለማውጣት የሚፈጀው የምርምር ጊዜ ታዲያ ቀላል አይደለም። እስከ ዓመት ድረስ የሚወስዱ ምርምሮች ይኖራሉ የሚሉት ዶ ር በድሩ አማካይ የምርምር ጊዜያት ግን ከአምስት እስከ ሰባት ዓመታት እንደሆነ ይገልጻሉ። በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከአንድ የምርምር ውጤት በላይ እንደማያወጡ የሚገልጹት የማዕከሉ ዳይሬክተር ምክንያቱን እንዲህ ያስረዳሉ። እንደ ዶ ር በድሩ ገለጻ ከአንድ በላይ የምርምር ዝርያ ማውጣቱ ዋናው ጥያቄ ሊሆን አይገባም። ይልቁንም መታየት ያለበት የወጣው ምን ያህል ጥቅም ላይ ይውላል የሚለው ነው ይላሉ። በእነርሱ የምርምር ማዕከል በኩል የሚወጡ አዳዲስ ዝርያዎችን እንደሚፈለገው ለአርሶ አደሩ ተዳርሶ እንደው ሲጠየቁ እንደተፈለገው አልደረሰም፤ አይደርስምም ሲሉ ምላሽ ይሰጣሉ። ይህን ችግር ለመፍታት ብዙ ጊዜ ተሞክሯል የሚሉት ዶ ር በድሩ የምርምር ውጤቶችን አባዝቶ ለህብረተሰቡ ማድረስ ላይ አሁንም ችግር አለ ይላሉ። ኢትዮጵያ በፌደራል ደረጃ ፣ በክልሎች ደግሞ ከ የሚልቁ የግብርና ምርምር ማዕከላትን ይዛ የህዝቧን የምግብ እጥረት ማቃለል የሚችሉ የምርምር ውጤቶችን በስፋት ማዳረስ ከተሳናት እንደ መልካሳ ያሉ ማዕከላት ታዲያ ውጤታማነታቸው ምኑ ላይ ነው የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ባለሙያው አቶ አበበ ችግሩ የምርምር ማዕከላቱ ጋር አይደለም ባይ ናቸው። ሙሉ መሰናዶውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። ተስፋለም ወልደየስ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ፖለቲካ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የመልካሳ የምርምር ማዕከል የ ዓመት ጉዞ መግቢያ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ሥቃይ እና መከራችን እየበዛ ነው በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሥቃያችን፣ እንግልታችን እና መከራችን እየበዛ ነው እያሉ ነው። አንዲት ወጣት ሕፃናት እየሞቱብን ነው፤ እህት ወንድሞቻችን እየተሰቃዩብን ነው። ነፍሰ ጡር ሴቶች እየተሰቃዩ ነው ብላለች። አገሪቱ የስደተኞች ሕጓን ካሻሻለች በኋላ ጉዳዩ መወሳሰቡን በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ተናግረዋል በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው እየተለየ ሞት እስር ግፍና መከራ እየተፈፀመባቸው መሆኑ ተገለፀ ኢትዮጵያኑ እንደሚሉት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ጭምር ቤታቸው እየተሰበረ ከነልጆቻቸው ወደእስር ቤት በመወርወር ላይ ናቸው በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ችግሩ እጅግ ውስብስብ እንደሆነና ዜጎችን ወደሃገራቸው የመመለስ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል ታሪኩ ኃይሉ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓመቱ የመጀመሪያው ስብሰባ
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ መስከረም ፣ ዓም ለህዝብ ተወካዮች እና ለፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የዓመቱን የትኩረት አቅጣጫዎች የጠቆሙበትን ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል።ከዚህ ሌላ ምክር ቤቱ ዛሬ በ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የ ዓም የመጀመሪያ ስብሰባው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ መስከረም ፣ ዓም ለህዝብ ተወካዮች እና ለፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የዓመቱን የትኩረት አቅጣጫዎች የጠቆሙበትን ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል።ከዚህ ሌላ ምክር ቤቱ በዚሁ በ ኛ ዓመት የስራ ዘመን ኛ መደበኛ ስብሰባው በ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መምራቱን ውይይቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዘግቧል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
በሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሮሮ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ሁለት ሱዳናውያን ስደተኞች በሊቢያ የባሕር በር ጠባቂዎች ተገደሉ
የሊቢያ የባሕር በር ጠባቂ ኃይል ሁለት ሱዳናውያን ስደተኞች መግደሉን እና አምስት ማቁሰሉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ስደተኞቹ የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ሲሞክሩ ተይዘው ወደ ኹምስ እንዲመለሱ ከተደረጉ በኋላ ትንናት ምሽት የባሕር በር ጠባቂዎች በከፈቱት ተኩስ መገደላቸውን ድርጅቱ አስታውቋል የሊቢያ የባሕር በር ጠባቂ ኃይል ሁለት ሱዳናውያን ስደተኞች መግደሉን እና አምስት ማቁሰሉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ስደተኞቹ የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ሲሞክሩ በሊቢያ የባሕር በር ጠባቂ ኃይል ኹምስ ወደ ተባለ የወደብ ከተማ እንዲመለሱ ከተደረጉ በኋላ ትንናት ምሽት የባሕር በር ጠባቂዎች በከፈቱት ተኩስ መገደላቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። በኹምስ የሚገኙ የዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት ሰራተኛ ስደተኞቹ ከተጫኑበት ጀልባ በወረዱበት ቅጽበት ለማምለጥ ሲሞክሩ በተከፈተ ተኩስ ሁለት ሱዳናውያን መገደላቸውን እና ሌሎች አምስት መቁሰላቸውን እንዳረጋገጡ ተቋሙ በዛሬው ዕለት ባወጣው ገልጿል። በመግለጫ መሠረት የቆሰሉ ስደተኞች በአካባቢው ወደ ሚገኝ ሆስፒታል ሲወሰዱ የቀሩት ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። በሊቢያ የስደተኞች ስቃይ መታገስ የማይቻል ነው ሲሉ በሊቢያ ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት ኃላፊ ፌዴሪኮ ሶዳ ተናግረዋል። ያልተመጣጠነ ኃይል ጥቅም ላይ በመዋሉ እንደገና የሰው ሕይወት ትርጉም አልባ በሆነ መንገድ ጠፍቷል ያሉት ፌዴሪኮ ሶዳ የስደተኞችን ደሕንነት ለመጠበቅ በአካባቢው ባለው አሰራር ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የቀረበው ጥሪ ሰሚ ማጣቱን አስታውሰዋል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት በጦርነት ታምሳ መረጋጋት የራቃት ሊቢያ ያለው ነባራዊ ኹኔታ ለስደተኞች አስጊ በመሆኑ ተጋላጭ የሆኑትን ወደ አገሪቱ መመለስ አይገባም ሲል ለአውሮፓ ኅብረት ጥሪ አቅርቧል። ድርጅቱ እንደሚለው በባሕር ላይ ሳሉ በጸጥታ አስከባሪዎች የሚያዙ ስደተኞች ደሕንነታቸው ወደሚጠበቅበት ወደብ የሚያመሩበት ሥርዓት ሊበጅ ይገባል። በአውሮፓ አገራት እና ስደተኞቹ በቀጥታ የሚጓዙባቸው የሜድትራኒያን አካባቢ መንግሥታት ጠንካራ ትብብር ሊኖራቸው ያሻል ሲልም ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት አሳስቧል። ባለፉት አመታት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ ስደተኞች የሜድትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ሲያቅዱ ሊቢያን እንደ መሸጋገሪያ ሲጠቀሙ ቆይተዋል።
አሳሳቢው የኮቪድ ፅኑ ህሙማን ህክምና
በኢትዮጵያ የኮሮና ተዋህሲ ስርጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመምጣቱ በበሽታው የሚያዙ ፤ ወደ ፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ እና በተዋህሲው ህይወታቸውን የሚያጡ ስዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ በበሽታው ሳቢያ ወደ ፅኑ ህክምና ለሚገቡ ሰዎች የመተንፈሻ ኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ ነው ተብሏል። በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፅኑ ህክምና ባለሙያ ዶክተር አስቻለው ወርቁ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት በኮቪድ በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ፤ በዚያው መጠን ወደ ፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ ስዎች ቁጥርም እየጨመረ ነው።በዚህ የተነሳ እሳቸው በሚሰሩበት ክፍል ለፅኑ ህሙማን የሚሆን የኦክስጅን ችግር ያጋጥማል። ችግሩ ተባብሶ የነበረው ከታማሚዎች ቁጥር መጨመር ባሻገር አንድ የኦክስጅን አምራች ፋብሪካ በብልሽት ምክንያት ምርት በማቆሙ በተፈጠረ ክፍተት መሆኑንም ገለፀዋል።ምንም እንኳ ችግሩ በአሁኑ ወቅት ሆስፒታሎች በራሳቸው በመጀመራቸው በመጠኑም ቢሆን የተቃለለ ቢሆንም፤ የኮቪድ ህሙማን ቁጥር አሁንም ቢሆን በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ በመምጣቱ፤ዝግጅትን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። ይሁን እንጅ የኮቪድ በሽታ የዳበረ የጤና ስርዓት ያላቸውን ሀገሮች ሳይቀር አቅም የፈተነ በመሆኑ፤ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ካላደረገ የቱንም ያህል ዝግጅት ቢደረግ ፤ፍላጎት እና አቅርቦትን ማጣጣም አስቸጋሪ ነው ሲሉ ገልፀዋል።ስለሆነም ህብረተሰቡ የመከላከያ መንገዶችን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። እንደ ዶክተር አስቻለው ገለፃ እየታዬ ያለው ችግር ህይወት የማዳኑን ስራ አስቸጋሪ ከማድረጉም በላይ፤ የጤና ተቋማት ሌሎች ታካሚዎችን ለማስተናገድ እንዲቸገሩ ያደርጋል።በሌላ በኩል ኮቪድ በራሳቸው በጤና ባለሙያዎቹ ጤና ላይም እየፈጠረ ያለው ጫና ቀላል አለመሆኑን አስረድተዋል። በዓለም ላይ በኮቪድ በሽታ ከ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም እስከ ትናንት ድረስ ከ በላይ ሰዎች በበሽታው ሳቢያ ለሞት ተዳርገዋል።
ሁሉን አካታች ሀገር አቀፍ ውይይት
በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ሁሉን አካታች ውይይት ማድረግ በምርጫ እና በድኅረ ምርጫ ሊያጋጥሙ ለሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላት ሊተጉ ይገባል ተባለ። በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ሁሉን አካታች ውይይት ማድረግ በምርጫ እና በድኅረ ምርጫ ሊያጋጥሙ ለሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላት ሊተጉ ይገባል ተባለ። ዓለም አቀፍ ሪቫይቫል ሚኒስትሪ የተባለ ሀገር አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች እና የሲቪክ ማኅበራትጋር ዛሬ ከሰአት በኋላ በጉዳዮ ላይ መክሯል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አሳሳቢው የኮቪድ ፅኑ ህሙማን ህክምና ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ባለድርሻ አካላት ሊተጉ ይገባል ተባለ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ሙሉ ሥርጭት፤ ሰኔ ቀን ማክሰኞ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ሥራአጥ ፈላስያንና የአውሮፓ ሕብረት ፍ ቤት
የአውሮፓ ፍርድ ቤት ትናንት ሉክስምቡርግ ላይ ባስቻለው ችሎት የጀርመን መንግሥት ፣ ኤልሳቤት ዳኖቭ ለምትባለው ሩሜኔያዊት የስራ አጥ ድጎማ መከልከሉ አግባብነት ያለውና በሕግም የተመሠረተ ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ወጣቷ ሩሜኒያዊት፤ እ ጎ አ ከ ዓ ም አንስቶ ጀርመን ውስጥ በላይፕትዚግ ከተማ የምትኖር ሲሆን ፤ መስተዳድሩ ለአንድ ልጇ ከሚሰጠው የልጅ አበል ውጭ ለሥራ አጦች የሚከፈለውን ገንዘብ ስለከለከላት ፣ ለአውሮፓ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብላ ስትከራከር ከቆየች በኋ ነው ፍርድ ቤቱ፤ የላይፕትዚግ ማሕበራዊ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በማጽናት ሥራ ለሌላቸው ዜጎች የሚሰጠው አበል ባለመብት ልትሆን እንደማትችል የበየነው። ገበያው ንጉሤ
የማክሰኞ ግንቦት ቀን፣ ዓ ም ዜና መጽሄት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሐሙስ ግንቦት ቀን፣ ዓ ም ዜና መጽሄት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ሙሉ ሥርጭት፤ ሰኔ ቀን ዓ ም ሰኞ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ዩሪ ጋጋሪን የዓለማችን የመጀመሪያው የጠፈር ተጓዥ
ከ ዓመታት በፊት የሩሲያው ጠፈርተኛ ዩሪ አሌክሲይቪች ጋጋሪን ቫስቶክ መንኮራኩረን ይዞ ወደ ህዋ በመጓዝ የመጀመሪያው ሰው በመሆን ታሪክ ሰርቷል። ይህንን ጠፈርተኛ ሩሲያውያን በሳምንቱ መጀመሪያ ዘክረውታል። ጠፈርተኛወ ንድፈ ሀሳብን ወደ ተግባር በመለወጥ ለህዋ ሳይንስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል። በጎርጎሪያኑ ሚያዚያ ቀን ዓ ም የሩሲያው ጠፈርተኛ ዩሪ አሌክሲይቪች ጋጋሪን ቫስቶክ በተባለች ሮኬት ወደ ጠፈር በመጓዝ ምድርን የዞረ የመጀመሪያው ሰው በመሆን ታሪክ ሰርቷል። ይህ የጋጋሪን ታሪካዊ ጉዞ ደቂቃዎችን የፈጀ ሲሆን ያለፈው ሰኞ ኛ አመቱን ደፍኗል።፤ከስድስት አሥርተ ዓመታት በፊት ዩሪጋጋሪን በሞስኮ ቀዩ አደባባይ የተቀበሉት ሩሲያውያንም ለዩሪ ጋጋሪ ክብር ከካርቶን እና ከፕላስቲክ የተሰሩ ሮኬቶችን ወደ ሰማይ በመተኮስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያውያን በሳምንቱ መጀመሪያ በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ የጠፈርተኛው ቀን ዘክረዋል።በዓሉ ላይ የታደሙት ቭላድሚር ክራስኪን ከ ዓመታት በፊት በተካሄደው የጠፈር ጉዞ መሬት ላይ ሆነው በረራውን ከሚቆጣጠሩ ሰራተኞች አንዱ ነበሩ። የ ዓመት አዛውንቱ ከ ዓመት በፊት የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ያስታውሱታል። በዚያን ወቅት ከሚያዚያ ቀን በፊት ጥቂት እንቅልፍ አልቫ ሌሊቶች ነበሩን።ስለዚህ የዚያን ዕለት በጣም የጭንቀት ስሜት ነበረን። እውነቱን ለመናገር መተኛት ያስፈልገኝ ነበር። ግን ደግሞ በጣም ተጨንቄ ስለነበር አይኖቼን እንኳ መጨፈን አልቻልኩም። ስራችንን መቀጠልም ነበረብን። ወቅቱ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ እና በቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት መካከል በነበረው የርዕዮተ ዓለም ልዩነት የተነሳ ከሚያደርጉት ቀዝቃዛ ጦርነት ባሻገር የህዋ ምርምር ፉክክርም በሀገራቱ መካከል እያደገ ስለነበር፤ ይህ አስደናቂ የዩሪ ጋጋሪን የጠፈር ጉዞ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ክስተት ነበር፡፡ የጋጋሪን ስኬት ሶቬት ህብረት የህዋ ምርምር ዕውቀትን ለማሳደግ ከአሜሪካ ጋር በነበረው ውድድር ወሳኝ ምዕራፍ ቢሆንም፤ ሰርጌ ኒኪታ ኩሩሾፍ እንደሚሉት ተልዕኮው ሙሉ በሙሉ በታቀደው መንገድ የሄደ አልነበረም፡፡ በወቅቱ ጋጋሪን ከታቀደው ከፍታ በላይ ወደ ምህዋር ውስጥ በመግባቱ ጉዞው ሊሰናከል ይችላል፤ወይም የእርሱን ወደ መሬት መመለስ ሊያዘገይ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አሳድሮ ነበር ። የጋጋሪን በሕዋ ውስጥ ረዘም ያለ ጊዜ መቆየት ደግሞ በሂደት የምግብ ፣ የመጠጥ እና የኦክስጂን እጥረት ሊያጋጥመው ስለሚችል፤ ህይወቱ አደጋ ላይ ሊሆን ይችላል የሚል ሌላ ስጋት ፈጥሮ ነበር፡፡ ያም ሆኖ ቮስቶክ መንኮራኩር ጋጋሪን ይዛ በሰላም ወደ ምድር ተመለሰች።የደረሰው ግን እንዲያርፍ ከተወሰነለት ቦታ ርቆ በሩሲያ ሳራቶቭ ክልል ውስጥ አንዲት አሮጊትና የልጅ ልጃቸው ድንች በሚቆፍሩበት አንድ ማሳ ላይ ነበር። እንደ ኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ሶሎሞን በላይ የጋጋሪን ጉዞ ምንም እንኳ በቀዝቃዛው ጦርነት ላይ የተመሠረተ ቢሆንም፣ ንድፈ ሀሳብን ወደ ተግባር በመለወጥ ለህዋ ሳይንስ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው። የሁለቱ ሀያላን ርዕዮተ ዓለም በሁለት ጎራ መከፈል ጋር ተያይዞ ሀገራት ለዩሪ ጋጋሪንና ለጉዞው የነበራቸው እይታ የተለያዬ ቢሆንም፤ ሶቪየት ህብረት ለቀድሞዋ ምስራቅ ጀርመንን ፣ ሮማኒያን ፣ ቡልጋሪያና ፖላንድን የመሳሰሉ የሶሻሊስት ሀገሮች የራሳቸውን የጠፈር ተጓዞች ወደ ምህዋር እንዲልኩ ጥረት ታደርግ ስለነበር ፤ለነዚህ ሀገራት የጋጋሪን ዝና ከ ዓመታት በኋላ አልደበዘዘም። የዩሪጋጋሪ ንድፈ ሀሳብን ወደ ተግባር የመለወጥ ስራም በአሁኑ ወቅት ከነዚህ ሀገሮች አልፎ የዓለምን አመለካከት ጭምር የለወጠ መሆኑን ዶክተር ሶሎሞን ያስረዳሉ። ሶቪዬት ህብረት በጋጋሪን በረራ ስኬታማነት ለጊዜው አሜሪካን መብለጥ ብትችልም፤ በሶስት ሳምንት ልዩነት ውስጥ ግንቦት ቀን ዓ ም አሜሪካ አላን ሸፓርድን ወደ ህዋ መላክ ችላለች።ጠፈርተኛው የንዑስ ምህዋር በረራ በማድረግም ሁለተኛው ሰው ሆኗል።በየካቲት ቀን ደግሞ ደግሞ አትላስ ሮኬትን ይዞ አሜሪካዊ ጠፈርተኛ ጆን ግሌን ወደ ህዋ ተጓዘ። ግሌን ከጋጋሪን የበለጠ ምድርን ሦስት ጊዜ በመዞር ክብረወሰንን ሰበረ። የሶቪዬት ህብረትም ከጋጋሪን ጉዞ ከሁለት ዓመት በኋላ፤ የመጀመሪያዋን ሴት ጠፈርተኛ ወደ ህዋ ላከች። ቫለንቲና ተሬሽኮቫ ቮስቶክ በተባለች መንኮራኩር ለሦስት ቀናት ያህል ያሳለፈች ሲሆን መሬትን ጊዜ መዞር ችላለች።ሐምሌ ቀን ኒል አርምስትሮንግ እና ባዝ አልድሪን ጨረቃን በመርገጣቸው፤አሜሪካ የጠፈር ፉክክሩን የበላይነት ያዘች። በዚህ ሁኔታ የቀጠለው የሁለቱ ኀያላን ፉክክር ለሳይንሱ እድገት አስተዋፅኦ ማበርከቱን ዶክተር ሶሎሞን ይገልፃሉ። በ ዓመቱ በ ዓ ም የሚሰለጥንበት ተዋጊ ጀት በመከስከሱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የሪ ጋጋሪን፤ወደ ህዋ በመጓዝ ዛሬም ድረስ የዘለቀውን የሶቪዬት ህብረት የጠፈር ምርምር ልዕለ ኃያልነት ሚና አጠናከሯል። የምስራቅና የምዕራቡ ፍጥጫ ማብቃትና የርዕዮተ ዓለም ልዩነት መደብዘዝ ተከትሎ በዘርፉ የነበረው ፉክክር ወደ ትብብር አድጓል። ትብብሩ በ ዎቹ መገባደጃ ላይ ሶቪዬቶች ምዕራባውያን ጠፈርተኞችን ሚር የተባለውን የጠፈር ጣቢያቸውን እንዲጎበኙ መጋበዛቸውን ተከትሎ የመጣ ሲሆን፤በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፍ የጠፈር መርምር ጣቢያ ጥረቶች ትብብር ላይ ያተኮሩ ናቸው። የምርምር ጣቢያው ከሩሲያ እና ከአሜሪካ በተጨማሪ የአውሮፓ ህዋ ኤጀንሲ ፣ካናዳ እና ጃፓንንም ያካትታል። ከዩሪ ጋጋሪን የመጀመሪያው ታሪካዊ የጠፈር ጉዞ በኋላ ወደ ህዋ የሚደረጉ የጠፈር ጉዞዎችም መደበኛ ሆነዋል። ምንም እንኳን የዓለም አቀፍ ግንኙነት መልኮች ልክ እንደ ቴክኖሎጂው ሁሉ የተለወጡ ቢሆንም፤ የጠፈር ምርምር የኃይልና የክብር ማሳያ መሆኑ ግን አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ነው። ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ። ፀሀይ ጫኔ
የኮቪድ ወረርሽኝ በዘርፍ ላይ ላሳደረው ተፅዕኖ ስልት ተነድፏል ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኬንያ ዉሳኔ እና አንድምታዉ
ኬንያ ከተመድ ጋር በገባችበት ዉዝግብ ምክንያት የደቡብ ሱዳን ሰላማዊ ዜጎች ሰብዓዊ ይዞታ ለአደጋ መጋለጥ እንደማይኖርበት የሚያሳስቡ ዘገባዎች እየወጡ ነዉ። ናይሮቢ ደቡብ ሱዳን የሚገኙ ሰላም አስከባሪዎች ሲቪሉን ዜጋ ለጥቃት መከላከል አልቻሉም በሚል ከመንግሥታቱ ድርጅት በቀረበ ትችት እና እዚያ የሚገኙ የሰላም አስከባሪዉ ኃይል የበላይ የሆኑ ዜጋዋ ከቦታዉ መነሳታቸዉን አልተቀበለችም። ሰላም አስከባሪ ሠራዊቷን ከደቡብ ሱዳን እንደምታስወጣ እና በመንግሥታቱ ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮም እንደማትሳተፍ አስታዉቃለች። የኬንያ ርምጃ ሊያስከትል የሚችለዉን ከወዲሁ በመመዘን ተግባራዊ ማድረግ እንደሌለባት የሚመክሩ እንዳሉ ሁሉ፤ የተመድ ክስ በአካባቢዉ የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴ የናይሮቢን ሚና ከግምት አላስገባም የሚሉም አሉ። ከናይሮቢ ጋዜጠኛ ፍቅረማርያም መኮንንን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በጉዳዩ ላይ አነጋግረነዋል። ፍቅረማርያም መኮንን
የቅዳሜ ሰኔ ቀን፤ ዓ ም የዓለም ዜና ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሀገር ደህንነትና የፖለቲካ ልዩነቶች
በወሎ ዩኒቨርቲቲ የህግ መምህርና የፖለቲካ ተንታኝ ደጀን የማነህ ለ እንዳሉት ባለብዙ ፍላጎትና ዋልታ ረገጥ የሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካን ለማዘመን እውነተኛ የሽግግር ፍትህ ተቋማትን በማጠናከር የንግግር ባህል ማዳበር አንዱ የመፍትሄ አቅጣጫ ነው ይላሉ።መጪው ምርጫ የፀጥታ ስጋት እንዳይጫጫነው ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን መንግስት እየገለጸ ነው፡፡ በምርጫ ወቅት የተለየና ላቅ ያለ የፖለቲካ እንቅስቃሴና የሀሳብ መግለጫ አውዶች የሚፈቀዱ በመሆኑ መንግስት የሀገር ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን በሚወጣበት ወቅት የፖለቲካ መብቶች ረገጣ እንዳይስተዋሉ መጠንቀቅ ይኖርበታል ተባለ፡፡ በወሎ ዩኒቨርቲቲ የህግ መምህርና የፖለቲካ ተንታኝ ደጀን የማነህ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ባለብዙ ፍላጎትና ዋልታ ረገጥ የሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካን ለማዘመን እውነተኛ የሽግግር ፍትህ ተቋማትን በማጠናከር የንግግር ባህል ማዳበር አንዱ የመፍትሄ አቅጣጫ ነው ባይ ናቸው፡፡ መጪው ምርጫ ብዙም እንዳሰጋው የፀጥታ ስጋት እንዳይጫጫነው ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱ እና ዝግጅት መደረጉን መንግስት በፊናው እየገለጸ ነው፡፡ ስዩም ጌቱ
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባለብዙ ፍላጎትና ዋልታ ረገጥ ነው ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሐሙስ ግንቦት ቀን፣ ዓ ም ሙሉ ሥርጭት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሰኔ ቀን ዓ ም ሙሉ ሥርጭት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ዜና መፅሔት፣ ኃምሌ ፣ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የየካቲት ቀን፣ ዓ ም መጽሄተ ዜና ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ዜና መፅሔት፣ ኃምሌ ፣ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ዜና መፅሔት፣ ኃምሌ ፣ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የአማራ ወጣቶች ማኅበር ስለመጪው ምርጫ
የአማራ ወጣቶች ማኅበር መጪው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ አመለከተ። ምርጫው ከኹከት የፀዳ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች በርትተው እንዲሠሩም በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአማራ ቅርንጫፍ ጽ ቤት ጠይቋል። አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ አባላት እንዳሉት የሚናገረው የአማራ ወጣቶች ማኅበር መጪው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አመለከተ። ማኅበሩ በክልሉ ከወረዳ እስከ ዞን ድረስ የተዘረጉ አባላቶች እንዳሉትም ይነገራል። መጪውን ምርጫ ምክንያት በማድረግም ከአባላቱ ጋር የምክክር መድረክ መክፈቱ ተገልጧል። ቀጣዩ ምርጫ ከኹከት የፀዳ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች በርትተው እንዲሠሩም በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአማራ ቅርንጫፍ ጽ ቤት ጠይቋል። የአማራ ወጣቶች ማኅበር ምጪውን ምርጫ ምክንያት በማድረግ ከአባላቱ ጋር በባሕር ዳር ምክክር እያደረገ ነው። የአማራ ወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ወጣት ዓባይነህ ጌጡ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገረው ወጣቶች ግንዛቤያቸውን አሳድገው የተሻለ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ፓርቲ እንዲመርጡና ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የውይይት መድረኩ ተዘጋጅቷል። ከምርጫ ውጤት በኋላ አሸናፊም ሆነ ተሸናፊ የሆኑ ፓርቲዎች ወጣቱን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይወስዱት ውይይቱ ጠቃሚ መሆኑንም ወጣት ዓባይነህ ገልጧል፡፡ ምርጫውን ሰበብ በማድረግ በአማራ ክልል ምንም ዓይነት ችግር እንደማይፈጠር ግንዛቤ መያዙንም ሊቀመንበሩ አብራርቷል፡፡ በምክክሩ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ ቤት ኃላፊ አቶ መኳንንት መከተ በበኩላቸው ምርጫው ፍትሐዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የወጣቶች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ወጣቶች በምርጫው በንቃት እንዲሳተፉ ጠይቀዋል፡፡ ወጣት የኔነሽ ስጦታው ኅብረተሰቡ ይሆነኛል የሚለውን ፓርቲ እንዲመርጥ በአካባቢዋ ግንዛቤ እየፈጠረች እንደሆነ ለዶይቼ ቬለ ተናግራለች፡፡ የአማራ ወጣቶች ማኅበር የተመሰረተው በ ዓ ም ሲሆን በአማራ ክልል ከወረዳ እስከ ዞን ባሉ መዋቅሮች የተደራጀ ነው፡፡ እንደማኅበሩ ሊቀመንበር ዓባይነህ ጌጡ ማህበሩ ሚሊዮን ሺህ አባላት አሉት፡፡ ምርጫን ተመለከተ ማህበሩ በአማራ ክልል ወረዳዎችና ዞኖች የግንዘቤ ሥራዎችን የሰራ ሲሆን በሕግ ማስከበሩ ወቅት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብስቧል፣ ግንባር ድረስ በመሄድም የምግብ ሬሽን ለሰራዊቱ አቅርቧል ሲል ወጣት ዓባይነህ ተናግሯል፡፡ ዓለምነው መኮንን
አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ አባላት እንዳሉት ይናገራል ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሀዘን መግለጫ ከሉድገር ሻዶምስኪ
ዛሬ ሥርዓተ ቀብሩ በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ የተፈጸመው የአንጋፋው ባልደረባችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ሕልፈተ ሕይወትን አስመልክቶ ከተለያዩ ወገኖች የሚደርሱን የሀዘን መግለጫዎች እንደቀጠሉ ናቸው። ከዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ቋንቋ ክፍል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሉድገር ሻዶምስኪ የተላለፈ የሀዘን መግለጫ ይህ ነው።
የመስከረም ቀን ዓ ም የዓለም ዜና ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የሰሬብሬኒሳ ጭፍጨፋ ኛ ዓመት ዝክር ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኅዳር ቀን ዓ ም፤ የዓለም ዜና
የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ከ ሃገራት የተዉጣጡ አፍሪቃ ሃገራት መንግሥታት ባለስልጥናት አዲስ አበባ ላይ የሁለት ቀናት ዉይይት አካሄዱ። የፍርድ ቤቱ አባላት አብዛኞቹ የአፍሪቃ ሃገራት መሆናቸዉ ይታወቃል። የሰብዓዊ ጉዳዮች አያያዝ ላይ ለመምከር የጀርመንዋ መከላከያ ሚኒስቴር ኡርዙላ ፎን ደር ላይን በወግ አጥባቂ እስልምና መርህ የምትተዳደረዉን ስዑድ አረብያን ለመጀመርያ ጊዜ በመጎብኘት ላይ መሆናቸዉ ተገለጠ። በሃገሪቱ በያዝነዉ ዓመት ብቻ ከ ሰዎች በላይ የግድያ ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል። በዓለማችን የሚገኙ ቀጭኔዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን በመቀነሱ የመጥፋት ስጋት እንደተጋረጠባቸዉ የዓለም የተፈጥሮ ጥበቃ ማኅበር ገለፀ። በመረጃዉ መሰረት በዓለም ዙርያ ያሉት ቀጭኔዎች ቁጥር ሺህ አይበልጥም። አዜብ ታደሰ
አስተያየት በአዲስ አበባው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ
በአንድ ወገን ሰልፉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ያሉ እንደመኖራቸው በሌላ ወገን ደግሞ ሰልፉ መካሄዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች ቆም ብላ እንድታጤን የሚረዳ ነው በማለት የደገፉም አሉ።ሰልፉን የተቃወሙ ሁለት ፓርቲዎች ሰልፉ በኢትዮጵያ ጉዳይ የኃያላኑ ግብግብ እንዲፈጠር የሚያበረታታ ነው ሲሉ ነቅፈዋል። ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ትናንት በአዲስ አበባ የተደረገው ሰልፍ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። በአንድ ወገን ሰልፉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ያሉ እንደመኖራቸው በሌላ ወገን ደግሞ ሰልፉ መካሄዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች ቆም ብላ እንድታጤን የሚረዳ ነው በማለት የደገፉም አሉ።ሰልፉን የተቃወሙ ሁለት ፓርቲዎች በሰልፉ ላይ ተቃዋሚዎች ዩናይትድ ስቴትስ በውስጥ ጉዳይ እንዳትገባ ጠይቆ ሌሎች ኃያላን አገሮች ግን እንዲገቡ የመጠይቅ አዝማሚያ መታየቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ የኃያላኑ ግብግብ እንዲፈጠር የሚያበረታታ ነው ሲሉ ነቅፈዋል።አንድ ምሁር ደግሞ ተቃውሞን ማሰማት አሜሪካ ራሷ የምትፈቅደው መብት በመሆኑ ሰልፉ መደረጉ ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሰሎሞን ሙጬ
አስተያየት በአዲስ አበባው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ተቃውሞ ቢረግብም ስጋት አለ
ተቃውሞው ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት የመቀየር አዝማሚያ መያዙ በታየባቸው የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬም ውጥረት ሰፍኖ እንዳለ የአይን እማኞች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በድሬዳዋ፣ አዳማ እና ባሌ ሮቤ ከተሞች ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለ ከየከተሞቹ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በድሬዳዋ ግጭቱ ረገብም ዛሬ ከነጋ አንድ ባጃጅ መቃጠሉ ተነግሯል። የኦሮሚያ ክልል ፣ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ጥቅምት ጀምሮ በበርካታ ከተሞች ሲካሄድ የነበረው ተቃውሞ ድብቅ ዓላማቸውን መራመድ በሚፈልጉ ኃይሎች የተጠለፈ ነበር አለ። በክልሉ በርካታ ከተሞች ሲካሄድ የነበረው ደም አፋሳሽ እና በግጭት የተሞላ ሰልፍ ዛሬ ረገብ ማለቱን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዴሬሳ ተረፈ ዛሬ አርብ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ተቃውሞን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ የተወጣው ሰልፍ መልኩን ቀይሮ ለሰዎች ሞት እና ለንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል በማለት ተናረዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት በኦሮሚያ ከተሞች በብዙ አካባቢዎች ሰልፍ ነበር ፤ ያው ሰልፎቹ በብዙ ቦታዎች ላይ በሰላማዊ መንገድ ነው የተጠናቀቁት ። ሰልፈኞች ያው ያላቸውን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ አቅርበው ነው ወደ ቤታቸው የተመለሱት ። ሆኖም ግን አንዳንድ ቦታዎች ላይ ላይ ወደ ግጭት ነው የተቀየረው፤ የሃይማኖት መልክ ይዞ ። የሃይማኖት ግጭት ወደዛ መውሰድ የፈለጉ የፖሎቲካ አላማቸውን ለማሳካት የሚሰሩ አካላት ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው ህዝቡን በሃይማኖት ለማጋጨት ጥረት አድርገዋል ፤ በዚህም የሰው ህይወት አልፏል፤ የአካል መጉደልም ፣ የንብረት መውደምም ያጋጠመበት ሁኔታ አለ በአንዳንድ ከተሞች። አቶ ዴሬሳ በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ነውጥ የተነሳ በጥቅሉ ሰዎች መሞታቸውንና ንብረት መውደሙን ከመጥቀስ ባሻገር በሰው ላይ የደረሰውን የሞት እና የአካል ጉዳትን ጨምሮ የደረሰውን የንብረት ውድመት አሁን ላይ በቁጥር መግለጽ እንደማይችሉ ተናግረዋል። የሁለቱ ቀናት ተቃውሞ ወደ ሃይማኖታዊ ግጭት የመቀየር አዝማሚያ መያዙን በታየባቸው የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬም ውጥረት ሰፍኖ እንዳለ የአይን እማኞች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። በድሬዳዋ፣ አዳማ እና ባሌ ሮቤ ከተሞች ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለ ከየከተሞቹ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በድሬዳዋ ከተማ የተቃውሞ ሰልፉን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት ረገብ ቢልም ዛሬ ከነጋ አንድ ባጃጅ መቃጠሉን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የከተማይቱ ነዋሪዎች ከአንዱ ሰፈር ወደ ሌላኛው ሰፈር ለመሄድ እንደሚቸገሩም እኚሁ ነዋሪ አስረድተዋል። እኔ አሁን ድሬዳዋ ውስጥ ነው ያለሁት ፤ ጎሮ የሚባል ቦታ ነው ያለሁት ፤ አሁን ባለሁበት አንድ ባጃጅ ተቃጥሏል። አንድ ልጅ የተደበደበ አለ። በካባድ ሁኔታ የተጎዳ ልጅ አለ። አሁንም አዝማሚያው ያው ሰፈር ለሰፈር ተካሎ ነው እንጂ ቁጭ ብሎ ያለው ሰላማዊ ነገር የለም። እንደልብህ ተነስተህ አትሄድም ። ከሰፈርህ ሶስት ብሎክ ተሻግረህ ለመሄድ ደውለህ ነው። የሆነ ነገር እንዴት ነው ብለህ ነው። በድሬዳዋ ከተማ ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ባንተአለም ግርማ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ሌላኛው የድሬዳዋ ነዋሪ ደግሞ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቦሮዳ በተሰኘች መንደር ትናንት ሐሙስ በአንድ ላይ የተገደሉ ሁለት ወንድማማቾችን አስክሬን ወደ ድሬዳዋ ወስደው ለመቅበር ቢጠይቁም መከልከላቸውን ተናግረዋል። በቦሮዳ ያሉ የመንግስት ኃላፊዎች ሟቾቹ እዚሁ ነው የሚቀበሩት በሚል መከልከላቸውን ወንድማማቾቹ ቅርበት ያላቸው የድሬዳዋ ነዋሪ ገልጸዋል። በተከሰተው ግጭት ቦረዳ ላይ ሰዎች ሞተዋል፤ወንድማማቾች ናቸው የተገደሉት ፤ሬሳቸውን ወደዚህ ወደሚኖሩበት ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለማምጣት አልተቻለም። ሁለቱንም ሬሳዎች ወደዚህ ለማምጣት እየተሞከረ ነበር፤ መከላከያዎችም ተነገራቸው ፤ መከላከያዎች ሊያደርጉት የቻሉት አንድም ነገር የለም። ቤተሰቦች ወዳሉበት ቦታ ሬሳውን አግኝተን መቅበር እንኳ አልቻልንም። እዚህ ድሬዳዋ ከንቲባ ቢሮ ተነጋግረናል፣ መከላከያ ጋር ተነጋግረናል፤ እዚያ ያሉት መከላከያዎች ጋር ተሞክሯል፤ ማንም ምንም የሚል ነገር የለም በቃ እዚያው ነው የሚቀበሩት እንጂ ሬሳውን አታገኙም ነው የተባልነው። የግለሰቡን ቅሬታ በተመለከተ የቦሮዳ ሃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።የተፈጠረውን የጸጥታ መድፈረስ ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት ከተሰማባቸው የኦሮሚያ ከተሞች አንዷ በሆነችው በባሌ ሮቤ ከተማ ዛሬ ከሰሞኑ ነውጥ ረገብ ማለቷን እና ትናንት ሀሙስ የሞቱትን ሰዎች በመቅበር ላይ መሆናቸውን አንዲት የከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል። የተጀመረው ከትናንት ወዲያ ነው። የክርስትያን ቤቶችን ነው እየመራረጡ ያቃጠሉት፤ በዚያ የተነሳ ነው ትናንትና ወደማይሆን ነገር ወደ ቤተክርስትያን ማቃጠል ሲኬድ ነው ሰው የተቀየረው። አሁን ሰላም ነው፤ ማለት ፌዴራሎች እየዞሩ ጥበቃ ላይ ናቸው፤ ግን ህዝቡ አይን በአይን እየተጠባበቀ ነው፤ ማለት ከእኛ ሰው ብዙ ሞቷል፤ የኦርቶዶክሱም የሙስሊሙም የእኛ ሰው ነው ብዙ የተጎዳው የማለት ማለት ነው። ነገሩ የሚበርድ አይመስል። ያው የተጎዱ ችግር እንደሚያመጣ ነው፤ ቂም ላይ ነው ሰው ያለው። በአዳማ ከተማ የነበረው ውጥረት ረገብ ብሎ በየቀበሌው ውይይት መጀመሩን የነገሩን አንድ የአዳማ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት ከሆነ መንግስት ከህዝቡ ጋር ወደ ውይይት ቢገባም አሁንም ድረስ በስጋት እና በጥርጣሬ መተያየት አለ ብለዋል። አሁን ሰውጋ ያለው ስሜት አብዛኛው ሰው የተወሰኑ ሱቆች ያልተከፈቱበት ምክንያት በመፈራራት እርስ በእርስ ፍራቻ አለ። ጓደኛ ከጓደኛ፣ ጎረቤት ከጎረቤት ፣ ፍራቻ አለ እና ያንን ፍራቻ ጠዋት እንዳየሁት አንዳንድ የቀበሌ አመራሮች ሰዎችን የሃይማኖት ተቋማትን ሰብስበው እያወያዩ ነው። የሃይማኖት ተቋማትም እንደምታውቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ከትናንት ጀምሮ ሲጸልዩ ነበር ። ዛሬም ከተማ ውስጥ ሰዎች ሄደው እየጸለዩ ወደ ሙስሊሙም ሄደው ዱዓ እያደረጉ ነው ያሉት። ጥሩ ነገር ነው፤ ነገ እና ከነገ ወዲያ በዚህ ሳምንት ከተማዋ ወደ ሰላማዊ መንገድ ትመለሳለች የሚል ግምት ነው ያለኝ። የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ቀን ላይ ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በሰጠው መግለጫ የተፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታትና የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት ከአባ ገዳዎችና ከኅብረተሰቡ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል። ታምራት ዲንሳ
ባልደራስ ሠላማዊ ሰልፍ ጠራ
መንግሥት ማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶችን ማስቆም አለመቻሉ፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የፍትሕ እጦት፣ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳይ እንዲሁም የሱዳን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጣስ ላይ ታይቷል ያለው ቸልታ ሰልፍ ለመጥራት እንደገፋው ፓርቲው አሳውቋል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በአጭር መጠሪያው ባልደራስ ዋና ዋና ባላቸው አራት ጉዳዮች ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ለጥር ዘጠኝ ቀን ሠላማዊ ሰልፍ መጥራቱን አስታወቀ። መንግሥት ማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶችን ማስቆም አለመቻሉ፣ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የፍትሕ እጦት፣ የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳይ እንዲሁም የሱዳን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጣስ ላይ ታይቷል ያለው ቸልታ ሰልፍ ለመጥራት እንደገፋው ፓርቲው አሳውቋል። ሰልፉ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ያለው ፓርቲው፣ በሌሎች ከተሞች ስለመካሄድ አለመካሄዱ ተቋቁሟል የተባለው ግብረ ኃይል ያሳውቃል ብሏል።ስለጉዳዩ የፓርቲውን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል። ሰሎሞን ሙጬ
ድብቅ ዓላማቸውን መራመድ በሚፈልጉ ኃይሎች የተጠለፈ ነበር ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
አንድ የፖለቲካ ተንታኝ እንደሚሉት ማዕቀቡ የሁለቱ ሐገራት የቆየ ግንኙነት እየሻከረ ለመምጣቱ ማረጋገጪያ ነዉ።
አውዲዮውን ያዳምጡ። የአሜሪካ ማዕቀብ፣ የተንታኙ ምክንርና የፖለቲከኛዉ አስተያየት ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ በኤርትራና በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሕወሓት ባለስልጣናትና በቅርብ ቤተሰቦቻቸዉ ላይ የጣለችዉ የመግቢያ ፈቃድ ቪዛ እገዳና በኢትዮጵያ ላይ የጣለችዉ የምጣኔ ሐብት ማዕቀብ ዛሬም ለ ኛ ቀን ኢትዮጵያዉያንን እያነጋገረ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ ያነጋገራቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ እንደሚሉት ማዕቀቡ የሁለቱ ሐገራት የቆየ ግንኙነት እየሻከረ ለመምጣቱ ማረጋገጪያ ነዉ።ግንኙነቱን ለማሻሻል የኢትዮጵያ መንግስት አበክሮ መጣር እንዳለበትም የፖለቲካ አዋቂዉ መክረዋል።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር ሙላቱ ገመቹ ግን የዩናይትድ ስቴትስ ርምጃ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የመጣስ ምግባር ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ባይ ናቸዉ። ስዩም ጌቱ
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መግለጫ በወቅታዊ ጉዳዮች
አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ ማዕቀብ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥን፣ ቀጣናውንም ችግር ላይ የሚጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገለፀ። ሚኒስቴሩ ርምጃውን የሁለቱን አገራት የመቶ ሀያ ዓመታት ግንኙነት በዜሮ የሚያባዛም ብሎታል። አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ ማዕቀብ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥን፣ ቀጣናውንም ችግር ላይ የሚጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገለፀ። ሚኒስቴሩ ርምጃውን የሁለቱን አገራት የመቶ ሀያ ዓመታት ግንኙነት በዜሮ የሚያባዛም ብሎታል። ይህ ርምጃ ኢትዮጵያ በፀረ አልሸባብ የሽብር ድርጊት መከላከል እና በሰላም ጥበቃ ያላትን ጉልህ ሚና የሚጎዳ መሆኑም ተገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ ነገሩን ማጋጋል እንደማትፈልግ ገልፀው ነገር ግን የኢትዮጵያ ነፃነትና ሉዓላዊነት በገንዘብ የማይቀየር ቀይ መሥመር ነው ብለዋል። ሰለሞን ሙጬ
የምዕራቡ ዓለም ሃገራት በኢትዮጵያ ጣልቃ አይግቡ ተብሏል ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ማእቀቡ ቀጣናውን ችግር ላይ የሚጥል ነው ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የአሜሪካ ማዕቀብ፣ የተንታኙ ምክንርና የፖለቲከኛዉ አስተያየት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ኮት ዲ ቯር ም ቤታዊ ምርጫ፥ ቀውስ በካሜሩን፣ ብይን በሰው አሸጋጋሪዎች ላይ ፣ ማዕቀብ በኮንጎ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
አፍሪቃውያን አፍሪቃዊነትን እንዴት ይገልፁታል
አብዛኛውን ጊዜ አፍሪቃ ከአህጉሯ ሰዎች ይልቅ በምዕብራባዊያን እይታ ወይም እነሱ በጻፉት እና በተናገሩት ስትገለፅ ይዘወተራል። የጥቁሮች አህጉር፣ የ ኛው ዓለም፣ በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት፣ እየተባለ ለአፍሪቃ ማኅበረሰብ የተለያዩ ስሞች ወጥተዋል። አፍሪቃውያንስ ስለ ራሳቸው ምን ይላሉ
አሸናፊዎቹ ቤዛ ኃይሉ፣ አብርሃም ገዛኸኝ፣ ድርብድል አሰፋ፣ ሕይዎት አድማሱ እና ሄኖክ መብራቱ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ጊዜዬን የማጠፋው ድርሰት በመፃፍ ነው ሰለሞን ደመቀ
ሰለሞን ደመቀ ይባላል። ዓመቱ ነው። የፊልም ክህሎት፣ፍቅርና ትልቅ ዓላማ ያለኝ ወጣት ነኝ ይላል። የካሜራ ባለሙያ ነው። ከዚህም ባሻገር የተለያዩ የጀብዱ ድርሰቶችን በመፃፍ ሀገሬን በዓለም ለማስተዋወቅ ተዘጋጅቻለሁ ይላል። ሰለሞን ደመቀ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር የካሜራ ባለሙያ ነው። በአሁኑ ሰዓት ተቀጥሮ ዩቲውብ ላይ የሚለቀቁ ቃለ መጠይቆችን ይቀርፃል። ለፊልም የተለየ ፍቅር እና ተሰጥዎ አለኝ የሚለው ሰለሞን እስካሁን አምስት የፊልም ድርሰቶች ፅፎ ጨርሷል። ከሁሉም ፅሁፎች የጀብዱ ዘውግ መፃፍ ያስደስተኛል ይላል። ምናባዊ ነው፤ ጥንት በነበሩ ድርጊቶች ነው የሚከናወነው። ፊልሙ ላይ ጀግና ይኖራል። ያ ጀግና ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው። ወጣቱ የፃፋቸው የፊልም ድርሰቶች ግጭቶችን ያካተተ ቢሆንም ፊልሙን በሁሉም የእድሜ ክልል ያለ ኢትዮጵያዊ ሊያየው እንዲችል አድርጌ ነው የፃፍኩት ይላል ፤ ለዚህም ምክንያት አለው። በተለይ ለአዲሱ ትውልድ በጥንት ጀግኖቻችንን እንዲያውቁ የልጆችን ልብ መያዝ በሚችል አቀራረብ ያንን ታሪክ እንዲያውቁ ማድረግ ነው። እነዚህ ገፀ ባህሪያትም የሚገጥማቸውን ችግሮች ሲፈቱ አሳያለው ወጣቱ። እነዚህንም ድርሰቶች ለመፃፍ የተለያዩ ከግዕዝ የተተረጎሙ መጽሐፍትን ማንበብ እንደነበረበት ሰለሞን ይናገራል። ወጣቱን እምብዛም ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተለመዱ ድርሰቶችን እንዲፅፍ ይበልጥ ያነቃቁት እሱ እንደሚለው የሚያነባቸው መጽሐፍት እና የውጭ ሀገር ፊልሞች ናቸው። ውጪ ላይ ያሉት ፊልሞች ከእኛ ከተተረጎሙት ፊልሞች ጋር ይቀራረባሉ። እና እኛ የነበሩንን መፅሐፍት ወደ ፊልም እየቀየርን እየተጠቀምንበት አይደለም ድርሰቶቹም አጫጭር እና ተከታታይ ታሪኮች ናቸው ይላል ሰለሞን። የሰለሞን ትልቁ ፈተና ይህንን ፊልም ዕውን የሚያደርግለት ፕሮዲውሰር ማጣቱ ነው። አፃፃፉን ቢወዱትም ገንዘብ አውጥተው ፕሮዲውስ ለማድረግ የሚቸግራቸው ነገር የጊዜ ጉዳይ ነው። ቶሎ አያልቅም፣ ገንዘብ አያመጣም፣ ህዝቡ የፍቅር እና ኮሜዲ ነው የሚወደው ይሉኛል ይላል። ሌላው ደግሞ ገፀ ባህሪዎቹን እንዴት እንደምንሰራ አላውቅም ይሉኛል ይላል። የካሜራ ባለሙያ የሆነው የ ዓመቱ ወጣት ግን ባለ ሙሉ ተስፋ ነው። እነዚህን ምናባዊ ገፀ ባህሪያትም በፊልሙ የሚያካትትበትን መንገድ ታሳቢ አድርጌ ነው የፃፍኩት ይላል። ከልጅነቴ አንስቶ ለትምህርት ቤቶች አጫጭር ታሪኮችን ፅፌ አቅርብ ነበር የሚለው ሰለሞን ምንም እንኳን እስካሁን የፊልም ህልሙን እውን ማድረግ ባይችልም፤ እዚህ ደረጃ ለመድረስ ያበቃው የግል ጥረቱ ከፍተኛ በመሆኑ እንደሆነ ይናገራል። ራሴን ማስተማር ነበረብኝ። ድርሰቱን በየቀኑ ነው የምፅፈው። መውጫው ብቻ ነው የጠፋብኝ ይላል የጀብዱ ድርሰቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ጀግኖችን በማካተት የተለየ ፊልም ይዞ ለመቅረብ የተነሳው የካሜራና የፊልም ባለሙያ ሰለሞን ደመቀ። ልደት አበበ
ልጆችን ስለ ወሲብ መቼ እና ምን ማስተማር ያሻል
ከሰሀራ በስተደቡብ የሚኖረዉ የአፍሪቃ ሕዝብ ከመቶው ከ ዓመት በታች ይሆናል ተብሎ እንደሚገመት ከዚህ በፊት ገልጸናል። በዚህ ወጣቱ በሚያመዝንበት ማህበረሰብ ውስጥ ግን ስለ ወሲብ ማውራት እንብዛም አይደፈርም። ለምን አፍሪቃውያን ወላጆች ልጆቻቸውን ስለዚህ ጉዳይ ማስተማር እንደሚከብዳቸው ኬንያንና ዮጋንዳን እንደምሳሌ በመውሰድ እንቃኛለን። ልጆችን መቼ ነው ስለ ወሲብ ማስተማር የሚገባው ምንስ ነው ማወቅ ያለባቸው ይህ እንደየሀገሩ ባህል እና አመለካከት ይለያያል። አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የኬንያ መንግሥት በየትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት መለስ ብሎ እንዲቃኝ ፊርማ እያሰባሰበ ነዉ። ፊርማውን የፈረሙት የሚጠጉ ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ማውራቱ የሚያሳስት እና አፍሪቃዊ አይደለም ብለው ያወግዛሉ። ሀቁ ኬንያ ውስጥ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ በላይ እድሜያቸው ከ ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎች በእርግዝና ምክንያት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል። ብዙ ወላጆች ጉዳዩን አንስተው ከልጆቻቸው ጋር ለማውራት ስለማይደፍሩም ልጆቻቸው ያላቸው አማራጭ መረጃ ከኢንተርኔት አልያም ከጓደኞቻቸው ማፈላለግ እንደሆነ ይገልፃሉ። የ ዓመቷ ክሪስቲና እንደምትለው ወላጆች ስለዚህ ርዕስ ለማውራት ስለሚያፍሩ ነው። እናቴ ስለ ወሲብ አውርታኝ አታውቅም። ከዛም በ ዓመቴ አረገዝኩ። እርጉዝ መሆኔን ስነግራት ለምን ኮንዶም እንዳልተጠቀምኩ ጠየቀችኝ። ኮንዶም የማገኝበት መንገድ ከየት ታዉቃለች ብለሽ እ ትጠብቂ ነበር አልኳት። በዚህ በጎርጎሮሲያዊው ዓመት የዩንቨርስቲ ትምህርቷን መከታተል የምትጀምረው ክሪስቲና ከወላጆቿ ጋር ነው የምትኖረው። የልጇ አባትም ልጇን እንደሚንከባከብ እና ብዙም ችግር እንደሌለባት ትናገራለች። ዛሬ ላይ መለስ ብላ ስታስበው ግን ወላጆቿ ስለ ወሲብ አስተምረዋት ወይም ነግረዋት ቢሆን ኖሮ ትምህርቷን እስክትጨርስ ድረስ አታረግዝም ነበር። በወጣትነት እድሜዬ የበለጠ ባውቅ ኖሮ እያልኩ እመኝ ነበር። ዛሬ ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ያሉ ልጆችን ስመለከት ቀደም ብለው ሊነገራቸው ይገባል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም አንዳንድ ልጃገረዶች ገና በ ዓመታቸው የወር አበባ ይታያቸዋል። የኬንያ የጤና ሚኒስቴር ባደረገው ጥናት በርካታ ልጃገረዶች ክብረ ንፅሕናቸዉን ያጡበት አማካይ እድሜ ዓመት ነው። ባለፈው ዓመት ከ በላይ እድሜያቸው ከ ዓመት የሆኑ ልጃ ገረዶች ላልተፈለገ እርግዝና ተዳርገዋል። ምንም እንኳን ብዙዎች ስለዚህ ርዕስ ማውራት ባይደፍሩም ሲትዝን ጎ የተሰኘ አንድ የመብት ተሟጋች ድርጅት የኬንያ መንግሥት ስለ ወሲባዊ ግንኙነት የቀረፀው ትምህርት ጠቃሚ አይደለም ሲል ፊርማ ያሰባስባል። የዚህ ዘመቻ አስተባባሪ የሆኑት አነ ኪኮ መንግሥት ስለ ወሲባዊ ግንኙነት ማስተማሩ ልጆቹን ልቅ እንዲሆኑ እንጂ እንዲቆጠቡ አልረዳም። ይህንን ስርዓት የማንቀበልበት ምክንያት ይህ ከውጭ ወደ አፍሪቃ በተለይም ኬንያ የመጣ ስርዓት በመሆኑ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ነው። ከዛም ብሪታንያ ውስጥ ተግባራዊ ሆነ፤ ቀጥሎም ራሳቸውን አደግን ብለው የሚጠሩት ሀገራት ላይ ይተገበር ጀመር። ይህ ስርዓት ልጆች ከተወለዱ ጀምሮ ለወሲባዊ ግንኙነት የተፈጠሩ እንደሆነ የሚያስተምር ነው። ከአምስት ዓመታቸው ጀምሮ በአካላቸው ማድረግ እንደሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ የሚያበረታታ ነው። እንደ ኬንያ መንግሥት ከሆነ ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት የሚሰጠው ልጆች አግባብ የሆነ እድሜ ላይ ሲደርሱ ነው። ይህም በቂ እውቀት እንዲቀስሙ ይረድቷቸዋል። ለአካለ መጠን የደረሱ ወጣቶችን ጉዳይ የሚመለከት የጥናት ተቋም ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አልበርት ኦቢዩ እንደሚሉት ትምህርት እና መፅሀፍ ቅዱስ ለየብቻቸው መታየት የለባቸውም። ሌላው ደግሞ ይህ ባህል እና ሐይማኖታችንን የሚቃወም ሀሳብ ነው የሚለው ነው። ሁላችንም ለእምነታችን የተገዛን ቢሆን ኖሮ ስለ ወሲብ ማውራት ባላስፈለገ ነበር። ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ልጆች ባላረገዙ ፣ የፆታ ጥቃቶች ባልተፈፀሙም ነበር። ስለዚህ ለእነዚህ ጉዳዮች ተጨባጭ ምላሽ ያስፈልገናል። እኛ የምንለው እና የምናስተምረው መፅሀፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ጋር ወጥ የሆነ ይመስለኛል። የአፍሪቃ የህዝብ እና ጤና ጥናት ማዕከል እኢአ በ ዓም ባደረገው ጥናት መሠረት ኬንያውያን ወጣቶች ስለ ኮንዶም፣ የእርግዝና መከላከያ ኪኒኖች እና መርፌዎች አጠቃቀም በትምህርት ቤት መማር ይሻሉ። ከዚህም በተጨማሪ በግብረ ስጋ ግንኙነት ስለሚተላለፉ በሽታዎች እና እነዚህንም እንዴት መከላከል እንደሚቻል ዋወቅ ይሻሉ። እኛ ሀገር ያለው ችግር አካባቢያዊ እንደሆኑ አካባቢያዊ መፍትሄ ይሻሉ። ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ልጆች እርግዝና ፣ የስነ ተዋልዶ አካል መተልተል ሌላው የውጪው ዓለም ክፍል ያስገደደን አይደለም ይህ ልንሸሸገው የማንችለው የራሳችን ችግር ነው። ቁጥብነት ዩጋንዳ ውስጥ ትልቅ ርዕስ ነው። በተለይ ወጣቶችን እና ወሲባዊ ግንኙነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ። የዩጋንዳ መንግሥት ወጣቶች ትዳር እስኪመሰርቱ ድረስ ወሲብ ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ያበረታታል። ይሁንና ይህ መልዕክት በወጣቱ ዘንድ ችላ የተባለ ይመስላል። የዶይቸ ቬለው ፍራንክ ይጋ ወጣት ዩጋንዳውያን መንግሥት የሚሰብከውን እንዴት እንደሚቀበሉት አጠያይቆ ነበር። ዛሬ ወንዶች ድንግል የሆነች ልጅ አይደለም የሚፈልጉት። ልምዱ ያላቸውን ነው የሚፈልጉት። ድንግልን ይህን እና ያንን ማስተማር ያስፈልጋል፤ ሌላኛዋ ግን ሁሉም ነገር የገባት ናት በሚል ነው። ቁጥብነት መጥፎ አይደለም። አሁን ተቆጥቤ ነው ያለሁት ፤ ጥያቄው ግን እስከመቼ የሚለው ነው ይላሉ ቫኒ እና አኖልድ የተባሉት የዮንቨርስቲ ተማሪዎች። በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በሚገኝ ቪክቶሪ የተሰኘ ቤተክርስትያን ውስጥ ግን ቄሱ ቁጥብነትን በግልፅ ይሰብካሉ። መፅሀፍ ቅዱስ በግልፅ ለወጣት ሴት እና ወንዶች ራሳቸውን እንዲቆጣጠሩ እና በስሜታዊ ፍላጎት እንዳይመሩ ይገልፃል። ወሲባዊ ስሜታቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ትዳር እንዲመሰርቱ ይመክራል። መልዕክቴ ግልፅ የሆነ ይመስለኛል እንደ መፅሀፍ ቅዱስ ከሆነ ወሲባዊ ግንኙነት ትዳር ለመሰረቱ ብቻ ነው። ከቤተክርስትያን ውጪ ለልጆች ስለ ወሲብ ለማወቅ ከባድ ነው። በባህሉ መሠረት ልጆችን ስለ ወሲብ እንዲያስተምሩ የሚፈቀድላቸው ወላጆች ሳይሆኑ በአባት በኩል ያሉ አክስቶች ብቻ ናቸው። ጡረታ ላይ ያሉት መምህር አሌክስ ዋንዴባ ወላጆች ልጆቻቸውን ከማስተማር ማመንታታቸው ወጣቶች ከወሲብ እንዳይቆጠቡ እና ስህተት እንዲሰሩ ምክንያት ነው ብለው ያምናሉ። አንዳንድ ጊዜ ወላጆች የሚገባቸውን ሚና አይፈፅሙም። አብዛኞቹ ወላጆች ስለዚህ ጉዳይ ከልጆቻቸው ጋር ለማውራት ይፈራሉ። ይሄ የአፍሪቃውያን አስተሳሰብ ደግሞ አለ።ወላጆች ወሲብን የሚመለከት ጉዳይን አስመልክቶ ለማውራት ግልጽ አይደሉም። ልጆች መንገዱን ሲያገኙ ደግሞ አዲስ ነገር መሞከር ይፈልጋሉ። ስለዚህ ወሲብ ከመፈፀም ለመቆጠብ ከባድ ያደርግባቸዋል። ይህ አመለካከትም በሙባራ ዮንቨርስቲም ይስተዋላል። ዩንቨርስቲ ስገባ እና ስለ ቁጥብነት ሳወራ ጅል ይሉኝ ነገር። አንዳንዶች ራስሽን ከቆጠብሽ ሰውነትሽ ጤነኛ አይደለም ማለት ነው ይሉኝ ነበር። ያን ጊዜ ቁጥብ መሆኑን ለመተው ወሰንኩ። እንደ አኮል አማዚማ ያሉ አንዳንድ ዩጋንዳውያን መምህራን ደግሞ ወጣቱ ፍላጎት እያደረበት እንዲቆጠብ መገፋፋቱ ይበልጥ አደገኛ ለሆነ ችግር ሊጋልጥ ይችላል። በ እና በ ዓመት መካለል ያለው ዕድሜ ለወጣቱ እጅግ አደገኛው ጊዜ ነው። ጀብድ መስራት ይፈልጋሉ። ብዙ የአካል ለውጦች የሚያዩበት ጊዜ ነው ። እና ወሲብ ከመፈፀም እንዲቆጠቡ መንገሩ የማይሆን ነገርን እንደመንገር ማለት ነው። ከመቶው ዩጋንዳዊ እድሜው ከ ዓመት በታች ነው። ከነዚህ መካከል የተወሰነ ከመቶው እንኳን የህይወቱን አቅጣጫ ከሳተ ወይም ትምርቱን ለማቋረጥ ከተገደደ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሁኔታው ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። በሌላ በኩል ደግሞ በርካታ ወጣት የሚያወግዘው የመንግሥት አቋም ዳግም መፈተሽን ይሻል። እናንተስ ልጆችን ስለ ወሲብ መቼ እና ምን ማስተማር ያሻል ትላላችሁ የወላጅ እና የትምህርት ቤት ሚናስ ምን ሊሆን ይገባል ሀሳባችሁን አጋሩን። ሮዳ ኦዲአምቦ ፍራንክ ይጋ ልደት አበበ
የተቀነባበረ የተባለው የድምጽ ቅጂና ማስተባበያው፤ምርጫ የማይካሄድባቸው የምርጫ ክልሎችና ትችቱ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና፣የብልጽግና ፓርቲ የተሰራጨው የዐቢይ ድምጽ ከንግግሮቻቸው ተቆርጠው የተቀጠሉ እና ሀሰተኛ መረጃዎች ናቸው ሲሉ አስተባብለዋል። መሐመድ አሰፋ የስብሰባውን ትክክለኛ ያልተቆራረጠ ቅጂ በሚዲያ ልቀቁና እንመናችሁ ብለዋል። ከብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ ተብሎ ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተሰራጨው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ንግግር በዚህ ሳምንት በርካታ አስተያየቶችን ካስተናገዱት መካከል ግንባር ቀደሙ ነው።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ብሔራዊ ምርጫ በሚካሄድበት ሰኔ ቀን ዓም በ የምርጫ ክልሎች የፀጥታ ችግርን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ድምጽ እንደማይሰጥ ማስታወቁም አነጋጋሪ ነበር። እናስቃኛችኋለን። ከብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ንግግር በሚል በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ኬሎ ሚድያ በተባለው ድረ ገጽ የተሰራጨው ድምጽ ብዙ አነጋግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ ተብሎ ከቀረበው ድምጽ ውስጥ እሞታታለሁ እንጂ ሥልጣን አልሰጥም ፤ ምርጫውን አጨናግፈን የሚፎካከሩ ኃይሎች ተስፋ እንዲቆርጡ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና፣የብልጽግና ፓርቲ የተሰራጨው የዐቢይ ድምጽ ከንግግሮቻቸው ተቆርጠው የተቀጠሉ እና ሀሰተኛ መረጃዎች ናቸው ሲሉ አስተባብለዋል። የመንግሥት መገናኛ ብዙሀንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በሌላ መድረክ ካደረጉት ንግግር ተወስዶ የተሰራ ሀሰተኛ የድምጽ ቅንበር ነው ሲሉ በማስረጃ አስደግፈው ባጠናቀሯቸው ዘገባዎች አሳይተዋል።ሰኞ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሀን የተሰራጨውን ይህን ድምጽ በሚመለከት በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።ከመካከላቸው ዘለፋ፣ፍረጃና ጽንፍ የያዙና ክብረ ነክ ሃሳቦችን ያካተቱትን በመተው በታረመ አንድበት የቀረቡትን ሃሳቦች እናስቃኛችኋለን ። ሚፍታ ሸምሱ ኡመር ሀሳብ የሌላቸው አካላት በተንኮል እና በሴራ መፎካከር ውስጥ በይፋ ገብተዋል ።ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ በፌስቡክ አስተያየታቸውን አስፍረዋል። አንድ ብሂል አለ ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል እንደሚባለው ነው የናንተ ነገር ያሉት ደግሞ ዮናስ ባህታ ናቸው በፌስቡክ ።አበበ ገብረእየሱስ እንዲህ ሲሉ ለመንግሥት መገናኛ ብዙሀን መልዕክት አስተላልፈዋል። ውሸት መሆኑን በመረጃ አስደግፋችሁ መናገራችሁ በጣም ጥሩ ነው ።ወደፊትም እንደዚህ አይነት ዜናዎች ሲወጡ በእንደዚህ አይነት መንገድ ውሸታሞችን ማጋለጥ ይገባል ። መሐመድ አሰፋ ደግሞ የስብሰባውን ትክክለኛ ያልተቆራረጠ ቅጂ በሚዲያ ልቀቁና እንመናችሁ ብለዋል። ኧረ ባካችሁ ሃገርን አታተረማምሱ ሲሉ ሃሳባቸውን በምሬት የጀመሩት ቅድስት በላይ ቆይ ሌላ ስራ ጠፍቶ ነው ይሄንን ቁጭ ብላችሁ ስታቀነባብሩ የከረማችሁት ኧረ ምስኪኑ ህዝብ ሰርቶ ይብላበት ሰርቶ አዳሪው ዳቦ ፈላጊው ይኑርበት ይሄንን ህዝብ ተውት ይበቃል በማለት መልዕክታቸው አጠቃለዋል።ገዛኽኝ ጠበቃ በሚል የፌስቡክ ስም የቀረበ አስተያየት የተጠያቂነትን ጉዳይ ያነሳል የአብይ ደጋፊ ባልሆንም ይህ አሳሳች መንገድ ስለሆነ ኬሎ ሚዲያ ሊጠየቅ ይገባል። በማለት ።ዚያድ አር አብዱልም ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል። ይህን የውሸት ወሬ ብዙዎች የተረዱ ቢሆንም ሌሎች ያልተረዱ ማወቅ ያለባቸው፣ የተሰራጨው ወሬ ፍጹም ውሸት መሆኑን እና በተለያየ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩትን በመቀጣጠል የተሰራ መሆኑን ነው። ይህ ድርጊት በህግ የሚያስጠይቅ ወንጀል በመሆኑ የሚመለከተው አካል የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ የህግ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል ብለን እንጠብቃለን።ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ሥራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው ያሉት ደረጀ ታዴ ወሬ ዳቦ አይሆንም በሥራ እንስተጋባው በማለት አሳስበዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ ቤት ፣ባለፈው ሳምንት በብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባለ በማስመሰል የተለቀቀው የድምፅ ፋይል በውሸት የተቀነባበረና ጠ ሚኒስትሩ በተለያየ ግዜ የተናገሩትን በመቁረጥና በመቀጠል የተፈጠረ የሀሰት መረጃ መሆኑን ያረጋግጣል ሲል በፌስቡክ አስተባብሏል፡፡ጽህፈት ቤቱ በዚህ የሀሰት መረጃ ዘመን እና ምርጫው እየተቃረበ ባለበት ወቅት ዜጎች፣ አለመግባባትን በመፍጠር ላይ ባተኮሩ ፣በነዚህ አሳሳች የመረጃ ዘመቻ ዓይነቶች እንዳይታለል ሲል አሳስቧል የብልጽግና ፓርቲም በፌስቡክ ባወጣው መግለጫ የሃሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ተራ ተግባር ነው ሲል አጣጥሏል።የፓርቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶ ር ቢቂላ ሁሪሳ ባወጡት መግለጫ የተሰራጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ ሃሰትና የፓርቲው ፕሬዝዳንት በተለያየ መድረክ ላይ ካደረጉት ንግግሮች ተቆራርጦ የተፈበረከ ነው ፤ማለታቸው በፌስቡክ ተገልጿል።አለማውም ህዝቡን ማደናገርና ህዝብና መንግስት መካከል ያለመተማመን ብሎም ውጥረትና ያለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ ነው ያሉት ዶ ር ቢቂላ ተግባሩንም ተቀባይነት የሌለው ሃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የሚሰራጭ ብለውታል፡፡ሃላፊው መሰል የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት፣ባለፉት ቅርብ አመታት እየተለመደ መጥተዋል ሲሉ ገልጸው ህዝቡ መሰረት ከሌላቸውና ምንጫቸው ካልታወቀ መረጃ እንዲጠበቅና መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲመርጥ አሳስበዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በ የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንደማይካሄድ ማስታወቁ ሌላው ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ያነጋገረ ጉዳይ ነበር ።ቦርዱ በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በኦሮምያ በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንደማይካሄድ አስታውቋል።በነዚህ ቦታዎች ምርጫ የማይካሄደውም በፀጥታ ችግር ፣የመራጮች ምዝገባ ባለመጀመሩ፣የመራጮች ምዝገባ ተጀምሮ በመቋረጡና የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ በመቅረቡ ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል። በሶማሌ ክልልም በ የምርጫ ክልሎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ላይ አለ የተባለውን ችግር እያጣራ መሆኑንም ገልጿል። አንድነን ይበጃል በሚል የፌስቡክ ስም ከምርጫ በፊት ሀገራዊ እርቅ ይቅደም ሲባል ሀገሩ ሰላም ነው ምርጫ ማካሄድ ይቻላል አላቹሁ፣ አሁን ደሞ በተወሰነ ቦታ ችግር ስላለ በአንዳንድ ቦታዎች ድምፅ አይሰጥም። አስቲ በጥሞና አስረዱን።የሚል ጥያቄ ቀርቧል። ይህ ሁሉ የምርጫ ክልል ካልመረጠ ምርጫዉ ምርጫ ነዉ እንበል ወይስ ሲል የሚጠይቀው ዋናው ነገር ጤና በሚል የፌስቡክ ስም የሰፈረ ሃሳብ ነው። ናቲ ጎበዜም ይጠይቃሉ። የእነዚህን ሁሉ ቦታዎች ሰላም ያልጠበቀ መንግስት እንዴት ይወዳደራል ሲሉ ሁሉ ሰላም የሌለበት ሀገር ሆነ ሰለዚህ የት ሀገር ነው ምርጫ የሚካሄደው ለማንኛውም የዜጎች ሰለም ይቅደም፣ ገበሬ ይመለስ ወደርሻ ያሉት ደግሞ መሱድ መሀመድ ናቸው ኡስማን ከዲር ወይ ምኑን ተካዬደ ተዳያ ሲሉ ዘሌ አየለ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ምርጫ መቆም አለበት ሲሉ የበኩላቸው ሃሳብ ሰጥተዋል።ታዲያ በዚህ ሁሉ ቦታ ላይ ምርጫ የማይካሄድ ከሆነ የኢትዮጵያ ምርጫ ነው የሚባለው ወይስ፣ በከፊል ኢትዮጵያ የሚካሄድ ምርጫ ያሉትደግሞ ኤልያስ እያሱ ናቸው እንዲህም በተቆራረጠ መንገድ ምርጫ አለ እንዴ በማለት የጠየቁት ሀብቴ ተሾመ ምርጫ የማይካቸሄድባቸው አካባቢዎች ሰላማቸው ከምርጫ ጋር ተያይዞ ነው ወይስ በእነዚህ አካባቢወች ሰላም የመስስከበር ተግባሩ መንግስት አይመለከተውም ይህ ደግሞ የኑረዲን መሀመድ አስተያየት ነው። አብውቃው ደባልቀው እንደተባለ ከሆነ ፣አብዛኛው ቦታ ማለት ይቻላል ምርጫ የማይካሄድበት ነው።ታዲያ ምርጫውን አቁሞ ሰላሙ ላይ መስራት እና ሁሉም ቦታ ላይ ፍፁም ሰላም ማረግ አይሻልም ብለዋል። ምርጫ ቦርድ ምርጫው የማይካሄድባቸውን ቦታዎች የመለየት ስራ መስራቱ ጥሩ ነው ነወ።ለምሳሌ በጉራፋርዳ ወረዳ ካሉት ቀበሌዎች በከፊሉ በሰላም እጦት ምክንያትሰዎች ቀዬ አቸውን ለቀው ተሰደዋል። ልክ እንደ ምርጫ ቦርድ ሁሉ መንግስት ለተፈናቀሉት ዜጎችም የመፍትሄ ውሳኔ ቢሰጥ የሚለው የማስረሻ አራጌ አስተያየት ነው ኂሩት መለሰ
የጠ ሚንስትሩ መልዕክተኛ አደም ፋራህ ምን አሉ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸውን ወደተለያዩ ሃገራት እየላኩ ነው። የጠቅላይ ሚንስትሩን መልዕክት ካደረሱት ባለሥልጣናት መካከል የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አ ደም ፋራህ አንዱ ናቸው ። አደም ፋራህ መልዕክቱን የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ አንዳንድ ለአንዳንድ የህብረቱ አባል ሃገራት አድርሰዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸውን ወደተለያዩ ሃገራት እየላኩ ነው። የጠቅላይ ሚንስትሩን መልዕክት ካደረሱት ባለሥልጣናት መካከል የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አ ደም ፋራህ አንዱ ናቸው ። አደም ፋራህ መልዕክቱን የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ አንዳንድ ለአንዳንድ የህብረቱ አባል ሃገራት አድርሰዋል። የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ አፈ ጉባኤው ይዘው ስለመጡት መልዕክት እና ስለተሰጣቸው ምላሽ አነጋግሯቸዋል። ገበያው ንጉሤ
የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክተኛ አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ምን አሉ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ዶ ር አረጋዊ በርሔ ተሾሙ
ዶ ር አረጋዊ በርሔ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ዶ ር አረጋዊ በጠቅላይ ሚንስትሩ የተሾሙት ትናንት ረቡዕ ጥቅምት ቀን ዓ ም ነው። ዶ ር አረጋዊ በርሔ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ዶ ር አረጋዊ በጠቅላይ ሚንስትሩ የተሾሙት ትናንት ረቡዕ ጥቅምት ቀን ዓ ም ነው። በዚህም መሠረት ዶ ር አረጋዊ በርሔ ቀደም ሲል ጽህፈት ቤቱን በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩና በጡረታ የተሰናበቱትን ወ ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴን ይተካሉ። ወ ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴ ከአራት ዓመታት በላይ ጽህፈት ቤቱን በዋና ዳይሬክተርነት የመሩ መሆናቸውን የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብረሃም ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ሕዝባዊ ወያኔ ኣርነት ትግራይ ሕወሓት በቅርቡ በፌዴራል መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት በማገልገል ላይ ለነበሩ የፓርቲው አባላት ጥሪ አድርጓል። ይህ ጥሪ ከተደረገላቸው ኃላፊዎች መካከል ወ ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴ አንዷ ነበሩ። ነገር ግን አቶ ኃይሉ እንደሚሉት ወ ሮ ሮማን ኃላፊነቱን የለቀቁት በ ዓ ም በጡረታ ለመልቀቅ ባመለከቱት መሠረት ነው። እናም ጡረታቸው ተጠብቆ ጽሕፈት ቤቱ አሸኛኘት እንዳደረገላቸውም የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ኃይሉ አክለው ገልጸዋል። ዶይቸ ቬለ የወ ሮ ሮማንን ሃሳብ ለማካተት በተደጋጋሚ በእጅ ስልካቸው ላይ ቢደውልም ስልካቸው ባለመሥራቱ አልተሳካም። አዲሱ ተሿሚ ዶ ር አረጋዊ በርሔ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ትዴት ሊቀመንበር ናቸው ። ታምራት ዲንሳ
የተቀነባበረ የተባለው የድምጽ ቅጂና ማስተባበያው ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ግጭት በአማራና በአፋር አጎራባች ቀበሌዎች
በአማራና በአፋር ክልል በሚገኙ አጎራባች ቀበሌዎች መካከል ግጭት መፈጠሩን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ገለፁ። በግጭቱ የሰዉ ህይወት የጠፋ ሲሆን ግጭቱን ለማርገብ በአጎራባች ቀበሌዎቹ መካከል የፌደራል ፖሊስ ሰፍሮ እንደሚገኝ ተገልጿል። ነዋሪዎች እንደሚሉት በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳና በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሀብሩ ወረዳ የሚኖሩ የሁለቱ ብሔረሰብ ተወላጆች በየጊዜዉ ይጋጫሉ። ጉዳዩን ለአካባቢዉ የአስተዳደር አካላት ቢያሳዉቁም አሁንም ድረስ ችግሩ እልባት አላገኜም ነዉ የሚሉት። ባለፈዉ ሰኞም በሀብሩ ወረዳ ቀበሌ ፣ እና በተባሉ አካባቢዎች በሁለቱ ወገኖች መካከል ግጭት መነሳቱን አመልክተዋል። በግጭቱ ከሁለቱም ወገኖች የሰዉ ህይወት መጥፋቱን የአካባቢዉ ነዋሪወች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።ተጨማሪ የንብረትና የህይወት ጉዳት ይደርስብናል የሚል ስጋት እንዳላቸዉም ነዋሪወቹ ገልፀዋል። እንደ ነዋሪወቹ ገለፃ የሁለቱ አጎራባች ክልል ነዋሪዎች በሰላም አብረዉ ይኖሩ ነበር። ካለፈዉ አመት ሀምሌ ወር ጀምሮ ግን በግጭቶቹ የሰዉ ህይወት በመጥፋቱ ሳቢያ በገበያ ቦታ እንኳን እንደማይገናኙ አስረድተዋል።የግጭቱ መንስኤም የድንበር ጉዳይ ነዉ ይላሉ። የአፋር ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልሰመድ መሀመድን ለማነጋገር ብንሞክርም በጉዳዩ ላይ መረጃ የለኝም ከማለት ዉጭ ማብራሪያ ሊሰጡን አልቻሉም። በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ ቤት ሀላፊ አቶ ልባሴ አሊጋዝ በበኩላቸዉ ካለፈዉ ሚያዚያ ወር ጀምሮ ግጭቱ መከሰቱንና የሰዉ ህይወት መጥፋቱን አምነዉ የግጭቱ መንስኤ የዉሃና የግጦሽ መሬት ፍለጋ መሆኑን አስረድተዋል።ይህም ቢሆን በተወሰኑ ግለሰቦች የተደረገ ነዉ ብለዋል። እንደ ሀላፊዉ ችግሩን ለመፍታት የሁለቱ ክልል አመራሮች ና የሀገር ሽማግሌወች በተደጋጋሚ ዉይይት አድርገዋል።በመጪዉ ነሀሴ ም ሌላ ዙር ዉይይት እንደሚካሄድ ገልጸዋል። አጥፊወቹን ለማጋለጥና ወደ ህግ ለማቅረብም የመረማሪ ኮሚቴ መቋቋሙን ይናገራሉ። ባለፈዉ ሰኞ የተቀሰቀሰዉን ግጭት ለማረጋጋት በሁለቱ አጎራባች ወረዳዎች መካከል የፌደራል ፖሊስ ሰፍሮ እንደሚገኝም ሀላፊዉ ጨምረዉ አመልክተዋል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ማዕቀፉ ያድምጡ። ፀሐይ ጫኔ
በድንበር ውዝግብ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ተፈናቅለዋል
የኢትዮጵያ መንግሥት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች የድንበር ውዝግብ የተፈናቀሉ ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ጥረት ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የመረጃ ቋት ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ከ ሚሊዮን ዶላር በላይ መመደቡን አስታውቋል። ከኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ የድንበር አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀደመ መንደራቸው መመለስ ቅድሚያ ተሰጥቶታል። ቀሪዎቹ ተፈናቃዮች በሌሎች አካባቢዎች የሚሰፍሩ ይሆናል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ በ ከተሞች ተፈናቃዮችን ለማስፈር ጥረት በማድረግ ላይ ነው። በተመረጡ ከተሞች የመኖሪያ ቤቶች በመገንባት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት በድንበር ውዝግቡ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙባቸውን ቆሎጂ እና ቆሎጂ የተባሉ መጠለያዎች ለመዝጋት መወሰኑንም አስታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የድንበር ውዝግብ ከአንድ ሚሊዮን በላይ መፈናቀላቸውን ቀደም ብሎ መግለፁ አይዘነጋም። መክብብ ሸዋ
አዲሱ የእስራኤል መንግሥት
በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ዛሬ ቃለ መሃላ የፈጸሙት የ ዓመቱ የአይሁድ ብሔረተኞች ፓርቲ መሪ ናፍታሊ ቤኔት ሰላሳ ስድስተኛውን የእስራኤል መንግሥት ዛሬ መስርተዋል። ። ዛሬ በተሰየመው የአዲሱ መንግሥት ካቢኔ ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ሚኒስትር ይገኙበታል። በእስራኤል ዛሬ አዲስ መንግሥት ተመስርቷል። የቤንያሚን ነታንያሁ የ ዓመታት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ዛሬ አብቅቷል። የተለያየ አቋም የያዙ ፓርቲዎች የተሰባሰቡበት ሰላሳ ስድስተኛው የእስራኤል መንግሥት ዛሬ ሥራውን ጀምሯል። በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ዛሬ ቃለ መሃላ የፈጸሙት የ ዓመቱ የአይሁድ ብሔረተኞች ፓርቲ መሪ ናፍታሊ ቤኔት ከሀገሪቱ ብሔራዊ የፀጥታ ጉዳዮች አማካሪ ማብራሪያ ተስጥቷቸዋል። ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ዛሬ በተሰየመው የአዲሱ መንግሥት ካቢኔ ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ሚኒስትር ይገኙበታል። ስለ አዲሱ መንግሥት ምንነት ፈተናዎቹና የህዝቡና የመገናና ብዙሀን አስተያየት የኢየሩሳሌሙን ዘጋቢያችንን አነጋግረናዋል። ሰሎሞን ሙጬ
አዲሱ የእስራኤል መንግሥት ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኢትዮጵያውያን አሜሪካዉያን ተቃውሞ በአሜሪካ ኤምባሲ
በቁጥር አርባ የሚሆኑት ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን በአዲስ አበባ ለአሜሪካ ኤምባሲ በፃፉት ደብዳቤ የዩናይትድ ስቴትስን ርምጃ ዴሞክራሲን የሚጻረር ብለዉታል። ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችዉን ማዕቀብ አዲስ አበባ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን አሜሪካውያን ተቃወሙ።በቁጥር አርባ የሚሆኑት ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን በአዲስ አበባ ለአሜሪካ ኤምባሲ በፃፉት ደብዳቤ የዩናይትድ ስቴትስን ርምጃ ዴሞክራሲን የሚጻረር ብለዉታል።የሰልፈኞቹ ተወካዮች ከኤምባሲው የፖለቲካ ተወካይ ጋር መወያየታቸውን አስታዉቀዋልም። ሥዩም ጌቱ
የኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን ተቃዉሞ በአዲስ አበባ ራድዮ
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ከሁለቱ አዛዉንቶች ማን ይሆን
የአሜሪካ ምርጫ ትራምፕ ከዓለም እያላተሙ ከዓለም ሁሉ ሊያስቀድሙ የፈከሩ፣ቃል የገቡ፣ሕዝብ ያሳደሙላት አሜሪካ በኮሮና ተሕዋሲ በተያዘና በሞተ ሰዉ ቁጥር በርግጥ ከዓለም ቀድማለች።ከዓለም የቀደመችበት በሽታና በሽታዉን ለመከላከል የሚወሰደዉ ርምጃም ወይም መርሕም ብዙዎች እንደሚሉት ለአሜሪካኖች ምርጫ ቀዳሚና ወሳኝ ነዉ። ያንድ ዘመን ዉልዶች ናቸዉ፤ በ ዓመት የሚበላለጡ አዛዉንቶች።ዉልደት፣የልጅነት ኑሮ ዕድገታቸዉ ግን ለነጩ አሜሪካዊ ልክ እንደ ራሷ እንደ አሜሪካ የደሐ ሐብታም ማነፃፀሪያ አብነቶች፣ ደግሞ ተቃራኒ ግን እኩል ፖለቲከኛ ናቸዉ። ዶናልድ ጆን ትራምፕ እና ጆሴፍ ሮቢኔት ባይደን ጁኒየር። ጆ ባይደን ሲያጥር። እኩል ፖለቲከኛ የመሆናቸዉን ያክል እንደ አሜሪካ ልዩነት፣ እንደ ዉልደት፣ እድገት ኑሯቸዉ ርቀት፣ ስብዕና ባሕሪ፣ የፖለቲካ ፓርቲ፣ መርሕ፣አላማ፣ርዕያቸዉ ሁሉ ተፃራሪ ነው። ሁለቱም በነገዉ ምርጫ አሸናፋለሁ ባይ ናቸዉ። ትራምፕ ባለፈዉ ሳምንት። ፔንስሌቬንያን እናሸንፋለን። አለቀ፤ አለቀ። ፔንስሌቬንያ የባይደን የትዉልድ ግዛት ናት። እና ባይደን በዚያዉ ሳምንት ግን ከሌላ ግዛት ዶናልድ ትራምፕ ሻንጣዉን ሸክፎ ወደ መጣበት መሔጃዉ ጊዜ አሁን ነዉ አሉ። ማን ያሸንፍ ይሆን እሱ፤ነሐሴ ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ነዉ ኒዮርክ ዉስጥ ተወለደ።ከቤተሰቡ አምስት ልጆች አራተኛዉ ነዉ። ዶናልድ ተባለም። አዱኛ የሰገደችለት የቤት ገንቢና ሻጭ ሪል ስቴት ኩባንያ ባለቤት የሚሊየነር ልጅ ነዉ። የተባለዉ መፅሐፍ ደራሲ ቲም ኦ ብሬይን የዶናልድን ዉልደት እድገት አይተሕ ማንነቱን ትረዳለሕ ይላሉ። አስተዳደጉ እንደመካከለኛ መደብ ልጅ አይደለም። ቤተሰቡ ሾፌር ነበረዉ። ትምሕርት ቤት የሚሔደዉ በሊሞዚን ነዉ። ተቀጥሮ ወይም መደበኛ ሥራ ሠርቶ አያዉቅም። ዶናልድ ሲወለድ ጆሴፍ የ ዓመት ከስምንት ወር ገደማ ልጅ ነበር። ከሁለት ታናሾቹ ቀድሞ ሕዳር ፣ ሴክራንተን ፔንስልቬኒያ ተወለደ። የትዉልድ ከተማዉ የአሜሪካ መካከለኛና አነስተኛ መደብ ማሕበረሰብ መኖሪያ አብነት ናት። ጆሴፍ ከመወለዱ በፊት ቤተ ሰቡ ጥሩ የሚኖር ደሕና ገቢ የነበረዉ ነበር። ሊወለድ አካባቢ ግን አባት ከሰሩ። ኑሮም መረረ። ጠንካራዉ አባት ለልጆቻቸዉ የሚመክሩ፣የሚያስተምሩ የሚያሳዩትም ወድቆ መነሳትን፣ አጥቶ ማግኘትን፣ ከስሮ መንሰርን ነበር። አባቴ የወደቀዉ መጥፎ ጊዜ ነበር። ሁል ጊዜ የሚነግረኝ ግን ስትወድቅ ተነስ እያለ ነበር። አባት ወድቀዉ አልቀሩም። ተፍጨርጭረዉ ተነሱ። እንደ ድሮዉም ባይሆን የተሳካላቸዉ የአሮጌ መኪና ነጋዴ ሆኑ። ጆሴፍ ድሕነትን ለማምለጥ፣ ዶናልድ ይበልጥ ለመንደላቀቅ በየፊናቸዉ ይዉተረተሩ ገቡ። ጆሴፍ በመጀመሪያና በሁለተኛ ደረጃ ተማሪነቱ በቀለሙ ደከም፣ በስፖርቱ በተለይም በአሜሪካኖቹ ፉትቦል ጠንከር ያለ ነበር። ከሁሉም በላይ የየክፍሉ አለቃ ሆኖ መሪነትን ገና በልጅነቱ ይለማመድ ያዘ። ሲናገር አፉን ያዝ ወይም ቀርፈፍ ወይም ደንቀፍቀፍ ያደርገዉ ነበር። መደነቃቀፉን ለማስወገድ ግጥምን እየሸመደደ፣ በቃሉ ግን ጮክ ብሎ መድገም እንደ ፍቱን ሕክምና ተጠቀመበት።ረዳዉ። የዶናልድ ችግር ግን ሌላ ነበር። ዶናልድ ችግር ፈጣሪ ብቻ አልነበረም። እብሪተኛም ነበር። እንደነገረኝ አስተማሪዎች አድርግ የሚሉትን ማድረግ ካልፈለገ እቀጣቸዉ ነበር ይላል። አሉ ኦ ብሬይን። ወላጆቹ ዘየዱ። ሥርዓት እንዲማር ብለዉ ኒዮርክ ወታደራዊ አካዳሚ አስገቡት። ለጆሴፍ ፉት ቦል፣ ለዶናልድ ደግሞ ቤዝ ቦል ነበር። የቤዝ ቦል ተጫዋች መሆን ነበር የምፈልገዉ።ጎበዝ ተጨዋች ነበርኩ። ጆሴፍ በ በታሪክና በፖለቲካ ሳይንስ፣ ዶናልድ ደግሞ በ በኤኮኖሚክስ ተመረቁ።ከእንግዲሕ አንቱ ናቸዉ።ባይደን ካገቡ በኋላ፣ በመጀመሪያዉ ዲግሪ ላይ ሌላ የሕግ ዲግሪ አከሉበት። ትራምፕም በንግዱ እንጂ ወደ ትምሕርቱ ተመልሰዉ አልገቡም።ያገቡትም ከባይደን ዓመት ያክል ዘግይተዉ ነዉ። ብቻ ሁለቱም ረጅሙን የሕይወት ጎዳና ያዘግሙበት ገቡ።ባይደን ላጭር ጊዜ በጥብቅና ከሰሩ በኋላ በዴሞክራቲክ ፓርቲ በኩል ፖለቲካዉን ተቀየጡ። ።በዚያዉ ዓመት በደልዌር ክፍለ ግዛት የኒዉ ካስል ወረዳ ምክር ቤት አባል ሆነዉ ተመረጡ። ትራምፕ ግን ከአባታቸዉ ኩባንያ ስራ አስኪያጅነት ወደ ራሳቸዉ ኩባንያ መስራችነት፣ ከሚሊዮነርነት ወደ ቢሊየነርነት ይመነደጉ፣ ዶላር እየሰበሰቡ ዶላር ይረጩ ያዙ።ባይደን ዘንድሮ ለትልቂቱ ሐገር ትልቅ ሥልጣን ለመወዳደር የበቁት ከወረዳ ምክር ቤት አባልነት እስከ ሴናተርነት፣ ከሴናተርነት እስከ ምክርትል ፕሬዝደንትነት ፖለቲካዉን ከግማሽ ምዕተ ዓመታት በላይ ከቀዙፉ ከዋኙበት በኋላ ነዉ። ትራምፕ ግን ከጥቂት አመታት በላይ ዋይት ሐዉስ ለመግባት ገንዘብ፣ገንዘብ የሚያገዝፈዉ ስም፣ በቴሌቪዥን መስኮት ደጋግሞ መታየት በቂያቸዉ ነበር።እርግ ነዉ በ ዎቹ ፕሬዝደንት እሆናለሁ ይሉ ነበር የሚሉ ጓደኞች አሏቸዉ።ይሁንና ፌዝና ቁምነገሩን ለይተዉ የማይናገሩት ነጋዴ አሉት የተባለዉን ካጀታቸዉ ይሁን ካንገት በዉል የሚያዉቅ የለም። የሚታወቀዉ ለፖለቲካ ፍላጎት እንዳላቸዉ በይፋ የታየበት የ ኙ አጋጣሚ ነበር።ያኔ ትራምፕ ከሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊነት ሪፎርም ፓርቲ ወደተባለዉ ደጋፊነት ቀየሩ። ባመቱ ግን የምትገባን አሜሪካ ያሉትን መፅሐፍ አሳተሙ።መፅሐፉ ምጣኔ ሐብቱን ከመንግስት ጫና ነፃ ሊብራል ማድረግ፣ ፖለቲካዊን ግን ጠጠር ያለ ወግ አጥባቂ መርሕ እንዲከተል ማድረግ የሚል ይዘት ነበረዉ። በ ቱ ተመልሰዉ የሪፐብሊካን ፓርቲን ተቀየጡ።የያኔዉን ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማን አሜሪካ ዉስጥ አልተወለዱም በማለት በሐሰት ስም ማጥፋት የጀመሩትም ያኔ ነበር።ዉንጀላዉ ዉሸት ቢሆንም ስድብ፣ማንጓጠጥ፣ማበሻቀጣቸዉ የብዙ ቀኝ አክራሪ አሜሪካዉያንን ጆር መሳቡ አልቀረም። በ ከዝነኛዉ የዴሞክራቶች ፕሬዝደንት ከቢል ክሊንተን ባለቤት፣ ከኦባማ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትርና ከመጀመሪያዋ አሜሪካዊት ሴት ዕጩ ፕሬዝደንት ከሒላሪ ክሊንተን ጋር ተወዳደሩ።የመርሐቸዉ ማጠንጠኛ ቅድሚያ ለአሜሪካ ወይም አሜሪካ ትቅደም ነበር። ዛሬ እዚሕ የተሰበሰብነዉ በሁሉም ከተማ፣ በሁሉም የዉጪ ርዕሠ ከተሞች፣ በሁሉም የስልጣን ደረጃ ሊሰማ የሚገባ መርሕ ለማወጅ ነዉ።ከዛሬ ጀምሮ ሐገራችንን የሚመራዉ አዲስ ርዕይ ነዉ።ከእንግዲሕ መርሐችን አ ሜሪካ ትቅደም የሚለዉ ብቻ ነዉ።አሜሪካ ትቅደም። አሸነፉም።ቢሊዮነር፣ ቅምጥል፣ ቀኝ አክራሪ፣ ያሻቸዉን የሚናገሩት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ዘመነ ሥልጣን ለመመረጥ ከፖለቲካና ታሪክ አዋቂዉ፣ ከለዘብተኛዉ፣ አንጋፋ ፖለቲከኛ ከቀድሞዉ ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋር እየተናነቁ ነዉ። ሁለቱ ፖለቲከኞች እና ፓርቲዎቻቸዉ በብዙ ነገር ይለያያሉ።ብዙዎች እንደሚሉት የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት በቀጥታ የሚነኩት ግን የጤና መርሕ፣ ምጣኔ ሐብቱ፣ ዘረኝነት እና ፀንስ ማስወረድ ከቀዳሚዎቹ አራቱ ጉዳዮች ናቸዉ።ግን ማን እንደ ኮሮና።አምና ይሕን ጊዜ ምንም የማይታወቀዉ የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትና ስርጭቱን ለመግታት ዕጩዎቹ የሚከተሉትን መርሕ የሚስተካከል በርግጥ የለም። ትራምፕ ከዓለም እያላተሙ ከዓለም ሁሉ ሊያስቀድሙ የፈከሩ፣ቃል የገቡ፣ሕዝብ ያሳደሙላት አሜሪካ በኮሮና ተሕዋሲ በተያዘና በሞተ ሰዉ ቁጥር በርግጥ ከዓለም ቀድማለች።ከዓለም የቀደመችበት በሽታና በሽታዉን ለመከላከል የሚወሰደዉ ርምጃም ወይም መርሕም ብዙዎች እንደሚሉት ለአሜሪካኖች ምርጫ ቀዳሚና ወሳኝ ነዉ። የኮሎንቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር አሽዊን ቫሳን እንደሚሉት በነገዉ ምርጫ የኮሮና ተሕዋሲን ያክል ትኩረት የሚስብ መርሕ ሊኖር አይችልም። በአሜሪካ መራጮች አዕምሮ ዉስጥ የኮሮና ተሕዋሲ ቀዳሚና ማዕከላዊዉን ሥፍራ ይዟል።ምክንያቱም የሕዝብ ጤና ቀዉስ ብቻ ሳይሆን በምጣኔ ሐብቱ፣ በሥራ፣ በትምሕርት፣ በትራንስፖርት እና በሁሉም የሕብረተሰባችን ክፍል ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል።ይሕ ተፅዕኖ በድምፁ ጫና ያሳድራል። እስከ ዛሬ ከ ሚሊዮን የሚበልጥ አሜሪካዊ ድምፁን ሰጥቷል።እስካሁን በተሰባሰበዉ የቅድመ ምርጫ አስተያየት የዶሞክራቶቹ ዕጩ ጆ ባይደን ከፕሬዝደንት ትራምዕ የተሻለ ድጋፍ እንዳላቸዉ ይጠቁማል። ወሳኙ ግን ነገ የሚሰጠዉ ድምፅ ነዉ። ነጋሽ መሐመድ
በትግራይ ክልል ያለው የተረጂ ቁጥርና የባለስልጣናት መግለጫ መጣረስ
በትግራይ ክልል ከ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለአስከፊ ርሀብ መጋለጡን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ፣ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ በመንግስት የሚታወቀው በክልሉ ያለ ተረጂ ከ ነጥብ አይበልጥም ብሏል፡፡ በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ህዝብ መፈናቀሉንና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ለርሀብ መጋለጡን የትግራ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ የጊዜዊ አስተዳደሩ ሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሀ ደስታ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ሚሊዮን ሺህ ህዝብ ለአስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ እህል ተጋልጧል፡፡ በተቻለ መጠን እርዳታ እየተዳረሰ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች ግን ቁጥሩ ባይታወቅም በርሀብ የሞቱ እንዳሉ ገልፀዋል፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ይህን ቢልም የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳን ጠቅሶ ብሔራዊ የአገሪቱ ቴሌቪዥን ትናንት እንደዘገበው ደግሞ በትግራይ ክልል ለርሀብ ተጋልጧል እየተባለ የሚነገረው የተጋነነና በፌደራል መንግስት ያልተረጋገጠ ነው ብለዋል፣ በተጨባጭ በክልሉ የተረጂው ቁጥርም ሚሊዮን ሺህ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ምትኩ፣ አብዛኛው እርዳታ ፈላጊ ከህግ ማስከበሩ በፊት በምግብ ዋስትና ማዕቀፍ ውስጥ የነበረ እንደነበረም አስረድተዋል፡፡ አቶ ምትኩ እንደሚሉት ለ ሚሊዮን ሺህ እርዳታ ፈላጊ የክልሉ ህዝብ በ የእርዳታ ማሰራጫ ማዕከላት እርዳታ እየተሰጠው እንደሆነና በርሀብ ሞት ስለመመዝገቡ ግን መረጃ እንደሌላቸው አብራርተዋል፡፡ ከአቅም በላይ ካልሆነ በስተቀር እርዳታ በአግባቡ ለተረጂው እየደረሰ እንደሆነ ያመለከቱት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ ር ሙሉ ነጋ በአንዳንድ ወገኖች የእርዳታ እህል ለእርዳታ ፈላጊው አይደርሰውም እየተባለ የሚወራውም ሀሰትና የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ ኃይሎች ወሬ ነው ሲሉ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ተናግረዋል፡፡ እንደኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገባ ከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር ሚለሊዮን ብር የሚገመት መድኃኒትም በቅርቡ ወደ አካባቢው ተልኮ ለየጤና ተቋማት እየተከፋፈለ ነው፡፡ በትግራይ ክልል የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ለወራት ደመወዝ ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን በቅርቡ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ ር ሙሉ ነጋ ደመወዝ የሚከፈልበት አቅጣጫ በመቀመጡ ሰራተኞች በቅርቡ ደመወዛቸው እንደሚከፈል አመልክተዋል፡፡ ዓለምነው መኮንን
የደቡብ ክልል መስተዳድር ከ ሚሊዮን ብር በላይ እያስመለስኩ ነው አለ
ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ርእስቱ ይርዳው በሪፖርታቸው ያቀረቡት ሰነድ በክልሉ በበጀት ዓመቱ በሙስና ፣ በታክስ ማጭበርበር እና በውል አስተዳደር ብር ተመዝብሯል ብሏል። ነገር ግን በክልሉ ተካሂዷል ያለው ምዝበራ በየትኞቹ ተቋማትና በእነማን እንደተፈጸመ በሪፖርቱ አልተገለጸም ። በደቡብ ክልል በተለያየ መንገድ የተመዘበረ ነጥብ ቢሊየን ብር እያስመለሰ መሆኑን የክልሉ መስተዳድር አስታወቀ ። የክልሉ መንግስት ይህን ያስታወቀው ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ በተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት ኛ ዙር ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የመንግስታቸውን ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ነው። ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ርእስቱ ይርዳው በሪፖርታቸው ያቀረቡት ሰነድ በክልሉ በበጀት ዓመቱ በሙስና ፣ በታክስ ማጭበርበር እና በውል አስተዳደር ብር ተመዝብሯል ብሏል። ነገር ግን በክልሉ ተካሂዷል ያለው ምዝበራ በየትኞቹ ተቋማትና በእነማን እንደተፈጸመ በሪፖርቱ አልተገለጸም ። ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ዓለማችን በኮሮና የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር ጨመረ
ዓለማችን በኮሮና የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር ጨመረ በዓለማችን በአንድ ቀን በኮሮና የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር መጨመሩ እንዳሳሰበዉ የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ። ሜክሲኮ በኮሮና ሟቾች ቁጥር ጣልያንን ቀድማለች። በዓለማችን በኮሮና በብዛት የሞተባቸዉ ሃገራት አሜሪካ፤ ብራዚል እና እንጊሊዝ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ቅደም ተከተልን ይዘዋል። በዓለማችን በአንድ ቀን በኮሮና የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር መጨመሩ እንዳሳሰበዉ የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ። ዤኔብ የሚገኘዉ የድርጅቱ ዋና ጽፈት ቤት ይፋ እንደረገዉ ባለፉት ሰዓታት ብቻ በዓለም ላይ ሰዎች በኮሮና ተኅዋሲ መያዛቸዉ ተረጋግጦአል። የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት ከታወቀበት ካለፈዉ የጎርጎረሳዉያን ታህሳስ ወር ወዲህ በዓለም ላይ ሚሊዮን ሕዝብ በኮሮና ቫይረስ ተይዞአል፤ ሺህ ሰዉ ደግሞ ኮሮና ባስከተለዉ ሕመም ሕይወቱን አጥቶአል። ዛሬ በወጣዉ የመዘርዝር ጥናት መሰረት ዩናይትድ ስቴትስ በዓለማችን በኮሮና በርካታ ሰዉ የሞተባት እና በኮሮና ተኅዋሲ የተያዘባት ሃገር ናት። ደቡብ አሜሪካዊትዋ ሃገር ሜክሲኮ በዓለማችን በኮሮና ሕመም በርካታ ሰዎች የሞቱባት አራተኛ ሃገር መሆንዋ ተገለፀ። የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ እስካሁን ሰዎች ኮሮና ባስከተለባቸዉ ሕመም ሞተዋል። በዚህም ሜክሲኮ በኮሮና ሟቾች ቁጥር ጣልያንን ቀድማለች። በዓለማችን በኮሮና በብዛት የሞተባቸዉ ሃገራት አሜሪካ፤ ብራዚል እና እንጊሊዝ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ቅደም ተከተልን ይዘዋል። በአራተኛነት ሚክሲኮ፤ አምስተኛ ጣልያን በመሆን በዓለም የኮሮና ሕመም የሟቾች መዘርዝር ላይ መቀመጣቸዉን የአሜሪካዉ የተኅዋሲዎች ጉዳይ ምርምር ተቋም ጆን ሆፕኪን ዩንቨርስቲ አስታዉቋል። እስካሁን በዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች በኮሮና ሞተዋል። በብራዚል በእንጊሊዝ ደግሞ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ባስከተለዉ ሕመም ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን የተቋሙ መዘርዝር መረጃ ያሳያል። በደቡብ አፍሪቃ የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት እጅግ ማየሉን ተከትሎ ሃገሪቱ አዲስ የዝዉዉር ሕግን አጠበቀች፤ የአልኮል መጠጥ ሽያጭንም አቅባለች። የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ቀርበዉ ይፋ እንዳደረጉት በሃገሪቱ የኮሮና ተኅዋሲ በስፋት እየተሰራጨ ነዉ፤ የሃገሪቱን አቅምም እየተፈታተነ ነዉ። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሺህ መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል። እንደ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ገለፃ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም ሺህ ደርሶአል። በዓለም አቀፉ የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት መረጃ መዘርዝር መሰረት በኢትዮጵያ የኮሮና ተኅዋሲ ባስከተለባቸዉ ህመም እስካሁን ሰዎች ሞተዋል።
የጤፍ የባለቤትነት መብትን የማስመለስ ዘመቻ
የኢትዮጵያውን እና ኤርትራውያን ብቻ ምግብ ተደርጎ ይወሰድ የነበረው ጤፍ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አድማሱን አስፍቶ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና በአውስትራሊያ ይመረት ይዟል፡፡ ለጤና ተስማሚነቱ ከተመሰከረለት በኋላ ደግሞ የፈላጊዎቹ ቁጥር ጨምሯል፡፡ በዚህ መሀል ግን ኢትዮጵያ ተነጠቀችው የሚባለው የጤፍ የባለቤትነት መብት ብዙዎችን ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡ ፕሮፌሰር መላኩ ገቦየ ይባላሉ፡፡ በብሪታንያ ሌስተር ከተማ በሚገኘው ደሞንት ፎርት ዩኒቨርስቲ የዓለም አቀፍ የንግድ ህግ መምህር ናቸው፡፡ በሚያስተምሩበት የህግ ዘርፍ የግብርና ምርቶች እንዴት እንደሚበየኑ የሚተነትን ባለ ገጽ መጽሐፍ ከዓመታት በፊት ለንባብ አብቅተዋል፡፡ በየጊዜው በሚያሳትሟቸው ጥናታዊ ጽሁፎችም የግብርና ምርቶችን ከዓለም አቀፍ የንግድ ድርጅት አሰራር አንጻር ፈትሸዋል፡፡ ከእርሻ ምርቶች ጋር በተያያዘ ለልባቸው ቅርብ የሆነ አንድ ጉዳይ ግን ሲከነክናቸው ቆይቷል፡፡ ጉዳዩ የጤፍ የባለቤትነት መብት በአንድ የኔዘርላንድስ ድርጅት ተወሰደ መባሉ ነው፡፡ እንደእርሳቸው የዓለም አቀፍ የንግድ ጉዳዮችን ስራዬ ብለው በሚከታተሉ ዘንድ ብቻ ሳይሆን ለመረጃ ቅርብ የሆኑ ኢትዮጵያዊያንንም ጭምር ለዓመታት ያነጋገረው የዚህ ውዝግብ መንስኤ ከዛሬ ዓመት በፊት የተደረገ አንድ ውል ነው፡፡ ፕሮፌሰር መላኩ ውሉ እንዴት እንደተደረገ እና ያስከተለውን ጦስ ያብራራሉ፡፡ በጎርጎሮሳዊው መጋቢት አካባቢ በኢትዮጵያ የእርሻ ምርምር ድርጅት እና በሆላንዱ ኤስ ኤንድ ሲ በሚባል ኩባንያ መካከል የመግባባት ሰነድ ተፈረመ፡፡ በዚያ መሰረት ለእነሱ ወደ ኪሎ የሚሆን፣ ወደ ኩንታል ወይም ከዚያ በላይ የሚሆን አይነት ዝርያ ያላቸው የጤፍ አይነቶች ምርምር እንዲደረገባቸው ወደ ሆላንድ ተላኩላቸው፡፡ ከዚያ በኋላ እነርሱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ይህን እያደረጉ በጎን ሐምሌ ላይ የሆላንድ መንግስት ቢሮ ሄደው የባለቤትነት መብት ፓተንት ይገባናል ብለው ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ያኔ ያወቀ አይመስልም፤ ቢያውቅ ኖሮ ያነሳው ነበር ብለን ስለምንገምት ማለት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ በዓመቱ ሐምሌ ላይ ይሄ ኩባንያ ስሙን ቀይሮ ፣ የሚባል ኩባንያ ሆኖ ለአውሮፓ ፓተንት ቢሮ የባለቤትነት መብት ይገባኛል ብሎ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ይሄን እያደረጉ እያሉ በሚያዝያ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ኮንትራንት ተፈራረሙ፡፡ በዚያ ውል ኮንትራት መሰረት የሆላንዱ ኩባንያ ጤፍን በአውሮፓ ገበያ እንዲያስተዋውቅላቸው፣ የተለያዩ ስራዎች እንዲሰራ ነው ስምምነቱ የተፈረመው፡፡ ከዚያ በኋላ ህዳር፣ ታህሳስ አካባቢ ለሚባለው ኩባንያ የባለቤትነት መብቱ ተሰጣቸው፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ እነርሱ ራሳቸው ከሰርን ብለው ከገበያ ወጡ፡፡ ያ ሲሆን ግን ያ የተቀበሉት የባለቤትነት መብት ሲከስሩ የት ሄደ የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ያ የባለቤትነት መብት የትም አልሄደም፡፡ የመጀመሪያው የባለቤትነቱን መብት ያገኘው ኩባንያ ሰዎች ሌላ ኩባንያ ፈጥረው፣ የኩባንያው ዳይሬክተሮች ሆነው በአሁኑ ሰዓት እየተጠቀሙበት ነው ያሉት ይላሉ ፕሮፌሰር መላኩ። በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ለአንድ ምርት አሊያም ያንን ምርት ለመስራት ለሚያስፈልገው ሂደት የባለቤትነት መብት እንዲሰጠው የሚጠይቅ አካል ሶስት ነገሮች ማሟላት እንዳለበት ፕሮፌሰር መላኩ ይናገራሉ፡፡ የመጀመሪያው መመዘኛ የነገሩ አዲስነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መብት በሚጠየቅበት ምርት ላይ የተጨመረ ፈጠራ ነው፡፡ ሶስተኛው መስፈርት ለጠቀሜታ ወይም ለተግባር የመዋሉን ጉዳይ የሚመዘነበት ነው፡፡ ፕሮፌሰር መላኩ የኔዘርላንድሱ ኩባንያ የባለቤትነት መብቱን ሲያገኝ ያቀረባቸውን ሰነዶች በእነዚህ ሶስት መመዘኛዎች ፈትሸውታል፡፡ ከሶስቱ ውስጥ ትኩረት ሊሰጥ የሚገባው ኩባንያው ፈጥሬያቸዋለሁ የሚላቸው ነገሮች ላይ ነው ይላሉ፡፡ የመጀመሪያው አዲስ መሆን አለበት ነው፡፡ ግሎተን የሚባል ችግር ላለባቸው ሰዎች፣ ሰውነታቸው መፍጨት ለማይችሉ ሰዎች፣ ከግሎቱን ነጻ የሆነ ምግብ ማቅረብ እችላለሁ ብሎ ነው የቀረበው፡፡ አዲስነቱ በዓለም ደረጃ ከታየ ጥያቄ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይዛው የኖረችው ምግብ ነው፡፡ ነገር ግን እዚያ ቦታ ላይ ሲያቀርበው ቢያንስ ቢያንስ ይህንን ልናልፈው እንችላለን፡፡ አዲስነቱን እንደተውኩት ሁሉ የኢንዱስትሪ ጠቀሜታ የሚለውን ነገር የተውኩበት ምክንያት ለምንድነው መጀመሪያውኑ እንደመመዘኛ የሆነበት ምክንያት ራሱ ዝም ብሎ ንደፈ ሀሳባዊ የሆኑ፣ ፍልስፍናዊ የሆኑ ፈጠራዎች ለፓተንት እንደማይገቡ ለማድረግ፣ የፓተንት ዓላማ ገበያ ላይ የሚቀርብ ዕቃን ሊያመርቱ የሚችሉ ፈጠራዎችን በደንብ ለማስገዛት የተዘጋጀ ስለሆነ ነው፡፡ ሁለተኛው ደረጃ፣ የተፈጠረውን ነገር ምንድነው ብለን ስንነሳ የሚያስቀው ነገር ጤፍ እንዴት እንደሚፈጭ፣ እንዴት እንደሚቦካ፣ እንዴት እንደሚጋገር እኔ የፈጠርኩት ዘዴ አለ ብሎ የሚነገረን እናቶቻችን ለዘመናት፣ በሺህ ዓመታት ለሚቆጠሩ ጊዜያት ሲያደርጉ የነበረውን ነገር ነው አውሮፓ ሄዶ አዲስ ነገር ፈጥሬያለሁ ብሎ የመጣው፡፡ ያ ማለት ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ከጤፍ የተመረተ ማንኛውንም ምርት ወይም ደግሞ ጤፉን ወደ አውሮፓ ልከን አውሮፓ ውስጥ ከጤፍ የተመረተ ብስኩት፣ ፓስታ፣ ገንፎ፣ ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል በአውሮፓ ገበያ እንዳይሸጥ መከልከል እንደሚያስችል ስናይ ነው ከመሳቅ ወደ ማልቀስ የምንሄደው ማለት ነው ሲሉ ቁጭት በሚነበብበት ድምጽ ይገልጻሉ። ፕሮፌሰር መላኩ ኩባንያው ይህንን መብቱን ተጠቅሞ ወደፊት በኢትዮጵያ ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ብቻ አይደለም የሚያሳስባቸው፡፡ ከተለያዩ ቦታ ያገኟቸው መረጃዎችን ጠቅሰው ኩባንያው የባለቤትነት መብቱን ተጠቅሞ በዚያ መስክ ሊሰማሩ የሚፈልጉ ባለሙያዎችን እያስፈራራ ነው ሲሉ ይከሳሉ፡፡ በኩባንያ ደረጃ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ ሲሉም ያክላሉ፡፡ የጤፍ የባለቤትነት መብት ጣጣ ቶሎ እልባት ካልተገኘለት ከዚህም የባሱ ችግሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ የተሰማቸው ፕሮፌሰር መላኩ እንደእርሳቸው ጉዳዩ ካሳሰባቸው ሰዎች ጋር ተቀናጅተው ግንዛቤ የመፍጠር ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ የዘመቻቸው መነሻ መንግስታዊው የኢትዮጵያ የአእምሮአዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ባለፈው የካቲት ወር ከጤፍ የባለቤትነት መብት ጋር በተያያዘ ያወጣው መረጃ ነው፡፡ ጽህፈት ቤቱ በወቅቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የጤፍ የባለቤትነት መብት ለኢትዮጵያ ለማስመለስ የተቋቋመው ኮሚቴ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ በጽህፈት ቤቱ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ብሩክ ወርቅነህ በኔዘርላንዱ ኩባንያ የተያዘውን የጤፍ የባለቤትነት መብት ለማስመለስ እየተደረገ ስላለው ጥረት እና ስለውሳኔዎቹ ማብራሪያ አላቸው፡፡ የጤፍ ባለቤትነት መብትን ለማስመለስ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ በመጀመሪያ ደረጃ እንደሀገር አቀፍ ጉዳይ ተይዞ የሚመለከታቸው አምስት መስሪያ ቤቶች የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት፣ የብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ፣ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እነዚህ ሆነው ኮሚቴ ተቋቁሞ ክትትል እየተደረገ ነው፡፡ ንግግሮች ወይም ደግሞ ከኩባንያው ውይይት በሚካሄድበጽ ጊዜ ኩባንያው አካሄዱን እየቀያየረ እስከዛሬ ድረስ ሊቆይ ችሏል፡፡ ከሰርኩኝ በሚል እና ሌሎች ምክንያቶች በማቅረብ ኩባንያው ተገቢውን ምላሽ አይሰጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ያንን የሚመለከታቸው አካላት፣ እነዚህ መስሪያ ቤቶች በአንድ ላይ በመሆን ሶስት የእንቅስቃሴ መንገዶች አወጡ፡፡ ከሶስቱ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ዲፕሎማሲ አንዱ ነው፡፡ ውጭ ጉዳይ ነው አንዱ መስሪያ ቤት፡፡ በውጭ ጉዳይ አማካኝነት ዲፕሎማሲው እየተደረገ ዲፕሎማሲው ካልሰራ አንደኛው አማራጭ የህዝብ ንቅናቄ እንዲኖር ወይም ደግሞ ተገቢ ያልሆነ የባለቤትነት መብት ስለወሰደ ያንን የሚቃወም በህብረተሰቡ፣ በህዝብ ዘንድ እንዲሰራጭበት ነው፡፡ ሌላኛው በህግ አግባብ ለመክሰስ እና የባለቤትነት መብቱን ለማስመለስ ነው ጥረት እየተደረገ ያለው ይላሉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው። የአእምሮአዊ ንብረት ጽህፈት ቤት የጀመረው ጥረት ያነቃቃቸው እነ ፕሮፌሰር መላኩ በራሳቸው የጀመሩት የማህበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ ከጽህፈት ቤቱ ሁለተኛ አማራጭ ጋር የተጣጣመ ሆኗል፡፡ በዘመቻው የኔዘርላንድሱ ኩባንያ በአውሮፓ የባለቤትነት መብት ያገኘበት የዕውቅና ሰነድ ተያይዞ ውግዘት ሲደርስበት ሰንብቷል፡፡ የኔዘርላንድሱ ኩባንያ በአሜሪካም የባለቤትነት መብት አግኝቷል ተብሎ በዘመቻው መጀመሪያ ተጠቅሶ የነበረ ቢሆንም ስህተት መሆኑ ተደርሶበት በስተኋላ መታረሙን ፕሮፌሰር መላኩ ያስረዳሉ። ኩባንያው በአሜሪካ አመለከተ እንጂ እውቅና አልተሰጠውም ይላሉ መምህሩ። የዩኒቨርስቲ መምህሩ የጤፍን የባለቤትነት መብት ማስመለስ ከተሰኘው ዘመቻቸው ምን ለማሳካት እንዳሰቡ እንዲህ ያብራራሉ፡፡ የአእምሮአዊ ንብረት ጽህፈት ቤት የሚባለው ጤፋችንን ማስመለስ አለብን ብለው እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡ እና ያንን ሲጀምሩ በተቃራኒው በኩል በጣም ጠንካራ የሆነ መከላከል እንደሚደረግ በዚህ ጉዳይ ላይ ቀረብ ያለ መረጃ ያለን ሰዎች እርግጠኞች ነን፡፡ ስለዚህ በህዝብ ዘንድ ይህ ነገር ምን ማለት እንደሆነ እንዲታወቅ ነው የማህበራዊ መገናኛዎች ዘመቻው የተጀመረው፡፡ እስካሁን ድረስ ኢመደበኛ በሆነ ሁኔታ ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው፡፡ አለን ብዙ ሰዎች ግን ያንን መልክ አስይዞ አስፈላጊ ሲሆን ወደፊት የኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡ ፍርድ ቤት ሄደው ለመሟገት እንዲችሉ በተለያየ መንገድ ድጋፍ ያስፈልገዋል፡፡ አንደኛ በገንዘብ፣ ሁለተኛ በተለይም ደግሞ አውሮፓውያን ራሳቸውን ይሄ የባለቤትነት መብት አለኝ የሚለው ኩባንያ እንዴት አስቂኝ እና አሳዛኝ ስራ እየሰራ፣ የኢትዮጵያን ገበሬዎች ዕድል እየነጠቀ እንዳለ እንዲያውቁ የማህበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው፡፡ እንጂ ስራው በአጠቃላይ ሄዶ ሄዶ በህግ መሰረት ነው መታየት ያለበት፡፡ ለፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ጫና ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለዚያ ነው እንግዲህ ይህን እንቅስቃሴ የጀመርነው ሲሉ ያገባኛል የሚል ሁሉ ሊሳተፍበት ይገባል ስለሚሉት ዘመቻቸው አብራርተዋል። ተስፋለም ወልደየስ
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት
ፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌ ይባላሉ።የቁስ ሳይንስና የምህንድስና ሊቅ ሲሆኑ፤የመጀመሪያውን ጠጣር የአሲድ ነዳጅ ለዓለም ያስተዋወቁ ሳይንቲስት ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ ከ በላይ የምርምር ፅሁፎችን አሳትመው በ ቱ የባለቤትነት መብት አግኝተዋል። በሳይንሱ ዘርፍ ባበረከቱት አስተዋፅኦም የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት ናቸው። ፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌ ትውልዳቸው አዲስ አበባ እድገታቸው ደግሞ አሜሪካን ሀገር ነው።ፕሮፌሰሯ የቁስ ሳይንስና የምህንድስና ሊቅ ሲሆኑ፤የመጀመሪያውን የጠጣር የአሲድ ነዳጅ ለዓለም ያስተዋወቁ ሳይንቲስት ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ ከ በላይ የምርምር ፅሁፎችን አሳትመው በ ቱ የባለቤትነት መብት አግኝተዋል።ለነዚህ ስራዎቻቸውም በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል።የዛሬው የሳይንስና ቴክኖሎጅ ዝግጅት እኝህን ሳይንቲስት ያስተዋውቃል። ፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ አሜሪካዊ የቁስ ሳይንስና የምህንድስና ሊቅ ናቸው።ያም ሆኖ ስኬታቸው አልጋ በአልጋ አልነበረም።በኢትዮጵያ በ ዓ ም በነበረው አብዮት አባታቸው እውቁ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ የደርግን መንግስት በመቃወማቸው የጥቃት ሰለቫ በመሆን ክፉኛ ቆስለው ለህክምና ከነ ቤተሰባቸው ሀገር ለቀው ሲወጡ ፕሮፈሰር ሶስና ገና የ ዓመት ልጅ ነበሩ።የአባታቸው ክፉኛ መጎዳትና የዕድሜ ልክ የአካል ጉዳተኛ መሆን የመጡበት ሀገር የተለየ ባህል፣ ቋንቋና የቀለም ልዩነት በዚያ በልጅነት ዕድሚያቸው የተጋፈጡት አሁንም ድረስ የሚያስታውሱት ፈተና ነበር። እውነት ለመናገር ልጆች የበለጠ ችግርን ይቋቋማሉ ብዬ አስባለሁ። አላውቅም። ማለቴ ተቋቋምነው።በእርግጥ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነበር።ነገር ግን ለወላጆቼ የበለጠ ከባድ ጊዜ ነበር ብዬ አስባለሁ። በጣም በልጅነት ዕድሜዬ ነው ዩኤስ መኖር የጀመርኩት።ትንሽ ትንሽ አስታውሳለሁ።ብዙ አስፈሪ አልነበረም ።ነገር ግን በጣም እንግዳ ነገር ነበር።ኢትዮጵያ የት እንደምትገኝ የሚያውቅ የለም።ትምርት ቤት መስራት ይችላሉ ብለው አይጠብቁም።ወደ መካከለኛ ክፍል ይወስዱናል።ግን ተቋቋምነው።አሰቃቂ የሆነብኝ የሀገርና የማኅበረሰቡ ፍራቻ ሳይሆን በአባቴ ላይ የደረሰው ነው። ይህንን ፈተና ተቋቁመው ግን ፕሮፌሰር ሶስና በቁሳዊ ሳይንስና በምህንድስና በጎርጎሪያኑ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአሜሪካው የማሳቹሴት የቴክኖሎጅ ዩንቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በ ከካሊፎርኒያ በርክሌይ ዩንቨርሲቲ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በ ከማሳቹሴት ዩንቨርሲቲ በተመሳሳይ የትምህርት መስክ አግኝተዋል። በንድፈ ሀሳብ የቀሰሙትን ዕውቀት ወደተግባር ለመለወጥም በታዳሽና በዘላቂ የሀይል አቅርቦት ቴክኖሎጂ ዘርፍ በርካታ ምርምሮችን አድርገዋል።በጎርጎሪያኑ ዎቹ መገባደጃ ላይም ሱፐር ፕሮቶኒክ የተባለ አዲስ ውህድ በመጠቀም የመጀመሪያውን ጠጣር የአሲድ ነዳጅ በእንግሊዝኛው አጠራር ሶሊድ አሲድ ፊውል ሴል በመፍጠር ለዓለም አስተዋውቀዋል።እሳቸው እንደሚሉት ፈጠራው ከሀይል አማራጭነቱ በተጨማሪ የአካባቢ ብክለትን የሚከላከል ጭምር ነው። የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጫ መንገድ ነው።ስለዚህ በኢንዱስትሪ በበለፀገው ዓለም የቅሪተ አካል ነዳጅን እንጠቀማለን።ፔትሮሌምን፣ ዘይትን የድንጋይ ከሰልን፣ ፣የተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ እንጠቀማለን። እኔ የፈጠርኩት ግን መኪናዎች ከሚጠቀሙት ተለምዷዊ ሞተር ጋር ሲነፃፀር በጣም ንፁህ በሆነ መንገድ የኤሌክትሪክ ኃይልን ማመንጨት የሚችል ነው። መኪና የሚንቀሳቀሰው ውስጡ ያለውን ነዳጅ በማቃጠል ነው። ይህ ሂደት ብዙ ብክለትን ያስከትላል። ስለዚህ ጠጣር ነዳጁ ኤሌክትሪክ እንዲያመርት በማድረግ በተለየ መንገድ የመጠቀም ዘዴ ነው ።ያም በአከባቢ ጥበቃ ረገድ የበለጠ ዘላቂ ነው። ፈጠራው በመላው ዓለም እየጨመረ የመጣውን የኤለክትሪክ ሀይል ፍላጎት ለማሟላት አስፈላጊ ሲሆን፤፤እንደ ኢትዮጵያ ታንዛኒያና ዩጋንዳ ላሉ ብዙ የፀሐይ ብርሃንና የውሃ ኃይል ላላቸው የምስራቅ አፍሪቃ ሀገራት የኤለክትሪክ ሀይል አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያስፈልገው፤የተሻለ የኤሌክትሪክ ፍርግርግ ወይም ደግሞ የሀይል ማከማቻ ቢሆንም፤ በተለያዬ ሁኔታ የውሃ መቀነስ ቢያጋጥም፤እሳቸው የፈጠሩት የሀይል አማራጭ እንደ ባትሪ ሊያገለግል እንደሚችልም ያስረዳሉ። እውነት ለመናገር ያለው የውሃና የፀሀይ ሀይል አቅም የሀይል ፍላጎትን ለማሟላት በቂ ነው።የሚያስፈልገው የሀይል ማከማቻ ነው። በተለይ ለፀሀይ ሀይል።የውሃ ሀይልም ቢሆን የተወሰኑ ዓመታት ዝናብ ሊኖር የተወሰኑ ዓመታት ደግሞ ዝናብ ሊጠፋ ስለሚችል፤የረዥም ጊዜ ማከማቻ ያስፈልጋል።ስለዚህ በቤተሙከራ የሰራናቸው መሳሪያዎችና ጠጣር የአሲድ ነዳጅ ልክ እንደ ባትሪ ሊሰሩ ይችላሉ።ለአስፈላጊ ጊዜ ሀይልን ያከማቻሉ።ያለ ብዙ ቴክኒካዊ ስራ የሀይድሮጅን ነዳጅ የመፍጠር አቅም አላቸው።ከዚያም የሀይድሮጅን ነዳጅ በመጠቀም ኤለክትሪክ ማምረት ይቻላል። ሳይንቲስቷ ከጎርጎሪያኑ ጀምሮ በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በረዳት ፕሮፌሰርነት፣ከ ጀምሮ በካሊፎርኒያ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቁሳቁስ ሳይንስ ፕሮፌሰር በመሆን ለ ዓመታት ያገለገለገሉ ሲሆን፤ በ ዓ ም በኢንጂነሪንግ እና በተግባራዊ ሳይንስ ክፍል ውስጥ ሊቀመንበር ሆነው ከተሾሙ ሁለት የመጀመሪያ ሴቶች አንዷ ናቸው። ከ ዓ ም ወዲህ ደግሞ በችካጎ በኖርዝ ዌስት ዩኒቨርስቲ በማስተማር ላይ ይገኛሉ።ከዚህ የማስተማር ስራቸው በተጨማሪ በፈጣን ባትሪዎች ፣መፈተሻዎች ወይም ሴንሰሮች የኤለክትሪክ ፓምፖች እና ጠጣር የአሲድ ነዳጅ ላይ፣ ቴርሞኤሌክትሪክ እና ፌሮኤሌክትሪክ በተባሉ ሙቀትና ብረት ነክ ኤለክትሪካዊ ቁሶች ላይ፣ እንዲሁም ለአነስተኛና ተንቀሳቃሽ የሀይል ማመንጫዎች በሚሆኑ የመሣሪዎች ላይ ምርምር ያደርጋሉ።አነስተኛ ዋጋ ባላቸው ግብዓቶች ላይ እሴት በመጨመር ወደ ምርት እንዲለወጥም ይሰራሉ። እነዚህ ስራዎቻቸው የሀይል አቅርቦትና አማራጭ መስክ ወደ አዳዲስ ግንዛቤ እና አፈፃፀም እንዲሄድ አድርጓል።ከዚህ በተጨማሪ የፕሮፌሰር ሶስና ስራዎች በዓለም ላይ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማርካት ነፋስንና የፀሐይ ብርሃንን በመጠቀም ረገድ አዳዲስ መንገዶችን ፈጥረዋል።ፕሮፌሰሯ በመስኩ ከ በላይ የምርምር ፅሁፎችን ያሳተሙ ሲሆን፤በ ቱ የባለቤትነት መብቶችን ይዘዋል ፡፡ በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ዕድል ላላገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በሳይንስ ዘርፍ የትምህርት እና የምርምር እድሎችን እንዲያገኙ በማድረግ ንቁ ተሳታፊ ናቸው።ከዚህ አኳያ በሳይንሱ ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆን ዓለምን ብዙ አሳጥቷል ይላሉ። ዓለም በቀላሉ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ።ነገር ግን በዚህ አስፈላጊ ጥረት ውስጥ ግማሹን የዓለም ህዝብ አለማካተት በጣም ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ያሳጣል።ለሴቶች ለራሳቸውም ይህ አስደሳች ሙያ ነው።አስፈላጊ ግንቶችን መስራት ዓለምን የመለወጥ ተፅዕኖ አለው። ስለዚህ ማንንም መከልከል ተገቢ አይደለም። እኔ ለሴቶች የምመክረው ሞክሩት ትወዱታላችሁ። ሌሎች አትችሉም እንዲሏችሁ አትፍቀዱ።እኔ ሁል ጊዜ በሆነ መንገድ አንዳንድ አስተማሪዎች የሆነ ነገር መስራት እንደማልችል ሲያስቡ፤ ያ በጣም ነው የሚያስደስተኝ።ምክንያቱም እነሱ የተሳሳቱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በጣም በርተቼ ነው የምሰራው። በሙከራና በንድፈ ሃሳባዊ ምርምር አማካኝነት መሰረታዊ የሳይንስ ዕውቀትን በማስጨበጥ ለሙያው ላባረከቱት አስተዋፅኦ በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል።ከነዚህም ጥቂቶቹ በሳይንሱ ዘርፍ ለሰው ልጆች ህይወት መሻሻል ላበረከቱት አስታዋፅኦ በጎርጎሪያኑ ካገኙት የሰብአዊነት ሽልማት ጨምሮ፤ በጎርጎሪያኑ የብሔራዊ ሳይንስ ፋውንዴሽን ብሔራዊ የወጣት ተመራማሪ ሽልማትን፣በ ቲ ኤም ኤስ ሮበርት ላንሲግ ሃርዲ ሽልማትን፣በ ዓ ም ከአሜሪካ የሴራሚክ ማኅበረሰብ ሽልማትን፣ በ ዓ ም የጄ ቢ ዋግነር ሽልማት ከኤለክትሮ ሜካኒካል ማኅበረሰብ ተሸልመዋል። በማስተማርና በማማከር ስራ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የቁስ ሳይንስና የምህንድስና የሳይንስ ሊቃውንት በአሜሪካዊ የቁስ ሳይንስ ሊቅ ዴቪድ ተርንቡል ስም በሚሰጠው ሽልማትም የ ተሸላሚ ናቸው። የዓለም አቀፍ የቁስ ሳይንስ ምርምር ማህበረሰብ፣የአፍሪካ እንዲሁም የኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ ባልደረባም ናቸው።ፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌ በርትቶ በመስራት የሚያምኑ ሳይንቲስት፣ እናት፣አማካሪና መምህር ሲሆኑ፤ የወላጆቻቸው ትልቅ ድጋፍ የስኬታቸው ቁልፍ መሆኑን ይገልፃሉ።ስኬትና ስራ መጨረሻ የለውም የሚሉት ፕሮፌሰር ሶስና፤ለወደፊትም ይህንኑ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ይገልፃሉ። አባቴ ዓመቱ ነው።ግን ሁል ጊዜም ይሰራል። ምክንያቱም ሊሰሩ የሚገባቸው ብዙ ህትመቶች እንዳሉ ያውቃል። ሊፃፍ የሚችል ብዙ ታሪክ አለ። ሊሰራ የሚችል ብዙ ነገር አለ።ስራ አያልቅም። እናም ለውጥ ማምጣት የምትችል ሰው ሆኖ ከተሰማህ በትክክል መቀዛቀዝ አትፈልግም። ብዙ የሚከናወኑ ነገሮች አሉ። እናም እንዳልኩት ይህንን ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም።ቤተሙከራዬ ውስጥ አነስተኛ ጅምር ስራ አለኝ። አሁንም እውነተኛ ቴክኖሎጂን ለመስራት እየሞከርን ነው። ከዩኒቨርሲቲ ትምህርት እና በምርምር ደረጃ ከምንሰራው በተጨማሪ ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ የተወሰኑት በእውነተኛው ዓለም ለውጥ እንደሚያመጡ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ ሳይኒቲስቷ በቁስ ሳይንስ ዘርፍ ያደረጉትን አበርቶት በማድነቅ የአሜሪካው ኒውስ ዊክ መፅሄት በ ዓ ም ሊታዩ ከሚገባቸው ሰዎች ውስጥ አንዷ በሚል ሰይሟቸው ነበር።የተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃንም ታሪክ ሰሪዋ በሚል ስራዎቻቸውን በማወደስ ዘግበዋል።ለቃለ መጠይቁ ፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌን እናመሰግናለን። ፀሀይ ጫኔ
ፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የሳይንስ ሊቅ ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የወላይታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማስጠንቀቂያ
በወላይታ ዞን በምርጫው ሂደት ላይ እየተፈጸሙ ነው ባሏቸው ስህተቶች ምክንያት መጪው ምርጫ ፍትሓዊ እና ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ወብን እና የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ወህዴግ ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። በወላይታ ዞን በምርጫው ሂደት ላይ እየተፈጸሙ ነው ባሏቸው ስህተቶች ምክንያት መጪው ምርጫ ፍትሓዊ እና ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ወብን እና የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ወህዴግ ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ፓርቲዎቹ እንዳሉት ሁኔታው ካልታረመ በምርጫው የመሳተፋቸውን ጉዳይ እንደሚያጤኑ ገልጸዋል። የዞኑ የምርጫ ቦርድ ጽ ቤት በበኩሉ በምርጫ ሂደቱ ላይ የተጠቀሱ ችግሮች እንዳሉ አምኖ ፤ ለችግሩ ገዢውን ፓርቲ እና ተፎካካሪዎችን ተጠያቂ አድርጓል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አከተመ በቃ የኤልያስ መልካ የቀድሞ መምህር
መምህራኑ ጭምር በልጅነቱ የነበረው ችሎታ የሚገርም ነበር ሲሉ የሚመሰክሩለት ኤልያስ መልካ በ አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ከ በላይ አልበሞች ከ በላይ ሙዚቃዎች እንደሰራ የሚነገርለት ኤልያስ ባለሙያዎች ፍትኃዊ ክፍያ ያገኙ ዘንድ እስከ ዕለተ ሞቱ ሲታገል ቆይቷል። ኤልያስ መልካ ከአስራ አንደኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጦ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤትን ሲቀላቀል ቼሎ ያስተማሩት አቶ ገዛኸኝ ኃይሌ የሰሙትን ማመን አቅቷቸዋል። ኤልያስ መልካ ከተማሪዎቼ አንዱ ነበረ። በጣም የምኮራበት እና የምመካበት ልጅ ነበረ። ምክሬን የሚቀበል፤ የምመክረውን የሚሰማ፣ ትምህርቱን የሚያከብር ጎበዝ እና ታታሪ ተማሪ እንደነበር አውቃለሁ ሲሉ ይገልጹታል። ኤልያስ በቼሎ ብቻ ሳይሆን በፒያኖም ጎበዝ ነው። በጊታርም ጎበዝ ነው፤ ሜጀሩ ቼሎ ነው፤ ነገር ግን በአገር ባሕል የሙዚቃ መሳሪያ፣ በፒያኖ እና በጊታር ተከታታይ ትምህርቶች ነበሩት። በዚህ ሁሉ ኤልያስ ጉብዝና ነበረው፣ ስሜትም ነበረው። ለሙዚቃ ዋናው ስሜት ነው የሚሉት መምህር የሞቱ ዜና ግን አልተዋጠላቸውም። የኤልያስ መልካ ሞት ከቀድሞ መምህሩ ባሻገር ለሥራ ባልደረቦቹ፣ ለሙዚቃ ባለሙያዎች እና የሙዚቃ ወዳጆች አስደንጋጭ ሆኗል። የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ጊታሪስት የዜማ እና ግጥም ደራሲ የነበረው ኤልያስ ትናንት መስከረም ቀን ዓ ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የኩላሊት እና የስኳር ሕመም የነበረበት ኤልያስ ትናንት ምሽት ሕመሙ ጠንቶበት በአዲስ አበባ ወደሚገኘው ኢትዮ ጠቢብ ጠቅላላ ሆስፒታል ተወስዶ በዚያው ሕይወቱ ማለፉን የቅርብ የሥራ ባልደረቦቹ ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ላለፈው አንድ አመት ገደማ በሳምንት ሶስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት ሕክምናውን እየተከታተለ የነበረ ቢሆንም አዳዲስ የሙዚቃ አልበሞች ዝግጅትን ጨምሮ በበርካታ ሥራዎች ጫና ውስጥ መቆየቱ በጤናው ላይ ጫና እንዳሳደረበት በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ። ከሌሎች የሙያ አጋሮቹ ጋር በመሆን ለሶስት አመታት የለፋበት እና በቅርቡ ሥራ ላይ በዋለው አውታር የሙዚቃ መገበያያ ሥርዓት ሶማሊኛ እና አፋርኛን ጨምሮ በገበያው እምብዛም ቦታ ያላገኙ ማኅበረሰቦችን ሙዚቃዎች ለሽያጭ ለማብቃት ግፊት በማድረግ ላይ ነበር። ድምፃውያንን ጨምሮ የሙዚቃ ባለሙያዎች ከሥራዎቻቸው ተገቢውን ጥቅም ማግኘት አለባቸው የሚል አቋም የነበረው ኤልያስ፤ ዮሐንስ በቀለ ጆኒ ራጋ ኃይለሚካኤል ጌትነት ኃይሌ ሩትስ እና ዳዊት ንጉሴ ከተባሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ባቋቋመው አውታር መልቲሚዲያ በኩል አውታር የተባለውን መገበያያ ሥራ ላይ አውሏል። የሙዚቃ ሥራዎች ለሽያጭ ሲቀርቡ ድምፃዊ፣ የግጥም ጸሐፊ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማ ደራሲ ጨምሮ ሁሉንም ባለሙያዎች እኩል ተጠቃሚ ያደርጋል ብሎ ያመነበትን የአውታር መገበያያ ሥርዓት ለማጠናከር ከባልደረቦቹ ጋር ጥረት ላይ ነበር። በአዲስ አበባ በተለምዶ አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ታኅሳስ ቀን ዓ ም የተወለደው ኤልያስ በልጅነቱ እግር ኳስ መጫወት ይወድ የነበረ ቢሆንም ወደ ሙዚቃ የማዘንበል ፍላጎት ያሳይ ነበር። ይሁነኝ ብሎ ከአስራ አንደኛ ክፍል ወደ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ከማምራቱ በፊት በቤተ ክርስቲያን ሙዚቃ ተጫውቷል። በ ዓ ም ሙዚቃን ለመማር ወደ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሲያመራ በፍላጎት፣ በፍቅር እና በተሰጥዖ እንደነበር በመዲና ባንድ አብረውት ሙዚቃ የተጫወቱት ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ ያስታውሳሉ። በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በዋናነት ያጠናው ቼሎ ተብሎ የሚጠራውን የሙዚቃ መሳሪያ ነው። ከዚያ ባሻገር ክራር እና ፒያኖ ተምሯል። ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ከተመረቀ በኋላ በያኔው መዲና ባንድ ለሶስት አመታት ጊታር ተጫውቷል። እኔ ሙዚቃ ትምህርት ቤት እያስተማርኩ ከጓደኞቼ ጋር መዲና ባንድ የሚባል ነበረን። እዚያ ጊታር እንዲጫወት ወስደንው ነበር። በልጅነቱ የነበረው ችሎታ የሚገርም ነበር። በሚሰራቸው ሥራዎች ጓደኞቼም እኔም በጣም ነበር የምናደንቀው። ጎበዝ ልጅ ነበር ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ ስለ ኤልያስ ይመሰክራሉ። ኤልያስ ቦሌ አካባቢ ያቋቋመው በገና ስቱዲዮ ላለፉት አመታት የበርካታ ሙዚቀኞች ቀልብ ማረፊያ ሆኖ ቆይቷል። ባለሙያዎች እንደሚሉት ኤልያስ ባለፉት ገደማ አመታት ከ በላይ አልበሞች እና ከ በላይ ሙዚቃዎች ሰርቷል። ሙዚቃ ካዘጋጀላቸው መካከል ቴዎድሮስ ካሳሁን፤ሚካያ በኃይሉ፣እዮብ መኮንን፣ ኩኩ ሰብስቤ፣ ኤደን ገብረ ስላሴ፣ ትዕግስት በቀለ፣ ኃይሌ ሩትስ፣ አረጋኸኝ ወራሽ፣ ዘሪቱ ከበደ ይጠቀሳሉ። ኤልያስ ባጨዋወቱ የራሱ የሆኑ ነገሮችን ማሳረፍ ችሏል። ቅንብሮቹን ትለያቸዋለህ የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ ዘውዴ ሥራዎቹም ቢሆኑ ስኬታማ ሆነዋል ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ጊታር፣ ኤሌክትሪክ ቤዝ፣ ክራር እና ፒያኖ ኪቦርድ ላይ ያለውን ጥንካሬ ስታይ ፖፕ አርት ውስጥ በጣም ጥሩ የሚባል ሙዚቀኛ ነበር ማለት እችላለሁ። በሰራቸው ሥራዎች ትልልቅ አሻራ ማሳረፍ የቻለ ወጣት ሙዚቀኛ ነበረ፤ ባለ ተሰጥዖ ሙዚቀኛ ነበረ የሚሉት አክሊሉ ኤልያስ እና መሰል ባለሙያዎች ሥራቸውን የሚያከናውኑበት መንገድ ጫና የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው የፋና ቴሌቭዥን የባለ ተሰጥዖዎች ውድድር ተብሎ ተጋብዤ እዛ ሳገኘው በጣም ነው ያዘንኩት ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ የለሊት ሥራ በጣም ከባድ ነው፤ ያላቸውን ኃይል ሁሉ የሚጨርሱበት አይነት ነው ብለዋል። የኤልያስ መልካ ሞት የቀድሞ መምህራኑን፣ የሥራ ባልደረቦቹን እና የሙዚቃ ወዳጆችን አስደንግጧል። ባለፉት ሳምንታት አብረውት በስራ ላይ የነበሩ የሕመሙን መባባስ በቅርብ ቢያውቁም በሞቱ ደንግጠው በቅጡ መናገር ተስኗቸዋል። እኔ እኮራበታለሁ የሚሉት የቀድሞ መምህሩ አቶ ገዛኸኝ ኃይሌ ከእንባቸው እየተናነቁ አከተመ በቃ የምለው የለኝም ብለዋል። በመዲና ባንድ አብረውት ሙዚቃ የተጫወቱት አክሊሉ ዘውዴ በበኩላቸው በልጅነቱ ነው የሔደው፣ ትንሽ ልጅ ነበር። ገና ብዙ በሚሰራበት ዕድሜ ነው። ተቀጨ ሲሉ ሐዘናቸውን ገልጸዋል። በመጪው ሰኞ መስከረም ቀን ዓ ም ኤልያስ መልካ በተማረበት ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሽኝት ሊደረግለት መታቀዱ ተሰምቷል።
የኮሮና ወረርሽኝ እና የሕዝቡ ቸልተኝነት ውጤት
በኢትዮጵያ የኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል ህብረተሰቡ እያሳየ ያለው ቸልተኝነት ለተሕዋሲው መስፋፋት አይነተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው። የተህዋሲውን ስርጭት መግታት የሚቻለው እያንዳንዱ ሰው በተናጥል የሚያደርገው የጥንቃቄ እርምጃ ጠበቅ ያለ እንደሆን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬለ የሰጡ ሰዎች ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል ኅብረተሰቡ እያሳየ ያለው ቸልተኝነት ለተሕዋሲው መስፋፋት አይነተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው። የትሕዋሲውን ስርጭት ለመግታት በመንግሥት የሚወሰዱ የጥንቃቄ እርምጃዎች እና መመሪያዎች ብቻቸውን አጥጋቢ ሆነው እንዳልተገኙም ተነግሯል። የተህዋሲውን ስርጭት መግታት የሚቻለው እያንዳንዱ ሰው በተናጥል የሚያደርገው የጥንቃቄ እርምጃ ጠበቅ ያለ እንደሆን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬለ የሰጡ ሰዎች ገልጸዋል። ሰለሞን ሙጬ የነዋሪዎችን አስተያየቶች አሰባስቧል። ሰለሞን ሙጬ
በኮቪድ ላይ የሕዝቡ ቸልተኝነት ዋጋ እያስከፈለ ነው ይዘት
ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የአሜሪካን የህዝብ ተወካዮች ም ቤት ትራምፕን ሊከስ ነው
የምክር ቤቱ አባላት በክሱ ላይ ረቡዕ ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሏል።ባለ አራት ገጹ የምክር ቤቱ ደብዳቤ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ፣የዩናይትድ ስቴትስን ደህንነትና የመንግሥት ተቋማት እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ለአደጋ በማጋለጥና ሰላማዊ ሽግግርን በማወክ ይከሳል።ትራምፕ ለሐገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ዴሞክራሲና ሕገ መንግሥት አስጊ መሆናቸው ተጠቅሷል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች መቀመጫ ካፒቶል ሂል አመጽ በማስነሳት ሊከሰሱ ነው። የአሜሪካን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ክሱን ያቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። በአሶስየትድ ፕሬስ ዘገባ መሠረት የምክር ቤቱ አባላት በክሱ ላይ ረቡዕ ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሏል። ባለ አራት ገጹ የምክር ቤቱ ደብዳቤ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ፣ የዩናይትድ ስቴትስን ደህንነትና የመንግሥት ተቋማት እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ለአደጋ በማጋለጥና ሰላማዊ ሽግግርን በማወክ ይከሳል። ትራምፕ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ከተደረገ አሁንም ለሐገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ዴሞክራሲ እና ሕገ መንግሥት አስጊ መሆናቸው በደብዳቤው ተጠቅሷል። በትራምፕ ላይ ይመሰረታል ስለሚባለው ክስ የዋሽንግተን ዲሲውን ዘጋቢያችንን አነጋግረናቸዋል። አበበ ፈለቀ
ህፃን ዲናና የጀርመን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን
ከዛሬ አንድ ዓመት ገደማ በፊት በደቡብ ምዕራብ ጀርመንዋ ከተማ በሾፕፈንሀይም ነዋሪ የሆነችው ዲና ሁንዴ የተባለች የአስር ዓመት ልጅ ወደ ኢትዮጵያ እንዳትሄድ አንድ የጀርመን ፍርድ ቤት ወስኖ ነበር ። ዲና ወደ ኢትዮጵያ የምትሄደው ልትገረዝ ነው ሲል ፍርድ ቤቱ ያሳለፈውን ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም የዲና ወላጆች ለጀርመን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው በልጃቸው ላይ የተጣለው የጉዞ ዕገዳ በቅርቡ ተነስቶላታል ። ልደት አበበ ዝርዝሩን ታቀርብልናለች ። ልደት አበበ አርያም ተክሌ