context
stringclasses
367 values
question
stringlengths
10
114
answer
stringlengths
1
90
answer_start
int64
0
3.22k
ቱርክመንኛ ቱርክመንኛ (Türkmen) የቱርክምኒስታን ብሔራዊ ቋንቋ ነው። በቱርክመኒስታን 3,430,000 ተናጋሪዎች ሲኖሩ ከቱርክመኒስታን ውጭ ደግሞ 3 ሚሊዮን የሚያሕሉ ተናጋሪዎች በተለይም በኢራን (2 ሚሊዮን) በአፍጋኒስታን (500,000) እና በቱርክ (1000) አሉ። ቱርክመንኛ በቱርኪክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይከተታል። ይህም አንዳንዴ በትልቁ አልታይ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይደመራል። ቀድሞ የተጻፈበት ወይም በቂርሎስ ወይም በ አረብ ፊደሎች ነበር፤ አሁን ግን የቱርክመኒስታን መሪ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ አዋጀ። በ1994 አ.ም. ደግሞ የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ እንደ አቶ ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።
ቱርክመንኛ በፊት በየትኞቹ ቋንቋዎች ፊደላት ነበር የሚጻፈው?
በቂርሎስ ወይም በ አረብ ፊደሎች
261
ሜሪላንድ ሜሪላንድ (እንግሊዝኛ፦ Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያ ፣ ቨርጂኚያ ፣ ዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳይንስና የሕክምና ተቋማት በዚሁ ክፍላገር ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ1996 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መዓከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።
በ2003 እ.ኤ.ኣ. የሜሪላንድ ስቴት ነዋሪዎች ዓመታዊ ገቢ ምን ያህል ነበር?
37,446 የአሜሪካን ዶላር
505
አዲስ አበባ መስከረም 15/2012 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሰራተኞቹ ጋር በሬድዬ ግንኙነት በመፍጠር አገልግሎቱን የሚያቀላጥፍበት የአስትሮ ሞቶሮላ የሬድዬ ኮሙኒኬሽን ፕሮጀክት አስመረቀ። የፕሮጀክቱ ምረቃ ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር በተገኙበት በእንጦጦ ማሪያም የቴሌ ማይክሮዌቭ ማሰራጭያ ጣቢያ ተካሂዷል። በሁለት ምዕራፍ የተከፈለውን ፕሮጀክት ወደ ሥራ ለማስገባት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ሐምሌ 15 /2017 በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በሞቶሮላ ሶሉሽን ኩባንያ መካከል ስምምነት ተፈርሞ ነበር። የመጀመሪያው ምዕራፍ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ሲሆን በአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ኦሮሚያ ዞን ላይ ተግባራዊ ሆኗል። የኤሌክትሪክ የአገልግሎት አሰራሩን በማቀላጠፍ ለዜጎች የተሻለ አገልግሎት እንደሚሰጥ የታመነበት ይሄው ፕሮጀክት 6 ቡድኖችን በመያዝ በ 8 የግንኙነት ቻናሎች በጋራ እና በእኩል ሁኔታ እንዲጠቀሙ የሚያግዝ ነውም ተብሏል። የአስቸኳይ ጥገና ሥራን ማቀላጠፍ፣ ከሰብ ስቴሽን ጋር የሚኖረውን ግኝኑነት ማሳለጥ፣ በግንኙነት ክፍተት ሊፈጠሩ የሚችሉ የሰውና የንብረት አደጋን መቀነስ እንዲሁም የኃላፊዎችን መረጃ የመቀበልና መልዕክት የማስተላለፍ ሥራውን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተገልጿል። በኤሌክትሪክ አገልግሎት የአውቶሜሽንና ኢነርጂ ማኔጅመንት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ደመቀ ሮቢ አገልግሎቱ ስራውን የሚያከናውነው በስልክ እንደነበር አስታውሰው ይህም የሚሰጠው አገልግሎት ቅልጥፍና እንዳይኖረው አድርጎት ቆይቷል ይላሉ። ዛሬ የተመረቀው የሬድዮ ኮሙኒኬሽን ፕሮጀክት መስክ የወጡ የጥገና ሰራተኞች ቢሮ ካሉ ሰራተኞች ጋር በፍጥነት እንዲገናኙ ከማድረጉም ባለፈ ከፍተኛና ዝቅተኛ ኃይል መስመር ላይ ካሉ ኦፕሬተሮች ጋርም በቀላሉ በመገናኘት ፍጥነት ያለው የጥገና አገልግሎቶች እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል። በዚሁ የመጀመሪያው ምዕራፍም በአዲስ አበባና ዙሪያ በእጅ የሚያዙ 300 እንዲሁም 200 መኪና ላይ የሚገጠሙና 100 በጥሪ ማዕከልና በአስቸኳይ ጥገና ማዕከላት ላይ የሚገጠሙ ዲጂታል ሬዲዮኖች ጥቅም ላይ ውለዋል። እንደ አቶ ደመቀ ገለጻ ምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክቱንም ለማካሄድ ከአዲስ አበባ ውጪ 8 ከተሞች የተመረጡ ሲሆን ለዚህም ከ4 ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት ተይዞለታል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሠራተኞቹ ጋር የሚገናኝበት ሬዲዮ ምን ይባላል?
የአስትሮ ሞቶሮላ
88
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በተያዘው የበጀት ዓመት የመጀመርያው ሦስት ወራት፣ ከ12.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ ቢሮው እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የሚዘልቅ ግብር የማሳወቅና የመሰብሰብ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጾ፣ እስከ መስከረም 2014 ዓ.ም. መጨረሻ ሳምንት ባለው ጊዜ ከግብር አሰባሰቡ የተገኘው ገቢ ከታቀደው በላይ እንደሆነ አስታወቋል፡፡ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊነትን አዲስ በተመረጠው የከተማ አስተዳደር እንዲመሩ በድጋሚ የተመረጡት አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ገቢዎች ቢሮው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተጀመሩትን የከተማዋን ገቢ በተጠናከረ ሁኔታ የመሰብሰብ ሥራ ዘመናዊ በሆነ ሥርዓትና ቅንጅታዊ አተገባበር እየተከናወነ ነው፡፡ በተያዘው በሩብ ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ የታቀደው የግብር ገቢ 11.5 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ያስታወቁት ኃላፊው፣ ከሦስት ያላነሱ ቀናት የገቢ አሰባሰብ መረጃ ሳይካተት እስከ መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 12.26 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
ዓመታዊ የግብር ማሳወቅና አሰባሰብ እስከ መቼ ይቆያል?
ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም.
104
ሴት ተማሪዎች በትርፍ ጊዜያቸው ችግር ፈቺ የሞባይል አፕሊኬሽን እና ኮዲንግ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የሚያግዝ ስምምነት  መፈረሙን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ስምምነቱ የተፈረመውም ከኮኖቬሽን ኢንተርፕረንርሺፕ ዲቨሎፕመንት ከተባለ ድርጅት ጋር መሆኑ ተነግሯል፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት  ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ÷ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች  ሲመደቡላቸው ተቀብሎ ከማስተማር ጎን ለጎን በአከባቢያቸው ካሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር ትስስር በመፍጠር ፣ተማሪዎችን በቀጣይ የዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ውጤታማ የሚያደርጉና በሳይንስ ዘርፉም ፍላጎት እንዲያድርባቸው የሚያግዙ ስራዎችን ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። ዩኒቨርሲቲዎች በአይሲቲ ዘርፍ ያላቸውን አቅርቦት ለስልጠናው በማመቻቸትና መምህራንንም በማሳተፍ ሴት ተማሪዎች በሞባይል አፕሊኬሽን እና ኮዲንግ ላይ የሚሰጣቸውን ስልጠና  ይደግፋሉ፡፡ ይህ ስምምነት  ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዩኒቨርሲቲዎች ባሉበት አከባቢ የማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ ለሚሰራው ስራ እና የሳይንስ ባህል ግንባታ ላይ የሰጠው ትኩረት አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡ የኮኖቬሽን ኢንተርፕረንርሺፕ ዲቨሎፕመንት  በኢትዮጵያ አስተባባሪ  አቶ ብርሃኑ ገብረሚካኤል÷  ሴት ተማሪዎች በሳይንስ ዘርፍ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል። ፕሮጀክቱ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው ጀምሮ ሳይንስ ውስጥ እንዲገቡ የሚያግዙ ስልጠናዎችን በማመቻቸት በሳይንስ ዘርፍ የሚመረቁ ሴት ተማሪዎችን ቁጥር ከፍ የማድረግ ዓላማ አለው ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱን እውን ለማደረግ የዩኒቨርሲቲዎች ድጋፍ ወሳኝ መሆኑንና በፕሮግራሙ ታቅፈው ስልጠናውን ተከታትለው ጥሩ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ሴት ተማሪዎችም የነፃ ትምህርት እድሎችን እንደሚያመመቻቹ  ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱን ለመጀመሪያ ጊዜ በተመረጡ ዩኒቨርስቲዎች እንደሚጀምሩና ከዚያም በመነሳት በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የማስፋፋት እቅድ እንዳላቸውም አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር  ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ተማሪዎች የአይ ሲ ቲ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ ማመቻቸቱን  አስታውቀዋል፡፡ በተለይም ዲጂታል ሊትሬሲ በሚል የክረምት የስልጠና ፕሮግራም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በማካሄድ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት መሰረታዊ የዲጂታል ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ተናግረዋል። በቀጣይም የዚህ አይነት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሮፌሰር አፈወርቅ መግለጻቸውን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሴት ተማሪዎች በትርፍ ጊዜያቸው ችግር ፈቺ የሞባይል አፕሊኬሽን እና ኮዲንግ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የሚያግዝ ስምምነት የተፈረመው ለምን ዓላማ ነው?
በሳይንስ ዘርፍ የሚመረቁ ሴት ተማሪዎችን ቁጥር ከፍ የማድረግ ዓላማ
828
ከ1881 እስከ 1905 ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በአፍሪካ ይዞታቸውን እያሰፉ የነበሩትን የአውሮፖ ሀይሎችን ጥቃት በመከላከል ኢትዮጵያን በስርዓት አስተዳድረዋል፡፡ በዚያን ጊዜ ጣልያን ኤርትራን በከፊል ቅኝ ገዝታ የነበረችበትና በ1880ዎቹ አጋማሽ ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ቅኝ ገዝታት የነበረችበት ጊዜ ስለነበር ከሌሎች አውሮፖ አገራት በበለጠ ለኢትዮጵያ አስጊ ነበረች፡፡ በ1880 ግን እስከዛሬ ድረስ ዝነኛ በሆነው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ጣልያንን ድል በማድረግ በአፍሪካ የባእዳን ገዥ ሀይሎችን ያሸነፈች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የቅኝ ገዥዎችን ወረራና መስፋፋት በመመከትና ድልን በመቀዳጀት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በባርነት ቀንበር ተጠምደዉ ለሚማቅቁ የመላዉ ዓለም ህዝቦች ከፍተኛ ክብርና ተስፋን አጎናጥፈዋል በ1908 የዳግማዊ ሚኒሊክ ልጅ የሆኑትን እቴጌ ዘውዲቱ ስልጣን ያዙ ፡፡ የሳቸው የቅርብ የስጋ ዘመድ የነበሩት ራስ ተፈሪ መኮንንም ሞግዚት አስተዳደርና ወራሽ ሆነው ተሹመዋል፡፡ እቴጌ ዘውዲቱ በ1922 ሲሞቱ ተተኪያቸው ዐጼ ሀይለስላሴ ስልጣን ያዙ ፡፡ ነገር ግን በ1928 ዓ.ም የጣልያን ሀይሎች ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ ወረው ሲቆጣጠሩ ግዛታቸው ተቋርጦ ነበር፡፡
የዳግማዊ ሚኒሊክ ልጅ መቼ ሥልጣን ያዙ?
በ1908
461
የአባ ጊዮርጊስ ትምህርታቸው የአባ ጊዮርጊስ አባት ሕዝበ ጽዮን በቤተ መንግሥት በንጉሡ ስዕል ቤት ከሚያገለግሉት ካህናት ጋር ይሠሩ ስለነበር ልጃቸው በመልካም አስተዳደግና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በማስተማር በዕውቀት አሳድገዋቸዋል። በድቁናም አሹመዋቸዋል። ከዚያም በኋላ በንጉሥ ዳዊት ዘመን (፲፫፻፸፮ ፥ ፲፬፻፭) በደብረ ሐይቅ ባሕር ወደምትገኘው የቅዱስ እስጢፋኖስ አባ እየሱስ ሞዐ ገዳምና ታዋቂ ትምህርት ቤት ወስደው ከታላቁ ዓቃቤ ሰዓት አባ ሠረቀ ብርሃን ጉባዔ ተቀላቅለው እንዲማሩ አድርገዋል ። ይሁን እንጂ አባ ጊዮርጊስ በትምህርት ቤቱ የሚሰጡትን የቀለም ትምህርቶች ቶሎ ለማጥናት አልቻሉም ። ወደ ኋላ የመቅረታቸው ዋናው ምክኒያትም አባ ጊዮርጊስ ከመማሩ ይልቅ የማረካቸው በሥራ እየደከሙ የገዳሙን አባቶች መርዳትና የብትህውናው ሕይወት መሆኑ ነው ። ጉዋደኞቻቸው በትምህርት ሲቀድሙአቸው ባዩ ጊዜ እጅግ አዘኑ ። በጾምና ጸሎትም ወደ እግዚአብሔር ጮሁ በፍፁም ልባቸውም አምነው ብርቱ ልመናን ከእመቤታችን ሥዕል ፊት ቁሞ በጠለቀ ተመስጦልቦና እንባን በማፍሰስ ወደ እግዚአብሔር " የአባቶቻችን አምላክ የምህረት ጌታ ሁሉን በቃልህ የፈጠርክ ሰውንም በረቂቅ ጥበብህ የፈጠርክ አቤቱ አንተ ከልዑል ጌትነትህ ጥበብን ስጠኝ በእውነትም አትናቀኝ እኔ ባሪያህ ነኝ የባሪያህም ልጅ ነኝና " በማለት ለመኑ ። ከዚህም በኋላ የዓለም ንግሥት የአምላክ እናት ተገለጸችላቸው ። በነሐሴ ፳፩ ቀንም ወደርሳቸው መጣች ፣ በዕውቀትና በትምህርት የሚተጉበትን ኃይል ሰጠቻቸው ። ከዚያም የዜማ የቅኔና የመጽሐፍትን ትርጉዋሜ ትምህርታቸውን በሚገባ አጠናቀቁ ብዙ መጽሐፍትንም ደረሱ ። በዚህም በቀሰሙት ዕውቀታቸው በዜማ በኩል ከቅዱስ ያሬድ ቀጥለው የሚጠሩ አባ ጊዮርጊስ ናቸው። በቤተመቅደስም ዘማሪ ማኅሌታይ ተብለው ይጠራሉ። በዚያም ዘመን ለነገሥት ፣ ለካህናት ፣ ለመኳንንት ፣ ለንቡራነእድ ፣ ለመሳፍንት ፣ ለሁሉም የቤተመንግሥት ሠራተኞች አስተማሪ ሆኑ ። በአንድ ወቅት ግብፃዊው ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ “ሥላሴን አንድ ገጽ” ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜነገሩን እንዲያጣሩ ከተመረጡት ከቄስ ሐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስት አበውጳጳሱን ካነጋገሩ በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡ ሊቅነታቸውን የተረዱት ዓፄ ዳዊት አባ ጊዮርጊስን ወደ ቤተመንግሥታቸው በማስገባት የስምንቱም ልጆቻቸው መምህር አድርገዋቸው ነበር ። ከእነርሱም ውስጥ ቅዱስ የተባለው ንጉሥ ቴዎድሮስ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜ የነገሡት ንጉሥ እንድርያስ ፣ ዓፄ ይስሐቅ ፣ ንግሥት እሌኒ እና ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ይገኙበታል። ዐፄ ዳዊት በጋብቻ እንዲዛመዱዋቸው ጥረው ነበር ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ ራሳቸውን የመንግሥተ ሰማያት ጃንደረባ ማድረግን ስለመረጡ በማስተማሩና በብሕትናው ጸንተው የአመክሮ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው መንኩሰዋል።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ በየት ተማሩ?
በደብረ ሐይቅ ባሕር ወደምትገኘው የቅዱስ እስጢፋኖስ አባ እየሱስ ሞዐ ገዳምና ታዋቂ ትምህርት ቤት
200
ቱርክ በዊኪፒዲያ ላይ ላለፉት ሶስት ዓመታት ጥላው የነበረውን እገዳ በማንሳት ተጠቃሚዎች ድረ ገፁን ማግኘት እንዲችሉ ፈቀደች። የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት እገዳው የመናገር መብትን ይጥሳል ሲል እግዱ እንዲነሳ ውሳኔ አሳልፏል። ዊኪፒዲያ በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 2017 የቱርክን መንግስት የሚተች ፅሁፍ ለማንሳት ፈቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ የቱርክ መንግስት እገዳ ማሳላፉ ይታወሳል። በወቅቱ በዊኪፒዲያ ላይ የሰፈረው ፅሁፍ የቱርክ መንግስት ከአይ ኤስ እና አል ቃይዳ ጋር ትብብር አለው የሚል መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። ይህንን ተከትሎም እገዳው ላለፉት 991 ቀናት ተግባራዊ ሆኖ መቆየቱን የኢንተርኔት ክትትል ተቋም የሆነው ኔትብሎክስ አስታውቋል። እገዳው በሂደት ቀስ በቀስ የሚነሳ በመሆኑ እና የተወሰኑ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ዊኪፒዲያን ለመመለስ እየሰሩ በመሆኑ በቱርክ የሚገኙ ሁሉም ተጠቃሚዎች ድረ ገፁን ማግኘት አይችሉም ተብሏል፡፡ ዊኪፒዲያ በበርካታ የዓለም ሀገራት ሳንሱር የሚደረግ ሲሆን በቻይና አሁንም ታግዶ ይገኛል።
ዊኪፒዲያ በቱርክ ለስንተ ቀናት ታገደ?
991
354
መዓዛ ብሩ መዓዛ የተወለደችው እዚህ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሲሆን ዘመኑም 1951 ዓ.ም ነበር፡፡ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ክፍል በሐረርጌ ክፍለ ሀገር በሒርና ከተማ ተምራ፣ ከአራተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርቷን ደግሞ በቅድስት ማርያም ትምህርት ቤት ተከታትላ ፈጽማለች፡፡ መዓዛ በትምህርት ቤቷ በክፍል ውስጥ አጫጭር ታሪኮችን ለተማሪዎች በማንበብ ከመታወቋም ሌላ ከፍ ያለ የሥነ - ጽሑፍ ዝንባሌ እንደነበራት የሚያስታውሱት መምህራኗ “አንድ ቀን ታላቅ የጥበብ ሰው እንደሚወጣት እናውቅ ነበር” ይላሉ፡፡ መዓዛ በ1971 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ - ቋንቋ ጥናት ተቋም ውስጥ በሥነ-ልሣን ትምህርት ክፍል ተመደበች፡፡ ሥነ-ልሣን መዓዛ የምትፈልገው ጥናት ባለመሆኑ በምደባው ቅር ብትሰኝም፤ በንዑስ ትምህርት ደረጃ የምትወስደው የውጭ ቋንቋና ሥነ - ጽሑፍ በመሆኑ ለነበራት ቅሬታ እንደማካካሻ ሆኖላታል፡፡ በዚህ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዓመት ተማሪ ሳለች የተፈጠረ አንድ አጋጣሚ ደግሞ መዓዛንና ሬዲዮንን የሚያስተሳስር ይሆናል፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ ሬዲዮ የፕሮግራሞች ኃላፊ የነበረው አቶ ታደሰ ሙሉነህ ለሚያዘጋጀው የእሁድ የሬዲዮ ፕሮግራም ድራማ የሚጫወቱ ሸጋ ድምጽ ያላቸው ወጣቶችን ሲያፈላልግ ከመዓዛ ጋር ይተዋወቃል፡፡ ድራማው አስታጥቃቸው ይሁን ያሰናዳው ሲሆን የመዓዛ ድምጽ ለሙከራ በስቱዲዮ ተቀርጾ ሲሰማው፣ ታደሰ ሙሉነህ የሚፈልገውና የሚወደው ድምጽ ሆኖ ስላገኘው ይደሰታል፡፡ ከዚህ በኋላም ለእሁድ ፕሮግራም የሚሆኑ ጽሑፎችን በየሳምንቱ እንድታነብለት ያግባባትና የመዓዛና የሬዲዮ ፍቅር በኢትዮጵያ ሬዲዮ ይወለዳል፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የመዓዛ ድምጽ በእሁድ የሬዲዮ ፕሮግራም አድማጮች ዘንድ የተለመደና የተወደደ ሆነ፡፡ መዓዛም የሌሎችን ጽሑፎች በማንበብ ብቻ ሳትወሰን የራሷን ጽሁፎች እያዘጋጀች የምታቀርብ ንቁ ተሳታፊ በመሆን ከሬዲዮ ፕሮግራሙ ቤተሰቦች እንደ አንዱ ሆነች፡፡ በ1974 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲ ተመርቃ ትምህርቷ ፍጻሜውን እስካገኘ ድረስም መዓዛ ሬዲዮና ትምህርትን ጎን ለጎን ስታስኬድ ቆይታለች፡፡ የመዓዛ የሥራ ዓለም የተጀመረው ግን በምትወደውና በምትፈልገው በኢትዮጵያ ሬዲዮ ውስጥ ሳይሆን መንግስት በመደባት በባህል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ ስራዋም ባህልና ስፖርት የተባለው የመስሪያ ቤቱ መምሪያ በሚያሳትመው “መርሐ ስፖርት” የተሰኘ ወርሃዊ የስፖርት መጽሔት (በኋላ ጋዜጣ) ላይ ሆነ፡፡ ምንም እንኳ አዲሱ ስራዋ ከራዲዮ የሚያርቃት ቢሆንም መዓዛ ግን ሳትሸነፍ ሬዲዮን በትርፍ ጊዜ ሥራነት ተያያዘችው፡፡ ሬዲዮ ጣቢያው የሚሠጣትን አነስተኛ ክፍያ እየተቀበለችም ልዩ ልዩ ጭውውቶችን እና መጣጥፎችን በግልና በጋራ በማቅረብ ተወዳጅ ሥራዎቿን ለሕዝብ አበርክታለች፡፡
መዓዛ ብሩ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መቼ ገባች?
በ1971 ዓ.ም
327
ደቡብ አፍሪካ በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ። ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውን፣ ብሉምፎንቴንና ፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው። ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው። የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ። የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካ የቬንዳ ቋንቋ በተናጋሪ ብዛት ስንተኛው ነው?
10ኛው
225
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጎ ያስገነባቸው አራት የአየር መቆጣጠሪያ ታወሮች ነገ እንደሚመረቁ ተገለጸ፡፡ ታወሮቹ የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል ባሌ ሮቤ ከተማ፣ በአማራ ክልል ኮምቦልቻ፣ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ እና በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ መሆኑን ከባለስልጣኑ ማህበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ለአየር መቆጣጠሪያ ስንት ታወሮች ገነባ?
አራት
57
ፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ "The Nation"፣ "The Chinese Recorder"፣ "Asia" እና "The Atlantic Monthly" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል።
ፐርል በክ ከ70 በላይ ስራዎቿን ለንባብ አቅርባ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው መቼ ነው?
በ1973 ዓ.ም
1,118
ዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
ዩጋንዳ በአፍሪካ በየት አቅጣጫ ትገኛለች?
በምስራቅ
27
መጠነ እንቅፋት የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት (ሬዚስታንስ) የሚባለው አንድ ኤሌክትሪክ አባል በውስጡ ሊያልፍ የሚሞክር የኤሌክትሪክ ጅረትን የሚያደናቅፍበት መጠን ልኬት ነው። የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት ከሰበቃ ጋር ተመሳሳይ ባህርይ አለው። የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት የተደረሰበት በ1819 ዓ፣ም በጆርጅ ኦም ሲሆን፤ በዚህ ሰው ጥናት መሰረት የአንድ ነገር ኤሌክትሪካዊ መጠነ እንቅፋት በዚያ ነገር ላይ ያለ የቮልቴጅ ለ በውስጡ የሚያልፍ ጅረት ሲካፈል ጋር እኩል ነው። በሒሳብ ቋንቋ፡ ለብዙ ቁሶችና ሁኔታዎች፣ የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት R ጸንቶ የሚቆይ ቋሚ ቁጥር ነው። ማለት በኤሌክትሪክ ጅረትና በቮልቴጅ መጠን አይቀየርም። እነዚህ ነገሮች ኦማዊ ቁሶች ይባላሉ። የአንድ ሽቦ መጠነ እንቅፋት መጠን በርዝመቱና በስፋቱ ይወሰናል። የሽቦው ርዝመት በጨመረ ቁጥር እንቅፋቱ እየጨመረ ይሄዳል፣ በአንጻሩ ስፋቱ ሲጨምር እንቅፋቱ ይቀንሳል። ልክ ውሃ በሰፊ ቱቦ ውስጥ በቶሎ ሊሄድ እንደሚችልና፣ በረጅም ቱቦ ውስጥ ብዙ ሰበቃ ስለሚገጥመው በቀስታ እንደሚጓዝ ሁሉ። ከዚህ በተጨማሪ የሽቦው መጠነ እንቅፋት ሽቦው ከተሰራበት ዕቃ ተፈጥሮ ጋር ይዛመዳል። ስለሆነም የአንድ ሽቦን መጠነ እንቅፋት በሒሳብ ለማስላት የሚከተለው ቀመር ይጠቅማል፡ ሽቦው የተሰራበት ቁስ ልዩ መጠነ እንቅፋት ሲሆን የሚለካውም በ ኦም-ሜትር ነው።
አንድ ኤሌክትሪክ አካል በውስጡ ሊያልፍ የሚሞክር የኤሌክትሪክ ጅረትን የሚያደናቅፍበት መጠን ልኬት ምን ይባላል?
የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት (ሬዚስታንስ)
10
ከ1936 ጀምሮ ኤርትራ የኢኮኖሚ እድገት ማሳየት ችሏል። በ30ዎቹ መጨረሻ 2፣198 የኢንደስትሪ ተቋሞች በአገሪቱ ተመስርተዋል። ይሁንና ጣሊያኖች አገሪቱ እራሷን እንድትችል ሳይሆን የነርሱ ጥገኛ እንድትሆን ነበር ያደረጉት፣ ለዚህ ሲሉ አብዛኛው ምርት ከውጭ ያስመጡ ነበር። ከ10-15% የሚሆነው የአገሬው ወንድ ሃይል በኢንደስትሪ፣ በእርሻና በጥቃቅን የተላላኪ ስራወች ተቀጥርው ይሰሩ ነበር። ከ1936-41 ድረስ አብዛኛውን የአግሬውን ወንድ ቀጥሮ ያሰራ የነበረው የቅኝ ገዥው ውትድርና ተቋም ነበር (40% ወይም 60፣000 ለአቅመ አዳም የደርሱ ወንዶችን)። እኒህ ወታደሮች ኢትዮጵያን ለመውረር ያገለገሉ ሲሆን ለዚህ ታማኝነታቸው ምክንያቱ ቅኝ ገዥወች በኤርትራ ላይ ያሰፈኑት ፖለቲካዊ መረጋጋት እንደምክንያት ይጠቀሳል። የጤና፣ የገበያ ኢኮኖሚ እንዲሁም ቁሳዊ ፍጆታ መስፋፋት በ1905ዓ.ም. 250 ሺህ ብቻ የነበረው የኤርትራ ህዝብ ወደ 614 ሺሕ በ1935 ዓ.ም. እንዲያድግ አድርጓል። ትግርኛ ተናጋሪው ክፍል በዚህ ጊዜ 54% የአገሪቱ ክፍል ነበር። እኒህ ለውጦች በአገሬው ላይ የስነ ልቦና ለውጥን አስከተሉ፣ ስለሆነም ከኢትዮጵያውያን ጐረቤቶቻቸው የተለዩ ህዝቦች የመሆን ማንነትን ፈጠረ። ሁለተኛው የአለም ጦርነትን ተከትሎ እንግሊዞች ከአንግሎ ግብጻዊ ሱዳን በመነሳት ጥር 1941 በኤርትራ ላይ ጥቃት አደረሱ። ከሶስት ወር በኋላ የከረን ጦርነትን በማሸነፍ ሚያዝያ 1941 ሙሉ ኤርትራን ተቆጣጠሩ። የእንግሊዝ ወታደራዊ አገዛዝ(BMA) በጣሊያኖች ምትክ አገሪቱን ማስተዳደር ጀመረ። 1947 ጣሊያን በፈረመችው የሰላም ውል መሰረት ኤርትራ ለአራቱ ሃይላት ተሰጠች። ከዚህ በኋላ ኤርትራ የጣሊያን ቅኝ መሆኗ አበቃላት።
በ1935 በኤርትራ የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ምን ያህል ነበሩ?
54%
582
ቢል ክሊንተን ያደጉት በሆት ስፕሪንግስ፣ አርካንሳው ነው። የቢል ክሊንተን አባት ዊሊያም ጄፈርሰን ብላይዝ ጁኚየር፣ ቢል ክሊንተን ከመወለዱ ሶስት ወር በፊት በመኪና አደጋ ሞተዋል። የቢል ክሊንተን እናት ቨርጂኒያ ክሊንተን ኬሊ፣ በ1950 እ.ኤ.ኣ. ሮጀር ክሊንተን የሚባል ሰዉ አገባች። 14 ዓመቱ ሲሆን ቢል ክሊንተን የመጨረሻ ስሙን ወደ ክሊንተን ለወጠ። ክሊንተን በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ፥ ዋሽንግተን ዲ.ሲ.፣ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ፥ ኢንግላንድ፣ እና ዬል ዩኒቨርሲቲ፥ ኮነቲኬት ተምረዋል። በ1975 እ.ኤ.ኣ. ሂለሪ ሮድሃምን አገቡና በሊትል ሮክ፥ አርካንሳው መኖር ጀመሩ። ከዚያም በዩኒቨርሲቴ ኦፍ አርካንሳው የሕግ ፐሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል። ቢል ክሊንተን የአርካንሳው አስተዳዳሪ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በ1978 እ.ኤ.ኣ. ነው። በዛ ጊዜ ከአሜሪካ በዕድሜ ትንሹ አስተዳዳሪ ነበሩ። በ1980 እ.ኤ.ኣ. በፍራንክ ዲ ዋይት ከተሸነፉ በኋላ በ1982 እ.ኤ.ኣ. እንደገና ተመረጡ። ከዛ ጀምሮ እስከ 1992 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ለአራት ጊዜ አስተዳዳሪ ሆነው መርተዋል። በ1984 እ.ኤ.ኣ. የአስተዳዳሪ የስልጣን ዕድሜ ከ2 ዓመት ወደ 4 ዓመት አራዝመዋል። በ1992 እ.ኤ.ኣ. ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድርው አሸንፈዋል። በ1996 እንደገና ተወዳድረው አሸንፈዋል።
ቢል ክሊንተን ወደዚህ ምድር ከመምጣታቸው ከስንት ጊዜ በፊት ነው አባታቸው የሞቱት?
ሶስት ወር
88
የመደመር መንገድ መጽሐፍ ሁለት ዓላማ ያነገበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ ይህም በአንድ በኩል ሐሳብ ማስተላለፍ በሌላ በኩል በገቢው ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ የመጽሐፉ የነጠላ መሸጫ ዋጋ 350 ብር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አንባቢዎች ሊዳረስ የሚችል በቂ ቅጅ ስላለ ከዚህ በላይ ከሚሸጡት እንዳይገዙም አሳስበዋል፡፡
የመደመር መንገድ መጽሐፍ ስንት ዓላማዎች አሉት?
ሁለት
16
ኃይሌ ገብረሥላሴ ኃይሌ ገብረሥላሴ በ ሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፷፭ (1965) ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ፣ አርሲ ክፍለ ሀገር የተወለደ አቻ ያልተገኘለት ድንቅ የረጅም ርቀት ኢትዮጵያዊ ሯጭ ነው። ኃይሌ በሩጫ ዘመኑ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ፣ በግማሽ ማራቶን፣ በማራቶንና እንዲሁም በሌሎቹ የሩጫ ዓይነቶች ከ ፲፩ በላይ የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብሯል። ኃይሌ በሩጫ ችሎታው ጠንካራ የሆነበት ምናልባትም ከመንደሩ ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ነው ተብሎ ቢታመንም የተፈጥሮ ጥንካሬው ዓለምን ያስደነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ኃይሌ ሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከመሆኑም በላይ በ፴፫ ዓመት ዕድሜው ፪ ሰዓት ከ፬ ደቂቃ በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለምን ማራቶን ክብረ-ወሰን ሊሰብር ችሏል። ኃይሌ ገብረሥላሴ እስካሁን ድረስ ፳፮ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን ሰብሯል። ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ በሲድኒ እና በአትላንታ ኦሊምፒኮች በ፲ ሺህ ሜትር ሩጫዎች ወርቅ አስመዝግቧል። በ ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. ኤንዱራንስ (Endurance) የተባለ ስለ እራሱ የእሩጫ ድል ፊልም ተሠርቷል።
ኃይሌ ገብረሥላሴ የተወለደው የት ሀገር ነው?
ኢትዮጵያ
105
የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ ስማርት ከተሞችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አንዱ ግብዓት መሆኑን ስማርት ሲቲ ፕረስ ያትታል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ኢትዮ ቴሌኮም ደምበኞች የዳታ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን ስማርት ምሰሶ በእንጦጦ ፓርክ ማስመረቁ ይታወሳል፡፡ የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ ከተለመዱት የመንገድ ዳር ምሰሶዎች ጋር የሚመሳሰል ነገር ግን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የያዘ ነው፡፡ ከሚሰጠው አገልግሎት መካከል አንዱ፥ ሰፊ አካባቢን መሸፈን የሚችል እጅግ ፈጣን የአራተኛ ትውልድ (4ጂ)፣ አምስተኛ ትውልድ ( 5ጂ) እና የዋይፋይ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ሌላው መኪና እና ታርጋን በቀላሉ መለየት የሚችሉ፣ የፊት ገፅታ ልየታን የሚያከናውኑ፣ ከፍተኛ የሆነ የቀለም ጥራት እና አጉልቶ የማሳየት አቅም ያላቸው የደህንነት ካሜራዎች ይኖሩታል፡፡ በተጨማሪም የአየር እና የድምፅ ብክለትን የሚለዩ፣ አደጋዎችን እና ወንጀሎችን በፍጥነት ለይቶ በመጠቆም የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ አሰጣጡን የሚያቀላጥፉ መጠቆሚያዎችን ይይዛል፡፡ እንዲሁም የመንገድ መጨናነቅ እና አደጋን የመሰሉ እንዲሁም ሌሎች የድንገተኛ ጊዜ መልዕክቶች የሚሰራጩበት ዲጂታል ስክሪንም የሚኖረው ይሆናል፡፡ የስማርት ምሰሶ አገልግሎቶች በዚህ ብቻ የተገደበ ሳይሆን “ሁሉን በአንድ” በሚለው የቴክኖሎጂው መርህ መሰረት ሰዎች ከያዙት መሳሪያ ጋር በቀላሉ ተናቦ ለሌሎች አገልግሎቶች እንደሚውል ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በእንጦጦ ፓርክ ያስመረቀው የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ ምን ጥቅም አለው?
ስማርት ከተሞችን ለመገንባት
17
የጥምቀት በዓል በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዓ/ም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ በዓል ነው። መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው። በአገራችን፣ ጥር ፲ ቀን፣ በከተራ፣ በገጠር ወራጅ ውሃ የሚከተርበት፣ ታቦታት ከየአቢያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በምዕመናን ታጅበው እየዘመሩ ይሄዳሉ። እዚያም በየተዘጋጀው ድንኳን እንዲያርፉ ተደርጎ ሌሊቱን እዛው ያሳልፋሉ።በከተሞች ግን ሰው ሰራሽ ግድብ ይሰራል። ጥር ፲፩ ቀን የጥምቀት ዕለት፤ በገጠር፣ ጎኅ ሲቀድ ምእመናን እዚያው በድንኳኑ ዙሪያ አስቀድሰው ሲጨርሱ በካህናት መሪነት ሁሉም ወደከተራው ያመራና ውሃውም ተባርኮ ሕዝቡ ይረጫል። «ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ፤ ሰማያዊው በመሬታዊው እጅ ተጠመቀ» የሚለው የዕለቱ ቀለም በሊቃውንቱ አንደበት በያሬዳዊ ዜማ ጎልቶ ይሰማል። ከዚህ ሥነ ሥርዓት በኋላ በመቋሚያ፣ በከበሮና በጽናፅል በሚታጀብ ኃይማኖታዊ ዝማሬ፣ ወንዱ በሆታ፤ ሴቱ በእልልታ፤ ካህኑ በሃሌታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየ ቤተክርሲያናቸው ይመለሳሉ። በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየጥምቀተ ባሕሩ የሚከበሩ በመኾናቸው፣ ሀገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብ በመፍጠሩ፣ ቱሪስቶችን መሳቡ አልቀረም። ጥቁርና ነጭ፣ ቀይና ብጫ ያለም ዘር፣ ከአዲስ አበባ እስከ ላሊበላ፣ ከአክሱም እስከ ጎንደር በሁሉም ሥፍራዎች በዚሁ ዓይነት ደምቆ ይከበራል። የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ ፍፁም በሚማርክ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁል ጊዜ አዲስ ነው። ሊቃውንቱ እንደሚናገሩት፣ ዘመነ አስተርእዮ የሚባለው፣ ከጥር ፲፩ ቀን ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አምላክ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር መታወቁ፣ በቃና ዘገሊላ በተደረገው ሠርግ ላይ የመጀመሪያው ተዐምር በመፈጸሙ፣ አምላካዊ ኃይሉ መገለጡ፣ እየታሰበ ምስጋና ይቀርባል። ይህ ሁነት ኢትዮጵያ ብሂልን ከባህል ጋር አዛምዳ ከሌላው የክርስቲያን ዓለም በተለየ አከባበር በዓሉን ማክበሯ፣ አያሌ ቱሪስቶችን ለመሳብ አስችሏታል።
የከተራ በዓል መች ይከበራል?
ጥር ፲ ቀን
201
ቶማስ ጄፈርሰን ቶማስ ጄፈርሰን (ሚያዝያ 7 ቀን 1735 ~ ሰኔ 28 ቀን 1818 ዓ.ም.) ከየካቲት 26 ቀን 1793 እስከ የካቲት 25 ቀን 1801 ዓ.ም. ድረስ የአሜሪካ 3ኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኚያን ያቋቋሙት ጄፈርሰንም ነበሩ። ቶማስ ጄፈርሰን ከአባቱ ከፒተር ጄፈርስን እና ከእናቱ ጄን ራንዶልፍ ተወለዱ። ቶማስ በአሜሪካ አብዮት ጊዜ በ1768 ዓ.ም. ከእንግሊዝ ንጉሥ የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ ጻፉ። በኋላ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመርከብ ሃያላት ወደ አልጀርስ ላኩ፣ ከናፖሌዎን ደግሞ ሰፊ መሬት በሚሲሲፒ ወንዝ አቅራቢያ (የሉዊዚያና አቅራቢያ የተባለው) ገዝተው ነበር። ይህ ድርጊት የአሜሪካ ስፋት በሁለት እጅ አስፋፋ።
ቶማስ ጄፈርሰን መቼ ሞቱ?
ሰኔ 28 ቀን 1818 ዓ.ም.
38
የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፳ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በብራዚል ይካሄዳል። ብራዚል ይህን ውድድር ስታዘጋጅ ይሄ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው። ፊፋ የ2014 እ.ኤ.አ. ውድድር በደቡብ አሜሪካ እንደሚካሄድ በ2007 እ.ኤ.አ. ካወጀ በኋላ ብራዚል ያለማንም ተቀናቃኝ አዘጋጅ አገር ሆና ተመርጣለች። የ፴፩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች ከጁን 2011 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮችን በማለፍ ከብራዚል ጋር በመጨረሻው ውድድር ላይ ለመሳተፍ በቅተዋል። በጠቅላላው ፷፬ ጨዋታዎች በ፲፪ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አዲስ የተገነቡ ወይም የተሻሻሉ ስታዲየሞች ይከናወናሉ። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎል ላይን ቴክኖሎጂ በጥቅም ላይ ውሏል። በ1930 እ.ኤ.አ. ከተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጀምሮ ሁሉም የዓለም ዋንጫ ሻምፕዮን አገራት (ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን፣ ኢጣልያ፣ እስፓንያ እና ኡራጓይ) በዚህ ውድድር ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። ከዚህ በፊት በደቡብ አሜሪካ የተዘጋጁትን ዋንጫዎች እንዳለ የወሰዱት የደቡብ አሜሪካ ቡድኖች ናቸው። ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $576 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2010 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የ፴፯ ከመቶ ዕድገት አለው። ከዚህ ውስጥ $70 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1.5 ሚሊዮን የተረከበ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ እንደሚመለከተው ተከፋፍሏል፦ $8 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በምድብ ደረጃ የወደቀ ቡድን (፲፮ ቡድኖች) $9 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በየ፲፮ ዙር የወደቀ ቡድን (፰ ቡድኖች) $14 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በሩብ ፍፃሜ የወደቀ ቡድን (፬ ቡድኖች) $20 ሚሊዮን - በአራተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $22 ሚሊዮን - በሶስተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $25 ሚሊዮን - በሁለተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $35 ሚሊዮን - ለአሸናፊው ቡድን በአስራ ሁለት ከተማዎች የሚገኙ አስራ ሁለት ስታዲየሞች ለውድድሩ ተዘጋጅተዋል። ሰባቱ አዲስ የተገነቡ ሲሆን አምስቱ ደግሞ የተሻሻሉ ስታዲየሞች ናቸው።
የ2014 እ.ኤ.አ. የፊፋ የዓለም ዋንጫ ስንተኛው ነው?
፳ኛው
50
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ በጥሩ ጎናቸው ከሚነሱ የቅርብ ጊዜያት ተጫዋቾች መካከል አዳነ ግርማ ይገኝበታል።ተጫዋቹ በበርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታንም ይዟል።አዳነ ግርማ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን መነቃቃት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ተጫዋቹ በብሄራዊ ቡድኑ ውስጥ ለ10 ዓመታት በመጫወትም አንጋፋ ለመሆን በቅቷል። አዳነ ግርማን ስናስብ ሁለት ጨዋታዎች ሁሌም ከፊታችን ድቅን ይላሉ።ደቡብ አፍሪካ ላስተናገደ ችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡደን ከሱዳን አቻው ጋር ሲጫወት በግንባሩ ገጭቶ ያስቆጠራት ግብ መቼም ቢሆን አዳነ እንዲታወስ ያደረገችም የምታደርግ ናት።ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ያረገችው ወሳኝ ግብም ሆናለች። በአፍሪካ ዋንጫው ከ 39 ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛምቢያ ላይ ያስቆጠራት ግብም አዳነን ሁሌም እንድናስበው ያረገች ሌላዋ ግቡ ናት። ተጫዋቹ ከዋልያዎቹ ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገና የቡድኑ ምሰሶ እንደነበርም ይታወቃል።በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዘመን አዳነ ቡድኑን በአምበልነት መርቷል። የአትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከሰውነት ቢሻው የተረከቡት አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ቡድኑን እንደ አዲስ ሲያዋቅሩ አዳነ ግርማን መቀነሳቸው ሲሰማ በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ ቅሬታ ቢፈጠርም፣ ተጫዋቹ ግን ውሳኔውን አሜን ብሎ ነው የተቀበለው። በወቅቱም አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ለተጫዋቹ መቀነስ ምክንያታቸው ያደረጉት የተጫዋቹ «ብቃትና አቅም ወርዷል» የሚል ነው። ተጫዋቹ ግን በወቅቱ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ያረጋገጠው ምንም አይነት የአቋም መዋዠቅም እንደሌለበት ነው። የብቃት መውረድ እንዳላሳየም ገልጿል። የመቀነሱ ሚስጥር ለሱም እንቆቅልሽ እንደሆነበት ነበር ያስታወቀው። ይህን ተከትሎ ራሱን ከብሄራዊ ቡድን ያገለለው አዳነ በአዲሱ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሰሞኑን ጥሪ ተደርጎለት ነበር:: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄሪያ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ በአጥቂ እጥረት ላይ ቢገኝም አዳነ ግርማ ከቤተሰቦቼ ጋር ተመካክሬ የወሰንክይት ውሳኔ ነው በሚል ለብሔራዊ ቡድኑ እንደማይጫወት አስታውቋል:: በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሁለት የተደለደለውና በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአልጀሪያ አቻው ጋር ላለበት የምድቡ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን መጥራቱ ይታወሳል። አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ሁለት ተጫዋቾችን ከአገር ውጭ ቀሪዎቹን 22 ደግሞ ከአገር ውስጥ ሊጎች የመረጡ ቢሆንም የአዳማ ከነማው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ባጋጠመው ጉዳት ከቡድኑ ውጭ ሆኗል። እርሱን ለመተካት ሳልሃዲንና አዳነን ቢጠሩም እምቢ ተብለዋል:: ሆኖም ግን አሰልጣኙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የመረጧቸውን አምስት ተጫዋቾችና ከአገር ውጭ ከሚጫወቱት ሕመልስ በቀለና ጌታነህ ከበደ በስተቀር 15 ተጫዋቾችን ይዘው ልምምዳቸውን ዛሬ ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከ39 ዓመታት በኋላ ስንተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳተፈ?
29ኛው
279
የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፱ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የነበረ ሲሆን ከሰኔ ፬ እስከ ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ተካሄዷል። ውድድሩን ለማቅረብ የተካሄደው ዕጣ ውስጥ የአፍሪካ ሀገሮች ብቻ እንዲሳተፉ ነበር የተፈቀደው። ደቡብ አፍሪካ ግብፅና ሞሮኮን በማሸነፍ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫን ያቀረበች አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $420 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2006 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የስልሳ ከመቶ ዕድገት አለው። ከዚህ ውስጥ $40 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1 ሚሊዮን ተረከበ። ግጥሚያዎቹ በዘጠኝ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አስር ስታዲየሞች ውስጥ ነው የተካሄዱት። የዋንጫ ጨዋታው በጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኘው ሶከር ሲቲ ስታዲየም ነው የተከናወነው። የምድብ ድልድል ሥነ ስርዓቱ በኬፕ ታውን፣ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ኬፕ ታውን ዓለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል በኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ተከናወነ። ሥነ ስርዓቱ የቀረበው በደቡብ አፍሪካዊቷ ተዋናይ ሻርሊዝ ቴሮን እና የፊፋ ዋና ጸሐፊ ዠሮም ቫልክ ነው። የዕጣ ኳሶቹን ያወጡት ዴቪድ ቤክሃም፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ጆን ስሚት፣ መካያ ንቲኒ፣ ማቲው ቡዝ እና ሲምፊዌ ድሉድሉ ናቸው። የፊፋ ዳኛዎች ኮሚቴ ፳፱ ዳኛዎችን ለዓለም ዋንጫ መርጧል። እነዚህም ከኤ.ኤፍ.ሲ. አራት፣ ከካፍ አስር፣ ከኮንሜቦል ስድስት፣ ከኮንካካፍ አራት፣ ከኦ.ኤፍ.ሲ. ሁለት እና ከዩኤፋ አስር ዳኛዎችን ያጠቃልላል። እንግሊዛዊው ዳኛ ሀዋርድ ዌብ የዋንጫ ጨዋታውን እንዲዳኝ ተመርጧል።
የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ የፊፋ ዓለም ዋንጫን ያዘጋጀች ሀገር ማን ናት?
ደቡብ አፍሪካ
106
ሳህሌ ደጋጎ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል። በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ መሆኑን የሕይወት ታሪኩ ላይ ተጠቅሷል። ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ (በተቋቋመ ጊዜ ) በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁር ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር። ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ፣ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል።
ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ የት ተወለዱ?
በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ
77
ዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘውድ እንደጫኑ የአገሪቱን የመጀመሪያ ሕገ-መንግሥት እንዲዘጋጅ አዝዘው በዘውዱ አንደኛ ዓመት በዓል ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. በአዲሱ ምክር ቤት (ፓርላማ) ለሕዝብ ቀረበ። ከዚህም በላይ ብዙ የቴክኖዎሎጂ ስራዎችና መሻሻያዎች ወደ ኢትዮጵያ ከውጭ አገር አስገቡ። በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. የሙሶሊኒ ፋሺስት ሠራዊት ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ጃንሆይ ሕዝባቸውን ወራሪውን በሙሉ ለመቃወም እንዳስነሡና የከተት ዐዋጆቻቸው በታሪክ ገጾች ይዘገባሉ። በዐዋጅ መሠረት የዘመቻው ጊዜ እስቲያልቅ ድረስ ለሚታግሉ ነጋዶች ከቀረጥ አስተስርየት ሰጣቸው። እራሳቸው በቆራጥነት ከታገሉ በኋላ የጠላቱ ጦር ኅይል ግን በመጨረሻ ወደ እንግሊዝ አገር ለጊዜው አሰደዳቸው። ወደ ጄኔቭ ስዊስ ወደ ዓለም መንግሥታት ማኅበር ሄደው ስለ ጣልያኖች የዓለምን እርዳታ በመጠየቅ ተናገሩ። የዓለም መንግሥታት ግን ብዙ አላደረጉም። በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ግን አውሮፓ ሁሉ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተያዘ። የእንግሊዝ ሠራዊቶች ለኢትዮጵያ አርበኞች እርዳታ በመስጠት ጣልያኖች ተሸንፈው በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ኢትዮጵያን ተዉ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ አዲስ አበባን እንደገና የገቡበት ቀን ከወጡበት ቀን በልኩ ዕለት አምስት ዓመት በኋላ ነበረ። ከዚህ በኋላ በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የሕዝቦችን መብቶችና ተከፋይነት በመንግሥት አስፋፍቶ ሁለቱ ምክር ቤቶች እንደመረጡ አደረገ። በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ግርማዊነታቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአዲስ አበባ እንዲመሠረት ብዙ ድጋፍ ሰጡ። በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ወደ ካሪቢያን ጉብኝት አድርገው የጃማይካ ራስታዎች ተገኛኙ። በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. በማርክሲስት አብዮት ደርግ ሥልጣን ያዙና እሳቸው በእሥር ቤት ታሰሩ። በሚከተለው ዓመት ከተፈጥሮ ጠንቅ እንደ አረፉ አሉ ፤ ሆኖም ለምን እንደ ሞቱ ስለሚለው ጥያቄ ትንሽ ክርክር አለ። ብዙ ራስታዎች ደግሞ አሁን እንደሚኖሩ ይላሉ። የዓፄ ኃይለ ሥላሴ የትውልድ ስም ልጅ ተፈሪ መኮንን ነው። ስመ-መንግሥታቸው ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነበር። ሞዓ አንበሣ ዘእምነገደ ይሁዳ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የሚለው የሰሎሞናዊ ሥረወ-መንግሥት ነገሥታት መጠሪያም በንጉሠ-ነገሥቱ አርማ እና ሌሎች ይፋዊ ጽሑፎች ላይ ከመደበኛው ማዕረግ ጋር ይጠቀስ ነበር። ጃንሆይ ፣ ታላቁ መሪ እና አባ ጠቅል በመባልም ይታወቁ ነበር።
በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያው ሕገ መንግሥት እንዲዘጋጅ የተደረገው በማን ነበር?
ዓጼ ኃይለ ሥላሴ
0
ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ እንግሊዝ ሀገር አንደደረሰም የወቅቱ የእንግሊዝ ንግስት ከነበረችው ንግስት ቪክቶሪያ ጋር ተገናኘ፡፡ ንግስቲቱም ልዑሉ የፈለገው እና ያሻው ይደረግለት ዘንድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡ ልዑሉ በመቅደላ የነበረውን እልቂት በመጠኑም ቢሆን በማየቱ እና የአባቱ እና የእናቱ ተከታታይ ሞትም በልጅ አዕምሮው ሊቀበለው ከሚችለው በላይ ስለነበር እጅግ ታውኮ እንደነበር በተደጋጋሚ ተፅፎ እናገኛለን፡፡ በ1861 ዓ.ም ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ አንዲት ከተማ አዛዥ ሆኖ ስለተሾመ የ8 ዓመቱን አለማየሁን እና ሚስቱን ይዞ ወደዛው አቀና፡፡ በሄዱበት ሀገርም አለማየሁ ትምህርቱን መከታተሉን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን ከመደበኛው ትምህርት በዘለለም ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንም ያዘወትር ነበር፡፡ 1867 ዓ.ም አለማየሁ ወደ ራግቢ ትምህርት ቤት ተዛወረ፡፡ በዚህም ከቄስ ብሌክ ቤት ወጥቶ ወደ ሊው ዋርነር ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በዚህ ግን ደስተኛ ስላልነበር በቀጣዩ አመት ሚስተር ድራፐር ቤት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ቄስ ብሌክም ካዩት የልዑሉ ባህሪ በመነሳት ልዑሉ ወታደርነት ላይ ቢያተኩር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ በዚህም ንግግር መሰረት የወታደር ትምህርት ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በአንድ ወቅት አለማየሁ ወደ ሊድስ በመሄድ በሰር ራምሰን ቤት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት በመርዝ ተመረዘ። መርዙ ህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከሩብ በተወለደ በ19 ዓመቱ ከዚህ አለም እንዲሰናበት አደረገው፡፡ አስከሬኑም ዊንድሶር ባለው የነገስታት መቀበርያ በክብር አረፈ፡፡ በመቃብሩም ላይ “የሀበሻው ልዑል አለማየሁ” የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበት እስካሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል፡፡
በልዑል አለማየሁ መቃብር ላይ ምን ተብሎ ነው ፅኁፍ የተፃፈለት?
“የሀበሻው ልዑል አለማየሁ”
895
ስዋሂሊ ስዋሂሊ ፡ (ወይም ፡ ኪሷሂሊ Kiswahili) ፡ በምሥራቅ ፡ አፍሪቃ ፡ የሚናገር ፡ የባንቱ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የስዋሂሊ ፡ ሕዝብ (፭ ፡ ሚሊዮን ፡ ተናጋሪዎች) ፡ ልደት ፡ ቋንቋ ፡ ከመሆኑ ፡ በላይ ፡ ለ ፴ ፡ እስከ ፡ ፶ ፡ ሚሊዮን ፡ ሌሎች ፡ ሰዎች ፡ ሁለተኛ ፡ ቋንቋ ፡ ሆኗል። የስዋሂሊ ፡ ስም ፡ መነሻ ፡ ከዓረብኛ ፡ ቃል ፡ «ሰዋሂል» ፡ ነበር ፤ ይህም ፡ የ«ሳኸል» ፡ (ማለት ፡ ዳር) ፡ ብዙ ፡ ቁጥር ፡ ነው። ስለዚህ ፡ የ«ስዋሂሊ» ፡ ትርጉም ፡ የ(ባሕር) ፡ ዳረኞች ፡ ቋንቋ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል። የቋንቋው ፡ ቤተሰብ ፡ ባንቱ ፡ ሲሆን ፡ ተናጋሪዎቹ ፡ መርከበኞችና ፡ ነጋዴዎች ፡ በመሆናቸው ፡ መጠን ፡ ከዓረብኛ ፣ ከፋርስ ፣ ከህንዲ ፣ እና ፡ ከቻይንኛ ፡ ቢሆንም ፡ ብዙ ፡ ቃሎች ፡ ተበድረዋል።
የስዋሂሊ ቋንቋ የአፍ መፍቻቸው የሆኑ ምን ያህል ሕዝቦች አሉ?
፭ ፡ ሚሊዮን
105
አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ በሃገራችን ኢትዮጵያ ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅ እና ቅድስት እድና ይባላሉ ። የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው ። ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረአምላክ ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ። በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል። "የት ልሒድ?" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለስምንት ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየኋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከስምንቱ ጋር ከቃልኬዶን ጉባዔ በኋላ በ፬፻፶፩ ዓም ወደ ኢትዮጵያ መጡ ። ከዘጠኙ ቅዳሳን ወደ ኢትዮጵያ ከሮምና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከፈለሱት አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው ። በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል ። አቡነ አረጋዊ ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል ። በመጨረሻም ደብረ ዳሞ ማረካቸዋለች ። ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል ፡፡
ለአቡነ አረጋዊ ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም ማን ይባላል?
ዘሚካኤል
188
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012(ኤፍቢሲ) ቻይና በዋና ከተማዋ ቤጂንግ እና በሀቤይ ግዛት ዘሃንግጃኩ መካከል የተዘረጋውን ፈጣን ባቡር ለገልግሎት ክፍት ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል። ቻይና የፈጣን ባቡሩን ለአገልግሎት ክፍት የምታደርገው በአውሮፓውያኑ 2022 የምታስተናግደውን የክረምት ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ተነግሯል። ፈጣኑ ባቡር በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን፥ በዓለማችን ላይ የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ ባቡር እንደሚሆንም ተነግሮለታል። የ 174 ኪሎ ሜትር ያለው የባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቱ ለ2022 የክረምት ኦሎምፒክ እና የፓራሎምፒክ  ታስቦ የተሰራ መሆኑም ታውቋል። የባቡር መስመሩ የክረምት ኦሎምፒኩን በሚያስተናግዱት በሁለቱ ከተሞች መካከል የነበረውን የ3 ሰዓት መንገድ ወደ 47 ደቂቃ የሚቀንስ መሆኑ የቻይና ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል። ምንጭ፦ newsus.cgtn.com
ቻይና በክረምቱ ኦሎምፒክ ምክንያት ለአገልግሎት ክፍት የምታደርገው ፈጣን ባቡር በሰዓት ምን ያህል ኪ.ሜ ይጓዛል?
350 ኪሎ ሜትር
224
አዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።
እቴጌ ጣይቱ አዲስ አበባ የሚለውን ስም ለከተማዋ የሰጡት መች ነበር?
ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም.
36
አዳኝ አንበሶች በጣም ቀልጣፋና ፈጣን ቢሆኑም እንኳ በአደን ጊዜ የሚሳካላቸው 30 በመቶ ብቻ ነው። በመሆኑም አንበሶች ከተደቀኑባቸው ትልልቅ አደጋዎች አንዱ ረኃብ ነው። ለአካለ መጠን የደረሰ አንድ አንበሳ ያለው ጥንካሬ እጅግ የሚያስገርም ነው። በቤተሰብ ደረጃ የሚያድኑ እንደ መሆናቸው መጠን ከ1,300 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያላቸውን እንስሳት የመጣልና የመግደል አቅም እንዳላቸው ይነገራል። አንበሶች በመጀመሪያ ላይ በሰዓት እስከ 59 ኪሎ ሜትር ድረስ ሊሮጡ ይችላሉ፤ ሆኖም ይህ ፍጥነታቸው እስከ መጨረሻ አይዘልቅም። በዚህ ምክንያት ቀለባቸውን ለማግኘት አድብቶ የመያዝ ዘዴ ይጠቀማሉ። የማደኑን ተግባር 90 በመቶ የሚያከናውኑት ሴቶቹ አንበሶች ቢሆኑም በሚበሉበት ጊዜ ትልቁን ድርሻ የሚያገኙት ትልልቆቹ ወንድ አንበሶች ናቸው። አደን በሚጠፋበት ጊዜ አንዳንዴ አንበሶች በጣም ስለሚርባቸው ያገኙትን መብል ለራሳቸው ግልገሎች እንኳ ለማካፈል ፈቃደኛ አይሆኑም። ታዳኝ ከብዙ ዓመታት በፊት ባለ ግርማ ሞገሱ አንበሳ በመላው የአፍሪካ አህጉር እንዲሁም በእስያ፣ በአውሮፓ፣ በህንድና በፍልስጤም አንዳንድ ቦታዎች ይገኝ ነበር። አዳኝ እንደመሆኑ መጠን ሰውን እየተቀናቀነ የሚኖር እንስሳ ነው። በከብቶች ላይ አደጋ የሚጥልና በሰዎች ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ አንበሳ ገና እንደታየ በጥይት የሚገደል ፍጡር ሆነ። የሕዝብ ቁጥር ፍንዳታ የአንበሳን መኖሪያ በእጅጉ አመናምኖታል። ዛሬ ከአፍሪካ ውጪ ባለው የዓለም ክፍል በዱር የሚኖሩት አንበሶች በጥቂት መቶዎች ብቻ የሚቆጠሩ ሆነዋል። በአሁኑ ጊዜ አንበሶች ሰው ከሚያደርስባቸው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተጠብቀው መኖር የሚችሉት ጥበቃ በሚደረግባቸው ክልሎች ውስጥና በዱር አራዊት መጠበቂያ ቦታዎች ብቻ ሆኗል። አንበሳ ሲያገሣ አንበሶች በሚያገሡበት ጊዜ በብዙ ኪሎ ሜትር ርቀት ሊሰማ የሚችል ከፍተኛ ድምፅ የማውጣት ልዩ ችሎታ አላቸው። አንበሳ ሲያገሣ የሚያሰማው ድምፅ “እጅግ ማራኪ ከሆኑት የተፈጥሮ ድምፆች” አንዱ እንደሆነ ይነገራል። ብዙውን ጊዜ አንበሶች በጨለማ ሰዓትና ንጋት ላይ ያገሣሉ። ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ አንበሶች የሚያገሡ ሲሆን አንዳንዴም የመንጋው አባላት በአንድነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያገሣሉ። በአንበሶች ላይ ጥናት የሚያካሂዱ ሳይንቲስቶች አንበሶች የሚያገሡባቸው የተወሰኑ ምክንያቶች እንዳሉ ይናገራሉ። ወንዶቹ አንበሶች የሚኖሩበትን ክልል ድንበር ለማሳወቅ እንዲሁም ሌሎች ወንድ አንበሶች ወደ ክልላቸው እንዳይገቡ ለማስጠንቀቅ ሲሉ ያገሣሉ። በርቀት ወይም በጨለማ ተነጣጥለው ያሉ የአንድ መንጋ አባላት ያሉበትን ቦታ ለመጠቆም ያገሣሉ። በተጨማሪም አንድ እንስሳ ከገደሉ በኋላ ለሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት ምግቡ ያለበትን ቦታ ለማሳወቅ ያገሣሉ። አንበሶች በሚያድኑበት ጊዜ የሚያድኗቸውን እንስሳት ለማስደንበር ብለው አያገሡም። ሪቻርድ ኤስቲዝ ዘ ቢሄቭየር ጋይድ ቱ አፍሪካን ማማልስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “አንበሶች የሚያድኑትን እንስሳ ለማጥመድ ሲሉ ሆን ብለው እንደሚያገሡ የሚጠቁም ምንም ነገር የለም (በተሞክሮዬ እንዳየሁት በአንበሳ የሚታደኑ እንስሳት አንበሳ ለሚያሰማው የግሣት ድምፅ ብዙም ትኩረት አይሰጡም)።
አንድ እንስሳ ከገደሉ በኋላ ለሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት ምግቡ ያለበትን ቦታ ለማሳወቅ አንበሶች ምን ያደርጋሉ?
ያገሣሉ
1,506

አዳኝ አንበሶች በጣም ቀልጣፋና ፈጣን ቢሆኑም እንኳ አደን ጊዜ የሚሳካላቸው ስንት በመቶ ነው?
30 በመቶ ብቻ ነው
49
አልፍሬድ ኢልግ ቢትወደድ አልፍሬድ ኢልግበዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ኑሮውን ኢትዮጵያ ውስጥ የመሠረተ፤ የስዊትዘርላንድ ዜጋ ነበር። ኢልግ በምሕንድስና ሙያው ባቡር እና የቧንቧ ውሐ ለአገራችን ካስተዋወቃቸው ብዙ ዘመናዊ የሥልጣኔ መስመሮች ሁለቱ ሲሆኑ በንጉሠ ነገሥቱ ፊት ታላቅ ታማኝነትን በማፍራቱ የዘውድ አማካሪ እና የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ እስከመምራትም የበቃ ሰው ነበር። ቢትወደድ ኢልግ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ሚና ከተጫወቱ አውሮፓውያን መሃል ባገሪቱ ባሳለፋቸው ሃያ ሰባት ዓመታት እና ባስቀመጣቸው የልማት አሻራዎቹ የታሪክ ሥፍራው በጣም የጎላ ሆኖ እናገኘዋለን። ኢልግ በስዊትዘርላንድ፣ ፍራውንፌልድ በሚባል ከዙሪክ ከተማ በሰሜን-ምሥራቅ አቅጣጫ በሚገኝ ሥፍራ በ መጋቢት ወር ፲፰፻፵፮ ዓ/ም ተወልዶ በስድሳ ሁለት ዓመቱ የገና ዕለት (ታሕሣሥ ፳፱ ቀን) ፲፱፻፰ ዓ/ም ዙሪክ ላይ በልብ ምታት ምክንያት አረፈ። ታዋቂው የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ዳግማዊ ምኒልክ ገና በልጅነታቸው የዓፄ ተዎድሮስ እስረኛ በነበሩ ጊዜ ቴዎድሮስ አጠገባቸው የነበሩትን አውሮፓዊ ወንጌላያን መድፍና መሣሪያዎች እንዲሠሩላቸው ማግባባታቸውን ልብ አድርገው ነበርና የሸዋ ንጉሥ ሲሆኑ በ ኤደን ላይ የነበረ አንድ የስዊትዘርላንድ ዜጋ ነጋዴ ምሕንድስና የሚያውቁ አውሮፓውያን ባለሙያዎችን እንዲፈልግላቸው ጠይቀውት ነበር ይላል። ኢልግ እና ሁለት የአገሩ ሰዎች በ፲፰፻፸ ዓ/ም አካባቢ ጉዞዋቸውን ወደኢትዮጵያ አምርተው ሸዋ ሲገቡ ንጉሥ ምኒልክ መጫሚያ እንዲሠራላቸው ያዙትና ሠርቶ ባበረከተላቸውም መጫሚያ እጅግ እንደተደሰቱ ይነገራል። በሌላ ዘገባ ደግሞ ንጉሡ ኢልግን ጠመንጃ እንዲሠራላቸው አዘዙት። ኢልግ ጠመንጃ ለመሥራት ሙያ እንደሌለውና ከውጭ የሚመጣ መሣሪያ እሱ ከሚሠራው እጅግ የላቀ እንደሚሆን ቢያስረዳም፤ ምኒልክ ኃሳባቸውን የማይለውጡ ሆኑ። እሱም እንደተጠየቀው የሙከራውን ውጤት ሲያሳቸው ንጉሡ ተደስተው ይሄንኑ ጠመንጃ በግምጃ ቤታቸው የክብር ቦታ ሰጡት። ያም ሆነ ይህ ኢልግ በንጉሡ በኩል ዘለቄታ የነበረው የበጎ አስተያየትን እንዳተረፈ ግልጽ ነው። ወዲያው በምሕንድስና ሥራ በደሞዘኝነት ቀጥረውት በየወሩ ሰባት ወይም ስምንት ፓውንድ በጠገራ ብር ይከፍሉት እንደነበር ፓንክኸርስት ዘግቧል።
ኢልግ በደሞዘኝነት ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረው የስራ ዘርፍ ምንድን ነው?
በምሕንድስና ሥራ
1,183
ፍቅር እስከ መቃብር ፍቅር እስከ መቃብር በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያትን ፍቅር ይተርካል። ይህ ድርሰት ከሌሎች ልብወለድ ሥራዎች ለየት የሚያደርገው ደራሲው ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በፊደል አጠቃቀም ላይ ለውጥ አድርገው በማቅረባቸው ነው። ይኸውም ለምሳሌ ያህል ሦስት «ሀ»ዎች፣ ሁለት «ሰ»ዎች፣ ሁለት «ኣ»ዎች የመሳሰሉትን እንደ አንድ ወይም የመጀመሪያውን ብቻ በመያዝ ነው። በተጨማሪም ጠብቀው በሚነገሩ ቃላት ላይ ከላይ አንድ ነጥብ በማስቀመጥ ይታወቃሉ።ሀዲስ ኣለማየሁ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሑፍ የራሳቸው ትልቅ አሻራ አኑረው ያለፉ አንጋፋ ደራሲ ናቸው። የታሪኩ ማጠቃለያ በዛብህ‌ ‌ጎጃም‌ ‌ማንኩሳ‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከእናቱ‌ ‌ከውድነሽ‌ ‌በጣሙና‌ ‌ከአባቱን‌ ‌ከቦጋለ‌ ‌መብራት‌ ‌ይወለዳል።‌ ‌በሽታ‌ ‌ይበዛበትና‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይባላል።‌ ‌እናቱ‌ ‌ከበሽታው‌ ‌እንዲድን‌ ‌ስእለት‌ ‌ይሳላሉ።‌ ‌ዕድል‌ ‌ሆኖ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይተርፋል፤‌ ‌አድጎ‌ ‌ጎበዝ‌ ‌ልጅ‌ ‌ይሆናል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌በሽታ፣‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ዕውቀትና‌ ‌ፍቅር‌ ‌(የሰው‌ ‌መውደድ)‌ ‌ይበዛበታል።‌ ‌በወጣትነቱ‌ ‌ይቀድስና‌ ‌ለቤተሰቡ‌ ‌ገንዘብ‌ ‌ማምጣት‌ ‌ይጀምራል።‌ ‌ቀድሞ‌ ‌የስእለት‌ ‌ልጅ‌ ‌መባልን‌ ‌አይጠላም‌ ‌ነበር።‌ ‌ሲያድግ‌ ‌ግን‌ ‌ትርጉሙን‌ ‌በመረዳቱ‌ ‌ነጻነቱን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌ዲማን‌ ‌ጥሎ‌ ‌ወደደብረ‌ ‌ወርቅ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌እዚያም‌ ‌ከእመት‌ ‌ጠጂቱ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይጠጋል።‌ ‌ትንሽ‌ ‌ዜማና‌ ‌ቅኔም‌ ‌ይማራል።‌ ‌ደብተራ‌ ‌በየነ‌ ‌መጥቶ‌ ‌የወላጆቹን‌ ‌ሞት‌ ‌ሲያረዳው‌ ‌ወደዲማ‌ ‌ይወርዳል።‌ ‌በተክለ‌ ‌አልፍአው‌ ‌በዓል‌ ‌በመልካም‌ ‌ድምጹ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻንና‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትን‌ ‌ያወድሳል።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻም‌ ‌የሰብለ‌ ‌መምህር‌ ‌አድርገው‌ ‌ይቀጥሩታል።‌ ‌ሰብለና‌ ‌በዛብህ‌ ‌የሕይወት‌ ‌ገጠመኞቻቸው‌ ‌በመጠኑ‌ ‌ስለሚመሳሰል‌ ‌ይግባባሉ።‌ ‌በመሃል‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌አሰጋኸኝ‌ ‌ሰብለን‌ ‌በፈት‌ ‌ወግ‌ ‌አገባለሁ‌ ‌በማለቱ‌ ‌በርሱና‌ ‌በፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌መካከል‌ ‌ጥል‌ ‌ተፈጠረ፤‌ ‌ሆኖም‌ ‌በሃይማኖት‌ ‌ጣልቃገብነት‌ ‌ሳይዋጉ‌ ‌ቀሩ።‌ ‌ከዚያም‌ ‌ደግሞ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከባላገሮች‌ ‌ጋራ‌ ‌በግብር‌ ‌ጉዳይ‌ ‌ተጣሉ።‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ተማርከው‌ ‌ሳለ‌ ‌የበዛብህንና‌ ‌የሰብለወንጌልን‌ ‌የፍቅር‌ ‌ዜና‌ ‌ይሰማሉ።‌ ‌ወዲያውም‌ ‌መጥተው‌ ‌ሰብለን‌ ‌በሌሊት‌ ‌ያስሯታል።‌ ‌የሰብለ‌‌አጎት‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ሁለቱን‌ ‌ለማስመለጥ‌ ‌ወጣ፣‌ ‌ወረደ።‌ ‌የዕጣ‌ ‌ነገር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ግን‌ ‌ሳይሳካ‌ ‌ቀረ።‌ ‌በዛብህ‌ ‌ግን‌ ‌በግራጌታ‌ ‌ቀለመወርቅና‌ ‌በጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጥረት‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ይሄዳል።‌ ‌በራጉኤል‌ ‌ቤተክርስቲያንም‌ ‌የቅኔ‌ ‌መምህር‌ ‌ሆኖ‌ ‌ይቀጠራል።‌ ‌ባደረጉላቸው‌ ‌ውለታ‌ ‌ምክንያት‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌መሸሻ‌ ‌ሰብለን‌ ‌ለፊታውራሪ‌ ‌ታፈሰ‌ ‌ሊድሯት‌ ‌ይሞክራሉ።‌ ‌የሰብለን‌ ‌አቋም‌ ‌አውቀው‌ ‌አባ‌ ‌ተክለሃይማኖት‌ ‌በተባሉ‌ ‌መነኩሴ‌ ‌ያስጠብቋቷል።‌ ‌መነኩሴው‌ ‌ግን‌ ‌ሰክረው‌ ‌ሰብለ‌ ‌ታመልጣለች።‌ ‌ፍለጋ‌ ‌ሲሄዱ‌ ‌ፊታውራሪ‌ ‌ከፈረስ‌ ‌ላይ‌ ‌ተወርውረው፣‌ ‌ተንኮታክተው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ወይዘሮ‌ ‌ጥሩአይነትም‌ ‌ቤተክርስቲያን‌ ‌ውስጥ‌ ‌ከደረጃ‌ ‌ላይ‌ ‌ተንሸራትተው‌ ‌ወድቀው‌ ‌ይሞታሉ።‌ ‌ሰብለ‌ ‌ደግሞ‌ ‌በዛብህን‌ ‌ለማግኘት‌ ‌መነኩሴ‌ ‌መስላ‌ ‌ወደአዲስ‌ ‌አበባ‌ ‌ትሄዳለች።‌ ‌ደርሳም‌ ‌በዛብህ‌ ‌አለመኖሩን‌ ‌ትሰማና‌ ‌ጎሃጽዮን‌ ‌ትወርዳለች።‌ ‌በዚያም‌ ‌በዛብህ‌ ‌ተደብድቦ፣‌ ‌ነፍስ‌ ‌ውጪ‌ ነፍስ‌ ‌ግቢ‌ ‌አይነት‌ ‌ሁኔታ‌ ‌ላይ‌ ‌ሳለ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌እንደምንም‌ ‌ብለው‌ ‌ሥጋ‌ ‌ወደሙን‌ ‌ይቀበላሉ።‌ ‌ጥቂት‌ ‌ቆይቶ‌ ‌በዛብህ‌ ‌ይሞታል።‌ ‌ሰብለም‌ ‌መንኩሳ፣‌ ‌የበዛብህን‌ ‌አስከሬን‌ ‌ባጠገቧ‌ ‌አድርጋ‌ ‌ስትኖር‌ ‌ከጉዱ‌ ‌ካሳ‌ ‌ጋራ‌ ‌ይገናኛሉ።‌ ‌ጉዱ‌ ‌የተሰኘው‌ ‌ካሳ‌ ‌ዳምጤም‌ ‌እርሷ‌ ‌ዘንድ‌ ‌ይቀመጣል።‌ ‌አስራ‌ ‌አምስት‌ ‌ቀናት‌ ‌አንድ‌ ‌ላይ‌ ‌ይኖሩና‌ ‌ሰብለ‌ ‌የልብ‌ ‌በሽታዋ‌ ‌ተነሥቶባት‌ ‌ትሞታለች፣‌ ‌ጉዱ‌ ‌ካሳም‌ ‌ከበዛብህ‌ ‌አጠገብ‌ ‌ያስተኛታል።‌ ‌በሦስተኛው‌ ‌አመት‌ ‌ጉዱም‌ ‌አረፍተ‌ ‌ዘመን‌ ‌ይገታዋል።‌
ፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ ማን ነው?
ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ
160
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ላሉት መጻሕፍት አርእስት የሰጡት ሠለስቱ ምዕት ናቸው፡፡ በምን ምክንያት ቢሉ ድዮቅልጥያኖስ መክስምያኖስ የሚባለ ሁለት ዓላውያን ነገስታት ተነስተው "አብያተ ጣዖታት ይትረኃዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትዓፀዋ" ብለው አዋጅ አስነገሩ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትና ቅዱሳት መፃህፍት ተዘረፉ፤ ተቃጠሉ፡፡ ከምዕመናን ወገን ብዘዎች ሞቱ የተረፉትም ተሰደዱ፡፡ እጅግ ከፍተኛ እልቂትና ስደት በቤተክርስቲያን ላይ ሆነ፡፡ ከመከራው ጽናት የተነሳ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ተባለ (ከ285 - 395)፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መፍቀሬ ሃይማኖት የሆነውን ቆስጠንጢኖስን አነገሰው፡፡ የቆስጠንጢኖስ አባቱ ኮስታንዲዮስ(ቁንስጣ) ሲሆን እናቱ ደግሞ እላኒ ትባላለች፡፡ ቆስጠንጢኖስም የድዮቅልጥያኖስን አዋጅ በአዋጅ ሽሮ "አብያተ ክርስቲያናት ይትረኃዋ አብያተ ጣዖታት ይትዓፀዋ" ብሎ አወጀ፡፡ በዘመኑ አርዮስ የተባለ መናፍቅ ወልድ ፍጡር በመለኮቱ ብሎ ተነሳ፡፡ በዚህ ጊዜ ጉባኤ በኒቂያ ተደረገ፡፡ ሶስት መቶ ዓሥራ ስምንት የቤተክርስቲያን ሉቃውንት ተሰብስበው አርዮስን በማውገዝ ሃይማኖትን አጽንተው በሚለያዩበት ጊዜ ለመጻህፍት ሁሉ አርእስት ሰጥተዋል፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ለሚገኙት መጻሕፍት ርእስ የተሰጠው በየት በተደረገ ጉባኤ ነበር?
በኒቂያ
550
መጋቢት ፪ ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን ያዘ። ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት (በኋላ ፕሬዚዳንት) ሪቻርድ ኒክሰን ኢትዮጵያን ጎበኙ ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ሊትዌኒያ እራሷን ከሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ውጭ ነጻ መሆኗን አወጀች። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ በልብ ምታት አረፈ።
ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ ያረፈው በምን ምክንያት ነው?
በልብ ምታት
665
አብርሀም ሊንከን (የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፰ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም.) ድረስ የኖሩ ከ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትተው ተገደሉ። የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜሪ ቶድን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር መኖር ትንሽ የተቸገሩ ቢሆነም ከጊዜ ብዛት ግን ለምደዉ 4 ወንድ ልጆችን በተከተሉት አመታት ወለዱ። በ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን ሪፐብሊካን ፓርቲ መሥርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም. የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ። በጦርነቱ የስሜን ሠራዊት ከብዛታቸው የተነሣ በአራት ዓመት ውስጥ አሸነፉ። በዚህ ጊዜ ላይ ሊንከን ለአመጸኖቹ ባርዮች ነጻነት አዋጁ። ያላመጹ ዜጎች ባርያዎች ግን በዚያን ጊዜ ነጻ አልወጡም። በ፲፰፻፶፮ዓ.ም.ምርጫ ሊንከን በቀላል ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ተመረጡ። በሚያዝያ ፪ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. የኮንፌደራት ሠራዊት እጁን ሰጠ። ነገር ግን ሚያዝያ ፯ ቀን የመድረክ ትርዒት ሲያዩ በነፍሰ ገዳዩ በጆን ዊልክስ ቡዝ እጅ በጥይት ተመትተው በማግሥቱ ሞቱ። ከዚህም ትንሽ በኋላ ባርነት በሕግ በሙሉ ተክለክሎ የተረፉት ባርያዎች ነጻነት አገኙ።
አብርሃም ሊንከንን ማን ገደላቸው?
ጆን ዊልክስ ቡዝ
157
በ1240 አካባቢ በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ፍትሐ ነገሥት በአረብኛ ጻፉ። እብን አል-አሣል ሕጎቹን የወሰዱት በከፊል ከሃዋርያት ጽህፈቶችና ከሕገ ሙሴ፤ በከፊልም ከድሮ ቢዛንታይን ነገስታት ሕጎች ነበር። መጽሐፉ በግዕዝ ተተርጉሞ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ወቅት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በ1450 አከባቢ እንደነበር የሚል ታሪካዊ መዝገብ አለ። ቢሆንም መጀመርያ እንደ ሕገ ምንግሥት መጠቀሙን የተመዘገበው በዓፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን (ከ1555 ጀምሮ) ነው። ፍትሐ ነገስት እስከ 1923 ዓ.ም. የብሄሩን ዋና ሕግ ሆኖ ቆየ። በ1904 ዓ.ም. ዐጼ 2 ምኒልክ የዘመናዊ ሕገ መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ ተረድተው በጸሀፊው መምሬ ብስራት አንድ ሕገ መንግሥት የሚመስል ሰነድ ታተመ፤ ይህ ግን በውነት ሕገ መንግሥት አይባልም። «በምኒሊክ ስለተቋቋሙት ሚኒስቴሮች በምሳሌ የቀረበ ጽሑፍ» በምሳሌና በትርጓሜ የእያንዳንዱን ሚኒስቴር ሥራ እንደ ሰውነት አካላት አስመሰለ። ለምሳሌ፦ ኢትዮጵያ መጀመርያ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት የተቀበለችው በ1923 አመተ ምኅረት በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የታወጀ ሲሆን የሕግ አማካሪ ቤቶች በሁለት ያስከፈለ ነው። ይህ የመንግሥታቸው ዋና መሠረት ሆኖ እስከ 1948 አ.ም. አገለገለ፤ በዚያ አመት ተሻሽሎ በወጣ ሕገ መንግሥት ሕዝቦች በመንግሥት ሥራ የሚጫወቱት ሚና እንደገና ተስፋፋ። ይህ ብቻ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሆኖ እስከ 1967 አ.ም. ቆየ፤ የዛኔ በደርግ (በሕገ መንግስት እራሱ ባልሆነ ሂደት) ተሰረዘ።
በኢትዮጵያ ለመጀመረያ ጊዜ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት የታወጀው በማን ነበር?
በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
609
ሰቆጣ ሰቆጣ ከ1956 ጀምሮ የዋግ አውራጃ ማዕከል እና የሰቆጣ ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከሰቆጣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የውቅሮ መስቀል ክርስቶስ አለት ውቅር ቤ.ክ. ይገኛል። በዚሁ ቤተ ክርስቲያን ላስታን ከሰቆጣ ሆነው ያስተዳደሩ ዋግሹሞች ደረቅ ቅሪቶች ይገኛሉ። ከአክሱም መዳከም በኋላ በአረብ ጸሐፊዎች ዘንድ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማነት ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰውኩባር የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ገናና ማዕከል ሰቆጣ እንደነበር በታሪክ ግንዛቤ አለ። ስለሆነም ይመስላል፣ ላስታን በዋግ ሹም ማዕረግ ያስተዳደሩ ገዢዎች መቀመጫቸው ሰቆጣ ነበር። ከጥፋት በተረፉ መዝገቦች ዘንድ ሰቆጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅሶ የምናገኘው በ1738ዓ.ም. ሲሆን፣ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ወደ ላስታ ባደረጉት ዘመቻ ሰቆጣ ውስጥ በዋግ ሹም ነዓኩቶ ለአብ (የዋግ ሹም ቴዎድሮስ አባት) ቤት ለ5ቀን እንዳረፉ ዜና መዋዕላቸው በማተቱ ነው ። ከዚያም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ የአውሮጳ ተጓዦች ሰቆጣን ሲጎበኙ፣ ዋልተር ፕላውዴን ለምሳሌ በኢትዮጵያ ከሚገኙ 5 ብቻ ነጋድራሶች አንዱ በሰቆጣ ይገኝ እንደነበር መዝግቧል። ከዚያም በ1800ዎቹ መጨረሻ ሰቆጣን የጎበኘው ኤ.ቢ.ዋይልድ ሰቆጣን የላስታ ዋና ከተማ አድርጎ ሲጠቅስ፣ የሰቆጣ ቤተ መንግስት ባለ ሶስት ፎቅና በ1650ዎቹ የተገነባ እንደነበር ያትታል። ቤተ መንግስቱን የሰሩት የፋሲል ግቢን አናጺዎ እደሆኑም መላምት ያቀርባል። ይሄው የአውሮጳ ተጓዝ፣ በ1880ዎቹ የሰቆጣ ገበያ ከአካባቢው ካሉት ሁሉ ግዙፉ እንደነበር ፣ የዝሆን ጥርስ እና በቅሎ ገበያው የደራ እንደነበር፣ እንዲሁም 21፣000 በሬዎች፣ 2፣900 ላሞች፣ 10ሺህ ፍየሎች፣ 1፣500 በጎች በየአመቱ ለግብይት ይቀርቡበት እንደነበር ሳይጠቅስ አላለፈም። ጥር 2፣ 1929 ጣሊያኖች በሰቆጣ ላይ የመርዝ ጋዝ ቦምብ እንደጣሉ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
ጣሊያኖች በሰቆጣ ላይ የመርዝ ጋዝ ቦምብ የጣሉት መቼ ነው?
ጥር 2፣ 1929
983
ዓጼ ኃይለ ሥላሴ ዘውድ እንደጫኑ የአገሪቱን የመጀመሪያ ሕገ-መንግሥት እንዲዘጋጅ አዝዘው በዘውዱ አንደኛ ዓመት በዓል ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. በአዲሱ ምክር ቤት (ፓርላማ) ለሕዝብ ቀረበ። ከዚህም በላይ ብዙ የቴክኖዎሎጂ ስራዎችና መሻሻያዎች ወደ ኢትዮጵያ ከውጭ አገር አስገቡ። በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. የሙሶሊኒ ፋሺስት ሠራዊት ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ጃንሆይ ሕዝባቸውን ወራሪውን በሙሉ ለመቃወም እንዳስነሡና የከተት ዐዋጆቻቸው በታሪክ ገጾች ይዘገባሉ። በዐዋጅ መሠረት የዘመቻው ጊዜ እስቲያልቅ ድረስ ለሚታግሉ ነጋዶች ከቀረጥ አስተስርየት ሰጣቸው። እራሳቸው በቆራጥነት ከታገሉ በኋላ የጠላቱ ጦር ኅይል ግን በመጨረሻ ወደ እንግሊዝ አገር ለጊዜው አሰደዳቸው። ወደ ጄኔቭ ስዊስ ወደ ዓለም መንግሥታት ማኅበር ሄደው ስለ ጣልያኖች የዓለምን እርዳታ በመጠየቅ ተናገሩ። የዓለም መንግሥታት ግን ብዙ አላደረጉም። በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ግን አውሮፓ ሁሉ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተያዘ። የእንግሊዝ ሠራዊቶች ለኢትዮጵያ አርበኞች እርዳታ በመስጠት ጣልያኖች ተሸንፈው በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ኢትዮጵያን ተዉ። ዓፄ ኃይለ ሥላሴ አዲስ አበባን እንደገና የገቡበት ቀን ከወጡበት ቀን በልኩ ዕለት አምስት ዓመት በኋላ ነበረ። ከዚህ በኋላ በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የሕዝቦችን መብቶችና ተከፋይነት በመንግሥት አስፋፍቶ ሁለቱ ምክር ቤቶች እንደመረጡ አደረገ። በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ግርማዊነታቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአዲስ አበባ እንዲመሠረት ብዙ ድጋፍ ሰጡ። በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ወደ ካሪቢያን ጉብኝት አድርገው የጃማይካ ራስታዎች ተገኛኙ። በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. በማርክሲስት አብዮት ደርግ ሥልጣን ያዙና እሳቸው በእሥር ቤት ታሰሩ። በሚከተለው ዓመት ከተፈጥሮ ጠንቅ እንደ አረፉ አሉ ፤ ሆኖም ለምን እንደ ሞቱ ስለሚለው ጥያቄ ትንሽ ክርክር አለ። ብዙ ራስታዎች ደግሞ አሁን እንደሚኖሩ ይላሉ። የዓፄ ኃይለ ሥላሴ የትውልድ ስም ልጅ ተፈሪ መኮንን ነው። ስመ-መንግሥታቸው ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነበር። ሞዓ አንበሣ ዘእምነገደ ይሁዳ ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ የሚለው የሰሎሞናዊ ሥረወ-መንግሥት ነገሥታት መጠሪያም በንጉሠ-ነገሥቱ አርማ እና ሌሎች ይፋዊ ጽሑፎች ላይ ከመደበኛው ማዕረግ ጋር ይጠቀስ ነበር። ጃንሆይ ፣ ታላቁ መሪ እና አባ ጠቅል በመባልም ይታወቁ ነበር።
የጣልያን ፋሺስት ጦር ኢትዮጵያን በ፲፱፻፳፰ ሲወር ንጉሠ ነገሥት የነበሩት ማን ናቸው?
ዓጼ ኃይለ ሥላሴ
0
ራስ መኮንን ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የሸዋ ንጉሥ የነበሩት የሣህለ ሥላሴ ልጅ የልዕልት ተናኘወርቅ እና የደጃዝማች ወልደሚካኤል ልጅ ናቸው። ግንቦት ፩ ቀን ፲፰፻፵፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ እስከ ፲፬ ዓመት ዕድሜያቸው ከአባታቸው ጋር ከኖሩ በኋላ ያጐታቸው የንጉሥ ኃይለ መለኮት ልጅ ዳግማዊ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ እንደነበሩ፡ ወደርሳቸው ቤተ መንግሥት መጥተው፡ ባለሟል ሆኑ። በ፲፰፻፷፰ ዓ.ም ዕድሜያቸው ሀያ አራት ዓመት ሲሆን ከወይዘሮ የሺ እመቤት ጋር ተጋብተው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም የወደፊቱን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ወለዱ።
ልዑል ራስ መኮንን ልጃቸውን አጼ ኃይለ ሥላሴን የወለዱት መቼ ነበር?
ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም
320
ክልሉ የትልልቅ ወንዞች ባለቤት ሲሆን በአጠቃላይ በሦስት ዋና ዋና ተፋሰሶች ተከፋፍሎ ሊታይ የሚችል ነው። እነርሱም የዓባይ፣ የተከዜ እና የአዋሽ ተፋሰስ ናቸው። ወደነዚህ ተፋሰሶች የሚገቡና ዓመቱን በሙሉ የማይደርቁ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ትልልቅ ወንዞች ያሉ ሲሆን በክልሉ በጥቅም ላይ ያልዋለ ሰፊ የውሐ ሀብት መኖሩን ያመለክታሉ። ከነዚህ በተጨማሪ እንደ ጣናና አርዲቦ የመሳሰሉ ሐይቆችም በክልሉ ውስጥ ይገኛሉ። በአጠቃላይ በክልሉ ውስጥ ባሉ ትልልቅ ወንዞችና መጋቢ ወንዞች የመስኖ ልማት ለማካሄድ የሚያስችል ከፍተኛ የውሐ ሐብት ክምችት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ይሁን እንጅ እስከ አሁን ጥቅም ላይ የዋለው በጣም አነስተኛ ነው። በአመዛኙ አብዛኛው የክልሉ ምጣኔ ሀብት በግብርና እና ከብት እርባታ ላይ የተመሠረተ ነው። በአጠቃላይ ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ቁጥር፣ ለእርሻና ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ የሆነ መሬት፣ የአየር ንብረት እና የውሐ ሀብቶች ያሉት በመሆኑ በተለይም የሰብል እና የእንስሳት ሀብት ልማት ለማካሄድ የማይናቅ አቅም አለው። በዝናብም ሆነ የመስኖ እርሻ ልማት በማስፋፋት በክልሉ በገበያ የሚውሉ የተለያዩ የአገዳ፣ የጥራጥሬ፣ የቅባት፣የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን ማምረት ይቻላል። ጤፍ፣ ገብስ፣በቆሎ፣ ማሽላ፣ዳጉሣ፣ ስንዴ፣አተር፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ ጓያ፣ምስር፣ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ተልባ፣ ወዘተ የመሳሰሉት በክልሉ ውስጥ ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በእንስሳት ሀብት ረገድም በወተት ምርታማነታቸው የታወቁ የፎገራ ዝርያዎችና በፀጉር ምርት የታወቁት የመንዝ በግ ዝርያዎች በክልሉ ይገኛሉ። በቱሪዝም የሥራ መስክ ሊበለጽጉ ፣በሰፊው አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ እና በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈሩት የጐንደር ቤተ መንስግት ህንፃዎች፣ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም ልዩ ልዩ የቱሪዝም መስሕቦች አሉት፣ ይሁን እንጅ ክልሉ ሰፊ የሆነ የቱሪዝም እምቅ ሀብት ያለው ቢሆንም በሚፈለገው መጠን በጥቅም ላይ ውሏል ማለት አያስደፍርም። በዚህ ረገድ፤አካባቢዉ የብዙ ታሪካዊ ገዳማትና የታሪካዊ ቅርሶችም ባለሀብት ነው።
በአማራ ክልል ውስጥ በወተት ምርታቸው የታወቁት የየት አካባቢ ከብት ዝርያዎች ናቸው?
የፎገራ
844
ሴኔጋል ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒና ጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 14 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል። የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ። በአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋል፣ ኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።
የኬፕ ቨርድ ደሴቶች በየትኛው ውቅያኖስ ይገኛሉ?
በአትላንቲክ
375
ብጉር ብጉር ማለት የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎች ከቆዳ ስር በሚገኙ የወዝ እጢዎች በሚመነጭ ቅባት ወይም ወዝ እና በሞቱ የቆዳ ህዋሳት በብዛት መከማቸትና በቀዳዳው መደፈን የሚፈጠር እባጭ ነው። በርካታ ጥናቶች ጭንቀት ብጉርን ከማባባሱም በላይ የቆዳ ጤንነት ችግር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል ይላሉ። ብጉር በጣም ከተለመዱት የቆዳ ችግሮች ውስጥ አንዱ ነው። ዕድሜ ዘርና ጾታ ሳይገድበው ሁሉንም ያጠቃል። ቆዳችን ላይ ብዙ ጥቃቅን ቀዳዳዎች አሉ። በነዚህ ቀዳዳዎች ውስጥ ደግሞ ቅባታማ ፈሳሽ የሚያመነጩ ዕጢዎች አሉ። የቅባታማ ፈሳሽና የቀዳዳዎቹ ጥቅም የሞቱ የቆዳችን ህዋሳትን ለማስወገድ ነው፡፡ ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች እነዚህ ቀዳዳዎች ሲዘጉ ቅባታማ ፈሳሹ በቆዳችን ውስጥ ስለሚጠራቀም ብጉር ይፈጠራል፡፡ የተጠራቀመው ቅባትም ለህዋሳት መራባት ዕድል ስለሚከፍት አንዳነዴ መግል ይይዛል፡፡ የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎች ከ'ስቤሸስ ግላንድ' ጋር የተያያዙ ናቸው፡ እነዚህ እጢዎች ሴበም የሚባል ንጥረነገር ሲያመነጩ ንጥረነገሩም በጸጉር መውጫ ቀዳዳ ወደላይ ወደቆዳ የሚወጣ እና ቆዳችን ላይ የሚያርፍ ነው። የብጉር መፈጠር የቆዳ ህዋሳትን ያበዛል። ይህ እባጭ የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎችን ግርግዳ በመግፋት ነጫጭ የብጉር ሽፍታዎች ሲፈጥር የቀዳዳዎችን ግርግዳ በመጎተት ደግሞ ጥቋቁር የብጉር ሽፍታዎች (blackheads) ቆዳችን ላይ ሊፈጥር ይችላል። ብጉር በብዛት ሊወጣ የሚችልባቸው ቦታዎች፣ ፊት ላይ፣ በደረት፣ በኣንገት፣ በትከሻ ፣ እና በጀርባ ላይ ነው።
የጸጉር መውጫ ቀዳዳዎች ከቆዳ ስር በሚገኙ የወዝ እጢዎች በሚመነጭ ቅባት ወይም ወዝ እና በሞቱ የቆዳ ህዋሳት በብዛት መከማቸትና በቀዳዳው መደፈን የሚፈጠር እባጭ ምን ይባላል?
ብጉር
0
ኤርትራ ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አገሮች አንዷ ስትሆን በስሜን-ምዕራብ ከሱዳን፣ በሰሜን-ምስራቅ ከቀይ ባህር፣ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ በደቡብ-ምስራቅ ጅቡቲ ጋር ድንበር ትካለላለች። ኤርትራ የሚለው ስም ከላቲን የተወሰደ እና ስረ-መሰረቱ የግሪክ ሐረግ ሲሆን ትርጉሙም ቀይ ማለት ነው። ይህን ስም ለአካባቢው የሰጡት ጣሊያኖች በጥር ፲፰፻፺ ቅኝ ግዛታቸውን ሲያውጁ ነበር (ተመሳሳይ ስም በጀርመኖች 1870 እና ግብጾች ፲፰፻፷ወቹ በጥቅም ላይ ውለዋል፣ ነገር ግን የትኛውን ክፍል ስሙ እንደሚመለከት ግልጽ አልነበረም)። ኤርትራ፣ እንደ ሐገር፣ በጣሊያኖች ከተመሰረተች በኋላ በ5 ልዩ ሂደቶች ውስጥ በማለፍ ነው ያሁኑን ቁመናዋን የያዘችው። ከ1890 በፊት የነበረው የአካባቢው ታሪክ በ«ኤርትራ» ስር የሚጠና ባህይሆንም ስለአዲሱ ኤርትራ ግንዛቤ ስለሚያስጨብጥ ታሪክ ተመራማሪዎች ከ፲፰፻፺ በፊት ያለውንም ታሪክ ማጥናት ተገቢ እንደሆነ ይስማማሉ። በ1860ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ፣ የግብጹ መሪ ኢስማኤል ከዴቭ ፓሻ በናይል ተፋሰስ ላይ ሰፊ የግብጽ ቅኝ ግዛት ለማበጀት ተነሳ። ለዚህ አዲሱ ግዛቱ ካርቱምን ዋና ከተማው በማድረግ የሱዳን ግዛቱን አጸና። ቀጥሎም የቀይ ባህርን ጠረፎች በ1865 ከተቆጣጠረ በኋላ በ1870ዎቹ መጀመሪያ ሐረርንና ተሻግሮ ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ግዛቶችን አበጀ። እንግዲህ በኒህ ግዛቶቹና በሱዳን መካከል የነበረው ብቸኛ መገናኛ መንገድ ካርቱም-ከሰላ- ከረን -ምፅዋ ብሎ የሚዘልቅ ነበር። ስለሆነም በ1872 ይህን ስልታዊ መንገድ የክዴቭ ፓሻ ሰራዊቶች ተቆጣጠሩ። መቆጣጠር ብቻ አይደለም በየመንገዱ ምሽግ እየሰሩና የአውሮጳ ምስዮናውያንን እርሻ ቦታ እየሰጡ ቅኝ ግዛት አበጁ። በዚህ ሳይቆጠቡ፣ የመንገዱን ደህንነት ዋስትና ለማስጠበቅ ሲሉ የአካባቢውን ደጋማ ክፍል መያዝ ግድ አላቸው። ደጋማው ክፍል በዚህ ወቅት በአጼ ዮሐንስ ግዛት ስር ነበር።
ኤርትራ በሰሜን-ምዕራብ በኩል ከማን ጋር ትዋሰናለች?
ከሱዳን
50
ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት ቀረቡ። በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ  ኢትዮጵያን በመወከል  ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ነው የተነገረው። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋና የቋንቋ ጥናት ክፍል ለረጅም ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።
ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የምን ሚንስቲር ሆነው ሰርተዋል?
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
201
ቢል ክሊንተን ያደጉት በሆት ስፕሪንግስ፣ አርካንሳው ነው። የቢል ክሊንተን አባት ዊሊያም ጄፈርሰን ብላይዝ ጁኚየር፣ ቢል ክሊንተን ከመወለዱ ሶስት ወር በፊት በመኪና አደጋ ሞተዋል። የቢል ክሊንተን እናት ቨርጂኒያ ክሊንተን ኬሊ፣ በ1950 እ.ኤ.ኣ. ሮጀር ክሊንተን የሚባል ሰዉ አገባች። 14 ዓመቱ ሲሆን ቢል ክሊንተን የመጨረሻ ስሙን ወደ ክሊንተን ለወጠ። ክሊንተን በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ፥ ዋሽንግተን ዲ.ሲ.፣ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ፥ ኢንግላንድ፣ እና ዬል ዩኒቨርሲቲ፥ ኮነቲኬት ተምረዋል። በ1975 እ.ኤ.ኣ. ሂለሪ ሮድሃምን አገቡና በሊትል ሮክ፥ አርካንሳው መኖር ጀመሩ። ከዚያም በዩኒቨርሲቴ ኦፍ አርካንሳው የሕግ ፐሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል። ቢል ክሊንተን የአርካንሳው አስተዳዳሪ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በ1978 እ.ኤ.ኣ. ነው። በዛ ጊዜ ከአሜሪካ በዕድሜ ትንሹ አስተዳዳሪ ነበሩ። በ1980 እ.ኤ.ኣ. በፍራንክ ዲ ዋይት ከተሸነፉ በኋላ በ1982 እ.ኤ.ኣ. እንደገና ተመረጡ። ከዛ ጀምሮ እስከ 1992 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ለአራት ጊዜ አስተዳዳሪ ሆነው መርተዋል። በ1984 እ.ኤ.ኣ. የአስተዳዳሪ የስልጣን ዕድሜ ከ2 ዓመት ወደ 4 ዓመት አራዝመዋል። በ1992 እ.ኤ.ኣ. ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድርው አሸንፈዋል። በ1996 እንደገና ተወዳድረው አሸንፈዋል።
ቢል ክሊንተን ትዳር መቼ ያዙ?
በ1975 እ.ኤ.ኣ.
310
በሕንድ ንጉሥ አሾካ መንግሥት የአሾካ አዋጆች ሕግጋት በ264 አክልበ. መሠረቱ። ከምዕራቡ ሮማ መንግሥት ውድቀት ደግሞ ወደ ተረፈው ሕዋእ ውስጥ ከፈለሱት ጀርመናውያን ወገኖች አብዛኛው የራሳቸውን ሕጎች ዝርዝር በጽሑፍ አወጡ። በተለይ የሚታወቁም የቪዚጎቶች አለቃ ዩሪክ ሕግ (463 ዓ.ም.)፣ የቡርጎንዳውያን ሕግጋት (እኚህ ለጀርመናውያንና ለሮማውያን የተለያየ ፍትሕ ነበራቸው)፣ የአላማናውያን ሕግጋትና፣ የፍራንኮች ሕግጋት ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የተጻፉት ከ492 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። በ498 ዓ.ም. የቪዚጎቶች አለቃ 2ኛ አላሪክ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስና አንዳንድ የተለያዩ የቀድሞ ሮማ ሐገጋት አከማችተው አዋጁአቸው። ከዚህም በኋላ የታዩ ሕጎች የሎምባርዶች ሕግጋት (635 ዓ.ም.)፣ የቪዚጎቶች አዳዲስ ሕግጋት (646 ዓ.ም.)፣ የአላማናውያን አዳዲስ ሕግጋት (722 ዓ.ም.) እና የፍሪዝያውያን ሕግጋት (777 ዓ.ም.) አሉ። በአውሮፓ አኅጉር ላይ የተጻፉት እነኚህ ፍትሖች ሁሉ በሮማይስጥ ቢጻፉም፣ በእንግሊዝ አገር ግን የተጠቀሙት ሕጎች ከኬንት ንጉሥ ኤጠልቤርት ሕጎች (594 ዓ.ም.) ጀምሮ በጥንታዊ እንግሊዝኛ የተቀነባበሩ ነበሩ። በ885 ዓ.ም. ታላቁ አልፍሬድ ይህንንና ሁለት የድሮ ፍትሖች ከሕገ ሙሴና ከሕገ ወንጌል ጋራ አጋጥመው የእንግሊዝ ሕገ መንግሥት ዶም ቦክ ሠርተዋል።
የአሾካ አዋጆች ሕግጋት በ264 አክልበ. የታወጀው በማን ነበር?
በሕንድ ንጉሥ አሾካ
0
ዳምጠው አየለ ዳምጠው አየለ (23.11. 1944 አ/ም – 27.10. 2006 አ/ም) ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፋኝ ነበር። በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል። ዳምጠው ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል። ዳምጠው መራቤቴ እያለ በየባእላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። ባጋጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል። ዳምጠው አየለ ኖርዌይ ሃገር በስደት ለ 8 አመት ያክል ኖሯል። ኢትዮጵያም ከገባ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብራኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ 62 አመቱ ሰኔ 27 2006 አ/ም ቀን ህይወቱ አልፏል። የቀብር ስነስርአቱም ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።
ዳምጠው አየለ ከኢትዮጵያ ውጭ የት አገር ኖሯል?
ኖርዌይ
1,163
አዶልፍ ሂትለር አዶልፍ ሂትለር (ጀርመንኛ Adolf Hitler አዶልፍ ሂትለ) እ.አ.አ. ከ1933 ጀምሮ የጀርመን ቻንስለር እንዲሁም ከ1934 ጀምሮ ደግሞ የጀርመን መሪም (Führer) ጭምር የነበረ ሰው ነው። ሂትለር በሚያዝያ 13 ቀን 1881 ዓ.ም. (20 አፕሪይል 1889 እ.ኤ.አ.) በዛሬይቷ ኦስትሪያ ተወለደ። በሚያዝያ 22 ቀን 1937 ዓ.ም. (30 አፕሪይል 1945 እ.ኤ.አ.) በርሊን ውስጥ ከአንድ ቀን በፊት ካገባት ሚስቱ ኤቫ ብራውን ጋር የራሱን ህይወት አጠፋ። በ1925 ዓ.ም. መጀመርያ የሂትለር ናዚ ወገን ከጓደኞቹ ወገን ጋር በራይክስታግ ምክር ቤት ትብብር መንግሥት ለመሥራት በቂ መንበሮች አልነበራቸውም። ተቃራኒዎቻቸው የኰሙኒስት ወገን 17% መንበሮች ስለ ነበራቸው የሂትለር ወገኖች የድምጽ ብዛት ሊያገኙ አልተቻላቸውም ነበር። በዚያው ዓመት ግን ከምርጫው ትንሽ በፊት የራይክስታግ ሕንጻ በእሳት ተቃጠለ። ይህ የኰሙኒስቶች ሥራ ነው ብለው የሂትለር ወገን ኰሙኒስት ፓርቲ ቶሎ እንዲከለከል አደረጉ። ስለዚህ ከምርጫው በኋላ የኰሙኒስትን መንበሮች ስለ አጡ የሂትለርም ወገኖች አሁን ከ50% መንበሮች በላይ ስላገኙ፣ የትብብር መንግሥት ሠሩና ወዲያው በድንጋጌ አቶ ሂትለር ባለሙሉ ሥልጣን አደረጉት። ሂትለር የጻፈው የርዮተ አለሙ ጽሑፍ «የኔ ትግል» (Mein Kampf) ሟርት ብቻ ነው። ለመጥቀስ ያህል፦ «ትኩረቴ ወደ አይሁዶች ስለ ተሳበ፣ ቪየናን ከበፊት በሌላ ብርሃን ለማየት ጀመርኩ። በሄድኩበት ሁሉ አይሁዶችን አየሁዋቸው፤ በብዛትም እያየኋቸው፣ ከሌሎች ሰዎች ፈጽሞ እንድለያቸው ጀመርኩ።»... «የግዛቱ (ኦስትሪያ-ሀንጋሪ) ዋና ከተማ የከሠተውን የዘሮች ውሑድ ጠላሁት፤ የዚህን ሁሉ የቼኮች፣ ፖሎች፣ ሀንጋርዮች፣ ሩጤኖች፣ ሰርቦች፣ ክሮዋቶች ወዘተ. የዘሮች ድብልቀት፤ በሁላቸውም መካከል፣ እንደ ሰው ልጅ መከፋፈል ሻገቶ፣ አይሁዶችና ተጨማሪ አይሁዶች።» በነበረው ዘረኛ አስተዳደሩ 6 ሚሊዮን የአውሮፓ አይሁዶችን እና 5 ሚሊዮን ሌሎች የተለያዩ ሀገራት ህዝቦችን (በተለይም ስላቮችን) በገፍ (በሆሎኮስት) አስጨርሷል። በሂትለር ሥር የናዚዎች ፍልስፍና በሂንዱኢዝም እንደሚገኘው በዘር የተከፋፈለ ካስት ሲስተም መመሥረት አይነተኛ ነበር። «አርያኖች» የተባሉት ዘሮች በተለይም የጀርመናውያን ብሔሮች ከሁሉ ላዕላይነት እንዲገኙ አሠቡ። ይህ ዝብረት የተነሣ በርግ ቬዳ ዘንድ በ1500 ዓክልበ. ያህል ወደ ሕንድ የወረሩት ነገዶች «አርያን» ስለ ተባሉ ነው፤ በጥንትም «አሪያና» የአፍጋኒስታን አካባቢ ስም የዘመናዊው ኢራንም ሞክሼ ነበር። በናዚዎቹ እንደ ተዛበው ግን ታሪካዊ ባይሆንም የ«አርያኖች» ትርጓሜ ጀርመናውያን ብቻ ነበሩ፤ ስላቮች (በተለይ የሩስያና የፖሎኝ ሕዝቦች) ግን አርያኖች ሳይሆኑ እንደ ዝቅተኞች ተቆጠሩ። የሂትለር እብደት እየተራመደ በ1926 ዓም የሀንጋሪ ሕዝብ ደግሞ «አርያኖች» ተደረጉ፣ በ1928 ዓም የጃፓን ሕዝብ እንኳን በይፋ «አርያኖች» ተደረጉ፤ በ1934 ዓም የፊንላንድ ሕዝብ ወደ «አርያኖች» በሂትለር ዐዋጅ ተጨመሩ። በሙሶሊኒ ሥር የፋሺስት ጣልያኖች እኛም አርያኖች ነን ቢሉም ጣልያኖች አርያን መሆናቸው በናዚዎች ዘንድ መቸም አልተቀበለም ነበር።
የአዶልፍ ሂትለር መንግሥት የጃፓን ሕዝቦችን መቼ ነበር እንደ አርያኖች ዘር የቆጠረው?
በ1928 ዓም
1,596
ሰቆጣ ሰቆጣ ከ1956 ጀምሮ የዋግ አውራጃ ማዕከል እና የሰቆጣ ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከሰቆጣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የውቅሮ መስቀል ክርስቶስ አለት ውቅር ቤ.ክ. ይገኛል። በዚሁ ቤተ ክርስቲያን ላስታን ከሰቆጣ ሆነው ያስተዳደሩ ዋግሹሞች ደረቅ ቅሪቶች ይገኛሉ። ከአክሱም መዳከም በኋላ በአረብ ጸሐፊዎች ዘንድ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማነት ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰውኩባር የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ገናና ማዕከል ሰቆጣ እንደነበር በታሪክ ግንዛቤ አለ። ስለሆነም ይመስላል፣ ላስታን በዋግ ሹም ማዕረግ ያስተዳደሩ ገዢዎች መቀመጫቸው ሰቆጣ ነበር። ከጥፋት በተረፉ መዝገቦች ዘንድ ሰቆጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅሶ የምናገኘው በ1738ዓ.ም. ሲሆን፣ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ወደ ላስታ ባደረጉት ዘመቻ ሰቆጣ ውስጥ በዋግ ሹም ነዓኩቶ ለአብ (የዋግ ሹም ቴዎድሮስ አባት) ቤት ለ5ቀን እንዳረፉ ዜና መዋዕላቸው በማተቱ ነው ። ከዚያም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ የአውሮጳ ተጓዦች ሰቆጣን ሲጎበኙ፣ ዋልተር ፕላውዴን ለምሳሌ በኢትዮጵያ ከሚገኙ 5 ብቻ ነጋድራሶች አንዱ በሰቆጣ ይገኝ እንደነበር መዝግቧል። ከዚያም በ1800ዎቹ መጨረሻ ሰቆጣን የጎበኘው ኤ.ቢ.ዋይልድ ሰቆጣን የላስታ ዋና ከተማ አድርጎ ሲጠቅስ፣ የሰቆጣ ቤተ መንግስት ባለ ሶስት ፎቅና በ1650ዎቹ የተገነባ እንደነበር ያትታል። ቤተ መንግስቱን የሰሩት የፋሲል ግቢን አናጺዎ እደሆኑም መላምት ያቀርባል። ይሄው የአውሮጳ ተጓዝ፣ በ1880ዎቹ የሰቆጣ ገበያ ከአካባቢው ካሉት ሁሉ ግዙፉ እንደነበር ፣ የዝሆን ጥርስ እና በቅሎ ገበያው የደራ እንደነበር፣ እንዲሁም 21፣000 በሬዎች፣ 2፣900 ላሞች፣ 10ሺህ ፍየሎች፣ 1፣500 በጎች በየአመቱ ለግብይት ይቀርቡበት እንደነበር ሳይጠቅስ አላለፈም። ጥር 2፣ 1929 ጣሊያኖች በሰቆጣ ላይ የመርዝ ጋዝ ቦምብ እንደጣሉ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
ከሰቆጣ ምን ያህል ርቆ የውቅሮ መስቀል ክርስቶስ አለት ውቅር ቤተክርስቲያን ይገኛል?
6 ኪሎ ሜትር
60
ቱርክመንኛ ቱርክመንኛ (Türkmen) የቱርክምኒስታን ብሔራዊ ቋንቋ ነው። በቱርክመኒስታን 3,430,000 ተናጋሪዎች ሲኖሩ ከቱርክመኒስታን ውጭ ደግሞ 3 ሚሊዮን የሚያሕሉ ተናጋሪዎች በተለይም በኢራን (2 ሚሊዮን) በአፍጋኒስታን (500,000) እና በቱርክ (1000) አሉ። ቱርክመንኛ በቱርኪክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይከተታል። ይህም አንዳንዴ በትልቁ አልታይ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይደመራል። ቀድሞ የተጻፈበት ወይም በቂርሎስ ወይም በ አረብ ፊደሎች ነበር፤ አሁን ግን የቱርክመኒስታን መሪ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ አዋጀ። በ1994 አ.ም. ደግሞ የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ እንደ አቶ ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።
ቱርክመንኛ በላቲን ፊደላት እንዲጻፉ ያወጀው ሳፓርሙራት ኒያዞቭ ኃላፊነቱ ምን ነበር?
የቱርክመኒስታን መሪ
294
ዳምጠው አየለ ዳምጠው አየለ (23.11. 1944 አ/ም – 27.10. 2006 አ/ም) ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፋኝ ነበር። በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል። ዳምጠው ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል። ዳምጠው መራቤቴ እያለ በየባእላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። ባጋጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል። ዳምጠው አየለ ኖርዌይ ሃገር በስደት ለ 8 አመት ያክል ኖሯል። ኢትዮጵያም ከገባ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብራኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ 62 አመቱ ሰኔ 27 2006 አ/ም ቀን ህይወቱ አልፏል። የቀብር ስነስርአቱም ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።
ዳምጠው አየለ የመጀመሪያው አልበሙ ምን ይሰኝ ነበር?
ወፌ ላላ
1,100
ናሚቢያ ናሚቢያ በደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ፣ በስሜን በአንጎላና በዛምቢያ፣ በምስራቅ በቦትስዋና፣ በደቡብም በደቡብ አፍሪቃ ትካለላለች። በ1982 አመተ ምኅረት ነጻነትዋን ከደቡብ አፍሪቃ ስላገኘች በጣም አዲስ አገር ነች። ዋና ከተማዋ ዊንድሁክ ነው። የናሚቢያ በረኅ አውራጃ ከጥንት ጀምሮ በሳን (ቡሽማን)፣ በዳማራና በናማቋ ሕዝቦች ተሰፈረ። በ14ኛው መቶ ዘመን፣ የባንቱ ወገኖች ባስፋፉ ጊዜ አገሩን ሠፈሩ። ክልሉ ግን ከ19ኛው መቶ ዘመን በፊት በአውሮጳውያን አልተዘለቀም። በዚያን ጊዜ ጀርመን ደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ ተብላ አገሪቱ የጀርመን ቅኝ ግዛት ሆነች። ዳሩ ግን ዋልቪስ በይ የተባለው ትንሽ ወደብ ብቻ የእንግሊዝ ግዛት ነበር።
ናሚቢያ ዋና ከተማዋ ማነው?
ዊንድሁክ
179
መዓዛ ብሩ በእሁድ የሬዲዮ ፕሮግራም ታቀርባቸው የነበሩት ሥራዎች ይዘት ማህበራዊ ሕይወት እንዲሠምር በመጣር ላይ ያተኮሩ ሆነው ግልጽ፣ ቀላልና ለዛ ያልተለያቸው ስለነበሩ ከሶስት አሥርት ዓመታት በኋላም ትውስታቸው ከአድማጭ ህሊና አልጠፉም፡፡ በዚሁ ፕሮግራም ላይ መዓዛ ካበረከተቻቸው የፈጠራ ሥራዎቿ ውስጥ ጎልቶ የሚታወሰው “የአዲሱ ቤተሰብ” የተሰኘ ባለ ሰማንያ ስድስት ክፍል ድራማ ሲሆን በዘመኑ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉም የሚያደምጠው ተወዳጅ የቤተሰብ ድራማ ነበር፡፡ መዓዛ በ “መርሀ ስፖርት” እና በሬዲዮ መካከል ሆና ከአራት ዓመት በላይ ከቆየች በኋላ በ1979 ዓ.ም የባህል ሚኒስቴርን ለቃ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጠረች፡፡ አዲሱን መስሪያ ቤቷን ከተቀላቀለችበት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከሬዲዮ እየራቀች መጣች፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የቆየችው ለሶስት ዓመታት ያህል ሲሆን ከዚያ በኋላ የግሏን የማስታወቂያ ሥራ ድርጅት መሥርታ የራስዋ ተቀጣሪ ሆናለች፡፡ ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1992 ዓ.ም ባሉት የአስራ ሶስት ዓመታት ጊዜ ግን መዓዛና ሬዲዮ ተራራቁ፡፡ መዓዛና ሬዲዮ ዳግም የተዋደዱት ከላይ እንደተገለጸው በ1992 ዓ.ም ሳምንታዊውን የ “ጨዋታ” ፕሮግራም በኤፍ ኤም 97.1 ከተፈሪ ዓለሙ ጋር በጋራ ማቅረብ ሲጀምሩ ነበር፡፡ የ “ጨዋታ” ፕሮግራም እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ በአድማጮቹ እንደተወደደ በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ መንግሥት ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ፈቃዶችን ለግሉ ዘርፍ ለመስጠት ሲዘጋጅ፣ ዝርዝር የሥራ እቅድ አቅርባ ባመለከተችው መሠረት፤ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ከአስር አመልካቾች መካከል አንዷ ሆና የመጀመሪያ የግል የኤፍ ኤም ሬዲዮ ባለቤት ያደረጋትን ፈቃድ ተቀበለች፡፡ መዓዛ የሬዲዮ ማሰራጫ መሳሪያዎችን ውድነት፣ የማሰራጫ ቦታ እና የባለሙያ እጦትን ተቋቁማ ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮን በታህሳስ 1999 ዓ.ም አበረከተችልን፡፡ ባለትዳርና የሶስት ልጆች እናት የሆነችው መዓዛ እንደ ባለቤት፣ ሥራ አስኪያጅና ጋዜጠኛ በመሆን በኢትዮጵያ ተወዳጁንና የመጀመሪያውን የግል የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ትመራለች፡ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!”እያለች::
መዓዛ ብሩ ሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ራድዮ ጣብያን መቼ አቋቋመች?
በታህሳስ 1999 ዓ.ም
1,048
የሆሊውዱ የፊልም ኩባንያ ዋርነር ብሮስ የቦክስ ኦፊስን የደረጃ ሰንጠረዥ በሰው ሰራሽ መሳሪያ (አርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ) መገመት ሊጀምር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ሰው ሰራሽ መሳሪያው ዋርነር ብሮስ የሚያዘጋጃቸው ፊልሞች ምን ያህል ስኬታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምቱን ያስቀምጣል ተብሏል፡፡ ይህ አሰራር የተዋናይ አመራረጥን፣ የማከፋፈሉን ሂደት እና የሚለቀቅበትን ጊዜ መነሻ በማድረግ ትርፋማነቱን ይገመግማል ነው የተባለው፡፡ በሆሊውድ መንደር ከስድስት ትልልቅ የፊልም ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ዋርነር ብሮስ ይህን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ከኤልኤ ስታርት አፕ ሲኔለይቲክ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ የመገመቻ መሳሪያው ባለፈው ዓመት ይፋ የሆነ ሲሆን ለዘርፉ አዲስ ይዘት እና አሰራርን ይዞ መምጣቱ ሲኔለይቲክ በድረ ገፁ አስነብቧል፡፡ መሳሪያው የተለያዩ መረጃዎችን በመጠቀም የቦክስ ኦፊስ የደረጃ ሰንጠረዥን በትክክል እንደሚገምት ተጠቁሟል፡፡ አንዱ የዚህ መሳሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ተዋንያን የሚመርጡበት ሂደት እንዴት በፊልሙ ትርፋማነት ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር መመልከት እንዲችሉ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡ ምንጭ፡-ስካይ ኒውስ
የሆሊውዱ የፊልም ኩባንያ ዋርነር ብሮስ በሰው ሰራሽ መሳሪያ (አርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ) ለማስገመት ያሰበው ምንን ነው?
የቦክስ ኦፊስን የደረጃ ሰንጠረዥ
26
አፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። አፈወርቅ ተክሌ በእንግሊዝ አገር የአዳሪ ተማሪ ቤትን ኑሮ ሲያስታውሱ የባዕድ ባህላት፣ የአየር ለውጥ እና የተለመደው የተማሪ ቤት ዝንጠላ እንዳስቸገራቸው ያወሳሉ። ቢሆንም ትምሕርታቸውን በትጋት ሲከታተሉ ቆዩ። በተለይም በሒሣብ፣ በኬሚስትሪ እና በታሪክ ትምሕርቶች ጥሩ ውጤት በማምጣት ሰለጠኑ። ነገር ግን አስተማሪዎቻቸው የተፈጥሮ ስጦታቸው ኪነ ጥበብ እንደሆነ ለመገንዘብ ብዙ ጊዜም አልወሰደባቸውም። በነሱም አበረታችነት በእዚህ ስጦታቸው ላይ የበለጠ ለማተኮር ወስነው በሎንዶን የኪነ ጥበብ ማእከላዊ ትምሕርት ቤት ተመዝግበው ገቡ እዚህ ትምህርት ቤት ጥምሕርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለከፍተኛ ጥናት በስመ ጥሩው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ የስሌድ ኪነ ጥበብ ማዕከል የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ተማሪ (ከተከተሏቸው አፍሪቃውያን አንዱ የሱዳን ተወላጁ ኢብራሂም ኤል ሳላሂ ናቸው) በመሆን ገቡ። እዚህ በስዕል፣ ቅርጽ እና በአርክቴክቸር ጥናቶች ላይ አተኩረው ተመረቁ። ትምሕርታቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ፣ በየጥቅላይ ግዛቶቹ እየተዘዋወሩ፣ በየቦታው እስከ ሦስት ወራት በመቀመጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እና የብሔረሰቦቿን ባህልና ወግ በሚገባ አጥንተዋል።
አፈወርቅ ተክሌ የምህንድስና ትምህርታቸውን ትተው ኪነጥበብ ለማጥናት ለመጀመሪያ ጊዜ የገቡበት ትምህርት ቤት ምን ይባላል?
በሎንዶን የኪነ ጥበብ ማእከላዊ ትምሕርት ቤት
903
ኬንያ የኬንያ ሪፐብሊክ በምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በሰሜን ከኢትዮጵያ፣ በሰሜን-ምስራቅ ከሶማሊያ፣ በደቡብ ከታንዛኒያ፣ በምስራቅ ከዩጋንዳ፣ በስሜን-ምዕራብ ከደቡብ ሱዳን፣ በደቡብ-ምስራቅ ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር ድንበር ትጋራለች። አውሮፓውያን አካባቢውን ማሰስ የጀመሩት ከ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲሆን የብሪታንያ መንግሥት የምሥራቅ አፍሪካ ፕሮቴክቶሬትን በ1895 እ.ኤ.አ. አቋቁሟል። ይህ ፕሮቴክቶሬት በ1920 እ.ኤ.አ. የኬንያ ግዛት ተብሎ ተሰይሟል። ነፃ የኬንያ ሪፐብሊክ በዲሴምበር 1963 እ.ኤ.አ. ታወጀ። የኬንያ ስም የመጣው በአፍሪካ በከፍታ ሁለተኛ ከሆነው ከደብረ ኬንያ ተራራ ነው። በዚሁ ተራራ ዙሪያ የሚኖሩት ነገዶች ስሙን «ኪኛ» (በካምባኛ)፣ «ኪሪማራ» (በአመሩኛ)፣ «ኪሬኛ» (በኤምቡኛ)፣ «ኪሪኛጋ» (በኪኩዩ)፣ ወይም «ኬሪ» (በመዓሳይኛ) ይሉታል። የነዚህ ስሞች ሁሉ ትርጉሞች «ቡራቡሬ» ሲሆኑ ይህም ደግሞ «ሰጎን» ማለት ነው፤ አመዳይ ያለበት የተራራው ጫፍ ለተመልካች ቡራቡሬ ወንድ ሰጎንን ያሳስባልና። በኦገስት 2010 እ.ኤ.አ. በተካሄደ ውሳኔ ሕዝብ መሠረት ከብሪታንያ የተወረሰው ሕገ መንግሥት በአዲስ ሕገ መንግሥት ተለውጧል። በአሁኑ ጊዜ ኬንያ በ፵፯ ካውንቲዎች (የአስተዳደር ክፍሎች) ተዋቅራለች። እነዚህ ካውንቲዎች በሕዝብ በተመረጡ ሰዎች የሚስተዳደሩ ሲሆን በናይሮቢ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግሥት በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ። የኬንያ ዋና ከተማ እና ትልቋ ከተማ ናይሮቢ ናት። የኬንያ ኢኮኖሚ በምሥራቅና መካከለኛው አፍሪቃ በጂ.ዲ.ፒ. ትልቁ ነው። ግብርና በአገሪቱ ትልቅ የሥራ ዘርፍ ሲሆን ከኤክስፖርቶች መካከል ሻይ፣ ቡና እና ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ አበባዎች ይገኛሉ። እንዲሁም ቱሪስምና ፔትሮሊየም አቢይ ዘርፎች ናቸው።
የኬንያ ሕገ መንግሥት በሕዝበ ውሳኔ የተሻሻለው መቼ ነው?
በኦገስት 2010 እ.ኤ.አ.
596
ዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
በዩጋንዳ ብዙ ተናጋሪ ያለው ቋንቋ ምንድን ነው?
ሉጋንዳ
1,446
ኤርትራ ኤርትራ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አገሮች አንዷ ስትሆን በስሜን-ምዕራብ ከሱዳን፣ በሰሜን-ምስራቅ ከቀይ ባህር፣ በደቡብ ከኢትዮጵያ፣ በደቡብ-ምስራቅ ጅቡቲ ጋር ድንበር ትካለላለች። ኤርትራ የሚለው ስም ከላቲን የተወሰደ እና ስረ-መሰረቱ የግሪክ ሐረግ ሲሆን ትርጉሙም ቀይ ማለት ነው። ይህን ስም ለአካባቢው የሰጡት ጣሊያኖች በጥር ፲፰፻፺ ቅኝ ግዛታቸውን ሲያውጁ ነበር (ተመሳሳይ ስም በጀርመኖች 1870 እና ግብጾች ፲፰፻፷ወቹ በጥቅም ላይ ውለዋል፣ ነገር ግን የትኛውን ክፍል ስሙ እንደሚመለከት ግልጽ አልነበረም)። ኤርትራ፣ እንደ ሐገር፣ በጣሊያኖች ከተመሰረተች በኋላ በ5 ልዩ ሂደቶች ውስጥ በማለፍ ነው ያሁኑን ቁመናዋን የያዘችው። ከ1890 በፊት የነበረው የአካባቢው ታሪክ በ«ኤርትራ» ስር የሚጠና ባህይሆንም ስለአዲሱ ኤርትራ ግንዛቤ ስለሚያስጨብጥ ታሪክ ተመራማሪዎች ከ፲፰፻፺ በፊት ያለውንም ታሪክ ማጥናት ተገቢ እንደሆነ ይስማማሉ። በ1860ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ፣ የግብጹ መሪ ኢስማኤል ከዴቭ ፓሻ በናይል ተፋሰስ ላይ ሰፊ የግብጽ ቅኝ ግዛት ለማበጀት ተነሳ። ለዚህ አዲሱ ግዛቱ ካርቱምን ዋና ከተማው በማድረግ የሱዳን ግዛቱን አጸና። ቀጥሎም የቀይ ባህርን ጠረፎች በ1865 ከተቆጣጠረ በኋላ በ1870ዎቹ መጀመሪያ ሐረርንና ተሻግሮ ሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ ግዛቶችን አበጀ። እንግዲህ በኒህ ግዛቶቹና በሱዳን መካከል የነበረው ብቸኛ መገናኛ መንገድ ካርቱም-ከሰላ- ከረን -ምፅዋ ብሎ የሚዘልቅ ነበር። ስለሆነም በ1872 ይህን ስልታዊ መንገድ የክዴቭ ፓሻ ሰራዊቶች ተቆጣጠሩ። መቆጣጠር ብቻ አይደለም በየመንገዱ ምሽግ እየሰሩና የአውሮጳ ምስዮናውያንን እርሻ ቦታ እየሰጡ ቅኝ ግዛት አበጁ። በዚህ ሳይቆጠቡ፣ የመንገዱን ደህንነት ዋስትና ለማስጠበቅ ሲሉ የአካባቢውን ደጋማ ክፍል መያዝ ግድ አላቸው። ደጋማው ክፍል በዚህ ወቅት በአጼ ዮሐንስ ግዛት ስር ነበር።
ኤርትራ ከሱዳን ጋር የምትዋሰነው በየት አቅጣጫ ነው?
በስሜን-ምዕራብ
40
አማ አታ አዪዶ ክሪስቲና አማ አታ አዪዶ በማርች 23፣ 1942 እ.ኤ.አ. ጋና ውስጥ ተወለደች። ትምህርቷን በዌስሊ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት፣ በመቀጠልም በጋና ዩኒቨርስቲ ተከታትላ በ1964 ዓ.ም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች። የመጀመሪያ የድርሰት ስራዋ የሆነውን «The Dilemma of a Ghost»ን በዚያ ዓመት ለማጠናቀቅ የበቃች ሲሆን ይሄው ድርሰቷ በሎንግማን አሳታሚ ድርጅት አማካይነት በቀጣዩ ዓመት ታትሞላታል። አዪዶ በልብ-ወለድ ደራሲነት ብቻ አይደለም እውቅናን ያተረፈችው፤ በጸሃፌ-ተውኔትነት እና ገጣሚነትም እንጂ። ጽሁፎቿ በአብዛኛው የዘመኑ የአፍሪካ ሴቶች ስላላቸው ሚና እና የምእራባዊው ባህል ስለሚያሳድርባቸው ኢርቱእ ተጽኖ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው። አዪዶ በ1982 የጋና የትምህርት ሚኒስትር ሆና ብትሾምም በስራው ላይ የቆየችው ለ18 ወራት ያህል ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት በብራውን ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ጥናት ክፍል ውስጥ ተጋባዥ ፕሮፌሰር በመሆን ትሰራለች።
አማ አታ አዪዶ ክሪስቲና መቼ ተወለደች?
በማርች 23፣ 1942 እ.ኤ.አ
27
ልዑል ራስ መኮንን የንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክ ተወካይ ሆነው ሁለት ጊዜ የአውሮፓን አገሮች ጎብኝተዋል። በዚህ ጊዜ እሳቸው ኢጣሊያን ሲጎበኙ በነበረ ጊዜ የኢጣሊያ ጋዘጦች የውጫሌ ውልን በተመለከተ፤ «...በውጫሌ ውል ላይ ኢትዮጵያ የኢጣሊያን ጥገኝነት ተቀብላ ውል ከፈረመች በኋላ የጀርመን ንጉሠ ነገሥት ከኢትዮጵያ የሚላከውን ማንኛውንም ደብዳቤም ሆን ጉዳይ በኢጣሊያ መንግሥት በኩል መቀበል ሲገባቸው በቀጥታ ከምኒልክ የተጻፈውን ደብዳቤ ተቀብለዋል...» እያሉ የጻፉትን ራስ መኮንን ተቃውሞአቸውን ለኢጣሊያ መንግሥት ከነገሩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የውሉን መበላሸት ለአጤ ምኒልክ አሳወቁ። ከኢጣሊያንም ጋር በተደረገውም ጦርነት ራስ መኮንን ፲፭ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ይዘው ከምኒልክ እና ታላላቅ ጦር አዛዦች ጋር ዘምተዋል። በ፲፰፻፺፰ ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለኅክምና ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ጥር ፬ ቀን ከከተማቸው ከሐረር ተነሱ። ጥር ፱ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የጥምቀትን በዓል አክብረው ከዋሉ በኋላ ሕመሙ ስለጸናባቸው ወደ ኋላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር። እዚሁም ሲታመሙ ከቆዩ በኋላ መጋቢት ፲፫ ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም ቁልቢ ላይ አርፈው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ። ዐፄ ምኒልክም የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው አዲስ አበባ እንዲሆን ባዘዙት መሠረት፤ ሰኞ ሚያዝያ ፳፪ ቀን በአዲስ አበባና በዙሪያው ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የክርስቲያን የፍታት ጸሎት ተድርጎ በማግስቱም ማክሰኞ የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ ፳፫ቀን ፲፰፻፺፰ ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ፤ መኳንንቱና ሠራዊቱ ተሰብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውና የራስ ወርቃቸው፤ ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸው ተይዞ ፈረስና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊቱ መካከል እየተመላለሱ ታላቅ ልቅሶ ተለቀሰላቸው።
ራስ መኮንን የዳግማዊ ምኒልክ ተወካይ በመሆን አውሮፓን የጎበኙት ስንት ጊዜ ነው?
ሁለት ጊዜ
41
ሞሪታኒያ ሞሪታኒያ (አረብኛ፡ موريتانيا‎) በይፋ የሞሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ፣ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ ከአትላንቲክ ውቂያኖስ፣ በደቡብ-ምዕራብ ከሴኔጋል፣ በምሥራቅና ደቡብ-ምሥራቅ ከማሊ፣ በሰሜን-ምሥራቅ ከአልጄሪያ፣ እና በሰሜን-ምዕራብ ከምዕራባዊ ሣህራ ጋር ትዋሰናለች። የአገሩዋ ስም የመጣው ከጥንቱ የሞሪታኒያ መንግሥት ነው። ዋና እና ትልቁዋ ከተማዋ ኑዋክሾት ናት። በዛሬው ሞሪታንኒያ በመጀመሪያ የሠፈሩት የባፎር ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ስዎች ከዘላን ሕይወት ወደ ግብርና ከተቀየሩት የመጀመሪያ የሰሃራ ሕዝቦች አንዱ ናቸው። ከ5ኛው እስከ 7ኛው ምዕተ ዓመት፣ ባፎሮች በበርበር ህዝቦች ፍልሰት ምክኒያት ተፈናቀሉ። ብዙዎቹ የሞሪታኒያ ሕዝብ በመቆያ ግብርና ቢኖሩም ይሄ ወደ ውጭ አገር ለመላክ አይደለም። በተለይ ወደ ውጭ የሚላከው ብረት፣ ፔትሮሊየም፣ እና ዓሣ ናቸው። ሞሪታኒያ በ12 ዊላያ በሚባሉ ክልሎችና በአንድ የአስተዳደር አካባቢ ተከፍላልች። እነዚህም ክልሎች በ44 ሙጋታ በሚባሉ ክፍሎች ተከፍለዋል።
ሞሪታንያ በአፍሪካ በየት አቅጣጫ ትገኛለች?
በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ
55
ጨረቃ ላይ መውጣት ጨረቃ ላይ መውጣት የምንለው ማናቸውም ሰው ሰራሽ መንኮራኩሮች ጨረቃ ገጽ ላይ ሲያርፉ ያለውን ክንውን ነው። ይህ እንግዲህ ሰውንም ሆነ ያለሰው የተደረጉ በጨረቃ የማረፍ ክንውኖችን ይጠቀላላል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰራሽ የሆነ ነገር ጨረቃ ላይ ያረፈው በመስከረም 13፣ 1959 እ.ኤ.አ. ሲሆን ይኸውም የሶቭዬት ህብረት ሉና 2 ሚሲዮን ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ እራሱ ጨረቃ ላይ የወጣው ሐምሌ 20፣ 1969 እ.ኤ.አ. ሲሆን ይኸውን በአሜሪካው የአፖሎ 11 ሚሲዮን መንኮራኩር ነበር። ባጠቃላይ 24 አሜሪካውያን ወደጨረቃ ተጉዘዋል፣ 12ቱ የጨረቃን ምድር በእግራቸው ረግጠዋል። በዚህ ወቅት ሶቪየት ህብረትም የራሷን ጠፈርተኞች ለመላክ ሞክራለች። ለዚህ እንዲረዳት ጨረቃ ላይ አራፊ LK የተሰኘ መንኮራኩር ሰራች፣ ሆኖም ግን ይህን መንኮራኩር ወደ ጨረቃ የሚወስድ ከባድ ሃይል ያለው ሮኬት ከአሜሪካ ቀድማ መስራት ስላልቻለች ተቀደመች። ዩጂን ከርናን የጨረቃን ምድር የረገጠው የመጨረሻው ሰው ነው።
ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ እራሱ ጨረቃ ላይ የወጣው መቼ ነው?
ሐምሌ 20፣ 1969 እ.ኤ.አ.
261
ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ እና የወይዘሮ ጥሩወርቅ ውቤ ልጅ ነበር። በ1860 ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ጦርነት ልጃቸው ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ወደ እንግሊዝ ሀገር ተወስዶ ነበር፡፡ ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡ በልዑሉ ውልደት የተደሰቱት አፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500 ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ በኋላ ከእድሜው ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴን ስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እና አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞዚቶች እና አጫዋቾች ተመረጡለት፡፡ አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብ ተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡ በመርከቢቱ ላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀ ወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉ አለማየሁን ማስከተል ያዘወትር ነበር፡፡ ይህንን የሁለቱን ፍቅር ያየው ጀነራል ናፒየርም ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ይልቁንም የአለማየሁን ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ ካፕቴን ስፒዲ እንዲረከብ ስለወሰነ ሁለቱ ሞግዚቶች ጉዞው ተጠናቆ እንግሊዝ ሀገር ሳይደርሱ ከስዊዝ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡ ከሶስት ወራት የመርከብ ላይ ጉዞ በኃላ አለማየሁ እንግሊዝ ሀገር ደረሰ፡፡
ልዑል አለማየሁ እና ጠባቂው ተሳፍረውበት ወደ እንግሊዝ ያቀኑባት መርከብ ማን ትባላለች?
ፌሬዝ
551
አብርሀም ሊንከን (የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፰ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም.) ድረስ የኖሩ ከ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትተው ተገደሉ። የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜሪ ቶድን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር መኖር ትንሽ የተቸገሩ ቢሆነም ከጊዜ ብዛት ግን ለምደዉ 4 ወንድ ልጆችን በተከተሉት አመታት ወለዱ። በ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን ሪፐብሊካን ፓርቲ መሥርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም. የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ። በጦርነቱ የስሜን ሠራዊት ከብዛታቸው የተነሣ በአራት ዓመት ውስጥ አሸነፉ። በዚህ ጊዜ ላይ ሊንከን ለአመጸኖቹ ባርዮች ነጻነት አዋጁ። ያላመጹ ዜጎች ባርያዎች ግን በዚያን ጊዜ ነጻ አልወጡም። በ፲፰፻፶፮ዓ.ም.ምርጫ ሊንከን በቀላል ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ተመረጡ። በሚያዝያ ፪ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. የኮንፌደራት ሠራዊት እጁን ሰጠ። ነገር ግን ሚያዝያ ፯ ቀን የመድረክ ትርዒት ሲያዩ በነፍሰ ገዳዩ በጆን ዊልክስ ቡዝ እጅ በጥይት ተመትተው በማግሥቱ ሞቱ። ከዚህም ትንሽ በኋላ ባርነት በሕግ በሙሉ ተክለክሎ የተረፉት ባርያዎች ነጻነት አገኙ።
አብርሃም ሊንከን መቼ ሞተ?
፲፰፻፶፯ ዓ.ም.
44
ታንዛኒያዊው ደራሲ አብዱልራዛቅ ጉራህ የ2021 የኖቤል የሥነ ጽሑፍ አሸናፊ መሆናቸውን የስዊድን አካዴሚ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1986 ዎሌ ሾይንካ በሥነ ጽሑፍ የኖቤል ተሸላሚ ከሆኑ ከ35 ዓመታት በኋላ አብዱልራዛቅ ጉራህ ሁለተኛው ጥቁር አፍሪካዊ ያሰኛቸውን ክብር ተቀዳጅተዋል፡፡ በመላው አፍሪካ ደረጃ ስድስተኛ ተሸላሚ ናቸው፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ አብዱልራዛቅ ለአሸናፊነታቸው ከስዊድኑ የኖቤል ሽልማት ድርጀት 10 ሚሊዮን ክራውን ወይም 1.14 ሚሊዮን ዶላር ያገኛሉ፡፡ የ73 ዓመቱ አዛውንት ጉራህ ጎልተው የሚታወቁትን ‹‹ፓራዳይዝ›› (Paradise) እና ‹‹ዲዘርሽን›› (Desertion) ጨምሮ የ10 ልብ ወለዶች ደራሲ ናቸው፡፡
ደራሲ አብዱልራዛቅ ጉራህ የስንት ዓመት ሰው ናቸው?
የ73
326
በኢትዮጵያ የሚገኙ በርካታ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች መንግሥት ተገቢውን ክትትል እያደረገ ባለመሆኑና ኩባንያዎች በክህሎት የበቁ ኢትዮጵያዊያን በሥልጠና ዕገዛ ባለማድረጋቸው ምክንያት፣ አብዛኛዎቹ በሲሚንቶ ፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሠሩት ሠራተኞች የውጭ ዜጎች መሆናቸው ተገለጸ፡፡ በኢትዮጵያ ምርት በማምረትና በግንባታ ላይ የሚገኙትን ጨምሮ 17 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚገኙ ሲሆን፣ 12ቱ በተለያየ የማምረት መጠን ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በበርካታ ፋብሪካዎች በተለይም ግዙፍ በሚባሉት ዳንጎት፣ ሙገርና ደርባ ኩባንያዎች ውስጥ የውጭ ዜጎች የማኔጅመንቱንና ቴክኒካል ሥራውን በበላይነት እንደሚይዙ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ስምረት ግርማ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም በሥራ ላይ በሚገኙት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች እንዳሉ የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሯ፣ ኢትዮጵያውያን እየሠሩባቸው ያሉ ዘርፎችም ቢሆን በዝቅተኛ ዕርከንና በጉልበት ሥራ ላይ የሚገኙ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ስምረት ግርማ ያላቸው ኃላፊነት ምንድን ነው?
የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር
371
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነስርአት ተካሄደ። የፋብሪካው ግንባታ በ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የሚከናወን ሲሆን በሀገሪቱ ያለውን የሲሚንቶ እጥረት ሊቀርፍ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ የት ነው የተቀመጠው?
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ
0
ሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው። ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ የእንግሊዝን አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ። ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በሩሲያኖች የተገነባው የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ እራሳቸውን ከሥልጣናቸው አስወገዱ። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - አቶ ለገሰ ዜናዊ አስረስ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አድዋ ላይ ተወለዱ።
የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት እምባቦ በተባለው ቦታ ላይ ውጊያ ገጠሙት በስንት ዓመተ ምህረት ነው?
ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት
238
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ስብሐት (ስብሐት ለአብ) ገብረ እግዚአብሔር (ሚያዝያ 27 [1928]ዓ.ም. - ሰኞ፣ ቀን ትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደ ፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው። ስብሐት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ በመነን መጽሄት የዝግጅት ክፍል ውስጥ ሰርቷል። በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲቋቋም በአርታኢነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በመንግሥት ትእዛዝም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን የካርል ማርክስ ሥራ የሆነውን ካፒታልን ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመመለስ ሥራ ላይ ተሳትፏል። ብዙዎቹ የስብሐት ሥራዎች በተጻፉበት ጊዜ ለመታተም ባይታደሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የህትመትን ብርሃን ለማየት በቅተዋል። ጽሁፎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይታተሙ ለመቆየታቸው ዋነኛው ምክንያቱ ስብሐት በመጽሐፉ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ባህል ያደገ አንባቢን አይን የሚያስፈጥጡ፣ ጆሮ የሚያስይዙ በመሆናቸው ነው። በገበያ ላይ በቅርብ የወጡት ድርሰቶቹ ከመጀመሪያ ቅጂያቸው ብዙ ለውጥ እና የአርትኦት ሥራ የተደረገባቸው እንደሆኑ ይነገራል። ስለዚሁ ጉዳይ ለአዲስ ላይቭ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገር «በጨለማ ያልተደረገውን ነገር አንድም የጻፍኩት የለም... ያለውን እንዳለ ነው የምጽፈው» ብሏል። ይህንኑም ከኤሚል ዞላ የአጻጻፍ ዘይቤ የወሰደው እንደሆነ ይናገራል። ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ደራሲ፣ አርታኢ፣ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም - የልብ-ወለድ ድርሰት ገጸባህርይም ነው። ደራሲው የተሰኘው የበአሉ ግርማ ልብ-ወለድ በስብሐት ህይወት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው። ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች አባት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነው።
ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በምን ዘርፍ ነው?
በትምህርት አስተዳደር
220
ጉጃራቲ ጉጃራቲ (ગુજરાતી) በህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ የሚገኝ ቋንቋ ነው። በዓለሙ ውስጥ በ46 ሚልዮን ሰዎች ይናገራል፤ ከነዚህም 45.5 ሚልዮን በህንደኬ፣ 250,000 በታንዛኒያ፣ 150,000 በዩጋንዳ፣ 100,000 በፓኪስታንና 50,000 በኬንያ አሉ። በሕዝብ ብዛት የዓለሙ 23ኛ ቋንቋ ነው። በምእራብ ህንደኬ ያለው የጉጃራት ክፍላገር ይፋዊ ቋንቋ ነው። የጉጃር ሕዝብ ወደ ህንደኬ የደረሱ በ5ኛው መቶ ዘመን ሲሆን በ6ኛው መቶ ዘመን ዛሬ ጉጃራት በሚባለው አገር ሰፈሩ። የራሳቸውን ቋንቋ ቶሎ ትተው እንደ አገሩ ሰዎች ሳንስክሪት ለመናገር ጀመሩ። በ12ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሳንስክሪት ተለውጦ ብዙ አዲስ ቋንቋዎች ተወለዱ። ከነዚሁም አንድ ጉጃራቲ ነበር። አብዛኛው ተናጋሪዎቹ የህንድ ሃይማኖት ተከታዮች ቢሆኑም ለረጅም ዘመን የእስላም ገዢዎች ስለነበሩባቸው ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከፋርስ ሆኗል። ከዚያ በላይ በንግድ ምክንያት ብዙ ቃሎች ከፖርቱጊዝ ወይም ከእንግሊዝኛ ተበደሩ። የሚጻፍበት በራሱ ጉጃራቲ ፊደል ነው፤ ይህም ከላይኛ መስመር በማጣቱ በስተቀር የህንዲ ደቫናጋሪ ፊደል ይመስላል።
ጉጃራቲ ቋንቋ 50,000 ያህል ተናጋሪዎች ያሉት በየት ነው?
በኬንያ
162
ጁፒተር እና ሳተርን ጁፒተር እና ሳተርን ከ4 መቶ አመት በሆላ ትላንት ምሽት በአንድ ላይ ገጥመው አንድ ፕላኔት መስለው ታይተዋል፡፡ ፕላኔቶቹ ከቀን ቀን እየተቀራረቡ መጥተው ትላንት ምሽት በአንድ ላይ በመግጠም ደማቅ ብርሃን ፈንጥቀዋል፡፡ የሁለቱ ግዙፍ ፕላኔቶች ምህዋር  በየ20 ዓመቱ የሚገናኙ ሲሆን ክስተቱ በብዛት በቀን ውስጥ ስለሚሆን በዓይን ለማየት ከባድ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ‘ዘ ስታር ኦፍ ቤቴልሄም’ ወይም የቤቴልሄም ኮከብ ተብሎ በሚጠራው በዚህ ክስተት ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ሰማይ ላይ እጅግ ደማቅ ብርሃን ታይቶ እንደነበር ሳይንቲስቶች መናገራቸውን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡
የቤተልሄም ኮከብ ተብሎ የሚጠራው ክስተት ከስንት አመታት በፊት ነበር?
ከ2 ሺህ
292
አዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።
አዲስ አበባ የተመሰረተችው መች ነው?
በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም.
571
ጣይቱ ብጡል «ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ዓ/ም በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ በ ፹ ቀናቸው ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፴፫ ዓ/ም በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ። እናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ከባለቤታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ከሞቱ በኋላ በጅሮንድ መዩ የተባሉትን የዓፄ ቴዎድሮስን ባለሟል አግብተው ነበር። እሳቸውም ጣይቱ ብጡል ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ ልዩ መምህር ቀጥረውላቸው እንደነበር ይታወቃል። እቴጌ ጣይቱ በማኅደረ ማርያም ሆነው ሲማሩና መፃሕፍትን ይቀጽሉ በነበሩበት ጊዜ ለቤተክርስቲያን መጋረጃ መሥሪያ በትርፍ ጊዜያቸው ፈትል እየፈተሉ ያቀርቡ ነበር። በበገና ቅኝትና ድርደራም በኩል የታወቁ ባለሙያ እንደነበሩ ይተረክላቸዋል። የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የዓፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ/ም በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገብተው በነሐሴ ፳፬ ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከተጫጩ ከሁለት ዓመት በኋላ ወይዘሮ ጣይቱን ለማስመጣት በቤተ መንግሥቱ በተደረገው ምክር መሠረት አለቃ ተክለማርያም ወልደ ሚካኤል ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ተላኩ። በዚያም አስፈላጊው ሁሉ በተፋጠነ ሁኔታ ተሟልቶ በጐጃም በኩል ደንገጡሮችና አሽከሮች አስከትለው ጉዞውን ጀመሩ። ደብረ ብርሃንም በገቡ ጊዜ ንጉሡ /ምኒልክ/ ታላቅ አቀባበል አደረጉላቸው። ከዚያም ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌ ብጡል ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የጋብቻቸው ስነ-ሥርዓት የፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ/ም በአንኮበር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ተጋቡ።
እቴጌ ጣይቱ ከንጉስ ምኒልክ ጋር በስንት ዓ.ም ተጋቡ?
ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ/ም
1,068
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍቢሲ) ኡበርና ሃዩንዳይ በራሪ ታክሲዎችን በጋራ ሊሰሩ መሆኑን አስታወቁ። ሁሉቱ ኩባንያዎች አዲስ የሚሰሩትን በራሪ ተሽከርካሪ በላስ ቬጋሱ የንግድ ትርኢት ይዘው እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል። አራት ተሳፋሪዎችን የሚይዘው በራሪ ታክሲ በሰዓት እስከ 320 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል ተገልጿል። ሁለቱ ኩባንያዎች በዚህ ሳምንት በላስ ቬጋስ በሚደረገው የንግድ ትርኢት ላይ የታክሲ አገልግሎት ይሰጣል ያሉትን በራሪ ተሽከርካሪ ሞዴል ይፋ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል። ኡበር በፈረንጆቹ 2023 ለደንበኞቹ የበራሪ ታክሲ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ነው የገለጸው።
ኡበር በራሪ ታክሲዎችን መቼ ለደንበኞቹ ለማቅረብ አቅዷል?
በፈረንጆቹ 2023
317
125ኛውን የአድዋ ድል በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለማክበር የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ካሳው አሶሳ ከተማ ገቡ። በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራርም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በዓሉም ከዛሬ ጀምሮ በፓናል ውይይት እና ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘት እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
125ኛው የአድዋ ድል የት ነው የሚከበረው?
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
19
በሕንድ ንጉሥ አሾካ መንግሥት የአሾካ አዋጆች ሕግጋት በ264 አክልበ. መሠረቱ። ከምዕራቡ ሮማ መንግሥት ውድቀት ደግሞ ወደ ተረፈው ሕዋእ ውስጥ ከፈለሱት ጀርመናውያን ወገኖች አብዛኛው የራሳቸውን ሕጎች ዝርዝር በጽሑፍ አወጡ። በተለይ የሚታወቁም የቪዚጎቶች አለቃ ዩሪክ ሕግ (463 ዓ.ም.)፣ የቡርጎንዳውያን ሕግጋት (እኚህ ለጀርመናውያንና ለሮማውያን የተለያየ ፍትሕ ነበራቸው)፣ የአላማናውያን ሕግጋትና፣ የፍራንኮች ሕግጋት ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የተጻፉት ከ492 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። በ498 ዓ.ም. የቪዚጎቶች አለቃ 2ኛ አላሪክ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስና አንዳንድ የተለያዩ የቀድሞ ሮማ ሐገጋት አከማችተው አዋጁአቸው። ከዚህም በኋላ የታዩ ሕጎች የሎምባርዶች ሕግጋት (635 ዓ.ም.)፣ የቪዚጎቶች አዳዲስ ሕግጋት (646 ዓ.ም.)፣ የአላማናውያን አዳዲስ ሕግጋት (722 ዓ.ም.) እና የፍሪዝያውያን ሕግጋት (777 ዓ.ም.) አሉ። በአውሮፓ አኅጉር ላይ የተጻፉት እነኚህ ፍትሖች ሁሉ በሮማይስጥ ቢጻፉም፣ በእንግሊዝ አገር ግን የተጠቀሙት ሕጎች ከኬንት ንጉሥ ኤጠልቤርት ሕጎች (594 ዓ.ም.) ጀምሮ በጥንታዊ እንግሊዝኛ የተቀነባበሩ ነበሩ። በ885 ዓ.ም. ታላቁ አልፍሬድ ይህንንና ሁለት የድሮ ፍትሖች ከሕገ ሙሴና ከሕገ ወንጌል ጋራ አጋጥመው የእንግሊዝ ሕገ መንግሥት ዶም ቦክ ሠርተዋል።
የሎምባርዶች ሕግጋት መች ነበር የታወጀው?
635 ዓ.ም.
417
መጋቢት ፪ ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን ያዘ። ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት (በኋላ ፕሬዚዳንት) ሪቻርድ ኒክሰን ኢትዮጵያን ጎበኙ ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ሊትዌኒያ እራሷን ከሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ውጭ ነጻ መሆኗን አወጀች። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ በልብ ምታት አረፈ።
ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ ማን ይባላል?
አሌክሳንደር ፍሌሚንግ
651
ዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።
በዩጋንዳ ዋናው የንግድ ቋንቋቸው ምንድን ነው?
ኪስዋሂሊ
1,479
ኃይሌ ገብረሥላሴ ኃይሌ ገብረሥላሴ በ ሚያዝያ ፲ ቀን ፲፱፻፷፭ (1965) ዓ.ም. በአሰላ ከተማ ፣ አርሲ ክፍለ ሀገር የተወለደ አቻ ያልተገኘለት ድንቅ የረጅም ርቀት ኢትዮጵያዊ ሯጭ ነው። ኃይሌ በሩጫ ዘመኑ በ ፲ ሺህ ፣ በ ፭ ሺህ፣ በግማሽ ማራቶን፣ በማራቶንና እንዲሁም በሌሎቹ የሩጫ ዓይነቶች ከ ፲፩ በላይ የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብሯል። ኃይሌ በሩጫ ችሎታው ጠንካራ የሆነበት ምናልባትም ከመንደሩ ከባሕር ጠለል በላይ ከፍታ ነው ተብሎ ቢታመንም የተፈጥሮ ጥንካሬው ዓለምን ያስደነቀ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ነው። ኃይሌ ሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ከመሆኑም በላይ በ፴፫ ዓመት ዕድሜው ፪ ሰዓት ከ፬ ደቂቃ በሆነ ጊዜ በመግባት የዓለምን ማራቶን ክብረ-ወሰን ሊሰብር ችሏል። ኃይሌ ገብረሥላሴ እስካሁን ድረስ ፳፮ የዓለም ክብረ-ወሰኖችን ሰብሯል። ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ በሲድኒ እና በአትላንታ ኦሊምፒኮች በ፲ ሺህ ሜትር ሩጫዎች ወርቅ አስመዝግቧል። በ ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም. ኤንዱራንስ (Endurance) የተባለ ስለ እራሱ የእሩጫ ድል ፊልም ተሠርቷል።
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ያሻሻለው ውድድሩን በምን ያህል ሰዓት በመሮጥ ነው?
፪ ሰዓት ከ፬ ደቂቃ
376
ኢንስታግራም እና ፌስቡክ በአሜሪካ የተገደሉትን የኢራኑ ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒን ሃሳብ የሚደግፉ መረጃዎችን ከገጻቸው እያስወገዱ ነው። የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ መተግበሪያዎቹ መረጃዎቹን ከገጸቸው የሚያስወገዱት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ተከትሎ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ መሰረት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ደንበኞች የጀኔራል ሱለይማኒን ሃሳብ ደግፈው በመተግበሪያዎቹ የሚያሰራጯቸውን መረጃዎች እያስወገዱ መሆኑ ተመላክቷል። በተለይም በኢራን የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ጄኔራሉን ደግፈው የሚያሰራጩትን መረጃ ከገጻቸው እያስወገዱ መሆኑንም አስታውቀዋል። ይህን ተከትሎም ኢራናውያን ኢንስታግራም እና ፌስ ቡክ በፈፀሙት ህገ ወጥ ተግባር እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። የኢራን መንግስት ቃል አቀባይ አሊ ሬቤይ በበኩላቸው፥ ድርጊቱን ዴሞክራሲያዊ አሰራርን ያልተከተለ እና ሃላፊነት የጎደለው ሲሉ ኮንነውታል። የኢራኑ ጀኔራል ቃሲም ሱለይማኒ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ትዕዛዝ በኢራቅ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ በሀገራቱ መካከል ውጥረት መንገሱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም አሜሪካ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው በተለያዩ ኢራናያውያን ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። ኢንስታግራም እና ፌስ ቡክም አሜሪካ ማዕቀብ በጣለችባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ሲተዳደሩ የነበሩ ገጾችን ከመተግበሪያቸው ማስወገዳቸውን አስታውቀዋል። ምንጭ ፥ ሲ ኤን ኤን
ኢንስታግራም እና ፌስቡክ የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ በኢራን ጀነራል አሟሟት ጋር በተየያዘ መረጃዎቹን ከገጸቸው የሚያስወገዱት በምን ምክንያት ነው?
አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ተከትሎ
135
ቅልልቦሽ ቅልልቦሽ የኢትዮጵያ ህጻናት በጠጠር የሚጫወቱት ሲሆን አጨዋወቱም አንዱዋን ጠጠር ወደአየር በማጉናት እሱዋ ባየር ላይ እያለች የተቻለን ያክል ጠጠር ከመሬት ማፈስ ነው። ባየር ላይ ያለችው ጠጠር ስትመለስ በተጫዋቹ እጅ "መቀለብ" ወይም "መያዝ" ይኖርባታል። ሳትያዝ መሬት ላይ ከወደቀች፣ ጨዋታው አለቀ ማለት ነው። ጨዋታው "ጠጠር" በመባልም ይጠራል። ብዙ አይነት የቅልልብልቦሽ ጨዋታዎች ሲኖሩ፡ በጣም የታወቀው "ዓይጥ አለብሽ" በመባባል የሚጫወቱት ነው። ልጆቹ ሁለት ወይም ሶስት ይሆኑና፡ አምስት ቆንጆ ድብልብል ጠጠሮች፡ ስፋትና ርዝመታቸው ከግማሽ ኢንች የማይበልጡ፡ ይለቅሙና መሬት ይቀመጣሉ። ቀድሞ "ብጀ" ያለ መጀመርያ ይጀምራል። ብጀ ማለት ብጀምር ማለት ነው። ያንን ለማለት እሽቅድምድም ነው።"ብቀ" ያለ ከርሱ የሚከተል ነው ማለት ነው፡፡ ብቀ ማለት ብቀጥል ማለት ነው። ሁለት ልጆች እኩል "ብቀ" ካሉ በድምጽም ቢሆን ቀድሞ "ብ!" ከአፉ የወጣው ሰው ሁለተኛነቱን ያገኛል። "ብቀጣጥል!" ያለ ሶስተኛ ነው። "እንጀራ ብጋግር!" ያለ አራተኛ ነው። አምስተኛ ካለ "ወጥ ብሰራ!" ብሎ ተራውን ያሳውቃል። በዚህ ተራ ተስማምተው ጀማሪው ይጀምራል።
በጣም የታወቀው የቅልብልቦሽ አይነት የትኛው ነው?
ዓይጥ አለብሽ
267
አሪዞና አሪዞና (Arizona) በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ክፍላገር ነው። ኒው ሜክሲኮ ፣ ዩታህ ፣ ኔቫዳ ፣ ካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ያዋስኑታል። የአሪዞና ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ የ30 ሰው ሴኔት እና የ60 ሰው ምክር-ቤት አለው። የሪፑብሊካን ፓርቲ በስቴቱ ዋነኛው ፓርቲ ነው። በ2002 እ.ኤ.አ. የአሪዞና ስቴት ሕግ-አውጪ ቅርንጫፍ በጀት 14.3 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በጀት ደግሞ 13.8 ቢሊዮን ዶላር ነው። የስቴቱ ሴኔተሮች እና ምክር-ቤት ተወካዮች ለሁለት-ዓመት ጊዜ ላልተወሰነ ብዛት ይመረጣሉ። ከ4 ጊዜ በላይ በተካካይ መመረጥ ግን አይችሉም። የሕግ-አስፈጻሚ ቅርንጫፍ በአስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን ለ4 ዓመት ሥልጣን ላይ ይቆያል። ያልተወሰነ ጊዜ መወዳደር ሲቻል ከሁለት ጊዜ በላይ ግን በተካካይ መመረጥ አይፈቀድም።
የአሪዞና ሕግ አስፈጻሚ ዘርፍ አስተዳዳሪነት ከስንት ጊዜ በላይ በተከታታይ መመረጥን ይከለከላል?
ከሁለት
442
ጨኖ ጨኖ ግራጫ ቢጤ የሆነ፣ ፈርጠም ያለ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ አፍሪቃ፣ በተጨማሪም በኮንጎ ደኖች የሚገኝ ዝንጀሮ ነው። በኢትዮጵያ የሚገኘው ዓይነት ጨኖ የፀጉሩ ቀለም ግራጫና ጥቁር የሆነ፣ ፊቱ የጠቆረ ሰማያዊ የሆነ፣ አገጭና አንገቱ ነጭ ነው። የወንዶቹ ክብደት እስከ 12 ኪ.ግ. ሲሆን፤ አማካዩ 4.5 ኪ.ግ ይመዝናሉ። ጨኖ የደን ዝንጀሮ ነው። የደን ዝንጀሮች ብዙ ጊዜ ከዝናባማ ሥፍራዎች ደኖች ውጪ አይገኙም። ጨኖ ግን ከነዚህ ደኖች ውጪም በሚገኙ ደኖች ውስጥ ይኖራል። በኢትዮጵያ፣ በጎደሬ ደን ውስጥ፣ ቴፒ አጠገብ ሜጢ አካባቢ ይገኛሉ። በተራራማ ሥፍራዎች ደኖችም እስከ 3000 ሜትር ከፍታ ድረስ ይገኛሉ። እጅጉን በዛፍ ላይ የሚገኝ ዝንጀሮ ነው። የሚገኘው በደን ዛፎች ግማሽ ላይ ነው። በተለያዩ ዓይነት ተግባሮች መገለጫ የሚሆኑ ሰባት ዓይነት ድምፆች አሏቸው። በቡድናቸው ውስጥ የሚታየው አብዛኛው ፀብ፣ በዋናው ወንድና ለአካለ መጠን ባልደረሱና ጎረምሳ ወንዶች መሃል የሚታየው ነው። በሴቶቹና ሕፃናትን በሚገድሉ ወንዶች መኻከል ከባድ ግጭት ያድጋል። በቡድኖች መኻከል የሚደረግ ግጭት የሚሆነው አልፎ አልፎ ነው። እንዲህ ያለ ግጭት የሚነሳው በድንበር አካባቢ በምግብ ሽኩቻ የተነሳ ነው። የእርግዝና ጊዜአቸውን 140 ቀን ነው። የልጆቻቸውን እድገትም ቀስ ያለ ነው። ከወለዱ ወዲያ ለሚቀጥለው እርግዝና 15 ወራት መቆየት አለባቸው።
ጨኖዎች በተራራማ ሥፍራዎች በምን ያህል ከፍታ ላይ ይገኛሉ?
እስከ 3000 ሜትር
370
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ላይ የሚሰራውን የተ.መ.ድ አካል (UNAIDS) ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊኒ ቢያንዩማን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ እና የዩኤን ኤድስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊኒ ቢያንዩማን በኢትዮጵያ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በተያዙ ዕቅዶች ላይ መምከራቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የተ.መ.ድ አካል ዩኤን ኤድስ በምን ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራል?
በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ላይ
17
ባሕር-ዳር ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች። ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎሜትር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት። ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ "ከባሕሩ-ዳር" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል። ባሕር-ዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕር-ዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር-ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር-ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር-ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ።
ባሕር ዳር በኢትዮያ በየትኛው አቅጣጫ የምትገኝ ከተማ ናት?
በሰሜን-ምዕራብ
35
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በአውሮፓ አገሮች መኻል ከ ፲፱፻፮ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፲፩ ዓ/ም መግቢያ፣ ለአራት ዓመታት የተካሄደ ጦርነት ነው። ይኼ ግጭት የዘመኑ ኃያላን አገራት በሁለት ተቃራኒ ወገን ተሰልፈው ያካሄዱት ግብግብ ሲሆን እስከ ሰባ ሚሊዮን ታጣቂዎች የተካፈሉበትና እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ትልቅ ጦርነት ነው። ለጦርነቱ ቅስቀሳ ብዙ ምክንያቶች በታሪክ ምሑራን ይጠቀሳሉ። ዓቢይ ከሚባሉት ነገሮች ግን የወቅቱ ኃያላን መንግሥታት የውጭ ጉዳይ ተልዕኮዎች ሲሆኑ የክብሪቱ መጫሪያ ምክንያት ግን የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያው ዘውድ አልጋወራሽ፣ አውስትሪያዊው አርች ዱክ ፍራንዝ ፈርዲናንድ በዩጎዝላቪያዊ ነፍሰ ገዳይ እጅ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም መገደል ነው። የሳቸውን መገደል ምክንያት በማድረግ የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ለ ሰርቢያ ንጉዛት ሊያሟሉት የማይችሉትን፣ አስር ነጥብ ያዘለ የእላፊ ገደብ ማስጠንቀቂያ ይሰጡና ገደቡ ሲያልፍ ቅድሚያውን እንደወጠኑት በሰርቢያ ላይ የጦር አዋጅ አወጁ። ይሄም የታቀደ ትንኮሳ ከአስር ዓመታት በፊት ተመሥርተው የነበሩትን ብዙ የትብብር ውሎችን የሚያንቀሳቅስ ሁኔታ ስለነበረ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሁሉንም ኃያላን መንግሥታት ጦርነቱ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስገደዳቸው። እያንዳንዳቸው ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሚያስተዳድሯቸው ቅኝ ግዛቶች ስለነበሯቸው እነዚህንም ቅኝ ግዛቶች በዚሁ ግብግብ ተሳታፊ አደረጋቸው። የአለማኛ ሠራዊት በ፲፱፻፻፲ ዓ/ም የምዕራብ የጦርነቱን ግንባር ማጥቃት ከጀመሩ በኋላ የአሜሪካ ሠራዊት ከአጋሮቹ ጋር ሲሰለፍ፣ የምዕራብ አገሮች ቡድን አለማኞቹን በማጥቃት እያቸነፏቸው መጡ። መጨረሻ ላይ ተሸናፊው የአለማኛ ሠራዊት መሸነፉን አምኖ ኅዳር ፩ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ/ም የእጅ መስጫ ውል ሲፈርም፤ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም የተለኮሰው ጦርነት አከተመ። አብሮትም የአውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ግዛት፣ የኦቶማን ግዛት ሲጠፉ የጀርመን እና የሩሲያ ኃያልነት በፖለቲካም ሆነ በጉልበት ተደምስሰው የአራቱንም ቅኝ ግዛቶች አሸናፊዎቹ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ተከፋፈሏቸው። የቀድሞ ኃያላን መንግሥታትትን ውድመት ያስከተለ ክስተት ከመሆኑም ሌላ፤ በመካከለኛ አውሮፓ የብዙ ትናንሽ ሉዓላዊ አገሮችን መወለድ፤ የዓለም መንግሥታት ማኅበርን መቋቋሚያ መንስዔ፤ ከሁሉም በላይ ግን በአውሮፓ አኅጉር የብሔራዊነትን መንፈስ የቀሰቀሰና የጀርመን ሽንፈትን ያረጋገጠው የቬርሳይ ውል በጀርመኖች ላይ ያስከተለው የጭቆና ስሜት አገራችን ኢትዮጵያ በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በፋሽስት ኢጣልያ በግፍ ስትወረር የተለኮሰውን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሻ ምክንያት መሆኑ ነው።
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ከመቼ እስከ መቼ ተካሄደ?
ከ ፲፱፻፮ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፲፩ ዓ/ም መግቢያ
51
ጣይቱ ብጡል «ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ዓ/ም በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ በ ፹ ቀናቸው ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፴፫ ዓ/ም በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ። እናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ከባለቤታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ከሞቱ በኋላ በጅሮንድ መዩ የተባሉትን የዓፄ ቴዎድሮስን ባለሟል አግብተው ነበር። እሳቸውም ጣይቱ ብጡል ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ ልዩ መምህር ቀጥረውላቸው እንደነበር ይታወቃል። እቴጌ ጣይቱ በማኅደረ ማርያም ሆነው ሲማሩና መፃሕፍትን ይቀጽሉ በነበሩበት ጊዜ ለቤተክርስቲያን መጋረጃ መሥሪያ በትርፍ ጊዜያቸው ፈትል እየፈተሉ ያቀርቡ ነበር። በበገና ቅኝትና ድርደራም በኩል የታወቁ ባለሙያ እንደነበሩ ይተረክላቸዋል። የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የዓፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ/ም በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገብተው በነሐሴ ፳፬ ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከተጫጩ ከሁለት ዓመት በኋላ ወይዘሮ ጣይቱን ለማስመጣት በቤተ መንግሥቱ በተደረገው ምክር መሠረት አለቃ ተክለማርያም ወልደ ሚካኤል ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ተላኩ። በዚያም አስፈላጊው ሁሉ በተፋጠነ ሁኔታ ተሟልቶ በጐጃም በኩል ደንገጡሮችና አሽከሮች አስከትለው ጉዞውን ጀመሩ። ደብረ ብርሃንም በገቡ ጊዜ ንጉሡ /ምኒልክ/ ታላቅ አቀባበል አደረጉላቸው። ከዚያም ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌ ብጡል ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የጋብቻቸው ስነ-ሥርዓት የፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ/ም በአንኮበር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ተጋቡ።
እቴጌ ጣይቱ በምን ሙያ ይታወቁ ነበር?
በበገና ቅኝትና ድርደራ
513
የቻይናው ግዙፉ የቴሌኮም  ኩባንያ ሁዋዌ በፈረንጆቹ 2019 240 ሚሊየን ስልኮችን ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ኩባንያው የሽያጭ ገቢው 850 ቢሊየን ዩዋን ወይም 122 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል ፡፡ ሽያጩ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ 18 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን፥ የተጠበቀውን ያክል ገቢ አለመገኘቱም ተመላክቷል ፡፡ የኩባንያው  መሳሪያዎቹን በመጠቀም ስለላ ሊያካሂድ ይችላል በሚል በአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ባለሥልጣናት  ላይ ስጋትን በመጫሩ ከአሜሪካ የግንኙነት መረቦች በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዛዝ መታገዱ ይታወሳል ፡፡ ይህም ለሁዋዌ አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሮ  ቆይቷል፡፡ ኩባንያው በ2020ም የተፈጠረውን ችግር በመቋቋም ገበያው ላይ መቆየት ተቀዳሚ አላማው መሆኑን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል። ምንጭ፡-www.cnet.com/
የሁዋዌ የ2019 ዓ.ም. ዓመታዊ ሽያጭ ከ2018 ዓ.ም. አንጻር በመቶኛ ምን ያህል ይልቃል?
18 በመቶ
173
መስከረም 24 ቀን 2012 የደቡብ ክልልን ሁለንተናዊ መረጃ የያዘ አትላስ እና የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ሥርአት ተመርቀው ለአገልግለት ተዘጋጁ፡፡ በደቡብ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አማካይነት በአዲስ መልክ ተዘጋጅቶ ትናንት የተመረቀው አትላስ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ዲሞግራፊያዊና መልክአ-ምድራዊ መረጃዎችን አካቶ መያዙ ተገልጿል። የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአቱም (የመረጃ ቋቱ) ላለፉት 10 ተከታታይ ዓመታት የነበሩ ሁለንተናዊ መረጃዎችን በድህረ-ገጽ አማካይነት ለማሰራጨት የሚያስችል ነው፡፡ በምርቃ ሥነ-ሥርዐቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሄለን ደበበ የስታቲስቲክስና መልክዐ-ምድር መረጃ ሥርዐት አስተዳደር የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ከያዛቸው የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ ከዚህ በፊት የነበረው የክልሉን አኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ዲሞግራፊያዊና መልክዐ ምድራዊ መረጃዎችን የያዘ አትላስ ላለፉት 15 ዓመታት ማገልግሉንና በአሁኑ ወቅት ያለውን ሁለንተናዊ የክልሉን እድገት ያካተተ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው አትላስ አስከ 2009 ዓ.ም ያለውን ክልላዊ መረጃ የያዘ እንደሆነ ገልጸው አጠቃላይ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የተመዘገቡትን ውጤቶች፣ የመሰረተልማት ስርጭቶችን፣ ዴሞግራፊያዊ፣ መልክዐ-ምድራዊና ሌሎች መረጃዎችን ማካተቱን ተናግረዋል ፡፡ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ለዕቅድ መነሻ የሚሆኑ መረጃዎች ታች ካሉ መዋቅሮች ብቻ እንደሚሰበሰቡ ገልፀው ይህም ተአማኒ መረጃ ለማግኘት የሚስቸግር አሰራር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ይፋ የተደረጉት አትላስና የመረጃ ቋት ይህንን የመረጃ ክፍተት የሚሸፍኑና በቀላሉም ተደራሽ የሚሆኑ በመሆናቸው በፍትሀዊነት ላይ የተመሰረቱ ዕቅዶችን ለማዘጋጀት ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ ብለዋል ፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዐቱ ላይ የደቡብ ክልል፣ የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር አካላት ተገኝተዋል፡፡
በአዲስ መልክ የተዘጋጀው የመረጃ አያያዝ ምን ምን መረጃዎችን አካቶ ይዟል?
የክልሉን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ዲሞግራፊያዊና መልክአ-ምድራዊ
162
ደቡብ አፍሪካ በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ። ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውን፣ ብሉምፎንቴንና ፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው። ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው። የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ። የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካ በተናጋሪ ብዛት 10ኛውን ደረጃ የያዘው ቋንቋ የቱ ነው?
ቬንዳ
221
ሰቆጣ ሰቆጣ ከ1956 ጀምሮ የዋግ አውራጃ ማዕከል እና የሰቆጣ ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከሰቆጣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የውቅሮ መስቀል ክርስቶስ አለት ውቅር ቤ.ክ. ይገኛል። በዚሁ ቤተ ክርስቲያን ላስታን ከሰቆጣ ሆነው ያስተዳደሩ ዋግሹሞች ደረቅ ቅሪቶች ይገኛሉ። ከአክሱም መዳከም በኋላ በአረብ ጸሐፊዎች ዘንድ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማነት ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰውኩባር የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ገናና ማዕከል ሰቆጣ እንደነበር በታሪክ ግንዛቤ አለ። ስለሆነም ይመስላል፣ ላስታን በዋግ ሹም ማዕረግ ያስተዳደሩ ገዢዎች መቀመጫቸው ሰቆጣ ነበር። ከጥፋት በተረፉ መዝገቦች ዘንድ ሰቆጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅሶ የምናገኘው በ1738ዓ.ም. ሲሆን፣ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ወደ ላስታ ባደረጉት ዘመቻ ሰቆጣ ውስጥ በዋግ ሹም ነዓኩቶ ለአብ (የዋግ ሹም ቴዎድሮስ አባት) ቤት ለ5ቀን እንዳረፉ ዜና መዋዕላቸው በማተቱ ነው ። ከዚያም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ የአውሮጳ ተጓዦች ሰቆጣን ሲጎበኙ፣ ዋልተር ፕላውዴን ለምሳሌ በኢትዮጵያ ከሚገኙ 5 ብቻ ነጋድራሶች አንዱ በሰቆጣ ይገኝ እንደነበር መዝግቧል። ከዚያም በ1800ዎቹ መጨረሻ ሰቆጣን የጎበኘው ኤ.ቢ.ዋይልድ ሰቆጣን የላስታ ዋና ከተማ አድርጎ ሲጠቅስ፣ የሰቆጣ ቤተ መንግስት ባለ ሶስት ፎቅና በ1650ዎቹ የተገነባ እንደነበር ያትታል። ቤተ መንግስቱን የሰሩት የፋሲል ግቢን አናጺዎ እደሆኑም መላምት ያቀርባል። ይሄው የአውሮጳ ተጓዝ፣ በ1880ዎቹ የሰቆጣ ገበያ ከአካባቢው ካሉት ሁሉ ግዙፉ እንደነበር ፣ የዝሆን ጥርስ እና በቅሎ ገበያው የደራ እንደነበር፣ እንዲሁም 21፣000 በሬዎች፣ 2፣900 ላሞች፣ 10ሺህ ፍየሎች፣ 1፣500 በጎች በየአመቱ ለግብይት ይቀርቡበት እንደነበር ሳይጠቅስ አላለፈም። ጥር 2፣ 1929 ጣሊያኖች በሰቆጣ ላይ የመርዝ ጋዝ ቦምብ እንደጣሉ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
ሰቆጣ መቼ ነዉ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የነበረችው?
ከአክሱም መዳከም በኋላ
168
የጥምቀት በዓል በክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዓ/ም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ በዓል ነው። መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው። በአገራችን፣ ጥር ፲ ቀን፣ በከተራ፣ በገጠር ወራጅ ውሃ የሚከተርበት፣ ታቦታት ከየአቢያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በምዕመናን ታጅበው እየዘመሩ ይሄዳሉ። እዚያም በየተዘጋጀው ድንኳን እንዲያርፉ ተደርጎ ሌሊቱን እዛው ያሳልፋሉ።በከተሞች ግን ሰው ሰራሽ ግድብ ይሰራል። ጥር ፲፩ ቀን የጥምቀት ዕለት፤ በገጠር፣ ጎኅ ሲቀድ ምእመናን እዚያው በድንኳኑ ዙሪያ አስቀድሰው ሲጨርሱ በካህናት መሪነት ሁሉም ወደከተራው ያመራና ውሃውም ተባርኮ ሕዝቡ ይረጫል። «ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ፤ ሰማያዊው በመሬታዊው እጅ ተጠመቀ» የሚለው የዕለቱ ቀለም በሊቃውንቱ አንደበት በያሬዳዊ ዜማ ጎልቶ ይሰማል። ከዚህ ሥነ ሥርዓት በኋላ በመቋሚያ፣ በከበሮና በጽናፅል በሚታጀብ ኃይማኖታዊ ዝማሬ፣ ወንዱ በሆታ፤ ሴቱ በእልልታ፤ ካህኑ በሃሌታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደያመጣጣቸው ወደየ ቤተክርሲያናቸው ይመለሳሉ። በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየጥምቀተ ባሕሩ የሚከበሩ በመኾናቸው፣ ሀገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብ በመፍጠሩ፣ ቱሪስቶችን መሳቡ አልቀረም። ጥቁርና ነጭ፣ ቀይና ብጫ ያለም ዘር፣ ከአዲስ አበባ እስከ ላሊበላ፣ ከአክሱም እስከ ጎንደር በሁሉም ሥፍራዎች በዚሁ ዓይነት ደምቆ ይከበራል። የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ ፍፁም በሚማርክ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁል ጊዜ አዲስ ነው። ሊቃውንቱ እንደሚናገሩት፣ ዘመነ አስተርእዮ የሚባለው፣ ከጥር ፲፩ ቀን ጀምሮ እስከ ጾመ ነነዌ ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ አምላክ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡ፣ በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር መታወቁ፣ በቃና ዘገሊላ በተደረገው ሠርግ ላይ የመጀመሪያው ተዐምር በመፈጸሙ፣ አምላካዊ ኃይሉ መገለጡ፣ እየታሰበ ምስጋና ይቀርባል። ይህ ሁነት ኢትዮጵያ ብሂልን ከባህል ጋር አዛምዳ ከሌላው የክርስቲያን ዓለም በተለየ አከባበር በዓሉን ማክበሯ፣ አያሌ ቱሪስቶችን ለመሳብ አስችሏታል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስንት ዓመተ ምህረት ተጠመቀ?
በ፴ ዓ/ም
76
ጎጉል እና አፕል ለስለላ ጥቅም ላይ ይውላል በማለት የጠረጠሩትን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን መተግበሪያ ቶቶክን ማስወገዳቸው ተገለፀ፡፡ ቶቶክ የተሰኘው ይህ መተግበሪያ ሰዎች በቀላሉ በተንቀሳቃሽ ምስል እና በፅሁፍ  እንዲያወሩ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ ኔውዮር ታይምስ አንደዘገበው ከዋትስ አፕ ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጠው ቶቶክ  በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ለስለላ መሳሪያት ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል፡፡ ኔውዮርክ ታይምስ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ በዘገባው እንዳሰፈረው ቶቶክ የተሰኘው መተግበሪያ ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሰላዮች የተጠቃሚዎችን ውይይት ፣ እንቅስቃሴ  እና ፎቶ መሰል የግል መረጃዎች  አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ጎግል ይህን መተግበሪያ ባለፈው ሀሙስ ማጥፋቱ የተገለፀ ሲሆን አፕልም  ጎግልን በመከተል በቀጣዩ ቀን ከመተግበሪያ ዝርዝሮቹ ውስጥ ማጥፋቱ ተጠቁሟል፡፡ ቶቶክ መተግበሪያ ለተጠቃሚዎቹ በቅርቡ በአፕ ስቶር እንደሚመለስ  አስታውቋል፡፡ ኩባንያው ባስተላለፈው መልዕክት በጎግል ስቶር እና በአፕል ስቶር በጊዜያዊነት እንደማይገኝ የገለፀ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የቴክኒክ ጉዳይ መሆኑን ገልጿል፡፡ ምንጭ፡- ቢቢሲ በፌቨን ቢሻው  
ጎጉል እና አፕል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን መተግበሪያ ቶቶክን ማስወገዳቸው በምን ምክንያት ነው?
ለስለላ ጥቅም ላይ ይውላል በማለት
12
እንደ ፕላቶ ዘገባ፣ የሶቅራጠስ እናት ፌናርት የተሰኘች አዋላጅ ነበረች። ሶቅራጠስ እናቱ ሴቶች ልጅ እንዲወልዱ እንደምትረዳ ሁሉ እርሱ ደግሞ ሰዎች አዳዲስ አሳቦችን እንዲወልዱ ለመርዳት እንደሚሞክር መናገሩ ይጠቀሳል። የሶቅራጠስ አባት ድንጋይ አናጢ የነበረው ሶፍሮኒስከስ እንደነበር ይጠቀሳል። ሶቅራጠስ በዘመኑ ድሃ የነበረ ሲሆን ለዚህ ምክንያቱ ከገንዘብ ይልቅ እውቀት ይበልጣል ብሎ ስለሚያምን ነበር። ሶቅራጠስ ስራ እንደማይሰራና በፍልስፍና ሃሳብና ክርክር ጊዜውን እንደሚያሳልፍ ፕላቶ ዘግቦት ይገኛል። ዛንቲፕ የተሰኘች ከርሱ በዕድሜ በጣም የምታንስ ሴትን አግብቶ ሶስት ልጆች እንደነበሩት ፕላቶ ጽፏል። ሶቅራጠስ 70 ዓመት በሞላው ጊዜ የአቴና መንግስት እንዲያዝና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረገ። በወቅቱ ሁለት ክሶች ሲቀርቡበት አንደኛው "በትምህርትህ ወጣቱን አበላሽተሃል" የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ለግሪክ ጣዖታት አልተገዛህም" የሚል ነበር። እንደ ፕላቶ ዘገባ ግን ሶቅራጠስ የግሪክ ጣኦታት አምላኪ ነበር። በአንድ አንድ ተመራማርወች ዘንድ የአቴንስ መንግስት ያቀረባቸው ክሶች በውሸት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የሆኖ ሆኖ፣ ክሪቶ የተሰኘው የፈላስፋው ጓደኛ ለጠባቂወቹ ጉቦ በመስጠት እንዲያመልጥ ሁኔታውን አመቻችቶ ነበር። ሶቅራጠስ ግን እምቢ በማለት ቀረ እንጂ አላመለጠም። ሶቅራጠስ ለፍርድ በቀረበ ጊዜ ሰፊ የሆነ የመከላከያ ክርክር በማቅረብ የአቴናን መንግስት ክስ ውድቅ ለማደርግ ሞክሯል። ከዚህ በኋላ ዳኞቹ ምን አይነት ቅጣት እንዲበይኑበት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት፣ ለአቴና ህብረተሰብ ካበረከተው ጥሩ ተግባራቱ አንጻር በቀሪው ዘመኑ ሁሉ ነጻ እራት እንዲያመጡለት ተናገረ። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ወይ በቅጣት እንዲለቀቅ ወይንም ደግሞ እንዲገደል የእጅ ምርጫ አደረገ። ውጤቱም ሶቅራጠስ እንዲገደል የሚል ሆነ። ይሁንና ሶቅራጠስ ሞትን አይፈራም ነበር። ሞቱን ለማስቀረት ይቅርታም ሆነ ሌላ ማባበያ አላቀረበም። በርሱ ሥነ ምግባር መሰረት ላመነበት ነገር እስከመጨረሻ መቆሙ ሰናይ ድርጊት ነበር። ስለሆነም ሄምሎክ የተሰኘ መርዝ ጠጥቶ እንዲሞት ስለታዘዘ፣ መርዙን በመጠጣት አለፈ።
የሶቅራጥስ አባት ማን ይባላል?
ሶፍሮኒስከስ
163
አዳም ረታ አዳም ረታ ልቦለድና ግጥም በአማርኛ የሚጽፍ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነው። አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በትምህርት አለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው ልቦለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት። ከተደራሲው ጋር የተዋወቀበት እና በኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ተከታታዮችና አንባቢዎች ልብ ውስጥ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠበት “አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት የታተመው በ1977 ዓ.ም ነው። (በዚህ መድብል ውስጥ አራት ስራዎችን አዋጥቷል፡ “ድብድብ”፣ “ዕብዱ ሺበሺ”፣ “ሲሮኮ” እና “ሲፊንክስ”) ሜጋ አሳታሚ ድርጅት በ1990 ዓ.ም ባሳተመው “ጭጋግና ጠል” የአጭር ታሪኮች ስብስብ “ዘላን” የተባለው ልቦለዱ ታትሟል። እነዚህ ሁለቱ ከሌሎች ደራሲዎች ስራዎች ጋር የታተሙለት ስለሆነ እንደ ወጥ ሳይቆጠሩ ነው ከላይ የሰፈረው የተባለው። በ1981 ዓ.ም በኩራዝ አሳታሚ የታተመው “ማህሌት” የደራሲው የመጀመሪያ ወጥ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መፅሀፍ ነው። በሻማ ቡክስ በ1997 ዓ.ም የታተመው “ግራጫ ቃጭሎች” እንደ ብሉይ (classic) ሥራ ሊታይ የሚችልና የደራሲው ልዩ ብቃት የታየበት ወጥ ረጅም ልብወለድ ነው። በ2001 ዓ.ም ሁለት ልዩ ስራዎች ይዞ የቀረበው አዳም፡ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነው “አለንጋና ምስር” እና እርስ በርሳቸው በቀጭን የታሪክ ክር የሚገናኙ ልብወለዶች (ኖቬላዎች) ያካተተው “እቴሜቴ ሎሚ ሽታ” ለአንባቢያን አበርክቷል። ይህ የአጻጻፍ ስልቱ ሕጽናዊነት የሚባል ሲሆን ደራሲው በሌሎቹ መጻሕፍቱም ውስጥ በስፋት ተጠቅሞበታል፡፡ በቀጠሉት ሦስት ዓመታት በየዓመቱ አንዳንድ መፅሐፍ ለአንባቢያ ያደረሰ ሲሆን በ2002 ዓ.ም “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር”፣ በ2003 ዓ.ም “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” እና በ2004 ዓ.ም “ሕማማት እና በገና” ታትመው ለንባብ በቅተዋል። “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር” በተሰኘው መፅሀፉ ድንቅ የፋንታሲ (“ፈንጠዚያ”) ሥራዎች የተካተቱ ሲሆን በ”ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” ለመጀመሪያ ጊዜ መቼቱን ከሀገር ውጭ በማድረግ የውጭውን ሕይወት በስሱ የዳሰሰ ሲሆን ከሌሎቹ ስራዎቹ በተለየ መልኩ ስለሀገራችን ፖለቲካ ወጣ-ገባ መንገድ በታዛቢ አይን ምልከታው፣ ትውስታውን … አስፍሯል፡፡ ሕማማትና በገና የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ ሲሆን ለየት ያለ ቅርፅ ያላቸው አንዳንድ ልቦለዶች ተካተውበታል። ፍልስፍናውና ስልቱ ሕፅናዊነት በሚል ስያሜው ይፋ ሆኗል።
የአዳም ረታ የመጀመርያ መፅሃፍ ምንድን ነው?
አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች
352
ነሐሴ ፳፯ ነሐሴ ፳፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፰ ዕለታት ይቀራሉ። ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ። ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አረፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ነጻነትን አስከትሎ በጃዋሃርላል ኔህሩ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ የሕንድ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት።
ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ለመቀበል የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን ከቀየሩ በኋላ በስንት ዓመት ዘግይታለች?
በሁለት መቶ
255
አፋር (ክልል) አፋር ክልል (ክልል 2) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ዋና ከተማው ሰመራ ሲሆን የቀድሞዋ ከተማ ግን አሳይታ ነበረች። 96,707 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሸፍን በ1999 እ.ኤ.አ. የሕዝብ ብዛቱ 1,188,000 ነው። የድንቅ ነሽ ወይም ሉሲ አጽም በአፋር ክልል ውስጥ በ, 1967 (Nov. 24, 1974 እ.ኤ.አ.) ነው የተገኘው። በማርች 5, 2005 ደግሞ ሌላ 3.8 ሚሊዮን ዓመት የሚገመት አጽምም በዚሁ ክልል ተገኝቷል።
በአፋር ክልል ውስጥ የተገኘችው ረጅም እድሜ ያስቆጠረችው የሰው ቅሪተ አካል ማን ትባላለች?
ሉሲ
176