doc_no
int64
1
12.6k
doc_text
stringlengths
81
395k
relevant_topic_nos
sequencelengths
0
1
relevant_topic_titles
sequencelengths
0
1
relevant_topic_descriptions
sequencelengths
0
1
relevant_topic_narratives
sequencelengths
0
1
11,901
1  የእስራኤል ንጉሥ፣ የዳዊት ልጅ የሰለሞን ምሳሌዎች፦ 2  ጥበብንና ተግሣጽን ለመማር፣ጥበብ ያዘሉ አባባሎችን ለመረዳት፣ 3  ጥልቅ ማስተዋል፣ ጽድቅ፣ ጥሩ ፍርድናቅንነት የሚያስገኝ ተግሣጽ ለመቀበል፣ 4  ተሞክሮ ለሌላቸው ብልሃትን፣ለወጣቶች እውቀትንና የማመዛዘን ችሎታን ለመስጠት። 5  ጥበበኛ ሰው ያዳምጣል፤ ደግሞም ተጨማሪ ትምህርት ይቀስማል፤ማስተዋል ያለው ሰውም ጥበብ ያለበትን መመሪያ ይቀበላል፤ 6  ይህም ምሳሌንና ስውር የሆነ አባባልንእንዲሁም የጥበበኞችን ቃላትና የሚናገሩትን እንቆቅልሽ ይረዳ ዘንድ ነው። 7  ይሖዋን መፍራት የእውቀት መጀመሪያ ነው። ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው። 8  ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ተግሣጽ አዳምጥ፤የእናትህንም መመሪያ አትተው። 9  ለራስህ የሚያምር የአበባ ጉንጉን፣ለአንገትህም ውብ ጌጥ ይሆንልሃል። 10  ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች ሊያግባቡህ ቢሞክሩ እሺ አትበላቸው። 11  እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ና አብረን እንሂድ። ደም ለማፍሰስ እናድባ። ንጹሐን ሰዎችን ያለምክንያት ለማጥቃት እናደፍጣለን። 12  እንደ መቃብር፣ በሕይወት እንዳሉ እንውጣቸዋለን፤ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንሰለቅጣቸዋለን። 13  ውድ ሀብታቸውን ሁሉ እንውሰድባቸው፤ቤቶቻችንን በዘረፍናቸው ነገሮች እንሞላለን። 14  ከእኛ ጋር ልትተባበር ይገባል፤ሁላችንም የሰረቅነውን እኩል እንካፈላለን።” 15  ልጄ ሆይ፣ አትከተላቸው። እግርህን ከመንገዳቸው አርቅ፤ 16  እግሮቻቸው ክፉ ነገር ለመሥራት ይሮጣሉና፤ደም ለማፍሰስ ይጣደፋሉ። 17  ወፎች ዓይናቸው እያየ እነሱን ለማጥመድ መረብ መዘርጋት ከንቱ ነው። 18  እነዚህ ሰዎች ደም ለማፍሰስ የሚያደቡት ለዚህ ነው፤የሰዎችን ሕይወት ለማጥፋት ያደፍጣሉ። 19  በማጭበርበር ትርፍ ለማግኘት የሚሹ መንገዳቸው ይህ ነው፤እንዲህ ያለው ትርፍ የተጠቃሚዎቹን ሕይወት ያጠፋል። 20  እውነተኛ ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮኻለች። በአደባባይ ላይ ያለማቋረጥ ድምፅዋን ታሰማለች። 21  ሰው በሚበዛባቸው ጎዳናዎች ማዕዘን ላይ ሆና ትጣራለች። በከተማው መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ ትላለች፦ 22  “እናንተ አላዋቂዎች እስከ መቼ አላዋቂነትን ትወዳላችሁ? እናንተ ፌዘኞች እስከ መቼ በሌሎች ላይ በማፌዝ ትደሰታላችሁ? እናንተ ሞኞች እስከ መቼ እውቀትን ትጠላላችሁ? 23  ለወቀሳዬ ምላሽ ስጡ። እንዲህ ብታደርጉ መንፈሴን አፈስላችኋለሁ፤ቃሌን አሳውቃችኋለሁ። 24  በተጣራሁ ጊዜ በእንቢተኝነታችሁ ጸንታችኋል፤እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ትኩረት አልሰጠም፤ 25  ምክሬን ሁሉ ችላ ብላችኋል፤ወቀሳዬንም አልተቀበላችሁም፤ 26  እኔም ጥፋት ሲደርስባችሁ እስቃለሁ፤የፈራችሁት ነገር ሲደርስ አላግጥባችኋለሁ፤ 27  የፈራችሁት ነገር እንደ ማዕበል ሲደርስባችሁ፣ጥፋታችሁም እንደ አውሎ ነፋስ ከተፍ ሲልባችሁ፣ጭንቀትና መከራ ሲመጣባችሁ አፌዝባችኋለሁ። 28  በዚያን ጊዜ ደጋግመው ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ሆኖም አያገኙኝም፤ 29  ምክንያቱም እውቀትን ጠልተዋል፤ይሖዋን መፍራትንም አልወደዱም። 30  ምክሬን አልተቀበሉም፤ወቀሳዬን ሁሉ አቃለዋል። 31  ስለዚህ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ ይቀበላሉ፤በገዛ ራሳቸውም ምክር ከልክ በላይ ይጠግባሉ። 32  ተሞክሮ የሌላቸውን ሰዎች ጋጠወጥነታቸው ይገድላቸዋልና፤ሞኞችን ደግሞ ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል። 33  እኔን የሚሰማ ሰው ግን ተረጋግቶ ይኖራል፤መከራ ይደርስብኛል የሚል ስጋትም አያድርበትም።”
[]
[]
[]
[]
11,902
10  የሰለሞን ምሳሌዎች። ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ሞኝ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናል። 2  በክፋት የተገኘ ሀብት ምንም ፋይዳ የለውም፤ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል። 3  ይሖዋ ጻድቅ ሰው እንዲራብ አያደርግም፤የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል። 4  ሥራ የፈቱ እጆች ያደኸያሉ፤ትጉ እጆች ግን ብልጽግና ያስገኛሉ። 5  ጥልቅ ማስተዋል ያለው ልጅ እህሉን በበጋ ይሰበስባል፤አሳፋሪ ልጅ ግን በመከር ወቅት ለጥ ብሎ ይተኛል። 6  በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፤የክፉዎች አፍ ግን የዓመፅ ዕቅዳቸውን ይሰውራል። 7  የጻድቅ መታሰቢያ በረከት ያስገኛል፤የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል። 8  ጥበበኛ ልብ ያለው ሰው መመሪያዎችን ይቀበላል፤በሞኝነት የሚናገር ሰው ግን ጥፋት ይደርስበታል። 9  ንጹሕ አቋሙን ጠብቆ የሚሄድ ያለስጋት ይመላለሳል፤መንገዱን ጠማማ የሚያደርግ ግን ይጋለጣል። 10  በተንኮል የሚጣቀስ ሐዘን ያመጣል፤በሞኝነት የሚናገር ሰውም ጥፋት ይደርስበታል። 11  የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፤የክፉዎች አፍ ግን የዓመፅ ዕቅዳቸውን ይሰውራል። 12  ጥላቻ ጭቅጭቅ ያስነሳል፤ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ይሸፍናል። 13  አስተዋይ በሆነ ሰው ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፤በትር ግን ማስተዋል ለጎደለው ሰው ጀርባ ነው። 14  ጥበበኞች እውቀትን እንደ ውድ ሀብት ያከማቻሉ፤የሞኝ ሰው አፍ ግን ጥፋት ይጋብዛል። 15  የባለጸጋ ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው። ድሆችን የሚያጠፋቸው ድህነታቸው ነው። 16  የጻድቅ ሰው ሥራ ወደ ሕይወት ይመራል፤የክፉ ሰው ፍሬ ግን ወደ ኃጢአት ይመራል። 17  ተግሣጽን የሚቀበል ለሌሎች የሕይወት መንገድ ይሆናል፤ወቀሳን ችላ የሚል ግን ሌሎች መንገድ እንዲስቱ ያደርጋል። 18  ጥላቻውን የሚሸፋፍን ሰው ሐሰት ይናገራል፤ተንኮል ያዘለ ወሬ የሚያስፋፋ ሰውም ሞኝ ነው። 19  ከቃላት ብዛት ስህተት አይታጣም፤ከንፈሩን የሚገታ ግን ልባም ሰው ነው። 20  የጻድቅ አንደበት ጥራት ያለው ብር ነው፤የክፉ ሰው ልብ ግን እርባና የለውም። 21  የጻድቅ ከንፈሮች ብዙዎችን ይመግባሉ፤ሞኞች ግን ማስተዋል ስለሚጎድላቸው ይሞታሉ። 22  የይሖዋ በረከት ባለጸጋ ታደርጋለች፤እሱም ከበረከቱ ጋር ሥቃይን አይጨምርም። 23  አሳፋሪ ምግባር መፈጸም ለሞኝ ሰው እንደ ጨዋታ ነው፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ጥበበኛ ነው። 24  ክፉ ሰው የፈራው ነገር ይደርስበታል፤ጻድቅ ግን የተመኘውን ያገኛል። 25  አውሎ ነፋስ ሲያልፍ ክፉ ሰው ተጠርጎ ይወሰዳል፤ጻድቅ ግን ለዘላለም እንደሚኖር መሠረት ነው። 26  ኮምጣጤ ጥርስን፣ ጭስም ዓይንን እንደሚጎዳ፣ሰነፍም ለሚልከው ሰው እንዲሁ ነው። 27  ይሖዋን መፍራት ዕድሜን ያስረዝማል፤የክፉዎች ዕድሜ ግን በአጭሩ ይቀጫል። 28  የጻድቃን ተስፋ ደስታ ያስገኛል፤የክፉዎች ተስፋ ግን መና ይቀራል። 29  የይሖዋ መንገድ፣ ያለነቀፋ ለሚመላለስ ሰው መሸሸጊያ ነው፤ለክፉ አድራጊዎች ግን መጥፊያቸው ነው። 30  ጻድቅ ሰው ምንም ነገር አይጥለውም፤ክፉዎች ግን በምድር ላይ መኖራቸውን አይቀጥሉም። 31  የጻድቅ አፍ ጥበብን ያፈልቃል፤ጠማማ ምላስ ግን ትቆረጣለች። 32  የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ደስ የሚያሰኘው ነገር ምን እንደሆነ ያውቃሉ፤የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነው።
[]
[]
[]
[]
11,903
11  አባይ ሚዛን በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሰኘዋል። 2  እብሪት ከመጣ ውርደት ይከተላል፤ልካቸውን በሚያውቁ ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች። 3  ቅኖችን ንጹሕ አቋማቸው ይመራቸዋል፤ከዳተኞችን ግን ተንኮላቸው ያጠፋቸዋል። 4  በቁጣ ቀን ሀብት ፋይዳ አይኖረውም፤ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል። 5  ነቀፋ የሌለበት ሰው የሚሠራው ጽድቅ መንገዱን ቀና ያደርግለታል፤ክፉ ሰው ግን በገዛ ክፋቱ ይወድቃል። 6  ቅኖችን ጽድቃቸው ያድናቸዋል፤ከዳተኞች ግን በገዛ ምኞታቸው ይጠመዳሉ። 7  ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው መና ይቀራል፤በኃይሉ ተመክቶ ተስፋ የሚያደርገው ነገርም ይጠፋል። 8  ጻድቅ ከመከራ ይድናል፤ክፉ ሰው ደግሞ በእሱ ቦታ ይተካል። 9  ከሃዲ ሰው በአፉ ባልንጀራውን ያጠፋል፤ጻድቃን ግን በእውቀት ይድናሉ። 10  በጻድቃን ጥሩነት ከተማ ሐሴት ታደርጋለች፤ክፉዎች ሲጠፉም እልልታ ይሆናል። 11  በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤የክፉዎች አፍ ግን ያፈራርሳታል። 12  ማስተዋል የጎደለው ሰው ባልንጀራውን ይንቃል፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ዝም ይላል። 13  ስም የሚያጠፋ ሰው እየዞረ የሌሎችን ሚስጥር ይገልጣል፤እምነት የሚጣልበት ሰው ግን ሚስጥር ይጠብቃል። 14  ጥበብ ያለበት አመራር ሲጓደል ሕዝብ ይጎዳል፤ብዙ አማካሪዎች ባሉበት ግን ስኬት ይገኛል። 15  የማያውቀው ሰው ለወሰደው ብድር ዋስ የሚሆን ጉዳት ላይ መውደቁ አይቀርም፤እጅ በመምታት ቃል ከመግባት የሚቆጠብ ግን ምንም አይደርስበትም። 16  ሞገስ ያላት ሴት ክብር ታገኛለች፤ጨካኞች ግን ሀብት ያካብታሉ። 17  ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤ጨካኝ ሰው ግን በራሱ ላይ መከራ ያመጣል። 18  ክፉ ሰው የሚያገኘው ደሞዝ እርባና የለውም፤ጽድቅን የሚዘራ ግን እውነተኛ ብድራት ያገኛል። 19  ለጽድቅ ጽኑ አቋም ያለው ሰው ሕይወት የማግኘት ተስፋ አለው፤ክፋትን የሚያሳድድ ግን ለሞት መዳረጉ አይቀርም። 20  ይሖዋ ጠማማ ልብ ያላቸውን ሰዎች ይጸየፋል፤ነቀፋ በሌለበት ጎዳና የሚመላለሱ ግን ደስ ያሰኙታል። 21  ይህን አትጠራጠር፦ ክፉ ሰው ከቅጣት አያመልጥም፤የጻድቃን ልጆች ግን ይድናሉ። 22  ማስተዋልን የምትንቅ ቆንጆ ሴት፣በአሳማ አፍንጫ ላይ እንዳለ የወርቅ ቀለበት ናት። 23  የጻድቅ ምኞት መልካም ነገር ያስገኛል፤የክፉ ሰው ተስፋ ግን ወደ ቁጣ ይመራል። 24  አንዱ በልግስና ይሰጣል፤ ሆኖም ተጨማሪ ያገኛል፤ሌላው ደግሞ ለመስጠት ይሰስታል፤ ነገር ግን ለድህነት ይዳረጋል። 25  ለጋስ ሰው ይበለጽጋል፤ሌሎችን የሚያረካም እሱ ራሱ ይረካል። 26  እህል ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነውን ሕዝቡ ይረግመዋል፤የሚሸጠውን ግን ይባርከዋል። 27  መልካም ነገር ለማድረግ የሚተጋ ሞገስ ለማግኘት ይጥራል፤መጥፎ ነገር ለማድረግ የሚፈልግ ግን ክፋቱ በራሱ ላይ እንደሚመጣ የተረጋገጠ ነው። 28  በሀብቱ የሚታመን ሰው ይወድቃል፤ጻድቅ ግን እንዳማረ ቅጠል ይለመልማል። 29  ቤተሰቡ ላይ ችግር የሚያመጣ ሰው ሁሉ ነፋስን ይወርሳል፤ሞኝ ሰውም ጥበበኛ ልብ ላለው ሰው አገልጋይ ይሆናል። 30  የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ነው፤ነፍሳትንም የሚማርክ ጥበበኛ ነው። 31  በእርግጥ ጻድቅ በምድር ላይ የሚገባውን ብድራት የሚቀበል ከሆነክፉውና ኃጢአተኛው የሚቀበሉት ብድራትማ ምንኛ የከፋ ይሆን!
[]
[]
[]
[]
11,904
12  ተግሣጽን የሚወድ እውቀትን ይወዳል፤ወቀሳን የሚጠላ ግን የማመዛዘን ችሎታ ይጎድለዋል። 2  ጥሩ ሰው የይሖዋን ሞገስ ያገኛል፤ክፋት የሚያሴርን ሰው ግን እሱ ይፈርድበታል። 3  በክፋት ጸንቶ መቆም የሚችል ሰው የለም፤ጻድቅ ግን ፈጽሞ አይነቀልም። 4  ጥሩ ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት፤አሳፋሪ ሚስት ግን አጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት። 5  የጻድቃን ሐሳብ ፍትሐዊ ነው፤የክፉዎች ምክር ግን አሳሳች ነው። 6  የክፉዎች ቃል ገዳይ ወጥመድ ነው፤የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል። 7  ክፉዎች ሲገለበጡ ደብዛቸው ይጠፋል፤የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል። 8  ሰው አስተዋይ በሆነ አንደበቱ ይመሰገናል፤ልቡ ጠማማ የሆነ ግን ይናቃል። 9  የሚበላው ሳይኖረው ራሱን ከፍ ከፍ ከሚያደርግ ሰው ይልቅአገልጋይ ኖሮት ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚኖር ሰው ይሻላል። 10  ጻድቅ የቤት እንስሳቱን ይንከባከባል፤ክፉዎች ግን ርኅራኄያቸው እንኳ ጭካኔ ነው። 11  መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን ማስተዋል ይጎድለዋል። 12  ክፉ ሰው፣ ሌሎች መጥፎ ሰዎች ባጠመዱት ነገር ይቀናል፤የጻድቃን ሥር ግን ፍሬ ያፈራል። 13  መጥፎ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፤ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል። 14  ሰው ከአፉ ፍሬ መልካም ነገር ይጠግባል፤የእጁ ሥራም ብድራት ይከፍለዋል። 15  የሞኝ መንገድ በራሱ ዓይን ትክክል ነው፤ጥበበኛ ግን ምክር ይቀበላል። 16  ሞኝ ሰው ቁጣውን ወዲያውኑ ይገልጻል፤ብልህ ሰው ግን ስድብን ችላ ብሎ ያልፋል። 17  ታማኝ ምሥክር እውነቱን ይናገራል፤ውሸታም ምሥክር ግን ያታልላል። 18  ሳይታሰብበት የሚነገር ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤የጥበበኞች ምላስ ግን ፈውስ ነው። 19  እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ሐሰተኛ ምላስ ግን የሚቆየው ለቅጽበት ብቻ ነው። 20  ተንኮል በሚሸርቡ ሰዎች ልብ ውስጥ ማታለያ አለ፤ሰላምን የሚያራምዱ ግን ደስተኞች ናቸው። 21  ጻድቅ ምንም ዓይነት ጉዳት አያገኘውም፤የክፉዎች ሕይወት ግን በመከራ የተሞላ ይሆናል። 22  ይሖዋ ውሸታም ከንፈሮችን ይጸየፋል፤በታማኝነት የሚመላለሱ ግን ደስ ያሰኙታል። 23  ብልህ ሰው እውቀቱን ይሰውራል፤የሞኝ ልብ ግን ሞኝነቱን ይዘከዝካል። 24  የትጉ ሰዎች እጅ ገዢ ትሆናለች፤ሥራ ፈት እጆች ግን ለባርነት ይዳረጋሉ። 25  በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል፤መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል። 26  ጻድቅ የግጦሽ መሬቱን በሚገባ ይቃኛል፤የክፉዎች መንገድ ግን እንዲባዝኑ ያደርጋቸዋል። 27  ሰነፍ ሰው አደኑን አሳድዶ አይዝም፤ትጋት ግን የሰው ውድ ሀብት ነው። 28  የጽድቅ ጎዳና ወደ ሕይወት ይመራል፤በጎዳናው ላይ ሞት የለም።
[]
[]
[]
[]
11,905
13  ጥበበኛ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይቀበላል፤ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም። 2  ሰው ከአፉ ፍሬ መልካም ነገር ይበላል፤ከዳተኞች ግን ዓመፅን ይመኛሉ። 3  አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል። አፉን የሚከፍት ግን ይጠፋል። 4  ሰነፍ ሰው ይመኛል፤ ነገር ግን ምንም አያገኝም፤ትጉ ሰው ግን በሚገባ ይጠግባል። 5  ጻድቅ ውሸትን ይጠላል፤የክፉ ሰው ድርጊት ግን ኀፍረትና ውርደት ያመጣበታል። 6  በመንገዱ ነቀፋ የሌለበትን ሰው ጽድቅ ትጠብቀዋለች፤ክፋት ግን ኃጢአተኛውን ትጥለዋለች። 7  ምንም ሳይኖረው ባለጸጋ መስሎ ለመታየት የሚሞክር ሰው አለ፤ሌላው ደግሞ ብዙ ሀብት እያለው ድሃ መስሎ ይኖራል። 8  የሰው ሀብት ለሕይወቱ ቤዛ ነው፤ድሃ ግን ምንም ዓይነት ስጋት የለበትም። 9  የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል። 10  እብሪተኝነት ጠብ ከመፍጠር ውጭ የሚያመጣው ነገር የለም፤ምክር በሚሹ ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች። 11  በፍጥነት የተገኘ ሀብት ይመናመናል፤ጥቂት በጥቂት የሚያጠራቅም ሰው ግን ሀብቱ ይጨምራል። 12  የዘገየ ተስፋ ልብን ያሳምማል፤የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው። 13  መመሪያን የሚንቅ ሁሉ ይቀጣል፤ትእዛዝን የሚያከብር ግን ብድራት ያገኛል። 14  የጥበበኛ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው፤ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል። 15  ጥልቅ ማስተዋል ሞገስ ያስገኛል፤የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው። 16  ብልህ ሰው ተግባሩን በእውቀት ያከናውናል፤ሞኝ ሰው ግን የገዛ ራሱን ሞኝነት ይገልጣል። 17  ክፉ መልእክተኛ ችግር ውስጥ ይወድቃል፤ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስ ያመጣል። 18  ተግሣጽን ችላ የሚል ሁሉ ይደኸያል፤ ይዋረዳልም፤እርማትን የሚቀበል ግን ይከበራል። 19  ሰው የተመኘው ነገር ሲፈጸም ደስ ይለዋል፤ሞኞች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ። 20  ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል፤ከሞኞች ጋር የሚገጥም ግን ጉዳት ይደርስበታል። 21  ኃጢአተኞችን ጥፋት ያሳድዳቸዋል፤ጻድቃንን ግን ብልጽግና ይክሳቸዋል። 22  ጥሩ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ይተዋል፤የኃጢአተኛ ሀብት ግን ለጻድቅ ይከማቻል። 23  የድሃ እርሻ ብዙ እህል ያስገኛል፤ሆኖም ከፍትሕ መጓደል የተነሳ ተጠራርጎ ይጠፋል። 24  ልጁን በበትር ከመምታት ወደኋላ የሚል ይጠላዋል፤የሚወደው ግን ተግቶ ይገሥጸዋል። 25  ጻድቅ ይበላል፤ የምግብ ፍላጎቱንም ያረካል፤የክፉ ሰው ሆድ ግን ባዶ ነው።
[]
[]
[]
[]
11,906
14  ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትገነባለች፤ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች። 2  አካሄዱ ቅን የሆነ ሰው ይሖዋን ይፈራል፤መንገዱ መሠሪ የሆነ ግን ይንቀዋል። 3  በሞኝ ሰው አፍ የትዕቢት በትር አለ፤የጥበበኞች ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። 4  ከብት በሌለበት ግርግሙ ንጹሕ ይሆናል፤የበሬ ጉልበት ግን ብዙ ምርት ያስገኛል። 5  ሐቀኛ ምሥክር አይዋሽም፤ሐሰተኛ ምሥክር ግን ባወራ ቁጥር ይዋሻል። 6  ፌዘኛ ጥበብን ይፈልጋል፤ ሆኖም አያገኛትም፤አስተዋይ ሰው ግን እውቀትን በቀላሉ ያገኛል። 7  ከሞኝ ሰው ራቅ፤ከከንፈሮቹ ምንም ዓይነት እውቀት አታገኝምና። 8  ብልህ ሰው የሚሄድበትን መንገድ በጥበብ ያስተውላል፤ሞኞች ግን በቂልነታቸው ይታለላሉ። 9  ሞኞች በደል ፈጽመው ያፌዛሉ፤ቅኖች ግን እርቅ ለመፍጠር ፈቃደኞች ናቸው። 10  ልብ የራሱን ምሬት ያውቃል፤ደስታውንም ሌላ ሰው ሊጋራው አይችልም። 11  የክፉዎች ቤት ይወድማል፤የቅኖች ድንኳን ግን ይበለጽጋል። 12  ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል። 13  አንድ ሰው እየሳቀ እንኳ ልቡ ሊያዝን ይችላል፤ደስታም በሐዘን ሊቋጭ ይችላል። 14  በልቡ ጋጠወጥ የሆነ ሰው አካሄዱ የሚያስከትለውን መዘዝ ይቀበላል፤ጥሩ ሰው ግን የሥራውን ውጤት ያገኛል። 15  ተላላ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ብልህ ግን አካሄዱን አንድ በአንድ ያጤናል። 16  ጥበበኛ ሰው ጠንቃቃ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ሞኝ ግን ደንታ ቢስ ነው፤ ደግሞም ከልክ በላይ በራሱ ይመካል። 17  ለቁጣ የሚቸኩል ሰው የሞኝነት ተግባር ይፈጽማል፤በጥሞና የሚያስብ ሰው አይወደድም። 18  ተላሎች ሞኝነትን ይወርሳሉ፤ብልሆች ግን እውቀትን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ። 19  መጥፎ ሰዎች በጥሩ ሰዎች ፊት፣ክፉዎችም በጻድቅ ደጃፍ ይሰግዳሉ። 20  ድሃ በባልንጀሮቹ ዘንድ እንኳ የተጠላ ነው፤የባለጸጋ ወዳጆች ግን ብዙ ናቸው። 21  ባልንጀራውን የሚንቅ ኃጢአት ይሆንበታል፤ለችግረኞች የሚራራ ግን ደስተኛ ነው። 22  ተንኮል የሚሸርቡ ሰዎች መንገድ ይስቱ የለም? መልካም ነገር ለመሥራት የሚያስቡ ሰዎች ግን ታማኝ ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ። 23  በትጋት ያከናወኑት ነገር ሁሉ ጥቅም ያስገኛል፤እንዲሁ ማውራት ግን ችግር ላይ ይጥላል። 24  የጥበበኞች ዘውድ ሀብታቸው ነው፤የሞኞች ቂልነት ግን ለከፋ ሞኝነት ይዳርጋል። 25  እውነተኛ ምሥክር ሕይወትን ይታደጋል፤አታላይ ግን ባወራ ቁጥር ይዋሻል። 26  ይሖዋን የሚፈራ ሁሉ በማንኛውም ነገር በእሱ ይታመናል፤ልጆቹም መጠጊያ ያገኛሉ። 27  ይሖዋን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል። 28  የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ግርማ ነው፤ተገዢዎች የሌሉት ገዢ ግን ይጠፋል። 29  ቶሎ የማይቆጣ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ትዕግሥት የሌለው ሰው ግን ሞኝነቱን ይገልጣል። 30  የሰከነ ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ቅናት ግን አጥንትን ያነቅዛል። 31  ችግረኛን የሚያጭበረብር ፈጣሪውን ይሰድባል፤ለድሃ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል። 32  ክፉ ሰው በገዛ ክፋቱ ይወድቃል፤ጻድቅ ግን ንጹሕ አቋሙ መጠጊያ ያስገኝለታል። 33  ጥበብ በአስተዋይ ልብ ውስጥ በጸጥታ ታርፋለች፤በሞኞች መካከል ግን ራሷን ትገልጣለች። 34  ጽድቅ አንድን ብሔር ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ኃጢአት ግን ሕዝብን ታዋርዳለች። 35  ንጉሥ አስተውሎ በሚሠራ አገልጋይ ደስ ይሰኛል፤አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም አገልጋይ ላይ ግን ይቆጣል።
[]
[]
[]
[]
11,907
15  የለዘበ መልስ ቁጣን ያበርዳል፤ክፉ ቃል ግን ቁጣን ያነሳሳል። 2  የጥበበኞች ምላስ እውቀትን በሚገባ ይጠቀማል፤የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይገልጣል። 3  የይሖዋ ዓይኖች በሁሉም ቦታ ናቸው፤ክፉዎችንም ሆነ ጥሩ ሰዎችን ይመለከታሉ። 4  የረጋ አንደበት የሕይወት ዛፍ ነው፤ጠማማ ንግግር ግን ተስፋ ያስቆርጣል። 5  ሞኝ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፤ብልህ ግን እርማትን ይቀበላል። 6  በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ሀብት አለ፤የክፉ ሰው ምርት ግን ችግር ያስከትልበታል። 7  የጥበበኞች ከንፈር እውቀትን ታስፋፋለች፤የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም። 8  ይሖዋ የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል። 9  ይሖዋ የክፉውን መንገድ ይጸየፋል፤ጽድቅን የሚከታተለውን ግን ይወደዋል። 10  ከመንገድ የሚወጣ ሰው፣ ተግሣጽ መጥፎ ነገር ይመስለዋል፤ወቀሳን የሚጠላ ሁሉ ግን ይሞታል። 11  መቃብርና የጥፋት ቦታ በይሖዋ ፊት ወለል ብለው ይታያሉ። የሰዎች ልብማ በፊቱ ምንኛ የተገለጠ ነው! 12  ፌዘኛ የሚያርመውን ሰው አይወድም። ጥበበኞችን አያማክርም። 13  ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፤የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይደቁሳል። 14  አስተዋይ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፤የሞኞች አፍ ግን ቂልነትን ይመገባል። 15  ጎስቋላ ሰው ዘመኑ ሁሉ አስከፊ ነው፤ደስተኛ ልብ ያለው ሰው ግን ሁልጊዜ ግብዣ ላይ ያለ ያህል ነው። 16  ከጭንቀት ጋር ከሚገኝ ብዙ ሀብት ይልቅይሖዋን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል። 17  ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይልቅፍቅር ባለበት አትክልት መብላት ይሻላል። 18  ግልፍተኛ ሰው ጭቅጭቅ ይፈጥራል፤ቶሎ የማይቆጣ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል። 19  የሰነፍ መንገድ እንደ እሾህ አጥር ነው፤የቅኖች መንገድ ግን እንደተስተካከለ አውራ ጎዳና ነው። 20  ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ሞኝ ግን እናቱን ያቃልላል። 21  ማስተዋል የጎደለው ሰው ሞኝነት ያስደስተዋል፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ቀጥተኛውን መንገድ ተከትሎ ይሄዳል። 22  መመካከር ከሌለ የታቀደው ነገር ሳይሳካ ይቀራል፤በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል። 23  ሰው ትክክለኛውን መልስ በመስጠት ሐሴት ያደርጋል፤በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃልም ምንኛ መልካም ነው! 24  ጥልቅ ማስተዋል ያለው ሰው ወደ መቃብር ከመውረድ ይድን ዘንድየሕይወት መንገድ ወደ ላይ ይመራዋል። 25  ይሖዋ የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤የመበለቲቱን ወሰን ግን ያስከብራል። 26  ይሖዋ የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤ያማረ ቃል ግን በፊቱ ንጹሕ ነው። 27  በማጭበርበር የተገኘ ትርፍ የሚያጋብስ ሰው በቤተሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤ጉቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል። 28  የጻድቅ ልብ፣ መልስ ከመስጠቱ በፊት ያሰላስላል፤የክፉዎች አፍ ግን መጥፎ ነገር ይዘከዝካል። 29  ይሖዋ ከክፉዎች እጅግ የራቀ ነው፤የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። 30  ብሩህ ዓይን ልብን ደስ ያሰኛል፤መልካም ዜናም አጥንትን ያበረታል። 31  ሕይወት የሚያስገኝ ወቀሳን የሚሰማ፣በጥበበኛ ሰዎች መካከል ይኖራል። 32  ተግሣጽን ገሸሽ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ሕይወቱን ያቃልላል፤ወቀሳን የሚሰማ ሁሉ ግን ማስተዋል ያገኛል። 33  ይሖዋን መፍራት ጥበብን ያስተምራል፤ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።
[]
[]
[]
[]
11,908
16  ሰው የልቡን ሐሳብ ያዘጋጃል፤የሚሰጠው መልስ ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው። 2  ሰው መንገዱ ሁሉ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤ይሖዋ ግን ውስጣዊ ዓላማን ይመረምራል። 3  የምታደርገውን ሁሉ ለይሖዋ አደራ ስጥ፤ዕቅድህም ሁሉ ይሳካል። 4  ይሖዋ ማንኛውንም ነገር ያዘጋጀው ለራሱ ዓላማ ነው፤ክፉውም ሰው እንኳ በመዓት ቀን እንዲጠፋ ያደርጋል። 5  ይሖዋ ኩሩ ልብ ያለውን ሁሉ ይጸየፋል። እንዲህ ያለው ሰው ሳይቀጣ እንደማይቀር እርግጠኛ ሁን። 6  በታማኝ ፍቅርና በታማኝነት በደል ይሰረያል፤ሰውም ይሖዋን በመፍራት ከክፋት ይርቃል። 7  ይሖዋ በሰው አካሄድ ደስ በሚሰኝበት ጊዜጠላቶቹ እንኳ ሳይቀሩ ከሰውየው ጋር ሰላም እንዲኖራቸው ያደርጋል። 8  አግባብ ባልሆነ መንገድ ከሚገኝ ብዙ ገቢ ይልቅበጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል። 9  ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ይሖዋ ግን አካሄዱን ይመራለታል። 10  የንጉሥ ከንፈር በመንፈስ ተመርቶ ውሳኔ መስጠት ይገባዋል፤ፍትሕን ፈጽሞ ማዛባት የለበትም። 11  ትክክለኛ መለኪያና ሚዛን ከይሖዋ ናቸው፤በከረጢት ውስጥ ያሉት መለኪያዎች ሁሉ የእሱ ሥራ ናቸው። 12  ክፉ ድርጊት በነገሥታት ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና። 13  ነገሥታት የጽድቅ ንግግር ደስ ያሰኛቸዋል። ሐቁን የሚናገር ሰው ይወዳሉ። 14  የንጉሥ ቁጣ እንደ ሞት መልእክተኛ ነው፤ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ያበርደዋል። 15  የንጉሥ ፊት ሲፈካ ሰው በደስታ ይኖራል፤ሞገሱም ዝናብ እንዳዘለ የበልግ ደመና ነው። 16  ጥበብን ማግኘት ወርቅ ከማግኘት ምንኛ የተሻለ ነው! ማስተዋልን ማግኘትም ብር ከማግኘት ይመረጣል። 17  ቅኖች ከክፋት ጎዳና ይርቃሉ። መንገዱን የሚጠብቅ ሁሉ በሕይወት ይኖራል። 18  ኩራት ጥፋትን፣የትዕቢት መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል። 19  የትዕቢተኞችን ምርኮ ከመካፈል ይልቅከየዋሆች ጋር የትሕትና መንፈስ ማሳየት ይሻላል። 20  አንድን ነገር ጠለቅ ብሎ የሚያስተውል ሰው ስኬታማ ይሆናል፤በይሖዋ የሚታመንም ደስተኛ ነው። 21  ልቡ ጥበበኛ የሆነ ሰው አስተዋይ ይባላል፤በደግነት የሚናገርም የማሳመን ችሎታ አለው። 22  ጥልቅ ማስተዋል ለባለቤቱ የሕይወት ምንጭ ነው፤ሞኞች ግን በገዛ ሞኝነታቸው ይቀጣሉ። 23  የጥበበኛ ሰው ልብ፣ አንደበቱ ጥልቅ ማስተዋል እንዲኖረው ያደርጋል፤ለንግግሩም የማሳመን ችሎታ ይጨምርለታል። 24  ደስ የሚያሰኝ ቃል እንደ ማር እንጀራ ነው፤ለነፍስ ጣፋጭ፣ ለአጥንትም ፈውስ ነው። 25  ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል። 26  ሠራተኛን የምግብ ፍላጎቱ ተግቶ እንዲሠራ ያደርገዋል፤ረሃቡ እንዲህ እንዲያደርግ ያስገድደዋልና። 27  የማይረባ ሰው ክፋትን ይምሳል፤ንግግሩ እንደሚለበልብ እሳት ነው። 28  ነገረኛ ሰው ጭቅጭቅ ያስነሳል፤ስም አጥፊም የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል። 29  ዓመፀኛ ሰው ባልንጀራውን ክፉ ነገር እንዲሠራ ያግባባዋል፤ወደተሳሳተ መንገድም ይመራዋል። 30  በዓይኑ እየጠቀሰ ተንኮል ይሸርባል። ከንፈሮቹን ነክሶ ሸር ይሠራል። 31  ሽበት በጽድቅ መንገድ ሲገኝየውበት ዘውድ ነው። 32  ቶሎ የማይቆጣ ሰው ከኃያል ሰው፣ስሜቱን የሚቆጣጠርም ከተማን ድል ከሚያደርግ ሰው ይሻላል። 33  ዕጣ ጭን ላይ ይጣላል፤ውሳኔውን በሙሉ የሚያስተላልፈው ግን ይሖዋ ነው።
[]
[]
[]
[]
11,909
17  ጠብ እያለ ትልቅ ድግስ ከተደገሰበት ቤት ይልቅሰላም ባለበት ደረቅ የዳቦ ቁራሽ መብላት ይሻላል። 2  ጥልቅ ማስተዋል ያለው አገልጋይ አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ከወንድማማቾቹ እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል። 3  ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤ልብን የሚመረምር ግን ይሖዋ ነው። 4  ክፉ ሰው ጎጂ የሆነን ንግግር በትኩረት ያዳምጣል፤አታላይ ሰውም ተንኮለኛ የሆነን አንደበት ያዳምጣል። 5  በድሃ የሚያፌዝ ሁሉ ፈጣሪውን ይሳደባል፤በሌላው ሰው ላይ በደረሰው መከራ የሚደሰትም ሁሉ ከቅጣት አያመልጥም። 6  የልጅ ልጆች የሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፤አባቶችም ለወንዶች ልጆቻቸው ክብር ናቸው። 7  ለሞኝ ሰው ቀና ንግግር አይስማማውም። ለገዢ ደግሞ ሐሰተኛ ንግግር ጨርሶ አይሆነውም! 8  ስጦታ ለባለቤቱ እንደከበረ ድንጋይ ነው፤በሄደበት ሁሉ ስኬት ያስገኝለታል። 9  በደልን ይቅር የሚል ሁሉ ፍቅርን ይሻል፤አንድን ጉዳይ ደጋግሞ የሚያወራ ግን የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል። 10  ሞኝን ሰው መቶ ጊዜ ከመግረፍ ይልቅማስተዋል ያለውን ሰው አንድ ጊዜ መገሠጽ የተሻለ ውጤት ያስገኛል። 11  ክፉ ሰው የሚሻው ዓመፅን ብቻ ነው፤ሆኖም እሱን እንዲቀጣ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል። 12  የቂል ሥራ እየሠራ ካለ ሞኝ ሰው ጋር ከመገናኘት ይልቅግልገሎቿን ካጣች ድብ ጋር መገናኘት ይሻላል። 13  ማንኛውም ሰው ለመልካም ነገር ክፉ የሚመልስ ከሆነክፉ ነገር ከቤቱ አይጠፋም። 14  ጠብ መጫር ግድብን ከመሸንቆር ተለይቶ አይታይም፤ስለዚህ ጥል ከመነሳቱ በፊት ከአካባቢው ራቅ። 15  ክፉውን ነፃ የሚያደርግ፣ በጻድቁም ላይ የሚፈርድ፣ሁለቱም በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው። 16  ሞኝ ሰው ጥበብን የራሱ የሚያደርግበት ልብ ከሌለውጥበብ የሚያገኝበት መንገድ ቢኖር ምን ይጠቅማል? 17  እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው። 18  ማስተዋል የጎደለው ሰውበባልንጀራው ፊት እጅ በመጨበጥ ዋስ ለመሆን ይስማማል። 19  ጠብ የሚወድ ሁሉ በደልን ይወዳል። በሩን ወደ ላይ አስረዝሞ የሚሠራ ጥፋትን ይጋብዛል። 20  ልቡ ጠማማ የሆነ አይሳካለትም፤በምላሱም የሚያታልል ጥፋት ይደርስበታል። 21  የሞኝ ልጅ አባት ሐዘን ላይ ይወድቃል፤የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ልጅ የወለደም ደስታ አይኖረውም። 22  ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው፤የተደቆሰ መንፈስ ግን ኃይል ያሟጥጣል። 23  ክፉ ሰው ፍትሕን ለማዛባትበስውር ጉቦ ይቀበላል። 24  ጥልቅ ግንዛቤ ባለው ሰው ፊት ጥበብ ትገኛለች፤የሞኝ ሰው ዓይን ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታል። 25  ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤እናቱም እንድትመረር ያደርጋል። 26  ጻድቁን መቅጣት መልካም አይደለም። የተከበሩ ሰዎችንም መግረፍ ትክክል አይደለም። 27  አዋቂ ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰውም የተረጋጋ ነው። 28  ሞኝ ሰው እንኳ ዝም ሲል እንደ ጥበበኛ ይቆጠራል፤ከንፈሮቹንም የሚዘጋ ማስተዋል እንዳለው ተደርጎ ይታያል።
[]
[]
[]
[]
11,910
18  ራሱን የሚያገል ሰው ሁሉ የራስ ወዳድነት ምኞቱን ያሳድዳል፤ጥበብንም ሁሉ ይቃወማል። 2  ሞኝ ሰው ማስተዋል አያስደስተውም፤ይልቁንም በልቡ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል። 3  ክፉ ሰው ሲመጣ ንቀትም ይመጣል፤ከውርደትም ጋር ኀፍረት ይመጣል። 4  ከሰው አፍ የሚወጣ ቃል ጥልቅ ውኃ ነው። የጥበብ ምንጭ የሚንዶለዶል ጅረት ነው። 5  ለክፉ ሰው ማድላት፣ጻድቁንም ፍትሕ መንፈግ መልካም አይደለም። 6  የሞኝ ሰው ንግግር ጠብ ያስነሳል፤አፉም ዱላ ይጋብዛል። 7  የሞኝ አንደበት መጥፊያው ነው፤ከንፈሮቹም ለሕይወቱ ወጥመድ ናቸው። 8  ስም አጥፊ የሚናገረው ቃል ጣፋጭ እንደሆነ ቁራሽ ምግብ ነው፤በፍጥነት ተውጦ በቀጥታ ወደ ሆድ ይገባል። 9  በሥራው ታካች የሆነ ሰው ሁሉ፣የአጥፊ ወንድም ነው። 10  የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው። ጻድቅ ወደዚያ በመሮጥ ጥበቃ ያገኛል። 11  የባለጸጋ ሰው ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው፤በሐሳቡም ጥበቃ እንደሚያስገኝ ግንብ አድርጎ ይመለከተዋል። 12  ሰው ለውድቀት ከመዳረጉ በፊት ልቡ ይታበያል፤ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች። 13  እውነታውን ከመስማቱ በፊት መልስ የሚሰጥ ሰው፣ሞኝነት ይሆንበታል፤ ውርደትም ይከናነባል። 14  ጠንካራ መንፈስ ያለው ሰው ሕመሙን መቋቋም ይችላል፤የተደቆሰን መንፈስ ግን ማን ሊቋቋም ይችላል? 15  የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፤የጥበበኛም ጆሮ እውቀትን ለማግኘት ይጥራል። 16  ስጦታ ለሰጪው መንገዱን ይከፍትለታል፤በታላላቅ ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል። 17  ክሱን አስቀድሞ ያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ይህም ሌላው ወገን መጥቶ እስኪመረምረው ድረስ ነው። 18  ዕጣ መጣል ጭቅጭቅ እንዲያበቃ ያደርጋል፤ኃይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል። 19  የተበደለ ወንድም ከተመሸገች ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤እንደ ግንብ በሮች መቀርቀሪያም የጠነከረ ጠብ አለ። 20  ሰው በአፉ ፍሬ ሆዱ ይሞላል፤ከንፈሩም በሚያስገኘው ምርት ይረካል። 21  አንደበት የሞትና የሕይወት ኃይል አላት፤ሊጠቀምባት የሚወድ ፍሬዋን ይበላል። 22  ጥሩ ሚስት ያገኘ ጥሩ ነገር አግኝቷል፤የይሖዋንም ሞገስ ያገኛል። 23  ድሃ እየተለማመጠ ይናገራል፤ሀብታም ግን በኃይለ ቃል ይመልሳል። 24  እርስ በርስ ከመጠፋፋት ወደኋላ የማይሉ ጓደኛሞች አሉ፤ነገር ግን ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ አለ።
[]
[]
[]
[]
11,911
19  ሞኝ ከመሆንና ውሸት ከመናገርድሃ ሆኖ ንጹሕ አቋምን ጠብቆ መመላለስ ይሻላል። 2  እውቀት የሌለው ሰው ጥሩ አይደለም፤ችኩል ሰውም ኃጢአት ይሠራል። 3  የሰውን መንገድ የሚያጣምምበት የገዛ ሞኝነቱ ነው፤ልቡም በይሖዋ ላይ ይቆጣል። 4  ሀብት ብዙ ወዳጆችን ይስባል፤ድሃን ግን ጓደኛው እንኳ ይተወዋል። 5  ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ከቅጣት አያመልጥም። 6  ብዙዎች በተከበረ ሰው ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ይጥራሉ፤ስጦታ ከሚሰጥ ሰው ጋር ደግሞ ሁሉም ይወዳጃል። 7  ድሃን ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤ጓደኞቹማ ምን ያህል ይርቁት! እየተከታተለ ሊለማመጣቸው ይሞክራል፤ ምላሽ የሚሰጠው ግን የለም። 8  ማስተዋል የሚያገኝ ሰው ሁሉ ራሱን ይወዳል። ጥልቅ ግንዛቤን እንደ ውድ ሀብት አድርጎ የሚመለከት ሁሉ ይሳካለታል። 9  ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ይጠፋል። 10  ሞኝ ሰው ተንደላቆ መኖር አይገባውም፤አገልጋይ መኳንንትን ቢገዛማ ምንኛ የከፋ ነው! 11  ጥልቅ ማስተዋል ሰውን ቶሎ እንዳይቆጣ ያደርገዋል፤በደልንም መተዉ ውበት ያጎናጽፈዋል። 12  የንጉሥ ቁጣ እንደ አንበሳ ግሳት ነው፤ሞገሱ ግን በሣር ላይ እንዳለ ጤዛ ነው። 13  ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ መከራ ያመጣል፤ጨቅጫቃ ሚስትም ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት። 14  ቤትና ሀብት ከአባቶች ይወረሳል፤ልባም ሚስት ግን የምትገኘው ከይሖዋ ነው። 15  ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ታካች ሰውም ይራባል። 16  ትእዛዝን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤መንገዱን ቸል የሚል ይሞታል። 17  ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤ላደረገውም ነገር ብድራት ይከፍለዋል። 18  ገና ተስፋ ሳለ ልጅህን ገሥጽ፤ለእሱም ሞት ተጠያቂ አትሁን። 19  ግልፍተኛ ሰው ይቀጣል፤ልታድነው ብትሞክር እንኳ በተደጋጋሚ እንዲህ ለማድረግ ትገደዳለህ። 20  የኋላ ኋላ ጥበበኛ እንድትሆንምክርን ስማ፤ ተግሣጽንም ተቀበል። 21  ሰው በልቡ ብዙ ነገር ያቅዳል፤የሚፈጸመው ግን የይሖዋ ፈቃድ ነው። 22  የሰው ተወዳጅ ባሕርይ ታማኝ ፍቅሩ ነው፤ውሸታም ከመሆን ድሃ መሆን ይሻላል። 23  ይሖዋን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤እንዲህ የሚያደርግ ሰው ጥሩ እረፍት ያገኛል፤ ጉዳትም አይደርስበትም። 24  ሰነፍ እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፤ሆኖም ወደ አፉ እንኳ መመለስ ይሳነዋል። 25  ተሞክሮ የሌለው ብልህ እንዲሆን ፌዘኛን ምታው፤ተጨማሪ እውቀት እንዲያገኝም አስተዋይ የሆነን ሰው ውቀሰው። 26  አባቱን የሚበድልና እናቱን የሚያባርር ልጅኀፍረትና ውርደት ያመጣል። 27  ልጄ ሆይ፣ ተግሣጽን መስማት ከተውክእውቀት ከሚገኝበት ቃል ትርቃለህ። 28  የማይረባ ምሥክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤የክፉዎችም አፍ ክፋትን ይሰለቅጣል። 29  ፌዘኞች ፍርድ ይጠብቃቸዋል፤ለሞኞች ጀርባ ደግሞ ዱላ ተዘጋጅቷል።
[]
[]
[]
[]
11,912
2  ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበልናትእዛዛቴን እንደ ውድ ሀብት ብታስቀምጥ፣ 2  ይህን ለማድረግ ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ልብህን ብታዘነብል፣ 3  ደግሞም ማስተዋልን ብትጣራናጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ድምፅህን ብታሰማ፣ 4  እንደ ብር ተግተህ ብትፈልጋት፣እንዲሁም እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣ 5  ያን ጊዜ ይሖዋን መፍራት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ፤ደግሞም ስለ አምላክ እውቀት ትቀስማለህ። 6  ይሖዋ ራሱ ጥበብ ይሰጣልና፤ከአፉ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ይወጣል። 7  ለቅኖች ጥበብን እንደ ውድ ሀብት ያከማቻል፤ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀው ለሚመላለሱት ጋሻ ነው። 8  የፍትሕን ጎዳና ይከታተላል፤የታማኞቹንም መንገድ ይጠብቃል። 9  በዚህ ጊዜ ጽድቅ፣ ፍትሕና ትክክል የሆነውን ነገርይኸውም የጥሩነትን ጎዳና በሙሉ ትረዳለህ። 10  ጥበብ ወደ ልብህ ስትገባናእውቀት ነፍስህን ደስ ስታሰኝ፣ 11  የማመዛዘን ችሎታ ምንጊዜም ይጠብቅሃል፤ጥልቅ ግንዛቤም ይጋርድሃል፤ 12  ይህም አንተን ከክፉ መንገድ ለማዳንእንዲሁም ጠማማ ነገር ከሚናገር ሰው፣ 13  በጨለማ መንገድ ለመጓዝቀናውን ጎዳና ከሚተዉ፣ 14  መጥፎ ድርጊት በመፈጸም ሐሴት ከሚያደርጉ፣ጠማማ በሆኑ ክፉ ነገሮች ከሚደሰቱ፣ 15  መንገዳቸው ጠማማ ከሆነናአካሄዳቸው በተንኮል ከተሞላ ሰዎች አንተን ለመታደግ ነው። 16  ጋጠወጥ ከሆነች ሴት፣ባለጌ ሴት ከምትናገረው የሚያባብል ቃል ያድንሃል፤ 17  ይህች ሴት በወጣትነቷ የነበራትን የቅርብ ወዳጇን የምትተውእንዲሁም ከአምላኳ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን የምትረሳ ናት፤ 18  ቤቷ ሰውን ይዞ ወደ ሞት ይወርዳልና፤አካሄዷም በሞት ወደተረቱት ይወስዳል። 19  ከእሷ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁሉ አይመለሱም፤የሕይወትንም መንገድ ዳግመኛ አያገኙም። 20  በመሆኑም የጥሩ ሰዎችን መንገድ ተከተል፤እንዲሁም ከጻድቃን ጎዳና አትውጣ፤ 21  በምድር ላይ የሚኖሩት ቅኖች ብቻ ናቸውና፤በእሷም ላይ የሚቀሩት ነቀፋ የሌለባቸው ናቸው። 22  ክፉዎች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፤ከዳተኞችም ከእሷ ይወገዳሉ።
[]
[]
[]
[]
11,913
20  የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ የሚያሰክር መጠጥም ሥርዓት አልበኛ ያደርጋል፤በዚህ ምክንያት ከትክክለኛው መንገድ የሚወጣ ሁሉ ጥበበኛ አይደለም። 2  ንጉሥ የሚፈጥረው ሽብር እንደ አንበሳ ግሳት ነው፤የእሱን ቁጣ የሚያነሳሳ ሁሉ ሕይወቱን ለአደጋ ያጋልጣል። 3  ሰው ከጠብ መራቁ ያስከብረዋል፤ሞኝ የሆነ ሁሉ ግን ጥል ውስጥ ይዘፈቃል። 4  ሰነፍ ሰው በክረምት አያርስም፤በመሆኑም በመከር ወራት ባዶውን ሲቀር ይለምናል። 5  በሰው ልብ ውስጥ ያለ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤አስተዋይ ሰው ግን ቀድቶ ያወጣዋል። 6  ብዙ ሰዎች ስለ ራሳቸው ታማኝ ፍቅር ያወራሉ፤ይሁንና ታማኝ የሆነን ሰው ማን ሊያገኘው ይችላል? 7  ጻድቅ ንጹሕ አቋሙን ጠብቆ ይመላለሳል። ከእሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቹ ደስተኞች ናቸው። 8  ንጉሥ ለመፍረድ በዙፋን ላይ ሲቀመጥ፣ክፋትን ሁሉ በዓይኖቹ ያበጥራል። 9  “ልቤን አንጽቻለሁ፤ከኃጢአቴም ነጽቻለሁ” ሊል የሚችል ማን ነው? 10  አባይ ሚዛንና የሐሰት መለኪያ፣ሁለቱም በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ናቸው። 11  ሕፃን እንኳ ባሕርይው ንጹሕና ትክክል መሆኑበአድራጎቱ ይታወቃል። 12  የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፣ሁለቱንም የሠራው ይሖዋ ነው። 13  እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድሃ ትሆናለህ። ዓይንህን ግለጥ፤ የተትረፈረፈ ምግብም ታገኛለህ። 14  ዕቃ የሚገዛ ሰው “የማይረባ ነው፣ የማይረባ ነው!” ይላል፤ከሄደ በኋላ ግን በራሱ ይኩራራል። 15  ወርቅ አለ፤ ዛጎልም ተትረፍርፏል፤እውቀትን የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ውድ ናቸው። 16  አንድ ሰው ለማያውቀው ሰው ዋስ ከሆነ ልብሱን ውሰድበት፤ይህን ያደረገው ለባዕድ ሴት ብሎ ከሆነ መያዣውን ውሰድ። 17  ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ያስደስተዋል፤በኋላ ግን አፉን ኮረት ይሞላዋል። 18  መመካከር ሲኖር የታቀደው ነገር ይሳካል፤ለውጊያም ስትወጣ ጥበብ ያለበት አመራር ተቀበል። 19  ስም የሚያጠፋ ሰው እየዞረ የሌሎችን ሚስጥር ይገልጣል፤ማማት ከሚወድ ሰው ጋር አትወዳጅ። 20  አባቱንና እናቱን የሚረግም ሁሉጨለማ ሲሆን መብራቱ ይጠፋበታል። 21  በመጀመሪያ በስግብግብነት የተገኘ ውርስ፣የኋላ ኋላ በረከት አይሆንም። 22  “ቆይ፣ ብድሬን ባልመልስ!” አትበል። ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ እሱም ያድንሃል። 23  አባይ ሚዛን በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ለማጭበርበር የሚያገለግሉ መለኪያዎችንም መጠቀም ጥሩ አይደለም። 24  ይሖዋ የሰውን አካሄድ ይመራል፤ሰው የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል? 25  ሰው ቸኩሎ “የተቀደሰ ነው!” ቢልና ከተሳለ በኋላ ስእለቱን መልሶ ማጤን ቢጀምር ወጥመድ ይሆንበታል። 26  ጥበበኛ ንጉሥ ክፉ ሰዎችን ያበጥራል፤የመውቂያ መንኮራኩርም በላያቸው ያስኬዳል። 27  የሰው እስትንፋስ የይሖዋ መብራት ነው፤ውስጣዊ ማንነቱን በሚገባ ይመረምራል። 28  ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቃሉ፤በታማኝ ፍቅርም ዙፋኑን ያጸናል። 29  የወጣቶች ክብር ጉልበታቸው ነው፤የአረጋውያንም ግርማ ሽበታቸው ነው። 30  ሰንበርና ቁስል ክፋትን ያስወግዳል፤ግርፋትም የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ያጠራል።
[]
[]
[]
[]
11,914
21  የንጉሥ ልብ በይሖዋ እጅ እንዳለ ጅረት ነው። እሱ ደስ ወዳሰኘው አቅጣጫ ሁሉ ይመራዋል። 2  ሰው መንገዱ ሁሉ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤ይሖዋ ግን ልብን ይመረምራል። 3  መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅትክክልና ፍትሐዊ የሆነ ነገር ማድረግ ይሖዋን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል። 4  ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብየክፉዎች መብራት ናቸው፤ ደግሞም ኃጢአት ናቸው። 5  የትጉ ሰው ዕቅድ ለስኬት ያበቃዋል፤ችኩሎች ሁሉ ግን ለድህነት ይዳረጋሉ። 6  በሐሰተኛ ምላስ የሚገኝ ውድ ሀብትወዲያው እንደሚጠፋ ጉም ነው፤ ገዳይ ወጥመድም ነው። 7  ክፉዎች ፍትሕን ማስፈን ስለማይፈልጉየሚፈጽሙት ግፍ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል። 8  የበደለኛ ሰው መንገድ ጠማማ ነው፤የንጹሕ ሰው ሥራ ግን ቀና ነው። 9  ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖርበጣሪያ ማዕዘን ላይ መኖር ይሻላል። 10  ክፉ ሰው መጥፎ ነገር ይመኛል፤ለባልንጀራው ሞገስ አያሳይም። 11  ፌዘኛ ሲቀጣ ተሞክሮ የሌለው ሰው ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ጥበበኛ ሰው ጥልቅ ማስተዋል ሲያገኝም እውቀት ይቀስማል። 12  ጻድቅ የሆነው አምላክ፣ የክፉውን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ክፉዎችንም ይጠፉ ዘንድ ይገለብጣቸዋል። 13  ችግረኛው የሚያሰማውን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን ሁሉ፣እሱ ራሱ ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም። 14  በድብቅ የተሰጠ ስጦታ ቁጣን ያበርዳል፤በስውር የተሰጠ ጉቦም ኃይለኛ ቁጣ እንዲከስም ያደርጋል። 15  ጻድቅ ፍትሐዊ ነገር ማድረግ ያስደስተዋል፤ክፉ ድርጊት ለሚፈጽሙ ግን አስከፊ ነገር ነው። 16  ከማስተዋል መንገድ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣በሞት ከተረቱት ጋር ያርፋል። 17  ፈንጠዝያ የሚወድ ሰው ይደኸያል፤የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድ ባለጸጋ አይሆንም። 18  ክፉ ሰው ለጻድቅ ቤዛ ነው፤ከዳተኛ የሆነ ሰውም በቅን ሰው ፋንታ ይወሰዳል። 19  ጨቅጫቃና ቁጡ ከሆነች ሚስት ጋር ከመኖርበምድረ በዳ መኖር ይሻላል። 20  ውድ ሀብትና ምርጥ ዘይት በጥበበኛ ሰው ቤት ይገኛል፤ሞኝ ሰው ግን ያለውን ያባክናል። 21  ጽድቅንና ታማኝ ፍቅርን የሚከታተል ሰው ሁሉሕይወትን፣ ጽድቅንና ክብርን ያገኛል። 22  ጥበበኛ ሰው የኃያላን ሰዎች ከተማ ላይ ይወጣል፤የሚታመኑበትንም ብርታት ያዳክማል። 23  አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ፣ራሱን ከችግር ይጠብቃል። 24  በእብሪት የመሰለውን የሚያደርግ ሰውእብሪተኛና ጉረኛ ይባላል። 25  ሰነፍ ሰው ምኞቱ ይገድለዋል፤እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና። 26  ቀኑን ሙሉ በስግብግብነት ሲመኝ ይውላል፤ጻድቅ ግን ምንም ሳይሰስት ይሰጣል። 27  የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው። በክፉ ዓላማ ተነሳስቶ ሲያቀርብማ ምንኛ የከፋ ይሆናል! 28  ውሸታም ምሥክር ይጠፋል፤በጥሞና የሚያዳምጥ ሰው ግን የምሥክርነት ቃሉ ተቀባይነት ያገኛል። 29  ክፉ ሰው ኀፍረት የሚባል ነገር አያውቅም፤የቅን ሰው አካሄድ ግን አስተማማኝ ነው። 30  ይሖዋን የሚጻረር ጥበብ፣ ማስተዋልም ሆነ ምክር ከንቱ ነው። 31  ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤መዳን ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው።
[]
[]
[]
[]
11,915
22  መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይመረጣል፤መከበር ከብርና ከወርቅ ይሻላል። 2  ሀብታምንና ድሃን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፦ ሁለቱንም የፈጠረው ይሖዋ ነው። 3  ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል፤ተሞክሮ የሌለው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም ይቀበላል። 4  ትሕትናና ይሖዋን መፍራትሀብት፣ ክብርና ሕይወት ያስገኛል። 5  በጠማማ ሰው መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤ለሕይወቱ ትልቅ ግምት የሚሰጥ ሁሉ ግን ከእነዚህ ይርቃል። 6  ልጅን ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው፤በሚያረጅበት ጊዜም እንኳ ከዚያ ፈቀቅ አይልም። 7  ሀብታም ድሃን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪው ባሪያ ነው። 8  ክፋትን የሚዘራ ሁሉ ጥፋትን ያጭዳል፤የቁጣውም በትር ያከትማል። 9  ለጋስ ሰው ይባረካል፤ምግቡን ለድሃ ያካፍላልና። 10  ንቀት የሚያሳይን ሰው አባረው፤ጭቅጭቅም ይቀራል፤ጥልና ስድብ ያከትማል። 11  ንጹሕ ልብ የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፣የንጉሥ ወዳጅ ይሆናል። 12  የይሖዋ ዓይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፤የከዳተኛን ቃል ግን ይሽራል። 13  ሰነፍ “ውጭ አንበሳ አለ! አደባባይ ላይ እገደላለሁ!” ይላል። 14  የጋጠወጥ ሴት አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው። ይሖዋ ያወገዘው ሰው እዚያ ውስጥ ይወድቃል። 15  ሞኝነት በልጅ ልብ ውስጥ ታስሯል፤የተግሣጽ በትር ግን ከእሱ ያርቀዋል። 16  ሀብቱን ለመጨመር ድሃውን የሚያጭበረብርእንዲሁም ለባለጸጋ ስጦታ የሚሰጥ ሰውየኋላ ኋላ ይደኸያል። 17  እውቀቴን በሙሉ ልብ እንድትቀበልጆሮህን አዘንብል፤ የጥበበኞችንም ቃል አዳምጥ፤ 18  ምንጊዜም ይህ ቃል ሙሉ በሙሉ በከንፈሮችህ ላይ እንዲሆንቃሉን በውስጥህ መያዝህ መልካም ነውና። 19  በይሖዋ እንድትተማመን፣ዛሬ እውቀት እሰጥሃለሁ። 20  ከዚህ ቀደም ምክርናእውቀት የያዙ ሐሳቦች አልጻፍኩልህም? 21  ይህን ያደረግኩት ለላከህ ትክክለኛ ወሬ ይዘህ እንድትመለስ፣እውነት የሆነውንና እምነት የሚጣልበትን ቃል ላስተምርህ አይደለም? 22  ድሃውን ድሃ ስለሆነ ብቻ አትዝረፈው፤ችግረኛውንም በከተማው በር ላይ ግፍ አትፈጽምበት፤ 23  ይሖዋ ራሱ ይሟገትላቸዋልና፤የሚያጭበረብሯቸውንም ሰዎች ሕይወት ያጠፋል። 24  ከግልፍተኛ ሰው ጋር አትግጠም፤በቀላሉ ቱግ ከሚል ሰውም ጋር አትቀራረብ፤ 25  አለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ለራስህም ወጥመድ ይሆናል። 26  ዋስ ለመሆን እጅ እንደሚመቱ፣ለብድር ተያዥ እንደሚሆኑ ሰዎች አትሁን። 27  የምትከፍለው ካጣህየተኛህበት አልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል! 28  አባቶችህ ያደረጉትንየጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ። 29  በሥራው የተካነን ሰው አይተሃል? በነገሥታት ፊት ይቆማል፤ተራ በሆኑ ሰዎች ፊት አይቆምም።
[]
[]
[]
[]
11,916
23  ከንጉሥ ጋር ለመመገብ ስትቀመጥ፣በፊትህ ያለውን በሚገባ አስተውል፤ 2  ለመብላት ብትቋምጥ እንኳበጉሮሮህ ላይ ቢላ አስቀምጥ። 3  የእሱ ጣፋጭ ምግብ አያስጎምጅህ፤ምግቡ አታላይ ነውና። 4  ሀብት ለማግኘት አትልፋ። ይህን ትተህ በማስተዋል ተመላለስ። 5  ዓይንህን ስትጥልበት በዚያ አታገኘውም፤የንስር ዓይነት ክንፎች አውጥቶ ወደ ሰማይ ይበርራልና። 6  የስስታምን ምግብ አትብላ፤ጣፋጭ ምግቡ አያስጎምጅህ፤ 7  እሱ ሒሳብ እንደሚይዝ ሰው ነውና። “ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ የሚናገረው ግን ከልቡ አይደለም። 8  የበላሃትን ቁራሽ ምግብ ታስመልሳለህ፤የተናገርካቸው የምስጋና ቃላትም ከንቱ ይሆናሉ። 9  የምትናገራቸውን ጥበብ ያዘሉ ቃላት ስለሚንቅለሞኝ ሰው ምንም አትናገር። 10  የጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ፤ደግሞም አባት የሌላቸውን ልጆች መሬት አትያዝ። 11  የሚከራከርላቸው ብርቱ ነውና፤እሱ ራሱ ከአንተ ጋር ይሟገትላቸዋል። 12  ልብህን ለተግሣጽ፣ጆሮህንም ለእውቀት ቃል ስጥ። 13  ልጅን ከመገሠጽ ወደኋላ አትበል። በበትር ብትመታው አይሞትም። 14  ከመቃብር ታድነው ዘንድበበትር ምታው። 15  ልጄ ሆይ፣ ልብህ ጥበበኛ ቢሆን፣የእኔ ልብ ሐሴት ያደርጋል። 16  ከንፈሮችህ ትክክል የሆነውን ሲናገሩውስጤ ደስ ይለዋል። 17  ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ከዚህ ይልቅ ቀኑን ሙሉ ይሖዋን በመፍራት ተመላለስ፤ 18  እንዲህ ብታደርግ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤ተስፋህም ከንቱ አይሆንም። 19  ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ ጥበበኛም ሁን፤ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ምራ። 20  ብዙ የወይን ጠጅ እንደሚጠጡ፣ሥጋም ያለልክ እንደሚሰለቅጡ ሰዎች አትሁን፤ 21  ሰካራምና ሆዳም ይደኸያሉና፤ድብታ ሰውን የተቦጫጨቀ ልብስ ያስለብሰዋል። 22  የወለደህን አባትህን ስማ፤እናትህንም ስላረጀች አትናቃት። 23  እውነትንና ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ግዛ፤ፈጽሞም አትሽጣቸው። 24  የጻድቅ አባት ደስ ይለዋል፤ጥበበኛ ልጅ የወለደ ሁሉ በልጁ ሐሴት ያደርጋል። 25  አባትህና እናትህ ሐሴት ያደርጋሉ፤አንተን የወለደችም ደስ ይላታል። 26  ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፤ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ። 27  ዝሙት አዳሪ ጥልቅ ጉድጓድ፣ባለጌ ሴትም ጠባብ ጉድጓድ ናትና። 28  እንደ ዘራፊ ታደባለች፤ታማኝ ያልሆኑ ወንዶችን ቁጥር ታበዛለች። 29  ዋይታ የማን ነው? ጭንቀት የማን ነው? ጠብ የማን ነው? እሮሮ የማን ነው? ያለምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን ቅላት የማን ነው? 30  ይህ ሁሉ የሚደርሰው የወይን ጠጅ በመጠጣት ረጅም ጊዜ በሚያሳልፉ፣የተደባለቀም ወይን ጠጅ ፍለጋ በሚዞሩ ሰዎች ላይ ነው። 31  በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣እየጣፈጠም ሲወርድ በወይን ጠጅ ቅላት ዓይንህ አይማረክ፤ 32  በመጨረሻ እንደ እባብ ይናደፋልና፤እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል። 33  ዓይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤ልብህም ጠማማ ነገር ይናገራል። 34  በባሕር መካከል እንደተኛ፣በመርከብ ምሰሶም ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ። 35  እንዲህ ትላለህ፦ “መቱኝ፤ ሆኖም አልተሰማኝም። ደበደቡኝ፤ ሆኖም አልታወቀኝም። ተጨማሪ መጠጥ እጠጣ ዘንድ የምነቃው መቼ ነው?”
[]
[]
[]
[]
11,917
24  በክፉ ሰዎች አትቅና፤ከእነሱም ጋር ለመሆን አትጓጓ፤ 2  ልባቸው ዓመፅን ያውጠነጥናልና፤ከንፈራቸውም ተንኮልን ያወራል። 3  ቤት በጥበብ ይገነባል፤በማስተዋልም ይጸናል። 4  በእውቀት አማካኝነት ክፍሎቹበተለያዩ ውድ የሆኑና ያማሩ ነገሮች ተሞልተዋል። 5  ጥበበኛ ሰው ኃያል ነው፤ሰውም በእውቀት ኃይሉን ይጨምራል። 6  ጥበብ ያለበት አመራር ተቀብለህ ለውጊያ ትወጣለህ፤በብዙ አማካሪዎችም ድል ይገኛል። 7  ለሞኝ ሰው እውነተኛ ጥበብ ሊገኝ የማይችል ነገር ነው፤በከተማው በር ላይ አንዳች የሚናገረው ነገር የለውም። 8  መጥፎ ነገር ለማድረግ የሚያሴር ሁሉሴራ በመጠንሰስ የተካነ ተብሎ ይጠራል። 9  በሞኝነት የሚጠነሰስ ሴራ ኃጢአት ነው፤ሰዎችም ፌዘኛን ይጸየፋሉ። 10  በመከራ ቀን ተስፋ የምትቆርጥ ከሆነጉልበትህ እጅግ ይዳከማል። 11  ወደ ሞት እየተወሰዱ ያሉትን ታደግ፤ለእርድ እየተውተረተሩ የሚሄዱትንም አስጥል። 12  “እኛ ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም አናውቅም” ብትል፣ ልብን የሚመረምረው እሱ ይህን አያስተውልም? አዎ፣ አንተን የሚመለከተው አምላክ ያውቃል፤ለእያንዳንዱም ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል። 13  ልጄ ሆይ፣ መልካም ስለሆነ ማር ብላ፤ከማር እንጀራ የሚገኝ ማር ጣፋጭ ጣዕም አለው። 14  በተመሳሳይም ጥበብ ለአንተ መልካም እንደሆነ እወቅ። ጥበብን ብታገኝ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤ተስፋህም ከንቱ አይሆንም። 15  በጻድቁ ቤት ላይ በክፋት አትሸምቅ፤ማረፊያ ቦታውንም አታፍርስበት። 16  ጻድቅ ሰባት ጊዜ ቢወድቅ እንኳ መልሶ ይነሳልና፤ክፉ ሰው ግን በሚደርስበት መከራ ይሰናከላል። 17  ጠላትህ ሲወድቅ ሐሴት አታድርግ፤ሲሰናከልም ልብህ ደስ አይበለው፤ 18  አለዚያ ይሖዋ ይህን አይቶ ያዝናል፤ቁጣውንም ከእሱ ይመልሳል። 19  መጥፎ በሆኑ ሰዎች አትበሳጭ፤በክፉዎች አትቅና፤ 20  መጥፎ ሰው ሁሉ ምንም ተስፋ የለውምና፤የክፉዎች መብራት ይጠፋል። 21  ልጄ ሆይ፣ ይሖዋንና ንጉሥን ፍራ። ከተቃዋሚዎች ጋር አትተባበር፤ 22  ጥፋታቸው ድንገት ይመጣልና። ሁለቱም በእነሱ ላይ የሚያመጡትን ጥፋት ማን ያውቃል? 23  እነዚህም አባባሎች የጥበበኞች ናቸው፦ በፍርድ ማዳላት ጥሩ አይደለም። 24  ክፉውን “አንተ ጻድቅ ነህ” የሚለውን ሰው ሁሉ ሕዝቦች ይረግሙታል፤ ብሔራትም ያወግዙታል። 25  እሱን የሚወቅሱት ግን መልካም ይሆንላቸዋል፤በመልካም ነገሮችም ይባረካሉ። 26  ሰዎች በሐቀኝነት መልስ የሚሰጥን ሰው ከንፈር ይስማሉ። 27  በደጅ ያለህን ሥራ አሰናዳ፤ በእርሻም ላይ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አዘጋጅ፤ከዚያ በኋላ ቤትህን ሥራ። 28  ምንም መሠረት ሳይኖርህ በባልንጀራህ ላይ አትመሥክር። በከንፈሮችህ ሌሎችን አታታል። 29  “እሱ እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ፤እንደ ሥራው እከፍለዋለሁ” አትበል። 30  በሰነፍ ሰው እርሻ፣ማስተዋል በጎደለው ሰው የወይን ቦታ አለፍኩ። 31  እርሻው አረም ወርሶት አየሁ፤መሬቱን ሳማ ሸፍኖት፣የድንጋዩም አጥር ፈራርሶ ነበር። 32  ይህን ተመልክቼ በጥሞና አሰብኩበት፤ካየሁትም ነገር ይህን ትምህርት አገኘሁ፦ 33  ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣ 34  ድህነት እንደ ወንበዴ፣ችጋርም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።
[]
[]
[]
[]
11,918
25  እነዚህም የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ሰዎች የጻፏቸው የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፦ 2  አንድን ጉዳይ መሰወር ለአምላክ ክብሩ ነው፤ጉዳይን በሚገባ መመርመር ደግሞ ለነገሥታት ክብራቸው ነው። 3  ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉየንጉሥም ልብ አይመረመርም። 4  የብርን ቆሻሻ አስወግድ፤ሙሉ በሙሉም የጠራ ይሆናል። 5  ክፉን ሰው ከንጉሥ ፊት አስወግድ፤ዙፋኑም በጽድቅ ይጸናል። 6  በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ታላላቅ ሰዎችም ባሉበት ስፍራ አትቀመጥ፤ 7  በተከበረ ሰው ፊት ከሚያዋርድህ እሱ ራሱ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና። 8  ክስ ለመመሥረት አትቸኩል፤የኋላ ኋላ ባልንጀራህ ቢያዋርድህ ምን ይውጥሃል? 9  ከባልንጀራህ ጋር ስለ ራስህ ጉዳይ ተሟገት፤ሆኖም በሚስጥር የተነገረህን ጉዳይ አትግለጥ፤ 10  አለዚያ የሚሰማህ ሰው ያዋርድሃል፤ያናፈስከውንም መጥፎ ወሬ መመለስ አትችልም። 11  በተገቢው ጊዜ የተነገረ ቃልከብር በተሠራ ዕቃ ላይ እንዳለ የወርቅ ፖም ነው። 12  በጥበብ ወቀሳ የሚሰጥ ሰው፣ የሚሰማ ጆሮ ላለውእንደ ወርቅ ጉትቻና ከጥሩ ወርቅ እንደተሠራ ጌጥ ነው። 13  ታማኝ መልእክተኛ ለላኩት ሰዎችበመከር ወቅት እንደሚገኝ የበረዶ ቅዝቃዜ ነው፤የጌታውን መንፈስ ያድሳልና። 14  የማይሰጠውን ስጦታ እሰጣለሁ እያለ ጉራውን የሚነዛ ሰውዝናብ እንደማያመጣ ደመናና ነፋስ ነው። 15  በትዕግሥት አዛዥን ማሸነፍ ይቻላል፤ለስላሳም አንደበት አጥንትን ይሰብራል። 16  ማር ካገኘህ የሚበቃህን ያህል ብቻ ብላ፤ከልክ በላይ ከበላህ ሊያስመልስህ ይችላልና። 17  እንዳይሰለችህና እንዳይጠላህወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ። 18  በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሠክርእንደ ቆመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ሹል ፍላጻ ነው። 19  በችግር ወቅት እምነት በማይጣልበት ሰው መተማመን፣እንደተሰበረ ጥርስና እንደሰለለ እግር ነው። 20  ላዘነ ልብ የሚዘምር ሰው፣በብርድ ቀን ልብሱን እንደሚያወልቅ፣በሶዳም ላይ እንደተጨመረ ኮምጣጤ ነው። 21  ጠላትህ ቢራብ ምግብ ስጠው፤ቢጠማ ውኃ ስጠው፤ 22  ይህን ብታደርግ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህና፤ይሖዋም ወሮታ ይከፍልሃል። 23  የሰሜን ነፋስ ኃይለኛ ዝናብ ያመጣል፤ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቆጣል። 24  ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖርበጣሪያ ማዕዘን ላይ መኖር ይሻላል። 25  ቀዝቃዛ ውኃ የዛለችን ነፍስ እንደሚያረካ ሁሉከሩቅ አገር የመጣ መልካም ወሬም እንዲሁ ነው። 26  ለክፉ ሰው የሚንበረከክ ጻድቅ፣እንደጨቀየ ምንጭና እንደተበከለ የውኃ ጉድጓድ ነው። 27  ብዙ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤የራስንም ክብር መሻት አያስከብርም። 28  ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ሰውቅጥር እንደሌላት የፈረሰች ከተማ ነው።
[]
[]
[]
[]
11,919
26  በረዶ በበጋ፣ ዝናብም በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም። 2  ወፍ ቱር የምትልበት፣ ወንጭፊትም የምትበርበት ምክንያት እንዳላት ሁሉእርግማንም ያለበቂ ምክንያት አይመጣም። 3  አለንጋ ለፈረስ፣ ልጓም ለአህያ፣በትርም ለሞኞች ጀርባ ነው። 4  ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ አትመልስለት፤አለዚያ አንተም የእሱ ቢጤ ትሆናለህ። 5  ጥበበኛ የሆነ እንዳይመስለውለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት። 6  አንድን ጉዳይ ለሞኝ በአደራ የሚሰጥእግሩን ከሚያሽመደምድና ራሱን ከሚጎዳ ሰው ተለይቶ አይታይም። 7  በሞኞች አፍ የሚነገር ምሳሌ፣እንደ አንካሳ ሰው እግር ነው። 8  ለሞኝ ክብር መስጠት፣በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው። 9  በሞኞች አፍ የሚነገር ምሳሌበሰካራም እጅ እንዳለ እሾህ ነው። 10  ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር፣በነሲብ ያገኘውን ሁሉ እንደሚያቆስል ቀስተኛ ነው። 11  ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ፣ሞኝ ሰውም ሞኝነቱን ይደጋግማል። 12  ጥበበኛ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው አይተህ ታውቃለህ? ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው። 13  ሰነፍ “በመንገድ ላይ ደቦል አንበሳ፣በአደባባይም አንበሳ አለ!” ይላል። 14  በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ሰነፍም በአልጋው ላይ ይገላበጣል። 15  ሰነፍ እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፤ወደ አፉ ለመመለስ ግን እጅግ ይታክታል። 16  ሰነፍ ሰው በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ሰባት ሰዎች ይበልጥጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል። 17  በሌሎች ጠብ የሚቆጣ መንገደኛየውሻ ጆሮ እንደሚይዝ ሰው ነው። 18  የሚንበለበሉ ተወንጫፊ መሣሪያዎችን፣ ፍላጻዎችንና ሞትን እንደሚወረውር እብድ፣ 19  ባልንጀራውን አታሎ ሲያበቃ “ቀልዴን እኮ ነው!” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው። 20  እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ስም አጥፊ ከሌለ ደግሞ ጭቅጭቅ ይበርዳል። 21  ከሰል ፍምን፣ እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥልጨቅጫቃ ሰውም ጠብ ይጭራል። 22  ስም አጥፊ የሚናገረው ቃል ጣፋጭ እንደሆነ ቁራሽ ምግብ ነው፤በፍጥነት ተውጦ በቀጥታ ወደ ሆድ ይገባል። 23  ከክፉ ልብ የሚወጡ የፍቅር ቃላት፣በቀለጠ ብር እንደተለበጠ የሸክላ ዕቃ ስባሪ ናቸው። 24  ሌሎችን የሚጠላ ሰው ጥላቻውን በከንፈሩ ይደብቃል፤በውስጡ ግን ተንኮል ይቋጥራል። 25  አነጋገሩን ቢያሳምርም እንኳ አትመነው፤በልቡ ውስጥ ሰባት አስጸያፊ ነገሮች አሉና። 26  ጥላቻው በተንኮል ቢሸፈንምክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል። 27  ጉድጓድ የሚቆፍር እሱ ራሱ እዚያ ውስጥ ይወድቃል፤ድንጋይ የሚያንከባልልም ወደ እሱ ተመልሶ ይመጣበታል። 28  ውሸታም ምላስ የጎዳቻቸውን ሰዎች ትጠላለች፤የሚሸነግል አንደበትም ጥፋት ያስከትላል።
[]
[]
[]
[]
11,920
27  ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ፤ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና። 2  የገዛ አፍህ ሳይሆን ሌላ ሰው ያመስግንህ፤የገዛ ከንፈርህ ሳይሆን ሌሎች ያወድሱህ። 3  ድንጋይ ከባድ ነው፤ አሸዋም ሸክም ነው፤የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም ይከብዳል። 4  ንዴት ጨካኝ ነው፤ ቁጣም ጎርፍ ነው፤ይሁንና ቅናትን ማን ሊቋቋም ይችላል? 5  ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ወቀሳ ይሻላል። 6  የወዳጅ ማቁሰል ከታማኝነት የሚመነጭ ነው፤የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው። 7  የጠገበ ሰው ከማር እንጀራ የሚገኝን ማር አይፈልግም፤የተራበ ግን የሚመር ነገር እንኳ ይጣፍጠዋል። 8  ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰውከጎጆዋ ወጥታ እንደምትባዝን ወፍ ነው። 9  ዘይትና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤በቀና ምክር ላይ የተመሠረተ ጥሩ ወዳጅነትም እንዲሁ ነው። 10  መከራ ባጋጠመህ ቀን የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ ትተህወደ ገዛ ወንድምህ ቤት አትግባ፤ሩቅ ቦታ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል። 11  ልጄ ሆይ፣ ለሚነቅፈኝ መልስ መስጠት እችል ዘንድጥበበኛ ሁን፤ ልቤንም ደስ አሰኘው። 12  ብልህ ሰው አደጋ አይቶ ይሸሸጋል፤ተሞክሮ የሌለው ሰው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም ይቀበላል። 13  አንድ ሰው ለማያውቀው ሰው ዋስ ከሆነ ልብሱን ውሰድበት፤ይህን ያደረገው ለባዕድ ሴት ብሎ ከሆነ መያዣውን ውሰድ። 14  ሰው በማለዳ ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን ቢባርክእንደ እርግማን ይቆጠርበታል። 15  ጨቅጫቃ ሚስት በዝናባማ ቀን ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት። 16  እሷን መግታት የሚችል ሁሉ ነፋስን መግታት፣ዘይትንም በቀኝ እጁ መጨበጥ ይችላል። 17  ብረት ብረትን እንደሚስል ሁሉሰውም ጓደኛውን ይስለዋል። 18  የበለስን ዛፍ የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ጌታውንም የሚንከባከብ ክብር ይጎናጸፋል። 19  ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያንጸባርቅ ሁሉ፣የሰውም ልብ የሌላ ሰው ልብ ነጸብራቅ ነው። 20  መቃብርና የጥፋት ቦታ አይጠግቡም፤ልክ እንደዚሁም የሰው ዓይን ፈጽሞ አይጠግብም። 21  ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤ሰውም በሚቀበለው ውዳሴ ይፈተናል። 22  ሞኝን ሙቀጫ ውስጥ ከተህ በዘነዘና ብትወቅጠውናእንደ እህል ብታደቀው እንኳሞኝነቱ ከእሱ አይወገድም። 23  የመንጋህን ሁኔታ በሚገባ እወቅ። በጎችህን በደንብ ተንከባከብ፤ 24  ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤አክሊልም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም። 25  ሣሩ በቦታው የለም፤ አዲስ ሣርም በቅሏል፤በተራሮች ላይ ያለው ተክልም ተሰብስቧል። 26  የበግ ጠቦቶች ለልብስ፣አውራ ፍየሎችም ለመሬት መግዣ ይሆኑልሃል። 27  ደግሞም አንተንና ቤተሰብህን ለመመገብ፣ልጃገረዶችህንም በሕይወት ለማኖር የሚያስችል በቂ የፍየል ወተት ይኖርሃል።
[]
[]
[]
[]
11,921
28  ክፉዎች ማንም ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ፤ጻድቃን ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ናቸው። 2  በአንድ አገር ውስጥ ሕግ ተላላፊነት ሲነግሥ ብዙ ገዢዎች ይፈራረቁበታል፤ይሁንና ጥልቅ ግንዛቤና እውቀት ያለው ሰው በሚያበረክተው እርዳታ ገዢ ለረጅም ዘመን ይቆያል። 3  ችግረኞችን የሚበዘብዝ ድሃ፣እህሉን ሁሉ ጠራርጎ እንደሚወስድ ዝናብ ነው። 4  ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ሰዎች ግን በእነሱ ላይ ይቆጣሉ። 5  ክፉዎች ፍትሕን መረዳት አይችሉም፤ይሖዋን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር መረዳት ይችላሉ። 6  መንገዱ ብልሹ ከሆነ ሀብታም ይልቅንጹሕ አቋም ይዞ የሚመላለስ ድሃ ይሻላል። 7  አስተዋይ ልጅ ሕግን ይጠብቃል፤ከሆዳሞች ጋር የሚወዳጅ ግን አባቱን ያዋርዳል። 8  ወለድና አራጣ በማስከፈል ሀብት የሚያካብት፣ለድሆች ሞገስ ለሚያሳይ ሰው ያከማችለታል። 9  ሕግን ለመስማት አሻፈረኝ የሚል ሰው፣ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው። 10  ቅኖችን አሳስቶ ወደ መጥፎ መንገድ የሚመራ፣ እሱ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል፤ነቀፋ የሌለባቸው ሰዎች ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ። 11  ሀብታም ሰው በገዛ ዓይኖቹ ፊት ጥበበኛ ነው፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ድሃ ግን ማንነቱን ይደርስበታል። 12  ጻድቃን ድል ሲያደርጉ ታላቅ ክብር ይሆናል፤ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሰዎች ይሸሸጋሉ። 13  የሠራውን በደል የሚሸፋፍን አይሳካለትም፤የሚናዘዝና የሚተወው ሁሉ ግን ምሕረት ያገኛል። 14  ምንጊዜም ተጠንቅቆ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው፤ልቡን የሚያደነድን ሁሉ ግን ለጥፋት ይዳረጋል። 15  ምስኪን በሆነ ሕዝብ ላይ የተሾመ ክፉ ገዢ፣እንደሚያገሳ አንበሳና ተንደርድሮ እንደሚመጣ ድብ ነው። 16  ጥልቅ ግንዛቤ የሌለው መሪ ሥልጣኑን አላግባብ ይጠቀማል፤በማጭበርበር የሚገኝን ትርፍ የሚጠላ ግን ዕድሜውን ያራዝማል። 17  የሰው ሕይወት በማጥፋቱ የደም ባለ ዕዳ የሆነ ሰው መቃብር እስኪገባ ድረስ ሲሸሽ ይኖራል። እንዲህ ያለውን ሰው ማንም አይርዳው። 18  እንከን የለሽ በሆነ መንገድ የሚመላለስ ሰው ይድናል፤መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ድንገት ይወድቃል። 19  መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ የሆኑ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን እጅግ ይደኸያል። 20  ታማኝ ሰው ብዙ በረከት ያገኛል፤ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ንጽሕናውን ማጉደፉ አይቀርም። 21  አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤ሆኖም ሰው ለቁራሽ ዳቦ ብሎ ስህተት ሊፈጽም ይችላል። 22  ቀናተኛ ሰው ሀብት ለማግኘት ይጓጓል፤ድህነት ላይ እንደሚወድቅ አያውቅም። 23  በምላሱ ከሚሸነግል ይልቅሰውን የሚወቅስ የኋላ ኋላ ይበልጥ ሞገስ ያገኛል። 24  አባቱንና እናቱን እየዘረፈ “ምንም ጥፋት የለበትም” የሚል ሁሉ የአጥፊ ተባባሪ ነው። 25  ስግብግብ ሰው ጠብ ያነሳሳል፤በይሖዋ የሚታመን ግን ይበለጽጋል። 26  በገዛ ልቡ የሚታመን ሁሉ ሞኝ ነው፤በጥበብ የሚመላለስ ግን ክፉ አያገኘውም። 27  ለድሃ የሚሰጥ ሁሉ አይቸገርም፤እነሱን ላለማየት ዓይኖቹን የሚከድን ግን ብዙ እርግማን ይደርስበታል። 28  ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ሰው ራሱን ይሸሽጋል፤ክፉዎች ሲጠፉ ግን ጻድቃን ይበዛሉ።
[]
[]
[]
[]
11,922
29  ብዙ ጊዜ ተወቅሶ አንገቱን ያደነደነ ሰው፣ሊፈወስ በማይችል ሁኔታ በድንገት ይሰበራል። 2  ጻድቃን ሲበዙ ሕዝብ ሐሴት ያደርጋል፤ክፉ ሰው ሲገዛ ግን ሕዝብ ይቃትታል። 3  ጥበብን የሚወድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤ከዝሙት አዳሪዎች ጋር የሚወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል። 4  ንጉሥ ፍትሕ በማስፈን አገርን ያረጋጋል፤ጉቦ የሚፈልግ ሰው ግን ያወድማታል። 5  ባልንጀራውን የሚሸነግል ሰው፣ለእግሩ ወጥመድ ይዘረጋበታል። 6  መጥፎ ሰው በደሉ ወጥመድ ይሆንበታል፤ጻድቅ ግን እልል ይላል፤ ሐሴትም ያደርጋል። 7  ጻድቅ ለድሆች መብት ይቆረቆራል፤ክፉ ሰው ግን ለእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ደንታ የለውም። 8  ጉራ የሚነዙ ሰዎች ከተማን ያቃጥላሉ፤ጥበበኞች ግን ቁጣን ያበርዳሉ። 9  ጥበበኛ ሰው ከሞኝ ጋር ቢሟገት፣ሁከትና ፌዝ ይነግሣል፤ ደስታ ግን አይኖርም። 10  ደም የተጠሙ ሰዎች ንጹሕ የሆነን ሰው ሁሉ ይጠላሉ፤ቅን የሆነውን ሰው ሕይወት ለማጥፋት ይሻሉ። 11  ሞኝ ስሜቱን ሁሉ እንዳሻው ይገልጻል፤ጥበበኛ ግን ስሜቱን ይቆጣጠራል። 12  ገዢ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣አገልጋዮቹ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ። 13  ድሃንና ጨቋኝን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፦ ይሖዋ ለሁለቱም የዓይን ብርሃን ይሰጣል። 14  ንጉሥ ለድሆች በትክክል ሲፈርድ፣ዙፋኑ ምንጊዜም ጸንቶ ይኖራል። 15  በትርና ወቀሳ ጥበብ ያስገኛሉ፤መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል። 16  ክፉዎች ሲበዙ ክፋት ይበዛል፤ጻድቃን ግን የእነሱን ውድቀት ያያሉ። 17  ልጅህን ገሥጸው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ደግሞም እጅግ ደስ ያሰኝሃል። 18  ራእይ ከሌለ ሕዝብ እንዳሻው ይሆናል፤ሕግን የሚጠብቁ ግን ደስተኞች ናቸው። 19  አገልጋይ በቃል ብቻ ለመታረም ፈቃደኛ አይሆንም፤የሚነገረውን ነገር ቢረዳውም እንኳ እሺ ብሎ አይታዘዝምና። 20  ለመናገር የሚቸኩል ሰው አይተህ ታውቃለህ? ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው። 21  አገልጋይ ከልጅነቱ ጀምሮ ከተሞላቀቀ፣የኋላ ኋላ ምስጋና ቢስ ይሆናል። 22  በቀላሉ የሚቆጣ ሰው ጠብ ያስነሳል፤ግልፍተኛ የሆነም ብዙ በደል ይፈጽማል። 23  ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብር ይጎናጸፋል። 24  የሌባ ግብረ አበር ራሱን ይጠላል። እንዲመሠክር የቀረበለትን ጥሪ ቢሰማም ምንም አይናገርም። 25  ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው፤በይሖዋ የሚታመን ግን ጥበቃ ያገኛል። 26  ብዙዎች ከገዢ ጋር ተገናኝተው መነጋገር ይሻሉ፤ሰው ግን ፍትሕ የሚያገኘው ከይሖዋ ነው። 27  ጻድቅ ፍትሐዊ ያልሆነን ሰው ይጸየፋል፤ክፉ ሰው ግን በቀና መንገድ የሚሄደውን ይጸየፋል።
[]
[]
[]
[]
11,923
3  ልጄ ሆይ፣ ትምህርቴን አትርሳ፤ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ፤ 2  ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመንእንዲሁም ሰላም ያስገኙልሃልና። 3  ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት አይለዩህ። በአንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፋቸው፤ 4  ያን ጊዜ በአምላክና በሰው ፊት ሞገስ ታገኛለህ፤እንዲሁም ጥሩ ማስተዋል እንዳለህ ታስመሠክራለህ። 5  በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን፤ደግሞም በገዛ ራስህ ማስተዋል አትመካ። 6  በመንገድህ ሁሉ እሱን ግምት ውስጥ አስገባ፤እሱም ጎዳናህን ቀና ያደርገዋል። 7  በራስህ አመለካከት ጥበበኛ አትሁን። ይሖዋን ፍራ፤ ከክፉም ራቅ። 8  ለሰውነትህ ፈውስ፣ለአጥንትህም ብርታት ይሆንልሃል። 9  ባሉህ ውድ ነገሮች፣ከምርትህ ሁሉ በኩራት ይሖዋን አክብር፤ 10  ይህን ካደረግክ ጎተራዎችህ ጢም ብለው ይሞላሉ፤በወይን መጭመቂያዎችህም አዲስ የወይን ጠጅ ሞልቶ ይፈስሳል። 11  ልጄ ሆይ፣ የይሖዋን ተግሣጽ ለመቀበል እንቢተኛ አትሁን፤ወቀሳውም አያስመርርህ፤ 12  አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚወቅስ ሁሉይሖዋም የሚወዳቸውን ይወቅሳልና። 13  ጥበብን የሚያገኝ፣ጥልቅ ግንዛቤንም የራሱ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው፤ 14  ጥበብን ማግኘት ብርን ከማግኘት የተሻለ ነው፤እሷንም ማትረፍ ወርቅ ከማግኘት የተሻለ ነው። 15  ከዛጎል ይበልጥ ውድ ናት፤አንተ የምትመኘው ማንኛውም ነገር ሊተካከላት አይችልም። 16  በቀኟ ረጅም ዕድሜ አለ፤በግራዋም ሀብትና ክብር ይገኛል። 17  መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም የሰፈነበት ነው። 18  ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፤አጥብቀው የሚይዟትም ደስተኞች ይባላሉ። 19  ይሖዋ በጥበብ ምድርን መሠረተ። በማስተዋል ሰማያትን አጸና። 20  በእውቀቱ ጥልቅ ውኃዎች ተከፈሉ፤ደመና ያዘሉ ሰማያትም ጠል አንጠባጠቡ። 21  ልጄ ሆይ፣ እነዚህ ባሕርያት ከእይታህ አይራቁ። ጥበብንና የማመዛዘን ችሎታን ጠብቅ፤ 22  ሕይወት ያስገኙልሃል፤ለአንገትህም ጌጥ ይሆናሉ፤ 23  በዚያን ጊዜ በመንገድህ ላይ ተማምነህ ትሄዳለህ፤እግርህም ፈጽሞ አይሰናከልም። 24  በምትተኛበት ጊዜ አትፈራም፤ትተኛለህ፤ እንቅልፍህም ጣፋጭ ይሆናል። 25  ድንገት የሚከሰት የሚያሸብር ነገርም ሆነበክፉ ሰዎች ላይ የሚመጣ መዓት አያስፈራህም። 26  ይሖዋ መታመኛህ ይሆናልና፤እግርህን በወጥመድ እንዳይያዝ ይጠብቃል። 27  ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል አቅም ካለህለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትበል። 28  ለባልንጀራህ አሁኑኑ መስጠት እየቻልክ “ሂድና በኋላ ተመልሰህ ና! ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው። 29  ከአንተ ጋር ተማምኖ እየኖረ ሳለባልንጀራህን ለመጉዳት አታሲር። 30  መጥፎ ነገር ካላደረገብህከሰው ጋር ያለምክንያት አትጣላ። 31  በዓመፀኛ ሰው አትቅና፤የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ፤ 32  ይሖዋ ተንኮለኛን ሰው ይጸየፋልና፤ከቅኖች ጋር ግን የጠበቀ ወዳጅነት አለው። 33  ይሖዋ የክፉውን ቤት ይረግማል፤የጻድቁን መኖሪያ ግን ይባርካል። 34  በፌዘኞች ላይ ይሳለቃል፤ለየዋሆች ግን ሞገስ ያሳያል። 35  ጥበበኞች ክብርን ይወርሳሉ፤ሞኞች ግን ለውርደት የሚዳርግን ነገር ከፍ አድርገው ይመለከታሉ።
[]
[]
[]
[]
11,924
30  የያቄ ልጅ አጉር ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለዑካል የተናገራቸው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘሉ ቃላት። 2  እኔ ከማንም የባሰ አላዋቂ ነኝ፤ሰው ሊኖረው የሚገባው ማስተዋልም የለኝም። 3  ጥበብን አልተማርኩም፤እጅግ ቅዱስ የሆነው አምላክ እውቀትም የለኝም። 4  ወደ ሰማይ የወጣ፣ ከዚያም የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእፍኙ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው? ውኃን በልብሱ የጠቀለለ ማን ነው? የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ ማን ነው? ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው? ታውቅ እንደሆነ ንገረኝ። 5  የአምላክ ቃል ሁሉ የነጠረ ነው። እሱ፣ መጠጊያቸው ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው። 6  በቃሉ ላይ ምንም አትጨምር፤አለዚያ ይወቅስሃል፤ሐሰተኛም ሆነህ ትገኛለህ። 7  ሁለት ነገር እንድታደርግልኝ እለምንሃለሁ። እነሱንም ከመሞቴ በፊት አትንፈገኝ። 8  ውሸትንና ሐሰትን ከእኔ አርቅ። ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ። ብቻ የሚያስፈልገኝን ቀለብ አታሳጣኝ፤ 9  አለዚያ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ከዚያም “ይሖዋ ማን ነው?” እላለሁ፤ ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ አትፍቀድ። 10  እንዳይረግምህና በደለኛ ሆነህ እንዳትገኝበጌታው ፊት የአገልጋዩን ስም አታጥፋ። 11  አባቱን የሚረግም፣እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ። 12  በገዛ ዓይኑ ፊት ንጹሕ የሆነ፣ሆኖም ከቆሻሻው ያልነጻ ትውልድ አለ። 13  እጅግ ትዕቢተኛ ዓይን ያለው ትውልድ አለ፤ዓይኖቹም በታላቅ እብሪት ይመለከታሉ! 14  ጥርሱ ሰይፍ፣መንገጭላው ደግሞ ቢላ የሆነ ትውልድ አለ፤በምድር ላይ ያሉ ምስኪኖችን፣በሰው ዘር መካከል ያሉ ድሆችንም ይውጣል። 15  አልቅቶች “ስጡን! ስጡን!” እያሉ የሚጮኹ ሁለት ሴቶች ልጆች አሏቸው። ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤ደግሞም “በቃኝ!” የማያውቁ አራት ነገሮች አሉ። 16  እነሱም መቃብር፣ መሃን የሆነ ማህፀን፣ውኃ የተጠማ መሬትእንዲሁም “በቃኝ!” የማይል እሳት ናቸው። 17  በአባቷ ላይ የምታፌዝን፣ የእናቷንም ትእዛዝ የምትንቅን ዓይንየሸለቆ ቁራዎች ይጎጠጉጧታል፤የንስር ጫጩቶችም ይበሏታል። 18  ከመረዳት አቅሜ በላይ የሆኑ ሦስት ነገሮች አሉ፤የማልገነዘባቸውም አራት ነገሮች አሉ፦ 19  ንስር በሰማያት የሚበርበት መንገድ፣እባብ በዓለት ላይ የሚሄድበት መንገድ፣መርከብ በባሕር ላይ የሚጓዝበት መንገድ፣ሰውም ከሴት ልጅ ጋር የሚሄድበት መንገድ ናቸው። 20  የአመንዝራ ሴት መንገድ ይህ ነው፦ በልታ አፏን ከጠራረገች በኋላ“ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም” ትላለች። 21  ምድርን የሚያናውጡ ሦስት ነገሮች አሉ፤መታገሥ የማትችላቸውም አራት ነገሮች አሉ፦ 22  ባሪያ ንጉሥ ሆኖ ሲገዛ፣ሞኝ በልቶ ሲጠግብ፣ 23  የተጠላች ሴት ባል ስታገኝ፣ሴት አገልጋይም የእመቤቷን ቦታ ስትወስድ የሚከሰቱ ሁኔታዎች ናቸው። 24  በምድር ላይ በጣም ትናንሽ የሆኑ አራት ፍጥረታት አሉ፤ሆኖም በደመ ነፍስ ጥበበኞች ናቸው፦ 25  ጉንዳኖች ኃይል የሌላቸው ፍጥረታት ናቸው፤ይሁንና ምግባቸውን በበጋ ያዘጋጃሉ። 26  ሽኮኮዎች ኃያላን ፍጥረታት አይደሉም፤ነገር ግን መኖሪያቸውን በቋጥኞች ውስጥ ያደርጋሉ። 27  አንበጦች ንጉሥ የላቸውም፤ሆኖም ሁሉም በሰልፍ ወደ ፊት ይጓዛሉ። 28  እንሽላሊት በእግሮቿ ቆንጥጣ ትይዛለች፤ወደ ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ትገባለች። 29  ግርማ የተላበሰ አረማመድ ያላቸው ሦስት ፍጥረታት አሉ፤አዎ፣ እየተጎማለሉ የሚሄዱ አራት ፍጥረታት አሉ፦ 30  ከአራዊት ሁሉ ኃያል የሆነውናማንንም አይቶ ወደ ኋላ የማይመለሰው አንበሳ፣ 31  አዳኝ ውሻ፣ አውራ ፍየል፣እንዲሁም በሠራዊቱ የታጀበ ንጉሥ ናቸው። 32  በሞኝነት ራስህን ከፍ ከፍ ካደረግክ፣ወይም እንዲህ ለማድረግ ካሰብክእጅህን በአፍህ ላይ አድርግ። 33  ወተት ሲናጥ ቅቤ እንደሚወጣው፣አፍንጫም ሲጨመቅ እንደሚደማ ሁሉቁጣን ማነሳሳትም ጠብ ያስከትላል።
[]
[]
[]
[]
11,925
31  የንጉሥ ልሙኤል ቃል፤ እናቱ እሱን ለማስተማር የተናገረችው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘለ መልእክት፦ 2  ልጄ ሆይ፣ ምን ልበልህ?የማህፀኔ ልጅ ሆይ፣ ምን ልበልህ?የስእለቴ ልጅ ሆይ፣ ምን ልበልህ? 3  ጉልበትህን ለሴቶች አትስጥ፤ነገሥታትንም ለጥፋት የሚዳርግ መንገድ አትከተል። 4  ልሙኤል ሆይ፣ ነገሥታት የወይን ጠጅ መጠጣት የለባቸውም፤አዎ፣ ነገሥታት ይህን ማድረግ አይገባቸውም፤ገዢዎችም “መጠጤ የት አለ?” ሊሉ አይገባም። 5  አለዚያ ጠጥተው የተደነገገውን ሕግ ይረሳሉ፤የችግረኞችንም መብት ይጥሳሉ። 6  ሊጠፉ ለተቃረቡ ሰዎች መጠጥ፣ከባድ ጭንቀት ለደረሰባቸውም የወይን ጠጅ ስጧቸው። 7  ጠጥተው ድህነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ዳግመኛ አያስታውሱ። 8  ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት አንተ ተናገርላቸው፤ሊጠፉ ለተቃረቡት ሰዎች ሁሉ መብት ተሟገት። 9  ተናገር፤ በጽድቅም ፍረድ፤ለችግረኛውና ለድሃው መብት ጥብቅና ቁም። 10  ባለሙያ ሚስትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከዛጎል እጅግ ይበልጣል። 11  ባሏ ከልቡ ይታመንባታል፤አንዳችም ጠቃሚ ነገር አይጎድልበትም። 12  በሕይወቷ ዘመን ሁሉመልካም ነገር ታደርግለታለች እንጂ ክፉ ነገር አታደርግበትም። 13  ሱፍና በፍታ ታመጣለች፤በእጆቿ መሥራት ያስደስታታል። 14  እሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤ምግቧን ከሩቅ ቦታ ታመጣለች። 15  ገና ሳይነጋም ትነሳለች፤ለቤተሰቦቿም ምግባቸውን፣ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች። 16  በጥሞና ካሰበችበት በኋላ መሬት ትገዛለች፤በራሷ ጥረት ወይን ትተክላለች። 17  ወገቧን ታጥቃ ለሥራ ትነሳለች፤ክንዶቿንም ታበረታለች። 18  ንግዷ ትርፋማ እንደሆነ ታስተውላለች፤መብራቷ በሌሊት አይጠፋም። 19  እጆቿ አመልማሎ የያዘ ዘንግ ይጨብጣሉ፤ጣቶቿም እንዝርት ይይዛሉ። 20  እጆቿን ለተቸገረ ሰው ትዘረጋለች፤ለድሃውም እጇን ትከፍታለች። 21  ቤተሰቦቿ ሁሉ የሚያሞቅ ልብስ ስለሚለብሱበበረዶ ወቅት እንኳ አትሰጋም። 22  ለራሷ የአልጋ ልብስ ትሠራለች። ልብሷ ከበፍታና ከሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው። 23  ባሏ ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር በሚቀመጥበት በከተማዋ በሮችበሰዎች ዘንድ በሰፊው የታወቀ ነው። 24  የበፍታ ልብሶች እየሠራች ትሸጣለች፤ለነጋዴዎችም ቀበቶ ታስረክባለች። 25  ብርታትንና ግርማን ትጎናጸፋለች፤የወደፊቱንም ጊዜ በልበ ሙሉነት ትጠባበቃለች። 26  አፏን በጥበብ ትከፍታለች፤የደግነት ሕግም በአንደበቷ አለ። 27  የቤተሰቧን እንቅስቃሴ በደንብ ትከታተላለች፤የስንፍናንም ምግብ አትበላም። 28  ልጆቿ ተነስተው ደስተኛ ይሏታል፤ባሏ ተነስቶ ያወድሳታል። 29  ባለሙያ የሆኑ ብዙ ሴቶች አሉ፤አንቺ ግን፣ አዎ አንቺ ከሁሉም ትበልጫለሽ። 30  ውበት ሐሰት፣ ቁንጅናም አላፊ ነው፤ይሖዋን የምትፈራ ሴት ግን ትመሰገናለች። 31  ላከናወነችው ነገር ሽልማት ስጧት፤ሥራዎቿም በከተማዋ በሮች ያስመስግኗት።
[]
[]
[]
[]
11,926
4  ልጆቼ ሆይ፣ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፤ማስተዋል እንድታገኙ በትኩረት አዳምጡ፤ 2  ጥሩ መመሪያ እሰጣችኋለሁና፤ትምህርቴን አትተዉ። 3  እኔ ለአባቴ ጥሩ ልጅ ነበርኩ፤እናቴም ለእኔ ልዩ ፍቅር ነበራት። 4  አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፦ “ልብህ ቃሌን አጥብቆ ይያዝ። ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ። 5  ጥበብን አግኝ፤ ማስተዋልንም አዳብር። የምናገረውን ነገር አትርሳ፤ ከእሱም ፈቀቅ አትበል። 6  ጥበብን አትተዋት፤ እሷም ትጠብቅሃለች። ውደዳት፤ እሷም ትከልልሃለች። 7  ጥበብ በጣም አስፈላጊ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኝ፤ደግሞም ባለህ ነገር ሁሉ ማስተዋልን ለማግኘት ጥረት አድርግ። 8  ለጥበብ የላቀ ዋጋ ስጥ፤ እሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች። ብታቅፋት ታከብርሃለች። 9  በራስህ ላይ የሚያምር የአበባ ጉንጉን ትደፋልሃለች፤በውበት አክሊልም ታስጌጥሃለች።” 10  ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ የምናገረውንም ተቀበል፤የሕይወትህም ዘመን ይረዝማል። 11  በጥበብ መንገድ እንድትሄድ አስተምርሃለሁ፤ቀና በሆነ ጎዳና እመራሃለሁ። 12  በምትጓዝበት ጊዜ እርምጃህ አይስተጓጎልም፤ብትሮጥም አትሰናከልም። 13  ተግሣጽን ያዛት፤ አትልቀቃትም። ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና። 14  ወደ ክፉዎች መንገድ አትግባ፤በመጥፎ ሰዎች ጎዳናም አትሂድ። 15  ከእሱ ራቅ፤ በዚያም አትሂድ፤ከዚያ ጎዳና ፈቀቅ በል፤ ደግሞም አልፈኸው ሂድ። 16  እነሱ ክፋት ካልሠሩ አይተኙምና። ሰውን ለውድቀት ካልዳረጉ እንቅልፍ በዓይናቸው አይዞርም። 17  የክፋት ምግብ ይበላሉ፤የዓመፅም ወይን ጠጅ ይጠጣሉ። 18  የጻድቃን መንገድ ግን ፍንትው ብሎ እንደሚወጣ የማለዳ ብርሃን ነው፤እንደ ቀትር ብርሃን ቦግ ብሎ እስኪበራም ድረስ እየደመቀ ይሄዳል። 19  የክፉዎች መንገድ እንደ ጨለማ ነው፤ምን እንደሚያሰናክላቸው አያውቁም። 20  ልጄ ሆይ፣ ቃሌን በትኩረት ተከታተል፤ንግግሬን በጥሞና አዳምጥ። 21  ከእይታህ አይራቅ፤በልብህ ውስጥ አስቀምጠው፤ 22  ለሚያገኙት ሕይወት ነውና፤ለመላ አካላቸውም ጤና ነው። 23  ከምንም ነገር በላይ ልብህን ጠብቅ፤የሕይወት ምንጭ ከእሱ ዘንድ ነውና። 24  ጠማማ አንደበትን ከአንተ አስወግድ፤አታላይ የሆነን ንግግርም ከአንተ አርቅ። 25  ዓይኖችህ በቀጥታ ይዩ፤አዎ፣ ፊት ለፊት በትኩረት ተመልከት። 26  የእግርህን መንገድ ደልዳላ አድርግ፤መንገድህም ሁሉ አስተማማኝ ይሆናል። 27  ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል። እግርህን ከክፉ ነገር መልስ።
[]
[]
[]
[]
11,927
5  ልጄ ሆይ፣ ጥበቤን ልብ በል። ማስተዋልን በተመለከተ የምሰጠውን ትምህርት በጥሞና አዳምጥ፤ 2  ይህም የማመዛዘን ችሎታህን እንድትጠብቅ፣በከንፈሮችህም እውቀትን በጥንቃቄ እንድትይዝ ነው። 3  የጋጠወጥ ሴት ከንፈር እንደ ማር እንጀራ ያንጠባጥባልና፤አፏም ከዘይት ይለሰልሳል። 4  በመጨረሻ ግን እንደ ጭቁኝ ትመርራለች፤ደግሞም በሁለት በኩል እንደተሳለ ሰይፍ ትሆናለች። 5  እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ። እርምጃዎቿ በቀጥታ ወደ መቃብር ይመራሉ። 6  ስለ ሕይወት መንገድ ግድ የላትም። በጎዳናዎቿ ላይ ትባዝናለች፤ ወዴት እንደሚወስዱም አታውቅም። 7  እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤ከምናገረውም ቃል አትራቁ። 8  ከእሷ ራቅ፤ወደ ቤቷም ደጃፍ አትቅረብ፤ 9  ይህም ክብርህን ለሌሎች አሳልፈህ እንዳትሰጥ ነው፤ቀሪ የሕይወት ዘመንህም በመከራ የተሞላ እንዳይሆን ነው፤ 10  ደግሞም እንግዳ የሆኑ ሰዎች ጥሪትህን እንዳያሟጥጡ፣የለፋህበትንም ነገር የባዕድ አገር ሰው እንዳይወርሰው ነው። 11  አለዚያ በሕይወትህ ማብቂያሥጋህና መላ ሰውነትህ እየመነመነ ሲሄድ ትቃትታለህ፤ 12  ደግሞም እንዲህ ትላለህ፦ “ምነው ተግሣጽን ጠላሁ! ልቤስ ምነው ወቀሳን ናቀ! 13  የአስተማሪዎቼን ቃል አላዳመጥኩም፤መምህሮቼንም በጥሞና አልሰማሁም። 14  በመላው ጉባኤ መካከልሙሉ በሙሉ ልጠፋ ምንም አልቀረኝም ነበር።” 15  ከራስህ ጉድጓድ እንዲሁምከገዛ ምንጭህ የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ። 16  ምንጮችህ ወደ ውጭ፣ጅረቶችህም በአደባባይ ሊፈሱ ይገባል? 17  ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ። 18  ምንጭህ የተባረከ ይሁን፤ከወጣትነት ሚስትህም ጋር ደስ ይበልህ፤ 19  እሷ እንደምትወደድ ሚዳቋና እንደምታምር የተራራ ፍየል ናት። ጡቶቿ ምንጊዜም ያርኩህ። ፍቅሯ ምንጊዜም ይማርክህ። 20  ልጄ ሆይ፣ ጋጠወጥ ሴት ለምን ትማርክሃለች?ባለጌ ሴትንስ ለምን ታቅፋለህ? 21  የሰው መንገድ በይሖዋ ዓይኖች ፊት ነውና፤እሱ መንገዱን ሁሉ ይመረምራል። 22  ክፉ ሰው የገዛ ጥፋቱ ወጥመድ ይሆንበታል፤ኃጢአቱም እንደ ገመድ ተብትቦ ይይዘዋል። 23  ተግሣጽ ከማጣቱ የተነሳ ይሞታል፤በጣም ሞኝ ከመሆኑም የተነሳ መንገድ ይስታል።
[]
[]
[]
[]
11,928
6  ልጄ ሆይ፣ ለባልንጀራህ ዋስ ብትሆን፣የማታውቀውን ሰው እጅ ብትመታ፣ 2  በገባኸው ቃል ብትጠመድ፣ከአፍህ በወጣው ቃል ብትያዝ፣ 3  ልጄ ሆይ፣ በባልንጀራህ እጅ ወድቀሃልና፣ይህን በማድረግ ራስህን ነፃ አውጣ፦ ሂድና ባልንጀራህን በትሕትና አጥብቀህ ለምነው። 4  ይህን ሳታደርግ አትተኛ፤በዓይንህም እንቅልፍ አይዙር። 5  እንደ ሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣እንደ ወፍም ከወፍ አዳኝ እጅ ራስህን አድን። 6  አንተ ሰነፍ፣ ወደ ጉንዳን ሂድ፤መንገዷንም በጥሞና ተመልክተህ ጥበበኛ ሁን። 7  አዛዥ፣ አለቃ ወይም ገዢ ባይኖራትም እንኳ፣ 8  ምግቧን በበጋ ታዘጋጃለች፤ቀለቧንም በመከር ወቅት ትሰበስባለች። 9  አንተ ሰነፍ፣ የምትጋደመው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህ የምትነሳውስ መቼ ነው? 10  ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣ 11  ድህነት እንደ ወንበዴ፣እጦትም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። 12  የማይረባና ክፉ ሰው ንግግሩ ጠማማ ነው፤ 13  በዓይኑ ይጣቀሳል፤ በእግሩ ምልክት ይሰጣል፤ በጣቶቹም ይጠቁማል። 14  ጠማማ በሆነው ልቡ፣ነጋ ጠባ ሴራ ይጠነስሳል፤ ጠብም ይዘራል። 15  በመሆኑም ጥፋት በድንገት ይመጣበታል፤እንደማይጠገን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል። 16  ይሖዋ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤እንዲያውም እሱ የሚጸየፋቸው ነገሮች ሰባት ናቸው፦ 17  ትዕቢተኛ ዓይን፣ ውሸታም ምላስ፣ ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣ 18  ክፉ ሐሳብ የሚያውጠነጥን ልብና ወደ ክፋት በፍጥነት የሚሮጡ እግሮች፣ 19  ባወራ ቁጥር ውሸት የሚናገር ሐሰተኛ ምሥክርናበወንድማማቾች መካከል ጠብ የሚዘራ ሰው። 20  ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፤የእናትህንም መመሪያ ቸል አትበል። 21  ምንጊዜም በልብህ አኑራቸው፤በአንገትህም ዙሪያ እሰራቸው። 22  በምትሄድበት ሁሉ ይመራሃል፤ስትተኛም ይጠብቅሃል፤ስትነቃም ያነጋግርሃል። 23  ትእዛዙ መብራት ነውና፤ሕጉም ብርሃን ነው፤የተግሣጽ ወቀሳም ወደ ሕይወት ይመራል። 24  ከክፉ ሴት፣ ከባለጌ ሴትምየሚያባብል አንደበት ይጠብቁሃል። 25  ውበቷን በልብህ አትመኝ፤የሚያማምሩ ዓይኖቿም አይማርኩህ፤ 26  አንድ ሰው በዝሙት አዳሪ የተነሳ ለድህነት ይዳረጋልና፤አመንዝራ ሴት ደግሞ የሰውን ውድ ሕይወት ታጠምዳለች። 27  በጉያው እሳት ታቅፎ ልብሱ የማይቃጠልበት ሰው አለ? 28  ወይስ በፍም ላይ ተራምዶ እግሮቹ የማይቃጠሉበት ሰው ይኖራል? 29  ከባልንጀራው ሚስት ጋር የሚተኛ ሰውም እንደዚሁ ነው፤የሚነካት ሁሉ መቀጣቱ አይቀርም። 30  ሌባ በተራበ ጊዜ ራሱን ሊያጠግብ ቢሰርቅ፣ሰዎች በንቀት አያዩትም። 31  በተያዘ ጊዜ ግን ሰባት እጥፍ ይከፍላል፤በቤቱ ያለውን ውድ ነገር ሁሉ ያስረክባል። 32  ከሴት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሁሉ ማስተዋል ይጎድለዋል፤እንዲህ የሚያደርግ ሰው በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል። 33  የሚያተርፈው ነገር ቢኖር ቁስልና ውርደት ነው፤ኀፍረቱም መቼም አይወገድም። 34  ቅናት ባልን እጅግ ያስቆጣዋልና፤ለበቀል በሚነሳበት ጊዜም ፈጽሞ ርኅራኄ አያሳይም። 35  ማንኛውንም ዓይነት ካሳ አይቀበልም፤ምንም ያህል ስጦታ ብታቀርብለት ቁጣው አይበርድም።
[]
[]
[]
[]
11,929
7  ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ጠብቅ፤ትእዛዛቴንም እንደ ውድ ሀብት ያዝ። 2  ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ፤መመሪያዬን እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ። 3  በጣቶችህ ላይ እሰራቸው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፋቸው። 4  ጥበብን “እህቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፤ 5  ጋጠወጥና ባለጌ ከሆነች ሴት፣እንዲሁም ከምትናገረው የሚያባብል ቃል ይጠብቁሃል። 6  በቤቴ መስኮት በፍርግርጉ በኩልአጮልቄ ወደ ታች ተመለከትኩ፤ 7  ደግሞም ሞኞችን ትክ ብዬ በማይበት ጊዜ፣በዚያ ከነበሩት ወንዶች ልጆች መካከል ማስተዋል የጎደለውን አንድ ወጣት አየሁ። 8  በቤቷ አቅራቢያ በሚገኝ መታጠፊያ አልፎወደ ቤቷ አቅጣጫ አመራ፤ 9  ቀኑ መሸትሸት ብሎ ለዓይን ያዝ አድርጓል፤የሌሊቱ ጨለማ እየተቃረበ ነበር። 10  ከዚያም እንደ ዝሙት አዳሪ የለበሰችናበልቧ አታላይ የሆነች ሴት ከእሱ ጋር ስትገናኝ አየሁ። 11  ሴትየዋ ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ነች። ፈጽሞ ቤቷ አትቀመጥም። 12  አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ ትታያለች፤በየመንገዱ መታጠፊያም ታደባለች። 13  አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ያላንዳች ኀፍረትም እንዲህ አለችው፦ 14  “የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ። ዛሬ ስእለቴን ፈጽሜአለሁ። 15  አንተን ለማግኘት የወጣሁት ለዚህ ነው፤አንተን ፍለጋ ወጣሁ፤ ደግሞም አገኘሁህ! 16  መኝታዬን ባማረ የአልጋ ልብስ፣ከግብፅ በመጣ በቀለማት ያሸበረቀ በፍታ አስጊጬዋለሁ። 17  አልጋዬ ላይ ከርቤ፣ እሬትና ቀረፋ አርከፍክፌአለሁ። 18  ና፣ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፤እርስ በርሳችን ፍቅራችንን በመግለጽ እንደሰት፤ 19  ባሌ ቤት የለምና፤ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል። 20  በከረጢት ገንዘብ ይዟል፤ደግሞም ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን ድረስ ወደ ቤት አይመለስም።” 21  እንደ ምንም ብላ አግባብታ ታሳስተዋለች። በለሰለሰ አንደበቷ ታታልለዋለች። 22  ለእርድ እንደሚነዳ በሬ፣ለቅጣትም በእግር ግንድ እንደታሰረ ሞኝ ሰው በድንገት ይከተላታል፤ 23  ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ፣በወጥመድ ለመያዝ እንደምትቸኩል ወፍ ተከትሏት ይሄዳል፤ ሕይወቱን ሊያሳጣው እንደሚችል አላወቀም። 24  እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤የምናገረውንም ቃል በትኩረት ስሙ። 25  ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ። መንገድ ስታችሁ ወደ ጎዳናዋ አትግቡ፤ 26  ተሰይፈው እንዲወድቁ ያደረገቻቸው ብዙ ናቸውና፤እሷ የገደለቻቸውም እጅግ ብዙ ናቸው። 27  ቤቷ ወደ መቃብር ይወስዳል፤ሙታን ወዳሉበት ስፍራም ይወርዳል።
[]
[]
[]
[]
11,930
8  ጥበብ እየተጣራች አይደለም? ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እያሰማች አይደለም? 2  በጎዳና አጠገብ በሚገኙ ከፍታ ቦታዎች፣መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ ላይ ቆማለች። 3  ወደ ከተማዋ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣በደጆቹ መግቢያዎች ላይድምፅዋን ከፍ አድርጋ ትጮኻለች፦ 4  “ሰዎች ሆይ፣ የምጣራው እናንተን ነው፤ድምፄን ከፍ አድርጌ የማሰማው ለሁሉም ነው። 5  እናንተ ተሞክሮ የሌላችሁ፣ ብልሃትን ተማሩ፤እናንተ ሞኞች፣ አስተዋይ ልብ ይኑራችሁ። 6  የምናገረው ነገር በጣም አስፈላጊ ስለሆነ አዳምጡኝ፤ከንፈሮቼ ትክክል የሆነውን ይናገራሉ፤ 7  አንደበቴ በለሰለሰ ድምፅ እውነትን ይናገራልና፤ከንፈሮቼም ክፋትን ይጸየፋሉ። 8  ከአፌ የሚወጡት ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው። የተጣመመ ወይም የተወላገደ ነገር አይገኝባቸውም። 9  ጥልቅ ግንዛቤ ላለው፣ ሁሉም ቀና ናቸው፤እውቀት ላላቸውም ትክክል ናቸው። 10  ከብር ይልቅ ተግሣጼን፣ጥራት ካለውም ወርቅ ይልቅ እውቀትን ተቀበሉ፤ 11  ጥበብ ከዛጎል ትበልጣለችና፤ተፈላጊ የሆኑ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ከእሷ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም። 12  እኔ ጥበብ፣ ከብልሃት ጋር አብሬ እኖራለሁ፤እውቀትና የማመዛዘን ችሎታ አግኝቻለሁ። 13  ይሖዋን መፍራት ማለት ክፉ ነገርን መጥላት ነው። ትዕቢትን፣ ኩራትን፣ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ። 14  ጥሩ ምክር መስጠት እችላለሁ፤ ማስተዋል የታከለበት ጥበብም አለኝ፤ማስተዋልና ኃይል የእኔ ናቸው። 15  ነገሥታት የሚገዙት በእኔ ነው፤ከፍተኛ ባለሥልጣናትም የጽድቅ ድንጋጌ የሚያወጡት በእኔ ነው። 16  መኳንንት የሚገዙት በእኔ ነው፤ታላላቅ ሰዎችም በጽድቅ የሚፈርዱት በእኔ ነው። 17  የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፤የሚፈልጉኝም ያገኙኛል። 18  ሀብትና ክብር፣ዘላቂ ብልጽግናና ጽድቅ በእኔ ዘንድ አሉ። 19  ፍሬዬ ከወርቅ፣ አልፎ ተርፎም ከጠራ ወርቅ ይሻላል፤ከእኔ የምታገኙት ስጦታም ጥራት ካለው ብር ይበልጣል። 20  በጽድቅ መንገድ፣በፍትሕ ጎዳና መካከል እጓዛለሁ፤ 21  ለሚወዱኝ ውድ የሆኑ ነገሮችን አወርሳለሁ፤ግምጃ ቤቶቻቸውንም እሞላለሁ። 22  ይሖዋ የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፤ከብዙ ዘመን በፊት ካከናወናቸው ሥራዎች ቀዳሚው አደረገኝ። 23  ከጥንት፣ ከመጀመሪያው አንስቶ፣ምድርም ከመፈጠሯ አስቀድሞ ከፍ ያለ ቦታ ተሰጠኝ። 24  ጥልቅ ውኃዎች ባልነበሩበት ጊዜ፣ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድኩ። 25  ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣ከኮረብቶች በፊት ተወለድኩ፤ 26  ምድርንም ሆነ ሜዳዎቹን እንዲሁምየመጀመሪያዎቹን የአፈር ጓሎች ከመሥራቱ በፊት ተወለድኩ። 27  ሰማያትን ባዘጋጀ ጊዜ በዚያ ነበርኩ፤በውኃዎች ላይ የአድማስን ምልክት ባደረገ ጊዜ፣ 28  ደመናትን በላይ ባዘጋጀ ጊዜ፣የጥልቅ ውኃ ምንጮችን በመሠረተ ጊዜ፣ 29  የባሕሩ ውኃከትእዛዙ አልፎ እንዳይሄድ በደነገገ ጊዜ፣የምድርን መሠረቶች ባቆመ ጊዜ፣ 30  በዚያን ወቅት የተዋጣለት ሠራተኛ ሆኜ ከጎኑ ነበርኩ። በየዕለቱ በእኔ የተነሳ ልዩ ደስታ ይሰማው ነበር፤እኔም በፊቱ ሁልጊዜ ሐሴት አደርግ ነበር፤ 31  እሱ በፈጠረው፣ ሰው በሚኖርበት ምድር ሐሴት አደረግኩ፤በተለይ ደግሞ በሰው ልጆች እጅግ እደሰት ነበር። 32  እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤አዎ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ደስተኞች ናቸው። 33  ተግሣጽን ስሙ፤ ጥበበኞችም ሁኑ፤ፈጽሞም ቸል አትበሉት። 34  በየዕለቱ በማለዳ በራፌ ላይ መጥቶ፣በበሬ መቃን አጠገብ ቆሞ በመጠባበቅየሚያዳምጠኝ ሰው ደስተኛ ነው፤ 35  እኔን የሚያገኝ ሕይወትን ያገኛልና፤በይሖዋም ዘንድ ሞገስ ያገኛል። 36  እኔን ችላ የሚል ግን ራሱን ይጎዳል፤የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወዳሉ።”
[]
[]
[]
[]
11,931
9  እውነተኛ ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አዘጋጀች። 2  ሥጋዋን በሚገባ አዘጋጀች፤የወይን ጠጇንም ደባለቀች፤ደግሞም ገበታዋን አሰናዳች። 3  ከከተማዋ በላይ ባሉ ከፍታ ቦታዎች ላይ ሆነውእንዲህ ብለው እንዲጣሩ ሴት አገልጋዮቿን ላከች፦ 4  “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።” ማስተዋል ለጎደለው እንዲህ ትላለች፦ 5  “ኑ፣ ያዘጋጀሁትን ምግብ ብሉ፤የደባለቅኩትንም የወይን ጠጅ ጠጡ። 6  አላዋቂነታችሁን ተዉ፤ በሕይወትም ኑሩ፤በማስተዋል መንገድ ወደ ፊት ሂዱ።” 7  ፌዘኛን የሚያርም በራሱ ላይ ውርደት ያመጣል፤ክፉን ሰው የሚወቅስም ሁሉ ጉዳት ይደርስበታል። 8  ፌዘኛን አትውቀስ፤ አለዚያ ይጠላሃል። ጥበበኛን ሰው ውቀሰው፤ እሱም ይወድሃል። 9  ጥበበኛን ሰው አስተምረው፤ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል። ጻድቅን ሰው አስተምረው፤ ተጨማሪ እውቀት ያገኛል። 10  የጥበብ መጀመሪያ ይሖዋን መፍራት ነው፤እጅግ ቅዱስ ስለሆነው አምላክ ማወቅም ማስተዋል ነው። 11  በእኔ ምክንያት ዘመንህ ይረዝማል፤በሕይወትህም ላይ ዕድሜ ይጨመርልሃል። 12  ጥበበኛ ብትሆን፣ ጥበበኛነትህ የሚጠቅመው ራስህን ነው፤ፌዘኛ ብትሆን ግን መዘዙን የምትቀበለው አንተው ነህ። 13  ማስተዋል የጎደላት ሴት ጯኺ ናት። እሷ ጨርሶ ማመዛዘን አትችልም፤ ደግሞም አንዳች ነገር አታውቅም። 14  በከተማዋ ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ፣በቤቷ ደጃፍ ወንበር ላይ ትቀመጣለች፤ 15  በጎዳናው የሚያልፉትን፣ቀጥ ብለው በመንገዳቸው የሚሄዱትን ትጣራለች፦ 16  “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።” ማስተዋል ለጎደላቸው ሁሉ እንዲህ ትላለች፦ 17  “የተሰረቀ ውኃ ይጣፍጣል፤ተደብቀው የበሉት ምግብም ይጥማል።” 18  እሱ ግን በሞት የተረቱት በዚያ እንዳሉ፣እንግዶቿም በመቃብር ጥልቅ ውስጥ እንደሚገኙ አያውቅም።
[]
[]
[]
[]
11,932
1  በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን እንዴት ብቻዋን ቀረች! ከሌሎች ብሔራት ይበልጥ ብዙ ሕዝብ የነበረባት ከተማ እንዴት እንደ መበለት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው ከተማ እንዴት ለባርነት ተዳረገች! 2  በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋም በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል። ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል አንድም የሚያጽናናት የለም። ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላት ሆነውባታል። 3  ይሁዳ ተጎሳቁላና ለአስከፊ ባርነት ተዳርጋ በግዞት ተወስዳለች። በብሔራት መካከል ትቀመጣለች፤ ምንም ማረፊያ ስፍራ አታገኝም። በተጨነቀች ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ ያዟት። 4  በዓል ለማክበር የሚመጣ ስለሌለ ወደ ጽዮን የሚወስዱት መንገዶች አዝነዋል። በሮቿ ሁሉ ወና ሆነዋል፤ ካህናቷም ሲቃ ይዟቸዋል። ደናግሏ አዝነዋል፤ እሷም አስከፊ ሥቃይ ደርሶባታል። 5  ባላጋራዎቿ አሁን ጌቶቿ ሆነዋል፤ ጠላቶቿ ጭንቀት የለባቸውም። ከበደሏ ብዛት የተነሳ ይሖዋ ሐዘን አምጥቶባታልና። ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው ተወስደዋል። 6  የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተገፏል። መኳንንቷ መሰማሪያ ቦታ እንዳጡ አጋዘኖች ሆነዋል፤በሚያሳድዳቸውም ፊት አቅም አጥተው ይጓዛሉ። 7  ኢየሩሳሌም በምትጎሳቆልበትና መኖሪያ በምታጣበት ጊዜ፣በጥንት ዘመን የነበሯትን ውድ ነገሮች ሁሉ ታስታውሳለች። ሕዝቧ በጠላት እጅ በወደቀበትና የሚረዳት ባልነበረበት ጊዜጠላቶቿ አዩአት፤ በደረሰባትም ውድቀት ሳቁ። ח[ኼት] 8  ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ፈጽማለች። አስጸያፊ ነገር የሆነችው ለዚህ ነው። ያከብሯት የነበሩ ሁሉ አሁን ናቋት፤ እርቃኗን አይተዋልና። እሷ ራሷም ትቃትታለች፤ በኀፍረትም ፊቷን ታዞራለች። 9  ርኩሰቷ ቀሚሷ ላይ አለ። ወደፊት የሚገጥማትን ቆም ብላ አላሰበችም። ውድቀቷ አስደንጋጭ ነበር፤ የሚያጽናናትም የለም። ይሖዋ ሆይ፣ ጉስቁልናዬን ተመልከት፤ ጠላት ራሱን ከፍ ከፍ አድርጓልና። 10  ጠላት በውድ ሀብቶቿ ሁሉ ላይ እጁን አሳርፏል። ወደ አንተ ጉባኤ እንዳይገቡ ያዘዝካቸው ብሔራትወደ መቅደሷ ሲገቡ አይታለችና። 11  ነዋሪዎቿ ሁሉ ሲቃ ይዟቸዋል፤ የሚበላ ነገር ይፈልጋሉ። ምግብ ለማግኘትና በሕይወት ለመቆየት ብቻ ሲሉ ያሏቸውን ውድ ነገሮች ሰጥተዋል። ይሖዋ ሆይ፣ እይ ደግሞም ተመልከት፤ እንደማትረባ ሴት ሆኛለሁና። 12  በዚህ መንገድ የምታልፉ ሁሉ፣ ይህ ለእናንተ ከምንም የማይቆጠር ነገር ነው? እዩ፤ ደግሞም ተመልከቱ! ይሖዋ በሚነድ ቁጣው ቀን እንድሠቃይ ያደረገበትን፣በእኔ ላይ የደረሰውን ሥቃይ የመሰለ ሥቃይ አለ? 13  ከከፍታ ቦታ ወደ አጥንቶቼ እሳት ላከ፤ በእያንዳንዳቸውም ላይ አየለባቸው። ለእግሬ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላ እንድመለስ አስገደደኝ። የተጣለች ሴት አድርጎኛል። ቀኑን ሙሉ ታምሜአለሁ። 14  በደሎቼ እንደ ቀንበር ታስረዋል፤ በእጁም ተገምደዋል። አንገቴ ላይ ተደርገዋል፤ ጉልበቴም ተዳክሟል። ይሖዋ መቋቋም ለማልችላቸው ሰዎች አሳልፎ ሰጥቶኛል። 15  ይሖዋ በውስጤ ያሉትን ኃያላን በሙሉ አስወገደ። ወጣቶቼን ለማድቀቅ በእኔ ላይ ጉባኤ ጠርቷል። ይሖዋ ድንግሊቱን የይሁዳን ልጅ በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረግጧል። 16  በእነዚህ ነገሮች የተነሳ አለቅሳለሁ፤ ዓይኖቼ እንባ ያፈሳሉ። ሊያጽናናኝ ወይም መንፈሴን ሊያድስ የሚችል ሰው ከእኔ ርቋልና። ወንዶች ልጆቼ ተጥለዋል፤ ጠላት አይሏልና። 17  ጽዮን እጆቿን ዘረጋች፤ የሚያጽናናትም የለም። በያዕቆብ ዙሪያ ያሉት ሁሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ ይሖዋ ትእዛዝ አስተላልፏል። ኢየሩሳሌም ለእነሱ አስጸያፊ ነገር ሆናለች። 18  ይሖዋ ጻድቅ ነው፤ ትእዛዙን ተላልፌአለሁና። እናንተ ሰዎች ሁሉ፣ አዳምጡ፤ ሥቃዬንም ተመልከቱ። ደናግሌና ወጣት ወንዶቼ በግዞት ተወስደዋል። 19  ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነሱ ግን ከዱኝ። ካህናቴና ሽማግሌዎቼ በሕይወት ለመቆየት ብለውየሚበላ ነገር ሲፈልጉ በከተማዋ ውስጥ አለቁ። 20  ይሖዋ ሆይ፣ ተመልከት፤ በከባድ ጭንቀት ተውጫለሁና። አንጀቴም ተላወሰ። ልቤ በውስጤ እጅግ ተረብሿል፤ የለየለት ዓመፀኛ ሆኛለሁና። በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤ በቤት ውስጥ ደግሞ ሞት አለ። 21  ሰዎች ሲቃዬን ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝም የለም። ጠላቶቼ ሁሉ ስለደረሰብኝ ጥፋት ሰምተዋል። ይህን ጥፋት ስላመጣህ ደስ ተሰኝተዋል። አንተ ግን የተናገርከውን ቀን በእነሱ ላይ ታመጣለህ፤ በዚያን ጊዜ እነሱ እንደ እኔ ይሆናሉ። 22  ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ በሠራኋቸው በደሎች ሁሉ የተነሳእኔን እንደቀጣኸኝ፣ እነሱንም ቅጣቸው። ለቅሶዬ በዝቷልና፤ ልቤም ታሟል።
[]
[]
[]
[]
11,933
2  ይሖዋ የጽዮንን ሴት ልጅ በቁጣው ደመና እንዴት ሸፈናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጥሏል። በቁጣው ቀን የእግሩን ማሳረፊያ አላስታወሰም። 2  ይሖዋ የያዕቆብን መኖሪያዎች በሙሉ ያላንዳች ርኅራኄ ውጧል። የይሁዳን ሴት ልጅ የተመሸጉ ቦታዎች በቁጣው አፈራርሷል። መንግሥቱንና መኳንንቷን ወደ መሬት ጥሏል፤ ደግሞም አርክሷል። 3  የእስራኤልን ብርታት ሁሉ በታላቅ ቁጣ ቆረጠ። ጠላት በቀረበ ጊዜ እሱ ቀኝ እጁን መለሰ፤በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ እሳትም ቁጣው በያዕቆብ ላይ ነደደ። 4  እንደ ጠላት ደጋኑን ወጠረ፤ ቀኝ እጁም እንደ ባላጋራ ተዘጋጀች፤ለዓይን የሚማርኩትን ሁሉ ገደለ። በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳንም ላይ ቁጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ። 5  ይሖዋ እንደ ጠላት ሆነ፤እስራኤልን ዋጠ። ማማዎቿን ሁሉ ዋጠ፤የተመሸጉ ስፍራዎቿን ሁሉ አወደመ። በይሁዳ ሴት ልጅ ዘንድ ለቅሶንና ዋይታን አበዛ። 6  የራሱን ዳስ በአትክልት ቦታ እንዳለች ጎጆ አፈረሰ። በዓሉ እንዲያከትም አደረገ። ይሖዋ በጽዮን፣ በዓልና ሰንበት እንዲረሳ አድርጓል፤በኃይለኛ ቁጣውም ንጉሡንና ካህኑን አቃሏል። 7  ይሖዋ መሠዊያውን ናቀ፤መቅደሱን ተወ። የማይደፈሩ ማማዎቿን ግንቦች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ። በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ በይሖዋ ቤት በታላቅ ድምፅ ጮኹ። 8  ይሖዋ የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ለማፍረስ ቆርጧል። የመለኪያ ገመዱን ዘርግቷል። ከማጥፋትም እጁን አልመለሰም። የመከላከያ ግንቡና ቅጥሩ እንዲያዝኑ አደረገ። በአንድነትም ደከሙ። 9  በሮቿ ወደ መሬት ሰጠሙ። መቀርቀሪያዎቿን አስወገደ፤ ደግሞም ሰባበረ። ንጉሥዋና መኳንንቷ በብሔራት መካከል ናቸው። ሕግ የለም፤ ነቢያቷም እንኳ ከይሖዋ የተገለጠላቸው ራእይ የለም። 10  የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው መሬት ላይ ይቀመጣሉ። በራሳቸው ላይ አቧራ ይነሰንሳሉ፤ ማቅም ይለብሳሉ። የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ መሬት ደፍተዋል። 11  ከማልቀሴ ብዛት ዓይኖቼ ፈዘዙ። አንጀቴ ተላወሰ። በሕዝቤ ሴት ልጅ ላይ ከደረሰው ውድቀትእንዲሁም በከተማዋ አደባባዮች ተዝለፍልፈው ከወደቁት ልጆችና ሕፃናት የተነሳ ጉበቴ መሬት ላይ ፈሰሰ። 12  ልክ እንደቆሰለ ሰው በከተማዋ አደባባዮች ተዝለፍልፈው ሲወድቁና በእናቶቻቸው ጉያ ሆነው ለመሞት ሲያጣጥሩ፣እናቶቻቸውን “እህልና የወይን ጠጅ የት አለ?” ብለው ይጠይቃሉ። 13  የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ ምሥክር የሚሆን ምን ነገር ላቀርብልሽ እችላለሁ?ከምንስ ጋር ላመሳስልሽ እችላለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ አጽናናሽ ዘንድ ከማን ጋር ላወዳድርሽ እችላለሁ? የደረሰብሽ ጥፋት እንደ ባሕር ሰፊ ነውና። ማን ሊፈውስሽ ይችላል? 14  ነቢያትሽ ያዩልሽ ራእይ ሐሰትና ከንቱ ነው፤ተማርከሽ እንዳትወሰጂ ለማድረግ በደልሽን አላጋለጡም፤ይልቁንም ራእይ ተገለጠልን እያሉ ሐሰትና አሳሳች ቃል ይነግሩሻል። 15  በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በማሾፍ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል። “‘ፍጹም ውበት የተላበሰችና የምድር ሁሉ ደስታ’ በማለት ይጠሯት የነበረችው ከተማ ይህች ናት?” እያሉ በመገረም በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፏጫሉ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ። 16  ጠላቶችሽ ሁሉ በአንቺ ላይ አፋቸውን ከፍተዋል። እነሱ ያፏጫሉ፤ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ፤ ደግሞም “ዋጥናት። ስንጠብቀው የነበረው ቀን ይህ ነው! ጊዜው ደርሶ ለማየት በቃን!” ይላሉ። 17  ይሖዋ ያሰበውን አድርጓል፤የተናገረውን፣ ከጥንትም ጀምሮ ያዘዘውን ፈጽሟል። ያላንዳች ርኅራኄ አፍርሷል። ጠላት በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ደስ እንዲሰኝ፣ የባላጋራዎችሽም ብርታት ከፍ ከፍ እንዲል አድርጓል። 18  የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፣ ልባቸው ወደ ይሖዋ ይጮኻል። እንባሽ እንደ ጅረት ቀን ከሌት ይፍሰስ። ለራስሽ ፋታ አትስጪ፤ ዓይንሽ እንባ ማፍሰሱን አያቋርጥ። 19  ተነሺ! ሌሊት፣ ክፍለ ሌሊቶቹ ሲጀምሩ ጩኺ። በይሖዋ ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ። በረሃብ ምክንያት በየመንገዱ ማዕዘን ተዝለፍልፈው ለወደቁት ልጆችሽ ሕይወት ስትዪ፣እጆችሽን ወደ እሱ ዘርጊ። 20  ይሖዋ ሆይ፣ ክፉኛ የቀጣኸውን እይ፤ ደግሞም ተመልከት። ሴቶች የሆዳቸውን ፍሬ፣ የገዛ ራሳቸውን ልጆች ይብሉ?ደግሞስ ካህናቱና ነቢያቱ በይሖዋ መቅደስ ውስጥ ይገደሉ? 21  ወንድ ልጅና ሽማግሌ ሞተው በየመንገዱ ተዘርረዋል። ደናግሌና ወጣት ወንዶቼ በሰይፍ ወድቀዋል። በቁጣህ ቀን ገደልክ፤ ያላንዳች ርኅራኄ አረድክ። 22  በበዓል ቀን እንደሚደረገው ሁሉ ሽብርን ከየአቅጣጫው ጠራህ። በይሖዋ የቁጣ ቀን ያመለጠም ሆነ በሕይወት የተረፈ የለም፤የወለድኳቸውንና ያሳደግኳቸውን ልጆች ጠላቴ ፈጃቸው።
[]
[]
[]
[]
11,934
3  እኔ ከቁጣው በትር የተነሳ መከራ ያየሁ ሰው ነኝ። 2  ወደ ውጭ አስወጥቶኛል፤ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ ውስጥ እንድሄድ አድርጎኛል። 3  ቀኑን ሙሉ በተደጋጋሚ እጁን በእኔ ላይ ሰነዘረ። 4  ሥጋዬና ቆዳዬ እንዲያልቅ አደረገ፤አጥንቶቼን ሰባበረ። 5  ቅጥር ሠራብኝ፤ በመራራ መርዝና በመከራ ዙሪያዬን ከበበኝ። 6  ከሞቱ ብዙ ጊዜ እንደሆናቸው ሰዎች፣ በጨለማ ስፍራዎች እንድቀመጥ አስገደደኝ። 7  ማምለጥ እንዳልችል በቅጥር ዘጋብኝ፤ከመዳብ በተሠራ ከባድ የእግር ብረት አሰረኝ። 8  ደግሞም እርዳታ ለማግኘት አምርሬ ስጮኽ ጸሎቴን አይሰማም። 9  መንገዶቼን በተጠረቡ ድንጋዮች ዘጋ፤ጎዳናዎቼን አጣመመ። 10  እንደ ድብ፣ እንዳደፈጠ አንበሳም አድብቶ ይጠብቀኛል። 11  ከመንገድ ገፍትሮ አስወጣኝ፤ ገነጣጠለኝም፤ወና አስቀረኝ። 12  ደጋኑን ወጠረ፤ የፍላጻውም ዒላማ አደረገኝ። 13  ኮሮጆው ውስጥ በያዛቸው ፍላጻዎች ኩላሊቴን ወጋ። 14  የሕዝብ ሁሉ ማላገጫ ሆንኩ፤ ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ እየዘፈኑ ይሳለቁብኛል። 15  መራራ ነገሮችን እስኪበቃኝ ድረስ አበላኝ፤ ጭቁኝም አጠገበኝ። 16  ጥርሶቼን በጠጠር ይሰብራል፤አመድ ላይ ይጥለኛል። 17  ሰላም ነፈግከኝ፤ ጥሩ ነገር ምን እንደሆነ እንኳ ረሳሁ። 18  ስለዚህ “ግርማ ሞገሴ ተገፏል፤ ከይሖዋ የጠበቅኩት ነገርም ጠፍቷል” እላለሁ። 19  መጎሳቆሌንና ዱር አዳሪ መሆኔን እንዲሁም ጭቁኝና መራራ መርዝ መብላቴን አስታውስ። 20  አንተ በእርግጥ ታስታውሳለህ፤ እኔን ለመርዳትም ታጎነብሳለህ። 21  ይህ ከልቤ አይጠፋም፤ ከዚህም የተነሳ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ። 22  ከይሖዋ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ሙሉ በሙሉ አልጠፋንም፤ምሕረቱ ፈጽሞ አያልቅምና። 23  በየማለዳው አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ እጅግ ብዙ ነው። 24  እኔ “ይሖዋ ድርሻዬ ነው” አልኩ፤ “እሱን በትዕግሥት የምጠባበቀው ለዚህ ነው።” 25  ይሖዋ በእሱ ተስፋ ለሚያደርግ፣ እሱንም ዘወትር ለሚሻ ሰው ጥሩ ነው። 26  የይሖዋን ማዳን ዝም ብሎ መጠባበቅ ጥሩ ነው። 27  ሰው በልጅነቱ ቀንበር ቢሸከም ጥሩ ነው። 28  አምላክ ቀንበሩን በእሱ ላይ ሲጥልበት ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ። 29  ፊቱን አቧራ ውስጥ ይቅበር፤ ገና ተስፋ ሊኖር ይችላል። 30  ጉንጩን፣ ለሚመታው ሰው ይስጥ፤ ስድብንም ይጥገብ። 31  ይሖዋ ለዘላለም አይጥለንምና። 32  ለሐዘን የዳረገን ቢሆንም እንኳ እንደ ታማኝ ፍቅሩ ብዛት ምሕረት ያሳያል። 33  የልቡ ፍላጎት የሰው ልጆች እንዲጎሳቆሉ ወይም እንዲያዝኑ ማድረግ አይደለምና። 34  የምድር እስረኞች ሁሉ በእግር ሲረገጡ፣ 35  በልዑል አምላክ ፊት ሰው ፍትሕ ሲነፈግ፣ 36  ሰው ከፍርድ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሲጭበረበር፣ይሖዋ እንዲህ ያለውን ነገር በቸልታ አያልፍም። 37  ይሖዋ ካላዘዘ በቀር አንድን ነገር ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው? 38  ከልዑሉ አምላክ አፍክፉ ነገርና መልካም ነገር በአንድነት አይወጣም። 39  ሕያው የሆነ ሰው ኃጢአቱ ባስከተለበት መዘዝ ለምን ያጉረመርማል? 40  መንገዳችንን እንመርምር፤ ደግሞም እንፈትን፤ ከዚያም ወደ ይሖዋ እንመለስ። 41  በሰማያት ወዳለው አምላክ እጃችንን ዘርግተን ከልብ የመነጨ ልመና እናቅርብ፦ 42  “እኛ በድለናል፤ ደግሞም ዓምፀናል፤ አንተም ይቅር አላልክም። 43  ጨርሶ እንዳንቀርብ በቁጣ አገድከን፤አሳደድከን፤ ያለርኅራኄም ገደልከን። 44  ጸሎታችን እንዳያልፍ ወደ አንተ መቅረብ የሚቻልበትን መንገድ በደመና ዘጋህ። 45  በሕዝቦች መካከል ጥራጊና ቆሻሻ አደረግከን።” 46  ጠላቶቻችን ሁሉ በእኛ ላይ አፋቸውን ከፈቱ። 47  ፍርሃትና ወጥመድ፣ ባድማነትና ጥፋት ዕጣ ፋንታችን ሆነ። 48  ከሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት የተነሳ ዓይኔ የእንባ ጎርፍ አፈሰሰ። 49  ዓይኖቼ ያለማቋረጥና ያለእረፍት ያነባሉ፤ 50  ይሖዋ ከሰማይ ወደ ታች እስኪያይና እስኪመለከት ድረስ ያነባሉ። 51  በከተማዬ ሴቶች ልጆች ሁሉ ላይ የደረሰውን በማየቴ አዘንኩ። 52  ጠላቶቼ ያለምክንያት እንደ ወፍ አደኑኝ። 53  ሕይወቴን በጉድጓድ ውስጥ ጸጥ ሊያደርጓት ሞከሩ፤ በላዬም ላይ የድንጋይ ናዳ ያወርዱብኛል። 54  በራሴ ላይ ውኃ ጎረፈ፤ እኔም “አለቀልኝ!” አልኩ። 55  ይሖዋ ሆይ፣ ከጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ስምህን ጠራሁ። 56  ድምፄን ስማ፤ እርዳታና እፎይታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ላለመስማት ጆሮህን አትድፈን። 57   በጠራሁህ ቀን ወደ እኔ ቀረብክ። “አትፍራ” አልከኝ። 58  ይሖዋ ሆይ፣ ተሟገትክልኝ፤ ሕይወቴን ዋጀህ። 59  ይሖዋ ሆይ፣ በእኔ ላይ የደረሰውን በደል አይተሃል፤ እባክህ ፍትሕ እንዳገኝ አድርግ። 60  በቀላቸውን ሁሉ፣ በእኔም ላይ ያሴሩትን ሁሉ ተመልክተሃል። 61  ይሖዋ ሆይ፣ ዘለፋቸውን፣ በእኔም ላይ ያሴሩትን ሁሉ ሰምተሃል፤ 62  ከባላንጣዎቼ አፍ የሚወጣውን ቃልና ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ የሚያንሾካሹኩትን ነገር ሰምተሃል። 63  እያቸው፤ ተቀምጠውም ሆነ ቆመው በዘፈናቸው ይሳለቁብኛል! 64  ይሖዋ ሆይ፣ እንደ ሥራቸው መልሰህ ትከፍላቸዋለህ። 65  እርግማንህን በእነሱ ላይ በማውረድ ደንዳና ልብ እንዲኖራቸው ታደርጋለህ። 66  ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣ ታሳድዳቸዋለህ፤ ከሰማያትህም በታች ታጠፋቸዋለህ።
[]
[]
[]
[]
11,935
4  ያንጸባርቅ የነበረው ጥሩው ወርቅ፣ ምንኛ ደበዘዘ! የተቀደሱት ድንጋዮች በየመንገዱ ማዕዘኖች ላይ እንዴት ተበተኑ! 2  በጠራ ወርቅ የተመዘኑት የጽዮን ውድ ልጆች፣የሸክላ ሠሪ እጅ እንደሠራውየሸክላ ዕቃ እንዴት ተቆጠሩ! 3  ቀበሮዎች እንኳ ግልገሎቻቸውን ለማጥባት ጡታቸውን ይሰጣሉ፤የሕዝቤ ሴት ልጅ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች ጨካኝ ሆነች። 4  ከውኃ ጥም የተነሳ፣ የሚጠባው ሕፃን ምላስ ከላንቃው ጋር ይጣበቃል። ልጆች ምግብ ይለምናሉ፤ አንዳች ነገር የሚሰጣቸው ግን የለም። 5  ምርጥ ምግብ ይበሉ የነበሩ ሰዎች በየጎዳናው ላይ ጠኔ ይዟቸው ይተኛሉ። ውድ ልብስ ለብሰው ያደጉም የአመድ ቁልል ያቅፋሉ። 6  የሕዝቤ ሴት ልጅ የደረሰባት ቅጣት፣የማንም እጅ ሳይረዳት በድንገት የተገለበጠችው ሰዶም፣ በሠራችው ኃጢአት የተነሳ ከደረሰባት ቅጣት ይበልጥ ታላቅ ነው። 7  ናዝራውያኗ ከበረዶ ይልቅ የጠሩ፣ ከወተትም ይልቅ የነጡ ነበሩ። ከዛጎል ይበልጥ የቀሉ ነበሩ፤ እንደተወለወለም ሰንፔር ነበሩ። 8  መልካቸው ከጥላሸት ይልቅ ጠቁሯል፤በጎዳና ላይ ማንነታቸውን መለየት የቻለ የለም። ቆዳቸው ተሸብሽቦ አጥንታቸው ላይ ተጣብቋል፤ እንደደረቀ እንጨት ሆኗል። 9  በሰይፍ የሚወድቁት በረሃብ ከሚያልቁት ይሻላሉ፤እነዚህ የምድርን ፍሬ በማጣታቸው መንምነው ያልቃሉ። 10  ሩኅሩኅ የሆኑ ሴቶች በገዛ እጃቸው ልጆቻቸውን ቀቅለዋል። የሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት በደረሰባት ጊዜ እንደ እዝን እንጀራ ሆነውላቸዋል። 11  ይሖዋ ቁጣውን ገልጿል፤የሚነድ ቁጣውንም አፍስሷል። በጽዮን መሠረቶቿን የሚበላ እሳት አንድዷል። 12  የምድር ነገሥታትና የምድር ነዋሪዎች ሁሉባላጋራም ሆነ ጠላት በኢየሩሳሌም በሮች ይገባል የሚል እምነት አልነበራቸውም። 13  ይህ የደረሰው ነቢያቷ በሠሩት ኃጢአትና ካህናቷ በፈጸሙት በደል የተነሳ ነው፤እነሱ በመካከሏ የነበሩትን ጻድቃን ደም አፍስሰዋል። 14  ታውረው በየጎዳናው ተቅበዘበዙ። በደም ስለተበከሉማንም ልብሳቸውን ለመንካት አይደፍርም። 15  “እናንተ ርኩሳን! ሂዱ!” ይሏቸዋል። “ሂዱ! ሂዱ! አትንኩን!” ብለው ይጮኹባቸዋል። መኖሪያ አጥተው ይቅበዘበዛሉና። በብሔራት መካከል ያሉ ሰዎች እንዲህ ብለዋል፦ “ከእንግዲህ ከእኛ ጋር እዚህ መኖር አይችሉም። 16  ይሖዋ ራሱ በታትኗቸዋል፤ዳግመኛም በሞገስ ዓይን አይመለከታቸውም። ሰዎች ለካህናቱ አክብሮት አይኖራቸውም፤ ለሽማግሌዎቹም ሞገስ አያሳዩም።” 17  አሁንም እንኳ እርዳታ እናገኛለን ብለን በከንቱ ስንጠባበቅ ዓይኖቻችን ደከሙ። ሊያድነን ከማይችል ብሔር እርዳታ ለማግኘት ስንጠባበቅ ቆየን። 18  እግር በእግር ተከታተሉን፤ በመሆኑም በአደባባዮቻችን መንቀሳቀስ አልቻልንም። መጨረሻችን ቀርቧል፤ የሕይወት ዘመናችን አብቅቷል፤ ፍጻሜያችን ደርሷልና። 19  አሳዳጆቻችን በሰማይ ከሚበርሩ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ። በተራሮች ላይ አጥብቀው አሳደዱን፤ በምድረ በዳ አድፍጠው አጠቁን። 20  በይሖዋ የተቀባው፣ የሕይወታችን እስትንፋስ፣ ጥልቅ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ፤“በእሱ ጥላ ሥር በብሔራት መካከል እንኖራለን” ብለን ነበር። 21  በዑጽ ምድር የምትኖሪ የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣ ሐሴት አድርጊ፤ ደስም ይበልሽ። ይሁንና ጽዋው ለአንቺም ይደርስሻል፤ ትሰክሪያለሽ፤ እርቃንሽንም ትገልጫለሽ። 22  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ በበደልሽ ምክንያት የደረሰብሽ ቅጣት አብቅቷል። ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ግዞት አይወስድሽም። ይሁንና የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፣ ትኩረቱን በሠራሽው በደል ላይ ያደርጋል። ኃጢአትሽን ይገልጣል።
[]
[]
[]
[]
11,936
5  ይሖዋ ሆይ፣ የደረሰብንን ነገር አስታውስ። ውርደታችንን እይ፤ ደግሞም ተመልከት። 2  ርስታችን ለእንግዶች፣ ቤቶቻችን ለባዕድ አገር ሰዎች ተሰጡ። 3  አባት እንደሌላቸው ወላጅ አልባ ልጆች ሆንን፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆኑ። 4  የገዛ ራሳችንን ውኃ ለመጠጣት መክፈል ነበረብን፤ የገዛ እንጨታችንን የምናገኘውም በግዢ ነበር። 5  አሳዳጆቻችን አንገታችንን ሊይዙ ተቃረቡ፤ዝለናል፤ እረፍት የሚባል ነገርም አላገኘንም። 6  በቂ ምግብ ለማግኘት ወደ ግብፅና ወደ አሦር እጃችንን ዘረጋን። 7  ኃጢአት የሠሩት አባቶቻችን አሁን በሕይወት የሉም፤ እኛ ግን የእነሱን በደል ለመሸከም ተገደድን። 8  አሁን አገልጋዮች ይገዙናል፤ ከእጃቸው የሚያስጥለን ማንም የለም። 9  በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሳ ምግባችንን የምናመጣው በሕይወታችን ቆርጠን ነው። 10  ከከባድ ረሃብ የተነሳ ቆዳችን እንደ ምድጃ ጋለ። 11  በጽዮን ያሉ ሚስቶችና በይሁዳ ከተሞች ያሉ ደናግል ተዋረዱ። 12  መኳንንቱ በእጃቸው ተንጠለጠሉ፤ ሽማግሌዎችም አልተከበሩም። 13  ወጣቶች ወፍጮውን ይሸከማሉ፤ ልጆችም ከባድ እንጨት ሲሸከሙ ይደናቀፋሉ። 14  ሽማግሌዎች ከከተማዋ በር ሄደዋል፤ ወጣቶችም ሙዚቃቸውን መጫወት አቁመዋል። 15  ደስታ ከልባችን ራቀ፤ ጭፈራችን በሐዘን ተተካ። 16  ራሳችን ላይ ያለው አክሊል ወድቋል። ኃጢአት ስለሠራን ወዮልን! 17  ከዚህ የተነሳ ልባችን ታመመ፤ከእነዚህም ነገሮች የተነሳ ዓይኖቻችን ፈዘዙ፤ 18  ባድማ የሆነችው የጽዮን ተራራ አሁን የቀበሮዎች መፈንጫ ሆናለችና። 19  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ላይ ትቀመጣለህ። ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው። 20  ለዘላለም የረሳኸንና ለረጅም ዘመን የተውከን ለምንድን ነው? 21  ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም በፈቃደኝነት እንመለሳለን። ዘመናችንን እንደቀድሞው አድስልን። 22  አንተ ግን ፈጽሞ ጥለኸናል። አሁንም በእኛ ላይ እጅግ እንደተቆጣህ ነህ።
[]
[]
[]
[]
11,937
1  በይሁዳ ንጉሥ በአምዖን ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያህ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኩሺ ልጅ፣ ወደ ሶፎንያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ 2  “ማንኛውንም ነገር ሙሉ በሙሉ ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ” ይላል ይሖዋ። 3  “ሰውንና እንስሳን ጠራርጌ አጠፋለሁ። የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣንእንዲሁም ማሰናከያዎቹንና ክፉ ሰዎችን ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ደግሞም የሰውን ዘር ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ” ይላል ይሖዋ። 4  “በይሁዳና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ላይእጄን እዘረጋለሁ፤የባአልን ቀሪዎች ሁሉና የባዕድ አምላክ ካህናትን ስምከሌሎቹ ካህናት ጋር ከዚህ ስፍራ ፈጽሜ አስወግዳለሁ፤ 5  በቤት ጣሪያዎች ላይ ሆነው ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትንእንዲሁም በአንድ በኩል ለይሖዋ እየሰገዱና ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል እየገቡበሌላ በኩል ግን ለማልካም ታማኝ እንደሚሆኑ ቃል የሚገቡትን አጠፋለሁ፤ 6  ደግሞም ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ የሚሉትን፣ይሖዋን የማይፈልጉትን ወይም እሱን የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።” 7  በሉዓላዊው ጌታ በይሖዋ ፊት ዝም በሉ፤ የይሖዋ ቀን ቀርቧልና። ይሖዋ መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውን ቀድሷል። 8  “በይሖዋ የመሥዋዕት ቀን መኳንንቱን፣የንጉሡን ወንዶች ልጆችና የባዕዳንን ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ። 9  በዚያም ቀን መድረኩ ላይ የሚወጡትን ሁሉ፣የጌቶቻቸውንም ቤት በዓመፅና በማታለል የሚሞሉትን እቀጣለሁ። 10  በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ከዓሣ በር የጩኸት ድምፅ፣ከከተማዋም ሁለተኛ ክፍል ዋይታ፣ከኮረብቶቹም ታላቅ ሁከት ይሰማል። 11  እናንተ የማክተሽ ነዋሪዎች፣ ዋይ በሉ፤ነጋዴዎቹ ሁሉ እንዳልነበሩ ሆነዋልና፤ብር የሚመዝኑትም ሁሉ ጠፍተዋል። 12  በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ደግሞም ቸልተኛ የሆኑትንናበልባቸው ‘ይሖዋ መልካምም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ። 13  ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይወድማሉ። ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሆኖም አይኖሩባቸውም፤ወይንም ይተክላሉ፤ ሆኖም የወይን ጠጁን አይጠጡም። 14  ታላቁ የይሖዋ ቀን ቅርብ ነው! ቅርብ ነው፤ ደግሞም በፍጥነት እየቀረበ ነው! የይሖዋ ቀን ድምፅ አስፈሪ ነው። በዚያ ተዋጊው ይጮኻል። 15  ያ ቀን የታላቅ ቁጣ ቀን፣የጭንቀትና የሥቃይ ቀን፣የአውሎ ነፋስና የጥፋት ቀን፣የጨለማና የጭጋግ ቀን፣የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤ 16  በተመሸጉ ከተሞችና በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ባሉ ረጃጅም ማማዎች ላይየቀንደ መለከትና የጦርነት ሁካታ ድምፅ የሚሰማበት ቀን ይሆናል። 17  በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣለሁ፤እነሱም እንደ ዕውር ይሄዳሉ፤ምክንያቱም በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠርተዋል። ደማቸው እንደ አቧራ፣አንጀታቸውም እንደ ፋንድያ ይፈስሳል። 18  በይሖዋ ታላቅ ቁጣ ቀን ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤መላዋ ምድር በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፤ምክንያቱም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሁሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋቸዋል።”
[]
[]
[]
[]
11,938
2  እናንተ ኀፍረት የማይሰማችሁ ሕዝቦች ሆይ፣በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አዎ ተሰብሰቡ። 2  የተላለፈው ውሳኔ ከመፈጸሙ በፊት፣ቀኑ እንደ ገለባ ከማለፉ በፊት፣የሚነደው የይሖዋ ቁጣ ሳይመጣባችሁ፣የይሖዋ የቁጣ ቀን ሳይደርስባችሁ፣ 3  እናንተ የጽድቅ ድንጋጌዎቹን የምታከብሩ፣በምድር ላይ የምትኖሩ የዋሆች ሁሉ ይሖዋን ፈልጉ። ጽድቅን ፈልጉ፤ የዋህነትን ፈልጉ። ምናልባት በይሖዋ የቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል። 4  ጋዛ የተተወች ከተማ ትሆናለችና፤አስቀሎንም ባድማ ትሆናለች። አሽዶድ በጠራራ ፀሐይ ትባረራለች፤ኤቅሮንም ከሥሯ ትመነገላለች። 5  “በባሕሩ ዳርቻ ለሚኖረው ሕዝብ ይኸውም ለከሪታውያን ብሔር ወዮለት! የይሖዋ ቃል በአንተ ላይ ነው። የፍልስጤማውያን ምድር የሆንሽው ከነአን ሆይ፣ አጠፋሻለሁ፤አንድም ነዋሪ አይተርፍም። 6  የባሕሩ ዳርቻም መሰማሪያ ይሆናል፤ለእረኞች የውኃ ጉድጓድና ለበጎች ከድንጋይ የተሠራ ጉረኖ ይኖረዋል። 7  ከይሁዳ ቤት ለቀሩት ሰዎች መኖሪያ ስፍራ ይሆናል፤በዚያም የግጦሽ ቦታ ያገኛሉ። በምሽት በአስቀሎን ቤቶች ውስጥ ይተኛሉ። አምላካቸው ይሖዋ ትኩረቱን በእነሱ ላይ ያደርጋልና፤የተማረኩባቸውንም ሰዎች መልሶ ይሰበስባል።” 8  “ሞዓብ የሰነዘረችውን ነቀፋና የአሞናውያንን ስድብ ሰምቻለሁ፤እነሱ በሕዝቤ ላይ ተሳልቀዋል፤ ግዛታቸውንም ለመውሰድ በእብሪት ዝተዋል። 9  ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣“ሞዓብ እንደ ሰዶም፣አሞናውያንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ሳማ የወረሰው ምድርና የጨው ጉድጓድ ይሆናሉ፤ ለዘለቄታውም ባድማ ሆነው ይቀራሉ። የሕዝቤ ቀሪዎች ይዘርፏቸዋል፤ከገዛ ብሔሬ የቀሩት ሰዎችም ይወርሷቸዋል። 10  ከኩራታቸው የተነሳ ይህ ይደርስባቸዋል፤ምክንያቱም በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ሕዝብ ላይ ተሳልቀዋል፤ ራሳቸውንም ከፍ ከፍ አድርገዋል። 11  ይሖዋ በእነሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤በምድር ላይ ያሉትን አማልክት ሁሉ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋልና፤የብሔራት ደሴቶች ሁሉ በያሉበት ሆነውለእሱ ይሰግዳሉ። 12  እናንተም ኢትዮጵያውያን በሰይፌ ትገደላላችሁ። 13  እሱ እጁን ወደ ሰሜን ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌንም ባድማና እንደ በረሃ ደረቅ ያደርጋታል። 14  መንጎች ይኸውም ሁሉም ዓይነት የዱር እንስሳት በውስጧ ይተኛሉ። ሻላ እና ጃርት በፈራረሱት ዓምዶቿ መካከል ያድራሉ። የዝማሬ ድምፅ በመስኮት ይሰማል። ደጃፍ ላይ ፍርስራሽ ይኖራል፤የአርዘ ሊባኖስ እንጨቶቹ እንዲጋለጡ ያደርጋልና። 15  በልቧ ‘እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም’ ስትል የነበረችውያለስጋት የተቀመጠችው ኩሩዋ ከተማ ይህች ናት። ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች!የዱር እንስሳት የሚተኙባት ስፍራ ሆናለች። በእሷ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ያፏጫል፤ ራሱንም ይነቀንቃል።”
[]
[]
[]
[]
11,939
3  ዓመፀኛ ለሆነችው፣ ለረከሰችውና ለጨቋኟ ከተማ ወዮላት! 2  ማንንም ለመታዘዝ ፈቃደኛ አልሆነችም፤ ምንም ዓይነት ተግሣጽ አልተቀበለችም። በይሖዋ አልታመነችም፤ ወደ አምላኳም አልቀረበችም። 3  በውስጧ ያሉት መኳንንቷ የሚያገሱ አንበሶች ናቸው። ፈራጆቿ የሌሊት ተኩላዎች ናቸው፤ለጠዋት ምንም ሳያስቀሩ አጥንቱን ሁሉ ይግጣሉ። 4  ነቢያቷ እብሪተኞችና አታላዮች ናቸው። ካህናቷ ቅዱስ የሆነውን ነገር ያረክሳሉ፤በሕጉ ላይ ያምፃሉ። 5  በመካከሏ ያለው ይሖዋ ጻድቅ ነው፤ እሱ ምንም ዓይነት ስህተት አይፈጽምም። ፍርዱን እንደማይነጥፍ የንጋት ብርሃን፣በየማለዳው ያሳውቃል። ክፉ ሰው ግን ኀፍረት የሚባል ነገር አያውቅም። 6  “ብሔራትን አጥፍቻለሁ፤ በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ያሉ ማማዎቻቸው ወድመዋል። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፍርሻለሁ። ከተሞቻቸው ፈራርሰዋል፤ በዚያ አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም አይገኝባቸውም። 7  እኔም ‘በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፤ ተግሣጽም ትቀበያለሽ’ አልኩ፤ ይህም መኖሪያዋ እንዳይጠፋ ነው፤ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ተጠያቂ አደርጋታለሁ። እነሱ ግን ብልሹ ነገር ለመፈጸም ይበልጥ ጓጉ። 8  ‘ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሳበት ቀን ድረስእኔን በተስፋ ተጠባበቁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ብሔራትን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፣በእነሱም ላይ መዓቴንና የሚነደውን ቁጣዬን ሁሉ ለማውረድ የፍርድ ውሳኔ አስተላልፌአለሁና፤መላዋ ምድር በቅንዓቴ እሳት ትበላለች። 9  በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የይሖዋን ስም እንዲጠሩናእጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲያገለግሉትቋንቋቸውን ለውጬ ንጹሕ ቋንቋ እሰጣቸዋለሁ።’ 10  የሚለምኑኝ ሰዎች ይኸውም የተበተኑት ሕዝቦቼየኢትዮጵያ ወንዞች ከሚገኙበት ስፍራ ስጦታ ያመጡልኛል። 11  በዚያን ቀን በእኔ ላይ በማመፅ በፈጸምሻቸው ሥራዎች ሁሉለኀፍረት አትዳረጊም፤በዚያን ጊዜ በትዕቢት ጉራ የሚነዙትን ከመካከልሽ አስወግዳለሁና፤አንቺም ከእንግዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ ፈጽሞ አትታበዪም። 12  እኔም ትሑት የሆነና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብ በመካከላችሁ እንዲቀር አደርጋለሁ፤እነሱም የይሖዋን ስም መጠጊያቸው ያደርጉታል። 13  የእስራኤል ቀሪዎች ምንም ዓይነት ክፋት አይሠሩም፤ውሸት አይናገሩም፤ በአፋቸውም ውስጥ አታላይ ምላስ አይገኝም፤ይልቁንም ይመገባሉ፤ ይተኛሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።” 14  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ! እስራኤል ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ! የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በሙሉ ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊ! 15  ይሖዋ በአንቺ ላይ የተላለፈውን ፍርድ ሽሯል። ጠላትሽን ከአንቺ መልሷል። የእስራኤል ንጉሥ ይሖዋ በመካከልሽ ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት አያስፈራሽም። 16  በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይባላል፦ “ጽዮን ሆይ፣ አትፍሪ። እጆችሽ አይዛሉ። 17  አምላክሽ ይሖዋ በመካከልሽ ነው። እንደ ኃያል ተዋጊ ያድናል። በታላቅ ደስታ በአንቺ ሐሴት ያደርጋል። ለአንቺ ፍቅር በማሳየቱ ረክቶ ዝም ይላል። በእልልታ በአንቺ ሐሴት ያደርጋል። 18  በበዓላትሽ ላይ ባለመገኘታቸው ያዘኑትን ሰዎች እሰበስባለሁ፤ለእሷ ሲሉ በደረሰባቸው ነቀፋ የተነሳ ወደ አንቺ አልመጡም። 19  እነሆ፣ በዚያን ጊዜ በሚጨቁኑሽ ሁሉ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤የምታነክሰውንም አድናታለሁ፤የተበተነችውንም እሰበስባለሁ። ኀፍረት በተከናነቡበት ምድር ሁሉእንዲወደሱና ዝና እንዲያተርፉ አደርጋቸዋለሁ። 20  በዚያን ጊዜ መልሼ አመጣችኋለሁ፤አዎ፣ በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ። ተማርከው የተወሰዱባችሁን ሰዎች በፊታችሁ መልሼ በምሰበስብበት ጊዜበምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ዝና እንድታተርፉና እንድትወደሱ አደርጋለሁና” ይላል ይሖዋ።
[]
[]
[]
[]
11,940
1  የክርስቶስ ኢየሱስ ባሪያ ከሆነው፣ ሐዋርያ እንዲሆን ከተጠራውና የአምላክን ምሥራች እንዲያውጅ ከተሾመው ከጳውሎስ፤ 2  ይህ ምሥራች አምላክ በነቢያቱ አማካኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አስቀድሞ የሰጠው የተስፋ ቃል ሲሆን 3  በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለተወለደው ልጁ የሚገልጽ ነው፤ 4  ይሁንና እሱ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የአምላክ ልጅ መሆኑ እንዲታወቅ ተደርጓል። ይህም የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በተነሳ ጊዜ ነው። 5  ለስሙ ክብር በብሔራት ሁሉ መካከል በእምነት የሚታዘዙ ሰዎች እንዲገኙ ሲባል በእሱ አማካኝነት ጸጋና ሐዋርያነት ተቀብለናል፤ 6  የኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሆኑ ከአሕዛብ ከተጠሩት መካከል እናንተም ትገኙበታላችሁ። 7  ቅዱሳን እንድትሆኑ ለተጠራችሁና በአምላክ ለተወደዳችሁ በሮም ለምትኖሩ ሁሉ፦ አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። 8  ከሁሉ አስቀድሜ፣ ስለ እምነታችሁ በመላው ዓለም ስለሚወራ ስለ ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለአምላኬ ምስጋና አቀርባለሁ። 9  ያለማቋረጥ ዘወትር በጸሎቴ እናንተን ሳልጠቅስ እንደማላልፍ፣ ስለ ልጁ የሚገልጸውን ምሥራች በማወጅ በሙሉ ልቤ ቅዱስ አገልግሎት የማቀርብለት አምላክ ምሥክሬ ነው፤ 10  ደግሞም በአምላክ ፈቃድ አሁን በመጨረሻ እንደ ምንም ተሳክቶልኝ ወደ እናንተ መምጣት እንድችል ልመና እያቀረብኩ ነው። 11  ለመጽናት የሚያስችላችሁን መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እጓጓለሁና፤ 12  ይህን ስል እኔ በእናንተ እምነት እናንተም በእኔ እምነት እርስ በርሳችን እንድንበረታታ ነው። 13  ይሁንና ወንድሞች፣ በሌሎች አሕዛብ መካከል ፍሬ እንዳፈራሁ ሁሉ በእናንተም መካከል ፍሬ አፈራ ዘንድ ወደ እናንተ ለመምጣት ብዙ ጊዜ አቅጄ እንደነበር እንድታውቁ እፈልጋለሁ። ሆኖም ለመምጣት ባሰብኩ ቁጥር የሆነ እንቅፋት ያጋጥመኛል። 14  ለግሪካውያንም ሆነ ግሪካውያን ላልሆኑ እንዲሁም ለጠቢባንም ሆነ ላልተማሩ ዕዳ አለብኝ፤ 15  በመሆኑም በሮም ላላችሁት ለእናንተም ምሥራቹን ለማወጅ እጓጓለሁ። 16  እኔ በምሥራቹ አላፍርምና፤ እንዲያውም ለሚያምን ሁሉ ይኸውም በመጀመሪያ ለአይሁዳዊ ከዚያም ለግሪካዊ ምሥራቹ መዳን የሚያስገኝ የአምላክ ኃይል ነው። 17  ምክንያቱም “ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደተጻፈ ሁሉ እምነት ያላቸው ሰዎች፣ አምላክ በምሥራቹ አማካኝነት ጽድቁን እንደሚገልጥ ይረዳሉ፤ ይህ ደግሞ እምነታቸውን ያጠነክርላቸዋል። 18  እውነትን ለማፈን የተንኮል ዘዴ የሚጠቀሙ ሰዎች በሚፈጽሙት አምላክን የሚጻረር ድርጊትና ክፋት ሁሉ ላይ የአምላክ ቁጣ ከሰማይ እየተገለጠ ነው፤ 19  ምክንያቱም ስለ አምላክ ሊታወቅ የሚችለው ነገር በእነሱ ዘንድ በግልጽ የታወቀ ነው፤ ይህም የሆነው አምላክ ይህን ግልጽ ስላደረገላቸው ነው። 20  የማይታዩት ባሕርያቱ ይኸውም ዘላለማዊ ኃይሉና አምላክነቱ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ ይታያሉ፤ ምክንያቱም ባሕርያቱን ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል፤ ስለሆነም የሚያመካኙበት ነገር የላቸውም። 21  አምላክን የሚያውቁ ቢሆኑም እንኳ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም ብሎም አላመሰገኑትም፤ ከዚህ ይልቅ አስተሳሰባቸው ከንቱ ሆነ፤ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ። 22  ጥበበኞች ነን ቢሉም ሞኞች ሆኑ፤ 23  ሊጠፋ የማይችለውን አምላክ ክብር ጠፊ በሆነው ሰው፣ በወፎች፣ አራት እግር ባላቸው እንስሳትና በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት ምስል ለወጡት። 24  ስለሆነም አምላክ እንደ ልባቸው ምኞት የገዛ ራሳቸውን አካል እንዲያስነውሩ ለርኩሰት አሳልፎ ሰጣቸው። 25  እነዚህ ሰዎች የአምላክን እውነት በሐሰት ለውጠዋል፤ በፈጣሪ ፋንታ ለፍጥረት ክብር ሰጥተዋል፤ ደግሞም ቅዱስ አገልግሎት አቅርበዋል፤ ይሁንና ለዘላለም ሊወደስ የሚገባው ፈጣሪ ብቻ ነው። አሜን። 26  አምላክ ልቅ ለሆነ የፆታ ምኞት አሳልፎ የሰጣቸው በዚህ ምክንያት ነው፤ ሴቶቻቸውም ተፈጥሯዊ የሆነውን ግንኙነት ከተፈጥሮ ውጭ በሆነ ግንኙነት ለወጡ፤ 27  ወንዶቹም ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከሴቶች ጋር መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው ኃይለኛ በሆነ የፆታ ስሜት ተቃጠሉ፤ ወንዶች ከወንዶች ጋር አስነዋሪ ነገር ፈጸሙ፤ እነሱ ራሳቸውም ለጥፋታቸው የሚገባውን ቅጣት እየተቀበሉ ነው። 28  ለአምላክ እውቅና መስጠት ተገቢ መስሎ ስላልታያቸው መደረግ የማይገባውን ነገር እንዲያደርጉ አምላክ በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ለሌለው አስተሳሰብ አሳልፎ ሰጣቸው። 29  ደግሞም እነዚህ ሰዎች በዓመፅ፣ በኃጢአተኝነት፣ በስግብግብነት፣ በክፋት፣ በቅናት፣ በነፍሰ ገዳይነት፣ በጥል፣ በማታለልና በተንኮል የተሞሉ ናቸው፤ እንዲሁም ስም አጥፊዎች፣ 30  ሐሜተኞች፣ አምላክን የሚጠሉ፣ ተሳዳቢዎች፣ ትዕቢተኞች፣ ጉረኞች፣ ክፋት ጠንሳሾች፣ ለወላጆች የማይታዘዙ፣ 31  የማያስተውሉ፣ ቃላቸውን የማይጠብቁ፣ ለሰው ፍቅር የሌላቸውና ምሕረት የለሾች ናቸው። 32  እነዚህ ሰዎች ‘እንዲህ ያሉ ነገሮችን የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል’ የሚለውን የአምላክን የጽድቅ ሕግ በሚገባ የሚያውቁ ቢሆኑም በዚህ ድርጊታቸው መግፋት ብቻ ሳይሆን ይህን የሚያደርጉትንም ይደግፋሉ።
[]
[]
[]
[]
11,941
10  ወንድሞች፣ ለእስራኤላውያን ከልቤ የምመኘውና ስለ እነሱ ለአምላክ ምልጃ የማቀርበው እንዲድኑ ነው። 2  ለአምላክ ቅንዓት እንዳላቸው እመሠክርላቸዋለሁና፤ ሆኖም ቅንዓታቸው በትክክለኛ እውቀት ላይ የተመሠረተ አይደለም። 3  የአምላክን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውን ጽድቅ ለመመሥረት ስለፈለጉ ራሳቸውን ለአምላክ ጽድቅ አላስገዙም። 4  የሚያምን ሁሉ መጽደቅ ይችል ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። 5  ሙሴ በሕጉ አማካኝነት ስለሚገኘው ጽድቅ ሲገልጽ “እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት ይኖራል” ሲል ጽፏል። 6  ሆኖም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ በተመለከተ እንዲህ ተብሏል፦ “በልብህ ‘ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?’ አትበል፤ ይህም ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ 7  ወይም ‘ወደ ጥልቁ ማን ይወርዳል?’ አትበል፤ ይህም ክርስቶስን ከሞት ለማስነሳት ነው።” 8  ይሁንና ቅዱስ መጽሐፉ ምን ይላል? “ቃሉ ለአንተ ቅርብ ነው፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው”፤ ይህም እኛ የምንሰብከው የእምነት “ቃል” ነው። 9  ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ በይፋ ብትናገር እንዲሁም አምላክ ከሞት እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና። 10  ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና፤ በአፉ ደግሞ እምነቱን በይፋ ተናግሮ ይድናል። 11  ቅዱስ መጽሐፉ “በእሱ ላይ እምነት የሚጥል ሁሉ አያፍርም” ይላል። 12  በአይሁዳዊና በግሪካዊ መካከል ምንም ልዩነት የለምና። የሁሉም ጌታ አንድ ነው፤ እሱም የሚለምኑትን ሁሉ አብዝቶ ይባርካል። 13  “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።” 14  ይሁንና ካላመኑበት እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ስለ እሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምኑበታል? ደግሞስ የሚሰብክላቸው ሳይኖር እንዴት ይሰማሉ? 15  ካልተላኩስ እንዴት ይሰብካሉ? ይህም “የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ምሥራች የሚናገሩ ሰዎች እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው!” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 16  ሆኖም ምሥራቹን የታዘዙት ሁሉም አይደሉም። ኢሳይያስ “ይሖዋ ሆይ፣ ከእኛ የሰማውን ነገር ያመነ ማን ነው?” ብሏልና። 17  ስለዚህ እምነት የሚገኘው ቃሉን ከመስማት ነው። ቃሉን መስማት የሚቻለው ደግሞ ስለ ክርስቶስ የሚናገር ሰው ሲኖር ነው። 18  ይሁንና ‘ሳይሰሙ ቀርተው ይሆን?’ ብዬ እጠይቃለሁ። በእርግጥ ሰምተዋል፤ “ጩኸታቸው ወደ መላው ምድር ወጣ፤ መልእክታቸውም እስከ ዓለም ዳርቻዎች ተሰማ” ተብሏልና። 19  ይሁንና ‘እስራኤላውያን ሳያውቁ ቀርተው ይሆን?’ ብዬ እጠይቃለሁ። ሙሴ አስቀድሞ “እናንተን፣ ሕዝብ ባልሆኑት አስቀናችኋለሁ፤ ሞኝ በሆነ ብሔር አማካኝነትም ክፉኛ አስቆጣችኋለሁ” ብሏል። 20  ኢሳይያስም በድፍረት “ያልፈለጉኝ ሰዎች አገኙኝ፤ እኔን ለማግኘት ባልጠየቁ ሰዎችም ዘንድ የታወቅኩ ሆንኩ” ብሏል። 21  እስራኤልን በተመለከተ ግን “ወደማይታዘዝና ልበ ደንዳና ወደሆነ ሕዝብ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ” ብሏል።
[]
[]
[]
[]
11,942
11  እንግዲያው ‘አምላክ ሕዝቡን ትቷል ማለት ነው?’ ብዬ እጠይቃለሁ፤ በፍጹም! ምክንያቱም እኔም ራሴ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከአብርሃም ዘር፣ ከቢንያም ነገድ ነኝ። 2  አምላክ መጀመሪያ እውቅና የሰጣቸውን ሰዎች አልተዋቸውም። ቅዱስ መጽሐፉ ኤልያስ እስራኤልን በአምላክ ፊት በከሰሰበት ጊዜ የሆነውን ነገር በተመለከተ ምን እንደሚል አታውቁም? 3  “ይሖዋ ሆይ፣ ነቢያትህን ገድለዋል፤ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋል፤ እኔ ብቻ ቀረሁ፤ አሁንም ሕይወቴን ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ነው።” 4  ይሁንና አምላክ የሰጠው መልስ ምን ነበር? “ለባአል ያልተንበረከኩ 7,000 ሰዎች አሉኝ።” 5  ስለዚህ በዚህ መንገድ በጸጋ የተመረጡ ቀሪዎች በአሁኑ ዘመንም አሉ። 6  የተመረጡት በጸጋ ከሆነ በሥራ መሆኑ ቀርቷል፤ አለዚያ ጸጋው ጸጋ መሆኑ በቀረ ነበር። 7  እንግዲህ ምን ማለት እንችላለን? እስራኤል አጥብቆ ይፈልገው የነበረውን ነገር አላገኘም፤ የተመረጡት ግን አገኙት። የቀሩት የማስተዋል ስሜታቸው ደነዘዘ፤ 8  ይህም “አምላክ እስከ ዛሬ ኃይለኛ የእንቅልፍ መንፈስ ጣለባቸው፤ የማያይ ዓይንና የማይሰማ ጆሮ ሰጣቸው” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 9  በተጨማሪም ዳዊት እንዲህ ብሏል፦ “ማዕዳቸው ወጥመድና አሽክላ እንዲሁም እንቅፋትና ቅጣት ይሁንባቸው። 10  ዓይኖቻቸው ማየት እንዳይችሉ ይጨልሙ፤ ጀርባቸውም ጎብጦ እንዲቀር አድርግ።” 11  በመሆኑም ‘የተሰናከሉት ወድቀው እንዲቀሩ ነው?’ ብዬ እጠይቃለሁ፤ በፍጹም! ከዚህ ይልቅ እነሱ ሕጉን በመተላለፋቸው ለአሕዛብ የመዳን መንገድ ተከፈተ፤ ይህም የሆነው እነሱን ለማስቀናት ነው። 12  እነሱ ሕጉን መተላለፋቸው ለዓለም በረከት ከሆነና የእነሱ ማነስ ለአሕዛብ በረከት ካስገኘ ቁጥራቸው መሙላቱማ ምን ያህል ታላቅ በረከት ያስገኝ ይሆን! 13  አሁን ደግሞ የምናገረው ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁት ነው። ለአሕዛብ የተላክሁ ሐዋርያ እንደመሆኔ መጠን አገልግሎቴን አከብራለሁ፤ 14  ይህን የማደርገው የገዛ ወገኖቼ የሆኑትን በማስቀናት ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹን ማዳን እችል እንደሆነ ብዬ ነው። 15  የእነሱ መጣል ለዓለም እርቅ ካስገኘ፣ ተቀባይነት ማግኘታቸውማ ከሞት ወደ ሕይወት መሻገር ማለት አይሆንም? 16  በተጨማሪም በኩራት ተደርጎ የተወሰደው የሊጡ ክፍል ቅዱስ ከሆነ ሊጡ በሙሉ ቅዱስ ነው፤ እንዲሁም ሥሩ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹም ቅዱሳን ናቸው። 17  ይሁን እንጂ ከቅርንጫፎቹ መካከል አንዳንዶቹ ቢሰበሩና አንተ የዱር ወይራ ሆነህ ሳለህ በእነሱ መካከል ከተጣበቅክ እንዲሁም ከወይራው ዛፍ ሥር ከሚገኘው በረከት ተካፋይ ከሆንክ 18  በተሰበሩት ቅርንጫፎች ላይ አትታበይ። በእነሱ ላይ የምትታበይ ከሆነ ግን አንተን የተሸከመህ ሥሩ ነው እንጂ አንተ ሥሩን እንዳልተሸከምከው አስታውስ። 19  ይሁንና “ቅርንጫፎቹ የተሰበሩት እኔ በቦታቸው እንድጣበቅ ነው” ብለህ ታስብ ይሆናል። 20  እውነት ነው! እነሱ ባለማመናቸው ተሰብረዋል፤ አንተ ግን በእምነት ቆመሃል። ቢሆንም መፍራት እንጂ መታበይ አይገባህም። 21  አምላክ በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት ካልራራ ለአንተም አይራራምና። 22  ስለዚህ አምላክ ደግም ጥብቅም እንደሆነ ተመልከት። በወደቁት ላይ ጥብቅ ይሆናል፤ አንተ ግን የአምላክ ደግነት የሚገባህ ሆነህ እስከተገኘህ ድረስ ደግነቱን ያሳይሃል፤ አለዚያ ግን አንተም ተቆርጠህ ትጣላለህ። 23  እነሱም እምነት የለሽ ሆነው ካልቀጠሉ ይጣበቃሉ፤ አምላክ መልሶ ሊያጣብቃቸው ይችላልና። 24  አንተ በተፈጥሮ የዱር ከሆነው የወይራ ዛፍ ተቆርጠህ፣ ከተፈጥሮ ውጭ በሆነ መንገድ በጓሮ የወይራ ዛፍ ላይ መጣበቅ ከቻልክ እነዚህ ተፈጥሯዊ የሆኑት ቅርንጫፎችማ በራሳቸው የወይራ ዛፍ ላይ ተመልሰው መጣበቅ እንደሚችሉ የታወቀ ነው! 25  ወንድሞች፣ በራሳችሁ ዓይን ጥበበኞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ቅዱስ ሚስጥር እንድታውቁ እፈልጋለሁ፦ የአሕዛብ ቁጥር እስኪሞላ ድረስ የእስራኤል ሕዝብ በከፊል ስሜቱ ደንዝዟል፤ 26  በዚህም መንገድ እስራኤል ሁሉ ይድናል። ይህም እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈው ነው፦ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ የያዕቆብም ዘሮች የክፋት ድርጊታቸውን እንዲተዉ ያደርጋል። 27  ኃጢአታቸውንም በማስወግድበት ጊዜ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው።” 28  እርግጥ ከምሥራቹ ጋር በተያያዘ ለእናንተ ጥቅም ሲባል የአምላክ ጠላቶች ናቸው፤ በአምላክ ምርጫ መሠረት ግን ለአባቶቻቸው በተገባው የተስፋ ቃል የተነሳ በአምላክ ዘንድ የተወደዱ ናቸው። 29  አምላክ በስጦታውና በጠራቸው ሰዎች አይጸጸትምና። 30  በአንድ ወቅት እናንተ አምላክን የማትታዘዙ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በእነሱ አለመታዘዝ ምክንያት ምሕረት አግኝታችኋል። 31  ስለዚህ አይሁዳውያን ሳይታዘዙ በመቅረታቸው አምላክ ለእናንተ ምሕረት አሳይቷችኋል፤ ከዚህም የተነሳ ለእነሱም ምሕረት ሊያሳያቸው ይችላል። 32  አምላክ ለሁሉም ምሕረት ያሳይ ዘንድ ሁሉም ያለመታዘዝ እስረኞች እንዲሆኑ ፈቅዷልና። 33  የአምላክ ብልጽግና፣ ጥበብና እውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱም ፈጽሞ የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይደረስበት ነው! 34  እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ “የይሖዋን ሐሳብ ማወቅ የቻለ ማን ነው? አማካሪውስ የሆነ ማን ነው?” 35  ወይስ “መልሶ ይከፍለው ዘንድ ለእሱ ያበደረ ማን ነው?” 36  ምክንያቱም ሁሉም ነገር የተገኘው ከእሱ፣ በእሱና ለእሱ ነው። ለእሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።
[]
[]
[]
[]
11,943
12  እንግዲህ ወንድሞች፣ ሰውነታችሁን ሕያው፣ ቅዱስና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት አድርጋችሁ እንድታቀርቡ በአምላክ ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም የማሰብ ችሎታችሁን ተጠቅማችሁ የምታቀርቡት ቅዱስ አገልግሎት ነው። 2  በተጨማሪም ይህ ሥርዓት እንዲቀርጻችሁ አትፍቀዱ፤ ከዚህ ይልቅ ጥሩ የሆነውን፣ ተቀባይነት ያለውንና ፍጹም የሆነውን የአምላክ ፈቃድ መርምራችሁ ማረጋገጥ ትችሉ ዘንድ አእምሯችሁን በማደስ ተለወጡ። 3  እያንዳንዱ ሰው ከሚገባው በላይ ስለ ራሱ በማሰብ ራሱን ከፍ አድርጎ አይመልከት፤ ከዚህ ይልቅ አምላክ ለእያንዳንዱ በሰጠው እምነት መሠረት ጤናማ አስተሳሰብ እንዳለው በሚያሳይ መንገድ እንዲያስብ፣ በመካከላችሁ ያለውን እያንዳንዱን ሰው በተሰጠኝ ጸጋ እመክራለሁ። 4  በአንድ አካል ላይ ብዙ የአካል ክፍሎች አሉን፤ ደግሞም ሁሉም የአካል ክፍሎች አንድ ዓይነት ተግባር አያከናውኑም፤ 5  ልክ እንደዚሁ እኛም ብዙ ብንሆንም እንኳ ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት አንድ አካል ነን፤ ደግሞም አንዳችን የሌላው የአካል ክፍል ነን። 6  በመሆኑም በተሰጠን ጸጋ መሠረት የተለያዩ ስጦታዎች ስላሉን ስጦታችን ትንቢት መናገር ከሆነ በተሰጠን እምነት መሠረት ትንቢት እንናገር፤ 7  ማገልገል ከሆነ ማገልገላችንን እንቀጥል፤ የሚያስተምርም ቢሆን ማስተማሩን ይቀጥል፤ 8  የሚያበረታታም ቢሆን ማበረታቻ መስጠቱን ይቀጥል፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚያስተዳድር በትጋት ያስተዳድር፤ የሚምር በደስታ ይማር። 9  ፍቅራችሁ ግብዝነት የሌለበት ይሁን። ክፉ የሆነውን ተጸየፉ፤ ጥሩ የሆነውን አጥብቃችሁ ያዙ። 10  በወንድማማች ፍቅር እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ። አንዳችሁ ሌላውን ለማክበር ቀዳሚ ሁኑ። 11  ታታሪዎች ሁኑ እንጂ አትስነፉ። በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ። ይሖዋን እንደ ባሪያ አገልግሉ። 12  በተስፋው ደስ ይበላችሁ። መከራን በጽናት ተቋቋሙ። ሳትታክቱ ጸልዩ። 13  ለቅዱሳን እንደየችግራቸው ያላችሁን አካፍሉ። የእንግዳ ተቀባይነትን ባሕል አዳብሩ። 14  ስደት የሚያደርሱባችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። 15  ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ። 16  ለራሳችሁ ያላችሁ ዓይነት አመለካከት ለሌሎችም ይኑራችሁ፤ የትዕቢት ዝንባሌ እንዳያድርባችሁ ተጠንቀቁ፤ ትሕትና የሚንጸባረቅበት አስተሳሰብ ይኑራችሁ። ጥበበኞች እንደሆናችሁ አድርጋችሁ አታስቡ። 17  ለማንም በክፉ ፋንታ ክፉ አትመልሱ። በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ጥረት አድርጉ። 18  ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር በእናንተ በኩል የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ። 19  የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ከዚህ ይልቅ “‘በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ’ ይላል ይሖዋ” ተብሎ ስለተጻፈ ለቁጣው ዕድል ስጡ። 20  ነገር ግን “ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህ።” 21  በክፉ አትሸነፍ፤ ከዚህ ይልቅ ምንጊዜም ክፉውን በመልካም አሸንፍ።
[]
[]
[]
[]
11,944
13  ሰው ሁሉ ለበላይ ባለሥልጣናት ይገዛ፤ ሥልጣን ሁሉ የሚገኘው ከአምላክ ነውና፤ ያሉት ባለሥልጣናት አንጻራዊ ቦታቸውን ያገኙት ከአምላክ ነው። 2  ስለዚህ ባለሥልጣንን የሚቃወም ሁሉ አምላክ ያደረገውን ዝግጅት ይቃወማል፤ ይህን ዝግጅት የሚቃወሙ በራሳቸው ላይ ፍርድ ያመጣሉ። 3  ገዢዎች የሚያስፈሩት ክፉ ለሚያደርጉ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ አይደለምና። እንግዲያው ባለሥልጣንን መፍራት የማትፈልግ ከሆነ መልካም ማድረግህን ቀጥል፤ ከእሱም ምስጋና ታገኛለህ፤ 4  ለአንተ ጥቅም ሲባል የተሾመ የአምላክ አገልጋይ ነውና። ክፉ የምታደርግ ከሆነ ግን ልትፈራ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ሰይፍ የሚታጠቀው እንዲያው በከንቱ አይደለም። ክፉ የሚሠራን በመቅጣት የሚበቀል የአምላክ አገልጋይ ነው። 5  ስለዚህ ቁጣውን በመፍራት ብቻ ሳይሆን ስለ ሕሊናችሁ ስትሉም መገዛታችሁ አስፈላጊ ነው። 6  ቀረጥ የምትከፍሉትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም እነሱ ሕዝባዊ አገልግሎት የሚያከናውኑ የአምላክ አገልጋዮች ናቸው፤ የዘወትር ተግባራቸውም ይኸው ነው። 7  ለሁሉም የሚገባውን አስረክቡ፤ ቀረጥ ለሚጠይቅ ቀረጥ፣ ግብር ለሚጠይቅ ግብር ስጡ፤ መፈራት የሚፈልገውን ፍሩ፤ መከበር የሚፈልገውን አክብሩ። 8  እርስ በርስ ከመዋደድ በቀር በማንም ላይ ምንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤ ሰውን የሚወድ ሁሉ ሕጉን ፈጽሟልና። 9  ምክንያቱም “አታመንዝር፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ አትጎምጅ” የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል። 10  ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። 11  ምን ዓይነት ዘመን ላይ እንደምንገኝ ስለምታውቁም ይህን አድርጉ፤ አማኞች ከሆንበት ጊዜ ይልቅ አሁን መዳናችን ይበልጥ ስለቀረበ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን ነው። 12  ሌሊቱ እየተገባደደ ነው፤ ቀኑም ቀርቧል። ስለዚህ ከጨለማ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን አውልቀን የብርሃንን የጦር ዕቃዎች እንልበስ። 13  መረን በለቀቀ ፈንጠዝያና በስካር፣ ልቅ በሆነ የፆታ ግንኙነትና ዓይን ባወጣ ምግባር እንዲሁም በጠብና በቅናት ሳይሆን በቀን ብርሃን እንደምንመላለስ በጨዋነት እንመላለስ። 14  ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ የሥጋ ፍላጎታችሁን ለማርካት ዕቅድ አታውጡ።
[]
[]
[]
[]
11,945
14  በእምነቱ ጠንካራ ያልሆነውን ሰው ተቀበሉት እንጂ በአመለካከት ልዩነት ላይ ተመሥርታችሁ አትፍረዱ። 2  አንድ ሰው እምነቱ ማንኛውንም ነገር እንዲበላ ይፈቅድለታል፤ በእምነቱ ጠንካራ ያልሆነ ሰው ግን አትክልት ብቻ ይበላል። 3  ማንኛውንም ነገር የሚበላ የማይበላውን አይናቅ፤ የማይበላው ደግሞ በሚበላው ላይ አይፍረድ፤ ይህን ሰው አምላክ ተቀብሎታልና። 4  በሌላው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? እሱ ቢቆምም ሆነ ቢወድቅ ለጌታው ነው። እንዲያውም ይሖዋ እንዲቆም ሊያደርገው ስለሚችል ይቆማል። 5  አንድ ሰው አንዱ ቀን ከሌላው ቀን የበለጠ እንደሆነ አድርጎ ያስባል፤ ሌላው ደግሞ አንዱ ቀን ከሌሎቹ ቀናት ሁሉ የተለየ እንዳልሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ ሰው ሙሉ በሙሉ ያመነበትን ውሳኔ ያድርግ። 6  አንድን ቀን የሚያከብር ለይሖዋ ብሎ ያከብራል። ማንኛውንም ነገር የሚበላም አምላክን ስለሚያመሰግን ለይሖዋ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለይሖዋ ብሎ አይበላም፤ ይሁንና አምላክን ያመሰግናል። 7  እንዲያውም ከመካከላችን ለራሱ ብቻ ብሎ የሚኖር የለም፤ ለራሱ ብቻ ብሎም የሚሞት የለም። 8  ብንኖር የምንኖረው ለይሖዋ ነውና፤ ብንሞትም የምንሞተው ለይሖዋ ነው። ስለዚህ ብንኖርም ሆነ ብንሞት የይሖዋ ነን። 9  ክርስቶስ የሞተውና ዳግም ሕያው የሆነው ለዚህ ዓላማ ይኸውም በሙታንም ሆነ በሕያዋን ላይ ጌታ ይሆን ዘንድ ነውና። 10  ታዲያ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? አንተ ደግሞ ወንድምህን ለምን ትንቃለህ? ሁላችንም በአምላክ የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና። 11  “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ይሖዋ፣ ‘ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ እኔ አምላክ መሆኔን በይፋ ይመሠክራል’” ተብሎ ተጽፏልና። 12  ስለዚህ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለአምላክ መልስ እንሰጣለን። 13  ስለሆነም ከእንግዲህ አንዳችን በሌላው ላይ አንፍረድ፤ ከዚህ ይልቅ በአንድ ወንድም ፊት የሚያደናቅፍ ወይም የሚያሰናክል ነገር ላለማስቀመጥ ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ። 14  የጌታ ኢየሱስ ተከታይ እንደመሆኔ መጠን ማንኛውም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ አውቄአለሁ ደግሞም አምኛለሁ፤ አንድ ነገር ለአንድ ሰው ርኩስ የሚሆነው ያ ነገር ርኩስ ነው ብሎ ሲያስብ ብቻ ነው። 15  አንተ በምግብ የተነሳ ወንድምህ ቅር እንዲሰኝ ካደረግክ በፍቅር መመላለስህን ትተሃል ማለት ነው። ስለዚህ ክርስቶስ የሞተለት ይህ ሰው በምትበላው ምግብ ምክንያት እንዲጠፋ አታድርግ። 16  በመሆኑም መልካም ነው ብላችሁ የምታደርጉት ነገር በሌሎች ዘንድ በመጥፎ እንዳይነሳ ተጠንቀቁ። 17  የአምላክ መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ ነው እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም። 18  በዚህ መንገድ ክርስቶስን እንደ ባሪያ የሚያገለግል ሁሉ በአምላክ ፊት ተቀባይነት፣ በሰዎችም ዘንድ ሞገስ ያገኛልና። 19  ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችን የምንተናነጽበትን ነገር ለማድረግ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናድርግ። 20  ለምግብ ብለህ የአምላክን ሥራ ማፍረስ ተው። እርግጥ ነው፣ ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ሆኖም አንድ ሰው መብላቱ ሌሎችን የሚያደናቅፍ ከሆነ ጎጂ ነው። 21  ወንድምህ የሚሰናከልበት ከሆነ ሥጋ አለመብላት፣ የወይን ጠጅ አለመጠጣት ወይም ማንኛውንም የሚያሰናክል ነገር አለማድረግ የተሻለ ነው። 22  እንግዲህ እምነትህ በአንተና በአምላክ መካከል ያለ ጉዳይ ይሁን። ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ካደረገ በኋላ መልሶ ራሱን የማይኮንን ሰው ደስተኛ ነው። 23  እየተጠራጠረ ከበላ ግን የበላው በእምነት ስላልሆነ ቀድሞውንም ተኮንኗል። ደግሞም በእምነት ያልተደረገ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው።
[]
[]
[]
[]
11,946
15  እኛ በእምነት ጠንካሮች የሆን ጠንካሮች ያልሆኑትን ሰዎች ድክመት ልንሸከም ይገባል እንጂ ራሳችንን የምናስደስት መሆን የለብንም። 2  እያንዳንዳችን ባልንጀራችንን የሚጠቅመውንና የሚያንጸውን ነገር በማድረግ እናስደስተው። 3  ክርስቶስ እንኳ ራሱን አላስደሰተምና፤ ይህም “ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋ በእኔ ላይ ደረሰ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 4  በምናሳየው ጽናትና ከቅዱሳን መጻሕፍት በምናገኘው መጽናኛ ተስፋ ይኖረን ዘንድ ቀደም ብሎ የተጻፈው ነገር ሁሉ ለእኛ ትምህርት እንዲሆን ተጽፏልና። 5  ጽናትንና መጽናኛን የሚሰጠው አምላክ፣ ሁላችሁም ክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ዓይነት አስተሳሰብ እንዲኖራችሁ ያድርግ፤ 6  ይኸውም በኅብረትና በአንድ ድምፅ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታከብሩ ነው። 7  ስለዚህ ክርስቶስ እኛን እንደተቀበለን ሁሉ አምላክ እንዲከበር እናንተም አንዳችሁ ሌላውን ተቀበሉ። 8  ክርስቶስ፣ አምላክ እውነተኛ መሆኑን ለማሳየት ሲል ለተገረዙት አገልጋይ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ፤ በተጨማሪም አገልጋይ የሆነው፣ አምላክ ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ለማረጋገጥ 9  እንዲሁም ብሔራት አምላክን ስለ ምሕረቱ ያከብሩት ዘንድ ነው። ይህም “ስለዚህ በብሔራት መካከል በይፋ አወድስሃለሁ፤ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 10  ደግሞም “እናንተ ብሔራት፣ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ” ይላል። 11  እንደገናም “ብሔራት ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱት፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያወድሱት” ይላል። 12  እንዲሁም ኢሳይያስ “የእሴይ ሥር ይገለጣል፤ ብሔራትንም የሚገዛው ይነሳል፤ ብሔራትም ተስፋቸውን በእሱ ላይ ይጥላሉ” ይላል። 13  በእሱ በመታመናችሁ የተነሳ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተስፋ እንዲትረፈረፍላችሁ ተስፋ የሚሰጠው አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ። 14  ወንድሞቼ ሆይ፣ እናንተ ራሳችሁ በጥሩነት የተሞላችሁ እንደሆናችሁ፣ የተሟላ እውቀት እንዳላችሁና አንዳችሁ ሌላውን መምከር እንደምትችሉ እኔ ራሴ ስለ እናንተ እርግጠኛ መሆን ችያለሁ። 15  ይሁን እንጂ አንዳንድ ጉዳዮችን ግልጥልጥ አድርጌ የጻፍኩላችሁ ተጨማሪ ማሳሰቢያ ልሰጣችሁ ስለፈለግኩ ነው። ይህን የማደርገው ከአምላክ በተሰጠኝ ጸጋ የተነሳ ነው። 16  ይህ ጸጋ የተሰጠኝም ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው። የአምላክን ምሥራች በማወጁ ቅዱስ ሥራ የምካፈለው እነዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰ፣ ተቀባይነት ያለው መባ ሆነው ለአምላክ እንዲቀርቡ ነው። 17  ስለዚህ ለአምላክ ከማቀርበው አገልግሎት ጋር በተያያዘ በክርስቶስ ኢየሱስ ሐሴት የማደርግበት ምክንያት አለኝ። 18  አሕዛብ ታዛዦች እንዲሆኑ ክርስቶስ በእኔ አማካኝነት ስላከናወነው ነገር ካልሆነ በቀር ስለ ሌላ ነገር ለመናገር አልደፍርም። ይህን ያከናወነው እኔ በተናገርኩትና ባደረግኩት ነገር 19  እንዲሁም በተአምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ደግሞም በአምላክ መንፈስ ኃይል ነው፤ በመሆኑም ከኢየሩሳሌም አንስቶ ዙሪያውን እስከ እልዋሪቆን ድረስ ስለ ክርስቶስ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ ሰብኬአለሁ። 20  በዚህ መንገድ የክርስቶስ ስም አስቀድሞ በታወቀበት ቦታ ምሥራቹን ላለመስበክ የተቻለኝን ሁሉ ጥረት አድርጌአለሁ፤ ይህን ያደረግኩት ሌላ ሰው በጣለው መሠረት ላይ መገንባት ስላልፈለግኩ ነው፤ 21  ይህም “ከዚህ በፊት ስለ እሱ ምንም ያልተነገራቸው ያያሉ፤ ያልሰሙም ያስተውላሉ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 22  በተደጋጋሚ ጊዜያት ወደ እናንተ መምጣት ሳልችል የቀረሁትም በዚህ ምክንያት ነው። 23  አሁን ግን በዚህ አካባቢ ባሉት አገሮች ያልሰበክሁበት ክልል የለም፤ ደግሞም ለብዙ ዓመታት ወደ እናንተ ለመምጣት ስጓጓ ቆይቻለሁ። 24  በመሆኑም ወደ ስፔን በምጓዝበት ጊዜ እንደማገኛችሁና እናንተ ጋ ለተወሰነ ጊዜ ቆይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ ጥቂት መንገድ እንደምትሸኙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። 25  አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም ልጓዝ ነው። 26  በመቄዶንያና በአካይያ ያሉት ወንድሞች በኢየሩሳሌም ባሉት ቅዱሳን መካከል ለሚገኙት ድሆች መዋጮ በመስጠት ያላቸውን ነገር በደስታ አካፍለዋልና። 27  አዎ፣ ይህን ያደረጉት በፈቃደኝነት ነው፤ ደግሞም የእነሱ ዕዳ ነበረባቸው፤ ምክንያቱም አሕዛብ የእነሱን መንፈሳዊ ነገር ከተካፈሉ እነሱ ደግሞ ለሚያስፈልጓቸው ቁሳዊ ነገሮች የማዋጣት ዕዳ አለባቸው። 28  ስለሆነም ይህን ሥራ ካከናወንኩና መዋጮውን ካስረከብኳቸው በኋላ በእናንተ በኩል አድርጌ ወደ ስፔን እሄዳለሁ። 29  ደግሞም ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ የክርስቶስን የተትረፈረፈ በረከት ይዤላችሁ እንደምመጣ አውቃለሁ። 30  እንግዲህ ወንድሞች፣ ስለ እኔ አምላክን በመለመን ከእኔ ጋር አብራችሁ በጸሎት እንድትተጉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና ከመንፈስ በሚገኘው ፍቅር አበረታታችኋለሁ፤ 31  በይሁዳ ካሉት የማያምኑ ሰዎች እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ለሚገኙት ቅዱሳን የማቀርበው አገልግሎት በእነሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩልኝ፤ 32  ይኸውም አምላክ ከፈቀደ ወደ እናንተ በደስታ እንድመጣና ከእናንተ ጋር በመሆን መንፈሴ እንዲታደስ ነው። 33  ሰላም የሚሰጠው አምላክ ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
[]
[]
[]
[]
11,947
16  በክንክራኦስ ጉባኤ የምታገለግለውን እህታችንን ፌበንን ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ፤ 2  በጌታ የእምነት ባልደረባችሁ እንደመሆኗ መጠን ለቅዱሳን በሚገባ ሁኔታ ተቀበሏት፤ የምትፈልገውንም እርዳታ ሁሉ አድርጉላት፤ ምክንያቱም እሷ እኔን ጨምሮ ለብዙ ወንድሞች ድጋፍ ሆናለች። 3  በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ 4  እነሱ ለእኔ ሲሉ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠዋል፤ እኔ ብቻ ሳልሆን በአሕዛብ መካከል የሚገኙ ጉባኤዎችም ሁሉ ያመሰግኗቸዋል። 5  በቤታቸው ላለው ጉባኤም ሰላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ከመጀመሪያዎቹ የክርስቶስ ተከታዮች አንዱ የሆነውን የምወደውን ኤጲኔጦስን ሰላም በሉልኝ። 6  ለእናንተ ብዙ የደከመችውን ማርያምን ሰላም በሉልኝ። 7  ዘመዶቼ የሆኑትንና አብረውኝ የታሰሩትን እንዲሁም በሐዋርያት ዘንድ ስመጥር የሆኑትንና ከእኔ ቀደም ብለው የክርስቶስ ተከታዮች የሆኑትን አንድሮኒኮስንና ዩኒያስን ሰላም በሉልኝ። 8  በጌታ ለምወደው ለአምጵልያጦስ ሰላምታዬን አቅርቡልኝ። 9  በክርስቶስ አብሮን የሚሠራውን ኡርባኖስንና የምወደውን እስጣኩስን ሰላም በሉልኝ። 10  በክርስቶስ ዘንድ መልካም ስም ያተረፈውን አጵሌስን ሰላም በሉልኝ። የአርስጦቡሉስ ቤተሰብ ለሆኑት ሰላምታ አቅርቡልኝ። 11  ዘመዴን ሄሮድዮንን ሰላም በሉልኝ። የጌታ ተከታዮች የሆኑትን የናርኪሰስን ቤተሰቦች ሰላም በሉልኝ። 12  በጌታ ሆነው በትጋት የሚሠሩትን ጥራይፊናና ጥራይፎሳ የተባሉትን ሴቶች ሰላም በሉልኝ። የምንወዳትን ጰርሲስን ሰላም በሉልኝ፤ በጌታ ሥራ ብዙ ደክማለችና። 13  የጌታ ምርጥ አገልጋይ ለሆነው ለሩፎስ እንዲሁም እኔም እንደ እናቴ ለማያት ለእናቱ ሰላምታ አቅርቡልኝ። 14  አሲንክሪጦስን፣ ፍሌጎንን፣ ሄርሜስን፣ ጳጥሮባን፣ ሄርማስንና ከእነሱ ጋር ያሉትን ወንድሞች ሰላም በሉልኝ። 15  ፊሎሎጎስንና ዩልያን፣ ኔርዩስንና እህቱን፣ ኦሊምጳስን እንዲሁም ከእነሱ ጋር ያሉትን ቅዱሳን ሁሉ ሰላም በሉልኝ። 16  በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ። የክርስቶስ ጉባኤዎች በሙሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። 17  እንግዲህ ወንድሞች፣ ክፍፍል ከሚፈጥሩና ለእንቅፋት ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ከሚያመጡ ሰዎች እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች የተማራችሁትን ትምህርት የሚጻረሩ ናቸው፤ ይህን ከሚያደርጉ ሰዎች ራቁ። 18  እንዲህ ዓይነቶቹ ሰዎች ለጌታችን ለክርስቶስ ሳይሆን ለራሳቸው ፍላጎት ባሪያዎች ናቸው፤ በለሰለሰ አንደበትና በሽንገላ ቃላት የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ። 19  ታዛዥነታችሁ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ሆኗል፤ ስለዚህ እኔ በእናንተ እጅግ እደሰታለሁ። ይሁንና ለመልካም ነገር ጥበበኞች እንድትሆኑ፣ ለክፉ ነገር ደግሞ አላዋቂዎች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። 20  ሰላም የሚሰጠው አምላክ በቅርቡ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ይጨፈልቀዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። 21  የሥራ አጋሬ ጢሞቴዎስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ ዘመዶቼ የሆኑት ሉክዮስ፣ ያሶንና ሶሲጳጥሮስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። 22  ይህን ደብዳቤ በጽሑፍ ያሰፈርኩት እኔ ጤርጥዮስም በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ። 23  እኔንም ሆነ መላውን ጉባኤ የሚያስተናግደው ጋይዮስ ሰላም ይላችኋል። የከተማዋ የግምጃ ቤት ሹም ኤርስጦስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ ወንድሙ ቁአስጥሮስም ሰላም ይላችኋል። 24  —— 25  አምላክ ለረጅም ዘመናት ተሰውሮ ከቆየው ቅዱስ ሚስጥር መገለጥ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እኔ በማውጀው ምሥራችና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰበከው መልእክት መሠረት ሊያጸናችሁ ይችላል። 26  አሁን ግን ሕዝቦች ሁሉ እምነት እንዲኖራቸውና እሱን እንዲታዘዙ ቅዱሱ ሚስጥር፣ በዘላለማዊው አምላክ ትእዛዝ መሠረት ትንቢታዊ በሆኑ ቅዱሳን መጻሕፍት አማካኝነት በሕዝቦች ሁሉ መካከል እንዲገለጥና እንዲታወቅ ተደርጓል፤ 27  እሱ ብቻ ጥበበኛ ለሆነው አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።
[]
[]
[]
[]
11,948
2  ስለዚህ አንተ ሰው፣ ማንም ሆንክ ማን በሌላው ላይ የምትፈርድ ከሆነ ምንም የምታመካኝበት ነገር የለህም፤ በሌላው ላይ ስትፈርድ ራስህንም ኮነንክ ማለት ነው፤ ምክንያቱም በሌላው ላይ የምትፈርድ አንተ ራስህ እነዚያኑ ነገሮች በተደጋጋሚ ታደርጋለህ። 2  አምላክ እንዲህ ያሉትን ነገሮች በሚፈጽሙ ሰዎች ላይ እንደሚፈርድ እናውቃለን፤ ፍርዱ ደግሞ ከእውነት ጋር የሚስማማ ነው። 3  ይሁን እንጂ አንተ ሰው፣ እንዲህ ያሉትን ነገሮች በሚፈጽሙ ሰዎች ላይ እየፈረድክ አንተ ግን እነዚያኑ ነገሮች የምታደርግ ከሆነ ከአምላክ ፍርድ አመልጣለሁ ብለህ ታስባለህ? 4  ወይስ አምላክ በደግነቱ ወደ ንስሐ ሊመራህ እየሞከረ እንዳለ ሳታውቅ የደግነቱን፣ የቻይነቱንና የትዕግሥቱን ብዛት ትንቃለህ? 5  እንግዲህ በግትርነትህና ንስሐ በማይገባው ልብህ የተነሳ በራስህ ላይ ቁጣ ታከማቻለህ። ይህ ቁጣ አምላክ የጽድቅ ፍርድ በሚፈርድበት ቀን ይገለጣል። 6  እሱም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል፦ 7  በመልካም ሥራ በመጽናት ክብርን፣ ሞገስንና ሊጠፋ የማይችል ሕይወትን ለሚፈልጉ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ 8  ይሁን እንጂ ጠብ ወዳዶች በሆኑትና ለእውነት ከመታዘዝ ይልቅ ለዓመፅ በሚታዘዙት ላይ ቁጣና መዓት ይወርድባቸዋል። 9  ክፉ ሥራ በሚሠራ ሰው ሁሉ ላይ ይኸውም በመጀመሪያ በአይሁዳዊ ከዚያም በግሪካዊ ላይ መከራና ጭንቀት ይመጣል፤ 10  ሆኖም መልካም ሥራ የሚሠራ ሁሉ ይኸውም በመጀመሪያ አይሁዳዊ ከዚያም ግሪካዊ ክብር፣ ሞገስና ሰላም ያገኛል። 11  በአምላክ ዘንድ አድልዎ የለምና። 12  ሕግ ሳይኖራቸው ኃጢአት የሠሩ ሁሉ ያለሕግ ይጠፋሉና፤ ሆኖም ሕግ እያላቸው ኃጢአት የሠሩ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል። 13  ምክንያቱም በአምላክ ፊት ጻድቅ የሆኑት ሕግን የሚሰሙ አይደሉም፤ ከዚህ ይልቅ ጻድቃን ናችሁ የሚባሉት ሕግን የሚፈጽሙ ናቸው። 14  ሕግ የሌላቸው አሕዛብ በተፈጥሮ በሕጉ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሲያደርጉ እነዚህ ሰዎች ሕግ ባይኖራቸውም እንኳ እነሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና። 15  የሕጉ መሠረታዊ ሐሳብ በልባቸው እንደተጻፈ የሚያሳዩት እነሱ ራሳቸው ናቸው፤ ሕሊናቸው ከእነሱ ጋር ሆኖ በሚመሠክርበት ጊዜ ሐሳባቸው በውስጣቸው እየተሟገተ አንዴ ይከሳቸዋል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥፋተኛ አይደላችሁም ይላቸዋል። 16  ይህ የሚሆነው እኔ በማውጀው ምሥራች መሠረት አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ሰዎች በስውር በሚያስቧቸውና በሚያደርጓቸው ነገሮች ላይ በሚፈርድበት ቀን ነው። 17  አንተ አይሁዳዊ ተብለህ የምትጠራ፣ በሕጉ የምትመካ፣ ከአምላክ ጋር ባለህ ዝምድና የምትኩራራ፣ 18  ፈቃዱን የምታውቅ፣ በሕጉ ውስጥ ያለውን ነገር የተማርክ በመሆንህ የላቀ ዋጋ ያላቸውን ነገሮች በሚገባ የምትገነዘብ፣ 19  ለዕውር መሪ፣ በጨለማ ላሉት ብርሃን ነኝ ብለህ የምታምን፣ 20  ማስተዋል የጎደላቸውን የማሠለጥንና ሕፃናትን የማስተምር ነኝ የምትል እንዲሁም በሕጉ ውስጥ ያሉትን የእውቀትና የእውነት መሠረታዊ ገጽታዎች የምታውቅ ከሆንክ፣ 21  ታዲያ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርም? አንተ “አትስረቅ” ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህ? 22  አንተ “አታመንዝር” የምትል ታመነዝራለህ? አንተ ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህ? 23  አንተ በሕግ የምትኩራራ ሕጉን በመተላለፍ አምላክን ታዋርዳለህ? 24  ይህም “በእናንተ ምክንያት የአምላክ ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባል” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 25  መገረዝ ጥቅም የሚኖረው ሕጉን እስካከበርክ ድረስ ነው፤ ሕጉን የምትተላለፍ ከሆነ ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ይቆጠራል። 26  ያልተገረዘ ሰው በሕጉ ውስጥ ያሉትን የጽድቅ መሥፈርቶች የሚጠብቅ ከሆነ አለመገረዙ እንደ መገረዝ አይቆጠርም? 27  እንግዲህ አንተ የተጻፈ ሕግ ያለህና የተገረዝክ ሆነህ ሳለ ሕግን የምትጥስ ከሆነ በሥጋ ያልተገረዘ ሆኖ ሕግን የሚፈጽም ሰው ይፈርድብሃል። 28  ምክንያቱም እውነተኛ አይሁዳዊነት በውጫዊ ገጽታ የሚገለጽ አይደለም፤ ግርዘቱም ውጫዊና ሥጋዊ ግርዘት አይደለም። 29  ከዚህ ይልቅ በውስጡ አይሁዳዊ የሆነ እሱ አይሁዳዊ ነው፤ ግርዘቱም በተጻፈ ሕግ ሳይሆን በመንፈስ የሆነ የልብ ግርዘት ነው። እንዲህ ዓይነቱ ሰው ውዳሴ የሚያገኘው ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው።
[]
[]
[]
[]
11,949
3  ታዲያ አይሁዳዊ መሆን ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው? ግርዘትስ ፋይዳው ምንድን ነው? 2  በሁሉም መንገድ ትልቅ ጥቅም አለው። በመጀመሪያ ደረጃ የአምላክ ቅዱስ ቃል በአደራ ተሰጥቷቸዋል። 3  አንዳንድ አይሁዳውያን እምነት ቢጎድላቸውስ? የእነሱ እምነት ማጣት ሰዎች በአምላክ እንዳይታመኑ ሊያደርግ ይችላል? 4  በፍጹም! ከዚህ ይልቅ “በቃልህ ጻድቅ ሆነህ ትገኝ ዘንድ፣ በፍርድም ፊት ትረታ ዘንድ” ተብሎ እንደተጻፈ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ሆኖ ቢገኝ እንኳ የአምላክ እውነተኝነት የተረጋገጠ ነው። 5  ይሁን እንጂ የእኛ ክፋት የአምላክን ጽድቅ አጉልቶ የሚያሳይ ከሆነ ምን ማለት እንችላለን? አምላክ ቁጣውን መግለጹ ኢፍትሐዊ ያሰኘዋል እንዴ? (አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት ማለት ነው።) 6  በፍጹም! አለዚያ አምላክ በዓለም ላይ እንዴት ይፈርዳል? 7  ይሁንና በእኔ ውሸት የተነሳ የአምላክ እውነት ለእሱ ክብር በሚያመጣ መንገድ ይበልጥ ጎልቶ የሚወጣ ከሆነ ታዲያ እኔ ለምን ኃጢአተኛ ተብዬ ይፈረድብኛል? 8  እንዲህ ከሆነማ አንዳንድ ሰዎች “ጥሩ ነገር እንዲገኝ መጥፎ ነገር እንሥራ” ይላሉ በማለት በሐሰት እንደሚያስወሩብን ለምን አንልም? በእነዚህ ሰዎች ላይ የሚበየነው ፍርድ ፍትሐዊ ነው። 9  እንግዲህ ምን ማለት ይቻላል? እኛ የተሻልን ነን ማለት ነው? በፍጹም! ምክንያቱም አይሁዳውያንም ሆኑ ግሪካውያን ሁሉም የኃጢአት ተገዢዎች እንደሆኑ በመናገር አስቀድመን ከሰናቸዋል፤ 10  ይህም እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈው ነው፦ “ጻድቅ ሰው የለም፤ አንድም እንኳ የለም፤ 11  ማስተዋል ያለው አንድም ሰው የለም፤ ደግሞም አምላክን የሚፈልግ አንድም ሰው የለም። 12  ሁሉም መንገድ ስተዋል፤ ሁሉም የማይረቡ ሆነዋል፤ ደግነት የሚያሳይ አንድም ሰው የለም፤ አንድም እንኳ አይገኝም።” 13  “ጉሮሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ።” “ከከንፈራቸው ሥር የእባብ መርዝ አለ።” 14  “አፋቸውም በእርግማንና በምሬት የተሞላ ነው።” 15  “እግሮቻቸው ደም ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው።” 16  “በመንገዳቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ፤ 17  የሰላምንም መንገድ አያውቁም።” 18  “በዓይኖቻቸው ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።” 19  እንግዲህ አፍ ሁሉ እንዲዘጋና ዓለም በሙሉ በአምላክ ፊት ተጠያቂ እንዲሆን ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሆነ እናውቃለን። 20  ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ማንም ሰው በፊቱ ጻድቅ ነህ ሊባል አይችልም፤ ምክንያቱም ስለ ኃጢአት ትክክለኛ ግንዛቤ የሚገኘው በሕጉ አማካኝነት ነው። 21  አሁን ግን ሕግ ሳያስፈልግ፣ በሕጉና በነቢያት የተመሠከረለት የአምላክ ጽድቅ ግልጽ ሆኗል፤ 22  እምነት ያላቸው ሁሉ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት የአምላክን ጽድቅ ያገኛሉ። ይህም የሆነው በሰዎች መካከል ምንም ልዩነት ስለሌለ ነው። 23  ምክንያቱም ሁሉም ኃጢአት ሠርተዋል፤ የአምላክንም ክብር ማንጸባረቅ ተስኗቸዋል፤ 24  ይሁንና ክርስቶስ ኢየሱስ የከፈለው ቤዛ በሚያስገኘው ነፃነት አማካኝነት በጸጋው ጻድቃን ናችሁ መባላቸው እንዲሁ የተገኘ ነፃ ስጦታ ነው። 25  በኢየሱስ ደም የሚያምኑ ሁሉ ማስተሰረያ ያገኙ ዘንድ አምላክ እሱን መባ አድርጎ አቅርቦታል። አምላክ ይህን ያደረገው የራሱን ጽድቅ ለማሳየት ነው፤ ምክንያቱም አምላክ ቻይ በመሆን በቀደሙት ዘመናት የተፈጸሙትን ኃጢአቶች ይቅር ብሏል። 26  ይህን ያደረገው በዚህም ዘመን የራሱን ጽድቅ ለማሳየት ነው፤ ይህም በኢየሱስ የሚያምነውን ሰው ጻድቅ ነህ በማለት እሱ ራሱ ጻድቅ ይሆን ዘንድ ነው። 27  ታዲያ እንድንኮራ የሚያደርገን ነገር ይኖራል? ምንም ነገር የለም። እንዳንኮራ የሚያደርገን ሕግ የትኛው ነው? የሥራ ሕግ ነው? በፍጹም አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ እንዳንኮራ የሚያደርገን የእምነት ሕግ ነው። 28  ምክንያቱም አንድ ሰው ጻድቅ ነህ የሚባለው የሕግን ሥራ በመፈጸም ሳይሆን በእምነት እንደሆነ እንረዳለን። 29  ወይስ አምላክ የአይሁዳውያን አምላክ ብቻ ነው? የአሕዛብስ አምላክ አይደለም? አዎ፣ የአሕዛብም አምላክ ነው። 30  አምላክ አንድ ስለሆነ የተገረዙትን ከእምነት የተነሳ ጻድቃን ይላቸዋል፤ ያልተገረዙትንም በእምነታቸው አማካኝነት ጻድቃን ናችሁ ይላቸዋል። 31  ታዲያ በእምነታችን አማካኝነት ሕግን እንሽራለን ማለት ነው? በፍጹም! እንዲያውም ሕግን እንደግፋለን።
[]
[]
[]
[]
11,950
4  እንዲህ ከሆነ ታዲያ በሥጋ አባታችን የሆነው አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? 2  ለምሳሌ አብርሃም ጻድቅ የተባለው በሥራ ቢሆን ኖሮ የሚመካበት ነገር በኖረው ነበር፤ ሆኖም በአምላክ ፊት ሊመካ አይችልም። 3  የቅዱስ መጽሐፉስ ቃል ምን ይላል? “አብርሃም በይሖዋ አመነ፤ ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።” 4  ይሁንና ለሚሠራ ሰው ደሞዙ እንደ ሥራው ዋጋ እንጂ እንደ ጸጋ ስጦታ ተደርጎ አይቆጠርለትም። 5  በሌላ በኩል ግን በራሱ ሥራ ከመመካት ይልቅ ኃጢአተኛውን ጻድቅ ነህ ብሎ በሚጠራው አምላክ የሚያምን እምነቱ እንደ ጽድቅ ይቆጠርለታል። 6  ይህም ዳዊት፣ አምላክ ያለሥራ እንደ ጻድቅ አድርጎ የሚቆጥረው ሰው ስለሚያገኘው ደስታ እንዲህ ብሎ እንደተናገረው ነው፦ 7  “የዓመፅ ሥራቸው ይቅር የተባለላቸው፣ ኃጢአታቸውም የተሸፈነላቸው ደስተኞች ናቸው፤ 8  ይሖዋ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ደስተኛ ነው።” 9  ታዲያ ይህን ደስታ የሚያገኙት የተገረዙ ሰዎች ብቻ ናቸው ወይስ ያልተገረዙትም ጭምር? ምክንያቱም “አብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት” ብለናል። 10  ታዲያ እምነቱ እንደ ጽድቅ የተቆጠረው በምን ዓይነት ሁኔታ እያለ ነው? ተገርዞ እያለ ነው ወይስ ከመገረዙ በፊት? ተገርዞ እያለ ሳይሆን ከመገረዙ በፊት ነው። 11  ገና ከመገረዙ በፊት በነበረው እምነት ላገኘው ጽድቅ ምልክት ሆኖ የሚያገለግለውን ግርዘትን እንደ ማኅተም ተቀበለ፤ ስለዚህ ባይገረዙም እንኳ በእምነታቸው የተነሳ እንደ ጻድቃን ለተቆጠሩት ሁሉ አባት ሆኗል፤ 12  ለተገረዙት ዘሮቹም አባት ነው፤ ይሁንና ግርዘትን አጥብቀው ለሚከተሉት ብቻ ሳይሆን አባታችን አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን እምነት ተከትለው በሥርዓት ለሚመላለሱ ሰዎችም ሁሉ አባት ነው። 13  ምክንያቱም አብርሃም ወይም ዘሩ የዓለም ወራሽ እንደሚሆን ተስፋ የተሰጠው በሕግ አማካኝነት ሳይሆን በእምነት በሚገኘው ጽድቅ ነው። 14  ወራሾች የሚሆኑት ሕጉን በጥብቅ የሚከተሉ ቢሆኑ ኖሮ እምነት ከንቱ በሆነ ነበርና፤ የተስፋውም ቃል ባከተመ ነበር። 15  እንደ እውነቱ ከሆነ ሕጉ ቁጣ ያስከትላል፤ ሆኖም ሕግ ከሌለ ሕግን መተላለፍ የሚባል ነገር አይኖርም። 16  በመሆኑም ተስፋው በእምነት የተገኘ ነው፤ ይህም የሆነው ተስፋው በጸጋ ላይ የተመሠረተ እንዲሆንና ለዘሩ ሁሉ ይኸውም ሕጉን በጥብቅ ለሚከተል ብቻ ሳይሆን የሁላችንም አባት የሆነውን የአብርሃምን እምነት በጥብቅ ለሚከተል ጭምር የተረጋገጠ እንዲሆን ነው። 17  (ይህም “ለብዙ ብሔራት አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።) ይህ የሆነው እሱ ባመነበት ማለትም ሙታንን ሕያው በሚያደርገውና የሌለውን እንዳለ አድርጎ በሚጠራው አምላክ ፊት ነው። 18  ተስፋ ለማድረግ የሚያበቃ ምንም መሠረት ባይኖርም እንኳ “የአንተም ዘር እጅግ ይበዛል” ተብሎ በተነገረው መሠረት የብዙ ብሔራት አባት እንደሚሆን በተሰጠው ተስፋ አምኗል። 19  እምነቱ ባይዳከምም እንኳ 100 ዓመት ገደማ ሆኖት ስለነበር የሞተ ያህል ስለሆነው የገዛ ራሱ አካል እንዲሁም ሙት ስለሆነው የሣራ ማህፀን አሰበ። 20  ሆኖም አምላክ ከሰጠው የተስፋ ቃል የተነሳ ለአምላክ ክብር በመስጠት በእምነት በረታ እንጂ እምነት በማጣት አልወላወለም፤ 21  ደግሞም አምላክ የሰጠውን ተስፋ መፈጸም እንደሚችል ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነበር። 22  በመሆኑም “ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።” 23  ሆኖም “ተቆጠረለት” ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ብቻ አይደለም፤ 24  ከዚህ ይልቅ እንደ ጻድቃን ስለምንቆጠረው ስለ እኛም ጭምር ነው፤ ምክንያቱም ጌታችንን ኢየሱስን ከሞት ባስነሳው በእሱ እናምናለን። 25  ኢየሱስ ስለ በደላችን ለሞት አልፎ ተሰጠ፤ አምላክ ጻድቃን ናችሁ ብሎ እንዲያስታውቅልንም ከሞት ተነሳ።
[]
[]
[]
[]
11,951
5  ስለዚህ አሁን በእምነት አማካኝነት ጻድቃን ናችሁ ስለተባልን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከአምላክ ጋር ያለንን ሰላም ጠብቀን እንኑር፤ 2  ደግሞም በኢየሱስ አማካኝነት የአምላክን ጸጋ ለማግኘት በእምነት ወደ እሱ መቅረብ የቻልን ሲሆን ይህን ጸጋ አሁን አግኝተናል፤ የአምላክንም ክብር እንደምናገኝ ተስፋ በማድረግ እጅግ እንደሰት። 3  በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራ ውስጥ እያለንም እጅግ እንደሰት፤ ምክንያቱም መከራ ጽናትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን፤ 4  ጽናትም በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንድናገኝ ያስችለናል፤ ተቀባይነት ማግኘት ደግሞ ተስፋን ያጎናጽፋል፤ 5  ተስፋውም ሳይፈጸም ቀርቶ ለሐዘን አይዳርገንም፤ ምክንያቱም የአምላክ ፍቅር፣ በተሰጠን መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በልባችን ውስጥ ፈሷል። 6  ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ ለኃጢአተኞች ሞቷልና። 7  ለጻድቅ ሰው የሚሞት ማግኘት በጣም አዳጋች ነው፤ ለጥሩ ሰው ለመሞት የሚደፍር ግን ምናልባት ይገኝ ይሆናል። 8  ሆኖም አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል። 9  ከእንግዲህ በደሙ ጻድቃን ናችሁ ስለተባልን በእሱ አማካኝነት ከአምላክ ቁጣ እንደምንድን ይበልጥ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። 10  ጠላቶች ሆነን ሳለን በልጁ ሞት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ከታረቅን አሁን ታርቀን ሳለንማ በእሱ ሕይወት እንደምንድን የተረጋገጠ ነው። 11  ይህም ብቻ ሳይሆን አሁን እርቅ ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በአምላክ ሐሴት እያደረግን ነው። 12  ስለሆነም በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ። 13  ሕጉ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በዓለም ላይ ነበርና፤ ሆኖም ሕግ በሌለበት ማንም በኃጢአት አይጠየቅም። 14  ይሁንና አዳም ትእዛዝ በመተላለፍ የሠራውን ዓይነት ኃጢአት ባልሠሩት ላይም እንኳ ሳይቀር ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት በሁሉ ላይ ነገሠ፤ አዳም በኋላ ለሚመጣው አምሳያ ነበር። 15  ሆኖም ስጦታው ያስገኘው ነገር በደሉ ካስከተለው ነገር የተለየ ነው። ምክንያቱም በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ሞተዋል፤ ይሁንና የአምላክ ጸጋና ነፃ ስጦታው በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ አማካኝነት ለብዙ ሰዎች ወደር የሌለው ጥቅም አስገኝቷል! 16  በተጨማሪም ነፃ ስጦታው ያስገኘው ውጤት የአንዱ ሰው ኃጢአት ካመጣው ውጤት የተለየ ነው። ምክንያቱም አንድን በደል ተከትሎ የመጣው ፍርድ ኩነኔን አስከትሏል፤ ብዙዎች በደል ከፈጸሙ በኋላ ግን አምላክ ጻድቃን እንዲባሉ የሚያስችል ስጦታ ሰጥቷል። 17  በአንድ ሰው በደል የተነሳ ሞት በዚህ ሰው በኩል ከነገሠ የአምላክን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅን ነፃ ስጦታ የሚቀበሉትማ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ሕይወት አግኝተው ነገሥታት ሆነው እንደሚገዙ ይበልጥ የተረጋገጠ ነው! 18  ስለዚህ አንድ በደል ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲኮነኑ እንዳደረገ ሁሉ አንድ የጽድቅ ድርጊትም ሁሉም ዓይነት ሰዎች ጻድቃን ናችሁ ተብለው ለሕይወት እንዲበቁ ያስችላል። 19  ምክንያቱም በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደሆኑ ሁሉ በአንዱ ሰው መታዘዝም ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። 20  ሕጉ የመጣው ሰዎች ብዙ በደል እንደሚፈጽሙ ለማሳየት ነው። ይሁን እንጂ ሰዎች ብዙ ኃጢአት ሲፈጽሙ አምላክ ታላቅ ጸጋ አሳያቸው። 21  ይህ የሆነው ለምንድን ነው? ኃጢአት ከሞት ጋር እንደነገሠ ሁሉ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ አማካኝነት እንዲነግሥ ነው።
[]
[]
[]
[]
11,952
6  እንግዲህ ምን እንበል? ጸጋ እንዲበዛ ኃጢአት መሥራታችንን እንቀጥል? 2  በፍጹም! እኛ ለኃጢአት የሞትን ሆነን ሳለን ከእንግዲህ እንዴት በኃጢአት ውስጥ መኖራችንን እንቀጥላለን? 3  ወይስ ክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ የተጠመቅን ሁላችን እሱ ሞት ውስጥ እንደተጠመቅን አታውቁም? 4  ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደተነሳ ሁሉ እኛም አዲስ ሕይወት እንድንኖር እሱ ሞት ውስጥ በመጠመቅ ከእሱ ጋር ተቀብረናል። 5  ሞቱን በሚመስል ሞት ከእሱ ጋር አንድ ከሆንን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእሱ ጋር አንድ እንደምንሆን ጥርጥር የለውም። 6  ምክንያቱም ኃጢአተኛው ሰውነታችን በእኛ ላይ ምንም ኃይል እንዳይኖረውና ከእንግዲህ የኃጢአት ባሪያዎች ሆነን እንዳንኖር አሮጌው ስብዕናችን ከእሱ ጋር በእንጨት ላይ እንደተቸነከረ እናውቃለን። 7  የሞተ ከኃጢአቱ ነፃ ወጥቷልና። 8  በተጨማሪም ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእሱ ጋር እንደምንኖር እናምናለን። 9  ክርስቶስ አሁን ከሞት እንደተነሳና ዳግመኛ እንደማይሞት እናውቃለን፤ ከእንግዲህ ሞት በእሱ ላይ እንደ ጌታ ሊሠለጥን አይችልም። 10  ምክንያቱም እሱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኃጢአት ሞቷል፤ ሆኖም አሁን እየኖረ ያለውን ሕይወት የሚኖረው ለአምላክ ነው። 11  በተመሳሳይም እናንተ ለኃጢአት እንደሞታችሁ ሆኖም በክርስቶስ ኢየሱስ ለአምላክ እንደምትኖሩ አድርጋችሁ አስቡ። 12  በመሆኑም ኃጢአት ለሰውነታችሁ ምኞት ተገዢ እንድትሆኑ በማድረግ ሟች በሆነው ሰውነታችሁ ላይ መንገሡን እንዲቀጥል አትፍቀዱ። 13  በተጨማሪም ሰውነታችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፤ ከዚህ ይልቅ ከሞት ወደ ሕይወት እንደተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለአምላክ አቅርቡ፤ ሰውነታችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለአምላክ አቅርቡ። 14  ምክንያቱም በጸጋ ሥር እንጂ በሕግ ሥር ስላልሆናችሁ ኃጢአት በእናንተ ላይ ጌታ ሊሆን አይገባም። 15  እንግዲህ ከዚህ በመነሳት ምን ማለት እንችላለን? በጸጋ ሥር እንጂ በሕግ ሥር ስላልሆንን ኃጢአት እንሥራ ማለት ነው? በፍጹም! 16  ለማንም ቢሆን ታዛዥ ባሪያዎች ሆናችሁ ራሳችሁን ካቀረባችሁ ለዚያ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደሆናችሁ አታውቁም? በመሆኑም ሞት ለሚያስከትለው ለኃጢአት አለዚያም ጽድቅ ለሚያስገኘው ለታዛዥነት ባሪያዎች ናችሁ። 17  ሆኖም እናንተ በአንድ ወቅት የኃጢአት ባሪያዎች የነበራችሁ ቢሆንም እንድትከተሉት ለተሰጣችሁ ለእንዲህ ዓይነቱ ትምህርት ከልብ ስለታዘዛችሁ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። 18  አዎ፣ ከኃጢአት ነፃ ስለወጣችሁ የጽድቅ ባሪያዎች ሆናችኋል። 19  እኔ ሰዎች በሚረዱት ቋንቋ የምናገረው በሥጋችሁ ድክመት የተነሳ ነው፤ የአካል ክፍሎቻችሁን ክፉ ድርጊት ለመፈጸም ለርኩሰትና ለክፋት ባሪያዎች አድርጋችሁ አቅርባችሁ እንደነበረ ሁሉ አሁን ደግሞ የአካል ክፍሎቻችሁን ቅዱስ ሥራ ለመሥራት የጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ። 20  የኃጢአት ባሪያዎች በነበራችሁበት ጊዜ በጽድቅ ሥር አልነበራችሁምና። 21  ታዲያ በዚያን ጊዜ ታፈሯቸው የነበሩት ፍሬዎች ምን ዓይነት ነበሩ? አሁን የምታፍሩባቸው ነገሮች ናቸው። የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና። 22  ይሁን እንጂ አሁን ከኃጢአት ነፃ ወጥታችሁ የአምላክ ባሪያዎች ስለሆናችሁ በቅድስና ጎዳና ፍሬ እያፈራችሁ ነው፤ የዚህም መጨረሻ የዘላለም ሕይወት ነው። 23  የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና፤ አምላክ የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።
[]
[]
[]
[]
11,953
7  ወንድሞች፣ (እየተናገርኩ ያለሁት ሕግ ለሚያውቁ ሰዎች ነው፤) ሕጉ በአንድ ሰው ላይ ሥልጣን የሚኖረው በሕይወት እስከኖረ ድረስ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? 2  ለምሳሌ ያህል፣ ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ በሕግ ለእሱ የታሰረች ናት፤ ባሏ ከሞተ ግን ከባሏ ሕግ ነፃ ትወጣለች። 3  በመሆኑም ባሏ በሕይወት እያለ የሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች። ባሏ ከሞተ ግን ከእሱ ሕግ ነፃ ስለምትሆን የሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አትባልም። 4  ስለዚህ ወንድሞቼ፣ እናንተም የሌላ ይኸውም ከሞት የተነሳው የክርስቶስ እንድትሆኑ በእሱ አካል አማካኝነት ለሕጉ ሞታችኋል፤ ይህም የሆነው ለአምላክ ፍሬ እንድናፈራ ነው። 5  ምክንያቱም እንደ ሥጋ ፍላጎት እንኖር በነበረበት ጊዜ ሕጉ ይፋ ያወጣቸው የኃጢአት ምኞቶች ለሞት ፍሬ እንድናፈራ በሰውነታችን ውስጥ ይሠሩ ነበር። 6  አሁን ግን አሮጌ በሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን በአዲስ መልክ በመንፈስ ባሪያዎች እንሆን ዘንድ አስሮ ይዞን ለነበረው ሕግ ስለሞትን ከሕጉ ነፃ ወጥተናል። 7  እንግዲህ ምን እንበል? ሕጉ ጉድለት አለበት ማለት ነው? በፍጹም! እንደ እውነቱ ከሆነ ሕጉ ባይኖር ኖሮ ኃጢአት ምን እንደሆነ ባላወቅኩ ነበር። ለምሳሌ ሕጉ “አትጎምጅ” ባይል ኖሮ መጎምጀት ምን እንደሆነ ባላወቅኩ ነበር። 8  ሆኖም ኃጢአት፣ ይህ ትእዛዝ ባስገኘው አጋጣሚ ተጠቅሞ ማንኛውንም ዓይነት ነገር የመጎምጀት ፍላጎት በውስጤ እንዲያድር አደረገ፤ ሕግ ባልነበረበት ጊዜ ኃጢአት የሞተ ነበርና። 9  በእርግጥ ሕግ ባልነበረበት ጊዜ ሕያው ነበርኩ። ትእዛዙ ሲመጣ ግን ኃጢአት ዳግመኛ ሕያው ሆነ፤ እኔ ግን ሞትኩ። 10  ወደ ሕይወት እንዲመራ የታሰበውም ትእዛዝ ሞት እንዳመጣ ተገነዘብኩ። 11  ምክንያቱም ኃጢአት ትእዛዙ ባስገኘው አጋጣሚ ተጠቅሞ አታሎኛል፤ እንዲሁም በትእዛዙ አማካኝነት ገድሎኛል። 12  ስለዚህ ሕጉ በራሱ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዙም ቅዱስ፣ ጻድቅና ጥሩ ነው። 13  ታዲያ ይህ ጥሩ የሆነው ነገር ሞት አመጣብኝ ማለት ነው? በፍጹም! ከዚህ ይልቅ የገደለኝ ኃጢአት ነው። የኃጢአት ምንነት እንዲገለጥ ጥሩ በሆነው ነገር አማካኝነት ሞት ያመጣብኝ ኃጢአት ነው። ትእዛዙም ኃጢአት ምን ያህል ክፉ እንደሆነ አሳይቷል። 14  ሕጉ መንፈሳዊ እንደሆነ እናውቃለንና፤ እኔ ግን ለኃጢአት የተሸጥኩ ሥጋዊ ነኝ። 15  ለምን እንዲህ እንደማደርግ አላውቅም። ለማድረግ የምፈልገውን ነገር አላደርግምና፤ ከዚህ ይልቅ የማደርገው የምጠላውን ነገር ነው። 16  ይሁን እንጂ የማደርገው የማልፈልገውን ከሆነ ሕጉ መልካም ነው በሚለው እስማማለሁ። 17  ሆኖም አሁን ይህን የሚያደርገው በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኃጢአት ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። 18  ምክንያቱም በውስጤ ማለትም በሥጋዬ ውስጥ የሚኖር ምንም ጥሩ ነገር የለም፤ መልካም የሆነውን ነገር የማድረግ ፍላጎት እንጂ የመፈጸም ችሎታ የለኝም። 19  የምመኘውን መልካም ነገር አላደርግምና፤ የማልፈልገውን መጥፎ ነገር ግን አደርጋለሁ። 20  እንግዲህ የማደርገው የማልፈልገውን ነገር ከሆነ ይህን የማደርገው እኔ ሳልሆን በውስጤ የሚኖረው ኃጢአት ነው። 21  እንግዲያው ይህ ሕግ በራሴ ላይ ሲሠራ አያለሁ፦ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ስፈልግ ከእኔ ጋር ያለው ግን መጥፎ ነገር ነው። 22  በውስጤ በአምላክ ሕግ እጅግ ደስ ይለኛል፤ 23  በሰውነቴ ውስጥ ግን ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በሰውነቴ ውስጥ ላለው የኃጢአት ሕግ ምርኮኛ አድርጎ የሚሰጠኝን ሌላ ሕግ አያለሁ። 24  እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! እንዲህ ወዳለው ሞት ከሚመራኝ ሰውነት ማን ይታደገኛል? 25  በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሚታደገኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን! ስለዚህ እኔ ራሴ በአእምሮዬ ለአምላክ ሕግ ባሪያ ስሆን በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ ባሪያ ነኝ።
[]
[]
[]
[]
11,954
8  ስለዚህ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ያላቸው ኩነኔ የለባቸውም። 2  ምክንያቱም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድነት ላላቸው ሰዎች ሕይወት የሚያስገኘው መንፈስ ሕግ፣ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ አውጥቷችኋል። 3  ሕጉ ከሰብዓዊ አለፍጽምና የተነሳ ደካማ በመሆኑ ሊፈጽመው ያልቻለውን ነገር አምላክ ኃጢአትን ለማስወገድ የገዛ ራሱን ልጅ ኃጢአተኛ በሆኑ ሰዎች አምሳል በመላክ ፈጽሞታል። እንዲህ በማድረግም የሥጋን ኃጢአት ኮንኗል፤ 4  ይህም የሆነው የሕጉ የጽድቅ መሥፈርት እንደ ሥጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ መንፈስ ፈቃድ በምንመላለሰው በእኛ እንዲፈጸም ነው። 5  እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ አእምሯቸው በሥጋዊ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን አእምሯቸው በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው። 6  በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ሞት ያስከትላልና፤ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ግን ሕይወትና ሰላም ያስገኛል፤ 7  ሥጋ ለአምላክ ሕግ ስለማይገዛና ደግሞም ሊገዛ ስለማይችል በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር የአምላክ ጠላት ያደርጋል። 8  ስለሆነም እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚመላለሱ አምላክን ማስደሰት አይችሉም። 9  ይሁን እንጂ የአምላክ መንፈስ በእርግጥ በውስጣችሁ የሚኖር ከሆነ ከሥጋ ጋር ሳይሆን ከመንፈስ ጋር ስምም ናችሁ። ሆኖም አንድ ሰው የክርስቶስ መንፈስ ከሌለው ይህ ሰው የክርስቶስ አይደለም። 10  ይሁንና ክርስቶስ ከእናንተ ጋር አንድነት ካለው፣ ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ቢሆንም እንኳ መንፈስ ከጽድቅ የተነሳ ሕይወት ያስገኛል። 11  እንግዲህ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው የአምላክ መንፈስ በእናንተ ውስጥ የሚኖር ከሆነ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው እሱ በእናንተ ውስጥ በሚኖረው መንፈሱ አማካኝነት ሟች ሰውነታችሁንም ሕያው ያደርገዋል። 12  ስለዚህ ወንድሞች ግዴታ አለብን፤ ይሁንና ግዴታችን እንደ ሥጋ ፈቃድ መኖር አይደለም፤ 13  እንደ ሥጋ ፈቃድ የምትኖሩ ከሆነ መሞታችሁ የማይቀር ነውና፤ ይሁን እንጂ ሰውነታችሁ የሚፈጽመውን ሥራ በመንፈስ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። 14  በአምላክ መንፈስ የሚመሩ ሁሉ በእርግጥ የአምላክ ልጆች ናቸውና። 15  ዳግመኛ ለፍርሃት የሚዳርጋችሁን የባርነት መንፈስ አልተቀበላችሁም፤ ከዚህ ይልቅ አምላክ ልጆቹ አድርጎ እንዲወስዳችሁ የሚያስችል መንፈስ አግኝታችኋል፤ ይህም መንፈስ “አባ፣ አባት!” ብለን እንድንጣራ ይገፋፋናል። 16  የአምላክ ልጆች መሆናችንን ይህ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ሆኖ ይመሠክራል። 17  እንግዲህ ልጆች ከሆን ወራሾች ነን፤ ይኸውም ከአምላክ ውርሻ እንቀበላለን፤ ይሁንና የምንወርሰው ከክርስቶስ ጋር ነው፤ አሁን አብረነው መከራ ከተቀበልን፣ በኋላ ደግሞ አብረነው ክብር እንጎናጸፋለን። 18  በአሁኑ ጊዜ የሚደርስብን መከራ በእኛ ላይ ከሚገለጠው ክብር ጋር ሲነጻጸር ከምንም ሊቆጠር እንደማይችል አምናለሁ። 19  ፍጥረት የአምላክን ልጆች መገለጥ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠባበቀ ነው። 20  ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቷልና፤ የተገዛው ግን በገዛ ፈቃዱ ሳይሆን በተስፋ እንዲገዛ ባደረገው በእሱ አማካኝነት ነው፤ 21  ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከመበስበስ ባርነት ነፃ ወጥቶ የአምላክ ልጆች የሚያገኙት ዓይነት ክብራማ ነፃነት ማግኘት ነው። 22  ፍጥረት ሁሉ እስካሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በመሠቃየት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን። 23  ይህም ብቻ ሳይሆን የውርሻችንን በኩራት ይኸውም መንፈስን ያገኘን እኛ ራሳችንም በቤዛው አማካኝነት ከሥጋዊ አካላችን ነፃ በመውጣት አምላክ ልጆቹ አድርጎ እንዲወስደን በጉጉት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን። 24  በዚህ ተስፋ ድነናል፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረገው ነገር የሚታይ ከሆነ ተስፋ መሆኑ ይቀራል፤ ደግሞስ አንድ ሰው የሚያየውን ነገር ተስፋ ያደርጋል? 25  የማናየውን ነገር ተስፋ የምናደርግ ከሆነ ግን ጸንተን በጉጉት እንጠባበቀዋለን። 26  በተመሳሳይም መንፈስ በድካማችን ይረዳናል። ምን ብለን መጸለይ እንዳለብን ግራ የምንጋባበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥመንና ስሜታችንን በቃላት መግለጽ ተስኖን ስንቃትት መንፈስ ራሱ ስለ እኛ ይማልዳል። 27  ይሁንና ልብን የሚመረምረው አምላክ የመንፈስን ዓላማ ያውቃል፤ ምክንያቱም መንፈስ ለቅዱሳን የሚማልደው ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ ነው። 28  አምላክ ለሚወዱት ይኸውም ከእሱ ዓላማ ጋር በሚስማማ መንገድ ለተጠሩት ሥራውን ሁሉ አቀናጅቶ ለበጎ እንዲሆንላቸው እንደሚያደርግ እናውቃለን፤ 29  ምክንያቱም መጀመሪያ እውቅና የሰጣቸው ሰዎች የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወስኗል፤ ይኸውም ልጁ ከብዙ ወንድሞች መካከል በኩር እንዲሆን ነው። 30  ከዚህም በተጨማሪ አስቀድሞ የወሰናቸውን እነዚህን ጠራቸው፤ የጠራቸውን እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው። በመጨረሻም ያጸደቃቸውን እነዚህን አከበራቸው። 31  እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንበል? አምላክ ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል? 32  ለገዛ ልጁ እንኳ ያልሳሳው፣ ከዚህ ይልቅ ለእኛ ለሁላችን አሳልፎ የሰጠው አምላክ፣ ከእሱ ጋር አብሮ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ እንዴት በደግነት አይሰጠንም? 33  አምላክ የመረጣቸውን ማን ሊከሳቸው ይችላል? ምክንያቱም የሚያጸድቃቸው አምላክ ራሱ ነው። 34  እነሱን የሚኮንን ማን ነው? ምክንያቱም የሞተው ብሎም ከሞት የተነሳውና በአምላክ ቀኝ የተቀመጠው እንዲሁም ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። 35  ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ወይስ ጭንቀት ወይስ ስደት ወይስ ረሃብ ወይስ ራቁትነት ወይስ አደጋ ወይስ ሰይፍ? 36  ይህም “ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ሞትን እንጋፈጣለን፤ እንደ እርድ በጎችም ተቆጠርን” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 37  ከዚህ ይልቅ በወደደን በእሱ አማካኝነት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ በድል አድራጊነት እንወጣለን። 38  ምክንያቱም ሞትም ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣ መንግሥታትም ቢሆኑ፣ አሁን ያሉት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ወደፊት የሚመጡት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ማንኛውም ኃይል ቢሆን፣ 39  ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ሌላ ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ከተገለጸው የአምላክ ፍቅር ሊለየን እንደማይችል ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነኝ።
[]
[]
[]
[]
11,955
9  የክርስቶስ ተከታይ እንደመሆኔ መጠን የምናገረው እውነት ነው፤ ሕሊናዬ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚመሠክር አልዋሽም፤ 2  ታላቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ሥቃይ በልቤ ውስጥ አለ። 3  የሥጋ ዘመዶቼ ስለሆኑት ስለ ወንድሞቼ ስል እኔ ራሴ የተረገምኩ ሆኜ ከክርስቶስ ብለይ በወደድኩ ነበርና። 4  እነሱ እስራኤላውያን ናቸው፤ አምላክ ልጆቹ አድርጎ የወሰዳቸው፣ ክብር ያገኙት፣ ቃል ኪዳን የተገባላቸው፣ ሕግ የተሰጣቸው፣ ቅዱስ አገልግሎት የማቅረብ መብት ያገኙትና ተስፋ የተሰጣቸው እነሱ ናቸው። 5  አባቶችም የእነሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የተገኘው ከእነሱ ነው። የሁሉ የበላይ የሆነው አምላክ ለዘላለም ይወደስ። አሜን። 6  ይሁን እንጂ የአምላክ ቃል ከንቱ ሆኖ ቀርቷል ማለት አይደለም። ከእስራኤል የተወለደ ሁሉ በእርግጥ “እስራኤል” አይደለምና። 7  በተጨማሪም የአብርሃም ዘር ስለሆኑ ሁሉም ልጆቹ ናቸው ማለት አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ “ዘርህ የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ይሆናል” ተብሎ ተጽፏል። 8  ይህም ሲባል በሥጋ ልጆች የሆኑ በእርግጥ የአምላክ ልጆች አይደሉም፤ በተስፋው ልጆች የሆኑት ግን ዘሩ እንደሆኑ ተደርገው ይቆጠራሉ። 9  የተስፋው ቃል “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ እመጣለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች” ይላልና። 10  ተስፋው የተሰጠው በዚያን ጊዜ ብቻ ሳይሆን ርብቃ ከአባታችን ከይስሐቅ መንታ ልጆች በፀነሰች ጊዜ ጭምር ነው፤ 11  ምርጫውን በተመለከተ የአምላክ ዓላማ በሥራ ሳይሆን በጠሪው ላይ የተመካ ሆኖ ይቀጥል ዘንድ ልጆቹ ከመወለዳቸውና ጥሩም ሆነ ክፉ ከማድረጋቸው በፊት 12  ርብቃ “ታላቁ የታናሹ ባሪያ ይሆናል” ተብሎ ተነግሯት ነበር። 13  ይህም “ያዕቆብን ወደድኩ፤ ኤሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 14  እንግዲህ ምን እንበል? አምላክ ፍትሕ ያዛባል ማለት ነው? በፍጹም! 15  ሙሴን “ልምረው የምፈልገውን እምረዋለሁ፤ ልራራለት የምፈልገውን ደግሞ እራራለታለሁ” ብሎታልና። 16  ስለዚህ ይህ የተመካው በአንድ ሰው ፍላጎት ወይም ጥረት ሳይሆን ምሕረት በሚያደርገው አምላክ ላይ ነው። 17  ቅዱስ መጽሐፉ ስለ ፈርዖን ሲናገር “በሕይወት ያቆየሁህ ኃይሌን በአንተ ለማሳየትና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ለማድረግ ነው” ይላል። 18  ስለዚህ አምላክ የፈለገውን ይምራል፤ የፈለገውን ደግሞ ግትር እንዲሆን ይፈቅዳል። 19  በመሆኑም “እንደዚህ ከሆነ ታዲያ ሰዎችን ለምን ይወቅሳል? ደግሞስ ፈቃዱን ማን መቃወም ይችላል?” ትለኝ ይሆናል። 20  ለመሆኑ ለአምላክ የምትመልሰው አንተ ማን ነህ? አንድ ዕቃ ቅርጽ አውጥቶ የሠራውን ሰው “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋል? 21  ሸክላ ሠሪው ከዚያው ከአንዱ ጭቃ፣ አንዱን ዕቃ ክቡር ለሆነ አገልግሎት ሌላውን ዕቃ ደግሞ ክብር ለሌለው አገልግሎት ለመሥራት በጭቃው ላይ ሥልጣን እንዳለው አታውቅም? 22  አምላክ ቁጣውን ለማሳየትና ኃይሉ እንዲታወቅ ለማድረግ ቢፈልግም እንኳ ጥፋት የሚገባቸውን የቁጣ ዕቃዎች በብዙ ትዕግሥት ችሏቸው እንደሆነስ ምን ታውቃለህ? 23  ይህን ያደረገው ታላቅ ክብሩን አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው የምሕረት ዕቃዎች ላይ ለመግለጥ 24  ይኸውም ከአይሁዳውያን ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብም በጠራን በእኛ ላይ ታላቅ ክብሩን ለመግለጥ ቢሆንስ? 25  ይህም በሆሴዕ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብሎ እንደተናገረው ነው፦ “ሕዝቤ ያልሆኑትን ‘ሕዝቤ’ ብዬ፣ ያልተወደደችውንም ‘የተወደደች’ ብዬ እጠራለሁ፤ 26  ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብሎ በተነገራቸው ስፍራም በዚያ ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።” 27  ከዚህም በተጨማሪ ኢሳይያስ ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፦ “የእስራኤል ልጆች ቁጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም እንኳ የሚድኑት ቀሪዎች ብቻ ናቸው። 28  ይሖዋ በምድር የሚኖሩትን ይፋረዳልና፤ ይህን ደግሞ ሳይዘገይ ይፈጽመዋል።” 29  ደግሞም ኢሳይያስ አስቀድሞ እንደተናገረው “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን፣ ገሞራንም በመሰልን ነበር።” 30  እንግዲህ ምን እንበል? አሕዛብ ጽድቅን ባይከታተሉም እንኳ ጽድቅን ይኸውም በእምነት አማካኝነት የሚገኘውን ጽድቅ አገኙ፤ 31  ሆኖም እስራኤል የጽድቅን ሕግ ቢከታተልም ግቡ ላይ አልደረሰም፤ ይኸውም ሕጉን አልፈጸመም። 32  ይህ የሆነው ለምንድን ነው? በእምነት ሳይሆን በሥራ የሚገኝ እንደሆነ አድርገው ስለተከታተሉት ነው። ስለዚህ “በማሰናከያ ድንጋይ” ተሰናከሉ፤ 33  ይህም “እነሆ፣ በጽዮን የሚያደናቅፍ ድንጋይና የሚያሰናክል ዓለት አኖራለሁ፤ በእሱ ላይ እምነት የሚጥል ግን አያፍርም” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
[]
[]
[]
[]
11,956
1  መሳፍንት ፍትሕን ያስፈጽሙ በነበረበት ዘመን በምድሪቱ ላይ ረሃብ ተከሰተ፤ አንድ ሰው ከሚስቱና ከሁለት ወንዶች ልጆቹ ጋር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ለመኖር በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተልሔም ተነስቶ ወደ ሞዓብ ምድር አቀና። 2  የሰውየው ስም ኤሊሜሌክ፣ የሚስቱ ስም ናኦሚ፣ የሁለቱ ወንዶች ልጆቹ ስም ደግሞ ማህሎን እና ኪሊዮን ነበር። እነሱም በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም የሚኖሩ ኤፍራታውያን ነበሩ። ወደ ሞዓብም መጥተው በዚያ መኖር ጀመሩ። 3  ከጊዜ በኋላም የናኦሚ ባል ኤሊሜሌክ ሞተ፤ ስለሆነም ናኦሚ ከሁለት ልጆቿ ጋር ቀረች። 4  በኋላም ልጆቿ ሞዓባውያን ሴቶችን አገቡ፤ የአንደኛዋ ስም ዖርፋ፣ የሌላኛዋ ደግሞ ሩት ነበር። በዚያም ለአሥር ዓመት ያህል ኖሩ። 5  ከዚያም ሁለቱ ወንዶች ልጆቿ ማህሎንና ኪሊዮን ሞቱ፤ ናኦሚም ሁለት ልጆቿንና ባሏን አጥታ ብቻዋን ቀረች። 6  እሷም በሞዓብ ምድር ሳለች ይሖዋ ለሕዝቡ እህል በመስጠት ፊቱን ወደ እነሱ እንደመለሰ ስለሰማች ከምራቶቿ ጋር ወደ አገሯ ለመመለስ ከሞዓብ ተነሳች። 7  ከሁለቱ ምራቶቿም ጋር ትኖርበት የነበረውን ቦታ ትታ ሄደች። ወደ ይሁዳ ምድር ለመመለስ ወደዚያ የሚወስደውን መንገድ ይዘው እየሄዱ ሳሉም 8  ናኦሚ ሁለቱን ምራቶቿን እንዲህ አለቻቸው፦ “ሂዱ፣ ሁለታችሁም ወደ እናቶቻችሁ ቤት ተመለሱ። ለሞቱት ባሎቻችሁና ለእኔ ታማኝ ፍቅር እንዳሳያችሁ ሁሉ ይሖዋም ለእናንተ ታማኝ ፍቅር ያሳያችሁ። 9  ይሖዋ በየባላችሁ ቤት ያለስጋት እንድትኖሩ ያድርጋችሁ።” ከዚያም ሳመቻቸው፤ እነሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ማልቀስ ጀመሩ። 10  እንዲህም አሏት፦ “በፍጹም! ከአንቺ ጋር ወደ ወገኖችሽ እንሄዳለን።” 11  ናኦሚ ግን እንዲህ አለቻቸው፦ “ልጆቼ፣ ተመለሱ። ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ለእናንተ ባሎች ሊሆኑ የሚችሉ ወንዶች ልጆች አሁንም ልወልድ የምችል ይመስላችኋል? 12  ልጆቼ፣ ተመለሱ። እኔ እንደሆነ በጣም ስላረጀሁ ከእንግዲህ ባል ላገባ አልችልም፤ ስለዚህ ሂዱ። ዛሬ ማታ ባል የማግኘትና ልጆች የመውለድ ተስፋ ቢኖረኝ እንኳ 13  እስኪያድጉ ድረስ ትጠብቃላችሁ? እነሱን በመጠበቅስ ባል ሳታገቡ ትቆያላችሁ? ልጆቼ፣ ይሄማ አይሆንም፤ የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ስለተነሳ የእናንተን ሁኔታ ሳስብ ሕይወቴ መራራ ይሆንብኛል።” 14  እነሱም እንደገና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ከዚያም ዖርፋ አማቷን ስማ ተሰናበተቻት። ሩት ግን ከእሷ ላለመለየት የሙጥኝ አለች። 15  ናኦሚም “ተመልከች፣ መበለት የሆነችው የባልሽ ወንድም ሚስት ወደ ወገኖቿና ወደ አማልክቷ ተመልሳለች። አብረሻት ተመለሽ” አለቻት። 16  ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ከአንቺ እንድለይና ትቼሽ እንድመለስ አትማጸኚኝ፤ እኔ እንደሆነ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምታድሪበት አድራለሁ። ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል። 17  በምትሞቺበት እሞታለሁ፤ በዚያም እቀበራለሁ። ከሞት በቀር ከአንቺ የሚለየኝ ቢኖር ይሖዋ አንዳች ነገር ያምጣብኝ፤ ከዚያም የከፋ ያድርግብኝ።” 18  ናኦሚ፣ ሩት ከእሷ ጋር ለመሄድ እንደቆረጠች ስታውቅ መወትወቷን አቆመች። 19  ከዚያም ወደ ቤተልሔም ጉዟቸውን ቀጠሉ። ቤተልሔም እንደደረሱም በእነሱ ምክንያት መላ ከተማዋ ታመሰች፤ ሴቶቹም “ይህች ናኦሚ አይደለችም እንዴ?” ይሉ ነበር። 20  እሷም እንዲህ ትላቸው ነበር፦ “ናኦሚ ብላችሁ አትጥሩኝ። ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሕይወቴን መራራ አድርጎታልና ማራ ብላችሁ ጥሩኝ። 21  ከዚህ ስወጣ ሙሉ ነበርኩ፤ ይሖዋ ግን ባዶ እጄን እንድመለስ አደረገኝ። ይሖዋ ተቃውሞኝና ሁሉን የሚችለው አምላክ መከራ አምጥቶብኝ ሳለ ለምን ናኦሚ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ?” 22  እንግዲህ ናኦሚ ምራቷ ከሆነችው ከሞዓባዊቷ ሩት ጋር ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር። ቤተልሔም የደረሱትም የገብስ አዝመራ መሰብሰብ በጀመረበት ወቅት ነበር።
[]
[]
[]
[]
11,957
2  ናኦሚ በባሏ በኩል ሀብታም የሆነ የቅርብ ዘመድ ነበራት፤ ይህ ሰው ቦዔዝ የሚባል ሲሆን የኤሊሜሌክ ቤተሰብ ነበር። 2  ሞዓባዊቷም ሩት ናኦሚን “እባክሽ ወደ እርሻ ቦታዎቹ ልሂድና ሞገስ የሚያሳየኝ ሰው ካገኘሁ እህል ልቃርም” አለቻት። ናኦሚም “ልጄ ሆይ፣ ሂጂ” አለቻት። 3  ሩትም ሄደች፤ በማሳውም ውስጥ ከአጫጆቹ ኋላ እየተከተለች መቃረም ጀመረች። እንደ አጋጣሚ ሆኖ የገባችው የኤሊሜሌክ ቤተሰብ ወደሆነው ወደ ቦዔዝ እርሻ ነበር። 4  በዚህ ጊዜ ቦዔዝ ከቤተልሔም መጣ፤ አጫጆቹንም “ይሖዋ ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው። እነሱም “ይሖዋ ይባርክህ” ብለው መለሱለት። 5  ከዚያም ቦዔዝ የአጫጆቹ አለቃ የሆነውን ወጣት “ይህች ወጣት የማን ነች?” ሲል ጠየቀው። 6  የአጫጆቹ አለቃ የሆነው ወጣትም እንዲህ በማለት መለሰ፦ “ወጣቷ፣ ናኦሚ ከሞዓብ ምድር ስትመለስ አብራት የመጣች ሞዓባዊት ነች። 7  እሷም ‘እባክህ፣ ከአጫጆቹ ኋላ እየተከተልኩ የወደቁትን ዛላዎች መቃረም እችላለሁ?’ አለችኝ። ይኸው ወደዚህ ከመጣችበት ከጠዋት አንስቶ ወደ ዳሱ ገብታ ጥቂት አረፍ እስካለችበት እስካሁን ድረስ አንዴም እንኳ ቁጭ አላለችም።” 8  ከዚያም ቦዔዝ ሩትን እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ፣ ስሚኝ። ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፤ የትም አትሂጂ፤ ከወጣት ሴት ሠራተኞቼም አትራቂ። 9  የሚያጭዱበትን ማሳ እያየሽ አብረሻቸው ሂጂ። ወጣቶቹም ወንዶች እንዳይነኩሽ አዝዣቸዋለሁ። ውኃ ሲጠማሽ ወደ እንስራዎቹ ሄደሽ ወጣቶቹ ቀድተው ካስቀመጡት ጠጪ።” 10  እሷም መሬት ላይ በግንባሯ ተደፍታ በመስገድ “እኔ የባዕድ አገር ሰው ሆኜ ሳለሁ በፊትህ ሞገስ ላገኝ የበቃሁትና ትኩረት ልትሰጠኝ የቻልከው እንዴት ነው?” አለችው። 11  ቦዔዝም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “ባልሽ ከሞተ በኋላ ለአማትሽ ያደረግሽላትን ሁሉ እንዲሁም አባትሽን፣ እናትሽንና ዘመዶችሽ የሚኖሩበትን አገር ትተሽ ቀድሞ ወደማታውቂው ሕዝብ እንዴት እንደመጣሽ በሚገባ ሰምቻለሁ። 12  ላደረግሽው ሁሉ ይሖዋ ብድራትሽን ይመልስልሽ፤ በክንፎቹ ሥር ለመጠለል ብለሽ ወደ እሱ የመጣሽበት የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሙሉ ዋጋሽን ይክፈልሽ።” 13  እሷም መልሳ “ጌታዬ ሆይ፣ እኔ ከሴት አገልጋዮችህ አንዷ ባልሆንም እንኳ ስላጽናናኸኝና እኔን አገልጋይህን በሚያበረታታ መንገድ ስላነጋገርከኝ ምንጊዜም በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለችው። 14  የምግብ ሰዓትም ሲደርስ ቦዔዝ “ወደዚህ ቀረብ በይ፤ ዳቦ ወስደሽ ብዪ፤ የቆረስሽውንም ሆምጣጤ ውስጥ አጥቅሺ” አላት። በመሆኑም ከአጫጆቹ ጋር ተቀመጠች። እሱም ቆሎ ዘግኖ ሰጣት፤ እሷም እስክትጠግብ ድረስ በላች፤ የተወሰነም ተረፋት። 15  ለመቃረም በተነሳች ጊዜም ቦዔዝ ወጣቶቹን ወንዶች እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ከታጨዱት ዛላዎች ላይ እንኳ ሳይቀር ትቃርም፤ ምንም እንዳትበድሏት። 16  ከታሰረው ነዶ ላይም የተወሰኑ ዛላዎችን እየመዘዛችሁ ጣሉላትና ትቃርም፤ ማንም እንዳይከለክላት።” 17  እሷም እስከ ማታ ድረስ ስትቃርም ቆየች። የቃረመችውንም ገብስ በወቃችው ጊዜ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህል ሆነ። 18  እህሉንም ይዛ ወደ ከተማ ሄደች፤ አማቷም ምን ያህል እንደቃረመች አየች። በተጨማሪም ሩት በልታ ከጠገበች በኋላ አስተርፋ ያመጣችውን ምግብ አውጥታ ለአማቷ ሰጠቻት። 19  በዚህ ጊዜ አማቷ “ዛሬ የቃረምሽው የት ነው? የትስ ስትሠሪ ዋልሽ? ትኩረት የሰጠሽ ሰው የተባረከ ይሁን” አለቻት። እሷም “ዛሬ ስሠራ የዋልኩት ቦዔዝ በተባለ ሰው እርሻ ውስጥ ነው” በማለት ከማን ጋር ስትሠራ እንደዋለች ለአማቷ ነገረቻት። 20  ናኦሚም ምራቷን “ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ታማኝ ፍቅሩን ከማሳየት ወደኋላ የማይለው ይሖዋ ይባርከው” አለቻት። አክላም “ሰውየው ዘመዳችን ነው። ከሚቤዡን ሰዎች አንዱ ነው” አለች። 21  ከዚያም ሞዓባዊቷ ሩት “ደግሞም ‘ወጣቶቹ ሠራተኞቼ አዝመራዬን በሙሉ ሰብስበው እስኪጨርሱ ድረስ ከእነሱ አትራቂ’ ብሎኛል” አለቻት። 22  ናኦሚም ምራቷን ሩትን “ልጄ ሆይ፣ ወደ ሌላ እርሻ ብትሄጂ ሊተናኮሉሽ ስለሚችሉ ከእሱ ሴት ሠራተኞች ጋር አብረሽ መሆን ይሻልሻል” አለቻት። 23  ስለዚህ ሩት የገብሱ አዝመራና የስንዴው አዝመራ ተሰብስቦ እስኪያልቅ ድረስ ከቦዔዝ ሴት ሠራተኞች ሳትርቅ ስትቃርም ቆየች። ከአማቷም ጋር መኖሯን ቀጠለች።
[]
[]
[]
[]
11,958
3  ከዚያም አማቷ ናኦሚ እንዲህ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ፣ መልካም ይሆንልሽ ዘንድ ቤት ልፈልግልሽ አይገባም? 2  ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለም? አብረሻቸው የነበርሽው ወጣት ሴቶች የእሱ ናቸው። ዛሬ ማታ በአውድማው ላይ ገብስ ያዘራል። 3  ስለዚህ ተነስተሽ ተጣጠቢና ሰውነትሽን ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ተቀቢ፤ ከዚያም ልብስሽን ለባብሰሽ ወደ አውድማው ውረጂ። ሰውየው በልቶና ጠጥቶ እስኪጨርስ ድረስ እዚያ መኖርሽን እንዲያውቅ ማድረግ የለብሽም። 4  ሲተኛም የሚተኛበትን ቦታ ልብ ብለሽ እዪ፤ ከዚያም ሄደሽ እግሩን ገልጠሽ ተኚ። እሱም ምን ማድረግ እንዳለብሽ ይነግርሻል።” 5  እሷም “ያልሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት። 6  ስለዚህ ሩት ወደ አውድማው በመውረድ ሁሉንም ነገር ልክ አማቷ እንዳዘዘቻት አደረገች። 7  ቦዔዝም ከበላና ከጠጣ በኋላ ልቡ በደስታ ተሞላ። ከዚያም ሄዶ የተቆለለው እህል አጠገብ ተኛ። ሩትም በቀስታ መጥታ እግሩን ገልጣ ተኛች። 8  እኩለ ሌሊትም ሲሆን ቦዔዝ እየተንቀጠቀጠ ከእንቅልፉ ባነነ፤ ቀና ሲልም አንዲት ሴት እግሩ ሥር ተኝታ ተመለከተ። 9  እሱም “ለመሆኑ አንቺ ማን ነሽ?” አላት። እሷም መልሳ “እኔ አገልጋይህ ሩት ነኝ። መቤዠት የሚገባህ አንተ ስለሆንክ መጎናጸፊያህን በአገልጋይህ ላይ ጣል” አለችው። 10  በዚህ ጊዜ እንዲህ አላት፦ “ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ ይባርክሽ። ሀብታምም ሆኑ ድሃ፣ ወጣት ወንዶችን ተከትለሽ ባለመሄድሽ ከበፊቱ ይልቅ አሁን ያሳየሽው ታማኝ ፍቅር በለጠ። 11  ስለዚህ የእኔ ልጅ፣ አትፍሪ። አንቺ ምግባረ መልካም ሴት መሆንሽን የከተማው ሰው ሁሉ ስለሚያውቅ ያልሽውን ሁሉ አደርግልሻለሁ። 12  እኔ መቤዠት እንዳለብኝ የማይካድ ቢሆንም ከእኔ ይልቅ የቅርብ ዘመድ የሆነ መቤዠት የሚችል ሰው አለ። 13  ዛሬ እዚሁ እደሪ፤ ሲነጋም ሰውዬው የሚቤዥሽ ከሆነ፣ መልካም! እሱ ይቤዥሽ። ሊቤዥሽ የማይፈልግ ከሆነ ግን ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ እኔው ራሴ እቤዥሻለሁ። እስከ ማለዳ ድረስ ግን እዚሁ ተኚ።” 14  በመሆኑም እስኪነጋ ድረስ እግሩ ሥር ተኛች፤ ከዚያም ጎህ ቀዶ ሰውን በውል መለየት የሚያስችል ብርሃን ከመውጣቱ በፊት ተነሳች። እሱም “አንዲት ሴት ወደ አውድማው መጥታ እንደነበር ማንም አይወቅ” አለ። 15  በተጨማሪም “የለበስሽውን ኩታ ዘርግተሽ ያዢው” አላት። ስትዘረጋለትም ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፈረላትና አሸከማት፤ በኋላም ወደ ከተማ ሄደ። 16  እሷም ወደ አማቷ ሄደች፤ አማቷም “ልጄ ሆይ፣ እንዴት ሆነልሽ?” አለቻት። ሩትም ሰውየው ያደረገላትን ሁሉ አንድ በአንድ ነገረቻት። 17  እንዲሁም “‘ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትሂጂ’ ብሎ ይህን ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰጠኝ” አለቻት። 18  በዚህ ጊዜ ናኦሚ እንዲህ አለቻት፦ “ልጄ ሆይ፣ ከዚህ በኋላ ቁርጡ እስኪታወቅ ድረስ ዝም ብለሽ ተቀመጪ፤ ምክንያቱም ሰውየው ዛሬውኑ ለጉዳዩ እልባት ሳያበጅ ዝም ብሎ አይቀመጥም።”
[]
[]
[]
[]
11,959
4  ከዚያም ቦዔዝ ወደ ከተማዋ በር ሄዶ በዚያ ተቀመጠ። በዚህ ጊዜ ቦዔዝ ቀደም ሲል ጠቅሶት የነበረው የሚቤዠው ሰው በዚያ ሲያልፍ ተመለከተ። ቦዔዝም “እገሌ፣ አንዴ ወደዚህ ና፤ እዚህ ተቀመጥ” አለው። ሰውየውም መጥቶ ተቀመጠ። 2  ከዚያም ቦዔዝ ከከተማዋ ሽማግሌዎች መካከል አሥር ሰዎች አምጥቶ “እዚህ ተቀመጡ” አላቸው። እነሱም ተቀመጡ። 3  ቦዔዝም የሚቤዠውን ሰው እንዲህ አለው፦ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ናኦሚ የወንድማችንን የኤሊሜሌክን የእርሻ ቦታ ልትሸጠው ነው። 4  ስለዚህ ጉዳዩን ለአንተ ላሳውቅህና እንዲህ ልልህ አሰብኩ፦ ‘እዚህ በተሰበሰቡት ነዋሪዎችና በአገሬ ሽማግሌዎች ፊት ግዛው። ልትቤዠው የምትፈልግ ከሆነ ተቤዠው። ልትቤዠው የማትፈልግ ከሆነ ግን ንገረኝና ልወቀው፤ ምክንያቱም በቅድሚያ የመቤዠት መብት ያለህ አንተ ነህ፤ እኔ ደግሞ ከአንተ ቀጥሎ ነኝ።’” ሰውየውም “ልቤዠው ፈቃደኛ ነኝ” አለ። 5  ከዚያም ቦዔዝ “መሬቱን ከናኦሚ በምትገዛበት ቀን ውርሱ በሟቹ ስም እንዲጠራ ለማድረግ የሟቹ ሚስት ከሆነችው ከሞዓባዊቷ ሩት ላይም መግዛት እንዳለብህ እወቅ” አለው። 6  የሚቤዠውም ሰው “የገዛ ርስቴን አደጋ ላይ ልጥል ስለምችል ልቤዠው አልችልም። እኔ ልቤዠው ስለማልችል በእኔ የመቤዠት መብት ተጠቅመህ አንተ ለራስህ ተቤዠው” አለው። 7  በጥንት ዘመን በእስራኤል ውስጥ በነበረው ልማድ መሠረት ከመቤዠት መብትም ሆነ ይህን መብት ለሌላ ሰው ከማስተላለፍ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት የሚጸድቀው አንድ ሰው ጫማውን አውልቆ ለሌላው ወገን ሲሰጥ ነበር፤ በእስራኤል ውስጥ አንድ ውል የሚጸናው በዚህ መንገድ ሲከናወን ነበር። 8  በመሆኑም የሚቤዠው ሰው ቦዔዝን “አንተ ለራስህ ግዛው” በማለት ጫማውን አወለቀ። 9  ከዚያም ቦዔዝ ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ “የኤሊሜሌክ የሆነውን ሁሉ እንዲሁም የኪሊዮንና የማህሎን የሆነውን ሁሉ ከናኦሚ ለመግዛቴ ዛሬ እናንተ ምሥክሮች ናችሁ። 10  በተጨማሪም የሟቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል እንዲሁም ከሚኖርባት ከተማ በር እንዳይጠፋ የሟቹን ስም ዳግም በርስቱ ለማስጠራት የማህሎን ሚስት የሆነችውን ሞዓባዊቷን ሩትን ሚስት አድርጌ ወስጃታለሁ። ለዚህም እናንተ ዛሬ ምሥክሮች ናችሁ።” 11  በዚህ ጊዜ በከተማዋ በር ላይ የነበሩት ሰዎች ሁሉና ሽማግሌዎቹ እንዲህ አሉ፦ “እኛ ምሥክሮች ነን! ይሖዋ ወደ ቤትህ የምትገባውን ሚስት የእስራኤልን ቤት እንደገነቡት እንደ ራሔልና እንደ ሊያ ያድርጋት። አንተም በኤፍራታ የበለጸግክ ሁን፤ በቤተልሔምም መልካም ስም አትርፍ። 12  እንዲሁም ይሖዋ ከዚህች ወጣት ሴት በሚሰጥህ ዘር አማካኝነት ቤትህ ትዕማር ለይሁዳ እንደወለደችለት እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን።” 13  በመሆኑም ቦዔዝ ሩትን ወሰዳት፤ ሚስቱም ሆነች። ከእሷም ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ ይሖዋም እንድትፀንስ አደረጋት፤ ወንድ ልጅም ወለደች። 14  ሴቶቹም ናኦሚን እንዲህ አሏት፦ “ዛሬ የሚቤዥ ሰው ያላሳጣሽ ይሖዋ ይወደስ። ስሙም በእስራኤል ይታወጅ! 15  የምትወድሽና ከሰባት ወንዶች ልጆች የምትበልጥብሽ ምራትሽ የወለደችው ስለሆነ እሱ ሕይወትሽን የሚያድስ ይሆናል፤ በእርጅናሽም ዘመን ይጦርሻል።” 16  ናኦሚም ልጁን ወስዳ አቀፈችው፤ ትንከባከበውም ጀመር። 17  ከዚያም ጎረቤቶቿ የሆኑ ሴቶች ስም አወጡለት። እንዲሁም “ለናኦሚ ወንድ ልጅ ተወለደላት” አሉ፤ ስሙንም ኢዮቤድ አሉት። እሱም የዳዊት አባት የሆነው የእሴይ አባት ነው። 18  እንግዲህ የፋሬስ የትውልድ ሐረግ ይህ ነው፦ ፋሬስ ኤስሮንን ወለደ፤ 19  ኤስሮንም ራምን ወለደ፤ ራምም አሚናዳብን ወለደ፤ 20  አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ 21  ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ 22  ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ።
[]
[]
[]
[]
11,960
1  በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚገባቸውን ነገሮች ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ አምላክ ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውና እሱ የገለጠው ራእይ ይህ ነው። ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ በምልክቶች ገለጠለት፤ 2  ዮሐንስም አምላክ ስለሰጠው ቃልና ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰጠው ምሥክርነት ይኸውም ስላያቸው ነገሮች ሁሉ መሥክሯል። 3  የዚህን ትንቢት ቃል ጮክ ብሎ የሚያነብ ደስተኛ ነው፤ እንዲሁም ቃሉን የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፉትን ነገሮች የሚጠብቁት ደስተኞች ናቸው፤ የተወሰነው ጊዜ ቀርቧልና። 4  ከዮሐንስ፣ በእስያ አውራጃ ለሚገኙ ለሰባቱ ጉባኤዎች፦ “ካለው፣ ከነበረውና ከሚመጣው” እንዲሁም በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ 5  በተጨማሪም “ታማኝ ምሥክር፣” “ከሙታን በኩር” እና “የምድር ነገሥታት ገዢ” ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደንና በገዛ ደሙ አማካኝነት ከኃጢአታችን ነፃ ላወጣን፣ 6  ነገሥታት እንዲሁም ለአምላኩና ለአባቱ ካህናት ላደረገን ለእሱ ክብርና ኃይል ለዘላለም ይሁን። አሜን። 7  እነሆ፣ ከደመናት ጋር ይመጣል፤ ዓይኖች ሁሉ፣ የወጉትም ያዩታል፤ በእሱም የተነሳ የምድር ነገዶች ሁሉ በሐዘን ደረታቸውን ይደቃሉ። አዎ፣ ይህ በእርግጥ ይሆናል። አሜን። 8  “እኔ አልፋና ኦሜጋ፣ ያለው፣ የነበረውና የሚመጣው፣ ሁሉን ቻይ ነኝ” ይላል ይሖዋ አምላክ። 9  የኢየሱስ ተከታይ በመሆኔ ከእናንተ ጋር የመከራው፣ የመንግሥቱና የጽናቱ ተካፋይ የሆንኩ እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ፣ ስለ አምላክ በመናገሬና ስለ ኢየሱስ በመመሥከሬ ጳጥሞስ በምትባል ደሴት ነበርኩ። 10  በመንፈስ ወደ ጌታ ቀን ተወሰድኩ፤ ከኋላዬም እንደ መለከት ያለ ኃይለኛ ድምፅ ሰማሁ፤ 11  እንዲህም አለኝ፦ “የምታየውን በመጽሐፍ ጥቅልል ላይ ጽፈህ በኤፌሶን፣ በሰምርኔስ፣ በጴርጋሞን፣ በትያጥሮን፣ በሰርዴስ፣ በፊላደልፊያና በሎዶቅያ ለሚገኙት ለሰባቱ ጉባኤዎች ላከው።” 12  እኔም እያናገረኝ ያለው ማን እንደሆነ ለማየት ዞር አልኩ፤ በዚህ ጊዜም ሰባት የወርቅ መቅረዞች ተመለከትኩ፤ 13  በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስል አየሁ፤ እሱም እስከ እግሩ የሚደርስ ልብስ የለበሰና ደረቱ ላይ የወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር። 14  በተጨማሪም ራሱና ፀጉሩ እንደ ነጭ ሱፍ፣ እንደ በረዶም ነጭ ነበር፤ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤ 15  እግሮቹም እቶን ውስጥ እንደጋለ የጠራ መዳብ ነበሩ፤ ድምፁም እንደ ውኃ ፏፏቴ ነበር። 16  በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ ከአፉም በሁለቱም በኩል ስለት ያለው ረጅም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሐይ ነበር። 17  ባየሁት ጊዜ እንደሞተ ሰው ሆኜ እግሩ ሥር ወደቅኩ። እሱም ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፦ “አትፍራ። እኔ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ፤ 18  ሕያው የሆነውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበር፤ አሁን ግን ለዘላለም እኖራለሁ፤ የሞትና የመቃብር ቁልፎችም አሉኝ። 19  ስለዚህ ያየሃቸውን ነገሮች፣ አሁን እየተከናወኑ ያሉትንና ከእነዚህ በኋላ የሚፈጸሙትን ነገሮች ጻፍ። 20  በቀኝ እጄ ላይ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብት እንዲሁም የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ቅዱስ ሚስጥር ይህ ነው፦ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱን ጉባኤዎች መላእክት ያመለክታሉ፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱን ጉባኤዎች ያመለክታሉ።
[]
[]
[]
[]
11,961
10  እኔም ደመና የተጎናጸፈ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበር፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ፣ ቅልጥሞቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፤ 2  በእጁም የተከፈተች ትንሽ ጥቅልል ይዞ ነበር። እሱም ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፣ ግራ እግሩን ደግሞ በምድር ላይ አሳረፈ፤ 3  እንደሚያገሣ አንበሳም በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በጮኸም ጊዜ የሰባቱ ነጎድጓዶች ድምፆች ተናገሩ። 4  ሰባቱ ነጎድጓዶች በተናገሩም ጊዜ ለመጻፍ ተዘጋጀሁ፤ ሆኖም ከሰማይ “ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሯቸውን ነገሮች በማኅተም አሽጋቸው እንጂ አትጻፋቸው” የሚል ድምፅ ሰማሁ። 5  በባሕሩና በምድሩ ላይ ቆሞ ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አነሳ፤ 6  ሰማይንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች፣ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች እንዲሁም ባሕርንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች በፈጠረውና ለዘላለም በሚኖረው በመማል እንዲህ አለ፦ “ከእንግዲህ ወዲህ መዘግየት አይኖርም። 7  ሆኖም ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ሊነፋ በተዘጋጀባቸው ቀኖች አምላክ የገዛ ራሱ ባሪያዎች ለሆኑት ለነቢያት እንደ ምሥራች ያበሰረው ቅዱስ ሚስጥር በእርግጥ ይፈጸማል።” 8  ከሰማይ የመጣውም ድምፅ እንደገና ሲያናግረኝ ሰማሁ፤ እንዲህም አለኝ፦ “ሂድ፣ በባሕሩና በምድሩ ላይ በቆመው መልአክ እጅ ያለችውን የተከፈተች ጥቅልል ውሰድ።” 9  እኔም ወደ መልአኩ ሄጄ ትንሿን ጥቅልል እንዲሰጠኝ ጠየቅኩት። እሱም “ውሰድና ብላት፤ ሆድህን መራራ ታደርገዋለች፤ አፍህ ላይ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች” አለኝ። 10  ትንሿን ጥቅልል ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ። 11  እነሱም “ሕዝቦችን፣ ብሔራትን፣ ቋንቋዎችንና ብዙ ነገሥታትን በተመለከተ እንደገና ትንቢት መናገር አለብህ” አሉኝ።
[]
[]
[]
[]
11,962
11  እኔም ዘንግ የሚመስል ሸምበቆ ተሰጠኝ፤ እንዲህም አለኝ፦ “ተነስና የአምላክን ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስፍራ፣ መሠዊያውንና በዚያ የሚያመልኩትን ለካ። 2  ሆኖም ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ውጭ ያለውን ግቢ ሙሉ በሙሉ ተወው፤ አትለካው፤ ምክንያቱም ለአሕዛብ ተሰጥቷል፤ እነሱም የተቀደሰችውን ከተማ ለ42 ወራት ይረግጧታል። 3  እኔም ሁለቱ ምሥክሮቼ ማቅ ለብሰው ለ1,260 ቀናት ትንቢት እንዲናገሩ አደርጋለሁ።” 4  እነዚህ በሁለቱ የወይራ ዛፎችና በሁለቱ መቅረዞች ተመስለዋል፤ እነሱም በምድር ጌታ ፊት ቆመዋል። 5  ማንም እነሱን ሊጎዳ ቢፈልግ እሳት ከአፋቸው ወጥቶ ጠላቶቻቸውን ይበላል። ማንም ሊጎዳቸው ቢፈልግ በዚህ ዓይነት ሁኔታ መገደል አለበት። 6  እነዚህ ሰዎች ትንቢት በሚናገሩባቸው ቀናት ምንም ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የመዝጋት ሥልጣን አላቸው፤ እንዲሁም ውኃዎችን ወደ ደም የመለወጥና የፈለጉትን ጊዜ ያህል፣ በማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት ምድርን የመምታት ሥልጣን አላቸው። 7  የምሥክርነት ሥራቸውን ባጠናቀቁ ጊዜ፣ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ውጊያ ይከፍትባቸዋል፤ ድል ይነሳቸዋል፤ እንዲሁም ይገድላቸዋል። 8  አስከሬናቸውም በመንፈሳዊ ሁኔታ ሰዶምና ግብፅ ተብላ በምትጠራውና የእነሱም ጌታ በእንጨት ላይ በተሰቀለባት በታላቂቱ ከተማ አውራ ጎዳና ላይ ይጋደማል። 9  ከተለያዩ ሕዝቦች፣ ነገዶች፣ ቋንቋዎችና ብሔራት የተውጣጡ ሰዎችም ለሦስት ቀን ተኩል አስከሬናቸውን ያያሉ፤ አስከሬናቸውም እንዲቀበር አይፈቅዱም። 10  እነዚህ ሁለት ነቢያት በምድር ላይ የሚኖሩትን አሠቃይተው ስለነበር በምድር ላይ የሚኖሩት በእነሱ ሞት ይደሰታሉ፤ ሐሴትም ያደርጋሉ እንዲሁም እርስ በርሳቸው ስጦታ ይሰጣጣሉ። 11  ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከአምላክ የመጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ያዩአቸውም ሰዎች በታላቅ ፍርሃት ተዋጡ። 12  ከሰማይም አንድ ታላቅ ድምፅ “ወደዚህ ውጡ” ሲላቸው ሰሙ። እነሱም በደመና ውስጥ ሆነው ወደ ሰማይ ወጡ፤ ጠላቶቻቸውም አዩአቸው። 13  በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር ነውጥ ተከሰተ፤ የከተማዋ አንድ አሥረኛም ወደቀ፤ በምድር ነውጡም 7,000 ሰዎች ሞቱ፤ የቀሩትም ፍርሃት አደረባቸው፤ ለሰማይ አምላክም ክብር ሰጡ። 14  ሁለተኛው ወዮታ አልፏል። እነሆ፣ ሦስተኛው ወዮታ በፍጥነት ይመጣል። 15  ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። በሰማይም ታላላቅ ድምፆች እንዲህ ሲሉ ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የእሱ መሲሕ መንግሥት ሆነ፤ እሱም ለዘላለም ይነግሣል።” 16  በአምላክ ፊት በዙፋኖቻቸው ላይ ተቀምጠው የነበሩት 24ቱ ሽማግሌዎችም በግንባራቸው ተደፍተው ለአምላክ ሰገዱ፤ 17  እንዲህም አሉ፦ “ያለህና የነበርክ፣ ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ታላቅ ኃይልህን ስለያዝክና ንጉሥ ሆነህ መግዛት ስለጀመርክ እናመሰግንሃለን። 18  ሆኖም ብሔራት ተቆጡ፤ የአንተም ቁጣ መጣ፤ በሙታን ላይ የምትፈርድበት፣ ለባሪያዎችህ ለነቢያት፣ ለቅዱሳንና ስምህን ለሚፈሩ ለታናናሾችና ለታላላቆች ወሮታ የምትከፍልበት እንዲሁም ምድርን እያጠፉ ያሉትን የምታጠፋበት የተወሰነው ጊዜ መጣ።” 19  በሰማይ ያለው የአምላክ ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስፍራ ተከፍቶ ነበር፤ የቃል ኪዳኑ ታቦትም በቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ታየ። እንዲሁም የመብረቅ ብልጭታ፣ ድምፅ፣ ነጎድጓድ፣ የምድር ነውጥና ታላቅ በረዶ ተከሰተ።
[]
[]
[]
[]
11,963
12  ከዚያም በሰማይ ታላቅ ምልክት ታየ፦ አንዲት ሴት ፀሐይን ተጎናጽፋ ነበር፤ ጨረቃም ከእግሯ ሥር ነበረች፤ በራሷም ላይ 12 ከዋክብት ያሉት አክሊል ነበር፤ 2  እሷም ነፍሰ ጡር ነበረች። ልትወልድ ስትል ምጥ ይዟት በጭንቅ ትጮኽ ነበር። 3  ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ። እነሆ፣ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉት፣ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች የደፋ፣ ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ታላቅ ዘንዶ ታየ፤ 4  ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት አንድ ሦስተኛ ጎትቶ ወደ ምድር ወረወረ። ዘንዶውም በምትወልድበት ጊዜ ልጇን ለመዋጥ ፈልጎ ልትወልድ በተቃረበችው ሴት ፊት ቆሞ ይጠብቅ ነበር። 5  እሷም ብሔራትን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛውን ልጅ አዎ፣ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጇም ወደ አምላክና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። 6  ሴቲቱም 1,260 ቀን በዚያ እንዲመግቧት አምላክ ወዳዘጋጀላት ስፍራ ወደ ምድረ በዳ ሸሸች። 7  በሰማይም ጦርነት ተነሳ፦ ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም ተዋጓቸው፤ 8  ነገር ግን አልቻሏቸውም፤ ከዚያ በኋላም በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። 9  ስለሆነም ታላቁ ዘንዶ ይኸውም መላውን ዓለም እያሳሳተ ያለው ዲያብሎስና ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የጥንቱ እባብ ወደ ታች ተወረወረ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእሱ ጋር ተወረወሩ። 10  በሰማይ እንዲህ የሚል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፦ “አሁን የአምላካችን ማዳን፣ ኃይልና መንግሥት እንዲሁም የእሱ መሲሕ ሥልጣን ሆኗል፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ወደ ታች ተወርውሯል! 11  እነሱም ከበጉ ደም የተነሳና ከምሥክርነታቸው ቃል የተነሳ ድል ነሱት፤ እስከ ሞት ድረስ እንኳ ለነፍሳቸው አልሳሱም። 12  ስለዚህ እናንተ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ምድርና ባሕር ግን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ዲያብሎስ ጥቂት ጊዜ እንደቀረው ስላወቀ በታላቅ ቁጣ ተሞልቶ ወደ እናንተ ወርዷል።” 13  ዘንዶውም ወደ ምድር እንደተወረወረ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ በወለደችው ሴት ላይ ስደት አደረሰባት። 14  ሆኖም ሴቲቱ ከእባቡ ፊት ርቃ ለአንድ ዘመን፣ ለዘመናትና ለግማሽ ዘመን ወደምትመገብበት በምድረ በዳ ወደተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንድትችል የታላቅ ንስር ሁለት ክንፎች ተሰጧት። 15  እባቡም ሴቲቱ በወንዝ ውስጥ እንድትሰምጥ ከአፉ የወጣ እንደ ወንዝ ያለ ውኃ ከኋላዋ ለቀቀባት። 16  ይሁን እንጂ ምድሪቱ ለሴቲቱ ደረሰችላት፤ ምድሪቱም አፏን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ የለቀቀውን ወንዝ ዋጠች። 17  ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ እጅግ ተቆጥቶ የአምላክን ትእዛዛት የሚጠብቁትንና ስለ ኢየሱስ የመመሥከር ሥራ የተሰጣቸውን ከዘሯ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ።
[]
[]
[]
[]
11,964
13  እሱም በባሕር አሸዋ ላይ ቆመ። እኔም አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ያሉት አንድ አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች የነበሩት ሲሆን በራሶቹ ላይ አምላክን የሚሰድቡ ስሞች ነበሩት። 2  ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ ግን የድብ እግር፣ አፉ ደግሞ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ዘንዶውምለአውሬው ኃይልና ዙፋን እንዲሁም ታላቅ ሥልጣን ሰጠው። 3  እኔም አየሁ፤ ከአውሬው ራሶች አንዱ የሞተ ያህል እስኪሆን ድረስ ቆስሎ ነበር፤ ሆኖም ለሞት የሚዳርገው ቁስሉ ዳነ፤ ምድርም ሁሉ አውሬውን በአድናቆት ተከተለው። 4  ሰዎችም ዘንዶው ለአውሬው ሥልጣን ስለሰጠው ዘንዶውን አመለኩ፤ እንዲሁም “እንደ አውሬው ያለ ማን ነው? ከእሱስ ጋር ማን ሊዋጋ ይችላል?” በማለት አውሬውን አመለኩ። 5  እሱም የትዕቢት ቃል የሚናገርበትና አምላክን የሚሳደብበት አፍ ተሰጠው፤ ደግሞም ለ42 ወር የፈለገውን እንዲያደርግ ሥልጣን ተሰጠው። 6  አምላክን ለመሳደብ ይኸውም የአምላክን ስምና የአምላክን መኖሪያ እንዲሁም በሰማይ የሚኖሩትን ለመሳደብ አፉን ከፈተ። 7  ቅዱሳኑን እንዲዋጋና ድል እንዲያደርጋቸው ተፈቀደለት፤ ደግሞም በነገድ፣ በሕዝብ፣ በቋንቋና በብሔር ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው። 8  በምድር ላይ የሚኖሩም ሁሉ ያመልኩታል። ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የአንዳቸውም ስም በታረደው በግ የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ላይ አልሰፈረም። 9  ጆሮ ያለው ካለ ይስማ። 10  ማንም ሰው መማረክ ካለበት ይማረካል። በሰይፍ የሚገድል ካለ በሰይፍ መገደል አለበት። ቅዱሳን ጽናትና እምነት ማሳየት የሚያስፈልጋቸው እዚህ ላይ ነው። 11  ከዚያም ሌላ አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ እሱም እንደ በግ ሁለት ቀንዶች ነበሩት፤ ሆኖም እንደ ዘንዶ መናገር ጀመረ። 12  በመጀመሪያው አውሬ ፊት የመጀመሪያውን አውሬ ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀማል። ምድርና የምድር ነዋሪዎች፣ ለሞት የሚዳርገው ቁስል የዳነለትን የመጀመሪያውን አውሬ እንዲያመልኩ ያደርጋል። 13  በሰው ልጆችም ፊት ታላላቅ ምልክቶችን ይፈጽማል፤ እሳትንም እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር ያወርዳል። 14  በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በሰይፍ ቆስሎ ለነበረው በኋላ ግን ላገገመው አውሬ፣ ምስል እንዲሠሩ እያዘዘ በአውሬው ፊት እንዲፈጽማቸው በተፈቀዱለት ምልክቶች አማካኝነት በምድር ላይ የሚኖሩትን ያስታል። 15  እንዲሁም ለአውሬው ምስል እስትንፋስ እንዲሰጠው ተፈቀደለት፤ ይህም የሆነው የአውሬው ምስል መናገር እንዲችልና የአውሬውን ምስል የማያመልኩትን ሁሉ እንዲያስገድል ነው። 16  ሰዎች ሁሉ ማለትም ታናናሾችና ታላላቆች፣ ሀብታሞችና ድሆች እንዲሁም ነፃ ሰዎችና ባሪያዎች በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ ምልክት እንዲደረግባቸው አስገደደ፤ 17  ይህም የሆነው ምልክቱ ይኸውም የአውሬው ስም ወይም የስሙ ቁጥር ካለው ሰው በስተቀር ማንም መግዛት ወይም መሸጥ እንዳይችል ነው። 18  ጥበብ የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው፦ የማስተዋል ችሎታ ያለው ሰው የአውሬውን ቁጥር ያስላ፤ ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና፤ ቁጥሩም 666 ነው።
[]
[]
[]
[]
11,965
14  ከዚያም አየሁ፤ እነሆ፣ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሟል፤ ከእሱም ጋር የእሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው 144,000 ነበሩ። 2  ከሰማይ እንደ ብዙ ውኃዎችና እንደ ኃይለኛ የነጎድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሲወጣ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ በገናቸውን እየደረደሩ የሚዘምሩ ዘማሪዎች ዓይነት ድምፅ ነው። 3  እነሱም በዙፋኑ ፊት እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ የሚመስል መዝሙር እየዘመሩ ነበር፤ ከምድር ከተዋጁት ከ144,000ዎቹ በስተቀር ማንም ይህን መዝሙር ጠንቅቆ ሊያውቀው አልቻለም። 4  እነዚህ ራሳቸውን በሴቶች ያላረከሱ ናቸው፤ እንዲያውም ደናግል ናቸው። ምንጊዜም በጉ በሄደበት ሁሉ ይከተሉታል። እነዚህ ለአምላክና ለበጉ እንደ በኩራት ሆነው ከሰዎች መካከል ተዋጅተዋል፤ 5  በአፋቸውም የማታለያ ቃል አልተገኘም፤ ምንም ዓይነት እንከን የለባቸውም። 6  ሌላም መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ እሱም በምድር ላይ ለሚኖር ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ ሁሉ የሚያበስረው የዘላለም ምሥራች ይዞ ነበር። 7  እሱም በታላቅ ድምፅ “አምላክን ፍሩ፤ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም የሚፈርድበት ሰዓት ደርሷል፤ በመሆኑም ሰማይን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የውኃ ምንጮችን የሠራውን አምልኩ” አለ። 8  ሌላ ሁለተኛ መልአክ “ወደቀች! ብሔራት ሁሉ የዝሙቷን የፍትወት ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገችው ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች!” እያለ ተከተለው። 9  ሌላ ሦስተኛ መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፦ “ማንም አውሬውንና ምስሉን የሚያመልክና በግንባሩ ወይም በእጁ ላይ ምልክት የሚቀበል ከሆነ 10  እሱም፣ ሳይበረዝ ወደ ቁጣው ጽዋ የተቀዳውን የአምላክ የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ እንዲሁም በቅዱሳኑ መላእክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በድኝ ይሠቃያል። 11  የሥቃያቸውም ጭስ ለዘላለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ደግሞም አውሬውንና ምስሉን የሚያመልኩ እንዲሁም የስሙን ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ምንም እረፍት አይኖራቸውም። 12  የአምላክን ትእዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስን እምነት አጥብቀው የሚከተሉ ቅዱሳን፣ መጽናት የሚያስፈልጋቸው እዚህ ላይ ነው።” 13  ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፦ “ይህን ጻፍ፦ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከጌታ ጋር ያላቸውን አንድነት ጠብቀው የሚሞቱ ደስተኞች ናቸው። መንፈስም ‘አዎ፣ ያከናወኑት ሥራ ወዲያው ስለሚከተላቸው ከድካማቸው ይረፉ’ ይላል።” 14  ከዚያም አየሁ፤ እነሆም፣ ነጭ ደመና ነበር፤ በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጧል፤ እሱም በራሱ ላይ የወርቅ አክሊል ደፍቷል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዟል። 15  ሌላ መልአክ ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የአጨዳው ሰዓት ስለደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ ምክንያቱም የምድር መከር ደርሷል” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ። 16  በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደ፤ ምድርም ታጨደች። 17  አሁንም ሌላ መልአክ በሰማይ ካለው ቤተ መቅደስ ቅዱስ ስፍራ ወጣ፤ እሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር። 18  እንደገናም ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጣ፤ እሱም በእሳቱ ላይ ሥልጣን ነበረው። በታላቅ ድምፅ ጮኾም ስለታም ማጭድ የያዘውን መልአክ “የምድሪቱ የወይን ፍሬዎች ስለበሰሉ ስለታም ማጭድህን ስደድና የምድርን የወይን ዘለላዎች ሰብስብ” አለው። 19  መልአኩ ማጭዱን ወደ ምድር በመስደድ የምድርን ወይን ሰበሰበ፤ ከዚያም ወደ ታላቁ የአምላክ የቁጣ ወይን መጭመቂያ ወረወረው። 20  ወይኑ ከከተማው ውጭ ተረገጠ፤ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስ ከፍታ ያለውና 296 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ያለው ደም ወጣ።
[]
[]
[]
[]
11,966
15  እኔም ሌላ ታላቅና አስደናቂ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ ሰባት መቅሰፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ነበሩ። የአምላክ ቁጣ የሚደመደመው በእነዚህ ስለሆነ እነዚህ መቅሰፍቶች የመጨረሻዎቹ ናቸው። 2  እኔም ከእሳት ጋር የተቀላቀለ የብርጭቆ ባሕር የሚመስል ነገር አየሁ፤ እንዲሁም አውሬውን፣ ምስሉንና የስሙን ቁጥር ድል የነሱት የአምላክን በገናዎች ይዘው በብርጭቆው ባሕር አጠገብ ቆመው ነበር። 3  የአምላክን ባሪያ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፦ “ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ሥራዎችህ ታላቅና አስደናቂ ናቸው። የዘላለም ንጉሥ ሆይ፣ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው። 4  ይሖዋ ሆይ፣ ለመሆኑ አንተን የማይፈራና ስምህን ከፍ ከፍ የማያደርግ ማን ነው? አንተ ብቻ ታማኝ ነህና! የጽድቅ ድንጋጌዎችህ ስለተገለጡ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።” 5  ከዚህ በኋላ አየሁ፤ የምሥክሩ ድንኳን ቅዱስ ስፍራ በሰማይ ተከፍቶ ነበር፤ 6  ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባቱ መላእክትም ንጹሕና የሚያንጸባርቅ በፍታ ለብሰው እንዲሁም ደረታቸውን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቀው ከቅዱሱ ስፍራ ወጡ። 7  ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት አንዱ ለዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ የተሞሉ ሰባት የወርቅ ሳህኖችን ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው። 8  ቅዱሱ ስፍራም ከአምላክ ክብርና ከኃይሉ የተነሳ በጭስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባት መቅሰፍቶች እስኪፈጸሙ ድረስም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ማንም መግባት አልቻለም።
[]
[]
[]
[]
11,967
16  እኔም ከቅዱሱ ስፍራ የወጣ ታላቅ ድምፅ ሰባቱን መላእክት “ሂዱና የአምላክን ቁጣ የያዙትን ሰባቱን ሳህኖች በምድር ላይ አፍስሱ” ሲል ሰማሁ። 2  የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በምድር ላይ አፈሰሰው። በዚህ ጊዜም የአውሬው ምልክት በነበራቸውና ምስሉን ያመልኩ በነበሩት ሰዎች ላይ ጉዳት የሚያስከትልና አስከፊ የሆነ ቁስል ወጣባቸው። 3  ሁለተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን ወደ ባሕር አፈሰሰው። ባሕሩም እንደሞተ ሰው ደም ሆነ፤ በባሕሩም ውስጥ ያለ ሕያው ፍጡር ሁሉ ሞተ። 4  ሦስተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን ወደ ወንዞችና ወደ ውኃ ምንጮች አፈሰሰው። እነሱም ደም ሆኑ። 5  እኔም በውኃዎች ላይ ሥልጣን ያለው መልአክ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “ያለህና የነበርክ ታማኝ አምላካችን፣ እነዚህን የፍርድ ውሳኔዎች ስላስተላለፍክ አንተ ጻድቅ ነህ፤ 6  ምክንያቱም የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም አፍስሰዋል፤ አንተም ደም እንዲጠጡ ሰጥተሃቸዋል፤ ደግሞም ይገባቸዋል።” 7  መሠዊያውም “አዎ፣ ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣ ፍርድህ ሁሉ እውነትና ጽድቅ ነው” ሲል ሰማሁ። 8  አራተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰው፤ ፀሐይም ሰዎችን በእሳት እንድትለበልብ ተፈቀደላት። 9  ሰዎቹም በኃይለኛ ሙቀት ተለበለቡ፤ ሆኖም እነሱ በእነዚህ መቅሰፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን አምላክ ስም ተሳደቡ እንጂ ንስሐ አልገቡም፤ ለእሱም ክብር አልሰጡም። 10  አምስተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰው። መንግሥቱም በጨለማ ተዋጠ፤ እነሱም ከሥቃያቸው የተነሳ ምላሳቸውን ያኝኩ ጀመር፤ 11  ይሁንና ከሥቃያቸውና ከቁስላቸው የተነሳ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ከሥራቸውም ንስሐ አልገቡም። 12  ስድስተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ላይ አፈሰሰው፤ ከፀሐይ መውጫ ለሚመጡት ነገሥታት መንገድ እንዲዘጋጅላቸውም የወንዙ ውኃ ደረቀ። 13  እኔም እንቁራሪት የሚመስሉ በመንፈስ የተነገሩ ሦስት ርኩሳን ቃላት ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ እንዲሁም ከሐሰተኛው ነቢይ አፍ ሲወጡ አየሁ። 14  እንዲያውም እነዚህ በአጋንንት መንፈስ የተነገሩ ቃላት ናቸው፤ ተአምራዊ ምልክቶችም ይፈጽማሉ፤ እነሱም ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን ወደሚካሄደው ጦርነት ሊሰበስቧቸው ወደ ዓለም ነገሥታት ሁሉ ይወጣሉ። 15  “እነሆ፣ እንደ ሌባ እመጣለሁ። ራቁቱን እንዳይሄድና ሰዎች ኀፍረቱን እንዳያዩበት ነቅቶ የሚኖርና መደረቢያውን የሚጠብቅ ሰው ደስተኛ ነው።” 16  እነሱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ ሰበሰቧቸው። 17  ሰባተኛው መልአክ በሳህኑ ውስጥ ያለውን በአየር ላይ አፈሰሰው። በዚህ ጊዜ ከቅዱሱ ስፍራ፣ ከዙፋኑ “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ወጣ። 18  እንዲሁም የመብረቅ ብልጭታ፣ ድምፅና ነጎድጓድ ተከሰተ፤ ሰው በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ታይቶ የማያውቅ ታላቅ የምድር ነውጥም ተከሰተ፤ የምድር ነውጡ መጠነ ሰፊና እጅግ ታላቅ ነበር። 19  ታላቂቱ ከተማ ለሦስት ተከፈለች፤ የብሔራት ከተሞችም ፈራረሱ፤ አምላክም የመዓቱን የቁጣ ወይን ጠጅ የያዘውን ጽዋ ይሰጣት ዘንድ ታላቂቱ ባቢሎንን አስታወሳት። 20  ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ፤ ተራሮችም ሊገኙ አልቻሉም። 21  ከዚያም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ከሰማይ በሰዎች ላይ ወረደ፤ እያንዳንዱ የበረዶ ድንጋይ አንድ ታላንት ይመዝን ነበር፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ስለነበር ሰዎቹ ከበረዶው መቅሰፍት የተነሳ አምላክን ተሳደቡ።
[]
[]
[]
[]
11,968
17  ሰባቱን ሳህኖች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት አንዱ መጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “ና፣ በብዙ ውኃዎች ላይ በምትቀመጠው በታላቂቱ አመንዝራ ላይ የተበየነውን ፍርድ አሳይሃለሁ፤ 2  የምድር ነገሥታት ከእሷ ጋር አመነዘሩ፤ የምድር ነዋሪዎች ደግሞ በዝሙቷ ወይን ጠጅ ሰከሩ።” 3  እሱም በመንፈስ ኃይል ወደ ምድረ በዳ ወሰደኝ። በዚያም አንዲት ሴት አምላክን የሚሰድቡ ስሞች በሞሉበት እንዲሁም ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ባሉት ደማቅ ቀይ አውሬ ላይ ተቀምጣ አየሁ። 4  ሴቲቱ ሐምራዊና ደማቅ ቀይ ልብስ ለብሳ እንዲሁም በወርቅ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቁዎች አጊጣ ነበር፤ በእጇም አስጸያፊ ነገሮችና የዝሙቷ ርኩሰት የሞላበት የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር። 5  በግንባሯ ላይ “ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር አስጸያፊ ነገሮች እናት” የሚል ሚስጥራዊ ስም ተጽፎ ነበር። 6  እኔም ሴቲቱ በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምሥክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ተደነቅኩ። 7  መልአኩም እንዲህ አለኝ፦ “የተደነቅከው ለምንድን ነው? የሴቲቱን እንዲሁም እሷ የተቀመጠችበትን ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉት አውሬ ሚስጥር እነግርሃለሁ፦ 8  ያየኸው አውሬ ከዚህ በፊት ነበር፤ አሁን ግን የለም፤ ይሁንና በቅርቡ ከጥልቁ ይወጣል፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል። ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ላይ ያልተጻፈው የምድር ነዋሪዎች አውሬው ከዚህ በፊት እንደነበረ፣ አሁን ግን እንደሌለና ወደፊት እንደሚኖር ሲያዩ በአድናቆት ይዋጣሉ። 9  “ይህ ነገር ጥበብ ያለው አእምሮ ይጠይቃል፦ ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸውን ሰባት ተራሮች ያመለክታሉ። 10  ደግሞም ሰባት ነገሥታት ናቸው፦ አምስቱ ወድቀዋል፤ አንዱ አለ፤ ሌላው ደግሞ ገና አልመጣም፤ በሚመጣበት ጊዜ ግን ለአጭር ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል። 11  ከዚህ በፊት የነበረው፣ አሁን ግን የሌለው አውሬም ስምንተኛ ንጉሥ ነው፤ የሚወጣው ግን ከሰባቱ ነው፤ እሱም ወደ ጥፋት ይሄዳል። 12  “ያየሃቸው አሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታትን ያመለክታሉ፤ ይሁንና ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንዲነግሡ ሥልጣን ይቀበላሉ። 13  እነዚህ አንድ ዓይነት ሐሳብ አላቸው፤ በመሆኑም ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውን ለአውሬው ይሰጣሉ። 14  እነዚህ ከበጉ ጋር ይዋጋሉ፤ ሆኖም በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ ድል ይነሳቸዋል። ከእሱ ጋር ያሉት የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ድል ያደርጋሉ።” 15  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “አመንዝራዋ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውኃዎች ወገኖችን፣ ብዙ ሕዝብን፣ ብሔራትንና ቋንቋዎችን ያመለክታሉ። 16  ያየሃቸው አሥሩ ቀንዶችና አውሬውም አመንዝራዋን ይጠሏታል፤ ከዚያም ይበዘብዟታል፤ ራቁቷንም ያስቀሯታል፤ እንዲሁም ሥጋዋን ይበላሉ፤ ሙሉ በሙሉም በእሳት ያቃጥሏታል። 17  አምላክ ቃሉ ፍጻሜውን እስኪያገኝ ድረስ ሐሳቡን ዳር እንዲያደርሱ አዎ፣ መንግሥታቸውን ለአውሬው በመስጠት አንድ የሆነውን የራሳቸውን ሐሳብ እንዲፈጽሙ ይህን በልባቸው አኑሯልና። 18  ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ መንግሥት ያላትን ታላቂቱን ከተማ ታመለክታለች።”
[]
[]
[]
[]
11,969
18  ከዚህ በኋላ ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሳ ምድር በብርሃን ደመቀች። 2  እሱም በኃይለኛ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፦ “ወደቀች! ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩስ መንፈስ ሁሉ እንዲሁም የርኩሳንና የተጠሉ ወፎች ሁሉ መሰወሪያ ሆነች! 3  ብሔራት ሁሉ የዝሙቷ የፍትወት ወይን ጠጅ ሰለባ ሆነዋል፤ የምድር ነገሥታትም ከእሷ ጋር አመንዝረዋል፤ የምድር ነጋዴዎችም ያላንዳች ኀፍረት ባከማቸቻቸው ውድ ነገሮች በልጽገዋል።” 4  ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “ሕዝቤ ሆይ፣ የኃጢአቷ ተባባሪ መሆን የማትፈልጉና የሚደርስባት መቅሰፍት ተካፋይ መሆን የማትፈልጉ ከሆነ ከእሷ ውጡ። 5  ኃጢአቷ እስከ ሰማይ ድረስ ተቆልሏልና፤ አምላክም የፈጸመቻቸውን ኢፍትሐዊ ድርጊቶች አስቧል። 6  በሌሎች ላይ በፈጸመችው በዚያው መንገድ ብድራቷን መልሱላት፤ አዎ፣ ለሠራቻቸው ነገሮች እጥፍ ክፈሏት፤ በቀላቀለችበት ጽዋ እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት። 7  ለራሷ ክብር የሰጠችውንና ያላንዳች ኀፍረት ውድ ነገሮች በማከማቸት የተቀማጠለችውን ያህል፣ በዚያው ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጧት። ሁልጊዜ በልቧ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ፈጽሞ አይደርስብኝም’ ትላለችና። 8  መቅሰፍቶቿ ይኸውም ሞትና ሐዘን እንዲሁም ረሃብ በአንድ ቀን የሚመጡባት ለዚህ ነው፤ ሙሉ በሙሉም በእሳት ትቃጠላለች፤ ምክንያቱም የፈረደባት ይሖዋ አምላክ ብርቱ ነው። 9  “ከእሷ ጋር ያመነዘሩና ያላንዳች ኀፍረት ከእሷ ጋር በቅንጦት የኖሩ የምድር ነገሥታትም እሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጭስ በሚያዩበት ጊዜ ስለ እሷ ያለቅሳሉ እንዲሁም በሐዘን ደረታቸውን ይደቃሉ። 10  ደግሞም ሥቃይዋን በመፍራት በሩቅ ቆመው ‘አንቺ ታላቂቱ ከተማ፣ አንቺ ብርቱ የሆንሽው ከተማ ባቢሎን፣ እንዴት ያሳዝናል! እንዴት ያሳዝናል! ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ተፈጽሟልና’ ይላሉ። 11  “የምድር ነጋዴዎችም ከዚህ በኋላ ብዛት ያለውን ሸቀጣቸውን የሚገዛቸው ስለማይኖር ስለ እሷ ያለቅሳሉ እንዲሁም ያዝናሉ፤ 12  ብዛት ያለው ሸቀጣቸውም ወርቅን፣ ብርን፣ የከበሩ ድንጋዮችን፣ ዕንቁን፣ ጥሩ በፍታን፣ ሐምራዊ ጨርቅን፣ ሐርንና ደማቅ ቀይ ጨርቅን ያካተተ ነው፤ በተጨማሪም ጥሩ መዓዛ ካለው እንጨት የተሠራ ነገር ሁሉ፣ ከዝሆን ጥርስ፣ ውድ ከሆነ እንጨት፣ ከመዳብ፣ ከብረትና ከእብነ በረድ የተሠራ ማንኛውም ዓይነት ዕቃ ሁሉ ይገኝበታል፤ 13  ደግሞም ቀረፋ፣ የሕንድ ቅመም፣ ዕጣን፣ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት፣ ነጭ ዕጣን፣ ወይን፣ የወይራ ዘይት፣ የላመ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ከብቶች፣ በጎች፣ ፈረሶች፣ ሠረገላዎች፣ ባሪያዎችና ሰዎች ይገኙበታል። 14  አዎ፣ የተመኘሽው ጥሩ ፍሬ ከአንቺ ርቋል፤ ምርጥና ማራኪ የሆኑ ነገሮችም ሁሉ ከአንቺ ጠፍተዋል፤ ዳግመኛም አይገኙም። 15  “እነዚህን ነገሮች በመሸጥ በእሷ የበለጸጉ ነጋዴዎች ሥቃይዋን በመፍራት በሩቅ ቆመው እያለቀሱና እያዘኑ 16  እንዲህ ይላሉ፦ ‘ጥሩ በፍታ፣ ሐምራዊና ደማቅ ቀይ ልብስ የለበሰችው እንዲሁም በወርቅ ጌጣጌጥ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቁዎች የተንቆጠቆጠችው ታላቂቱ ከተማ፣ እንዴት ያሳዝናል! እንዴት ያሳዝናል! 17  ምክንያቱም ያ ሁሉ ታላቅ ሀብት በአንድ ሰዓት ውስጥ እንዳልነበረ ሆኗል።’ “የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በባሕር ላይ የሚጓዙ ሁሉ፣ መርከበኞችና መተዳደሪያቸው በባሕር ላይ የተመሠረተ ሁሉ በሩቅ ቆመው 18  እሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጭስ እያዩ ‘እንደ ታላቂቱ ከተማ ያለ ከተማ የት ይገኛል?’ በማለት ጮኹ። 19  በራሳቸው ላይ አቧራ በትነው እያለቀሱና እያዘኑ እንዲህ ሲሉ ጮኹ፦ ‘በባሕር ላይ መርከቦች ያሏቸውን ሁሉ በሀብቷ ያበለጸገችው ታላቂቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ውስጥ መጥፋቷ እንዴት ያሳዝናል! እንዴት ያሳዝናል!’ 20  “ሰማይ ሆይ፣ በእሷ ላይ በደረሰው ነገር ደስ ይበልህ፤ ደግሞም እናንተ ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያት ደስ ይበላችሁ፤ ምክንያቱም አምላክ ለእናንተ ሲል ፈርዶባታል!” 21  አንድ ብርቱ መልአክም ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስል ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር በመወርወር እንዲህ አለ፦ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ በፍጥነት ቁልቁል ትወረወራለች፤ ዳግመኛም አትገኝም። 22  በተጨማሪም ራሳቸውን በበገና የሚያጅቡ ዘማሪዎች፣ የሙዚቀኞች፣ የዋሽንት ነፊዎችና የመለከት ነፊዎች ድምፅ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ፈጽሞ አይሰማም። ደግሞም የማንኛውም ዓይነት የእጅ ጥበብ ባለሙያ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ እንዲሁም የወፍጮ ድምፅ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም። 23  የመብራት ብርሃን ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽሪት ድምፅም ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ይህም የሚሆነው ነጋዴዎችሽ የምድር ታላላቅ ሰዎች ስለነበሩና በመናፍስታዊ ድርጊቶችሽ ብሔራት ሁሉ ስለተሳሳቱ ነው። 24  በእሷም ውስጥ የነቢያት፣ የቅዱሳንና በምድር ላይ የታረዱ ሰዎች ሁሉ ደም ተገኝቷል።”
[]
[]
[]
[]
11,970
19  ከዚህ በኋላ በሰማይ እንደ ብዙ ሠራዊት ድምፅ ያለ ታላቅ ድምፅ ሰማሁ። እንዲህም አሉ፦ “ያህን አወድሱ! ማዳን፣ ክብርና ኃይል የአምላካችን ነው፤ 2  ምክንያቱም ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸው። ምድርን በዝሙቷ ባረከሰችው በታላቂቱ አመንዝራ ላይ የፍርድ እርምጃ ወስዷልና፤ እንዲሁም ስለ ባሪያዎቹ ደም ተበቅሏታል።” 3  ወዲያውኑም ለሁለተኛ ጊዜ “ያህን አወድሱ! ከእሷ የሚወጣው ጭስም ለዘላለም ወደ ላይ ይወጣል” አሉ። 4  ደግሞም 24ቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ ሰገዱ፤ እንዲሁም “አሜን! ያህን አወድሱ!” አሉ። 5  በተጨማሪም ከዙፋኑ የወጣ አንድ ድምፅ “እሱን የምትፈሩ ባሪያዎቹ ሁሉ፣ ታናናሾችና ታላላቆች፣ አምላካችንን አወድሱ” አለ። 6  እንደ ብዙ ሠራዊት ድምፅ፣ እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅና እንደ ኃይለኛ ነጎድጓድ ድምፅ ያለ ነገር ሰማሁ። እንዲህም አሉ፦ “ያህን አወድሱ፤ ምክንያቱም ሁሉን ቻይ የሆነው አምላካችን ይሖዋ ነግሦአል! 7  የበጉ ሠርግ ስለደረሰና ሙሽራዋ ራሷን ስላዘጋጀች እንደሰት፤ ሐሴትም እናድርግ፤ ለእሱም ክብር እንስጠው። 8  አዎ፣ የሚያንጸባርቅና ንጹሕ የሆነ ጥሩ በፍታ እንድትለብስ ተሰጥቷታል፤ ይህ ጥሩ በፍታ የቅዱሳንን የጽድቅ ተግባር ያመለክታልና።” 9  እሱም “ይህን ጻፍ፦ ወደ በጉ ሠርግ የራት ግብዣ የተጠሩ ደስተኞች ናቸው” አለኝ። ደግሞም “እነዚህ እውነተኛ የአምላክ ቃሎች ናቸው” አለኝ። 10  እኔም በዚህ ጊዜ ልሰግድለት በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እሱ ግን “ተጠንቀቅ! ፈጽሞ እንዳታደርገው! እኔ ከአንተም ሆነ ስለ ኢየሱስ የመመሥከር ሥራ ካላቸው ወንድሞችህ ጋር አብሬ የማገለግል ባሪያ ነኝ። ለአምላክ ስገድ! ትንቢት የሚነገረው ስለ ኢየሱስ ለመመሥከር ነውና” አለኝ። 11  እኔም ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም፣ ነጭ ፈረስ ነበር። በእሱም ላይ የተቀመጠው “ታማኝና እውነተኛ” ተብሎ ይጠራል፤ እሱም በጽድቅ ይፈርዳል እንዲሁም ይዋጋል። 12  ዓይኖቹ የእሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱም ላይ ብዙ ዘውዶች አሉ። ከራሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም ተጽፎበታል፤ 13  ደም የነካው መደረቢያም ለብሷል፤ ደግሞም “የአምላክ ቃል” በሚል ስም ይጠራል። 14  በተጨማሪም በሰማይ ያሉት ሠራዊቶች በነጭ ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር፤ እነሱም ነጭና ንጹሕ የሆነ ጥሩ በፍታ ለብሰው ነበር። 15  እሱም ብሔራትን ይመታበት ዘንድ ከአፉ ረጅም ስለታም ሰይፍ ይወጣል፤ እንደ እረኛም በብረት በትር ይገዛቸዋል። በተጨማሪም ሁሉን ቻይ የሆነውን የአምላክን የመዓቱን የቁጣ ወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል። 16  በመደረቢያው አዎ፣ በጭኑ ላይ “የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ” የሚል ስም ተጽፏል። 17  በተጨማሪም አንድ መልአክ በፀሐይ መካከል ቆሞ አየሁ፤ እሱም በታላቅ ድምፅ ጮኾ በሰማይ መካከል ለሚበርሩት ወፎች ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ወደዚህ ኑ፤ ወደ ታላቁ የአምላክ ራት ተሰብሰቡ፤ 18  የነገሥታትን ሥጋ፣ የጦር አዛዦችን ሥጋ፣ የብርቱ ሰዎችን ሥጋ፣ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ እንዲሁም የሁሉንም ሥጋ ይኸውም የነፃ ሰዎችንና የባሪያዎችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ ብሉ።” 19  ከዚህ በኋላ አውሬው፣ የምድር ነገሥታትና ሠራዊታቸው በፈረሱ ላይ ከተቀመጠውና ከሠራዊቱ ጋር ለመዋጋት ተሰብስበው አየሁ። 20  አውሬውም ተያዘ፤ በፊቱ ተአምራዊ ምልክቶች የፈጸመው ሐሰተኛው ነቢይም ከእሱ ጋር ተያዘ፤ ይህ ነቢይ በእነዚህ ምልክቶች አማካኝነት፣ የአውሬውን ምስል የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አስቷል። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በድኝ ወደሚነደው የእሳት ሐይቅ ተወረወሩ። 21  የቀሩት ግን በፈረሱ ላይ ከተቀመጠው አፍ በወጣው ረጅም ሰይፍ ተገደሉ። ወፎችም ሁሉ ሥጋቸውን በልተው ጠገቡ።
[]
[]
[]
[]
11,971
2  “በኤፌሶን ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘውና በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፦ 2  ‘ሥራህን፣ ድካምህንና ጽናትህን አውቃለሁ፤ ደግሞም መጥፎ ሰዎችን መታገሥ እንደማትችል እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትን ፈትነህ ውሸታሞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ። 3  በተጨማሪም በአቋምህ ጸንተሃል፤ ስለ ስሜም ስትል ብዙ ችግሮችን ተቋቁመሃል፤ ደግሞም አልታከትክም። 4  ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ይኸውም መጀመሪያ ላይ የነበረህን ፍቅር ትተሃል። 5  “‘ስለዚህ ከየት እንደወደቅክ አስታውስ፤ ንስሐም ግባ፤ ቀድሞ ታደርገው የነበረውንም ነገር አድርግ። አለዚያ እመጣብሃለሁ፤ ንስሐ ካልገባህ መቅረዝህን ከስፍራው አነሳዋለሁ። 6  ያም ሆኖ አንድ የሚያስመሰግንህ ነገር አለ፦ እኔም የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ትጠላለህ። 7  መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፦ ድል ለሚነሳ በአምላክ ገነት ውስጥ ካለው የሕይወት ዛፍ እንዲበላ እፈቅድለታለሁ።’ 8  “በሰምርኔስ ላለው ጉባኤ መልአክም እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ‘የመጀመሪያውና የመጨረሻው፣’ ሞቶ የነበረውና ዳግም ሕያው የሆነው እንዲህ ይላል፦ 9  ‘መከራህንና ድህነትህን አውቃለሁ፤ ይሁንና ሀብታም ነህ፤ አይሁዳውያን ሳይሆኑ አይሁዳውያን ነን የሚሉት የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ፤ እነሱ የሰይጣን ምኩራብ ናቸው። 10  ሊደርስብህ ያለውን መከራ አትፍራ። እነሆ፣ ሙሉ በሙሉ እንድትፈተኑና ለአሥር ቀን መከራ እንድትቀበሉ ዲያብሎስ አንዳንዶቻችሁን እስር ቤት ይከታል። እስከ ሞት ድረስ ታማኝነትህን አስመሥክር፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ። 11  መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፦ ድል የሚነሳ በሁለተኛው ሞት ከቶ አይጎዳም።’ 12  “በጴርጋሞን ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ በሁለቱም በኩል ስለት ያለው ረጅም ሰይፍ የያዘው እንዲህ ይላል፦ 13  ‘የምትኖረው የሰይጣን ዙፋን ባለበት እንደሆነ አውቃለሁ፤ ያም ሆኖ ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል፤ ሰይጣን በሚኖርበት፣ እናንተ ባላችሁበት ቦታ በተገደለው በታማኙ ምሥክሬ በአንቲጳስ ዘመን እንኳ በእኔ ላይ ያለህን እምነት አልካድክም። 14  “‘ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገሮች አሉኝ፤ የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሠዉ ነገሮችን እንዲበሉና የፆታ ብልግና እንዲፈጽሙ በፊታቸው ማሰናከያ እንዲያስቀምጥ ባላቅን ያስተማረውን የበለዓምን ትምህርት አጥብቀው የሚከተሉ በመካከልህ አሉ። 15  እንደዚሁም የኒቆላዎስን የኑፋቄ ትምህርት አጥብቀው የሚከተሉ ሰዎች በመካከልህ አሉ። 16  ስለዚህ ንስሐ ግባ። አለዚያ በፍጥነት ወደ አንተ እመጣለሁ፤ በአፌም ረጅም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ። 17  “‘መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፦ ድል ለሚነሳ ከተሰወረው መና ላይ እሰጠዋለሁ፤ እንዲሁም ነጭ ጠጠር እሰጠዋለሁ፤ በጠጠሩም ላይ ከሚቀበለው ሰው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም ተጽፎበታል።’ 18  “በትያጥሮን ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዓይኖችና እንደጠራ መዳብ ያሉ እግሮች ያሉት የአምላክ ልጅ እንዲህ ይላል፦ 19  ‘ሥራህን፣ ፍቅርህን፣ እምነትህን፣ አገልግሎትህንና ጽናትህን አውቃለሁ፤ ደግሞም ከመጀመሪያው ሥራህ ይልቅ የአሁኑ እንደሚበልጥ አውቃለሁ። 20  “‘ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ራሷን ነቢዪት ብላ የምትጠራውን ያቺን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል፤ እሷም የፆታ ብልግና እንዲፈጽሙና ለጣዖት የተሠዉ ነገሮችን እንዲበሉ ባሪያዎቼን ታስተምራለች እንዲሁም ታሳስታለች። 21  እኔም ንስሐ እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት፤ እሷ ግን ለፈጸመችው የፆታ ብልግና ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ አይደለችም። 22  እነሆ፣ የአልጋ ቁራኛ ላደርጋት ነው፤ ከእሷ ጋር ምንዝር የሚፈጽሙትም ከሥራዋ ንስሐ ካልገቡ ታላቅ መከራ አመጣባቸዋለሁ። 23  እንዲሁም እኔ የውስጥ ሐሳብንና ልብን የምመረምር እንደሆንኩ ጉባኤዎቹ ሁሉ እንዲያውቁ ልጆቿን በገዳይ መቅሰፍት እፈጃለሁ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ። 24  “‘ነገር ግን ይህን ትምህርት ለማትከተሉ ሁሉና “የሰይጣን ጥልቅ ነገሮች” የሚባሉትን ለማታውቁ፣ በትያጥሮን ለምትገኙ ለቀራችሁት ይህን እላለሁ፦ በእናንተ ላይ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ሸክም አልጭንባችሁም። 25  ብቻ እኔ እስክመጣ ድረስ ያላችሁን አጥብቃችሁ ያዙ። 26  ደግሞም ድል ለሚነሳና በሥራዬ እስከ መጨረሻ ለሚጸና በብሔራት ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ፤ 27  ይህም ከአባቴ የተቀበልኩት ዓይነት ሥልጣን ነው። ድል የነሳውም ሕዝቦችን እንደ ሸክላ ዕቃ እንዲደቅቁ በብረት በትር ይገዛቸዋል። 28  እኔም አጥቢያ ኮከብ እሰጠዋለሁ። 29  መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።’
[]
[]
[]
[]
11,972
20  እኔም የጥልቁን ቁልፍና ታላቅ ሰንሰለት በእጁ የያዘ አንድ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። 2  እሱም ዘንዶውን ያዘውና ለ1,000 ዓመት አሰረው፤ ይህም ዘንዶ ዲያብሎስና ሰይጣን የሆነው የጥንቱ እባብ ነው። 3  ደግሞም ይህ 1,000 ዓመት እስኪያበቃ ድረስ ከእንግዲህ ሕዝቦችን እንዳያሳስት ወደ ጥልቁ ወረወረውና ዘጋበት፤ በማኅተምም አሸገው። ከዚያ በኋላ ለጥቂት ጊዜ ሊፈታ ይገባዋል። 4  ዙፋኖችንም አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ ለተቀመጡት የመፍረድ ሥልጣን ተሰጣቸው። ስለ ኢየሱስ በመመሥከራቸውና ስለ አምላክ በመናገራቸው የተነሳ የተገደሉትን ሰዎች ነፍሳት እንዲሁም አውሬውን ወይም ምስሉን ያላመለኩትንና ምልክቱን በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያልተቀበሉትን ሰዎች አየሁ። እነሱም ሕያው ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ነገሡ። 5  (የቀሩት ሙታን ይህ 1,000 ዓመት እስኪያበቃ ድረስ ሕያው አልሆኑም።) ይህ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው። 6  በመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑ ሁሉ ደስተኞችና ቅዱሳን ናቸው፤ ሁለተኛው ሞት በእነዚህ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእሱም ጋር ለ1,000 ዓመት ይነግሣሉ። 7  ይህ 1,000 ዓመት እንዳበቃም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤ 8  እሱም በአራቱም የምድር ማዕዘናት ያሉትን ብሔራት፣ ጎግንና ማጎግን ለማሳሳትና ለጦርነቱ አንድ ላይ ለመሰብሰብ ይወጣል። የእነዚህም ቁጥር በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነው። 9  እነሱም በምድር ሁሉ ተሰራጩ፤ እንዲሁም የቅዱሳኑን ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ። ሆኖም እሳት ከሰማይ ወርዶ በላቸው። 10  ሲያሳስታቸው የነበረው ዲያብሎስም፣ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ድኙ ሐይቅ ተወረወረ፤ እነሱም ለዘላለም ቀንና ሌሊት ይሠቃያሉ። 11  እኔም አንድ ትልቅ ነጭ ዙፋንና በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም። 12  ከዚያም ሙታንን፣ ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ የመጽሐፍ ጥቅልሎችም ተከፈቱ። ሌላም ጥቅልል ተከፈተ፤ ይህም የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ነው። ሙታን በጥቅልሎቹ ውስጥ በተጻፉት ነገሮች መሠረት እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው። 13  ባሕርም በውስጡ ያሉትን ሙታን ሰጠ፤ ሞትና መቃብርም በውስጣቸው ያሉትን ሙታን ሰጡ፤ እነሱም እያንዳንዳቸው እንደየሥራቸው ፍርድ ተሰጣቸው። 14  ሞትና መቃብርም ወደ እሳቱ ሐይቅ ተወረወሩ። ይህም የእሳት ሐይቅ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል። 15  በተጨማሪም በሕይወት መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳቱ ሐይቅ ተወረወረ።
[]
[]
[]
[]
11,973
21  እኔም አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የቀድሞው ሰማይና የቀድሞው ምድር አልፈዋልና፤ ባሕሩም ከእንግዲህ ወዲህ የለም። 2  ደግሞም ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከአምላክ ዘንድ ስትወርድ አየሁ፤ እሷም ለባሏ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ ነበር። 3  በዚህ ጊዜ ከዙፋኑ አንድ ታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “እነሆ፣ የአምላክ ድንኳን ከሰዎች ጋር ነው፤ እሱም ከእነሱ ጋር ይኖራል፤ እነሱም ሕዝቡ ይሆናሉ። አምላክ ራሱም ከእነሱ ጋር ይሆናል። 4  እሱም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። ቀድሞ የነበሩት ነገሮች አልፈዋል።” 5  በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው “እነሆ፣ ሁሉንም ነገር አዲስ አደርጋለሁ” አለ። ደግሞም “እነዚህ ቃላት አስተማማኝና እውነት ስለሆኑ ጻፍ” አለኝ። 6  እንዲህም አለኝ፦ “እነዚህ ነገሮች ተፈጽመዋል! እኔ አልፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ። ለተጠማ ሁሉ ከሕይወት ውኃ ምንጭ በነፃ እሰጣለሁ። 7  ድል የሚነሳ ሁሉ እነዚህን ነገሮች ይወርሳል፤ እኔ አምላክ እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል። 8  ይሁን እንጂ የፈሪዎች፣ የእምነት የለሾች፣ ርኩስና አስጸያፊ የሆኑ ሰዎች፣ የነፍሰ ገዳዮች፣ የሴሰኞች፣ መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ የጣዖት አምላኪዎችና የውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ፋንታቸው በእሳትና በድኝ በሚቃጠል ሐይቅ ውስጥ መጣል ነው። ይህ ሁለተኛውን ሞት ያመለክታል።” 9  በሰባቱ የመጨረሻ መቅሰፍቶች የተሞሉትን ሰባቱን ሳህኖች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፣ የበጉን ሚስት፣ ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ” አለኝ። 10  ከዚያም በመንፈስ ኃይል ወደ አንድ ትልቅና ረጅም ተራራ ወሰደኝና ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከአምላክ ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ 11  እሷም የአምላክን ክብር ተላብሳ ነበር። የብርሃኗም ድምቀት እጅግ እንደከበረ ድንጋይ ይኸውም እንደ ኢያስጲድ ነበር፤ ደግሞም እንደ ክሪስታል ጥርት ብሎ ያንጸባርቅ ነበር። 12  ትልቅና ረጅም የግንብ አጥር እንዲሁም 12 በሮች ነበሯት፤ በበሮቹም ላይ 12 መላእክት ነበሩ፤ የ12ቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስም በበሮቹ ላይ ተቀርጾ ነበር። 13  በምሥራቅ ሦስት በሮች፣ በሰሜን ሦስት በሮች፣ በደቡብ ሦስት በሮችና በምዕራብ ሦስት በሮች ነበሩ። 14  በተጨማሪም የከተማዋ የግንብ አጥር 12 የመሠረት ድንጋዮች ነበሩት፤ በእነሱም ላይ የ12ቱ የበጉ ሐዋርያት 12 ስሞች ተጽፈው ነበር። 15  እያነጋገረኝ የነበረው መልአክም ከተማዋን፣ በሮቿንና የግንብ አጥሯን ለመለካት የሚያገለግል የወርቅ ዘንግ ይዞ ነበር። 16  ከተማዋ አራት ማዕዘን ቅርጽ ያላት ሲሆን ርዝመቷ ከወርዷ ጋር እኩል ነው። እሱም ከተማዋን በዘንጉ ሲለካት 2,220 ኪሎ ሜትር ገደማ ሆና ተገኘች፤ ርዝመቷ፣ ወርዷና ከፍታዋ እኩል ነው። 17  በተጨማሪም የግንብ አጥሯን ለካ፤ አጥሩም በሰው መለኪያ፣ በመልአክም መለኪያ 144 ክንድ ሆኖ ተገኘ። 18  የከተማዋ የግንብ አጥር የተገነባው ከኢያስጲድ ነበር፤ ከተማዋም የጠራ መስተዋት የሚመስል ንጹሕ ወርቅ ነበረች። 19  የከተማዋ የግንብ አጥር መሠረቶች በተለያዩ የከበሩ ድንጋዮች ያጌጡ ነበሩ፦ የመጀመሪያው መሠረት ኢያስጲድ፣ ሁለተኛው ሰንፔር፣ ሦስተኛው ኬልቄዶን፣ አራተኛው መረግድ፣ 20  አምስተኛው ሰርዶንክስ፣ ስድስተኛው ሰርድዮን፣ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፣ ስምንተኛው ቢረሌ፣ ዘጠነኛው ቶጳዝዮን፣ አሥረኛው ክርስጵራስስ፣ አሥራ አንደኛው ያክንትና አሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበር። 21  በተጨማሪም 12ቱ በሮች 12 ዕንቁዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱ በር ከአንድ ዕንቁ የተሠራ ነበር። የከተማዋ አውራ ጎዳናም ብርሃን እንደሚያስተላልፍ መስተዋት ንጹሕ ወርቅ ነበር። 22  በከተማዋ ውስጥ ቤተ መቅደስ አላየሁም፤ ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ አምላክና በጉ ቤተ መቅደሷ ናቸውና። 23  ከተማዋ የፀሐይም ሆነ የጨረቃ ብርሃን አላስፈለጋትም፤ የአምላክ ክብር ብርሃን ሰጥቷታልና፤ በጉም መብራቷ ነበር። 24  ብሔራትም በእሷ ብርሃን ይጓዛሉ፤ የምድር ነገሥታትም ክብራቸውን ወደ እሷ ያመጣሉ። 25  በሮቿ በቀን አይዘጉም፤ በዚያም ሌሊት ፈጽሞ አይኖርም። 26  የብሔራትን ግርማና ክብርም ወደ እሷ ያመጣሉ። 27  ሆኖም የረከሰ ማንኛውም ነገር እንዲሁም አስጸያፊ ነገር የሚያደርግና የሚያታልል ማንኛውም ሰው በምንም ዓይነት ወደ እሷ አይገባም፤ ወደ እሷ የሚገቡት በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል ላይ የተጻፉ ብቻ ናቸው።
[]
[]
[]
[]
11,974
22  መልአኩም ከአምላክና ከበጉ ዙፋን ወጥቶ የሚፈሰውን እንደ ክሪስታል የጠራ የሕይወት ውኃ ወንዝ አሳየኝ፤ 2  ወንዙም በከተማዋ አውራ ጎዳና መካከል ቁልቁል ይፈስ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ በየወሩ እያፈሩ በዓመት 12 ጊዜ ፍሬ የሚሰጡ የሕይወት ዛፎች ነበሩ። የዛፎቹም ቅጠሎች ሕዝቦችን ለመፈወስ የሚያገለግሉ ነበሩ። 3  በዚያም ከእንግዲህ እርግማን አይኖርም። ከዚህ ይልቅ የአምላክና የበጉ ዙፋን በከተማዋ ውስጥ ይሆናል፤ ባሪያዎቹም ቅዱስ አገልግሎት ያቀርቡለታል፤ 4  ፊቱንም ያያሉ፤ ስሙም በግንባራቸው ላይ ይሆናል። 5  በተጨማሪም ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ይሖዋ አምላክ በእነሱ ላይ ብርሃን ስለሚፈነጥቅ የመብራት ብርሃንም ሆነ የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ደግሞም ለዘላለም ይነግሣሉ። 6  መልአኩም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ቃላት አስተማማኝና እውነት ናቸው፤ አዎ፣ ነቢያት በመንፈስ መሪነት እንዲናገሩ የሚያደርገው ይሖዋ አምላክ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ መፈጸም ያለባቸውን ነገሮች ለባሪያዎቹ ለማሳየት መልአኩን ልኳል። 7  እነሆ፣ እኔ ቶሎ እመጣለሁ። በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሚገኙትን የትንቢት ቃላት የሚጠብቅ ማንኛውም ሰው ደስተኛ ነው።” 8  እነዚህን ነገሮች ስሰማና ስመለከት የነበርኩት እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን ነገሮች በሰማሁና ባየሁ ጊዜ እያሳየኝ ለነበረው መልአክ ልሰግድ እግሩ ሥር ተደፋሁ። 9  እሱ ግን “ተጠንቀቅ! ፈጽሞ እንዳታደርገው! እኔ ከአንተም ሆነ ነቢያት ከሆኑት ወንድሞችህና በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሰፈሩትን ቃላት ከሚጠብቁት ሁሉ ጋር አብሬ የማገለግል ባሪያ ነኝ። ለአምላክ ስገድ” አለኝ። 10  ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ “የተወሰነው ጊዜ ስለቀረበ በዚህ ጥቅልል ውስጥ የሰፈሩትን የትንቢት ቃላት በማኅተም አታሽጋቸው። 11  ጻድቅ ያልሆነ፣ በዓመፅ ጎዳናው ይቀጥል፤ ርኩስ የሆነውም በርኩሰቱ ይቀጥል፤ ጻድቅ የሆነው ግን በጽድቅ ጎዳና መመላለሱን ይቀጥል፤ ቅዱስ የሆነውም በቅድስና ይቀጥል። 12  “‘እነሆ፣ እኔ ቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ብድራት ከእኔ ጋር ነው። 13  እኔ አልፋና ኦሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፣ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ። 14  ከሕይወት ዛፎች ፍሬ የመብላት መብት እንዲያገኙና በበሮቿ በኩል ወደ ከተማዋ መግባት እንዲፈቀድላቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ ደስተኞች ናቸው። 15  ውሾች፣ መናፍስታዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች እንዲሁም ውሸትን የሚወዱና የሚዋሹ ሁሉ ከከተማዋ ውጭ አሉ።’ 16  “‘እኔ ኢየሱስ ለጉባኤዎቹ ጥቅም ስል ስለ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ለመመሥከር መልአኬን ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር እንዲሁም ደማቅ አጥቢያ ኮከብ ነኝ።’” 17  መንፈሱና ሙሽራይቱም “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም ሁሉ “ና!” ይበል፤ የተጠማም ሁሉ ይምጣ፤ የሚፈልግ ሁሉ የሕይወትን ውኃ በነፃ ይውሰድ። 18  “በዚህ ጥቅልል ላይ የሰፈሩትን የትንቢት ቃላት ለሚሰማ ሁሉ እመሠክራለሁ፦ ማንም በእነዚህ ነገሮች ላይ አንዲት ነገር ቢጨምር አምላክ በዚህ ጥቅልል ውስጥ የተጻፉትን መቅሰፍቶች ይጨምርበታል፤ 19  ማንም በዚህ የትንቢት መጽሐፍ ጥቅልል ላይ ከሰፈሩት ቃላት አንዲት ነገር ቢያጎድል አምላክ በዚህ ጥቅልል ላይ ከተጠቀሱት የሕይወት ዛፎችና ከቅድስቲቱ ከተማ ዕጣ ፋንታውን ይወስድበታል። 20  “ስለ እነዚህ ነገሮች የሚመሠክረው ‘አዎ፣ ቶሎ እመጣለሁ’ ይላል።” “አሜን! ጌታ ኢየሱስ፣ ና።” 21  የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከቅዱሳኑ ጋር ይሁን።
[]
[]
[]
[]
11,975
3  “በሰርዴስ ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ሰባቱ የአምላክ መናፍስት ያሉትና ሰባቱን ከዋክብት የያዘው እንዲህ ይላል፦ ‘ሥራህን አውቃለሁ፤ ሕያው ነው የሚል ስም አለህ፤ ነገር ግን ሞተሃል። 2  ሥራህን በአምላኬ ፊት በተሟላ ሁኔታ ተጠናቆ ስላላገኘሁት ንቃ፤ ሊሞቱ የተቃረቡትን የቀሩትን ነገሮችም አጠናክር። 3  ስለዚህ የተቀበልከውንና የሰማኸውን ምንጊዜም አስብ፤ እንዲሁም ዘወትር ጠብቀው፤ ንስሐም ግባ። ካልነቃህ ግን እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ በየትኛው ሰዓት ከተፍ እንደምልብህም ፈጽሞ አታውቅም። 4  “‘ይሁን እንጂ ልብሳቸውን ያላረከሱ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር በሰርዴስ አሉ፤ እነሱም የሚገባቸው ስለሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ። 5  ድል የሚነሳምልክ እንዲሁ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ እኔም ስሙን ከሕይወት መጽሐፍ በምንም ዓይነት አልደመስስም፤ ከዚህ ይልቅ በአባቴ ፊትና በመላእክቱ ፊት ለስሙ እመሠክራለሁ። 6  መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።’ 7  “በፊላደልፊያ ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፣ የዳዊት ቁልፍ ያለው፣ ማንም እንዳይዘጋ፣ የሚከፍተው እንዲሁም ማንም እንዳይከፍት፣ የሚዘጋው እሱ እንዲህ ይላል፦ 8  ‘ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፣ ማንም ሊዘጋው የማይችል የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌአለሁ። ደግሞም ጥቂት ኃይል እንዳለህ አውቃለሁ፤ ቃሌንም ጠብቀሃል፤ ስሜንም አልካድክም። 9  እነሆ፣ አይሁዳውያን ሳይሆኑ አይሁዳውያን ነን እያሉ የሚዋሹት፣ ከሰይጣን ምኩራብ የሆኑት ወደ አንተ መጥተው በእግርህ ፊት እንዲሰግዱ አደርጋለሁ፤ እንዲሁም እንደወደድኩህ እንዲያውቁ አደርጋለሁ። 10  ስለ ጽናቴ የተነገረውን ቃል ስለጠበቅክ እኔም በምድር ላይ የሚኖሩትን ለመፈተን በመላው ምድር ላይ ከሚመጣው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ። 11  ቶሎ እመጣለሁ። ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን ምንጊዜም አጥብቀህ ያዝ። 12  “‘ድል የሚነሳውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዓምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያ በኋላም በምንም ዓይነት ከዚያ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን የአምላኬን ከተማ የአዲሲቱን ኢየሩሳሌም ስም እንዲሁም የእኔን አዲስ ስም በእሱ ላይ እጽፋለሁ። 13  መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።’ 14  “በሎዶቅያ ላለው ጉባኤ መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ አሜን የሆነው፣ ታማኝና እውነተኛ ምሥክር እንዲሁም ከአምላክ ፍጥረት የመጀመሪያ የሆነው እንዲህ ይላል፦ 15  ‘ሥራህን አውቃለሁ፤ ወይ ቀዝቃዛ ወይ ትኩስ አይደለህም። ቀዝቃዛ ወይም ደግሞ ትኩስ ብትሆን ደስ ባለኝ ነበር። 16  ለብ ያልክ እንጂ ትኩስም ሆነ ቀዝቃዛ ስላልሆንክ ከአፌ አውጥቼ ልተፋህ ነው። 17  ምክንያቱም “ሀብታም ነኝ፤ ደግሞም ብዙ ሀብት አከማችቻለሁ፤ ምንም ነገር አያስፈልገኝም” ትላለህ፤ ነገር ግን ጎስቋላ፣ ምስኪን፣ ድሃ፣ ዕውርና የተራቆትክ መሆንህን አታውቅም፤ 18  ሀብታም እንድትሆን በእሳት የነጠረ ወርቅ፣ ልብስ እንድትለብስና ለኀፍረት የሚዳርገው እርቃንህ እንዲሸፈን ነጭ ልብስ እንዲሁም ማየት እንድትችል ዓይንህን የምትኳለው ኩል ከእኔ እንድትገዛ እመክርሃለሁ። 19  “‘እኔ፣ የምወዳቸውን ሁሉ እወቅሳለሁ እንዲሁም እገሥጻለሁ። ስለዚህ ቀናተኛ ሁን፤ ንስሐም ግባ። 20  እነሆ፣ በር ላይ ቆሜ እያንኳኳሁ ነው። ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ከከፈተልኝ ወደ ቤቱ እገባለሁ፤ ከእሱም ጋር ራት እበላለሁ፤ እሱም ከእኔ ጋር ይበላል። 21  እኔ ድል ነስቼ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥኩ ሁሉ ድል የሚነሳውንም ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ። 22  መንፈስ ለጉባኤዎቹ የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።’”
[]
[]
[]
[]
11,976
4  ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም፣ በሰማይ የተከፈተ በር ነበር፤ በመጀመሪያ ሲያናግረኝ የሰማሁት ድምፅ እንደ መለከት ድምፅ ያለ ነበር፤ እንዲህም አለኝ፦ “ና ወደዚህ ውጣ፤ መፈጸም ያለባቸውን ነገሮች አሳይሃለሁ።” 2  ከዚያም ወዲያውኑ የአምላክ መንፈስ ወረደብኝ፦ እነሆም፣ በሰማይ አንድ ዙፋን ተቀምጦ ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠ ነበር። 3  በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው የኢያስጲድ ድንጋይና የሰርድዮን ድንጋይ ዓይነት መልክ ነበረው፤ በዙፋኑም ዙሪያ መረግድ የሚመስል ቀስተ ደመና ነበር። 4  በዙፋኑ ዙሪያ 24 ዙፋኖች ነበሩ፤ በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ 24 ሽማግሌዎች ተቀምጠው አየሁ። 5  ከዙፋኑ መብረቅ፣ ድምፅና ነጎድጓድ ይወጣ ነበር፤ በዙፋኑም ፊት የሚነድዱ ሰባት የእሳት መብራቶች ነበሩ፤ እነዚህም ሰባቱን የአምላክ መናፍስት ያመለክታሉ። 6  በዙፋኑ ፊት የክሪስታል መልክ ያለው እንደ ብርጭቆ ያለ ባሕር የሚመስል ነገር ነበር። በዙፋኑ መካከል እና በዙፋኑ ዙሪያ ከፊትም ሆነ ከኋላ በዓይኖች የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጥረታት ነበሩ። 7  የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ይመስላል፤ ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ወይፈን ይመስላል፤ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛው ሕያው ፍጡር ደግሞ የሚበር ንስር ይመስላል። 8  እነዚህ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች አሏቸው፤ ክንፎቹ በዙሪያቸውና በውስጥ በኩል በዓይኖች የተሞሉ ናቸው። ያለማቋረጥም ቀንና ሌሊት “የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፣ ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ አምላክ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው” ይላሉ። 9  ሕያዋን ፍጥረታቱ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውንና ለዘላለም የሚኖረውን ከፍ ከፍ ባደረጉ ቁጥር እንዲሁም እሱን ባከበሩና ባመሰገኑ ቁጥር 10  ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው ለዘላለም ለሚኖረው አምልኮ ያቀርባሉ፤ እንዲሁም አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት ጥለው እንዲህ ይላሉ፦ 11  “ይሖዋ አምላካችን፣ ሁሉንም ነገሮች ስለፈጠርክ እንዲሁም ወደ ሕልውና የመጡትም ሆነ የተፈጠሩት በአንተ ፈቃድ ስለሆነ ግርማ፣ ክብርና ኃይል ልትቀበል ይገባሃል።”
[]
[]
[]
[]
11,977
5  እኔም በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው በሁለቱም በኩል የተጻፈበትና በሰባት ማኅተሞች በደንብ የታሸገ ጥቅልል በቀኝ እጁ ይዞ ተመለከትኩ። 2  አንድ ብርቱ መልአክም በታላቅ ድምፅ “ማኅተሞቹን ሊያነሳና ጥቅልሉን ሊከፍት የሚገባው ማን ነው?” ብሎ ሲያውጅ አየሁ። 3  ሆኖም በሰማይም ሆነ በምድር እንዲሁም ከምድር በታች ጥቅልሉን ሊከፍትም ሆነ ውስጡን ሊመለከት የሚችል ማንም አልነበረም። 4  ጥቅልሉን ሊከፍትም ሆነ ውስጡን ሊመለከት የሚገባው ማንም ባለመገኘቱ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። 5  ሆኖም ከሽማግሌዎቹ አንዱ “አታልቅስ። እነሆ፣ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፣ የዳዊት ሥር ድል ስላደረገ ሰባቱን ማኅተሞችና ጥቅልሉን ሊከፍት ይችላል” አለኝ። 6  በዙፋኑ መካከል፣ በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት መካከልና በሽማግሌዎቹ መካከል የታረደ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ፤ በጉም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች አሉት፤ ዓይኖቹም ወደ መላው ምድር የተላኩትን ሰባቱን የአምላክ መናፍስት ያመለክታሉ። 7  እሱም ወዲያውኑ ወደ ፊት ቀርቦ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ ጥቅልሉን ወሰደ። 8  ጥቅልሉን በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታትና 24ቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም በገናና ዕጣን የተሞሉ የወርቅ ሳህኖች ነበሯቸው። (ዕጣኑ የቅዱሳኑን ጸሎት ያመለክታል።) 9  እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፦ “ጥቅልሉን ልትወስድና ማኅተሞቹን ልትከፍት ይገባሃል፤ ታርደሃልና፤ በደምህም ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ ሰዎችን ለአምላክ ዋጅተሃል፤ 10  እንዲሁም ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤ በምድርም ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።” 11  እኔም አየሁ፤ ደግሞም በዙፋኑ፣ በሕያዋን ፍጥረታቱና በሽማግሌዎቹ ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቁጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺዎች ጊዜ ሺዎች ነበር፤ 12  እነሱም በታላቅ ድምፅ “ታርዶ የነበረው በግ ኃይል፣ ብልጽግና፣ ጥበብ፣ ብርታት፣ ክብር፣ ግርማና በረከት ሊቀበል ይገባዋል” አሉ። 13  እንዲሁም በሰማይ፣ በምድር፣ ከምድር በታችና በባሕር ያለ ፍጡር ሁሉ፣ አዎ በውስጣቸው ያሉ ነገሮች ሁሉ “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉ በረከት፣ ክብር፣ ግርማና ኃይል ለዘላለም ይሁን” ብለው ሲናገሩ ሰማሁ። 14  አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት “አሜን!” ይሉ ነበር፤ ሽማግሌዎቹም ተደፍተው ሰገዱ።
[]
[]
[]
[]
11,978
6  እኔም በጉ ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን ሲከፍት አየሁ፤ ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታትም አንዱ እንደ ነጎድጓድ ባለ ድምፅ “ና!” ሲል ሰማሁ። 2  እኔም አየሁ፣ እነሆ ነጭ ፈረስ ነበር፤ በእሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ እሱም ድል እያደረገ ወጣ፤ ድሉንም ለማጠናቀቅ ወደ ፊት ገሰገሰ። 3  ሁለተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ሁለተኛው ሕያው ፍጡር “ና!” ሲል ሰማሁ። 4  ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ሌላ ፈረስ ወጣ፤ በእሱም ላይ ለተቀመጠው ሰዎች እርስ በርሳቸው ይተራረዱ ዘንድ ሰላምን ከምድር እንዲወስድ ተፈቀደለት፤ እንዲሁም ትልቅ ሰይፍ ተሰጠው። 5  ሦስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር “ና!” ሲል ሰማሁ። እኔም አየሁ፣ እነሆ ጥቁር ፈረስ ነበር፤ በእሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር። 6  ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት መካከል እንደ ድምፅ ያለ ነገር “አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር፣ ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፤ ደግሞም የወይራ ዘይቱንና ወይኑን አትጉዳ” ሲል ሰማሁ። 7  አራተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ አራተኛው ሕያው ፍጡር “ና!” ሲል ሰማሁ። 8  እኔም አየሁ፣ እነሆ ግራጫ ፈረስ ነበር፤ በእሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበር። መቃብርም በቅርብ ይከተለው ነበር። ሞትና መቃብርም በረጅም ሰይፍ፣ በምግብ እጥረት፣ በገዳይ መቅሰፍትና በምድር አራዊት እንዲገድሉ በምድር አንድ አራተኛ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው። 9  አምስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ በአምላክ ቃል የተነሳና በሰጡት ምሥክርነት የተነሳ የታረዱትን ሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያው በታች አየሁ። 10  እነሱም “ቅዱስና እውነተኛ የሆንከው ሉዓላዊ ጌታ ሆይ፣ በምድር በሚኖሩት ላይ የማትፈርደውና ደማችንን የማትበቀለው እስከ መቼ ነው?” ብለው በታላቅ ድምፅ ጮኹ። 11  ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንዲሁም ወደፊት እንደ እነሱ የሚገደሉት ባልንጀሮቻቸው የሆኑ ባሪያዎችና የወንድሞቻቸው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንዲጠብቁ ተነገራቸው። 12  ስድስተኛውንም ማኅተም ሲከፍት አየሁ፤ ታላቅ የምድር ነውጥም ተከሰተ፤ ፀሐይም ከፀጉር እንደተሠራ ማቅ ጠቆረች፤ ጨረቃም ሙሉ በሙሉ ደም መሰለች፤ 13  ኃይለኛ ነፋስ የበለስን ዛፍ ሲያወዛውዝ ያልበሰሉት ፍሬዎች ከዛፉ ላይ እንደሚረግፉ፣ የሰማይ ከዋክብትም ወደ ምድር ወደቁ። 14  ሰማይም እየተጠቀለለ እንዳለ የመጽሐፍ ጥቅልል ከቦታው ተነሳ፤ እንዲሁም ተራሮች ሁሉና ደሴቶች ሁሉ ከቦታቸው ተወገዱ። 15  ከዚያም የምድር ነገሥታት፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የጦር አዛዦች፣ ሀብታሞች፣ ብርቱዎች፣ ባሪያዎች ሁሉና ነፃ ሰዎች ሁሉ በዋሻዎች ውስጥና ተራራ ላይ ባሉ ዓለቶች መካከል ተደበቁ። 16  ተራሮቹንና ዓለቶቹንም እንዲህ እያሉ ተማጸኑ፦ “በላያችን ውደቁና በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊትና ከበጉ ቁጣ ሰውሩን፤ 17  ምክንያቱም ቁጣቸውን የሚገልጹበት ታላቁ ቀን መጥቷል፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?”
[]
[]
[]
[]
11,979
7  ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱ የምድር ማዕዘናት ቆመው አየሁ፤ እነሱም በምድር ወይም በባሕር ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ ምንም ነፋስ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳት አጥብቀው ይዘው ነበር። 2  እንዲሁም የሕያው አምላክ ማኅተም ያለው ሌላ መልአክ ከፀሐይ መውጫ ወደ ላይ ሲወጣ አየሁ፤ እሱም ምድርንና ባሕርን እንዲጎዱ ሥልጣን የተሰጣቸውን አራቱን መላእክት በታላቅ ድምፅ 3  እንዲህ አላቸው፦ “የአምላካችንን ባሪያዎች ግንባራቸው ላይ ማኅተም እስክናደርግባቸው ድረስ ምድርን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጉዱ።” 4  የታተሙትን ሰዎች ቁጥር ሰማሁ፤ ቁጥራቸው 144,000 ሲሆን የታተሙትም ከእያንዳንዱ የእስራኤል ልጆች ነገድ ነበር፦ 5  ከይሁዳ ነገድ 12,000 ታተሙ፤ከሮቤል ነገድ 12,000፣ከጋድ ነገድ 12,000፣ 6  ከአሴር ነገድ 12,000፣ከንፍታሌም ነገድ 12,000፣ከምናሴ ነገድ 12,000፣ 7  ከስምዖን ነገድ 12,000፣ከሌዊ ነገድ 12,000፣ከይሳኮር ነገድ 12,000፣ 8  ከዛብሎን ነገድ 12,000፣ከዮሴፍ ነገድ 12,000፣ከቢንያም ነገድ 12,000 ታተሙ። 9  ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም፣ ከሁሉም ብሔራት፣ ነገዶች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች የተውጣጡ አንድም ሰው ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሕዝብ ነጭ ልብስ ለብሰው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ነበር፤ የዘንባባ ዝንጣፊዎችንም በእጆቻቸው ይዘው ነበር። 10  በታላቅም ድምፅ እየጮኹ “መዳን ያገኘነው በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከአምላካችን እንዲሁም ከበጉ ነው” ይሉ ነበር። 11  መላእክቱ ሁሉ በዙፋኑ፣ በሽማግሌዎቹና በአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት ዙሪያ ቆመው ነበር፤ እነሱም በዙፋኑ ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ለአምላክ ሰገዱ፤ 12  እንዲህም አሉ፦ “አሜን! ውዳሴ፣ ግርማ፣ ጥበብ፣ ምስጋና፣ ክብር፣ ኃይልና ብርታት ለዘላለም ለአምላካችን ይሁን። አሜን።” 13  ከሽማግሌዎቹ አንዱ መልሶ “እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱት እነማን ናቸው? ከወዴትስ የመጡ ናቸው?” አለኝ። 14  እኔም ወዲያውኑ “ጌታዬ፣ የምታውቀው አንተ ነህ” አልኩት። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ታላቁን መከራ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል። 15  በአምላክ ዙፋን ፊት ያሉትም ለዚህ ነው፤ በቤተ መቅደሱም ቀንና ሌሊት ቅዱስ አገልግሎት እያቀረቡለት ነው፤ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውም ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል። 16  ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም እንዲሁም አይጠሙም፤ ፀሐይ አይመታቸውም፤ ሐሩሩም አያቃጥላቸውም፤ 17  ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናል፤ ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭም ይመራቸዋል። አምላክም እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።”
[]
[]
[]
[]
11,980
8  ሰባተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ጸጥታ ሰፈነ። 2  እኔም በአምላክ ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፤ ሰባት መለከትም ተሰጣቸው። 3  የወርቅ ጥና የያዘ ሌላ መልአክ መጥቶ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ እሱም የቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት እየተሰማ በነበረበት ወቅት በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቁ መሠዊያ ላይ እንዲያቀርበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዕጣን ተሰጠው። 4  በመልአኩ እጅ ያለው የዕጣኑ ጭስ እንዲሁም የቅዱሳኑ ጸሎት በአምላክ ፊት ወደ ላይ ወጣ። 5  ሆኖም መልአኩ ወዲያውኑ ጥናውን ይዞ ከመሠዊያው ላይ እሳት በመውሰድ ጥናውን ሞላውና እሳቱን ወደ ምድር ወረወረው። ከዚያም ነጎድጓድ፣ ድምፅ፣ የመብረቅ ብልጭታና የምድር ነውጥ ተከሰተ። 6  ሰባቱን መለከቶች የያዙት ሰባቱ መላእክትም ሊነፉ ተዘጋጁ። 7  የመጀመሪያው መለከቱን ነፋ። ከደም ጋር የተቀላቀለ በረዶና እሳት ታየ፤ ወደ ምድርም ተወረወረ፤ የምድር አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለሙ ተክሎችም ሁሉ ተቃጠሉ። 8  ሁለተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። በእሳት የተቀጣጠለ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገርም ወደ ባሕር ተወረወረ። የባሕሩም አንድ ሦስተኛ ደም ሆነ፤ 9  በባሕር ውስጥ ካሉ ሕያዋን ፍጥረታትም አንድ ሦስተኛው ሞተ፤ ከመርከቦችም አንድ ሦስተኛው ወደመ። 10  ሦስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። እንደ መብራት ቦግ ያለ አንድ ትልቅ ኮከብም ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞች አንድ ሦስተኛና በውኃ ምንጮች ላይ ወደቀ። 11  ኮከቡ ጭቁኝ ይባላል። የውኃውም አንድ ሦስተኛ እንደ ጭቁኝ መራራ ሆነ፤ ውኃውም መራራ ከመሆኑ የተነሳ ብዙ ሰዎች በውኃው ጠንቅ ሞቱ። 12  አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፣ የጨረቃ አንድ ሦስተኛና የከዋክብት አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ይህም የሆነው የእነዚህ አካላት አንድ ሦስተኛው እንዲጨልም እንዲሁም የቀኑ አንድ ሦስተኛና የሌሊቱ አንድ ሦስተኛ ብርሃን እንዳያገኝ ነው። 13  እኔም አየሁ፤ አንድ ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “መለከቶቻቸውን ሊነፉ የተዘጋጁት ሦስቱ መላእክት በሚያሰሟቸው በቀሩት ኃይለኛ የመለከት ድምፆች የተነሳ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!”
[]
[]
[]
[]
11,981
9  አምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። እኔም ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀ አንድ ኮከብ አየሁ፤ ለእሱም የጥልቁ መግቢያ ቁልፍ ተሰጠው። 2  የጥልቁንም መግቢያ ከፈተው፤ በመግቢያውም በኩል ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጭስ ያለ ጭስ ወጣ፤ ከዚያ በወጣው ጭስም ፀሐይ ጨለመች፤ አየሩም ጠቆረ። 3  ከጭሱም አንበጦች ወጥተው ወደ ምድር ወረዱ፤ እነሱም በምድር ላይ ያሉ ጊንጦች ያላቸው ዓይነት ሥልጣን ተሰጣቸው። 4  የአምላክ ማኅተም በግንባራቸው ላይ የሌላቸውን ሰዎች ብቻ እንጂ ማንኛውንም የምድር ተክል ወይም ማንኛውንም ዕፀዋት ወይም ማንኛውንም ዛፍ እንዳይጎዱ ተነገራቸው። 5  አንበጦቹም ሰዎቹን እንዲገድሏቸው ሳይሆን ለአምስት ወር እንዲያሠቃዩአቸው ተፈቀደላቸው፤ በእነሱም ላይ የሚደርሰው ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዓይነት ሥቃይ ነው። 6  በእነዚያ ቀኖች ሰዎች ሞትን ይሻሉ፤ ሆኖም ፈጽሞ አያገኙትም፤ ለመሞት ይመኛሉ፤ ሞት ግን ከእነሱ ይሸሻል። 7  የአንበጦቹም ገጽታ ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶች ይመስል ነበር፤ በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊሎች የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ፤ ፊታቸው ደግሞ የሰው ፊት ይመስል ነበር፤ 8  ፀጉራቸው የሴት ፀጉር ይመስል ነበር። ጥርሳቸው ግን የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር፤ 9  የብረት ጥሩር የሚመስል ጥሩርም ነበራቸው። የክንፎቻቸው ድምፅም ወደ ጦርነት የሚገሰግሱ በፈረስ የሚጎተቱ ሠረገላዎች ድምፅ ይመስል ነበር። 10  በተጨማሪም የጊንጥ ዓይነት ተናዳፊ ጅራት አላቸው፤ ደግሞም ሰዎቹን ለአምስት ወር የሚጎዱበት ሥልጣን በጅራታቸው ላይ ነበር። 11  በእነሱ ላይ የተሾመ ንጉሥ አላቸው፤ እሱም የጥልቁ መልአክ ነው። በዕብራይስጥ ስሙ አባዶን ሲሆን በግሪክኛ ደግሞ ስሙ አጶልዮን ነው። 12  አንዱ ወዮታ አልፏል። እነሆ፣ ከዚህ በኋላ ሌሎች ሁለት ወዮታዎች ይመጣሉ። 13  ስድስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ። ደግሞም በአምላክ ፊት ካለው የወርቅ መሠዊያ ቀንዶች የወጣ አንድ ድምፅ ሰማሁ፤ 14  ድምፁም መለከት የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ “በታላቁ ወንዝ፣ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው” አለው። 15  ለዚህ ሰዓት፣ ቀን፣ ወርና ዓመት ተዘጋጅተው የነበሩት አራቱ መላእክትም ከሰዎቹ አንድ ሦስተኛውን እንዲገድሉ ተፈቱ። 16  የፈረሰኞቹ ሠራዊት ብዛት ሁለት እልፍ ጊዜ እልፍ ነበር፤ ቁጥራቸውንም ሰማሁ። 17  በራእዩ ላይ ያየኋቸው ፈረሶችና በላያቸው የተቀመጡት ይህን ይመስሉ ነበር፦ እንደ እሳት ቀይ፣ እንደ ያክንት ሰማያዊና እንደ ድኝ ቢጫ የሆነ ጥሩር ነበራቸው፤ የፈረሶቹም ራስ እንደ አንበሳ ራስ ነበር፤ ከአፋቸውም እሳት፣ ጭስና ድኝ ወጣ። 18  ከአፋቸው በወጡት በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች ይኸውም በእሳቱ፣ በጭሱና በድኙ ከሰዎቹ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ተገደሉ። 19  የፈረሶቹ ሥልጣን ያለው በአፋቸውና በጅራታቸው ላይ ነውና፤ ጅራታቸው እባብ የሚመስል ሲሆን ራስም አለው፤ ጉዳት የሚያደርሱትም በዚህ ነው። 20  ሆኖም በእነዚህ መቅሰፍቶች ያልተገደሉት የቀሩት ሰዎች ከእጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም፤ ደግሞም አጋንንትን እንዲሁም ማየት፣ መስማትም ሆነ መሄድ የማይችሉትን ከወርቅ፣ ከብር፣ ከመዳብ፣ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩትን ጣዖቶች ማምለካቸውን አልተዉም። 21  እንዲሁም ከፈጸሙት የነፍስ ግድያ፣ ከመናፍስታዊ ድርጊቶቻቸው፣ ከፆታ ብልግናቸውም ሆነ ከሌብነታቸው ንስሐ አልገቡም።
[]
[]
[]
[]
11,982
1  በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያ፣ በኢዮዓታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ እንዲሁም በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ቤኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የይሖዋ ቃል። 2  ይሖዋ በሆሴዕ አማካኝነት ቃሉን መናገር ሲጀምር ይሖዋ ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ሄደህ ዝሙት አዳሪ ሴት አግባ፤ እሷ በምትፈጽመውም ምንዝር ልጆች ይወለዱልሃል፤ ምክንያቱም በምንዝር የተነሳ ምድሪቱ ይሖዋን ከመከተል ሙሉ በሙሉ ርቃለች።” 3  ስለዚህ ሄዶ የዲብላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት። 4  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ልጁን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፤ በኢይዝራኤል ለፈሰሰው ደም የኢዩን ቤት በቅርቡ ተጠያቂ አደርጋለሁና፤ የእስራኤል ቤት ንጉሣዊ አገዛዝም እንዲያከትም አደርጋለሁ። 5  በዚያ ቀን የእስራኤልን ቀስት በኢይዝራኤል ሸለቆ እሰብራለሁ።” 6  እሷም ዳግመኛ ፀነሰች፤ ሴት ልጅም ወለደች። አምላክም እንዲህ አለው፦ “ልጅቷን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት፤ ምክንያቱም ከእንግዲህ ለእስራኤል ቤት ምሕረት አላሳይም፤ በእርግጥ አስወግዳቸዋለሁ። 7  ለይሁዳ ቤት ግን ምሕረት አደርጋለሁ፤ በቀስት፣ በሰይፍ፣ በጦርነት፣ በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በይሖዋ አድናቸዋለሁ።” 8  ጎሜር፣ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለች በኋላ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። 9  ከዚያም አምላክ እንዲህ አለው፦ “ልጁን ሎአሚ ብለህ ጥራው፤ ምክንያቱም እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም፤ እኔም አምላካችሁ አይደለሁም። 10  “የእስራኤልም ሕዝብ ብዛት ሊሰፈር ወይም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል። ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብሎ በተነገራቸው ስፍራም ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ይባላሉ። 11  የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ተሰብስበው አንድ ይሆናሉ፤ ለራሳቸውም አንድ መሪ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።
[]
[]
[]
[]
11,983
10  “እስራኤል ፍሬ የሚሰጥ እየተበላሸ ያለ ወይን ነው። ፍሬው በበዛ መጠን መሠዊያዎቹንም በዚያው ልክ አበዛ፤ምድሩ የተሻለ ምርት ባስገኘ መጠን ይበልጥ ያማሩ የማምለኪያ ዓምዶችን ሠራ። 2  ልባቸው ግብዝ ነው፤በመሆኑም በደለኞች ናቸው። መሠዊያዎቻቸውን የሚሰባብር፣ ዓምዶቻቸውንም የሚያፈራርስ አለ። 3  እነሱም ‘ንጉሥ የለንም፤ ይሖዋን አልፈራንምና። ንጉሥ ቢኖረንስ ምን ሊያደርግልን ይችላል?’ ይላሉ። 4  ከንቱ ቃል ይናገራሉ፤ በሐሰት ይምላሉ፤ ቃል ኪዳንም ይገባሉ፤ስለዚህ የሚፈረደው ፍርድ በእርሻ ትልም ውስጥ እንዳለ መርዛማ አረም ነው። 5  የሰማርያ ነዋሪዎች በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ስጋት ያድርባቸዋል። ሕዝቡም ሆኑ በእሱና በክብሩ ሐሴት ያደረጉት የባዕድ አምላክ ካህናትለእሱ ያዝናሉ፤ከእነሱ ተለይቶ በግዞት ይወሰዳልና። 6  ለአንድ ታላቅ ንጉሥ እንደሚቀርብ ስጦታ ወደ አሦር ይወሰዳል። ኤፍሬም ውርደት ይከናነባል፤እስራኤልም በተከተለው ምክር የተነሳ ያፍራል። 7  ሰማርያና ንጉሥዋ ተቆርጦ ውኃ ላይ እንደወደቀ ቅርንጫፍተጠራርገው ይጠፋሉ። 8  የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት በቤትአዌን የሚገኙ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ይወድማሉ። መሠዊያዎቻቸውን እሾህና አሜኬላ ይወርሷቸዋል። ሰዎች ተራሮቹን ‘ሸሽጉን!’ ኮረብቶቹንም ‘በላያችን ውደቁ!’ ይሏቸዋል። 9  የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ከጊብዓ ዘመን ጀምሮ ኃጢአት ሠርታችኋል። እነሱ በዚያ ጸንተዋል። በጊብዓ የተካሄደው ጦርነት የዓመፅን ልጆች አልፈጃቸውም። 10  በፈለግኩ ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ። ሁለቱ በደሎቻቸው በላያቸው በሚጫኑበት ጊዜሕዝቦች በእነሱ ላይ ይሰበሰባሉ። 11  ኤፍሬም ማበራየት የምትወድ የተገራች ጊደር ነው፤በመሆኑም ያማረ አንገቷን አተረፍኩ። ሰውም ኤፍሬምን እንዲጋልብ አደርጋለሁ። ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ለእሱ ያለሰልሳል። 12  ለራሳችሁ የጽድቅን ዘር ዝሩ፤ ታማኝ ፍቅርንም እጨዱ። ይሖዋን መፈለግ የምትችሉበት ጊዜ ከማለፉ በፊት፣እሱም መጥቶ በጽድቅ መመሪያ እስኪሰጣችሁ ድረስያልለማውን መሬት ለራሳችሁ እረሱ። 13  እናንተ ግን ክፋትን አረሳችሁ፤ዓመፅን አጨዳችሁ፤የማታለልንም ፍሬ በላችሁ፤በገዛ ራሳችሁ መንገድ፣በተዋጊዎቻችሁም ብዛት ታምናችኋልና። 14  በሕዝባችሁ ላይ ሁከት ይነሳል፤እናቶች ከልጆቻቸው ጋር በተጨፈጨፉበት የውጊያ ቀንሻልማን፣ ቤትአርቤልን እንዳወደመ ሁሉ፣የተመሸጉ ከተሞቻችሁ በሙሉ ይወድማሉ። 15  ቤቴል ሆይ፣ ክፋትሽ ታላቅ ስለሆነ እንዲሁ ይደረግብሻል። ጎህ ሲቀድ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።”
[]
[]
[]
[]
11,984
11  “እስራኤል ገና ልጅ ሳለ ወደድኩት፤ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት። 2  እነሱ ደጋግመው በጠሯቸው መጠንበዚያው ልክ ከእነሱ ራቁ። ለባአል ምስሎች መሠዋታቸውን፣ለተቀረጹት ምስሎችም መሥዋዕት ማቅረባቸውን ቀጠሉ። 3  እኔ ግን ኤፍሬምን መራመድ አስተማርኩት፤ በክንዶቼም ተሸከምኳቸው፤የፈወስኳቸውም እኔ እንደሆንኩ አምነው አልተቀበሉም። 4  በሰዎች ገመድ፣ በፍቅርም ማሰሪያ ሳብኳቸው፤ደግሞም ከጫንቃቸው ላይ ቀንበር እንደሚያነሳ ሰው ሆንኩላቸው፤ለእያንዳንዳቸውም በደግነት ምግብ አቀረብኩላቸው። 5  እነሱ ወደ ግብፅ ምድር አይመለሱም፤ ሆኖም አሦር ንጉሣቸው ይሆናል፤ምክንያቱም ወደ እኔ ለመመለስ አሻፈረን ብለዋል። 6  በጠነሰሱት ሴራ የተነሳ በከተሞቹ ላይ ሰይፍ ያንዣብባል፤መቀርቀሪያዎቹንም ይሰባብራል፤ ይበላቸዋልም። 7  ሕዝቤ በእኔ ላይ ክህደት ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም። ወደ ላይ ቢጠሯቸውም ማንም አይነሳም። 8  ኤፍሬም ሆይ፣ እንዴት ልተውህ እችላለሁ? እስራኤል ሆይ፣ እንዴት አሳልፌ ልሰጥህ እችላለሁ? እንዴትስ እንደ አድማህ አደርግሃለሁ? ደግሞስ እንዴት እንደ ጸቦይም ላደርግህ እችላለሁ? ስለ አንተ ያለኝ አመለካከት ተለወጠ፤የርኅራኄ ስሜቴም ተቀሰቀሰ። 9  የሚነድ ቁጣዬን አልገልጽም። ኤፍሬምን ዳግመኛ አላጠፋም፤እኔ አምላክ እንጂ ሰው አይደለሁምና፤በመካከልህ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ፤በአንተም ላይ በቁጣ አልመጣም። 10  እነሱ ይሖዋን ተከትለው ይሄዳሉ፤ እሱም እንደ አንበሳ ያገሳል፤እሱ ሲያገሳ ልጆቹ ከምዕራብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ። 11  ከግብፅ ሲወጡ እንደ ወፍ፣ከአሦርም ምድር ሲወጡ እንደ ርግብ ይርገፈገፋሉ፤እኔም በየቤታቸው እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ” ይላል ይሖዋ። 12  “ኤፍሬም በውሸት፣የእስራኤልም ቤት በማታለል ከበበኝ። ይሁዳ ግን አሁንም ከአምላክ ጋር ይሄዳል፤እጅግ ቅዱስ ለሆነውም አምላክ ታማኝ ነው።”
[]
[]
[]
[]
11,985
12  “ኤፍሬም ነፋስን ይመገባል። ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል። ውሸትንና ዓመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ፤ ወደ ግብፅም ዘይት ይወስዳሉ። 2  ይሖዋ በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፤ያዕቆብን እንደ መንገዱ ይቀጣዋል፤እንደ ድርጊቱም ብድራት ይከፍለዋል። 3  በማህፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ባለ በሌለ ኃይሉም ከአምላክ ጋር ታገለ። 4  ከመልአክ ጋር መታገሉን ቀጠለ፤ ደግሞም አሸነፈ። ሞገስ እንዲያሳየው አልቅሶ ለመነው።” አምላክ በቤቴል አገኘው፤ በዚያም እኛን አነጋገረን፤ 5  እሱ የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው።የመታሰቢያ ስሙ ይሖዋ ነው። 6  “ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ታማኝ ፍቅርንና ፍትሕን ጠብቅ፤ምንጊዜም በአምላክህ ተስፋ አድርግ። 7  ይሁንና በነጋዴው እጅ አታላይ ሚዛን አለ፤እሱ ማጭበርበር ይወዳል። 8  ኤፍሬም ‘በእርግጥ እኔ ባለጸጋ ሆኛለሁ፤ሀብት አካብቻለሁ። ደግሞም ከደከምኩበት ነገር ሁሉ ጋር በተያያዘ በደልም ሆነ ኃጢአት አያገኙብኝም’ ይላል። 9  ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ። በተወሰነው ጊዜ እንደነበረው ሁሉ፣እንደገና በድንኳኖች እንድትቀመጡ አደርጋችኋለሁ። 10  ለነቢያቱ ተናገርኩ፤ራእዮቻቸውን አበዛሁ፤በነቢያቱም በኩል ምሳሌዎችን ተናገርኩ። 11  በጊልያድ ማታለልና ውሸት አለ። በጊልጋል በሬዎችን ሠውተዋል፤በተጨማሪም መሠዊያዎቻቸው በእርሻ ትልም ላይ እንዳለ የድንጋይ ክምር ናቸው። 12  ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፤እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል በዚያ አገለገለ፤ሚስት ለማግኘትም ሲል በግ ጠባቂ ሆነ። 13  ይሖዋ በነቢይ አማካኝነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣው፤በነቢይም አማካኝነት ጠበቀው። 14  ኤፍሬም ግን እጅግ በደለው፤ደም በማፍሰስ የፈጸመው በደል በላዩ ላይ ይሆናል፤ላመጣበትም ነቀፋ ጌታው ብድራት ይከፍለዋል።”
[]
[]
[]
[]
11,986
13  “ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤በእስራኤል ነገዶች መካከል ትልቅ ቦታ ነበረው። ሆኖም ባአልን በማምለክ በደል በመፈጸሙ ሞተ። 2  አሁንም ተጨማሪ ኃጢአት ይሠራሉ፤በብራቸውም ለራሳቸው የብረት ምስሎች ይሠራሉ፤በጥበብ ጣዖቶችን ያበጃሉ፤ ሁሉም የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራቸው ናቸው። ‘መሥዋዕት የሚያቀርቡት ሰዎች ጥጃዎቹን ይሳሙ’ በማለት ለእነሱ ይናገራሉ። 3  ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ይሆናሉ፤አውሎ ነፋስ ከአውድማ ላይ ጠራርጎ እንደሚወስደው እብቅ፣በጭስ ማውጫም በኩል እንደሚወጣ ጭስ ይሆናሉ። 4  ይሁንና ከግብፅ ምድር አንስቶ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ፤ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም ነበር፤ከእኔም ሌላ አዳኝ የለም። 5  እኔ በምድረ በዳ፣ ድርቅ ባለበትም ምድር ተንከባከብኩህ። 6  በግጦሽ መሬታቸው ላይ ከበሉ በኋላ ጠገቡ፤በጠገቡም ጊዜ ልባቸው ታበየ። ከዚህም የተነሳ ረሱኝ። 7  ስለዚህ እንደ አንበሳ፣በመንገድም ዳር እንደሚያደባ ነብር እሆንባቸዋለሁ። 8  ግልገሎቿን እንደተነጠቀች ድብ ሆኜ እመጣባቸዋለሁ፤ደረታቸውንም እዘነጥላለሁ። በዚያ እንደ አንበሳ እውጣቸዋለሁ፤የዱር አውሬ ይቦጫጭቃቸዋል። 9  እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ላይ ስለተነሳህ፣ረዳትህንም ስለተቃወምክ ያጠፋሃል። 10  ‘ንጉሥና መኳንንት ስጠኝ’ ብለህ ነበር፤ታዲያ በከተሞችህ ሁሉ ያድንህ ዘንድንጉሥህ የት አለ? ገዢዎችህስ የት አሉ? 11  እኔም ተቆጥቼ ንጉሥ ሰጠሁህ፤በታላቅ ቁጣዬም አስወግደዋለሁ። 12  የኤፍሬም በደል ታሽጎ ተቀምጧል፤ኃጢአቱም ተከማችቷል። 13  ምጥ እንደያዛት ሴት ይሆናል። እሱ ግን ጥበበኛ ልጅ አይደለም፤የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ በቦታው ላይ አይገኝም። 14  ከመቃብር እጅ እዋጃቸዋለሁ፤ከሞትም እታደጋቸዋለሁ። ሞት ሆይ፣ መንደፊያህ የት አለ? መቃብር ሆይ፣ አጥፊነትህ የት አለ? ርኅራኄ ከዓይኔ ፊት ይሰወራል። 15  በቄጠማዎች መካከል ተመችቶት ቢያድግ እንኳየምሥራቅ ነፋስ ይኸውም የይሖዋ ነፋስ ይመጣል፤የውኃ ጉድጓዱ እንዲደርቅ፣ ምንጩም እንዲነጥፍ ለማድረግ ከበረሃ ይመጣል። ውድ የሆኑ ንብረቶቹ ሁሉ የሚገኙበትን ግምጃ ቤቱን ይበዘብዛል። 16  ሰማርያ በአምላኳ ላይ ስላመፀች ተጠያቂ ትሆናለች። በሰይፍ ይወድቃሉ፤ልጆቻቸው ይፈጠፈጣሉ፤የእርጉዝ ሴቶቻቸውም ሆድ ይቀደዳል።”
[]
[]
[]
[]
11,987
14   “እስራኤል ሆይ፣ በበደልህ ስለተሰናከልክወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ተመለስ። 2  ይህን ቃል ይዛችሁ ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤እንዲህ በሉት፦ ‘በደላችንን ይቅር በለን፤ መልካም የሆነውንም ነገር ተቀበለን፤እኛም ወይፈኖች እንደምናቀርብ፣ የከንፈራችንን ውዳሴ እናቀርብልሃለን። 3  አሦር አያድነንም። ፈረሶችን አንጋልብም፤ከእንግዲህም ወዲህ የገዛ እጆቻችን የሠሩትን “አምላካችን ሆይ!” አንልም፤አባት የሌለው ልጅ ምሕረት ያገኘው በአንተ ነውና።’ 4  እኔም ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ። በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤ምክንያቱም ቁጣዬ ከእሱ ተመልሷል። 5  እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤እሱም እንደ አበባ ያብባል፤እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥሮቹን ይሰዳል። 6  ቀንበጦቹ ይንሰራፋሉ፤ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣መዓዛውም እንደ ሊባኖስ ዛፍ ይሆናል። 7  እነሱም ዳግመኛ በጥላው ሥር ይኖራሉ። እህል ያበቅላሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ። ዝናው እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይሆናል። 8  ኤፍሬም ‘ከእንግዲህ ከጣዖቶች ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?’ ይላል። መልስ እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም እጠብቀዋለሁ። እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ እሆናለሁ። ከእኔም ፍሬ ታገኛላችሁ።” 9  ጥበበኛ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ያስተውል። ልባም የሆነ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ይወቅ። የይሖዋ መንገዶች ቀና ናቸውና፤ጻድቃንም በመንገዶቹ ላይ ይሄዳሉ፤በደለኞች ግን በእነሱ ይሰናከላሉ።
[]
[]
[]
[]
11,988
2  “ወንድሞቻችሁን ‘ሕዝቤ!’ እህቶቻችሁን ደግሞ ‘ምሕረት የተደረገልሽ ሴት!’ በሏቸው። 2  እናታችሁን ክሰሷት፤ እሷ ሚስቴ ስላልሆነች፣እኔም ባሏ ስላልሆንኩ ክሰሷት። ከእሷ ዘንድ ዘማዊነቷን፣ከጡቶቿም መካከል ምንዝሯን ታስወግድ፤ 3  አለዚያ ራቁቷን አስቀራታለሁ፤ በተወለደችበት ቀን እንደነበረችውም አደርጋታለሁ፤እንደ ምድረ በዳ፣ውኃ እንደሌለበትም ምድር አደርጋታለሁ፤በውኃ ጥምም እገድላታለሁ። 4  ወንዶች ልጆቿ የምንዝር ልጆች ስለሆኑምሕረት አላደርግላቸውም። 5  እናታቸው አመንዝራለችና። እነሱን የፀነሰችው ሴት አሳፋሪ ድርጊት ፈጽማለች፤‘አጥብቀው የሚወዱኝን፣ደግሞም ምግቤንና ውኃዬን፣የሱፍ ልብሴንና በፍታዬን እንዲሁም ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝን ተከትዬ እሄዳለሁ’ ብላለችና። 6  ስለዚህ መንገዷን በእሾህ አጥር እዘጋለሁ፤መውጫ መንገድ እንዳታገኝምዙሪያዋን በድንጋይ አጥራለሁ። 7  አጥብቀው የሚወዷትን ተከትላ ትሄዳለች፤ ሆኖም አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች፤ ሆኖም አታገኛቸውም። ከዚያም ‘ተመልሼ ወደ መጀመሪያው ባሌ እሄዳለሁ፤ከአሁኑ ኑሮዬ ይልቅ የበፊቱ ይሻለኛልና’ ትላለች። 8  እህሉን፣ አዲሱን የወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋትእንዲሁም ለባአል አምልኮ የተጠቀሙበትን ብርና ወርቅበብዛት እንድታገኝ ያደረግኩት እኔ እንደሆንኩ አልተገነዘበችም። 9  ‘ስለዚህ ሐሳቤን ቀይሬ፣ እህሌን በጊዜው፣አዲሱን የወይን ጠጄንም በወቅቱ እወስዳለሁ፤እርቃኗን የምትሸፍንበትንም የሱፍ ልብሴንና በፍታዬን እነጥቃታለሁ። 10  አሁንም ኀፍረተ ሥጋዋን አጥብቀው በሚወዷት ፊት እገልጣለሁ፤ከእጄም የሚያስጥላት ሰው አይኖርም። 11  ደስታዋን፣ በዓሏን፣ የወር መባቻዋንና ሰንበቷን ሁሉእንዲሁም የተወሰኑትን የበዓል ወቅቶቿን ሁሉ አስቀራለሁ። 12  “አጥብቀው የሚወዱኝ ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ደሞዜ ናቸው” የምትላቸውን የወይን ተክሏንና የበለስ ዛፏን አወድማለሁ፤ጫካም አደርጋቸዋለሁ፤የዱር አራዊትም ይበሏቸዋል። 13  ለባአል ምስሎች መሥዋዕት ባቀረበችባቸው፣ በጉትቻዋና በጌጦቿ በተንቆጠቆጠችባቸውእንዲሁም አጥብቀው የሚወዷትን በተከተለችባቸው ቀናት የተነሳ ተጠያቂ አደርጋታለሁ፤እኔንም ረስታኝ ነበር’ ይላል ይሖዋ። 14  ‘ስለዚህ አግባብቼ አሳምናታለሁ፤ወደ ምድረ በዳ እመራታለሁ፤ልቧን በሚማርክ መንገድ አናግራታለሁ። 15  ከዚያን ጊዜ አንስቶ የወይን እርሻዎቿን መልሼ እሰጣታለሁ፤የአኮርም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤በዚያም እንደ ልጅነቷ ጊዜናከግብፅ ምድር እንደወጣችበት ቀን መልስ ትሰጠኛለች። 16  በዚያም ቀን’ ይላል ይሖዋ፣‘ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ ከእንግዲህ ጌታዬ ብለሽ አትጠሪኝም።’ 17  ‘የባአልን ምስሎች ስሞች ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤ስማቸውም ከእንግዲህ አይታወስም። 18  በዚያም ቀን ለእነሱ ጥቅም ስል ከዱር አራዊት፣ከሰማይ ወፎችና መሬት ለመሬት ከሚሳቡ ፍጥረታት ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፤ያለስጋት እንዲያርፉም አደርጋለሁ። 19  ለዘላለም አጭሻለሁ፤በጽድቅ፣ በፍትሕ፣ በታማኝ ፍቅርናበምሕረት አጭሻለሁ። 20  በታማኝነት አጭሻለሁ፤አንቺም በእርግጥ ይሖዋን ታውቂያለሽ።’ 21  ‘በዚያም ቀን መልስ እሰጣለሁ’ ይላል ይሖዋ፤‘ለሰማያት መልስ እሰጣለሁ፤እነሱ ደግሞ ለምድር መልስ ይሰጣሉ፤ 22  ምድር ደግሞ ለእህሉ፣ ለአዲሱ የወይን ጠጅና ለዘይቱ መልስ ትሰጣለች፤እነሱም ለኢይዝራኤል መልስ ይሰጣሉ። 23  በምድር ላይ ለራሴ እንደ ዘር እዘራታለሁ፤ደግሞም ምሕረት ላልተደረገላት ለእሷ ምሕረት አደርግላታለሁ፤ሕዝቤ ያልሆኑትን “እናንተ ሕዝቤ ናችሁ” እላቸዋለሁ፤ እነሱ ደግሞ “አንተ አምላኬ ነህ” ይላሉ።’”
[]
[]
[]
[]
11,989
3  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሌሎች አማልክትን የሚከተሉና የዘቢብ ቂጣ የሚወዱ ሆነው ሳለ ይሖዋ እንደወደዳቸው ሁሉ፣ አንተም ሄደህ በሌላ ሰው የተወደደችውንና ምንዝር የምትፈጽመውን ሴት ዳግመኛ ውደዳት።” 2  በመሆኑም በ15 የብር ሰቅልና በአንድ ተኩል የሆሜር መስፈሪያ ገብስ ለራሴ ገዛኋት። 3  ከዚያም እንዲህ አልኳት፦ “ለብዙ ቀናት የእኔ ሆነሽ ትቀመጫለሽ። አታመንዝሪ፤ ከሌላ ሰውም ጋር ግንኙነት አታድርጊ፤ እኔም ከአንቺ ጋር ግንኙነት አልፈጽምም።” 4  ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ ለረጅም ጊዜ ያለንጉሥ፣ ያለገዢ፣ ያለመሥዋዕት፣ ያለዓምድ፣ ያለኤፉድና ያለተራፊም ምስል ይኖራሉ። 5  ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ተመልሰው አምላካቸውን ይሖዋንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በዘመኑም መጨረሻ ወደ ይሖዋና ወደ ጥሩነቱ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።
[]
[]
[]
[]
11,990
4  የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ይሖዋ ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ስለሚፋረድ የይሖዋን ቃል ስሙ፤ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ እውነት፣ ታማኝ ፍቅርና አምላክን ማወቅ የለም። 2  የሐሰት መሐላ፣ ውሸት፣ ነፍስ ግድያ፣ስርቆትና ምንዝር ተስፋፍቷል፤ደም የማፍሰስ ወንጀልም በላይ በላዩ ይፈጸማል። 3  ከዚህም የተነሳ ምድሪቱ ታዝናለች፤በእሷም ላይ የሚኖሩ ሁሉ ይመነምናሉ፤የዱር እንስሳትና የሰማይ ወፎችየባሕር ዓሣዎችም እንኳ ሳይቀሩ ይጠፋሉ። 4  “ይሁን እንጂ ማንም ሰው አይሟገት ወይም ሌላውን አይውቀስ፤ሕዝብህ ከካህን ጋር እንደሚሟገት ሰው ነውና። 5  ስለዚህ እናንተ በጠራራ ፀሐይ ትሰናከላላችሁ፤የጨለመ ይመስል ነቢዩም ከእናንተ ጋር ይሰናከላል። እናታችሁንም ጸጥ አሰኛታለሁ። 6  ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ይጠፋል። እናንተ እውቀትን ስለናቃችሁእኔም ካህናት ሆናችሁ እንዳታገለግሉኝ እንቃችኋለሁ፤የአምላካችሁን ሕግ ስለረሳችሁእኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ። 7  እነሱ በበዙ ቁጥር በእኔ ላይ የሚሠሩት ኃጢአት በዝቷል። ክብራቸውን ወደ ውርደት እለውጣለሁ። 8  የሕዝቤ ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፤ደግሞም እነሱ በደል እንዲሠሩ ይቋምጣሉ። 9  ሕዝቡንም ሆነ ካህኑንለተከተሉት መንገድ ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤አድራጎታቸው ያስከተለውንም መዘዝ በላያቸው አመጣለሁ። 10  ይበላሉ፤ ሆኖም አይጠግቡም። ሴሰኞች ይሆናሉ፤ ሆኖም ቁጥራቸው አይጨምርም፤ምክንያቱም ይሖዋን ችላ ብለዋል። 11  ምንዝር፣ ያረጀ የወይን ጠጅና አዲስ የወይን ጠጅ፣ሰው ትክክል የሆነውን ነገር ለመፈጸም ያለውን ልባዊ ፍላጎት ያጠፋሉ። 12  ሕዝቤ ከእንጨት የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን ያማክራሉ፤በትራቸው የሚላቸውን ነገር ያደርጋሉ፤ምክንያቱም የአመንዝራነት መንፈስ እንዲባዝኑ ያደርጋቸዋል፤በአመንዝራነታቸው የተነሳም ለአምላካቸው ለመገዛት አሻፈረን ይላሉ። 13  በተራሮች አናት ላይ ይሠዋሉ፤ደግሞም በኮረብቶች ላይእንዲሁም በባሉጥ ዛፎች፣ በሊብነህ ዛፎችና በትልቅ ዛፍ ሁሉ ሥር የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ምክንያቱም የዛፎቹ ጥላ መልካም ነው። ከዚህም የተነሳ ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች ይሆናሉ፤ምራቶቻችሁም ያመነዝራሉ። 14  ሴቶች ልጆቻችሁ ዝሙት አዳሪዎች በመሆናቸው፣ምራቶቻችሁም በማመንዘራቸው አልቀጣቸውም። ወንዶቹ ከጋለሞታዎች ጋር ተያይዘው ይሄዳሉና፤ከቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪዎችም ጋር መሥዋዕት ያቀርባሉ፤እንዲህ ያለ ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ይጠፋል። 15  እስራኤል ሆይ፣ አንቺ ብታመነዝሪምይሁዳ ግን ተመሳሳይ በደል አትፈጽም። ወደ ጊልጋል ወይም ወደ ቤትአዌን አትሂዱ፤‘ሕያው ይሖዋን!’ ብላችሁም አትማሉ። 16  እስራኤል እንደ እልኸኛ በሬ እልኸኛ ሆናለችና። ታዲያ ይሖዋ እንደ በግ ጠቦት በተንጣለለ የግጦሽ መስክ ያሰማራቸዋል? 17  ኤፍሬም ከጣዖቶች ጋር ተቆራኝቷል። በቃ ተዉት! 18  መጠጣቸው ሲያልቅሴሰኞች ይሆናሉ። ገዢዎቿም ነውርን አጥብቀው ይወዳሉ። 19  ነፋስ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፤እነሱም ባቀረቧቸው መሥዋዕቶች ያፍራሉ።”
[]
[]
[]
[]
11,991
5  “እናንተ ካህናት፣ ይህን ስሙ፤እናንተ የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ በትኩረት አዳምጡ፤እናንተም የንጉሡ ቤት ሰዎች፣ አዳምጡ፤ፍርዱ እናንተንም ይጨምራልና፤ምክንያቱም ለምጽጳ ወጥመድ፣በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል። 2  ከትክክለኛው መንገድ የራቁት ሰዎች ደም በማፍሰስ ወንጀል ተዘፍቀዋል፤እኔም ለሁሉም ማስጠንቀቂያ እሰጣለሁ። 3  ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፤እስራኤልም ከእኔ የተሰወረ አይደለም። ኤፍሬም ሆይ፣ አሁን አንተ ሴሰኛ ሆነሃል፤እስራኤል ራሱን አርክሷል። 4  የሠሩት ሥራ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ምክንያቱም በመካከላቸው የአመንዝራነት መንፈስ አለ፤ለይሖዋም እውቅና አይሰጡም። 5  የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ መሥክሮበታል፤እስራኤልና ኤፍሬም የሠሩት በደል አሰናክሏቸዋል፤ይሁዳም ከእነሱ ጋር ተሰናክሏል። 6  መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ይዘው ይሖዋን ፍለጋ ሄዱ፤ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉም። እሱ ከእነሱ ርቋል። 7  እነሱ ይሖዋን ከድተዋል፤ባዕድ ወንዶች ልጆች ወልደዋልና። አሁንም አንድ ወር፣ እነሱንና ድርሻቸውን ይውጣል። 8  በጊብዓ ቀንደ መለከት፣ በራማም መለከት ንፉ! ‘ቢንያም ሆይ፣ ከኋላህ ነን!’ ብላችሁ በቤትአዌን ቀረርቶ አሰሙ። 9  ኤፍሬም ሆይ፣ በምትቀጣበት ቀን መቀጣጫ ትሆናለህ። በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ምን እንደሚከሰት አሳውቄአለሁ። 10  የይሁዳ መኳንንት ወሰን እንደሚገፉ ሰዎች ናቸው። በእነሱ ላይ ቁጣዬን እንደ ውኃ አፈሳለሁ። 11  ኤፍሬም ተጨቁኗል፤ በፍርድ ተረግጧል፤ባላጋራውን ለመከተል ቆርጧልና። 12  በመሆኑም እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ለይሁዳ ቤት ደግሞ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ። 13  ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቁስሉን ሲመለከትኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ታላቅ ንጉሥም መልእክተኞች ላከ። ይሁንና ንጉሡ እናንተን ሊፈውሳችሁ አልቻለም፤ቁስላችሁንም ሊያድን አልቻለም። 14  እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም ቤት እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና። እኔ ራሴ ቦጫጭቄአቸው እሄዳለሁ፤ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ የሚታደጋቸውም አይኖርም። 15  እሄዳለሁ፤ በደላቸው የሚያስከትልባቸውን መዘዝ እስኪሸከሙም ድረስ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤በዚህ ጊዜም ሞገሴን ይሻሉ። በጭንቀት በሚዋጡበት ጊዜ እኔን ይሻሉ።”
[]
[]
[]
[]
11,992
6  “ኑ ወደ ይሖዋ እንመለስ፤እሱ ቦጫጭቆናል፤ ሆኖም ይፈውሰናል። እሱ መቶናል፤ ሆኖም ቁስላችንን ይጠግናል። 2  ከሁለት ቀናት በኋላ ያነቃናል። በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል፤እኛም በፊቱ እንኖራለን። 3  ይሖዋን እናውቀዋለን፤ እሱን ለማወቅ ልባዊ ጥረት እናደርጋለን። የእሱ መውጣት እንደ ንጋት ብርሃን የተረጋገጠ ነው፤እንደ ዶፍ ዝናብ፣ ምድርንም እንደሚያጠግበው የኋለኛው ዝናብወደ እኛ ይመጣል።” 4  “ኤፍሬም ሆይ፣ ምን ላድርግህ? ይሁዳ ሆይ፣ ምን ላድርግህ? ታማኝ ፍቅራችሁ እንደ ጠዋት ጉም፣ወዲያው እንደሚጠፋም ጤዛ ነውና። 5  ከዚህም የተነሳ በነቢያቴ አማካኝነት እቆራርጣቸዋለሁ፤በአፌም ቃል እገድላቸዋለሁ። በእናንተም ላይ የምፈርደው ፍርድ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል። 6  ከመሥዋዕት ይልቅ ታማኝ ፍቅር፣ሙሉ በሙሉ ከሚቃጠል መባም ይልቅ አምላክን ማወቅ ያስደስተኛልና። 7  እነሱ ግን እንደ ተራ ሰዎች ቃል ኪዳኑን ተላለፉ። በዚያም እኔን ከዱኝ። 8  ጊልያድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ናት፤ከተማዋ በደም ጨቅይታለች። 9  የካህናቱ ማኅበር ሰውን አድብቶ እንደሚጠብቅ የወራሪዎች ቡድን ነው። በሴኬም መንገድ ላይ ሰው ይገድላሉ፤ምግባራቸው አሳፋሪ ነውና። 10  በእስራኤል ቤት የሚሰቀጥጥ ነገር አይቻለሁ። በዚያ ኤፍሬም ያመነዝራል፤እስራኤል ራሱን አርክሷል። 11  በአንጻሩ ግን ይሁዳ ሆይ፣ የሕዝቤን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜመከር ይጠብቅሃል።”
[]
[]
[]
[]
11,993
7  “እስራኤልን ለመፈወስ በሞከርኩ ቁጥርየኤፍሬም በደል፣የሰማርያም ክፋት ይገለጣል። እነሱ ያታልላሉና፤ሌቦች ሰብረው ይገባሉ፤ የወራሪዎች ቡድን በውጭ ጥቃት ይሰነዝራል። 2  እነሱ ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ ልብ አይሉም። የገዛ ድርጊታቸው ከቧቸዋል፤የሠሩት ሥራ ሁሉ በፊቴ ነው። 3  ንጉሡን በክፋታቸው፣መኳንንቱንም አታላይ በሆነ ድርጊታቸው ያስደስታሉ። 4  ሁሉም አመንዝሮች ናቸው፤አንድ ዳቦ ጋጋሪ እሳቱን አንዴ ካቀጣጠለው በኋላ፣ያቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንደማያስፈልገው የጋለ ምድጃ ናቸው። 5  በንጉሣችን ክብረ በዓል ቀን፣ መኳንንቱ ታመሙ፤በወይን ጠጅ የተነሳ በቁጣ ተሞሉ። ንጉሡ ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ። 6  እንደ ምድጃ የሚነድ ልብ ይዘው ይቀርባሉና። ዳቦ ጋጋሪው ሌሊቱን ሙሉ ይተኛል፤በማለዳ ምድጃው እንደሚንበለበል እሳት ይንቀለቀላል። 7  ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ገዢዎቻቸውንም ይውጣሉ። ነገሥታታቸው ሁሉ ወድቀዋል፤ከእነሱ መካከል ወደ እኔ የሚጮኽ ማንም የለም። 8  ኤፍሬም ከብሔራት ጋር ይቀላቀላል። እሱ እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው። 9  እንግዶች ጉልበቱን በዘበዙ፤ እሱ ግን ይህን አላወቀም። ራሱንም ሽበት ወረሰው፤ እሱ ግን ይህን ልብ አላለም። 10  የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ መሥክሮበታል፤ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ አልተመለሱም፤እሱንም አልፈለጉትም። 11  ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላት ሞኝ ርግብ ነው። ግብፅን ተጣሩ፤ ወደ አሦርም ሄዱ። 12  የትም ቢሄዱ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ። እንደ ሰማይ ወፎች ወደ ታች አወርዳቸዋለሁ። ለጉባኤያቸው በሰጠሁት ማስጠንቀቂያ መሠረት እገሥጻቸዋለሁ። 13  ከእኔ ስለሸሹ ወዮላቸው! በእኔ ላይ በደል ስለፈጸሙ ጥፋት ይምጣባቸው! እነሱን ለመዋጀት ዝግጁ ነበርኩ፤ እነሱ ግን በእኔ ላይ ውሸት ተናገሩ። 14  በአልጋቸው ላይ ሆነው ዋይ ዋይ ቢሉምእርዳታ ለማግኘት ከልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም። ለእህላቸውና ለአዲስ ወይናቸው ሲሉ ሰውነታቸውን ይተለትላሉ፤በእኔም ላይ ዓመፁ። 15  ያሠለጠንኳቸውና ክንዳቸውን ያበረታሁ ቢሆንምክፉ ነገር በማሴር በእኔ ላይ ተነስተዋል። 16  አካሄዳቸውን ለወጡ፤ ከፍ ወዳለ ነገር ግን አይደለም፤ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ሆነዋል። አለቆቻቸው እብሪተኛ ከሆነው አንደበታቸው የተነሳ በሰይፍ ይወድቃሉ። በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር መሳለቂያ ይሆናሉ።”
[]
[]
[]
[]
11,994
8  “ቀንደ መለከት ንፋ! ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና ሕጌን ስለጣሱበይሖዋ ቤት ላይ ጠላት እንደ ንስር ይመጣል። 2  ‘አምላካችን ሆይ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች እናውቅሃለን!’ እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ። 3  እስራኤል መልካም የሆነውን ነገር ገሸሽ አድርጓል። ጠላት ያሳደው። 4  እኔ ሳልላቸው ነገሥታትን አነገሡ። መኳንንትን ሾሙ፤ እኔ ግን እውቅና አልሰጠኋቸውም። በገዛ ራሳቸው ላይ ጥፋት ለማምጣትበብራቸውና በወርቃቸው ጣዖቶች ሠሩ። 5  ሰማርያ ሆይ፣ የጥጃ ጣዖትሽ ተጥሏል። ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል። ንጹሕ መሆን የሚሳናቸው እስከ መቼ ነው? 6  ይህ ከእስራኤል ነውና። የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ አምላክ አይደለም፤የሰማርያ ጥጃ ተሰባብሮ እንዳልነበረ ይሆናል። 7  ነፋስን ይዘራሉ፤አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ። አገዳው፣ የደረሰ ፍሬ የለውም፤እህሉ፣ ዱቄት አላስገኘም። ፍሬ ቢያፈራ እንኳ ባዕዳን ይበሉታል። 8  የእስራኤል ሰዎች ይዋጣሉ። በብሔራት መካከልማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ይሆናሉ። 9  ተገልሎ እንደሚኖር የዱር አህያ ወደ አሦር ሄደዋልና። ኤፍሬም በገንዘብ ፍቅረኞች አፍርቷል። 10  ፍቅረኞቻቸውን ያፈሩት ከብሔራት ቢሆንም፣እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ንጉሥና መኳንንት በጫኑባቸው ሸክም የተነሳ ሥቃይ ይደርስባቸዋል። 11  ኤፍሬም ኃጢአት ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቷል። ኃጢአት የሚፈጽምባቸው መሠዊያዎች ሆነውለታል። 12  በሕጌ ውስጥ ያለውን አብዛኛውን ነገር ጽፌለታለሁ፤እነሱ ግን እንግዳ ነገር አድርገው ቆጠሩት። 13  መሥዋዕቶችን ስጦታ አድርገው ለእኔ ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ይሖዋ ግን በእነሱ አልተደሰተም። በደላቸውን ያስታውሳል፤ ለሠሯቸውም ኃጢአቶች ይቀጣቸዋል። እነሱ ወደ ግብፅ ተመልሰዋል። 14  እስራኤል ፈጣሪውን ረስቷል፤ ቤተ መቅደሶችንም ገንብቷል፤ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አብዝቷል። እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤እሳቱም የእያንዳንዳቸውን ማማዎች ይበላል።”
[]
[]
[]
[]
11,995
9  “እስራኤል ሆይ፣ ሐሴት አታድርግ፤እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች ደስ አይበልህ። ምንዝር በመፈጸም ከአምላክህ ርቀሃልና። በየእህል አውድማ ላይ ለዝሙት አዳሪ የሚከፈለውን ደሞዝ ወደኸዋል። 2  ሆኖም የእህል አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፤አዲሱም የወይን ጠጅ ይቋረጥባቸዋል። 3  በይሖዋ ምድር ላይ አይኖሩም፤ይልቁንም ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤በአሦርም የረከሰ ነገር ይበላሉ። 4  ከእንግዲህ ለይሖዋ የወይን ጠጅ መባ አያፈሱም፤መሥዋዕታቸውም አያስደስተውም። እንደ እዝን እንጀራ ናቸው፤የሚበሉትም ሁሉ ራሳቸውን ያረክሳሉ። ምግባቸው ለራሳቸው ብቻ ነውና፤ወደ ይሖዋ ቤት አይገባም። 5  የምትሰበሰቡበትና ለይሖዋ በዓል የምታከብሩበት ቀን ሲደርስምን ታደርጉ ይሆን? 6  እነሆ፣ ምድሪቱ በመውደሟ ለመሸሽ ይገደዳሉ። ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ደግሞ ትቀብራቸዋለች። ከብር የተሠሩ ውድ ንብረቶቻቸውን ሳማ ይወርሰዋል፤በድንኳኖቻቸውም ውስጥ እሾሃማ ቁጥቋጦ ይበቅላል። 7  ምርመራ የሚካሄድበት ጊዜ ይመጣል፤የበቀል ቀን ይመጣል፤እስራኤልም ይህን ይወቅ! የእነሱ ነቢይ ሞኝ፣ በመንፈስ የሚናገረውም ሰው እንደ እብድ ይሆናል፤ምክንያቱም በደልህ ብዙ ነው፤ በአንተም ላይ የሚደርሰው ጥላቻ በዝቷል።” 8  የኤፍሬም ጠባቂ ከአምላኬ ጋር ነበር። አሁን ግን የነቢያቱ መንገዶች ሁሉ እንደ ወፍ አዳኝ ወጥመዶች ናቸው፤በአምላኩ ቤት ጠላትነት አለ። 9  በጊብዓ ዘመን እንደነበረው፣ ጥፋት በሚያስከትሉ ነገሮች ተዘፍቀዋል። እሱ በደላቸውን ያስባል፤ በሠሩትም ኃጢአት የተነሳ ይቀጣቸዋል። 10  “እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ ወይን ሆኖ አገኘሁት። አባቶቻችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ባፈራ የበለስ ዛፍ ላይ እንደ ጎመራ የበለስ ፍሬ ሆነው አየኋቸው። ሆኖም ወደ ፌጎር ባአል ሄዱ፤ለአሳፋሪውም ነገር ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤እንደወደዱትም ነገር አስጸያፊዎች ሆኑ። 11  የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤መውለድ፣ ማርገዝም ሆነ መፀነስ የለም። 12  ልጆች ቢያሳድጉም እንኳአንድም ሰው እስከማይቀር ድረስ የወላድ መሃን አደርጋቸዋለሁ፤አዎ፣ ከእነሱ በራቅኩ ጊዜ ወዮላቸው! 13  በግጦሽ ስፍራ የተተከለው ኤፍሬም ለእኔ እንደ ጢሮስ ነበር፤አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለእርድ አሳልፎ ይሰጣል።” 14  ይሖዋ ሆይ፣ ልትሰጣቸው የሚገባውን ስጣቸው፤የሚጨነግፍ ማህፀንና የደረቁ ጡቶች ስጣቸው። 15  “ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ በጊልጋል ፈጸሙ፤ እኔም በዚያ ጠላኋቸው። በሠሩት ክፉ ድርጊት የተነሳ ከቤቴ አባርራቸዋለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ ፍቅሬን እነፍጋቸዋለሁ፤አለቆቻቸው ሁሉ እልኸኞች ናቸው። 16  ኤፍሬም ጉዳት ይደርስበታል። ሥራቸው ይደርቃል፤ አንዳችም ፍሬ አያፈሩም። ቢወልዱ እንኳ የሚወዷቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።” 17  እሱን ስላልሰሙትአምላኬ ይተዋቸዋል፤በብሔራትም መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።
[]
[]
[]
[]
11,996
1  ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል በነቢዩ ሐጌ በኩል የይሁዳ ገዢ ወደሆነው ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህናት ወደሆነው ወደ የሆጼዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነዚህ ሰዎች “የይሖዋ ቤት የሚገነባበት ጊዜ ገና አልደረሰም” ይላሉ።’” 3  የይሖዋም ቃል በነቢዩ ሐጌ በኩል እንዲህ ሲል በድጋሚ መጣ፦ 4  “ይህ ቤት ፈርሶ እያለ፣ እናንተ በሚያምር እንጨት በተለበጡ ቤቶቻችሁ ውስጥ የምትኖሩበት ጊዜ ነው? 5  አሁንም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘መንገዳችሁን ልብ በሉ። 6  ብዙ ዘር ዘራችሁ፤ የምትሰበስቡት ግን ጥቂት ነው። ትበላላችሁ፤ ሆኖም አትጠግቡም። ትጠጣላችሁ፤ ሆኖም አትረኩም። ትለብሳላችሁ፤ የሚሞቀው ሰው ግን የለም። ተቀጥሮ የሚሠራው ደሞዙን ብዙ ቀዳዳዎች ባሉት ከረጢት ውስጥ ያስቀምጣል።’” 7  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘መንገዳችሁን ልብ በሉ።’ 8  “‘ወደ ተራራው ወጥታችሁ ጥርብ እንጨት አምጡ። እኔ ደስ እንድሰኝበትና እንድከበርበት ቤቱን ሥሩ’ ይላል ይሖዋ።” 9  “‘ብዙ ነገር ጠበቃችሁ፤ ሆኖም ያገኛችሁት ጥቂት ነው፤ ወደ ቤት ባመጣችሁትም ጊዜ እፍ ብዬ በተንኩት። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። ‘የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ እያንዳንዳችሁ የገዛ ቤታችሁን ለማሳመር ስለምትሯሯጡ ነው። 10  ስለዚህ ከእናንተ በላይ ያሉት ሰማያት ጠል ማዝነባቸውን አቆሙ፤ ምድርም ፍሬዋን አልሰጥ አለች። 11  እኔም በምድር ላይ፣ በተራሮች ላይ፣ በእህሉ ላይ፣ በአዲሱ የወይን ጠጅ ላይ፣ በዘይቱ ላይ፣ ምድሪቱ በምታበቅለው ነገር ላይ፣ በሰዎች ላይ፣ በመንጎች ላይ እንዲሁም እጆቻችሁ በደከሙበት ነገር ሁሉ ላይ ድርቅን ጠራሁ።’” 12  የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፣ የየሆጼዴቅ ልጅ ሊቀ ካህናቱ ኢያሱና የቀረው ሕዝብ በሙሉ የአምላካቸውን የይሖዋን ድምፅ እንዲሁም ነቢዩ ሐጌ የተናገረውን ቃል ሰሙ፤ አምላካቸው ይሖዋ ልኮታልና፤ ሕዝቡም ከይሖዋ የተነሳ ፈሩ። 13  ከዚያም የይሖዋ መልእክተኛ የሆነው ሐጌ ከይሖዋ በተሰጠው ተልእኮ መሠረት ለሕዝቡ “‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ይላል ይሖዋ” የሚል መልእክት ተናገረ። 14  ስለዚህ ይሖዋ የይሁዳን ገዢ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የየሆጼዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ እንዲሁም የቀረውን ሕዝብ መንፈስ በሙሉ አነሳሳ፤ እነሱም መጥተው የአምላካቸውን የሠራዊት ጌታ የይሖዋን ቤት መሥራት ጀመሩ። 15  ይህ የሆነው ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን ነበር።
[]
[]
[]
[]
11,997
2  በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ21ኛው ቀን የይሖዋ ቃል በነቢዩ ሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፦ 2  “የይሁዳን ገዢ የሰላትያልን ልጅ ዘሩባቤልንና ሊቀ ካህናቱን የየሆጼዴቅን ልጅ ኢያሱን እንዲሁም የቀረውን ሕዝብ እባክህ እንዲህ ብለህ ጠይቃቸው፦ 3  ‘የዚህ ቤት የቀድሞ ክብሩ እንዴት እንደነበረ ያየ ሰው በመካከላችሁ አለ? አሁንስ እንዴት ሆኖ ይታያችኋል? ከቀድሞው ጋር ሲነጻጸር ከምንም የማይቆጠር አይደለም?’ 4  “‘አሁን ግን ዘሩባቤል፣ በርታ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የየሆጼዴቅ ልጅ ሊቀ ካህናቱ ኢያሱ፣ አንተም በርታ።’ “‘እናንተም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ፣ በርቱና ሥሩ’ ይላል ይሖዋ። “‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 5  ‘ከግብፅ በወጣችሁበት ጊዜ የገባሁላችሁን ቃል አስታውሱ፤ መንፈሴም በመካከላችሁ ይኖራል። አትፍሩ።’” 6  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ሰማያትን፣ ምድርን፣ ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ።’ 7  “‘ብሔራትንም ሁሉ አናውጣለሁ፤ በብሔራትም ሁሉ መካከል ያሉ የከበሩ ነገሮች ይመጣሉ፤ ደግሞም ይህን ቤት በክብር እሞላዋለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 8  “‘ብሩ የእኔ ነው፤ ወርቁም የእኔ ነው’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 9  “‘ይህ ቤት ወደፊት የሚጎናጸፈው ክብር ከቀድሞው የበለጠ ይሆናል’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “‘በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።” 10  ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቃል ወደ ነቢዩ ሐጌ እንዲህ ሲል መጣ፦ 11  “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እባክህ፣ ካህናቱን ስለ ሕጉ እንዲህ ብለህ ጠይቃቸው፦ 12  “አንድ ሰው በልብሱ እጥፋት የተቀደሰ ሥጋ ቢይዝና ልብሱ ዳቦ፣ ወጥ፣ የወይን ጠጅ፣ ዘይት ወይም ሌላ ማንኛውም ዓይነት ምግብ ቢነካ፣ የነካው ነገር ቅዱስ ይሆናል?”’” ካህናቱ “አይሆንም!” ብለው መለሱ። 13  ከዚያም ሐጌ እንዲህ ሲል ጠየቀ፦ “አስከሬን በመንካቱ የረከሰ ሰው ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱን ቢነካ የተነካው ነገር ይረክሳል?” ካህናቱ “አዎ፣ ይረክሳል” ብለው መለሱ። 14  ሐጌም እንዲህ አለ፦ “‘ይህም ሕዝብ እንዲሁ ነው፤ ይህም ብሔር በፊቴ እንዲሁ ነው’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የእጆቻቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፤ በዚያ የሚያቀርቡት ማንኛውም ነገር የረከሰ ነው።’ 15  “‘አሁን ግን እባካችሁ ከዚህ ቀን ጀምሮ፣ ይህን ልብ በሉ፦ በይሖዋ ቤተ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመነባበሩ በፊት፣ 16  ያኔ ሁኔታው ምን ይመስል ነበር? አንድ ሰው 20 መስፈሪያ አገኛለሁ ብሎ እህል ወደተከመረበት ቦታ በመጣ ጊዜ 10 መስፈሪያ ብቻ አገኘ፤ ደግሞም አንድ ሰው 50 መለኪያ የወይን ጠጅ ለማግኘት ወደ ወይን መጭመቂያው በመጣ ጊዜ 20 መለኪያ ብቻ አገኘ፤ 17  እናንተን ይኸውም የእጃችሁን ሥራ ሁሉ በሚለበልብና በሚያደርቅ ነፋስ፣ በዋግና በበረዶ መታሁ፤ ይሁንና አንዳችሁም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል ይሖዋ። 18  “‘በዛሬው ዕለት ይኸውም በዘጠነኛው ወር፣ ከወሩም በ24ኛው ቀን የይሖዋ ቤተ መቅደስ መሠረት ተጥሏል። እባካችሁ ከዚህ ቀን ጀምሮ ይህን ልብ በሉ፦ 19  በጎተራ ውስጥ የቀረ ዘር አሁንም አለ? የወይን ተክሉ፣ በለሱ፣ ሮማኑና የወይራ ዛፉ እስካሁን ድረስ ፍሬ አላፈሩም። ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ።’” 20  በወሩ 24ኛ ቀን የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ሐጌ መጣ፦ 21  “ለይሁዳ ገዢ ለዘሩባቤል እንዲህ በለው፦ ‘ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ። 22  የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የብሔራት መንግሥታትንም ብርታት አጠፋለሁ፤ ሠረገላውንና የሚቀመጡበትን ሰዎች እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቹና ጋላቢዎቻቸውም እያንዳንዳቸው በገዛ ወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።’” 23  “‘የሰላትያል ልጅ አገልጋዬ ዘሩባቤል ሆይ’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ ‘በዚያ ቀን እወስድሃለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ደግሞም እንደ ማኅተም ቀለበት አደርግሃለሁ፤ ምክንያቱም የመረጥኩት አንተን ነው’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
11,998
1  ብዙዎች እኛ ሙሉ እምነት የጣልንባቸውን መረጃዎች ለማጠናቀር የተቻላቸውን ጥረት አድርገዋል፤ 2  ደግሞም ከመጀመሪያው አንስቶ የዓይን ምሥክሮች የነበሩ ሰዎችና መልእክቱን የሚያውጁ አገልጋዮች እነዚህን መረጃዎች ለእኛ አስተላልፈዋል። 3  ክቡር ቴዎፍሎስ ሆይ፣ እኔም በበኩሌ ሁሉንም ነገር ከመጀመሪያው አንስቶ በጥንቃቄ ስለመረመርኩ ታሪኩን በቅደም ተከተል ልጽፍልህ ወሰንኩ። 4  ይህን ያደረግኩት በቃል የተማርካቸው ነገሮች እርግጠኛ መሆናቸውን በሚገባ እንድታውቅ ነው። 5  በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን፣ በአቢያህ የክህነት ምድብ ውስጥ የሚያገለግል ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበር። ሚስቱ የአሮን ዘር ስትሆን ስሟም ኤልሳቤጥ ነበር። 6  ሁለቱም በአምላክ ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ የይሖዋን ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ እየጠበቁ ያለነቀፋ ይኖሩ ነበር። 7  ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መሃን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፤ እንዲሁም ሁለቱም በዕድሜ የገፉ ነበሩ። 8  አንድ ቀን ዘካርያስ እሱ ያለበት ምድብ ተራው ደርሶ በአምላክ ፊት በክህነት እያገለገለ ሳለ 9  በክህነት ሥርዓቱ መሠረት ወደ ይሖዋ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን የሚያጥንበት ተራ ደረሰው። 10  ዕጣን በሚቀርብበትም ሰዓት ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ሆነው ይጸልዩ ነበር። 11  የይሖዋም መልአክ ከዕጣን መሠዊያው በስተ ቀኝ ቆሞ ታየው። 12  ዘካርያስም መልአኩን ባየው ጊዜ ደነገጠ፤ በፍርሃትም ተዋጠ። 13  መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ፣ አትፍራ፤ ምክንያቱም አምላክ ያቀረብከውን ምልጃ ሰምቷል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ። 14  አንተም ደስ ይልሃል፤ ሐሴትም ታደርጋለህ፤ ብዙዎችም በእሱ መወለድ ደስ ይላቸዋል፤ 15  በይሖዋ ፊት ታላቅ ይሆናልና። ይሁንና የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ ፈጽሞ መጠጣት የለበትም፤ ከመወለዱ በፊት እንኳ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፤ 16  ከእስራኤል ልጆች መካከልም ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ ይመልሳል። 17  በተጨማሪም ሰዎችን ለይሖዋ ያዘጋጅ ዘንድ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ ለማድረግ፣ የማይታዘዙትንም ሰዎች ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በአምላክ ፊት ይሄዳል።” 18  ዘካርያስ መልአኩን “ይህ እንደሚሆን እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ? እኔ እንደሆነ አርጅቻለሁ፤ ሚስቴም ዕድሜዋ ገፍቷል” አለው። 19  መልአኩም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እኔ በአምላክ አጠገብ በፊቱ የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ አንተን እንዳነጋግርህና ይህን ምሥራች እንዳበስርህ ተልኬአለሁ። 20  ሆኖም የተወሰነለትን ጊዜ ጠብቆ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንክ ይህ ነገር እስኪፈጸም ድረስ ዱዳ ትሆናለህ! መናገርም አትችልም።” 21  ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕዝቡ ዘካርያስን በመጠባበቅ ላይ ነበሩ፤ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ብዙ በመቆየቱም ግራ ተጋቡ። 22  በወጣ ጊዜም ሊያናግራቸው አልቻለም፤ እነሱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ አንድ ራእይ እንዳየ ተገነዘቡ። ከዚያ በኋላ ዱዳ ስለሆነ በምልክት ብቻ ያናግራቸው ነበር። 23  በቤተ መቅደሱ ውስጥ ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርብባቸው ቀናት ሲያበቁ ወደ ቤቱ ሄደ። 24  ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፤ ለአምስት ወርም ከቤት ሳትወጣ ቆየች፤ እንዲህም አለች፦ 25  “ይሖዋ በዚህ ወቅት ይህን አደረገልኝ። በሰዎች መካከል ይደርስብኝ የነበረውን ነቀፋ ለማስወገድ ፊቱን ወደ እኔ መለሰ።” 26  ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድስተኛ ወሯ አምላክ መልአኩ ገብርኤልን በገሊላ ወደምትገኝ ናዝሬት ወደተባለች ከተማ ላከው፤ 27  የተላከውም ከዳዊት ቤት ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች አንዲት ድንግል ሲሆን የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር። 28  መልአኩም ገብቶ “እጅግ የተባረክሽ ሆይ፣ ሰላም ለአንቺ ይሁን፤ ይሖዋ ከአንቺ ጋር ነው” አላት። 29  እሷ ግን በንግግሩ በጣም ደንግጣ ይህ ሰላምታ ምን ትርጉም እንዳለው ለመረዳት በውስጧ ታስብ ጀመር። 30  ስለዚህ መልአኩ እንዲህ አላት፦ “ማርያም ሆይ፣ በአምላክ ፊት ሞገስ ስላገኘሽ አትፍሪ። 31  እነሆም፣ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። 32  እሱም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤ ይሖዋ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ 33  በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።” 34  ማርያም ግን መልአኩን “እኔ ከወንድ ጋር ግንኙነት ፈጽሜ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለችው። 35  መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑሉም ኃይል በአንቺ ላይ ያርፋል። ስለሆነም የሚወለደው ልጅ ቅዱስና የአምላክ ልጅ ይባላል። 36  እነሆ፣ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መሃን ትባል የነበረ ቢሆንም ይኸው ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤ 37  አምላክ የተናገረው ቃል ሳይፈጸም አይቀርምና።” 38  በዚህ ጊዜ ማርያም “እነሆ፣ እኔ የይሖዋ ባሪያ ነኝ! እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” አለች። ከዚያም መልአኩ ተለይቷት ሄደ። 39  ማርያምም በዚያው ሰሞን ተነስታ በተራራማው አገር ወደምትገኝ አንዲት የይሁዳ ከተማ በፍጥነት ሄደች፤ 40  ወደ ዘካርያስ ቤት ገብታም ኤልሳቤጥን ሰላም አለቻት። 41  ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ በማህፀኗ ውስጥ ያለው ፅንስ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤ 42  ድምፅዋንም ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፦ “አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፤ የማህፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው! 43  የጌታዬ እናት ወደ እኔ መምጣቷ ለእኔ እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው! 44  እነሆ፣ የሰላምታሽን ድምፅ እንደሰማሁ በማህፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘሏልና። 45  ይሖዋ የነገራት ነገር ሙሉ በሙሉ የሚፈጸም በመሆኑ ይህን ያመነች ደስተኛ ነች።” 46  ማርያምም እንዲህ አለች፦ “ነፍሴ ይሖዋን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤ 47  መንፈሴም አዳኜ በሆነው አምላክ እጅግ ደስ ይሰኛል፤ 48  ምክንያቱም የባሪያውን መዋረድ ተመልክቷል። እነሆ፣ ከአሁን ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ደስተኛ ይሉኛል፤ 49  ምክንያቱም ኃያል የሆነው አምላክ ታላላቅ ነገሮች አድርጎልኛል፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤ 50  ምሕረቱም በሚፈሩት ሁሉ ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል። 51  በክንዱም ታላላቅ ሥራዎች አከናውኗል፤ በልባቸው ሐሳብ ትዕቢተኛ የሆኑትንም በትኗቸዋል። 52  ኃያላን ሰዎችን ከዙፋናቸው አውርዷል፤ ዝቅ ያሉትንም ከፍ አድርጓል፤ 53   የተራቡትን በመልካም ነገሮች አጥግቧል፤ ሀብታሞችንም ባዶ እጃቸውን ሰዷቸዋል። 54  ምሕረቱን በማስታወስ አገልጋዩን እስራኤልን ረድቷል፤ 55  ይህን ያደረገው ለአባቶቻችን በገባው ቃል መሠረት ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረት ለማሳየት ነው።” 56  ማርያምም ከኤልሳቤጥ ጋር ሦስት ወር ያህል ከቆየች በኋላ ወደ ቤቷ ተመለሰች። 57   ኤልሳቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰና ወንድ ልጅ ወለደች። 58  ጎረቤቶቿና ዘመዶቿም ይሖዋ ታላቅ ምሕረት እንዳደረገላት ሰምተው የደስታዋ ተካፋዮች ሆኑ። 59  በስምንተኛው ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ብለው ሊጠሩት ፈልገው ነበር። 60  እናትየው ግን መልሳ “አይሆንም! ዮሐንስ ይባል” አለች። 61  በዚህ ጊዜ “ከዘመዶችሽ መካከል በዚህ ስም የተጠራ ማንም የለም” አሏት። 62  ከዚያም አባቱን ማን ተብሎ እንዲጠራ እንደሚፈልግ በምልክት ጠየቁት። 63  እሱም የእንጨት ጽላት እንዲያመጡለት ጠየቀና “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ። በዚህ ጊዜ ሁሉም ተደነቁ። 64  ወዲያውም አፉ ተከፈተ፤ ምላሱም ተፈቶ መናገር ጀመረ፤ አምላክንም አወደሰ። 65  ጎረቤቶቻቸውም ሁሉ በፍርሃት ተዋጡ፤ የሆነውም ነገር ሁሉ በተራራማው የይሁዳ አገር በሙሉ ይወራ ጀመር። 66  ይህን የሰሙም ሁሉ “የዚህ ሕፃን መጨረሻ ምን ይሆን?” በማለት ነገሩን በልባቸው ያዙ። የይሖዋ እጅ ከእሱ ጋር እንደሆነ በግልጽ ይታይ ነበርና። 67  ከዚያም አባቱ ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፦ 68  “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ፊቱን ወደ ሕዝቡ ስለመለሰና ሕዝቡን ስላዳነ ውዳሴ ይድረሰው። 69  ደግሞም በአገልጋዩ በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድ አስነስቶልናል፤ 70  ይህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ በነበሩት ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ በተናገረው መሠረት ነው። 71  ከባላጋራዎቻችንና ከሚጠሉን ሰዎች ሁሉ እጅ እንደሚያድነን ቃል ገብቷል። 72  ለአባቶቻችን በሰጠው ተስፋ መሠረት ምሕረት ያሳየናል፤ ቅዱስ ቃል ኪዳኑንም ያስታውሳል። 73  ይህም ቃል ኪዳን ለአባታችን ለአብርሃም የማለው መሐላ ነው፤ 74  በመሐላው መሠረትም ከጠላቶቻችን እጅ ነፃ ካወጣን በኋላ ለእሱ ያለፍርሃት ቅዱስ አገልግሎት የማቅረብ መብት ይሰጠናል፤ 75  ይህም ታማኝ እንድንሆንና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ጽድቅ የሆነውን ነገር እንድናደርግ ነው። 76  ደግሞም አንተ ሕፃን፣ መንገዱን ለማዘጋጀት ቀድመህ በይሖዋ ፊት ስለምትሄድ የልዑሉ ነቢይ ትባላለህ፤ 77  ለሕዝቡም ኃጢአታቸው ይቅር ተብሎላቸው መዳን እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን እውቀት ትሰጣቸዋለህ፤ 78  ይህም የሆነው አምላካችን ከአንጀት ስለራራልን ነው። ከዚህ ርኅራኄም የተነሳ እንደ ንጋት ፀሐይ የሚያበራ ብርሃን ከላይ ይወጣልናል፤ 79  ይኸውም በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለተቀመጡት ብርሃን ለመስጠት እንዲሁም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ለመምራት ነው።” 80  ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤልም በይፋ እስከታየበት ቀን ድረስ በበረሃ ኖረ።
[]
[]
[]
[]
11,999
10  ከዚህ በኋላ ጌታ ሌሎች 70 ሰዎችን ሾመ፤ እሱ ሊሄድበት ወዳሰበው ከተማና ቦታ ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱም ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው። 2  ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “አዎ፣ አዝመራው ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂት ናቸው። ስለዚህ የመከሩ ሥራ ኃላፊ ወደ መከሩ፣ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት። 3  እንግዲህ ሂዱ! እነሆ፣ በተኩላዎች መካከል እንዳሉ በጎች እልካችኋለሁ። 4  የገንዘብ ኮሮጆ ወይም የምግብ ከረጢት ወይም ትርፍ ጫማ አትያዙ፤ በመንገድም ላይ ቆማችሁ ከማንም ጋር ሰላምታ አትለዋወጡ። 5  ወደ ማንኛውም ቤት ስትገቡ በቅድሚያ ‘ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን’ በሉ። 6  በዚያም ሰላም ወዳድ ሰው ካለ ሰላማችሁ ያርፍበታል። ሰላም ወዳድ ሰው ከሌለ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል። 7  ለሠራተኛ ደሞዙ ስለሚገባውያቀረቡላችሁን ነገር እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ቆዩ። ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ። 8  “በተጨማሪም ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ ሰዎቹ ከተቀበሏችሁ ያቀረቡላችሁን ብሉ፤ 9  እንዲሁም በዚያ ያሉትን በሽተኞች ፈውሱ፤ ደግሞም ‘የአምላክ መንግሥት ወደ እናንተ ቀርቧል’ በሏቸው። 10  ሆኖም ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ ሰዎቹ ካልተቀበሏችሁ ወደ አውራ ጎዳናዎች ወጥታችሁ እንዲህ በሉ፦ 11  ‘በእግራችን ላይ ያለውን የከተማችሁን አቧራ እንኳ ሳይቀር አራግፈንላችሁ እንሄዳለን። ይሁንና የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ እወቁ።’ 12  እላችኋለሁ፦ በዚያ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል። 13  “ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ ውስጥ የተደረጉት ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ማቅ ለብሰውና አመድ ላይ ተቀምጠው ንስሐ በገቡ ነበር። 14  ስለዚህ በፍርድ ወቅት ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። 15  አንቺም ቅፍርናሆም ወደ ሰማይ ከፍ የምትዪ ይመስልሻል? በፍጹም! ወደ መቃብር ትወርጃለሽ! 16  “እናንተን የሚሰማ ሁሉ እኔንም ይሰማል። እናንተን የማይቀበል ሁሉ ደግሞ እኔንም አይቀበልም። ከዚህም በላይ እኔን የማይቀበል ሁሉ የላከኝንም አይቀበልም።” 17  ከዚያም 70ዎቹ ደስ እያላቸው ተመልሰው “ጌታ ሆይ፣ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዙልን” አሉት። 18  በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። 19  እነሆ፣ እባቦችንና ጊንጦችን እንድትረግጡ እንዲሁም የጠላትን ኃይል ሁሉ እንድትቋቋሙ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፤ የሚጎዳችሁም አንዳች ነገር አይኖርም። 20  ይሁን እንጂ መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፤ ከዚህ ይልቅ ስማችሁ በሰማያት ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ።” 21  በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሴት አድርጎ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከአዋቂዎች ሰውረህ ለትናንሽ ልጆች ስለገለጥክላቸው በይፋ አወድስሃለሁ። አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ የአንተ ፈቃድ ነውና። 22  ሁሉንም ነገር አባቴ ሰጥቶኛል፤ ከአብ በስተቀር ወልድ ማን እንደሆነ የሚያውቅ የለም፤ እንዲሁም ከወልድና ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በስተቀር አብ ማን እንደሆነ የሚያውቅ የለም።” 23  ከዚያም ብቻቸውን በነበሩበት ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ አሁን የምታዩትን ነገር የሚያዩ ዓይኖች ደስተኞች ናቸው። 24  እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ አሁን የምታዩትን ነገር ለማየት ተመኝተው ነበር፤ ግን አላዩም፤ አሁን የምትሰሙትን ነገር ለመስማት ተመኝተው ነበር፤ ግን አልሰሙም።” 25  እነሆም አንድ ሕግ አዋቂ ኢየሱስን ሊፈትነው ተነስቶ “መምህር፣ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ አለብኝ?” አለው። 26  ኢየሱስም “በሕጉ ላይ የተጻፈው ምንድን ነው? አንተስ ምን ትረዳለህ?” አለው። 27  እሱም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ ኃይልህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ’፤ እንዲሁም ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ’” አለው። 28  ኢየሱስም “በትክክል መልሰሃል፤ ዘወትር ይህን አድርግ፤ ሕይወትም ታገኛለህ” አለው። 29  ሰውየው ግን ጻድቅ መሆኑን ለማሳየት ፈልጎ ኢየሱስን “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” አለው። 30  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ በዘራፊዎች እጅ ወደቀ፤ እነሱም ከገፈፉትና ከደበደቡት በኋላ በሞትና በሕይወት መካከል ጥለውት ሄዱ። 31  እንደ አጋጣሚ አንድ ካህን በዚያ መንገድ ሲወርድ ሰውየውን አየውና ራቅ ብሎ አልፎት ሄደ። 32  በተመሳሳይም አንድ ሌዋዊ እዚያ ቦታ ሲደርስ አየውና ገለል ብሎ አልፎት ሄደ። 33  ሆኖም አንድ ሳምራዊ በዚያ መንገድ ሲጓዝ ሰውየው ወዳለበት ቦታ ደረሰ፤ ባየውም ጊዜ በጣም አዘነለት። 34  ስለሆነም ወደ ሰውየው ቀርቦ በቁስሎቹ ላይ ዘይትና የወይን ጠጅ አፍስሶ በጨርቅ አሰረለት። ከዚያም በራሱ አህያ ላይ ካስቀመጠው በኋላ ወደ አንድ የእንግዶች ማረፊያ በመውሰድ ተንከባከበው። 35  በማግስቱ ሁለት ዲናር አውጥቶ ለእንግዶች ማረፊያ ቤቱ ባለቤት ሰጠውና ‘ይህን ሰው አስታመው፤ ከዚህ በላይ የምታወጣውን ተጨማሪ ወጪ ሁሉ ስመለስ እከፍልሃለሁ’ አለው። 36  ታዲያ ከእነዚህ ሦስት ሰዎች መካከል በዘራፊዎች እጅ ለወደቀው ሰው ባልንጀራ ሆኖ የተገኘው የትኛው ይመስልሃል?” 37  እሱም “ምሕረት በማሳየት የረዳው ነው” አለ። ከዚያም ኢየሱስ “አንተም ሂድና እንዲሁ አድርግ” አለው። 38  እየተጓዙም ሳሉ ወደ አንድ መንደር ገባ። በዚያም ማርታ የምትባል አንዲት ሴት በቤቷ በእንግድነት ተቀበለችው። 39  እሷም ማርያም የምትባል እህት ነበረቻት፤ ማርያምም በጌታ እግር ሥር ተቀምጣ የሚናገረውን ታዳምጥ ነበር። 40  ማርታ ግን በብዙ ሥራ ተጠምዳ ትባክን ነበር። በመሆኑም ወደ እሱ መጥታ “ጌታ ሆይ፣ እህቴ ሥራውን ሁሉ ለእኔ ጥላ ስትቀመጥ ምንም ግድ አይሰጥህም? መጥታ እንድታግዘኝ ንገራት እንጂ” አለችው። 41  ጌታም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ማርታ፣ ማርታ፣ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ደግሞም ትጠበቢያለሽ። 42  ይሁንና የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር ብቻ ነው። ማርያም በበኩሏ ጥሩ የሆነውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእሷ አይወሰድም።”
[]
[]
[]
[]
12,000
11  አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ እየጸለየ ነበር፤ ጸሎቱንም ሲጨርስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ “ጌታ ሆይ፣ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው ሁሉ አንተም እንዴት እንደምንጸልይ አስተምረን” አለው። 2  በመሆኑም እንዲህ አላቸው፦ “በምትጸልዩበት ጊዜ ሁሉ እንዲህ በሉ፦ ‘አባት ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ። መንግሥትህ ይምጣ። 3  የዕለቱን ምግባችንን ለዕለቱ የሚያስፈልገንን ያህል ስጠን። 4  እኛ የበደሉንን ሁሉ ይቅር ስለምንል ኃጢአታችንን ይቅር በለን፤ ወደ ፈተናም አታግባን።’” 5  ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ መካከል አንዱ፣ አንድ ወዳጅ አለው እንበል፤ በእኩለ ሌሊትም ወደ እሱ ሄዶ እንዲህ አለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ፣ እባክህ ሦስት ዳቦ አበድረኝ፤ 6  አንድ ወዳጄ ከመንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ነገር አጣሁ።’ 7  ወዳጁ ግን ከውስጥ ሆኖ ‘ባክህ አታስቸግረኝ። በሩ ተቆልፏል፤ ልጆቼም አብረውኝ ተኝተዋል። አሁን ተነስቼ ምንም ነገር ልሰጥህ አልችልም’ ይለዋል። 8  እላችኋለሁ፣ ወዳጁ ስለሆነ ተነስቶ ባይሰጠው እንኳ ስለ ውትወታው ሲል ተነስቶ የፈለገውን ሁሉ ይሰጠዋል። 9  ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ደጋግማችሁ ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ሳታሰልሱ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ ደጋግማችሁ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል። 10  ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋል፤ የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል፤ የሚያንኳኳም ሁሉ ይከፈትለታል። 11  ደግሞስ ከመካከላችሁ ልጁ ዓሣ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ የሚሰጥ አባት ይኖራል? 12  ወይስ እንቁላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋል? 13  ታዲያ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባትማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸው!” 14  ከጊዜ በኋላ፣ ኢየሱስ ዱዳ የሚያደርግ ጋኔን አስወጣ። ጋኔኑ ከወጣ በኋላ ዱዳው ሰው መናገር ጀመረ፤ ሕዝቡም ተደነቀ። 15  ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል ነው” አሉ። 16  ሌሎች ደግሞ ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ይጠይቁት ጀመር። 17  ኢየሱስም ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ እንዲሁም እርስ በርሱ የሚከፋፈል ቤት ይወድቃል። 18  በተመሳሳይም ሰይጣን እርስ በርሱ ከተከፋፈለ መንግሥቱ እንዴት ይቆማል? እናንተ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል እንደሆነ ትናገራላችሁና። 19  እኔ አጋንንትን የማስወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ የሚያስወጧቸው ታዲያ በማን ነው? ልጆቻችሁ ፈራጆች የሚሆኑባችሁ ለዚህ ነው። 20  ሆኖም አጋንንትን የማስወጣው በአምላክ ጣት ከሆነ የአምላክ መንግሥት ሳታስቡት ደርሶባችኋል ማለት ነው። 21  አንድ ብርቱ ሰው በደንብ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ ንብረቱ ምንም አይነካበትም። 22  ይሁን እንጂ ከእሱ ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው ካጠቃውና ካሸነፈው ተማምኖበት የነበረውን መሣሪያ ሁሉ ይነጥቀዋል፤ ከእሱ የወሰደውንም ለሌሎች ያካፍላል። 23  ከእኔ ጎን ያልቆመ ሁሉ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ሁሉ ይበትናል። 24  “ርኩስ መንፈስ ከሰው ሲወጣ የሚያርፍበት ቦታ ፍለጋ ውኃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ የሚያርፍበት ቦታ ሲያጣ ግን ‘ወደለቀቅኩት ቤቴ እመለሳለሁ’ ይላል። 25  ሲመለስም ቤቱ ጸድቶና አጊጦ ያገኘዋል። 26  ከዚያም ሄዶ ከእሱ የከፉ ሌሎች ሰባት መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውም ይኖሩበታል። በመሆኑም የዚያ ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከቀድሞው የከፋ ይሆንበታል።” 27  ይህን እየተናገረ ሳለ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ “አንተን የተሸከመች ማህፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ደስተኞች ናቸው!” አለችው። 28  እሱ ግን “ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!” አለ። 29  ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክትም ማየት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከዮናስ ምልክት በስተቀር ምንም ምልክት አይሰጠውም። 30  ምክንያቱም ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። 31  የደቡብ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለመጣች በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነስታ ትኮንናቸዋለች። ነገር ግን ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ። 32  የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሐ ስለገቡ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይኮንኑታል። ነገር ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ። 33  አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ በሰዋራ ቦታ አያስቀምጠውም ወይም እንቅብ አይደፋበትም፤ ከዚህ ይልቅ ወደ ቤት የሚገቡ ሁሉ ብርሃን እንዲያገኙ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል። 34  የሰውነት መብራት ዓይን ነው። ዓይንህ በአንድ ነገር ላይ ሲያተኩር መላ ሰውነትህም ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ ምቀኛ ሲሆን ግን መላ ሰውነትህም ጨለማ ይሆናል። 35  ስለዚህ በውስጥህ ያለው ብርሃን፣ ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። 36  እንግዲህ መላ ሰውነትህ ምንም ጨለማ ሳይኖርበት ብሩህ ከሆነ፣ ልክ ብርሃን እንደሚፈነጥቅልህ መብራት ሁለንተናህ ብሩህ ይሆናል።” 37  ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ አንድ ፈሪሳዊ አብሮት እንዲበላ ጋበዘው። እሱም ወደ ቤቱ ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። 38  ይሁን እንጂ ፈሪሳዊው ኢየሱስ ከምሳ በፊት እጁን እንዳልታጠበ ባየ ጊዜ ተገረመ። 39  ጌታ ግን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ፈሪሳውያን ጽዋውንና ሳህኑን ከውጭ በኩል ታጸዳላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን በስግብግብነትና በክፋት የተሞላ ነው። 40  እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁ! የውስጡንስ የሠራው የውጭውን የሠራው አይደለም? 41  ስለዚህ በልባችሁ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፤ ያን ጊዜ በሁሉም ነገር ንጹሕ ትሆናላችሁ። 42  እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ከኮሰረት፣ ከጤና አዳምና ከሌሎች አትክልቶች ሁሉ አሥራት ትሰጣላችሁ፤ ነገር ግን የአምላክን ፍትሕና እሱን መውደድን ችላ ትላላችሁ። እርግጥ አሥራት የመስጠት ግዴታ አለባችሁ፤ ሆኖም ሌሎቹን ነገሮች ችላ ማለት አልነበረባችሁም። 43  እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም በምኩራብ ከፊት መቀመጥ፣ በገበያ ቦታ ደግሞ ሰዎች እጅ እንዲነሷችሁ ትፈልጋላችሁ። 44  ሰዎች ሳያውቁ በላዩ ላይ የሚሄዱበትን የተሰወረ መቃብር ስለምትመስሉ ወዮላችሁ!” 45  ከሕጉ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ “መምህር፣ እንዲህ ስትል እኮ እኛንም መስደብህ ነው” አለው። 46  በዚህ ጊዜ እንዲህ አለ፦ “እናንተ የሕጉ አዋቂዎችም ወዮላችሁ! ምክንያቱም ለመሸከም የሚከብድ ሸክም በሰው ላይ ትጭናላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ ግን ሸክሙን በጣታችሁ እንኳ አትነኩትም። 47  “አባቶቻችሁ የገደሏቸውን ነቢያት መቃብሮች ስለምትሠሩ ወዮላችሁ! 48  እንግዲህ እናንተ ለአባቶቻችሁ ሥራ ምሥክሮች ናችሁ፤ ያም ሆኖ የእነሱን ሥራ ትደግፋላችሁ፤ ምክንያቱም እነሱ ነቢያትን ገደሉ፤ እናንተ ደግሞ መቃብሮቻቸውን ትሠራላችሁ። 49  ስለዚህ የአምላክ ጥበብ እንዲህ አለች፦ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነሱ እልካለሁ፤ እነሱም አንዳንዶቹን ይገድላሉ በአንዳንዶቹም ላይ ስደት ያደርሳሉ፤ 50  በመሆኑም ይህ ትውልድ ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ሁሉ ተጠያቂ ነው፤ 51  ከአቤል አንስቶ በመሠዊያውና በቤቱ መካከል እስከተገደለው እስከ ዘካርያስ ድረስ ለፈሰሰው ደም ተጠያቂ ነው።’ አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል። 52  “እናንተ የሕጉ አዋቂዎች ወዮላችሁ! ምክንያቱም የእውቀትን ቁልፍ ነጥቃችሁ ወስዳችኋል። እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁም፤ ለመግባት የሚሞክሩትንም ትከለክላላችሁ።” 53   ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ሲሄድ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ከበው እያጨናነቁት ስለተለያዩ ነገሮች በመጠየቅ ያዋክቡት ጀመር፤ 54  በሚናገረውም ነገር ሊያጠምዱት ያደቡ ነበር።
[]
[]
[]
[]