id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-51541454
https://www.bbc.com/amharic/news-51541454
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ካምፓስ በጸጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎችን ወደ ቤታቸው እየሸኘ ነው
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በአካባቢው በተፈጠረ አለመረጋጋት የተነሳ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ መወሰኑ ተሰማ።
ውሳኔው የተሰማው የዩኒቨርስቲው ሴኔት ካደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ተማሪዎች ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ተወስኗል። ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከአስተዳደራዊ የመዋቅር ጥያቄ ጋር ተያያዘ በሸካ ዞን ሚዛን ቴፒ ከተማ ግጭት ተቀስቅሶ የሠው ህይወት ሲጠፋ ንብረትም መውደሙ ተገልጿል። በቴፒ ያለው የፀጥታ ችግር ሊረጋጋ ባለመቻሉ የሚዛን ቴፔ ዩኒቨርስቲ ሴኔት በየካቲት 7/ 2012 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ተማሪዎች ከትናንት ሰኞ የካቲት 9/2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ እንደተነገራቸው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተማሪዎች ገልፀዋል። በዩኒቨርስቲው ተማሪ የሆነችውና ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራት ተማሪ እንደምትለው ከሆነ "ዩኒቨርስቲው ይህንን ባይወስን እንኳ ተማሪው ሊሄድ ወስኖ ነበር።" ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ወደ ቤተሰቦቻቸው የሸኘው ነባር ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጨርሰዉ የማጠቃለያ ፈተና ሳይፈተኑ እና አዲሶቹ ደግሞ ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ መሆኑን ተማሪዎች ይናገራሉ። ተማሪዎቹ አክለውም በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሠላም ቢሆንም በአካባቢው ያለው አለመረጋጋት ግን የዩኒቨርስቲው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች በነጻነት ተንቀሳቅሰው የትምህርት ሥራውን ለማካሄድ ተቸግረዋል። በዚህም የተነሳ ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ በሚል ለሦስት ሳምንት ያህል ትምህርት መቋረጡንረና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ መወሰኑን ይናገራሉ። በዩኒቨርስቲው የሥነ ሕይወት (ባዮሎጂ) መምህር የሆኑት አቶ ድሪባ ወርቅነህ ዩኒቨርስቲው እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበን ምክንያት ሲያስረዱ ከሦስት ሳምንት በፊት ትምህርት መቋረጡን በማስታወስ ነው። "ተማሪዎች ፈተና እንዳይቀመጡ በታጣቂዎች ማስፈራሪያ ይደርስባቸው ነበር" ሲሉም ይናገራሉ። ከዚያ በኋላም ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ከግቢ እንዲወጡ ተወሰነ ይላሉ። በአሁን ሰዓት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦ ተማሪዎችን ከአካባቢው የማስወጣት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ይናገራሉ። አካባቢው ስለሚገኝበት ሁኔታ የጠየቅናቸው የሸካ ዞን ሕዝብ ግንኙነት አቶ አስማማው ኃይሉ ሲናገሩ ከሳምንት ወዲህ ሁኔታው መሻሻል ቢያሳይም "ትንኮሳው አልቆመም" ይላሉ። በአካባቢው አሁንም ተኩስ እንደሚሰማ በሰውና በንብረት ላይም ጉዳት እየደረሰ መሆኑን አቶ አስማማው ጨምረው ያስረዳሉ። የፀጥታ ኃይሉ፣ የዞኑ አመራር፣ ኮማንድ ፖስትና የክልሉ ደጋፊ ኃይሎች ችግር ፈጣሪ ናቸው ያሏቸውን አካላት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ መሆኑን ያስረዳሉ። "ጥቃት አድራሾቹ እዚህም እዚያም ስላሉ የሕዝብ ተሳትፎና ድጋፍ ያስፈልጋል" የሚሉት አቶ አስማማው፣ በሚፈፀሙ ተኩሶች ሰዎች እየሞቱ ነው በማለት ስጋቱ መኖሩን ይናገራሉ። ይህ የከተማው ችግር በዩኒቨርስቲውም ላይ ስጋት በመፍጠሩ ተማሪዎች አንድ ፈተና ከተፈተኑ በኋላ ተቋርጦ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ መወሰኑን ይገልጻሉ። ማስፈራሪያ የሚያደርሱ አካላት መኖራቸውንም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የምትገኘው ሸካ ዞን የተለያዩ ግጭቶች መሰማት ከጀመሩ ከዓመት በላይ አስቆጥረዋል። ይህም ያለመረጋጋት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ ተማሪዎችን የትምህርት ጉዳይ ሲያስተጓጉል ይህ የመጀመሪያው አይደለም። የዚህ ችግር መንስኤ በእነዚህ ጥቂት ዓመታት የተከሰተ ሳይሆን ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ የሸኮ ሕዝብ ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድር የሚለው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ በመቅረቱ እንደሆነ በአንድ ወቅት ያነጋግርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልን ነበር። ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ተከስቶ በነበረ የጸጥታ ችግር ምክንያት አካባቢው ለረጅም ጊዜ በኮማንድ ፖስት ስር እየተዳደረ ይገኛል።
54546136
https://www.bbc.com/amharic/54546136
ትምህርት ቤት፡ በትግራይ የዳስ ትምህርት ቤት መምህርቷ ተሞክሮ
በትግራይ ክልል ጥቁር ሰሌዳ የሌላቸው፣ የአጋዥ መማሪያ መጽሐፍት እጥረት ያለባቸው፣ በእጃቸው እንጨት ይዘው ድንጋይ በከበበው ጥላ ስር የሚያስተምሩ አስተማሪዎች፣ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የሚማሩ ተማሪዎች የሚገኙባቸው "ትምህርት ቤቶች" አሉ።
ትምህርት ቤቶቹ በቆላማ ስፍራ የሚገኙ ከሆነ ደግሞ ፀሐይዋ የሚቀመጡባትን ድንጋይ ስለምታግል፣ ተማሪዎቹ " ድንጋዩን ጭቃ ቀብተው" ለመቀመጥ ይገደዳሉ። የዚህ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም ጠዋትና ማታ ድንጋይ ስር ቁጭ ብለው፣ በዙርያቸው ሳር እየጋጡ ከሚጮሁ የቤት እንስሳት፣ በድንጋይ ስር ከሚሹለከለኩ ተሳቢ ነፍሳት ጋር ጸሐይና ንፋስና እየተፈራረቀባቸው በዳስ ስር ይማራሉ። ይህ እውነት የትግራይ የዳስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የእለት ተእለት እውነታ ነው። የመምህራኖቹም የሕይወት ተሞክሮ። የመማሪያ ክፍሎቹ መቀመጫ፣ መምህራንም ቋሚ ቢሮ የላቸውም። ትምህርት ቤቶቹ በክረምት ወቅት ፈርሰው መስከረም ሲጠባ ዳግም በተማሪዎች ወላጆች ተጠግነው ነው አገልግሎት የሚሰጡት። በክፍሎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች በንፋስና ፀሐይ ይታወካሉ። ዝናብ በሚመጣበት ጊዜ መማሪያ ክፍላቸው ስለማያስጠልል ትምህርት ይቋረጣል። መምህርት ሙሉብርሃን አረጋዊ፡ በትግራይ ምእራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ በሚገኘው ሶላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪም ርእሰ መምህርትም ሆና ሰርታለች። "በአካባቢው በርካታ የዳስ ክፍሎች ስላሉ፤ ተማሪዎች ትምህርት የመቀበል አቅማቸው ከ50 በመቶ በታች ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም" ትላለች። 'የተፈጥሮ አደጋ፣ እንስሳት ወይም ሌላ ይመጣብን ይሆን?' ተማሪዎቿ በትምህርታቸው መካከል የሚጠይቋት ጥያቄ ነው። በዚህ ምክንያት ትኩረታቸው ከምትሰጣቸው ትምህርትና መጽሐፋቸው ላይ ሳይሆን፤ አይኖቻቸው ውጪ ውጪ እያማተረ በተከፋፈለ ስሜት ነው ተምረው ነው ወደ ቤት የሚመለሱት። "ድንጋይ ስር ጸሐይና ንፋስ እየመታው የሚማር ተማሪ ዝቅተኛ የትምህርት ውጤት ሊኖረው ግድ ይላል። በተለይ ህጻናት ስለሆኑ፡ በዚህ ሁኔታ ማለፋቸው እጅግ አስቸጋሪ ነው። ሁሉም ነገር ባልተሟላበት ክፍል ውስጥ ገብቶ የሚማር ተማሪም በእያንዳንዱ ነገር ትኩረቱ ስለሚሰረቅ የሚፈለገውን ያክል እውቀት መያዝ አይችልም" ትላለች መምህርቷ። በአካባቢው አሁንም ለውጥ የለም፤ ብዙዎቹ በዳስ ትምህርት ቤቶች መማራቸው አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። አስተማሪዎቹም ቢሆን የሚመችና በቂ ማረፈያና ቢሮዎች እንደሌላቸው መምህርት ሙሉብርሀን ትገልጻለች። "በረሃ ላይ ለአምስት አመታት አስተምሬያለሁ። ሁለት ህንጻና አንድ የአስተማሪዎች ጽህፈት ቤት አለ። ከዛ ውጪ በየአመቱ እየፈረሰና ኗሪዎች እያደሱት የምናስተምርባቸው የዳስ ክፍሎች ናቸው ያሉት"። የሑመራ አካባቢ ጸሐይና ሙቀት የሚበረታበት ስለሆነ፤ ተማሪዎቹ ድንጋዩን በጭቃ እየቀቡ ለመማር እንደሚጥሩ አስተማሪዋ ትናገራለች። በዚህ ምክንያት ከአንድም ሦስቴ በምታየው ነገር ጭንቀት ይፈጥርባት እንደነበረ ገልጻለች። "በዚህ ሁኔታ አይደለም ርእሰ መምህርትና አስተማሪ ሆኜ አንድም ሌሊት የማሳልፍ አይመስለኝም ነበር። በጊዜ ሂደት ግን ከህብረተሰቡ አልበልጥም ብዬ ተቀበልኩት" ብላለች። በጊዜው ምንድን ነው የማስተምረው? በሚል ሃሳብ ትጨነቅ እንደነበረ የምትናገረው መምህርት ሙሉብርሃን፡ "ምቾት በሌለበት የምትሰራው ሁሉ እርካታ የለውም" ስትል ሁኔታውን ትገልጻለች። "በዚህ ተስፋ ቆርጠው ወደ ውጪ የሄዱ አሉ" ትምህርት ሲነሳ በቀዳሚነት ስሟ ከሚጠቀሰው አገር መካከል አንዷ ሲንጋፖር ነች። ሲንጋፖር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እንደ ሃገር በአንድነት እንትድጠነክር ካደረጓት ነገሮች መካከል አንዱ ትምህርት ነው። አገሪቷ ለአስተማሪዎች ባላት ትኩረት በትምህርት፤ በተለይ ደግሞ በሒሳብና በሳይንስ በቀዳሚነት የምትጠራ ሲሆን በቆዳ ስፋት ትንሽ ብትሆንም በትምህርትና እውቀት ግን ታላላቅ አገሮችን እየመራች ነው። በሲንጋፖር በትምህርት ጉዳይ ቀልድ የለም፤ ወላጆች የልጆቻቸውን የእውቀት ደረጃ የማይገነቡ እና ደረጃውን ወደ ጠበቀ ትምህርት ቤት የማይልኩ እንደሆነ፡ በህግ ስለሚጠየቁ ጠንቃቃ ናቸው። ሲንጋፖር ለአስተማሪዎች ክብር ከሚሰጡት 10 የዓለማችን አገራት መካከል አንዷ ስለሆነች፤ ወላጆች ልጆቻቸውን መምህር እንዲሆኑ ያበረታታሉ። ሙሉብርሃንም፤ "ፈጣሪም እንኳ መምህር ስለሆነ 'ረቡኒ' አይደል የሚሉት? እኔም ትልቅ ክብር እየሰጠሁት መምህርት እንድሆን እየተመኘሁ አደግኩ" ስትል፤ የ20 አመት ወጣት ሆና ማስተማር እንደጀመረች ገልጻለች። "አዲስ ሆኜ ስቀጠር ከአንድ እስከ ስምንተኛ አስተምራለሁ። ተማሪዎች አይደለም ወንበር የሚጽፉበት ጥቁር ሰሌዳ የላቸውም። ይሄንን ሳይ ተስፋ እቆርጥ ነበር፤ እነሱ ግን በጭንቅ ነጭ ጨርቅ ላይ ጥቁር ቀለም ቀብተው ያዘጋጁ ነበር" ብላለች። በዚህ ምክንያት ብዙ ህጻናትና ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደሚያቋርጡ የምትናገረው መምህርት ሙሉብርሃን፤ "ምንም ነገር በሌለበት አካባቢ የሚፈለገው ርቀት መጓዝ አትችልም። ለዚህ ነው የተማርኩት? ብለው ተስፋ በማጣት ወደ ውጪ የሄዱ አሉ፤ እንደ ሁኔታው ብለው የቀጠሉም አሉ" ስትል የሁኔታው አስከፊነት ትገልጻለች። ይሄንን፡ አስተማሪዎች ተገቢውን መልእክት ለማስተላለፍ ስለማያበረታታቸው፤ ደስተኛና ጠንካራ ትውልድ ማነጽ ላይ ተጽእኖ ያሳድርባቸዋል። "አንድ ቀን ሱፐርቫይዝ [ክትትል] ላደርግ ወደ አንድ ዳስ ገባሁ። አስተማሪው እያስተማረ እያለ በመሃል ከብቶች እየተጋፉ ገቡ። ሌሎች የበረሃ እንስሳትም ይመጣሉ። ይህ ልጆቹ ላይ የሚፈጥረው ድንጋጤና የትምህርት ሰአት መስተጓጎል ቀላል አይደለም" ስትል ከገጠመኞቿ አንዱን ታወሳለች። መምህርት ሙሉብርሃን ባለው የትግራይ የትምህርት ሁኔታ ደስተኛ ባትሆንም "ቤት ያፈራውን ስለምትጠቀም፣ ባለው ሁኔታ እየሰራን መጥተናል። ግን በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለበትም" በማለት ነገ የተሻለ ይሆን ዘንድ ተስፋ ታደርጋለች።
news-51353269
https://www.bbc.com/amharic/news-51353269
አውስትራሊያ ከቻይና ተመላሾችን ራቅ ወዳለች ደሴት ማጓጓዝ ጀመረች
አውስትራሊያ ከቻይና ተመላሽ ዜጎቿን ራቅ ወዳለች ደሴት ማጓጓዝ ጀመረች።
አውስትራሊያ ዜጎች በዉሃን አየር ማረፊያ ከቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተነሱት የአውስትራሊያ ዜጎች የስደተኞች ማቆያ ቦታ ተደርጋ ወደምትታወቀው ክርሲማስ ደሴት እየተጓጓዙ ነው። ደሴቷ ከአውስትራሊያ በ2700 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ደሴቷ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞች ለማቆያ ስፍራነት አገልግሎት ስትሰጥ ነበር። በአሁኑ ወቅት 4 የሴሪላንካ ዜግነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ብቻ ናቸው በደሴቷ ላይ እየኖሩ የሚገኙት። ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በቻይና ከቻይና እየተጓጓዙ ያሉት አውስትራሊያውያን ለሁለት ሳምንት በደሴቷ ላይ ይቆያሉ። 89 ታዳጊዎችን ጨምሮ ዛሬ ጠዋት 243 ዜጎች እና የአውስትራሊያ ቋሚ ነዋሪዎች ወደ ደሴቷ ለመጓዝ አውሮፕላን መሳፈራቸውን የአውስትራሊያ መንግሥት አስታውቋል። ከ600 በላይ የአውስትራሊያ ዜጎች ቫይረሱ በተከሰተበት ሁቤይ ግዛት ውስጥ ይኖራሉ። የተቀሩ ዜጎችን ለማጓጓዝ ተጨማሪ በረራዎች እንደሚዘጋጁ መንግሥት አስታውቋል። የህክምና መስጫ ስፋራዎች ቀደም ብለው በክሪስማስ ደሴት ላይ ተዘጋጅተዋል። ኮሮናቫይረስ በመላዋ ቻይና መዛመቱ ተነገረ፤ የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ ነው ኮሮናቫይረስ፡ የወቅቱ አሳሳቢው የዓለማችን የጤና ስጋት የአውስትራሊያ መንግሥት ስደተኞች ለማቆያ በሚጠቀምበት ደሴት ላይ ዜጎቹን ለይቶ ለማቆየት መወሰኑ ከበርካቶች ትችት ተሰንዝሮበታል። ከዚህ በተጨማሪ መንግሥት በደሴቱ ላይ ያዘጋጀው የህክምና መስጫ ስፍራዎች ደረጃ ዝቅ ያለ ነው የሚሉም በርካቶች ናቸው። መንግሥት ግን 24 ዶክተሮችን እና ነርሶችን ማስማራቱን እና ከዚህ ቀደም እያንዳንዱ ከቻይና የሚጓጓዝ ዜጋ ወይም ቋሚ ነዋሪ እንዲከፍል ተጠይቆ የነበረው 1ሺህ የአውስትራሊያ ዶላር እንዲቀር ተወስኗል ብሏል። 24 ዶክተሮችን እና ነርሶችን ወደ ደሴቷ መሰማራታቸውን መንግሥት አስታውቋል። በአውስትራሊያ 12 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ሶስቱ ከቫይረሱ ድነው ከሆስፒታል ወጥተዋል። እስካሁን በጠቅላላው 360 ሰዎች በላይ በቫይረሱ የሞቱ ሲሆን፤ ከ17ሺህ በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው ተረጋግጧል። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ እና ጃፓን ዜጎቻቸውን ከቻይና ካስወጡ አገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
news-45755986
https://www.bbc.com/amharic/news-45755986
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ በደቡብ ሱዳን ላበረከተው አስተዋፅኦ በተባበሩት መንግሥታት ሜዳሊያ ተበረከተለት
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ በደቡብ ሱዳን ላበረከተው አስተዋፅኦ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሽልማት ተበረከተለት።
605 አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ባታሊየን 1 አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሙሉጌታ ንጉሴ እንዳሉት "የመንገዱ ምቹ አለመሆንና ለግምት አስቸጋሪ የሆነው የፀጥታ ሁኔታ ተልዕኮውን በእጅጉ ፈታኝ አድርጎት ነበር" በማለት ወታደሮቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በጥሩ ሥነ ምግባርና ሙያቸውን ባከበረ መልኩ ማከናወናቸውን ገልፀዋል። • ደቡብ ሱዳን ለበጎ ፍቃደኞች አስጊ ሃገር ተባለች ይህ የኢትዮጵያ ጦር ጁባ ከሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት መጠለያ ጎን ሰፍረው የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን ይጠብቅ ነበር። ጦሩ በመጠለያ ጣቢያው ዙሪያ ከጦር መሳሪያ ነፃ በሆነው ስፍራ እየተንቀሳቀሰ ጥበቃ ያደርግ የነበረ ሲሆን በከተማው መሀል ግጭቶች እንዳይከሳቱም መስራቱ ተገልጿል። • ደቡብ ሱዳን ለመኪና መግዣ 16 ሚሊየን ዶላር አወጣች ሰላም አስከባሪው ኃይል ርቀው የሚገኙ ማህበረሰቦችን ለማግኘት የሚንቀሳቀሱትን በማጀብ፣ የፈራረሱ መሰረተ ልማቶችን የሚጠግኑ መሃንዲሶችን ከለላ በመስጠትና በሀገሪቱ ያምቢዮ ክፍለ ሃገር ተመድቦ ሰላም የማስከበር ሥራውን ይሰሩ ነበር ተብሏል። • በኢትዮጵያ ስላሉ ስደተኞች አንዳንድ ነጥቦች የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ፀሐፊ ተወካይ የሆኑት ሙስጠፋ ሶማሬ እንዳሉት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ጦር በደቡብ ሱዳናዊያን ህይወት ላይ አዎንታዊ ለውጥ አምጥቷል። አክለውም ጦሩ ሰላም ለማስከበር በተሰማራበት ሁሉ መልካም ስም እንዳለው ገልፀው "ሰላም ለማስከበር በተሰማራችሁበት ስፍራ ያሉትን ከፍተኛ ተግዳሮቶች የተወጣችሁበትን ትጋታችሁን እና መሰጠታችሁን አደንቃለሁ" ብለዋል። ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ሰላም የማስከበር ተግባርን ከማከናወቷ ባሻገርም በተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲወርድ አስተዋፅኦ አድርጋለች። በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍሰሃ ሻወል እንደተናገሩት "የደቡብ ሱዳን ሰላም የእኛም ሰላም ነው፤ የኢትዮጵያ ሰላም የደቡብ ሱዳናዊያን ሰላም ነው። በቀጥታ የሚገናኝ ነገር ነው። እዚህ እየሰራችሁ ያላችሁት ይህንን ነው። " በማለት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰላም ማስከበሩ ጎን ለጎን በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። • ማቻር እና ሳልቫ ኪር እርቅ አወረዱ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም ለማስከበር በሚያደርገው ጥረት ውስጥ 8ሺህ ያህል ሠራዊት በማዋጣት ከቀዳሚዎቹ አንዷናት። ይህ ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት በዓለም ዙሪያ ካሉት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች መካከል 8 በመቶ ያህሉ ነው። ኢትዮጵያ ሴት የሰላም አስከባሪዎችንም በማዋጣትም ቀዳሚ ሃገር ናት።
news-53337835
https://www.bbc.com/amharic/news-53337835
ሜሪ ትራምፕ የፃፉት መፅሐፍ ስለ ፕሬዝደንት ትራምፕ ምስጢራት አዝሏል እየተባለ ነው
የትራምፕ ወንድም ልጅ ሜሪ ትራምፕ የፃፉት መጽሐፍ ፕሬዝደንቱን 'እጅጉን ራስ ወዳድ' ሲል ይገልፃቸዋል። 'የእያንዳንዱ አሜሪካዊ ሕይወት አደጋ ላይ ነው' የሚል አንቀፅም ሰፍሮበታል።
ከዶናልድ ትራምፕ ጀርባ የሚታየው የአባትና እናታቸው ፎቶ በዋይት ሃውስ ቢሯቸው ጠረጴዛ የሚገኝ ነው ሜሪ ትራምፕ የዶናልድ ትራምፕ ታላቅ ወንድም ልጅ ናቸው። ከሰሞኑ ስማቸው የመገናኛ ብዙሃን አፍ መሟሻ ሆኗል። ምክንያቱ ደግሞ የትራምፕን ግላዊ ምስጢርን የያዘ መጽሐፍ ሊያስትሙ መሆኑ ነው። የመጽሐፉ ርዕስ በግርድፉ 'ቤተሰቤ የፈጠረው የዓለማችን አደገኛው ሰው' ይሰኛል። የእንግሊዝኛው ርዕስ፡ Too Much and Never Enough: How My Family Created the World's Most Dangerous Man የትራምፕ አስተዳደር መጽሐፉ ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንድ ውንጀላዎች ስህተት ናቸው ይላል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የመጽሐፉ ቅጅ ደርሷቸዋል። የትራምፕ ቤተሰብ መጽሐፉ አይታተም ሲል ከሷል። 'እጅግ ራስ ወዳድ' የ55 ዓመቷ ሜሪ ናቸው አጎታቸው ዶናልድ ትራምፕን 'እጅግ ራስ ወዳድ' ሲሉ የገለጿቸው። ሜሪ፤ በክሊኒካል ሳይኮሎጂ ዶክትሬት ድግሪ አላቸው። "ትራምፕ ደካማ ብቻ አይደሉም" ይላሉ። "በየደቂቃው ስለሳቸው አንድ ነገር መነገር አለበት። ምክንያቱም የሚያወሩትን ዓይነት ሰው እንዳልሆኑ ውስጣቸው ያውቀዋል።" ሜሪ፤ ዶናልድ ትራምፕ በአባታቸው ፍሬድ ትልቁ ጥላ ሥር እንዳደጉ ይናገራሉ። የትራምፕ አባት፤ የሜሪ አባትን ይበድሏቸው እንደነበርም ጽፈዋል። የሜሪ አባት የመጠጥ ሱሰኛ ነበሩ። ሜሪ የ16 ዓመት ታዳጊ ሳሉ ነው አባታቸውን ያጡት። የትራምፕ ቤተሰብ በሪል እስቴት ብር የናጠጠ ነው። የትራምፕ አባት፤ የሜሪ አባት የቤተሰቡን ብር እንዳይወርሱ የቻሉትን ሁሉ ያደርጉ እንደነበር የሜሪ አዲሱ መጽሐፍ ያትታል። ትራምፕ ትልቁ የሚወዱት ልጃቸውን በመጠጥ ሱስ ሲነጠቁ የነበራቸው አማራጭ ሃብታቸውን ለዶናልድ ትራምፕ አባት ማውረስ እንደነበር አዲሱ መጽሐፍ ያስነብባል። ዋይት ሃውስ የዶናልድ ትራምፕ አባት ወንድማቸውን ይበድሉ ነበር የተባለው ሐሰት ነው ሲል ያጣጥላል። ዶናልድ ትራምፕና አባታቸው ፍሬድ በ1980 ዓመተ ምህረት ኒው ዮርክ ውስጥ የተነሱት ፎቶ የግብር ጉዳይ ሜሪ ትራምፕ ኒው ዮርክ ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ ግብር የከፈሉበትን መረጃ ያቅርቡ ሲላቸው እንዳቀረቡ ጽፈዋል። ጋዜጣው በወቅቱ የምርመራ ዘገባ በዶናልድ ትራምፕ ግብር መክፈል አለመክፈል ውዝግብ ዙሪያ ሰርቷል። ሴትዬዋ ፕሬዝደንት "ትራምፕ ግብር ላለመክፈል ያልሄደበት መንገድ የለም" ሲሉ ይከሳሉ። 'አጭበርባሪ ተማሪ' ሜሪ፤ አጎቷ ዶናልድ የአገሪቱን ብሔራዊ ፈተና ለሌላ ሰው ከፍለው እንዳስፈተኑ በአዲሱ መጽሐፋቸው ላይ ጽፈዋል። ፈተናው አሜሪካውያን ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት የሚፈተኑት ነው። ሜሪ እንደሚሉት ዶናልድት ትራምፕ ይህን ያደረጉት ራሳቸው ቢፈተኑ ውጤታቸው ለዩኒቨርሲቲ ላያበቃቸው ስለሚችል ነው። በምትኩ 'ትምህርት የዘለቀው ሌላ ልጅ ቀጥረው ፈተናውን በእሳቸው ስም እንዲፈተን እንዳደረጉ' ይናገራሉ። "ዶናልድ እንደሆኑ ኪሳቸው ሁሌም ሙሉ ነው። ለተፈተነላቸው ልጅ ጫን ያለ ገንዘብ ነው የከፈሉት።" ዶናልድ ትራምፕ ኒው ዮርክ የሚገኘው ፎርድሃም ዩኒቨርሲቲ ገብተው ትምህርታቸው መከታተል ከጀመሩ ከቆይታ በኋላ ወደ ፔንሲልቪኒያ ዩኒቨርሲቲ ተዛውረው ነው ዲፕሎማቸውን የጫኑት። ዋይት ሐውስ፤ ፕሬዝደንቱ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት አጭበርብረዋል የተባለው ሐሰት ነው ሲል ያጣጥላል። 'ከሴቶች ጋር ያለ ግንኙት' ሜሪ፤ "ዶናልድ ትራምፕ the Art of the Comeback [ግርድፍ ትርጉም፡ አፈር ልሶ የመነሳት ጥበብ] የተሰኘ መጽሐፍ እንድጽፍለት ጠይቆኝ ነበር" ይላሉ። ለመጽሐፉ እንዲሆን የሰጧቸው ሃተታ ላይ ዶናልት ሊተኟቸው የሚፈልጓቸው ነገር ግን ፊት የነሷቸው ሴቶችን በሚያንቋሽሽ ቋንቋ የተፃፈ እንደሆነ ሜሪ አዲሱ መፅሐፋቸው ላይ አስፍረዋል። አልፎም ሜሪ የ29 ዓመት ወጣት ሳሉ ስለተክለ ሰውነታቸው ተገቢ ያልሆነ አስተያየት ይሰጧቸው እንደነበርም ጽፈዋል። በወቅቱ ዶናልድ ትራምፕ ከሁለተኛ ሚስታቸው ማርላ ማፕልስ ጋር ነበሩ። ትራምፕ ለቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ 'ሜሪ የዕፅ ሱሰኛ ናት፤ በዚህ ምክንያትም ነው ትምህርቷን ያቋረጠችው' ብለው ነግረዋታል ይላል በቅርቡ ይወጣል ተብሎ የሚጠበቀው መጽሐፍ። ሜሪ፤ "እርግጥ ነው ትምህርቴን አቋርጬ ነበር ነገር ግን በዕፅ ምክንያት አይደለም" ይላሉ። ሜሪ ትራምፕ አጎታቸው ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ከአደባባይ ርቀዋል። ነገር ግን ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝደንት ከመሆናቸው በፊት ጀምሮ አጥብቀው ይተቿቸው እንደነበር ይታወቃል። ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ እንደዘገበው ሜሪ፤ ትራምፕ ምርጫ ያሸነፉበትን ምሽት "በሕይወቴ መጥፎው ምሽት" ሲሉ ገልፀውታል። በወቅቱ ትዊተር ገፃቸው ላይ "ለእናት አገሬ ሃዘን አድርሳለሁ" ሲሉ ፅፈው ነበር።
48973392
https://www.bbc.com/amharic/48973392
ፌስቡክ 5 ቢሊየን ዶላር ሊቀጣ ነው
የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች [ሬጉሌተርስ] ፌስቡክ 5 ቢሊየን ዶላር አንዲቀጣ ወሰኑ። ውሳኔው እስከዛሬ ከተላለፉ የገንዘብ ቅጣቶች ሁሉ ከፍተኛው ነው ተብሏል።
ፌስቡክ ቅጣቱ የተጣለበት የተጠቃሚዎቹን የግል ማህደር መረጃን ሳይጠብቅ ቀርቷል በሚል ነው። የፌደራሉ የንግድ ኮሚሽን፣ የፖለቲካ ጉዳዮች አማካሪ የሆነው ካምብሪጅ አናሊቲካ፤ የ87 ሚሊየን የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን መረጃ ያለ አግባብ ወስዷል በሚል ምርመራ ሲያደርግ ነበር። ይህ ቅጣት በንግድ ኮሚሽኑ ውስጥ በአብላጫ ድምፅ መፅደቁ ታውቋል። • ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ • ፌስቡክ ግላዊ መረጃን አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ • የእናቷን አስክሬን ለሦስት ዓመት ቤት ውስጥ ያቆየችው ታሠረች ፌስቡክም ሆነ የፌደራሉ የንግድ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ከመስጠት ተቆጥበዋል። የፌደራል የንግድ ኮሚሽን ፌስቡክ ላይ ምርመራውን የጀመረው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ሲሆን፤ በወቅቱ ካምብሪጅ አናላቲካ የተሰኘው የፖለቲካ አማካሪ ድርጅት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ በሕገ ወጥ መንገድ ማግኘቱ ተዘግቦ ነበር። ምርመራው ያተኮረው ፌስቡክ በ2011 የተደረሰውን፤ ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ያለ ፈቃዳቸው ለሦስተኛ አካል ማጋራት የሚከለክለውን ስምምነት ጥሷል ወይስ አልጣሰም የሚለው ላይ ነበር። ውስጥ አዋቂዎች ለወል ስትሪት ጆርናል እንዳረጋገጡት፤ ፌስቡክ 5ቢሊየን ዶላር እንዲቀጣ ተወስኗል። ውሳኔው ግን አሁንም ሪፐብሊካን ኮሚሽነሮችና ዲሞክራቶች መካከል ልዩነትን የፈጠረ እንደነበር መረጃዎቹ ይጠቁማሉ። ሪፐብሊካን ውሳኔውን ደግፈው ዲሞክራቶች ደግሞ የተቃወሙ ሲሆን፤ ቅጣቱ ተፈፃሚ የሚሆነው በፍትህ ክፍሉ እንደፀደቀ መሆኑ ታውቋል። ይህ ግን ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ እስካሁን አልታወቀም። ፌስቡክና የፌደራል የንግድ ኮሚሽኑ የዜናውን ትክክለኛነት ያላረጋገጡ ሲሆን፤ ነገር ግን ለቢቢሲ አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። ቅጣቱ ፌስቡክ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ እስከ 5 ቢሊየን ዶላር ድረስ እንደሚጠብቃቸው ከተናገሩት ጋር ተመሳሳይ ነው። ይህ ቅጣት እውነት ከሆነ የፌደራሉ የንግድ ኮሚሽን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ከጣለው ቅጣት ሁሉ ትልቁ ይሆናል።
news-48701206
https://www.bbc.com/amharic/news-48701206
የኢትዮጵያና የኤርትራ አዲስ ግንኙነት በአንደኛ ዓመት
ልክ የዛሬ አንድ ዓመት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ሰኔ 13 የሚዘከረው የሰማዕታት ቀንን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበው የሰላም ጥሪ እንደተቀበለው እና ከፍተኛ የመንግስት ልኡካን ወደ አዲስ አበባ እንደሚልክ ተናግረው ነበር።
እነሆ ያች ቀን አንድ ዓመት ሞላት። ባለፉት 12 ወራት ሁለቱ ሃገራት የት ደረሱ? ጎልተው ከሚጠቀሱት ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ጥቂቶቹን ልናስታውሳቹ ወደድን። • ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት • በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል • ግንቦት 29/2010 - የመከረው የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦችን ሰላም ለማስጠበቅ የአልጀርስ ስምምነት ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ፤ • ሰኔ ወር መገባደጃ ገደማ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልሕ እና የፕሬዝደንት ኢሳያስ አማካሪ የማነ ገብረአብ የመሩት ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ አዲስ አበባ ገባ፤ • ሐምሌ 1/2010 - የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ፤ ከ20 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው የሆነውን ታሪካዊ ይፋ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አስመራ ገቡ፤ • ሐምሌ 14/2010 - በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥሪ መሠረት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ደረሱ፤ • ሐምሌ 2/2010 - ሁለቱ ሃገራት አስመራ ላይ በደረሱት 'የሰላምና የወዳጅነት አዋጅ' መሠረት ለ20 ዓመታት ያክል ተቋርጦ የነበረውን የአየር በረራ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካይነት እንደ አዲስ ጀመረ፤ • የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ሁለቱ ሃገራት በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ላደረጉት አስተዋጽኦ "ኒሻን ዛይድ" ለጠ/ሚር አብይ እና ለፕሬዝደንት ኢሳያስ አጠለቀች፤ • በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል ነሐሴ • ነሐሴ 30/2010 - ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የሶማሊያው ፕሬዝደንት መሐመድ ፎርማጆ አስመራ ላይ ተገናኝተው የሃገራቱን ግንኙነት የሚያጠናክር ያሉትን የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ፤ መስከረም • መስከረም 1/2011 - ኤርትራንና ኢትዮጵያ ከሚያገናኙት የምድር ትራንስፖርት መንገዶች ሁለት ማለትም ደባይሲማ-ቡሬ እና ሰርሐ-ዛላምበሳ ከ20 ዓመታት በኋላ ተከፈቱ። ይህንን በሥፋራው በመገኘት ያበሰሩት ደግሞ የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ነበሩ፤ • የድንበሩን መከፈት ተከትሎ 'የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዝምድና ሰላማዊ መልክ ለማስያዝ ባደረጉት አስተዋጽኦ' በሚል የሳዑዲ አራቢያ መንግሥት "የንጉስ አብደልአዚዝ ኒሻን" ሽልማትን አበረከተላቸው፤ • መስከረም 18/2011 - ከኢትዮ-ኤርትራ እርቅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤርትራ የሚኒስትሮች ካቢኔ ተሰበሰበ። ካቢኔው በቀጠናው ስለሚታዩ ስትራቴጂካዊ ትብብሮች ሰፊ ውይይት አካሄደ፤ • ኤርትራ ካሳ ጠየቀች ታኅሣሥ • መስከረም ወር ላይ የተከፈተው የዛላምበሳ-ሰርሓ ድንበር ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ጉዳይ ከፌደራል መንግስት ፍቃድ ለሌላቸው ተጓዦች ዝግ እንደሆነ ተነገረ። ቀጥሎ ታኅሣሥ 27 የራማ-ክሳድ-ዒቃ መስመር በተመሳሳይ ምክንያት ተዘጋ፤ ጥር • ጥር 13/2011 - ጣሊያን ከባጽዕ ወደ አዲስ አባባ የሚገነባው የባቡር መስመርን ለማገዝ ፍቃደኛ ነኝ አለች፤ በወቅቱ ጣልያን የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ነበሩ ይህን ያበሰሩት፤ ግንቦት • ግንቦት /2011 - የኤርትራ የነጻነት ቀን አከባበር ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝደንት ኢሳያስ 'ለለውጥ ጥድፊያ አያስፈልግም' ሲሉ ተደመጡ፤ ሰኔ • ሰኔ 12/2011 - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኤርትራ ልዑክ ጋር ተገናኙ። ልዑኩን እየመሩ የመጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኡስማን ሳልሕና የፕሬዝደንቱ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ ነናቸው። ባለፉት 12 ወራት ኢትዮጵያ ሆነ ኤርትራ በውስጥ ሃገር ፖለቲካ የተረጋጋ የሚባል ጊዜ አልነበራቸውም፤ ስኬታማ ተብለው ሊጠቀሱ የሚችሉ ሥራዎች መሠረታቸው ሳይዘነጋ። ነገር ግን ሁለቱ ሃገራት ብዙ የተባለለትን የሰላም ስምምነት በአግባቡ አልተጠቀሙበትም ሲሉ የሚተቹ በርካቶች ናቸው፤ ከዳያስፖራው ማሕበረሰብ ጫና የበረታባቸው ፕሬዝደንት ኢሳያስ 'ለውጥ ጥድፊያ አይወድም' ቢሉም ቅሉ። ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያ ጉዟቸው ምን ይመስላል?
news-55700768
https://www.bbc.com/amharic/news-55700768
ሱዳን ዳርፉር ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት 83 ሰዎች ተገደሉ
በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ግዛት በሁለት ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት በትንሹ 83 ሰዎች ተገድለዋል።
የሱዳን ዜና አገልግሎት የሐኪሞች ማኅበርን ጠቅሶ እንደጻፈው ግጭቱ በዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ ኢል ገነይና ቅዳሜ ዕለት ነው የተከሰተው። የግጭቱ መነሻ አንድ ሰው በጩቤ ተወግቶ መገደሉ ነው ተብሏል። አሁን ግጭቱን ተከትሎ በዳርፉር ሰዓት እላፊ የታወጀ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሒ ሐምዶክ አንድ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ግጭቱን እንዲመረምር ወደዚያው ልከዋል። በፈረንጆች በ2003 ዓ/ም የጀመረው የዳርፉር ግጭት በሚሊዯን የሚቆጠሩ ሕዝቦችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰላም አስከባሪ ኃይል ገብቶ የማረጋጋት ሥራ ሰርቷል። የሰላም ንግግሮችም ቀጥለዋል። ሆኖም አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ነው። የቅዳሜ ግጭት የተቀሰቀሰው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የአፍሪካ ኀብረት የሰላም ማስከበሩን ተግባር ለ13 ዓመታት ካስጠበቁ በኋላ ለሱዳን አስረክበው መውጣታቸውን ተከትሎ ነው። ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ በኢል ገነይና ከተማ የአረብ ዝርያ ያላቸው አርብቶ አደሮች አረብ ካልሆኑት ቡድኖች ጋር ተጋጭተው ደም ፈሷል። የቅዳሜው ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸው ብቻ ሳይሆን መቶ ስድሳ ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ያደረገ ነው። ግጭቱ በካምፕ ውስጥ ተጀምሮ በኋላ ላይ ግን የታጠቁ ሚሊሻዎችን እንዳሳተፈ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ብዙዎቹን በዳርፉር የሚንቀሳቀሱ አካላትን ያሳተፈ የሰላም ስምምነት የተፈረመው ባለፈው ዓመት ነበር። ሆኖም ስምምነቱ ሁሉንም ተፎካካሪ ኃይሎችና ጎሳዎችን ያሳተፈ አልነበረም። በዓለም ላይ ከፍተኛ መፈናቀልን አስከትሏል ከሚባሉ ግጭቶች አንዱ የዳርፉር ጦርነት ነው። የአረብ ዘርያ ባላቸውና አረብ ባልሆኑ ጎሳዎች መካከል በሚቀሰቀስ የጥቅም ግጭት በርካቶች ጭዳ ሆነዋል። የአረብ ዝርያ ያለባቸው ወታደሮችን የሚዘወረው አደገኛው የጃንጃዊድ ሚሊሻ ገድሏቸዋል የሚባሉ መቶ ሺህዎች አሁንም ድረስ ፍትሕ አላገኙም። ኦማር ሐሰን አልበሽር ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት በተቀሰቀሰው ግጭት 300ሺህ ሰዎች በግጭቱ ተገድለው 2 ሚሊዯን ተኩል ሕዝቦች ተፈናቅለዋል። አልበሽር በጦር ወንጀል ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የክስ ወረቀት እንዲቆርጥባቸው ያደረገውም ይኸው ነበር። አልበሽር በ2019 በሕዝባዊ ተቃውሞ ከሥልጣናቸው ሲነሱም በተቃውሞ እንቅስቃሴው የዳርፉር ጉዳይ ትልቅ የቅስቀሳ አጀንዳ ሆኖ ነበር። በቅርቡ ለቅቆ የወጣው የዳርፉር የሰላም አስከባሪ ቡድን ኢትዮጵያ ተሳትፋበት እንደነበር አይዘነጋም።
50709582
https://www.bbc.com/amharic/50709582
ከአሥመራ መጥቶ ባሕር ዳርን ያስዋበው ዘምባባ
አዛውንቱ አቶ ዋሴ አካሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፤ የባህር ዳር ልዩ ምልክት የሆነውን ዘንባባ በመትከል እና በመንከባከብ ከፍተኛውን ድርሻ ተወጥተዋል።
የባሕር ዳር መለያ የሆኑትን ዘምባባዎች ማን ተከላቸው? አቶ ዋሴ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ሁለት ክፍል ቤቶችን በራሳቸው ቦታ ላይ አሠርቶ እንዳስረከባቸው የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት አስነብቧል። አቶ ዋሴ ከጥቂት ወራት በፊት ከቢቢሲ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ከዚህ በታች ይመልከቱ። ከ50 ዓመት በላይ በቆየው የሥራ ህይወታቸው በተለያዩ ሙያዎች ውስጥ አገልግለዋል። "ምን ያልሰራሁበት አለ መሃንዲስ ክፍል፣ እሳት አደጋ፣ የመንግሥት ካዝና መጠበቅ ያለሰራሁት አይገኝም" ይላሉ። "...እሳት ሲነሳ መኪና የብረት ቆብ እና የብረት ዝናር አለ አጥፍተን እንመለሳለን ማታ የለም ቀን የለም" ሲሉ ያስታውሳሉ። በተጨማሪም የባህር ዳር የጽዳት እና አትክልት ኃላፊ በመሆንም አገልግለዋል። • ክፍል 1 ፡በፅኑ የታመመው የዓባይ ወንዝ • ባህር ዳር፡ ዘመቻ 90 ደቂቃ በዚህ ወቅት ነው ባህር ዳር የምትታወቅበትን ዘንባባዎች ለመትከል እና ለመንከባከብ እድል ያገኙት። አቶ ዋሴ ስለዚህ ጉዳይ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ዘርዘር አድርገው አውግተዋል። ስንት ዓመትዎ ነው? 95 ዓመቴ ነው። ልጆች አለዎት? 10 ልጆች ነበሩኝ 4 በህይወት የሉም። የት የት ሠሩ? ምን ያልሠራሁበት አለ መሃንዲስ ክፍል እሳት አደጋ ዘብ የመንግሥት ካዝና መጠበቅ ያለሰራሁት አይገኝም። እሳት ሲነሳ የብረት ቆብ እና የብረት ዝናር አለ አጥፍተን እንመለሳለን፤ ማታ የለም፣ ቀን የለም። ምን ያህል ዓመት ሠሩ? አሁን ጡረታ ነኝ በ55 ዓመቴ ጡረታ ወጣሁ። ብዙ ነበርን አብረን የምንሠራው። ከእኔ ጋር እነ ሙሼ ጸጋ፣ አበበ አላምረው፣ እነ አዲስ ያየህ. . . ምንኑን እቆጥረዋለሁ። አሁን 10 አይሞሉም [በህይወት] ያሉት። እንዴት ነበር የባህር ዳር ዘንባባን የመትከል ሃሳቡ የመጣው? የጽዳት እና አትክልት ኃላፊ ነበርኩ። ፊታውራሪ ሐብተማርያም [የባህር ዳር አስተዳዳሪ ነበሩ] መጥተው ባህር ዳርን ሲያስተዳድሩ የዘንባባ ችግኙን አስመጡት። በስምንት መኪና ነው ከአሥመራ የመጣው። • ትኩረት የተነፈገው የባህር ዳር መለያ ባህላዊ ጥበብ በዚያ ወቅት 50 ሰው በስሬ አሠራ ነበር። ዘንባባው ከዚህ [አጂፕ ከሚባለው የባህር ዳር ሰፈር] እስከ ኳስ ሜዳ ከኳስ ሜዳ እስከ ጢስ አባይ መንገድ ተተከለ። ኋላ ሲደረጅ ከሥር ውሃ ይጠጣል፤ ማንም ቆሻሻ አይጥልበትም። በስር በስር እየሆነ ውሃ ይጠጣ ነበር። ሌላ ደግሞ በራሱ ቀይ የሚያፈራ ይሄን ሁሉ በደንብ እይዝ ነበር። ዛሬ ከተማይቱ ከተማ ሆነች። መቼ ነው ዘንባባዎቹ የመጡት? ዘንባባዎቹ በ1949 ዓ.ም ከአስመራ ነው የመጡት። ዘንባባውን ያከፋፈልኩበት መዝገብ እስካሁን ድረስ አለ። በወቅቱ የዘንባባዎቹ መተከል ሰዉ እንግዳ ሆኖበት ነበር። አሁን ግን ይኸው የባህር ዳር ከተማ ጌጥ ለመሆን በቅቷል። እኔ ወጣ ብዬ ሳየው ደስ ይለኛል። በተለይ በክረምት ወቅት በጣም ደስ ነው የሚለኝ። እንግዳ ነገር ነው፤ በጣም የሚያስገርም ነው። መቼ መትከል ተጀመረ? ከዛሬ 63 ዓመት በፊት ነው ዘንባባው እንደመጣ ወዲያውኑ ነበር መትከል የተመጀመረው። አስታውሳለሁ መትከል የተጀመረው ጥቅምት 01/1949 ዓ.ም ነበር። እርስዎ ከሠራተኞቹ ጋር አብረው ይሠሩ ነበር? ዋናው ማን ሆነና። አብሬ በል እንደዚህ ትከል፤ እንደዚህ አድርግ ውሃ ስጥ እል ነበር። ውሃ የሚሰጥ በነጋታው ነው። ይሄን ሁሉ የተከታተልኩት እኔ ነኝ፤ የሚተክሉትን ሃምሳ ሰዎች በሙሉ እኔው ነበርኩ የማስተባብረው። • ሀሁ አስቆጣሪው ጃማይካዊ በስር ስር ምግብ እየሰጠን አለ። አሁን ደግሞ ተረካቢዎች ጥሩ ይዘውታል። ወጣ ብዬ ሳየው በጣም ደስ ይለኛል። ከዚህ እስከ ኳስ ሜዳ ሲያዩት ደስ ሲል። የሚያልፍ የሚያገድመው እንዳንጋጠጠ ነው። የሚመጣው ባለስልጣን ጋዜጠኛ ሁሉ አመስግኖ መርቋት [ባህር ዳርን] ይሄዳል። እኔ በዚያ ወቅት ሁሉንም ነገር ነበር የምሠራው። በህልምም በእውንም ይታየኛል። የማስበው ስለከተማዋ ጽዳት ነው። ለዚህ ሥራ የተሰጠን ምስክር ወረቀትም ነበረ ጠፋ እንጂ አሁን፤ ሁሉ ነገር ሲያልፍ ይገርማል። እርጅና መጣ ይህችን 95 ዓመት እንደምንም ብዬ ባልፋት ጥሩ ነው። ፊታውራሪ ምን ይሉ ነበር? ፊታውራሪ ይጠራሃል ይላሉ ሄጄ ጠጅ ጠጥቼ ጮማ በልቼ እመጣለሁ። ምን ተደረገልዎ? አሁን በዚህ ምክንያት ቤት ይሠራለት ተብሎ ሦስት ክፍል ቤት ተጀምሮልኛል። ቤትዎስ ዘንባባ ተክለዋል? ለቤቴ አልተከልኩም ለከተማው ነው እንጂ የተከልኩት።
news-49950128
https://www.bbc.com/amharic/news-49950128
የፍሎሪዳ ዳኛ፡ እንቅልፍ ጥሎት ከችሎት የቀረው 'ዳኛ' ለእስር ተዳረገ
እንቅልፍ ጥሎዎት በሕይወትዎ ያመለጥዎት መልካም እድል አሊያም የተቀጡበት አጋጣሚ ይኖር ይሆናል። ከወደ ፍሎሪዳ የተሰማው ግን በርካቶችን ያነጋገረ ነው።
እንቅልፍ ጥሎት ከተራው ህዝብ ተመርጠው ለዳኝነት ከሚቀመጡ ግለሰቦች(ጁሪ) መካከል ከችሎት የቀረው አንደኛው 10 ቀናትን በእስር እንዲያሳልፍ ተበይኖበታል። • ስለ እንቅልፍ የተሳሳቱ አመለካከቶች • እንቅልፍ እንዲህ ጠቃሚ ነገር ኖሯል? ከዌስት ፓልም ቢች የመጣው የ21 ዓመቱ 'ዳኛ' ዲንድሬ ሶመርቪሌ ዳኛ ሆኖ እንዲያገለግል የተመረጠው ባሳለፍነው ነሃሴ ወር ነበር። ዲንድሬ ከተራው ህዝብ ተመርጠው ለዳኝነት ከሚቀመጡ ግለሰቦች (ጁሪ) ስድስት 'ዳኞች' አንዱ ሲሆን ችሎቱ የመጀመሪያው ነበር። ይሁን እንጂ ገና በመጀመሪያው ቀን የፍርድ ቤት ውሎ እንቅልፍ ጥሎት በትንሹ ለሁለት ሰዓታት ያህል የፍርዱን ሂደት አስተጓጉሎታል። ይህም ሲሆን ፍርድቤቱን አላሳወቀም ተብሏል። ግለሰቡን ፍርድ ቤት ያቆሙት ዳኛ ጆን ካሰትሬኔክስ ከ10 ቀናት እስሩ በተጨማሪ 150 ሰዓታት ከማህበራዊ አገልግሎት እንዲታገድ እና 223 ዶላር የገንዘብ ቅጣት እንዲጣልበት ወስነዋል። የተጣለበትን ጊዜ በእስር ያሳለፈው ግለሰብ ውሳኔው የተጋነነ ነው ሲል በፍርዱ ላይ ቅሬታውን አሰምቷል። ባሳለፍነው አርብ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ "አሁን ስሜ በጥፋት ተመዝግቧል፤ ወንጀለኛ እንደሆንኩ ነው የሚሰማኝ። ከዚህ በኋላ ለሚዲያ በምሰጠው እያንዳንዱ ቃለ ምልልስ ሁሉንም ነገር ማብራራት ይጠበቅብኛል" ሲል ለአገሪቷ መገናኛ ብዙሃን ተናግሯል። ዲንድሬ ሶመርቪሌ የእስር ጊዜውን አጠናቋል ዲንድሬ ለመገናኛ ብዙኃን እንዳስረዳው የማንቂያ ደወል ሞልቶ የተኛ ቢሆንም ከሰዓታት በኋላ ሲነቃ ችሎቱ የሚካሄድበትን ሰዓት እንደዘነጋው መገንዘቡን ያስረዳል። በሰዓቱ ደንግጦ ስለነበር ስለ ሁኔታው ስልክ በመደወል ለፍርድ ቤቱ ሳያሳውቅ ቀርቷል። እሱ አንደሚለው ከዚያ በኋላ በከተማዋ መናፈሻ እና መዝናኛ ክፍል ሥራ ስለነበረው ወደዚያው አምርቷል። ለድርጊቱ ቀላል ቅጣት ቢጠብቅም የከፋ ሆኖ አግኝቶታል። • ለ21 ዓመታት የኢትዮጵያን ቅርስ ደብቀው ያቆዩት ኢትዮጵያዊ ፖሊስ ግለሰቡ ከአያቶቹ ጋር የሚኖርበት ቤት ድረስ በመሄድ የመጥሪያ ወረቀቱን አቀብሎታል። ወደ ፍርድ ቤቱም ካቀና በኋላ "እውነቱን ለመናገር አዎ እንቅልፍ ጥሎኝ ነበር፤ ግን ይህንን ያህል መዘዝ ያስከትላል ብየ አላሰብኩም" ብሏል። አክሎም ከዚህ ቀደም በምንም ዓይነት ጉዳይ ፍርድ ቤት ቀርቦም ሆነ ታስሮ እንደማያውቅ አስረድቷል። ይሁን እንጅ ዳኛው ካስተርኔክስ ሃሳባቸውን አልወጡም። "አንተ ትመጣለህ በማለት በትንሹ ለአንድ ሰዓት ያህል ጠብቀንሃል፤ ግን አልመጣህም" ሲሉ ከውሳኔያቸው ፈቀቅ እንደማይሉ በአፅንኦት ገልፀዋል። ዳኛው አክለውም 100 ቃላት የሚሆን የይቅርታ ደብዳቤ እንዲፅፍ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
news-48394951
https://www.bbc.com/amharic/news-48394951
ፌስቡክ ሦስት ቢሊዮን አካውንቶችን አገደ
ፌስቡክ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከጥቅምት እስከ መጋቢት ድረስ በነበሩት ስድት ወራት ውስጥ ከሦስት ቢሊየን በሚልቁ ሐሰተኛ አካውንቶችን በማገድ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
በተጨማሪም ከሰባት ሚሊየን የሚበልጡ "የጥላቻ ንግግሮችን" የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን ማስወገዱንም ይፋ አድርጓል። • ፌስቡክ ግላዊ መረጃን አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ ፌስቡክ ይህንን የገለጸው ከጥቅምት እስከ የካቲት ወር በማኅበራዊ መድረኩ በኩል የተሰራጩ ምን ያህል ተቀባይነት የሌላቸው መረጃዎችና የፌስቡክ ገጾች ላይ እርምጃ እንደወሰደ ባስታወቀበት ሪፖርቱ ላይ ነው። በፌስቡክ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፌስቡክ ገጾች ላይ እንዲሰረዙ በተደረጉ መልዕክቶች ምክንያት ምን ያህሎቹ ማብራራሪያ እንደጠየቁና ምን ያህሎቹም ምርመራ ከተደረገባቸው በኋላ ወደገጾቻቸው እንዲመለሱ እንደተደረገ ይፋ አድርጓል። • ፌስቡክ የጽንፈኛ አመለካከት አራማጆችን ሊያግድ ነው ፌስቡክ እንዳለው፤ እንዲወገዱ የተደረጉት ሐሰተኛ አካውንቶች ቁጥር መጨመር ምክንያቱ "መጥፎ" ያላቸው አካላት የተለየ ዘዴን በመጠቀም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ገጾች መክፈት በመቻላቸው ነው። ነገር ግን ፌስቡክ ከእነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ "ጉዳት ለማድረስ" የሚያስችላቸውን አጋጣሚ ከማግኘታቸው በፊት በተከፈቱ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በመለየት እንዲሰረዙ ማድረጉን አሳውቋል። • ፌስቡክ የምንጠቀምበት ሰዓት ሊገደብ ነው የማኅበራዊ መገናኛ መድረኩ ጨምሮ እንደገለጸው፤ እፆችና የጦር መሣሪያዎችን የመሳሰሉ ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ነገሮች ሽያጭ የተመለከቱ ምን ያህል መልዕክቶች እንዲነሱ እንዳደረገ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል። ፌስቡክ አሁን ያወጣው ሪፖርት ላይ እንዳመለከተው፤ ባለፉት ስድት ወራት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የጦር መሣሪያ ሽያጭን የተመለከቱ መልዕክቶች እንዲነሱ አድርጓል።
55246625
https://www.bbc.com/amharic/55246625
የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል ያሳሰባት ጃፓን ውሃ አጣጭ ለሚያገናኙ ገንዘብ ልትሰጥ ነው
የሕዝብ ቁጥር መቀነስ ያሳሰባት ጃፓን ጥንዶችን ለሚያገናኝ መተግበሪያ የገንዘብ ድጎማ እንደምታደርግ አስታውቃለች።
ሰው ሠራሽ ልህቀት (አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ) ተጠቅመው ጃፓናውያን የፍቅር ጓደኛ እንዲያገኙ የሚያግዙ ግዛቶች ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ የገንዘብ ማበረታቻ ከጃፓን መንግሥት ይሰጣቸዋል። አምና በጃፓን የተወለዱ ልጆች ቁጥር ከ865,000 በታች ሆኗል። ቁጥሩ እስካሁን ከታየው እጅግ ዝቅተኛው ነው። ጃፓን የአዛውንቶች አገር ሆናለች። በዓለም ዝቅተኛ የወሊድ መጠን ካላቸው አንዷም ናት። ለመተግበሪያዎች የገንዘብ ፈሰስ ማድረግ የልጆችን ቁጥር ለመጨመር ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል ይጠቀሳል። በሚመጣው ዓመት ለሚተገበረው ፕሮጀክት 19 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ኤኤፍፒ ዘግቧል። ጥንዶች አገናኞች ሰዎች ውሃ አጣጭ እንዲያገኙ የሚያግዙ ተቋሞች ሰው ሠራሽ ክህሎት መጠቀም ጀምረዋል። ከዚህ ቀደም በሰው ኃይል ታግዘው ይሠሩ የነበሩት ተቋሞች፤ ቴክኖሎጂው የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ያምናሉ። የፍቅር አጋር ለማግኘት የሚቀርቡ ማመልከቻዎችን በተሻለ መንገድ መገምገምም ይችላሉ። እነዚህ ተቋሞች ሰዎችን ሲያገናኙ ከግምት የሚያስገቡት እድሜ፣ ወርሀዊ ገቢና የመሳሰሉትን ነው። እነዚህ መስፈርቶች ደግሞ ትክክለኛውን አቻ አያገናኙም። መንግሥት ለመተግበሪያዎች ድጋፍ ማድረግ ሲጀምር አሠራሩ ይዘምናል ተብሎ ይጠበቃል። ሰዎች የትርፍ ጊዜያቸውን በምን ያሳልፋሉ? የሕይወት መርሀቸው ምንድን ነው? በሚሉት መስፈርቶች መሠረት እንዲገናኙ ይደረጋል። አንድ የምክር ቤት አባል ለኤኤፍፒ "ኤአይን ተጠቅመው ጥንዶችን ለሚያገናኙ ግዛቶች ድጋፍ ለማድረግ አቅደናል። የልጆች ቁጥርን ለመጨመር ይረዳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። እአአ 2017 128 ነበረው የጃፓን የሕዝብ ቁጥር በምዕተ ዓመቱ መጨረሻ ደግሞ ቁጥሩ ወደ 53 ሚሊዮን እንደሚወርድ ተፈርቷል። እአአ 2017 የጃፓን የሕዝብ ቁጥር ወደ128 ሚሊዮን ያሽቆለቁላል የሚል ስጋት አለ። በምዕተ ዓመቱ መጨረሻ ደግሞ ቁጥሩ ወደ 53 ሚሊዮን እንደሚወርድ ተፈርቷል። "የፍቅር ግንኙነት መመስረት ካልፈለጉ ውሃ አጣጭ መተግበሪያው ውጤት አይኖረውም" የማኅበራዊ፣ ባህላዊ እና ሕክምና ጥናት ባለሙያዋ ዶ/ር ሳችኮ ሆሪጉቺ፤ መንግሥት ጥንዶችን የሚያገናኙ መተግበሪያዎችን ከመደገፍ የተሻለ አማራጭ አለው ትላለች። እንደ ምሳሌ የምትጠቅሰው ወጣቶች የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ ማስቻልን ነው። ባለሙያዋ በማስረጃነት የምታቀርበው አንድ በቅርቡ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወጣቶች የፍቅር ግንኙነት የመመስረት ፍላጎት አያሳዩም። "የፍቅር ግንኙነት መመስረት ካልፈለጉ ውሃ አጣጭ መተግበሪያው ውጤት አይኖረውም" ብለዋል። ባለ ሥራ ጃፓናዊ እናቶች ድጋፍ እንደማያገኙ ብዙ ተንታኞች ይናገራሉ። ሴቶች ልጅ እንዲንከባከቡ፣ የቤት ሥራን እንዲያከናውኑና ከነዚህ በተጨማሪ የቢሮ ሥራም እንዲሠሩ ይጠበቃል። መንግሥት ሴቶች የሙሉ ጊዜ ሥራ እንዲኖራቸው አበረታታለሁ ቢልም የፆታ ክፍተቱ ሰፊ ነው። አምና የወጣ የፆታ እኩልነት ሰንጠረዥ ላይ ጃፓን ከ153 አገሮች መካከል 121ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ከዛ ቀደም ከነበራት 11 ደረጃ ዝቅ ማለቷን የወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም አሃዝ ያመለክታል።
news-52705132
https://www.bbc.com/amharic/news-52705132
ኮሮናቫይረስ፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት
ከሰሞኑ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሚከናወንበት ጉባ ወረዳ አንድ በቫይረሱ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ሚንስቴር እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጡት ዕለታዊ መግለጫ ላይ ማስታወቃቸው ተሰምቷል።
የግድቡ ግንባታ በሚካሄድበት ወረዳ ውስጥ በበሽታ የተያዘ ሰው መገኘት በግንባታው ላይ ምን አይነት ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል? ሠራተኞቹስ በምን አይነት ስሜት ውስጥ ይገኛሉ የሚሉ ጥያቄዎችን አጭሮ ነበር። ከ7000 በላይ ሰራተኞች ያሉት የአፍሪካ ግዙፉ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ሊያስከትልበት የሚችለውን ጫና ለመቋቋም ምን እየተደረገ ነው ስንል የፕሮጀክቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮን አነጋግረናል። • ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያን ሃሳብ አልቀበልም አለች "ፕሮጀክቱ ምንም እንኳ ከጉባ ወረዳ ቢገኝም፤ በቫይረሱ መያዙ በምርመራ የተረጋገጠው ግለሰብ የሚኖርበት ቦታ እና ፕሮጀክቱ ያለበት ስፍራ ይራራቃሉ" ይላሉ። የጉባ ወረዳ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወረዳዎች ሰፊው መሆኑን ያስታወሱት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "በቫይረሱ የተያዘው ሰው የተገኘበት ፓዊ በሚባል በቫይረሱ ተጠርጥረው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች መካከል ነው። በዛ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ደግሞ ከሱዳን የሚመጡ ሰዎች ተለይተው የሚቆዩበት ቦታ ነው። ከፕሮጀክታችን ጋር አይገናኘም" ብለዋል። ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በኋላ በግንባታ ሂደቱ ላይ ምን ተቀየረ? የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ ተከትሎ አሰሪዎች ሰራተኞቻቸው ርቀታቸውን ጠብቀው በጥንቃቄ እንዲሰሩ አልያም ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ትዕዛዝ ሲያስተላልፉ ታይተዋል። በርቀት ሆኖ ሥራን ማከናወን ከማይቻልባቸው መካከል አንዱ የግንባታ ሥራ ነው የሚሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "ጥንቃቄን በማጠናከር ከመስራት ውጪ ሠራተኞችን መቀነስ ወይም ከርቀት ሆነው እንዲሰሩ ማድረግ አልቻልንም" ይላሉ። "ሠራተኞች በሥራ ቦታ ላይ ርቀታቸውን እና ንጽህናቸውን ይጠበቃሉ። የፊት እና አፍ መሸፈኛ ጭንብል እያደረጉ ነው" ብለዋል። "እንደ ከዚህ ቀደሙ የፕሮጀክት ግንባታ ጉብኝት እንዲቆም ተደርጓል። እንዳጋጣሚ ወደ ፕሮጀክቱ የሚገባ ካለ ለ14 ቀን ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገባ ተደርጎ እና ከክትትል በኋላ ነው ከሠራተኞች ጋር የሚቀላቀለው" ይላሉ የፕሮጅክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ። • ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ ኢንጀነር ክፍሌ እንደሚሉት ሌላው ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉት የግንባታ ግብዓቶችን ጭነው የሚመጡ መኪኖች ናቸው። እንደ ኢንጂነሩ ገለጻ ከሆነ ተሽከርካሪዎቾ ወደ ግንባታው ከመቃረባቸው በፊት በጸረ-ተዋሲያን እንዲጸዱ ይደረጋሉ። ሠራተኞቹም ቢሆኑ ከአሽርከርካሪዎቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖራቸው ይደረጋል። ለቻይኖች አዲስ ዓመት በዓል የፕሮጀክቱ ሠራተኞች የነበሩ ቻይናውያን ወደ አገራቸው ተጉዘው እንደነበረ ያስታወሱት ኢንጅነር ክፍሌ፤ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ በአዲስ አበባ ለ14 ቀናት በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ መቆየታቸውን እና ወደ ፕሮጀክቱ ሥፍራ በልዩ አውሮፕላን እንደተመለሱ፤ በግድቡ ግንባታም ክትትል ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል። ከቻይናውያን በተጨማሪ በህዳሴ ግድብ ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ የጣሊያን፣ ጃፓን እና ጀርመን ዜጎች እንዳሉ ይታወቃል። ኢንጅነር ክፍሌ የቫይረሱን መከሰት ተከትሎ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ሆነው ወደ ትውልድ አገራቸው የተመለሱ የውጪ አገር ዜጎች እንደሌሉ ተናግረዋል። ኮሮናቫይረስ በፕሮጀክቱ ውስጥ ቢከሰት ዝግጅቱ ምን ይመሥላል? መንግሥት ለዚህ ፕሮጅከት ከፍተኛ ትኩርት ሰጥቷል ያሉት ኢንጅነር ክፍሌ፤ "በጥበቃ ረገድም ተጨማሪ የጸጥታ ኃይል ተመድቦ የደህንነት ስራውን በቅርበት እያከናወኑ ይገኛሉ። የጤና ሚንስቴር እና አሶሳ የሚገኘው ማዕከል ለፕሮጀክቱ ሠራተኞች ልዩ ትኩረት ሰጥተዋል" ብለዋል። በሽታው እንዳይከሰት የቅድመ ጥንቃቄ ሠራዎች መሠራታቸውን ቀጥለዋል ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ "ድንገት ኮሮናቫይረስ ቢከሰት እንኳ እዚህ ያዘጋጀነውን የህክምና ማዕከል እና በአሶሳ ያለው ለመጠቀም ከስምምነት ላይ ደርሰናል" ብለዋል።
news-54666317
https://www.bbc.com/amharic/news-54666317
የአየር ብክለት፡ ትራምፕ ስለ ሕንድ የአየር ብክለት የተናገሩት በርካቶችን አስቆጣ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሕንድ ዜጎች ስለሚነፍሰው አየር በሰጡት አስተያየት ምክንያት በርካታ ሕንዳውያን ቁጣቸውን እየገለፁ ነው። ፕሬዝዳንቱ በምርጫ ክርክር ወቅት ነበር የሕንድን አየር 'አስጸያፊ' በማለት የገለጹት።
የፕሬዝዳንቱ አስተያየት ቁጣም መገረምም የፈጠረ ሲሆን አንዳንድ ሕንዳውያን እንደውም ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሆነ ነገር እንዲያደርጉ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። ሌሎች ደግሞ የዋናዋ ከተማዋ ደልሂ አየር በጣም የተበከለ እንደሆነና ከዓለም እጅግ መጥፎው አየር እንደሆነ ሀሳባቸውን ገልጸዋል። በቅርብ ሳምንታት የከተማዋ አየር ንጽህና በእጅጉ እየተባባሰ እንደመጣና ነዋሪዎቹ የመተንፈስ እክል ጭምር እያጋጠማቸው እንደሆነ ተገልጾ ነበር። የሕንድ የአየር ብክለት ደረጃ ከፍተኛ የሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን አየሩ በካይ የሆኑ ንጥረነገሮችን በውስጡ በብዛት የያዘ ነው ተብሏል። በዋና ከተማዋ ያለው የብክለት መጠን ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ከሚያስቀምጠው የጤናማ አየር ልክ በ12 እጥፍ ከፍ ያለ ነው። ''ቻይናን ተመልከቱ፤ እንዴት አስጸያፊ እንደሆነ። ሕንድንም ተመልከቱ። እዛም ቢሆን አየሩ አስጸያፊ ነው። ከፓሪሱ የአየር ጸባይ ለውጥ ድርድር ላይ ጥዬ የወጣሁት በማይገባ መልኩ በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እየከሰርን ስለነበረ ነው'' ብለዋል። ምንም እንኳን ቻይናን የተመለከቱት አብዛኛዎቹ አስተያየቶች እውነት ባይሆኑም ስለሕንድ የተናገሩት ግን በርካቶችን አስማምቷል። በሰሜናዊ ሕንድ በርካታ ከተሞች የአየር ብክለት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ለሕዳር እስከ የካቲት ባሉት ወራት ደግሞ አርሶ አደሮች ለቀጣዩ ዓመት ማሳቸውን ለማዘጋጀት በርካታ ማሳዎችን በእሳት ያቃጥላሉ። በተጨማሪም በሕንድ ያለው የመኪና ጭስ ብክለት ከፍተኛ ሲሆን ትልልቅ የማምረቻ ፋብሪካዎችም ቢሆኑ በካይ ንጥረነገሮችን ወደ ከባቢ አየር በብዛት እንደሚለቁ ይታወቃል። በነዚህ ወራት ደግሞ ሕንዳውያን የተለያዩ በአላትን ለማክበር በማሰብ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ርችት ወደ ሰማይ ይተኩሳሉ። ይህ ደግሞ በዚህ ወቅት የአየር ብክለትን ይጨምራል። ባለፈው ዓመት በህንዷ ዋና ከተማ ዴልሂ ባጋጠመ የአየር ብክለት ምክንያት ሃላፊዎች የማህበረሰብ ጤና ድገተኛ አደጋ አዋጅ ለማወጅ መገደዳቸው ይታወሳል። በተጨማሪም በከተማዋ ለሚገኙ 5 ሚሊየን ተማሪዎች አፍ መሸፈኛ ማስክ ሲከፋፈል ነበር። የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ባስቀመጠው መለኪያ መሰረት ጎጂ ጥቃቅን አካላቱ በአንድ ቀን ውስጥ ከ 25 ማይክሮግራሞች መብለጥ የሌለበት ሰሆን በዴልሂ ኤር ውስጥ ግን 533 ማይክሮግራሞች የበለጠ ጎጂ ንጥረነገር ወደ ሳንባ ይገባል። የፕሬዝዳንቱን አስተያየት ተከትሎ ፖለቲከኞችና ታዋቂ ሰዎች አስተያየታቸውን እየሰጡ ሲሆን የሕንድ ተቀናቃኝ ፓርቲ ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ካፒል ሲባል ትራምፕ ይህንን ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ካላቸው ቅርበትና ጓደኝነት ነው ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል።
news-53296770
https://www.bbc.com/amharic/news-53296770
በሶማሊያ አልሽባብ ምግብ ቤት ላይ ባደረሰው ጥቃት ስድስት ሰዎች ተገደሉ
በሶማሊያ ደቡባዊ ከተማ ባይዶአ በአንድ ምግብ ቤት ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ገለፁ።
በሌላም በኩል በዋና መዲናዋ ሞቃዲሾ ወደብ አቅራቢያ በአጥፍቶ ጠፊ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል። እስላማዊ ታጣቂ ቡድኑ አልሽባብ ከሁለቱም ጥቃቶች ጀርባ እንዳለ ተናግሯል። ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎቹ በባይዶአ ምግብ ቤቱ ውስጥ ስብሰባ እያካሄዱ የነበሩ ግብር ሰብሳቢዎችና ወታደሮችን ኢላማ አድርገው እንደነበር ተናግረዋል። በጥቃቱ ሁለት ወታደሮች መገደላቸውን ታጣቂ ቡድኑ ቢያስታውቅም ባለሥልጣናት ግን ሁሉም ተጎጂዎች ሰላማዊ ናቸው ብሏል። የሞቃዲሾ ባለሥልጣናት ቦምብ የተጠመደበት መኪና በፍተሻ ጣቢያው ላይ አልቆም ሲል ተኩስ ከፍተው እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል። አጥፍቶ ጠፊው መኪናውን እያሽከረከረ ከወደቡ ፊት ለፊት ያለውን ፖሊስ ጣቢያ ለመምታት ቢሞክርም የፀጥታ አካላት እንደተኮሱበትና ከዚያም ተሽከርካሪው እንደፈነዳ አክለዋል። በዚህም ሁለት ፖሊሶችና በአካባቢው ሲተላለፉ የነበሩ አምስት ሰላማዊ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንድ የወደቡ ሰራተኛ “በወደቡ ውስጥ የእንጨትና የብረት ቁርጥራጮች በሁላችንም ላይ ወደቁብን፤ ከዚያም ተኩስ ሰማን” ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ለሮይተርስ ተናግረዋል። በአሜሪካ የሚደገፈው የሶማሊያ መንግሥት ላለፉት አስር ዓመታት አገሪቷን ለመቆጣጠር ከአልሽባብ ጋር እየተፋለመ ይገኛል።
news-52526790
https://www.bbc.com/amharic/news-52526790
በጂቡቲ የኮቪድ-19 መጨመር ለአፋር ክልል ስጋት መሆኑ ተነገረ
በጂቡቲ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር ለአፋር ክልል ስጋት መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
ሰመራ ከተማ አፋር የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ በተለይ ለቢቢሲ እንደተናግሩት "ስጋቱ በጣም ከባድ ነው ምከንያቱም ጂቡቲ ውስጥ በርካታ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ተገኝተዋል። ከክልሉ ሕዝብ ጋር ተመሳሳይ ባሕልና አኗኗር ስላለ ወረርሽኙ ድንበር ሊሻገር የሚችልበት ሰፊ ዕድል አለ" በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። አስካሁን ድረስ አንድ ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ባላት በጂቡቲ ውስጥ ከ1100 በላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን፤ የህሙማኑ ቁጥርም በየዕለቱ እየጨመረ እንደሚሄድ የአገሪቱ መንግሥት የሚያወጣው መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያ ለገቢና ወጪ ንግዷበዋነኝነት ከምትጠቀምበት የጂቡቲ ወደብን ሲሆን ሁለቱን አገራት የሚያገናኘው ዋና መንገድም በአፋር ክልል የሚያልፍ ከመሆኑ በተጨማሪ ክልሉ ከጂቡቲ ጋር ይዋሰናል። በአሁኑ ወቅት ከጂቡቲ በተለያየ ምክንያቶች ወደ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሰዎች 510 በአፋር ክልል በተዘጋጁ የለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ኃላፊው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ትላንት ብቻ "በተለያዩ መንገዶች ከጂቡቲ ወደ ክልሉ የገቡ 130 ሰዎች አሉ። ይህ ቁጥር በለይቶ ማቆያ ከሚገኙ 485 ሰዎች በተጨማሪ ማለት ነው። ከጂቡቲ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ብለዋል አቶ ያሲን። ከጂቡቲ ተመልሰው በለይቶ ማቆያ ከሚገኙ እና በጥቆማ እና ቤት ለቤት በተደረጉ ቅኝቶች 296 ናሙናዎች ወደ አዲስ አበባ ተልከው 273ቱ ነጻ መሆናቸው ሲታወቅ የሌሎቹ ውጤት እየተጠበቀ እንደሚገኝም ኃላፊው አመልክተዋል። በአፋር ክልል እስካሁን አንድ ሰው በኮሮናቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል። በገዋኔ ነዋሪ ከነበረው ግለሰብ ጋር በቅርብ ንክክኪ የነበራት ግለሰብ በተደረገላት ምርመራ ከበሽታው ነጻ ሆና ተገኝታለች። ከጂቡቲ የሚገቡ ሰዎች በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ይደረግና ቁጥራቸው ሲጨምር ናሙናዎች ተሰብስበው ወደ አዲስ አበባ ይላኩ ነበር። "ውጤቱን መጠበቅ ትንሽ ጊዜ ይፈጅ ነበር። ውጤቱ በተቻለ መጠን በየሁለት ቀኑ ወይም በ24 ሰዓት ይመጣል። ሆኖም ናሙናዎቹ ወደተለያዩ ቤተ-ሙከራዎች ስለሚላኩ ውጤቱ አንድ ላይ አይመጣም" ሲሉ ያለውን አካሄድ ገልጸዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የክልሉ መንግሥት ከፌደራል መንግሥት እና ከጤና ጥበቃ ሚንስትር ጋር በመሆን ያዘጋጀው ቤተ-ሙከራ ዛሬ ሥራ መጀመሩን አቶ ያሲን ገልጸው፤ ቤተ-ሙከራው "ለሕዝቡም ለእኛም ትልቅ እፎይታ ነው" ብለዋል። በሰመራ ከተማ ውስጥ በአፋር ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚገኘው ቤተ ሙከራ "ከ160 እስከ 200" ናሙናዎችን በየቀኑ መመርመር ይችላል ብለዋል። ክልሉ የቤት ለቤት ትምህርት እና ልየታም እያካሄደ ይገኛል። እስካሁን በ29,578 እማወራና አባወራዎች ላይ ቅኝት እንደተደረገ ያመለከቱት ምክት የጤና ቢሮ ኃላፊው ትኩሳትና ሌሎች ምልክቶች ያላቸው እየተለዩ መሆኑንም ጠቁመዋል። "ሰዉ መረጃ ቢኖረውም መጠንቀቅ ላይ አሁንም ክፍፈተት አለ። የእምነት አባቶችና ሽማግሌዎችም ከፍ ያለ ርብርብ እያደረጉ ነው። መስጅዶች ላይ ጸሎት የለም አዛን ብቻ ነው፤ ለውጥ አለ። ሥራዎች ግን ይቀሩናል" ሲሉ ገልጸዋል። በክልሉ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የነበሩ እና ለ14 ቀናት የቆዩ 143 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው ነጻ በመሆናቸው ወደ ቀዬአቸው እንደሚመለሱ አቶ ያሲን ተናግረዋል።
news-46383537
https://www.bbc.com/amharic/news-46383537
ኢትዮጵያ በዲፕሎማቶቿ ላይ ሽግሽግና ለውጥ ልታደርግ ነው
ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ያሉ ግማሽ ያህል ዲፕሎማቶቿን ቀደም ሲል ከነበሩባቸው የዲፕሎማቲክ መቀመጫዎች ወደ ሌላ ቦታ እንደሚዘዋወሩና አዲስ ከሚሾሙ አምባሳደሮች መካከልም ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚካተቱ ተጠቆመ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም እንደተናገሩት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በሃምሳ ዘጠኝ ኤምባሲ እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የሠራተኛ ድልድል አጠናቅቆ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል። የአምባሳደሮች ሹመት በቅርቡ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በመስሪያ ቤቱ ካገለገሉ ዲፕሎማቶች በተጨማሪ ምሁራንና ታዋቂ ግለሰቦችንም ያካተት እንዲሆን ይደረጋል በማለት "ምደባው ዕውቀትን እና ሙያዊ ብቃትን ብቻ መሰረት ያደረገ ነው" ብለዋል። • "ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም • ". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ የአምባሳደሮቹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰየሙ ሲሆን እነማን እንደሆኑና ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ቃል አቀባዩ ከመጥቀስ ተቆጥበዋል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በየኤምባሲው እና የቆንስላ ፅህፈት ቤቱ ካሏት 412 ዲፕሎማቶች ግማሽ ያህሉ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ይደረጋል ብለዋል ቃል አቀባዩ። "ሠራተኞች አዲሱን ምደባቸውን እንዲያውቁ ተደርጓል፤ አዲስ መዋቅር ደግሞ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ሥራ ላይ ውሏል" ያሉት አቶ መለስ በዚሁ መዋቅር መሰረት አምስት ቋሚ ተጠሪዎች ሥራ ላይ መሰየማቸውን ገልፀዋል። "የአሁኑ ድልድልና የባለፈው ሳምንት የመዋቅር ማሻሻያ መስሪያ ቤቱን ከወትሮው በተለየ ከፍ ያለ እርምጃ ነው ብለን እናስባለን" ሲሉም አክለው ተናግረዋል። ለዘመነ ሉላዊነት ከሚጠብቅበት ኃላፊነት አንፃር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ራሱን መፈተሽ እንዳለበት መገንዘቡን ያስረዱት አቶ መለስ የሚገባውን ሠራተኛ ከተገቢው የሥራ ድርሻ ጋር የማገናኘት ዓላማን ያነገበ ሽግሽግ ማደረጉን ገልፀዋል። • የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ተዋሃዱ • ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች "የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ የማሻሻያ እርምጃ ሩጫ ውስጥ ይገኛል" ያሉት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር "የዜሮ ውጥረት ፖሊሲን" እንደምትከተል አትተው ይህን ታሳቢ ባደረገ አኳኋን የካበተ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማቶች በጎረቤት አገራት እንደሚመደቡ ጠቁመዋል። "ተደራድሮ የሚያሸንፍ፣ ተናግሮ የሚያሳምን፣ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የልማት ጥረት ገንዘብ ማምጣት የሚችል ዲፕሎማት ይፈለጋል" ብለዋል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ ጥሩ ወዳጅ ማፍራት እና በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በኤምባሲዎች እና በቆንስላ ፅህፈት ቤቶች የትኩረት አቅጣጫን ለመወሰን ያገለገሉ መስፈርቶች ናቸውም ብለዋል። ይህም በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን አንደሚታለብ ላም ከማየት አባዜ መውጣት እንደሚያስፈልግም አክለው ተናግረዋል። በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር ከ2000 በላይ በተለያዩ አገራት እስር ቤት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን የማስመጣት ተግባርን በማከናወን ላይ እንደሆኑ አቶ መለስ ተናግረዋል። ኢትዮጵያዊያኑ ይመለሱባቸዋል የተባሉት አገራት የመን፣ ታንዛንኒያ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ሊቢያ ናቸው። እንደቃል አቀባዩ ገለፃ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 205 ኢትዮጵያዊያን ከየመን እንዲመለሱ ተደርጓል።
41920414
https://www.bbc.com/amharic/41920414
ትራምፕ ከዢ ጋር ስለሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ይነጋገራሉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ቻይና ባደረጉት ጉብኝት ትኩረታቸውን በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ በማድረግ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።
ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ ፓርላማ ተገኝተው ቻይና ሰሜን ኮሪያን ይበልጥ እንድታገል ከጠየቁ በኋላ ነው ቤጂንግ የደረሱት። ቻይና የሰሜን ኮሪያን ኒውክለር ፕሮግራም ልትቆጣጠረው ትችላለች ብላ ብታስብም ቤጂንግ በበቂ ሁኔታ እየተንቀሳቀስኩ ነው ብላለች። የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ትራምፕን ሞቅ ባለ ስነ-ስርዓት ተቀብለዋቸዋል። "ከታላቅ ፖለቲካዊ ድል" በኋላ ዢንን ለማግኘት በመዘጋጀታቸው ትራምፕ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ለዢ ሙገሳ ችረዋል። ትራምፕ በቻይና ምን ዓይነት አቀባበል ጠበቃቸው? ትራምፕ እና ባለቤታቸው ሜላኒያ ቤጂንግ ሲደርሱ በቀይ ምንጣፍ፣ ወታደራዊ ባንድ እና ሁለቱን ሃገራት ሰንደቅ ዓላማ በያዙ ህጻናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የቀድሞው አሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከስልጣን ከመውረዳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ወደ ቻይና ሲያቀኑ ቀይ ምንጣፍ ያልነበረ ሲሆን ይህም ታስቦ የተደረገበት ነው ተብሏል። ፕሬዝዳንት ትራምፕና ቀዳማዊ እመቤት ሜላኒያ የቻይና ነገስታት መቀመጫ የነበረችውን ፎርቢደን ሲቲን የጎበኙ ሲሆን ከሰዓት በኋላ የሻይ ግብዣ ተደርጎላቸዋል። ትራምፕ የልጅ ልጃቸው በማንዳሪን ቋንቋ ስትዘፍን የሚያሳይ ቪዲዮ ለዢ ማሳየታቸውን የቻይና መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ዢ ቪዲዮው አስደናቂ መሆኑን መናገራቸውንም ጠቁመዋል። ከሌሎች አሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በተለየ መልኩ ትራምፕና ሜላንያ ከቻይናው መሪ እና ባለቤታቸው ጋር በጋራ በፎርቢደን ከተማ እራት እንደሚመገቡ ሲ ኤን ኤን ዘግቧል። "ለማይረሳው ቀንና ምሽት" ሲሉ ሲሉ ትራምፕ ለቻይናው መሪ ምስጋናቸውን በትዊተር ገጻቸው አስተላልፈዋል።
news-52498224
https://www.bbc.com/amharic/news-52498224
ኮሮናቫይረስ፤ ለስምንት ልጆቿ ድንጋይ የቀቀለችው ኬንያዊት ሃገር ጉድ አስባለች
ስምንት ልጆቿ ጠኔ ቢበረታባቸው ጊዜ ምግብ እንዲመስላቸው ድንጋይ በብረት ድስት የቀቀለችው ኬንያዊት እናት ጉዳይ አገር ጉድ አስብሏል።
ነገሩ እንዲህ ነው፤ ፔኒናህ ባሃቲ የተሰኘችው ይህች ሴት ነዋሪነቷ በባሕር ዳርቻዋ የሞምባሳ ከተማ ነው። ፔኒናህ የስምንት ልጆች እናት ናት። ነገር ግን ባለቤቷ መሞቱ ኑሮን አክብዶባታል። ይባስ ብሎ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰውን ከሰው መለየቱ የእሷንም ኑሮ ከድጡ ወደማጡ አድርጎታል። ከዚያ በፊት በየሰዉ ቤት እየተዘዋወረች ልብስ በማጠብ ነበር የልጆቿን አፍ የምታረጥበው። ስምንት ልጆቿ እራት አይቀርብም ወይ እያሉ ሲወትወቷት ግን አንድ መላ ፈየደች። እራት እስኪቀርብ ጋደም በሉ ትላቸውና ብረት ድስት ውስጥ ድንች መሳይ ነገር ትከት ጀመር። በወቅቱ ረሃብ ያንገላታቸው ልጆቿ በሚበስለው 'ድንጋይ' ተዘናግተው እንቅልፍ በቀላሉ ሊወስዳቸው እንዳልቻለ እናት ፔኒናህ ተናግራለች። "'እየዋሸሽን ነው' ሲሉ ወቀሱኝ። እኔ ግን ምንም የማበላቸው ነገር ስላልነበር የማደርገው ጠፋኝ።" የፔኒናህ ጎረቤት የስምንቱን ሕፃናት ለቅሶ ሰምታ ነው ጉዳዩን ለማጣራት ብቅ ያለችው። ይህን ጉድ ያስተዋለች ጎረቤት ናት ጉዳዩን ለመገናኛ ብዙሃን ሹክ ያለችው። የፔኒናህ ታሪክ ኤንቲቪ በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣብያ ላይ ከቀረበ በኋላ ኬንያውያን ለእርዳት እጃቸውን ከመዝርጋት አላመነቱም። የሞባይል ስልኳ አስሬ ይንቃጨል ጀመር [በሞባይል ባንኪንግ በሚገባላት እርዳታ] አልፎም ፔኒናህ መፃፍና ማንበብ ስለማትችል በጎረቤቷ ስም በተዘጋጀ የባንክ አካውን ወገኖቿ "አለንልሽ" እያሏት ነው። ያለ ውሃና መብራት ባለሁለት ክፍል ቤት ውስጥ ከስምንት ልጆቿ ጋር የምትኖረው ፔኒናህ የወገኖቿን እርዳታ 'ተዓምር' ስትል ነው የገለፀችው። 'ኬንያዊያን እንዲህ ዓይነት ፍቅር ይለግሱኛል ብዬ አስቤ አላውቅም። ከሁሉ አቅጣጫ ነበር እየደወሉልኝ እንዴት እናግዝሽ ሲሉኝ የነበረው' ብላለች። የኬንያ መንግሥት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ እንኳን መምራት ላልቻሉ ዜጎቹ ነፃ የምግብ እርዳታ አቅርቧል። ነገር ግን ይህ እርዳታ ከፔኒናህ ደጃፍ አልደረሰም። የፔኒናህ ባልና የስምንት ልጆቿ አባት ባለፈው ዓመት ነበር በአመፀኛ ወጣቶች ሕይወቱን ያጣው። የፔኒናህ ጎረቤት ወገኖቿንና የኬንያ ቀይ መስቀልን ለእርዳታቸው አመስግናለች። ዕድሜ ለፔኒና አሁን ሞምባሳ ውስጥ ያሉ ራሳቸውን መመገብ ያልቻሉ ኬንያዊያን እርዳታ እየተደረገላቸው ነው። የኬንያ መንግሥት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በሚል ሞምባሳን ጨምሮ ወደ ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች መግባትም ሆነ መውጣት ከልክሏል። አልፎም በመላ አገሪቱ ከምሽት 1 ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት የሚቆይ ሰዓት እላፊ ታውጇል። በርካታ ድርጅቶች በራቸውን ዘግተዋል። የተቀሩት ደግሞ በአነስተና ሠራተኛ ለመንቀሳቀስ ተገደዋል። ይህ ደግሞ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ኬንያዊያን ከሥራ ውጪ አድርጓቸዋል። ለኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲሆን ከዓለም ባንክ ወፈር ያለ ዶላር የተቀበለው የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገንዘቡን በሻይ፣ ብስኩትና በሞባይል ካርድ ነው የጨረሰው የሚል ሪፖርት ወጥቷል። ይህ ዜና ከፔኒናህ ታሪክ ጋር መግጠሙ ኬንያዊያንን አስቆጥቷል። ማኅበራዊ ድር-አምባዎች ላይ ገዥውን መንግሥት በወቀሳና ስድብ የጠራረጉትም አልጠፉም። ኬንያ 395 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ያረጋገጠች ሲሆን 17 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል።
55792462
https://www.bbc.com/amharic/55792462
በአንድ ሮኬት ብዙ ሳተላይት ወደ ሕዋ የመላክ ክብረ ወሰን ተሰበረ
በአንድ ጊዜ በአንድ መንኮራኩር ወደ ህዋ የሚላኩ የሳተላይቶች ብዛት ክብረ ወሰን ተሻሻለ፡፡
የተለያዩ ቅርጽና መጠን ያላቸው 143 ሳተላይቶች በአንድ ሮኬት ተጭነው ከፍሎሪዳ ወደ ህዋ ተመንጥቀዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ በአንድ ሮኬት ብዙ ሳተላይት ተልኮ የነበረው በፈረንጆቹ 2017 ሲሆን የሳተላይቶቹ ብዛትም 104 ብቻ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ሳተላይቶቹን ያሳፈረው መንኩራኮር ሕንድ ሠራሽ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አሁን ክብረ ወሰኑን የሰበረው የዓለም ቁጥር 1 ቢሊየነር ኤለን መስክ ኩባንያ የፈጠረው ስፔስኤክስ- ፋልከን ነው፡፡ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሳተላይቶች በአንድ ጊዜ መላክ መቻሉ ቀስ በቀስ የአሠራርና የቴክኖሎጂ አብዮት እየተደረገ እንደሆነ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ማለት አንድን ሳተላይት በመጠኑ አሳንሶ፣ በሥራ ቅልጥፍና አዘምኖ በትንንሽ ግብአቶች አምርቶ ወደ ህዋ ማሳፈር መቻሉ ነው፡፡ አሁን አሁን ማንም ኩባንያ ልክ የእጅ ስልክ ማምረት እንደሚችለው ሳተላይቶችን ማምረት የሚችልበት አቅም መፈጠሩን ያስመሰከረ ነው ብለውታል ባለሙያዎች፡፡ አዲሱ የህዋ ታክሲ ስፔስኤክስ (SpaceX) እነዚህ ቀላል ሳተላይቶችን ወደ ኦርቢት ለመላክ ከ1 ሚሊዮን ዶላር ባነሰ ዋጋ መጠየቁ ወደፊት ዘርፉ ለትንንሽ ኩባንያዎች እየተከፈተ እንደሚመጣ አመላካች ነው ተብሏል፡፡ ስፔስኤክስ የራሱ የሆኑ 10 ሳተላይቶች ያሉት ሲሆን በዓለም ዙርያ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ግንኙነቶችን መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡ በዚህ ክብረ ወሰንን በሰበረው የሮኬት ጉዞ የሳንፍራንሲስኮው ፕላኔት የተባለ ኩባንያ 48 ሳተላይቶችን በመላክ ከፍተኛውን የሳተላይት ቁጥር አስመዝግቧል፡፡ እነዚህ የፕላኔት ኩባንያ ንብረት የሆኑ ሳተላይቶች ‹ሱፕርዶቭ› ሞዴል የሚባሉ ሲሆን የመሬትን ገጽታ በየቀኑ በከፍተኛ ጥራት ፎቶ የሚያነሱ ናቸው፡፡ አሁን የላካቸውን 48 ሳተላይቶች ጨምሮ ይህ የሳንፍራንሲስኮው ፕላኔት ኩባንያ በህዋ የሚኖሩት የሳተላይቶች ቁጥር ወደ 200 የሚያደርሰው ይሆናል፡፡ ሱፐርዶቭስ የሚባሉት እነዚህ ሳተላይቶች መጠናቸው የሊስትሮ ሳጥን ቢያክል ነው፡፡ ሌሎቹ በፋልከን ሮኬት የተጫኑት ደግሞ ከአንድ የሻይ ኩባያ መጠን ብዙም የሚበልጡ አይደሉም፡፡ አሁን አሁን ቴክኖሎጂው እየተረቃቀ ሲመጣ የሳተላይቶች ተግባር ሳይቀንስ፣ ነገር ግን መጠናቸው እጅግ እያነሰ ሄዶ ‹ስፔስቢስ› የሚባሉ ‹የህዋ-ንብ› ሊባሉ የሚችሉ ትንንሽ ሳተላይቶች እየተፈጠሩ ነው፡፡ የነዚህ ሳተላይቶች ጠቅላላ መጠን 10 ሴንቲ ሜትር በ10 ሴንቲሜትር ብቻ ቢሆን ነው፡፡ እነዚህ ‹ስፔስቢስ› የሚባሉት የሳተላይት ጉጦች ሳተላይትን መሬት ላይ ካለ ማንኛውም ቁስ ጋር የማገናኘት ተግባር ይሰጣሉ፡፡ ስፔስቢስ ለምሳሌ ከአገር አገር እየበረሩ ያሉ አእዋፋት ወይም እንሰሳት ወይም ደግሞ መርከቦች ወይም ሌላ ቁስን ህዋ ላይ ካለ ሳተላይት ጋር የሚያገናኙ የሳተላይት ጉጦች ናቸው፡፡ በዚች የስፔስኤክስ ፋልከን መንኮራኩር ትልልቅ ሳተላይቶች የተጫኑ ሲሆን እነዚህ በመጠን ትልቅ የተባሉት ግን አንድ የሳምሶናይት የእጅ ሻንጣ ቢያክሉ ነው፡፡ ብዙዎቹ የራዳር ሳተላይቶች ናቸው፡፡ በተለምዶ የራዳር ሳተላይቶች እጅግ ግዙፍና ብዙ ቶን የሚመዝኑ ሲሆን ወደ ህዋ ለመላክ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች ያስፈልጉ ነበር፡፡ ይህም ማለት እነዚህን የራዳር ሳተላይቶች በፊት ግዙፍ የወታደር ተቋም ወይም የስፔስ ኤጀንሲዎች ካልሆኑ ማንም የሚደፍራቸው አልነበሩም፡፡ አሁን አሁን ግን ቴክኖሎጂዎች መራቀቃቸውን ተከትሎ በሚደንቅ ሁኔታ ክብደታቸው ከ100 ኪሎ ግራም እያነሰ ወደ ህዋ ማሳፈርያ ዋጋቸውም ከ2 ሚሊዮን ዶላር ሳይበልጥ ማሳካት ተችሏል፡፡ በትናንቱ የህዋ ጉዞ አይሲየ (Iceye) ከፊንንላንድ፣ አምብራ (Umbra) ከአሜሪካ፣ አይኦፒኤስ (iQPS) ከጃፓን ሳተላይቶችን ልከዋል፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ለዘርፉ ገና ጀማሪዎች ናቸው፡፡ ሳተላይቶቻቸው የመሬትን ምሥል በተከታታይ ይልኩላቸዋል፡፡ ራዳር ከኦፕቲካል ካሜራዎች በተለየ ደመናን ጥሶ በማለፍ የመሬትን ከባቢና ወለል በተሸለ ጥራት ፎቶ የማንሳት አቅም አለው፡፡ በቀን እና ብራ የአየር ሁኔታ ብቻ ሳይሆን በድቅድቅ ጨለማም ምሥል ማንሳት ይችላል፡፡ ይህም ማለት ምድር ላይ የምትፈጸም አንዳች እንቅስቃሴ በቀላሉ የምትታይበት ዘመን እየመጣ እንደሆነ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
44790615
https://www.bbc.com/amharic/44790615
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ሦስተኛ ወገን አልነበረበትም ተባለ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በቅርቡ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንዳልነበረበት አስታወቁ፡፡
ጽ/ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ባለፉት 100ቀናት የተቀዳጇቸውን የውጭ ጉዳይ እና ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን በዘከረበት መግለጫ ላይ ፤ከኤርትራ ጋር የነበረውን ጦርነት ለማቆም የተደረሰውን መግባባት ‹ትልቅ ድል› ሲል ገልጾታል፡፡ ስምምነቱ ‹‹ያለምንም ጣልቃ ገብነት እና ሽምግልና የተፈረመ›› ነው ሲልም አክሏል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ከስምምነቱ በፊት የተባበሩት አረብ ኤመሬትስን የመሰሉ ሀገራት በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እያደረጉ ስለመሆናቸው መሰማቱ አይዘነጋም፡፡ በዛሬው ዕለት በወጣው የተባበሩት አረብ ኤመሬትስ አንጋፋ ጋዜጣ ከሃሊጅ ታይምስ ላይ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ፣በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካካል የተደረሰው የሰላም ስምምነት የልዑል ሼክ መሃመድ ቤን ዛይድ ‹ከፍተኛ ጥረት› ውጤት መሆኑ መናገራቸውን ብሎም ምስጋና ማቅረባቸውን አስነብቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጽ/ቤቱ ባለፉት 100 ቀናት ኢትዮጵያ የወሰደቻቸው ርምጃዎች የምስራቅ አፍሪቃ ቀጠና ጂኦፖለቲካል ሁናቴን ለማረጋጋት ፣ኢጋድን የመሰሉ ቀጠናዊ ተቋማትን ለማጠንከር የነበረውን ሚና ዘርዝሯል፡፡
news-53564191
https://www.bbc.com/amharic/news-53564191
ለ3 ቢሊዮን እንስሳት" መጥፋት" ምክንያት የሆነው የአውስትራሊያ ሰደድ እሳት
ባለፈው ዓመት በአውስትራሊያ ተከስቶ በነበረው ሰደድ እሳት 3 ቢሊየን የሚጠጉ እንስሳት ሳይሞቱ ወይም ሳይሰደዱ እንዳልቀረ ተመራማሪዎች አስታወቁ።
ይህንን ሪፖርት ያወጣው በዱር እንስሳትና በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራው ግብረ ሰናይ ድርጅት [WWF] የጥናቱ ውጤት በዘመናዊ የዓለም ታሪክ ካጋጠሙ በጣም አስከፊው አደጋዎች አንዱ መሆኑን አመላክቷል ብሏል። ባለፈው ዓመት የተከሰተው ይህ የሰደድ እሳት በተለያዩ አውስትራሊያ ግዛቶች ተስፋፍቶ ቢያንስ የ33 ሰዎችን ሕይወት ነጥቋል። አጥቢ እና ተሳቢ እንስሳት፣ ወፎች እና እንቁራሪቶች በነበልባሉ ሞተዋል አሊያም ምቹ ሁኔታ በማጣት ጠፍተዋል። የእሳት አደጋው በተስፋፋበት ጥር ወር ላይም ተመራማሪዎች በኒው ሳውዝ ዌልስ እና ቪክቶሪያ ብቻ 1.25 ቢሊየን እንስሳት እንደሞቱ ግምታቸውን አስቀምጠው ነበር። ይሁን አንጂ አሁን አዲስ የወጣው ግምት ሌሎች ቦታዎችንም አካቷል። ከእንግሊዝ ስፋት ጋር የሚስተካከል 11.46 ሚሊየን ሄክታር መሬትም ከመስከረም እስከ የካቲት ድረስ ባሉት ወራት ውስጥ በእሳት ወድሟል። የሰደድ እሳቱ ያሳደረው ተፅእኖ ምን ነበር? በአውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲዎች 10 ተመራማሪዎች የቀረበውን ፕሮጀክት የተከታተሉት ፐሮፌሰር ክሪስ ዲክማን ጉዳቱን አስመልክቶ "3 ቢሊዮን የሚጠጉ እንስሳት መጥፋታቸው ሲታሰብ በጣም ከፍተኛ ጉዳት ነው፤ ለማሰብ የሚከብድ ቁጥር ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ፕሮፌሰሩ አክለውም በአደጋው ምን ያህል እንስሳት እንደሞቱ ትክክለኛ ቁጥሩን ማስቀመጥ ባይችሉም፤ እንስሳቱ ከእሳት ነበልባሉ የማምለጥ እና በሕይወት የመገኘት እድላቸው በምግብና በመጠለያ እጥረት ምክንያት "ያን ያህል ሰፊ አይደለም" ብለዋል። የተገለፀው ቁጥር የተቀመጠው አደጋው ከመከሰቱ በፊት በአካባቢዎቹ ያሉ እንስሳት ቁጥርን መሰረት መሆኑን የተገለፀ ሲሆን፤ በመረጃ ውስንነት ምክንያትም የጀርባ አጥንት የሌላቸው እንስሳት በሪፖርቱ ውስጥ አልተካተቱም። የካቲት ወር ላይ የአውስትራሊያ መንግሥት ከሰደድ እሳቱ በኋላ አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ 113 የእንስሳት ዝርያዎችን ለይቶ ነበር። በዚህም በዝርዝሩ ውስጥ ያሉት ሁሉም ለማለት በሚያስችል መልኩ 30 በመቶ የሚሆነውን መኖሪያቸውን አጥተዋል። ይህንንም ተከትሎ መንግሥት ለዱር እንስሳትና አካባቢ ጥበቃ 35 ሚሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል ቢገባም የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ግን አውስትራሊያ የአካባቢ ጥበቃ ሕጓን እንዲታጠብቅ ጠይቀዋል። አውስትራሊያ አደጋውን አስመልክቶ ልዩ ምርመራ እያደረገች ሲሆን ውጤቱም ህዳር ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። በተደጋጋሚና ባልተጠበቀ መልኩ ለሚነሳው የሰደድ እሳት ምክንያቱ የአየር ንብረት ለውጥ መሆኑንም በርካታ ተመራማሪዎች እየገለፁ ነው። ባለሙያዎቹ አክለውም ከእሳቱ ይወጣ ከነበረው ጭስ ጋር ተያይዞም ከ445 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስታውቀዋል።
news-45716837
https://www.bbc.com/amharic/news-45716837
የኩዌት ባለስልጣን በፓኪስታን ዲፕሎማት የኪስ ቦርሳቸው ተሰረቀ
በፓኪስታን ከፍተኛ የመንግስት ተቀጣሪ የሆነ ሰው የኩዌት ልኡካን ቡድን አባል ያስቀመጠውን የኪስ ቦርሳ ሲሰርቅ የሚያሳይ ምስል ከተለቀቀ በኋላ ፓኪስታን በሰውዬው ላይ ምርመራ መጀመሯን አስታውቃለች።
ነገሩ ይባስ ብሎ በሃገር ውስጥ መገናኝ ብዙሃን እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠርጣሪው ዛራር ሃይደር ክሃን ይሄ ነው ተብሎ የተለቀቀው ምስል ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው በአሜሪካ የሚኖር ሰው ነው። የፓኪስታን የመረጃ ሚኒስትሩ ፋዋድ ቻድሪይ እንዳሉት ተጠርጣሪው በሃገሪቱ የኢንዱስትሪና ምርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ሃላፊነት ያለው ተቀጣሪ ሲሆን፤ ሃገሪቱን የማይወክል ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል። • የአይኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያዊያንን ገደሉ • አቶ መላኩና ጄነራል አሳምነው ለማዕከላዊ ኮሚቴ ተመረጡ የፓኪስታን መንግስት እንዳስታወቀው አቶ ሃይደር ከስራቸው ተሰናብተዋል፤ ተግባሩም መላው የሃገሪቱን ዜጎችና መንግስትን ያዋረደ ነው ብሏል። በኩዌትና ፓኪስታን መካከል የንግድ ሁኔታዎችን ለመነጋገር ፓኪስታን የገባው ልኡካን ቡድን አባል የሆኑት ሰው የኪስ ቦርሳቸውን የተቀመጡበት ጠረጴዛ ላይ ትተውት የሄዱ ሲሆን፤ ተጠርጣሪውም የኪስ ቦርሳቸውን ሲያነሳ በተንቀሳቃሽ ምስል ተቀርጿል። የኪስ ቦርሳቸው መጥፋቱን ያስተዋሉት የኩዌት ሃላፊም ጉዳዩን ለፓኪስታን ሃላፊዎች አሳውቀው፤ ተጠርጣሪው መታወቁን በሰሙ ጊዜም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድና ማንነቱ እንዲነገራቸው ጠይቀዋል። • ሁለቱ ኮሪያዎች የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማንሳት ጀመሩ በቦርሳው ውስጥም ጠቀም ያለ የኩዌት ዲናር እንደነበረ አንድ የፓኪስታን ጋዜጣ ዘግቧል። እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ታዋቂነትን ያተረፈው የኪስ ቦርሳው ሲሰረቅ የሚሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል በሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ጭምር የታየ ሲሆን፤ ብዙ ፓኪስታናውያን አዋረደን በማለት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። መልኩን በደንብ መለየት በማይቻለው ተንቀሳቃሽ ምስል ምክንያት ተጠርጣሪ ተብሎ ፎቶው በመገናኛ ብዙሃን የቀረበው ሰው ግን ዛራር ሃይደር ሳይሆን አሜሪካ ውስጥ የአደጋ መከላከል ባለሙያ የሆነውና ተቀራራቢ ስም ያለው ዛይድ ሃይደር ነው። በተለይ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያዎች በተሰራጨው የተሳሳተ የዛይድ ሃይደር ምስል ስር ብዙ ፓኪስታናውያን ቁጣቸውን በስድብና አዋረድከን መልዕክቶች እየገለጹ ነው። • በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት በጉዳዩ ዙሪያ የተጠየቀው የአሜሪካ ነዋሪው '' እኔ ምንም የማውቀው ነገር ነገር የለም፤ ስሜ ዛራር ሃይደር ሳይሆን ዛይድ ሃይደር ነው።'' ብሏል። እስካሁንም ግን የተጠርጣሪው ዛራር ሃይደር ትክክለኛ ምስል አልተገኘም። በፓኪስታን የተንሰራፋውን የሙስና ችግር ለማጥፋት እዋጋዋለሁ ብለው ከሁለት ወራት በፊት የተመረጡት የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ክሃን ገና ከጅምሩ ያልጠበቁት አጋጣሚ ወዳጃቸው ኩዌትን አስቆጥቶባቸዋል።
news-55226540
https://www.bbc.com/amharic/news-55226540
ኮሮናቫይረስ ፡ የ90 ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴከ ክትባትን በመከተብ በዓለም የመጀመሪያዋ ሆኑ
ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ዛሬ ለዜጎቿ መስጠት ስትጀምር የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሆኑ።
አዛውንቷ ማርግሬት ኪናን ክትባቱን ከመውሰዳቸው በፊት በሰሜን አየርላንድ ኢኒስኪለን ነዋሪ ሆኑት የዘጠና ዓመቷ የእድሜ ባለጸጋ ማርግሬት ኪናን የፋይዘር/ባዮንቴክ የኮቪድ-19 ክትባትን ከሙከራ ውጪ በመውሰድ በምድራችን የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። አዛውንቷ ማርግሬት በመርፌ የሚሰጠውን ክትባት ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በኮቬንትሪ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚገኘው የክትባት ማእከል ተገኝተው ነው የወሰዱት። አሁን መሰጠት የተጀመረው የኮቪድ-19 ክትባት በዋናነት ትኩረት ያደረገው ለበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ የሆኑትን ሰዎች ሲሆን በቀጣይም ለሌሎች እንደሚዳረስ ተነግሯል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ ያበለጸጉት ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ለዜጎቿ እንዲሰጥ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መፍቀዱ ይታወሳል። በዚህም ዩኬ ይህን ክትባት በመጠቀም የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ክትባቱን ዛሬ ከሚወስዱት መካከል የ87 ዓመቱ ዶ/ር ሃሪ ሹክላ አንዱ ናቸው። ዶ/ር ሃሪ ክትባቱን ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ኒውካስትል በሚገኝ ሆስፒታል እንደሚወስዱ ገልጸው በዚህም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የክትባት አሰጣጥ መረሃ ግብሩ ቅድሚያ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑትን በማስቀደም ሕይወት ወደቀደመ መልኩ እንድትመለስ ይረዳል ተብሏል። "ቪ-ዴይ" ወይም የድል ቀን የሚል ስያሜ በተሰጠው ዕለት የሚጀመረው የክትባቱ መርሃ ግብር፤ ዜጎች ክትባቱን የመከተብ ግዴታ አይኖርባቸውም ተብሏል። ጠቅላይ ሚንሰትር ቦሪስ ጆንሰን፤ "ዩናይትድ ኪንግደም ከኮሮናቫይረስ ጋር በምታደርገው ትግል የዛሬዋ ቀን ሌላ ምዕራፍ ከፍታለች" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ክትባቱን ለዜጎች ለማዳረስ ወራትን ሊፈጅ እንደሚችል አስታውሰው እስከዚያው ድረስ ግን መንግሥት ያስተላለፋቸው የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን ዜጎች እንዲተገብሩ አስታውሰዋል። እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ከ60ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። መንግሥት በአሁኑ ወቅት 800 ሺህ የክትባት ብልቃጦችን ዝግጁ ያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 40 ሚሊዮን ክትባቶችንም አዟል። ይህም ለ20 ሚሊዮን ሕዝብ በቂ ነው። 95 በመቶ ቫይረሱን የመከላከል አቅምን ያጎለብታል የተባለለትን ክትባት ሰዎች በ21 ቀናት ልዩነት ሁለት ጊዜ መወጋት ይኖርባቸዋል። ሰዎች ከቫይረሱ እራሳቸውን መከላከያ የሚጀምሩት ሁለተኛውን ክትባት ከወሰዱ ከሰባተኛው ቀን በኋላ ነው ተብሏል። ባለፉት ሁለት ቀናት ክትባቱን የያዙ ማቀዝቀዣዎች ከሚመረቱበት ቤልጄየም ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሲገቡ ቆይተዋል። በቀጣይ ሦስት ሳምንታት ውስጥም ተጨማሪ 10 ሚሊዮን የክትባት ብልቃቶች ወደ ዩኬ ገብተው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ይሰራጫሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሳምንታት በኋላ ደግሞ በስታዲየሞች እና በግዙፍ መሰብሰቢያ አዳራሾች ለበርካታ ሰዎች በአንድ ጊዜ ክትባት መስጠት ይጀመራል ተብሏል።
news-54857576
https://www.bbc.com/amharic/news-54857576
ካማላ ሃሪስ፡ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት
ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ታሪክ ሰርተዋል።
ካማላ ሃሪስ፡ ባለታሪኳ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት ይህም ብቻ የመጀመሪያዋ ጥቁር እና እስያ አሜሪካዊ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን በታሪክ መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ። ካማላ ሕንዳዊ ከሆኑት እናታቸው እና ጃማይካዊ ከሆኑት አባታቸው በካሊፎርኒያ ነበር የተወለዱት። የ55 ዓመቷ የካሊፎርኒያ ሴናተር በዚህ ወሳኝ ወቅት ከተመራጩ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋር በመሆን አሜሪካንን ለቀጣይ አራት ዓመታት ይመራሉ። ካማላ ገና በልጅነታቸው ወላጆቿ መፋታታቸውን ተከትሎ እናታቸው ነበሩ ያሳደገቿው። የካማላ እናት እውቅ የካንስር ሕመም ተመራማሪ እና የመብት ተሟጋች ነበሩ። ካማላ አስተዳደጋቸው የህንድ ባህል የተከተለ ነበር። ከወላጅ እናታቸው ጋር በተደጋጋሚ ለጉብኝት ወደ ህንድ ይጓዙ ነበር። ይሁን እንጂ ካማላ ወደ ፖለቲካው ከገቡ በኋላ ወላጅ እናታቸው ያሳደጓቸው የጥቁር አሜሪካውያንን ባህል እና አኗኗርን በተከተለ መልኩ ነበር። "እናቴ ሁለት ጥቁር አሜሪካውያንን እያሳደገች እንደሆነ ነው የምትረዳው። ያደግነበት ማህብረስብ እኔን እና እህቴን እንደ ጥቁር ሴቶች አድርጎ እንደሚቀበለን ተረድታ ነበር" በማለት ካማላ የሕይወት ታሪካቸውን በያዘው መጽሐፍ ላይ አስፍረዋል። ካማላ በልጅነት እድሜያቸው በካናዳ ኖረዋል። ወላጅ እናታቸው ካናዳ በሚገኘው ማክጊል ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ። በካናዳዋ ሞንትሪያል ለአምስት ዓመታት ኖረዋል። የኮሌጅ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ደግሞ በአሜሪካዋ ሆዋርድ ዩኒቨርሲቲ ነው። ከአራት ዓመታት የትምህርት ቆይታ በኋላ ካማላ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ለመስራት ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያን ተቀላቅለዋል። ካማላ ዐቃቤ ሕግ በመሆን ረዘም ላለ ዓመታት አገልግለዋል። እአአ 2003 ላይ ካማላ የመጀመሪያዋ የካሊፎርኒያ ጥቁር ሴት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በመሆን ተመርጠዋል። እአአ 2014 ላይ የሕግ ባለሙያ ከሆኑት ዶግ ኤምሆፍ ጋር ትዳር መስረተዋል።
news-53911409
https://www.bbc.com/amharic/news-53911409
አሜሪካ ፡ የፖምፔዮ ጉብኝት አንድምታና ለኢትዮጵያ ያለው ፋይዳ
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ጎረቤት አገር ሱዳን ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም ወደ ካርቱም አቅንተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮና የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ፖምፔዮ ከሰባት ዓመታት በኋላ ሱዳን የጎበኙ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ናቸው። ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ልዑክ ሱዳን የጎበኘው በፈረንጆቹ 2013 ሲሆን የኦባማ ውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ኮንዶሊዛ ራይስ ነበሩ ካርቱምን የረገጡት። ፖምፔዮ በእስራኤል የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ነው ወደ ሱዳን የመጡት። ለመሆኑ የማይክ ፓምፔዮ ወደ ሱዳን ማቅንት አንደምታው ምንድነው? የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በሥፍራው መገኘት ፋይዳስ? የሰውዬው ጉብኝት ለሱዳንም ሆነ ለቀጣናው ትልቅ ፋይዳ አለው የሚሉት በኪል ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አወል አሎ (ዶክተር) ናቸው። "እንደሚታወቀው ሱዳን ለውጥ ላይ ናት። አሁን ሥልጣን ላይ ካለው የሽግግር አስተዳደር በፊት የነበረው መንግሥት ከአሜሪካ ጋር እንዲሁም ከሌሎች የአውሮፓ አገራት ጋር የነበረው ግንኙነት ሻካራ ነበር።" ይሁን እንጂ የሽግግር መንግሥቱ ከእነዚህ አገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ነበር ይላሉ ባለሙያው። "ጥረት ከማድረግ አልፎ አሜሪካ እንደ ቅደም ሁኔታ ያስቀመጠችውን ነገር ማሟላት ጀምረዋል። ለምሳሌ የቀድሞው ፕሬዝደንት ኦማር አል-ባሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኞ እንደሆኑ ሲገልፁ ነበር። የሁለቱን አገራት ግንኙነትን ለማሻሻል እየሠሩ እንዳለ ማሳያ ነው።" አወል (ዶ/ር) ሱዳን ካሳየችው ፈቃደኝነት ባለፈ የትራምፕ መንግሥት ወደ ሁለተኛ ዙር ምርጫ እየሄደ ስለሆነ በውጭ ጉዳይ በኩል የታየውን ደካማ ሥራ ማከም ይፈልጋና ለዚህ ነው የሚኒስትሩ አመጣጥ ይላሉ። በዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስና በእስራኤል መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነትም የዚህ አካልም እንደሆ ይጠቅሳሉ። ሱዳን፤ በአሜሪካ መንግሥት ሽብርን ከሚደግፉ ተብለው ከተዘረዘሩ አገራት መካከል ናት። ባለሙያው፤ አሜሪካ ሱዳን ከዚህ መዝገብ ላይ ብትፋቅ የትራምፕ አስተዳደር የበለጠ ይጠቀማል ይላሉ። የአባይ ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሐምዶክና ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ጋር ስለ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ይወያያሉ ተብሎ በብዙዎች ዘንድ ግምቱ አለ፤ ምንም እንኳን የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጉብኝት አጋጣሚ ነው ወይስ የታሰበበት? "በጭራሽ የአንድ አገር መሪና ለዚያውም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአጋጣሚ ሊገናኙ አይችሉም" ይላሉ አወል (ዶ/ር)። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሱዳን ጉብኝት የተቃደና የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ሊሆን ከተቻለም የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ሌላው መነጋገሪያ አጀንዳ እንደሚሆን ባለሙያው ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሜሪካ ጠንከር ያለ የግብጽን ፍላጎት የሚደግፍ የሚመስል አቅጣጫ እየተከለች ነው። አሜሪካ ይህን እያደረገች ያለችው መርህ ላይ በተመሠረተ መልኩ አይደለም። እርግጥ ነው ሁለቱ አገራት [ግብጽና አሜሪካ] ለረዠም ጊዜያት አጋር ሆነው ቆይተዋል። ይህ እስራኤልንም የሚመለከት ነው" ይላሉ አወል (ዶ/ር)። አክለውም "ግብጽ አሜሪካና አንዳንድ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትን በመጠቀም ጫና እያሳደረች ነበር። ስለዚህ የአሜሪካ አቅጣጫ ምን እንደሆነ መገመት ይቻላል። ሐሳባቸው ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የቀረበውን ስምምነት እንደትቀበል ነው። በአርግጠኝነት ፖምፔዮና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በዚህ ጉዳይ ላይ ይወያያሉ" በማለት ሊነሱ ከሚችሉ ጉዳዮች መካከል ይጠቅሳሉ። ማይክ ፖምፒዮ የኮንግረስ አባላት ጥያቄ በቅርቡ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር የሚጠይቅ ደብዳቤ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ መፃፋቸው አይዘነጋም። ቢዘህ ጉዳይ ላይ ውይይት ያደርጉ ይሆን? "ይሄ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ መነሳቱ ምንም ጥያቄ የለውም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኮንግረስ የፃፈላቸውን ደብዳቤ እንዲሁ ችላ ማለት አይችሉም። ስለዚህ ይህንን ርዕስ ማንሳታቸው የሚቀር አይደለም" ይላሉ። ባለሙያው አሜሪካ የራሷን ጥቅም ለማስከበር ስትል እንጂ ለሰብዓዊ መብት በማለት ምንም ነገር እንደማታደርግ አፅንዖት በመስጠት ይናገራሉ። "ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር ሰብዓዊ መብትን ለማስከበር ሳይሆን አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት ይህንን አጋጣሚ ልትጠቀምበት ትችላለች።" አሜሪካ ከኢትዮጵያ ምን ትፈልጋለች? አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትሻው ትልቁ ነገር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሆነ ባለሙያው ያስረግጣሉ። "ፕሬዝደንቱ [ትራምፕ] አሁን በቀጣይ ኅዳር ወር ላይ ለሚካሄደው ምርጫ የሚፈልጉት ነገር ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፍ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ስምምነት ላይ ደረሱ የሚለውን ጉዳይ ነው። ይሄ ለፕሬዝደንቱ ትልቅ ድል ነው።" እንደማንኛውም ከዚህ ቀደም የነበረ ፕሬዝደንት የአሁኑ ፕሬዝደንትም የውጭ ጉዳይን በተለመከተ ያገኙት ድል ምንድነው? የሚለው ይነሳል። ስለዚህ አሜሪካ በተቻለ መጠን ኢትዮጵያን ተጭናም ቢሆን ስምምነቱን እንድትቀበል ለማድረግ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ያምናሉ። ባለሙያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ መለሳለስ ያሳያሉ አያሳዩም የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው፤ ነገር ግን ምላሹን መገመት ያዳግታል ይላሉ። የአሜሪካን ፍላጎት መገመት ግን ብዙም አዳጋች አይደለም እንዳልሆነ ያምናሉ። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ የሱዳን ጉብኝት፤ በእስራኤል፣ በባህሬንና በተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች የሚያደርጉት የጉዞ ፕሮግራማቸው አካል ነው።
news-56372133
https://www.bbc.com/amharic/news-56372133
የማሌዥያ ፍርድ ቤት ክርስቲያኖች 'አላህ'ን የአምላካቸው መጠሪያ ማድረግ ይችላሉ አለ
የማሌዥያው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክርስቲያኖች አምላካቸውን ለመጥራት ሲፈልጉ 'አላህ' የሚለው ቃል መጠቀም አይችሉም የሚለውን ፖሊሲ ከሰሞኑ ቀልብሷል።
ጉዳዩ ለአስርት አመታትም ያህል ያከራከረ ነው ተብሏል። የእስልምና እምነት ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች "አላህ" የሚለውን ቃል መጠቀም ጉዳይ ማሌዥያን ለውጥረት ዳርጓታል። ከዚህ ቀደምም በርካታ ግጭቶችም ተነስተዋል። በአገሪቱ ውስጥ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሲሆን 2/3ኛውንም ይይዛሉ ተብሏል። ነገር ግን ቀላል የማይባል የክርስትና እምነት ተከታይ ነዋሪዎችም አሉ። የክርስቲያኑ ማህበረሰብ እንደሚከራከሩት ለዘመናት ያህል ከአረብኛ ተወስዶ በአገሬው ቋንቋ ማሌይ የተወረሰውን "አላህ" የሚለውን ቃል አምላካቸውን ለመግለፅ ሲጠቀሙበት እንደኖሩ ነው። ክልከላውም "መብታችንን ይጥሳል" በማለት ሲከራከሩ ነበር። የማሌዥያ ህገ መንግሥት የእምነት ነፃነት ላይ ግልፅ ያለ ህግ ቢኖረውም በቅርብ አመታት በተለያዩ እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ውጥረት እንደነገሰ ይነገራል። ህገወጥና ኢ-ህገመንግሥታዊ ነው በአውሮፓውያኑ 2008 የማሌዥያ ባለስልጣናት የማሌይ ቋንቋ የሰፈረበት ሲዲ ጂል አየርላንድ ላውረንስ ከምትባል ርስቲያን ግለሰብ ወሰዱ። በሲዲው ላይ አላህ የሚል ቃል የሰፈረበት ሲሆን በወቅቱም አየር ማረፊያ ላይ ነበረች ተብሏል። ይህቸው ግለሰብ በአውሮፓውያኑ ክርስቲያኖች አላህ የሚለውን ቃል በህትመቶቻቸው መጠቀም አይችሉም የሚለውን ህግ ለማስቀየር ክስ ከፈተች። ከአስር አመታት በኋላ በያዝነው ሳምንት ረቡዕ የኩዋላ ላምፑር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግለሰቧ በእምነቷ ምክንያት ልትገለል አይገባም ፤ የሃይማኖት ነፃነቷም ሊከበር ይገባል የሚል ውሳኔን አስተላለፈ። ዳኛ ኖር ቢ ባስተላለፉት ውያኔ መሰረት አላህ የሚለውን የአረብኛ ቃል ጨምሮ 'ካባህ' (በመካ የሚገኝ ቅዱስ ቦታ)፣ ባይቱላህ (ቤተ መቅደስ)ና ሰላት (ፀሎት) የሚሉ ቃላቶችን ክርስቲያኖች መጠቀም ይችላሉ ብለዋል። ዳኛዋ ውሳኔውን ባስተላለፉበት ወቅት እነዚህን ቃላቶች መጠቀም ያገደው አዋጅ "ህገ ወጥና ኢ-ህገመንግሥታዊ ነው" ብለዋል።
news-45365268
https://www.bbc.com/amharic/news-45365268
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የውጪ ሃገራት ዜጎች ንብረት ተዘረፈ
ጆሃንስበርግ አቅራቢያ በምትገኘው ሶዌቶ በምትባል ትንሽዬ ከተማ ኢትዮጵያዊያን እና ሶማሊያዊያን ነጋዴዎች ላይ ባነጣጠረ ዝርፊያ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደሰማነው ከሆነ ሟቾቹ የሶማሊያ፣ የደቡብ አፍሪካ እና የፓኪስታን ዜጎች ናቸው። ይሁን እንጂ የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ከሟቾቹ መካከል አንዱ ኢትዮጵያዊ ነው ብሏል። የሶዌቶ ፖሊስ ሪፖርት እንደሚያሳየው የውጪ ሃገራት ነጋዴዎች ላይ በተሰነዘረው ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል። የጆሃንስበርግ ከተማ ነዋሪ የሆነው ኢትዮጲያዊው ሞሐመድ ኑር ''የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ምርቶች ትሸጣላችሁ በሚል ያጠቁናል እንጂ 'የውጪ ሃገር ዜጋ እኛን ሥራ ያሳጣሉ' የሚል አቋም አላቸው'' ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ሞሐመድ እንደሚለው ከሆነ ፖሊስ የውጪ ሃገር ነጋዴዎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው የለፈባቸውን ምርቶች ለገብያ እንደማያቀርቡ አረጋግጧል። • የውጭ ሀገራት ዜጎች በደቡብ አፍሪካዋ ሶዌቶ ጥቃትን እየሸሹ ነው ምንም እንኳን ጊዜው ያለፈበት እና ደረጃውን ያልጠበቅ ምርት ነው የምትሸጡት ቢሉም መልሰው ይህንኑ ንብረት ነው የሚዘርፉት ሲል ሞሐመድ ይናገራል። በ'ዋትስአፕ የመገናኛ አውታር የአካባቢው ሰዎች ሶማሊያዊ ተከራዮችን ከቤታቸው እንዲያስወጡ ካልሆነ ግን ጥቃቱ ለእነሱም እንደሚተርፍ ቀነ ገደብ የተቀመጠለት የዛቻ መልዕክት እንደተሰራጨም ተነግሯል። ''ከመዘረፍ ባሻገር የተደበደቡ ጓደኞች አሉኝ፤ እንዲሁም የታሰሩ አሉ'' ሲል ሞሐመድ ይናገራል። ''የአካባቢው ማህብረሰብ ለኛ መልካም ያልሆነ አመለካከት ነው ያለው። እንደ ሰው እንኳን አይቆጥሩንም'' በማለት የውጪ ሃገራት ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌላቸው ያስረዳል። ባሳለፍነው ዕሮብ በሶዌቶ የውጪ ሃገራት ዜጎች መደብሮች ተዘርፈዋል ሌለው ነዋሪነቱን በደቡብ አፍሪካዋ ራንድፎንቴን ያደረገው ኢትዮጵያዊ ኢብራሂም በድሩ ከዝርፊያው ጋር በተያያዘ ከተገደሉት ሶስት ግለሰቦች መካከል አንዱ የ15 ዓመት ደቡብ አፍሪካዊ ሲሆን ሁለቱ የሶማሊያ እና የፓኪስታን ዜጎች ናቸው ብሎናል። የዋትስ አፕ መልእክቱ የተላለፈው ለመላው ደቡብ አፍሪካውያን ቢሆንም ምላሽ ለመስጠት የቀደሙት የሶዌቶ ነዋሪዎች ነበሩ ሲል ሁኔታውን ያስረዳል። ግርግሩ ሲጀመርም ሱቃቸው ከተዘረፈባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ የሶማሊያ ዜጋ ንብረቱን ለመከላከል የጦር መሳሪያ በመጠቀም አንድ የ15 ዓመት ደቡብ አፍሪካዊ መግደሉንና ከዚያም በኋላ ነገሮች እንደተባባሱ ለቢቢሲ ተናግሯል። ግርግሩና ዝርፊያው በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች ቀጥሏል ወይ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ ኢብራሂም ሲመልስ ''ለጊዜው ችግሩ ያለው በሶዌቶ ብቻ ቢሆንም፤ በሌሎች ከተሞች የሚኖሩ የሌላ ሃገራት ዜጎች ግን በፍርሃት ንብረታቸውን እያሸሹ ነው'' ይላል። ነገር ግን ሌላ ዘረፋ ለማካሄድ በዋትስ አፕ ዘመቻ እንደተጀመረና እስከ መስከረም ስምነት ድረስ የሚቆይ የደቦ ጥቃት እየታሰበ እንደሆነ መስማቱን ኢብራሂም ይናገራል። ፖሊስ እስከ አሁን ድረስ 27 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውያለው ያለ ሲሆን ጥቃቶቹንም አውግዟል። • ጤፍ ሃገሩ የት ነው? ደቡብ አፍሪካ? አውስትራሊያ? . . . ንብረቱን እንደ ተዘረፈ የሚናገረው አንድ ሶማሊያዊ ነጋዴም ''ከአሁን በኋላ እንዴት አድርጌ የንግድ ሥራዬን እንደምቀጥል አላውቅም'' ይላል። ወደ ደቡብ አፍሪካ ከመጣ ስምንት ዓመታት እንዳስቆጠረ እና በእነዚህ ዓመታት ሶስት ጊዜ መዘረፉን ይሁን እንጂ የትኛውም የሃገሪቱ የመንግሥት አካል እንዳላነጋገረው በምሬት ያስረዳል። ሌላኛው ያነጋገርነው አህመድ ዳንኤል ደግሞ የሚኖረው ሜሴር በሚባል አካባቢ ሲሆን፤ የሚሰራው ግን ''ዋይት ሲቲ'' ሶዌቶ ውስጥ ነው። እሱ እንደሚለው በደቡብ አፍሪካ እንደዚህ አይነት ዝርፊያዎች የተለመዱ ናቸው። ''የአካባቢው ተወላጆች ማንኛውም አይነት ጥያቄ ሲኖራቸው መጀመሪያ የሚመጡት የሌላ ሃገር ተወላጆች ወደሚሰሩበት የንግድ ቦታ ነው'' ይላል። ''ጥያቄው የውሃ ሊሆን ይችላል፤ ጥያቄው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ጥያቄውን ለመንግሥት አቅርበው የኛን ሱቆች ዘርፈው ነው የሚሄዱት'' ሲል በምሬት ለቢቢሲ ተናግሯል። ''አሁንም ቢሆን ያቀረቡት ጥያቄ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምርቶች እየሸጡ ነው የሚል ቢሆንም፤ አንደኛ ምንም ማስረጃ የላቸውም ሁለተኛ ደግሞ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት ከሆነ ለምን ዘርፈው ይበሉታል?'' በማለት ይጠይቃል። የዋትስ አፕ መልእክቱን እንደሰማም ከሱቁ አንዳንድ እቃዎችን ለማሸሽ እንደሞከረና የተረፈውን ግን በአካባቢው ሰዎች እንዲሁም ፖሊሶች እርዳታ ማዳን እንደቻለ ነግሮናል። በሶዌቶ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሶማሊያዊያን፣ ዚምባብዌያዊያን እና ፓኪስታንያዊያን ሱቆችን ከፍተው ይሰራሉ። በፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሶዌቶና አካባቢዋ በሚገኙ የኢትዮጵያውያን ዜጎች ንብረትና ሀብት ላይ ጥቃት መድረሱን መስማቱን እና ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ በፌስቡክ ገጹ ላይ አሳታውቋል። ኤምባሲው ጨምሮም ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና እርዳት የሚሹ ከሆነ ወደ ኤምባሲው ስልክ መደወል እንደሚችሉ ገልጿል። • ደቡብ አፍሪካ፡መውጫ አጥተው የነበሩ 955 የማእድን ቁፋሮ ሰራተኞች ወጡ
49750890
https://www.bbc.com/amharic/49750890
የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ በዘረኛ ፎቶግራፋቸው እየተተቹ ነው
ከሁለት አሠርት ዓመታት በፊት በአንድ የግል ትምህርት ቤት ውስጥ በተካሄደ ድግስ ላይ፤ የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ፊታቸውን ቡናማ ቀለም ተቀብተው የሚያሳይ ፎቶግራፍ በ 'ታይም' መጽሔት ይፋ ተደርጓል።
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2001 ላይ ጀስቲን ትሮዶ ቡናማ ቀለም ፊታቸውን ተቀብተው የተነሱት ፎቶግራፍ ፎቶው ይፋ ከተደገ በኋላ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ "ባደረግኩት ነገር እጅጉን ተጸጽቻለሁ፤ የተሻልኩ ሰው ሁኜ መገኘት ነበረብኝ" ብለዋል። ድግሱ የተከናወነው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2001 ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ያስተምሩበት በነበረ አንድ የግል ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር። ጀስቲን ቆዳ የሚያጠቁር 'ሜክ-አፕ' (መዋቢያ) ፊታቸውን እንዲሁም እጃቸውንም ተቀብተውም ነበር። • ካናዳ ዕፀ ፋርስን ህጋዊ አደረገች • ወደ ካናዳ መሄድ አስበዋል? ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ፒየሬ ትሮዶ ልጅ የሆኑት ጀስቲን ትሩዶ፤ የፊታችን ጥቅምት ላይ የምርጫ ውድድር ይጠብቃቸዋል። 'ታይም' የጠቅላይ ሚንትሩን ፎቶ የያዘ ዘገባ ካስነበበ በኋላ፤ ድርጊታቸው ዘረኛ እንደነበረ አምነው "ማድረግ አልነበረብኝም" ብለዋል። 'አረቢያን ናይትስ' በሚል የተሰየመው ድግስ ላይ አላዲን የተባለውን ገጸ ባህሪ ተላብሰው እንደተገኙም ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። ጋዜጠኞች፤ ጠቅላይ ሚንስሩ ከ2001ዱ ድግስ በፊት ወይም በኋላ ፊታቸውን ቡናማ ቀለም ተቀብተው እንደሆነ ጠይቀዋቸው ነበር። "የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለሁ በተደረገ የተሰጥኦ ውድድር ላይ ቡናማ ቀለም ተቀብቼ ነበር" ብለው ምላሽ ሰጥተዋል። 'ናሽናል ካውንስል ኦፍ ክኔዲያን ሙስሊምስ' የተባለው የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ማኅበር የጠቅላይ ሚንስትሩን ድርጊት ኮንነዋል። • ትሩዶ፡ ከሁዋዌ ባልደረባ እስር ጀርባ ፖለቲካ የለም • የካናዳ ፓርላማ የሳን ሱ ኪን የክብር ዜግነት ገፈፈ የማኅበሩ ዋና ኃላፊ ሙስጠፋ ፋሩቅ "ጠቅላይ ሚንስትሩ ቡናማ ወይም ጥቁር ቀለም ተቀብተው ማየት እጅግ ያሳዝናል። የምሥራቁ ዓለም በተዛባ መንገድ ወደሚሳልበት ዘረኛ ዘመን የሚወስድም ነው" ብለዋል። የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪ የሆኑት አንድሪው ሺር፤ "ፎቶው በ2001 ዘረኛ እንደነበረው ሁሉ አሁን ባለንበት ዘመንም ዘረኛ ነው፤ አገሪቱን ለመምራት ብቁ አይደሉም" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩን ወቅሰዋል። 'ኒው ዴሞክራቲክ ፓርቲ' የተባለው ፓርቲ መሪና የሲክ ሀይማኖት ተከታይ የሆኑት ጃግመንት ሲንግህ "ፎቶው ክብረ ነክ ነው" ብለዋል። ጃግመንት ሲንግህ ቶሮንቶ ውስጥ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ ሳለ "አንድ ሰው ቡናማ ወይም ጥቁር ቀለም ሲቀባ በጥቁሮች ላይ እየተሳለቀ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የ 'ግሪን ፓርቲዋ' ኤልዛቤጥ ሜይም ጠቅላይ ሚንስትሩን ተችተዋል። ይህ ፎቶግራፍ ተራማጅ ፖሊሲዎች አሉኝ የሚሉት ጀስቲን ትሩዶን ገጽታ የሚያጠለሽ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ ለመመረጥ እየተወዳደሩ ያሉት ጀስቲን፤ በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ያጡ ይሆን? የሚል ጥያቄም አጭሯል።
news-44372142
https://www.bbc.com/amharic/news-44372142
የፕሮፌሰሩ ዳንስ ሕንዶችን አስደንቋል
ሰውዬው በከፍተኛ የትምህርት ተቋም የተከበሩ የኤሌክትሮኒክስ ፕሮፌሰር ናቸው።
በአጋጣሚ ነው ነገሩ የተከሰተው። በተጠሩበት ሠርግ ድንገት ነሸጥ አድርጓቸው ወደ መድረክ ከወጡ በኋላ ባሳዩት ልዩ የዳንስ እንቅስቃሴ ታዳሚውን አስደምመዋል። "እንዴት አንድ ከጸጉራቸው ገባ፣ ከሆዳቸው ገፋ ያሉ ፕሮፌሰር በዚህ ዓይነት ቅልጥፍና ሊደንሱ ይችላሉ?" የሚለው ሕንዳዊያንን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን እያነጋገረ ይገኛል። በፍጹም በዚህ ቅጽበት እንዲህ ዝነኛ እሆናለሁ አላልኩም ብለዋል ፕሮፌሰሩ ለጋዜጠኞች። የእርሳቸው ቪዲዮ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በፍጥነት መዘዋወሩን ተከትሎ እጅግ ዝነኛ ሕንዳዊ ሙዚቀኞችና አርቲስቶች ሳይቀሩ ፕሮፌሰሩን ለማድነቅ ወደ ትዊተር ገጻቸው አቅንተዋል። የፕሮፌሰሩ ትዊተር ገጽ በአጭር ጊዜ 3ሺህ ተከታዮችን አግኝቷል። በሕንድ ትዊተር ገጾች #ዳንሰኛው-አጎቴ ወይም #dancinguncle በሚል "ሀሽታግ" ተጥለቅልቀው ውለዋል። "ባለፉት ቀናት እንቅልፌን መተኛት እንኳን አልቻልኩም" ይላሉ ፕሮፌሰሩ ዝና እረፍት እንደነሳቸው ሲያብራሩ።
news-54009939
https://www.bbc.com/amharic/news-54009939
ኬንያ አል-ሸባብን በገንዘብ ይደግፋሉ ያለቻቸው ሰዎች ንብረት ላይ እገዳ ጣለች
ጽንፈኛውን ቡድን አል-ሸባብ በፋይናንስ ይደግፋሉ የተባሉ የ9 ሰዎች ንብረት እንዳይንቀሳቀስ የኬንያ መንግሥት እገዳ ጣለ።
የኬንያው የአገር ውስጥ ሚንስትር ይህ የመንግሥት ውሳኔ ኬንያ ‘የአገር ውስጥ ሽብርን’ ለመግታት ከወሰደቻቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ ነው ብለዋል። ንብረታቸውን እንዳይንቀሳቀስ እገዳ የተጣለባቸው ዘጠኙ ግለሰቦች የኬንያ ዜጎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የግለሰቦቹ ማንነትም ይሁን አሁን ስለሚገኙበት ሁኔታ የተባለ ነገር የለም። ሚንስትሩ ፍሬድ ማቲአንጊ የዘጠኙ ግለሰቦች ንብረት ላይ እገዳ መጣሉ በኬንያ ሆነው አል-ሸባብን እንዳይደግፉ ያረጋል ብለዋል። ሚንስትሩ ጨምረውም፤ መቀመጫውን ሶማሊያ ያደረገው አል-ሸባብ በኬንያ የሽብር ጥቃቶች ለመፈጸም ምለመላዎችን እያካሄደ እና በሲቪሉ ሕዝብ ውስጥ የራሱን ሰዎች አስርጎ እያስገባ ነው ብለዋል። ይህ የኬንያ መንግሥት ውሳኔ የተሰማው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በኮቪድ-19 ምክንያት በቀጠናው የሽብር እንቅስቃሴዎች መጨመራቸውን ከገለጹ በኋላ ነው። ፕሬዝደንት ኡሁሩ ከሌሎች አገራት መሪዎች ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ የሽብር እንቅስቃሴዎች፣ የስደተኞች ቁጥር እና የጦር መሣሪያ ዝውውር በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ባሉ አገራት ውስጥ ጭምሯል ብለዋል። ኬንያ እአአ 2011 ላይ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ካዘመተች በኋላ በጽንፈኛው ቡድን በርካታ ጥቃቶች ተፈጽመውባታል። ከእነዚህም መካከል እአአ 2013 ላይ ዌስት ጌት ተብሎ በሚጠራው የገበያ ማዕከል ውስጥ አል-ሸባብ ባደረሰው ጥቃት ከ60 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። በቅርቡም በመዲናዋ በሚገኘው ቅንጡ ዱሲትዲ2 ሆቴል በአል-ሸባብ በተፈጸመ ጥቃት 21 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።
news-56264107
https://www.bbc.com/amharic/news-56264107
ሱዳንና ግብጽ የጋራ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
ሱዳንና ግብጽ በከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናቶቻቸው በተከታታይ ዙሮች ሲያካሂዱት የነበረውን ውይይት አጠናቀው የጋራ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን ሱና ዘገበ።
የግብጽ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ሌፍተናንት ጀነራል ሞሐመድ ፋሪድ እና የሱዳን ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሞሐመድ ኦስማን አል ሁሴን የሱዳን ዜና አገልግሎት-ሱና ይህ ስምምነት የተፈረመው የግብጽ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ሌፍተናንት ጀነራል ሞሐመድ ፋሪድ ካርቱም ውስጥ ያደረጉት ጉብኝት ማብቂያ ላይ ነው። የሱዳን ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሞሐመድ ኦስማን አል ሁሴን "ስምምነቱ ለሁለቱ አገራት ብሔራዊ ደኅንነትና በልምድ የዳበረ ጦር ሠራዊት ለመገንባት ያለመ ነው" ማለታቸውን እና ግብጽ ለሱዳን ለምታደርገውን ድጋፍ አድናቆታቸውን እንደገለጹ የቻይና ዜና ወኪል ዢንዋ ዘግቧል። የግብጹ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን ሞሐመድ ፋሪድም አገራቸው ከሱዳን ጋር ያላትን ግንኙነት በሁሉም መስኮች ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸው "ወታደራዊና ደኅንነት መስክ" የተለየ ትኩረታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ማክሰኞ ዕለት በተፈረመው የሁለቱ አገራት ወታደራዊ ስምምነት መሰረት የአገራቱ ብሔራዊ ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሚቻለው ነገር ሁሉ ተባብረው ለመስራት ከስምምነት እንደደረሱ የግብጹ አል አህራም ጋጤጣ ዘግቧል። "የጋራ የሆኑ አካባቢያዊ ስጋቶች አሉብን፤ ስለዚህም እነዚህን ስጋቶች በሁሉም መስክ በጋራ ለመቋቋም በጋራ መስራት አለብን" ሲሉ የግብጹ ወታደራዊ ባለስልጣን ሞሐመድ ፋሪድ ተናግረዋል። ከሁለት ቀናት በፊት የሱዳን መከላከያ ሚንስቴር የግብጽ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹሙ ወደ ካርቱም ማምራቸውን አስታውቆ፤ ኤታማዦር ሹሙ ከሱዳን ጦር ጋር ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ውይይቶች እንደሚደረጉ ገልጾ ነበር። ሱዳንና ግብጽ ከዚህ ቀደም የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ያደረጉ ሲሆን ተመሳሳይ ልምምዶች በቀጣይነት እንደሚኖሩ ይጠበቃል። የየአገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በካርቱምና በካይሮ መካከል እየተመላለሱ ውይይቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው የተነገረ ሲሆን አል አህራም የተባለው የግብጽ ጋዜጣ እንደዘገበው የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ በሐሙስና በቅዳሜ መካከል ባሉት ቀናት ውስጥ ለጉብኝት ወደ ሱዳን ይሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ግብጽ እና ሱዳን፡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ታሸማግለን ይህ በእንዲህ እንዳለ ግብጽ እና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንድታሸማግል ፍላጎታቸውን አሳይተዋል። አገራቱ ይህን ያሉት የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቲሼኬዲ የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበርነት ቦታን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት መረከባቸውን ተከትሎ ነው። የሁለቱ አገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ባወጡት ጥምር መግለጫ የአፍሪካ ሕብረት፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ሕብረት እና የተባበሩት መንግሥታት በድርድሩ እንዲሳተፉ ድጋፋቸውን ገልጸዋል። ሚንስቴር መስሪያ ቤቶቹ በመግለጫቸው፤ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ዙር የግድቡን ውሃ ሙሊት የምታካሂድ ከሆነ በሁለቱ አገራት የውሃ አቅርቦት ደኅንነት ላይ ቀጥተኛ ስጋትን ይፈጥራል ብለዋል። ሁለቱ አገራት ኢትየጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባቸው ባለችው ኃይል ማመንጫ ግድብ ምክንያት የምናገኘው የውሃ መጠን ይቀንሳል በሚል ስጋት አላቸው። ሁለቱ አገራት በአንድ ላይ ቆመው ጥቅማቸውን የሚያስከብር አሳሪ ስምምነት እንዲፈረም ጥረት እያደረጉ ነው። ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው ግድብ በወንዙ የውሃ ፍሰት ላይ ጉዳት የማስከትል መሆኑን በመግለጽ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ከመሆኗ ባሻገር ብሔራዊ ጥቅሟን የማያስከበር ስምምነት ውስጥ ለመግባት ፍቃደኛ አለመሆኗን በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች። በሦስቱ አገራት መካከል ያለውን አለመግባባት በውይይት ለመፍታት ለዓመታት የዘለቀ ውይይት ቢካሄድም ሁሉንም በሚያስማማ ሁኔታ ሳይቋጭ አስካሁን የቆየ ሲሆን በአፍሪካ ሕብረት አሸማጋይነት ሲካሄድ በቆየው ድርድር ግብጽና ሱዳን በአንድ ላይ በመቆም ጥቅማቸውን ለማስከበር እየጣሩ ነው። በተጨማሪም ካለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ ሱዳን ወታደሮቿን በማሰማራት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ሰፍረውበት የነበረውንና የእራሴ ግዛት አካል ናቸው የምታላቸው ቦታዎች በቁጥጥሯ ስር ማስገባቷ ይታወሳል። ኢትዮጵያም በሱዳን ሠራዊት ወረራ እንደተፈጸመባት በመግለጽ ወታደሮቿ ከግዛቷ እንዲወጡና የድንበሩ ጉዳይ ቀደም ሲል በተጀመረው ውይይት እንዲፈታ እየጠየቀች ትገኛለች።
news-44736722
https://www.bbc.com/amharic/news-44736722
ቢጫና ቀይ ካርዶችን ማንና ለምን ፈጠራቸው?
አንዳንድ የእግር ኳስ ጨዋታዎች በጣም ትግል የበዛባቸው ከመሆናቸው የተነሳ የጦር አውድማ መሆን ይቃጣቸዋል፤ ማረጋጊያ መንገድ እስኪጠፋ ድረስ። ፖሊስ ገብቶ የገላገላቸው በርካታ ጨዋታዎች መኖራቸውን ልብ ይሏል። ይህን የተመለከተው ሰው ያመጣው ዘዴ እስከዛሬ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው።
«መኪናዬን እያሽከረከርኩ አንድ መንገድ ላይ የትራፊክ መብራት ያዘኝ፤ ቁጭ ብዬ አሰላስል ያዝኩ። ቢጫ ተጠንቀቅ ነው ቀይ ደግሞ ቁም።» ይህች ቅፅበት እግር ኳስን የቀየረች ሆና ተመዘገበች። እንግሊዛዊው አርቢትር ኬኔት ጆርጅ አስተን ይህን ዘዴ ለምን እግር ኳስ ላይ አይተገበርም የሚል ሃሳብ ብልጭ አለለት። ጊዜው በፈረንጆቹ 1960ዎቹ ገደማ፤ 'ኧረ በሕግ' ባይ ያጡ የሁለት እግር ኳስ ቡድን አባላት ቡጢ ገጠሙ፤ ሜዳው የፀብ አውድማ ሆነ። የተጎዱ ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ። ይህ የሆነው በፈረንጆቹ 1960 ላይ በቺሊ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ነበር። የሳንቲያጎ አውድማ በመክፈቻው ጨዋታ ሶቪየት ሕብረትና ዩጎዝላቪያ ጨዋታ ገጠሙ፤ ኧረ ቡጢ ገጠሙ ማለት ይቀላል። ጀርመን እና ጣልያን ያደረጉት ጨዋታም እንዲሁ መፈነካከት የተሞላ ነበር። አጥንቶች ተሰበሩ፤ የአርቢትሩም ፊሽካ የሚሰማ ጠፋ። 'እስቲ ዛሬ እንኳን ሰላማዊ ጨዋታ እንይ' ብለው ሦስተኛውን ቀን የጠበቁ ተመልካቾች በቼኮዝሎቫኪያ እና በስፔን መካከል የተደረገውን ግጥሚያ. . . ይቅርታ. . .ፍልሚያ ሊያዩ ግድ ሆነ፤ አንዳንድ ተጫዋቾች ቡጢው ራሳቸውን አሳታቸው። አርጀንቲናና ቡልጋሪያም እንዲሁ ሜዳውን ወደ የግብግብ አውድማነት ቀየሩት። 'መች ተለካካንና' ያሉ የሚመስሉት የጣልያንና የቺሊ ብሔራዊ ቡደኖች ታሪክ ፃፉ፤ የሳንቲያጎ አውድማ ተብሎ የሚጠራውን ታሪክ። ቡጢ፣ ካራቴ፣ ጥፊ . . . ብቻ ጨዋታው ደንበኛ በድርጊት የተሞላ (Action) ሲኒማ ሆኖ አረፈው። ጨዋታው በቺሊ 2 ለምንም አሸናፊነት ተቋጨ። አርቢትሩ ግን ከትችት አልተረፉም፤ ኧረ ቡጠም ቀምሰዋል። ዳኛው እንግሊዛዊው ኬኔት ጆርጅ አስተን ነበሩ፤ የቢጫና ቀይ ካርድ ሃሳብ ብልጭ ያለላቸው ግለሰብ። ጊዜው በፈረንጆቹ 1970 ዓ.ም፤ የሜክሲኮ ዓለም ዋንጫ። አርቢትር አስተን 'ግድ የላችሁም አንዲት ሃሳብ አለኝ፤ አድምጡኝ' ሲሉ ተሰሙ። «እኔኮ የእግር ኳስ ዳኝነት ሳይሆን በሁለት ቦክሰኛ መካከል ያለ አቧቃሽ ነበርኩ» ክስተቱን እንዲህ ነበር የዘከሩት። ኬኔት አስተን 22 ተዋናዮች የሚሳተፉበት ደንበኛ ሲኒማ አርቢትሩ 1963 ላይ 'አሁንስ በቃኝ ባይሆን ከሜዳ ውጭ ባለው ላግዛችሁ' ብለው የፊፋ ዳኞች ኮሚቴን ተቀላቀሉ። ኮሚቴውን በፕሬዝደንትነት መምራት ዕድሉን ያገኙት አስተን 1966 ላይ ሃገራቸው እንግሊዝ ከአርጀንቲና ስትጫወት የተፈጠረው ነገር ሰቅዞ ያዛቸው። የዕለቱ አርቢትር ጀርመናዊው ሩዶልፍ ነበሩ፤ ጥፋት ፈፅሟል ያሉትን የአርጀነቲና አምበል ከሜዳ እንዲወጣ አዘዙ፤ አምበሉ ግን አሻፈረኝ አለ። ችግሩ የነበረው ዳኛው ሰፓኒሽ አለመቻላቸው፤ ተጫዋቹ ደግሞ ጆሮው ቢቆረጥ ጀርመንኛም ሆነ እንግሊዝኛ አለመቻሉ ነው። አስተርጓሚ እስኪመጣ በሚል ለ10 ደቂቃ ያህል ጨዋታው ተቋረጠ። ትርጉሙን የሰሙ የአርጀንቲና ተጫዋቾች ግን 'ፍንክች የአባቢላዋ ልጅ'። ሁኔታው ያልጣማቸው የእንግሊዝ ፖሊሶች ዳኛው ከበው ከሜዳ አሸሿቸው። የጊዜው የዳኞች ኮሚቴ አለቃ አስተን ወደሜዳ ገብተው ሁኔታውን ካረጋጉ በኋላ ጨዋታው እንዲቋረጥ ሆነ። ይሄኔ ነው ሰውዬው ለዚህ ጉዳይ መላ መዘየድ ግድ ሆኖ የታያቸው፤ የትራፊክ መብራቱ ሃሳብም እውን እንዲሆን መንገድ ተጠረገ። «እግር ኳስ 22 ተዋናዮች የሚሣተፉበት ዳኛው ደግሞ እንደ አዘጋጅ ሆኖ ማገልገል ያለበት መድረክ ነው» ሲሉ ነበር አርቢትሩ ስለኳስ ያላቸውን እምነት ያንፀባረቁት። «ስክሪፕት የሌለው፣ መጀመሪያውም መደምደሚያውም ወረቀት ላይ ያልሰፈረ ትዕይንት ሊሆን ይገባል፤ ፍርደ ገምድልነት ግን ሊንፀባረቅበት የማይገባ» ሲሉ አስረግጠዋል።
news-51094936
https://www.bbc.com/amharic/news-51094936
የሁለት ሳምንት አስክሬን አስነሳለሁ ያለችው 'አማኝ' በገንዘብ ተቀጣች
በኦሮሚያ ክልል ቦሰት ወረዳ ወለንጪቲ ከተማ ከሞተ ሁለት ሳምንት የሆነውን የሁለት ወር ህፃን "ከሞት እንዳስነሳ ራዕይ ታይቶኛል" በማለት መቃብር ያስቆፈረችው 'አማኝ' በማጭበርበር መቀጣቷን ፖሊስ ለቢቢሲ ገልጿል።
ህጻኑ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከሞተ በኋላ ራዕይ ታይቶኛል ያለችው ሴት፤ የህጻኑን እናት እና አንዲት ሌላ ሴት በመያዝ ወደ መቃብር ሥፍራ በመሄድ ቆፍረው ማውጣታቸውን የቦሰት ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ካሰኝ ደምሴ ገልጸዋል። ''ግለሰቧ እንደ ለቅሶ ደራሽ በመሆን ወደ እናት ቤት በመሄድ ልጅሽ አልሞተም፤ በሕይወት ነው ያለው፤ ከሞት እንዳስነሳውም ራዕይ ታይቶኛል" ትላታለች። መቃብር ሥፍራም ሄዳ ጸሎት ማድረግ እንደምትፈልግ ትነግራታለች። እናትም እውነት መስሏት ተያይዘው ወደ መቃብር ሥፍራው ሄደዋል። ዋና ኢንስፔክተር ካሰኝ እንዳሉት መቃብር ሥፍራ ከደረሱ በኋላ ህጻኑን ቆፍራ አውጥታ እዛው ስትቀመጥ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ተመልክተው ለፖሊስ ጥቆማ አደረሱ። ከዚያም ፖሊስ በቦታው ደርሶ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ህብረተሰቡን አስተባብረው አስክሬኑ እንዲቀበር አድርገዋል። • በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው በአዞ ተገደሉ • በምሥራቅ ወለጋ የአራት ቀን ሬሳ አስነሳለሁ ብሎ መቃብር ያስቆፈረው 'ነብይ' በቁጥጥር ሥር ዋለ ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታተለው ቆይቶ ግለሰቧ ለፈጸመችው ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርባ ተገቢውን ቅጣት እንዳገኘች ዋና ኢንስፔክተር ካሰኝ ደምሴ ነግረውናል። በብይኑ መሰረትም ጥፋተኛ መሆኗ ስለተረጋገጠ በ2000 ብር ተቀጥታለች። 'አማኟ' በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላት ኃላፊነት ምን ነበር? ያልናቸው ኢንስፔክተሩ፤ ''ከታሪኳ እንደምንረዳው አማኝ ነች እንጂ፤ አገልጋይም ወይም ሌላ ነገርም አይደለችም'' ብለዋል። ከተቀበረ ሁለት ሳምንታት የሞላውን ህጻን ፈጣሪ ራዕይ አሳይቶኛል በማለት አስክሬኑ ተቆፍሮ እንዲወጣ መደረጉ የአካባቢውን ነዋሪ በጣም ያስቆጣና የተከበረውን የመቃብር ቦታ ክብር የሚነካ እንደሆነ ዋና ኢንስፔክተር ካሰኝ ገልጸዋል። ፍርድ ካገኘችው ይህች ሴት በተጨማሪ እናት እና 'አማኟን' ይዛት የመጣች አንዲት ሌላ ሴት በወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ የተደረገባቸው ሲሆን ሁለቱ ጥፋተኛ አለመሆናቸው ስለተረጋገጠ በነጻ ተሰናብተዋል። • ሰባኪው አውሮፕላን ግዙልኝ አለ እናትም ለፖሊስ በሰጠችው ቃል "ልክ እንደ ማንኛውም ለቅሶ የሚደርስ ሰው ወደ ቤት ከመጣች በኋላ 'ራዕይ ታይቶኛል፤ ልጅሽን አስነሳለሁ' ብላ በመጀመሪያ ቤት ውስጥ ጸሎት ካደረገች በኋላ ወደ መቃብር ሥፍራው ሄደን አስክሬኑን አወጣነው። ያው የእናት አንጀት ሆኖብኝ አመንኳት'' ብላለች። 'ራዕይ ታይቶኛል' ያለችውን 'አማኝ' ወደ ቤት ይዛት የመጣችው ሌላኛዋ ሴት ከልጁ አባት ጋር በአንድ መሥሪያ ቤት አብረው እንደሚሰሩም ዋና ኢንስፔክተሩ አስረድተዋል። አስክሬኑ ተቆፍሮ በወጣበት ወቅት "እንዴት አንድ ጤናማ ሰው ከተቀበረ ሁለት ሳምንት የሆነውን አስክሬን አውጥቶ፤ ይዞ ይቀመጣል?" በሚል የአካባቢው ነዋሪ በመረበሹ ግርግር ተፈጥሮም እንደነበረ ዋና ኢንስፔክተሩ አክለዋል።
46134514
https://www.bbc.com/amharic/46134514
ፓኪስታን ክርስትያኗን አሲያ ቢቢን ከእስር ለቀቀች
ፓኪስታናዊቷ ክርስቲያን በእስልምና ሃይማኖት ላይ ስድብ ሰንዝረሻል ተብላ ሞት ተፈርዶባት ስምንት ዓመት በእስር ቤት ካሳለፈች በኋላ ከእስር ነፃ መውጣቷን ጠበቃዋ ተናገሩ።
አንዳንዶች ከእስር ቤት እንደወጣች አውሮፕላን መሳፈሯን የዘገቡ ሲሆን መዳረሻዋ ግን ገና አልታወቀም። የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከአክራሪዎች ዘንድ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን መንግሥትም ፓኪስታንን ለቅቃ እንዳትሄድ አደርጋለሁ ብሎ ነበር። • የፓኪስታን ፍርድ ቤት ሞት የተፈረደባትን ክርስቲያን ነፃ ለቀቀ • የፓኪስታን ዲፕሎማት የኪስ ቦርሳ ሰረቁ • «አማካሪ አያስፈልገኝም ብሎ የሚያስብ መሪ አልገባውም» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ባለቤቷም ሕይወታቸው ስጋት ውስጥ መውደቁን ተናግሮ ሀገራት ጥገኝነት እንዲሰጧቸው ጠይቆ ነበር። የአምስት ልጆች እናት የሆነችው አሲያ ቢቢ ሙልታን ከተማ ከሚገኘው እስር ቤት መለቀቋን ጠበቃዋ ሰይፍ ሙሎክ ተናግሯል። ቢቢ አሲያ ኖሪን በመባልም የምትታወቅ ሲሆን በ2010 ነበር በእስልምና ሃይማኖት ላይ ስድብ ሰንዝረሻል በሚል የተከሰሰችው። ከዚያ በኋላም በርካታ ሐገራት ጥገኝነት ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነዋል። • በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች ቢቢ እንደምትለቀቅና ሀገር ለቅቃ እንደምትወጣ ከተሰማ በኋላ በርካቶች የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ነበር። የፓኪስታን መንግሥት ከእስር ብትለቀቅም ከሀገር እንዳትወጣ እንዲከለከል በፍርድ ቤት እንደሚጠይቅ ተናግሮ ነበር። በርካታ ተቃዋሚዎች የእስልምና ሃይማኖትን በመሳደብ የሚደርሰውን የሕግ ቅጣት የሚደግፉና አሲያ ቢቢ በስቅላት እንድትገደል የሚጠይቁ ናቸው። የአንድ እስላማዊ ቡድን መሪ ሶስቱም የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች "ሊገደሉ ይገባል" ሲል ተናግሯል። በጠንካራ ተቃውሞው የሚታወቀው ቲ ሊፒ ፓርቲ የቢቢ መለቀቅ ከመንግሥት ጋር ያለን ስምምነት መፍረስ ምልክት ነው ብሎታል። "መሪዎቹ ታማኝ እንዳልሆኑ አሳይተውናል" ብሏል የፓርቲው ቃል አቀባይ ኢጃዝ አሻሪፍ ለሮይተርስ። በፓኪስታን ከ1990 ጀምሮ ቢያንስ 65 ሰዎች የእስልምና ሃይማኖት ላይ ስድብ ሰንዝረዋል በሚል ተገድለዋል።
news-50259097
https://www.bbc.com/amharic/news-50259097
የስፔኑ ፍርድ ቤት ኃይል አልተጠቀሙም ያላቸውን 5 አስገድዶ ደፋሪዎች ነፃ አለ
የስፔኗ ባርሴሎና ፍርድ ቤት የ14 ዓመት ታዳጊ ላይ ፆታዊ ጥቃት በመፈፀም ተጠርጥረው እስር ላይ የነበሩ 5 ወንድ ልጆችን "ድርጊቱን ለመፈፀም ኃይል አልተጠቀሙም" ሲል በነፃ ማሰናበቱ በከተማዋ ተቃውሞ ቀስቅሷል።
ስለዚህ ታዳጊዎቹ በአስገድዶ መድፈር ሳይሆን በዝቅተኛ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል የሚጠየቁ ይሆናል። በስፔን ሕግ ፆታዊ ጥቃት አስገድዶ መድፈር የሚሆነው ኃይልን በመጠቀም ወይም በማስፈራራት ሲፈፀም ነው። የስፔን መንግሥት በአሁኑ ወቅት ይህን ሕግ ለማሻሻል እየሠራ ነው። ከዚህ በመነሳት የ14 ዓመቷ ታዳጊ ሰክራ ሯሷን ታውቅ ስላልነበር ወንዶቹ እሷ ላይ ፆታዊ ጥቃት ለመፈፀም ኃይል አልተጠቀሙም በሚል ነው ከአስገድዶ መደፈር ክስ ነፃ ያላቸው ፍርድ ቤቱ። ቀደም ሲልም በዚህ ክስ መዝገብ ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፎ የነበረ ቢሆንም የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን ሽሮት ነበር። አሁን ደግሞ የባርሴሎናው ፍርድ ቤት የቀደመውን ውሳኔ አፅንቶ ታዳጊዎቹን ከአስገድዶ መድፈር ክስ ነፃ ብሏቸዋል። መጀመሪያ ላይ በዚህ የክስ መዝገብ 6 ሰዎች ተከሰው 5ቱ ጥፋተኛ ተብለው ከአስር እስከ አስራ ሁለት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው ነበር። በመጨረሻ ግን ፍርድ ቤቱ ተጠቂዋ በወቅቱ ምን እንዳደረገችና እንዳላደረገች አታውቅም፤ በነገሩ ለመስማማት ላለመስማማትም የምትችልበት አዕምሯዊ ብቃት አልነበራትም ብሏል። በዚህ ምክንያት ግለሰቦቹ ኃይልን ሳይጠቀሙ ወሲብ መፈፀም ችለዋል ብሏል። ስለዚህም ለተፈፀመባት "በጣም መጥፎ ዓይነት ጥቃት" ካሳ ለተጠቂዋ አስር ሺህ ፓውንድ እንዲሰጣት ውስኗል። • ለ26 ዓመቱ ወጣት የ250 ዓመት የእስር ፍርድ • የዙሉው ንጉሥ ማኮላሸት አስገድዶ መድፈርን ያስቀራል አሉ • ሀርቪ ዋንስታይን 44 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍል ነው
52307086
https://www.bbc.com/amharic/52307086
ኮሮናቫይረስ አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የአውሮፓ እግር ኳስ
በአሁኑ ሰአት ተቋርጦ የሚገኘው የአውሮፓ እግር ኳስ ከዚህ በኋላ በዝግ ስታዲየሞች እንዲደሚካሄድ ግልጽ ቢሆንም መቼ የሚለው ጥያቄ ግን ምላሽ አላገኘም።
ይህንን ያለው በአውሮፓ የሚገኙ ሊጎችን የሚወክለው ማህበር ነው። የማህበሩ ምክትል ኃላፊ አልቤርቶ ኮሎምቦ እንዳሉት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተቋረጠው የአውሮፓ ሊግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብቷል። ‘’አብዛኛዎቹ የማህበሩ አባል ሊጎች በተለይም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች እንዲጀመሩ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ነገር ግን እንደ ቤልጂየም ያሉ ጥቂት አገራት ከነጭራሹ የዘንድሮው ውድድር እንዲሰረዝ ሀሳብ አቅርበዋል’’ ብለዋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርብ ዕለት የወደፊት እርምጃዎችን በተመለከተ ስብሰባ እንደሚያደርግ የሚጠበቅ ሲሆን ዘጠኝ ጨዋታዎች የሚቀሩት ሊግ መቼ ይቀጥል? የሚለው ዋና ርዕስ እንደሚሆን ይጠበቃል። ባለፈው ሳምንት አንዳንድ የጀርመን ክለቦች ወደ ስልጠና መመለሳቸውን ተከትሎ እግር ኳስ ማህበራትና የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በተስፋ ተሞልተው ነበር። አልቤርቶ ኮሎምቦ ግን ዋናው ትኩረታችን መሆን ያለበት ሐምሌ እና ነሀሴ ላይ ጨዋታዎቹን እንዴት ማስቀጠል አለብን የሚለው ላይ ነው፤ ከዛ በፊት ያሉት ወራት ላይ ጨዋታዎችን ማካሄድ የማይታሰብ ሊሆን ይችላል ብለዋል። ‘’በመጀመሪያ የተጫዋቾች ስልጠና መጀመር አለባቸው። በመቀጠል የጨዋታዎቹ አዘጋጆች የደህንነት ማረጋገጫ ስራዎችን ይሰራሉ። ጨዋታዎቹ በዝግ ስታዲየሞች መከናወናቸው የማይቀር ነገር ነው።‘’ ‘’እኛ ሀሳብ እናቀርባለን እንጂ የመጨረሻው ውሳኔ ያለው የአገራቱ መንግስት ላይ ነው። የተጣሉት እገዳዎች እንደተነሱ ጨዋታዎችን ከከፍተኛ ጥንቃቄ ጋር በዝግ ስታዲየም እናከናውናለን።‘’ የጣልያን እግር ኳስ ፌደሬሽን እግር ኳስ ተጫዋቾች ሌላው ቢቀር ልምምዳቸውን መስራት እንዲጀምሩ በማሰብ ከመጪው ግንቦት ወር ጀምሮ ተጫዋቾቹ ላይ የኮሮናቫይረስ ምርምራ ማድረግ እንደሚጀምር አስታውቋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር በበኩሉ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተከሰተውን የሊጎችና ውድድሮች መቋረጥን በተመለከተ በሚቀጥለው ሳምንት ስብሰባ ያደርጋል ተብሏል።
news-41269937
https://www.bbc.com/amharic/news-41269937
የሁለቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ወግ፡ ኑሮና ጥቅማጥቅም ከርዕሰ ብሔርነት በኋላ
በቀድሞ ሁለት ፕሬዝዳንቶችን መኖሪያ ቤት ተገኝተን ባነጋገርናቸው ወቅት የሚገኙበት የኑሮ ሁኔታ ሰፊ ልዩነት ያለው መሆኑን ለመረዳት አላዳገተንም። በኑሯቸው ብቻም አይደለም፤ ግንኘነታቸውም ያን ያህል እንደኑሯቸው የተራራቀ ነው።
የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የተለያየ የኑሮ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ነበሩ። አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ደግሞ መንበረ ሥልጣኑንን ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በመቀበል ሃገሪቷን ለ12 ዓመታት በርዕሰ ብሔርነት አገልግለዋል። ዛሬ ላይ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ? ዶ/ር ነጋሶ ሃገሪቷ የምትመራበት መንገድ ሳያስማማቸው ቀርቶ ስልጣን በራሳቸው ፍቃድ ከለቀቁ አስራ ስድስት ዓመታት አልፈዋል። የመጀመሪያዎቹን አራት ዓመታት መጸህፍት በማንበበ እንዳሳለፉና ከዚያም በኋላ በተለያዩ የማህበራዊና ፖለቲካዊ አንቅስቃሴዎች ውስጥ ለረጅም ዓመታት ንቁ ተሳትፎ እንደነበራቸው ይናገራሉ። በ 1997 ዓ.ም በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ በግል ዕጩነት የሕዝብ ድምጽ አግኝተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንደነበሩም ይታወሳል። ዶ/ር ነጋሶ እንደሚሉት ከሆነ ከሶስት ዓመታት በፊት ከፖለቲካ ፓርቲያቸው ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሙሉ በሙሉ ፖለቲካን እርግፍ አድረገው እንደተዉ ይናገራሉ። ዶ/ር ነጋሶ እንደነገሩን በአሁኑ ሰዓት ብቸኛው የገቢ ምንጫቸው ለተለያዩ አካላት ስርተው የሚያቀርቧቸው ጥናታዊ ጽሁፎች ናቸው። አቶ ግርማ በንጉሱ ዘመንም በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ላይ ህዝብና ምንግሥትን አገልግለዋል በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ዘመን የፓርላማ አባል የነበሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አሁንም ቢሮ መግባታቸውን አላቆሙም። በቅርቡ ዘጠና ሁለት ዓመት የሚሞላቸው አቶ ግርማ፤ ''ከፕሬዝዳንትነት በኋላ ላለፉት አራት ዓመታት ሕዝብን ይጠቅማሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ሥራዎች ስሰራ ቆይቻለው'' ይላሉ። ''ዲጂታል የሆነ ቤተ-መጻህፍት ለሕዝብ ገንብቻለሁ። ሥልጣን ላይ ከነበርኩበት ወቅት ይልቅ አሁን ብዙ ሥራ እየሰራሁ እንደሆነ ይሰማኛል'' የሚሉት አቶ ግርማ ሆላንድ ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ ያሰሩት ቤተ-መጻህፍት በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ነግረውናል። ኑሮ ከስልጣን በኋላ ከሃላፊነት የተነሱ የሀገርና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባሎችና ዳኞች የሚያገኟቸውን መብትና ጥቅሞች ለመወሰን በወጣው በአዋጅ ቁጥር 653/2001 ዓ.ም መሠረት ተሰናባች ፕሬዝዳንቶች የደሞዝ፣ የመኖሪያ ቤትና ቢሮ፣ የጤና አገልግሎት፣ የጥበቃና የመጓጓዣ አገልግሎቶችን ጨምሮ በርካታ ጥቅማጥቀሞችን የማግኘት መብት እዳላቸው ይደነግጋል። ይሁን እንጂ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስልጣን ከለቀቁ ከአራት ዓመታት በኋላ በፖለቲካ ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ የተነሳ ያገኙት የነበረው ጥቅማጥቅም እንዲቋረጠባቸው መደረጉን ይናገራሉ። የፖለቲካ ተሳትፎ ከማድረጌ በፊት በወቅቱ የነበሩትን የምርጫ ቦረድ ሃላፊዎች አማክሬ የፖለቲካ ፓርቲ እስካልተቀላቀልኩ ድረስ በግል በማደርገው የፖለቲካ ተሳትፎ ምክንያት የማገኛቸው ጥቅማጥቅሞች እንደማላጣ አረጋግጠውልኝ ነበር ይላሉ ዶ/ር ነጋሶ። ከዚያ በኋላ ተሻሽሎ የወጣውም አዋጅ የማገኛቸውን ጥቅማጥቅሞች ለማስቀረት እንደወጣ ይሰማኛል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶ/ር ነጋሶ ብስራተ ገብርኤል አከባቢ ከሚገኘው መንግሥት ከሰጣቸው ቤት እንዲወጡ ቢነገራቸውም እየኖሩበት ይገኛሉ ዶ/ር ነጋሶ በአሁኑ ወቅት ብስራተ ገብርኤል አካባቢ በሚገኝ የመንግሥት ቤት ውስጥ ይኖራሉ። ''ይህን ቤት ለቅቄ እንድወጣ ከአንድም ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ተጽፎልኛል። አንድ ቀን መጥተው ከዚህ ቤት ሊያስወጡኝ ይችላሉ'' ይላሉ። ዶ/ር ነጋሶ የሚኖሩበት ግቢ እጅጉን ጭር ያለ ነው። ምግብ ከምታበስልላቸው የቤት ሰራተኛቸውና የተለያየ ሥራ በመስራት ከሚያግዛቸው አንድ ግለሰብ ውጪ በግቢው ውስጥ ማንም አይታይም። ጀርመናዊቷ ባለቤታቸውም አሁን በሃገር ውስጥ አይገኙም። ከቤታቸው ጀርባ ያለው የቴኒስ መጫወቻ ሜዳም ሳር በቅሎበት ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ በቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ መኖሪያ ግቢ ውስጥ 3 መኪኖች ቆመው ይታያሉ። የሚኖሩበት ቅጥር ግቢ እጅ ሰፊ የሚባል ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት ለአቶ ግርማ የቤት ኪራይ ወጪ የሚደረገው የገንዘብ መጠን ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በዚህ ሰፊ ግቢ ውስጥ የመኖሪያ ቤት፣ ቢሮዎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ቤተ-መጻሓፍት፣ ማዕድ ቤቶች እንዲሁም የሰራተኛ መኖሪያ ክፍሎች ይገኛሉ። የአቶ ግርማን ህይወት ቀላል የሚያደርጉ የተለያዩ ወጪዎችን መንግሥት ይሸፍናል መኖሪያ ቤታቸው 24 ሰዓት ጥበቃ ይደረግለታል። ግቢያቸውም እጅግ ንጹህና ያማረ ነው። ''ምንም የቀረብኝ ነገር የለም። መንግሥት የሚያስፈልገኝን ሁሉ አሟልቶልኛል። በህግ የተሰጠኝን መብት ሙሉ በሙሉ እየተጠቀመኩበት ነው። ከዚህ በላይ ደግሞ ምንም አልፈልግም'' ይላሉ አቶ ግርማ። ይህ ሁሉ ልዩነት ለምን? ዶ/ር ነጋሶ በ1997 ዓ.ም የደምቢዶሎን ከተማ ሕዝብ በመወከል በግል እጩነት የተወካዮች ምክር ቤት ወንበርን ካገኙ በኋላ ያገኟቸው የነበሩት ጥቅማ ጥቅሞች እንደተቋረጡባቸው ይናገራሉ። ''መጀመሪያ ላይ በቤቱ ውስጥ የሚረዱኝ ሦስት ሰዎች፣ አትክልተኛና ሁለት መኪኖች ከአሽከርካሪ ጋር እንዲሁም ሁሉን የሚያቀናጅልኝ አንድ ሰው ነበር። አሁን ግን ይህ ሁሉ የለም'' ይላሉ ዶ/ር ነጋሶ። ስልጣን ከለቀቁ በኋላ መንግስት ለኔ ምንም የሚበጅ ነገር እያደረገልኝ አይደለም ይላሉ ዶ/ር ነጋሶና አቶ ግርማ ተገኛኘተው ያውቁ ይሆን? ''ብዙም አንገናኝም'' ይላሉ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ። ዶ/ር ነጋሶም ተመሳሳይ መልስ ነው ያላቸው፤ ከዚህ በፊት ቢበዛ ለሦስት ጊዜ ያክል ብቻ እንደተያዩ ያስታውሳሉ። ከአቶ ግርማን ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኘነው ፕሬዝዳንት ሳሉ ነበር። ''በአዋጁ ምክንያት የተቋረጠብኝን ጥቅማጥቅም ለማስመለስ ፕሬዝዳንት ግርማን ባማክራቸውም ሳይሳካልኝ ቀርቷል።'' የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ ''በጥያቄዬ እንደማይስማሙ ነገሩኝ ከዚያም በኋላ ተስፋ በመቁረጥ ሳልጠይቃቸው ቀርቻለሁ'' ይላሉ ዶ/ር ነጋሶ። የሚገባኝን ጥቅማጥቅም ለማስመለስ ለህዝብ ተወካዮች መክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሶስት ግዜ ደብዳቤ ብጽፍም መልስ አላገኘሁም የሚሉት ዶ/ር ነጋሶ ጥቅማጥቅሞቼ እስኪመለሱልኝ ድረስ አስፈላጊውን ጥረት አደርጋለው ብለዋል። ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ሃገሪቱን በተመሳሳይ የሃላፊነት ቦታ ላይ ያገለገሉ ቢሆንም ከሥልጣን በኋላ በሚያገኙት ጥቅም ግን ተለያይተዋል።
49444575
https://www.bbc.com/amharic/49444575
'የዓለም ሳምባ' የሚባለው አማዞን ጫካ በአስፈሪ ሁኔታ እየነደደ ነው
የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ይህ ዓለማቀፍ መቅሰፍት ነው። በበለጸጉ አገራት ጂ7 ስብሰባም ዋናው መነጋገሪያችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በትዊተር ሰሌዳቸው ማክሮን "ቤታችን እየነደደ ነው" ብለዋል። የብራዚሉ ርዕሰ ብሔር ቦልሶናሮ በበኩላቸው ማክሮንን ወርፈዋል። ጉዳዩን ፖለቲካዊ ገጽታ ለማላበስ ይሞክራሉ በማለት። ብራዚል በሌለችበት የጂ7 በበለጸጉ አገራት ስብሰባለ ላይ የአማዞንን ሰደድ እሳት ጉዳይ ለማድረግ መሞከር ምዕራባዊያን አሁንም ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ አለመላቀቃቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል፤ ቦልሶናሮ። በብሔራዊ የህዋ ምርምር የወጣ አንድ የሳተላይት መረጃ እንዳመለከተው በብራዚል የእሳት ቃጠሎ 85 ከመቶ ጨምሯል። ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን መቶኛ የሚይዘው ደግሞ የአማዞን ሰደድ እሳት ነው። ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች የብራዚሉ አዲስ ርዕሰ ብሔር ሚስተር ቦልሶራኖ ለሰደድ እሳቱ ተጠያቂ ናቸው ይላሉ። ምክንያቱ ደግሞ ገበሬዎችንና ሥራ አጦችን ዛፉን እንዲመነጥሩ አበረታትታዋል። ቦልሳራኖ በበኩላቸው ግብረሰናይ ድርጅቶች እሳቱን ለኩሰዋል ሲሉ ከሰዋል። ነገር ግን ለዚህ ክሳቸው መረጃ እንደሌላቸው አምነዋል። በሰሜን ተራሮች በድጋሚ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር ጥረቱ ቀጥሏል ከግሪኩ ሰደድ እሳት የተረፉትን ፍለጋው ቀጥሏል በዓለም እጅግ ሰፊ ሽፋን ደን የሆነው አማዞን የዓለም ሳምባ በሚል ይሞካሻል። የዓለም ሙቀት መጨመርን በትንሹ ያረግባል የሚባልለት አማዞን አሁን ምን ያህሉ የደን ሽፋን በሰደድ እሳቱ እንደተበላ የማያወላዳ መረጃ ገና አልተገኘም። ሆኖም የዘንድሮው ባለፉት 10 ዓመታት በአማዞን ከተሰከቱት ሰደድ እሳቶች ሁሉ የከፋው ነው። አንዳንድ መረጃዎች የሰደድ እሳቱ ጭስ እስከ አትላንቲክ ጠረፍ እንደደረሰ ይገልጻሉ። በሳዎፖሎ ደግሞ ሰማዩን የሰደድ እሳቱ ጭስ ጋርዶታል። ሳዎ ፖሎ ከሚነደው አማዞን በ2ሺ ማይል ትርቃለች። "የምድርን 20 እጅ ኦክሲጅን የሚያመነጨውን የአማዞን ጫካ ጉዳይ በስብሰባችን ካላነሳን ምኑን ተሰበሰብን" ብለዋል የፈረንሳዩ ማክሮን። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጉቴረስ በበኩላቸው "ነገሩ ክፉኛ አሳስቦኛል" ብለዋል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከቃጠሎው በኋላ
news-47797549
https://www.bbc.com/amharic/news-47797549
የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ ከስልጣናቸው ተነሱ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮን ላለፉት ስድስት ወራት ሲመሩ የቆዩት ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ከስልጣናው እንዲነሱ መደረጋቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።
''ሰኞ ዕለት የተላከልኝ ደብዳቤ ከሥራ እንደተሰናበትኩ ይገልጻል'' ሲሉ ብ/ጄኔራል ከማል ይናገራሉ። ''አይታወቅም፤ የተገለጸ ነገር የለም'' በማለት ከሥራ የተሰናበቱበትን ምክንያት እንደማያውቁ ብ/ጄኔራል ከማል ጨምረው ተናግረዋል። የሥራ ስንብት ደብዳቤው ከመድረሱ በፊት ውይይቶች እና ግምገማዎች እንዳልነበሩ የሚያስታውሱት ብ/ጄኔራል ከማል በስንብት ደብዳቤው ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ ፊርማ እንዳረፈበት ያስረዳሉ። • ከጄኔራሎቹ ሹመት ጀርባ? ብርጋዴር ጄኔራል ከማል የክልሉ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ሊደርስ እንደሚችል ቀድመው ይገምቱ እንደነበር ተናግረዋል። ለዚህ ግምታቸውም ሁለት ምክንያቶች እንዳሏቸው የሚገልጹት ብ/ጀ ከማል "በአስተዳደሩ ውስጥ የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራ የሚሰሩበት መንገድ በእኔ ፓርቲም ሆነ በግል እምነቴ ተቀባይነት የለውም። በመንግሥት የዕለት ተዕለት ሥራ ላይ ፓርቲ ጣልቃ መግባት አለበት ብለን አናምንም" ሲሉ አንደኛውን ምክንያታቸውን አስቀምጠዋል። አክለውም ሁለተኛውን ምክንያት ሲጠቅሱ " መለስ ብዬ ሳስበው የፖለቲካ ተቀባይነት ለማግኘት ሲባል እኔ ወደ ስልጣን እንድመጣ የተደረገው ውሳኔ አመራሩን ጥያቄ ውስጥ የጣለው ይመስለኛል'' ሲሉ ይናገራሉ። • የኦነግና የኦዴፓ እርቀ ሰላም ብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ ከ13 ዓመታት በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩን የሰላም ጥሪ ተከትለው ከኤርትራ ባለፈው ዓመት ወደ ሃገር መግባታቸው ይታወሳል። ከዚያም ጥቅምት ወር ላይ ነበር የክልሉ የአስተዳደርና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት። ብ/ጄኔራሉ ክልሉን ያሚያስተዳድረው የኦሮሞ ዲሞክራቲ ፓርቲ (ኦዲፓ) አባል አለመሆናቸው እና እራሳቸው የሚመሩት ፓርቲ መኖሩ ሹመታቸው በርካቶችን አስገርሞ ነበር። ብ/ጄኔራሉ በሥራ ቆይታቸው በቢሮው የሰው ኃይል ስምሪት እና ቁጥጥር ላይ ገዢው የኦሮሞ ዲሞክራቲ ፓርቲ (ኦዲፓ) የበላይነት አለ ሲሉም ይወቅሳሉ። በጉዳዩ ላይ የክልሉ መንግሥትም ሆነ ኦዲፓ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። • ኦዲፒ 'በፌዴራሊዝም አልደራደርም' ሲል ምን ማለቱ ነው? ብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመሩት የኦሮሚያ አንድነት እና ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ዲሞክራቲ ፓርቲ (ኦዲፓ) 'እስከ ሽግግሩ ድረስ' አብሮ ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። ስለሁለቱ ፓርቲዎች ስምምነት ሲናገሩ ''በሃሳብ ደረጃ ተስማማን እንጂ በጽሑፍ የተቀመጠ ነገር የለም'' ሲሉ ብ/ጄኔራል ይናገራሉ። የብ/ጄኔራሉ ፓርቲ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ከተሸጋገር በኋላ ስያሜውን ወደ የኦሮሚያ ብሄራዊ ፓርቲ ቀይሯል።
51102387
https://www.bbc.com/amharic/51102387
የግዙፉ ግድብ ግንባታ፡ የኢትዮጵያና ግብፅ ቅራኔ ወደየት ያመራ ይሆን?
ኢትዮጵያና ግብፅ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባት ዙሪያ ሊግባቡ የቻሉ አይመስልም። የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ከትናንት ጀምሮ በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተው እየመከሩ ይገኛሉ።
አራት የቴክኒክ ውይይቶችን አድርገው ከመግባባት ላይ ሊደርሱ ያልቻሉት ኢትዮጵያና ግብፅ ዛሬ የመጨረሻውን ውይይት አድርገው ከስምምነት መድረስ የማይቻል ከሆነ ከዚህ ቀደም ሶስቱ ሃገራት የተፈራረሙት 'ዲክላሬሽን ኦፍ ፕሪንስፕልስ' አንቀጽ 10 ተግባራዊ ይደረጋል። የሕዳሴው ግድብ ሲጠናቀቅ በአፍሪቃ ግዙፉ ከውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ግድብ ይሆናል ተብሎ ይጠቃል። ግንባታው 2003 ላይ የተጀመረው ይህ ግድብ፤ 85 በመቶ ውሃ ለናይል ወንዝ የሚያበርከትው አባይ ወንዝን መሠረት አድርጎ ነው የሚታነፀው። ነገር ግን የግድቡ ግንባታ ለግብፅ ሰላም የሰጣት አይመስልም። ከግድቡ ግንባታ መጀመር አንስቶ ኢትዮጵያ እና ግብጽ አንድ ጊዜ ሲኮራረፉ በሌላኛው ሲታረቁ ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ ቅራኔ ሳቢያ ሳዑዲ አራቢያ ሁለቱን ሃገራት ለማግባባት በሚል ደፋ ቀና ስትል ጉዳዩ ወደ ጦርነት ሊያመራ ይችላል ተብሎ ተሰግቶ ነበር። አሁን ደግሞ አሜሪካ ሁለቱን ሃገራት 'ላስታርቅ' እያለች ነው። ምንም እንኳ የትራምፕ መንግሥት ለግብፅ ይወግናል ሲሉ የአሜሪካንን ጣልቃ ገብነት ያልስደሰታቸው ቢኖሩም። የግብጽ ስጋት የግብፅ ፍራቻ ኢትዮጵያ ግድቡን መሙላት ስትጀምር ከአባይ ወንዝ ወደ ናይል የሚወርደው የውሃ መጠን ይቀንሳል ነው። ይህ ደግሞ በተዘዋዋሪ ለኢትዮጵያ ኃያልነት ያድላታል። ምንም እንኳ በውሃ የሚሠሩ ኃይል አመንጭ ግድቦች ውሃ ባያባክኑም ኢትዮጵያ በምን ያህል ነው ግድቡን የምትሞላው የሚለው ግብፅን ከሚያሳስቡ ጉዳዮች አንዱ ነው። ግድቡ ሲጠናቀቅ ግሬተር ሎንዶን [74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ] በላይ ቦታ ይይዛል የሚባልለት የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመሙላት የሚወስድባት ጊዜ ረዘም ያለ ከሆነ ግብፅ ይህን ያህል ጭንቀት ይኖርባታል ተብሎ አይታሰብም። ሶስቱ ሃገራት ከዚህ ቀደም በነበራቸው ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ግድቡን በሰባት ዓመታት ሞልታ ማጠናቀቅ ትፈልጋለች። «ዕቅዳችን በሚመጣው ክረምት ሙሙላት መጀመር ነው። በሁለት ማመንጫዎች [ተርባይን] በመታገዝ ታኅሣሥ 2013 ላይ ኃይል ማመንጨት እንጀምራለን» ሲሉ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ [ዶ/ር ኢንጅነር] መናገራቸው አይዘነጋም። ግብጽ ግን ሰባት ዓመት የሚለው የተዋጣላት አይመስልም። ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት የጠቀሰችው ውሃው በአንድ ጊዜ መጠኑ እንዳይቀንስ የሚል ነው። የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ [ዶ/ር ኢንጅነር] ባፈለው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ ሶስቱ ሃገራት ተገናኝተው ያደረጉት ውይይት ፍሬያማ አልሆነም። የውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትሩ ግብፅ ስምምነት ላይ የመድረስ ሃሳብ የላትም ሲሉ ይወቅሳሉ። «ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ ሆነው የመጡ አልመሰለኝም። በዚያ ላይ አዲስ የሙሊት መርሃ ግብር ይዘው መጥተዋል። ይህ መርሃ ግብር ከ12-21 ዓመታት የሚል ነው። ይህ ደግሞ በፍፁም ተቀባይነት የለውም።» የግብፁ ውሃ ሚኒስትር ሞሐመድ አብደል አቲ በበኩላቸው ሶስቱ ወገኖች በግድቡ አሞላል ዙሪያ አሁን የተሻለ መግባባት ላይ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። የግብፅ አቋም ግብፅ 90 በመቶ የውሃ ፍላጎቷን የምታሟላው ከናይል ወንዝ ነው። ሃገሪቱ ሁልጊዜም ስትል እንደምትደመጠው የናይል ወንዝ ሕልውና ማለት የግብፅ ሕልውና ማለት ነው። የግብፁ ፕሬዝደንት አብድል ፋታህ አል-ሲሲ ባለፈው መስከረም ግብፅ የራሷ ችግር ላይ [የአረቡ ዓለም አብዮት] ባትሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባት ስትጀምርም ነበር ማለታቸው ይታወሳል። ከአባይ ወንዝ የሚመጣው የውሃ ኃይል ቀነሰ ማለት የናስር ሐይቅ አቅም ተዳከመ ማለት ነው። ናስር ኃይቅ ደግሞ ግብፅ አብዛኛውን የኤሌክትሪክ ኃይሏን የምታገኝበት የአስዋን ግድብ ደጀን ነው። ግብፅ እንደ ቅድመ መስማሚያ ካስቀመጠቻቸው ሃሰቦች አንዱ የአስዋን ግድብና የሕዳሴ ግድብ ይገናኙ የሚል ነው። 'ይህ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም' ብለው ለግብጽ ተደራዳሪዎች እንደ ነገሯቸው ሚኒስትር ስለሺ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ግዙፍ ግድብ መገንባት ለምን አስፈለጋት? በብዙ ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ዕድገት ልብ ምት ተደርጎ ይቆጠራል። ግድቡ ሲጠናቀቅ 6ሺህ ዋት የኤልክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል። በርካታ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደልብ ለማያገኝባት ኢትዮጵያ የግድቡ አስፈላጊነት የማያጠያይቅ ነው። ከዚህ ባለፈም እያደገ ለመጣው የማኒዩፋከቸሪንግ ዘርፍ ትልቅ እፎይታን የሚሰጥ ነው። ኢትዮጵያ ግድቡ ሙሉ በሙለ ኃይል ማመንጨት ሲጀምርላት ለጎቤት ሃገራትም ኮረንቲ መሸጥ ትችላለች። ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራና ጂቡቲ ከሕዳሴው ግድብ ጥቅም ሊያገኙ ይችላሉ። ሌላኛው ኢትዮጵያ ከግድቡ የምታገኘው ጥቅም በገንዘብ የማይለካ ነው ይላሉ ባለሙያዎች - ሉዓላዊነት። ሁኔታዎች ወደ ጦርነት ያመሩ ይሆን? ሁለቱ ሃገራት ካልተስማሙ ወደ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ፍራቻ ነበር። 2005 ላይ የተለቀቀ አንድ ተንቀሳቃሸ ምስል የግብፅ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያ ላይ ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶች ላይ ሲመክሩ አሳይቷል። ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲም ግብፅ የትኛውንም ዓይነት እርምጃ ትወስዳለች ሲሉ ተሰምተዋል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አበይ አሕመድም ለሕዝብ እንደራሴዎች ባደረጉት ንግግር የትኛውም ዓይነት ኃይል ኢትዮጵያን አያቆማትም ሲሉ ተናግረዋል። አሜሪካ በሁለቱ ሃገራት መካከል ጣልቃ መግባቷ የጉዳዩን አሳሳቢነት ያሳያል። ግብጽ የአሜሪካን አደራዳሪነት ቀድም ጠይቃ ነበር። ኢትዮጵያ በበኩሏ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት አልፈቀደችም ነበር። በአሁኑ ወቅት የሶስቱ ሃገራት የቴክኒክ ኮሚቴዎች ባደረጓቸው ውይይቶች ላይ አሜሪካ እና የዓለም ባንክ የታዛቢነት ድርሻ ኖሯቸው በውይይቶቹ ላይ ተካፋይ ሆነው ቆይተዋል። በቀጣይስ? የሶስቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ከትናነት ጀምሮ አሜሪካ ላይ ተገናኝተው በመምከር ላይ ናቸው። ሃገራቱ በቀጠሯቸው መሠረት ጥር 6/2012 መስማማት ላይ ካልደረሱ ጉዳዩ ወደየ ሃገራት መሪዎች ወይም ወደ ሶስተኛ አደራዳሪ አካል ሊመራ ይችላል። «የመጀመሪያው አማራጭ ከአወያይ አካል ቁጭ ብሎ ለመስማማት መሞከር ነው። ሶስቱም ሃገራት መስማማት አለባቸው። አንቀፅ 10 በአንድ ሃገር ይሁንታ ላይ ብቻ ተመሥርቶ ሃሳብ ይፅደቅ አይልም» ይላል የኢትዮጵያ ውሃ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ።
news-56151105
https://www.bbc.com/amharic/news-56151105
የትግራይ ቀውስ፡ በትግራይ ክልል እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተነገረ
ከፍተኛ ጉዳት ባስከተለው የትግራይ ክልል ግጭት ምክንያት እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር "እጅግ ከፍተኛ " መሆኑን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አሳሰበ።
የኮሚቴው የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ዶሚኒክ ስቲልሃርት ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ለቢቢሲ እንደገለጹት "የትግራይ ክልል ሰዎች. . . ሰብል መሰብሰቢያ ወቅታቸውን አጥተዋል" ብለዋል። ጨምረውም "የሕክምና እርዳታ አቅርቦትን በተለመከተ ከበድ ያሉ ጉዳዮች አሉ" ብለዋል ዳይሬክተሩ። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት እርዳታ ማቅረቡንና በዚህም 1.5 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ማግኘት እንደቻሉ አሳውቆ ነበር። በግጭቱ ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የተዘገበ ሲሆን፤ እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለዋል። በትግራይ ክልል ባሉ የተባበሩት መንግሥታት መጠለያ ጣቢያዎች የሚኖሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች በግጭቱ መሃል ተይዘዋል። ግጭቱ የተከሰተው ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በክልሉ በሚገኘውን የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ነው። ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው ፓርቲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ጋር ቁርሾ ከገባ ሰንበትበት ብሎ ነበር። ጦርነቱን ማሸነፉን ያወጀው ማዕከላዊው መንግሥት ወደ ክልሉ የእርዳታ ድርጅቶችና የመገናኛ ብዙሃን እንዲገቡ አልፈቀደም ተብሎ ይተቻል። የግጭቱ መንስዔ ምንድነው? ህወሓት የትግራይ ክልል ለ30 ዓመታት ያክል ያስተዳደረ ፓርቲ ሲሆን በግምት 250 ሺህ ተዋጊዎች እንዳሉት ይነገራል። ፓርቲው ከሥልጣን የተወገደው የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች ኅዳር 19/2013 የክልሉን ዋና ከተማ መቀለ ከተቆጣጠሩ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ሕወሓት የኢትዮጵያን አንድነት ተፈታትኗል፤ እንዲሁም ወታደራዊ ዕዞችን በመያዝ ማዕከላዊውን መንግሥት ለመጣል ጥሯል ሲሉ ይከሳሉ። ህወሓት በበኩሉ የሰሜን ዕዝን የያዘው ከፌዴራል መንግሥት የሚመጣ ጣልቃ ገብነት ለመከላከል በማሰብ እንደሆነ ይናገራል። ህወሓት ባለፈው ነሐሴ በክልል ምርጫ አዘጋጅቶ እንደነበር አይዘነጋም። ይህ ደግሞ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርጫው በሁሉም አካባቢዎች እንዲራዘም ካደረገው የፌዴራል መንግሥት እርምጃ በተቃራኒ ነው። የፌደራሉ መንግሥት ምርጫውን ሕጋዊ አይደለም ሲሉ መኮነኑ ይታወሳል። ነገር ግን ሕወሓት በአፀፋው ማዕከላዊው መንግሥት "ሕጋዊ አይደለም"፤ ኢትዮጵያን የማስተዳደር ሥልጣን የለውም ሲል ቆይቷል። በዚህ ምክንያት ከጊዜ ጊዜ የተባባሰው ውጥረት ወደ ግጭት አምርቷል።
news-49520710
https://www.bbc.com/amharic/news-49520710
በጃፓን የሴቶችን መቀመጫ የሚጎነትሉ ወንዶችን ለመከላከል ሥውር ማኅተም ተዘጋጀ
ሁነኛ ጸረ-ለከፋ መሣሪያ በጃፓን ተመርቷል። ዋና ዓለማው በአውቶቡስና በባቡር እንዲሁም ሕዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች የሴቶችን ዳሌና መቀመጫ "ቸብ" የሚያደርጉ አጉራ ዘለል ወንዶችን ለመቆጣጠር ነው።
ዲጂታል ሥውር ማኀተሙ የመዳፍ ቅርጽ ያለው ሆኖ የተሠራ ሲሆን ሴቶች ጥቃት አድራሹ ላይ ፈጥነው ምልክት እንዲያደርጉ ያግዛቸዋል ተብሏል። • "ወፍራም ሴቶች ለአገርም ለቤተሰብም ሸክም ናቸው" የግብፅ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ • "አትግደሉን!"፡ የቱርክ ሴቶች ስለዚህ ሌሎች ሰዎች ወይም የሕግ አካላት ጥቃት አድራሹን በቀላሉ በተለደፈበት ማኅተም ምክንያት ዳናውን ተከትለው ነቅሰው ያወጡታል። ይህንን ሥውር ማኅተም የፈበረከው ኩባንያ ዓላማዬ የሴቶችን ጥቃት መከላከል ነው ብሏል። ሆኖም በሴቶች መብት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ሐሳቡን ሙሉ በሙሉ ወደውታል ማለት አያስደፍርም። "መሣሪያው ተጠቂዋ ላይ ሥራ የሚያበዛ ነው" ይላሉ። ኩባንያው ግን የፈበረኩት መሣሪያ የሴት ዳሌን ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ «ቸብ» ማድረግ የለመዱ 'ቅሌታሞችን' ለማደን እንዲረዳ ነው ይላል። ኩባንያው ረቂቅ ማኀተሙን ለመሥራት ያነሳሳው ባለፈው ግንቦት ማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ በብዛት የታየውን ሁለት ሴት ተማሪዎች ጥቃት አድራሽ የሆነን ግለሰብ በቪዲዮ እየቀረጹ ሲያሳድዱት የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምሥል ተከትሎ ነው። በእንግሊዝና ዌልስ የጾታ ጥቃቶች ላይ የሚሠራ አንድ ቡድን ቃለ አቀባይ ለቢቢሲ ስለ ረቂቁ ማኀተም በሰጠችው አስተያየት « የሴቶች ጥቃት ላይ ንግድ ነው የተያዘው» ብላለች። በሰዎች ጥቃትና ፍርሃት መነገድ መልካም ነገር አይደለም ስትል አክላለች። የቶኪዮ ከተማ ዙርያ ፖሊስ ባወጣው አሐዝ በ2017 ብቻ ወደ 3ሺ የሚጠጉ ሴቶች "ወንዶች በባቡር ውስጥ አላስፈላጊ ንክኪ አድርገውብናል" ሲሉ መክሰሳቸውን ተናግረዋል። ይህ ተላካፊ ወንዶችን የሚያድነው መሣሪያ ለገበያ በቀረበ በግማሽ ሰዓት ውስጥ 500 ቅጂ ተሸጧል። የአንዱ ዋጋ 20 ፓውንድ ይደርሳል። • መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው ከዚህ ቀደም በየባቡር ጣቢያው የሴቶችን መቀመጫ የሚነካኩ ጋጠወጦችን ለመቆጣጠር በርካታ ካሜራዎች ባቡር ውስጥ ጭምር መተከላቸው ይታወሳል። ካሜራውን መሠረት በማድረግም 6ሺህ ወንዶች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። የሴቶችን መቀመጫ ከመጎንተልም አልፎ በሞባይል መቅረጽ በጃፓን የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል። ጃፓን የጾታ እኩልነትን በማስከበር ረገድ በዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ሰንጠረዥ ከ149 አገራት 110ኛ ደረጃ ነው ያላት።
news-42048606
https://www.bbc.com/amharic/news-42048606
በሊቢያ ''የባሪያ ንግድ'' እየተካሄደ እንደሆነ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ድንጋጤን ፍጥሯል
በሊቢያ አፍሪካዊያን ስደተኞች ለባሪያ ንግድ በጨረታ ሲቀርቡ የሚያሳይ ምስል ከወጣ በኋላ የአፍሪካ ሕብረት ድርጊቱ እጅጉን አስደንግጦኛል ብሏል።
ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በሊቢያ የባርያ ንግድ ስለመኖሩ መረጃዎች አሉኝ ብሏል ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ሲኤንኤን ይዞት የወጣው ቪዲዮ አፍሪካውያን ስደተኞች በጨረታ ለእርሻ ሥራ ሲሸጡ ያሳያል። የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የጊኒው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ይህን ከዘመናት በፊት የተሻረውን አጸያፊ ተግባር የሚፈፅሙ መጠየቅ አለባቸው ብለዋል። አውሮፓ ለመግባት ከሃገራቸው የሚወጡት አፍሪካውያን ስደተኞች በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች በግድ ተይዘው አነስተኛ ገንዘብ ወይም ያለክፍያ የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ይገደዳሉ። በሲኤንኤን ቪዲዮ ላይ ከኒጀር እና ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት የመጡ ስደተኞችን ተጫራቾች እሰከ 300 የአሜሪካ ዶላር (8000 ብር ገደማ) ሲገዙ ያሳያል። የሊቢያ መንግሥት ጉዳዩን ማጣራት እንደጀመረ ሲኤንኤን ዓርብ ዕለት ዘግቧል። በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች አውሮፓ ለመግባት ሜድትራንያን ባህርን ለማቋረጥ ይጥራሉ ከዚህ በፊት ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በሊቢያ የባሪያ ንግድ ስለመኖሩ መረጃዎችን አሰባስቢያለሁ ብሎ ነበር። በሊቢያ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ሃላፊ ኦትማን ቤልቢሲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ስደተኞቹ የዋጋ ግምት የሚወጣላቸው እንደ ችሎታቸው መጠን ነው ይላሉ። ''ስደተኞቹ ወይም ቤተሰቦቻቸው ህግወጥ አዘዋዋሪዎቹ የሚጠይቁትን ገንዘብ መክፈል ስለማይችሉ በአነስተኛ ገንዘብ ይሸጣሉ'' ብለዋል። ''ስደተኞቹ ከፍ ባለ ዋጋ ሊሸጡ የሚችሉት በሚኖራቸው ችሎታ ነው። ለምሳሌ ቀለም መቀባት የሚችል ወይም የግንባት ሥራ መስራት የሚችል ከሆነ ከፍ ባለ ዋጋ ሊሸጥ ይችላል'' ሲሉ ኦትማን ያስረዳሉ።
49850089
https://www.bbc.com/amharic/49850089
ፌስቡክ 'የላይክ' ቁጥርን ማሳየት ሊያቆም ነው
ፌስቡክ ኢንስታግራም ላይ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በእያንዳንዱ የፌስ ቡክ የተጠቃሚዎች መልዕክት ስር የተሰጡ የመውደድ (ላይክ) ቁጥሮችን አለማሳየት ሙከራ እርምጃውን አውስትራሊያ ውስጥ መጀመሩን አስታወቀ።
ከዛሬ አርብ ጀምሮ አውስትራሊያ ውስጥ ያሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በሌሎች መልዕክት ላይ የተሰጡ የላይክ እንዲሁም የሌሎች ምላሽ ቁጥሮችን መመልከት አይችሉም። አወዛጋቢ የሆነው ይህ ውሳኔ የፌስቡክ ተዛማጅ ማኅበራዊ መድረክ በሆነው ኢንስታግራም ላይ ከሐምሌ ወር ጀምሮ በበርካታ ሃገራት ውስጥ ተግባረዊ ተደርጓል። ፌስቡክ ለአንድ መልዕክት የሚሰጡ የላይክ ቁጥሮችን ከባለቤቶቹ ውጪ ሌሎች እንዳያዩ የሚያደርገውን እርምጃውን ለመውሰድ የወሰነው በተጠቃሚዎች ላይ የሚደርሰውን ማኅበራዊ ጫና ለመቀነስ በማሰብ ነው ተብሏል። • ፌስቡክ የጽንፈኛ አመለካከት አራማጆችን ሊያግድ ነው • ፌስቡክ ሦስት ቢሊዮን አካውንቶችን አገደ • ፌስቡክ የምንጠቀምበት ሰዓት ሊገደብ ነው ኩባንያው እንዳለው የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በራሳቸው መልዕክቶች ስር የሚሰጡ 'የመውደድ' ምላሾችን መመልከት ግን ይችላሉ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሚያ ጋርሊክ ለአውስትራሊያ አሶሺየትድ ፕሬስ እንዳሉት "የቁጥርን ነገር ከጉዳዩ ስናወጣ፤ ተጣቃሚው ዋና ትኩረትን በተሰጡ የላይክና የሌሎች ምላሾች ብዛት ላይ ሳይሆን በሚደረጉ ምልልሶችና በቀረቡ መረጃዎች ጥራት ላይ ብቻ ያደርጋል" ብለዋል። ቃል አቀባዩ አክለውም ድርጅታቸው ይህንን ለውጥ ከማድረጉ በፊት የሥነ አእምሮ ባለሙያዎችንና ማንጓጠጥ እንዲሁም ማስፈራራትን የሚከላከሉ ቡድኖችን ማማከሩን ገልጸዋል። በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው አንዳንድ ሰዎች ግን በአንድ መልዕክት ላይ የሚታይ የመውደድ አሃዝ ለሚያገኙት ገቢ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ እርምጃውንተቃውመውታል።
49806683
https://www.bbc.com/amharic/49806683
አልሲሲን ለመቃወም አደባባይ የወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብፃውያን ታሰሩ
በመንግሥት የሚፈፀምን ሙስና ተቃውመው አደባባይ ከወጡ ግብፃውያን መካከል 500 ያህሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተናገሩ።
የተቃውሞ ሠልፎቹ በካይሮ፣ አሌክሳንድሪያ እና ሌሎች ከተሞች አርብ ማታ የተካሄዱ ሲሆን፤ በወደብ ከተማዋ ስዊዝ ደግሞ ቅዳሜ ምሽት ተከናውኗል። የመንግሥት ባለስልጣናት የታሳሪዎቹን ቁጥር እስካሁን ድረስ አልገለፁም። • ቦይንግ ለሟች ቤተሰቦች ካሳ ሊከፍል ነው • በተያዘው ዓመት ለሁለት የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፍቃድ ይሰጣል ተባለ የፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ አገዛዝ ተቃውመውት አልያም ተችተውት ድምፃቸውን በሚያሰሙ፣ ሠልፍ በሚያደርጉ ላይ እርምጃ በመውሰድ ይታወቃል። እኤአ ከ2013 ጀምሮ አልሲሲ በሕዝብ የተመረጡት ሙርሲን በወታደራዊ ኃይል ከስልጣን ካወረዱ በኋላ፤ በሕዝብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች ከ10 ሰው በላይ ሆኖ መገኘት የተከለከለ ሆኖ ቆይቷል። የመብት ተሟጋቾች እንደሚሉት፤ ባለፉት ስድስት አመታት ከ60 ሺህ ግብፃውያን በላይ የሙርሲ ደጋፊ ናችሁ፣ አልያም በሕግ የታገደው የሙስሊም ወንድማማቾች አባል ናችሁ በሚል በእስር ቤት የሚገኙ ሲሆን፤ የተወሰኑት በፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶባቸዋል። የደረሱበት የማይታወቅ ግለሰቦችም አሉ ብለዋል። አርብ ምሽት በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በዋና ከተማዋ ካይሮ ታሕሪር አደባባይ አቅራቢያ፣ አሌክሳንድሪያ፣ ዳሚታ እና ማሀላ አልኩብራ በሚባሉ ስፍራዎች ሠልፍ ማድረጋቸውን የአይን ምስክሮች እና ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል። ተቃዋሚ ሠልፈኞቹን ፖሊስ ከመበተኑ በፊት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው "አልሲሲ ይውረድ" እንዲሁም "ሕዝቡ ሥርዓቱ እንዲፈርስ ይፈልጋል" እያሉ ሲጮሁ እንደነበር ተዘግቧል። አንድ የሕግ ባለሙያ ለቢቢሲ 500 ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረው፤ በሚቀጥሉት ቀናትም ይህ ቁጥር እያሻቀበ እንደሚሄድ ያላቸውን እምነት አስረድተዋል። መንግስታዊ ያልሆነው የግብፅ ምጣኔ ኃብትና ማኅበራዊ መብት ማዕከልም የታሳሪዎች ቁጥር 516 እንደሆነ ተናግሯል። በቁጥጥር ስር የዋሉት በሕግ በታገደ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ፣ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት፣ ያልተፈቀደ ሰልፍ ላይ በመሳተፍና በሌሎች ወንጀሎች ተጠያቂ ይሆናሉ ተብሏል። ከታሰሩት መካከል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆነም ይገኝበታል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ታዋቂ የሰብዓዊ መብት ጠበቃዋ ማሄኑር አል ማስሪ ትገኝበታለች። እንደ ፈረንሳዩ የዜና ወኪል ከሆነ ጠበቃዋ በቁጥጥር ስር የዋለችው ቅዳሜ እለት ካይሮ ወደሚገኘው አቃቤ ሕግ ቢሮ የታሰሩ ሰዎችን በመወከል ከሄደች በኋላ ነው። • ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዙት የአል ሸባብና የአይ ኤስ አባላት ማንነት ይፋ ሆነ • እስር ላይ የሚገኙት የ'ቡድን 15' የቀድሞ የኤርትራ ባለስልጣናት እነማን ናቸው? በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ መገናኛ ብዙኀን፤ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ሠልፍ ተደረገ ተብለው የሚሰራጩ ምስሎች በ2011 የተካሄደው ሠልፍ ምስሎች መሆናቸውን በመጥቀስ ሕዝቡን ለማወናበድ ሆን ተብለው የተደረጉ ሲል ገልጿቸዋል። በመላው ዓለም ኢንተርኔትን የሚከታተለው ኔት ብሎክስ የተባለው ድርጅት በበኩሉ፤ ቅዳሜ ግብፅ ውስጥ የፌስቡክ መልዕክት መቀበያና መላኪያ፣ ቢቢሲ እና ሌሎች የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ሰርቨሮች እቀባ ተጥሎባቸው ነበር ብሏል። በግብፅ ተቃዋሚ ሠልፈኞች አደባባይ የወጡት በስፔን በስደት ላይ የሚገኘው ባለሀብት በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ ፕሬዝዳንት አልሲሲንና ወታደራዊ ባለስልጣናትን በሙስና የሚከስ ተንቀሳቃሽ ምስል ከለቀቀ በኋላ ነው። ይህ ግለሰብ ግብፃውያን ፕሬዝዳንት አልሲሲ ከስልጣን እንዲወርዱ ለመጠየቅ አርብ ዕለት ሕዝባዊ ሰልፍ እንዲወጡ ጠርቶ ነበር። ፕሬዝዳንት አል ሲሲ የግለሰቡን ክስ "ሐሰተኛና ስም ማጥፋት ነው"ሲሉ አጣጥለውታል።
46556014
https://www.bbc.com/amharic/46556014
የቀድሞ የአልሸባብ መሪ በኢትዮጵያ ሠራዊት በሶማሊያ በቁጥጥር ሥር ዋለ
የሶማሊያን ደቡብ ምዕራብ ግዛት ለማስተዳደር እየተወዳደረ የሚገኘው የቀድሞው የአልሸባብ መስራች እና አባል ሙክታር ሮቦው በሶማሊያዋ ባይዶዋ ከተማ በቁጥጥር ሥር ዋለ።
ሙክታር ሮቦው በቀጣዩ ሳምንት የሚካሄደውን ምርጫ በማሸነፍ የሶማሊያን ደቡብ ምዕራብ ግዛት ሊያስተዳድሩ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱ እጩዎች መካከል አንዱ ነበር። ሙክታር ሮቦው ዛሬ ጠዋት በባይዶዋ በታጣቂዎች እና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው። ይህንንም ተከትሎ በከተማዋ የቴሌኮም አውታሮች የተቋረጡ ሲሆን፤ እስካሁን ሙክታር ሮቦው ለምን በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም። • የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት ፈጸመ • በጎሳ ታጣቂዎች እና በአልሸባብ ወታደሮች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ ቢቢሲ ሶማሊኛ ያነጋገራቸው የሶማሊያ ፓርላማ አባላት እንዳረጋገጡ የአሚሶም የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል በሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች ነው ሙክታር ሮቦን በቁጥጥር ሥር ያዋሉት። የቀድሞ የአልሸባብ መሪ እና መስራች ከሁለት ወራት በፊት ግዛቶችን ለማስተዳደር በምርጫ ለመሳተፍ ያቀረቡትን ጥያቄ የሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ፍቃድ ቢነፍግም የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ግን በምርጫው እንዲሳተፉ ፈቅዷል። • "ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ተስፋና ስጋት አለ" ኦባንግ ሜቶ • ''ወንጀለኞቹ ማንም ይሁኑ ማን . . . አድነን ለሕግ ማቅረባችን አይቀሬ ነው'' ዐብይ አህመድ ሙክታር ሮቦው የሶማሊያ የፌደራል መንግሥት በደቡብ ምዕራብ ተሰሚነት እንዳይኖረው ክፍተኛ ጫና ያሳድራሉ። አንዳንዶች ሙክታር ሮቦው አልሸባብን ለመውጋት ሁነኛ ሰዎች ናቸው ሲሉ፤ ሌሎች በበኩላቸው ሙክታር ከዚህ ቀደም ከአሸባሪ ቡድኑ ጋር በነበራቸው ታሪክ ምክንያት በጥርጣሬ ይመለከቷቸዋል። ሙክታር ዛሬ ማለዳ በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉ ታዋቂነቱን ክፍ የሚያደርገው ሲሆን፤ በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና ተባባሪው የውጪ ሃገራት ላይ ግን ጥላቻን ይጨምራል የሚሉ በርካቶች ናቸው። ሙክታር ከአልሸባብ ኃላፊነቱን እራሱን ማግለሉን በማሳወቅ የሶማሊያ ሕዝብ ይቅርታ ያድርግልኝ ሲል ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ዕርቅ ለማውረድ ሞክሮ ነበር። በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው የአሚሶም የጸጥታ አስከባሪ አባላት ከኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ቡሩንዲ፣ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የተወጣጡ የጦር አባላት አሉት።
news-49260751
https://www.bbc.com/amharic/news-49260751
ማዳጋስካር፡ ከአውሮፕላን ላይ የወደቀችው ተማሪ አላና ኩትላንድ አስክሬን ተገኘ
በማዳጋስካር ከአንድ አነስተኛ አውሮፕላን ላይ የወደቀችው የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ አስክሬን መገኘቱ ተገለፀ።
አላና ኩትላንድ በካምብሪጅ ሮቢንሰን ኮሌጅ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት እያጠናች ነበር ከደቡብ ምስራቃዊ ክፍል ሚልተን ኬይኔስ የመጣችዋ የ19 ዓመቷ አላና ከትላንድ፤ ከአነስተኛ አውሮፕላኑ ላይ የወደቀችው ባሳለፍነው የአውሮፓዊያኑ ሐምሌ 25 ነበር። • «ሙሉ ቤተሰቤን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ» • ታዳጊዎቹ በገጣጠሟት አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ተነስተው ካይሮ ገቡ የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ ሲኖላ ኖሜንጃሃሪይ እንደገለፁት የተማሪዋ አስክሬን ትናንት በአንድ ገጠራማ አካባቢ ተገኝቷል። ከትላንድ በሮቢንሰን ኮሌጅ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቷን እየተከታተለች የነበረ ሲሆን በሞተችበት ወቅት በአፍሪካዊቷ ደሴት በሥራ ልምምድ ላይ ነበረች ተብሏል። ከትላንድ ከአውሮፕላኑ ላይ የመውደቅ አደጋ ያጋጠማት የአውሮፕላኑን በር በመክፈቷ እንደነበር ፖሊስ የገለፀ ሲሆን ያንን ያደረገችበት ምክንያት ግን እስካሁን ግልፅ አይደለም። ትወስደው የነበረው የወባ መድሃኒት የፈጠረባት ስሜት ለፈፀመችው ድርጊት ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ቢገመትም ጉዳዩ ግን አሁንም እየተጣራ ነው። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ኮሎኔል ዲ ይ ላ ፔክስ እንደተናገሩት ከሆነ ተማሪዋ እየሰራችው በነበረው ጥናት ስጋት እንዳደረባትና ደስተኛ እንዳልነበረች ተናግረዋል። እርሳቸው እንዳሉት ማዳጋስካር በደረሰች በቀናት ውስጥ የጀመረችው ፕሮጀክት እየተሳካ እንዳልሆነ ተናግራ ጉዳዩን ለመቋጨት ያሰበች ትመስል ነበር ብለዋል። ተማሪ ከትላንድ ማዳጋስካር በገባች በሁለተኛ ቀኗ በሥራዋ ክትትል የሚያደርጉላትን ግለሰብ (ሱፐርቫይዘር) በትንሹ ሁለት ጊዜ እንዳገኘቻቸው ኮሎኔል አክለዋል። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? ባለፈው ሳምንት ከውጭ ጉዳይ ቢሮ በኩል በወጣው መግለጫ የተማሪዋ ቤተሰቦች ተስፋ ባላት እና ጠንካራ በሆነችው ልጃቸው ሞት ክፉኛ ልባቸው በሀዘን እንደተሰበረ ገልፀዋል። "ሁል ጊዜ መልካምና ቤተሰቦቿን መርዳት የምትወድ ፣ በሕይወቷ ከብዙ ሰዎች ጋር ጥብቅ ቁርኝትና መግባባት የነበራት ነበረች፤ ሁልጊዜም ትናፍቀናለች። " ሲሉ ቤተሰቦቿ ሀዘናቸውን ገልፀዋል። ትምህርቷን ስትከታተልበት ከነበረው ሮቢንሰን ኮሌጅ ዴቪድ ውድማን በበኩላቸው "በአላን ሞት በጣም ነው የደነገጥነው" ብለዋል። በኮሌጁ ውስጥ በነበራት የሁለት ዓመታት ቆይታም በተለያየ መልኩ ለኮሌጁ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ስታበረክት እንደነበር በመግለፅ " ሁላችንም እንናፍቃታለን " ሲሉ ጥልቅ ሀዘናቸውን ገልፀዋል።
53243268
https://www.bbc.com/amharic/53243268
በአዲስ አበባ በተከሰቱ የቦምብ ፍንዳታ ሙከራዎች ጉዳት መድረሱ ተገለፀ
በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በተሞከሩ የቦምብ ፍንዳታዎች የሰው ህይወት መጥፋቱን እንዲሁም በርካቶች መቁሰላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው ጣሰው ገልፀዋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽር እንደሻው ጣሰው የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መኪና ውስጥ መገደል ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ላይ የተሞከሩት ቦምብ ፍንዳታዎች ሦስት ቦታዎች ላይ መሆናቸውንም ኮሚሽነሩ የአርቲስቱን አሟሟት በተመለከተ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል። "የሚያፈነዱት ጭምር ቆስለዋል፣ የሚያፈነዱት ሰዎች ጭምር ሞተዋል፤ ሃሳባቸውን ለመግለፅ የወጡ ንፁሃን ዜጎችም የዚህ ጉዳት ሰለባ ሆነዋል" ያሉት ኮሚሽነሩ ምን ያህል ሰው እንደሞተ እንዲሁም የቆሰሉ ሰዎችን ቁጥርም አልጠቀሱም። የት አካባቢ የቦምብ ፍንዳታዎቹም እንደተሞከሩ ኮሚሽነሩ ባይጠቅሱም በከተማዋ ከዚህ ቀደም በተደረገ ጥናት "ከተማዋን ለማተራመስ የታጠቁ ኃይሎች ከውጭም ከውስጥም የተለያዩ ሥራዎች ለመስራት ሞክረዋል" ብለዋል። አክለውም "እንግዲህ ጥይት ሲተኮስ፣ ቦምብ ሲፈነዳ እከሌ ወዳጄ ነው እከሌ ጠላቴ ነው ብሎ አይለይም። ሰላም ሁሉንም ለመጠቅለል አቅም አለው። ችግር ግን ሁሉንም አይጠቀልልም፤ ችግሩ ባለበት ብቻ ያሉ ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሶ ያልፋል" በማለት አስረድተዋል። የፌደራል ፖሊስ አዛዡ የአርቲስቱን ሞት ተከትሎ በተነሱ ተቃውሞዎች የተለያዩ ጉዳቶች እንዲሁም የንብረት መውደሞች መድረሳቸውንም ተናግረዋል። ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን በተመለከተ የተጠናቀረ መረጃ ባይኖርም በአዳማ፣ ሐረር፣ ዝዋይ፣ ቡልቡላ፣ ሻሸመኔ የመሳሰሉት አካባቢዎች ከፊሎቹ ናቸው ብለዋል። የጉዳት መጠንም በአሁኑ ሰዓት ለመግለፅ አስቸጋሪ እንደሆነ የገለፁት ኮሚሽነሩ ሆቴሎችና ፋብሪካ የሚመስሉ ተቋማት እንደተቃጠሉም ለጋዜጠኞች አስረድተዋል። በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች ላይ ስለደረሱ የጉዳት መጠኖች መረጃው እንደተጠናቀረ ለኅብረተሰቡ የሚያደርሱ መሆናቸውን የገለፁት ኮሚሽነሩ ሕዝብ በፍራቻ ተሸብቦ የሚኖርበት ሁኔታ መፈጠር እንደሌለበትም አፅንኦት ሰጥተዋል። "እንዲህ ትልልቅ ከተሞች ላይ ግለሰቦች ቦምብ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ሌሎች ደግሞ እየፈሩ የሚሄዱበት ነገር እንዲፈጠር መፍቀድ የለብንም" ያሉት ኮሚሽነር እንዳሻው ኅብረተሰቡ እጅና ጓንት ሆኖ ነገሮችን እየመረመረ በማረጋጋቱ ሥራ ላይ ከመንግሥት ጎን እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለሕዝቡ በተለይም ለአገር ሽማግሌዎች ጥሪ ያቀረቡት ኮሚሽነር እንዳሻው አሁን የተፈጠረው ችግር በአጭር ጊዜ እንዲቋጭ የራሳቸውን ሚናም እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
news-45675496
https://www.bbc.com/amharic/news-45675496
የካናዳ ፓርላማ የምንያማሯ መሪ የሳን ሱ ኪን የክብር ዜግነት ገፈፈ
የካናዳ ፓርላማ አባላት ለምያንማሯ መሪ ሳን ሱ ኪ ሰጥቶ የነበረውን የክብር ዜግነት እንዲነሳ በሙሉ ድምጽ ወሰነ።
የክብር ዜግነታቸው እንዲነሳ የተወሰነባቸው የምያንማሯ መሪ በሃገራቸው የሮሂንጂያ ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ጥቃት ማስቆም አልቻሉም ተብሎ ነው። ሳን ሱ ኪ በወታደራዊ ቁጥጥር በነበረችው የቀድሞዋ በርማ የአሁኗ ምያንማር ላመጡት ከፍተኛ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እ.አ.አ በ1991 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸንፈው ነበር። የተባበሩት መንግስታት ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት የምያንማር ወታደራዊ መሪዎች ሮሂንጂያዎች ላይ ለፈጸሙት አሰቃቂ ተግባር በዘር ማጥፋት ወንጀል መጠየቅ አለባቸው ብሏል። • የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች • ከደሴ - አሰብ የሞላ? ባለፉት 12 ወራት ብቻ እስከ 700 ሺ የሚደርሱ ሮሂንጂያዎች ጥቃቱን በመሸሽ መኖሪያ ስፍራቸውን በመተው ተሰደዋል። የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትራዴዉ ለምያንማሯ መሪ የተሰጠውን የክብር ዜግነት ለማንሳት የተወካዮች ምክር ቤቱ እያሰበበት ነው ማለታቸውን ተከትሎ ከአንድ ቀን በኋላ ነው የፓርላማ አባላቱ የካናዳ የክብር ዜግነታችውን የገፈፈው። ሳን ሱ ኪ በ2007 የክብር ዜግነት ሲያገኙ በካናዳ ታሪክ ስድስተኛዋ ሰው ናቸው። ከዚህ በኋላ የካናዳ መንግስት ምን እንደሚወስን ባይታወቅም ፓርላማው ግን ሮሂንጂያዎች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል የዘር ማጥፋት ነው ብሎ እንዳጸደቀው የፓርላማው አባል የሆኑት አንድሪው ሌዝሊ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። • ንቦች የአውሮፕላን በረራ አስተጓጎሉ ፕሬዚዳንቷ ምንም እንኳን በምያንማር የተፈጸመውን ጥቃት እንዲያወግዙ ከመላው አለም ግፊት ቢደረግባቸውም፤ እስካሁን ያሉት ምንም ነገር የለም።
news-42320036
https://www.bbc.com/amharic/news-42320036
የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ለሕፃናት ደፋሪዎች ይቅርታ አደረጉ
የሕፃናት መብት አቀንቃኞች የታንዛንያው ፕሬዚዳንት ለሁለት ሕፃናትን የደፈሩ ወንጀለኞች ይቅርታ ማድረጋቸውን አውግዘውታል።
አሩሻ የሚገኘው ኮሙዩኒቲ ፎር ችልድረን ራይትስ ድርጅት ዳይሬክተር ኬት ማክአልፓይን "አስደንጋጭ ግን አስደናቂ ያልሆነ" ብለውታል። ጆን ማግፉሊ ይህንን ይቅርታ ያደረጉት ቅዳሜ የነፃነት ቀን ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። 10 የአንደኛ ደረጃ ሴት ተማሪዎችን የደፈሩት ዘፋኙ እንጉዛ ቫይኪንግ ወይም በቅጽል ስሙ ባቡ ሴያ እንዲሁም ልጁ ጆንሰን እንጉዛ ናቸው። ፕሬዝዳንቱ ከእስረኞቹ መሀል የባህርይ ለውጥ አምጥተዋል ያሉዋቸውን እስረኞች እንዲለቀቁ ወስነዋል። ኬት ማክአልፓይን ይህ ይቅርታ ፕሬዝዳንቱ በሕፃናት ላይ የሚደረግ ጭካኔን ወይም ሰብዓዊ መብት ጥሰትን መረዳት እንዳቃታቸው ማሳያ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ይህ ንግግራቸውን ባለፈው ሰኔ እርጉዝ የሆኑ ተማሪዎች ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ ካሉት አዋጅ ጋር አያይዘውታል። "ሕፃናትን ተጠቂ አድርገው ማየት የማይችሉ እውር ናቸው። ህፃናት ተማሪዎች እርጉዝ የሆኑት ጥቃት ስለደረሰባቸው ነው" ብለዋል። የሕፃናት መብት አቀንቃኟ ሄለን ኪጆ ቢሲምባ ለቢቢሲዋ ሙኒራ ሁሴይን እንደተናገሩት "እነዚህን ወንጀለኞች ይቅር ማለት ለቤተሰቡና ለወላጆች ህመምን መጨመር ነው" ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ተመሳሳይ ነገርም እንዳይፈፅሙ ሕገ-መንግሥቱ ሊያግዳቸው እንዲገባ ዘመቻ እያደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በታንዛንያ ሕፃናት ሲደፈሩ በቤተሰብ ስምምነት እንዲፈታ ከመደረጉም በላይ በብዙ አጋጣሚዎች ደፋሪዎች ፖሊስን ወይም የፍርድ ቤት ሠራተኞችን እንደሚከፍሉ ማክአልፓይን ይናገራሉ። "የሕፃናት መደፈር ጉዳይን ወደ ፍርድ ቤት ማምራት ማለት እንደ መስቀል ወፍ ነው" ያሉት ማክአልፓይን ወንጀለኞችም የዕድሜ ልክ ፍርድ ሲፈረድባቸውም አይታይም ብለዋል። ይህም ሆኖ ቫይኪንግ እና እንጉዛ በአውሮፓውያኑ 2003 ዕድሜያቸው ከ6-8 ዓመት የሚገመቱ በዳሬሰላም የሚገኙ 10 ሕፃናትን በመድፈራቸው የዕድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶባቸው ነበር። እሰከተለቀቁባት ቅዳሜ ድረስም ለ13 ዓመታትም በእስር ቆይተዋል። የሀገሪቱ ሚዲያ እንደዘገቡትም ከእስር ቤት ሲወጡ ደጋፊዎቻቸው በጭብጨባ ተቀብለዋቸዋል።
53915684
https://www.bbc.com/amharic/53915684
ሰሜን ኮሪያ፡ ታመዋል ሲባሉ የነበሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ድንገት ተከሰቱ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ታመዋል ከሚለው ጀምሮ፣ አብቅቶላቸዋል፣ ሞተዋል እየተባለም ብዙ ይወራባቸው ነበር፡፡
ድንገት በፓርቲ ስብሰባ ተከስተው መመርያ ሰጥተዋል፣ ትናንት፡፡ ሰሜን ኮሪያ ትልቅ አደጋ ከፊቷ ተደቅኗል ያሉት ኪም ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲሆን አዘዋል፡፡ ትልቅ አደጋ እየመጣ ነው ያሉት ኪም አደጋዎቹ በዋናነት ሁለት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ አንዱ ኮሮና ቫይረስ ሲሆን ሌላው ደግሞ አውሎ ንፋስ ነው፡፡ ኪም ከሰሞኑ ጠፍተው ስለነበር የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ስለነበረ ምናልባት ሞተው ይሆን? ሲባል ነበር፡፡ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን አንድም ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘብኝም ስትል ታስተባብላለች፡፡ አይበለውና ወረርሽኙ ወደዚያች አገር ቢገባ ባላት ደካማ የጤና መሰረተ ልማት ከፍተኛ አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ባቪ የሚሰኝ አደገኛ አውሎ ነፋስ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሰሜን ኮሪያን ሊመታት ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የፖሊትቢሮ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ኪም በስብሰባው ላይ ንግግር እያደረጉ ሲያጨሱ ይታዩ ነበር፡፡ በዚህ ንግግራቸው ኮቪድን በተመለከተ አንዳንድ ችግሮች ተስተውለዋል ብለዋል፡፡ ምን ማለታቸው እንደሆነ ግን የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ ፒዮንግያንግ ለረዥም ጊዜ ወረርሽኙ እኔ ጋ ድርሽ አላለም ስትል እያስተባበለች ቆይታለች፡፡ ነገር ግን ይህን የሰሜን ኮሪያን አስተያየት ብዙዎች በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት፡፡ አንድም በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የለም ስትል የነበረው ሰሜን ኮሪያ በቫይረሱ አጠባበቅ ዙርያ ችግሮች ታይተዋል ማለቷ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል፡፡ ሰሜን ኮሪያ ከጥርጣሬ የተነሳ አንዲት የድንበር ከተማ ሰዎች ተገለው እንዲቀመጡ ያደረገች ሲሆን ነገር ግን ከዚህ የዘለለ ስለተያዘ አንድም ሰው ተጠቅሶ አያውቅም፡፡ ኪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክብደት እየጨመሩ ስለሆነ በወጣትነታቸው ሊቀጠፉ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች በስፋት ይሰነዘሩ ነበር፡፡ በቅርቡም ለእህታቸው ኪም ዮ ጆንግ በርከት ያሉ ሥልጣኖችን ሰጥተዋት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ እንደ ኑዛዜ የወሰዱት ሚዲያዎችም ነበሩ፡፡ ሰሜን ኮሪያ 25 ሚሊዮን ዜጎች አሏት፡፡ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎቿ የረሀብ አደጋ ገጥሟቸዋል ይላል የተባበሩት መንግሥታት፡፡ የረባ የንግድ ግንኙነት ከአገራት ጋር ያልመሰረተችው ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር የምታደርገው ንግድ ወሳኝ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ይህም በኮሮና ምክንያት እክል ገጥሞታል፡፡ በፒዮንግያንግ መቀመጫቸውን ያደረጉ በርካታ ግብረሰናይ ድርጅቶችና የኤምባሲ ሰራተኞች አገሪቱን ለቀው እንደወጡ ተዘግቧል፡፡
52254173
https://www.bbc.com/amharic/52254173
ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች?
እስከ ሚያዝያ አንድ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ስድሳ አምስት ሰዎችን አጥቅቶ፣ ሦስቱን ለሞት ያበቃው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፤ እንደሌሎች የዓለም ክፍሎች ሁሉ ተያያዥ የሥነ ጤና፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ኃብታዊ ጠንቆችን እንደሚያስከትል ይጠበቃል።
ወረርሽኙ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ አኳኋን በፍጥነት መዛመት፤ ይዟቸው የሚመጣቸውን ጣጣዎችም በዚያው ልክ የገዘፉ እንዲሁም በዓለም ዙርያ የተሰራጩ አድርጓቸዋል። በዚያውም ልክ መጭውን ለመተነብይም አዳጋች ሆኗል። ይሁንና በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሞያዎች የጉዳቱን መጠን ለመስፈር፤ የድኅረ-ወረርሽኝ አቅጣጫዎችንም ለመቀየስ መሞከራቸው አልቀረም። ወረርሽኙ በሰዎች የሥራ እና የገቢ ሁኔታ ላይ የሚያሳርፈውን ጡጫ በተመለከተ ጥናት ያደረገው ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (አይ.ኤል.ኦ) እ.ኤ.አ መጋቢት 18 ቀን 2020 ባሳተመው ግምገማው ምንም እንኳ የኮሮናቫይረስ በዕድሜ የገፉትን እና ቀደም ሲል በሽታ የነበረባቸውን ግለሰቦችን የማጥቃት ከፍ ያለ ዕድል ቢኖረውም፤ ከወረርሽኙ በኋላ የሚከሰት የሥራ አጥነት ቀውስ ወትሮውኑም ሥራ ማጣት የሚያበረታባቸው ወጣቶች ላይ ሊጠነክር ይችላል ይላል። በአገልግሎት ዘርፍ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት ሴቶች፣ ዋስትና አልባ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች (ለምሳሌ የራሳቸውን ሥራ የሚሰሩ እና በጊዜያዊነት የተቀጠሩ) አንዲሁም ስደተኛ ሠራተኞች አንዲሁ ክፉኛ በሥራ አልባነት ማዕበል ክፉኛ ሊደቆሱ ይችላሉ ይላል የአይ.ኤል.ኦ ግምገማ። በምጣኔ ኃብት ያልጠነከሩ አገራት ኢትዮጵያም ወረርሽኙ የሚያስከትለውን የጤና ቀውስ ለመቋቋም ከምታደርጋቸው ጥረቶች ባሻገር ይዞት የሚመጣው የምጣኔ ኃብት ጡጫ ያሳሰባት ይመስላል። ከሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የበለፀጉ አገራት ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ የአፍሪካ አገራት የዕዳ ቅነሳ እና የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ይታወሳል። ባገባደድነው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ በተደረገ የድረ ገፅ ላይ ውይይት የሥራ ፈጠራ ኮሚሽነሩ ኤፍሬም ተክሌ ሌማንጎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሥራዎቻቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ መናገራቸው ተዘግቧል። የሥራ ዕጦቱ በአገሪቱ ትልቁ ኩባንያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጀመረ ይመስላል። የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ድርጅታቸው ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 550 ሚሊዮን ዶላር ማጣቱን በገለፁበት መገለጫቸው ላይ ቋሚ ያልሆኑ ሠራተኞችን ለጊዜው ሥራ እንዲያቆሙ መደረጋቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት ማኅበር ያሳተመው የአራት ባለሞያዎች ምልከታ ከወረርሽኑም በፊት ለብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን መሠረታዊ ግልጋሎቶችን ማግኘት አዳጋች ነበር፤ ይህም ወረርሽኙን ለመከላከል መደረግ ያለባቸውን እርምጃዎች ቀላል እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል ይላል። እንደአብነትም ከጠቅላላው ሕዝብ መካከል ስድስት በመቶ የሚሆነው ያህል በመኖርያው አቅራቢያ የመታጠቢያ ውሃ አለው ይላል። • “ገደቦችን በአጭር ጊዜ ማንሳት ወረርሽኙ በአስከፊ ሁኔታ እንዲሰራጭ ያደርጋል” ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም • ኮሮናቫይረስ ካለበት ሰው ጋር ንክኪ ላደረጉ ሰዎች ጥቆማ የሚሰጥ መሣሪያ እየተሠራ ነው ባለሞያዎቹ ብሔራዊው የስታትስቲክስ ድርጅት በማጠቀስ ከአራት ዓመት በፊት በተጠናቀረ መረጃ መሠረት አገሪቱ ውስጥ ካሉ ቤቶች ሰማንያ አምስት በመቶው ባለአንድ ወይንም ባለሁለት ክፍል መሆናቸውን አስታውሰው በኮቪድ 19 በሽታ ጥርጣሬ ቤት ውስጥ ተነጥሎ መቀመጥ አዋጭ አማራጭ ያለመሆኑን ይናገራሉ። ወረርሽኑ የሚፈጥረው የምጣኔ ኃብት ንዝረት የአገልግሎት ዘርፉን፣ ቱሪዝምን እና የመስተንገዶ ኢንዱስትሪውን፣ የውጭ ንግድን እና የመጓጓዣ ዘርፍን ሊጎዳ እንደሚችል የሚገምተው የባለሞያዎቹ ምልከታ ግብርናም ቢሆን ከዚህ የሚተርፍ አይደለም ይላል- በተለይ በቀላሉ የሚበላሹ ምርቶች አብቃዮች እና አከፋፋዮች ለጉዳት ተጋላጭ መሆናቸው አይቀርም። ወረርሽኙ የአቅርቦት ሰንሰለትን ያውካል። የሥራ መቀዛቀዝ በሚፈጥረው የገቢ እጥረት እንዲሁም የሚመጣው አይታወቅም በሚል ስጋት ምክንያት ሰዎች ገንዘብ ከማውጣት ስለሚቆጠቡ የፍላጎት እጥረትን ያስከትላል፤ አንዲሁም የንግድ ተቋማት የመንቀሳቀሻ ገንዘብ እጥረት እንዲያጋጥማቸው፣ ዕዳ መክፈል እንዲሳናቸውም ሊያደርግ ይችላል የባለሞያዎቹ ግምገማ እንደሚያመላክተው። እነዚህ ችግሮች እርስ በእርስ እየተመጋገቡ የምጣኔ ኃብት እንቅስቃሴው በአዝጋሚነት ዘለግ ላለ ጊዝ የሚዘልቅ ከሆነ ምጣኔ ኃብታዊ መኮማተር (ሪሰሽን) ሊከተልም ይችላል። ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂ.ዲ.ፒ.) ሰላሳ ዘጠኝ በመቶውን ድርሻ የሚይዘው የአገልገሎት ዘርፍ በወረርሽኙ ከሌሎች ዘርፎች በበለጠ ሊጎሳቆል ይችላል። ሰላሳ ሦሰት በመቶውን ድርሻ የሚይዘው ግብርና ግን ቢያንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአንፃራዊነት ያነሰ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። በባለሞያዎቹ ግምት መሠረት ወረርሽኙ አነስ ባለ የጉዳት ለሦስት ወራት ያህል ቢቆይ እንኳ ምጣኔ ኃብቱ እስከ 44 ቢሊዮን ብር የሚደርስ እጦትን ሊያስተናግድ ይችላል። ወረርሽኙ ለስድስት ወራት ቢቆይና የከፋ ጉዳት የሚያደርስ ቢሆን የእጦቱ መጠን ከሁለት መቶ ቢሊዮን ብር ይሻገራል። ኮሮናቫይረስ ሠራተኞች ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ የተሠራ አንድ ጥናት 3 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ሥራ-አጥ ሊሆኑ ይችላሉ ይላል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማኅበር ያሳተመው ጥናት ቫይረሱ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ በርካቶች ሥራ-አጥ ሊሆኑ ይችላሉ ባይ ነው። በቅርቡ የኢትዮጵያ ሥራ ፈጠራ ኮሚሽን በሠራው ጥናት እንደሚጠቁመው ቫይረሱ ለስድስት ወራት የሚቆይ ከሆነ በማኒዩፈክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ 60 በመቶ ሰዎች ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ።በተመሳሳይም በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ 74 በመቶ ሰዎች ሥራ-አጥ ይሆናሉ። ጥናቱ አክሎም ከ9 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተሰማርተውበታል በሚባለው የአገልግሎት ዘርፍ ብቻ 3 ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን ሊያጡ ይችላሉ ይላል። ቫይረሱ በኅብረተሰቡ ውስጥ ከተንሰራፋ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ ያስጠነቅቃል።ጥናቱ የተሠራው የቫይረሱን ቆይታ በሁለት በመከፋፈል ነው። የመጀመሪያው ለሦስት ወራት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ስድስት ወራት ነው። የቫይረሱ ተፅዕኖ የከፋ ከሆነ ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ችግር ላይ ሊወድቁ ይችላሉ ይላል።
news-50953900
https://www.bbc.com/amharic/news-50953900
ኤም ቲ ኤን ለአልቃይዳና ታሊባን ጉቦ በመስጠት ተወነጀለ
በአፍሪካ ግዙፉ የሞባይል ኩባንያ ኤም ቲ ኤን አሸባሪ ለተባሉት ታሊባንና አልቃይዳ ቡድኖች ጉቦ በመስጠት በአሜሪካ ፌደራል ፍርድ ቤት ክስ ቀረበበት።
ኩባንያው ለእነዚህ ቡድኖች ገንዘብ የሰጠው አፍጋኒስታን ውስጥ የሚገኝና ትልቅ ኢንቨስትመንት ያደረገባቸው የኔትዎርክ ታዎሮች ላይ ጥቃት እንዳይደርስበት ለጥበቃ ነው ተብሏል። በውንጀላው መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉ ሌሎች አምስት ኩባንያዎችም ያሉ ሲሆን ክሱ የቀረበው አፍጋኒስታን ውስጥ በተገደሉ የአሜሪካ ዜጎች ስም ነው። • ጃዋር ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን መቀላቀሉ ተረጋገጠ • ሱዳን በ29 ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈች • "ሙስና ለመጣው ፖለቲካዊ ለውጥ አንድ ምክንያት ነው" በቀረበው ክስ እንደተባለው ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች ከኤም ቲ ኤን ያገኙትን ገንዘብ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2009 እስከ 2017 አፍጋኒስታን ውስጥ ላካሄዷቸው የጥቃት ዘመቻዎች ተጠቅመውበታል። ይህ ደግሞ የአሜሪካን የፀረ ሽብር አዋጅን የሚፃረር ነው፤ ስለዚህም ኤም ቲ ኤን ይህን ህግ ተላልፏል ተብሏል። ኩባንያው ግን በየትኛውም ቦታ ስራውን የሚያካሂደው ሃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንደሆነ ገልጿል። ኤም ቲ ኤን በአፍሪካ ግዙፉ፤ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከስምንት ትልልቅ ኩባንያዎች አንዱ ነው። ከ240 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች በላይም አለው ተብሎ ይታመናል። በ2015 ያልተመዘገቡ ሲም ካርዶችን ባለመሰረዝ በናይጄሪያ ባለስልጣናት በቀረበበት ክስ 5 ቢሊዮን ዶላር እንዲቀጣ ተፈርዶበት፤ ከረዥም ክርክር በኋላ እንዲሁም የያኔው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮም ዙማ በጉዳዩ ጣልቃ ገብተው ቅጣቱ ወደ 1.7 ቢሊዮን ዶላር እንደወረደለት የሚታወስ ነው። የዛሬ ዓመትም በኢራን የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኤምቲኤን ኢራን ውስጥ እንዲሰራና የ 31.6 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት እንዲያሸንፍ ጉቦ ተቀብለዋል በሚል መታሰራቸውም ይታወሳል።
news-55305979
https://www.bbc.com/amharic/news-55305979
ኮሮናቫይረስ ፡ በለንደን የኮቪድ-19 ስርጭት በመጨመሩ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ሊጣል ነው
በእንግሊዝ ለንደን ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ በመሆኑ ጥብቅ ነው የተባለ የእንቅስቃሴ ገደብ በመጪዎቹ ቀናት ሊጣል መሆኑን ቢቢሲ ከምንጮቹ መረዳት ችሏል።
የአገሪቱ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በለንደን ከተማ ያለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር "በእጅጉ እንዳሳሰባቸው" ሲገልፁ ነበር። ቢቢሲ ከመረጃ ምንጮቹ መረዳት እንደቻለው የለንደን ከተማ የሕዝብ እንደራሴዎች ስለ ጉዳዩ የተነገራቸው ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ አልተደረሰም ተብሏል። የለንደን ከተማ ከንቲባ ሳዲቅ ካኻን ሚኒስትሮችን የከተማዋን ምጣኔ ሀብት በማይጎዳ መልኩ "በአስተውሎት" ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ ጥሪ አቅርበዋል። እንደ ከንቲባው ከሆነ በከተማዋ ሦስተኛ ደረጃ የተባለው የእንቅስቃሴ ገደብ የሚጣል ከሆነ የአገልግሎት ሰጪ እና የቱሪዝም ዘርፉ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ይኖረዋል። አንዳንድ የከተማዋ ምክር ቤት አባላት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መጨመርን ተከትሎ "ከደረጃ ሦስት ከፍያለ" እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። ደረጃ ሦስት የእንቅስቃሴ ገደብ ምን ይዟል? በለንደን ያለው የኮሮናቫይረስ ስርጭት መጨመሩን ተከትሎ ይጣላል የተባለው ደረጃ ሦስት የእንቅስቃሴ ገደብ በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጪ ከቤተሰብ አባላት በአንድነት መሆንን ይከለክላል። እንዲሁም በመናፈሻ ስፍራዎች በባህር ዳርቻዎችና ከከተማ ውጪ እስከ ስድስት ሰዎች ድረስ በመሆን አብሮ ማሳለፍ ይቻላል። የንግድ መደብሮች፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የውበት ሳሎኖች ክፍት ሆነው ሊቆዩ ይችላሉ። መጠጥ ቤቶች፣ ካፌዎች፣ ምግብ ቤቶች ግን ወደ ቤት ወስደው ለሚጠቀሙ ካልሆነ በስተቀር ዝግ ሆነው ይቆያሉ። የስፖርታዊ ውድድር አፍቃሪዎች በስታዲየሞች ተገኝተው ውድድሩን መከታተል አይችሉም። ሲኒማ ቤቶችም ሆኑ ሌሎች የቤት ውስጥ ስፖርቶች ዝግ እንዲሆኑ ይደረጋል። የደረጃ ሦስት የእንቅስቃሴ ገደብ የተጣለበት ከተማ ነዋሪዎች ወደየትኛውም የአገሪቱ ክፍል እንዳይንቀሳቀሱ ይከለከላሉ። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ማት ሐንኮክ በዛሬው ዕለት ለእንደራሴዎች ምክር ቤት ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን በማስከተልም መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እያለ የለንደን ከተማ ከንቲባ መንግሥት በከተማዋ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ከገና በዓል በፊት እንዲዘጉ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ሳዲቅ ካኻን እድሜያቸው ከ10 እስከ 19 የሆኑ ታዳጊዎች ላይ የኮቪድ-19 ስርጭት ከፍ ብሎ በመታየቱ ረዥም የእረፍት ጊዜ እንዲወሰዱ ይፈልጋሉ። ባለፉት ሳምንታት በለንደን ከተማ ውስጥ እና ውጪ የሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች በከፍተኛ ቁጥር የኮሮናቫይረስ መጨመር ታይቶባቸዋል። በኅዳር ወር ለንደን ዝቅተኛ የቫይረሱ ስርጭትን ካስመዘገቡ የእንግሊዝ ከተሞች መካከል አንዷ የነበረች ሲሆን አሁን ግን "ከፍተኛ" በተባለ ፍጥነት ቫይረሱ በከተማዋ እየተስፋፋ ነው። የጤና ባለሙያዎች ለንደን የኮሮናቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ሞትን ለመቀነስ በደረጃ ሦስተኛ የጥንቃቄ እርምጃ ላይ እንድትቀመጥ ሲወተውቱ ከርመዋል። ምሥራቅ ለንደን እና የተወሰኑ የኢሴክስ ከተማ ክፍሎች የኮቪድ-19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የታየባቸው ናቸው።
news-46134434
https://www.bbc.com/amharic/news-46134434
ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጄፍ ሴሽንስን አባረሩ
የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ጄፍ ሴሽንስ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተባረሩ።
''ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ጄፍ ሴሽንስ ለአገልግሎታቸው እናመሰግናለን፤ መልካም ሁሉ አንዲገጥማቸው እንመኛለን!'' ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ዶናልድ ትራምፕ አስፍረዋል። ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ ጋር በተያያዘ የተካሄደባቸውን ምርመራ ጄፍ ሴሽንስን በተደጋጋሚ ይወቅሱ ነበር። • ትራምፕ ሬክስ ቲለርሰንን ከስልጣን አባረሩ • ዜግነት ለማግኘት ሲባል አሜሪካ ሄዶ መውለድ ሊቀር ይሆን? ትራምፕ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ በፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ማቲው ዊትኬር እንደሚተኩ አስታውቀዋል። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 የአላባማ ሴናተር እና ቀደም ሲል የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ የነበሩት ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ጄፍ ሴሽንስ ለዋይት ሃውስ ባስገቡት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ይህ የሥራ መልቀቅ ውሳኔ ከእራሳቸው እንዳልመጣ በግልጽ አስፈረዋል። • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ ''ክቡር ፕሬዚዳንት፤ በእርስዎ ጥያቄ መሰረት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብቻለሁ'' ሲሉ ቀኑ ባልተገለጽ ደብዳቤ ላይ ጽፈዋል። እኤአ 2017 ጄፍ ሴሸንስ የሩሲያ ምርመራ በሚካሄድበት ወቅት ራሳቸውን ገሸሸ በማድረጋቸው ዶናልድ ትራምፕ የሕግ አሰፈጻሚ አካሉን አምርረው ሲወቅሱ ነበር። ምረመራው የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳና በወቅቱ ሞስኮ የነበራትን ተሳትፎ ለማወቅ የተካሄደ ነበር። በዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ ዲሞክራቶች ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል። ዲሞክራቶች አዲሱ ተሿሚ ሹመታቸው በሴኔቱ መጽደቅ አለበት ሲሉ ይሞግታሉ።
news-48578597
https://www.bbc.com/amharic/news-48578597
በሆንግ ኮንግ የተነሳው ተቃውሞ በውጭ ኃይሎችን የታገዘ ነው ሲል የመንግሥት ሚድያ ወቅሷል
'የውጭ ኃይሎች' ሆንግ ኮንግ ውስጥ ብጥብጥ በመፍጠር ቻይናን ለመጉዳት እየሞከሩ ነው ሲል የቻይና መንግሥት ጋዜጣ ቅሬታ አሰምቷል።
ዕለተ ሰንበት ሺዎች አደባባይ ወጥተው የሃገሪቱ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሊያፀድቀው ያሰበውን አዋጅ አውግዘዋል፤ ረቂቁ የሆንግ ኮንግ ተቃዋሚዎችን አአከርካሪ ለመስበር ያለመ ነው በማለት። በፖሊስ እና ተቃዋሚዎች መካከል ግጭት መፈጠሩ አልቀረም። ቢያንስ ሶስት ፖሊሶች እና አንድ ጋዜጠኛ ተጎድቷል ይላል የፖሊስ ዘገባ። የቻይና መንግሥት ግን ረቂቁ በእቅዱ መሠረት መሄዱን ይቀጥላል ሲል ተደምጧል። • ቻይና የዶናልድ ትራምፕን ስልክ ጠልፋው ይሆን? የተቃውሞ ሰልፉ አዘጋጆች አንድ ሚሊዮን ሰው ወጥቷል ሲሉ ፖሊስ 240 ሺህ ብቻ ነው ያየሁት ሲል አስተባብሏል። 'ቻይና ደይሊ' የተሰኘው ጋዜጣ በርዕሰ አንቀፁ 'አንዳንድ የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች በተቃዋሚ ፓርቲዎች እና በውጭ አጋሮቻቸው ምላስ ተታለው ረቂቅ አዋጁን ሊቃወሙ ወጥተዋል' ሲል አትቷል። ጋዜጣው አክሎም 'መቼም በጤናው ያለው ሰው ይህን በጉጉት የተጠበቀ አዋጅ አይቃወምም' በማለት የሰልፈኞቹን አእምሮ ጤና ተጠራጥሯል። ተቺዎች አዲሱ ሕግ በልዩ አስተዳድር የምትመራው ሆንግ ኮንግ ያላትን አንፃራዊ ነፃነት የሚቀማ ነው ባይ ናቸው። • ከኢትዮ- ቻይና ወዳጅነት ጀርባ ረቂቁ ዜጎች ወንጀል ሠርተው ታይዋን ወይንም ሆንግ ኮንግ ውስጥ ቢደበቁ እንኳ ከእሥር አያመልጡም የሚል አንቀፅ አዝሏል። ከዚህ በፊት በታይዋን እና ሆንግ ኮንግ መካከል እሥረኛ አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ባለመኖሩ ቻይናውያንን ይህንን ቀዳዳ ይጠቀሙበት እንደነበር ተነግሯል። ሆንግ ኮንግ የቻይና ግዛት ብትሆንም በልዩ አስተዳደር የምትመራ መሆኗ ለዒ ሺን ፒንግ መንግሥት ነገሮችን ያወሳሰበ ይመስላል። • ሁሉንም በደህንነት ካሜራ የምትመለከተው ቻይና
news-45937014
https://www.bbc.com/amharic/news-45937014
ስለ ሳዑዲው ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂ አሟሟት እስካሁን የምናውቀው
የሳዑዲ ዜግነት ያለው ዝነኛው ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂ ቱርክ ኢስታንቡል ወደ ሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ገብቶ ደብዛው ከጠፋ ሁለት ሳምንታት አልፈው ነበር።
በወቅቱ የቱርክ ባለስልጣናት በሳዑዲ ሰዎች ስለመገደሉ የድምጽ ማስረጃ አለን ብለዋል ። ሳዑዲ ግን በተደጋጋሚ ጀማል ወደ ቆንስላው ከገባ ከደቂቃዎች በኋላ ቆንስላውን ለቅቆ ወጥቷል ብትልም አሁን ግን መገደሉን አምናለች። • የሳዑዲ እገዳ ለየመን ጥፋት ነው • የአውሮፓ አገራት የተገደለው የሳዑዲ ጋዜጠኛ ምርመራ እንዲቀጥል አሳሰቡ ሳዑዲ ጀማል መገደሉን ከማመኗ በፊት የሃገሪቱ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ በቆንስላው ውስጥ በነበሩ ሰዎች እና ጀማል መካከል በተፈጠረ ጸብ ምክንያት ሊሞት ችሏል ብለው ነበር። ስለ ጀማል ኻሾጂ አሟሟት እስካሁን የምናውቃቸው እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው። ጀማል ኻሾጂ ማን ነበር? ጀማል በሳዑዲ ዝነኛ ጋዜጠኛ ነበር፤ የሶቪየት ሕብረት የአፍጋኒስታን ወረራን በዝርዝር ዘግቧል። እንደ ኦሳማ ቢን ላድን ከመሳሰሉ ግለሰቦች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። ለበርካታ አስርት ዓመታት ለሳዑዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ የቅርብ ሰው ነበር፤ የሳዑዲ መንግሥት የመገናኛ ብዙሃን አማካሪ ሆኖም ሰርቷል። ባለፈው ዓመት ግን ከሳዑዲ መንግሥት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሃገር ጥሎ ወደ አሜሪካ ተሰደደ። አሜሪካም ሆኖ የዋሽንግተን ፖስት አምደኛ ሆነ። በጽሑፎቹ የሳዑዲ አረቢያውን ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማንን ይተች ነበር። • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ • "የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተለው ዲፕሎማሲ ቀለም አልባ ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን ከሳዑዲ መንግሥት ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ እንዳስገባው በርካቶች ይናገራሉ። ወደ ሳዑዲ ቆንስላ ለምን አቀና? ጀማል ወደ ቆንስላው የሄደው ከቀድሞ ሚስቱ ጋር መፋታቱ የሚያረጋገጥ ዶሴ ለማግኘት፣ ከዚያም ቱርካዊት እጮኛውን ለማግባት በእለተ አርብ ሴብቴምበር 28 በቆንስላው ተገኘ። በቆንስላው ያሉ ሰዎች ግን ለማክሰኞ ኦክቶበር 2 ቀጠሩት። ''ቱርክ ውስጥ በሚገኝ የሳዑዲ ቆንስላ ውስጥ ምንም ሊያደርጉኝ አይችሉም ብሎ ገምቶ ነበር'' ስትል እጮኛው ለዋሽንግተን ፖስት ጽፋለች። ''ጀማል ምንም እንደማይገጥመው እርግጠኛ ነበር'' ማክሰኞ ሴብቴምበር 2 ከቀጠሮ ሰዓት 15 ደቂቃ ቀደም ብሎ ወደ ቆንስላው ሲገባ በተንቀሳቃሽ ምስል ይታያል። ጀማል ወደ ቆንስላው ከመግባቱ በፊት ለእጮኛው ሁለት ስልክ ቁጥሮች ሰጥቷት ካልተመለስኩ ለቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ታይር ኤርዶጋን አማካሪዎች ደውለሽ ንገሪያቸው ብሏት ነበር። እጮኛው ሳትታክት ለ10 ስዓታት በቆንስላው በር ላይ ጠበቀችው። በነጋታውም ወደ ቆንስላው ሄዳ ጠበቀችው ጀማል ግን የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። የጀማል እጮኛ ሳትታክት ለ10 ስዓታት በቆንስላው በር ላይ ጠብቃው ነበር። በጉዳዩ ላይ የሳዑዲ አረቢያ ምላሽ ምን ነበር? ለሁለት ሳምንታት ያክል ሳዑዲ በጀማል እጣ ፈንታ ላይ የማውቀው ነገር የለም ስትል ቆይታ ነበር። ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ለብሉምበርግ ሲናገሩ ''ጀማል ላይ ስለሆነው ነገር ለማወቅ ጓጉችያለሁ። ከደቂቃዎች በኋላ ወይም ከአንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ ጉዳዩን ጨርሶ ወጥቷል'' ብለው ነበር። ''ምንም የምንደብቀው ነገር የለም'' ሲሉም ተደምጠዋል። ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ የሳዑዲ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛው በቆንስላው ውስጥ በተፈጠረ ጸብ ምክንያት ለሞት ተዳርጓል ሲል ዘገበ። ብሔራዊ የቴሌቪዝን ጣቢያው ጨምሮ እንደዘገበው ከጀማል ግድያ ጋር በተያያዘ 18 የሳዑዲ ዜጎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። በኢስታንቡል የሚገኘው የሳዑዲ ቀንጽላ ቱርክ ጀማል ላይ ምን ደረሰ አለች? የቱርክ ባለስልጣናት ጀማል በሳዑዲ የጸጥታ ኃይሎች በቆንጽላ ውስጥ እንዲሰቃይ ተደርጎ ተገድሏል፤ ከዚያም አስክሬኑ በሰዋራ ስፍራ ተጥሏል ይላሉ። ቱርኮች ይህን የሚያረጋግጥ የቪዲዮ እና የድምጽ ማስረጃ አለን ይላሉ። ይሁን እንጂ የቪዲዮ እና የድምጽ መረጃዎቹ ለህዝብ ይፋ አልሆኑም። ሳብሃ የተሰኘ የቱርክ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ በቆንጽላው ውስጥ የሚሰሩ የቱርክ ዜግነት ያላቸው ሰራተኞች በጀማል ቀጠሮ ዕለት በፍጥነት ቆንጽላውን ጥለው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር። በጀማል ግድያ እጃቸው አለበት የተባሉት የሳዑዲ የጸጥታ ኃይል አባላት እነማን ናቸው? የቱርክ መገናኛ ብዙሃን 15 አባላት ያሉት የሳዑዲ ቡድን የጀማል ደብዛ የጠፋ ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢስታንቡል ቱርክ በግል አውሮፕላን መጥተዋል። ከ15 ሰዎች መካከል ማህር ሙትሬብ የተባለው ግለሰብ ሎንዶን በሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ የጸጥታ እና ደህንነት አባል መሆኑን ቢቢሲ አረጋግጧል። አራት ግለሰቦች ደግሞ ከልዑል አልጋ ወራሹ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ጋር ቅርርብ አላቸው። የቱርክ መገናኛ ብዙሃን እንደሚሉት ከሆነ 15ቱ ግለሰቦች አጥንት መቁረጫ መጋዝ ይዘው ነው የመጡት። ከግለሰቦቹም መካከል አንዱ የሬሳ ምርመራ ባለሙያ ነው። የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ይዘውት የወጡት ቪዲዮ እንደሚያሳየው ከጀማል የቀጠሮ ሰዓት አንድ ሰዓት ቀድም ብሎ የቡድኑ አባላት መኪና እያሽከረከሩ ወደ ቆንስላው ሲያመሩ ያሳያል። ከዚያም የቡድን አባላቱ ለሁለት ተከፍለው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተመልሰው ሄደዋል። ምረመራው እንዴት እየሄደ ነው? ጀማል ከተሰወረ ከ13 ቀናት በኋላ የቱርክ መርማሪዎች ወደ ቆንስላው እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው ነበር። የመርማሪ ቡድን አባላቱ ወደ ቆንስላው ከመግባታቸው በፊት የሳዑዲ ባለስልጣናት እና የጽዳት ሰራተኞች ቀድመው ገብተው ነበር። በቆንጽላው አቅራቢያ በሚገኙ ወንዞችና ጫካዎች አቅራቢያ ምረመራዎች ተደርገዋል። ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ ወደነዚህ ስፍራዎች ከቆንጽላው የተነሱ መኪኖች ሲያቀኑ ታይተዋል። ''ጀማል ተገድሏል'' ዛሬ ጠዋት ሳዑዲ ጀማል ስለመገደሉ አምናለች። የሳዑዲ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አደል አል-ጁቤር ለፎክስ ኒውስ ሲናገሩ ''ከፍተኛ ስህተት ተፈጽሟል'' ካሉ በኋላ በዚህ ጉዳይ ላይ የልዑል አልጋ ወራሹ እጅ እንደሌለበት ተናግረዋል። የተፈጸመውን ሁሉ ለማጣራት ቁርጠኛ ነን። በጉደዩ ላይ የተሳተፉትን ሁሉ እንቀጣለን'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሳዑዲ የሚተቹ ሁሉ እምጥ ይግቡ እስምጥ የማይታወቀው ለምንድን ነው?
51971180
https://www.bbc.com/amharic/51971180
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች ተገኙ
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በሦስት ጨምሮ ዘጠኝ መድረሱን የጤና ጥበቃ ሜኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቁ።
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በሦስት ጨምሮ ዘጠኝ መድረሱን የጤና ጥበቃ ሜኒስቴርና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታውቀዋል በአገሪቱ ውስጥ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው የመጀመሪያ ግለሰብ የዛሬ ሳምንት መጋቢት 04/2012 ዓ.ም ይፋ ከተደረገ በኋላ በሽታው የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አሁን ዘጠኝ ደርሷል። በሽታው ከተገኘባቸው ከአዲሶቹ ሦስት ሰዎች መካከል አንደኛው የ44 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ጃፓናዊ፣ ሌላው የ39 ዓመት ኦስትሪያዊ፣ እንዲሁም ሦስተኛዋ የ85 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያዊት መሆናቸው ተገልጿል። አዲስ በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጡት ሦስት ሰዎች ውስጥ ጃፓናዊው ግለሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ መጀመሪያ በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠው ጃፓናዊ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሲኾኑ፣ የ85 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ደግሞ ከሁለት ሳምንት በፊት ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው። • በአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ ምልክት ከታየባቸው አራቱ ነፃ ሆነው መገኘታቸው ተነገረ • በኮሮናቫይረስ ስጋት የዶ/ር ካትሪን ቀብር ውስን ሰዎች በሚገኙበት ሰኞ ይፈጸማል • የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምን እያደረጉ ነው? ዘጠነኛው በበሽታው መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ ደግሞ ኦስትሪያዊ ዜግነት ያለው ሲሆን ከቀናት በፊት ከስዊትዘርላንድ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ ተገልጿል። ግለሰቡ እራሱን ለይቶ ካቆየ በኋላ የበሽታው ምልክቶች ስለታየበት ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገባ መደረጉንና በተደረገለት ምርመራ ቫይረሱ ሊገኝበት መቻሉ ተገልጿል። እስካሁን በሽታው እንዳለባቸው ከተረጋገጡት ሰዎች አራቱ ጃፓናዊያን፣ ሶስቱ ኢትዮጵያዊያን፣ አንዷ እንግሊዛዊት እና አንዱ ኦስትሪያዊ ናቸው። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳመለከተው ቀደም ሲል በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጦ በህክምና ላይ ከሚገኙት ስድስት ሰዎች መካከል አራቱ ከበሽታው ማገገማቸውን ሁለቱ ድግሞ እያገገሙ እንደሆነ አመልክቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 250,000 የደረሰ ሲሆን የሞቱት ደግሞ 9,900 መሆናቸው ተነግሯል። ኢትዮጵያ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመከላከል ትምህርት ቤቶችን ለሁለት ሳምንታት መዝጋቷና ህዝባዊ ስብሰባዎችን መከልከሏ ይታወሳል።
news-52845067
https://www.bbc.com/amharic/news-52845067
ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት የለም የሚለው ጥሪ ተቀባይነት የለውም፡ የኦሮሚያ ክልል
ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት የለም በማለት ብጥብጥ ለማንሳት መንቀሳቀስ ተቀባይነት የለውም ሲል የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ገለጸ።
አቶ ጌታቸው ባልቻ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት "ወረርሽኝ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሕዝብን ለተቃውሞ መጥራትና ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት የለም በማለት ብጥብጥ ለማንሳት የሚደረግ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል። "የመንግሥት ስልጣንን ከምርጫ ውጪ በአቋራጭ ለመያዝ የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው በድጋሚ ማስታወስ እንፈልጋለን" ብለዋል የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ። የክልሉ መንግሥት ከምን ጊዜውም በላይ የሕዝቡን ሠላምና ጤና ለመጠበቅ እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ጌታቸው፤ "እነዚህ ኃይሎች ስልጣን ለመያዝ ሲሉ ሰው ቢሞት ለእነሱ ምንም ማለት አይደለም። የሞት ጥሪ ለሕዝቡ እያደረጉ ነው" በማለት "ይህ ትልቅ ስህተት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል" ብለዋል። የኮሮናቫይረስ በሽታ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሰዎችን ለተቃውሞ ሰልፍ ወደ አደባባይ መጥራት ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው ሲሉ አሳስበዋል። "የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ መንግሥት እና የጤና ባለሙያዎች የዜጎችን ህይወት ለመታገድ ጥረት በሚያደርጉበት ጊዜ ሰዎችን ለተቃውሞ ስልፍ አደባባይ የሚጠሩ አካላት ስልጣንን በአቋራጭ መያዝ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው" ብለዋል። አቶ ጌታቸው በሰጡት መግለጫ ላይ መሳሪያ በመተኮስ፣ የመንግሥት ባለስልጣናትን በመግደል፣ በማስፈራራት እና የታችኛው የመንግሥት መዋቅርን በመናድ የሚገኝ ሰልጣን የለም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጨምረውም "ለ27 ዓመታት ይህችን አገር ዘረፈው፤ ይህም አልበቃ ብሏቸው በመቀሌ መሽገው ተቀምጠው አገሪቷ ሰላም የሚነሱ" ያሏቸው ወገኖች የክልሉ ሠላም ለማደፍረስ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ሲያብራሩም "ኦሮሚያ የግጭት ሜዳ ለማድረግ፣ 'ኦሮሚያ ካልተረበሸች ኢትዮጵያ መረበሽ አንችልም' የሚል ስልት ቀይሰው፤ በኦሮሚያም ግጭት እንዲፈጠር ድጋፍ የሚያርጉ፣ እና የእነሱ ተላላኪዎች ይህ አካሄድ የሚያዛልቃቸው ባለመሆኑ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግሥት ጥሪ ያቀርብላቸዋል" ብለዋል። ከዚህ በዘለለ በክልሉ ሁከት ለመፍጠር እየሰሩ ናቸው ያሏቸውን፣ የተቃውሞ ሰልፍ እየጠሩ ነው ብለው ያነሷቸውንና ከመስከረም በኋላ መንግሥት የለም ብለዋል ያሏቸውን ወገኖች በስም አልጠቀሱም።
54874861
https://www.bbc.com/amharic/54874861
ኮሮናቫይረስ፡ 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ተሰራ
ኮሮናቫይረስን በመከላከል 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ይፋ ሆነ።።
ይህ በሁለት ኩባንያዎች ይፋ የተደረገው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ክትባት 90 በመቶ ሰዎችን በኮቪድ-19 ከመያዝ ታድጓል ተብሏል፡፡ ክትባቱ ይፋ ያደረጉት ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ ኩባንያዎች ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ እድል ነው ብለዋል። ኩባንያዎች በስድስት የተለያዩ ሃገራት 43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን የገለፁ ሲሆን አንድም ጊዜ አሳሳቢ የጤና ችግር አልታየም ብለዋል። ፋይዘርና ባዮኤንቴክ ክትባቱን በፈረንጆቹ የህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በቁጥር የበዙ ክትባቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን ይህ ክትባት ተስፋ ከተጣለባቸው ውስጥ ቀዳሚው ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም የተደረገው ሙከራ ክትባቱ ሰውነታችን ከበሽታው ጋር እንዲለማመድና አንቲቦዲዎችን እንዲያዳብር መርዳቱ የተስተዋለ ሲሆን ሌላው ደግሞ ቲ-ሴል በመባል የሚታወቀው የመከላከል አቅምን የኮሮናቫይረስን መዋጋት እንዲችል አድርጎታል ተብሏል። ለሙከራው በሁለት ዙር በሶስት ሳምንት ልዩነት ክትባቱ መሰጠቱ ታውቋል። ሙከራው በአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ቱርክ የተካሄደ ሲሆን የሁለተኛ ዙር ክትባት ከተሰጠ ወዲህ 90 በመቶ መከላከል መቻሉን መስተዋሉ ተገልጿል። ፋይዘርበና ባዮኤንቴክ የተሰኙት ኩባንያዎች 50 ሚሊዮን መጠን ያለው ክትባት በፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ እንደሚያቀርቡ የገለጹ ሲሆን በ2021 ደግሞ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን እንደሚያመርቱ ነው ይፋ ያደረጉት፡፡ መድሃኒቱ ግን ከአሁኑ ተግዳሮት እንደገጠመው እየተነገረ ነው። ክትባቱ መቀመጥ ያለበት ከዜሮ በታች 80 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሚቀዘቅዝ ስፍራ ነው ተብሏል። ሌላው የመድሃኒት አምራቾቹ መድሃኒቱ በእድሜ ተከፋፍሎ ያለውን ውጤት ያላቀረቡ ሲሆን የሚየዓዳብረው የመከላከል አቅምም ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አልታወቀም። ዩናይትድ ኪንግደም ይህንን ክትባት 30 ሚሊየን ያህሉን ለመግዛት ትዕዛዟን ቀድማ አስገብታለች። ክትባት እንዴት ሊሰራ ይችላል?
42985385
https://www.bbc.com/amharic/42985385
የግዕዝን ቋንቋ ለዘፈን?
ግእዝ በዓለማችን ረጅም ዕድሜ ካስቆጠሩት ቋንቋዎች አንዱ ነው።
በሃገራችን ለሚነገሩ ሌሎች ቋንቋዎችም መሰረት እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን የቋንቋው ተናጋሪዎች ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ በቤተ ክርስትያን ብቻ የተገደበ ሆኗል። ይህንን ጥንታዊ ቋንቋ ለትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም በጥንት ዘመን የተፃፉ መፃሕፍትንም ለመረዳት ይደረጉ የነበሩ ጥረቶች በአሁኑ ወቅት እየቀነሰ መጥቷል። እንደ ፀሐዬ ክንፈ ያሉት ግን የግእዝ ቋንቋን በተለየ መንገድ በማቅረብ በዘፈንም ይዞ የቀረበ ድምፃዊ ነው። የግዕዝንም ቋንቋ ለዘፈንነት መጠቀም ሲጅምር ካደነቀውና ካበረታታው ይልቅ የሰደበውና ያጥላላው ሰው ይበዛ እንደነበር ይገልፃል። በርግጥ ቁጥራችው ብዙ ባይባልም የተለያዩ ዘፈኖች ሲሰሩ በመግቢያ፣ በመሃል አለያም በመዝጊያ ላይ አንዳነድ የግዕዝ ቃላትን መጨመር አሁን አሁን እየተለመደ ነው። ሙሉ ነጠላ ዜማ ከዛም አልፎ በአልበም ውስጥ በርከት ያሉ ዘፈኖችን ሰርቶ ለአድማጮች ማድረስ ግን ያልተለመደ ነው። በቤተ ክርስተያን ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት እየተከታተለ ያደገው ድምፃዊ ፀሐዬ ግእዝ ቋንቋን ያጠናው በህፃንነቱ ነው። ከዚያም ሙዚቃውን እንዴት በግዕዝ ቋንቋ ማድረግ እንደሚችልም ማሰብና ማሰላሰልም ጀመረ። የመጀመርያውን ነጠላ ዜማ በግዕዝ ቋንቋም ሲስራም ምላሹ ጥሩ እንዳልነበር የሚናገረው ፀሐዬ ስድብና ርግማንም አጋጥሞኛል ይላል። "የዚህም ምክንያት የቤተ ክርስቲያኒቱን ቋንቋ እንዴት ታረክሳለህ" የሚል እንደነበረ ያስረዳል። ቤተ-ክርሥቲያን ለግዕዝ ያላትን አስተዋፅኦ የሚያደንቀው ፀሐዬ ምንም እንኳን ድጋፍ የሚሰጠው ሰው ባይኖርም ተስፋ ሳይቆርጥ እንደገፋበትም ይናገራል። " በርታ የሚሉኝ ጥቂቶች ነበሩ ቢሆኑም በዚህ ተስፋ አልቆረጥኩም አልበም ወደ ማዘጋጀቱ ቀጠልኩበት። ያን በመጥፋት ላይ ያለውን ቋንቋ በሙዚቃ ለማስቀጠልም ከተቻለ ወደ ነበረበት ለመመለስ ነው ዓላማዬ" ይላል ፀሐዬ። ዜና ዜማ የሚል ስያሜ የሰጠውም ይህ አዲስ አልበምም 10 ዘፈኖችን ያካተተ ሲሆን አራቱ በግእዝ የተሰሩ ናቸው። ግጥሞቹን የሚያዘጋጀው ራሱ ብቻ ሳይሆን ቋንቋውን አሳምረው የሚያውቁ ሰዎችንም በማናገር ነው። ግጥሞቹ በሀገር፣ በማህበራዊ ህይወትና በፍቅር ላይ ያተኮሩ ሲሆን ከመጀመርያ ስራው በተሻለ ተቀባይነት እንዳገኙም ይናገራል። "አብዛኛው ሰው ግእዝ የማይሰማና የማይናገር በመሆኑ ዘፈኖቹ ላይ የተወሰነ የትግርኛ ትርጉም ስለምሰራለት ምን እያልኩ እንደሆነ ይገባዋል።" በማለት ይገልፃል። ግዕዝ ቋንቋን ለዘፈንነት በመጠቀሙ አዋረድከው በማለት የሰደቡትና የረገሙት ሰዎችም ከዚህ አልበም በኋላም ብርታትን እየለገሱት እንደሆነም ያስረዳል። ፀሐዬ እስካሁን የሰራው ስራ እንደጅማሮ እንጂ እንደ ሙሉ ስራ እንደማይቆጥረውም ይናገራል። ገና ወደ ስቱዲዮ ያልገቡ ስራዎች እንዳሉት የሚናገሩት ፀሐዬ የግዕዝን ታሪክን ለመጠበቅ ጥረት እንደሚያደርግም ይናገራል። በተለይም ጥንታዊውን ቋንቋ ወደ ወጣቱ ትውልድ ለማስረፅ በባህላዊ መንገድ ከሚሰራው ዘፈን በተጨማሪ በዘመናዊ ሙዚቃ የግእዝ ዘፈኖችን የማዘጋጀት እቅድ አለው።
43222375
https://www.bbc.com/amharic/43222375
ሰሜን ኮሪያ ለሶሪያ የኬሚካል ጦር መሳረያ ማምረቻ ቁሶችን ታቀርባለች ተባለ
ሰሜን ኮሪያ የኬሚካል ጦር መሳሪያዎችን ለማምረት የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን ለሶሪያ ትልክ እንደነበረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎች ያገኙትን መረጃ በመጥቀስ በአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ተዘገበ።
ቁሳቁሶቹ አሲድን መቋቋም የሚችሉ የወለል ንጣፎች፣ ቱቦዎችና ተያያዥ እቃዎች እንደሆኑ ሪፖርቱ አመልክቷል። ገና ይፋ ያልሆነው በእዚህ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ላይ እንደሰፈረው፤ የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ባለሙያዎች በሶሪያ የጦር መሳሪያ ማምረቻ ተቋማት ውስጥ መታየታቸውን ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል። ምንም እንኳን መንግሥት ቢያስተባብልም የሶሪያ ኃይሎች ክሎሪን የተባለውን መርዘኛ ጋዝ እየተጠቀሙ መሆናቸውን የሚያመለክቱ አዳዲስ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው ይህ መረጃ የወጣው። በአሁኑ ጊዜ ሰሜን ኮሪያ በምታካሂደው የኑክሌር ፕሮግራም ምክንያት ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ተጥሎባት ይገኛል። ከሰሜን ኮሪያ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሶሪያ ተላኩ ከተባሉት ቁሳቁሶች መካከል ከፍተኛ ሙቀትና አሲድን የሚቋቋሙ የወለል ንጣፎችና ሌሎች ተያያዥ ቁሶች ናቸው። የወለል ንጣፎቹ የኬሚካል ጦር መሳሪያዎችን ለመስራት የሚያስችሉ ተቋማትን ለመገንባት እንደሚውሉ ተነግሯል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ አምስት ጊዜ በአንድ የቻይና የንግድ ተቋም በኩል ቁሳቁሶች ወደ ሶሪያ መላካቸውን ዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ አመልክቷል። እነዚህም በበርካታ ዓመታት ውስጥ ከተጓጓዙት ቁሶች መካከል የተወሰኑት እንደሆኑም ተገልጿል። ሰሜን ኮሪያ ላቀረበቻቸው ቁሳቁሶች በተለያዩ ኩባንያዎች በኩል የሶሪያ መንግሥት ተቋም በሆነው የሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ማዕከል አማካይነት ክፍያ እንደሚፈፀምላት ጋዜጣው ዘግቧል።
news-52689211
https://www.bbc.com/amharic/news-52689211
ዶናልድ ትራምፕ ‘ክትባት ተገኘም አልተገኘም እንቅስቃሴ እንጀምራለን’ እያሉ ነው
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ለኮቪድ-19 ክትባት ተገኘም፣ አልተገኘም አገሪቱ ወደ እንቅስቃሴ ትመለሳለች ብለዋል።
ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ኒውክሌር መሣሪያ ለማግኘት ከተደረገው ሙከራ ጋር አነጻጽረውታል። ፕሬዘዳንቱ፤ ለበሽታው ክትባት ባይገኝም እንኳን ዜጎች ወደመደበኛ ሕይወታቸው ይመለሳሉ ብለዋል። የአሜሪካ የክትባት ምርምር ‘ኦፕሬሽን ራፕ ስፒድ’ የተባለው ፕሮጀክት 14 ተስፋ የተጣለባቸው የኮቪድ-19 የክትባት ምርምሮች ላይ እንደሚያተኩር ትራምፕ ትላንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። “አገራችን እንዲህ አይነት የሳይንስ፣ የኢንዱስትሪም ምርምር አድርጋ አታውቅም” ሲሉ ፕሮጀክቱን አወድሰዋል። የቀድሞ የወታደርና የጤና ኃላፊ ከመንግሥትና ከግል ዘርፍ ጋር በመጣመር ፕሮጀክሩን ይመራሉ ተብሏል። የክትባት ምርምር ዘርፉን የሚመሩት ሞንሴፍ ስላውኒ “በዚህ ዓመት መጨረሻ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክትባቶች እንደምናመርት እተማመናለሁ” ብለዋል። ከዚህ ቀደም ከኒው ዮርክ ታይምስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ክትባት ይገኛል ተብሎ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ አጭር ነው ብለው ነበር። በርካታ ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ አሜሪካ ምጣኔ ኃብቷን ዳግመኛ ማንቀሳቀስ የምትችለው ክትባት ሲገኝ ነው። ትራምፕ ግን “ሁሉም ነገር ክትባትን የተመረኮዘ ነው ብላችሁ እንድታስቡ አልፈልግም” ብለዋል። “ክትባት ቢገኝም፣ ባይገኝም ሂደቱን እየጀመርን ነው” ሲሉም ተደምጠዋል። “ብዙ በሽታዎች ክትባት ሳይገኝላቸው፣ ቫይረሱን ወይም ጉንፋኑን ሰዎች ይታገላሉ። አንዳንዶቹ በሽታዎች ደግሞ ክትባት እስከነጭራሹ ሳይገኝላቸው ይጠፋሉ” ብለዋል ፕሬዘዳንቱ። ትራምፕ ትምህርት ቤቶች መከፈት አለባቸው ቢሉም፤ ኮሮናቫይረስ የመከላከል ግብረ ኃይልን የሚመሩት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ለዚህ ውሳኔ ገና እንደሆኑ ለምክር ቤቱ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ዶናልድ ትራምፕ ትላንት መግለጫውን ሲሰጡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) አላደረጉም ነበር። አንዲት ጋዜጠኛ ጥያቄ ስታቀርብላቸው፤ ድምጿ በአግባቡ እንዲሰማ ያደረገችውን ጭምብል እንድታወልቅ አዘዋል። በ2020 ለሽታው መፍትሔ ይገኛል? ኢቦላ እአአ ከ2014 እስከ 2016 በተቀሰቀሰበት ወቅት የአሜሪካ የመድኃኒት ቁጥጥር ክፍል የመጀመሪያው ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል የፈቀደው በ2019 ነበር። ከዋይት ኃውስ የሚወጣው የጊዜ ገደብ ላይ ብዙ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ያነሳሉ። በባይለር ኮሌጅ የኮሮናቫይረስ ምርምር ላይ የሚሠሩት ዶ/ር ፒተር ሆቴዝ “ቢያንስ እስከ 2021 ድረስ ክትባቶች ፍቃድ ይሰጣቸዋል ብዬ አላስብም” ብለዋል። ዶ/ር ሪክ ራይት የተባሉ የቀድሞ የአሜሪካ ክትባት ዘርፍ ዳይሬክተር፤ የኮሮናቫይረስ ሕክምና ላይ ከዋይት ኃውስ ፖለቲካዊ ጫና እየተደረገ ነው ሲሉ ቃላቸውን ለምክር ቤት ሰጥተዋል።
news-55421175
https://www.bbc.com/amharic/news-55421175
መቀመጫቸው የተቀደዱ የፒጃማ ማስታወቂያዎች ጉዳይ እያነጋገረ ነው
በተለያዩ የኢንተርኔት ገጾች ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያልተጠበቁ ማስታወቂያዎች ብቅ እያሉ ነው።
ከእነዚህ የሚበዙት የፒጃማ ሱሪዎች ሲሆኑ ልዩ የሚያደርጋቸው ደግሞ መቀመጫቸው አካባቢ መጣፊያ እንኳ ሳያበጁ ሽንቁር የተው መሆናቸው ነው። ይህ ለብዙዎች አሳፋሪ፣ ለሌሎች የሳቅ ምንጭ ለአንዳንዶች ደግሞ ብልህ የማስታወቂያ ስልት ሆኖ እያነጋገረ ነው። ፒጃማ አምራቾች በስፋት እያስተዋወቋቸው ያሉት እነዚህ የምሽት አልባሳት ለምን ይህንን የማስተዋወቅ ዘዴ ለመጠቀም ቻሉ የሚለው በስፋት አነጋግሯል። በማኅበራዊ የትስስር ገጾች ነገሩ ትልቅ ክርክር አስነስቷል። ከባሕል፣ ከማስታወቂያ ሕግና ደንብ፣ ከንግድ እንዲሁም ከሸማቾች መብት አንጻር ጉዳዩ በስፋት እያነጋገረ ነው። እነዚህ ማስታወቂያዎች ኢንተርኔት ላይ እንደ አሸን የፈሉት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ነው። አንዳንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ለምን እነዚህ ማስታወቂያዎች እነሱን ዒላማ ሊያደርጉ እንደቻሉ አብዝተው ይጠይቃሉ። ጉግል ማስታወቂያዎችን በኢንተርኔት ሲበትን ከአሳሹ ባህሪና የፍላጎት አዝማሚያ ጋር የሚቀራረቡትን መርጦ እንደሆነ ተለምዷዊ የአልጎሪዝም አሰራሩ ያሳያል። አንድ የማስታወቂያ ባለሙያ ምናልባት እነዚህ መቀመጫ ላይ መጣፊያ እንኳ የሌላቸው የፒጃማ ማስታወቂያዎች ከኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መረጃ ለመሰብሰብ የታለሙ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገምተዋል። እነዚህ መቀመጫቸው የተቦደሱ ፒጃማዎች በስፋት ሲተዋወቁ ነበር የተባለው አይቪሮዝ (IVRose) ለተሰኘው የንግድ ምርት መለያ (ብራንድ) ነው። የአይቪሮዝ የፌስቡክ ገጽና ማስታወቂያ ክንፉ የሚተዳደረው ደግሞ ሻንጋይ ሊሻንግ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ በተባለ የቻይና ድርጅት ነው። ይህንን ፒጃማ እያስተዋወቁ ያሉ በርከት ያሉ የልብስ አምራች ድርጅቶች የማስታወቂያ ውክልናቸውን ለዚህ ድርጅት እንደሰጡ ይገመታል። አልክማንድ ኢስቴት ሊሚትድ የሚያስተዳድራቸው በርካታ የልብስ አምራቾች ድረ ገጾች ይህንኑ ተመሳሳይ የፒጃማ ማስታወቂያን እያሰራጩት ይገኛሉ። አሁን ጥያቄ የሆነው በዚህ መንገድ ማስታወቂያውን በገፍ ወደ ኢንተርኔት ዓለም መልቀቁ ለምን አስፈለገ? ዓላማውስ ምንድነው? የማስታወቂያ ደንብና ሥነ ምግባሩስ ይፈቅዳል ወይ? የሚለው ነው። ዲጂታል ዊስኪ የተሰኘው ኩባንያ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ማት ሞሪሰን በዚህ ጉዳይ ላይ ለቢቢሲ የግል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እሳቸው እንደሚሉት ወትሮም የቻይና ማስታወቂያ ድርጅቶች በአንድ ጊዜ አነጋጋሪ ሊሆኑ የሚችሉ፣ እንደ ወረርሽኝ የሚዛመቱ፣ አንዳንዴም ሰዎችን ሊያናደዱ የሚችሉ ከተለምዶ ወጣ ያሉ ማስታወቂያዎችን በመሥራት የታወቁ ናቸው። በአንድ ጊዜ ኢንተርኔቱን ማጥለቅለቃቸው ደግሞ አስተዋዋቂዎቹ ምርቶቹ ለየትኛው አገር፣ በየትኛው እድሜና ፍላጎት ላይ ላለ የሚለውን ቅጽ ሲሞሉ ሁሉንም አካታች አድርገው በዘፈቀደ ስለሚሞሉት ነው ይህ የፒጃማ ማስታወቂያ ዓለምን ያጥለቀለቀው ብለዋል። የተወሰነ ጾታና የዕድሜ ክልልን ዒላማ ማድረግ በማስታወቂያ ተፈላጊውን ውጤት በአጭር ጊዜ እንደሚያመጣ ይታመናል፤ ከማስታወቂያ በጀት አንጻርም የሚመከረው ይኽው አሰራር ነው። ሆኖም በቻይና ማስታወቂያ ድርጅቶች ከዚህ የተለየ ዘዴን መጠቀም አዲስ አይደለም፤ ውጤትም አግኝተውበታል የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። ሚስተር ሞሪሰን እንደሚሉት የአንዳንድ ማስታወቂያዎች ግብ ምርቱን ማሻሻጥ ብቻ ነው ብሎ መደምደም ስህተት ነው ይላሉ። አንዳንድ ጊዜ የሸማችን መረጃ ለመሰብሰብ፣ ምን ያህል ሰው በምን ዓይነት ጉዳይ ይማረካል የሚለውን ለማየት፣ ወይም ገሸሽ የተደረገን ምርት አነጋጋሪ አድርጎ ዳግም ከሞት ለማስነሳት ማስታወቂያዎች በገፍ ኢንተርኔት ላይ ሊፈሱ ይችላሉ ብለዋል። የመቀመጫን ሸንቁር የሚያሳዩ ማስታወቂያዎች እንዴት የኢንተርኔት ደንብን ሊተላለፉ እንደቻሉ ሲያስረዱም ነገሩ በቀጭን ክር እንደመራመድ ነው ይላሉ። የኢንተርኔት ማስታወቂያ አታሚዎችን ደንቦች ባለመተላለፍና ግን ደግሞ የሸማቾችን ሙሉ ትኩረት በማግኘት መሀል የተዘየደ ብልህ የማስታወቂያ ስልት ነው ይላሉ ሞሪሰን። እርቃን ወጥተዋል እንዳይባሉ አይደሉም፣ ግን ደግሞ ለዓይን የሚስቡና አይረሴ ናቸው፣ ደግሞ አነጋጋሪ ሆነዋል፤ የሚፈለገውም ይኽው ነበር። ምን ጊዜም ማስታወቂያ ሸማቾቹን በትንሹ ማስቆጣት አለበት፤ አለበለዚያ ትኩረት ይነፈገዋል። አንድ ሰው በኢንተርኔት ማስታወቂያ ላይ ጥቁምታ (ክሊክ) ሲያደርግ ቀጥሎ በሚያደርገው የኢንተርኔት አሰሳ ተመሳሳይ ምርቶች ወደእሱ እንዲደርሱ በሩን ከፈተ ማለት ነው። እነዚህ የመቀመጫ ሽንቁርን ሆን ብለው የተዉት የፒጃማ ማስታወቂያዎችም ዓላማቸው ሸማቾችን በቀጣይነት የፍላጎት መረጃቸውን ሰብስቦ ዒላማ ማድረግ ነው። ቢቢሲ የምርቶቹን ባለቤቶች አይቪሮዝን እና ቺክ ሚ ኩባንያዎችን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
50010588
https://www.bbc.com/amharic/50010588
ቱርክ ከሶሪያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ በፈፀመችው ጥቃት በርካቶች ተገደሉ
ቱርክ በሶሪያዊ ሰሜናዊ ክፍል በኩርዶች ቁጥጥር ስር ያሉ ስፍራዎች ላይ በፈፀመችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተሰማ።
ቢያንስ 11 ንፁኀን ዜጎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን እንዲሁም በኩርዶች የሚመራው እና ከቱርክ መገንጠል የሚደግፈው ቡድን ወታደሮችም መሞታቸው ታውቋል። የቱርክ ወታደራዊ ኃይል አንድ ወታደር እንደተገደለበትና ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉበት አስታውቋል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥቃቱ እንዲቆም እየጠየቀ ይገኛል። • ሪፐብሊካን ቱርክ ላይ ማዕቀብ ይጣልልን እያሉ ነው • ጠ/ሚ ዐብይ ለኖቤል በመታጨት ሁለተኛው የኢትዮጵያ መሪ መሆናቸውን ያውቃሉ? ሐሙስ እለት የቱርክ ወታደሮች በድንበር አቅራቢያ የሚገኙትን ራስ አል አይንና ታል አብያድ ከተሞች መክበባቸው ተነግሯል። በኩርድ የሚንቀሳቀሰው ቀይ ጨረቃ፣ 11 ንፁኀን ዜጎች መሞታቸውን አረጋግጦ 28 ክፉኛ ተጎድተዋል ብሏል። ከሟቾቹ መካከል ሕፃናት እንደሚገኙበትም ለማወቅ ተችሏል። 29 የሶሪያ ዲሞክራቲክ ግንባር የተሰኘውና በኩርድ ወታደሮች የተመሰረተው ግንባር አባላት እንዲሁም 17 የሌላ አማፂያን ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል። እስካሁን ድረስ 10 መንደሮች በቱርክ ወታደሮች እጅ ገብተዋል። የአሜሪካውያን ተቃውሞ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የሚገኙ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ቱርክ በሶሪያ ለከፈተችው ጥቃት ማዕቀብ እንዲጣል የሚመክር ሰነድ ለማዘጋጀት እያሰቡ መሆኑን ተናግረዋል። የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ሊዝ ቼኒ እንደሚሉት ከሆነ ቱርክ " የኩርድ አጋሮቻችን ላይ ያለ ርህራሄ ጥቃት በመክፈቷ ጠንካራ ርምጃ መውሰድ አለብን" ብለዋል። ዲሞክራቶች በበላይነት በሚቆጣጠሩት ምክር ቤት የሚገኙ 29 ሪፐብሊካን ቱርክ ላይ ማዕቀብ የሚጥል ሕግ አስተዋውቀዋል። ይህ የምክር ቤቱ አባላት ንግግር የተሰማው ዶናልድ ትራምፕ በግጭቱ ዙሪያ ለማሸማገል ሀሳብ እንዳላቸው ከገለፁ በኋላ ነው። • በበዴሳ ከተማ ታዳጊውን ለመታደግ የሞከሩ 4 ሰዎች የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሞቱ ቱርክ ወደ ሰሜናዊ ሶሪያ ረቡዕ እለት በመግባት ጥቃት የከፈተችው አሜሪካ ጦሯን ከአካባቢው ማስወጣቷን ተከትሎ ነው። "ቱርክ ከአሜሪካ ወዳጆች እንደ አንዷ መስተናገድ ከፈለገች፣ ጠባይዋ እንደ አንዳቸው መሆን አለበት" ያሉት ቼኒ " በኩርድ አጋሮቻችን ላይ ጦርነት በመክፈቷ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል" ሰሲሉ ተደምጠዋል። ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ አካላት አሜሪካ ጦሯን ከአካባቢው ማስወጣቷ ለቱርክ ጥቃት ይኹንታን የሰጠ ነው በማለት የተቹ ሲሆን፣ ጣይብ ኤርዶጋን ግን 480 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው የሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ " ደህንነቱ የተጠበቀ ቀጠና ለመፍጠር" መሆኑን ተናግረዋል። ይህንን ድንበር አካባቢ ይቆጣጠሩ የነበሩት የኩርድ ወታደሮች ሲሆኑ ቱርክ "ሽብርተኞች" ፀረ ቱርክ አቋምን የሚደግፉ ስትል ትወነጅላቸዋለች። ይህ የሶሪያ ዲሞክራቲክ ግንባር የተሰኘውና በኩርድ ወታደሮች የተመሰረተው ግንባር የአሜሪካ ብርቱ አጋር የነበረ ሲሆን አሜሪካ በአካባቢው አይ ኤስን እንድታስወግድ ከረዷት አጋሮች መካከል አንዱ ነው። • ኦሳማ ቢን ላደንን ለማግኘት ሲ አይ ኤን የረዱት ዶክተር የአሁኑ የአሜሪካ መንግሥት ውሳኔ ግን ወዳጅነታቸውን ያላገናዘበ " ከጀርባ የተሰራ ደባ" እንደሆነ እንዲሰማቸው እንዳደረገ እየተነገረ ነው። ይህ የቱርክ ጥቃት ዳግመኛ አይ ኤስ በስፍራው እንዲያንሰራራ እና ኩርዶችን ለይቶ በማጥቃት ወደ ዘር ጭፍጨፋ እንዲይሄድ በሩን እንዳይከፍት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው የአሜሪካ ወታደሮችን ለማስወጣት መወሰናቸው ትክክል መሆኑን እየገለፁ ነው። በአንድ ንግግራቸውም ኩርዶችን " በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት አልረዱንም" ሲሉ ተደምጠዋል።
news-53891759
https://www.bbc.com/amharic/news-53891759
ጃዋር መሐመድ፡ ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ ጃዋርን የባንክ ሒሳብ አለማገዱን ተናገረ
የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በትናንት ቀጠሮው በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ቅድመ ምርመራ መዝገብ የዐቃቤ ሕግን የቃል ምስክር ሰምቷል።
ከዚህ ውጪ ደግሞ ባለፈው ቀጠሮ በተጠርጣሪዎች እንዲሁም ደግሞ በዐቃቤ ሕግ ለተነሱ አቤቱታዎች ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከዚያ ውስጥ አንዱ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ በፊት ሚዲያዎች ከእኛ ፈቃድ ውጪ ፎቶ እያነሱን ነው እንዲሁም ቪዲዮ እየቀረፁን ነው ይህ እንዲቆም ትዕዛዝ ይሰጥልን ሲሉ ጥያቄ አቅርበው ነበር። ፍርድ ቤቱም በዚህ ጉዳይ ላይ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህ ጉዳይ የተጠርጣሪዎችን ነጻ ሆኖ፣ የመታየት መብት የሚጋፋ ነው። ስለዚህም ሚዲያዎች የችሎቱን የዕለት ውሎ ከመዘገብ ውጪ ያለተጠርጣሪዎች ፈቃድ ፎቶ ማንሳትም ሆነ ቪዲዮ መቅረጽ እንደማይችሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል ችሎት ውስጥ በብዛት እየታዩ እና እየታደሙ ያሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት ናቸው፤ ስለዚህ ቤተሰቦቻችን ገብተው እንዲታደሙ ፈቃድ ይሰጠን ሲሉ ባለፈው ቀጠሮ ላይ አቤቱታ አቅርበው ነበር። ፍርድ ቤቱም ፖሊሶቹ በብዛት የሚገኙት ለደኅንነትና ለጥበቃ እንደሆነ በመግለጽ ከአራት ያልበለጡ የተጠርጣሪዎች ቤተሰቦች ችሎቱን እንዲታደሙ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል የኦኤምኤን ጋዜጠኛ የሆነው ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለፍርድ ቤቱ ቤተሰቦቹን በስልክ ማግኘት እንዲችል ያቀረበው አቤቱታ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። መለሰ ድሪብሳ፤ ሌሎች ተጠርጣሪዎች በስልክ ቤተሰቦቻቸውን እንዲያገኙ እየተፈቀደላቸው ነው። ይሁንና እኛ ግን ከሌሎች በተለየ መልኩ ቤተሰቦቻችንን በስልክ እንዳናገኝ ተደርገናል ሲል አቤቱታውን አቅርቦ ነበር። ፍርድ ቤቱም በትናንት ውሎው ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳ ቤተሰቦቹን በስልክ ማግኘት እንዲችል ትዕዛዝ ሰጥቷል። ሌላው በትናንትናው ችሎት የተነሳው ጠበቆች ያነሱት የስልክ ጉዳይ ነበር። የተጠርጣሪ ጠበቆች ባለፈው ችሎት ላይ ዐቃቤ ሕጎች ስልክ ይዘው እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል። እኛ ግን እየተከለከልን ነው። ስለዚህ ሁለታችንም እንከልከል አልያም ሁለታችንም ይፈቀድልን ሲሉ አቤቱታቸውን አሰምተው ነበር። ችሎቱም ሁለቱም አካላት ወደ ችሎቱ ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል። አቶ ጃዋር መሐመድ በትናንትናው ዕለት ያቀረቡት አቤቱታ ሲራጅ የሚባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች ንብረታቸው እንዲታገድ መደረጉን በተመለከተ ነው። በተለይም የምዕራብ ሐረርጌ የተለያዩ ወረዳዎች ስም በመጥቀስ እንዲሁም ደግሞ አርሲ ውስጥ ባለሐብቶች በጃዋር ገንዘብ ነው የምትነግዱት በመባል ንብረታቸው እየታገደ እና እየተቀሙ እንደሆነ ይህም እንዲቆም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። አቶ ጃዋር አክለውም የቤተሰባቸውም ሆነ የእርሳቸው የባንክ ሒሳብ ታግዶ እንደሚገኝ በመግለጽ ፖሊስ ምርመራውን ስለጨረሰ ይህ እግድ ወይንም ትዕዛዝ ይነሳልን ሲሉ ችሎቱን ጠይቀዋል። ችሎቱም ፍርድ ቤቱ የአቶ ጃዋርንም ሆነ የቤተሰባቸውን የባንክ ሂሳብ እንዳላገደ ገልጾ፤ ያገደውን አካል መጠየቅ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸው በሚዲያዎች ከፍተኛ የሆነ ዘመቻ እየተካሄደብን ነው። "ይህም መንግሥት ምርጫ ላይ እንዳንሳተፍ ወይንም ደግሞ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምርጫ ላይ እንዳይሳተፉ እየተጠቀመበት ያለ ዘዴ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። "ይህ በሚዲያዎች የሚደረግብን ዘመቻ በእኛም ሆነ በቤተሰቦቻችን ህይወት ላይ አደጋን ጥሏል። ስለዚህ መንግሥት ይህንን ጉዳይ ያስቁምልን" ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። እንዲሁም ደግሞ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው። ቤተሰቦቻችን ግን ጥበቃ እያገኙ አይደለም፤ የቤተሰባችንም ሕይወት አደጋ ላይ ስለወደቀ ጥበቃ ይደረግልን ሲሉ ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የዐቃቤ ሕግ ቀሪ ምስክሮች ለመስማት ለረቡዕ ነሐሴ 20/2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
news-52740286
https://www.bbc.com/amharic/news-52740286
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተደናቀፈው ጣናን ከእምቦጭ የማጽዳት ሥራ
የኮሮናቫይረስ ከተከሰተና የሰዎች እንቅስቃሴ በእጅጉ ከተገታ በኋላ የጣና ሐይቅን ህልውና ስጋት ላይ የጣለውን የእምቦጭ አረምን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት እንዲቀዛቀዝ ማድረጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በጎ ፈቃደኖች ከዚህ ቀደም በጣና ሐይቅ ያለውን አረም በማስወገድ ዘመቻ ላይ በወረርሽኙ ምክንያት በሐይቁ ላይ እየተንሰራፋ ያለውን አደገኛ አረም በተቻለ መጠን ለማስወገድ ከዚህ ቀደም ይወጣ የነበረው ሰው አሁን የለም ያሉን የአካባቢው አርሶ አደር አቶ ጎባው ደመቀ "የሕዝብ ተሳትፎ ቆሟል" ሲሉ ያለውን ሁኔታ ገልጸውልናል። አሁን አረሙን በማስወገድ በኩል በክፍያ ከሚሰሩ ሰዎች በስተቀር በበጎ ፈቃደኝነት የሚያግዙ ሰዎች እየተሳተፉ አይደለም በተጨማሪም ዝናብ በመጀመሩ ምክንያት ሕብረተሰቡ ወደ ግል የእርሻ ሥራው እየተመለሰ ነው መሆኑን አመልክተዋል። በዚህ ምክንያትም በሐይቁ ላይ እየተንሰራፋ ያለው የእምቦጭ አረም እየጨመረና ይዞታውን እያሰፋ መሆኑን ይገልጻሉ። ባለፉት 15 ዓመታት በጣና ሃይቅ ላይ በዓሳ ማስገር እና ንግድ ላይ የተሰማራው ብርሃኑ ውብነህ እንዳለው ደግሞ በአምስት ወረዳዎች በሚገኙ 27 ቀበሌዎች "የሐይቁን ሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ ተከትሎ ከጎርጎራ እስከ ጣና ጊዮርጊስ ያለው ዳርቻ ላይ እምቦጩ ሰፊ ሽፋን አለው።" በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የገጠር መሬትና አጠቃቀም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድኖ አስማረ በበኩላቸው በወረዳው በሚገኙ አምስት ቀበሌዎች ከነበረው አንጻር አረሙ መጨመሩን ነግረውናል። አረሙን ለማስወገድ በቀበሌዎቹ በሚገኙ ነዋሪዎች ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ሲሠሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው እስከ የካቲት ድረስ በኅብረተሰቡ ጉልበት ሲሠራ ቢቆይም ካለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንጻር ይህንን መቀጠል አልተቻለም ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አረሙን በሰው ጉልበት ለማስወገድ እየተደረገ በነበረው ጥረት ላይ ትልቅ እንቅፋት መሆኑን ጠቅሰው "የዚህን ዓመት ዕቅድ ማሳካት አልቻልንም። በሐይቁ ላይ ያለው የአረሙ ሽፋንም ጨምሯል" ብለዋል። የጣና ሐይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አያሌው ወንዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው አረሙ ካለባቸው ሰባት ወረዳዎች በአምስቱ ቢታረምም ሥራው አለመቀጠሉን ለቢቢሲ ገልጸዋል። "የአረሙ ሁኔታ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ነው የሚባለውን ግን ትክክል አይደልም" ሲሉ አጣጥለውታል። "ከዚህ በፊት ከነበረው ቢያንስ እንጂ አይበዛም" ሲሉም አክለዋል። "ከየካቲት በኋላ ዕቅዳችን ተበላሽቷል" ያሉት አያሌው (ዶ/ር) "እስከ ጥር ድረስ በነጻ ተሠርቷል። ከጥር እስከ ሰኔ ወጣቶችን አደራጅተን በመጠነኛ ክፍያ እንሠራለን ያለነው ንክኪ ስላለው ቋሞል" ብለዋል። እምቦጭ በጣና ሐይቅ ላይ ያደረሰውን ጉዳት "በቃላት መግለጽ ከባድ ነው" የሚለው ብርሃኑ አረሙ የሐይቁን ብዝሐ ህይወት ከመጉዳት ባለፈ በዓሣ ምርት፣ በመጠጥ ውሃ እና እርሻ ላይም ተዕጽኖ መፍጠሩን ይናገራል። አቶ ጎባው በበኩላቸው መንግሥት፣ ወጣቱ እና የአካባቢው ማኅበረሰብ በጋራ በመቀናጀት "በክፍያም ቢሆን እየተሠራ በየጊዜው እንዲቀንስ ቢደረግ" የሚል ሃሳብ አላቸው። ከሰባቱ ወረዳዎች በአምስቱ ውስጥ አረሙ ታርሞ መቃጠል ደረጃ ላይ ሲደርስ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ በመከሰቱ ምክንያት የማረሙ ሥራ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተጻራሪ የሰዎች በጋራ መሰባሰብ እና ንክኪ ስላለው አማራጭ እየፈለግን ነው ብለዋል አያሌው (ዶ/ር)። ትራክተር እና ጥቂት ሰዎችን በማቀናጀት አረሙን ለመሳብ በማሰብ 10 ትራክተሮች ሥራ የመጀመሩ ሲሆን በተጨማሪም አነስተኛ የኪስ ገንዘብ በመስጠት በቤተሰብ ደረጃ መታረም ያለበት ተለክቶ እየተሰጠ እንዲታረም ለማድረግ እየታሰበ መሆኑንም አስረድተዋል። እንደማሽን፣ ኬሚካል እና ጢንዚዛ ያሉ አረሙን ሊያጠፉ ይችላሉ የተባሉ አማራጮችን መጠቀምን በተመለከተ "ዕቅዳችን አዋጪ የሆነውንና ጉዳት የማያደርሱትን አማራጮች ሁሉንም በማቀናጀት ጥቅም ላይ አውሎ አረሙን ማጥፋት ነው" ያሉትዋና ሥራ አስኪያጁ በዚህ ዓመት አምስት ዘዴዎችን መሞከራቸውን አስታውቀዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት ቢደናቀፍም ዋነኛው ዘዴ የሰው ጉልበት መሆኑን ጠቅሰው ከተሞከሩት ዘዴዎች "የተሻለው በትራክተር አማካይነት የሚጎተተው ነው" ብለዋል ዋና ሥራ አስኪያጁ። "ዘንድሮ ችግሮችን በደንብ በመለየት ለሚቀጥለው ዓመት ጥሩ እንሠራለን" ሲሉም ለቀጣይ ዓመት ያለቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
news-50805308
https://www.bbc.com/amharic/news-50805308
ቆንጆ እንቅልፍ ምንድነው? ለእንቅልፍስ እንዴት መዘጋጀት አለብን?
ሁሌም ድካም ይሰማዎታል? ብቻዎን አይደሉም። በጣም ደክሞዎት ለመተኛት ወደ አልጋዎ ሲሄዱ እንቅልፍዎ የገባበት ጠፍቶብዎት ያውቃል?
ይህ ነገር በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰትና አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማድረግ ሊስተካከል የሚችል ችግር ነው። በጣም ጥሩ የሆነ እንቅልፍ ለማግኘት እነዚህ ከስር የተጠቀሱት አምስት ነጥቦች በጣም ወሳኝ ስለመሆናቸው በርካቶችን አነጋግረን በምርምር ደርሰንበታል ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። 'የማለዳ ወፍ' ነዎት ወይስ 'የሌሊት'? ስለ እንቅልፍ የተሳሳቱ አመለካከቶች 1. በእርግጥም ደክሞዎት እንደሆነ ያረጋግጡ ምናልባት ቀላል ነገር ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ሰውነታችን በእውነትም ለእንቅልፍ ዝግጁ መሆኑን ማወቅ ጠቃሚ ነው። ለሰውነታችን ውስን የእንቅልፍ ሰዓት መስጠትና እራሳችንን ለጠዋት ፀሐይ ማጋለጥ ደግሞ ጠቃሚ ናቸው። እያንዳንዱ ሰው የፀሐይን መውጣትና መግባት ተከትሎ የራሱ የእንቅልፍ ሰዓት አቆጣጠር አለው። ለዚህም ነው ሲመሽ እየተኛን፤ ሲነጋ የምንነቃው። ይሁን እንጂ ይህ ለሁሉም ሰው ላይሰራ ይችላል፤ ምክንያቱም የአንዳንድ ሰዎች ሰዓት ከሌሎቹ ዘግይቶ ይዘውራልና። ስለዚህ በትክክል ሰውነትዎ ለእንቅልፍ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። ሰውነታችን በአካላዊ እንቅስቃሴዎች ሲደክምም እንቅልፍ ቀላል ይሆናል፤ ነገር ግን ከእንቅልፍ አራት ሰአት በፊት ምንም አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግም ጠቃሚ ነው። 2. የሚበሉትና የሚጠጡትን ነገር ይከታተሉ ወደ አልጋ ከመሄድ በፊት አልኮል አንድ ሁለት ማለት ጥሩ እንቅልፍ ያስተኛል የሚባል አስተሳሰብ በብዙዎች ዘንድ ቢኖርም ይህ ፍፁም ትክክል አይደለም ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። በተለይም ለትምህርትና ትውስታ የሚጠቅመውን የእንቅልፍ ሂደት REM (rapid eye movement) ያውካል አልኮል። አልኮል የሚፈጥረው የፊኛ መወጠርም ሌላ ለእንቅልፍ መረበሽ ምክንያት ነው። በጥቅሉ ከእንቅልፍ ጋር በተያያዘ አልኮል ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። • እንቅልፍ እንዲህ ጠቃሚ ነገር ኖሯል? ቡና ወይም ሻይም ቢሆን ከእንቅልፍ ስድስት ሰአት በፊት መጠጣት አይመከርም። ለአንዳንዶች ደግሞ በባዶ ሆድ ወደ አልጋ መሄድ የማይታሰብ ነገር ቢሆንም ጠግቦ እንደ መተኛት ግን የእንቅልፍ ጠላት የለም። ቢቻል ቀለል ያሉ ምግቦችን ከእንቅልፍ አራት ሰአት በፊት መመገብ እንቅልፍን ጥሩ ያደርገዋል። 3. ከእንቅልፍ በፊት የሚወዱትን ነገር ያድርጉ በጣም የሚያስደስትዎትን ነገር ከእንቅልፍ በፊት ሁሌም ማድረግ አካላዊና ስነልቦናዊ እረፍትን ይሰጣል። ሁሌም ከሚደረጉ ነገሮች መካከል ሞቅ ባለ ውሃ ገላን መታጠብ፣ መፃህፍት ማንበብ፣ ሙዚቃ መስማትና በተመስጦ ማሰላሰል ይጠቀሳሉ። ነገር ግን እነዚህ የዕለት ተዕለት ተግባራት ተመሳሳይ ናቸው ማለት አይደለም፤ ለእናንተ የሚስማሟችሁና ለእንቅልፍ የሚረዱ ሌሎች ነገሮች ካሉ እነሱን ሁሌም ቢሆን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል። 4. ንጹህ የእንቅልፍ ቦታ ያዘጋጁ ይሄ ማለት ከእንቅልፍ በፊት ገላን መታጠብና ጥርስን መቦረሽ አይደለም። ነገር ግን እነሱም ጥሩ ልማዶች ናቸው። ንጹህ የእንቅልፍ ቦታ ማለት ምቹ የሆነ አካባቢን ማዘጋጀት ነው። የመኝታ ክፍሎቻችን ዋነኛ አገልግሎታቸው እንቅልፍና ከእንቅልፍ ጋር ለተያያዙ ነገሮች ብቻ መሆን አለበት። ምናልባት ለአንዳንድ ሰዎች ባይሰራ እንጂ የመኝታ ክፍል ጨለማ ሲሆንና ቀዝቀዝ ያለ የአየር ጸባይ ሲኖረው ብዙ ሰዎች ቶሎ እንደሚተኙና ጥሩ እንቅልፍ እንደሚወስዳቸው ይናገራሉ። ከእንቅልፍ በፊት በተለይ ደግሞ አልጋ ውስጥ ሆኖ ሞባይልና ላፕቶፕ መጠቀምም ቢሆን ለእንቅልፍ ጠቃሚ አይደሉም። ረዘም ያለ ሰአት በስክሪን ላይ አፍጥጠን የምንቆይ ከሆነ የምንተኛው እንቅልፍ ጥራት የጎደለው ይሆናል። 5. ለእንቅልፍዎ ቅድሚያ ይስጡ ምናልባት በርካታ የዓለማችን ስኬታማ ሰዎችና መሪዎች በቀን ለአራት ሰአት ብቻ እንደሚተኙ በኩራት ሲናገሩ ሰምተን ይሆናል፤ ነገር ግን እውነታው ሁሉም ሊያደርገው አይችልም ነው። ለጤናችንም ብዙ እክሎችን ያስከትላል። የእንቅልፍ ሰአትዎን በአንድ ሰአት ቢቀንሱ ወዲያውኑ ለውጡን ሊያስተውሉት አይችሉ ይሆናል፤ ነገር ግን ቀስ በቀስ ሰውነትዎ እየተዳከመ ይመጣል። በተጨማሪም ትንሽ የእንቅልፍ ጊዜ ለተለያዩ የልብ በሽታዎች፣ ስትሮክ እና ካንሰር ያጋልጣል። ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ለእንቅልፍ ቅድሚያ መስጠትና ቢያንስ ለሰባት ወይም ስምንት ሰአት መተኛት ያስፈልጋል። በጠዋት መነሳትም ተገቢ ነው።
news-45470153
https://www.bbc.com/amharic/news-45470153
"ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ ከመታሰቡ በፊት ሰላምና መረጋጋት ሊሰፍን እንደሚገባ ትናንት የንቅናቄያቸውን አመራሮችና አባላትን በመምራት አዲስ አበባ የገቡት የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።
በአሁኑ ወቅት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ምርጫና ውድድር ሳይሆን በሰከነ ሁኔታ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት የሚያጠናክር ሰላምና መረጋጋት በሃገሪቱ እንዲኖር ማድረግ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ምርጫ የሚካሄድበትን የጊዜ ሰሌዳ ከማስቀመጥ በፊት ምርጫውን በተገቢው ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችሉና ሕብረተሰቡ የሚተማመንባቸው ተቋማትን በቀዳሚነት በተገቢው ቦታ ላይ መኖራቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል። • ያልተጠበቁ ክስተቶች የታዩበት ዓመት • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? • ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? "ትኩረታችን መሆን ያለበት የተቀመጠን የምርጫ ጊዜን ማሳካት ላይ ሳይሆን፤ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስፈልጉት ተቋማትን እውን በማድረግ ላይ መሆን አለበት" ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ። አሁን ኢትዮጵያ እያስተዳደረ ያለው መንግሥት ሃገሪቱን ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ከፍ ያለ ጥረት እያደረገ መሆኑን የተናገሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ አሁን በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ሀገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ከመሆን ውጭ ሌላ መደራሻ የለውም ሲሉም ብለዋል። አርበኞች ግንቦት 7 ወደ ሰላማዊና ህጋዊ ፓርቲነት የመጣው በሀገሪቱ የተጀመረውን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከርና የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት መሆኑን የድርጅቱ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል። በበርካታ ወጣቶች ባካሄዱት ትግልና መስዋፅትነት እንዲሁም በኢህአዴግ ውስጥ ባሉ ለውጥ ፈላጊዎች አሁን የተገኘው ለውጥ ያለው መዳረሻ አንድ መሆኑን ያመለከቱት ፐሮፌስር ብርሃኑ እሱም "ኢትዮጵያን እውነተኛ ዲሞክራሲያዊት ሃገር ማድረግ ነው" ብለዋል። ለዚህም ሃገሪቱን ማረጋጋት ቀዳሚው ተግባር መሆን እንዳለበት አመልከተው፤ በማስከተልም ለዴሞክራሲያው ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ የሆኑ ተቋማት የሚገነቡበት ጊዜ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። • "ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው'' አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ • «የሠራዊታችን አባላት በክብር ይሸኛሉ» ግንቦት 7 • በኢሳትና ኦ ኤም ኤን ላይ የተከፈቱ ክሶች ተቋረጡ ጨምረውም ለውጡ እውን እንዲሆን መስዋዕትነት ለከፈሉ መላው የሃገሪቱ ሕዝቦች ፤ እንዲሁም መብታችን ይከበር ብለው ባዶ እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው ታግለው ለተሰዉ ወጣቶችም ምስጋና አቅርበዋል። በተመሳሳይም የሕዝቡን ትግል በመረዳት ከፍ ያላ ሃላፊነት በመውሰድ በኢህአዴግ ውስጥ የለውጥ ኃይል ለሆኑት እንዲሁም የእርቅና የአንድነት መንፈስን ላጠናከሩት የመንግሥት ባለስልጣናት አድናቆታቸውን ገልፀዋል። በቁጥር በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይዞ በተናጠል መንቀሳቀስ ለሕዝቡም ሆነ ለሃገሪቱ የሚኖረው ፋይዳ ጠቃሚ ስለማይሆን ፓርቲዎች በአመለካከት ከሚቀራረቧቸው ጋር እየተዋሃዱ ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ መፍጠር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሚመራው መንግሥት እንዲሁም ለለውጥ ከሚታገሉ ከየትኛው ወገኖች ጋር በትብብር ለመስራት ንቅናቄያቸው ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። መንቀሳቀሻውን ኤርትራ ውስጥ በማድረግ የትጥቅ ሲኣደርግ የቆየው የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አዲስ አበባ በገቡበት ጊዜ በደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
news-42050483
https://www.bbc.com/amharic/news-42050483
በጀርባቸው የሚተኙ ነፍሰጡሮች ልጃቸው ሞቶ የመወለድን ዕድል በእጥፍ ይጨምራሉ
ሴቶች በመጨረሻ እርግዝናቸው ሶስት ወራት ፅንሱ ሞቶ እንዳይወለድ በጎን በኩል መተኛት እንዳለባቸው አዳዲስ ጥናቶች እያሳዩ ነው።
በአንድ ሺ እርጉዞች በመጨረሻ እርግዝናቸው ወቅት በተደረገ ጥናት በጀርባቸው መተኛታቸው ፅንሱ ሞቶ የመወለዱን አደጋ እጥፍ እንደሆነ ያሳያሉ። ይህ ጥናትም 291 ሞተው የተወለዱ ፅንሶችንና 735 በህይወት የተወለዱ ፅንሶች ላይ ምርምር አድርጓል። ተመራማሪዎቹ የእርጉዝ ሴቶች አተኛኝ ለፅንሳቸው ደህንነት በጣም ጠቃሚ እንደሆነና ድንገት ሲነቁም በጀርባቸው ተኝተው ራሳቸውን ቢያገኙትም መጨነቅ እንደሌለባቸውም ይገልፃሉ። ይህ በእንግሊዝ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ከ225 እርግዝናዎች ውስጥ አንደኛው ፅንስ እንደሚሞትና ሴቶች በጎን በኩል ቢተኙ 130 የሚሆኑ ፅንሶች በየዓመቱ በህይወት መወለድ ይችሉ ነበር ይላል። ብሪትሽ ጆርናል ኦፍ ኦብስተትሪክስና እና ጋይናኮሎጂ በሚማል ጆርናል የታተመው ይህ ሚነስ የተባለው ጥናት በዘርፉ ከተደረጉ ጥናቶች ትልቁ ሲሆን በኒውዚላንድና በአውስትራሊያ የተደረጉ ትንንሽ ጥናቶችንም አካቷል። በጀርባዎ ተኝተው መንቃት ችግር ያመጣ ይሆን ? ማንችስተር በሚገኘው ቅድስት ማርያም ሆስፒታል በሚገኘው የቶሚ ስቲልበርዝ የምርምር ማዕከል የክሊኒክ ዳይሬክተር የሆኑትና ምርምሩንም በዋናነት የሚመሩት ፕሮፌሰር አሌክሳንደር ሔዝል እንደሚመክሩት ከሆነ እርጉዝ ሴቶች በመጨረሻው እርግዝናቸው ሶስት ወራት ወቅት ጋደም በሚሉበት ሆነ በሚተኙበት ወቅት በጎናቸው እንዲሆን ይመክራሉ። "ድንገት በሚነቁበት ወቅት በጀርባየ ነው የነቃሁት ልጄን ጎድቸዋለሁ ብለው ማሰብ የለባቸውም" የሚሉት ፕሮፌሰሩ "ዋናው ነገር በየትኛው በኩል እንደሚተኙና እናም ረዥም ሰአት ተኝተው የሚያሳልፉበትን ማወቅ ጠቃሚ ነው" ይላሉ። "ሰዎች በየትኛው በኩል መንቃት እንዳለባቸው መቆጣጠር ባይችሉም በየት በኩል መተኛት እንዳለባቸው ግን መወሰን ይችላሉ" ብለዋል። በጎን ለመተኛት የሚጠቅሙ አንዳንድ ነጥቦች ተመራማሪዎቹ በእርግጠኝነት ሞተው የሚወለዱ ፅንሶች ለምን እንደጨመረ በእርግጠኝነት መናገር ባይችሉም ነገር ግን ብዙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እርጉዝ ሴት በጀርባዋ በምትተኛበት ወቅት የሷ ክብደትና ማህፀኗ ልጇን በሚጫኑበት ወቅት የፅንሱን የደም መስመር ስለሚጫነው ደምና ኦክስጅን መተላለፍ ስለሚቸግር ነው። ከዚሁ ጆርናል የመጡት ኤድዋርድ ሞሪስም አዲሱን የምርምር ስራ "በከፍተኛ ደረጃ ተቀባይነትን እንዳገኘ" ተናግረዋል። "ይህ ጥናት በጣም ጠቃሚ ነው ምክንያቱም በመጨረሻዎቹ እርግዝና ወቅቶች አተኛኘት የፅንሱን አወላለድ አደጋ ስለሚቀንስ ነው" ብለዋል። እርጉዝ ሴቶችም በጎናቸው እንዲተኙና አደጋውንም ለመቀነስ የተለያዩ ዘመቻዎች እየተካሄዱ ነው። ሚሼል ኮትል የተባለች የስነ-አዕምሮ ባለሙያ በባለፈው አመት በ37ኛ ሳምንት የእርግዝና ወቅት ፅንሱ ሞቶ የተወለደ ሲሆን ከዛ በፊት ግን ፅንሱ ላይ ችግር እንደነበሩ የሚያሳዪ ምንም አይነት ምልክቶች አልነበሩም። "ዲር ኦርላ" (ውድ ኦርላ) በሚል ርዕስ ድረ-ገፅ ላይ የምትፅፍ ሲሆን በዚሁ ስር ያለፉ ሴቶችንም ልምድ ታጋራለች። በአሁኑ ወቅት ሚሼል ጤነኛ ልጅ የወለደች ሲሆን እርጉዝ ሴቶቸ በተግባር ሊተገብሩት የሚችሉትም ምክር ማግኘታቸው በጣም ጠቃሚና ሁሉ ነገር በቁጥጥራቸው ስር እንደሆነ እንዲሰማቸው እንደሚያደርግም ፅፋለች። "በእውነቱ ከሆነ ሰዎች ጥንካሬ እንዲሰማቸውና ደህንነቱ ለተጠበቀ እርግዝና የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉና የተሻለም ውጤት እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል" በማለት የምትናገረው ሚሼል "ወደኋላ ተመልሼ ሁለተኛ እርግዝናየን ሳስበው በጣም ያስጨንቀኛል ምክንያቱም በፍራቻ የተሞላ ነበር" " ድንገት የፅንሱ እንቅስቃሴ በሚያቆምበት ወቅት በህይወት ይኑር አይኑር ስለማይታወቅ በጣም አስደንጋጭ ነው" የሚሼል ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እርጉዝ ሴቶች በሚተኙበት ወቅት ፍራቻ እንደሚሰማቸው ትናገራለች። "በተለይም ሌሊቱ በጣም አስፈሪ ነው ምክንያቱም ብዙዎች በሚተኙበት ወቅት ፅንሱ እንደሞተ ይሰማቸዋል። መተኛት ግዴታም መሆኑ ሂደቱን አስፈሪ ያደርገዋል" ብላለች።
news-49202523
https://www.bbc.com/amharic/news-49202523
ፌስ ቡክ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን የፕሮፓጋንዳ ገጾች አገደ
ፌስቡክ ከሳዑዲ መንግሥት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸው ሰዎች ሐሰተኛ አካውንቶች በመክፈት ገጹን ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት እየተጠቀሙበት መሆኑን ደርሼበታለሁ አለ።
የፕሮፓጋንዳ ዘመቻው ትኩረት ያደረገው መካከለኛው ምስራቅንና ሰሜን አፍሪካን ሲሆን አብዛኛዎቹ ይዘታቸው የሚቀርበው በአረብኛ እንደሆነ ተገልጿል። ከ350 በላይ ገጾች መዘጋታቸውን የገለጸው ፌስ ቡክ፤ ከመንግሥት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ገጾችን በይፋ ከመንግሥት ጋር ግንኙነት አላችሁ ሲል ብዙ ጊዜ አይሰማም ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ሳዑዲ አረቢያ ለጊዜው ዝምታን መርጣለች። • ፌስቡክ ሦስት ቢሊዮን አካውንቶችን አገደ • የኩላሊት በሽታን የሚመረምረው መተግበሪያ • ለኬንያ ፓርላማ የተላከው ጭነት ባዶውን ተገኘ ፌስ ቡክ በመግለጫው ላይ በዚህ ሳምንት የወሰደው ርምጃ እርሱ በሚያስተዳድራቸው በፌስ ቡክም ሆነ በኢንስታግራም ላይ "የተደራጀና ያልተገባ ባሕሪን" ለመከላከል መሆኑን ገልጿል። እነዚህ ገጾች የተከፈቱት የየሀገራቱ ዜጎች የሀገራቸው የዜና አውታር ገጽን እንዲመስላቸው ተደርገው የተደራጁና የተከፈቱ ናቸው ሲል አትቷል። ፌስቡክ ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ገጾችን በመከላከል ረገድ ኋላቀርነት አለበት በሚል ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። ድርጅቱ አክሎም ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ባይኖራቸውም ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ያላቸውንና በተባበሩት የአረብ ኤምሬትና ግብፅ የተከፈቱ ገጾችንም መዝጋቱን አስታውቋል። የፌስ ቡክ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ የበላይ ኃላፊ እንዳብራሩት ከሆነ " ገጾቹን የሚያስተዳድሩ አካላት በአረብኛ አካባቢውን የሚመለከት ዜናና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን አንስተው፣ ስለ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተሐድሶ፣ ስለሳዑዲ ጦር ስኬት፣ በይበልጥ ደግሞ በየመን ግጭት ወቅት ስላለው የሚጽፉ ናቸው" ብለዋል። "ምንም እንኳ እነዚህ ሰዎች ማንነታቸው ለመደበቅ ቢሞክሩም ባደረግነው ጥናት ግለሰቦቹ ከሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ደርሰንበታል" ሲሉ አክለዋል። እነዚህ ፌስቡክ ያገዳቸውን ገጾች 1.4 ሚሊየን ሰዎች ይከተሏቸው ነበር። ፌስቡክ እንዳለው ከሆነ ዘመቻው ለማስታወቂያ ብቻ 108 ሺህ ዶላር ያወጣል።
51541453
https://www.bbc.com/amharic/51541453
ኢትዮጵያዊቷ ከኤርትራዊት ጎረቤታቸው ከ20 ዓመት በፊት የተረከቡትን መለሱ
ወ/ሮ ሻሽቱ ንጉሤ ጠይም፣ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ናቸው። መጀመሪያ ቀበሌ ሦስት ነዋሪ የነበሩት፤ በኋላ ላይ ግን አዚያው ጎንደር ውስጥ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤት ገዝተው ገቡ። በወቅቱ የፍርድ ቤት ሠራተኛ ነበሩ።
ያኔ የፎገራ ሆቴል ገንዘብ ያዥ የነበሩት ኤርትራዊቷ ወ/ሮ ምግብ ተመስገን ደግሞ ቀድሞ ከሚኖሩበት ቀበሌ አራት፣ መሬት ተመርተው እዚያው ደብረብርሃን ሥላሴ ቤት ሠሩ። የሁለቱ ሴቶች ጉርብትናም የተመሠረተው ያኔ ነበር። አዲስ ሠፈር አዲስ ጉርብትና ቢሆንም በበዓል መጠራራት የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን በጋራ መከወን የተለመደ ነበር ይላሉ ወ/ሮ ምግብ። ጉርብትናቸው ብዙም ሳይጠነክር፤ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው ፖለቲካዊ ሁኔታ ለያያቸው። ወ/ሮ ምግብ ሦስት ወልደው ያሳደጉበት፣ ከጎረቤቶቻቸው ክፉ ደግ ያዩበት ቤትን ጥሎ መሄድ ከባድ እንደነበር ይናገራሉ። ወ/ሮ ምግብ ጎንደር ለ26 ዓመታት ያህል ኖረዋል። ኢትዮጵያዊ አግብተው ወልደው ከብደዋል። በወቅቱ በነበረው ፖለቲካዊ ሁኔታ ኤርትራዊያን ወደ አገራችው ግቡ በተባለው መሠረት ቤት ንብረታቸውን ትተው ልጆቻቸውን ብቻ ይዘው አገራቸው ገቡ። በርግጥ ይላሉ ወ/ሮ ሻሺቱ፣ ወ/ሮ ምግብ ቀበሌ ሦስት ሲኖሩ አበልጆች ነበሯቸው። ቀበሌ አራትም ሲኖሩ የሚያውቋቸው ወዳጆች ብዙ ነበሩ። ነገር ግን እቃ መሸከፍ ሳይቻል በድንገት ከአገር እንዲወጡ ሲደረግ ንብረታቸውን አደራ ብለው የሄዱት በቅርብ ጊዜ ለሚያውቋቸው ወ/ሮ ሻሽቱ ነበር። ወቅቱ ጭንቅ ስለነበር ወ/ሮ ምግብ ማቄን ጨርቄን ሳይሉ ነበርና ጥለው የወጡት እቃቸውን መልክ መልክ ማስያዝም የወ/ሮ ሻሽቱ ኃላፊነት ነበር። የቤት እቃዎቻቸው የተወሰኑት ተሸጠው አዲስ አበባ ለሚገኙት እህታቸው እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ ለቀረው ልጃቸው እንዲሰጥላቸው አደራ አሉ፤ ወ/ሮ ምግብ። ይህንን ለማድረግ ወ/ሮ ሻሺቱ አደራ ተቀብለው በአግባቡ መከወናቸውን ይናገራሉ። አደራውን የሠጧቸው ከአገር እንዲወጡ በተደረገበት ምሽት አካባቢያቸውን ማህበራዊ ፍርድቤት ሠራተኛ እማኝ አድርገው ነበር። 'እንደምን አደራችሁ? እንዴት ናችሁ?' ከሚል ጉርብትና ውጪ ዝምድና የሌላቸው ወ/ሮ ሻሺቱና ወ/ሮ ምግብ፤ በቃል የተሰጣጡትን አደራ አክብረው ዛሬ ይገናኛሉ። የተወሰነ እቃ ደግሞ ለጎረቤታቸው እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፤ ስለዚህ እንደቃላቸው አደረጉ። የቀረው ቤት ነው። ቤታቸው ከጭቃ የተሰራ ሲሆን ያረፈው ደግሞ 200 ካሬ ሜትር በሚሆን መሬት ላይ መሆኑን ይናገራሉ። በዘመኑ አጠራር አሞራ ክንፍ በሚባል ቅርጽ የተሰራው ይህ ቤት ሌሎች የሚከራዩ ሁለት ሰርቪስ ክፍሎችም በግቢው ውስጥ አሉ። ወ/ሮ ሻሺቱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የቤት ኪራይ ገንዘብ እየሰበሰቡ አስቀምጠውላቸዋል። በርግጥ የቤት ኪራይ ቤቱ በሚገኝበት ደብረብርሃን ሥላሴ ውድ አይደለም። ቢሆንም የወር ኪራዩን ተቀብለው በባንክ በማስቀመጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኘው ልጃቸው፣ በአንድ ወቅት እርሳቸውም በመጡበት ወቅት ለእርሳቸው መስጠታቸውን ይናገራሉ። ይህንንም ወ/ሮ ምግብ እንደሚያስታውሱ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት አረጋግጠዋል። ቤቱን በሚመለከት የሚደረገውን መዋጮ፣ ዓመታዊ ግብር ከፍለው፣ ወ/ሮ ሻሺቱ ተመዝግበው የሄዱትን ውሃ አስገብተው እንዳቆይዋቸው ይናገራሉ። በየጊዜው ከሰጧቸው የኪራይ ገንዘብ በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት ከ50 ሺህ እስከ 60 ሺህ ብር በባንክ ማስቀመጣቸውን ወ/ሮ ሻሺቱ ይናገራሉ። ወ/ሮ ምግብ አንድ ጊዜ መጥተው ቤታቸውን አይተዋል። ቤታቸውን ትተው ሲሄዱ ተመልሼ አገኘው ይሆናል ብለው ያስቡ እንደነበር ያስታውሳሉ። ለቃላቸው ታማኝ የሆኑት፣ ቃላቸውን ጠብቀው ያቆዩት ወ/ሮ ሻሺቱ የወ/ሮ ምግብን ተስፋ አሳክተዋል። ከዚህ በፊት በመጡበት ወቅትም ቤታቸውና በህይወት የቆዩትን ጎረቤቶቸቸውን ሲያገኙ የነበረውንም ደስታ አይረሱትም። ቤታቸው ሳይሸጥ አደራቸውን ጠብቀው በማቆየታቸው የተሰማቸውን ደስታ ወደር እንደሌለው ይናገራሉ። "በጨለማ የሰጡኝን በብርሃን እንዳስረክብ ፈጣረዬን እለምን ነበር" ይላሉ አደራ ጠባቂዋ ወ/ሮ ሻሺቱ። ወ/ሮ ምግብም ቤታቸውን ተረክበው የዘመመውን አቅንተው ለመኖር እንደሚያስቡ ይናገራሉ። ልጆቻቸውም የተወለዱበት ቤት እናታቸው ለመኖር ማሰባቸውን ሲሰሙ ሃሳባቸውን መደገፉ ይናገራሉ። ወ/ሮ ሻሺቱ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ወደ አሜሪካ ሲሄዱ ቤታቸውን እንዲጠብቅ ውክልና ለሰጡት ሰው የጎረቤታቸውን የወ/ሮ ምግብ ቤትም አደራ ብለው ውክልና ሰጥተው መሄዳቸውን ያስታውሳሉ። በአደራ የተሰጠኝን ቤት ሳየው እንደራሴ ቤት ነው የሚሰማኝ የሚሉት ወ/ሮ ሻሼ ይህንን በአደራ የተሰጣቸውን ቤት ሲጠብቁ በርካታ ውጣ ውረዶች ማሳለፋቸውን ይናገራሉ። የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው ከተከራይ ጋር መነጋገር፣ አጥር ፈርሶ ቢናገሩ፣ ግቢያቸው ተከብሮ እንዲቆይ በማድረግ ውስጥ ክፉ የሚናገር የአካባቢ ሰው አይጠፋም ነበር። ሁለቱ ግለሰቦች ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት አንዳቸው ሚኒሶታ ሌላኛቸው ዳላስ ቢሆኑም ያሉበት ድረስ በመሄድ መጠያየቃቸውን አጫውተውናል። ወ/ሮ ሻሺቲ ከ20 ዓመታት በላይ በአደራ ጠብቀው ያቆዩትን ቤት ለባለቤቷ ወ/ሮ ምግብ በዛሬው ዕለት ማክሰኞ የካቲት 10/2010 ዓ.ም እዚያው ጎንደር ውስጥ እንደሚያስረክቡ ተናገረዋል።
53407889
https://www.bbc.com/amharic/53407889
የሃጫሉ ግድያ፡ ከሁከቱ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ወደ 5 ሺህ ተጠግቷል ተባለ
ባለፈው ሰሞን ተከስቶ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 5 ሺህ እንደሚጠጋ የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለቢቢሲ ተናገሩ።
አቶ ንጉሡ በአሁኑ ጊዜ የአገሪቱ የጸጥታ ወደ ተረጋጋ ሁኔታ እየተመለሰ መሆኑን ጠቁመው፤ ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተከስቶ በነበረው ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 5 ሺህ ገደማ እንደሆነ ገልጸዋል። ክስተቱን ተከትሎ "የጸጥታ መዋቅሩ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ነው" ያሉት አቶ ንጉሡ፤ አሁንም በጸጥታ አካሉ እየተፈለጉ ያሉ ሰዎች መኖራቸውን አመልከተዋል። አቶ ንጉሡ ጨምረው እንደተናገረት ተከስቶ በነበረው ሁከት በሰው እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ከፌደራል እና ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተወጣጣ አካል አለመረጋጋቱ አጋጥሞባቸው ወደነበሩት ስፍራዎች ማምራቱን ተናግረዋል። የደረሰውን ጉዳት በሚመለከትም ግብረ ኃይሉ የሚያጠናቅረው ዝርዝር መረጃ ዝግጁ ሲሆን ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል። በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ የመንግሥት ባለስልጣናት እስር ከሃጫሉ ግድያ በኋላ የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ የመንግሥት ባለስልጣናት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን ያረጋገጡት አቶ ንጉሡ፤ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ "ሁሉም አይነት አመራር ይኖራል። የሚልቀው ብጥብጡ እና ቀውሱን ለመቆጣጠር የሚታገል ነው" በማለት አብዛኛው አካል አውንታዊ ጥረት ማደረጉን አመልክተዋል። "ከዚህ ውጪ ሁለት ቦታ የሚረግጥ ይኖራል፣ የተሳሳተ ይኖራል አልያም ደግሞ የብቃት ችግር ያለበት ይኖራል" ያሉ ሲሆን፤ ሁሉም እንደ አግባቡ "በሕግ የሚጠየቀው በሕግ ይጠየቃል፣ ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚያስፈልገው ፖለቲካዊ ውሳኔ ይተላለፍበታል እንዲሁም አስተዳደራዊ እርምጃ የሚሰጣቸውም ይኖራሉ" ብለዋል። ችግር የፈጠሩ፣ ያባባሱና አይተው እንዳለየዩ ያለፉ አመራሮች እንዲሁም የጸጥታ አስከባሪ አካላት መኖራቸውን ጠቁመው በጉዳዩ ላይ በቀጣይ የማጣራት ሥራ እንደሚሰራ አቶ ንጉሡ ተናግረዋል። የጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች እስር "በሚዲያው በሚረጨው መርዝ ዜጎች ህይወታቸው የሚቀጠፍበትና ኢትዮጵያ የምትፈርስበት እድል ሊፈቀድ አይደገባም" ያሉት አቶ ንጉሡ፤ "የሚኖሩበትን ሕዝብና አገር እያጫረሱ እንዲፈርስ እየጣሩ የሚዲያ ተቋም ነን ሊሉ አይችሉም፤ ጋዜጠኛ ነን ሊሉም አይችሉም" ያሉ ሲሆን መሰል ግለሰቦች ላይ "ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል" ብለዋል። የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግንድያ በኋላ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ መንግሥት በመላው አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወሳል። ይህንንም በተመለከተ የኢንትኔት አገልግሎት ወደ ነበረበት የሚመለስበትን ጊዜ ቢቢሲ አቶ ንጉሡን ጥይቆ ነበር። "ኢንተርኔት የተዘጋው ለጸጥታ ሲባል ነው" ያሉት አቶ ንጉሡ፤ ጨምረውም የአገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ሲረጋገጥ ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደሚለቀቅ ተናግረዋል። አቶ ንጉሱ ጨምረውም "አሁንም ቢሆን ሕዝቡ 'ፌስቡክ የሚባለውን ያዝ አድርጉልን። በብሔርና በሐይማኖት ላይ የክተት ጥሪ እየተጠራ ነው' የሚሉ አስተያየት እየሰጡን ነው" በማለት በሕዝቡ ዘንድ ከኢንተርኔት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ስጋት እንዳለ እንደሚገነዘቡ ጠቅሰዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከማክሰኞ ከሰዓት ኋላ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በከፊል የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍት መደረጉን ቢቢሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በዚህም መሰረት ከአዲስ አበባ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በተለያዩ ቦታዎች ላይ የዋይፋይ ኢንተርኔት አገልግሎት ክፍት ቢደረግም በርካቶች የሚጠቀሙት የሞባይል ዳታ የኢንተርኔት አገልግሎት ግን አሁንም እንደተዘጋ ነው።
news-41799655
https://www.bbc.com/amharic/news-41799655
ሳዑዲ ሴቶች ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ልትፈቅድ ነው
ሳዑዲ አረቢያ ሴቶች በስታዲየሞች ተገኝተው ስፖርታዊ ውድድሮችን እንዲመለከቱ ልትፈቅድ መሆኑን ባለሥልጣናቱ ገለጹ።
ሴቶች ለመጀመሪያ በሪሃድ ንጉስ ፋህድ ስታዲየም ተገኝተው ብሄራዊ ቀንን ማክበራቸው ከሃገሪቱ ወግ አጥባቂዎች የሰላ ትችት ገጥሞታል በሪያድ፣ ጂዳህና ዳማም ባሉ ስታዲየሞች የቤተሰብ አባላት በጋራ መግባት ይችላሉ። ከፍተኛ የጾታ መድልዎ ያለባት ሳዑዲ፤ ሴቶች መኪና እንዳያሽከረክሩ የሚከለክለውን ህግ ካነሳች በኋላ የፈቀደችው ሌላኛው ነጻነት ነው ተብሏል። ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን የሃገራቸውን ማህበረሰብ ለማዘመን እና ኢኮኖሚውን ለማሳደግ እየሰሩ ነው። የሳዑዲ የስፖርት ኃላፊዎች እንዳሉት "ቤተሰቦችን ከመጪው ጥር ጀምሮ ለመቀበል እንዲቻል" ስታዲሞች ዝግጅት በማድረግ ላይ ናቸው። ለውጡን ተከትሎ ምግብ ቤቶች፣ካፌዎች እና የመቆጣጠሪያ መሣሪያዎች በስታዲየሞቹ ውስጥ እንደሚሠሩም ታውቋል። እስካሁን ድረስ ስታዲየሞቹ ወንዶችን ብቻ ነበር የሚያስተናግዱት። ለውጦች እነዚህ ማሻሻያዎች የ32 ዓመቱ ልዑል መሐመድ በነዳጅ ሃብት ላይ ጥገኛ የሆነችውን ሃገራቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለመለወጥ የተያዘው የራዕይ 2030 ዕቅድ አካል ነው። ከመጪው ሰኔ ጀምሮ ሴቶች መኪና ማሽከርከር እንደሚችሉ ባለፈው ወር ይፋ መደረጉ ይታወሳል። የሙዚቃ ዝግጅቶችንና ሲኒማዎችንም ማሻሻያው በቅርቡ እንደሚያካትታቸው ይታወቃል። የሃገሪቱ ሴቶች አሁንም ቢሆን ከፍተኛ እገዳ ተጥሎባቸዋል ባለሙያዎች ግን ዕቅዱ ፈተናዎች ሊገጥሙት ይችላሉ ይላሉ። ሴቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ወር በሪሃድ ንጉስ ፋህድ ስታዲየም ተገኝተው ብሄራዊ ቀንን ማክበራቸው ከሃገሪቱ ወግ አጥባቂዎችና በማህበራዊ ድረ-ገፆች የሰላ ትችት ገጥሟቸዋል። የሃገሪቱ ሴቶች አሁንም ቢሆን ከፍተኛ እገዳ ተጥሎባቸዋል። ሴቶች ጠንካራ የአለባበስ ህግን የሚከተሉ ሲሆን ከቤተሰባቸው ውጭ ከሚገኝ ወይንም ከማይታወቅ ወንድ ጋር መታየት አይፈቀድላቸውም። ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ፣ ለመሥራትና የጤና አገልግሎት ለማግኘት ከወንዶች ጋር መሄድ ወይንም የወንዶችን ፈቃድ እንዲያመጡ ይጠበቅባቸዋል።
news-54536600
https://www.bbc.com/amharic/news-54536600
ሃጫሉ ሁንዴሳ ፡ በግድያው የተጠረጠሩት ሰዎች ወንጀሉን አልፈጸምንም አሉ
በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን አልፈጸምንም ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናገሩ።
አርቲስት ሃጫሉ በአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት አራቱ ተጠርጣሪዎች ማለትም ጥላሁን ያሚ፣ ከበደ ገመቹ፣ አብዲ አለማየሁ እና ላምሮት ከማል እያንዳንዳቸው "ወንጀሉን አልፈጸምንም። ጥፋትም የለንም" በማለት ዛሬ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል። ተጠርጣሪዎቹ ይህን ያሉት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሕግ እና ጸረ ሽብር ችሎት ዛሬ ረቡዕ በቀረቡበት ወቅት ነው። ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤት ቀርበው በነበረበት ወቅት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉት ተጠርጣሪዎች ጠበቃ የማቆም አቅሙ የለንም ያሉ ሲሆን፤ 4ኛ ተጠርጣሪ ላምሮት ከማል በበኩሏ ጠበቃ ለማቆም ብፈልግም ሊወክለኝ ፍቃደኛ የሆነ ጠበቃ ላገኝ አልቻልኩም ብላ ነበር። ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎቹ መከላከያ ካላቸው እንዲያቀርቡ እና መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ሲል ውሳኔ አስተላልፎ ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። በዚሁ መሠረት በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች የተመደቡ ጠበቃ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ይሁን እንጂ የተመደቡት ጠበቃ የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 20.5ን በመጥቀስ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ላሉት ተከሳሾች መቆም እንደሚችሉ ጠቅሰው፤ 4ኛዋን ተከሳሽ [ላምሮት ከማልን] ግን ለመወከል የተሰጣቸው ውክልና እንዲነሳ ጠይቀዋል። ስለተከሰሱ ሰዎች በሚያትተው አንቀጽ 20.5 ተከሳሾች በመረጡት የሕግ ጠበቃ የመወከል ወይም ጠበቃ ለማቆም አቅም በማጣታቸው ፍትሕ ሊጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከመንግሥት ጠበቃ የማግኘት መብት አላቸው ይላል። ጠበቃውም አረተኛዋ ተከሳሽ ፍቃደኛ ሆኖ የሚቆምላት ጠበቃ አጣች እንጂ ጠበቃ የማቆም አቅም አላነሳትም ስለዚህም "ውክልናችን ትክክል አይደለም" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ የጠበቃውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ መንግሥት የመደባቸው ጠበቃ አራተኛዋ ተከሳሽንም እንዲወክሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል። በሌላ በኩል የተከሳሾች ጠበቃ ተከሳሾቹ የክስ መከላከያ እንደሌላቸው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። ዐቃቤ ሕግም ፖሊስ መስክሮችን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ይሰጠ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ፍርድ ቤቱ ግን ዐቃቤ ሕግ ራሱ መስክሮቹን ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ አዟል። በዚሁ መሠረት ከኅዳር 23 እስከ 25/2013 ዓ.ም ምስክሮቹን ይዞ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተዕእዛዝ ሰጥቷል። አራቱ ተከሳሾች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንጽ 32/1 ሀ እና ለ አንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 3/2 በመተላለፍ መከሰሳቸው ይታወሳል። ታዋቂው የኦሮምኛ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ባለፈው ዓመት ሰኔ 22/2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ምሽት ላይ በተተኮሰበት ጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉን ይታወሳል። የአርቲስቱን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት እና አለመረጋጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸው እና በሺዎቹ የሚቆጠሩ ደግሞ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል።
news-47235750
https://www.bbc.com/amharic/news-47235750
በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ለ20 ዓመታት ያህል ዘልቆ የነበረው ሰላምም ሆነ ጦርነት ያልነበረበት ፍጥጫ ከወራት በፊት በተደረሰው የሰላም ስምምነት መቋጫውን አግኝቷል።
ናቅፋ እና ብር የሚመነዝሩ ነጋዴዎች ከአዲስ አበባ ወደ አሥመራ የሚደረገው በረራ የቀጠለ ቢሆንም፤ ቪዛ እና የቀረጥ ጉዳዮችን መልክ ለማስያዝ በሚል ምክንያት በእግር እና በመኪና ድንበር ማቋረጥ ተከልክሎ ቆይቷል። ይሁን እንጂ የድንበር ከተሞች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በድንበር ከተሞቹ ላይ ንግዳቸውን ከማጧጧፍ ያገዳቸው የለም። • ወደ አሥመራ የሚደረገው በረራ ጀመረ • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች • ሻምፓኝ እና ፅጌረዳ ያጀበው የአዲስ አበባ-አሥመራ በረራ ለሱዳን ቅርብ የሆነው ሁመራ-ኦመሃጀር ድንበር በቅርቡ መከፈቱ ይታወሳል። ድንበሩ መከፈቱን ተከትሎም በድንበር አቅራቢያ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ ፍሰት እየተስተዋለ ነው። ኢትዮ-ኤርትራ ሁመራ-ኦመሃጀር ድንበር በሁመራ ገንዘብ መንዛሪዎች ከመቼውም በላይ ንግድ ደርቶላቸዋል። አንድ ዶላር የሚመነዘረው በ15 ናቅፋ ገደማ ሲሆን፤ አንድ ዶላር ደግሞ 28 ብር ገደማ ይመነዘራል። በአካባቢውም ብር ወደ ናቅፋ የሚመነዝሩ ነጋዴዎች ይገኛሉ። በሁመራም የሚገኙ ገንዘብ መንዛሪዎች በምስሉ ላይ የሚታየውን አልጋ የሚሰሩ እና የሚሸጡ ሰዎች የደንበኞቻቸው ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ይናገራሉ። አካባቢው እጅጉን ሞቃታማ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች በእነዚህ አልጋዎች ላይ ከቤት ውጪ ይተኛሉ። በሁለቱ ሀገራት መካከል ተከስቶ በነበረው ግጭት የአንድ ቤተሰብ አባላት በሁለት ሀገራት ተከፍለው ለዓመታት ሳይገናኙ ቆይተዋል። የሰላም ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ ለዓመታት ተለያይተው የቆዩ ሰዎች እየተገናኙ ነው። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሀገር ጥለው የወጡ በርካቶች ናቸው። ከእነዚህ መካከል ከዚህ በታች የሚታዩት ኤርትራውያን ይገኙበታል። እኚህ ሁለት ሰዎች እንደሚሉት፤ ከሁለት አሰርት ዓመታት በፊት ጥለው የሄዱትን ንብረት ይገባኛል የሚል ጥያቄ ሊያነሱ ሁመራ ተገኝተዋል። እኚህ ሁለት ሰዎች እንደሚሉት፤ ከሁለት አሰርት ዓመታት በፊት ጥለው የሄዱትን ንብረት ይገባኛል የሚል ጥያቄ ሊያነሱ ሁመራ ተገኝተዋል።
news-50279611
https://www.bbc.com/amharic/news-50279611
የዓለማችን እጅግ ትርፋማው የሳዑዲ ድርጅት አክሲዮኑን ለሕዝብ ክፍት ሊያደርግ ነው
አርማኮ የተሰኘው የሳዑዲ ነዳጅ አምራች ድርጅት አክሲዮኑን በሽያጭ ለሕዝብ ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑን በትዊተር ገፁ ይፋ አድርጓል።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ንብረት የሆነው ይህ ድርጅት ባለፈው አርብ በአረብኛ በለቀቀው መግለጫ ነው ይህንን መረጃ ያወጣው። መረጃዎች ድርጅቱ ምናልባትም 1 ወይም 2 በመቶ ድርሻውን ብቻ ለሕዝብ ቢያቀርብ ነው ይላሉ። እንዲያም ሆኖ አክሲዮን ለሕዝብ ይፋ ከሆነ በዓለም ገበያ ትልቁ የአክሲዮን ድርሻ ይሆናል። ምንም እንኳ የሳዑዲ መንግሥት 2 ትሪሊዮን ነው ብሎ ብሎ ቢከራከርም፤ ሳዑዲ አርምኮ 1.2 ትሪሊዮን ዶላር የሚያወጣ ድርጅት እንደሆነ ይገመታል ሲል የቢዝነስ ዜና የሚያሰራጨው ብሉምበርግ ዘግቧል። 1933 [በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር] ነበር ሳዑዲ ከአንድ የአሜሪካ ድርጅት ጋር ነዳጅ ለማውጣት የተዋዋለችው። በ1980 ደግሞ ሳዑዲ ሙሉ በሙሉ ድርጅቱን የራሷ አደረገችው። ሳዑዲ ከቬንዝዌላ በመቀጠል በርካታ የነዳጅ ክምችት ያለባት አገር እንደሆነች ይነገራል። በምርት ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አርምኮ በያዝነው 2019 አጋማሽ ብቻ 46.9 ቢሊዮን ዶላር አትርፏል። በተነፃፃሪ አፕል የተሰኘው ኩባንያ 21.6 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ አጋብሷል። ድርጅቱ አክሲዮኑን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ያስፈለገው ሃገሪቱ ነዳጅ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ ነው ተብሏል። አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐማድ ቢን ሰልማን የሃገራቸው ምጣኔ ሃብት የተሰባጠረ እንዲሆን ርዕይ 2030 የሚል ዕቅድ ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ነው። ባለፈው መስከረም ንጉሣዊው ቤተሰብ ሳዑዲ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ነፃ አገር እንድትሆን እየሠራሁ ነው ሲል ተደምጧል። ለ49 ሃገራት ከቪዛ ነፃ ሥርዓት በመዘርጋት የቱሪዝም ፍሰቱን ለማፋጠን እየሠራሁ ነው ትላለች ሳዑዲ። የድርጅቱ አክሲዮኑን ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ በፖለቲካ መነፅር ሲታይ ብዙ ዓይነት ቀለም አለው ይላሉ ተንታኞች። በተለይ ደግሞ ከጃማል ኻሾግጂ ግድያ በኋላ የሳዑዲ መንግሥት ከጭካኔ ጋር መያያዙን በመጥቀስ።
news-57278889
https://www.bbc.com/amharic/news-57278889
የማሊ መፈንቅለ መንግሥት መሪ የሽግግር አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰየሙ
የማሊ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት በአገሪቱ የተደረገው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መሪ ኮሎኔል አሲሚ ጎይታን የሽግግር ጊዜ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሰየመ።
ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ኮሎኔል ጎይታ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ሁለተኛውን መፈንቅለ መንግሥት አድርገው ሥልጣን ከያዙ ከሁለት ቀናት በኋላ ባለፈው ረቡዕ የማሊ ጊዜያዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አድርገው እራሳቸውን ሾመዋል። በምርጫ ሥልጣን ይዘው የነበሩትን ፕሬዝዳንት ቡባካር ኬይታን ከመንበራቸው ባለፈው ነሐሴ ወር ያስወገዱት ወታደራዊ መሪው፤ የፕሬዝደንትነት ቦታውን እንዲይዙ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ከመጀመሪያው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ ማሊን ወደ ሲቪል መንግሥት የሚመልሰውን አስተዳደር በጊዜያዊ ፕሬዝዳንትነት እና በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲመሩ የነበሩት ባህ ዳዋ እና ሞክታር ኦኔ በሁለተኛው መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎች ተይዘው ታስረዋል። ኮሎኔል ጎይታ ባልተጠበቀ ሁኔታ ፕሬዝዳንቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል እንዲታሰሩ አድርገዋል። ነገር ግን ሁለቱ መሪዎች ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ከተደረገ በኋላ ሐሙስ ዕለት ከእስር ተለቀዋል። አርብ እለት በፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ኮሎኔል ጎይታ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው "የአገሪቱን የሽግግር ሂደት አስከፍጻሜው እንዲመሩ" ኃላፊነት እንደተሰጣቸው አመልክቷል። የባለፈው ዓመት የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ የሽግግሩ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። መፈንቅለ መንግሥቱ የተካሄደው ጊዜያዊ አስተዳደሩ የአገሪቱ ጦር ሠራዊትን ሁለት ከፍተኛ መኮንኖችን ከሥልጣናቸው በማንሳት በሌላ ከተተኩ ከሰዓታት በኋላ ነበር። ይህን ተከትሎ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሹም ሽር በማድረጉ ኮሎኔል ጎይታ ቅሬታ አድሮበት ነው እርምጃውን የወሰደው ተብሏል። አርብ እለት ኮሎኔሉ ሥልጣን በኃይል ከያዙ በኋላ ለሕዝቡ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው "በጦር ሠራዊቱና በጸጥታ ኃይሉ መካከል ሊከሰት ከሚችለው ሥርዓት አልበኝነት ይልቅ መተባበርን መርጣናል" ሲሉ ለመፈንቅለ መንግሥቱ ምክንያታቸውን ጠቅሰዋል። ኮሎኔል ጎይታ ጨምረውም አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሾምና ምርጫ በሚቀጥለው ዓመት በተያዘለት ጊዜ ይካሄዳል ማለታቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል። የወታደራዊ ቡድኑ መሪ ኮሎኔል ጎይታ ባለፈው ዓመት የመሩትን መፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ የ18 ወራት የሽግግር ምክር ቤት ተሰይሞ ነበር። ኮሎኔል ጎይታ የአገሪቱን ተመራጭ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ባቦካር ኬይታን ከሥልጣን በኃይል ሲያስወግዱ የአገሪቱ በርካታ የአገሪቱ ሕዝብ በደስታ አደባባይ ወጥቶ ነበር። ሆኖም ባለፉት 9 ወራት የታየው አዝጋሚ የለውጥ ሂደት ዜጎችን ቅሬታ ውስጥ ከቷቸው ነበር። የሠራተኛው ማኅበር የጠራው የሥራ ማቆም አድማም የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት ማሽመድመድ ይዞ ነበር። ባለፈው ዓመትም መፈንቅለ መንግሥቱን ተከትሎ የምዕራብ አፍሪካ አገራት ማኅበር የሆነው ኢኮዋስ በዚያች አገር ማዕቀብ እጥላለሁ በማለቱ ነበር የሽግግር መንግሥት መመሥረት የተቻለው። በአገሪቱ እጇ ረዥም ነው የምትባለውና ማሊን ለዓመታት በቅኝ የገዛችው ፈረንሳይ፤ የአውሮፓ ኅብረት ማዕቀብ እንዲጥል አስደርጋለሁ ስትል ዝታለች። የባሕር በር አልባዋ ማሊ በአፍሪካ ድሃ አገራት ተርታ የምትመደብ ሲሆን የአገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ልማት የማያውቃቸው ናቸው።
news-45095530
https://www.bbc.com/amharic/news-45095530
ከወንጀልነት ወደቀዳሚ መዋቢያነት የተሸጋገረው የከንፈር ቀለም
በመላው ዓለም 800 ሚሊየን ዶላር ለከንፈር ቀለም እንደሚፈስ ያውቃሉ? ለዘመናት እምባዛም ተቀባይነት ያልነበረው የከንፈር ቀለም (ሊፒስቲክ ሌላ ስሙ ነው) እንዴት ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት ያለበት መዋቢያ ሆነ ብሎ መጠየቁ አይቀርም። ታሪኩን ወደኋላ መለስ ብሎ ማየት ምላሽ ይሰጣል።
በእርግጥ በጥንታዊ ስልጣኔም ሴቶች ከንፈራቸውን ያቀልሙ ነበር። 5,000 ዘመናት ወደኋላ ብንጓዝ በሜሲፖታሚያ ጥቅም ላይ ይውል ነበር። ዛሬ በሚታወቅበት ቅርጽ ባይሆንም ጥንታዊ ሳሞርያኖች የከንፈር ቀለምን እንደፈጠሩ ይነገርላቸዋል። ቀለሙን ከንፈር ላይ ብቻ ሳይሆን አይናቸውንም ለማስዋብ ይጠቀሙበት ነበር። ለግብጻውያን ደግሞ የመደብ መገለጫ ነበር። የክሊዩፓትራ የከንፈር ቀለም ከጉንዳንና ሌሎችም ነፍሳት የተሰራ ነበር። • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት • የሒጃብ ፋሽን ድዛይነሯ በማጭበርበር ወንጀል ለእስር ተዳረገች • "ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች ጠጣር የከንፈር ቀለም ወደ አለም የተሰራጨው ከመካከለኛውም ምስራቅ ተነስቶ ነው። የእንግሊዟ ንግስት ኤልዛቤት አንደኛ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የከንፈር ቀለምን እውቅና አሳድገዋል። በወቅቱ የከንፈር ቀለም ከቅጠላ ቅጠል ይዘጋጅ ነበር። በሀገረ ቻይና የታንግ ዘመነ መንግሥት ላይ የከንፈር ቀለም ለስለስ እንዲል፤ መዓዛ ያለው ቅባታማ ፈሳሽ ይታከልበት ጀመር። የክሊዩፓትራ የከንፈር ቀለም ከጉንዳንና ሌሎችም ነፍሳት የተሰራ ነበር ቀጥሎ በመጡት ዘመናት የከንፈር ቀለምን የሚጠቀሙት ተዋንያን አልያም ሴተኛ አዳሪዎች ነበሩ። የከንፈር ቀለም ሲሰራ መርዛማ ኬሚካሎችን መጨመር የተጀመረውም በዚሁ ጊዜ ነው። በአንዳንድ ማህበረሰቦች የከንፈር ቀለም የሚጠቀሙት ጠንቋዮች እንደሆኑ ስለሚታመን መዋቢያው ክልክል ነበር። አሜሪካዊቷ ኤልዛቤት አርደን ለከንፈር ቀለምና ሌሎችም መዋቢያዎች ያለውን የተዛባ አመለካከት በመስበር የመዋዋቢያዎች ማምረቻ አቋቋመች። እንደ አውሮፓውያኑ በ1912 ሴቶች በምርጫ እንዲሳተፉ በተካሄደ ሰልፍ ለተሳተፉ ሴቶች የከንፈር ቀለም መሸጧም አይዘነጋም። እንደ አውሮፓውያኑ በ1912 ሴቶች ያደረጉት ሰልፍ የፈረንሳዩ ጉሬሊን የመዋቢያ ተቋም እንደ አውሮፓውያኑ በ1870 የከንፈር ቀለም መሸጥ የጀመረ ሲሆን ፈረንሳይኛ መጠሪያው ወደ አማርኛ ሲመለስ 'አትዘንጉኝ' የሚል ነው። ለከንፈር ቀለም ማስቀመጫ የሚሆንና መጠነኛ ትቦ የሚመስል የብረት እቃ መዘጋጀት የጀመረውም በዛው ወቅት ነው። እንደ አውሮፓውያኑ ከ1930ዎቹ ወዲህ የከንፈር ቀለም መወገዙ እየቀረለት መጣ። እውቅናው ከመጨመሩ የተነሳ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የነበረው ትርምስ እንኳን የከንፈር ቀለም ከመጠቀም አላስቆመም። የከንፈር ቀለም መጠቀም አስፈላጊ ነው በተባለበት በዚያ ወቅት የከንፈር ቀለም ለመግዛት አቅም ያልነበራቸው ሴቶች ከሰል ወይም ቀይ ስር ይጠቀሙ ነበር። ፒ ኤንድ ኤስ የተሰኘ ተቋም በሰራው ጥናት የከንፈር ቀለም እስከዛሬ ዕውቅ ሆኖ የዘለቀው በቀላሉ ሊሸመት የሚችል መዋቢያ በመሆኑ ነው። በጥናቱ መሰረት የከንፈር ቀለም ገናናነት እየጨመረ ቢሄድ እንጂ አያሽቆለቁልም። የከተሜነት መስፋፋትና የኑሮ ዘዬ መለወጥ ለከንፈር ቀለም ታዋቂነት ምክንያት ከሆኑት መካከል ይጠቀሳሉ።
45951482
https://www.bbc.com/amharic/45951482
ደብረ ብርሃን አቅራቢያ አንጎለላና ጠራ ውስጥ በርካታ ሰዎች በትራፊክ አደጋ የሞቱበት መንገድ
በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ከደብረብርሃን ተሳፋሪዎችን ይዞ ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሰ የነበረ አንድ ዲ ፎር ዲ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ከድንጋይ ገልባጭ መኪና ጋር በመጋጨቱ ምክንያት የ 12 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ሦስት ሰዎች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሁለት ሰዎች ደግሞ ቀላል ጉዳት አጋጥሟቸዋል። የወረዳው ፖሊስ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ነገሩኝ እንዳለው መለስተኛ የህዝብ ማመላሻው ርቀቱን ሳይጠብቅ ለመቅደም ሲሞክር ከተቃራኒ አቅጣጫ ከሚመጣው የጭነት መኪና ጋር ተጋጭቷል። • በሰሜን ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ • የትራፊክ አደጋንና የባርቴንደር ሙያን ምን ያገናኛቸዋል? • በጫጫ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ በአንጎለላ ጠራ ወረዳ ከግንቦት 21 ጀምሮ ብቻ ሦስት ከፍተኛ የትራፊክ አደጋዎች ደርሰዋል። የአንጎለላ ጠራ ወረዳ ፓሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዳግም አጣለ ለደረሱ አደጋዎች በዋናነት የሙያ ብቃት ማነስን እንደምክንያት ያነሳሉ። በተጨማሪም መንገዱ የፍጥነት መቀነሻ እንደሚያስፈልገው የተናገሩ ሲሆን በቅርብ ጊዜ በደረሱት 2 የመኪና አደጋዎች ብቻ 1.2 ሚሊየን ብር አካባቢ የሚገመት የንብረት ውድመት ደርሷል ብለዋል። እንደ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር መሠረት ላዕቀ ከሆነ በአምስት ወር ውስጥ ለደረሱት ሦስት ከባድ አደጋዎች መንስዔው ፍጥነት ነው። "ስፍራው ሜዳማ ይምሰል እንጂ መታጠፊያዎች አሉት" ያሉት ምክትል ኮማንደር መሠረት አሽከርካሪዎች አደጋን ተከላክለው ማሽከርከር ይገባቸዋል ሲሉ መክረዋል። ያን ባለማድረጋቸው ብቻ እነዚህን ሦስት አደጋዎች አስተናግደናል ሲሉ ተናግረዋል። • ስልክዎ ጥሩ አሽከርካሪ ሊያደርግዎ እንደሚችል ያስባሉ? የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት በስፍራው ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ይገባል ያሉትን ነገር አጥንተው ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረባቸውን የተናገሩት ምክትል ኮማንደር መሰረት ላዕቀ ወደፊት ፍጥነትን የሚገቱ ነገሮችን እንደሚሰሩ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል። እስከዚያው ግን የተጠናከረ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ አስታውሰዋል። ዋና ኢንስፔክተር ዳግምም መንገዱን የሚያስተዳድረው የፌደራል መንግሥት መሆኑን አስታውሰው የፍጥነት መቆጣጠሪያ ለማሰራት ለሚመለከታቸው አካላት ደብዳቤ መፃፋቸውን ተናግረዋል። የትራፊክ አደጋና የባርቴንዲግ ሙያ ምን ያገናኛቸዋል?
news-52131801
https://www.bbc.com/amharic/news-52131801
የሐጅ ተጓዦች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እስኪለይለት ታገሱ ተባሉ
ዓመታዊው የሙስሊሞች መንፈሳዊ ጉዞ (ሐጅ) ዘንድሮ የመሆኑ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። ሳኡድ አረቢያ "እባካችሁ ተረጋጉ፤ ነገሮች እስኪለይላቸው" ብላለች በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞችን።
የሐጅ ጉዳዮች ሚኒስትር ሙሐመድ ባንቴን ባስተላለፉት መልዕክት አገራቸው ሳኡዲ ከመላው ዓለም ለሚመጡ መንፈሳዊ ተጓዦች ደኅንነት ትጨነቃለች፤ ስለዚህም ነገሮች እስኪለይላቸው የጉዞ እቅድ እንዳታወጡ እንመክራለን ብለዋል። በቀጣይ ሐምሌና ነሐሴ ወራት በትንሹ 2 ሚሊዮን የሐጂ መንፈሳዊ ተጓዦች ወደ መካና መዲና ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ከአምስቱ የእስልምና መሰረቶች አንዱ የሐጅ ጉዞ ሲሆን ማንኛውም የእስልምና ተከታይ አቅሙ ሲፈቅድ ቢያንስ አንድ ጊዜ በሕይወት ዘመኑ የሐጅ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲሳተፍ ይጠበቃል። በብዛት ከሐጅ ቀደም ብሎ ይደረግ የነበረው የኡምራ ሥነ ሥርዓት ዘንድሮ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል። ሆኖም ኡምራ በማንኛውም የዓመቱ ወቅት የሚካሄድ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ነው። በአሁኑ ወቅት ከመንፈሳዊ ተጓዦች ውጭም ቢሆን መካና መዲና እንዲሁም ዋና ከተማዋ ሪያድ ድንበሮቻቸውን ዘግተዋል። ኮቪድ -19 በሳኡዲ አረቢያ 1563 ሰዎች ማጥቃቱ የተረጋገጠ ሲሆን 10 ሰዎችንም ገድሏል። "ሳኡዲ በሁሉም ጊዜና ሁኔታ አማኞችን ትቀበላለች፤ አሁን በመላው ዓለም በሆነው ነገር የፈጣሪን ምሕረት እንጠይቃለን፤ እንግዶቻችንን ደኅንነት ለመጠበቅ ስንል ለጊዜው የጉዞ እቅድ እንዳያደርጉ አደራ እንላለን" ብለዋል ሼክ ባንተን። ሚኒስትሩ ጨምረው እንዳሉት ለኡምራ ከኮሮናቫይረስ ከስተት በፊት ወደ አገሪቱ በገቡ መንፈሳዊ ተጓዦችና እነርሱን ባስተናገዱ ሆቴሎች ላይ ጽዳት እየተደረገ ነው። የተጠረጠሩ እንግዶቹንም ወደ ለይቶ ማቆያ የማስገባት ተግባርም ተካሄዷል። ሚኒስትሩ ለኡምራ ቪዛ ገዝተው የነበሩ አማኞች ገንዘባቸው እንደሚመለስላቸው አረጋግጠዋል።
news-54786957
https://www.bbc.com/amharic/news-54786957
የአውሮፓ ሕብረት 'የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦኛል' አለ
የአውሮፓ ሕብረት ሰኞ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው አስታውቋል።
የአውሮፓ ሕብረት ባንዲራ የሕብረቱ ምክትል ፕሬዝደንትና የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል ባወጡት መግለጫ ነው የሕብረቱን አቋም ያንፀባረቁት። 'ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው' የሚለው መግለጫው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችና ጎረቤት አገራት ውጥረት ለመቀነስ መጣር እንዳለባቸው አሳስቧል። . "ትግራይ ክልል እና የፌደራል መንግሥት ቅድመ ሁኔታዎችን አለዝበው መደራደር አለባቸው" . በትግራይ ያለው ምርጫ የማካሄድ ፍላጎት ወዴት ያመራል? መግለጫው አክሎ ሁሉም ቡድኖች "ግጭት ቀስቃሽ ቃላት" መጠቀም ማቆም እንዳለባቸውና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን መግታት እንዳለባቸው አሳስቧል። "ይህ መሆን ካልቻለ ግን" ይላል መግለጫው፤ "ይህ መሆን ካልቻለ ግን ጉዳቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናውም ነው" ይላል። መግለጫው ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር አገር አቀፍ ውይይቶች እንደሚያስፈልጉ አትቷል። በዚህ ውይይት ላይ ሁሉም የፖለቲካ ተዋናዮች ተሳታፊም እንዲሆኑም ጥሪ አቅርቧል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ መፃዒ ተስፋና ብልፅግና ብሔራዊ መግባባት እንጂ ግጭት መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል የምክትል ፕሬዝደንቱ መግለጫ ያትታል። የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያን ለውጥ ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆኑም ጆሴፍ በመግለጫቸው ተናግረዋል። የሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት መከበር በ2021 [በአውሮፓውያኑ] የሚካሄደው ምርጭ ነፃ፣ ተዓማናኒና ፍትሃዊ እንዲሆን ያግዛል ይላል የሕብረቱ መግለጫ። ምንም እንኳ የሕብረቱ መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎችንም ሆነ የጎረቤት አገራትን ስም ባይጠቅስም በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ ክልል ገዥ ፓርቲ ሕወሓት መካከል ያለው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። አልፎም የኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናትና በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ ሕወሓትን የሚወርፍ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል። በምላሹ የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት ጌታቸው ረዳ መግለጫውን አጣጥለው በማሕበራዊ ድረ ገፆቻቸው ላይ ፅፈዋል። ዛሬ ከሰዓቱን ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል [ዶ/ር] በበኩላቸው ከፌዴራል መንግሥት ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ቢቢሲ የፌዴራል መከላከለያ ሠራዊትንም ሆነ ሌሎች የመንግሥት አካላትን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፤ በማዕከላዊው መንግሥትና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ ሁለቱ አካላት ቅድመ ሁኔታዎችን አለዝበው ድርድር እንዲያደርጉ ማሳሰቡ አይዘነጋም።
news-55482491
https://www.bbc.com/amharic/news-55482491
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በሻይ ስኒ አልኮል እንዳይሸጥ ከለከለ
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ሚኒስትር ምግብ ቤቶች ለደንበኞቻቸው በሻይ ብርጭቆ አልኮል እንዳይቀርቡ አስጠንቅቀዋል።
ደቡብ አፍሪካ ኮሮናቫይረስ ከገባ ለሁለተኛ ጊዜ አልኮል እንዳይሸጥ ከልክላለች። ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ሰዎች አልኮል ጠጥተው "የሚተገብሩት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር" ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምክንያት ነው ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት አዲሱን መመሪያ ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው። በፍጥነት እየተዛመተ ያለው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ደቡብ አፍሪካ ገብቷል። ራማፎሳ አዲሱ ዝርያ በደቡብ አፍሪካ በፍጥት እየተዛመተ ነው ብለዋል። ደቡብ አፍሪካዊያን ለቀብር ካልሆነ በቀር ሰብሰብ ብለው እንዳይታዩ ታግደዋል። ከምሽት 3 እስከ ንጋት 12 ሰዓት የሚፀና ሰዓት እላፊም ታውጇል። ሱቆች፣ ምግብ ቤቶችና መጠጥ ቤቶች ምሽት 2 ሰዓት ላይ በራቸውን እንዲዘጉ ታዝዘዋል። የፖሊስ ሚኒስትሩ ቤኪ ሴሌ ምግብ ቤቶች ሕግ ጥሰው የሚገኙ ከሆነ የንግድ ፈቃዳቸውን ይነጠቃሉ ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አልፎም የተላለፈውን ደንብ ጥሰው በሻይ ስኒ 'ካቲካላ' ሲሸጡ የተገኙ በሕግ ይቀጣሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "በሻይ ስኒ አልኮል እንዳትሸጡ። 0% አልኮል የሚል ምልክት ባላቸው ኮዳዎችውም አልኮል ስትሸጡ እንዳትታዩ። ማታለያ መንገዶቻችሁን እናውቃለን። እንዳትሞክሯት" ብለዋል ሚኒስትሩ። "በሻይ ብርጭቆ ውስጥ ከሻይ ውጭ ሌላ ነገር ብናገኝ - የንግድ ፈቃዳችሁን ነው የምንነጥቃችሁ።" ደቡብ አፍሪካ ባለፈው ሚያዚያና ግንቦት ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ ገደብ ጥላ ነበር። በወቅቱ አልኮልና ትምባሆ በየትኛው ሥፍራ እንዳይሸጡ ተከልክሎ እንደነበር ይታወሳል። ይህ ያልተዋጠላቸው ምግብ ቤቶች ለደንበኞቻቸው በሻይና ቡና ስኒ እንዲሁም በሌሎች ኮዳዎች ጠንከር ያለ ካቲካላ ሲቸበችቡ ቆይተዋል። ባለፈው ሰኞ የተላለፈው አልኮል ያለመሸጥ ገደብ እስከሚቀጥለው ቀር አጋማሽ ድረስ ይቆያል። የሃገሪቱ ፖሊስ ከወታደሮች ጋር በመተባበር ይህን እንዲያስፈፅም ታዟል። ያሳለፍነው እሁድ ደቡብ አፍሪካ አንድ ሚሊዮን በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ያሉባት ብቸኛዋ የአህጉሪቱ ሃገር ሆናለች። ወረርሽኙ ወደ ሃገሪቱ ከገባበት ወርሃ መጋቢት ጀምሮ 27 ሺህ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ሞተዋል። በሃገሪቱ ኮሮናቫይረስ እንደ አዲስ አገርሽቷል። ባለፈው ሳምንት ብቻ 11 ሺህ 700 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። ይህም እስከዛሬ ከታየው ቁጥር ከፍተኛው ነው ተብሏል።
44052561
https://www.bbc.com/amharic/44052561
አዲሱ መድኃኒት ራሰ በራዎችን ይታደግ ይሆን?
ራሰ በራነት የሚያስጨንቃቸው ሰዎች የራስ ቅላቸውን በጸጉር ለመሸፈን የተለያዩ መድኃኒቶች ይሞክራሉ። አዳዲስ መድኃኒቶች ገበያውን ሲቀላቀሉም ሸማቻቸው ብዙ ነው።
ቀደም ሲል ራሰ በራነትን ይፈውሳሉ ከተባሉ መድኃኒቶች በላቀ ውጤታማ እንደሚሆን ተስፋ የተጣለበት አዲስ መድኃኒት ይፋ ተደርጓል። መድኃኒቱ የተሰራው ጸጉር በማሳደግ ምስጉን ከሆኑ ንጥረ ነገሮች መሆኑ ተመልክቷል። የአጥንት መዳከም በሽታን (ኦስትዮፕሮሲስ) ለማከም የሚውል ንጥረ ነገር ይገኝበታል። ሳይክሎስፖሪን ኤ የተሰኘው መድኃኒትና ኤስኤፍአርፒዋ-1 የተሰኘው ፕሮቲን ጸጉር በማሳደግ ስለሚታወቁ በአዲሱ መድኃኒት ተካተዋል። መድኃኒቱ ዌይ-316606 በተባለ ንጥረ ነገርም ተሞልቷል። የመድኃኒት ቅመማ ፕሮጀክቱ መሪ ዶ/ር ናታን ሀውክሻው ለቢቢሲ እንደተናጉት "መድኃኒቱ ጸጉራቸውን ያጡ ሰዎችን ህይወት ሊቀይር ይችላል" በማለት የመድኃኒቱን ፍቱንነት ለመፈተሽ ተጨማሪ ሙከራዎች እንደሚጠብቋቸውም ገልፀዋል። ፒኤልኦኤስ በተሰኘው የሥነ-ህይወት መጽሔት ላይ የወጣው ጥናት እንደሚያሳየው፤ መድኃኒቱን ለመቀመም የጸጉር ቀዶ ህክምና ለማድረግ እየተጠባበቁ የነበሩ 40 ወንዶች ከራስ ቅላቸው የህዋስ ናሙና ሰጥተዋል። የእንግሊዝ የቆዳ ሀኪሞች ማህበር ቃል አቀባይ ጥናቱን "ግሩም" ሲሉ ገልፀውታል። "የጸጉር መሸሽ በራስ መተማመንን ዝቅ በማድረግ ሥነ-ልቦናዊ ተፅእኖ ያሳድራል።" የሚሉት ቃል አቀባዩ መድኃኒቱ አገልግሎት ላይ ከመዋሉ በፊት ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም በርካታ የራሰ በራነት መድኃኒቶች መክሸፋቸውን በማስታወስ "እስከአሁን ዓለም አቀፍ የሆነ ውጤታማ መድኃኒት የለም" በማለት ያስረዳሉ። አዳዲስ ጥናቶች መካሔዳቸውና መድኃኒቶች መቀመማቸው፣ ለራሰ በራዎች ተስፋ ሰጪ ከመሆኑ ጎን ለጎን የህክምና አማራጭን እንደሚያሰፋም ተናግረዋል። አሁን ገበያ ላይ ያሉት መድሀኒቶች ለሴቶችም ለወንዶችም የሚሆነው ሚኖክሲዲልና ወንዶች ብቻ የሚጠቀሙበት ፊናስትራይድ ናቸው። ሁለቱ መድኃኒቶች ለጤና እክል ስለሚዳርጉ ብዙዎች ጸጉር ለማግኘት ቀዶ ጥገና ማድረግ ይመርጣሉ።
news-55329586
https://www.bbc.com/amharic/news-55329586
የናይጄሪያ ወጣቶች ሶስት ፖሊስ ጣቢያዎችን አቃጠሉ
በናይጄሪያ ደቡብ ምስራቅ የምትገኘው አናምብራ ግዛት የሚገኙ የተቆጡ ወጣቶች ሶስት ፖሊስ ጣቢያዎችን አቃጠሉ።
ለቁጣቸው ምክንያት አንድ በሞተር ሳይክል ታክሲ የሚተዳደር ግለሰብ በፖሊስ ተገድሏል መባሉን ተከትሎ ነው። ኤበሬ ንዎግባ የተባለው ግለሰብ የኮሮናቫይረስ የሰዓት እላፊ መመሪያን ጥሰሃል በሚልም ፖሊሶች በቁጥጥር ስር አውለውት ነበር። ፖሊሶቹ ከበውትም እያለ በአካባቢው የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበረ ሲሆን ይህንንም ለመበተን ፖሊሶች ሽጉጥ እንደተኮሱም የአይን እማኞች ተናግረዋል። ከተተኮሱትም ሽጉጦች መካከል የሟቹን ሆድ እንደመታውም የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። "ፖሊሶቹ በሽጉጥ ከመቱት በኋላ መንገድ ላይ ትተውት በሞተር ሳይክላቸው ሄደዋል። በዚህም ምክንያት ሞቷል" በማለት ኦካፎዙ ኡጎቹክው የሚባል ነዋሪ ተናግረዋል። ግለሰቡ የተገደለው ማክሰኞ እለት ሲሆን በቁጣ የነደዱ ወጣቶችም በትናንትናው ዕለት ወደ ከተማው ፖሊስ ጣቢያዎች በመሄድ በእሳት አጋይተዋቸዋል። ሰልፈኞቹ ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ወደ አቅራቢያዋ ባሉ ኤክውሎቢያና ኦኮ ወደተባሉ ከተሞች በመሄድም ነው ፖሊስ ጣቢያዎቹን ያቃጠሏቸው። የግዛቲቷ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ ጆን አባንጋ በበኩላቸው ከግለሰቡ ግድያ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ፖሊሶች ክስ ይመሰረታል ብለዋል።
news-41897057
https://www.bbc.com/amharic/news-41897057
አልማዝ አያና እና ሞ ፋራህ ለዓመቱ ምርጥ አትሌት የመጨረሻው ደረጃ ተፋላሚዎች መካከል ናቸው
የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት ምርጫ 18 ቀናት ያህል ሲቀሩት በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና በወንዶች ደግሞ እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ የመጨረሻው ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታውቋል።
ግሪካዊቷ ኤካትሪኒ ስቴፋኒዲ እና ቤልጄማዊቷ ናፊሳቶ ቲያም የአልማዝ ተፎካካሪ ሆነው ሲቀርቡ ሙታዝ ኢሳ ባርሺም ከኳታር እንዲሁም ዌይድ ቫን ኒከርክ ከደቡብ አፍሪካ ከሞ ፋራህ ጋር የሚፎካከሩ አትሌቶች መሆናቸውን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማሕበር አስታውቋል። የ5 እና 10 ሺህ ሜትሮች ሯጯ አልማዝ ዘንድሮ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በ10 ሺህ ሜትር አንደኛ ስትወጣ፤ በ5 ሺህ ሜትር ሁለተኛ በመውጣት ተሸላሚ መሆኗ ይታዋሳል። አልማዝ ያለፈው ዓመት የሴቶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ውድድር አሸናፊ ነበረች። በሌላ በኩል በወንዶቹ የለንደን የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ትውለደ ሶማሊያ እና የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ሞ ፋራህ ከኒከርክና ባርሺም ጋር ተናንቋል። የ34 ዓመቱ ፋራህ ከትራክ ውድድር ራሱን አግልሎ አሁን ላይ ወደ ማራቶን ማድላቱ ተነግሯል። አሸናፊዎቹ ኅዳር 15/2010 በሞናኮ በሚደረግ ዝግጅት ይፋ እንደሚደረጉ ታውቋል።
news-44818396
https://www.bbc.com/amharic/news-44818396
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአዲስ አበባና ሃዋሳ ጉብኝት ያደርጋሉ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከአዲስ አበባ ባሻገር ወደ ሃዋሳ እንደሚያቀኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምኒዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአሥመራ እንዲሁም ሚንስትር መሥሪያ ቤቱን ጠቅሶ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት እንደገና ይከፈታል። ሚንስትሩ በመግለጫቸውም በአዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው የቀድሞ የኤርትራ ኤምባሲ እድሳት እንደተደረገለት አስታውቀዋል። ሚንስትሩ ሕዝቡ ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል እንዲያደርግ ጥሪ ባደረጉበትና በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ፕሬዝዳንቱ አትዮጵያ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ የተለያዩ ዝግጅቶች ይኖራሉ። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ምዕራፍ • የዐብይ ቀጣይ ፈተናዎች ከእነዚህም መካከል እሁድ ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ 25 ሺህ ሰው የሚታደምበት ዝግጅት እንዳለና በዚሁ ስፍራ ሁለቱም መሪዎች ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ጨምሮ ተገልጿል። በዝግጅቱ ላይ ኢትዮጵያዊያንና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አባላት እንደሚገኙ አመልክተዋል። ኢሳያስ አፈወርቂ ለጉብኝት ቅዳሜ ሐምሌ 07/2010 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ እራሳቸው ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር ማረጋገጣቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ገልፀው ነበር። የኤርትራ ማስታወቂ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል እንደገለፁት ሳዋ ውስጥ በተደረገ ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረውን ግንኙነት ለማጠናከር "በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ ልዑክ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛል ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በኢትዮጵያ የሚደርጉት ጉብኝት ለሦስት ቀናት እንደሚቆይ አመልክተዋል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በ100 የሥራ ቀናት የት የት ሄዱ? ምን ምን ሠሩ? የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ እንደሚመጡ በተለያዩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ከትናንት ጀምሮ ሲዘገብ የቆየ ቢሆንም ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ በኩል ማረጋገጫ አልተገኘም ነበር፡፡ ይህ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝት ከሃያ ዓመታት በላይ ከዘለቀ ጊዜ በኋላ በኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን የሚደረግ የመጀመሪያው ይፋዊ ጉብኝት ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፈው ሳምንት ወደ አሥመራ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና ከከፍተኛ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት በሁለቱ ሃገራት መካከል ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት የሚያሻሽሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ለፕሬዝዳንቱ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሚታደሙበት ዝግጅት ላይ የተለያዩ ታዋቂ ድምፃዊያን ዜማቸውን እንደሚያቀርቡም ለመንግሥት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እየተናገሩ ነው። እስካሁን ማረጋገጥ ባይቻልም አሊ ቢራ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና ሃጫሉ ሁንዴሳ ስማቸው እየተነሳ ካሉት ድምፃዊያን መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው።
news-50457411
https://www.bbc.com/amharic/news-50457411
የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ሐሙስ እንደሚታወቅ ይጠበቃል
በሲዳማ ዞን የሚካሄደው የሕዝበ ውሳኔ ውጤት በሚቀጥለው ሐሙስ አመሻሽ ላይ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ገለጹ።
ሰብሳቢዋ ዛሬ በሐዋሳ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የሕዝበ ውሳኔ ሂደቱ በመራጮች ምዝገባ ከተጀመረ በኋላ መረጃዎችን የማጓጓዝ እና በፍጥነት የማድረስ ችግር መስተዋሉን ልብ ማለታቸውን ጠቅሰው ይህም ችግር ውጤት በማሳወቂያ ጊዜ ላይ ሊንፀባረቅ እንደሚችል አመልክተዋል። ሰብሳቢዋ አክለውም ቢሆንም ግን ይህ ክስተት ውጤት የማሳወቂያውን ጊዜ ከአንድ ወይንም ከሁለት ቀን በላይ ያራዝመዋል ብለው እንደማያስቡ ተናገረዋል። • "ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? የሲዳማ ዞን ራሱን የቻለ ክልላዊ አስተዳደር ይሁን ወይስ አሁን ባለበት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ይቀጥል በሚለው የዞኑ ነዋሪ በመጪው ረቡዕ በሚከናወነውን ሕዝበ ውሳኔ ይታወቃል። በመግለጫቸውም የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 2.3 ሚሊዮን እንደሚጠጋ ተናግረዋል። የሕዝበ ውሳኔው አስፈፃሚዎች በቁጥር ከስድስት ሺህ በላይ ሲሆኑ እነርሱም በ1692 የምርጫ ጣቢያዎች ተሰማርተዋል። የድምፅ ሰጭዎች ምዝገባ ከጥቅምት 27 ቀን እስከ ኅዳር 06 ድረስ የተከናወነ ሲሆን ምዝገባውም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን ምርጫ ቦርድ ከጋዜጣዊ መግለጫው ጋር አያይዞ ያሰናዳው ፅሁፍ ያስረዳል። አንድ መቶ ስድሳ ያህል ቋሚ አና ተዘዋዋሪ ታዛቢዎች ከሲቪል ማኅበረሰብ የተዘጋጁ ሲሆን የተወሰኑት እስካሁን ያለውን ሒደት በመዘዋወር ሲቃኙ ቆይተዋል ብለዋል ብርቱካን። ከዚህም በተጨማሪ ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሚወከሉ ታዛቢዎች ይገኛሉ። ወኪሎችን በተመለከተ ሁለቱም የሲዳማ ዞን ራሱን የቻለ ክልል እንዲሆን እና ካለበት ክልል ጋር እንዲቀጥል የሚጠይቁ ድምፆች እንዲሰሙ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ክልልን እና የሲዳማ ዞንን ቢጠይቅም የዞኑ አስተዳደር ተወካይ ሲያስቀምጥ ክልሉ ሳይወክል ቀርቷል። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች "ይህም ያሳዝናል ብለዋል" ያሉት ሰብሳቢዋ "በሁሉም ጣብያዎች የሲዳማ ዞን ወኪሎች ልኳል። የደቡብ ክልል ምክር ቤት ግን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም፣ ሊልክልን አልቻለም። ከምክር ቤት ቀጥለን አስተዳደሩን ጠይቀናል፣ ተወካይ አልላኩልንም።" ከዚህም የተነሳ ወደምርጫ ጣቢያዎች የተንቀሳቀሰ አካል ማግኘት የሚችለውን የአንደኛውን ወገን ብቻ ወኪል መሆኑን ጨምረው ተናገረዋል። የሕዝበ ውሳኔ ሒደቱን በደረሰው ሪፖርት እና በመስክ ጉብኝቶች ታዝቧቸው የእርምት እርምጃዎች መካከል የአስተዳደር አካላት እና የአገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ በምርጫ ጣቢያዎች በሁለት መቶ ሜትር ርቀት መገኘት የማይገባቸው ሰዎች እንዲሁም የተከለከሉ ምልክቶች መታየት አንደኛው እንደሆነ የምርጫ ቦርድ መግለጫ አመልክቷል። • ስጋት ያጠላበት የሲዳማ የክልልነት ጥያቄና የሀዋሳ ክራሞት የሕዝበ ውሳኔው በሚካሄድበት ዕለተ ረቡዕ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች ዝግ እንደሚሆኑ ቀድሞ ተገልፆ የነበረ ሲሆን፤ ይህ የሥራ ክልከላ የግል የንግድ ተቋማትንም እንደሚጨምር ብርቱካን ተናግረዋል። እንደ ሰብሳቢዋ ገለፃ ለሕዝበ ውሳኔው የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ከአዲስ አበባ ተነስተው በመከላከያ ሠራዊት አባላት ጥበቃ እየተደረገለት ወደዞኑ በመምጣት ላይ ነው። ከፍተኛ የተመዝጋቢ ቁጥር የታየባቸውን የምርጫ ጣቢያዎችን በመለየት ተጨማሪ 175 ጣቢያዎችን ቀደሞ ምዝገባ ከተደረገባቸው ጣቢያዎች ጎን የሚያቋቁም መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።
news-53337603
https://www.bbc.com/amharic/news-53337603
ዴሞክራቱ ባይደን ምርጫውን ካሸነፉ የትራምፕን የዓለም ጤና ድርጅት ውሳኔ እንደሚቀለብሱ ተናገሩ
የዴሞክራት እጩው ጆ ባይደን ምርጫውን ካሸነፉ፤ አሜሪካን ከዓለም ጤና ድርጅት ያስወጣውን የፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ እንደሚቀለብሱ ተናገሩ።
ፕሬዘዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት እንደምትወጣ የተናገሩት ግንቦት ላይ ነበር። ሂደቱን የጀመሩት ደግሞ በዚህ ሳምንት ነው። ሂደቱ ቢያንስ አንድ ዓመት ይወስዳል። ትራምፕ፤ የዓለም ጤና ድርጅት በቻይና ቁጥጥር ሥር ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው ከድርጅቱ አሜሪካን ለማግለል ውሳኔ ያሳለፉት። ለፕሬዘዳንትነት በሚፎካከሩት ትራምፕና በባይደን መካከል የአስር ነጥብ ልዩነት አለ። በርካታ መራጮች ወቅታዊው አስተዳደር ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሰጠው ምላሽና የአገሪቱ ምጣኔ ኃብት ጉዳይ ላይ ጥያቄ አላቸው። በአገሪቱ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሲሆኑ፤ ከ130,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ጆ ባይደን ባለፈው ማክሰኞ በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት፤ አሜሪካ የጤናን ጉዳይ በተመለከተ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ብትተባበር መልካም ነው። “ፕሬዝዳንት ከሆንኩ በኋላ በመጀመሪያው የሥራ ቀን የዓለም ጤና ድርጅትን በተመለከተ የተወሰነውን ቀልብሼ ወደ ዓለም አቀፍ መሪነታችን እንድንመለስ አደርጋለሁ” ብለዋል። በአገሪቱ ምክር ቤት የውጪ ጉዳይ ክፍል ካሉ ዴሞክራቶች አንዱ የሆኑት ሮበርት መነንዴዝ፤ “በወረርሽኝ ወቅት ፕሬዘዳንቱ አሜሪካን ከዓለም ጤና ድርጅት አስወጥተዋል፤ አሜሪካን የሚያሳምም፣ አሜሪካውያንን ብቸኛ ሚያደርግ ውሳኔ ነው” ብለዋል። ቻይናም ድሃ አገራት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል ስትል የፕሬዘዳንት ዶናልድን ውሳኔ ኮንናለች። የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዛሆ ሊያን “የአሜሪካ ውሳኔ ዓለም አቀፍ ትብብርን ያንኳስሳል። በተለይም ዓለም አቀፍ ድጋፍ የሚፈልጉ ታዳጊ አገሮች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል” ብለዋል። አሜሪካ ዓለም አቀፍ ግዴታዋን እንድትወጣም አሳስበዋል። አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት የምትወጣው ለምንድን ነው? አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ለሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት፤ የዓለም ጤና ድርጅት የአሠራር ለውጥ እንዲያደርግ አሜሪካ ብትጠይቅም ድርጅቱ ፈቃደኛ አልሆነም። አሜሪካ ከድርጅቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማቋረጥ የተወሰነውም ለዚህ ነው። ፕሬዘዳንት ትራምፕ፤ ድርጅቱ ራሱን እንዲያሻሽል ግንቦት ላይ የ30 ቀን ገደብ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል። ካልሆነ ግን ከድርጅቱ ወጥተው ድጋፋቸውን ወደ ሌሎች ዓለም አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና የተራድኦ ድርጅቶች እንደሚያዞሩ ተናግረዋል። “ቻይና ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ቀስቅሳለች። በቻይና መንግሥት ስህተት ሳቢያ ዓለም እየተንገላታ ነው” ብለውም ነበር። ፕሬዘዳንቱ ማስረጃ ባያቀርቡም፤ ቻይና የዓለም ጤና ድርጅት ዓለምን እንዲያሳስት አድርጋለች ሲሉ ተደምጠዋል። አሜሪካ ከድርጅቱ አባል አገራት ከፍተኛውን የገንዘብ አስተዋጽኦ ታደርጋለች። ባለፈው ዓመት 440 ሚሊዮን ዶላር የደጎመች ሲሆን፤ ይህም ከድርጅቱ ጠቅላላ በጀት 15 በመቶው ነው። እአአ 1948 ላይ በወጣ የአገሪቱ ሕግ መሠረት፤ አሜሪካ የአንድ ዓመት ማሳሳቢያ ሰጥታ፣ ክፍያ ፈጽማ ከድርጅቱ መውጣት እንደምትችል ተደንግጓል። 1948 ላይ የተቋቋመው የዓለም ጤና ድርጅት 194 አባላት አሉት። ከአባል አገራት ክፍያ በተጨማሪ በበጎ ፍቃደኞች እርዳታ ይንቀሳቀሳል።
news-56391279
https://www.bbc.com/amharic/news-56391279
ተቃዋሚዎች የአርጀንቲናው ፕሬዝደንት ያሉበትን መኪና መስታወት ሰባበሩ
በርካታ ተቃዋሚዎች የአርጀንቲው ፕሬዝደንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝን የያዘችውን መኪና ማጥቃታቸው ተሰማ።
ይህ የሆነው ፓታጎኒያ በተሰኘችው ግዛት ሲሆን ፕሬዝደንቱ 'ሚኒባስ' ውስጥ ነበሩ ተብሏል። በደቡባዊቷ የአርጀንቲና ክፍለ ግዛት ቹቡት በሚገኝ አንድ የሕብረተሰብ ማዕከል ውስጥ የነበሩት ፕሬዝደንቱ በተቃዋሚዎች ተከበው ድንጋይ ተወርውሮባቸዋል። ተቀዋሚዎቹ የፕሬዝደንቱ መኪና በመክበብ ተሽከርካሪዋ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። ፕሬዝደንቱ ወደ ሥፍራው ያቀኑት በአካባቢው የተነሳውን ሰደድ እሣት ተከትሎ አንድ ሰው መሞቱን በርካቶች መጎዳታቸውን በማስመልከት ነው። ነገር ግን ተቃውሞው በቹቡት ግዛት ሊካሄድ ነው የተባለውን የማዕድን ቁፋሮ የተመለከተ ነው። ተቃዋሚዎቹ መንግሥት ለትላልቅ ማዕድን ቆፋሪ ድርጅቶች ፈቃድ ለመስጠት ረቂቅ ማውጣቱን በመቃወም ድምፃቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። አካባቢው ወርቅ፣ ብርና ዩራኒየምን በመሳሰሉ ማዕድናት የበለፀገ ነው ሲል ክላሪን ጋዜጣ ዘግቧል። በሥፍራው የነበረውን ግርግር የሚያሳዩ ተንቃሳቃሽ ምስሎች ላይ ፕሬዝደንቱ ከማሕበረሰብ ማዕከሉ ወጥተው ወደ መኪናቸው ሲሄዱ ተቃዋሚዎች የማዕከሉ በር ላይ ተኮልኩለው ይታያሉ። ከዚያ ተቃዋሚዎቹ ፕሬዝደንቱን ተከትለው የተሳፉበትን ሚኒባስ ሲደበድቡና እንዳይንቀሳቀስ ሲያግዱት ተስተውሏል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች የመኪናዋ መስታወት ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ነበር። ምንም እንኳ ፕሬዝደንቱ የነበሩባት መኪና ሕዝቡን ተሻግራ ማለፈው ብትችልም በርካታ መስኮቶች ተሰባብረዋል። በአርጀንቲናዋ ፓታጎኒያ ግዛት የተነሳው ሰደድ እሣት በርካቶች ቀያቸውን ጥለው እንዲወጡ አስገድዷል። በሰደዱ እሣቱ ምክንያት እስካሁን ድረስ ቢያንስ 200 ቤቶች ተቃጥለዋል። የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውና የውሃ አቅርቦት ማግኘት ያልቻሉ በርካቶች ናቸውም ተብሏል። ምንም እንኳ የሰደድ እሣቱ መንስዔ ባይታወቅም የሃገር ውስጥ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ይላል።
news-48332119
https://www.bbc.com/amharic/news-48332119
ሳዑዲ አረቢያ ለሱዳን የገንዘብ ድጋፍ አደረገች
ሱዳን ያጋጠማትን ምጣኔ ኃብታዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ለማስታገስ ይረዳታል በሚል ሳዑዲ አረቢያ 250 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ በሱዳን ማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ እንዳደረገች አስታውቃለች።
የገንዘብ ስጦታው ከዚህ ቀደም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከለገሰችው ገንዘብ ጋር ተደምሮ አገሪቷ የገባችበትን የምጣኔ ኃብት ቀውስ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ያስታግስላታል ተብሏል። ይህም የአገሬው ሰው ገንዘብ ለማውጣት በባንክ ደጅ የሚያደርገውን ሰልፍ ይቀንሳልም ተብሏል። በሱዳን ከባንክ ወጪ ማድረግ የሚቻለው ከፍተኛው ገንዘብ 40 ዶላር (አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር ገደማ) ሲሆን፤ ነዳጅ ለመሙላትም በሚያቃጥለው ሙቀት ለሰዓታት መሰለፍን ይጠይቃል። በአውሮፓውያኑ 2011 ደቡብ ሱዳን የአገሪቱን አብዛኛውን የነዳጅ ሃብት ይዛ ከተገነጠለች ወዲህ ሱዳን ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። • "ልጄ ከአሁን አሁን ነቅቶ ይጠራኛል እያልኩ ስጠብቅ 12 ዓመት ሆነኝ" • ኢትዮጵያ ለሱዳንና ለጅቡቲ ኃይል ማቅረብ ማቋረጧ ተገለፀ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ይጠቀሙት የነበረውና ሥልጣናቸውን ለማራዘም ሲሉ ያወጡት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው። የቀድሞው ፕሬዚደንት ኦማር አል በሽር አብዛኛውን በጀት ያውሉት የነበረው ለደህንነትና ለወታደራዊ ወጭዎች ነው። ፕሬዚደንቱ ከቻይና፣ ኳታርና ሳዑዲ አረቢያ ጋር በፈጠሩት ጥብቅ ግንኙነትም የገንዘብ ድጋፍና ብድር ያገኙ ነበር፤ የተደረገላቸውን የገንዘብ ድጋፍ ለመክፈልም በየመን በሳዑዲ ለሚመራው ጦር በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ልከዋል። በሱዳን ከፍተኛ ሆነ የሕዝብ ተቃውሞ የተቀሰቀሰው በአገሪቱ የምግብና የነዳጅ ዘይት ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ ሲሆን ባለፈው ወር ፕሬዚደንቱ ከሥልጣናቸው መውረዳቸው ይታወሳል። • ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን? ሱዳን በወታደራዊው የሽግግር መንግሥት እየተዳደረች ሲሆን ተቃዋሚዎች ግን እስካሁን ድረስ አገሪቷ እየተመራች ያለችው በቀድሞው ፕሬዚደንት ኦማር አል በሽር ወታደር ሲሆን ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ጥብቅ ግንኙነትም አላቸው ብለዋል። በመሆኑም አገሪቷን ለማረጋጋት አጠቃላይና ተገቢ የሆነ ለውጥ እንፈልጋለን በማለት ባለው የሽግግር መንግሥት ላይ ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል። አገሪቷን በዚህ የሽግግር ወቅት የሚመሩት ጄነራሎች ይህንን ሕልማቸውን ለማሳካት እንደቆሙ እየተናገሩ ነው።
news-46423331
https://www.bbc.com/amharic/news-46423331
የእጮኝነት ቀለበት ሴቶችን እንዴት ይገልፃቸዋል?
ጥንዶች ወደ ትዳር ከመግባታቸው አስቀድሞ ለትዳር ይተጫጫሉ፤ መተጫጨታቸውን የሚያሳዩበት አንዱ መንገድ ደግሞ ለሴቷ ቀለበት ማድረግ ነው።
ማቲልዴ ባታገባም ከሕይወት አጋሯ ጋር ነው የምትኖረው እዚህ ላይ ወንዱ በእጮኝነት ላይ እያለ ለምን ቀለበት አያደርግም? የሚል ጥያቄ ወደ እዕምሮዎ ይመጣ ይሆናል። በእርግጥ ወንዶች ፈርጥ ያለው፣ ያማረ፣ የእጮኝነት ቀለበት ለምን አያጠልቁም? ሴቶች ብቻ ለምን ያጠልቃሉ? የማቲልዴ ጥያቄ ነው። • ሴቶችና ወጣቶች የራቁት የተቃውሞ ፖለቲካ የሚዲያ ባለሙያዋ ማቲልዴ ሱስከም ግን ይህ በባህላችን ለሴቶች የሚጠለቀው በጣም ውድ የሆነ የእጮኝነት ቀለበት ለሴቶች የውድቀትና የጥገኝነት ማሳያ ነው ትላለች። እንዲህ ዓይነት ድርጊቶችም ሊያበቃላቸው ይገባል ስትልም በተደጋጋሚ ፅፋለች፤ መለወጥ ያለበት ልማድ ነው ስትል አበክራ ትሞግታለች። ሁለት ጊዜ ትዳር መስርታ እንደነበርና ወደፊትም ልታገባ እንደምትችል የምትናገረው ማቲልዴ "መቼም ቢሆን ቀለበት አልፈልግምም፤ አላደርግምም" ትላለች። ቀለበት ፀረ ሴቶች እንደሆነ ታምናለች፤ ጥገኛ ያልሆነች ሴት ላይ ያለውን አመለካከት የሚቃረን ነው፤ ይህም ማለት ቀለበቱን ያደረገችው ሴት የሌላ ናት ፤ተይዛለች የሚል መልዕክት አለው። • በአዲስ አበባ አፍላ ወጣቶች በከፍተኛ መጠን በኤች አይቪ እየተያዙ ነው ከዚህም ባሻገር አቅምንና የኑሮ ደረጃን የምናሳይበት እየሆነ ነው፤ በአሜሪካ ሃገር ቀለበቱን ለመግዛት በአማካይ 6351 ዶላር ( 172 ሺህ ብር ገደማ) ያወጣሉ። የአልማዝ ፈርጥ ያለው ትልቅ ቀለበት፤ ቀለበቱ ምን ያህል ውድ እንደሆነ ያመላክታል። በውስጠ ታዋቂ በምን ያህል እንደተሸጠች ያሳብቃል የምትለው ማቲልዴ በምትኖርበት አሜሪካ የሚኖሩት ጓደኞቿ በሙሉ ያላቸው አመለካከት ከእርሷ በተቃራኒ እንደሆነ ትናገራለች። "አብዛኞቹ በእጮኝነት የተደረገላቸው የአልማዝ ቀለበት አላቸው፤ የአንዳንዶቹ ብዙ ገንዘብ የፈሰሰበት ትልቅ ነው። በኩራት ፎቶ እየተነሱ በየማህበራዊ ሚዲያው ይለጥፉታል፣ ይኩራሩበታል፤ ከእኔም ጋር ስንገናኝ ያሳዩኛል፤ ሰው እንዲያይላቸው ይፈልጋሉ" ትላለች። ለእርሷ ግን የሚያስገርምና የሚያስቅ ጉዳይ እንጂ ምንም ደስታን የሚሰጥ አይደለም። በእርግጥ ይህንን ሃሳቧን የሚቃወሙት በርሷ ዕድሜ የሚገኙ ጓደኞቿ ብቻ ሳይሆኑ ልጇም በአስተሳሰቧ ታሾፍባታለች። ምክንያቱ ደግሞ ወደ ፍቅር ዓለም ስትገባ እርሷም በጣም ውድ የሆነና አብረቅራቂ ቀለበት እንዲደረግላት ስለምትፈልግ ነው። • የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው? ድርጊቱ ሲወርድ ሲወራረድ የመጣና ያደገችበት ባህል በመሆኑ የልጇን ሕልምና ሃሳብ ትረዳለች፤ ቢሆንም ግን በእዚህ አስተሳሰብ መቼም እንደማትስማማ ጠንካራ አቋሟ አላት። ለጋብቻ አንድን ሰው እጩ የሚደረግበት የተለመደ ሥርዓት ያሰለቻታል፤ ባልየው በጉልበቱ ተንበርክኮ፣ የሚያጫትን ሴት እጅ ይዞ፤ 'ታገቢኛለሽ ?' የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ያስገርማታል። ይህን ድርጊት የሚፈፅሙት ደግሞ ሰዎች በተሰበሰቡበት፣ ባልታሰበ አጋጣሚ፣ እርሷ ምንም መናገር በማትችልበትና እድል በማይሰጥበት ቦታ አሊያም በካሜራ ፊት በመሆኑ ሴቷን ተጋላጭ ማድረግ ለማቲልዴ ተቀባይነት የለውም። ጋብቻ አንዱ ለአንዱ የሚያሳያው ሳይሆን የሁለቱ የጋራ ስምምነት መሆኑን እንደ ምክንያት ታስቀምጣለች። "የቀድሞው ባለቤቴ የጋብቻ ጥያቄ ሲያቀርብልኝ በተለመደው መልኩ ነበር፤ በወቅቱ ጣም ነበር ያሳቀኝ፤ ግን ያሰብነው አልሆነም፤ ጋብቻችን አልሰመረም፤ ምክንያቱም ዋናው ነገር ተግባቦት ነው " በማለት በቀለበት ሳይሆን የጥንዶቹ ውሳኔ ነው መሆን ያለበት ስትል ታክላለች። ምንም እንኳን ብዙም ያልተለመደና ቁጥራቸው አናሳ ቢሆንም ተንብርክከው የጋብቻ ጥያቄ የሚያቀርቡ ሴቶችም አሉ። • «የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ያሳስበኛል» ፖፕ ፍራንሲስ ቢሆንም ግን ማህበረሰቡም ሆነ ሚዲያ ሴቶች ህልም እንዲኖራቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ማስተማር እንዳለባቸው ታምናለች፤ ቀለበቱን አድርግላት (Put a ring on it) የሚለውን የቢዮንሴን ዘፈን እየሰሙ ያድጉና ጋብቻ ሁሉንም የሕይወታቸውን ችግር እንደሚፈታላቸው ያስባሉ። ይሁንና ሴቶች ጋብቻንና ቀለበትን ከማለም ይልቅ ጥገኛ ላለመሆን፤ በትምህርት የተሻለ ስለመሆን፣ ስለ እድገት፣ እንዴት ደስተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቢያስቡ ይበጃል ስትል ታስረዳለች። "አንዳንዴ ይሄን የሕይወት ፍልስፍናዬን በጋዜጣዎች አሊያም በድረ ገፆች ላይ ስፅፍ ሰዎች ቀንደኛ የሴቶች መብት ተሟጋች አድርገው ያስቡኛል" የምትለው ማቲልዴ አንዳንዶቹ እንደውም 'የፍቅር ጠር' እያሉ እንደሚጠሯት ትናገራለች። እርሷ ግን እንደ እኔ የፍቅር ሰው የለም ትላለች። የማትስማማበት ጉዳይ ቢኖር ቀለበት ይዞ ሊያጠልቅላት የሚመጣን ወንድ መጠበቁ ላይ ነው። ጋብቻ አንድን ሰው ማፍቀርና ለፍቅሩም ተገዥ መሆን እንጂ ቀለበት ማጥለቁ ላይ አይደለም ትላለች።
news-48822307
https://www.bbc.com/amharic/news-48822307
ጥሩ ሰው ምን አይነት ነው?
የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት ይችላሉ ወይስ ሁሉም ሰው ሊያጠቃዎት እንደሆነ ያስባሉ? ከሰዎች ጋር በሚያደርጉት ንግግር ሁሌም ግልጽ ነዎት ወይስ ሁሉንም ነገር አስልተውና ተጠንቅቀው ነው የሚናገሩት?
ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሽ በዕለት ተዕለት የህይወት ዘይቤዎ በቀላል አገላለጽ "ቅዱስ" የሚባሉ አይነት ሰው ስለመሆንዎ እና አለመሆንዎ የመናገር አቅም አላቸው። በቅርቡ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ባወጡት መዘርዝር መሰረት ሰዎችን ጥሩ የሚያስብሏቸው ምን አይነት ባህሪያት እንደሆኑና መጥፎም የሚያስብሏቸው የትኞቹ እንደሆነ አስቀምጠዋል። • ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች ከሁለት አስርታት በፊት የወቅቱ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች የሰው ልጅን ጥሩም ሆነ መጥፎ ባህሪያትን ለመረዳት በማሰብ ሦስት ዋና ዋና መገለጫዎችን ለይተው ነበር። የመጀመሪያው ከእራስ ጋር በፍቅር መውደቅ ወይም 'ናርሲሲዝም' ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራስን ጥቅም ለማስጠበቅ የትኛውንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ መሆንን የተመለከተ ነው። የመጨረሻው መገለጫ ደግሞ ከባድ የሥነ ልቦና ችግር ማስተናገድ ነው። ከዚህ ግኝት በኋላ የዘመኑ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እነዚህን መገለጫዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ሰዎች በሥራ ቦታ እንዴት ስኬታማ እንደሚሆኑ፣ ግንኙነቶች እንዴት እንደሚመሰረቱና እንደሚፈርሱ እንዲሁም ውስጣዊ እርካታ እንዴት እንደሚገኝ ለማጥናት ሞክረዋል። በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ባለሙያና መምህር የሆኑት ስኮት ቤሪ ኮፍማን እንደሚሉት ሰዎች ብዙ ጊዜ ከጥሩው ባህሪያቸውና ማንነታቸው ይልቅ ወደ መጥፎውና በመጠራጠር የተሞላውን ውስጣዊ ስሜት እንደሚመርጡ ይናገራሉ። "ልናበረታታውና ሁሌም ልንንከባከበው የሚገባንን ባህሪ ለምን ገሸሽ እንደምናደረገው አይገባኝም'' ይላሉ። ስኮት ቤሪ ኮፍማን ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በሰሩት ጥናት መሰረት ደግሞ ሰዎች ጥሩ ባህሪ እንዳላቸው ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ መገለጫዎችን አስቀምተዋል። በዚህም መሰረት በጥናቱ የተሳተፉት ሰዎች፤ የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት እና ይቅር ባይነት፣ የሌሎችን ስኬት ማድነቅ እንዲሁም ሰዎችን ያለፍላጎታቸው አንድ ነገር እንዲያደርጉ ከማስገደድ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ምልክቶችን አሳይተዋል። የመጀመሪያው መገለጫ 'ሂዩማኒዝም' ወይም ሰብአዊነት ነው። ይህም የሰዎችን ክብርና ሙሉ አቅም በቀላሉ መረዳት መቻል ነው። ሁለተኛው 'ካንቲያኒዝም' የሚባል ሲሆን ስያሜው ኢማኑኤል ካንት ከተባለው ፈላስፋ የመጣ ሲሆን ሰዎችን ከእራሳችን መነጽር ብቻ መመልከት እንደሌለብን የሚያትት ነው። ሦስተኛው ደግሞ 'ፌዝ ኢን ሂዩማኒቲ' በሰው ልጆች እምነት መጣል እንደ ማለት ሲሆን በዚህኛው መገለጫ ሰዎች ሁሌም ጥሩ ናቸው ብሎ መረዳትና የትኛውም ሰው ማንንም ለመጉዳት አያስብም ብሎ ማሰብን ያካትታል። • የ 'ምን ልታዘዝ' ድራማ ሰምና ወርቅ የሥነ ልቦና ባለሙያው ዊሊያም ፍሊሰን እንደሚለው የሰው ልጆች በባህሪያቸው ጥሩ ናቸው ብሎ ማሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነው። እሱ እንደሚለው ሰዎች በአጠቃላይ ጥሩ ናቸው ብለን ባሰብን ቁጥር እራሳችንን ከሰዎች መከላከል አለብን የሚለው ተፈጥሮአዊ ስሜት እየቀነሰ ይመጣል። ስለዚህም መጥፎ ነገር እንኳን ቢፈጽሙ ለመቅጣት ወይም ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ከማሰብ ይልቅ ይቅርታ ማድረግ ቀላል ይሆናል ማለት ነው። ስኮት ቤሪ ኮፍማን አረጋግጫለሁ እንደሚሉት በሄዱበት ሁሉ ለሰዎች ደግነትንና ጥሩነትን የሚያሳዩ ሰዎች በህይወታቸው ደስታና የእርካታ ስሜትን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ከዚህም ባለፈ ከፍ ያለ የራስ መተማመንና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ይስተዋልባቸዋል። ነገር ግን የጥሩ ሰዎች መገለጫዎች ምንድናቸው? ፍቅር፣ ደግነት፣ የቡድን ሥራ፣ ይቅር ባይነት፣ አመስጋኝነት፣ በሰዎች ስኬት አለመቅናት፣ አሳቢነት ወይስ ለብዙዎች ጥቅም መቆም? መረር ያለና መጥፎ ሊባል የሚችል አይነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ ማከናወን የሚችሉና ደፋሮች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የመምራትና የፈጠራ አቅማቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ጥናቱ ይጠቁማል። • በጂንስ የተሞሸሩት ጥንዶች ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ጥሩ የሚባል ባህሪ ያላቸው ሰዎች ያለምንም ችግር ስኬታማ ይሆናሉ ማለት ከባድ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ መጥፎ የሚባሉትን ባህሪዎች መቀላቀል ከባድና አስቸጋሪ የሚባሉ ሁኔታዎችን ለመወጣት በእጅጉ ሊጠቅሙ ይችላሉ። ዋናው ሚስጥር ያለው ጥሩ በሚባሉትና መጥፎ በሚባሉት ባህሪያት መካከል ማረፍያ ቦታ ማግኘት መቻል ነው።
50909603
https://www.bbc.com/amharic/50909603
የዘረፈውን ገንዘብ 'መልካም በዓል' እያለ የበተነው አዛውንት በቁጥጥር ስር ዋለ
ሰኞ ምሳ ሰዓት ላይ በኮሎራዶ ወደሚገኘው የአካዴሚ ባንክ የ65 ዓመቱ አዛውንት ያመሩት እንደ 'ገና አባት' ስጦታ ይዘው ቸር እየተመኙ በዓሉን ለማድመቅ አልነበረም።
ለመዝረፍ ነው። ባንኩን ከዘረፉ በኋላ ጎዳና ላይ በመውጣት "መልካም በዓል፤ መልካም ገና'' እያሉ ገንዘቡን መበተን። • ሲሰርቁ የታዩት አምባሳደር ሥልጣን ለቀቁ • የአንድ የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች ሰጥመው ሞቱ ምናልባት በአእምሯቸው ውስጥ የገና አባትን ለሚጠብቁ ምንዱባን ልድረስላቸው ብለው ይሆናል። ይህ ግን ከእርሳቸው ቃል አልተረጋገጠም። ጢማሙን አዛውንትና ተግባራቸውን ያዩ ለኮሎራዶ ጋዜጠኞች ቃላቸውን ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል። " ባንኩን ዘርፎ ከወጣ በኋላ ገንዘቡን በየአቅጣጫው አርከፈከፈው" ፖሊስም " ነጭ ጢማም አዛውንት" ሰኞ ምሳ ሰዓት ላይ በኮሎራዶ አካዴሚ ባንክን ዘርፏል ሲል አስረድቷል። የዓይመን እማኙ አክለው " 'መልካም ገና' እያለ ገንዘቡን ከቦርሳው እያወጣ በተነው።" ብለዋል። ሁኔታቸውን ለተመለከተ ባንክ የሚዘርፉ ሳይሆን እርዳታ የሚጠይቁ አዛውንት ይምሰሉ እንጂ እርሳቸው ግን ፊቴ ቢያረጅም ልቤ አላረጀም ያሉ ይመስላል። • አሜሪካ አነፍናፊ ውሻዎቿን ወደ ግብጽና ዮርዳኖስ ላለመላክ ወሰነች ባንኩን ከዘረፉ በኋላ፤ ገንዘቡን እንደቄጤማ ጎዳናው ላይ ጎዝጉዘው ወደ ስታር ባክስ ቡና መሸጫ ሄዱ። አንድ ወፍራም ቡና እንደወረደ ለማለት አልነበረም። ፖሊስ ለመጠበቅ። ፖሊስ እንዳልጠፋብህ እዚህ ተቀምጫለሁ ዓይነት ነው። ፖሊስ ካቴናውን እያቅጨለጨለ መጥቶ ከወሰዳቸው በኋላ ቁጥር ሰጥቶ ስም አስፍሮ ፎቶ አንስቶ እስር ቤት ወርውሯቸዋል። በወቅቱ በዚያ መንገድ ላይ እግር ጥሏቸው የተገኙ መንገደኞች እጃቸው የቻለውን ያህል ሰብስበው አልወሰዱም። ይልቅስ አንድ ሁለት ብለው ቆጥረው ለተዘረፈው ባንክ መመለሳቸው ታውቋል። ኮሎራዶ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ግለሰብ ስሙ ዴቪድ ዋይን እንደሚባል ገልጾ እድሜው 65 ነው ካለ በኋላ፤ ማንም አልረዳውም ወንጀሉን ብቻውን ነው የፈፀመው ብሏል።
news-57184357
https://www.bbc.com/amharic/news-57184357
ባለፉት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ስምንት የእርዳታ ሠራተኞች መገደላቸው ተነገረ
በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ስምንት የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞች መገደላቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ።
ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ከኅዳር ወር ወዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ ከተገደሉት የረድኤት ተቋማት ሠራተኞች ሰባቱ ግጭት ባጋጠመበት በትግራይ ክልል ውስጥ መሞታቸው ሲታወቅ አንደኛው ግን በሌላ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ መገደሉን ገልጿል። የተገደሉት የእርዳታ ሠራተኞች ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን ለመደገፍ ሥራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ መሆኑን የኤምባሲው መግለጫ አመልክቶ፤ ድርጊቱን አጥብቆ አውግዞታል። እንዲህ አይነቱ ጥቃት እንዲቆም የጠየቀ ሲሆን ተጠያቂዎቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል። በዚህም የአሜሪካ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች ለረድኤት ድርጅቶች ሠራተኞች ህይወት እና ሥራ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። መግለጫው ጨምሮም የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ ሥራ የሚያከናውኑ ሠራተኞችን ጨምሮ የሰላማዊ ሰዎችን ደኅንነት የመጠበቅ ዋነኛ ሚናው መሆኑን ጠቅሶ፤ የታጠቁ ኃይሎችም በዓለም አቀፍ የሰብአዊ አቅርቦት ሕግ መሠረት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል። ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች የረድኤት ሠራተኞችና የሚያቀርቡት እርዳታ ደኅንነት ተጠብቆ ሳይገደብ፣ ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ድጋፍ ለሚፈልጉ ለሁሉም ሰዎች እንዲደርስ እንዲያደርጉ ጠይቋል። በቅርቡ የተከሰተውን የእርዳታ ሠራተኛ ግድያ ያነሳው መግለጫ፤ የዩኤስኤይድ አጋር የሆነ ድርጅት ሠራተኛ ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ ትግራይ ቆላ ተንቤን ውስጥ "በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች" መገደሉን ገልጿል። መግለጫው የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንዳለው የእርዳታ ሠራተኛው በግልጽ የረድኤት ሠራተኛ መሆኑን በመግለጽ እንዳይገድሉት ሲማጸን እንደነበር አመልክቷል። እንዲህ አይነቱ ሁኔታ "የእርዳታ ሠራተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ በየዕለቱ እየተባባሰ ባለ የደኅንነት ሁኔታ ውስጥ እየሰሩ መሆናቸውንና አሳሳቢ የሰብአዊ እርዳታ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ቀውስን ያንጸባርቃል" ብሏል። መግለጫው በማጠቃለያው ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ በእርዳታ ሠራተኞችና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎቹን እንዲያወግዝና ምርመራ በማድረግ አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ አጥብቆ ጠይቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤአይዲ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት በትግራይ ክልል ውስጥ "የከፋ ረሃብ" እንዳለ አስጠንቅቀዋል። ኃላፊዋ እንዳሉት የአሜሪካ የአደጋ ጊዜ የምግብ አቅርቦት ክትትል ተቋም በአካባቢው "ደረጃ 5 የአደጋ ስጋት" እንዳለ መለየቱን ጠቅሰው ይህም ከፍተኛው እንደሆነ ገልጸዋል። ሳማንታ ጨምረውም በክልሉ ያለው ግጭት እንዲቆምና ለእርዳታ ሠራተኞች መንገዶች እንዲመቻቹ ጠይቀዋል። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም እንደሚለው በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ክልል ውስጥ 5.2 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እርዳታ አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል።
news-52430765
https://www.bbc.com/amharic/news-52430765
ኮሮናቫይረስ፡ የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለባቸው አገራት ያሉ ሙስሊሞች ረመዳንን እንዴት እያሳለፉ ነው?
የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አገራት ያሳለፉትን እርምጃዎች ተከትሎ መስጊዶች በመዘጋታቸውና መሰባሰብ በመከልከሉ ምክንያት በዓለም ላይ ያሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ዘንድሮ ረመዳንን በተለየ መንገድ እያሳለፉ ነው።
በኔፓል፤ ካትማንዱ በወረርሽኙ ሳቢያ መንግሥት የጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ተከትሎ አንድ ሙስሊም በረመዳን የመጀመሪያው ቀን ብቻውን ሰግዷል። በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ቦታ በሚሰጠው የረመዳን ወር፤ 1.8 ቢሊየን የዓለማችን ህዝቦች ጎህ ሲቀድ ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከሲጋራ እንዲሁም ከግብረ ስጋ ግንኙነት የሚታቀቡበት ነው። በዚህ ወቅት ቤተሰብና ወዳጆች ሰብሰብ ብለው ማፍጠር፣ በሕብረት ማምለክና መስገድ የተለመደ ነው። ይሁን እንጅ በዚህ ዓመት ይህንን የተቀደሰ የፆም ወር ብቻቸውን በቤታቸው እንዲያሳልፉ ተገደዋል። በእየሩሳሌም የሚገኘው አል አቅሳ መስጊድ ግቢ ከባለፈው ወር አጋማሽ ጀምሮ ተዘግቷል፤ ለረመዳንም አይከፈትም። የእስልምና ቅዱስ ከተማ ተብላ የምትጠራዋ የሳዑዲ አረቢያዋ መካም በቫይረሱ ተጠቅታለች። ለመሆኑ ረመዳን በተለያዩ አገራት እንዴት እያለፈ ነው? በመካ የሚገኘው ታላቁ መስጊድ በረመዳን ወቅት በአማኞች ይሞላ ነበር፤ አሁን ግን ባዶውን ቀርቷል። በኒው ዮርክ፤ እኝህ ኢማም በባዶ መስጊድ ውስጥ ብቻቸውን አዛን አድርገዋል። በፓኪስታን ላሆር ደንበኞች ለማፍጠሪያ የሚሆኑ ምግቦችን ለመግዛት ርቀታቸውን ጠብቀዋል። በህንድ የእንቅስቃሴ ገደቡን ተከትሎ በተዘጋው የደልሂ ጃማ መስጊድ ደጅ አንድ ግለሰብ ብቻቸውን ቁጭ ብለው አፍጥረዋል። በእየሩሳሌም የሚገኙ ሙስሊሞች የጁመዓን ሶላት ጎዳና ላይ ሰግደዋል።
news-49604857
https://www.bbc.com/amharic/news-49604857
ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘጋች
ደቡብ አፍሪካ በናይጀሪያ የሚገኘውን ኢምባሲዋን መዝጋቷ ተሰምቷል። በደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያዊያን የሚደርስባቸውን ጥቃት ተከትሎ ናይጄሪያውያን በአቡጃ የአጸፋ እርምጃ ይወስዳሉ በሚል ስጋት ነው በጊዜያዊነት ኤምባሲው የተዘጋው።
በንግድ እንቅስቃሴዋ በምትታወቀው ጆሃንስበርግ ከእሁድ እስከ ረቡዕ በተካሄደው ጥቃትና ዘረፋ በርካታ ሱቆች መዘረፋቸው ተነግሯል። ይህንን ተከትሎም 420 ሰዎች ታስረዋል። የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ናለዲ ፓንዶር ክስተቱን "አሳፋሪ" ብለውታል። • ታዋቂ አፍሪካውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ አንሄድም አሉ "በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎች ላይ በደረሰው ጥቃትና ዘረፋ መንግሥታችን ከልብ ተጸጽቷል" በማለት አክለዋል በመግለጫቸው። በመሆኑም ዲፕሎማቶች ላይ በሚደርሰው ማስፈራሪያ ምክንያት በናይጄሪያ አቡጃ የሚገኘውን ከፍተኛ ኮሚሽንና የሌጎስ ሚሲዮን እንዲዘጋ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ናይጄሪያውያን ተገድለዋልን? በማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወሩት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ናይጄሪያውያን መገደላቸውን የሚገልጹ ሲሆን ችግሩን አባብሶታል። ይህንን ተከትሎ ማክሰኞና ረቡዕ በበርካታ የናይጄሪያ ከተሞች የደቡብ አፍሪካውያን የቢዝነስ ሱቆች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የደቡብ አፍሪካው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ ኤም ቲ ኤንም በክስተቱ በመስጋት ተዘግቷል። ሁለት ታዋቂ የናይጀሪያ ዘፋኞችም (ቡርና ቦይ እና ቲዋ ሳቬጅ) የደቡብ አፍሪካ ሥራቸውን ማቋረጣቸውን ተናግረዋል። በግርግሩ ቢያንስ ሁለት የውጭ ሀሃገር ዜጎችን ጨምሮ 10 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል ናይጄሪያውያን ስለመኖራቸው ግን የተረጋገጠ ነገር የለም። ረቡዕ ዕለት የናይጄሪያ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ጂኦፍሪ ኦንያማ "በናይጄሪያውያን ላይ ብዙ ነገር ይባላል። ከህንጻ እንደተወረወሩና እንደተቃጠሉም ይነገራል። ጉዳዩ ግን ይህ አይደለም" ብለዋል። • በአውሮፕላን ውስጥ ለቀልድ "ቦምብ" ያለው ኢትዮጵያዊ ለእስር ተዳረገ ናይጀሪያውያን ስለመገደላቸው መረጃ ባይኖረንም እንደመንግሥት ግን የናይጄሪያውያን ንብረት ኢላማ ስለመደረጉ እርግጠኞች ነን ብለዋል ሚንስትሩ። በጥፋቱ ፕሬዝዳንት ቡሃሪ ሳይቀሩ መጨነቃቸውን በመግለጽ ናይጄሪያውያን በደቡብ አፍሪካውያን የቢዝነስ ተቋማት ላይ የሚያደርጉትን የበቀል እርምጃ እንዲያቆሙም አሳስበዋል። የናይጄሪያ መንግሥት ለምን መናገር ፈለገ? በቅርቡ በኬፕታውን የሚካሄደውን የአለም የኢኮኖሚ ፎረም የናይጀሪያ መንግሥት ግርግሩን በመቃወም ሳይሳተፍ ቀርቷል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ "ለዚህ ጉዳይ ቢያንስ የሞራል ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል" በማለት የጉባኤውን መቅረት ገልጸውታል። ፕሬዝዳንቱም በግርግሩ የተሰማችውን መከፋት ለመግለጽ ወደ ደቡብ አፍሪካ ልዑክ ልከዋል። ናይጀሪያውያን መንግሥት በውጭ ሃገር ለሚደርሰው ችግር የሚያሳየውን ፍጥነት በሃገር ውስጥ ሲሆን ግን አይደግመውም ብለዋል። ሌሎች አፍሪካውያንስ ምን አሉ? ትናንት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል። በመዲናዋ ኪንሻሳም አነስተኛ ሰልፍ ተካሂዷል። የታንዛኒያ አውሮፕላንም ወደ ጆሃንስበርግ እንደይበር የታንዛኒያ የትራንስፖርት ሚንስትር አስታውቋል። የማዳጋስካር እግር ኳስ ፌደሬሽንም ቅዳሜ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ ቡድኑን እንደማይልክ ተናግሯል። ረቡዕ ዕለት በዛምቢያ ዋና ከተማ ሉሳካ ተማሪዎች የደቡብ አፍሪካውያንን ሱቆች አዘግተዋል። • ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም የአፍሪካ ኅብረትም ጥፋቱን የሚያወግዝ መግለጫ አውጥቷል። ዘረፋውና ጥቃቱን በምን ተነሳ? ጥቃቱ የደረሰው የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች የውጭ ሃገር ሰዎች መቀጠር የለባቸውም በማለት አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። አድማ ከማድረግም በተጨማሪ መንገዶችን በመዝጋት የውጭ ሃገር አሽከርካሪዎችን መደብደብ ሲጀምሩ ጥቃቱ በብዙ ቦታዎች ተቀጣጠለ። ምክንያቱም በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ሥራ አልባ የሆኑት በውጭ ዜጎች ምክንያት እንደሆነ ያስባሉ። በአሁኑ ወቅት የደቡብ አፍሪካ የሥራ አጥነት መጠን 28 በመቶ እንደሆነ ይነገራል። አሃዙ ከ11 ዓመታት በኋላ ከፍተኛው እንደሆነ ተገልጿል።
news-42242662
https://www.bbc.com/amharic/news-42242662
አሜሪካ ለእየሩሳሌም የእሥራኤል መዲናነት እውቅና ልትሰጥ ነው
አሜሪካ ለእየሩሳሌም የእስራኤል መዲናነት እውቅና ልትሰጥ መሆኑ ተረጋገጠ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእየሩሳሌም በእስራኤል ዋና ከተማነት እውቅና ሊሰጡ እንደሆነ አንድ የመንግሥት ኃላፊ ገልፀዋል። ይህን አወዛጋቢ ጉዳይ ዛሬ በሚያደርጉት ንግግር ግልፅ ይሆናል። ኤምባሲው በፍጥነት የሚዘዋወር ባይሆንም ትራምፕ ቴል አቪቭ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ዝውውር እንደሚያፀድቁ ይጠበቃል። እስራኤል ይህንን በይሁንታ የምትቀበለው ሲሆን ፍልስጥኤምና የአረብ ሃገራት መሪዎች ግን የተጀመሩትን የሰላም ስምምነቶች እንዳያኮሽ አስጠንቅቀዋል። የአሜሪካ አጋር የሆነችው ሳዑዲ አረቢያ ይህንን ለውጥ ሙስሊሞችን ለመተንኮስ የተደረገ እርምጃ ብላዋለች። እስራኤል ኢየሩሳሌምን እንደ ዋና ከተማዋ ለዘመናት ትመለከት የነበረ ሲሆን በተቃራኒው ፍልሥጥኤም ምስራቅ እየሩሳሌምን የወደፊቱ መዲናዋ የማድረግ ፍላጎት አላት። እስራኤል ከተቋቋመችበት ከአውሮፓውያኑ 1948 ጀምሮ ለእየሩሳሌም በእስራኤል ዋና ከተማነት እውቅና ስትሰጥ አሜሪካ የመጀመሪያዋ ሆናለች። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የአሜሪካው መሪ ዶናልድ ትራምፕ ለዘመናት አወዛጋቢ የሆነችው እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርገው ዕውቅና ሊሰጡ መሆኑ አሳሳቢ ነው ይላሉ። አከራካሪ የሆነችው ከተማን በሚመለከት ማንኛውም ውሳኔ ሲወሰን 'በእሥራኤልና በፍልሥጥኤም ስምምነት መሰረት መሆን አለበት" በማለት ማክሮን ተናግረዋል። ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያዎችም ከተለያዩ አረብና ሙስሊም ሀገራትም እየተሰሙ ነው። አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚያሳዪት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ በማድረግ ዕውቅና ሊሰጡ ይችላሉ። ነገር ግን እስራኤል እና ፍልሥጥኤም ዋና ከተማችን ናት በሚል አቋማቸው እንደፀኑ ነው። ከዋይት ሀውስ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ትራምፕ ሰኞ ዕለት ቴልአቪቭ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ እየሩሳሌም መዘዋወሩን አስመልክቶ ፊርማቸውን ማኖር የነበረባቸው ቢሆንም ቀኑ አልፏል። ነገር ግን የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ሆጋን ጊድሌይ እንደሚሉት " ፕሬዚዳንቱ ከመጀመሪያው ጀምሮ በዚህ ጉዳይ ግልፅ አቋም ነው ያላቸው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ መዘዋወሩ ምንም ጥርጥር የለውም" ብለዋል። የአሜሪካ ኮንግረስ በአውሮፓውያኑ 1995 ኤምባሲው ወደ እየሩሳሌም እንዲዛወር ጥያቄ ከቀረበ በኋላ ትራምፕን ጨምሮ እያንዳንዱ ፕሬዚዳንት በየስድስት ወሩ መዛወሩን መቀበል አለመቀበላቸውን በሚመለከት መፈረም አለባቸው። አከራካሪው ጉዳይ ምንድን ነው? በእስራኤልና በፍልሥጥኤም ግጭት ዋነኛ የሚባለው ጉዳይ የእየሩሳሌም ጥያቄ ነው። ከተማዋ በተለይም ምስራቅ እየሩሳሌም ለሶስቱ እምነቶች እስልምና፣ ክርስትናና አይሁድ የተቀደሰች ከተማ ተደርጋ ነው የምትታየው። በአውሮፓውያኑ 1967 እስራኤል ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በኋላ ከተማዋን የተቆጣጠረች ሲሆን የእሥራኤል ዋና ከተማ እንደሆነችም እሳቤ አለ። ፍልስጤም ወደፊት ምስራቅ እየሩሳሌምን ዋና ከተማ የማድረግ ሃሳብ ያላት ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1993 የተደረገው የእስራኤልና የፍልሥጥኤም የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ደረጃ የከተማዋን ሁኔታ በሁለቱ ሥምምነት የሚወሰን ይሆናል። እስራኤል እየሩሳሌም ላይ አለኝ የምትለው ሉአላዊነት በአለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና ያልተሰተጠው ሲሆን የእስራኤል ወዳጅ የሆነችው አሜሪካን ጨምሮ አገራት በሙሉ ኤምባሲዎቻቸውን ያደረጉት በቴል አቪቭ ነው። እስራኤል እንደ አውሮፓውያኑ ከ1967 ጀምሮ በምስራቃዊ እየሩሳሌም 200 ሺህ ለሚሆኑ እስራኤላዊያን መኖሪያ ቤት ገንብታለች። ይህ ምንም እንኳን ከዓለም አቀፍ ህግ አንፃር ህገወጥ ቢሆንም እስራኤል ግን አይደለም በማለት ትከራከራለች። አሜሪካ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ አድርጋ እውቅና ብትሰጥ በአሁኑ ወቅት አለም አቀፉ ማህበረሰብ በጉዳዪ ላይ ያለውን አቋም ሊያዛባ ይቸላል። እስራኤል በምስራቅ እየሩሳሌም የምታደርገው ሰፈራም ተቀባይነትን ያገኛል። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ ምን ይመስላል? ሳውዲ አረቢያ ሰኞ እለት የዚህ አይነቱ የሰላም ስምምነት ሳይጠናቀቅ የሚደረግ እርምጃ የሰላም ስምምነቱ ላይ ተፅኖ እንደሚኖረው ገልፃለች። የፍልስጥኤሙ ፕሬዚዳንት ሙሃሙድ አባስ "የዚህ አይነቱ የአሜሪካ እርምጃ የሰላም ስምምነቱን ያበላሸዋል" በማለት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል። ዮርዳኖስ ከባድ ቀውስ እንዳይፈጠር ስታስጠነቅቅ የአረብ ሊጉ ዋና ፀሃፊ አብዱል ጊት የዚህ አይነቱ ነገር አክራሪነት እንዲሰፍንና ብጥብጥ እንዲቀሰቀስ በር የሚከፍት እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። የቱርኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በኪር ቦዝዳግ ደግሞ ነገሩ "ከፍተኛ ጥፋት እንዳይሆን" ብለዋል።
news-54306899
https://www.bbc.com/amharic/news-54306899
“ክትባት ቢገኝም ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ”
የዓለም ጤና ድርጅት ክትባት በስፋት ከመሰራጨቱ በፊት በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ሁለት ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ አለ።
ዶ/ር ማይክ ራየን የድርጅቱ የድንገተኛ ቡድን መሪ ዶ/ር ማይክ ራየን እንዳሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካልተባበረ የሟቾች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል። ወረርሽኙ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ ወደ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። 32 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል። በአንዳንድ አገራት በሽታው እያገረሸ ሲሆን፤ አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ውስጥ በአጠቃላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰው ታሟል። በሽታው ባገረሸባቸው የአውሮፓ አገራት ዳግመኛ የእንቅስቃሴ ገደብ የመጣል እቅድ አለ። አውሮፓ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ማይክ፤ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣል በፊት ምርመራ በማካሄድና በሽታው ካለባቸው ጋር ንክኪ ያላቸውን በመለየት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መሞከር ያዋጣል ብለዋል። ስለ ሟቾች ቁጥር ምን ተባለ? ክትባት መሰራጨት ከመጀመሩ በፊት ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ዶ/ር ማይክ “ሊሆን ይችላል” ብለዋል። ለበሽታው የሚሰጠው ህክምና እየተሻሻለ መምጣቱ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር መቀነሱን ቢናገሩም፤ ውጤታማ ክትባት ቢገኝም እንኳን የሟቾች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን እንደሚያልፍ አስረድተዋል። መንግሥታት ኃላፊነታቸውን በመወጣት የሰዎችን ሕይወት እንዲታደጉም አሳስበዋል። በተለያዩ አገራች ጥብቅ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ለምሳሌ በስፔን በሽታው በበረታበት ማድሪድ በከፊል እንቅስቃሴ የመግታት እቅድ ነበር። ተቃውሞ ስለገጠመው ተግባራዊ አልሆነም። ፈረንሳይ ውስጥም የባርና ሬስቶራንት ተቀጣሪዎች ንግዳቸው እንዳይዘጋ ተቃውመዋል። ዩናይትድ ኪንግደም አዳዲስ የጥንቃቄ እርምጃዎች ወስዳለች። እስራኤልም ንግድና በረራ ላይ ጥብቅ ገደብ ጥላለች። በሌላ በኩል በሽታው የከፋባት አሜሪካ ንግድ ተቋሞች ላይ ተጥሎ የነበረውን ገደብ አንስታለች። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ እንደሚሉት፤ አሜሪካ የወረርሽኙን የመጀመሪያ ዙር ስርጭት ገና አላለፈችም።