context
stringclasses
367 values
question
stringlengths
10
114
answer
stringlengths
1
90
answer_start
int64
0
3.22k
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ስብሐት (ስብሐት ለአብ) ገብረ እግዚአብሔር (ሚያዝያ 27 [1928]ዓ.ም. - ሰኞ፣ ቀን ትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደ ፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው። ስብሐት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ በመነን መጽሄት የዝግጅት ክፍል ውስጥ ሰርቷል። በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲቋቋም በአርታኢነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በመንግሥት ትእዛዝም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን የካርል ማርክስ ሥራ የሆነውን ካፒታልን ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመመለስ ሥራ ላይ ተሳትፏል። ብዙዎቹ የስብሐት ሥራዎች በተጻፉበት ጊዜ ለመታተም ባይታደሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የህትመትን ብርሃን ለማየት በቅተዋል። ጽሁፎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይታተሙ ለመቆየታቸው ዋነኛው ምክንያቱ ስብሐት በመጽሐፉ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ባህል ያደገ አንባቢን አይን የሚያስፈጥጡ፣ ጆሮ የሚያስይዙ በመሆናቸው ነው። በገበያ ላይ በቅርብ የወጡት ድርሰቶቹ ከመጀመሪያ ቅጂያቸው ብዙ ለውጥ እና የአርትኦት ሥራ የተደረገባቸው እንደሆኑ ይነገራል። ስለዚሁ ጉዳይ ለአዲስ ላይቭ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገር «በጨለማ ያልተደረገውን ነገር አንድም የጻፍኩት የለም... ያለውን እንዳለ ነው የምጽፈው» ብሏል። ይህንኑም ከኤሚል ዞላ የአጻጻፍ ዘይቤ የወሰደው እንደሆነ ይናገራል። ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ደራሲ፣ አርታኢ፣ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም - የልብ-ወለድ ድርሰት ገጸባህርይም ነው። ደራሲው የተሰኘው የበአሉ ግርማ ልብ-ወለድ በስብሐት ህይወት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው። ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች አባት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነው።
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት ያገለገለው በየትኛው ትምህርት ቤት ነው?
በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት
254
ስዋሂሊ ስዋሂሊ ፡ (ወይም ፡ ኪሷሂሊ Kiswahili) ፡ በምሥራቅ ፡ አፍሪቃ ፡ የሚናገር ፡ የባንቱ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የስዋሂሊ ፡ ሕዝብ (፭ ፡ ሚሊዮን ፡ ተናጋሪዎች) ፡ ልደት ፡ ቋንቋ ፡ ከመሆኑ ፡ በላይ ፡ ለ ፴ ፡ እስከ ፡ ፶ ፡ ሚሊዮን ፡ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ሁለተኛ ፡ ቋንቋ ፡ ሆኗል። የስዋሂሊ ፡ ስም ፡ መነሻ ፡ ከዓረብኛ ፡ ቃል ፡ «ሰዋሂል» ፡ ነበር ፤ ይህም ፡ የ«ሳኸል» ፡ (ማለት ፡ ዳር) ፡ ብዙ ፡ ቁጥር ፡ ነው። ስለዚህ ፡ የ«ስዋሂሊ» ፡ ትርጉም ፡ የ(ባሕር) ፡ ዳረኞች ፡ ቋንቋ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል። የቋንቋው ፡ ቤተሰብ ፡ ባንቱ ፡ ሲሆን ፡ ተናጋሪዎቹ ፡ መርከበኞችና ፡ ነጋዴዎች ፡ በመሆናቸው ፡ መጠን ፡ ከዓረብኛ ፣ ከፋርስ ፣ ከህንዲ ፣ እና ፡ ከቻይንኛ ፡ ቢሆንም ፡ ብዙ ፡ ቃሎች ፡ ተበድረዋል።
ስዋሂሊ የሚለው ቃል ምንጩ ከምን ቋንቋ ነው?
ከዓረብኛ
223
አል የተባለ ሰው ሰራሽ መሳሪያ የጡት ካንሰር መመርመሪያ መሳሪያን በማንበብ ረገድ ከሐኪሞች በተሻለ ትክክለኛ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ። ሰው ሰራሹ መሳሪያ የጡት ካንሰር መመርመሪያ መሳሪያን በማንበብ ረገድ ሁለት ሐኪሞች በጋራ ከሚሰሩት በተሻለ መልኩ ትክክለኛ መሆኑን ባለሙያዎቹ አረጋግጠናል ብለዋል። ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣው ቡድን አል የተባለው ሰው ሰራሽ መሳሪያን ይዘው በ29 ሺህ ሴቶች ላይ ሙከራ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም መሳሪያው የጡት ካንሰርን በመለየት ረገድ የስድስት ራዲዮሎጂ ባለሙያዎችን ያክል ውጤታማ መሆኑንም ገልጸዋል። ይህም ሁለት የዘርፉ ሐኪሞች (ዶክተሮች) ከሚሰሩት ስራ ጋር እኩል ውጤት ያለው ስለመሆኑም በጥናት ውጤታችን አረጋግጠናል ነው ያሉት። ከዚህ ባለፈም መሳሪያው እንደ ሐኪሞቹና ራዲዮሎጂስቶቹ የግለሰቧን የቀደመ የጤና ሁኔታ የሚገልጽ መረጃ ሳይኖረው የጡት ካንሰሩን መለየት መቻሉም የተሻለ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል። ባለው አሰራር ሁለት የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች ችግሩን ለመለየት የጡት ካንሰር መለያ መሳሪያውን የሚያነቡ ሲሆን፥ ባልተስማሙባቸው ጉዳዮች ላይ ሦስተኛ ሐኪም ተጨምሮ ምስሎቹን እንዲገመግም ይደረጋል። አዲሱ መሳሪያ ራሱን ችሎ ከማንበቡም በላይ ችግሩን ለይቶ በመረዳት በኩል ውጤታማ ስለመሆኑ በባለሙያዎቹ ተመስክሮለታል። መሳሪያው የጡት ካንሰር ምርመራ ውጤት ላይ ከባለሙያዎቹ የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡም ተገልጿል፤ በዚህም ለታካሚዋ የጡት ካንሰር አለብሽ በሚል በባለሙያ የሚነገራትን ሃሰተኛ የምርመራ ውጤት በ1 ነጥብ 2 በመቶ ቀንሷል። ከዚህ ባለፈም በምርመራ ወቅት የጡት ካንሰር የለም በሚል የሚነገር የተሳሳተ ውጤት ደግሞ ከባለሙያ አንጻር መሳሪያው በ2 ነጥብ 7 በመቶ መቀነሱን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል። ምንጭ፦ ቢቢሲ
አል የተባለው የጡት ካንሰር መመርመሪያ ከባለሙያ አንጻር ያለውን ስህተት በምን ያህል ቀነሰ?
በ2 ነጥብ 7 በመቶ
955
ብርቱካን ብርቱካን (ወይም ኦሬንጅ) ማለት የዛፍ አይነትም ሆነ በተለይ የዚሁ ዛፍ ፍሬ ማለት ነው። የሌሎች አትክልት ክልስ ሆኖ ከጥንት እንደ ለማ ይታሥባል። እርዝማኔው እስከ 10 ሜትር ድረስ ቢደርስም ዛፉ ትንሽ ይባላል፤ ቡቃያው እሾህ አለበትና ቅጠሎቹ ከ4 እስከ 10 ሳንቲሜትር ድረስ የሚዘረጉ እንደ ጥድም ወገን መቸም የማይረግፉ ናቸው። የፍሬው መጀመርያ ትውልድ በደቡብ-ምሥራቃዊ እስያ በህንደኬ፣ በቬትናም ወይም በደቡብ ቻይና ተገኘ። የብርቱካን እርሻ በብዙ አገሮች ምጣኔ ሀብት በጣም ታላቅ የንግድ ሥራ ነው። እዚህ ማለት በአሜሪካ፣ በሜዲቴራኔያን አገሮች፣ በሮማንያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በቻይና፣ በአውስትራልያም ይከትታል።
የብርቱካን ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው የት ነው?
በደቡብ-ምሥራቃዊ እስያ በህንደኬ፣ በቬትናም
232
የህንዱ ኩባንያ በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ዞን ጉማሬ ወረዳ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ 3,012 ሔክታር መሬት ለሻይ ቅጠል ልማት ተሰጥቶታል፡፡ ይህ ቦታ መሰጠቱ አግባብ አለመሆኑ ተጠቅሶ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎችና የአካባቢ ጉዳይ ተሟጋቾች ቅሬታ ቢያቀርቡም፣ መሬቱን የሰጠው ግብርና ሚኒስቴር ቦታው ላይ ያሉት ዛፎች ትልልቅ ሳይሆኑ ቁጥቋጦ ናቸው በማለት ሲቀርብ የነበረውን ቅሬታ ውድቅ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ኩባንያው ጣውላ በሕገወጥ መንገድ ሲያመርት በመገኘቱ የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከሦስት ዓመታት በኋላ ቬርዳንታ ሐርቨስት በዓለም አቀፍ ሕግጋትም ሆነ በኢትዮጵያ ሕግ በፅኑ የተከለከለውን የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ ማካሄዱ፣ በአካባቢው ባለሥልጣናት ቁጣ መቀስቀሱ እየተነገረ ነው፡፡ ‹‹ሠራተኛ መቅጠር ከፈለገ በሠራተኛና በአሠሪ ሕግ መሠረት መሆን ይኖርበታል፤›› በማለት አቶ ዮናስ ኩባንያው የፈጸመው ተግባር ሕገወጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁት የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጋት ሉዋክ ቱሉና ምክትላቸው ኢንጂነር ኦሌሮ ኤፒዮ በጉዳዩ ላይ መረጃው እንዳልቀረበላቸው ተናግረዋል፡፡
በቬርዳንታ ሐርቨስት ኃላፊ ድርጅታቸው በሰራው ሕገ ወጥ ስራ የተያዙት መቼ ነበር?
ሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ.ም.
329
የቅኝ ግዛት ጊዜ በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠረች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ. ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ፳ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተቆጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር። ነፃነትና የእርስ በርስ ጦርነት አንጎላ ነጻነቷን በኅዳር ፲፱፻፷፰ ከተቀዳጀች በኋላ ግን ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሚቀጥል የእርስ በርስ ጦርነት ገጠማት። ይህ ውጊያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞትና ስደት አብቅቷል። ከአልቮር ስምምነት በኋላ ሶስቱ ትልቅ የትግል ግንባሮች የሽግግር መንግሥትን ለማቋቋም በጃኑዋሪ 1975 እ.ኤ.አ. ተስማሙ። ነገር ግን በሁለት ወራት ውስጥ እነዚህ ግንባሮች ወደ ውጊያ ተመልሰው አገሯ ወደ ክፍፍል እያመራች ነበር። በዚህ ወቅት የቀዝቃዛው ጦርነት ኃያል አገራት የነበሩት የሶቭየት ሕብረትና አሜሪካ አንዱን ወይም ሌላውን ወገን ደግፈው ወደ ጦርነቱ ገብተዋል። ሌሎችም እንደ ፖርቱጋል፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካና ኩባ የመሳሰሉት ሀገራትም ከማገዝ ወደ ኋላ አላሉም። ፖለቲካ የአንጎላ የሕግ አስፈፃሚ አካል ፕሬዝዳንቱን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱንና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱን ያጠቃልላል። ለብዙ ዓመታት አብዛኛው ሥልጣን በፕሬዝዳንቱ እጅ ነው ያተኮረው። የ፲፰ቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። የ1992 እ.ኤ.አ. ሕገ መንግሥት የመንግሥቱን አወቃቀርና የዜጎችን መብቶችና ግዴታዎች ይዘረዝራል። የሀገሩ ሕግ ተርጓሚ አካል የፖርቱጋል ሥርዓትን ይከተላል። ጦር ኃይል የአንጎላ ጦር ኃይሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ሲሆኑ በሦስት ይከፈላሉ። እነዚህም ምድር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና አየር ኃይል ናቸው። የሀገሩ ጠቅላላ ሠራዊት ፻፲ ሺህ ይሆናል። የጦር ኃይሉ ንብረቶች መካከል በሩሲያ የተሰሩ ተዋጊ፣ ቦምብ ጣይና አጓጓዥ አውሮፕላኖች ይገኛሉ። አንዳንድ የጦር ኃይሉ ክፍሎች በኮንጎ ኪንሻሳና ኮንጎ ብራዛቪል ተመድበዋል።
የበርሊኑ ጉባኤ መች ነበር የፖርቱጋልን የቅኝ ግዛት ድንበር የወሰነው?
በ1885 እ.ኤ.አ
217
ሚስተር ኤልቤሽቲ ባደረጉት ንግግር፣ ሊቢያ ኦይል ለአፍሪካ ልዩ ትኩረት በመስጠት በመሥራት ላይ መሆኑን ገልጸው፣ በኢነርጂ መስክ አፍሪካ ውስጥ አስተማማኝ አጋር ሆኖ መሥራት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ሊቢያ ኦይል በ18 የአፍሪካ አሮች 1,015 የነዳጅ ማደያዎች አሉት፡፡ ሊቢያ ኦይል ሆልዲንግ በሊቢያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን እ.ኤ.አ. በ2004 የተመሠረተ ኩባንያ ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ ያሉትን ቢዝነስ የገዛው ከሼልና ከኤክሶን ሞቢል ኩባንያዎች ነው፡፡ በቅርቡ ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ (ኖክ) ሊቢያ ኦይል ጂቡቲን በ450 ሚሊዮን ብር መግዛቱን አስታውቋል፡፡ ሊቢያ ኦይል የጂቡቲ ንብረቱን አለመሸጡንና ኖክ ኩባንያውን የገዛው ከጂቡቲ መንግሥት እንደሆነ አስረድቷል፡፡ ሊቢያ ኦይል ወደ ጂቡቲ ከመግባቱ ከብዙ ዓመታት በፊት በተፈጠረ የባህር ውኃ ብክለት ምክንያት የጂቡቲ መንግሥት ከፍተኛ የካሳ ክፍያ በመጠየቁ በተፈጠረ አለመግባባት፣ የጂቡቲ መንግሥት የኦይል ሊቢያ ጂቡቲና የቶታል ጂቡቲ ንብረቶችን ወርሷል፡፡ የጂቡቲ መንግሥት የሊቢያ ኦይልና የቶታል ንብረቶችን ለሽያጭ አቅርቦ ሊቢያ ኦይል ጂቡቲን ኖክ፣ ቶታልን ደግሞ አንድ የፈረንሣይ ኩባንያ መግዛታቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡
ሊቢያ ኦይል በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ስንት ነዳጅ ማደያዎች አሉት?
1,015
148
ሊቢያ ኦይል ከኢትዮጵያ የተሰናበተውን ሼል ኢትዮጵያ ሊሚትድ በመግዛት የኢትዮጵያን የነዳጅ ገበያ የተቀላቀለው በ2000 ዓ.ም. ነበር፡፡ ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ 143 የነዳጅ ማደያዎች ሲኖሩት፣ 24 በመቶ የገበያ ድርሻ አለው፡፡ ኩባንያው በየዓመቱ ዘጠኝ ማደያዎች በመክፈት እ.ኤ.አ. በ2020 የነዳጅ ማደያዎቹን ቁጥር 185 ለማድረስ፣ የገበያ ድርሻውን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ አቅዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኩባንያው ዓመታዊ ሽያጭ 13 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡ ሊቢያ ኦይል 50 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የአቪዬሽን ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያና በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የነዳጅ ዲፖ የኤታኖል ማደባለቂያ ገንብቷል፡፡ ኩባንያው እስከዛሬ እንደ አዲስ የገነባቸው ስምንት የነዳጅ ኩባንያዎችን ብቻ ነው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ለግንባታ የሚሆን ቦታ የማግኘት ችግር በመኖሩ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዘካሪያስ፣ ከሼል ኩባንያ ግዢ ጋር የተፈጠረው የታክስ ክርክር የኩባንያውን ዕድገት እንደጎተተው ያስረዳሉ፡፡ የታክስ ክርክሩ እልባት ያገኘ በመሆኑ ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ቆርጦ መነሳቱን አስታውቋል፡፡ ሊቢያ ኦይል ባለፈው ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ አዳዲስ የሞተር ዘይትና ቅባቶችን አስተዋውቋል፡፡ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ የሊቢያ ኦይል የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፣ የሊቢያ ኦይል ምርቶች አከፋፋዮችና የትራንስፖርት ኩባንያዎች የሊቢያ ኦይል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሙስባሕ ኤልቤሽቲ ሽልማቶች አበርክተዋል፡፡
ሊቢያ ኦይል በእቅዱ መሰረት በ2020 ኢትዮጵያ ውስጥ የገበያ ድርሻውን ስንት እንደሚሆንለት ገምቷል?
30 በመቶ
227
ከ 60 ዓመት በኋላ ወባን ለማከም የሚረዳ ኪኒን በአሜሪካ ባለስልጣናት ፈቃድ አገኘ። መድሃኒቱ በየአመቱ 8 ሚሊየን ሰዎች ላይ የሚያገረሸውን የወባ አይነት ለማከም የሚረዳ ነው። ይህ አይነት የወባ በሽታ በጉበት ውስጥ ለረጅም ዓመት ተደብቆ የመቆየት ባህሪ አለው። ተመራማሪዎች ይህንን "ድንቅ ስኬት ሲሉ አሞካሽተውታል"። ደጋግሞ የሚያገረሽ የወባ በሽታ ፕላስሞዲየም ቪቫክስ በሚሰኝ ጥገኛ ተዋህሲያን የሚከሰት ሲሆን በአፍሪካ በዋናነት ከሚጠቀሱ የበሽታ አይነቶች መካከል አንዱ ነው። አሁን የአሜሪካው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ታፌኖኪውይን ለተሰኘው መድሃኒት እውቅና ሰጥቷል። መድሃኒቱ በሽታዋ ከተደበቀበችበት ጉበት አውጥቶ በመግደል ሰዎች በህመሙ ዳግመኛ እንዳይሰቃዩ ያደርጋል። በአሁን ሰዓት ጉበት ውስጥ የተደበቀች ወባን ለማከም የሚረዳ ፕሪማኪውን የተሰኘ መድሃኒት አለ። ነገር ግን አንድ ታፌንኪውንን ወስዶ ከሚገኘው ፈውስ ጋር ሲነፃፀር ፕሪማኪውንን ለ 14 ቀን መውሰድ ይጠይቃል።
ጉበት ውስጥ የምትደበቀውን የወባ በሽታ ለማዳን ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው መድሃኒት ምን ይባላል?
ፕሪማኪውን
474
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል። በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። የገብላዊ ልጆች የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል። ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው። ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው። ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ማን ይባላል?
ናጊብ ማህፉዝ
0
ጋሊልዮ ጋሊልዮ ጋሊሊ ታህሳስ 15, 1564 – ጥር 8, 1642 የነበረ የጣሊያን ሥነ-ፈለክ አጥኝና ተመራማሪ ነበር። ጋሊልዩ በዘመኑ የራሱን አጉሊ መነጽር በመስራት ጨረቃ ተራራ እንዳላት፣ ጁፒተር የተባለው ፈለክ ልክ እንደ መሬት የራሱ የሆኑ 4 ጨረቃወች እንዳሉት፣ ረጨቶች ከከዋክብት ስብስብ እንደተሰሩ፣ ፀሐይ ጥቁር ነጠብጣቦች እንዳሏት፣ ቬነስ ልክ እንደ ጨረቃ የተለያየ ቅርጽ በጥልቁ እንደምትይዝ የመሰከረና በኋላም መጽሃፍ ጽፎ ያሳተመ ሳይንቲስት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ጋሊልዮ የተፈጥሮ ህጎችን/ጉልበቶችን አጥንቷል። በትውፊት እንደሚነገር ጣልያን ውስጥ ባለው የተንጋደደው የፒሳ ግንብ ላይ በመውጣት፣ የተለያዩ ክብደት ያላቸውን የብረት ኳሶች ወደመሬት በመልቀቅ፣ ሁሉም በዕኩል ሰዓት መሬትን እንደሚመቱ አረጋግጧል። ከዚህ በመነሳት እስከሱ ዘመን ይሰራበት የነበረውን የአሪስቶትል አስተሳሰብ (ከባድ ነገሮች ከቀላል ነገሮች በበለጠ ፍጥነት ወደመሬት ይወድቃሉ) ፉርሽ አድርጓል። ሆኖም ግን በጊዜው የአሪስቶትል አስተሳሰብ በህብረተሰቡ ህሊና ውስጥ በጥብቅ ስለሰረጸ ቆይቶ ኢሳቅ ኒውተን የጋሊልዮን አስተሳሰብ ልክ መሆኑን በግስበት ጥናቱ እስካረጋገጠበት ድረስ የአሪስቶትል አስተሳሰብ ተቀባይነት ነበረው። ጋሊልዩ ከሱ ቀድሞ የተነሳውን የኮፐርኒከስን ሃሳብ (መሬት ሳትሆን ፀሓይ የአለም መካከለኛ ናት) በመደገፉ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ለእስር ተዳርጎ ነበር። ይህም በዚያ ዘመን የነበሩ የቤ/ክርስቲያኒቱ አዋቂወች ያምኑት እንደነበረው መሬት ቆማ ሌላው አለም ሁሉ በመሬት ዙሪያ ይሽከረከራሉ የሚለውን ስለተቃወመ ነበር። ከዚህ በኋላ እስከ አረፈበት 1642 ድረስ የቤት እስረኛ ሆኖ ዘልቋል። በቅርቡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የሮማው ፓፓ ጆን ፓውል 2ኛ ጋሊልዮን "የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት] አባት" በማለት የካቶሊክ ቤ/ክርስቲያ ከ400 አመት በፊት በጋሊልዮ ላይ ለፈጸመችው ግፍ ይቅርታ ጠይቀዋል።
የጋሊልዮ ጥናት ትክክለኛ እንደነበር በማመን የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ወክለው ስለደረሰበት ግፍ ይቅርታ የጠየቁት ማናቸው?
የሮማው ፓፓ ጆን ፓውል 2ኛ
958
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ተፈሪ መኰንን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺ እመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ፲፰፻፺፱ የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. የሐረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ። የሐረርጌ አገረ ገዥ ሲሆኑ ፣ በጣም ብዙ ሺህ ተከታዮች ነበሩዋቸውና ልጅ እያሱን ከእንደራሴነት በኅይል እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ተፈሪን ከሐረር አገረ ገዥነት እንዳይሽሯቸው የሚል ስምምነት ተዋዋሉ። ዳሩ ግን እያሱ ሃይማኖታቸውን ከክርስትና ወደ እስልምና እንደቀየሩ የሚል ማስረጃ ቀረበና ብዙ መኳንንትና ቀሳውስት ስለዚህ ኢያሱን አልወደዱዋቸውም ነበር። ከዚህም በላይ እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት ስምምነታቸው እንግዲህ ተሠርዞ ተፈሪ ደግሞ ለወገናቸው ከስምምነቱ ተለቅቀው በዚያን ጊዜ እሳቸው እያሱን ከእንደራሴነት አስወጡ። እንግዲህ በ፲፱፻፱ ዓ.ም. መኳንንቱ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ሆነው አድርገዋቸው ተፈሪ ደግሞ እንደራሴ ሆኑ። ከዚህ ወቅት ጀምሮ ተፈሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙሉ ሥልጣን ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. የንጉሥነት ማዕረግ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ አርፈው ንጉሠ ነገሥት ሆኑና ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ብዙ የውጭ ልዑካን በተገኙበት ታላቅ ሥነ-ሥርዓት ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው እሳቸውና ሚስታቸው እቴጌ መነን ዘውድ ጫኑ። በንግሥ በዓሉ ዋዜማ ጥቅምት ፳፪ ቀን የትልቁ ንጉሠ-ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለዘውድ በዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት ፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ። ለንግሥ ስርዐቱ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገር ልኡካን ከየአገራቸው ጋዜጠኞች ጋር ከጥቅምት ፰ ቀን ጀምሮ በየተራ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ስለነበር ሥርዓቱ በዓለም ዜና ማሰራጫ በየአገሩ ታይቶ ነበር። በተለይም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት በጃማይካ አንዳንድ ድሀ ጥቁር ሕዝቦች ስለ ማዕረጋቸው ተረድተው የተመለሰ መሢህ ነው ብለው ይሰብኩ ጀመር። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ፊተኛው ስማቸው «ራስ ተፈሪ» ትዝታ ራሳቸውን «ራስታፋራይ» (ራሰተፈሪያውያን) ብለዋል።
መስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. ራስ ተፈሪ መኮንን ከእንደራሴነት ስልጣን በተጨማሪ ያገኙት ኃላፊነት ምን ነበር?
የንጉሥነት ማዕረግ
757
ቢል ክሊንተን ዊልያም ጄፈርሰን «ቢል» ክሊንተን (William Jefferson Bill Clinton) (የትውልድ ስም፦ ዊልያም ጄፈርስን ብላይዝ ፬ኛ፣ እንግሊዘኛ፡ William Jefferson Blythe IV) በነሐሴ 13 ቀን፣ 1938 ዓ.ም.(1946 እ.ኤ.አ.) በሆፕ አርካንሳው የተወለዱ ሲሆን ከ1993 እስከ 2001 እ.ኤ.ኣ. ድረስ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ፕሬዝዳንት ከመሆናቸዉ በፊት አምስት ጊዜ የአርካንሳው ስቴት አስተዳዳሪ ነበሩ።
ቢል ክሊንተን የት ተወለደ?
በሆፕ አርካንሳው
167
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ በመሳተፍ በ58 ኪ.ግ ምድብ 7ኛ በመያዝ ዲፕሎማ አግኝታለች፡፡ ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ የወከለው አትሌት ሰለሞን ቱፋ እየተካሄደ ባለው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ58 ኪ .ግ ምድብ ባደረገው ውድድር 7ኛ ደረጃ በመያዝ ዲፕሎማ መገኘቱን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በወርልድ ቴኳንዶ ስንተኛ ደረጃ አገኘች?
7ኛ
56
ዝናሽ ማሞ በኢትዮጵያ ሬድዮ በእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ከ1979 ጀምሮ በመስራት ትታወቃለች፡፡ በኢትዮጵያ ሬድዮ ለ 16 አመት ያገለገለችው ዝናሽ ከእነ ታደሰ ሙሉነህ ፤ ታምራት አሰፋ ጋር በትጋት የሰራች ሲሆን ከ20 አመት በፊት ከእነ ቤተሰቦችዋ ወደ ምድረ አሜሪካ አቅንታለች፡፡ እምብዛም ልደት መከበር ባልተለመደበት በዚያን ዘመን ከተወለደች ከአንድ አመቷ ጀምሮ እስከ 16 አመቷ ድረስ ቤተሰቦቿ የልደት በዐልዋን እያከበሩላት ያደገችው ዝናሽ ማሞ አብዲበአዲስ አበባ ከተማ ግንቦት 21 ቀን 1954 አ.ም መወለድዋን ለማስታወስ አልተቸገረችም:: ትውልዷም እድገቷም ጠብመንጃ ያዥ ወይም በቅሎ ቤትበሚባለው አካባቢ ነበርእናትና አባቷ ወ/ሮ ሽብሬ ወ/ሃናና አቶ ማሞ አብዲ ይባላሉ:: ዝናሽ ማሞ መጀመሪያ በቄስ ትምህርት ቤት ከፊደል እስከ መልእክተ ዮሀንስ ተምራ ፊደላትን ከለየች በኋላ በበቅሎ ቤት አካባቢ በነበረው አስቀድሞ ኤስ አይ ኤም የልጃገረዶች ክርስቲያን አካዳሚ ተብሎ ይታወቅ በነበረው ጂሲኤ የልጃገረዶች ት/ቤት ከ አንደኛ እስከ ስድስተኛቀጥሎም ይኸው ት/ቤት የፀጋ ክርስቲያን አካዳሚ በመባል ስሙ ተቀይሮ ወንዶችም አብረው መማር በጀመሩበት ት/ቤት ከሰባተኛ እስከ አስረኛበመጨረሻም በጊዜው የነበረው የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ት/ቤቱን ወደ መንግስት ንብረትነት በማዘዋወር የአብዬት ቅርስ ተብሎ ከሰየመው በኋላ አስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛ ክፍልን እዚያው ተምራለች::
ዝናሽ ማሞ መቼ ተወለደች?
ግንቦት 21 ቀን 1954 አ.ም
301
አዶልፍ ሂትለር አዶልፍ ሂትለር (ጀርመንኛ Adolf Hitler አዶልፍ ሂትለ) እ.አ.አ. ከ1933 ጀምሮ የጀርመን ቻንስለር እንዲሁም ከ1934 ጀምሮ ደግሞ የጀርመን መሪም (Führer) ጭምር የነበረ ሰው ነው። ሂትለር በሚያዝያ 13 ቀን 1881 ዓ.ም. (20 አፕሪይል 1889 እ.ኤ.አ.) በዛሬይቷ ኦስትሪያ ተወለደ። በሚያዝያ 22 ቀን 1937 ዓ.ም. (30 አፕሪይል 1945 እ.ኤ.አ.) በርሊን ውስጥ ከአንድ ቀን በፊት ካገባት ሚስቱ ኤቫ ብራውን ጋር የራሱን ህይወት አጠፋ። በ1925 ዓ.ም. መጀመርያ የሂትለር ናዚ ወገን ከጓደኞቹ ወገን ጋር በራይክስታግ ምክር ቤት ትብብር መንግሥት ለመሥራት በቂ መንበሮች አልነበራቸውም። ተቃራኒዎቻቸው የኰሙኒስት ወገን 17% መንበሮች ስለ ነበራቸው የሂትለር ወገኖች የድምጽ ብዛት ሊያገኙ አልተቻላቸውም ነበር። በዚያው ዓመት ግን ከምርጫው ትንሽ በፊት የራይክስታግ ሕንጻ በእሳት ተቃጠለ። ይህ የኰሙኒስቶች ሥራ ነው ብለው የሂትለር ወገን ኰሙኒስት ፓርቲ ቶሎ እንዲከለከል አደረጉ። ስለዚህ ከምርጫው በኋላ የኰሙኒስትን መንበሮች ስለ አጡ የሂትለርም ወገኖች አሁን ከ50% መንበሮች በላይ ስላገኙ፣ የትብብር መንግሥት ሠሩና ወዲያው በድንጋጌ አቶ ሂትለር ባለሙሉ ሥልጣን አደረጉት። ሂትለር የጻፈው የርዮተ አለሙ ጽሑፍ «የኔ ትግል» (Mein Kampf) ሟርት ብቻ ነው። ለመጥቀስ ያህል፦ «ትኩረቴ ወደ አይሁዶች ስለ ተሳበ፣ ቪየናን ከበፊት በሌላ ብርሃን ለማየት ጀመርኩ። በሄድኩበት ሁሉ አይሁዶችን አየሁዋቸው፤ በብዛትም እያየኋቸው፣ ከሌሎች ሰዎች ፈጽሞ እንድለያቸው ጀመርኩ።»... «የግዛቱ (ኦስትሪያ-ሀንጋሪ) ዋና ከተማ የከሠተውን የዘሮች ውሑድ ጠላሁት፤ የዚህን ሁሉ የቼኮች፣ ፖሎች፣ ሀንጋርዮች፣ ሩጤኖች፣ ሰርቦች፣ ክሮዋቶች ወዘተ. የዘሮች ድብልቀት፤ በሁላቸውም መካከል፣ እንደ ሰው ልጅ መከፋፈል ሻገቶ፣ አይሁዶችና ተጨማሪ አይሁዶች።» በነበረው ዘረኛ አስተዳደሩ 6 ሚሊዮን የአውሮፓ አይሁዶችን እና 5 ሚሊዮን ሌሎች የተለያዩ ሀገራት ህዝቦችን (በተለይም ስላቮችን) በገፍ (በሆሎኮስት) አስጨርሷል። በሂትለር ሥር የናዚዎች ፍልስፍና በሂንዱኢዝም እንደሚገኘው በዘር የተከፋፈለ ካስት ሲስተም መመሥረት አይነተኛ ነበር። «አርያኖች» የተባሉት ዘሮች በተለይም የጀርመናውያን ብሔሮች ከሁሉ ላዕላይነት እንዲገኙ አሠቡ። ይህ ዝብረት የተነሣ በርግ ቬዳ ዘንድ በ1500 ዓክልበ. ያህል ወደ ሕንድ የወረሩት ነገዶች «አርያን» ስለ ተባሉ ነው፤ በጥንትም «አሪያና» የአፍጋኒስታን አካባቢ ስም የዘመናዊው ኢራንም ሞክሼ ነበር። በናዚዎቹ እንደ ተዛበው ግን ታሪካዊ ባይሆንም የ«አርያኖች» ትርጓሜ ጀርመናውያን ብቻ ነበሩ፤ ስላቮች (በተለይ የሩስያና የፖሎኝ ሕዝቦች) ግን አርያኖች ሳይሆኑ እንደ ዝቅተኞች ተቆጠሩ። የሂትለር እብደት እየተራመደ በ1926 ዓም የሀንጋሪ ሕዝብ ደግሞ «አርያኖች» ተደረጉ፣ በ1928 ዓም የጃፓን ሕዝብ እንኳን በይፋ «አርያኖች» ተደረጉ፤ በ1934 ዓም የፊንላንድ ሕዝብ ወደ «አርያኖች» በሂትለር ዐዋጅ ተጨመሩ። በሙሶሊኒ ሥር የፋሺስት ጣልያኖች እኛም አርያኖች ነን ቢሉም ጣልያኖች አርያን መሆናቸው በናዚዎች ዘንድ መቸም አልተቀበለም ነበር።
አዶልፍ ሂትለር መቼ ተወለደ?
በሚያዝያ 13 ቀን 1881 ዓ.ም. (20 አፕሪይል 1889 እ.ኤ.አ.)
139
ሄርበርት ሁቨር (1866 - 1957 ዓ.ም.) ከ1921 እስከ 1925 ዓ.ም. ድረስ 31ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። የሁቨር ቤተሠብ ከስዊስና ጀርመን ትውልድ ሲሆን ሃይማኖቱ የክዌከር ('የሚንቀጠቀጡ' ማለት ነው) ቤተ ክርስቲያን ነበረ። ወላጆቹ በልጅነቱ ጊዜ ካረፉ አንስቶ ድሃ አደግ ሆነና ከአጎቱ ጋር አደገ። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቴ መጀመርያ ክፍል በመሆኑ ትምህርቱ በነጻ ተቀበለ። ከዚያ በላይ የዩኒቬርሲቴው የቤስባልና የፉትቦል ቡድኖች አለቃ ሆነ። በ1887 ዓ.ም. የጂዮሎጂ ዲግሪ ይዘው ተመረቁ። ለ20 ዓመት የማዕደን ሊቅ ሲሆኑ እንኳን በአውስትራልያና በእንግሊዝ በማዕደን ዘርፍ የሠሩት ሥራ ስመ ጥሩ ሆነ። መጀመርያው ታላቅ አለማዊ ጦርነት በ1906 ዓ.ም. በጀመረበት ወቅት ሁቨር ከራሳቸው ኪስ ለጋሥነት አውጥተው 120,000 አሜሪካውያን ቱሪስቶችና ሠራተኞችን ከአውሮፓ ወደ አገራቸው አስመለሷቸው። ከዚያ በጀርመኖች በተወረረው በቤልጅግ ውስጥ የኖሩት ረሃብተኞች ምግብ እንዲደርሳቸው ብዙ አደረጉ። በዚህ አይነት ሥራ በጦርነት ጊዜ የሁቨር ስም ጀግና እንዳለው ሁኔታ በመገኘት ላይ ሄዶ ነበር። ጦርነቱም ከተጨረሰ በኋላ ለምሥራቅ አውሮጳ ድሃ ሕዝብ እስከ ሩስያም ድረስ በረሃብ ላሉት ሰዎች ምግብ አደረሷቸው።
ሄርበርት ሁቨር በምን ተመረቀ?
ጂዮሎጂ ዲግሪ
299
ንጉሡ «አፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» የሚለውን ስም በተቀዳጁ በማግሥቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ተብለው ተሰየሙ። እቴጌ ጣይቱም ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ከንጉሠ ነገሥቱ እጅ የተቀበሉትን ዘውድ ደፉላቸው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በታወቁበት «እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል የክብር ስም ማኅተም ተቀረፀላቸው። እቴጌ ጣይቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳትፏቸው የገነነውና በአገር አስተዳደርም ውስጥ ከፍተኛ ሚና መጫወት የጀመሩት ኢትዮጵያ ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፹፩ ዓ/ም በውጫሌ ላይ ከኢጣሊያ ጋር በተፈራረመችው ውል ውስጥ በጣልያንኛው ትርጉም ሀገሪቷን ነፃነት እንደሌላት ጥገኛ በማስመሰል ዓላማ ላይ የተመረኮዘ ውንብድና መኖሩ ከታወቀ ወዲህ ነው። ይህ ለአድዋ ጦርነት መነሳት ምክንያትና ዋነኛ መንስዔ የሆነው ጉዳይ ሊታወቅ የቻለው እቴጌ ጣይቱ የውጫሌው ውል አንቀፅ ፲፯ ላይ ዓለቃ ዓፅመ ጊዮርጊስ የተባሉት ቋንቋ አዋቂ ዓፄ ምኒልክ በሰጧቸው ትዕዛዝ መሠረት የውሉን ሰነድ በመመርመር የውሉ አስራ ሰባተኛው አንቀፅ የያዘውን የትርጉም መዛባት በመግለፅ ጉዳዮ ኢትዮጵያ የምትጐዳበት ስለመለሆኑ ጭምር በማስረዳት በሰጡት ቃል ሲሆን እቴጌ በዚህ ወቅት ነገሮችን በጥንቃቄ የሚከታተሉ ስለነበር ዓፄ ምኒልክ በመጀመሪያ ሳይረዱ ዓለቃ ዓፅመ ጊዮርጊስ እንዲታሰሩ ቢያደርጉም እቴጌ ጣይቱ ግን እኒህ ሰው ትክክለኛ የኢትዮጵያ ወዳጅ መሆናቸውን ለዓፄ ምኒልክ በማስረዳት ከሦስት ዓመታት እስራት በኋላ ማስፈታቸው ይታወቃል። እቴጌ እንደተናገሩትም «ዓፅመ ጊዮርጊስ ቢታሰር ቢፈታም ለሀገሩ የሚገባውን ሠርቶ ነው። ኧረ ለመሆኑ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው ዮሴፍ፣ ጣሊያኖች በተንኮል ገብተው በማታለል ይህን የመሰለ ሥራ ሲሠሩ አነጋጋሪ ሆኖ ሳለ እንዴት ሳይስጠነቅቅዎ ቀረ?» በማለት የእቴጌ ጣይቱ የቁጣ መዓት ወደ ዮሴፍ ዞረ።
የውጫሌ ውል በስንት ዓ.ም የተደረገ ስምምነት ነው?
ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፹፩ ዓ/ም
299
ቴምፕላርስ ቴምፕላር ወይም በሙሉ ስማቸው የክርሰቶስ እና የሰለሞን መቅደስ ምስኪን ወታደሮች የሚባሉት በጣም ታላቅ እና ሃይለኛ ከነበሩት ክርስቲያናዊ ወታደራዊ ስርአቶች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ይህ ስርዓት በ1088 ዓ.ም. ከተካሄደው አንደኛው የመስቀል ጦርነት በኋላ ማለትም በ1110 ዓ.ም. አዲስ የተቋቋመውን የእየሩሳሌም መንግስት ከእስላሞች ለመከላከልና ወደ ከአውሮፓ ወደ እየሩሳሌም የሚጎርፉትን ተሳላሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ የተመሰረተ ነው። ቴምፕላሮች የተዋቀሩት በገዳማዊ ስርዓት ሲሆን ይኸውም የሲሰተርሲያን ስርዓት መስራች የነበረው የክላርቮው በርናርድ በዘረጋላቸው ህግጋት መሰረት ነው። ቴምፕላሮች ከብዙ መሳፍንት ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው እና ጳጳሱም እነሱ ከሚቆጣጠሩዓቸው ቦታዎች ሁሉ ግብርና አስራት እንዲሰበስቡ ስለፈቀደላቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝነኛና ሃይለኛ ለመሆን ችለዋል። ቴምፕላሮቹ አራት ዋና ክፍሎች የነበሩአቸው ሲሆን እነዚሁም ዋነኞቹ ወታደሮች ወይም ናይትስ የሚባሉት ሙሉ የፈረሰኛ ትጥቅ የታጠቁ ከዝቅተኛ የህብረተሰቡ ክፍል የተውጣጡት ወይም ሰርጀንትስ በመባል የሚታወቁት፤ መለስተኛ የፈረሰኛ ትጥቅ የታጠቁ ገበሬዎች ዋነኛው ስራቸው የስርዓቱን ንብረት ማስተዳደር የነበረ፤ እንዲሁም ካህናት ስራቸው የስርዓቱን መንፈሳዊ ህይወት መከታተል የነበረ ናቸው።
አንደኛው የመስቀል ጦርነት የተካሄደው መቼ ነበር?
በ1088 ዓ.ም.
128
አፄ ዘርአ ያዕቆብ አጼ ዘርአ ያዕቆብ በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስት ክብረ እግዚእ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮውፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ(ከቀኝ ያለውን ካርታ ይመልከቱ) ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው። የዘርዓ ያዕቆብ አባት ቀዳማዊ ዳዊት ባረፉ ጊዜ፣ እንደ ጥንቱ የኢትዮጵያ ባህል ወግ መሰረት፣ ታላቅ ወንድማቸው የነበሩት ቀዳማዊ ቴወድሮስ በ1414 ሲነግሱ ታናሽ ወንድማቸውን በግዞት ወደ አምባ ግሽን እንዲሄድ አደረጉ። አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሀፈ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው መሰረት እስከ ነገሱበት ሰኔ 20 ፣ 1434 ዓ.ም. ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ (አምባ ግሸን) ላይ ለሚቀጥሉት 20 አመታት በእስር ኖሩ። ሆኖም ግን በግዞት እያሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊያቸው መጠን እየበዛ ሄደ። በነዚህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዓመት ወደ ዓመት እይተበላሸ ሂዶ በመጨረሻ ከአምባው ላይ ለሹመት ሲወርዱ አገሪቱ በእርስበርስ ሽኩቻ እየታመሰች፣ በሃይማኖት በኩልም መከፋፈል ተፈጥሮ የውጭ ሀይሎችም ከነገ ዛሬ አጠቁን እየተባለ ይሚፈራበት ሁኔታ ገጠመው። የወደፊቱ ንጉስ ብዙ እድሜውን ያሳለፈው ከሰው ተለይቶ አምባ ላይ ስለነበር፣ የዲፕሎማሲ ጥቅሙ አልተረዳውም ነበር። ይልቁኑ ፊት ለፊት የተጋረጡትን የሃገሪቱን ችግሮች በሚያስፈራ ድፍረት እና ምንም በማያወላዳ ጽናት ተጋፈጠው። ዓፄ ዘርአ ያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ንግስት እሌኒን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ። በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤተክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን ቆይቱ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳተ በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል ። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቀ እስጢፋ ወገኖች እምነት ነው። እነዚህ እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴ ባስተማራቸው መሰረት ለመስቀል መስገድና ለስእል አድኅኖ ለድንግል ማርያም መስገድ አይገባም የሚሉ ነበሩ።ተከራክረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ አሸንፈዋል። በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀው ግዛታቸውን ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር። በ1456 ዓ.ም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ በነበሩበት ቦታ ታላቅ ብርሃን ስለታየ የነበሩበትን ቦታ ደብረ ብርሃን በማለት የሃገሪቱ ዋና ከተማ አድርገው ቆርቁረዋል። እስከ እለት ህልፈታቸውም ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበረች።ኢትዮጵያዊ መንፈሳዊ ፈላስፋ። አጼ ዘርአ ያዕቆብ በጦር ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን የሚታወቁት፣ ከ 20 በላይ መጻህፍትንም በመድረስና ለትውልድ በማቅረብ ጭምርም ነው።
አጼ ዘርአ ያዕቆብ ከደቀ እስጢፎ እምነት ተከታዮች ከነበሩት ጋር የተከራከሩት በምን ጉዳይ ነው?
ለመስቀል መስገድና ለስእል አድኅኖ ለድንግል ማርያም መስገድ አይገባም
1,159
ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ በሌላ አጠራሩ ታላቁ ቅዱስ ባስሊዮስ በቀጰዶቂያ የቄሣርያ ኤጲስ ቆጶስ ነበር። የንቂያን የሊቃውንት ጉባዔ የሚደግፍና አርያኒዝምንና የአፖሊናረስን ተከታዮችን የክርስትና አመለካከት ተቃውሞ ትክክለኛውን መንገድ ያስተማረ ታላቅ አሳማኝ የሃይማኖት ፈላስፋና መሪ ነበር ። ቅዱስ ባስሊዮስ ከሃይማኖት ፈላስፋነቱ ሌላ ድሆችንና ኑሮን ማሸነፍ ያቃታቸውን በመንከባከብ ይታወቃል ። በተጨማሪም የማኅበራዊ ኑሮ ፣ የሥርዐተ ጸሎትና የጉልበት ሥራ ለገዳማዊ ኑሮ መመሪያን መሥርቷል። ባስሊዮስ ከቅዱስ ጳኩሚስ ጋር የማኅበራዊ ገዳማዊነት አባት ተብሎ በምሥራቃዊ ክርስትና ይታሰባል ። ዳሮግን በምሥራቅም በምዕራብም በቅዱስ ደረጃ ነው የሚከበረው ። እነዚህ ሁለት ጎራዎች ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት የሚለውን ስያሜ ከዮሐንስ አፍወርቅና ከግሬጎሪዮ ናዚያንዘስ ጋር ሰተውታል። ባስሊዮስ ከቀዳማዊ ባስሊዮስና ከኤሚልያ የቄሣሪያዋ በ፫፻፳ ዓም አካባቢ በቀጰዶቂያ ተወለደ ። እናትና አባቱ እግዚአአብሔርን በጣም የሚወዱና ጸሎተኞች የነበሩ ሰዎች ነበሩ ። የእናቱ አባት ከቆስጠጢኖስ ፩ኛ በክርስትና ማመን በፊት ሰማዕት ሆኖ ያለፈ ሰው ነበረ። ጸሎተኛ ባልቴቱ ማክሪናም የጎርጎርዮስ ታውማታርገስ (የኒዎ ቄሣርያን ቤተክርስቲያን በአቅራቢያው የመሠረተ) ተከታይ የነበረች ባስሊዎስንና አራቱን ወንድሞቹንና እህቱን ፣ ወጣትዋ ማክሪና ፣ ናውክራቲየስ ፣ ጴጥሮስ የሰባስቴውንና ፣ ጎርጎርዮስ የኒሳውን (ወደፊት ታላቅና የተከበሩ ቅዱሳን የሚሆኑ) በክርስትና ሃይማኖት ሥርዐት አሳደገች ። ባስሊዮስ በቄሣርያ ማዛካ ቀጰዶቂያ በአሁኑ ዘመን አጠራር ካይዜሪ (ቱርክ) ትምህርት ቤት በ፫፻፵፪ ፵፫ ዓ.ም.አካባቢ ተምሩዋል ። እዛም ጎርጎርዮስ ናዚያንዘስን የረጅም ጊዜ ጉዋደኛ የሚሆነውን ተዋውቋል። ባስሊዮስና ጎርጎርዮስ አንድላይ በመሆን ለከፍተኛ ትምህርትና በተጨማሪ የሊባኒየስን ትምህርታዊ ንግግር ለማጥናት ወደ ቁስጥጥኒያ አምርተዋል ። ሁለቱ በአቴንስ በ፫፵፪ ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ ለስድስት ዓመት ተቀምጠዋል። በዛም ቆይታቸው ጁሊያን ዘአፖስቴት ወደፊት ንጉሥ የሚሆን ተማሪ ተዋውቀዋል። ባስሊዮስ አቴንስን በ፫፵፰ ለቆ ወደ ግብፅና ሶርያ ከተጉዋዘ በኋላ አገሩ ቄሣርያ የሕግ ሥራ በመለማመድና የንግግር ችሎታ ሲያስተምር ቆየ።
ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ የት ተማሩ?
ካይዜሪ (ቱርክ) ትምህርት ቤት
916
ዶናልድ ጆን ትራምፕ ዶናልድ ጆን ትራምፕ (ጁን 14 ቀን 1946 እ.ኤ.አ. ተወለደ) አሜሪካዊ ነጋዴ ፣ ፖለቲከኛ ፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቹ ታዋቂ እና 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፕሬዚደንት ነው። ሥልጣኑንም እ.ኤ.አ. በጃኑዌሪ 20 ቀን 2017 ተረክቧል። በክዊንስ ኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው አቶ ትራምፕ በሪል እስቴት ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የፍሬድ ትራምፕ ልጅ ነው። በኮሌጅ እያለም ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ በተባለው ድርጅት ይሠራ ነበር። በእ.ኤ.አ. 1968 ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ ያንን ድርጅት ተቀላቀለ። በእ.ኤ.አ. 1971 ደግሞ ሙሉ ሥልጣን ከተሠጠው በኋላ የድርጅቱን ስም ወደ "ዘ ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን" ለወጠው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ካሲኖዎችን ፣ የጎልፍ ሜዳዎችን ፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች በእርሱ ስም የሚጠሩ ንብረቶችን አፍርቷል። እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2015 ድረስ ዘ አፕሬንቲስ የተባለ ፕሮግራምን በኤን ቢ ሲ ላይ ያቀርብ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የሪፎርም ፓርቲ እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ ቴድ ክሩዝ እና ጆን ካሲች ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታወጀ። በእ.ኤ.አ. ኖቬምበር 8 ቀን 2016 ላይ የፕሬዚደንትነት ምርጫውን አሸነፈ። ማሸነፉንም ተከትሎ ብዙ የተቃውሞ ሠልፎች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በ70 ዓመቱም ሥልጣን ላይ በመውጣቱ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ፕሬዚደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ያደርገዋል።
45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፕሬዚደንት ማን ነው?
ዶናልድ ጆን ትራምፕ
0
ሞሪታኒያ ሞሪታኒያ (አረብኛ፡ موريتانيا‎) በይፋ የሞሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ፣ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ ከአትላንቲክ ውቂያኖስ፣ በደቡብ-ምዕራብ ከሴኔጋል፣ በምሥራቅና ደቡብ-ምሥራቅ ከማሊ፣ በሰሜን-ምሥራቅ ከአልጄሪያ፣ እና በሰሜን-ምዕራብ ከምዕራባዊ ሣህራ ጋር ትዋሰናለች። የአገሩዋ ስም የመጣው ከጥንቱ የሞሪታኒያ መንግሥት ነው። ዋና እና ትልቁዋ ከተማዋ ኑዋክሾት ናት። በዛሬው ሞሪታንኒያ በመጀመሪያ የሠፈሩት የባፎር ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ስዎች ከዘላን ሕይወት ወደ ግብርና ከተቀየሩት የመጀመሪያ የሰሃራ ሕዝቦች አንዱ ናቸው። ከ5ኛው እስከ 7ኛው ምዕተ ዓመት፣ ባፎሮች በበርበር ህዝቦች ፍልሰት ምክኒያት ተፈናቀሉ። ብዙዎቹ የሞሪታኒያ ሕዝብ በመቆያ ግብርና ቢኖሩም ይሄ ወደ ውጭ አገር ለመላክ አይደለም። በተለይ ወደ ውጭ የሚላከው ብረት፣ ፔትሮሊየም፣ እና ዓሣ ናቸው። ሞሪታኒያ በ12 ዊላያ በሚባሉ ክልሎችና በአንድ የአስተዳደር አካባቢ ተከፍላልች። እነዚህም ክልሎች በ44 ሙጋታ በሚባሉ ክፍሎች ተከፍለዋል።
ሞሪታንያ ከአልጄሪያ ጋር በየት አቅጣጫ ትዋሰናለች?
በሰሜን-ምሥራቅ
143
አንኮበር በ፲፯፻፳ ዓ/ም በሸዋው ነጋሲ በመርድ አዝማች አብዬ የተመሠረተችና በአልጋ ወሪሹ መርድ አዝማች አምኀ ኢየሱስ የተስፋፋች የሸዋ ከተማ ስትሆን ከደብረ ብርሃን ምስራቃዊ አቅጣጫ ፵፫ ኪሎ ሜትር ርቀት የስምጥ ሸለቆው አፋፍ ላይ ትገኛለች። አንኮበር ከዓፄ ይኵኖ አምላክ (፲፪፻፸-፲፪፻፹፭ ዓ/ም) ዘመን ጀምሮ ለኢትዮጰያ ነገሥታት በማረፊያነት አገልግላለች። ዓፄ አምደ ጽዮን ፲፫፻፲፬-፲፫፻፵፬ ዓ/ም የድንኳን ከተማቸውን እንደተከሉባት ይነገራል። አስቲት ኪዳነ ምሕረት የርሳቸው ትክል ናት። ጦረኛዉ ዓፄ አምደ ጽዮን በ፲፫፻፴፭ ዓ/ም አዳልን ለማስገበር የዐማራን፣ የዳሞትን፣ የጐዣምን ሠራዊት ይዘው አንኮበር ሠፈሩ።ለ፬ ወራት ያህል እስከ ዘይላና በርበራ ድረስ በመዝለቅ ድል አድርገው አስገብረውታል። ዓፄ ልብነ ድንግል (፲፭፻፰-፲፭፻፵ ዓ/ም) ደግሞ በተሻለ ሁኔታ በቦለድ የባለወልድን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ጀምረው እንደነበር የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ። የከተማነት ታሪኳ የጐላው ግን ከግራኝ ወረራ በኋላ ተበታትኖ የቆየውን የጥንታዊ ሸዋን ግዛት አንድ ለማድረግ የሸዋ ስርወ-መንግሥት በአቤቶ ነጋሲ በመንዝ አጋንቻ ላይ በ፲፮፻፷፭ ዓ/ም ተጀምሮ በተከታታይ እስከ ፲፰፻፹፩ ዓ.ም የጥንት ኢትዮጶያ ግዛትን ለማስመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ ነው። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ወደ ፲፫ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሥር መሠረቱ የረር | እንጦጦ እስከዞረበትና በኋላም አዲስ አበባ እስከተቆረቆረችበት ጊዜ ድረስ በቀዝቃዛ አየሯ የምትታወቀው አንኮበር ለአምስት የሸዋ ነገሥታት በማእከልነት አገልግላለች።
አንኮበር ከተማ በማን ተቆረቆረች?
በሸዋው ነጋሲ በመርድ አዝማች አብዬ
16
በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ። ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ። በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች። አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው። ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።
የሴኔጋል ፕሬዝዳንት አብዱ ዲዮፍ በምርጫ ስንት ዙር አሸነፈ?
ለአራት
1,032
የፀሓይ አካል ለፍጹም ሉል የቀረበ ቅርጽ አለው፤ ዋልታዎቿን የሚያገናኘው ዳያሜትር ከወገቧ ዳያሜትር የሚያንሰው በ10 ኪሎ ሜትር ብቻ ነውና። ኮከባችን ፀሓይ በሥነ ፈለክ ሊቃውንት እጅግ ብዙ ጥናት ተደርጎባታል። ኾኖም ኮከቢቱን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ገና አልተመለሱም። ለምሳሌ በገሃድ የሚታየው የፀሓይ ገጽ ስኂን 6,000 ኬ (ኬልቪን) ኾኖ ሳለ፣ የዳርቻ ከባቢ አየሯ ስኂን ከሚሊዮን ኬ በላይ እንዴት ሊኾን እንደቻለ አይታወቅም። የፀሓይ ዕድሜ በአንዳንድ ሊቃውንት እሳቤ 4.6 ቢሊዮን ዓመት ገደማ ነውና በዕድሜ እኩሌታዋ ላይ የምትገኝ ኮከብ ተደርጋ ትታያለች። የኮከቢቱ መጠነ-ቁስ ጥንቅር 74% ሃይድሮጂን፣ 25% ሂሊየም ሲኾን፣ ቀሪው 1% ደግሞ ክብደት ያላቸው ርዝራዥ የብረቴ ንጥረ-ነገሮች ጥርቅም ነው። ስለ ፀሓይ የሰው ልጅ ቀዳሚ መሠረታዊ ግንዛቤ ብርሃን-ሰጭ ሰማያዊ ጻሕል መኾኗን፣ ደግሞም ከአድማስ በላይ እና በታች በመኾን ለመዓልትና ሌሊት መኖር ምክንያት መኾኗን መረዳት ነበር። በብዙ የቅድመ-ታሪክ እና የጥንት ዘመን ባህሎች ፀሓይ እንደ ብርሃናዊ አምላክ ወይም እንደ ዲበ-ተፈጥሯዊ ክሥተት ትታይ ነበር። የፀሓይ አምልኮ ለምሳሌ የ-ኢንካ (ደቡብ አሜሪካ) እና አዝቴክ (የዛሬዋ ሜክሲኮ) ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዐይነተኛ ገጽታ ነበር። ከፀሓያዊ ክሥትቶች ጋር የተያያዙ ብዙ ጥንታዊ ሐውልቶች ተገንብተው እንደነበር ለማሰብ የሐጋይ ሶልስቲስን ለማስታወቅ የተገነቡትን የድንጋይ ሜጋሊት በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። ከችንክር ከዋክብት አንጻር ስትታይ ፀሓይ የግርዶሽ መስመርን ተከትላ በዞዲያክ ውስጥ በዓመት አንድ ዑደት የምታደርግ ትመስላለች። ስለዚህ በጥንት የግሪክ የሥነ-ከዋክብት ሊቃውንት ዘንድ ፀሓይ ታዋቂ ከነበሩ ሰባት ፈለኮች እንደ አንዱ ትቈጠር ነበር። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሰባቱ የሳምንት ዕለታት በነዚህ ፈለኮች ይጠራሉ።
በሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ግምት የፀሀይ እድሜ ስንት ነው?
4.6 ቢሊዮን ዓመት
299
እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው የአውስትራሊያ የእንቁራሪት ዝርያ (ጋስትሪክ ብሩዲንግ ፍሮግ) ያልተለመደ ዓይነት የመራቢያ ሥርዓት አላት፤ የዚህች እንቁራሪት ዝርያ ከ2002 ጀምሮ እንደጠፋ ይታሰባል የሚለው ጄደብሊው ዶት ኦርግ ድረ ገጽ ነው።
እንቁላሏን በሆዷ የምትታቀፈው የእንቁራሪት ዝርያ የየት ሀገር ነች?
የአውስትራሊያ
23
ቴሌቪዥን ቴሌቪዥን የስዕል እና ድምጽ ምልክቶችን ከማሰራጫ የሚቀበል የመገናኛ ዘዴ ነው። «ቴሌ-» የሚለው ክፍል በግሪክ «ሩቅ» ማለት ቢሆን «-ቪዥን» ደግሞ ከሮማይስጥ visio /ዊዚዮ/ «ማየት» («ትርዒት») ተወስዷል። በአጠቃላይ ቴሌቪዥን ማለት ተንቀሳቃሽ ምስልን (ብዙ ጊዜ ከድምፅ ጋር) ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ የሚረዳ የመልዕክት ማስራጫ መንገድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ቴሌቪዥን ምስል መቅጃውንም ሆነ ምስል መቀበያውን መሳሪያ ሁሉ ያጠቃልላል ግን በተለምዶ ቴሌቪዥን የምንለው ምስል መቀበያውን ብቻ ነው። በ1873 እ.ኤ.አ. (1865 ዓም) የእንግላንድ ኤንጅኔር ውሎቢ ስሚስ ባደረገው ጥረት ጥንተ ንጥሩ ሴሌኒይም ብርሃን-አስተላልፎሽ መሆኑን ገለጸ። በ1884 እ.ኤ.አ. ፓውል ጎትሊብ ኒፕኮው የተባለ ጀርመናዊ ክብ የሆነ ዲስክን በስፓይራል በምብሳት ይህ ዲስክ በተሽከረከረ ቁጥር ከፊትለፊቱ የሚመጣውን ብርሃን በቀዳዶቹ በማሾለክ ከሴሌኒይም በተሰራ የካሜራ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ አደረገ። ግድግዳው ብርሃን ሲነካው ያንን ብርሃን ወደ ኮሬንቲ ሃይል በመቀየር ምስልን በኮሬንቲ መልክ በሽቦ ለመላክ ቻለ። ነገር ግን በዚህ ጊዜ አምፕሊፋየር ስላልነበር የሚላከው ምስል እምብዛም አመርቂ አልነበረም። ከ27 አመታት በኋላ በ1911 እ.ኤ.አ. የራሻው ቦሪስ ሮዚንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሲርቲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም፣ አሁንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ምስልን ለመላክና ለመቀብል ቻለ። ነገር ግን የሚንቀሳቀሱት ምስሎች የጂዎሜትሪ ቅርጽ ነበራቸው ማለትም ሶስት ማዕዘን፣ አራት ማእዘን ወዘተ... ከ7 አመታት በኋላ በ1925 እ.ኤ.አ. ጆን ሎጂ ቤርድ የተሰኘው የስኮትላንድ ተመራማሪ 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመላክ ቻለ ከዚያም በ1926 እ.ኤ.አ. ጥቁርና ነጭ የሆኑ ምስሎችን ለማስተላለፍ በቃ። በዚህ ጊዜ የሚላኩት ምስል ጥራት 30 መስመር በአንድ ጊዜ ነበር፣ በዚህም ምክንያት የሰውን ፊት ለመለየት አስቸጋሪ ቢሆንም ግን ይቻል ነበር። አቶ ቤርድ በ 1918 ዓ.ም. (26 January 1926 እ.ኤ.አ.) የመጀመሪያውን የቴሌቪዥን መግለጫ ሰጠ። በ1927 እ.ኤ.አ. ኸርበርት አይቭስ የተሰኘው የቤል ላብራቷር ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በራዲዮ ወደ ዊፓኒ ኒው ጀርሲ ለመላክ በቃ። በዚያው አመት ፊሎ ፍራንስዎርዝ የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ ስካኒንግ ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በስከነክተዲ፣ ኒው ዮርክ ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።
በ1925 እ.ኤ.አ. 2ቅጥ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በቴሌቪዥን ለመላክ የቻለው የስኮትላንድ ተመራማሪ ማን ይባላል?
ጆን ሎጂ ቤርድ
911
ከ6 አመት ጦርነት በኋላ ገላውዲወስ ተገደለና ሚናስ ስልጣን ላይ ወጣ። ለሚቀጥሉት 4 አመታት፣ እንደቀደመችው ንግስት እሌኒ በመንግስቱ ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነትን አገኘች። ቀጥሎም በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት መካከል በተነሳው ሽኩቻ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በመደገፍ በጽናት ቆማለች። ይሁንና በዚህ ምክንያት በተነሳው ጸብ የፖርቹጋል ካቶሊኮች ሊገደሉ ሲሉ በማማለድ ስራ ጉዳት እንዳይደርስባቸው አድርጋለች። ቤርሙዴዝ የተባለው ታውቂው የፖርቹጋል ተጓዥም ንጉሱን ገላውዲወስን በማናደዱ ከመገደል የተረፈው በሰብለ ወንጌል ተራዳኢነት ነበር። የስፔኑ ጀስዊት ፓትሪያርክ ኦቨዶም ከሞት የተረፈው በንግስቲቱ ምክንያት ነበር። ሠርፀ ድንግልን ወደስልጣን እንዲወጣም ከጦረኞቹ በላይ ያገዘችው እናት ንግስት ሰብለ ወንጌል ነበረች። ይህ ምርጫዋ የተሳካ ነበር ምክንያቱም ሰርጸ ድንግል ለ34 አመት ሲገዛ አገሪቱን በመከላከል ወደ ሰላም አሸጋግሯል። ሰብለ ወንጌል በአጼሠርፀ ድንግል ዘመን፣ በ1560 ዓ.ም. አመድ በር በተባለ ቦታ አረፈች። አጼ ልብነ ድንግል የራሱንና የሰብለ ወንጌልን ምስሎች የክሪት ሠዓሊ በመቅጥር ካሳለ በኋላ ግብጽ ወደ ሚገኘው ቅዱስ አትናቲዮስ ገዳም እንዳስላከው ተመዝግቦ ይገኛል።
ሰብለ ወንጌል በየት አረፈች?
አመድ በር በተባለ ቦታ
569
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በህፃናት ልብ ህክምን ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ዶክተር በላይ አበጋዝ እና 30ኛ አመቱን በማክበር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልብ ህክምና ማዕከል ያላቸውን አስተዋፅኦ በማድነቅ ሽልማት አበረከቱ።
ዶ/ር በላይ አበጋዝ በህፃናት ልብ ህክምና ላበረከቱት አስተዋፅኦ በማዕከሉ 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ማን ሸለማቸው?
ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
11
አሦር አሦር (አሹር) ማለት በጥንታዊ ዘመን በላይኛ ጤግሮስ ወንዝ አጠገብ የተገኘ ከተማና አካባቢው ነበረ። በኋለኛ ጊዜ የአሦር መንግሥት ሃይለኛ ሆኖ መላ መሬት እስከ ግብጽ ድረስ ገዛ። በጥንታዊ አሦር ከተማና በጤግሮስ አጠገብ ያሉትም ተራሮች እስከ ዛሬው አርሜንያ ድረስ 'የአሦር ተራሮች' ይሰየሙ ነበር። በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት አሦር (አሹር) ከኖኅ ልጅ ሴም ልጆች አንዱ ሲሆን፥ ከሰናዖር ወጥቶ አንዳንድ ከተማ ሠራ። በአሦራውያንም እምነት ዘንድ 'አሹር' ከተማውን የመሠረተው አምላክ ስም ነበረ። ከቅድመኛው ዘመን አውራጃው ሹቡር ተብሎ ከሰናዖር (ሹመር)፣ ማሪ ወይም ከአካድ ይገዛ ነበር። ሹቡር በታላቁ ሳርጎን መንግሥት ውስጥ ክፍል ሆኖ ጉታውያን እስከ አጠፉት ድረስ ቆየ። በኋላ እስከ 1879 ዓክልበ. ግ. ከኡር 3ኛ ሥርወ መንግሥት ይቆጣጠር ነበር። የዑር መንግሥት ሲወድቅ የአሦር ከተማ ነገሥታት ሊሙ ስሞች ይመዘገባሉ። በዚህ ወቅት አሦር ከተማ-አገር ብቻ ነበረ። ሆኖም አሦራውያን የብረታብረት ንግዳቸውን ለማስፋፋት በማሰብ አንዳንድ ቅኝ-ከተማ (ካሩም) በሐቲ (ዛሬው ቱርክ) ውስጥ መሠረቱ። ከነዚህም ዋነኛው ካነሽ የተባለው ከተማ ነበር። በ1720 ዓክልበ. ግ. አሞራዊው ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ አገሩን ከነአሦር ከተማ አቀና። ልጁን 1 እሽመ-ዳጋን (1688-1678 ዓክልበ.) በአሦር ላይ ሾመው። ነገር ግን የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ ድል አድርጎት ዙሪያው ወደ ባቢሎን መንግሥት ተሳለፈ። ከትንሹ እስያ ይካሄድ የነበረው የብረታብረት ንግድ በዚያን ጊዜ ተቋረጠ። ለሚከተለው መቶ አመት አሦር ለባቢሎን ተገዥ ነበር። በ1507 ዓክልበ. ግ. ባቢሎን ለካሣውያን ከወደቀ በኋላ፥ አሦር በሚታኒ መንግሥት (ሑራውያን) በ1441 ዓክልበ.ግ. ይሸነፍ ነበር። ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ ግን የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ (1366 ዓክልበ. ያህል)። ከዚህ በላይ ይህ አሹር-ኡባሊት የራሱን ልጅ ኩሪጋልዙን በባቢሎን ዙፋን ላይ አሾመው። በ1290 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥት አሸነፈ። የአዳድ-ኒራሪ ተከታይ 1 ስልምናሶር መንግሥቱን በከጢያውያን አግጣጫ እስከ ከርከሚሽ ድረስ አስፋፋ። የስልምናሶርም ልጅ 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ እንኳን በባቢሎን ላይ ገዛ። ሆኖም በቅርብ ጊዜ ባቢሎን በአሦር ላይ አመጽ ታደርግ ነበር። በ1200 ዓክልበ.. አካባቢ የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ስለ ወደቀ፥ ባቢሎንና አሦር ለአሞራውያን መሬት ተወዳዳሪዎች ሆኑ። የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በዚህ አቅራቢያ በ1140 ዓክልበ. በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ። የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ 1 ቴልጌልቴልፌልሶር የመንግሥቱን ጠረፍ በጣም አስፋፋ። ከርከሚሽን ከመማረኩ በላይ በሙሽኪ ላይ እስከ ጥቁር ባሕር ድረስ ዘመቻ አደረገ። ደግሞ እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ ሲዘረጋ ፊንቄን (ሊባኖስ) ያዘ። ከ1 ቴልጌልቴልፌልሶር በኋላ ከጎረቤቶቹ ከአራማውያንና ከኡራርቱ የተነሣ የአሦር ኅይል ደክሞ ነበር። በ920 ዓክልበ. ግን 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆሞ የአሦር ሃይል ታደሰ። ደግሞ ወደ ስሜን የኖሩትን ሕዝቦች በሙሉ በሰፈራ አፈለሳቸው። ይሁንና መንግሥቱ ከአቦር ወንዝ ወደ ምዕራብ አልዘረጋም። ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ከ890 ዓክልበ. ጀምሮ ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹም አስፋፋ። ከአቦርና ከኤፍራጥስ መካከል ያሉትን አራማውያን ድል አድርጎ በሜድትራኒያን ሲደርስ ፊንቄን ቀረጠ። ካልሁንም ዋና ከተማው እንዲሆን አደረገው። በልጁ 3 ስልምናሶር 34 አመት ዘመን (865-831 ዓክልበ.) አሦር በየአመቱ ለጦርነት ሠለፈ። ባቢሎን ተወርሮ ተቀረጠ። የሶርያ (አራም-ደማስቆ) ንጉስ ወልደ አዴር (አድርአዛር) ከእስራኤል ንጉስ አክዓብ ጋራ በቃርቃር ፍልሚያ ስልምናሶርን አጋጠመው። ስልምናሶርም ፊንቄንና የእስራኤል ንጉስ ኢዩን አስቀረጠ። በዋና ከተማው በካልሁ የተገኘው ጥቁር ሐውልት ስለ 3 ስልምናሶር ዘመን ድርጊቶች ይመሰክራል።
1688-1678 ዓክልበ. በአሦር ላይ የተሾመው የንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ ልጅ ማን ይባላል?
እሽመ-ዳጋን
726
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012(ኤፍቢሲ) ኡበር የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ተባባሪ መስራች ትራቪስ ካላኒክ በዓመቱ መጨረሻ ከቦርድ  አባልነታቸው ሊለቁ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡ ይሁን እንጂ የ43 ዓመቱ ትራቪስ በድርጅቱ ውስጥ ካሉ ዘጠኙ ዳይሬክተሮች ውስጥ አንዱ ሆነው የሚቀጥሉ መሆኑን  ነው የተናገሩት። ትራቪስ ካላኒክ  እንደ አውሮፓውያ ኑ አቆጣጠር 2017 ላይ በድርጅቱ በተስተዋሉ የተለያዩ የሙስና ቅሌቶች  ምክንያት ስራ ለማቆም ጫፍ ደርሰው  ነበር ። ይህን ተከትሎም  በኡበር ድርጅት ውስጥ  ያላቸውን  አብዛኛውን የአክሲዮን ድርሻ መሸጣቸው ነው የተነገረው። ትራቪስ ካላኒክ በአስር ዓመቱ መገባደጃ  ኩባንያው ያለው የሕዝብ ግንኙነት እና በጎ አድራጎት ላይ ለማተኮር ለእኔ ትክክለኛ ጊዜ ይመስለኛል፤ በዚህም ደስተኛ ነኝ ተናግረዋል ፡፡ ካናኒክ በጣም ዝነኛ የሆነው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት በመመስረት በዓለም ዙሪያ የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ  ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ምንጭ፣ ቢቢሲ
በኡበር የታክሲ አገልግሎት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በቦርድ አባልነት ያገለገሉት ትራቪስ ካላኒክ መቼ በተስተዋለው የሙስና ችግር ምክንያት ነው ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ያሰቡት?
2017
234
የትነበርሽ ንጉሴ የትነበርሽ ንጉሴ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ እና የአካል ጉዳተኛ መብትቶች ተሟጋች ናት ፡ እ.ኤ.አ በ 2017 "የአካል ጉዳተኞችን መብቶችን እና ማካተቶችን በማስተዋወቅ እንዲሁም  በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉየአእምሮ ውቅርን መለወጥ የሚያበረታታ ሥራዋ"  ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድን ተሸልማለች። የትነበርሽ ንጉሴ የአይን ብርሃኗን ያጣችው በ 5 ዓመቷ ነበር ። ይህ አጋጣሚ በተወለድችበት በአማራ ክልል በስፋት ይተገበር ከነበረው ያለ አድሜ ጋብቻ  አንድታመልጥ እድሉን እንደፈጠረላት ትናገራለች። ፡፡የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሻሸመኔ ካቶሊክ የዓይነ ስውራን  ት/ቤት ተከታትላ ወደ ዳግማዊ  ምኒልክ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (አካታች ትምህርት ቤት) ገብታ እስከ 12 ኛ ክፍል እዚያ ተማረች። በትምህርት ቤቱ ካላት አካዳሚክ ተሳትፎ በተጨማሪ የተማሪዎችን አማካሪ ጨምሮ ከ 6 በላይ የክለቦችን ክበባት መርታለች ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በመቀላቀል የመጀመሪያ ዲግሪ በሕግ ሁለተኛ ዲግሪ በማኅበራዊ ሥራ አግኝ ታለች፡፡ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ  በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በተከታታይ  ትሳተፋለች በዚህም  የመኢአድ የፀረ ኤድስ እንቅስቃሴን ከ2004 - 05 በመምራት በ 2006 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (አአዩ) ሴት ተማሪዎች ማህበርን በመመስረት እንዲሁም የማህበሩ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት በመሆን  አገልግላለች ፡፡
የትነበርሽ በ2006ዓ.ም የምን ማህበር መሰረተች?
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ (አአዩ) ሴት ተማሪዎች ማህበር
699
መንግስቱ ለማ መንግሥቱ ለማ (1924-1988) በጣሊያን ወረራ ዋዜማ በሀረር ሀደሬ ጢቆ መካነ ሥላሴ ተወልዶ ከቆሎ ተማሪነት ተነስቶ የለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ደቀመዝሙርነት እስከመሆን በቅቶ የቅኔ ቤት ሊቅነት ሳይበቃው የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ቀደምቶች መሃከል ለመደብለቅ የበቃ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ድንቅ ገጣምያን/ፀሃፌ ተውኔቶች አንዱ ነው። አባቱ አለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ-ታሪክ (ታሪክ የእናታቸው ስም ነው - ምናልባት በኢትዮጵያ ታሪክ የእናታቸውን ስም ከስማቸው አስተባብረው በመጻፍ የመጀመሪያው ሳይሆኑ አይቀሩም) ታዋቂ የቤተክርስቲያን ሊቅ የነበሩ ሲሆን በመጀመሪያ ላይ የመንግስቱን የአስኳላ (በወቅቱ ዘመናዊ ትምህርት የሚጠራው እንዲህ ነበር) ትምህርት ባይወዱለትም ጣሊያኖቹ ልጁን የማያስተምር ሰው ሁሉ ይቀጡ ስለነበር ለማስተማር ተገደዋል። ሁዋላ ላይ ግን እሳቸው አዲስ አበባ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ ተቀይረው መጥተው እሱ የኮተቤ ተማሪ ከሆነና የትምህርት ውጤቱም እስደሳች ሲሆን የቀድሞ ቅዋሜያቸውን ሳያላሉት አልቀሩም። መንግስቱ በእንግሊዝ አገር ወደ ስድስት አመት ቢቆይም ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ ነው በ1956 ዓ.ም ወደ አገሩ ለመመለስ የበቃው። ይሁን እና በቆይታው ከብዙ የእንግሊዝ ደራስያን ጋር ለመተዋወቅ በቅቷል። በተለይም ከጆርጅ በርናርድ ሾው ጋር ወዳጆች እንደነበሩ ይነገራል። መንግሥቱ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በሁዋላ የተሰማራው ወደ መንግስት ሥራ ሲሆን በህንድ አገር ዲፕሎማት ሆኖ ከሄደ በሁዋላ ምናልባትም በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ዘመናዊ ኮሜድ ተውኔት «ጠልፎ በኪሴ"ን ደርሷል ከዚያ በሁዋላ የደረሳቸው እነ «ያላቻ ጋብቻ»፣ «ጸረ-ኮሎኒያሊስት»፣ «ባለካባና ባለዳባ» የመንግስቱን ስም በኢትዮጵያ የስነ-ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ካደረጉት ስራዎቹ መካከል ናቸው። በተጨማሪም «The bear» የተሰኘውን እና የታዋቂው የሩሲያ ደራሲ አንቷን ቼኾቭ ተውኔት የሆነውን «ዳንዴዎ ጨቡዴ» በሚል የተረጎመ ሲሆን የጄ.ቢ. ፕሪስትሊን «The Inspector Calls»ን ተርጉሞ ለመድረክ አብቅቷል። መንግስቱ ከተውኔቱ በተጨማሪም በስነ-ግጥም የተዋጣለት እንደነበር ስራዎቹ ይመሰክራሉ። «የግጥም ጉባኤ» የተሰኘው ስብስብ መንግስቱ የግጥም መክሊት የተቸረው ደራሲ እንደነበር ይመሰክራል። መንግሥቱ ደራሲም ብቻ አልነበረም፤ በተማሪዎቹ የተወደደ መምህር በሳል ተመራማሪ ለባህሉ እና ለቋንቋው ሙት የነበረ ከኢትዮጵያ ብርቅዬዎች አንዱ ነው።
መንግስቱ ከተውኔቱ ውጪ የሚታወቅበት ሙያ ምን ነበር?
በስነ-ግጥም
1,176
ጣና ሐይቅ ጣና ሐይቅ ቅዱሱ ሐይቅም ይባላል። ከኢትዮጵያ አንደኛ እና ትልቁ ሐይቅ ነው። 84 ከ.ሜ. ረጅም እና 66 ኪ.ሜ. ሰፊ ነው። ባጠቃላይ 3,500 ካሬ ኪ.ሜ. ይሸፍናል። በቁጥር ከ35 በላይ ደሴቶች በሐይቁ ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥም 22ቱ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት ናቸው። ባንዳንዶቹ ላይም (ለምሳሌ በዳጋ ደሴት) የድሮ የኢትዮጵያ መሪዎች መቃብሮች ሲገኙ ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትናን ለመጀመሪያ ያስተዋወቀው አቡነ ሰላማ መቃብርም በዚሁ ሃይቅ ይገኛሉ። የጣና ሃይቅን የሚመግቡ 3ቱ ዋና ወንዞች ርብ፣ ጉማራ ወንዝ ና ትንሹ አባይ በመባል ይታወቃሉ። አሁን ባለው ይዞታ የጣና ሃይቅ 1,454 ቶን አሳ በአመት ይመረታል። ነገር ግን ይሄ የምርት ሃይቁ ያለምንም ችግር ሊያስተናግድው ከሚችለው 15 በመቶው ያህል ብቻ ነው።
በኢትዮጵያ በመጠኑ አንደኛ የሆነው ሐይቅ የቱ ነው?
ጣና ሐይቅ
7
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል። በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። የገብላዊ ልጆች የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል። ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው። ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው። ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
ናጊብ ማህፉዝ ለዓለም በርካታ ስራዎችን አበርክቶ ከዚህ ዓለም ያረፈው መቼ ነው?
ኦገስት 30 ቀን፣ 2006
1,374
ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ለወጣት ለአዛውንት የሚመቹ ደግ እናት፡፡ በኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክ ስም ያተረፉ፡፡ ለምርምር የማይደክሙ፡፡ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን እነሆ ታሪካቸውን አቀረበ፡፡ ጋዜጠኛዋ በ79 አመታቸው ሀምሌ 14 2013 ህይወታቸው አልፏል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ በ1934 አመተ ምህረት ከአባታቸው ከአቶ መኩሪያ ወልደስላሴ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሶስና ወርቅነህ ተወለዱ፡፡ እናታቸው ወይዘሮ ሶስና ወርቅነህ የሀኪም ወርቅነህ እሸቴ ልጅ ናቸው፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሳንፎርድ ተማሪ ቤት ነበር የተከታተሉት፡፡ ወይዘሮ እሌኒ ያደጉት ካዛንቺስ አካባቢ ሲሆን የልጅነት ዘመናቸው በደስታ የተሞላ ነበር፡፡ በተለይ በሳንፎርድ ተማሪ ቤት ጥሩ የእንግሊዝኛ ችሎታቸውን ከማዳበራቸው በላይ ደስ የሚል የመዝናኛ ጊዜን አሳለፈው ነበር፡፡ ቴኒስ መጫወት ፤ ዋና መዋኘት ፣ ቴአትር ማየት እና መተወን ደስ ይላቸው ነበር፡፡ እንዲያውም ለልኡል መኮንን ሆስፒታል ማሰሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ቴአትር መስራታቸውን ወይዘሮ እሌኒ በህይወት በነበሩ ጊዜ ተናግረዋል፡፡ በተለይ አያታቸው ክቡር ሀኪም ወርቅነህ እሸቴ ዳንስ ያለማምዷቸው እንደነበር አይዘነጉትም፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ፣ ማህበራዊ ሳይንስ የማጥናት ግብ ቢኖራቸውም ቤሩት የነጻ የትምህርት እድል አግኝተው ወደዚያ በ1951 ግድም ያቀናሉ፡፡ ነገር ግን የነርስነትን ትምህርት ቢጀምሩም አቋርጠው ወደ እናት ሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡ በመቀጠልም ወደ ብስራተ ወንጌል ሬድዮ በማቅናት በእንግሊዝኛው ክፍል ተቀጠሩ፡፡ ያኔ በሬድዮ ከወይዘሮ እሌኒ ጋር ይሰሩ ከነበሩት ባለሙያዎች መካከልም ጋዜጠኛ ልኡልሰገድ ኩምሳ ይጠቀሳል፡፡ ወይዘሮ እሌኒና ጋዜጠኛ ልኡልሰገድ ዜና ሲያቀርቡ ያለበት ቪድዮ ከዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ዘንድ ይገኛል፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር በግንቦት 18 1955 ሲፈረም ጋዜጠኛ ከነበሩት መካከል ወይዘሮ እሌኒ ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱ ገና የ21 አመት ወጣት የነበሩት ወይዘሮ እሌኒ መሪዎች ሲመጡ የተደረገውን ታሪካዊ አቀባበል በፍጹም አይዘነጉትም፡፡
ወ/ሮ እሌኒ መቼ ተወለዱ?
በ1934
174
ሩሲያ ለአለም አቀፍ በይነመረብ አማራጭ የሚሆን አር ዩ ኔት  የተሰኘ ኢንተርኔት  በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን  የሀገሪቱ  መንግስት አስታውቋል ፡፡ ይሁን እንጂ  የተከናወነውን ሙከራ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ አለመሰጠቱ  በዘገባው ተመላክቷል። እንደ ሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር  መረጃ ፥ማንኛውም ተጠቃሚ  በተደረገው ሙከራ ወቅት  ምንም አይነት ለውጥ ማስተዋል አለመቻሉን አስታውቋል፡፡ የሙከራ ውጤቱም  ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት  ቭላድሚር ፑቲን ይቀርባል ነው የተባለው ፡፡ ምሁራኖችበ አንዳንድ ሀገሮች በበይነ መረብ የሚደርስ ጥፋትን እንዳለ ይጠቅሳሉ። በጥናቱ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒተር ሳይንቲስት የሆኑት ፕሮፌሰር አላን ውድዋርድ እንዳሉት፥ በሚያሳዝን ሁኔታ የበይነመረብ  ሰርጎ ገቦች መበራከት የሩሲያ የጉዞ አቅጣጫ ሌላ ደረጃ እያደረሰ ነው። ቁጥራቸው እየጨመረ ያሉ ሃያላን መንግስታት ዜጎች የሚያዩትን መቆጣጠር የሚፈልጉ ስለመሆናቸው ከኢራን እና ከቻይና መመልከት ይቻላል። ይህ ማለት ሰዎች ሀገራቸው ውስጥ ስለሚሆነው ነገር የመነጋገር እድል አይኖራቸውም፡፡ የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው  ባለስልጣኖች እና የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ውጤታማ ምላሽ በመስጠት   አደጋዎች እና ስጋቶችን ማስወገድ እንዲሁም በሁለቱም በይነመረብ እና ቴሌኮሙዩኒኬሽን አውታር መረብ ውስጥ የተስተካከለ አሠራር  በሩሲያ ፌዴሬሽን እንዲኖር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው ተነግሯል።
አር ዩ ኔት የተሰኘ ዓለም አቀፍ የበይነ መረብ አማራጭ በኢንተርኔት በተሳካ ሁኔታ የሞከረችው ሀገር ማናት?
ሩሲያ
0
በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ለ25 ዓመታት ያገለገሉት ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ሀጎስ ስዩም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልእኮ አዛዥ ሆነው ተሰየሙ። ብርጋዴየር ጄነራል መአሾ  በተመድ የላይቤሪያ እንዲሁም ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ማገልገላቸውም ታውቋል። አዲሱን ሹመት ከጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደተሰጣቸውም በተመድ መረጃ ላይ ተገልጿል።
ብርጋዴር ጄነራል መአሾ ስዩም ከዚህ በፊት የት ሠርተዋል?
በተመድ የላይቤሪያ እንዲሁም ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ
132
ቀጭኔ ቀጭኔ በአፍሪካ የሚኖር ባለሙሉ ጣት ሸሆኔ ጡት አጥቢ አራዊት ሲሆን በምድር ከሚገኙ እንሰሳት በርዝማኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። ወንዱ ከ 4.4 እስከ 5.5 ሜትር ርዝማኔና 1,360 ኪሎግራም ክብደት ያስመዘግባል። እስካሁን በሪኮርድ የተያዘው የ 5.87ሜና የ2000ኪ.ግ ቀጭኔ ነው። ሴቶቹ በጥቁቱ አነስ ብለው ይታያሉ። እነዚህን ፍጥረታት በአራዊት ማቆያ ቦታዎች አንገታቸውን ከታጠሩበት አጥር በላይ ወጣ አድርገው የተመለከተ ሰው በአፍሪካ ቁጥቋጦዎች ነፃ ሆነው ሲሮጡ ያላቸውን ውበትና ግርማ መገመት ያስቸግራል። የቀጭኔ እንቅስቃሴ ትልቅ ግርማ ያለውና እንደ ውኃ ሙላት የሚፈስ ነው። በገላጣው የግጦሽ መስክ ላይ በሚጋልቡበት ጊዜ ቁመናቸው ትንሽ እንቅፋት ቢነካቸው ወድቀው የሚሰባበሩ ያስመስላቸዋል። ይሁን እንጂ እስከ 1, 300 ኪሎ ግራም የሚደርስ ክብደት ያላቸው ወንድ ቀጭኔዎች ቀልጣፋና ምንም የማያደናቅፋቸው ሯጭ ከመሆናቸውም በላይ በሰዓት እስከ 60 ኪሎ ሜትር ሊሮጡ ይችላሉ። ይህች አስደናቂ ፍጡር የምትገኘው በአፍሪካ ብቻ ነው። እርጋታዋና ሰላማዊ ተፈጥሮዋ ዓይን ይስባል። የቀጭኔ ፊት በዓይነቱ ልዩ የሆነና ቆንጆ ሊባል የሚችል ሲሆን ረዥምና ጠባብ ጆሮዎች፣ ሁለት ትናንሽ ቀንዶች እንዲሁም ጠቆር ያለ ለስላሳ ጠጉር አላት። ዓይኖቿ በጣም ትላልቅና ጥቁር ሲሆኑ ረዣዥም በሆኑ ቅንድቦች ይጠበቃሉ። ቀጭኔ ያን በመሰለ ከፍታ ላይ ሆና ሩቅ ስትመለከት ፊቷ ላይ የየዋህነት ገጽታ ይታይባታል። በጥንት ዘመናት ቀጭኔ ባላት አስደሳች ቁመና እንዲሁም ጨዋ፣ ዓይነ አፋርና ሰላማዊ ባሕርይ ያላት በመሆኑ በጣም ተወዳጅና ትልቅ ግምት የሚሰጣት ነበረች። በብሔራት መካከል ሰላምና በጎ ፈቃድ መኖሩን ለማመልከት የቀጭኔ ግልገሎች ለነገሥታትና ለገዥዎች በገጸ በረከትነት ይሰጡ ነበር። ጥንታዊ በሆኑት የአፍሪካ አለቶች ላይ ቀለማቸው የደበዘዘ የቀጭኔ ሥዕሎች እስከ ዛሬ ይታያል። ከእንስሳት ሁሉ ቀጭኔን በቁመት የሚወዳደር የለም። ሙሉ ዕድሜ ላይ የደረሱ ወንድ ቀጭኔዎች ከእግራቸው ኮቴ አንስቶ እስከ ቀንዳቸው ድረስ ከ5.5 ሜትር የሚበልጥ ርዝመት አላቸው። በግብፃውያን ጥንታዊ ሥዕላዊ የአጻጻፍ ዘዴ ቀጭኔ በረዥም ቁመቷና አርቆ በመመልከት ችሎታዋ ምክንያት “መተንበይ” የሚለውን ግሥ ትወክል ነበር። ቀጭኔ በአፍሪካ መስኮች በሚሰማሩት የሜዳ አህዮች፣ ሰጎኖች፣ አጋዘኖችና ሌሎች እንስሳት መካከል ስትቆም እንደ ማማ ሆና ትታያለች። ቁመቷና አርቆ የማየት ችሎታዋ ማንኛውንም አደጋ ገና ከሩቅ ለማወቅ ያስችላታል። ስለዚህ የቀጭኔ መኖር ለሌሎች እንስሳት የመረጋጋት ስሜት እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም።
በቀጭኔ ክብደት ላይ እስከ አሁን በሪከርድነት የተያዘው ከፍተኛው ክብደት ስንት ኪ.ግ ነው?
2000ኪ.ግ
173
ዶናልድ ጆን ትራምፕ ዶናልድ ጆን ትራምፕ (ጁን 14 ቀን 1946 እ.ኤ.አ. ተወለደ) አሜሪካዊ ነጋዴ ፣ ፖለቲከኛ ፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቹ ታዋቂ እና 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፕሬዚደንት ነው። ሥልጣኑንም እ.ኤ.አ. በጃኑዌሪ 20 ቀን 2017 ተረክቧል። በክዊንስ ኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው አቶ ትራምፕ በሪል እስቴት ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የፍሬድ ትራምፕ ልጅ ነው። በኮሌጅ እያለም ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ በተባለው ድርጅት ይሠራ ነበር። በእ.ኤ.አ. 1968 ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ ያንን ድርጅት ተቀላቀለ። በእ.ኤ.አ. 1971 ደግሞ ሙሉ ሥልጣን ከተሠጠው በኋላ የድርጅቱን ስም ወደ "ዘ ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን" ለወጠው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ካሲኖዎችን ፣ የጎልፍ ሜዳዎችን ፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች በእርሱ ስም የሚጠሩ ንብረቶችን አፍርቷል። እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2015 ድረስ ዘ አፕሬንቲስ የተባለ ፕሮግራምን በኤን ቢ ሲ ላይ ያቀርብ ነበር። እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የሪፎርም ፓርቲ እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ ቴድ ክሩዝ እና ጆን ካሲች ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታወጀ። በእ.ኤ.አ. ኖቬምበር 8 ቀን 2016 ላይ የፕሬዚደንትነት ምርጫውን አሸነፈ። ማሸነፉንም ተከትሎ ብዙ የተቃውሞ ሠልፎች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በ70 ዓመቱም ሥልጣን ላይ በመውጣቱ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ፕሬዚደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ያደርገዋል።
ትራምፕ በኮሌጅ እያለ የት ድርጅት ይሰራ ነበር?
ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ
255
ኢትዮጵያ ከ ፹ (80) በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የቻለች ሀገር ነች። ትልልቆቹ ብሄረሰቦች ፣ የአማራ ፣ እና የኦሮሞ የትግራይ እንደሁም የሶማሌ ሲሆኑ እነዚሁ ብሄረሰቦች ከጠቅላላው የሀገሪቷ ሕዝብ ቁጥር ከ 3/4ኛ በላይ የሚሆነውን ይይዛሉ። በሃይማኖት በኩልም ሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖቶች ክርስትና እና እስልምና በስፋት የሚስተዋልባት አገር ናት። የክርስትና እምነት ተከታዮች ከ 55%-60 % ፣ እስልምና ከ35% እሰከ 40% እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ወደ 5%-8% የሚሆነውን ይይዛሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ከ ፹ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን በቋንቋም በኩል ከ ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሀገር ናት። በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚነገሩት ቋንቋዎች አማርኛ እና ኦሮምኛ ሲሆኑ ፤ አማርኛ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች የመማሪያ ፤ የመገበያያ እንዲሁም የስራ ቋንቋ ሆኖ የቆየ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የስራ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነገሩት ቋንቋዎች አፍሮ-ኤስያዊ እና ናይሎ ሳህራዊ በሚባሉ ሁለት ዋና የቋንቋ ክፍሎች ሊካተቱ ይችላሉ። በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ ውስጥም ኩሻዊ፣ ኦሞአዊ እና ሴማዊ የሚባሉ ንዑስ ክፍሎች አሉ። ኩሻዊ ከሚባሉት ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ አፋን ኦሮሞ ፣ ሶማልኛ ፣ አፋርኛ ፣ ሲዳምኛ ፣ ሃዲያኛ እና ከምባትኛ ሲሆኑ ከአባይ-ሰሃራዊ የቋንቋ ምድብ የሚካተቱት በርታኛ ፣ ኩናማኛ ፣ ጉሙዝኛ ፣ ሙርሲኛ እና የመሳሰሉት ናቸው።
ኩሻዊ ቋንቋ በምን መደብ ይካተታል?
በአፍሮ-ኤስያዊ የቋንቋ ቤተሰብ
654
ጉጃራቲ ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው። የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር። አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።
ጉጃራቲ ቋንቋ 250,000 ያህል ተናጋሪዎች ያሉት በየት ነው?
በታንዛኒያ
116
ኤስፔራንቶ ኤስፔራንቶ (Esperanto) ከሁሉም አለማቀፋዊ ሠው ሰራሽ ቋንቋዎች እጅጉን የተስፋፋ ቋንቋ ነው። በ1859 እ.ኤ.አ. በዛሬይቷ ፖሎኝ የተወለደውና በሞያው የአይን ሀኪም የሆነው ሉድዊክ ሌይዛር ዛመንሆፍ በ1887 እ.ኤ.አ. ቋንቋውን ለህዝብ አሳወቀ። አላማው ኤስፔራንቶን በቀላሉ ሊማሩት የሚቻል፣ የጋራ የሆነና ለአለማቀፋዊ መግባባት የሚረዳ ግን ያሉትን ቋንቋዎች የማይተካ ቋንቋ ማድረግ ነበር። ኤስፔራንቶ ከ1,600,000 በላይ ተናጋሪዎች ቢኖሩትም የቋንቋው ደጋፊ ያልሆኑ እንግሊዝኛን ከመስፋፋቱ አንፃር ለአለማቀፋዊ ቋንቋነት በተሻለ ይመርጡታል።
ሉድዊክ ሌይዛር ዛመንሆፍ ኤስፔራንቶ የተሰኘውን ዓለም አቀፋዊ ቋንቋ ያስተዋወቀው መቼ ነበር?
በ1887 እ.ኤ.አ.
136
ከዛሬ ፶00 ዓመት በፊት የሶሎሞን ስረወ መንግስት ሸዋ (መንዝንና ተጉለት) ላይ  ሆኖ ለረጅም ዘመን ኢትዮጵያን ካስተዳደረ በሁዋል  የግራኝ መሃመድ ወረራ በአጼ ልብነድንግል ዘመን ተካሄደ።  ኢትዮጵውያን በግራኝ መሃመድ ወረራ የተነሳ ከፖርቱጋሎች ጋር ግንኙነትን መሰረቱ፡ በ፩፮፴ ተጀምሮ ለረጅም ጊዜ የተካሄደው ግጭት ከውጪ የመጡትን ሚሲዮናዊያን በሙሉ ከኢትዮጵያ በማባረር ሰላም ተመልሷል፡፡ ይህ የከፋ የግጭት ጊዜ ኢትዮጵያ የውጭ ክርስትያኖች ላይ እና አውሮፖውያኖች ላይ እስከ ሀያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ፊቷን እንድታዞር አስተዋጾ ከማድረጉም በተጨማሪ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ ከመላው አለም ተገልላ እንድትቆይ አድርጓታል፡፡ ከ1700 ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አገዛዝ ሳይኖሯት ቆይታለች፡፡ ይህም “ዘመነ መሳፍንት”  ሲሆን በ1869 አፄ ቴዎድሮስ መሳፍንቶቹን ሁሉ አስገብረው ኢትዮጵያን አንድ አድርገዋል
በኢትዮጵያ ዘመነ መሳፍንት ያበቃበት ዓመተ ምሕረት መቼ ነበር?
በ1869
485
የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፳ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በብራዚል ይካሄዳል። ብራዚል ይህን ውድድር ስታዘጋጅ ይሄ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው። ፊፋ የ2014 እ.ኤ.አ. ውድድር በደቡብ አሜሪካ እንደሚካሄድ በ2007 እ.ኤ.አ. ካወጀ በኋላ ብራዚል ያለማንም ተቀናቃኝ አዘጋጅ አገር ሆና ተመርጣለች። የ፴፩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች ከጁን 2011 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮችን በማለፍ ከብራዚል ጋር በመጨረሻው ውድድር ላይ ለመሳተፍ በቅተዋል። በጠቅላላው ፷፬ ጨዋታዎች በ፲፪ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አዲስ የተገነቡ ወይም የተሻሻሉ ስታዲየሞች ይከናወናሉ። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎል ላይን ቴክኖሎጂ በጥቅም ላይ ውሏል። በ1930 እ.ኤ.አ. ከተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጀምሮ ሁሉም የዓለም ዋንጫ ሻምፕዮን አገራት (ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን፣ ኢጣልያ፣ እስፓንያ እና ኡራጓይ) በዚህ ውድድር ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። ከዚህ በፊት በደቡብ አሜሪካ የተዘጋጁትን ዋንጫዎች እንዳለ የወሰዱት የደቡብ አሜሪካ ቡድኖች ናቸው። ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $576 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2010 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የ፴፯ ከመቶ ዕድገት አለው። ከዚህ ውስጥ $70 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1.5 ሚሊዮን የተረከበ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ እንደሚመለከተው ተከፋፍሏል፦ $8 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በምድብ ደረጃ የወደቀ ቡድን (፲፮ ቡድኖች) $9 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በየ፲፮ ዙር የወደቀ ቡድን (፰ ቡድኖች) $14 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በሩብ ፍፃሜ የወደቀ ቡድን (፬ ቡድኖች) $20 ሚሊዮን - በአራተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $22 ሚሊዮን - በሶስተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $25 ሚሊዮን - በሁለተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $35 ሚሊዮን - ለአሸናፊው ቡድን በአስራ ሁለት ከተማዎች የሚገኙ አስራ ሁለት ስታዲየሞች ለውድድሩ ተዘጋጅተዋል። ሰባቱ አዲስ የተገነቡ ሲሆን አምስቱ ደግሞ የተሻሻሉ ስታዲየሞች ናቸው።
ብራዚል በ2014 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ስታዘጋጅ ስንተኛዋ ነበር
ሁለተኛ
135
ዐምደ ጽዮን ቀዳማዊ አጼ ዐምደ ጽዮን (የዙፋን ስም ገብረ መስቀል) ከ1314 እስከ 1344 ዓ.ም. የነገሡ ሲሆን በጥንቱ ዘመን ከተነሱ ነገሥታት ውስጥ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሰፋ ያለ አሻራ ትተው ካለፉት (ለምሳሌ፦ ዘርአ ያዕቆብ) ጎን ወይም በላይ ስማቸው ይጠቀሳል። አጼ ዐምደ ጽዮን የአጼ ይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅና የአጼ ወድም አራድ ልጅ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ይኩኖ አምላክ አዲሱን የሰሎሞን ስርወ መንግስት ቢመሰርቱም፣ በልጅ ልጆቻቸው የነበረው ፉክክርና አዲስ ከሚስፋፋው የእስልምና ሃይማኖት የሚሰነዘረው ጥቃት ስርዓቱን ስጋት ላይ የጣለ ነበር። አጼ አምደ ጽዮን ይህን ፉክክር በማስቆምና በዘመናት በማይደበዝዘው ጀግንነታቸው የኢትዮጵያን ድንበር ከሞላ ጎደል አሁን በሚታወቀው መልኩ በማስቀመጥ፣ የአዲሱን ስርወ መንግስት መሰረት በማጽናት እንዲሁም በማረጋጋት ዝናቸው በጥንቱ አለም ክአፍሪቃ ቀንድ እስከ አውሮጳ የተንሰራፋ ነበር።
የአጼ ዐምደ ጽዮን አያት ማን ናቸው?
የአጼ ወድም አራድ
205
የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በአፋር ክልል ዲቼቶ አካባቢ የተገነባውን የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቆያ ተርሚናል ዛሬ ተመረቀ። ተርሚናሉ በ12 ሂክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድ ጊዜ 800 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑ ተገልጿል። የዲቾቶ የከባድ ተሽከርካሪ ተርሚናል 99 ሚሊየን 279 ሺህ 944 ብር ወጭ ተደረጎበት መገንባቱ ተነግሯል።
በአፋር ክልል ዲቼቶ አካባቢ የተገነባውን የጭነት መቆያ ተርሚናል በአንድ ጊዜ ስንት ከባድ ተሽከርካሪዎች ማስተናገድ ይችላል?
800
125
ላይቤሪያ ላይቤሪያ (እንግሊዝኛ፦ Liberia)፣ በይፋ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ፦ Republic of Liberia)፣ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በጊኒ፣ ኮት ዲቯር፣ ሴራሊዮን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። ላይቤሪያ የቅኝ ግዛት ሆና በ1822 እ.ኤ.አ. ከአሜሪካ በመጡ ነጻ የወጡ ባሪያዎች የተመሠረተች ሲሆን በአካባቢው ግን የተለያዩ ብሔሮች ለብዙ ምእተ አመታት ኖረዋል። መሥራቾቹ ዋና ከተማቸውን ሞንሮቪያ ብለው ለአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጄምስ ሞንሮው ሰይመውታል። ሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፴፱ ዓ/ም ነጻነት አወጁና ግዛቷ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ሆነች። በ1980 እ.ኤ.አ. በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት የላይቤሪያ አመራር ከወረደ በኋላ ከ1989 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ድረስ ሀገሩዋ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀሉና የሀገሩዋን ኢኮኖሚ ያቃወሱ ሁለት የእርስ-በርስ ጦርነቶችን አይታለች። የአንትሮፖሎጂ ምርምር እንደሚያሳየው ከሆነ፣ በላይቤሪያ ላይ ከ12ኛው ክፍለ-ዘመን ወይም ከዛ በፊት ጀምሮ ሰው ሠፍሯል። መንዴ (Mende) የሚባል ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ ምዕራብ ሲስፋፉ፣ ሌሎች ታናናሽ ብሄረሰቦችን ወደ ደቡብ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ገፍተዋቸዋል። ዴዪ፣ ባሳ፣ ክሩ፣ ጎላ እና ኪሲ የሚባሉ ጎሳዎች በአካባቢው ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደነበሩ በማስረጃ ይታወቃል። ይህ ፍልሰት የጨመረው የማሊ ግዛት በ1375 እ.ኤ.አ. እና የሶንጋይ ግዛት በ1591 እ.ኤ.አ. ሲዳከሙ ነው። በተጨማሪም ወደ ውስጥ ያለው ሥፍራ ወደ በርሃነት እየተለወጠ ስለመጣ፣ ነዋሪዎቹ ወደ እርጥቡ ፔፐር ጠረፍ (Pepper Coast) እንዲሄዱ ተገደዱ። ከማሊና ሶንጋይ ግዛቶች የመጡ አዳዲስ ነዋሪዎች ጥጥ ማሽከርከር፣ ልብስ መስፋት፣ ብረት ማቅለጥ እና ሩዝና ማሽላ ማብቀልን የመሳሰሉ ጥበቦች ለቦታው አስተዋወቁ። መኔ ሰዎች (ከመንዴ ወታደሮች የመጡ) አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ ቫይ የሚባል የማሊ ግዛት ከፈረሰ በኋላ ለመሰደድ የተገደደ ብሔር ወደ ግራንድ ኬፕ ማውንት (Grand Cape Mount) የሚባለው ሥፍራ ፈለሱ። የክሩ ብሔር የቫይን ፍልሰት ተቃወሙ። ከመኔ ብሔር ጋር አንድ ላይ በመሆንም የቫይ ብሔርን ከግራንድ ኬፕ ማውንት አልፈው እንዳይስፋፉ አገዱ። በጠረፍ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ታንኳ ሰርተው ከካፕ-ቨርት እስከ የወርቅ ጠረፍ (Gold Coast) ድረስ ካሉት ሌሎች ምዕራብ አፍሪካውያን ጋር ይገበያዩ ነበር። የክሩ ጎሳ በመጀመሪያ ለአውሮፓውያን ሰው ያልሆኑ ነገሮችን ይሸጡ ነበር። ግን በኋላ በየአፍሪካ ባሪያ ንግድ ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ። የክሩ ሠራተኞች ቦታቸውን ትተው በትልቅ እርሻዎችና የግንባታ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል። አንዳንዶቹም የስዊዝና ፓናማ መስኖዎች ለመገንባት ረድተዋል። ሌላ ግሌቦ የሚባሉ ሰዎች የመኔ ጎሳ አካባቢያቸውን ሲወር፣ በኋላ የላይቤሪያ ወደ ሚሆነው ጠረፍ አመሩ። በ1461 እ.ኤ.አ. እና 17ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ መካከል ፖርቱጋላዊ፣ ሆላንዳዊና ብራታንያዊ ነጋዴዎች በላይቤሪያ የንግድ ቦታ አቋቁመው ነበር። በተጨማሪም የአንድ የሚጥሚጣ አይነት ፍሬ በመብዛቱ ፖርቱጋላዊያን አካባቢውን Costa da Pimenta (ኮስታ ዳ ፒሜንታ) ማለትም የፍሬ ጠረፍ ብለው ሰይመውት ነበር። በ1822 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የቅኝ መግዛት ማህበር ላይቤሪያን ባሪያ የነበሩ ጥቁር ሰዎች የሚላኩበት ቦታ አድርጎ አቋቋመ። ከሌሎች ባሪያ ያልነበሩ ጥቁር አሜሪካውያንም ወደ ላይቤሪያ ለመሄድ የመረጡ ነበሩ። ወደ እዛ የሄዱት አሜሪካዊ ላቤሪያዊያን በመባል ይታወቃሉ። በሐምሌ 20 ቀን 1839 ዓ.ም. እነዚህ ሰፋሪዎች የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ነፃነትን አወጁ። አርባ ከመቶ የሚሆነው የሀገሩ ሕዝብ ክርስቲያን ነው። ሌላ ሀያ ከመቶ የሚሆን ሕዝብ የራሱ የአገሬው ሀይማኖት አለው። የቀረው አርባ ከመቶ ሕዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው። የላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሞንሮቪያ ይገኛል። በ1862 እ.ኤ.አ. የተከፈተ ሲሆን ከአፍሪካ ቀደምት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው። በእርስ-በርስ ጦርነት ጊዜ በጣም የተጎዳ ሲሆን አሁን እንደገና እየተገነባ ነው። ከቲንግተን ዩኒቨርሲቲ በየአሜሪካ ኢጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን በ1889 እ.ኤ.አ. ተመሥርቷል። ግቢው በሱዋኮኮ፣ ቦንግ የአገዛዝ ክፍል ይገኛል።
የላይቤሪያ ዋና ከተማ ስም ማን ይባላል?
ሞንሮቪያ
269
የፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ ምርምሮች በቫይረስ ጥቃት በእንስሳትና በሰው ላይ ለሚከሰቱ በሽታዎች በዘረመል ምህንድስና ጥበብ ክትባት ወይም መከላከያ መድሃኒት ግኝቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው። በዚህም የበርካታ በሽታዎች ክትባትና መድሃኒት ግኝቶች ባለቤት ሲሆኑ በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ያደረጋቸው ደስታ በተሰኘውና ከ100 ዓመት በፊት በአውሮጳና በአፍሪካ ከፍተኛ ዕልቂት ላደረሰው የከብቶች መቅሰፍት በሽታ ክትባት መፈልሰፋቸው ነው። ይህን ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በርካታ የምርምር ተቋማት ደክመው ያላሳኩትን የደስታ በሽታ ክትባት ማግኘታቸው በህክምና ግኝቶች መስፈርት አንቱ አስብሏቸዋል፤ ዓለምንም በደስታ በሽታ ከሚደርሰው እልቂት ታድገዋል። በእንግሊዝና በጣሊያን ወታደሮች ሴራ ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ከብቶች በተዛመተው የደስታ በሽታ እ.አ.አ ከ1888-1892 ለአራት ዓመታት በኢትዮጵያ በደረሰው እልቂት ከፍተኛ ረሀብ መከሰቱን ያስታወሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን የምርምራቸው መነሻ ከወላጆቻቸው ስለ ከብት መቅሰፍት ሲሰሙ ማደጋቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሰውና በእንስሳት ህክምና ዕውቀት በሁለቱም ሰይፍ የተካኑት አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ ለኤች አይ ቪ/ኤዲስ ቫይረስ ክትባት ለማግኘትም ደክመዋል። ከ124 በላይ የሚሆኑ የምርምር ግኝቶች በስመ ጥር ዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔቶች የታተሙላቸው ሲሆን በአሜሪካና በቻይና በሚገኙ በርካታ ተቋማትም የአካዳሚ አባልነት ተመርጠዋል፤ በአማካሪነትም እየሰሩ ይገኛል። በተማሩበት ብሎም ባስተማሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጨምሮ በአሜሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ዕውቅናና ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን ለአብነትም የዩኒቨርሲቲዎች የምርጥ አስተማሪነትና ተመራማሪነት ሽልማት፣ የእንስሳት ህክምና ዘርፍ ከፍተኛውን ዓለም አቀፍ ሽልማት፣ የልዩ አገልግሎት ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል። እርሳቸው ባቋቋሙትና በዳይሬክተርነት በሚመሩት የዓለም አቀፉ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የምርምር ማዕከል ከተለያዩ ታዳጊ አገራት በርካታ ሳይንቲስቶችንም አፍርተዋል። በትምህርትና ምርምር ዘመናቸው የነጮችን የዘረኝነት ጫና በመቋቋም ከስኬት ማማ ላይ የደረሱት ፕሮፌሰር ጥላሁን፤ አሁን ላይ በማደግ ላይ በሚገኙ አገራት ወጣት ሳይንቲስቶችን በማስተማርና በማበረታት ላይ ትኩረት አድርገው በመስራት ላይ ይገኛሉ።
በእንግሊዝና በጣሊያን ወታደሮች ሴራ ወደ ኢትዮጵያ በገቡ ከብቶች በተዛመተው የደስታ በሽታ ከብቶች በማለቃቸው ለምን ያህል ጊዜ ረሀብ ነበር?
ለአራት ዓመታት
485
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
በ1981 ዓ.ም. ንጉሥ ሌቤንጉላ የማዕድን ማውጣት ፈቃድ የሰጠው ለማን ነበር?
ሴሲል ሮድስ
802
ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር (1906-2001) የሴኔጋል የመጀመሪያው መራሄ መንግስት በመሆን ከ1960 እስከ 1980 ድረስ ያገለገሉ፣ ኔግሪቲዩድ የሚባለው ፍልስፍና ዋነኛ አቀንቃኝ የነበሩ እና በግጥሞቹም አድናቆትን ያተረፉ አፍሪካዊ የሥነጽሁፍ ሰው ናቸው። ሴንጎር የሴኔጋል ዋና ከተማ ከሆነችው ዳካር 70 ማይልስ ያህል በምትርቅ እና ጆአል ላ ፖርቱጊዝ (ጆአል ፖርቱጊዛዊቱዋ) በምትባል ትንሽ የአሳ አጥማጆች መንደር በ1906 ተወለዱ። አባታችው ነጋዴ ከሆኑ ሴሬር ከሚባሉ ጎሳ የተወለዱ ሲሆን እናታቸው ግን ፔውል ከተባለ የሙስሊም ዘላን አርብቶአደሮች ጎሳ የተወለዱ ሴት ናቸው። ሴንጎር ኋላ ላይ ሲጽፉ «ተወልጄ ያደኩት በአፍሪካ መኸል፣ የጎሳዎች እና ዘሮች መገናኛ ላይ ነው» ብለዋል። በ12 ዓመታችው የካቶሊክ ሚሲዮን ትምህርት ቤት ተመዝግበው ትምህርታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከዛ በኋላ በሌሎች ትምህርት ቤቶችም በመማር በ1928 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ከዚያም ፓሪስ ከሚገኘው ሊሴ ፓሪ ለግራንድ ከተባለው ትምህርት ቤት በ1931 ተመርቀዋል።
የሴኔጋል ዋና ከተማ ምን ትባላላች?
ዳካር
198
ጉጃራቲ ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው። የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር። አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።
ጉጃራቲ ቋንቋ በምድር በምን ያህል ተናጋሪዎች ለመግባቢያነት ያገለግላል?
በ46 ሚልዮን
65
ሚስተር ኤልቤሽቲ ባደረጉት ንግግር፣ ሊቢያ ኦይል ለአፍሪካ ልዩ ትኩረት በመስጠት በመሥራት ላይ መሆኑን ገልጸው፣ በኢነርጂ መስክ አፍሪካ ውስጥ አስተማማኝ አጋር ሆኖ መሥራት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ሊቢያ ኦይል በ18 የአፍሪካ አሮች 1,015 የነዳጅ ማደያዎች አሉት፡፡ ሊቢያ ኦይል ሆልዲንግ በሊቢያ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣን እ.ኤ.አ. በ2004 የተመሠረተ ኩባንያ ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ ያሉትን ቢዝነስ የገዛው ከሼልና ከኤክሶን ሞቢል ኩባንያዎች ነው፡፡ በቅርቡ ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ (ኖክ) ሊቢያ ኦይል ጂቡቲን በ450 ሚሊዮን ብር መግዛቱን አስታውቋል፡፡ ሊቢያ ኦይል የጂቡቲ ንብረቱን አለመሸጡንና ኖክ ኩባንያውን የገዛው ከጂቡቲ መንግሥት እንደሆነ አስረድቷል፡፡ ሊቢያ ኦይል ወደ ጂቡቲ ከመግባቱ ከብዙ ዓመታት በፊት በተፈጠረ የባህር ውኃ ብክለት ምክንያት የጂቡቲ መንግሥት ከፍተኛ የካሳ ክፍያ በመጠየቁ በተፈጠረ አለመግባባት፣ የጂቡቲ መንግሥት የኦይል ሊቢያ ጂቡቲና የቶታል ጂቡቲ ንብረቶችን ወርሷል፡፡ የጂቡቲ መንግሥት የሊቢያ ኦይልና የቶታል ንብረቶችን ለሽያጭ አቅርቦ ሊቢያ ኦይል ጂቡቲን ኖክ፣ ቶታልን ደግሞ አንድ የፈረንሣይ ኩባንያ መግዛታቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡
ሊቢያ ኦይል ሆልዲንግ ኩባንያ አፍሪካ ውስጥ ያለውን ቢዝነስ የገዛው ከእነማን ነው?
ከሼልና ከኤክሶን ሞቢል ኩባንያዎች
260
ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የወይዘሮ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ ነበር። በ1860 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ጦርነት ልጃቸው ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ሀገር ተወስዶ ነበር፡፡ ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡ በልዑሉ ውልደት የተደሰቱት አፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500 ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ በኋላ ከእድሜው ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴን ስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እና አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች እና አጫዋቾች ተመረጡለት፡፡ አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብ ተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡ በመርከቢቱ ላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀ ወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉ አለማየሁን ማስከተል ያዘወትር ነበር፡፡ ይህንን የሁለቱን ፍቅር ያየው ጀነራል ናፒየርም ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይልቁንም የአለማየሁን ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ካፕቴን ስፒዲ እንዲረከብ ስለወሰነ ሁለቱ ሞግዚቶች ጉዞው ተጠናቆ እንግሊዝ ሀገር ሳይደርሱ ከስዊዝ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡ ከሶስት ወራት የመርከብ ላይ ጉዞ በኃላ አለማየሁ እንግሊዝ ሀገር ደረሰ፡፡
ልዑል አለማየሁ ከምን ያህል የመርርብ ጉዞ በኋላ እንግሊዝ ደረሰ?
ከሶስት ወራት
874
ማሊ የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያ፣ ኒጄር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኔ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች። ማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር። ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር። ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች። ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ። ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅ፣ ዩራኒየም፣ ፎስፌት፣ ካዎሊን፣ ጨው፣ ኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ። የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት። ማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው።
በማሊ አብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል በምን በረሃ ውስጥ ይገኛል?
በሰሐራ
948
አብርሀም ሊንከን (የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፰ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም.) ድረስ የኖሩ ከ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትተው ተገደሉ። የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜሪ ቶድን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር መኖር ትንሽ የተቸገሩ ቢሆነም ከጊዜ ብዛት ግን ለምደዉ 4 ወንድ ልጆችን በተከተሉት አመታት ወለዱ። በ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን ሪፐብሊካን ፓርቲ መሥርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም. የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ። በጦርነቱ የስሜን ሠራዊት ከብዛታቸው የተነሣ በአራት ዓመት ውስጥ አሸነፉ። በዚህ ጊዜ ላይ ሊንከን ለአመጸኖቹ ባርዮች ነጻነት አዋጁ። ያላመጹ ዜጎች ባርያዎች ግን በዚያን ጊዜ ነጻ አልወጡም። በ፲፰፻፶፮ዓ.ም.ምርጫ ሊንከን በቀላል ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ተመረጡ። በሚያዝያ ፪ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. የኮንፌደራት ሠራዊት እጁን ሰጠ። ነገር ግን ሚያዝያ ፯ ቀን የመድረክ ትርዒት ሲያዩ በነፍሰ ገዳዩ በጆን ዊልክስ ቡዝ እጅ በጥይት ተመትተው በማግሥቱ ሞቱ። ከዚህም ትንሽ በኋላ ባርነት በሕግ በሙሉ ተክለክሎ የተረፉት ባርያዎች ነጻነት አገኙ።
አብርሃም ሊንክን መች ተወለዱ?
የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም.
12
በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ስለ ፀሓይ ሳይንሳዊ መግለጫ ለመስጠት ከቻሉ ቀዳሚ ሰዎች አንዱ ግሪካዊው ፈላስፋ አናክሳጎራስ ነበር። ፀሓይ በእሳታዊ ነበልባል የምትንቀለቀል እጅግ ግዙፍ የብረት ኳስ እንጂ የሄሊዮስ ሰረገላ እንዳልነበረች በምክንያት የተደገፈ ትንተና አቀረበ። ይህንን እንደ ኑፋቄ የተቈጠረ ሐተታ በማስተማሩም ታሰረ፤ በሞት እንዲቀጣም ተፈርዶበት ነበር፤ በፔሪክልስ አማላጅነት እንዲፈታ ተፈቀደለት እንጂ። የባለሥልጣናት መዓት የወደቀበት ሌላው የሳይንስ ሊቅ ኒቆላዎስ ቆጰርኒቆስ ነበር። በ16ኛው ምእት ውስጥ የኖረው ቆጰርኒቆስ ምድር ፀሓይን በቀለበትማ ምሕዋር ትዞራለች እንጂ፣ ፀሓይ ምድርን አትዞርም የሚል ኀልዮ አቅርቦ ነበር። በ17ኛው ምእት ጋሊሌዮ በቴሌስኮፕ ለታገዘ የፀሓይ ጥናት ፈር-ቀዳጅ ሊቅ ኾነ። አይዛክ ኒውተን ደግሞ በፕሪዝም አማካይነት የፀሓይ ብርሃን ልዩ ልዩ ቀለማት ካላቸው ብርሃናት የተጠናቀረ እንደኾነ አሳየ። 19ኛው ምእት ዊሊያም ኸርሽል የኢንፍራሬድ ጨረር ግኝት ባለቤት የኾነበት፣ በስፔክትሮስኮፕ ስለ ፀሓይ የሚደረገው ጥናትም እጅግ የመጠቀበት ምእት ኾነ። ዛሬ በብዙ አገሮች ልማድ ፀሓይ እንደ ባህላዊ ምልክት ትታያለች። ለምሳሌ በሜክሲኮ ኪነ ጥበብ አበክራ የምትታይ ሞቲፍ በመባል ትታወቃለች። በኛ ሥርዐተ-ፀሓይ ዋናዋ ትልቅ አካል ራሷ ፀሓይ ናት። በመላው ሥርዐተ-ፀሓይ ውስጥ ከሚገኘው ክብደት 99.86% የፀሓይ ነው። ለምሳሌ ከታላቁ ፈለክ ከጁፒተር ሲነጻጸር የፀሐይ ክብደት 1000 ዕጥፍ ይበልጣል። የፀሓይ ክብደት ከምድር 1.3 ሚሊዮን ጊዜ ይበልጣል። በጣም ግዙፍ እና ከባድ የኾነችው ኮከብ ከምድር ያለችበት ርቀት በጣም የሚያስደንቅ ነው። በምድር እና በፀሓይ መካከል ያለው ርቀት የምድርን ዳያሜትር በ12,000 ጊዜ ይበልጣል። ብርሃን ይህን ርቀት ለመጓዝ 8.5 ደቂቃ ይፈጅበታል።
የፀሓይ ብርሃን ጨረር መሬት ላይ በምን ያህል ፍጥነት ይደርሳል?
8.5 ደቂቃ
1,005
አብርሀም ሊንከን (የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፰ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም.) ድረስ የኖሩ ከ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትተው ተገደሉ። የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜሪ ቶድን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር መኖር ትንሽ የተቸገሩ ቢሆነም ከጊዜ ብዛት ግን ለምደዉ 4 ወንድ ልጆችን በተከተሉት አመታት ወለዱ። በ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን ሪፐብሊካን ፓርቲ መሥርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም. የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ። በጦርነቱ የስሜን ሠራዊት ከብዛታቸው የተነሣ በአራት ዓመት ውስጥ አሸነፉ። በዚህ ጊዜ ላይ ሊንከን ለአመጸኖቹ ባርዮች ነጻነት አዋጁ። ያላመጹ ዜጎች ባርያዎች ግን በዚያን ጊዜ ነጻ አልወጡም። በ፲፰፻፶፮ዓ.ም.ምርጫ ሊንከን በቀላል ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ተመረጡ። በሚያዝያ ፪ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. የኮንፌደራት ሠራዊት እጁን ሰጠ። ነገር ግን ሚያዝያ ፯ ቀን የመድረክ ትርዒት ሲያዩ በነፍሰ ገዳዩ በጆን ዊልክስ ቡዝ እጅ በጥይት ተመትተው በማግሥቱ ሞቱ። ከዚህም ትንሽ በኋላ ባርነት በሕግ በሙሉ ተክለክሎ የተረፉት ባርያዎች ነጻነት አገኙ።
የአብርሃም ሊንከን አባት ስራቸውስ ምን ነበር?
ገበሬ
217
ሃሙራቢ ሃሙራቢ (አካድኛ፤ ከአሞርኛ አሙራፒ) ከ1705 እስከ 1662 ዓክልበ. ድረስ ('ኡልትራ አጭር አቆጣጠር') የባቢሎን ንጉሥ ነበረ። አባቱ ሲን-ሙባሊት ማዕረጉን ከተወ በኋላ ወራሹ ሃሙራቢ የባቢሎንን መንግሥት ግዛት በሜስፖጦምያ በጦርነት አስፋፋ። ሃሙራቢ በተለይ የሃሙራቢ ሕገ ፍትሕ ስለሚባለው የ1704 ዓክልበ. ሕገ ፍትሕ ይታወቃል። ሕግጋቱ የተቀረጹ ቁመቱ 2.4 ሜትር በሆነ ድንጋይ ሲሆን በ1893 ዓ.ም. ለሥነ ቅርስ ተገኝቷል። ሃሙራቢ እንደ ሕግ-ሰጪ ንጉሥ ዝነኛ ስለሚሆን፣ ምስሉ በአሜሪካ መንግስት ቤቶች ዛሬው ሊታይ ይችላል። ዋሺንግተን ዲሲ በአሜሪካ ምክር ቤት ውስጥ በእብነ በረድ ተቀርጸው ከ23 ታሪካዊ ሕግ-ሰጪዎች ምስሎች መካከል የሃሙራቢ ምስል አንዱ ነው። በአሜሪካ ላይኛ ችሎት ቤት ውስጥ በደቡብ ግድግዳ ላይ ሃሙራቢ ከታሪካዊ ሕግ-ሰጪዎች ጋራ የሚያሳይ ትርዒት አለ።
የሃሙራቢ ወራሽ ከሆነ በኃላ በሜስፓጦምያ በጦርነት የትኛውን መንግስት አስፍፍ?
የባቢሎንን መንግሥት ግዛት
123
ጉጃራቲ ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው። የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር። አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።
ጉጃራቲ ቋንቋ ፊደላት የማንን ፊደላት ይመስላሉ?
የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል
612
አዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዕውቁና አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ በውጭ አገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች ወጣቶችን በሳይንስ በማነጽ ተግባር እንዲሰማሩ፤ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር ጥላሁን በቻይና ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የአፍሪካ ሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል ሊያቋቁሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚዘጋጀው ወርኃዊ የሳይንስ ገለጻ መድረክ ወጣቱን ትውልድ ማስተማርና ማነጽ ለኢትዮጵያ ተስፋ፤ የቻይና ተምሳሌትነት በሚል ትናንት ምሽት ገለጻ አድርገዋል። በአውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 1943 በኢትዮጵያ የተወለዱት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች አጠናቀው በቀድሞው የአለማያ እርሻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት በኮሌጅ ቆይታቸው ባሳዩት የላቀ ውጤትም አሜሪካን አገር በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህር ቤት ተልከው ትምህርታቸውን በማጥናት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት አስተምረዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላም ወደ ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በደቂቀ ሥነ ሕይወት መስክ በማጥናት በአውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1980-2006 በተማሩበት ካሊፎርኒያ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አስተምረዋል፤ ተመራምረዋል። እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ደግሞ የዲስቲንጉሽድ ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.አ.አ ከ1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል በማቋቋም በዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ።
ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በአረማያ እርሻ ኮሌጅ ለስንት ዓመት ተማሩ?
ለሁለት
594
አዶልፍ ሂትለር አዶልፍ ሂትለር (ጀርመንኛ Adolf Hitler አዶልፍ ሂትለ) እ.አ.አ. ከ1933 ጀምሮ የጀርመን ቻንስለር እንዲሁም ከ1934 ጀምሮ ደግሞ የጀርመን መሪም (Führer) ጭምር የነበረ ሰው ነው። ሂትለር በሚያዝያ 13 ቀን 1881 ዓ.ም. (20 አፕሪይል 1889 እ.ኤ.አ.) በዛሬይቷ ኦስትሪያ ተወለደ። በሚያዝያ 22 ቀን 1937 ዓ.ም. (30 አፕሪይል 1945 እ.ኤ.አ.) በርሊን ውስጥ ከአንድ ቀን በፊት ካገባት ሚስቱ ኤቫ ብራውን ጋር የራሱን ህይወት አጠፋ። በ1925 ዓ.ም. መጀመርያ የሂትለር ናዚ ወገን ከጓደኞቹ ወገን ጋር በራይክስታግ ምክር ቤት ትብብር መንግሥት ለመሥራት በቂ መንበሮች አልነበራቸውም። ተቃራኒዎቻቸው የኰሙኒስት ወገን 17% መንበሮች ስለ ነበራቸው የሂትለር ወገኖች የድምጽ ብዛት ሊያገኙ አልተቻላቸውም ነበር። በዚያው ዓመት ግን ከምርጫው ትንሽ በፊት የራይክስታግ ሕንጻ በእሳት ተቃጠለ። ይህ የኰሙኒስቶች ሥራ ነው ብለው የሂትለር ወገን ኰሙኒስት ፓርቲ ቶሎ እንዲከለከል አደረጉ። ስለዚህ ከምርጫው በኋላ የኰሙኒስትን መንበሮች ስለ አጡ የሂትለርም ወገኖች አሁን ከ50% መንበሮች በላይ ስላገኙ፣ የትብብር መንግሥት ሠሩና ወዲያው በድንጋጌ አቶ ሂትለር ባለሙሉ ሥልጣን አደረጉት። ሂትለር የጻፈው የርዮተ አለሙ ጽሑፍ «የኔ ትግል» (Mein Kampf) ሟርት ብቻ ነው። ለመጥቀስ ያህል፦ «ትኩረቴ ወደ አይሁዶች ስለ ተሳበ፣ ቪየናን ከበፊት በሌላ ብርሃን ለማየት ጀመርኩ። በሄድኩበት ሁሉ አይሁዶችን አየሁዋቸው፤ በብዛትም እያየኋቸው፣ ከሌሎች ሰዎች ፈጽሞ እንድለያቸው ጀመርኩ።»... «የግዛቱ (ኦስትሪያ-ሀንጋሪ) ዋና ከተማ የከሠተውን የዘሮች ውሑድ ጠላሁት፤ የዚህን ሁሉ የቼኮች፣ ፖሎች፣ ሀንጋርዮች፣ ሩጤኖች፣ ሰርቦች፣ ክሮዋቶች ወዘተ. የዘሮች ድብልቀት፤ በሁላቸውም መካከል፣ እንደ ሰው ልጅ መከፋፈል ሻገቶ፣ አይሁዶችና ተጨማሪ አይሁዶች።» በነበረው ዘረኛ አስተዳደሩ 6 ሚሊዮን የአውሮፓ አይሁዶችን እና 5 ሚሊዮን ሌሎች የተለያዩ ሀገራት ህዝቦችን (በተለይም ስላቮችን) በገፍ (በሆሎኮስት) አስጨርሷል። በሂትለር ሥር የናዚዎች ፍልስፍና በሂንዱኢዝም እንደሚገኘው በዘር የተከፋፈለ ካስት ሲስተም መመሥረት አይነተኛ ነበር። «አርያኖች» የተባሉት ዘሮች በተለይም የጀርመናውያን ብሔሮች ከሁሉ ላዕላይነት እንዲገኙ አሠቡ። ይህ ዝብረት የተነሣ በርግ ቬዳ ዘንድ በ1500 ዓክልበ. ያህል ወደ ሕንድ የወረሩት ነገዶች «አርያን» ስለ ተባሉ ነው፤ በጥንትም «አሪያና» የአፍጋኒስታን አካባቢ ስም የዘመናዊው ኢራንም ሞክሼ ነበር። በናዚዎቹ እንደ ተዛበው ግን ታሪካዊ ባይሆንም የ«አርያኖች» ትርጓሜ ጀርመናውያን ብቻ ነበሩ፤ ስላቮች (በተለይ የሩስያና የፖሎኝ ሕዝቦች) ግን አርያኖች ሳይሆኑ እንደ ዝቅተኞች ተቆጠሩ። የሂትለር እብደት እየተራመደ በ1926 ዓም የሀንጋሪ ሕዝብ ደግሞ «አርያኖች» ተደረጉ፣ በ1928 ዓም የጃፓን ሕዝብ እንኳን በይፋ «አርያኖች» ተደረጉ፤ በ1934 ዓም የፊንላንድ ሕዝብ ወደ «አርያኖች» በሂትለር ዐዋጅ ተጨመሩ። በሙሶሊኒ ሥር የፋሺስት ጣልያኖች እኛም አርያኖች ነን ቢሉም ጣልያኖች አርያን መሆናቸው በናዚዎች ዘንድ መቸም አልተቀበለም ነበር።
በአዶልፍ ሂትለር መንግሥት በ1934 ዓም የማን ሕዝቦች ናቸው የአርያኖች ዘር የተደረጉት?
የፊንላንድ
1,646
ኒኑስ ኒኑስ በጥንታዊ የግሪክ ታሪክ ጸሃፊዎች ዘንድ የነነዌ መስራችና የአሦር ንጉስ ነበረ። ለዘመናዊ ሥነ ቅርስ የታወቀ አንድ ግለሰብ አይመስልም፤ ዳሩ ግን የአያሌ ታሪካዊ ወይም አፈ ታሪካዊ ግለሰቦች ትዝታ በአንድ ስም በግሪኮች በኋለኛ ዘመን እንደ ተዘከረ አሁን ይታስባል። የንጉሥ ኒኑስና ሚስቱ ንግሥት ሴሚራሚስ ስሞች በጽሁፍ መጀመርያ የተገኘው ክቴስያስ ዘክኒዱስ (400 ዓክልበ. ገዳማ) በጻፈው በፋርስ አገር ታሪክ ነው። ክቴስያስ ለ2 አርጤክስስ (2 አርታሕሻጽታ) የመንግሥት ሀኪም ሆኖ የፋርስ ነገሥታት ታሪካዊ መዝገቦች አንብቤያለሁ ብሎ አሳመነ። ከዚህ በኋላ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ የክቴስያስን ወሬ አስፋፋ። የአለም ታሪክ ሊቃውንት እስከ 1880ዎቹ ድረስ የኒኑስ ታሪክ ዕውነት መሆኑን ይቈጠሩት ነበር። በዚያን ጊዜ የኩኔይፎርም ጽሕፈት ፍች ስለ ተፈታ፣ በሜስፖጦምያና በነነዌ ብዙ ቅርሶችም በመገኘታቸው፣ የአሦር ትክክለኛ ታሪክ ዕውቀት ተጨመረልን። ኒኑስ የቤሉስ ወይም ቤል ልጅ ተባለ፤ ይህም ምናልባት በሴማዊ ቋንቋ ሥር «ባል» (ጌታ) የመሰለ ማዕረግ ሊሆን ይችላል። በካስቶር ዘሮድስ ዘንድ ኒኑስ ለ52 ዓመታት ነገሰ፤ ክቴስያስም እንዳለው መጀመርያው ዓመተ መንግሥቱ 2198 ዓክልበ. ነበረ። በ17 አመታት ውስጥ ኒኑስ በአረቢያ ንጉስ አርያዎስ እርዳታ ምዕራብ እስያን በሙሉ እንዳሸነፈ ተብሏል። ከዚህ ቀጥሎ የአርመን ንጉስ ባርዛኔስን (ይቅርታ የሰጠውን) እና የሜዶን ንጉስ ፋርኖስን (በስቅለት ይሙት በቃ የሰጠውን) ድል በማድረግ የአለም መጀመርያ ንጉሠ ነገስት እንደ ሆነ ተብሏል።
ኑኒስ በእነማን እርዳታ ነው ምዕራብ እስያን ማሸነፍ የቻለው?
በአረቢያ ንጉስ አርያዎስ
724
ሞሪታኒያ ሞሪታኒያ (አረብኛ፡ موريتانيا‎) በይፋ የሞሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ፣ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ ከአትላንቲክ ውቂያኖስ፣ በደቡብ-ምዕራብ ከሴኔጋል፣ በምሥራቅና ደቡብ-ምሥራቅ ከማሊ፣ በሰሜን-ምሥራቅ ከአልጄሪያ፣ እና በሰሜን-ምዕራብ ከምዕራባዊ ሣህራ ጋር ትዋሰናለች። የአገሩዋ ስም የመጣው ከጥንቱ የሞሪታኒያ መንግሥት ነው። ዋና እና ትልቁዋ ከተማዋ ኑዋክሾት ናት። በዛሬው ሞሪታንኒያ በመጀመሪያ የሠፈሩት የባፎር ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ስዎች ከዘላን ሕይወት ወደ ግብርና ከተቀየሩት የመጀመሪያ የሰሃራ ሕዝቦች አንዱ ናቸው። ከ5ኛው እስከ 7ኛው ምዕተ ዓመት፣ ባፎሮች በበርበር ህዝቦች ፍልሰት ምክኒያት ተፈናቀሉ። ብዙዎቹ የሞሪታኒያ ሕዝብ በመቆያ ግብርና ቢኖሩም ይሄ ወደ ውጭ አገር ለመላክ አይደለም። በተለይ ወደ ውጭ የሚላከው ብረት፣ ፔትሮሊየም፣ እና ዓሣ ናቸው። ሞሪታኒያ በ12 ዊላያ በሚባሉ ክልሎችና በአንድ የአስተዳደር አካባቢ ተከፍላልች። እነዚህም ክልሎች በ44 ሙጋታ በሚባሉ ክፍሎች ተከፍለዋል።
ሞሪታንያ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር በየት አቅጣጫ ትዋሰናለች?
በምዕራብ
84
ጨረቃ ላይ መውጣት ጨረቃ ላይ መውጣት የምንለው ማናቸውም ሰው ሰራሽ መንኮራኩሮች ጨረቃ ገጽ ላይ ሲያርፉ ያለውን ክንውን ነው። ይህ እንግዲህ ሰውንም ሆነ ያለሰው የተደረጉ በጨረቃ የማረፍ ክንውኖችን ይጠቀላላል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰራሽ የሆነ ነገር ጨረቃ ላይ ያረፈው በመስከረም 13፣ 1959 እ.ኤ.አ. ሲሆን ይኸውም የሶቭዬት ህብረት ሉና 2 ሚሲዮን ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ እራሱ ጨረቃ ላይ የወጣው ሐምሌ 20፣ 1969 እ.ኤ.አ. ሲሆን ይኸውን በአሜሪካው የአፖሎ 11 ሚሲዮን መንኮራኩር ነበር። ባጠቃላይ 24 አሜሪካውያን ወደጨረቃ ተጉዘዋል፣ 12ቱ የጨረቃን ምድር በእግራቸው ረግጠዋል። በዚህ ወቅት ሶቪየት ህብረትም የራሷን ጠፈርተኞች ለመላክ ሞክራለች። ለዚህ እንዲረዳት ጨረቃ ላይ አራፊ LK የተሰኘ መንኮራኩር ሰራች፣ ሆኖም ግን ይህን መንኮራኩር ወደ ጨረቃ የሚወስድ ከባድ ሃይል ያለው ሮኬት ከአሜሪካ ቀድማ መስራት ስላልቻለች ተቀደመች። ዩጂን ከርናን የጨረቃን ምድር የረገጠው የመጨረሻው ሰው ነው።
የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ ላይ የወጣው በምን መንኮራኩር ተጠቅሞ ነበር?
በአሜሪካው የአፖሎ 11 ሚሲዮን
290
ናጊብ ማህፉዝ ናጊብ ማህፉዝ በ1988 እ.ኤ.አ. በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን የተቀዳጀ ግብጻዊ ደራሲ ነው። ማህፉዝ ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር ዲሴምበር 11፣ 1911 እ.ኤ.አ. ተወለድ። የመጠሪያ ስሙን የወረሰው ሲወለድ አዋላጅ ሃኪም ከነበሩት ከፕሮፌሰር ናጊብ ማህፉዝ ፓሻ ነው። ማህፉዝ ለረጅም ዘመን በመንግስት መስሪያቤቶች ውስጥ ያገለገል ሲሆን በስነ-ጽሁፉም ዘርፍ 34 ወጥ ልብ-ወለዶች፣ ከ350 የሚዘሉ አጫጭር ታሪኮች፣ ከደርዘን በላይ የሲኒማ ድርሰቶች፣ እና አምስት ተውኔቶችን አበርክቷል። በ1971 ያሳተመው «ጭውውት በአባይ ወንዝ ላይ» የተሰኘው ድርሰቱ ተወዳጅነትን ካተረፉለት ስራዎቹ መካከል ሲሆን የገማል አብድል ናስር አገዛዝ በግብጽ ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን ዝቅጠት የሚተች ነው። የገብላዊ ልጆች የተሰኘው ሌላው ልብ-ወለዱ ተምሳሌታዊ በሆነ መልክ እግዚአብሄርን እና የታላላቆቹን እምነቶች መስራቾች (ሙሴን፣ እየሱስን እና መሃመድን) በገጸባህርይነት የቀረጸበት በመሆኑ አምላክን በመገዳደር አስወንጅሎት መጽሃፉም በግብጽ ውስጥ እንዳይሰራጭ ለረጅም ጊዜ ታግዶ ቆይቷል። በ1989 ሳልማን ሩሽዲ ሰይጣናዊ ጥቅሶች (Satanic Verses) የተሰኘ መጽሃፉን በማሳተሙ የኢራኑ መሪ አያቶላህ ሮላህ ኾሚኒ የግድያ ትእዛዝ ካስተላለፉበት በኋላ ግብጻዊው የስነ-መለኮት መርማሪ ኦማር አብዱል ራህማን ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-መጠይቅ ላይ «ማህፉዝ 'የገብላዊ ልጆች'ን ሲያሳትም ተገቢው ቅጣት ተሰጥቶት ቢሆን ኖሮ ሩሽዲ 'ሰይጣናዊ ጥቅሶች'ን ለማሳተም ባልደፈረ ነበር» በማለቱ ይህንኑ ቃሉን እንደ ግድያ ትእዛዝ የወሰዱ ጽንፈኞች በ1994 ዓ.ም ማህፉዝን በስለት አንገቱ ላይ በመውጋት ጉዳት አድርሰውበታል። አጥቂዎቹ አላማቸው ማህፉዝን መግደል ነበር ቢባልም እሱ ግን በህይወት ለመትረፍ ችሏል። ይኽ መጽሃፍ ከ2006 መጀመሪያ ወሮች አንስቶ እንደ አዲስ ግብጽ ውስጥ ታትሞ መሰራጨት ጀምሯል። ማህፉዝ የአንዋር ሳዳት መንግስት ደጋፊነቱ የታወቀ ሲሆን ግብጽ ከእስራኤል መንግስት ጋር በካምፕ ዴቪድ ያደረገችው የሰላም ስምምነት ደጋፊም ስለነበር ድርሰቶቹ ለብዙ ዓመታት በአረብ አገራት ታግደው ቆይተው እገዳው የተነሳላቸው የኖቤል ሽልማትን እንዳሸነፈ ከተሰማ በኋላ ነው። ማህፉዝ የኖቤልን ሽልማት ለመቀበል ለግብጽም ሆነ ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያው ሲሆን በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ የረጅም እድሜ ባለቤት በመሆን ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሰው ነው። ማህፉዝ ኦገስት 30 ቀን፣ 2006 አርፎ ቀብሩ በኦገስት 31 ቀን ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአል ረሽዳን መስጊድ ተፈጽሟል።
ናጊብ ማህፉዝ የትውል ቦታው የት ነው?
ካይሮ ውስጥ ገማልያ በተባለው ሰፈር
74
ቀጭኔ ቀጭኔ በአፍሪካ የሚኖር ባለሙሉ ጣት ሸሆኔ ጡት አጥቢ አራዊት ሲሆን በምድር ከሚገኙ እንሰሳት በርዝማኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። ወንዱ ከ 4.4 እስከ 5.5 ሜትር ርዝማኔና 1,360 ኪሎግራም ክብደት ያስመዘግባል። እስካሁን በሪኮርድ የተያዘው የ 5.87ሜና የ2000ኪ.ግ ቀጭኔ ነው። ሴቶቹ በጥቁቱ አነስ ብለው ይታያሉ። እነዚህን ፍጥረታት በአራዊት ማቆያ ቦታዎች አንገታቸውን ከታጠሩበት አጥር በላይ ወጣ አድርገው የተመለከተ ሰው በአፍሪካ ቁጥቋጦዎች ነፃ ሆነው ሲሮጡ ያላቸውን ውበትና ግርማ መገመት ያስቸግራል። የቀጭኔ እንቅስቃሴ ትልቅ ግርማ ያለውና እንደ ውኃ ሙላት የሚፈስ ነው። በገላጣው የግጦሽ መስክ ላይ በሚጋልቡበት ጊዜ ቁመናቸው ትንሽ እንቅፋት ቢነካቸው ወድቀው የሚሰባበሩ ያስመስላቸዋል። ይሁን እንጂ እስከ 1, 300 ኪሎ ግራም የሚደርስ ክብደት ያላቸው ወንድ ቀጭኔዎች ቀልጣፋና ምንም የማያደናቅፋቸው ሯጭ ከመሆናቸውም በላይ በሰዓት እስከ 60 ኪሎ ሜትር ሊሮጡ ይችላሉ። ይህች አስደናቂ ፍጡር የምትገኘው በአፍሪካ ብቻ ነው። እርጋታዋና ሰላማዊ ተፈጥሮዋ ዓይን ይስባል። የቀጭኔ ፊት በዓይነቱ ልዩ የሆነና ቆንጆ ሊባል የሚችል ሲሆን ረዥምና ጠባብ ጆሮዎች፣ ሁለት ትናንሽ ቀንዶች እንዲሁም ጠቆር ያለ ለስላሳ ጠጉር አላት። ዓይኖቿ በጣም ትላልቅና ጥቁር ሲሆኑ ረዣዥም በሆኑ ቅንድቦች ይጠበቃሉ። ቀጭኔ ያን በመሰለ ከፍታ ላይ ሆና ሩቅ ስትመለከት ፊቷ ላይ የየዋህነት ገጽታ ይታይባታል። በጥንት ዘመናት ቀጭኔ ባላት አስደሳች ቁመና እንዲሁም ጨዋ፣ ዓይነ አፋርና ሰላማዊ ባሕርይ ያላት በመሆኑ በጣም ተወዳጅና ትልቅ ግምት የሚሰጣት ነበረች። በብሔራት መካከል ሰላምና በጎ ፈቃድ መኖሩን ለማመልከት የቀጭኔ ግልገሎች ለነገሥታትና ለገዥዎች በገጸ በረከትነት ይሰጡ ነበር። ጥንታዊ በሆኑት የአፍሪካ አለቶች ላይ ቀለማቸው የደበዘዘ የቀጭኔ ሥዕሎች እስከ ዛሬ ይታያል። ከእንስሳት ሁሉ ቀጭኔን በቁመት የሚወዳደር የለም። ሙሉ ዕድሜ ላይ የደረሱ ወንድ ቀጭኔዎች ከእግራቸው ኮቴ አንስቶ እስከ ቀንዳቸው ድረስ ከ5.5 ሜትር የሚበልጥ ርዝመት አላቸው። በግብፃውያን ጥንታዊ ሥዕላዊ የአጻጻፍ ዘዴ ቀጭኔ በረዥም ቁመቷና አርቆ በመመልከት ችሎታዋ ምክንያት “መተንበይ” የሚለውን ግሥ ትወክል ነበር። ቀጭኔ በአፍሪካ መስኮች በሚሰማሩት የሜዳ አህዮች፣ ሰጎኖች፣ አጋዘኖችና ሌሎች እንስሳት መካከል ስትቆም እንደ ማማ ሆና ትታያለች። ቁመቷና አርቆ የማየት ችሎታዋ ማንኛውንም አደጋ ገና ከሩቅ ለማወቅ ያስችላታል። ስለዚህ የቀጭኔ መኖር ለሌሎች እንስሳት የመረጋጋት ስሜት እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም።
ቀጭኔዎች በሰዓት ምን ያህል ኪ.ሜ ሊሮጡ ይችላሉ?
በሰዓት እስከ 60 ኪሎ ሜትር
538
ከ1881 እስከ 1905 ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በአፍሪካ ይዞታቸውን እያሰፉ የነበሩትን የአውሮፖ ሀይሎችን ጥቃት በመከላከል ኢትዮጵያን በስርዓት አስተዳድረዋል፡፡ በዚያን ጊዜ ጣልያን ኤርትራን በከፊል ቅኝ ገዝታ የነበረችበትና በ1880ዎቹ አጋማሽ ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ቅኝ ገዝታት የነበረችበት ጊዜ ስለነበር ከሌሎች አውሮፖ አገራት በበለጠ ለኢትዮጵያ አስጊ ነበረች፡፡ በ1880 ግን እስከዛሬ ድረስ ዝነኛ በሆነው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ጣልያንን ድል በማድረግ በአፍሪካ የባእዳን ገዥ ሀይሎችን ያሸነፈች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የቅኝ ገዥዎችን ወረራና መስፋፋት በመመከትና ድልን በመቀዳጀት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በባርነት ቀንበር ተጠምደዉ ለሚማቅቁ የመላዉ ዓለም ህዝቦች ከፍተኛ ክብርና ተስፋን አጎናጥፈዋል በ1908 የዳግማዊ ሚኒሊክ ልጅ የሆኑትን እቴጌ ዘውዲቱ ስልጣን ያዙ ፡፡ የሳቸው የቅርብ የስጋ ዘመድ የነበሩት ራስ ተፈሪ መኮንንም ሞግዚት አስተዳደርና ወራሽ ሆነው ተሹመዋል፡፡ እቴጌ ዘውዲቱ በ1922 ሲሞቱ ተተኪያቸው ዐጼ ሀይለስላሴ ስልጣን ያዙ ፡፡ ነገር ግን በ1928 ዓ.ም የጣልያን ሀይሎች ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ ወረው ሲቆጣጠሩ ግዛታቸው ተቋርጦ ነበር፡፡
እቴጌ ዘውዲቱ የአባታቸውን መንበር መቼ ያዙ?
በ1908
462
ቀጭኔ ቀጭኔ በአፍሪካ የሚኖር ባለሙሉ ጣት ሸሆኔ ጡት አጥቢ አራዊት ሲሆን በምድር ከሚገኙ እንሰሳት በርዝማኔ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። ወንዱ ከ 4.4 እስከ 5.5 ሜትር ርዝማኔና 1,360 ኪሎግራም ክብደት ያስመዘግባል። እስካሁን በሪኮርድ የተያዘው የ 5.87ሜና የ2000ኪ.ግ ቀጭኔ ነው። ሴቶቹ በጥቁቱ አነስ ብለው ይታያሉ። እነዚህን ፍጥረታት በአራዊት ማቆያ ቦታዎች አንገታቸውን ከታጠሩበት አጥር በላይ ወጣ አድርገው የተመለከተ ሰው በአፍሪካ ቁጥቋጦዎች ነፃ ሆነው ሲሮጡ ያላቸውን ውበትና ግርማ መገመት ያስቸግራል። የቀጭኔ እንቅስቃሴ ትልቅ ግርማ ያለውና እንደ ውኃ ሙላት የሚፈስ ነው። በገላጣው የግጦሽ መስክ ላይ በሚጋልቡበት ጊዜ ቁመናቸው ትንሽ እንቅፋት ቢነካቸው ወድቀው የሚሰባበሩ ያስመስላቸዋል። ይሁን እንጂ እስከ 1, 300 ኪሎ ግራም የሚደርስ ክብደት ያላቸው ወንድ ቀጭኔዎች ቀልጣፋና ምንም የማያደናቅፋቸው ሯጭ ከመሆናቸውም በላይ በሰዓት እስከ 60 ኪሎ ሜትር ሊሮጡ ይችላሉ። ይህች አስደናቂ ፍጡር የምትገኘው በአፍሪካ ብቻ ነው። እርጋታዋና ሰላማዊ ተፈጥሮዋ ዓይን ይስባል። የቀጭኔ ፊት በዓይነቱ ልዩ የሆነና ቆንጆ ሊባል የሚችል ሲሆን ረዥምና ጠባብ ጆሮዎች፣ ሁለት ትናንሽ ቀንዶች እንዲሁም ጠቆር ያለ ለስላሳ ጠጉር አላት። ዓይኖቿ በጣም ትላልቅና ጥቁር ሲሆኑ ረዣዥም በሆኑ ቅንድቦች ይጠበቃሉ። ቀጭኔ ያን በመሰለ ከፍታ ላይ ሆና ሩቅ ስትመለከት ፊቷ ላይ የየዋህነት ገጽታ ይታይባታል። በጥንት ዘመናት ቀጭኔ ባላት አስደሳች ቁመና እንዲሁም ጨዋ፣ ዓይነ አፋርና ሰላማዊ ባሕርይ ያላት በመሆኑ በጣም ተወዳጅና ትልቅ ግምት የሚሰጣት ነበረች። በብሔራት መካከል ሰላምና በጎ ፈቃድ መኖሩን ለማመልከት የቀጭኔ ግልገሎች ለነገሥታትና ለገዥዎች በገጸ በረከትነት ይሰጡ ነበር። ጥንታዊ በሆኑት የአፍሪካ አለቶች ላይ ቀለማቸው የደበዘዘ የቀጭኔ ሥዕሎች እስከ ዛሬ ይታያል። ከእንስሳት ሁሉ ቀጭኔን በቁመት የሚወዳደር የለም። ሙሉ ዕድሜ ላይ የደረሱ ወንድ ቀጭኔዎች ከእግራቸው ኮቴ አንስቶ እስከ ቀንዳቸው ድረስ ከ5.5 ሜትር የሚበልጥ ርዝመት አላቸው። በግብፃውያን ጥንታዊ ሥዕላዊ የአጻጻፍ ዘዴ ቀጭኔ በረዥም ቁመቷና አርቆ በመመልከት ችሎታዋ ምክንያት “መተንበይ” የሚለውን ግሥ ትወክል ነበር። ቀጭኔ በአፍሪካ መስኮች በሚሰማሩት የሜዳ አህዮች፣ ሰጎኖች፣ አጋዘኖችና ሌሎች እንስሳት መካከል ስትቆም እንደ ማማ ሆና ትታያለች። ቁመቷና አርቆ የማየት ችሎታዋ ማንኛውንም አደጋ ገና ከሩቅ ለማወቅ ያስችላታል። ስለዚህ የቀጭኔ መኖር ለሌሎች እንስሳት የመረጋጋት ስሜት እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም።
ወንዱ ቀጭኔ ርዝማኔው ምን ያህል ይሆናል?
ከ 4.4 እስከ 5.5 ሜትር
95
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የመናገሻ አምባ ማርያምን ገዳም እያስተዳደሩ ሳሉ፤ ከዚህ ሥልጣናቸው በተጨማሪ የአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መምህርነት በየካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ/ም ተሰጣቸው። ከዚያም ቀጥሎ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፭ዓ/ም በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያን ገዳማት በመንፈሳዊ መሪነት አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ለሁለት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ወደአገራቸው ተመለሱ። የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፯ ዓ/ም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት መንበር፥ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ዘነበረ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተብለው፥ አምሣ-ዘጠነኛው ዕጨጌ ሆነውተሽሙ። በዚሁ በዕጨጌነታቸው ዘመን የፋሺስት ወረራ ኢትዮጵያን ባጠቃ ጊዜ፣ በጦርነቱ ግምባር ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተሰልፈው አብያተ ክርስቲያናትንና መጻሕፍትን የሚያቃጥል የምእመናንን ዘር የሚያጠፋ ጠላት መጥቷልና በሃይማኖት፤ በጸሎት፣ በምህላ በርታ እያሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያጽናኑ ቆዩ። በጦርነቱም ጊዜ የተቀመጡበት በቅሎ በአረር ተመቶ እስኪወድቅና የለበሱትም ካባ አምስት ላይ በጥይት እስኪበሳሳ ድረስ ከንጉሠ ነገሥቱ ሳይለዩ የቆራጥነት ሥራ ሠርተዋል። ሠራዊቱም ድል ህኖ በተፈታ ጊዜ ክንጉሠ ነገሥቱ ጋር በስደት ወደኢየሩሳሌም አቅንተው እስከ ድል ጊዜ ድረስ በስደት ቆይተዋል። በዚሁ በስደት ዘመናቸውም ሳሉ በርካታ ሐዋሪያዊ መልእክቶችን ለአርበኞችም፤ ለሕዝቡም በመላክ የማጽናናትና የሃይማኖታዊ ጣምሮችን ያስተላልፉ ነበር። ንጉሠ ነገሥቱ በስደት ከነበሩበት ከ’ባዝ’ (ብሪታንያ) ፥ ጥር ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም በጊዜው በስደት ኢየሩሳሌም ለነበሩት ወደ ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ አንድ ፅላትና ለአገልግሎት የሚበቁ አምስት መነኮሳትን ወደ እንግሊዝ አገር እንዲልኩላቸው በአባ ሐና ጅማ በላኩት ደብዳቤ መሠረት፣ ዛሬ ምስካዬ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም የተባለውን የመድኀኔ ዓለምን ጽላት ወደንጉሠ ነገሥቱ ወዳሉበት ባዝ የላኩት እሳቸው ነበሩ፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፥ ጥር ፲፪ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በኢትዮጵያ ጠረፍ በኡም-ኢድላ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ-ዓላማ ሲተክሉ ዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስም አብረዋቸው ነበሩ።
አቡነ ባስልዮስ በመጀመርያ የምን ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ነበሩ?
በኢየሩሳሌም ያሉ የኢትዮጵያን ገዳማት
168
አዳማ /ኢዜአ/መስከረም 23/2012 የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ስምንት የምርምርና የልህቀት ማእከላት እያደራጀ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሾመ አብዶ ለኢዜአ እንደገለጹት ግንባታቸው ከ90 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው የምርምር ፓርኮችንና የልህቀት ማዕከላትን በመሳሪያ ለማደራጀት 86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት ተመድቦ እየተሰራ ነው ብለዋል። በዚህም ሁለት ሊትል ስታር የተባሉ ሳተላይቶች በደቡብ ኮሪያና ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች በመገጣጠም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የፋርማቲካል የልህቀት ማእከሉ የባህል መድኋኒቶችን በመቀመምና በምርምር በማዘጋጀት ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ምርት እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ተሾመ በተለይም በባህላዊ መድኋኒቶች ዙሪያ በትኩረት የምርምር ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል። የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በ19 የትምህርት ፕሮግራሞች ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በኤክስቴሽን ፕሮግራም ተቀብሎ ማስተማር ላይ ይገኛል።
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በምን ያህል ዶላር የምርምርና ልህቀት ማእከላትን እያደራጀ ይገኛል?
በ86 ሚሊዮን
47
ክልሉ የትልልቅ ወንዞች ባለቤት ሲሆን በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ተፋሰሶች ተከፋፍሎ ሊታይ የሚችል ነው። እነርሱም የዓባይ፣ የተከዜ እና የአዋሽ ተፋሰስ ናቸው። ወደነዚህ ተፋሰሶች የሚገቡና ዓመቱን በሙሉ የማይደርቁ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ትልልቅ ወንዞች ያሉ ሲሆን በክልሉ በጥቅም ላይ ያልዋለ ሰፊ የውሐ ሀብት መኖሩን ያመለክታሉ። ከነዚህ በተጨማሪ እንደ ጣናና አርዲቦ የመሳሰሉ ሐይቆችም በክልሉ ውስጥ ይገኛሉ። በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ ባሉ ትልልቅ ወንዞችና መጋቢ ወንዞች የመስኖ ልማት ለማካሄድ የሚያስችል ከፍተኛ የውሐ ሐብት ክምችት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጅ እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው በጣም አነስተኛ ነው። በአመዛኙ አብዛኛው የክልሉ ምጣኔ ሀብት በግብርና እና ከብት እርባታ ላይ የተመሠረተ ነው። በአጠቃላይ ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጥር፣ ለእርሻና ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ የሆነ መሬት፣ የአየር ንብረት እና የውሐ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ በተለይም የሰብል እና የእንስሳት ሀብት ልማት ለማካሄድ የማይናቅ አቅም አለው። በዝናብም ሆነ የመስኖ እርሻ ልማት በማስፋፋት በክልሉ በገበያ የሚውሉ የተለያዩ የአገዳ፣ የጥራጥሬ፣ የቅባት፣የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን ማምረት ይቻላል። ጤፍ፣ ገብስ፣በቆሎ፣ ማሽላ፣ዳጉሣ፣ ስንዴ፣አተር፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ ጓያ፣ምስር፣ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ተልባ፣ ወዘተ የመሳሰሉት በክልሉ ውስጥ ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በእንስሳት ሀብት ረገድም በወተት ምርታማነታቸው የታወቁ የፎገራ ዝርያዎችና በፀጉር ምርት የታወቁት የመንዝ በግ ዝርያዎች በክልሉ ይገኛሉ። በቱሪዝም የሥራ መስክ ሊበለጽጉ ፣በሰፊው አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ እና በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈሩት የጐንደር ቤተ መንስግት ህንፃዎች፣ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቱሪዝም መስሕቦች አሉት፣ ይሁን እንጅ ክልሉ ሰፊ የሆነ የቱሪዝም እምቅ ሀብት ያለው ቢሆንም በሚፈለገው መጠን በጥቅም ላይ ውሏል ማለት አያስደፍርም። በዚህ ረገድ፤አካባቢዉ የብዙ ታሪካዊ ገዳማትና የታሪካዊ ቅርሶችም ባለሀብት ነው።
በአማራ ክልል ውስጥ ተጠቃሽ ከሆኑት ሐይቆች እነማን ይገኛሉ?
ጣናና አርዲቦ
225
አዳማ /ኢዜአ/መስከረም 23/2012 የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ስምንት የምርምርና የልህቀት ማእከላት እያደራጀ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሾመ አብዶ ለኢዜአ እንደገለጹት ግንባታቸው ከ90 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው የምርምር ፓርኮችንና የልህቀት ማዕከላትን በመሳሪያ ለማደራጀት 86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት ተመድቦ እየተሰራ ነው ብለዋል። በዚህም ሁለት ሊትል ስታር የተባሉ ሳተላይቶች በደቡብ ኮሪያና ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች በመገጣጠም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የፋርማቲካል የልህቀት ማእከሉ የባህል መድኋኒቶችን በመቀመምና በምርምር በማዘጋጀት ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ምርት እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ተሾመ በተለይም በባህላዊ መድኋኒቶች ዙሪያ በትኩረት የምርምር ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል። የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በ19 የትምህርት ፕሮግራሞች ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በኤክስቴሽን ፕሮግራም ተቀብሎ ማስተማር ላይ ይገኛል።
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ማን ይባላሉ?
ዶክተር ተሾመ አብዶ
143
ዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ።
የብሪታንያው ድርጅት ሰሜናዊ ሮዴዢያ ብሎ ይጠራው የነበረው የዛምቤዚያን አካባቢ አሁን ምን ተብሎ ይታወቃል?
ዛምቢያ
1,159
መስከረም 23/12 ዓ ም ሽሬ ኢዜአ  የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ይሁንታ ያገኘው የ35 ዓመት ወጣት ሔሊኮፕተር ሰርቶ ለሙከራ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ ። ወጣት ዕበ ለገሰ ይባላል ። በመደበኛ ትምህርት ብዙ ገፍቶ ባይሔድም በፈጣራ ብቃቱ ግን በርካታ ስራዎች ለህዝብ እንዲያደርስ አድርጎታል ። የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ ምጣድ ጥገና ሥራ የጀመረው ወጣት አሁን ላይ ትልቅ ራእይ አንግቦ የራሱ የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን በማቅረብ ውጤታማነቱን በተጠቃሚዎች ዘንድ እየተመሰከረለት መጥቷል ። የምጣድ ጥገና ስራው ለታናሽ ወንድሙ በመልቀቅ የወርቅ መአድን መፈለጊያ መሳሪያ ወደ ማሻሻል መሸጋገሩን ይገልፃል ። በራሱ ፈጠራ ያሻሻለው የወርቅ መፈለጊያ መሳሪያ በባህላዊ መንገድ ወርቅ ለሚያመርቱ ሰዎች በሽያጭ በማቅረብ የፍለጋ ሥራቸውን እንዲቃለል እንዳስቻላቸው ተጠቃሚዎቹ ይናገራሉ ። ቀደም ሲል የነበረው ‘’ጂ አር ዜድ’’ የተባለው የወርቅ መፈለጊያ መሳሪያ ከ70 እስከ 80 ሳንቲ ሜትር ጥልቀት ባለው መሬት ውስጥ የሚገኝ የደለል ወርቅ የሚጠቁም ነበር ። ወጣቱ ያሻሸለው ግን በአንድ ሜትር ጥልቀት የሚገኘውን የደለል ወርቅ በቀላሉ መለየት የሚያስችል መሳርያ ሆኖ ተገኝቷል ። እንዲሁም ከድንጋይ ጋር ተደባልቆ የሚገኝ ወርቅ በቀላሉ መለየት የሚያስችል የድንጋይ ወፍጮ በመፍጠር ለተጠቃሚዎቹ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም ወጣት  ለገሰ ይናገራል ። ባለፉት አምስት ዓመታት አምስት የድንጋይ ወፍጮዎችን በመስራት ለተጣቀሚዎቹ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርቧል ። በተጠናቀቀው ዓመት በራሱ ፈጠራ ሶስት ሰዎች የማሳፈር አቅም ያለት ሔሊኮፕተር ሰርቶ በሙከራ ደረጃ ለህዝብ እይታ አቅርቦ የነበረው ወጣቱ ዘንድሮ ለማብረር እየተዘጋጀ መሆኑንም ተናግሯል ። የፈጠራ ሥራዬ ስኬትና ሚስጥር “ይቻላል” የሚል ጽኑ እምነት ስላለኝ ነው የሚለው ወጣቱ ከኢንተርኔት የሚያገኛቸው የፈጠራ ሥራዎችም እገዛ እንዳደረጉለት ጠቁሟል። ሥራ ፈጣሪ ወጣቱ ወደ ገበያ በሚያቀርባቸው የፈጠራ ውጤቱ ጥሩ ገቢ ከማግኘቱም ባሻገር ለሌሎች 10 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግሯል። የወጣቱ የፈጠራ ወጤት ተጠቃሚ ከሆኑትና በባህላዊ መንገድ በደለል ወርቅ ምርት ፍለጋ ከተሰማሩ ማህበራት መካከል የ“ስምረት” ማህበር አንዱ ነው። የማህበሩ አባል የሆነው ወጣት በላይ ተክለሃይማኖት በሰጠው አስተያየት ” ከወጣቱ የገዛነው የደለል ወርቅ ጠቋሚ መሳርያ ሥራችንን ከማቃለል በተጨማሪ በወርቅ ፍለጋው ስኬታማ እንድንሆን አግዞናል” ብሏል። ሌላው የማህበሩ አባል ወጣት ተስፋይ በላይ በበኩሉ ” ከድንጋይ ጋር ተደባልቆ የሚገኝ ወርቅ ለመለየት እጅግ አድካሚ የነበረው ሥራ ወጣቱ ባቀረበልን አነስተኛ የድንጋይ ወፍጮ በመጠቀም የድካማችንን ዋጋ ማግኘት አስችሎናል ” በማለት አድናቆቱን ገልፆለታል ። የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ጎይቶኦም ይሰማ እንዳሉትም ደግሞ የወጣቱን የፈጠራ ክህሎት እንዲሰፋና ሄሊኮፕተሯ ለህዝብ እይታ እንድትበቃ አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረግለታል ። የሽሬ እንደስላሴ ፖሊ ቴክኒክና ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋይ ገብረሚካኤል በበኩላቸው የፈጠራ ባለቤት የሆነው ወጣት እበ ለገሰ የፈጠራ ስራዎች የሚያተኩሩት በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ በሚታዩ መሰረታዊ ችግሮች ዙሪያ በመሆናቸው ተቀባይነታቸው የጎላ ነው ብለዋል ። ወጣቱ የሚያሳየው ትጋት የተሞላበት የፈጠራ ስራ ለሌሎች ወጣቶችም አርአያ በመሆን መነቃቃት መፍጠሩን የኮሌጁ ዲን መስክረውለታል ።
ወጣት እበ ለገሰ ከድንጋይ ጋር የተቀላለን ወርቅ ለመለየት ምን ዓይነት ነገር ፈጠረ?
የድንጋይ ወፍጮ
757
ቅዱስ ላሊበላ ቅዱስ ላሊበላ በ 1101 አ.ም ትህሳስ 29 ቀን ከ እናቱ ከኬርዮርና ከአባቱ ዛንስዮም ላሰታ ቡግና ወረዳ ሮሃ ከተባለች ቦታ ከፍልፍል ቤተ መቅደስ ውስጥ ተወለደ በዚህ ፍልፍል ቤተ-መቅደስ ውስጥ እድገቱን አደረገ ስድስት አመት ሲሞላው ቤተ-መንግስት አባ ዳንእል የተባሉ መምህር ተቀጥረውለት ከ ፊደል እስከ ዳዊት አጠናቆ ከዚያም የተማረውን የዕሁፍ ጥበብ በቤተ ጎሎጎታ ደብረ ሲና በሚገኘው ከ ኪዳነ ምህረት መንበር ታቦት ዙሪያ ላይ እራሱ የተዓፋቸው የሚዐለይበት ዕሁፎቸች ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ላሊበላ 12 አመት ሲሞላው አባቱ ዘንሳዮም 40 አመት ነግሶ በተወለደ በ 76 አመቱ ከዚህ አለም በ ሞት ተለየ ወድያው ብዙም ሳይቖይ እናቱ ኬርዮርና በሞት ተለየች፡፡ ቅዱስ ላሊበላ በ እናቱ ና አባቱ ህልፈተ ህይወተ በደረሰበት ሀዘን የተነሳ ሁሉን ነገር ለመርሳት ና የትምህርት ፍላጎት ለሞሞላት ጉዞውን ወደ ጎጃም በማድረገ አለም ስላሴ ከተባለው ደብር ከመምህር ኬፋ ሃዲሳቱን አጠናቖ በመመረቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ በወቅቱም በኤትዮጵያ ላይ ነግሶ የነበረው ታላቅ ወንድሙ ቅዱሰ ገብረ ማሪያም ነበር ይህ እንዲህ እያለ በእህቱ ላይ እሱ ሊነግስ መሆኑ ቅናት አሳደረባት ቅዱስ ላሊበላ ሁሌም እሚጠጣው ባህላዊ መድሃኒት ውስጥ መርዝ በመጨመር ታስቀምጥለታለች አትሙት ያላት ነፍስ ግን የሃገሬውን በሃል ምክንያት አድርጎ ሳይቀመስ አይሰጥምና አብሮት የነበረው ዲያቖን የተቀመጠውን መድሃኒት ቀምሶ ወደ ነበረበት ጠረቤዛ ላይ አንዳሰቀመጠው ወድያውኑ ህይወቱ ታልፋለች ቅዱስ ላሊበላ ይህን ባየ ጊዚ እኔን ለማጥፋት የመጣው መድሃኒት የሌላውን ነፍስ አጠፋች በማለት የቀረውን መድሃኒት በመጠጣት ለሶሰት ለሊት እንደ ወደቀ ቀረ ከዚያም ነዋሪው ገንዞ ለመቅበር ሲዘጋጁ የሰውነቱ ሙቀት አልተለየውም ነበር ይሄን ጊዜ ወድያው ቅዱስ ላሊበላ ነቃ የተመለከቱት ሰዎች ተደናገጡ ከዚያም ይህ ሁሉ ነገር በእህቱ መደረጉ ያሳዘነው ቅዱስ ላሊበላ በመነሳት ጉዞውን ወደ ጫካ አደረገ ኑሮውንም ለረጅም አመት እዚያው አደረገ ይህ እንዲ እንዳለ ሚስት እምትሆነውን ሴት አገኝ ቤተሰቧን በማስጠየቅ በቤተክርስትያን ስርአት ተጋብተው ጥቂት አመት እንደቆዩ ጉዞውን እየሩሳሌም አደረገ ለተከታታይ 13 አመታትም ቆይታ በኋላ ወደ ባለቤቱ ተመልሶ ከወንድሙ ከ ቅዱስ ገብረ ማሪያም ጋር እርቅ በማውረድ ቅዱስ ገብረ ማሪያም ንግስናውን ለቅዱስ ላሊበላ በተወለደ በ57 አመቱ በማስረከብ ኑሮውን በገዳም አደረገ፡፡
ቅዱስ ላሊበላ መቼ ተወለደ?
በ 1101 አ.ም ትህሳስ 29 ቀን
18
ነሐሴ ፲፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፩ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፭ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፬ ቀናት ይቀራሉ። ፲፰፻፶ ዓ/ም - በብሪታኒያ ንጉዛት እና በአሜሪካ ኅብረት መኻል በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የተዘረጋውን አዲሱን የቴሌግራፍ መስመር በመመረቅ ንግሥት ቪክቶሪያ እና የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጄምስ ቡካነን የሰላምታ መልእክት ተለዋወጡ። ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአገሪቱን የመጀመሪያ አየር-ዠበብ (አውሮፕላን) በዚህ ዕለት ተረከበ። ሁለተኛው አየር-ዠበብ ከጂቡቲ ወደብ እስከ ድሬዳዋ በባቡር ተጭኖ፤ ከድሬ ዳዋ ደግሞ እስከ አዲስ አበባ አሥራ ስምንት የአውሮፓ የፖስታ ቦርሳዎችን ጭኖ እየበረረ ነሐሴ ፴ ቀን ገባ። ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ዋና መላክተኛ አምባሳደር ዳግላስ ራይት በኢትዮጵያ እና በኬንያ መኻል ያለውን ድንበር ለመስማማት የተዘጋጀውን የውል ረቂቅ ለኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ አስረከበ። ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከ ፲፰፻፸፯ ዓ/ም ጀምሮ በፈረንሳይ ሥር በቅኝ ግዛትነት ትተዳደር የነበረችው ጋቦን በዚህ ዕለት ነፃ ወጣች። ሊዮን ምባ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ሽግግር የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የክብር ዘበኛ ሠራዊት አዛዥ የነበሩት ማዮር ጄነራል ታፈሰ ለማ በደርግ ተይዘው ታሠሩ። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነብሩት አቡነ ቴዎፍሎስ አዲስ በተዘጋጀው ረቂቅ ሕገ-መንግሥት ውስጥ በተካተቱ አንዳንድ አንቀጾች ላይ ቅዋሜ እንዳላቸው አስታወቁ። ፳፻፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ከገዛቸው አሥር ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አየር-ዠበቦች የመጀመሪያውና በሰሌዳ ቁጥር ET-AOQ የተመዘገበው አየር-ዠበብ በዚህ ዕለት ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስቶ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ልጅ ልዕልት ፀሐይ በተወለዱ በ፳፫ ዓመታቸው በዚህ ዕለት አረፉ።
በፈረንሳይ ሥር በቅኝ ግዛትነት ትተዳደር የነበረችው ጋቦን ነፃ የወጣችው መቼ ነው?
፲፱፻፶፪ ዓ/ም
688
አፄ ዘርአ ያዕቆብ አጼ ዘርአ ያዕቆብ በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስት ክብረ እግዚእ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮውፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ(ከቀኝ ያለውን ካርታ ይመልከቱ) ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው። የዘርዓ ያዕቆብ አባት ቀዳማዊ ዳዊት ባረፉ ጊዜ፣ እንደ ጥንቱ የኢትዮጵያ ባህል ወግ መሰረት፣ ታላቅ ወንድማቸው የነበሩት ቀዳማዊ ቴወድሮስ በ1414 ሲነግሱ ታናሽ ወንድማቸውን በግዞት ወደ አምባ ግሽን እንዲሄድ አደረጉ። አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሀፈ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው መሰረት እስከ ነገሱበት ሰኔ 20 ፣ 1434 ዓ.ም. ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ (አምባ ግሸን) ላይ ለሚቀጥሉት 20 አመታት በእስር ኖሩ። ሆኖም ግን በግዞት እያሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊያቸው መጠን እየበዛ ሄደ። በነዚህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዓመት ወደ ዓመት እይተበላሸ ሂዶ በመጨረሻ ከአምባው ላይ ለሹመት ሲወርዱ አገሪቱ በእርስበርስ ሽኩቻ እየታመሰች፣ በሃይማኖት በኩልም መከፋፈል ተፈጥሮ የውጭ ሀይሎችም ከነገ ዛሬ አጠቁን እየተባለ ይሚፈራበት ሁኔታ ገጠመው። የወደፊቱ ንጉስ ብዙ እድሜውን ያሳለፈው ከሰው ተለይቶ አምባ ላይ ስለነበር፣ የዲፕሎማሲ ጥቅሙ አልተረዳውም ነበር። ይልቁኑ ፊት ለፊት የተጋረጡትን የሃገሪቱን ችግሮች በሚያስፈራ ድፍረት እና ምንም በማያወላዳ ጽናት ተጋፈጠው። ዓፄ ዘርአ ያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ንግስት እሌኒን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ። በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤተክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን ቆይቱ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳተ በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል ። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቀ እስጢፋ ወገኖች እምነት ነው። እነዚህ እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴ ባስተማራቸው መሰረት ለመስቀል መስገድና ለስእል አድኅኖ ለድንግል ማርያም መስገድ አይገባም የሚሉ ነበሩ።ተከራክረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ አሸንፈዋል። በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀው ግዛታቸውን ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር። በ1456 ዓ.ም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ በነበሩበት ቦታ ታላቅ ብርሃን ስለታየ የነበሩበትን ቦታ ደብረ ብርሃን በማለት የሃገሪቱ ዋና ከተማ አድርገው ቆርቁረዋል። እስከ እለት ህልፈታቸውም ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበረች።ኢትዮጵያዊ መንፈሳዊ ፈላስፋ። አጼ ዘርአ ያዕቆብ በጦር ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን የሚታወቁት፣ ከ 20 በላይ መጻህፍትንም በመድረስና ለትውልድ በማቅረብ ጭምርም ነው።
የአጼ ዘርአ ያዕቆብ የዘውድ ስማቸው ማን ይባላል?
ቆስጠንጥንዮስ
34
ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በአዲስ አበባ ከተማ በደቡብ-ምሥራቅ አቅጣጫ ከአራዳ በስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የአገሪቱ ዋና አድማሳዊ የንግድና የግንኙነት በር ነው። አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጀመሩት በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ በጃን ሜዳ እና አቃቂ ያርፉ እንደነበር በታሪክ ተዘግቧል። የመጀመሪያው ቋሚ የአውሮፕላን ጣቢያ ግን የተሠራው በአምሥቱ የፋሺስት ዘመናት ሲሆን የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ/ም አክሱም አካባቢ ላይ ከነጥያራው ተከስክሶ በሞተው አብራሪያቸው፣ “ኢቮ ኦሊቬቲ” ስም ሠይመውት የነበረው የልደታ የጥያራ ጣቢያ ነው። በዚሁ በፋሺስት ወረራ ዘመን ‘አላ ሊቶሪያ’ የተሰኘው ኩባንያ በአገር ውስጥ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ነገሌን፤ ሞቃዲሾን፤ ድሬ ዳዋን፤ ጎራኄን፤ ጂቡቲን፤ አሰብን፤ ጂማን፣ ጋምቤላን ደምቢ ዶሎን፤ ጎንደርን አስመራን፤ ደሴን፤ ለቀምትን እና አሶሳን የሚያገለግሉ የበረራ መሥመሮች ሲኖረው ከአድማስ ባሻገር ደግሞ ከተማዋን በካርቱም፣ ዋዲ ሃይፋ፤ ካይሮ፣ ቤንጋዚ እና ሲራኩሳ አድርጎ ከሮማ ጋር የሚያገናኝ የበረራ መሥመርም ነበረው። ከድል ወዲህ ልደታ አውሮፕላን ጣቢያ፤ የብሪታኒያ ጦር ኃይሎች ሲገለገሉበት ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ሲመሠረት ዋና ጣቢያው እዚያው ነበር። ዳሩ ግን የአየር መንገዱ አገልግሎት እየተስፋፋ ሲመጣና ትላልቅ ጄት አውሮፕላኖች እንደሚያስፈልጉት ግልጽ ሲሆን፣ የልደታ አየር ጣቢያ ብቃት እንደሌለው እና ለጄት አየር ዠበቦችም ማሳረፊያ የማይስማማ መሆኑ ታምኖበት የአማራጭ ሥፍራ ፍለጋ ተጀመረ። የአዲሱንም አየር ጣቢያ ዝርዝር ጥናት እንዲያዘጋጅ ውሉ ለአሜሪካዊው ‘አማን እና ዊትኒ’ ኩባንያ ተሰጥቶ፤ ጥናቱ በ፲፱፻፶ ዓ/ም ተገባዶ አማራጩ ሥፍራ ቦሌ እንዲሆን ተወሰነ። የአየር ጣቢያውን የግንባታ ወጪ ከአሜሪካዊው ‘ኤክስፖርት-ኢምፖርት’ ባንክ በተገኘ ብድር ተሸፍኖ ሥራው ተጀመረ። ጠቅላላ ግንባታው ተጠናቆ ሲያልቅ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ/ም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተብሎ፣ በንጉሠ ነገሥቱ ተመርቆ ተከፈተ።
የመጀመሪያው ቋሚ የአውሮፕላን ጣቢያ የተሠራው ስያሜ ምን ነበር?
ኢቮ ኦሊቬቲ
352
ደቡብ አፍሪካ በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ። ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውን፣ ብሉምፎንቴንና ፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው። ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው። የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ። የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካ የንዴቤሌም ቋንቋ በተናጋሪ ብዛት ስንተኛው ነው?
11ኛው
237
ገብረሃና ገብረማሪያም አለቃ ገብረሃና ገብረማሪያም (፲፯፻፺፯ - ፲፰፻፺፬ ዓ.ም.) ዕውቅ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። አባታቸው መምህር ገብረ ማርያም ምጥኑ ሲባሉ እናታቸው ወይዘሮ ሳህሊቱ ተክሌ ይባሉ ነበር። ገብረሃና ገብረማሪያም በቤገምድር ጠቅላይ ግዛት በደብረታቦር አውራጃ በፎገራ ወረዳ ልዩ ስሟ ናበጋ ጊዮርጊስ በምትባል ቦታ በ፲፯፻፺፯ ዓ.ም. ተወለዱ። ገብረሃና እቴጌ መነንን መዝሙርን፣ ውዳሴ ማርያምንና ሌሎችንም አስተምረው ከጨረሱ በኋላ ለከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በእቴጌይቱ ትዕዛዝ ወደ ጎንደር ተላኩ። ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላም በእቴጌይቱ ትዕዛዝ የአለቃነት ማዕረግ ተሰጣቸው። ከዚያም ገብረሃና በጎንደር አካባቢ የሚገኙትን ቤተ ክርስቲያናት ብቃት በተሞላበት ሁኔታ ያስተዳድሩ ጀመር። እንደ ትልቅ ምሁር ይታዩ ጀመር። በተለይ ፍትሐ ነገስትን በመተርጎም የሚወዳደራቸው ወይም የሚስተካከላቸው አልነበረም። አለቃ ገብረሃና አቶ ሙንሮዝ በተባለ አውሮጳዊ በ1890 ዓ.ም. ፎት እንደተነሱ ሞላቨር ይገልጻል። ዓፄ ቴዎድሮስ ስልጣን ከያዙና እራሳቸውንም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ብለው ዙፋናቸውን በጫኑበት ጊዜ በሀገሪቱ ከፍትሐ ነገስት ሌላ የተፃፈ ሕግ ባለመኖሩ አለቃ ገብረሃና በተለይ ፍትሐ ነገስትን መሠረት በማድረግ ንጉሡ ሀገርን እንዲያስተዳድሩ ይረዱዋቸው ነበር። በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ቤተክርስቲያን ብሉይ ኪዳንንና አዲስ ኪዳንን በመተርጎም ትልቅ አገልግሉት ቢያደርጉም ትልቁን አስተዋጽዖ ያደረጉት በሕግና በቤተ ክርስቲያን ዜማና አቋቋም ነበር። እንደዚሁም የፈጠሩት አዲስ ዓይነት የቤተክርስቲያን አቋቋም ከደብረታቦር ወደ ሸዋ እና ትግራይ ተሰራጭቷል። ይህንንም አቋቋም ከብቸኛው ልጃቸው በኋላ ተክለ ብለው ሰየሙት። ይህም አቋቋም አስደሳችና ማራኪ የአቋቋም ዘዴ ነው።
ገብረሃና ገብረማሪያም የአለቅነት ማዕረጋቸውን እንዴት አገኙ?
ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላም በእቴጌይቱ ትዕዛዝ የአለቃነት ማዕረግ ተሰጣቸው።
328
አማራ (ክልል) አማራ (ክልል 3) ከዘጠኙ የኢትዮጵያ ክልሎች አንዱ ሲሆን ከ 1994 በፊት አራት የሀገሪቱን ዋና ወና ክፍለ ሀገራት የ ካትት ነበር እነሱም በጌምድር ጐጃም ወሎና ሸዋ ነበሩ ።የአማራ ብሔራዊ ክልል ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ በ8° 45 እስከ 13° 45 ሰሜን የኬንትሮስ እና በ35° 46 እስከ 40° 25 ምስራቅ የኬንትሮስ መስመር ውስጥ ይገኛል። በምስራቅ የአፋርና የኦሮሚያ ክልሎች፣ በምዕራብ ሱዳን እና ቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል፣ በሰሜን የትግራይ ክልልና በደቡብ የኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል። የቆዳ ስፋቱ ፻፶፯ሺ፸፮ ካሬ ሜትር ሲሆን ከአገሪቱ አሥራ አምስት በመቶ ድርሻ ይይዛል። የክልሉ ሕዝብ ብዛት ደግሞ በ፳፻፪ ዓ/ም 20,875,456 እንደነበር የተገመተ ሲሆን ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ 33.9% አካባቢ ድርሻ ይይዛል ተብሎ ይገመታል። ክልሉ በ፲ ዞኖችና በ፻፷፮ የገጠርና የከተማ ወረዳ አስተዳደሮች የተከፋፈለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ፴፰ የሚሆኑት የከተማ አስተዳደሮች ናቸው። የአማራ፣ የአገው፣ የኦሮሞና የሌሎች ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት ክልል ነው። እንዲሁም የአማራ ክልል አሁን ላይ የክልል ከተማው ባህር ዳር ነው። በክልሉ አልፎ አልፎ ከሚታዩ የመንግሥትና የማኅበራት ደኖች፣ በደሴቶች፣ በአብያተ ክርስቲያናት፣ በወንዞች ዳርቻና ሰው ሊደርስባቸው በማይችሉ ገደላማና ተራራማ ስፍራዎች ከሚገኙ ጥቂት ደኖች በስተቀር ሊጠቀስ የሚችል ከፍተኛ የደን ሀብት ጋር በቅርብ የተያያዘ ነው። በዚህ ረገድ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ እንደ ቀይ ቀበሮ፣ ዋልያ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እንዲሁም በምዕራባዊው የክልሉ አካባቢ ዝሆን አንበሳና ነብር፣ ሰጐንና የተለያዩ አዕዋፋት በስተቀር ከፍተኛ የዱር እንስሳት ክምችት ካለመኖሩም በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ጥቂት የደን ቅሪቶችና ዋሻዎች የነበሩት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አራዊቶችም ለዘመናት በደረሰው የደን መጨፍጨፍና መራቆት ምክንያት ከክልሉ ወደ ሌላ አካባቢ እንደተሰደዱ ይታወቃል። ክልሉን የማዕድን ሀብት አስመልክቶ በሚገባ የተጠናከረ ጥናት ባይኖርም ከክልሉ ስነ-ምድራዊ ሁኔታዎችና ከተካሄዱ አንዳንድ ጠቋሚ ጥናቶች መረዳት እንደሚቻለው በክልሉ ውስጥ የተለያዩ ማዕድናት እንደአሉ ይገመታል። በዚህም መሠረት በሰሜን ሸዋ የኦፓል ማዕድን፣ በሰሜን ጐንደር፣ በጭልጋና በደቡብ ወሎ በአምባሰል ወረዳ የድንጋይ ከሰል ክምችት እንዳሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ለግንባታ ሥራ የሚውል በቂ የድንጋይ፣ የኖራ ድንጋይ፣የሸክላ አፈር፣ ጅኘሲየም፣ የጌጣጌጥ ማዕድናት እንዲሁም በዓባይ ሸለቆ የዕብነ በረድ ሐብቶች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይሁን እንጅ በውል የሚታወቀው ሐብትም ቢሆን በበቂ ሁኔታ አልለማም።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምን ማዕድን ይገኛል?
የኦፓል ማዕድን
1,246
የቻይና ስነ ፈለክ ተመራማሪዎች የመጀመሪዋን ከፀሀይ ስርዓት ውጪ የሆች ኤክሶፕላኔት ማግኘታቸው ተገለፀ። በቻይና የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች የተገኘችው ይህች ፕላኔት  “ወንግሹ” እና “ዢሂ” የሚል ስያሜ ተሰቷታል። ይህም ማለት የጨረቃ አምላክ ወይም የጸሃይ አምላክ የሚል ትርጉም አለው። ሁለቱ ስሞች የሚያሳዩት የኮኮብ እና ፕላኔትን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ዩንቨርስን የማሳስ ሂደት የሚወክል ወይም ምሳሌ የሚሆን ነው ተብሏል። የፕላኔትዋ መጠን ከፀሐይ ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፥ ከጁፒተርም በ2 ነጥብ 7 እጥፍ ትበልጣለች፤ በዚህም ከጸሃይ ስርዓት ውስጥ ትልቋ ነው የተባለችው በብሔራዊ የሥነ ፈለክ ምርምር ተቋም። የቻይና የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በአውሮፓውያኑ በ2008 ከቻይና 10 ምርጥ የሥነ ፈለክ እድገቶች መካከል አንዱ ሆነው የተመረጡት ትልቁን ኤክስፕላኔት HD173416b’ን አገኝታለች። ምንጭ፡-ሲጂቲኤን በፌቨን ቢሻው
የቻይና የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኟት ፕላኔት ስሟ ማነው?
“ወንግሹ” እና “ዢሂ”
105
ለሴት ልጆች ትምህርትን አጥብቃ በመስራቷ እ.ኤ.አ. በ 2003 በደቡብ አፍሪካ የተቀበለችውን የአማኒታሪ ሽልማትን (አፍሪካዊ አጋርነት ለወሲባዊ እና ስነተዋልዶ ጤና እና የሴቶች መብቶች ) ጨምሮ ለፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴ ባገለገለችበት ወቅት በርካታ ብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አግኝታለች ። ፡፡ ወ / ሮ የትነበርሽ ከአካዳሚክ ህይወቷ ባሻገር በበጎፈቃደኝነት ከ 20 በላይ ድርጅቶች ውስጥ ያገለገለች ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን የሴቶች ክንፍ ማህበር ለ 4 ዓመታት (እ.ኤ.አ. ከ 2003 እስከ 2007) መርታለች ፡፡ ከዚያም በመቀጠል የአካል ጉዳተኞች ኢኮኖሚያዊ መብትን ጨምሮ በተለያዩ የልማት መርሃ ግብሮች ውስጥ እንዲካተቱ ለማበረታታት የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞችና የልማት ማዕከል (ኢ.ሲ.ዲ.ዲ.) የተባለ አገር በቀል ድርጅት ለማቋቋም ወሰነች ፡፡ከ2016 ጀምሮ ደግሞ  ቀደም ሲል በዓለምአቀፍ አምባሳደሮች  ቦርድ አባልነት ወክላው  ከነበረው የአካል ጉዳተኞች እና ልማት ብርሃን ለኣለም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት  ጋር በመተባበር ላይ ትሰራለች ፡ የትነበርሽ ንጉሴ የአካል ጉዳተኞችን መብትና ማካተት በማስተዋወቋ እና ሙሉ አቅማቸውን እንዲገነዘቡ የሚያስችላቸው አነቃቂ ሥራ  በመስራት በማህበረሰቡ ውስጥ የአስተሳሰብ ለውጥ በመፍጠሯ  እ.ኤ.አ. በመስከረም ወር 2017 ላይ የተባበሩት መንግስታት ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ ፣ “አማራጭ የኖቤል ሽልማት” ፡ እና የአሜሪካ የአካባቢ ጠበቃ ጋር በመጋራት ተሸላሚ ሆናለች። ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድን በማሸነፏ እና በሄለን ኬለር ሽልማት መንፈስ የተበረታታችው የትነበርሽ ንጉሴ በህይወታቸው እና በስራ መስካቸው  ታላቅ ውጤት ያስመዘገቡ የአካል ጉዳተኛ ሴቶችን ለማክበር ከብርሃን ለኣለም ጋር በመሆን ‹የእርሷ ችሎታዎች ሽልማትን› ኣስጀምራለች፡፡
የትነበርሽ ንጉሴ በ2017 ምን ተሸለመች?
ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ
779
በ17ኛው ክፍለ ዘመን ፖርቱጋል ክርስትናን ለመታደግ ሚሲዮናውያንንና ወታደሮችን ወደ ኢትዮጵያ በላከችበት ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ ፓድሬ ፔሬዝ የተባለ ሚሲዮናዊ፣ ጢስ እሳትንና የላይኛውን አባይን ለማየቱ ምስክርነቱን ሰጠ። በ18ኛው ክፍለ ዘመን ጄምስ ብሩስ የተባለ የስኮትላንድ ተወላጅ ከካይሮ እስከ ጣና ተጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ የአባይ መነሾ ጣና ሐይቅ ነው በማለት አወጀ።እስከዚያ ጊዜ ድረስ ማንም የውጭ ዜጋ አባይ (Abay) ከጣና እንደሚነሳ አያውቅም ነበር። samuel bakerሳሙኤል ቤከር(1821-1893) ሪቻርድ በርተን(1821-1890)ጆን ሀኒንግ ስፔክ (1827-1864) የአባይን መነሻ ፈልገው ወደ ታንጋኒካ ሐይቅ አመሩ እንጂ አንዳቸውም ወደ ኢትዮጵያ አልመጡም። በ1937 ቡክሀርት ባልደክኼር፣የተባለ የጀርመን ተወላጅ፣ የአባይን ምንጭ ከኢትዮጵያ ተራሮች ስር ማግኘቱን ለአለም አበሰረ።ታሪካችን በነ ባልድክኬርና በብሩስ ሲፃፍ ስታሮቹ እነሱ ናቸው።የታሪካችን ሞተር የሚንቀሳቀሰው በነሱ ነው። ቢሆንም በ1937 ጀርመናዊው ቡርክኸርት ወደ ኢትዮጵያ ሳይመጣ ኢትዮጵያዊው አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “መፅሐፈ ሰዋሰው ወግስ፡ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚለው በ1929 ባሳተሙት መፅሐፍ በገፅ 313 313“ ከአፍሪቃ ወንዞች ተለይተው፣ ነጭ ኒል፣ ጥቁር ኒል የሚመስሉ፤ በኦሪትም ግዮንና ኤፌሶን የሚባሉ ነጭ አባይና ጥቁር አባይ ናቸው ይባላል። እሊህም ኹለቱ ወንድማማቾች ወንዞች ከየምንጮቻቸው በኅይል ተነስተው፣ ግርማቸውን ለብሰው፣ተሰልፈው፣በየፊታቸው ያለውን ሐይቅ እንደመርከብ ሠንጥቀው አልፈው ሠራዊታቸውን ከፊትና ከኋላ አስከትለው እንደ ኹለት ንጉሥ ካርቱም ላይ ሲገናኙ ሁለትነታቸው ይቀርና፣ አንድ ወንዝ ብቻ ይሆናሉ፤ ከካርቱም ደግሞ እስካትባራ ወርደው ከተከዜ ጋር ይገጥማሉ።ከዚያ በኋላ ግን የሌላ ወንዝ ውኃ ሳይጨምሩ ባንድነት መላ ምድረ ግብፅን ከላይ እስከታች አጠጥተው አጥግበው አርክተው፣ አልፈው ተርፈው ወደ ሰሜን ጎርፈው ሜዲተራኒ ከሚባለው ከታላቁ ባሕር ይገባሉ።” በማለት መፃፋቸውን ሳንጠቅስ አናልፍም። በ1995 ዓ.ም ግሼ ሜዳ ላይ ከብቶች የሚጠብቅ 11 ዓመት ያልሞላው የውልሰው የተባለ እረኛ አገኘሁና “የአባይ ምንጭ የት ነው ብዬ ስጠይቀው” መሬት ቸክሎ የተደገፈውን በትር ከመሬቱ ላይ ነቅሎ ወደ ግልገል አባይ እያሳየኝ ከዚህ ነዋ አለኝ። አባባሉ ስንት ፈረንጆች የአባይን ምንጭ አገኘን ብለው የቦረቁበት ግኝት አይመስልም። “ እንዴት አወቅክ?” ስለው “ከብቶቼን የማጠጣ ከዚሁም አይደል? የከተማ ሰው አላዋቂ ነውሳ!” ብሎ ሸረደደኝ። በሆዴ ፈረንጆቹ የአባይን ምንጭ ከአንተ በፊት አገኘን እንደሚሉ ባወቅክ ስል፣ ውስጤን ያነበበ ይመስል፣ “ለፈረንጅ ሁሉ የአባይን ምንጭ እጃቸውን ጎትተን የምናሳይ እኛም አይዶለን እንዴ?” ብሎ አስደመመኝ። ግልገል አባይ ጣና ገብቶ መውጣቱን ያጠኑት ፈረንጆች ካልነገሩት ይህ እረኛ በምን ያውቃል ብዬ በጥያቄ ላፋጥጠው፤ ግልገል አባይ ጣና ገብቶ አባይን ሆኖ መውጣቱን ማን ነገረህ? ስለው “ጣና” “ጣና ነገረኝ” ሲለኝ ያው የተለመደውን የጎጃምን ዘፈን “ነገረኝ ጣና ነገረኝ፡አባይ” የሚለውን ዘፈን ሊዘፍን መስሎኝ ነበር። ያ የጎጃም እረኛ “ ማስረጃህ ምንድነው?” ስለው በክረምት አባይ ሲደፈርስ ግልገል አባይ የደፈረሰ ውኃ ይዞ ጣና ይገባና ከጣና ተንሳፎ ሲወጣ ጥርት አርጎ ይታያል።” ብሎ እረኛው ጂኦሎጂስት አስገረመኝ።
በ18ኛው ክፍለ ዘመን ከካይሮ እስከ ጣና ተጉዞ የአባይ ወንዝ መነሻ ጣና ሐይቅ ነው ያለው ጄምስ ብሩስ የምን ሀገር ዜጋ ነው?
የስኮትላንድ
165
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ተፈሪ መኰንን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺ እመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ፲፰፻፺፱ የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. የሐረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ። የሐረርጌ አገረ ገዥ ሲሆኑ ፣ በጣም ብዙ ሺህ ተከታዮች ነበሩዋቸውና ልጅ እያሱን ከእንደራሴነት በኅይል እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ተፈሪን ከሐረር አገረ ገዥነት እንዳይሽሯቸው የሚል ስምምነት ተዋዋሉ። ዳሩ ግን እያሱ ሃይማኖታቸውን ከክርስትና ወደ እስልምና እንደቀየሩ የሚል ማስረጃ ቀረበና ብዙ መኳንንትና ቀሳውስት ስለዚህ ኢያሱን አልወደዱዋቸውም ነበር። ከዚህም በላይ እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት ስምምነታቸው እንግዲህ ተሠርዞ ተፈሪ ደግሞ ለወገናቸው ከስምምነቱ ተለቅቀው በዚያን ጊዜ እሳቸው እያሱን ከእንደራሴነት አስወጡ። እንግዲህ በ፲፱፻፱ ዓ.ም. መኳንንቱ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ሆነው አድርገዋቸው ተፈሪ ደግሞ እንደራሴ ሆኑ። ከዚህ ወቅት ጀምሮ ተፈሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙሉ ሥልጣን ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. የንጉሥነት ማዕረግ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ አርፈው ንጉሠ ነገሥት ሆኑና ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ብዙ የውጭ ልዑካን በተገኙበት ታላቅ ሥነ-ሥርዓት ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው እሳቸውና ሚስታቸው እቴጌ መነን ዘውድ ጫኑ። በንግሥ በዓሉ ዋዜማ ጥቅምት ፳፪ ቀን የትልቁ ንጉሠ-ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለዘውድ በዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት ፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ። ለንግሥ ስርዐቱ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገር ልኡካን ከየአገራቸው ጋዜጠኞች ጋር ከጥቅምት ፰ ቀን ጀምሮ በየተራ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ስለነበር ሥርዓቱ በዓለም ዜና ማሰራጫ በየአገሩ ታይቶ ነበር። በተለይም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት በጃማይካ አንዳንድ ድሀ ጥቁር ሕዝቦች ስለ ማዕረጋቸው ተረድተው የተመለሰ መሢህ ነው ብለው ይሰብኩ ጀመር። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ፊተኛው ስማቸው «ራስ ተፈሪ» ትዝታ ራሳቸውን «ራስታፋራይ» (ራሰተፈሪያውያን) ብለዋል።
የአጼ ኃይለሥላሴ ወላጅ እናት ማን ይባላሉ?
ወይዘሮ የሺ እመቤት
164
በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ። ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ። በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች። አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው። ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።
አብዱ ዲዮፍ ከመቼ እስከ መቼ የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ነበሩ?
ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ.
863
የማይዳሰሱ (ኢንታንጀብል) ባህላዊ ቅርሶችን የሚመለከተው የዩኔስኮ አካል በይነ መንግሥታዊው ኮሚቴ 10ኛ ስብሰባውን ከኅዳር 20 እስከ ኅዳር 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በናሚቢያ መዲና ዊንድሆክ በተደረገው 10ኛ የዩኔስኮ ጉባዔ ለውሳኔ ከቀረቡት 35 (ሠላሳ  አምስት) ባሕላዊ ቅርሶች መካከል የሲዳማ ብሔር የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ የሆነው ፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ የ2003 የኢንታጀብል ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ዓለም አቀፍ ስምምነት መስፈርቶችን አሟልቶ በመገኘቱ አባል አገሮች ውይይት ካደረጉበት በኋላ ፍቼ ጫምባላላ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ከመስቀል በዓል ቀጥሎ የኢትዮጵያ ሁለተኛው የማይዳሰስ ዓለም አቀፍ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ ሕዳር 22 ቀን 2008 ዓ.ም በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር 9፡40 በፋይል ቁጥር (01054) በውሳኔ ቁጥር 10.com.10.b.16 ተመዝግቧል፡፡ በ2004 በጀት ዓመት የመስቀል በዓል አከባበርን በዩኔስኮ ማስመዝገብ የሚያስችል የጥናት ሰነድ ተዘጋጅቶ ለዩኔስኮ የተላከ ሲሆን በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ከህዳር 23-28 ቀን 2006 ዓ.ም በተካሄደው 8ኛው የዩኔስኮ የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ የኢንተርገቨርንመንታል ኮሚቴ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔ መሰረት የመስቀል በዓል አከባበር በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡ በ2006 የበጀት ዓመት የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው ፊቼ ጫምበላላን በሰው ልጆች ወካይ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ የሚያስችል የጥናት ሰነድ (ኖሚኔሽን ፋይል) ተዘጋጅቶ ለዩኔስኮ የተላከውና ህዳር 22 ቀን 2008 ዓ.ም የተመዘገበው የተደረገው  ፊቼ ጫምበላላ ሰነዶች በሚከተለው የዩኔስኮ ድረ ገጽ ላይ ለመላው ዓለም ተለቀው ይገኛል፡፡ በተመሳሳይም በ2007 የበጀት ዓመት ኦሮሞ ህዝብ የማንነት መገለጫ የሆነው የገዳ ስርዓትን በሰው ልጆች ወካይ ኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ለማካተት የሚያስችል የኖሚኔሽን ሰነድ ተዘጋጅቶ ለዩኔስኮ መጋቢት 2007 ዓ.ም ተልኳል፡፡
የገዳ ስርአት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥናታዊ ሰነድ መቼ ተላከ?
መጋቢት 2007 ዓ.ም
1,145
ለአጽዋማትና በዓላት ማውጫ ወሳኝ የሆነው ነጥብ መባጃ ሐመር ነው፡፡ መባጃ ሐመር መባጊያ ሐመር እየተባለም ይጠራል፡፡ መባጊያ ሐመር ሲሆን የበጋ መመላለሻ የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡ በሌላ በኩል መባጃ በራሱ ማቆያ፣ ማክረሚያ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ሐመር መርከብ፣ መጓጓዣ የሚለውን ትርጉም ያስገኛል፡፡ መባጃ ሐመር የመጥቅዕና የዕለታት ተውሳክ ድምር ሆኖ አጽዋማትና በዓላት የሚውሉበትን ቀን ያመለክታል፡፡ በሐመር የተመሰለውም አጽዋማትና በዓላት ወደ ላይና ወደታች የሚመላለሱበት ሥርዓት /መርከብ/ ስለሆነ ነው፡፡ በአጠቃላይ መባጃ ሐመር ማለት የአጽዋማትንና የበዓላትን መዋያ ወይም መግቢያ ቀን ለማወቅ የሚያገለግል ልዩ ቁጥር ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አራቱ በመባጃ ሐመር መሠረት በየዓመቱ እየተቀያየሩ ወይም ቀመር እየተሠራላቸው የሚወጡ ሲሆን፣ ሦስቱ ግን ያለ መባጃ ሐመር በየዓመቱ በተመሳሳይ ወቅት ይባጃሉ፡፡ በመባጃ ሐመር የሚባጁት አራት አጽዋማት ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌና ጾመ ሐዋርያት ሲሆኑ፣ ያለ ማባጃ ሐመር በየዓመቱ ቋሚ ጊዜ ይዘው የሚብቱት ሦስቱ አጽዋማት ደግሞ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ገሃድና ጾመ ማርያም /ፍልሰታ/ ናቸው፡፡ ከላይ በተመለከትነው መሠረት መባጃ ሐመር የአጽዋማትና የበዓላት ማስገኛ ልዩ ቁጥር ነው ካልን ቁጥሩ እንዴት እንደሚገኝ ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ እንደምራለን፡፡
የአጽዋማትንና የበዓላትን መዋያ ወይም መግቢያ ቀን ለማወቅ የሚያገለግል ልዩ ቁጥር ምን ይባላል?
መባጃ ሐመር
327
ራስ መኮንን ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የሸዋ ንጉሥ የነበሩት የሣህለ ሥላሴ ልጅ የልዕልት ተናኘወርቅ እና የደጃዝማች ወልደሚካኤል ልጅ ናቸው። ግንቦት ፩ ቀን ፲፰፻፵፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ እስከ ፲፬ ዓመት ዕድሜያቸው ከአባታቸው ጋር ከኖሩ በኋላ ያጐታቸው የንጉሥ ኃይለ መለኮት ልጅ ዳግማዊ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ እንደነበሩ፡ ወደርሳቸው ቤተ መንግሥት መጥተው፡ ባለሟል ሆኑ። በ፲፰፻፷፰ ዓ.ም ዕድሜያቸው ሀያ አራት ዓመት ሲሆን ከወይዘሮ የሺ እመቤት ጋር ተጋብተው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም የወደፊቱን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ወለዱ።
ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል አጎታቸው ማን ነበሩ?
ንጉሥ ኃይለ መለኮት
188
አንበሳ አንበሳ ጡት አጥቢ የእንስሶች መደብ ውስጥ ሲሆን ግዙፍ ድመቶች ከሚባሉት 4 አራዊት አንዱ ነው። ከነዚህም መካከል ነብር ከሚባለው ግሥላ መሳይ አውሬ ቀጥሎ በቁመቱና ክብደቱ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አንበሳ ዛሬ በአፍሪካ (ከነኢትዮጵያ) እና በህንድ ብቻ የሚገኝ ሲሆን በታሪክ እስያና በደቡብ አውሮፓ እንደነበርና እንደጠፋ ይታወቃል። አንበሶች በጣም ቁጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሙጭሊትን ያህል ገራምና ተጫዋች ይሆናሉ። ሲጠግቡ በዝግታ የሚያንኮራፉ ቢሆንም እንኳ እስከ ስምንት ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሰማ በሚችል ኃይለኛ ድምፅ ሊያገሡ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ሰነፎችና ልፍስፍሶች ይመስሉ ይሆናል፤ ሆኖም በሚያስገርም ፍጥነት የመንቀሳቀስ ችሎታ አላቸው። የሰው ልጅ፣ አንበሳ ባለው ድፍረት ለዘላለም ሲወሳ እንዲኖር አድርጓል፤ በመሆኑም ደፋር ሰው አንበሳ ተብሎ ይጠራል። አንበሶች በማኅበር ከሚኖሩት የድመት ወገን የሆኑ እንስሶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በትልልቅ መንጋ ተከፋፍለው የሚኖሩ ሲሆን እያንዳንዱ መንጋ ከጥቂት አባሎች አንስቶ ከ30 በላይ ሊደርስ ይችላል። አንድ መንጋ የጠበቀ ዝምድና ያላቸው በርከት ያሉ ሴት አንበሶች ይኖሩታል። አንድ ላይ ይኖራሉ፣ ያድናሉ እንዲሁም ይወልዳሉ። ዕድሜ ልካቸውን ሊዘልቅ የሚችለው ይህ የጠበቀ ትስስር ለመንጋው ጠንካራ መሠረት የሚጥል ከመሆኑም በላይ ለመንጋው ሕልውና ጥሩ ዋስትና ይሆናል። እያንዳንዱ መንጋ እየተዘዋወሩ የሚጠብቁና የመንጋውን የክልል ወሰን የሚያወጡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ለአካለ መጠን የደረሱ ወንድ አንበሶች ይኖሩታል። እነዚህ ዕጹብ ድንቅ የሆኑ አውሬዎች ከጥቁሩ የአፍንጫቸው ጫፍ አንስቶ እስከ ጭራቸው ጫፍ ድረስ ከሦስት ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ሲሆን ከ225 ኪሎ ግራም በላይ ሊመዝኑ ይችላሉ። ቤተሰቡን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ወንዶቹ ቢሆኑም አመራር የሚሰጡት ግን ሴቶቹ ናቸው። ወደ ጥላ ሥፍራ መሄድን ወይም አደን መጀመርን በመሳሰሉት ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ መንጋውን ለአንድ ዓይነት እንቅስቃሴ የሚያነሳሱት ሴቶቹ አንበሶች ናቸው። ሴት አንበሶች በአብዛኛው በየሁለት ዓመቱ ይወልዳሉ። ግልገሎቹ በሚወለዱበት ጊዜ ምንም ዓይነት አቅም አይኖራቸውም። ግልገሎችን ማሳደግ የሁሉም የጋራ ሥራ ነው፤ በመሆኑም ሴቶቹ አንበሶች በሙሉ በመንጋው ውስጥ ያሉትን ግልገሎች ይጠብቃሉ እንዲሁም ያጠባሉ። የግልገሎቹ ዕድገት ፈጣን ሲሆን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ መሮጥና መቦረቅ ይጀምራሉ። ልክ እንደ ሙጭሊቶች እየተንደባለሉ ይጫወታሉ፤ ከሚያጫውቷቸው ጋር ይታገላሉ፤ እንዲሁም በረጃጅሙ ሣር ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይዘላሉ። እያንዳንዱ የሚንቀሳቀስ ነገር ሁሉ ስሜታቸውን ይማርከዋል፤ ቢራቢሮዎችን ለመያዝ ይዘላሉ፣ ትናንሽ ነፍሳትን ያሳድዳሉ፣ ከየጭራሮና ከየሐረጉ ጋር ይታገላሉ። ይበልጥ ስሜታቸውን የሚማርከው ግን እነርሱን ለማጫወት እናታቸው ወዲያና ወዲህ የምታወናጭፈው ጭራዋ ነው። እያንዳንዱ መንጋ የሚኖርበት በደንብ የተከለለ ቦታ ያለው ሲሆን ይህ መኖሪያ ብዙ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ሊኖረው ይችላል። አንበሶች ውኃ እንደ ልብ ባለበትና ከቀትር ሐሩር የሚከላከል ጥላ በሚያገኙበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ መኖር ይመርጣሉ። በእንዲህ ዓይነቱ ሥፍራ ከዝሆኖች፣ ከቀጭኔዎች፣ ከጎሽና ከሌሎች ሜዳማ በሆኑ ሥፍራዎች ከሚኖሩ እንስሶች ጋር በአንድነት ይኖራሉ። አንበሳ አብዛኛውን ጊዜውን በእንቅልፍ ጥቂቱን ጊዜ ደግሞ በአደንና በተዋስቦ ያሳልፋል። እንዲያውም አንበሶች በቀን ውስጥ ወደ 20 የሚጠጋውን ሰዓት የሚያሳልፉት በዕረፍት፣ በመተኛት ወይም በመቀመጥ ነው። ከባድ እንቅልፍ ተኝተው ሲታዩ ሰላማዊና ለማዳ ይመስላሉ። ይሁን እንጂ በዚህ መታለል የለብህም፤ አንበሳ እጅግ ቁጡ ከሆኑት አራዊት መካከል አንዱ ነው!
የአንባሳ ግልገሎቹ ዕድገት ፈጣን ሲሆን በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መሮጥና መቦረቅ ይጀምራሉ?
በሁለት ወር
1,331
በኢትዮጵያ የሚገኙ በርካታ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች መንግሥት ተገቢውን ክትትል እያደረገ ባለመሆኑና ኩባንያዎች በክህሎት የበቁ ኢትዮጵያዊያን በሥልጠና ዕገዛ ባለማድረጋቸው ምክንያት፣ አብዛኛዎቹ በሲሚንቶ ፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሠሩት ሠራተኞች የውጭ ዜጎች መሆናቸው ተገለጸ፡፡ በኢትዮጵያ ምርት በማምረትና በግንባታ ላይ የሚገኙትን ጨምሮ 17 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚገኙ ሲሆን፣ 12ቱ በተለያየ የማምረት መጠን ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በበርካታ ፋብሪካዎች በተለይም ግዙፍ በሚባሉት ዳንጎት፣ ሙገርና ደርባ ኩባንያዎች ውስጥ የውጭ ዜጎች የማኔጅመንቱንና ቴክኒካል ሥራውን በበላይነት እንደሚይዙ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ስምረት ግርማ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም በሥራ ላይ በሚገኙት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች እንዳሉ የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሯ፣ ኢትዮጵያውያን እየሠሩባቸው ያሉ ዘርፎችም ቢሆን በዝቅተኛ ዕርከንና በጉልበት ሥራ ላይ የሚገኙ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ማን ይባላሉ?
ወ/ሮ ስምረት ግርማ
424
ዓረብኛ ዓረብኛ የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ሆኖ የዕብራይስጥ የአረማያ እንዲሁም የአማርኛ ቅርብ ዘመድ ነው። ፪፻፶ (250) ሚሊዮን የሚያሕሉ ሰዎች እንደ እናት ቋንቋ ይናገሩታል። ከዚህም በላይ በጣም ብዙ ሰዎች እንደ ፪ኛ ቋንቋ ተምረውታል። የሚጻፈው በዓረብኛ ፊደል ነው። በዓረብ አለም ውስጥ አያሌ ቀበሌኞች ይገኛሉ። ቋንቋው በእስልምና ታላቅ ሚና አጫውቷል። እስላሞች አላህ ለሙሐማድ ቁርዓንን ሲገልጽ በዓረብኛ እንደ ሆነ ስለሚያምኑ እንደ ቅዱስ ቋንቋ ይቆጥሩታል። አብዛኛው ዓረብኛ ተናጋሪዎች ሙስሊሞች ናቸው። ዛሬ በምዕራብ ዓለም ደግሞ ብዙ ሰዎች አረብኛ እያጠኑ ነው። በታሪክ ከፍተኛ ሚና በማጫወቱ መጠን ፤ ብዙ የዓረብኛ ቃላት ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ገብተዋል።
ዓረብኛ ዓረብኛ ከየትኛው ቋንቋዎች ቤተሠብ ውስጥ ይመደባል?
የሴማዊ
10
ዝግመተ ለውጥ የአንድ ሕይወት ያለው ማህብረሰብ የዘር ውርስ ባህሪይ ከትውልድ ወደትውልድ እየተቀየረ መሄዱ ዝግመተ ለውጥ ይባላል። ቻርለስ ዳርዊን ይህን ኩነት በማስተዋልና በሳይንሳዊ አመክንዮ አሰደግፎ በመተንተኑ የመጀመሪያው ሰው ነው። ዳርዊን በተጨማሪ የተፈጥሮ ምርጫ ባለው ኅልዮቱ ሕይወት ያላቸው ማህበረሰቦች ዝግመተ ለውጥ እሚያካሂዱት ምንም እንኳ በዘፈቀደ ስህተት እየፈጸሙ ቢሆንም፣ ተፈጥሮ እራሷ በምትፈጥረው መሰናክሎች እኒህን መሰናክሎች አልፈው የሚሄዱትን በመምረጧ ነው። ዳርዊን የተፈጥሮ ምርጫን አስተሳሰብ ከ፫ የሚታዩ ነገሮች አንጥሮ ነበር ያወጣው፦ ፩) እንስሳትም ሆነ እጽዋት ወደፊት ሊኖር ከሚችሉ ዘሮች በላይ አተረፍርፈው ነው እሚራቡት ፪) ሕይወት ያላቸው እያንዳንዳቸው ነገሮች ሁልጊዜ የተለያየ ጸባይ ነው ያላቸው፣ ስለሆነም እያንዳንዳንቸው በቀጣይ የመኖር ዕድላቸው የተለያየ ነው ፫) ስለሆነም የአንድ ማህበረሰብ አባላት ሲሞቱ፣ የሚገላቸውን ነገር ጠንክረው እሚቋቋሙት ግለሰቦች ብቻ በሕይወት ቆይተው ወደፊት መራባች ይችላሉ። ስለሆነም ቀስ በቀስ እነዚህ በህይወት ያሉ፣ በህይወት የሌሉትን አይነቶች እየተኩ ይሄዳሉ። በ፳ኛው ክፍለ ዘመን ጄኔቲክስ (ሥነ በራሂ) እና ዝግመተ ለውጥ ተዋህደው ማህበረሰባዊ ጄኔትክስ እሚባለውን ጥናት ለመፍጠር ችለዋል። አንድ ማህበርሰብ ለየት ያለ ግለሰቦችን ለመፍጠር ከሚያስችሉት መንገዶች አንዱ ሙቴሽን የተባለው ሂደት ሲሆን፣ ሙቴሽን እሚፈጠረው የዚያ ግለሰብ ዲ ኤን ኤ ከወላጆች ሲወረስ በሚደረግ ስህተት (ወይም እቅድ) ነው።
ማህበረሰባዊ ጄኔትክስ እሚባለው የምን ጥናት ውህድ ነው?
ጄኔቲክስ (ሥነ በራሂ) እና ዝግመተ ለውጥ
667
የአባ ጊዮርጊስ ትምህርታቸው የአባ ጊዮርጊስ አባት ሕዝበ ጽዮን በቤተ መንግሥት በንጉሡ ስዕል ቤት ከሚያገለግሉት ካህናት ጋር ይሠሩ ስለነበር ልጃቸው በመልካም አስተዳደግና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በማስተማር በዕውቀት አሳድገዋቸዋል። በድቁናም አሹመዋቸዋል። ከዚያም በኋላ በንጉሥ ዳዊት ዘመን (፲፫፻፸፮ ፥ ፲፬፻፭) በደብረ ሐይቅ ባሕር ወደምትገኘው የቅዱስ እስጢፋኖስ አባ እየሱስ ሞዐ ገዳምና ታዋቂ ትምህርት ቤት ወስደው ከታላቁ ዓቃቤ ሰዓት አባ ሠረቀ ብርሃን ጉባዔ ተቀላቅለው እንዲማሩ አድርገዋል ። ይሁን እንጂ አባ ጊዮርጊስ በትምህርት ቤቱ የሚሰጡትን የቀለም ትምህርቶች ቶሎ ለማጥናት አልቻሉም ። ወደ ኋላ የመቅረታቸው ዋናው ምክኒያትም አባ ጊዮርጊስ ከመማሩ ይልቅ የማረካቸው በሥራ እየደከሙ የገዳሙን አባቶች መርዳትና የብትህውናው ሕይወት መሆኑ ነው ። ጉዋደኞቻቸው በትምህርት ሲቀድሙአቸው ባዩ ጊዜ እጅግ አዘኑ ። በጾምና ጸሎትም ወደ እግዚአብሔር ጮሁ በፍፁም ልባቸውም አምነው ብርቱ ልመናን ከእመቤታችን ሥዕል ፊት ቁሞ በጠለቀ ተመስጦልቦና እንባን በማፍሰስ ወደ እግዚአብሔር " የአባቶቻችን አምላክ የምህረት ጌታ ሁሉን በቃልህ የፈጠርክ ሰውንም በረቂቅ ጥበብህ የፈጠርክ አቤቱ አንተ ከልዑል ጌትነትህ ጥበብን ስጠኝ በእውነትም አትናቀኝ እኔ ባሪያህ ነኝ የባሪያህም ልጅ ነኝና " በማለት ለመኑ ። ከዚህም በኋላ የዓለም ንግሥት የአምላክ እናት ተገለጸችላቸው ። በነሐሴ ፳፩ ቀንም ወደርሳቸው መጣች ፣ በዕውቀትና በትምህርት የሚተጉበትን ኃይል ሰጠቻቸው ። ከዚያም የዜማ የቅኔና የመጽሐፍትን ትርጉዋሜ ትምህርታቸውን በሚገባ አጠናቀቁ ብዙ መጽሐፍትንም ደረሱ ። በዚህም በቀሰሙት ዕውቀታቸው በዜማ በኩል ከቅዱስ ያሬድ ቀጥለው የሚጠሩ አባ ጊዮርጊስ ናቸው። በቤተመቅደስም ዘማሪ ማኅሌታይ ተብለው ይጠራሉ። በዚያም ዘመን ለነገሥት ፣ ለካህናት ፣ ለመኳንንት ፣ ለንቡራነእድ ፣ ለመሳፍንት ፣ ለሁሉም የቤተመንግሥት ሠራተኞች አስተማሪ ሆኑ ። በአንድ ወቅት ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ “ሥላሴን አንድ ገጽ” ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜነገሩን እንዲያጣሩ ከተመረጡት ከቄስ ሐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት አበውጳጳሱን ካነጋገሩ በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡ ሊቅነታቸውን የተረዱት ዓፄ ዳዊት አባ ጊዮርጊስን ወደ ቤተመንግሥታቸው በማስገባት የስምንቱም ልጆቻቸው መምህር አድርገዋቸው ነበር ። ከእነርሱም ውስጥ ቅዱስ የተባለው ንጉሥ ቴዎድሮስ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜ የነገሡት ንጉሥ እንድርያስ ፣ ዓፄ ይስሐቅ ፣ ንግሥት እሌኒ እና ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ይገኙበታል። ዐፄ ዳዊት በጋብቻ እንዲዛመዱዋቸው ጥረው ነበር ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ ራሳቸውን የመንግሥተ ሰማያት ጃንደረባ ማድረግን ስለመረጡ በማስተማሩና በብሕትናው ጸንተው የአመክሮ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው መንኩሰዋል።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ በየት መነኮሱ?
አቡነ በጸሎተ ሚካኤል
1,643
የሕገ መንግሥት ታሪክ የሱመር ከተማ ላጋሽ አለቃ ኡሩካጊና በ2093 ዓክልበ. ያሕል ያዋጀ ሕገ ፍትሕ በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያ የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይታወቃል። ከዚህ በኋላ ብዙ መንግሥታት በተጻፈ ሕግ እንዲገዙ ልዩ ስርዓት ነበራቸው። ከተገኙት ሕግጋት ሁሉ ጥንታዊ የሆነው በ1983 ዓክልበ. የገዙ የኡር ንጉሥ የኡር-ናሙ ሕግጋት ነው። በተለይ ዕውቅ የሆኑ የጥንት መንግሥት ሕጎች የኢሲን ንጉሥ ሊፒት-እሽታር ሕግጋት (1832 ዓክልበ.) ፤ የኤሽኑና ሕግጋት (ምናልባት 1775 ዓክልበ. ግድም)፤ የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ሕግጋት (1704 ዓክልበ.) እና፤ ሕገ ሙሴ ለእስራኤል (1661 ዓክልበ.) ናቸው። ሕገ ሙሴ በተለይ በኦሪት ዘጸአት 21 እና 22 ያህዌ አስተካክሎ ከነዚህ ሁሉ የተሻሸሉት ብያኔዎች ይጠቅልላል። በኋላ ኬጢያውያን (1488 ዓክልበ. ግድም) እና አሦር (1080 ዓክልበ. ግድም) በበኩላቸው ለራሳቸው ሕግጋት አወጡ።
የባቢሎኑ ንጉሥ ሃሙራቢ ሕግጋት የታወጀው መች ነበር?
1704 ዓክልበ.
472
የእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት የእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት በእስክንድርያ፣ ግብጽ በጥንት (54-373 ዓም ያህል) የተገኘ የክርስትና ሥነ መለኮት ትምህርት ተቋም ነበረ። ተቋሙን የመሠረተው የኢየሱስ ሐዋርያ እና መጀመርያው የእስክንድርያ ጳጳስ፣ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ በ54 ዓም እንደ ሆነ ተጽፏል። የተቋሙ መጀመርያው መሪ በኋላ የእስክንድያ ፮ኛው ጳጳስ የሆነው ዩስቱስ እንደ ተሾመ ይታመናል። ተቋሙ ያስተማረው ከሥነ መለኮት፣ መጽሐፍ ቅዱስና ክርስትናን ጭምር፣ የግሪክኛና የሮማይስጥ ስነ ጽሁፍ፣ ሥነ ጥበብ፣ ስነ አመክንዮ፣ ሥነ ቁጥርና ስነ-ተፈጥሮ ጥናቶች ነበሩ። ለዕውሮችም ማስተማርያ አገልግሎት አቀረቡ። በፓንታይኖስ መሪነት (173-182 ዓም) ተቋሙ ስለ ትምህርቱ ዝነኛ ሆነ። ፓንታይኖስ በክርስትና ከመጠመቁ በፊት፣ የግሪኮች «ስቶዊሲሲም» ፍልስፍና ተከታይ ሆኖ ነበር። ፓንታይኖስ የግሪክ ፍልስፍና ከክርስትና ርዕዮተ አለም ጋር እንዳዋሐደ ይታስባል። ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ ከ182-194 ዓም በተቋሙ መሪነት ተከተለው። ብዙ አረመኔዎች በዚያን ጊዜ ለትምህርት ስለመጡ ከፍልስፍና መሠረት ጀምሮ የክርስትናን ትምህርት ያሳውቃቸው ነበር። በ194 ዓም የሮሜ መንግሥት ቄሣር በክርስቲያኖች ላይ ስላዘረጋው ማሳደድ፣ ቀሌምንጦስ ለጊዜው ከእስክንድርያ ሸሸ። እሱም የጻፋቻው ትልቅ መጻሕፍት ተርፈውልናል። የቀሌምንጦስ ተከታይ ኦሪገኔስ በመከራ ጊዜ ቢሆንም ተቋሙን በ195 ዓም ዳግመኛ አቆመ። ኦሪገኔስ ደግሞ ብሉይ ኪዳን በስድስት ትይዩ ዕብራይስጥና ግሪክኛ ትርጉሞች (ሄክሳፕላ) ያሳተመው እና ብዙ አንድምታ የጻፈው ዝነኛ መምህር ነው። በ373 ዓም በተካሄደው በቁስጥንጥንያ ጉባኤ፣ የጵጵሳት ቅድምንትነት ለሮሜ ፓፓ፣ ከርሱም ቀጥሎ ለአንጾኪያ ጳጳስ እንዲሰጥ የሚል ብያኔ ወረደ። ስለሆነም፣ የእስክንድርያ ጳጳስ የቀድሞ ቀድምትነቱን በማጣቱ፣ በእስክንድርያ ከተማ ውስጥ ትልቅ ሁከት ደረሰ። በዚያም ጊዜ በተደረገው ጉዳት የማስተማርያ ተቋሙ ጠፋ።
ፓንታይኖስ ከመጠመቁ በፊት የምን ፍልስፍና ተከታይ ነበር?
የግሪኮች «ስቶዊሲሲም»
459
ግብፅ ግብፅ ወይም ምጽር፣ ምሥር በሰሜን ምስራቅ ኣፍሪካ የምትገኝ አገር ናት። 77 ሚሊዮን ከሚሆነው ህዝቧ አብዛኛው ከናይል ወንዝ ዳርቻ በአንድ ኪሎሜትር ክልል ውስጥ ይገኛል። የግብፅ አብዛኛው መሬት በሰሃራ በረሃ ክልል ውስጥ ይገኛል። ዋና ከተማዋ ካይሮ ስትሆን ከአፍሪካም ትልቋ ከተማ ናት። ሌላ ትኩረት የሚሰጣት ከተማ አሌክሳንድሪያ (እስክንድርያ) ናት። አሌክሳንድሪያ የአገሪቱ ዋና ወደብ ስትሆን በህዝብ ብዛት ከአገሪቱ ሁለተኛ ናት። ግብፅ በሰሜን ከሜዴቴራኒያን ባሕር በምሥራቅ ከቀይ ባሕር፤ በደቡብ ከኖብያ፤ በምዕራብ ከምድረ በዳው አገር ይዋሰናል። ነጭ አባይ በግብፅ መካከል ያደርግና ከደቡብ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል። የአባይ ወንዝ የሚሞላው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በግብፅ የሚዘንበው አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ስለ ሆነ ግብፅ በአባይ ለምቶ ይኖራል።
ከግብጽ ከተሞች በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ የሆነችው ከተማ ማናት?
አሌክሳንድሪያ
227
ሜሪላንድ ሜሪላንድ (እንግሊዝኛ፦ Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያ ፣ ቨርጂኚያ ፣ ዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳይንስና የሕክምና ተቋማት በዚሁ ክፍላገር ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ1996 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መዓከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።
በሜሪላንድ ስቴት ትልቁ የከፍታ ቦታ የት ነው?
የባክቦን ተራራ
276