input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
በሱዳን ቶጎ ጊኒ ኮናክሪ ኮት ዲ ቯር ምርጫዎጥ የሃገራቱ ርዕሳነ ብሔር በስልጣን ኮርቻ እንደተቆናጠጡ መቆየቱ ተሳክቶላቸዋል።
|
በስነ ቴክኒኩ ዘርፍ የተመዘገቡት ለውጦች ግዙፍ ሚና የተጫወቱ ይመስለኛል።
|
ስለዚህ እንደድሮው በምርጫ ወቅት በቀላሉ የማጭበርበር ተግባር መፈፀም አይቻልም።
|
የፖለቲካ ተንታኞች ይህንኑ ለውጥ መንግሥታት አመራራቸውን መቀየር እንደሚኖርባቸው ያመላከተ መልካም ዜና አድርገው ተመልክተውታል።
|
ይሁን እንጂ በአህጉሩ በስልጣን አላግባብ መጠቀምን የሚያስወግድ መሳሪያ እስከዛሬ አልተፈጠረም።
|
የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ እና የኮንጎ ብራዛቪል ሕዝቦች አዲስ ርዕሰ ብሔር ይመርጣሉ።
|
የሚያሳዝነው ይህንኑ የፕሬዚደንቱን እቅድ ተቃውሞ በወጣው ሕዝብ አንፃር በተወሰደ ርምጃ ሰዎች ተገድለዋል ቆስለዋል።
|
በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ የሚታየው ሁኔታም ከጎረቤት ብራዛቪል የተለየ አይደለም።
|
ፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላ የርዕሰ ብሔሩን የስልጣን ዘመን በሁለት የሚገድበውን ሕገ መንግሥት የሚያከብሩ አይመስልም።
|
ፕሬዚደንቱ በሕገ መንግሥቱ መሰረት ጊዚያቸው ሲደርስ ከስልጣን ሊወርዱ እንደሚገባ በደብዳቤ የጠየቁዋቸውን ሰባት የጥምሩ መንግሥት ባለስልጣናትን ከስራ አሰናብተዋል።
|
የቡሩንዲ ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ ርምጃን ሌሎች ያካባቢ መሪዎችን ሳያበረታታ እንዳልቀረ ጃኪ ሲልየ ገምተዋል።
|
በቡሩንዲ የተከሰቱት ሁኔታዎች ለሌሎች ያካባቢው ሃገራት አሉታዊ ምሳሌ በመሆናቸው የርዋንዳ እና የኮንጎ መሪዎችም ለሶስተኛ ጊዜ በስልጣን የመቆየት ጥረታቸውን ቀጥለውበታል።
|
ታዲያ ለአስር ተከታታይ ቀናት የጀርመን ቆይታው የአየር መጓጓዣውን ጨምሮ ወጪውን የሚችለው የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ነው።
|
ወርቃማው ድብ የበርሊናሌ ሽልማት ከታዋቂ የሆሊውድ ብርቅዬ አርቲስቶች አንስቶ እስከ ታላላቅ የዓለማችን የፖለቲካ መሪዎች ተመላልሰውበታል፥
|
ለአስር ተከታታይ ቀናት በበርሊን ከተማ በደመቀ መልኩ ሲከበር ቆይቶ ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀው በርሊናሌ ፊልም ፌስቲቫል በስተመጨረሻ አስደናቂ ሆኖ ነበር የዋለው።
|
በፊልሙ ዓለም ፈፅሞ የማትታወቀው የፔሩ ተወላጅ ሴት የፊልም ዳይሬክተር ክላውዲያ ሎዛ ቀዩ ምንጣፍ ላይ በብቸኝነት ተራምዳለች።
|
በደመቀ ጭብጨባ ታጅባም የወተት ሀዘን በሚል ርዕስ ያቀረበችው ፊልሟ በአንደኝነት ተመርጦ ተሸላሚ አድርጓታል።
|
የመድኃኒት ቁጥጥርና ክትትል ከሳምንታት በፊት ወደሀገር ዉስጥ መድኃኒቶች በሕገወጥ መንገድ ገብተዉ መያዛቸዉ ተሰምቷል።
|
መድኃኒቶችንም ሆነ ምግቦችን በተመለከተ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ተገቢዉ ጥንቃቄ እንዲደረግ መጠቆም የሚችሉበትን አድራሻ ያዉቃሉ
|
ይህን ዉል አንዳንዶች በአወንታዊ ጎኑ ሲመለከቱት አንዳንዶች ደግሞ በልጅ ጥፋት ወላጅን የሚጠይቅ በመሆኑ ይተቹታል።
|
በሀገሪቱ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቃቸዉን ሚንስትሯ ገልፀዋል።
|
በዚህ የኃላፊነት መዉሰጃ ቅፅ ከወላጆችና ከተማሪዎች ዉጭ የትምህርት ፅፈት ቤቶቹና ተማሪዎቹ የሚገቡባቸዉ ዩንቨርሲቲ ሀላፊዎችም ይፈርሙበታል።
|
ይህም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚከሰቱ ችግሮች ባለድርሻ አካላት ሁሉ ሀላፊነት እንዲወስዱ ይጠቅማል ነዉ የተባለዉ።
|
ወጣቱ በሚኖርበት የባህርዳር ከተማ የትምህርት ፅ ቤት ያለፈዉ ቅዳሜ እሱና ወላጆቹ በተዘጋጀዉ ቅፅ ላይ መፈረማቸዉን ገልጿል።
|
ያም ሆኖ ግን ቅፁ ጥቅልና ያልተብራራ መብትና ግዴታን ተንትኖ የላስቀመጠ ነዉ ብሏል።
|
ይሁን እንጅ ነገሩ አዲስና ያልተለመደ በመሆኑ በወላጆች ላይ ስጋት ማሳደሩን ተናገራለች።
|
ከ ዓመት በላይና አዋቂ ቢባልም አብዛኛዉ የካምፓስ ተማሪ የቤተሰቡ ጥገኛ ሆኖ ነዉ የሚኖረዉ።
|
እንደ ወጣት ብሩክ ቅፁ ምንም ይሁን ምን በዩንቨርሲቲ ቆይታዉ ትምህርቱ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርግ ገልጿል።
|
የሚታየውን ችግር የየክልሉ ፖለቲከኞች እና ለክልሉ ሕዝብ ቆመናል የሚሉ አንዳንዶች ጥንቃቄ በጎደለው መልኩ የሚሰነዝሩት አስተያየት እያባባሰው መሆኑንም ያመለክታሉ።
|
ትምሕርት ለሁሉም ዓመታዊ ዘገባ ኢትዮጵያ ትምህርት አገልግሎትን በማስፋፋትና መምህራንን በመቅጠር የተሻለ እድገት ካሳዩ ሃገሮች ተርታ ተመድባለች።
|
እሸቴ በቀለ የሪፖርቱን ከፍተኛ የፖሊሲ ተንታኝ አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ አዘጋጅቷል።
|
እ ኤ አ ከ ጀምሮ ኢትዮጵያ የትምህርት ተደራሽነትንና የክልሎችን ተሳትፎ በማሳደግ ከፍ ያለ ውጤት አስመዝግባለች።
|
በአዲስ አበባ ና የሶማሌ ክልል መካከል የነበረው ልዩነት ከ በመቶ ወደ በመቶ ዝቅ ማለቱን ሪፖርቱ በምሳሌነት አስፍሯል።
|
እ ኤ አ በ እና መካከል ለትምህርት የሚመደደበው በጀት በእጥፍ አድጎ አሁን ከአመታዊ በጀቱ አንድ አራተኛው ለትምህርት የተመደበ ነው።
|
በዚህ ሪፖርት በፋይናንስ በኩል ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በአግባቡ እየተጠቀመች እንዳልሆነ ተመልክተናል።
|
ኢትዮጵያ ከታክስ የምትሰበስበውን አመታዊ ገቢ ከ በመቶ ወደ በመቶ ማሳደግ ብትችል በ የትምህርት ዘርፉን ለመደጎም የሚያስችል ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ትችላለች።
|
በሪፖርቱ መሰረት ኢትዮጵያ ትምህርት አገልግሎትን በማስፋፋትና መምህራንን በመቅጠር የተሻለ እድገት ካሳዩ ሃገሮች ተርታ ተመድባለች።
|
እንደ ማኖስ አንቶኒኒስ ከሆነ ከኢትዮጵያ የአንደኛ ደረጃ መምህራን መካከል በቂ የሙያ ስልጠና ያገኙት በመቶው ብቻ ናቸው።
|
እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሃገሮች የትምህርት ዘርፉን በጥራት ለማሳደግ የሚያስችሏቸው አራት መሰረታዊ ነጥቦች በሪፖርቱ ተካተዋል።
|
አዳዲስ መምህራንን ማሰልጠን እና ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው።
|
በኢትዮጵያ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም እጩ መምህራን ወደስራ አለም ሲገቡ የሚደረግላቸው ድጋፍ በምሳሌነት ይጠቀሳል።
|
በብዙ ሃገሮች እንደሚታየው ለመምህራን የሚሰጠው ስልጠና የመማሪያ ክፍሎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ የዘነጋ ነው።
|
በትምህርት ስልጠናም በዚህ ረገድ ለሚገጥማቸው ችግር መፍትሄ ለመስጠት እንዲችሉ ማዘጋጀት ያሻል።
|
በብዙ ሃገሮች በአግባቡ ያልሰለጠኑ መምህራንን ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመመደብ ሁኔታ ይታያል።
|
መንግስታት ምርጥ መምህራንን እግጅ አስፈላጊ ወደሆኑበት የገጠር አካባቢዎችና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መመደብ መቻል አለባቸው።
|
አራተኛውና የመጨረሻው መንግስታት ለመምህራን አስፈላጊውን ጥቅማ ጥቅም በመስጠት በሙያቸው እንዲቆዩ ማድረግ ነው።
|
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ ግጭት ስለድንበሩ ግጭት መረጃ ካካባቢው ነዋሪዎች መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
የዋጋው ግሽበት ከአሥር በመቶ ያላነሰ የኤኮኖሚ ዕድገት ታየባቸው በሚባሉት ባለፉት ዓመታት ውስጥም እየጨመረ ሲሄድ ቆይቷል።
|
ግሽበቱ በተከታታይ ለአራተኛ ወር ሲቀንስ በተጠቀሰው ጊዜ የምግብ ዋጋ ግሽበት ከ ወደ ከመቶ ማቆልቆሉም ነው።
|
በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት በጥቂቱ መጨመሩ ተመልክቷል።
|
የጡት ልጅ በፊልም ሥራ ባለሞያዉ ግን ገንዘቡ ይሰጠዉ እተባለበት እጅ ሳይደርስ ቀርቶአል።
|
ለሚለዉ ጥያቄ ፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማ ጀርመኑ የሥራ አጋሪ በመታመሙ ገንዘቡ ወጭ ሳይሆን ቀረ።
|
በአዉሮጳ ሕብረት ዉስጥ ያለዉ ኤ ሲ ፒ የሚባለዉ ተቋም ገንዘቡን መልሶ ወሰደዉ ።
|
እነሱ ይህን ገንዘብ መልሰዉ ሲወስዱት ነዉ እዳዉ የመጣዉ ገንዘቡን ባገኝ ኖሮ እንደዉም ፊልሙን እስካሁን በማቀናበር እጨርሰዉ ነበር።
|
ብዙም የማዉቀዉ ነገር የለኝም እዉነቱን ለመናገር ይህን ሁሉ የሚሰሩልኝ ወጣት ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን በገዛ ፈቃዳቸዉ ተሰብስበዉ ነዉ።
|
ገንዘብ እንደማላገኝ የሚገልፀዉ ዜና ከአዉሮጳዉ ሕብረት ሲመጣ ወጣቶቹ ተሰብስበዉ መላ ፈልገዉ ነዉ የገንዘብ ማሰባሰብያዉን ዘመቻ የጀመሩት።
|
ይህን አይነት ሥራ ሰርቼ ስለማላዉቅ የማዉቀዉ ብዙ ነገር የለም።
|
እኔ እንደዉም ከተጠየኩ ላይቀር ብዙ ጊዜዬን ለማጠፋዉ ወይም የዓድዋ ልጆች ከ ዓመት በኃላ ለተሰኘዉ ፊልም ነዉ።
|
ፊልሙን ለመሥራት በፊልም ያሰባሰብኩዋቸዉን መረጃዎች በመቁረጥ ነዉ አብዛኛዉን ጊዜዬን የማጠፋዉ።
|
በአገራችን የጣልያኑ የሞሶሎኒ ጦርነት እንደሳቸዉ እንደ ፕሮፊሰር ኃይሌም ሆነ እንደአባታቸዉ የሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት የጀመረበት ነዉ።
|
አባቴ አርበኛ ስለነበር ለአባቴ ሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት የጀመረዉ ኢትዮጵያ በጣሊያን ጦርነት በሞሶሎኒ ፋሽስት ስትወረር ነዉ።
|
ግርያዝያኒን ለመግደል ሙከራ ከተደረገ በኃላ በመጣዉ መአት እጅግ ብዜ ኢትዮጵያዉያኖችም አልቀዋል።
|
ጣልያኖችም ቢሆኑ አሁን በዝያን ጊዜ ያለቀዉን ህዝብ ቁጥር ለማወቅ ብዙ ጥናን ጀምረዋል ነገሩ አዲስ ነገር አይደለም።
|
አዉሮጳዉያን ሂትለር ኦስትርያና ፖላንድን ሲወር ነዉ ሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ተጀመረ ብለዉ ታሪክን ያስቀመጡት።
|
ለኃያላኑ አገራትም የሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት በዚህ ጊዜ ተጀመረ ብለዉ ነዉ የሚሉት።
|
ለፊልሙ ትረካዉን ጽፊ ጨርሻለሁ ያሉን ፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማ ይህን በፊልም መልክ በማቀናበር ከ ዓመታት በላይ እንደሰሩ ተናግረዋል።
|
የዚህን ታሪክ በፊልም ለማስቀመጥ ካቀድኩ ቆየሁ ስራዉን ከጀመርኩ ከ ዓመታ በላይ ሆነኝ።
|
አርበኞችን ባገኘሁ ቁጥር በፊልም መልክ እየቀዳሁ ስብስቤ አስቀምጥ ነበር።
|
እናም አርበኞችን በፊል የቀርፅኩ ታሪኩን የሚዉቁ የታሪክ ሰዎችን እየጠየኩ እስካሁን ፊልሙን ስሠራ ነበር።
|
ጤዛ የተሰኘዉንም ፊልሜን ስሠራ ወጣ ገባ እያልኩ በጎን የዓድዋ ልጆች ከ ዓመት በኃላ የሚሰኘዉን ፊልሜን ሳቀነባብር ስሠራ ነበር።
|
እስከ ፊታችን መስከረም ወር ያልቃል የሚል ተስፋ አለኝ ለሥራ ማስኬጃ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ወደ አዉሮጳ ይዤዉ ሳልመጣ አልቀርም።
|
ጤዛ ፊልም የፊልም ባለሞያው የኃይሌ ገሪማ ወዳጆችና አድናቂዎች በዋሽንግተን ዲሲ ለፊልሙ መስሪያ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰብያ ምሽት አዘጋጅተዋል።
|
በዝግጅቱ ላይ የኃይሌ ፊልም ይቀርባል ዉይይትም እንደሚኖር ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነዉ ጋዜጠኛና ደራሲ ታምራት ነገራ ገልፆአል።
|
በዲሲ የምንገኝ አብዛኛዎቻችን ኢትዮጵያዉያን ፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማን ጋሼ ኃይሌ ነዉ የምንለዉ።
|
ጋሽ ኃይሌ በአሜሪካ ዉስጥ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ካደረጉ ሰዎች መካከል አንዱ ነዉ።
|
በአጠቃላይ በፊልም ኢንዱስትሪ ሁለት ነገር አለ የቴክኒክ እጥረት ሁለተኛዉ ጥቁርን በመልካም ነገር የመግለፅ ችግር ነዉ።
|
ሆን ተብሎ ተቋማዊ ዘረኝነት ከሚገለፅባቸዉ መድረክ አንደኛዉ ፊልሞች ናቸዉ።
|
ጠጋ ብዬ ጋሽ ኃይሌን ስከታተለዉ በጣም የሚገርም ስራዎችን ነዉ እየሰራ ያለዉ።
|
እዚህ ዲሲ መኖር ከጀመርኩ ጀምሮ ሳንኮፋ በተሰኘዉ መገናኛ ቤቱ እናገኘዋለን እንጫወታለን በጣም ጋሽ ኃይሌ ለሰዉ ቅቡል ሰዉ ነዉ።
|
ስቱድዮ አስገብቶ እንዴት እንደሚሰራ ምን ምን ፕሮጀክት እንዳለዉ የሚያካፍል ሰዉ ነዉ።
|
ለተሰኘዉ ጥያቄ ጋዜጠኛና ደራሲ ታምራት ነገራ አንድ ሰዉ በዚህ አይነት ፕሮጀክት ላይ የሚሳተፈዉ የተፈለገዉ ብር ይሟላል ብሎ አይደለም።
|
ይህ ገንዘብ በትልልቅ ካንፓኒዎች ወይም በሃገር ደረጃ ድጋፍ ካላገኘ ይህን ያህል ብር መሰብሰብ ላይሆን ይችላል።
|
ግን በዚህ ምክንያት ብቻ የሚፈጠረዉ ማህበረሰብ በራሱ ትልቅ ነገር ነዉ።
|
በሌላ በኩል በዚህ መድረክ የጡት ልጅ የተባለዉ የፊልም ስራ እቅድ ላይ መሆኑ መታወቁ በራሱ ትልቅ ጉዳይ ነዉ።
|
ግን የራሳችንን ሥራ የራሳችንን ባህል የራሳችንን ታሪክ ራሳችን በጀት መመደብ እንዲህ ነዉ የምንለማመደዉ።
|
ፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማ ዩኤስ አሜሪካና ኢትዮጵያ የተመዘገበዉ የፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማ የፊልም ድርጅት ነጎድጓድ ፕሮዳክሽን ይባላል።
|
የፊልም ባለሞያዉ ዋሽንግተን ላይ ሳንኮፋ የሚል የመገናኛ መደብርም እንዳለቸዉ ነዉ የገለፁት እንደ አንዱ የፊልማቸዉ ስያሜ።
|
ኃይሌ ገሪማ ኢንዲጎጎ የርዳታ ማሰባሰብያ በእኛም ሃገር ለሚገኙት ጥሩ ጥሩ ወጣት ፊልም ሰራተኛ ወጣቶች መደገፍያ መለመድ እንዳለበት ሳይገልፁ አላለፉም።
|
በርግጥ ይህ አይነቱ የገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላሉት የፊልም ሰራተኞች ሊታሰብ የሚገባ ነዉ።
|
ግዜ ሳያመልጠን የዓይን ምስካሪዎች ከጃችን ሳይሾልኩ በፊልም ሰራተኞች እገዛ ታሪካችንን ጽፈን ለተቀሪዉ ትዉልድ ልናስተላልፍ ይገባል ብለዋል።
|
የራሳችንን ፊልሞች የራሳችንን ትያትሮች የራሳችንን መፅሐፎች በራሳችን ቋንቋ መስራት መቻል አለብን እላለሁ።
|
ለምሳሌ ጤዛ የተሰኘዉ የጋሽ ኃይሌ ፊልም በጀርመኖች ርዳታ ነዉ የተሰራዉ ይኸዉ ፊልም የተለያዩ ዓለማቀፍ ሽልማትችን አግኝቶአል።
|
ከዚህ በኃላ ግን እኛም ራሳችን መስራት መቻል አለብን ራሳችን መጀመር አለብን።
|
የራሳችንን የፊልም ሥራ ባለሞያዎች የራሳችን ደራሲዎች የራሳችን ከያኒዎች እኛ መሸከም መጀመር አለብን ።
|
እስካሁን ግን የአድዋ ድል በተሳካ መልኩ ተሰርቶ በርካታ ህዝብ ሲያየዉ አላየንም።
|
እናም የራሱን ታሪክ ማየት የሚሻ ሰዉ ይህን ፕሮጀክት እንዲረዳ እጋብዛለሁ።
|
ለፊልም ሥራዉ የሚያስፈልገው ገንዘብ ተሟልቶ የጡት ልጅ ፊልም ከፍጻሜ ደርሶ ለተመልካች እንዲቀርብ እንመኛለን።
|
እስካሁን ሺ ተማሪዎች ብቻ ናቸዉ ትምህርታቸውን የሚከታተሉት ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
ተከታዩ ዘገባ ስለ ክሬሚያ መያዝ እና ስለ ዩክሬይን ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፖሮሼንኮን የበርሊን ጉብኝት ይመለከታል።
|
ኢትዮጵያዉያን የትልቁ ቱጃር የሼክ መሐመድ ሁሴይን አል አሙዲ መታሰርን ትልቅ ርዕሳቸዉ እድርገዉ እየተከራከሩ ነዉ።
|
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.