context
stringclasses
367 values
question
stringlengths
10
114
answer
stringlengths
1
90
answer_start
int64
0
3.22k
ሚያዝያ ፲፰ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፳፰ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፯ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኙት ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው አንድ አገር መሠረቱ። ይሄም የተዋሕዶ አገር ከሁለቱም ስም በተውጣጣው አዲሱ ስም ታንዛኒያ ተብሎ ተሰየመ። ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - የኡዝቤኪስታን ርዕሰ ከተማ ታሽኬንት በትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ክስተት ስትወድም ሰብ ስምንት ሺ መኖሪያ ቤቶች በመጥፋታቸው ከሦስት መቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎቿ መኖሪያ ቢስ ሆነዋል። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በሼክ ሞሀመድ ማህሙድ ኤል ሳዋ የተመራ የሳዑዲ አረቢያ ልዑካን ቡድን ለአጭር ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ከደርግ በተላለፈ ትእዛዝ መሠረት፣ የፖሊስ አለቆች፤ የቀድሞ ሚኒስትሮችና ባለ ሥልጣናት ታሠሩ። ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ የቸርኖቢል የኑክሊዬር መብራት ኃይል ማምረቻ ክፉ አደጋ ተከሰተ። የዚህን አደጋ ክስተት የስካንዲናቪያ አገሮች ይፋ እስካደረጉት ድረስ የሶቪዬት ሕብረት ባለ ሥልጣናት ደፋፍነውት ነበር።
የሳዑዲ አረቢያ ልዑካን ቡድን በሼክ ሞሀመድ ማህሙድ ኤል ሳዋ እየተመራ ለአጭር ጉብኝት በስንት ዓመተ ምህረት አዲስ አበባ ገባ?
፲፱፻፷፭ ዓ/ም
437
ሳዑዲ አረቢያ የሣውዲ አረቢያ ግዛት 28.7 ሚሊዬን የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡ ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ ኤዥያ ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡ የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡ ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡ የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡ አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡ የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በ1932 እ.ኤ.አ. በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡ ኢብን ሣኡድ ቀድሞ በ1894 ዓም (1902 እ.ኤ.አ.) ከብሪታንያ ግዛት ከኩወይት ዘምቶ ሪያድን ያዘ። ኢብን ሳኡድ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስልምና ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ የነዳጅ አምራች ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ሀይድሮ ካርቦን ክምችት ካላቸው አገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሀገሪቱ ባለው የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛ ክምችት ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ እና የህዝብ ቁጥር እድገት ከያዙ ሀገራት ጋር ትመደባለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ G-2ዐ ተብለው ከሚታወቁት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የሀገራት ቡድን ውስጥ ብቸኛዋ የአረቡ ዓለም አገር ናት፡፡ ይህም ቢሆን የሣውዲ ኢኮኖሚ በአብዛኛው በአንድ ቡድን የተያዘ ነው፡፡ የሣውዲ አረብያን ፈላጭ ቆራጭ በሆነ የመንግስት ስርዓት በመመራት “ነጻነት የለም” በሚል “ነጻነት ቤት” በሚል በሚታወቀው ድርጅት ተሰይማለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ለጦር ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያወጡ አገሮች ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2ዐ1ዐ-2ዐ14 በስኘሪ ተብሎ በሚታወቅ ድርጅት በተደረገው ጥናት ሣውዲ አረቢያ ዓለም ላይ ከሚገኙ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ደረጃ በማስገባት ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡ ሣውዲ አረቢያ በአካባቢው ካሉ ሀገሮች በዓለም ላይ ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማድረግ ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የኦፔክ፣ ጂሲስ እና የእስላም ግሩፕ አባል ናት፡፡
ሳውዲ አረብያ በደቡብ ምስራቅ የሚያዋስናት ሀገር የትኛው ነው ?
የመን
290
የጥንቶቹ ሰወች እቃን በቃ በመለዋወጥ መገበያየት ቻሉ። ይህም በማይተዋወቁ ሰወች ዘንድ ነበር። በሚተዋወቁ ግን የስጦታ ልውውጥ ይደረግ ነበር። ቀስ ብሎ የተለያዩ ባህሎች ኮሞዲቲ ገንዘብ መጠቀም ጀመሩ። ከሁሉ አስቀድሞ ከብትና እህል (ገብስ) መደበኛ ነበሩ። በተለይ ዛጎል በብዙ ህብረተሶቦች ዘንድ እንደ መገበባያ ገንዘብ ይጠቅም ነበር። መዳብ፣ ብረት፣ ብርና ወርቅ በክብደት ለመግዣ ቢጠቀሙም፣ ሰዎች ውዱን ብረታብረት ከርካሹ ጋራ ስላቀላቀሉት በአማካኝ ጥረቱ እየቀነሰ ሄደ። በ660 ዓክልበ. ያሕል ጥረቱን እንዲመረምሩ የፈተና ደንጊያ ዕውቀት ስላገኙ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ሳንቲም እና የብር ሳንቲም መጠቀም የጀመሩት ልድያውያን ነበር።. በኢትዮጵያም በአክሱም ነገሥታት የታተሙ የወርቅ ሳንቲሞች ስራ ላይ ውለዋል። ከዚህ ቀጥሎ የተነሳው ተወካይ ገንዘብ የሚባለው ገንዘብ አመጣጡ እንዲህ ነው። ወርቅና ብር ነጋዴወች ለደንበኞቻቸው ደረሰኝ በመጻፍ፣ ያንን ደረሰኝ ደምበኞች በማምጣት በፈለጉት ሰዓት ወርቁንና ብሩን ማግኘት ቻሉ። ቀስ በቀስ ደረሰኙ በወርቁና በብሩ ቦታ ተተክቶ እንደ ሙሉ ገንዘብ መስራት ጀመረ። የወረቀት ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በሶንግ ስርወ መንግስት (970 ዓ.ም. - 1276 ዓ.ም.) ዘመን በቻይና አገር ነበር፣ ብሮቹም ያወዚ ይባሉ ነበር፣ አመጣጣቸውም ከላይ እንደተገለጸው የደረሰኝ ጽሁፈትን ተከትሎ ነው። አውሮጳ ውስጥ የወረቀት ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በ1661፣ ስዊድን አገር ነበር። በዚህ ወቅት እያንዳንዱ ጥሬ የወረቀት ብር ወደ ተወሰነ የወርቅ ክብደት የሚቀየርበት ስሌት ነበረው። ሆኖም ስዊድን የወረቀት ብር ያወጣው ምክንያት ጦርነት ለማድረግ ፈልጎ በቂ ወርቅ ወይም ሌላ ገንዘብ በአገሩ ስላልነበረው ነው። አሁን ወዲያው የስዊድን መንግሥት ፈቃዱን እንዲፈጽሙ ሥራተኖች መክፈል ቻለ። በጥቂት ዓመት ውስት የስዎድን ወረቀት ገንዘብ ወደቀ። ነገር ግን ከትንሽ በኋላ የእንግላንድ መንግሥት በፈረንሣይ ላይ በጦርነት ተይዞ ለጦርነትም ያህል በቂ ሀብት ባለመኖሩ እንዲህ አይነት መፍትሄ መረጡ፤ የኢንግላንድ ፓውንድ ድፍን ጀመሩ። ስለዚህ ከዚህ በኋላ አገራት ፈቃዳቸውን ለመፈጽም አዲስ የወርቅ ወይም የብር ማዕድን ማግነት አስፈላጊ አልነበረም። በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ይህ በወርቅ የተደገፈ የተሰኘው የገንዘብ ስርዓት በይፋ በመላው ዓለም ተንሰራፋ። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በብሬቶን ውድስ ስብሰባ፣ አብዛኞቹ የአለማችን አገሮች ፊያት ገንዘብን በማጽደቅ ገንዘባቸውን በቀጥታ በወርቅ ከመደገፍ ይልቅ ከአሜሪካን ዶላር አንጻር እንዲተረጎም አደረጉ። የአሜሪካን ዶላር በተራው በወርቅ የተደገፈ ነበር። በ1971 የአሜሪካን መንግስት ዶላሩን በወርቅ መደገፍ/መተርጎም አቆመ። ከዚህ በኋላ ሌሎቹም አገሮች የየራሳቸውን ገንዘብ ከአሜሪካን ዶላር አንጻር መተርጎም አቆሙ። በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የአለማችን ገንዘቦች በወርቅም ሆነ በሌላ ቋሚ ነገር የሚደገፉ ሳይሆን በየአገሩ ባሉ መንግስታት እንደ ህጋዊ መገበባያ በወጡ አዋጆች ምክንያት ነው።
የወረቀት ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በየት ሀገር ነው?
በቻይና
712
ውትድርና የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት ሀገሯን የመከላከል፣ የሀገሯን ፍላጎት የማስጠበቅ እና ፀጥታ አስጠባቂ ጥረቶችን የመደገፍ ግዴታ አለበት። ሠራዊቱ የምድር፣ የባህርና የአየር ኃይል አለው። ሠራዊቱ ከነፃነት ጀምሮ በሀገሯ ታሪክ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በተለያዩ ጊዜያት የውትድርና ጁንታዎች ሥልጣን በመያዝ አገሯን አስተዳድረዋል። የናይጄራያ ሠራዊት በፀጥታ ጠባቂነት ደረጃ ከ1995 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በላይቤሪያ (1997 እ.ኤ.አ.)፣ አይቮሪ ኮስት (ከ1997 እስከ 1999 እ.ኤ.አ. ) እና ሲየራ ሊዮን (ከ1997 እ.ኤ.አ. 1999 እ.ኤ.አ.) ተሰማርቷል። ምጣኔ ሀብት በግብርና ናይጄሪያ በዋናነት ለአለም የምታቀርበው ምርቶች በተለይ ካካውና ጎማ ናቸው። እንዲሁም ፔትሮሊየም ከሚያቀርቡት አገራት 12ኛ ነች። በተጨማሪ፣ የመኪና ሥራ ድርጅት (ኢኖሶን ተሽከርካሪ መፈብረክ) ይኖራል። መልከዓ ምድር ናይጄሪያ በምዕራብ አፍሪካ በጊኒ ባሕረ ሰላጤ ላይ ትገኛለች። የቆዳ ስፋቷ 923,768 ካሬ ኪ.ሚ. ሲሆን ከዓለም ፴፪ኛዋ ትልቅ ሀገር ናት። ድንበሯ 4,047 ኪ.ሜ. ርዝመት ሲኖረው ከቤኒን 773 ኪ.ሜ.፣ ኒጄር 1,497 ኪ.ሜ.፣ ቻድ 87 ኪ.ሜ.፣ ካሜሩን 1,690 ኪ.ሜ. ትዋሰናለች። በተጨማሪም 853 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ጠረፍ አላት። በናይጄሪያ ውስጥ ከፍተኛው ቦታ ቻፓል ዋዲ ተራራ ሲሆን ከፍታው 2,419 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ነው። የአገሯ ዋና ወንዞች ኒጄር እና ቤንዌ ሲሆን ወደ ኒጄር ደለል ይፈሳሉ።
በናይጄሪያ ትልልቆቹ ወንዞች ማንና ማን ናቸው?
ኒጄር እና ቤንዌ
803
ነሐሴ ፳፰ ነሐሴ ፳፰ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፰ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፰ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፯ ዕለታት ይቀራሉ። 1862 - የፕሩሲያ (ጀርመን) ሠራዊት 3ኛ ናፖሊዎንን ከ100,000 ጭፍሮች ጋር በሰዳን ውግያ አሸነፈ። 1890 - በኦምዱርማን ውግያ ሱዳንን የእንግሊዝ ሠራዊት ድል በማድረግ ቅኝ አገር አደረጉት። 1935 - በ2ኛ አለማዊ ጦርነት ኢጣልያ በጓደኞቿ ሃያላት (በጀርመን ኃይል) ተወረረች። 1946 - የቻይና ኃያላት የደቡብ ኮርያ ደሴቶችን በቦምብ ደበደቡ። ፲፱፻፸፱ ዓ/ም በቡሩንዲ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሻለቃ ፒዬር ቡዮያ የአገሪቱን ፕሬዚደንት ዣን ባፕቲስት ባጋዛን ከሥልጣን አስወረዱ።
በቡሩንዲ በ፲፱፻፸፱ ዓ/ም ሻለቃ ፒዬር ቡዮያ በመፈንቅለ መንግሥት ስልጣን የያዘው ማንን ሽሮ ነው?
ፕሬዚደንት ዣን ባፕቲስት ባጋዛን
425
የኮምፒዩተር አውታር የኮምፒዩተር አውታር (ኔትወርክ) ማለት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ኮምፒዩተሮችን ማገናኘት ነው። እነዚህ ኮምፒዩተሮች ሲገናኙ መረጃ መለዋወጥ ይቻላል። አውታሩ ውስጥ ያሉት ኮምፒዩተሮች በአንደ ክፍል ውስጥ ወይም በጣም በተራራቁ ሕንጻዎች ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ። ኮምፒዩተሮቹ በኤሌትሪክ ገመድ ፣ በገመድ የለሽ ግንኙነት ወይም በሞደም ሊገናኙ ይችላሉ። አውታሩ ላይ ሌሎች የኮምፒዩተር መሣሪያዎችንም መግጠም ይቻላል። ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር አውታር ውስጥ አገናኝቶ አውታሩ ውስጥ ከሚገኝ ማንኘውም ኮምፒዩተር ወደዛ ፕሪንተር ማተም ይቻላል። የአውታሩን ኮምፒዩተሮች ሁሉንም እኩል ሥልጣን መስጠት ይቻላል ወይም ለአንዳንድ ኮምፒዩተሮች የተለዩ ሥራዎች መሥራት እንዲችሉ ማድረግ ይቻላል። ሁለተኛው ዘዴ ክላየንት-ሰርቨር ይባላል። አብዛኛው ጊዜ ሰርቨሮቹ ሀይለኛና ትልቅ ሲሆኑ ክላየንቶቹ ደግሞ አነስተኛ ናቸው።
በኮምፒዩተሮች አውታር ምን ማድረግ ይቻላል?
መረጃ መለዋወጥ
96
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል። በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። የገብላዊ ልጆች የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል። ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው። ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው። ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
ናጊብ ማህፉዝ መቼ ተወለደ?
ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ
97
ኮንታ የኮንታ ብሔረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ኮንቲኛ ሲሆን፣ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ ከንግግር ቋንቋነት ባሻገር የትምህርትና የሥራ ቋንቋ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አብዛኛው የብሔረሰቡ አባላት ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ ዳውሮኛ፣ ጋሞኛ፣ ወላይትኛና አማርኛ ይናገራሉ። የኮንታ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር መዋቅር ተዋረዳዊ ኃላፊነትና ተግባር ባላቸው የተለያዩ ክፍሎች የተደራጀ ነው፡፡ በእዚህ መዋቅር የሁሉም የበላይ ካዎ ወይም ንጉስ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከማላ ጎሳ ይመረጣል፡፡ በኮንታ ብሔረሰብ ስድስት ባህላዊ የጋብቻ ዓይነቶች ያሉ ሲሆን፣ እነዚህም በቤተሰብ ስምምነት የሚፈጸም ጋብቻ (ቦሣ) የለፋ ጋብቻ (ላታ) በተጋቢዎች ስምምነት የሚፈጸም ጋብቻ (ማቆ) የቃል ጋብቻ (ያኤኤኩዎ) እና ሚሽቶ (የምትክ ጋብቻ) በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህ የጋብቻ ዓይነቶች በብዛት ሲከናወን የሚስተዋለው በቤተሰብ ስምምነት የሚፈጸመው የቦሣ ጋብቻ ነው፡፡ ከብሔረሰቡ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ፂፄ፣ ጫቻ፣ ዛይ፣ዲንኬ እና ኡልዱዶ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ የትንፋሽና የምት የሙዚቃ መሣሪያዎች ለለቅሶና ለደስታ ጊዜ ያገለግላሉ፡፡ በተለይ ኡላዱዶ የተሰኘው የትንፋሽ መሣሪያ ከድኩላ ቀንድ ተበስቶ የሚሠራ ሲሆን ከብቶቻቸው ሆራ (ጨውነት ያለው ውሃ) ሊያጠጡ የሚወስዱ እረኞች ይነፉታል፡፡ የኮንታ ባህላዊ የቤት አሠራር ከፍልጥ እንጨት፣ ከቀርከሀ ከሰንበሌጥና ከሣር የሚዘጋጅ ሲሆን በደጋውና በቆላው አካባቢ ልዩነት አለው፡፡ ሱልሶ፣ ሲሊሶ፣ ኡስታ፣ ጨዲያ፣ ኩበዋ፣ ቦሩዋ (ዱቢያ) እና ባጨራ የኮንታ ብሔረሰብ ዋነኛ ባህላዊ ምግቦች ናቸው፡፡ ሲልሶ ለአብነት ከምን እንደሚሠራ እንይ፡፡ ሲልሶ ከጥሬ ሥጋ፣ ከቅቤ፣ ከደም፣ ከሀሞት እና ከተለያዩ የማጣፈጫ ቅመሞች ከተዘጋጀ በኋላ ከተለበለበና በክብ በተቆረጠ የእንሰት ቅጠል ላይ ለቤተሰቡ አባላት ይቀርብና በቡላ ወይም በቆጮ ይበላል፡፡ በብሔረሰቡ ወንዶች ከአቡጀዲ በእጅ የተሰፋ እጀ ጠባብ ሸሚዝና ሱሪ እንዲሁም ሀሲያ የተባለ በእጅ የተፈተለ ልብስ ሲለብሱ ሴቶች በኋላ በኩል ባለወጥ ጥለት የሆነውን ማዳ የተባለ የእጅ ፈትል ይለብሳሉ፡፡
የኮንታ ብሔረሰብ ባህላዊ ምግብ ምንድን ነው?
ሱልሶ፣ ሲሊሶ፣ ኡስታ፣ ጨዲያ፣ ኩበዋ፣ ቦሩዋ (ዱቢያ) እና ባጨራ
830
በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ። ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ። በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች። አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው። ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።
ሴኔጋል የፕሬዘንዳቶች ምርጫ ከ2001 ዓ.ም. በኋላ በየስንት ዓመቱ ማድረግ ጀመረች?
በየአምስት
1,286
ፍሪዩልያን ፍሪዩልያን (Furlan) በስሜን-ምሥራቅ እጣልያ በ600,000 ሰዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። ከነዚህ ተናጋሪውዎች አብዛኞቹ ደግሞ ጣልኛ የሚችሉ ናቸው። የቋንቋ ስም በጣልኛ ፍሪዩልያኖ ሲሆን በራሱ ግን ፉርላን ወይም ማሪለንጌ ይባላል። ላዲን ለሚባለው ቋንቋ ቅርብ ዝምድና ስላለው አንዳንዴ "ምስራቅ ላዲን" ይሰየማል። ከዚያ በላይ በስዊስ አገር ለሚናገረው ለሮማንሽ ቅርብ ዘመድ ነው። ዛሬ በጣልያ መንግሥት በኩል ፍሪዩልያን ይፋዊ ሁኔታ አለውና በብዙ ትምህርት ቤቶች ይማራል። ጥቂት ሥነ ጽሑፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ ዘፈኖችና አንዳንድ የመንገድ ምልክት፣ ደግሞ የድረ-ገጽ ጋዜጣ በፍሪዩልያን አለ። ባለፈው አመት ውስጥ የቢራ ማስታወቂያ ቢሆንም በፍሪዩልያን በጣልያ ቴሌቪዥን ታይቷል። ስለዚህ ዱሮ ቋንቋው በጣም ትንሽ ከሆነ አሁን ግን በጉልበት እየተመለሠ ነው።
ፍሪዩልያን ቋንቋ በጣልያን በምን ያህል ሰዎች ይነገራል?
በ600,000
38
ሳህሌ ደጋጎ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል። በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ መሆኑን የሕይወት ታሪኩ ላይ ተጠቅሷል። ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ (በተቋቋመ ጊዜ ) በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁር ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር። ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ፣ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል።
ሣህሌ ደጋጎ በክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ እፁብ ድንቅ በማድረግ የበኩላቸውን ሚና የተጫውቱት ከነማን ጋር ነው?
ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር
770
እንደ ፕላቶ ዘገባ፣ የሶቅራጠስ እናት ፌናርት የተሰኘች አዋላጅ ነበረች። ሶቅራጠስ እናቱ ሴቶች ልጅ እንዲወልዱ እንደምትረዳ ሁሉ እርሱ ደግሞ ሰዎች አዳዲስ አሳቦችን እንዲወልዱ ለመርዳት እንደሚሞክር መናገሩ ይጠቀሳል። የሶቅራጠስ አባት ድንጋይ አናጢ የነበረው ሶፍሮኒስከስ እንደነበር ይጠቀሳል። ሶቅራጠስ በዘመኑ ድሃ የነበረ ሲሆን ለዚህ ምክንያቱ ከገንዘብ ይልቅ እውቀት ይበልጣል ብሎ ስለሚያምን ነበር። ሶቅራጠስ ስራ እንደማይሰራና በፍልስፍና ሃሳብና ክርክር ጊዜውን እንደሚያሳልፍ ፕላቶ ዘግቦት ይገኛል። ዛንቲፕ የተሰኘች ከርሱ በዕድሜ በጣም የምታንስ ሴትን አግብቶ ሶስት ልጆች እንደነበሩት ፕላቶ ጽፏል። ሶቅራጠስ 70 ዓመት በሞላው ጊዜ የአቴና መንግስት እንዲያዝና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረገ። በወቅቱ ሁለት ክሶች ሲቀርቡበት አንደኛው "በትምህርትህ ወጣቱን አበላሽተሃል" የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ለግሪክ ጣዖታት አልተገዛህም" የሚል ነበር። እንደ ፕላቶ ዘገባ ግን ሶቅራጠስ የግሪክ ጣኦታት አምላኪ ነበር። በአንድ አንድ ተመራማርወች ዘንድ የአቴንስ መንግስት ያቀረባቸው ክሶች በውሸት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የሆኖ ሆኖ፣ ክሪቶ የተሰኘው የፈላስፋው ጓደኛ ለጠባቂወቹ ጉቦ በመስጠት እንዲያመልጥ ሁኔታውን አመቻችቶ ነበር። ሶቅራጠስ ግን እምቢ በማለት ቀረ እንጂ አላመለጠም። ሶቅራጠስ ለፍርድ በቀረበ ጊዜ ሰፊ የሆነ የመከላከያ ክርክር በማቅረብ የአቴናን መንግስት ክስ ውድቅ ለማደርግ ሞክሯል። ከዚህ በኋላ ዳኞቹ ምን አይነት ቅጣት እንዲበይኑበት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት፣ ለአቴና ህብረተሰብ ካበረከተው ጥሩ ተግባራቱ አንጻር በቀሪው ዘመኑ ሁሉ ነጻ እራት እንዲያመጡለት ተናገረ። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ወይ በቅጣት እንዲለቀቅ ወይንም ደግሞ እንዲገደል የእጅ ምርጫ አደረገ። ውጤቱም ሶቅራጠስ እንዲገደል የሚል ሆነ። ይሁንና ሶቅራጠስ ሞትን አይፈራም ነበር። ሞቱን ለማስቀረት ይቅርታም ሆነ ሌላ ማባበያ አላቀረበም። በርሱ ሥነ ምግባር መሰረት ላመነበት ነገር እስከመጨረሻ መቆሙ ሰናይ ድርጊት ነበር። ስለሆነም ሄምሎክ የተሰኘ መርዝ ጠጥቶ እንዲሞት ስለታዘዘ፣ መርዙን በመጠጣት አለፈ።
ዳኞች ምን ዓይነት ቅጣት እንዲበይኑበት ሲጠየቅ የሶቅራጥስ መልስ ምን ነበር?
በቀሪው ዘመኑ ሁሉ ነጻ እራት እንዲያመጡለት
899
የቅርጫት ኳስ የቅርጫት ኳስ ወይም ባስኬትቦል በዓለም ዙሪያ በቡድኖች የሚጫወት የኳስ እስፖርት ነው። ጨወታው በ1885 ዓም በካናዳዊው ዶ/ር ጄምስ ነይስሚስ በአሜሪካ አገር ተፈጠረ። በመላው አለም ተወዳጅነትን ያተረፈ የቡድን ስፖርት አይነት ነው፡፡ ጨዋታው እኤአ በ1891 በካናዳዊው ዶ.ር ጀምስ ኒስሚዝ በአሜሪካ አገር ተፈጠረ፡፡ የቅርጫት ኳስ ወይም ባስኬት ቦል፡፡ ጨዋታው በእጅ የሚከናወን ሲሆን በመሰረታዊነት የ4 መአዘን ሬክታንግል ቅርፅ ያለው መጫወቻ ኮርት 5 ተጫዋቾ ያሉት ሁለት ቡድኖች እና በእጅ የሚወረወረው ድቡልቡል ኳስ ለጨዋታው አስፈላጊ የሆኑ ቁሶች ናቸው፡፡ 5ቱ ተጫዋቾ ሁልጊዜም የተጫዋቾችን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ከተጫዋቾቹ በቁመት ረጅም የሆነው ተጫዋች አብዛኛውን ጊዜ የመሀል ቦታ ይይዛል፡፡ እኤአ በ1891 በካናዳዊው የጂም መምህር ጀምስ ኒስሚዝ በስፕንግ ፊልድ ማሳቹስትስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተፈጠረው የቅርጫት ኳስ በአሁኑ ሰአት በአለማችን ላይ እጅግ ታዋቂና በመላው አለም በርካታ ተመልካቾች ያሉት የስፖርት አይነት ነው፡፡ የናሽናል ባስኬት ቦል አሶሴሽን ለአለም ፕፌሽናል ባስኬት ቦል በማሳደግና በማስተዋወቅ በክፍያ በተሰጥኦና በውድድር ብቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቶለታል፡፡ ከሰሜን አሜሪካ ውጪ ያሉ የብሄራዊ ሊግ መስፈርትን ያሟሉ ታላላቅ ክለቦች ለአህጉራዊ ቻምፒየን ሺፕ እንደ ኢሮሊግ እና FIBA አሜሪካ ሊግ የናሽናል ባስኬት ቦል አሶሴሽን አስተዋፅኦ ማሳያ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የFIBA ባስኬት ቦል ወርልድ ካፕ እና men’s Olympic basketball ውድድር ዋና ዋና የአለማቀፍ ዝግጅቶችን እና የብሄራዊ ቡድኑ በርካታ ተጫዋቾችን መሳብ የቻሉ ውድድሮች ናቸው፡፡
የቅርጫት ኳስ ጨዋታ የተፈጠረው ምናዊ ዜግነት ባለው ሰው ነው?
በካናዳዊው
78
ፋሽስት ቅዲስቲቱዋን ኢትዮጵያን ለማዋረድ ለመዝረፍና ለመግዛት ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ዝግጅቱን አጠናቆ በ1928 ዓም 300, 000 ሰራዊት 160 ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች 450 ታንኮች 2000 የመጉዋጉዋዣ መኪናዎችን በማሰማራት ድንበር አልፎ ጦርነት በመክፈት ከገጠር እስከ ከተማ ህዝቡን ያለ እርህራሄ ጨፈጨፈ። በዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ላይ የመጀመሪያውን ህይወት ያለዉን ነገር ሁሉ የሚያጠፋውን “ማስተርድ ጋዝ” የሚባል ኬሚካል መሳሪያ በመጠቀም ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ፈጸመ። በዚያን ክፉ ቀን የነጻነትና የሀገር ትርጉም የገባቸው የቁርጥ ቀን ልጆች በየአካባቢያቸው ፋኖዎችን በመምራት የእብሪተኛዉን የፋሽ ስት ጦር መግቢያ መዉጫ በማሳጣት ኢትዮጵያ ዉስጥ በሰላም መኖር እንደማይችል ተስፋ አስቆርጠዉታል። ከነዚህ ነበልባል የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች መካከል ጠላትን በተከታታይ ዝርክርኩን አዉጥተው ከደቡብ ያሳደዱትና በመጨረሻው ዉጊያ ላይ ኢትዮጵያዊ በሚመስሉ የተሀሬ ስርጎ ገብ ባንዶች ቆሰለው የተያዙትና በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ዉዱ የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ልጅ ራስ ደስታ ዳምጠው ነበሩ።
ፋሺሽት ጣልያን ድጋሚ ኢትዮጵያን ሲወር የተጠቀመበት መርዛማ ኬሚካል ምን ይባላል?
ማስተርድ ጋዝ
247
ማሊ የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያ፣ ኒጄር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኔ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች። ማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር። ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር። ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች። ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ። ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅ፣ ዩራኒየም፣ ፎስፌት፣ ካዎሊን፣ ጨው፣ ኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ። የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት። ማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው።
በማሊ በእርሻና በዓሣ ማጥመድ የሚተዳደረው በመቶኛ ምን ያህል ሕዝብ ይሆናል?
80 ከመቶ
1,217
ባለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል። በዚህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ተደርሶ የነበረው ስምምነት ወደ ትግበራ ገብቷል። ባለፉት ስደስት ወራት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች መረጣ እና ተመሳሳይነት ልየታም ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህ መሰረት 25 የህንድ የቴክኖሎጂ ባላሙያዎችና ድርጅቶች ከ57 የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መመስረታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በቅንጅት በመስራት ታምናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር፥ የሁለቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጥምርታ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የቴክኖሎጂው ዘርፍ የእውቀት ሽግግር እንዲያመጣ፣ ሃብት እና የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ ኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራንግ ስትራቫስታቫ በበኩላቸው፥ኢትዮጵያ እና ህንድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመሩት ስራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን ተናግረዋ። በኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ፕሮግራም በሚቀጥሉት አምስት አመታት 50 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ለመፍጠር እቅድ መያዙ ተመላክቷል። ባለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ተጠናቋል። በዚህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ለመፍጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ተደርሶ የነበረው ስምምነት ወደ ትግበራ ገብቷል። ባለፉት ስደስት ወራት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችና ድርጅቶች መረጣ እና ተመሳሳይነት ልየታም ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህ መሰረት 25 የህንድ የቴክኖሎጂ ባላሙያዎችና ድርጅቶች ከ57 የኢትዮጵያ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት መመስረታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በቅንጅት በመስራት ታምናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር፥ የሁለቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጥምርታ ውጤታማ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የቴክኖሎጂው ዘርፍ የእውቀት ሽግግር እንዲያመጣ፣ ሃብት እና የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ ኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታን እየፈጠረች እንደምትገኝም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኑራንግ ስትራቫስታቫ በበኩላቸው፥ኢትዮጵያ እና ህንድ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመሩት ስራ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን ተናግረዋ። በኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ፕሮግራም በሚቀጥሉት አምስት አመታት 50 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ለመፍጠር እቅድ መያዙ ተመላክቷል።
በኢትዮ-ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ገበያ ትስስር ኤክስፖ ላይ ምን ያህል የሕንድ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ተሳተፉ?
25
261
ግንቦት ፳፮ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፷፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፷፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፺፱ ቀናት ይቀራሉ። ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የኤር ፍራንስ ቦይንግ ፯፻፯ አየር ዠበብ ከፓሪስ ኦርሊ ማረፊያ ተነስቶ ወደ አትላንታ ለመብረር ሲነሳ በደረሰበት አደጋ ፻፴ መንገደኞችና የዓየር መንገዱ ባልደረቦች ሞተዋል። ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የአሜሪካው ‘ኖርዝ ዌስት ኤየርላይንስ’ ዲ-ሲ-፯ አየር ዠበብ በረራ በሰላማዊ ውቅያኖስ ላይ ውድቆ ሲሰምጥ ፻፩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኮንኮርድ አየር ዠበብ አምሳል የተሠራው የሶቪዬት ቱፖሌቭ ቲ-ዩ-፻፵፬ ፈረንሳይ ላይ በደረሰበት የበረራ አደጋ ሲከሰከስ ፲፬ ሰዎች ሞተዋል። ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ አካላት የነበሩት ሰርቢያ እና ሞንቴኔግሮ የውሕደት ስምምነታቸውን በሞንቴኔግሮ የሉዐላዊነት አዋጅ ምክንያት ሰረዙ። ፲፯፻፷፭ ዓ/ም - የዓፄ በካፋ ሚስት የነበሩት እቴጌ ምንትዋብ በዚህ ዕለት አርፈው በቁስቋም ደብረ ጸሐይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
በሞንቴኔግሮ የሉዐላዊነት አዋጅ ምክንያት - የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ አካላት የነበሩት ሰርቢያ እና ሞንቴኔግሮ ስምምነታቸውን መቼ አፈረሱ?
፲፱፻፺፰ ዓ/ም
497
ነሐሴ ፯ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፯ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፱ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፰ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፭፻ ዓ/ም - በስመ መንግሥት አንበሳ በፀር ይባሉ የነበሩት ዓፄ ናዖድ በዚህ ዕለት አርፈው የ፲፪ ዓመት ልጃቸው ዓፄ ልብነ ድንግል ወናግሰገድ ተብለው ነገሡ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በኩባ ደሴት በእስፓኝ እና በአሜሪካ መኻል የነበረው የማስተዳደር ፍልሚያ ትግል አከተመ። ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ከፈረንሳይ ቅኝ ተገዢነት ነፃነቷን አወጀች። ዴቪድ ዳኮ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ። ፲፭፻ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ናዖድ በዚህ ዕለት አረፉ።
የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት አፄ ናኦድ በስንት ዓመተ ምህረት አረፉ?
፲፭፻ ዓ/ም
447
መጋቢት ፪ ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን ያዘ። ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት (በኋላ ፕሬዚዳንት) ሪቻርድ ኒክሰን ኢትዮጵያን ጎበኙ ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ሊትዌኒያ እራሷን ከሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ውጭ ነጻ መሆኗን አወጀች። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ በልብ ምታት አረፈ።
ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው መቼ ነው?
፲፱፻፵፯ ዓ/ም
615
የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። ውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ። ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል።
አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ የሥራ ፈጠራ ይዘው በመቅረብ በጤና ዘርፍ አሸናፊ የሆኑት ግለሰብ ማን ይባላሉ?
ውለታ ለማ (ዶ/ር)
415
መለጋሲ መለጋሲ (Malagasy) ከአውስትሮኔዚያን የቋንቋ ቤተሠብ ቋንቋዎች ሁሉ ምእራበኛው ሲሆን የማዳጋስካር መደበኛ ቋንቋ ነው። 1500-2000 አመታት ከዛሬ በፊት ከእንዶኔዚያ የመጡ የማዳጋስካር ኗሪዎች ቋንቋ በመሆኑ፣ ከቃላቱ መዝገብ 90% ከመቶ በቦርኔዮ እንዶኔዚያ ከተገኘው ቋንቋ ከማአንያን ጋራ ተመሳሳይ ነው። የቀሩትም 10% ቃላት በተለይ ከአፍሪቃ ቋንቋዎች (ከባንቱ) እና ከአረብኛ ተበድረዋል። በአረፍተ ነገር ውስጥ ግሡ ከሁሉ ይቀድማል። ይህ ተራ እንደ ዕብራይስጥ ይመስላል እንጂ ለብዙዎች ቋንቋዎች የተለመደ አይደለም። በየቃሉ ውስጥ ከመጨረሻው ክፍለ-ቃል በፊት የሆነው ክፍለ-ቃል አናባቢ ይጠበቃል፤ ሌሎቹ አናባቢዎችም ይነበነባሉ (በሙሉ አይስሙም)፤ ስለዚህ "Malagasy" እንደ ፈረንሳይኛ አጻጻፉ "Malgache" (መልጋሽ) ይመስላል።
የመለጋሲ ቋንቋ ከማአንያን ቋንቋ ጋር በመቶኛ ምን ያህል የሚመሳሰሉ ቃላትን ይዟል?
90%
151
አዋሽ ብሔራዊ የመዝናኛ እና የዱር አራዊት ጥበቃ ክልል የአዋሽ ብሔራዊ መዝናኛ እና የዱር አራዊት ጥበቃ ክልል በ፲፱፻፶፰ ዓ/ም የተመሠረተ ክልል ሲሆን ከአዲስ አበባ በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በ፪መቶ ፲፩ ኪሎሜትር ርቀት ፤ በአፋርና በኦሮሚያ አዋሳኝ ክልሎች ሥር ይገኛል። ይህ ክልል ሲመሠረት በ ፱፻፮ ካሬ ኪሎሜትር የቆዳ ስፋት (ቦልቶን ፲፱፻፷፰) የነበረው ቢሆንም፤ ባሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ማስረጃ እንዳስቀመጠው የክልሉ የቆዳ ስፋት ፯መቶ ፶፮ ካሬ ኪሎ-ሜትር ነው። የክልሉ ደቡባዊ ድንበር የአዋሽ ወንዝ ሲሆን፣ የተሠየመውም በዚሁ ታላቅ ወንዝ ስም ነው። ክልሉ የብዙ ዓይነት አራዊት እና አዕዋፍ መጠለያ ከመሆኑም ባሻገር ፍል-ውሓ እና የፋንታሌ ተራራ ይገኙበታል። የአገሪቱ የዱር አራዊት ጥበቃ ባለ-ሥልጣን ሲመሠረት ለንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት በአማካሪነት የተመደበው እንግሊዛዊ ባቀረበው ኃሣብ መሠረት የመጀመሪያው ብሔራዊ የዱር አራዊት ጥበቃ ባለ-ሥጣን ከተመሠረተ በኋላ የቅድሚያ ሥራ የተደረገው፤ በታቀዱት ክልሎች የሚገኙትን የአገሪቱን የዱር አራዊት ኃብት መጠን ማረጋገጥ ነበር። ለዚህም ሥራ ከብሪታኒያ ተመልምሎ የተቀጠረው ባለ-ሙያ እንግሊዛዊው የሥነ-ሕይወት ባለሙያ ሜልቪን ቦልቶን ነበር። የአዋሽ ብሔራዊ መዝናኛ እና የዱር አራዊት ጥበቃ ክልል የበርካታ የዱር አራዊት፤ አዕዋፋት እና የውሐ አራዊት መኖሪያ ነው። በደቡብ አዋሳኙ በሆነው የአዋሽ ወንዝ አዞ እና ጉማሬ ሲገኝበት፤ በሰሜን ክፍሉ ደግሞ ጦጣና ዝንጀሮ፤ እንዲሁም ጅብ እና አጋዘን ይገኙበታል። በክልሉ ከሚገኙት የዱር አራዊት በከፊሉ፦ ጉሬዛ፤ ተራ ዝንጀሮ፤ ነጭ ዝንጀሮ፤ ጦጣ፤ ሳላ፤ የሜዳ ፍየል፤ ሚዳቋ፤ ትልቁ የቆላ አጋዘን ፤ አምባራይሌ፤ ከርከሮ፤ ቆርኪ በብዛት የሚገኙ ሲሆን አንበሣ፤ ነብር፤ ጀርባ-ጥቁር እና ተራ ቀበሮ፤ዳልጋ አንበሣ፤ አነር እና የዱር ድመት ደግም አልፎ-አልፎ ይታያሉ። ባለፉት አሥር ዓመታት ጊዜ ውስጥ በተካሄደ ምዝገባ እንደተረጋገጠው፣ በክልሉ ውስጥ ፬መቶ ፷፪ ዓይነት የወፍ ዝርያዎች ተመዝግበዋል። ከነዚህም መኻል ስድስቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ናቸው። እነዚህም መንቆረ-ጥቁር ጋርደም፤ ግንደ-ቆርቁር፤ ክንፈ-ነጭ የገደል-ቻት፤ ጅራተ-ረጅም ወማይ፤ ቁራ እና ጋጋኖ ናቸው።
በክልሉ ስድስቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙት የወፍ ዝርያዎች ስማቸውን ጥቀስ?
መንቆረ-ጥቁር ጋርደም፤ ግንደ-ቆርቁር፤ ክንፈ-ነጭ የገደል-ቻት፤ ጅራተ-ረጅም ወማይ፤ ቁራ እና ጋጋኖ
1,202
ስዋሂሊ ስዋሂሊ ፡ (ወይም ፡ ኪሷሂሊ Kiswahili) ፡ በምሥራቅ ፡ አፍሪቃ ፡ የሚናገር ፡ የባንቱ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የስዋሂሊ ፡ ሕዝብ (፭ ፡ ሚሊዮን ፡ ተናጋሪዎች) ፡ ልደት ፡ ቋንቋ ፡ ከመሆኑ ፡ በላይ ፡ ለ ፴ ፡ እስከ ፡ ፶ ፡ ሚሊዮን ፡ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ሁለተኛ ፡ ቋንቋ ፡ ሆኗል። የስዋሂሊ ፡ ስም ፡ መነሻ ፡ ከዓረብኛ ፡ ቃል ፡ «ሰዋሂል» ፡ ነበር ፤ ይህም ፡ የ«ሳኸል» ፡ (ማለት ፡ ዳር) ፡ ብዙ ፡ ቁጥር ፡ ነው። ስለዚህ ፡ የ«ስዋሂሊ» ፡ ትርጉም ፡ የ(ባሕር) ፡ ዳረኞች ፡ ቋንቋ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል። የቋንቋው ፡ ቤተሰብ ፡ ባንቱ ፡ ሲሆን ፡ ተናጋሪዎቹ ፡ መርከበኞችና ፡ ነጋዴዎች ፡ በመሆናቸው ፡ መጠን ፡ ከዓረብኛ ፣ ከፋርስ ፣ ከህንዲ ፣ እና ፡ ከቻይንኛ ፡ ቢሆንም ፡ ብዙ ፡ ቃሎች ፡ ተበድረዋል።
ስዋሂሊ የምን ቋንቋ ቤተሰብ ነው?
የባንቱ
60
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እስካሁን ግብይት የሚያስፈጽመው ግዥና ሻጭን መድረክ ላይ በማገናኘት በድምፅ ዋጋ በመንገርና በመጫረት ነው፡፡ ይህ የተለመደው አሠራር የበለጠ ውጤታማ የሚሆነው ግን በድረ ገጽ ግብይት ሲደረግ በመሆኑ ይህንን የድረ ገጽ ግብይት ለማስጀመር ከሦስት ዓመት በፊት ሥራው የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሥራው ተጠናቅቆ ወደ ትግበራ ሊገባ ችሏል፡፡ በተለመደው የመድረክ የግብይት አሠራር በቀን የሚፈጸመው የግብይት መጠን ከ200 እስከ 300 የሚደርስ ነው፡፡ ይህም የግብይት መጠኑ ውሱን መሆኑን ያሳያል፡፡ ስለዚህ የድረ ገጽ ግብይት መጀመሩ ግን ይህንን በመለወጥ ከፍተኛ አቅም ይሰጣል፡፡ ይህም አሠራሩን ተግባራዊ ከማድረጉ በፊትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባለው ተቋም ጭምር ዕውቅና አግኝቶበታል፡፡ እንደ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ያሉ ተቋማትም ይህንን አገልግሎት ፈትሸው ማረጋገጫ ተሰጥቶት እየተሠራበት ስለመሆኑም የምርት ገበያው የሥራ ኃላፊዎች ያስረዳሉ፡፡ ይህንን ዘመናዊ አገልግሎት ሥራ ለማስጀመር ከመጀመሪያው ጀምሮ የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየው የኢንቨስትመንት ክላይሜት ፋሲሊቲ ፎር አፍሪካ (ICF) የተባለው ተቋም ሲሆን፣ ለዚህ ፕሮጀክት 2.2 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ይህ ግብይት በቡና የተጀመረ ሲሆን፣ ሁሉም በዚህ የግብይት ሥርዓት እንዲጠቀሙ ይደረጋል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ አዲስ በመሆኑ በዚህ ለመጠቀም ተገበያዮች ሥልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ እስካሁንም 380 ተገበያዮች በድረ ገጽ ለመገበያየት ሥልጠና ወስደው ብቁ መሆናቸው ተረጋግጦ ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የድረ ገጽ የግብይት ሥርዓትን ለማበልጸግ ከICF ምን ያህል ገንዘብ አገኘ?
2.2 ሚሊዮን ዶላር
685
የንግዱን ዘርፍ በማዘመን ሸማችን ከአምራች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት (ኢ-ኮሜርስ) ይፋ ሆነ:: በአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ የበለፀገው የኢ-ኮሜርስ ቴክኖሎጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በሚገኝበት አካባቢ አምራችን በቀላል እንዲሁም ቀጥተኛ በሆነ መንገድ የሚያገናኝ ቴክኖሎጂ መሆኑ ተገልጿል:: ቴክኖሎጂው የንግድ ሰንሰለትን በማሳጠር የዋጋ ንረትን በማስቀረት ረገድ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል:: ዘመኑን የዋጀ የግብይት ሥርአትን መፍጠር የንግድ ዘርፉን በማነቃቃት ረገድ አበርክቶው የላቀ በመሆኑ የኢ-ኮሜርስም የሀገርን ምጣኔ ሀብት የማሳደግ አቅም እንዳለው ከግምት ውስጥ በማስገባት የንግዱ አለም ተዋናዮች ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ተብሏል::
የንግዱን ዘርፍ በማዘመን ሸማችን ከአምራች በቀጥታ የሚያገናኝ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ምን ይባላል?
ኢ-ኮሜርስ
58
የቴክኖሎጂ ኩባንያው አፕል 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ተቀጣ። ኩባንያው በፈረንሳይ የንግድ ውድድርና ሸማች ባለስልጣን ከንግድ ውድድር ህጉ ውጭ ተንቀሳቅሷል በሚል ነው ለቅጣት የተዳረገው። ቅጣቱ የተጣለበት መስሪያ ቤቱ በኩባንያው ላይ ለ10 ዓመት ምርመራ ካደረገ በኋላ ነው ተብሏል። አፕል ከንግድ ውድድር ህጉ ውጭ ዋጋዎችን በመወሰንና በሌሎች የገበያ ተወዳዳሪነት ላይ ተፅዕኖ አሳርፏል በሚል ቅጣቱ እንደተወሰነበትም ታውቋል። ከዚህ ባለፈም ሁለት የአፕል አከፋፋዮች ላይ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። አካፋፋዮቹ አፕል ገበያውን ብቻውን እንዲቆጣጠር በማሴር ነው ማዕቀብ የተጣለባቸው። ኩባንያው በፈረንሳይ የ40 ዓመት አገልግሎት በመስጠት ለ240 ሺህ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።
አፕል የምን ዘርፍ ኩባንያ ነው?
የቴክኖሎጂ
1
ታኅሣሥ ፳፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፲፫ተኛው እና የመፀው ወቅት ፹፰ተኛው ቀን ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየወሩ ፳፫ኛ ቀን የሰማዕታትን ዓለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስንን ታስታውሳለች። ፲፯፻፷፰ ዓ/ም - የእንግሊዝ ሠራዊት የክዌቤክ ከተማን ከአሜሪካ አስመለሰ። ፲፯፻፺፮ ዓ/ም - በሀይቲ ደሴት የፈረንሳይ ሉዐላዊነት ሲያከትም ደሴቷ በሰሜን አሜሪካ አኅጉር ከአሜሪካ ኅብረት ተከትላ ሁለተኛዋ ነፃ ሪፑብሊክ ሆነች። ፲፰፻ ዓ/ም - በባርነት የተገዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ ኅብረት እንዳይገቡ የሚከለክል ሕግ ተደነገገ። ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ተመሰረተ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ፩ሚሊዮን ፱መቶ ሺ ኪሎ የመዳብ ሽያጭ ወደጃፓን ላከች። መዳቡ በኤርትራ ውስጥ ከሚገኘው የድባሮ መዳብ ማዕድን ቁፋሮ የተገኘ ነው። ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ባንኮችንና የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን የብሔራዊ ንብረት አድርጎ ወረሰ። ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - ጋናዊው ዲፕሎማት ኮፊ አናን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፯ተኛው ዋና ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ።
በሀይቲ ደሴት ላይ የነበረው የፈረንሳይ ሉዐላዊነት ያከተመው በስንት ዓመተ ምህተት ነው?
፲፯፻፺፮ ዓ/ም
189
አዲስ ዘመን (ጋዜጣ) አዲስ ዘመን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥር የምተዳደር ነዉ ፣ በየዕለቱ የሚታተም ብሔራዊ ጋዜጣ ነው። አዲስ ዘመን በአሁኑ ጊዜ ከ ፵ በላይ ጋዜጠኞች ያሉት ሲሆን የጋዜጣው መጠን ‘መካከለኛ’ /በርሊነር/ (31.5 cm × 47 cm (12.4 in × 18.5 in) ) ሆኖ የፊትና ጀርባ ገፆችን በሙሉ ቀለም ያቀርባል። ይህ ጋዜጣ የአገሪቱ ብቸኛው ዕለታዊ ጋዜጣ ሲሆን የመንግሥትን አቋም የሚያንፀባርቅ እና በየዕለቱ የተለያዩ ልማታዊ ዜናዎችን ይዞ ይወጣል። ከአምሥት ዓመት የኢጣልያ ወረራ በኋላ የኢትዮጵያ ነፃነት መመለሱን ተከትሎ ንጉሠ ነገሥቱ ዙፋናቸው እንደ ተረከቡ ካከናወኗቸው ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ተግባራት አንዱ የመገናኛ ብዙኀን በማደራጀትና በማቋቋም ላይ ያተኮረ ነበር። በዚህም መሠረት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ቅዳሜ፣ ግንቦት ፴ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በይፋ ሥራ ጀመረ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከጠላት ወረራ በኋላ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ሲገቡ ባደረጉት ንግግር የመግቢያው አንቀጽ፦ «የሰማይ መላእክት የምድር ሠራዊት ሊያስቡትና ሊያውቁት ይቻላቸው ባልነበረ በዚህ በዛሬው ቀን ቸር እግዚአብሔር በመካከላችሁ ለመገኘት ስላበቃኝ በሰው አፍ የሚነገር ምስጋና የሚበቃ አይደለም። ከማናቸውም አስቀድሞ ለሁላችሁ ልነግራችሁና ልትረዱት የምፈልገው፣ ይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የአዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ መሆኑን ነው። በዚሁ በአዲሱ ዘመን ሁላችንም መፈጸም ያለብን አዲስ ሥራ ይጀመራል።» የሚል ነበር የጋዜጣውም ሥያሜ «ይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የአዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ ነው» ማለታቸውን መሠረት ያደርጋል። የጋዜጣው ድረ-ገጽ ስለጋዜጣው ታሪክ ሲዘግብ፤«የመጀመሪያ ዕትም ባለሁለት ገፅ፣ አርበ ጠባብ /ታብሎይድ/» (43.2 cm X 27.9 cm (17 in X 11 in)) እንደነበረና ስርጭቱም ፲ሺ ቅጂ እንደነበር ይገልጽና፤በዚሁ የመጀመሪያ ዕትም ርዕሰ አንቀጽ «"የአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጀመር" በሚል ርዕስ ባስነበበው ጽሑፍ ‹ይህ አዲስ ዘመን ተብሎ የተሰየመው ጋዜጣ ከዛሬ ጀምሮ ወደፊት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱን ሥራ ይሠራ ዘንድ ተመሠረተ› በማለት የተቋቋመበትን ዓላማ ያስረዳል» ይለናል። ቀጥሎም ያንኑ የመጀመሪያውን ርዕሰ አንቀጽ በመጥቀስ፤ «‹ይህ ጋዜጣ የፕሮፖጋንዳ ጋዜጣ ሳይሆን እውነትን፣ አገልግሎትን፣ ረዳትነትን መሰረት አድርጐ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ በአዲስ ሥራ ተመርቶ እንዲረዳ የቆመ ነው› ቢልም ‹አገልግሎት ስንል የኢትዮጵያን ነፃነት ሲመሰስ ራሳቸውን መስዋዕት አድርገው፤ የነበራቸውን ጥቅም ሁሉ አስወግደው፤ ለሕዝባቸውና ለአገራቸው ሲሉ የሰው አቅም ሊሸከመው የማይችለውን ድካም ተቀብለው፤ ማናቸውም ሰው ሊያደርገው ያልቻለውን በኢትዮጵያ ሕይወት ውስጥ እስከ ዛሬ ያልታየውን ሥራ ከፍፃሜ ላደረሱ ለንጉሠ ነገሥታችንና ላቆሙት መንግሥት የሚያገለግል እንዲሆነ ነው።› በማለትም በዋነኝነት የተቋቋመበትን ዓላማ በግልፅ ይተነትናል።» የሚል ዘገባ እንደነበር የጋዜጣው ድረ-ገጽ አስቀምጦታል። አዲስ ዘመን ከተጀመረበት ጊዜ እስከ ታኅሣሥ ወር ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ድረስ በየሳምንቱ፤በአርበ-ጠባብ፣ በመካከለኛና በአርበ-ሰፊ /ብሮድሺት/ (74.9cm X 59.7cm (291⁄2 in X 231⁄2 in)) መጠን ሲታተም ከቆየ በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ፲፱፻፶ ዓ/ም ያቋቋመው የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ ጽሕፈት ቤቱን አዲስ አበባ ላይ ማድረጉን ምክንያት በማድረግ የጋዜጣው ዕትመት በሳምንት ወደ ስድስት ቀን ተሸጋግሯል። ከመስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ ጋዜጣው ከሰኞ እስከ እሑድ በሳምንት ሰባት ቀናት ወደመታተምከተሸጋገር በኋላ የጋዜጣው መጠን ከታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ጀምሮ ወደ መካከለኛ ጋዜጣነት /በርሊነር/ ዝቅ ብሏል።
አዲስ ዘመን የተለያዩ ቅርፆች የነበሩት ሲሆን ጋዜጣው መካከለኛ ጋዜጣነት /በርሊነር/ ቅርፅ የያዘው መቼ ነው?
ከታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
2,060
ነሐሴ ፳፰ ነሐሴ ፳፰ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፰ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፰ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፯ ዕለታት ይቀራሉ። 1862 - የፕሩሲያ (ጀርመን) ሠራዊት 3ኛ ናፖሊዎንን ከ100,000 ጭፍሮች ጋር በሰዳን ውግያ አሸነፈ። 1890 - በኦምዱርማን ውግያ ሱዳንን የእንግሊዝ ሠራዊት ድል በማድረግ ቅኝ አገር አደረጉት። 1935 - በ2ኛ አለማዊ ጦርነት ኢጣልያ በጓደኞቿ ሃያላት (በጀርመን ኃይል) ተወረረች። 1946 - የቻይና ኃያላት የደቡብ ኮርያ ደሴቶችን በቦምብ ደበደቡ። ፲፱፻፸፱ ዓ/ም በቡሩንዲ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሻለቃ ፒዬር ቡዮያ የአገሪቱን ፕሬዚደንት ዣን ባፕቲስት ባጋዛን ከሥልጣን አስወረዱ።
በቡሩንዲ በ፲፱፻፸፱ ዓ/ም ሻለቃ ፒዬር ቡዮያ በመፈንቅለ መንግሥት ዣን ባፕቲስት ባጋዛን ከስልጣን በማስወገድ የሀገሪቱ ምን ሆነ?
ፕሬዚደንት
425
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በጥሩ ጎናቸው ከሚነሱ የቅርብ ጊዜያት ተጫዋቾች መካከል አዳነ ግርማ ይገኝበታል።ተጫዋቹ በበርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታንም ይዟል።አዳነ ግርማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን መነቃቃት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ተጫዋቹ በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ለ10 ዓመታት በመጫወትም አንጋፋ ለመሆን በቅቷል። አዳነ ግርማን ስናስብ ሁለት ጨዋታዎች ሁሌም ከፊታችን ድቅን ይላሉ።ደቡብ አፍሪካ ላስተናገደ ችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡደን ከሱዳን አቻው ጋር ሲጫወት በግንባሩ ገጭቶ ያስቆጠራት ግብ መቼም ቢሆን አዳነ እንዲታወስ ያደረገችም የምታደርግ ናት።ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ያረገችው ወሳኝ ግብም ሆናለች። በአፍሪካ ዋንጫው ከ 39 ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛምቢያ ላይ ያስቆጠራት ግብም አዳነን ሁሌም እንድናስበው ያረገች ሌላዋ ግቡ ናት። ተጫዋቹ ከዋልያዎቹ ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገና የቡድኑ ምሰሶ እንደነበርም ይታወቃል።በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዘመን አዳነ ቡድኑን በአምበልነት መርቷል። የአትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሰውነት ቢሻው የተረከቡት አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ቡድኑን እንደ አዲስ ሲያዋቅሩ አዳነ ግርማን መቀነሳቸው ሲሰማ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ ቅሬታ ቢፈጠርም፣ ተጫዋቹ ግን ውሳኔውን አሜን ብሎ ነው የተቀበለው። በወቅቱም አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ለተጫዋቹ መቀነስ ምክንያታቸው ያደረጉት የተጫዋቹ «ብቃትና አቅም ወርዷል» የሚል ነው። ተጫዋቹ ግን በወቅቱ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ያረጋገጠው ምንም አይነት የአቋም መዋዠቅም እንደሌለበት ነው። የብቃት መውረድ እንዳላሳየም ገልጿል። የመቀነሱ ሚስጥር ለሱም እንቆቅልሽ እንደሆነበት ነበር ያስታወቀው። ይህን ተከትሎ ራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው አዳነ በአዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሰሞኑን ጥሪ ተደርጎለት ነበር:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ በአጥቂ እጥረት ላይ ቢገኝም አዳነ ግርማ ከቤተሰቦቼ ጋር ተመካክሬ የወሰንክይት ውሳኔ ነው በሚል ለብሔራዊ ቡድኑ እንደማይጫወት አስታውቋል:: በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሁለት የተደለደለውና በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጀሪያ አቻው ጋር ላለበት የምድቡ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን መጥራቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ሁለት ተጫዋቾችን ከአገር ውጭ ቀሪዎቹን 22 ደግሞ ከአገር ውስጥ ሊጎች የመረጡ ቢሆንም የአዳማ ከነማው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ባጋጠመው ጉዳት ከቡድኑ ውጭ ሆኗል። እርሱን ለመተካት ሳልሃዲንና አዳነን ቢጠሩም እምቢ ተብለዋል:: ሆኖም ግን አሰልጣኙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የመረጧቸውን አምስት ተጫዋቾችና ከአገር ውጭ ከሚጫወቱት ሕመልስ በቀለና ጌታነህ ከበደ በስተቀር 15 ተጫዋቾችን ይዘው ልምምዳቸውን ዛሬ ጀምረዋል።
ኢትዮጵያ በ29ኛው የእግር ኳስ የአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው ከስንት ጌዜ በኋላ ነው?
ከ 39 ዓመታት
475
በቁርጥራጭ ብረትና ያገለገሉ ማሽኖች ንግድ የተሰማራው ሳርፌ ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ የግንባታ ብረታ ብረቶች ማምረቻ ፋብሪካ በዱከም ከተማ ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የሳርፌ ቢዝነስ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክብርይስፋ ተክሌ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኩባንያው እስካሁን ቁርጥራጭ ብረቶች ከውጭ በማስመጣትና ከአገር ውስጥ በመግዛት ለብረት አቅላጮች ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ የብረት ማቅለጫው ማሽኖች ከህንድ ተገዝተው የሚመጡ ሲሆን፣ የብረት መዋቅሩ ደግሞ ከቻይና ይገዛል፡፡ የፋብሪካው ጠቅላላ የኢንቨስትመንት ወጪ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት የተናገሩት አቶ ክብርይስፋ፣ ፋብሪካው ለ300 ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ ሳርፌ ቢዝነስ ለብረት ፋብሪካው ግንባታ የሚሆን 30,000 ካሬ ሜትር ቦታ በሊዝ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከዱከም ከተማ አስተዳደር በቅርቡ መረከቡን ገልጸው፣ ኩባንያቸው ተገቢውን የአዋጭነት ጥናት ማሠራቱን አስረድተዋል፡፡
አቶ ክብርይስፋ ተክሌ በሳርፌ ቢዝነስ ውስጥ ኃላፊነታቸው ምንድን ነው?
ዋና ሥራ አስኪያጅ
146
አል የተባለ ሰው ሰራሽ መሳሪያ የጡት ካንሰር መመርመሪያ መሳሪያን በማንበብ ረገድ ከሐኪሞች በተሻለ ትክክለኛ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ። ሰው ሰራሹ መሳሪያ የጡት ካንሰር መመርመሪያ መሳሪያን በማንበብ ረገድ ሁለት ሐኪሞች በጋራ ከሚሰሩት በተሻለ መልኩ ትክክለኛ መሆኑን ባለሙያዎቹ አረጋግጠናል ብለዋል። ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣው ቡድን አል የተባለው ሰው ሰራሽ መሳሪያን ይዘው በ29 ሺህ ሴቶች ላይ ሙከራ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም መሳሪያው የጡት ካንሰርን በመለየት ረገድ የስድስት ራዲዮሎጂ ባለሙያዎችን ያክል ውጤታማ መሆኑንም ገልጸዋል። ይህም ሁለት የዘርፉ ሐኪሞች (ዶክተሮች) ከሚሰሩት ስራ ጋር እኩል ውጤት ያለው ስለመሆኑም በጥናት ውጤታችን አረጋግጠናል ነው ያሉት። ከዚህ ባለፈም መሳሪያው እንደ ሐኪሞቹና ራዲዮሎጂስቶቹ የግለሰቧን የቀደመ የጤና ሁኔታ የሚገልጽ መረጃ ሳይኖረው የጡት ካንሰሩን መለየት መቻሉም የተሻለ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል። ባለው አሰራር ሁለት የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች ችግሩን ለመለየት የጡት ካንሰር መለያ መሳሪያውን የሚያነቡ ሲሆን፥ ባልተስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ሦስተኛ ሐኪም ተጨምሮ ምስሎቹን እንዲገመግም ይደረጋል። አዲሱ መሳሪያ ራሱን ችሎ ከማንበቡም በላይ ችግሩን ለይቶ በመረዳት በኩል ውጤታማ ስለመሆኑ በባለሙያዎቹ ተመስክሮለታል። መሳሪያው የጡት ካንሰር ምርመራ ውጤት ላይ ከባለሙያዎቹ የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡም ተገልጿል፤ በዚህም ለታካሚዋ የጡት ካንሰር አለብሽ በሚል በባለሙያ የሚነገራትን ሃሰተኛ የምርመራ ውጤት በ1 ነጥብ 2 በመቶ ቀንሷል። ከዚህ ባለፈም በምርመራ ወቅት የጡት ካንሰር የለም በሚል የሚነገር የተሳሳተ ውጤት ደግሞ ከባለሙያ አንጻር መሳሪያው በ2 ነጥብ 7 በመቶ መቀነሱን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል። ምንጭ፦ ቢቢሲ
አል የተባለው ሰው ሰራሽ መሳሪያ ምንን ለመመርመር ነው ስራ ላይ የዋለው?
የጡት ካንሰር
21
የኮምፒዩተር አውታር የኮምፒዩተር አውታር (ኔትወርክ) ማለት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ኮምፒዩተሮችን ማገናኘት ነው። እነዚህ ኮምፒዩተሮች ሲገናኙ መረጃ መለዋወጥ ይቻላል። አውታሩ ውስጥ ያሉት ኮምፒዩተሮች በአንደ ክፍል ውስጥ ወይም በጣም በተራራቁ ሕንጻዎች ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ። ኮምፒዩተሮቹ በኤሌትሪክ ገመድ ፣ በገመድ የለሽ ግንኙነት ወይም በሞደም ሊገናኙ ይችላሉ። አውታሩ ላይ ሌሎች የኮምፒዩተር መሣሪያዎችንም መግጠም ይቻላል። ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር አውታር ውስጥ አገናኝቶ አውታሩ ውስጥ ከሚገኝ ማንኘውም ኮምፒዩተር ወደዛ ፕሪንተር ማተም ይቻላል። የአውታሩን ኮምፒዩተሮች ሁሉንም እኩል ሥልጣን መስጠት ይቻላል ወይም ለአንዳንድ ኮምፒዩተሮች የተለዩ ሥራዎች መሥራት እንዲችሉ ማድረግ ይቻላል። ሁለተኛው ዘዴ ክላየንት-ሰርቨር ይባላል። አብዛኛው ጊዜ ሰርቨሮቹ ሀይለኛና ትልቅ ሲሆኑ ክላየንቶቹ ደግሞ አነስተኛ ናቸው።
የኮምፒዩተሮች አውታር ስንፈጥር ኮምፒዩተሮቹን በምን በምን መንገድ ልናገናኛቸው እንችላለን?
በኤሌትሪክ ገመድ ፣ በገመድ የለሽ ግንኙነት ወይም በሞደም
188
ሌሎች የፍልስፍና ባህሎች ከምዕራባውያን ፍልስፍና በተለየ በነዚህ ጉዳዮች ላይ በዙም አላተኮሩም። ምንም እንኳን የሂንዱ ፍልስፍና በዚህ አንፃር ከምዕራባውያኑ ቢመሳሰለም እስከ 19ኛው ምዕት-አመት ድረስ በኮሪይኛ፣ በጃፓንኛ፣ እና በቻይንኛ ውስጥ "ፍልስፍና" የሚል ቃል ይገኝ አልነበረም። በተለይ የቻይና ፈላስፎች ከግሪኮቹ ለየት ያለ የምደባ ስርዓት ይከተሉ ነበር። የምዕራቡ አለም ፍልስፍና የሚጀምረው ከግሪኮች ሲሆን የመጀመሪያው ፈላስፋ ተብሎ የሚታወቀው ታሊዝ ነው። ይህ ሰው የኖረበትን ጊዜ ለማወቅ ብዙም አስቸጋሪ አይደለም። ይኸውም በ593 ዓክልበ. (ዓም) የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚኖር በመተንበዩ ከዚህ ጊዜ የተወሰነ አመት ቀደመ ብሎ ማይሌጠስ በተባለችው የትንሹ እስያ (የአሁኑ ቱርክ) ክፍል እንደተወለደ የታወቀ ነው። ታሊዝ ዓለም እና በውስጡ ያሉ ነገሮች ሁሉ ከውሃ እንደተፈጠሩ ያምን ነበረ። ከሱ በኋላ የተነሱ የግሪክ ፈላስፎች የሱኑ መንገድ በመከተል ዓለም ከአንድ ወይም ከሌላ ነገረ እንደተፈጠረች አስተምረዋል። ለምሳሌ አናክሲሜነስ የዓለም ጥንተመሰረቷ አየር ነው ሲል፣ ሄራቅሊጠስ እሳት ነው ብሏል። አናክሲማንደር ከነዚህ ሁሉ ለየት በማለት የዓለም መሰረቷ ይህ ነው የማይባል «apeiron» ወይም የትየለሌ የሆነ ነገር ነው ይላል። የምእራቡን ዓለም ፍልስፍና እስክ 1900 ድረስ ቅርጽ እንዳስያዙ የሚነግርላቸው ፈላስፋዎች የሚከተሉት ናቸው፡ ሶቅራጥስ፣ አሪስጣጣሪስ፣ ፕላጦ፣ አክዊናስ፣ ኤራስመስ፣ ማኪአቬሌ፣ ቶማስ ሞር፣ ሞንታጝ፣ ግሮቲየስ፣ ዴካርት፣ ሆበስ፣ ስፒኖዛ፣ ሎክ፣ ሌብኒሽት፣ በርክሌ፣ ሑሜ፣ ቮልቴይ፣ ሩሶ፣ ካንት፣ ሺለር፣ ሄግል፣ ሾፐናዎር፣ ጆን ኦስቲን፣ ጄ.ኤስ. ሚል፣ ኮምቴ፣ ዳርዊን፣ ማርክስ፣ እንግልስ፣ ፍሬደሪሕ ኚሼ፣ ዱርካሂም የምስራቁ አለም ፍልስፍና መነሻ ኢትዮጲያ ናት፡፡እንደውም የመላው አለም፡፡ በተለይ ኮከባቸው ጀምኒ የሆኑት የሐበሻ ተወላጆች የኮከባቸውን ሀያልነት በመጠቀም ወደ አረቡ አለም በመገስገስ የምድራችንን የፍልስፍና መንገድ ቀይሠዋል፡፡
የዚህ ዓለም ጥንተ ፍጥረቱ ከእሳት እንደሆነ የሚያምን የነበረው ፈላስፋ ማነው?
ሄራቅሊጠስ
618
በሊትር እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ የምትችል ተሸከርካሪ በኢትዮጵያዊ ወጣት መሰራቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ነዋሪ የሆነው ታዳጊ አጃዬ ማጆር ተሸከርካሪዋን ከወዳደቁ ብረቶች እንደሰራት ተነግሯል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባደረገለት ድጋፍ የተሰራችው  የባለ ሁለት እግር ተሸከርካሪ ሞተርን በመጠቀም የተሰራች ሲሆን ወደ ኋላ መሄድ እንድትችል ተደርጋ ተሻሽላ ተሰርታለች፡፡ አራት ኩንታል ክብደት ያላት ተሽከርካሪዋ እስከ 4 ሰዎች የመጫን አቅም ያላት ሲሆን በአንድ ሊትር እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ ትችላለች ተብሏል፡፡ ታዳጊው የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ መኪና መስራቱ ተገልጿል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለታዳጊው የተለያዩ ድጋፎችን  እንደሚያደርግ  ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በኢትዮጵያዊው ወጣት የተሰራው ተሽከርካሪ ምን ያህል ክበደት አለው?
አራት ኩንታል
269
ጎግል ስለኮሮና ቫይረስ መረጃዎችን ለማቅረብ የኤስ ኦ ኤስ ማንቂያን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ። ኩባንያው በትናንትናው ዕለት ወደ ስራ ያስገባው ማንቂያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማድረስ ያግዛል ተብሏል። ስለኮሮና ቫይረስ እና ተያያዥ ጉዳዮች ሰዎች መረጃዎችን በሚፈልጉበት ወቅት ጎግል “በነጭ ካርድ መደብ” ላይ የኤስ ኦ ኤስ ማንቂያውን በማሳየት ተፈላጊውን መረጃ ለተጠቃሚዎቹ በቀጥታ ያጋራልም ነው የተባለው። ጎግል ለዓለም አቀፍ መረጃ ፈላጊዎች በማንቂያው ላይ የዓለም ጤና ድርጅት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራሎችን አድራሻ ማካተቱንም አስታውቋል። አስፈላጊ ከሆነም በሂደት ማንቂያውን ለአካባቢያዊ መረጃ ፈላጊዎች በሚሆን መልኩ እንደሚያካትትም ገልጿል። በቀጣይም ስለ ኮሮና ቫይረስ ጠቃሚ መረጃ፣ ያለበትን ሁኔታ እና ጥያቄና መልሶችን ያካተቱ አንቀጾች ያሉበት “የእርዳታ እና መረጃ” ማፈላለጊያን ከዓለም ጤና ድርጅት አድራሻ ጋር በማያያዝ አቀርባለሁ ብሏል። ኩባንያው በአስፈላጊ እና ወሳኝ ወቅት ላይ ተጨማሪ የመረጃ ማሻሻያ እንደሚያደርግ በመግለፅ የማንቂያ ስርዓቱ ለኮሮና ቫይረስ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲገኙ ያስችላል ነው ያለው። በሞባይሎች እና ድረ ገፆች ላይ የሚገኘው ኤስ ኦ ኤስ ማንቂያ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት እንዲሁም በአጠቃላይ የሰዎች ደህንነት አደጋ ላይ በሚሆንበት ወቅት ጥቅም ላይ የሚውል ነው። ከዚህ ባለፈም ኩባንያው ለቻይና የቀይ መስቀል ማህበር የ250 ሺህ ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ በመረጃ ማፈላለጊያ ገጹ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በተከፈተ ዘመቻ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰብ ተችሏል። ምንጭ፦ ጎግል
ኤስ ኦ ኤስ ማንቂያ ምን ዓይነት ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት ስራ ላይ የሚውል ማንቂያ ነው?
ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች
734
አዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዕውቁና አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ በውጭ አገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች ወጣቶችን በሳይንስ በማነጽ ተግባር እንዲሰማሩ፤ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር ጥላሁን በቻይና ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የአፍሪካ ሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል ሊያቋቁሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚዘጋጀው ወርኃዊ የሳይንስ ገለጻ መድረክ ወጣቱን ትውልድ ማስተማርና ማነጽ ለኢትዮጵያ ተስፋ፤ የቻይና ተምሳሌትነት በሚል ትናንት ምሽት ገለጻ አድርገዋል። በአውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 1943 በኢትዮጵያ የተወለዱት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች አጠናቀው በቀድሞው የአለማያ እርሻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት በኮሌጅ ቆይታቸው ባሳዩት የላቀ ውጤትም አሜሪካን አገር በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህር ቤት ተልከው ትምህርታቸውን በማጥናት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት አስተምረዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላም ወደ ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በደቂቀ ሥነ ሕይወት መስክ በማጥናት በአውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1980-2006 በተማሩበት ካሊፎርኒያ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አስተምረዋል፤ ተመራምረዋል። እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ደግሞ የዲስቲንጉሽድ ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.አ.አ ከ1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል በማቋቋም በዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ያስተማሩት የት ነው?
በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት
743
ዳምጠው አየለ ዳምጠው አየለ (23.11. 1944 አ/ም – 27.10. 2006 አ/ም) ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፋኝ ነበር። በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል። ዳምጠው ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል። ዳምጠው መራቤቴ እያለ በየባእላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። ባጋጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል። ዳምጠው አየለ ኖርዌይ ሃገር በስደት ለ 8 አመት ያክል ኖሯል። ኢትዮጵያም ከገባ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብራኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ 62 አመቱ ሰኔ 27 2006 አ/ም ቀን ህይወቱ አልፏል። የቀብር ስነስርአቱም ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።
ምድር ጦር የሙዚቃ ቡድን መቼ ተመሰረተ መቼስ ፈረሰ?
በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም
734
አንድ ወጣት ተማሪ ከወዳደቁ ቁሳቁሶች በውሃ ላይ የሚነዳ የብስክሌት ጀልባ መስራቱ ተገለጸ፡፡ ጌታባለው መኩሪያው የተባለው ወጣት በባህርዳር ዩኒቨርስቲ 3ኛ ዓመት የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወጣቱ የወዳደቁ ፒፒሲ ትቦዎች፣ የላሜራ ብረቶችና ፌሮዎች እንዲሁም አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የብስክሌት አካላትን ተጠቅሞ ነው የብስክሌት ጀልባ (Pedal-Boat) መስራት የቻለው፡፡ ጌታባለው መኩሪያው ከወዳደቁ ቁሳቁሶች የሰራውን የብስክሌት ጀልባ በውሃ ላይ በመንዳት ሙከራ ማድረጉም ተገልጿል፡፡
ፈጠራውን እንዴት አድርጎ ለማሳየት ሞከረ?
በውሃ ላይ በመንዳት
281
ከአፍሪካ ህዝብ ውስጥ 24 በመቶ ብቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸውን ዓለም ባንክ አስታወቀ፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት አለመስፋፋት በአህጉሪቱ አዳዲስ ዲጂታል ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ የስራ ዕድል ፈጠራዎችን ለማስፋፋት አዳጋች እንደሚሆን ነው ባንኩ የገለጸው፡፡ በአፍሪካ እኤአ ከ2015 እስከ 2035 ባለው ጊዜ ውስጥ 450 ሚሊዮን ስራ ፈላጊ ወጣቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ የዓለም ባንክና የአፍሪካ ልማት ባንክ በጥምረት ያወጡት ሪፖርት ያመለክታል፡፡ እንደ ኢኮሜርስ እና ፋይናንስ ያሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ የስራ ዘርፎችን በአፍሪካ በማስፋፋት ከፍተኛ የስራ እድልን መፍጠር እንደሚቻል ተጠቅሷል፡፡ በዚህም፣ ወጣቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች በቂ እውቀት እንዲኖራቸው በማድረግ ማሰማራት እንደሚገባ ተነግሯል፡፡
በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከ2015-2035 እ.ኤ.አ ምን ያህል ስራ ፈላጊ ሰዎች ይኖራሉ?
450 ሚሊዮን
202
አሪዞና አሪዞና (Arizona) በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ክፍላገር ነው። ኒው ሜክሲኮ ፣ ዩታህ ፣ ኔቫዳ ፣ ካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ያዋስኑታል። የአሪዞና ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ የ30 ሰው ሴኔት እና የ60 ሰው ምክር-ቤት አለው። የሪፑብሊካን ፓርቲ በስቴቱ ዋነኛው ፓርቲ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. የአሪዞና ስቴት ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ በጀት 14.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በጀት ደግሞ 13.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። የስቴቱ ሴኔተሮች እና ምክር-ቤት ተወካዮች ለሁለት-ዓመት ጊዜ ላልተወሰነ ብዛት ይመረጣሉ። ከ4 ጊዜ በላይ በተካካይ መመረጥ ግን አይችሉም። የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በአስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን ለ4 ዓመት ሥልጣን ላይ ይቆያል። ያልተወሰነ ጊዜ መወዳደር ሲቻል ከሁለት ጊዜ በላይ ግን በተካካይ መመረጥ አይፈቀድም።
በአሪዞና ሴናተሮችና የምክር ቤት አባላት ከስንት ጊዜ በላይ በተከታታይ መመረጥ አይችሉም?
ከ4 ጊዜ በላይ
337
 ቴክኖ ካሞን 17 በዘጋቢ ፊልም ታግዞ ወደ ገበያ መግባቱን ኩባንያው አስታወቀ :: በዓለም አቀፍ ደረጃ በአዲሱ ትውልድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ቴክኖ ሞባይል ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም በለቀቀው አዲሱ የCAMON 17 ተከታታይ ስልክ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ መቻሉን ኩባንያው አስታውቋል:: ይህ ፈጠራ የታከለበት ቴክኖ ካሞን 17 ስልክ ማጠንጠኛውን በሰልፊ ላይ ባደረገ ዘጋቢ ፊልም የተመረቀ ሲሆን ድርጅቱ ምርቱን ከማስተዋወቅ ባለፈ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና በሰብዓዊነት ዘርፎች ላይ የበለጠ ጥረት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል:: “The Rise of Selfie” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ዘጋቢ ፊልም ፊልም በማስመረቂያ ፕሮግራሙ ላይ የቀረበ ሲሆን ታዳሚዎቹ በእርግጥም ቴክኖ የዚህን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት በተጨባጭ እና በስሜት እየሰራ መሆኑን ስለመገንዘባቸው ድርጅቱ ገልጿል:: አዲሱ የቴክኖ የንግድ አምባሳደር ክሪስ ኢቫንስ “ሕያው እና በስሜት የተሞላ ምስል ትፈልጉ ይሆናል፣ ነገር ግን መልካም ምስል የሚያደርገው ‘እጅግ ግለሰባዊ’ ስለሆነ ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም ቴክኖ በፅኑ ከሚያምንበት እና ከሚታወቅበት ሃሳብ ጋር ይጣጣማል ብለዋል፡፡ የስማርት ስልክ ፅንሰ ሃሳብ ብራንዱ ላይ ሳይሆን ተጠቃሚው ላይ ማውጠንጠን እንዳለበትም ነው የንግድ አምባሳደሯ የጠቆሙት፡፡ የፋሽን ሞዴል የሆኑት ሣል በፊልሙ ላይ እንዳሉት እንደ ቴክኖ ካሞን 17 ያሉ የሰልፊ ስልኮች ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ምስል ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ተወዳጅ ፎቶዎችን በማንሳት ምስላቸውን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል:: በተጨማሪም የተሻለ ማንነት እንዲኖር ለማድረግ እዲሁም በደመነብስ ወደተሻለ እኛነት እንድንመጣ ለራሳችን የምንጠቁምበት መንገድ ነው ብለዋል:: ቴክኖ ካሞን 17 ሁልጊዜ “በልባቸው ወጣት” ለሆኑ እና ለአዳዲስ ነገሮች ራሳቸውን ለሚያነሳሱ ተጠቃሚዎች ምልክት ለመሆን የተሰራ ነው ያለው ድርጅቱ፥ ሰዎች ራሳቸውን በይበልጥ ለመግለጽ እንዲችሉ ያስችላቸዋልም ብሏል፡፡ ኮቪድ19 ባስከተለው ተጽዕኖ ሰዎች ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ለመገናኘት ሰልፊን ማዘውተራቸው የሰልፊን ተግባር ይበልጥ አስፈላጊ ያደረገው በመሆኑ ጉዳዩን ቴክኖ እና ሌሎች የስልክ አምራቾች በአጽንኦት እንዲያጤኑት አድርጓቸዋል:: በቴክኖ ካሞን 17 ስልክ ሰዎች ህይወት ያላቸው የሚመስሉ ፎቶዎችን ማጣጣም ብቻ ሳይሆን በFHD ስክሪን ላይ በጣም ግልጽ የሆነ ምስልን ማየት እንደሚያስችላቸው ነው የተገለጸው:: ይህ ከፍተኛ ጥራት ያለው ስክሪን ተጠቃሚዎች በቪዲዮ ጥሪዎች ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ተወዳዳሪ የሌለው ግልጽነት የሚሰጣቸው ሲሆን ተጠቃሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መመልከት እና ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ጌሞችን መጫወት እንደሚችሉም ነው ኩባንያው የገለጸው፡፡ ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!  
በዘጋቢ ፊልም ታጅቦ የቀረበው አዲስ የቴክኖ ሞባይል ምን ተብሎ ይጠራል?
ቴክኖ ካሞን 17
1
ቻይና በማርስ ላይ የምታካሂደውን የመጀመሪያ ሳይንሳዊ ጥናት የፊታችን ሃምሌ ወር እንደምትጀምር ይፋ አድርጋለች። ጥናቱን የምታከናውነው ሳተላይት ሎንግ ማርች 5-ዋይ 4 በተሰኘ ሮኬት ወደ ህዋ እንደምትላክም የቻይና የጠፈር ምርምር ተቋም አስታውቋል። ሮኬቱ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅ የሚያሰችል አቅም እንዳለው በሙከራ ተረጋግጧልም ነው የተባለው። ከሃይድሮጅን እና ኦክስጅን ጋዞች የተሰራ ሞተር ያለው ሮኬት በተያዘው ዓመት በርካታ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ያደርሳል ተብሎ ታምኖበታል። ወደ ህዋ የምትላከው ሳተላይትም በማርስ ፕላኔት ዙሪያ በርካታ አዳዲስ ግኝቶች እና መረጃዎችን ለምርምር ተቋሙ ታደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።
ቻይና የምትልከው ሳተላይት ምን በሚባል ሮኬት ወደ ህዋ ይላካል?
ሎንግ ማርች 5-ዋይ 4
92
አልፍሬድ ኢልግ ቢትወደድ አልፍሬድ ኢልግበዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ኑሮውን ኢትዮጵያ ውስጥ የመሠረተ፤ የስዊትዘርላንድ ዜጋ ነበር። ኢልግ በምሕንድስና ሙያው ባቡር እና የቧንቧ ውሐ ለአገራችን ካስተዋወቃቸው ብዙ ዘመናዊ የሥልጣኔ መስመሮች ሁለቱ ሲሆኑ በንጉሠ ነገሥቱ ፊት ታላቅ ታማኝነትን በማፍራቱ የዘውድ አማካሪ እና የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ እስከመምራትም የበቃ ሰው ነበር። ቢትወደድ ኢልግ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ሚና ከተጫወቱ አውሮፓውያን መሃል ባገሪቱ ባሳለፋቸው ሃያ ሰባት ዓመታት እና ባስቀመጣቸው የልማት አሻራዎቹ የታሪክ ሥፍራው በጣም የጎላ ሆኖ እናገኘዋለን። ኢልግ በስዊትዘርላንድ፣ ፍራውንፌልድ በሚባል ከዙሪክ ከተማ በሰሜን-ምሥራቅ አቅጣጫ በሚገኝ ሥፍራ በ መጋቢት ወር ፲፰፻፵፮ ዓ/ም ተወልዶ በስድሳ ሁለት ዓመቱ የገና ዕለት (ታሕሣሥ ፳፱ ቀን) ፲፱፻፰ ዓ/ም ዙሪክ ላይ በልብ ምታት ምክንያት አረፈ። ታዋቂው የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ዳግማዊ ምኒልክ ገና በልጅነታቸው የዓፄ ተዎድሮስ እስረኛ በነበሩ ጊዜ ቴዎድሮስ አጠገባቸው የነበሩትን አውሮፓዊ ወንጌላያን መድፍና መሣሪያዎች እንዲሠሩላቸው ማግባባታቸውን ልብ አድርገው ነበርና የሸዋ ንጉሥ ሲሆኑ በ ኤደን ላይ የነበረ አንድ የስዊትዘርላንድ ዜጋ ነጋዴ ምሕንድስና የሚያውቁ አውሮፓውያን ባለሙያዎችን እንዲፈልግላቸው ጠይቀውት ነበር ይላል። ኢልግ እና ሁለት የአገሩ ሰዎች በ፲፰፻፸ ዓ/ም አካባቢ ጉዞዋቸውን ወደኢትዮጵያ አምርተው ሸዋ ሲገቡ ንጉሥ ምኒልክ መጫሚያ እንዲሠራላቸው ያዙትና ሠርቶ ባበረከተላቸውም መጫሚያ እጅግ እንደተደሰቱ ይነገራል። በሌላ ዘገባ ደግሞ ንጉሡ ኢልግን ጠመንጃ እንዲሠራላቸው አዘዙት። ኢልግ ጠመንጃ ለመሥራት ሙያ እንደሌለውና ከውጭ የሚመጣ መሣሪያ እሱ ከሚሠራው እጅግ የላቀ እንደሚሆን ቢያስረዳም፤ ምኒልክ ኃሳባቸውን የማይለውጡ ሆኑ። እሱም እንደተጠየቀው የሙከራውን ውጤት ሲያሳቸው ንጉሡ ተደስተው ይሄንኑ ጠመንጃ በግምጃ ቤታቸው የክብር ቦታ ሰጡት። ያም ሆነ ይህ ኢልግ በንጉሡ በኩል ዘለቄታ የነበረው የበጎ አስተያየትን እንዳተረፈ ግልጽ ነው። ወዲያው በምሕንድስና ሥራ በደሞዘኝነት ቀጥረውት በየወሩ ሰባት ወይም ስምንት ፓውንድ በጠገራ ብር ይከፍሉት እንደነበር ፓንክኸርስት ዘግቧል።
ንጉስ ምኒልክ ኢልግ እንዲሰራላቸው ያዘዙት ምን ነበር?
ጠመንጃ
929
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል። በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። የገብላዊ ልጆች የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል። ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው። ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው። ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
ተወዳጅነት ካተረፈበት ስራዎቹ መካከል በ1971 ያሳተመውጀ ድርሰቱ ምን ይባላል?
ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ
334
አሦር አሦር (አሹር) ማለት በጥንታዊ ዘመን በላይኛ ጤግሮስ ወንዝ አጠገብ የተገኘ ከተማና አካባቢው ነበረ። በኋለኛ ጊዜ የአሦር መንግሥት ሃይለኛ ሆኖ መላ መሬት እስከ ግብጽ ድረስ ገዛ። በጥንታዊ አሦር ከተማና በጤግሮስ አጠገብ ያሉትም ተራሮች እስከ ዛሬው አርሜንያ ድረስ 'የአሦር ተራሮች' ይሰየሙ ነበር። በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት አሦር (አሹር) ከኖኅ ልጅ ሴም ልጆች አንዱ ሲሆን፥ ከሰናዖር ወጥቶ አንዳንድ ከተማ ሠራ። በአሦራውያንም እምነት ዘንድ 'አሹር' ከተማውን የመሠረተው አምላክ ስም ነበረ። ከቅድመኛው ዘመን አውራጃው ሹቡር ተብሎ ከሰናዖር (ሹመር)፣ ማሪ ወይም ከአካድ ይገዛ ነበር። ሹቡር በታላቁ ሳርጎን መንግሥት ውስጥ ክፍል ሆኖ ጉታውያን እስከ አጠፉት ድረስ ቆየ። በኋላ እስከ 1879 ዓክልበ. ግ. ከኡር 3ኛ ሥርወ መንግሥት ይቆጣጠር ነበር። የዑር መንግሥት ሲወድቅ የአሦር ከተማ ነገሥታት ሊሙ ስሞች ይመዘገባሉ። በዚህ ወቅት አሦር ከተማ-አገር ብቻ ነበረ። ሆኖም አሦራውያን የብረታብረት ንግዳቸውን ለማስፋፋት በማሰብ አንዳንድ ቅኝ-ከተማ (ካሩም) በሐቲ (ዛሬው ቱርክ) ውስጥ መሠረቱ። ከነዚህም ዋነኛው ካነሽ የተባለው ከተማ ነበር። በ1720 ዓክልበ. ግ. አሞራዊው ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ አገሩን ከነአሦር ከተማ አቀና። ልጁን 1 እሽመ-ዳጋን (1688-1678 ዓክልበ.) በአሦር ላይ ሾመው። ነገር ግን የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ ድል አድርጎት ዙሪያው ወደ ባቢሎን መንግሥት ተሳለፈ። ከትንሹ እስያ ይካሄድ የነበረው የብረታብረት ንግድ በዚያን ጊዜ ተቋረጠ። ለሚከተለው መቶ አመት አሦር ለባቢሎን ተገዥ ነበር። በ1507 ዓክልበ. ግ. ባቢሎን ለካሣውያን ከወደቀ በኋላ፥ አሦር በሚታኒ መንግሥት (ሑራውያን) በ1441 ዓክልበ.ግ. ይሸነፍ ነበር። ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ ግን የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ (1366 ዓክልበ. ያህል)። ከዚህ በላይ ይህ አሹር-ኡባሊት የራሱን ልጅ ኩሪጋልዙን በባቢሎን ዙፋን ላይ አሾመው። በ1290 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥት አሸነፈ። የአዳድ-ኒራሪ ተከታይ 1 ስልምናሶር መንግሥቱን በከጢያውያን አግጣጫ እስከ ከርከሚሽ ድረስ አስፋፋ። የስልምናሶርም ልጅ 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ እንኳን በባቢሎን ላይ ገዛ። ሆኖም በቅርብ ጊዜ ባቢሎን በአሦር ላይ አመጽ ታደርግ ነበር። በ1200 ዓክልበ.. አካባቢ የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ስለ ወደቀ፥ ባቢሎንና አሦር ለአሞራውያን መሬት ተወዳዳሪዎች ሆኑ። የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በዚህ አቅራቢያ በ1140 ዓክልበ. በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ። የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ 1 ቴልጌልቴልፌልሶር የመንግሥቱን ጠረፍ በጣም አስፋፋ። ከርከሚሽን ከመማረኩ በላይ በሙሽኪ ላይ እስከ ጥቁር ባሕር ድረስ ዘመቻ አደረገ። ደግሞ እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ ሲዘረጋ ፊንቄን (ሊባኖስ) ያዘ። ከ1 ቴልጌልቴልፌልሶር በኋላ ከጎረቤቶቹ ከአራማውያንና ከኡራርቱ የተነሣ የአሦር ኅይል ደክሞ ነበር። በ920 ዓክልበ. ግን 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆሞ የአሦር ሃይል ታደሰ። ደግሞ ወደ ስሜን የኖሩትን ሕዝቦች በሙሉ በሰፈራ አፈለሳቸው። ይሁንና መንግሥቱ ከአቦር ወንዝ ወደ ምዕራብ አልዘረጋም። ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ከ890 ዓክልበ. ጀምሮ ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹም አስፋፋ። ከአቦርና ከኤፍራጥስ መካከል ያሉትን አራማውያን ድል አድርጎ በሜድትራኒያን ሲደርስ ፊንቄን ቀረጠ። ካልሁንም ዋና ከተማው እንዲሆን አደረገው። በልጁ 3 ስልምናሶር 34 አመት ዘመን (865-831 ዓክልበ.) አሦር በየአመቱ ለጦርነት ሠለፈ። ባቢሎን ተወርሮ ተቀረጠ። የሶርያ (አራም-ደማስቆ) ንጉስ ወልደ አዴር (አድርአዛር) ከእስራኤል ንጉስ አክዓብ ጋራ በቃርቃር ፍልሚያ ስልምናሶርን አጋጠመው። ስልምናሶርም ፊንቄንና የእስራኤል ንጉስ ኢዩን አስቀረጠ። በዋና ከተማው በካልሁ የተገኘው ጥቁር ሐውልት ስለ 3 ስልምናሶር ዘመን ድርጊቶች ይመሰክራል።
በ1720 ዓክልበ. ግ. ከነአሦር ከተማን ያቀናው የአሞራዊው ንጉሥ ማን ይባላል?
ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ
685
አፋር (ክልል) አፋር ክልል (ክልል 2) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ዋና ከተማው ሰመራ ሲሆን የቀድሞዋ ከተማ ግን አሳይታ ነበረች። 96,707 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሸፍን በ1999 እ.ኤ.አ. የሕዝብ ብዛቱ 1,188,000 ነው። የድንቅ ነሽ ወይም ሉሲ አጽም በአፋር ክልል ውስጥ በ, 1967 (Nov. 24, 1974 እ.ኤ.አ.) ነው የተገኘው። በማርች 5, 2005 ደግሞ ሌላ 3.8 ሚሊዮን ዓመት የሚገመት አጽምም በዚሁ ክልል ተገኝቷል።
በአፋር ክልል ከሉሲ በተጨማሪ አዲስ የተገኘችው የሰው ቅሪተ አካል መቼ ተገኘች?
3.8 ሚሊዮን ዓመት
256
አፄ ዘርአ ያዕቆብ አጼ ዘርአ ያዕቆብ በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስት ክብረ እግዚእ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮውፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ(ከቀኝ ያለውን ካርታ ይመልከቱ) ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው። የዘርዓ ያዕቆብ አባት ቀዳማዊ ዳዊት ባረፉ ጊዜ፣ እንደ ጥንቱ የኢትዮጵያ ባህል ወግ መሰረት፣ ታላቅ ወንድማቸው የነበሩት ቀዳማዊ ቴወድሮስ በ1414 ሲነግሱ ታናሽ ወንድማቸውን በግዞት ወደ አምባ ግሽን እንዲሄድ አደረጉ። አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሀፈ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው መሰረት እስከ ነገሱበት ሰኔ 20 ፣ 1434 ዓ.ም. ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ (አምባ ግሸን) ላይ ለሚቀጥሉት 20 አመታት በእስር ኖሩ። ሆኖም ግን በግዞት እያሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊያቸው መጠን እየበዛ ሄደ። በነዚህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዓመት ወደ ዓመት እይተበላሸ ሂዶ በመጨረሻ ከአምባው ላይ ለሹመት ሲወርዱ አገሪቱ በእርስበርስ ሽኩቻ እየታመሰች፣ በሃይማኖት በኩልም መከፋፈል ተፈጥሮ የውጭ ሀይሎችም ከነገ ዛሬ አጠቁን እየተባለ ይሚፈራበት ሁኔታ ገጠመው። የወደፊቱ ንጉስ ብዙ እድሜውን ያሳለፈው ከሰው ተለይቶ አምባ ላይ ስለነበር፣ የዲፕሎማሲ ጥቅሙ አልተረዳውም ነበር። ይልቁኑ ፊት ለፊት የተጋረጡትን የሃገሪቱን ችግሮች በሚያስፈራ ድፍረት እና ምንም በማያወላዳ ጽናት ተጋፈጠው። ዓፄ ዘርአ ያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ንግስት እሌኒን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ። በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤተክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን ቆይቱ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳተ በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል ። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቀ እስጢፋ ወገኖች እምነት ነው። እነዚህ እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴ ባስተማራቸው መሰረት ለመስቀል መስገድና ለስእል አድኅኖ ለድንግል ማርያም መስገድ አይገባም የሚሉ ነበሩ።ተከራክረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ አሸንፈዋል። በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀው ግዛታቸውን ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር። በ1456 ዓ.ም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ በነበሩበት ቦታ ታላቅ ብርሃን ስለታየ የነበሩበትን ቦታ ደብረ ብርሃን በማለት የሃገሪቱ ዋና ከተማ አድርገው ቆርቁረዋል። እስከ እለት ህልፈታቸውም ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበረች።ኢትዮጵያዊ መንፈሳዊ ፈላስፋ። አጼ ዘርአ ያዕቆብ በጦር ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን የሚታወቁት፣ ከ 20 በላይ መጻህፍትንም በመድረስና ለትውልድ በማቅረብ ጭምርም ነው።
አጼ ዘርአ ያዕቆብ የነበሩበት ከተማ እንዴት ደብረ ብርሃን ብለው ሊያወጡለት ቻሉ?
በነበሩበት ቦታ ታላቅ ብርሃን ስለታየ
1,343
ሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው። ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ የእንግሊዝን አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ። ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በሩሲያኖች የተገነባው የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ እራሳቸውን ከሥልጣናቸው አስወገዱ። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - አቶ ለገሰ ዜናዊ አስረስ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አድዋ ላይ ተወለዱ።
የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት በገጠሙት ውጊያ የተማረከው ንጉስ ማን ይባላል?
ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት
238
ሴኔጋል ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒና ጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 14 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል። የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ። በአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋል፣ ኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።
ሴኔጋል የቆዳ ስፋቷ ምን ያህል ነው?
197,000 ካሬ ኪ.ሜ
170
የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ላይ በአሜሪካ፣ በቺሊና በፔሩ በተደረገ ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት የሌለውና አስተማማኝ መሆኑን የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በሶስቱ አገሮች በሁሉም የእድሜ ክልል በሚገኙ 32 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ላይ ባደረገው ምርምር ክትባቱ ውጤታማና ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው መሆኑን ማረጋገጡን የሮይተርስን ዋቢ አድርጓ ኢዜአ ዘገቧል ፡፡
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት አስተማማኝነት በተመለከተ በስንት ሀገሮች ጥናት አደረገ?
በሶስቱ
112
አዳማ /ኢዜአ/መስከረም 23/2012 የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ስምንት የምርምርና የልህቀት ማእከላት እያደራጀ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሾመ አብዶ ለኢዜአ እንደገለጹት ግንባታቸው ከ90 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው የምርምር ፓርኮችንና የልህቀት ማዕከላትን በመሳሪያ ለማደራጀት 86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት ተመድቦ እየተሰራ ነው ብለዋል። በዚህም ሁለት ሊትል ስታር የተባሉ ሳተላይቶች በደቡብ ኮሪያና ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች በመገጣጠም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የፋርማቲካል የልህቀት ማእከሉ የባህል መድኋኒቶችን በመቀመምና በምርምር በማዘጋጀት ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ምርት እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ተሾመ በተለይም በባህላዊ መድኋኒቶች ዙሪያ በትኩረት የምርምር ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል። የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በ19 የትምህርት ፕሮግራሞች ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በኤክስቴሽን ፕሮግራም ተቀብሎ ማስተማር ላይ ይገኛል።
የአዳማ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ባሉት የትምህርቶች ፕሮግራሞች ምን ያህል ተማሪዎችን እያስተማረ ነው?
ከ6 ሺህ በላይ
567
አዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።
በኢትዮጵያ ከባህር ጠለል 2500 ሜትር ከፍታ የምትገኝ እንዲሁም በሀገሪቱ ትልቋ ከተማ ማን ትባላለች?
አዲስ አበባ
167
ሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው። ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ የእንግሊዝን አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ። ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በሩሲያኖች የተገነባው የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ እራሳቸውን ከሥልጣናቸው አስወገዱ። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - አቶ ለገሰ ዜናዊ አስረስ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አድዋ ላይ ተወለዱ።
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ይባላሉ?
ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ
850
ልዑል ራስ መኮንን የንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክ ተወካይ ሆነው ሁለት ጊዜ የአውሮፓን አገሮች ጎብኝተዋል። በዚህ ጊዜ እሳቸው ኢጣሊያን ሲጎበኙ በነበረ ጊዜ የኢጣሊያ ጋዘጦች የውጫሌ ውልን በተመለከተ፤ «...በውጫሌ ውል ላይ ኢትዮጵያ የኢጣሊያን ጥገኝነት ተቀብላ ውል ከፈረመች በኋላ የጀርመን ንጉሠ ነገሥት ከኢትዮጵያ የሚላከውን ማንኛውንም ደብዳቤም ሆን ጉዳይ በኢጣሊያ መንግሥት በኩል መቀበል ሲገባቸው በቀጥታ ከምኒልክ የተጻፈውን ደብዳቤ ተቀብለዋል...» እያሉ የጻፉትን ራስ መኮንን ተቃውሞአቸውን ለኢጣሊያ መንግሥት ከነገሩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የውሉን መበላሸት ለአጤ ምኒልክ አሳወቁ። ከኢጣሊያንም ጋር በተደረገውም ጦርነት ራስ መኮንን ፲፭ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ይዘው ከምኒልክ እና ታላላቅ ጦር አዛዦች ጋር ዘምተዋል። በ፲፰፻፺፰ ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለኅክምና ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ጥር ፬ ቀን ከከተማቸው ከሐረር ተነሱ። ጥር ፱ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የጥምቀትን በዓል አክብረው ከዋሉ በኋላ ሕመሙ ስለጸናባቸው ወደ ኋላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር። እዚሁም ሲታመሙ ከቆዩ በኋላ መጋቢት ፲፫ ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም ቁልቢ ላይ አርፈው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ። ዐፄ ምኒልክም የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው አዲስ አበባ እንዲሆን ባዘዙት መሠረት፤ ሰኞ ሚያዝያ ፳፪ ቀን በአዲስ አበባና በዙሪያው ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የክርስቲያን የፍታት ጸሎት ተድርጎ በማግስቱም ማክሰኞ የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ ፳፫ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ፤ መኳንንቱና ሠራዊቱ ተሰብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውና የራስ ወርቃቸው፤ ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸው ተይዞ ፈረስና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊቱ መካከል እየተመላለሱ ታላቅ ልቅሶ ተለቀሰላቸው።
የኢጣልያ ጋዜጦች የውጫሌ ውል ስምምነትን አላከበሩም ብለው የጀርመንን ንጉሠ ነገስት የወቀሱት ምን በማድረጋቸው ነበር?
ከኢትዮጵያ የሚላከውን ማንኛውንም ደብዳቤም ሆን ጉዳይ በኢጣሊያ መንግሥት በኩል መቀበል ሲገባቸው በቀጥታ ከምኒልክ የተጻፈውን ደብዳቤ ተቀብለዋል
194
ጮቄ አስደሳቹ ስፊውና ማራኪው ጮቄ በቢቡኝ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ የተፈጥሮ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ወረዳዋ በስፋት የምትታወቅበት አስደናቂና ከፍተኛ የሆነ ተራራማ ቦታ ነው። ጮቄ ከወረዳዋ ድጓ ፅዮን ከተማ 10 ኪ/ሜ ፣ ከዞን ዋና ከተማ ከደ/ማርቆስ 61 ኪ.ሜ፣ ከክልል ዋና ከተማ ከባህር ዳር 325 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ጮቄ በእፅዋት ብዝሀነት የታደለና ከ85 በላይ አገር በቀል እፅዋት የሚበቅልበት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዋና ዋናዎቹ፡- ጅባራ፣ ጓሳ፣ አስታ፣ ቅርቅሃ፣ አምጃ፣ አሸንግድየ፣ ዝግባ/ግምይ/ ተጠቃሽ ናቸው። አባይን ያረገዘ ጮቄ አካባቢው የአባይ ወንዝ የውሃ ምንጭ ሲሆን የአባይ ተፋሰስ የውሃ ማማ እንደሆናና ከአባይ 9.5% ተፋሰስ ድርሻ ያለው ተራራማ የውሃ ስፍራ ነው። እንደ አጠቃላይ ሲታይ የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ (East Africa water Tower) የሆነው ጮቄ የአባይ ገባር የሆኑ 273 ትናንሽ የውሃ ጅረትና ከ23 በላይ የሚሆኑ ታላላቅ ወንዞች መፍለቂያ ነው። ከታላላቅ ወንዞች መካከል እናት ሙጋ፣ ግልገል ሙጋ፣ ተምጫ፣ ዝምብል፣ ትልቁ አብያ፣ ትንሹ አብያ፣ ጨሞጋ፣ ጌደብ፣ ጥጃን፣ ጠፍ፣ ጦመ፣አዝዋሪ፣ ተጠቃሽ ሲሆኑ ከነዚህም ቢቡኝ ወረዳ ውስጥ የሚገኙት፡- ዝምብል፣ ትልቁ አብያና ትንሹ አብያ ናቸው። የጮቄ ተራራ ከባህር ወለል በላይ 4088 ሜትር አካባቢ ከፍታ ያለው በመሆኑ የጎጃም ጣራ ( The roof of Gojjam) በመባል ይታወቃል። የጮቄ ተራሮች በምስራቅ ጎጃምና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች ዘጠኝ ወረዳዎች ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ጠቅላላ ስፋቱም 53558 ሄክታር በላይ እንደሚደርስ ጥናቶች ያመለክታሉ። ጮቄ በጣም ሰፊ ከመሆኑም የተነሳ ገና ብዙ ያልታወቁ ዋሻዎች፣ ጥንታዊ መኖሪያዎችና ያልተዳሰሱ አስደሳች የተፈጥሮ መስህቦች አሉት ፡፡ የጮቄ አካባቢ፡- በስተ ምስራቅ እነማይና እናርጅ እናውጋ፣ በስተ ሰሜን ምስራቅ 2 እጁ እነሴ በስተ ሰሜን ቢቡኝ በምዕራብ ማቻከል፣ በስተ ደቡብ ስናን እንዲሁም በስተ ደቡብ ምስራቅ ደባይ ጥላት ግን ወረዳዎች ያዋስናል። ይህ ተራራ በዋናነት በቢቡኝ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አምስት ቀበሌዎችን ያቀፈ ነው፡፡ እነሱም፡- አሩሲ መሰሳቢያ ደድ ደብረ ፅዮን ደብረ ጊዮርጊስና ወንበር ቅዱስ ዮሐንስ ቀበሌዎች በዋናነት ይገኛሉ፡፡
በጮቄ ወረዳ ምን ያህል የአባይ ገባሮች እና የውሃ ጅረቶች ይገኙበታል?
የአባይ ገባር የሆኑ 273 ትናንሽ የውሃ ጅረትና ከ23 በላይ የሚሆኑ ታላላቅ ወንዞች መፍለቂያ
524
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በህፃናት ልብ ህክምን ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ዶክተር በላይ አበጋዝ እና 30ኛ አመቱን በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልብ ህክምና ማዕከል ያላቸውን አስተዋፅኦ በማድነቅ ሽልማት አበረከቱ።
በኢትዮጵያ ልብ ህክምና ማዕከል 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ዶ/ር አብይ አህመድ ዶ/ር በላይ አበጋዝን በምን ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው የሸለሟቸው?
በህፃናት ልብ ህክምን
25
ኤስፔራንቶ ኤስፔራንቶ (Esperanto) ከሁሉም አለማቀፋዊ ሠው ሰራሽ ቋንቋዎች እጅጉን የተስፋፋ ቋንቋ ነው። በ1859 እ.ኤ.አ. በዛሬይቷ ፖሎኝ የተወለደውና በሞያው የአይን ሀኪም የሆነው ሉድዊክ ሌይዛር ዛመንሆፍ በ1887 እ.ኤ.አ. ቋንቋውን ለህዝብ አሳወቀ። አላማው ኤስፔራንቶን በቀላሉ ሊማሩት የሚቻል፣ የጋራ የሆነና ለአለማቀፋዊ መግባባት የሚረዳ ግን ያሉትን ቋንቋዎች የማይተካ ቋንቋ ማድረግ ነበር። ኤስፔራንቶ ከ1,600,000 በላይ ተናጋሪዎች ቢኖሩትም የቋንቋው ደጋፊ ያልሆኑ እንግሊዝኛን ከመስፋፋቱ አንፃር ለአለማቀፋዊ ቋንቋነት በተሻለ ይመርጡታል።
ኤስፔራንቶ የተሰኘውን ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ ያስተዋወቀው ሉድዊክ ሌይዛር ዛመንሆፍ የተወለደው መቼ ነው?
በ1859 እ.ኤ.አ.
70
የቴክኖሎጂ ኩባንያው አፕል 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ተቀጣ። ኩባንያው በፈረንሳይ የንግድ ውድድርና ሸማች ባለስልጣን ከንግድ ውድድር ህጉ ውጭ ተንቀሳቅሷል በሚል ነው ለቅጣት የተዳረገው። ቅጣቱ የተጣለበት መስሪያ ቤቱ በኩባንያው ላይ ለ10 ዓመት ምርመራ ካደረገ በኋላ ነው ተብሏል። አፕል ከንግድ ውድድር ህጉ ውጭ ዋጋዎችን በመወሰንና በሌሎች የገበያ ተወዳዳሪነት ላይ ተፅዕኖ አሳርፏል በሚል ቅጣቱ እንደተወሰነበትም ታውቋል። ከዚህ ባለፈም ሁለት የአፕል አከፋፋዮች ላይ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል። አካፋፋዮቹ አፕል ገበያውን ብቻውን እንዲቆጣጠር በማሴር ነው ማዕቀብ የተጣለባቸው። ኩባንያው በፈረንሳይ የ40 ዓመት አገልግሎት በመስጠት ለ240 ሺህ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በአፕል ኩባንያ ላይ ስንት አመት ምርመራ ከተደረገ በሁዋላ ነው የተቀጣው?
ለ10 ዓመት
148
የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች አሉ። እነዚህም መሣሪያዎች የጅማት፣ የትንፋሽና የምት ተብለው ወደ ሶስት ይከፈላሉ። የክር ሙዚቃ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በንዝረት ነው፤ ክራር መሰንቆ ከዚህ የሙዚቃ መሳርያዎች ወገን ይመደባሉ፡፡ የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በትንፋሽ ኃይል ነው ምሳሌ ዋሽንት። የምት የሙዚቃ መሣርያ እንደ ከበሮ ሲመቱ ድምጽ የሚያወጡ ናቸው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የባህል ሙዚቃ መሳሪያዎች መደቦች ምን ምን ናቸው?
የጅማት፣ የትንፋሽና የምት
72
ፀሐይ ፀሓይ በምድር ሥርዐተ-ፈለክ መኻል ያለች ኮከብ ናት። ምድር ሞላላ ቀለበት በሚመስል የዑደት ምሕዋር እየተጓዘች ፀሓይን ትዞራታለች። ሌሎች ሰማያዊ አካላትም፣ ፈለኮች፣ ፈለክ-አስተኔዎች፣ ጅራታም ከዋክብት እና ኅዋዊ ብናኞች በፀሓይ ዙሪያ ይዞራሉ። ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገውን አንድ ዙር ጉዞ ለመጨረስ አንድ ዓመት ይፈጅባታል፤ ይህን ጉዞ ስታደርግም በገዛ ራሷ ዘንጎ ወይም ምሽዋር ዙሪያ እየሾረች ነው። ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገው ዙረት ወቅቶች በዓመታዊ ዑደት እንዲለዋወጡ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ሲኾን፣ በራሷ ዘንጎ ዙሪያ የምታደርገው ሹረት ደግሞ በዕለታዊ ዑደት መዓልት (ቀን) እና ሌሊት ለሚያደርጉት መፈራረቅ ምክንያት ነው። ፀሓይ ለሥርዐተ-ፈለካችን በጣም ብሩህ የኾነ ብርሃን ትሰጣለች። ያለ ፀሓይ ብርሃን ሙቀትም ኾነ ሕይወት በምድር አይኖርም ነበር። ለምሳሌ አረንጓዴ ዕፅዋት ያለ ፀሓይ ብርሃን ሊኖሩ አይችሉም፤ ለህልውናቸው የሚያስፈልጓቸውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አልሚ ምግቦች ለማስተጻመር የሚችሉት በፀሓይ ብርሃን ብቻ ነውና። ከምድር ይልቅ ለፀሓይ ይበልጥ ቅርብ የኾኑ ፈለኮች ለከፍተኛ ጨረር እና ግለት የተጋለጡ በመኾናቸው በምድር ላይ ላለው ዐይነት ሕይወት ተስማሚ አይደሉም። ከምድር ጋር ሲነጻጸር ከፀሓይ በጣም ርቀው ያሉ ፈለኮችም ለሕይወት መኖር ምቹ ኹኔታዎች የሏቸውም፤ በቂ ብርሃን እና ሙቀት ካለማግኘታቸው የተነሣ።
መሬት በጸሐይ ዙሪያ የምታደርገው ዑደት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
አንድ ዓመት
196
የህንዱ ኩባንያ በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጉማሬ ወረዳ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ 3,012 ሔክታር መሬት ለሻይ ቅጠል ልማት ተሰጥቶታል፡፡ ይህ ቦታ መሰጠቱ አግባብ አለመሆኑ ተጠቅሶ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎችና የአካባቢ ጉዳይ ተሟጋቾች ቅሬታ ቢያቀርቡም፣ መሬቱን የሰጠው ግብርና ሚኒስቴር ቦታው ላይ ያሉት ዛፎች ትልልቅ ሳይሆኑ ቁጥቋጦ ናቸው በማለት ሲቀርብ የነበረውን ቅሬታ ውድቅ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ኩባንያው ጣውላ በሕገወጥ መንገድ ሲያመርት በመገኘቱ የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከሦስት ዓመታት በኋላ ቬርዳንታ ሐርቨስት በዓለም አቀፍ ሕግጋትም ሆነ በኢትዮጵያ ሕግ በፅኑ የተከለከለውን የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ ማካሄዱ፣ በአካባቢው ባለሥልጣናት ቁጣ መቀስቀሱ እየተነገረ ነው፡፡ ‹‹ሠራተኛ መቅጠር ከፈለገ በሠራተኛና በአሠሪ ሕግ መሠረት መሆን ይኖርበታል፤›› በማለት አቶ ዮናስ ኩባንያው የፈጸመው ተግባር ሕገወጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጋት ሉዋክ ቱሉና ምክትላቸው ኢንጂነር ኦሌሮ ኤፒዮ በጉዳዩ ላይ መረጃው እንዳልቀረበላቸው ተናግረዋል፡፡
በቬርዳንታ ሐርቨስት ትላልቅ ዛፎችን ጨፍጭፏል ተብሎ የቀረበበትን ክስ የነበሩት ትላልቅ ዛፎች ሳይሆኑ ቁጥቋጦዎች ናቸው ብሎ የገለጸው መስሪያ ቤት ማነው?
ግብርና ሚኒስቴር
195
አፖሎ 11 አፖሎ 11 ለመጀመሪያ ጊዜ ሰወችን ከመሬት ወደ ጨረቃ ለማጓጓዝ የተዘጋጀ የመንኮራኩር ሚስዮን ነው። ይህ ጉዞ የተቀናበረው በአሜሪካው የጠፈር አጥኝ ተቋም ናሳ ነበር። መንኮራኩሩ ሐምሌ16 1961ዓ.ም ከመሬት ሲመጥቅ፣ በውስጡ ሶስት ጠፈርተኞችን፣ ማለትም ኔል አርምስትሮንግ፣ በዝ አልድሪንና ማይክል ኮሊንስን የያዘ ነበር። መጓጓዣ መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ ከ4 ቀን በኋላ ሐምሌ 20 ሲደረስ፣ በዚሁ ቀን አርምስትሮንግና አልድሪን የጨረቃን ምድር በእግራቸው በመርገጥ የመጀመሪያወቹ ሰዎች ሆኑ። ኮሊንስ ባንጻሩ በጨረቃ ከባቢ በመብረር ከላይ ይጠብቃቸው ስለነበር ጨረቃን አልረገጠም። ይህ ድርጊት በፕሬዘደንት ኬኔዲ "የሰወች ልጅን ጨረቃ ላይ አሳርፎ በሰላም መመለስ" አላማ ያሳካ ነበር። የአፖሎ 11 ሚሲዮን ወደ ጠፈር ሲመነጠቅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰወች በአለም ዙሪያ በቴለቪዥናቸው ተመልክተውታል። ይህን ሚሲዮን ይዞ የተጓዘው ሮኬት ሳተርን ፬ ሲባል ችቦው እየተንቀለቀለ ወደ ሰማይ ጉዞ የጀመረው ኬኔዲ ጠፈር ማዕከል፣ 1961 ዓ.ም. ነበር። መሬትን ከለቀቀ ከ2 ሰዓት በኋላ የጨረቃ ትዕዛዝ ማዕከልና ማረፊያ ሞጅሎቹ ዋናውን ሮኬት ለቀው በጠፈር ጉዞ ቀጠሉ። ከ3 ቀን በኋላ ትዕዛዝ ማዕከሉና ማረፊያው ሞዱል የጨረቃን ምህዋር ተከትለው ጨረቃን መዞር ጀመሩ። ከአንድ ቀን በኋላ ማረፊያው ሞዱል ከትዕዛዝ ማዕከሉ ተላቆ ጨረቃ ላይ አረፈ። በዚህ የማረፍ ተግባር ወቅት የኮምፒውተር ስህተት ስለገጠመ ማረፊያው ሞዱል በኔል አርምስትሮንግ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር ነበር። የሆኖ ሆኖ ለ25 ሰኮንዶች በቂ የሆነ ነዳጅ ሲቀር ማረፊያው መንኮራኩር ኔል አርምስትሮንግንና አልድሪንን ይዞ ጨረቃ ላይ በሰላም አረፈ። ጨረቃ ላይ ስራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሁለቱ ጠፈርተኞች ወደ ማረፊያ መንኮራኩራቸው በመመለስ ለ7 ሰዓት ጨረቃ ላይ ከተኙ በኋላ ከላይ በኮሊንስ ወደ ሚበረው የትዕዛዝ ማዕከል ለመብረር ዝግጅት ጀመሩ። እነ አርምስትሮንግ በጨረቃ ላይ በነበሩበት ጊዜ ብዙ ቁሶችን ትተው ተመልሰዋል። ለምሳሌ ከ73 የአለም መሪወች የተላለፉ መልዕክቶችን፣ የሰላምታ መልክዕት በሁሉ የመሬት ላይ ቋንቋወችና የሁለት ሰው ልጆች ስዕሎችን ትተው ተመልሰዋል። የአሜሪካንንም ባንዲራ በጨረቃ ተክለዋል። ሓምሌ 24 የትዕዛዝ ማዕከሉ መሬት ላይ ሲደርስ ምናልባትም ጠፈርተኞቹ ያልታወቀ አደገኛ ቫይረስ ጨረቃ ላይ አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል በሚል በኳረንታይን ለ3 ሳምንት ከሰው ልጆች ተለይተው ተቀመጡ። ከኳረንታይን ሲወጡ፣ በርግጥም እንደ ታላላቅ ጀግኖች በተለያዩ የአለም ክፍሎች ስማቸው ተጠራ በዋሽንግተን ዲሲና በሜክሲኮ ሲቲ ለጠፈርተኞቹ ትልቅ ሰልፍ ሆነ።
የሳተርን ሮኬት አፖሎ 11 ሚሲዮንን ይዞ ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ጨረቃ ላይ ደረሰ?
ከ2 ሰዓት
607
መጋቢት ፪ ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን ያዘ። ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት (በኋላ ፕሬዚዳንት) ሪቻርድ ኒክሰን ኢትዮጵያን ጎበኙ ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ሊትዌኒያ እራሷን ከሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ውጭ ነጻ መሆኗን አወጀች። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ በልብ ምታት አረፈ።
የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ የተካሄደው መቼ ነው?
፲፱፻፳፱ ዓ/ም
62
በማደግ ላይ ባሉ አገራት የሚኖሩ ህዝቦች ግንባር ቀደም ገዳይ ከሚባሉት በሽታዎች አንዱ የሆነውን የቲቢ በሽታ ለማስቆም የሚያስችል ”EndTB” የተሰኘ ንቅናቄ ተካሄደ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባለፈው ረቡዕ በሒልተን ሆቴል በይፋ ያስጀመረው ቲቢን እናስቁም ንቅናቄ እ.ኤ.አ በ2032 በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ100 ሺህ አስር ብቻ ለማድረስ የታለመ ነው፡፡ ከአዳሱ የፈረንጆች ዓመት እስከ 2032 ዓ.ም ይደረጋል በተባለው በዚሁ “ቲቢን እናስቁም” ንቅናቄ፤ አገራት ሁሉ፤ ተሳታፊ በመሆን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለውን የቲቢ በሽታ ለመግታትና በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በትጋት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው ፕሮግራም ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የግሎባል ቲቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ማርዮ ራቨግሊዮን እንደገለፁት፤ በሽታው በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ስርጭት 133 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች ሲሆን በኢትዮጵያ ቁጥሩ 200 ሰዎች ከ100 ሺህ ሰዎች ይደርሳል ብለዋል፡፡ በሽታውን ለማስቆም በተያዘው ዕቅድ መሰረትም፤ እ.ኤ.አ ከ2016-2032 ዓ.ም ድረስ በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ከ100ሺ አስር ለማድረስ መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡ ዕቅዱ እንዲሳካም አገራት ከፍተኛ ሥራ እንደሚጠበቅባቸውና ለተግባራዊነቱም የመንግስታቱን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የግሎባል ቲቢ ፕሮግራም ዳይሬክተር ማን ይባላሉ?
ዶ/ር ማርዮ ራቨግሊዮን
473
በደቡብ ሱዳን መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ጆንሰን ጁማ ኡኮት የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ልዑኩ አዲስ አበባ ሲገባ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ እና በሌሎች ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
የደቡብ ሱዳንን መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ማን ናቸው?
ጀኔራል ጆንሰን ጁማ ኡኮት
29
ሳህሌ ደጋጎ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል። በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ መሆኑን የሕይወት ታሪኩ ላይ ተጠቅሷል። ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ (በተቋቋመ ጊዜ ) በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁር ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር። ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ፣ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል።
ሣህሌ ደጋጎ የአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች የሚያንቆረቁሩት በየትኛው የራዲዮ ጣቢያ ነው?
በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ
669
ኢትዮጵያ በዓለም ዉስጥ ክሚገኙ ጥንታዊ አገሮች ኢትዮጵያ ቀዳሚ በመሆን ከሁሉም የበለጠ ረጅም እድሜ አስቆጥራለች፡፡ በግእዝ/ዓማርኛ እና በመጽሀፍ ቅዱስ ከተመዘገቡት ተጨባጭ መረጃዎች በተጨማሪ አምስት ሚሊዮን አመት የሚሆነውና በጣም ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የሰው ቅሪት የተገኘው በኢትዮጵያ አዋሽ ሸለቆ አካባቢ ሲሆን ይህም፣ 3.2 ሚሊዮን አመት የሆነውን እዛው አካባቢ የተገኘውን የሉሲን (ድንቅነሽን) አጽም በእድሜ ይበልጣል፡፡ ግብጽን ሲገዛ የነበረው ሄሮደስ የሚባለው ንጉስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ታሪክ ፀሀፊ የጥንቷን ኢትዮጵያ በጽሁፎቹ ላይ ይገልፃታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይም ብዙ ግዜ የምትወሳ ስትሖን በተለይም ብሉይ ኪዳን ላይም የንግስት ሳባ (መከዳ) ኢየሩሳሌም መሄድና ለንጉስ ሰለሞን ከባድ የሆኑ ጥያቄዎች ማንሳቷ ተጽፏል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ያላትን መልክ እንድትይዝ ያደረጋት ንጉስ ሚኒሊክ የንግስት ሳባና የንጉስ ሰለሞን ዘር ናቸው፡፡ የንግስት ሳባ ቤተ መንግስት ፍርስራሽ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በአክሱም አካባቢ ይገኛል፡፡ ክርስትናን ኢትዮጵያዉያን ከመቀበላቸዉ በፊት (ኣስቅድመዉ)  የኦሪትን ህግ ሰለሚያዉቁ ኣመተ ዓለምን ወደታች እየቆጠሩ የጌታን መወለድ ይጠብቁ ሰለነበረ ክርስትናን ለመቀበል ኣላስቸገራቸዉም፡፡ ነገር ግን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በእስልምና መስፋፋት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአውሮፖውያኑ ክርስትያን ርቃ ቆይታለች፡፡
በዓለም ጥንታዊ ከሚባሉት ሀገሮች አንዷ የሆነችው ማናት?
ኢትዮጵያ
30
ነሐሴ ፲፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፩ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፭ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፬ ቀናት ይቀራሉ። ፲፰፻፶ ዓ/ም - በብሪታኒያ ንጉዛት እና በአሜሪካ ኅብረት መኻል በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የተዘረጋውን አዲሱን የቴሌግራፍ መስመር በመመረቅ ንግሥት ቪክቶሪያ እና የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጄምስ ቡካነን የሰላምታ መልእክት ተለዋወጡ። ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአገሪቱን የመጀመሪያ አየር-ዠበብ (አውሮፕላን) በዚህ ዕለት ተረከበ። ሁለተኛው አየር-ዠበብ ከጂቡቲ ወደብ እስከ ድሬዳዋ በባቡር ተጭኖ፤ ከድሬ ዳዋ ደግሞ እስከ አዲስ አበባ አሥራ ስምንት የአውሮፓ የፖስታ ቦርሳዎችን ጭኖ እየበረረ ነሐሴ ፴ ቀን ገባ። ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ዋና መላክተኛ አምባሳደር ዳግላስ ራይት በኢትዮጵያ እና በኬንያ መኻል ያለውን ድንበር ለመስማማት የተዘጋጀውን የውል ረቂቅ ለኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ አስረከበ። ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከ ፲፰፻፸፯ ዓ/ም ጀምሮ በፈረንሳይ ሥር በቅኝ ግዛትነት ትተዳደር የነበረችው ጋቦን በዚህ ዕለት ነፃ ወጣች። ሊዮን ምባ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ሽግግር የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የክብር ዘበኛ ሠራዊት አዛዥ የነበሩት ማዮር ጄነራል ታፈሰ ለማ በደርግ ተይዘው ታሠሩ። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነብሩት አቡነ ቴዎፍሎስ አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ ሕገ-መንግሥት ውስጥ በተካተቱ አንዳንድ አንቀጾች ላይ ቅዋሜ እንዳላቸው አስታወቁ። ፳፻፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ከገዛቸው አሥር ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አየር-ዠበቦች የመጀመሪያውና በሰሌዳ ቁጥር ET-AOQ የተመዘገበው አየር-ዠበብ በዚህ ዕለት ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስቶ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ልጅ ልዕልት ፀሐይ በተወለዱ በ፳፫ ዓመታቸው በዚህ ዕለት አረፉ።
በኢትዮጵያ አብዮታዊ ሽግግር የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የክብር ዘበኛ ሠራዊት አዛዥ የነበሩት ማዮር ጄነራል ታፈሰ ለማ በደርግ መቼ ታሠሩ?
፲፱፻፷፮ ዓ/ም
801
ታኅሣሥ ፳፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፲፫ተኛው እና የመፀው ወቅት ፹፰ተኛው ቀን ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየወሩ ፳፫ኛ ቀን የሰማዕታትን ዓለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስንን ታስታውሳለች። ፲፯፻፷፰ ዓ/ም - የእንግሊዝ ሠራዊት የክዌቤክ ከተማን ከአሜሪካ አስመለሰ። ፲፯፻፺፮ ዓ/ም - በሀይቲ ደሴት የፈረንሳይ ሉዐላዊነት ሲያከትም ደሴቷ በሰሜን አሜሪካ አኅጉር ከአሜሪካ ኅብረት ተከትላ ሁለተኛዋ ነፃ ሪፑብሊክ ሆነች። ፲፰፻ ዓ/ም - በባርነት የተገዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ ኅብረት እንዳይገቡ የሚከለክል ሕግ ተደነገገ። ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ተመሰረተ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ፩ሚሊዮን ፱መቶ ሺ ኪሎ የመዳብ ሽያጭ ወደጃፓን ላከች። መዳቡ በኤርትራ ውስጥ ከሚገኘው የድባሮ መዳብ ማዕድን ቁፋሮ የተገኘ ነው። ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ባንኮችንና የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን የብሔራዊ ንብረት አድርጎ ወረሰ። ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - ጋናዊው ዲፕሎማት ኮፊ አናን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፯ተኛው ዋና ጸሐፊ ሆነው ተሾሙ።
ጋናዊው ዲፕሎማት ኮፊ አናን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሆነው የተሸሙት መቼ ነው?
፲፱፻፹፱ ዓ/ም
573
የኩላሊት ጠጠር የኩላሊት ጠጠር የሚባለው በኩላሊት ውስጥ የጠጣር ነገሮች መጋገር ወይም መሰብሰብ ሲሆን የጠጣር ነገሮቹም ምንጭ በሽንት ውስጥ የሚገኙ የምግብ ንጥረ ነገሮች ናቸው። ፹ በመቶ (80%) ወንዶች በአብዛኛው የኩላሊት ጠጠር ህመም ከ ፴(30)-፵(40) ባለው እድሜአቸው ሲጀምራቸው ሴቶች ላይ ግን ዘግይቶ ይከሰታል። የኩላሊት ጠጠሮች በአመዛኙ ምንም የህመም ስሜትና ጉዳት ሳያስከትሉ በሽንት መስመር ውስጥ አልፈው ከሰውነት ይወገዳሉ ነገር ግን ጠጠሮቹ በመጠን ከጨመሩ (፫(3) ሚሜ አካባቢ ከደረሱ) የሽንት ትቦ ሊዘጉ ይችላሉ የሽንት ትቦ በጠጠር መዘጋት ሽንት በቀላሉ እንዳይተላለፍ (ፓስቴርናል አዞቶሚያ) ብሎም ሽንት ወደ ሁዋላ በመመለስና በኩላሊት ውስጥ በመከማቸት ሃይድሮኔፕሮሊስ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል:: ይሄ ችግር (ሃይድሮኔፕሮሊስ) ከታችኛው የጎድን አጥንት አንስቶ እስከ የዳሌ አጥንት ድረስ ባለው ቦታ በብሽሽትና በታችኛው የምግብ መፍጫ ክፍሎች አካባቢ ለህመም ስሜት (ሬናል ኮሊክ) ይዳርጋል። የኩላሊት ጠጠር ከማቅለሽለሽና የማስታወክ ስሜቶች ትኩሳት በሽንት ውስጥ ደም መኖር በሽንት ውስጥ መግል የሚመስል ፈሰሽ እና በሽንት ጊዜ ከከፍተኛ የህመም ስሜት ጋር ሊያያዝ ይችላል። የኩላሊት ጠጠር መኖር በሰውነት አቁዋም ምርመራዎች (ፊዚካል ኤግዛሚኔሽን) በሽንት ምርመራ በራጅ ምርመራ እንዲሁም በበሽተኛው የበፊት የጤና ምርመራ ውጤቶች ድጋፍ ይታወቃል። የአልትራሳውንድ እና የደም ምርመራዎችም የኩላሊት ጠጠር በሽታ መኖሩን ለማወቅ አጋዥ ይሆናሉ። ለኩላሊት ጠጠር መፈጠር ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉ የአመጋገብ ልምዶች መካከል፤ ውሃ በበቂ አለመጠጣት፣ ከፍተኛ የሆነ የእንሥሳት ሥጋ (ፕሮቲን) መመገብ፣ ጨው (ሶዲየም)፣ የተጣሩ ስኳሮች፣ የፍራፍሬ ስኳር (ፍሩክቶስ)፣ ኦክሳሌት የያዙ ምግቦች (ኦክሳሌት በብዙ ዕፅዋት ውሥጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን በተለይም በሰባ ዶሮ፣ በጥቀር አዝሙድ፣ ፐርስሊ፣ ስፒናች፣ ካካዎ፣ ቸኮላት፣ ኦቾሎኒ፣ አብዛኛዎቹ እንጆሬዎች ውስጥ ይገኛል)፣ የአፕል ጭማቂ እና የኮላ መጠጦች ናቸው።
አንድ ሰው የኩላሊት ህመምተኛ ነው የሚባለው የጠጠሩ መጠን ስንት ሲሆን ነው?
፫(3) ሚሜ
301
ሱዳን ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ (አረብኛ السودان) ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ከሊቢያ ጋር ድንበር ትካለላለች። የአባይ ወንዝ (ናይል) ሀገሪቱዋን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ይከፍላል። የአረብ ባህል ደንበኛ ሲሆን አብዛኛው ሕብዝ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው። ሱዳን ከግብፅ የተጣመረ ረዥም ታሪክ አላት። የመጀመሪያው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1955 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ከዚያም ሁለተኛው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1983 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ተከስቷል። በ1989 እ.ኤ.አ. በሰላማዊ መፈንቅለ መንግሥት ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር ሥልጣን ላይ የወጡ ሲሆን እራሳቸውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ብለው ሾመዋል። የእርስ በርስ ጦርነቱ በሰላም ውል የቆመ ሲሆን ይህ ውል ያኔ የሀገሪቱዋ ደቡባዊ ክፍል ለነበረው ቦታ ራስን የመምራት መብት ሰጥቷል። በጃኑዋሪ 2011 እ.ኤ.አ. በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት በሱዳን ፈቃድ ደቡብ ሱዳን ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ሉዓላዊ ሀገር ሆነች። ዋና ከተማዋ ካርቱም የሱዳን የፖለቲካ፣ ባህል እና ንግድ ማዕከል ናት። የሀገሪቱዋ መንግሥት በይፋ ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ቢሆንም ስልጣን ላይ ያለው ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (National Congress Party) በሁሉም የመንግሥት አካላት ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት በብዙ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ዘንድ መንግሥቱ አምባገነናዊ ተብሎ ይቆጠራል።
የሱዳን ዋና መዲና ማናት?
ካርቱም
95
ኮምፒዩተር ኮምፕዩተር ማለት ማንኛውንም ኢንፎርሜሽን ፕሮሰስ የሚያደርግ ማሽን ነው። ይህንም የሚያደርገው በተርታ የተቀመጡ ትዕዛዞች በመፈጸም ነው። ለብዙ ሰዎች ኮምፒዩተር ሲባል ዐዕምሯቸው ላይ የሚመጣው የግል (ፐርሰናል) ኮምፒዩተር ነው። ነገር ግን ኮምፒዩተር ሲባል በጣም ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል። ላፕቶፕ ፣ ዴስክቶፕ ፣ ማይክሮ-ኮምፒዩተር ፣ ሱፐር-ኮምፒዩተር ፣ ካልኩሌተር ፣ዲጂታል ካሜራ እና ሌሎችንም ያጠቃልላል። ቀድሞ አስሊ ማለት አንድ በሒሳባዊ ትዕዛዝ የተለያዩ የጥንት መሣሪያዎችን እየተጠቀመ ቁጥሮችን የሚያሰላ ሰው ነበር። እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ የተለያዩ ጠቃሚ መሣሪያዎች ተሰርተዋል። ከዛ በኋላ ትልልቅ ማሸኖች መሠራት ጀመሩ። እነዚህ ማሽኖች ከዛሬው ኮምፒዩተሮች(አስሊዎች) ጋር ሲወዳደሩ በጣም ትልቅና ቀርፋፋ ናቸው። የኮምፕዩተር የውስጥ ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው፡- 1.ሞኒተር - የምንሰራውን ነገር እንዲያሳየን፤ምስል፣ጽሑፍ፣ ቪዲዮ ወይም ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ሞኒተር 14 ኢንች፣ 15 ኢንች፣ ወዘተ. እየተባለ ይገላጻል፡፡ 2.ማዘርቦርድ - እናት ሰሌዳ ሁሉም የኮምፕዩተር ክፍሎች(ዕቃዎች)የሚቀዳጁበት 3.ሲፒዩ - የኮምፕዩተሩ አእማሮ እንደማለት ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን ሲፒዩን ከሰው አእምሮ ጋር አንድ ነው ማለት አይደለም፡፡ 4.ሜሞሪ - የምንሰራውን ስራ ወይም ፋይል በጊዚያዊነት አስቀምጠንበት የምንሰራበት፡፡ ሜሞሪበባይት (Bytes) ይለካል፡፡ ከ Bytes ፊት Kilo፣ ማለትም ኪሎባይት (kilobytes)([1,024 ባይቶች ወይም Bytes ማለት ነው፡፡ ] ፣ Mega[1,048,576 ባይቶች ወይም Bytes ] ፣ Giga [1,073,741,824 ባይቶች ወይም Bytes]፣ ወዘተ የሚሉትን ቃላት በመጠቀም ኪሎባይት(kilobyte)፣ ሜጋባይት (megabyte)፣ ጊጋባይት (gigabyte) እያልን የኮምፒዩተር ሜሞሪ መግለፅ እንገልጻለን፡፡ ለምሳሌ 10 MegaBytes ወይም ባጭሩ ሲጸፍ 10MB ይህ ማለት 10,485,760 Bytes ይሆናል ማለት ነው፡፡ 5.ኤክስፓንሽ ስሎት 6.የኤሌክትሪክ ሀይል ማቅረቢያ (power supply) 7.የሲዲ ማሰሪያ (cd drive) 8.ሀርድ ዲስክ (የምንሰራውን ወይም የምንጠቀምበትን ፋይል በቋሚነት ለማስቀመጥ) 9. መሎጊያ (ማውስ) 10.የፊደል ገበታ (ኪቦርድ) የመጀመሪያቹ ኮምፕዩተሮች የሚሠሩት በእንግሊዝኛ ፊደል ብቻ ነበር። ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ ኣገሮች ሊቃውንት በየራሳቸው ፊደላት እንዲሠሩ ኣደረጉ። ኮምፕዩተር በእያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈጠረው ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኣበራ ሞላ ነው። በቅርቡም አያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝና ምልክት ዩኒኮድ የሚባል የዓለም ፊደላት መደብ ውስጥ መግባት ቀጥሏል።
ኮምፒዩተር ላይ የሚታዩ ነገሮችን ለማሳየት የሚጠቅመው ክፍል ምን ይባላል?
ሞኒተር
505
ለሚያንኮራፉ ሰዎች መፍትሄ ይሆናል የተባለው አዲሱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ  ይፋ ተደርጓል። ሚሊዮኖች የሚሰቃዩበት ማንኮራፋት ከጤና መቃወስ ጋር በተያያዘ በቂ የሆነ እንቅልፍ ከመከልከሉ በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኙትን ሰዎች በመረበሽ ማህበራዊ ኑሯችንን ያውካል፡፡ መንስኤዎቹ የመተንፈሻ አካላት የተፈጥሮ ሁኔታና ህመም ሲሆኑ ከ60 እሰከ 80 በመቶ ከ50 አመት በላይ በሆኑ ወንዶች ላይ አንደሚከሰት ጥናቱ ያመላክታል፡፡ አዲሱ ፈጠራም  የመተንፈሻ አካላትን የአተነፋፈስ ስረዓት በማሻሻል እና በማገዝ ማንኮራፋትን የሚያስወግድ ነው ተብሏል፡፡ ቴክኖሎጂው በአፍንጫ የሚቀመጥ ሲሆን ነርቮችን በማነቃቃት የአተነፋፈስ ስርዓትን በማስተካከል አየር በአግባቡ እንዲዘዋወርና ማንኮራፋትን በማስወገድ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት ያስችላል ተብሏል፡፡
ማንኮራፋት የሚያመጣው ጉዳት ምንድን ነው?
በቂ የሆነ እንቅልፍ ከመከልከሉ በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኙትን ሰዎች በመረበሽ
93
ተክለጻድቅ መኩርያ ተክለጻድቅ መኩርያ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አሳግርት ልዩ ስሙ ሳር አምባ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ መጀመሪያ ከአባታቸውና ቀጥሎም በአጥቢያቸው ባህላዊውን ትምሕርት እስከቅኔ ያለውን ቀስመዋል። ከዚያም አዲስ አበባ መጥተው አሊያንስ ፍራንሴዝና ተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ገብተው የጊዜውን የትምሕርት ደረጃ አጠናቀዋል። ኢጣልያ አገራችንን የወረረች ጊዜም በየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ፍጅት ተይዘው ወደ ሶማሌ ደናኔ ተግዘው ለሦስት ዓመታት ታስረዋል። ከነጻነትም መልስ አገራቸውን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል። መጀመሪያ ተቀጥረው ያገለገሉት በትምሕርትና ሥነጥበብ ሚኒስቴር ነበር። እዚያም ሳሉ በአገራችን ሰው የተጻፈ የአገራችን ታሪክ አንድም ባለመኖሩ በቁጭትና በመቆርቆር ነበር ‘መጻፍ አለብኝ’ ብለው በደንብ ከሚታወቀው ከቅርቡ ጊዜ በቅጡ ወደማይታወቀው የሩቁ ዘመን መጻፍ የጀመሩት። የመጀመሪያውን መጽሐፍ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ” የሚለውን በ ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. አሳተሙ። ከጫፍ እስከ ጫፍ ጽፈው የመጨረቻውን መጽሐፍ፣ የታሪካችን መጀመሪያ የሚሆነውን “የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ-አክሱም-ዛጉዬ እስከ ዓፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት” የሚለውን በ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. አቅርበዋል። እኒህኑ መጻሕፍት ትምሕርት ሚኒስቴር ታሪክ ለማስተማሪያ በትምሕርት ቤት ተጠቅሞባቸዋል። ተክለጻድቅ ከታሪክ ውጭ የጻፏቸው “የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ” እና በሚዮቶሎዢያ (አፈ ታሪክ) ላይ ያተኮረ “ከጣዖት አምልኮ እስከ ክርስትና” የሚሉም መጽሐፎች አሏቸው። ተክለጻድቅ በምድር ባቡር በዋና ጸሐፊነት፥ በቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዋና ሥራ አስኪያጅነት፥ እንዲሁም በፈረንሳይ፥ በእስራኤል፥ በዩጎዝላቪያ በዲፕሎማሲ ሥራ በመጨረሻም የትምሕርትና የባህል ሚኒስቴር ሆነው አግልግለዋል። በፈቃዳቸው ጡረታም ከወጡ በኋላ በምርምር የታገዙ ሦስት ታላላቅ የታሪክ ሥራዎችን አቅርበዋል። ተክለጻድቅ ከረጅም የአገልግሎት ዘመን በኋላ በተወለዱ በ ሰማንያ ስድስት ዓመታቸው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. አርፈዋል።
ተክለጻድቅ መኩርያ የመጀመሪያውን መጽሐፋቸውን መቼ አሳተሙ?
በ ፲፱፻፴፰ ዓ.ም.
607
አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ በሃገራችን ኢትዮጵያ ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅ እና ቅድስት እድና ይባላሉ ። የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው ። ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረአምላክ ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ። በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል። "የት ልሒድ?" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለስምንት ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየኋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከስምንቱ ጋር ከቃልኬዶን ጉባዔ በኋላ በ፬፻፶፩ ዓም ወደ ኢትዮጵያ መጡ ። ከዘጠኙ ቅዳሳን ወደ ኢትዮጵያ ከሮምና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከፈለሱት አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው ። በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል ። አቡነ አረጋዊ ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል ። በመጨረሻም ደብረ ዳሞ ማረካቸዋለች ። ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል ፡፡
አቡነ አረጋዊ ከብዙ ፍለጋ በኋላ በስተመጨረሻ በየት ተቀመጡ?
ደብረ ዳሞ
905
ኮንግ-ፉጸ ኮንግ-ፉጸ ወይም ኮንፉክዩስ 558-487 ዓክልበ. የኖረ ቻይናዊ ፋላስፋ ነበረ። ፍልስፍናውና ትምህርቱ «የኮንግፉጸ ትምህርት» በተለይ በቻይና፣ በኮርያ፣ በጃፓንና በቬትናም አገር ባህሎች ላይ ጥልቅ ያለ ተጽእኖ አሳድሮዋል። በእርሱ ፍልስፍና፣ የግለሰብና የመንግሥት ግብረገብ፣ የኅብረተሠባዊ ግንኙነቶች ትክከለኛነት፣ የወላጆች ክብር፣ ፍርድና ቅንነት ልዩ ትኩረት አገኙ። ኮንግ-ፉጸ በሉ ክፍላገር የተወለደ ሲሆን፣ በክፍላገሩ ውስጥ የፖለቲካ ሰው ነበር። በ509 ዓክልበ. የአንድ ከተማ ከንቲባ ከመሆኑ በኋላ፤ የክፍላገሩ ወንጀል ሚኒስትር ሆነ። ነገር ግን በፖለቲካ ረገድ በሙሉ ስኬታማ አልነበረም። ከክፍላገሩ ሦስት ታላላቅ ኃይለኛ ቤተሠቦች ወገኖች፣ ሁለቱ አምባዎቻቸው እንዲፈርሱ በመጨረሻ ተስማሙ፣ እንጂ ሦስተኛው እምቢ ብሎ ለኮንግ-ፉጸ እቅድ አልተከናወነለትም። ስለዚህ በ505 ዓክልበ. ኮንግ-ፉጸ ከሉ ክፍላገር ሸሽቶ ለጊዜው በስደት ኖረ። ከዚያ እስከ 491 ዓክልበ. ድረስ ወደየክፍላገሩ ቤተ መንግሥት ጎብኝቶ የፖለቲካ ፍልስፍናውን ያስተምር ነበር፤ ሆኖም ሁላቸው ምክሩን ስላላስገቡ ይህ ደግሞ በጣም ስኬታም አልነበረም። በ491 ዓክልበ. ወደ ሉ በክብር ተመልሶ ከዚያ እስከ ዕረፍቱ ድረስ ወይም ለ4 ዓመታት ዕውቀቱን ለ77 ደቃ መዛሙርት (ተማሪዎች) ያስተምር ነበር። ከኮንግፉጸ ሕይወት በኋላ ትምህርቶቹ ተከታይነት አገኙ፤ በ148 ዓክልበ. የሃን ሥርወ መንግሥት የኮንግ-ፉጸ ትምህርት ይፋዊ አደረጉት። ወደ ማዕረግ ለመሾም ዕጩዎቹ በዚህ እምነት መጻሕፍት ይፈተኑ ነበር። ከ212 እስከ 1360 ዓም ድረስ ግን ልዩ ልዩ የቻይና ግዛቶች ዳዊስም ወይም ቡዲስም የመንግሥት ሃይማኖት አድርገው ነበር። እንደገና 1360-1903 ዓም ዘመናዊው የኮንግፉጸ ትምሕርት በቻይና ይፋዊ ሆነ። በዳዊስም ሃይማኖት ዘንድ፣ የእምነቱ መሥራች ላው ድዙ በ539 ዓክልበ. ያሕል ዳው ዴ ቺንግ እንደ ጻፈ፣ እንዲሁም አንዴ ከኮንግ-ፉጸ ጋራ እንደ ተገናኙ ይታመናል። በዘመናዊ ዳዊስም በኩል፣ ላው ድዙና ኮንግ-ፉጸ ሁለቱ እንደ አማልክት ይከብራሉ። በተለይ በፓኪስታን የሚታወቅ ከእስልምና የወጣ ክፍልፋይ አሕማዲያ እስልምና እንዳለው፣ ኮንግ-ፉጸ እና ላው ድዙ ሁለቱ የአላህ ነቢዮች ነበሩ።
በቻይና ዘመናዊው የኮንግ-ፉጸ ትምሕርት መቼ ይፋ ሆነ?
1360-1903 ዓም
961
ፍቅር እስከ መቃብር ፍቅር እስከ መቃብር በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያትን ፍቅር ይተርካል። ይህ ድርሰት ከሌሎች ልብወለድ ሥራዎች ለየት የሚያደርገው ደራሲው ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በፊደል አጠቃቀም ላይ ለውጥ አድርገው በማቅረባቸው ነው። ይኸውም ለምሳሌ ያህል ሦስት «ሀ»ዎች፣ ሁለት «ሰ»ዎች፣ ሁለት «ኣ»ዎች የመሳሰሉትን እንደ አንድ ወይም የመጀመሪያውን ብቻ በመያዝ ነው። በተጨማሪም ጠብቀው በሚነገሩ ቃላት ላይ ከላይ አንድ ነጥብ በማስቀመጥ ይታወቃሉ።ሀዲስ ኣለማየሁ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሑፍ የራሳቸው ትልቅ አሻራ አኑረው ያለፉ አንጋፋ ደራሲ ናቸው። የታሪኩ ማጠቃለያ በዛብህ‌ ‌ጎጃም‌ ‌ማንኩሳ‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከእናቱ‌ ‌ከውድነሽ‌ ‌በጣሙና‌ ‌ከአባቱን‌ ‌ከቦጋለ‌ ‌መብራት‌ ‌ይወለዳል።‌ ‌በሽታ‌ ‌ይበዛበትና‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይባላል።‌ ‌እናቱ‌ ‌ከበሽታው‌ ‌እንዲድን‌ ‌ስእለት‌ ‌ይሳላሉ።‌ ‌ዕድል‌ ‌ሆኖ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይተርፋል፤‌ ‌አድጎ‌ ‌ጎበዝ‌ ‌ልጅ‌ ‌ይሆናል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌በሽታ፣‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ዕውቀትና‌ ‌ፍቅር‌ ‌(የሰው‌ ‌መውደድ)‌ ‌ይበዛበታል።‌ ‌በወጣትነቱ‌ ‌ይቀድስና‌ ‌ለቤተሰቡ‌ ‌ገንዘብ‌ ‌ማምጣት‌ ‌ይጀምራል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌የስእለት‌ ‌ልጅ‌ ‌መባልን‌ ‌አይጠላም‌ ‌ነበር።‌ ‌ሲያድግ‌ ‌ግን‌ ‌ትርጉሙን‌ ‌በመረዳቱ‌ ‌ነጻነቱን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌ዲማን‌ ‌ጥሎ‌ ‌ወደደብረ‌ ‌ወርቅ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌እዚያም‌ ‌ከእመት‌ ‌ጠጂቱ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይጠጋል።‌ ‌ትንሽ‌ ‌ዜማና‌ ‌ቅኔም‌ ‌ይማራል።‌ ‌ደብተራ‌ ‌በየነ‌ ‌መጥቶ‌ ‌የወላጆቹን‌ ‌ሞት‌ ‌ሲያረዳው‌ ‌ወደዲማ‌ ‌ይወርዳል።‌ ‌በተክለ‌ ‌አልፍአው‌ ‌በዓል‌ ‌በመልካም‌ ‌ድምጹ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻንና‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትን‌ ‌ያወድሳል።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻም‌ ‌የሰብለ‌ ‌መምህር‌ ‌አድርገው‌ ‌ይቀጥሩታል።‌ ‌ሰብለና‌ ‌በዛብህ‌ ‌የሕይወት‌ ‌ገጠመኞቻቸው‌ ‌በመጠኑ‌ ‌ስለሚመሳሰል‌ ‌ይግባባሉ።‌ ‌በመሃል‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌አሰጋኸኝ‌ ‌ሰብለን‌ ‌በፈት‌ ‌ወግ‌ ‌አገባለሁ‌ ‌በማለቱ‌ ‌በርሱና‌ ‌በፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌መካከል‌ ‌ጥል‌ ‌ተፈጠረ፤‌ ‌ሆኖም‌ ‌በሃይማኖት‌ ‌ጣልቃገብነት‌ ‌ሳይዋጉ‌ ‌ቀሩ።‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከባላገሮች‌ ‌ጋራ‌ ‌በግብር‌ ‌ጉዳይ‌ ‌ተጣሉ።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ተማርከው‌ ‌ሳለ‌ ‌የበዛብህንና‌ ‌የሰብለወንጌልን‌ ‌የፍቅር‌ ‌ዜና‌ ‌ይሰማሉ።‌ ‌ወዲያውም‌ ‌መጥተው‌ ‌ሰብለን‌ ‌በሌሊት‌ ‌ያስሯታል።‌ ‌የሰብለ‌‌አጎት‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ሁለቱን‌ ‌ለማስመለጥ‌ ‌ወጣ፣‌ ‌ወረደ።‌ ‌የዕጣ‌ ‌ነገር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ግን‌ ‌ሳይሳካ‌ ‌ቀረ።‌ ‌በዛብህ‌ ‌ግን‌ ‌በግራጌታ‌ ‌ቀለመወርቅና‌ ‌በጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጥረት‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌በራጉኤል‌ ‌ቤተክርስቲያንም‌ ‌የቅኔ‌ ‌መምህር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ይቀጠራል።‌ ‌ባደረጉላቸው‌ ‌ውለታ‌ ‌ምክንያት‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌ሰብለን‌ ‌ለፊታውራሪ‌ ‌ታፈሰ‌ ‌ሊድሯት‌ ‌ይሞክራሉ።‌ ‌የሰብለን‌ ‌አቋም‌ ‌አውቀው‌ ‌አባ‌ ‌ተክለሃይማኖት‌ ‌በተባሉ‌ ‌መነኩሴ‌ ‌ያስጠብቋቷል።‌ ‌መነኩሴው‌ ‌ግን‌ ‌ሰክረው‌ ‌ሰብለ‌ ‌ታመልጣለች።‌ ‌ፍለጋ‌ ‌ሲሄዱ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከፈረስ‌ ‌ላይ‌ ‌ተወርውረው፣‌ ‌ተንኮታክተው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትም‌ ‌ቤተክርስቲያን‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከደረጃ‌ ‌ላይ‌ ‌ተንሸራትተው‌ ‌ወድቀው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ሰብለ‌ ‌ደግሞ‌ ‌በዛብህን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌መነኩሴ‌ ‌መስላ‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ትሄዳለች።‌ ‌ደርሳም‌ ‌በዛብህ‌ ‌አለመኖሩን‌ ‌ትሰማና‌ ‌ጎሃጽዮን‌ ‌ትወርዳለች።‌ ‌በዚያም‌ ‌በዛብህ‌ ‌ተደብድቦ፣‌ ‌ነፍስ‌ ‌ውጪ‌ ነፍስ‌ ‌ግቢ‌ ‌አይነት‌ ‌ሁኔታ‌ ‌ላይ‌ ‌ሳለ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌እንደምንም‌ ‌ብለው‌ ‌ሥጋ‌ ‌ወደሙን‌ ‌ይቀበላሉ።‌ ‌ጥቂት‌ ‌ቆይቶ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይሞታል።‌ ‌ሰብለም‌ ‌መንኩሳ፣‌ ‌የበዛብህን‌ ‌አስከሬን‌ ‌ባጠገቧ‌ ‌አድርጋ‌ ‌ስትኖር‌ ‌ከጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጋራ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌ጉዱ‌ ‌የተሰኘው‌ ‌ካሳ‌ ‌ዳምጤም‌ ‌እርሷ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይቀመጣል።‌ ‌አስራ‌ ‌አምስት‌ ‌ቀናት‌ ‌አንድ‌ ‌ላይ‌ ‌ይኖሩና‌ ‌ሰብለ‌ ‌የልብ‌ ‌በሽታዋ‌ ‌ተነሥቶባት‌ ‌ትሞታለች፣‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ከበዛብህ‌ ‌አጠገብ‌ ‌ያስተኛታል።‌ ‌በሦስተኛው‌ ‌አመት‌ ‌ጉዱም‌ ‌አረፍተ‌ ‌ዘመን‌ ‌ይገታዋል።‌
በዛብህ ለምን የትውልድ ቦታውን ጥሎ ሄደ?
ነጻነቱን‌ ‌ለማግኘት‌
799
ሚስተር ኤልቤሽቲ ባደረጉት ንግግር፣ ሊቢያ ኦይል ለአፍሪካ ልዩ ትኩረት በመስጠት በመሥራት ላይ መሆኑን ገልጸው፣ በኢነርጂ መስክ አፍሪካ ውስጥ አስተማማኝ አጋር ሆኖ መሥራት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ሊቢያ ኦይል በ18 የአፍሪካ አሮች 1,015 የነዳጅ ማደያዎች አሉት፡፡ ሊቢያ ኦይል ሆልዲንግ በሊቢያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን እ.ኤ.አ. በ2004 የተመሠረተ ኩባንያ ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ ያሉትን ቢዝነስ የገዛው ከሼልና ከኤክሶን ሞቢል ኩባንያዎች ነው፡፡ በቅርቡ ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ (ኖክ) ሊቢያ ኦይል ጂቡቲን በ450 ሚሊዮን ብር መግዛቱን አስታውቋል፡፡ ሊቢያ ኦይል የጂቡቲ ንብረቱን አለመሸጡንና ኖክ ኩባንያውን የገዛው ከጂቡቲ መንግሥት እንደሆነ አስረድቷል፡፡ ሊቢያ ኦይል ወደ ጂቡቲ ከመግባቱ ከብዙ ዓመታት በፊት በተፈጠረ የባህር ውኃ ብክለት ምክንያት የጂቡቲ መንግሥት ከፍተኛ የካሳ ክፍያ በመጠየቁ በተፈጠረ አለመግባባት፣ የጂቡቲ መንግሥት የኦይል ሊቢያ ጂቡቲና የቶታል ጂቡቲ ንብረቶችን ወርሷል፡፡ የጂቡቲ መንግሥት የሊቢያ ኦይልና የቶታል ንብረቶችን ለሽያጭ አቅርቦ ሊቢያ ኦይል ጂቡቲን ኖክ፣ ቶታልን ደግሞ አንድ የፈረንሣይ ኩባንያ መግዛታቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡
በባህር ውኃ ብክለት ምክንያት የጂቡቲ መንግሥት የወረሳቸው የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች እነማን ናቸው?
የኦይል ሊቢያ ጂቡቲና የቶታል ጂቡቲ
535
የባሕል ጥናት የባህል ጥናት፣ ሥነ ኅብረተሠብ ወይን ሥነ ማኅበረሰብ ሌላ ስሙ ሶሲዮሎጂ የሰው ልጆች በቡድንና በተናጥል ያላቸውን ባሕል፣ ጠባይና አደረጃጀት የሚያጠና ክፍል ነው። በዚህም ውስጥ አንትሮፖሎጂ ወይም የሰው ልጅ ጥናት (ሥነ ሰብእ) አለ። ሶሲዮሎጂ የሚለው ቃል በፈረንሳያዊው ጸሐፊ ኤማኑወል-ዦሰፍ ሲዬ በ1772 ዓ.ም. ከሮማይስጥ ሶኪውስ (ባልንጀራ፣ ጓደኛ) እና ከግሪክ ሎጎስ (ቃል ወይም ጥናት) በማጋጠም ተፈጠረ። የፈረንሳይ ፈላስፋ ኦጉስት ኮምፕት ከ1830 ዓ.ም. ጀምሮ በሰፊ ጠቀመው። የኅብረተሰብ ጥናት ሲሆን የኅብረተሰብ ጽንሰ ሀሣብ በሮማይስጥ ትርጉም ሶኪየታስ ወይም የባልንጀሮች ግንኙነት ያመልከታል።
ሶሲዮሎጂ የሚለው ቃል መቼ ተፈጠረ?
በ1772 ዓ.ም.
197
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በጥሩ ጎናቸው ከሚነሱ የቅርብ ጊዜያት ተጫዋቾች መካከል አዳነ ግርማ ይገኝበታል።ተጫዋቹ በበርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታንም ይዟል።አዳነ ግርማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን መነቃቃት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ተጫዋቹ በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ለ10 ዓመታት በመጫወትም አንጋፋ ለመሆን በቅቷል። አዳነ ግርማን ስናስብ ሁለት ጨዋታዎች ሁሌም ከፊታችን ድቅን ይላሉ።ደቡብ አፍሪካ ላስተናገደ ችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡደን ከሱዳን አቻው ጋር ሲጫወት በግንባሩ ገጭቶ ያስቆጠራት ግብ መቼም ቢሆን አዳነ እንዲታወስ ያደረገችም የምታደርግ ናት።ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ያረገችው ወሳኝ ግብም ሆናለች። በአፍሪካ ዋንጫው ከ 39 ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛምቢያ ላይ ያስቆጠራት ግብም አዳነን ሁሌም እንድናስበው ያረገች ሌላዋ ግቡ ናት። ተጫዋቹ ከዋልያዎቹ ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገና የቡድኑ ምሰሶ እንደነበርም ይታወቃል።በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዘመን አዳነ ቡድኑን በአምበልነት መርቷል። የአትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሰውነት ቢሻው የተረከቡት አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ቡድኑን እንደ አዲስ ሲያዋቅሩ አዳነ ግርማን መቀነሳቸው ሲሰማ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ ቅሬታ ቢፈጠርም፣ ተጫዋቹ ግን ውሳኔውን አሜን ብሎ ነው የተቀበለው። በወቅቱም አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ለተጫዋቹ መቀነስ ምክንያታቸው ያደረጉት የተጫዋቹ «ብቃትና አቅም ወርዷል» የሚል ነው። ተጫዋቹ ግን በወቅቱ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ያረጋገጠው ምንም አይነት የአቋም መዋዠቅም እንደሌለበት ነው። የብቃት መውረድ እንዳላሳየም ገልጿል። የመቀነሱ ሚስጥር ለሱም እንቆቅልሽ እንደሆነበት ነበር ያስታወቀው። ይህን ተከትሎ ራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው አዳነ በአዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሰሞኑን ጥሪ ተደርጎለት ነበር:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ በአጥቂ እጥረት ላይ ቢገኝም አዳነ ግርማ ከቤተሰቦቼ ጋር ተመካክሬ የወሰንክይት ውሳኔ ነው በሚል ለብሔራዊ ቡድኑ እንደማይጫወት አስታውቋል:: በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሁለት የተደለደለውና በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጀሪያ አቻው ጋር ላለበት የምድቡ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን መጥራቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ሁለት ተጫዋቾችን ከአገር ውጭ ቀሪዎቹን 22 ደግሞ ከአገር ውስጥ ሊጎች የመረጡ ቢሆንም የአዳማ ከነማው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ባጋጠመው ጉዳት ከቡድኑ ውጭ ሆኗል። እርሱን ለመተካት ሳልሃዲንና አዳነን ቢጠሩም እምቢ ተብለዋል:: ሆኖም ግን አሰልጣኙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የመረጧቸውን አምስት ተጫዋቾችና ከአገር ውጭ ከሚጫወቱት ሕመልስ በቀለና ጌታነህ ከበደ በስተቀር 15 ተጫዋቾችን ይዘው ልምምዳቸውን ዛሬ ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን የተካው ማነው?
ማሪያኖ ባሬቶ
730
በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ። ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ። በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች። አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው። ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።
በሴኔጋል ከቅኝ ግዛት ነጻነት በኋላ የመጀመሪያ ፕሬዘዳንት የሆነው ሊዎፖልድ ሴንግሆርም ስልጣን የያዘው መቼ ነበር?
በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ.
262
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የኢያን ስሚዝ አመራር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ሲፈራረም ዚምባቡያውያን በማን እየተመሩ ነበር?
በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ
2,010
ጋና ጋና በአፍሪካ አትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት። የጋና ስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይም ትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ 1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑ ማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያ አሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ። ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ። የጋና ዋና ምርቶች ካካዎ፣ ዘይት፣ አልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል። እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤ፣ ጐርጠብ፣ የስኳር ድንች፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ኦቾሎኒ፣ ባሚያና ሩዝ ይሠራል።
በዓለም ከሚገኙ ሰው ሰራሽ ሐይቆች ትልቁ የት ሀገር ይገኛል?
በጋና
815
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
የዚምባቡዌ ሀገር በአፍሪካ በየትኛው ክልል ይገኛል?
በደቡብ
57
አዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።
አዲስ አበባ የሚለውን ስም ለከተማዋ የሰጡት ማናቸው?
እቴጌ ጣይቱ
28
አንበሳ አንበሳ ጡት አጥቢ የእንስሶች መደብ ውስጥ ሲሆን ግዙፍ ድመቶች ከሚባሉት 4 አራዊት አንዱ ነው። ከነዚህም መካከል ነብር ከሚባለው ግሥላ መሳይ አውሬ ቀጥሎ በቁመቱና ክብደቱ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አንበሳ ዛሬ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በህንድ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በታሪክ እስያና በደቡብ አውሮፓ እንደነበርና እንደጠፋ ይታወቃል። አንበሶች በጣም ቁጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሙጭሊትን ያህል ገራምና ተጫዋች ይሆናሉ። ሲጠግቡ በዝግታ የሚያንኮራፉ ቢሆንም እንኳ እስከ ስምንት ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሰማ በሚችል ኃይለኛ ድምፅ ሊያገሡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰነፎችና ልፍስፍሶች ይመስሉ ይሆናል፤ ሆኖም በሚያስገርም ፍጥነት የመንቀሳቀስ ችሎታ አላቸው። የሰው ልጅ፣ አንበሳ ባለው ድፍረት ለዘላለም ሲወሳ እንዲኖር አድርጓል፤ በመሆኑም ደፋር ሰው አንበሳ ተብሎ ይጠራል። አንበሶች በማኅበር ከሚኖሩት የድመት ወገን የሆኑ እንስሶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በትልልቅ መንጋ ተከፋፍለው የሚኖሩ ሲሆን እያንዳንዱ መንጋ ከጥቂት አባሎች አንስቶ ከ30 በላይ ሊደርስ ይችላል። አንድ መንጋ የጠበቀ ዝምድና ያላቸው በርከት ያሉ ሴት አንበሶች ይኖሩታል። አንድ ላይ ይኖራሉ፣ ያድናሉ እንዲሁም ይወልዳሉ። ዕድሜ ልካቸውን ሊዘልቅ የሚችለው ይህ የጠበቀ ትስስር ለመንጋው ጠንካራ መሠረት የሚጥል ከመሆኑም በላይ ለመንጋው ሕልውና ጥሩ ዋስትና ይሆናል። እያንዳንዱ መንጋ እየተዘዋወሩ የሚጠብቁና የመንጋውን የክልል ወሰን የሚያወጡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ለአካለ መጠን የደረሱ ወንድ አንበሶች ይኖሩታል። እነዚህ ዕጹብ ድንቅ የሆኑ አውሬዎች ከጥቁሩ የአፍንጫቸው ጫፍ አንስቶ እስከ ጭራቸው ጫፍ ድረስ ከሦስት ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን ከ225 ኪሎ ግራም በላይ ሊመዝኑ ይችላሉ። ቤተሰቡን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ወንዶቹ ቢሆኑም አመራር የሚሰጡት ግን ሴቶቹ ናቸው። ወደ ጥላ ሥፍራ መሄድን ወይም አደን መጀመርን በመሳሰሉት ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ መንጋውን ለአንድ ዓይነት እንቅስቃሴ የሚያነሳሱት ሴቶቹ አንበሶች ናቸው። ሴት አንበሶች በአብዛኛው በየሁለት ዓመቱ ይወልዳሉ። ግልገሎቹ በሚወለዱበት ጊዜ ምንም ዓይነት አቅም አይኖራቸውም። ግልገሎችን ማሳደግ የሁሉም የጋራ ሥራ ነው፤ በመሆኑም ሴቶቹ አንበሶች በሙሉ በመንጋው ውስጥ ያሉትን ግልገሎች ይጠብቃሉ እንዲሁም ያጠባሉ። የግልገሎቹ ዕድገት ፈጣን ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ መሮጥና መቦረቅ ይጀምራሉ። ልክ እንደ ሙጭሊቶች እየተንደባለሉ ይጫወታሉ፤ ከሚያጫውቷቸው ጋር ይታገላሉ፤ እንዲሁም በረጃጅሙ ሣር ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይዘላሉ። እያንዳንዱ የሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ ስሜታቸውን ይማርከዋል፤ ቢራቢሮዎችን ለመያዝ ይዘላሉ፣ ትናንሽ ነፍሳትን ያሳድዳሉ፣ ከየጭራሮና ከየሐረጉ ጋር ይታገላሉ። ይበልጥ ስሜታቸውን የሚማርከው ግን እነርሱን ለማጫወት እናታቸው ወዲያና ወዲህ የምታወናጭፈው ጭራዋ ነው። እያንዳንዱ መንጋ የሚኖርበት በደንብ የተከለለ ቦታ ያለው ሲሆን ይህ መኖሪያ ብዙ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ሊኖረው ይችላል። አንበሶች ውኃ እንደ ልብ ባለበትና ከቀትር ሐሩር የሚከላከል ጥላ በሚያገኙበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ መኖር ይመርጣሉ። በእንዲህ ዓይነቱ ሥፍራ ከዝሆኖች፣ ከቀጭኔዎች፣ ከጎሽና ከሌሎች ሜዳማ በሆኑ ሥፍራዎች ከሚኖሩ እንስሶች ጋር በአንድነት ይኖራሉ። አንበሳ አብዛኛውን ጊዜውን በእንቅልፍ ጥቂቱን ጊዜ ደግሞ በአደንና በተዋስቦ ያሳልፋል። እንዲያውም አንበሶች በቀን ውስጥ ወደ 20 የሚጠጋውን ሰዓት የሚያሳልፉት በዕረፍት፣ በመተኛት ወይም በመቀመጥ ነው። ከባድ እንቅልፍ ተኝተው ሲታዩ ሰላማዊና ለማዳ ይመስላሉ። ይሁን እንጂ በዚህ መታለል የለብህም፤ አንበሳ እጅግ ቁጡ ከሆኑት አራዊት መካከል አንዱ ነው!
በአንበሶች ዘንድ መንጋውን እየተዘዋወሩ የሚጠብቁና የመንጋውን የክልል ወሰን የሚያወጡ የትኞቹ አንበሶች ናቸው?
ለአካለ መጠን የደረሱ ወንድ አንበሶች
857
አሜሪካ ለሁዋዌ ተጨማሪ ሽያጮችን ልታግድ መሆኑን አስታወቀች። አሜሪካ የምታመርታቸውን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት የተመረቱ የቴሌኮም ምርቶችን ለግዙፉ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያ እንዳይሸጡ ለማገድ ስለመዘጋጀቷም ነው የገለጸችው። የትራምፕ አስተዳደር ሁዋዌ የሃገሪቱን ደህንነት ስጋት ላይ ይጥላል በሚል ኩባንያው ላይ ጫና እያሳደረ ነው። የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ ኩባንያውን በጥቁር መዝገብ አስፍሮት እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይም ለኩባንያው ከአሜሪካም ሆነ ከሌሎች ሃገራት የሚጓጓዙ የቴክኖሎጅ ቁሳቁሶች ላይ ገደብ መጣል የሚያስችል ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጻለች። የአሜሪካ ግምጃ ቤት አሁን ባለው ህግ የአሜሪካ የቴክኖሎጅ ምርቶች ከፍ ያለውን ዋጋ ከያዙ ወደ ቻይና የሚላኩ የሌሎች ሃገራትን የቴክኖሎጅ ምርቶች የማገድ ወይም የማስገቢያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላል። አሜሪካ ባለፈው ዓመት በደህንነት ስጋት ምክንያት ለሁዋዌ እና 68 ተዛማጅ ኩባንያዎች የቴክኖሎጂና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዳይሸጡ ገደብ መጣሏ የሚታወስ ነው። አሜሪካ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችን አገልግሎት መጠቀም ሊያስከትል የሚችለውን የደህንነት ስጋት የሚያሳይ ማስረጃ በማቅረብ በተለይም ምዕራባውያን አጋሮቿ እንዳይጠቀሙ እየወተወተች ትገኛለች። ምንጭ፦ አልጀዚራ
አሜሪካ ለቻይና ድርጅቶች እንዳይሸጡ የከለከለቻቸው ምርቶች ምን ምን ናቸው?
የቴክኖሎጅ ቁሳቁሶች
319
ጥንታውያን የግብጽ ባለሥልጣኖች በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ከማየ አይኅ ቀጥሎ መጀመሪያ የአፍሪካ ሕዝብ የኖኅ ልጅ የካም ዘሮች ናቸው፤ ይህ አገር ሰናዖር ለሚሉት ቅርብ ስለ ነበር የባብል ግንብ ከተሠራ በኋላ ከዚህ ተነስተው ወደ ግብፅ ወረዱ። የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት ዋና ጥንታዊ ነው፤ የመሠረተውም ፈርዖን ሜኒስ የተባለው ነው። ጸሓፊው ጊዮርጊስ ስንቄሎስ (፰፻ ዓ.ም. አካባቢ የጻፈው) ይህ ፈርዖን ሜኒስ በዕውነት የካም ልጅ ምጽራይም እንደ ነበረ ገመተ። ዳሩ ግን አባ አውሳብዮስ በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ (፫፻፲፯ ዓ.ም. ተጽፎ)፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ ማኔጦን (፫ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከማየ አይህ አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በእስላም ጸሐፊዎች በግብጻዊው እብን አብድ ኤል-ሀከም እና በፋርሳውያን አል-ታባሪና ሙሐመድ ቈንዳሚር መጻሕፍት ሲገኝ፣ ፒራሚዶች፣ እስፊንክስ ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም ('ማሣር' ወይም 'መሥር') ተሠጠ ብለው ጻፉ።
በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ካም የማን ልጅ ነው?
የኖኅ
63
ጾመ ነቢያት በአራቱም ዘመናት ምን ጊዜም ኅዳር ዐሥራ አምስት እንዲጾም ተወስኗል፡፡ ጾመ ገሀድ የምትክ ጾም ነው፡፡ ይህ ጾም ዓርብንና ሮብን የሚያሽር በዓል በዓርብና በሮብ ሲውል በምትኩ በዋዜማው የሚጾም ጾም ነው፡፡ ለምሳሌ ጥምቀት ዓርብ ቢውል ሐሙስ ጾመ ገሀድ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አበው ለጾም ማድላት አለብን በማለት ጾመ ገሀድ ምንጊዜም ጥምቀት በጾም ቀን ዋለም አልዋለም በዋዜማው እንዲጾም ወስነዋል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያት የእመቤታችንን ትንሣኤ ለማየት ይበቁ ዘንድ ሱባኤ ገብተው የጾሙት ጾም ሲሆን ምንጊዜም ነሐሴ አንድ ቀን ገብቶ ከሁለት ሱባኤ በኋላ የእመቤታችን ዕርገት ይፈጸማል፡፡
በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ለሁለት ሣምንት የሚጾመው ጾም ምንድን ነው?
ጾመ ፍልሰታ
258
ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ለወጣት ለአዛውንት የሚመቹ ደግ እናት፡፡ በኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክ ስም ያተረፉ፡፡ ለምርምር የማይደክሙ፡፡ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን እነሆ ታሪካቸውን አቀረበ፡፡ ጋዜጠኛዋ በ79 አመታቸው ሀምሌ 14 2013 ህይወታቸው አልፏል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ በ1934 አመተ ምህረት ከአባታቸው ከአቶ መኩሪያ ወልደስላሴ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሶስና ወርቅነህ ተወለዱ፡፡ እናታቸው ወይዘሮ ሶስና ወርቅነህ የሀኪም ወርቅነህ እሸቴ ልጅ ናቸው፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሳንፎርድ ተማሪ ቤት ነበር የተከታተሉት፡፡ ወይዘሮ እሌኒ ያደጉት ካዛንቺስ አካባቢ ሲሆን የልጅነት ዘመናቸው በደስታ የተሞላ ነበር፡፡ በተለይ በሳንፎርድ ተማሪ ቤት ጥሩ የእንግሊዝኛ ችሎታቸውን ከማዳበራቸው በላይ ደስ የሚል የመዝናኛ ጊዜን አሳለፈው ነበር፡፡ ቴኒስ መጫወት ፤ ዋና መዋኘት ፣ ቴአትር ማየት እና መተወን ደስ ይላቸው ነበር፡፡ እንዲያውም ለልኡል መኮንን ሆስፒታል ማሰሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ቴአትር መስራታቸውን ወይዘሮ እሌኒ በህይወት በነበሩ ጊዜ ተናግረዋል፡፡ በተለይ አያታቸው ክቡር ሀኪም ወርቅነህ እሸቴ ዳንስ ያለማምዷቸው እንደነበር አይዘነጉትም፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ፣ ማህበራዊ ሳይንስ የማጥናት ግብ ቢኖራቸውም ቤሩት የነጻ የትምህርት እድል አግኝተው ወደዚያ በ1951 ግድም ያቀናሉ፡፡ ነገር ግን የነርስነትን ትምህርት ቢጀምሩም አቋርጠው ወደ እናት ሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡ በመቀጠልም ወደ ብስራተ ወንጌል ሬድዮ በማቅናት በእንግሊዝኛው ክፍል ተቀጠሩ፡፡ ያኔ በሬድዮ ከወይዘሮ እሌኒ ጋር ይሰሩ ከነበሩት ባለሙያዎች መካከልም ጋዜጠኛ ልኡልሰገድ ኩምሳ ይጠቀሳል፡፡ ወይዘሮ እሌኒና ጋዜጠኛ ልኡልሰገድ ዜና ሲያቀርቡ ያለበት ቪድዮ ከዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ዘንድ ይገኛል፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር በግንቦት 18 1955 ሲፈረም ጋዜጠኛ ከነበሩት መካከል ወይዘሮ እሌኒ ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱ ገና የ21 አመት ወጣት የነበሩት ወይዘሮ እሌኒ መሪዎች ሲመጡ የተደረገውን ታሪካዊ አቀባበል በፍጹም አይዘነጉትም፡፡
ወ/ሮ እሌኒ እድገታቸው በየት ነው?
ካዛንቺስ አካባቢ
379
ሜሪላንድ ሜሪላንድ (እንግሊዝኛ፦ Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያ ፣ ቨርጂኚያ ፣ ዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳይንስና የሕክምና ተቋማት በዚሁ ክፍላገር ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ1996 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መዓከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።
በ2003 እ.ኤ.ኣ. የሜሪላንድ ስቴት ዓመታዊ ምርት ምን ያህል ነበር?
212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር
444
የጥምቀት በዓል በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዓ/ም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ በዓል ነው። መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው። በአገራችን፣ ጥር ፲ ቀን፣ በከተራ፣ በገጠር ወራጅ ውሃ የሚከተርበት፣ ታቦታት ከየአቢያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በምዕመናን ታጅበው እየዘመሩ ይሄዳሉ። እዚያም በየተዘጋጀው ድንኳን እንዲያርፉ ተደርጎ ሌሊቱን እዛው ያሳልፋሉ።በከተሞች ግን ሰው ሰራሽ ግድብ ይሰራል። ጥር ፲፩ ቀን የጥምቀት ዕለት፤ በገጠር፣ ጎኅ ሲቀድ ምእመናን እዚያው በድንኳኑ ዙሪያ አስቀድሰው ሲጨርሱ በካህናት መሪነት ሁሉም ወደከተራው ያመራና ውሃውም ተባርኮ ሕዝቡ ይረጫል። «ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ፤ ሰማያዊው በመሬታዊው እጅ ተጠመቀ» የሚለው የዕለቱ ቀለም በሊቃውንቱ አንደበት በያሬዳዊ ዜማ ጎልቶ ይሰማል። ከዚህ ሥነ ሥርዓት በኋላ በመቋሚያ፣ በከበሮና በጽናፅል በሚታጀብ ኃይማኖታዊ ዝማሬ፣ ወንዱ በሆታ፤ ሴቱ በእልልታ፤ ካህኑ በሃሌታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየ ቤተክርሲያናቸው ይመለሳሉ። በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየጥምቀተ ባሕሩ የሚከበሩ በመኾናቸው፣ ሀገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብ በመፍጠሩ፣ ቱሪስቶችን መሳቡ አልቀረም። ጥቁርና ነጭ፣ ቀይና ብጫ ያለም ዘር፣ ከአዲስ አበባ እስከ ላሊበላ፣ ከአክሱም እስከ ጎንደር በሁሉም ሥፍራዎች በዚሁ ዓይነት ደምቆ ይከበራል። የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ ፍፁም በሚማርክ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁል ጊዜ አዲስ ነው። ሊቃውንቱ እንደሚናገሩት፣ ዘመነ አስተርእዮ የሚባለው፣ ከጥር ፲፩ ቀን ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አምላክ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር መታወቁ፣ በቃና ዘገሊላ በተደረገው ሠርግ ላይ የመጀመሪያው ተዐምር በመፈጸሙ፣ አምላካዊ ኃይሉ መገለጡ፣ እየታሰበ ምስጋና ይቀርባል። ይህ ሁነት ኢትዮጵያ ብሂልን ከባህል ጋር አዛምዳ ከሌላው የክርስቲያን ዓለም በተለየ አከባበር በዓሉን ማክበሯ፣ አያሌ ቱሪስቶችን ለመሳብ አስችሏታል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የት ተጠመቀ?
ፈለገ ዮርዳኖስ
84
ክልሉ የትልልቅ ወንዞች ባለቤት ሲሆን በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ተፋሰሶች ተከፋፍሎ ሊታይ የሚችል ነው። እነርሱም የዓባይ፣ የተከዜ እና የአዋሽ ተፋሰስ ናቸው። ወደነዚህ ተፋሰሶች የሚገቡና ዓመቱን በሙሉ የማይደርቁ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ትልልቅ ወንዞች ያሉ ሲሆን በክልሉ በጥቅም ላይ ያልዋለ ሰፊ የውሐ ሀብት መኖሩን ያመለክታሉ። ከነዚህ በተጨማሪ እንደ ጣናና አርዲቦ የመሳሰሉ ሐይቆችም በክልሉ ውስጥ ይገኛሉ። በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ ባሉ ትልልቅ ወንዞችና መጋቢ ወንዞች የመስኖ ልማት ለማካሄድ የሚያስችል ከፍተኛ የውሐ ሐብት ክምችት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጅ እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው በጣም አነስተኛ ነው። በአመዛኙ አብዛኛው የክልሉ ምጣኔ ሀብት በግብርና እና ከብት እርባታ ላይ የተመሠረተ ነው። በአጠቃላይ ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጥር፣ ለእርሻና ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ የሆነ መሬት፣ የአየር ንብረት እና የውሐ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ በተለይም የሰብል እና የእንስሳት ሀብት ልማት ለማካሄድ የማይናቅ አቅም አለው። በዝናብም ሆነ የመስኖ እርሻ ልማት በማስፋፋት በክልሉ በገበያ የሚውሉ የተለያዩ የአገዳ፣ የጥራጥሬ፣ የቅባት፣የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን ማምረት ይቻላል። ጤፍ፣ ገብስ፣በቆሎ፣ ማሽላ፣ዳጉሣ፣ ስንዴ፣አተር፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ ጓያ፣ምስር፣ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ተልባ፣ ወዘተ የመሳሰሉት በክልሉ ውስጥ ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በእንስሳት ሀብት ረገድም በወተት ምርታማነታቸው የታወቁ የፎገራ ዝርያዎችና በፀጉር ምርት የታወቁት የመንዝ በግ ዝርያዎች በክልሉ ይገኛሉ። በቱሪዝም የሥራ መስክ ሊበለጽጉ ፣በሰፊው አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ እና በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈሩት የጐንደር ቤተ መንስግት ህንፃዎች፣ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቱሪዝም መስሕቦች አሉት፣ ይሁን እንጅ ክልሉ ሰፊ የሆነ የቱሪዝም እምቅ ሀብት ያለው ቢሆንም በሚፈለገው መጠን በጥቅም ላይ ውሏል ማለት አያስደፍርም። በዚህ ረገድ፤አካባቢዉ የብዙ ታሪካዊ ገዳማትና የታሪካዊ ቅርሶችም ባለሀብት ነው።
በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ ወንዞችን በስንት ዋና ዋና ተፋሰሶች መክፈል ይቻላል?
በሦስት
31
ቴሌቪዥን ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው። በ1873 እ.ኤ.አ. (1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ። በ1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም። ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ... ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በ 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ። በ1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።
በ1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ በሽቦ ያስተላለፈው ተንቀሳቃሽ ምስል በሰከንድ ምን ያህል የምስል ገጽታ ነበር?
16 የምስል ገጽታ
1,224
ፀሐይ ፀሓይ በምድር ሥርዐተ-ፈለክ መኻል ያለች ኮከብ ናት። ምድር ሞላላ ቀለበት በሚመስል የዑደት ምሕዋር እየተጓዘች ፀሓይን ትዞራታለች። ሌሎች ሰማያዊ አካላትም፣ ፈለኮች፣ ፈለክ-አስተኔዎች፣ ጅራታም ከዋክብት እና ኅዋዊ ብናኞች በፀሓይ ዙሪያ ይዞራሉ። ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገውን አንድ ዙር ጉዞ ለመጨረስ አንድ ዓመት ይፈጅባታል፤ ይህን ጉዞ ስታደርግም በገዛ ራሷ ዘንጎ ወይም ምሽዋር ዙሪያ እየሾረች ነው። ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገው ዙረት ወቅቶች በዓመታዊ ዑደት እንዲለዋወጡ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ ሲኾን፣ በራሷ ዘንጎ ዙሪያ የምታደርገው ሹረት ደግሞ በዕለታዊ ዑደት መዓልት (ቀን) እና ሌሊት ለሚያደርጉት መፈራረቅ ምክንያት ነው። ፀሓይ ለሥርዐተ-ፈለካችን በጣም ብሩህ የኾነ ብርሃን ትሰጣለች። ያለ ፀሓይ ብርሃን ሙቀትም ኾነ ሕይወት በምድር አይኖርም ነበር። ለምሳሌ አረንጓዴ ዕፅዋት ያለ ፀሓይ ብርሃን ሊኖሩ አይችሉም፤ ለህልውናቸው የሚያስፈልጓቸውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አልሚ ምግቦች ለማስተጻመር የሚችሉት በፀሓይ ብርሃን ብቻ ነውና። ከምድር ይልቅ ለፀሓይ ይበልጥ ቅርብ የኾኑ ፈለኮች ለከፍተኛ ጨረር እና ግለት የተጋለጡ በመኾናቸው በምድር ላይ ላለው ዐይነት ሕይወት ተስማሚ አይደሉም። ከምድር ጋር ሲነጻጸር ከፀሓይ በጣም ርቀው ያሉ ፈለኮችም ለሕይወት መኖር ምቹ ኹኔታዎች የሏቸውም፤ በቂ ብርሃን እና ሙቀት ካለማግኘታቸው የተነሣ።
በስርዓተ-ፈለክ ውሥጥ ያሉ አካላት የብርሃን ምንጫቸው ማናት?
ፀሓይ
412
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
በዚምባብዌ በስሚዝ አመራር ወቅት የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት በማን ይመራ ነበር?
በጆሱዋ ንኮሞ
1,915
ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት ቀረቡ። በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ  ኢትዮጵያን በመወከል  ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ነው የተነገረው። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋና የቋንቋ ጥናት ክፍል ለረጅም ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።
ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት እጩ የቀረቡት ማን ናቸው?
ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም
0
በ596 ዓ.ም. በጃፓን 17 አንቀጽ ያለ ሕገ መንግሥት በልዑል ሾታኩ እንደተጻፈ ይታመናል። እንዲሁም በ614 ዓ.ም. ከነቢዩ መሐመድ የወጣው የመዲና ሕገ መንግሥት ዕጅግ ጥንታዊ ምሳሌ ነው። በዌልስ በ940 ዓ.ም. አካባቢ ንጉስ ህወል ዳ ሕጎቹን ጻፉ። በዛሬው ሩሲያ ደግሞ የክዬቭ ታላቅ መስፍን ያሮስላቭ ጥበበኛው ፕራቭዳ ያሮስላቫ የተባለውን ሕገ መንግሥት በ1009 ዓ.ም. ያህል ሠሩ። ይህ ሕግ በ1046 ታድሶ በኪዬቭ ሩስ በሙሉ ህጝ ሆነ። በስሜን አሜሪካ የኖሩ ኗሪ ጎሣ ሆደነሾኒ 'የአፈ ቃል' ሕገ መንግሥት «ጋያነሸጎዋ» የነበራችው ከ1080-1140 ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ሕግ በከፊል ለአሜሪካ ሕገ መንግሥት ተጽእኖ እንደነበረው ይታመናልና የአሜሪካ ምክር ቤት በ1981 ዓ.ም. ይህንን ግንዛቤ አስታወቀ። በእንግሊዝ አገር በ1092 ዓ.ም. ንጉስ 1 ሄንሪ የነጻነት ሥርአት የተባለውን ሰነድ አዋጀ። ይህ መጀመርያ የንጉሱን ሥልጣን ወሰኖ ንጉሡ ለቤተ ካህናትና ለቤተ መሳፍንት ወገኖች የሚገባውን እንቅብቃቤ ገለጸ። ይህም መሰረት በመኳንንቱ ሲዘረጋ በ1207 ዓ.ም. የእንግሊዝ ንጉሱን ዮሃንስ (ጆን) ማግና ካርታ («ታላቅ ሥርዓት») የሚባለውን ሰነድ እንዲፈርሙት አስገደዱዋቸው። ከዚሁ መሃል ቁም ነገር የሆነው ንጉሡ ያለ ሕጋዊ ሂደት ማንንም ሰው እንዳይገድሉ፣ ከአገር እንዳያሳደዱ፣ ወይም እስር ቤት እንዳያስገቡ ከለከላቸው። በዚያ ወቅት ያ ሰነድ በእንግሊዝ አገር የነጻነት መሠረት ሆነ። በ1212 እና 1222 ዓ.ም. መካከል አንድ የሳቅሰን አስተዳዳሪ አይከ ቮን ረፕጎቭ ያቀነባበረው ሕግጋት ሳቅሰንሽፒግል በአንዳንድ ጀርመን ክፍላገር እስከ 1892 ዓ.ም. ድረስ ላይኛ ሕገ መንግሥት ሆነ። በ1228 ዓ.ም. ሱንዲያታ ከይታ ማሊ መንግሥትን ለማወሐድ የ'አፈ ቃል' ሕገ መንግሥት አወጡ። ይህ ሕግ 'ኩሩካን ፉጋ' ተብሎ ነበር።
በ1009 ዓ.ም. የክዬቩ ታላቅ መስፍን ያሮስላቭ ያዘጋጀው ሕገ መንግሥቱ ጥቅም ላይ የዋለው የት ሀገር ነበር?
ሩሲያ
164
ከዛሬ ፶00 ዓመት በፊት የሶሎሞን ስረወ መንግስት ሸዋ (መንዝንና ተጉለት) ላይ  ሆኖ ለረጅም ዘመን ኢትዮጵያን ካስተዳደረ በሁዋል  የግራኝ መሃመድ ወረራ በአጼ ልብነድንግል ዘመን ተካሄደ።  ኢትዮጵውያን በግራኝ መሃመድ ወረራ የተነሳ ከፖርቱጋሎች ጋር ግንኙነትን መሰረቱ፡ በ፩፮፴ ተጀምሮ ለረጅም ጊዜ የተካሄደው ግጭት ከውጪ የመጡትን ሚሲዮናዊያን በሙሉ ከኢትዮጵያ በማባረር ሰላም ተመልሷል፡፡ ይህ የከፋ የግጭት ጊዜ ኢትዮጵያ የውጭ ክርስትያኖች ላይ እና አውሮፖውያኖች ላይ እስከ ሀያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ፊቷን እንድታዞር አስተዋጾ ከማድረጉም በተጨማሪ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ ከመላው አለም ተገልላ እንድትቆይ አድርጓታል፡፡ ከ1700 ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አገዛዝ ሳይኖሯት ቆይታለች፡፡ ይህም “ዘመነ መሳፍንት”  ሲሆን በ1869 አፄ ቴዎድሮስ መሳፍንቶቹን ሁሉ አስገብረው ኢትዮጵያን አንድ አድርገዋል
በግራኝ መሃመድ ወረራ ወቅት ኢትዮጵያ ከማን ጋር ግንኙነት ፈጠረች?
ከፖርቱጋሎች
148