doc_no
int64
1
12.6k
doc_text
stringlengths
81
395k
relevant_topic_nos
sequencelengths
0
1
relevant_topic_titles
sequencelengths
0
1
relevant_topic_descriptions
sequencelengths
0
1
relevant_topic_narratives
sequencelengths
0
1
12,001
12  በዚያን ጊዜ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ እርስ በርስ እየተጋፋ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ ኢየሱስ በቅድሚያ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ከፈሪሳውያን እርሾ ይኸውም ከግብዝነት ተጠንቀቁ። 2  ይሁንና የተሰወረ መገለጡ፣ ሚስጥር የሆነም መታወቁ አይቀርም። 3  ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፤ በጓዳ የምታንሾካሹኩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። 4  በተጨማሪም ወዳጆቼ ሆይ፣ እላችኋለሁ፣ ሥጋን የሚገድሉትን ከዚያ በላይ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ። 5  ይልቁንስ ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ አሳያችኋለሁ፦ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም የመጣል ሥልጣን ያለውን ፍሩ። አዎ፣ እላችኋለሁ እሱን ፍሩ። 6  አምስት ድንቢጦች አነስተኛ ዋጋ ባላቸው ሁለት ሳንቲሞች ይሸጡ የለም? ሆኖም አንዷም እንኳ በአምላክ ዘንድ አትረሳም። 7  የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል። አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ። 8  “እላችኋለሁ፣ በሰዎች ፊት የሚመሠክርልኝን ሁሉ የሰው ልጅም በአምላክ መላእክት ፊት ይመሠክርለታል። 9  በሰዎች ፊት የሚክደኝ ሁሉ ግን በአምላክ መላእክት ፊት ይካዳል። 10  በሰው ልጅ ላይ ክፉ ቃል የሚናገር ሁሉ ይቅር ይባልለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ሁሉ ግን ይቅር አይባልም። 11  በሕዝባዊ ሸንጎዎች እንዲሁም በመንግሥት ሹማምንትና ባለሥልጣናት ፊት ሲያቀርቧችሁ እንዴት ብለን ወይም ምን ብለን የመከላከያ መልስ እንሰጣለን ወይም ደግሞ ምን እንላለን ብላችሁ አትጨነቁ፤ 12  ምን መናገር እንዳለባችሁ መንፈስ ቅዱስ በዚያኑ ሰዓት ያስተምራችኋልና።” 13  ከዚያም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው “መምህር፣ ወንድሜ ውርሳችንን እንዲያካፍለኝ ንገረው” አለው። 14  ኢየሱስም “አንተ ሰው፣ በእናንተ መካከል ፈራጅና ዳኛ እንድሆን ማን ሾመኝ?” አለው። 15  ከዚያም “አንድ ሰው ሀብታም ቢሆንም እንኳ ንብረቱ ሕይወት ሊያስገኝለት አይችልም፤ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም ሁሉ ተጠበቁ” አላቸው። 16  ይህን ካለ በኋላ እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “አንድ ሀብታም ሰው መሬቱ ብዙ ምርት አስገኘለት። 17  በመሆኑም ‘ምርቴን የማከማችበት ቦታ ስለሌለኝ ምን ባደርግ ይሻላል?’ ብሎ በልቡ ማሰብ ጀመረ። 18  ከዚያም እንዲህ አለ፦ ‘እንዲህ አደርጋለሁ፦ ያሉኝን ጎተራዎች አፈርስና ትላልቅ ጎተራዎች እሠራለሁ፤ በዚያም እህሌንና ንብረቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤ 19  ነፍሴንም “ነፍሴ ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ የተከማቸ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ዘና በይ፣ ብዪ፣ ጠጪ፣ ደስም ይበልሽ” እላታለሁ።’ 20  አምላክ ግን ‘አንተ ማስተዋል የጎደለህ፣ በዚህች ሌሊት ሕይወትህን ይፈልጓታል። ታዲያ ያከማቸኸው ነገር ለማን ይሆናል?’ አለው። 21  ለራሱ ሀብት የሚያከማች በአምላክ ዘንድ ግን ሀብታም ያልሆነ ሰው መጨረሻው ይኸው ነው።” 22  ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንበላለን ወይም ደግሞ ስለ ሰውነታችሁ ምን እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ። 23  ሕይወት ከምግብ ሰውነትም ከልብስ የላቀ ዋጋ አለውና። 24  ቁራዎችን ተመልከቱ፦ አይዘሩም፣ አያጭዱም እንዲሁም የእህል ማከማቻ ወይም ጎተራ የላቸውም፤ ሆኖም አምላክ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ የላቀ ዋጋ የላችሁም? 25  ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ርዝማኔ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ይኖራል? 26  ታዲያ እንዲህ ያለውን ትንሽ ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ ስለ ሌሎች ነገሮች ለምን ትጨነቃላችሁ? 27  እስቲ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ፦ አይለፉም ወይም አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ያን ያህል ክብር የነበረው ሰለሞን እንኳ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዷ አላጌጠም። 28  አምላክ ዛሬ ያለውንና ነገ ወደ ምድጃ የሚጣለውን በሜዳ ያለ ተክል እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁ! 29  ስለዚህ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት ነገር ከልክ በላይ አታስቡ፤ እንዲሁም አትጨነቁ፤ 30  እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዓለም ያሉ ሰዎች አጥብቀው የሚፈልጓቸው ናቸው፤ ይሁንና አባታችሁ እነዚህ ነገሮች እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። 31  ይልቁንስ ዘወትር መንግሥቱን ፈልጉ፤ እነዚህም ነገሮች ይሰጧችኋል። 32  “አንተ ትንሽ መንጋ አትፍራ፤ አባታችሁ መንግሥት ሊሰጣችሁ ወስኗልና። 33  ያላችሁን ንብረት ሸጣችሁ ምጽዋት ስጡ። የማያረጁ የገንዘብ ኮሮጆዎች አዘጋጁ፤ አዎ፣ ሌባ በማይደርስበት፣ ብልም ሊበላው በማይችልበት በሰማያት ለራሳችሁ የማያልቅ ውድ ሀብት አከማቹ። 34  ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም በዚያ ይሆናልና። 35  “ወገባችሁን ታጠቁ፤ መብራታችሁንም አብሩ፤ 36  ጌታቸው ከሠርግ እስኪመለስ እንደሚጠባበቁና መጥቶ በሩን ሲያንኳኳ ወዲያው ለመክፈት እንደተዘጋጁ ዓይነት ሰዎች ሁኑ። 37  ጌታቸው በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው ሲጠባበቁ የሚያገኛቸው ባሪያዎች ደስተኞች ናቸው! እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታቸው ለሥራ ካሸረጠና በማዕድ እንዲቀመጡ ካደረገ በኋላ ቆሞ ያስተናግዳቸዋል። 38  በሁለተኛው ክፍለ ሌሊትም ይምጣ በሦስተኛው፣ ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ካገኛቸው ደስተኞች ናቸው! 39  ነገር ግን ይህን እወቁ፤ አንድ ሰው ሌባ በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ ቤቱ እንዳይደፈር በተከላከለ ነበር። 40  እናንተም የሰው ልጅ ይመጣል ብላችሁ ባላሰባችሁት ሰዓት ስለሚመጣ ዝግጁ ሆናችሁ ጠብቁ።” 41  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ምሳሌ እየተናገርክ ያለኸው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሁሉም?” አለው። 42  ጌታም እንዲህ አለ፦ “ጌታው ምንጊዜም የሚያስፈልጋቸውን ምግብ በተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው በአገልጋዮቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ በእርግጥ ማን ነው? 43  ጌታው ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ካገኘው ያ ባሪያ ደስተኛ ነው! 44  እውነት እላችኋለሁ፣ ጌታው በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል። 45  ነገር ግን ያ ባሪያ በልቡ ‘ጌታዬ የሚመጣው ዘግይቶ ነው’ ብሎ ቢያስብና ወንድና ሴት አገልጋዮችን መደብደብ እንዲሁም መብላት፣ መጠጣትና መስከር ቢጀምር 46  የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላሰበው ሰዓት ይመጣል፤ ከባድ ቅጣት ይቀጣዋል፤ ዕጣውንም ታማኝ ካልሆኑ ሰዎች ጋር ያደርገዋል። 47  ደግሞም የጌታውን ፈቃድ እያወቀ ተዘጋጅቶ ያልጠበቀው ወይም ጌታው የጠየቀውን ነገር ያላደረገው ያ ባሪያ ብዙ ግርፋት ይገረፋል። 48  ነገር ግን ሳያውቅ፣ ግርፋት የሚገባው ድርጊት የፈጸመ ጥቂት ይገረፋል። በእርግጥም ብዙ ከተሰጠው ሁሉ ብዙ ይጠበቅበታል፤ ብዙ ኃላፊነት የተሰጠውም ብዙ ይጠበቅበታል። 49  “እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኮስ ነው፤ ታዲያ እሳቱ ከተቀጣጠለ ከዚህ በላይ ምን እፈልጋለሁ? 50  እርግጥ እኔ የምጠመቀው አንድ ጥምቀት አለኝ፤ ይህ እስኪፈጸም ድረስ በጣም ተጨንቄአለሁ! 51  የመጣሁት በምድር ላይ ሰላም ለማስፈን ይመስላችኋል? በፍጹም አይደለም፤ እላችኋለሁ፣ የመጣሁት ሰላም ለማስፈን ሳይሆን ለመከፋፈል ነው። 52  ከአሁን ጀምሮ በአንድ ቤት ውስጥ እርስ በርስ የተከፋፈሉ አምስት ሰዎች ይኖራሉ፤ ሦስቱ በሁለቱ ላይ ሁለቱ ደግሞ በሦስቱ ላይ ይነሳሉ። 53   አባት በልጁ፣ ልጅ በአባቱ፣ እናት በልጇ፣ ልጅ በእናቷ፣ አማት በምራቷ፣ ምራት በአማቷ ላይ በመነሳት እርስ በርስ ይከፋፈላሉ።” 54  ከዚያም ለሕዝቡ ደግሞ እንዲህ አለ፦ “ከምዕራብ በኩል ደመና ሲመጣ ስታዩ ወዲያውኑ ‘ዶፍ ዝናብ ሊጥል ነው’ ትላላችሁ፤ እንዳላችሁትም ይሆናል። 55  የደቡብ ነፋስ ሲነፍስ ስታዩ ደግሞ ‘ኃይለኛ ሙቀት ይሆናል’ ትላላችሁ፤ በእርግጥም ይሆናል። 56  እናንተ ግብዞች፣ የምድሩንና የሰማዩን መልክ አይታችሁ መረዳት ትችላላችሁ፤ ታዲያ ይህን የአሁኑን ዘመን መርምራችሁ መረዳት እንዴት ተሳናችሁ? 57   ደግሞስ ጽድቅ የሆነውን ነገር ለራሳችሁ ለምን አትፈርዱም? 58  ለምሳሌ ከከሳሽህ ጋር ወደ አንድ ባለሥልጣን እየሄድክ ሳለ፣ ከእሱ ጋር ያለህን ቅራኔ እዚያው በመንገድ ላይ ለመፍታት ጥረት አድርግ፤ አለዚያ ዳኛ ፊት ያቀርብሃል፤ ዳኛውም ለፍርድ ቤቱ መኮንን አሳልፎ ይሰጥሃል፤ መኮንኑ ደግሞ እስር ቤት ያስገባሃል። 59  እልሃለሁ፣ የመጨረሻዋን ትንሽ ሳንቲም ከፍለህ እስክትጨርስ ድረስ ከዚያ ፈጽሞ አትወጣም።”
[]
[]
[]
[]
12,002
13  በወቅቱ፣ በዚያ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስለደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች ለኢየሱስ አወሩለት። 2  እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለደረሰባቸው ከሌሎቹ የገሊላ ሰዎች ይበልጥ ኃጢአተኞች እንደሆኑ አድርጋችሁ ታስባላችሁ? 3  በፍጹም፤ ነገር ግን ንስሐ ካልገባችሁ ሁላችሁም እንደ እነሱ ትጠፋላችሁ። 4  ወይም ደግሞ የሰሊሆም ግንብ ተንዶባቸው የሞቱት 18 ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ይበልጥ በደለኞች የነበሩ ይመስላችኋል? 5  በፍጹም፤ ነገር ግን ንስሐ ካልገባችሁ ሁላችሁም ልክ እንደ እነሱ ትጠፋላችሁ።” 6  ከዚያም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ተናገረ፦ “አንድ ሰው በወይን እርሻው ውስጥ የተተከለች አንዲት የበለስ ዛፍ ነበረችው፤ እሱም ከዛፏ ፍሬ ሊለቅም መጣ፤ ሆኖም ምንም አላገኘባትም። 7  በዚህ ጊዜ የወይን አትክልት ሠራተኛውን ‘ከዚህች የበለስ ዛፍ ፍሬ ለማግኘት ሦስት ዓመት ሙሉ ተመላለስኩ፤ ሆኖም ምንም አላገኘሁባትም። ስለዚህ ቁረጣት! ለምን በከንቱ ቦታ ትይዛለች?’ አለው። 8  እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ ‘ጌታዬ፣ ዙሪያዋን ቆፍሬ ፍግ ላድርግባትና እስቲ ለአንድ ዓመት ደግሞ እንያት። 9  ወደፊት ፍሬ ካፈራች ጥሩ፤ ካልሆነ ግን ትቆርጣታለህ።’” 10  ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድ ምኩራብ ውስጥ እያስተማረ ነበር። 11  በዚያም ባደረባት ክፉ መንፈስ የተነሳ ለ18 ዓመት በበሽታ ስትማቅቅ የኖረች አንዲት ሴት ነበረች፤ በጣም ከመጉበጧም የተነሳ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር። 12  ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና “አንቺ ሴት፣ ከበሽታሽ ተገላግለሻል” አላት። 13  እጁንም ጫነባት፤ ወዲያውም ቀጥ አለች፤ አምላክንም ማመስገን ጀመረች። 14  የምኩራቡ አለቃ ግን ኢየሱስ በሰንበት ቀን በመፈወሱ ተቆጥቶ ሕዝቡን “ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አላቸው። 15  ይሁን እንጂ ጌታ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እናንተ ግብዞች፣ እያንዳንዳችሁ በሰንበት ቀን በሬያችሁን ወይም አህያችሁን ከጋጣው ፈታችሁ ውኃ ለማጠጣት ትወስዱ የለም? 16  ታዲያ የአብርሃም ልጅ የሆነችውና 18 ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ የኖረችው ይህች ሴት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራቷ መፈታት አይገባትም?” 17  ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ሁሉ በኀፍረት ተሸማቀቁ፤ ሕዝቡ በሙሉ ግን እሱ ባደረጋቸው አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ይደሰቱ ጀመር። 18  ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የአምላክ መንግሥት ከምን ጋር ይመሳሰላል? ከምንስ ጋር ላነጻጽረው? 19  አንድ ሰው ወስዶ በአትክልት ቦታው ከዘራት የሰናፍጭ ዘር ጋር ይመሳሰላል፤ ይህች ዘር አድጋ ዛፍ ሆነች፤ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎቿ ላይ ሰፈሩ።” 20  ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የአምላክን መንግሥት ከምን ጋር ላነጻጽረው? 21  አንዲት ሴት ወስዳ ሊጡ በሙሉ እስኪቦካ ድረስ ከሦስት ትላልቅ መስፈሪያ ዱቄት ጋር ከደባለቀችው እርሾ ጋር ይመሳሰላል።” 22  ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዘ ሳለ በየከተማውና በየመንደሩ እያስተማረ ያልፍ ነበር። 23  በዚህ ጊዜ አንድ ሰው “ጌታ ሆይ፣ የሚድኑት ጥቂቶች ናቸው?” ሲል ጠየቀው። እሱም እንዲህ አላቸው፦ 24  “በጠባቡ በር ለመግባት ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጉ፤ እላችኋለሁ፦ ብዙዎች ለመግባት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን አይችሉም። 25  የቤቱ ባለቤት ተነስቶ አንዴ በሩን ከዘጋው በኋላ ውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ፣ ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ብታንኳኩ ‘ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም’ ብሎ ይመልስላችኋል። 26  በዚህ ጊዜ ‘አብረንህ እኮ በልተናል፤ ደግሞም ጠጥተናል፤ በአውራ ጎዳናዎቻችንም አስተምረሃል’ ማለት ትጀምራላችሁ። 27  እሱ ግን ‘ከየት እንደመጣችሁ አላውቅም። እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፣ ከእኔ ራቁ!’ ይላችኋል። 28  አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብንና ነቢያትን ሁሉ በአምላክ መንግሥት ውስጥ ስታዩና እናንተ ግን በውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ በዚያ ታለቅሳላችሁ፤ ጥርሳችሁንም ታፋጫላችሁ። 29  በተጨማሪም ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ እንዲሁም ከሰሜንና ከደቡብ መጥተው በአምላክ መንግሥት በማዕድ ይቀመጣሉ። 30  ደግሞም ከኋለኞች መካከል ፊተኞች የሚሆኑ፣ ከፊተኞች መካከልም ኋለኞች የሚሆኑ አሉ።” 31  በዚያን ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን መጥተው “ሄሮድስ ሊገድልህ ስለሚፈልግ ከዚህ ውጣና ሂድ” አሉት። 32  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሄዳችሁ ያንን ቀበሮ ‘ዛሬና ነገ አጋንንትን አስወጣለሁ እንዲሁም ሰዎችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ሥራዬን አጠናቅቃለሁ’ በሉት። 33  ይሁንና ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ሊገደል ስለማይችል ዛሬና ነገ እንዲሁም ከነገ ወዲያ ጉዞዬን መቀጠል አለብኝ። 34  ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም፣ ነቢያትን የምትገድል፤ ወደ እሷ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግር፤ ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግኩ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም። 35  እነሆ፣ ቤታችሁ ለእናንተ የተተወ ይሆናል። እላችኋለሁ፣ ‘በይሖዋ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!’ እስክትሉ ድረስ ፈጽሞ አታዩኝም።”
[]
[]
[]
[]
12,003
14  በሌላ ወቅት ኢየሱስ በአንድ የሰንበት ቀን ከፈሪሳውያን መሪዎች ወደ አንዱ ቤት ምግብ ሊበላ በገባ ጊዜ በቤቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች በትኩረት ይከታተሉት ነበር። 2  በዚያም ሰውነት የሚያሳብጥ በሽታ የያዘው አንድ ሰው ከፊት ለፊቱ ነበር። 3  ኢየሱስም ሕግ አዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን “በሰንበት መፈወስ በሕግ ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?” ሲል ጠየቃቸው። 4  እነሱ ግን ዝም አሉ። በዚህ ጊዜ በሰውየው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሰውና አሰናበተው። 5  ከዚያም “ከእናንተ መካከል ልጁ ወይም በሬው በሰንበት ቀን የውኃ ጉድጓድ ውስጥ ቢወድቅ ወዲያውኑ ጎትቶ የማያወጣው ማን ነው?” አላቸው። 6  እነሱም ለዚህ መልስ ሊሰጡ አልቻሉም። 7  ኢየሱስ የተጋበዙት ሰዎች ለራሳቸው የክብር ቦታ ሲመርጡ ተመልክቶ እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ 8  “አንድ ሰው ወደ ሠርግ ሲጠራህ በክብር ቦታ አትቀመጥ። ምናልባት ከአንተ የበለጠ የተከበረ ሰው ተጠርቶ ሊሆን ይችላል። 9  በመሆኑም ሁለታችሁንም የጋበዘው ሰው መጥቶ ‘ቦታውን ለዚህ ሰው ልቀቅለት’ ይልሃል። በዚህ ጊዜ እያፈርክ ወደ ዝቅተኛው ቦታ ትሄዳለህ። 10  አንተ ግን ስትጋበዝ ሄደህ በዝቅተኛው ስፍራ ተቀመጥ፤ የጋበዘህም ሰው ሲመጣ ‘ወዳጄ ሆይ፣ ወደ ላይ ከፍ በል’ ይልሃል። በዚህ ጊዜ አብረውህ በተጋበዙት ሰዎች ሁሉ ፊት ክብር ታገኛለህ። 11  ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ይደረጋልና፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ደግሞ ከፍ ይደረጋል።” 12  ቀጥሎ ደግሞ የጋበዘውን ሰው እንዲህ አለው፦ “የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ጓደኞችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ሀብታም ጎረቤቶችህን አትጥራ። አለዚያ እነሱም ሊጋብዙህና ብድር ሊመልሱልህ ይችላሉ። 13  ሆኖም ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውራንን ጥራ፤ 14  ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ ደስተኛ ትሆናለህ። ምክንያቱም በጻድቃን ትንሣኤ ብድራት ይመለስልሃል።” 15  ከተጋበዙት መካከል አንዱ ይህን ሲሰማ “በአምላክ መንግሥት፣ ከማዕድ የሚበላ ደስተኛ ነው” አለው። 16  ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “አንድ ሰው ትልቅ የራት ግብዣ አዘጋጅቶ ብዙ ሰዎች ጠራ። 17  የራት ግብዣው ሰዓት በደረሰ ጊዜ የተጋበዙትን ሰዎች ‘አሁን ሁሉም ነገር ስለተዘጋጀ ኑ’ ብሎ እንዲጠራቸው ባሪያውን ላከ። 18  ይሁን እንጂ ሁሉም ሰበብ ያቀርቡ ጀመር። የመጀመሪያው ‘እርሻ ስለገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝ፤ ስለዚህ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለው። 19  ሌላውም ‘አምስት ጥማድ በሬዎች ገዝቻለሁ፤ ልፈትናቸው ስለሆነ እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ’ አለ። 20  ሌላኛው ደግሞ ‘ገና ማግባቴ ስለሆነ መምጣት አልችልም’ አለ። 21  ባሪያውም መጥቶ ለጌታው ይህን ነገረው። በዚህ ጊዜ የቤቱ ጌታ ተቆጣ፤ ከዚያም ባሪያውን ‘ፈጥነህ ወደ ከተማው አውራ ጎዳናዎችና ስላች መንገዶች ሄደህ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ ዓይነ ስውራንንና አንካሶችን ወደዚህ አምጣቸው’ አለው። 22  በኋላም ባሪያው ‘ጌታዬ፣ ያዘዝከው ተፈጽሟል፤ ያም ሆኖ አሁንም ቦታ አለ’ አለው። 23  በመሆኑም ጌታው ባሪያውን እንዲህ አለው፦ ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ጎዳናዎችና ወደ ስላች መንገዶች ሄደህ ያገኘሃቸውን ሰዎች በግድ አምጥተህ አስገባ። 24  እላችኋለሁ፣ ከእነዚያ ከተጋበዙት ሰዎች መካከል አንዳቸውም ያዘጋጀሁትን ራት አይቀምሱም።’” 25  ከዚያም እጅግ ብዙ ሕዝብ አብሮት እየተጓዘ ሳለ ወደ እነሱ ዞሮ እንዲህ አላቸው፦ 26  “ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱን፣ እናቱን፣ ሚስቱን፣ ልጆቹን፣ ወንድሞቹንና እህቶቹን ሌላው ቀርቶ የገዛ ራሱን ሕይወት እንኳ የማይጠላ ከሆነ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። 27  የራሱን የመከራ እንጨት ተሸክሞ የማይከተለኝ ሁሉ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። 28  ለምሳሌ ከእናንተ መካከል፣ ግንብ ለመገንባት ፈልጎ ለመጨረስ የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ በመጀመሪያ ተቀምጦ ወጪውን የማያሰላ ማን ነው? 29  እንዲህ ካላደረገ ግን መሠረቱን ከጣለ በኋላ ፍጻሜ ላይ ማድረስ ሊያቅተውና የሚያዩት ሰዎች ሁሉ ሊያፌዙበት ይችላሉ፤ 30  ‘ይህ ሰው መገንባት ጀምሮ ነበር፤ መጨረስ ግን አቃተው’ ይሉታል። 31  ወይም ደግሞ አንድ ንጉሥ ሌላን ንጉሥ ጦርነት ለመግጠም በሚነሳበት ጊዜ 20,000 ሠራዊት አስከትቶ የመጣበትን ንጉሥ በ10,000 ሠራዊት ሊቋቋመው ይችል እንደሆነ ለማወቅ በቅድሚያ ተቀምጦ አይማከርም? 32  መቋቋም የማይችል ከሆነ ሊገጥመው የሚመጣው ንጉሥ ገና ሩቅ ሳለ አምባሳደሮች ልኮ እርቅ ለመፍጠር ይደራደራል። 33  እንደዚሁም ከእናንተ መካከል ያለውን ንብረት ሁሉ የማይሰናበት ፈጽሞ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። 34  “ጨው ጥሩ ነገር እንደሆነ የታወቀ ነው። ሆኖም ጨው ራሱ የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን በምን መመለስ ይቻላል? 35  እንዲህ ያለ ጨው ለአፈር የሚሰጠው ጥቅም የለም፤ ማዳበሪያም ሊሆን አይችልም። በመሆኑም ሰዎች ወደ ውጭ ይጥሉታል። ስለዚህ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
[]
[]
[]
[]
12,004
15  አንድ ቀን ቀራጮችና ኃጢአተኞች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት በዙሪያው ተሰበሰቡ። 2  ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም “ይህ ሰው ኃጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነሱም ጋር ይበላል” እያሉ አጉረመረሙ። 3  በዚህ ጊዜ የሚከተለውን ምሳሌ ነገራቸው፦ 4  “ከእናንተ መካከል 100 በጎች ያሉት ሰው አንዷ ብትጠፋበት 99ኙን በምድረ በዳ ትቶ የጠፋችውን እስኪያገኝ ድረስ አይፈልግም? 5  በሚያገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ላይ ይሸከማታል። 6  ቤት ሲደርስም ጓደኞቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋችውን በጌን ስላገኘኋት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ይላቸዋል። 7  እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ መግባት ከማያስፈልጋቸው 99 ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል። 8  “ወይም ደግሞ አሥር ድራክማ ሳንቲሞች ያሏት አንዲት ሴት አንዱ ድራክማ ቢጠፋባት መብራት አብርታ ቤቷን በመጥረግ እስክታገኘው ድረስ በደንብ አትፈልገውም? 9  ሳንቲሙን ባገኘችው ጊዜም ጓደኞቿንና ጎረቤቶቿን በአንድነት ጠርታ ‘የጠፋብኝን ድራክማ ሳንቲም ስላገኘሁት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ትላቸዋለች። 10  እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በአምላክ መላእክት ዘንድ ደስታ ይሆናል።” 11  ከዚያም እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት። 12  ታናሽየውም ልጅ አባቱን ‘አባቴ ሆይ፣ ከንብረትህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው። በመሆኑም አባትየው ንብረቱን ለልጆቹ አካፈላቸው። 13  ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሽየው ልጅ ያለውን ነገር ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ተጓዘ፤ በዚያም ልቅ የሆነ ሕይወት በመኖር ንብረቱን አባከነ። 14  ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ በዚያ አገር በሙሉ ከባድ ረሃብ ተከሰተ፤ በዚህ ጊዜ ችግር ላይ ወደቀ። 15  ከችግሩም የተነሳ ከዚያ አገር ሰዎች ወደ አንዱ ሄዶ የሙጥኝ አለ፤ ሰውየውም አሳማ እንዲጠብቅለት ወደ ሜዳ ላከው። 16  እሱም አሳማዎቹ የሚመገቡትን ምግብ በልቶ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ ነገር ግን የሚሰጠው አልነበረም። 17  “ወደ ልቦናው ሲመለስ ግን እንዲህ አለ፦ ‘ስንቶቹ የአባቴ ቅጥር ሠራተኞች ምግብ ተርፏቸው እኔ እዚህ በረሃብ ልሞት ነው! 18  ተነስቼ ወደ አባቴ በመሄድ እንዲህ እለዋለሁ፦ “አባቴ ሆይ፣ በአምላክና በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ። 19  ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም። ከቅጥር ሠራተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ።”’ 20  ስለዚህ ተነስቶ ወደ አባቱ ሄደ። ገና ሩቅ ሳለም አባቱ አየው፤ በዚህ ጊዜ አንጀቱ ተላወሰ፤ እየሮጠ ሄዶም አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ሳመው። 21  ከዚያም ልጁ ‘አባቴ ሆይ፣ በአምላክና በአንተ ላይ በደል ፈጽሜአለሁ። ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው። 22  አባትየው ግን ባሪያዎቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ቶሎ በሉ! ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጥታችሁ አልብሱት፤ ለእጁ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት። 23  የሰባውንም ጥጃ አምጥታችሁ እረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት። 24  ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል። ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል።’ ከዚያም ይደሰቱ ጀመር። 25  “በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ በእርሻ ቦታ ነበር፤ ተመልሶ መጥቶ ወደ ቤት በተቃረበ ጊዜ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ። 26  ስለዚህ ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ ነገሩ ምን እንደሆነ ጠየቀው። 27  አገልጋዩም ‘ወንድምህ መጥቷል፤ በደህና ስለመጣም አባትህ የሰባውን ጥጃ አርዶለታል’ አለው። 28  እሱ ግን ተቆጣ፤ ወደ ቤት ለመግባትም አሻፈረኝ አለ። ከዚያም አባቱ ወጥቶ ይለምነው ጀመር። 29  እሱም መልሶ አባቱን እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ እኔ ስንት ዓመት ሙሉ እንደ ባሪያ ሳገለግልህ ኖርኩ፤ መቼም ቢሆን ከትእዛዝህ ዝንፍ ብዬ አላውቅም፤ አንተ ግን ከጓደኞቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ጠቦት እንኳ ሰጥተኸኝ አታውቅም። 30  ሆኖም ሀብትህን ከዝሙት አዳሪዎች ጋር ያወደመው ይህ ልጅህ ገና ከመምጣቱ የሰባውን ጥጃ አረድክለት።’ 31  በዚህ ጊዜ አባቱ እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ ደግሞም የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው። 32  ሆኖም ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኝቷል። ስለዚህ ልንደሰትና ሐሴት ልናደርግ ይገባል።’”
[]
[]
[]
[]
12,005
16  ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ ሀብታም ሰው አንድ መጋቢ ነበረው፤ ይህ ሰው፣ መጋቢው ንብረቱን እያባከነበት እንዳለ የሚገልጽ ክስ ደረሰው። 2  ስለዚህ መጋቢውን ጠራውና ‘ይህ ስለ አንተ የምሰማው ነገር ምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ቤቱን ማስተዳደር ስለማትችል በመጋቢነት ስትሠራበት የነበረውን የሒሳብ መዝገብ አስረክበኝ’ አለው። 3  በዚህ ጊዜ መጋቢው በልቡ እንዲህ አለ፦ ‘ጌታዬ የመጋቢነት ኃላፊነቴን ሊወስድብኝ ነው፤ ታዲያ ምን ባደርግ ይሻላል? እንዳልቆፍር አቅም የለኝም፤ እንዳልለምን ያሳፍረኛል። 4  ቆይ፣ ምን እንደማደርግ አውቃለሁ! ከመጋቢነት ኃላፊነቴ ስነሳ ሰዎች በቤታቸው እንዲቀበሉኝ አንድ ነገር አደርጋለሁ።’ 5  ከዚያም ከጌታው የተበደሩትን ሰዎች አንድ በአንድ በመጥራት የመጀመሪያውን ‘ከጌታዬ የተበደርከው ምን ያህል ነው?’ አለው። 6  እሱም ‘አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ የወይራ ዘይት’ ሲል መለሰለት። መጋቢውም ‘የውል ሰነድህ ይኸውልህ፤ ቁጭ በልና ቶሎ ብለህ 50 ብለህ ጻፍ’ አለው። 7  ቀጥሎም ሌላውን ‘አንተስ፣ የተበደርከው ምን ያህል ነው?’ አለው። እሱም ‘አንድ መቶ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ’ አለው። መጋቢውም ‘የውል ሰነድህ ይኸውልህ፤ 80 ብለህ ጻፍ’ አለው። 8  ጌታውም መጋቢው ዓመፀኛ ቢሆንም እንኳ አርቆ በማሰብ ባደረገው ነገር አደነቀው፤ ምክንያቱም የዚህ ሥርዓት ልጆች በእነሱ ትውልድ ካሉት ሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ረገድ ከብርሃን ልጆች ይበልጥ ብልሆች ናቸው። 9  “ደግሞም እላችኋለሁ፦ በዓመፅ ሀብት ለራሳችሁ ወዳጆች አፍሩ፤ እነሱም የዓመፅ ሀብት ሲያልቅ በዘላለማዊ መኖሪያ ይቀበሏችኋል። 10  በትንሽ ነገር ታማኝ የሆነ ሰው በብዙ ነገርም ታማኝ ነው፤ በትንሽ ነገር ታማኝ ያልሆነ ሰው ደግሞ በብዙ ነገርም ታማኝ አይሆንም። 11  ስለዚህ በዓመፅ ሀብት ታማኝ ሆናችሁ ካልተገኛችሁ እውነተኛውን ሀብት ማን በአደራ ይሰጣችኋል? 12  የሌላ ሰው በሆነው ነገር ታማኝ ሆናችሁ ካልተገኛችሁ ለእናንተ የታሰበውን ማን ይሰጣችኋል? 13  ለሁለት ጌቶች ባሪያ መሆን የሚችል አገልጋይ የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል ወይም አንዱን ደግፎ ሌላውን ይንቃል። ለአምላክም ለሀብትም በአንድ ጊዜ ባሪያ መሆን አትችሉም።” 14  ገንዘብ ወዳድ የሆኑት ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሲናገር ሰምተው ያፌዙበት ጀመር። 15  በመሆኑም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ በሰዎች ፊት ጻድቅ መስላችሁ ትቀርባላችሁ፤ አምላክ ግን ልባችሁን ያውቃል። በሰዎች ፊት ከፍ ተደርጎ የሚታየው ነገር በአምላክ ፊት አስጸያፊ ነውና። 16  “ሕጉም ሆነ የነቢያት ቃል እስከ ዮሐንስ ድረስ ሲነገሩ ቆይተዋል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የአምላክ መንግሥት ምሥራች እየታወጀ ነው፤ የተለያዩ ዓይነት ሰዎችም ወደዚያ ለመግባት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ነው። 17  እንደ እውነቱ ከሆነ ከሕጉ የአንዷ ፊደል ጭረት ሳትፈጸም ከምትቀር ሰማይና ምድር ቢያልፉ ይቀላል። 18  “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ባሏ የፈታትንም ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል። 19  “አንድ ሀብታም ሰው ነበር፤ ይህ ሰው ሐምራዊ ልብስና በፍታ ይለብስ የነበረ ከመሆኑም በላይ ዕለት ተዕለት በደስታና በቅንጦት ይኖር ነበር። 20  ይሁን እንጂ እዚህ ሰው ደጃፍ ላይ እያመጡ የሚያስቀምጡት መላ ሰውነቱን ቁስል የወረሰው አልዓዛር የሚባል አንድ ለማኝ ነበር፤ 21  እሱም ከሀብታሙ ማዕድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ በልቶ ለመጥገብ ይመኝ ነበር። ውሾችም ሳይቀር እየመጡ ቁስሉን ይልሱ ነበር። 22  ከጊዜ በኋላ ለማኙ ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት። “ሀብታሙም ሰው ሞተና ተቀበረ። 23  በመቃብርም ሆኖ እየተሠቃየ ሳለ አሻቅቦ ሲመለከት ከሩቅ አብርሃምንና በእቅፉ ያለውን አልዓዛርን አየ። 24  በዚህ ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ‘አብርሃም አባት ሆይ፣ በዚህ የሚንቀለቀል እሳት እየተሠቃየሁ ስለሆነ እባክህ ራራልኝና አልዓዛር የጣቱን ጫፍ ውኃ ውስጥ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ ላከው’ አለ። 25  አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፣ አንተ በሕይወት ዘመንህ መልካም ነገሮችን ሁሉ እንደተቀበልክ፣ አልዓዛር ግን መጥፎ ነገሮች እንደደረሱበት አስታውስ። አሁን ግን እሱ እዚህ ሲጽናና አንተ ትሠቃያለህ። 26  ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ከእኛ ወደ እናንተ መሻገር የሚፈልጉ መሻገር እንዳይችሉ እንዲሁም ሰዎች ከእናንተ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል ተደርጓል።’ 27  በዚህ ጊዜ ሀብታሙ ሰው እንዲህ አለ፦ ‘አባት ሆይ፣ እንደዚያ ከሆነ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትልከው እለምንሃለሁ፤ 28  አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነሱም ወደዚህ የሥቃይ ስፍራ እንዳይገቡ በሚገባ ይመሥክርላቸው።’ 29  አብርሃም ግን ‘ሙሴና ነቢያት አሉላቸው፤ እነሱን ይስሙ’ አለው። 30  እሱም ‘አይ፣ እንደሱ አይደለም፤ አብርሃም አባት ሆይ፣ አንድ ሰው ከሞት ተነስቶ ወደ እነሱ ቢሄድ ንስሐ ይገባሉ’ አለ። 31  አብርሃም ግን ‘ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ አንድ ሰው ከሞት ቢነሳም አምነው አይቀበሉም’ አለው።”
[]
[]
[]
[]
12,006
17  ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ሰዎችን የሚያሰናክሉ ነገሮች መከሰታቸው የማይቀር ነው። ሆኖም ለመሰናክሉ ምክንያት ለሚሆነው ለዚያ ሰው ወዮለት! 2  ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል። 3  ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ከተጸጸተም ይቅር በለው። 4  በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህ እንኳ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ሰባት ጊዜ ወደ አንተ ከመጣ ይቅር ልትለው ይገባል።” 5  በዚህ ጊዜ ሐዋርያቱ ጌታን “እምነት ጨምርልን” አሉት። 6  ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰናፍጭ ዘር የሚያህል እምነት ካላችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ ባሕሩ ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዛችኋል። 7  “ከእናንተ መካከል አራሽ ወይም እረኛ የሆነ ባሪያ ያለው ሰው ቢኖር፣ ባሪያው ከእርሻ ሲመለስ ‘ቶሎ ናና ወደ ማዕድ ቅረብ’ ይለዋል? 8  ከዚህ ይልቅ ‘ራቴን አዘጋጅልኝ፤ በልቼና ጠጥቼ እስክጨርስም ድረስ አሸርጠህ አገልግለኝ፤ ከዚያ በኋላ መብላትና መጠጣት ትችላለህ’ አይለውም? 9  ባሪያው የተሰጠውን ሥራ በማከናወኑ ጌታው የሚያመሰግነው ይመስላችኋል? 10  በተመሳሳይ እናንተም የተሰጣችሁን ሥራ ሁሉ ባከናወናችሁ ጊዜ ‘ምንም የማንጠቅም ባሪያዎች ነን። ያደረግነው ልናደርገው የሚገባንን ነገር ነው’ በሉ።” 11  ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደ ሳለ በሰማርያና በገሊላ መካከል አለፈ። 12  ወደ አንድ መንደር እየገባም ሳለ የሥጋ ደዌ የያዛቸው አሥር ሰዎች አዩት፤ እነሱም በርቀት ቆሙ። 13  ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ “ኢየሱስ፣ መምህር፣ ምሕረት አድርግልን!” አሉ። 14  እሱም ባያቸው ጊዜ “ሄዳችሁ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ” አላቸው። ከዚያም እየሄዱ ሳሉ ነጹ። 15  ከእነሱ አንዱ እንደተፈወሰ ባየ ጊዜ አምላክን በታላቅ ድምፅ እያመሰገነ ተመለሰ። 16  ኢየሱስ እግር ላይ ተደፍቶም አመሰገነው። ሰውየውም ሳምራዊ ነበር። 17  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ “የነጹት አሥሩም አይደሉም እንዴ? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ? 18  ከዚህ ከባዕድ አገር ሰው በስተቀር አምላክን ለማመስገን የተመለሰ ሌላ አንድም ሰው የለም?” 19  ከዚያም ሰውየውን “ተነስና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው። 20  ፈሪሳውያን የአምላክ መንግሥት መቼ እንደሚመጣ ሲጠይቁት እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “የአምላክ መንግሥት በግልጽ በሚታይ ሁኔታ አይመጣም፤ 21  ሰዎችም ‘እነሆ እዚህ ነው!’ ወይም ‘እዚያ ነው!’ አይሉም። እነሆ፣ የአምላክ መንግሥት በመካከላችሁ ነውና።” 22  ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትመኙበት ጊዜ ይመጣል፤ ግን አታዩትም። 23  ሰዎችም ‘እዚያ ነው!’ ወይም ‘እዚህ ነው!’ ይሏችኋል። ነገር ግን አትሂዱ ወይም አትከተሏቸው። 24  ምክንያቱም መብረቅ ከአንዱ የሰማይ ክፍል እስከ ሌላኛው የሰማይ ክፍል እንደሚያበራ ሁሉ የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንዲሁ ይሆናል። 25  በመጀመሪያ ግን ብዙ መከራ መቀበሉና በዚህ ትውልድ ተቀባይነት ማጣቱ የግድ ነው። 26  በተጨማሪም በኖኅ ዘመን እንደተከሰተው ሁሉ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል፦ 27  ኖኅ ወደ መርከቡ እስከገባበትና የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉንም እስካጠፋበት ቀን ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ እንዲሁም ወንዶች ያገቡ፣ ሴቶችም ይዳሩ ነበር። 28  በተመሳሳይም በሎጥ ዘመን እንደተከሰተው ሁሉ እንዲሁ ይሆናል፦ ሰዎች ይበሉ፣ ይጠጡ፣ ይገዙ፣ ይሸጡ፣ ይተክሉና ቤቶችን ይገነቡ ነበር። 29  ሆኖም ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ከሰማይ እሳትና ድኝ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋቸው። 30  የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንዲሁ ይሆናል። 31  “በዚያን ቀን በጣሪያ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ ለመውሰድ አይውረድ፤ እርሻም ላይ ያለ ሰው በኋላው ያለውን ነገር ለመውሰድ አይመለስ። 32  የሎጥን ሚስት አስታውሱ። 33  ሕይወቱን ጠብቆ ለማቆየት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ሕይወቱን የሚያጣት ሁሉ ግን በሕይወት ጠብቆ ያቆያታል። 34  እላችኋለሁ፣ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ላይ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላኛው ግን ይተዋል። 35  ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላኛዋ ግን ትተዋለች።” 36  —— 37  እነሱም መልሰው “ጌታ ሆይ፣ የት?” አሉት። እሱም “በድን ባለበት ንስሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው።
[]
[]
[]
[]
12,007
18  ከዚያም ምንጊዜም ተስፋ ሳይቆርጡ የመጸለይን አስፈላጊነት በተመለከተ ለደቀ መዛሙርቱ አንድ ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፤ 2  እንዲህም አላቸው፦ “በአንዲት ከተማ አምላክን የማይፈራና ሰውን የማያከብር አንድ ዳኛ ነበር። 3  በዚያች ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ በየጊዜው ወደ እሱ እየሄደች ‘ከባላጋራዬ ጋር ለምከራከርበት ጉዳይ ፍረድልኝ’ ትለው ነበር። 4  ይሁንና ዳኛው ለተወሰነ ጊዜ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ፤ በኋላ ግን በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፦ ‘ምንም እንኳ አምላክን የማልፈራ፣ ሰውንም የማላከብር ብሆን 5  ይህች መበለት ሁልጊዜ እየመጣች ስለምታስቸግረኝ ፍትሕ እንድታገኝ አደርጋለሁ፤ አለዚያ በየጊዜው እየመጣች ትነዘንዘኛለች።’” 6  ከዚያም ጌታ እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ዳኛው ዓመፀኛ ቢሆንም ምን እንዳለ ልብ በሉ! 7  ታዲያ አምላክ በትዕግሥት የሚይዛቸውና ቀን ከሌት ወደ እሱ የሚጮኹት ምርጦቹ ፍትሕ እንዲያገኙ አያደርግም? 8  እላችኋለሁ፣ በቶሎ ፍትሕ እንዲያገኙ ያደርጋል። ሆኖም የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ በእርግጥ እምነት ያገኝ ይሆን?” 9  በራሳቸው ጽድቅ ለሚታመኑና ሌሎችን በንቀት ዓይን ለሚመለከቱ ደግሞ የሚከተለውን ምሳሌ ተናገረ፦ 10  “ሁለት ሰዎች ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፤ አንደኛው ፈሪሳዊ፣ ሌላኛው ደግሞ ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር። 11  ፈሪሳዊው ቆሞ በልቡ እንዲህ ሲል ይጸልይ ጀመር፦ ‘አምላክ ሆይ፣ እንደ ሌላው ሰው ቀማኛ፣ ዓመፀኛ፣ አመንዝራ፣ በተለይ ደግሞ እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ። 12  በሳምንት ሁለቴ እጾማለሁ፤ ከማገኘውም ነገር ሁሉ አሥራት እሰጣለሁ።’ 13  ቀረጥ ሰብሳቢው ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ለማየትም እንኳ አልደፈረም፤ እንዲያውም ‘አምላክ ሆይ፣ ኃጢአተኛ ለሆንኩት ለእኔ ቸርነት አድርግልኝ’ እያለ ደረቱን ይደቃ ነበር። 14  እላችኋለሁ፣ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይሄኛው ሰው ይበልጥ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ምክንያቱም ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሁሉ ግን ከፍ ይደረጋል።” 15  ሰዎችም ኢየሱስ እጁን እንዲጭንባቸው ሕፃናትን ወደ እሱ ያመጡ ጀመር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ይህን ሲያዩ ገሠጿቸው። 16  ይሁን እንጂ ኢየሱስ ሕፃናቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አለ፦ “ልጆቹ ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ የአምላክ መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ነውና። 17  እውነት እላችኋለሁ፣ የአምላክን መንግሥት እንደ አንድ ትንሽ ልጅ ሆኖ የማይቀበል ሁሉ ፈጽሞ ወደዚህ መንግሥት አይገባም።” 18  ከአይሁዳውያን አለቆችም አንዱ “ጥሩ መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” ሲል ጠየቀው። 19  ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “ለምን ጥሩ ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከአምላክ በቀር ጥሩ የለም። 20  ‘አታመንዝር፣ አትግደል፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመሥክር፣ አባትህንና እናትህን አክብር’ የሚሉትን ትእዛዛት ታውቃለህ።” 21  ሰውየውም “እነዚህን ሁሉ ከልጅነቴ ጀምሮ ስጠብቅ ኖሬአለሁ” አለ። 22  ኢየሱስ ይህን ከሰማ በኋላ “አሁንም አንድ የሚቀርህ ነገር አለ፤ ያለህን ነገር ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድሆች አከፋፍል፤ በሰማያትም ውድ ሀብት ታገኛለህ፤ ደግሞም መጥተህ ተከታዬ ሁን” አለው። 23  ሰውየው በጣም ሀብታም ስለነበረ ይህን ሲሰማ እጅግ አዘነ። 24  ኢየሱስም ሰውየውን ተመልክቶ እንዲህ አለ፦ “ገንዘብ ላላቸው ሰዎች ወደ አምላክ መንግሥት መግባት ምንኛ አስቸጋሪ ነው! 25  እንዲያውም ሀብታም ሰው ወደ አምላክ መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀልላል።” 26  ይህን የሰሙ ሰዎች “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ። 27  እሱም “በሰዎች ዘንድ የማይቻል፣ በአምላክ ዘንድ ይቻላል” አለ። 28  ጴጥሮስ ግን “እነሆ፣ እኛ ያለንን ነገር ትተን ተከትለንሃል” አለ። 29  ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ለአምላክ መንግሥት ሲል ቤትን ወይም ሚስትን ወይም ወንድሞችን ወይም ወላጆችን ወይም ልጆችን የተወ ሁሉ፣ 30  አሁን በዚህ ዘመን ብዙ እጥፍ፣ በሚመጣው ሥርዓት ደግሞ የዘላለም ሕይወት ያገኛል።” 31  ከዚያም አሥራ ሁለቱን ገለል አድርጎ በመውሰድ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ! ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰውን ልጅ በተመለከተም በነቢያት የተጻፉት ነገሮች ሁሉ ይፈጸማሉ። 32  ለምሳሌ ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ ያፌዙበታል፤ ያንገላቱታል እንዲሁም ይተፉበታል። 33  ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤ በሦስተኛው ቀን ግን ይነሳል።” 34  ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ መካከል አንዱንም አልተረዱም፤ የተናገረው ቃል ተሰውሮባቸው ነበርና፤ የተባለውም ነገር አልገባቸውም። 35  ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ እየተቃረበ ሳለ አንድ ዓይነ ስውር መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር። 36  ዓይነ ስውሩም ብዙ ሕዝብ በዚያ ሲያልፍ ሰምቶ ስለ ሁኔታው ይጠይቅ ጀመር። 37  ሰዎቹም “የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ እያለፈ ነው!” ብለው ነገሩት። 38  በዚህ ጊዜ “ኢየሱስ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” ሲል ጮኸ። 39  ከፊት ከፊት የሚሄዱትም ሰዎች ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” እያለ ይበልጥ መጮኹን ቀጠለ። 40  ኢየሱስም ቆመና ሰውየውን ወደ እሱ እንዲያመጡት አዘዘ። ሰውየው ወደ እሱ በቀረበ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ 41  “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” እሱም “ጌታ ሆይ፣ የዓይኔን ብርሃን መልስልኝ” አለው። 42  ስለዚህ ኢየሱስ “የዓይንህ ብርሃን ይመለስልህ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው። 43  ወዲያውም የዓይኑ ብርሃን ተመለሰለት፤ አምላክን እያመሰገነም ይከተለው ጀመር። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ አምላክን አወደሱ።
[]
[]
[]
[]
12,008
19  ከዚያም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ እያለፈ ነበር። 2  በዚያም ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሀብታም ሰው የነበረ ሲሆን ይህ ሰው የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ ነበር። 3  እሱም ኢየሱስ የሚባለው ማን እንደሆነ ለማየት ይፈልግ ነበር፤ ሆኖም አጭር በመሆኑ ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ማየት አልቻለም። 4  ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለነበር ዘኬዎስ ሮጦ ወደ ፊት በመሄድ እሱን ለማየት አንድ የሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። 5  ኢየሱስ እዚያ ቦታ በደረሰ ጊዜ ቀና ብሎ ተመለከተውና “ዘኬዎስ፣ ዛሬ ወደ አንተ ቤት ስለምመጣ ቶሎ ውረድ” አለው። 6  በዚህ ጊዜ በፍጥነት ወርዶ ደስ እያለው በእንግድነት ተቀበለው። 7  ሰዎቹ ይህን ባዩ ጊዜ “ኃጢአተኛ ሰው ቤት ሊስተናገድ ገባ” ብለው ሁሉም አጉተመተሙ። 8  ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን “ጌታ ሆይ፣ ካለኝ ሀብት ግማሹን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ከሰው የቀማሁትንም ሁሉ አራት እጥፍ እመልሳለሁ” አለው። 9  በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ይህም ሰው የአብርሃም ልጅ ስለሆነ ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን መጥቷል። 10  ምክንያቱም የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ለመፈለግና ለማዳን ነው።” 11  እነሱም እነዚህን ነገሮች እየሰሙ ሳሉ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ ይህን የተናገረው ኢየሩሳሌም ሲደርሱ የአምላክ መንግሥት ወዲያውኑ የሚገለጥ ስለመሰላቸው ነው። 12  ስለዚህ እንዲህ አለ፦ “አንድ መስፍን ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተረክቦ ለመመለስ ወደ ሩቅ አገር ሊሄድ ተነሳ። 13  ከባሪያዎቹ መካከል አሥሩን ጠርቶ አሥር ምናን ሰጣቸውና ‘እስክመጣ ድረስ ነግዱበት’ አላቸው። 14  የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ስለነበር እሱ ከሄደ በኋላ ‘ይህ ሰው በእኛ ላይ እንዲነግሥ አንፈልግም’ ብለው እንዲነግሩላቸው መልእክተኞች ላኩ። 15  “ከጊዜ በኋላ ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተረክቦ ሲመጣ ገንዘብ የሰጣቸው ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ለማወቅ አስጠራቸው። 16  በመሆኑም የመጀመሪያው ቀርቦ ‘ጌታዬ፣ ምናንህ አሥር ምናን ትርፍ አስገኝቷል’ አለው። 17  ጌታው ‘ጎበዝ፣ አንተ ጥሩ ባሪያ! በጣም አነስተኛ በሆነው ነገር ታማኝ ሆነህ ስለተገኘህ በአሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ተሰጥቶሃል’ አለው። 18  ሁለተኛው ደግሞ ቀርቦ ‘ጌታዬ፣ ምናንህ አምስት ምናን አስገኝቷል’ አለ። 19  ይሄኛውንም ‘አንተም በአምስት ከተሞች ላይ ተሹመሃል’ አለው። 20  ሆኖም ሌላኛው መጥቶ እንዲህ አለ፦ ‘ጌታዬ፣ በጨርቅ ጠቅልዬ የደበቅኩት ምናንህ ይኸውልህ። 21  ይህን ያደረግኩት ጨካኝ ሰው ስለሆንክ ፈርቼህ ነው፤ አንተ ያላስቀመጥከውን የምትወስድ፣ ያልዘራኸውንም የምታጭድ ሰው ነህ።’ 22  ጌታውም እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፣ በራስህ ቃል እፈርድብሃለሁ። ያላስቀመጥኩትን የምወስድ፣ ያልዘራሁትንም የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደሆንኩ ታውቅ ኖሯል ማለት ነው? 23  ታዲያ ገንዘቤን ለምን ለገንዘብ ለዋጮች አልሰጠህም? እንደዚህ አድርገህ ቢሆን ኖሮ ስመጣ ከነወለዱ እወስደው ነበር።’ 24  “ከዚያም በዚያ ቆመው የነበሩትን ሰዎች ‘ምናኑን ውሰዱበትና አሥር ምናን ላለው ስጡት’ አላቸው። 25  እነሱ ግን ‘ጌታ ሆይ፣ እሱ እኮ አሥር ምናን አለው’ አሉት። እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ 26  ‘እላችኋለሁ፣ ላለው ሁሉ ተጨማሪ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ሰው ላይ ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። 27  በተጨማሪም በእነሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡና በፊቴ ግደሏቸው።’” 28  ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ጉዞውን በመቀጠል ወደ ኢየሩሳሌም አቀና። 29  ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ ወደሚገኙት ወደ ቤተፋጌ እና ወደ ቢታንያ በተቃረበ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ላካቸው፤ 30  እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ ወደ መንደሩ ከገባችሁም በኋላ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ ውርንጭላ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደዚህ አምጡት። 31  ይሁን እንጂ ማንም ሰው ‘የምትፈቱት ለምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ ‘ጌታ ይፈልገዋል’ ብላችሁ ንገሩት።” 32  የተላኩትም ሄደው ልክ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት። 33  ውርንጭላውን እየፈቱ ሳሉ ግን ባለቤቶቹ “ውርንጭላውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። 34  እነሱም “ጌታ ይፈልገዋል” አሉ። 35  ከዚያም ውርንጭላውን ወደ ኢየሱስ ወሰዱት፤ መደረቢያቸውንም በውርንጭላው ላይ ጣል አድርገው ኢየሱስን በላዩ አስቀመጡት። 36  እየተጓዘም ሳለ መደረቢያቸውን በመንገዱ ላይ ያነጥፉ ነበር። 37  ከደብረ ዘይት ተራራ ቁልቁል ወደሚወስደው መንገድ እንደተቃረበ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደቀ መዛሙርቱ ባዩአቸው ተአምራት መደሰትና አምላክን በታላቅ ድምፅ ማወደስ ጀመሩ፤ 38  እንዲህም ይሉ ነበር፦ “በይሖዋ ስም ንጉሥ ሆኖ የሚመጣ የተባረከ ነው! በሰማይ ሰላም፣ በአርያም ላለውም ክብር ይሁን!” 39  በሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያን ግን “መምህር፣ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው እንጂ” አሉት። 40  እሱ ግን መልሶ “እላችኋለሁ፣ እነዚህ ዝም ቢሉ እንኳ ድንጋዮች ይጮኻሉ” አላቸው። 41  ወደ ኢየሩሳሌም በተቃረበ ጊዜም ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤ 42  እንዲህም አለ፦ “አንቺ፣ አዎ አንቺ ራስሽ፣ ሰላም የሚያስገኙልሽን ነገሮች ምነው ዛሬ በተረዳሽ ኖሮ፤ አሁን ግን ከዓይኖችሽ ተሰውረዋል። 43  ምክንያቱም ጠላቶችሽ በሾለ እንጨት በዙሪያሽ ቅጥር ቀጥረው አንቺን የሚከቡበትና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣል። 44  አንቺንና በውስጥሽ የሚኖሩትን ልጆችሽን ፈጥፍጠው ከአፈር ይደባልቃሉ፤ በአንቺ ውስጥም ሳያፈርሱ እንደተነባበረ የሚተዉት ድንጋይ አይኖርም፤ ምክንያቱም በአንቺ ላይ ምርመራ የተካሄደበትን ጊዜ አልተገነዘብሽም።” 45  ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ ገብቶ በዚያ የሚሸጡትን ያስወጣ ጀመር፤ 46  እንዲህም አላቸው፦ “‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል’ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት።” 47  እሱም በየዕለቱ በቤተ መቅደሱ ማስተማሩን ቀጠለ። ሆኖም የካህናት አለቆችና ጸሐፍት እንዲሁም የሕዝቡ መሪዎች ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፤ 48  ይሁንና ሕዝቡ ሁሉ እሱን ለመስማት ከአጠገቡ ስለማይለይ ምን እንደሚያደርጉ ግራ ገባቸው።
[]
[]
[]
[]
12,009
2  በዚያ ዘመን፣ አውግስጦስ ቄሳር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲመዘገብ አዋጅ አወጣ። 2  (ይህ የመጀመሪያ ምዝገባ የተካሄደው ቄሬኔዎስ የሶርያ አገረ ገዢ በነበረበት ጊዜ ነው።) 3  ሁሉም ሰው ለመመዝገብ ወደየራሱ ከተማ ሄደ። 4  ዮሴፍም ከዳዊት ቤትና ወገን ስለነበር በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነስቶ በይሁዳ ወዳለች ቤተልሔም ተብላ ወደምትጠራ የዳዊት ከተማ ወጣ። 5  ለመመዝገብ የሄደውም በታጨችለት መሠረት ካገባትና የመውለጃ ጊዜዋ ከተቃረበው ከማርያም ጋር ነበር። 6  በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ። 7  የበኩር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅም ወለደች፤ በእንግዶች ማረፊያም፣ ቦታ ስላላገኙ ልጁን በጨርቅ ጠቅልላ በግርግም ውስጥ አስተኛችው። 8  በዚያው ክልል፣ ሌሊት ሜዳ ላይ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። 9  በድንገት የይሖዋ መልአክ መጥቶ በፊታቸው ቆመ፤ የይሖዋም ክብር በዙሪያቸው አንጸባረቀ፤ እነሱም በታላቅ ፍርሃት ተዋጡ። 10  መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፤ እነሆ፣ ለሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚያስገኝ ምሥራች እነግራችኋለሁ፤ 11  በዛሬው ዕለት በዳዊት ከተማ አዳኝ ተወልዶላችኋልና፤ እሱም ጌታ ክርስቶስ ነው። 12  ይህም ምልክት ይሁናችሁ፦ አንድ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ።” 13  በድንገት ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ታዩ፤ አምላክንም እያመሰገኑ እንዲህ አሉ፦ 14  “በሰማያት ለአምላክ ክብር ይሁን፤ በምድርም አምላክ ሞገስ ለሚያሳያቸው ሰዎች ሰላም ይሁን።” 15  መላእክቱም ከእነሱ ተለይተው ወደ ሰማይ ከሄዱ በኋላ እረኞቹ እርስ በርሳቸው “አሁኑኑ ወደ ቤተልሔም ሄደን ይሖዋ በገለጠልን መሠረት በዚያ የተፈጸመውን ነገር ማየት አለብን” ተባባሉ። 16  በፍጥነትም ሄደው ማርያምንና ዮሴፍን አገኟቸው፤ ሕፃኑም በግርግም ተኝቶ ነበር። 17  ይህን ባዩ ጊዜ ስለ ሕፃኑ የተነገራቸውን መልእክት አወሩ። 18  ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር ተደነቁ፤ 19  ማርያም ግን የሰማቻቸውን ነገሮች በውስጧ ይዛ በልቧ ታሰላስል ነበር። 20  እረኞቹም የሰሙትና ያዩት ነገር ሁሉ ልክ እንደተነገራቸው ሆኖ ስላገኙት አምላክን እያከበሩና እያወደሱ ተመለሱ። 21  ከስምንት ቀን በኋላ፣ ሕፃኑ የሚገረዝበት ጊዜ ሲደርስ ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ባወጣለት ስም ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ። 22  በተጨማሪም በሙሴ ሕግ መሠረት የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ ሕፃኑን በይሖዋ ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት መጡ፤ 23  ይህን ያደረጉት “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ ለይሖዋ የተቀደሰ መሆን አለበት” ተብሎ በይሖዋ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ነው። 24  ደግሞም የይሖዋ ሕግ በሚያዘው መሠረት “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች” መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። 25  እነሆም፣ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እሱም አምላክ እስራኤልን የሚያጽናናበትን ጊዜ የሚጠባበቅ ጻድቅና ለአምላክ ያደረ ሰው ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእሱ ላይ ነበር። 26  በተጨማሪም ይሖዋ የቀባውን ሳያይ እንደማይሞት አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ገልጦለት ነበር። 27  እሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መጣ፤ ሕጉ ለልጁ እንዲደረግ በሚያዘው የተለመደ ሥርዓት መሠረት ወላጆቹ ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘውት በገቡ ጊዜ 28  ስምዖን ሕፃኑን ተቀብሎ አቀፈውና አምላክን አወደሰ፤ እንዲህም አለ፦ 29  “ሉዓላዊው ጌታ ሆይ፣ በተናገርከው ቃል መሠረት አሁን ባሪያህን በሰላም እንዲያርፍ ታደርገዋለህ፤ 30  ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤ 31  ይህም በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፤ 32  ደግሞም ብሔራትን የጋረደውን መሸፈኛ የሚገልጥ ብርሃን እንዲሁም የሕዝብህ የእስራኤል ክብር ነው።” 33  አባቱና እናቱም ስለ ልጁ በሚነገሩት ነገሮች ይደነቁ ነበር። 34  ስምዖንም እነሱን ከባረካቸው በኋላ እናቱን ማርያምን እንዲህ አላት፦ “እነሆ፣ ይህ ልጅ በእስራኤል ለብዙዎች መውደቅም ሆነ መነሳት ምክንያት ይሆናል፤ እንዲሁም ብዙዎች የሚቃወሙት ምልክት ይሆናል፤ 35  ይህም የሚሆነው በብዙዎች ልብ ውስጥ ያለው ሐሳብ ይገለጥ ዘንድ ነው፤ በአንቺም ውስጥ ትልቅ ሰይፍ ያልፋል።” 36  ከአሴር ነገድ፣ የፋኑኤል ልጅ የሆነች ሐና የምትባል ነቢዪት ነበረች። ይህች ሴት በዕድሜ የገፋች ነበረች፤ ካገባች በኋላ ከባሏ ጋር የኖረችው ለሰባት ዓመት ብቻ ነበር፤ 37  በዚህ ጊዜ 84 ዓመት የሆናት መበለት ነበረች። ሌትና ቀንም በጾምና በምልጃ ቅዱስ አገልግሎት እያቀረበች ከቤተ መቅደስ ፈጽሞ አትጠፋም ነበር። 38  በዚያን ሰዓትም ቀርባ አምላክን ታመሰግን ጀመር፤ አምላክ ኢየሩሳሌምን ነፃ ያወጣል ብለው ለሚጠባበቁም ሁሉ ስለ ሕፃኑ መናገር ጀመረች። 39  የይሖዋ ሕግ በሚለው መሠረት ሁሉንም ነገር ከፈጸሙ በኋላ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ መኖሪያ ከተማቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ። 40  ሕፃኑም እያደገና እየጠነከረ እንዲሁም በጥበብ እየተሞላ ሄደ፤ የአምላክም ሞገስ በእሱ ላይ ነበር። 41  ወላጆቹም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም የመሄድ ልማድ ነበራቸው። 42  ኢየሱስ የ12 ዓመት ልጅ ሳለ እንደተለመደው በዓሉን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ። 43  በዓሉ የሚከበርባቸው ቀናት ተጠናቀው መመለስ በጀመሩ ጊዜ ኢየሱስ እዚያው ኢየሩሳሌም ቀረ፤ ወላጆቹም ይህን አላስተዋሉም ነበር። 44  አብረዋቸው ከሚጓዙት ሰዎች ጋር ያለ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላም ዘመዶቻቸውና የሚያውቋቸው ሰዎች ጋ ይፈልጉት ጀመር። 45  ባጡት ጊዜ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እሱን ለማግኘትም ብዙ ደከሙ። 46  በመጨረሻም ከሦስት ቀን በኋላ ቤተ መቅደሱ ውስጥ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲያዳምጣቸውና ሲጠይቃቸው አገኙት። 47  በዚያ የነበሩት ሰዎችም ሁሉ በመረዳት ችሎታውና በመልሱ ተደንቀው ያዳምጡት ነበር። 48  ወላጆቹም ባዩት ጊዜ ተገረሙ፤ እናቱም “ልጄ፣ ምነው እንዲህ አደረግከን? እኔና አባትህ እኮ በጣም ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” አለችው። 49  እሱ ግን “ለምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት መሆን እንደሚገባኝ አታውቁም?” አላቸው። 50  እነሱ ግን ምን እያላቸው እንዳለ አልገባቸውም። 51  ከዚያም ኢየሱስ አብሯቸው ወደ ናዝሬት ተመለሰ፤ እንደ ወትሮውም ይገዛላቸው ነበር። እናቱም የተባሉትን ነገሮች ሁሉ በልቧ ትይዝ ነበር። 52  ኢየሱስም በአካልና በጥበብ እያደገ እንዲሁም በአምላክና በሰው ፊት ይበልጥ ሞገስ እያገኘ ሄደ።
[]
[]
[]
[]
12,010
20  አንድ ቀን ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሕዝቡን እያስተማረና ምሥራቹን እያወጀ ሳለ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር መጡ፤ 2  ከዚያም “እስቲ ንገረን፤ እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ይህን ሥልጣን የሰጠህስ ማን ነው?” አሉት። 3  እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም መልሱልኝ፦ 4  ዮሐንስ የማጥመቅ ሥልጣን ያገኘው ከአምላክ ነው ወይስ ከሰው?” 5  እነሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ “‘ከአምላክ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ 6  ‘ከሰው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ ነው ብለው ስለሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።” 7  ስለዚህ ‘ከየት እንደሆነ አናውቅም’ ብለው መለሱለት። 8  ኢየሱስም “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው። 9  ከዚያም ለሕዝቡ የሚከተለውን ምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ አለማና ለገበሬዎች አከራየ፤ ወደ ሌላ አገር ሄዶም ረዘም ላለ ጊዜ ቆየ። 10  ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን እንዲልኩለት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ። ይሁንና ገበሬዎቹ ባሪያውን ከደበደቡት በኋላ ባዶ እጁን ሰደዱት። 11  እሱ ግን በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። ይሄኛውንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን ሰደዱት። 12  አሁንም ሦስተኛ ባሪያ ላከ፤ እሱንም ካቆሰሉት በኋላ አውጥተው ጣሉት። 13  በዚህ ጊዜ የወይን እርሻው ባለቤት ‘ምን ባደርግ ይሻላል? የምወደውን ልጄን እልካለሁ። መቼም እሱን ያከብሩታል’ አለ። 14  ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይሄ ነው። ርስቱ የእኛ እንዲሆን እንግደለው’ ተባባሉ። 15  ከዚያም ከወይን እርሻው ጎትተው በማውጣት ገደሉት። ታዲያ የወይኑ እርሻ ባለቤት ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል? 16  ይመጣና እነዚህን ገበሬዎች ይገድላል፤ የወይን እርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል።” ሕዝቡም ይህን ሲሰሙ “ይህስ ከቶ አይሁን!” አሉ። 17  ኢየሱስም እነሱን ትኩር ብሎ በመመልከት እንዲህ አለ፦ “ታዲያ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እሱ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ሆነ’ ተብሎ የተጻፈው ትርጉሙ ምንድን ነው? 18  በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል። ድንጋዩ የሚወድቅበት ሰው ሁሉ ደግሞ ይደቅቃል።” 19  በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና የካህናት አለቆች ይህን ምሳሌ የተናገረው እነሱን አስቦ እንደሆነ ስለተረዱ በዚያኑ ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፤ ሆኖም ሕዝቡን ፈሩ። 20  በቅርብ ሲከታተሉት ከቆዩ በኋላ በንግግሩ እንዲያጠምዱት ጻድቅ መስለው የሚቀርቡ ሰዎችን በድብቅ ቀጥረው ላኩ፤ ይህን ያደረጉት ለመንግሥትና ለአገረ ገዢው አሳልፈው ለመስጠት ነው። 21  የተላኩትም ሰዎች እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦ “መምህር፣ አንተ ትክክለኛውን ነገር እንደምትናገርና እንደምታስተምር እንዲሁም እንደማታዳላ፣ ከዚህ ይልቅ የአምላክን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፦ 22  ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባናል ወይስ አይገባንም?” 23  እሱ ግን ተንኮላቸው ገብቶት እንዲህ አላቸው፦ 24  “እስቲ አንድ ዲናር አሳዩኝ። በላዩ ላይ ያለው ምስልና የተቀረጸው ጽሑፍ የማን ነው?” እነሱም “የቄሳር” አሉ። 25  እሱም “እንግዲያው የቄሳር የሆነውን ለቄሳር፣ የአምላክ የሆነውን ደግሞ ለአምላክ ስጡ” አላቸው። 26  እነሱም በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም፤ ከዚህ ይልቅ በመልሱ በመገረም ዝም አሉ። 27  ሆኖም በትንሣኤ ከማያምኑት ሰዱቃውያን መካከል አንዳንዶቹ መጥተው ጥያቄ አቀረቡለት፦ 28  “መምህር፣ ሙሴ ‘አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ ሚስትየዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር መተካት አለበት’ ብሎ ጽፎልናል። 29  እንግዲህ ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ። የመጀመሪያው ሚስት አገባ፤ ሆኖም ልጅ ሳይወልድ ሞተ። 30  ሁለተኛውም እንደዚሁ፤ 31  ሦስተኛውም አገባት። በዚሁ አኳኋን ሰባቱም አግብተዋት ልጆች ሳይወልዱ ሞቱ። 32  በመጨረሻም ሴትየዋ ሞተች። 33  እንግዲህ ሰባቱም ስላገቧት በትንሣኤ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች?” 34  ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “የዚህ ሥርዓት ልጆች ያገባሉ እንዲሁም ይዳራሉ፤ 35  ሆኖም የሚመጣውን ሥርዓት መውረስና የሙታን ትንሣኤን ማግኘት የሚገባቸው አያገቡም እንዲሁም አይዳሩም። 36  እንዲያውም እንደ መላእክት ስለሆኑ ከዚያ በኋላ ሊሞቱ አይችሉም፤ የትንሣኤ ልጆች ስለሆኑም የአምላክ ልጆች ናቸው። 37  ይሁንና ሙሴም እንኳ ስለ ቁጥቋጦው በሚገልጸው ታሪክ ላይ ይሖዋን ‘የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ’ ብሎ በጠራው ጊዜ ሙታን እንደሚነሡ አስታውቋል። 38  እሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፤ በእሱ ፊት ሁሉም ሕያዋን ናቸውና።” 39  በዚህ ጊዜ አንዳንድ ጸሐፍት “መምህር፣ ጥሩ ብለሃል” አሉ። 40  ከዚያ በኋላ አንድም ጥያቄ ሊጠይቁት አልደፈሩም። 41  እሱ ደግሞ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ “ሰዎች ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ? 42  ምክንያቱም ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ ላይ እንዲህ ብሏል፦ ‘ይሖዋ ጌታዬን እንዲህ ብሎታል፦ “በቀኜ ተቀመጥ፤ 43  ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ሁን።”’ 44  ስለዚህ ዳዊት ‘ጌታ’ ብሎ ጠርቶታል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል?” 45  ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ 46  “ዘርፋፋ ልብስ ለብሰው መዞር ከሚወዱ፣ በገበያ ቦታ ሰዎች እጅ እንዲነሷቸው ከሚሹ እንዲሁም በምኩራብ ከፊት መቀመጥ፣ በራት ግብዣ ላይም የክብር ቦታ መያዝ ከሚፈልጉ ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ 47  እነሱ የመበለቶችን ቤት ያራቁታሉ፤ ለታይታ ብለውም ጸሎታቸውን ያስረዝማሉ። እነዚህ የከፋ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።”
[]
[]
[]
[]
12,011
21  ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታሞች በመዋጮ ሣጥኖቹ ውስጥ መባቸውን ሲከቱ አየ። 2  ከዚያም አንዲት ድሃ መበለት በጣም አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች ስትከት አይቶ 3  እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ የበለጠ የሰጠችው ይህች ድሃ መበለት ነች። 4  ሁሉም መባ የሰጡት ከትርፋቸው ነውና፤ እሷ ግን በድሃ አቅሟ ያላትን መተዳደሪያ ሁሉ ሰጥታለች።” 5  በኋላም አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ ውብ በሆኑ ድንጋዮችና ለአምላክ በተሰጡ ስጦታዎች እንዴት እንዳጌጠ በተናገሩ ጊዜ 6  “ይህ የምታዩት ነገር ሁሉ የሚፈርስበት ጊዜ ይመጣል፤ እንዲህ ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ አይኖርም” አለ። 7  እነሱም “መምህር፣ እነዚህ ነገሮች በእርግጥ የሚፈጸሙት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙበትን ጊዜ የሚጠቁመው ምልክትስ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት። 8  እሱም እንዲህ አለ፦ “እንዳያሳስቷችሁ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች ‘እኔ እሱ ነኝ’ እንዲሁም ‘ጊዜው ቀርቧል’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና። እነሱን አትከተሉ። 9  በተጨማሪም ስለ ጦርነትና ብጥብጥ ስትሰሙ አትሸበሩ። በመጀመሪያ እነዚህ ነገሮች መፈጸም አለባቸውና፤ ፍጻሜው ግን ወዲያው አይመጣም።” 10  ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳል። 11  ታላላቅ የምድር ነውጦች ይከሰታሉ፤ በተለያየ ስፍራም የምግብ እጥረትና ቸነፈር ይሆናል፤ ደግሞም የሚያስፈሩ ነገሮች እንዲሁም ከሰማይ ታላላቅ ምልክቶች ይታያሉ። 12  “እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ግን ሰዎች ይይዟችኋል፤ ስደት ያደርሱባችኋል እንዲሁም ለምኩራብና ለወህኒ ቤት አሳልፈው ይሰጧችኋል። በስሜም ምክንያት በነገሥታትና በገዢዎች ፊት ያቀርቧችኋል። 13  ይህም ለመመሥከር የሚያስችል አጋጣሚ ይከፍትላችኋል። 14  የምትሰጡትን መልስ አስቀድማችሁ መዘጋጀት እንደማያስፈልጋችሁ ልብ በሉ፤ 15  ተቃዋሚዎቻችሁ ሁሉ በአንድነት ሆነው ሊቋቋሙት ወይም ሊከራከሩት የማይችሉት አንደበትና ጥበብ እሰጣችኋለሁና። 16  ከዚህም በተጨማሪ ወላጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁና ጓደኞቻችሁ እንኳ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ አንዳንዶቻችሁንም ይገድላሉ፤ 17  በስሜ የተነሳም ሰዎች ሁሉ ይጠሏችኋል። 18  ይሁን እንጂ ከራሳችሁ ፀጉር አንዷ እንኳ አትጠፋም። 19  ከጸናችሁ ሕይወታችሁን ታተርፋላችሁ። 20  “ይሁንና ኢየሩሳሌም በጦር ሠራዊት ተከባ ስታዩ መጥፊያዋ እንደቀረበ እወቁ። 21  በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤ በከተማዋ ውስጥ ያሉም ከዚያ ይውጡ፤ በገጠር ያሉም ወደ እሷ አይግቡ፤ 22  ምክንያቱም የተጻፈው ነገር ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይህ የፍትሕ እርምጃ የሚወሰድበት ጊዜ ነው። 23  በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቁጣ ይመጣል። 24  በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ተማርከውም ወደየአገሩ ይወሰዳሉ፤ የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት እስኪፈጸሙ ድረስም ኢየሩሳሌም በአሕዛብ ትረገጣለች። 25  “እንዲሁም በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክቶች ይታያሉ፤ በምድርም ላይ ሕዝቦች ከባሕሩ ድምፅና ነውጥ የተነሳ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ይጨነቃሉ። 26  የሰማያት ኃይላት ስለሚናወጡ ሰዎች ከፍርሃትና በዓለም ላይ የሚመጡትን ነገሮች ከመጠበቅ የተነሳ ይዝለፈለፋሉ። 27  ከዚያም የሰው ልጅ በኃይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። 28  ሆኖም እነዚህ ነገሮች መከሰት ሲጀምሩ መዳናችሁ እየቀረበ ስለሆነ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ቀና አድርጉ።” 29  ከዚያም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “የበለስ ዛፍንና ሌሎች ዛፎችን ሁሉ ተመልከቱ። 30  ዛፎቹ ሲያቆጠቁጡ ራሳችሁ አይታችሁ በጋ እንደቀረበ ታውቃላችሁ። 31  በተመሳሳይ እናንተም እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ ስታዩ የአምላክ መንግሥት እንደቀረበ እርግጠኞች ሁኑ። 32  እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ ፈጽሞ አያልፍም። 33  ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም። 34  “ይሁንና ከልክ በላይ በመብላትና በመጠጣት እንዲሁም ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ ሸክም እንዳይበዛበት ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ አለዚያ ያ ቀን ድንገት ሳታስቡት 35  እንደ ወጥመድ ይመጣባችኋል። ይህ በመላው ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይደርስባቸዋልና። 36  እንግዲያው መፈጸማቸው ከማይቀረው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ማምለጥና በሰው ልጅ ፊት መቆም እንድትችሉ ሁልጊዜ ምልጃ እያቀረባችሁ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።” 37  ኢየሱስ ቀን ቀን በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሲመሽ ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ ያድር ነበር። 38  ሕዝቡም ሁሉ በቤተ መቅደስ እሱን ለመስማት በማለዳ ወደ እሱ ይመጡ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,012
22  ፋሲካ የሚባለው የቂጣ በዓል የሚከበርበት ጊዜ ተቃርቦ ነበር። 2  የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም ሕዝቡን ይፈሩ ስለነበር እሱን የሚገድሉበትን ከሁሉ የተሻለ መንገድ እየፈለጉ ነበር። 3  ከዚያም ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ሆኖ በተቆጠረውና አስቆሮቱ ተብሎ በሚጠራው በይሁዳ ሰይጣን ገባበት፤ 4  ይሁዳም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደሱ ሹሞች ሄዶ ኢየሱስን ለእነሱ አሳልፎ መስጠት ስለሚችልበት መንገድ ተነጋገረ። 5  እነሱም በጉዳዩ ተደስተው የብር ገንዘብ ሊሰጡት ተስማሙ። 6  እሱም በዚህ ተስማምቶ ሕዝብ በሌለበት እሱን አሳልፎ መስጠት የሚችልበትን ምቹ አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር። 7  የቂጣ በዓል የሚከበርበት ቀን ደረሰ፤ በዚህ ዕለት የፋሲካ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር፤ 8  ስለዚህ ኢየሱስ “ሄዳችሁ ፋሲካን እንድንበላ አዘጋጁልን” ብሎ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላካቸው። 9  እነሱም “የት እንድናዘጋጅ ትፈልጋለህ?” አሉት። 10  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ወደ ከተማው ስትገቡ የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። እሱን ተከትላችሁ ወደሚገባበት ቤት ሂዱ። 11  የቤቱንም ባለቤት ‘መምህሩ “ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሎሃል’ በሉት። 12  ሰውየውም የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁ።” 13  እነሱም ሄዱ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ። 14  ሰዓቱ በደረሰ ጊዜም ከሐዋርያቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ። 15  እንዲህም አላቸው፦ “መከራ ከመቀበሌ በፊት ይህን ፋሲካ አብሬያችሁ ለመብላት በጣም ስመኝ ነበር፤ 16  እላችኋለሁና፣ የዚህ ፋሲካ ትርጉም በአምላክ መንግሥት ፍጻሜውን እስኪያገኝ ድረስ ፋሲካን ዳግመኛ አልበላም።” 17  ከዚያም ጽዋ ተቀብሎ አምላክን ካመሰገነ በኋላ እንዲህ አለ፦ “እንኩ፣ ይህን ጽዋ እየተቀባበላችሁ ጠጡ፤ 18  እላችኋለሁና፣ ከአሁን ጀምሮ የአምላክ መንግሥት እስኪመጣ ድረስ ከዚህ ወይን ዳግመኛ አልጠጣም።” 19  በተጨማሪም ቂጣ አንስቶ አመሰገነ፣ ከቆረሰውም በኋላ ሰጣቸውና “ይህ ስለ እናንተ የሚሰጠውን ሥጋዬን ያመለክታል። ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አላቸው። 20  በተጨማሪም ራት ከበሉ በኋላ ጽዋውን አንስቶ ልክ እንደዚሁ አደረገ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ አማካኝነት የሚመሠረተውን አዲሱን ቃል ኪዳን ያመለክታል። 21  “ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ ከእኔ ጋር በማዕድ ነው። 22  እርግጥ የሰው ልጅ አስቀድሞ በተወሰነው መሠረት ይሄዳል፤ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!” 23  ስለዚህ ከመካከላቸው በእርግጥ ይህን የሚያደርገው ማን ሊሆን እንደሚችል እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር። 24  ደግሞም ‘ከመካከላችን ታላቅ የሆነው ማን ነው?’ በሚል በመካከላቸው የጦፈ ክርክር ተነሳ። 25  እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “የአሕዛብ ነገሥታት በእነሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ፤ እንዲሁም በሕዝባቸው ላይ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች በጎ አድራጊዎች ተብለው ይጠራሉ። 26  እናንተ ግን እንዲህ አትሁኑ። ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን፤ አመራር የሚሰጥም እንደ አገልጋይ ይሁን። 27  ለመሆኑ በማዕድ ከተቀመጠና ቆሞ ከሚያገለግል ማን ይበልጣል? በማዕድ የተቀመጠው አይደለም? እኔ ግን በመካከላችሁ ያለሁት እንደ አገልጋይ ሆኜ ነው። 28  “ይሁን እንጂ እናንተ በፈተናዎቼ ከጎኔ ሳትለዩ ቆይታችኋል፤ 29  አባቴ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን እንዳደረገ ሁሉ እኔም ከእናንተ ጋር ለመንግሥት ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ 30  ይኸውም በመንግሥቴ ከማዕዴ እንድትበሉና እንድትጠጡ እንዲሁም በዙፋን ተቀምጣችሁ በ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ እንድትፈርዱ ነው። 31  “ስምዖን፣ ስምዖን፣ ሰይጣን ሁላችሁንም እንደ ስንዴ ያበጥራችሁ ዘንድ ጥያቄ አቅርቧል። 32  እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ምልጃ አቀረብኩ፤ አንተም በተመለስክ ጊዜ ወንድሞችህን አበርታ።” 33  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ወደ ወህኒ ለመውረድም ሆነ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው። 34  እሱ ግን “ጴጥሮስ ሆይ፣ እውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ ዶሮ ከመጮኹ በፊት፣ አላውቀውም ብለህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው። 35  በተጨማሪም እንዲህ አላቸው፦ “ያለገንዘብ ኮሮጆ፣ ያለምግብ ከረጢትና ያለትርፍ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ የጎደለባችሁ ነገር ነበር?” እነሱም “ምንም አልጎደለብንም” አሉ። 36  በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ግን የገንዘብ ኮሮጆ ያለው ኮሮጆውን ይያዝ፤ የምግብ ከረጢት ያለውም እንዲሁ፤ ሰይፍ የሌለው ደግሞ መደረቢያውን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ። 37  ይህን የምላችሁ ‘ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ’ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ላይ መፈጸም ስላለበት ነው። ስለ እኔ የተነገረው ነገር ፍጻሜውን እያገኘ ነውና።” 38  እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ይኸው ሁለት ሰይፎች አሉ” አሉት። እሱም “በቂ ነው” አላቸው። 39  ከዚያ ወጥቶም እንደ ልማዱ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት። 40  እዚያም በደረሱ ጊዜ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ” አላቸው። 41  እሱም የድንጋይ ውርወራ ያህል ከእነሱ በመራቅ ተንበርክኮ መጸለይ ጀመረ፤ 42  እንዲህም አለ፦ “አባት ሆይ፣ ፈቃድህ ከሆነ ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ። ይሁንና የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም።” 43  ከዚያም አንድ መልአክ ከሰማይ ተገልጦለት አበረታታው። 44  ሆኖም በከፍተኛ ጭንቀት ተውጦ ከበፊቱ ይበልጥ አጥብቆ መጸለዩን ቀጠለ፤ ላቡም መሬት ላይ እንደሚንጠባጠብ ደም ሆኖ ነበር። 45  ከጸለየም በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲሄድ ከሐዘን የተነሳ ደክሟቸው ስለነበር ሲያንቀላፉ አገኛቸው። 46  እሱም “ለምን ትተኛላችሁ? ተነሱ፤ ደግሞም ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ” አላቸው። 47  ገና እየተናገረ ሳለ ብዙ ሰዎች መጡ፤ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ የተባለውም ሰው ይመራቸው ነበር፤ ሊስመውም ወደ ኢየሱስ ተጠጋ። 48  ኢየሱስ ግን “ይሁዳ፣ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህ?” አለው። 49  በዙሪያው የነበሩትም አዝማሚያውን ሲያዩ “ጌታ ሆይ፣ በሰይፍ እንምታቸው?” አሉት። 50  እንዲያውም ከመካከላቸው አንዱ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው። 51  ኢየሱስ ግን መልሶ “ተዉ!” አለ። ጆሮውንም ዳሶ ፈወሰው። 52  ከዚያም ኢየሱስ እሱን ለመያዝ የመጡትን የካህናት አለቆች፣ የቤተ መቅደሱን ሹሞችና ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፦ “ወንበዴ የምትይዙ ይመስል ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ መጣችሁ? 53   በየዕለቱ በቤተ መቅደስ አብሬያችሁ ሳለሁ እኔን ለመያዝ እጃችሁን አላነሳችሁብኝም። ይሁንና ይህ የእናንተ ሰዓትና ጨለማ የሚነግሥበት ሰዓት ነው።” 54  ከዚያም ሰዎቹ ይዘው ወሰዱትና ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት አመጡት፤ ጴጥሮስም በርቀት ይከተል ነበር። 55  በግቢው መካከል እሳት አንድደው አንድ ላይ ተቀምጠው ሳለ ጴጥሮስም ከእነሱ ጋር ተቀመጠ። 56  ይሁንና አንዲት አገልጋይ እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሲሞቅ አየችውና ትኩር ብላ ከተመለከተችው በኋላ “ይህ ሰውም ከእሱ ጋር ነበር” አለች። 57   እሱ ግን “አንቺ ሴት፣ እኔ አላውቀውም” ሲል ካደ። 58  ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ ሰው አየውና “አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ አይደለሁም” አለ። 59  አንድ ሰዓት ያህል ካለፈ በኋላ ደግሞ አንድ ሌላ ሰው “ይህ ሰው፣ የገሊላ ሰው ስለሆነ በእርግጥ ከእሱ ጋር ነበር!” በማለት አጥብቆ ይናገር ጀመር። 60  ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው፣ ምን እንደምታወራ አላውቅም” አለ። ገና እየተናገረም ሳለ ዶሮ ጮኸ። 61  በዚህ ጊዜ ጌታ ዞር ብሎ ጴጥሮስን ትክ ብሎ አየው፤ ጴጥሮስም “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” በማለት ጌታ የተናገረውን ቃል አስታወሰ። 62  ከዚያም ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ። 63  ኢየሱስን የያዙት ሰዎችም እየመቱት ያሾፉበት ጀመር፤ 64  ፊቱንም ከሸፈኑት በኋላ “እስቲ ትንቢት ተናገር! የመታህ ማን ነው?” እያሉ ይጠይቁት ነበር። 65  በእሱም ላይ ሌላ ብዙ የስድብ ቃል ይሰነዝሩ ነበር። 66  በነጋም ጊዜ የካህናት አለቆችንና ጸሐፍትን ጨምሮ የሕዝቡ ሽማግሌዎች ጉባኤ አንድ ላይ ተሰበሰበ፤ ኢየሱስንም ወደ ሳንሄድሪን ሸንጎ አዳራሻቸው አምጥተው እንዲህ አሉት፦ 67  “አንተ ክርስቶስ ከሆንክ ንገረን።” እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ብነግራችሁም እንኳ ፈጽሞ አታምኑም። 68  ብጠይቃችሁም አትመልሱም። 69  ያም ሆነ ይህ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በኃያሉ አምላክ ቀኝ ይቀመጣል።” 70  በዚህ ጊዜ ሁሉም “ስለዚህ የአምላክ ልጅ ነህ ማለት ነው?” አሉት። እሱም “የአምላክ ልጅ መሆኔን እናንተው ራሳችሁ እየተናገራችሁ ነው” አላቸው። 71  እነሱም “ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ያስፈልገናል? እኛ ራሳችን ከገዛ አፉ ሰምተነዋል” አሉ።
[]
[]
[]
[]
12,013
23  ስለዚህ በዚያ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች በሙሉ ተነስተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱት። 2  ከዚያም እንዲህ እያሉ ይከሱት ጀመር፦ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያሳምፅ፣ ለቄሳር ግብር እንዳይከፈል ሲከለክልና ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ’ ሲል አግኝተነዋል።” 3  በዚህ ጊዜ ጲላጦስ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “አንተው ራስህ እኮ እየተናገርከው ነው” አለው። 4  ከዚያም ጲላጦስ ለካህናት አለቆቹና ለሕዝቡ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም” አለ። 5  እነሱ ግን “በመላው ይሁዳ፣ ከገሊላ አንስቶ እስከዚህ ድረስ እያስተማረ ሕዝቡን ይቀሰቅሳል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ። 6  ጲላጦስ ይህን ሲሰማ ሰውየው የገሊላ ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቀ። 7  ከሄሮድስ ግዛት የመጣ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ወደነበረው ወደ ሄሮድስ ላከው። 8  ሄሮድስ ኢየሱስን ሲያየው በጣም ደስ አለው። ስለ እሱ ብዙ ነገር ሰምቶ ስለነበር ለረጅም ጊዜ እሱን ለማየት ይፈልግ ነበር፤ አንዳንድ ተአምራት ሲፈጽም ለማየትም ተስፋ ያደርግ ነበር። 9  በመሆኑም ብዙ ጥያቄ ይጠይቀው ጀመር፤ እሱ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም። 10  ይሁን እንጂ የካህናት አለቆቹና ጸሐፍት በተደጋጋሚ እየተነሱ አጥብቀው ይከሱት ነበር። 11  ከዚያም ሄሮድስ ከወታደሮቹ ጋር ሆኖ አቃለለው፤ እንዲሁም ያማረ ልብስ አልብሶ ካፌዘበት በኋላ መልሶ ወደ ጲላጦስ ላከው። 12  በዚያን ዕለት ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ፤ ከዚያ በፊት በመካከላቸው ጠላትነት ነበር። 13  ከዚያም ጲላጦስ የካህናት አለቆቹን፣ ገዢዎቹንና ሕዝቡን በአንድነት ጠርቶ 14  እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁት ሕዝቡን ለዓመፅ ያነሳሳል ብላችሁ ነበር። ይኸው በፊታችሁ መረመርኩት፤ ሆኖም በእሱ ላይ ያቀረባችሁትን ክስ የሚደግፍ ምንም ነገር አላገኘሁም። 15  ሄሮድስም ቢሆን ምንም ጥፋት ስላላገኘበት ወደ እኛ መልሶ ልኮታል፤ በመሆኑም ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር አልፈጸመም። 16  ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ።” 17  —— 18  ሕዝቡ ሁሉ ግን “ይህን ሰው ግደለው፤ በርባንን ግን ፍታልን!” እያሉ ጮኹ። 19  (ይህ ሰው በከተማው ውስጥ በተከሰተ የሕዝብ ዓመፅና በነፍስ ግድያ የታሰረ ነበር።) 20  ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታው ስለፈለገ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንደገና ለሕዝቡ ተናገረ። 21  እነሱ ግን “ይሰቀል! ይሰቀል!” እያሉ ይጮኹ ጀመር። 22  እሱም ለሦስተኛ ጊዜ “ለምን? ይህ ሰው ምን ያጠፋው ነገር አለ? ለሞት የሚያበቃ ምንም ነገር አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ቀጥቼ እፈታዋለሁ” አላቸው። 23  በዚህ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ኢየሱስ እንዲገደል አጥብቀው ወተወቱት፤ ድምፃቸውም አየለ። 24  ስለዚህ ጲላጦስ የጠየቁት እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላለፈ። 25  ሕዝብ በማሳመፅና በነፍስ ግድያ ታስሮ የነበረውንና እንዲፈታላቸው የጠየቁትን ሰው ለቀቀው፤ ኢየሱስን ግን የፈለጉትን እንዲያደርጉበት አሳልፎ ሰጣቸው። 26  ይዘውትም እየሄዱ ሳሉ ከገጠር እየመጣ የነበረውን ስምዖን የተባለ አንድ የቀሬና ሰው ያዙትና የመከራውን እንጨት አሸክመው ከኢየሱስ ኋላ እንዲሄድ አደረጉት። 27  ብዙ ሕዝብም ይከተለው ነበር፤ ከእነሱም መካከል በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ የሚያለቅሱለት ሴቶች ነበሩ። 28  ኢየሱስም ወደ ሴቶቹ ዞር ብሎ እንዲህ አለ፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፣ ለእኔ አታልቅሱ። ይልቁንስ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ፤ 29  ሰዎች ‘መሃን የሆኑ ሴቶች፣ ያልወለዱ ማህፀኖችና ያላጠቡ ጡቶች ደስተኞች ናቸው!’ የሚሉበት ቀን ይመጣልና። 30  በዚያን ጊዜ ተራሮችን ‘በላያችን ውደቁ!’ ኮረብቶችንም ‘ሸሽጉን!’ ይላሉ። 31  ዛፉ እርጥብ ሆኖ ሳለ እንዲህ ካደረጉ በደረቀ ጊዜማ ምን ይከሰት ይሆን?” 32  ወንጀለኞች የሆኑ ሌሎች ሁለት ሰዎችም ከእሱ ጋር ሊገደሉ እየተወሰዱ ነበር። 33  የራስ ቅል ወደተባለ ቦታ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስን በዚያ ከወንጀለኞቹ ጋር በእንጨት ላይ ቸነከሩት፤ ወንጀለኞቹም አንዱ በቀኙ ሌላው ደግሞ በግራው ተሰቅለው ነበር። 34  ኢየሱስም “አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን ስለማያውቁ ይቅር በላቸው” ይል ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ልብሶቹን ለመከፋፈል ዕጣ ተጣጣሉ። 35  ሕዝቡም ቆሞ ይመለከት ነበር። የሃይማኖት መሪዎቹ ግን “ሌሎችን አዳነ፤ የተመረጠው የአምላክ ክርስቶስ እሱ ከሆነ እስቲ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌዙበት ነበር። 36  ወታደሮቹ እንኳ ሳይቀሩ ወደ እሱ ቀርበው የኮመጠጠ ወይን በመስጠት አፌዙበት፤ 37  እንዲሁም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ከሆንክ ራስህን አድን” ይሉት ነበር። 38  በተጨማሪም ከበላዩ “ይህ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነው” የሚል ጽሑፍ ነበር። 39  ከዚያም በዚያ ከተሰቀሉት ወንጀለኞች አንዱ “አንተ ክርስቶስ አይደለህም እንዴ? እስቲ ራስህንም እኛንም አድን!” እያለ ይዘልፈው ጀመር። 40  ሌላኛው ግን መልሶ እንዲህ ሲል ገሠጸው፦ “አንተ ራስህ ተመሳሳይ ፍርድ ተቀብለህ እያለ ትንሽ እንኳ አምላክን አትፈራም? 41  እኛስ ላደረግነው ነገር የሚገባንን ቅጣት በሙሉ እየተቀበልን ስለሆነ በእኛ ላይ የተፈጸመው ፍርድ ተገቢ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም የሠራው ጥፋት የለም።” 42  ቀጥሎም “ኢየሱስ ሆይ፣ ወደ መንግሥትህ ስትመጣ አስበኝ” አለው። 43  እሱም “እውነት እልሃለሁ ዛሬ፣ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” አለው። 44  ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ የነበረ ቢሆንም ምድሪቱ በሙሉ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በጨለማ ተሸፈነች፤ 45  ይህም የሆነው የፀሐይ ብርሃን በመጥፋቱ ነው፤ ከዚያም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ መሃል ለመሃል ተቀደደ። 46  ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ “አባት ሆይ፣ መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ” አለ። ይህን ካለ በኋላ ሞተ። 47  መኮንኑም የተፈጸመውን ነገር በማየቱ “ይህ ሰው በእርግጥ ጻድቅ ነበር” በማለት ለአምላክ ክብር ይሰጥ ጀመር። 48  ይህን ለማየት በቦታው ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ሁሉ የተከሰቱትን ነገሮች ሲመለከቱ በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ወደ ቤታቸው ተመለሱ። 49  በቅርብ የሚያውቁትም ሁሉ በርቀት ቆመው ነበር። እንዲሁም ከገሊላ አንስቶ አብረውት የተጓዙት ሴቶች በዚያ ተገኝተው እነዚህን ነገሮች ይመለከቱ ነበር። 50  እነሆም፣ የሸንጎ አባል የሆነ ዮሴፍ የሚባል አንድ ጥሩና ጻድቅ ሰው ነበረ። 51  (ይህ ሰው ሴራቸውንና ድርጊታቸውን በመደገፍ ድምፅ አልሰጠም ነበር።) እሱም የአይሁዳውያን ከተማ የሆነችው የአርማትያስ ሰው ሲሆን የአምላክን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር። 52  ይህም ሰው ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ። 53   አስከሬኑንም አውርዶ በበፍታ ገነዘው፤ ከዚያም ማንም ሰው ተቀብሮበት በማያውቅ ከዓለት ተፈልፍሎ በተሠራ መቃብር ውስጥ አኖረው። 54  ዕለቱ የዝግጅት ቀን ነበር፤ ሰንበት የሚጀምርበት ጊዜም ተቃርቦ ነበር። 55  ከገሊላ ከኢየሱስ ጋር አብረው የመጡት ሴቶች ግን ተከትለው በመሄድ መቃብሩን አዩ፤ አስከሬኑም እንዴት እንዳረፈ ተመለከቱ። 56  ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞችና ዘይቶች ለማዘጋጀትም ተመልሰው ሄዱ። ሆኖም ሕጉ በሚያዘው መሠረት በሰንበት አረፉ።
[]
[]
[]
[]
12,014
24  ይሁን እንጂ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ ያዘጋጇቸውን ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞች ይዘው ጠዋት በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄዱ። 2  ሆኖም ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፤ 3  ወደ ውስጥ ሲገቡም የጌታ ኢየሱስን አስከሬን አላገኙም። 4  በሁኔታው ግራ ተጋብተው እያሉ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች ድንገት አጠገባቸው ቆሙ። 5  ሴቶቹ ፈርተው ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ ሰዎቹ እንዲህ አሏቸው፦ “ሕያው የሆነውን ለምን ከሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ? 6  እሱ እዚህ የለም፤ ከሞት ተነስቷል። ገና በገሊላ በነበረበት ጊዜ ምን እንዳላችሁ አስታውሱ፤ 7  ‘የሰውን ልጅ ለኃጢአተኞች አሳልፈው ሊሰጡት፣ በእንጨት ላይ ሊሰቀልና በሦስተኛው ቀን ሊነሳ ይገባል’ ብሎ ነበር።” 8  በዚህ ጊዜ ሴቶቹ የተናገረውን ቃል አስታወሱ፤ 9  ከዚያም መቃብሩ ካለበት ስፍራ ተመልሰው እነዚህን ነገሮች በሙሉ ለአሥራ አንዱና ለቀሩት ሁሉ ነገሯቸው። 10  እነሱም መግደላዊቷ ማርያም፣ ዮሐናና የያዕቆብ እናት ማርያም ነበሩ። ከእነሱ ጋር የነበሩት ሌሎቹ ሴቶችም እነዚህን ነገሮች ለሐዋርያት ነገሯቸው። 11  ይሁን እንጂ እንዲሁ የሚቀባጥሩ ስለመሰላቸው ሴቶቹ የሚናገሩትን አላመኗቸውም። 12  ጴጥሮስ ግን ተነስቶ ወደ መቃብሩ ሮጠ፤ ጎንበስ ብሎም ወደ ውስጥ ሲመለከት በፍታውን ብቻ አየ። በሆነውም ነገር እየተገረመ ከዚያ ሄደ። 13  ይሁንና በዚያው ቀን ከመካከላቸው ሁለቱ ከኢየሩሳሌም አሥራ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ ወደምትገኝ ኤማሁስ ወደምትባል መንደር እየተጓዙ ነበር፤ 14  እነሱም ስለሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው እየተነጋገሩ ነበር። 15  ስለዚህ ጉዳይ እየተነጋገሩና እየተወያዩ ሳሉም ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ አብሯቸው መሄድ ጀመረ፤ 16  ሆኖም ማንነቱን እንዳይለዩ ዓይናቸው ተጋርዶ ነበር። 17  እሱም “እየተጓዛችሁ እንዲህ እርስ በርስ የምትወያዩበት ጉዳይ ምንድን ነው?” አላቸው። በዚህ ጊዜ በሐዘን እንደተዋጡ ባሉበት ቆሙ። 18  ቀለዮጳ የተባለውም መልሶ “በኢየሩሳሌም ውስጥ ለብቻህ የምትኖር እንግዳ ሰው ነህ እንዴ? ሰሞኑን በዚያ የተፈጸመውን ነገር አታውቅም ማለት ነው?” አለው። 19  እሱም “ምን ተፈጸመ?” አላቸው። እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በአምላክና በሰው ሁሉ ፊት በሥራም ሆነ በቃል ኃያል ነቢይ ከሆነው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ነገር ነዋ! 20  የካህናት አለቆቻችንና ገዢዎቻችን ለሞት ፍርድ አሳልፈው ሰጡት፤ እንዲሁም በእንጨት ላይ ቸነከሩት። 21  እኛ ግን ይህ ሰው እስራኤልን ነፃ ያወጣል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር። ከዚህም በላይ ይህ ነገር ከተፈጸመ እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ነው። 22  ደግሞም ከእኛው መካከል አንዳንድ ሴቶች በማለዳ ወደ መቃብሩ ሄደው ስለነበር የሚያስገርም ነገር ነገሩን፤ 23  አስከሬኑንም ባጡ ጊዜ ተመልሰው መጥተው በተአምር የተገለጡላቸውንና እሱ ሕያው እንደሆነ የነገሯቸውን መላእክት እንዳዩ ነገሩን። 24  ከዚያም ከእኛ መካከል አንዳንዶች ወደ መቃብሩ ሄደው ነበር፤ እነሱም ሴቶቹ እንደተናገሩት ሆኖ አገኙት፤ እሱን ግን አላዩትም።” 25  እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁና ነቢያት የተናገሩትን ሁሉ ከማመን ልባችሁ የዘገየ! 26  ክርስቶስ እነዚህን መከራዎች መቀበልና ክብር ማግኘት አይገባውም?” 27  ከዚያም ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እሱ በቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን በሚገባ አብራራላቸው። 28  በመጨረሻም ወደሚሄዱበት መንደር ተቃረቡ፤ ይሁንና እሱ አልፎ የሚሄድ ይመስል ነበር። 29  እነሱ ግን “ቀኑ እየተገባደደና ምሽቱ እየተቃረበ ስለሆነ እኛ ጋ እደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት። እሱም እነሱ ጋ ለማደር ገባ። 30  ከእነሱ ጋር እየበላ ሳለም ዳቦውን አንስቶ ባረከ፤ ቆርሶም ይሰጣቸው ጀመር። 31  በዚህ ጊዜ ዓይናቸው ሙሉ በሙሉ ተከፈተና ማን መሆኑን በሚገባ አወቁ፤ እሱ ግን ከአጠገባቸው ተሰወረ። 32  እነሱም እርስ በርሳቸው “በመንገድ ላይ ሲያነጋግረንና ቅዱሳን መጻሕፍትን በሚገባ ሲገልጥልን ልባችን እንደ እሳት ይቃጠልብን አልነበረም?” ተባባሉ። 33  በዚያኑም ሰዓት ተነስተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ አሥራ አንዱንና ከእነሱ ጋር የነበሩትንም አንድ ላይ ተሰብስበው አገኟቸው፤ 34  እነሱም “ጌታ በእርግጥ ተነስቷል፤ ለስምዖንም ተገልጦለታል!” ይሉ ነበር። 35  ሁለቱ ደግሞ በመንገድ ላይ ያጋጠማቸውን ነገርና ዳቦውን በቆረሰበት ጊዜ እንዴት እንዳወቁት ተረኩላቸው። 36  እነዚህን ነገሮች እየተነጋገሩ ሳለ እሱ ራሱ በመካከላቸው ቆመ፤ ከዚያም “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። 37  እነሱ ግን ከመደንገጣቸውና ከመፍራታቸው የተነሳ መንፈስ ያዩ መሰላቸው። 38  በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ለምን ትረበሻላችሁ? ለምንስ በልባችሁ ውስጥ ጥርጣሬ ያድራል? 39  እኔ ራሴ መሆኔን እንድታውቁ እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ ደግሞም ዳስሳችሁኝ እዩ፤ መንፈስ በእኔ ላይ እንደምታዩት ሥጋና አጥንት የለውምና።” 40  ይህን እያለም እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። 41  እነሱ ግን በጣም ከመደሰታቸው የተነሳ ለማመን ተቸግረው በነገሩ እየተገረሙ ሳሉ “የሚበላ ነገር አላችሁ?” አላቸው። 42  እነሱም የተጠበሰ ቁራሽ ዓሣ ሰጡት፤ 43  እሱም ተቀብሎ በፊታቸው በላ። 44  ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ‘በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙራት ስለ እኔ የተጻፉት ነገሮች ሁሉ መፈጸም አለባቸው’ ብዬ የነገርኳችሁ ቃሌ ይህ ነው።” 45  ከዚያም የቅዱሳን መጻሕፍትን ትርጉም መረዳት እንዲችሉ አእምሯቸውን ከፈተላቸው፤ 46  እንዲህም አላቸው፦ “እንደሚከተለው ተብሎ ተጽፏል፤ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳል፤ 47  በስሙም የኃጢአት ይቅርታ የሚያስገኝ ንስሐ ከኢየሩሳሌም አንስቶ ለብሔራት ሁሉ ይሰበካል። 48  እናንተም ለእነዚህ ነገሮች ምሥክር ትሆናላችሁ። 49  እኔም አባቴ ቃል የገባውን ነገር እልክላችኋለሁ። እናንተ ግን ከላይ የሚመጣውን ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በከተማዋ ውስጥ ቆዩ።” 50  ከዚያም እስከ ቢታንያ ይዟቸው ሄደ፤ እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው። 51  እየባረካቸውም ሳለ ከእነሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ተወሰደ። 52  እነሱም ሰገዱለት፤ ከዚያም በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። 53   ዘወትር በቤተ መቅደስ እየተገኙም አምላክን ያወድሱ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,015
3  ጢባርዮስ ቄሳር በነገሠ በ15ኛው ዓመት፣ ጳንጥዮስ ጲላጦስ የይሁዳ አገረ ገዢ፣ ሄሮድስ የገሊላ አውራጃ ገዢ፣ ወንድሙ ፊልጶስ ደግሞ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አውራጃ ገዢ፣ ሊሳኒዮስ የአቢላኒስ አውራጃ ገዢ በነበሩበት ጊዜ 2  እንዲሁም ቀያፋና የካህናት አለቃው ሐና በነበሩበት ዘመን የአምላክ ቃል በምድረ በዳ ወደነበረው ወደ ዘካርያስ ልጅ ወደ ዮሐንስ መጣ። 3  ዮሐንስም ለኃጢአት ይቅርታ፣ የንስሐ ምልክት የሆነውን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለው አገር ሁሉ ሄደ፤ 4  ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ተብሎ በተጻፈው ቃል መሠረት ነው፦ “አንድ ሰው በምድረ በዳ ‘የይሖዋን መንገድ አዘጋጁ! ጎዳናዎቹንም አቅኑ’ በማለት ይጮኻል። 5  ‘ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤ ተራራውና ኮረብታው ሁሉ ይደልደል፤ ጠማማው መንገድ ቀጥ ያለ፣ ጎርበጥባጣውም መንገድ ለጥ ያለ ይሁን፤ 6  ሥጋም ሁሉ የአምላክን ማዳን ያያል።’” 7  በመሆኑም ዮሐንስ በእሱ እጅ ለመጠመቅ የሚመጡትን ሰዎች እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ያስጠነቀቃችሁ ማን ነው? 8  እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ። ‘እኛ እኮ አባታችን አብርሃም ነው’ እያላችሁ ራሳችሁን አታጽናኑ። አምላክ ለአብርሃም ከእነዚህ ድንጋዮች ልጆች ማስነሳት እንደማይሳነው ልነግራችሁ እወዳለሁ። 9  እንዲያውም መጥረቢያው ዛፎቹ ሥር ተቀምጧል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ እሳት ውስጥ ይጣላል።” 10  በዚህ ጊዜ ሕዝቡ “ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” ብለው ይጠይቁት ነበር። 11  እሱም መልሶ “ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ምንም ለሌለው ይስጥ፤ ምግብ ያለውም እንዲሁ ያድርግ” አላቸው። 12  ቀረጥ ሰብሳቢዎች እንኳ ሳይቀሩ ለመጠመቅ ወደ እሱ መጥተው “መምህር፣ ምን እናድርግ?” አሉት። 13  እሱም “ከተተመነው ቀረጥ በላይ አትጠይቁ” አላቸው። 14  ወታደሮች ደግሞ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እሱም “በማንም ላይ ግፍ አትሥሩ ወይም ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፤ ከዚህ ይልቅ ባላችሁ መተዳደሪያ ረክታችሁ ኑሩ” አላቸው። 15  ሕዝቡ ክርስቶስን ይጠባበቁ ስለነበር “ይህ ሰው ክርስቶስ ይሆን?” እያሉ ሁሉም በልባቸው ስለ ዮሐንስ ያስቡ ነበር። 16  ዮሐንስ ለሁሉም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ሆኖም ከእኔ የሚበረታ የሚመጣ ሲሆን እኔ የጫማውን ማሰሪያ እንኳ ለመፍታት አልበቃም። እሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል። 17  አውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን ወደ ጎተራ ለማስገባት ላይዳውን በእጁ ይዟል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።” 18  በተጨማሪም ዮሐንስ በተለያዩ መንገዶች ምክር በመስጠት ለሕዝቡ ምሥራች ማብሰሩን ቀጠለ። 19  ሆኖም የአውራጃ ገዢ የሆነው ሄሮድስ የወንድሙ ሚስት በሆነችው በሄሮድያዳ ምክንያትና በሠራቸው ሌሎች ክፉ ድርጊቶች የተነሳ ዮሐንስ ስለወቀሰው 20  በክፋት ላይ ክፋት በመጨመር ዮሐንስን ወህኒ ቤት አስገባው። 21  ሕዝቡም ሁሉ እየተጠመቁ በነበረ ጊዜ ኢየሱስም ተጠመቀ። እየጸለየም ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤ 22  መንፈስ ቅዱስም አካላዊ ቅርጽ ይዞ በርግብ መልክ በእሱ ላይ ወረደ፤ ከዚያም “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። 23  ኢየሱስ ሥራውን ሲጀምር 30 ዓመት ገደማ ሆኖት ነበር፤ ሕዝቡም የዮሴፍ ልጅ እንደሆነ አድርገው ያስቡ ነበር፤ዮሴፍ የሄሊ ልጅ፣ 24  ሄሊ የማታት ልጅ፣ማታት የሌዊ ልጅ፣ሌዊ የሚልኪ ልጅ፣ሚልኪ የያና ልጅ፣ያና የዮሴፍ ልጅ፣ 25  ዮሴፍ የማታትዩ ልጅ፣ማታትዩ የአሞጽ ልጅ፣አሞጽ የናሆም ልጅ፣ናሆም የኤስሊ ልጅ፣ኤስሊ የናጌ ልጅ፣ 26  ናጌ የማአት ልጅ፣ማአት የማታትዩ ልጅ፣ማታትዩ የሴሜይ ልጅ፣ሴሜይ የዮሴክ ልጅ፣ዮሴክ የዮዳ ልጅ፣ 27  ዮዳ የዮናን ልጅ፣ዮናን የሬስ ልጅ፣ሬስ የዘሩባቤል ልጅ፣ዘሩባቤል የሰላትያል ልጅ፣ሰላትያል የኔሪ ልጅ፣ 28  ኔሪ የሚልኪ ልጅ፣ሚልኪ የሐዲ ልጅ፣ሐዲ የቆሳም ልጅ፣ቆሳም የኤልሞዳም ልጅ፣ኤልሞዳም የኤር ልጅ፣ 29  ኤር የኢየሱስ ልጅ፣ኢየሱስ የኤሊዔዘር ልጅ፣ኤሊዔዘር የዮሪም ልጅ፣ዮሪም የማታት ልጅ፣ማታት የሌዊ ልጅ፣ 30  ሌዊ የሲምዖን ልጅ፣ሲምዖን የይሁዳ ልጅ፣ይሁዳ የዮሴፍ ልጅ፣ዮሴፍ የዮናም ልጅ፣ዮናም የኤልያቄም ልጅ፣ 31  ኤልያቄም የሜልያ ልጅ፣ሜልያ የሜና ልጅ፣ሜና የማጣታ ልጅ፣ማጣታ የናታን ልጅ፣ናታን የዳዊት ልጅ፣ 32  ዳዊት የእሴይ ልጅ፣እሴይ የኢዮቤድ ልጅ፣ኢዮቤድ የቦዔዝ ልጅ፣ቦዔዝ የሰልሞን ልጅ፣ሰልሞን የነአሶን ልጅ፣ 33  ነአሶን የአሚናዳብ ልጅ፣አሚናዳብ የአርናይ ልጅ፣አርናይ የኤስሮን ልጅ፣ኤስሮን የፋሬስ ልጅ፣ፋሬስ የይሁዳ ልጅ፣ 34  ይሁዳ የያዕቆብ ልጅ፣ያዕቆብ የይስሐቅ ልጅ፣ይስሐቅ የአብርሃም ልጅ፣አብርሃም የታራ ልጅ፣ታራ የናኮር ልጅ፣ 35  ናኮር የሴሮህ ልጅ፣ሴሮህ የረኡ ልጅ፣ረኡ የፋሌቅ ልጅ፣ፋሌቅ የኤቤር ልጅ፣ኤቤር የሴሎም ልጅ፣ 36  ሴሎም የቃይናን ልጅ፣ቃይናን የአርፋክስድ ልጅ፣አርፋክስድ የሴም ልጅ፣ሴም የኖኅ ልጅ፣ኖኅ የላሜህ ልጅ፣ 37  ላሜህ የማቱሳላ ልጅ፣ማቱሳላ የሄኖክ ልጅ፣ሄኖክ የያሬድ ልጅ፣ያሬድ የመላልኤል ልጅ፣መላልኤል የቃይናን ልጅ፣ 38  ቃይናን የሄኖስ ልጅ፣ሄኖስ የሴት ልጅ፣ሴት የአዳም ልጅ፣አዳም የአምላክ ልጅ።
[]
[]
[]
[]
12,016
4  ከዚያም ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ተመለሰ፤ በምድረ በዳም ሳለ መንፈስ ይመራው ነበር፤ 2  በዚያም 40 ቀን ቆየ፤ ዲያብሎስም ፈተነው። በእነዚህም ቀናት ምንም ስላልበላ መጨረሻ ላይ ተራበ። 3  በዚህ ጊዜ ዲያብሎስ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ይህ ድንጋይ ዳቦ እንዲሆን እዘዝ” አለው። 4  ኢየሱስ ግን “‘ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰለት። 5  ቀጥሎም ዲያብሎስ ወደ አንድ ከፍ ያለ ቦታ አወጣውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው። 6  ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ይህ ሁሉ ሥልጣንና የእነዚህ መንግሥታት ክብር ተሰጥቶኛል፤ እኔ ደግሞ ለፈለግኩት መስጠት ስለምችል ለአንተ እሰጥሃለሁ። 7  ስለዚህ አንድ ጊዜ በፊቴ ተደፍተህ ብታመልከኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።” 8  ኢየሱስም መልሶ “‘ይሖዋ አምላክህን ብቻ አምልክ፤ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው። 9  ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት ላይ አቁሞ እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ 10  እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘አንተን እንዲጠብቁ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ 11  እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’” 12  ኢየሱስም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን አትፈታተነው’ ተብሏል” አለው። 13  ዲያብሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ትቶት ሄደ። 14  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ። ዝናውም በዙሪያው ባለ አገር ሁሉ ተሰራጨ። 15  በተጨማሪም በምኩራቦቻቸው ማስተማር ጀመረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ያከብረው ነበር። 16  ከዚያም ወዳደገበት ቦታ ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባ፤ ሊያነብም ተነስቶ ቆመ። 17  የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልልም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም ተርትሮ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ፦ 18  “የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ምክንያቱም ለድሆች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል። ለተማረኩት ነፃነትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቆኑትን ነፃ እንዳወጣ 19  እንዲሁም የይሖዋን ሞገስ ስለሚያገኙበት ዓመት እንድሰብክ ልኮኛል።” 20  ከዚያም ጥቅልሉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኩራቡ ውስጥ ያሉት ሰዎችም ሁሉ ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር። 21  እሱም “ይህ አሁን የሰማችሁት የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል ዛሬ ተፈጸመ” አላቸው። 22  ሁሉም ስለ እሱ መልካም ነገር ይናገሩ ጀመር፤ ከአፉ በሚወጡት የሚማርኩ ቃላትም በመደነቅ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለም እንዴ?” ይሉ ነበር። 23  በዚህ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “‘አንተ ሐኪም፣ እስቲ ራስህን አድን’ የሚለውን አባባል እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም። ‘በቅፍርናሆም እንደተደረገ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ አገርም አድርግ’ ትሉኛላችሁ።” 24  እንዲህም አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ነቢይ በገዛ አገሩ ተቀባይነት አያገኝም። 25  እውነቱን ልንገራችሁ፦ ለምሳሌ በኤልያስ ዘመን ሰማይ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር በተዘጋና በምድሪቱ ሁሉ ላይ ጽኑ ረሃብ በተከሰተ ጊዜ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ። 26  ሆኖም ኤልያስ በሲዶና አገር በሰራፕታ ትኖር ወደነበረች አንዲት መበለት ተላከ እንጂ ከእነዚህ ሴቶች ወደ አንዷም አልተላከም። 27  በተጨማሪም በነቢዩ ኤልሳዕ ዘመን በእስራኤል ብዙ የሥጋ ደዌ በሽተኞች ነበሩ፤ ሆኖም ከሶርያዊው ከንዕማን በስተቀር ከእነሱ መካከል አንድም ሰው አልነጻም።” 28  በምኩራቡ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ይህን ሲሰሙ እጅግ ተቆጡ፤ 29  ተነስተውም እያጣደፉ ከከተማው አስወጡት፤ ቁልቁል ገፍትረው ሊጥሉትም ፈልገው ከተማቸው ወደምትገኝበት ተራራ አፋፍ ወሰዱት። 30  እሱ ግን በመካከላቸው ሰንጥቆ ሄደ። 31  ከዚያም በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ሄደ። እዚያም በሰንበት ሕዝቡን ያስተምር ነበር፤ 32  በሥልጣን ይናገር ስለነበረም ሕዝቡ በትምህርት አሰጣጡ እጅግ ተደነቁ። 33  በምኩራቡም ውስጥ ርኩስ መንፈስ ማለትም ጋኔን ያደረበት አንድ ሰው ነበር፤ ሰውየውም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ጮኸ፦ 34  “እንዴ! የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን? የመጣኸው ልታጠፋን ነው? ማን እንደሆንክ በሚገባ አውቃለሁ፤ አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ ነህ።” 35  ሆኖም ኢየሱስ “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም ሰውየውን በሕዝቡ ፊት ከጣለው በኋላ ምንም ሳይጎዳው ለቆት ወጣ። 36  በዚህ ጊዜ ሁሉም በመገረም “እንዴ! ይህ ምን ዓይነት አነጋገር ነው? ርኩሳን መናፍስትን በሥልጣንና በኃይል ያዛል፤ እነሱም ታዘው ይወጣሉ!” ሲሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር። 37  ስለ ኢየሱስ የሚወራው ወሬም በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተዳረሰ። 38  ኢየሱስ ከምኩራቡ ከወጣ በኋላ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት ኃይለኛ ትኩሳት ይዟት እየተሠቃየች ነበር፤ እነሱም እንዲረዳት ለመኑት። 39  እሱም አጠገቧ ቆመና ጎንበስ ብሎ ትኩሳቱን ገሠጸው፤ ትኩሳቱም ለቀቃት። ወዲያውም ተነስታ ታገለግላቸው ጀመር። 40  ፀሐይ ስትጠልቅም ሰዎች በተለያየ በሽታ የተያዙ ሕመምተኞቻቸውን ወደ እሱ አመጡ። እሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው። 41  አጋንንትም “አንተ የአምላክ ልጅ ነህ” እያሉና እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ወጡ። እሱ ግን ገሠጻቸው፤ ክርስቶስ መሆኑንም አውቀው ስለነበር እንዳይናገሩ ከለከላቸው። 42  በነጋም ጊዜ ወጥቶ ገለል ወዳለ ስፍራ ሄደ። ሕዝቡ ግን ፈልገው ፈላልገው ያለበት ቦታ ድረስ መጡ፤ እንዳይሄድባቸውም ለመኑት። 43  እሱ ግን “ለሌሎች ከተሞችም የአምላክን መንግሥት ምሥራች ማወጅ አለብኝ፤ ምክንያቱም የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው” አላቸው። 44  በመሆኑም በይሁዳ ምኩራቦች መስበኩን ቀጠለ።
[]
[]
[]
[]
12,017
5  አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሴሬጥ ሐይቅ ዳርቻ ቆሞ የአምላክን ቃል ሲያስተምር ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ያዳምጡት ነበር፤ ከዚያም ሰዎቹ እየተገፋፉ ያጨናንቁት ጀመር። 2  በዚህ ጊዜ ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ዳርቻ ቆመው ተመለከተ፤ ዓሣ አጥማጆቹ ግን ከጀልባዎቹ ላይ ወርደው መረቦቻቸውን እያጠቡ ነበር። 3  ኢየሱስም አንደኛዋ ጀልባ ላይ ወጣ፤ የጀልባዋ ባለቤት የሆነውን ስምዖንንም ከየብስ ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ጠየቀው። ከዚያም ጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር። 4  ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ስምዖንን “ጥልቅ ወደሆነው አካባቢ ፈቀቅ በልና መረቦቻችሁን ጥላችሁ አጥምዱ” አለው። 5  ሆኖም ስምዖን መልሶ “መምህር፣ ሌሊቱን ሙሉ ስንደክም አድረን ምንም አልያዝንም፤ አንተ ካልክ ግን መረቦቹን እጥላለሁ” አለው። 6  እንደተባሉት ባደረጉም ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ። እንዲያውም መረቦቻቸው መበጣጠስ ጀመሩ። 7  በመሆኑም በሌላኛው ጀልባ ላይ የነበሩትን የሥራ ባልደረቦቻቸውን መጥተው እንዲያግዟቸው በምልክት ጠሯቸው፤ እነሱም መጡ፤ ሁለቱንም ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፤ ከዚህም የተነሳ ጀልባዎቹ መስጠም ጀመሩ። 8  ስምዖን ጴጥሮስ ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ እግር ሥር ተንበርክኮ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ስለሆንኩ ከእኔ ራቅ” አለው። 9  ይህን ያለው እሱና ከእሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ከያዙት ዓሣ ብዛት የተነሳ በጣም ስለተደነቁ ነው፤ 10  የስምዖን የሥራ ባልደረቦች የሆኑት የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም በጣም ተደንቀው ነበር። ኢየሱስ ግን ስምዖንን “አይዞህ አትፍራ፤ ከአሁን ጀምሮ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ” አለው። 11  ስለዚህ ጀልባዎቹን መልሰው ወደ የብስ ካስጠጉ በኋላ ሁሉን ነገር ትተው ተከተሉት። 12  በሌላ ጊዜ ደግሞ በአንድ ከተማ ውስጥ በነበረበት ጊዜ መላ ሰውነቱን የሥጋ ደዌ የወረሰው ሰው በዚያ ነበር። ሰውየውም ኢየሱስን ባየው ጊዜ በግንባሩ ተደፍቶ “ጌታ ሆይ፣ ብትፈልግ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ሲል ለመነው። 13  ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው። ወዲያውኑ የሥጋ ደዌው ለቀቀው። 14  ከዚያም ኢየሱስ ሰውየውን ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ስለ መንጻትህ መባ አቅርብ፤ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ” አለው። 15  ሆኖም ስለ እሱ የሚወራው ወሬ ይበልጥ እየተሰራጨ ሄደ፤ በጣም ብዙ ሰዎችም የሚናገረውን ለመስማትና ከበሽታቸው ለመፈወስ ይሰበሰቡ ነበር። 16  ይሁን እንጂ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ጭር ወዳሉ ስፍራዎች በመሄድ ይጸልይ ነበር። 17  አንድ ቀን ኢየሱስ እያስተማረ ሳለ ከገሊላ፣ ከይሁዳ መንደሮች ሁሉ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕጉ መምህራን በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ ሰዎችንም ለመፈወስ የሚያስችለው የይሖዋ ኃይል ከኢየሱስ ጋር ነበር። 18  በዚያን ጊዜም አንድ ሽባ ሰው በቃሬዛ የተሸከሙ ሰዎች መጡ፤ ሽባውን ወደ ውስጥ ለማስገባትና ኢየሱስ ፊት ለማስቀመጥ ጥረት አደረጉ። 19  ከሕዝቡም ብዛት የተነሳ መግቢያ ስላላገኙ ጣራው ላይ ወጥተው ጡቡን ካነሱ በኋላ የተኛበትን ቃሬዛ አሾልከው፣ ሽባውን ኢየሱስ ፊት በነበሩት ሰዎች መካከል አወረዱት። 20  ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት “አንተ ሰው፣ ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው። 21  በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን “አምላክን የሚዳፈረው ይሄ ማን ነው? ከአምላክ በቀር ኃጢአትን ማን ይቅር ሊል ይችላል?” ይባባሉ ጀመር። 22  ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ተረድቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በልባችሁ የምታስቡት ምንድን ነው? 23  ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሏል’ ከማለትና ‘ተነስተህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀላል? 24  ይሁንና የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ . . .” አላቸውና ሽባውን “ተነስ፣ ቃሬዛህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ” አለው። 25  በዚህ ጊዜ ሰውየው በፊታቸው ተነስቶ ተኝቶበት የነበረውን ቃሬዛ ተሸከመና አምላክን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ። 26  ይህን ሲያዩ ሁሉም በአድናቆት ተውጠው አምላክን ማመስገን ጀመሩ፤ ታላቅ ፍርሃትም አድሮባቸው “ዛሬ የሚያስደንቅ ነገር አየን!” አሉ። 27  ይህ ከሆነም በኋላ ኢየሱስ ወጥቶ ሲሄድ ሌዊ የሚባል ቀረጥ ሰብሳቢ በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየና “ተከታዬ ሁን” አለው። 28  እሱም ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጎ በመተው ተነስቶ ይከተለው ጀመር። 29  ከዚያም ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ በግብዣውም ላይ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ሰዎች ከእነሱ ጋር ይበሉ ነበር። 30  ፈሪሳውያንና ከእነሱ ወገን የሆኑ ጸሐፍት ይህን ባዩ ጊዜ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” በማለት በደቀ መዛሙርቱ ላይ ማጉረምረም ጀመሩ። 31  ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም። 32  እኔ የመጣሁት ኃጢአተኞች ንስሐ እንዲገቡ ለመጥራት እንጂ ጻድቃንን ለመጥራት አይደለም።” 33  እነሱም “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ እንዲሁም ምልጃ ያቀርባሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ፣ ይጠጣሉ” አሉት። 34  ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው ከእነሱ ጋር እያለ የሙሽራው ጓደኞች እንዲጾሙ ልታደርጓቸው ትችላላችሁ? 35  ሆኖም ሙሽራው ከእነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።” 36  በተጨማሪም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “ከአዲስ ልብስ ላይ ቁራጭ ጨርቅ ወስዶ በአሮጌ ልብስ ላይ የሚጥፍ ሰው የለም። እንዲህ ቢያደርግ ግን አዲሱ ቁራጭ ጨርቅ ተቦጭቆ ይነሳል፤ ከአዲሱ ልብስ የተቆረጠው ጨርቅ ከአሮጌው ልብስ ጋር አይስማማም። 37  ደግሞም ባረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያስቀምጥ ሰው የለም። እንዲህ ቢያደርግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ ወይኑ ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። 38  ስለዚህ አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ መቀመጥ አለበት። 39  አሮጌ የወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲሱን የሚፈልግ የለም፤ ምክንያቱም ‘አሮጌው ግሩም ነው’ ይላል።”
[]
[]
[]
[]
12,018
6  በአንድ የሰንበት ቀን ኢየሱስ በእህል እርሻ መካከል እያለፈ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ እሸት ቀጥፈው በእጃቸው እያሹ ይበሉ ነበር። 2  በዚህ ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን “በሰንበት ቀን በሕግ የተከለከለ ነገር የምታደርጉት ለምንድን ነው?” አሏቸው። 3  ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ዳዊት እሱና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ነገር ፈጽሞ አላነበባችሁም? 4  ወደ አምላክ ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር ማንም እንዲበላው ያልተፈቀደውን በአምላክ ፊት የቀረበ ኅብስት ተቀብሎ እንደበላና ከእሱ ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው አላነበባችሁም?” 5  ከዚያም “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው” አላቸው። 6  በሌላ የሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ ያስተምር ጀመር። በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለ አንድ ሰው ነበር። 7  ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም ኢየሱስን የሚከሱበት ምክንያት ማግኘት ይፈልጉ ስለነበር በሰንበት ይፈውስ እንደሆነ ለማየት በትኩረት ይከታተሉት ነበር። 8  እሱ ግን ሐሳባቸውን አውቆ ስለነበር እጁ የሰለለበትን ሰው “ተነሳና መሃል ላይ ቁም” አለው። ሰውየውም ተነስቶ በዚያ ቆመ። 9  ከዚያም ኢየሱስ “እስቲ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ፤ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት ማዳን ነው ወይስ ማጥፋት?” አላቸው። 10  በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ” አለው። ሰውየውም እንደተባለው አደረገ፤ እጁም ዳነለት። 11  እነሱ ግን እጅግ ተቆጡ፤ በኢየሱስ ላይ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉም እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር። 12  በዚያው ሰሞን ኢየሱስ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊቱንም ሙሉ ወደ አምላክ ሲጸልይ አደረ። 13  በነጋ ጊዜም ደቀ መዛሙርቱን ወደ እሱ ጠርቶ ከመካከላቸው 12 ሰዎች መረጠ፤ ሐዋርያት ብሎም ሰየማቸው፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦ 14  ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፣ ወንድሙ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣ በርቶሎሜዎስ፣ 15  ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ “ቀናተኛው” የሚባለው ስምዖን፣ 16  የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና በኋላ ከሃዲ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ። 17  ከእነሱም ጋር ከተራራው ወርዶ ደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፤ ደቀ መዛሙርቱ የሆኑ እጅግ ብዙ ሰዎችም በዚያ ነበሩ፤ በተጨማሪም እሱን ለመስማትና ከበሽታቸው ለመፈወስ ከይሁዳ ሁሉና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አካባቢ ከሚገኙት ከጢሮስና ከሲዶና የመጡ በጣም ብዙ ሰዎች ነበሩ። 18  በርኩሳን መናፍስት ይሠቃዩ የነበሩ ሰዎችም እንኳ ተፈወሱ። 19  ኃይል ከእሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለነበር ሕዝቡ ሁሉ ሊነካው ይፈልግ ነበር። 20  ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ቀና ብሎ በመመልከት እንዲህ ይል ጀመር፦ “እናንተ ድሆች የሆናችሁ ደስተኞች ናችሁ፤ የአምላክ መንግሥት የእናንተ ነውና። 21  “እናንተ አሁን የምትራቡ ደስተኞች ናችሁ፤ ኋላ ትጠግባላችሁና። “እናንተ አሁን የምታለቅሱ ደስተኞች ናችሁ፤ ኋላ ትስቃላችሁና። 22  “ሰዎች፣ በሰው ልጅ ምክንያት በሚጠሏችሁ፣ በሚያገሏችሁ፣ በሚነቅፏችሁና ክፉ እንደሆናችሁ አድርገው ያለስማችሁ ስም በሚሰጧችሁ ጊዜ ሁሉ ደስተኞች ናችሁ። 23  በሰማይ ታላቅ ሽልማት ስለሚጠብቃችሁ በዚያን ቀን ሐሴት አድርጉ፤ በደስታም ፈንጥዙ፤ አባቶቻቸው በነቢያት ላይ እንዲሁ ያደርጉ ነበርና። 24  “ነገር ግን እናንተ ሀብታሞች ወዮላችሁ፤ መጽናኛችሁን በሙሉ አግኝታችኋልና። 25  “እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፤ ኋላ ትራባላችሁና። “እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፤ ኋላ ታዝናላችሁና፤ እንዲሁም ታለቅሳላችሁ። 26  “ሰዎች ስለ እናንተ መልካም ነገር በሚናገሩበት ጊዜ ሁሉ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኛ ነቢያት እንዲህ ያለ ነገር አድርገው ነበርና። 27  “ለእናንተ ለምትሰሙ ግን እላችኋለሁ፦ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ፤ 28  የሚረግሟችሁን መርቁ፤ እንዲሁም ለሚሰድቧችሁ ጸልዩ። 29  አንዱን ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን ስጠው፤ መደረቢያህን ለሚወስድብህ እጀ ጠባብህንም አትከልክለው። 30  ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፤ ንብረትህን የሚወስድብህንም ሰው እንዲመልስ አትጠይቀው። 31  “በተጨማሪም ልክ ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ እንደምትፈልጉት ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው። 32  “የሚወዷችሁን ብቻ ብትወዱ ምን የሚያስመሰግን ነገር አለው? ኃጢአተኞችም እንኳ የሚወዷቸውን ይወዳሉና። 33  መልካም ለሚያደርጉላችሁ መልካም ብታደርጉስ ምን ዋጋ አለው? ኃጢአተኞችም እንኳ እንዲሁ ያደርጋሉ። 34  እንዲሁም ይመልስልኛል ብላችሁ ለምታስቡት ሰው ብታበድሩ ምን ፋይዳ አለው? ኃጢአተኞችም እንኳ የሰጡትን ያህል መልሰው ለመቀበል ለኃጢአተኞች ያበድራሉ። 35  ከዚህ ይልቅ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ደግሞም በምላሹ ምንም ሳትጠብቁ አበድሩ፤ ሽልማታችሁም ታላቅ ይሆናል፤ ደግሞም የልዑሉ አምላክ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ደግ ነውና። 36  አባታችሁ መሐሪ እንደሆነ ሁሉ እናንተም መሐሪዎች ሁኑ። 37  “በተጨማሪም በሌሎች ላይ አትፍረዱ፤ በእናንተም ላይ ፈጽሞ አይፈረድባችሁም፤ ሌሎችን አትኮንኑ፤ እናንተም ፈጽሞ አትኮነኑም። ምንጊዜም ሌሎችን ይቅር በሉ፤ እናንተም ይቅር ትባላላችሁ። 38  ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል። ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና በተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው በእቅፋችሁ ይሰጧችኋል። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።” 39  ከዚያም እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላል? ሁለቱም ተያይዘው ጉድጓድ ውስጥ አይወድቁም? 40  ተማሪ ከአስተማሪው አይበልጥም፤ በሚገባ የተማረ ሁሉ ግን እንደ አስተማሪው ይሆናል። 41  ታዲያ በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለምን ታያለህ? 42  በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ ወንድምህን ‘ዓይንህ ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! መጀመሪያ በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ማየት ትችላለህ። 43  “መልካም ዛፍ ሆኖ ሳለ የበሰበሰ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም፤ እንዲሁም የበሰበሰ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም። 44  እያንዳንዱ ዛፍ በፍሬው ይታወቃል። ለምሳሌ ሰዎች ከእሾህ በለስ አይለቅሙም፤ ወይም ከእሾሃማ ቁጥቋጦ ወይን አይቆርጡም። 45  ጥሩ ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ነገር ጥሩ ነገር ያወጣል፤ ክፉ ሰው ግን ካከማቸው መጥፎ ነገር ክፉ ነገር ያወጣል፤ አንደበቱ የሚናገረው በልቡ ውስጥ የሞላውን ነውና። 46  “ታዲያ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!’ የምትሉኝ፣ የምለውን ግን የማታደርጉት ለምንድን ነው? 47  ወደ እኔ የሚመጣ፣ ቃሌን የሚሰማና የሚያደርግ ሁሉ ከማን ጋር እንደሚመሳሰል ልንገራችሁ፦ 48  ቤት ለመሥራት በጥልቀት ቆፍሮ በዓለት ላይ መሠረቱን ከጣለ ሰው ጋር ይመሳሰላል። በኋላም ጎርፍ በመጣ ጊዜ ወንዙ ቤቱን በኃይል መታው፤ ሆኖም ቤቱ በደንብ ስለተገነባ ሊያነቃንቀው አልቻለም። 49  በሌላ በኩል ደግሞ ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ሰው ሁሉ መሠረት ሳይጥል፣ በአፈር ላይ ቤት ከሠራ ሰው ጋር ይመሳሰላል። ወንዙም ቤቱን በኃይል መታው፤ ወዲያውም ተደረመሰ፤ እንዳልነበረም ሆነ።”
[]
[]
[]
[]
12,019
7  ኢየሱስ ለሕዝቡ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ። 2  በዚያም አንድ የጦር መኮንን ነበር፤ በጣም የሚወደው ባሪያውም በጠና ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር። 3  እሱም ስለ ኢየሱስ ሲሰማ መጥቶ ባሪያውን እንዲፈውስለት ይለምኑለት ዘንድ የተወሰኑ አይሁዳውያን ሽማግሌዎችን ላከ። 4  እነሱም ወደ ኢየሱስ መጥተው እንዲህ በማለት ተማጸኑት፦ “ይህን ሰው ልትረዳው ይገባል፤ 5  ምክንያቱም ሕዝባችንን ይወዳል፤ ምኩራባችንንም ያሠራልን እሱ ነው።” 6  ስለዚህ ኢየሱስ አብሯቸው ሄደ። ሆኖም ወደ ቤቱ በተቃረበ ጊዜ መኮንኑ ወዳጆቹን እንዲህ ሲል ወደ ኢየሱስ ላከ፦ “ጌታዬ፣ በቤቴ ጣሪያ ሥር ልትገባ የሚገባኝ ሰው ስላልሆንኩ አትድከም። 7  ከዚህም የተነሳ አንተ ፊት መቅረብ የሚገባኝ ሰው እንደሆንኩ አልተሰማኝም። ስለዚህ አንተ አንድ ቃል ተናገርና አገልጋዬ ይፈወስ። 8  እኔ ራሴ የምታዘዛቸው የበላይ አዛዦች አሉ፤ ለእኔም የሚታዘዙ የበታች ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።” 9  ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ በሰውየው በጣም ተደንቆ ይከተለው ወደነበረው ሕዝብ ዞር በማለት “እላችኋለሁ፣ በእስራኤል ውስጥ እንኳ እንዲህ ዓይነት ታላቅ እምነት አላገኘሁም” አለ። 10  የተላኩትም ሰዎች ወደ ቤት ሲመለሱ ባሪያው ድኖ አገኙት። 11  ከዚህ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ናይን ወደምትባል ከተማ ተጓዘ፤ ደቀ መዛሙርቱና ሌሎች ብዙ ሰዎችም አብረውት ይጓዙ ነበር። 12  ወደ ከተማዋ መግቢያ ሲቃረብ ሰዎች የአንድ ሰው አስከሬን ተሸክመው በመውጣት ላይ ነበሩ፤ ሟቹ ለእናቱ አንድ ልጇ ነበር። በተጨማሪም እናቱ መበለት ነበረች። ብዙ የከተማዋ ሕዝብም ከእሷ ጋር ነበር። 13  ጌታ ባያት ጊዜ በጣም አዘነላትና “በቃ፣ አታልቅሺ” አላት። 14  ከዚያም ቀረብ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙት ሰዎችም ባሉበት ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት፣ ተነስ እልሃለሁ!” አለ። 15  የሞተውም ሰው ቀና ብሎ ተቀመጠና መናገር ጀመረ፤ ኢየሱስም ለእናቱ ሰጣት። 16  በዚህ ጊዜ ሁሉም በፍርሃት ተውጠው “ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነስቷል፤” እንዲሁም “አምላክ ሕዝቡን አሰበ” እያሉ አምላክን ያወድሱ ጀመር። 17  ኢየሱስ ያከናወነውም ነገር በይሁዳ ሁሉና በአካባቢው ባለ አገር ሁሉ ተሰማ። 18  በዚህ ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ይህን ሁሉ አወሩለት። 19  ዮሐንስም ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ጠርቶ “ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው እንዲጠይቁት ወደ ጌታ ላካቸው። 20  ሰዎቹም ወደ ኢየሱስ መጥተው “መጥምቁ ዮሐንስ፣ ‘ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?’ ብለን እንድንጠይቅህ ወደ አንተ ልኮናል” አሉት። 21  ኢየሱስ በዚያኑ ሰዓት ብዙዎችን ከሕመምና ከከባድ በሽታ ፈወሳቸው፤ እንዲሁም ያደሩባቸውን ክፉ መናፍስት አወጣ፤ የብዙ ዓይነ ስውራንንም ዓይን አበራ። 22  እሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሄዳችሁ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፦ ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው። 23  በእኔ ምክንያት የማይሰናከል ደስተኛ ነው።” 24  የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ይናገር ጀመር፦ “ወደ ምድረ በዳ የሄዳችሁት ምን ለማየት ነበር? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆ? 25  ታዲያ ምን ለማየት ነበር የሄዳችሁት? ምርጥ ልብስ የለበሰ ሰው ለማየት? የተንቆጠቆጠ ልብስ የሚለብሱና በቅንጦት የሚኖሩማ የሚገኙት በቤተ መንግሥት ነው። 26  ታዲያ ምን ለማየት ሄዳችሁ? ነቢይ? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጥ ነው። 27  ‘እነሆ፣ ከፊትህ እየሄደ መንገድህን እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ’ ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ነው። 28  እላችኋለሁ፣ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ የለም፤ ሆኖም በአምላክ መንግሥት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።” 29  (ሕዝቡ ሁሉ እንዲሁም ቀራጮች ይህን በሰሙ ጊዜ በዮሐንስ ጥምቀት ተጠምቀው ስለነበር አምላክ ጻድቅ መሆኑን አምነው ተቀበሉ። 30  ሆኖም ፈሪሳውያንና የሕጉ አዋቂዎች በዮሐንስ ባለመጠመቃቸው የአምላክን ምክር አቃለሉ።) 31  ኢየሱስ በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የዚህን ትውልድ ሰዎች ከማን ጋር ላነጻጽራቸው? ማንንስ ይመስላሉ? 32  በገበያ ስፍራ ተቀምጠው እርስ በርሳቸው እየተጠራሩ ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ እናንተ ግን አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ እናንተ ግን አላለቀሳችሁም’ ከሚባባሉ ልጆች ጋር ይመሳሰላሉ። 33  በተመሳሳይም መጥምቁ ዮሐንስ እህል ሳይበላና ወይን ጠጅ ሳይጠጣ መጣ፤ እናንተ ግን ‘ጋኔን አለበት’ አላችሁ። 34  የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እናንተ ግን ‘እዩ፣ ይህን ሆዳምና ለወይን ጠጅ ያደረ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኃጢአተኞች ወዳጅ!’ አላችሁ። 35  የሆነ ሆኖ፣ ጥበብ ጻድቅ መሆኗ በልጆቿ ሁሉ ተረጋግጧል።” 36  ከዚህ በኋላ ከፈሪሳውያን አንዱ አብሮት እንዲበላ ኢየሱስን ደጋግሞ ለመነው። ስለሆነም ኢየሱስ ወደ ፈሪሳዊው ቤት ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። 37  እነሆም፣ በከተማው ውስጥ በኃጢአተኝነቷ የምትታወቅ አንዲት ሴት ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት እየበላ መሆኑን በሰማች ጊዜ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች። 38  እሷም ከበስተ ኋላ እግሩ አጠገብ ሆና እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመር፤ ከዚያም በፀጉሯ አበሰችው። በተጨማሪም እግሩን እየሳመች ዘይቱን ቀባችው። 39  የጋበዘው ፈሪሳዊም ይህን ሲያይ “ይህ ሰው በእርግጥ ነቢይ ቢሆን ኖሮ የምትነካው ማን መሆኗንና ምን ዓይነት ሴት እንደሆነች ይኸውም ኃጢአተኛ መሆኗን ባወቀ ነበር” ብሎ በልቡ አሰበ። 40  ኢየሱስ ግን መልሶ “ስምዖን፣ አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። እሱም “መምህር፣ እሺ ንገረኝ” አለው። 41  “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንዱ 500 ሌላው ደግሞ 50 ዲናር ተበድረው ነበር። 42  ሁለቱም የተበደሩትን መክፈል ባቃታቸው ጊዜ አበዳሪው ዕዳቸውን ሙሉ በሙሉ ተወላቸው። እንግዲህ ከሁለቱ ሰዎች አበዳሪውን አብልጦ የሚወደው የትኛው ነው?” 43  ስምዖንም መልሶ “ብዙ ዕዳ የተተወለት ይመስለኛል” አለው። እሱም “በትክክል ፈርደሃል” አለው። 44  ከዚያም ወደ ሴቲቱ ዞር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያታለህ? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ይሁንና አንተ ለእግሬ ውኃ አልሰጠኸኝም። ይህች ሴት ግን እግሬን በእንባዋ እያራሰች በፀጉሯ አበሰች። 45  አንተ አልሳምከኝም፤ ይህች ሴት ግን ከገባሁበት ሰዓት አንስቶ እግሬን መሳሟን አላቋረጠችም። 46  አንተ ራሴን ዘይት አልቀባህም፤ ይህች ሴት ግን እግሬን ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ቀባች። 47  ስለዚህ እልሃለሁ፣ ኃጢአቷ ብዙ ቢሆንም ይቅር ተብሎላታል፤ ምክንያቱም ታላቅ ፍቅር አሳይታለች። በትንሹ ይቅር የተባለ ግን የሚያሳየውም ፍቅር አነስተኛ ነው።” 48  ከዚያም ሴትየዋን “ኃጢአትሽ ይቅር ተብሎልሻል” አላት። 49  በማዕድ አብረውት የተቀመጡት በልባቸው “ኃጢአትን እንኳ ይቅር የሚል ይህ ሰው ማን ነው?” ይሉ ጀመር። 50  ኢየሱስ ግን ሴትየዋን “እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ” አላት።
[]
[]
[]
[]
12,020
8  ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የአምላክን መንግሥት ምሥራች እየሰበከና እያወጀ ከከተማ ወደ ከተማ እንዲሁም ከመንደር ወደ መንደር ተጓዘ። አሥራ ሁለቱም ከእሱ ጋር ነበሩ፤ 2  በተጨማሪም ከክፉ መናፍስትና ከበሽታ የተፈወሱ አንዳንድ ሴቶች አብረውት ነበሩ፦ ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የተባለችው ማርያም፣ 3  የሄሮድስ ቤት አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐና፣ ሶስና እንዲሁም ሌሎች ብዙ ሴቶች የነበሩ ሲሆን በንብረታቸው ያገለግሏቸው ነበር። 4  ኢየሱስም የየከተማው ሕዝብ ተከትሎት በመጣ ጊዜና እጅግ ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት ወቅት እንዲህ ሲል በምሳሌ ተናገረ፦ 5  “አንድ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ። በሚዘራበት ጊዜ አንዳንዶቹ ዘሮች መንገድ ዳር ወድቀው ተረጋገጡ፤ የሰማይ ወፎችም መጥተው ለቀሟቸው። 6  አንዳንዶቹ ዓለት ላይ ወደቁ፤ ከበቀሉም በኋላ እርጥበት ስላላገኙ ደረቁ። 7  ሌሎቹ ደግሞ በእሾህ መካከል ወደቁ፤ አብሯቸው ያደገውም እሾህ አነቃቸው። 8  ሌሎቹ ግን ጥሩ አፈር ላይ ወደቁ፤ ከበቀሉም በኋላ 100 እጥፍ አፈሩ።” ይህን ከተናገረ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ “የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” አለ። 9  ደቀ መዛሙርቱ ግን የዚህን ምሳሌ ትርጉም ጠየቁት። 10  እሱም እንዲህ አለ፦ “ለእናንተ የአምላክን መንግሥት ቅዱስ ሚስጥሮች የመረዳት ችሎታ ተሰጥቷችኋል፤ ለቀሩት ግን በምሳሌ እነግራቸዋለሁ፤ ይኸውም እያዩ እንዳያስተውሉ እንዲሁም እየሰሙ ትርጉሙን እንዳይረዱ ነው። 11  እንግዲህ የምሳሌው ትርጉም ይህ ነው፦ ዘሩ የአምላክ ቃል ነው። 12  በመንገድ ዳር የወደቁት ቃሉን የሰሙ ናቸው፤ ከዚያ በኋላ ግን አምነው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል። 13  በዓለት ላይ የወደቁት ቃሉን ሲሰሙ በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ ነገር ግን ሥር የላቸውም። ለጊዜው አምነው ቢቀበሉም በፈተና ወቅት ይወድቃሉ። 14  በእሾህ መካከል የወደቁት ቃሉን የሰሙ ናቸው፤ ሆኖም በዚህ ዓለም የኑሮ ጭንቀት፣ ሀብትና ሥጋዊ ደስታ ትኩረታቸው ተከፋፍሎ ሙሉ በሙሉ ይታነቃሉ፤ ለፍሬም አይበቁም። 15  በጥሩ አፈር ላይ የወደቁት ደግሞ ቃሉን በመልካምና በጥሩ ልብ ሰምተው በውስጣቸው በማኖር በጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው። 16  “መብራት አብርቶ ዕቃ የሚከድንበት ወይም አልጋ ሥር የሚያስቀምጥ ሰው የለም፤ ከዚህ ይልቅ ወደ ቤት የሚገቡ ሁሉ ብርሃን እንዲያገኙ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል። 17  በመሆኑም ተሸሽጎ የማይገለጥ፣ በሚገባ ቢሰወርም የማይታወቅና ይፋ የማይወጣ ነገር የለም። 18  ስለዚህ እንዴት እንደምታዳምጡ በጥሞና አስቡ፤ ላለው ተጨማሪ ይሰጠዋልና፤ የሌለው ግን እንዳለው አድርጎ የሚያስበው ነገር እንኳ ይወሰድበታል።” 19  ከዚህ በኋላ እናቱና ወንድሞቹ እሱ ወዳለበት መጡ፤ ሆኖም ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ወደ እሱ ሊቀርቡ አልቻሉም። 20  ስለዚህ “እናትህና ወንድሞችህ ሊያገኙህ ፈልገው ውጭ ቆመዋል” ተብሎ ተነገረው። 21  እሱም መልሶ “እናቴና ወንድሞቼ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት እነዚህ ናቸው” አላቸው። 22  አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጀልባ ከተሳፈረ በኋላ “ወደ ሐይቁ ማዶ እንሻገር” አላቸው። በመሆኑም ጉዞ ጀመሩ። 23  እየተጓዙም ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደው። በዚህ ጊዜ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በሐይቁ ላይ ተነሳ፤ ጀልባቸውም በውኃ መሞላት ስለጀመረች አደጋ ላይ ወደቁ። 24  ስለዚህ ሄደው ቀሰቀሱትና “መምህር፣ መምህር ማለቃችን እኮ ነው!” አሉት። እሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ ነፋሱንና የሚናወጠውን ውኃ ገሠጸ፤ በዚህ ጊዜ ነፋሱ ቆመ፤ ጸጥታም ሰፈነ። 25  ከዚያም “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነሱ ግን በፍርሃት ተውጠውና በጣም ተደንቀው እርስ በርሳቸው “ለመሆኑ ይህ ማን ነው? ነፋስና ውኃ እንኳ ይታዘዙለታል” ተባባሉ። 26  ከዚያም በገሊላ ማዶ ወደሚገኘው ጌርጌሴኖን ወደተባለው ክልል የባሕር ዳርቻ ደረሱ። 27  ኢየሱስ ከጀልባዋ ወደ የብስ በወረደ ጊዜ አጋንንት ያደሩበት በአቅራቢያው በሚገኝ ከተማ የሚኖር አንድ ሰው አገኘው። ይህ ሰው ልብስ መልበስ ከተወ ብዙ ጊዜ ሆኖት ነበር፤ የሚኖረውም በቤት ውስጥ ሳይሆን በመቃብር ስፍራ ነበር። 28  ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እየጮኸ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም “የልዑል አምላክ ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለ። 29  (ይህን ያለውም ኢየሱስ ርኩሱ መንፈስ ከሰውየው እንዲወጣ እያዘዘው ስለነበረ ነው። ርኩሱ መንፈስ ሰውየውን ብዙ ጊዜ ይይዘው ነበር፤ ሰውየው በተደጋጋሚ በሰንሰለትና በእግር ብረት እየታሰረ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም የታሰረበትን ሰንሰለት ይበጣጥስ ነበር፤ ጋኔኑም ጭር ወዳሉ ቦታዎች ይነዳው ነበር።) 30  ኢየሱስ “ስምህ ማን ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ስለነበር “ሌጌዎን” አለው። 31  አጋንንቱም ወደ ጥልቁ እንዲሄዱ እንዳያዛቸው ተማጸኑት። 32  በዚያም በተራራው ላይ ብዛት ያለው የአሳማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ ስለዚህ ወደ አሳማዎቹ ይገቡ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ተማጸኑት፤ እሱም ፈቀደላቸው። 33  በዚህ ጊዜ አጋንንቱ ከሰውየው ወጥተው አሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ የአሳማውም መንጋ ከገደሉ አፋፍ እየተንደረደረ በመውረድ ሐይቁ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። 34  እረኞቹ ግን የሆነውን ነገር ሲያዩ ሸሽተው በመሄድ ወሬውን በከተማውና በገጠሩ አዳረሱ። 35  በዚህ ጊዜ ሕዝቡ የሆነውን ነገር ለማየት ወጡ። ወደ ኢየሱስ ሲመጡም አጋንንት የወጡለት ሰው ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጦ አገኙት፤ በዚህ ጊዜ ፍርሃት አደረባቸው። 36  የተፈጸመውን ነገር ያዩ ሰዎች አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው እንዴት ጤናማ ሊሆን እንደቻለ አወሩላቸው። 37  በዚህ ጊዜ ከጌርጌሴኖን ክልል የመጡት ሰዎች በሙሉ ታላቅ ፍርሃት ስላደረባቸው ኢየሱስን ከዚያ እንዲሄድላቸው ለመኑት። እሱም ከዚያ ለመሄድ ጀልባዋ ላይ ተሳፈረ። 38  አጋንንት የወጡለት ሰው ግን አብሮት ይሆን ዘንድ ደጋግሞ ለመነው፤ ሆኖም ኢየሱስ ሰውየውን እንዲህ ሲል አሰናበተው፦ 39  “ወደ ቤትህ ተመለስ፤ አምላክ ያደረገልህንም ነገር ተናገር።” ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ነገር በከተማው ሁሉ እያወጀ ሄደ። 40  ሕዝቡ እየጠበቁት ስለነበር ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ ሁሉም በደስታ ተቀበሉት። 41  በዚህ ጊዜ ኢያኢሮስ የሚባል አንድ የምኩራብ አለቃ መጣ። ኢየሱስ እግር ላይም ወድቆ ወደ ቤቱ እንዲገባ ይማጸነው ጀመር፤ 42  ይህን ያደረገው 12 ዓመት ገደማ የሆናት አንዲት ልጁ ልትሞት ተቃርባ ስለነበር ነው። ኢየሱስ እየተጓዘ ሳለ ሕዝቡ እየተጋፋ ያጨናንቀው ነበር። 43  በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈስሳት የኖረች አንዲት ሴት የነበረች ሲሆን ይህችን ሴት ሊፈውሳት የቻለ አንድም ሰው አልነበረም። 44  ከኋላም መጥታ የልብሱን ዘርፍ ነካች፤ ይፈሳት የነበረውም ደም ወዲያውኑ ቆመ። 45  በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፣ ጴጥሮስ “መምህር፣ ሕዝቡ ከቦህ እየተጋፋህ ነው የሚሄደው” አለው። 46  ኢየሱስ ግን “ኃይል ከእኔ እንደወጣ ስለታወቀኝ አንድ ሰው ነክቶኛል” አለ። 47  ሴትየዋም ሳይታወቅባት መሄድ እንዳልቻለች በተረዳች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ ከዚያም ለምን እንደነካችውና እንዴት ወዲያውኑ እንደተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት ተናገረች። 48  እሱ ግን “ልጄ ሆይ፣ እምነትሽ አድኖሻል። በሰላም ሂጂ” አላት። 49  ገና እየተናገረ ሳለ ከምኩራብ አለቃው ቤት የተላከ አንድ ሰው መጥቶ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታስቸግረው” አለው። 50  ኢየሱስ ይህን ሲሰማ “አትፍራ፤ ብቻ እመን፤ ልጅህ ትድናለች” አለው። 51  ወደ ኢያኢሮስ ቤት በደረሰ ጊዜ ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቷ አባትና እናት በስተቀር ማንም አብሮት ወደ ውስጥ እንዲገባ አልፈቀደም። 52  በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ ለልጅቷ እያለቀሱና በሐዘን ደረታቸውን እየደቁ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ “በቃ አታልቅሱ፤ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው። 53   ይህን ሲሰሙ ልጅቷ እንደሞተች ያውቁ ስለነበር በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። 54  እሱ ግን እጇን በመያዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” አለ። 55  የልጅቷም መንፈስ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሳች፤ የምትበላውም ነገር እንዲሰጧት አዘዘ። 56  ወላጆቿም የሚሆኑት ጠፋቸው፤ እሱ ግን የሆነውን ነገር ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
[]
[]
[]
[]
12,021
9  ከዚያም አሥራ ሁለቱን አንድ ላይ ጠርቶ አጋንንትን ሁሉ የማዘዝ እንዲሁም በሽታን የመፈወስ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው። 2  ደግሞም የአምላክን መንግሥት እንዲሰብኩና የታመሙትን እንዲፈውሱ ላካቸው፤ 3  እንዲህም አላቸው፦ “ለጉዟችሁ ምንም ነገር አትያዙ፤ በትርም ሆነ የምግብ ከረጢት፣ ዳቦም ሆነ ገንዘብ እንዲሁም ሁለት ልብስ አትያዙ። 4  ሆኖም ወደ አንድ ቤት ስትገቡ ከተማዋን ለቃችሁ እስክትሄዱ ድረስ እዚያው ቆዩ፤ ከዚያም ተነስታችሁ ሂዱ። 5  በየትኛውም ከተማ የሚቀበላችሁ ሰው ካጣችሁ፣ ከዚያ ከተማ ስትወጡ ምሥክር እንዲሆንባቸው የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።” 6  እነሱም ወጥተው በሄዱበት ሁሉ ምሥራቹን እየተናገሩና የታመሙትን እየፈወሱ ከመንደር ወደ መንደር በመሄድ ክልሉን አዳረሱ። 7  በዚህ ጊዜ የአውራጃ ገዢ የሆነው ሄሮድስ የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ አንዳንዶች ዮሐንስ ከሞት ተነስቷል ይሉ ስለነበረም በጣም ግራ ተጋባ፤ 8  ይሁንና ሌሎች ኤልያስ ተገልጧል፤ ሌሎች ደግሞ ከጥንት ነቢያት አንዱ ተነስቷል ይሉ ነበር። 9  ሄሮድስም “ዮሐንስን አንገቱን ቆርጬዋለሁ። ታዲያ እንዲህ ሲወራለት የምሰማው ይህ ሰው ማን ነው?” አለ። ስለሆነም ሊያየው ይፈልግ ነበር። 10  ሐዋርያቱም በተመለሱ ጊዜ ያደረጉትን ነገር ሁሉ ለኢየሱስ ተረኩለት። እሱም ቤተሳይዳ ወደምትባል ከተማ ብቻቸውን ይዟቸው ሄደ። 11  ሆኖም ሕዝቡ ይህን ስላወቁ ተከተሉት። እሱም በደግነት ተቀብሎ ስለ አምላክ መንግሥት ይነግራቸው ጀመር፤ ፈውስ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው። 12  ቀኑም መምሸት ሲጀምር አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ወደ እሱ መጥተው “ያለንበት ስፍራ ገለል ያለ ስለሆነ ሕዝቡ በአካባቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት። 13  እሱ ግን “እናንተ የሚበሉት ነገር ስጧቸው” አላቸው። እነሱም “ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ምግብ ካልገዛን በስተቀር ከአምስት ዳቦና ከሁለት ዓሣ ሌላ ምንም የለንም” አሉት። 14  በዚያም 5,000 ያህል ወንዶች ነበሩ። እሱ ግን ደቀ መዛሙርቱን “ሕዝቡን በሃምሳ በሃምሳ ከፋፍላችሁ አስቀምጧቸው” አላቸው። 15  እነሱም በታዘዙት መሠረት ሕዝቡ እንዲቀመጥ አደረጉ። 16  ከዚያም አምስቱን ዳቦና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ባረከ። ቆርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። 17  ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ። 18  በኋላም ብቻውን ሆኖ እየጸለየ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እሱ መጡ፤ እሱም “ሕዝቡ እኔን ማን ይሉኛል?” ሲል ጠየቃቸው። 19  እነሱም መልሰው “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ከጥንት ነቢያት አንዱ ተነስቷል ይላሉ” አሉት። 20  እሱም “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ “የአምላክ መሲሕ ነህ” አለው። 21  ከዚያም ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አስጠነቀቃቸው፤ 22  ቀጥሎም “የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበሉ፣ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፍት ተቀባይነት ማጣቱ ብሎም መገደሉና በሦስተኛው ቀን መነሳቱ አይቀርም” አላቸው። 23  ከዚያም ለሁሉም እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤ የራሱን የመከራ እንጨት በየዕለቱ ይሸከም፤ ያለማቋረጥም ይከተለኝ። 24  ሕይወቱን ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔ ሲል ሕይወቱን የሚያጣ ሁሉ ግን ያድናታል። 25  ደግሞስ አንድ ሰው ዓለምን ሁሉ የራሱ ቢያደርግ፣ ነገር ግን ሕይወቱን ቢያጣ ወይም ለጉዳት ቢዳረግ ምን ይጠቅመዋል? 26  በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅም በክብሩ እንዲሁም በአብና በቅዱሳን መላእክት ክብር ሲመጣ ያፍርበታል። 27  እውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆሙት መካከል አንዳንዶች የአምላክን መንግሥት እስኪያዩ ድረስ ፈጽሞ ሞትን አይቀምሱም።” 28  በመሆኑም ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ያህል በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። 29  እየጸለየም ሳለ የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ነጭ ሆኖ አንጸባረቀ። 30  እነሆም ሁለት ሰዎች ይኸውም ሙሴና ኤልያስ ከእሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር። 31  እነሱም በክብር ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ስለሚፈጸመውና ከዚህ ዓለም ተለይቶ ስለሚሄድበት ሁኔታ ይነጋገሩ ጀመር። 32  በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና አብረውት የነበሩት እንቅልፍ ተጫጭኗቸው ነበር፤ ሙሉ በሙሉ ሲነቁ ግን የኢየሱስን ክብር እንዲሁም አብረውት የቆሙትን ሁለት ሰዎች አዩ። 33  ሰዎቹ ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ ጴጥሮስ ኢየሱስን “መምህር፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው። ስለዚህ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴና አንድ ለኤልያስ ሦስት ድንኳኖች እንትከል” አለው፤ ምን እየተናገረ እንዳለ አላስተዋለም ነበር። 34  ይህን እየተናገረ ሳለ ግን ደመና መጥቶ ጋረዳቸው። ደመናው ሲሸፍናቸው ፍርሃት አደረባቸው። 35  ከዚያም ከደመናው “የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው። እሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ። 36  ድምፁም በተሰማ ጊዜ ኢየሱስን ብቻውን ሆኖ አዩት። እነሱም ዝም አሉ፤ ያዩትንም ነገር በዚያን ወቅት ለማንም አልተናገሩም። 37  በማግስቱ ከተራራው ሲወርዱ እጅግ ብዙ ሕዝብ ከኢየሱስ ጋር ተገናኘ። 38  እነሆም ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “መምህር፣ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ፤ ምክንያቱም ያለኝ ልጅ አንድ እሱ ብቻ ነው። 39  እነሆም፣ ርኩስ መንፈስ ይይዘውና በድንገት ይጮኻል፤ ጥሎም በአፉ አረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ጉዳት ካደረሰበትም በኋላ በስንት መከራ ይለቀዋል። 40  ደቀ መዛሙርትህ እንዲያስወጡት ለመንኳቸው፤ እነሱ ግን አልቻሉም።” 41  ኢየሱስም መልሶ “እምነት የለሽና ጠማማ ትውልድ ሆይ፣ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር መቆየትና እናንተን መታገሥ ሊኖርብኝ ነው? እስቲ ልጅህን ወደዚህ አምጣው” አለ። 42  ሆኖም ወደ እሱ እየመጣ ሳለ ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ በኃይል አንፈራገጠው። ይሁንና ኢየሱስ ርኩሱን መንፈስ ገሠጸውና ልጁን ፈወሰው፤ ከዚያም ለአባቱ መልሶ ሰጠው። 43  በዚህ ጊዜ ሁሉም በአምላክ ታላቅ ኃይል ተደነቁ። ሰዎቹ ኢየሱስ ባደረገው ነገር ሁሉ እየተደነቁ ሳሉ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ 44  “ይህን የምነግራችሁን ቃል በጥሞና አዳምጡ፤ ደግሞም አስታውሱ፤ የሰውን ልጅ ለሰዎች አሳልፈው ይሰጡታልና።” 45  እነሱ ግን የነገራቸው ነገር አልገባቸውም። እንዲያውም እንዳያስተውሉት ነገሩ ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ጉዳይ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። 46  ከዚህ በኋላ ከመካከላቸው ማን እንደሚበልጥ እርስ በርሳቸው ይከራከሩ ጀመር። 47  ኢየሱስ የልባቸውን ሐሳብ ስላወቀ አንድ ትንሽ ልጅ አምጥቶ አጠገቡ አቆመ፤ 48  ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔንም ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝንም ይቀበላል። ምክንያቱም ታላቅ የሚባለው ራሱን ከሁላችሁ እንደሚያንስ አድርጎ የሚቆጥር ነው።” 49  ዮሐንስም “መምህር፣ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያስወጣ አየን፤ ይሁንና ከእኛ ጋር ሆኖ አንተን ስለማይከተል ልንከለክለው ሞከርን” አለው። 50  ኢየሱስ ግን “የማይቃወማችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ስለሆነ አትከልክሉት” አለው። 51  ኢየሱስ የሚያርግበት ጊዜ ሲቃረብ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቆርጦ ተነሳ። 52  ስለዚህ አስቀድሞ መልእክተኞች ላከ። እነሱም ሄደው ለእሱ የሚያስፈልገውን ነገር ለማዘጋጀት ወደ አንድ የሳምራውያን መንደር ገቡ። 53   ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቆርጦ እንደተነሳ ስላወቁ አልተቀበሉትም። 54  ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ “ጌታ ሆይ፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝ ትፈልጋለህ?” አሉት። 55  እሱ ግን ዞር ብሎ ገሠጻቸው። 56  ስለዚህ ወደ ሌላ መንደር ሄዱ። 57   በመንገድ እየተጓዙም ሳሉ አንድ ሰው “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው። 58  ኢየሱስ ግን “ቀበሮዎች ጉድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ቦታ የለውም” አለው። 59  ከዚያም ሌላውን “ተከታዬ ሁን” አለው። ሰውየውም “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው። 60  እሱ ግን “ሙታን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤ አንተ ግን ሄደህ የአምላክን መንግሥት በየቦታው አውጅ” አለው። 61  አንድ ሌላ ሰው ደግሞ “ጌታ ሆይ፣ እኔ እከተልሃለሁ፤ በመጀመሪያ ግን ቤተሰቤን እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለው። 62  ኢየሱስም “ዕርፍ ጨብጦ በኋላው ያሉትን ነገሮች የሚመለከት ሰው ለአምላክ መንግሥት የሚገባ አይደለም” አለው።
[]
[]
[]
[]
12,022
1  በ30ኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፣ በኬባር ወንዝ አጠገብ በግዞት በተወሰደው ሕዝብ መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው አምላክ የገለጠልኝን ራእዮች ማየት ጀመርኩ። 2  ከወሩ በአምስተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ዮአኪን በግዞት በተወሰደ በአምስተኛው ዓመት፣ 3  በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የይሖዋ ቃል የካህኑ የቡዚ ልጅ ወደሆነው ወደ ሕዝቅኤል መጣ። በዚያም የይሖዋ ኃይል በእሱ ላይ ወረደ። 4  እኔም በማየት ላይ ሳለሁ ከሰሜን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ሲመጣ ተመለከትኩ፤ በዚያም ታላቅ ደመናና በደማቅ ብርሃን የተከበበ የእሳት ብልጭታ ነበር፤ ከእሳቱም መካከል የሚያብረቀርቅ ብረት የሚመስል ነገር ይወጣ ነበር። 5  በመካከሉም የአራት ሕያዋን ፍጥረታት አምሳያ ነበር፤ የእያንዳንዳቸውም መልክ እንደ ሰው መልክ ነበር። 6  እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው። 7  እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእግራቸውም ኮቴ የጥጃ ኮቴ ይመስል ነበር፤ እግሮቻቸውም እንደተወለወለ መዳብ ያብረቀርቃሉ። 8  በአራቱም ጎኖቻቸው ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጆች ነበሯቸው፤ አራቱም ፊቶችና ክንፎች ነበሯቸው። 9  ክንፎቻቸውም እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም፤ እያንዳንዳቸውም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር። 10  የፊታቸው መልክ ይህን ይመስል ነበር፦ አራቱም የሰው ፊት ነበራቸው፤ በስተ ቀኝ የአንበሳ ፊት፣ በስተ ግራ የበሬ ፊት ነበራቸው፤ ደግሞም አራቱም የንስር ፊት ነበራቸው። 11  ፊታቸው ይህን ይመስላል። ክንፎቻቸው ከእነሱ በላይ ተዘርግተዋል። እያንዳንዳቸው እርስ በርሳቸው የሚነካኩ ሁለት ክንፎች ነበሯቸው፤ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር። 12  እያንዳንዳቸው መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ ሁሉ ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር። በሚሄዱበት ጊዜ አይዞሩም። 13  የሕያዋን ፍጥረታቱ መልክ የሚነድ የከሰል ፍም ይመስላል፤ በሕያዋን ፍጥረታቱም መካከል እየነደደ ያለ ችቦ የሚመስል ነገር ወዲያና ወዲህ ይል ነበር፤ ከእሳቱም መካከል መብረቅ ይወጣ ነበር። 14  ሕያዋን ፍጥረታቱም ወዲያና ወዲህ ሲሄዱ እንቅስቃሴያቸው የመብረቅ ብልጭታ ይመስል ነበር። 15  እኔም ሕያዋን ፍጥረታቱን ስመለከት አራት ፊቶች ባሉት በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አጠገብ በምድር ላይ አንድ አንድ መንኮራኩር አየሁ። 16  መንኮራኩሮቹ በአጠቃላይ ሲታዩ እንደ ክርስቲሎቤ የሚያብረቀርቅ መልክ ነበራቸው፤ አራቱም ይመሳሰላሉ። መልካቸውና አሠራራቸው ሲታይ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስላል። 17  በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መዞር ሳያስፈልጋቸው በአራቱም ጎን በፈለጉበት አቅጣጫ መሄድ ይችላሉ። 18  የመንኮራኩሮቹም ጠርዝ እጅግ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ የሚያስፈራ ነበር፤ የአራቱም መንኮራኩሮች ጠርዝ ዙሪያውን በዓይኖች የተሞላ ነበር። 19  ሕያዋን ፍጥረታቱ በተንቀሳቀሱ ቁጥር፣ መንኮራኩሮቹም ከእነሱ ጋር አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ሕያዋን ፍጥረታቱ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከፍ ከፍ ይላሉ። 20  መንፈሱ ወደመራቸው አቅጣጫ፣ መንፈሱ ወደሚሄድበት ቦታ ሁሉ ይሄዳሉ። መንኮራኩሮቹ ከእነሱ ጋር አብረው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ በመንኮራኩሮቹም ውስጥ ነበርና። 21  ሕያዋን ፍጥረታቱ ሲንቀሳቀሱ እነሱም ይንቀሳቀሳሉ፤ ሕያዋን ፍጥረታቱ ሲቆሙ እነሱም ይቆማሉ፤ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከእነሱ ጋር አብረው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ በመንኮራኩሮቹም ውስጥ ነበርና። 22  ከሕያዋን ፍጥረታቱ ራስ በላይ እጅግ አስደናቂ እንደሆነ በረዶ የሚያብረቀርቅ ጠፈር የሚመስል ነገር ነበር፤ ይህም ከራሳቸው በላይ ተዘርግቶ ነበር። 23  ከጠፈሩ በታች ክንፎቻቸው አንዳቸው ወደ ሌላው ቀጥ ብለው ነበር። እያንዳንዳቸውም በዚህ ጎንና በዚያኛው ጎን ሰውነታቸውን የሚሸፍኑባቸው ሁለት ሁለት ክንፎች ነበሯቸው። 24  የክንፎቻቸውን ድምፅ ስሰማ እንደሚጎርፍ ውኃ ድምፅ፣ ደግሞም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ድምፅ ነበር። በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ድምፁ እንደ ሠራዊት ድምፅ ነበር። በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻቸውን ወደ ታች ያደርጋሉ። 25  ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር በላይ አንድ ድምፅ ይሰማ ነበር። (በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻቸውን ወደ ታች ያደርጉ ነበር።) 26  ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የመሰለ እንደ ዙፋን ያለ ነገር ነበር። ከላይ በኩል ባለው በዙፋኑ ላይ መልኩ የሰው መልክ የሚመስል ተቀምጦ ነበር። 27  ወገቡ ከሚመስለው ነገር ጀምሮ ወደ ላይ፣ እሳት የሚመስል እንደ ብረት የሚያብረቀርቅ ነገር ሲወጣ አየሁ፤ ደግሞም ከወገቡ ጀምሮ ወደ ታች፣ እሳት የሚመስል ነገር አየሁ። በዙሪያውም ደማቅ ብርሃን ነበር፤ 28  ይህም ዝናባማ በሆነ ቀን በደመና ውስጥ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ነበር። በዙሪያው ያለው ደማቅ ብርሃን ይህን ይመስላል። ደግሞም የይሖዋን ክብር ይመስል ነበር። እኔም ባየሁት ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፤ ከዚያም አንዱ ሲናገር ድምፅ ሰማሁ።
[]
[]
[]
[]
12,023
10  እኔም እያየሁ ሳለ ከኪሩቦቹ ራስ በላይ ካለው ጠፈር በላይ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ ነገር ተገለጠ፤ መልኩም ዙፋን ይመስል ነበር። 2  ከዚያም አምላክ በፍታ የለበሰውን ሰው “በኪሩቦቹ ሥር ወደሚገኙት የሚሽከረከሩ መንኮራኩሮች መሃል ግባና በኪሩቦቹ መካከል ካለው ፍም በእጆችህ ዘግነህ በከተማዋ ላይ በትነው” አለው። እሱም እኔ እያየሁት ገባ። 3  ሰውየው ወደዚያ ሲገባ ኪሩቦቹ ከቤተ መቅደሱ በስተ ቀኝ ቆመው ነበር፤ ደመናውም የውስጠኛውን ግቢ ሞላው። 4  የይሖዋም ክብር ከኪሩቦቹ ላይ ተነስቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ሄደ፤ ቤተ መቅደሱም ቀስ በቀስ በደመናው ተሞላ፤ ግቢውም በይሖዋ ክብር ብርሃን ተሞላ። 5  የኪሩቦቹም ክንፎች ድምፅ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሲናገር እንደሚሰማው ድምፅ እስከ ውጨኛው ግቢ ድረስ ይሰማ ነበር። 6  ከዚያም አምላክ፣ በፍታ የለበሰውን ሰው “ከሚሽከረከሩት መንኮራኩሮች መካከልና ከኪሩቦቹ መሃል እሳት ውሰድ” ብሎ አዘዘው፤ ሰውየውም ገብቶ ከመንኮራኩሩ አጠገብ ቆመ። 7  ከዚያም አንዱ ኪሩብ፣ በኪሩቦቹ መካከል ወዳለው እሳት እጁን ዘረጋ። የተወሰነ እሳት ወስዶ በፍታ በለበሰው ሰው እጆች ላይ አደረገ፤ እሱም እሳቱን ይዞ ወጣ። 8  ኪሩቦቹ ከክንፎቻቸው ሥር የሰው እጅ የሚመስል ነገር ነበራቸው። 9  እኔም እያየሁ ሳለ በኪሩቦቹ አጠገብ አራት መንኮራኩሮች ተመለከትኩ፤ በእያንዳንዱ ኪሩብ አጠገብ አንድ መንኮራኩር ነበር፤ መንኮራኩሮቹም እንደ ክርስቲሎቤ ድንጋይ የሚያብረቀርቅ መልክ ነበራቸው። 10  የአራቱም መልክ ይመሳሰል ነበር፤ በአንድ መንኮራኩር ውስጥ በጎን በኩል ሌላ መንኮራኩር የተሰካ ይመስል ነበር። 11  በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መዞር ሳያስፈልጋቸው በአራቱም አቅጣጫ መሄድ ይችሉ ነበር፤ ምክንያቱም መዞር ሳያስፈልጋቸው ፊታቸው ወደሚያይበት አቅጣጫ ሁሉ ይሄዱ ነበር። 12  ሰውነታቸው ሁሉ፣ ጀርባቸው፣ እጃቸው፣ ክንፋቸው እንዲሁም መንኮራኩሮቹ ይኸውም የአራቱም መንኮራኩሮች ሁለመና በዓይን የተሞላ ነበር። 13  አንድ ድምፅ መንኮራኩሮቹን “ተሽከርካሪ መንኮራኩሮች!” ብሎ ሲጠራቸው ሰማሁ። 14  እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊት ነበራቸው። የመጀመሪያው ፊት የኪሩብ ፊት፣ ሁለተኛው ፊት የሰው ፊት፣ ሦስተኛውም የአንበሳ ፊት፣ አራተኛው ደግሞ የንስር ፊት ነበር። 15  ኪሩቦቹም ወደ ላይ ተነሱ፤ በኬባር ወንዝ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት እነዚሁ ነበሩ፤ 16  ኪሩቦቹ ሲንቀሳቀሱ፣ መንኮራኩሮቹም አጠገባቸው ሆነው ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ኪሩቦቹ ከምድር በላይ ከፍ ከፍ ለማለት ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ሲዘረጉ መንኮራኩሮቹ ከአጠገባቸው አይለዩም ወይም አይርቁም ነበር። 17  እነሱ ሲቆሙ፣ መንኮራኩሮቹም ይቆማሉ፤ እነሱ ከፍ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር፤ በሕያዋን ፍጥረታቱ ላይ የሚሠራው መንፈስ በውስጣቸው ነበርና። 18  ከዚያም የይሖዋ ክብር ከቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ተነስቶ በመሄድ ከኪሩቦቹ በላይ ቆመ። 19  ኪሩቦቹ እኔ እያየኋቸው ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘርግተው ከምድር ተነሱ። እነሱ ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም አብረዋቸው ነበሩ። በይሖዋ ቤት በስተ ምሥራቅ በሚገኘው በር መግቢያም ላይ ቆሙ፤ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር። 20  እነዚህ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረታት ናቸው፤ በመሆኑም ኪሩቦች መሆናቸውን አወቅኩ። 21  አራቱም፣ አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበራቸው፤ ከክንፎቻቸውም ሥር የሰው እጆች የሚመስሉ ነገሮች ነበሯቸው። 22  የፊታቸውም መልክ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ እንዳየኋቸው ፊቶች ነበር። እያንዳንዳቸው ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,024
11  መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው የይሖዋ ቤት የምሥራቅ በር አመጣኝ። በዚያም በበሩ መግቢያ ላይ 25 ሰዎች አየሁ፤ ከእነሱም መካከል የሕዝቡ አለቆች የሆኑት የአዙር ልጅ ያአዛንያህና የበናያህ ልጅ ጰላጥያህ ነበሩ። 2  ከዚያም አምላክ እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ክፋትን የሚያቅዱና በዚህች ከተማ መጥፎ ምክር የሚመክሩ ናቸው። 3  እነሱ ‘አሁን ቤት የምንሠራበት ጊዜ አይደለም? ከተማዋ ድስት ናት፤ እኛ ደግሞ ሥጋ ነን’ ይላሉ። 4  “ስለዚህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር።” 5  ከዚያም የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ መጣ፤ እንዲህም አለኝ፦ “እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ የተናገራችሁት ነገር ትክክል ነው፤ የምታስቡትን ነገር አውቃለሁ። 6  በዚህች ከተማ ብዙዎች እንዲሞቱ አድርጋችኋል፤ ጎዳናዎቿንም በሙታን ሞልታችኋል።”’” 7  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ በከተማዋ ዙሪያ የጣላችኋቸው ሬሳዎች፣ እነሱ ሥጋው ናቸው፤ ከተማዋ ደግሞ ድስቱ ናት። እናንተ ግን ከውስጧ ትወሰዳላችሁ።’” 8  “‘ሰይፍን ፈርታችኋል፤ እኔም ሰይፍ አመጣባችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 9  ‘ከእሷ አውጥቼ ለባዕዳን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የፍርድ እርምጃም እወስድባችኋለሁ። 10  በሰይፍ ትወድቃላችሁ። በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። 11  ከተማዋ ድስት አትሆንላችሁም፤ እናንተም በውስጧ እንዳለ ሥጋ አትሆኑም፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ 12  እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። በሥርዓቴ አልተመላለሳችሁምና፤ ድንጋጌዎቼንም አላከበራችሁም፤ ይልቁንም በዙሪያችሁ ያሉትን ብሔራት ድንጋጌዎች ተከተላችሁ።’” 13  ትንቢት ተናግሬ እንደጨረስኩ የበናያህ ልጅ ጰላጥያህ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ተደፍቼ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! የእስራኤልን ቀሪዎች ፈጽመህ ልታጠፋ ነው?” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኽኩ። 14  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 15  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች፣ ወንድሞችህን ይኸውም የመቤዠት መብት ያላቸውን ወንድሞችህንና የእስራኤልን ቤት ሁሉ ‘ከይሖዋ ራቁ። ምድሪቱ የእኛ ናት፤ ለእኛ ርስት ሆና ተሰጥታለች’ ብለዋቸዋል። 16  ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሩቅ ወዳሉ ብሔራት በግዞት እንዲወሰዱና በብዙ አገሮች መካከል እንዲበተኑ ባደርግም በሄዱባቸው አገሮች ውስጥ ለጥቂት ጊዜ መቅደስ እሆናቸዋለሁ።”’ 17  “ስለዚህ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ደግሞም ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች አመጣችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ። 18  እነሱም ወደዚያ ይመለሳሉ፤ በላይዋም ላይ ያሉትን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉና ጸያፍ የሆኑ ልማዶች ሁሉ ያስወግዳሉ። 19  እኔም ያልተከፋፈለ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አኖራለሁ፤ ድንጋይ የሆነውንም ልብ ከሰውነታቸው አውጥቼ የሥጋ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ 20  ይህም ደንቦቼን አክብረው እንዲመላለሱ እንዲሁም ድንጋጌዎቼን እንዲጠብቁና እንዲታዘዙ ነው። በዚህ ጊዜ እነሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።”’ 21  “‘“ሆኖም አስጸያፊ ነገሮቻቸውንና ጸያፍ የሆኑ ልማዶቻቸውን አጥብቀው ለመከተል በልባቸው ቆርጠው የተነሱትን በተመለከተ፣ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’” 22  በዚህ ጊዜ ኪሩቦቹ ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ዘረጉ፤ መንኮራኩሮቹም በአጠገባቸው ነበሩ፤ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ነበር። 23  ከዚያም የይሖዋ ክብር ከከተማዋ ተነስቶ ወደ ላይ ወጣ፤ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ ባለው ተራራም ላይ ቆመ። 24  ከዚያም መንፈስ፣ በአምላክ ኃይል አማካኝነት በተሰጠኝ ራእይ ወደ ላይ አነሳኝ፤ ደግሞም በከለዳውያን ምድር ወዳሉት ግዞተኞች አመጣኝ። ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ተለየ። 25  እኔም ይሖዋ ያሳየኝን ነገር ሁሉ በግዞት ላሉት ሰዎች መናገር ጀመርኩ።
[]
[]
[]
[]
12,025
12  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የምትኖረው በዓመፀኛ ሕዝብ መካከል ነው። እነሱ የሚያዩበት ዓይን አላቸው፣ ግን አያዩም፤ የሚሰሙበት ጆሮ አላቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም፤ እነሱ ዓመፀኛ ሕዝብ ናቸውና። 3  የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተ ግን በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ለመሄድ ጓዝህን አዘጋጅ። ከዚያም እነሱ እያዩህ በቀን ጉዞ ጀምር። እነሱ እያዩህ ከቤትህ ተነስተህ ወደ ሌላ ቦታ እንደ ግዞተኛ ሂድ። ዓመፀኛ ሕዝብ ቢሆኑም እንኳ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይገባቸው ይሆናል። 4  በቀን እነሱ እያዩህ በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ለመሄድ ጓዝህን አዘጋጅተህ አውጣ፤ ከዚያም ምሽት ላይ እነሱ እያዩህ በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ውጣ። 5  “እነሱ እያዩ ግንቡን ነድለህ በዚያ በኩል ጓዝህን ተሸክመህ ውጣ። 6  እነሱ እያዩ ጓዝህን በትከሻህ ተሸክመህ በጨለማ ይዘኸው ውጣ። መሬቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን፤ ለእስራኤል ቤት ምልክት አደርግሃለሁና።” 7  እኔም ልክ እንደታዘዝኩት አደረግኩ። ቀን ላይ በግዞት እንደሚሄድ ሰው ጓዝ፣ ጓዜን ጠቅልዬ አወጣሁ፤ ከዚያም ምሽት ላይ ግንቡን በእጄ ነደልኩት። ሲጨልምም ዓይናቸው እያየ ጓዜን በትከሻዬ ተሸክሜ ወጣሁ። 8  ጠዋት ላይ የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 9  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ዓመፀኛ ሕዝብ የሆኑት የእስራኤል ቤት ሰዎች ‘ምን እያደረግክ ነው?’ ብለው አልጠየቁህም? 10  እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ቃል የተነገረው በኢየሩሳሌም ለሚኖረው አለቃና በከተማዋ ውስጥ ለሚኖረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ነው።”’ 11  “እንዲህ በል፦ ‘እኔ ለእናንተ ምልክት ነኝ። ልክ እኔ እንዳደረግኩት በእነሱም ላይ እንዲሁ ይደረግባቸዋል። ተማርከው በግዞት ይወሰዳሉ። 12  በመካከላቸው ያለው አለቃ በጨለማ ጓዙን በትከሻው ተሸክሞ ይወጣል። ግንቡን ይነድልና ጓዙን ተሸክሞ በዚያ በኩል ይወጣል። መሬቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።’ 13  መረቤን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል። ከዚያም ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ምድሪቱን ግን አያይም፤ በዚያም ይሞታል። 14  በእሱም ዙሪያ ያሉትን ሁሉ ይኸውም ረዳቶቹንና ወታደሮቹን በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፤ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ። 15  በብሔራት መካከል ስበትናቸውና በአገሮችም መካከል ስዘራቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 16  ይሁንና በሚሄዱባቸው ብሔራት መካከል አስጸያፊ ስለሆኑት ልማዶቻቸው ሁሉ እንዲናገሩ ከእነሱ መካከል ጥቂት ሰዎች ከሰይፍ፣ ከረሃብና ከቸነፈር እንዲተርፉ አደርጋለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።” 17  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 18  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ምግብህን እየተንቀጠቀጥክ ብላ፤ ውኃህንም በስጋትና በጭንቀት ጠጣ። 19  ለምድሪቱም ሕዝብ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእስራኤል ምድር ላሉት የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ ይላል፦ “ምግባቸውን በጭንቀት ይበላሉ፤ ውኃቸውንም በፍርሃት ይጠጣሉ፤ በምድሪቱ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ከሚፈጽሙት ዓመፅ የተነሳ ምድራቸው ፈጽማ ባድማ ትሆናለችና። 20  ሰው ይኖርባቸው የነበሩት ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም ወና ትሆናለች፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’” 21  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 22  “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል ምድር ‘ዘመኑ አልፏል፤ ራእይም ሁሉ መና ቀርቷል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው? 23  ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህን አባባል አስቀራለሁ፤ በእስራኤልም ምድር ይህን አባባል ዳግመኛ አይጠቀሙበትም።”’ ሆኖም እንዲህ በላቸው፦ ‘ዘመኑ ቀርቧል፤ እያንዳንዱም ራእይ ይፈጸማል።’ 24  በእስራኤል ቤት መካከል ከእንግዲህ የሐሰት ራእይ ወይም አሳሳች ሟርት አይኖርምና። 25  ‘“እኔ ይሖዋ እናገራለሁና። የተናገርኩት ቃል ሁሉ ከእንግዲህ ሳይዘገይ ይፈጸማል። ዓመፀኛው ቤት ሆይ፣ በእናንተ ዘመን እኔ እናገራለሁ፤ የተናገርኩትንም እፈጽማለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’” 26  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 27  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ሰዎች ‘እሱ የሚያየው ራእይ የሚፈጸመው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፤ ትንቢት የሚናገረውም በጣም ሩቅ ስለሆነ ጊዜ ነው’ ይላሉ። 28  ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ከተናገርኩት ቃል ውስጥ የሚዘገይ አይኖርም፤ የተናገርኩት ቃል ሁሉ ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’”
[]
[]
[]
[]
12,026
13  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤ የገዛ ራሳቸውን ትንቢት ፈጥረው የሚናገሩትንም እንዲህ በላቸው፦ ‘የይሖዋን ቃል ስሙ። 3  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ምንም ያዩት ነገር ሳይኖር የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉት ሞኝ ነቢያት ወዮላቸው! 4  እስራኤል ሆይ፣ ነቢያትህ በፍርስራሽ መካከል እንደሚኖሩ ቀበሮዎች ሆነዋል። 5  እስራኤል፣ በይሖዋ ቀን በሚኖረው ውጊያ ጸንቶ ይቆም ዘንድ በድንጋይ ቅጥሩ ላይ የሚገኙትን የፈረሱ ቦታዎች ለእስራኤል ቤት መልሳችሁ ለመገንባት ወደዚያ አትሄዱም።” 6  “ይሖዋ ሳይልካቸው ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል’ የሚሉ ሰዎች ያዩአቸው ራእዮች ውሸት ናቸው፤ ትንቢታቸውም ሐሰት ነው፤ ይሁንና ቃላቸው እንዲፈጸም ይጠብቃሉ። 7  እኔ የተናገርኩት ነገር ሳይኖር ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል’ ስትሉ ያያችሁት ራእይ ውሸት፣ የተናገራችሁትም ትንቢት ሐሰት መሆኑ አይደለም?”’ 8  “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ውሸት ስለተናገራችሁና ያያችኋቸው ራእዮች ሐሰት ስለሆኑ እኔ በእናንተ ላይ ተነስቻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 9  እጄ የውሸት ራእዮች በሚያዩና የሐሰት ትንቢት በሚናገሩ ነቢያት ላይ ተነስታለች። ሚስጥሬን ከማካፍላቸው ሰዎች መካከል አይሆኑም፤ በእስራኤል ቤት መዝገብም ላይ አይጻፉም፤ ወደ እስራኤልም ምድር አይመለሱም፤ እናንተም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። 10  ይህ ሁሉ የሚሆነው ሰላም ሳይኖር “ሰላም አለ!” እያሉ ሕዝቤን በማሳታቸው ነው። ሕዝቡ ጥንካሬ የሌለው ግድግዳ ሲሠራ እነሱ በኖራ ይለስኑታል።’ 11  “በኖራ የሚለስኑትን ሰዎች ግድግዳው ይፈርሳል በላቸው። ከባድ ዶፍ ይጥላል፤ የበረዶ ድንጋይ ይወርዳል፤ ኃይለኛ አውሎ ነፋስም ግድግዳውን ያፈርሰዋል። 12  ግድግዳው በሚወድቅበት ጊዜም ‘የለሰናችሁት ልስን የት አለ?’ ብለው ይጠይቋችኋል። 13  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በታላቅ ቁጣዬ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እንዲነሳ አደርጋለሁ፤ በቁጣዬም ከባድ ዶፍ አዘንባለሁ፤ ደግሞም ጥፋት በሚያስከትል ታላቅ ንዴት የበረዶ ድንጋይ አወርዳለሁ። 14  እናንተ በኖራ የለሰናችሁትን ግድግዳ አፍርሼ ከመሬት እደባልቀዋለሁ፤ መሠረቱም ይታያል። ከተማዋ ስትወድቅ በውስጧ ትጠፋላችሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ 15  “‘ቁጣዬን ሁሉ በግድግዳውና ግድግዳውን በኖራ በለሰኑት ሰዎች ላይ በማወርድበት ጊዜ እንዲህ እላችኋለሁ፦ “ግድግዳው ፈርሷል፤ በኖራ የለሰኑት ሰዎችም የሉም። 16  ለኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩትና ሰላም ሳይኖር የሰላም ራእዮች የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ጠፍተዋል”’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 17  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ የገዛ ራሳቸውን ትንቢት ፈጥረው ወደሚናገሩት የሕዝብህ ሴቶች ልጆች ፊትህን አዙር፤ በእነሱም ላይ ትንቢት ተናገር። 18  እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሰዎችን ሕይወት ለማደን፣ በክንድ ሁሉ ላይ የሚታሰር ቀጭን ጨርቅ ለሚሰፉና ለሰው እንደየቁመቱ የራስ መሸፈኛ ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤን ሕይወት እያደናችሁ የራሳችሁን ሕይወት ለማዳን ትጥራላችሁ? 19  የእናንተን ውሸት ለሚያዳምጠው ሕዝቤ ውሸት እየተናገራችሁ መሞት የማይገባቸውን ሰዎች በመግደልና መኖር የማይገባቸውን ሰዎች በሕይወት በማቆየት፣ ለጥቂት እፍኝ ገብስና ለቁርስራሽ ዳቦ ብላችሁ በሕዝቤ መካከል ታረክሱኛላችሁ?”’ 20  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ ሴቶች፣ እነሆ ሰዎችን እንደ ወፎች ለማደን በምትጠቀሙበት ጨርቅ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤ ከክንዳችሁም ላይ እቀደዋለሁ፤ እንደ ወፎች ያደናችኋቸውንም ሰዎች ነፃ አወጣለሁ። 21  የራስ መሸፈኛችሁን እቀዳለሁ፤ ሕዝቤንም ከእጃችሁ እታደጋለሁ፤ ከእንግዲህ አድናችሁ አትይዟቸውም፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። 22  እኔ እንዲያዝን ያላደረግኩትን ጻድቅ ሰው ሐሰት በመናገር ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጋችኋልና፤ ደግሞም ክፉው ሰው ከክፋት መንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዳይኖር እጁን አበርትታችኋል። 23  ስለዚህ እናንተ ሴቶች፣ ከእንግዲህ የውሸት ራእዮች አታዩም፤ ሟርትም አታሟርቱም፤ ሕዝቤንም ከእጃችሁ እታደጋለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”
[]
[]
[]
[]
12,027
14  ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። 2  ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 3  “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ለመከተል ቆርጠው ተነስተዋል፤ ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጠዋል። ታዲያ እኔን እንዲጠይቁኝ ልፈቅድላቸው ይገባል? 4  እንግዲህ ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ እስራኤላዊ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ አንድን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ እኔ ይሖዋ፣ እንደ አስጸያፊ ጣዖቶቹ ብዛት በተገቢው መንገድ እመልስለታለሁ። 5  የእስራኤልን ቤት ሰዎች ልብ አሸብራለሁና፤ ምክንያቱም ሁሉም ከእኔ ርቀዋል፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ተከትለዋል።”’ 6  “ስለሆነም የእስራኤልን ቤት ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ተመለሱ፤ አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻችሁ ራቁ፤ ቀፋፊ ከሆኑት ልማዶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ። 7  ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ከእኔ በመለየት አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቹን ለመከተል ቆርጦ ተነስቶና ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ አስቀምጦ የእኔን ነቢይ ለመጠየቅ ቢመጣ እኔ ይሖዋ፣ አዎ እኔ ራሴ እመልስለታለሁ። 8  ፊቴን ወደዚህ ሰው አዞራለሁ፤ መቀጣጫና መተረቻ አደርገዋለሁ፤ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’ 9  “‘ይሁንና ነቢዩ ቢሞኝና ምላሽ ቢሰጥ፣ ያንን ነቢይ ያሞኘሁት እኔ ይሖዋ ነኝ። ከዚያም እጄን በእሱ ላይ ዘርግቼ ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ። 10  የፈጸሙት በደል የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይሸከማሉ፤ ነቢዩን ሊጠይቅ የመጣው ሰው በደል ነቢዩ ከፈጸመው በደል ጋር አንድ ዓይነት ይሆናል፤ 11  ይህም የሚሆነው የእስራኤል ቤት ሰዎች ከእኔ ርቀው እንዳይባዝኑና በሚፈጽሙት በደል ሁሉ ራሳቸውን ከማርከስ እንዲቆጠቡ ነው። እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 12  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 13  “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ አገር ታማኝ ሳይሆን ቀርቶ በእኔ ላይ ኃጢአት ቢፈጽም እጄን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ የምግብ አቅርቦቱም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤ ረሃብም እሰድበታለሁ እንዲሁም ሰውንም ሆነ እንስሳን ከዚያ አጠፋለሁ።” 14  “‘እነዚህ ሦስት ሰዎች ይኸውም ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ በዚያ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 15  “‘ወይም አደገኛ የዱር አራዊትን ወደዚያ አገር ብሰድ፣ በአገሩ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ቢፈጁና አገሩ በዱር አራዊቱ የተነሳ ማንም ሰው የማያልፍበት ወና እንዲሆን ቢያደርጉ፣ 16  በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው፤ አገሩም ባድማ ይሆናል።’” 17  “‘ወይም ደግሞ በአገሩ ላይ ሰይፍ ባመጣና “በአገሩ መካከል ሰይፍ ይለፍ” ብል፣ በአገሩም ላይ ያለውን ሰውም ሆነ እንስሳ ባጠፋ፣ 18  እነዚህ ሦስት ሰዎች በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው።’” 19  “‘ወይም በአገሩ ላይ ቸነፈር ብሰድና ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት ደም በማፍሰስ በአገሩ ላይ ቁጣዬን ባወርድ፣ 20  ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ በዚያ ቢኖሩ እንኳ፣ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ወንዶችንም ሆነ ሴቶች ልጆቻቸውን ማዳን አይችሉም፤ በጽድቃቸው የሚያድኑት ራሳቸውን ብቻ ነው።’” 21  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውንም ሆነ እንስሳን ለማጥፋት በኢየሩሳሌም ላይ አራት ቅጣቶቼን ይኸውም ሰይፍን፣ ረሃብን፣ አደገኛ የዱር አራዊትንና ቸነፈርን በምሰድበት ጊዜ ምንኛ የከፋ ይሆን! 22  ሆኖም በዚያ የሚቀሩ አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በሕይወት ይተርፋሉ፤ ደግሞም ከዚያ ይወሰዳሉ። ወደ እናንተ ይመጣሉ፤ መንገዳቸውንና ሥራቸውንም በምታዩበት ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ ካመጣሁት ጥፋት፣ በእሷም ላይ ካደረስኩት ነገር ሁሉ በእርግጥ ትጽናናላችሁ።’” 23  “‘መንገዳቸውንና ሥራቸውን ስታዩ ያጽናኗችኋል፤ በእሷም ላይ ላደርገው የሚገባኝን ነገር ያደረግኩት ያለምክንያት አለመሆኑን ትገነዘባላችሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,028
15  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የወይን ተክል እንጨት በጫካ ዛፎች መካከል ካለ ከየትኛውም ዛፍ ወይም ቅርንጫፍ ከተወሰደ እንጨት ጋር እንዴት ሊወዳደር ይችላል? 3  ከወይን ተክል የሚገኝ ግንድ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? ወይስ ሰዎች ግንዱን ተጠቅመው ዕቃ ለማንጠልጠል የሚያገለግል ኩላብ ይሠራሉ? 4  እነሆ፣ ማገዶ እንዲሆን እሳት ውስጥ ይጣላል፤ እሳቱ ጫፍና ጫፉን ይበላዋል፤ መሃሉንም ይለበልበዋል። ከዚህ በኋላ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? 5  ምንም ነገር ሳይነካውም እንኳ ለምንም ነገር ሊያገለግል አይችልም። እሳት ሲበላውና ሲለበልበውማ ጨርሶ ከጥቅም ውጭ ይሆናል!” 6  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ማገዶ እንዲሆን ለእሳት አሳልፌ እንደሰጠሁት በጫካ ዛፎች መካከል እንዳለ የወይን ተክል እንጨት ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ። 7  ፊቴን በእነሱ ላይ አድርጌአለሁ። ከእሳቱ ቢያመልጡም እሳት ይበላቸዋል። ፊቴንም በእነሱ ላይ በማደርግበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’” 8  “‘ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸውም ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,029
16  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለኢየሩሳሌም አስጸያፊ ልማዶቿን አሳውቃት። 3  እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላል፦ “መገኛሽና ትውልድሽ በከነአናውያን ምድር ነው። አባትሽ አሞራዊ፣ እናትሽም ሂታዊት ነበሩ። 4  አወላለድሽንም በተመለከተ፣ በተወለድሽበት ቀን እትብትሽ አልተቆረጠም፤ ንጹሕም እንድትሆኚ በውኃ አልታጠብሽም፤ በጨውም አልታሸሽም፤ ደግሞም በጨርቅ አልተጠቀለልሽም። 5  ለአንቺ አዝኖ ከእነዚህ ነገሮች አንዱንም እንኳ ያደረገልሽ የለም። የራራልሽም የለም። ይልቁንም በተወለድሽበት ቀን ስለተጠላሽ አውላላ ሜዳ ላይ ተጣልሽ። 6  “‘“በአጠገብሽ ሳልፍ በደምሽ ላይ ስትንፈራገጪ አየሁሽ፤ ደግሞም በደምሽ ላይ ተኝተሽ ሳለ ‘በሕይወት ኑሪ!’ አልኩሽ። አዎ፣ በደምሽ ላይ ተኝተሽ ሳለ ‘በሕይወት ኑሪ!’ አልኩሽ። 7  በሜዳ ላይ እንደሚበቅሉ ዕፀዋት እጅግ እንድትበዢ አደረግኩ፤ አንቺም አደግሽ፤ ደግሞም ሙሉ ሰው ሆንሽ፤ እጅግ ያማረ ጌጥም አደረግሽ። ጡቶችሽ አጎጠጎጡ፤ ፀጉርሽም አደገ፤ ይሁንና በዚህ ጊዜም እርቃንሽንና ራቁትሽን ነበርሽ።”’ 8  “‘በአጠገብሽ ሳልፍ አየሁሽ፤ የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ዕድሜሽ እንደደረሰ አስተዋልኩ። ስለዚህ ልብሴን በአንቺ ላይ ዘርግቼ እርቃንሽን ሸፈንኩ፤ ደግሞም ማልኩልሽ፤ ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን አደረግኩ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘አንቺም የእኔ ሆንሽ። 9  በተጨማሪም በውኃ አጠብኩሽ፤ ከደምሽም አነጻሁሽ፤ ዘይትም ቀባሁሽ። 10  ከዚያም የተጠለፈ ሸማ አለበስኩሽ፤ ከጥሩ ቆዳ የተሠራ ጫማም ሰጠሁሽ፤ በጥሩ በፍታም ጠቀለልኩሽ፤ እጅግ ውድ የሆነ ልብስም አለበስኩሽ። 11  በጌጣጌጥ አንቆጠቆጥኩሽ፤ በእጆችሽ አምባር፣ በአንገትሽም ሐብል አጠለቅኩልሽ። 12  በተጨማሪም በአፍንጫሽ ቀለበት፣ በጆሮዎችሽ ጉትቻ፣ በራስሽም ላይ የሚያምር አክሊል አደረግኩልሽ። 13  ራስሽን በወርቅና በብር አስጌጥሽ፤ ልብስሽም ጥሩ በፍታ፣ እጅግ ውድ በሆነ ጨርቅ የተሠራና የተጠለፈ ሸማ ነበር። ምግብሽም የላመ ዱቄት፣ ማርና ዘይት ነበር፤ እጅግ ውብ ሆንሽ፤ ንግሥት ለመሆንም በቃሽ።’” 14  “‘ከውበትሽ የተነሳ ዝናሽ በብሔራት መካከል ገነነ፤ ውበትሽ በአንቺ ላይ ካኖርኩት ግርማዬ የተነሳ ፍጹም ሆኖ ነበርና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 15  “‘ሆኖም አንቺ በውበትሽ መመካት ጀመርሽ፤ ዝናሽንም ለዝሙት አዳሪነት ተጠቀምሽበት። ከአላፊ አግዳሚው ጋር ያለገደብ አመነዘርሽ፤ ውበትሽንም ለማንም አሳልፈሽ ሰጠሽ። 16  የተለያዩ ቀለማት ካሏቸው ልብሶችሽ አንዳንዶቹን ወስደሽ የምታመነዝሪባቸውን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችሽን አስጌጥሽባቸው፤ እነዚህ ነገሮች መሆን የለባቸውም፤ ጨርሶ ሊፈጸሙም አይገባም። 17  ደግሞም በሰጠሁሽ ወርቅና ብር የተሠሩትን ያማሩ ጌጣጌጦችሽን ወስደሽ ለራስሽ የወንድ ምስሎች ሠራሽ፤ ከእነሱም ጋር አመነዘርሽ። 18  የተጠለፉ ሸማዎችሽንም ወስደሽ አለበስሻቸው፤ ዘይቴንና ዕጣኔንም አቀረብሽላቸው። 19  ደግሞም እንድትበዪው የሰጠሁሽን ከላመ ዱቄት፣ ከዘይትና ከማር የተዘጋጀ ምግብ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ አድርገሽ አቀረብሽላቸው። የተፈጸመው ነገር ይኸው ነው’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 20  “‘ለእኔ የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ወስደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ለጣዖቶቹ ሠዋሽላቸው፤ የምትፈጽሚው ምንዝር እጅግ አልበዛም? 21  ወንዶች ልጆቼን አረድሽ፤ በእሳትም አሳልፈሽ መሥዋዕት አድርገሽ አቀረብሻቸው። 22  አስጸያፊ ልማዶችሽንና ምንዝርሽን ሁሉ ስትፈጽሚ እርቃንሽንና ራቁትሽን ሆነሽ በገዛ ደምሽ ላይ ስትንፈራገጪ የነበርሽበትን የልጅነትሽን ጊዜ አላስታወስሽም። 23  ይህን ሁሉ ክፋት ከፈጸምሽ በኋላ ወዮ፣ ወዮልሽ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 24  ‘ለራስሽ ጉብታ አበጀሽ፤ በየአደባባዩም ከፍ ያለ ቦታ ሠራሽ። 25  በየመንገዱ ላይ በሚገኝ የታወቀ ስፍራ ሁሉ ከፍ ያለ ቦታ ሠራሽ፤ ለአላፊ አግዳሚው ሁሉ ራስሽን በመስጠት ውበትሽን ወደ አስጸያፊ ነገር ለወጥሽ፤ የምትፈጽሚውንም ምንዝር አበዛሽ። 26  በፍትወት ከተቃጠሉ ጎረቤቶችሽ ይኸውም ከግብፅ ወንዶች ልጆች ጋር አመነዘርሽ፤ ገደብ በሌለው ምንዝርሽ አስቆጣሽኝ። 27  አሁን እጄን በአንቺ ላይ እዘረጋለሁ፤ ቀለብሽንም እቀንሳለሁ፤ በጸያፍ ተግባርሽ የተነሳ የሚሸማቀቁትና የሚጠሉሽ ሴቶች ይኸውም የፍልስጤም ሴቶች ልጆች ያሻቸውን እንዲያደርጉብሽ አሳልፌ እሰጥሻለሁ። 28  “‘እርካታ ባለማግኘትሽ ከአሦር ወንዶች ልጆች ጋር ደግሞ አመነዘርሽ፤ ሆኖም ከእነሱ ጋር ካመነዘርሽ በኋላም እንኳ አልረካሽም። 29  ስለዚህ ምንዝርሽን በነጋዴዎች ምድርና በከለዳውያን ምድር አበዛሽ፤ ያም ሆኖ እንኳ አልረካሽም። 30  ዓይን አውጣ እንደሆነች ዝሙት አዳሪ ይህን ሁሉ ነገር የፈጸምሽው ልብሽ ምንኛ ታማሚ ቢሆን ነው!’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 31  ‘ይሁንና በየመንገዱ ላይ በሚገኝ የታወቀ ስፍራ ሁሉ ጉብታሽን ስታበጂና በየአደባባዩ ለራስሽ ከፍ ያለ ቦታ ስትሠሪ እንደ ዝሙት አዳሪ አልሆንሽም፤ ምክንያቱም ምንም ዓይነት ክፍያ አትቀበዪም። 32  አንቺ በባሏ ፋንታ እንግዳ የሆኑ ሰዎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ሚስት ነሽ! 33  ሰዎች ለዝሙት አዳሪዎች ሁሉ ስጦታ ይሰጣሉ፤ በፍትወት ለሚመኙሽ ሁሉ ስጦታ የሰጠሽው ግን አንቺ ነሽ፤ ደግሞም ከየቦታው መጥተው ከአንቺ ጋር እንዲያመነዝሩ ጉቦ ትሰጫቸዋለሽ። 34  አንቺ ከሌሎች ዝሙት አዳሪ ሴቶች ፈጽሞ የተለየሽ ነሽ። አንቺ የፈጸምሽው ዓይነት ምንዝር የፈጸመ ሰው ታይቶ አይታወቅም! አንቺ ትከፍያቸዋለሽ እንጂ እነሱ አይከፍሉሽም። የአንቺ አድራጎት ተቃራኒ ነው።’ 35  “በመሆኑም አንቺ ዝሙት አዳሪ፣ የይሖዋን ቃል ስሚ። 36  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከፍቅረኞችሽና የወንዶች ልጆችሽን ደም መሥዋዕት አድርገሽ ካቀረብሽላቸው አስጸያፊና ቀፋፊ ጣዖቶችሽ ሁሉ ጋር ባመነዘርሽ ጊዜ ከልክ በላይ በፍትወት ስለተቃጠልሽና እርቃንሽ ስለተገለጠ፣ 37  እኔ ደስ ያሰኘሻቸውን ፍቅረኞችሽን ሁሉ፣ የወደድሻቸውንም ሆነ የጠላሻቸውን ሁሉ አንድ ላይ እሰበስባለሁ። እነሱን ከየቦታው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ እርቃንሽን ለእነሱ እገልጣለሁ፤ እነሱም ሙሉ በሙሉ እርቃንሽን ሆነሽ ያዩሻል። 38  “‘አመንዝሮችና ደም የሚያፈሱ ሴቶች ሊፈረድባቸው በሚገባው ፍርድ እቀጣሻለሁ፤ ደግሞም በቁጣና በቅናት ደምሽ ይፈስሳል። 39  በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነሱም ጉብታዎችሽን ያፈርሳሉ፤ ከፍ ያሉ ቦታዎችሽንም ያወድማሉ፤ ልብሶችሽንም ይገፉሻል፤ ያማሩ ጌጣጌጦችሽንም ይወስዳሉ፤ እርቃንሽንና ራቁትሽንም ያስቀሩሻል። 40  ብዙ ሰዎችን ያነሳሱብሻል፤ በድንጋይም ይወግሩሻል፤ በሰይፋቸውም ያርዱሻል። 41  ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፤ በብዙ ሴቶችም ፊት በአንቺ ላይ ፍርዴን ይፈጽማሉ፤ ምንዝርሽንም አስተውሻለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ዋጋ አትከፍዪም። 42  በአንቺ ላይ የነበረው ቁጣዬ ይበርዳል፤ ንዴቴም ከአንቺ ይርቃል። እኔም እረጋጋለሁ፤ ከእንግዲህም አልቆጣም።’ 43  “‘የልጅነት ጊዜሽን ስላላስታወስሽና እነዚህን ነገሮች ሁሉ በማድረግ ስላስቆጣሽኝ እኔም የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራስሽ ላይ አመጣብሻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘አንቺም ከእንግዲህ ወዲህ አስነዋሪ ምግባርሽንና አስጸያፊ የሆኑ ልማዶችሽን ሁሉ አትፈጽሚም። 44  “‘እነሆ፣ ምሳሌያዊ አባባል የሚጠቀም ሁሉ “ልጅቷም በእናቷ ወጣች!” እያለ ይተርትብሻል። 45  አንቺ የእናትሽ ልጅ ነሽ፤ እሷ ባሏንና ልጆቿን ትንቃለች። ደግሞም ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን የናቁት የእህቶችሽ እህት ነሽ። እናታችሁ ሂታዊት፣ አባታችሁ ደግሞ አሞራዊ ነበሩ።’” 46  “‘ታላቅ እህትሽ ከሴቶች ልጆቿ ጋር ከአንቺ በስተ ሰሜን የምትኖረው ሰማርያ ናት፤ ታናሽ እህትሽም ከሴቶች ልጆቿ ጋር ከአንቺ በስተ ደቡብ የምትኖረው ሰዶም ናት። 47  በእነሱ መንገድ መሄድና የእነሱን አስጸያፊ ልማዶች መከተል ብቻ ሳይሆን በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምግባርሽ ሁሉ ከእነሱ ይበልጥ ብልሹ ሆንሽ። 48  በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘አንቺና ሴቶች ልጆችሽ ያደረጋችሁትን እህትሽ ሰዶምና ሴቶች ልጆቿ አላደረጉትም። 49  እነሆ፣ የእህትሽ የሰዶም በደል ይህ ነበር፦ እሷና ሴቶች ልጆቿ ኩራተኞች ነበሩ፤ የተትረፈረፈ ምግብ የነበራቸው ሲሆን ያለጭንቀት ተረጋግተው ይኖሩ ነበር፤ ይሁንና ጎስቋላውንና ድሃውን አልደገፉም። 50  እነሱም ትዕቢታቸውን አላስወገዱም፤ በፊቴም አስጸያፊ የሆኑ ልማዶችን መፈጸማቸውን ቀጠሉ፤ በመሆኑም እነሱን ማስወገድ ተገቢ ሆኖ አገኘሁት። 51  “‘ሰማርያም ብትሆን አንቺ የሠራሽውን ኃጢአት ግማሹን እንኳ አልሠራችም። አንቺ ከምትፈጽሚያቸው አስጸያፊ ልማዶች ሁሉ የተነሳ እህቶችሽ ጻድቃን መስለው እስኪታዩ ድረስ ከእነሱ ይበልጥ ብዙ አስጸያፊ ልማዶች መፈጸምሽን ቀጠልሽ። 52  የእህቶችሽ ምግባር ተገቢ መስሎ እንዲታይ ስላደረግሽ አሁን ኀፍረትሽን ተከናነቢ። ከእነሱ ይበልጥ አስጸያፊ በሆነ መንገድ ከፈጸምሽው ኃጢአት የተነሳ እነሱ ከአንቺ ይልቅ ጻድቃን ሆነዋል። እንግዲህ እህቶችሽን ጻድቃን ስላስመሰልሻቸው ኀፍረት ተከናነቢ፤ ውርደትሽንም ተሸከሚ።’ 53   “‘በምርኮ የተወሰዱባቸውን ይኸውም ከሰዶምና ከሴቶች ልጆቿ የተማረኩትን እንዲሁም ከሰማርያና ከሴቶች ልጆቿ የተማረኩትን እሰበስባለሁ፤ በተጨማሪም ከአንቺ የተማረኩትን ከእነሱ ጋር እሰበስባለሁ፤ 54  ይህም የሚሆነው ውርደትሽን እንድትሸከሚ ነው፤ ደግሞም እነሱን በማጽናናት ባደረግሽው ነገር የተነሳ ውርደት ትከናነቢያለሽ። 55  የገዛ እህቶችሽ፣ ሰዶምና ሴቶች ልጆቿ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ፤ እንዲሁም ሰማርያና ሴቶች ልጆቿ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ፤ አንቺና ሴቶች ልጆችሽም ቀድሞ ወደነበራችሁበት ሁኔታ ትመለሳላችሁ። 56  ኩሩ በነበርሽበት ቀን እህትሽ ሰዶም በአንደበትሽ ለመጠራት እንኳ የምትበቃ አልነበረችም፤ 57   ይህም የሆነው ክፋትሽ ከመጋለጡ በፊት ነበር። አሁን ግን የሶርያ ሴቶች ልጆችና ጎረቤቶቿ በአንቺ ላይ ነቀፋ ይሰነዝራሉ፤ እንዲሁም የፍልስጤማውያን ሴቶች ልጆች፣ በዙሪያሽም ያሉ ሁሉ በንቀት ያዩሻል። 58  አስነዋሪ ምግባርሽና አስጸያፊ ልማዶችሽ የሚያስከትሉብሽን መዘዝ ትቀበያለሽ’ ይላል ይሖዋ።” 59  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እንግዲህ ቃል ኪዳኔን በማፍረስ መሐላውን ስለናቅሽ እኔም እንዳደረግሽው አደርግብሻለሁ። 60  ይሁንና እኔ ራሴ በልጅነትሽ ጊዜ ከአንቺ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤ ደግሞም ከአንቺ ጋር ዘላቂ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ። 61  ታላላቆችሽና ታናናሾችሽ የሆኑትን እህቶችሽን ስትቀበዪ ምግባርሽን ታስታውሻለሽ፤ ደግሞም ታፍሪያለሽ፤ እኔም እነሱን ሴቶች ልጆች አድርጌ እሰጥሻለሁ፤ ይህን የማደርገው ግን ከአንቺ ጋር በገባሁት ቃል ኪዳን የተነሳ አይደለም።’ 62  “‘እኔ ራሴም ከአንቺ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አጸናለሁ፤ አንቺም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ። 63  ከዚያም፣ ያን ሁሉ ነገር ብታደርጊም እንኳ ለአንቺ ባስተሰረይኩልሽ ጊዜ ሥራሽን ታስታውሻለሽ፤ ከደረሰብሽም ውርደት የተነሳ አፍሽን ለመክፈት እጅግ ታፍሪያለሽ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,030
17  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ እስራኤል ቤት እንቆቅልሽና ምሳሌ ተናገር። 3  እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ትላልቅ ክንፎችና ረጃጅም ማርገብገቢያዎች ያሉት እንዲሁም መላ አካሉ ዥጉርጉር በሆኑ ላባዎች የተሸፈነው ታላቁ ንስር ወደ ሊባኖስ መጥቶ የአርዘ ሊባኖስን ጫፍ ያዘ። 4  አናቱ ላይ ያለውን ቀንበጥ ቀጥፎ ወደ ነጋዴዎች ምድር አመጣው፤ በነጋዴዎችም ከተማ ተከለው። 5  ከዚያም ከምድሪቱ ዘር የተወሰነውን ወስዶ ለም በሆነ መሬት ላይ ዘራው። እንደ ሪጋ ዛፍ ብዙ ውኃ ባለበት ቦታ አጠገብ ተከለው። 6  በመሆኑም ዘሩ በቀለ፤ አጭርና የተንሰራፋ እንዲሁም ወደ ራሱ አቅጣጫ የበቀሉ ቅጠሎች ያሉት የወይን ተክል ሆነ፤ ሥሮቹም ከበታቹ አደጉ። በዚህ ሁኔታ የወይን ተክል ሆነ፤ ቀንበጦችና ቅርንጫፎችም አወጣ። 7  “‘“ደግሞም ትላልቅ ክንፎች ያሉትና የክንፎቹ ላባዎች ረጃጅም የሆኑ ሌላ ታላቅ ንስር መጣ። ከዚያም ይህ የወይን ተክል ሥሮቹን ከተተከለበት የአትክልት መደብ አሻግሮ በታላቅ ጉጉት ወደ እሱ ዘረጋ፤ ውኃ ያጠጣውም ዘንድ ቅርንጫፎቹን ወደ እሱ ሰደደ። 8  ቅርንጫፎችን እንዲያወጣና ፍሬ እንዲያፈራ እንዲሁም ያማረ የወይን ተክል እንዲሆን ብዙ ውኃ ባለበት አቅራቢያ መልካም መሬት ላይ ተተክሎ ነበር።”’ 9  “እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ያድግ ይሆን? ሰው ሥሮቹን ነቅሎ አይጥልም? ፍሬው እንዲበሰብስ አያደርግም? ቀንበጦቹስ እንዲጠወልጉ አያደርግም? የወይኑ ተክል በጣም ስለሚደርቅ ከሥሩ ለመንቀል ብርቱ ክንድም ሆነ ብዙ ሰው አያስፈልግም። 10  ተነቅሎ በሌላ ቦታ ቢተከልስ ያድግ ይሆን? የምሥራቅ ነፋስ ሲነፍስበት ሙሉ በሙሉ አይደርቅም? በበቀለበት የአትክልት መደብ ላይ ይደርቃል።”’” 11  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 12  “እባክህ፣ ለዓመፀኛው ቤት ይህን ተናገር፦ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትገነዘቡም?’ እንዲህ በል፦ ‘እነሆ፣ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ንጉሥዋንና መኳንንቷን ማረከ፤ ወደ ባቢሎንም ይዟቸው ተመለሰ። 13  በተጨማሪም ከንጉሣውያን ዘር አንዱን ወስዶ ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ በመሐላም ቃል አስገባው። ከዚያም የምድሪቱን ታላላቅ ሰዎች ወሰደ፤ 14  ይህም መንግሥቲቱ ዝቅ እንድትልና ማንሰራራት እንዳትችል እንዲሁም የእሱን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ብቻ እንድትኖር ለማድረግ ነው። 15  ንጉሡ ግን በመጨረሻ ፈረሶችና ብዙ ሠራዊት እንዲልኩለት መልእክተኞቹን ወደ ግብፅ በመስደድ በእሱ ላይ ዓመፀ። ታዲያ ይሳካለት ይሆን? እነዚህን ነገሮች ያደረገው ከቅጣት ያመልጣል? ቃል ኪዳኑንስ አፍርሶ ማምለጥ ይችላል?’ 16  “‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “እሱን ንጉሥ አድርጎ የሾመው ንጉሥ በሚኖርበት ቦታ ይኸውም በባቢሎን ይሞታል፤ ይህ ሰው መሐላውን አቃሎበታል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሶበታል። 17  ብዙ ሕይወት ለማጥፋት የአፈር ቁልል በሚደለደልበትና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ በሚሠራበት ጊዜ የፈርዖን ታላቅ ሠራዊትና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወታደሮች ሊረዱት አይችሉም። 18  እሱ መሐላውን አቃሏል፤ ቃል ኪዳኑንም አፍርሷል። ቃል ቢገባለትም እንኳ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርጓል፤ ስለዚህ ፈጽሞ አያመልጥም።”’ 19  “‘በመሆኑም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ መሐላዬን መናቁና ቃል ኪዳኔን ማፍረሱ የሚያስከትልበትን መዘዝ በራሱ ላይ አመጣበታለሁ። 20  መረቤን በላዩ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል። ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ በእኔ ላይ ክህደት ስለፈጸመ በዚያ እፋረደዋለሁ። 21  ከወታደሮቹ መካከል የሸሹት ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በሕይወት የተረፉትም በየአቅጣጫው ይበታተናሉ። በዚህ ጊዜም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩ ታውቃላችሁ።”’ 22  “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከረጅሙ የአርዘ ሊባኖስ ጫፍ ላይ ቀንበጥ ቀጥፌ እተክለዋለሁ፤ ከቀንበጦቹም ጫፍ ላይ ለጋ የሆነውን ቀጥፌ ረጅምና ግዙፍ በሆነ ተራራ ላይ እኔ ራሴ እተክለዋለሁ። 23  ረጅም በሆነ የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎቹም ያድጋሉ፤ ፍሬም ያፈራል፤ ደግሞም የሚያምር አርዘ ሊባኖስ ይሆናል። በሥሩም የወፍ ዓይነቶች ሁሉ ይኖራሉ፤ በቅጠሎቹም ጥላ ሥር ያርፋሉ። 24  የዱር ዛፎች ሁሉ፣ ከፍ ያለውን ዛፍ ዝቅ ዝቅ ያደረግኩት፣ ዝቅ ያለውን ዛፍ ደግሞ ከፍ ከፍ ያደረግኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ ለምለሙን ዛፍ አድርቄአለሁ፤ ደረቁም ዛፍ እንዲለመልም አድርጌአለሁ። እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አድርጌአለሁ።”’”
[]
[]
[]
[]
12,031
18  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “በእስራኤል ምድር ‘ጎምዛዛ ወይን የበሉት አባቶች ሆነው ሳለ የልጆቹ ጥርስ ጠረሰ’ የሚለውን ምሳሌያዊ አባባል የምትጠቅሱት ምን ለማለት ነው? 3  “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ከእንግዲህ በእስራኤል ይህን ምሳሌ አትጠቅሱም። 4  እነሆ፣ ነፍስ ሁሉ የእኔ ነው። የአባት ነፍስ የእኔ እንደሆነች ሁሉ የልጅም ነፍስ የእኔ ናት። ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች። 5  “‘አንድ ሰው ጻድቅ ነው እንበል፤ ይህ ሰው ፍትሐዊና ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋል። 6  በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን አይበላም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት የእስራኤል ቤት ጣዖቶች አይመለከትም፤ የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም ወይም ከሴት ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ግንኙነት አይፈጽምም፤ 7  ማንንም ሰው አይበድልም፤ ይልቁንም ተበዳሪ መያዣ አድርጎ የሰጠውን ይመልሳል፤ ማንንም ሰው አይዘርፍም፤ ይልቁንም ለተራበ ሰው የራሱን ምግብ ይሰጣል፤ እንዲሁም የተራቆተውን ያለብሰዋል፤ 8  ወለድ አይጠይቅም ወይም በአራጣ አያበድርም፤ ይልቁንም ፍትሕ የጎደለው ድርጊት ከመፈጸም ይቆጠባል፤ በሰዎች መካከል እውነተኛ ፍትሕ ያሰፍናል፤ 9  ያወጣኋቸውን ደንቦች ይከተላል፤ እንዲሁም በታማኝነት ይመላለስ ዘንድ ድንጋጌዎቼን ይጠብቃል። እንዲህ ያለው ሰው ጻድቅ ነው፤ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 10  “‘ይሁንና ይህ ሰው ዘራፊ ወይም ነፍሰ ገዳይ የሆነ ወይም ከእነዚህ ነገሮች አንዱን የሚያደርግ ልጅ አለው እንበል፤ 11  (አባቱ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱንም ባያደርግ እንኳ) ልጁ በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን ይበላል፤ የባልንጀራውን ሚስት ያባልጋል፤ 12  የተቸገረውንና ድሃውን ይበድላል፤ ሰዎችን ይዘርፋል፤ መያዣ አድርጎ የወሰደውን አይመልስም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት ጣዖቶች ይመለከታል፤ ጸያፍ የሆኑ ልማዶችን ይፈጽማል፤ 13  በአራጣ ያበድራል፤ እንዲሁም ወለድ ይቀበላል፤ በመሆኑም ይህ ልጅ ፈጽሞ በሕይወት አይኖርም። እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች በመሥራቱ በእርግጥ ይሞታል። ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል። 14  “‘ይሁንና አንድ አባት የተለያዩ ኃጢአቶች ሲሠራ ልጁ ይመለከተዋል እንበል፤ ልጁ ይህን ቢመለከትም እንዲህ ያሉ ነገሮች አይሠራም። 15  በተራሮች ላይ ለጣዖት የተሠዋውን አይበላም፤ አስጸያፊ ወደሆኑት የእስራኤል ቤት ጣዖቶች አይመለከትም፤ የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም፤ 16  ማንንም ሰው አይበድልም፤ መያዣ እንዲሆን የተሰጠውን አይወስድም፤ ከሰው ላይ ምንም ነገር አይዘርፍም፤ ለተራበ ሰው የራሱን ምግብ ይሰጣል፤ እንዲሁም የተራቆተውን ያለብሰዋል፤ 17  ድሃውን ሰው ከመጨቆን ይቆጠባል፤ በአራጣ አያበድርም ወይም ወለድ አይጠይቅም፤ ድንጋጌዎቼንም ያከብራል፤ እንዲሁም ያወጣኋቸውን ደንቦች ይከተላል። እንዲህ ያለ ሰው አባቱ በፈጸመው በደል የተነሳ አይሞትም። በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። 18  አባቱ ግን የማጭበርበር ድርጊት በመፈጸሙ፣ ወንድሙን በመዝረፉና በሕዝቡ መካከል መጥፎ የሆነ ነገር በመሥራቱ በፈጸመው በደል የተነሳ ይሞታል። 19  “‘እናንተ ግን “ልጅ፣ አባቱ በሠራው በደል ተጠያቂ የማይሆነው ለምንድን ነው?” ትላላችሁ። ልጁ ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ስላደረገ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ሁሉ ስለጠበቀና በሥራ ላይ ስላዋለ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። 20  ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች። ልጅ፣ አባቱ በሠራው በደል ተጠያቂ አይሆንም፤ አባትም ልጁ በሠራው በደል ተጠያቂ አይሆንም። የጻድቁ ሰው ጽድቅ የሚታሰብለት ለራሱ ብቻ ነው፤ የክፉውም ሰው ክፋት የሚታሰበው በራሱ ላይ ብቻ ነው። 21  “‘ክፉ ሰው ከሠራው ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ቢጠብቅ እንዲሁም ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም። 22  ከሠራው በደል ውስጥ አንዱም አይታሰብበትም። በሠራው ጽድቅ የተነሳ በሕይወት ይኖራል።’ 23  “‘እኔ በክፉ ሰው ሞት ደስ እሰኛለሁ?’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘እኔ ደስ የምሰኘው ከመንገዱ ቢመለስና በሕይወት ቢኖር አይደለም?’ 24  “‘ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ ደግሞም ክፉው ሰው እንደሚያደርገው አስጸያፊ ነገሮችን ሁሉ ቢሠራ በሕይወት ይኖራል? ካከናወነው የጽድቅ ሥራ መካከል አንዱም አይታወስም። ታማኝነቱን በማጉደሉና ኃጢአት በመሥራቱ የተነሳ ይሞታል። 25  “‘ይሁንና እናንተ “የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም” ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እባካችሁ ስሙ! በእርግጥ መንገዴ ፍትሐዊ አይደለም? ይልቁንስ ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም? 26  “‘ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ በዚህም የተነሳ ቢሞት፣ የሚሞተው በገዛ ራሱ በደል ነው። 27  “‘ክፉ ሰው ከሠራው ክፉ ድርጊት ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ማድረግ ቢጀምር የራሱን ሕይወት ያድናል። 28  የሠራውን በደል ሁሉ ተገንዝቦ ከዚያ ቢመለስ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም። 29  “‘ይሁንና የእስራኤል ቤት ሰዎች “የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም” ይላሉ። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእርግጥ መንገዴ ፍትሐዊ አይደለም? ይልቁንስ ፍትሐዊ ያልሆነው የእናንተ መንገድ አይደለም?’ 30  “‘ስለዚህ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደየመንገዳችሁ እፈርዳለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ተመለሱ፤ አዎ፣ ተጠያቂ እንድትሆኑ የሚያደርግ የማሰናከያ ድንጋይ እንዳይሆንባችሁ ከሠራችሁት በደል ሁሉ ሙሉ በሙሉ ተመለሱ። 31  የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ ከራሳችሁ ላይ አስወግዱ፤ ደግሞም አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይኑራችሁ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለምን ትሞታላችሁ?’ 32  “‘እኔ በማንም ሰው ሞት ደስ አልሰኝም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።’”
[]
[]
[]
[]
12,032
19  “ስለ እስራኤል አለቆች ሙሾ አውጣ፤ 2  እንዲህም በል፦‘እናትህ ምን ነበረች? በአንበሶች መካከል ያለች እንስት አንበሳ ነበረች። በብርቱ ደቦል አንበሶች መሃል ተኛች፤ ግልገሎቿንም በዚያ አሳደገች። 3  ከግልገሎቿ መካከል አንዱን ተንከባክባ አሳደገችው፤ እሱም ብርቱ ደቦል አንበሳ ሆነ። አድኖ መብላት ተማረ፤ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ። 4  ብሔራት ስለ እሱ ሰሙ፤ ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶም ያዙት፤በስናግም እየጎተቱ ወደ ግብፅ ምድር አመጡት። 5  እሷም በትዕግሥት ስትጠባበቅ ከቆየች በኋላ የመመለስ ተስፋ እንደሌለው ተገነዘበች። በመሆኑም ከግልገሎቿ መካከል ሌላውን ወስዳ እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ አድርጋ ላከችው። 6  እሱም በአንበሶች መካከል ይጎማለል ጀመር፤ ብርቱ ደቦል አንበሳም ሆነ። አድኖ መብላት ተማረ፤ ሰዎችንም እንኳ ሳይቀር በላ። 7  በማይደፈሩት ማማዎቻቸው መካከል አደባ፤ ከተሞቻቸውንም አወደመ፤ከዚህም የተነሳ ግሳቱ ወና በሆነችው ምድር ላይ አስተጋባ። 8  በዙሪያው ባሉ ግዛቶች ያሉ ብሔራት መረባቸውን በእሱ ላይ ለመዘርጋት ተነሱበት፤እሱም ጉድጓዳቸው ውስጥ ገብቶ ተያዘ። 9  በስናግ ጎትተው በእንስሳት ጎጆ ውስጥ በመክተት ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት። ከዚያ በኋላ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ እንዳይሰማ በዚያ አሰሩት። 10  እናትህ በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣ በደምህ ውስጥ ያለ የወይን ተክል ነበረች። ከውኃው ብዛት የተነሳ ፍሬ አፈራች፤ ብዙ ቅርንጫፎችም ነበሯት። 11  ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆኑ ጠንካራ ቅርንጫፎች አወጣች። አድጋ ከሌሎች ዛፎች ይበልጥ ረጅም ሆነች፤ደግሞም ከርዝመቷና ከቅጠሎቿ ብዛት የተነሳ ጎልታ ታየች። 12  ሆኖም በቁጣ ተነቀለች፤ ወደ ምድርም ተጣለች፤የምሥራቅም ነፋስ ፍሬዋን አደረቀው። ጠንካራ ቅርንጫፎቿ ተሰብረው ደረቁ፤ እሳትም በላቸው። 13  በዚህ ጊዜ በምድረ በዳ፣ውኃ በሌለበት ደረቅ ምድር ተተከለች። 14  እሳት ከቅርንጫፎቿ ወጥቶ ቀንበጦቿንና ፍሬዋን በላ፤በእሷም ላይ አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ፣ ለገዢዎችም የሚሆን በትረ መንግሥት አልተረፈም። “‘ይህ ሙሾ ነው፤ ሙሾ ሆኖም ያገለግላል።’”
[]
[]
[]
[]
12,033
2  ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ተነስተህ በእግርህ ቁም፤ እኔም አናግርሃለሁ” አለኝ። 2  እሱም ባናገረኝ ጊዜ መንፈስ ወደ ውስጤ ገባ፤ የሚያነጋግረኝንም እሰማ ዘንድ በእግሬ አቆመኝ። 3  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ሕዝብ፣ በእኔ ላይ ወዳመፁት ወደ ዓመፀኞቹ ብሔራት እልክሃለሁ። እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው እስከዚህች ቀን ድረስ ሕጌን ተላልፈዋል። 4  ግትርና ልበ ደንዳና ወደሆኑ ልጆች እልክሃለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው። 5  እነሱ ዓመፀኛ ቤት ስለሆኑ ቢሰሙም ባይሰሙም በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ በእርግጥ ያውቃሉ። 6  “አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፣ በአሜኬላና በእሾህ የተከበብክ እንዲሁም በጊንጦች መካከል የምትኖር ቢሆንም እነሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ። እነሱ ዓመፀኛ ቤት ስለሆኑ የሚናገሩትን አትፍራ፤ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር። 7  እነሱ ዓመፀኛ ስለሆኑ ቢሰሙም ባይሰሙም ቃሌን ንገራቸው። 8  “አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ስማ። እንደዚህ ዓመፀኛ ቤት፣ ዓመፀኛ አትሁን። አፍህን ክፈት፤ የምሰጥህንም ብላ።” 9  እኔም ባየሁ ጊዜ ወደ እኔ የተዘረጋ እጅ ተመለከትኩ፤ ደግሞም የተጻፈበት ጥቅልል አየሁ። 10  እሱም በፊቴ ጥቅልሉን ሲተረትረው፣ ከፊትና ከኋላ ተጽፎበት ነበር። በላዩ ላይ የሙሾ፣ የሐዘንና የዋይታ ቃላት ተጽፈውበት ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,034
20  በሰባተኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል አንዳንዶቹ ይሖዋን ለመጠየቅ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። 2  ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 3  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመጣችሁት እኔን ለመጠየቅ ነው? ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’ 4  “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነሱ ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅተሃል? በእነሱ ላይ ለመፍረድ ተዘጋጅተሃል? አባቶቻቸው የሠሯቸውን አስጸያፊ ነገሮች አሳውቃቸው። 5  እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤልን በመረጥኩበት ቀን፣ ለያዕቆብ ቤት ዘሮች ማልኩላቸው፤ በግብፅም ምድር ራሴን አሳወቅኳቸው። አዎ፣ ማልኩላቸው፤ ደግሞም ‘እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ’ አልኳቸው። 6  በዚያ ቀን፣ ከግብፅ ምድር አውጥቼ ለእነሱ ወደመረጥኳት ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር እንደማስገባቸው ማልኩላቸው። እሷም ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ ነበረች። 7  ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እያንዳንዳችሁ በዓይናችሁ ፊት ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አስወግዱ፤ አስጸያፊ በሆኑት የግብፅ ጣዖቶች ራሳችሁን አታርክሱ። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’ 8  “‘“እነሱ ግን በእኔ ላይ ዓመፁ፤ እኔን ለመስማትም ፈቃደኞች አልነበሩም። በፊታቸው ያሉትን ጸያፍ ነገሮች አላስወገዱም፤ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑትን የግብፅ ጣዖቶች አልተዉም። በመሆኑም በግብፅ ምድር ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ። 9  ይሁንና እነሱ በሚኖሩባቸው ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ። እነሱን ከግብፅ ምድር ባወጣሁበት ጊዜ በእነዚህ ብሔራት ፊት ማንነቴን አሳውቄአቸዋለሁና። 10  ስለሆነም ከግብፅ ምድር አውጥቼ ወደ ምድረ በዳ መራኋቸው። 11  “‘“ከዚያም ደንቦቼን ሰጠኋቸው፤ ድንጋጌዎቼንም አሳወቅኳቸው፤ ይህን ያደረግኩት እነሱን የሚከተል ሰው በእነሱ አማካኝነት በሕይወት እንዲኖር ነው። 12  ደግሞም በእኔና በእነሱ መካከል ምልክት እንዲሆን ሰንበቶቼን ሰጠኋቸው፤ ይህን ያደረግኩት የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ እንዲያውቁ ነው። 13  “‘“ሆኖም የእስራኤል ቤት ሰዎች በምድረ በዳ በእኔ ላይ ዓመፁ። ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አቃለዋል። ሰንበቶቼንም ፈጽሞ አረከሱ። በመሆኑም ጨርሶ አጠፋቸው ዘንድ በምድረ በዳ በእነሱ ላይ ታላቅ ቁጣዬን ለማፍሰስ ቃል ገባሁ። 14  እነሱን ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል ስለ ስሜ እርምጃ ወሰድኩ። 15  ደግሞም ለእነሱ ወደሰጠኋት ወተትና ማር ወደምታፈሰው፣ ከሌሎች አገሮች ሁሉ ይበልጥ ውብ ወደሆነችው ምድር እንደማላስገባቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤ 16  ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አቃለዋል፤ ደንቦቼንም አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰንበቶቼንም አርክሰዋል፤ ልባቸው አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻቸውን ተከትሏልና። 17  “‘“እኔ ግን እንዳላጠፋቸው ራራሁላቸው፤ ደግሞም አላጠፋኋቸውም፤ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም። 18  በምድረ በዳ ልጆቻቸውን እንዲህ አልኳቸው፦ ‘የአባቶቻችሁን ሥርዓት አትከተሉ፤ ድንጋጌዎቻቸውንም አታክብሩ፤ ወይም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራሳችሁን አታርክሱ። 19  እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ደንቦቼን አክብራችሁ ተመላለሱ፤ ድንጋጌዎቼንም ጠብቁ፤ በሥራም አውሏቸው። 20  ደግሞም ሰንበቶቼን ቀድሱ፤ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ሆነው ያገለግላሉ።’ 21  “‘“ሆኖም ልጆቹ በእኔ ላይ ያምፁ ጀመር። ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደግሞም በሥራ ላይ አላዋሉም። ሰንበቶቼን አረከሱ። በመሆኑም በምድረ በዳ ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ። 22  ይሁንና እነሱን ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል እጄን መለስኩ፤ ስለ ስሜም ስል እርምጃ ወሰድኩ። 23  ደግሞም በብሔራት መካከል እንደምበታትናቸውና ወደተለያዩ አገሮች እንደምሰዳቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤ 24  ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደንቦቼንም አቃለዋል፤ ሰንበቶቼን አርክሰዋል፤ ደግሞም እነሱ አስጸያፊ የሆኑትን የአባቶቻቸውን ጣዖቶች ተከትለዋል። 25  እኔም ጥሩ ባልሆነ ሥርዓት እንዲመላለሱና ሕይወት የማያስገኙላቸውን ድንጋጌዎች እንዲከተሉ ተውኳቸው። 26  አስከፊ ሁኔታ ይደርስባቸው ዘንድ እያንዳንዱን የበኩር ልጅ ለእሳት አሳልፈው ሲሰጡ በገዛ መሥዋዕታቸው እንዲረክሱ አደረግኩ፤ ይህም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ነው።”’ 27  “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በዚህም መንገድ አባቶቻችሁ ለእኔ ያላቸውን ታማኝነት በማጉደል ሰደቡኝ። 28  ለእነሱ ለመስጠት ወደማልኩላቸው ምድር አመጣኋቸው። ከፍ ያለ ኮረብታና የለመለመ ዛፍ ሁሉ ባዩ ጊዜ በዚያ መሥዋዕታቸውንና ቁጣ የሚያነሳሳ መባቸውን ያቀርቡ ጀመር። በዚያም ደስ የሚያሰኘውን የመሥዋዕቶቻቸውን መዓዛ አቀረቡ፤ የመጠጥ መባቸውንም አፈሰሱ። 29  እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እናንተ የምትሄዱበት ይህ ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ምንድን ነው? (ይህ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ባማ ተብሎ ይጠራል።)’”’ 30  “እንግዲህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ አስጸያፊ ከሆኑ ጣዖቶቻቸው ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ሲሉ እነሱን በመከተል ራሳቸውን እንዳረከሱ ሁሉ እናንተም ራሳችሁን ታረክሳላችሁ? 31  አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻችሁ ሁሉ መሥዋዕት በማቅረብ ይኸውም ልጆቻችሁን ለእሳት አሳልፋችሁ በመስጠት እስከ ዛሬ ድረስ ራሳችሁን እያረከሳችሁ ነው? የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ታዲያ እንዲህ እያደረጋችሁ ለጥያቄያችሁ ምላሽ መስጠት ይኖርብኛል?”’ “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም። 32  “እንጨትና ድንጋይ እንደሚያመልኩት ብሔራት፣ እንደ ሌሎቹም አገሮች ሕዝቦች እንሁን” በማለት የምታውጠነጥኑት ሐሳብ ፈጽሞ አይሳካም።’” 33  “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ በእናንተ ላይ ንጉሥ ሆኜ እገዛለሁ። 34  በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ ከሕዝቦች መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ። 35  ወደ ሕዝቦች ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ፤ በዚያም ፊት ለፊት እፋረዳችኋለሁ። 36  “‘አባቶቻችሁን በግብፅ ምድረ በዳ እንደተፋረድኳቸው ሁሉ እናንተንም እፋረዳችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 37  ‘ከእረኛ በትር በታች አሳልፋችኋለሁ፤ ደግሞም በቃል ኪዳኑ ግዴታ ውስጥ እንድትገቡ አደርጋለሁ። 38  ሆኖም በእኔ ላይ የሚያምፁትንና በደል የሚፈጽሙትን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ። የባዕድ አገር ሰው ሆነው ከሚኖሩበት ምድር አወጣቸዋለሁና፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ 39  “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እናንተን በተመለከተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሄዳችሁ አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻችሁን አገልግሉ። ከዚያ በኋላ ግን እኔን ባለመስማታችሁ መዘዙን ትቀበላላችሁ፤ በመሥዋዕቶቻችሁና አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ቅዱስ ስሜን አታረክሱም።’ 40  “‘በቅዱሱ ተራራዬ፣ ከፍ ባለውም የእስራኤል ተራራ ላይ፣’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘መላው የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ አዎ ሁሉም በዚያ በምድሪቱ ላይ ያገለግሉኛልና። በዚያም በእነሱ ደስ እሰኛለሁ፤ ደግሞም ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቻችሁ ሁሉ መዋጮዎቻችሁንና የመባችሁን የፍሬ በኩራት እሻለሁ። 41  ከሕዝቦች መካከል በማወጣችሁና ከተበተናችሁባቸው አገሮች በምሰበስባችሁ ጊዜ ደስ በሚያሰኘው መዓዛ የተነሳ በእናንተ እረካለሁ፤ በብሔራትም ፊት በእናንተ መካከል እቀደሳለሁ።’ 42  “‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት ወደማልኩላቸው አገር፣ ወደ እስራኤል ምድር ሳመጣችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። 43  በዚያም ራሳችሁን ያረከሳችሁባቸውን ምግባራችሁንና ድርጊቶቻችሁን ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በሠራችኋቸውም መጥፎ ነገሮች ሁሉ የተነሳ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ። 44  የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እንደ ክፉ ምግባራችሁ ወይም እንደ ብልሹ ተግባራችሁ ሳይሆን፣ ስለ ስሜ ስል እርምጃ በምወስድበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 45  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 46  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን በስተ ደቡብ አቅጣጫ አዙረህ ወደ ደቡብ ተናገር፤ በደቡብም ምድር ባለው ደን ላይ ትንቢት ተናገር። 47  በደቡብ ለሚገኘው ደን እንዲህ በል፦ ‘የይሖዋን ቃል ስማ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንተ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ እሳቱም በአንተ ውስጥ ያለውን የለመለመውንና ደረቁን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንቦገቦገው ነበልባል አይጠፋም፤ እሱም ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት ሁሉ ይለበልባል። 48  ሥጋ ለባሽም ሁሉ እሳቱን ያነደድኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያያል፤ በመሆኑም እሳቱ አይጠፋም።”’” 49  እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሱ ስለ እኔ ‘ሁልጊዜ የሚናገረው እንቆቅልሽ ነው’ ይላሉ።”
[]
[]
[]
[]
12,035
21  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አዙረህ ቅዱስ በሆኑት ስፍራዎች ላይ አውጅ፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር። 3  ለእስራኤል ምድር እንዲህ በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ሰይፌንም ከሰገባው መዝዤ ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ከአንቺ አስወግዳለሁ። 4  ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ከአንቺ ስለማስወግድ ሰይፌ ከደቡብ እስከ ሰሜን ድረስ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል። 5  ሰዎች ሁሉ ሰይፌን ከሰገባው የመዘዝኩት እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሆንኩ ያውቃሉ። ዳግመኛ ወደ ሰገባው አይመለስም።”’ 6  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ እየተንቀጠቀጥክ አቃስት፤ አዎ፣ በፊታቸው በምሬት አቃስት። 7  ‘የምታቃስተው ለምንድን ነው?’ ቢሉህ ‘ከሰማሁት ወሬ የተነሳ ነው’ ትላለህ። በእርግጥ ይመጣልና፤ ልብም ሁሉ በፍርሃት ይቀልጣል፤ እጅ ሁሉ ይዝላል፤ መንፈስ ሁሉ ያዝናል፤ ጉልበትም ሁሉ በውኃ ይርሳል። ‘እነሆ፣ በእርግጥ ይመጣል! ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 8  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 9  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ሰይፍ! ሰይፍ ተስሏል፤ ደግሞም ተወልውሏል። 10  የተሳለው ታላቅ እልቂት ለማስከተል ነው፤ የተወለወለውም እንደ መብረቅ እንዲያበራ ነው’ በል።”’” “ታዲያ ደስ ሊለን አይገባም?” “‘ማንኛውንም ዛፍ እንደሚንቅ ሁሉ የገዛ ልጄን በትረ መንግሥት ይንቃል? 11  “‘እንዲወለወልና በእጅ እንዲያዝ ተሰጥቷል። ገዳዩ በእጁ እንዲይዘው ይህ ሰይፍ ተስሏል፤ ደግሞም ተወልውሏል። 12  “‘የሰው ልጅ ሆይ፣ ሰይፍ በሕዝቤ ላይ ስለመጣ ጩኽ፤ ደግሞም ዋይ ዋይ በል፤ በእስራኤል አለቆች ሁሉ ላይ ተነስቷል። እነዚህ ሰዎች ከሕዝቤ ጋር በአንድ ላይ የሰይፍ ሰለባ ይሆናሉ። ስለዚህ ጭንህን በሐዘን ምታ። 13  ሰይፉ ተፈትሿልና፤ ደግሞስ በትረ መንግሥቱን ከናቀው ምን ይሆናል? ከሕልውና ውጭ ይሆናል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 14  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ በእጅህም አጨብጭብ፤ ደግሞም ‘ሰይፍ!’ የሚለውን ቃል ሦስት ጊዜ ደጋግመህ ተናገር። ሰለባዎቹን የሚገድልና ታላቅ እልቂት የሚያስከትል፣ እነሱን የሚከብ ሰይፍ ነው። 15  ልባቸው በፍርሃት ይቀልጣል፤ ብዙዎችም በከተሞቻቸው በር ላይ ይወድቃሉ፤ እኔም በሰይፉ እገድላለሁ። አዎ፣ ሰይፉ እንደ መብረቅ ያበራል፤ ለመግደልም ተወልውሏል! 16  በስተ ቀኝ በኩል በኃይል ቁረጥ! በስተ ግራ በኩል ተንቀሳቀስ! ስለትህ በዞረበት አቅጣጫ ሁሉ ሂድ! 17  እኔም በእጄ አጨበጭባለሁ፤ ቁጣዬንም አበርዳለሁ። እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።” 18  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 19  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ የሚመጣባቸውን ሁለት መንገዶች ንድፍ አውጣ። ሁለቱም መንገዶች የሚነሱት ከአንድ ምድር ነው፤ መንገዱ ወደ ሁለቱ ከተሞች የሚገነጠልበት ቦታ ላይ ምልክት አድርግ። 20  ሰይፍ በአሞናውያን ከተማ በራባ ላይ ይመጣ ዘንድ አንደኛውን መንገድ አመልክት፤ እንዲሁም በይሁዳ በምትገኘው በተመሸገችው ኢየሩሳሌም ላይ ይመጣ ዘንድ ሌላኛውን መንገድ አመልክት። 21  የባቢሎን ንጉሥ ያሟርት ዘንድ በመንታ መንገድ ይኸውም በሁለቱ መንገዶች መገንጠያ ላይ ይቆማልና። ፍላጾችን ይወዘውዛል። ጣዖቶቹን ያማክራል፤ ጉበት ይመረምራል። 22  በቀኝ እጁ የወጣው ሟርት የመደርመሻ መሣሪያዎችን ለመደገን፣ የግድያ ትእዛዝ ለማስተላለፍ፣ የጦርነት ሁካታ ለማሰማት፣ በበሮቿ ላይ የመደርመሻ መሣሪያዎች ለመደገን፣ በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ለመደልደልና ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ለመሥራት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ አመለከተው። 23  ቃለ መሐላዎች የገቡላቸው ሰዎች ግን ይህ የሐሰት ሟርት ይመስላቸዋል። ይሁንና እሱ በደላቸውን በማስታወስ ማርኮ ይወስዳቸዋል። 24  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምትፈጽሙት ድርጊት ሁሉ መተላለፋችሁ እንዲገለጥና ኃጢአታችሁ እንዲታይ በማድረግ በደላችሁ እንዲታሰብ አድርጋችኋል። እናንተም አሁን ስለታሰባችሁ በኃይል ትወሰዳላችሁ።’ 25  “አንተ ክፉኛ የቆሰልከው፣ መጥፎው የእስራኤል አለቃ፣ ቀንህ ይኸውም የመጨረሻ ቅጣት የምትቀበልበት ጊዜ ደርሷል። 26  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጥምጥሙን ፍታ፤ አክሊሉንም አንሳ። ይህ እንደ በፊቱ አይሆንም። ዝቅ ያለውን ከፍ አድርግ፤ ከፍ ያለውን ደግሞ ዝቅ አድርግ። 27  ባድማ፣ ባድማ፣ ባድማ አደርጋታለሁ። እሷም ሕጋዊ መብት ያለው እስኪመጣ ድረስ ለማንም አትሆንም፤ ለእሱም እሰጣታለሁ።’ 28  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ስለ አሞናውያንና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል።’ እንዲህ በል፦ ‘ሰይፍ! ሰይፍ ለግድያ ተመዟል፤ እንዲበላና እንደ መብረቅ እንዲያበራ ተወልውሏል። 29  ስለ ራስሽ የሐሰት ራእዮች ያየሽና የውሸት ሟርት ያሟረትሽ ቢሆንም ቀናቸው፣ የመጨረሻ ቅጣት የሚቀበሉበት ጊዜ በደረሰባቸው ክፉዎች ማለትም በሚገደሉት ሰዎች ላይ ትከመሪያለሽ። 30  ሰይፉ ወደ ሰገባው ይመለስ። በተፈጠርሽበት ስፍራ፣ በተገኘሽበትም ምድር እፈርድብሻለሁ። 31  ቁጣዬን በአንቺ ላይ አወርዳለሁ። የታላቅ ቁጣዬን እሳት በላይሽ ላይ አነዳለሁ፤ በማጥፋትም ለተካኑ ጨካኝ ሰዎች አሳልፌ እሰጥሻለሁ። 32  ለእሳት ማገዶ ትሆኛለሽ፤ የገዛ ደምሽ በምድሪቱ ላይ ይፈስሳል፤ ደግሞም ከእንግዲህ ወዲህ አትታወሺም፤ እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁና።’”
[]
[]
[]
[]
12,036
22  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተስ የደም ዕዳ ባለባት ከተማ ላይ ፍርድ ለማወጅና አስጸያፊ ነገሮቿን ሁሉ ለማሳወቅ ተዘጋጅተሃል? 3  እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በመካከልሽ ደም የምታፈሺ፣ ፍርድ የምትቀበዪበት ጊዜ የደረሰብሽ፣ ትረክሺም ዘንድ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶች የምትሠሪ ከተማ ሆይ፣ 4  ያፈሰስሽው ደም በደለኛ አድርጎሻል፤ ደግሞም አስጸያፊ ጣዖቶችሽ አርክሰውሻል። የቀኖችሽን መጨረሻ አፋጥነሻል፤ የዘመኖችሽም መጨረሻ ደርሷል። ስለዚህ ብሔራት ነቀፋ እንዲሰነዝሩብሽ፣ አገሩም ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ። 5  አንቺ ስምሽ ርኩስ የሆነና ሽብር የሞላብሽ ከተማ ሆይ፣ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉት አገሮች ይሳለቁብሻል። 6  እነሆ፣ በመካከልሽ ያለ እያንዳንዱ የእስራኤል አለቃ ሥልጣኑን ደም ለማፍሰስ ይጠቀምበታል። 7  በአንቺ ውስጥ ያሉት ሰዎች አባቶቻቸውንና እናቶቻቸውን ያቃልላሉ። ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ያጭበረብራሉ፤ ደግሞም አባት የሌለውን ልጅና መበለቲቱን ይበድላሉ።”’” 8  “‘ቅዱስ ስፍራዎቼን ታቃልያለሽ፤ ሰንበቶቼንም ታረክሻለሽ። 9  በአንቺ ውስጥ ደም የማፍሰስ ዓላማ ያላቸው ስም አጥፊዎች አሉ። በአንቺ ውስጥ በተራሮች ላይ መሥዋዕቶችን ይበላሉ፤ በመካከልሽም ጸያፍ ምግባር ይፈጽማሉ። 10  በአንቺ ውስጥ የአባታቸውን መኝታ ያረክሳሉ፤ ደግሞም በወር አበባዋ የረከሰችን ሴት አስገድደው ይደፍራሉ። 11  በአንቺ ውስጥ አንዱ ከባልንጀራው ሚስት ጋር አስጸያፊ ነገር ይሠራል፤ ሌላው ጸያፍ ምግባር በመፈጸም የገዛ ምራቱን ያረክሳታል፤ ሌላው ደግሞ የገዛ አባቱ ልጅ የሆነችውን እህቱን አስገድዶ ይደፍራል። 12  በአንቺ ውስጥ ያሉ ሰዎች ደም ለማፍሰስ ጉቦ ይቀበላሉ። ወለድና ትርፍ ለማግኘት ታበድሪያለሽ፤ የባልንጀሮችሽንም ገንዘብ ትቀሚያለሽ። አዎ፣ እኔን ጨርሶ ረስተሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 13  “‘እነሆ፣ ያገኘሽውን አግባብ ያልሆነ ጥቅምና በመካከልሽ ያፈሰስሽውን ደም በመጸየፍ አጨበጭባለሁ። 14  በአንቺ ላይ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ልብሽ ሊጸና፣ እጆችሽስ ብርቱ ሆነው ሊቀጥሉ ይችላሉ? እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አደርገዋለሁ። 15  በብሔራት መካከል እበትንሻለሁ፤ በየአገሩም እዘራሻለሁ፤ ርኩሰትሽንም አስወግዳለሁ። 16  አንቺም በብሔራት ፊት ትዋረጃለሽ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ።’” 17  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 18  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ሆነውብኛል። ሁሉም ምድጃ ውስጥ ያለ መዳብ፣ ቆርቆሮ፣ ብረትና እርሳስ ናቸው። ብር ሲቀልጥ ከላይ እንደሚሰፍ ቆሻሻ ሆነዋል። 19  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሁላችሁም ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ስለሆናችሁ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰበስባችኋለሁ። 20  እሳት በላያቸው ላይ እንዲነድባቸውና እንዲቀልጡ ብር፣ መዳብ፣ ብረት፣ እርሳስና ቆርቆሮ በምድጃ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ሁሉ እኔም እናንተን በንዴትና በታላቅ ቁጣ እሰበስባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ እሳት በማንደድ አቀልጣችኋለሁ። 21  አንድ ላይ እሰበስባችኋለሁ፤ በላያችሁም ላይ የቁጣዬን እሳት አነዳለሁ፤ እናንተም በውስጧ ትቀልጣላችሁ። 22  ብር በምድጃ ውስጥ እንደሚቀልጥ ሁሉ እናንተም በውስጧ ትቀልጣላችሁ፤ በእናንተ ላይ ቁጣዬን ያፈሰስኩት እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’” 23  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 24  “የሰው ልጅ ሆይ፣ እንዲህ በላት፦ ‘አንቺ በቁጣ ቀን የማትጸጂ ወይም ዝናብ የማይዘንብብሽ ምድር ነሽ። 25  ነቢያቷ ያደነውን እንስሳ እንደሚቦጫጭቅ የሚያገሳ አንበሳ በውስጧ ሴራ ጠንስሰዋል። ሰዎችን ይውጣሉ። ውድ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ። በውስጧ ያሉትን ብዙ ሴቶች መበለት አድርገዋል። 26  ካህናቷ ሕጌን ጥሰዋል፤ ቅዱስ ስፍራዎቼንም ያረክሳሉ። ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው ነገር መካከል ምንም ልዩነት አያደርጉም፤ ደግሞም ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አያስታውቁም፤ ሰንበቶቼንም ለማክበር አሻፈረኝ ይላሉ፤ እኔም በመካከላቸው ረከስኩ። 27  በመካከሏ ያሉት አለቆቿ ያደኑትን እንስሳ እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው፤ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ደም ያፈሳሉ፤ የሰዎችንም ሕይወት ያጠፋሉ። 28  ነቢያቷ ግን እነሱ የሚያደርጉትን ነገር በኖራ ይለስናሉ። የሐሰት ራእዮች ያያሉ፤ የውሸት ሟርትም ያሟርታሉ፤ ደግሞም ይሖዋ ራሱ ምንም ሳይናገር “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል” ይላሉ። 29  የምድሪቱ ሰዎች የማጭበርበር ድርጊት ፈጽመዋል፤ ሌሎችን ዘርፈዋል፤ ችግረኛውንና ድሃውን በድለዋል፤ ደግሞም ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አጭበርብረዋል፤ ፍትሕንም ነፍገውታል።’ 30  “‘ከመካከላቸው የድንጋይ ቅጥሩን የሚጠግን ወይም ምድሪቱ እንዳትጠፋ በፈረሰው ቦታ ላይ በፊቴ የሚቆምላት ሰው ይኖር እንደሆነ ተመለከትኩ፤ ሆኖም አንድም ሰው አላገኘሁም። 31  ስለዚህ ቁጣዬን በእነሱ ላይ አወርዳለሁ፤ በታላቅ ቁጣዬም እሳት ፈጽሜ አጠፋቸዋለሁ። የመረጡት መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,037
23  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ከአንድ እናት የተወለዱ ሁለት ሴቶች ነበሩ። 3  እነሱም በግብፅ ዝሙት አዳሪዎች ሆኑ፤ ከወጣትነታቸው ጊዜ ጀምሮ አመነዘሩ። በዚያም ጡታቸው ተሻሸ፤ የድንግልናቸውም ጉያ ተዳበሰ። 4  የታላቂቱ ስም ኦሆላ፣ የእህቷም ስም ኦሆሊባ ነበር። እነሱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውን በተመለከተ፣ ኦሆላ ሰማርያ ስትሆን ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት። 5  “ኦሆላ የእኔ ሆና ሳለች ታመነዝር ጀመር። ጎረቤቶቿ የሆኑትን ፍቅረኞቿን አሦራውያንን በፍትወት ተመኘች። 6  እነሱ ሰማያዊ ልብስ የለበሱ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች ሲሆኑ ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች እንዲሁም ፈረሰኞች ነበሩ። 7  እሷ ምርጥ ከሆኑት የአሦር ልጆች ሁሉ ጋር ማመንዘሯን ቀጠለች፤ ደግሞም በፍትወት የምትመኛቸው ሰዎች በሚያመልኳቸው አስጸያፊ ጣዖቶች ራሷን አረከሰች። 8  በግብፅ ትፈጽመው የነበረውን ምንዝር አልተወችም፤ እነሱ በወጣትነቷ ከእሷ ጋር ተኝተዋልና፤ የድንግልናዋን ጉያ ዳብሰዋል እንዲሁም ፍትወታቸውን በእሷ ላይ አፍስሰዋል። 9  ስለዚህ በፍትወት ለተመኘቻቸው፣ ፍቅረኞቿ ለሆኑት አሦራውያን አሳልፌ ሰጠኋት። 10  እነሱ እርቃኗን ገለጡ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ማረኩ፤ እሷንም በሰይፍ ገደሏት። በሴቶች መካከል መጥፎ ስም አተረፈች፤ እነሱም የፍርድ እርምጃ ወሰዱባት። 11  “እህቷ ኦሆሊባ ይህን ስትመለከት ፍትወቷ እጅግ የከፋ ሆነ፤ አመንዝራነቷም ከእህቷ የባሰ ሆነ። 12  ጎረቤቶቿ የሆኑትን የአሦርን ልጆች በፍትወት ተመኘች፤ እነሱ ያማረ ልብስ የለበሱ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ሲሆኑ ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች ነበሩ። 13  እሷ ራሷን ባረከሰች ጊዜ ሁለቱም በአንድ መንገድ እንደሄዱ ተገነዘብኩ። 14  ይሁን እንጂ እሷ በአመንዝራነቷ ገፋችበት። በግድግዳው ላይ የተቀረጹትን የወንድ ምስሎች ይኸውም ቀይ ቀለም የተቀቡትን የከለዳውያን የተቀረጹ ምስሎች አየች፤ 15  እነሱ ወገባቸው ላይ ቀበቶ ታጥቀዋል፤ በራሳቸውም ላይ የተንዘረፈፈ ጥምጥም አድርገዋል፤ ደግሞም ተዋጊዎች ይመስላሉ፤ ሁሉም በከለዳውያን ምድር የተወለዱትን ባቢሎናውያን ያመለክታሉ። 16  እሷም እነሱን እንዳየቻቸው በፍትወት ትመኛቸው ጀመር፤ ወደ ከለዳውያንም ምድር መልእክተኞች ላከችባቸው። 17  በመሆኑም የባቢሎን ልጆች ከእሷ ጋር ለመተኛት ወደ እሷ መምጣታቸውን ቀጠሉ፤ በፍትወታቸውም አረከሷት። በእነሱ ከረከሰች በኋላ ተጸይፋቸው ከእነሱ ራቀች። 18  “ዓይን አውጣ በመሆን ማመንዘሯንና እርቃኗን መግለጧን በቀጠለች ጊዜ እህቷን ተጸይፌ እንደራቅኳት ሁሉ እሷንም ተጸይፌ ራቅኳት። 19  እሷ ግን በግብፅ ምድር ስታመነዝር የነበረበትን የወጣትነቷን ዘመን በማስታወስ በአመንዝራነቷ ይባስ ገፋችበት። 20  ብልታቸው እንደ አህያ ብልት፣ አባለዘራቸውም እንደ ፈረስ አባለዘር በሆኑ ወንዶች የተያዙ ቁባቶች እንደሚያደርጉት እሷም በፍትወት ተመኘቻቸው። 21  በግብፅ ምድር ጉያሽን በዳበሱበት፣ የወጣትነትሽንም ጡቶች ባሻሹበት ጊዜ በወጣትነትሽ ትፈጽሚው የነበረውን ጸያፍ ምግባር ተመኘሽ። 22  “ስለዚህ ኦሆሊባ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ተጸይፈሽ የራቅሻቸውን ፍቅረኞችሽን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ፤ እነሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤ 23  እነሱም የባቢሎን ልጆችና ከለዳውያን ሁሉ እንዲሁም የአሦርን ልጆች ሁሉ ጨምሮ የጰቆድ፣ የሾአ እና የቆአ ሰዎች ናቸው። ሁሉም መልከ ቀና ወጣቶች፣ ገዢዎችና የበታች ገዢዎች፣ ተዋጊዎችና የተመረጡ አማካሪዎች እንዲሁም ፈረሰኞች ናቸው። 24  እነሱም የጦር ሠረገሎችንና መንኮራኩሮችን ሁሉ እያንጋጉ፣ ትልቅና ትንሽ ጋሻ የያዘ እንዲሁም የራስ ቁር የደፋ ብዙ ሠራዊት አስከትለው ጥቃት ይሰነዝሩብሻል። በዙሪያሽም ይሰለፋሉ፤ እኔም የመፍረድ ሥልጣን እሰጣቸዋለሁ፤ እነሱም ትክክል መስሎ በታያቸው መንገድ ይፈርዱብሻል። 25  እኔም ቁጣዬን በአንቺ ላይ እገልጣለሁ፤ እነሱም በታላቅ ቁጣ እርምጃ ይወስዱብሻል። አፍንጫሽንና ጆሮዎችሽን ይቆርጣሉ፤ ከአንቺም የቀሩት በሰይፍ ይወድቃሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዳሉ፤ ከአንቺም የቀሩት በእሳት ይበላሉ። 26  ልብሶችሽን ይገፉሻል፤ ያማሩ ጌጣጌጦችሽንም ይነጥቁሻል። 27  በግብፅ ምድር የጀመርሽው ጸያፍ ምግባርና አመንዝራነትሽ እንዲያበቃ አደርጋለሁ። ከእንግዲህ ዓይንሽን ወደ እነሱ አታነሺም፤ ግብፅንም አታስታውሺም።’ 28  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ ለጠላሻቸው ሰዎች፣ ተጸይፈሽ ለራቅሻቸው ሰዎች አሳልፌ ልሰጥሽ ነው። 29  እነሱ በጥላቻ እርምጃ ይወስዱብሻል፤ የደከምሽበትን ነገር ሁሉ ይወስዳሉ፤ ራቁትሽንና እርቃንሽን ያስቀሩሻል። የፆታ ብልግና ስትፈጽሚ የተገለጠው አሳፋሪ የሆነው እርቃንሽ፣ ጸያፍ ምግባርሽና አመንዝራነትሽ ይፋ ይወጣል። 30  እንደ ዝሙት አዳሪ ብሔራትን ተከትለሽ ስለሄድሽና አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራስሽን ስላረከስሽ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይፈጸሙብሻል። 31  የእህትሽን መንገድ ተከትለሻል፤ ስለዚህ የእሷን ጽዋ አስጨብጥሻለሁ።’ 32  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጥልቅና ሰፊ የሆነውን የእህትሽን ጽዋ ትጠጫለሽ፤ደግሞም መሳቂያና መሳለቂያ ትሆኛለሽ፤ ጽዋውም በዚህ የተሞላ ነው። 33  በስካርና በሐዘን፣በሽብርና በጥፋት ጽዋ ትዋጫለሽ፤ይህም የእህትሽ የሰማርያ ጽዋ ነው። 34  ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽ፤ የጽዋውንም ስብርባሪዎች ትቆረጣጥሚያለሽ፤ከዚያም ጡቶችሽን ትቆርጫለሽ። “እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’ 35  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለረሳሽኝና ጨርሶ ቸል ስላልሽኝ ጸያፍ ምግባርሽና አመንዝራነትሽ የሚያስከትለውን መዘዝ ትቀበያለሽ።’” 36  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በኦሆላና በኦሆሊባ ላይ ትፈርዳለህ? አስጸያፊ ተግባራቸውንስ ፊት ለፊት ትነግራቸዋለህ? 37  እነሱ አመንዝረዋል፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል። አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻቸው ጋር ከማመንዘራቸውም በተጨማሪ ለእኔ የወለዷቸውን ልጆች ለጣዖቶቻቸው መብል እንዲሆኑ ለእሳት አሳልፈው ሰጥተዋል። 38  በተጨማሪም በእኔ ላይ እንዲህ አድርገዋል፦ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል፤ ሰንበቶቼንም አቃለዋል። 39  ልጆቻቸውን አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻቸው ከሠዉ በኋላ በዚያው ቀን ወደ መቅደሴ መጥተው አረከሱት። እንግዲህ በቤቴ ውስጥ ይህን አድርገዋል። 40  አልፎ ተርፎም ከሩቅ ቦታ ወንዶች እንዲመጡላቸው መልእክተኛ ላኩ። እነሱ በመጡ ጊዜ ገላሽን ታጠብሽ፤ ዓይንሽን ተኳልሽ፤ በጌጣጌጥም ተዋብሽ። 41  እጅግ ባማረ ድንክ አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፤ በፊቱም በተሰናዳ ማዕድ ላይ ዕጣኔንና ዘይቴን አኖርሽ። 42  በዚያም በፈንጠዝያ ላይ ያሉ ብዙ ወንዶች ሁካታ ይሰማ ነበር፤ በመካከላቸውም ከምድረ በዳ የመጡ ሰካራሞች ነበሩ። እነሱም በሴቶቹ እጆች ላይ አምባር አጠለቁ፤ በራሳቸውም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉላቸው። 43  “ከዚያም እኔ ሰውነቷ በምንዝር ስላለቀው ሴት፣ ‘አሁንም ማመንዘሯን ትቀጥላለች’ አልኩ። 44  ሰው ወደ ዝሙት አዳሪ እንደሚሄድ ሁሉ እነሱም ወደ እሷ መሄዳቸውን ቀጠሉ። በዚህ መንገድ፣ ባለጌ ወደሆኑት ወደ ኦሆላና ወደ ኦሆሊባ ገቡ። 45  ጻድቃን ግን ለምንዝርና ለደም አፍሳሽነት የሚገባውን ፍርድ ይፈርዱባታል፤ እነሱ አመንዝሮች ናቸውና፤ እጃቸውም በደም ተበክሏል። 46  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘መቀጣጫ ያደርጋቸውና ለብዝበዛ ይዳርጋቸው ዘንድ በእነሱ ላይ ብዙ ሠራዊት ይሰበሰባል። 47  ሠራዊቱ ድንጋይ ይወረውርባቸዋል፤ በሰይፉም ይቆራርጣቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ይገድላል፤ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላል። 48  በምድሪቱ ላይ የሚፈጸመው ጸያፍ ምግባር እንዲወገድ አደርጋለሁ፤ ሴቶቹም ሁሉ ከዚህ ይማራሉ፤ የእናንተንም ጸያፍ ምግባር ከመከተል ይርቃሉ። 49  የፈጸማችሁት ጸያፍ ምግባር እንዲሁም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ የሠራችሁት ኃጢአት የሚያስከትለውን መዘዝ እንድትቀበሉ ያደርጋሉ፤ እኔም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”
[]
[]
[]
[]
12,038
24  የይሖዋ ቃል በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን እንዲህ ሲል ዳግመኛ ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ቀን፣ አዎ ይህንኑ ቀን መዝግብ። የባቢሎን ንጉሥ በዚሁ ቀን በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት መሰንዘር ጀምሯል። 3  ዓመፀኛውን ቤት አስመልክቶ ምሳሌ ተናገር፤ ስለ እነሱም እንዲህ በል፦ “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ድስቱን ጣደው፤ እሳት ላይ ጣደው፤ ውኃም ጨምርበት። 4  ጭኑንና ወርቹን ጨምሮ ጥሩ ጥሩ የሆነውን ሙዳ ሥጋ ሁሉ ሰብስበህ ጨምርበት፤ምርጥ የሆኑ አጥንቶችንም ሙላበት። 5  ከመንጋው ምርጥ የሆነውን በግ ውሰድ፤ በድስቱም ሥር ዙሪያውን ማገዶ ጨምር። ሥጋውን ቀቅለው፤ በውስጡ ያለውንም አጥንት አብስለው።”’ 6  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የዛገ ድስት ለሆነችውና ዝገቷ ላለቀቀው እንዲሁም ደም አፍሳሽ ለሆነችው ከተማ ወዮላት! ሥጋውን አንድ በአንድ አውጣ፤ ዕጣ መጣል አያስፈልግህም። 7  ያፈሰሰችው ደም በውስጧ ይገኛልና፤ በገላጣ ዓለት ላይ አፍስሳዋለች። በአፈር እንዲሸፈን መሬት ላይ አላፈሰሰችውም። 8  ቁጣዬ ተነሳስቶ እበቀላት ዘንድያፈሰሰችው ደም እንዳይሸፈንደሙን በሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለት ላይ አደረግኩት።’ 9  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ደም አፍሳሽ ለሆነችው ከተማ ወዮላት! ማገዶውን እቆልለዋለሁ። 10  እንጨቱን ከምር፤ እሳቱን አቀጣጥል፤ሥጋውን በደንብ ቀቅል፤ መረቁን አፍስ፤ አጥንቶቹም ይረሩ። 11  ባዶውን ድስት እንዲግል ፍሙ ላይ ጣደው፤መዳቡም በጣም ይግላል። ቆሻሻው በውስጡ ይቀልጣል፤ ዝገቱንም እሳት ይበላዋል። 12  ድስቱ በጣም ከመዛጉ የተነሳ ስለማይለቅ ከንቱ ልፋት ነው፤ደግሞም እንዲሁ ድካም ብቻ ነው። ከነዝገቱ እሳት ውስጥ ጣለው!’ 13  “‘በጸያፍ ምግባርሽ የተነሳ ረክሰሻል። ላነጻሽ ሞክሬ ነበር፤ አንቺ ግን ከርኩሰትሽ ንጹሕ ልትሆኚ አትችዪም። በአንቺ ላይ ያደረብኝ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ንጹሕ አትሆኚም። 14  እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ። በእርግጥ ይፈጸማል። ምንም ሳላቅማማ፣ ያላንዳች ሐዘንና ጸጸት እርምጃ እወስዳለሁ። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 15  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 16  “የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ተወዳጅ የሆነውን በአንድ ምት ልወስድብህ ነው። አንተም ዋይታ አታሰማ ወይም አታልቅስ ወይም ደግሞ እንባህን አታፍስ። 17  ሐዘንህን በውስጥህ አምቀህ ያዝ፤ ለሞተው በወጉ መሠረት ሐዘንህን አትግለጽ። ጥምጥምህን እሰር፤ ጫማህንም አድርግ። ሪዝህን አትሸፍን፤ ሰዎች የሚያመጡልህንም ምግብ አትብላ።” 18  እኔም በጠዋት ለሕዝቡ ተናገርኩ፤ ሚስቴም ማታ ላይ ሞተች። ስለሆነም ጠዋት፣ ልክ እንደታዘዝኩት አደረግኩ። 19  ሕዝቡም “ይህ የምታደርገው ነገር ለእኛ ምን መልእክት እንዳለው አትነግረንም?” አሉኝ። 20  እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ “የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 21  ‘ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እጅግ የምትኮሩበትን፣ በፊታችሁ ተወዳጅ የሆነውንና የልባችሁ ምኞት የሆነውን መቅደሴን ላረክስ ነው። ትታችኋቸው የሄዳችሁት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። 22  ከዚያም እኔ እንዳደረግኩት ታደርጋላችሁ። ሪዛችሁን አትሸፍኑም፤ ሰዎች የሚያመጡላችሁንም ምግብ አትበሉም። 23  ጥምጥማችሁ አይፈታም፤ ጫማችሁ ከእግራችሁ ላይ አይወልቅም። ዋይታ አታሰሙም ወይም አታለቅሱም። ይልቁንም በበደላችሁ ትመነምናላችሁ፤ አንዳችሁ ለሌላው እሮሮ ታሰማላችሁ። 24  ሕዝቅኤል ምልክት ይሆንላችኋል። እሱ እንዳደረገው ሁሉ ታደርጋላችሁ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”’” 25  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ምሽጋቸውን ይኸውም ደስ የሚሰኙበትን ያማረ ነገር፣ በፊታቸው ተወዳጅ የሆነውን ነገርና የልባቸውን ምኞት እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በምወስድባቸው ቀን፣ 26  አምልጦ የመጣ ሰው ወሬውን ይነግርሃል። 27  በዚያን ቀን አፍህን ከፍተህ፣ ካመለጠው ሰው ጋር ትነጋገራለህ፤ ከዚያ በኋላ ዱዳ አትሆንም። ምልክት ትሆንላቸዋለህ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”
[]
[]
[]
[]
12,039
25  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ አሞናውያን አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። 3  አሞናውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መቅደሴ በረከሰ ጊዜና የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ እንዲሁም የይሁዳ ቤት ሰዎች በግዞት በተወሰዱ ጊዜ ‘እሰይ!’ ስላላችሁ 4  ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እነሱ በእናንተ ውስጥ ይሰፍራሉ፤ ድንኳኖቻቸውንም በመካከላችሁ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ፤ ወተታችሁንም ይጠጣሉ። 5  ራባን የግመሎች መሰማሪያ፣ የአሞናውያንን ምድርም መንጋ የሚያርፍበት ስፍራ አደርጋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’” 6  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በእጅህ ስላጨበጨብክና በእግርህ መሬቱን ስለመታህ እንዲሁም በእስራኤል ምድር ላይ የደረሰውን ሁኔታ ስታይ በንቀት ተሞልተህ ሐሴት ስላደረግክ፣ 7  ብሔራት እንዲበዘብዙህ ለእነሱ አሳልፌ እሰጥህ ዘንድ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ። ከሕዝቦች መካከል አስወግድሃለሁ፤ ከአገራትም መካከል ለይቼ አጠፋሃለሁ። እደመስስሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ።’ 8  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሞዓብና ሴይር “እነሆ፣ የይሁዳ ቤት ልክ እንደ ሌሎቹ ብሔራት ነው” ስላሉ፣ 9  በድንበሩ ላይ የሚገኙትና የምድሪቱ ውበት የሆኑት ከተሞች ማለትም ከቤትየሺሞትና ከበዓልመዖን አንስቶ እስከ ቂርያታይምድረስ ያለው የሞዓብ ክንፍ ለጠላት እንዲጋለጥ አደርጋለሁ። 10  ከአሞናውያን ጋር ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ እሰጠዋለሁ፤ ይህም አሞናውያን በብሔራት መካከል እንዳይታወሱ ለማድረግ ነው። 11  በሞዓብም ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’ 12  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ኤዶም በቂም በቀል ተነሳስቶ በይሁዳ ቤት ላይ እርምጃ ወስዷል፤ ደግሞም እነሱን በመበቀል ከፍተኛ በደል ፈጽሟል፤ 13  ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ። ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ። 14  ‘በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ። እነሱም፣ ኤዶም የምወስደውን የበቀል እርምጃ ይቀምስ ዘንድ ቁጣዬንና መዓቴን በኤዶም ላይ ያወርዳሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’ 15  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ፍልስጤማውያን በማይበርድ የጠላትነት ስሜት ተነሳስተው በክፋት የበቀል እርምጃ ለመውሰድና ጥፋት ለማድረስ ጥረት አድርገዋል። 16  ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በፍልስጤማውያን ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ከሪታውያንንም አጠፋለሁ፤ በባሕሩ ዳርቻ ላይ የቀሩትንም ነዋሪዎች እደመስሳለሁ። 17  ኃይለኛ ቅጣት በመቅጣት ታላቅ የበቀል እርምጃ እወስድባቸዋለሁ፤ በምበቀላቸውም ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
[]
[]
[]
[]
12,040
26  በ11ኛው ዓመት፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ጢሮስ ስለ ኢየሩሳሌም ‘እሰይ! የሕዝቦች በር ተሰበረች! አሁን እሷ ስለጠፋች ሁሉም ነገር ይሳካልኛል፤ ደግሞም እበለጽጋለሁ’ ስላለች፣ 3  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ፣ እነሆ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ባሕር ሞገዱን እንደሚያስነሳ ብዙ ብሔራትን በአንቺ ላይ አስነሳለሁ። 4  እነሱ የጢሮስን ቅጥሮች ያፈርሳሉ፤ ማማዎቿንም ያወድማሉ፤ አፈሯን ከላይዋ ጠርጌ አስወግዳለሁ፤ የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርጋታለሁ። 5  በባሕር መካከል የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆናለች።’ “‘እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና፣’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራትም ይበዘብዟታል። 6  በገጠር ያሉ ሰፈሮቿም በሰይፍ ይመታሉ፤ ሰዎችም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’ 7  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እነሆ፣ በጢሮስ ላይ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ከሰሜን አመጣለሁ፤ እሱ ፈረሶችን፣ የጦር ሠረገሎችን፣ ፈረሰኞችንና ብዙ ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ያለው የነገሥታት ንጉሥ ነው። 8  በገጠር ያሉ ሰፈሮችሽን በሰይፍ ያወድማል፤ በአንቺም ላይ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ይገነባል፤ የአፈር ቁልልም ይደለድላል፤ በአንቺም ላይ ትልቅ ጋሻ ያነሳል። 9  ቅጥሮችሽን በግንብ መደርመሻ መሣሪያ ይደበድባል፤ ማማዎችሽንም በመጥረቢያ ያፈርሳል። 10  ፈረሶቹ እጅግ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ አቧራ ያለብሱሻል፤ ሰዎች ቅጥሮቿ ወደፈረሱባት ከተማ እንደሚገቡ ሁሉ እሱም በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ የፈረሰኞቹ፣ የመንኮራኩሮቹና የሠረገሎቹ ድምፅ ቅጥሮችሽን ያናውጣል። 11  የፈረሶቹ ኮቴዎች ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረግጣሉ፤ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ግዙፍ የሆኑት ዓምዶችሽ መሬት ላይ ይንኮታኮታሉ። 12  ሀብትሽን ይበዘብዛሉ፤ ሸቀጥሽን ይዘርፋሉ፤ ቅጥሮችሽን ያፈርሳሉ፤ የሚያማምሩ ቤቶችሽንም ያወድማሉ፤ ከዚያም ድንጋዮችሽን፣ ሳንቃዎችሽንና አፈርሽን ወደ ባሕር ይጥላሉ።’ 13  “‘የዘፈንሽ ጩኸት ጸጥ እንዲል አደርጋለሁ፤ የበገናሽም ድምፅ ከእንግዲህ አይሰማም። 14  የሚያንጸባርቅ ገላጣ ዓለትም አደርግሻለሁ፤ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆኛለሽ። ዳግመኛ አትገነቢም፤ እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 15  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ጢሮስን እንዲህ ይላል፦ ‘ሞት አፋፍ ላይ ያሉት ሲያቃስቱና በመካከልሽ ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሳ ደሴቶች አይናወጡም? 16  የባሕርም ገዢዎች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ የተጠለፉ ሸማዎቻቸውንም አውልቀው ይጥላሉ፤ ደግሞም በጣም ይንቀጠቀጣሉ። መሬት ላይ ተቀምጠው ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ፤ በመገረምም አተኩረው ይመለከቱሻል። 17  በአንቺም ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፤ እንዲህም ይሉሻል፦ “ባሕር አቋርጠው የመጡ ሰዎች የሰፈሩብሽ፣ የተወደስሽ ከተማ ሆይ፣ እንዴት ጠፋሽ!አንቺም ሆንሽ ነዋሪዎችሽ በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይሽብር የምትነዙ የባሕር ላይ ኃያላን ነበራችሁ። 18  በምትወድቂበት ቀን ደሴቶች ይንቀጠቀጣሉ፤ጥፋት በሚደርስብሽ ጊዜ በባሕር ላይ ያሉ ደሴቶች ይሸበራሉ።”’ 19  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የሚያጥለቀልቅ ውኃ ሳመጣብሽና ኃይለኛ ውኃ ሲሸፍንሽ፣ 20  አንቺንም ሆነ ከአንቺ ጋር ወደ ጉድጓድ የሚወርዱትን፣ የጥንት ዘመን ሰዎች ወዳሉበት አወርዳችኋለሁ፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር፣ ጥንት እንደወደሙት ቦታዎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ምድር እንድትኖሪ አደርጋለሁ፤ ይህም የሚሆነው ሰው እንዳይኖርብሽ ነው። ከዚያ በኋላ የሕያዋንን ምድር ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። 21  “‘በአንቺ ላይ ድንገተኛ ሽብር አመጣለሁ፤ ከእንግዲህም አትኖሪም። ይፈልጉሻል ግን ፈጽሞ አትገኚም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,041
27  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጢሮስ ላይ ሙሾ አውርድ፤ 3  ጢሮስንም እንዲህ በላት፦‘አንቺ በባሕሩ መግቢያዎች ላይ የምትኖሪናበብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር የንግድ ልውውጥ የምታደርጊ፣ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጢሮስ ሆይ፣ አንቺ ራስሽ ‘ፍጹም ውብ ነኝ’ ብለሻል። 4  ግዛትሽ በባሕሩ መካከል ነው፤የገነቡሽ ሰዎችም ውበትሽን ፍጹም አድርገውታል። 5  ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሰኒር በመጣ የጥድ እንጨት ሠሩ፤ለአንቺም የመርከብ ምሰሶ ለመሥራት ከሊባኖስ፣ አርዘ ሊባኖስ አመጡ። 6  በባሳን የባሉጥ ዛፎች መቅዘፊያዎችሽን ሠሩ፤የፊተኛውን ክፍልሽንም ከኪቲም ደሴቶች በመጣ በዝሆን ጥርስ በተለበጠ የጥድ እንጨት ሠሩ። 7  ከግብፅ የመጣው የተለያየ ቀለም ያለው በፍታ የመርከብ ሸራሽን ለመሥራት አገልግሏል፤የላይኛው መድረክ መሸፈኛዎችሽም ከኤሊሻ ደሴቶች በመጣ ሰማያዊ ክርና ሐምራዊ ሱፍ የተሠሩ ናቸው። 8  ቀዛፊዎችሽ የሲዶና እና የአርዋድ ነዋሪዎች ነበሩ። ጢሮስ ሆይ፣ የገዛ ራስሽ ባለሙያዎች መርከበኞችሽ ነበሩ። 9  ልምድ ያካበቱት የጌባል ባለሙያዎች ስንጥቆችሽን ይደፍናሉ። በባሕር ላይ የሚጓዙ መርከቦችና ባሕረኞቻቸው ሁሉ ሸቀጣ ሸቀጦችን ለመገበያየት ወደ አንቺ ይመጡ ነበር። 10  የፋርስ፣ የሉድና የፑጥ ሰዎች ተዋጊዎች ሆነው በጦር ሠራዊትሽ ውስጥ ያገለግሉ ነበር። ጋሻቸውንና የራስ ቁራቸውን በአንቺ ውስጥ ሰቀሉ፤ ደግሞም ግርማ ሞገስ አጎናጸፉሽ። 11  በሠራዊትሽ ውስጥ ያሉት የአርዋድ ሰዎች በቅጥሮችሽ ላይ ዙሪያውን ቆመው ነበር፤ጀግኖችም በማማዎችሽ ላይ ነበሩ። ክብ የሆኑ ጋሻዎቻቸውን በቅጥሮችሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ። 12  “‘“ከተትረፈረፈው ውድ ሀብትሽ የተነሳ ተርሴስ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር። ሸቀጣ ሸቀጦችሽን በብር፣ በብረት፣ በቆርቆሮና በእርሳስ ይለውጡ ነበር። 13  ያዋን፣ ቱባልና መሼቅ ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በባሪያዎችና በመዳብ ዕቃዎች ይለውጡ ነበር። 14  የቶጋርማ ሰዎች ደግሞ ሸቀጦችሽን በጭነት ፈረሶች፣ በጦር ፈረሶችና በበቅሎዎች ይለውጡ ነበር። 15  የዴዳን ሰዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ በብዙ ደሴቶች ላይ ነጋዴዎች ቀጠርሽ፤ የዝሆን ጥርስና ዞጲ በግብር መልክ ያመጡልሽ ነበር። 16  ከምታመርቻቸው ዕቃዎች ብዛት የተነሳ ኤዶም ከአንቺ ጋር ትነግድ ነበር። ሸቀጦችሽን በበሉር፣ በሐምራዊ ሱፍ፣ የተለያዩ ቀለማት ባላቸው ጥልፎች፣ ጥራት ባለው ልብስ፣ በዛጎልና በሩቢ ይለውጡ ነበር። 17  “‘“ይሁዳና የእስራኤል ምድር ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በሚኒት ስንዴ፣ ምርጥ በሆኑ ምግቦች፣ በማር፣ በዘይትና በበለሳን ይለውጡ ነበር። 18  “‘“ደማስቆ ከተትረፈረፈው ምርትሽና ከሀብትሽ የተነሳ ከአንቺ ጋር ትነግድ ነበር፤ የሄልቦን የወይን ጠጅና የዛሃር ሱፍ ጨርቅ ትሸጥልሽ ነበር። 19  በዑዛል አቅራቢያ የሚገኙት ዌዳንና ያዋን ሸቀጦችሽን በሚተጣጠፍ ብረት፣ በብርጉድና በጠጅ ሣር ይለውጡ ነበር። 20  ዴዳን፣ በከብት ላይ ለመቀመጥ የሚያገለግል ግላስ በማቅረብ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር። 21  የጠቦቶች፣ የአውራ በጎችና የፍየሎች ነጋዴ የሆኑ ዓረቦችንና የቄዳር አለቆችን ሁሉ ቀጠርሽ። 22  የሳባና የራአማ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር፤ ሸቀጦችሽን በሁሉም ዓይነት ምርጥ የሆኑ ሽቶዎች፣ የከበሩ ድንጋዮችና በወርቅ ይለውጡ ነበር። 23  ካራን፣ ካኔህና ኤደን እንዲሁም የሳባ፣ የአሹርና የኪልማድ ነጋዴዎች ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር። 24  በገበያ ቦታሽ ያማሩ ልብሶችን፣ በሰማያዊ ጨርቅና የተለያዩ ቀለማት ባለው ጥልፍ የተሠራን ካባ እንዲሁም ብዙ ዓይነት ቀለም ያላቸውን ምንጣፎች ይነግዱ የነበረ ሲሆን ሁሉም በገመድ በጥብቅ የታሰሩ ነበሩ። 25  የተርሴስ መርከቦች ሸቀጦችሽን ያጓጉዙልሽ ነበር፤በመሆኑም በባሕሩ መካከል በሀብት ተሞልተሽና ጭነት በዝቶልሽ ነበር። 26  ቀዛፊዎችሽ ወደ ታላቅ ባሕር አምጥተውሻል፤የምሥራቁ ነፋስ በተንጣለለው ባሕር መካከል ሰባብሮሻል። 27  ውድቀት በሚደርስብሽ ቀን ሀብትሽ፣ ሸቀጦችሽ፣ የምትነግጃቸው ዕቃዎች፣ ባሕረኞችሽ፣ መርከበኞችሽ፣ስንጥቆችሽን የሚደፍኑልሽ ሰዎች፣ ነጋዴዎችሽና ተዋጊዎችሽ ሁሉይኸውም በአንቺ ውስጥ ያለው ሕዝብ ሁሉበተንጣለለው ባሕር መካከል ይሰምጣል። 28  መርከበኞችሽ ሲጮኹ የባሕሩ ጠረፍ ይናወጣል። 29  ቀዛፊዎቹ፣ ባሕረኞቹና መርከበኞቹ ሁሉከመርከቦቻቸው ይወርዳሉ፤ መሬት ላይም ይቆማሉ። 30  በአንቺ የተነሳ በራሳቸው ላይ አቧራ እየነሰነሱና በአመድ ላይ እየተንከባለሉድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ምርር ብለውም ያለቅሳሉ። 31  በአንቺ የተነሳ ራሳቸውን ይላጫሉ፣ ማቅ ይለብሳሉእንዲሁም ዋይ ዋይ እያሉ አምርረው ያለቅሳሉ። 32  ለአንቺም በሚያለቅሱበት ጊዜ ሙሾ ያወርዳሉ፤ የሐዘን እንጉርጉሮም ያንጎራጉራሉ፦ ‘በባሕር መካከል ጸጥ እንዳለችው እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው? 33  ሸቀጥሽ ከተንጣለለው ባሕር በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችን አጥግበሻል። የተትረፈረፈው ሀብትሽና ሸቀጣ ሸቀጥሽ የምድርን ነገሥታት አበልጽጓል። 34  አሁን ግን በተንጣለለው ባሕር ላይ ተሰባብረሽ ጥልቁ ውኃ ውስጥ ሰምጠሻል፤ሸቀጥሽና ሕዝብሽ ሁሉ አብረውሽ ሰምጠዋል። 35  የደሴቶቹም ነዋሪዎች ሁሉ በመገረም አተኩረው ይመለከቱሻል፤ነገሥታታቸውም በታላቅ ፍርሃት ይርዳሉ፤ ፊታቸውም ይለዋወጣል። 36  በብሔራት መካከል ያሉ ነጋዴዎች በአንቺ ላይ ከደረሰው ነገር የተነሳ ያፏጫሉ። ፍጻሜሽ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆኛለሽ።’”’”
[]
[]
[]
[]
12,042
28  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የጢሮስን ገዢ እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልብህ ከመታበዩ የተነሳ ‘እኔ አምላክ ነኝ። በባሕሩ መካከል በአምላክ ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ’ ትላለህ። በልብህ አምላክ እንደሆንክ የምታስብ ቢሆንምአንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም። 3  እነሆ፣ አንተ ከዳንኤል ይበልጥ ጥበበኛ እንደሆንክ ይሰማሃል። ከአንተ የተሰወረ ሚስጥር እንደሌለ አድርገህ ታስባለህ። 4  በጥበብህና በማስተዋልህ ራስህን አበልጽገሃል፤በግምጃ ቤቶችህም ውስጥ ወርቅና ብር ማከማቸትህን ቀጥለሃል። 5  በንግድህ ስኬታማ ከመሆንህ የተነሳ ብዙ ሀብት አፈራህ፤ካካበትከውም ሀብት የተነሳ ልብህ ታበየ።”’ 6  “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በልብህ አምላክ እንደሆንክ ስለተሰማህ፣ 7  ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑትን ባዕዳን አመጣብሃለሁ፤እነሱም በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ታላቅ ግርማህንም ያረክሳሉ። 8  ወደ ጉድጓድ ያወርዱሃል፤በተንጣለለውም ባሕር መካከል አስከፊ ሞት ትሞታለህ። 9  ያም ሆኖ በገዳይህ ፊት ‘እኔ አምላክ ነኝ’ ትላለህ? በሚያረክሱህ ሰዎች እጅ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።”’ 10  ‘በባዕዳን እጅ፣ ያልተገረዙ ሰዎችን አሟሟት ትሞታለህ፤እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 11  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 12  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ጢሮስ ንጉሥ ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተ ጥበብ የተሞላህና ፍጹም ውበት የተላበስክየፍጽምና ተምሳሌት ነበርክ። 13  በአምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ነበርክ። በከበሩ ድንጋዮች ሁሉይኸውም በሩቢ፣ በቶጳዝዮን፣ በኢያስጲድ፣በክርስቲሎቤ፣ በኦኒክስ፣ በጄድ፣ በሰንፔር፣ በበሉርና በመረግድ አጊጠህ ነበር፤እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች የተሰኩባቸው ማቀፊያዎችም ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ። በተፈጠርክበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር። 14  የተቀባህ፣ የምትጋርድ ኪሩብ አድርጌ ሾምኩህ። በአምላክ ቅዱስ ተራራ ላይ ነበርክ፤ በእሳታማ ድንጋዮችም መካከል ትመላለስ ነበር። 15  ከተፈጠርክበት ቀን አንስቶ ዓመፅ እስከተገኘብህ ጊዜ ድረስበመንገድህ ሁሉ ምንም እንከን አልነበረብህም። 16  ከንግድህ ብዛት የተነሳውስጥህ በዓመፅ ተሞላ፤ ኃጢአትም መሥራት ጀመርክ። የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፣ እንደ ርኩስ ቆጥሬ ከአምላክ ተራራ እጥልሃለሁ፤ከእሳታማዎቹ ድንጋዮች መካከልም አስወግድሃለሁ። 17  በውበትህ ምክንያት ልብህ ታበየ። ከታላቅ ግርማህ የተነሳ ጥበብህን አበላሸህ። ወደ ምድር እጥልሃለሁ። በነገሥታት ፊት ትዕይንት አደርግሃለሁ። 18  ታላቅ በደል በመፈጸምና በንግድ ሥራ በማጭበርበር መቅደሶችህን አረከስክ። እኔም ከመካከልህ እሳት እንዲወጣ አደርጋለሁ፤ እሳቱም ይበላሃል። በሚያዩህ ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አደርግሃለሁ። 19  ከሕዝቦች መካከል የሚያውቁህ ሁሉ በመገረም አተኩረው ያዩሃል። ፍጻሜህ ድንገተኛና አስከፊ ይሆናል፤ደግሞም ለዘላለም ከሕልውና ውጭ ትሆናለህ።”’” 20  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 21  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ሲዶና አዙረህ በእሷ ላይ ትንቢት ተናገር። 22  እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሲዶና ሆይ፣ እነሆ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ በመካከልሽም እከበራለሁ፤ደግሞም በእሷ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበትና በእሷ አማካኝነት በምቀደስበት ጊዜ ሰዎች እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 23  በእሷ ላይ ቸነፈር እሰዳለሁ፤ በጎዳናዎቿም ላይ ደም ይፈስሳል። ከየአቅጣጫው ሰይፍ በሚመጣባት ጊዜ የታረዱት ሰዎች በመካከሏ ይወድቃሉ፤እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 24  “‘“ከዚያ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ አደገኛ በሆነ አሜኬላና በሚያሠቃይ እሾህ ይኸውም በሚንቁት ብሔራት ዳግመኛ አይከበብም፤ ሰዎችም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’ 25  “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቤት ሰዎች ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል ዳግመኛ በምሰበስባቸው ጊዜ በብሔራት ፊት በእነሱ መካከል እቀደሳለሁ። እነሱም ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድራቸው ላይ ይኖራሉ። 26  በላይዋ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይንም ይተክላሉ፤ ደግሞም በዙሪያቸው ባሉት በሚንቋቸው ሁሉ ላይ የፍርድ እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ያለስጋት ይኖራሉ፤ እኔም አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
[]
[]
[]
[]
12,043
29  በአሥረኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በ12ኛው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን አዙረህ በእሱና በመላዋ ግብፅ ላይ ትንቢት ተናገር። 3  እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በአባይ ጅረቶች መካከል የተጋደምክና‘የአባይ ወንዝ የእኔ ነው።የሠራሁት ለገዛ ራሴ ነው’ የምትል አንተ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት፣ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን፣ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። 4  በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፤ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ከቅርፊትህ ጋር እንዲጣበቁ አደርጋለሁ። ቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁት የአባይ ዓሣዎች ሁሉ ጋር ከአባይ ወንዝህ መካከል አወጣሃለሁ። 5  አንተንም ሆነ በአባይ ወንዝህ ውስጥ ያሉትን ዓሣዎች ሁሉ በረሃ ላይ እጥላለሁ። አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ የሚሰበስብህም ሆነ የሚያነሳህ አይኖርም። ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ። 6  በዚያን ጊዜ የግብፅ ነዋሪዎች ሁሉ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ለእስራኤል ቤት ከአገዳ የተሻለ ድጋፍ መሆን አልቻሉምና። 7  እጅህን ሲይዙህ ተሰበርክ፤ትከሻቸውንም ወጋህ። በተመረኮዙህ ጊዜ ተሰበርክ፤እግራቸውም እንዲብረከረክ አደረግክ።” 8  “‘ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፤ በአንተ ዘንድ የሚገኘውን ሰውም ሆነ እንስሳ አጠፋለሁ። 9  የግብፅ ምድር ባድማና ወና ይሆናል፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ አንተ ‘የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ የሠራሁት እኔ ነኝ’ ብለሃልና። 10  ስለዚህ በአንተና በአባይ ወንዝህ ላይ ተነስቻለሁ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል እስከ ሰዌኔ ብሎም እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ ባድማ፣ ደረቅና ወና አደርጋለሁ። 11  የሰው እግርም ሆነ የከብት ኮቴ አያልፍባትም፤ ለ40 ዓመትም ማንም አይኖርባትም። 12  የግብፅን ምድር ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ለ40 ዓመት ያህል ባድማ ይሆናሉ፤ ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።” 13  “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ከ40 ዓመት በኋላ ግብፃውያንን ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል እሰበስባቸዋለሁ፤ 14  የተማረኩትን ግብፃውያን ወደ ትውልድ አገራቸው ወደ ጳትሮስ ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ በዚያም ደካማ መንግሥት ይሆናሉ። 15  ግብፅ ከሌሎቹ መንግሥታት ያነሰች ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ሌሎች ብሔራትን አትጨቁንም፤ ደግሞም በጣም ትንሽ ስለማደርጋቸው ሌሎች ብሔራትን መግዛት አይችሉም። 16  ግብፅ ለእስራኤል ቤት ዳግመኛ መታመኛ አትሆንም፤ ይልቁንም ከግብፃውያን እርዳታ በመሻት ለሠሩት ስህተት መታሰቢያ ትሆናለች። እነሱም እኔ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’” 17  በ27ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 18  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ሠራዊቱ በጢሮስ ላይ ታላቅ ግዳጅ እንዲፈጽም አደረገ። ራስ ሁሉ ተመልጧል፤ ትከሻም ሁሉ ተልጧል። ይሁን እንጂ እሱም ሆነ ሠራዊቱ በጢሮስ ላይ ላፈሰሱት ጉልበት ያገኙት ዋጋ የለም። 19  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ የግብፅን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር እሰጣለሁ፤ እሱም ሀብቷን ያግዛል፤ በእጅጉ ይበዘብዛል እንዲሁም ይመዘብራል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደሞዝ ይሆናል።’ 20  “‘በእሷ ላይ ላፈሰሰው ጉልበት የግብፅን ምድር ካሳ አድርጌ እሰጠዋለሁ፤ ምክንያቱም ይህን ያደረጉት ለእኔ ነው’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 21  “በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ እንዲበቅል አደርጋለሁ፤ ለአንተም በእነሱ መካከል መናገር የምትችልበት አጋጣሚ እከፍትልሃለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”
[]
[]
[]
[]
12,044
3  ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ በፊትህ ያለውን ብላ። ይህን ጥቅልል ብላ፤ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር” አለኝ። 2  ስለዚህ አፌን ከፈትኩ፤ እሱም ጥቅልሉን እንድበላው ሰጠኝ። 3  ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን የሰጠሁህን ጥቅልል ብላ፤ ሆድህንም ሙላ” አለኝ። እኔም ጥቅልሉን መብላት ጀመርኩ፤ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠኝ። 4  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ቤት ሂድ፤ ቃሌንም ንገራቸው። 5  የተላክኸው ወደ እስራኤል ቤት እንጂ ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገር ሕዝብ አይደለምና። 6  ለመረዳት የሚያዳግት ቋንቋ ወይም የማይታወቅ ልሳን ወደሚናገሩና ቃላቸው ሊገባህ ወደማይችል ብዙ ሕዝቦች አልተላክህም። ወደ እነሱ ብልክህማ ኖሮ ይሰሙህ ነበር። 7  የእስራኤል ቤት ግን ሊሰሙህ አይፈልጉም፤ እኔን መስማት አይፈልጉምና። የእስራኤል ቤት ወገኖች ሁሉ ግትርና ልበ ደንዳና ናቸው። 8  እነሆ፣ ፊትህን ልክ እንደ እነሱ ፊት ጠንካራ አድርጌዋለሁ፤ ግንባርህንም ልክ እንደ እነሱ ግንባር አጠንክሬዋለሁ። 9  ግንባርህን እንደ አልማዝ፣ ከባልጩትም ይበልጥ ጠንካራ አድርጌዋለሁ። አትፍራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር፤ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።” 10  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ቃል ሁሉ በልብህ ያዝ፤ ደግሞም አዳምጥ። 11  በምርኮ ወደተወሰዱት ወገኖችህ ሄደህ ንገራቸው። ቢሰሙም ባይሰሙም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።” 12  ከዚያም መንፈስ ወደ ላይ አነሳኝ፤ ከበስተ ኋላዬም ታላቅ የጉምጉምታ ድምፅ “የይሖዋ ክብር ከስፍራው ይወደስ” ሲል ሰማሁ። 13  በዚያም የሕያዋን ፍጥረታቱ ክንፎች እርስ በርስ ሲነካኩ የሚያሰሙት ድምፅ፣ በአጠገባቸው ያሉት መንኮራኩሮች የሚያሰሙት ድምፅና የታላቅ ጉምጉምታ ድምፅ ነበር። 14  መንፈስም ወደ ላይ አንስቶ ወሰደኝ፤ እኔም ተማርሬና መንፈሴ ተቆጥቶ ሄድኩ፤ የይሖዋም ብርቱ እጅ በእኔ ላይ አርፋ ነበር። 15  ስለሆነም በቴልአቢብ፣ በኬባር ወንዝ አቅራቢያ ይኖሩ ወደነበሩት በግዞት የተወሰዱ ሰዎች ሄድኩ፤ እነሱም በሚኖሩበት ስፍራ ተቀመጥኩ፤ በድንጋጤ ፈዝዤም በመካከላቸው ሰባት ቀን ቆየሁ። 16  ሰባቱ ቀናት ካለፉ በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦ 17  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው። 18  ክፉውን ሰው ‘በእርግጥ ትሞታለህ’ ባልኩት ጊዜ ባታስጠነቅቀው፣ ደግሞም ክፉው ሰው በሕይወት ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ማስጠንቀቂያ ባትሰጠው፣ እሱ ክፉ በመሆኑ በሠራው በደል ይሞታል፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ። 19  ሆኖም ክፉውን ሰው አስጠንቅቀኸው ከክፋቱና ከክፉ መንገዱ ባይመለስ፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን በእርግጥ ታድናለህ። 20  ይሁንና ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ እኔ በፊቱ መሰናክል አስቀምጣለሁ፤ እሱም ይሞታል። ሳታስጠነቅቀው ከቀረህ በሠራው ኃጢአት የተነሳ ይሞታል፤ ያከናወነውም የጽድቅ ሥራ አይታወስም፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ። 21  ሆኖም ጻድቁን ሰው ኃጢአት እንዳይሠራ ብታስጠነቅቀውና ኃጢአት ባይሠራ፣ ማስጠንቀቂያውን በመስማቱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤ አንተም የገዛ ሕይወትህን ታድናለህ።” 22  በዚያም የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ሆነች፤ እሱም “ተነስተህ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሂድ፤ በዚያም አናግርሃለሁ” አለኝ። 23  ስለዚህ ተነስቼ ወደ ሸለቋማው ሜዳ ሄድኩ፤ እነሆም በኬባር ወንዝ አጠገብ ያየሁትን ክብር የሚመስል የይሖዋ ክብር በዚያ ነበር፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ። 24  ከዚያም መንፈስ ወደ ውስጤ ገብቶ በእግሬ አቆመኝ፤ አምላክም አናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፦ “ወደ ቤትህ ሄደህ በርህን ዘግተህ ተቀመጥ። 25  የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን በገመድ ይጠፍሩሃል፤ በመካከላቸውም እንዳትመላለስ ያስሩሃል። 26  እኔም ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቃለሁ፤ ዱዳም ትሆናለህ፤ ልትወቅሳቸውም አትችልም፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው። 27  በማናግርህ ጊዜ ግን አፍህን እከፍታለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው። የሚሰማ ይስማ፤ የማይሰማም አይስማ፤ ምክንያቱም እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸው።
[]
[]
[]
[]
12,045
30  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ዋይ ዋይ በሉ፤ ‘ቀኑ ስለቀረበ ወዮ!’ 3  ቀኑ ቀርቧልና፤ አዎ፣ የይሖዋ ቀን ቀርቧል። የደመናት ቀን፣ በብሔራትም ላይ የሚፈረድበት ቀን ይሆናል። 4  ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል፤ የታረዱት በግብፅ ሲወድቁ፣ሀብቷ ሲወሰድ እንዲሁም መሠረቶቿ ሲፈራርሱ ኢትዮጵያ በሽብር ትዋጣለች። 5  ኢትዮጵያ፣ ፑጥ፣ ሉድና ድብልቅ ሕዝቦች ሁሉእንዲሁም ኩብ፣ ከቃል ኪዳኑ ምድር ልጆች ጋርሁሉም በሰይፍ ይወድቃሉ።”’ 6  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለግብፅ ድጋፍ የሚሰጡም ይወድቃሉ፤የምትታበይበት ኃይሏም ይወገዳል።’ “‘ከሚግዶል እስከ ሰዌኔ በምድሪቱ ላይ በሰይፍ ይወድቃሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 7  ‘ከሌሎች አገሮች በከፋ ሁኔታ ባድማ ይሆናሉ፤ ከተሞቿም ከሌሎች ከተሞች በከፋ ሁኔታ ይወድማሉ። 8  በግብፅም ላይ እሳት በማነድበትና ተባባሪዎቿ ሁሉ በሚደቁበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 9  በዚያን ቀን በራሷ የምትታመነውን ኢትዮጵያን ለማንቀጥቀጥ መልእክተኞችን በመርከብ እልካለሁ፤ ግብፅ በምትጠፋበት ቀን በሽብር ይዋጣሉ፤ ቀኑ በእርግጥ ይመጣልና።’ 10  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ስፍር ቁጥር የሌለውን የግብፅ ሕዝብ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነጾር እጅ አጠፋለሁ። 11  ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እሱና ሠራዊቱ ምድሪቱን ለማውደም ይመጣሉ። እነሱም በግብፅ ላይ ሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ። 12  የአባይን የመስኖ ቦዮች አደርቃለሁ፤ ምድሪቱንም ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ። ምድሪቱና በውስጧ ያለው ሁሉ በባዕዳን እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ። እኔ ይሖዋ ራሴ ይህን ተናግሬአለሁ።’ 13  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አስጸያፊ የሆኑትንም ጣዖቶች አጠፋለሁ፤ ከንቱ የሆኑትንም የኖፍ አማልክት አስወግዳለሁ። ከእንግዲህ ከግብፅ ምድር የሚወጣ ገዢ አይኖርም፤ በግብፅም ምድር ፍርሃት እሰዳለሁ። 14  ጳትሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤ በጾዓን እሳት አነዳለሁ፤ ደግሞም በኖእ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ። 15  የግብፅ ምሽግ በሆነችው በሲን ላይ ቁጣዬን አፈስሳለሁ፤ የኖእንም ሕዝብ አጠፋለሁ። 16  በግብፅ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ ሲን በሽብር ትዋጣለች፤ ኖእ ቅጥሯ ይፈርሳል፤ ኖፍ ደግሞ በጠራራ ፀሐይ ጥቃት ይሰነዘርባታል! 17  የኦንና የጲበሰት ወጣቶች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ የከተሞቹም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ። 18  በዚያ የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ በጣፍነስ ቀኑ ይጨልማል። የምትታበይበት ኃይሏ ይጠፋል፤ ደመናት ይሸፍኗታል፤ የከተሞቿም ነዋሪዎች በግዞት ይወሰዳሉ። 19  በግብፅ ላይ የፍርድ እርምጃ እወስዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’” 20  በ11ኛውም ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በሰባተኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 21  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ እንዲድን አይታሰርም፤ ወይም ጠንክሮ ሰይፍ እንዲይዝ በጨርቅ አይጠቀለልም።” 22  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ እኔ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነስቻለሁ፤ ብርቱውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ ላይ እንዲወድቅ አደርጋለሁ። 23  ከዚያም ግብፃውያንን በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ። 24  የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስጨብጠዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንዶች እሰብራለሁ፤ እሱም ሊሞት እያጣጣረ እንዳለ ሰው በፊቱ እጅግ ያቃስታል። 25  የባቢሎንን ንጉሥ ክንዶች አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንዶች ግን ይዝላሉ፤ ሰይፌንም ለባቢሎን ንጉሥ ሳስጨብጠውና በግብፅ ምድር ላይ ሲሰነዝረው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 26  ግብፃውያንንም በብሔራት መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
[]
[]
[]
[]
12,046
31  በ11ኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖንና ስፍር ቁጥር ለሌለው ሕዝቡ እንዲህ በል፦‘በታላቅነትህ ከማን ጋር ትመሳሰላለህ? 3  አንድ አሦራዊ፣ በሊባኖስ ያደገ አርዘ ሊባኖስ ነበር፤አርዘ ሊባኖሱ ጥላ እንደሚሰጡ ችፍግ ብለው ያደጉ ዛፎች፣ የሚያማምሩ ቅርንጫፎች ያሉት እጅግ ረጅም ዛፍ ሲሆንጫፉም ደመናትን ይነካ ነበር። 4  ውኃዎቹ ትልቅ ዛፍ እንዲሆን አደረጉት፤ ጥልቅ ከሆኑት ምንጮች የተነሳ ዛፉ በጣም ረጅም ሆነ። በተተከለበት ቦታ ዙሪያ ጅረቶች ነበሩ፤የውኃ መውረጃዎቻቸውም በሜዳ ያሉትን ዛፎች ሁሉ ያጠጡ ነበር። 5  ከዚህም የተነሳ ቁመቱ በሜዳ ካሉት ከሌሎቹ ዛፎች ሁሉ ረዘመ። ብዙ ቅርንጫፎች አወጣ፤ ጅረቶቹ ብዙ ውኃ ስለነበራቸውቅርንጫፎቹ ረጃጅም ሆኑ። 6  የሰማይ ወፎች ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ጎጇቸውን ሠሩ፤የዱር እንስሳትም ሁሉ ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ፤ከጥላውም ሥር ብዙ ሕዝብ ያላቸው ብሔራት ሁሉ ሰፈሩ። 7  ከውበቱና ከቅርንጫፎቹ ርዝመት የተነሳ ግርማ ሞገስ ተላበሰ፤ሥሮቹን ብዙ ውኃ ወዳለበት ስፍራ ሰዶ ነበርና። 8  በአምላክ የአትክልት ስፍራ ያሉ ሌሎች አርዘ ሊባኖሶች ሊተካከሉት አልቻሉም። ከጥድ ዛፎች መካከል የእሱ ዓይነት ቅርንጫፎች ያሉት አንድም ዛፍ የለም፤የአርሞን ዛፎችም ከእሱ ቅርንጫፎች ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም። በአምላክ የአትክልት ስፍራ ያለ የትኛውም ዛፍ በውበቱ አይወዳደረውም። 9  ብዙ ቅጠሎች ያሉት ውብ ዛፍ አድርጌ ሠራሁት፤በእውነተኛው አምላክ የአትክልት ስፍራ በኤደን ያሉ ሌሎች ዛፎችም ሁሉ ቀኑበት።’ 10  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቁመቱ እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ጫፉን በደመናት መካከል ከፍ ስላደረገና በቁመቱ የተነሳ ልቡ ስለታበየ፣ 11  ኃያል ለሆነ የብሔራት ገዢ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። እሱም በእርግጥ ይነሳበታል፤ በክፋቱም የተነሳ እጥለዋለሁ። 12  ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኝ የሆኑት ባዕዳን ቆርጠው ይጥሉታል፤ በተራሮችም ላይ ጥለውት ይሄዳሉ፤ ቅጠሎቹም በየሸለቆው ይረግፋሉ፤ ቅርንጫፎቹም በምድሪቱ ላይ ባሉ ጅረቶች ሁሉ ላይ ተሰባብረው ይወድቃሉ። የምድር ሕዝቦች ሁሉ ከጥላው ሥር ወጥተው ትተውት ይሄዳሉ። 13  የሰማይ ወፎች ሁሉ በወደቀው ግንዱ ላይ ይሰፍራሉ፤ የዱር እንስሳትም ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ይኖራሉ። 14  ይህም የሚሆነው በውኃዎች አጠገብ ካሉ ዛፎች መካከል አንዳቸውም ቁመታቸው በጣም እንዳይረዝም ወይም ጫፋቸውን በደመናት መካከል ከፍ እንዳያደርጉ እንዲሁም ውኃ የጠገበ አንድም ዛፍ ቁመቱ እነሱ ጋ እንዳይደርስ ነው። ሁሉም ለሞት ይዳረጋሉና፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት የሰው ልጆች ጋር በአንድነት ከምድር በታች ይወርዳሉ።’ 15  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ መቃብር በሚወርድበት ቀን ሰዎች እንዲያዝኑ አደርጋለሁ። ስለዚህ ጥልቅ የሆኑትን ውኃዎች እሸፍናለሁ፤ ጅረቶቹንም እገታለሁ፤ ይህም በገፍ የሚፈስሱት ውኃዎች ይቋረጡ ዘንድ ነው። ከእሱ የተነሳ ሊባኖስን አጨልማለሁ፤ በሜዳም ያሉ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ። 16  ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ሁሉ ጋር ወደ መቃብር በማወርደው ጊዜ ሲወድቅ በሚሰማው ድምፅ ብሔራት እንዲናወጡ አደርጋለሁ፤ ከምድርም በታች የኤደን ዛፎች ሁሉ፣ ምርጥና ግሩም የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እንዲሁም ውኃ የጠገቡት ዛፎች ሁሉ ይጽናናሉ። 17  ከእሱ ጋር እንዲሁም በብሔራት መካከል በጥላው ሥር ይኖሩ ከነበሩት ደጋፊዎቹ ጋር በሰይፍ የታረዱት ወዳሉበት ወደ መቃብር ወርደዋል።’ 18  “‘በኤደን ካሉት ዛፎች መካከል የአንተ ዓይነት ክብርና ታላቅነት ያለው የትኛው ነው? ይሁንና ከኤደን ዛፎች ጋር ከምድር በታች ትወርዳለህ። ባልተገረዙት መካከል፣ በሰይፍ ከታረዱት ጋር ትጋደማለህ። ይህ በፈርዖንና ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቡ ላይ ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,047
32  በ12ኛውም ዓመት፣ በ12ኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፦‘በብሔራት መካከል እንደ ብርቱ ደቦል አንበሳ ነበርክ፤አሁን ግን አክትሞልሃል። አንተ እንደ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት ነበርክ፤ በወንዞችህ ውስጥ ትንቦጫረቅ፣በእግርህም ውኃውን ታደፈርስ፣ ወንዞቹንም ታቆሽሽ ነበር።’ 3  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በብዙ ብሔራት ጉባኤ አማካኝነት መረቤን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤እነሱም በማጥመጃ መረቤ ጎትተው ያወጡሃል። 4  በምድር ላይ እተውሃለሁ፤አውላላ ሜዳ ላይ እጥልሃለሁ። የሰማይ ወፎች ሁሉ በአንተ ላይ እንዲሰፍሩ አደርጋለሁ፤በመላው ምድር የሚገኙትን የዱር እንስሳትም በአንተ አጠግባለሁ። 5  ሥጋህን በተራሮች ላይ እጥላለሁ፤ከሬሳህ በተረፉት ነገሮችም ሸለቆዎቹን እሞላለሁ። 6  ምድሪቷ እስከ ተራሮች ድረስ በሚፈሰው ደምህ እንድትርስ አደርጋለሁ፤ጅረቶችም በደምህ ይሞላሉ።’ 7  ‘አንተም በምትጠፋበት ጊዜ ሰማያትን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብታቸውንም አጨልማለሁ። ፀሐይን በደመና እሸፍናለሁ፤ጨረቃም ብርሃኗን አትፈነጥቅም። 8  በሰማያት ያሉትን ብርሃን ሰጪ አካላት ሁሉ ከአንተ የተነሳ አጨልማቸዋለሁ፤ምድርህንም ጨለማ አለብሳለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 9  ‘ከአንተ የተማረኩትን ወደ ሌሎች ብሔራት ይኸውም ወደማታውቃቸው አገሮች በምወስድበት ጊዜየብዙ ሰዎችን ልብ አስጨንቃለሁ። 10  ብዙ ሕዝቦች እንዲደነግጡ አደርጋለሁ፤ሰይፌንም በፊታቸው ሳወዛውዝ ከአንተ የተነሳ ንጉሦቻቸው በፍርሃት ይርዳሉ። አንተ በምትወድቅበት ቀንእያንዳንዳቸው ለሕይወታቸው በመፍራት ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጣሉ።’ 11  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል። 12  ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብህ በኃያላን ተዋጊዎች ሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ሁሉም ከብሔራት መካከል እጅግ ጨካኞች ናቸው። እነሱም የግብፅን ኩራት ያንኮታኩታሉ፤ ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቧም ሁሉ ይደመሰሳል። 13  ከብቶቿን ሁሉ ከብዙ ውኃዎቿ አጠገብ አጠፋለሁ፤የሰው እግርም ሆነ የከብቶች ኮቴ ዳግመኛ አያደፈርሳቸውም።’ 14  ‘በዚያን ጊዜ ውኃዎቻቸውን አጠራለሁ፤ወንዞቻቸውም እንደ ዘይት እንዲፈስሱ አደርጋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 15  ‘ግብፅን ባድማና ወና በማድረግ ምድሪቱን የሞላውን ነገር ሁሉ በማስወግድበት ጊዜ፣ነዋሪዎቿንም ሁሉ በምመታበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 16  ይህ ሙሾ ነው፤ ሰዎችም ያንጎራጉሩታል፤የብሔራት ሴቶች ልጆች ያንጎራጉሩታል። በግብፅና ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቧ ሁሉ የተነሳ ያንጎራጉሩታል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 17  ከዚያም በ12ኛው ዓመት፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 18  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስፍር ቁጥር ለሌለው የግብፅ ሕዝብ ዋይ ዋይ በል፤ እሷንና የኃያላን ብሔራትን ሴቶች ልጆች ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር ከምድር በታች አውርዳቸው። 19  “‘በውበት ማንን ትበልጣለህ? ወደ ታች ውረድ፤ ካልተገረዙትም ጋር ተጋደም!’ 20  “‘በሰይፍ በታረዱት መካከል ይወድቃሉ። እሷ ለሰይፍ ተሰጥታለች፤ እሷንም ሆነ ስፍር ቁጥር የሌለውን ሕዝቧን ሁሉ ጎትቱ። 21  “‘ኃያላኑ ተዋጊዎች እሱንና ረዳቶቹን ከጥልቅ መቃብር ውስጥ ያነጋግሯቸዋል። እነሱ በእርግጥ ወደ ታች ይወርዳሉ፤ ደግሞም በሰይፍ ታርደው፣ እንዳልተገረዙት ሰዎች ይጋደማሉ። 22  አሦር ከመላ ጉባኤዋ ጋር በዚያ ትገኛለች። መቃብሮቻቸው በእሱ ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀዋል። 23  መቃብሮቿ በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ይገኛሉ፤ ጉባኤዋም በመቃብሯ ዙሪያ አለ፤ ሁሉም በሰይፍ ተመትተው ወድቀዋል፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረው ነበር። 24  “‘ኤላም ስፍር ቁጥር ከሌለው ሕዝቧ ሁሉ ጋር በመቃብሯ ዙሪያ ትገኛለች፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀዋል። በሕያዋን ምድር ሽብር የፈጠሩት እነዚህ ሰዎች ሳይገረዙ ከምድር በታች ወርደዋል። ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። 25  በመቃብሯ ዙሪያ ከሚገኘው ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቧ ሁሉ ጋር፣ በታረዱት መካከል መኝታ አዘጋጅተውላታል። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የታረዱ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረው ነበር፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። እሱ በታረዱት መካከል እንዲቀመጥ ተደርጓል። 26  “‘መሼቅና ቱባል እንዲሁም ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝባቸው ሁሉ በዚያ ይገኛሉ። መቃብሮቿ በዙሪያው ናቸው። ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተወጉ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕያዋን ምድር ሽብር ፈጥረዋል። 27  እነሱ፣ ከወደቁትና ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር ወደ መቃብር ከወረዱት ያልተገረዙ ኃያላን ተዋጊዎች ጋር ይጋደሙ የለም? ሰይፎቻቸውን ከራሳቸው በታች ያደርጋሉ፤ በኃጢአታቸውም የተነሳ የሚደርስባቸው ቅጣት በአጥንታቸው ላይ ይሆናል፤ ምክንያቱም እነዚህ ኃያላን ተዋጊዎች የሕያዋንን ምድር አሸብረዋል። 28  አንተ ግን ባልተገረዙት መካከል ትደቅቃለህ፤ በሰይፍ ከታረዱትም ጋር ትጋደማለህ። 29  “‘ኤዶም፣ ነገሥታቷና አለቆቿ ሁሉ በዚያ ይገኛሉ፤ ኃያላን ሆነው ሳለ በሰይፍ በታረዱት መካከል ተጋድመዋል፤ እነሱም ካልተገረዙትና ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር ይጋደማሉ። 30  “‘የሰሜን ገዢዎች በሙሉ ከሲዶናውያን ሁሉ ጋር በዚያ ይገኛሉ፤ ኃይላቸው ሽብር የፈጠረ ቢሆንም ከታረዱት ሰዎች ጋር ኀፍረት ተከናንበው ወርደዋል። በሰይፍ ከታረዱት ጋር ሳይገረዙ ይጋደማሉ፤ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱትም ጋር ኀፍረታቸውን ይከናነባሉ። 31  “‘ፈርዖን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይመለከታል፤ ደግሞም ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝቡ ላይ ከደረሰው ነገር ሁሉ ይጽናናል፤ ፈርዖንና ሠራዊቱ ሁሉ በሰይፍ ይታረዳሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 32  “‘በሕያዋን ምድር ሽብር ስለፈጠረ ፈርዖንና ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝቡ ሁሉ በሰይፍ ከታረዱት፣ ካልተገረዙት ሰዎች ጋር ለማረፍ ይጋደማሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,048
33  የይሖዋም ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ለሕዝብህ ልጆች ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ “‘በአንድ አገር ላይ ሰይፍ አመጣሁ እንበል፤ በዚህ ጊዜ የአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ አንድ ሰው በመምረጥ ጠባቂ አድርጎ ሾመው፤ 3  እሱም በአገሪቱ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ ቀንደ መለከት በመንፋት ሕዝቡን አስጠነቀቀ። 4  አንድ ሰው የቀንደ መለከቱን ድምፅ ሰምቶ ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ ሳያደርግ ቢቀር፣ ሰይፍም መጥቶ ሕይወቱን ቢያጠፋ፣ ደሙ በገዛ ራሱ ላይ ይሆናል። 5  የቀንደ መለከቱን ድምፅ ቢሰማም ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ አላደረገም። ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል። ቢጠነቀቅ ኖሮ ሕይወቱ በተረፈ ነበር። 6  “‘ነገር ግን ጠባቂው ሰይፍ ሲመጣ አይቶ ቀንደ መለከት ባይነፋና ሕዝቡን ባያስጠነቅቅ፣ ሰይፍም መጥቶ ከመካከላቸው የአንዱን ሰው ሕይወት ቢያጠፋ፣ ይህ ሰው በገዛ በደሉ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከጠባቂው እጅ እሻለሁ።’ 7  “የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተን ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌ ሾሜሃለሁ፤ ከአፌ የሚወጣውንም ቃል ስትሰማ ማስጠንቀቂያዬን ንገራቸው። 8  ክፉውን ሰው ‘አንተ ክፉ ሰው፣ በእርግጥ ትሞታለህ!’ ባልኩት ጊዜ፣ ክፉውን ሰው አካሄዱን እንዲያስተካክል ባታስጠነቅቀው፣ እሱ ክፉ በመሆኑ ከሠራው በደል የተነሳ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከአንተ እጅ እሻዋለሁ። 9  ሆኖም ክፉውን ሰው ከመንገዱ እንዲመለስ አስጠንቅቀኸው አካሄዱን ለማስተካከል ፈቃደኛ ባይሆን፣ እሱ በሠራው በደል ይሞታል፤ አንተ ግን የገዛ ሕይወትህን በእርግጥ ታድናለህ። 10  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ‘እናንተ እንዲህ ብላችኋል፦ “ዓመፃችንና ኃጢአታችን እጅግ ከብዶናል፤ በዚህም የተነሳ እየመነመንን ሄደናል፤ ታዲያ እንዴት በሕይወት መቀጠል እንችላለን?”’ 11  እንዲህ በላቸው፦ ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “በክፉው ሰው ሞት ደስ አልሰኝም፤ ይልቁንም ክፉው ሰው አካሄዱን አስተካክሎ በሕይወት እንዲኖር እፈልጋለሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ተመለሱ፤ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለምን ትሞታላችሁ?”’ 12  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ለሕዝብህ ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ‘ጻድቁ ሰው በሚያምፅበት ጊዜ ጽድቁ አያድነውም፤ ክፉውም ሰው ከክፋቱ በሚመለስበት ጊዜ በክፋቱ አይሰናከልም፤ ደግሞም ጻድቅ የሆነ ማንኛውም ሰው ኃጢአት በሚሠራበት ቀን በጽድቁ በሕይወት ሊኖር አይችልም። 13  ጻድቁን ሰው “በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ” ባልኩት ጊዜ በገዛ ጽድቁ ታምኖ መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ ከጽድቅ ሥራው መካከል አንዱም አይታሰብም፤ ይልቁንም መጥፎ ነገር በመፈጸሙ ይሞታል። 14  “‘እንዲሁም ክፉውን ሰው “በእርግጥ ትሞታለህ” ባልኩት ጊዜ ከኃጢአቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣ 15  ደግሞም ክፉው ሰው መያዣ አድርጎ የወሰደውን ቢመልስ፣ የሰረቀውን መልሶ ቢሰጥና መጥፎ ነገር ከመፈጸም ተቆጥቦ ሕይወት የሚያስገኙትን ደንቦች ቢከተል፣ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም። 16  ከሠራቸው ኃጢአቶች ውስጥ አንዱም አይታወስበትም። ፍትሕና ጽድቅ የሆነውን ነገር ስላደረገ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።’ 17  “ይሁንና ወገኖችህ ፍትሐዊ ያልሆነው የእነሱ መንገድ ሆኖ ሳለ ‘የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም’ ብለዋል። 18  “ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረጉን ቢተውና መጥፎ ነገር ቢፈጽም፣ በዚህ የተነሳ ይሞታል። 19  ሆኖም ክፉ ሰው ከክፋቱ ቢመለስና ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ፣ ይህን በማድረጉ በሕይወት ይኖራል። 20  “ይሁንና እናንተ ‘የይሖዋ መንገድ ፍትሐዊ አይደለም’ ብላችኋል። የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።” 21  ከረጅም ጊዜ በኋላ ይኸውም በተማረክን በ12ኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ ሰው ወደ እኔ መጥቶ “ከተማዋ ተመታች!” አለኝ። 22  ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ ሰውየው ጠዋት ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት፣ አምላክ አፌን ከፈተልኝ። እኔም አፌ ተከፍቶ በድጋሚ መናገር ቻልኩ። 23  ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 24  “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእነዚህ የፈራረሱ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች ስለ እስራኤል ምድር እንዲህ በማለት ይናገራሉ፦ ‘አብርሃም አንድ ራሱ ብቻ ነበር፤ ይሁንና ምድሪቱን ወረሰ። እኛ ግን ብዙ ነን፤ በእርግጥ ምድሪቱ ርስት ሆና ተሰጥታናለች።’ 25  “ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዓይኖቻችሁን አስጸያፊ ወደሆኑት ጣዖቶቻችሁ ታነሳላችሁ፤ ደምም ታፈሳላችሁ። ታዲያ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል? 26  በሰይፋችሁ ታምናችኋል፤ አስጸያፊ ልማዶች ትፈጽማላችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የባልንጀራችሁን ሚስት አርክሳችኋል። ታዲያ ምድሪቱን ልትወርሱ ይገባችኋል?”’ 27  “አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕያውነቴ እምላለሁ፤ በፈራረሱት ቦታዎች የሚኖሩት ሰዎች በሰይፍ ይወድቃሉ፤ አውላላ ሜዳ ላይ ያሉትንም ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ በምሽጎችና በዋሻዎች ውስጥ ያሉትም በበሽታ ይሞታሉ። 28  ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከልክ ያለፈ ኩራቷም ይጠፋል፤ የእስራኤልም ተራሮች ባድማ ይሆናሉ፤ የሚያልፍባቸውም አይኖርም። 29  ደግሞም በፈጸሟቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ ምድሪቱን ፈጽሞ ባድማ በማደርግበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’ 30  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወገኖችህ በየግድግዳው ሥርና በየቤቱ በራፍ ላይ ሆነው እርስ በርሳቸው ስለ አንተ ይነጋገራሉ። አንዱ ሌላውን፣ እያንዳንዱም ወንድሙን፣ ‘ና፣ ከይሖዋ የመጣውን ቃል እንስማ’ ይለዋል። 31  እንደ ሕዝቤ በፊትህ ለመቀመጥ ተሰብስበው ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም በተግባር አያውሉትም። በአፋቸው ይሸነግሉሃልና፤ ልባቸው ግን አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይስገበገባል። 32  እነሆ፣ አንተ ለእነሱ ባማረ ድምፅ እንደሚዘፈንና በባለ አውታር መሣሪያ አሳምረው እንደሚጫወቱት የፍቅር ዘፈን ሆነህላቸዋል። ቃልህን ይሰማሉ፤ ሆኖም አንዳቸውም አያደርጉትም። 33  ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ፣ ደግሞም ይፈጸማል፣ በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ ያውቃሉ።”
[]
[]
[]
[]
12,049
34  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር። ትንቢት ተናገር፤ እረኞቹንም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ራሳቸውን ለሚመግቡ የእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞቹ ሊመግቡ የሚገባው መንጋውን አይደለም? 3  ጮማውን ትበላላችሁ፤ ሱፉን ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም እንስሳ ታርዳላችሁ፤ መንጋውን ግን አትመግቡም። 4  የደከመውን አላበረታችሁም፣ የታመመውን አልፈወሳችሁም፣ የተጎዳውን በጨርቅ አላሰራችሁትም፣ የባዘኑትን መልሳችሁ አላመጣችሁም ወይም የጠፋውን አልፈለጋችሁም፤ ከዚህ ይልቅ በጭካኔና በግፍ ገዛችኋቸው። 5  በጎቹ እረኛ በማጣታቸው ተበታተኑ፤ ተበታትነው ለዱር አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ። 6  በጎቼ በየተራራውና ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ባዘኑ፤ በምድር ሁሉ ላይ ተበተኑ፤ የፈለጋቸው ወይም እነሱን ለማግኘት የጣረ አንድም ሰው የለም። 7  “‘“ስለዚህ እናንተ እረኞች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ 8  ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ “በጎቼ እረኛ ስላጡና እረኞቼ በጎቼን ስላልፈለጉ፣ ይልቁንም እረኞቹ ራሳቸውን ስለመገቡና በጎቼን ስላልመገቡ፣ በጎቼ ለአደን ተዳርገዋል፤ ለዱር አራዊትም ሁሉ መብል ሆነዋል፤”’ 9  ስለዚህ እናንተ እረኞች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። 10  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ በእረኞቹ ላይ ተነስቻለሁ፤ ስለ በጎቼ እጠይቃቸዋለሁ፤ በጎቼን እንዳያሰማሩም እከለክላቸዋለሁ፤ እረኞቹም ከእንግዲህ ራሳቸውን አይመግቡም። በጎቼን ከአፋቸው አስጥላለሁ፤ ከእንግዲህ ለእነሱ መብል አይሆኑም።’” 11  “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ ደግሞም እንከባከባቸዋለሁ። 12  የተበታተኑትን በጎቹን አግኝቶ እንደሚመግብ እረኛ በጎቼን እንከባከባለሁ። በደመናትና በድቅድቅ ጨለማ ቀን ከተበተኑባቸው ቦታዎች ሁሉ እታደጋቸዋለሁ። 13  ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ። 14  ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል። በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።” 15  “‘“በጎቼን እኔ ራሴ አሰማራለሁ፤ እኔ ራሴም አሳርፋቸዋለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 16  “የጠፋውን እፈልጋለሁ፤ የባዘነውን መልሼ አመጣለሁ፤ የተጎዳውን በጨርቅ አስራለሁ፤ የደከመውን አበረታለሁ፤ የወፈረውንና ጠንካራ የሆነውን ግን አጠፋለሁ። እፈርድበታለሁ፤ ተገቢውንም ቅጣት እሰጠዋለሁ።” 17  “‘በጎቼ ስለሆናችሁት ስለ እናንተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በበግና በበግ መካከል እንዲሁም በአውራ በጎችና በአውራ ፍየሎች መካከል ልፈርድ ነው። 18  እናንተ ምርጥ ከሆነው የግጦሽ ስፍራ መመገባችሁ አነሳችሁ? የቀሩትን የግጦሽ ስፍራዎች ደግሞ በእግራችሁ መረጋገጥ ይገባችኋል? እጅግ የጠራውን ውኃ ከጠጣችሁ በኋላስ ውኃውን በእግራችሁ እየመታችሁ ማደፍረሳችሁ ተገቢ ነው? 19  ታዲያ በጎቼ በእግራችሁ በረጋገጣችሁት የግጦሽ መስክ ላይ መሰማራትና በእግራችሁ እየመታችሁ ያደፈረሳችሁትን ውኃ መጠጣት ይኖርባቸዋል?” 20  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላቸዋል፦ “እነሆኝ፣ እኔ ራሴ በሰባው በግና ከሲታ በሆነው በግ መካከል እፈርዳለሁ፤ 21  እናንተ የታመሙት ሁሉ በየአቅጣጫው እስኪበታተኑ ድረስ በጎናችሁና በትከሻችሁ ገፍታችኋቸዋልና፤ በቀንዳችሁም ገፍትራችኋቸዋል። 22  በጎቼንም አድናለሁ፤ እነሱም ከእንግዲህ ለአደን አይዳረጉም፤ እኔም በበግና በበግ መካከል እፈርዳለሁ። 23  በእነሱ ላይ አንድ እረኛ ይኸውም አገልጋዬን ዳዊትን አስነሳለሁ፤ እሱም ይመግባቸዋል። እሱ ራሱ ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል። 24  ደግሞም እኔ ይሖዋ አምላካቸው እሆናለሁ፤ አገልጋዬ ዳዊት ደግሞ በመካከላቸው አለቃ ይሆናል። እኔ ይሖዋ ራሴ ተናግሬአለሁ። 25  “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አደገኛ የሆኑ የዱር አራዊትንም ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ፤ በመሆኑም በምድረ በዳ ያለስጋት ይኖራሉ፤ በጫካዎችም ውስጥ ይተኛሉ። 26  እነሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያለውን ቦታ በረከት አደርጋቸዋለሁ፤ ዝናብም በወቅቱ እንዲዘንብ አደርጋለሁ። በረከት እንደ ዝናብ ይወርዳል። 27  የሜዳው ዛፎች ፍሬያቸውን ይሰጣሉ፤ መሬቱም ፍሬ ይሰጣል፤ እነሱም በምድሪቱ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ። ቀንበራቸውን በምሰብርበትና ባሪያ አድርገው ከሚገዟቸው እጅ በማድናቸው ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 28  ከእንግዲህ ወዲህ ብሔራት እነሱን ለማደን አይነሱም፤ የምድር አራዊትም አይበሏቸውም፤ ያለስጋትም ይኖራሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም። 29  “‘“ዝና የሚያስገኝ የእርሻ ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ በምድሪቱ ላይ በረሃብ አያልቁም፤ ደግሞም ከእንግዲህ ወዲህ ብሔራት አያዋርዷቸውም። 30  ‘በዚህ ጊዜ እኔ አምላካቸው ይሖዋ ከእነሱ ጋር እንደሆንኩና እነሱ ይኸውም የእስራኤል ቤት ሕዝቤ እንደሆኑ ያውቃሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’ 31  “‘እናንተ በጎቼ፣ የምንከባከባችሁ በጎች፣ ከአፈር የተሠራችሁ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አምላካችሁ ነኝ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,050
35  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ተራራማ ወደሆነው የሴይር ምድር አዙረህ በእሱ ላይ ትንቢት ተናገር። 3  እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ እነሆ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ፤ እጄን በአንተ ላይ እዘረጋለሁ፤ ባድማና ወና አደርግሃለሁ። 4  ከተሞችህን አፈራርሳለሁ፤ አንተም ባድማና ወና ትሆናለህ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃለህ። 5  የእስራኤል ልጆች ጥፋት በደረሰባቸውና የመጨረሻውን ቅጣት በተቀበሉበት ጊዜ የማያባራ የጠላትነት ስሜት በማሳየት ለሰይፍ አሳልፈህ ሰጥተሃቸዋልና።”’ 6  “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለእርድ አዘጋጅሃለሁ፤ ደምህም ይፈስሳል። ደም ጠልተህ ስለነበር ደምህ ይፈስሳል። 7  የሴይርን ተራራማ ምድር ባድማና ወና አደርጋለሁ፤ በዚያ የሚያልፈውንም ሆነ የሚመለሰውን ማንኛውንም ሰው አጠፋለሁ። 8  ተራሮቹን በታረዱ ሰዎች እሞላለሁ፤ በሰይፍ የታረዱት በኮረብቶችህ፣ በሸለቆዎችህና በጅረቶችህ ላይ ይወድቃሉ። 9  ለዘላለም ባድማ አደርግሃለሁ፤ ከተሞችህም ሰው አልባ ይሆናሉ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ 10  “ይሖዋ ራሱ በዚያ ቢኖርም እንኳ፣ አንተ ‘እነዚህ ሁለት ብሔራትና ሁለት አገሮች የእኔ ይሆናሉ፤ እኛም ሁለቱን አገሮች እንወርሳለን’ ስላልክ፣ 11  ‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለእነሱ ካደረብህ የጥላቻ ስሜት የተነሳ በእነሱ ላይ በገለጥከው በዚያው ዓይነት ቁጣና ቅናት እኔም እርምጃ እወስድብሃለሁ፤ በአንተም ላይ በምፈርድበት ጊዜ በእነሱ መካከል ማንነቴ እንዲታወቅ አደርጋለሁ። 12  አንተ “ወና ሆነዋል፤ ለእኛም እንደ መብል ተሰጥተዋል” ባልክ ጊዜ በእስራኤል ተራሮች ላይ በንቀት የተናገርከውን ነገር ሁሉ እኔ ይሖዋ ራሴ እንደሰማሁ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።” 13  እናንተ በእኔ ላይ በእብሪት ተናግራችኋል፤ ደግሞም በእኔ ላይ ብዙ ነገር ተናግራችኋል። የተናገራችሁትን ሁሉ ሰምቻለሁ።’ 14  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን ባድማና ወና በማደርግበት ጊዜ መላዋ ምድር ሐሴት ታደርጋለች። 15  የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነበት ጊዜ ስለተደሰትክ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራማ ምድር ሆይ፣ አንተም ሆንክ መላው የኤዶም ምድር ሙሉ በሙሉ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
[]
[]
[]
[]
12,051
36  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ እስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። 2  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ጠላት ስለ እናንተ ‘እሰይ! የጥንቶቹ ከፍ ያሉ ቦታዎች ሳይቀሩ የእኛ ርስት ሆነዋል!’ ብሏል።”’ 3  “ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከብሔራት መካከል ለተረፉት ርስት እንድትሆኑ ባድማ ስላደረጓችሁና ከየአቅጣጫው ጥቃት ስለሰነዘሩባችሁ እንዲሁም ሰው አፍ ውስጥ ስለገባችሁና ሰዎች ስማችሁን ስላጠፉ፣ 4  የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ የተናገረውን ቃል ስሙ! ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለተራሮችና ለኮረብቶች፣ ለጅረቶችና ለሸለቆዎች፣ ፈራርሰው ባድማ ለሆኑት ቦታዎችና በዙሪያቸው ባሉት ከጥፋት የተረፉ ብሔራት ለተበዘበዙት እንዲሁም መሳለቂያ ለሆኑት የተተዉ ከተሞች ይህን ቃል ተናግሯል፤ 5  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እነሱን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ ‘የግጦሽ ቦታዎቿን ለመውሰድና ምድሪቱን ለመበዝበዝ ሲሉ በታላቅ ደስታና በከፍተኛ ንቀት ምድሬን የገዛ ርስታቸው እንደሆነ አድርገው በተናገሩት፣ ከጥፋት በተረፉት ብሔራትና በመላዋ ኤዶም ላይ በቅንዓቴ እሳት እናገራለሁ።’”’ 6  “ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፤ ለተራሮችና ለኮረብቶች፣ ለጅረቶችና ለሸለቆዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ብሔራት ያደረሱባችሁን ውርደት ስለተሸከማችሁ በቅንዓቴና በቁጣዬ እናገራለሁ።”’ 7  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዙሪያችሁ ያሉት ብሔራት የገዛ ራሳቸውን ኀፍረት ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቼ ምያለሁ። 8  የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ግን ለሕዝቤ ለእስራኤል ቅርንጫፍ ታወጣላችሁ፤ ፍሬም ታፈራላችሁ፤ እነሱ በቅርቡ ይመለሳሉና። 9  እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ፊቴንም ወደ እናንተ እመልሳለሁ፤ እናንተም ትታረሳላችሁ፤ ደግሞም ዘር ይዘራባችኋል። 10  ሕዝባችሁን ይኸውም መላውን የእስራኤል ቤት አበዛለሁ፤ ከተሞቹም የሰው መኖሪያ ይሆናሉ፤ የፈራረሱትም ስፍራዎች ዳግመኛ ይገነባሉ። 11  አዎ፣ ሕዝባችሁንና ከብቶቻችሁን አበዛለሁ፤ እነሱም ይበዛሉ፤ ፍሬያማም ይሆናሉ። እንደቀድሞው ዘመን ሰዎች እንዲኖሩባችሁ አደርጋለሁ፤ ደግሞም ከበፊቱ የበለጠ አበለጽጋችኋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። 12  በእናንተ ላይ ሰዎች ይኸውም ሕዝቤ እስራኤል እንዲመላለሱ አደርጋለሁ፤ እነሱም ይወርሷችኋል። የእነሱ ርስት ትሆናላችሁ፤ ከእንግዲህ ልጅ አልባ አታደርጓቸውም።’” 13  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ሰዎችን የምትበላና በላይዋ ያሉትን ብሔራት የወላድ መሃን የምታደርግ ምድር ናችሁ” ስለሚሏችሁ፣’ 14  ‘ከእንግዲህ ሰው አትበሉም ወይም በምድሪቱ ላይ ያሉትን ብሔራት ልጅ አልባ አታደርጉም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 15  ‘ከእንግዲህ ብሔራት እናንተን እንዲሰድቡ ወይም ሰዎች የሚሰነዝሩባችሁን ዘለፋ እንድትሸከሙ አልፈቅድም፤ ደግሞም በምድሪቱ ላይ ላሉት ብሔራት መሰናክል አትሆኑም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” 16  የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 17  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በምድራቸው ላይ ይኖሩ በነበረበት ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው ምድሪቱን አረከሷት። መንገዳቸው በፊቴ እንደ ወር አበባ ርኩሰት ነበር። 18  በምድሪቱ ላይ ደም ስላፈሰሱና ምድሪቱን አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቻቸው ስላረከሱ ቁጣዬን አፈሰስኩባቸው። 19  ደግሞም በብሔራት መካከል በተንኳቸው፤ በየአገሩም ዘራኋቸው። እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው ፈረድኩባቸው። 20  ሆኖም ወደ እነዚህ ብሔራት በመጡ ጊዜ ሰዎች ስለ እነሱ ‘እነዚህ የይሖዋ ሕዝብ ናቸው፤ ይሁን እንጂ ከእሱ ምድር ለመፈናቀል ተገደዱ’ እያሉ ቅዱስ ስሜን አረከሱ። 21  በመሆኑም የእስራኤል ቤት በሄዱባቸው ብሔራት መካከል ያረከሱት ቅዱስ ስሜ ያሳስበኛል።” 22  “ስለዚህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እርምጃ የምወስደው ለእናንተ ብዬ ሳይሆን በሄዳችሁባቸው ብሔራት መካከል ላረከሳችሁት ቅዱስ ስሜ ስል ነው።”’ 23  ‘በብሔራት መካከል የረከሰውን፣ ይኸውም በእነሱ መካከል ያረከሳችሁትን ታላቅ ስሜን በእርግጥ እቀድሰዋለሁ፤ ዓይኖቻቸው እያዩ በመካከላችሁ በምቀደስበት ጊዜ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ብሔራት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 24  ከብሔራት መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየአገሩም ሁሉ ሰብስቤ ወደ ምድራችሁ አመጣችኋለሁ። 25  ንጹሕ ውኃ እረጫችኋለሁ፤ እናንተም ንጹሕ ትሆናላችሁ፤ ከርኩሰታችሁ ሁሉና አስጸያፊ ከሆኑት ጣዖቶቻችሁ ሁሉ አነጻችኋለሁ። 26  አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ በውስጣችሁም አዲስ መንፈስ አሳድራለሁ። የድንጋይ ልባችሁን ከሰውነታችሁ አስወግጄ የሥጋ ልብ እሰጣችኋለሁ። 27  መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ በሥርዓቴም እንድትመላለሱ አደርጋለሁ፤ ድንጋጌዎቼንም ትጠብቃላችሁ፣ በተግባርም ታውሏቸዋላችሁ። 28  በዚያን ጊዜ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ላይ ትኖራላችሁ፤ ሕዝቤም ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።’ 29  “‘ከርኩሰታችሁ ሁሉ አድናችኋለሁ፤ እህሉን እጠራዋለሁ፤ ደግሞም አበዛዋለሁ፤ ረሃብም አላመጣባችሁም። 30  በረሃብ የተነሳ በብሔራት መካከል ዳግመኛ ውርደት እንዳይደርስባችሁ፣ የዛፉን ፍሬና የእርሻውን ምርት አበዛለሁ። 31  በዚያን ጊዜ ክፉ መንገዳችሁንና መጥፎ ሥራችሁን ታስታውሳላችሁ፤ በበደላችሁና በምትፈጽሟቸው አስጸያፊ ልማዶች የተነሳ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ። 32  ይሁንና ይህን እወቁ፦ ይህን የማደርገው ለእናንተ ብዬ አይደለም’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ይልቁንም የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ ከመንገዳችሁ የተነሳ እፈሩ፤ ደግሞም ተሸማቀቁ።’ 33  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከበደላችሁ ሁሉ በማነጻችሁ ቀን ከተሞቹ የሰው መኖሪያ እንዲሆኑ፣ የፈራረሱትም ቦታዎች እንደገና እንዲገነቡ አደርጋለሁ። 34  አላፊ አግዳሚው ሁሉ ጠፍ ሆኖ ሲያየው የነበረው ባድማ መሬት ይታረሳል። 35  ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፦ “ባድማ የነበረው ምድር እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ ሆነ፤ ፈራርሰው ባድማና ወና ሆነው የነበሩት ከተሞችም አሁን የተመሸጉ ከተሞችና የሰው መኖሪያ ሆነዋል።” 36  ደግሞም ከጥፋት የተረፉት በዙሪያችሁ ያሉት ብሔራት፣ የፈረሰውን የገነባሁትና ባድማ የሆነውን ምድር ያለማሁት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። እኔ ይሖዋ ተናግሬአለሁ፤ ደግሞም አድርጌዋለሁ።’ 37  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የእስራኤል ቤት ሰዎችም ይህን እንዳደርግላቸው እንዲጠይቁኝ እፈቅድላቸዋለሁ፦ ሕዝባቸውን እንደ መንጋ አበዛዋለሁ። 38  እንደ ቅዱሳን መንጋና በበዓል ወቅት በኢየሩሳሌም ውስጥ እንደሚገኘው መንጋ፣ ፈራርሰው የነበሩት ከተሞችም በሰው መንጋ ይሞላሉ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
[]
[]
[]
[]
12,052
37  የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ ይሖዋም በመንፈሱ ወሰደኝ፤ በሸለቋማው ሜዳ መካከልም አኖረኝ፤ ስፍራውም በአጥንቶች ተሞልቶ ነበር። 2  እሱም በዙሪያቸው እንዳልፍ አደረገኝ፤ በሸለቋማው ሜዳ ላይ በጣም ብዙ አጥንቶች ወድቀው አየሁ፤ አጥንቶቹም በጣም ደርቀው ነበር። 3  እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች ሕያው ሊሆኑ ይችላሉ?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ የምታውቀው አንተ ነህ” አልኩ። 4  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ስለ እነዚህ አጥንቶች ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እናንተ ደረቅ አጥንቶች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ 5  “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ “እስትንፋስ እንዲገባባችሁ አደርጋለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ። 6  ጅማት አደርግላችኋለሁ፤ ሥጋም አለብሳችኋለሁ፤ በቆዳም እሸፍናችኋለሁ፤ እስትንፋስም አስገባባችኋለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’” 7  ከዚያም በታዘዝኩት መሠረት ትንቢት ተናገርኩ። ትንቢቱን እንደተናገርኩ የሚንኮሻኮሽ ድምፅ ተሰማ፤ አጥንቶቹም እርስ በርስ መገጣጠም ጀመሩ። 8  ከዚያም አጥንቶቹ ጅማትና ሥጋ ሲለብሱ አየሁ፤ በቆዳም ተሸፈኑ። ሆኖም በውስጣቸው ገና እስትንፋስ አልነበረም። 9  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ለነፋሱ ትንቢት ተናገር። የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ ነፋሱንም እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ነፋስ ሆይ፣ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፤ ሕያው እንዲሆኑም በእነዚህ በተገደሉት ሰዎች ላይ ንፈስ።”’” 10  ስለዚህ ባዘዘኝ መሠረት ትንቢት ተናገርኩ፤ እስትንፋስም ገባባቸው፤ እነሱም ሕያው ሆነው በእግራቸው ቆሙ፤ እጅግ ታላቅ ሠራዊትም ሆኑ። 11  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው። እነሱ ‘አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጨልሟል። ከሌሎች ጋር ሙሉ በሙሉ ተቆራርጠናል’ ይላሉ። 12  ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ሆይ፣ መቃብሮቻችሁን እከፍታለሁ፤ ከመቃብሮቻችሁም ውስጥ አስነሳችኋለሁ፤ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣችኋለሁ። 13  ሕዝቤ ሆይ፣ መቃብሮቻችሁን ስከፍትና ከመቃብሮቻችሁ ውስጥ ሳስነሳችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’ 14  ‘መንፈሴን በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ እናንተም ሕያው ትሆናላችሁ፤ በምድራችሁም ላይ አሰፍራችኋለሁ፤ እናንተም እኔ ይሖዋ ራሴ እንደተናገርኩና ይህን እንዳደረግኩ ታውቃላችሁ’ ይላል ይሖዋ።” 15  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 16  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በትር ወስደህ ‘ለይሁዳና ከእሱ ጋር ላሉት የእስራኤል ሰዎች’ ብለህ ጻፍበት። ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ ‘ለዮሴፍ ይኸውም ኤፍሬምን ለሚወክለው በትርና ከእሱ ጋር ላሉት የእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ’ ብለህ ጻፍበት። 17  ከዚያም በእጅህ ውስጥ አንድ በትር ይሆኑ ዘንድ ሁለቱንም አንድ ላይ ያዛቸው። 18  ወገኖችህ ‘የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምን እንደሆነ አትነግረንም?’ ብለው ሲጠይቁህ፣ 19  እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በኤፍሬም እጅ ውስጥ ያለውን የዮሴፍንና ከእሱ ጋር ያሉትን የእስራኤልን ነገዶች በትር ወስጄ ከይሁዳ በትር ጋር አያይዘዋለሁ፤ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፤ እነሱም በእጄ ላይ አንድ በትር ይሆናሉ።”’ 20  የጻፍክባቸውን በትሮች ማየት እንዲችሉ በእጅህ ያዝ። 21  “ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያንን ከሄዱባቸው ብሔራት መካከል አመጣቸዋለሁ፤ ከየአቅጣጫውም ሰብስቤ ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ። 22  በምድሪቱ፣ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ብሔር አደርጋቸዋለሁ፤ በሁሉም ላይ አንድ ንጉሥ ይገዛል፤ ከእንግዲህ ሁለት ብሔራት አይሆኑም፤ ደግሞም ተከፍለው ሁለት መንግሥታት አይሆኑም። 23  ከእንግዲህ ወዲህ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው፣ ጸያፍ በሆኑት ልማዶቻቸውና በሚፈጽሟቸው በደሎች ሁሉ ራሳቸውን አያረክሱም። ታማኝነት በማጉደል ከሠሩት ኃጢአት ሁሉ እታደጋቸዋለሁ፤ ደግሞም አነጻቸዋለሁ። እነሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔ ራሴም አምላካቸው እሆናለሁ። 24  “‘“አገልጋዬ ዳዊት ንጉሣቸው ይሆናል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል። ድንጋጌዎቼን አክብረው ይመላለሳሉ፤ ደንቦቼንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ። 25  አባቶቻችሁ በኖሩባት፣ ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይቀመጣሉ፤ እነሱና ልጆቻቸው እንዲሁም የልጅ ልጆቻቸው በእሷ ላይ ለዘላለም ይኖራሉ፤ አገልጋዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃቸው ይሆናል። 26  “‘“ከእነሱም ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ዘላለማዊ ይሆናል። እነሱንም አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ እንዲሁም መቅደሴን በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ። 27  ድንኳኔ ከእነሱ ጋር ይሆናል፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። 28  መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሚሆንበት ጊዜ፣ ብሔራት እስራኤልን የቀደስኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።”’”
[]
[]
[]
[]
12,053
38  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን የመሼቅና የቱባል ዋና አለቃ በሆነውና በማጎግ ምድር በሚገኘው በጎግ ላይ አድርገህ በእሱ ላይ ትንቢት ተናገር። 3  እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል ዋና አለቃ የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። 4  እመልስሃለሁ፤ በመንጋጋህም መንጠቆ አስገባለሁ፤ ከመላው ሠራዊትህ ይኸውም ከፈረሶች፣ ያማረ ልብስ ከለበሱ ፈረሰኞች፣ ትልቅ ጋሻና ትንሽ ጋሻ ከያዘ እንዲሁም ሰይፍ ከሚመዝ ታላቅ ጉባኤ ጋር አወጣሃለሁ፤ 5  ትንሽ ጋሻ የያዙና የራስ ቁር የደፉ የፋርስ፣ የኢትዮጵያና የፑጥ ሰዎች ከእነሱ ጋር አሉ፤ 6  ጎሜርንና ወታደሮቹን ሁሉ፣ ራቅ ባለው የሰሜን ምድር የሚገኙትን የቶጋርማ ቤት ሰዎችንና ወታደሮቻቸውን ሁሉ ጨምሮ ብዙ ሕዝቦች ከአንተ ጋር አሉ። 7  “‘“አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር የተሰበሰበው ሠራዊትህ ሁሉ ተነሡ፣ ተዘጋጁም፤ አንተም አዛዣቸው ትሆናለህ። 8  “‘“ከብዙ ቀናት በኋላ በአንተ ላይ ትኩረት ይደረጋል። በመጨረሻዎቹ ዓመታት ከሰይፍ ጥቃት የተረፈውንና ከብዙ ሕዝቦች መካከል ተሰብስቦ ለብዙ ጊዜ ባድማ ሆነው ወደቆዩት የእስራኤል ተራሮች የተመለሰውን ሕዝብ ምድር ትወራለህ። የምድሪቱ ነዋሪዎች ከተለያዩ ሕዝቦች መካከል ተመልሰው የመጡ ናቸው፤ ደግሞም ሁሉም ያለስጋት ተቀምጠዋል። 9  አንተም በእነሱ ላይ እንደ አውሎ ነፋስ ትመጣለህ፤ አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር ያሉት ብዙ ሕዝቦች ምድሪቱን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።”’ 10  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያ ቀን ሐሳብ ወደ ልብህ ይገባል፤ ክፉ ዕቅድም ታወጣለህ፤ 11  እንዲህ ትላለህ፦ “ከለላ የሌላቸው ሰፈሮች የሚገኙበትን ምድር እወራለሁ። ያለስጋት ተረጋግተው በሚኖሩት ላይ እመጣለሁ፤ ሁሉም የሚኖሩት ቅጥር፣ መቀርቀሪያና በር በሌላቸው ሰፈሮች ነው።” 12  ዓላማህ ብዙ ሀብት መበዝበዝና መዝረፍ፣ ደግሞም አሁን የሰው መኖሪያ የሆኑትን ባድማ የነበሩ ስፍራዎችና ከብሔራት ሁሉ መካከል ዳግመኛ የተሰበሰበውን ሕዝብ ማጥቃት ነው፤ ይህ ሕዝብ ሀብትና ንብረት አከማችቷል፤ በምድርም እምብርት ላይ ይኖራል። 13  “‘ሳባ፣ ዴዳን፣ የተርሴስ ነጋዴዎችና ተዋጊዎቹ ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “ወረራ የምታካሂደው ብዙ ሀብት ለመበዝበዝና ለመዝረፍ ነው? ሠራዊትህን የሰበሰብከው ብርና ወርቅ ለማጋበስ፣ ሀብትና ንብረት ለመውሰድ እንዲሁም ብዙ ምርኮ ለመንጠቅ ነው?”’ 14  “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ትንቢት ተናገር፤ ጎግንም እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እስራኤል ያለስጋት በሚቀመጥበት ጊዜ፣ አንተ በዚያን ቀን ይህን ማወቅህ ይቀራል? 15  አንተ ከስፍራህ ይኸውም ርቆ ከሚገኘው የሰሜን ምድር ትመጣለህ፤ አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ብዙ ሕዝቦች ትመጣላችሁ፤ ሁሉም በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፣ ታላቅ ጉባኤና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ናቸው። 16  ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ሆነህ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትመጣለህ። ጎግ ሆይ፣ በዘመኑ መጨረሻ በአንተ አማካኝነት በፊታቸው ራሴን በምቀድስበት ጊዜ ብሔራት ያውቁኝ ዘንድ በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።”’ 17  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን በእነሱ ላይ እንደማመጣ ለብዙ ዓመታት ትንቢት በተናገሩትና አገልጋዮቼ በሆኑት የእስራኤል ነቢያት አማካኝነት በቀድሞ ዘመን የተናገርኩት ስለ አንተው አይደለም?’ 18  “‘በዚያ ቀን፣ ጎግ የእስራኤልን ምድር በሚወርበት ቀን’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ታላቅ ቁጣዬ ይነድዳል። 19  በቅንዓቴና በቁጣዬ እሳት እናገራለሁ፤ ደግሞም በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይከሰታል። 20  የባሕር ዓሣዎች፣ የሰማይ ወፎች፣ የዱር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ እንስሳት ሁሉና በምድር ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ ከእኔ የተነሳ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮችም ይናዳሉ፤ ገደላማ ቦታዎችም ይደረመሳሉ፤ ቅጥሩም ሁሉ ይፈርሳል።’ 21  “‘በተራሮቼ ሁሉ፣ በጎግ ላይ ሰይፍ እጠራለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘የእያንዳንዱ ሰው ሰይፍ በገዛ ወንድሙ ላይ ይሆናል። 22  እኔም በቸነፈርና በደም መፋሰስ እፈርድበታለሁ፤ በእሱ፣ በወታደሮቹና ከእሱ ጋር ባሉ ብዙ ሕዝቦች ላይ ኃይለኛ ዶፍ፣ በረዶ፣ እሳትና ድኝ አዘንባለሁ። 23  ደግሞም ራሴን ገናና አደርጋለሁ፤ እንዲሁም ራሴን እቀድሳለሁ፤ በብዙ ብሔራትም ፊት ማንነቴ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’
[]
[]
[]
[]
12,054
39  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የመሼቅና የቱባል ዋና አለቃ የሆንከው ጎግ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ተነስቻለሁ። 2  እመልስሃለሁ፤ ደግሞም እነዳሃለሁ፤ ራቅ ካለውም የሰሜን ምድር አምጥቼ ወደ እስራኤል ተራሮች እወስድሃለሁ። 3  በግራ እጅህ ያለውን ደጋንህንም ሆነ በቀኝ እጅህ የያዝካቸውን ፍላጻዎችህን አስጥልሃለሁ። 4  አንተና ወታደሮችህ ሁሉ እንዲሁም ከአንተ ጋር የሚሆኑት ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ። ለተለያዩ አዳኝ አሞሮች ሁሉና ለዱር አራዊት መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።”’ 5  “‘አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 6  “‘በማጎግና ያለስጋት በደሴቶች በሚኖሩት ላይም እሳት እሰዳለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 7  ቅዱስ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜ እንዲረክስ አልፈቅድም፤ ብሔራትም እኔ ይሖዋ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’ 8  “‘አዎ፣ በትንቢት የተነገረው ነገር ይመጣል፤ ደግሞም ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘ያ ያልኩት ቀን ይህ ነው። 9  በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ወጥተው፣ የጦር መሣሪያዎቹን ይኸውም ትናንሾቹንና ትላልቆቹን ጋሻዎች፣ ደጋኖቹን፣ ፍላጻዎቹን፣ የጦር ቆመጦቹንና ጦሮቹን እሳት ያነዱባቸዋል። ለሰባት ዓመታትም እሳት ለማንደድ ይጠቀሙባቸዋል። 10  የጦር መሣሪያዎቹን እሳት ለማንደድ ስለሚጠቀሙባቸው ከሜዳ እንጨት መልቀም ወይም ከጫካ ማገዶ መሰብሰብ አያስፈልጋቸውም።’ “‘የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ የመዘበሯቸውንም ይመዘብራሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 11  “‘በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር፣ ከባሕሩ በስተ ምሥራቅ በሚጓዙት ሰዎች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ በዚያ የሚያልፉትንም ሰዎች መንገድ ይዘጋል። ጎግንና ስፍር ቁጥር የሌለውን ሠራዊቱን ሁሉ በዚያ ይቀብራሉ፤ ሸለቆውንም የሃሞን ጎግ ሸለቆ ብለው ይጠሩታል። 12  የእስራኤል ቤት ሰዎች እነሱን ቀብረው ምድሪቱን ለማንጻት ሰባት ወር ይፈጅባቸዋል። 13  የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ እነሱን ይቀብራል፤ ይህም ራሴን በማስከብርበት ቀን ዝና ያስገኝላቸዋል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 14  “‘ምድሪቱ ትነጻ ዘንድ፣ ሰዎች በየጊዜው በምድሪቱ ላይ እንዲያልፉና በምድሪቱ ላይ የቀሩትን አስከሬኖች እንዲቀብሩ ይመደባሉ። ለሰባት ወራትም ፍለጋቸውን ይቀጥላሉ። 15  በምድሪቱ ላይ የሚያልፉት ሰዎች የሰው አፅም ሲያዩ በአጠገቡ ምልክት ያደርጋሉ። ከዚያም እንዲቀብሩ የተመደቡት አፅሙን በሃሞን ጎግ ሸለቆ ይቀብሩታል። 16  በዚያም ሃሞና ተብላ የምትጠራ ከተማ ትኖራለች። እነሱም ምድሪቱን ያነጻሉ።’ 17  “አንተም፣ የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለተለያዩ ወፎችና ለዱር አራዊት ሁሉ እንዲህ በል፦ “አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ኑ። ለእናንተ በማዘጋጀው መሥዋዕቴ ዙሪያ ተሰብሰቡ፤ ይህም በእስራኤል ተራሮች ላይ የሚዘጋጅ ታላቅ መሥዋዕት ነው። ሥጋ ትበላላችሁ፤ ደምም ትጠጣላችሁ። 18  የኃያላንን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም አለቆች ደም ትጠጣላችሁ፤ እነሱ አውራ በጎች፣ ጠቦቶች፣ አውራ ፍየሎችና ወይፈኖች ሲሆኑ ሁሉም የሰቡ የባሳን ከብቶች ናቸው። 19  እናንተም እኔ ከማዘጋጅላችሁ መሥዋዕት፣ እስክትጠግቡ ድረስ ስብ ትሰለቅጣላችሁ፤ እስክትሰክሩም ደም ትጠጣላችሁ።”’ 20  “‘በማዕዴም ፈረሶችንና ሠረገለኞችን እንዲሁም ኃያላን ሰዎችንና ሁሉንም ዓይነት ተዋጊዎች እስክትጠግቡ ትበላላችሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 21  “‘በብሔራት መካከል ክብሬን እገልጣለሁ፤ ብሔራት ሁሉ የወሰድኩትን የፍርድ እርምጃና በእነሱ መካከል የገለጥኩትን ኃይል ያያሉ። 22  ከዚያ ቀን አንስቶ የእስራኤል ቤት ሰዎች እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 23  ብሔራትም የእስራኤል ቤት ሰዎች በግዞት የተወሰዱት በገዛ ራሳቸው በደል ይኸውም ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እንደሆነ ያውቃሉ። ስለዚህ ፊቴን ከእነሱ ሰወርኩ፤ ለጠላቶቻቸውም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ። 24  እንደ ርኩሰታቸውና እንደ በደላቸው መጠን አደረግኩባቸው፤ ፊቴንም ከእነሱ ሰወርኩ።’ 25  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በምርኮ የተወሰዱትን የያዕቆብ ወገኖች እመልሳለሁ፤ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ሁሉ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ የስሜንም ቅድስና አስከብራለሁ። 26  ለእኔ ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ውርደት ከደረሰባቸው በኋላ የሚያስፈራቸው ሳይኖር በምድራቸው ላይ ያለስጋት ይኖራሉ። 27  ከሕዝቦች መካከል መልሼ ሳመጣቸውና ከጠላቶቻቸው አገሮች ስሰበስባቸው፣ በብዙ ብሔራት ፊት፣ በመካከላቸው ራሴን እቀድሳለሁ።’ 28  “‘በብሔራት መካከል በግዞት እንዲኖሩ ሳደርግና ከዚያም አንዳቸውንም ሳላስቀር ወደ ገዛ ምድራቸው መልሼ ሳመጣቸው፣ እኔ አምላካቸው ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 29  ከእንግዲህ ፊቴን ከእስራኤል ቤት ሰዎች አልሰውርም፤ በእነሱ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁና’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,055
4  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ አንድ ጡብ ወስደህ በፊትህ አስቀምጥ። በላዩም ላይ የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅረጽበት። 2  ከተማዋን ክበብ፤ ለከበባ የሚያገለግል ግንብ ሥራባት፤ የአፈር ቁልል ደልድልባት፤ የጦር ሰፈሮችን ሥራባት እንዲሁም በዙሪያዋ የመደርመሻ መሣሪያዎችን ደግንባት። 3  የብረት ምጣድ ወስደህ በአንተና በከተማዋ መካከል እንደ ብረት ቅጥር አቁመው። ፊትህንም በእሷ ላይ አዙር፤ ከተማዋም ትከበባለች፤ አንተም ትከባታለህ። ይህ ለእስራኤል ቤት ምልክት ይሆናል። 4  “ከዚያም በግራ ጎንህ ትተኛለህ፤ የእስራኤልንም ቤት በደል በላይህ ላይ ታኖራለህ። በጎንህ በተኛህበት ቀን ቁጥር በደላቸውን ትሸከማለህ። 5  እኔም በደል በፈጸሙባቸው ዓመታት መጠን 390 ቀናት በአንተ ላይ እመድባለሁ፤ አንተም የእስራኤልን ቤት በደል ትሸከማለህ። 6  እነዚህንም ቀናት ማጠናቀቅ ይኖርብሃል። “ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ በቀኝ ጎንህ ትተኛለህ፤ የይሁዳንም ቤት በደል ለ40 ቀናት ትሸከማለህ። ለአንድ ዓመት አንድ ቀን፣ ለአንድ ዓመት አንድ ቀን ሰጥቼሃለሁ። 7  ክንድህን ገልጠህ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም ከበባ ታዞራለህ፤ በእሷም ላይ ትንቢት ትናገራለህ። 8  “እነሆ፣ የከበባህን ጊዜ እስክታጠናቅቅ ድረስ ከአንዱ ጎንህ ወደ ሌላው መገላበጥ እንዳትችል በገመድ አስርሃለሁ። 9  “አንተም ስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ ምስር፣ ማሽላና አጃ ወስደህ በአንድ ዕቃ ውስጥ አስቀምጣቸው፤ ለራስህም ዳቦ ጋግር። በጎንህ በምትተኛባቸው 390 ቀናት ትበላዋለህ። 10  በየቀኑ 20 ሰቅል እየመዘንክ ትበላለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትበላዋለህ። 11  “ደግሞም የሂን አንድ ስድስተኛ ለክተህ ውኃ ትጠጣለህ። በየተወሰነ ጊዜ ትጠጣዋለህ። 12  “የገብስ ሙልሙል እንደምትበላ ትበላዋለህ፤ የደረቀን የሰው ዓይነ ምድር እንደ ማገዶ ተጠቅመህ በፊታቸው ትጋግረዋለህ።” 13  ከዚያም ይሖዋ “ልክ እንደዚሁ እስራኤላውያንም እነሱን በምበትንባቸው ብሔራት መካከል የረከሰ ምግብ ይበላሉ” አለ። 14  ከዚያም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ይህስ አይሁን! እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሞቶ የተገኘም ሆነ አውሬ የቦጫጨቀው እንስሳ ሥጋ በልቼ የረከስኩበት ጊዜ የለም፤ የረከሰም ሥጋ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም።” 15  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “መልካም፣ በሰው ዓይነ ምድር ፋንታ የከብት ኩበት እንድትጠቀም ፈቅጄልሃለሁ፤ የምትበላውንም ዳቦ በእሱ ትጋግራለህ።” 16  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የኢየሩሳሌም የምግብ አቅርቦት እንዲቋረጥ አደርጋለሁ፤ እነሱም እየተመጠነ የሚሰጣቸውን ዳቦ በሚዛን እየለኩ በከፍተኛ ጭንቀት ይበላሉ፤ እየተመጠነ የሚሰጣቸውንም ውኃ እየለኩ በስጋት ይጠጣሉ። 17  ይህም የሚሆነው ምግብና ውኃ አጥተው እርስ በርስ በድንጋጤ እንዲተያዩ እንዲሁም ከበደላቸው የተነሳ እንዲመነምኑ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,056
40  በግዞት በተወሰድን በ25ኛው ዓመት፣ በዓመቱ መጀመሪያ፣ በወሩ አሥረኛ ቀን፣ ከተማዋ በወደቀች በ14ኛው ዓመት፣ በዚያው ዕለት የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ እሱም ወደ ከተማዋ ወሰደኝ። 2  አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ በአንድ ትልቅ ተራራም ላይ አስቀመጠኝ፤ በዚያም በስተ ደቡብ በኩል ከተማ የሚመስል ሕንፃ ነበር። 3  ወደዚያ በወሰደኝ ጊዜ መዳብ የሚመስል መልክ ያለው አንድ ሰው አየሁ። በእጁም ከተልባ እግር የተሠራ ገመድና የመለኪያ ዘንግ ይዞ መግቢያው ላይ ቆሞ ነበር። 4  ሰውየው እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ በደንብ ተመልከት፤ በጥሞና አዳምጥ፤ የማሳይህንም ሁሉ በትኩረት ተመልከት፤ እዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና። የምታየውን ነገር ሁሉ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ተናገር።” 5  ከቤተ መቅደሱ ውጭ በዙሪያው ያለውን ቅጥር አየሁ። ሰውየው ስድስት ክንድ ርዝመት ያለው የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበር፤ እያንዳንዱ ክንድ አንድ ጋት ተጨምሮበት ነበር። እሱም ቅጥሩን መለካት ጀመረ፤ የቅጥሩ ውፍረት አንድ ዘንግ፣ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር። 6  ከዚያም በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው በር መጣ፤ በደረጃዎቹም ወጣ። የበሩን ደፍ ሲለካ ወርዱ አንድ ዘንግ ነበር፤ የሌላኛውም ደፍ ወርድ አንድ ዘንግ ነበር። 7  እያንዳንዱ የዘብ ጠባቂ ክፍል ርዝመቱ አንድ ዘንግ፣ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበር፤ በዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ መካከል ደግሞ አምስት ክንድ ስፋት ነበር። ከበሩ በረንዳ አጠገብ በውስጥ በኩል ያለው የበሩ ደፍ አንድ ዘንግ ነበር። 8  በውስጥ በኩል ያለውን የበሩን በረንዳ ለካ፤ አንድ ዘንግም ሆነ። 9  ከዚያም የበሩን በረንዳ ሲለካ ስምንት ክንድ ሆነ፤ በጎን በኩል ያሉትን ዓምዶችም ሲለካ ሁለት ክንድ ሆኑ፤ የበሩም በረንዳ በውስጥ በኩል ነበር። 10  በምሥራቁ በር ግራና ቀኝ ሦስት ሦስት የዘብ ጠባቂ ክፍሎች ነበሩ። ሦስቱም መጠናቸው እኩል ነበር፤ በሁለቱም በኩል ያሉት ዓምዶችም መጠናቸው እኩል ነበር። 11  ከዚያም የበሩን መግቢያ ወርድ ሲለካ 10 ክንድ ሆነ፤ የበሩ ስፋት ከውጭ በኩል 13 ክንድ ነበር። 12  ከዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ ፊት ለፊት ያለው የተከለለ ቦታ በሁለቱም በኩል አንድ አንድ ክንድ ነበር። የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ በሁለቱም በኩል ስድስት ስድስት ክንድ ነበሩ። 13  ከዚያም በሩን ከአንዱ የዘብ ጠባቂ ክፍል ጣሪያ እስከ ሌላኛው የዘብ ጠባቂ ክፍል ጣሪያ ድረስ ለካ፤ ወርዱም 25 ክንድ ነበር፤ አንደኛው መግቢያ ከሌላኛው መግቢያ ትይዩ ነበር። 14  ከዚያም በጎንና በጎን በኩል ያሉትን ዓምዶች ቁመት ሲለካ 60 ክንድ ሆነ፤ በግቢው ዙሪያ በሚገኙት በሮች ላይ ያሉትንም ዓምዶች ለካ። 15  ከመግቢያው በር ፊት አንስቶ በበሩ ውስጠኛ ክፍል በኩል እስካለው በረንዳ ፊት ድረስ 50 ክንድ ነበር። 16  ከበሩ በውስጥ በኩል በግራና በቀኝ፣ የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹና በጎን ያሉት ዓምዶቻቸው እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶች ነበሯቸው። በረንዳዎቹም በውስጥ በኩል፣ በግራም በቀኝም መስኮቶች ነበሯቸው፤ በጎን ያሉት ዓምዶች ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸውባቸው ነበር። 17  ከዚያም ወደ ውጨኛው ግቢ አመጣኝ፤ በግቢውም ዙሪያ የመመገቢያ ክፍሎችና መመላለሻ መንገድ አየሁ። በመንገዱ ላይ 30 የመመገቢያ ክፍሎች ነበሩ። 18  በበሮቹ ጎን ያለው መመላለሻ መንገድ ከበሮቹ ርዝመት ጋር እኩል ነበር፤ ይህም የታችኛው መመላለሻ መንገድ ነበር። 19  ከዚያም ከታችኛው በር አንስቶ ወደ ውስጠኛው ግቢ እስከሚያስገባው በር ድረስ ያለውን ርቀት ለካ። በምሥራቅም ሆነ በሰሜን በኩል ያለው ርቀት 100 ክንድ ነበር። 20  የውጨኛው ግቢ ከሰሜን ጋር ትይዩ የሆነ በር ነበረው፤ እሱም ርዝመቱንና ወርዱን ለካ። 21  በሁለቱም ጎን ሦስት ሦስት የዘብ ጠባቂ ክፍሎች ነበሩ። በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከመጀመሪያው በር ጋር እኩል ነበር። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 22  የመስኮቶቹ፣ የበረንዳውና የዘንባባ ዛፍ ምስሎቹ መጠን በምሥራቁ በር ካሉት ጋር እኩል ነበር። ሰዎች ሰባት ደረጃዎች ወጥተው ወደዚያ መግባት ይችላሉ፤ በረንዳውም ከፊት ለፊታቸው ነበር። 23  በውስጠኛው ግቢ፣ ከሰሜኑ በር ትይዩ አንድ በር፣ ከምሥራቁ በር ትይዩ ደግሞ ሌላ በር ነበር። እሱም ከአንደኛው በር እስከ ሌላኛው በር ሲለካ 100 ክንድ ሆነ። 24  ከዚያም ወደ ደቡብ አቅጣጫ አመጣኝ፤ በስተ ደቡብ በኩል አንድ በር አየሁ። እሱም በጎን ያሉትን ዓምዶቹንና በረንዳውን ለካ፤ መጠናቸውም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። 25  በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ እንደ ሌሎቹ ዓይነት መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 26  ወደዚያ የሚወስዱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ በረንዳውም ከፊት ለፊታቸው ነበር። በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች ላይ አንድ አንድ የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጾ ነበር። 27  የውስጠኛው ግቢ ከደቡብ ጋር ትይዩ የሆነ በር ነበረው፤ እሱም ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከአንደኛው በር እስከ ሌላኛው በር ለካ፤ ርቀቱም 100 ክንድ ሆነ። 28  ከዚያም በደቡብ በር በኩል ወደ ውስጠኛው ግቢ ወሰደኝ፤ የደቡቡን በር ሲለካ መጠኑ ከሌሎቹ ጋር እኩል ሆነ። 29  የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 30  ዙሪያውን በረንዳዎች ነበሩ፤ ርዝመታቸው 25 ክንድ፣ ወርዳቸው ደግሞ 5 ክንድ ነበር። 31  በረንዳው ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበር፤ በጎን ባሉት ዓምዶቹም ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ነበሩ፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ። 32  በምሥራቅ በኩል ወደ ውስጠኛው ግቢ ሲወስደኝ በሩን ለካ፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። 33  የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር፤ በበሩና በበረንዳው ግራና ቀኝ መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 34  በረንዳው ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበር፤ በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶች ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ። 35  ከዚያም ወደ ሰሜን በር ወሰደኝና ለካው፤ መጠኑ ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። 36  የዘብ ጠባቂ ክፍሎቹ፣ በጎን ያሉት ዓምዶቹና በረንዳው መጠናቸው ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር። በግራና በቀኝ መስኮቶች ነበሩት። ርዝመቱ 50 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 25 ክንድ ነበር። 37  በጎን ያሉት ዓምዶቹ ከውጨኛው ግቢ ጋር ትይዩ ነበሩ፤ በግራና በቀኝ ባሉት ዓምዶቹ ላይ የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር፤ ወደዚያም የሚወስዱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ። 38  በበሮቹ ጎንና ጎን ባሉት ዓምዶች አጠገብ የመመገቢያ ክፍል ነበር፤ መግቢያም ነበረው፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ የሚያጥቡት በዚያ ነበር። 39  በበሩም በረንዳ ላይ በግራና በቀኝ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣ የኃጢአት መባና የበደል መባ የሚታረድባቸው ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። 40  ወደ ሰሜን በር በሚወስደው መንገድ ላይ ከመግቢያው ውጭ ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። በተጨማሪም ከበሩ በረንዳ በሌላኛው በኩል ሁለት ጠረጴዛዎች ነበሩ። 41  በበሩ ግራና ቀኝ አራት አራት ጠረጴዛዎች፣ በድምሩ መሥዋዕት የታረደባቸው ስምንት ጠረጴዛዎች ነበሩ። 42  ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ የሚያገለግሉት አራቱ ጠረጴዛዎች ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ ነበሩ። ርዝመታቸው አንድ ክንድ ተኩል፣ ወርዳቸው አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመታቸው ደግሞ አንድ ክንድ ነበር። በእነሱም ላይ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕቱን ለማረድ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ተቀምጠው ነበር። 43  ከውስጠኛው ግንብ ጋር ተያይዘው ዙሪያውን የተሠሩ መደርደሪያዎች የነበሩ ሲሆን ወርዳቸው አንድ ጋት ነበር፤ በጠረጴዛዎቹም ላይ የስጦታ መባው ሥጋ ይቀመጥ ነበር። 44  ከውስጠኛው በር ውጭ የዘማሪዎቹ መመገቢያ ክፍሎች ነበሩ፤ ክፍሎቹ ከደቡብ ትይዩ ባለው የሰሜን በር አጠገብ በሚገኘው በውስጠኛው ግቢ ውስጥ ነበሩ። ከሰሜን ትይዩ ባለው የምሥራቅ በር አጠገብ ሌላ የመመገቢያ ክፍል ነበር። 45  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “በደቡብ ትይዩ ያለው ይህ የመመገቢያ ክፍል የቤተ መቅደሱን አገልግሎት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት ለተጣለባቸው ካህናት የተመደበ ነው። 46  በሰሜን ትይዩ ያለው የመመገቢያ ክፍል ከመሠዊያው ጋር የተያያዘ አገልግሎት እንዲያከናውኑ ኃላፊነት ለተጣለባቸው ካህናት የተመደበ ነው። እነዚህ የሳዶቅ ልጆች ሲሆኑ ከሌዋውያን መካከል ይሖዋን ለማገልገል ወደ እሱ እንዲቀርቡ የተመደቡ ናቸው።” 47  ከዚያም የውስጠኛውን ግቢ ለካ። ርዝመቱ 100 ክንድ፣ ወርዱም 100 ክንድ የሆነ አራት ማዕዘን ነበር። መሠዊያው ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ነበር። 48  ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ በረንዳ አመጣኝ፤ በጎን በኩል ያለውንም የበረንዳውን ዓምድ ለካ፤ ዓምዱም በአንደኛው ጎን አምስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን አምስት ክንድ ነበር። የበሩ ወርድ በአንደኛው ጎን ሦስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን ሦስት ክንድ ነበር። 49  የበረንዳው ርዝመት 20 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 11 ክንድ ነበር። ሰዎች ወደዚያ የሚወጡት በደረጃዎች ነበር። በጎንና በጎን ባሉት ምሰሶዎች አጠገብ በግራና በቀኝ አንድ አንድ ዓምድ ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,057
41  ከዚያም ወደ ውጨኛው መቅደስ አስገባኝ፤ በጎንና በጎን ያሉትንም ዓምዶች ለካ፤ የዓምዶቹ ወርድ በአንደኛው ጎን ስድስት ክንድ፣ በሌላኛውም ጎን ስድስት ክንድ ሆነ። 2  የመግቢያው ወርድ አሥር ክንድ ነበር፤ በመግቢያው ግራና ቀኝ ያሉት ግንቦች አምስት አምስት ክንድ ነበሩ። የውጨኛውን መቅደስ ርዝመት ሲለካ 40 ክንድ ሆነ፤ ወርዱ ደግሞ 20 ክንድ ሆነ። 3  ከዚያም ወደ ውስጥ ገብቶ በመግቢያው ጎን ላይ ያለውን ዓምድ ውፍረት ሲለካ ሁለት ክንድ ሆነ፤ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበር። በመግቢያው ግራና ቀኝ ያሉት ግንቦች ሰባት ክንድ ነበሩ። 4  ከዚያም ከውጨኛው መቅደስ ትይዩ ያለውን ክፍል ለካ፤ ርዝመቱም 20 ክንድ፣ ወርዱም 20 ክንድ ሆነ። እሱም “ይህ ቅድስተ ቅዱሳኑ ነው” አለኝ። 5  ከዚያም የቤተ መቅደሱን ግንብ ሲለካ ውፍረቱ ስድስት ክንድ ሆነ። በቤተ መቅደሱ ጎን ዙሪያውን ያሉት ክፍሎች ወርድ አራት ክንድ ነበር። 6  በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች ከበላያቸው ሁለት ፎቅ ነበራቸው፤ በእያንዳንዱ ፎቅ ላይ 30 ክፍሎች ነበሩ። በቤተ መቅደሱ ግንብ ዙሪያ፣ በጎን በኩል ያሉትን ክፍሎች ደግፈው የሚይዙ ተሸካሚዎች ነበሩ፤ በመሆኑም እነዚህ ተሸካሚዎች ወደ ቤተ መቅደሱ ግንብ ዘልቀው አልገቡም። 7  በቤተ መቅደሱ ግራና ቀኝ ጠመዝማዛ መተላለፊያ ነበር፤ ላይ ወደሚገኙት ክፍሎች ሲወጣ የመወጣጫዎቹ ወርድ ይጨምር ነበር። አንድ ሰው ከታች ተነስቶ በመካከለኛው ፎቅ በኩል ወደ መጨረሻው ፎቅ ሲወጣ ፎቁ እየሰፋ ይሄድ ነበር። 8  በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ከፍ ያለ መሠረት መኖሩን አየሁ፤ በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች መሠረትም እስከ ማዕዘኑ ድረስ ሙሉ ዘንግ ይኸውም ስድስት ክንድ ነበር። 9  በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች የውጨኛው ግንብ ወርድ አምስት ክንድ ነበር። በጎን ካሉት ክፍሎች አጠገብ የቤተ መቅደሱ ክፍል የሆነ ክፍት ቦታ ነበር። 10  በቤተ መቅደሱና በመመገቢያ ክፍሎቹ መካከል በሁለቱም በኩል ወርዱ 20 ክንድ የሆነ ቦታ ነበር። 11  በሰሜን አቅጣጫ፣ በጎን በኩል ባሉት ክፍሎችና ክፍት በሆነው ቦታ መካከል መግቢያ ነበር፤ በደቡብ አቅጣጫም ሌላ መግቢያ ነበር። ክፍት የሆነው ቦታ በሁሉም አቅጣጫ ወርዱ አምስት ክንድ ነበር። 12  በምዕራብ በኩል ክፍት ከሆነው ስፍራ ትይዩ ያለው ሕንፃ ወርዱ 70 ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ 90 ክንድ ነበር፤ የሕንፃው ግንብ ውፍረት ዙሪያውን አምስት ክንድ ነበር። 13  ቤተ መቅደሱን ሲለካ ርዝመቱ 100 ክንድ ሆነ። ክፍት የሆነው ስፍራ፣ ሕንፃውና ግንቦቹ ርዝመታቸው 100 ክንድ ነበር። 14  ከምሥራቅ ትይዩ የሆነው የቤተ መቅደሱ የፊተኛው ክፍልና ክፍት የሆነው ስፍራ ወርድ 100 ክንድ ነበር። 15  በሁለቱም ጎን ያሉትን መተላለፊያዎቹን ጨምሮ በጀርባ በኩል ክፍት ከሆነው ስፍራ ጋር ትይዩ የሆነውን ሕንፃ ርዝመት ሲለካ 100 ክንድ ሆነ። እንዲሁም ውጨኛውን መቅደስ፣ ውስጠኛውን መቅደስና የግቢውን በረንዳዎች ለካ፤ 16  ደግሞም በሦስቱም ቦታዎች ያሉትን ደፎች፣ እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶችና መተላለፊያዎች ለካ። ከደፉ አጠገብ ከወለሉ አንስቶ እስከ መስኮቶቹ ድረስ የእንጨት ማስጌጫዎች ነበሩ፤ መስኮቶቹም ተሸፍነው ነበር። 17  ከመግቢያው በላይ ያለው፣ የቤተ መቅደሱ ውስጥና ውጭ እንዲሁም በዙሪያው ያለው ግንብ ሁሉ ተለካ። 18  ግንቡ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ምስል ተቀርጸውበት ነበር፤ በሁለት ኪሩቤል መካከል የዘንባባ ዛፍ ምስል ነበር፤ እያንዳንዱ ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው። 19  ሰው የሚመስለው ፊት በአንድ በኩል ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ምስል የዞረ ሲሆን፣ አንበሳ የሚመስለው ፊት ደግሞ በሌላ በኩል ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ዞሮ ነበር። በዚህ መንገድ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ተቀርጸው ነበር። 20  በመቅደሱ ግድግዳ ላይ ከወለሉ አንስቶ ከመግቢያው በላይ እስካለው ስፍራ ድረስ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ተቀርጸው ነበር። 21  የመቅደሱ መቃኖች አራት ማዕዘን ናቸው። ከቅዱሱ ስፍራ ፊት ለፊት 22  ቁመቱ ሦስት ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ ሁለት ክንድ የሆነ ከእንጨት የተሠራ መሠዊያ የሚመስል ነገር ነበር። የማዕዘን ቋሚዎች ነበሩት፤ መሠረቱና ጎኖቹ ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ። እሱም “በይሖዋ ፊት ያለው ጠረጴዛ ይህ ነው” አለኝ። 23  የውጨኛው መቅደስና ቅዱሱ ስፍራ እያንዳንዳቸው ሁለት በሮች ነበሯቸው። 24  በሮቹ ታጣፊ የሆኑ ሁለት ሳንቃዎች ነበሯቸው፤ እያንዳንዱ በር ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት። 25  በግድግዳው ላይ ያሉት ዓይነት ኪሩቦችና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች በመቅደሱ በሮች ላይ ተቀርጸው ነበር። በተጨማሪም በውጭ በኩል ከፊት ለፊት በረንዳው ላይ ከእንጨት የተሠራ ወጣ ያለ ነገር ነበር። 26  እንዲሁም በበረንዳው ግራና ቀኝ፣ ከቤተ መቅደሱ ጎን ባሉት ክፍሎች ላይና በታዛው አካባቢ እየጠበቡ የሚሄዱ ክፈፎች ያሏቸው መስኮቶችና የዘንባባ ዛፍ ምስሎች ነበሩ።
[]
[]
[]
[]
12,058
42  ከዚያም በስተ ሰሜን ወዳለው ወደ ውጨኛው ግቢ ወሰደኝ። ደግሞም በአቅራቢያው ከሚገኘው ሕንፃ በስተ ሰሜን፣ ክፍት ከሆነው ስፍራ አጠገብ ወዳሉት የመመገቢያ ክፍሎች ያሏቸው ሕንፃዎች አመጣኝ። 2  ሕንፃዎቹ በሰሜኑ መግቢያ በኩል ርዝመታቸው 100 ክንድ ነበር፤ ወርዳቸው ደግሞ 50 ክንድ ነበር። 3  ሕንፃዎቹ የሚገኙት ወርዱ 20 ክንድ በሆነው በውስጠኛው ግቢና በውጨኛው ግቢ መመላለሻ መንገድ መካከል ነበር። ሕንፃዎቹ ባለ ሁለት ፎቅ ሲሆኑ ትይዩ ሆነው የተሠሩ ሰገነቶች ነበሯቸው። 4  በመመገቢያ ክፍሎቹ ፊት ወርዱ 10 ክንድ፣ ርዝመቱ ደግሞ 100 ክንድ የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር፤ የክፍሎቹም መግቢያዎች የሚገኙት በስተ ሰሜን በኩል ነበር። 5  ከላይ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ከታች ካሉትና መካከል ላይ ካሉት የሕንፃው ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያሉ ነበሩ፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ሰፋ ያለ ቦታ ይዘውባቸው ነበር። 6  የመመገቢያ ክፍሎቹ ባለ ሁለት ፎቅ ነበሩ፤ ይሁንና በግቢው ውስጥ እንዳሉት ዓይነት ዓምዶች አልነበሯቸውም። ከታች ካሉትና መካከል ላይ ካሉት ይበልጥ ከላይኛው ፎቅ ክፍሎች ሰፊ ቦታ የተወሰደው ለዚህ ነው። 7  ከሌሎቹ የመመገቢያ ክፍሎች ጋር ትይዩ ከሆኑትና በውጨኛው ግቢ በኩል ካሉት የመመገቢያ ክፍሎች አጠገብ የሚገኘው የውጨኛው የድንጋይ ቅጥር ርዝመት 50 ክንድ ነበር። 8  በውጨኛው ግቢ በኩል ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ርዝመት 50 ክንድ ሲሆን ከመቅደሱ ትይዩ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች ርዝመት ግን 100 ክንድ ነበር። 9  የመመገቢያ ክፍሎቹ በስተ ምሥራቅ በኩል፣ ከውጨኛው ግቢ ወደ ክፍሎቹ የሚወስድ መግቢያ ነበራቸው። 10  በደቡብም በኩል ክፍት በሆነው ስፍራና በሕንፃው አቅራቢያ፣ በስተ ምሥራቅ ባለው የግቢው የድንጋይ ቅጥር ውስጥ የመመገቢያ ክፍሎች ነበሩ። 11  በስተ ሰሜን እንዳሉት የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉ በእነዚህ የመመገቢያ ክፍሎች ፊትም መተላለፊያ ነበር። ክፍሎቹ ተመሳሳይ ርዝመትና ወርድ ነበራቸው፤ መውጫዎቻቸውም ሆኑ ንድፎቻቸው ተመሳሳይ ነበሩ። መግቢያዎቻቸው 12  በደቡብ በኩል ከሚገኙት የመመገቢያ ክፍሎች መግቢያዎች ጋር ተመሳሳይ ነበሩ። በስተ ምሥራቅ በኩል በአቅራቢያው ካለው የድንጋይ ቅጥር ፊት፣ በመተላለፊያው መንገድ መነሻ ላይ ሰው ሊገባበት የሚችል መግቢያ ነበር። 13  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ክፍት ከሆነው ስፍራ አጠገብ የሚገኙት በስተ ሰሜን ያሉት የመመገቢያ ክፍሎችና በስተ ደቡብ ያሉት የመመገቢያ ክፍሎች፣ ወደ ይሖዋ የሚቀርቡት ካህናት እጅግ ቅዱስ የሆኑትን መባዎች የሚበሉባቸው የተቀደሱ መመገቢያ ክፍሎች ናቸው። በዚያም እጅግ ቅዱስ የሆኑትን መባዎች፣ የእህል መባ፣ የኃጢአት መባና የበደል መባ ያስቀምጣሉ፤ ምክንያቱም ቦታው ቅዱስ ነው። 14  ካህናቱ በሚገቡበት ጊዜ፣ ሲያገለግሉ የሚለብሱትን ልብስ ሳያወልቁ ከቅዱሱ ስፍራ ወደ ውጨኛው አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ ልብሶቹ ቅዱስ ናቸውና። ለሕዝቡ ወደተፈቀዱት ቦታዎች ከመሄዳቸው በፊት ልብሳቸውን ይቀይሩ ነበር።” 15  የቤተ መቅደሱን የውስጠኛውን ስፍራ ለክቶ ሲጨርስ ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው በር በሚወስደው መተላለፊያ በኩል ይዞኝ ወጣ፤ ከዚያም ስፍራውን በጠቅላላ ለካ። 16  በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን በመለኪያ ዘንግ ለካ። በመለኪያ ዘንጉ ከአንዱ ጎን እስከ ሌላው ጎን ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ። 17  በስተ ሰሜን በኩል ያለውን ለካ፤ በመለኪያ ዘንጉም ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ። 18  በስተ ደቡብ በኩል ያለውን ለካ፤ በመለኪያ ዘንጉም ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ። 19  ከዚያም ወደ ምዕራብ ዞረ። በመለኪያ ዘንጉ ሲለካ ርዝመቱ 500 ዘንግ ሆነ። 20  ስፍራውን በአራቱም ጎን ለካ። ቅዱስ የሆነውንና ቅዱስ ያልሆነውን ስፍራ ለመለየት የሚያገለግል ርዝመቱ 500 ዘንግ፣ ወርዱም 500 ዘንግ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበር።
[]
[]
[]
[]
12,059
43  ከዚያም ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው በር ወሰደኝ። 2  በዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤ ድምፁም እንደሚጎርፍ ውኃ ድምፅ ነበር፤ ከክብሩም የተነሳ ምድር አበራች። 3  ያየሁት ነገር ከተማዋን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ ያየሁትን ራእይ ይመስል ነበር፤ ደግሞም በኬባር ወንዝ አቅራቢያ አይቼው ከነበረው ነገር ጋር ይመሳሰል ነበር፤ እኔም መሬት ላይ በግንባሬ ተደፋሁ። 4  ከዚያም የይሖዋ ክብር ከምሥራቅ ትይዩ በሆነው በር በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ። 5  መንፈስም አንስቶ ወደ ውስጠኛው ግቢ አመጣኝ፤ እኔም ቤተ መቅደሱ በይሖዋ ክብር ተሞልቶ አየሁ። 6  ከዚያም አንድ ሰው ከቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲያናግረኝ ሰማሁ፤ ሰውየውም መጥቶ አጠገቤ ቆመ። 7  አምላክም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህ የዙፋኔ መቀመጫ፣ የእግሬ ማሳረፊያና በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምኖርበት ስፍራ ነው። የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ እነሱም ሆኑ ንጉሦቻቸው በሚፈጽሙት መንፈሳዊ ምንዝርና በሞቱት ንጉሦቻቸው ሬሳ ከእንግዲህ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም። 8  በእኔና በእነሱ መካከል ግንቡ ብቻ ሲቀር፣ ደፋቸውን ከቤቴ ደፍ አጠገብ፣ መቃናቸውንም ከቤቴ መቃን አጠገብ በማድረግ በሠሯቸው አስጸያፊ ነገሮች ቅዱስ ስሜን አርክሰዋል፤ ስለዚህ በቁጣዬ አጠፋኋቸው። 9  ከእንግዲህ የሚፈጽሙትን መንፈሳዊ ምንዝር ያስወግዱ፤ የንጉሦቻቸውንም ሬሳ ከእኔ ያርቁ፤ እኔም በመካከላቸው ለዘላለም እኖራለሁ። 10  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ ከሠሩት በደል የተነሳ ኀፍረት እንዲሰማቸው ለእስራኤል ቤት ሰዎች ስለ ቤተ መቅደሱ ግለጽላቸው፤ ንድፉንም ያጥኑ። 11  በሠሩት ነገር ሁሉ ኀፍረት ከተሰማቸው የቤተ መቅደሱን ንድፍ፣ አቀማመጡን፣ መውጫዎቹንና መግቢያዎቹን አሳውቃቸው። አጠቃላይ ንድፉንና ደንቦቹን፣ ንድፉንና ሕጎቹን አሳያቸው፤ ደግሞም እነሱ እያዩ ጻፋቸው፤ ይህን የምታደርገው አጠቃላይ ንድፉንና ደንቦቹን አስተውለው በተግባር እንዲያውሉ ነው። 12  የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው። በተራራው አናት ዙሪያ ያለው ቦታ ሁሉ እጅግ ቅዱስ ነው። እነሆ፣ የቤተ መቅደሱ ሕግ ይህ ነው። 13  “የመሠዊያው ልክ በክንድ ሲለካ መጠኑ ይህ ነው፤ እያንዳንዱ ክንድ አንድ ጋት ተጨምሮበት ነበር። የመሠዊያው መሠረት አንድ ክንድ ነው፤ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። በጠርዙ ዙሪያ፣ ወርዱ አንድ ስንዝር የሆነ ክፈፍ አለው። ይህ የመሠዊያው መሠረት ነው። 14  መሬት ላይ ካረፈው መሠረት አንስቶ በዙሪያው እስካለው የታችኛው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ ሲሆን ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ነው። በዙሪያው ካለው ከትንሹ እርከን እስከ ትልቁ እርከን ድረስ አራት ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ አንድ ክንድ ነው። 15  የመሠዊያው ምድጃ ከፍታ አራት ክንድ ሲሆን ከምድጃው በላይ ወጣ ወጣ ያሉ አራት ቀንዶች አሉ። 16  የመሠዊያው ምድጃ አራት ማዕዘን ሲሆን ርዝመቱ 12 ክንድ፣ ወርዱም 12 ክንድ ነው። 17  በዙሪያው ያለው እርከን አራቱም ጎኖች ርዝመታቸው 14 ክንድ፣ ወርዳቸውም 14 ክንድ ነው፤ በዙሪያውም ያለው ክፈፍ ግማሽ ክንድ ሲሆን መሠረቱም በሁሉም ጎኖች አንድ ክንድ ነው። “ደረጃዎቹም ከምሥራቅ ትይዩ ነበሩ።” 18  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመሠዊያው ላይ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ እንዲቀርብና በላዩ ላይ ደም እንዲረጭበት፣ መሠዊያው ሲሠራ ሊከተሏቸው የሚገቡት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው።’ 19  “‘እኔን ለማገልገል በፊቴ ለሚቀርቡት የሳዶቅ ዘር ለሆኑት ሌዋውያን ካህናት፣ ከመንጋው መካከል ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ ወይፈን ትሰጣቸዋለህ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 20  ‘ከደሙ ጥቂት ወስደህ በመሠዊያው አራት ቀንዶች፣ በዙሪያው ባለው እርከን አራት ጎኖችና በዙሪያው ባለው ጠርዝ ላይ አድርግ፤ ይህን የምታደርገው መሠዊያውን ከኃጢአት ለማንጻትና ለመሠዊያው ማስተሰረያ ለማቅረብ ነው። 21  ከዚያም ከመቅደሱ ውጭ፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተመደበው ቦታ ታቃጥለው ዘንድ የኃጢአት መባ የሆነውን ወይፈን ውሰድ። 22  በሁለተኛው ቀን የኃጢአት መባ የሚሆን እንከን የሌለበት ተባዕት ፍየል ታቀርባለህ፤ እነሱም በወይፈኑ መሠዊያውን ከኃጢአት እንዳነጹት ሁሉ በዚህም መሠዊያውን ከኃጢአት ያነጹታል።’ 23  “‘መሠዊያውን ከኃጢአት ካነጻህ በኋላ ከከብቶቹ መካከል እንከን የሌለበት አንድ ወይፈንና ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበት አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ። 24  ለይሖዋ ታቀርባቸዋለህ፤ ካህናቱም ጨው ከነሰነሱባቸው በኋላ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገው ያቀርቧቸዋል። 25  በየዕለቱ፣ ለሰባት ቀናት አንድ አውራ ፍየል የኃጢአት መባ አድርገህ ታቀርባለህ፤ እንዲሁም ከከብቶቹ መካከል አንድ ወይፈንና ከመንጋው መካከል አንድ አውራ በግ ታቀርባለህ፤ የምታቀርባቸው እንስሳት እንከን የሌለባቸው ይሁኑ። 26  ለሰባት ቀናት ለመሠዊያው ማስተሰረያ ያቀርባሉ፤ መሠዊያውንም ያነጹታል እንዲሁም ለአገልግሎት ያዘጋጁታል። 27  እነዚህ ቀናት ከተፈጸሙ በኋላ ከስምንተኛው ቀን አንስቶ ካህናቱ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በመሠዊያው ላይ ያቀርባሉ፤ እኔም በእናንተ ደስ እሰኛለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”
[]
[]
[]
[]
12,060
44  ከምሥራቅ ትይዩ ወደሆነው ወደ ውጨኛው የመቅደሱ በር ወደሚወስደው መንገድ መልሶ አመጣኝ፤ በሩም ዝግ ነበር። 2  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ይህ በር እንደተዘጋ ይኖራል። መከፈት የለበትም፤ ደግሞም ማንም ሰው አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ በዚያ በኩል ገብቷልና፤ ስለዚህ እንደተዘጋ ይኖራል። 3  አለቃው ግን አለቃ ስለሆነ በይሖዋ ፊት ምግብ ለመብላት በዚያ ይቀመጣል። በበሩ መተላለፊያ በረንዳ በኩል ይገባል፤ በዚያም ይወጣል።” 4  ከዚያም በስተ ሰሜን በሚገኘው በር በኩል ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ወዳለው ቦታ አመጣኝ። እኔም ባየሁ ጊዜ የይሖዋ ክብር፣ የይሖዋን ቤተ መቅደስ ሞልቶት ተመለከትኩ። በዚህ ጊዜ በግንባሬ መሬት ላይ ተደፋሁ። 5  ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ስለ ይሖዋ ቤተ መቅደስ ደንቦችና ሕጎች የምነግርህን ሁሉ በትኩረት ተከታተል፤ በዓይኖችህም ተመልከት እንዲሁም በጥሞና አዳምጥ። የቤተ መቅደሱን መግቢያና የመቅደሱን መውጫዎች ሁሉ ልብ በል። 6  ዓመፀኛ ለሆኑት የእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ አስጸያፊ ልማድ መፈጸማችሁ ከእንግዲህ ይብቃ! 7  ልባቸውንና ሥጋቸውን ያልተገረዙትን የባዕድ አገር ሰዎች ወደ መቅደሴ ስታመጧቸው ቤተ መቅደሴን ያረክሳሉ። በምትፈጽሟቸው አስጸያፊ ልማዶች ሁሉ የተነሳ ቃል ኪዳኔ እየፈረሰ ሳለ እናንተ ግን ምግቤን ይኸውም ስቡንና ደሙን ታቀርባላችሁ። 8  ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቼ ጋር በተያያዘ ያለባችሁን ኃላፊነት አልተወጣችሁም። ይልቁንም በመቅደሴ ውስጥ ያሉትን ሥራዎች እንዲያከናውኑ ሌሎች ሰዎችን መደባችሁ።”’ 9  “‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልቡንና ሥጋውን ያልተገረዘ በእስራኤል የሚኖር ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው ወደ መቅደሴ አይግባ።”’ 10  “‘ይሁንና እስራኤላውያን አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ለመከተል ሲሉ ከእኔ በራቁ ጊዜ ከእኔ የራቁት ሌዋውያን በደላቸው የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይቀበላሉ። 11  ከዚያም በመቅደሴ የቤተ መቅደሱን በሮች የሚቆጣጠሩ እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉ አገልጋዮች ይሆናሉ። ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕት ለሕዝቡ ያርዳሉ፤ ደግሞም ሕዝቡን ለማገልገል በፊታቸው ይቆማሉ። 12  አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ፊት ስላገለገሏቸውና የእስራኤል ቤት ሰዎች ኃጢአት እንዲሠሩ የማሰናከያ ድንጋይ ስለሆኑባቸው በመሐላ እጄን በእነሱ ላይ አንስቻለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፤ ‘እነሱም የሠሩት በደል የሚያስከትልባቸውን መዘዝ ይሸከማሉ። 13  ካህናቴ ሆነው ለማገልገል ወደ እኔ አይቀርቡም፤ ደግሞም ቅዱስ ወይም እጅግ ቅዱስ ወደሆኑት ነገሮቼ አይቀርቡም፤ በሠሯቸውም አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ የሚደርስባቸውን ኀፍረት ይሸከማሉ። 14  ይሁንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ በኃላፊነት እንዲሠሩ ይኸውም በውስጡ የሚካሄደውን አገልግሎትና መሠራት ያለበትን ሥራ ሁሉ እንዲያከናውኑ አደርጋለሁ።’ 15  “‘እስራኤላውያን ከእኔ በራቁ ጊዜ የመቅደሴን አገልግሎት ያከናውኑ የነበሩት የሳዶቅ ልጆች የሆኑት ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ለእኔም ስቡንና ደሙን ለማቅረብ በፊቴ ይቆማሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 16  ‘ወደ መቅደሴ የሚገቡት እነሱ ናቸው፤ እኔን ለማገልገልም ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ፤ በእኔ ፊት ያለባቸውንም ኃላፊነት ይወጣሉ። 17  “‘ወደ ውስጠኛው ግቢ በሚያስገቡት በሮች በሚገቡበት ጊዜ በፍታ መልበስ ይኖርባቸዋል። በውስጠኛው ግቢ በሮች ወይም በውስጥ ባሉት ቦታዎች ሲያገለግሉ የሱፍ ልብስ መልበስ የለባቸውም። 18  በራሳቸው ላይ ከበፍታ የተሠራ ጥምጥም ያድርጉ፤ በወገባቸውም ላይ የበፍታ ቁምጣ ይታጠቁ። እንዲያልባቸው የሚያደርግ ማንኛውም ዓይነት ልብስ መልበስ የለባቸውም። 19  ወደ ውጨኛው ግቢ ይኸውም ሕዝቡ ወዳለበት ግቢ ከመውጣታቸው በፊት አገልግሎታቸውን ሲያከናውኑ ለብሰውት የነበረውን ልብስ አውልቀው ቅዱስ በሆኑት የመመገቢያ ክፍሎች ውስጥ ማስቀመጥ አለባቸው። ከዚያም ቅድስናን ወደ ሕዝቡ እንዳያስተላልፉ ሌላ ልብስ ይለብሳሉ። 20  ራሳቸውን አይላጩ፤ ወይም ፀጉራቸውን አያስረዝሙ። ይልቁንም ፀጉራቸውን ይከርክሙ። 21  ካህናቱ ወደ ውስጠኛው ግቢ በሚገቡበት ጊዜ የወይን ጠጅ አይጠጡ። 22  መበለት የሆነች ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት አያግቡ፤ ይሁንና የእስራኤል ዘር የሆነች ድንግል ወይም የካህን ሚስት የነበረች መበለት ማግባት ይችላሉ።’ 23  “‘ቅዱስ በሆነና ተራ በሆነ ነገር መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምሩ፤ ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውንም ልዩነት ያሳውቋቸው። 24  ፍርድ ነክ ጉዳዮችን ይዳኙ፤ በድንጋጌዎቼ መሠረት ይፍረዱ። ከሁሉም በዓሎቼ ጋር የተያያዙትን ሕጎቼንና ደንቦቼን ይጠብቁ፤ እንዲሁም ሰንበቶቼን ይቀድሱ። 25  ወደ ሞተ ሰው አይቅረቡ፤ አለዚያ ይረክሳሉ። ሆኖም ለአባታቸው፣ ለእናታቸው፣ ለወንድ ወይም ለሴት ልጃቸው፣ ለወንድማቸው ወይም ላላገባች እህታቸው ሲሉ ራሳቸውን ሊያረክሱ ይችላሉ። 26  ደግሞም አንድ ካህን ከነጻ በኋላ ለሰባት ቀን ሊያቆዩት ይገባል። 27  በተቀደሰው ስፍራ ለማገልገል፣ በውስጠኛው ግቢ ወደሚገኘው ቅዱስ ስፍራ በሚገባበት ቀን የኃጢአት መባውን ያቅርብ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 28  “‘የእነሱም ውርሻ ይህ ይሆናል፦ ውርሻቸው እኔ ነኝ። በእስራኤል ምንም ዓይነት ርስት አትስጧቸው፤ ርስታቸው እኔ ነኝና። 29  የእህሉን መባ፣ የኃጢአቱን መባና የበደሉን መባ ይበላሉ፤ በእስራኤል ምድር ቅዱስ ለሆነ ነገር የተለየ ሁሉ የእነሱ ይሆናል። 30  መጀመሪያ ላይ ከደረሱት ፍሬዎች ሁሉና መዋጮ አድርጋችሁ ከምትሰጡት ነገር ሁሉ ምርጥ የሆነው ለካህናቱ ይሆናል። የተፈጨውንም የእህል በኩር ለካህኑ ስጡ። እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ ቤተሰቦቻችሁ ይባረካሉ። 31  ካህናቱ ሞቶ የተገኘውንም ሆነ በአራዊት የተዘነጠለውን ማንኛውም ወፍ ወይም እንስሳ መብላት የለባቸውም።’
[]
[]
[]
[]
12,061
45  “‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በምትከፋፈሉበት ጊዜ ከምድሪቱ ላይ ቅዱስ የሆነ ድርሻ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ስጡ። ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሁን። ስፍራው በሙሉ ቅዱስ ድርሻ ይሆናል። 2  በዚህ ቦታ ውስጥ ለቅዱሱ ስፍራ የሚያገለግል 500 ክንድ በ500 ክንድ የሆነ አራት ማዕዘን ቦታ ይኖራል፤ በሁሉም በኩል 50 ክንድ የሆነ የግጦሽ መሬት ይኖረዋል። 3  ከተለካው መሬት ላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 የሆነ ስፍራ ለካ፤ እጅግ ቅዱስ የሆነውም መቅደስ በዚያ ውስጥ ይሆናል። 4  ይሖዋን ለማገልገል ለሚቀርቡትና በመቅደሱ ለሚያገለግሉት ካህናት ቅዱስ ድርሻ ይሆናል። ለቤቶቻቸው እንዲሁም ለመቅደሱ የሚሆን ቅዱስ ስፍራ ይሆናል። 5  “‘በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉት ሌዋውያን ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል፤ እነሱም 20 የመመገቢያ ክፍሎችን ርስት አድርገው ይወስዳሉ። 6  “‘እናንተም የከተማዋ ርስት እንዲሆን ርዝመቱ 25,000 ክንድ (መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ ትይዩ የሆነ) ወርዱ ደግሞ 5,000 ክንድ የሆነ ቦታ ትሰጣላችሁ። ይህም ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል። 7  “‘አለቃው መዋጮ ተደርጎ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ለከተማዋ ከተሰጠው ቦታ ግራና ቀኝ መሬት ይኖረዋል። መሬቱ መዋጮ ተደርጎ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከከተማዋ ይዞታ አጠገብ ይሆናል። ደግሞም በስተ ምዕራብና በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይሆናል። ከምዕራቡ ወሰን እስከ ምሥራቁ ወሰን ድረስ ያለው ርዝመት ለአንዱ ነገድ ከተሰጠው ድርሻ ጋር ተመሳሳይ ነው። 8  ይህ መሬት በእስራኤል ምድር የእሱ ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ አለቆቼ በሕዝቤ ላይ ግፍ አይፈጽሙም፤ ምድሪቱንም ለእስራኤል ቤት ሰዎች በየነገዳቸው ይሰጧቸዋል።’ 9  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ የእስራኤል አለቆች፣ በጣም አብዝታችሁታል!’ “‘ግፍና ጭቆና መፈጸማችሁን አቁሙ፤ ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ። የሕዝቤን ንብረት መቀማታችሁን ተዉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 10  ‘ትክክለኛ ሚዛን፣ ትክክለኛ የኢፍ መስፈሪያና ትክክለኛ የባዶስ መስፈሪያ ተጠቀሙ። 11  ለኢፍ መስፈሪያና ለባዶስ መስፈሪያ ቋሚ የሆነ መመዘኛ መኖር አለበት። የባዶስ መስፈሪያው አንድ አሥረኛ ሆሜር የሚይዝ ይሁን፤ የኢፍ መስፈሪያውም አንድ አሥረኛ ሆሜር የሚይዝ ይሁን። ሆሜር መደበኛ መመዘኛ ይሆናል። 12  አንድ ሰቅል 20 ጌራ ይሁን። ደግሞም 20 ሰቅል፣ 25 ሰቅልና 15 ሰቅል አንድ ላይ ሲደመር አንድ ማኔህ ይሁንላችሁ።’ 13  “‘የምትሰጡት መዋጮ ይህ ነው፦ ከእያንዳንዱ ሆሜር ስንዴ የኢፍ አንድ ስድስተኛ፣ ከእያንዳንዱ ሆሜር ገብስ ደግሞ የኢፍ አንድ ስድስተኛ መዋጮ ታደርጋላችሁ። 14  የሚሰጠው ዘይት የሚለካው በባዶስ መስፈሪያ ይሆናል። አንድ ባዶስ፣ የቆሮስ አንድ አሥረኛ ነው፤ አሥር ባዶስ ደግሞ አንድ ሆሜር ነው፤ አሥር ባዶስ ከአንድ ሆሜር ጋር እኩል ነውና። 15  ደግሞም ከእስራኤል መንጎች መካከል ከየሁለት መቶው አንድ በግ ስጡ። እነዚህ ስጦታዎች ለሕዝቡ ማስተሰረያ እንዲሆኑ ለእህል መባ፣ ሙሉ በሙሉ ለሚቃጠል መባና ለኅብረት መሥዋዕት ይውላሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 16  “‘የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ይህን መዋጮ ለእስራኤል አለቃ ይሰጣል። 17  አለቃውም በበዓላት፣ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ወቅት፣ በየሰንበቱና ለእስራኤል ቤት ሰዎች በተወሰኑት በዓላት ወቅት ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ፣ የእህሉን መባና የመጠጡን መባ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት። ለእስራኤል ቤት ሰዎች ማስተሰረያ እንዲሆን የኃጢአት መባ፣ የእህል መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርበው እሱ ነው።’ 18  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከከብቶቹ መካከል ምንም እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ወስደህ መቅደሱን ከኃጢአት አንጻው። 19  ካህኑ የኃጢአት መባ ሆኖ ከቀረበው ደም የተወሰነውን ወስዶ በቤተ መቅደሱ መቃን፣ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን አራት ማዕዘኖችና በውስጠኛው ግቢ በር መቃን ላይ ያድርግ። 20  አንድ ሰው በስህተትና ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ ከወሩ በሰባተኛው ቀን እንዲሁ አድርግ፤ እናንተም ለቤተ መቅደሱ ማስተሰረያ ታቀርባላችሁ። 21  “‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በ14ኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ። ለሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። 22  በዚያም ቀን አለቃው ለራሱና ለምድሩ ነዋሪ ሁሉ የኃጢአት መባ እንዲሆን አንድ ወይፈን ያቀርባል። 23  በዓሉ በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀናት፣ በእያንዳንዱ ቀን፣ እንከን የሌለባቸውን ሰባት ወይፈኖችና እንከን የሌለባቸውን ሰባት አውራ በጎች ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል፤ ደግሞም ለኃጢአት መባ በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቀርባል። 24  በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ወይፈን አንድ ኢፍ፣ ለእያንዳንዱም አውራ በግ አንድ ኢፍ የእህል መባ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ። 25  “‘በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ በበዓሉ ወቅት ለሰባት ቀናት ይህንኑ የኃጢአት መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣ የእህል መባና ዘይት ያቅርብ።’”
[]
[]
[]
[]
12,062
46  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከምሥራቅ ትይዩ የሆነው የውስጠኛው ግቢ በር በስድስቱ የሥራ ቀናት ዝግ እንደሆነ ይቆይ፤ ሆኖም በሰንበት ቀንና አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን ይከፈት። 2  አለቃው ከውጭ በኩል በበሩ በረንዳ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቆማል። ካህናቱ የእሱን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ እሱም በበሩ ደፍ ላይ ይሰግዳል፤ ከዚያም ይወጣል። በሩ ግን እስከ ምሽት ድረስ አይዘጋ። 3  የምድሪቱም ነዋሪዎች በየሰንበቱና አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን በበሩ መግቢያ ላይ በይሖዋ ፊት ይሰግዳሉ። 4  “‘አለቃው በሰንበት ቀን እንከን የሌለባቸው ስድስት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና እንከን የሌለበት አንድ አውራ በግ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል። 5  ለአውራ በጉ አንድ ኢፍ የእህል መባ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹም መስጠት የሚችለውን ያህል የእህል መባ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቀርባል። 6  አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን ከከብቶቹ መካከል እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን፣ ስድስት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና አንድ አውራ በግ ያቀርባል፤ ሁሉም እንከን የሌለባቸው ይሁኑ። 7  ለወይፈኑ አንድ ኢፍ፣ ለአውራ በጉም አንድ ኢፍ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ ደግሞ መስጠት የሚችለውን ያህል እንደ እህል መባ አድርጎ ያቅርብ። እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ። 8  “‘አለቃው ሲገባ፣ በበሩ በረንዳ በኩል ይግባ፤ ሲወጣም በዚያው በኩል ይውጣ። 9  የምድሪቱም ነዋሪዎች በበዓል ወቅቶች በይሖዋ ፊት በሚቀርቡበት ጊዜ፣ የአምልኮ ሥርዓት ለመፈጸም በሰሜን በር የሚገቡ፣ በደቡብ በር ይውጡ፤ በደቡብ በር የሚገቡ ደግሞ በሰሜን በር ይውጡ። ማንም ሰው በገባበት በር ተመልሶ አይውጣ፤ ይልቁንም በተቃራኒ አቅጣጫ ባለው በር ይውጣ። 10  በመካከላቸው ያለው አለቃ እነሱ በሚገቡበት ጊዜ ይግባ፤ እነሱ በሚወጡበት ጊዜም ይውጣ። 11  በበዓላትና በተወሰኑት የበዓል ወቅቶች፣ ለወይፈኑ አንድ ኢፍ፣ ለአውራ በጉ አንድ ኢፍ፣ ለተባዕት የበግ ጠቦቶቹ ደግሞ መስጠት የሚችለውን ያህል የእህል መባ ያቅርብ፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን ዘይት ያቅርብ። 12  “‘አለቃው ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባን ወይም የኅብረት መሥዋዕትን የፈቃደኝነት መባ አድርጎ ለይሖዋ የሚያቀርብ ከሆነ በምሥራቅ ትይዩ ያለው በር ይከፈትለታል፤ በሰንበት ቀን እንደሚያደርገው ሁሉ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባውንና የኅብረት መሥዋዕቱን ያቀርባል። ከወጣ በኋላ በሩ ይዘጋ። 13  “‘በየዕለቱ፣ እንከን የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባዕት የበግ ጠቦት ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርብ። ይህን በየማለዳው አድርግ። 14  ከዚህም ጋር በየማለዳው የኢፍ አንድ ስድስተኛ የእህል መባ እንዲሁም በላመው ዱቄት ላይ የሚፈስ የሂን አንድ ሦስተኛ ዘይት የዘወትር የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ አቅርብ። ይህ የዘላለም ደንብ ነው። 15  ተባዕቱን የበግ ጠቦት፣ የእህል መባውንና ዘይቱን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል የዘወትር መባ አድርገው በየማለዳው ያቅርቡ።’ 16  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አለቃው ለወንዶች ልጆቹ፣ ለእያንዳንዳቸው ውርስ አድርጎ ስጦታ ቢሰጣቸው፣ ስጦታው የልጆቹ ንብረት ይሆናል። ይህ በውርስ ያገኙት ንብረታቸው ነው። 17  ሆኖም ከአገልጋዮቹ ለአንዱ ከርስቱ ላይ ስጦታ ቢሰጥ፣ ነፃ እስከሚወጣበት ዓመት ድረስ ስጦታው የእሱ ይሆናል፤ ከዚያም ለአለቃው ይመለስለታል። ርስቱን ለዘለቄታው የራሳቸው አድርገው መያዝ የሚችሉት ወንዶች ልጆቹ ብቻ ናቸው። 18  አለቃው ሕዝቡን ከይዞታቸው በማፈናቀል የትኛውንም ርስት ሊወስድባቸው አይገባም። ከሕዝቤ መካከል አንዳቸውም ከይዞታቸው እንዳይፈናቀሉ ለወንዶች ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ይዞታ ላይ ነው።’” 19  ከዚያም ከሰሜን ትይዩ ወደሚገኙት ቅዱስ ወደሆኑት የካህናቱ መመገቢያ ክፍሎች ከሚወስደው በር አጠገብ ባለው መግቢያ በኩል አድርጎ አመጣኝ፤ በዚያም በምዕራብ በኩል ከበስተ ኋላ አንድ ቦታ አየሁ። 20  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ካህናቱ አንድም ነገር ወደ ውጨኛው ግቢ ይዘው በመውጣት ቅድስናን ወደ ሕዝቡ እንዳያስተላልፉ ሲባል የበደል መባውንና የኃጢአት መባውን የሚቀቅሉት እንዲሁም የእህል መባውን የሚጋግሩት በዚህ ቦታ ነው።” 21  ከዚያም ወደ ውጨኛው ግቢ ከወሰደኝ በኋላ በአራቱ የግቢው ማዕዘኖች በኩል አዞረኝ፤ በውጨኛው ግቢ በአራቱም ማዕዘኖች በኩል ግቢ አየሁ። 22  በአራቱም የግቢው ማዕዘኖች፣ ርዝመታቸው 40 ክንድ፣ ወርዳቸው 30 ክንድ የሆኑ ትናንሽ ግቢዎች ነበሩ። አራቱም መጠናቸው እኩል ነበር። 23  በአራቱም ዙሪያ እርከን የነበረ ሲሆን ከእርከኑ ሥር መባዎቹ የሚቀቀሉባቸው ቦታዎች ተሠርተው ነበር። 24  ከዚያም “እነዚህ፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ቦታዎች ናቸው” አለኝ።
[]
[]
[]
[]
12,063
47  ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ መልሶ አመጣኝ፤ በዚያም ከቤተ መቅደሱ ደፍ ሥር ወደ ምሥራቅ የሚፈስ ውኃ ተመለከትኩ፤ የቤተ መቅደሱ ፊት ከምሥራቅ ትይዩ ነበር። ውኃው ከቤተ መቅደሱ በስተ ቀኝ ከሥር ወጥቶ ከመሠዊያው በስተ ደቡብ ይወርድ ነበር። 2  ከዚያም ወደ ሰሜን በር በሚወስደው መንገድ በኩል አምጥቶ ወደ ውጭ ካወጣኝ በኋላ ከምሥራቅ ትይዩ ወዳለው የውጨኛው በር አዙሮ አመጣኝ፤ እኔም በስተ ቀኝ በኩል ቀስ እያለ የሚፈስ ውኃ አየሁ። 3  ሰውየው መለኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ በመሄድ 1,000 ክንድ ለካ፤ ከዚያም በውኃው መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃው እስከ ቁርጭምጭሚት ይደርስ ነበር። 4  ከዚያም 1,000 ክንድ ለካ፤ በውኃውም መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃውም እስከ ጉልበት ደረሰ። ደግሞም 1,000 ክንድ ለካ፤ በውኃውም መካከል እንዳልፍ አደረገኝ፤ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ። 5  እንደገናም 1,000 ክንድ በለካ ጊዜ ውኃው ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ እጅግ ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ በዋና ካልሆነ በስተቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ወንዝ ሆኖ ነበር። 6  እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ?” ሲል ጠየቀኝ። ከዚያም መልሶ ወደ ጅረቱ ዳርቻ ወሰደኝ። 7  በተመለስኩ ጊዜ በጅረቱ ዳርቻ፣ በግራና በቀኝ በጣም ብዙ ዛፎች አየሁ። 8  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “ይህ ውኃ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ምድር ይፈስሳል፤ አረባን አቋርጦም ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም ይገባል። ወደ ባሕሩ በሚገባበት ጊዜ በዚያ ያለው ውኃ ይፈወሳል። 9  ውኃዎቹ በሚፈስሱበት ቦታ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕያዋን ፍጥረታት በሕይወት መኖር ይችላሉ። ይህ ውኃ ወደዚያ ስለሚፈስ በዚያ እጅግ ብዙ ዓሣዎች ይኖራሉ። የባሕሩ ውኃ ይፈወሳል፤ ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል። 10  “ከኤንገዲ እስከ ኤንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች በዳርቻው ይቆማሉ፤ በዚያም መረባቸውን የሚያሰጡበት ቦታ ይኖራል። በታላቁ ባሕር እንዳሉት ዓሣዎች በዚያም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ብዙ ዓይነት ዓሣዎች ይኖራሉ። 11  “ረግረጋማ የሆኑና ውኃ ያቆሩ ቦታዎች ይኖሩታል፤ እነዚህ ቦታዎች አይፈወሱም። ጨዋማ እንደሆኑ ይቀራሉ። 12  “በወንዙ ዳርና ዳር ለመብል የሚሆኑ ብዙ ዓይነት ዛፎች ይበቅላሉ። ቅጠላቸው አይጠወልግም፤ ፍሬ ማፍራትም አያቆሙም። ከመቅደሱ የሚወጣውን ውኃ ስለሚጠጡ በየወሩ አዲስ ፍሬ ይሰጣሉ። ፍሬያቸው ለመብል፣ ቅጠላቸውም ለመድኃኒት ይሆናል።” 13  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ክልል ይህች ናት፤ ዮሴፍ ሁለት ድርሻ ይኖረዋል። 14  እናንተ ትወርሷታላችሁ፤ እኩል ድርሻም ታገኛላችሁ። ለአባቶቻችሁ ይህችን ምድር እንደምሰጣቸው ምዬላቸው ነበር፤ አሁንም ይህች ምድር ርስት ሆና ተሰጥታችኋለች። 15  “በስተ ሰሜን በኩል የምድሪቱ ወሰን ይህ ነው፦ ከታላቁ ባሕር ተነስቶ ወደ ሄትሎን በሚወስደው መንገድ በኩል እስከ ጼዳድ ይደርሳል፤ 16  ከዚያም እስከ ሃማት፣ እስከ ቤሮታ እንዲሁም በደማስቆ ክልልና በሃማት ክልል መካከል እስካለው እስከ ሲብራይም ብሎም በሃውራን ወሰን እስከሚገኘው እስከ ሃጸርሃቲኮን ይዘልቃል። 17  ስለዚህ ወሰኑ ከባሕሩ በመነሳት በስተ ሰሜን በደማስቆ ድንበርና በሃማት ድንበር በኩል እስከ ሃጻርኤናን ድረስ ይዘልቃል። በሰሜን በኩል ወሰኑ ይህ ነው። 18  “በምሥራቅ በኩል ወሰኑ ከሃውራን እስከ ደማስቆ እንዲሁም በዮርዳኖስ አጠገብ ከጊልያድ እስከ እስራኤል ምድር ይዘልቃል። ከወሰኑ አንስቶ እስከ ምሥራቁ ባሕር ድረስ ትለካላችሁ። በምሥራቅ በኩል ወሰኑ ይህ ነው። 19  “በደቡብ በኩል ያለው ወሰን ከትዕማር ተነስቶ እስከ መሪባትቃዴስ ውኃዎች፣ ከዚያም እስከ ደረቁ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ይደርሳል። በደቡብ በኩል ወሰኑ ይህ ነው። 20  “በምዕራብ በኩል ታላቁ ባሕር የሚገኝ ሲሆን ይህም ከወሰኑ አንስቶ ከሌቦሃማት ትይዩ እስካለው ቦታ ድረስ ይዘልቃል። በምዕራብ በኩል ወሰኑ ይህ ነው።” 21  “ይህችን ምድር ለእናንተ ይኸውም ለ12ቱ የእስራኤል ነገዶች ታከፋፍላላችሁ። 22  ምድሪቱን ለእናንተ እንዲሁም በመካከላችሁ በመኖር ልጆች ለወለዱት፣ አብረዋችሁ ለሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች ርስት አድርጋችሁ አከፋፍሉ፤ እነሱም የአገሪቱ ተወላጆች እንደሆኑት እስራኤላውያን ይሆናሉ። እንደ እስራኤል ነገዶች ከእናንተ ጋር ርስት ያገኛሉ። 23  ከባዕድ አገር ለመጣው ሰው በሚኖርበት ነገድ ክልል ውስጥ ርስት ልትሰጡት ይገባል” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።
[]
[]
[]
[]
12,064
48  “ከሰሜናዊ ጫፍ አንስቶ የነገዶቹ ስም ይህ ነው፦ የዳን ድርሻ የሄትሎንን መንገድ ተከትሎ እስከ ሌቦሃማት እንዲሁም በስተ ሰሜን በደማስቆ ድንበር በኩል፣ ከሃማት አጠገብ እስካለው እስከ ሃጻርኤናን ድረስ ይዘልቃል፤ ድርሻውም ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 2  የአሴር ድርሻ ከዳን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 3  የንፍታሌም ድርሻ ከአሴር ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 4  የምናሴ ድርሻ ከንፍታሌም ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 5  የኤፍሬም ድርሻ ከምናሴ ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 6  የሮቤል ድርሻ ከኤፍሬም ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 7  የይሁዳ ድርሻ ከሮቤል ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 8  በይሁዳ ድንበር፣ ከምሥራቁ ወሰን አንስቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ መዋጮ አድርጋችሁ ለመስጠት የምትለዩት መሬት ወርዱ 25,000 ክንድ ይሁን፤ ደግሞም ይህ መሬት ከምሥራቁ ወሰን አንስቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ርዝመቱ ከሌሎቹ ነገዶች ድርሻ ጋር እኩል ይሁን። መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል። 9  “መዋጮ አድርጋችሁ በመስጠት ለይሖዋ የምትለዩት መሬት ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሆናል። 10  ይህ ለካህናቱ የሚሰጥ የተቀደሰ መዋጮ ይሆናል። በሰሜን በኩል 25,000 ክንድ፣ በምዕራብ በኩል 10,000፣ በምሥራቅ በኩል 10,000፣ በደቡብ በኩል ደግሞ 25,000 ይሆናል። የይሖዋ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። 11  ይህ የሳዶቅ ልጆች ለሆኑት የተቀደሱ ካህናት ይሆናል፤ እነሱ በእኔ ፊት ያለባቸውን ኃላፊነት ተወጥተዋል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንና ሌዋውያን በባዘኑ ጊዜ ከእነሱ ጋር አልባዘኑም። 12  በሌዋውያን ድንበር በኩል፣ እጅግ ቅዱስ ተደርጎ ከተለየውና መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው መሬት ላይ ድርሻ ያገኛሉ። 13  ሌዋውያኑ ከካህናቱ መሬት አጠገብ ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል። (አጠቃላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ይሆናል።) 14  ምርጥ ከሆነው ከዚህ የመሬቱ ድርሻ ላይ የትኛውንም ቦታ መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ለሌሎች አሳልፈው መስጠት የለባቸውም፤ ለይሖዋ የተቀደሰ ነውና። 15  “ደግሞም 25,000 ክንድ ከሆነው ወሰን አጠገብ የሚገኘው፣ ወርዱ 5,000 ክንድ የሆነው የቀረው ቦታ ለከተማዋ የጋራ ጥቅም፣ ለመኖሪያ ቤትና ለግጦሽ መሬት ይውላል። ከተማዋ በመካከሉ ትሆናለች። 16  የከተማዋም መጠን ይህ ነው፦ የሰሜኑ ወሰን 4,500፣ የደቡቡ ወሰን 4,500፣ የምሥራቁ ወሰን 4,500 እንዲሁም የምዕራቡ ወሰን 4,500 ክንድ ነው። 17  የከተማዋ የግጦሽ መሬት በስተ ሰሜን 250፣ በስተ ደቡብ 250፣ በስተ ምሥራቅ 250 እና በስተ ምዕራብ 250 ክንድ ይሆናል። 18  “የቀረው ድርሻ ርዝመቱ በመዋጮ ከተሰጠው የተቀደሰ መሬት ጋር እኩል ይሆናል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ 10,000፣ በስተ ምዕራብም 10,000 ክንድ ይሆናል። ርዝመቱ በመዋጮ ከተሰጠው የተቀደሰ መሬት ጋር እኩል ይሆናል፤ በዚያም የሚመረተው ከተማዋን ለሚያገለግሉ ምግብ ይሆናል። 19  ከተማዋን የሚያገለግሉ ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ሰዎች መሬቱን ያርሳሉ። 20  “በመዋጮ የተሰጠው መሬት በአጠቃላይ አራቱም ማዕዘኑ እኩል ሲሆን እያንዳንዱ ማዕዘን 25,000 ክንድ ነው። ከከተማዋ ይዞታ ጋር፣ በመዋጮ የተሰጠ የተቀደሰ መሬት አድርጋችሁ ትለዩታላችሁ። 21  “በመዋጮ ከተሰጠው የተቀደሰ መሬትና ከከተማዋ ይዞታ ግራና ቀኝ ያለው የቀረው ቦታ የአለቃው ይሆናል። ይህ ቦታ በመዋጮ ከተሰጠው መሬት በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ከሚገኙት 25,000 ክንድ ከሆኑት ወሰኖች አጠገብ ይሆናል። በአቅራቢያው ካሉት የነገዶቹ ድርሻዎች ጋር ይዋሰናል፤ ይህም ለአለቃው ይሆናል። በመዋጮ የተሰጠው የተቀደሰ መሬትና የቤተ መቅደሱ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። 22  “የሌዋውያኑ ይዞታና የከተማዋ ይዞታ በአለቃው ክልል መካከል ይሆናል። የአለቃው ክልል በይሁዳ ድንበርና በቢንያም ድንበር መካከል ይሆናል። 23  “የቀሩትን ነገዶች በተመለከተ፣ የቢንያም ድርሻ ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 24  የስምዖን ድርሻ ከቢንያም ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 25  የይሳኮር ድርሻ ከስምዖን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 26  የዛብሎን ድርሻ ከይሳኮር ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 27  የጋድ ድርሻ ከዛብሎን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። 28  በጋድ ወሰን በኩል ያለው ደቡባዊ ድንበር ከትዕማር እስከ የመሪባትቃዴስ ውኃዎች፣ እስከ ደረቁ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል። 29  “ለእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ምድር ይህች ናት፤ ይህም ድርሻቸው ይሆናል” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 30  “የከተማዋ መውጫዎች እነዚህ ይሆናሉ፦ በሰሜን በኩል ያለው 4,500 ክንድ ነው። 31  “የከተማዋ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይሰየማሉ። በስተ ሰሜን ሦስት በሮች ያሉ ሲሆን አንዱ በር ለሮቤል፣ አንዱ በር ለይሁዳ፣ አንዱ በር ደግሞ ለሌዊ ይሆናል። 32  “ምሥራቃዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለዮሴፍ፣ አንዱ በር ለቢንያም፣ አንዱ በር ደግሞ ለዳን ይሆናል። 33  “ደቡባዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለስምዖን፣ አንዱ በር ለይሳኮር፣ አንዱ በር ደግሞ ለዛብሎን ይሆናል። 34  “ምዕራባዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለጋድ፣ አንዱ በር ለአሴር፣ አንዱ በር ደግሞ ለንፍታሌም ይሆናል። 35  “ዙሪያውን መጠኑ 18,000 ክንድ ይሆናል። ከዚያን ቀን ጀምሮ ከተማዋ ‘ይሖዋ በዚያ አለ’ ተብላ ትጠራለች።”
[]
[]
[]
[]
12,065
5  “አንተም የሰው ልጅ ሆይ፣ እንደ ፀጉር አስተካካይ ምላጭ የምትጠቀምበት ስለታም ሰይፍ ውሰድ። የራስህን ፀጉርና ጢምህን ተላጭ፤ ከዚያም ሚዛን ወስደህ ፀጉሩን መዝነውና ከፋፍለው። 2  የከበባው ጊዜ ሲፈጸም አንድ ሦስተኛውን በከተማዋ ውስጥ በእሳት ታቃጥለዋለህ። ከዚያም ሌላ አንድ ሦስተኛ ወስደህ በከተማዋ ዙሪያ በሰይፍ ትመታዋለህ፤ የመጨረሻውንም አንድ ሦስተኛ ለነፋስ ትበትነዋለህ፤ እኔም እነሱን ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ። 3  “ደግሞም ከፀጉሮቹ ላይ ጥቂት ወስደህ በልብስህ እጥፋት ቋጥራቸው። 4  የተወሰነውን ደግሞ ወስደህ እሳት ውስጥ ጨምረው፤ ሙሉ በሙሉም በእሳት አቃጥለው። ይህ እሳት ወጥቶ በእስራኤል ቤት ሁሉ ይሰራጫል። 5  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህች ኢየሩሳሌም ናት። አገሮችን በዙሪያዋ አድርጌ፣ በብሔራት መካከል አስቀምጫታለሁ። 6  እሷ ግን ከብሔራትና በዙሪያዋ ካሉ አገሮች ሁሉ የባሰ ክፋት በመሥራት በድንጋጌዎቼና ባወጣኋቸው ደንቦች ላይ ዓምፃለች። ሕዝቡ ድንጋጌዎቼን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጓልና፤ ደንቦቼንም አክብሮ አልተመላለሰም።’ 7  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዙሪያችሁ ካሉት ብሔራት ይበልጥ አስቸጋሪ በመሆናችሁ፣ ደንቦቼን አክብራችሁ ባለመመላለሳችሁ ወይም ድንጋጌዎቼን ባለመጠበቃችሁ፣ ይልቁንም በዙሪያችሁ ያሉትን ብሔራት ድንጋጌዎች በመከተላችሁ፣ 8  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንቺ ከተማ ሆይ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ፤ ደግሞም እኔ ራሴ በብሔራት ፊት በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ። 9  በአስጸያፊ ድርጊቶችሽ ሁሉ የተነሳ ከዚህ በፊት ፈጽሞ ያላደረግኩትን፣ ከዚህም በኋላ የማልደግመውን በአንቺ ላይ አደርጋለሁ። 10  “‘“ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ በመካከልሽ ፍርዴን አስፈጽማለሁ፤ ከአንቺ የቀሩትንም በሙሉ በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ።”’ 11  “‘ስለዚህ በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በአስጸያፊ ጣዖቶችሽ ሁሉና ጸያፍ በሆኑ ድርጊቶችሽ ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፣ እኔ ራሴ እተውሻለሁ፤ ዓይኔ አያዝንም ደግሞም አልራራም። 12  ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር ይሞታል ወይም በመካከልሽ በረሃብ ያልቃል። ሌላ አንድ ሦስተኛ ደግሞ በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል። የመጨረሻውን አንድ ሦስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው እበትነዋለሁ፤ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ። 13  ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፤ በእነሱም ላይ የነደደው ቁጣዬ ይበርዳል፤ እኔም እረካለሁ። በእነሱም ላይ ቁጣዬን ፈጽሜ ባወረድኩ ጊዜ፣ እኔ ብቻ መመለክ የምፈልገው፣ እኔ ይሖዋ ይህን እንደተናገርኩ ያውቃሉ። 14  “‘በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት መካከል እንዲሁም በአጠገብሽ በሚያልፉ ሁሉ ፊት ባድማና መሳለቂያ አደርግሻለሁ። 15  በቁጣ፣ በንዴትና በኃይለኛ ቅጣት የፍርድ እርምጃ ስወስድብሽ በዙሪያሽ ባሉ ብሔራት ዘንድ መሳለቂያና መዘባበቻ ደግሞም የማስጠንቀቂያ ምሳሌና ማስፈራሪያ ትሆኛለሽ። እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ። 16  “‘እነሱን ለማጥፋት ገዳይ የሆኑ የረሃብ ፍላጻዎችን እሰድባቸዋለሁ። የምሰዳቸው የረሃብ ፍላጻዎች ያጠፏችኋል። የምግብ አቅርቦታችሁ እንዲቋረጥ በማድረግ ረሃቡን አባብሳለሁ። 17  በእናንተ ላይ ረሃብንና አደገኛ የዱር አራዊትን እሰዳለሁ፤ እነሱም የወላድ መሃን ያደርጓችኋል። ቸነፈርና ደም መፋሰስ ያጥለቀልቋችኋል፤ ሰይፍም አመጣባችኋለሁ። እኔ ይሖዋ ይህን ተናግሬአለሁ።’”
[]
[]
[]
[]
12,066
6  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙረህ በእነሱ ላይ ትንቢት ተናገር። 3  እንዲህም በል፦ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ የሉዓላዊውን ጌታ የይሖዋን ቃል ስሙ፦ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለተራሮቹ፣ ለኮረብቶቹ፣ ለጅረቶቹና ለሸለቆዎቹ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ በእናንተ ላይ ሰይፍ አመጣለሁ፤ ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎቻችሁንም አጠፋለሁ። 4  መሠዊያዎቻችሁ ይፈርሳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ይሰባበራሉ፤ የታረዱ ወገኖቻችሁንም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ፊት እጥላለሁ። 5  የእስራኤልን ሕዝብ ሬሳ አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ፊት እጥላለሁ፤ አጥንቶቻችሁንም በመሠዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ። 6  በምትኖሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ያሉት ከተሞች ይወድማሉ፤ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎቹም ፈራርሰው ባድማ ይሆናሉ። መሠዊያዎቻችሁ ፈራርሰው እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ አስጸያፊ የሆኑት ጣዖቶቻችሁ ይወገዳሉ፤ የዕጣን ማጨሻዎቻችሁ ተገንድሰው ይወድቃሉ፤ የሠራችኋቸው ሥራዎችም ተጠራርገው ይጠፋሉ። 7  የታረዱትም ሰዎች በመካከላችሁ ይወድቃሉ፤ እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። 8  “‘“ይሁንና የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ በየአገሩ በምትበተኑበት ጊዜ፣ ከእናንተ ውስጥ አንዳንዶቻችሁ በብሔራት መካከል ስትኖሩ ከሰይፍ ታመልጣላችሁና። 9  የተረፉትም ሰዎች በምርኮ በተወሰዱባቸው ብሔራት መካከል ሆነው እኔን ያስታውሳሉ። ከእኔ በራቀው ከሃዲ ልባቸውና አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን በፍትወት ስሜት በተመለከቱት ዓይኖቻቸው የተነሳ ምን ያህል ልቤ እንዳዘነ ይገነዘባሉ። በሠሯቸው መጥፎና አስነዋሪ ነገሮች ሁሉ ያፍራሉ፤ እነዚህንም ነገሮች ይጸየፋሉ። 10  እኔ ይሖዋ እንደሆንኩና ይህን ጥፋት እንደማመጣባቸው የዛትኩት በከንቱ እንዳልሆነ ያውቃሉ።”’ 11  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የእስራኤል ቤት ሰዎች በሠሯቸው ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሳ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ስለሚወድቁ በእጅህ እያጨበጨብክ፣ በእግርህም መሬቱን እየደበደብክ አልቅስ። 12  በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፤ በቅርብ ያለው በሰይፍ ይወድቃል፤ ከእነዚህ ነገሮች ያመለጠና በሕይወት የተረፈ ሁሉ በረሃብ ያልቃል፤ ቁጣዬንም ሁሉ በእነሱ ላይ አወርዳለሁ። 13  የታረዱት ወገኖቻቸው አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው መካከል፣ በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፣ ከፍ ባለ ኮረብታ ሁሉና በተራሮች አናት ሁሉ ላይ፣ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች እንዲሁም በትላልቅ ዛፎች ቅርንጫፎች ሥር ይኸውም አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቻቸውን ሁሉ ቁጣ ለማብረድ፣ ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያላቸው መባዎች ባቀረቡባቸው ቦታዎች በሚወድቁበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። 14  በእነሱ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መኖሪያ ቦታዎቻቸውም ሁሉ በዲብላ አቅራቢያ ካለው ምድረ በዳ የባሰ ባድማ ይሆናሉ። እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
[]
[]
[]
[]
12,067
7  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ 2  “አንተ የሰው ልጅ ሆይ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ‘ፍጻሜ! በአራቱ የምድሪቱ ማዕዘናት ላይ ፍጻሜ መጥቷል። 3  አሁን ፍጻሜሽ ደርሷል፤ ቁጣዬንም በአንቺ ላይ አወርዳለሁ፤ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፤ ለፈጸምሻቸውም አስጸያፊ ድርጊቶች ሁሉ ተጠያቂ አደርግሻለሁ። 4  ዓይኔ አያዝንልሽም፤ ደግሞም አልራራልሽም፤ የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን ውጤት አመጣብሻለሁና፤ የፈጸምሻቸው አስጸያፊ ድርጊቶች የሚያስከትሉትን መዘዝ ትቀምሻለሽ። እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ 5  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ ጥፋት፣ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥፋት እየመጣ ነው! 6  ፍጻሜ እየመጣ ነው፤ ፍጻሜው ይመጣል፤ በአንቺ ላይ ይነሳል። እነሆ፣ ፍጻሜው እየመጣ ነው! 7  አንቺ በምድሪቱ የምትኖሪ፣ ተራሽ ደርሷል። ጊዜው እየደረሰ ነው፤ ቀኑ ቀርቧል። በተራሮች ላይ የእልልታ ሳይሆን የሁከት ድምፅ ይሰማል። 8  “‘በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ አወርዳለሁ፤ ንዴቴንም ሁሉ በአንቺ ላይ እወጣለሁ፤ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፤ ለፈጸምሻቸውም አስጸያፊ ድርጊቶች ሁሉ ተጠያቂ አደርግሻለሁ። 9  ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም። የተከተልሽው መንገድ የሚያስከትለውን ውጤት አመጣብሻለሁ፤ የፈጸምሻቸው አስጸያፊ ድርጊቶች የሚያስከትሉብሽን መዘዝ ትቀምሻለሽ። እናንተም የምመታችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። 10  “‘እነሆ ቀኑ! እነሆ ቀኑ እየመጣ ነው! ተራሽ ደርሷል፤ በትሩ አብቧል፤ እብሪትም አቆጥቁጧል። 11  ዓመፅ አድጎ የክፋት በትር ሆኗል። እነሱም ሆኑ ሀብታቸው ደግሞም ሕዝባቸውም ሆነ ታላቅነታቸው ይጠፋል። 12  ጊዜው ይደርሳል፤ ቀኑም ይመጣል። የሚገዛ አይደሰት፤ የሚሸጥም አይዘን፤ በሕዝባቸው ሁሉ ላይ ቁጣ ነዷልና። 13  ሻጩ በሕይወት ቢተርፍ እንኳ ወደተሸጠው ነገር አይመለስም፤ ራእዩ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ነውና። ማንም አይመለስም፤ ከፈጸመውም በደል የተነሳ ማንም ሕይወቱን ማትረፍ አይችልም። 14  “‘መለከት ነፍተዋል፤ ሁሉም ቢዘጋጁም ወደ ውጊያ የሚሄድ አንድም ሰው የለም፤ ምክንያቱም ቁጣዬ በሕዝቡ ሁሉ ላይ ነዷል። 15  በውጭ ሰይፍ፣ በውስጥ ደግሞ ቸነፈርና ረሃብ አለ። በሜዳ ያለ ሁሉ በሰይፍ ይሞታል፤ በከተማዋ ውስጥ ያሉትን ደግሞ ረሃብና ቸነፈር ይፈጃቸዋል። 16  አምልጠው መትረፍ የቻሉት ሁሉ ወደ ተራሮች ይሄዳሉ፤ እያንዳንዳቸውም በሸለቆ ውስጥ እንዳሉ ርግቦች በበደላቸው ይቃትታሉ። 17  እጃቸው ሁሉ ይዝላል፤ ጉልበታቸውም ሁሉ በውኃ ይርሳል። 18  ማቅ ለብሰዋል፤ ብርክም ይዟቸዋል። ሁሉም ኀፍረት ይከናነባሉ፤ ራስም ሁሉ ይመለጣል። 19  “‘ብራቸውን በየጎዳናው ይጥላሉ፤ ወርቃቸውም አስጸያፊ ነገር ይሆንባቸዋል። በይሖዋ የቁጣ ቀን ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም። በልተው አይጠግቡም፤ ሆዳቸውንም አይሞሉም፤ በኃጢአት እንዲወድቁ እንቅፋት ሆኖባቸዋልና። 20  በጌጦቻቸው ውበት ታበዩ፤ በእነዚህም ጸያፍ የሆኑ ምስሎቻቸውን ይኸውም አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን ሠሩ። በዚህም ምክንያት ብሩንና ወርቁን ርኩስ ነገር አደርግባቸዋለሁ። 21  ባዕዳን የሆኑ ሰዎች እንዲዘርፉት፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ክፉ ሰዎችም እንዲበዘብዙት አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እነሱም ያረክሱታል። 22  “‘ፊቴን ከእነሱ አዞራለሁ፤ እነሱም የተሰወረውን ቦታዬን ያረክሳሉ፤ ዘራፊዎችም ወደ እሷ ይገባሉ፤ ደግሞም ያረክሷታል። 23  “‘ምድሪቱ ነፍስ ግድያ በሚያስከትል የተዛባ ፍርድ ስለተሞላች፣ ከተማዋም በዓመፅ ስለተሞላች ሰንሰለት ሥራ። 24  ከብሔራት መካከል እጅግ የከፉትን አመጣለሁ፤ እነሱም ቤቶቻቸውን ይወርሳሉ፤ የብርቱዎቹንም ኩራት አጠፋለሁ፤ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ። 25  መከራ ሲመጣባቸው ሰላምን ይሻሉ፤ ሆኖም ሰላም አይኖርም። 26  በጥፋት ላይ ጥፋት ይመጣል፤ በወሬም ላይ ወሬ ይናፈሳል፤ ሰዎችም ከነቢይ ራእይ ይሻሉ፤ ሆኖም ሕግ ከካህን፣ ምክርም ከሽማግሌዎች ዘንድ ይጠፋል። 27  ንጉሡ ያለቅሳል፤ አለቃውም በተስፋ መቁረጥ ስሜት ይዋጣል፤ የምድሪቱም ሕዝብ ከመሸበሩ የተነሳ እጁ ይንቀጠቀጣል። እንደ መንገዳቸው አደርግባቸዋለሁ፤ ደግሞም እነሱ እንደፈረዱት እፈርድባቸዋለሁ። እኔም ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።’”
[]
[]
[]
[]
12,068
8  በስድስተኛውም ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ በዚያ የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ እጅ ያዘኝ። 2  እነሆም እሳት የሚመስል ነገር ተመለከትኩ፤ ወገቡ ከሚመስለው ነገር በታች እሳት ነበር፤ ደግሞም ከወገቡ በላይ መልኩ እንደሚያብረቀርቅ ብረት ደማቅ ነበር። 3  ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘርግቶ የራስ ፀጉሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል ይዞ ወሰደኝ፤ አምላክ በገለጠልኝ ራእዮች አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ይኸውም ቅናት የሚቀሰቅሰው የቅናት ጣዖት ምልክት ወደቆመበት በሰሜን ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው ግቢ በር አመጣኝ። 4  እነሆም፣ በሸለቋማው ሜዳ አይቼው የነበረውን የሚመስል የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበር። 5  ከዚያም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እባክህ ዓይንህን አንስተህ ወደ ሰሜን ተመልከት” አለኝ። ስለዚህ ወደ ሰሜን ተመለከትኩ፤ በዚያም ከመሠዊያው በር በስተ ሰሜን በኩል መግቢያው ላይ ይህ የቅናት ምልክት ነበር። 6  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ከመቅደሴ እንድርቅ የሚያደርጉ ነገሮች ይኸውም የሚፈጽሟቸውን አስከፊና አስጸያፊ ነገሮች ትመለከታለህ? ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮችን ገና ታያለህ።” 7  ከዚያም ወደ ቅጥር ግቢው መግቢያ አመጣኝ፤ እኔም ስመለከት በግድግዳው ላይ አንድ ቀዳዳ አየሁ። 8  እሱም “የሰው ልጅ ሆይ፣ እስቲ ግድግዳውን ንደለው” አለኝ። እኔም ግድግዳውን ነደልኩት፤ አንድ መግቢያም ተመለከትኩ። 9  እሱም “ወደ ውስጥ ግባና በዚህ ቦታ የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት” አለኝ። 10  እኔም ገብቼ አየሁ፤ መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታትንና የሚያስጠሉ አራዊትን ሁሉ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ የእስራኤል ቤት ጣዖቶችን ሁሉ ምስል ተመለከትኩ፤ ምስላቸውም በግድግዳው ዙሪያ ተቀርጾ ነበር። 11  ደግሞም 70 የሚሆኑ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በምስሎቹ ፊት ቆመው ነበር፤ የሳፋን ልጅ ያአዛንያህ በመካከላቸው ቆሞ ነበር። እያንዳንዳቸውም በእጃቸው ጥና የያዙ ሲሆን መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጭስም እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር። 12  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዳቸው ጣዖቶቻቸው ባሉባቸው እልፍኞች ውስጥ በጨለማ ምን እንደሚያደርጉ ታያለህ? እነሱ ‘ይሖዋ አያየንም። ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል’ ይላሉና።” 13  ደግሞም “እነሱ የሚሠሯቸውን ይበልጥ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ። 14  በመሆኑም በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ይሖዋ ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ በዚያም ሴቶች ተቀምጠው ታሙዝ ለተባለው አምላክ ሲያለቅሱ አየሁ። 15  እሱም በመቀጠል “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? ከእነዚህ የባሰ አስከፊ የሆኑ አስጸያፊ ነገሮች ታያለህ” አለኝ። 16  በመሆኑም ወደ ይሖዋ ቤት ውስጠኛው ግቢ አመጣኝ። በዚያም በይሖዋ ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ በበረንዳውና በመሠዊያው መካከል 25 ያህል ወንዶች ነበሩ፤ እነሱም ጀርባቸውን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ ሰጥተው ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ነበር፤ ደግሞም በምሥራቅ አቅጣጫ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር። 17  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ? የይሁዳ ቤት እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች መፈጸማቸው፣ ምድሪቱን በዓመፅ መሙላታቸውና እኔን ማስቆጣታቸው ቀላል ነገር ነው? እነሆ፣ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫዬ አቅርበዋል። 18  በመሆኑም በቁጣ እርምጃ እወስዳለሁ። ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም። በታላቅ ድምፅ ወደ ጆሮዬ ቢጮኹም አልሰማቸውም።”
[]
[]
[]
[]
12,069
9  ከዚያም በጆሮዬ እየሰማሁ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከተማዋን የሚቀጡት፣ እያንዳንዳቸው አጥፊ መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው እንዲመጡ ጥሯቸው!” አለ። 2  እኔም እያንዳንዳቸው በእጃቸው የማጥፊያ መሣሪያ የያዙ ስድስት ሰዎች በሰሜን ትይዩ ባለው በላይኛው በር በኩል ሲመጡ አየሁ፤ ከእነሱም ጋር በፍታ የለበሰ፣ በወገቡ ላይም የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘ አንድ ሰው ነበር፤ እነሱም መጥተው ከመዳብ በተሠራው መሠዊያ አጠገብ ቆሙ። 3  ከዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር፣ አርፎበት ከነበረው ከኪሩቦቹ በላይ ተነስቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ደጃፍ ሄደ፤ አምላክም በፍታ የለበሰውንና በወገቡ ላይ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራው። 4  ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “በከተማዋ መካከል ይኸውም በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፤ በከተማዋ ውስጥ እየተፈጸሙ ባሉት አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ እያዘኑና እየቃተቱ ባሉት ሰዎች ግንባር ላይም ምልክት አድርግ።” 5  ሌሎቹን ደግሞ እኔ እየሰማሁ እንዲህ አላቸው፦ “እሱን ተከትላችሁ በከተማዋ መካከል እለፉ፤ ሰዉንም ግደሉ። ዓይናችሁ አይዘን፤ ደግሞም አትራሩ። 6  ሽማግሌውን፣ ወጣቱን፣ ድንግሊቱን፣ ሕፃኑንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ። ምልክቱ ወዳለበት ወደ ማንኛውም ሰው ግን አትቅረቡ። ከመቅደሴም ጀምሩ።” ስለዚህ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት በነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ። 7  ከዚያም “ቤተ መቅደሱን አርክሱ፤ ግቢዎቹንም ሬሳ በሬሳ አድርጓቸው። ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የከተማዋን ሕዝብ ገደሉ። 8  እነሱ ሰዉን እየገደሉ ሳሉ ብቻዬን ቀረሁ፤ በግንባሬም ተደፍቼ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣህን በማፍሰስ የእስራኤልን ቀሪዎች ሁሉ ልታጠፋ ነው?” በማለት ጮኽኩ። 9  እሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት በደል እጅግ በጣም ታላቅ ነው። ምድሪቱ በደም ተጥለቅልቃለች፤ ከተማዋም በክፋት ተሞልታለች። ‘ይሖዋ ምድሪቱን ትቷታል፤ ይሖዋም አያይም’ ይላሉና። 10  እኔ ግን ዓይኔ አያዝንም፤ ደግሞም አልራራም። የተከተሉት መንገድ የሚያስከትለውን መዘዝ በራሳቸው ላይ አመጣባቸዋለሁ።” 11  ከዚያም በፍታ የለበሰውና በወገቡ ላይ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው ተመልሶ መጥቶ “ልክ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ” አለ።
[]
[]
[]
[]
12,070
1  በይሁዳ ነገሥታት በኢዮዓታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞረሸታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው እንዲሁም ሚክያስ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ ያየው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።” 2  “እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁም ስሙ! ምድርና በውስጧ ያሉ ሁሉ፣ በትኩረት ያዳምጡ፤ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ነው። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእናንተ ላይ ይመሥክርባችሁ። 3  እነሆ፣ ይሖዋ ከስፍራው ይወጣል፤ወደ ታች ወርዶ የምድርን ከፍ ያሉ ቦታዎች ይረግጣል። 4  በእሳት ፊት እንዳለ ሰምናበገደል ላይ እንደሚወርድ ውኃተራሮቹ ከሥሩ ይቀልጣሉ፤ሸለቆዎቹም ይሰነጠቃሉ። 5  ይህ ሁሉ የሆነው በያዕቆብ ዓመፅ፣በእስራኤልም ቤት ኃጢአት የተነሳ ነው። ለያዕቆብ ዓመፅ ተጠያቂው ማን ነው? ሰማርያ አይደለችም? በይሁዳ ለሚገኙት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችስ ተጠያቂው ማን ነው? ኢየሩሳሌም አይደለችም? 6  ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የፍርስራሽ ክምር፣ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፤መሠረቶቿንም አራቁታለሁ። 7  የተቀረጹ ምስሎቿ በሙሉ ይደቅቃሉ፤ለዝሙት አዳሪነቷ የተሰጧት ስጦታዎች ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ። ጣዖቶቿን ሁሉ እደመስሳለሁ። እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሰበሰበችው ለዝሙት አዳሪነቷ በተከፈላት ደሞዝ ነው፤አሁን ደግሞ እነዚህ ነገሮች በሌላ ቦታ ላሉ ዝሙት አዳሪዎች ክፍያ እንዲሆኑ ይወሰዳሉ።” 8  ከዚህ የተነሳ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ ደግሞም አላዝናለሁ፤ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ። እንደ ቀበሮዎች አላዝናለሁ፤እንደ ሰጎኖችም አለቅሳለሁ። 9  ቁስሏ ሊፈወስ አይችልም፤እስከ ይሁዳ ድረስ ተሰራጭቷል። መቅሰፍቱ እስከ ሕዝቤ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ተዛምቷል። 10  “በጌት አታውሩት፤ከቶም አታልቅሱ። በቤትአፍራ በአፈር ላይ ተንከባለሉ። 11  የሻፊር ነዋሪዎች ሆይ፣ እርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ተሻገሩ። የጻናን ነዋሪዎች አልወጡም። በቤትዔጼል ዋይታ ይኖራል፤ ለእናንተ ድጋፍ መስጠቱንም ያቆማል። 12  የማሮት ነዋሪዎች መልካም ነገርን ተጠባበቁ፤ይሁንና ከይሖዋ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም በር የወረደው ክፉ ነገር ነው። 13  የለኪሶ ነዋሪዎች ሆይ፣ ፈረሶቹን ከሠረገላው ጋር እሰሩ። ለጽዮን ሴት ልጅ የኃጢአት መጀመሪያ ነበራችሁ፤በእናንተ ውስጥ የእስራኤል ዓመፅ ተገኝቷልና። 14  ስለዚህ ለሞረሸትጋት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጫለሽ። የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት ማታለያ ነበሩ። 15  የማሬሻህ ነዋሪዎች ሆይ፣ ድል አድራጊውን ገና አመጣባችኋለሁ። የእስራኤል ክብር እስከ አዱላም ድረስ ይመጣል። 16  ለምትወዷቸው ልጆቻችሁ ፀጉራችሁን ተቆረጡ፤ ራሳችሁንም ተላጩ። እንደ ንስር ተመለጡ፤ልጆቻችሁ በግዞት ተወስደውባችኋልና።”
[]
[]
[]
[]
12,071
2  “መጥፎ ነገር ለሚሸርቡናበአልጋቸው ላይ ሆነው ክፉ ነገር ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ጠዋት ሲነጋ ያሰቡትን ይፈጽማሉ፤ምክንያቱም ይህን የሚያደርጉበት ኃይል በእጃቸው ነው። 2  እርሻን ይመኛሉ፤ ነጥቀውም ይይዙታል፤ቤቶችንም ይመኛሉ፤ ደግሞም ይወስዳሉ፤የሰውን ቤት፣የሰውንም ርስት አታለው ይወስዳሉ። 3  ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል።” ‘እነሆ፣ በዚህ ወገን ላይ ጥፋት ላመጣ አስቤአለሁ፤ እናንተም ከዚህ ጥፋት አታመልጡም። ከእንግዲህ ወዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤ ይህ የጥፋት ጊዜ ነውና። 4  በዚያም ቀን ሰዎች እናንተን አስመልክተው ምሳሌ ይናገራሉ፤በእናንተም የተነሳ አምርረው ያለቅሳሉ። እንዲህ ይላሉ፦ “እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል! የሕዝቤን ድርሻ ለሌሎች ሰጥቷል፤ ከእኔም ወስዶታል! እርሻዎቻችንን ለከዳተኛው ይሰጣል።” 5  ስለዚህ በይሖዋ ጉባኤ ውስጥ፣ምድሪቷን ለማከፋፈል በገመድ የሚለካ ሰው አይኖርህም። 6  “አትስበኩ!” ብለው ይሰብካሉ፤“እነዚህን ነገሮች መስበክ አይገባቸውም፤ውርደት አይደርስብንም!” 7  የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ “የይሖዋ መንፈስ አይታገሥም? እነዚህንስ ነገሮች ያደረገው እሱ ነው?” ሲባል ሰምተሃል? ቀና በሆነ መንገድ ለሚሄዱ የገዛ ቃሌ መልካም ነገር አያስገኝም? 8  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የገዛ ሕዝቤ ጠላት ሆኖ ተነስቷል። ከጦርነት እንደሚመለሱ ሰዎች በልበ ሙሉነት ከሚያልፉት ላይየሚያምረውን ጌጥ ከልብሱ ጋር በይፋ ገፈፋችሁ። 9  የሕዝቤን ሴቶች ከሚያምረው ቤታቸው አፈናቀላችኋቸው፤ክብሬን ከልጆቻቸው ለዘላለም ወሰዳችሁ። 10  ተነሱና ከዚህ ሂዱ፤ ይህ የማረፊያ ቦታ አይደለምና። ከርኩሰት የተነሳ ጥፋት ይመጣል፤ ጥፋቱም ከባድ ነው። 11  አንድ ሰው ነፋስንና ማታለያን ተከትሎ ቢሄድና “ስለ ወይን ጠጅና ስለ መጠጥ እሰብክላችኋለሁ” ብሎ ውሸት ቢናገር ይህ ሰው ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ሰባኪ ይሆናል! 12  ያዕቆብ ሆይ፣ ሁላችሁንም በእርግጥ እሰበስባለሁ፤ከእስራኤል የቀሩትን ያላንዳች ጥርጥር አንድ ላይ እሰበስባለሁ። በጉረኖ ውስጥ እንዳለ በግ፣በግጦሽ መስክ ላይ እንዳለም መንጋ በአንድነት አኖራቸዋለሁ፤ቦታውም በሕዝብ ሁካታ ይሞላል።’ 13  የሚሰብረውም ከፊታቸው ይሄዳል፤እነሱም ሰብረው በበሩ በኩል ያልፋሉ፤ በዚያም ወጥተው ይሄዳሉ። ንጉሣቸው በፊታቸው ያልፋል፤ይሖዋም ከፊታቸው ይሄዳል።”
[]
[]
[]
[]
12,072
3  እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎችናየእስራኤል ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ስሙ። ትክክል የሆነውን ነገር ማወቅ አይገባችሁም? 2  ሆኖም እናንተ መልካም የሆነውን ትጠላላችሁ፤ ክፉ የሆነውን ደግሞ ትወዳላችሁ፤የሕዝቤን ቆዳ ትገፍፋላችሁ፤ ሥጋቸውንም ከአጥንቶቻቸው ትለያላችሁ። 3  የሕዝቤንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ቆዳቸውንም ትገፍፋላችሁ፤አጥንቶቻቸውንም ትሰባብራላችሁ፤በድስት ውስጥ እንዳለ አጥንትና በአፍላል ውስጥ እንዳለ ሥጋ ትቆራርጧቸዋላችሁ። 4  በዚያን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤እሱ ግን አይመልስላቸውም። ክፉ ድርጊት በመፈጸማቸው፣በዚያን ጊዜ ፊቱን ይሰውርባቸዋል። 5  ሕዝቤ እንዲባዝን በሚያደርጉ፣በጥርሳቸው ሲነክሱ ‘ሰላም!’ እያሉ በሚያውጁ፣አፋቸው ላይ የሚያደርጉት ነገር በማይሰጣቸው ሰው ሁሉ ላይ ግን ጦርነት በሚያውጁ ነቢያት ላይ ይሖዋ እንዲህ ይላል።” 6  ‘ሌሊት ይመጣባችኋል፤ ራእይም አታዩም፤ጨለማ ብቻ ይሆንባችኋል፤ ሟርትም አታሟርቱም። ፀሐይ በነቢያቱ ላይ ትጠልቅባቸዋለች፤ቀኑም ወደ ጨለማ ይለወጥባቸዋል። 7  ባለ ራእዮች ኀፍረት ይከናነባሉ፤ሟርተኞችም ይዋረዳሉ። ከአምላክ ዘንድ መልስ ስለማይኖርሁሉም አፋቸውን ይሸፍናሉ።’” 8  እኔ በበኩሌ ለያዕቆብ ዓመፁን፣ ለእስራኤልም ኃጢአቱን እንድነግርበይሖዋ መንፈስ ኃይልን፣ፍትሕንና ብርታትን ተሞልቻለሁ። 9  ፍትሕን የምትጸየፉና ቀና የሆነውን ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፣እናንተ የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣የእስራኤልም ቤት ገዢዎች፣ እባካችሁ ይህን ስሙ፤ 10  ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምንም በዓመፅ የምትገነቡ፣ ስሙ። 11  መሪዎቿ በጉቦ ይፈርዳሉ፤ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፤ነቢያቷም በገንዘብ ያሟርታሉ። ያም ሆኖ “ይሖዋ ከእኛ ጋር አይደለም? ምንም ዓይነት ጥፋት አይደርስብንም” እያሉ በይሖዋ ይመካሉ። 12  ስለዚህ በእናንተ የተነሳጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፤ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤የቤቱም ተራራ፣ በጫካ እንዳሉ ከፍ ያሉ ቦታዎች ይሆናል።
[]
[]
[]
[]
12,073
4  በዘመኑ መጨረሻየይሖዋ ቤት ተራራከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ወደዚያ ይጎርፋሉ። 2  ብዙ ብሔራትም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦ “ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራናወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ። እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፣የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና። 3  እሱ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤በሩቅ ካሉ ኃያላን ብሔራት ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል። እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ። አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም። 4  እያንዳንዱም ከወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ይቀመጣል፤የሚያስፈራቸውም አይኖርም፤የሠራዊት ጌታ የይሖዋ አፍ ተናግሯልና። 5  ሕዝቦች ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው በአምላካቸው ስም ይሄዳሉ፤እኛ ግን በአምላካችን በይሖዋ ስም ለዘላለም እንሄዳለን። 6  “በዚያ ቀን” ይላል ይሖዋ፣“የሚያነክሰውን እሰበስባለሁ፤ደግሞም የተበተኑትንናያንገላታኋቸውን ሰዎች አንድ ላይ እሰበስባለሁ። 7  የሚያነክሰው የተወሰኑ ቀሪዎች እንዲኖሩት አደርጋለሁ፤ወደ ሩቅ ስፍራ የተወሰደውንም ኃያል ብሔር አደርገዋለሁ፤ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበጽዮን ተራራ በእነሱ ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል። 8  አንተም የመንጋው ማማ፣የጽዮን ሴት ልጅ ጉብታ ሆይ፣አንተ ወዳለህበት ይመለሳል፤ አዎ፣ የመጀመሪያው ግዛትህ፣የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለሳል። 9  አሁንስ ድምፅሽን ከፍ አድርገሽ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ንጉሥ የለሽም?ወይስ አማካሪሽ ጠፍቷል?ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት የምትሠቃዪው ለዚህ ነው? 10  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልትወልድ እንደተቃረበች ሴትተንፈራገጪ፤ አቃስቺም፤አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትሰፍሪያለሽና። እስከ ባቢሎን ድረስ ትሄጃለሽ፤በዚያም ይታደግሻል፤በዚያ ይሖዋ ከጠላቶችሽ እጅ ይዋጅሻል። 11  አሁንም ብዙ ብሔራት በአንቺ ላይ ይሰበሰባሉ፤እነሱም ‘የረከሰች ትሁን፤ዓይኖቻችንም ይህ በጽዮን ላይ ሲደርስ ይመልከቱ’ ይላሉ። 12  ይሁንና የይሖዋን ሐሳብ አያውቁም፤ዓላማውንም አይረዱም፤እሱ ገና እንደታጨደ እህል ወደ አውድማ ይሰበስባቸዋልና። 13  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ተነስተሽ እህሉን ውቂ፤ቀንድሽን ወደ ብረት፣ሰኮናሽንም ወደ መዳብ እለውጣለሁና፤አንቺም ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ። በማጭበርበር ያገኙት ትርፍ ለይሖዋ የተወሰነ እንዲሆን፣ሀብታቸውም ለምድር ሁሉ ጌታ ብቻ እንዲውል ታደርጊያለሽ።”
[]
[]
[]
[]
12,074
5  “አንቺ ጥቃት የተሰነዘረብሽ ሴት ልጅ ሆይ፣አሁን ሰውነትሽን ትተለትያለሽ፤ዙሪያችንን ተከበናል። የእስራኤልን ፈራጅ ጉንጩን በዱላ ይመቱታል። 2  ከይሁዳ አእላፋት መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽውቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል። 3  ስለዚህ ልትወልድ የተቃረበችው ሴት እስክትወልድ ድረስአሳልፎ ይሰጣቸዋል። የቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ። 4  እሱ በይሖዋ ብርታትና በአምላኩ በይሖዋ ስም ታላቅነት ይነሳል፤መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል። እነሱም በዚያ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤በዚያን ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳልና። 5  እሱም ሰላም ያመጣል። አሦራዊው ምድራችንን ከወረረና የማይደፈሩ ማማዎቻችንን ከረገጠበእሱ ላይ ሰባት እረኞችን፣ አዎ ከሰው ልጆች መካከል ስምንት አለቆችን እናስነሳበታለን። 6  እነሱ የአሦርን ምድር በሰይፍ ይቀጣሉ፤የናምሩድንም ምድር መግቢያዎች ይቆጣጠራሉ። አሦራዊው ምድራችንን ሲወርና ክልላችንን ሲረግጥእሱ ይታደገናል። 7  የተረፉት የያዕቆብ ወገኖች በብዙ ሕዝቦች መካከል፣ከይሖዋ ዘንድ እንደሚወርድናሰውን ተስፋ እንደማያደርግወይም የሰው ልጆችን እንደማይጠባበቅ ጠል፣በአትክልትም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ። 8  በዱር እንስሳት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በሚያልፍበት ጊዜ እየረጋገጠና እየሰባበረ እንደሚሄድ፣በበግ መንጎች መካከል እንዳለ ደቦል አንበሳ፣የተረፉት የያዕቆብ ወገኖችም በብሔራት፣በብዙ ሕዝቦችም መካከል እንዲሁ ይሆናሉ፤ሊያስጥል የሚችልም አይኖርም። 9  እጅህ ከባላጋራዎችህ በላይ ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይወገዳሉ።” 10  “በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ፈረሶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ ሠረገሎችህንም አጠፋለሁ። 11  በምድርህ ላይ የሚገኙትን ከተሞች እደመስሳለሁ፤የተመሸጉ ስፍራዎችህንም ሁሉ አፈራርሳለሁ። 12  ጥንቆላህን አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም አስማተኛ በመካከልህ አይኖርም። 13  የተቀረጹ ምስሎችህንና ዓምዶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ወዲህ ለእጆችህ ሥራ አትሰግድም። 14  የማምለኪያ ግንዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፤ከተሞችህንም እደመስሳለሁ። 15  ታዛዥ ያልሆኑትን ብሔራት፣በቁጣና በንዴት እበቀላለሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,075
6  ይሖዋ የሚለውን እባካችሁ ስሙ። ተነሱ፤ በተራሮች ፊት ሙግታችሁን አቅርቡ፤ኮረብቶችም ቃላችሁን ይስሙ። 2  ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ጽኑ የምድር መሠረቶች፣የይሖዋን ሙግት ስሙ፤ይሖዋ ከሕዝቡ ጋር ሙግት አለውና፤ከእስራኤልም ጋር ይከራከራል፦ 3  “ሕዝቤ ሆይ፣ ምን ያደረግኩህ ነገር አለ? ያደከምኩህስ ምን አድርጌ ነው? እስቲ መሥክርብኝ። 4  ከግብፅ ምድር አወጣሁህ፤ከባርነትም ቤት ዋጀሁህ፤ሙሴን፣ አሮንንና ሚርያምን በፊትህ ላክሁ። 5  ሕዝቤ ሆይ፣ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያሴረብህን ነገር፣የቢዖር ልጅ በለዓምም የሰጠውን መልስ እባክህ አስታውስ፤የይሖዋን የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድከሺቲም እስከ ጊልጋል ድረስ የሆነውን ነገር አስታውስ።” 6  በይሖዋ ፊት ምን ይዤ ልቅረብ? ከፍ ባለ ስፍራ በሚኖረው አምላክ ፊት ምን ይዤ ልስገድ? ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችናየአንድ ዓመት ጥጃዎች ይዤ ልቅረብ? 7  ይሖዋ በሺህ በሚቆጠሩ አውራ በጎችወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋል? ለሠራሁት በደል የበኩር ወንድ ልጄን፣ለሠራሁትም ኃጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብ? 8  ሰው ሆይ፣ መልካም የሆነውን ነግሮሃል። ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን እንድታደርግ፣ ታማኝነትን እንድትወድናልክህን አውቀህ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ ብቻ ነው! 9  የይሖዋ ድምፅ ከተማዋን ይጣራል፤ጥበበኞች ስምህን ይፈራሉ። የበትሩን ድምፅና ቅጣቱን የወሰነውን ስሙ። 10  ክፉ በሆነ ሰው ቤት፣ በክፋት የተገኘ ሀብትእንዲሁም አስጸያፊ የሆነ ጎዶሎ የኢፍ መስፈሪያ አሁንም አለ? 11  አባይ ሚዛንና የተዛቡ የድንጋይ መለኪያዎች የያዘ ከረጢት እየተጠቀምኩንጹሕ ሥነ ምግባር ሊኖረኝ ይችላል? 12  ባለጸጎቿ በግፍ የተሞሉ ናቸው፤ነዋሪዎቿም ውሸት ይናገራሉ፤ምላሳቸው በአፋቸው ውስጥ አታላይ ነው። 13  “ስለዚህ መትቼ አቆስልሃለሁ፤ከኃጢአትህ የተነሳ አጠፋሃለሁ። 14  ትበላለህ፤ ግን አትጠግብም፤ሆድህም ባዶ ይሆናል። የምትወስዳቸውን ነገሮች ጠብቀህ ማቆየት አትችልም፤ጠብቀህ ያቆየኸውንም ነገር ሁሉ ለሰይፍ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። 15  ዘር ትዘራለህ፤ ሆኖም የምታጭደው ነገር አይኖርም። የወይራ ፍሬ ትጨምቃለህ፤ ሆኖም ዘይቱን አትጠቀምበትም፤ደግሞም አዲስ ወይን ትጨምቃለህ፤ ሆኖም የወይን ጠጅ አትጠጣም። 16  የኦምሪን ደንቦችና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ትከተላላችሁና፤ምክራቸውንም ተከትላችሁ ትሄዳላችሁ። ስለዚህ አንተን መቀጣጫ፣ነዋሪዎቿንም ማፏጫ አደርጋለሁ፤የሰዎችንም ፌዝ ትሸከማላችሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,076
7  ወዮልኝ! የበጋ ፍሬ ከተሰበሰበናወይን የሚሰበሰብበት ጊዜ አብቅቶቃርሚያ ከተለቀመ በኋላየሚበላ የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ሆኛለሁ፤በጣም የምመኘውን፣ በመጀመሪያው ወቅት የሚደርሰውን በለስም አላገኘሁም። 2  ታማኝ ሰው ከምድሪቱ ጠፍቷል፤ከሰው ልጆችም መካከል ቅን የሆነ የለም። ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባሉ። እያንዳንዱም የገዛ ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል። 3  እጆቻቸው መጥፎ ነገር በማድረግ የተካኑ ናቸው፤ገዢው የሆነ ነገር እንዲደረግለት ይጠይቃል፤ፈራጁ ክፍያ ይጠይቃል፤ታዋቂ የሆነው ሰው የራሱን ፍላጎት ይገልጻል፤እነሱም አንድ ላይ ሆነው ያሴራሉ። 4  ከእነሱ መካከል የተሻለ የተባለው እንደ እሾህ ነው፤እጅግ ቅን የተባለው ደግሞ ከእሾህ ቁጥቋጦ የከፋ ነው። ጠባቂዎችህ የተናገሩለት፣ አንተ የምትጎበኝበት ቀን ይመጣል። እነሱ አሁን ይሸበራሉ። 5  ባልንጀራህን አትመን፤ወይም በቅርብ ወዳጅህ አትታመን። በእቅፍህ ለምትተኛው ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ። 6  ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፤ሴት ልጅ በእናቷ ላይ ትነሳለች፤ምራት ደግሞ በአማቷ ላይ ትነሳለች፤የሰው ጠላቶቹ ቤተሰቦቹ ናቸው። 7  እኔ ግን ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ። የሚያድነኝን አምላክ በትዕግሥት እጠብቃለሁ። አምላኬ ይሰማኛል። 8  ጠላቴ ሆይ፣ በእኔ ላይ በደረሰው ነገር ሐሴት አታድርጊ። ብወድቅም እንኳ እነሳለሁ፤በጨለማ ውስጥ ብቀመጥም ይሖዋ ብርሃን ይሆንልኛል። 9  በእሱ ላይ ኃጢአት ስለሠራሁለእኔ እስኪሟገትልኝና ፍትሕ እንዳገኝ እስከሚያደርግ ድረስየይሖዋን ቁጣ ችዬ እኖራለሁ። እሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤እኔም የእሱን ጽድቅ አያለሁ። 10  “አምላክህ ይሖዋ የት አለ?”ስትለኝ የነበረችው ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትም ትከናነባለች። ዓይኖቼም ያዩአታል። በዚያን ጊዜ በጎዳና ላይ እንዳለ ጭቃ የምትረገጥ ቦታ ትሆናለች። 11  የድንጋይ ቅጥሮችሽ የሚገነቡበት ቀን ይሆናል፤በዚያ ቀን ድንበሩ ይሰፋል። 12  በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች፣ከግብፅ አንስቶ እስከ ወንዙ ድረስ፣ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከተራራም እስከ ተራራ ድረስ ያሉ ሰዎችወደ አንቺ ይመጣሉ። 13  ምድሪቱም ከነዋሪዎቿና ከሠሩት ነገር የተነሳባድማ ትሆናለች። 14  ሕዝብህን ይኸውም በጫካ ውስጥ በፍራፍሬ እርሻ መካከል ብቻውን ያለውን፣የርስትህን መንጋ እንደ እረኛ በበትር ጠብቅ። እንደ ድሮው ዘመን በባሳንና በጊልያድ ይሰማሩ። 15  “ከግብፅ ምድር በወጣችሁበት ዘመን እንደነበረውድንቅ ሥራዎችን አሳያችኋለሁ። 16  ብሔራትም ያያሉ፤ ታላቅ ኃይል ቢኖራቸውም ያፍራሉ። እጃቸውን በአፋቸው ላይ ይጭናሉ፤ጆሯቸው ይደነቁራል። 17  እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፤በምድር ላይ እንደሚሳቡ እንስሳት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጎቻቸው ይወጣሉ። በፍርሃት ተውጠው ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመጣሉ፤አንተንም ይፈሩሃል።” 18  የርስቱን ቀሪዎች ኃጢአት ይቅር የሚል፣ በደላቸውንም የሚያልፍእንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? እሱ ለዘላለም አይቆጣም፤ታማኝ ፍቅር በማሳየት ደስ ይሰኛልና። 19  ዳግመኛ ምሕረት ያሳየናል፤ በደላችንን በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል። ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ ጥልቅ ባሕር ትጥላለህ። 20  በጥንት ዘመን ለአባቶቻችን በማልክላቸው መሠረትለያዕቆብ ታማኝነትን፣ለአብርሃም ደግሞ ታማኝ ፍቅርን ታሳያለህ።
[]
[]
[]
[]
12,077
1  የፍርድ መልእክት፦ በሚልክያስ በኩል ለእስራኤል የተነገረው የይሖዋ ቃል ይህ ነው፦ 2  “እኔ ፍቅር አሳይቻችኋለሁ” ይላል ይሖዋ። እናንተ ግን “ፍቅር ያሳየኸን እንዴት ነው?” አላችሁ። “ኤሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረም?” ይላል ይሖዋ። “እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ፤ 3  ኤሳውንም ጠላሁ፤ ተራሮቹን ባድማ አደረግኩ፤ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮዎች ሰጠሁ።” 4  “ኤዶም ‘ተደምስሰናል፤ ሆኖም ተመልሰን የፈራረሱትን ዳግመኛ እንገነባለን’ ቢልም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ይገነባሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ቦታዎቹ “የክፋት ምድር፣” እነሱ ደግሞ “ይሖዋ ለዘላለም ያወገዘው ሕዝብ” ተብለው ይጠራሉ። 5  የገዛ ዓይናችሁ ይህን ያያል፤ እናንተም “ይሖዋ በእስራኤል ምድር ከፍ ከፍ ይበል” ትላላችሁ።’” 6  “እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፣ ‘ልጅ አባቱን፣ አገልጋይም ጌታውን ያከብራል። እኔ አባት ከሆንኩ ለእኔ የሚገባው ክብር የት አለ? ጌታስ ከሆንኩ መፈራቴ የት አለ?’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “‘እናንተ ግን “ስምህን ያቃለልነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ።’ 7  “‘በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ በማቅረብ ነው።’ “‘ደግሞም “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ።’ “‘“የይሖዋ ገበታ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው። 8  ዕውሩን እንስሳ መሥዋዕት አድርጋችሁ ስታቀርቡ “ምንም ችግር የለውም” ትላላችሁ። ደግሞም አንካሳ ወይም የታመመ እንስሳ ስታቀርቡ “ምንም ችግር የለውም” ትላላችሁ።’” “እነዚህን እንስሳት እስቲ ለገዢህ ለማቅረብ ሞክር። በአንተ ደስ ይለዋል? ወይስ በሞገስ ዓይን ይቀበልሃል?” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 9  “አሁንም እባካችሁ፣ ሞገስ እንዲያሳየን አምላክን ተማጸኑ። እንዲህ ያሉ መባዎች በገዛ እጃችሁ ስታቀርቡ ከእናንተ መካከል የእሱን ሞገስ የሚያገኝ ይኖራል?” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 10  “ከእናንተ መካከል በሮቹን ለመዝጋት ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው? በመሠዊያዬ ላይ እሳት ለማንደድ እንኳ ክፍያ ትጠይቃላችሁና። በእናንተ ፈጽሞ ደስ አልሰኝም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ስጦታ አድርጋችሁ በምታቀርቡት በየትኛውም መባ አልደሰትም።” 11  “ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል። በየቦታው ለስሜ የሚጨስ መሥዋዕትና መባ ተቀባይነት ያለው ስጦታ ሆኖ ይቀርባል፤ ምክንያቱም ስሜ በብሔራት መካከል ታላቅ ይሆናል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 12  “እናንተ ግን ‘የይሖዋ ገበታ የረከሰ ነው፤ ፍሬው ይኸውም ምግቡ የተናቀ ነው’ በማለት ታረክሱታላችሁ። 13  በተጨማሪም እናንተ ‘እንዴት አድካሚ ነው!’ ትላላችሁ፤ ደግሞም ትጸየፉታላችሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “የተሰረቀን፣ አንካሳውንና የታመመውን እንስሳ ታመጣላችሁ። አዎ፣ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ስጦታ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ! ታዲያ ይህን ከእጃችሁ ልቀበል ይገባል?” ይላል ይሖዋ። 14  “በመንጎቹ መካከል ተባዕት እንስሳ እያለው፣ ስእለት ተስሎ እንከን ያለበትን ለይሖዋ መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ የሚያታልል የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ስሜም በብሔራት መካከል የተፈራ ይሆናል።”
[]
[]
[]
[]
12,078
2  “አሁንም ካህናት ሆይ፣ ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው። 2  ለመስማት አሻፈረኝ ብትሉና ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ በልባችሁ ባታኖሩት” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “በእናንተ ላይ እርግማን እሰዳለሁ፤ በረከታችሁንም ወደ እርግማን እለውጣለሁ። አዎ፣ በልባችሁ ስላላኖራችሁት እያንዳንዱን በረከት ወደ እርግማን ለውጫለሁ።” 3  “እነሆ፣ በእናንተ የተነሳ የዘራችሁትን ዘር አጠፋለሁ፤ ፈርሱንም ይኸውም በበዓሎቻችሁ ላይ የምትሠዉአቸውን እንስሳት ፈርስ ፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ እናንተንም ወደዚያ ወስደው ይጥሏችኋል። 4  ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ ከሌዊ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ጸንቶ እንዲኖር መሆኑን ታውቃላችሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 5  “ከእሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነው፤ እነዚህን በረከቶች በማግኘቱ እኔን ለመፍራት ተነሳሳ። አዎ፣ ለስሜ ታላቅ አክብሮት አሳየ። 6  የእውነት ሕግ በአፉ ውስጥ ነበር፤ በከንፈሮቹም ክፋት አልተገኘም። ከእኔ ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፤ ብዙዎቹንም ከስህተት ጎዳና መለሰ። 7  ካህኑ ምንጊዜም በከንፈሮቹ ላይ እውቀት ሊኖረው ይገባል፤ ሰዎችም ሕጉን ከአፉ ሊሹ ይገባል፤ ምክንያቱም እሱ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ መልእክተኛ ነው። 8  “እናንተ ግን ከመንገዱ ፈቀቅ ብላችኋል። ብዙዎች ከሕጉ ጋር በተያያዘ እንዲሰናከሉ አድርጋችኋል። የሌዊን ቃል ኪዳን አርክሳችኋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 9  “ስለዚህ በሰዎች ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ እንድትሆኑ አደርጋለሁ፤ ምክንያቱም መንገዶቼን አልጠበቃችሁም፤ ከዚህ ይልቅ ሕጉን ተግባራዊ ስታደርጉ አድልዎ ፈጽማችኋል።” 10  “የሁላችንም አባት አንድ አይደለም? የፈጠረንስ አምላክ አንድ አይደለም? ታዲያ የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን በማርከስ አንዳችን በሌላው ላይ ክህደት የምንፈጽመው ለምንድን ነው? 11  ይሁዳ ክህደት ፈጽሟል፤ በእስራኤልና በኢየሩሳሌምም አስጸያፊ ነገር ተፈጽሟል፤ ይሁዳ፣ ይሖዋ የሚወደውን ቅድስናውን አርክሷልና፤ ደግሞም የባዕድ አምላክ ሴት ልጅን አግብቷል። 12  ይህን የሚያደርግ ማንኛውም ሰው ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ስጦታ አድርጎ መባ ቢያቀርብም እንኳ ይሖዋ ከያዕቆብ ድንኳኖች ያስወግደዋል።” 13  “ሌላም የምታደርጉት ነገር አለ፤ ይህም የይሖዋ መሠዊያ በእንባ፣ በለቅሶና በሐዘን እንዲሞላ ምክንያት ሆኗል፤ በመሆኑም ስጦታ አድርጋችሁ የምታቀርቧቸውን መባዎች ከእንግዲህ አይቀበልም፤ የምታቀርቡትንም ነገር ሁሉ በሞገስ ዓይን አይመለከትም። 14  እናንተም ‘ይህ የሆነው ለምንድን ነው?’ ብላችኋል። ይህ የሆነው ይሖዋ በአንተ ላይ ስለመሠከረብህ ነው፤ ምክንያቱም እሷ አጋርህና የቃል ኪዳን ሚስትህ ሆና ሳለ በወጣትነት ሚስትህ ላይ ክህደት ፈጽመሃል። 15  ሆኖም እንዲህ ያላደረገ አለ፤ እሱ በተወሰነ መጠን የአምላክ መንፈስ ነበረው። ፍላጎቱስ ምን ነበር? የአምላክ ዘር ነበር። በመሆኑም መንፈሳችሁን ጠብቁ፤ በወጣትነት ሚስታችሁም ላይ ክህደት አትፈጽሙ። 16  እኔ ፍቺን እጠላለሁና” ይላል የእስራኤል አምላክ ይሖዋ፤ “ልብሱን በግፍ ድርጊት የሚሸፍነውንም እጠላለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “መንፈሳችሁን ጠብቁ፤ ክህደትም አትፈጽሙ። 17  “ይሖዋን በቃላችሁ አታክታችሁታል። እናንተ ግን ‘ያታከትነው እንዴት ነው?’ ትላላችሁ። ‘ክፉ ድርጊት የሚፈጽም ሁሉ በይሖዋ ዓይን ጥሩ ነው፤ እሱ እንዲህ ባለ ሰው ደስ ይሰኛል’ ወይም ‘የፍትሕ አምላክ የት አለ?’ በማለታችሁ ነው።”
[]
[]
[]
[]
12,079
3  “እነሆ፣ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ እሱም በፊቴ መንገድ ይጠርጋል። እናንተ የምትፈልጉት እውነተኛው ጌታ በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ ደስ የምትሰኙበት የቃል ኪዳኑ መልእክተኛም ይመጣል። እነሆ፣ እሱ በእርግጥ ይመጣል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 2  “ይሁንና እሱ የሚመጣበትን ቀን ሊቋቋም የሚችል ማን ነው? እሱ በሚገለጥበት ጊዜስ ማን ሊቆም ይችላል? እሱ እንደ አንጥረኛ እሳት፣ እንደ ልብስ አጣቢም እንዶድ ይሆናልና። 3  ደግሞም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች ያነጻል፤ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያጠራቸዋል፤ ይሖዋም በጽድቅ መባ የሚያቀርብ ሕዝብ ይኖረዋል። 4  ይሁዳና ኢየሩሳሌም ስጦታ አድርገው የሚያቀርቡት መባ በቀድሞው ጊዜና በጥንት ዘመን እንደነበረው ይሖዋን ደስ ያሰኘዋል። 5  “ለመፍረድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በመተተኞቹ፣ በአመንዝሮቹ፣ በሐሰት በሚምሉት ሰዎች እንዲሁም ቅጥር ሠራተኛውን፣ መበለቲቱንና አባት የሌለውን ልጅ በሚያጭበረብሩትና ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ በማይሆኑት ላይ ወዲያውኑ እመሠክርባቸዋለሁ። እነዚህ ሰዎች እኔን አልፈሩም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 6  “እኔ ይሖዋ ነኝና፤ አልለወጥም። እናንተም የያዕቆብ ልጆች ናችሁ፤ ገና አልጠፋችሁም። 7  ከአባቶቻችሁ ዘመን አንስቶ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፤ ደግሞም ሥርዓቴን አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። እናንተ ግን “የምንመለሰው እንዴት ነው?” ትላላችሁ። 8  “በውኑ ተራ ሰው አምላክን ይሰርቃል? እናንተ ግን እኔን ትሰርቁኛላችሁ።” እናንተም “የሰረቅንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “በምትሰጡት አሥራትና መዋጮ ነው። 9  እናንተ በእርግጥ የተረገማችሁ ናችሁ፤ ትሰርቁኛላችሁና፤ አዎ፣ መላው ብሔር እንዲህ ያደርጋል። 10  በቤቴ ውስጥ እህል እንዲኖር አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራው አስገቡ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “የሰማያትን መስኮቶች ከፍቼ ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የተትረፈረፈ በረከት ባላፈስላችሁ፣ እስቲ በዚህ ፈትኑኝ።” 11  “ለእናንተም ስል፣ በላተኛውን እገሥጻለሁ፤ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፤ በእርሻችሁ ላይ ያለው የወይን ተክልም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 12  “እናንተ የደስታ ምድር ስለምትሆኑ ብሔራት ሁሉ ደስተኞች ብለው ይጠሯችኋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 13  “በእኔ ላይ ኃይለ ቃል ተናግራችኋል” ይላል ይሖዋ። እናንተም “በአንተ ላይ የተናገርነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ። 14  “እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘አምላክን ማገልገል ዋጋ የለውም። ለእሱ ያለብንን ግዴታ በመጠበቃችንና በኃጢአታችን የተነሳ ማዘናችንን በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ፊት በማሳየታችን ምን ተጠቀምን? 15  አሁን እብሪተኛ የሆኑ ሰዎችን ደስተኞች እንደሆኑ አድርገን እንመለከታቸዋለን። ደግሞም ክፉ አድራጊዎች ስኬታማ ሆነዋል። እነሱ በድፍረት አምላክን ይፈታተናሉ፤ ከቅጣትም ያመልጣሉ።’” 16  በዚያ ጊዜ ይሖዋን የሚፈሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው፣ ከባልንጀሮቻቸው ጋር ተነጋገሩ፤ ይሖዋም በትኩረት አዳመጠ፤ ደግሞም ሰማ። ይሖዋንም ለሚፈሩና በስሙ ላይ ለሚያሰላስሉ በፊቱ የመታሰቢያ መጽሐፍ ተጻፈ። 17  “የእኔ ልዩ ንብረት በማደርጋቸውም ቀን እነሱ የእኔ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። “አባት ለሚታዘዝለት ልጁ እንደሚራራ እኔም እራራላቸዋለሁ። 18  እናንተም በጻድቁና በክፉው እንዲሁም አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው ሰው መካከል ያለውን ልዩነት ዳግመኛ ታያላችሁ።”
[]
[]
[]
[]
12,080
4  “እነሆ፣ ያ ቀን እንደ ምድጃ እየነደደ ይመጣል፤ በዚያ ጊዜ እብሪተኞች ሁሉና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ እንደ ገለባ ይሆናሉ። የሚመጣው ቀን በእርግጥ ይበላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤ “ሥርም ሆነ ቅርንጫፍ አይተውላቸውም። 2  ስሜን ለምታከብሩት ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ በጨረሮቿ ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም እንደሰቡ ጥጆች ትቦርቃላችሁ።” 3  “እኔም እርምጃ በምወስድበት ቀን ክፉዎችን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ሥር እንዳለ አቧራ ይሆናሉና” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 4  “የአገልጋዬን የሙሴን ሕግ ይኸውም መላው እስራኤል እንዲያከብረው በኮሬብ ያዘዝኩትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስታውሱ። 5  “እነሆ፣ ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን ከመምጣቱ በፊት ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ። 6  እሱም መጥቼ ምድርን እንዳልመታና ፈጽሜ እንዳላጠፋ የአባቶችን ልብ እንደ ልጆች ልብ፣ የልጆችንም ልብ እንደ አባቶች ልብ ያደርጋል።”
[]
[]
[]
[]
12,081
1  በኢየሩሳሌም የነገሠው የሰብሳቢው የዳዊት ልጅ ቃል። 2  ሰብሳቢው “የከንቱ ከንቱ ነው!የከንቱ ከንቱ ነው! ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” አለ። 3  ሰው ከፀሐይ በታች በትጋት ከሚያከናውነውና ከሚለፋበት ሥራ ሁሉየሚያገኘው ጥቅም ምንድን ነው? 4  ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች። 5  ፀሐይ ትወጣለች፤ ደግሞም ትጠልቃለች፤ከዚያም ዳግመኛ ወደምትወጣበት ቦታ ለመመለስ ትጣደፋለች። 6  ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ ወደ ሰሜንም ዞሮ ይሄዳል፤ክብ እየሠራ ያለማቋረጥ ይሽከረከራል፤ ደግሞም ነፋሱ ዑደቱን ይቀጥላል። 7  ጅረቶች ሁሉ ወደ ባሕር ይፈስሳሉ፤ ሆኖም ባሕሩ አይሞላም። ጅረቶቹ እንደገና ይፈስሱ ዘንድ ወደሚነሱበት ወደዚያው ቦታ ተመልሰው ይሄዳሉ። 8  ሁሉ ነገር አሰልቺ ነው፤ሁሉንም ነገር ሊገልጽ የሚችል ሰው የለም። ዓይን አይቶ አይጠግብም፤ጆሮም ሰምቶ አይሞላም። 9  ከዚህ በፊት የነበረው ነገር ወደፊትም ይሆናል፤ከዚህ በፊት የተደረገውም ነገር እንደገና ይደረጋል፤ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም። 10  አንድ ሰው “ተመልከት፣ ይህ አዲስ ነገር ነው” ሊል የሚችለው ነገር ይኖራል? ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነው፤ከእኛ ዘመን በፊት የነበረ ነው። 11  በቀድሞ ዘመን የነበሩትን ሰዎች ማንም አያስታውሳቸውም፤ከጊዜ በኋላ የሚመጡትንም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ከእነሱ በኋላ የሚነሱት ሰዎችም እንኳ አያስታውሷቸውም። 12  እኔ ሰብሳቢው በኢየሩሳሌም፣ የእስራኤል ንጉሥ ነበርኩ። 13  ከሰማይ በታች የተሠራውን ነገር ሁሉ ይኸውም አምላክ የሰው ልጆች እንዲጠመዱበት የሰጣቸውን አሰልቺ ሥራ በጥበብ ለማጥናትና ለመመርመር ከልቤ ጥረት አደረግኩ። 14  ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ ተመለከትኩ፤እነሆ፣ ሁሉም ከንቱ ነፋስንም እንደማሳደድ ነው። 15  የተጣመመ ነገር ሊቃና አይችልም፤የሌለም ነገር በምንም መንገድ ሊቆጠር አይችልም። 16  እኔም በልቤ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ እጅግ የላቀ ጥበብ አገኘሁ፤ ልቤም ከፍተኛ ጥበብና እውቀት አገኘ።” 17  እኔም ጥበብንና እብደትን እንዲሁም ሞኝነትን ለመረዳት ከልቤ ጥረት አደረግኩ፤ ይህም ቢሆን ነፋስን እንደማሳደድ ነው። 18  ጥበብ ሲበዛ ብስጭትም ይበዛልና፤በመሆኑም እውቀትን የሚጨምር ሁሉ ሥቃይንም ይጨምራል።
[]
[]
[]
[]
12,082
10  የሞቱ ዝንቦች በጥሩ ቀማሚ የተዘጋጀውን ሽቶ እንዲበላሽና እንዲገማ እንደሚያደርጉት ሁሉ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ዋጋ ያሳጣል። 2  የጥበበኛ ሰው ልብ በትክክለኛ መንገድ ይመራዋል፤ የሞኝ ልብ ግን በተሳሳተ መንገድ ይመራዋል። 3  ሞኝ ሰው በየትኛውም መንገድ ቢመላለስ ማስተዋል ይጎድለዋል፤ ሞኝ መሆኑንም ሰው ሁሉ እንዲያውቅ ያደርጋል። 4  የገዢ ቁጣ በአንተ ላይ ቢነድ ስፍራህን አትልቀቅ፤ የረጋ መንፈስ ታላቅ ኃጢአትን ጸጥ ያደርጋልና። 5  ከፀሐይ በታች ያየሁት አንድ የሚያስጨንቅ ነገር አለ፤ ይህም በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች እንደሚሠሩት ያለ ስህተት ነው፦ 6  ሞኞች በከፍተኛ የሥልጣን ቦታዎች ላይ ሲቀመጡ የናጠጡ ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ቦታዎች ላይ ይገኛሉ። 7  አገልጋዮች በፈረስ ተቀምጠው ሲጓዙ፣ መኳንንት ግን እንደ አገልጋዮች በእግራቸው ሲሄዱ አይቻለሁ። 8  ጉድጓድ የሚቆፍር ራሱ ሊገባበት ይችላል፤ ግንብን የሚያፈርስም በእባብ ሊነደፍ ይችላል። 9  ድንጋይ የሚፈነቅል ሰው በፈነቀለው ድንጋይ ሊጎዳ ይችላል፤ ግንድንም የሚፈልጥ አደጋ ሊያደርስበት ይችላል። 10  ከብረት የተሠራ መሣሪያ ቢደንዝ፣ ሰውም ባይስለው ብዙ ጉልበት መጠቀም ያስፈልገዋል። ጥበብ ግን ስኬታማ ለመሆን ይረዳል። 11  እባብ በድግምት ከመፍዘዙ በፊት ቢነድፍ፣ በድግምት የተካነው ሰው ምንም ጥቅም አያገኝም። 12  ጥበበኛ ሰው ከአፉ የሚወጡት ቃላት ሞገስ ያስገኙለታል፤ የሞኝ ሰው ከንፈር ግን ለጥፋት ይዳርገዋል። 13  ከአፉ የሚወጡት የመጀመሪያ ቃላት ሞኝነት ይንጸባረቅባቸዋል፤ የንግግሩ ማሳረጊያም የከፋ እብደት ነው። 14  ይሁንና ሞኙ ማውራቱን ይቀጥላል። ሰው ወደፊት የሚሆነውን ነገር አያውቅም፤ ከእሱ በኋላ የሚመጣውን ነገር ማን ሊነግረው ይችላል? 15  ሞኝ ሰው የሚሠራው አድካሚ ሥራ እንዲዝል ያደርገዋል፤ ወደ ከተማ የሚወስደውን መንገድ ማግኘት እንኳ አይችልምና። 16  አንዲት አገር ንጉሥዋ ልጅ ቢሆን፣ መኳንንቷ ደግሞ በጠዋት ግብዣ ላይ የሚገኙ ቢሆኑ ምንኛ አሳዛኝ ነው! 17  ከትልቅ ቤተሰብ የተወለደ ንጉሥ ያላት እንዲሁም ለስካር ሳይሆን ብርታት ለማግኘት በተገቢው ጊዜ የሚመገቡ መኳንንት ያሏት አገር ምንኛ ደስተኛ ናት! 18  ስንፍና ሲበዛ ጣሪያ ይዘብጣል፤ እጆችም ካልሠሩ ቤት ያፈሳል። 19  ምግብ ለሳቅ ይዘጋጃል፤ የወይን ጠጅም ሕይወትን አስደሳች ያደርጋል፤ ይሁን እንጂ ገንዘብ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያሟላል። 20  በሐሳብህ እንኳ ንጉሡን አትርገም፤ በመኝታ ቤትህም ሆነህ ባለጸጋውን አትርገም፤ ቃሉን ወፍ ልትወስደው አሊያም ክንፍ ያላት ፍጥረት የተወራውን ደግማ ልትናገር ትችላለችና።
[]
[]
[]
[]
12,083
11  ቂጣህን በውኃ ላይ ጣል፤ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና። 2  ካለህ ነገር ላይ ለሰባት፣ እንዲያውም ለስምንት አካፍለህ ስጥ፤ በምድር ላይ የሚመጣውን አደጋ አታውቅምና። 3  ደመናት ውኃ ካዘሉ በምድር ላይ ዶፍ ያወርዳሉ፤ እንዲሁም ዛፍ በስተ ደቡብ ወይም በስተ ሰሜን ከወደቀ በዚያው በወደቀበት ይቀራል። 4  ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም። 5  መንፈስ፣ በእርጉዝ ሴት ውስጥ በሚገኝ ሕፃን አጥንቶች ላይ እንዴት እንደሚሠራ እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉንም ነገር የሚያከናውነውን የእውነተኛውን አምላክ ሥራም አታውቅም። 6  በማለዳ ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ ይህ ወይም ያ የትኛው እንደሚያድግ ወይም ደግሞ ሁለቱም ይጸድቁ እንደሆነ አታውቅምና። 7  ብርሃን ደስ ያሰኛል፤ ፀሐይንም ማየት ለዓይን መልካም ነው። 8  ሰው የቱንም ያህል ብዙ ዓመት ቢኖር በእያንዳንዱ ቀን ደስ ይበለው። ሆኖም በጨለማ የተዋጡት ቀናት ብዙ ሊሆኑ እንደሚችሉ መዘንጋት አይኖርበትም፤ የሚመጣው ሁሉ ከንቱ ነው። 9  አንተ ወጣት፣ በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ይበለው። የልብህን መንገድ ተከተል፤ ዓይንህ በሚመራህም መንገድ ሂድ፤ ሆኖም ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እውነተኛው አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ እወቅ። 10  ስለዚህ የሚያስጨንቁ ነገሮችን ከልብህ አስወግድ፤ ጎጂ ነገሮችንም ከሰውነትህ አርቅ፤ ወጣትነትና የለጋነት ዕድሜ ከንቱ ናቸውና።
[]
[]
[]
[]
12,084
12  እንግዲያው አስጨናቂ የሆኑት ዘመናት ከመምጣታቸው እንዲሁም “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመታት ከመድረሳቸው በፊት በወጣትነትህ ጊዜ ታላቁን ፈጣሪህን አስብ፤ 2  ፀሐይ፣ ብርሃን፣ ጨረቃና ከዋክብት ከመጨለማቸው በፊት እንዲሁም ዶፍ ከጣለ በኋላ ደመናት ተመልሰው ከመምጣታቸው በፊት ፈጣሪህን አስብ፤ 3  በዚያን ጊዜ ቤት ጠባቂዎች ይንቀጠቀጣሉ፤ ጠንካራ የነበሩ ሰዎች ይጎብጣሉ፤ የሚፈጩ ሴቶች ጥቂት በመሆናቸው ሥራቸውን ያቆማሉ፤ በመስኮት የሚያዩ ወይዛዝርትም ይጨልምባቸዋል፤ 4  ወደ መንገድ የሚያወጡ በሮች ይዘጋሉ፤ የወፍጮ ድምፅ ይቀንሳል፤ ሰውም የወፍ ድምፅ ይቀሰቅሰዋል፤ ሴቶች ልጆችም ሁሉ ዝግ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ። 5  በተጨማሪም ሰው ከፍታ ያስፈራዋል፤ በመንገድ ሲሄድም ይሸበራል። የአልሞንድ ዛፍ ያብባል፤ ፌንጣም እየተጎተተ ይሄዳል፤ የምግብ ፍላጎት ይጠፋል፤ ምክንያቱም ሰው ለረጅም ጊዜ ወደሚኖርበት ቤት ይሄዳል፤ አልቃሾችም በጎዳና ይዞራሉ፤ 6  የብር ገመድ ሳይበጠስ፣ የወርቅ ሳህን ሳይሰበር፣ እንስራ በምንጭ አጠገብ ሳይከሰከስ፣ ከጉድጓድ ውኃ ለማውጣት የሚያገለግለው መንኮራኩር ሳይሰበር ፈጣሪህን አስብ። 7  አፈር ቀድሞ ወደነበረበት መሬት ይመለሳል፤ መንፈስም ወደ ሰጪው፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ይመለሳል። 8  ሰብሳቢው “የከንቱ ከንቱ ነው! ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ይላል። 9  ሰብሳቢው ጥበበኛ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሕዝቡ የሚያውቀውን ነገር ሁልጊዜ ያስተምር ነበር፤ ብዙ ምሳሌዎችንም ማጠናቀር ይችል ዘንድ አሰላሰለ እንዲሁም ሰፊ ምርምር አደረገ። 10  ሰብሳቢው ደስ የሚያሰኙ ቃላትን ለማግኘትና የእውነትን ቃል በትክክል ለመመዝገብ ጥረት አደረገ። 11  የጥበበኞች ቃላት እንደ በሬ መውጊያ ናቸው፤ የሰበሰቧቸው አባባሎችም በሚገባ እንደተቸነከሩ ምስማሮች ናቸው፤ እነዚህ ቃላት ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው። 12  ልጄ ሆይ፣ ከዚህም ሌላ ይህን ማስጠንቀቂያ ልብ በል፦ ብዙ መጻሕፍት መጻፍ ማብቂያ የለውም፤ በእነሱ ዙሪያ ምርምር ማብዛትም ሰውነትን ያደክማል። 13  ሁሉ ነገር ከተሰማ በኋላ መደምደሚያው ይህ ነው፦ እውነተኛውን አምላክ ፍራ፤ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው አጠቃላይ ግዴታ ነውና። 14  እውነተኛው አምላክ እያንዳንዱን የተሰወረ ነገር ጨምሮ ማንኛውንም ሥራ፣ ጥሩም ይሁን መጥፎ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።
[]
[]
[]
[]
12,085
2  እኔም በልቤ “እስቲ ደስታን ልፈትንና ምን መልካም ነገር እንደሚገኝ ልይ” አልኩ። ይሁንና ይህም ከንቱ ነበር። 2  ሳቅ “እብደት ነው!” ደስታም “ምን ይጠቅማል?” አልኩ። 3  በገዛ ጥበቤ እየተመራሁና ራሴን በወይን ጠጅ እያስደሰትኩ በጥልቀት መረመርኩ፤ ሰዎች አጭር በሆነው የሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ሊያደርጉት የሚችሉት ከሁሉ የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ በሞኝነት እንኳ ሳይቀር ተመላለስኩ። 4  ታላላቅ ሥራዎችን አከናወንኩ። ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይንም ተከልኩ። 5  ለራሴ የአትክልት ስፍራዎችንና መናፈሻዎችን አዘጋጀሁ፤ በእነዚህም ቦታዎች ሁሉንም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፎች ተከልኩ። 6  በእርሻው መሬት ላይ እያደጉ ያሉትን ዛፎች ለማጠጣት የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ሠራሁ። 7  ወንድና ሴት አገልጋዮች አስመጣሁ፤ በቤቴ የተወለዱ አገልጋዮችም ነበሩኝ። በተጨማሪም ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ብዛት ያላቸው እንስሶች፣ ከብቶችና መንጎች ነበሩኝ። 8  ለራሴም ብርና ወርቅ፣ የነገሥታትንና የአውራጃዎችን ውድ ሀብት አከማቸሁ። ወንድና ሴት ዘፋኞችን እንዲሁም የሰው ልጆች እጅግ የሚደሰቱባቸውን ብዙ ሴቶች ሰበሰብኩ። 9  በመሆኑም ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ሰው ሆንኩ። ደግሞም ጥበቤ ከእኔ አልተለየችም። 10  የተመኘሁትን ነገር ሁሉ ራሴን አልነፈግኩም። ልቤንም ደስ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አልከለከልኩትም፤ ልቤ በትጋት በማከናውነው ሥራ ሁሉ ደስ ይሰኝ ነበርና፤ ብዙ ለደከምኩበት ሥራ ሁሉ ያገኘሁት ወሮታ ይህ ነበር። 11  ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሥራ ሁሉና ዳር ለማድረስ የደከምኩበትን ሥራ ሁሉ መለስ ብዬ ሳስብ፣ ሁሉ ነገር ከንቱ፣ ነፋስንም እንደማሳደድ መሆኑን አስተዋልኩ፤ ከፀሐይም በታች እውነተኛ ፋይዳ ያለው አንዳች ነገር አልነበረም። 12  ከዚያም ትኩረቴን ወደ ጥበብ፣ እብደትና ሞኝነት አዞርኩ። (ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል? ሊያደርግ የሚችለው ቀደም ሲል የተደረገውን ነገር ብቻ ነው።) 13  እኔም ብርሃን ከጨለማ የተሻለ ጥቅም እንዳለው ሁሉ ጥበብም ከሞኝነት የተሻለ ጥቅም እንዳለው ተገነዘብኩ። 14  የጥበበኛ ሰው ዓይኖች ያሉት በራሱ ላይ ነው፤ ሞኝ ሰው ግን በጨለማ ውስጥ ይሄዳል። ደግሞም የሁለቱም ፍጻሜ አንድ እንደሆነ ተገነዘብኩ። 15  እኔም በልቤ “በሞኙ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል” አልኩ። ታዲያ እጅግ ጥበበኛ በመሆኔ ምን አተርፋለሁ? በልቤም “ይህም ከንቱ ነው” አልኩ። 16  ጥበበኛውም ሆነ ሞኙ ለዘለቄታው አይታወሱምና። ሁሉም በሚመጡት ዘመናት ይረሳሉ። ለመሆኑ ጥበበኛው የሚሞተው እንዴት ነው? ልክ እንደ ሞኙ ሰው ይሞታል። 17  እኔም ከፀሐይ በታች የሚሠራው ሥራ ሁሉ አስጨናቂ ሆኖ ስለታየኝ ሕይወትን ጠላሁ፤ ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደማሳደድ ነውና። 18  ከኋላዬ ለሚመጣው ሰው ትቼው ስለምሄድ ከፀሐይ በታች እጅግ የደከምኩበትን ሥራ ሁሉ ጠላሁ። 19  ጥበበኛ ወይም ሞኝ እንደሚሆን የሚያውቅ ማን ነው? ሆኖም ከፀሐይ በታች በድካሜና በጥበቤ ያፈራሁትን ነገር ሁሉ ይወርሰዋል። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። 20  በመሆኑም ከፀሐይ በታች በለፋሁበት አድካሚ ሥራ ሁሉ ልቤ ተስፋ መቁረጥ ጀመረ። 21  ሰው በጥበብ፣ በእውቀትና በብልሃት እየተመራ ሥራውን በትጋት ሊያከናውን ይችላል፤ ይሁንና ድርሻውን ምንም ላልደከመበት ሰው ያስረክባል። ይህም ከንቱና እጅግ አሳዛኝ ነው። 22  ሰው ከፀሐይ በታች ከደከመበት ሁሉና ተግቶ እንዲሠራ ከሚገፋፋው ብርቱ ፍላጎት የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? 23  በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሥራው የሚያስገኝለት ነገር ቢኖር ሥቃይና ብስጭት ነው፤ በሌሊትም እንኳ ልቡ አያርፍም። ይህም ከንቱ ነው። 24  ሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በመሥራት እርካታ ከማግኘት የሚሻለው ነገር የለም። ይህም ቢሆን ከእውነተኛው አምላክ እጅ የተገኘ መሆኑን ተገንዝቤአለሁ፤ 25  ደግሞስ ከእኔ የተሻለ የሚበላና የሚጠጣ ማን ነው? 26  አምላክ እሱን ለሚያስደስት ሰው ጥበብ፣ እውቀትና ደስታ ይሰጣል፤ ኃጢአተኛ ለሆነው ግን እውነተኛውን አምላክ ለሚያስደስት ሰው ይሰጥ ዘንድ የመሰብሰብና የማከማቸት ሥራ ሰጥቶታል። ይህም ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,086
3  ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ከሰማይ በታች ለሚከናወን ነገር ሁሉ ጊዜ አለው፦ 2  ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ለመትከል ጊዜ አለው፤ የተተከለውን ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ 3  ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ 4  ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ለዋይታ ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ 5  ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ለማቀፍ ጊዜ አለው፤ ከማቀፍ ለመቆጠብም ጊዜ አለው፤ 6  ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ጠፍቷል ብሎ ለመተውም ጊዜ አለው፤ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ 7  ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ዝም ለማለት ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ 8  ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው። 9  ሠራተኛ ከልፋቱ ሁሉ የሚያገኘው ጥቅም ምንድን ነው? 10  አምላክ የሰው ልጆች እንዲጠመዱበት የሰጣቸውን ሥራ ተመለከትኩ። 11  አምላክ ሁሉንም ነገር በወቅቱ ውብ አድርጎ ሠርቶታል። ደግሞም ዘላለማዊነትን በልባቸው ውስጥ አኑሯል፤ ይሁንና የሰው ልጆች እውነተኛው አምላክ ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ ያከናወነውን ሥራ በምንም ዓይነት መርምረው ሊደርሱበት አይችሉም። 12  ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ የተሻለ ነገር የለም ብዬ ደመደምኩ፤ 13  ደግሞም ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በሚሠራው ሥራ ሁሉ ደስታ ከማግኘት የተሻለ ነገር የለም። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው። 14  እውነተኛው አምላክ የሚሠራው ነገር ሁሉ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖር ተረድቻለሁ። በእሱ ላይ የሚጨመር ምንም ነገር የለም፤ ከእሱም ላይ የሚቀነስ ምንም ነገር የለም። እውነተኛው አምላክ በዚህ መንገድ የሠራው ሰዎች ይፈሩት ዘንድ ነው። 15  አሁን የሚሆነው ነገር ሁሉ ከዚህ በፊት የሆነ ነው፤ ወደፊት የሚመጣው ነገር ከዚህ በፊት የነበረ ነው፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ፣ ሲያሳድዱት የነበረውን አጥብቆ ይሻዋል። 16  ደግሞም ከፀሐይ በታች ይህን አየሁ፦ በፍትሕ ቦታ ክፋት፣ በጽድቅም ቦታ ክፋት ነበር። 17  እኔም በልቤ እንዲህ አልኩ፦ “እውነተኛው አምላክ በጻድቁም ሆነ በኃጢአተኛው ላይ ይፈርዳል፤ ማንኛውም ድርጊትና ማንኛውም ተግባር ጊዜ አለውና።” 18  እኔም በልቤ፣ እውነተኛው አምላክ የሰው ልጆችን ይፈትናቸዋል፤ እንደ እንስሳት መሆናቸውንም ያሳያቸዋል አልኩ፤ 19  የሰው ልጆች ፍጻሜና የእንስሳት ፍጻሜ ተመሳሳይ ነውና፤ የሁሉም ፍጻሜ አንድ ነው። አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው። በመሆኑም ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነውና። 20  ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ። ሁሉም የተገኙት ከአፈር ነው፤ ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳሉ። 21  የሰው ልጆች መንፈስ ወደ ላይ ይወጣ እንደሆነ፣ የእንስሳት መንፈስ ደግሞ ወደ ታች ወደ ምድር ይወርድ እንደሆነ በእርግጠኝነት የሚያውቅ ማን ነው? 22  ሰው በሥራው ደስ ከመሰኘት የተሻለ ነገር እንደሌለው አስተዋልኩ፤ ምክንያቱም ይህ ወሮታው ነው፤ እሱ ካለፈ በኋላ የሚከናወነውን ነገር ተመልሶ እንዲያይ ሊያደርገው የሚችል ማን ነው?
[]
[]
[]
[]
12,087
4  ከፀሐይ በታች የሚፈጸመውን ግፍ ሁሉ በድጋሚ ተመለከትኩ። ግፍ የተፈጸመባቸውን ሰዎች እንባ ተመለከትኩ፤ የሚያጽናናቸውም ሰው አልነበረም። ግፍ የሚፈጽሙባቸውም ሰዎች ኃይል ነበራቸው፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም። 2  እኔም ‘ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱ ሙታን ይሻላሉ’ አልኩ። 3  ደግሞም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው፣ ከፀሐይ በታች የሚፈጸሙትንም አስጨናቂ ድርጊቶች ያላየው ይሻላል። 4  እኔም በሰዎች መካከል ያለው ፉክክር፣ ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉና የተዋጣለት ሥራ እንዲያከናውኑ እንደሚያነሳሳቸው ተመለከትኩ፤ ይህም ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። 5  ሞኝ ሰው ሥጋው እየመነመነ ሲሄድ፣ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል። 6  ብዙ በመልፋትና ነፋስን በማሳደድ ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ ጥቂት እረፍት በማድረግ የሚገኝ አንድ እፍኝ ይሻላል። 7  እኔም ከፀሐይ በታች ያለውን ሌላ ከንቱ ነገር እንደገና ተመለከትኩ፦ 8  ብቸኛ የሆነና ጓደኛ የሌለው ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁንና የሚሠራው ሥራ ማብቂያ የለውም። ዓይኖቹ ሀብትን አይጠግቡም። ሆኖም ‘እንዲህ በትጋት የምሠራውና ራሴን መልካም ነገር የምነፍገው ለማን ብዬ ነው?’ ብሎ ራሱን ይጠይቃል? ይህም ቢሆን ከንቱና አሰልቺ ሥራ ነው። 9  አንድ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል፤ ምክንያቱም ሁለት ሆነው የሚያከናውኑት ሥራ ጥሩ ውጤት ያስገኝላቸዋል። 10  አንዱ ቢወድቅ ሁለተኛው ባልንጀራውን ደግፎ ሊያነሳው ይችላልና። ይሁንና ደግፎ የሚያነሳው ሰው በሌለበት አንዱ ቢወድቅ እንዴት ይሆናል? 11  በተጨማሪም ሁለት ሰዎች አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ ሆኖም አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ እንዴት ሊሞቀው ይችላል? 12  ደግሞም አንድ ሰው ብቻውን ያለን ሰው ሊያሸንፈው ይችል ይሆናል፤ ሁለት ከሆኑ ግን ሊቋቋሙት ይችላሉ። በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም። 13  የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ እንዳያደርግ ማስተዋል ከጎደለው በዕድሜ የገፋ ሞኝ ንጉሥ ይልቅ ድሃ የሆነ ጥበበኛ ልጅ ይሻላል። 14  በእሱ ግዛት ውስጥ ድሃ ሆኖ የተወለደ ቢሆንም ከእስር ቤት ወጥቶ ንጉሥ ይሆናል። 15  እኔም ከፀሐይ በታች የሚመላለሱት ሕያዋን ሁሉ እንዲሁም በንጉሡ ቦታ የሚተካው ልጅ ምን እንደሚገጥማቸው አጤንኩ። 16  ስፍር ቁጥር የሌላቸው ደጋፊዎች ቢኖሩትም በኋላ የሚመጡት ሰዎች በእሱ አይደሰቱም። ይህም ቢሆን ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው።
[]
[]
[]
[]
12,088
5  ወደ እውነተኛው አምላክ ቤት በምትሄድበት ጊዜ ሁሉ አካሄድህን ጠብቅ፤ ሞኞች እንደሚያደርጉት መሥዋዕት ለማቅረብ ከመሄድ ይልቅ ለመስማት መሄድ ይሻላል፤ እነሱ እየሠሩ ያሉት ነገር መጥፎ መሆኑን አያውቁምና። 2  በአፍህ ለመናገር አትጣደፍ፤ ልብህም በእውነተኛው አምላክ ፊት ለመናገር አይቸኩል፤ እውነተኛው አምላክ በሰማያት፣ አንተ ግን በምድር ላይ ነህና። ስለዚህ የምትናገራቸው ቃላት ጥቂት ሊሆኑ ይገባል። 3  ሐሳብ ሲበዛ ለቅዠት ይዳርጋል፤ የቃላት ብዛትም ሞኝን ሰው ለፍላፊ ያደርገዋል። 4  ለአምላክ ስእለት በምትሳልበት ጊዜ ሁሉ ስእለትህን ለመፈጸም አትዘግይ፤ እሱ በሞኞች አይደሰትምና። ስእለትህን ፈጽም። 5  ስእለት ተስለህ ሳትፈጽም ከምትቀር ባትሳል ይሻላል። 6  አፍህ ወደ ኃጢአት እንዲመራህ አትፍቀድ፤ በመልአክም ፊት “ተሳስቼ ነው” አትበል። እውነተኛው አምላክ በተናገርከው ነገር ተቆጥቶ የእጅህን ሥራ ለምን ያጥፋ? 7  ሐሳብ ሲበዛ ቅዠት እንደሚያስከትል፣ የቃላት ብዛት ደግሞ ከንቱነትን ያስከትላልና። አንተ ግን እውነተኛውን አምላክ ፍራ። 8  በምትኖርበት ግዛት ውስጥ በድሃ ላይ ግፍ ሲፈጸም፣ ፍትሕ ሲጓደልና ጽድቅ ወደ ጎን ገሸሽ ሲደረግ ብታይ በዚህ ጉዳይ አትገረም። ይህን ባለሥልጣን፣ ከእሱ ከፍ ያለ ቦታ ያለው ይመለከተዋልና፤ ከእነሱም በላይ የሆኑ ሌሎች አሉ። 9  ከምድሩ የሚገኘውን ትርፍ ሁሉም ይከፋፈሉታል፤ ንጉሡ እንኳ የሚያስፈልገውን ነገር የሚያገኘው ከእርሻው ነው። 10  ብርን የሚወድ ብርን አይጠግብም፤ ሀብትንም የሚወድ በሚያገኘው ገቢ አይረካም። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። 11  መልካም ነገሮች ሲበዙ፣ በላተኛውም ይበዛል። ታዲያ በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ይህ ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? 12  የሚበላው ጥቂትም ሆነ ብዙ፣ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ ባለጸጋ ሰው ያለው ብዙ ሀብት ግን እንቅልፍ ይነሳዋል። 13  ከፀሐይ በታች ያየሁት እጅግ አሳዛኝ የሆነ ነገር አለ፦ ይህም ባለቤቱ በገዛ ራሱ ላይ ጉዳት ለማምጣት ያከማቸው ሀብት ነው። 14  ይህ ሰው አደገኛ ነገር ውስጥ በመግባቱ ሀብቱን አጥቷል፤ ልጅ በሚወልድበት ጊዜም ለልጁ የሚያወርሰው ምንም ነገር አይኖረውም። 15  ሰው ከእናቱ ማህፀን ራቁቱን እንደወጣ ሁሉ፣ ልክ እንደዚያው ተመልሶ ይሄዳል። ደግሞም ከደከመበት ነገር ሁሉ ሊወስደው የሚችል አንዳች ነገር የለም። 16  ይህም ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው፦ ሰው በዚያው በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤ ለነፋስ የሚደክም ሰው የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? 17  ደግሞም በየቀኑ ጨለማ ውስጥ በከፍተኛ ብስጭት፣ በሕመምና በንዴት ይበላል። 18  እኔ ያየሁት መልካምና ተገቢ የሆነ ነገር፣ ሰው እውነተኛው አምላክ በሰጠው አጭር የሕይወት ዘመን ሁሉ መብላቱና መጠጣቱ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በደከመበትና በትጋት ባከናወነው ሥራ ሁሉ ደስታ ማግኘቱ ነው፤ ይህ ብድራቱ ነውና። 19  ደግሞም እውነተኛው አምላክ ለሰው ሀብትና ቁሳዊ ንብረት ብሎም በእነዚህ ነገሮች የመደሰት ችሎታ ሲሰጠው ብድራቱን ተቀብሎ በትጋት በሚያከናውነው ሥራ መደሰት ይገባዋል። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው። 20  እውነተኛው አምላክ ልቡን ደስ በሚያሰኙ ነገሮች እንዲጠመድ ስለሚያደርገው የሚያልፈውን የሕይወት ዘመኑን ፈጽሞ ልብ አይለውም።
[]
[]
[]
[]
12,089
6  ከፀሐይ በታች ያየሁት ሌላ አሳዛኝ ነገር አለ፤ ይህም በሰው ልጆች ላይ በተደጋጋሚ ሲከሰት ይታያል፦ 2  እውነተኛው አምላክ፣ ሰው የሚፈልገውን ነገር ሁሉ እንዳያጣ ሀብትን፣ ቁሳዊ ንብረትንና ክብርን ይሰጠዋል፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ በእነዚህ ነገሮች እንዲደሰት አያስችለውም፤ ከዚህ ይልቅ እንግዳ ሰው ይደሰትባቸዋል። ይህም ከንቱና እጅግ አስከፊ ነገር ነው። 3  አንድ ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፣ ብዙ ዓመት ቢኖርና ለእርጅና ቢበቃ፣ ወደ መቃብር ከመውረዱ በፊት ባሉት መልካም ነገሮች መደሰት ካልቻለ ከእሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ። 4  ከማህፀን የወጣው በከንቱ ነውና፤ በጨለማም ሄዷል፤ ስሙም በጨለማ ተሸፍኗል። 5  ፀሐይን ባያይና ምንም ነገር ባያውቅም እንኳ ከዚያኛው ይልቅ ይሄኛው ይሻላል። 6  ሰው ደስታ ካላገኘ ሁለት ጊዜ ሺህ ዓመት ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? ሁሉም የሚሄደው ወደ አንድ ቦታ አይደለም? 7  የሰው ልጅ በትጋት የሚሠራው ሆዱን ለመሙላት ነው፤ የምግብ ፍላጎቱ ግን ፈጽሞ አይረካም። 8  ታዲያ ጥበበኛው ከሞኙ ሰው የሚሻለው በምንድን ነው? ድሃስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዴት መኖር እንደሚችል ማወቁ የሚያስገኝለት ጥቅም ምንድን ነው? 9  በምኞት ከመቅበዝበዝ ይልቅ ዓይን በሚያየው መደሰት ይሻላል። ይህም ቢሆን ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። 10  አሁን ያለው ነገር ሁሉ አስቀድሞ ስያሜ የተሰጠው ነው፤ ደግሞም የሰው ምንነት የታወቀ ነው፤ ከእሱ ከሚበረታም ጋር ሊከራከር አይችልም። 11  ቃል ሲበዛ ከንቱነት ይበዛል፤ ታዲያ ይህ ለሰው ምን ጥቅም ያስገኛል? 12  ሰው በሕይወት ሳለ ይኸውም ከንቱ በሆነውና እንደ ጥላ በሚያልፈው አጭር የሕይወት ዘመኑ ሊያደርገው የሚችለው የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው? እሱ ካለፈስ በኋላ ከፀሐይ በታች የሚሆነውን ነገር ማን ሊነግረው ይችላል?
[]
[]
[]
[]
12,090
7  ጥሩ ስም ከጥሩ ዘይት፣ የሞትም ቀን ከልደት ቀን ይሻላል። 2  ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ይልቅ ወደ ሐዘን ቤት መሄድ ይሻላል፤ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ሞት ነውና፤ በሕይወት ያለ ሰውም ይህን ልብ ማለት ይገባዋል። 3  ከሳቅ ትካዜ ይሻላል፤ የፊት ሐዘን ለልብ መልካም ነውና። 4  የጥበበኞች ልብ በሐዘን ቤት ነው፤ የሞኞች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። 5  የሞኞችን መዝሙር ከመስማት ይልቅ የጥበበኛን ወቀሳ መስማት ይሻላል። 6  የሞኝ ሳቅ ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ የእሾህ ማገዶ ነው፤ ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። 7  ግፍ ጥበበኛውን ሊያሳብደው ይችላል፤ ጉቦም ልብን ያበላሻል። 8  የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል። ትዕቢተኛ ከመሆን ይልቅ ታጋሽ መሆን ይሻላል። 9  የሞኞች ቁጣ በጉያቸው ውስጥ ስለሆነ ለቁጣ አትቸኩል። 10  “የቀድሞው ዘመን ከአሁኑ ዘመን ለምን ተሻለ?” አትበል፤ እንዲህ ብሎ መጠየቅ ጥበብ አይደለምና። 11  ጥበብ ከውርስ ጋር መልካም ነገር ናት፤ የቀን ብርሃን ለሚያዩ ሰዎችም ጠቃሚ ነች። 12  ገንዘብ ጥበቃ እንደሚያስገኝ ሁሉ ጥበብም ጥበቃ ታስገኛለችና፤ የእውቀት ብልጫ ግን፣ ጥበብ የባለቤቷን ሕይወት ጠብቃ ማቆየት መቻሏ ነው። 13  እውነተኛው አምላክ ያከናወነውን ሥራ ልብ በል፤ እሱ ያጣመመውን ማን ሊያቃና ይችላል? 14  በጥሩ ቀን አንተም ይህን ጥሩነት መልሰህ አንጸባርቅ፤ በአስቸጋሪ ቀን ግን ይሄኛውንም ሆነ ያኛውን ያደረገው አምላክ እንደሆነ አስተውል፤ ይህም የሆነው ሰዎች ወደፊት የሚደርስባቸውን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ እርግጠኞች መሆን እንዳይችሉ ነው። 15  ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመኔ ሁሉንም ነገር አይቻለሁ፤ ጻድቁ ሰው በጽድቁ ሲጠፋ፣ ክፉው ሰው ደግሞ ክፉ ቢሆንም ረጅም ዘመን ሲኖር ተመልክቻለሁ። 16  ከልክ በላይ ጻድቅ አትሁን፤ እጅግም ጥበበኛ መስለህ ለመታየት አትሞክር። በራስህ ላይ ለምን ጥፋት ታመጣለህ? 17  እጅግ ክፉ አትሁን፤ ሞኝም አትሁን። ያለጊዜህ ለምን በሞት ትቀጫለህ? 18  አንደኛውን ማስጠንቀቂያ ሳትተው ሌላኛውንም አጥብቀህ መያዝህ የተሻለ ነው፤ አምላክን የሚፈራ ሰው ሁለቱንም ይሰማልና። 19  ጥበብ ጥበበኛውን ሰው፣ በአንድ ከተማ ካሉ አሥር ብርቱ ሰዎች ይበልጥ ኃያል ታደርገዋለች። 20  ሁልጊዜ ጥሩ ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኃጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለምና። 21  በተጨማሪም ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ሁሉ ትኩረት ሰጥተህ አትከታተል፤ አለዚያ አገልጋይህ ስለ አንተ መጥፎ ነገር ሲናገር ልትሰማ ትችላለህ፤ 22  አንተ ራስህ ስለ ሌሎች ብዙ ጊዜ መጥፎ ነገር እንደተናገርክ ልብህ በሚገባ ያውቃልና። 23  ይህን ሁሉ በጥበብ ፈተንኩ፤ እኔም “ጥበበኛ እሆናለሁ” አልኩ። ይህ ግን ከአቅሜ በላይ ነበር። 24  የተከናወነው ነገር ሁሉ ሊደረስበት የማይቻል ከመሆኑም ሌላ እጅግ ጥልቅ ነው። ማንስ ሊረዳው ይችላል? 25  እኔም ጥበብንና የነገሮችን መንስኤ ለመረዳት፣ ለመመርመርና ለማጥናት እንዲሁም የሞኝነትን ክፋትና የእብደትን ቂልነት ለመገንዘብ ልቤን አዘነበልኩ። 26  ከዚያም የሚከተለውን ነገር ተገነዘብኩ፦ እንደ አዳኝ ወጥመድ የሆነች ደግሞም እንደ መረብ ያለ ልብ፣ እንደ እስር ቤት ሰንሰለትም ያሉ እጆች ያሏት ሴት ከሞት እጅግ የመረረች ናት። እውነተኛውን አምላክ የሚያስደስት ሰው ከእሷ ያመልጣል፤ ኃጢአተኛ ግን በእሷ ይያዛል። 27  ሰብሳቢው እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ መርምሬ ያገኘሁት ነገር ይህ ነው። አንድ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ እያንዳንዱን ነገር በሚገባ አጠናሁ፤ 28  ሆኖም ስፈልገው የነበረውን ነገር ላገኘው አልቻልኩም። ከሺህ መካከል አንድ ወንድ አገኘሁ፤ ከእነዚህ ሁሉ መካከል ግን አንዲትም ሴት አላገኘሁም። 29  ይህን አንድ ነገር ብቻ አገኘሁ፦ እውነተኛው አምላክ የሰውን ልጆች ቅን አድርጎ ሠራቸው፤ እነሱ ግን ሌላ ብዙ ዕቅድ አወጡ።”
[]
[]
[]
[]
12,091
8  እንደ ጥበበኛው ሰው ያለ ማን ነው? የአንድን ችግር መፍትሔ የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱ እንዲበራ እንዲሁም ኮስታራ ፊቱ እንዲፈታ ታደርጋለች። 2  እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “በአምላክ ፊት በገባኸው መሐላ የተነሳ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር። 3  ከንጉሡ ፊት ለመውጣት አትቸኩል። መጥፎ የሆነውን ነገር ሁሉ አትደግፍ፤ እሱ ደስ ያሰኘውን ሁሉ ማድረግ ይችላልና፤ 4  ምክንያቱም የንጉሥ ቃል የማይሻር ነው፤ ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሊለው የሚችል ማን ነው?” 5  ትእዛዛትን የሚጠብቅ ሰው ጉዳት አይደርስበትም፤ ጥበበኛ ልብም ትክክለኛውን ጊዜና አሠራር ያውቃል። 6  የሰው ልጆች ብዙ መከራ ቢኖርባቸውም ማንኛውም ጉዳይ ትክክለኛ ጊዜና አሠራር አለው። 7  ወደፊት የሚሆነውን ነገር የሚያውቅ ሰው ስለሌለ ይህ እንዴት እንደሚሆን ሊነግረው የሚችል ማን ነው? 8  በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ወይም መንፈስን መግታት የሚችል ሰው እንደሌለ ሁሉ በሞት ቀን ላይም ሥልጣን ያለው የለም። በጦርነት ጊዜ ከግዳጅ የሚሰናበት እንደሌለ ሁሉ ክፋትም ክፋት የመሥራት ልማድ ያላቸውን ሰዎች እንዲያመልጡ ዕድል አይሰጣቸውም። 9  ይህን ሁሉ የተገነዘብኩት ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ በልቤ ከመረመርኩ በኋላ ነው። በዚህ ሁሉ ወቅት ሰው ሰውን የገዛው ለጉዳቱ ነው። 10  ደግሞም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይገቡና ይወጡ የነበሩት ክፉዎች ሲቀበሩ አይቻለሁ፤ ይሁንና ይህን ባደረጉበት ከተማ ወዲያው ተረሱ። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። 11  በክፉ ሥራ ላይ በአፋጣኝ ፍርድ ስለማይሰጥ የሰው ልጆች ልብ ክፉ ነገር ለማድረግ ተደፋፈረ። 12  ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ መጥፎ ነገር እየሠራ ረጅም ዘመን ቢኖር እንኳ እውነተኛውን አምላክ የሚፈሩ ሰዎች አምላክን በመፍራታቸው የኋላ ኋላ መልካም እንደሚሆንላቸው ተረድቻለሁ። 13  ክፉ ሰው ግን አምላክን ስለማይፈራ የኋላ ኋላ መልካም አይሆንለትም፤ እንደ ጥላ የሆነውን የሕይወት ዘመኑንም ማራዘም አይችልም። 14  በምድር ላይ የሚፈጸም አንድ ከንቱ ነገር አለ፦ ክፉ እንደሠሩ ተደርገው የሚታዩ ጻድቃን አሉ፤ ጽድቅ እንደሠሩ ተደርገው የሚታዩ ክፉ ሰዎችም አሉ። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው እላለሁ። 15  በመሆኑም ደስታ መልካም ነው አልኩ፤ ምክንያቱም ለሰው ከፀሐይ በታች ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ከመደሰት የተሻለ ነገር የለም፤ ከፀሐይ በታች እውነተኛው አምላክ በሚሰጠው የሕይወት ዘመን በትጋት ሲሠራ ይህ ደስታ ሊርቀው አይገባም። 16  ቀንም ሆነ ሌሊት እንቅልፍ በዓይኔ ሳይዞር ጥበብን ለማግኘትና በምድር ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ለማየት ከፍተኛ ጥረት አደረግኩ። 17  ከዚያም የእውነተኛውን አምላክ ሥራ ሁሉ አጤንኩ፤ የሰው ልጆች ከፀሐይ በታች የሚሆነውን ነገር ሁሉ መረዳት እንደማይችሉም ተገነዘብኩ። ሰዎች የቱንም ያህል ጥረት ቢያደርጉ ሊረዱት አይችሉም። ይህን ለማወቅ የሚያስችል ጥበብ አለን ቢሉም እንኳ ሊረዱት አይችሉም።
[]
[]
[]
[]
12,092
9  ስለዚህ ይህን ሁሉ በጥሞና ተመልክቼ ጻድቃንም ሆኑ ጥበበኞች እንዲሁም የሚያከናውኗቸው ሥራዎች በእውነተኛው አምላክ እጅ ናቸው ብዬ ደመደምኩ። ሰዎች ከእነሱ በፊት በነበረው ዘመን የታየውን ፍቅርና ጥላቻ አያውቁም። 2  ጻድቁና ክፉው ሰው፣ ጥሩው ሰውም ሆነ ንጹሕ የሆነውና ንጹሕ ያልሆነው ሰው፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡትም ሆኑ የማያቀርቡት ፍጻሜያቸው ተመሳሳይ ነው። ጥሩው ሰው ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ነው፤ የሚምለውም ሰው፣ ላለመማል ከሚጠነቀቀው ሰው ጋር አንድ ነው። 3  ከፀሐይ በታች የሚፈጸመው አስጨናቂ ነገር ይህ ነው፦ የሁሉም ፍጻሜ አንድ ስለሆነ የሰዎችም ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወታቸው ዘመን በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ ከዚያም ይሞታሉ! 4  በሕያዋን መካከል ያለ ማንኛውም ሰው ተስፋ አለው፤ ምክንያቱም በሕይወት ያለ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል። 5  ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም፤ ከእንግዲህም የሚያገኙት ብድራት የለም፤ ምክንያቱም የሚታወሱበት ነገር ሁሉ ተረስቷል። 6  በተጨማሪም ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸውና ቅናታቸው ጠፍቷል፤ ከዚህም በኋላ ከፀሐይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ ፈጽሞ ድርሻ አይኖራቸውም። 7  ሂድ፣ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ልብህም ደስ ብሎት ወይንህን ጠጣ፤ እውነተኛው አምላክ በሥራህ ደስ ተሰኝቷልና። 8  ልብስህ ምንጊዜም ነጭ ይሁን፤ ራስህንም ዘይት መቀባት አትዘንጋ። 9  አምላክ ከፀሐይ በታች በሰጠህ ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመንህ ሁሉ፣ ከንቱ በሆነውም ዕድሜህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ተደስተህ ኑር፤ በሕይወትህ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በምትደክምበትና በትጋት በምታከናውነው ሥራ ዕጣ ፋንታህ ይህ ነውና። 10  እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ አከናውን፤ አንተ በምትሄድበት በመቃብር ሥራም ሆነ ዕቅድ፣ እውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና። 11  እኔም ከፀሐይ በታች ሌላ ነገር ተመለከትኩ፤ ፈጣኖች በውድድር ሁልጊዜ አያሸንፉም፤ ኃያላን በውጊያ ሁልጊዜ ድል አይቀናቸውም፤ ጥበበኞች ሁልጊዜ ምግብ አያገኙም፤ አስተዋዮች ሁልጊዜ ሀብት አያገኙም፤ እውቀት ያላቸው ሰዎችም ሁልጊዜ ስኬታማ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ሁሉም መጥፎ ጊዜና ያልተጠበቁ ክስተቶች ያጋጥሟቸዋል። 12  ሰው የራሱን ጊዜ አያውቅምና። ዓሣዎች በአደገኛ መረብ እንደሚጠመዱና ወፎች በወጥመድ እንደሚያዙ፣ የሰው ልጆችም ድንገት በሚያጋጥማቸው ክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ። 13  ደግሞም ከፀሐይ በታች ስላለች ጥበብ ይህን አስተዋልኩ፤ በእሷም እጅግ ተገረምኩ፦ 14  ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኃያል ንጉሥም መጥቶ ከበባት፤ በዙሪያዋም ትልቅ ቅጥር ገነባ። 15  በከተማዋ ውስጥ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድሃ ሰው ነበር፤ እሱም በጥበቡ ከተማዋን አዳናት። ሆኖም ይህን ድሃ ማንም ሰው አላስታወሰውም። 16  እኔም ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ ‘ጥበብ ከኃይል ትበልጣለች፤ ይሁንና የድሃው ጥበብ ተናቀ፤ የተናገረውም ነገር ሰሚ አላገኘም።’ 17  ሞኞችን የሚገዛ ሰው ከሚያሰማው ጩኸት ይልቅ ጥበበኞች በዝግታ የሚናገሩትን ቃል መስማት ይሻላል። 18  ከጦር መሣሪያ ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካም ነገርን ሊያጠፋ ይችላል።
[]
[]
[]
[]
12,093
1  ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጠው የሰለሞን መዝሙር፦ 2  “በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ፤የፍቅር መግለጫዎችህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛሉና። 3  የዘይትህ መዓዛ ደስ ይላል። ስምህ ጥሩ መዓዛ እንዳለው የሚፈስ ዘይት ነው። ቆነጃጅት የሚወዱህ ለዚህ ነው። 4  ይዘኸኝ ሂድ፤ አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኞቹ አስገብቶኛል! በአንተ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ። ከወይን ጠጅ ይልቅ የፍቅር መግለጫዎችህን እናወድስ። አንተን መውደዳቸው ተገቢ ነው። 5  የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ እኔ ጥቁር ብሆንም ውብ ነኝ፤እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣ እንደ ሰለሞን ድንኳኖችም ነኝ። 6  ጥቁር ስለሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትዩኝ፤ፀሐይ ፊቴን አክስሎታልና። ወንድሞቼ በጣም ተቆጡኝ፤የወይን እርሻዎች ጠባቂ አደረጉኝ፤የገዛ ራሴን የወይን እርሻ ግን መጠበቅ አልቻልኩም። 7  “እጅግ የምወድህ ፍቅረኛዬ፣መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣እኩለ ቀንም ላይ የት እንደምታሳርፍ ንገረኝ። በጓደኞችህ መንጎች መካከልበመሸፈኛ ፊቷን ተሸፋፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?” 8  “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ የማታውቂ ከሆነየመንጋውን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።” 9  “ፍቅሬ ሆይ፣ የፈርዖንን ሠረገሎች በሚጎትቱ ፈረሶች መካከል እንዳለች ባዝራ ውብ ነሽ። 10  ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፤አንገትሽም በጨሌ ሐብል አጊጧል። 11  በብር ፈርጥ የተንቆጠቆጡየወርቅ ጌጦች እንሠራልሻለን።” 12  “ንጉሡ ክብ ጠረጴዛው ጋ ተቀምጦ ሳለየሽቶዬ መዓዛ አካባቢውን አወደው። 13  ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ ነው፤በጡቶቼ መካከል ያድራል። 14  ውዴ በኤንገዲ የወይን እርሻዎች መካከልእጅብ ብሎ እንደበቀለ የሂና ተክል ነው።” 15  “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው።” 16  “ውዴ ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ውብ ነህ፤ ደግሞም ደስ ትላለህ። አልጋችን በለምለም ቅጠል መካከል ነው። 17  የቤታችን ተሸካሚዎች አርዘ ሊባኖሶች፣ጣሪያችንም የጥድ ዛፎች ናቸው።
[]
[]
[]
[]
12,094
2  “እኔ ግን በባሕር ዳርቻ ላይ የሚበቅል የሳሮን አበባ ነኝ፤የሸለቆም አበባ ነኝ።” 2  “ፍቅሬ በሴቶች መካከል ስትታይበእሾህ መካከል እንዳለ አበባ ናት።” 3  “ውዴ በወንዶች መካከል ሲታይበዱር ዛፎች መካከል እንዳለ የፖም ዛፍ ነው። በጥላው ሥር ለመቀመጥ እጅግ እጓጓለሁ፤ፍሬውም ለአፌ ጣፋጭ ነው። 4  ወደ ግብዣ ቤት ወሰደኝ፤የፍቅር ዓርማውንም በእኔ ላይ አውለበለበ። 5  በዘቢብ ቂጣ ኃይሌን አድሱልኝ፤በፖም አበረታቱኝ፤በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና። 6  ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ቀኝ እጁም አቅፎኛል። 7  የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ፣ በሜዳ ፍየሎችና በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ። 8  እነሆ፣ ውዴ ተራሮቹን እየወጣና በኮረብቶቹ ላይ እየዘለለ ሲመጣድምፁ ይሰማኛል! 9  ውዴ፣ የሜዳ ፍየል ወይም የአጋዘን ግልገል ይመስላል። በመስኮት በኩል ትኩር ብሎ እየተመለከተ፣በፍርግርጉ በኩል አጮልቆ እያየከግድግዳችን ጀርባ ቆሟል። 10  ውዴ እንዲህ አለኝ፦ ‘ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽ፤የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ። 11  እነሆ፣ ክረምቱ አልፏል። ዝናቡ ቆሟል፤ ደግሞም ጠፍቷል። 12  በምድሩ ላይ አበቦች አብበዋል፤ተክሎች የሚገረዙበት ጊዜ ደርሷል፤በምድራችንም ላይ የዋኖስ ዝማሬ ተሰምቷል። 13  የበለስ ዛፏ መጀመሪያ ላይ ያፈራቻቸው ፍሬዎች በስለዋል፤የወይን ተክሎቹም አብበው መዓዛቸውን ሰጥተዋል። ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽና ነይ፤የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ። 14  በዓለቶች መሃል በሚገኝ መሸሸጊያ፣በገደላማ ስፍራ ባለ ሰዋራ ቦታ ያለሽ ርግቤ ሆይ፣እስቲ ልይሽ፤ ድምፅሽንም ልስማው፤ድምፅሽ ማራኪ፣ ቁመናሽም ያማረ ነውና።’” 15  “ቀበሮዎቹን ይኸውም የወይን እርሻዎቹን የሚያበላሹትንትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን፤የወይን እርሻችን አብቧልና።” 16  “ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእሱ ነኝ። መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው። 17  የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊትውዴ ሆይ፣ እንደ ሜዳ ፍየልወይም በመካከላችን ባሉት ተራሮች ላይ እንደሚገኝ የአጋዘን ግልገል በፍጥነት ተመለስ።
[]
[]
[]
[]
12,095
3  “ሌሊት በአልጋዬ ላይ ሆኜየምወደውን ሰው ለማግኘት ተመኘሁ። ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም። 2  ተነስቼ በከተማዋ ውስጥ እዘዋወራለሁ፤የምወደውን ሰውእስቲ በጎዳናዎቹና በአደባባዮቹ ልፈልገው። ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም። 3  በከተማዋ ውስጥ የሚዘዋወሩት ጠባቂዎች አገኙኝ። እኔም ‘የምወደውን ሰው አይታችሁታል?’ ብዬ ጠየቅኳቸው። 4  ከእነሱ ገና እልፍ እንዳልኩየምወደውን ሰው አገኘሁት። አጥብቄም ያዝኩት፤ወደ እናቴ ቤት፣ ወደ ፀነሰችኝም ሴት እልፍኝእስካስገባው ድረስ አለቀኩትም። 5  የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ በሜዳ ፍየሎችና በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።” 6  “በከርቤና በነጭ ዕጣን፣ጥሩ መዓዛ ባላቸውም የነጋዴ ቅመማ ቅመሞች ታውዶ፣እንደ ጭስ ዓምድ ከምድረ በዳ እየመጣ ያለው ይህ ነገር ምንድን ነው?” 7  “እነሆ፣ ይህ የሰለሞን ድንክ አልጋ ነው። ከእስራኤል ኃያላን የተውጣጡስልሳ ኃያላን አጅበውታል፤ 8  ሁሉም ሰይፍ የታጠቁናበውጊያ የሠለጠኑ ናቸው፤እያንዳንዳቸውም በሌሊት የሚያጋጥሙ አስፈሪ ነገሮችን ለመከላከልሰይፋቸውን ወገባቸው ላይ ታጥቀዋል።” 9  “ይህ፣ ንጉሥ ሰለሞን ከሊባኖስ እንጨትለራሱ ያሠራው የንጉሥ ድንክ አልጋ ነው። 10  ዓምዶቹን የሠራው ከብር፣መደገፊያዎቹን ደግሞ ከወርቅ ነው። መቀመጫው በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው፤ውስጡንም የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆችበፍቅር ተነሳስተው ለብጠውታል።” 11  “እናንተ የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፣ወጥታችሁ ንጉሥ ሰለሞንን ተመልከቱ፤በሠርጉ ዕለት፣ልቡ ሐሴት ባደረገበት በዚያ ቀን፣እናቱ የሠራችለትን የሠርግ አክሊል ደፍቷል።”
[]
[]
[]
[]
12,096
4  “ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው። ፀጉርሽ ከጊልያድ ተራሮችእየተግተለተለ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው። 2  ጥርሶችሽ ገና ተሸልተውናታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ የበግ መንጋ ናቸው፤ደግሞም ከመካከላቸው ግልገሉን ያጣ የለም። 3  ከንፈሮችሽ እንደ ደማቅ ቀይ ፈትል ናቸው፤ንግግርሽም አስደሳች ነው። በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽየተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። 4  አንገትሽ አንድ ሺህ ጋሻዎች፣ይኸውም ኃያላን ሰዎች የሚይዟቸው ክብ ጋሻዎች ሁሉ የተንጠለጠሉበትንናበንብርብር ድንጋዮች የተገነባውንየዳዊት ማማ ይመስላል። 5  ሁለቱ ጡቶችሽበአበቦች መካከል የተሰማሩ፣መንታ የሆኑ ሁለት የሜዳ ፍየል ግልገሎችን ይመስላሉ።” 6  “የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊትወደ ከርቤው ተራራናወደ ነጭ ዕጣኑ ኮረብታ እሄዳለሁ።” 7  “ፍቅሬ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤እንከንም የለብሽም። 8  ሙሽራዬ ሆይ፣ ተያይዘን ከሊባኖስ እንሂድ፤አዎ፣ ከሊባኖስ አብረን እንሂድ። ከአማና አናት፣ከሰኒር ጫፍ፣ ከሄርሞን አናት፣ከአንበሳ ዋሻዎች፣ ከነብር ተራሮች ውረጂ። 9  እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ ልቤን ማርከሽዋል፤በአንድ አፍታ እይታሽ፣ከሐብልሽ ዶቃዎች በአንዱ ልቤን ማርከሽዋል። 10  እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ የፍቅር መግለጫዎችሽ እንዴት ደስ ያሰኛሉ! የፍቅር መግለጫሽ ከወይን ጠጅ፣የሽቶሽም መዓዛ ከየትኛውም ዓይነት ቅመም እጅግ ይበልጣል! 11  ሙሽራዬ ሆይ፣ ከንፈሮችሽ የማር እንጀራ ወለላ ያንጠባጥባሉ። ከምላስሽ ሥር ማርና ወተት ይፈልቃል፤የልብሶችሽም ጠረን እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው። 12  እህቴ፣ ሙሽራዬ፣ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣አዎ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣ የታሸገም ምንጭ ናት። 13  ቡቃያሽ ሮማንና ምርጥ ፍራፍሬዎችደግሞም የሂና እና የናርዶስ ተክሎች የበቀሉበት ገነት ነው፤ 14  በተጨማሪም ናርዶስ፣ ሳፍሮን፣ ጠጅ ሣር፣ ቀረፋ፣ነጭ ዕጣን የሚገኝባቸው የተለያዩ ዛፎች፣ ከርቤ፣ እሬትናሁሉም ዓይነት ምርጥ ሽቶዎች ያሉበት ገነት ነው። 15  አንቺ በአትክልት ቦታ ያለ ምንጭ፣ ንጹሕ ውኃ የሚገኝበት ጉድጓድናከሊባኖስ የሚፈስሱ ጅረቶች ነሽ። 16  የሰሜን ነፋስ ሆይ፣ ንቃ፤የደቡብ ነፋስ ሆይ፣ ና። በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ። መዓዛውም አካባቢውን ያውደው።” “ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባናምርጥ የሆኑትን ፍራፍሬዎች ይብላ።”
[]
[]
[]
[]
12,097
5  “እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ወደ አትክልት ቦታዬ ገብቻለሁ። ከርቤዬንና ቅመሜን ወስጃለሁ። የማር እንጀራዬንና ወለላውን በልቻለሁ፤የወይን ጠጄንና ወተቴን ጠጥቻለሁ።” “ውድ ጓደኞቼ፣ ብሉ! ጠጥታችሁም በፍቅር መግለጫዎች ስከሩ!” 2  “እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል። ውዴ በሩን ሲያንኳኳ ይሰማኛል!” “እህቴ ሆይ፣ የእኔ ፍቅር፣እንከን የለሽ ርግቤ ሆይ፣ ክፈቺልኝ! ራሴ በጤዛ፣ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት ርሷል።” 3  “‘ልብሴን አውልቄአለሁ። መልሼ መልበስ ሊኖርብኝ ነው? እግሬን ታጥቤአለሁ። እንደገና ላቆሽሸው ነው?’ 4  ውዴ እጁን ከበሩ ቀዳዳ መለሰ፤ለእሱ ያለኝ ስሜትም ተነሳሳ። 5  እኔም ለውዴ በሩን ለመክፈት ተነሳሁ፤የመዝጊያው እጀታ ላይእጆቼ ከርቤ፣ጣቶቼም የከርቤ ፈሳሽ አንጠባጠቡ። 6  ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፤ውዴ ግን በዚያ አልነበረም፤ ሄዶ ነበር። በመሄዱም ተስፋ ቆረጥኩ። ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም። ጠራሁት፤ እሱ ግን አልመለሰልኝም። 7  ከተማዋን እየተዘዋወሩ የሚጠብቁት ሰዎች አገኙኝ። መቱኝ፤ አቆሰሉኝ። የቅጥሩ ጠባቂዎች ነጠላዬን ገፈፉኝ። 8  የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ውዴን ካገኛችሁት በፍቅሩ ተይዤ መታመሜንእንድትነግሩት አምላችኋለሁ።” 9  “አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው? እንዲህ ያለ መሐላ ያስገባሽን፣ለመሆኑ ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው?” 10  “ውዴ በጣም ቆንጆና ቀይ ነው፤በአሥር ሺህ ሰዎች መካከል እንኳ ጎልቶ ይታያል። 11  ራሱ እንደ ወርቅ፣ አዎ እንደጠራ ወርቅ ነው። ፀጉሩ እንደሚወዛወዝ የዘንባባ ዝንጣፊ ነው፤እንደ ቁራም ጥቁር ነው። 12  ዓይኖቹ በውኃ ጅረት አጠገብ እንዳሉ፣ጢም ብሎ በሞላ ኩሬ ዳርቻ ሆነውበወተት እንደሚታጠቡ ርግቦች ናቸው። 13  ጉንጮቹ የቅመማ ቅመም መደብ፣ጥሩ መዓዛ ያላቸው ዕፀዋት ክምር ይመስላሉ። ከንፈሮቹ ፈሳሽ ከርቤ የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው። 14  የእጆቹ ጣቶች ወርቅ፣ የጣቶቹም ጫፎች ክርስቲሎቤ ናቸው። ሆዱ በሰንፔር የተሸፈነ የተወለወለ የዝሆን ጥርስ ነው። 15  እግሮቹ ከምርጥ ወርቅ በተሠሩ መሰኪያዎች ላይ የቆሙ የእብነ በረድ ዓምዶች ናቸው። መልኩ እንደ ሊባኖስ ያማረ ነው፤ እንደ አርዘ ሊባኖስም አቻ የለውም። 16  አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፤ሁለመናውም ደስ ያሰኛል። የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ውዴ ይህ ነው፤ ፍቅሬ እንዲህ ያለ ነው።”
[]
[]
[]
[]
12,098
6  “ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ውድሽ የት ሄደ? ለመሆኑ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው? አብረንሽ እንፈልገው።” 2  “ውዴ መንጋውን በአትክልት ቦታዎቹ መካከል ለማሰማራትናአበቦችን ለመቅጠፍየቅመማ ቅመም ተክሎች መደብ ወዳለበትወደ አትክልት ቦታው ወርዷል። 3  እኔ የውዴ ነኝ፤ውዴም የእኔ ነው። እሱ መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።” 4  “ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ እንደ ቲርጻ ቆንጆ ነሽ፤እንደ ኢየሩሳሌምም ውብ ነሽ፤በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ ታምሪያለሽ። 5  ስሜቴን አውከውታልና፣ዓይኖችሽን ከእኔ ላይ አንሺ። ፀጉርሽ ከጊልያድ እየተግተለተለ እንደሚወርድየፍየል መንጋ ነው። 6  ጥርሶችሽ ታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱየበግ መንጋ ናቸው፤ከመካከላቸውም ግልገሉን ያጣ የለም። 7  በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽየተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። 8  እርግጥ 60 ንግሥቶች፣80 ቁባቶችናቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ቆነጃጅት ሊኖሩ ይችላሉ። 9  እንከን የሌለባት ርግቤ ግን አንድ ብቻ ናት። እሷ ለእናቷ ብርቅዬ ልጅ ናት። በወለደቻት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ናት። ሴቶች ልጆች አይተዋት ‘የታደልሽ ነሽ’ ይሏታል፤ንግሥቶችና ቁባቶችም ያወድሷታል። 10  ‘እንደ ማለዳ ወጋገን የምታበራ፣እንደ ሙሉ ጨረቃ ውብ የሆነች፣እንደ ፀሐይ ብርሃን የጠራች፣በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ የምታምረው ይህች ሴት ማን ናት?’” 11  “በሸለቆው ውስጥ ያቆጠቆጡትን ተክሎች ለማየት፣ደግሞም ወይኑ ለምልሞ፣የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለመመልከትየገውዝ ዛፎች ወዳሉበት ወደ አትክልት ቦታው ወረድኩ። 12  ምንም ሳይታወቀኝምኞቴ የተከበሩ ወገኖቼየያዟቸው ሠረገሎች ወዳሉበት ወሰደኝ።” 13  “አንቺ ሱላማዊት፣ ተመለሺ፤ ተመለሺ! እናይሽ ዘንድተመለሺ፤ ተመለሺ!” “በሱላማዊቷ ላይ የምታፈጡት ለምንድን ነው?” “እሷ የመሃናይምን ጭፈራ ትመስላለች!”
[]
[]
[]
[]
12,099
7  “አንቺ የተከበርሽ ልጃገረድ ሆይ፣እግሮችሽ በነጠላ ጫማሽ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ! የዳሌዎችሽ ቅርጽየእጅ ባለሙያ የተጠበበባቸው ጌጦች ይመስላሉ። 2  እምብርትሽ እንደ ክብ ሳህን ነው። የተደባለቀ ወይን ጠጅ ከእሱ አይታጣ። ሆድሽ ዙሪያውን በአበቦች እንደታጠረየስንዴ ክምር ነው። 3  ሁለቱ ጡቶችሽ ሁለት ግልገሎችን፣የሜዳ ፍየል መንታዎችን ይመስላሉ። 4  አንገትሽ በዝሆን ጥርስ የተሠራ ማማ ይመስላል። ዓይኖችሽ በባትራቢም በር አጠገብ እንዳሉትየሃሽቦን ኩሬዎች ናቸው። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከትየሊባኖስ ማማ ነው። 5  ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ አክሊል ሆኖልሻል፤ፀጉርሽ ሐምራዊ ሱፍ ይመስላል። ንጉሡ በዘንፋላው ፀጉርሽ ተማርኳል። 6  አንቺ የተወደድሽ ልጃገረድ ሆይ፣ ምንኛ ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!በጣም ከሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትማርኪያለሽ! 7  ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤ጡቶችሽ ደግሞ የቴምር ዘለላ ይመስላሉ። 8  እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘የቴምር ዘለላዎቹን መያዝ እንድችልዛፉ ላይ እወጣለሁ።’ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ይሁኑ፤የትንፋሽሽ መዓዛ እንደ ፖም ሽታ ይሁን፤ 9  አፍሽም እንደ ምርጥ ወይን ጠጅ ይሁን።” “ይህ የወይን ጠጅ ለውዴ እየተንቆረቆረ ይውረድ፤በተኙ ሰዎች ከንፈር በቀስታ ይፍሰስ። 10  እኔ የውዴ ነኝ፤እሱም የሚመኘው እኔን ነው። 11  ውዴ ሆይ፣ ና፤ወደ መስክ እንሂድ፤በሂና ተክሎች መካከል እንቀመጥ። 12  ወይኑ ለምልሞ፣አበባው ፈክቶ፣የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለማየትበማለዳ ተነስተን ወደ ወይን እርሻዎቹ እንሂድ። እኔም በዚያ ለአንተ ያለኝን ፍቅር እገልጽልሃለሁ። 13  የዱዳይም ፍሬዎቹ መዓዛቸውን ሰጥተዋል፤በደጆቻችንም ሁሉም ዓይነት ምርጥ ፍሬዎች አሉ። ውዴ ሆይ፣ አዲሶቹንም ሆነ በፊት የተቀጠፉትን ፍሬዎችለአንተ አስቀምጬልሃለሁ።
[]
[]
[]
[]
12,100
8  “ምነው አንተ፣ የእናቴን ጡት እንደጠባ፣እንደ ወንድሜ በሆንክ! እንዲህ ቢሆን ኖሮ ውጭ ሳገኝህ በሳምኩህ ነበር፤ማንም ባልናቀኝ ነበር። 2  እኔም ወዳስተማረችኝወደ እናቴ ቤት በወሰድኩህናወደዚያ ባስገባሁህ ነበር። ትጠጣው ዘንድ ቅመም የተጨመረበት ወይን ጠጅናየሮማን ጭማቂ በሰጠሁህ ነበር። 3  ግራ እጁን በተንተራስኩ፣ቀኝ እጁም ባቀፈኝ ነበር። 4  የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ አምላችኋለሁ።” 5  “ውዷን ደገፍ ብላከምድረ በዳ የምትመጣው ይህች ማን ናት?” “ከፖም ዛፍ ሥር ቀሰቀስኩህ። በዚያ እናትህ አንተን ለመውለድ አማጠች። በዚያም ወላጅ እናትህ ምጥ ይዟት ነበር። 6  እንደ ማኅተም በልብህ፣እንደ ማኅተም በክንድህ አስቀምጠኝ፤ፍቅር እንደ ሞት የበረታ ነውና፤ታማኝነትም እንደ መቃብር ጽኑ ነው፤ የፍቅር ወላፈን የእሳት ወላፈን ነው፤ የያህም ነበልባል ነው። 7  ጎርፍ ፍቅርን ሊያጠፋው አይችልም፤ወንዞችም ጠራርገው ሊወስዱት አይችሉም። አንድ ሰው ለፍቅር ሲል የቤቱን ሀብት ሁሉ ለመስጠት ቢያቀርብሰዎች በጣም ይንቁበታል።” 8  “ገና ጡት ያላወጣችትንሽ እህት አለችን። እሷን በሚጠይቁን ቀንለእህታችን ምን ብናደርግ ይሻላል?” 9  “እሷ ቅጥር ብትሆንበላይዋ ላይ የብር ጉልላት እንሠራለን፤በር ብትሆን ግንከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ ሳንቃ እናሽጋታለን።” 10  “እኔ ቅጥር ነኝ፤ጡቶቼም እንደ ማማ ናቸው። በእሱም ፊትሰላም እንዳገኘች ሴት ሆንኩ። 11  ሰለሞን በበዓልሃሞን የወይን እርሻ ነበረው። እሱም የወይን እርሻውን ለጠባቂዎች በአደራ ሰጠ። እያንዳንዳቸውም ለሚያገኙት ፍሬ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ያመጡ ነበር። 12  የራሴ የሆነ የወይን እርሻ አለኝ። ሰለሞን ሆይ፣ አንድ ሺው የብር ሰቅል የአንተ ነው፤ሁለት መቶው ደግሞ ፍሬውን ለሚጠብቁት ነው።” 13  “አንቺ በአትክልት ቦታዎቹ የምትኖሪ ሆይ፣ጓደኞቼ ድምፅሽን ያዳምጣሉ። እስቲ እኔም ልስማው።” 14  “ውዴ ሆይ፣ ቶሎ ና፤እንደ ሜዳ ፍየልወይም የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራሮች ላይ እንዳለየአጋዘን ግልገል ፍጠን።”
[]
[]
[]
[]