id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-46551607
https://www.bbc.com/amharic/news-46551607
በጥሞና ላይ የነበሩት የቡድሂስት መነኩሴ በአቦሸማኔ ተገደሉ
በህንዷ ግዛት ማሀራሽትራ በጥሞና ላይ የነበሩት መነኩሴ በአቦሸማኔ እንደተገደሉ የአካባቢው ባለስልጣናት ገለፁ።
ለነብሮች ተከልሎ በሚገኘው ታቦዳ ጫካ ውስጥ ራሁል ዋልኬ የተሰኙት መነኩሴ በጥሞና ላይ እንደነበሩ መገደላቸውን ፒቲአይ የተባለው የዜና ወኪል ለባለስልጣናቱ ገልጿል። በጫካው አካባቢ በሚገኘው የቡድሂስት ቤተመቅደስ ውስጥ ያገለግሉ የነበሩት ራሁል ለጥሞና በሚል ወደ ጫካው ራቅ ብሎ እንደገቡ ዘገባዎች ጠቁመዋል። በአካባቢው በጥበቃ ስራ የተሰማሩ ሰዎች መነኩሴው ከአካባቢው ራቅ ብሎ እንዳይሄዱ አስጠንቅቀውት እንደነበረም ገልፀዋል። •ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •ሴት እስረኞችና የማዕከላዊ ምርመራ ነገር ግን መነኩሴውን የገደለው አቦሸማኔ ለመያዝ እቅድ እንደተነደፈም የአካባቢው የጥበቃ ባለስልጣን የሆኑት ጂፒ ናራዋኒ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ይህንንም ለማከናወን ሁለት ዋሻዎችን ያዘጋጁ ሲሆን ወጥመድና ማደንዘዣንም ጨምረው እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል። የመንግሥት ባለስልጣናት ጨምረው እንዳሳወቁት ለሟቹ መነኩሴ ካሳ የሚሆንም 1.2 ሚሊዮን ሩፒ ወይም 16 ሺ ስምንት መቶ ዶላር ለቤተሰቦቹ ይከፈላቸዋል። በዚሁ ቤተመቅደስ የሚያገለግሉት ሌላኛው መነኩሴ ጥቃት ሲደርስባቸው የተመለከቱ ሲሆን እርዳታ ለመጠየቅ በሄዱበት ሰዓት ሞተው እንዳገኛቸው ገልፀዋል። ታዶባ ተብሎ የሚጠራው ጫካ 88 ነብሮች ያሉት ሲሆን፣ ከዚያም በተጨማሪ አቦሸማኔና ሌሎችም እንስሳቶች መኖሪያ ነው ተብሏል።
news-53180594
https://www.bbc.com/amharic/news-53180594
አብዮተኛው ቼ ጉዌቫራ የተወለደባት ቤት ለገበያ ቀረበች
የግራ ዘመሙ አብዮተኛ የቼ ጉዌቫራ የትውልድ ቤት ለሽያጭ ቀረበ።
ቼ ጉዌቫራ የተወለደበት የአርጀንቲናዋ ግዛት ሮዛሪዮ የሚገኘው ህንፃ የ20ኛው ክፍለ ዘመን አብዮተኛ ኤርነስቶ ቼ ጉዌቫራ የተወለደበት ቤት ለሽያጭ የቀረበው በአርጀንቲና ሮዛሪዮ ከተማ ነው፡፡ አሁን የቤቱ ባለቤት የሆነው ሰው ፍራንሲስኮ ፋሩጊያ ይባላል፡፡ ይህንን ታሪካዊ ቤት ገዝቶት የነበረው በነርሱ አቆጣጠር በ2002 ዓ. ም ነበር፡፡ ቼ የተወለደባት ይቺ 240 ካሬ የሆነች አፓርታማ በዓለም ላይ ልዩ ቦታ ከሚሰጣቸው መኖርያ ቤቶች አንዷ ናት፡፡ ልዩ ቦታ ያሰጣትም የአብዮተኛው የቼ ኩቬራ የትውልድ ቤት በመሆኗ ነው፡፡ የቤቱ ባለቤት የቼን የትውልድ ቤት የባሕል ማዕከል ለማድረግ ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡ ይህ አሁን ቤቱን ለገበያ ያቀረበው ነጋዴ ቤቱ የሚሸጥበትን ዋጋ ተመን ገና ይፋ አላደረገም፡፡ በሮዛሪዮ ከተማ እምብርት ላይ ኡርኩዛ እና በኢንትሬ ራዮስ በሚባሉ ጎዳናዎች መሀል የሚገኘው ይህ አፓርታማ ህንጻ ባለፉት ዓመታት በጎብኚዎች የሚዘወተር ስፍራ ነበር፡፡ የቼ ጉዌቫራን የትወልድ ቤት ከጎበኙ ታዋቂ ሰዎች መሀል የዩራጓዩ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆዜ ፔፔ እና የፊደል ካስትሮ ልጆች ይገኙበታል፡፡ ምናልባትም የዚህ ቤት ታሪካዊ ጎብኚ ተብለው ከተጠቀሱት ሰዎች መሀል አልቤርቶ ግራናዶስ ይገኝበታል፡፡ አልቤርቶ ከራሱ ከቼ ጉዌቫራ ጋር ድሮ ወጣት ሐኪም ሳለ በ1950ዎቹ በደቡብ አሜሪካ አገራት በሞተር ሳይክል ተጉዘው ነበር፡፡ በኛ አገር የግራ ዘመም ፖለቲካ ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው ቼ ኩቬራ የተወለደው እንደ ጎርጎሳውያኑ በ1928 በአርጀንቲና ነበር፡፡ ለጭቁኖች መብትና ነጻነት ሲታገል የኖረው ቼ የተወለደው እጅግ የተደላደለ ኑሮ ከሚመራ ሀብታም ቤተሰብ ነው፡፡ ነገር ግን በኋላ ላይ በደቡብ አሜሪካ አገራት በተለይም በቺሊ፣ በፔሩና በቪኒዝዌላ የተመለከተው ድህነትና ጭቆና ለትግል እንዳነሳሳው ይነገራል፡፡ ከ1953 እስከ 1959 (እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር) የተካሄደውን የኩባ አብዮትን ከፊት ከመሩት ሰዎች አንዱ ቼ ጉዌቫራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ አብዮት የዚያን ዘመኑ የኩባ አምባገነን ፉልጌንቺዮ ባቲስታ ከመንገበራቸው ተፈንግለዋል፡፡ ቼ ከዚህ ስኬታማ አብዮት በኋላ አርፎ አልተቀመጠም፡፡ ይባስ ብሎ ድንበር እየተሻገረ ለጭቁኖች ትግል ራሱን ሰጠ፡፡ ሌሎች የደቡብ አሜሪካና በመላው ዓለም የሚገኙ ጭቁን ሕዝቦችን ነጻ ለማውጣት ቆርጦ ተነሳ፡፡ ከኩባ ተነስቶ ወደ ቦሊቪያ በመሻገር በያኔው ፕሬዝዳንት ሬን ባሬንቶስ ላይ አመጽ ቀሰቀሰ፡፡ በመጨረሻ በአሜሪካ ልዩ እርዳታ የቦሊቪያ ጦር ቼ ኩቬራን ከነ ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡ እንደ ጎርጎሳውያኑ በጥቅምት 9፣ 1967 ላ ሂጓራ በምትባል ገጠር ውስጥ ተገደለ፤ ሬሳው የተቀበረውም ምስጢራዊ በሆነ ቦታ ነበር፡፡ ከተገደለ ከ30 ዓመታት በኋላ በ1997 ቼ የተቀበረበት ምስጢራዊ ስፍራ በመታወቁ ሬሳው ወደ ኩባ ተመልሶ በክብር በድጋሚ እንዲያርፍ ተደርጓል፡፡ ቼ አሁንም ድረስ በዓለም ሕዝቦች መሀል በሁለት አጽናፍ የሚታይ አወዛጋቢና ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ነው፡፡ አፍቃሪዎቹ አብዮተኛና ድንበር ያልገደበው ለሰው ልጆች ሁሉ የታገለ የጭቁኖች አባት አድርገው ሲመለከቱት ሌሎች ደግሞ ጨካኝና ጨፍጫፊ አድርገው ይስሉታል፡፡
news-52081420
https://www.bbc.com/amharic/news-52081420
ኮሮናቫይረስ፡ ስለኮቪድ-19 እስካሁን ያላወቅናቸው 9 ነገሮች ምንድን ናቸው?
የኮሮናቫይረስ በፊትም የነበረ ቢሆንም ዓለም ግን በደንብ የተገነዘበው ከባለፈው ታኅሳስ ወር ጀምሮ ነው።
የመድሃኒት ቅመማን የሚያሳይ ምስል ስለቫይረሱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በመላው ዓለም ሳይንቲስቶች የሚያደርጉት ብርቱ ጥረት ቢኖርም ብዙ የማናውቃቸው ነገሮች ግን አሁንም አሉ። አሁን በመላው ዓለም የዚህን አወዛጋቢ ቫይረስ ስውር ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት ሁላችንም የቤተ ሙከራ አካል ሆነናል። ምክንያቱም ቫይረሱ በምድራችን በመሰራጨት ሁላችንም ተጋላጭ የመሆናችን እድል ሰፍቷልና። የኮሮናቫይረስ ሲነሳ የሚከተሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ የሚሹ ናቸው። 1. ምን ያህል ሰዎች በወረርሽኙ ተይዘዋል? ይህ በጣም መሰረታዊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ ጥያቄም ነው። በእርግጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠርና በምርመራ የተረጋገጡ የታማሚዎች ቁጥር መኖሩ የታወቀ ነው። ይህ ግን ቫይረሱ ከያዛቸው ሰዎች ብዛት አንጻር በጣም ትንሽ ቁጥር ነው። ቁጥሩ በራሱ ትክክል የማይሆንበት ጊዜ አለ። ምክንያቱም ሰዎች በቫይረሱ ተይዘውም ምንም የህመም ምልክት ሳይታይባቸው እንደ ጤነኛ መንቀሳቀስ ይችላሉና። ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በፍጥነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሳሪያ ቢሰራ ለተመራማሪዎች ነገሩ ቀላል ይሆናል። ከዚያ በኋላ ነው ቫይረሱ በፍጥነት መሰራጨቱም ሆነ መገታቱ ሊታወቅ የሚችለው። 2. ኮሮናቫይረስ ምን ያህል ገዳይ ነው? በአጠቃላይ የቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥር እስካልታወቀ ድረስ የቫይረሱን የገዳይነት ደረጃ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። አሁን ባለው ሁኔታ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ሰዎች መካከል 1 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት ብቻ ሞተዋል። ነገር ግን በጣም በርካታ በሽታው ኖሮባቸው ምልክቱ ግን የማይታይባቸው ሰዎች ካሉ የሞት መጠኑ ከዚህም ያነሰ ነው ለማለት ይቻላል። ስለዚህ ትክክለኛ አሃዙን ወይም የገዳይነቱን ደረጃ ለማስቀመጥ ትክክለኛው የታማሚዎች ቁጥር መታወቅ አለበት ማለት ነው። 3. የቫይረሱ ምልክቶች ምን ምን ናቸው? ዋነኞቹ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ትኩሳትና ደረቅ ሳል ናቸው። እነዚህን በጥንቃቄ መከታተል ያስፈልጋል። የመተንፈሻ አካላት መድረቅን ተከትሎ የራስ ምታት የሚያስከትል ሲሆን በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ ደግሞ ተቅማጥም አሳይቷል። በሌላ በኩል አንዳንዶቹን ታማሚዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ የማሽተት አቅማቸውን ያጠፋዋል የሚሉም አሉ። ዋናው ጥያቄ ግን በአንዳንድ ታማሚዎች ላይ የጉንፋን ምልክት የሚመስሉ በአፍንጫ ፈሳሽ የማመንጨትና የማስነጠስ ምልክቶች መኖራቸው ነው። ዋናዎቹ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ትኩሳትና ደረቅ ሳል ናቸው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በዚህ ሳቢያ ሰዎች መታመማቸውን ሳያውቁ በበሽታው ሊጠቁ ይችላሉ። 4. በሽታውን በማሰራጨት ሕጻናት የሚኖራቸው ሚና ምንድን ነው? ህጻናት በትክክል በበሽታው ይያዛሉ። ነገር ግን ከሌሎች የዕድሜ ክልል ሰዎች ጋር ሲነጻጸር ህጻናት የሚታይባቸው የበሽታው ምልክት በጣም አናሳና የመሞት እድላቸውም ዝቅ ያለ ነው። ከዚህ አንጻር ህጻናት ዋነኛ የበሽታው አስተላለፊዎች ናቸው። ምክንያቱም አንደኛ የበሽታው ምልክት በብዛት አይታይባቸውም፤ ሁለተኛው ደግሞ ህጻናት ብዛት ካላቸው ሰዎች ጋር ይገናኛሉ፣ ይተቃቀፋሉ ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። በእርግጥ አሁን ባለው ሁኔታ ምን ያህሉ ስርጭት በህጻናት አማካይነት እንደሆነ ለማወቅ የተደረገ ጥርት ያለ የጥናት ውጤት የለም። 5. ቫይረሱ በትክክል ከየት ነው የመጣው? ቫይረሱ በፈረንጆቹ 2019 መጨረሻ አካባቢ ከቻይና ዉሃን ከተማ ውስጥ ከሚገኝ የእንስሳት ገበያ አካባቢ ካላ ቦታ እንደሆነ ይነገራል። ሳርስ-ኮቭ-2 ተብሎ የሚጠራው ኮሮናቫይረስ የሌሊት ወፍን ከሚያጠቃው ቫይረስ ጋር ተመሳሳይነት አለው። በመሆኑም ቫይረሱ ከሌሊት ወፍ ወደ ሌላ እንስሳ፤ ከዚያም ወደ ሰው ተሸጋግሯል የሚል ሰፊ ግምት አለ። በዚህ ሂደት ግን አስቸጋሪውና ፈጣን መልስ የሚሻው ጥያቄ በሰው እና በሌሊት ወፍ መካከል ቫይረሱን የሚያሸጋግረው እንስሳ ማን ነው የሚለው ነው? ይህ ጥያቄ ካልተመለሰ በመላው ዓለም ያለው የቫይረሱ ስርጭት በቁጥጥር ስር ቢውል እንኳ በዚህ ማንነቱ ባልታወቀው እንስሳ አማካኝነት ቫይረሱ ድጋሚ መከሰቱ የማይቀር ነው ማለት ነው። 6. ቫይረሱ በበጋ ወራት ስረጭቱ ሊቀንስ ይችላልን? ጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ ከበጋ ይልቅ በክረምት በብዛት ይከሰታሉ፤ ነገር ግን ኮሮናቫይረስን ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ስርጭቱን ሊገታው እንደሚችል ምንም የተረጋገጠ ነገር የለም። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት የሳይንስ አማካሪዎች ቫይረሱ በአየር ሁኔታ መለዋወጥ ስርጭቱ ስለመቀነሱም ሆነ ስለመጨመሩ የተረጋገጠ ነገር አለመኖሩን በመጥቀስ አስጠንቅቀዋል። በአጠቃላይ ግን በበጋ ወራት በሽታው ስርጭቱ ከፍተኛ ከሆነ በክረምት የባሰ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። በክረምት የተለመዱ በሽታዎች ሆስፒታሎችን ከማጨናነቃቸው ጋር ተዳምሮ ደግሞ ችግሩን ያገዝፈዋል። 7. አንዳንድ ሰዎች ለምን በጣም የጠና ምልክቶችን ያሳያሉ? ኮቪድ-19 ለብዙዎቹ ሰዎች ቀላል በሽታ ነው። ነገር ግን 20 በመቶ የሚሆኑት በሽታው ይጠናባቸዋል። ለምን? የሰዎች በሽታ የመከላከል አቅም ከበሽታው አይነት ጋር የሚኖረው ሁኔታ አንዱ ምክንያት ሲሆን የዝርያ ሁኔታም ግምት ውስጥ ሊገባ ይችላል። እነዚህን ምክንያቶች በሚገባ መረዳት ሰዎች የሚያስፈልጋችውን እንክብካቤ ለማድረግ ይጠቅማቸዋል። 8. በሽታው ምን ያክል ጊዜ ሊቆይ ይችላል? በድጋሚ ልንያዝስ እንችላለን? ብዙ የሚባሉ ነገሮች ቢኖሩም በግልጽ ቫይረሱ ምን ያህል ጊዜ ሊያጠቃን እንደሚችል የሚገልጹ በጥናት የተደገፉ መረጃዎች ውስን ናቸው። ቫይረሱን ለማሸነፍ ታማሚዎች በቂ በሽታውን የመከላከያ አቅም ሊያዳብሩ ግድ ይላቸዋል። ነገር ግን በሽታው ከተከሰተ ገና ጥቂት ወራትን ብቻ ያስቆጠረ በመሆኑ ሰፊ የመረጃና ትንተና ለመስጠት ጊዜው እራሱ አጭር ነው። ለሁለተኛ ጊዜ የተጠቁ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ማረጋገጥ ከባድ እንደሆነና በአብዛኛው ነጻ እንደሚባሉም ይነገራል። በሽታው ምን ያህል ጊዜ ሊያሰቃይ እንደሚችል ማወቁ ወደፊት ለቫይረሱ የሚደረጉ ህክምናዎችንና ጥንቃቄዎችን ለማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም ለጊዜው ግን የተረጋገጠ መረጃ የለም። 9. ቫይረሱ ቅርጹን ሊቀይር ይችላልን? ቫይረሶች ሁልጊዜ ቅርጻቸውን ይቀይራሉ፤ በዋናነት ከዝርያ መለያቸው አንጻር ሲታይ ግን ምንም የተለየ ለውጥ አይኖረውም። እንደ አጠቃላይ ቫይረሶች ረዘም ላለ ጊዜ በቆዩ ቁጥር ገዳይነታቸው እየቀነሰ ይሄዳል የሚል ጥቅል እውቀት አለ፤ ይህ ግን ለኮሮናቫይረስ ዋስትና ሊሆን አይችልም። አሁን ትልቁ አሳሳቢ ነገር ቫይረሱ ቅርጹን የሚቀያይር ከሆነ አንድና ተመሳሳይ የበሽታ ተከላካይ ክትባትን ለማበልጸግ ፈታኝ ይሆናል። ልክ ኢንፍሉዌንዛ ላይ ተሞክሮ እንዳልተሳካው ሁሉ ኮሮናቫይረስ ላይም ላይሆን ይችላል።
news-52217125
https://www.bbc.com/amharic/news-52217125
ከኮሮናቫይረስ በኋላ ኢኮኖሚያቸው በቶሎ ሊያገግም የሚችል አምስት አገራት
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አገራት ከበሽታ ጋር በሚያደርጉት ትግል በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። ከዚህ አንጻር ከወረርሽኙ በኋላ የትኞቹ አገራት በተሻለ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንደሚመለሱ ባለሙያዎች ለመገምገም ሞክረዋል።
ኒው ዮርክ ይህንን በተሻለ ለመረዳት የኢንሹራንስ ኩባንያ የሆነው ኤፍ ኤም ግሎባል የ2019 ዓለም አገራት የምጣኔ ሃብት ፈተናን የመቋቋም አቅም አመላካች ደረጃን ተመለከትን። በዚህም አገራት ለቫይረሱ የሰጡትን የመጀመሪያ ምላሽ ከግምት በማስገባት ቀውሱን በተረጋጋ መንገድ የሚወጡበትን ሁኔታና የመቋቋም ዕድላቸው ተቃኝቷል። ዴንማርክ በደረጃ ጠቋሚው በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠችው ዴንማርክ ከቫይረሱ ስርጭት አንፃር ማኅበራዊ ርቀት እንዲተገበር በፍጥነት እርምጃ ወስዳለች። ጥቂት በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንደተገኙ ነው ትምህርት ቤቶችን፣ አስፈላጊ ያልሆኑ ሥራዎችንና ድንበሯን በፍጥነት በመዝጋት ውሳኔዋ ውጤታማ መሆኑን ያረጋገጠችው። የዴንማርካዊያን ባህል የሆነው በመንግሥት ላይ እምነት ማሳደርና ለጋራ ዓላማ አብሮ የመቆም ፍላጎት በእርምጃዎቹ ውጤታማነት ላይ አውንታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። እናም ብዙ ሰዎች ለሕዝብ ጤና ሲሉ መስዋዕት የማድረግ የሞራል ግዴታ እንደሆነ ይሰማቸዋል። በዚህ ወቅት ዴንማርክ የሠራተኞችን ደመወዝ እስከ 90 በመቶ ድረስ ለመክፈል መወሰኗ እንደ ምሳሌ እንድትታይ አድርጓታል። ይህን ግን ቀላል አይደለም። እርምጃው ከጠቅላላው የአገሪቱ አጠቃላይ ምርት 13 በመቶውን ያህሉን ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ዴንማርክ ሲንጋፖር ሲንጋፖር በጠንካራ ኢኮኖሚዋ፣ በአነስተኛ የፖለቲካ አደጋ፣ ጠንካራ መሠረተ ልማት እና ዝቅተኛ ሙስና በደረጃ ጠቋሚው 21ኛ እንድትሆን አድርጓታል። አገሪቱ ቫይረሱን ለመቆጣጠር በፍጥነት ከመንቀሳቀስ ባለፈ ስርጭቱም የተረጋጋ ነው። ቫይረሱን በመዋጋት ረገድ በግልጽነት በሚሰራው መንግሥት ላይ ሕዝቡ ከፍተኛ እምነት አለን። መንግሥት አንድ ውሳኔ ካስተላለፈ ሁሉም ተገዢ ሆኖ ተግባራዊ ያደርጋል። እንደ ትንሽ አገርነቷ የሲንጋፖር በጣም ስኬታማ መልሶ የማንሰራራት ውጤት ለማስመዝገብ በተቀረው ዓለም የማገገም ሂደት ላይ የተመሠረተ ነው። ሴንጋፖር ዩናይትድ ስቴትስ የዩናይትድ ስቴትስ ሰፊ ጂኦግራፊያዊ ቦታ መያዟ በደረጃ ጠቋሚው ላይ በሦስት የተከፈለች ሲሆን በአጠቃላይ ጥሩ ደረጃ ይዛለች። ቫይረሱ እንደ ኒው ዮርክ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ ፈታኝ ሲሆን፤ የሥራ አጥነት መጠኑም ታሪካዊ በሚባል ደረጃ ከፍ ብሏል። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የተወሰደው አስገዳጅ የእንቅስቃሴ ገደብና ሌሎችም ለዚህ በምክንያትነት ተቀምጠዋል። ነገር ግን የአሜሪካ መንግሥት ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የማነቃቂያ እርምጃዎችን በፍጥነት መውሰዱና ማኅበራዊ ርቀት መጠበቅ መተግበሩ ውጤት በማምጣት የቫይረሱ አጠቃላይ ተፅእኖን ሊቀንስና ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ማገገም ሊያስገኝ ያስችላል። 21 ትሪሊየን ዶላር የኢኮኖሚ ማበረታቻ ይፋ ያደረገችው አሜሪካ፤ ሩብ ያህሉን የዓለም አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርትን በመያዟ ወሳኝ የሚያደርጋት ሲሆን የዓለም ምጣኔ ሃብት ማገገም በአሜሪካ ውጤታማነት ላይ ጥገኛ እንደሆነ ይነገራል። ሲያትል ሩዋንዳ በቅርብ በተደረጉት በኮርፖሬት አስተዳደር ማሻሻያዎች ምክንያት ሩዋንዳ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በደረጃ ጠቋሚዎች ውስጥ ትልቁን መሻሻል በማድረግ በዓለም ላይ የ77ኛ ደረጃን፣ ከአፍሪካ ደግሞ የአራተኛ ደረጃን ይዛለች። ከሁሉም በላይ ደግሞ በአውሮፓዊያኑ 2019 በጎረቤትዋ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ድንበር ላይ በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር ከቻለች በኋላ እንደዚህ ዓይነቱን ቀውስ ለመከላከል በጥሩ ሁኔታ የተቀመጠች ይመስላል። ሁለን አቀፍ የጤና አጠባበቅ፣ የህክምና ቁሳቁስን በሚያደርሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) እገዛ እና በድንበር ላይ የሙቀት ልየታ በማድረግ ሩዋንዳ በዚህ ቀውስ ወቅት ከሌሎች የአካባቢው አገራት አንጻር ጥንካሬዋን ጠብቃ ትቆያለች። ሩዋንዳ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ቤት ለቤት ነፃ ምግብ እያሰራጨች የምትገኝ ሲሆን ይህም ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት የመጀመሪያዋ ያደርጋታል። የቱሪዝም ዘርፉ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚገጥመው ይጠበቃል። ሩዋንዳም ለብዙ የዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖች ተወዳጅ መድረሻ ናት። አገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሚሆኑ እና በፍጥነት ለማገገም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳላት ይታመናል። ሩዋንዳ ኒውዚላንድ ኒውዚላንድ በደረጃ ጠቋሚው የ12ኛ ቦታን ይዛለች። አገሪቱ ድንበሮችን ለዓለም አቀፍ ተጓዦች በመዝጋትና አስፈላጊ ያልሆኑ ሥራዎችን በፍጥነት በመዝጋት የቫይረሱ ስርጭትን ለመቆጣጠር መንቀሳቀስ ችላለች። ቱሪዝምና የወጪ ንግድ የምጣኔ ሃብቷ ዋና አካል ሲሆኑ ኒውዚላንድ በቅርብ ጊዜ ውስጥ አንዳንድ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ያጋጥማታል ተብሎ ተሰግቷል። ነገር ግን ይህ የግድ መጥፎ ውጤት ላይኖረው ይችላል። ወረርሽኙ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳርፈው ጉዳት ቀላል የሚሆን ባይሆንም ኒወ ዚላንድ ግን ይህንን ተቋቁማ ለማገገም ብዙም እንደማትቸገር የምጣኔ ሃብት ሙያተኞች ያምናሉ። ኒውዚላንድ
48508663
https://www.bbc.com/amharic/48508663
የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የሰሞኑ ውጥንቅጥ መንስዔው ምን ይሆን?
የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጓጊ የሆነ ይመስላል። በቅርቡ ሊጉን የተቀላቀሉት ፋሲል ከነማ እና መቀለ 70 እንደርታ ዋንጫውን ለማንሳት አንገት ለአንገት ተናንቀዋል። ይህ አጓጊነቱ ግን የፕሪሚዬር ሊጉን አስቀያሚ ገፀታ መሸፈን የቻለ አይመስልም።
አሁን አሁን በአዲስ አበባም ሆነ የክልል ስታደዬሞች ገብቶ ኳስ መታደም የራስን ደህንነት አደጋ ላይ ከመጣል ጋር ይነፃፀር ጀምሯል። ጨዋነት የጎደላቸው ደጋፊዎች፣ ከዳኛ ጋር ቡጢ የሚገጥሙ ተጨዋቾችና የቡድን አባላት፣ እንዲሁም ኢ-ፍትሐዊ የሆኑ ውሳኔዎች የሊጉ መገለጫ ከሆኑ ሰነባብተዋል። እሁድ ግንቦት 25/2011 ከቀኑ 10 ሰዓት። ብርቅዬው የአዲስ አበባ ስታድዬም ኳስ እንዲጫወቱ ቀጠሮ በተያዘላቸው ኢትዮጵያ ቡና እና መቀለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች ጩኸት ደምቋል። • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ ኳሱ ሊካሄድ 60 ደቂቃ ገደማ ሲቀረው ግን ጨዋታው እንደተሠረዘና ለማክሰኞ እንደተላለፈ በመነገሩ ደጋፊዎች ተበትነው ወደ የመጡበት እንዲሄዱ ሆነ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግነኙነት ኃላፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ጨዋታው እንዲሠረዝ የሆነው ከፌዴራል ፖሊስ በደረሰን ትዕዛዝ መሠረት ነው ይላሉ። «መጀመሪያ ላይ 'ፕሪ ማች' ስብሰባ ነበር 4 ሰዓት ላይ። የሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች የት የት እንደሚሆኑ ተነጋገርን። ፕሪ ማቹ ላይ ቡና ኃላፊነት መውሰድ እንቸገራለን የሚል አቋም እንፀባርቆ ነበር። [ከመቀለ ጋር ተያይዞ ከዚህ በፊት የተፈጠረው ነገር መፍትሔ ባለማግኘቱ፤ አሁን ለሚፈጠረው ነገር 'ሪስኩን' አንወስድም] የሚል ነገር ነበር የተቀመጠው። ከዚያ የፀጥታ ኃይሎች በሁሉም አቅጣጫ እንዲከታተሉት ለማድረግ ተወሰነ።» ከዚያስ? «ከዚያ ጨዋታው ሊጀመር አካባቢ የነበረው 'ቫይብ' ሙሉ በሙሉ አስፈሪ ነበር። ምናልባትም የሰው ሕይወት ሊያልፍ ይችላል የሚል ስጋትም ነበር። ፌዴሬሽኑ ጨዋታው ለማድረግ ዝግጁ የነበረ ቢሆንም ከፀጥታ ኃይሎች በፍፁም የሚሆን አይደለም የሚል ሃሳብ መጣ። በዚህ ምክንያት ውድድሩ ተቋረጠ።» ከዚያም ሰኞ ዕለተ ፌዴሬሽኑ ጨዋታው ማክሰኞ 'ለት በአዳማ አበበ ቢቂላ በዝግ እንዲካሄድ መወሰኑን አስታወቀ። ቀጥሎ ደግሞ ወደ ሐሙስ መዛወሩ ተሰማ። «በዓሉ ዕሮብ ይሆናል ብለን ነበር ያሰብነው። አሁን በዓሉ ማክሰኞ ላይ በመዋሉ ወደ ሐሙስ ልናሻግረው ወስነናል።» ይላሉ አቶ ባሕሩ። ይህ ውሳኔ ለቡና የሚዋጥ ሆኖ አልተገኘም። ውሳኔውን በተመለከተ ቅዋሜያቸውን የሚገልፅ መግለጫ የሰጡት የቡና ፕሬዝዳንት መ/አለቃ ፍቃደ ማሞም ቡና አዳማ ድርሽ እንደማይሄድ ተናገሩ። «ደጋግሜ የምነግራችሁ ኢትዮጵያ ቡና ነገ ወደ አዳማ በመሄድ የሚያደርገው ጨዋታ እንደማይኖር ነው። ፌዴሬሽኑ ይህን ውሳኔያችንን የማይቀበል ከሆነ ለክለቡ ህልውና ስንል ጉዳዩን ወደ ፊፋ እና ካስ ይዘነው እንሄዳለን» ብለዋል ፕሬዝደንቱ። ቡና ውሳኔውን በመቃወም ባወጣው መግለጫ ''በእኛ በኩል ምንም ችግር ሳይኖር ጨዋታ ተሠርዟል፣ በሜዳችን ልናደርገው የሚገባ ጨዋታ በገልለተኛ ሜዳ ሆኖብናል፣ መቐለ ላይ የደረሰብን በደል ሳያንስ አሁን ደግሞ ተጨማሪ ወጭ አውጥተን ወደ አዳማ እንድንሄድ መወሰኑ አግባብ አይደለም'' የሚሉ አንኳር ሃሳቦች አንስቷል። አቶ ባህሩ ማንኛውም ቡድን የፌዴሬሽኑን ውሳኔ የመቃመው መብት ቢኖረውም ፌዴሬሽኑ የአንድን ጨዋታ ጊዜ እና ቦታ የማመቻቸት ኃላፊነት እንዳለበት ያስታውሳሉ። የመቀለ 70 እንደርታ ሥራ አስከያጅ አቶ ሽፈራው ተክለሃይማኖት እሁድ ያጋጠመው ችግር ቀድሞውንም ሊከሰት እንደሚችል ይታወቅ ነበር ይላሉ። «የቡና ደጋፊዎች ማህበርም ችግር ሊያጋጠም ስለሚችል 'ኃላፊነት መውሰድ አልችልም' በሚል ለፌደሬሽኑ በደብዳቤ አሳውቆ ነበር። እኛም በበኩላችን ማሕበሩ በደብዳቤ ከገለጸው ስጋትና እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን መሠረት በማድረግ ጨዋታው ባይቀየር እንኳ በዝግ ሜዳ እንዲካሄድ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፌደሬሽኑ ጽፈናል።» አቶ ሽፈራው አክለው «ቀን 8 ሰዓት ላይ ስልክ ተደውሎ 'ወደ ሜዳ እንዳትመጡ' የሚል መልዕክት ደረሰን። የቡድናችን ደጋፊዎችም በሥርዓቱ ከሜዳ እንዲወጡ ተደረገ። ግጭቱ በፖሊስና በቡና ደጋፊዎች መካከል ስለነበረ በደጋፊዎቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት የለም» ይላሉ። • ''ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን ጉዞ አንሰርዝም'' • በተቃውሞ እየተናጠች ባለችው ሱዳን ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ቀረበ የተራዘመው ጨዋታ ለሐሙስ ከሰዓት ቀጠሮ ተይዞለታል። ኢትዮጵያ ቡና አሁንም በአቋሙ እንደፀና ነው። መቀለ 70 እንደርታ ግን አዳማ ገብቶ ዝግጅት እያዳረገ እንደሚገኝ አቶ ባህሩ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ቡና ለጨዋታው ወደ አዳማ የማያቀና ከሆነ የጨዋታው 3 ነጥብ በፎርፌ ለመቀለ ሊሰጥ እንደሚችል ግምት አለ። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ግን እሱን ጊዜው ሲደርስ እናየዋለን፤ በፕሪሚዬር ሊጉ ደንብ መሠረት ውሳኔው የሚተላለፍ ይሆናል ይላሉ። የፕሪሚዬር ሊጉን ደረጃ እየመራ የሚገኘው ፋሲል የቡናና መቀለ ጨዋታ በዝግ ስታድዮም እንዲከናወን መወሰኑ አግባብ አይደለም የሚል መግለጫ አውጥቷል፤ ምንም እንኳ አቶ ሽፈራው ''በማይመለከት ጉዳይ እጅ እንደማስገባት ይቆጠራል'' በማለት ቢያጣጥሉትም። የቡና እና መቀለ ጉዳይ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግን አስቀያሚ ገፅታ አጉልቶ ያውጣው እንጂ ሌሎች ችላ ላይባሉ የሚገባቸው ጉዳዮች የኢትዮጵያን እግር ኳስ እግር ተወርች ወጥረው ይዘውታል። ያለንበት ጊዜ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፈታኙ ወቅት ይሆን ወይ? «አይደለም!» ይላሉ አቶ ባህሩ። ፌዴሬሽኑ ግን ከወቀሳ አልዳነም። የኢትዮጵያ እግር ኳስም ከዓመት ዓመት አንድ ወደ ኋላ እንጂ ወደፊት እየሄደ አይመስልም።
55561316
https://www.bbc.com/amharic/55561316
ናይጄሪያ በጥር ወር አጋማሽ የኮሮናቫይረስ ክትባትን እንደምታገኝ ተገለፀ
ናይጄሪያ የኮሮናቫይረስ ክትባት በጥር ወር አጋማሽ እንደምታገኝ የአገሪቱ የጤና ኤጀንሲ ባለሥልጣን ገለፁ።
ናይጄሪያ በዚህ ዓመት 40 በመቶ ያህል ዜጎቿን ለመከተብ አቅዳ እየተዘጋጀች ሲሆን፤ 30 በመቶ ያህሉን ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት እንደምትከትብ የጤና ኤጀንሲው ኃላፊ ፈይሰል ሲያብ ተናግረዋል። የመጀመሪያው ዙር ክትባት የተገኘው ከዓለም አቀፉ የክትባት መጋራት ጥምረት፣ ኮቫክስ በኩል ሲሆን ከፋይዘር/ባዮንቴክ 100 ሺህ ክትባቶች ወደ ናይጄሪያ እንደሚላኩ ተገልጿል። ናይጄሪያ መጀመሪያ ክትባቱን የምትሰጠው ለጤና ባለሙያዎቿ፣ በአደጋ ጊዜ የመጀመሪያ ምላሽ ለሚሰጡ ባለሙያዎች፣ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ ግለሰቦች፣ ለአረጋውያን እንዲሁም በተለያየ ሥልጣን እርከን ላይ ለሚገኙ ፖለቲከኞቿ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል። እንደ ፈይሰል ሲያብ ገለጻ ከሆነ ናይጄሪይ የአጠቃላይ ሕዝቧን አንድ አምስተኛ ለመከተብ ያቀደች ሲሆን ለዚህም የሚያስፈልጋትን 42 ሚሊዮን ክትባት እንደምታገኝ ተስፋ አድርጋለች። የዓለም ጤና ድርጅት ኮቫክስ የተሰኘውን የክትባት ጥምረትን የመሰረተው ድሃ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ሲሆን ሐብታም አገራት ያለውን ክትባት በሙሉ ጠራርገው ይሸምቱታል የሚል ስጋት በመኖሩ ጭምር ነው። በተያያዘ ዜና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ባለፈው ሳምነት አገራቸው በኮቫክስ በኩል የሚመጣውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት 19.3 ሚሊዮን ዶላር ብትከፍልም፣ የሚደርሳት ግን ከሦስት ወር በኋላ መሆኑን ተናግረው ነበር። የጤና ሚኒስትሩ ዝዌሊ ማክሄንዚ በበኩላቸው በሚቀጥለው ወር የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለማግኘት እንዲቻል ከግል የመድኃኒት አምራቾች ጋር መንግሥታቸው እየተነጋገረ መሆኑን ገልፀዋል። በደቡብ አፍሪካ በፍጥነት የሚዛመተው ቫይረስ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ መንግሥት ክትባቱን በአስቸኳይ አምጥቶ ለዜጎቹ እንዲያዳርስ ከፍተኛ ጫና እየተደረገበት ነው። ደቡብ አፍሪካ 1.1 ሚሊዮን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን በምርመራ አረጋግጣለች። ይህም በአህጉሪቱ ካሉት አገሮች በአጠቃላይ ከፍተኛው ነው። ናይጄሪያ በበኩሏ እስካሁን ድረስ 100 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በምርመራ ሲረጋገጥ ከሌላው ጊዜ ሁሉ በበለጠ ሰኞ ዕለት ብቻ 1ሺህ 200 ሰዎች ተይዘው መገኘታቸው ተገልጿል። ናይጄሪያ 200 ሚሊዮን ሕዝብ ብዛት በመያዝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ነች።
51471900
https://www.bbc.com/amharic/51471900
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድጋፍ ሠልፍ እና የኦፌኮ ሕዝባዊ ስብሰባ መከልከል በጅማ
በትናንትናው (3/6/2012) ዕለት በጅማና አጋሮ ከተሞች 'ለብልጽግና እንሩጥ' በሚል መሪ ቃል በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል የተባለ የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ።
የሠልፉ አላማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን መደገፍ እንደሆነ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች ተናግረዋል። ሠልፉ የተደረገው በትናንትናው ዕለት (3/6/2012) ኦፌኮ በጅማ ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር ሊያደርገው የነበረውን የትውውቅ መድረክ ከተሰማ በኋላ እንደነበር ተነግሯል። የኦፌኮ የጅማ ቅርንጫፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዑመር ጣሂር እንዳሉት በጅማ ስታዲየም ሊያደርጉት የነበረው ይህ ፕሮግራም በከተማው አስተዳደር ተከልክሏል። የኦፌኮ ህዝባዊ መድረክ ቢከለከልም በጅማ ከተማ አስተዳደርና በከተማዋ ወጣቶች የተዘጋጀው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረገ የድጋፍ ሠልፍ ግን ተካሂዷል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስል የታተመባቸው ቲሸርቶችና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ድጋፍ የሚገልፁና የሚያወድሱ ጽሑፎች በሰልፉ ላይ ታይተዋል። የሠልፉ ተሳታፊና አስተባባሪ የሆነው የጅማ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ ድማሙ ንጋቱ "ለውጡ መቀጠል አለበት፤ የኦሮሞ ሕዝብ መከፋፈል፤ መሰደብም የለበትም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ሌሎች የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ እንደ አገር የተወከሉ መሪዎች መከበር አለባቸው በሚል ሃሳብ ሠልፉ ተዘጋጅቷል" ሲል ያብራራል። የሠልፉ መነሻ ሃሳብ የኦፌኮ አባል የሆኑት አቶ ጃዋር መሐመድ በተለያየ መድረኮች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲወረፉ መሰማታቸውን ቅሬታ በመፍጠሩ እንደሆነም ጨምሮ ይናገራል። በሠልፉ ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሌላ የከተማዋ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በማስመልከት በተለያዩ ሕዝባዊ መድረኮች የሚናገሩት ንግግር ያልተገባ መሆኑንና ሕዝቡንም እንዳስከፋ ይገልጻሉ። ወጣት ድማሙ አክሎም "ሕዝቡ የወከላቸው መሪዎችን መስደብና ማንኳሰስ ሕዝቡን ራሱ እንደመስደብ ነው የሚቆጠረው" ካለ በኋላ በፖለቲካ የሃሳብ ልዩነት ያለ ቢሆንም ይህ የሃሳብ ልዩነት ሕዝቡን መከፋፈል የለበትም ሲል ያስረዳል። በጅማ በተደረገው የድጋፍ ሠልፍ ላይ አለመሳተፉን የሚናገረው ወጣት አሕመድ አባ መጫ ደግሞ "የኦሮሞ ህዝብ ዓላማ፣ ዋጋ ከፍሎ እዚህ ያደረሰውን ትግል የቀረውን ነገር አሟልቶ ከዳር ማድረስ ነው" በማለት የጅማ ወጣቶችና ሕዝቡ ፍላጎትም ይኸው ነው ሲል በሚኖርበት ከተማ ስለተደረገው ሠልፍ ዓላማ ይናገራል። "ጃዋር ተምሳሌታችን ነው" የሚለው ወጣት አሕመድ፣ ኦፌኮን ከተቀላቀለ በኋላ የሚናገራቸው አንዳንድ ንግግሮች እንዳስከፉት ይገልፃል። "ስሜታዊ ሆኜ የምናገራቸው ንግግሮች መጥፎ ነገር ያስከትላሉ፤ ስለዚህ ተከባብረን እየተደማመጥን በፕሮግራምና በፖሊሲ ላይም ቢሆን ክርክር ማድረግ እንጂ ጣት መቀሳርና መወራረፍ ጠቃሚ አይደለም" ሲል ይናገራል። የጅማ ሕዝብ ጥያቄና ሠልፉን ያደረገበት ምክንያትም ይኸው ነው ሲል ሃሳቡን ያጠቃልላል። በትናንትናው ዕለት በጅማና በአጋሮ የተካሄዱትን የድጋፍ ሠልፎች በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መንግሥት አበል ከፍሎ ማስተባበሩን የሚገልጹ አስተያየቶች ሲሰጡ ነበር። ይህንን በተመለከተ የሰልፉ አስተባባሪ ወጣት ድማሙ ግን " አበል መክፈል ይቅርና ቲሸርቶቹንና መፈክሮችን ለማሳተም እንኳ መንግሥት ምንም ዓይነት ገንዘብ አላወጣም" ይላል። የኦፌኮ ስብሰባ ለምን ተከለከለ? በትናንትናው ዕለት ኦፌኮ በጅማ ስታዲየም ከደጋፊዎቹ ጋር ሊያካሄድ የነበረው ስብሰባ ለምን እንደተከለከለ የድርጅቱ የጅማ ቅርንጫፍ ኃላፊ ሲናገሩ ከዞኑ አመራሮች ጋር በመግባባት ሲሰሩ እንደቆዩ በማስታወስ ነገር ግን ጃዋር ፓርቲያቸውን ከተቀላቀለ በኋላ አለመግባባቶች መከሰታቸውን ያስረዳሉ። "ጃዋር ከመጣ በኋላ ጥሩ አልነበረም። የኦፌኮ ልዑክ ወደ ጅማ ለመምጣት ከወሰነ በኋላ ደግሞ እንደ ጠላት ማሳደድ ጀመሩ" ይላሉ። ትልቅ ጫና እየደረሰብን ነው ያሉት አቶ ዑመር አባላቶቻቸው እየታሰሩ መሆኑንና ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ይናገራሉ። የተከለከሉት የምርጫ ቅስቀሳ ታካሂዳላችሁ ተብለው እንደሆነ የሚናገሩት ኃላፊው "እኛ የጠየቅነው የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ሳይሆን የሕዝብ ትውውቅ መድረክ ለማካሄድ ነው" ብለዋል። የጅማ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ መኪዩ መሐመድ ቢቢሲ ጉዳዩን አስመልክቶ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ሕጉን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ጠቅሰው "ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ቅስቀሳ እንዲያደርጉ አልፈቀደም፤ ኦፌኮ በሌሎች ዞኖች የሚያደርጋቸው እንቅስቀሴዎች የትውውቅ ሳይሆን የምርጫ ቅስቀሳ ነው" ይላሉ። በዚህም ምክንያት ስብሰባውን አለመፍቀዳቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የከተማው አስተዳደር ሳያውቅ ለሕዝብ ጥሪ መተላለፉንና ፀጥታን በተመለከተ በቂ ዝግጅት ባለመደረጉ ስታዲየሙ ውስጥ ስብሰባ እንዳይደረግ መከልከላቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከንቲባው አክለው ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ እንዳልተከለከለ አስተረድተው የትውውቅ መድረካቸውን ወደ ሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፉት ለፓርቲው አመራሮች እንደተነገራቸው ገልፀዋል።
55198051
https://www.bbc.com/amharic/55198051
ትራምፕ የአሜሪካ ወታደሮች ከሶማሊያ እንዲወጡ አዘዙ
ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከሶማሊያ እንዲወጡ አዘዙ።
ፔንታጎን እንዳለው፤ ወታደሮቹ ከጥር 15 በኋላ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተላልፏል። በአሁኑ ጊዜ የአል-ሸባብ እና የአይኤስ ታጣቂዎችን በመዋጋት ረገድ ድጋፍ የሚሰጡ ወደ 700 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች ሶማሊያ ውስጥ ይገኛሉ። የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፤ አንዳንዶቹ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ተለያዩ የሶማሊያ ጎረቤት አገሮች በመሻገርም ድጋፍ ሲሰጡ ቆይተዋል። ከዚህ ቀደም ትራምፕ ለዓመታት የቆዩት የአሜሪካ ወታደሮች ከኢራቅ እና አፍጋኒስታን እንዲወጡ ባለፈው ወር ማዘዛቸው ይታወሳል። በተለያዩ አገሮች የአሜሪካ ወታደሮች መሰማራታቸው ለከፍተኛ ወጪ እንደዳረጋቸው እና ውጤት አልባ እንደሆነም ትራምፕ ይናገራሉ። ወታደሮቹ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ሲወተውቱም ነበር። ተሰናባቹ ፕሬዘዳንት ትራምፕ ሥልጣናቸውን በይፋ ለባይደን ከማስረከባቸው በፊት ነው የአሜሪካ ወታደሮች ከሶማሊያ እንዲወጡ ያዘዙት። ወታደሮቹ ከሶማሊያ መውጣታቸው ተጽዕኖ ይኖረዋል? የአሜሪካ የቀድሞው የመከላከያ ሚንስትር ፀሐፊ ማርክ ኤስፐር ወታደሮቹ ሶማሊያ እንዲቆዩ ይፈልጉ ነበር። እኚህ ባለሥልጣን ባለፈው ወር ከሥራ የተባረሩ ሲሆን፤ የትራምፕ ውሳኔ የፀሐፊውን አቋም የሚጻረር ነው። ፔንታጎን ያወጣው መግለጫ እንደሚለው፤ አብዛኛውን የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይሎች ከሶማሊያ ማስወጣት ከአሜሪካ የፖሊሲ ለውጥ ጋር አይገናኝም። "ለአገራችን ስጋት የሚሆኑ ጽንፈኛ ኃይሎችን በመዋጋቱ እንቀጥልበታለን። ስትራቴጂያዊ ጥቅማችንን በማስከበር እና በኃይል አሰላለፉ ያለንን ቦታ በማስጠበቁም እንቀጥላለን" ይላል መግለጫው። ፔንታጎን እንዳለው፤ ሶማሊያ ውስጥ የሚቀሩ ወታደራዊ ኃይሎች መቀመጫቸው ሞቃዲሹ ትሆናለች። ተንታኞች እንደሚሉት፤ የአሜሪካ ወታደሮች ከሶማሊያ መውጣታቸው በምሥራቅ አፍሪካ የተንሰራፋውን የጽንፈኛ ታጣቂዎችን ስጋት ያባብሰዋል። ባለፈው ወር የአሜሪካ መንግሥት አማካሪዎች ወታደሮቻቸው ከሶማሊያ መውጣት የለባቸውም ብለው መክረው ነበር። ያለ አሜሪካ ወታደሮች እገዛ በቀጠናው ያሉ ታጣቂዎችን ለመግታት አዳጋች እንደሚሆንም አስጠንቅቀዋል። የሶማሊያ ባለሥልጣናት፤ የአሜሪካ ወታደሮች ከአካባቢው ከወጡ ቀውስ እንደሚከሰትና ሽብርተኞች እንደሚበረታቱ አመልክተዋል። ውሳኔው ላይ እንዴት ተደረሰ? ለአስርት ዓመታት በፖለቲካዊ ቀውስ ስትናጥ በነበረችው ሶማሊያ፤ የአፍሪካ ኅብረት እና የአሜሪካ ወታደሮች ተጣምረው ሞቃዲሹን መቆጣጠር ችለዋል። ከሞቃዲሹ በተጨማሪ ሌሎችም በአል-ሸባብ ይዞታ ስር የነበሩ ግዛቶችን አስለቅቀዋል። እአአ በ1993 ሞቃዲሹ ውስጥ 18 የአሜሪካ ልዩ ኃይል ወታደሮች ከታጣቂዎች ጋር ሲዋጉ መገደላቸውን ተከትሎ፤ የተለያዩ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች በሶማሊያ ጣልቃ ላለመግባት ሲያንገራግሩ ቆይተዋል። ዶናልድ ትራምፕ 2016 ላይ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ አሜሪካን "ማቆሚያ ከሌለው ጦርነት" ለማውጣት ቃል ገብተው ነበር። ሆኖም ግን በዋነኛነት የአየር ድብደባ በማድረግ ከአል-ሸባብ ጋር የሚደረገውን ፍልሚያ ገፍተውበታል። ባለፈው ወር የአሜሪካ መከላከያ ባለሥልጣኖች ወታደሮች ከኢራቅ እና አፍጋኒስታን እንዲቀነሱ አስታውቀዋል። በዚህ መሠረት፤ አፍጋኒስታን የሚገኙ ወታደሮች ከ5,000 ወደ 2,500 ይቀነሳሉ። ኢራቅ ያሉ ወታደሮች ቁጥር ደግሞ ከ3,000 ወደ 2,500 ይወርዳል ተብሏል።
news-52163643
https://www.bbc.com/amharic/news-52163643
ኮሮናቫይረስ፡ ባለስልጣኑ ወደ ለይቶ ማቆያ አልገባም በማለታቸው ታሰሩ
አንድ የኬንያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣን ከውጭ ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ ማንኛው ሰው መፈጸም ያለበትን ወደ ለይቶ ማቆያ የመግባት ግዴታን ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ታሰሩ።
የባሕር ዳርቻ የኬንያ ግዛት ኪሊፊ ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት ጌዲዮን ሳቡሪ በግድ ወደ ለይቶ ማቆያ ለ14 ቀናት ከገቡ በኋላ በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸው ህክምና ሲከታተሉ ቆይተዋል። ባለስልጣኑ በሺህዎች የሚቆጠሩ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከተገኙባት ጀርመን ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር ወደ ኬንያ የተመለሱት። ምክትል አስተዳዳሪው በአሁኑ ወቅት ከበሽታው ሙሉ በሙሉ በመዳናቸው የኬንያ መንግሥት ያወጣውን ደንብ ተላልፈዋል በሚል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። ባለስልጣኑ የኮቪድ-19 ቫይረስ ከተገኘባቸው በኋላ ከእርሳቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ100 በላይ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርገዋል። በዚህም የሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ በመጣል ክስ ሊመሰረትባቸው ይችላል ተብሏል። ምክትል አስተዳዳሪው በግድ ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ ለአንድ ጋዜጣ "በሰዎች ላይ ለፈጠርኩት ችግር አዝናለሁ" ሲሉ መጸጸታቸውን ገልጸው ነበር። በኬንያ ውስጥ እስከ አርብ ድረስ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል 122ቱ ላይ የኮሮናቫይረስ መገኘቱ ተረጋግጧል። የሞቱ ሰዎች ቁጥርም አምስት የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከልም ቀደም ያለ የጤና ችግር የነበረበት አንድ የስድስት ዓመት ታዳጊ ኮሮናቫይረስ የጤንነቱን ሁኔታ አባብሶት ህይወቱ በማለፉ በኬንያ በበሽታው የሞተ በዕድሜ ትንሹ መሆኑ ተነግሯል። ኬንያ የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን የወሰደች ሲሆን ከምሽት አንድ ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ ብትጥልም እስካሁን ግን ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴን አልገደበችም።
news-49386115
https://www.bbc.com/amharic/news-49386115
አፍጋኒስታን፡ ሠርግ ላይ የተወረወረ ቦንብ 63 ሰዎችን ገድሏል
በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል አንድ ሠርግ ላይ የፈነዳ ቦንብ 63 ሰዎችን ሲገድል 180 ሰዎችን አቀስሏል።
የዓይን እማኞች ፤ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቦንቡን ተሸክሞ መጥቶ እንዳፈነዳው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቦንቡ የፈነዳው ቅዳሜ ምሽት 4፡40 ገደማ ሲሆን ሥፍራው ደግሞ የሺያ ሙስሊሞች የሚያዘውትሩት የካቡል ምዕራባዊ ክፍል ነው ተብሏል። ታሊባን 'እኔ እጄ የበለትም' ሲል አስተባብሏል። እስካሁን ለጥፋቱ ኃላፊነት የወሰደ ቡድን የለም። ራሳቸውን ከሱኒ ሙስሊሞች ጋር የሚያቆራኙት ታሊባን እና አይ ኤስ ከዚህ በፊት የሺያ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ይታወሳል። • የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር መልቀቂያ አስገቡ የአፍጋኒስታን ሃገር ውስጥ ሚኒስትር አደጋው ከደረሰ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የሟቾችን እና የተጎጂዎችን ቁጥር ይፋ አድርገዋል። ወንዶች እና ሴቶች ለየብቻ ሆነው የሚስተናገዱበት የአፍጋኒስታን የሠርግ ሥነ-ሥርዓት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ይታደሙበታል። 'አጋጣሚ ሆኖ ቦንቡ ሲፈነዳ እኔ ከሴቶች ጎራ ነበርኩ' የሚለው ሞሐመድ ፋርሃግ 'ከፍንዳታው በኋላ ሰዎች ሁላ እግሬ አውጭኝ እያሉ ሲወጡ ተመልክቻለሁ' ሲሉ ኤኤፍፒ ለተሰኘው የዜና ወኪል ተናግሯል። • በአሜሪካ የአየር ጥቃት 23 ንፁሃን ዜጎች ተገደሉ ከ10 ቀናት በፊት ካቡል ውስጥ በሚገኝ አንድ ፖሊስ ጣብያ የፈንዳ ቦንብ የ14 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ አይዘነጋም። ታሊባን ጥፋቱን የፈፀምኩት እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነቱን ወስዷል። ባለፈው አርብ ደግሞ የታሊባን አለቃ ወንድም የሆነው ሂባቱላህ አኩንደዛዳ መስጅድ ውስጥ ሳለ በተመጠደ ቦንብ ሕይወቱ አልፏል። አፍጋኒስታን ውስጥ በርካታ ወታደሮች ያሏት አሜሪካ ከታሊባን ጋር ድርድር ውስጥ እንዳለች እና በጎ ጅማሬዎች እንደታዩ ዕለት አርብ ፕሬዝደንቷ ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ማወጃቸው አይዘነጋም። • አፍጋናዊቷ ስደተኛ በኢትዮጵያ
news-45140342
https://www.bbc.com/amharic/news-45140342
በኮምቦልቻ ከተማ በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል በተፈጠረ ችግር ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
ትናንት በኮምቦልቻ ቀበሌ 6 "ተቅዋ መስጂድ" መጠነኛ የቀኖና የአስተምህሮ ልዩነት ባላቸው የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል በተፈጠረ ግጭት 33 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደረሰባቸው።
በወቅቱ ጉዳት ያደረሱ 10 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ያለለት ዘገየ ለቢቢሲ ገልፀዋል። የተጎዱት በመስጂዱ መድረሳ ውስጥ ቁርአን ይቀሩ የነበሩ ተማሪዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከልም አስራ አንዱ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ተልከዋል። ቀሪዎቹ 22ቱ በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኙ ሁለት ጤና ጣቢያዎች ሕክምና አግኝተው ወደየቤታቸው መመለሳቸውን ኃላፊው ተናግረዋል። • ሰመጉ በወልዲያ እና አካባቢው የመብት ጥሰት ተፈጽሟል አለ • በደሴ ከተማ የሸዋበር መስጂድ ላይ በደረሰ ጥቃት ሰዎች ተጎዱ የፖሊስ ኃላፊው ጨምረው እንደሚናገሩት ይህ መስጂድ በ2004 በተካሄደው የእስልምና ምክር ቤት ምርጫ በመጅሊሱ ሥር እንዲተዳደር የተወሰነ ቢሆንም አሁን ግን 'መስጂዱን እኛ ነን የሠራነው፤ ይመለስልን፤ የሃይማኖት አባቶቹም ይመለሱ' የሚሉ ወገኖች መጥተዋል። ይህ የመጅሊስ ውሳኔ ያስኮረፋቸው አማኞች ወደ መስጊዱ መምጣት አቁመው የነበረ ቢኾንም በዚህ ዓመት ግን እነዚህ ወገኖች በረመዳን የጾም ወቅት ወደ መስጂዱ ገብተው መስገድ መጀመራቸውን ያስታውሳሉ። ኃላፊው እንደሚሉት ችግሩን ለረጅም ጊዜ በከተማው አስተዳደር፣ በፀጥታ አካላትም በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ውጤት አላስገኘም። በአማኞቹ መካከል አለመግባባት በመኖሩ የፖሊስ አባላት ለአንድ ወር ከአስር ቀን ሰላም ሲያስከብሩ እንደቆዩና ከዚህ በኋላ ግን ለሕይወታችን ያሰጋናል በሚል ተመልሰው ማመልከቻ በመጻፍ ለቅቀው እንደወጡ ይናገራሉ። ሰሞኑን በድጋሚ ለከተማው አስተዳደር ጥያቄያቸውን ማንሳታቸውን የሚያስታውሱት ኃላፊው ፖሊስ እና የከተማው አስተዳደር በእርቅ ለመፍታት ከተመረጡ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን እየሠራ እያለ ይህ ግጭት ተፈጥሯል ይላሉ። በፖሊስ ኃላፊው ሐሳብ የሚስማሙት እና ለቢቢሲ ምስክርነታቸውን የሰጡት የአካባቢው ነዋሪዎች የሱፍ መሃመድና መሃመድ አሊ በመስጂዱ ይማሩ የነበሩት ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ እንደነበሩ ይናገራሉ። መስጂዱ ለአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ ምንም ዓይነት አገልግሎት እየሰጠ አልነበረም የሚሉት እነዚህ ግለሰቦች መስጂዱን የሠራነው እኛ ነን በማለት የባለቤትነት ጥያቄ ያነሳሉ። • "ወሎዬው" መንዙማ • "የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ኪሮስም መስጂዱ ከዚህ በፊት የባለቤትነት ጥያቄ ይነሳበት እንደነበር ይናገራሉ። "መንግሥት ማንኛውም መስጂድ በመጅሊስ ሥር እንዲተዳደርና ሕዝበ ሙስሊሙ በጋራ እንዲጠቀምበት በወጣው መመሪያ መሠረት ሁሉም አማኝ በመስጂዱ ይጠቀሙ ነበር" በማለት ያስታውሳሉ። ነገር ግን በትናንትናው ዕለት ጠዋት 2፡00 ሰዓት አካባቢ አዳጊዎች ቁርአን እየቀሩ ባለበት ሰዓት መስጂዱ "ለኛ ይገባል" በሚሉ ወገኖች ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል። በመስጂዱ ከ14 -18 ዓመት ድረስ ያሉ አዳጊዎች እንደሚገኙበት የተናገሩት አቶ ሳሙዔል ጥቃት ያደረሱት ወገኖች በእጃቸው ዱላ፣ ፌሮ እና መዶሻ ይዘው እንደነበር መስክረዋል። ጤና ጣቢያ በሕክምና ላይ የሚገኙትን አማኞች እንዳናገሯቸው የሚናገሩት አቶ ሳሙኤል ቁርአን እየቀሩ ባሉበት ሁኔታ አጥሩን ገነጣጥለው ገብተው እንደደበደቧቸው እንደነገሯቸው ገልጸዋል። የኮምቦልቻ ወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ተጠሪ የሆኑት ሼህ ሰዒድ አሊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከሐሙስ በፊት መስጂዱ ይገባናል በሚሉትና በመጅሊሱ መካከል የከተማው ከንቲባ በተገኙበት ውይይት ማድረጋቸውንና ሽማግሌዎች ተመርጠው ውይይት አድርገው እንደነበር ያስታውሳሉ። ሐሙስ ማለዳ ከኮሚቴዎች ጋር ለመወያየት ተቀጣጥረው ሳለ መስጂዱን እናፀዳለን በሚል ሕዝበ ሙስሊሙን በነቂስ ቀስቅሰው እንደመጡ ይናገራሉ። "ስብሰባው የተጠራው ኻሊድ መስጂድ ነው፤ እዛ አይደለም" ቢባሉ እምቢ በማለት ችግር መፈጠሩን ይናገራሉ። መጅሊሱ ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ይሆናል ብሎ የሚያስበውን ምን እንደሆነ የተጠየቁት ሼህ ሰዒድ አሊ ከፌደራል የእስልምና ጉዳዮች እና የኡላማ ምክር ቤት ውሳኔ እስኪመጣ ድረስ መጠበቅ እንደሚኖርባቸው ያስረዳሉ። ይህንን ሐሳብ 'መስጂዱ ይገባናል' ላሉ ወገኖች አቅርበው የነበሩ ቢሆንም "ተበደልን፤ ልጆቻችን ቁርአን እየቀሩ አይደለም፣ ኢማሞቻችን ገብተው ያሰግዱ፤ የራሳችን ሰዎች እንሰይም'' የሚለው ጥያቄ ገፍቶ በመምጣቱ ችግሩ መፈጠሩን ያስረዳሉ። "እኛ ግን 'በመመሪያ የተሾሙ ሰዎች አሉ እርሱን መሻር አንችልም' ብንልም እነርሱ ስለቸኮሉ ይህ ጥፋት ደረሰ" ብለዋል። ከተማችን አሁን ስጋት ውስጥ ናት የሚሉት ሼህ ሰዒድ አሊ በፌደራል ያሉ አካላት መፍትሄ ይስጡን ሲሉ ተማፅኗቸውን ያቀርባሉ። መስጂዱን እስካሁን እያስተዳደርን የነበረው መጅሊሱ እንደነበር ሼክ ሰዒድ አሊ አስታውሰው አሁን ከግጭቱ በኋላ ግን የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እየጠበቁት እንደሚገኙም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
news-54271234
https://www.bbc.com/amharic/news-54271234
የትግራይ ምርጫ ፡ "እኛ በሕዝብ ድምፅ እንጂ በችሮታ ምክር ቤት አንገባም" ሳልሳይ ወያነ
ሕገወጥ ነው የተባለውና ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ አዲሱ ምክር ቤት ዛሬ ሥራውን ሲጀምር ተፎካካሪ ፓርቲዎች በምክር ቤቱ ያለድምጽ እንዲሳተፉ የሚያስችል አዲስ አዋጅ አፀደቀ።
በዚህ መሰረት በምርጫው ከሚያዘው 190 የምክር ቤቱ መቀመጫ ውጪ በምርጫው የተሳተፉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ያለድምጽ የሚሳተፉበት ተጨማሪ 15 ወንበሮች እንዲኖሩ ወስኗል። የመቀመጫው ክፍፍልን በሚመለከት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በድምር ያገኙት 183 ሺህ ድምጽ ለ15 የምክር ቤቱ ወንበሮች ተከፋፍሏል። በዚህ ስሌት መሰረትም ባይቶና ሰባት፣ ውናት አምስት፣ ሳልሳይ ወያነ ሁለት እንዲሁም አሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አንድ መቀመጫ በምክር ቤቱ ውስጥ ያለድምጽ እንዲያገኙ ተወስኗል። በትግራይ ክልል በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ህወሓት 189 ወንበር ሲያገኝ ባይቶና የቀረውን አንድ ወንበር ማግኘቱ የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ማሳወቁ ይታወሳል። በዚህ የምርጫ ውጤት ድልድል አንድ ወንበር ብቻ ለባይቶና ፓርቲ እንዲሰጥ ቢወሰንም ባይቶና ግን ምክር ቤት ለመግባት ፍቃደኛ እንዳልሆነ ለቢቢሲ ተናግሮ ነበር። የፓርቲዎች ምላሽ ይህንን ተከትሎም ሌሎች በምርጫው ድምጽ ያላገኙ አራት ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በምክር ቤቱ ውስጥ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በሚመለከት በትናንትናው ውይይት ማካሄዳቸው ተነግሮ ነበር። የትግራይ ምክር ቤትም አራቱን ተቀናቃኝ ፓርቲዎች በዝግ ስብሰባ በመጥራት "ድምጽ የማትሰጡበት ወንበር ብንሰጣችሁ ምን ይመስላችኋል?" የሚል ጥያቄ እንዳቀረበላቸው የትግራይ ነጻነት ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ግርማይ በርሄ ይናገራሉ። በዚህ ሐሳብ ላይ አራቱ ፓርቲዎች ያንፀባረቁት አቋም የተለያየ ነው። የሳልሳይ ወያነ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክንፈ ሐዱሽን "ምክር ቤት ትገባላችሁ ወይ?" ተብሎ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "እኛ ምክር ቤት መግባት የምንፈልገው ሕዝብ መርጦን እንጂ በችሮታ አይደለም። ድምፅ በማንሰጥበት በእነሱ በኩል ስጦታ በሚመስል መልኩ የተወሰነን ወንበር አንቀበልም" ብለዋል። አቶ ክንፈ ይህንን ሃሳብ ውድቅ ያደረጉበትንም ሦስት መሰረታዊ ምክንያቶችም ያስረዳሉ። "በተደረገው ምርጫ መሰረት መቶ በመቶ ህወሓት እንዳሸነፈ እየታወቀ ከዚያ ውጪ ያለ አሰራር ግን ሕጋዊ የሆነ መሰረት የለውም" ይላሉ። "ቀድሞ የወጣውን የምርጫ ሕግ መሰረት ያላደረገ ሥራ እንዲሰራ አንፈልግም። ላለፈ ምርጫ ሕግ አሁን ማውጣት አያስፈልግም ምክንያቱም ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ ስለማይሰራ" በማለት አካሄዱ ሕጋዊ እንዳልሆነ አመልክተዋል። የትግራይ ክልል ምርጫ ከመደረጉ በፊትም የምርጫ ሥርዓቱን በተመለከተ 'ሚክስድ ፐሮፖርሽን' [ቅይጥ ተመጣጣኝ] ተብሎ የሚጠራው አሰራር በአዋጁ እንዲካተት ፓርቲያቸው ሐሳብ ቢያቀርብም ተቀባይነት እንዳላገኘ ይናገራሉ። ይህ የውክልና ሥርዓት የአብላጫና ንፅፅራዊ (Majority and Proportional) የድምፅ አሰጣጥን የሚከተል ሥርዓት ነው። "ድሮም እንዲህ አይነት ችግሮችን ሊፈታ የሚችል ነበር፤ ይሄ የምርጫ ሥርዓት አዋጅ ሆኖ ቢወጣ ኖሮ አሁን የተፈጠረውን ችግር የሚፈታ ነበር። ነገር ግን እነሱ በጊዜው አልተቀበሉትም" ይላሉ። አቶ ግርማይ በርሄ በበኩላቸው የትግራይ ምክር ቤት የሰጣቸውን እድል እንደ አንድ የመታገያ መድረክ እንደሚቀበሉት አስታውቀዋል። "ምክርቤትም ሀሳባችን የምንገልፅበት አንድ መድረክ ነው። ስለዚህ ሀሳባችን የምንገልፅበት መድረክ ባገኘን ቁጥር ለመጠቀም ዝግጁ ነን፤ ለዚያም ነው ገብተን መታገያ እናደርገዋለን ነው እያለን ያለነው።" ይላሉ። ሆኖም ፓርቲያቸው የምርጫው ኮሚሽኑ ህግ ጥሰት ፈፅሟል ብለው እንደሚያምኑ ያስረዳሉ። በምርጫ አዋጁ 80/20 'ሚክስድ ፓራራል' መሰረት ከፍተኛ ድምፅ ኣግኝቷል የተባለው ህወሓት 190 ወንበሮች መውሰድ ይገባው ነበር የሚሉት አቶ ግርማይ "ኮሚሽኑ ግን የህግ ጥሰት በመፈፀም 189 ለህወሓት የተቀረችው አንዲት ወንበር ደግሞ ለባይቶና ሰጥቷል። ይህ ህጋዊ እንዳልሆነ እና በስሌቱ መሰረት አንዱ ወንበርም ለህወሓት እንደሚመለከት ገልፀናል" ይላሉ። የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን በተመጣጣኝ ውክልናው የመቀመጫ ድልድል ሕግ መሠረት ህወሓት ካገኛቸው 152 የምክር ቤት መቀመጫዎች በተጨማሪ 38 ወንበሮች አጠቃላላይ ለተወዳደሩት ፐርቲዎች ባገኙት ድምፅ መሰረት ይከፋፈላሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ነገር ግን ተርፈው ከነበሩትና በተመጣጣኝ ውክልና እንደሚከፋፈሉ ከተገለፀው 38 የምክር ቤት መቀመጫዎች ህወሓት 37.35ቱን አግኝቷል፤ በአጠቃላይ ድምርም 189 ወንበሮችን ወስዷል። በተመጣጣኝ ውክልናው ክፍፍል ቀመር መስረት ቀሪዋን 0.65 ወይም አንድ ወንበር ለባይቶና ቢሰጥም ባይቶናም ወንበሩ ለነሱ ስለማይመለከት እንደማይቀበሉት ባለፈው ሳምንት ለቢቢሲ መግለፃቸው ይታወሳል። አቶ ግርማይ በርሄም ወንበሮቹን ለባይቶና እንዲሰጥ የተደረገበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነና መቶ በመቶ ህወሃት ነው መውሰድ ያለበት ይላሉ። "በቀረችው አንዲት ወንበርም ብዙ ድምፅ ያለው ህወሓት ስለሆነ ስለዚህ በህጉ መሰረት ህወሓት 190 ወንበሮች መውሰድ አለበት ብለን ጨርሰናል።" ይላሉ ። ሆኖም ግን ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደምም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተውጣጥተው በምክርቤት በመግባት ሃሳባቸውን እንዲሰጡ የሚያደርግ አሰራር አለው የሚሉት አቶ ግርማይ ይህም ተሞክሮም በተለያዩ ሃገራትም ያለ ነው በማለት ፓርቲያቸው ድምጽ ባያገኝም ወደ ምክርቤቱ ለመግባት እንደወሰኑ ይናገራሉ። የአሲምባ ፓርቲ በትግራይ ምክር ቤት ድምጽ አልባ ሆኖ የመግባቱን ነገር እንደተቀበለው የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ዶሪ አስገዶም ለቢቢሲ ተናግረዋል። የትግራይ ምክር ቤት ተፎካካሪ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ለምን ሃሳብ አቀረበ የሚል ጥያቄ ለአቶ ክንፈ ሐዱሽ አቅርበን ነበር። "የምርጫ ውጤቱ ከታወቀ በኋላ ከሕዝቡም ሆነ ከተለያዩ ወገኖች የተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ምክር ቤት መግባት ነበረባቸው የሚሉ፤ እንዲሁም መቶ ፐርሰንት ተቀባይነት የለውም የሚል የተቃውሞ ድምፅ መምጣቱን ተከትሎ ያንን ለማረጋጋት ነውም" የሚሉት አቶ ክንፈ "በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ቅቡልነት እንዲኖረው ለማድረግ የታሰበ ይመስለናል" በማለትም ያስረዳሉ። ሆኖም "የገዢው ፓርቲ የሚያመጣቸው ሃሳቦች፣ ለገዢው ፓርቲ ብቻ የሚጠቅሙ ሃሳቦች ላይ መሳተፍ አንፈልግም፤ ሕዝባችንንም ሆነ ድርጅታችንን የሚጠቅም ሃሳብ ነው የምናስቀድመው" ይላሉ። ፓርቲው የቀረበለትን ግብዣ አለመቀበሉ ህወሓትን ሊያስከፋ አይችልም ወይ፣ ውሳኔውን ስትወስኑስ ከገዢው ፓርቲ ሊመጣ የሚችል ቅሬታ አያሰጋችሁም ወይ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ክንፈ። ሁሉም ፓርቲዎች አንቀበልም የሚል ምላሽ እንዳልሰጡና ውሳኔያቸው በገዢው ፓርቲ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በማየት አይደለም እንዳልሆነና "ለሚመጣውም ማንኛውም ሁኔታ ዝግጁ ንነ፤ ውሳኔያችን ከድርጅታችንና ከህዝባችን መርህና ጥቅም ጋር ይሄዳል ወይስ አይሄድም የሚል ነው" ብለዋል።
news-55717277
https://www.bbc.com/amharic/news-55717277
ትግራይ ፡ ሶማሊያ ወታደሮቿ በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ አልተሳተፉም አለች
የሶማሊያ መንግሥት ወታደሮቹ በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ተሳትፈዋል ሲሉ የወጡ ዘገባዎች ትክክል አይደሉም ሲል አስተባበለ።
የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ኦስማን አቡከር ዱቤ መንግሥት ይህንን ምላሽ የሰጠው የአገሪቱ የቀድሞ ከፍተኛ የደኅንነት ባለስልጣን ከጥቂት ወራት በፊት ኤርትራ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶማሊያ ወታደሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ተገድለዋል ካሉ በኋላ ነው። አብዲሰላም ጉሌድ የተባሉት የሶማሊያ ብሔራዊ የደኅንነትና መረጃ ተቋም የቀድሞ ምክትል ኃላፊ ምንም አይነት ተጨባጭ ማስረጃ ሳያቀርቡ ለአንድ የግል ሬዲዮ "400 የሚደርሱ የሶማሊያ ወታደሮች" በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ በቅርቡ በተካሄደው ውጊያ ተገድለዋል ሲሉ ተናግረው ነበር። የቀድሞው ባለስልጣን ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ጋር ተሰልፈው ሲዋጉ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገድለዋል ያሏቸው የሶማሊያ ወታደሮች በ20 እና በ30 ዓመት ዕድሜ ውስጥ የነበሩ ናቸው። ይህ የግለሰቡ ንግግርም በተለያዩ የሶማሊያ ክፍሎች ውስጥ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፤ ልጆቻቸው ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ውጪ አገራት የሄዱ ቤተሰቦች ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ የአገሪቱ መንግሥት ልጆቻቸው የት እንዳሉና በሕይወት ይኑሩ ወይም ይሙቱ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። ነገር ግን የሶማሊያው የማስታወቂያ ሚኒስትር ኦስማን አቡከር ዱቤ የተባለውን ውድቅ በማድረግ የሶማሊያ ኃይሎች በቅርቡ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ውጊያ ላይ አልተሳተፉም ብለዋል። ሚኒስትሩ ከቢቢሲ የሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ እንዳሉት "ከዚህ ቀደምም የሶማሊያ ወታደሮች በሊቢያና በአዘርባጃን ውስጥ በተካሄዱ ውጊያዎች ውስጥ ተሳትፈዋል ተብሎ ቢወራም ኋላ ላይ ወሬው ሐሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል" ብለዋል። ጨምረውም የሶማሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያው ግጭት ውስጥ ተሳትፈዋል የተባለው ወሬ ሐሰተኛ ነው ብለዋል። ይህንን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ አስካሁን ያሉት ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግሥት በህወሓት ኃይሎች ላይ በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ማከሄድ ከጀመረ በኋላ ከ50 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ግጭቱን በመሸሽ ወደሱዳን የገቡ መሆኑ ይነገራል። ምንም እንኳን የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግሥታት ቢያስተባብሉም የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል በተካሄደው ግጭት ውስጥ መሳተፋቸውን የሚገልጹ ወገኖች አሉ። በትግራይ ክልል የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ በአሁኑ ጊዜ የተባበሩት መንግሥታትና ሌሎች የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች የሰብአዊ ቀውስ ሊከሰት ይችላል በማለት እያስጠነቀቁ ነው።
news-54990090
https://www.bbc.com/amharic/news-54990090
ፋይዘር አዲሱ ክትባት ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች 94 በመቶ ይሠራል አለ
ኮሮናቫይረስን የሚከላከል ክትባት እየሠራ ያለው ፋይዘር የተሰኘው ኩባንያ አዲሱ ክትባት ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት ላሉ 94 በመቶ እንደሚሠራ አስታወቀ።
ፋይዘርና ባዮቴክ ያበለፀጉት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሶስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ የደረሰ ሲሆን ክትባቱ ለሁሉም ዕድሜ፣ ዘርና ጎሳ እኩል እንደሚሠራ ተነግሯል። አምራቾቹ ኩባንያዎች ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ክትባቱን ለማከፋፈል ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ፈቃድ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል። ክትባቱ በዓለም ዙሪያ ባሉ 41 ሺህ ሰዎች ላይ የተሞከረ ሲሆን በሁለት ደረጃ ነው የተሰጣቸው ተብሏል። ባለፈው ሳምንት ፋይዘር እና ባዮንቴክ የመጀመሪያ ዙር ጥናታናቸውን ውጤት ይፋ አድርገው ክትባቱ 90 በመቶ የተሳካ እንደሆነ አሳውቀው ነበር። የክትባቱ ደህንነትም አስተማማኝ እንደሆነ ድርጅቶቹ ባለፈው ሳምንት ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል። በሌላ በኩል የአሜሪካ ሞደርና የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ክትባት አምርቶ አስተማማኝነቱ 95 በመቶ ነው ሲል ከቀናት በፊት አሳውቆ ነበር። ዛሬ [ረቡዕ] ፋይዘርና ባዮንቴክ የለቀቁት መረጃ አዲሱ ክትባት 95 በመቶ የተዋጣለት እንደሆነ በ170 በጎ ፈቃደኞች ላይ ተሞክሯል ይላል። ከ170 ሰዎች መካከል ለ8 ሰዎች ነው ክትባቱ እንዲሰጥ የተደረገው። ኩባንያዎቹ ክትባቱ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለው አረጋግጠናል ይላሉ። ነገር ግን 2 በመቶ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞች ላይ ራስ ምታትና ድካም ተስተውሏል ብለዋል። ከበጎ ፈቃደኞች መካከል 42 በመቶዎቹ ከተለያዩ ሃገራትና ጎሳዎች ሲሆኑ 41 በመቶዎቹ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ56 እስከ 85 የሚደርስ ነው። የክትባቱ ሙከራ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የክትባቱን ደህንነትና ብቃት መከታተል እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል። ክትባቱ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ቱርክ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ብራዚልና አርጀንቲና በሚገኙ 150 ጣቢያዎች እየተሞከረ ይገኛል። ኩባንያዎቹ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት 50 ሚሊዮን በቀጣዩ ዓመት ደግሞ 1.3 ቢሊዮን ክትባቶች ለማምረት እንደተዘጋጁ አሳውቀዋል።
news-53231192
https://www.bbc.com/amharic/news-53231192
ኢትዮጵያ፡ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ተሰማ
በኢትዮጵያ ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች አረጋገጡ።
ዛሬ ማክሰኞ ከረፋድ ጀምሮ የቢቢሲ የኢንተርኔት እንቅስቃሴ መረጃ እንደሚያመለክተው ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የተጠቃሚዎች ቁጥር አሽቆልቁሏል። ይህንንም ተከትሎ በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በመቀሌና ነቀምቴ የሚገኙ ነዋሪዎችን በማናገር በተደረገው ማጣራት የኢንትርኔት አገልግሎት መቋረጡን ቢቢሲ ለመረዳት ችሏል። የኔት ብሎክስ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር አልፕ ቶከር ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት በመላው ኢትዮጵያ "ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚያስችል መልኩ" ኢንተርኔት መቋረጡን አጋግጠዋል። እርምጃው ሆን ተብሎ የተደረገ እና ቀጣይ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ በአካባቢው የቴክኒክ ችግር አለመኖሩን ገልፀዋል። ኃላፊው የኢንተርኔት መቋረጡን አስመልክቶ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ተጽዕኖም ሰያስረዱ ከባለፈው አመት የአማራ ክልል ባለስልጣናት እና የከፍተኛ ወታደራዊ ሹማምንቶች ግድያ ወዲህ የታየ ከፍተኛ አገር አቀፍ ተጽእኖ ያለው ነው ብለዋል። ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ በጥይት የተገደለውን ታዋቂው የኦሮምኛ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸውን ከነዋሪዎች ቢቢሲ ተረድቷል። የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ሐዘናቸውን ለመግለጽ እንዲሁም አስከሬኑን ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ ለመሸኘት የተሰባሰቡ በርካታ የድምጻዊው አድናቂዎች በአንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች ላይ በከፍተኛ ቁጥር መታየታቸውን የቢቢሲ ሪፖርተሮች ገልጸዋል። የኢንተርኔት መቋረጥ ከድምጻዊው ግድያ በተያያዘ ካለው እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የታወቀ ነገር ባይኖርም፤ ቀደም ባሉት ጊዜያት መንግሥት አለመረጋጋትና የጸጥታ ስጋቶች የሚላቸው ክስተቶች ሲያጋጥሙ በኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል።
news-53148774
https://www.bbc.com/amharic/news-53148774
ምርጫ ቦርድ ከትግራይ ክልል የቀረበለትን ጥያቄ እንዳልተቀበለው አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ምርጫን እንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄ ያልተቀበለው መሆኑን ገለጸ።
ቦርዱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ወረርሽኙን እየተከላከለ ስድስተኛውን ዙር ምርጫ ለማካሄድ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በሚያዘው መሰረት ምርጫውን እንዲያስፈጽም የሚያስፈልገውን ዝግጅት እንዲያደርግና ውሳኔውን ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቅ መጠየቁን ገልጾ ነው ይህንን ምላሽ የሰጠው። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው መልስ ላይ እንዳመለከተው በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ እንቅስቃሴዎችን በማከናወን ላይ እያለ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው ወረርሽኝ በኢትዮጵያም በመከሰቱ ምርጫውን ለማስፈፀም ሲያካሂዳቸው የነበሩት ሥራዎች እንደተስተጓጎሉ ገልጿል። በዚህም ምክንያት ያለውን ሁኔታ በመገምገምና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በማድረግ አገራዊው ጠቅላላ ምርጫ ቀደም ሲል ቦርዱ ባወጣው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማካሄድ የማይቻል በመሆኑ ይህንኑ ውሳኔ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ምክር ቤቱም የቀረበለትን የቦርዱን ውሳኔ ተቀብሎ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት መወሰኑ አስታውሷል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም በሰጠው ውሳኔ ምርጫውን ወረርሽኙ የሕዝብ ጤና ስጋት ሆኖ ባለበት ሁኔታ ማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የፌደራልና ክልል ምክርቤቶች የስልጣን ዘመን እንዲቀጥል መወሰኑን እንዲሁም አጠቃላይ ምርጫው ወረርሽኙ የሕዝብ ጤና ስጋት አለመሆኑን ካረጋገጡበት ጀምሮ ከዘጠኝ ወር እስከ አንድ አዓመት ባለው ጊዜ እንዲካሄድ መወሰኑን ገልጿል። ቦርዱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ላይ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የወረርሽኝ ሁኔታ እንደገና ተገምግሞ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ እስኪረጋገጥ ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ምርጫ አያካሄድም ሲል በመግለጫው አመልከልቷል። ጨምሮም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ መቆጣጠር እና ማስተዳደር፣ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ማውጣት፣ የምርጫውን ከተጽእኖ ነጻ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ማስፈጸም ስልጣን ያለው ብቸኛ ተቋም መሆኑን ገልጾ ስለዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳን፣ አፈጻጸምንም ሆነ ተያያዥ ሁኔታን የሚወስነውም ቦርዱ ብቻን እንደሆነ ገልጿል። በመሆኑም የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ውስጥ ስተኛውን ዙር የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም ቦርዱ ይህንን ውሳኔውን ተቀብሎ ሊያስፈጽም ይገባል የሚልበት ህጋዊ መሠረት የለውም ሲል ጥያቄውን እንዳልተቀበለው አስታውቋል።
news-55968701
https://www.bbc.com/amharic/news-55968701
ፖፕ ፍራንሲስ በሲኖዶሱ ከፍተኛ አመራር አድርገው የመጀመሪያዋን ሴት ሾሙ
የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በሲኖዶሱ ውስጥ ከፍተኛ የተባለውን ሹመት ለሴት ሰጥተዋል።
በሲኖዶሱ ውስጥ ከፍተኛ አመራር ውስጥ የተቀመጡ የመጀመሪያ ሴት ሆነዋል። ትውልዳቸው ከፈረንሳይ የሆኑት ናታሊ ቤኳርት በሲኖዶሱ ውስጥ የመምረጥ መብት ይኖራቸዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ፖፑን ማማከር እንዲሁም በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አወዛጋቢ ለሚባሉ ጉዳዮችም ቤተ ክርስቲያኗ ምን አይነት ውሳኔ ማሳለፍ አለበት ለሚለውም አንድ አማካሪና ወሳኝ ይሆናሉ። ናታሊ ቤኳርት ከአውሮፓውያኑ 2019 ጀምሮ ሲኖዶሱን በማማከር ሰርተዋል። የሲኖዶሱ ዋና ፀሃፊ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች ሹመቱ "በሩ እንደተከፈተ ማሳያ ነው" ማለታቸው ተዘግቧል። የፖፑ ውሳኔ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ቁልፍ የሚባሉ ውሳኔዎች ላይ የሴቶች ተሳትፎን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጨመር ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብለዋል ዋና ጸሃፊው ምንም እንኳን ይሄ ውሳኔ ሴቶችን የቅስና ማዕረግ ለመስጠት ጠቋሚ ባይሆንም የፖፑ ተችዎች የቅስና ማዕረግ ከመስጠት አቅጣጫ ጋር ሊያገናኙት እንደሚችሉ የቢቢሲው ጆን ማክ ማኑስ ዘግቧል። ከናታሊ በተጨማሪ ስፔናዊው ቄስ ሉዊስ ማሪን ደ ሳን ማርቲን በሲኖዶሱ ከፍተኛ ሹመት የተሰጣቸው ሌላኛው ሰው ናቸው። በቅርብ ዓመታት የጳጳሳቱ ሲኖዶስ ከፍቺ ጋር የተያያዙ የቀኖና ዶግማዎች ምን መሆን አለበት በሚለው ተወያይቷል። ፖፕ ፍራንሲስ ከሰሞኑ የሮማውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ህግ በመቀየር ሴቶች ቁርባንን ጨምሮ ሌሎች የቤተ ክርስቲያኗን አገልግሎቶችን እንዲያካሂዱ ፈቅደዋል። በተቀየረው ህግም መሰረት ሴቶች ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሆነው ማገልገልም ይችላሉ። ሆኖም የተቀቡት ቄስ በበላይነት ስርዓቱን እንደሚቆጣጠሩ አፅንኦት ሰጥተዋል። በተለያዩ በምዕራባውያን አገራት በሚገኙ የካቶሊክ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ ሴቶች እነዚህን አገልግሎቶች የሚያከናውኑ ሲሆን የፖፑ የአሁኑ ውሳኔ ለነዚህ ስፍራዎች እውቅናን እንዲያገኙ ሆኗቸዋል። ባለፈው አመት እንዲሁ ፖፑ የቫቲካንን የገንዘብ ሁኔታ በበላይነት የሚቆጣጠረው ምክር ቤት ስድስት ሴቶችን ሾመዋል።
news-53803504
https://www.bbc.com/amharic/news-53803504
ልደቱ አያሌው፡ ኢዴፓ አቶ ልደቱን በሚመለከት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ደብዳቤ ሊጽፍ ነው
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
አቶ ልደቱ ዛሬ ችሎት የቀረቡት ባለፈው ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ በተሰጠው ሰባት ቀናት መሰረት ነው። ጉዳያቸውን በቅርበት የሚከታተሉት የፓርቲው ፕሬዚደንት አቶ አዳነ ታደሰ ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንዳላቀረበ ገልፀው፤ ነገር ግን ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ የሕክምና ማስረጃ እንዲያቀርቡ በጠየቀው መሠረት የህክምና ማስረጃ ማቅረባቸውን አስረድተዋል። የሕክምና ማስረጃዎቹ ህመማቸው ለሕይወታቸው አስጊ መሆኑንና ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ መሆናቸውን እንዲሁም የሕክምና ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው የሚገልፁ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ አሜሪካ የሕክምና ቀጠሮ እንዳላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረባቸውንም አቶ አዳነ ገልፀውልናል። ነገር ግን ይህንን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ለማየት ተጨማሪ የሰባት ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። አቶ ልደቱን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው የሃጫሉን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት በማስተባበርና በመደገፍ ተጠርጥረው መሆኑ መገለፁ ይታወሳል። አቶ አዳነ ዳኞቹ በተለያየ ጊዜ በመለዋወጣቸው እና ጉዳዩ አዲስ እየሆነ በመምጣቱ እንደገና የሰባት ቀን ቀጠሮ ሊሰጣቸው ችሏል ብለዋል። ፖሊስ 'ቤታቸውን ስበረብር አገኘሁ'ት ያለውን መሳሪያም በተመለከተ አንደኛው ከአባታቸው በውርስ ያገኙትና የማይሰራ መሆኑን፤ ሌላኛው በ1998 ዓ.ም ከመንግሥት የተቀበለው ሕጋዊ ፈቃድ ያለው መሳሪያ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረባቸውን አቶ ልደቱ እንደነገሯቸው፤ ፕሬዝደንቱ ገልፀዋል። የሚቆምላቸው ጠበቃ ባለማግኘታቸው እስካሁን በራሳቸው ሲከራከሩ የቆዩት አቶ ልደቱ፤ ዛሬ በጠበቃ እንደተከራከሩ አቶ አዳነ ጨምረው ተናግረዋል። "አቶ ልደቱ ጠበቃ ማግኘት እንዳልቻሉ በየሚዲያው ከገለፅን በኋላ ባለፈው ሳምንት ኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኦሮምኛ ተናጋሪ ጠበቆች በነፃ እንቆምልሃለን ባሉት መሰረት ዛሬ የተከራከሩት ከአንድ ጠበቃ ጋር እየተመካከሩ ነው" ብለዋል። አቶ ልደቱ በሚሰጠው ቀጠሮ ተስፋ የቆረጡ ሲሆን 'ድንገት ከምርጫው በኋላ፣ ከሁለት ዓመት በኋላ ነው ልለቀቅ የምችለው እስከ ሁለት ዓመት ራሴን አዘጋጅቼ ነው ያለሁት' በማለት እንደነገሯቸው አቶ አዳነ አስረድተዋል። አቶ አዳነ የጤና ሁኔታቸውም ዛሬ ፍርድ ቤት ከገቡ ጀምሮ ነስር በተደጋጋሚ እያስቸገራቸው እንደነበር ገልፀው፤ ሕክምና እንዲያደርጉ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ቢኖርም ፍርድ ቤቱ ባለመፍቀዱ አቶ ልደቱ "የሞት ፍርድ የተፈረደብኝ ያህል ነው የምቆጥረው" ማለታቸውን አክለዋል። የፓርቲው ፕሬዚደንት አክለውም የሚመጣውን ውጤት ከመጠበቅ ውጭ በፍርድ ሂደቱ እኛም ተስፋ ቆርጠናል ብለዋል። "እስሩ ፖለቲካዊ ነው" ያሉት አቶ አዳነ ጉዳዩን በንግግር ለመፍታት ከዚህ በፊት ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ማስገባታቸውንና ለመወያየት ጥረት አድርገው እንደነበር፤ ይሁን እንጅ ፍርድ ቤት የያዘው ጉዳይ ስለሆነ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ እንደገለፁላቸው አስታውሰዋል። አሁን ለመጨረሻ ጊዜ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ደብዳቤ ለመፃፍ መዘጋጀታቸውን አቶ አዳነ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
54869295
https://www.bbc.com/amharic/54869295
በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ
በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ።
በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። ሮይተር በበኩሉ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር ማገርሸቱ ከተመዘገበው ቁጥር ውስጥ ሩብ ለሚሆነው ድርሻ አለው ሲል ዘግቧል፡፡ ቀደም ሲል የቫይረሱ ስርጭት ማዕከል የነበረችው አውሮፓ 12.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት 305,700 ደግሞ ህይወታቸው አልፎፋባት በድጋሚ የቫይረሱ ስርጭቱ ማዕከል ሆናለች፡፡ በአሜሪካ 10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በቀን ከ125,000 በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የችግሩን መጠን ከማሳነስ ባለፈ የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ እና አካላዊ ርቀት ማስጠበቅን ባይቀበሉም ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሙሉ ሃይላቸው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ባይደን በጥቂት ቀናት ከፍተኛ የሳይንስ ሊቃውንትን ያካተተ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል ለማቋቋም ቃል ገብተዋል። ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ እና ሁሉም አሜሪካዊያን ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ሲሆኑ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል እንዲያደርጉ ለመጠየቅ አቅደዋል። ባይደን ወረርሽኙ በአገሪቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ኃላፊነታቸውን ሊረከቡ ይችላሉ ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር ዶ/ር ስኮት ጎትሊብ ገልጸዋል። እንደ ዶ/ር ጎትሊብ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ጥር መጨረሻ ድረስ መቀነስ ይጀምራል። "ብቸኛው ጥያቄ በዚህ ጊዜ ውስጥ ስንት ሰዎች ይሞታሉ እና ምን ያህል ሰዎች ይያዛሉ የሚለው ነው" ብለዋል፡፡ በአውሮፓ ፈረንሳይ እሁድ 38,619 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ቅዳሜ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው የ86,852 ቁጥር ግን በጣም ያነሰ ነው፡፡ ሆኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ መረጃ የመሰብሰብ ችግሮች እንደነበሩበት በመግለጽ ሰኞ እርማት እንደሚያደረግ ገልጿል ፡፡ ህንድ እና ብራዚልም እንዲሁ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡
57056781
https://www.bbc.com/amharic/57056781
ሲኖዶስ፡ 'የፓትሪያርኩ መግለጫ የግላቸው እንጂ የሲኖዶሱ አቋም አይደለም'
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከሰሞኑ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም ተባለ።
የፓትሪያርኩ መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶሱን አሠራር ያልተከለተለ እና ከሲኖዶሱ ዕውቅና ውጭ የተካሄደ መሆኑን የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊና እና ሲዳማና የጌዲዮ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ገልጸዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ስለትግራይ እንዳልናገር "ድምጼ ታፍኗል" ማለታቸው ይታወሳል። ፓትርያርኩ በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ግጭት "የአረመኔነት ሥራ" በማለት ጠርተው፤ ዓለም አቀፍ መንግሥታት የንፁኀን ግድያ የሚቆምበትን መንገድ እንዲፈልጉ ሲሉ ተማጽኖአቸውን አቅርበዋል። ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ በበኩላቸው መሰል መግለጫዎች የሚሰጡት የምዕላተ ጉባኤውን እና የቋሚ ሲኖዶሱን አዎንታ ሲያገኙ መሆኑን አስታውሰው፤ "ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቋሚ ሲኖዶስ ሳይወስን ቅዱስ ፓትሪያርኩ በግላቸው ቤተክርስቲያን እና ቅዱስ ሲኖዶስን ወክለው መግለጫ መስጠት አይችሉም" ብለዋል። በዚህም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከሰሞኑ የሰጡት መግለጫ "በግላቸው የሰጡት እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም" ሲሉ ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያም በቀጣዩ ርክበካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ የሚነጋገርበት መሆኑንም ጭምር አስረድተዋል። "ቅዱስ ፓትሪያርኩ የሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያለመሆኑን እየገለጽን ይህንንም የዓለም መንግሥታት በሃገር ውስጥ እና በውጭ ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያውቁት እና ሊገነዘቡት ይገባል" ብለዋል። ይህ በእንዲህ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጌታ ፓሲ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን በመኖሪያ ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። አምባሳደሯ እና ፓርትሪያርኩ በኢትዮጵያ ስላለው ጉዳይ፣ በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ ቀውስ እንዲሁም ፓትሪያርኩ ስላስተላለፉት መልዕክት ተወያይተዋል ሲል የአሜሪካ ኤምባሲ በፌስቡክ ጽፏል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ማን ናቸው? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት የካቲት 24 2015 ዓ.ም ነበር። ሊቀ-ጳጳስ አባ ማትያስ "ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ፓትርያርክ ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ-ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ-ተክለ-ኃይማኖት'' ተብለው በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ሊቃነ-ጳጳሳት 6ኛ ፓትርያርክ በመሆን በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሲመተ-ፕትርክናቸውን ተከናውኗል። አባ ማቲያስ የተወለዱት በትግራይ ክልል በቀድሞ ስሙ ሱብሃና ሳዕስዕ ወረዳ በ1934 ዓ.ም ነው።በተወለዱበት አካባቢ ድቁናን ከአጎታቸው እንደተማሩ ይናገራሉ። ከዚህ በኋላ ትምህርት ፍለጋ ከሌሎች እኩዮቻቸው ጋር በመሆን ወደ ተንቤን በመሄድ ገዳም ገብተዋል። በተንቤን ገዳማት የሚያስፈልጋቸውን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ወደ አክሱም ጽየን በመሄድ ትምህርታቸውን ቀጥለዋል። ቀጥሎም ወደ ጎንደር በመሻገር ሐዲሳትን ተምረው መምህር ተብለዋል። አቡነ ማቲያስ ድቁና የተቀበሉት የኤርትራ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ነው። ክህነትን ደግሞ ከብፁዕ አቡነ ዮሐንስ መቀበላቸውን ይናገራሉ። በቅስና ቄሰ ገበዝ፣ መጋቢ በመሆን ገዳማትን ያገለገሉት አባ ማትያስ፤ ከዚያ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ማገልገል ጀምረዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ሆነው ሲመረጡ እርሳቸው አቡነ ቀሲስ ሆነው በመሾም ረዳት ፀኃፊ ሆነው በቤተክህነቱ ማገልገላቸውን ይናገራሉ። በዚሁ ወቅት በሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ስልጣናት በመሆን ገዳሙን እንዲያስተዳድሩ ቢመረጡም እርሳቸው ግን የቤተክህነት ኃላፊነታቸውን መርጠው ለሶስት ዓመት ያህል አቡነ ተክለሃይማኖትን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። በ1971 ዓ.ም የጳጳሳት ምርጫ ሲደረግ ተመርጠው ኤፊስ ቆጶስ በመሆን ተሹመው ወደ እየሩሳሌም ሊቀጳጳስ ሆነው ሄደዋል። በእየሩሳሌም ሳሉ ወታደራዊው መንግሥት ደርግ በኃይማኖቶች ላይ ያለውን አሉታዊ አቋም በመቃወም ካወገዙ በኋላ ወደ አሜሪካ አቅንተዋል። ደርግ ከሥልጣን ከተወገደ በኋላ ብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት መጥተዋል። በኋላም ሲኖዶሱ በአሜሪካ ያላቸውን ጵጵስና አጽድቆ በአሜሪካ የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አማኞችን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ከዚያ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ሞትን ተከትሎ ሊቀ-ጳጳስ አባ ማትያስ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ፓትርያርክ ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ-ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ-ተክለ-ኃይማኖት ተብለው ተሾመዋል።
news-53909748
https://www.bbc.com/amharic/news-53909748
ከዋንጫ ባለቤትነት ወደ ፀጉር ሥራ - የኦካፎር ጉዞ
'በአገሪቱ አለ ለተባለ ክለብ እየተጫወትሽ ቡድንሽ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የዋንጫ ባለቤት ስታደርጊ ሁሉም ነገር አልጋባ’ልጋ ይሆናል ብለሽ ታስቢያለሽ።'
ቺኔኔ ኦካፎር ቺኔኔ ኦካፎር ህልሟ ይህ ነበር። ዋንጫ ላይ ዋንጫ ማንሳት። ሜዳልያ ላይ ሜዳልያ መደረብ። ኦካፎር የፔሊካን ስታርስ አምበል ነበረች። የተከበረች፤ የተፈራች። ከሐምሌ በኋላ ግን ሙያ ቀይራለች። ከእግር ኳሰ ተጫዋችነት ወደ ፀጉር ሥራ። ይህን የሆነው ለአንድ ዓመት ያክል ደመወዝ ሳይከፈላት ኳስ መጫወቱን ከቀጠለችበት በኋላ ነው። ምንም እንኳ ለዚህ ምክንያቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቢሆንም የክለቡ ኃላፊዎችም የብዙ ሴት ተጫዋቾች ሕልም እንዲከስም አሉታዊ አስተዋፅዖ ነበራቸው። "ለሰዎች እግር ኳስ ተጫዋች ነኝ ብዬ መናገር ይከብደኛል። እሸማቀቃለሁ። 22 ዓመት ሙሉ በፍቅር የተጫወትኩት እግር ኳስ በስተመጨረሻ ሲክደኝ ጊዜ ምን ላድርግ?" ትላለች ናይጄሪያዊቷ። "አሁን ፀጉር ሠሪ ነኝ። ከ2፡30 እስከ አመሻሽ 11፡30 እሠራለሁ። ከሰኞ እስከ ቅዳሜ። ከባድ ቢሆንም ፈጣሪ ይመስገን እየለመድኩት ነው።" ኦካፎር በናይጄሪያ ታዋቂውን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የመራች ነበረች። ለዚያውም የሊጉን ዋንጫ 8 ጊዜ የበላው የኃያሉ ፔሊካን ስታርስን። ፔሊካን ቡድን ስድስት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ የበላችው በዘጠኝ ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነው። ነገር ግን የክለቡ ጉዞ ከድል አድራጊነት ወደ ኪሳራ ማምራት የጀመረው በጥቂት ዓመታት ውስጥ ነው። "አንዳንድ ጊዜ ጠዋት ተነስቼ ምንድነው የምበላው እያልኩ እጨነቅ ነበር" ትላለች ኮከቧ። የሰመረ ጅማሬ ኦካፎር ፔሊካን ስታርስን የተቀላቀለችው በፈረንጆቹ 2018 ነው። ነገር ግን ክለቡ በዚህ ዓመት እንኳን ዋንጫ ሊያነሳ ይቅርና በዋናው ሊግ መቆየት አቅቶት ወደታች ወረደ። ነገር ግን ውድቀትን እሺ ብለው መቀበል ያልሻቱት ኦካፎርና ጓደኞቿ ጠንክረው ሠርተው ክለቡን ወደ ፕሪሚዬር ሊግ መለሱት። ድሉ ጣፋጭ ነበር። ወደ ፕሪሚዬር ሊግ እንደገና ካደጉ በኋላ ግን ነገሮች ቅርፃቸውን መቀየር ያዙ። በወር ከ78 እስከ 182 ዶላር ለተጫዋቾቹ ይከፍል የነበረው ክለብ በዓመቱ አጋማሽ ደመወዝ ማዘግየት ጀመረ። ነገሮች መክፋት የጀመሩት የካቲት ላይ መከፈል የነበረበት ደመወዝ መጋቢት ላይ ሲመጣ ነው። ሰኔ ሲገባ ደግሞ ጭራሽ ደመወዝ መከፈል አቆመ። ይህ የሆነው ባለፈው ዓመት ነበር። የጨለመ ተስፋ የጠበቁት ደመወዝ ውሃ ሲበላው የክለቡ ተጫዋች ጩኸት ማሰማት ጀመሩ። ገና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሁሉንም በር አንኳኩቶ ምጣኔ ሃብት ማቃወስ ከመጀመሩ በፊት ኦካፋርና አጋሮቿ ሲያሻው በሚመጣ ሲያሻው በሚቀር ደመወዝ መንገላታት ጀመሩ። "ትዝ ይለኛል ወረርሽኙ ከመስፋፋቱ በፊት የክለቡ ምክትል ኃላፊ እሽግ ሩዝ ገዝቶ አከፋፈለን። አንዳንድ ጊዜ ካምፕ ውስጥ ምግብ እንጋራ ነበር። ግድ ሲሆንብን ደግሞ ተበድረን ምግብ እንገዛ ነበር።" ኦካፎርና ሌሎች ተጫዋቾች እጅግ ያበሳጫቸው የክለቡ ኃላፊዎች የወንዶቹን ቡድን እየደጎሙ ለእነሱ ግን ሩዝ በመግዛት ብቻ ሲደልሏቸው ሲመለከቱ ነው። "የወንዶቹ ቡድን ደመወዝ ይከፈለው ነበር። ምን እነሱ ብቻ ታዳጊዎችም ይከፈላቸው ነበር። የእኛ ደመወዝ ግን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተነፍጎን ነበር።" ባለፈው ሚያዚያ የክለቡ ተጫዋቾች በክለቡ ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ። "መሥሪያ ቤቱን የሚጠብቁ ሰዎች የጦር መሣሪያ አውጥተው አካባቢውን ለቀን እንድንሄድ አስፈራሩን። ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስላል እዚህ መሆን አትችሉም አሉን።" "በጣም ተሸማቀቅኩ። የቡድናችን ልጅ ታማ ነበር። የምትበላው አልነበራትም። በዚህ ምክንያት አሁን ኳስ መጫወት የምትችል አይመስለኝም።" የቡድኑ አባላት ለሁለተኛ ጊዜ ተቃውሞ ሲያደርጉ የክለቡ አስተዳዳሪዎች በሚያዝያ ወር መጨረሻ ሁሉም ይስተካከላል የሚል መልዕክት አስተላለፉ። ነገር ግን ኦካፎርና ጓደኞቿ ጉሮሯቸውን ለማርጠብ ሲሉ ወደ ሌላ ሙያ ለመሠማራት ሥር ፍለጋ ላይ ነበሩ። "አንዳንዶቻችን ፀጉር ሥራ ላይ ነን። ልብስ መስፋት የጀመሩም አሉ። ከቤተሰቦቻችንና ከሌሎች ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች እርዳታ ተችሮንም ያውቃል።" በመሃሉ የናይጄሪያ ሴቶች ሊግ ፔሊካን ስታርስ ለተጫዋቾቹ ደመወዝ ካልከፈለ በሊጉ መጫወት አይችልም ሲል ወሰነ። ቢሆንም እስከዛሬ ድረስ ክለቡ ለተጫዋቾቹ ቤሳቤስቲን አልሰጠም። ቺኔኔ ኦካፎር አንድ ቀን ወደ እግር ኳስ እመለሳለሁ የሚል ሕልም አላት። በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል መቀመጫውን ካደረገው ክለብ ለቃ አሁን ቤተሰቦቿ ወደ ሚገኙበት ሌጎስ መጥታለች። "አንድም ቀን ፀጉር ሥራ ላይ እሠማራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ምንም አማራጭ የለኝም። ቀስ በቀስ እየለመድኩት ነው። አንድ ቀን የራሴ የውበት ሳሎን ይኖረኝ ይሆናል።" ይሁን እንጂ አሁንም ለሌሎች ክለቦች ለመጫወት የመሞከር ፍላጎት እንዳላት አትሸሽግም። "አሁንም ከሥራ ስወጣ ልምምድ አደርጋለሁ። ራሴን ሁልጊዜም ብቁ ማድረግ እፈልጋለሁ። ሕልሜ ለብሔራዊ ቡድኑ መጫወት ነው። ሕልሜ አንድ ቀን እውን እንደሚሆን ደግሞ አልጠራጠርም። እግር ኳስ ደስታዬ ነው፤ ሕይወቴ ነው። ሁሉ ነገሬ ነው። መታገሌን እቀጥላለሁ።"
news-52260510
https://www.bbc.com/amharic/news-52260510
ኮሮናቫይረስ፡ ልናውቃቸው የሚገቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዝርዝር ይዘቶች
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መስፋፋትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ለአምስት ወራት በመላዋ አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዝርዝር ይዘት ወጥቷል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የወረርሽኙ ስርጭት እያስከተለ ያለውንና ሊያስከትል የሚችለውን ሰብዓዊ፣ ማኅበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳቶች ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስሉ የተከለከሉ ተግባራትን፣ የሚወሰዱ እምርምጃዎችንና የመብት እገዳዎችን በተመለከተ የሚያብራራ ደንብ አውጥቷል። በዚህም መሰረት በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያችላሉ የተባሉ መደረግ ያለባቸውና የተከለከሉ ጉዳዮችን በአዋጁ ማስፈጸሚያ ደንብ በዝርዝር አስቀምጧል። በዚህም መሠረት፡ 1. ለሐይማኖታዊ ወይም ማኅበራዊ አላማ፣ ለመንግሥታዊ ወይም ፖለቲካዊ ሥራ ወይም ሌላ መሰል አላማ አምልኮ በሚደረግባቸው ቦታዎች፣ በመንግሥት ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በማናቸውም የመሰብሰቢያ አዳራሾችና ቦታ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ ላይ መገኘት የተከለከለ ነው። 2. አስገዳጅ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም በኮሚቴው የሚቋቋሙና ውክልና የሚሰጣቸው በክልሎች፣ በከተማና በወረዳ ደረጃ ባሉ ንዑሳን ኮሚቴዎች ስብሰባ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል። 3. ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ ክልክል ነው። 4. ማንኛውም አገር-አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው በማንኛውም ጊዜ ከተሸከርካሪው ወንበር ብዛት ከ50 በመቶው በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። 5. ማናቸውም የከተማ ውስጥ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ታክሲ፣ አውቶቡስ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር ከ50 በመቶ በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። 6. ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ሾፌሩን ሳይጨምር ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50 ከመቶ በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። 7. የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከዚህ በፊት ሲጭን ከነበረው አቅሙ 25 በመቶ በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። 8. የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር ከወንበር ቁጥሩ 50 ከመቶ በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ ተከለከለ ነው። 9. ማንኛውንም ታራሚን ወይም ተጠርጣሪን በአካል በመገኘት በማረሚያ ቤት ወይም በፖሊስ ጣቢያ መጠየቅ ክልክል ነው። [ሆኖም ይህ ድንጋጌ በፖሊስ ጣቢያ ከሚገኝ ተጠርጣሪ ጋር በአካል ሳይገናኙ ስንቅ ማድረስን አይከለክልም] 10.በጭፈራ ቤቶችና በመጠጥ ቤቶች ማናቸውንም የመጠጥና መዝናኛ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው። 11.በማናቸውም ቦታ የሺሻ ማስጨስና ጫት ማስቃም መስጠት የተከለከለ ነው። 12. የሲኒማ፣ የቲያትርና በአንድ ቦታ ብዙ ሰዎችን የሚያሰባስቡ መሰል የመዝናኛ አገልግሎቶችን መስጠት ክልክል ነው። 13. ሆቴሎች፣ ካፌዎች ወይም ምግብ ቤቶች አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ በአንድ ጠረጴዛ ላይ ከሦስት ሰው በላይ እንዲቀመጥ ማድረግ የተከለከለ ሲሆን፤ ተገልጋዮች በሚቀመጡባቸው ጠረጴዛዎቹ መካከል ያለው ርቀትም ሁለት የአዋቂ እርምጃ መሆን አለበት፤ ሆኖም ተገልጋዮች የሚገለገሉት በጠረጴዛ ላይ ካልሆነ በመካከላቸው የሚኖረው ርቀት ሁለት የአዋቂ እርምጃ መሆን አለበት። 14. በድንበር አካባቢዎች በሚገኙ ኬላዎች በኩል ወደ አገር ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጪ መውጣት የተከለከለ ነው። [ነገር ግን በውጪ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በኬላዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል] 15. ፈቃድ ከተሰጠው ሰው ውጪ በማንኛውም የክልልም ሆነ የፌዴራል መንግሥት ባለስልጣን ወይም ባለሙያ ኮቪድ-19ን በተመለከተ የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥትን ወክሎ መግለጫ መስጠት የተከለከለ ነው። 16. ከላይ የተጠቀሰው ክልከላ ቫይረሱን አስመልክቶ የወጡ ሕጎችን በተመለከተ የሚደረግ የሙያ ትንተናን ወይም በህክምና ባለሙያዎች የሚደረጉ ማብራሪያዎችን ወይም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየዕለቱ የሚሰጡ መረጃዎችን አይመለከትም። 17.ማንኛውም የመኖሪያም ሆነ የንግድ ድርጅት ቤት አከራዮች በተከራዩ ስምምነት ካልሆነ በስተቀር ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ ወይም የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ ነው። 18.ማናቸውም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚተዳደሩ ሠራተኞችን የሚያስተዳደሩ የግል ድርጅቶች በሥራቸው ያሉ ሠራተኞችን የሥራ ውል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚያስቀምጠው ሥርዓት ውጪ ማቋረጥ የተከለከለ ነው። 19.ማንኛውም የመንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋም በትምህርት ቤት ወይም በሌላ ማናቸውም ቦታ አስተማሪና ተማሪዎች በአካል ተገናኝተው መማር ማስተማር ሥራ እንዲሰራ ማድረግ ወይም ማስተማር የተከለከለ ነው። 20.ማንኛውም ሁለትና ከዚያ በላይ ሰው በመሆን የሚጫወቱባቸውን ጨዋታዎች፣ ማጫወትም ሆነ መጫወት የተከለከለ ነው። 21.ማናቸውንም የስፖርት ውድድሮች ወይም የቡድን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የተከለከለ ነው። 22. የህፃናት ማጫዎቻ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው። በተጨማሪም ደንቡ በኮቪዲ-19 ምክንያት ህይወቱ ያለፈ የማንኛውም ሰው የቀብር ሥርዓት የሚፈጸመው በመንግሥት አማካኝነት ለዚሁ አላማ በተለዩ ቦታዎች ሲሆን በቀብሩ ላይ የሚገኘውን የሰው ብዛትና የቀብሩ ዝርዝር አፈፃፀምን በተመለከተ በመመሪያ እንደሚወሰን አመልክቷል። ይህ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈፀሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ተጨማሪ ዝርዝር ነገሮች የያዘ ሲሆን ተፈጻሚነቱም በመላው ኢትዮጵያ ለቀጣዮች አመስት ወራት ይሆናል።
43958911
https://www.bbc.com/amharic/43958911
"የክልሉን መንግሥት በእግዚአብሔር ስም ጠይቁልን..."
ወርሃ ጥቅምት ላይ ቤኒሻንጉል ከሚገኘው ካማሼ ዞን የነበሩ ዜጎች በሥፍራው በተነሳ ግጭት ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሰደዳቸውን ዘግበን ነበር።
ባለፈው ሳምንት ደግሞ እኒህ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች በጊዜያዊነት የባህርዳር የምግብ ዋስትና ግቢ መጋዘን ውስጥ እንደተጠለሉ ባልደረባችን በሥፍራው ተገኝቶ መዘገቡም ይታወሳል። አሁን ደግሞ በጊዜያዊነት ከተጠለሉበት መጋዘን መባረራቸውን ነው ቢቢሲ መረዳት የቻለው። የተፈናቃዮቹ ተወካይ የሆኑት አቶ አበባው ጌትነት ከ150 ሰዎች በላይ መጠለያ አጥተው እየተንከራተቱ እንደሆነ ነግረውናል። ከዚህም በተጨማሪ ስምንት ሰዎች ለሰዓታት ያክል ለእሥር ከተዳረጉ በኋላ እንደተፉም ለቢቢሲ አሳውቀዋል። "በመጀመሪየ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ነበር የቆየነው፤ ከዚያ የአካባቢው ህብረተሰብ ተሰባስቦ ምሳ አበላን። በመቀጠልም ጉዟችንን ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አደረግን። ወደዛ የሄድንበት ዋነኛው አላማችን የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋና አስተዳዳሪ ጳጳስ ማግኘትና የክልሉን መንግስት በእግዚአብሄር ስም እንዲጠይቁልን ለማድረግ ነበር።" "ጳጳሱም ሰላማዊ ሆነን እንድንንቀሳቀስ እና ምንም ዓይነት ወንጀል ውስጥ እስካልገባን ድረስ፤ የሚመለከተውን አካል በማነጋገር መፍትሄ ለማምጣት እንደሚሰሩ ቃል ገብተውልናል" ሲሉ ተወካዩ ነግረውናል። "እዛውም ቆይተን ምሳ እና እራታችንን በልተን፤ አዳራችንን በቤተክርስቲያኒቱ እንዲሆን ትእዛዝ ሰጥተው ሄዱ" በማለት አሁን ያሉበትን ሁኔታ ያስረዳሉ። ተፈናቃዮቹ ችግሮቻቸውን ይዘው ዘላቂ መፍትሄ ይበጅላቸው ዘንድ ለክልሉ አስተዳደር ፅህፈት ቤቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን ይናገራሉ፤ ከክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተቀምጠው መወያየታቸውንም ያስረዳሉ። ነገር ግን ክልሉ ያቀረበላቸው ሁለት አማራጮች ፤ ወደተፈናቀሉበት ካማሼ ዞን መመለስ ወይንም ቀድሞ ትተዋቸው በሄዷቸው የትውልድ ቀየዎቻቸው ዳግመኛ መስፈር፤ ያስደሰቷቸው አይመስልም። ቢቢሲ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአማራ ክልል ሕዝብ ግንኙነት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁንን እንዲሁም የክልሉን ባለሥልጣናት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
news-46541524
https://www.bbc.com/amharic/news-46541524
''ወንጀለኞቹ ማንም ይሁኑ ማን . . . አድነን ለሕግ ማቅረባችን አይቀሬ ነው'' ዐብይ አህመድ
'ግፍ ሠርቶ መደበቅ፣ ዘርፎ መንደላቀቅ አይቻልም' የሚለው ጠንከር ያለው የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክት ርዕስ ነበር።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ዛሬ አመሻሹ ላይ በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመልዕክታቸው መግቢያ ላይ ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የለውጥ ጉዞ ላይ መሆኗን ያስታወሱ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አምባገነናዊ ሥርዓትን የታገለው ግፍ እንዲቆም፣ ፍትሕ እንዲሰፍን እንጂ ሌሎች ግፈኞችን ለመተካት አይደለም ብለዋል። የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ማስከበር የሚቻለው ሰብአዊ መብቶችን የማስከበር እርምጃ በግለሰቦች ፍላጎትና ይሁንታ መመራቱ ቀርቶ 'የጋራ ፍላጎታችን በወለዳቸው' ተቋማት መመራት ሲጀመር ነው ብለዋል። ''. . . ሀገር የሚዘርፉ ጁንታዎች በኩራት በከተሞቻችን እየተንፈላሰሱ ሕግ ያልፈረደባቸው ዜጎች . . . ግፍ ይፈጸምባቸው ነበር። . . . በፖሊስ፣ በደኅንነት፣ በፍርድ ቤቶች፣ በማረሚያ ቤቶች . . . በሚገኙ ባለስልጣናት ፈቃጅነትና መሪነት፤ ኀሊናቸውን ሽጠው ለሆዳቸው ባደሩ የግፍ ሠራዊት ተላላኪነት በዜጎቻችን ላይ አራዊት የማይፈጽሙት ሰቆቃ ይወርድባቸው ነበር። ግፍ ፈጻሚዎቹ ከሳሽም፣ ምስክርም፣ መርማሪም፣ አሣሪም፣ ዐቃቤ ሕግም፣ ዳኛም ሆነው የግፉን ድራማ ተውነውታል።'' በማለት ጠንከር ባሉ ቃላቶች ከዚህ ቀደም በመንግሥት ኃይሎች ይፈጸሙ የነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ኮንነዋል። • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ • በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃና ግፍ ለተፈጸመባቸው ካሳ ሊጠየቅ ነው • የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች ጠቅላይ ሚንስትሩ በባለ ሶስት ገጽ መልዕክታቸው ለሞራል ድንጋጌዎች ከፍተኛ ቦታ የሚሰጥ ማኅበረሰብ አለን ያሉ ሲሆን። ''ታዲያ እነዚህ ሰዎች እንዴት ነው ይሄንን ሁሉ ግፍ ሊፈጽሙ የቻሉት?'' ሲሉም ይጠይቃሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ግፍ ፈጻሚዎች ናቸው ላሏቸው ግለሰቦች ሶስት ምላሽ መስጠት አለብን ይላሉ። እነዚህም፤ ጥፋተኞችን ለፍርድ ማቅረብ፣ ዳግም የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳይፈጸም አስተማማኝ ስርዓት መዘርጋት እና ''ሶስተኛው ከእነርሱ የተሻልን መሆናችንን በተግባር ማሳየት ነው።'' ብለዋል። ግፍ ፈጻሚዎቹ ይህን ሁሉ ግፍ የፈጸሙት ምንም ሳይመስላቸው በልተው ተኝተው እያደሩ ነበር የሚሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ''እኛ ግን ግፉ ይሰቀጥጠናል፣ ያመናል፣ ዕረፍት ይነሳናል።'' ብለዋል። ። ለየት ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ደብዳቤ ለየመኖች ''የግፍ ቀዳዳዎችን መድፈን፣ ሕጎችን ማሻሻል፣ አሠራሮችን ማስተካከል፣ ተቋማትን ማብቃት፣ የዝርፊያን እና የአምባገነን በሮችን መዝጋት አለብን።'' ይላል መልዕክታቸው። ''በምንም መልኩ ግፈኞቹ እራሳቸውን እንጂ፣ የበቀሉበትን ሕዝብ ግፋቸው እንደማይመለከተው እናምናለን። የትኛውም ብሄር ወይም የትኛውም ዘር ግፈኞችን፣ ገራፊዎችንና ጨቋኞችን ሊያበቅል ይችላል። . . . ግለሰቦች ባጠፉ የምንቀየመው ወይም ጣት የምንቀስርበት ብሔር አይኖርም። . . . ወንጀለኛ እራሱን ችሎ ወንጀለኛ ለመሆን ከምንም ጋር መለጠፍ እና ማንም ላይ መደገፍ አያስፈልገውም። . . . ግፍ የሠራው ሰው የሚናገረው ቋንቋ ኦሮምኛ ቢሆን ኦሮሞውን፣ ትግረኛ ቢናገር ትግሬውን . . . የሚወቅስ ሰው ካለ እሱ ከታሪክ የማይማር ደካማ ነው። . . . ለአንድ ገጽ ብለን መጽሐፍ የምንቀድ ሞኞች አይደለንም። . . . ሁሌም ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር፤ ወንጀለኞቹ ሊደበቁበት ከሚፈልጉት ብሔር ነጥለን ማየትና እስከመጨረሻው ለፍርድ ማቅረብ እንደሚገባን ነው።''ብለዋል። በመጨረሻም "ቂምና በቀልን ልናስበው አይገባም፤ ፍርድና ፍትሕን እንጂ። ይህን ሁሉ የምናደርገው እንደ እነርሱ ከጥላቻ ተነሥተን ሳይሆን የሕግ የበላይነት መስፈን ስላለበት ነው። ወንጀለኞቹ ማንም ይሁኑ ማን፣ ከየትኛውም ብሔር ገብተው ይደበቁ፣ የትኛውም ወገን ይጩህላቸው፣ በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ ካሉበት አድነን ለሕግ ማቅረባችን አይቀሬ ነው'' ይላል የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክት።
news-57217330
https://www.bbc.com/amharic/news-57217330
ኮሮናቫይረስ፡ የአስትራዜኒካና የፋይዘር ክትባቶች ለሕንዱ የኮቪድ ዝርያ ፍቱን እንደሆኑ ተደረሰበት
የኮቪድ ወረርሽኝ መስፋፋትን ተከትሎ በተለይ በሕንድ ይበልጥ ለተባዛው ገዳዩ ዝርያ አሁን በሥራ ላይ ያሉት ክትባቶች ምን ያህል ፈውስ ይሰጡ ይሆን የሚለው ጥያቄ የጤና ዘርፉን ሲያስጨንቅ ነበር፡፡
አንድ ትኩስ ጥናት መልካም ዜና ይዞ መጥቷል፡፡ ፋይዘርና አስትራዜኒካ ክትባቶች ሁለት ጊዜ ከተወሰዱ የሕንዱን ዝርያ ተህዋሲ የመፈወስ ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተደርሶበታል፡፡ ሁለቱ የክትባት ዓይነቶች ሙሉ በሙሉ ከተወሰዱ (ሁለት ጠብታዎችን አከታትሎ መውሰድ) ክትባቶቹ ልክ ሌላውን የኮቪድ ዝርያ እንደሚከላከሉት ሁሉ የሕንዱን ዝርያም መከላከል ይችላሉ ተብሏል፡፡ ሆኖም ግን ሁለቱም ክትባቶች አንድ ጊዜ ብቻ ከተወሰዱ (አንድ ጠብታ ብቻ ከሆነ) የሕንዱን ተህዋሲ ዝርያ መከላከል የሚችሉበት ምጣኔ 33% ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ይህም ውጤት ከኬንት ዝርያ ያነሰ የመከላከል አቅም ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ሁለቱ ክትባቶች አንድ አንድ ጊዜ ቢወሰዱ የኬንት ዝርያን 50 ከመቶ የመከላከል አቅም መፍጠር እንደቻሉ ተደርሶበት ነበር፡፡ ጥናቱን ያካሄደው ፐብሊክ ሄልዝ ኢንግላንድ ሲሆን እነዚህ ክትባቶች የሟቾችንም ቁጥር ሆነ ሆስፒታል የሚመጣውን ታማሚ ቁጥር በከፍተኛ መጠን እንደሚቀንሱ አረጋግጧል፡፡ የዩኬ የጤና ሚኒስትር ማት ሐንኮክ ይህ ጥናት ትልቅ በራስ መተማመንን የሚፈጥር ነው ሲሉ ደስታቸውን ገልጠዋል፡፡ ዩኬ በሰኔ መጨረሻ እቀባዎችን በከፍተኛ ሁናቴ ለማላላት የያዘቸውን ዕቅድም ነፍስ የዘራበት ጥናት ነው ማለታቸውን ተዘግቧል፡፡ ይህ ጥናት ያረጋገጠው ሌላው ነገር ቢኖር አስትራዜኒካም ሆነ ፋይዘር እጅግ ውጤታማ የመከላከል ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ሙሉ ጠብታ በሁለት ዙር መውሰድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡
news-50991622
https://www.bbc.com/amharic/news-50991622
ተታለው ልቅ የወሲብ ምስላቸው የተሰራጨባቸው ሴቶች ካሳ ተፈረደላቸው
የአሜሪካው ፍርድ ቤት ተታለው ልቅ የወሲብ ተንቀሳቃሽ ምስላቸው በልቅ የወሲብ ድረ-ገጾች ላይ የተራጨባቸው 22 ሴቶች ካሳ እንዲከፈላቸው በየነ።
እድሜያቸው ከ18-23 የሆኑት 22 ሴቶች ልቅ ወሲብ እየፈጸሙ ለመቀረጽ የተስማሙት፤ ምስሎቹ በድረ-ገጾች ላይ እንደማይወጣ ተስማምተው ቢሆንም 'ገርልስዱፖርን' [GirlsDoPorn] በተሰኘ ድረ-ገጽ እና በሌሎች ላይ ተሰራጭቷል። ለዚህም በጠቅላላው ለ22ቱ ሴቶች የ12.8 ሚሊዮን ዶላር (384 ሚሊዮን ብር በላይ) ካሳ እንዲከፈላቸው ተበይኗል። የፍርድ ቤቱ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ወጣቶቹ በክፍያ ቪዲዮን ለመቀረጽ የተስማሙት፤ ምስላቸው ለግለሰቦች ለግል ስብሰብ ግብዓት ብቻ እንደሚሆን ከተናገራቸው በኋላ ነው። የሳን ዲያጎ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ 'የገርልስዱፖርን' ሥራ አስኪያጅን ቪዲዮቹን ከድረ-ገጹ እና ከሌሎች ገጾች ላይ እንዲያነሳ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። 'ገርልስዱፖርን' በተሰኘው ድረ-ገጽ ላይ የሚታዩት ሴቶች፤ የወሲብ ፊልም ተዋናይ ሳይሆኑ ገንዘብ ያጠራቸው አንድ ግዜ ብቻ የወሲብ ቪዲዮ የተቀረጹ ወጣት ሴቶችን እንደሚያቀርብ የክስ መዝገቡ ላይ ተጠቅሷል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ እንዳለው፤ ድረ-ገጹ ሴቶቹ ምስላቸው በድረ-ገጾች ላይ እንደማይጫኑ፤ ትክክለኛ ስማቸውንም እንደማይጠቀም እንዲሁም የሚያውቋቸው ሰዎችም ምስሎቹን እንማይመለከቱ ቃል ገብቶላቸው ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን የሴቶቹ ተንቀሳቃሽ ምስል ድረ-ገጹ ላይ ከመዋሉም ባሻገር፤ ወጣቶቹ ሊለዩባቸው የሚችሉበት የግል መረጃ ይፋ አድርጓል። በዚህም ከሴቶቹ አልፎ የቤተሰብ አባላቶቻቸው በኢንተርኔት ላይ የተለያየ መልክ ያላቸው የመብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸው ፍርድ ቤቱ አረጋግጫለሁ ብሏል። የከሳሾቹ ጠበቃ፤ ደንበኞቹ ላይ የተለያየ አይነት ጥቃት ከመድረሱም ባሻገር፤ ለሞራል እና ለሥነ ልቦና ችግር ተዳርገዋል። ከሥራቸው የተሰናበቱ እና ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የተገደዱ ጭምር እንዳሉ ገልጿል። የ'ገርልስዱፖርን' ድረ-ገጽ ባለቤቶች ይግባኝ ማለት ከፈለጉ የ15 ቀናት ጊዜ ተሰጥቷቸዋል።
news-54040205
https://www.bbc.com/amharic/news-54040205
ቤንሻንጉል ጉሙዝ፡ በክልሉ በደረሰው ጥቃት የፀጥታ ኃይሎች መጎዳታቸው ተገለፀ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች በተፈጠረ አለመረጋጋት የፀጥታ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የህክምና ባለሙያ ለቢቢሲ እንዳስታወቁት በሚሠሩበት ቡለን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ትናንት ምሽት ከአንድ ሰዓት በኋላ ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የልዩ ሃይል አባላት የህክምና ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። ትናንት ህክምና የተደረገላቸው ከትናንት ወዲያ ጉዳት የደረሰባቸው የጸጥታ ኃይል አባላት መሆናቸውንም ጨምረው አስታውቀዋል። የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያው አክለውም በሆስፒታላቸው ሁለት የመከላከያ አባላት ህይወታቸው አልፎ አስከሬናቸውን መመልከታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። እንደባለሙያው ከሆነ የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታሉ የመጡት የጸጥታ ኃይል አባላት ስምንት ሲሆኑ አምስቱ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሦስቱ ደግሞ የልዩ ኃይል አባላት ናቸው። የጸጥታ አካላቱ ህክምና ከተደረገላቸው በኋላ የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ወደ ባህር ዳር የመከላከያ ሠራዊት ሆስፒታል የክልሉ የልዩ ኃይል አባላት ደግሞ ወደ ፓዊ ሆስፒታል መላካቸውን ጨምረው አስረድተዋል። ባለሙያው ወደ አካባቢዎቹ ተጨማሪ የጸጥታ አካላት ሲገቡ መመልከታቸውንም ተናግረዋል። ስለጉዳዩ ቢቢሲ ጥያቄ ያቀረበላቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ በጉዳዩ ላይ ስምሪት የተሰጠው የጸጥታ አካል መረጃ በሚሰጣቸው ጊዜ ትክክለኛ መረጃ ከመስጠት ውጭ አሁን መረጃ በደፈናው መስጠት የተሟላ አይሆንም ብለዋል። "በየአቅጣጫው የሚወራውን አሉባልታ መንገርም ለመረጃ የሚጠቅም ስለማይሆን፤ አንዳንድ አላስፈላጊ አሉባልታዎች ሊሆኑ ስለሚችሉ እሱን እንደ መረጃ መውሰድ አያስፈልግም። በእኛ በኩል ወደ አካባቢው የገባ የጸጥታ አካል አለ። ሥራውን ሠርቶ ሲወጣ ወይም ደግሞ በመሃል ላይ መረጃ ለመስጠት አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የተሟላ መረጃ በዚያ መልክ እንሰጣለን" ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። በአካባቢው ያለው ሁኔታ ከጸጥታ አካላቱ አቅም በላይ አለመሆኑን ጠቁመው፣ የጸጥታ ኃይሉ በተለያዩ አካባቢዎች በመግባት ህዝቡን በማረጋጋት ላይ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ ጎን ለጎንም 'ጸረ ሠላም' ያሏቸው ኃይሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን ጠቅሰው የተሟላ መረጃ እንደሚሰጡም አስታውቀዋል። "የጸጥታ አካሉ እዚያ ያለው ኔትዎርክ ደካማ በመሆኑ መረጃ ለማግኘት ትንሽ ተቸግረናል" ያሉ ሲሆን "የገባው የጸጥታ አካል ወጣ ብሎ ኔትዎርክ ያለበት ቦታ ሲሆን ነው ደውሎ መረጃ መስጠት የሚችለው። እና መረጃ ለመስጠት በኔትዎርክ ችግር ምክንያት አልቻልንም። እነሱ እንደወጡ መረጃውን ማድረስ እንችላለን" ሲሉ አክለው ተናግረዋል። 'የጸረ ሠላም ኃይሎች' ያሏቸው አካላት ከህብረተሰቡ ጋር የተቀላቀሉ መሆኑ እርምጃ ለመውሰድ ትንሽ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመው ከሠላማዊ ህብረተሰብ የመለየት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። በአካባቢው የተፈጠረው ችግር ከአንድ ወር በፊት በጉባ ከነበረው ጥቃት ጋር የተያያዘ መሆኑን ኮማንደር ነጋ ጠቁመው፣ በወቅቱ የጸጥታ አካለት በሠሩት ሥራ ተጠርጣሪዎችን ከነጦር መሣሪያቸው በመያዝ ለሕግ የማቅረብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። አሁን ላይ ጉባ ወረዳ ሠላማዊ መሆኑን ጠቅሰው፣ በመተከል ዞን በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች የጸጥታ አካላት ከገቡ በኋላ አንጻራዊ ሠላም መፈጠሩን አክለው አስረድተዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ባሉ ሁለት ወረዳዎች በቡድን የተደራጁ ኃይሎች በነዋሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የክልሉ ፖሊስ ለቢቢሲ በትናንትናው እለት ገልጿል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ ለቢቢሲ እንደገለጹት "ፀረ ሠላም" ያሏቸው ኃይሎች በወንበራ ወረዳ መልካ በምትባል ቀበሌ ሠላማዊ ሰዎችን በማገት፣ የጦር መሣሪያዎችን በመቀማትና በአካባቢው ማኅበረሰብ ንብረት ላይ ዘረፋ ፈጽመዋል ብለዋል። በቤንሻንጉል ክልል የተፈጠረው ምንድን ነው? በትላንትናው ዕለትም [ሰኞ] በቡለን ወረዳ ኤጳር በምትባል ቀበሌ እነዚሁ ኃይሎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የአፈናና የግድያ ወንጀል ከመፈጸማቸው በተጨማሪ የተለያዩ ጉዳቶችን ማድረሳቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ በአካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ጠይቆ እንደተረዳው በተለያዩ ጊዜያት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በሚፈጸመው ጥቃት የተነሳ የዕለት ከዕለት ተግባራቸውን በስጋት ውስጥ ሆነው እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል። በሚፈጸሙት ጥቃቶችም በሰው ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ በመሆኑ እንቅስቃሴያቸው መገደቡንና ክስተቱም ሁሉም በነጻነት እንዳይንቀሳቀስ በማድረጉ በአካባቢዎቹ ባለው ሥራ ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የወረዳው የመንግሥት ሠራተኛ ተናግረዋል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከአካባቢው ነዋሪዎች በተጨማሪ የጤናና ግብርና ባለሙያዎችን ለማፈን ከመሞከራቸውም በላይ በመንግሥት መዋቅር ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከሩ መሆኑን ጠቅሰው ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ወደ ሌላ ወረዳ መሸሻቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ በወጣው መረጃ መሰረት የአካባቢው ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ልዩ ኃይል በጋራ በመሆን ወደ ወረዳዎቹ በመግባት ጥቃቱን ለማስቆምና ፈጻሚዎቹን ለመቆጣጠር በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ በወረዳዎቹ እንደሚሉት ጉዳት እያስከተለ ያለው ጥቃት የሚፈጸመው ስሙን ለጊዜው መጥቀስ ባልፈለጉት "የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድን አባላት" መሆኑንና በቁጥጥር ስር እያዋሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ እስካሁን የታገቱ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር በተመለከከተ "በቁጥር ደረጃ በዝርዝር አልተለየም" ያሉት ኮማንደር ነጋ፤ መረጃው ተሰባሰቦ ሲያልቅ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ በክልሉ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ጋር በተያያዘ "ፀረ ሠላም" ያሏቸው ኃይሎች ከውጪ አገር ጭምር ድጋፍ እንደሚደረግላቸው መረጃ መገኘቱን ጠቅሰው "ወጣቶችን ለመመልመል እንደሚንቀሳቀሱም" ጨምረው ተናግረዋል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከቀናት በፊል መልካን በሚባል ቀበሌ 30 ሰዎችን አፍነው የነበረ ሲሆን አሁን እነሱን መልቀቃቸውን አመልክተው፤ የያዟቸውን ሰዎች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። በተለያዩ ጊዜያት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ማንነታቸው ያልተገጹ ቡድኖች በነዋሪዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው ባሻገር በተደጋጋሚ ሰዎችን እያገቱ እንደሚወስዱ ሲዘገብ ቆይቷል። ይህንንም ለማስቆም የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ከአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመቆጣጠርና ድርጊቱን ለማስቆም እየጣሩ መሆኑ ተገልጿል።
news-46890661
https://www.bbc.com/amharic/news-46890661
ዩቲውብ አደገኛ 'ፕራንክ' ሊያግድ ነው
ዩቲውብ አደገኛና አስደንጋጭ የ 'ፕራንክ' ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ሊያግድ ነው። 'ፕራንክ' ፤ አንድ ሰው ሌላ ሰውን ለማሸበር ወይም ለማስደንገጥ በማሰብ ሆነ ተብሎ የሚፈጸም ተግባር ነው።
ዩቲውብ አደገኛና አስደንጋጭ 'ፕራንክ' ሊያግድ ነው ዩቲውብ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በድረ ገጹ በስፋት የሚሰራጩ ሞትና የአካል ጉዳት ያስከተሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመቆጣጠር ነው። • ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ ዩቲውብ "መሰል ቪድዮዎች በዩቲውብ ቦታ የላቸውም" የሚል መልዕክት አስተላልፏል። ዩቲውብ ከቀድሞውም አደገኛ ይዘት ያላቸው መረጃዎችን ለመከላከል የወጣ ሕግ ቢኖረውም እየተከበረ አይደለም። ብዙ ጊዜ አደገኛ ይዘት ያላቸው ምስሎችን ከድረ ገጹ እንዲነሱ ተጠይቆ ለወራት ምላሽ አለመስጠቱም ተቋሙን ያስተቸዋል። ዩቲውብ የበርካታ 'ፕራንኮች' መገኛ መሆኑ ይታወቃል። 'ፕራንኮች' ብዙ ሚሊዮን ተመልካችም የያገኛሉ። ሆኖም ዩቲውብ፤ የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በትጋት እሠራለሁ ብሏል። • ፌስቡክ የትራምፕን ክስ ውድቅ አደረገ • ፌስቡክ ግላዊ መረጃን አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ "አስቂኝ የሚባል ቪድዮ መስመሩን አልፎ አደገኛ እንዳይሆን የምንከላለከልበት ፖሊሲ አለን" የሚል መልዕክት ከዩቲውብ ተላልፏል። ከዚህ በኋላ ሰዎች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ማንኛውም አይነት 'ፕራንኮች' እንደማይስተናግዱም አስረግጠው ተናግረዋል። አንድ ሰው በእውን አደጋ ውስጥ ሳይሆን፤ አደጋ ውስጥ እንዳለ በማስመሰል የሚሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የሚታገዱ ይሆናል። በተጨማሪም ህጻናትን የሚያስጨንቅና የሚያስፈራ ማንኛውም 'ፕራንክ' ስርጭቱ ይገታል ተብሏል።
news-48715601
https://www.bbc.com/amharic/news-48715601
'ኢራን፤ ትልቅ ስህተት ፈፅመሻል!' ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን ያስተላለፉት መልዕክት
ኢራን የአሜሪካን ወታደራዊ ድሮን [ሰው አልባ አውሮፕላን] መትታ መጣሏ 'እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት ነው' ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ተደምጠዋል።
'መቼም ከሰው ስህተት አይጠፋምና' ኢራን ተሳስታ ይሆናል ድሮኑን የመታችውም ብለዋል ትራምፕ። «እኔ በበኩሌ አራን ከልቧ ሆና ይህንን ታደርጋለች ብዬ አላምንም» ነበር ከጋዜጠኞች ለቀረለበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ። ኢራን ሰው አልባው አውሮፕላን 'ድንበሬን ጥሶ ገብቷል' ብትልም አሜሪካ ግን ወቀሳው ውሃ አያነሳም ባይ ናት። • ኢትዮጵያ የእየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማነት ከተቃወሙት አንዷ ነች ሁለቱ ሃገራት ጠብ ያለሽ በዳቦ ላይ ናቸው። ኢራን 'አሜሪካ ድንበሬን ጥሳ ገብታለች፤ ድሮኗ የመጣችው ለስለላ ነው' የሚል ክስ አሰናድታ ወደ ተባበሩት መንግሥታት ልትሄድ እንደሆነ የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዛሪፍ አሳውቀዋል። በነጩ ቤተ-መንግሥታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ የነበሩት ትራምፕ 'ድሮኗ በዓለም አቀፍ ከባቢ ላይ እንጂ የአራን ድንበርን አልጣሰችም» ብለዋል። «እኔ በበኩሌ ስህተት ነው 'ሚመስለኝ። እንደውም ሳስበው አንድ ግለሰብ ነው በስህተት ድሮኗ እንድትመታ ያዘዘው። አንድ ደደብ የሆነ ሰው ይሆናል ይህን የፈፀመው።» • አሜሪካ የቬንዙዌላ መንግሥትን አሰጠነቀቀች የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ጦርነት ቢከሰት መዘዙ የከፋ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የተባባሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉዌቴሬዝም ሁለቱ ሃገራት ረጋ ብለው እንዲያስቡ መልዕክት ልከዋል። የአሜሪካ ሕዝብ እንደራሴዎች አፈ-ጉባዔ ዴሞክራቷ ናንሲ ፔሎሲ 'አሜሪካ ለጦርነት ያላት አምሮት ቀንሷል' ሲሉ የቀጣዩ ምርጫ ተፎካካሪ የሆኑት የቀድሞው ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን 'በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው ውጥረት የትራምፕ 'ግብዝነት' ውጤት ነው ሲሉ ፕሬዝደንቱን ወርፈዋል። ሳዑዲ አራቢያ ለአሜሪካ የወገነች ትመስላለች፤ 'የኢራን ድርጊት ተቀባይነት የለውም' ባይም ነች። የሁለቱን ሃገራት ውጥረት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በ15 በመቶ ጨምሯል። • አፍሪካውያን ስደተኞች በአሜሪካ ድንበር ደጅ እየጠኑ ነው
news-52343221
https://www.bbc.com/amharic/news-52343221
የኮሮናቫይረስ ለሮቦቶች የሥራ ዕድል ይከፍት ይሆን?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን እንዲህ ወጥሮ በያዘበት ወቅት በርካታ የዓለማችን ሰራተኞችን ሲያስጨንቅ የነበረው ጉዳይ የተረሳ ይመስላል- የሮቦቶች ወደ ሥራው ዓለም መቀላቀል።
በቅርብም ሆነ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ሮቦቶች የሰው ልጆችን ስራ ለቃቅመው እንደሚረከቡ ሲነገር የቆየ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ መምጣት ግን ሂደቱን እንዳያፋጥነው ተሰግቷል። '' ሰዎች በሁሉም እንቅስቃሴያቸው ከሰዎች ጋር ይገናኙ ነበር፤ አሁን ግን ሁሉም በየቤቱ ተሰብስቦ መቀመጡ ሌሎች አማራጮች እንዲፈልጉ ያደርጋል" ይላሉ የዘርፉ ባለሙያ የሆኑት ማርቲን ፎርድ። • "መደብር ሄጄ የውጪ አገር ሰው አንቀበልም አሉኝ" ኢትዮጵያዊቷ በቻይና • በኮሮናቫይረስ ምክንያት ስጋት ውስጥ የወደቀው የጃፓን የጤና ሥርዓት እንደ እሳቸው ትንበያም ከሆነ የሰው ልጅ እንደዚህ በቀላሉ ከስራ ውጪ መሆነ ከቻለ ያለምንም ችግር በማንኛውም ሁኔታ መስራት የሚችሉ ሮቦቶች ተፈላጊነት በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ይሆናል። በጣም ትልልቅም ሆነ አነስተኛ የሚባሉ ድርጅቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሰራተኞቻቸው ከቤታቸው ሆነው መስራት የማይችሏቸውን ስራዎች በሮቦት ማሰራት ጀምረዋል። የአሜሪካው ትልቁ የጅምላ ንግድ ድርጅት 'ዎልማርት' ወለሎችን ለማጽዳት የሚውሉ ሮቦቶችን ወደ ስራ አስገብቷል። በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ሮቦቶች ደግሞ የሰዎችን የሰውነት ሙቀት በመለካትና የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮችን በማከፋፈል ተጠምደው ነበር። አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እስሚቀጥለው ዓመት ድረስ ሊተገበር ይገባል ማለታቸውን ተከትሎ ሮቦቶች ተፈላጊነት በእጅጉ ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል። በዴንማርክ የሚገኘውና የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሮቦቶችን የሚያመርተው 'ዩቪዲ ሮቦትስ' ሆስፒታሎችን የሚያጸዱ ሮቦቶቹ በጣም ተፈላጊ ሆነውለታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎም በመቶዎች የሚቆጠሩ ጽዳት የሚሰሩ ሮቦቶችን ቻይና እና አውሮፓ ለሚገኙ ሆስፒታሎች ሽጧል። ሱፕርማርኬቶችና ምግብ ቤቶችም ቢሆኑ እነዚህን ሮቦቶች መጠቀም ጀምረዋል። ሮቦቶች በቅርቡ ይረከቡታል ተብሎ የሚጠበቀው ደግሞ የምግብ ኢንዱስትሪውን ነው። የአሜሪካው ፈጣን ምግብ አምራች 'ማክዶናልድስ' ምግብ የሚያበስሉና የሚያቀርቡ ሮቦቶችን በመሞከር ላይ ይገኛል። • ኢንሹራንስና ቤት ለኮሮናቫይረስ ጤና አገልግሎት ሰጪዎች ምናልባት አንድን ሮቦት ገዝቶ ወደስራ ለማስገባትና ለማቀናጀት በርከት ያለ ገንዝብ ሊያስፈልግ ይችላል፤ ነገር ግን ሮቦቶቹ አንዴ ወደስራ ከገቡ በኋላ ለበርካታ ዓመታት ያለክፍያና ያለማቋረጥ መስራት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ለበርካታ ቀጣሪዎች ተቀዳሚው ምርጫ ያደርገዋል። ሌላው ቀርቶ ሰዎች እራሳቸው ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ብዙ ሰዎች የተሰበሰቡበት አካባቢ መገኘት ምቾት ላይሰጣቸው ይችላል። በዚህም ምክንያት ሮቦቶች የሚያስተናግዱበትና ምግብ የሚያበስሉበትን ምግብ ሊመርጡ ይችላሉ። አንድ ዓለም አቀፍ አማካሪ ቡድን በሰራው ጥናት መሰረት በፈረንጆቹ 2030 በአሜሪካ ከሚገኙ ስራዎች አንድ ሶስተኛው በሮቦቶች ይያዛል። ነገር ግን እንደ ኮሮና ያሉ ወረርሽኞች ከዚህም በቀረበ ጊዜ ሮቦቶችን እንደምንመለከታቸው ማሳያ ናቸው።
news-51764785
https://www.bbc.com/amharic/news-51764785
ለቀልድ ሲል አይስክሬም ከማቀዝቀዣ አውጥቶ የላሰው ወጣት እስር ተፈረደበት
አንድ ወጣት ቴክሳስ ውስጥ በሚገኝ መደብር ለማኅበራዊ ሚዲያ ቀልድ ሲል እራሱን በቪዲዮ እየቀረጸ ከማቀዝቀዣ አይስክሬም አውጥቶ ከላሰ በኋላ ወደ ማቀዝቀዣው በመመለሱ የ30 ቀናት እስር ተፈረደበት።
የ24 ዓመቱ ዳድሪን አንደርሰን የቀረጸው ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የታየው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ነበረ። በዎልማርት መደብር ውስጥ ያሉ ካሜራዎች በኋላ እንዳሳዩት ወጣቱ አይስክሬሙን ከማቀዝቀዣው አውጥቶ እንደከፈለበት አሳይተዋል። በዚህ ድርጊቱም ከእስሩ በተጨማሪ ለስድስት ወራት የሚቆይ የገደብ ቅጣት፣ የ100 ሰዓታት ያለክፍያ ሥራ፣ የአንድ ሺህ ዶላር ቅጣትና 1565 ዶላር ደግሞ ለአይስክሬም አምራቹ እንዲከፍል ተወስኖበታል። የኤቢሲ ቴሌቪዥን እመንደዘገበው አንደርሰንና አባቱ ወደ ፖሊስ ሄደው ለላሰው አይስክሬም የከፈሉ መሆናቸውን የሚያመለክት ደረሰኝ አሳይተው ነበር። ነገር ግን ተልሶ በተመለሰው አይስክሬም ምክንያት ለጥንቃቄ ሲል የአይስክሬም አማራቹ ድርጅት 1565 ዶላር የሚያወጡትን የቀሩትን አይስክሬሞች ለጥንቃቄ ሲል በማስወገድ በአዲስ ለመተካት ተገዶ ነበር። አንደርሰን የፈጸመውን ጥፋት አምኖ ተቀብሏል። ዎልማርት የተባለው መደብርም የአንደርሰን ድርጊት ይፋ ከተደረገ በኋላ ባወጣው መግለጫ "ለቀልድ በሚል በምግብ ምርቶች ላይ ተመሳሳይ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ሰዎችን ከሕግ አስከባሪዎች ጋር በመሆን እንዲቀጡ እንደርጋለን፤ ይህ ቀልድ አይደለም" ሲል አስጠንቅቋል። የአንደርሰን ድርጊት አነጋጋሪ ሆኖ ለቅጣት የተዳረገው ከወራት በኋላ አንዲት ታዳጊ ቴክሳስ ውስጥ በሚገኝ የዎልማርት መደብር ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ አይስክሬም ከማቀዝቀዣ አውጥታ ልሳ ስትመልስ የሚያሳይ ቪዲዮ ከታየ በኋላ ነው። ከ18 ዓመት በታች የሆነችው ታዳጊ አይስክሬሙን ያልገዛችው ሲሆን ቪዲዮው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከ13 ሚሊዮን ጊዜ በላይ ታይቷል። የአንደርሰንንም ጉዳይ ቀስቅሶ ለቅጣት ዳርጎታል።
news-53021262
https://www.bbc.com/amharic/news-53021262
ሰዎችን በፊት ገጽታቸው "ጉግል" ማድረግ ሊጀመር ነው
የምንፈልገውን ሰው ስሙን ጽፈን በበይነ መረብ ብንፈልገው እናገኘዋለን። ያም ካልሆነ በአድራሻው፣ ያም ካልሆነ በስልክ ቁጥሩ።
አሁን እየመጣ ያለው ቴክኖሎጂ ግን ሰዎችን በፊት መልካቸው ፈልፍሎ የሚያወጣ ሆኗል። ይህ ፒምአይስ የሚባል ነገር አንድ ሰው ራሱንም ሆነ የሌላ ሰው ፎቶ በማስገባት በይነ መረብ ተጨማሪ ምስሎችን ለቅሞ እንዲያመጣ የሚያደርግ ነው። ይህ ነገር ታዲያ የሰዎችን ምስጢርና የግላዊ መብት የሚጥስ ነው በሚል ተቃውሞ እየቀረበበት ነው። ፒምአይስ ግን ራሱን የሚገልጸው በዚህ መንገድ አይደለም። ሰዎች እንዲያውም ምስላቸው የት እንዳለ እንዲደርሱበት አግዣቸዋለሁ ይላል። "ቢግ ብራዘር ዋች" የተባለ በሰዎች ምስጢር ጥበቃ ላይ የተሰማራ ድርጅት የእዚህ ቴክኖሎጂ መፈጠር አገራት ዜጎቻቸውን በቀላሉ እንዲሰልሉ ያስችላቸዋል። ይህ ደግሞ ጥሩ ዜና አይደለም። ከዚህም ባሻገር ኩባንያዎች ሰዎችንና ምስላቸውን እንዲነግዱበት ይገፋፋቸዋል ይላል ቢግ ብራዘርስ። የፊት ገጽታ የበይነ መረብ አሰሳ የሰዎችን ግላዊ መብት የሚጋፋና እጅግ አደገኛ ውጤት እንዲሚኖረው ቢግ ራዘርስ ዋች ያሳስባል። አማዞን ከዚሁ ቴክኖሎጂ ጋር የሚቀራረብ ፊትን የሚለይ መሣሪያ ተግባር ላይ አውሎ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ይህን ተግባሩን ከሰሞኑ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ አቁሞታል። ይህ ፒምአይስ የተባለው ድረ ገጽ በፖላንድ አገር የተቋቋመ ሲሆን ሥራውን የጀመረው ከሦስት ዓመት በፊት በ2017 ነው። አጀማመሩ እንዲሁ እንደ ትርፍ ጊዜ ማሳለፍያ ሆኖ ወደ ንግድ ድርጅትነት የተቀየረው ባለፈው ዓመት ነበር። አሁን ከ6ሺህ በላይ አባላትና ተጠቃሚዎች አሉት። ይህ ደረ ገጽ ደንበኞቹ የፈለጉትን ፎቶ በነጻ እንዲለጥፉ ያበረታታል። የለጠፉትን ምስል ከግምት ውስጥ በማስገባት ያን ፎቶ የሚመስሉ ሰዎችን፣ ከጡመራ ገጾች፣ ከፌስቡክና ከሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች ጭምር ለቃቅሞ ያመጣል። የቢግ ብራዘር ዋች ዳይሬክተር ሲልኪ ካርሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ የዚህ ፎቶን የመበርበር ቴክኖሎጂ በሥራ ላይ መዋል አስደንጋጭ ነገር ነው። ሰዎችን ያለ ፈቃዳቸው የመከታተልና ሴቶችና ሕጻናትንም ለወሲብ ቀበኞች አሳልፎ የሚሰጥ ነው ብለዋል። ፒም አይስ ለዚህ ስጋት በሰጠው ምላሽ፣ የእኛ አገልግሎት ለጥፋት እንዲውል አንፈልግም፤ ኾኖም ግን ማንኛውም ቴክኖሎጂ ለጥሩም ለበጎም ሊውል እንደሚችል መዘንጋት የለበትም ብሏል። ድርጅቱ የሰዎችን ፎቶ ከፌስቡክ ገጻቸው እንደማይሰርቅ ቢናገርም ቢቢሲ በጋዜጠኞቹ ፎቶዎች ላይ ባደረገው የሙከራ ፍለጋ ፒም አይስ ይህን እንደሚያደርግ ደርሶበታል። ፒምአይስ ግን ያስተባብላል፣ ምናልባት ፎቶዎቹ ከፌስቡክ ተወስደው ሌሎች ድረገጾች ላይ ውለው ሊሆን ይችላል፤ እኛ ፎቶ የምንወስደው ይህንን እንደናደርግ ከፈቀዱ ድረገጾች ብቻ ነው ብሏል። የሰው ገጽታን የመለየት ሥራ ውስጥ የተሰማራው ክሊርቪዊኤአይ 6 ቢሊዮን ፎቶዎችን በቋቱ ውስጥ ማስገባቱ በቅርብ ጊዜ ውዝግብ መፍጠሩ ይታወሳል። ይህን ያደረገው የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ)ን ጨምሮ 600 መቶ የሚሆኑ የስለላ ድርጅቶች ወንጀለኞችን ለማደን እንዲጠቀሙበት በሚል ነው። ድርጅቱ ይህን ያደረገው የግለሰቦችን ፍቃድ ሳያገኝ ከዩቲዩብ፣ ከፌስቡክና ከትዊተር ገጾችም ነበር። እነዚህ ድርጅቶችም ከሊርቪውኤአይ ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ጠይቀው ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰዎች ልክ እንደ ጣት አሻራ ሁሉ ፊታቸውን የሚለዩ መሣሪያዎች እየተፈጠሩና አገልግሎት ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። እነዚህ መሣሪያዎች ግን የጥቁሮችን የፊት ገጽታ ለመለየት እየተቸገሩ ነው። ከዚህ በኋላ የሚኖረው ዓለም ምናልባት ሰዎች የግሌ ወይም ምስጢሬ ብለው ሊያስቀምጡት የሚችሉት ምንም ዓይነት ሰነድ እንዳይኖር የሚያደርግ ሊሆን ይችላል ብለው የሚሰጉ በርካቶች ናቸው። የሁሉም ሰዎች ምስጢር የአደባባይ ምስጢር የሚሆንበት ዘመን እየመጣ ያለ ይመስላል።
48319747
https://www.bbc.com/amharic/48319747
የአትሌቲክስ ቡድን ሀኪም 177 አትሌቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሷል ተባለ
አሜሪካ፣ 'ኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ' ውስጥ የሚገኝ የአትሌቲክስ ቡድን ሀኪም 177 አትሌቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ማድረሱ ተገለጸ።
ዩኒቨርስቲው ባደረገው ምርመራ፤ ሀኪሙ እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ1979 እስከ 1997 177 ወንድ ተማሪዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ማድረሱ ተረጋግጧል። ዶክተሩ 1998 ላይ በጡረታ ከሥራ ከተገለለ በኋላ 2005 ላይ ራሱን አጥፍቷል። ሀኪሙ ተማሪዎችን ይጎነትል ነበር፤ በ16 አይነት ዘርፍ ያሰለጥናቸው ለነበሩ አትሌቶች "ምርመራ አደርጋለሁ" በሚል ሽፋንም ጥቃት ያደረስም ነበር ተብሏል። • የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ለተቋሙ ቢያስታውቁም አንዳችም እርምጃ አልተወሰደም። ምርመራውን ያደረጉት ግለሰቦች ይፋ ባደረጉት ሪፖርት፤ ሀኪሙ በዩኒቨርስቲው የመታጠቢያ ክፍል፣ የፈተና ክፍልና ሌሎችም ቦታዎች ጥቃት ያደርስ እንደነበር ተመልክቷል። • ፖፑ የካቶሊክ ቄሶች ሴት መነኮሳትን የወሲብ ባሪያ ማድረጋቸውን አመኑ ብዙ አትሌቶች "አላስፈላጊ የመራቢያ አካል ምርመራ ተደርጎብናል" በማለት ለተቋሙ አሳውቀው ነበር። ይደርስባቸው የነበረው ጥቃት የአደባባይ ሚስጥር ቢሆንም ዩኒቨርስቲው ሀኪሙ ላይ እርምጃ አልወሰደም። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ማይክል ድሬክ "በተፈጠረው ነገር አዝነናል" ብለዋል። ፕሬዘዳንቱ ወሲባዊ ጥቃቱ የደረሰው ከሀያ ዓመታት በፊት በመሆኑ የዩኒቨርስቲውን ነባራዊ ሁኔታ አያሳይም ብለዋል። ሆኖም የዩኒቨርስቲው የቀድሞ ተማሪዎች ክስ ያቀረቡ ሲሆን፤ ተቋሙ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት እንዲወስድ ጠይቀዋል። • ወሲባዊ ትንኮሳን የሚከላከል ካፖርት ተፈለሰፈ የቀድሞው የኦሀዮ ስቴት ዋናተኛ ኬንት ኪልጎር "የብዙዎች ህልም ተቀጭቷል። በደረሰብን ጉዳት ሳቢያ ሰው ለማመን እንቸገራለን። ልጆቻችንን አብዝተን ስለምንቆጣጠርም ከልጆቻችን ጋር ያለን ግንኙነት የሻከረ ነው" ብለዋል።
news-51986049
https://www.bbc.com/amharic/news-51986049
ኮሮናቫይረስ፡ የዓለም ጤና ድርጅት ወጣቶች ኮሮናን ሊቋቋሙት አይችሉም አለ
የዓለም ጤና ድርጅት ወጣቶች በኮሮና ቫይረስ ስለሚያዙ ከአዛውንቶች ጋር ያለቸውን ቅርርብ እንዲሁም ከእድሜ አቻዎቻቸው ጋር ያላቸውን ማህበራዊነት ሊያጤኑት እንደሚገባ አስጠነቀቀ።
የድርጅቱ ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በወጣቶች የሚወሰደው እርምጃ " ለአንዳንዶች የሞትና የህይወት ጉዳይ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል። በዓለማችን ላይ በኮሮናቫይረስ ምክንያት እስካሁን ድረስ 11ሺህ ሰዎች ሲሞቱ 250ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል። • የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎችን ገቢ ክፉኛ የጎዳው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ • የኪነጥበብ ባለሙያዎች መልዕክት ስለ ኮሮናቫይረስ ዶ/ር ቴድሮስ፣ በበርካታ አገራት በእድሜ ከገፉ ሰዎች ተጋላጭ በመሆናቸው ብቻ በሚሰጡ የጤና ማሳሰቢያዎች ወጣቶች ቸል ማለት እንደታየባቸው ተናግረዋል። ኮሮና ከፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ቀደም ብሎ ባሉት ቀናት በቻይና የተከሰተ ቢሆንም አሁን ግን በአውሮፓ ስርጭት ተስፋፍቶ ይገኛል። በጣሊያን በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች በየትኛውም አገር ከሞቱት ሰዎች በላይ ሲሆን፣ አርብ እለት ብቻ 627 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል። ይህም በአገሪቱም ሆነ በዓለም ላይ በበሽታው ምክንያት በአንድ ቀን ይህን ያህል ሰው ሲሞት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጄኔቫ ከሚገኘው ቢሯቸው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት " ምንም እንኳ አዛውንቶች ለቫይረሱ ክፉኛ ተጋላጭ ቢሆኑም ወጣቶችም አያመልጡም" ብለዋል። • በኮሮናቫይረስ ስጋት ሰዎች እቃዎችን በገፍ እየገዙ እንዳያጠራቅሙ ምን ይደረግ? አክለውም ለወጣቶች መልዕክት አለኝ በማለት " ቫይረሱ ልትቋቋሙት አትችሉም። ቫይረሱ ለሳምንታት ሆስፒታል ሊያስተኛችሁ ከዚያም ሲያልፍ ልትሞቱ ትችላላችሁ። ባትታመሙ እንኳ ወዴት መንቀሳቀስ እንዳለባችሁ የምትወስኗቸው ውሳኔዎች ለሌሎች የሞትና የሕይወት ጉዳይ ሊሆኑ ይችላሉ" ብለዋል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በቫይረሱ የሚያዙ መሆናቸውን ነው። ነገር ግን በእድሜ የገፉና ከዚህ ቀደም የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ይበለጥ ተጋላጭ ናቸው ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ከሚለው ባሻገር በአካል አለመገናኘት ወይም ራስን ለይቶ ማቆየትን ለመከላከያው አንዱ መንገድ መሆኑን ይመክራል። • ኢራን በኮሮናቫይረስ ምክንያት 54ሺ እስረኞችን ፈታች • ኮሮናቫይረስ ሰዎችን ከእምነታቸው እየለየ ይሆን? • ስለ ኮሮናቫይረስ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች ወረርሽኝ ምንድን ነው? ዓለም እስካሁን ያስተናገደቻቸው ወረርሽኞችስ ምን ዓይነት ነበሩ?
news-53231189
https://www.bbc.com/amharic/news-53231189
"13 ሰው የገደልኩት 'ጄሪ' የሚባል መንፈስ ግደል ብሎኝ ነው"
የእኚህ አዛውንት ሙሉ ስም ጆሴፍ ጄምስ ዲአንጄሎ ይባላል። የአሜሪካ ሚዲያ የሚያውቃቸው ግን 'ወርቃማው ነፍሰ ገዳይ' በሚለው ቅጽል ስማቸው ነው።
አሁን 74 ዓመት አልፏቸዋል። እጃቸው በደም ተጨማልቋል። ብዙዎቹን ወንጀሎች የፈጸሙት በፈረንጆቹ በ1970ዎቹና 80ዎቹ አካባቢ ነው። በዚያ ዘመን ዘርፈዋል፣ ደፍረዋል፣ ገድለዋል። የፈጸሙትን ወንጀል ብዛት እርሳቸውም ዘንግተውታል። ፖሊስም ታክቶት ነበር። የሟች ቤተሰብ ብቻ ነው ያልዘነጋው። ዲ አንጄሎ የሚሉት 'ጄሪ' የሚባል ስም ያለው አንዳች ውስጤ የተቀመጠ መንፈስ ነው ሰዎችን አሰቃይቼ እንድገድላቸው የሚያዘኝ ይላሉ። በካሊፎርኒያ ከዓመታት በፊት ማን እንደሚፈጽማቸው የማይታወቁ ግድያዎች እዚያም እዚህም ይታዩ ነበር። ፖሊስ ወንጀለኛውን ሊደርስበት ሳይችል ቆይቷል። ሰው ይገደላል፣ ሴቶች ይደፈራሉ፣ ገንዘብ ይዘረፋል፤ ወንጀለኛው ግን አንዳች ዱካ ሳይተው ይሰወራል። ይህ በመሆኑ ነው 'ወርቃማው ነፍሰ ገዳይ' በሚል ቅጽል ብቻ ማንነቱ ያልታወቀ ወንጀለኛ ሲፈለግ እንዲኖር ያደረገው። በመጨረሻ ያን ሁሉ ወንጀል የፈጸሙት ሰው ጆሴፍ ጄምስ ዲ አንጄሎ መሆናቸው ተደረሰበት። ዴአንጄሎ ሕግ አስከባሪ ፖሊስ ነበሩ። በጎልማሳነት ዘመናቸው። በወጣትንት ዘመናቸው ቬትናምም ዘምተዋል። ከቬትናም መልስ ነው ፖሊስ የሆኑት። ካሊፎርኒያን እንደርሳቸው ያሸበረ የለም ነው የሚባለው። ይዘርፋሉ፣ ይደፍራሉ፣ ይገድላሉ። የገደሏቸው ሰዎች ብዛት ደርዘን ያልፋል። ይህን ሁሉ አድርገው ታዲያ ለዚህ ሁሉ ዓመታት አልተደረሰባቸው ነበር። ዲ አንጄሎ ታዲያ ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው 'አዎ እኔ ነበርኩ ስገድል የኖርኩት፣ ጥፋተኛ ነኝ' ሲሉ አምነዋል። ጆሴፍ ጄምስ ዲ አንጄሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት በ2018 ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቃል ተናግረው አያውቁም ነበር። ዝም ጭጭ እንዳሉ ቆዩ። ከዚያ በኋላ የሆነ ሰዓት ላይ፣ 'ጥፋተኛ ነኝ፣ ድርጊቱን ፈጽሚያለሁ' የሚሉ ቃላትን ብቻ ደጋግመው ያለማቋረጥ መናገር ጀመሩ። ፍርድ ቤት ቀርበውም ይህንኑ ነው ያሉት። ድርጊቱን ስለመፈጸማቸው ማመናቸው የሞት ፍርድን ያስቀርላቸዋል። ሆኖም ዕድሜ ልክ እስር ፍርድ ተሰጥቶባቸዋል። ምህረትም አመክሮም የሌለው እስር። ዲ አንጄሎ በ1980ዎቹ አጋማሽ ስለፈጸሟቸው ወንጀሎች እንደተናዘዙት ከሆነ ድፈር፣ ዝረፍ ግደል ሚለኝ 'ጄሪ' የሚባል ውስጤ የተቀመጠ መንፈስ ነው ብለዋል። "ውጣልኝ ለማለት አቅሙ አልነበረኝም። አብሮኝ ነበር የሚኖረው፣ አብሮኝ ነው የሚሄደው፣ የሚበላው የሚጠጣው፣ ጭንቅላቴ እርሱ ነበር፣ ጄሪ አድርግ ካለኝ ውጪ ማድረግ አልችልም ነበር፤ እሱ ነው ግደል እያለ ሰዎቹን ያስፈጀኝ። አሁን እሱ ወጥቶልኛል፣ ለጥፋቴ ዋጋ መክፈል ጀምሪያለሁ፣ ደስተኛ ነኝ" ብለዋል ሰውየው። የዲ አንጄሎ ፍርድ የታየው በአንድ ዩኒቨርስቲ ትልቅ አዳራሽ ነው። በርካታ ሰው በመገኘቱና መራራቅ ግድ ስለሚል ነበር ይህ አዳራሽ ፍርድ ለማስቻል የተመረጠው። ሰውየው ዊለቸየር እየተገፉ ነበር ፍርድ ቤት የመጡት። በ13 ሰዎች ግድያና ሌሎች በርካታ የመድፈር ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብለዋል፣ እርሳቸውም 'አዎ ነኝ' ብለዋል። የሟች ቤተሰቦች በአዳራሹ የተገኙ ሲሆን ለቅሷቸው ችሎቱን ሲረብሽ ነበር። ለምሳሌ በአዳራሹ ከተገኙት ውስጥ ጄኒፈር ካሮል አንዷ ነበረች። የሕግ ሰው የነበረው አባቷ ላይማን ስሚዝ በ1980ዎቹ በእኚህ ሰውዬ ተገድለውባታል። እናቷም የተገደሉት በሰውዬው ከተደፈሩ በኋላ ነበር። ጄኔፈር እንባዋን መቆጣጠር አልቻለችም። ሞገደኛው ሽማግሌ ወንጀለኛ ዲ አንጄሎ ከዚህ ሁሉ ግፍና ግድያ በኋላ በሰላምና በጤና ሲኖሩ ነበር። ፖሊስ ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያቂ በጭራሽ እርሳቸው ይሆናሉ ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር። ፖሊስ እንዴት ደረሰባቸው? ፖሊስ ሰውየውን ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ ሊደርስባቸው የቻለው በዲኤንኤ (የዘረመል ዱካ) አማካኝነት ነው። ያኔ ድሮ ወንጀሎ ከተፈጸመባቸው ስፍራዎች የተገኘው የዘረመል ቅንጣት ጋር የሚመሳሰል የሩቅ ዘመድ እንኳ ቢኖር በሚል ፖሊስ በበይነ መረብ የፍለጋ ሙከራ ጀመረ። አንድ የዘረመል ሰንሰለትን የሚያጠራቅም ዝነኛ ድረ ገጽ አለ። ይህ ቋት የዘረመል ቅንጣት ሰንሰለትንና የሰዎችን ዘርማንዘር በመዘርዘር ይታወቃል። ይህን ድረ ገጽ ፖሊስ እንደ ድንገት ሲፈትሽ የሰውየውን የዘመድ አዝማዶች ሰንሰለት ያገኛል። ሰንሰለቱን ተከትሎ ሲሄድ እኚህ ሰው ጋር ያደርሰዋል። ከዚያ በኋላ ፖሊስ በድብቅ ወደ ዲ አንጀሎ ቤት ይሄድና የእርሳቸው መኪና ጋር ሲደርስ ይቆማል። ከመኪናቸው በር ላይ የዘረመል ቅንጣት ይወስድና ድሮ ወንጀሎቹ ከተፈጸመባቸው ስፍራዎች ከተገኘው ቅንጣት ጋር ሲያመሳስለው አንድ ሆኖ ይገኛል። እርግጠኛ ለመሆን ዲ አንጀሎ አፉን የጠረገበት ሶፍት መኪና አጠገብ ወድቆ ስለነበር ይህንን አግኝቶ ከወርቃማው ወንጀለኛ ጋር ሲያመሳስለው አንድ ይሆናል። በዚህን ጊዜ ነበር ዲ አንጄሎ መጎደኛው ወንጀለኛ ስለመሆናቸው መቶ በመቶ የተረጋገጠው። ሽማግሌው ዴ አንጄሎ በነሐሴ ወር መጨረሻ ፍርድ ቤት በይፋ ዕድሜ ልክ ይፈርድባቸዋል። ዓለምን ለ45 ዓመታት ሲያነጋግር የኖረው ምስጢርም ፍጻሜውን ያገኛል።
news-56073532
https://www.bbc.com/amharic/news-56073532
አሜሪካ፡ “የካፒቶል ሒል ነውጥ”ን የሚመረምር ገለልተኛ ኮሚሽን ሊቋቋም ነው
በአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲ፣ "ኮንግረስ የካፒቶል ሒል ነውጥን የሚረምር ገለልተኛ ኮሚሽን ያቋቁማል" ሲሉ ተናገሩ።
ጥር 6፣ በተለምዶ "የካፒቶል ሒል ነውጥ" ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የሁለቱ ምክር ቤቶች መሰብሰብያና በርካታ የመንግሥት አስተዳደር ቢሮዎችን ሰብረው በመግባት የዲሞክራሲ ተምሳሌት ተደርጎ የሚታየውን ስፍራ እንዲሁም የአገሪቱን ስምና ክብር የሚያጎድፍ ተግባር የፈጸሙበት ዕለት ነው። አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲ ለሕግ አውጪው ምክር ቤት በጻፉት ጠንካራ ደብዳቤ "ገለልተኛ ኮሚሽኑ የመስከረም 11 በኒውዯርክ መንትያ ሕንጻዎችና በፔንታጎን የደረሰውን ጥቃት የሚመረምረው ኮሚሽን በተቋቋመበት መንገድ የሚቋቋም ይሆናል። "ነውጡ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ በጠራ መንገድ ማወቅ ይኖርብናል" ብለዋል ናንሲ። በአሜሪካ ታሪክ ለ2ኛ ጊዜ በመከሰስ የመጀመርያ ሆነው የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ አመጽን ቀስቅሶ ከመምራት ክስ ነጻ መደረጋቸው ይታወሳል። የአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ነጻ ያደረጋቸው ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ለክሱ በቂ ድጋፍ ሳይሰጡት በመቅረታቸው ነበር። ሆኖም ዲሞክራቶችና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች ጭምር ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን በመቋቋሙ ላይ ስምምነት አላቸው። በጥር 6ቱ ነውጥ አምስት ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። የሚቋቋመው ገለልተኛ ኮሚሽን ነውጡን ማን አነሳው፣ እንዴት ተመራ፣ እነማን ተሳተፉበት፣ የትኛው የመንግሥት ባለሥልጣንና አካል እገዛ ሰጠ፣ ማስቆም ለምን አልተቻለም በሚሉና በሌሎች ጉዳዮች ዙርያ አጥጋቢ መልስ ይዞ እንዲመጣ ይፈለጋል። በተለይም የካፒቶል ሒል ፖሊስ ነውጡን ለማስቆም የነበረው ዝግጁነትና ፍቃደኝነት ይመረምራል ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ ይህን ነውጥ በማነሳሳት ተከሰው የነበረ ቢሆንም ሴኔቱ ሁለት 3ኛ ድምጽ ሊሰጥ ባለመቻሉ ባለፈው ቅዳሜ ከክሱ ነጻ ተብለዋል። በድምጽ ሂደቱ 7 ሪፐብሊካኖችና 2 ገለልተኛ እንደራሴዎች ወደ ዲሞክራቶች በመወገን ይከሰሱ በሚል ድምጽ ሰጥተው የነበረ ቢሆንም ትራምፕን ለመክሰስ የሚሆነው የ2 ሦስተኛ የበላይነት ግን ሊገኝ አልቻለም። የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ከቀሰቀሱት ግርግር ጋር በተያያዘ አራት ሰዎች ሞቱ
51172541
https://www.bbc.com/amharic/51172541
አገሯን 'በሙስና ያራቆተችው' የአፍሪካ ሃብታሟ ሴት ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ
የአፍሪካ ባለጸጋዋ ሴት አገሯን በሙስና እንዴት እንዳራቆተቻት መረጃዎች እየወጡ ነው። የደቡብ አፍሪካዊቷ አገር አንጎላ ተበዝባዧ አገር ነች። በዝባዧ ደግሞ የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ልጅ ወይዘሮ ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ ናት።
ኤዛቤል ዶ ሳንቶስ የቀድሞው የአንጎላ ፕሬዝዳንት ልጅ የሆነችው ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ በመሬት፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ ዘይት ዘርፍ በመሰማራት የመንግሥትን እጅ በመጠምዘዝ ከድሃ አንጎላዊያን ጉሮሮ እየነጠቀች ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንዳካበተች ይነገራል። በተለይ አባቷ በመንግሥት ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የኢንቨስትመንት አማራጮች ለእርሷ ብቻ ተብለው የሚከፈቱና የሚዘጉ ነበሩ። ሰሞኑን ይፋ ሆነ የሚባለው ዶክሜንት በእነዚህ ሥራዎች እንዴት ለእርሷና ባሏ ሁኔታዎች ይመቻቹላቸው እንደነበሩና ለመንግሥት መክፈል የነበረባቸውን ገንዘብ እንዴት እንዳልከፈሉ ያሳያል። በእርግጥ ወይዘሮዋ ሁሉም የተቀናበረብኝ የሐሰት ክስ እንጅ እውነትነት የለውም የሚል ማስተባባያ ሰጥታለች። ኑሮዋን በእንግሊዝ ያደረገችው ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ በአገሯ ከዘረጋችው የቢዝነስ መረብ የምትሰበስበውን ረብጣ ዶላር በመጠቀም በማዕከላዊ ለንደን ፈርጠም ያሉ የቢዝነስ ተቋማትን እንደገነባች ይነገርላታል። አሁን በርካታ ሰነዶች የኢዛቤልን የሙስና ሂደቶች የሚያጋልጡ መረጃዎች ከየአቅጣጫው ብቅ ማለታቸውን ተከትሎና ከጥቂት ዓመታት በፊት ከሥልጣን የወረዱት አባቷ ልጃቸውን መከላከል በማይችሉበት ደረጃ ላይ ሲሆን የአንጎላ መንግሥት ኢዛቤል አንጎላ ውስጥ አላት የተባለው ሃብት ሁሉ ታግዶ ምርመራ እንዲካሄድበት አድርጓል። አሁን ቢቢሲ ከ700 ሺህ በላይ ያፈተለኩ መረጃዎች ስለወይዘሮዋ የቢዝነስ እንቅስቃሴና የሙስና መረቧ ደርሶታል። እነዚህ መረጃዎች በ37 ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተጠናቀሩ ናቸው። ከነዳጅ ጋር በተያያዘ አንድ የለንደን የነዳጅ አውጭ ኩባንያ በአገሯ እንዲሰራ በተጭበረበረ መንገድ ሲገባ ወይዘሮ ዶ ሳንቶስ የትወናው አካል ነበረች። በኋላ አባቷ ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ ኩባንያው ሲታገድ 58 ሚሊዮን ዶላር የከፈለችበት ደረሰኝ ተገኝቷል። ይህ ለምን እንደተፈጸመና ድርሻዋስ ምን ነበር የሚለው ያልተመለሰ ጥያቄ ነው። የወይዘሮ ኢዛቤል ዶ ሳንቶስ ጉዳይ በዚህ አያበቃም። አንድ ዱባይ ከሚገኝ ኩባንያ ጋርም በተመሳሳይ ተመሳጥራ ሁለት የክፍያ ሰነዶች እንደተላኩላት ማግኘት ተችሏል። ይህ ሕጋዊነት ይጎድለዋል የተባለው የክፍያ ሰነድም ለምን ክፍያው እንደሚፈጸም የሚያትተው ነገር የለም። በዚህ የሂሳብ መጠየቂያም በአንደኛው 472,196 ዩሮ ሁለተኛው ደግሞ 928,517 የአሜሪካን ዶላር ተጠይቆበታል። ይህም ሰነድ ህጋዊነቱ ያልተረጋገጠ ቢሆንም ወይዘሮዋ ግን ሕጋዊ መንገድን ተከትየ የፈጸምኩት ነው ብላለች። ለኢዛቤል የተላከ የክፍያ ሰነድ ሌላኛው ከነዳጅና ኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ለኢዛቤል የቀረበው ክስ በ2006 የአንጎላ የኃይል አቅርቦት ለመሥራት ስትስማማ በወቅቱ 15% ብቻ ከፍላ ቀሪው ዝቅተኛ ወለድ ተደርጎላት በተራዘመ ጊዜ እንድትከፍል ነበር። ላለፉት 11 ዓመታት ግን መክፈል የነበረባትን 70 ሚሊዮን ዶላር አልከፈለችም። አሁን ኢዛቤል በባለድርሻነት የምትመራው ኩባንያ አጠቃላይ ዋጋው 750 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። ተቋሟ እዳውን በ2017 ለመክፈል ተስማምቶ ነበር፤ ነገር ግን ቢያንስ ወለድ ተብሎ የታሰበውን 9% ማካተት ስላልቻለ ክፍያው እንዳይፈጸም ተደርጓል። ከአልማዝ ጋር በተያያዘ በሙስና ሥራው ኢዛቤል ብቻዋን አትሳተፍም። ባሏም አጋሯ ነው። በ2012 ባለቤቷ ሲንዲካ ዶኮሎ መንግሥት ከሚቆጣጠረው ሶዳየም ከሚባለው የአልማዝ ኩባንያ ጋር የአንድ ወገን ፊርማ ፈርሟል። በፊርማው መሰረት ሁለቱ ፈራሚዎች የፕሮጀክቱን ወጪ ግማሽ ግማሽ መቻል ነበረባቸው። ነገር ግን ሙሉ ወጭው የተሸፈነው በመንግሥት ነው። ሰሞኑን የሚዲያዎች እጅ ላይ የገባው ዶክመንት እንደሚያሳየው ከ18 ወራት በኋላ ዶኮሎ 79 ሚሊዮን ዶላር መክፈል ሲገባው የከፈለው የገንዘብ መጠን ግን 4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ ጉዳዩን ስለደለልኩ ሽልማት ይገባኛል ብሎ ከዚሁ ፕሮጀክት ውስጥ የኢዛቤል ባለቤት ዶኮሎ ተጨማሪ 5 ሚሊዮን ዶላር ራሱን ሸልሟል። ከዚህ ስምምነት የአንጎላ ሕዝብ የሚያገኘው ጥቅም ምንም ሲሆን በአንጻሩ ለኩባንያው መሥሪያ ተብሎ ከግል ባንክ ለተበደሩት 200 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ይከፍላሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የአንጎላ መንግሥት አልማዝ በዝቅተኛ ዋጋ መሽጡን ቢያምንም ምንጮች እንደሚሉት ግን እስከ 1 ቢሊዮን ዶላር ከስሯል። ከዚህ ጀርባ ማን ሊኖር ይችላል ሲባል ደግሞ የብዙዎቹ ግምት ኢዛቤል ደ ሳንቶስና ባለቤቷ መሆናቸውን አብዛኛው የአገሬው ሰው ይረዳዋል። ኤዛቤልና ባለቤቷ ከመሬት ጋር በተያያዘ ወይዘሮ ዶ ሳንቶስ መሬት ላይም ሁነኛ ተሳታፊ ናቸው። መረጃው እንደሚያሳየው ወይዘሮ ዶ ሳንቶስ በ2017 በዝቅተኛ ዋጋ መሬት እንድትገዛ መንግሥት አመቻችቶላታል። ይህንን በመዲናዋ ሉዋንዳ የባህር ዳርቻ የሚገኘውን ጋሻ መሬት የገዛችውም በአባቷ ረጅም እጅ በመታገዝ ነበር። ኮንትራቱ የሚለው መሬቱ 96 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ነው። ወይዘሮ ዶ ሳንቶስ ያወጣችው ግን 5% ብቻ ነው። ምስኪን ቦታው ላይ የነበሩ አንጎላዊያን ግን ይዞታቸው ለወይዘሮ ዶ ሳንቶስ በመሰጠቱ ከነበሩበት ዋና ከተማዋ ሉዋንዳ 50 ኪሎ ሜተር ርቀው ተጥለዋል። ከመሬት ጋር በተያያዘ በሌላ የኢዛቤል ዶ ሳንቶስ ፕሮጀክት ከ500 በላይ ቤተሰብ በእርሷ ምክንያት ተፈናቅሏል። ከቴሌኮም ዘርፍ ጋር በተያያዘ ቢሊየነሯ ከቴሌኮም ዘርፍም አንጎላ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ አግበስብሳለች። በአገሪቱ ከፍተኛው የሞባይል ስልክ አቅራቢ ኩባንያ ውስጥ 25 በመቶ ድርሻ አላት። ዩኒቴል የተባለው ይህ ኩባንያ በቀቅርቡ ለኢዛቤል 1 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ የሰጣት ሲሆን ቀሪ ኃብቷም ሌላ 1 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ተብሏል። ይሁንና ሴትዮዋ ከዘርፉ ገንዘብ የምታገኝበት ይህ ብቸኛ መንገድ አይደልም ተብሏል።
53245477
https://www.bbc.com/amharic/53245477
ከሃጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች መያዛቸውን ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ
የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች በተከሰተ አለመረጋጋትና ግጭት ቢያንስ የ50 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣን አስታወቁ።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ከሃጫሉ ሞት ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ከሃምሳ በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አክለውም የሞቱት በተቃውሞ የተሳተፉ እንዲሁም በጸጥታ ማስከበር ሥራ ላይ የነበሩ ኃይሎች መሆናቸውን ለሮይተርስ ገልጸዋል። በሰው ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የንግድ ተቋማትና መሥሪያ ቤቶች በእሳት የመቃጠል ውድመት እንደደረሰባቸው አቶ ጌታቸው አረጋግጠዋል። አቶ ጌታቸው በሰውና በንብረት ላይ ስላጋጠመው ጉዳት ለሮይተርስ "ለዚህ አልተዘጋጀንም ነበር" ሲሉ ተናግረዋል። በተያያዘ ዜናም ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ። ትናንት ማታ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና የኦሮሚያ ፖሊስ በጋራ በሰጡት መግለጫ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባል የሆነው ጃዋር መሐመድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል። አቶ ጃዋር እና ሌሎች 35 ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የአስከሬን ሽኝት መስተጓጎልና ከአንድ የፖሊስ አባል ግድያ ጋር በተያያዘ መሆኑ ተገልጿል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ የጃዋር ጠባቂዎች ይዘውት የነበሩት የጦር መሳሪያዎች እና መገናኛ ሬዲዮችም መያዛቸውን አመልክተዋል። በዚህም መሰረት 8 ክላሽ፣ 5 ሽጉጥ እና 9 የሬዲዮ መገናኛዎች ከጃዋር ጠባቂዎች ላይ ፖሊስ መያዙን ተገልጿል።
news-55444792
https://www.bbc.com/amharic/news-55444792
'በቆዳ ቀለሜ ምክንያት እንክብካቤ ተነፈገኝ' ያለችው ሀኪም በኮቪድ-19 ሞተች
በአሜሪካዋ ኢንዲያና የምትገኝ አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት የሕክምና ባለሙያ በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወቷ አልፋል።
ባለሙያዋ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሆስፒታል ብትገባም በቆዳ ቀለሟ ምክንያት ዶክተሮች ተገቢ እንክብካቤ እንዳላደረጉላት ስትናገር ቆይታለች። ሱዛን ሙር የተሰኘችው ሐኪም ከኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ በለቀቀችው ቪድዮ ላይ እንክብካቤ ለማግኘት ዶክተሮችን 'ትለምን' እንደነበር ትናገራለች። ሆስፒታሉ በሞቷ የተሰማውን ሃዘን ገልጿል። ዩኒቨርሲቲው የቀረበበትን ክስ እንደሚመለክትም ተናግሯል። ጥናቶች እንደሚያመለከቱት ጥቁሮች ከነጮች የበለጠ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የመሞት ዕድላቸው የሰፋ ነው። የ52 ዓመቷ ዶክተር ሙር ባለፈው እሁድ አንድ ሌላ ሆስፒታል ውስጥ ሳለች ነው ሕይወቷ ያለፈው። በያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ነበር በፌስቡክ ገጿ መልዕክቷን ያስተላለፈችው። ምንም እንኳ እያለቀሰችና ትንፋሽ እያጠራት ቢሆንም ነጭ ነው ያለችው ዶክተር ምን ያክል ሕመሟን አንደሚያጣጥል በቪድዮ መልዕክቷ ትናገራለች። "ሳንባዬን አላደመጠውም፣ በፍፁም ሊነካኝ ፈቃደኛ አልነበረም፣ ምንም ዓይነት አካላዊ ምርመራ አላደረገለኝም። ምን እንደሚሰማኝ ልትነግረኝ አትችልም ስል ነግሬው ነበር" ትላለች። ሆስፒታሉ 'ዘርን መሠረት ያደረገ እንክብካቤ መንፈግ እንደማይፈቅድ' አስታውቆ 'በቀረበው ክስ ላይ ምርመራ እንደሚያከናውን' በኦፌሴላዊ ምላሹ አስታውቋል። የመርሳት በሽታ ያለባቸው የዶክተሯ ወላጆችና የ19 ዓመት ወንድ ልጇ ከዩኒቨርሲቲ ሆስፔታሉ ወደ ሌላ ሆስፒታል እንድትዘዋወር ቢያደርጓትም ልትተርፍ አልቻለችም። የዶክተሯን ቤተሰቦች ወጭ ለመሸፈን የተቋቋመቀወ 'ጎፈንድሚ' የተሰኘው የበይነ መረብ ገንዘብ መሰብሰቢያ አስካሁን ድረስ 102 ሺህ ዶላር ተዋጥቶበታል። ዶክተር ሙር ኮቪድ-19 ከያዛት በኋላ ከፍተኛ ትኩሳትና የመተንፈስ ችግር አጋጥሟት ነበር። የሕክምና ባለሙያ በመሆኗ ተገቢው መድኃኒትና እንክብካቤ እንዲሰጣት ብትጠይቅም ዶክተሯ ለዚህ ሕክምና እንደማትመጥን በመናገር ወደ ቤት እንድትሄድ ነግሯት ነበር። "የሕክምና ባለሙያ እንደሆንኩ ያውቃል። የመድኃኒት ሱስ የለብኝም። እጅጉን እያመመኝ ነበር" ብላለች በመልዕክቷ። ዶክተር ሙር ከሆስታሉ ተገቢውን ሕክምና ሳታገኝ እንድትወጣ ከተደረገ በኋላ ባጋጠማት ሕመም ተመልሳ ገብታ ነበር። "ሁሌም እለዋለሁ - ነጭ ብሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ አይደርስብኝም ነበር።" የዶክተሯ ሞት አሜሪካ ውስጥ ጥቁር አሜሪካዊያን ተገቢውን ሕክምና እንደማያገኙ የሚያሳይ ነው ያሉ ብዙዎች ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ናቸው። ጥቁር አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ የመሞት ዕድላቸው ከነጭ አሜሪካዊያን በሶስት እጥፍ የላቀ ነው።
news-53690517
https://www.bbc.com/amharic/news-53690517
የቤይሩት ፍንዳታ፡ በዋና መዲናዋ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
ሐሙስ ዕለት በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ተቃውሞ ተቀስቅሶ ሰልፈኞች ከሃገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ጋር ተጋጭተዋል።
የፀጥታ ኃይሎች የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አካባቢ የነበሩ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመዋል። ተቃውሞ የተቀሰቀሰው ባለፈው ማክሰኞ ቤይሩት ውስጥ ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ ችላ ተብሎ ተከማችቶ የነበረ 2750 ቶን አለሙኒዬም ናይትሬት ፈንድቶ የበርካቶችን ሕይወት በመቅጠፉ ነው። በርካታ የሊባኖስ ዜጎች ፍንዳታው በመንግሥት ቸልተኝነት አማካይነት የተከሰተ ነው ይላሉ። በርካቶችን ባስደነገጠው ፍንዳታ ምክንያት እስካሁን ድረስ ቢያንስ 137 ሰዎች ሲሞቱ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ፍንዳታው በዋና ከተማዋ የነበረውን አንድ ሰፈር ሙሉ በሙሉ ሲያወድም አሁንም በርካታ ሰዎች ያሉበት አይታወቅም። የሃገሪቱ ዜና ወኪል እንደሚለው መንግሥት 16 ሰዎችን ይዞ ምርመራ እያደረገ ነው። ከፍንዳታው በኋላ ሁለት የመንግሥት ባለሥልጣናት በገዛ ፈቃዳቸው ሥራ ለቀዋል። የሕዝብ እንደራሴው ማርዋን ሃምዴሽ ባለፈው ረቡዕ ራሳቸውን ሲያገሉነ በጆርዳን የሊባኖስ አምባሳደር የሆኑት ትሬሲ ቻሞን ደግሞ ትላንት [ሐሙስ] ውድመቱ አዲስ መንግሥት እንደሚያስፈልግ የሚያሳይ ነው በማለት ሥልጣን ለቀዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ቤይሩትን ከጎበኙ በኋላ ሌባኖስ 'መሠረታዊ ለውጥ' ያስፈልጋታል ሲሉ ተናግረዋል። አልፎም የፍንዳታው መንስዔ በዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲጣራ ጥሪ አቅርበዋል። ቤይሩት የሚገኘው የቢቢሲው ኩዌንቲን ሰመርቪል የወደመው ሥፍራ ሊባኖስን ከዓለም የሚያገናኝ ነበር ይላል። 80 በመቶ የሚሆነው የሃገሪቱ ገቢ የሚመነጨው ከዚህ በፍንዳታው ምክንያት ከጥቅም ውጭ ከሆነው ወደብ ነው። "ቤይሩት ውስጥ ለአምስት ዓመታት ቆይቻለሁ። ነገር ግን አሁን ከተማዋ እንደዚህ የማላውቃት እስክትመስል ድረስ ተመሳቃቅላለች። የሚሰማው የአምቡላንስ ጩኸት ነው፤ ኦና ሕንፃ፣ ኦና መንገድ።" "መንገድ ላይ ሁሉም ሰው መጥረጊያ በእጁ ይዞ ያፀዳል። ነገር ግን የሚዘለቅ አይደለም። እንዴት የአንዲት ከተማን ወድመት በመጥረጊያ ማፅዳት ይቻላል?" ሲል ኩዌንተን ይጠይቃል በሕይወት የሚገኝ ሰው ይኖር ይሆን? የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በፍርስራሾች ስር በሕይወት ያሉ ሰዎች ካሉ በሚል ፍለጋቸውን ቀጥለዋል። የደህንነት ሰዎች ደግሞ አደጋው የደረሰበትን ሥፍራ ከልለው ምርመራ እያደረጉ ነው። የፈረንሳይ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ምናልባትም በሕይወት ያሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ይላሉ። ከሠራተኞቹ መካከል አንዱ ለፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ሰባት ወይም ስምንት የሚሆኑ ሰዎች በአንድ ሕንፃ የአደጋ ጊዜ ክፍል ውስጥ ታፍነው ይገኛሉ፤ እነሱን ለማዳን እየጣርን ነው ሲል ነግሯቸዋል።
news-53266626
https://www.bbc.com/amharic/news-53266626
ከሃጫሉ ግድያ በኋላ ያለፉት ሁለት ቀናትና የዛሬ የአዲስ አበባ ውሎ
ከሰሞኑ ገላን አካባቢ በመኪናው ውስጥ የተገደለው ድምፃዊና የፖለቲካ አቀንቃኙ የሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በርካቶችን አስደንግጧል፤ እንዲሁም በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎችም ተቃውሞዎች እንዲቀጣጠሉ ምክንያት ሆኗል።
ለአርቲስቱ ወዳጆችና አድናቂዎች እንዲህ ህይወቱ በአጭር መቀጠፉም ሆነ በኦሮሞ ትግል ውስጥ 'ነፀብራቅ' የሚሉት ድምፃዊ መቀጨት ብዙዎች አልተዋጠላቸውም። በሙዚቀኛው ሞት ማግስት በተለያዩ አዲስ አበባ አካባቢዎች መፈክሮችንና ሽለላዎችን እያሰሙ እንዲሁም ቁጣቸውን የሚገልፁ ወጣቶች ተስተውለዋል። ሃጫሉ በተገደለበት ገላን አካባቢም የተቃጠሉ የመኪና ጎማዎች ጎዳናውን ሞልተውት እንዲሁም አጥቁረውት ነበር። የተለያዩ ህንፃ መስታወቶች መሰባበር፣ ዘረፋና የንብረት መውደምም አጋጥሟል። ከፍተኛ የጥይት ድምፆች እንዲሁም ቆንጨራና ዱላ የያዙ በቡድን የተከፋፈሉ ወጣቶች በየጎዳናው መታየታቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል። በዚያኑ ቀንም ነው በአዲስ አበባ ሦስት የቦምብ ፍንዳታዎች ተከስተው ቁጥራቸው ያልተገለፁ ሰዎችም ህይወት መጥፋቱን እንዲሁም በርካቶችም መቁሰላቸው በፖሊስ የተነገረው። ቦምቡን ያፈነዱት መሞታቸውን፣ እንዲሁም የቆሰሉና የሌሎችም ዜጎች ህይወት ቢጠፋም ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ የፌደራል ፖሊስ አልጠቀሰም ነበር። በትናንትናው ዕለት ጥዋት ሁኔታዎች የተረጋጉ ቢመስሉም ከሰዓት በኋላ የተኩስ ድምፅ ከተለያየ አካባቢ ይሰማ እንደነበርም ቢቢሲ መረዳት ችሏል። በአዲሱ ገበያ፣ ላም በረት፣ ሲኤምሲና ሰሚት የካ አባዶና ሌሎች አካባቢዎች በብዛት ሰብሰብ ብለው እየጨፈሩ የነበሩ ወጣቶችም ተስተውለዋል። በተለይም አዲስ አበባ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙት ካራ፣ የካ አባዶና አያት አካባቢዎች ከማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ውጥረትና ፍርሃት ነግሶ ቆይቷል። የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ከሌላ አካባቢ በቡድን ሆነው ዱላና ብረት በመያዝ የመጡ ወጣቶች ናቸው ያሏቸው የመኪኖችን፣ የመኖሪያ ቤቶችንና ህንጻዎችን መስታወቶች በመስበር ጉዳት እንዳደረሱ ገልጸው፤ ሱቆች ላይ የዘረፋ ሙከራ ተደርጎ እንደነበርም ለቢቢሲ አስረድተዋል። በተለይ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ድርጊቱ መደጋገሙንና የወጣቶቹም ቁጥር ብዙ እንደነበር ገልጸው፤ ከነዋሪው ጋር ግጭት ውስጥ ተገብቶ ከባድ ችግር ይፈጠራል የሚል ስጋት እንደነበር ገልጸዋል። ነገር ግን አመሻሽ ላይ የጸጥታ ኃይሎች በብዛት በመሰማራታቸው ወጣቶቹ ወደ መጡበት ተመልሰዋል ብለዋል። በትናንትናው ዕለትም እንዲሁ ስጋትና አለመረጋጋቱ በተለያዩ ሰፈሮች የነበረ ሲሆን ሰሚት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከበራቸው ላይ ሆነው ሌሊቱን ሲጠብቁ እንደነበር አስረድተዋል። በተለይም ፍየል ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባሉ አፓርትመንቶች (የጋራ መኖሪያ ቤቶች) ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንዳስረዱት ምሽቱ ፍርሃት የነገሰበት እንደነበርና አንድ የንግድ ተቋምም ለመዝረፍ መሞከሩንም እንዲሁ አስረድተዋል። በተቃውሞ ጉዳት የደረሰበት የጋራ መኖሪያ ቤት በርካታ የፀጥታ አስከባሪዎችም በአካባቢው እንደተሰማሩም ገልፀዋል። በፈረንሳይ፣ ስድስት ኪሎ፣ ፒያሳና እንዲሁም በሌሎች ሰፈሮች ተኩስ መስማታቸውንም የተለያዩ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አስረድተዋል። ሃያ ሁለት ዘሪሁን ሕንጻ አካባቢ ትናንት ቀን ስምንት ሰዓት ላይ ተኩስ እንደነበር እና ከሌላ አካባቢ መጡ ያሏቸው ሰዎች ሊረብሹ መሞከራቸውን የተናገሩት አንድ ነዋሪ በዚህም የተነሳ ዛሬ ከቤታቸው ሳይወጡ መዋላቸው ይናገራሉ። እንዲሁ ኮተቤ አካባቢ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ተኩስ ይሰማ እንደነበር የተናገሩት ሌላ ነዋሪ ደግሞ ለሊቱ ሰላማዊ እንደነበር ተናግረዋል። ነገር ግን ወሰን አካባቢ በነበረ የመንገድ መዝጋትና ጎማ ማቃጠል የተነሳ ከቤታቸው ርቆ ለመንቀሳቀስ ፍርሃት እንዳለባቸው አልሸሸጉም። አያት አካባቢ የሚገኙ ኮንዶሚኒየሞች እና የአየር መንገድ ማኅበር ቤቶች አካባቢ ግን ምሽት በቡድን የመጡ ሰዎች ነዋሪዎችን ሰላም ነስተው እንደነበር ገልፀው የአካባቢው ነዋሪ በጋራ ለመከላከል መውጣቱን እንዲሁም የተወሰኑትን ለፖሊስ ማስያዙን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአየር መንገድ ማኅበር ቤቶች ውስጥ ግቢውን ሰብረው የገቡ ወጣቶች ረብሻ ለማስነሳትና ንብረት ለማውደም ቢሞክሩም ነዋሪዎች በጋራ መከላከላቸውንና በአሁኑ ሰዓትም በግቢያቸው ውስጥ የፖሊስ ኃይሎች እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ ወደ መገናኛ በአንድ ቢሮ ውስጥ ለሚሰሩ ግለሰብ ደውሎ ያለውን ሁኔታ ለማጣራት ሙከራ ያደረገ ሲሆን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ደካማ መሆኑን ነገር ግን መንገዱ ሰላማዊ እንደነበር ለመረዳት ችሏል። ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ምንም አይነት ግጭት ባይስተዋልም በአብዛኛው የከተማዋ ከፍል ፍርሃት እንዳንዣበበ መሆኑንም ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል። አዲስ አበባ ጭር ያለች ሆናለች፤ የተለመደው የወትሮው እንቅስቃሴም የማይታይባት ከተማም ሆናለች። በተለይም ትናንትና ይሰማ የነበረው ተኩስና ከአንዳንድ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ ከባድ ፍርሃት መፍጠሩንና ዛሬም ከቤት ሳይወጡ እንዳረፈዱም የተናገሩ በርካቶች ናቸው። ከአንዳንድ ውር ውር ከሚሉ ታክሲዎች በስተቀር ትራንስፖርትም አለመኖሩን እንዲሁም የንግድ እንቅስቃሴዎችም ቀጥ ማለታቸውን ተናግረዋል። ካፌዎች፣ ሬስቶራንቶች እንደተዘጉ ናቸው። የከተማው ፖሊስና የፌደራል ፖሊስ በርከት ብለው መታየታቸውን ቢቢሲ በተዘዋወረባቸው አካባቢዎች አይቷል። ከዚህም በተጨማሪ ሲኤምሲ፣ ሃያ ሁለት፣ ቦሌ አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት አባላት በፒክ አፕ ተጭነው የፀጥታ ሁኔታውን እየተቆጣጠሩ ነው። በከተማይቱ ውስጥ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት የስምንት ነዋሪዎችና የሁለት ጸጥታ አስከባሪዎች ህይወት ማለፉንም የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል። ትናንት ምሽት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንዳሉት ማክሰኞና ረቡዕ ስምንት የከተማዋ ነዋሪዎች ህይወት ማለፉን ገልጸዋል። እነዚህ ግለሰቦች የሞቱት "በቦምብ፣ ጥይት፣ በድንጋይ እና በመሳሰሉት ነው" ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በነበረው አለመረጋጋትም የግል እና የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል፤ ተሰባብረዋል። "የዜጎችን ያፈሩትን ሃብት እና ንብረት የመዝረፍ እንቅስቃሴ ነበር" በማለትም አስረድተዋል። እንደ ኮሚሽነሩ መግለጫ ንብረትነታቸው የግለሰብ እና የመንግሥት የሆኑ 250 ተሽከርካሪዎች ተሰባብረዋል፣ 20 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል።
47288756
https://www.bbc.com/amharic/47288756
በሚስቱ ሲደበደብ የኖረው ወጣት
አሌክስ ስኪል የ22 ዓመት እንግሊዛዊ ነው። ሴት ጓደኛው ለዓመታት የቤት ውስጥ ጥቃት ስታደርስበት ኖራለች። የስቃይ ታሪኩን ለቢቢሲ አጋርቷል።
የፈላ ውኃ ደፋችብኝ። ፍቅረኛዬ የፈላ ውኃ ላዬ ላይ የደፋችብኝን ቀን በፍጹም አልዘነጋውም። መጀመርያ በሻይ ማፍያው ውኃ አፈላች። ውኃው በደንብ ሲንተከተክ የፈላውን ውኃ በማንቆርቆርያ ይዛ ታስፈራራኝ ጀመር። መኝታ ቤት ጥግ ወስዳ ውኃውን ላዬ ላይ ለቀቀችው። ከጆርዳና ጋር ለሦስት ዓመታት አብረን ኖረናል። በመሀላችን ፍቅር አልነበረም ባልልም በትንሽ በትልቁ ስንነታረክ ነው የኖርነው። የሚገርመው ሁሉም ችግር የሚጀምረው ከትንንሽ ነገሮች መሆኑ ነው። የጸጉሬ ስታይል ወይ ደግሞ የለበስኩት ቲሸርት ለከባድ ንትርክ ሊዳርገን ይችላል። • የዩክሬን ባለሥልጣናት በአሲድ ጥቃት ክስ ተመሠረተባቸው • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ • አሲድን እንደ መሳሪያ የፈላ ውኃ ከደፋችብኝ በኋላ ሕመሙ የምቋቋመው አልሆነም። እያለቀስኩ ቀዝቃዛ ውኃ ውስጥ እንድነከር ለመንኳት። ፈቀደችልኝ። የተሰማኝ እፎይታ ከቃላት በላይ ነበር። የፈላ ውኃ እንደደፋችብኝ ለሰው ብናገር ቅጣቱ እንደሚበረታብኝ ነግራ አስፈራራችኝ። ዝም ጭጭ አልኩኝ። እስክንቀጠቀጥ ነው የምፈራት። ጤናማው የፍቅር ዘመናችን ጆርዳናና እኔ ኮሌጅ እያለን ነው የተዋወቅነው። ስተዋወቃት ሁለታችንም ገና 16 ዓመታችን ነበር። እሷ ጎበዝ ተማሪ ነበረች። ሰቃይ ተማሪ የምትባል ናት። ዩኒቨርስቲም መግባት ችላ ነበር። እኔ ግን ደካማ ተማሪ ነበርኩ። ነገሮች እየከፉ የመጡት የኋላ ኋላ ነበር። አብረን መኖር ስንጀምር ቀስ በቀስ ከሁሉም ጓደኞቼ ጋር እንዳልገናኝ ታስፈራራኝ ጀመር። ፌስቡክ እንዳልጠቀምም አስጠነቀቀችኝ። መጀመርያ እሷን እንዳይከፋት እያልኩ እሺ ነበር የምላት። በኋላ ግን አእምሮዬን ተቆጣጠረችው። ዘዴዋ ቀስ በቀስ ሠርቶላት የሷ ባሪያ አደረገችኝ። ሙሉ በሙሉ ቁጥጥሯ ሥር አድርጋኝ የቤት ውስጥ ጥቃት ታደርስብኝ ጀመር። ታስርበኛለች፣ አስራ ትገርፈኛለች። በርካታ ቀናት ምግብ ትከለክለኝ ጀመር። ራሴ አብስዬ መብላት አልቻልኩም። ከበላሁ አስራ ስለምትገርፈኝ ጾሜን መዋልና ማደር ጀመርኩ። በከፍተኛ ደረጃ ኪሎዬ ቀነሰ። ባህሪዋን ተቋቁሜ ስጋፈጣት ደግሞ ጥፋቱን አዙራ እኔ ላይ መጠምጠም ጀመረች። ይበልጥ የራሷን ጥፋት በኔ እያላከከች ታሰቃየኝ ጀመር። ለምሳሌ 'ያን ጫማህን አልወደድኩትም' ወይም ደግሞ 'ቡኒውን ሸሚዝህን እንዳትለብሰው' ስትለኝ እሷን ደስ ይበላት እያልኩ የምትለኝን አደርጋለሁ። ትእዛዟ ግን ማቆምያ አልነበረውም። ዓላማዋ እኔን የሷ ባሪያ ማድረግ ነበር። • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ ልጆች ወለድን ልጆች ስንወልድ ነገሮች ይለወጣሉ የሚል ተስፋ ነበረኝ፤ መሳሳቴን የተረዳሁት በኋላ ነው። እኔ ላይ የምታደርሰው ጥቃት እየጨመረ ሲመጣ ከኔ ይልቅ ለልጆቼ መፍራት ጀመርኩ። ጥያት ብሄድ ልጆቻችን ላይ አደጋ ልታደርስ እንደምችል እርግጠኛ እየሆንኩ መጣሁ። ከዚህ በኋላ ሕይወቴ በጭንቀት የተሞላ ሆነ። እርግጥ ነው የኔና የጆርዳና የፍቅር ሕይወት ጭቅጭቅና መከራ ብቻ አልነበረም። ደስ የሚሉ ጊዜያቶችንም አሳልፈናል። በነዚህ ጊዜዎች ግንኙነታችን መልክ እንደምይዝ በማሰብ ላነጋግራት እሞክራለሁ። ወዲያው ግን ታስፈራራኛለች። እንዳልለያት ደግሞ ከፍርሃቱም በላይ ፍቅሯ አስቀረኝ። ስቃዩን እየለመድኩት መጣሁ የሆነ ወቅት ድንገት ተነስታ 'ለሴቶች የስልክ መልዕክት ትልካለህ' ብላ ከሰሰችኝ። በፍጹም ያን እኔ አላደረኩም። ግን አስፈራርታ ይቅርታ እንድጠይቃት አደረገች። ያንን ማድረግ ነበር ደስታ የሚሰጣት። እኔን ማንበርከክ፣ መግረፍ፣ ማሸማቀቅ ነበር የደስታዋ ምንጭ። ሁልጊዜም ስትተኛ የቢራ ጠርሙስ ከጎኗ አድርጋ ነው። ከተነሳባት አናቴን በጠርሙስ ትበረቅሰዋለች። ስቃዩ ሲበዛብኝ መቻልና መላመድ ጀመርኩ። ይህ ይበልጥ አናደዳት። ጠርሙሱን ትታ በመዶሻ ጀርባዬን ትወግረው ጀመር። ከዚያ ደግሞ ቢላ ይዛ በስለቱ ታስፈራራኛለች። በርካታ ጊዜያት ከሞት አፋፍ ነው የተመለስኩት። በፈላ ውኃ ሦስተኛ ደረጃ ቃጠሎ አድርሳብኝ ታውቃለች። • ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ለመዋብ ምን ያህል ይከፍላሉ? ከዚህ ቀጥሎ ልትገድለኝ እንደምትችል እርግጠኛ እየሆንኩ መጣሁ። ለፖሊስ ለምን አላመለከትኩም? ይህ ሁሉ ሲሆን ለፖሊስ ሪፖርት አላደረኩም። አንድም ልጆቼ ላይ የከፋ አደጋ ታደርሳለች በሚል፣ አንድም ትበቀለኛለች በሚል... አደጋ አድርሳብኝ ሆስፒታል በወሰደችኝ ቁጥር አደጋውን ራሴ ላይ እንዳደረስኩ እንድናገር ታስፈራራኝ ነበር። ጎረቤቶቻችን የድረሱልኝ ጥሪዬን ሰምተው መጥተው ያውቃሉ። ኾኖም ፖሊስ ጋ እንዳይደውሉ እየዋሸሁ አሳስታቸው ነበር። በቡጢ ነርታኝ ፊቴ ሲበልዝ ሜካፕ ቀባብታ ታጠፋዋለች። ከሷ ጋ በነበርኩበት ወቅት በፍርሃትና ታደርስብኝ በነበረ የምግብ ቅጣት የተነሳ በድምሩ 30 ኪሎ ቀነስኩ። ሆስፒታል ወሰደችኝ። ከዚህ በኋላ ምግብ ለ10 ቀናት እንኳ በተገቢው ሁኔታ ባልመገብ ልሞት እንደምችል ነገሩኝ። ጆርዳናን እንዴት ተገላገልኳት? በ2018 ነገሮች መቋጫ አገኙ። ወለል ላይ አስተኝታ እየደበደበችኝ ነበር። ፖሊስ ደረሰልኝ። ፖሊስ ቤታችን ውስጥ በመጣበት ጊዜ የመጣው ይምጣ ብዬ ያደረገችኝ ዘከዘኩ። ፊቴ በላልዞና አባብጦ ነበር። በዚያ ወቅት ፖሊስ ባይደርስልኝ ኖሮ የሕይወቴ ፍጻሜ ሊሆን ይችል ነበር። • ወላጆች ለልጆቻቸው የሚመኟቸው ኢትዮጵያዊ መምህር • ሴቶችን ከመንቀሳቀስ የሚያግደው መተግበሪያ ሊመረመር ነው ፖሊሱ የሚያየወን ማመን ነው ያቃተው። ያን ሁሉ ታደርግ የነበረው በቅናት ተነሳስታ እንደሆነ ነው የገባኝ። እኔ ከቤተሰቤ ጋር ቅርብ ነበርኩ። ጓደኞቼም ጋር ጥሩ ጊዜ ነበረኝ። ከሁሉም ነገር ቀስ እያለች ነጠለችኝ። የሷ ብቻ አደረገችኝ። ለነገሩ በአንድ ወቅት አፍ አውጥታ "ሕይወትህን ገሀነም ማድረግ ነው ፍላጎቴ" ብላኝ ነበር። ምክር ለወንዶች ብዙ ወንዶች የቤት ውስጥ ጥቃት ሲደርስባቸው ለመናገር አይደፍሩም። ያሳፍራቸዋል። እኔም እንደዚያ ነበርኩ። በየቀኑ 'አንተ ደደብ፣ አንተ ደንቆሮ፣ አንተ ፈሪ፣ አንተ ልክስክስ...' እያለች ተሰድበኝ ነበር። ጆርዳና ባደረሰችብኝ ነገር አንድም ጊዜ ተጸጽታ አታውቅም። በጣም ያናደዳት እኔ ያደረሰችብኝን ለፖሊስ መናገሬና እሷ በቁጥጥር ሥር መዋሏ ነው። ለፍርድ ቤት ጥፋተኛ እንደሆነች አምናለች። ያን ያደረገችው ግን ፍርድ እንዲቀልላት ብቻ ነው። • በደቡብ ወሎ ሙሽራና ሚዜውን የገደለው ቦምብ የቤት ውስጥ ጥቃት የሚያደርሱ ሴቶች ያን ለምን እንደሚያደርጉ ሳስበው ሱስ መሰለኝ የሚሆንባቸው። ወንድ ጓደኛቸውን ሲያሰቃዩ ልዩ ደስታን ይጎናጸፋሉ። ነገሩ ልክ እንደ ሲጋራ፣ እንደ ኮኬይን ሱስ ነው... ትልቁ ጥፋት የቤት ውስጥ ጥቃት ከዛሬ ነገ ይቆማል ብሎ ማሰብ ነው። ያ ነው ትልቁ ስህተት። ጆርዳና በመጨረሻ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ፍርድ ቤት ሲወስን በመጨረሻም እንባው ታበሰ።
news-51530791
https://www.bbc.com/amharic/news-51530791
የጤፍ ባለቤትነት መብት ከኢትዮጵያ እጅ እንዴት ወጣ?
ከ2000 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያውያን ጤፍን በዋነኛ የምግብ ምንጭነት ሲጠቀሙበት ኖረዋል። ታዲያ እንዴት አንድ የደች ዜጋ በቀላሉ የጤፍ የባለቤትነት መብትን ሊያገኝ ቻለ?
በጎርጎሳውያኑ 1980ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረውን ድርቅ ተከትሎ በምግብ እጥረት የተጎዱ ህጻናት ምስል በመላው ዓለም በሚገኙ ምግብ ቤቶች ጭምር እየተለጠፈ በረድኤት ድርጅቶች አማካይነት ገንዘብ ተሰብስቧል። በርካቶችም ምስሎቹን ተመልክተው የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ጠቃሚ ቢሆንም በተለይ ምዕራባውያኑ የትኛውም ጎጂ ንጥረ ነገር የሌለው የምግብ አማራጭ ከዛች አገር ይገኛል ብለው እንዳያስቡ አድርጓቸዋል። • ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ • ጤፍን ሰዳ የምታሳድደው ኢትዮጵያ ጤፍን የተቀረው ዓለም የምግቦች ሁሉ ታላቅ ወይም 'ሱፐር ፉድ' እያለ ነው የሚጠሩት። ምድራችን በምታበቅላቸው አብዛኛዎቹ ሰብሎች ውስጥ የሚገኘውና በተለይ አውሮፓውያኑ ለጤና አስጊ ነው ብለው የሚፈሩት 'ግሉተን' ንጥረ ነገር በጤፍ ውስጥ አለመገኘቱ ደግሞ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ተፈላጊነቱ ከፍ እንዲል አድርጎታል። በኢትዮጵያና በኤርትራ ለ2000 ሺ ዓመታት ሲበቅል የነበረው ጤፍ ከፍተኛ ፕሮቲን፣ አይረን፣ ፋይበርና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረነገሮች በውስጡ ስለመያዙ ተመስክሮለታል። የቢቢሲዋ አንጄላ ሳውሪን ወደ ኢትዮጵያ በተጓዘችበት ወቅት ወዲያውኑ በእንጀራ ፍቅር እንደወደቀች ትገልጻለች። '' ኮምጠጥ ያለው ጣእሙና የትኛውም ዓለም ላይ የሌለው አይነት አሰራሩ ብዙ ጥያቄዎችን እንድጠይቅ አድርጎኛል። እንዴት ነው የሚሰሩት? ለምን የተለየ ጣእም ኖረው? ለምንስ ሰፋ ባለ ትሪ ሰብሰብ ብለው ይበሉታል? በጣም አስገራሚ ነው።'' '' እንጀራውን ከተለያዩ አትክልትና ስጋ ጋር አቀላቅለው ሲመገቡት ደግሞ በጣም ይጣፍጣል። እኔም ስሞክረው ደስ ብሎኛል። እንጀራውን ቆርሼ ከወጡ ጋር አቀላቅሎ መመገብ ለአያያዝ ትንሽ አስቸግሮኝ ነበር'' ብላለች። ይህን ያክል ተወዳጅነትና ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህይወት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ኖሮት እንዴት ጤፍን የማቀነባበርና ምርቶቹን የመሸጥ መብት በኔዘርላንድ ለሚገኝ ድርጅት ተሰጠ? ብላ ትጠይቃለች አንጄላ። ለሁለት ሳምንታት በዘለቀው ቆይታዋ "ኢትዮጵያውያን በቀን አንድ ጊዜ እንኳን እንጀራን ሳይመገቡ አላየሁም" የምትለው አንጄላ "ጤፍን በተለያየ መልኩ የመመገብ ፍላጎት ያላቸው እንኳን አይመስለኝም" ስትል ለእንጀራ የሚሰጠውን ክብር ገልጻለች። በጎርጎሳውያኑ 2003 የኢትዮጵያ ብዝኃ-ህይወት ኢንስቲትዩት ከኔዘርላንዳዊው የአፈርና እጽዋት ባለሙያ ጃንስ ሩስጄን ይሰራ ነበር። በዚሁም አጋጣሚ ነበር ኢንስቲትዩቱ ለምርምርና ስርጸት ይረዳል ብሎ በርካታ የጤፍ ዝርያዎችን ለዚሁ ባለሙያ ወደ ኔዘርላንድስ የላከው። ይህ ግለሰብ የጤፍን ምርቶች ለማሳደግ በሚልም ነበር ስምምነት የፈጠረው። ከአራት ዓመታት በኋላ ግን በአውሮፓ የባለቤትነት መብት የሚሰጠው ድርጅት 'ሄልዝ ኤንድ ፐርፎርማንስ ፉድ ኢንተርናሽናል' ወይም በአጭሩ 'ኤችፒኤፍአይ' ለተባለው ድርጅት የጤፍን ባለቤትነት መብት ሰጠው። በዚህም ድርጅቱ ጤፍን የማምረት፣ የማቀነባበርና ከጤፍ የተሰሩ የተለያዩ ምርቶችን የመሸጥ መብት አግኝቷል። ከወራት በፊትም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ የሄግ ዓለም አቀፍ የገላጋይ ድርጅት የጤፍ ባለቤትነት ይዞት የነበረው ድርጅት መብቱ መቀማቱን ጠቅሰው ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል እንደሆነ የደስታ መልዕክት አስተላልፈው ነበር። በዚሁ ትዊተር ገፅ ላይ የደች ፍርድ ቤት ውሳኔንም አብረው አያይዘውታል። በኋላ ላይ ግን ይህ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር በጭራሽ እንደማይገናኝና በሁለት የደች ኩባንያዎች መካከል የተካሄደ የጥቅም ክርክር እንደሆነ ተገልጿል። በሆላንድ የጤፍ ዱቄት አዘገጃጀት ላይ በባለቤትነት የተመዘገበው ኤንሺየንት ግሬይንስ የተባለ ኩባንያ ፍቃዴን ሳይጠይቅ የባለቤትነት መብቴን ተጋፍቷል ያለውን ቤክልስ የተባለ በጤፍ ምርቶች ዳቦና ኩኪስ የሚያመርት ድርጅት ላይ ክስ መስርቷል። • ፍርድ ቤት የቀረበው የጤፍ ባለቤትነት ጉዳይ በዚህም የሎያሊቲ (የባለቤትነት መብት) ክፍያ ሊከፈለኝ ይገባል፤ ለፈጠራዬ ገንዘብ ይሰጠኝ የሚል ክስ ማቅረቡን ተከትሎ፤ በምላሹ ቤክልስ የተሰኘው ድርጅት የባለቤትነት መብቱ ሊሰጠው አይገባም፤ ምክንያቱም አዲስ ፈጠራን ስላልጨመረ የባለቤትነት መብቱ ሊነጠቅ ይገባል የሚል መከራከሪያን ይዞ ቀርቧል። ፍርድ ቤቱም ኤንሺየንት ግሬይንስ የተባለው ድርጅት ምንም አይነት አዲስ ነገር ባለመጨመሩ የባለቤትነት መብቱን ከመንጠቅ በተጨማሪ ቤክልስ የተሰኘው ድርጅት ላወጣው ወጪ በሙሉ ካሳ እንዲከፈል ውሳኔ አስተላልፏል። ኢትዮጵያ ከባለቤትነት መብት ጋር በተገናኘ ዓለም አቀፍ ክርክር ውስጥ ስትገባ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። ከታዋቂው የአሜሪካ ቡና ሻጭ 'ስታርባክስ' ጋር በይርጋ ጨፌ ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ዓለማቀፍ ገላጋይ ፍርድ ቤት ሄዳ ነበር። ከበርካታ ድርድሮች በኋላም በጎርጎሳውያኑ 2007 ስታርባክስ የሀረር፣ሲዳማ እና ይርጋጨፌ ቡናዎችን እንዲያስተዋውቅና እንዲሸጥ ስምምነት ላይ መደረስ ተችሏል። በዚህ ክርክር መሀል ግን የኢትዮጵያ የቡና ዋጋ በዓለማቀፍ ገበያው ከፍ እንዲል ረድቶታል። የአገር በቀል ሰብሎች ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ቡላ ወዬሳ እንደሚሉት የኔዘርላንዱ ድርጅት በሚሊየን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ገበሬዎችን የባለቤትነት መብት የነጠቀ ነው ብለዋል።
news-53747876
https://www.bbc.com/amharic/news-53747876
ጃዋር መሐመድ ፡ ጋዜጠኛ ያሲን ጁማና አምስት የጃዋር ጠባቂዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ
በአቶ ጃዋር መዝገብ ከተከሰሱ ሰዎች መካከል አምስቱ እንዲሁም ኬንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል መባሉን ጠበቆቻቸው ለቢቢሲ አረጋገጡ።
በአቶ ጃዋር መዝገብ ለተከሰሱ 14 ሰዎች ጠበቃ ከሆኑት መካከል አንዱ ቶኩማ ዳባ (ዶ/ር) ለቢቢሲ የአቶ ጃዋር መሐመድ ጠባቂ የነበሩት አምስት ሰዎች ዛሬ በነበራቸው የፍርድ ቤት ውሎ አለመቅረባቸውን ገልፀው ለዚህም ዐቃቤ ህግ የሰጠው ምክንያት በኮቪድ-19 መያዛቸውን መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም በተጨማሪ ኬንያዊው ጋዜጠኛ የያሲን ጁማ ጠበቆች ከሆኑት መካከል አንዱ አቶ ከድር ቡሎ እንዲሁ ፖሊስ ጋዜጠኛው በኮሮናቫይረስ ተይዞ በለይቶ ማቆያ እንደሚገኝ ለችሎት ማስረዳቱንና ጋዜጠኛውም በነበረው የችሎት ቀጠሮ ላይ አለመገኘቱን አረጋግጠዋል። ቶኩማ (ዶ/ር) ለቢቢሲ እንደገለፁት በአቶ ጃዋር መሐመድ ጉዳይ ላይ ዛሬ ቀጠሮ መኖሩን የሰሙት ድንገት አምስት ሰዓት ተኩል አካባቢ መሆኑን እና አራት ጠበቆች ፍርድ ቤት በተገኙበትም ወቅት ዐቃቤ ሕግ ምስክር ለመስማት ቀጠሮ አስይዞ ቀርቦ እንደነበር ይናገራሉ። በወቅቱ በመዝገቡ ከተከሰሱ 14 ተጠርጣሪዎች መካከል ዘጠኝ ብቻ መቅረባቸውን የሚናገሩት ቶኩማ ዳባ (ዶ/ር) ጌቱ ተረፈ፣ በሽር ሁሴን፣ ሰቦቃ ኦልቀባ፣ ኬኔ እና ዳዊት ሆርዶፋ አልተገኙም ብለዋል። ያልተገኙበትን ምክንያት አቃቤ ሕግ ሲጠየቅ በኮቪድ-19 መያዛቸው ገልፆ ወደ ለይቶ ማቆያ መግባታቸውን ማስረዳቱን ጠበቃው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ዐቃቤ ሕግ መረጃውን ያገኘው ወደ 7፡30 ላይ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን በመናገር ዛሬ ሦስት ምስክሮች በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ ለመመስከር ተዘጋጅተው እንደነበር ጨምሮ ማስረዳቱን ገልፀዋል። አምስቱ ተጠርጣሪዎች ስላልቀረቡና ምስክሮቹን በዚህ ምክንያት ማሰማት ስለማልችል ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሎ መጠየቁን አስረድተዋል። የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው በኮቪድ-19 የተያዙት እነዚህ ግለሰቦች የጃዋር መሐመድ ጠባቂ የነበሩ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት እለት ጀምሮ ከሌሎች ተጠርጣሪዎች በተለየ ቤተሰቦቻቸውን እንዲያገኙ እንደማይፈቀድላቸው አመልክተዋል። በተጫመሪም ምግብ እንደማይገባላቸው፣ ለአንድ ወር ያለ ቅያሪ ልብስ መቆየታቸውን በመጥቀስ በተደጋጋሚ ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤት ማቅረባቸውን በሽታውም የያዛቸው እስር ቤት ውስጥ እያሉ በመሆኑ አያያዛቸው ላይ ጉድለት እንዳለ ማሳያ ነው በማለት መከራከራቸውን ይናገራሉ። በተጨማሪም እነዚህ እስረኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ከዐቃቤ ሕግ ከመስማት ውጪ ያየነው ማስረጃ ባለመኖሩ ለፍርድ ቤቱም ለእኛም ማስረጃ ይቅረብልን በማለት መከራከራቸውን ጠበቃው ቶኩማ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ተናግረዋል። አክለውም ከደንበኞቻቸው ጋር ተቀራርቦ በመመካከር ለምስክሮች መስቀለኛ ጥያቄ ማቅረብ እንዲችሉ ሁሉም የኮቪድ-19 ተመርምረው ውጤታቸው እንዲቀርብ፣ በቫይረሱ መያዛቸው የተገለጹት አምስት ሰዎች ማስረጃ እንዲቀርብ አቤቱታ ማቅረባቸውን ይገልጸዋል። ችሎቱም የግራ ቀኙን ክርክር አድምጦ በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል የተባሉ ማስረጃ ይቅረብ፣ ሌሎቹ ምርመራ ተደርጎ ውጤታቸው ይቅረብ፣ ስለአያያዛቸውም የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቀርቦ እንዲያስረዳ ብይን ሰጥቶ ምስክር ለመስማት ለነሐሴ 11/2012 ዓ.ም ሰኞ ቀጠሮ መስጠቱ ተናግረዋል። ለኬንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማም ለነሐሴ ደግሞ በቀጣይ ቀን ነሐሴ 12/2020 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠቱን ጠበቃው አረጋግጠዋል።
news-56059659
https://www.bbc.com/amharic/news-56059659
ኮሮናቫይረስ፡ የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት በህጻናት ላይ ሊሞከር ነው
የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት በህጻናት ላይ ምን ያህል ውጤታማ ይሆናል የሚለውን ለማጣራት አዲስ የክትባት ሙከራ መጀመሩ ተገልጿል።
የመጀመሪያዎቹ ዙር የክትባት ሙከራዎች በያዝነው ወር መጨረሻ አካባቢ የሚጀመሩ ሲሆን በነዚህ ሙከራዎችም እስከ 300 የሚደርሱ በጎ ፈቃደኛ ህጻናት ይሳተፋሉ ተብሏል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ይህ ሙከራ እድሜያቸው ከ6 እስከ 17 የሆኑ ህጻናት የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን ከወሰዱ በኋላ ምን ያህል የመከላከል አቅማቸው ይጠነክራል የሚለውን ለማወቅ ወሳኝ ነው። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮረናቫይረስ ምክንያት የሚከሰት ከፍተኛ ህመምን አልያም ሞትን ለመቀነስ ጥቅም ላይ እየዋለ ሲሆን የፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባትም ቢሆን ለተመሳሳይ አገልግሎት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። በህጻናቱ ላይ በሚደረገው ሙከራ እስከ 240 የሚደርሱት ተሳታፉዎች የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ የማጅራት ገትር መድሀኒት በተመጠነ መልኩ እንዲወስዱ ይደረጋሉ ተብሏል። የክትባት ሙከራው በሚደረግባቸው አራት ማዕከላት፤ ዩኒርሲቲ ኦፈ ኦክስፎርድ፣ ሴንት ጆርጅ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ ለንደን፣ ሳውዝሀም[ፕተን ዩኒቨርሲቲተ ሆስፒታል እና ብሪስቶል የህጻናት ሆስፒታል አቅራቢያ የሚኖሩ በጎ ፈቃደኞች በቶሎ እንዲመዘገቡ ተጠይቀዋል። ለመሳተፍ በጎ ፈቃደኛ የሆኑት ህጻናት ሙከራው ከመጀመሩ በፊት ግን ለይቶ ማቆያ መግባት ግዴታ እንደሆነ ተነግሯል። በዩናይትድ ኪንግደም እስካሁን የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባትን ለህጻናት ለመስጠት ምንም የታሰበ ነገር እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን ለጊዜው ግን እድሜያቸው ከ28 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው ክትባቱን እየወሰዱ የሚገኙት። የፋይዘር-ባዮንቴክ ክትባት ደግሞ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ተፈቅዷል። በክትባቱ አሰጣጥ ስርአት መሰረት እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ህጻናት በጠና ቢታመሙ እንኳን ክትባቱ አይሰጣቸውም። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ እድሜያቸው ከ6 እስከ 17 ለሆኑ ህጻናት ክትባቱን መስጠት ምን አይነት አሉታዊና አዎንታዊ ተጽዕኖዎች እንደሚኖሩት ለማወቅ የሚደረገው ይህ ሙከራ የመጀመሪያው ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ በርካታ ሙከራዎች እንደሚደረጉ አስታውቋል።
news-49712171
https://www.bbc.com/amharic/news-49712171
አውስትራሊያዊው ተናካሽ ቁራ ሲሸሽ ከብስክሌት ወድቆ ሞተ
የ76 ዓመቱ አውስትራሊያዊው ከተናካሽ ቁራ እራሱን ለማዳን ሲሸሽ ከብስክሌት ላይ ወድቆ ህይወቱ አለፈ።
ፖሊስ እንዳለው ብስክሌት ሲጋልብ የነበረው አዛውንት ከአደገኛው ወፍ ለማምለጥ ጥረት ሲያደርግ መንገድ ስቶ ከፓርክ አጥር ጋር ተጋጭቶ ህይወቱ አልፏል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወቱን ለማዳን ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ጭንቅላቱ ላይ የደረሰበት ጉዳት ከባድ ስለነበር ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። • 'ኒከርስ' የማይሸጥ የማይለወጠው ቁመተ ሎጋው በሬ • የዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች እነማን ናቸው? በአውስትራሊያ ጥቁር እና ነጭ ቀለም ያላቸው ቁራዎች በፍጥነት እየበረሩ በእግረኞች እና ብስክሌት በሚጋልቡ ሰዎች ላይ ጉዳት የማድረሳቸው ዜና የተለመደ ነው። በፓርኩ አቅራቢያ በወፎቹ በርካታ ተመሳሳይ ጥቃቶች መድረሳቸውን የአከባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ባለሙያዎች እንደሚሉት አእዋፋቱ በመራቢያቸው ወቅት በአካባቢያቸው የሚገኝ ማንኛውንም እንስሳ ያጠቃሉ። ከፈረንጆቹ ሞቃታማ ወራት በኋላ በሚኖሩት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ደግሞ የአዋፋቱ ጥቃት ይጨምራል። ከፈረንጆቹ ሞቃታማ ወራት በኋላ በሚኖሩት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የአዋፋቱ ጥቃት ይጨምራል። • ወደ ጫካነት የተቀየረው ስታዲየም በሲድኒ ከተማ የሚገኝ የአንድ አካባቢ ምክር ቤት በሰዎች ላይ ጥቃት እያደረሱ የሚገኙ ቁራዎችን ለመግደል ውሳኔ ማስተላለፉ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። የአውስትራሊያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደዘገበው ሌላ አንድ ነዋሪ ከቁራው ለመሸሸ ረዥም ሰዓት መሮጡን ተከትሎ ባጋጠመው የልብ ህመም ለሆስፒታል አልጋ ተዳርጓል።
news-42133753
https://www.bbc.com/amharic/news-42133753
ሩሲያ በሶሪያ ባደረሰችው ጥቃት 53 ሰዎች ተገደሉ
ሩሲያ በምስራቅ ሶሪያ በምትገኘው አል-ሻፋህ መንደር ባካሄደችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 53 ሰዎች መገደላቸውን አንድ የታዛቢ ቡድን ገለጸ።
ለዓመታት በዘለቀው ሶሪያ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ሩሲያ ከፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ጎን ጋር ቆማለች። መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው የሶሪያ ሰብዓዊ መብት ታዛቢ ቡድን እንዳለው እሑድ ጠዋት ከተደረገው ጥቃት በኋላ ከሞቱት ሰዎች መካከል 21 ህጻናት ይገኙበታል። መንደሩ አይ ኤስ በዲር አል-ዙር አካባቢ ከተቆጣጠራቸው ጥቂት ቦታዎች አንዱ ነው። በመኖሪያ አካባቢዎች በደረሰው ጥቃት 34 ሰዎች መሞታቸውን ታዛቢ ቡድኑ ገልጾ ነበር። "ቀኑን ሙሉ ፍርስራሾች የማንሳት ስራ ከተከናወነ በኋላ ነው የሟቾች ቁጥር መጨመሩ የታወቀው" ሲሉ ራሚ አብድል ራህማን አስታውቀዋል። ሩሲያ በበኩሏ በስድስት የጦር አውሮፕላኖች ተጠቅማ በአካባቢው ጥቃት ማድረሷን ብታሳውቅም ዒላማ ያደረገችው የታጣቂዎችን ጠንካራ ይዞታ መሆኑን ጠቁማለች። ለዓመታት በዘለቀው ሶሪያ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ሩሲያ ከፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ጎን ቆማለች። በአካባቢው ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ የሶሪያ ጦር በጀመረው ጥቃት 120 ሰዎች መሞተዋል ቀደም ሲል የተካሄዱ የሠላም ውይይቶች ባይሳኩም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያዘጋጀው ውይይት በሚቀጥለው ሳምንት በጄኔቫ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ እሁድ ዕለት በደማስቆ አካባቢ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በሚገኝ አካባቢ 23 ሰዎች ተገድለዋል። እንደታዛቢ ቡድኑ ገለጻ ከሆነ በምስራቅ ጉታ ከተሞች ከምድር እና ከአየር ጥቃቶች ተፈጽመዋል። ሪፖርቶቹን በገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልተቻለም። በአካባቢው ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ የሶሪያ ጦር በጀመረው ጥቃት 120 ሰዎች መሞታቸው የታዛቢ ቡድኑ አስታውቋል። ከጦርነቱ በተጨማሪ የ400 ሺህ ሰዎች መኖሪያ በሆነችው ምስራቅ ጉታ ሰዎች በረሃብ ምክንያት እየሞቱ ነው። እንደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከሆነ የምግብ እጥረት መኖሩን ተከትሎ ሰዎች የእንስሳት መኖ እና ቆሻሻ በመመገብ ላይ ይገኛሉ።
news-49838830
https://www.bbc.com/amharic/news-49838830
የዙሉው ንጉሥ ማኮላሸት አስገድዶ መድፈርን ያስቀራል አሉ
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙት የዙሉ ግዛት ንጉሥ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተይዘው ጥፋተኝነታቸው የተረጋገጠባቸው ግለሰቦች መኮላሸት ይገባቸዋል ማለታቸው ተዘገበ።
ንጉሥ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ አንድ የደቡብ አፍሪካ ድረገጽ ንጉሡ በአንድ ክብረ በዓል ላይ ለሕዝባቸው ያደረጉትን ንግግር ጠቅሶ እንደዘገበው አሳሳቢ የሆነውን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ለማስቆም ማኮላሸት መፍትሄ ነው ብለዋል። ንጉሥ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ "ማኮላሸት አስገድዶ መድፈርን ያስቆማል። ይህም የዙሉ ግዛት እንዲህ አይነቱን አሳፋሪ ድርጊት ፈጽሞ እንደማይታገሰው ለዓለም በሚያሳይ ሁኔታ መፈጸም አለበት" ማለታቸው ተጠቅሷል። • ደቡብ አፍሪካዊው 32 ሴቶችን በመድፈር 32 የተለያየ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት • በምዕራብ ጎጃም ታራሚ አስገድዶ የደፈረው ፓሊስ የእስራት ጊዜ ተጨመረበት አክለውም አስገድዶ የወንጀል ድርጊቱን በፈጸሙት ሰዎች ላይ የሚወሰደውን የማኮላሸት ርምጃም "እኛን የመሰሉ ወንዶች ያከናውኑታል" ማለታቸውም ተነግሯል። ንጉሡ ይህን የተናገሩት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶ የሃገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዋነኛ የዘገባ ርዕስ መሆኑን ተከትሎ ነው። ባለፈው ሳምንት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲለሪል ራማፎሳ በፓርላማ ውስጥ ባደረጉት ንግግር ላይ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሃዝ በጦርነት ውስጥ ካለ ሃገር ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በመግለጽ የጉዳዩን አሳሳቢነት አመልክተዋል። ከፈረንጆቹ 2018 ሚያዚያ ወር ወዲህ 41 ሺህ ሴቶች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ደርሶባቸዋል። ይህም አሃዝ በየ15 ደቂቃው ከአንዲት ሴት በላይ የጥቃቱ ሰለባ ትሆናለች ማለት ነው። • ተማሪዎች አስገድዶ ስለመድፈር በመቀለዳቸው ታገዱ • ባሏን በስለት የገደለችው ኑራ ሁሴን የዙሉው ንጉሥ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ በተጨማሪም "ግርዛትን እንደምናከናውነው ሁሉ አሁን ከዚህ ከፍ ያለ ቅጣትን መጣል አለብን። ደንብና ሥርዓትን ላስቀመጠው ለቀድሞ ንጉሣችን ሻካና ለማኅበረሰባችን ክብር ስንል ማኮላሸትን ሕጋችን ልናደርገው ይገባል። መከባበርን ወደ ቦታው መመለስ ይገባናል" ብለዋል። ነገር ግን ለጾታ ፍትህ በሚሰራ አንድ ተቋም ውስጥ ያለ የመብት ተከራካሪ ይህንን ጥሪ ተቃውሞታል። በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለማስቆም "አስከፊ ድርጊትን በፈጻሚዎቹ ላይ ማድረግ ፈጽሞ ለችግሩ መፍትሄ አይሰጥም" ማለቱ ተዘግቧል። አስገድዶ ደፋሪዎች እንዲኮላሹ ጠንካራ ጥሪ ያቀረቡት ንጉሥ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ ምንም እንኳን ፖለቲካዊ ስልጣን ባይኖራቸውም በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ትልቁ በሆነው የዙሉ አባላት ዘንድ ተሰሚነትና ተጽእኖ የመፍጠር አቅም አላቸው።
54617479
https://www.bbc.com/amharic/54617479
ዩናይትድ ኪንግደም ጤነኛ ሰዎችን በኮቪድ ተህዋሲ 'ልትለክፋቸው' ነው
የኮቪድ ክትባትን በማግኘት ጥረት ውስጥ ከፊት ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም የተለየ አይነት የክትባት ሙከራ ለማድረግ ቀዳሚዋ አገር ልትሆን ነው።
በጥር ወር ላይ 90 ጤነኛ ሰዎች ሆን ተብለው ለኮቪድ ተህዋሲ እንዲጋለጡ በማድረግ ነው አዲሱ ሙከራ የሚደረገው። ይህም ቶሎ ክትባት ለማግኘት ይረዳል ተብሏል። መንግሥት ከወዲሁ 33.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዚሁ ሙከራ መድቧል። ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግበታል የተባለው ይህ አዲስ የሙከራ ዘዴ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ከአገሪቱ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። በመድኃኒት ቅመማ ሂደት ‹ሂዩማን ቻሌንጅ› በሚል የሚታወቀው ይህ ጤነኞች ላይ በሽታ አምጪ ተህዋስን ሆን ብሎ በማጋባት ሙከራ ማድረግ ብዙም የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ከዚህ ቀደም በወባና በኢንፍሉዌዛ የመድኃኒት ግኝቶች ሂደት ውስጥ ተሞክሮ ውጤት ማስገኘቱን ኔቸር መጽሔት ዘግቧል። ሳይንቲስቶች በጥር ወር መጀመርያ ተግባራዊ ያደርጉታል በተባለው በዚህ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 30 የሚሆን ፍጹም ጤነኛ የሆኑ በጎ ፈቃደኞች ብቻ ናቸው። ሙከራው አንድን ሰው ምን ያህል የተህዋሲው መጠን ነው ለበሽታ የሚያጋልጠው የሚለውንም ለማወቅ ይረዳል ተብሏል። ለበጎ ፈቃደኞቹ በቅድሚያ ተህዋሲው በትንሽ መጠን ይሰጣቸዋል። ፍጹም ጤነኛ ሰዎችን እንደ አይጥ መሞከርያ ማድረግ ቶሎ ውጤት ለማግኘት አስፈላጊ ነው የሚሉ በርካታ ቢሆንም መድኃኒት በሌለው በሽታ ሰዎችን ሆን ብሎ መበከል ከሕክምና ሥነ ምግባር አንጻር ተገቢ አይደለም ሲሉ ነገሩን የሚተቹትም በርካታ ናቸው። ተህዋሲው ለበጎ ፈቃደኞቹ የሚሰጣቸው በአፍንጫቸው በኩል ይሆናል ተብሏል። ለ24 ሰዓታትም ጥብቅ ክትትል ይደረግላቸዋል። በጎ ፈቃደኞቹ ለከፋ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ጤነኞችና ወጣቶች በመሆናቸውና በጥንቃቄ ስለሚመረጡ ነው ይላሉ ተመራማሪዎች። ቅድመ ጥንቃቄው አስተማማኝ በሚባል ደረጃ ላይ ሲደርስ በበጎ ፈቃደኞቹ በአንዳንዶቹ ላይ ሙከራ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ይሰጧቸዋል። ለኮቪድ ተህዋሲው ከመገላጣቸው በፊትም ክትባት እንዲወስዱ የሚደረጉ ይኖራሉ። ክትባቱን የወሰዱት ለተህዋሲው ተጋልጠው ተህዋሲው ይይዛቸዋል ወይስ አይዛቸውም የሚለውም ምላሽ ያገኛል። የዚህ ምርምር መሪ የኢምፔሪያል ኮሌጁ ዶ/ር ክሪስ ቺዩ ሰዎች ያን ያህልም ሐሳብ ሊገባቸው አይገባም ይላሉ። ‹‹እኔና ባልደረቦቼ በዚህ መንገድ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ጤነኛ ሰዎች ላይ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ቫይረሶችን በመስጠት ስንሰራ ቆይተናል። እርግጥ ነው የትኛውም ጥናት ቢሆን የራሱ አደጋ የለውም አይባልም። ነገር ግን አደጋውን ለመቀነስ እንታገላለን›› ብለዋል። ረዳታቸው ፕሮፌሰር ፒተር ኦፔን ሻው በበኩላቸው ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲ ሆን ብሎ በመበከል ምርምር ማካሄድ በቀላሉ የሚታይ ነገር ባይሆንም ውጤት ለማግኘት ግን ወሳኝ ነው፤ ያግዛል ብለዋል። በአሁን ሰዓት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ ክትባቶች በመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራ ላይ ሲሆኑ ውጤት ያስገኛሉ ተብለው በጉጉት እየተጠበቁ ካሉት መካከል የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ተጠቃሽ ነው። በጥር ወር ጤነኛ ሰዎችን በተህዋሲው በመበከል የሚደረገው ምርምር ሌላ ፍቱን መድኃኒት ቀድሞ ቢገኝም የሚቋረጥ አይሆንም። ክትባቶች ከተገኙ በኋላ የትኛው ክትባት እጅግ ውጤታማ ነው የሚለው ጥናት ይቀጥላል። ተህዋሲውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመውሰድ የፈቀዱ የታላቋ ብሪታኒያ ዜጎች ለጊዜያቸውና ለደፋር ውሳኔያቸው የሚመጥን ነው የሚባል ገንዘብ ይከፈላቸዋል። ሙከራው ከተደረገባቸው በኋላም ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያለማቋረጥ የቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል።
54617477
https://www.bbc.com/amharic/54617477
ፈረንሳይ የሟቹን መምህር ግድያ አበረታቷል ያለችውን መስጊድ ዘጋች
የፈረንሳይ መንግሥት አንድ መስጊድ እንዲዘጋ አደረገ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የታሪክ መምህሩ ሳሙኤል ፓቲ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን ነው፡፡
ይህ መስጊድ እንዲዘጋ የተደረገው በዋናነት የመስጊዱ ኃላፊዎች ሟቹ መምህር ሳሙኤል ፓቲ የነብዩ መሐመድን ካርቱን ምሥል ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ ይህን ድርጊቱን የሚያወግዝ መልእክት በማሰራጨታቸው ነው፡፡ የዚህ መስጊድ ኃላፊዎች በመስጊዱ የፌስቡክ ገጽ ሟች ሳሙኤል ፓቲ ላይ እርምጃ እንዲወሰድበት የሚያበረታታ ይዘት ያለው ጽሑፍና መምህሩ የሚያስተምርበትን አድራሻ አጋርተው ነበር፡፡ መስጊዱ ለድርጊቱ ጸጸት እንደተሰማውና ይቅርታ እንደጠየቀም ተዘግቧል፡፡ ዘ ፓንቲን ተብሎ የሚጠራው መስጊድ የሚገኘው በሰሜን ፓሪስ ሲሆን ለሚቀጥሉት 6 ወራት ለምዕመናን ክፍት እንደማይደረግ የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡ የመስጊዱ ኃላፊዎች አጋሩት የተባለው የፌስቡክ መልእክት የመምህሩን ግድያ ተከትሎ ወዲያውኑ ተሰርዟል፡፡ ባሳለፍነው አርብ ትምህርት ቤት አቅራቢያ አንገቱን ተቀልቶ የተገደለው መምህር ሳሙኤል ፓቲ እጅግ ተወዳጅ መምህር እንደነበር ይነገራል፡፡ ለተማሪዎቹ የነብዩ መሐመድን ካርቱን ምሥል በማሳየት ስለ ፕሬስ ነጻነት ለማስተማር ከሞከረ በኋላ ነበር ይህ ጥቃት የደረሰበት፡፡ የሱን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደል ተከትሎ በፈረንሳይ ከፍተኛ ቁጣ የተቀሰቀሰ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ድርጊቱን ለማውገዝ እሑድ አደባባይ መውጣታቸው ይታወሳል፡፡ እንዲዘጋ የተወሰነበት መስጊድ 1ሺ500 ምዕመናን እየተገኙ የሚያመልኩበት ሥፍራ የነበረ ሲሆን በከተማዋ እምብርት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ የ18 ዓመቱ ጥቃት አድራሽ ፈረንሳዊ ስሙ አብዱላሂ ሲሆን ትውልዱ ከሩሲያ ግዛት ቺቺንያ ይመዘዛል፡፡ ይህ ወጣት መምህሩን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኋላ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ ወዲያውኑ ተገድሏል፡፡ ይህን አሰቃቂ ድርጊት ተከትሎ የፈረንሳይ መንግሥት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በሙስሊም ዜጎች ላይ ከፍተኛ ክትትልና ምርመራ እያደረገች ነው፡፡ አክራሪ የሆነ አተያይ ያላቸው አማኞችና የሪፐብሊኩን ነጻ አስተሳሰብ የሚቃረኑ ቡድኖችን እያደነችም ትገኛለች፡፡ እስካሁን በትንሹ 40 ቤቶች ላይ አሰሳ ተደርጓል፡፡ 51 የሚሆኑ ኢስላማዊ ማኅበራትና ድርጅቶች፣ እንዲሁም ግብረሰናይ ተግባር የሚሰሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ኢስላማዊ ተቋማት ተዘግተው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው፡፡ ግድያውን ተከትሎም 15 ፈረንሳዊያን በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የገዳዩ አያትና ቤተሰቦች እንዲሁም ታናሽ ወንድሙ ይገኙበታል፡፡ ገለልተኛ ወገኖች በጥቃት ፈጻሚው ላይ ባለፉት ቀናት ይታዩ የነበሩ እንግዳ ባህሪዎችን ተከትሎ ለፈረንሳይ መንግሥት ቅድመ ጥቆማ ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ምንም እርምጃ አለመውሰዱን ክፉኛ እየተቹት ይገኛሉ፡፡
news-53704849
https://www.bbc.com/amharic/news-53704849
አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ላይ ማዕቀብ ጣለች
የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር በሆንግ ኮንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬሪ ላም እና 10 የሆንግ ኮንግ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ጣለ።
የሆንግ ኮንግ ዋና ሥራ አስጸፋሚ ኬሪ ላም የገንዘብ ሚንስትሩ ስቲቨን ሙንሽን ማዕቀቡ ትኩረት ያደረገው የሆንግ ኮንግ ሉዓላዊነት ላይ ጫና የሚያሳድሩት ላይ ነው ብለዋል። "ዩናይትድ ስቴትስ ከሆንግ ኮንግ ህዝብ ጎን ናት” ብለዋል ስቲቨን ሙንሽን። ይህ የአሜሪካ ውሳኔ የመጣው ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ ብሄራዊ የደህንነት ሕግ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች በኋላ ነው። በርካቶች ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ የጣለችውን ሕግ የሆንግ ኮንግን ነጻነት የሚጋፋ ነው ይላሉ። ማዕቀብ ከተጣለባቸው መካከል የሆንግ ኮንግ ፖሊስ ኮሚሽነር እና በርካታ ፖለቲከኞች ይገኙበታል። አሜሪካ፤ የሆንግ ኮንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኬሪ ላም “ነጻነትን እና ዲሞክራሲያዊ ስርዓቱን የሚጎዱ የቤይጂግ ፖሊሲዎችን ሆንግ ኮንግ ላይ ያስፈጽማሉ” ስትል ትተቻለች። ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ የጣለችውን ብሄራዊ የደህንነት ሕግ ከአሜሪካ በተጨማሪ ሌሎች ምዕራባውያን አገራት አጥብቃ ይቃወሙታል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፔዮ፤ ሕጉ የሆንግ ኮንግ ሕዝብ መብት እና ነጻነትን የሚጥስ ነው ብለውታል። ቻይና በበኩሏ አጨቃጫቂ ሕጓ በሆንግ ኮንግ የውጪ ጣልቃ ገብነትን ለማስቆም አስፈላጊ ነው ስትል ትከራከራለች። የቀድሞ የሲአይኤ አለቃ የአሁኑ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ በግለሰቦቹ ላይ አሜሪካ የጣለችውን ማዕቀብ ይፋ ባደረጉበት ወቅት፤ “የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ የሆንግ ኮንግ ህዝብ ሉዓላዊነት እንደማያከብር አስመስክሯል” ብለዋል። “ፕሬዝደንት ትራምፕ ግልጽ እንዳደረጉት፤ አሜሪካ ሆንግ ኮንግን እንደ ‘አንድ አገር፤ አንድ ስርዓት’ አድርጋ ነው የምትመለከታት። የሆንግ ኮንግ ህዝብ ነጻነትን የሚጋፉ ግለሰቦች ላይም እርምጃ ይወሰዳል” ብለዋል። ማዕቀቡ የተጣለባቸው 11 ግለሰቦች በአሜሪካ የሚኖራቸው ንብረት የሚወረስ ሲሆን ገንዘባቸው ደግሞ እንዳይንቀሳቀስ ይደረጋል ተብሏል። ማዕቀቡ የተጣለባቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ከአንድ ወር በፊት አሜሪካ ማዕቀብ ልትጥልባቸው እንደምትችል በጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ “በአሜሪካ ምንም አይነት ንብረት የለኝም። አሜሪካ ሄዶ የመኖር ሃሳብም የለኝም” ብለው ነበር። ከዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በተጨማሪ የሆንግ ኮንግ ፖሊስ ኮሚሽነር የሆኑት ክሪስ ታንግ፣ እስከ እአአ 2019 ድረስ የሆንግ ኮንግ ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት ስቴጸን ሎ፣ የሆንግ ኮንግ ፍትህ ጸሃፊ ቴሬሳ ቼንግ እንዲሁም የደህንነት ጸሃፊ ጆን ሊ ማዕቀቡ ከተጣለባቸው 11 ግለቦች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
news-48905186
https://www.bbc.com/amharic/news-48905186
ወደ ጠፈር በመሄድ የመጀመሪያው ይሆን የነበረው አፍሪካዊ በሞተር አደጋ ሞተ
ወደ ጠፈር ለመሄድ እድል አግኝቶ የነበረው ደቡብ አፍሪካዊ በሞተር አደጋ ሕይወቱ አለፈ።
ማንዳላ ማሶኮ ደቡብ አፍሪካዊው ማንደላ ማሶኮ ወደ ጠፈር የመሄድ ምኞቱ ቢሳካ ኖሮ ወደ ጠፈር የተጓዘው የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ ይሆን ነበር። የ30 ዓመቱ ወጣት ማንዳላ ማሶኮ ቅዳሜ ዕለት በሞተር አደጋ ሕይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል። የደቡብ አፍሪካ አየር ኃይል አባል የነበረው ማንዳላ እአአ 2013 ላይ ወደ አሜሪካ ጠፈር አካዳሚ ለመግባት ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች ጋር ተወዳድሮ ከተመረጡ 23 ሰዎች መካከል አንዱ ለመሆን ችሎ ነበር። ስፔስቦይ (የጠፈር ልጅ) እየተባለ በጓደኞቹ የሚጠራው ማንዳላ ማሶኮ፤ በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት በሚገኘው የኬኔዲ ጠፈር ማዕከል ውስጥ ወደ ጠፈር የሚደረግ በረራ ልምምድ አድርጓል። • ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው • ጨረቃን የሚረግጠው የመጀመሪያው ጎብኚ ታወቀ • በ2024 እቃና ሰው ጫኝ መንኮራኩር ወደጨረቃ ይላካል ተባለ ማሶኮ "አፍሪካውያን ወጣቶችን ሊያነቃቃ የሚችል ነገር ማድረግ እፈልጋለሁ፤ ከየትም ይምጡ ማሳካት የሚፈልጉትን ማድረግ እንደሚችሉ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ" ይል ነበር። ማሶኮ ለቢቢሲ 'ከጠፈር ሆኘ እደውልላችኋለሁ" ሲል ተናግሯል። ''በቀጣዮቹ ዓመት ወደ ጠፈር ስሄድ የስልክ መስመር ይኖረኛል- ኒል አርምስትሮንግ እንደነበረው'' ብሎ ነበር። ኒል አርምስትሮንግ አሜሪካዊ ጠፈርተኛ ሲሆን በ82 ዓመቱ እአአ 2012 ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። አርምስትሮንግ እአአ 1969 ላይ በጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተራመደ ሰው ነበር። በጨረቃ ላይ የመጀመሪያ እርምጃውን እንዳደረገ ''ይህ ለአንድ ሰው ኢምንት እርምጃ ነው፤ ለሰው ልጆች ግን ግዙፍ ከፍታ ነው'' ሲል ተናግሮ ነበር።
news-53762529
https://www.bbc.com/amharic/news-53762529
የአሜሪካ ምርጫ፡ ዶናልድ ትራምፕ በካማላ ሐሪስ አሜሪካዊነት ላይ ጥያቄ አነሱ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለውዝግብ የፈጠራቸው ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ በካማላ ሐሪስ ላይ ተነስተውባታል፡፡
ከሰሞኑ የዲሞክራቱ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ጆ ባይደን የውድድር አጋራቸው አድርገው የመረጧት የካሊፎርኒዋን ሴናተር ካማላ ሐሪስን መሆኑ ይታወሳል፡፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሴት-ጠልና ጾተኛ አስተያየቶችን በመስጠት ይታወቃሉ፡፡ የሐሪስን መመረጥ ተከትሎ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹እንቅልፋሙ ጆ ምን ነካው? አስጠሊታ ሴት እንደሆነች ነው የማውቀው…ብለው ነበር፡፡ ትራምፕ ይህን አስጠሊታ (Nasty) የሚለውን ቃል ለሚጠሏቸው ወንድ ፖለቲከኞችም ቢሆን እምብዛምም አይጠቀሙትም፤ በሴት ፖለቲከኞች ላይ ግን በተደጋጋሚ ይለጥፉታል። ይህም ሰውየው የለየላቸው ጾተኛ መሆናቸውን ማሳያ ሆኗል። ትናንት በነበራቸው የጋዜጣዊ መግለጫ ስለ ካማላ ሐሪስ የተጠየቁት ትራምፕ፣ ሐሪስ ለአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር መስፈርቱን እንደማታሟላ ሰምቻለሁ ብለዋል፡፡ ይህን ዘረኛ የተባለ አስተያየት ለመስጠት ያበቃቸው በኒውስዊክ ላይ አንድ የሕግ አዋቂ ወ/ሮ ሐሪስ ከስደተኛ ቤተሰብ መወለዷን በማስታወስ ለፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ተሳትፎ ሕጉ አይፈቅድላትም የሚል ይዘት ያለው አስተያየት መጻፋቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሐሪስ የተወለደችው ከጃማይካዊ አባትና ከሕንዳዊት እናት በኦክላንድ፣ ካሊፎርኒያ በጥቅምት 20፣ 1964 ዓ. ም ነበር፤ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ አቆጣጠር፡፡ ወግ አጥባቂው የሕግ ፕሮፌሰር ግን ምንም እንኳ ካማላ ሐሪስ በአሜሪካ ብትወለድም ወላጆቿ በዚያን ጊዜ በተማሪ ቪዛ ላይ ከነበሩ ሕጉ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዳትሳተፍ ይከለክላታል የሚል ጭብጥ ያለው ሐሳብ አንጸባርቀዋል፡፡ ይህን በኒውስዊክ መጽሔት የታተመውን የወግ አጥባቂውን ፕሮፌሰር ሐሳብ ዶናልድ ትራምፕ ‹‹እጹብ ድንቅ›› ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡ ‹‹…በነገራችሁ ላይ ይሄ ፕሮፌሰር ቀላል ሰው እንዳይመስላችሁ፤ ሕግን ጠንቅቆ የሚያውቅና የብሩሕ አእምሮ ባለቤት ነው›› ብለዋል ትራምፕ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የትወልድ አገር ዙርያ እንዲሁ ሐሰት ሲነዙ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ኦባማ የተወለደው ኬንያ እንጂ አሜሪካ አይደለም፤ አሜሪካ በኬንያዊ ፕሬዝዳንት እየተመራች ነው ይሉ ነበር ድሮ፡፡ ጋዜጠኞች በዚህ የሕግ ፕሮፌሰር ጽሑፍ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የጠየቋቸው ዶናልድ ትራምፕ፣ ፕሮፌሰሩን ካዳነቁ በኋላ"…እየተባለ ያለው እኮ ሐሪስ በአሜሪካ ምድር አልተወለደችም ነው፤ ፕሮፌሰሩም ይህንኑ ነው የጻፈው›› ብለዋል፡፡ ጥያቄውን ያነሳላቸው ጋዜጠኛ ቀበል አድርጎ ‹‹ ክቡር ፕሬዝዳንት፣ የሕግ ፕሮፌሰሩ እኮ ካማላ ሐሪስ አሜሪካ አልተወለደችም አላሉም፡፡ ፕሮፌሰሩ ያሉት ቤተሰቦቿ እሷን ሲወልዱ ሕጋዊ የመኖርያ ፍቃድ አልነበራቸው ከነበረ ነው…›› በማለት ፕሬዝዳንቱን እዚያው መድረክ ላይ ኩም አድርጓቸዋል፡፡ ይህንን አወዛጋቢ አስተያየት በኒውስዊክ ላይ ያሳተሙት የሕግ ፕሮፌሰር ኢስትማን ይባላሉ፡፡ በጠርዘኛና ወግ አጥባቂ አቋማቸውም ይታወቃሉ፡፡ የሰውየው ሐሳብ በሌሎች የሕግ አዋቂዎች እንዴት ይታይ ይሆን? የበርክሌይ ዩኒቨርስቲ የሕግ ምሁርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አዋቂ ኤርዊን ኬመረንስኪ በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ የትራምፕም ሆነ የፕሮፌሰሩ በሐሪስ ዙርያ ያነሱት ሐሳብ ‹‹ውሃ የማይቋጥር›› ብለውታል፡፡ ‹‹እንዲያውም ወላጆቿ በስደተኛ ቪዛ ነበሩ ወይስ አልነበሩም፣ የመኖርያ ፍቃድ ነበራቸው ወይስ አልነበራቸውም የሚለው ሁሉ ግልብና ተያያዥነት የሌለው ነጥብ ነው፡፡ ሐሪስ በአሜሪካ ምድር ስለተወለደች አሜሪካዊ ዜጋ ናት፤ አለቀ ደቀቀ።›› ብለዋል የበርክሌይ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር፡፡ እርሳቸው ለዚህ መከራከርያቸው ያነሱት በአሜሪካ ሕገ መንግሥት 14ኛው አሜንድመንት፣ አንቀጽ አንድ ላይ የተጻፈውን ነው፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው በአሜሪካ ምድር ከተወለደ አሜሪካዊ ዜጋ ነው፡፡ በሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕገ መንግሥት መምህርና ተንታኝ ላውረንስ ትራይብ የትራምፕን በሐሪስ የትውልድ ቦታ ላይ ያነሱትን ነጥብ ‹‹ጅላ ጅል›› ብለውታል፡፡ በመጪው ኅዳር አሜሪካዊያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ እያሟሟቁ ነው፡፡ ጆ ባይደን ምርጫው ከቀናቸው ወ/ሮ ከመላ ሐሪስ በዚያች አገር ታሪክ የመጀመርያዋ ጥቁር እስያዊ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
news-46719267
https://www.bbc.com/amharic/news-46719267
የዴሞክራቲክ ኮንጎ ምርጫ መጓተት ህዝቡን አስቆጥቷል
በዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መጓተትና በአንዳንድ ቦታዎች ተራዝሟል መባሉ ብዙ የሃገሪቱ ዜጎችን አስቆጥቷል።
መሪያቸውን ለመምረጥ የተሰለፉ የዴሞክራቲክ ኮንጎ ዜጎች ለምርጫው መጓተት በምክንያትነት ከቀረቡት መካከል ደግሞ የምርጫ መቆጣጠሪያው መሳሪያ በትክክል መስራት አለመቻሉ ነው። ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ በአውሮፓውያኑ 1960 ነጻነቷን ከገኘች ወዲህ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ለመረካከብ የመጀመሪያው በሆነው ምርጫ የሃገሪቱ ዜጎች ድምጻቸውን ለመስጠት ከትላንት ጠዋት ጀምሮ ተሰልፈው ነበር። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች • በምዕራብ ኦሮሚያ የኦነግ ጦር አዛዥ ስለወቅታዊው ሁኔታ ምን ይላል? ለ17 ዓመታት ሃገሪቱን የመሩት ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ደግሞ ስልጣናቸውን በሰላማዊ መንገድ በመልቀቅ በምርጫው ለሚያሸንፈው ሰው ሥልጣናቸውን የሚያስረክቡ ይሆናል ተብሏል። የምርጫው ውጤትም በመጪው ሳምንት እንደሚገለጽ ታውቋል። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ከሁለት ዓመት በፊት መካሄድ የነበረበት ቢሆንም፤ መንግሥት ለምርጫው መሟላት የነበረባቸው አቅርቦቶች እጥረት አጋጥሞኛል በማለት ነበር ያራዘመው። በምርጫው ለመሳተፍ ከተመዘገቡት 40 ሚሊዮን ዜጎች በአራት ከተሞች የሚኖሩ 1.26 ሰዎች መምረጥ አይችሉም መባሉ ደግሞ ብዙዎችን ያስቆጣ ሲሆን፤ ነገሮች ተባብሰው ወደ አመጽ ተቀይረው ነበር። ምንም እንኳን የምርጫ ሂደቱ 11 ሰአት ላይ ቢጠናቀቅም፤ የመምረጥ እድል ያላገኙ ብዙ የሃገሪቱ ዜጎች እስከ ምሽት ድረስ ተሰልፈው ነበር ተብሏል። ይህ ደግሞ የሃገሪቱ ዜጎች ምን ያህል የመምረጥ ፍላጎት እንደነበራቸው ማሳያ ነው ተብሏል። በጠዋት ሊጀምር የነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በከባድ ዝናብ ምክንያት እንዲዘገይ የተገደደ ሲሆን፤ በኪንሻሳ ግዛት ደግሞ የምርጫ ማካሄጃ ማሽኖቹ በጊዜ ባለመቅረባቸው ህዝቡ ቁጣውን እየገለጸ ነበር። • "በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ • በምዕራብ ኦሮሚያ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደሉ ጉዳዩን ለመከታተል ወደ ቦታው ያቀኑት የሃገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ሃላፊ ኮርኔል ናንጋ ከፍተኛ ተቃውሞ ተሰንዝሮባቸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አንዳንድ መራጮች በሂደቱ ደስተኛ ባይሆኑም ለ17 ዓመት ሃገሪቱን የመሩት ፕሬዝዳንት በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ለማስረከብ በመወሰናቸውና የዚህ ታሪክ አካል መሆናቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል። ''በሃገራችን ለውጥ እንፈልጋለን፤ ሰላምና መረጋጋት ናፍቆናል፤ ብዙ የስራ እድልም ያስፈልገናል።'' በማለት ፊዴል ኢማኒ የተባለ መራጭ አስተያየየቱን ሰጥቷል። በተለያዩ ያሃገሪቱ ክፍሎች ከጸጥታ ችግር እስከ አስመራⶐች በሰአት አለመገኘት፤ ከኢቦላ ወረርሽኝ ስጋት እስከ ከባድ ዝናብ በፈተኑት ታሪካዊ ምርጫ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ መጠናቀቁ ለብዙ የሃገሪቱ ዜጎች እፎይታን የሰጠ ሆኖ አልፏል። ማርቲን ፋዩሉ፣ ፌሊክስ ሺሰኬዲ ሺሎምቦ እና ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪ ለፕሬዝዳንትነት የሚፎካከሩት እነማን ናቸው? ምንም እንኳን 21 እጩዎች ለፕሬዝዳንትነት እየተፎካከሩ ቢሆንም፤ የማሸነፍ እድል ያላቸው ግን ሶስቱ ብቻ ናቸው። በጸጥታ ችግርና በኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ምርጫው አይካሄድባቸውም በተባሉ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ደግሞ የራሳቸውን የምርጫ ወረቀት በማዘጋጀት በሃገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን እውቅና ያልተሰጠው ምርጫ ሲያካሂዱ እንደዋሉ ተገልጿል።
news-48659637
https://www.bbc.com/amharic/news-48659637
ደቡብ አፍሪካዊያኑ ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራቸውን አደረጉ
ደቡብ አፍሪካዊያኑ ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራቸውን ከኬፕታውን ወደ ካይሮ ያደረጉ ሲሆን በተሳካ ሁኔታም ለእረፍት ናሚቢያ አርፈዋል።
12 ሺ ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው ይህ በረራን ለማጠናቀቅም ስድስት ሳምንት ይፈጅባቸዋል ተብሏል። አራት መቀመጫ ያላት ይህች አውሮፕላን ከተለያየ ስፍራ በተውጣጡ 20 ተማሪዎች ነው የተገጣጠመችው። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ •"ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም "የዚህ ፕሮጀክት ዋናው አላማ አዕምሯችንን ይቻላል ብለን ካሳመንነው እንደሚቻል ለአፍሪካዊያን ለማሳየት ነው" በማለት የ17 ዓመቷ ፓይለት ሜጋን ዌርነር ትናገራለች። ታዳጊዎቹ አውሮፕላኗን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሦስት ሳምንታት የፈጀባቸው ሲሆን፤ የውስጥ አካሏን ከደቡብ አፍሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በመግዛት እንዲሁም በሺህዎች የሚቆጠሩ የውስጥ አካሏን መገጣጠም ችለዋል። •"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ "አውሮፕሏን ሳያት ማመን አልቻልኩም። በጣም ነው የኮራሁት፤ አውሮፕሏኗን ሳያት ልጄን ነው የምትመስለኝ። በጣም ነው የምወዳት" በማለት ከጓተንግ ግዛት የመጣችው የ15 ዓመቷ ኪያሞግትስዌ ሲመላ ገልፃለች። አክላም "ደስ በሚል ሁኔታ ነው አውሮፕላኗ የምትበረው፤ ዕይታው ልብን የሚሰርቅ" በማለት ከጆሃንስበርግ ኬፕታውን ከበረሩ በኋላ ተናግራለች። የአስራ አምስት ዓመቷ አውሮፕላን አብራሪ ይህ ሥራቸው ሌሎችንም እንደሚያነቃቃ ተስፋ አድርጋለች። "በመጀመሪያ የአካባቢው ማህበረሰብ በጣም ደንግጦ ነበር፤ አውሮፕላን ገጣጥመን ከኬፕታውን ካይሮ ልንበር ነው የሚለውን ዜና ማመን ከብዷቸው ነበር" የምትለው ታዳጊዋ ውጤቱን ካዩ በኋላ ግን ኩራት እንደተሰማቸው ተናግራለች። ይህንን ፕሮጀክት የጀመረችው የ17 ዓመቷ ሜጋን ስትሆን አንድ ሺ የሚሆኑ ተማሪዎች ፍላጎታቸውን ቢያሳዩም ባደረጉት ማጣራት20 ተማሪዎች ተመርጠዋል። የአብራሪነት ፍቃድ ካገኙት ስድስቱ ታዳጊዎች አንዷ ሜጋን ስትሆን፤ ግራጫ ቀለም ያላትንና በስፖንሰሮች አርማ የደመቀችውን አውሮፕላንን የማብረር ኃላፊነቱ በስድስቱም ትከሻ ላይ ወድቋል። ከየቀኑ ትምህርት በተጨማሪ የአብራሪነት ስልጠናዋን የወሰደችው ሜጋን "የአብራሪነት ፍቃድ ማለት ዲግሪ ማግኘት ማለት ነው" ትላለች። የአውሮፕላን አብራሪ አባቷ ደስ ዌርነር አራት ሰዎችን የሚይዝ አውሮፕላን ለመገጣጠም ሦስት ሺ ሰዓታት እንደሚወስድና ለ20 ታዳጊዎችም ሲከፋፈል ሦስት ሳምንታትን እንደሚፈጅ ሞያዊ አስተያየቱን ሰጥቷል። አንዳንድ የአውሮፕላኑ ክፍሎችና ሞተሩ በሰለጠኑ ሰዎች የተገጠሙ ሲሆን አጠቃላይ አውሮፕላኑ የተገጣጠመው በታዳጊዎቹ ነው። ታዳጊዎቹ በናሚቢያ ካረፉ በኋላ የመጨረሻ መዳረሻቸው ከሆነችው ግብፅ ከመድረሳቸው በፊት በዚምባብዌ፣ ማላዊ፣ ታንዛንያ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደሚያርፉ ተዘግቧል።
news-46285744
https://www.bbc.com/amharic/news-46285744
የወሎ ምድር ነዳጅ አፈለቀ እየተባለ ነው፤ ምን ያህል እውነት ነው?
በወሎ ነዳጅ ፈለቀ ተባለ፡፡ ወሬው በማኅበራዊ ሚዲያ ሞልቶ ፈሰሰ፡፡ አንዳንዶች ዜናውን በምሥልም በሰው ምስክርም አስደግፈውታል።
ቢቢሲ አማርኛ ወደ ደቡብ ወሎ ለገሂዳ ወረዳ በደወለበት ጊዜ አቶ ተመስገን አሰፋን አገኘ፡፡ ተመስገን የወረዳው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ነው፡፡ በአካል ቦታው ድረስ ሄዶ ነገሩ ሐቅ ስለመሆኑ አረጋግጧል፤ ነዳጁ ዓለት ሰንጥቆ በአቅራቢያው ወደሚገኝ 'መቸላ' ወንዝ እንደሚገባም ታዝቧል። በእርግጥ አቶ ተመስገን የተመለከተው ባዕድ ፈሳሽ ነዳጅ ነው? "ማህበረሰቡ በፕላስቲክ ጠርሙስ ነዳጅ እየቀዳ ይወስዳል" የቪዲዮና የፎቶግራፍ ማስረጃዎችን በጥንቃቄ የያዘው ተመስገን ነዳጅ ስለመሆኑ አንድ ሁለት እያለ ምስክር ይቆጥራል። "ከሚፈልቀው ነዳጅ ጨልፈን ክብሪት ስንለኩስበት ይቀጣጠላል" አንድ፤ "ነዋሪዎች ነዳጁን በፕላስቲክ ጠርሙስ እየቀዱ ይወስዱ ነበር" ሁለት፤ "ገና ከሩቁ የነዳጁ ሽታ ይጣራል" ሦስት፤ "ለሺ ዓመታት የነበረ ነው" የነዳጅ ክምችቱ ይገኝበታል የተባለው ሥፍራ በወረዳው 0-10 ቀበሌ ልዩ ቦታው ጎራና ት/ቤት አቅራቢያ ነው። አካባቢው ቆላማና ቁልቁለታማ በመሆኑ ከወረዳው ከተማ ወይን አምባ በእግር ለመድረስ አንድ ሰዓት ይወስዳል። ይሄ ወጣ ገባ መልክአ ምድር ለነዳጁ ጎብኚዎች ብቻ ሳይሆን ለነዳጅ አውጪዎችም ፈተና ሳይሆን አልቀረም። ስለዚህ ጉዳይ ወደ ኋላ ከባለሙያ ጋር እንመለስበት። • «በሸካ ዞን የመንግሥት ቢሮዎች ለወራት ሥራ ፈተዋል. . .» የወሎ ሰው በድንገተኛ አግራሞት ሲያዝ 'አጃኢብ' ነው ይላል፤ ለመሆኑ የሚመለከተው የፌዴራል መንግሥት ይህንን 'አጃኢብ' ሰምቶት ይሆን? በኢፌድሪ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል መንገሻ "ነገሩ ትንሽ ተጋኖ ይሆናል እንጂ ነዳጅስ ነዳጅ ነው" ካሉ በኋላ "ግን እኮ ይሄ አዲስ ነገር አይደለም" ይላሉ። "ነዳጁ የዐለት ግድቡን ጥሶ አካባቢውን አጥለቅልቆታል" የሚለውን የማኅበራዊ ሚዲያ ወሬን ነው 'ተጋኗል' ያሉት፡፡ "ታዲያ ያልተጋነነው እውነት ምንድነው?" አልናቸው፤ አቶ ሚካኤልን፡፡ "የታየው ነዳጅ ነው፡፡ የኛም ባለሙያዎች ሁለት ሦስት ጊዜ ሄደው ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡" ታዲያ ምንድነው የሚጠበቀው? ለምን አይወጣም…? ዶ/ር ቀጸላ ታደሰ በሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ ባለሙያ ናቸው፡፡ ይህንኑ ጥያቄ አነሳንላቸው፤ ‹‹እንደምትለውማ ቢሆን እኛው በዶማ ቆፈር ቆፈር አድርገን አናወጣውም ነበር?" ሲሉ ከቀለዱ በኋላ በደቡብ ወሎ የታየው ዘመን ያስቆጠረ እንጂ አዲስ ክስተት እንዳይደለ ያብራራሉ፡፡ የኢትዯጵያ የነዳጅ ፍለጋ እንክርት 70 ዓመት አልፎታል። እስከዛሬም አመርቂ ውጤት አልተገኘም። ከኦጋዴን በስተቀር። ያም ሆኖ በወሎ ዙሪያ ላለፉት አሥር ዓመታት የነዳጅ ፈላጊ ኩባንያዎች ጠፍተው አያውቁም፡፡ ዶ/ር ቀጸላ ነገሩን ከሥር መሠረቱ ያስረዳሉ። ለነዳጅ ፈላጊዎች ፍቃድ ሲሰጥ መጀመሪያ ለአራት ዓመት (Initial Exploration License) ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያ ይበል የሚያሰኙ ሁኔታዎች ሲታዩና የይራዘምልን ጥያቄ ሲያቀርቡ ተጨማሪ ሁለት-ሁለት ዓመት ይፈቀድላቸዋል፡፡ በድምሩ ስምንት ዓመት መሆኑ ነው፡፡ በእነዚህ የተራዘሙ የፍለጋ ዓመታት ታዲያ አንድ ኩባንያ ዝርዝር ጥናት አድርጎ፤ የከርሰ ምድር ናሙናዎችን ወስዶ አጥጋቢ ሲሆን ብቻ ወደ ቁፋሮ ሊገባ ይችላል፡፡ ያም ሆኖ የነዳጅ ክምችቱ ኖሮ ነገር ግን ነዳጁ ቢወጣ ለረዥም ዓመታት የማይዘልቅ ሲሆን፣ ወይም በሌላ የአዋጪነት ምዘና ፍለጋው ባይሰምር ለፍለጋ የወጣው ወጪ ቀልጦ ይቀራል፡፡ ይህ ወጪ በሁኔታዎች ተለዋዋጭ ቢሆንም ቀላል የሚባል አይደለም። በትንሹ ሩብ ቢሊዮን ብር ጠራርጎ ይወስዳል። • ባለፉት ሁለት ዓመታት 700 ሺህ ሰዎች ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለዋል በዚሁ የደቡብ ወሎ ነዳጅ ፈለቀ በተባለበት ሥፍራ ፋልከን የሚል ስም ያለው አንድ የእንግሊዝ ኩባንያ በፍለጋ ዘለግ ያሉ ዓመታትን ተንከራቷል። የሙከራ ቁፋሮ ለማድረግም በሦስት ማዕዘናት ዳስ ጥሎ ነበር፡፡ በፋይናንስ ምክንያት አልቀናውም፡፡ "አንዱ ችግር የጂኦሎጂውና የመልክዓ ምድሩ ምቹ አለመሆን ነው። ረቂቅ ቴክኖሎጂንም ይጠይቃል። አካባቢው ክምር አለው። እንደ ሶማሌ አካባቢ ዝርግ መሬት አይደለም። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ካፒታል ይጠይቃል። ፋልከን ያን ያህል ካፒታል አልነበረውም። ከአራት ዓመት በፊት ከአካባቢው ነቅሎ የወጣውም ለዚሁ ነው። ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ውል ያቋረጠበት ይህ ኩባንያ በአካባቢው ትምህርት ቤት ሳይቀር አስገንብቶ እንደነበር አቶ ሚካኤል ለቢቢሲ ተናግረዋል። "በቅርቡ ነዳጅ ፈላጊ ኩባንያ ይገባል" ዶ/ር ቀጸላና የሥራ ባልደረቦቻቸው ይህን የወሎ ክፍል በብዙ ተመላልሰውበታል። ጥናትም ሠርተውበታል። "ነዳጅ መፍለቁን እያየን ቸል ማለት ነው በቃ?" አልናቸው። "ገንፍሎ መውጣቱስ የሚነግረን ምንድነው?" "እርግጥ ነው ችላ ተብሎ የሚታለፍ አይደለም። መንግሥት ያውቀዋል፤ ባለሙያዎች ጥናት ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ። ነገር ግን አንድ ቦታ ፈለቀ ማለት ነዳጅ አለ ማለት አይደለም። ከብዙ ማይል ርቀት እየመጣ ሊሆን ይችላል።" ይህ ግን ምን ማለት ይሆን? መሬቱ በተለያየ ምክንያት በአንዳች ቦታ ስንጥቅ ይኖረዋል፤ ስንጥቅ አግድም ሊሆን ይችላል፡፡ ያንን ተከትሎ ነዳጅ ሊፈልቅ ይችላል። ነዳጁ ከዚያ ሥፍራ ስለመኖሩ መናገር የሚቻለው ግን በብዙ ጥናት ብቻ ነው። ዶክተር ቀጸላ ነገሩ ውስብስብ እንደሆነ ከገለጹ በኋላ ለማብራራት ሞክሩ። የጂኦሎጂ ሁኔታ ማለት 'በዘቀጤ ዐለት' የተሠራ ሊሆን እንደሚችል፣ እሳተ ጎመራ የወለደው ዐለት ወይም ሁሉንም ያቀላቀለ ዐለት ሊኖር ወይም በዘመናት የተቀየጠ እነዚህን ሁሉ ያቀላቀለ የጂኦሎጂ ዓይነት በቦታው ሊኖር እንደሚችል ዘረዘሩ። "ይህ በሙሉ ሳይጠና [ክምችቱ] ትንሽ ነው ትልቅ ነው አይባልም።" ደቡብ ወሎ ሰሞኑን ስለታየው ሲናገሩም "ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚባለው አይደለም፤ አገር እየበከለ ነው የሚባው ዉሸት ነው፤ ሆኖም በቅርቡ አዲስ ኩባንያ በወሎ ፍለጋ ሊጀምር በዝግጅት ላይ ነው።" "አንዳንዴ ዕድልም ይጠይቃል. . ." የነዳጅ ምልክቶች ከታዩ በኋላ ምን ያህል ጊዜን ይወስዳል? አቶ ሚካኤል "በብዙ ሁኔታዎች ይወሰናል" ይላሉ። የኩባንያው የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ብቃት፤ የአካባቢው የዐለት አፈጣጠር፤ ጠቅላላ መልክዓምድር፣ አዋጪነት. . .ወዘተ ጊዜውን ሊወስኑት ይችላሉ። ዶ/ር ቀጸላ በበኩላቸው የተፈጥሮ ጋዝም ሆነ ነዳጅ በጥምረት አልያም ለየብቻ ሊገኙ እንደሚችሉ ካወሱ በኋላ ሆኖም ሥራው ብዙ ሚሊዮን ዶላር እና ውስብስብ ቴክኖሎጂን እንደሚጠይቅ ያሰምሩበታል። "አንዳንዴ ዕድልም ሳይጠይቅ አይቀርም።" የወሎው ክስተት ግን ለአገሪቱ አዲስ አይደለም ይላሉ። ምዕራብ ኦጋዴን ደርከሌ፣ ገናሌ አካባቢ፣ በምሥራቅ ደግሞ ገለምሶ ልክ እንደ ወሎ ሁሉ ነዳጅ ፈልቆ ያውቃል። እንደ ኦጋዴን የተፈተሸ የኢትዮጵያ ክፍል ባይኖርም። እስከአሁን አገሪቱ የቀናትም በኦጋዴን ተፋሰስ በኩል ነው፤ በሂላላና በኤልኩራን። ለጊዜው ግን ወሎ የጠራ ነዳጅ ለማግኘት ዓመታትን መጠበቅ ሳይኖርባት አይቀርም። • ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ዘመቻው ብሔር ላይ ያነጣጠረ ነው?
news-44402803
https://www.bbc.com/amharic/news-44402803
የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ከሥልጣናቸው ተነሱ
ጄኔራል አደም መሐመድ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።
ጀኔራል አደም መሃመድ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳሬክተርነት ቦታን ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ነው የሚረከቡት። አቶ ጌታቸው አሰፋ ለበርካታ ዓመታት የሃገሪቱን የደህንነት መስሪያ ቤት በበላይነት የመሩ ሲሆን ስለእርሳቸው የአደባባይ ማንነት ብዙም የሚታወቅ ነገር የለም። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ለረጅም ዓመታት በቦታው ባገለገሉት ጀኔራል ሳሞራ የኑስ ቦታ ተተክተው የሃገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እንዲሆኑ ሾመዋቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ማዕረጋቸው ተነስቶ ከሠራዊቱ የተሰናበቱት ሜጄር ጀኔራል ዓለምእሸት ደግፌና ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ለሃገራቸው የከፈሉት መስዋዕትነትን እውቅና በመስጠት ማዕረጋቸው እንዲመለስና ከሙሉ የጡረታ ጥቅማቸው ጋር ጡረታ እንዲወጡ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ገልፀዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ጨምሮ እንደገለጸው፤ በተለያዩ የመንግሥት ሃላፊነቶች ላይ ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉት አቶ አባዱላ ገመዳ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት አቶ ግርማ ብሩ በጡረታ ተሰናብተዋል። አቶ አባዱላ ገመዳ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤነት ተነስተው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሆነው በመሾም ለሁለት ወራት ያህል ቆይተዋል።
45528565
https://www.bbc.com/amharic/45528565
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት ፈጸመ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አልሸባብ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ።
የምስራቅ ምድብ ሄሊኮፕተሮች ስኳድሮን አልሸባብ ላይ እርምጃ እንደወሰዱ አየር ኃይሉ ለኢቴቪ አስታውቋል። የተዋጊ ሄሊኮፕተሮቹ ከደቡብ ምስራቅ እዝ እግርኛ ጦር ጋር ቅንጅት በመፍጠር አልሸባብ ላይ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ ባካሄደው ኦፕሬሽን በአልሸባብ ላይ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ እና ሞራላዊ ውድመት አድርሰናል ሲሉ ለኢቴቪ ተናግረዋል። አየር ኃይሉ የሃገሪቱን የአየር ክልል ከመቼውም በላይ በአስተማማኝ ሁኔታ ከመጠበቅ በተጨማሪ ለምድር ኃይሉ ድጋፍ በመስጠት በሃገሪቱ ላይ ሊቃጣ የሚችል ማንኛውም አይነት ወረራ እና የሽብር ድርጊት በአጭር ጊዜ ለመመከት የሚያስችል ጠንካራ ተቋም ነው ሲሉ ብርጋዴር ጀነራሉ ተናግረዋል። ብርጋዴር ጀነራል ይልማ መርዳሳ በኦፕሬሽኑ ላይ የተሳተፉት የጦር ሥራዊት አባላትን አመስግነዋል።
news-50217646
https://www.bbc.com/amharic/news-50217646
የሠርጋቸው ቀን ምሽት ለትዳራቸው መፍረስ ምክንያት የሆነባቸው ሴቶች
ሠርግ በየትኛውም የዓለም ክፍል አስደሳች አጋጣሚ ቢሆንም የሠርግ ሥነ ሥርዓቶች ከባድ የሥነ ልቦና ስብራት የሚያስከትሉ የሚሆኑባቸው የዓለም ክፍሎችም አይታጡም።
በበርካታ የአረቡ አገራት ሴቶች ሲያገቡ ክብረ ንጽህናቸውን እንደጠበቁ እንዲሆኑ ይጠበቃል። የሠርጋቸው ዕለት ቀሪ ህይወታቸውን ሲኦል ያደረገባቸው ሴቶች የህይወት ልምዳቸውን ለቢቢሲ አጋርተዋል። የ23 ዓመቷ ሶማያ ትወደው የነበረው ፍቅረኛዋን እንድታገባ ስላልፈቀዱላት ከቤተሰቦቿ ጋር ትልቅ ግጭት ውስጥ ገብታ ነበር። ሶሪያዊቷ ሶማያ በደማስቆ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሁፍ ዲግሪዋን ለማግኘት ትምህርቷን ወደ ማጠናቀቁ ነበረች። ምንም እንኳ ቤተሰቦቿ ፍቅረኛዋ ኢብራሂምን እንዳታገባው ቢከለክሏትም ልታገባው ወሰነች። • "ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም'' የብዙ ሴቶች የጤና እክል የሠርጋቸው ዕለት ምሽት ግን ፍቅር የሚባል ነገር በመካከላቸው እንደነበር እስክትጠራጠር ድረስ ነገሮች ወደ መጥፎ ተቀየሩ። የሠርጋቸው ዕለት ምሽት ወደ መኝታቸው ሲሄዱ ፍቅረኛዋ እና ባሏ ኢብራሂም እሷ ምን እየተሰማት እንደሆነ ለማወቅ ግድም ሳይሰጠው ወሲብ እንዲፈፅሙ አደረገ። ሶማያ በዝምታ የሚፈልገውን እንዲያደረግ ከመፍቀድ ባለፈ ልትታገለው አልሞከረችም። አንሶላ ላይ ምንም ዓይነት ደም ባለማየቱ ኢብራሂም በጥርጣሬ ተመለከታት። ጥርጣሬው ገብቷት ነገሩን ለማብራራት ሞከረች። ብዙ ሴቶች ድንግልናቸው ሲገሰስ የሚደሙ ቢሆንም የማይደሙ እንዳሉም የህክምና ባለሙያዎች ያረጋግጣሉ። ሃኪሞች እንደሚሉት ነገሩ ከሴት ሴት ሊለያይም ይችላል። ድንግልናቸው የግድ በቀዶ ህክምና እንዲሄድ የሚደረጉም ሲኖሩ ያለ ድንግልና የሚወለዱ ሴቶች እንዳሉ እንዲሁም ልጅ ሳሉ በሚደርስ ድንገተኛ ጉዳት ድንግልናቸውን የሚያጡም አሉ። • እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ''ደካማ ነው'' ተባለ የሶማያ ማብራሪያ ለውጥ አላመጣም። "እንደ ጦር በሚወጉ አይኖቹ ተመለከተኝ። በዚህ አስተያየቱ ሳያውቀው እንደገደለኝ ነው የተሰማኝ" በማለት ያን አስደንጋጭ አጋጣሚ ትገልጻዋለች። ሊያናግራት አልፈለገም ችሎት የቀረበ ተጠርጣሪ የመሆን ስሜት ተሰማት። አንዳቸው ስለ ሌላኛቸው ብዙ እንደሚያውቁ ያስቡ የነበረ ቢሆንም የድንግልና ምልክት ባለመታየቱ ሁሉም ነገር እንዳልነበር ሆነ። 'ደም የነካ አንሶላ' ለወንዶች ምናቸው ነው? አያት ቅድመ አያቶቿ በዚህ ቢያልፉም ፍቅረኛዋ የተማረ ሰው በመሆኑ ራሷን እዚህ ቦታ ላይ አገኘዋለሁ ብላ አላሰበችም። የተገሰሰ ድንግልናን በቀዶ ህክምና መመለስ እንደሚቻል የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ። ባሏ ኢብራሂም በሠርጋቸው ማግስት ድንግል እንደነበች ለማረጋገጥ ወደ ዶክተር እንዲሄዱ ጠየቃት። • ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን? ምርመራ ያደረገላት የማህፀን ሃኪም ድንግልናዋ ወፍራም በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ሊገሰስ የሚችለው ስትወልድ ብቻ እንደሆነ ገለጸላቸው። ባሏ በእፎይታ ተንፍሶ በፈገግታ ተመለከታት። ግን ሶማያ ልትፈታው ወስናለችና ዘግይቶ ነበር። "የተሰማኝን በቃላት መግለጽ አልችልም። የኔነቴን ዋጋ ወደ አንድ ድንግልና የሚባል ተራ ነገር ከቀነሰ ሰው ጋር ቀሪ ህይወቴን ልኖር አልችልም። እኔ ሰው እንጂ ቁራጭ ሥጋ አደለሁም" ትላለች። አጋጣሚው ሶማያ ላይ ከባድ የሥነ ልቦና ጉዳት አድርሷል። ድንግል ነን ካሏቸው ፍቅረኞች ጋር ወሲብ በፈጸሙ በመጀመሪያ ቀን ደም ባያዩ ምን እንደሚሰማቸው እድሜያቸው ከ20 - 45 የሚሆኑ 20 ወንዶችን ቢቢሲ አስተያየት ጠይቋል። ከእነዚህ ውስጥ ምሁራን፣ ዶክተሮችና መምህራን ይገኙበታል። በጥቅሉ ሰፊ ምልከታ አላቸው የሚባሉ ወንዶች ናቸው አስተያየት ሰጪዎቹ። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የብዙዎቹ መልስ ደም ማየታቸው ለቀጣዩ ፍቅርና የትዳር ህይወታቸው አስፈላጊ ምልክት ነው የሚል ነበር። የ45 ዓመቷ ጁማናህ በሶሪያዋ አሌፖ የኖረችው ጁማናህ ወደ ቤልጀም የሄደችው እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ነበር። የ19 ዓመት ወጣት ሳለች ነው አባቷ ለቅርብ ዘመዳቸው የዳሯት። እንደ ብዙ ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ሁሉ በአካባቢያቸው በሠርግ ምሽት በሙሽሮች መኝታ ቤት ዙሪያ ሆኖ ድንግልና እስኪገሰስ መጠበቅ ባህል ነበር። ዛሬም ድረስ በደማቅ ትውስታ የሚታያት ያ ምሽት ለጁማናህ የስቃይ ነበር። ባሌ ነገሩን ቶሎ ፈጽሞ ውጭ ለሚጠብቁት ዘመዶቻችን የምስራቹን ለማድረስ ተጣደፈ። ምንም ሊያናግረኝ አልፈለገም። • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? "እንደዚያ ያለ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ስብራት ውስጥ ሆኜ የባሌ ብቸኛ ጭንቀት ደም የነካው ጨርቅ የማየት ነበር" ስትል ታስታውሳለች። "በዚያች ምሽት እኔ አልደማሁም ስለዚህ ባሌ ደምጹን አጥፍቶ ተቀመጠ። ዓይኑ ግን እንደ እሳት ገረፈኝ "የምትለው ጁማናህ ለአንድ ሰዓት ያህል በድንጋጤና በፍርሃት መናወጧን ትናገራለች። እስኪነጋ ለመጠበቅ ትዕግስት ያጡት ቤተሰቦቿ በዚያው የሠርጓ ዕለት ሌሊት ወደ ማህፀን ሃኪም ወሰዷት። "አስታውሳለሁ ሃኪሙ እንደ አባት ነበር ያጽናናኝ" ሳትፈልግ በቤተሰብ ተገዳ በአደባባይ ካዋረዳት ባሏ ጋር ለ20 ዓመታት ለመኖር ተደደች። በነዚህ ጊዜያት አራት ልጆችንም ወልዳለች። ድንግልናን በቀዶ ህክምና መመለስ ሮዛና ከዓምስት ዓመት እጮኛዋ ጋር ተለያይታለች። ምንም እንኳ ከጋብቻ በፊት ወሲብ አልፈፅምም ብላ ብትቆይም ዞሮ ዞሮ መጋባታችን አይቀርም ለሚለው የእጮኛዋ ውትወታ በመጨረሻ እጅ ትሰጣለች። ቅርብ ግንኙነት ያላቸው የሁለቱ ቤተሰቦች ተቀያይመው ይራራቃሉ። ከዚያም ሮዛናና እጮኛዋ ይለያያሉ። በአካባቢው ድንግል ሆኖ አለመገኘት የሞትና የሽረት ጉዳይ በመሆኑ ሮዛና ከባድ ችግር ውስጥ ወደቀች። በመጨረሻ በጓደኛዋ ምክር በቀዶ ህክምና ሰው ሰራሽ ድንግልና እንዲኖራት ለማድረግ ወሰነች። "በዚያ ቀላል ቀዶ ህክምና ባይሆን ዛሬ በህይወት አልኖርም ነበር" ትላለች ሮዛና።
news-47816901
https://www.bbc.com/amharic/news-47816901
አውሮፕላኑ 'ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ነበር'
የኢትዮጵያ አውሮፕላን ከመውደቁ በፊት በርካታ ጊዜ የአፍንጫ መደፈቅ ገጥሞት እንደነበር የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ አመልክቷል።
ባለስልጣናት እንደገለጹት አብራሪዎቹ አውሮፕላኑን ለማትረፍ በተደጋጋሚ የቦይንግን መመሪያ ተከትለው ጥረት አድርገዋል። የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ "አብራሪዎቹ ጥረት ቢያደርጉም ሊቆጣጠሩት ግን አልቻሉም፤ አደጋው እንዳይከሰትም አብራሪዎቹ ሁሉንም ማድረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄ አድርገዋል" ብለዋል። ሪፖርቱ ስለአውሮፕላኑ መከስከስ ምን ይላል? የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ማንንም ተወቃሽ አላደረገም። ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችንም ከመስጠት ተቆጥቧል፤ ነገር ግን ቦይንግ የአውሮፕላን መቆጣጠሪያ ሥርዓቱን ማስተካከል እንዳለበትና የአቪየሽን ባለስልጣናት ደግሞ ቦይንግ 737 ማክስ ከመብረሩ በፊት ሁሉንም ችግሮቹን መፍታቱን ቢያረጋግጥ መልካም ነው የሚል ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል። • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም አብራሪዎቹን እጅግ የሚኮሩባቸውና ከፍተኛ የሙያ ክህሎት ያላቸው ቢሆኑም እንዳለመታደል ሆኖ ግን የአውሮፕላኑን ከመከስከስ ሊያተርፉት አልቻሉም ብለዋል። የሪፖርቱ ውጤት ለቦይንግ ምን ትርጉም ይኖረዋል? በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሁለት የመከስከስ አደጋ አጋጥሞ 346 ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱም የመጀመሪያ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት የቦይንግ 737 ማክስ አዲሱ ስሪት አገልግሎት መስጠት ማቆሙንና አውሮፕላኑ በተደጋጋሚ የአፍንጫ መደፈቅ ገጥሞታል። ሁለቱም አደጋዎች ላይ አንድ አይነት ሃሳብ ነው የሚነሳው። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? በአደጋው ዘመድ ወዳጆቻቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርን መገመት ሊያዳግት ይችላል። ነገር ግን አምራቹ ኩባንያ ምን ያህል ትርፍ ሊያጣ እንደሚችልና ዝናው ዝቅ እንደሚል መገመት ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ እንዲሆኑ ተደርገዋል። በርካታ ትዕዛዞችም ተሰርዘዋል፤ ወደፊትም እንዳይታዘዝ ተጽዕኖ አሳድሯል። ቦይንግ በተፎካካሪው ኤር ባስ የተሰራውን ዘመናዊ እና ነዳጅ ቆጣቢ የሆነውን A320 ለመገዳደር ታሳቢ አድርጎ ነበር 737 ማክስን ለገበያ ያቀረበው። ይሁን እንጅ አንድ 737 አውሮፕላንን በማብረር ልምድ ያለው አብራሪ እንደገለጸው ለኤር ባስ ምላሽ ተብሎ የተሰራው አዲሱ አውሮፕላን ሁለቱን አደጋዎች ያስከተለና 'እንከን' ያለበት ነው። ቦይንግ ችግሩን ለማስተካከል እየሰራ ነው። አውሮፕላኑ የደህንነት ማረጋገጫ አግኝቶ አየር ላይ የሚወጣበትን መንገድ መፈለግም ይኖርበታል። ለመሆኑ ከአደጋው በኋላ ቦይንግ ምን አደረገ? ቦይንግ ለአብራሪዎች አውሮፕላኑን እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸው የበረራ ደህንነት መመሪያ አስተላልፏል። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? ለሁሉም ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ካሁን በፊት እንደ አማራጭ ያገለግሉ የነበሩትን ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን አዘጋጅቷል። ቦይንግ 737 ማክስን የመረዳት አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠናም እያዘጋጀ ነው። ይህ ማለት ግን አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ችግር ስላለበት እንዳልሆነ ቦይንግ ይከራከራል።
48778225
https://www.bbc.com/amharic/48778225
ከጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጋር አጭር ቆይታ
ቢቢሲ ትናንት የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁንን በስልክ ያነጋገራቸው የክልሉ አመራሮች የቀብር ሥነ-ስርዓት ለመካፈል ባህር ዳር ሳሉ ነበር።
አቶ ንጉሱ ትናንት በባህር ዳር በተካሄደው የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል የተወጣጡ እንግዶች፣ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ዘመድ እና ቤተሰብ እንዲሁም የክልል እና የፌደራል መንግሥት አካላት እንደተገኙ እና የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ፕሮቶኮሉ በሚፈቅደው መሠረት መካሄዱን ተናግረዋል። ''ትልቅ ቁጭት እና ሃዘን የታየበት ሥነ-ሥርዓት ነበር። እንግዶች ንግግር ሲያደርጉ ሲቃ እየተናነቃቸው ነበር። ለክልላቸው እና ለሃገራቸው የከፈሉትን መስዋዕትነት በማንሳት ከስማቸው በላይ ታሪክ ሠርተው ያለፉ መሆኑን የሚያመላክቱ መልዕክቶች በልጆቻቸው እና በሌሎች ተደምጧል'' ብለዋል። • የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ • የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ በላሊበላም የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን በማስታወስ፤ በላሊበላ የነበረው ስሜት እና ሥነ-ሥርዓት ምን ይመስል ነበር ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ንጉሱ ሲመልሱ፤ ''በባህር ዳር የነበረውን ሥነ-ሥርዓት ነበር ስንከታተል ነው የነበርነው። እዚያ ስለነበረው ነገር መረጃው የለኝም። መረጃው እንደደረሰን እናደርሳችኋላን'' በማለት በደምሳሳው አልፈውታል። የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው አሟሟት ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ አሟሟትን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን የተጠየቁት አቶ ንጉሱ ''ኦፕሬሽኑን ያከናወነው የጸጥታ መዋቅሩ ነው። ከባህር ዳር አቅራቢያ ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ነው ቦታው። ነገር ግን በዝርዝር የነበረውን ሂደት መረጃው ሲገኝ እናሳውቃለን። አሁን መረጃው የለኝም'' ብለዋል። ጄነራሎቹን ገድሏል ስለተባለው የግል ጠባቂ ቅዳሜ ሰኔ 15/2011 ምሽት ጠቅላይ ኤታማዦር ጄነራል ሰዓረ መኮንን ከአጋራቸው ጄነራል ገዛዒ አበራ ጋር በገዛ ጠባቂያቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው። በቀጣዩ ቀን የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት በሰጠው መግለጫ ጄኔራሉን እና ወዳጃቸውን በጥይት መትቶ ገድሏል የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ አስታውቆ ነበር። ሰኞ ከሰዓት ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሻው ጣሰው ጄኔራሎቹን ገድሏል የተባለው ጠባቂ ራሱን ማጥፋቱን ተናገሩ። ሰኞ ምሽቱን ደግሞ ፌደራል ፖሊስ ቀደም ሲል ራሱ የሰጠውን መግለጫ አስተባብሎ ጠባቂው በሕይወት እንደሚገኝ አስታውቀ። • የባለአደራ ምክር ቤት አባላት ከ'መፈንቅለ መንግሥቱ' ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ቀረቡ እኛም እርስ በእርስ የሚጣረሱ መረጃዎች እንዴት ሊወጡ ቻሉ? ጄነራሎቹን ገድሏል የተባለው ጠባቂስ አሁን በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛል? ስንል ለጠቅላይ ሚንሰትሩ የፕሬስ ሴክሬተሪያት ኃላፊ አቶ ንጉስ ጥላሁን ጥያቄያችንን አቅርበንላቸዋል። አቶ ንጉሱ የመረጃ ክፍተቱ እንዴት ሊፈጠር አንደቻለ ሲያስረዱ ''በአዲስ አበባም ይሁን በባህር ዳር የተፈጠረው ችግር ድንገተኛ ነው፤ አደናግጧል፤ አደናብሯል። ሁሉም መረጃ በአንድ ግዜ አይገኝም። በወቅቱ የሚደርሱ መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሃን ሲሰጡ ነበረ። መረጃዎች የሚስተካከል፤ የሚታረም ነገር ሊኖራቸው ይችላል። ሰው ነው የሚሰራው፤ ሰው ነው የሚናገረው። መረጃው ደግሞ ታቅዶ፣ ተደራጅቶ፣ ተገምግሞ የሚሰጥ ዓይነት መረጃ አይደለም። እንደዚህ አስቸኳይ በሆነበት ሰዓት፣ ሕብረተሰቡ መረጃ በሚፈልግበት ሰዓት፣ መገናኛ ብዙሃን በሚያጣድፉበት ሰዓት እንዲህ ዓይነት ስህተቶች አያጋጥሙም ማለት አይደለም'' ይላሉ። ተጠርጣሪው እንዴት በቁጥጥር ሥር እንደዋለ እና አሁን ስለሚገኝበት ሁኔታ የተጠየቁት አቶ ንጉሱ፤ ''የግል ጠባቂው በጄነራሎቹ ላይ እርምጃ ከወሰደ በኋላ ተታኩሶ ነበረ። በዚህም የተኩስ ልውውጥ እሱም ላይ እርምጃ እንደተወሰደበት እና ወደ ህክምና ሥፍራ ተወስዶ ጥበቃ እየተደረገለትና የጤና ክትትል እያደረገ ነው'' ነው ሲሉ መልሰዋል። ''የጤንነቱን ጉዳይ ሃኪሞች፤ የጥበቃውን ሁኔታ ደግሞ የጸጥታ መዋቅሩ እየሰሩ ነው። ሌሎች ጉዳዮች ወደፊት የሚጠሩ ይሆናሉ'' በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። 'በመፍንቅለ መንግሥቱ ሙከራ' ጉዳት የደረሰባቸው እና በቁጥጥር ሥር የዋሉ ምን ያክል ናቸው? ''ጉዳዩ ከተከሰተ ወዲህ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የተደረጉ ሰዎች አሉ። አሁንም ሥራው እየተሠራ ነው። ቁጥሩ በየጊዜው የሚለዋወጥ ስለሆነ በትክክል ይሄ ነው ብሎ መግለጽ አይቻልም። ሥራው የፖሊስ፣ የክልል ልዩ ኃይል እና የሃገር መከላከያ ሠራዊት ጥምር እንቅስቃሴ ነው። መረጃውም ያለው በጸጥታ መዋቅሩ እጅ ነው። የተደራጀ መረጃ ወደፊት ይሰጣል'' ሲሉ መልሰዋል። የኢንተርኔት ጉዳይ 'የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን' ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወሳል። የኢንተርኔት አገልግሎት ለምን እንዲቋረጥ ተደረገ? አግልግሎቱስ ክፍት የሚሆነው መቼ ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፤ ''በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ መስጠት አልችልም። የምገኘው ባህር ዳር ነው። ወንድሞቻችንን እየሸኘን ነው። ሌሎች አካላትን በጉዳዩ ላይ መጠይቅ ይቻላል'' በማለት አልፈውታል።
news-52452721
https://www.bbc.com/amharic/news-52452721
ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገሮችን እየረዳ ያለው ቢሊየነር ጃክ ማ ማነው?
በቻይና ቁጥር አንድ ባለ ሀብት ነው። ባለፈው ወር የትዊተር ገጽ ከፍቶ ከጻፋቸው መካከል “አንድ ዓለም አንድ ትግል” “በጋራ እናሸንፋለን” የሚሉት ይጠቀሳሉ።
ቢልየነሩ ጃክ ማ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ150 አገሮች የህክምና ቁሳቁስ እርዳታ አድርጓል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ ቬንትሌተርም ሰትቷል። ሆኖም ድርጊቱ ለተቺዎቹም ለደጋፊዎቹም ግልጽ የሆነ አይመስልም። የጃክ ማ ቸርነት የኮምኒስት ቻይና ነጸብራቅ ነው? ወይስ ግላዊ ጥረቱ ለፓርቲ ፕሮፖጋንዳ እየዋለ ይሆን? በእርግጥ እርዳታ የሚሰጣቸውን አገሮች ሲመርጥ የቻይናን ዲፕሎማሲ ተመርኩዞ ነው። ምናልባት ግን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በድርጊቱ ሳይቀኑ አልቀሩም። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ድጋፍ እናደርጋለን ካሉ የቴክኖሎጂ ሰዎች መካከል የትዊተር መስራች ጃክ ዶርሲ ይገኝበታል፤ አንድ ቢልየን ዶላር ሰጥቷል። ካንዲድ የተባለ ለኮቪድ-19 የተሰጡ እርዳታዎችን በደረጃ የሚያስቀምጥ ተቋም፤ የጃክ ማን አሊባባ 12ኛ ቦታ አስቀምጦታል። ይህም ቁሳቁስ ሳይቆጠር፣ ከገንዘብ እርዳታ አንጻር ብቻ ነው። እንደ ጃክ ማ የህክምና ቁሳቁስ ለሚያስፈልጋቸው አገሮች በስፋት ማከፋፈል የቻለ የለም። ካለፈው ወር መባቻ ጀምሮ ወደ አፍሪካ፣ እስያ፣ አውሮፓ እና ላቲን አሜሪካ ቁሳቁሶቹ ተልከዋል። ባለሀብቱ ለክትባት ምርምር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብም ሰጥቷል። በትውልድ ቀዬው ዢዣንግ የሚገኙ የህክምና ጥናቶች በ16 ቋንቋዎች እንዲተረጎሙም አድርጓል። የጃክ ማን ግለ ታሪክ የጻፈው ደንከን ክላርክ “የቻይና እርዳታ ሰጪ አውሮፕላን ከሃንግዡ አዲስ አበባ የመላክ አቅሙም ገንዘቡም አለው” ይላል። የብዙዎች ወዳጅ? ጃክ ማ ከተወዳጅ የእንግሊዘኛ መምህርነት ትልቁን የቻይና የቴክኖሎጂ ድርጅት ወደማቋቋም የተሸጋገረ ሰው ነው። ‘የምሥራቁ ዓለም አማዞን’ የተባለውን አሊባባ የጀመረው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1999 ሃንግዡ ከሚገኘው አነስተኛ ቤቱ ውስጥ ነበር። አሊባባ አሁን ላይ የዓለም ሁለተኛ ግዙፍ የምጣኔ ሀብት ማዕከል በሆነችው ቻይና ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ ሆኗል። በቻይና የድረ ገጽ ግብይት፣ በባንክና በመዝናኛ ዘርፍ ቁልፍ ቦታ አለው። መስራቹ ጃክ ማ ደግሞ ከ40 ቢሊዮን ዶላር በላይ አለው። ከቻይና ኃያላን አንዱም ነው። ከሦስት ዓመት በፊት ከአሊባባ መሪነት ወርዶ ትኩረቱን በጎ አድራጎት ላይ ቢያደርግም፤ አሁንም ከድርጅቱ ቦርድ የአንበሳውን ድርሻ የያዘው ጃክ ማ ነው። ኮሮናቫይረስን ለመዋጋት የሚያደርገው ድጋፍ የቻይና ፓርቲን ደንብ የተከተለ ይመስላል። የቻይና ጎረቤት እና ተፎካካሪ ከሆነችው ታይዋን ጋር ይፋዊ ግንኙነት ላላቸው አገሮች ድጎማ አልተሰጠም። ጃክ ማ ትዊተር ላይ ለ20 የላቲን አሜሪካ አገሮች እርዳታ እሰጣለሁ ብሏል። ታይዋንን የሚደግፉ እንደ ሄይቲ እና ሆንዱረስ ያሉ ግዛቶች የህክምና ቁሳቁስ እንደሚፈልጉ ቢያሳውቁም፤ ባለሀብቱ ከረዳቸው 150 አገሮች ዝርዝር ውስጥ የሉም። በእርግጥ የባለሀብቱ የተራድኦ ድርጅት ድጎማ የሚደረግላቸውን አገሮች ዝርዝር ይፋ ማውጣት እንደማይፈልጉ ገልጸዋል። ከኩባ እና ከኤርትራ ውጪ እርዳታ የተላከላቸው አገሮች ያለ ምንም ችግር ነው የደረሳቸው። ይህ ቸርነት ባለሀብቱን ዝነኛ አድርጎታል። የቻይና ሚዲያ የጃክ ማን ስም ከአገሪቱ መሪ ዢ ዢፒንግ ባልተናነሰ ሁኔታ ደጋግመው ሲጠሩም ይደመጣል። እንዲያውም ዢ ዢፒንግ ወረርሽኙ ከቁጥጥር ሳይወጣ በፊት ማስቆም ይችሉ ነበር ተብለው ሲተቹ፤ ጃክ ማ በአንጻሩ እየተሞገሰ ነው። የቻይና መንግሥት በኮቪድ-19 ክፉኛ ወደተጠቁ አገሮች የህክምና ባለሙያዎች እየላከ ነው። በተለይም የአውሮፓ እና ደቡብ ምሥራቅ እስያ አገሮች ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። ሆኖም ግን ቻይና የላከቻቸው የህክምና መሣሪያዎች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አይችሉም ተብሎ አገሪቱ ተተችታለች። ‘’የቻይና አፍሪካ ፕሮጀት’ ድረ ገጽ ዋና አርታኢ ኤሪክ ኦላንደር እንደሚለው፤ የጃክ ማ ድጎማ በመላው አፍሪካ እንዲመሰገን አድርጎታል። ባለሀብቱ መላው አፍሪካን እጎበኛለሁ ብሎ ቃል መግባቱ ይታወሳል። ከአሊባባ ኃላፊነቱ ከወረደ በኋላ ወደ አህጉሪቱ አዘውትሮ እየመጣም ነው። ከወራት በፊት አዲስ አበባ ተገኝቶ እንደነበርም ይታወሳል። ጃክ ማ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ዢ ዢፒንግ ጃክ ማን ይቀየሙት ይሆን? የቻይናው ፕሬዘዳንት ዢ ዢፒንግ ሁሌም መሞገስ ይፈልጋሉ። የሚቀናቀናቸውን ሰው መንግሥታቸው ኢላማ ሲያደርገም ታይቷል። ከዚህ ቀደም ታዋቂ ተዋንያን፣ ዜና አንባቢዎች፣ ቢልየነር በጎ አድራጊዎች ዘለግ ላለ ጊዜ ከሕዝብ እይታ ጠፍተው ነበር። አንዳንዶቹ ታስረዋል፤ የተቀሩት ደግሞ ፓርቲውን ለመደግፍ ቃል ከገቡ በኋላ ከእገታ ተለቀዋል። ጃክ ማ 2018 ላይ ከአሊባባ መሪነት የተነሳው ከኮምኒስት ፓርቲው በላይ እየገነነ ይሄዳል በሚል ፍራቻ ነው የሚል ጭምጭምታ እንደተሰማ አጥኚዋ አሽሊ ፌንግ ትናገራለች። ባለ ሀብቱ ግን በመንግሥት ግፊት ስልጣኑን እንዳልለቀቀ ተናግሯል። 2017 ላይ ጃክ ማ ከአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በትራምፕ ህንጻ ተገናኝተው ነበር። ዢ ዢፒንግ ግን ከትራም ጋር የተገናኙት ከወራት በኋላ ነበር። የባለሀብቱን ግለ ታሪክ የጻፈው ደንከን እንደሚለው፤ ጃክ ማ በወቅቱ ፈጣን እርምጃ ነበር የወሰደው። “ጃክ ማ በንግዱ ዘርፍ ለስለስ ያለ ውሳኔ ማስፈጸሚያ ነው። ፓርቲው እንዲህ አይነት ሚና የሚጫወቱ ሰዎች ስለሚስያቀኑት ነገሩ አስፈሪ ነው” ይላል። በእርግጥ ጃክ ማ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለ አንስቶ የኮምኒስት ፓርቲው አባል ነው። ነገር ግን “አሊባባ ፓርቲውን ቢወደውም ከፓርቲው ጋር በትዳር አይጣመርም” የሚል አዝማሚያ አለው። ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ድጎማ ሲያደርግ የፓርቲውን ይሁንታ ባይጠይቅም፤ የቻይና አምባሳደሮች እርዳታው በተላከባቸው አገሮች አውሮፕላና ማረፊያ በመገኘት አጋጣሚውን እየተጠቀሙበት ነው። ቻይና ታዋቂ ሰው እየፈለገች ስለሆነ፤ ከዚህ ቀደም ታዋቂነታቸው ችግር ውስጥ የከተታቸው ቻይናውያን የገጠማቸው አይነት እጣ ፈንታ ባለሀብቱ አይገጥመው ይሆናል። ኤሪክ ኦላንደር እንደሚለው፤ ጃክ ማ ለአፍሪካ የገባውን ቃል አክብሯል። ብዙ ታዋቂ ሰዎች እናደርጋለን ያሉትን ሳይፈጽሙ መቅረታቸውን እንደ ማሳያም ይጠቅሳል። ደንከን በበኩሉ፤ በአሊባባ ትርፋማነት ምክንያት ጃክ ማ ለቻይና ጠቃሚ ሰው ነው። ዓለም አቀፍ እውቅናውን እንዲሁም ከምድራችን ባለሀብቶች ጋር ያለውን ትስስር ተጠቅማ ቻይና ገጽታዋን ልትገነባም ትችላለች። ካንዲድ በተባለውና ለኮቪድ-19 የተሰጡ እርዳታዎችን በደረጃ በሚያስቀምጠው የአሜሪካ ተቋም ውስጥ የሚሠራው አንድሪው ግራቦይስ እንደሚናገረው፤ የጃክ ማ ልገሳ ቻይናንም እየጠቀማት ነው። “ቀድሞ አሜሪካ ትወስድ የነበረውን የድጋፍ መሪነት ሚና ቻይና እየወሰደች ነው” ይላል።
news-56156443
https://www.bbc.com/amharic/news-56156443
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጣልያን አምባሳደር በታጣቂዎች ተገደሉ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጣልያን አምባሳደር በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውን የጣልያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
አምባሳደር ሉቻ አታናሲዮ የተገደሉት ዛሬ ሲሆን ወደ ጎማ ለጉብኝት ከተንቀሳቀው የዓለም ምግብ ድርጅት ቡድን ጋር አብረው ነበሩ ተብሏል። የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለፈረንሳይ የዜና ወኪል እንዳረጋገጡት አምባሳደሩ ጥቃቱ እንደደረሰባቸው "ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል" ። አምባሳደሩን ለህልፈት ያበቃው ጥቃት የተፈፀመው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍል ነው። ከአምባሳደሩ በተጨማሪ የጣሊያን ፖሊስ ኃይል አባል የሆኑ ግለሰብ በካንያማሆሮ ከተማ አቅራብያ መገደላቸውን የጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጨምሮ በመግለጫው ላይ አመልክቷል። የፈረንሳይ ዜና ወኪል በበኩሉ በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ የአገሪቱን ጦር ኃይል ቃል አቀባይ ጠቅሶ እንደዘገበው ሁለት ሰዎች በጥቃቱ የተነሳ ህይወታቸው አልፏል። ቃል አቀባዩ ግን የሟቾችን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል። የቪሩንጋ ብሔራዊ ፓርክ ባለሥልጣን እንዳሉት ጥቃቱ እገታ ለመፈፀም ያለመ ነበር። በርካታ ታጣቂ ቡድኖች በሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ድንበር አካባቢ በሚገኘው የፓርኩ አካባቢ ይንቀሳቀሳሉ። የፓርኩ ጠባቂዎች በተደጋጋሚ በታጣቂዎች ጥቃት ይደርስባቸዋል፤ ይገደላሉም ተብሏል። የቪሩንጋ ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን በርካታ አገር ጎብኚዎች የሚያዘወትሩት ስፍራ ነው። ይህ በተራሮች እና በጥቅጥቅ ደኖች የተከበበው ብሔራዊ ፓርክ በ689 ጠባቂዎች ቢጠበቅም 200 ያህሉ በሥራ ላይ እያሉ መገደላቸውን የፓርኩ ባለስልጣናት ይናገራሉ።
news-45396559
https://www.bbc.com/amharic/news-45396559
የሳምንቱ የጋሬዝ ክሩክስ ምርጥ ቡድን ውስጥ፡ ላካዜት፣ ካትካርት እና ሉካኩ ተካተዋል
ቶተንሃም በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ሲያስተናግድ ዋትፎርድ ደግሞ አራተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
ማንቸስትር ዩናይትድ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል የተመለሰ ሲሆን፤ ዎልቭስም የመጀመሪያ ድሉን ዌስትሃም ላይ አስመዝገቧል። ቼልሲ እና ሊቨርፑል ደግሞ የማሸነፍ ጉዟቸው አስጠብቀዋል። በዚህ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች እነማን የጋሬት ክሩክስ ምርጥ ቡድን ውስጥ ተካተቱ? ግብ ጠባቂ - ሩዊ ፓትሪሲዮ ሩዊ ፓትሪሲዮ: ዎልቭሶች ዌስትሃምን 1 ለ 0 ያሸነፉበት መንገድ አስገራሚ ነው። ዌስትሃሞች ነጥብ ለማግኘት ያላደረጉት ሙከራ አልነበረም። እንደግብ ጠባቂው ሩዪ ፓትሪሲዮ ባይሆን ኖሮ የጨዋታው ውጤት ሌላ ይሆን ነበር። ይህን ያውቃሉ? ፓትሪሲዮ 50 በመቶ ግብ የሚሆኑ ትልልቅ ዕድሎችን በዘንድሮው ዓመት ማዳን ችሏል። ተከላካዮች - ካይል ዎከር፣ ጆይ ጎሜዝ፣ ክሬግ ካትካርት እና አንድሪው ሮበርትሰን ካይል ዎከር: ምን ዓይነት ምርጥ ጎል ነው ኒውካስል ላይ ያስቆጠረው? ዎከር ለማንችስተር ሲቲ የመጀመሪያ ጎሉን በድንቅ ሁኔታ ነው በማስቆጠር የጀመረው። • የሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ለመሆን የሚያስችለው ሥነ-ልቦና • አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ ይህን ያውቃሉ? ዎከር ይህን ጎል ለማንቸስተር ሲቲ ያስቆጠረው ከ52 ጨዋታዎች በኋላ ነው። ጆዬል ጎሜዝ: ትሬንት አሌክሳንደር- አርኖልድ እና አንድሪው ሮበርትስን የባለፈው ዓመት ግኝቶች ከሆኑ ጆዬል ጎሜዝ ደግሞ ዘንድሮ የተገኘ ተጫዋች ነው። ይህ ተጫዋች ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን መጫወት አለበት። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወደ ቦቢ ሙር የተጠጋጋ ችሎታ ያለው ተጫዋች ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ይህን ያውቃሉ? ሊቨርፑል ከሌስተር ጋር በነበረው ጨዋታ ጎሜዝ ከየትኛውም ተጫዋች በልጦ ኳሶችን አጨናግፏል። ክሬግ ካትካርት: ስፐርሶች እንዴት በዋትፎርድ ተሸነፉ? የቆሙ ኳሶችን መከላከል የማይችል ዋንጫ አያነሳም። ስፐርሶች የትሮይ ዴኒይን ቁርጠኝነት እና የክሬግ ካትካርትን በሳጥን ውስጥ ያላቸውን ሃይል አልነበራቸውም። አራት ተከታታይ ድል- ዋትፎርድ ውስጥ ምን እየተካሄደ ነው? ይህን ያውቃሉ? ክሬግ ካትከርት ለዋትፎርድ ያስቆጠራቸው አምስቱም ጎሎች በሜዳቸው ቪካሬጅ ሮድ ላይ የተገኙ ናቸው። አንድሪው ሮበርትሰን: ባለፈው ሳምንት ሙገሳዬን ለአሌክሳንደር- አርኖልድ አቅርቤ ነበር። በዚህ ሳምንት ሊቨርፑል ባስመዘገበው ድል ውስጥ የአንድሪው ሮበርትሰን ሚና ትልቅ ነበር። የሊቨርፑልን ጠንካራ ተከላካይ መስመር ከፈጠሩት ተጫዋቾች መካከል ሮበርትሰን እና አሌክሳንደር-አርኖልድ ይገኙበታል። ይህን ያውቃሉ? ጀምስ ሚልነር ብቻ ነው በተቃራኒ የግብ ክልል ከሮበርትሰን የበለጠ ኳስ ያቀበለው። አማካዮች - ራሂም ስተርሊንግ፣ ኤዲን ሃዛርድ እና ማርኮስ አሎንሶ ራሂም ስተርሊንግ: እግሊዛዊው ተጫዋች በልምምድ ቦታ ጠንክሮ በመስራት በተለይ ጎል ፊት ለፊት ያለውን አጨራረስ አሳድጓል። እንግሊዛዊያን ተጫዋቾችን በብዛት ስለማፍራት የሚወራ ሲሆን፤ ጥሩ እንግሊዛዊያን አሰልጣኞች ቢኖሩ ብዙ ጥሩ እንግሊዛዊ ተጫዋቾች ሊኖሩ ይችሉ ነበር። ይህን ያውቃሉ? ካለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ ሞሃመድ ሳላህ እና ሃሪ ኬን ብቻ ናቸው ብዙ ጎሎችን ከራሄም ስተርሊንግ በላይ ያስቆጠሩት። • ቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ማን ይሆን? ኤደን ሃዛርድ: ከቼልሲ ጠንካራ አጨዋወት በተጨማሪ የሃዛርድ ድንቅ መሆን ከበርንማውዝ ጋር የነበረውን ጨዋታ በቀላሉ የበላይ ሆነው እንዲያጠናቅዉ ረድቷቸዋል። ቼልሲ በአሁኑ ሰአት ከጆሴ ሞውሪንሆም ሆነ አንቶኒዮ ኮንቴ ጊዜ በተሻለ ለዓይን የሚስብ ቡድን ሆኗል። ይህን ያውቃሉ? በዚህ ሳምንት ከየትኛውም ተጫዋች በበለጠ ሃዛርድ ብዙ የግብ ዕድሎችን ፈጥሯል። ማርኮስ አሎንሶ: ለሶስተኛ ተከታታይ ሳምንት ማርኮስ አሎንሶ በሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ ተካቷል። ስፔናዊው ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ እየተጫወተ ይገኛል። ቼልሲ ጨዋታውን ሲያሸንፍ አሎንሶ ደግሞ የድሉ ዋነኛ መሠረት ነበር። ይህን ያውቃሉ? አሎንሶ በዘንድሮው ዓመት 12 የግብ ሙከራዎችን ያደረገ ሲሆን፤ ይህም ከየትኛውም የፕሪምር ሊጉ ተከላካይ የበለጠ ነው። አጥቂዎች - ሮሜሉ ሉካኩ፣ አሌክሳንደር ላካዜት፣ ሳዲዮ ማኔ ሮሜሉ ሉካኩ: ማንቸስተር ዩናይትዶች ቤልጂየማዊው አጥቂ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች በርንሌዮችን ማሸነፍ ችለዋል። ከማርከስ ራሽፎርድ በቀይ ካርድ ከሜዳው መሰናበት ውጭ ከእግር ኳስ ስነምግባር ያፈነገጠ ነገር አላየሁም። ይህን ያውቃሉ? ከመጀመሪያ ጨዋታው ወዲህ ሮሜሉ ሉካኩ ለማንቸስተር ዩናይትድ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር የመጀመሪያው ነው። አሌክሳንደር ላካዜት: ኡናይ ኤምሬ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች አሌክሳንደር ላካዜትና ፒዬር-ኤመሪክ ኦባምያንግን በጋራ ቢያጫውቱ የተለየ ውጤት ሊያገኙ ይችሉ ነበር። ሁለቱ ተጫዋቾች አንድ ላይ ሲጫወቱ ጥሩ መሆናቸውን ደግሞ በዚህ ሳምነት አስመስክረዋል። ይህን ያውቃሉ? ላካዜት የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስት በገባባቸው አምስት የሊግ ጨዋታዎች ሰባት ጎሎች ላይ አስተዋጽኦ አድርጓል። ሳዲዮ ማኔ: ከሌስትር ጋር በነበረው ጨዋታ ለሊቨርፑል ድንቅ መሆን የሳዲዮ ማኔ ሚና ትልቅ ነበር። ባላፈው ዓመት የሞ ሳላህ የበለጠ መድመቅ እንጂ ሴኔጋላዊው ጥሩ የውድድር ዘመን አሳልፏል። ጠንካራ እና አጥቂውን በሚደግፍ የተከላካይ መስመር ምን ማሳካት እንደሚቻል በመጨረሻም ቢሆን የርገን ክሎፕ ተረድተዋል። ይህን ለመረዳት ሶስት ዓመት ጠይቋል። ይህን ያውቃሉ? ማኔ ከሌስተር ጋር ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች በአራት ጎሎች ላይ ሚና ነበረው።
news-51322211
https://www.bbc.com/amharic/news-51322211
"የኮሮናቫይረስ ክስተት በአሜሪካ የሥራ ዕድልን ሊያሳድግ ይችላል"
ቻይና ውስጥ የተከሰተውና የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው የኮሮናቫይረስ ለአሜሪካ ኢኮኖሚ ሲሳይን ይዞ ሊመጣ እንደሚችል የአገሪቱ ንግድ ሚኒስትር ዊልበር ሮስ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ለአንድ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንዳሉት "የወረርሽኙ መከሰት የሥራ ዕድሎች ወደ ሰሜን አሜሪካ የሚመለሱበትን ሁኔታ የሚያፋጥነው ይመስለኛል" ሲሉ ተናግረዋል። ይህ የንግድ ሚኒስትሩ አስተያየት የትራምፕን አስተዳደር ከሚተቹ ወገኖች ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሷል። • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩት ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ተነገረ • ኮሮናቫይረስ በመላዋ ቻይና መዛመቱ ተነገረ፤ የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ ነው የበሽታው በፍጥነት መስፋፋት በቻይና ኢኮኖሚና በዓለም ዕድገት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ተሰግቷል። ሚኒስትሩ ከፎክስ ቢዝነስ ኒውስ በቻይና የተከሰተው ወረርሽኝ በአሜሪካ ኢኮኖሚ ላይ ስጋት ያስከትል እንደሆነ በተጠየቁ ጊዜ "የአሜሪካ ተቋማት የአቅርቦት ሰንሰለታቸውን መለስ ብለው መፈተሽ እንሚያስፈልጋቸውና ክስተቱ ወደ አሜሪካ የሚመለሰውን የሥራ ዕድል በከፍተኛ ደረጃ ሊያሳድገው ይችላል" ብለዋል። ይህን ንግግር ተከትሎ ከተለያዩ ወገኖች ትችቶች ተሰንዝረዋል ከእነዚህም መካከል የዲሞክራቲክ ፓርቲ የኮንግረስ አባል የሆኑት ዶን ቤየር በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ "ገዳይ ወረርሽኝ በተከሰተበት ጊዜ የንግድ አጋጣሚን መፈለግ" ሲሉ ወቀሳ ሰንዝረዋል። በኋላ ላይ ግን የመስሪያ ቤታቱ ቃል አቀባይ "ሚኒስትር ሪስ ግልጽ እንዳደረጉት የመጀመሪያው እርምጃ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የበሽታውን ሰለባዎች መርዳት ነው" ሲል አስተያየት ሰጥቷል። ቃል አቀባዩ ጨምረውም "በሕዝቧና በቀሪው ዓለም ላይ የተጋረጠን አደጋ በመሸፋፈን ረጅም ታሪክ ካላት አገር ጋር መስራት የሚያስከትለውን ጉዳት ማጤን አስፈላጊ ነው" ሲሉም ቻይናን በነገር ሸንቆጥ አድርገዋል። • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ቻይና ውስጥ ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለው ይህ በሽታ ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረውና ሳርስ በመባል ከሚታወቀው ወረርሽኝ በከፋ ሁኔታ በዓለም ምጣኔ ሐብት ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ባለሙያዎች ተናግረዋል። ከ18 ዓመት በፊት ተከስቶ የነበረው የሳርስ በሽታ ከ8 ሺህ በላይ ሰዎችን ይዞ የነበረ ሲሆን ከ700 በላዩን ለሞት ዳርጓል። በበሽታው ሳቢያ ዓለም አቀፉ ኢኮኖሚ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉዳት ደርሶበታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የቻይና ባለስልጣናት በመላው አገሪቱ የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣላቸው ግዙፎቹን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችና መኪና አምራቾች እንዲሁም የንግድ ተቋማት ለጊዜው ሥራ አቁመዋል።
news-47650244
https://www.bbc.com/amharic/news-47650244
በአውሮፕላኑ የአደጋ ስፍራ በየዕለቱ እየተገኙ የሚያለቅሱት እናት
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ጋር በተያያዘ በስፋት ከተሰራጩትና ለአደጋው ሰለባዎች መሪር ሃዘናቸውን ከሚገልፁ ፎቶግራፎች መካከል የአዛውንቷ የወይዘሮ ሙሉነሽ በጂጋ ፎቶ አንዱ ነው።
ከዚህ አንፃር የወይዘሮ ሙሉነሽ ታሪክ የተለየ የሚሆነው ደግሞ በአደጋው የሞተ ዘመድም ሆነ በቅርብ የሚያውቁት ሰው ሳይኖር በሰውነታቸው ብቻ ስለደረሰው አደጋ አዘውትረው ማዘናቸው ነው። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? አዛውንቷ ወይዘሮ ሙሉነሽ ነዋሪነታቸው በመጥፎ ዕጣ የ157 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው አውሮፕላን በተከሰከሰበት ስፍራ ሲሆን፤ በተመለከቱት አሰቃቂ ክስተት ሳቢያ ከዚያች ዕለት በኋላ እጅጉን አዝነው እንቅልፍ አጥተዋል። እንባቸውንም በአደጋው ለተቀጠፉት ለማያውቋቸው ሰዎች እያፈሰሱ ቀናት ተቆጥረዋል። የቱሉ ፈራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እኚህ እናት፤ ቤታቸውም አደጋው ከደረሰበት ሁለት ኪሎ ሜትር ያክል ርቀት ቢኖረውም ከአደጋው ቀን አንስቶ አንድም ቀን ከቦታው ርቀው አያውቁም። "እስካሁን ደጋግሜ ከአደጋው ቦታ ሄጄ ባለቅስም ሃዘኔ አልወጣልኝም" ይላሉ። • "በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት አሁንም በየቀኑ ወደ ስፍራው ከሚመጡ የአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች ጋር በመሆን ሃዘናቸውን ይገልፃሉ። "የሃገሪቷ ሁኔታ ነው የተበላሸው፤ ሰዎች ባህላቸውንና ወጋቸውን በመርሳታቸው የዚህ ሁሉ ሰው ደም ፈሰሰ" በማለት ጉዳዩን ከፈጣሪ ቁጣ ጋር ያያይዙታል። "ከዚህ በፊት በአያት ቅድመ አያቶቻችን ዘመን አይተንም ሰምተንም የማናቀውን ነገር በእኛ ቀዬ ሲፈጠር በጣም አስደነገጠኝ፤ ይህም ነው ቀን ከሌሊት እንዳለቅስ ያደረገኝ" ይላሉ ወይዘሮ ሙሉነሽ። እኚህ እናት እንዲህ በሃዘን የሚንገበገቡት ለኢትዮጵያዊያኑ ብቻ ሳይሆን በአውሮፕላኑ ውስጥ ለነበሩት የሰው ልጆች ነው። "የሰው ልጅ ኢትዮጵያ ሃገራችን መጥቶ ተቃጠለ። ደማቸው ባዶ ሜዳ ላይ መፍሰሱን ሳስብ ሆዴ ይረበሻል። በዕለቱ ስለተከሰከሰው የሰው አጥንትና ስለፈሰሰው ደም አልቅሼ ሊወጣልኝ አልቻለም" ሲሉ የሃዘናቸውን ጥልቀት ይናገራሉ። • አደጋው በአውሮፕላን አብራሪዎች ላይ ምን ስሜት ፈጠረ? አደጋው ከደረሰ በኋላ በስፍራው ስለተመለከቱት ነገርም ሲያስታውሱ፤ የአውሮፕላኑ አካል የተበተነ ወረቀት እንጂ የሰው ልጅ በውስጡ የያዘ አይመስልም ነበር። "ታዲያ ይሄ እንዴት ለእኔ እረፍት ይሰጠኛል? የእነርሱ ደም ነው የሚያቃጥለኝ" ይላሉ ወይዘሮ ሙሉነሽ። በተለይ ደግሞ አደጋ በልጆቻቸው ላይ ደርሶ ቢሆን ኖሮስ ብለው ሲያስቡ ሃዘናቸው የሚብሰው ወ/ሮ ሙሉነሽ "እኛም ልጆች አሉን፤ ልጆቻችንም በአየር ይበራሉ። ታዲያ ከእነዚህ መካከል የእኛ ልጆች ቢኖሩስ ብዬ አስባለሁ።" ወይዘሮ ሙሉነሽ በየዕለቱ አደጋው የደረሰበት ቦታ ይሄዳሉ። "አንድም ቀን ቀርቼ አላውቅም።" በየአጋጣሚውም እርሙን ለማውጣት ከሚመጣው ሰው ሁሉ ጋር ስለሞቱት ሰዎች ያለቅሳሉ። "ቤትም ስገባ ያ የፈሰሰው የሰው ደም ነው ትዝ የሚለኝ፤ ምግብም አስጠልቶኝ ቡናው እራሱ ቡና አይመስለኝም" ይላሉ። • ስለምንጓዝበት የአውሮፕላን አይነት እንዴት ማወቅ እንችላለን? ይህ አደጋ በወይዘሮ ሙሉነሽ ላይ የተለየ ጥልቅ ሀዘንን ፈጥሮባቸዋል። ከዚህ በፊት በቅርብ የሚያውቋቸውና ከቤተሰባቸው አባላት መካከልም የተለያዩ ሰዎች በሞት ተለይተዋቸዋል። ነገር ግን ይህን ያህል ሃዘን ውስጥ ገብተው እንደማያውቁ የሚናገሩት ወይዘሮ ሙሉነሽ ይህ ክስተት ለእርሳቸው የተለየ ነው። ወይዘሮ ሙሉነሽ ይህንን ሃዘናቸውን ልክ እንደ ቤተሰብ ለመግለፅ ባላቸው አቅም በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡት ሰዎች ኃይማኖታቸው በሚያዘው መሠረት የተዝካር ሥነ-ሥርዓት ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ይናገራሉ።
news-53864756
https://www.bbc.com/amharic/news-53864756
ኮሮናቫይረስ፡ በሕንድ ዴልሂ በኮቪድ-19 ከተጠቁት መካከል የሴቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው
በሕንድ ዋና ከተማ ከወንዶች በበለጠ ሴቶች በኮቪድ-19 መጠቃታቸውን በከተማዋ ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገ የአንቲቦዲ ምርመራ አረጋገጠ።
መንግሥት ባካሄደው በዚህ የዳሰሳ ጥናት የደም ናሙና ምርመራ ከተደረገላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የኮቪድ-19 አንቲቦዲ አዳብረው ተገኝተዋል። የመጀመሪያው የዳሰሳ ጥናት የተካሄደው በሐምሌ ወር ሲሆን ወደ 23.48 በመቶ ያህል የከተማዋ ነዋሪዎች የኮሮናቫይረስ አንቲቦዲ አዳብረው መገኘታቸውን ተረጋግጦ ነበር። በሕንድ ዴልሂ እስካሁን ድረስ 150 ሺህ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን በምርመራ ስታረጋግጥ ከእነዚህም መካከል 4,257 ሕይወታቸውን አጥተዋል። በቅርብ ጊዜ የተደረገው የዳሰሳ ጥናት የተካሄደው በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ሲሆን፣ በከተማዋ ከሚኖሩና ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል 32.2 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ለኮሮናቫይረስ አንቲቦዲ አዳብረው ተገኝተዋል። በአንጻሩ ወንዶች ደግሞ 28.3 በመቶ ያህሉ የኮሮናቫይረስ አንቲቦዲ ማዳበራቸው ተገልጿል። ለዚህ ምከንያቱ ምን ይሆናል ለሚለው ጥያቄ እስካሁን መልስ አልተገኘም። በአጠቃላይ ምርመራ ከተደረገላቸው የዴልሂ ከተማ ነዋሪዎች መካከል 29 በመቶ ያህሉ የኮቪድ-19 አንቲቦዲ አዳብረው መገኘታቸው በጥናቱ ላይ ይፋ ተደርጓል። ይህም ማለት 20 ሚሊየን ከሚሆነው የዴልሂ ከተማ ነዋሪ መካከል ስድስት ሚሊዮን ያህሉ በቫይረሱ ተይዘው አገግመዋል ማለት ነው። የዴልሂ የጤና ሚኒስትር ሳታዬንድራ ሤይን ከተማቸው ለወረርሽኙ በማህበረሰብ ደረጃ መከላከያውን አዳብረዋል ለማለት ጊዜው ገና መሆኑን አስታውቀዋል። በማህበረሰብ ደረጃ ተፈጥሯዊ መከላከያ ማዳበር (herd immunity) የሚባለው በቂ መጠን ያለው ሰው ቫይረሱን የመከላከል አቅም ሲያዳብር እና ስርጭቱን ባለበት ማቆም ሲቻል ነው። " መጀመሪያ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ላይ ከነበረው 23 በመቶ አሁን 29 በመቶ ያህል ሰዎች አገግመው አንቲቦዲዎችን ማዳበራቸው መልካም ነው፤ ነገር ግን የማህበረሰብ የመከላከል አቅም ዳበረ የምንለው ከ40 እስከ 70 በመቶ ያህሉ አዳብረው ሲገኙ ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ተመሳሳይ ጥናት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክፉኛ ባጠቃት ሙምባይና ፑኔ ከተሞች የተደረገ ሲሆን፣ ከተመረመሩት መካከል ከ40 በመቶ በላይ ሰዎች የቫይረሱን አንቲቦዲ አዳብረው ተገኝተዋል። በፑኔ ምርመራው ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አንቲቦዲ ማዳበራቸውን የዳሰሳ ጥናቱ ውጤት ያሳያል። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት እንዲህ አይነት ጥናቶች ባለስልጣናትን የቫይረሱ ስርጭት በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ግንዛቤ በመስጠት ረገድ ጥቅማቸው የትየለሌ ነው። ጥናቱ እንዲሁ የመመርመሪያ ጣብያዎችን በተገቢው መልኩ ለማደራጀት እንዲሁም አንድ አካባቢን ብቻ ለይቶ የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣልና ቫይረሱን ለመቆጣጣር ያግዛል። የሕንዷ ዴልሂ በቫይረሱ ክፉኛ ከተጎዱ የሕንድ ከተሞች መካከል አንዷ ስትሆን በሰኔ የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት የሆስፒታል አልጋዎች እጥረትም ተከስቶ ነበር። አሁን የሆስፒታሎች ቁሳቁስ የተሟላ ሲሆን በየዕለቱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ቀንሷል።
news-53640750
https://www.bbc.com/amharic/news-53640750
በአንድ ጀንበር ሚሊየነር የሆነው ታንዛኒያዊ ሌላ 2 ሚሊዮን ዶላር አገኘ
በጥቃቅንና አነስተኛ ደረጃ ተደራጅቶ ማዕድን ቆፋሪ ሆኖ ሲሰራ በለስ ቀንቶት በዓለም እጅግ ውድ ማዕድን አግኝቶ የነበረው ታንዛኒያዊ ሌላ ሚሊዮኖችን ወደ ኪሱ አስገብቷል፡፡
ሳኒኒዩ ላይዘር ባለፈው ሰኔ ነበር በድንገት ታንዛናይት የሚባልና ምናልባትም በሰሜን ታንዛኒያ ብቻ የሚገኝ እጅግ የከበረ ድንጋይ አግኝቶ በአንዲት ጀንበር የናጠጠ ሀብታም የሆነው፡፡ በሰኔ ወር ያገኛቸውን ሁለት የከበሩ ድንጋዮች በሦስት ሚሊዮን ተኩል ዶላር ሽጧቸው ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ የከበረ ድንጋይ በሁለት ሚሊዮን ዶላር ሽጦታል፡፡ የዚህ ሰው ሀብትም በአንድ ጊዜ አምስት ሚሊዮን ዶላር ተኩል ደርሷል፡፡ አሁን ያገኘው ማዕድን 6.3 ኪሎ ግራም የሚመዝን ነው፡፡ ላለው ይጨመርለታል ነው ነገሩ፡፡ ታንዛናይት ማዕድን ውድ ጌጣ ጌጦችን ለመሥራት የሚያገለግል የከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በዓለም ላይ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ከምድር ይጠፋሉ ከሚባሉ ማዕድኖች አንዱ ሲሆን በምድር ላይ የቀረው ታንዛናይት መጠን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ማዕድኑ በተለያዩ ቀለማት ሊገኝ ይችላል፡፡ አረንጓዴ፣ ቀይ፣ ሐምራዊና ሰማያዊ ቀለማት አሉት፡፡ የዋጋው ውድነት የሚወሰነው በቀለሙ ድምቀትና ጥራት ነው፡፡ ደማቅ ቀለም ያለው ታንዛናይት ውድ ዋጋ ያወጣል፡፡ አቶ ላዚየር ጥቃቅንና አነስተኛ ማዕድን አውጪዎችን' እኔን አርአያ በማድረግ ተስፋ ሳትቆርጡ ቆፍሩ' ብሏቸዋል፡፡ ማዕድን አውጪዎቹ የከበረ ድንጋዩን ሲያገኙ በውድ ዋጋ የሚሸጡት ለመንግሥት በሕጋዊ መንገድ ነው፡፡ የቢቢሲው አቡባካር ፋማኡ ከታንዛንያ ዋና ከተማ ዶዶማ እንደዘገበው በርካታ ጥቃቅንና አነስተኛ ማዕድን ቆፋሪዎች መንግሥት ክፍያ ያዘገይብናል ብለው ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡ ባለፈው ሰኔ 9.2 ኪሎ ግራምና 5.8 ኪ.ግራም የሚመዝኑ ሁለት የገበሩ ድንጋዮችን ካገኘ በኋላ አቶ ላይዘር ቅልጥ ያለ ድግስ አዘጋጃለሁ፣ የደስ ደስም አበላለሁ ብሎ ነበር ለቢቢሲ፡፡ ሰኞ ለታ ግን ሐሳቡን እንደቀየረ ተናግሯል፡፡ ከድግስ ይልቅ በአገሬ በማንያራ ገጠር ሲማንጂሮ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር አንድ ትምህርት ቤትና አንድ የጤና ማዕከል እገነባለሁ ብሏል፡፡ በሰኔ ወር ለቢቢሲ ‹ሚሊየነር መሆኔ አኗኗሬን አይለውጠውም፣ ሁለት ሺ የሚሆኑ ከብቶቼን እየተንከባከብኩ ሕይወቴን እቀጥላለሁ ብሎ ነበር፡፡ ሚሊየነር በመሆኔ አደጋ ይደርስብኛል ብዬም አልሰጋም፣ ጥበቃም አያስፈልገኝም ሲል ለቢቢሲ አረጋግጧል፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ታንዛንያዊያን ከመንግሥት ፍቃድ አግኝተው በማዕድን ማውጣት ቢሰማሩም ሕገ ወጥ ማዕድን አውጪዎችም የዛኑ ያህል በርካታ ናቸው፡፡ በተለይም ትልልቅ የማዕድን አውጪ የውጭ ኩባንያዎች በሚሰሩባቸው አካባቢዎች በርካታ ሕገ ወጥ ማዕድን ቆፋሪዎች ይሰማራሉ፡፡ በጎርጎሳውያኑ 2017 አወዛጋቢው የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ወታደሮቻቸው 24 ኪሎ ሜትር አጥር በማንያራ ሜሬላኒ የማዕድን አካባቢ እንዲያጥሩ አዘዋቸው ነበር፡፡ ይህ አካባቢ በአለም በብቸኝነት ታንዛናይት የከበረ ድንጋይ ይገኝበታል ተብሎ የሚታሰብ ቦታ ነው፡፡ አጥሩ ከታጠረ ከዓመት በኋላ መንግሥት በታንዛናይት ማዕድን የማገኘው ገቢ ጨምሯል፣ አጥር ማጠሬ በጄ ሲል አስታውቋል፡፡
47327964
https://www.bbc.com/amharic/47327964
አር ኬሊ ሴቶችን አስክሮ በመድፈር ውንጀላ ቀረበበት
አሜሪካዊው ድምፃዊ አር ኬሊ ለብዙዎቻችን ጆሮም ሆነ ዐይን እንግዳ አይደለም። ይህ የ52 ዓመቱ ድምፃዊ በድንቅ የሙዚቃ ችሎታውና ሙዚቃው የምናውቀው ያህልም በጾታዊ ትንኮሳም ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ነው።
ከዚህ በፊት አንዲት የ20 ዓመት ወጣት በግድ መጠጥ እንድትጠጣ አድርጎ ሩካቤ ሥጋ በመፈፀም አባላዘር በሽታ እንዳስያዛት በመናገር ክስ መሥርታ ነበር። አር ኬሊ የ27 ዓመት ወጣት ሳለ ነበር የ15 ዓመቷን ማሪስ አሊያህን በድብቅ ያገባው። ይህም የፍርድ ቤትና የመገናኛ ብዙኃን እሰጣገባ ውስጥ ከትቶት ብዙ ተባብሎበታል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነበር የተለያዩ ሴቶች ችሎት ፊትም ሆነ መገናኛ ብዙኃን ጋር እየቀረቡ፣ ተደፍረናል፤ ተተንኩሰናል፤ እሱ ያላደረገን ነገር የለም በማለት አቤቱታቸውን ማሰማት የጀመሩት። • ቢል ኮዝቢ ወደ ዘብጥያ ወረዱ • ቢል ኮዝቢና ፖላንስኪ ከኦስካር አካዳሚ ተባረሩ • የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ ዛሬም ሁለት ሴቶች እኛም በአር ኬሊ ጥቃት ደርሶብናል ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል። እነዚህ ሴቶች ሮሼል ዋሺንግተን እና ላትሬሳ ስካፍ ይባላሉ። በ1990ዎቹ በባልቲሞር በነበረ የሙዚቃ ድግስ ላይ ተገኝተው አር ኬሊን ሲታደሙ የኬሊ ጠባቂዎቹ ዐይን ውስጥ ይገባሉ። • ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከቀረበበት የመድፈር ክስ ጋር በተያያዘ የዘረመል ናሙና እንዲያቀርብ ታዘዘ • ናይኪ ሮናልዶ ላይ የቀረበው ውንጀላ"አሳስቦኛል" አለ • ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘች በወቅቱ አፍላ ጎረምሳ የነበሩትን እነዚህን ሴቶች የኬሊ አጃቢዎች ከሙዚቃ ድግሱ መካከል አውጥተው ከወሰዷቸው በኋላ መጠጥና አደንዛዣ ዕፅ እንደተሰጣቸው ገልፀዋል።። ይህ የሆነው በ1995 ወይንም በ1996 እንደሆነ ያስታውሳሉ። የዛሬዎቹ ከሳሾች በወቅቱ ስለነበረው ሲያስታውሱ ኮኬይን፣ ማሪዋና እና መጠጥ ቀርቦላቸው በድምፃዊው መኝታ ክፍል እንዲቆዩ ተደረገ። በመኝታ ክፍሉ እያሉ 'ድምፃዊው እየመጣ እንደሆነ' ተነግሯቸው ልብሳቸውን አውልቀው እንዲጠብቁት ታዘዙ። ድምፃዊው ሲመጣ የመራቢያ አካሉ ለወሲብ ዝግጁ ኾኖ ይታይ ነበር ብለዋል። ከዚያም ለ'ሦስትዮሽ-ወሲብ' ጋበዛቸው። ወይዘሪት ዋሺንግተን አሻፈረኝ በማለት ወደመታጠቢያ ክፍል ስታመራ ወይዘሪት ስካፍ ግን አብራው ተኛች። የወቅቱን ሁኔታ ስታስረዳም "በመጠጣቴና አደንዛዥ ዕፅ በመውሰዴ የምደራደርበት አቅም አልነበረኝም" ብላለች። አሁን ጉዳዩን ለመገናኛ ብዙኃን ይፋ ለማድረግ የፈለገችው ሌሎች እንደ እርሷ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በደላቸውን ማሰማት በመጀመራቸው ነው። የእነዚህን ሁለት ሴቶች ጉዳይ እንዲህ ዓይነት ጥፋቶች የፍትህ ፀሐይ እንዲሞቃቸውና ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ በማድረግ የሚታወቁት ስመጥር ጠበቃ ግሎሪያ አልሬድ ይዘውታል። አር ኬሊ ሙሉ ስሙ ሮበርት ሲልቨስተር ኬሊ ሲሆን ላለፉት 20 ዓመታት በወሲባዊ ጥቃትና ትንኮሳ የመገናኛ ብዙኃን የወሬ ማሟሻ ሆኖ ኖሯል። በቅርቡም በአሜሪካ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ በእርሱ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ላይ በሠራው ዘጋቢ ፊልም ያደረሰውን አካላዊ እና የስሜት ስብራት በጥልቀት አሳይቷል። ድምፃዊው በዕድሜ ለጋ ከሆኑ ሴቶች ጋር ይቃበጥ እንደነበር የሚገልፁ የተለያዩ ክሶችም ቀርበውበታል። የአር ኬሊ ጠበቆች ግን እንደተለመደው አጣጥለውታል። ድምፃዊው ራሱ የስምንት ዓመት ልጅ እያለ በዕድሜ የምትበልጠው ሴት በተደጋጋሚ ወሲባዊ ግንኙነት እንደፈፀመችበትና እንዳይናገር ታስፈራራው እንደነበር የሕይወት ታሪኩን ባስነበበት መጽሐፍ ላይ አስፍሯል።
news-51060161
https://www.bbc.com/amharic/news-51060161
በአዲሱ ሕግ መሠረት ማን፣ ምን መታጠቅ ይችላል?
መንግሥት የዜጎችን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የሕዝብን መብትና ደህንነት ለማስከበር የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥርን በተመለከተ አዲስ ሕግ ማውጣት አስፈልጎኛል ብሏል።
ፎቶ፡ ፋይል። እአአ 2015 ላይ የቻይና መንግሥት በቁጥጥር ሥር አውሎ ያወደማቸው የጦር መሳሪያዎች። ረቂቅ አዋጁም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ትናንት ታህሳስ 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጸድቋል። "ተቆጣጣሪ ተቋም" ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ውክልና የተሰጠው የክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሥሩ ብሔራዊ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የሥራ ክፍል አደራጅቶ አዋጁን ያስፈጽማል። ለመሆኑ ይህ ሕግ ምን ይላል? ማን፣ ምን፣ እንዴት መታጠቅ ይችላል? የጦር መሳሪያ ፍቃድ እና ሁኔታ? ለግለሰብ የሚፈቀደው አንድ አነስተኛ ወይም አንድ ቀላል የጦር መሳሪያ ብቻ ነው። ለድርጅትም ቢሆን የሚፈቀደው የጦር መሳሪያ አይነት አነስተኛ ወይም ቀላል የጦር መሳሪያ ሲሆን፤ ዝርዝሩ እና የጥይት ብዛት በተቆጣጣሪው ተቋም በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል። የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተጠየቀበት የጦር መሳሪያ ከዚህ ቀደም በሌላ ሰው ስም ፈቃድ ያልወጣበት እና የጦር መሳሪያው ወንጀል ያልተሰራበት መሆን አለበት። ፍቃድ የሚሰጥባቸው መስፈርቶች የተከለከሉ ተግባራት በዚህ አዋጅ መሰረት ከተፈቀደለት ሰው ውጪ ማንኛውም ሰው፤ የፀና ፍቃድ ሳይኖረው የጦር መሳሪያ እና መለዋወጫዎች ወይም አብረው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መሳሪያዎችን፣ ወደ ሀገር ማስገባት እና ማስወጣት፣ መያዝ፣ ማከማቸት፣ መገልገል፣ መደለል፣ መሸጥ፣ መግዛት፣ ማስተላለፍ፣ ማዘዋወር . . . ከተከለከሉ ተግባራት መካከል ይገኙበታል። የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት የማይቻልባቸው ሥፍራዎች መሳሪያ ታጥቀው ከላይ ወደ ተጠቀሱት ሥፍራዎች መግባት ካሰቡ በቅድሚያ የጦር መሳሪያውን ለተቋማቱ የጥበቃ ሰራተኞች ማስረከብ ይኖርብዎታል። የጦር መሳሪያ ፍቃድ የማይሰጣቸው ተቋማት ከላይ የተጠቀሱት ተቋማት ለጥበቃ ከሚያስፈልጋቸው የጦር መሳሪያ ውጪ ማንኛውም ዓይነት የጦር መሳሪያ ፍቃድ አይሰጣቸውም። በልማድ ለታጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች የጦር መሳሪያ ፍቃድ ስለመስጠት በተለምዶ የጦር መሳሪያ የሚያዝባቸው አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ እና የጦር መሳሪያ የያዙ ሰዎች፤ የያዙት የጦር መሳሪያ በዚህ አዋጅ ያልተከለከለ አይነት እስከሆነ ድረስ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተቆጣጣሪው ተቋም በአካባቢያቸው ተገኝቶ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በአካል ቀርበው ፈቃድ ሲጠይቁ ለአንድ ሰው አንድ የጦር መሳሪያ ፈቃድ በዚህ አዋጅ መሰረት ይሰጣል። በተገለፀው ጊዜ ገደብ ውስጥ ፈቃድ ያልወጣበት የጦር መሳሪያ ለተቆጣጣሪው ተቋም ገቢ መደረግ አለበት፣ በቁጥጥር በተገኘም ጊዜ ይወረሳል። የጦር መሳሪያ ፍቃድ ስለሚታደስበት ሥርዓት የጦር መሳሪያ ፍቃድ የተሰጠው ማንኛውም ሰው የፍቃዱ አገልግሎት ጊዜ ከማብቃቱ ከ60 ቀናት በፊት የእድሳት ጥያቄውን ለተቆጣጣሪው ተቋም ማቅረብ አለበት። ተቆጣጣሪው ተቋም ጥያቄው እንደቀረበለት በፍጥነት የፍቃድ መስጫ መስፈርቶቹ መሟላታቸውን ሲያረጋግጥ ፍቃዱን ያድሳል። የጦር መሳሪያ ፍቃድ ስለመሰረዝና መውረስ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ግዴታዎች የተቆጣጣሪ ተቋም ሥልጣንና ተግባር በአዋጁ መሠረት ተቆጣጣሪ ተቋሙ ከተሰጡት ሥልጣን እና ተግባራት መካከል፦ የወንጀል ተጠያቂነት የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 481 የተጠበቀ ሆኖ፤ ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ የተመለከተውን ክልከላ እና ግዴታ የተላለፈ ከአንድ አመት እስከ ሦስት ዓመታት በሚደርስ ቀላል እስራት እና ከአምስት ሺህ እስከ አስር ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል። • ካናዳ፣ አሜሪካ እና ዩኬ አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ እምነት አለን አሉ የተፈጸመው ወንጀል ብዛት ባለው የጦር መሳሪያ ሲሆን ቅጣቱ ከአምስት አመት እስከ አስራ አምስት አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እና ከሀምሳ ሺህ እስከ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ ገንዘብ ይቀጣል። በሕጋዊ መንገድ ያገኘውን የጦር መሳሪያ የሸጠ በማስያዣነት የተጠቀመ፣ ያከራየ ወይም በውሰት ለሦስተኛ ወገን ያስተላለፈ ማንኛውም ሰው ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ይቀጣል።
48456100
https://www.bbc.com/amharic/48456100
የቦይንግ ኃላፊ የሟቾችን ቤተሰቦች በይፋ ይቅርታ ጠየቁ
የቦይንግ ኃላፊ ዴኒስ ሙይንበርግ ከሲቢኤስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ በአውሮፕላን አደጋው ሕይወታቸው ያለፈ ግለሰቦችን ቤተሰቦች ይቅርታ ጠይቀዋል። ኃላፊው ከዚህ ቀደም በቪድዮ በሰጡት መግለጫ ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን፤ ይህ ሁለተኛቸው ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ባለፈው መጋቢት ወር ከተከሰከሰ ከሳምንታት በኋላ ኃላፊው በቦይንግ ስም ይቅርታ ቢጠይቁም፤ የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው አባት ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ የቦይንግ ይቅርታ "ዘግይቷል" ብለው ነበረ። • "ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት ኃላፊው ከሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቆይታ "የደረሱት አደጋዎች እጅግ አሳዝነውናል" ብለዋል። ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ በደረሰበት አደጋ 157 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ከአደጋው ከአምስት ወር በፊት የላየን ኤር አውሮፕላን ተከስክሶ 189 ሰዎች ሞተዋል። • ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ የቦይንግ ኃላፊ ዴኒስ ሙይንበርግ "ስለተፈጠረው ነገር ይቅርታ እንጠይቃለን። በሁለቱም አደጋዎች የሰዎች ሕይወት በመጥፋቱም ይቅርታ እንጠይቀለን" ብለዋል። ኃላፊው በአደጋው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ግለሰቦችን ይቅርታ ብለው፤ "የተፈጠረው ነገር እንደድርጅቱ መሪነቴ በቀጥታ ተጽዕኖ አሳድሮብኛል" ሲሉም ተደምጠዋል። "ቦይንግ ውስጥ ባሳለፍኩት 34 ዓመታት ከተፈጠሩ ነገሮች እጅግ ከባዱ ይህ ነው። የተፈጠረውን መቀየር ባንችልም በቀጣይ ለደህንነት ጉዳዮች የላቀ ትኩረት እንሰጣለን" ብለዋል። ኃላፊው ቦይንግ "ለወደፊቱም ደህንቱ አስተማማኝ" እንደሚሆንም ለሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል። የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ ከተከሰከሱ በኋላ ኃላፊው ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ የሲቢኤስ ኒውስ የመጀመሪያቸው ነው። • ቦይንግ "ችግሩ ተፈቷል" እያለ ነው የቦይንግ ኃላፊ በሁለቱ የአውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ካጡ ግለሰቦች ቤተሰቦችን በተጨማሪ በአውሮፕላን የሚጓጓዙ ሰዎችን በአጠቃላይም ይቅርታ ጠይቀዋል። "እምነት ያጡ ተጓጓዦችን ይቅርታ እንጠይቃለን። ደንበኞቻችን ላይ ተጽዕኖ ማሳደራችን ይጸጽተናል" ብለዋል። ቦይንግ ኃላፊነቱን ከመውሰድ ባሻገር አስፈላጊ ማሻሻያ እንደሚያደርግም አክለዋል።
news-46340515
https://www.bbc.com/amharic/news-46340515
ናይጀሪያ ኤኒና ሼል ባደረጉት የተጭበረበረ የነዳጅ ስምምነት 6 ቢሊዮን ዶላር ከነዳጅ አጣች
በጣሊያኗ ከተማ ሚላን የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት በነዳጅ አምራች ኩባንያዎቹ ኤኒኒና ሼል ክስ ለመክፈት መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ሁለቱ ኩባንያዎች ከናይጀሪያ ጋር ባደረጉት የተጭበረበረና ሙስና የተሞላበት የነዳጅ ስምምነት ምክንያት ሀገሪቷን 6 ቢሊዮን ዶላር በማሳጣታቸው ምክንያት ነው። በናይጀሪያ እየተካሄደ ያለውን የተጭበረበረ ስምምነት ላይ ዘመቻ እያካሄደ ያለው ግሎባል ዊትነስ የተባለው ድርጅት በአውሮፓውያኑ 2011 የተደረገው ኦፒኤል የተባለው የነዳጅ ስምምነት የሀገሪቱን አመታዊ የትምህርትና የጤና እጥፍ በጀት እያሳጣት እንደሆነ አስታውቋል። •የሜቴክ ሰራተኞች እስር ብሔር ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ ተገለፀ •ወ/ሪት ብርቱካን በወዳጆቻቸው አንደበት •በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ የጣልያኑ ኤኒና የእንግሊዝና ሆላንድ ንብረት የሆነው ሼልም የከፈሉት ገንዘብ ለጉቦ እንዲሆን ነው በሚልም ተወንጅለዋል። ኩባንያዎቹ ምንም አይነት ስህተት አልሰራንም በሚል የሆነውን ሁሉ ክደዋል። በጣልያን ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ ላይ የእንግሊዙ የደህንነት ድርጅት ኤም አይ 6 የቀድሞ አባላት፣ ኤፍ ቢ አይ፣ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የሁለቱ የነዳጅ ኩባንያ ስራ አስፈፃሚዎች በዚህ ሙስናና ማጭበርበር ላይ እንደተሳተፉበት ተገልጿል። የቀድሞው የናይጀሪያ የነዳጅ ሚኒስትር ዳን እቴቴ ፈረንሳይ በሚገኝ ፍርድ ቤት ጀልባና ቪላ ቤት ለመግዛት በሚል ገንዘብ በህገ-ወጥ በማዘዋወር ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። ፍርድ ቤቱ ጨምሮ እንደገለፀው አምስት ሺ ኪሎግራም የሚመዝን የመቶ ዶላር የብር ኖቶች ይዘው ነበር ብሏል። ግሎባል ዊትነስ ለአመታት የዘለቀው ምርምሩ እንደሚያሳየው ሼልና ኤኒ በኒጀር ዴልታ አካባቢ የነዳጅ ቁፋሮን መብት አግኝተው እንደነበር ነው። በኩባንያዎቹና በናይጀሪያ የተደረገው ስምምነት ኩባንያዎቹን ሆን ብሎ እንዲጠቅም የተደረገ ሲሆን በዚሀም ምክንያት ናይጀሪያ 5.86 ቢሊዮን ዶላር እንዳጣች ተገልጿል። ይህም ስምምነቱ ከተፈረመ ከአውሮፓውያኑ 2011 በኋላ ያለውን ነው። ናይጀሪያ ያጣችው ገንዘብም የታሰበው 70 ዶላር በበርሜል ተባዝቶ ነው ። ኤኒ የተባለው ኩባንያ ሂሳቡ የተሰራበትን መንገድ የተቸ ሲሆን፤ ናይጀሪያ ስምምነቱን የመከለስ መብት እንዲሁም ከነዳጅ ገቢው 50% መጠየቋን ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንደሆነ ተገልጿል።
news-51494053
https://www.bbc.com/amharic/news-51494053
ሱዳን በአልቃይዳ ጥቃት ለተገደሉ አሜሪካውያን ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማማች
ሱዳን እአአ 2000 በየመን ወደብ አል-ቃይድ በመፈጸመው ጥቃት ለተገደሉ 17 አሜሪካውያን ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማማች።
ሱዳን በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት የምትሻ ከሆነ ይህን ካሳ መክፈል እንደሚጠበቅባት በአሜሪካ እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦላት ነበር። ጥቃቱን የሰነዘሩት ሁለቱ አጥፍቶ ጠፊዎች ሥልጠና የወሰዱት በሱዳን ስለሆነ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የምትወስደው ሱዳን ነች ስትል አሜሪካ ደምድማ ነበር። ሱዳን ይህ ጥቃት እንዲፈጸም ለአል-ቃይዳ እና ቢን ላደን የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ አድርጋለች ተብሎ ይታመናል። ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ አጥፍቶ ጠፊዎቹ በሱዳን ልምምዶችን ከማድረጋቸውም በተጨማሪ፣ በሱዳን የንግድ ሥራ እንዲያከናውኑ እና ተቀጣጣይ ነገር ይዘው በሱዳን ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዶላቸው ነበር ትላለች። አዲሱ የሱዳን መንግሥት በአሜሪካ ተጥሎበት የሚገኘውን ማዕቀብ ማስነሳት ለነገ የማይለው ዋና እቅዱ አድርጓ እየተንቀሳቀሰ ነው። ሱዳን ለሟች አሜሪካውያን ቤተሰቦች ምን ያህል ገንዘብ ለመክፈል እንደተስማማች ይፋ ባይሆንም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ሰዎች ጠቅሶ ሬውተርስ እንደዘገበው ምናልባት ከ$30 ሚሊዮን ዶላር እንደማያንስ ይጠበቃል። እአአ በ2000 በተሰነዘረው ጥቃት ቢያንስ 40 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ካውንስል የቀድሞ መሪውን አል-በሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፎ እንዲሰጡ መወሰኑ ይታወሳል። የሽግግር ካውንስሉ ይህን ውሳኔ የወሰደው የአሜሪካን ፍላጎትን ለሟሟለት ነው የሚሉት በርካቶች ናቸው። ከአንድ ሳምንት በፊት ታሪካዊ በተባለ ሁኔታ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር መንግሥት ካውንስል ሰብሳቢ አብድል ፈታህ አል-ቡረሃን በኡጋንዳ ኢንቲቤ ተገናኝተው መምከራቸው ይታወሳል። ከሁለቱ መሪዎች ውይይት በኋላ ሱዳን እና እስራኤል ግንኙነት ለመጀመር መስማማታቸውን ተዘግቧል። የሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚንስትር ለአሶሲዬትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ከሱዳን ሌላ በኬንያ እና በታንዛኒያ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ አል-ቃይዳ ባደረሳቸው ጥቃቶች ለሟች አሜሪካውያን ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ውይይት እየተደረገ መሆኑን ተናግራል። በኤምባሲዎቹ ላይ በደረሰው ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። • የሶሪያ ጦር ወሳኝ ያላትን ከተማ ከታጣቂ ኃይሎች ነጻ ማውጣቱን አስታወቀ • በአንድ ቀን 1 ቢሊዮን ዶላር ያተረፈው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው? • የቢንላደን የቀድሞ ጠባቂ በጀርመን አሜሪካ ለምን ሱዳንን በጥቁር መዝገቧ ላይ አሰፈረቻት? በወቅቱ የአል-ቃይዳ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን እአአ በ1990ዎቹ የፕሬዝደንት አል-በሽር እንግዳ ሆኖ በሱዳን ለአምስት ዓመታት ኖሯል። በዚህ ሱዳን 1993 ላይ የአሜሪካ አሸባሪ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች። የሱዳን መንግሥት ግን በእነዚህ ጥቃቶች ውስጥ እጁ እንደሌለበት በተደጋጋሚ እየተናገረ ይገኛል። "ይህን ካሳ ለመክፈል የተስማማነው ሱዳንን ከዝርዝሩ ውስጥ ለማስወጣት በአሜረካ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ለማሟላት እና ከአሜሪካ እና ከተቀረው ዓለም ጋር መልካም ግነኙነት ለመፍጠር ነው" ሲል የሱዳን መንግሥት መግለጫ አውጥቷል። ጥቃቱ ከመሰንዘሩ ጥቂት ቀደም ብሎ መርከቡ በኤደን ወደብ ነዳጅ በመሙላት ላይ ነበር 2000 ላይ የመናዊ የሆኑ አጥፍቶ ጠፊዎች እስከ 225ኪ.ግራን የሚመዝን ተቀጣጣይ ነገር በመጠቀም በአሜሪካ መርከብ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። በዚህ 17 መርከበኞች ሲሞቱ ከ40 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል። አሜሪካ ከዚህ ጥቃት ጋር ግንኙነት ነበረው ያለችውን ጀማል አል-ባዳዊ የተባለን ግለሰብ ከ19 ዓመታት በኋላ ባሳለፍነው ዓመት የመን ውስጥ በአየር ጥቃት ገድላዋለች። ጥቃቱን አቀነባብሯል የሚል ክስ የቀረበበት የሳኡዲው ተወላጁ አብ አል-ናሽሪ በጓንታናሞ ቤይ በአሜሪካ ቁጥጥር ሥር ይገኛል። • በደቡብ ሱዳን የምሽት ክለቦች ታገዱ
news-49625534
https://www.bbc.com/amharic/news-49625534
የሆንግ ኮንግ ሰልፈኞች ፕሬዝደንት ትራምፕ እባክዎ ይታደጉን እያሉ ነው
ዲሞክራሲን የሚሹት ሰልፈኞች ፕሬዝደንት ትራምፕ 'ሆንግ ኮንግን ታደጉልን' ሲሉ በከተማዋ በሚገኘው የአሜሪካ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤተ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።
አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች የአሜሪካን ባንዲራ እያውለበለቡ "ፕሬዝደንት ትራምፕ እባክዎን ሆንግ ኮንግን ይታደጉ" እና "ሆንግ ኮንግን ወደ ቀድሞ ሃያልነቷ ይመልሱ" የሚሉ ጽሁፎችን አንግበው ነበር። • የሆንግ ኮንግ ፖሊስ፡ «ሰልፈኛ አስመስለን ፖሊስ አሰማርተናል» • የሆንግ ኮንጓ መሪ የተቃዋሚዎችን ድርጊት አወገዙ በሚሊዮን የሚቆጠሩት እና ለተቃውሞ አደባባይ የሚወጡት ሰልፈኞች ከቻይና ጋር ያላቸው ቁርኝት እንዲያበቃ የሚሹ ናቸው። የቀድሞዋ የእንግሊዝ ቀኝ ግዛት የሆነችው ሆንግ ኮንግ የቻይና አካል ስትሆን፤ ነዋሪዎቿም የዘረ ሃረጋቸው ከቻይና የሚመዘዝ ይሁን እንጂ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች እራሳቸውን እንደ "ቻናዊ" አይመለከቱም። የሆንግ ኮንግ ዩኒቨርሲቲ የዳሰሳ ጥናት እንዳመላከተው 71 በመቶ የሚሆኑት ነዋሪዎች እራሳቸው እንደ ሆንግ ኮንግ ዜጋ እንጂ እንደ ቻይናዊ አይመለከቱም። እንደ ጥናቱ ውጤት ከሆነ በተለይ ወጣቱ "ቻይናዊ" በመባሉ ኩራት አይሰጠውም። 14ኛ ሳምንቱን በያዘው የተቃውሞ ሰልፍ፤ ቻይና ሌሎች ሃገራት በጉዳዩ ላይ እጃቸውን እንዳያስገቡ አስጠንቅቃለች። ቻይና በተደጋጋሚ የሆንግ ኮንግ ጉዳይ የሃገር ውስጥ ጉዳይ መሆኑን እና ማናቸውም አይነት የውጪ ሃገራት ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት እንደማይኖረው አሳስባለች። ዛሬ በተደረገው ሰልፍ አሜሪካ ጣልቃ እንድትገባ የተጠየቀ ሲሆን፤ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች የአሜሪካን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር አሜሪካ ሆንግ ኮንግን ከቻይና 'ነጻ' እንድታወጣ ጠይቀዋል። ለተቃውሞ የወጡት ሰዎች የያዟቸው መልዕክቶች በቀጥታ ለፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የተላለፉ ነበሩ። የሆንግ ኮንግ ተቃውሞ መነሾ ምንድነው? በሆንግ ኮንግ ተቃውሞው የተጀመረው በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ከሆንግ ኮንግ ወደ ቻይና ተላልፈው እንዲሰጡ የሚያስችል ሕግ ተግባራዊ ሊደረግ መታሰቡን ተከትሎ ነበር። • ተቃውሞ በቻይና፡ መንግሥት 'የውጭ ኃይሎችን' እየወቀሰ ነው • ባህር አቋራጩ የቻይና ድልድይ ተከፈተ ምንም እንኳ ሆንግ ኮንግ የቻይና አካል ብትሆንም፤ የቻይና እና የሆንግ ኮንግ የሕግ ስርዓት የተለያየ ነው። ይህ ብዙ ያጨቃጨቀው ሕግ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ እንዲወድቅ ቢደረግም፤ የተቃዋሚዎች ጥያቄ መልኩን ቀይሮ አሁንም በሆንግ ኮንግ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ናቸው። በተቃውሞ ወቅት በቁጥጥር ሥር የዋሉት በምህረት እንዲለቀቁ እና በተቃውሞ ወቅት በፖሊስ ተፈጽመዋል የተባሉት የመብት ጥሰቶች እንዲመረመሩ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት እየጠየቁ ይገኛሉ።
44691074
https://www.bbc.com/amharic/44691074
ሮቦቷ ሶፊያ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኘች
ሮቦቷ ሶፊያ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር ዛሬ በቤተመንግሥት ተገናኘች።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከሮቦት ሶፊያ ጋር ለጠቅላይ ሚኒስትሩም "ኢትዮጵያ በመምጣቴ በጣም ደስ ብሎኛል፤ እኔ ኢትዮጵያን የምወድ ሮቦት ነኝ" ብላቸዋለች። ከመጣች አራተኛ ቀኗን ያስቆጠረችው ሶፊያ በቆይታዋ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተሰናዳው ዓለም አቀፍ አይ ሲቲ ኤክስፖ ላይ ተገኝታ ከታዳሚያን ጋር ተዋውቃለች። ባለስልጣናት፣ የጃዝ ሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄን ጨምሮ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በቶቶት የባህል አዳራሽ የዳንስ ትርዒትም አቅርባለች። ምንም እንኳን በጀርመን በርሊን ኤክስፖ ቆይታዋ የተወሰነ የአካል ክፍሏን የያዘ ሻንጣ መጥፋት አማርኛ መናገር እንዳትችል የተፈታተናት ቢሆንም በትንሹም ቢሆን ተናግራለች። "ከዚህ የበለጠ አማርኛ ስለምድ እናወራለን" ስትል ተናግራለች። ንግግሯ ጠቅላይ ሚንስትሩን ፈገግ ያሰኘ ነበር ። በዛሬው ዕለትም በብሔራዊ ሙዚየም ተገኝታ ድንቅነሽን እንደጎበኘች የ አይኮግ ላብስ ስራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ ለቢቢሲ ገልጿል።
news-53253254
https://www.bbc.com/amharic/news-53253254
ኮሮናቫይረስ፡ ሐሰተኛ ዜና በሕንድ ያስከተለው ጉዳት
ሐሰተኛ ወይንም አሳሳች መረጃዎች በርካቶችን ግራ ከማጋባት አልፈው ከባድ ጉዳት ያስከትላሉ። በተለይ ደግሞ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ብዙዎች በእንደዚህ አይነት መረጃዎች ተሳስተዋል። የዚህ ጉዳት ገፈት ቀማሽ ከሆኑት አገራት መካከል ሕንድ ተጠቃሽ ናት።
ይህም በሕንድ የሚገኙ በርካታ ታማኝና ትክክለኛ መረጃ የሚያደርሱ የዜና አውታሮች እንኳን ወረርሽኙን በተመለከተ ሥራቸውን በትክክል እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል። አንዳንድ ትንሽ ቁጥር ያላቸው ማኅበረሰቦች፤ በተለይ ደግሞ የሥጋው ኢንዱስትሪ ዘርፍ ሕንድ ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ነው። ሕንድ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ጀምሮ ሐይማኖትን የተመለከቱ ነገሮች በበይነ መረብ ላይ ልዩ የመነጋገሪያና የበርካታ ሐሰተኛ መረጃዎች የሚወጡበት ጉዳይ ነው። የቢቢሲ መረጃ ቡድን ባደረገው ማጣራት መሰረት በአምስት የሕንድ ድረገጾች ላይ 1447 መረጃዎች የተገኙ ሲሆን ከነዚህ መካከል 58 በመቶ የሚሆኑት ስለኮሮናቫይረስ የተሳሳተ አልያም ሐሰተኛ መረጃን የያዙ ናቸው። አብዛኞቹ ደግሞ ኮሮናቫይረስ መድኃኒት ተገኘለት የሚሉና ኮሮናቫይረስ እንዴት እንደተነሳ ትክክለኛ መረጃ አለን የሚሉ ሰዎች የጻፏቸው ሀሳቦች ናቸው። በአገሪቱ ኮሮናቫይረስ ብዙም ባልተሰራጨበት ከወርሃ ጥር ጀምሮ እስከ መጋቢት ባለው ጊዜ ውስጥ፤ ከሦስት የጎረቤት አገራት የሚመጡ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች የሕንድ ዜግነት ሊሰጣቸው ነው የሚል ዜና በስፋት ሲሰራጭ ነበር። ምንም እንኳን ዜናው ሐሰተኛ ቢሆንም በሕንድ በርካቶች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን እንዲገልጹ አድርጓል። ሙስሊሞችን የሚያገል ውሳኔ ነው በማለትም ብዙዎች ቁጣቸውን ገልጸው ነበር በወቅቱ። በርካታ ሙስሊሞች በሚኖሩባት ሰሜን ምሥራቅ ዴልሂ ደግሞ ሕይወት እስከመጥፋት ያደረሰ ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። በድረገጾቹ ላይ ከተለቀቁት መረጃዎች መካከል ሐሰተኛ ቪዲዮዎች፣ ከዚህ በፊት የተቀረጹ ቪዲዮዎችን እንደ አዲስ ማቅረብ፣ አጭር የጽሁፍ መልዕክቶች፣ ሐሰተኛ ምስሎችና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶች ይገኙበታል። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ደግሞ በርካታ ሐሰተኛና አሳሳች መረጃዎች በሕንድ ተሰራጭተዋል። በወቅቱ 'ታብሊጂ ጃማት’ የሚባል ኢስላማዊ ቡድን ያዘጋጀው ሐይማኖታዊ ዝግጅትን የታደሙ በርካታ ሙስሊሞች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገልጾ ነበር። ይህንን ተከትሎም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሕንዳውያን በቫይረሱ አለመያዝ ከፈለጉ ወደ ሙስሊሞች ሱቅ መሄድ እንዲያቆሙ መልዕክቶች በስፋት ይተላለፉ ነበር። በርካታ ዝግጅቱን የታደሙ ተጨማሪ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለበቸው ሲገለጽ ደግሞ ነገሮች እየተባባሱ መጡ። አትክልቶችን ይሸጥ የነበረው ኢምራን (ስሙ ተቀይሯል) ለቢቢሲ ሲገልጽ፤ በዋትስአፕ ይተላለፉ ከነበሩ መልዕክቶች ውስጥ አንድ ሙስሊም ነው የተባለ ሰው ዳቦዎች ላይ ምራቁን እየተፋ ለደንበኞቹ ሲሸጥ የሚያሳየው ሐሰተኛ ተንቀሳቃሽ ምስል ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ መገለል እንዲደርስ አድርጎ ነበር ይላል። "አትክልቶችን ለመሸጥ ወደ መንደር ለመግባት ፈርተን ነበር’’ ይላል። • ስለኮሮናቫይረስ ሐሰተኛ መረጃ እንዳይስፋፋ ምን ልናደርግ እንችላለን? • ሰዎች ለምን ስለኮሮናቫይረስ የሚነገሩ ሐሰተኛ ወሬዎችን ያምናሉ? • ፌስቡክ ሐሰተኛ ዜናዎችን መለየት ሊጀምር ነው በዋና ከተማዋ ዴልሂ ደግሞ ሙስሊሞች ወደ መኖሪያ መንደሮችና ገበያ ማዕከላት መግባት እንደተከለከሉ አንድ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ለፖሊስ አስታውቆ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ሕንድ ውስጥ የተሰራጨው ሌላኛው መረጃ ሥጋን ከነጭራሹ አለመመገብና አትክልቶችን ብቻ መብላት ከኮሮናቫይረስ ይከላከላል የሚለው ነው። የሕንድ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት ሐሰተኛ መረጃዎችን ሰዎችን እያሳሳቱ እንደሆነ ገልጾ ነበር። በተለይ በዋትስአፕና በፌስቡክ ይተላላፉ የነበሩት ሐሰተኛ መረጃዎች ሙስሊሞችንና በሥጋ መሸጥ ላይ ሕይወታቸውን የመሰረቱ ሰዎችን ጎድቷል። መንግሥት እንዳለውም ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የሥጋና የዶሮ ተዋጽኦ ዘርፉ ከሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ብቻ 1.4 ቢሊየን ፓውንድ ኪሳራ አጋጥሞታል። በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዴት መለየት ይቻላል? በዚህ ዙሪያ ከተላለፉት ሐሰተኛ መረጃዎች መካከል የቀድሞው ታዋቂ የክሪኬት ተጫዋች ሳቺን ቴንዱልካር የሥጋ መሸጫ ሱቆች መዘጋት አለባቸው ብሎ ጠይቋል የሚለው ነው። ከሐሰተኛ ዜናዎቹ በተጨማሪም ሰዎች በቆሎን የመሳሰሉ ጥራጥሬዎችን በብዛት መግዛት በመጀመራቸው ዶሮ አርቢዎች ዶሮዎቻቸውን የሚመግቡት በቆሎ እጥረት አጋጥሟቸው ነበር። በዚህ ምክንያት ዴልሂ ውስጥ ብቻ የእንቁላል ሽያጭ 30 በመቶ የቀነሰ ሲሆን ሙምባይ ውስጥ ደግሞ 21 በመቶ ቀንሷል። በቴላንጋና ግዛት ውስጥ በምትገኘው ሐይደርባድ ደግሞ የእንቁላል ሽያጭ 52 በመቶ አሽቆልቁሏል።
news-51541672
https://www.bbc.com/amharic/news-51541672
የእድሜ ባለጸጎችና ህሙማን በከፍተኛ ሁኔታ ለኮሮና ተጋላጭ ናቸው ተባለ
የቻይና የጤና ዘርፍ ኃላፊዎች ስለ ኮቪድ-19 (በኮሮናቫይረስ የሚከሰተው በሽታ) ዝርዝር መረጃ የያዘ ጥናት ይፋ አደረጉ።
የቻይና የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲሲዲሲ) ባወጣው ጥናት መሰረት፤ የእድሜ ባለጸጎችና ህሙማን ለበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናቸው። የህክምና ባለሙያዎችም በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው ሰፊ እንደሆነ ተመልክቷል። በኮቪድ-19 ቫይረስ በዋነኛነት በተስፋፋበት ሁቤይ ግዛት የሞት መጠን 2.9 በመቶ ሲሆን፤ በተቀረው ቻይና ደግሞ 0.4 በመቶ መሆኑ ተገልጿል። • ''ኮሮናቫይረስን ወደ አፍሪካ መውሰድ አልፈልግም'' • ኮሮና ቫይረስ መጠሪያ ስሙን አገኘ ይፋ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፤ እስካሁን በበሽታው ሳቢያ 1,868 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ 72,436 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል። ባለፉት 93 ቀናት 98 ሰዎች ሲሞቱ 1,886 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ከእነዚህ 1,807ቱ በሁቤይ ግዛት የተመዘገቡ ናቸው። የቻይና ኃላፊዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ ከ12,000 በላይ ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። ጥናቱ ቫይረሱ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ በበሽታው የተያዙ እንዲሁም ተይዘዋል የተባሉትን በአጠቃላይ ከግምት ያስገባ ነው። ከህሙማኑ 80.9 በመቶው መጠነኛ ስጋት ውስጥ፣ 13.8 በመቶው አስከፊና 4.7 በመቶው ደግሞ እጅግ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል። በከፍተኛ ደረጃ ለበሽታው የተጋለጡት እድሜያቸው 80 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ናቸው። እስካሁን ከዘጠኝ ዓመት በታች የሆነ ልጅ ሕይወት አለማለፉና፤ እስከ 39 ዓመት የሆናቸው ሰዎች የመሞት እድላቸው 0.2 በመቶ መሆኑንም ተመልክቷል። ወንዶች በበሽታው የመሞት እድላቸው 2.8 በመቶ የሴቶች ደግሞ 1.7 በመቶ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል። ከደም ዝውውር ጋር የተያያዘ ህመም ያለባቸው ሰዎች ለበሽታው የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ሲሆን፤ ስኳር እና ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተገናኘ በሽታ ያለባቸው ሰዎችም በቫይረሱ ሊያዙ እንደሚችሉ በጥናቱ ተጠቁሟል። እስካሁን 3,019 የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ እንደተያዙና ከእነዚህ አምስቱ መሞታቸውም ተገልጿል። • የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች ኮሮና ቫይረስን 'ሊያመርቱ' ነው • ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች ይፋ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፤ ቫይረሱ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከጥር 23 እስከ 26 ስርጭቱ ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፤ ወደ የካቲት 11 አካባቢ ቀንሷል። በሽታው በስፋት የተሰራጨባቸውን ከተሞች መለየት እንዲሁም ሰዎች ራሳቸውን ከቫይረሱ ለመከላከል መውሰድ የሚገባቸውን ጥንቃቄ (እጅ መታጠብ፣ አፍና አፍንጫ የሚሸፍን ጭንብል ማጥለቅ) ማሳወቅ፤ ስርጭቱ እንዲቀንስ እየረዳ እንደሚገኝ ጥናቱ ያሳያል።
news-43245528
https://www.bbc.com/amharic/news-43245528
አዲስ የፀረ-ተህዋስ ዝርያ በአፈር ውስጥ ተገኘ
የአሜሪካ ተመራማሪዎች አዲስ አይነት የፀረ-ተህዋስ ዝርያ በአፈር ናሙና ውስጥ አገኙ።
እነዚህ የተፈጥሮ ስብጥሮች ከባድ የሚባሉ ኢንፌክሽኖችን የማከም አቅም ያላቸው ናቸው ሲሉ በሮክፌለር ዩኒቨርሲቲ ያለው ቡድን ተስፋውን ገልጿል። የተደረጉት ምርምሮች ማሊሲዲንዝ የተሰኙት ስብጥሮች ባሉት የፀረ-ተህዋስ መድሃኒቶች የማይበገሩትን እንደ ኤምአርኤስኤ ያሉ የተለያዩ በባክቴሪያ የሚመጡ በሸታዎችን የማስወገድ አቅም አላቸው። ባለሙያዎች 'ኔቸር ማይክሮባዮሎጂ' በተሰኘው የድረ-ገጽ መጽሔት ላይ እንደገለጹት ፀረ-ተህዋስን በመፈለጉ ሩጫ ላይ ተስፋ እንዳለ ነው። መድሃኒት የማይበግራቸው በሽታዎች የዓለማችንን አጠቃላይ ጤና የሚያውኩ ናቸው። እነዚህ በሽታዎች በየዓመቱ እስከ 700 ሺህ ሰዎችን ይገላሉ ስለዚህም ነው አዳዲስ መፍትሔዎች በአስቸኳይ የሚያስፈልጉት። ከአፈር መድሃኒት አፈር በሚልዮን የሚቆጠሩና የተለያዩ ለዓይን የማይታዩ (ማይክሮ ኦርጋኒዝም) ፀረ-ተህዋስን ጨምሮ በርካታ ስብጥሮችን ይይዛል። በኒው ዮርክ የሚገኘው የሮክፌለር ዩኒቨርሲቲው የዶ/ር ሾን ብሬዲ ቡድን ደግሞ እነዚህን ሲፈልግ ቆይቷል። የጂን ማከታተያ (ጂን ሲክወንሲንግ) በመባል የሚታወቀውን ዘዴ በመጠቀም በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከ1000 የአፈር ናሙናዎች በላይ ሲያጠኑ ቆይተዋል። ማላሲዲንዝ የተሰኘውን ደግሞ በብዙ ናሙናዎች ላይ አግኝተውታል። ይህም በጣም አስፈላጊ መሆኑን እንዲገናዘቡ አድርጓቸዋል። ለአይጦች የፀረ-ተህዋሱን ስብጥርን ከሰጡ በኋላ በቆዳቸው ላይ ባለ ቁስል ላይ ያጋጠመን ኤምአርኤስኤ የተባለውንኢንፌክሽን ለማስወገድ ችለዋል። ተመራማሪዎቹም መድሃኒቱ ለሰዎች ማከሚያ ይሆናል በሚል ተስፋ በትክክል መሥራት አለመሥራቱን ሲያጠኑ ቆይተዋል። ዶ/ር ብሬዲ" ማላሲዲንዝን የመሰሉ መድሃኒቶችን ወደ ገበያ ለማምጣት መቼና እንዴት አንደሚሆን ለመናገር ይከብዳል'' ብለዋል። "ከግኝቱ እስከ ገበያ ድረስ ያለው ረዥምና ከባድ መንገድ ነው'' ሲሉም አክለዋል። በእንግሊዝ የፀረ-ተህዋስን ምርምር ፕሮፌሰር የሆኑት ኮሊን ጋርነር ኤምአርኤስኤን የመሰሉ በሽታዎችን ለማከም የሚችሉ መድሃኒቶችን ማግኘቱ በእራሱ ጥሩ ዜና ቢሆንም እንኳን፤ ከባዱን ችግር ለመቅረፍ አያስችልም ብለዋል። "የእኛ ስጋት እነዚህ ባክቴሪዎችን ለማስወገድ ከባድ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ፀረ-ተህዋስ መድሃኒቶችን የመቋቋም አቅማቸውን መጨመሩ ነው'' በማለትም ቀጥለዋል። "እንደ ኤምአርኤስኤ ያሉ ባክቴሪያዎች ኒሞንያ ያስከትላሉ በተጨማሪም የደምና የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽኖችንም ሊያመጡ ይችላሉ። እነዚህንም ለማስወገድ አዲስ የፀረ-ተህዋስ ዝርያ ያስፈልገናል'' ብለዋል።
42716243
https://www.bbc.com/amharic/42716243
ዶ/ር መረራ ጉዲና ተለቀቁ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ዛሬ ከእስር ሲፈቱ "ከ400 ቀናት በኋላ በሰላም ከእስር በመለቀቄ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። እንደምታየው ሰዎች በድምቀት ተቀብለውኛል" ሲሉ ለቢቢሲው ኢማኑኤል ኢጉንዛ ተናግረዋል።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለቢቢሲ ''ዶ/ር መረራ ነጻ ወጥተዋል'' ሲሉ ተናግረዋል። የዶ/ር መረራ የቤተሰብ አባላትና ወዳጆቻቸው መረራን ለመቀበል ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያቀኑት በማለዳ ቢሆንም፤ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ግን ራሳቸው አሸዋ ሜዳ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እንደሚወስዷቸው በመግለጽ እዚያው እንዲጠብቁ ነግረዋቸዋል። ደጋፊዎቹም ''እስር እና እንግልት የኦሮሞን ትግል ወደኋላ አይመልሰውም'' የሚል መልዕክት የያዙ ጽሑፎችን በመያዝ እና የዶ/ር መረራ ምስል የታተመበትን ቲሸርት በመልበስ በቤታቸው አቅራቢያ እየጠበቋቸው ነበር። ዶ/ር መረራ መኖሪያ ቤታቸው ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል። ዶ/ር መረራ ጉዲና ከየት ወዴት? ዶ/ር መረራ ጉዲና መንግሥትን መቃወም የጀመሩት አምቦ ውስጥ የሁለተኛ ደራጃ ተማሪ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። ከዚያም የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት እንዲወድቅ ምክንያት የነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥም ተሳታፊ ነበሩ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖሊቲካል ሳይንስ ተማሪ በነበሩበት ጊዜም የመንግሥቱ ኃይለማሪያምን ወታደራዊ አስተዳደር በመቃወም ቅስቀሳዎችን ያካሂዱ ነበረ። በዚህም ሳቢያ ያለክስ ለሰባት ዓመታት በእስር ቤት ቆይተዋል። ከእስር ቤት እንደተለቀቁም ካይሮ በሚገኘው የአሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትምህርት ለመቀጠል ወደ ግብፅ ተጓዙ። በመለስ ዜናዊ የሚመራው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ወታደራዊውን የመንግሥቱ ኃይለማሪያም አስተዳደር በማሸነፍ ሥልጣን ከያዘ ከአምስት ዓመታት በኋላ፤ መረራ ጉዲና የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) የተባለ ፓርቲ አደራጅተው ወደ ፖሊቲካው መድረክ ተመለሱ። መረራ ጉዲና የመሰረቱት አዲሱ የኦሮሞ ፓርቲ ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ቁጥር ያለውን የኦሮሞ ብሄር በራስ የመወሰን መብቱ እንዲከበርለት ማድረግ ነው። በተጨማሪም ፓርቲው የኦሮምኛ ቋንቋ ከአማርኛ ጎን ለጎን የሃገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን ፍላጎት አለው። ይህ በመረራ ጉዲና ይመራ የነበረው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) ስያሜ ከፓርቲው ለወጡ አባላት በ2000 ዓ.ም በመሰጠቱ የኦሮሞ ሕዝቦች ኮንግረስ (ኦሕኮ) በሚል አዲስ ስም ፓርቲያቸውን መልሰው አዋቀሩ። ዶ/ር መረራ ከዚህ በተጨማሪ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመሆን ሃገራዊ ትብብርን ለመፍጠር ''ኅብረት'' እና ''መድረክ'' የተባሉትን ትልልቅ የተቃዋሚዎች ስብስብ በማደራጀትና በመምራትም ከፍ ያለ ሚና ነበራቸው። ዶ/ር መረራ ከፖለቲካው ጎን ለጎን የሃገሪቱ አንጋፋና ትልቁ በሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመምህርነትና በትምህርት ክፍል ተጠሪነት ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል። ዶ/ር መረራ በተለያዩ ጊዜያት ለምክር ቤት አባልነት እጩ ሆነው የተወዳደሩ ሲሆን፤ አወዛጋቢና ግጭቶችን አስከትሎ በነበረው የ1997ቱ ምርጫ በትውልድ አካባቢያቸው ተወዳድረው በማሸነፍ ለአምስት ዓመታት በምክር ቤት አባልነት ቆይተዋል። ዶክተር መረራ የመሰረቱትና ለዓመታት ሲመሩት የቆየው የኦሮሞ ሕዝቦች ኮንግረስ (ኦሕኮ) ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመጣመር ጠንካራና በኦሮሚያ ክልል ብሎም በመላው ሃገሪቱ ሰፊ ተቀባይነት ያለው ፓርቲ እንዲመሰረት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ፤ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራቲክ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ጋር ፓርቲያቸውን በማዋሃድ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እንዲመሰረት አድርገዋል። በ2008 ዓ.ም በተለይ በኦሮሚያና በአማራ አካባቢዎች ተቀስቅሶ ለወራት የዘለቀውን ህዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ ''ከፀረ-ሠላም'' እና ''ከሽብር'' ቡድኖች ጋር ግንኙነት በማድረግ ለእስር መዳረጋቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዶክትር መረራ በፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪነታቸውና በተቃዋሚ ፓርቲ መሪነት ለዓመታት ባካበቱት እውቀትና ልምድ ስለኢትዮጵያ የተለያዩ ፅሁፎችንና ንግግሮችን እንዲያቀርቡ በተለያዩ መድረኮች በአስረጂነት ይጋበዛሉ። ከነዚህም መካከል እስር ቤት ከመግባታቸው ቀደም ብሎ ጥቅምት 30/2009 ዓ.ም በአውሮፓ ፓርላማ ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ሁኔታ ባደረጉት ንግግር በመንግሥት የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተችተው ነበረ። ደጋፊዎቻቸው ''እስር እና እንግልት የኦሮሞን ትግል ወደኋላ አይመልሰውም'' የሚል መልዕክት የታተመበት ባነር ይዘው እየጠበቋቸው ነው በተጨማሪም በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጩ ምስሎች ላይ በሃገሪቱ ፓርላማ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ቡድን መሪ ከሆኑት ዶክትር ብርሃኑ ነጋ ጎን ተቀምጠው መታየታቸውን አንዳንዶች ለእስራቸው እንደተጨማሪ ምክንያት ያነሳሉ። ክስ ዶክተር መረራ ከአውሮፓ መልስ ለእስር ከተዳረጉ በኋላ፤ በኦሮሚያ ሁከት እንዲከሰትና በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ጥሪ አስተላልፈዋል በሚል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሰርቶባቸዋል። ዶክተር መረራ የቀረቡባቸው ክሶች
news-51382239
https://www.bbc.com/amharic/news-51382239
ኬንያ ተማሪዎቿን ከቻይና ዉሃን ከተማ ልታስወጣ ነው
ኬንያ የኮሮናቫይረስ መነሻ በሆነችው ዉሃን ከተማ ያሉ 85 ተማሪዎቿን ልታስወጣ ነው።
ሲመለሱም በለይቶ ማቆያ እንዲገቡም ተወስኗል። የአገሪቱ የጤና አስተዳደር ፀሐፊ ለፓርላማው የጤና ኮሚቴ እንዳስታወቁት የማስወጣቱ ሥራ የሚከናወነው ቻይና በዉሃን ከተማ ላይ የጣለችው የመውጣትና የመግባት እግዳን ስታነሳ ነው። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ቢሮም ከተማሪዎቹ ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ የፓርላማ አባሏ ዶር ሜርሲ ምዋንጋንጊ ተናግረዋል። • ኮሮናቫይረስና የነዳጅ ዘይት ምን አገናኛቸው? • በኮሮናቫይረስ ከተጠረጠሩ አራት አዲስ ሰዎች አንዱ በአክሱም እንደሚገኝ ተገለፀ ለተማሪዎቹ በጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የለይቶ ማቆያ ሁለት ክፍሎች የተዘጋጀላቸው ሲሆን፤ በተመሳሳይም በኬንያታ ሆስፒታል የህክምና ክትትል የሚደረግባቸው ለይቶ ማቆያ ክፍሎች እንደተዘጋጁም ገልፀዋል። በተጨማሪም በናይሮቢ እንዲሁ ተጨማሪ ለይቶ ማቆያዎች ተዘጋጅተዋል። ወደ ዉሃን ከተማ መግባትና ከከተማዋ የመውጣት እግድ መቼ እንደሚነሳ ግልፅ ባይሆንም ብዙ አገራት ዜጎቻቸውን አውጥተዋል። ከአፍሪካም ዜጎቿን በማውጣት ግብፅን የቀደማት የለም። የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አፍሪካ የተረጋገጠ የኮሮናቫይረስ በሽታ ቢያጋጥማት ያላት ዝግጅት ላይ ስጋት እንዳለው መግለጹ ይታወሳል። በአፍሪካ የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ድንገተኛ መከላከል ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ሚካኤል ያዎ "አፍሪካ የደከመ የጤና መዋቅር ነው ያላት" ብለዋል። በአህጉሪቷ በአጠቃላይ ቫይረሱን መመርመር የሚችል ላብራቶሪ ያለው ስድስት ብቻ ሲሆን፤ እነዚህም ናይጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ሴራሊዮን፣ ጋናና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ናቸው ብለዋል። • ካሜሮናዊው በኮሮናቫይረስ በመያዝ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ • በሽታውን ለመደበቅ ባለስልጣናት ዶክተሮችን ያስፈራሩ ነበር እስካሁን ባለውም የደቡብ አፍሪካ ላብራቶሪ 71 ተጠርጣሪዎችን የመረመረ ሲሆን ሁሉም ነፃ ናቸው ተብሎም ተመልሷል። የዓለም አቀፉ ኤጅንሲ በበኩሉ ለሃያ አራት አገራት ቫይረሱን መመርመር የሚያስችል እርዳታን እንደሚለግስ አስታውቋል። ቫይረሱ 426 ሰዎችን በቻይና የገደለ ሲሆን፤ አንድ ግለሰብም ከቻይና ውጪ ሞቷል። በአፍሪካ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ ባይገኝም፤ በቻይና ተማሪ የሆነ አንድ ካሜሮናዊ ቫይረሱ ተገኝቶበታል።
news-55631986
https://www.bbc.com/amharic/news-55631986
እየተካረረ የመጣው የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ፍጥጫ
በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተቀሰቀሰው የድንበር ይገባኛል ውጥረት፣ወታደራዊ እንቅስቃሴን አስከትሎ ይፋዊ መወነጃጀል መሰማት ከጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል።
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሱዳን ወታደሮች ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባቸውን የእርሻ መሬቶችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አለዝባ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ያላትን ፍላጎት በመግለጫዎች ብታሳውቅም ነገሮች እየተጠናከሩና እየተባባሱ በመምጣት ላይ ናቸው። እርምጃው የሱዳን መንግሥት ፍላጎት ሳይሆን በድንበር አካባቢ ያሉ የሱዳኑ ግዛት አስተዳዳሪዎችና ወታደራዊ መኮንኖች የተናጠል ድርጊት በመሆኑ ከአገሪቱ መንግሥት ጋር በመነጋገር ሠላማዊ መፍትሔ ይገኝለታል በማለት ገልጻ ነበር። ነገር ግን የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት የአገራቸው ሠራዊት ግዛቴ ነው ከሚላቸው ቦታዎች ውስጥ አብዛኛውን መቆጣጠሩንና ይህም የማይቀለበስ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የሱዳን ሠራዊት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ጥሶ በመግባት የእርሻ ቦታዎችን ወርሮ እንደያዘና ንብረት እንደዘረፈ ገልጿል። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳሉት ወረራው የድንበር ላይ ውጥረቱን እንዳባባሰው በማመልከት ችግሩን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። ሱዳን በበኩሏ ባወጣችው መግለጫ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል አል ቁራይሻ ውስጥ 'የኢትዮጵያ ታጣቂዎች ወረራ' ያለችውን ፈጽመዋል ስትል አውግዛለች። የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አማራ ክልል በኩል የገቡ የታጠቁ ቡድኖች ፈጸሙት ያለውን ጥቃት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ በመግባት እንዲያወግዘው ጠይቋል። የሌሎች አገራት ጥረት ጉዳዩ ያሳሰባት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኢትዮጵያና ሱዳን ያላቸውን የድንበር ላይ ውዝግብ በሰላማዊ መንገድና በንግግር እንዲፈቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ ጠይቃለች። ከሁለቱም አገራት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላት አረብ ኤምሬቶች ችግሩን ሊያባብስ ከሚችሉ ነገሮች በመቆጠብ ለሕዝቦቻቸውና ለአካባቢው ሠላምና ብልጽግና በሚያግዝ መልኩ መፍትሄ እንዲፈልጉ ለአገራቱ ጥሪ አቅርባለች። ከዚህ ባሻገር የሁለቱ አገራት ወዳጅ የሆነችው ኤርትራ ባለፈው ሳምንት ባለሥልጣናቷን ወደ ካርቱም በላከችበትና የሱዳን ባለሥልጣናት ወደ አስመራ በመጡበት ጊዜ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የድንበር አለመግባባት ጉዳይ ተነስቶ መወያየታቸው ተዘግቧል። ወቅታዊ ሁኔታ የሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪና ነዋሪዎች የሱዳን ሠራዊት ወረራ ፈጽሞበታል ወደ ሚባሉት ስፍራዎች ዘልቆ መግባት የጀመረው በአካባቢው የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ ከጀመረ በኋላ በጥቅምት 29/2013 ዓ.ም እንደሆነ ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው በአካባቢው በእርሻ ሥራ ላይ ተሰማርተው የቆዩትና በሱዳን ሠራዊት ወረራ ማሳቸውን ትተው ወደ መተማ የሸሹት አቶ ከሰተ ውበቱ እንደገለጹት "ወታደሮቹ ድንበር አልፈው ከገቡ በኋላ ወደ ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎች በመግባት ማንኛውንም የሰው እንቅስቃሴ በተመለከቱ ቁጥር ተኩስ ይከፍታሉ።" በድንበር አካባቢ ወታደራዊ ግጭት እንዳጋጠመ ቢነገርም ቢቢሲ ያነጋገራቸው ፍጥጫ ባለበት የድንበር አካባቢ አቅራቢያ ያሉ ነዋሪዎች፣ አልፎ አልፎ ከባድ ተኩስ እንደሚሰማ፤ በሁለቱ ሠራዊት መካከል ግጭት ተከስቷል ለማለት የሚያስችል ሁኔታ እንዳልተመለከቱና እንዳልሰሙ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ቁጥሩ ያን ያክል የተጋነነ ባይሆንም ወደ ድንበር አካባቢ የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት አልፎ አልፎ ሲንቀሳቀስ እንደሚታይ ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንድ የአካባቢው የጸጥታ ባለስልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከቀናት በፊት በተለይ ከመተማ ወደ ምዕራብ አርማጭሆና ሁመራ የሚወስደውን መንገድ ለመዝጋት የሱዳን ሠራዊት ሙከራ አድርጎ እንደነበር፣ ነገር ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በቦታው በመድረሱ ገፍተው ለመሄድ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል ብለዋል። በድንበር አካባቢ ስላለው ወታደራዊ እንቅስቃሴን በተመለከተ በአካባቢ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አመራሮች መካከል አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ "በሥፍራው የተለየ የሠራዊት እንቅስቃሴ የለም ብለዋል። በአካባቢው የነበረው የጸጥታ ኃይል ግን ከስፍራ ስፍራ ስለሚዘዋወር ምናልባት ያንን እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሰዎች ተጨማሪ ኃይል እየተንቀሳቀሰ ነው ብለው አስበው ይሆናል" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነዋሪዎች በድንበር አካካቢ ይሰማል ስላሉት ተኩስ የተጠየቁት የሠራዊቱ አመራር፤ በተደጋጋሚ የሱዳን ወታደሮች ተኩስ እንደሚከፍቱ አረጋግጠው "ተኩሱ ግን በአብዛኛው እንዲሁ ተራራ ላይ የሚቀርና የእርሻ ሠራተኞች ወደ እነሱ እንዳይቀርቡ ለማስፈራራት ነው" ሲሉ በሁለቱ አገራት መካከል ግጭት ኖሮ እንዳልሆነ አመልክተዋል። ጨምረውም አስካሁን በድንበር አካባቢ በተከሰተው ፍጥጫ ምክንያት በሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያመለክት ዝርዝርና ሙሉ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው፤ ነገር ግን ከዚህ በፊት ከሚያጋጥመው "በተለየ መልኩ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ከሌሎች ሰዎች መስማታቸውን" ገልጸዋል። "ትዕግስትም ልክ አለው" በድንበር አካባቢ ያለውን አለመግባባት በተመለከተ ጉዳዩ በሁለቱ አገራት መንግሥታት አማካይነት በሠላማዊ መንገድ እንደሚፈታና ለዚህም ጥረት እያደረገች እንደሆነ ስትገልጽ የነበረችው ኢትዮጵያ ከሱዳን ሠራዊት በኩል የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዳሳሰባት ገልጻለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደተናገሩት በድንበር አካባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየበረታ መጥቷል። ከሁለት ወር በፊት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት በመጠቀም የሱዳን ጦር ድንበር ጥሶ መግባቱን የገለጹት ቃል አቀባዩ፣ አሁን ደግሞ "የሱዳን ወታደራዊ ኃይል በድንበር አካባቢ ወደ ተጨማሪ ቦታዎች ዘልቆ ለመግባት የተጠናከረ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው" ሲሉ ከስሰዋል። ችግሩን በትዕግስትና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት መሞከር "ፍርሃት ወይም መወላወል አይደለም" ያሉት አምባሳደር ዲና፣ አካባቢውን ከግጭት ለመጠበቅ ሲባል ኢትዮጵያ ጉዳዮች እንዳይካረሩ ለማድረግ እየጣረች ቢሆንም ይህ ታጋሽነት ገደብ እንዳለው አመልክተዋል። የቆየ የድንበር ውዝግብ ሁለቱ አገራት 750 ኪሊ ሜትሮች ያህል የጋራ ድንበር ሲኖራቸው፣ ለዓመታት በድንበር አካባቢ ግጭት ሲያጋጥም ነበር። በተለይ አል ፋሽቃ በሚባለው ለም የእርሻ መሬት ባለበት አካባቢ ግጭቶች በተለያዩ ጊዜያት መከሰታቸው ይነገራል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሱዳን ባለስልጣናት እንደከሰሱት በአካባቢው የኢትዮጵያ ኃይሎች ባካሄዱት ጥቃት አንዲት ሴትና ህጻንን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል። በድንበር አካካቢ ተከስቶ ሳምንታት ያስቆጠረው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሲሆን፣ በሠላማዊ ሰዎችና በወታደሮች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለመፈናቀል ተዳርገዋል። ውጥረቱን ለማርገብ በሁለቱ አራት ጠቅላይ ሚኒስትርና በሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት አማካይነት ንግግር ቢደረግም እስካሁን ለቀውሱ መፍትሄ አላስገኘም። የኢትዮጵያና የሱዳን መንግሥታት ከድንበር ውዝግቡ ባሻገር ኢትዮጵያ ወደ ማጠናቀቁ እያደረሰችው ባለው ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጽን ጨምሮ እያደረጉት የነበረው ድርድር በሱዳን ቅሬታ ምክንያት ወደፊት መራመድ ሳይችል መቋረጡ ተገልጿል።
news-47369088
https://www.bbc.com/amharic/news-47369088
ኢህአዴግ ከግንባር ወደ ውህድ ፓርቲ ያመራል?
በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከሐረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋርና ሶማሌ ክልል ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት አንድ ጠንካራ አገራዊ ፓርቲ መመሥረት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሚነጋገርበት፣ የሚወስንበት፣ ድምፁ የሚሰማበት ሥርዓት ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅላይ ሚንስትሩ በንግግራቸው ገልፀው ነበር። ይህንኑ ተከትሎ ሐሳቡ 'የምር ነው ወይስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍ ወለምታ?' ሲሉ በርካቶች መነጋጋሪያ አድርገውት ቆይተዋል። የኢህአዴግ የሕዝብና የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻን ኢህአዴግ አንድ ፓርቲ እሆናለሁ ማለቱ እውነት መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ "ኢህአዴግ በአራት ብሔራዊ ድርጅቶች ተመሥርቶ እንደ አንድ አገራዊ ፓርቲ እያገለገለ ነው" የሚሉት አቶ ሳዳት ፓርቲዎቹ ተመሳሳይ ፕሮግራም ስላላቸው፣ በልማት፣ በዲሞክራሲና ሰላምን በማስፈን በጋራ ሲሠሩ በመቆየታቸው ወደ አንድ አገራዊ ፓርቲ ላለመሸጋገር የሚያግዳቸው የለም ብለዋል። አቶ ሳዳት እንደሚሉት ኢህአዴግ አራቱ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ሌሎች አጋር ድርጅቶችም ድርጅቱ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማሰብ ይህንኑ የእንዋሃድ ጥያቄ በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ኢህአዴግ ከግንባር ወደ ፓርቲ መሸጋገር አለበት የሚል ጥያቄ ወደ ጉባዔም መጥቶ በተለይ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ አፅንኦት ተሰጥቶት አቅጣጫ ተቀምጧል። ኢህአዴግ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች የሐሳብ ልዩነቶች ስለመኖራቸው ጉምጉምታው ብዙ ነው። ታዲያ በዚህ ጊዜ ውህደቱ እውን ሊሆን ይችላል ወይ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ "ኢህአዴግ ውስጥ የተለመደ አሠራርና ልምድ አለ፤ ድርጅቱ የትግል ፓርቲ ነው፤ ስለሆነም ኢህአዴግን የመሠረቱት ፓርቲዎች የተለያዩ ክርክሮችና ሐሳቦችን ያቀርባሉ፤ ነገር ግን ኢህአዴግ ይህን እንደ ልዩነት አያየውም" ብለዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ከልዩነትም ይልቅ በውይይቶቹ ለሃገርና ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግምባታ ገዥ የሆነ ምክንያታዊ ሐሳቦች ይመጣሉ ብሎ ያምናል-ኢህአዴግ። • "በረከትና ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ አራቱ ፓርቲዎች በሐሳብ ስለመለያየታቸው ቢወራም ኢህአዴግ እንደዚያ ዓይነት ግምገማ እንደሌለውና ድርጅቱ በሥራ አስፈፃሚም ሆነ በምክር ቤት አጀንዳዎች ላይ ልዩነት ፈጥረው የወጡበት ጊዜ እንደሌለ በመግለጽ አቶ ሳዳት ሐሳባቸውን በምክንያት ያስደግፋሉ። በመሆኑም ወደ አንድ ድርጅታዊ ፓርቲ ለመምጣት የሚያግድ ነገር አለ ተብሎ እስካሁን አልተገመገመም ብለዋል። ሁሉም አባል ፓርቲዎች ወደ አንድ ፓርቲ ለመሸጋገር ከዚህ በፊት ባደረጉት ስምምነት መሠረት እየሄደ እንዳለም ገልፀው የድርጅቱ አባላትንም ሕዝብንም በውይይት ለማሳተፍ ተሞክሯል። ይህም የሁሉንም ድርጅቶች ፍላጎትን ያማከለ እንደሆነ ይገልፃሉ። ሐሳቡ መቼ ተነሳ? በማን? እርሳቸው እንደሚሉት ሐሳቡ በአንድ ጀምበር የተጠነሰሰ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በድርጀቱ ሲብላላ ቆይቷል። የዘጠነኛውና የአስረኛው ጉባኤን ጨምሮ በተደጋጋሚ በተለያዩ መድረኮች ላይ ሲነሳ የቆየ ሐሳብም ነው። ነገር ግን ከግንባር ወደ ፓርቲ መሻገር ያስፈልጋል በሚል አፅንኦት ተሰጥቶ የተነሳው በ11ኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው። ታዲያ እስካሁን ለምን ዘገየ ተብለው የተጠየቁት አቶ ሳዳት ጥያቄውን በሳይንሳዊ መንገድ በጥናት ለመመለስ ታስቦ እንደሆነ ተናግረዋል። ይኸው ጥናት በዚህ ዓመት መጨረሻ ፍጸሜውን አግኝቶ ለውይይት እንደሚቀርብም ይጠበቃል። "ሁሉም የፓርቲ አባላት ሐሳቡን አንስተዋል፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግን አራቱም ድርጅቶች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች አጋር ድርጅቶችም እኛም መካተት አለብን የሚል ጥያቄን ሲያርቡ ቆይተዋል" ብለዋል ኃላፊው። • "የሽግግር መንግሥት ተግባራዊ መደረግ አለበት" ይህ የውህደት ጉዳይ በዚህ ወቅት ለመነሳቱ ምን ገፊ ምክንያቶች ይኖሩ ይሆን? አቶ ሳዳት ለጉዳዩ ወቅታዊ ምክንያት የሚጠቀስ ባይኖርም በርካታ ፓርቲዎች መኖራቸው አስፈላጊ እንዳልሆነና ሰብሰብ ማለት እንደሚያሻ አስምረውበታል። ይህ ወደ አንድ ፓርቲ የመሰባሰቡ ነገር በተፎካካሪዎች ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግም ያስፈልጋል ብለዋል። ከዚህም ባሻገር ይላሉ አቶ ሳዳት ኢህአዴግ ጠንካራ ፓርቲ ሆኖ የአገሪቱ መሪ መሆን የሚችል ሰው የማፍራት አቅም ለማዳበር ታልሞ እንደሆነ ውህደቱ ያስፈለገበትን ምክንያት በዝርዝር ያስቀምጣሉ። ይሁን እንጂ አገሪቱ በለውጥ ጎዳና ላይ ከመሆኗ ጋር ተዛምዶ በተለይም ኢትዮጵያዊነት በድርጅቱ ሊቀመንበር ጎልቶ በሚቀነቀንበት ወቅት የውሕደት ሐሳቡ ወደፊት መምጣቱ ለአንዳንዶች በብሔር አደረጃጀትና በፌዴራሊዝም ላይ ለውጥ የሚያጣ ሆኖ ታይቷቸዋል። ፓርቲዎቹ በብሔር የተደራጁና ስማቸውም ብሔርን የሚወክሉ በመሆናቸው ኢህአዴግ ይዋሃዳል ሲባል ፓርቲዎቹ የነበራቸውን አጠቃላይ የብሔር ምንነትን ያጣሉ የሚል ስጋት መፍጠሩም አልቀረም። እርሳቸው ግን "ሁሉም የጋራ አስተዋፅኦ የሚያደርጉበት እንዲሆን የታሰበ እንጂ ኢህአዴግ በፌደራል ሥርዓቱ ላይ የሚፈጥረው ለውጥ የለም፤ ግምባሩን ወደ አንድ ፓርቲ ማምጣት ማለት ወደ አሃዳዊ ሥርዓት ይመጣል ከሚለው ሃሳብ ጋር አይገናንኝም" ሲሉ ሞግተዋል። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶ/ር ፍሰሐ ሐፍተ ጽዮን በበኩላቸው "ወደ ውህደት ከመኬዱ በፊት ብዙ የቤት ሥራዎች መሠራት ይኖርበታል" ሲሉ አቋማቸውን ይገልፃሉ። ቢያንስ በዋና ዋና የፓርቲው ምሰሶዎች በሆኑት፤ የህገ መንግሥት፣ የልማት ሁኔታዎች ላይ ተመሳሳይ አሊያም እጅግ ተቀራራቢ አረዳድ መኖር አለበት፤ እነዚህ ሳይሟሉ ወደ ውህደት ለመሄድ የሚደረገው ጥረት ስኬታማ ይሆናል የሚል እምነት እንደሌላቸው ይናገራሉ። ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሚመለከትም በሁሉም ፓርቲዎች ስምምነት እንደሌለ የአደባባይ ምስጢር ነው በማለት ያስረዳሉ። • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ "የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና አባላት ተቀራራቢ ወይም አንድ ዓይነት አቋም እንደሌላቸው ግልፅ ነው፤ ራሳቸውም በተለያየ ጊዜ የሚናገሩት ይህንኑ ነው" የሚሉት ዶ/ር ፍሰሐ ግምባሩም እንደ ግንባር ተቀራራቢ አቋም ሳይኖረው አንዳንዶቹ የግንባሩ ፓርቲዎች ከፍተኛ የሆነ የጎራ መደበላለቅ እያለ 'እንዋሃድ' ስለመባሉ ያላቸው ሃሳብ አወንታዊ እንዳልሆነ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። በውህደቱ የማይስማማ ፓርቲ ቢኖርስ? ለመሆኑ አንድ ፓርቲ በውህደቱ ባይስማማስ? ምን ሊፈጠር ይችላል? አቶ ሳዳት ይህን ይላሉ፤ "ፓርቲ ለመሆን ውህደት ለመፍጠር የአባል ድርጅት ፍላጎት ይጠይቃል። መሠረታዊ ፍላጎት አለ ብለን እናስባለን። ጥናቱም ያረጋገጠው እሱን ነው። ይህ ከሌለ ግን ወደ ፓርቲም ሳንሸጋገር ከግንባርም መውጣት የሚፈልግ መውጣት ይችላል።" ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ በገዢው ግንባር ውስጥ ያለው የሃሳብ ልዩነት ከውህደቱ በፊት እንዲጠብ ካልተደረገ የኢህአዴግ ዋነኛ አስኳል ሆኖ ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ የዘለቀው ህወሓት በሚመሰረተው ውህድ ፓርቲ ውስጥ የመዝለቁ ነገር አጠያያቂ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።
news-52850382
https://www.bbc.com/amharic/news-52850382
በአሜሪካ ግዛቶች የሰዓት እላፊ አዋጅ ቢጣልም በተቃውሞዎች እየተናጡ ነው
ነጭ ፖሊስ አንገቱ ላይ ተንበርክኮበት የሞተውን ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ አሟሟት ለመቃወም በወጡ ተቃዋሚዎችና በፖሊስ መካከል ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የሰዓት እላፊ ታውጇል።
ሚኒሶታ ውስጥ የተገደለው የጆርጅ ፍሎይድ ሞት በበርካታ አሜሪካ ግዛቶች ውስጥ ቁጣን አቀጣጥሏል። በዓመታት ውስጥ ጥቁር አሜሪካውያን እየደረሰባቸው ያለውን ጭቆና፣ ግፍና በደል ሊቃወሙ ብዙዎች ወጥተዋል። ፖሊሶች በአስለቃሽ ጋዝ ሰልፈኞቹን ለመበተን የሞከሩ ሲሆን በምላሹም የፖሊስ መኪኖች ተቃጥለዋል። በበርካታ ግዛቶች ቁጣና ተቃውሞው የገነፈለ ሲሆን፤ ቢያንስ በ30 ግዛቶች የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። በቺካጎ ተቃዋሚዎች ድንጋይ በመወርወር ቁጣቸውን የገለፁ ሲሆን ፖሊሶችም አስለቃሽ ጭስና ጋዝ ረጭተዋል፤ በርካታ ተቃዋሚዎችንም በቁጥጥር ስር አውለዋል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጆርጅ ፍሎይድ የግፍ አገዳደል ቁጣቸው የገነገፈለው ተቃዋሚዎችን "ዘራፊዎችና ሥርዓት አልበኞች" ብለው መወረፋቸው ቁጣን ቀስቅሷል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ዴሪክ ቾቪን የተባለ ነጭ ፖሊስ የአርባ ስድስት ዓመቱ ጆርጅ ፍሎይድን በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ፤ ለዘጠኝ ደቂቃዎች ያህል አንገቱ ላይ በመንበርከኩ መተንፈስ ሳይችል ህይወቱ አልፏል። መላው ዓለምን ያስደነገጠው ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው ጆርጅ ፍሎይድ "እባክህ መተንፈስ አልቻልኩም" እያለ ሲማፀን ነበር። በበርካታ ግዛቶች የተነሳውን ቁጣም ተከትሎ ዴሪክ ቾቪን እንዲሁም አብረውት የነበሩት ሦስት ፖሊሶች ከሥራ ተባረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ዴሪክ ቾቪን በጆርጅ ፍሎይድ ግድያም በቁጥጥር ስር ውሏል።. ተቃውሞዎችም ወደ ዋሺንግተን ያመራ ሲሆን በዋይት ሐውስም በርካቶች ተሰብስበው የትራምፕን አስተዳደር ተቃውመዋል። በአትላንታ አንዳንድ ህንፃዎች መሰባበራቸውን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተላልፏል። ጆርጅ ፍሎይድ በሞተባት ሚኒያፖሊስ ከፖሊስ በተጨማሪ የአገሪቱ ብሔራዊ ዘብ አካባቢውን አጥሮት የሚገኝ ሲሆን የሰዓት እላፊ አዋጅም ተጥሏል። ዘ ስታር ትሪቡን እንደዘገበው ብሔራዊ ዘብ የአገሪቱ ተጠባባቂ ኃይል ሲሆን በአገሪቱ ፕሬዚዳንት ወይም በአካካቢው ገዢ ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ ሲደረግላቸው ይመጣሉ ተብሏል። በአትላንታ፣ ሚኒያፖሊስ፣ ሎስ አንጀለስ፣ ፖርትላንድና ሉስቪልና ሌሎች ከተሞች የሰዓት እላፊ አዋጅ ቢጣልም አሁንም ተቃውሞች ቀጥለዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሚኒያፖሊስ ከንቲባን ተቃውሞችን በቁጥጥር ስር አለማዋላቸውን ተችተው ብሔራዊ ዘቡ ጣልቃ በመግባት በቁጥጥር ስር ያውለዋል ብለዋል። የፕሬዚዳንቱ ተቀናቃኝ ጆ ባይደን በበኩላቸው ጆርጅ ፍሎይድን የገደሉት ፖሊሶች ወደ ፍትህ ማቅረብ እንደሚገባቸውና ባለው መከፋፈል እሳት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወርፈዋቸዋል።
news-48306035
https://www.bbc.com/amharic/news-48306035
ትራምፕ፡ "ወጣትና የተማሩ ስደተኞችን እንቀበላለን"
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞችን በተመለከተ ባስተዋወቁት አዲስ ሕግ ወጣት፣ በደንብ የተማሩና እንግሊዝኛ መናገር የሚችሉ ግለሰቦች ላይ በትኩረት እንደሚሠሩ ገለጹ።
ፕሬዝዳንቱ በኋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፤ አሁን ያለውና አሜሪካ ውስጥ ዘመድ ወይም ጓደኛ ላላቸው ስደተኞች ቅድሚያ የሚሰጠውን ሕግ ወደጎን በማለት አዲሱ አሠራር መተግበር አለበት ብለዋል። • ትራምፕ ዲቪን ማስቀረት ይችላሉ? • ትራምፕ ከ'ነጩ ቤተ መንግሥት' ሊባረሩ ይችላሉ? አክለውም የድንበር ጥበቃ እንደሚጠናከርና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ጥብቅ ምርመራ እንደሚደረግ ተናገረዋል። ከፍተኛ ዴሞክራት ኃላፊዎች በበኩላቸው ውሳኔው ገና ተግባራዊ ሳይደረግ "ያበቃለት ነገር ነው" በማለት አጣጥለውታል። ትልቅ ህልም ሰንቀው ወደ አሜሪካ የሄዱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችና በልጅነታቸው ወደአሜሪካ አቅንተው እስካሁን ዜግነት ያላገኙ ሰዎችን የሚያገልና ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው በማለት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ አዲሱ ሕግ አሜሪካን ዓለም ሁሉ የሚመኛት ሃገር ያደርጋታል ቢሉም፤ ሕጉ ተግባራዊ እስኪደረግ ብዙ ፈተናዎች እንደሚኖርበት ይጠበቃል። ''ወደ ሃገራችን መግባት የሚፈልጉትን ሁሉ እጃችንን ዘርግተን እንቀበላቸዋለን። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ችሎታና እውቀት ላይ የተመሰረት መሆን አለበት'' ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። "ትልቅ ለውጥ ለማምጣት እየሠራን ሲሆን፤ ችሎታ ያላቸው ስደተኞችን ቁጥር ከ12 በመቶ ወደ 57 በመቶ ከፍ ለማድረግ አስበናል።'' ከዚህ በተጨማሪ ስደተኞች እንግሊዝኛ እንዲማሩ የሚገደዱ ሲሆን የሥነ ምግባር ትምህርትም ይሰጣቸዋል ተብሏል። • ሚሼል ኦባማ በአሜሪካ እጅግ ተወዳጇ ሴት ተባሉ • ዜግነት ለማግኘት ሲባል አሜሪካ ሄዶ መውለድ ሊቀር ይሆን? የታችኛውን ምክር ቤት ዴሞክራቶች በአብላጫ ድምጽ በሚመሩበት በዚህ ወቅት የዶናልድ ትራምፕ አዲሱ ሕግ በኮንግረሱ ይሁንታ ለማግኘት ሊከብደው ይችላል። ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በፊት የዲቪ ፕሮግራምን ለማስቀረት የቀረበውን ዕቅድ እንደሚደግፉ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ፕሮግራሙን የማስቀረት ስልጣን ስለሌላቸው የአሜሪካ ኮንግረስ አዲስ የስደተኞች ሕግ እስኪያወጣ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። አዲሱ ሕግ፤ በሃገሪቱ ሴኔት ውስጥ በወግ አጥባቂዎች ድጋፍ ያገኘውና የስደተኞችን ቁጥር በግማሽ ይቀንሳል የተባለውን እቅድ ለማሳካት ትራምፕን ይረዳቸዋል ተብሏል።
news-55715924
https://www.bbc.com/amharic/news-55715924
ባይደን በመጀመሪያ ቀናቸው አወዛጋቢ የተባለውን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት ይሰርዛሉ ተባለ
በነገው ዕለት በዓለ ሲመታቸውን የሚፈፅሙት ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በስልጣን የመጀመሪያ ቀናቸው አወዛጋቢ የሆነውን ኪስቶን ኤክስ ኤል የተባለውን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት እንደሚሰርዙ የአሜሪካ ሚዲያዎች ሪፖርት አድርገዋል።
የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው ፕሮጀክት አልሞ የነበረው የካናዳዊቷን ግዛት አልበርታንና የአሜሪካን ኔብራስካን ግዛትን የሚሸፍን 1 ሺህ 900 ኪሎሜትር እርዝማኔ እንዲኖረው ታቅዶ ነበር። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች እንዲሁም ቀደምት አሜሪካውያን ይህ ፕሮጀክት እውን እንዳይሆን ለአስር አመታት ያህል ታግለዋል። ፕሮጀክቱ በነበረበትም ጫና በተወሰነ መልኩ ስራዎች ተቋርጠው የነበረ ቢሆንም ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት አመታት በፊት እንዲጀመር አድርገውታል። ከትራምፕ በፊት በስልጣን ላይ የነበሩት ባራክ ኦባማ የማስተላላፊያ ቧንቧ ግንባታ ስራ እንዲቋረጥ የሚያዘውን ህግ በከፍተኛ ድምፅ እንዲፀድቅ ቢያደርጉም ትራምፕ ያንን ውሳኔ ቀልብሰውታል። የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሪጀክቱ 8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያስወጣልም ተብሎ ነበር። ባይደን ምን ሊሰሩ አቅደዋል? ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ቢሮ የተገኘ ደብዳቤ አይነተናል ያሉት የካናዳና አሜሪካ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ጆ ባይደን በበዓለ ሲመታቸው ቀን የኪስቶን ኤክስኤል ነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ፈቃድን ለመሰረዝ ፍፁማዊ ስልጣናቸውን እንደሚጠቀሙ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የካርበን ልቀትን ለመቀነስና ለመቆጣጠር የተፈረመውን አለም አቀፉን የፓሪስ ስምምነት አገራቸው እንድትመለስ ያደርጓታል። ትራምፕ ከአለም አቀፉ የፓሪስ ስምምነት አገራቸውን ያስወጧት በያዝነው አመት ህዳር ወር ላይ ነበር። ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአየር ንብረት ለውጥን መታገል አስተዳደራቸው የሚያስቀድመው ዋነኛ ተግባር ነው በማለትም አስምረዋል ። ከነዳጁ ማስተላለፊያ ቧንቧ ጋር በተያያዘም የአልበርታው መሪ ጃሰን ኬኒ የጆ ባይደን እቅድ ከፍተኛ ስጋት እንዳጨረባቸው ገልፀው የቧንቧ ዝርጋታው ፕሮጀክት የሚታጠፍ ከሆነ መንግሥታቸው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል። የኪስቶን ኤክስኤል የነዳጅ ቧንቧ 830 ሺህ በርሜል ያልተጣራ የነዳጅ ድፍድፍ ከአልበርታ ወደ ኔብራስካ እንዲያስተላልፍ ታቅዶ ነበር። ኔብራስካም ከደረሰም በኋላ እዚያው ያለው የማስተላለፊያ ቧንቧ ጋር በማገናኘት ሜክሲኮ ገልፍ ወዳለው ማጣሪያ ቦታም ይወሰዳል። የአልበርታ ነዳጅ ከአሸዋ፣ ውሃ፣ ሸክላ ጋር የተቀላቀለ በይዘቱም ወፈር ያለ ሲሆን፤ ነዳጁንም ለማጣራት ከፍተኛ የሆነ ኃይል ጉልበትና ወጪውም ጣራ የነካ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም የተነሳ እንደ ግሪን ፒስ ያሉ የአካባቢ መብት ጥበቃ ተሟጋቾች ከዚህ ነዳጅ የሚለቀቀው ጋዝ በተለምዶ ከሚታወቀው 30 በመቶ ጭማሬ አለው ይላሉ። ነገር ግን የካናዳ መንግሥት በበኩሉ ከባቢን በማይጎዳና ኃይልንም በማይጨርስ መልኩ ማጣራት የሚያስችል ቴክኖሎጂ አለ በማለት ይከራከራል። ቀደምት የአሜሪካ ህዝቦች በበኩላቸው የአልበርታን አካባቢ እንዲሁም የፌደራል መንግሥቱን ድፍድፍ ነዳጅ ለማውጣት በሚል ለ15 አመታት ላደረሱት ጉዳት ከሰዋል። ሰርተው የሚበሉበትንና መሬታቸውን ያለነሱ ፈቃድ ለከፍተኛ ጉዳት ዳርጎታልም በማለት ይከሳሉ።
54492471
https://www.bbc.com/amharic/54492471
ኮሮናቫይረስ ፡ አረጋዊያንን በመጦሪያና ማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ በአካል ሄዶ መጠየቅ ተከለከለ
የኢትዮጰያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳቢውን የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመግታትና ዋንኛ ተጠቂ የሆኑ ዜጎችን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲባል፤ ዜጎች በመጦርያና ማገገምያ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ አረጋዊያንን በአካል ሄደው ከመጠየቅ እንዲቆጠቡ አሳሰበ፡፡
ተቋሙ መስከረም 30/2013 ዓ. ም. ባወጣው ዘለግ ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ከዚህ ዕለት በኋላ ተግባራዊ የሚደረጉ ልዩ ልዩ መመርያዎችን በዝርዝር አስተላልፏል፡፡ ኮቪድ-19 ከተከሰተ ወዲህ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል አቋቁሞ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኘው ተቋሙ፤ ወረርሽኙን ለመከላከልና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ስለሚወሰዱ ክልከላዎች እና ግዴታዎች በሕግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው መመሪያዎቹን ያወጣሁት ብሏል። በመመርያው መሠረት፤ ማንኛውም ሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ መንቀሳቀስ የከለከለ ሲሆን፤ ከዚህ ክልከላ ነጻ የሆኑት ዕድሜያቸው ከስድስት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት እና በማስረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ችግር ያለባቸው ዜጎች ብቻ ናቸው፡፡ አገልግሎት ሰጪዎችን በተመለከተ፤ ማንኛውም መንግሥታዊ የሆነና መንግሥታዊ ያልሆነ የግል ተቋም ሠራተኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ በታች ተጠጋግተው እና የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ በጥብቅ ደንግጓል፡፡ ይህም ብቻም ሳይሆን የንግድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ላላደረገ ሰው አገልግሎት መስጠትን ክልክል አድርጓል፡፡ የግልና የመንግሥት የትምህርት ተቋማትም በአካል ተቀራርቦ ትምህርት መስጠት መጀመር እንዳለበት ይፋ ሳይደረግ ማንኛውንም ተማሪ ማስተናገድ እንደሌለባቸው ተወስቷል፡፡ በተለይም የህጻናት ማቆያ ማዕከሎች አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ሳይወሰንና አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ በተመለከተ በመመሪያ ሳይወጣ አገልግሎት መስጠት አይችሉም። የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በሕግ ከተወሰነው የመጫን አቅም በላይ ሰዎችን መጫን አይችሉም ይላል መመርያው፡፡ በተለይ ደግሞ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት መስጠት የለባቸውም ብሏል፡፡ የግንባታ ፕሮጀክት አሠሪዎች በተመለከተ፤ በግንባታ ቦታዎች ላይ አስፈላጊውን ንጽህና ለመጠበቅ የሚረዱ ግብአቶች ሳይሟሉ ሠራተኞችን ማሠራት ክልክል እንደሆነ በመግለጫው አሳስቧል፡፡ መመርያው ሃይማኖታዊ እና የአደባባይ በዓላት አከባበርን በተመለከተ እንዲሁም የጭፈራ፣ ሲኒማ፣ ቴአትር እና የሥዕል ጋላሪ ቤቶች በምን መንገድ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው እንዲሁም ተግባራዊ ማድረግ ስለሚገባቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ ሌላ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ የአረጋዊያን የመጦሪያ ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ በጥብቅ የከለከለ ሲሆን፤ በመመሪያ የተደነገጉ ክልከላዎችን እና ግዴታዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው የወንጀል ሕግ መሰረት ተጠያቂ ይሆናል ተብሏል። ይህ መመርያው ተግባራዊ የሆነው ከመስከረም 25/2013 ዓ. ም. ጀምሮ ነው፡፡
news-55335598
https://www.bbc.com/amharic/news-55335598
ኮሮናቫይረስ፡ የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 ክትባትን የሚያገኙት መቼ ነው?
የኮቪድ-19 ክትባቶች በዓለም ላይ ተስፋን አጭረዋል። ነገር ግን አሁንም የአፍሪካ አገራት ይህንን ክትባት እንዴትና መቼ እንደሚያገኙት ጥርት ያለ መልስ አልተገኘም።
የዓለም ጤና ድርጅት የሰራው አንድ ጥናት እንደሚያሳየው የኮቪድ-19 ክትባት ዝግጁ ከሆነ፣ 40 የአፍሪካ አገራት ክትባቱን ለመስጠት ዝግጁ ናቸው። ነገር ግን እነዚህ አገራት በሙሉ በተመሳሳይ ዝግጁነት ላይ ያሉ አይደሉም። አንዳንድ አገራት ግብረ ኃይል አቋቁመው ክትባቱ ሲመጣ እንዴት መከፋፈል እንዳለበት የሚያስረዳ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተዋል። ሌሎች ደግሞ ክትባቱን ለማከማቸት የሚያገለግል መጋዘን መግዛት አልያም ያላቸውን ለዚህ ዝግጁ እንዲሆን በማድረግ ላይ ናቸው። ነገር ግን እንደ ፋይዘር ያሉ የኮቪድ-19 ክትባቶች መሠረታዊ ችግራቸው የሚያስፈልጋቸው ማከማቻ መጋዘን ቅዝቃዜው ከዜሮ በታች 70 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መሆኑ ነው። ሌሎች አገራት ከፊታቸው የተደቀነባቸው ፈተና በተለያዩ የማሕበራዊ መገናኛ ብዙኀን ክትባቱ ላይ የሚሰራጩ ሐሰተኛ እና መሰረተ ቢስ መረጃዎች ናቸው። ይህንን ችግር ለማስወገድ የመረጃን እውነታነት የሚያጣሩ ተቋማት፣ እንዲህ አይነት መረጃዎችን በመሰብሰብ ሐሰተኛነታቸውን እያጋለጡ ሲሆን እንደ ዓለም ጤና ድርጅትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላሉ ተቋማት መረጃውን በማጋራት የተሻለ ምላሽ በሚያገኙበት መንገድ ላይ እየሰሩ ነው። በአፍሪካ የክትባቱ ሙከራ እየተካሄደ ነው? እስካሁን ድረስ አራት የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ እያደረጉ ነው። እነዚህም ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ እና ሞሮኮ ናቸው። ኬንያና ደቡብ አፍሪካ እየሞከሩት ያለው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እና አስትራዜኔካ የባለጸጉት ክትባት ነው። ግብጽ በበኩሏ ራሷ የሰራችውን እና "ኮቪድ ቫክ 1" ስትል የሰየመችውን ክትባት እየሞከረች ትገኛለች። ተመራማሪዎች የአፍሪካ አገራት በኮቪድ-19 ክትባት ምርምሮች ላይ አፍሪካውያን መሳተፋቸው ወሳኝ ነው ሲሉ ይመክራሉ። ይህ ካልሆነ ግን በመላው ዓለም የሚሰራ ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ያደናቅፈዋል ሲሉም ስጋታቸውን ይገልጻሉ። የአፍሪካ አገራት የኮቪድ ክትባቶችን መቼ ሊያገኙ ይችላሉ? የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ድርጅት እንደሚለው ከሆነ በአህጉሪቱ እስከ ሚያዚያ ወር ድረስ የኮቪድ-19 ክትባት ላይሰጥ ይችላል። እንደ ድርጅቱ ገለፃ ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ባለው ወር ውስጥ ሊጀመር ቢችልም የአህጉሪቱን ሕዝብ 60 በመቶ (700 ሚሊዮን) ሕዝብ ለመከተብ ከ ሁለት እስከ ሶስት ዓመት ድረስ ሊፈጅ እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል። ይህ ደግሞ አህጉሪቱ በክትባት እንዲሁም አስቀድመው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የጋርዮሽ የመከላከል አቅም (ሀርድ ኢሚዮኒቲ ) እንድታዳብር የራሱን አስተዋጽኦ የሚጫወት ሲሆን ይህም ቫይረሱ ከአንድ ሰው ወደ ሌላው የመተላለፍ እድሉን በእጅጉ ይቀንሰዋል ይላሉ። ድርጀቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ ጉባዔ እንዲያካሂድ እና የኮቪድ-19 ክትባትን በተሻለ ፍትኃዊነት ለአለም ሕዝብ እንዴት ማከፋፈል እንደሚቻል እንዲመክር ፍላጎት አለው። የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ጆን ንኬጋሶንግ እንዳሉት የገንዘብ አቅማቸው ፈርጣማ የሆነ አገራት የአፍሪካ አህጉር መድሃኒቱን ለማግኘት ስትራኮት ቁጭ ብለው የሚመለከቱ ከሆነ አሳዛኝ ነው። እነዚህ በምጣኔ ኃብታቸው ኃያል የሆኑ አገራትም ለሕዝባቸው ተጨማሪ ክትባቶችን ለማግኘት ከመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ጋር የሚያደርጉት ስምምነት እና የስምምነት ገንዘብ መጠንም አስጨንቋቸዋል። ከበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በምጣኔ ሃብታቸው ደካማ የሆኑ አገራት ይህ የሐብታም አገራት ጉዳይ ካልተፈታ ክትባት ማቅረብ የሚችሉት ከአስር ዜጎቻቸው መካከል ለአንዱን ብቻ ነው። አፍሪካ ከየትኞቹ አገራት መድሃኒቱን ለማግኘት ተማምናለች? በቅርቡ በተካሄደው የአፍሪካ ቻይና ጉባዔ ወቅት፣ ቻይና የምታዘጋጀው ክትባት ዝግጁ እንደሆነ ለአፍሪካ አገራት ቅድሚያ እንደምትሰጥ ቃል ገብታለች። ቻይና የክትባት ድጋፍ አደርጋለሁ ብላ ቃሏን ከሰጠቻቸው አገራት መካከል ዛምቢያና ቡርኪናፋሶ ይገኙበታል። ኬንያም አይኗን በቻይና ላይ የጣለች ሲሆን ከአገሪቷ ሕዝብ መካከል 20 በመቶ ያህሉን መከተብ የሚያስችላትን 24 ሚሊዮን ክትባቶች አዝዛለች። አንዳንድ አገራት ክትባቱን በቀጥታ ለመግዛት የተዘጋጁ ሲሆን፣ በርካቶች ግን ክትባቱን ለማግኘት ኮቫክስ ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል። ኮቫክስ ምንድን ነው? ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው። ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ኢኒሼቲቭ ተቀብለውታል። ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ኢኒሼቲቭ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች። እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል። ክትባቱን ቀድሞ የሚያገኘው ማን ነው? ይህ አገራቱ የኮቪድ-19 ክትባትን ስርጭት እንዴት ለማካሄድ በሚወስኑት ውሳኔ ላይ ይመሰረታል። የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና መካለከል ላይ ከፊት ያሉ በመሆኑ ክትባቱን ቅድሚያ ማግኘት እንዳለባቸው ያስቀምጣል። በመቀጠል ደግሞ ወደ አገራት መግቢያና መውጫ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦች፣ በእድሜ የገፉ ሰዎችና የተለያዩ ተያያዥ የጤና ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ክትባቱን ከሌሎች ዜጎች ቀድመው ያገኛሉ ሲል አስቀምጧል። ቀሪው ሕዝብ እነዚህ ዜጎች ከተከተቡ በኋላ ይሰጠዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት በመመሪያ ላይ አመልክቷል።
news-51625033
https://www.bbc.com/amharic/news-51625033
የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ደቡብ አፍሪካውያን እናቶች ያለእውቅናቸው እንዲመክኑ ተደርገዋል
ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝባቸው በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን እናቶች ለመውለድ ባቀኑበት የጤና ተቋም ከእውቅናቸው ውጪ ወይም ተገደው ዳግም እንዳይወልዱ እንዲመክኑ መደረጋቸውን መንግሥት ያደረገው ምረመራ አጋለጠ።
በበርካታ የመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሃኪሞች ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ እናቶች የሚያረግዙ ከሆነ የሚወለደውን ልጅ ህይወት አደጋ ላይ ይጥላሉ በማለት "እናቶችን በማስገደድ ሰብዓዊ ባልሆነ መንገድ መካን እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል" ተብሏል። የደቡብ አፍሪካ የጾታ እኩልነት ኮሚሽን ላለፉት አምስት ዓመታት የ48 እናቶችን ጉዳይ ሲመረምር ቆይቷል። ኮሚሽኑ ባደረገው ምረመራ እናቶቹ በሙሉ ቀዶ ህክምና ለመውለድ ወደ የመንግሥት ሆስፒታሎች ከሄዱ በኋላ፤ ሃኪሞች ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ እናቶች ማርገዝ እንደሌለባቸው እና የሚያረግዙ ከሆነ ደግሞ የሚወለደውን ልጅ ህይወቱ እንዲያልፍ እያደረጉ እንደሆነ እንደተነገራቸው ተረጋግጧል። "የተወሰኑት እናቶች ደግሞ ላለመውለድ በፊርማቸው እንዲያረጋግጡ የተደረጉት በምጥ ህመም ላይ ሳሉ እንደሆነ እና ፍቃደኛነታቸውን ያልገለጹ እናቶች ደግሞ በቅጾቹ ላይ ፊርማቸውን ካላኖሩ የህክምና እርዳታ እንደማይደረግላቸው ተነግሯቸዋል" ኮሚሽኑ ጨምሮ ከሆስፒታሎቹ የወላድ እናቶች ዶሴዎች እንዲሰወሩ ስለተደረጉ የጀመረውን ምረመራ አጥጋቢ በሆነ መልኩ መጨረስ አልቻልኩም ብሏል። የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚንስቴር ከጾታ እኩልነት ኮሚሽን ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ሬውተርስ ዘግቧል።
54903829
https://www.bbc.com/amharic/54903829
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጋዜጠኞች መታሰር እንዳሳሰበው ገለፀ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ያሉ ጋዜጠኞች መታሰር እንዳሳሰበው ገልጿል።
የአዲስ ስታንዳርድ መፅሄት አዘጋጅ መድሃኔ እቁባሚካኤል እንደገና ለእስር መዳረግ፣ የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው በቁጥጥር ስር መዋሉ እንዳሳሰባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በትናንትናው ዕለት ህዳር 1/ 2013 ዓ.ም ይህንን መልእክት ያሰፈሩት ኮሚሽነሩ ከሚዲያ ጋር የተገናኘ ጥፋት ጠፍቶም ከሆነ ፍትሃዊ በሆነ መንገድና ስርአትን በተከተለ ሁኔታም እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል። ሁኔታውንም በቅርበት እንደሚከታተሉም በትዊተር ገፃቸው መልዕክታቸውን አስፍረዋል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጠኞች ሃፍቱ ገብረ እግዚአብሐር፣ ፀጋዬ ሃዱሽና አብርሃ ሃጎስ እንዲሁም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርኩ ጋዜጠኛ ኡዲ ሙሳ ተጨማሪ አራት ጋዜጠኞች በአንድ ምሽት መታሰር ስጋት እንደፈጠረባቸውም በዛሬው ዕለት ህዳር 2/ 2013 ዓ.ም አክለው አስፍረዋል። "በማንኛውም ጊዜ የሰዎችን ከህግ አግባብ ውጪና ኢፍትሐዊ በሆነ መልኩ ያለመታሰር መብት እንዲከበር ጥሪ እናቀርባለን" በማለትም ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አትቷል። ሃብቶም ገብረ እግዚአብሔርና ፀጋዬ ሃጎስ በኢፕድ ስር በሚታተመው የእንግሊዝኛው ሄራልድ ጋዜጣ አዘጋጆች ሲሆኑ አብርሃ ሃጎስ ደግሞ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የአረብኛው ክፍል አል አለም በሪፖርተርነት ይሰራል። ቅዳሜ እለት ጥቅምት 28/2013 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው መድሃኔ ቢለቀቅም ሰኞ እለት ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም እንደገና እንደታሰረም ተገልጿል። ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በተጨማሪ በጋዜጠኞች መብት ላይ የሚሰራው ሲፒጄ በበኩሉ የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው እንዲፈታ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጥሪ አቅርቧል። ጋዜጠኛው ጥቅምት 25/ 2013 ዓ.ም በቁጥጥር ስር እንደዋለና ክስም እንዳልተመሰረተበት አስፍሯል። ሶስት የፖሊስ መለዮና አንድ የሲቪል ልብስ የለበሱ ግለሰቦች አዲስ አበባ ወደሚገኘው የአውሎ ሚዲያ ማዕከል ቢሮ በማምራት በቃሉን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ሲፒጄ የአውሎ ሚዲያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወልደጊዮርጊስ ተክላይን ጠቅሶ በዛሬው ዕለት ህዳር 2/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫው አካቷል። የአውሎ ሚዲያ ባወጣው መግለጫም ፖሊሶቹ የእስር ትዕዛዝም ይሁን የፍርድ ቤት ወረቀት እንዳላቀረቡና ጋዜጠኛውንም በቁጥጥር ስር ለምን እንዳዋሉትም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች የሚዲያው ሰራተኞችንም ስለ እስሩ እንዳይናገሩ ትእዛዝ ሰጥተዋል ብለዋል። የፖሊስ አባላቱ ቢሯቸውን በመፈተሽ ሶስት ላፕቶፖችን እንደወሰዱና፣ የበቃሉ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ማስታወሻ፣ የድምፅ መቅጫና 'ሃርድ ዲስክ' መውሰዳቸውንም ሲፒጄ ወልደጊዮርጊስን ዋቢ አድርጎ አስፍሯል። ጥቅምት 27/ 2013 ዓ.ም በፌደራል አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀርቦ የነበረ ሲሆን ሃሰተኛ መረጃን በማሰራጨትና የኢትዮጵያ መንግሥትን በማዋረድ፣ በምዕራብ ወለጋ የተገደሉ አማራዎችን በተመለከተ የብሄር ግጭት በማነሳሰት መወንጀሉም ተገልጿል። ፖሊስ የጠቀሳቸው ሪፖርቶች እንደለሌም ወልደጊዮርጊስ ይናገራል። በጠቅላይ አቃቤ ህግ የሰብዓዊ መብቶች አክሺን ፕላን ቢሮ ኃላፊ ይበቃል ግዛው በበኩላቸው በጥላቻ ህግና ሃሰተኛ መረጃን በማሰራጨት ህጉ ተጠርጥሮ እንደተከሰሰ አስረድተዋል። አቶ ይበቃል በቃሉ በሰራው ሪፖርት መንግሥትና መከላከያ ሰራዊት በምዕራብ ወለጋ 200 አማራዎችን ገድለዋል በማለት መንግሥትን በጥቃቱ ቀጥታ ተሳታፊ በማድረግ እንደሰራ ጠቅሰዋል። የትኛው ሪፖርት እንደሆነ ባይጠቅሱም የሟቾች ቁጥር ግን 34 ነው ብለዋል። ወልደጊዮርጊስ በኩሉ ሚዲያው የሟቾችን ቁጥር አስመልክቶ በጥቃቱም ሆነ ከጥቃቱ በኋላ ከባለስልጣናት የተሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ዋቢ በማድረግ ነው ብሏል። ሚዲያዎችም ሆነ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በጥቃቱ የሞቱትን ትክክለኛ ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ ዘግበዋል። ወልደጊዮርጊስ በበኩሉ መንግሥትን በግድያዎቹ ጥፋተኛ ባያደርጉም መንግሥትን የሚተቹ ሪፖርቶች አቅርበናል በማለት መናገሩን ሲፒጄ አስፍሯል።
47302288
https://www.bbc.com/amharic/47302288
አይ ኤስን ተቀላቅላ የነበረችው እንግሊዛዊ ታዳጊ ዜግነቷን ልትነጠቅ ነው
በ15 ዓመቷ እስላማዊ ቡድኑን በሶሪያ የተቀላቀለችው ሸሚማ ቤገም የእንግሊዝ ዜግነቷን ልታጣ እንደምትችል ተገለፀ።
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጮች እንዳስታወቁት የ19 ዓመቷ ወጣት የሌላ ሀገር ዜግነት ሊኖራት ስለሚችል የእንግሊዝ ዜግነቷን ልታጣ ትችላለች። የቤተሰቧ ጠበቃ የሆኑት ታስኒም አኩንጄ በውሳኔው ማዘናቸውን ገልፀው "ያሉትን ህጋዊ መንገዶች ሁሉ እንጠቀማለን" ብለዋል። ቤገም ለንደንን ለቅቃ የሄደችው በ2015 ሲሆን አሁን ግን መመለስ እንደምትፈልግ መዘገቡ ይታወሳል። • አይኤስን የተቀላቀለችው ተማሪ ወደ እንግሊዝ መመለስ እፈልጋለሁ እያለች ነው ባለፈው ሳምንት የአይ ኤስ እስላማዊ ቡድን ጠንካራ ግዛት ከነበረው ባጉዝ፣ መጥታ በሶሪያውያ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የተገኘች ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ላይም ወንድ ልጅ ተገላግላለች። በእንግሊዝ የዜግነት ሕግ መሰረት አንድ እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው ግለሰብ ዜግነቱን ሊያጣባቸው ከሚችልባቸው ምክንያቶች መካከል የሀገር ውስጥ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ "ለሕብረተሰቡ መልካም ጥቅም ሲባል" ብሎ ሲያምንና በሂደቱ ዜጋው ዜግነት አልባ የማይሆን ከሆነ ነው። የሀገር ውስጥ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት "ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች መስሪያ ቤቱ በግልፅ እንዳስቀመጠው ለሀገሪቱ ዜጎችና እዚህ ለሚኖሩ ግለሰቦች ደህንነት ቅድሚያ ይሰጣል።" አክለውም በግለሰቦች ጉዳይ አስተያየት እንደማይሰጡ ገልፀው "ያሉት መረጃዎች በሙሉ ከግምት ውስጥ ገብተውና አፅንኦት ተሰጥቶት የሚሰራ" ነው ብለውታል የአንድን ግለሰብ ዜግነት ስረዛ። • ትራምፕ ከ'ነጩ ቤተ መንግሥት' ሊባረሩ ይችላሉ? • አልሲሲ እስከ 2034 ግብጽን ሊገዙ ይችላሉ በሀገሪቱ የሽብርተኛ ህግ ላይ የሰሩ ግለሰቦች እንደሚሉት ከሆነ የቤገም እናት የባንግላዲሽ ዜግነት ካላት ልጅቷም በባንግላዲሽ ህግ መሰረት ዜግነት ይኖራታል። የቤገም ቤተሰቦች የባንግላዲሽ ዝርያ ያላቸው ሲሆን ቤገምን ቢቢሲ ስለ ጉዳዩ በጠየቃት ወቅት ግን አንድም ጊዜ ወደ ባንግላዲሽ ሄዳ እንደማታውቅና ፓስፖርትም እንደሌላት ገልፃለች። ከቤገም የተወለደው ልጅም በህጉ መሰረተ ዜግነቷ ከመፋቁ በፊት ስለተወለደ እንግሊዛዊ ዜግነት ይኖረዋል።
news-47621604
https://www.bbc.com/amharic/news-47621604
'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ?
በመጥፎ አጋጣሚ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ዕለተ እሁድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተሳፈሩ 157 ተጓዦች አውሮፕላኑ ጊምቢቹ ወረዳ ቱሉ ፈራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ ተከስክሶ አንዳቸውም አለመትረፋቸው ዓለምን አስደንግጧል።
አቶ ባትሪ ለማ እና አቶ ደቻሳ ጉተማ አደጋው የደረሰበት አካባቢ ነዋሪዎች ለማያውቋቸው የአደጋው ሰለባዎች ልባቸው በሀዘን ተሰብሮ ከመጣው ጋር ሲያለቅሱና ሃዘናቸውን ሲገልጹ የሰውነት ሩህሩህነታቸውን ለዓለም አሳይተው ርዕስ ሆነው ሰንብተዋል። • ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው ከሁሉ ከሁሉ ይህን የአውሮፕላን አደጋ መጥፎ ዕጣ የደረሰበት ቦታ ስያሜ የነገሮችን ግጥምጥሞሽ አነጋጋሪ ያደርገዋል። 'ቱሉ ፈራ' የሚለው የኦሮሚኛ ስያሜ 'መጥፎ ዕድል' እንደማለት እንደሆነ የይነገራል። በእርግጥም የዚህ ተራራ ስያሜ ከመጥፎው አጋጣሚ ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑንና እንዴትስ ስያሜውን እንዳገኘ ለማወቅ ቢቢሲ የአካባቢውን አዛውንቶች አነጋግሯል። አቶ ባትሪ ለማ በአካባቢው ከሚኖሩ አዛውንት አንዱ ናቸው። "ቱሉ ፈራ ይህን ስም ያገኘው በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ነው" ይላሉ። ቦታው ከፍታማ ስለሆነ የንፋሱ አቅጣጫ ወዴት እንደሚነፍስ ለማወቅ ያስቸግራል የሚሉት አቶ ባትሪ "በስፍራው ያለው ቅዝቃዜው ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች በተራራው ላይ መኖር ሲያቅታቸው ቱሉ ፈራ ብለው ሰየሙት። በአማርኛ የመጥፎ እድል ማለት ነው" በማለት ነው ይላሉ። • ሁለቱን የአውሮፕላን አደጋዎች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ እንደ አቶ ባትሪ አገላለፅ የአካባቢው ቦታዎች በሙሉ የተሰየሙት ባለው የአየር ሁሌታ ላይ ተመስርተው ነው። ለምሳሌ አውሮፕላን የወደቀበት ቦታ ሃማ ይባላል። ይህ ማለት ክፉ ወይም መጥፎ ማለት ነው። በአካባቢው የሚገኝ ተራራ ደግሞ ፈራ ተራራ ይባላል። አውሮፕላኑ ከወደቀበት ቦታ ቀጥሎ ያለው ደግሞ ነኑ እኩቢ ሲባል የበሽታ አካባቢ ማለት እንደሆነ አቶ ባትሪ ያስረዳሉ። በኦሮሚኛ ቱሉ ፈራ የሚሉት ቃላት በቀጥታ ሲተረጎሙ "መጥፎ ዕድል" የሚል ትርጉምን ይይዛሉ። በእርግጥም በአካባቢው ያጋጠመው አደጋ ሰለባዎች መጥፎ እድል ገጥሟቸው ሃዘኑ ከሃገር አልፎ ለዓለም ተርፏል። የቱሉ ፈራ ይሁን እንጂ ከአካባቢው ስያሜ አመጣጥ ጋር የተለያዩ ትርጉም የሚሰጡ ታሪካዊ ዳራዎችን የሚየጠቅሱ የአካባቢው አዛውንቶች አልጠፉም። ለዚህም ሌላኛው የጊምቢቹ ወረዳ አዛውንት አቶ ደቻሳ ጉተማ የሃማ ቁንጥሹሌ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፤ የፈራ ተራራ ስያሜ ምንጩ ሌላም ታሪክ እንዳለው ይጠቅሳሉ። • "እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ ተራራዎች ስያሜያቸውን ያገኙት በጥንት ዘመን አካባቢውን ሲያስተዳድሩ ከነበሩ ነገሥታት ጋር ተያይዞ እንደሆነ ይናገራሉ። "የፈራ ተራራ ስያሜውን ያገኘው በአፄ ዘረ ያዕቆብ ዘመን ነው። ለምሳሌ አንዱ የወቅቱ የአካባቢው አስተዳዳሪ የነበሩት መሪ ስም ቦካ ይባል ነበር። እሳቸውም ይኖሩበት የነበረውን ተራራ በስማቸው ጋራ ቦካ በማለት ሰይመውታል" ይላሉ አቶ ደቻሳ። በተመሳሳይ የፈራ ተራራ ስያሜ ከአህመድ ግራኝ ወረራ ጋር ተያያዥነት አለው ይላሉ። "ከአባቶቻችን እንደሰማነው ግራኝ አህመድ ወታደሮቹን ይዞ አካባቢውን መውረር ሲጀምር ለቦካ መልዕክት ላከ። መልዕክቱ 'ጭካኔን እንደ እናቴ መከታዬን ደግሞ እንደ አባቴ ሆኜ እየመጣሁልህ ነውና ተዘጋጅተህ ጠብቀኝ' የሚል ነበር" ይላሉ። • ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው አቶ ደቻሳ እንደሚሉት ቦካ የአህመድ ግራኝን መልዕክት እንደተቀበሉ ለሌላኛው የአካባቢው አስተዳዳሪ ለአቶ ቱሉ እየመጣብን ያለውን ጦርነት አብረን እንመክት ብሎ ጥያቄ አቀረቡ። መልዕክት አድራሹም ከአቶ ቱሉ ጋር ሲመለስ እንዴት እንደተሰማቸው ቦካ ሲጠይቁት ጦርነቱ እንዳስፈራቸውና እንዳሳሰባቸው ተገንዝቤአለሁ አላቸው ይላሉ አቶ ደቻሳ። ቦካም ይህንን ሲሰሙ 'አዪ! ቱሉ ፈራ ማለት ነው' በማለት የተራራው ስም ከዚያ በኋላ ቱሉ ፈራ ተብሎ እንደቀረ እንደተነገራቸው ያስረዳሉ። ሁለቱም አዛውንቶች ለስፍራው ለተሰጠው ለተሰጠው ስያሜ የተለያየ ምክንያት ቢሰጡም የሚስማሙበት አንድ ሃሳብ ግን ቱሉ የሚባል የአካባቢው አስተዳዳሪ በተራራው ላይ ይኖሩ እንደነበር ነው። አቶ ባትሪ ግን ሆን ተብሎ የተራራው ስያሜ ከአካባቢው የአየር ሁኔታ የመነጨ እንደሆነ አጠንክረው ይከራከራሉ። እንደሳቸው አባባል የአካባቢው አስተዳደር የነበሩት ሁሉ ጦርነት የሚፈሩ አልነበሩም።
news-51448721
https://www.bbc.com/amharic/news-51448721
መንግሥት ለቀድሞ የኬንያ መሪ ቀብር ቀድመው ለሚገኙ ነጻ ምግብና እና መጠጥ አዘጋጃለሁ አለ
ለቀድሞ የኬንያ ፕሬዝደንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ቀብር ቀድመው ለሚደርሱ ምግብና እና መጠጥ ተዘጋጅቷል ተብሏል።
ሞይ ነገ ሲቀበሩ ለቀብሩ ቀድመው ለሚደርሱ 30ሺህ ለቀስተኞች ዳቦ እና ለስላሳ መጠጥ በመንግሥት ወጪ እንደሚቀርብ አስተባባሪዎቹ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት አራፕ ሞይ የምሥራቅ አፍሪካዋን አገር ኬንያን ለ24 ዓመታት የመሩ ሲሆን፤ አገሪቱ ከእንግሊዝ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ስልጣን የያዙ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። ከቀብር ስነስርዓት አስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት ጆርጅ ናቴምቤያ እንዳሉት በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ ለሚገኙ 30 ሺህ ሰዎች የመቀመጫ ወንበር መዘጋጀቱን ጨምረው ተናግረዋል። ቀብሩ የሚከናወነው በፕሬዝደንቱ የትውልድ መንደር በሆነችው ካባራክ ሲሆን፤ ከመንደሯ 20 ኪ.ሜትር ርቃ ከምትገኘው ናኩሩ የትራንስፖርት አገልግሎት በነጻ እንደሚሰጥም ተነግሯል። በርካታ ኬንያውያን ግን መንግሥት ነጻ መግብ እና ትራንስፖርት አቀርባለሁ ማለቱን እየተቹ ይገኛሉ። ትችቱ መንግሥት ነጻ ምግብ እና ትራንስፖርት አገልግሎት አቀርባለሁ ያለው ለቀብር ስነ-ስርዓቱ የሚገኘው የህዝብ ቁጥር አነስተኛ እንዳይሆን በመስጋት ሰዎችን ለመደለል ነው የሚል ነው። ሞይ ኬንያን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በብቸኝነት ሲመሩ ቆይተው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት ነበር እንደ ጎርጎሳውያኑ 1992 ሌሎች ፓርቲዎች ወደ ምርጫው መድረክ እንዲመጡ የፈቀዱት። በስልጣን ዘመናቸው ሙስና፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ግርፋት እንዲሁም ሰቆቃን በመፈጸም ቢወቀሱም በርካታ የሃገሬውን ሰው ደግሞ በፍቅር ማሸነፍ ችለዋል ይባልላቸዋል።
45597873
https://www.bbc.com/amharic/45597873
ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኦዴፓ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በጅማ ከተማ ከረቡዕ ዕለት ጀምሮ ሲያካሂድ በነበረው ድርጅታዊ ጉባዔ ዶ/ር ዐብይ አህመድን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ በመምረጠ አጠናቀቀ።
አቶ ለማ መገርሳ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተሰይመዋል። ሊቀመንበሩ እና ምክትል ሊቀመንበሩ እስከቀጣዩ ጉባዔ ድረስ ኦዴፓን እንደሚመሩ ተገልጿል። ፓርቲው ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲሁም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን መምረጡም ታውቋል። የፓርቲው ጉባዔ ትናንት በእጩነት ከቀረቡት ስድሳ አባላቱ መካከል ሃምሳ አምስቱን ዛሬ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሰይሟል። ኦዴፓ ጉባዔውን ከመጀመሩ በፊት ሲል እንደነበረው ከሃምሳ አምስቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በርካታ አዳዲስና ወጣት አባላት እንደተካተቱበት ለማወቅ ተችሏል። የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ኦዴፓ ስሙን፣ አርማውን፣ ህገ ደንቡን፣ አመራሩን፣ አመለካከቱንና አደረጃጀቱን፤ የ21ኛው ከፍለ ዘመን የሚጠይቀውን አመራር ለመስጠት በሚያስችል መልኩ በመማዋቀር ዘጠነኛ ጉባዔው በድል መጠናቀቁን አስታውቀዋል። ድርጅቱ የተማሩ፣ ለመማር የተዘጋጁና ብቃት ያላቸው ወጣቶች ወደፊት በማምጣት ስያሜውን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወደፊት የሚያራምድ በመሆኑ፤ ሌሎች ለኢትዮጵያ ህዝቦች የሚታገሉ በሙሉ ከኦዴፓ ትምህርት ሊወስዱ ይገባል ብለዋል። በቅርቡ በደቡብ ክልል ንብረትንና ጥቃትን በባህላቸው መሠረት የተከላከሉ የጋሞ ሽማግሌዎች ያደረጉትን ገድል አድንቀዋል። በመጨረሻም ምርጫው ዲሞክራሲያዊ እና የተሳካ እንደነበር ገልጸዋል። • ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን? • ኦህዴድ ስሙና አርማውን ቀየረ ከእነዚህም ውስጥ ዶክተር ዐብይ አህመድ (ጠቅላይ ሚኒስትር)፣ አቶ ለማ መገርሳ (የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት)፣ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ (የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር)፣ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ (ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ)፣ ኢንጂነር ታከለ ኡማ (የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ)፣ ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን (የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት) ሲገኙበት። በተጨማሪም አቶ አዲሱ አረጋ (የፓርቲው ከፍተኛ ባለስልጣን)፣ ዶክተር ግርማ አመንቴ (ሚኒስትር)፣ አቶ ታዬ ደንደአ (የዐቃቤ ህግ ቃል አቀባይ)፣ አቶ ካሳሁን ጎፌ (መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ)፣ አቶ አህመድ ቱሳ (የቀድሞ ሚኒስትር)፣ አቶ አብዱልአዚዝ መሃመድ (የሜቴክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር) እና ሌሎችም ተካተውበታል። ፓርቲው ትናንት በርካታ መስራችና ነባር አባላቱን ያሰናበተ ሲሆን አዲስ የተተኩትም የተሰናባቾቹን ቦታ የያዙ ናቸው። በተጨማሪም ኦዴፓ አዲስ ስያሜና አርማን ይፋ አድርጓል።
news-53205375
https://www.bbc.com/amharic/news-53205375
ኮካ ኮላ ፌስቡክና ሌሎች ገፆች ላይ ማስታወቂያ ማስነገር አቆመ
ኮካ ኮላ ለሚቀጥሉት 30 ቀናት በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ላይ የሚያሰራውን ማስታወቂያ እንደሚያቋርጥ አስታወቀ።
ድርጅቱ ይህን የሚያደርገው ማኅበራዊ ሚድያዎች የጥላቻ ንግግርን እንዲቆጣጠሩ ጫና ለማሳደር ነው። የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጄምስ ክዊንሲ "ዓለም ለዘረኝነት ቦታ ሊኖራት አይገባም፤ ማኅበራዊ ድር-አምባዎችም ለዘረኝነት ቦታ ሊኖራቸው አይገባም" ሲሉ ተደምጠዋል። ማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፤ ግልፅ ሊሆኑም ይገባል ብለው ሥራ አስኪያጁ። ግዙፉ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ፌስቡክ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ መረጃዎችንና ሐሰተኛ ወሬዎችን አጋልጣለሁ ብሏል። የፌስቡክ ፈጣሪ ማርክ ዛከርበርግ የእሱ ድረ-ገፅ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች "ለተወሰነ የሰው ልጅ ጎሳ፣ ዜጋ፣ እምነት፣ ፆታ፣ ወይንም የስደት ሁኔታ" የሚያዳሉ ከሆነ አግዳለሁ ብሏል። በመገናኛ መድረኮች ላይ የሚወጡ የጥላቻ ንግግሮችን ለመቃወም እየተካሄደ ያለው (#StopHateforProfit) ዘመቻ አስተባባሪዎች ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎች እንዳይሰራጩ የድርሻውን አልተወጣም ሲሉ ይወቅሳሉ። ከ90 በላይ ድርጅቶች የዚህን እንቅስቃሴ ሐሳብ በመደገፍ ምርታቸውን ማስተዋወቅ አቁመዋል። ነገር ግን ኮካ ኮላ ማስታወቂያዎቹን ፌስቡክ ላይ ማስነገር ማቆሙ ዘመቻውን ተቀላቅሏል ማለት አይደለም ሲል ሲኤንቢሲ ለተሰኘው የቴሌቪዥን ጣብያ አሳውቋል። ሥራ አስኪያጁ በዓለም ደረጃ ማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የሚያደርጉትን የማስታወቂያ ሥራ አቁመው ስለ ማስታወቂያ ፖሊሲያቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊያጤኑ እንደሆነ ተናግረዋል። ልብስ አምራቹ ሊቫይ ስትራውስ ፌስቡክ ላይ ማስታወቂያ ማስነገር አቁሚያለሁ ብሏል። ድርጅቱ የዛከርበርግ ፌስቡክ ጠንካራ አቋም የለውም ሲል ወቅሷል። "ፌስቡክ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ቆራጥ እንዲሆን እንጠይቃለን" ብለዋል የድርጅቱ የማስታወቂያ ክፍል ኃላፊ ጄን ሰይ። ታላላቅ ተቋማት በጸረ ጥላቻ ንግግር እንቅስቃሴ ውስጥ እኣካሄደ ያለው ጥምረት ዛከርበርግ ከዚህ የበለጠ እርምጃ እንዲወስድ አሳ
news-57140212
https://www.bbc.com/amharic/news-57140212
በኢትዮጵያ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ተቋርጠው እንደነበር ተነገረ
የኢንተርኔት ነጻነትን የሚከታተከለው ኔትብሎክስ ኢትዮጵያ ውስጥ የማኅበራዊ ሚዲያ መገልገያ መተግበሪያዎች አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር አስታወቀ።
ኔትብሎክስ እንዳለው ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ፌስቡክን ጨምሮ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም አገልግሎቶች መቋረጣቸውን ያለው መረጃ እንደሚያመለክት ገልጿል። ከአዲስ አበባ የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው ፌስቡክ ለመጠቀም አስቸጋሪ እንደሆነ ነገር ግን ቪፒኤን በተባለው ተዘዋዋሪ የመጠቀሚያ መተግበሪያ አማካይነት መግባት እንዳስፈለገው አመልክቶ፤ ዋትስአፕን ለመጠቀም ምንም ችግር እንዳልገጠመው ገልጿል። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 ቢቢሲ ከአዲስ አበባ ውጭ ያለውን እነዚህን የማኅበራዊ ሚዲያ መገልገያዎች መቋረጥ በተመለከተ ከአንዳንድ ከተሞች ነዋሪዎች ለማጣራት ባደረገው ሙከራ ችግሩ በባሕር ዳር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በድሬዳዋና በሐዋሳ ማጋጠሙን አመልክተዋል። ነገር ግን አገልግሎቶቹ ለሰዓታት ተቋርጠው ከቆዩ በኋላ ሰኞ ረፋድ ከአራት ሰዓት በኋላ መመለሱን ነዋሪዎች ጨምረው ገልጸዋል። ቢቢሲ የተጠቀሱት የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ከአገልግሎት ውጪ መሆንን በተመለከተ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ከአንድ የኢትዮቴሌኮም ኃላፊ እንደተረዳው ክስተቱ ከተቋማቸው ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ያጋጠመ መሆኑን ተናግረዋል። የፌስቡክና የኢንስታግራም መተግበሪያዎቹ አገልግሎት ያቋረጠው እሁድ ለሰኞ አጥቢያ ከእኩለ ሌሊት በኋላ በመላው አገሪቱ ውስጥ እንደነበር ኃላፊው ገልጸዋል። እነዚህ ከአገልግሎት ውጪ ሆነው ለሰዓታት የቆዩት የማኅበራዊ ሚዲያ መገልገያዎች ከጠዋቱ አራት ሰዓት በኋላ መስራት መጀመራቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙ አለመረጋጋቶችን እንዲሁም ብሔራዊ ፈተናዎችን ተከትሎ የኢንተርኔትና የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶች በተደጋጋሚ መዘጋታቸው ይታወሳል። የማኅበራዊ ሚዲያዎች መቋረጥን በተመለከተ ኔትብሎክስ ያወጣው መረጃ
46368422
https://www.bbc.com/amharic/46368422
"ፓስፖርት መስጠት አልተከለከለም" የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ተቋም
አንዲት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አራተኛ ዓመት የሕክምና ሳይንስ ተማሪ ናይጄሪያ የሚገኝ ዩኒቨርስቲ በሚያካሄደው ጉባኤ ላይ እንድትገኝ ግብዣ ቀርቦላታል።
በምትማርበት ተቋም የምትመራው ኮሚቴን ወክላ ወደ ናይጄሪያ ለመጓዝ ግን ፓስፖርት ለማውጣት ወደ የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች መሥሪያ ቤት የቀበሌ መታወቂያዋንና ያስፈልጋል ያለችውን ክፍያ ይዛ ሄደች። ከመሥሪያ ቤቱ ያገኘችው መልስ ግን ከጋባዡ አካል ደብዳቤ እስካላመጣች ፓስፖርት ማግኘት አንደማትችል የሚገልፅ ሆነ። ምንም እንኳ ፓስፖርት ማግኘት እጅግ አዳጋች እንደሆነ የሚገልፁ መረጃዎች እየወጡ ቢሆንም ፓስፖርት ማግኘት የሁሉም ሰው የዜግነት መብት በመሆኑ አለመከልከሉን የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ዋና መመሪያ ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊ አቶ የማነ ገብረ መስቀል ለቢቢሲ ገልፀዋል። • ዜግነት ለመግዛት ምን ያህል ይከፍላሉ? • ፓስፖርት፡ የሰዎችን እንቅስቃሴ የወሰነ ሰነድ • "የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሦስት የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት አድርጓል ያሉት አቶ የማነ ከቀሪዎችም ጋር ለማድረግ እየተነጋገረ መሆኑን ገልፀዋል። መንግሥት ቀደም ሲል ወደ እነዚህ ሃገራት ይደረግ የነበረውን ሕገ ወጥ ጉዞ አስቁሟል ካሉም በኋላ ጉዞው ሕጋዊ በሚመስል ነገር ግን በሕገ ወጥ መንገድም ሲደረግ ቆይቷል በማለት ያስረዳሉ። እናም የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች መምሪያ አንደኛ የዜጎችን ሕጋዊ እንቅስቃሴን ፣ የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ እንዲሁም መንግሥት ባቋቋመው ግብረኃይል ውስጥም ስላለ ሕጋዊ ስምሪቱን እንዲጠናከር እያደረገ እንዳለ አቶ የማነ ይገልፃሉ። እሳቸው እንደሚሉት የተቋማቸው እንቅስቃሴ ከሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ የመጣ አንድ አዋጅ ከመንግሥትም የመጣ ሌላ ትእዛዝን መሠረት ያደረገ ነው። "መንቀሳቀስ የዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብት ነው። እየከለከልን አይደለም ልንከለክልም አንችልም። የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ ግን የተቋሙ ስልጣን ነው" የሚሉት አቶ የማነ የዜጎች ፓስፖርት የማግኘት መብት አሁንም ሕጉን ተከትሎ ተፈፃሚ እየሆነ እንዳለ ይገልፃሉ። ፓስፖርት የጉዞ ሰነድ እንጂ የቀበሌ መታወቂያን የሚተካ መሆን የለበትም የሚሉት ኃላፊው ቅርንጫፎቻቸውን ጨምሮ በቀን አስር ሺህ የሚሆን ፓስፖርት እንደሚሰጡ ገልፀዋል። ቢሆንም ግን የሚጠቀሙበት ጥቂቶች ብቻ እንደሆኑ ከዚህ ሲያልፍም ብዙዎቹ ፓስፖርታቸውን ለደላላ ሰጥተው በድጋሚ የሚያወጡ መሆናቸውንም ያስረዳሉ። እንደ የጉዟቸው ዜጎች ማቅረብ ያለባቸውን ሰነድ ካሟሉ ፓስፖርት ማግኘታቸው ምንም ጥያቄ እንደሌለው አቶ የማነ አስረግጠው ያስረዳሉ። አቶ የማነህ ማንኛውም ፓስፖርት የሚፈልግ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት ሰነዶች መካከል አንደኛው መታወቂያ ሲሆን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለሥራ ሊሄድ ከሆነ ግን አስፈላጊውን መስፈርት ማሟላታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ አለበት ብለዋል። ወደ ሌላ ሃገር ለጉብኝት የሚሄድ ከሆነ የጉብኝት ደብዳቤ፣ ሆቴል የያዘበትንናና የአየር ቲኬት የገዛበትን ማስረጃዎችን ማቅረብ ይጠበቅበታል ይላሉ። "የሕክምና ጉዞም ከሆነ በተለይም አስቸኳይ ከሆነ በአንድ ወይም በሁለት ቀን ፓስፖርት ይሠራል" ብለዋል ኃላፊው ። እንደዚህ ያሉ የሕክምና ተጓዦችም ማሳየት ያለባቸው የሚሄዱበት ሃገር ሆስፒታል ቀጠሮን ወይንም ከአገር ውስጥ ሐኪሞች የተፃፈላቸውን የሕክምና ማስረጃ ነው። • አፍሪካዊያን ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትን መጎብኘት ለምን ይከብዳቸዋል? ኃላፊው እንደሚሉት ፓስፖርት ለማደስም አካሄዱ ተመሳሳይ ነው። እንደ አቶ የማነ በአጠቃላይ ተቋማቸው በአሁኑ ወቅት ፓስፖርት አሰጣጥም ሆነ እድሳት ላይ እየተከተለ ያለው አሠራር በተለይም ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረግ ሕገወጥ ዝውውርን ከመቆጣጠርና ከመግታት ጋር የተያያዘ እንደሆነ አስረግጠው ተናግረዋል።
news-48970567
https://www.bbc.com/amharic/news-48970567
በቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ባለሙያ በታጣቂዎች ተገደሉ
በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን በየማለጊ ወለል ወረዳ የፀጥታና የደህንነት ባለሙያ አቶ ጫላ ነገሪ በታጣቂዎች ትላንት ሐምሌ 4፣2011ዓ.ም ተገደሉ።
የዞኑ የፀጥታና አስተዳዳሪ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ ቦሩ ለቢቢሲ እንደገለፁት ግለሰቡ ከደምቢዶሎ ወደ ተጆ በህዝብ መመላለሻ ትራንስፖርት በመሄድ ላይ እያሉ ዘጠኝ ታጣቂዎች መኪናውን በማስቆም እሳቸውንና አንድ ፖሊስ ለይተው በማውጣት ግለሰቡን ገድለዋቸዋል። ፖሊሱ እንዳመለጠም ተገልጿል። •"እስሩ አብንን ለማዳከም ያለመ ነው" ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) •“በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ ግለሰቡ ከ12 ዓመታት በላይ በፀጥታና ደህንነት ዘርፍ በተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን ቀብራቸውም ተጆ በምትባል ስፍራ ተፈፅሟል። የታጣቂዎቹን ማንነት አስመልክቶ ቢቢሲ አቶ መሀመድን የጠየቃቸው ሲሆን የቀድሞ የኦነግ ሰራዊት አባል የነበሩና በአሁኑ ሰዓት ተበታትነው በጫካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልፀዋል። •"አገሪቷ አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት ህወሓት ተጠያቂ ነው" አዴፓ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደምቢዶሎ አካባቢ በምትገኘው የሰዮ ወረዳ የኦዲፒ ፅ/ቤት ኃላፊ ከአዲስ አበባ ወደ ደምቢዶሎ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት በታጣቂዎች ተወስደው መገደላቸው የሚታወስ ነው። በተያያዘ ዜና ደምቢዶሎ ከተማ 07 ቀበሌ አካባቢ ፖሊስ ማንነታቸውን እያጣራ ባሉ ግለሰቦች በትናንትናው ዕለት በተወረወረ ቦንብ ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ገጥሟቸዋል።
news-55447034
https://www.bbc.com/amharic/news-55447034
ፍትህ ፡ በኦሮሚያ ክልል ባሕላዊ ፍርድ ቤት ሊቋቋም ነው
የኦሮሞ ሕዝብ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ የሚገጥሟቸውን እክሎች ማለትም የቤተሰብ እና የጎረቤት፣ እንዲሁም የጎሳ ግጭትን ከዘመናዊ ሕግ በተጨማሪ በሽምግልና ይፈታል።
ሽማግሌም ግራ ቀኙን ካዳመጠ በኋላ ጉዳዩን መዝኖ ያጠፋው እንዲቀጣ፣ የተጎዳው ደግሞ እንዲካስ ይወስናል። የኦሮሚያ ክልልም ይህንን ማኅበረሰቡን ግጭቶችንና ችግሮችን ሲፈታበት የቆየውን እሴት የሕግ እውቅና ባለው መንገድ እንዲሰራ ለማድረግ ባሕላዊ ፍርድ ቤት እያቋቋመ መሆኑን የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገልጿል። በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሙኑኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክተር አቶ ጎንፋ አቶማ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህ የሚቋቋመው ባሕላዊ ፍርድ ቤት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ላይ ያለውን ጫና የሚያቃልል ይሆናል። "ባሕላዊ ፍርድ ቤት ማለት በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለውን ባሕላዊ እሴት በመጠቀም ግጭቶቹን በፍርድ ቤት መፍታት ማለት ነው። ፍርድ ቤቱ የሚጠቀማቸው የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን ሕግ ሳይሆን ባሕላዊ ሕጎችን ነው።" የዚህ ባሕላዊ ፍርድ ቤት አመሰራረትም የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልልን ሕገ መንግሥትንና እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ምሥረታ እና ሥልጣን ድንጋጌ 216/11 መሰረት ያደረገ መሆኑን አክለው ገልፀዋል። ይህ ባሕላዊ ፍርድ ቤት በኦሮሞ እሴትና በገዳ ሥርዓት ላይ በመመስረት የሚሰራ ስለሆነ ለማኅበረሰቡ ባሕል መጎልበት የሚኖረው አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም ይላሉ ዳይሬክተሩ። በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ፍርድ ቤቶች በዓመት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የክስ መዝገቦችን ያስተናግዳሉ። ይህንን ባሕላዊ ፍርድ ቤት ለማቋቋም በተካሄደ ጥናት የኦሮሞ ባሕል ተጠናክሮ ባለባቸው አካባቢዎች የክስ መዝገቦች ቁጥር አናሳ መሆኑ መስተዋሉን አቶ ጎንፋ ይናገራሉ። እንደምሳሌም በቦረና ዞን፣ ጎዳዮች በባሕላዊ መንገዶች በሚፈቱበት አካባቢ የክስ መዛግብት አነስተኛ ናቸው። በሁሉም የቦረና ወረዳዎች በዓመት የሚታዩ ክሶች በሌሎች አካባቢ በአንድ ወረዳ ከሚታዩት መዝገቦች በታች ናቸው ሲሉ ያነጻጽራሉ። "ይህ ባሕላዊ ፍርድ ቤትም፣ የራሱ የሆነ መዋቅር ያለው ሽምግልና ነው፤ በቀበሌና በወረዳ ደረጃ የራሱ መዋቅሮች ይኖሩታል፤ የራሱ የሆነ ሥርዓት ዘርግቶ ባለመኖሩ ብቻ ነው ከሽምግልና ለየት የሚያደርገው" ብለዋል። ከመደበኛው ፍርድ ቤት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት በተመለከተም ሲያስረዱ፣ ጉዳዩ በባሕላዊ ፍርድ ቤት ሲታይ የነበረ በይግባኝ ሂደት ወደ መደበኛው ፍርድ ቤት መተላለፍ እንደሚችል ይናገራሉ። "በቀበሌ ደረጃ በባሕላዊ ፍርድ ቤት የሚታይ ጉዳይ በይግባኝ ወደ ወረዳ ባሕላዊ ፍርድ ቤት ሊሄድ ይችላል፤ ከዚህ አልፎ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ግድፈት ያለው ከሆነ ወደ ወረዳ መደበኛው ፍርድ ቤት በመወሰድ ይታያል" ብለዋል። በዚህ ባሕላዊ ፍርድ ቤት የሚሰሩት የሕግ ባለሙያዎች የሕግ ትምህርትን የተማሩ የሕግ ባለሙያዎች ሳይሆኑ የገዳ ሥርዓትና ባሕልን የሚያውቁ ሽማግሌዎች ናቸው። አባገዳዎች ምን ይላሉ? የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኦሮሞ ከጥንት አንስቶ በባሕላዊ እሴትና ሕግጋቶች የሚገጥሙትን ማኅበራዊ ችግሮች ሲፈታ እንደኖረ ይናገራሉ። አሁን ሊመሰረት ያለው የባሕላዊ ፍርድ ቤት በገዳ ሥርዓት ውስጥ የነበረውና ማኅበረሰቡ ችግሩን ሲፈታባቸው የነበሩትን እሴቶች መልሶ የሚያጠናክር ነው ሲሉም ያስረዳሉ። "ኦሮሞ የራሱን ሕግጋቶች በመቅረጽ ይተዳደር ነበር። አሁን ዘመናዊነት ተስፋፍቶ በዘመናዊ ሕግጋቶች ብቻ እንዲተዳደር ሆነ። ይህ እሴት ግን በደንብ ማኅበረሰቡ ውስጥ አለ። በተለይም የገዳ ሥርዓት በሚተገበርባቸው አካባቢዎች ሕዝቡ በግልጽነት ችግሩን በመናገር መፍትሔ ሲያገኝ ነው የኖረው" ይላሉ አባገዳ ጎበና። በሰላምና የአገር ጉዳዮች ላይ አባ ገዳዎች በባሕላዊ መንገድ እንዲሸመግሉ በተደረገባቸው አንዳንድ ቦታዎች ጥረታቸው ሳይሳካ የቀሩበት ሁኔታ እንዳለ አባገዳው ያስታውሳሉ። እንደዚህ ዓይነቶች ችግር ሊከሰቱ የቻሉት ግን የሽምግልና እሴቱ ችግርን ለመፍታት ዋጋ ቢስ ሆኖ ሳይሆን፣ የሽምግልናን ዋጋ ወዳልተረዱት አካላት በሚላክበት ጊዜ የሚገጥም ነው ይላሉ። "ኦሮሞ ሽምግልና የሚልከው ተስፋ ወደሚያደርግበት ቀዬ ነው፤ ዝም ብሎ በደመ ነፍስ አይሔድም። ሽምግልና የሚኬድባቸው አካላትም የሕዝቡን እሴት የተረዱ መሆን አለባቸው፤ የሽምግልናን ጥቅምና እሴት ወዳልተደረዱ ሰዎች ሽምግልና አይኬድም" ብለዋል።
51867057
https://www.bbc.com/amharic/51867057
ራሳችንን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ስልካችንን እንዴት እናጽዳ?
የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረረርሽኝ እንደሆነ ገልጿል። ድርጅቱ ይህ ወረርሽኝ ራሳችን ልንከላከለው የምንችለው መሆኑንም አስታውቋል።
ይህንንም ለማድረግ እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ፊታችንን በተደጋጋሚ አለመነካካት፣ በምናስነጥስበት አልያም በምናስልበት ወቅት አፍና አፍንጫችንን በሶፍት አልያም በክርናችን መሸፈን የሚጠቀሱ መከላከያዎች ናቸው። • የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ተረጋገጠ • ኬንያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው ማግኘቷን አስታወቀች • “የአባይ ውሃ ለኔ ፀበሌ ነው፤ ለኢትዮጵያ ህዝብም ፀበል ነው” ኪሮስ አስፋው በቤታችንም ሆነ በምንሰራበት ስፍራ በተደጋጋሚ የእጅ ንክኪ የሚበዛባቸው ስፍራዎችን ማጽዳት ከመከላከያ መንገዶቹ መካከል አንዱ ነው። ነገር ግን ስልካችንን በየደቂቃው የምንጠቀም እንደመሆናችን እንዴት ማጽዳት እንዳለብን እስካሁን ካላሰብን ቀጣዩ ጠቃሚ ነጥብ ይሆናል። ስልክዎን በኪስዎ፣ በቦርሳዎ አንዳንዴም ወደ በፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ይዘውት ይሄዳሉ። ምን ያህል ጀርም ስልክዎ ብቻ ተሸክሞ እንደሚገኝ አስበውታል? ኮሮናንስ ስላለመያዙ ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት? የአሜሪካን የጤና ስርዓት በበላይነት የሚቆጣጠረው ሲዲሲ በምናስነጥስበት አልያም በምናስልበት ወቅት ከሰውነታችን የሚወጣው ጀርም በሚረጭበት ስፍራ ላይ ለሰዓታት በሕይወት ይቆያል ብሏል። ስለዚህ ቆሽሸው የሚታዩን ነገሮችን በአጠቃላይ እንድናፀዳ ይመክራል። በማጽዳትና ከቫይረሱ ነጻ በማድረግ ረገድ ልዩነት እንዳለም ተቋሙ ያሳስባል። መጀመሪያ ቆሻሻውን ማጽዳት ቀጥሎም ከቫይረሱ ነፃ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባል። ስልካችንን ለማጽዳት 70 በመቶ አልኮል ያለው ዋይፐር መጠቀም የሚቻል ሲሆን በረኪና ግን አይመከርም። ቀላል ሳሙናና ውሃም ለማጽዳት እንደሚያገለግልም ባለሙያዎች ይመክራሉ። ዶ/ር ሌና ሲሪክ በዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ለንደን ማይክሮባዮሎጂስት ናቸው። እርሳቸው እንደሚመክሩት ከሆነ ስልክዎን ለማጽዳት ከቻርጀሩ መንቀል፣ መሸፈኛ ካለው ማውለቅ ቅድሚያ ልትወስዷቸው የሚገባው ተግባር ነው። ዋና ዋና የሚባሉት የስልክ አምራቾች ስልካችንን ለማጽዳት ኬሚካሎች፣ ለእጃችን ማፅጃነት የምንጠቀምባቸው ሌሎች እንዲሁም ሸካራ ነገርን ለማጽዳት የሚያገለግሉ ዋይፐሮችን መጠቀምን አይመክሩም። ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው የስልክዎን ስክሪን መከላከያ ይጎዳሉ አልያም ያወድማሉ የሚል ነው። ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ሌና፣ በቀላሉ በውሃና በሳሙና በተነከረ ጥጥ ወይም ከጥጥ በተመረተ ጨርቅ ማጽዳት በቂ ነው። በጥጥ ወይም በጨርቁ የስልክዎን ስክሪንም ሆነ ጀርባ እንዲሁም ጎኖች ማጽዳት ይችላሉ። በዚህ ወቅት ግን የሚያጸዱበት ፈሳሽ በስልኮቹ ክፍተቶች በኩል እንዳይገባ ጥንቃቄ ያድርጉ። በርግጥ አንዳንድ ውሃን የሚቋቋሙ ስልኮች ቢኖሩም ከጊዜ በኋላ ግን ይህንን ብቃታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በአግባቡ ከወለወሉ በኋላ በለስላሳ ጨርቅ ማድረቅ አይርሱ። ዶ/ር ሌና እንደሚሉት በሳሙናና ውሃ ስልክዎን ማጽዳት ቫይረሶችንና ጀርሞችን ከስልክዎት ላይ ያፀዳል። አይፎንን ስልኮችን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ አፕል ስልክዎን በአግባቡ 70 በመቶ አይሶፕሮፔል አልኮል ባላቸው ዋይፐሮች ማጽዳት እንደሚችሉ ይመክራል። እነዚህን ዋይፐሮች ከኮምፒውተር መለዋወጫዎች መሸጫ ሊያገኟቸው ይችላሉ። በዚህ ሁሉ ስልክዎን ካፀዱ በኋላ ባልታጠበ እጅዎ ከሆነ የሚጠቀሙት መልሶ ስልክዎ በጀርሞች ይሞላል። ስለዚህ እጅዎን በየጊዜው መታጠብ አይርሱ!
news-49274620
https://www.bbc.com/amharic/news-49274620
ያላሉትን እንዳሉ የሚያስመስለው የዋትስአፕ መተግበሪያ
ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ሲባልለት የነበረውን ዋትስአፕን ሰብሮ የሚገባና የተጠቃሚዎችን መልዕክት በመለወጥ ያላሉትን እንዳሉ አድርጎ የሚያቀርብ አዲስ መተግበሪያ [አፕ] እንዳለ ተደረሰበት።
የመረጃ መረብ ደህንንት (ሳይበርሴኪዩሪቲ) ባለሙያዎች፤ አንድ መተግበሪያ የዋትስአፕ መልዕክትን በመበዝበር ተጠቃሚዎች ያላሉትን ነገር እንዳሉ በማስመሰል ማጭበርበር እንደሚችል ደርሰንበታል እያሉ ነው። ኦዴዎ ቫኑኑ የተሰኙ ባለሙያ ለቢቢሲ ሲናገሩ መሣሪያው ተጠቃሚዎች ዋትስአፕ ላይ የተላላኩትን መልዕክት አጭበርባሪዎች እንደሚፈልጉት ማጣመም እንዲችሉ ዕድል ይሰጣል ይላሉ። • ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መልዕክት ማጋራትን አገደ ለምሳሌ እርስዎ ለወዳጅ ዘመድዎ የላኩትን የሰላምታ መልዕክት ወደ ሐሰተኛ ዜና በመቀየር ለሌላ የዋትስአፕ ተጠቃሚ ወይም ቡድን መላክ ያስችላል። ላስ ቬጋስ ላይ በተካሄደ አንድ የሳይበርሴኪዩሪቲ ምክክር ላይ ይፋ የተደረገው ይህ መዝባሪ መሣሪያ 'የኮምፒውተር መዝባሪዎች የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን መልዕክት እንዳሻቸው እንዲሾፍሩ ያስችላል' ተብሎለታል። የዋትስአፕ ባለቤት የሆነው ፌስቡክ ስለጉዳዩ አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠየቅም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። «ሰዎች ዋትስአፕ ላይ የፃፉትን የትኛውንም መልዕክት መቀየር ይቻላል» ይላሉ ኦዴዎ። አልፎም የእውነተኛውን ዋትስአፕ ተጠቃሚ ማንነት መቀየር እንዲሚያስችል ባለሙያው ይናገራሉ። አንድ መሰል አጭበርባሪ መተግበሪያ ደግሞ ለሰው 'ኢንቦክስ' ያደረጉትን መልዕክት አስተያየት [ኮሜንት] በማስመሰል ያወጣ ነበር። ነገር ግን ፌስቡክ ይህንን መተግበሪያ ማስወገድ መቻሉን ባለሙያው ይናገራሉ። • 'ዋትስአፕ' በቻይና እክል ገጥሞታል ይህኛውን የዋትስአፕ መልዕክት ቀማኛ ለመከላከል ግን ፌስቡክ አቅሙ የለኝም የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው የመረጃ መረብ ደህንንት ባለሙያው ኦዴዎ ይገልፃሉ። ይህንን መሣሪያ የፈጠሩት ሰዎች ዓላማ ምን ይሆን? ተብለው የተጠየቁት ባለሙያው ዋነኛው ሃሳብ ዋትስአፕ ተጋላጭ መሆኑን ለማሳየትና ደህንነቱን የበለጠ ሊያጠናክር እንደሚገባ ለማሳሰብ ነው ይላሉ። «ዋትስአፕ ከዓለም ሕዝብ 30 በመቶ ያህሉን ያገለግላል። እኛ ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን። ሐሰተኛ ዜና [ፌክ ኒውስ] ትልቅ አደጋ ጋርጦብናል። ሁለን እርግፍ አድርገን ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰል የለብንም።» • ወደ ድብቁ የዋትስአፕ መንደር ስንዘልቅ ዋትስአፕ የሐሰተኛ ዜና ማስፋፊያ አንዱ መድረክ እንደሆነ ይነገርለታል፤ በተለይ ደግሞ በሕንድ እና ብራዚል። የሃሰተኛ መረጃዎቹ ሥርጭት ግጭት ከማስነሳት አልፎ የሰው ሕይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል። ዋትስአፕ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ መላዎችን ቢያቀርብም አደጋው ሙሉ በሙሉ የተቀረፈ አይመስልም።