id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
52627587
https://www.bbc.com/amharic/52627587
ኮሮናቫይረስ፡ በሊባኖስ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ችግር ውስጥ ናቸው- የኢትዮጵያ ቆንስላ
በሊባኖስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። የተጣለው የሰዓት እላፊ ከነገ ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እስከ ሰኞ ማለዳ ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ ለአንድ ወር ያህል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ዜጎች " ቤታቸው መቀመጥ አለባቸው አስቸኳይ ጉዳይ ካልገጠማቸው በስተቀር ወደ የትም መሄድ የለባቸውም" ያሉት የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ማናል አብደል ሳማድ ናቸው። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ከሆነ በአገሪቱ 870 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 26 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የኛ ሰው በሊባኖስ በሊባኖስ በርካታ ኢትዮጵያውያን በዝቅተኛ ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያኖች ይናገራሉ። ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁን በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን "ችግራችን የጀመረው ባለፈው ጥቅምት ወር የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት በተጎዳበትና የዶላር መወደድ ሲጀምር ነው" ብለውናል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየሰዉ ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ የተባረሩበት፣ ደሞዛቸውን በግማሽ ቀንሰው መስራት የጀመሩበት እስካሁን ድረስም ሳይከፈላቸው የሚሰሩ መኖራቸውን ይገልፃሉ። "ያለ ክፍያ ለመስራት የመረጡት ቢያንስ የተገኘውን እየበሉ በሕይወት መቆየት ይሻላል ያሉ ናቸው" በማለትም ይህንን ተቋቁመን አልፈነው ነበር ብለዋል። የዓለምን ሕዝብ ያስጨነቀው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት "ሕይወታችንን ከድጡ ወደ ማጡ ከቶብናል" የሚሉት ኢትዮጵውያኑ፣ ልጅ ኣላቸው ልጃቸውን መመገብ፣ ቤት ኪራይ መክፈል ፈተና እነደሆነባቸው ይገልፃሉ። ሊባኖስ የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል ጥላው የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ ማንሳቷን ተከትሎ ያገኙትን ሰርቶ ለማደር ተስፋ ሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም ዳግም በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ተከትሎ መንግሥት ለተከታታይ አምስት ቀናት ከቤት መውጣትም መከልከሉን በመናገሩ ሌላ ስጋት እንደተደቀነባቸው ለቢቢሲ ያስረዳሉ። እገዳው ለአምስት ቀናት የተጣለ ሲሆን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኞ ማለዳ ድረስ የሚቆይ ነው በማለትም "ሳይሰራ እንዴት ቤት ኪራይ ይከፈላል?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብ ፣ ባለፉት አራት ቀናት ብቻ 100 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልፀው ነው የአምስት ቀኑ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን የተናገሩት። መንግሥት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ላይ ያወጣውን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ሰዎችንም " ግዴለሽና ሃላፊነት የጎደላቸው" በማለት ወርፈዋቸዋል። በሊባኖስ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ የአካላዊ ርቀት መጠበቅ ተግባራዊ እንዲሆን በማሳሰብ ሱቆችና የአምልኮ ስፍራዎች ተከፍተዋል። ይህ የሆነው ከሁለት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል። በቫይረሱ የተያዙ አዳዲስ ሰዎች የተገኙት በአብዛኛው ከአገር ውጪ የነበሩ ሊባኖሳውያን በመመለሳቸው መሆኑ ተገልጿል። ከአምስት ቀናት በፊት ከናይጄሪያ፣ ሌጎስ የመጡ ሁሉም ተሳፋሪዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር አስታውቆ ነበር። የእንቅስቃሴ ገደቡ ከተነሳ በኋላ ዜጎች በመገበያያ ስፍራዎች አካላዊ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ሲገበያዩ የታዩ ሲሆን፣ በአውራ ጎዳናዎችም ላይ ከተጠበቀው በላይ በርካታ ሰዎች ወጥተዋል። በሊባኖስ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ እየወደቀ የነበረው የአገሪቱ ምጣኔ ሃብትን ይበልጥ አባብሶታል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ቢቢሲ ያነጋገራትና ሊባኖስ ውስጥ ለ12 ዓመታት መኖሯን የምትናገረው ኢትዮጵያዊት በበኩሏ "እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ ፓስፖርትም ሆነ የመኖሪያ ፈቃድ የለንም" ስትል የስጋታቸውን መደራረብ ታስረዳለች። ከዚህ በፊትም ቢሆን የተለያዩ ችግሮችን አልፌያለሁ ያለችን ይህች ሴት የአሁኑ ግን ከምንጊዜውነም የከፋ ነው ትላለች። የኮሮናቫይረስ ከመከሰቱ በፊት ጀምሮ በሰዓት የሚከፈላት በግማሽ ተቀንሶ እየሰራች እንደነበር የተናገረችው ይህች ስደተኛ፣ የኮሮናቫይረስ ከመጣ በኋላም እጅጉን መታመሟን ታስታውሳለች። "ምናልባትም ኮሮና ይሆናል፤ እንደ ጉንፋን ያለ ነው" ትላለች በወቅቱ የነበራትን ሕመም ስታስታውስ። ለመመርመርም ሆነ ወደ ሆስፒታል ለመሄድና አገልግሎት ለማግኘት ፓስፖርትና የመኖሪያ ፈቃድ እንደምትጠየቅ በዚህም የተነሳ መታከም እንዳልቻለች ገልፃለች። ለተከታታይ 11 ቀናት ሳል እንደነበራት የምትናገረው ይህች በሊባኖስ የምትገኝ ስደተኛ፣ በአንድ ክፍል ውስጥ ስምንት ልጆች ሆነው እንደሚኖሩና እርሷ በቫይረሱ ብትያዝ ወደ ሌሎቹ የመተላለፍ እድሉ ሰፊ እንደነበር ታስረዳለች። "እኔ ብቻ ሳልሆን ሌሎችም ኢትዮጵያኖች አሉ ለአራትና ለአምስት በአንድ ክፍል የሚኖሩ" በማለትም ሕገወጥ ሆነው ሲኖሩ ኣለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጫና ታስረዳለች። ታምማ በነበረበት ሰዓት ከስራዋ ገበታ መቅረቷን የምታስታውሰው ይህች ሴት፣ እርሷና ጓደኞቿ ሕገወጥ ሆነው በመስራታቸው ለተለያዩ ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸውን ትናገራለች። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሥራ በመፍታታቸው ያላቸውን እየተጠቀሙ፣ መስራት ባለመቻላቸው የቤት ኪራይ የሚከፍሉት እንደሚቸግራቸው ወደ ጎዳና እንወጣለን የሚል ስጋት እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ልጅ ያላቸው ሴቶች መኖራቸውን በመጥቀስም ያለስራ፣ የቤት ኪራይ ሳይከፍሉ መኖር ሕይወታቸውን ማክበዱንና ነገን በተስፋ ለማየት መቸገራቸውን ይገልፃሉ። በሊባኖስ ቤሩት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ የሚናገሩት እነዚህ ስደተኞች በእስር ቤት፣ በሆስፒታል፣ ሞተው አስከሬናቸው ማቆያ ውስጥ ያለ በርካቶች መኖራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን የሊባኖስ የምጣኔ ሃብት ሁኔታ ወድቋል፣ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ሕገወጥ ሆኖ ለመስራትም ስላላስቻለ ወደ አገራችን ብንመለስ ፈቃደኛ ነን ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቆንስላ ምን ይላል? በቤሩት ሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ቆንስል የሆኑት አቶ አክሊሉ ታጠረ ውቤ ለቢቢሲ እንደገለፁት በቤይሩት ሊባኖስ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከአራት መቶ ሺህ በላይ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ "በሕገወጥ መልኩ" እንደሚኖሩ ተናግረዋል። በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኞቹ በሕጋዊ መንገድ ከመጡ በኋላ ከአሠሪዎቻቸው ጋር በተለያየ መንገድ ሳይግባቡ ሲቀሩ በመውጣት ቤት ተከራይተው "በሕገወጥ መልኩ" እንደሚኖሩ ይናገራሉ። ከእነዚህ መካከል ሰማንያ በመቶ ያህሉ ሕጋዊ ፓስፖርት፣ የመኖሪያም ሆነ የሥራ ፈቃድ የሌላቸው መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ ሊሆን የቻለው ከአሰሪዎቻቸው ጋር ሲጋጩ እዚያው ጥለው በመውጣታቸው መሆኑን ያስረዳሉ። በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያነሷቸው ችግሮች እውነት መሆናቸውን የተናገሩት አቶ አከሊሉ ኤምባሲው በተለያዩ ማህበረሰብ ቡድኖችና በኃይማኖት ተቋማት በኩል ስለወረርሽኙ ግንዛቤ ለመፍጠር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም ዜጎች ችግር ላይ እንዳይወድቁና እርስ በእርሳቸው እንዲረዳዱ ድጋፍ የመስጠት ሥራ መስራታቸውን ይገልፃሉ። በተጨማሪም ወደ አገር ቤት መመለስ ያለባቸው እስር ቤት፣ በተለያዩ መጠለያዎች ውስጥ የነበሩት ከአሁን በፊት ተመዝግበው የነበሩ 905 ዜጎችን ከሊባኖስ ለማስወጣት ከመንግሥት ጋር የመነጋገር፣ በረራ እና ለይቶ ማቆያ የማዘጋጀት ሥራዎች እየሰሩ መሆናቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ነገር ግን ይላሉ አቶ አክሊሉ "ከእነዚህ መካከል ስማቸው ተላልፎ የጉዞ ሰነድ ተዘጋጅቶ፣ ፎቶ ኑና ተነሱ ሲባል፣ 54 ሰዎች ስራ አግኝተናል መሄድ አንፈልግም በማለት የመጣውን እድል ሌሎች እንዳይጠቀሙበትም አስቀርተዋል።" ብለዋል ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ የሚገጥማቸውን የምግብ ችግር፣ የቤት ኪራይ መክፈል አለመቻልን በተመለከተ የተለያዩ ኃይማኖት ማህበራትና ተወካዮች የሚሰሩትን ስራ እንደሚደግፉ ገልፀዋል። ኤምባሲው የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ሳያሳድሱ ቀርተው ቅጣት ለሚጠብቃቸው ዜጎች ከሊባኖስ መንግሥት ጋር ተነጋግሮ ምንም ያህል ዓመት ሳያሳድሱ ቢቆዩ የአንድ አመት ብቻ እንዲከፍሉ ስምምነት ላይ መደረሱንም አክለው ተናግረዋል። አሁን ደግሞ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ይህ የቅጣት ክፍያ እንዲቀ ርእየተነጋገሩ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። በቫይረሱ የሚያዙ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩ ቀይ መስቀልና የአገሪቱ መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ እንደሚያሳክም የገለፁት አቶ አክሊሉ፣ ምንም ዓይነት ሰነድ ለሌላቸውና የተለያዩ የጤና ችግር ለሚገጥማቸውም ኤምባሲው ደብዳቤ እንደሚጽፍላቸውና በዚያ መታከም እንደሚችሉ ጨምረው አስረድተዋል። በሊባኖስ እስካሁን ድረስ በኮሮናቫይረስ የታመመ አንድም ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን አቶ አክሊሉ ጨምረው ተናግረዋል።
news-53446337
https://www.bbc.com/amharic/news-53446337
የሴቶች ስም መጠራት እንደ ውርደት የሚታይባት አፍጋኒስታን
አንዲት ሴት ለጊዜው ራቢያ ብለን እንጥራት። ራቢያ በምዕራባዊ አፍጋኒስታን ነዋሪ ናት። በአንድ እለትም ሰውነቷ የተቃጠለ እስኪመስላት ድረስ ከፍተኛ ሙቀት ተሰማት፤ ሰውነቷም ተንቀጠቀጠ። እናም ወደ ጤና ተቋም አመራች።
ስሜ የት አለ? ዘመቻ የተጀመረው ከሶስት አመታት በፊት ነው ዶክተሩ መረመራት እናም ህመሟ ኮሮናቫይረስ እንደሆነም ገለፀላት። ራቢያ ህክምናዋን ጨርሳ ወደቤቷ ተመለሰች። ቤትም ደርሳ ዶክተሩ ያዘዘላትን መድኃኒት እንዲገዛላት የማዘዣ ወረቀቱን ሰጠችው። የመድኃኒት ማዘዣ ወረቀቱን ተቀብሎ ስሟን ሲያየው በጣም ተናደደ። በከፍተኛ ሁኔታ ያስቆጣውም "ለእንግዳና ለማታውቀው ወንድ" ስሟን መንገሯ ነበር። ይህ ምናልባት ለሌሎች እንግዳ ሊሆን ይችላል። በአፍጋኒስታን ግን ባል ብቻ ሳይሆን ሌሎች የቤተሰቧ ወንድ አባላት ሴቶች ለውጪ ሰዎች ስማቸውን እንዳይናገሩ ያስገድዷቸዋል። ስማቸውንም ተናግረው ከተገኙ ክፉኛ ድብደባ ይደርስባቸዋል። ለአንዳንዶች ግን ይህ ያረጀ፣ ያፈጀና ኋላ ቀር ባህል አልተዋጠላቸውም፤ ለመቀየርም እየታገሉ ነው። 'ስሜ የት አለ' ዘመቻ? የችግሩ ምንጭ ሴት መሆንን በወጉ ካልተቀበለው ማኅበረሰብ ጋር በፅኑ የተቆራኘ ነው። ስትወለድ ይጀምራል። እንደ ጨቅላ ወንዶች ዳቦ ተቆርሶ፣ ድግስ ተደግሶ ቀድሞ ስም አይወጣላትም። ዓመታትም ይወስዳል ስሟ እስኪወጣላት ድረስ። ስታገባም ስሟ በምንም መልኩ አይጠራም። የሠርግ መጥሪያ ካርዱም ላይ ስሟ አይጠቀስም። እንዲሁ ስትታመመም ስሟ ለሐኪም መነገር የለበትም። በመድኃኒት ማዘዣ ወረቀቱም መስፈሩ የሐጥያት ያህል ይቆጠራል። በዚህ አያበቃም ህይወቷ ቢያልፍም በሞት ሰርቲፊኬት ላይ ጭራሽ ስሟ አይሰፍርም። ሐውልት ቢሰራም ስሟ አይጠቀስም፤ ባዶ ሐውልት። ለብዙዎች ስም ቀላል የሚመስለው ለአፍጋኒስታውያን ግን ደግሞ የነፃነት ጥያቄ ነው። ለዚያም ነው በነፃነት ስማቸው እንዲጠቀስና እንዲጠሩበት "ስሜ የት አለ?" የሚለው ዘመቻ የተጀመረው። ይህም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ዘንድ ከፍተኛ ንቅናቄንም እየፈጠረ ነው። "የወንድሜ፣ የአባቴና የእጮኛዬ ክብርስ?" ከራቢያ የትውልድ ቀዬ ሄራት የመጣች ሌላ ሴት ስሟን መንገር አትፈልግም፤ ስሟ አለመጠራቱም ለእሷ ምክንያታዊ ነው። "አንድ ሰው ስሜን ሲጠይቀኝ የወንድሜን፣ የአባቴንና የእጮኛዬን ክብር ላለማስደፈርና ለማስከበር ስል አልናገርም" የምትለው ይህች ግለሰብ "ለምን ቤተሰቦቼን አበሳጫቸዋለሁ? ስሜን መንገሩ ትርጉሙ ምንድን ነው?" "የእከሌ ልጅ፣ የእከሌ እህትና ለወደፊቱም የእከሌ ባለቤትና የልጄንም ስም ጠርተው የእከሌ እናት በሚል እንዲጠሩኝ ነው የምፈልገው" ብላለች። ይሄ ለሰሚው ግራ የሆነ ነገር ለሌላው ማኅበረሰብ አስደንጋጭ ቢሆንም በአፍጋኒስታን ግን የተለመደ ነው። እንዲያውም አንዲት ሴት በስሟ ብትጠራ ነው እንደ ነውር የሚታየው እንዲሁም ቤተሰቦቿን እንደሰደበችና እንዳዋረደች የሚቆጠረው። አብዛኞቹ አፍጋኒስታናዊያን ወንዶች ይህንን ተቀብለው የእህቶቻቸውን፣ የባለቤቶቻቸውን እንዲያውም የእናቶቻቸውን ስም በይፋ መጥራት እንደ አሳፋሪና መዋረድም ስለሚያዩት አክብረውትና አስከብረውትም ይኖራሉ። በባህሉም አንዲት ሴት የእከሌ እናት፣ እህት ተብላ የምትጠራ ሲሆን በቤትም ውስጥ ትልቅ ወንድም ካለም እሰዬው፤ ከእሱ ጋር በተያያዘ ይሆናል የሚጠሩት። በባህሉ ብቻ አይደለም በአፍጋኒስታን ሕግ መሰረት በልደት የምስክር ወረቀት ላይ መስፈር ያለበት የአባት ስም ብቻ ነው። ከባለቤታቸው ጋር የተለያዩትስ? ከባለቤቶቻቸው ጋር የተለያዩት በማን ይጠሩ ይሆን? ያለእድሜ ጋብቻ ተቀባይነት ባለበት አፍጋኒስታን ፋሪዳ ሳዳት ገና ነፍስ ሳታውቅ በጨቅላነቷ ተዳረች። የመጀመሪያ ልጇንም ሳትጠና በአስራ አምስት ዓመቷ ወለደች። አራት ልጆችም ከባለቤቷ ወለደች። ከባለቤቷ ጋር በይፋ ባትፋታም፣ ተለያይታ አራት ልጆቿን ይዛ ወደ ጀርመን ተሰደደች። የቀድሞ ባለቤቷ ልጆቹን በአካልም ሆነ በስልክም ጠይቋቸው አያውቅም። የህይወታቸው አካልም አይደለም። "ይህ ሰው እንዴት አባት ተብሎ ስሙ የልጆቹ መጠሪያ ይሆናል?" ስትልም ትጠይቃለች። ያላሳደጋቸውና አይቷቸው የማያውቅ አባት በልጆቿ መታወቂያ ካርድም ስሙ የመስፈር መብት እንደሌለውም ታምናለች። "ልጆቼን በራሴ ጥሬ ግሬ ነው ያሳደግኳቸው። ባለቤቴ አልፈታም ብሎኝ እንደገና ማግባትም አልቻልኩም" የምትለው ፋሪዳ "በልጆቼ መታወቂያም ስሙ እንዳይሰፍር አድርጌያለሁ።" "ልከ እንደ ቀድሞ ባለቤቴ በርካታ ሚስቶች ያሏቸው ልጆቻቸውንም ዘወር ብለው የማያዩ አፍጋኒስታናዊያን ወንዶች ብዙ ናቸው" ትላለች። "የእናቶች ስም በልጆቻቸው የልደት የምስክር ወረቀት ላይ መስፈር አለበት። የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንትም ሕጉን እንዲቀይሩ እማፀናለሁ" ብላለች። ፋሪዳ ሳዳትና ልጇ የዘመቻው መጧጧፍ "ይህ ሁኔታ በዚህ መቀጠል የለበትም" የ28 ዓመቷ አፍጋኒስታናዊት ከሦስት ዓመት በፊት ለእራሷ የገባችው ቃል ነበር። ከሄራት ግዛት የመጣችው ላሌህ ኦስማኒ ከመሰላቸቷና ጭቆናውን ለመቋቋምም ባለመምረጧ 'ስሜ የት አለ?' የሚል ዘመቻን ጀመረች። ዘመቻው መሰረታዊ የሚባለውን በስም የመጠራት መብታቸውን ለሴቶች ለመመለስ ያለመ ነው። ሳሌህና ጓደኞቿም አፍጋኒስታናዊያን ሴቶች ማንነታቸው ሲነጠቅ ዝም ብለው ለምን ይመለከታሉ በሚልም ዘመቻውን እንደጀመሩም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ዘመቻው በአሁኑ ወቅት የአፍጋኒስታን መንግሥት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳደረ ሲሆን፤ መንግሥት ሕጉን በመቀየር የልደት ሰርቲፊኬት ላይ ከአባቶች በተጨማሪ የእናቶች ስምም እንዲሰፍር በቅርቡ ያደርጋል የሚል እምነት አለን" ብላለች። የተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ማርያም ሳማ በቅርቡ የእናቶች ስም በልደት ሰርቲፊኬት እንዲካተት በፓርላማ የተናገሩ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ድጋፍም ለማሰባሰብም በሚል በትዊተር ገፃቸው ላይ መልዕክቱን አስፍረዋል። ተቃውሞ ሳሌህ በዘመቻው ጉዳይ ከቢቢሲ ጋር ያደረገችው ቆይታ በቢቢሰ ፌስቡክ መውጣቱን ተከትሎ ድጋፍ እንዲሁም ውግዘትን አስተናግዷል። አንዳንዶችም በፌዝና በስላቅ መልኩ የልደት የምስክር ወረቀት ላይ የዘመድ አዝማድ ስም እንዲካተት ዘመቻ ትጀመር ይሆናል ብለዋል። በቤተሰብ ውስጥ ሰላም መስፈን አለበት "የሚቀድመውን እወቂ" ያሏትም አልታጡም። በርካታ ወንዶች የልጇ ልደት ምስክር ወረቀት ላይ ስም እንዲሰፍር የምትጠይቀው አባቱን ስለማታውቀው ነው በማለት ለመዝለፍ ሞክረዋል። ሳሌህ በበኩሏ ነቃ ያሉና ነገሮችን ቀለል ባለና ሰፋ ባለ መልኩ ይመለከታሉ ብላ የምታስባቸው የወጣቱ ትውልድ አባላት እንዲህ አይነት አፀያፊ አስተያየቶች መስጠታቸው አሳዝኗታል። የታዋቂ ሰዎች ድጋፍ በአፍጋኒስታን ውስጥ ስመ ጥር የሆኑት ሙዚቀኛና የሙዚቃ አዘጋጅ ፋራሃድ ዳርያና ሙዚቀኛና የሙዚቃ ፀሐፊ የሆነችው አርያና ሳይድ ለዘመቻው ያላቸውን ድጋፍ አሰምተዋል። ፋርሃድ እንደሚለው ሴት እናት፣ እህት፣ ልጅ፣ ሚስት መሆኗ ሚና እንጂ የሴት ማንነት አይደለም። "ሴቶችን ባላቸው ሚና ብቻ ስንጠራቸው ዋናው ማንነታቸውን ማጥፋትና መደምሰስ ነው" በማለት ያስረዳል። አክሎም "ወንዶች የሴቶችን ማንነት ሲነጥቋቸውና ሲክዷቸው በጊዜያትም ውስጥ ሴቶች እራሳቸው ማንነታቸውን ያደበዝዙታል" ይላል። በአፍጋኒስታን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ዝናን ከተጎናፀፉት መካከል አርያና ሳይድ አንዷ ስትሆን የሴቶች መብትም ታጋይ ናት። ዘመቻውን ብትደግፍም እንዲህ በቀላሉ ይሳካል የሚል ተስፋ የላትም። "ፀሐይና ጨረቃ አላይዋትም " "የሴቶችን ማንነት የመንጠቅ መሰረቱ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሰፈነው ጨቋኙ አባታዊ ሥርዓት ሲሆን ለወንዶች ክብር ሲባል ሴቶች ሰውነታቸውን እንዲደብቁ ብቻ ሳይሆን ስማቸውም እንዳይጠራ ተደርጓል" በማለት አሊ ካቬህ የተባለው የማኅበረሰብ አጥኚ ይናገራል። "በአፍጋኒስታን ማኅበረሰብ ዘንድ ጨዋ (ድንቅ) ሴት የምትባለው ድምጿ የማይሰማ እንዲሁም ልታይ ልታይ የማትል ናት። ይህንንም ለማጠናከር ፀሐይና ጨረቃ አላይዋትም የሚባል አባባል አለ" ይላል። "ቆፍጠን ያሉ ወይም ደግሞ ጨካኝ ወንዶች በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚከበሩና ቦታ የሚሰጣቸው ናቸው። በቤተሰቡ ዘንድ ቀለል ያሉና ፈታ ያሉ ሴቶች ቅሌታምና ክብርን ያዋረዱ አድርገው ይቆጠራሉ" በማለትም ስር ስለሰደደው ሥርዓት ያስረዳል። በእንግሊዝ ተቀማጭነቱን ያደረገው ሱሬ ቴክኖሎጂ ማዕከል የቴክኖሎጂ ሥራዎች ፈጣሪ የሆነችውና በርካታ ሽልማቶችን የተጎናፀፈችው የህክምናና የፊዚክስ ባለሙያ ሻክሮዶክት ጃፋሪ "ለአፍጋኒስታን ሴቶች ከማንም ጥገኛ ያልሆነ ማንነት እንዲኖራቸው የገንዘብ፣ ማኅበራዊና ከሌሎችም ስሜቶች ነፃ ሊሆኑ ይገባል" ትላለች። አክላም እንደ አፍኒጋኒስታን ባለሉ አገሮችም "የሴቶችን ማንነት የሚነጥቁትም ሆነ የሚክዱት ላይ መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል" ትላለች። የታሊባን መንግሥት ከወደቀበት ከሁለት አስርታት በኋላ የአገሪቱ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሴቶች ወደ አደባባይ እንዲመለሱ እየሞከሩ ነው። ነገር ግን እንደ ራቢያ ያሉ ሴቶች ለሐኪሞች ስማቸውን በመንገራቸው አሁንም ክፉኛ ይደበደባሉ። ሻክሮዶክት እንደ አፍጋኒስታን ባለ ጨቋኝ አባታዊ ሥርዓት ስር በሰደደበት ባህላዊ ማኅበረሰብ ውስጥ የማኅበረሰቡ ትግል ብቻ ሳይሆን መንግሥት ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃትና ጭቆና ለማስቆም ሕጋዊ መንገዶችን ሊያረጋግጥ እንደሚገባም ትናገራለች። የስም ጉዳይ በአፍጋኒስታን ፓርላማ ውስጥ ቢነሳም ፖለቲከኞቹ 'ስሜ የት አለ?' ለሚለው ምን አይነት ምላሽ አላቸው የሚታይ ይሆናል።
53880314
https://www.bbc.com/amharic/53880314
ኮሮናቫይረስ ፡ ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ታዳጊዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አለባቸው ተባለ
የዓለም ጤና ድርጅት አዲስ የጤና መመሪያ አውጥቷል።
መመሪያው ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ታዳጊዎች ባሉበት አገር አሊያም አካባቢ ለአዋቂዎች በሚመከረው መሰረት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ይገባቸዋል ይላል። ህፃናት ቫይረሱን እንዴት ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ ብዙም የሚታወቅ ነገር እንደሌለ የገለፀው ድርጅቱ፤ ነገር ግን ልክ እንደ አዋቂዎች ሁሉ ታዳጊዎችም በሽታውን ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ የሚያመላክቱ መረጃዎችን ጠቅሷል። ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እንደሌለባቸው መክሯል። እስካሁን ዓለማችን ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ ቢያንስ 23 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አብዛኞቹም የተመዘገቡት በአሜሪካ፣ ብራዚል እና ሕንድ ነው። ይሁን እንጂ በቂ ምርመራ ባለመደረጉና የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው ሰዎች በመኖራቸው ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ይታመናል። በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም በደቡብ ኮሪያ ፣ በአውሮፓ ሕብረት አገራት እና በሊባኖስ በድጋሜ እያገረሸ ነው ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም በጎርጎሮሳዊያኑ 1918 የተከሰተውንና በአገራችን 'የኅዳር በሽታ' ተብሎ የሚጠራው 'የስፔን ጉንፋን' በሁለት ዓመት መጥፋቱን ገልፀው፤ ኮቪድ-19ም በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠፋ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ከፍተኛ የሳይንስ አማካሪ ግን ኮቪድ-19 በጭራሽ ላይጠፋ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ምክንያታቸው ደግሞ የዓለም የሕዝብ ብዛትና እንቅስቀሴ ከ100 ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር አይመሳሰልም፤ የሰዎች እንቅስቃሴም በሽታውን ያዛምተዋል የሚል ነው። በመሆኑም አማካሪው "በሽታው እንደ ሌሎች በሽታዎች አብሮን ሊኖር ይችላል፤ ሰዎችም በተወሰነ ጊዜ ልዩነት መደበኛ ክትባት ሊያስፈልጋቸው ይችላል" ብለዋል። ድርጅቱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን በተመለከተ ለህፃናት ያወጣው መመሪያ ምን ይላል? ድርጅቱ በድረ ገፁ ላይ ባተመው መመሪያ ላይ የህፃናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አጠቃቀምን በሦስት የዕድሜ ክልሎች ከፍሎ ተመልክቶታል። ይሁን እንጅ ዕድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ የሆናቸው ህፃናት ትምህርት ቤት ውስጥ የአፍና መሸፈኛ መጠቀም ይኖርባቸው እንደሆነ ድርጅቱ በመመሪያው ላይ ያለው ነገር የለም። ምን አልባት አዲሱ የትምህርት ዘመን ሲጀምር የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ የመማሪያ ክፍል ውስጥ ደንብ ሊሆን ይችላል። ፈረንሳይ በቅርቡ ከ11 ዓመት በላይ ያሉ ሕፃናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀምን አስገዳጅ አድርጋለች። ምንም እንኳን የመንግሥት መመሪያ ባይሆንም በዩናይትድ ኪንግደምም የሚገኙ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያደርጉ ወስነዋል። ከዚህም ባሻገር ድርጅቱ መምህራን የቫይረሱ ሥርጭት ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ሁሉም ከ60 ዓመት በታች የሆነና በጥሩ ጤንነት ላይ ያለ አዋቂ ሰው ቢያንስ አንድ ሜትር አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ካልቻለ ከጨርቅ የተሰሩ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን መጠቀም አለባቸው ብሏል። ይህ በተለይ ከህፃናት ጋር ለሚሰሩና ከህፃናት ጋር የቅርብ ግንኙነት ላላቸው ግለሰቦች በጣም ወሳኝ ነው። ከ60 ዓመት በላይ የሆኑና የጤና እክል ያለባቸው አረጋዊያንም የሕክምና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ [medical masks] ማድረግ እንደሚገባቸው ድርጅቱ መክሯል።
47565532
https://www.bbc.com/amharic/47565532
"እናቱ ስታየኝ 'ልጄ ያሬድ ይመጣል' እያለች ታለቅስ ነበር"- በናይሮቢ የካፒቴኑ ጸጉር አስተካካይ
ያሬድ ተክሌ ነው የምባለው። የምኖረው ናይሮቢ ነው።
ካፒቴን ያሬድ እኔ ጋ ነበር የሚስተካከለው። የረዥም ጊዜ ደንበኛዬ ነበር። በተለይ እረፍት ሲሆን፣ ለክሪስማስ እዚህ ኬንያ ሲመጣ እዚህ እኔ ጋ ነበር ጸጉሩን የሚስተካከለው። እኔ ሰው ከሞተ በኋላ እንዲህ ነው እንዲህ ነው ሲባል ብዙም ደስ አይለኝም። ግን እውነቴን ነው የምልህ ያሬድ በጣም የተለየ ልጅ ነበር። ሥነ ሥርዓት ያለው፣ ሰውን የሚያከብር፣ ሁሉንም እኩል የሚያይ። እኔን ራሱ ያሬድ ብሎ ጠርቶኝ እኮ አያውቅም። ሞክሼ ነበር የሚለኝ... (እንባ ተናነቀው ) •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ አንተ ጸጉር ቤት ከቤተሰቦቹ ጋ ነበር የሚመጣው? አዎ! ሁልጊዜም ከቤተሰቡ ጋ ነው። አንድ ወንድሙ ኢሲያ ትምህርት የሚማር ነበር። ደግሞ ብታይ ከእናት ከአባቱ ጋ ያላቸው ነገር ልዩ ነው። ፍቅራቸው። አባቱም ዶ/ር ጌታቸው ደንበኛዬ ነው። አብረው ነበር የሚመጡት። ያሬድ ግን በብዛት ከእናቱ ጋ ነበር የሚመጣው። እናቱ አምጥታው ነው ተስተከካክሎ ሲጨርስ የምትወስደው። ሂሳብ ራሱ « እሰኪ ዛሬ እኔ ልጋብዝህ እያለች እሷ ነበር የምትከፍልለት በብዛት» በጣም የሚያስቀና ቤተሰብ ነው። እሷ ሥራ ስላላት ቅዳሜ ወይ እሑድ ነበር እዚህ የሚመጡት። •የካፕቴን ያሬድ ሃይማኖታዊ የሀዘን ስርአት ያለ አስከሬን ተፈፀመ ብዙ ጊዜ ፀጉሩን ለመስተካከል የሚመጣው ከወላጆቹ ጋር እንደነበር አስተካካዩ ያሬድ ተክሌ ይናገራል ከእናቱ ጋ ስታያቸው በቃ ያስቀናሉ። መኪና እንኳ እንዲነዳ ብዙም ደስ አይላትም፤ ስለምትሳሳለት። "እዚህ [ናይሮቢ] መንገዱ ጥሩ አይደለም፣ ጠባብ ነው በቃ እኔ አደርስሀለሁ" ትለው ነበር። በቃ ምን ልበልህ፣ እሱምኮ አንዳንዴ መኪና ይዞባት ይመጣል፤ ግን በቃ እናቱ ብዙም ደስ አይላትም። ሁልጊዜም አብሯት እንዲሆን ነው የምትፈልገው። ከካፒቴን ያሬድ ጋ በምን ቋንቋ ነበር የምትግባቡት? እኔ በኪስዋሂሊ ነበር የማዋራው። እሱ ግን አማርኛ መልመድ ስለሚፈልግ በአማርኛ ማውራትን ይመርጣል። እኔ ሳውቀው ብዙም አልነበረም አማርኛ፤ ምክንያቱም እዚህ ኬንያ ተወልዶ ስላደገ በደንብ አይችልም ነበር። ከጊዜ በኋላ ነው አማርኛ ራሱ መሞከር የቻለው። መጨረሻ ላይ ጎበዝ እየሆነ ነበር። ለመቻል ጉጉት ነበረው። ሁለተኛ ደግሞ ከዌስትላንድ እዚህ [ሀበሻ ሬስቶራንት] ድረስ የሚመጣው ለኢትዯጵያ ፍቅር ስላለው እንጂ ሰፈሩ'ኮ የሕንዶችም የኬንያም ብዙ ጸጉር ቤት አለ። እናቱ ደግሞ አማርኛ አይችሉም። ግን አንዳንድ ነገር ይገባቸዋል። •ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው ምን ምን ያወራህ ነበር? ምን ትዝ ይልሃል? በኢትዮጵያዊነቱ ደስተኛ ነው። ሁሌም ስሜቱ ደስተኛ ነው። ኢትዮጵያ አየር መንገድ በመግባቱ በሥራው፣ ደስተኛ ነበር። ደቡብ አፍሪካም ሊሄድ ይፈልግ ነበር። ኬንያም መማር ያስብ ነበር። ግን በኋላ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲያገኝ በጣም ደስተኛ ነበር። ኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰፊ እድል እንዳለ ነበር የሚነግረኝ። የሞቱን ዜና እንዴት ነው የሰማኸው? እኔ እስከመጨረሻው ድረስ አውሮፕላን መከስከሱንና ሰዎች መሞታቸውን እንጂ ያሬድ ይኖርበታል ብዬ በጭራሽ አላሰብኩም። እና እዚሁ ጸጉር ቤት ውስጥ ሥራ ላይ እያለሁ « አብራሪው ግማሽ ኬንያ ነው አሉ...» ሲባል ደነገጥኩ። አንድ እሱን ነው የማውቀው እና ያሬድዬ ነው በቃ ብዬ ክው አልኩ። ከዚያ በኋላ ከባድ ጊዜ ነው ያሳለፍኩት። ስረጋጋ ቤተሰቦቹ ጋ ደወልኩ። ከዚያ በነገታው ሰኞ ጠዋት ዌስትላንድ ሄጄ እናቱ ጋ ለቅሶ ደረስኩ። በጣም ነው እናቱ የምታሳዝነው። ልጇ የመጣ ያህል ነው ስታየኝ ያለቀሰችው። አቅፋኝ በቃ አለቀሰች። የኔና የሱን ቅርበት ስለምታቅ በጣም አለቀሰች። "ልጄ ያሬድ እኮ አለ፤ ይመጣል" ትለኝ ነበር። ሞቱንም እንኳ ለመቀበል ተቸግራለች። (እንባ ይተናነቀዋል) እንግዲህ እግዚአብሔር የፈቀደውን ነው የሚያደርገው፤ ለቤተሰቦቹ መጽናናት ይስጠልን ከማለት ውጭ ምን ማድረግ ይቻላል?
news-56439789
https://www.bbc.com/amharic/news-56439789
ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ፡ 'ቡልዶዘር' የተባሉት የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ማን ነበሩ?
ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ ነው ሙሉ ስማቸው። ቡልዶዘር ነው ቅጽል ስማቸው።
ሲወለዱ የጭሰኛ ልጅ ነበሩ። ሲሞቱ ግን ፕሬዝዳንት ነበሩ። ቡልዶዘር የሚለው ቅጽል ስም ከየት መጣ? ቡልዶዘር (ሺዶማ) የተባሉት ያለምክንያት አይደለም። ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት የሥራና ከተማ ሚኒስትር ነበሩ። መንገድ በስፋት ያሠሩ ነበር ያን ጊዜ። የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ነፍሳቸው ነበር ማጉፉሊ። ሕዝቡ ቡልዶዘር ሲል ቅጽል አወጣላቸው። ይህ ቅጽል ስም ግን ኋላ ላይ እየሰፋ ሄዶ መነሻውን ሳተ። ቡልዶዘር የሚለው ስም ሰውየው የመንግሥት ወጪን በመቀነስና ሙሰኞችን መጠራረግ ስለሚወዱም ነው ተባለ። የአስተዳደር ዘያቸው መጠራረግ ስለነበር ስሙ የተስማማቸው ይመስላል። ማጉፉሊ ሚዲያ ማስደንበር ይወዳሉ፤ ነጻ ድምጾችን ያፍኑም ነበር። ተቃዋሚዎችን አሸብረዋል። ሆኖም ሞታቸውን ያጀበው ያ ሳይሆን ለኮሮናቫይረስ ያሳዩት የነበረው ንቀት ነበር። ምናልባት እሱው ይሆን ከዚህ ዓለም ያሰናበታቸው? "ኮሮናቫይረስ ጂኒ ነው" ኮሮናቫይረስ ታንዛኒያ ሲገባ ማጉፉሊ ተበሳጩ። ሕዝቡ ቀን ተሌት እንዲሠራ እንጂ ቤቱ እንዲቀመጥ በፍጹም አይፈልጉም። አንድ መላ ዘየዱ። "ሕዝቤ ሆይ! ለዚህ ተህዋሲ አትንበርከክ! ቤተክርስቲያን ሄደህ ጸልይ እንጂ በፍጹም ቤት አትቀመጥ" አሉ። ሕዝቡም ያን አደረገ። "ኮሮና ጂኒ ሰይጣን ነው እንጂ ተህዋሲ አይደለም" የሚለውን ሐሳብ በሕዝባቸው ውስጥ አሰረጹ። ሳይንስ ግን ሰውየውን ታዘባቸው። ቫይረሱም ሳይናደድባቸው አልቀረም። ከሰኔ 2020 ጀምሮ ማጉፉሊ አገሬ ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ ነች ሲሉ አወጁ። ጭምብል ማጥለቅን ተሳለቁበት። ኮቪድ-19ን ንቀው የዜና ማድመቂያ አደረጉት። በአገራቸው አልበቃ ብሎ ጎረቤት አገሮች የእንቅስቃሴ ገደብ ሲያደርጉ "የማይረቡ ፈሪዎች" አሏቸው። ለምዕራቡ ተንበርካኪ አድርገው ሳሏቸው። ማጉፉሊ በ2015 የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ፣ ታንዛኒያ የሚያስፈልጓት ዓይነት ፕሬዝዳንት ሆነው ነበር የተገኙት። ሙስናን የሚጸየፉና በሥራ የሚያምኑ። ቀን ተሌት ቢሠሩ አይደክማቸውም። ቡልዶዘራዊነታቸውን አጠናክረው ቀጠሉበት። ውጤት ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ነድፎ የማስፈጸም አቅማቸው ተደነቀላቸው። ለሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ምሳሌ መሆን ጀመሩ። ገና ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ በመጀመርያው ቀን የገንዘብ ሚኒስቴር ቢሮ ሄዱ። ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ተሟልተው አልተገኙም ነበር። ማጉፉሉ ጦፉ። ይህን በፍጹም እንደማይታገሱ እቅጩን ተናገሩ። ከሥራ የቀረ አለቀለት። ለደመወዝ ቀን ብቅ እያለ የሚጠፋ "ጎስት ዎርከርስ" እየተባለ የሚጠራን ታንዛኒያዊ ጠራርገው አባረሩ። ሥራውን የማይፈልግ የመንግሥት ሠራተኛ ብቻ ነው ከዚያ ወዲህ ከቢሮ ሥራ የሚቀር። ማጉፉሊ የዛቻ ብቻ አይደለም፤ የድርጊት ሰው ናቸው። ከሥራ የሚቀሩትን ብቻ ሳይሆን ሙሰኛ አለቆችን ጠራርገዋል። አንዳንድ ጊዜ ሹመኞችን የሚያባርሩት ታዲያ በቀጥታ በብሔራዊ ቴሌቪዥን እየታዩ ጭምር ነበር። ለሌላው መቀጣጫ እንዲሆኑ። በዚህ ጊዜ ቡልዶዘር ኑርልን አላቸው አገሬው። እሳቸውም ተበረታቱ። ማጉፉሊ ገና ድሮ ወጪ የሚባል ነገር ያበሳጫቸዋል። በተለይ ያልተገባ ብልጭልጭ ወጪ ታንዛኒያ ማውጣት የለባትም ብለው በጽኑ ያምኑ ነበር። "ምክንያቱም ድሆች ነን" ይላሉ። ማጉፉሊ በሥራ በዘመቻዎች በመሳተፍ ሠርተው ያሳዩ ነበር በዚህ የተነሳ በድምቀት ይከበሩ የነበሩ በርከት ያሉ ክብረ በዓላትን አስቀርተዋል። በ54 ዓመታት የታንዛኒያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የነጻነት ቀን እንዳይከበር ያደረጉት እሳቸው ናቸው። "ቸበርቻቻ አያስፈልግም ሥራ ነው እንጂ" አሉ። "ሕዝቤ ሆይ! ነጻ የምትወጣው የነጻነት በዓልን በማክበር ሳይሆን ተግቶ በመሥራት ነው፤ ስለዚህ እጅህ መቁሸሽ አለበት" ሲሉ ጮኹ። ማጉፉሉ ሕዝቡን በማዘዝ ወደ ቅንጡ ቤተ መንግሥት የሚገቡ ሰው አልነበሩም። እሳቸውም በዘመቻ ይሳተፉ ነበር። ሠርተው ያሳያሉ። ለምሳሌ የቤተ መንግሥቱን ደጅ የሚጠርጉት እሳቸው ራሳቸው ነበሩ። ኃላፊዎቻቸው በሆነ ባልሆነው ወደ አሜሪካና አውሮፓ ይጓዙ ነበር። ለሕክምና፣ ለጉብኝት፣ ወዘተ። ይህ ሁሉ የሚሆነው በሕዝብ ገንዘብ ነበር። አንድ ኃላፊ የውጭ አገር ጉዞ ቢያደርግ ወዮለት ብለው ደነገጉ። ተፈጻሚም ሆነ። ይህ እርምጃቸው በታንዛኒያውያን ዘንድ እጅግ ተወዶላቸው ነበር። እንዲያውም በማኅበራዊ የትስስር መድረክ መነጋገርያ ሆነው ነበር። "ማጉፉሊ ቀጥሎ ምን ያደርጋሉ" የሚል የድራምባ ሐረግ (Hashtag) ተፈጥሮም ነበር። ማጉፉሊ ከአገራቸው ባሻገር በሌሎች አፍሪካውያን ዘንድ ውስጥ ውስጡን አድናቆት ማግኘት ጀማምረውም ነበር። ለምሳሌ በ2017 አንድ እውቅ የኬንያ ፕሮፌሰር በዳሬ ሰላም ዩነቨርስቲ ተገኝተው በሰጡት የአደባባይ ዲስኩር "አፍሪካ አዲስ አስተዳደር ያሻታል" ካሉ በኋላ ይህ አፍሪካን የሚለውጠውን የአስተዳደርም ዘዬ "ማጉፉሊኬሽን" ሲሉ ሰይመውታል። ማጉፉሊ በዚህን ያህል ተጽእኖ መፍጠር ቢችሉም የዲሞክራሲ ጸር ሆነው ነበር የሚታዩት። ተቃዋሚ በማሽመድመድ፣ ነቃፊዎቻቸውን ነቅሶ በማሰር፣ ነጻ ሚዲያን በማፈን ስማቸው ይነሳል። ጆን ማጉፉሊ በአጭሩ ማጉፉሊ መጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ በሁለተኛ ወራቸው የፓርላማ የቀጥታ ሥርጭት እንዳይተላለፍ አገዱ። ያን ጊዜ ሰበብ ያደረጉት ወጪ ቅነሳን ነበር። ተቃዋሚዎች ግን ይህ ነገር ለሳንሱር እንዲመች አድርጎ የፓርላማን ክርክር ለሕዝብ ለማቅረብ ነው ብለው ከሰሷቸው። እንዲያውም ይህን እርምጃ ተቃውመን ሰልፍ እንወጣለን አሉ። ሆኖም ሰልፉ በማጉፉሊ ሰዎች እውቅና ተነፈገውና ታገደ። በ2017 ደግሞ ማጉፉሊ የታንዛኒያው ራፐር ናይ ዋ ሚቴጎ ዘፈን ዘፈነባቸው። ሚቴጎ ሙዚቃውን በለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ራሱን እስር ቤት አገኘው። ይህ ዘፋኝ በራፕ ሙዚቃው ያዜመው ግጥም በደምሳሳው ሲተረጎም እንዲህ የሚል ስንኞች ነበሩበት፣ እስኪ ንገሪኝ አገሬ፣ ነጻነት አለ ወይ በሰፈሬ ያሻኝን ብዘፍን ጉራማይሌ አገኘው ይሆን ራሴን ከርቸሌ? ማጉፉሊ ራፐሩን እንደምኞቱ ከርቸሌ ወረወሩት። በዳሬ ሰላም ማዕከላዊ እስር ቤት ታጎረ። በዚህም ማጉፉሊ ለትችት ቦታ እንደሌላቸው አሳዩ። ማጉፉሊ ለሚዲያ ርዕስ የሚመቹና አንዳንዴም አስቂኝ ሰው ነበሩ። ለምሳሌ ይህን ተቺ ሙዚቃ ያቀነቀነውን ናይ ዋ ሚቴጎን ከአንድ ቀን በኋላ ከእስር ሲያስፈቱት አንድ ምክር መከሩት። "ስለ ግብር አጭበርባሪዎች ሙዚቃ ሥራልኝ" በማለት። ፕሬዝዳንት ማጉፉሊን ግብር አጭበርባሪዎች በጣም ያናድዷቸው ስለነበር ነው ለዘፋኙ ይህን ምክር የሰጡት። በ2017 ደግሞ ዋንኛ ተቃዋሚያቸውና የምክር ቤት አባሉ ቱንዱ ሊሱ ቤታቸው ሳሉ ተተኮሰባቸውና ክፉኛ ቆሰሉ። የማጉፉሊ ሰዎች እንዳደረጉት ይታመናል። ሆኖም ሰውየው እንደምንም ድነው ከ3 ዓመት በኋላ ተገዳዳሪያቸው ሆነው ለፕሬዝዳንትነት ተወዳደሩ። ሚስተር ሊሱ የግድያ ሙከራ እንደተረገባቸውና ታንዛኒያን እየመሯት ያሉት ሰው አምባገነን እንደሆኑ በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር። ማጉፉሊ እስከወዲያኛው ያሰናብቱታል ቢባልም ተፎካካሪያቸው እንዲሆን ፈቀዱለት። ማጉፉሊ የአስተዳደር ዘይቤያቸው የተቀዳው ከአገሪቱ የነጻነት አባት ጁሊየስ ኔሬሬ እንደሆነ ይነገራል ምዕራብ ጠልነትና ማጉፉሊ ማጉፉሊ ምዕራባዊያን አፍሪካን በዝብዘዋታል ብለው ያምናሉ። ስለዚህ በተራችን እነሱን መበዝበዝ አለብን ሲሉ ያስባሉ። በዚህ ረገድ በየጊዜው የውጭ ድርጅቶችን የሚያስጨንቁ አዳዲስ መመርያዎችን ያወጡ ነበር። ከነዚህ መሐል የካናዳው ባሪክ ወርቅ እህት ኩባንያ የሆነውን አካሺያ ማዕድን ድርጅትን 190 ቢሊዮን ዶላር ለመንግሥት ክፈል ብለው አነቁት። ለምንድነው የምከፍለው ቢላቸው፣ በቃ እስከዛሬ የከበሩ ማዕድናትን ከታንዛኒያ ስታወጣ ነበር። ገቢህን ስንደምረው ታንዛኒያ ይህን ያህል ማግኘት እንዳለባት ደረስንበት አሉት። ኩባንያው ደነገጠ። ከብዙ ድርድር በኋላ 300 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ። ከዚህ ዕለት በኋላም ይህ የካናዳው ባሪክ ወርቅ አውጪ ኩባንያ ከሚያወጣቸው ማዕድናት 50 ከመቶውን ለመንግሥት ገቢ እንዲያደርግም ተገደደ። ማጉፉሊ የአስተዳደር ዘይቤያቸው የተቀዳው ከአገሪቱ የነጻነት አባት ጁሊየስ ኔሬሬ እንደሆነ ይነገራል። እሳቸውም ይህንን ብለውት ያውቃሉ። ማንም እንዴት አገሬን መምራት እንዳለብኝ ሊነግረኝ አይገባም ይሉ ነበር። በአንድ ወቅት ኮሮናቫይረስ የእንቅስቃሴ ገደብን በተመለከተ የተናገሩት ይህንኑ የሚመሰክር ነበር። "አባቶቻችን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እየተነገራቸው አይደለም ያስተዳደሩን።…እንዲህ ዓይነት ቤት ዘግታችሁ ተቀመጡ የሚል መመርያ የሚያወጡ ሰዎች ከሩቅ ሊያስተዳድሩን ነው የሚሹት። የእኛ አባቶች እንዲህ አይነቱን ነገር አይቀበሉም ነበር" ሲሉ ምዕራባዊያንን ተችተዋል። "ድህነት ምን ማለት እንደሆነ አውቀዋለሁ" ማጉፉሊ ከጭሰኛ ቤተሰብ በሰሜን ምዕራብ ቻቶ በሚባል ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነው የተወለዱት። "ድህነትን በደንብ አውቀዋለሁ" ይሉም ነበር። እሳቸው ልጅ እያሉ ታንዛኒያን የሚያስተዳድሯት ጁሊየስ ኔሬሬ ነበሩ። "ቤታችን ከጭቃ ነበር የተሰራው፣ በልጅነቴ ከብቶችን አግድ ነበር። ቤተሰቤን ለመታደግ ወተትና ዓሳ እያዞርኩ ነበር የምሸጠው። ድህነት ምን ማለት እንደሆነ ለእኔ አትነግሩኝም፤ ለዚህ ነው ድሆችን ለማገዝ ፖለቲካ ውስጥ የገባሁት" ሲሉም ተናግረዋል። ማጉፉሊ ጭሰኛ ሆነው ተወልደው ፕሬዝዳንት ሆነው ሞቱ። በተወለዱ በ61 ዓመታቸው።
55777885
https://www.bbc.com/amharic/55777885
ከዓመት በፊት ኮሮናቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘባት ዉሃን ምን ላይ ትገኛለች?
በዉሃን ኮሮናቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተገኘ ዓመት አለፈ።
መላው ዓለምን እንዳልነበረ ካደረገው ቫይረስ ጋር የፕ/ር ሺ ዢንግሊ ስም ተያይዞ ይነሳል። ሳርስ-ኮቭ-2 ከቤተ ሙከራ ያመለጠ ቫይረስ ነው ሲባልና ሌሎችም ጥያቄዎች ሲነሱ እኚህ ባለሙያም አብረው ይታወሳሉ። ዉሃን ውስጥ ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት እንደተገኘ መላምታቸውን በሳይንስ መጽሔት ይፋ አድርገዋል። ፕሮፌሰሯ እንደሚሉት ቫይረሱ በዉሃን ከመታየቱ በፊት ሌላ ቦታ ተከስቶ ነበር። ቫይረሱ ወደ ቻይና፣ ዉሃን የገቡ ምግቦች ላይ መገኘቱን በመጥቀስ ነው ምናልባትም ቫይረሱ ከዉሃን ውጪ እንደገባ ያስረዱት። መላምታቸው ብዙ ባለሙያዎችን ያነጋገረ ነው። ቻይና ውስጥ ቫይረሱ የመጣው "ከአሜሪካ ነው" ብለው የሚያምኑ ዜጎችም አሉ። አምና ጥር 23 የቻይና መንግሥት የዉሃን ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ፣ ትራንስፓርትም እንዲቋረጥ አዘዘ። የጤና ባለሙያዎች መጀመሪያ ላይ ስለ ቫይረሱ ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ሰሚ አላገኙም ነበር። ቻይናውያን መንግሥት ስለወረርሽኙ መረጃ ደብቋል ሲሉ ተችተውም ነበር። ይህ ከሆነ ከዓመት በኋላ ዉሃን ተረጋግታ ወደ መደበኛ ሕይወት እየተመለሰች ነው። ገበያ እየተሟሟቀ፣ ቫይረሱን ዉሃን ድል መንሳቷን የሚያወሳ ዐውደ ርዕይ እየተካሄደም ይገኛል። ፕሬዘዳንት ዢ ዢፒንግ ቫይረሱን በመታገል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ የሚጠቁም መልዕክት ተላልፏል። በእርግጥ ቻይና በርካታ ዜጎቿን በመመርመር፣ ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያደረጉ ሰዎችን በመለየትና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ ስኬታማ ሆናለች። በሌላ በኩል ደግሞ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደቦች ሰብአዊ መብት ጥሰዋል። ቻይና ቫይረሱን በተመለከተ ማንኛውም ምርመራ እንዲደረግ ብትፈቅድም፤ አሁንም ቫይረሱ ከየት መጣ? ለሚለው ጥያቄ ግልጽ መልስ አልተገኘም። ከኮሮናቫይረስ በፊት የተቀሰቀሱ ወረርሽኞችን ያጠኑ ባለሙያዎች ቫይረሱ ከሌሊት ወፍ ወደ ሰው ልጆች ተሸጋግሮ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ቻይና ውስጥ ይህንን መላምት የተመረኮዘ ጥናት እምብዛም አልተሠራም። "አደገኛው ቫይረስ ከየት እንደተነሳ ሳይታወቅ ወደቀደመው ሕይወት መመለስ አስጊ ነው" የሚሉት በኤምአይቲ እና ሀርቫርድ የቫይረስ አጥኚ የሆኑት አሊና ቻን ናቸው። ቻይና ቫይረሱ ወደ ዉሃን የገባው ከሌላ ቦታ ነው የሚለውን መከራከርያ አጉልታ ማሰማቷን ቀጥላለች። ሳይንሳዊ መረጃ ሳይኖር ቫይረሱ ወደ ዉሃን የመጣው ከሌላ ቦታ ነው ማለት ተገቢ ነው? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው የቻይና የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ሁዋ ቹያንግ፤ "ጥያቄው ለቻይና ያለውን የተዛባ አመለካከት ያሳያል" ሲሉ መልሰዋል። ቃል አቀባዩዋ እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡት ይህ ቫይረስ አምና በአውስትራሊያ፣ በጣልያን እና በሌሎችም አገራትም መገኘቱን ነው። ተመራማሪዋ አሊና በበኩላቸው ቫይረሱ ዉሃን ውስጥ ከመገኘቱ በፊት ሌላ ቦታ ስለመታየቱ ማስረጃ የለም ሲሉ ይከራከራሉ። "የመጀመሪያዎቹ ታማሚዎች ከዉሃን ነበሩ። ከዚያም ከዉሃን ወጥተው የተጓዙ ሰዎች ላይ በሽታው ተገኘ" ይላሉ። ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ ያመለጠ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ብዙ ሳይንቲስቶችን ያከራከረ ጉዳይ ነው። በአሜሪካ የበሽታ መከላከል ላይ የሚሠሩት ክርስቲን አንደርሰን፤ ቫይረሱ የታሸጉ ምግቦች ላይ ነው የተገኘው በሚለው ሐሳብ አይስማሙም። የቻይናዋ ፕ/ር ሺ ዢንግሊ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ አምልጧል ብለው የሚያምኑ ባለሙያዎች ወደ ዉሃን ሄደው እንዲመረምሩ ጥሪ አቅርበዋል። ቻይና ከብዙ ወራት ቆይታ በኋላ የዓለም ጤና ድርጅት የምርመራ ቡድን ወደ ዉሃን እንዲሄድ ፈቅዳለች። በዚህም አለ በዚያ ዉሃን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ቫይረስ የመላው ዓለም ራስ ምታት ሆኖ ዓመት ደፍኗል። የጤናው ዘርፍ ባለሙያዎች የዓለም ጤና ድርጅት ምርመራ አንዳች መልስ ይዞ እንደሚመጣ እየጠበቁ ነው።
news-53048606
https://www.bbc.com/amharic/news-53048606
በኢትዮጵያ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 መገኘቱ ምን ያመላክታል?
የጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም በጋራ በሚሰጡት ዕለታዊ መግለጫ ላይ፤ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 መገኘቱ ሲገለጽ ሰንብቷል። የሰኔ 7 ቀን 2012 ዓ. ም. ሪፖርትን እንኳ ብንመለከት በሁለት አስክሬኖች ላይ ኮቪድ-19 ተገኝቷል። ሁለቱም ግለሰቦች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነበሩ።
ለመሆኑ የሰዎች አስክሬን ተመርምሮ በኮቪድ-19 ተይዘው እንደነበረ ማወቁ ምን ያመላክታል? እነዚህ ሰዎች የሞቱት በኮሮናቫይረስ ነው ወይስ በተጓዳኝ ህመሞች? በሽታው በማኅበረሰቡ ውስጥ እየተሰራጨበት ስላለው ፍጥነትስ ምን ይነግረናል? ለእነዚህ ጥያቄዎች በስዊድን አገር ማላርጋለን ተብሎ በሚጠራው ዓለም አቀፍ የጤና ተቋም ውስጥ መምህርና የሕብረሰብ ጤና ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት በንቲ ገለታ ምላሽ አላቸው። እሳቸው እንደሚሉት፤ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ በቫይረሱ መያዛቸው የሚታወቅ ሰዎች መኖራቸው በሽታው ማኅበረሰቡ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራጨቱን ያሳያል። • በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለምን ተስፋፋ? • የኮሮናቫይረስ ውጤት መዘግየት ስጋት እየፈጠረ ነው “ባለፈው ሳምንት የተጠቀሰውን አሃዝ ብንወስድ ሕይወታቸው ካለፈ 27 ሰዎች መካከል አስራ አንዱ ከሞቱ በኋላ ቫይረሱ እንደነበረባቸው ታውቋል። ይህ ወደ 41 በመቶ አካባቢ ነው። ቀድሞ የሌሎች በሽታዎች መኖር ለቫይረሱ መባባስ ምክንያት ሊሆን ይችላል። የሞት ምክንያቱም በቫይረሱ ወይም ከዚህ ቀደም የነበረባቸው በሽታ ምክንያት ሊሆን ይችላል” ሲሉ ያስረዳሉ። አሁን ላይ በሕብረተሰቡ ውስጥ ያለው የበሽታ ቅኝት ደካማ መሆኑን ተመራማሪው ይናገራሉ። በአስከሬን ናሙና ምርመራ ኮቪድ-19 መገኘቱ ብዙ በሽታው እንዳለባቸው ያልታወቁ ሰዎች እንዳሉ እንደሚጠቁምም ያክላሉ። የጤና ባለሙያዎች ቤት ለቤት ተዘዋውረው የሙቀት ልኬት ማድረጋቸው ብቻውን በቂ እንዳልሆነና፤ ስለ በሽታው ምልክቶች ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ ሰጥቶ፤ ሰዎች ምልክቱን ሲያዩ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በአፋጣኝ እንዲሄዱ ማነሳሳት እንደሚያስፈልግም ይመክራሉ። “አሁን ባለው አካሄድ የበሽታውን ሥርጭት ማወቅና ትስስሩን ማግኘት አልተቻለም። የዓለም ጤና ድርጅትና ሌሎችም ከዚህ በፊት ለሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ሲጠቀሙበት የነበረው የማኅበረሰብ ጤና ቅኝት አሠራር ነው። እያንዳንዱ ሰው ዋና ዋና የበሽታውን ምልክቶች እንዲያውቅ መደረግ አለበት። ምልክቱን እንዳየ ለጤና ተቋም ያሳውቅና በጤና ባለሙያ ምርመራ ይደረግለታል።” የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ የበሽታውን ምልክት የማያሳዩ ነገር ግን ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች አሉ። ታድያ አንድ ሰው በሽታው ኖሮበት ምልክቱን ካላሳየ እንዴት ወደ ጤና ተቋም ያመራል? ስንል ለመምህር በንቲ ጥያቄ አቅርበን ነበር። • ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለኮሮናቫይረስ ያጋልጣል? • በኮቪድ-19 ምክንያት በአሜሪካ በኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ላይ የተባባሰው ጾታዊ ጥቃት እርሳቸው እንደሚያስረዱት፤ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። ምንም ሳይታወቅባቸው (ስፓንታንየስ ሪዞሉሽን የሚባለው) ሊድኑ ይችላሉ። ወደ 14 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ የበሽታውን ምልክት ቢያሳዩም ወደ ጤና ተቋም በሚያስኬድ ደረጃ በጠና አይታመሙም። የተቀሩት ስድስት በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ግን የሕክምና እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ከነዚህ መካከል ከበሽታው የሚያገግሙ፣ በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን የሚያጡም አሉ። “የበሽታውን ምልክት የማያሳይ ሰው ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው እንዳያስተላልፍ ለማድረግ መወሰድ ያለባቸው ጥንቅቃቄዎች አሉ። ማንኛውም ሰው በሽታው ኖረበትም አልኖረበትም እስካሁን ሲባሉ የነበሩ ጥንቃቄዎች መተግበር አለበት። ማለትም እጅ አዘውትሮ መታጠብ፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ ሲስሉም ሆነ ሲያስነጥሱ በክንድ አፍን መሸፈን መተግበር አለባቸው።” ከዚህ ቀደም ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 የተገኘባቸው አሉ። ከነዚህ መካከልም አዲስ አበባ ልደታ አካባቢ ይኖሩ የነበሩት አዛውንት ይጠቀሳሉ። አዛውንቷ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ተፈጽሞ፤ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሀዘን ተቀምጠው ሳለ ነበር ከአስክሬናቸው በተወሰደ ናሙና ኮቪድ-19 እንዳለባቸው የታወቀው። የአካባቢው ነዋሪዎች ለጥቂት ቀናት እንቅስቃሴ ገትተው እንደነበርም ይታወሳል። እንዲህ ያሉ ገጠመኞች፤ በሽታው እንዳለባቸው ሳይታወቅ በሚሞቱ ሰዎች ሳቢያ ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በአቅራቢያቸው የሚኖሩ ሰዎች ለወረርሽኙ ተጋላጭ አይሆኑም? የሚል ጥያቄ ያስከትላሉ። መምህሩም እነዚህ ግለሰቦች በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ለበሽታው ማጋለጣቸው እንደማይቀር ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ኮሮናቫይረስ ያለበት ሰው ሲገኝ፤ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሰዎች ከዛም ከእነርሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ግለሰቦችና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የነበሩ ሰዎች በግንባር ቀደምነት ሲመረመሩ ነበር። ተመራማሪው በንቲ እንደሚሉት፤ አሁን ላይ በሽታው በስፋት በማኅበረሰቡ ውስጥ ተሰራጭቷል። • በኮሮናቫይረስ ወቅት ጀርመኖችን በሙያዋ የምታግዘው ኢትዮጵያዊት • ከቀብር በኋላ በደረሰ የምርመራ ውጤት ሰበብ 53 ሰዎች በሰሜን ሸዋ ወደ ለይቶ ማቆያ ገቡ “የሚመረመረው ሰው በጨመረ ቁጥር በሽታው የሚገኝበትም ሰው እየጨመረ ነው። ማኅበረሰቡ ውስጥ በርካታ በበሽታው የተያዘ ሰው እንዳለና በተመረመረ ቁጥር የሚገኝ የማኅበረሰብ ክፍል እንዳለ ያሳያል። ከምንገምተውም በላይ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ሰው ቢመረመር ደግሞ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ይገኛል” ሲሉም ያስረዳሉ። አያይዘውም፤ በሽታውን አንዳች ነጥብ ላይ መግታት የሚቻልበት ተስፋ አለ? ወይስ መግታት የሚቻልበት ጊዜ አልፎ በሽታው ከቁጥጥር ወጥቷል? የሚለውን ጥያቄ መመለስ አዳጋች እንደሆነ ይናገራሉ። “በጣም ያስፈራኛል። ምክንያቱም አሁን ጫፉን [ፒክ] አላየንም” የሚሉት መምህሩ፤ ወደፊት የሚመጣውን መገመት አስቸጋሪ መሆኑን ይገልጻሉ። ሆኖም ግን የጤና ባለሙያዎች የሚያደርጉት ቅኝትና በሽታውን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ኃይል እንቅስቃሴ ብቻ በቂ አይደለም ይላሉ። ማኅበረሰቡ ስለ በሽታው ግንዛቤ ኖሮት ምልክቶችን ካየ እንዲያሳውቅ (ሰልፍ ሪፖርት የሚባለው) መደረግ እንዳለበት ያስረግጣሉ። “ሰው ሰልፍ ሪፓርት እንዲያደርግ ለማበረታታት በበሽታው የተያዙ ሰዎች ጥሩ እንክብካቤ እንደሚሰጣቸው ማሳየት ያስፈልጋል። በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ ሰዎች ክብራቸው ተጠብቆ አገልግሎት አንደሚሰጣቸው ሲታይም ሰዎች ሰልፍ ሪፖርት ለማድረግ ይደፋፈራሉ።”
news-48675263
https://www.bbc.com/amharic/news-48675263
ኢትዮጵያ ፡ የአዞ ቆዳና ሥጋ ለምን ገበያ ራቀው?
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ከምታገኝባቸው ነገሮች መካከል አንዱ የአዞ ሥጋና ቆዳ ነው። አሁን ላይ ግን ምርቱ ቢኖርም ለዓለም ገበያ ማቅረብ አልተቻለም ሲሉ የደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ለማ መሰለ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በደቡብ ክልል የባህል ቱሪዝም ቢሮ ሥር የሚተዳደረው የአዞ እርባታ ጣቢያው የተመሠረተው በ1976 ዓ.ም ነው። "ዋናው ዓላማው የናይል አዞ ዝርያን ማቆየት ነው" የሚሉት አቶ ለማ በሂደት ግን ዝርያውን ከማቆየት ባሻገር ቆዳውንና ሥጋውን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ታስቦ ዘመናዊ ቄራ ተዘጋጅቶ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን ይናገራሉ። • ካልጠፋ ዘመድ ከአዞ ጋር ፎቶ የተነሳችው አሜሪካዊት ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአዞ ቆዳንም ሆነ ሥጋውን ለገበያ ማቅረብ አልተቻለም ይላሉ። በዚህ ዓመትም ታጅለው የተዘጋጁ 1500 ቆዳዎች ቢኖሩም ገዥ እንደጠፋ ያስረዳሉ። ሥጋውም ቢሆን ገዥ በማጣቱ መልሶ ለአዞ ምግብነት ውሏል። የአዞ ቆዳ ለውጭ ገበያ በሚቀርብበትም ጊዜ ገቢው እምብዛም ባይሆን በዓመት ወደ 5 ሚሊየን ብር ገደማ ያስገኝ ነበር። ይህ ማለት ደግሞ ቢያንስ ለእርባታ ጣቢያው በዓመት ከመንግሥት ከሚበጀተው 8 ሚሊየን ብር ገደማ ከግማሽ በላዩን ራሱ ይሸፍን ነበር ማለት ነው። "የአዞ ቆዳ በሴንቲ ሜትር ነው የሚሸጠው፤ አንደኛ ደረጃ ቆዳ አንድ ሴንቲ ሜትር በአራት ዶላር ይሸጣል፤ በመሆኑም የአንድ አዞ ቆዳ አርባ ሴንቲ ሜትር ቢሆን 40 ዶላር ይሸጣል" ሲሉ የመሸጫ ዋጋውን ያስረዳሉ። ሥጋው ግን ከተሸጠ ብዙ በመቆየቱ ዋጋውን እንኳን በውል እንደማያስታውሱት ያስረዳሉ። በአሁኑ ሰዓት 3ሺህ የሚሆኑ አዞዎች በአርባ ምንጭ እርባታ ጣቢያው እንደሚገኙ የነገረን ደግሞ የጣቢያው ባለሙያ አቶ መሠረት ደምለው ነው። እነዚህ አዞዎች ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 29 ዓመት የሚደርስ ነው። ከእነዚህ መካከል ለእርድ የደረሱም ይገኙበታል። ብዙ ጊዜ ለእርድ የሚመረጡት ዕድሜያቸው ከ4 እስከ 8 ዓመት የሆናቸው ሲሆኑ ከዚያ ከፍ የሚሉት ደግሞ ለቱሪስት መስህብነት ያገለግላሉ። • ወንዶች አዞ ለመምሰል ቆዳቸውን የሚበሱባት ሃገር በአዞዎች ሥነ ሕይወት ከ120 እስከ 150 ዓመት ድረስ መኖር ቢችሉም በእርባታ ጣቢያው ውስጥ በዚህ የዕድሜ ክልል የሚገኙ አዞዎች ግን የሉም። ምክንያቱም እዚህ የእድሜ ደረጃ እስከሚደርሱ አይጠበቁም። አዞ ለእርድ እንዴት ይዘጋጃል? በጎችን ስንገዛ ወገባቸውን በእጃችን ጨበጥ ለቀቅ እያደርግን እንደምንለካው ሁሉ አዞዎችም ለእርድ መድረሳቸው የሚረጋገጠው ደረታቸውን በመለካት ነው። በዚህም መሠረት የደረት ስፋታቸው ከ25-50 ሴንቲ ሜትር የደረሱ አዞዎች ለገበያ ደርሰዋል ይባላል። አዞዎች ለገበያ መድረሳቸው የሚረጋገጠው በደረት ስፋታቸው ብቻም ሳይሆን ዕድሜያቸውም ከግምት ውስጥ ይገባል። ለእርድ የተመረጠው አዞ አበላለቱ በተለይ ከአሳ ጋር የመመሳሰል ባህሪ አለው። በመጀመሪያ ለእርድ የተዘጋጀው አዞ ካለበት ቦታ ላይ እያለ ይገደላል። አዞ አደገኛ በመሆኑ ዝም ተብሎ አይገደልም ታዲያ። አሳን መብላት በብልሃት እንደሚባለው ለእርሱም ብልሃት አለው። ጭንቅላቱ መሃል (አናቱ) ላይ ለእርሱ መግደያ ተብሎ በተዘጋጀ ብረት ይወጋል። ምክንያቱም በዚህ መልኩ ካልተወጋና ካልሞተ በስተቀር መያዝም ሆነ ቆዳውን መግፈፍ አይቻልም። አዞ የዱር እንስሳ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አደጋ እንዳያደርስ በተለይ በመያዝ ሂደቱ ላይ የተለያዩ ጥንቃቄዎች ይደረጋሉ። ይሁን እንጂ የሚያርዷቸውም እዚያው ሲንከባከቧቸው የሚውሉ ባለሙያዎች በመሆናቸው እምብዛም ጉዳት አያደርሱም። መሞቱ ከተረጋገጠ በኋላ እዚያው እርባታ ጣቢያው ወደሚገኝ የአዞዎች ቄራ ይጓዛል። እዚያም ደሙ እንዲንጠፈጠፍ ከተደረገ በኋላ ታርዶ ቆዳው ይገፈፋል። ቢቢሲ፡ የአዞ ሥጋ ብልት አለው እንዴ? አቶ መሠረት፡ ዝም ብሎ በክፍል በክፍል ይወጣል...የሚፈለገው የትኛው አካባቢ ነው በሚለው ላይ ተመስርቶ ሥጋው እየተለየ ይወጣል። አንዳንድ ሥጋ ፈላጊዎች ከቄራ ሠራተኞች ጋር ተነጋግረው የሚፈልጉትን ይወስዳሉ። ቢቢሲ፡ በአብዛኛው ግን የሚፈለገው የትኛውን የሥጋ ክፍል ነው? አቶ መሠረት፡ ሳቅ …ፍርንባው፣ ይሄ ከደረቱ ክፍል ያለው አለ አይደል…እርሱን ብዙ ሰው ይወደዋል። ቢቢሲ፡ የአዞ ጥሬ ሥጋ ይበላል እንዴ? እንዴት ነው ቁርጡ? አቶ መሠረት፡ በባህላችን የእኛ ሰው ጥሬውንብዙም አይመገብም ፤ነገር ግን በጥብስ መልክ የሚመገቡ አሉ። ቢቢሲ ፡ ኢትዮጵያዊያን? አቶ መሠረት፡ አዎ! ቢቢሲ፡ እንዲያው ግን ከቀዩ አሊያም ከነጩ ይደረግልኝ ብሎ ማማረጥ ይቻላል? አቶ መሠረት፡ ሳቅ… እንደውም ሥጋው ወደ ነጭ ያደላ ነው፤ ከአሳ ሥጋ ብዙ አይለይም፤ ግን ያው ሥጋ ተመጋቢ ስለሆነ ነጩ ይበዛል.. ስብ ነው። ቢሆንም ግን ከጀርባው አካባቢ ቀይ ሥጋም አለው። በአዞ እርባታ ጣቢያው የተለያዩ የውጭ አገር ዜጎች ጎራ ብለው ሥጋቸውን አስመዝነው ይዘው ይሄዳሉ እንጂ የአዞ ሥጋ ተጠብሶ የሚበላበት ምግብ ቤት የለም ይላሉ አቶ መሠረት። ገበያው ደርቶ አዞ የታረደ ከሆነ በሚመች መልኩ ሂደቱን ጨርሶ ማቀዝቀዣ በተገጠመላት መኪና ተደርጎ ይላካል። ገበያ ከሌለው ግን ቆዳው ተገፎ ሥጋውን መልሰው ለአዞዎቹ ይመግቧቸዋል። እርሳቸው በሥራ ላይ በቆዩበት ሁለት ዓመታት ውስጥ ወደ ውጭ አገር ከሚላከው የአዞ ሥጋ ይልቅ በተዘዋዋሪ ሰዎች ቦታው ድረስ በማቅናት ገዝተው የሚሄዱት የተሻለ እንደሆነና በእነዚህ ዓመታት ውስጥ የአዞ ሥጋ ወደ ውጭ እንዳልተላከ ይናገራሉ። በቂ የሥጋ ማቀነባበሪያ መሳሪያዎች ባለመኖራቸው ምክንያት ደረጃውን ጠብቆ መስራት ስላልተቻለ ተቋርጧል። • ፊቼ ጨምበላላ፦ የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመት የአዞ ቆዳ ከደረቱ ክፍል በኩል በጥንቃቄ ተገፎ በጨው ታጅሎ እስከ ብዙ ጊዜ ማቆየት ይቻላል። ገበያ ካልተገኘ እስከ ሁለት ወርና ሦስት ወርም ሊቆይ ይችላል። ገበያ ካልተገኘ ቆዳ ልማት ኢንስቲቲዩት ይገባል። አንድ የአዞ ቆዳ ከ2500-3000 ብር (104 የአሜሪካ ዶላር) ድረስ ይሸጣል፤ በዚህ ዓመትም 1500 የአዞ ቆዳዎችን ደረጃቸውን ለይተው ለኢትዮጵያ ቆዳ ልማት ኢንስቲቲዩት መላካቸውን ባለሙያው ገልፀዋል። ለውጭ ገበያ የሚቀርበው የቆዳ ስፋትም ከ20 ሴንቲ ሜትር እስከ 50 ሴንቲ ሜትር ቢሆንም ጥራቱ በስፋቱ ብቻ አይወሰንም። አንዳንዴ 50 ሴንቲ ሜትር ስፋት ኖሮት በጥራቱ ሁለተኛ ደረጃ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱ ደግሞ አዞው ከዚህ ቀደም ያጋጠመው በሽታ ካለ እና ቆዳው በሚገፈፍበት ወቅት እንከን ካለው የአዞ ቆዳው ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚያሳድር ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ የአዞ ሥጋንና ቆዳን ወደ ውጭ በመላክ የምታገኘው የውጪ ምንዛሬ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን የሚናገሩት ባለሙያው ከዚህ ቀደም ወደ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና አውስትራሊያ በአብዛኛው የአዞ ሥጋ ይላክ እንደነበር ያስታውሳሉ። የአዞ ቆዳና ሥጋ ገበያ ለምን አልደራም? ከዓመታት በፊት ያጋጠመው የዓለም ኢኮኖሚ መውደቅ ላለፉት አራትና አምስት ዓመታት የአዞ ገበያው ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንዳሳረ አቶ ለማ ያስረዳሉ። በመሆኑም አዞዎችን ከጫሞና ከአባያ ሐይቅ በማምጣትና እንቁላሎችን በማስፈልፈል የአዞ እርባታውን ሂደት ማስቀጠል አልተቻለም። በዚህም ሳቢያ ላለፉት አምስት ዓመታት የአዞ ቆዳ መሸጥ አለመቻሉን ይናገራሉ። "አብዛኛውን ጊዜ የሚገዙት የውጭ ድርጅቶች ናቸው" የሚሉት ኃላፊው የውጭ ገበያውን በማጥናት የዓለም ገበያ ፍላጎትን ማወቅ አለመቻላቸውንም እንደ ተጨማሪ ምክንያት ያስቀምጣሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አቅርቦታቸው ውስን በመሆኑ 2 ሺህ የአዞ ቆዳዎችን ብቻ ለመግዛት የሚመጣ ኩባንያ አለመኖሩንም ያነሳሉ። በመሆኑም በጥቃቅን ደረጃ ምርቱን የወሰዱ ድርጅቶች ቢኖሩም በብዛት ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ ግን አልተቻለም። ኃላፊው እንደሚሉት በአባያና ጫሞ ሐይቅ ብቻ የሚገኙትን የናይል አዞ ዝርያዎች ጠብቆ ለማቆየት ሲባል ለአዞ እርባታ ጣቢያው ብዙ በጀት ይመደባል። በመሆኑም ለቀለብ ብቻ በዓመት አንድ ሚሊዮን ብር ይወጣል። ከሌሎች ወጪዎች ጋር ሲደመር በዓመት እስከ 8 ሚሊየን ብር ገደማ በጀት ይመደባል። ይሁን እንጂ ይህንን የሚያካክስ ገንዘብ ከቆዳና ከሥጋ ምርቱ ባይገኝም ከቱሪዝም የተወሰነ ገቢ ይገኛል። ቢሆንም ግን ከቱሪዝም በዓመት የሚገኘው ከ1.5 እስከ 2 ሚሊዮን ብር ከወጪው ጋር የሚመጣጠን አለመሆኑን ኃላፊው አክለዋል። "የመንግሥት ዋናው ትኩረት ዝርያውን መጠበቅ ላይ ቢሆንም ንግዱን ግን ሌላ የግል ድርጅት እንዲሰራ ቢመቻቻች ውጤቱ አመርቂ ሊሆን ይችላል" ሲሉ አቶ ለማ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። ይህንንም በተለመለከተ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን አዲስ ዕቅድ እያዘጋጁ እንደሆነም ገልፀውልናል።
news-53081364
https://www.bbc.com/amharic/news-53081364
የነዳጅ ዘመን አብቅቶ የባትሪ ዘመን እየመጣ ይሆን?
ኢሎን መስክ ቢሊየነር ነው። ሁሌም እንደተሳካለት።
አዳዲስ ሃሳቦችን የሚያመነጨው ኢሎን መስክ በቅርቡ ወደ ህዋ ሳይንቲስቶችን ይዞ የመጠቀ የመንኮራኮር ታክሲ ሰርቶ ተሳካለት። ከዚያ በፊት እጅግ ዝነኞቹን የቴስላ መኪኖች ፈጥሮ ተሳክቶለታል። ከዚያ በፊት ፔይፓል የክፍያ ዘዴን ፈጥሮ፣ አትርፎ ሽጦታል። የፈጠራት የህዋ ታክሲ "ሰፔስ ኤክስ" ትባላለች። ማርስ አድርሳ ትመልሳለች። ጥሩ ብር ያለው መሳፈር ይችላል። ናሳ ራሱ የራሱን መንኩራኮሮች ጡረታ አስወጥቶ ሲያበቃ ከዚህ ሰውዬ ታክሲ መኮናተር ጀምሯል። ስፔስ ኤክስ የሰማይ ታክሲ ሲሆን ቴስላ ደግሞ እጅግ የረቀቀ የምድር ታክሲ ነው። በኤሌክትሪክ የሚሰራ፣ ራሱን በራሱ የሚሾፍር የነገ ዘመን ታክሲ። ይሄ ሰውዬ በ2012 ተስላ መኪናንም ሆነ ሰፔስ ኤክስን የሚያስንቅ የሳይንስ ልቦለድ የሚመስል ነገር ደግሞ አመጣ። ነገሩ የተጠነሰሰው የሰው ልጅ በትራንስፖርት ረገድ እንደ ግመል እየተንቀረፈፈ ለምን ይጓዛል ከሚል ቁጭት ነው። መኪናም፣ አውሮፕላንም ባቡርም ቀርፋፋ ናቸው ይላል ቢሊየነሩ ኢለን መስክ። እነ መኪና፣ እነ ባቡር እንዲህ የሚያንቀረፍፋቸው ሁለት ነገር ነው። አንዱ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚመጣ የአየር ግፊት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሰበቃ ነው። እነዚህን መቆጣጠር ቢቻልስ ብሎ አሰበ፣ ኢሎን። ሀይፐርሉፕ (hyperloop) የሚባል ነገር ፈጠረ። ሀይፐርሉፕ ልክ ይሄ ከአገር አገር በሚዘረጋ የጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦ ውስጥ እጅግ በፈጠነ ጉልበት መጓዝ ማለት ነው፤ በደምሳሳው። ለምሳሌ አዲስ አበባ አንድ ክፍለ ከተማ የሚሰራ ሰው ለሻይ ሰዓት መቀሌ ቆንጆ ቡና ጠጥቶ ወደ ቢሮው መመለስ ይችላል፣ በሀይፐርሉፕ። በሰዓት 700 ማይል ይምዘገዘጋል። የቀናት ጉዞ የደቂቃዎች ጉዳይ ይሆናል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? የማይመስል ነገር ነው? ሁሉም አሁን እውን የሆነ ቴክኖሎጂ ትናንት የማይመስል ነገር ነበር፡፡ እስኪሆን ድረስ ሁሉም ፈጠራ እብደት የሚመስል ነገር አለው። ሀይፐርሉፕም እንደዚያው ነው። ወደ ህዋ የተደረገው የስፔስኤክስ ጉዞ የፈለገ ቢሆን እንዴት በዚህ ፍጥነት መምዘግዘግ ይቻላል? ምክንያቱም መግነጢሳዊ ኃይል የትራንስፖርት ዘዴን ስለሚያዘምነው ነው። ተንሳፋፊ የመግነጢሳዊ ኃይል (Magnetic Levitation) ቴትራሳይክሊን ክኒን የመሰለውን የባቡር መሳፈሪያ ፉርጎ ከሚጓዝበት ሀዲድ አንሳፎ አየር ላይ ያበረዋል። ስለዚህ ሰበቃ አይፈጠርም። ሰበቃ ከሌለ ደግሞ ፍጥነት አለ። ይህ እንደ ንፋስ ውልብ ብሎ መጓዝ ቅዠት ከመሰለዎ ተሳስተዋል። በፈረንሳይም በእንግሊዝም ተግባር ላይ ሊውል በሙከራ፣ በፍተሻና በምርምር ላይ ነው። ስለ ሀይፐርሉፕ ተምዘግዛጊ ባቡር ለጊዜው እዚህ ላይ ገታ እናድርግ። ይሄ ቢሊየነርና የቴክኖሎጂ ፈጣሪ ኢሎን መስክ ተአምር ይሰራል፣ ዓለምንም ይገለባብጣታል የተባለው ከላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች አይደለም። ባትሪ ላይ እየፈጠረ ያለው ነገር ነው አሁን መነጋገሪያው። የኢሎን መስክ ባትሪ፤ የዓለም ዝሆኑ ባትሪ የኢሎን መስክ ቴክኖሎጂያዊ አብዮት ያመጣል የተባለለት ይህ የባትሪ ፈጠራ ምን ይሆን? የሊትየም ባትሪዎች መፈጠራቸው ነው አዲሱ ነገር። እጅግ ቀላል ክብደት የሚኖራቸው የሊትየም ባትሪዎች እውን ሲሆኑ እጅግ ጠፍጣፋና በጣም ቀጭን ስልኮች ይኖሩናል። በስልኮቻችን ስለ ባትሪ ሳንጨነቅ ለ40ኛ ዓመት ልደታችን ቻርጅ ያደረግነውን ስልክ በ70ኛው ዓመት ልደታችን "ባትሪዬ እያለቀ ነው እስኪ ቻርጀር አቀብሉኝ ልጆች!" ልንል እንችላለን። ለምሳሌ የኤሌክትሪክ መኪና ሊመጣ ነው ሲባል ብዙ ሰዎች 'የማይመስለውን' ሲሉ ተጠራጥረው ነበር። አሁን የኤሌክትሪክ መኪናዎች በአውሮፓ ጎዳና በየመንገዱ በተተከሉ ስልክ እንጨቶች ባትሪ ሲጠጡ ነው የሚያድሩት። በየጎዳናው የሚታየው ይኸው ነው። መንግሥታት ዜጎቻቸው የነዳጅ መኪናን እርግፍ አድርገው ትተው ወደ ባትሪ መኪና ጠቅልለው እንዲገቡላቸው ማበረታቻ ጭምር እየሰጡ ነው። በዚህ ረገድ ፈረንሳይ ዘምታበታለች። አሁን የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለመግዛት ስናስብ አንድ ነገር ያሳስበናል። ወይም ሁለት ነገር፤ ዋጋና ባትሪ ቻርጀር። መኪናዬን እየነዳሁት ባትሪ ቢጠፋስ? ተቀያሪ ባትሪ ትይዛለህ… ተቀያሪ ባትሪው ቢያልቅስ? የብዙዎች ጭንቀት ይህ ነው። የባትሪን ነገር በስልካችን ስለምናውቀው ቻርጅ ማድረግ የሚባል ነገር ሐሳቡ ራሱ ሳያስፈራን አልቀረም። ያም ሆኖ ዓለማችን ከነዳጅ ወደ ባትሪ ዘመን እየተሸጋገረች ነው። የነገሩ ጠንሳሽ ኢለን መስክም ሆነ ቴስላ የአክሲዮን ገበያው ደርቶላቸዋል። ባለፈው ዓመት ቴስላ እጅግ ስኬታማ የሆነውን የቶዮታ መኪና አምራች በአክሲዮን ገበያ በልጦት ነበር። ምንም እንኳ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ቶዮታ ከቴስላ በ30 እጥፍ መኪና የሸጠ ቢሆንም። አሁን ቴስላ ኩባንያ ስኬታማ የመሆን ምስጢሩ ይሄ ኢለን መስክ የሚባል ቢሊየነርና የቴክኖሎጂ ፈጣሪ እርሱ የነካው ነገር ሁሉ ስኬታማ እንደሚሆን እየታወቀ በመምጣቱ ሊሆን ይችላል። እሱ ደግሞ መጪው ዘመን የባትሪ ዘመን ነው ብሎ አውጇል። እሱ ካለ ነገሩ ትክክል ሳይሆን አይቀርም። የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ሲደረጉ የዓለም ዝሆን ባትሪ ምንድነው? ባትሪን ስናስብ ስልካችን ወይም መኪናዎቻችን ናቸው ቀድመው የሚመጡብን። ባትሪዎችን የከሰል ኃይልን እያጠፉት እንደሆነ እምብዛምም አላስተዋልን ይሆናል። ምናልባት ወደፊት ከሰልም ሆነ ትልልቅ የወንዝ ግድቦችን ማቆም ፋሽኑ ያለፈበት ነገር ሊሆን ይችለል። በመጪው ዘመን እጅግ ግዙፍ ባትሪዎች አንድ ከተማን በኤሌክትሪክ ሊያንቦገቡጓት ይችላሉ። ምናልባት ወደ አዲስ የኃይል መመንደግ ዘመን እየገባን ይሆናል ይላሉ ፕሮፌሰር ፖል ሺሪንግ። ፕ/ር ፖል በለንደን ዩነቪርስቲ ኮሌጅ የባትሪ ቴክኖሎጂ ተመራማሪ ናቸው። ፕሮፌሰር ፖል የኤሌክትሪክ መኪናዎች በመጪዎቹ 10 ዓመታት የአውሮፓን የባትሪ ፍላጎት በመቶ እጥፍ ያሳድጉታል ብለው ይጠብቃሉ። ይህ የባትሪ ፍላጎት የሚቆየው ታዲያ ባትሪዎች ዋጋቸው ሲረክስ፣ ዕድሜያቸው ሲረዝም እና የኃይል ፍላጎትን በአስተማማኝ ሲመልሱ ነው። ይህን ሁሉ ማሟላት ለአንድ ቴክኖሎጂ አይከብድም? ዋጋ ረክሶ፣ ፍጥነትና ጉልበት ጨምሮ፣ ዕድሜ ረዝሞ፣ ፍላጎት አሟልቶም እንዴት ይሆናል? "ሐሳብ አይግባዎ" ይላል ኢሎን መስክ። በእርግጠኝነት የባትሪ ዘመን እየመጣ ነው። የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ቻርጅ እየተደረጉ የማይሞት ባትሪ ሊመረት ይችላል? ባለፈው ሳምንት አንድ የቻይና ኩባንያ ጉድ ያስባለ ምርት ይዞ ወጥቷል። አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ አንድ ሚሊዮን ማይል መጓዝ የሚያስችል ባትሪን አምርቷል። በምህጻር ስሙ ካትል (CATL) የሚባለው ይህ የቻይና ኩባንያ ቴስላን ጨምሮ ለብዙ ኢንዱስትሪዎችና አምራቾች ባትሪ አቅራቢ ነው። አንድ መኪና 2 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር እንዲነዳ የሚያስችል ባትሪን ነው አመረትኩ የሚለው። ይህም ማለት አንድ መኪና ለ16 ዓመት ቻርጅ ሳይደረግ ሊነዳ ይችላል እንደማለት ነው። አሁን ባለው እውነታ ብዙዎቹ የመኪና ባትሪዎች ዋስትና የሚሰጡት ከ60 ሺህ እስከ 160 ሺህ ማይል አገልግሎት እንደሚሰጡ ቃል በመግባት ነው። ይህም ከ3 እስከ 8 ዓመት የመኪና ኤሌክትሪክ ባትሪ ዋስትና ማለት ነው። ይህ አዲስ ዝሆኔ ባትሪ ግን ነገሩን ሁሉ ወደ ሌላ ምዕራፍ አሳድጎታል። ባትሪውን ያመረተው ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ የዚህ ባትሪ ዋጋ ከሌሎች ከማናቸውም ባትሪዎች በ10 እጥፍ ሊበልጥ ይችላል ሲሉ ውድ ስለመሆኑ አረጋግጠዋል። ውድስ ቢሆን ማን ይፈራል? ዋናው አስተማማኝ አገልግሎቱ ነው። እርግጥ ነው ለኤሌክትሪክ መኪና አምራቾች አስር ጊዜ መቀያየር የማያስፈልገው፣ 10 ጊዜ ቻርጅ መደረግ የማያስፈልገው፣ የሕይወት ዘመኑ እንደ ማቱሳላ የሆነ ባትሪ ሲመረትላቸው ገበያቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉ አይቀርም። ሆኖም ይህ መልካም ዜና ለኤሌክትሪክ መኪና ብቻ ነው የሚጠቅመው ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል። ይህ ዜና ባትሪን ለሚፈልጉ ምርቶች ሁሉ የምሥራች ነው። ለምሳሌ ለንፋስ ኃይል ተርባይን፣ ወይም ለፀሐይ ኃይል ማጠራቀምያ ፓናሎች እጅግ አስደናቂ ዜና ነው። አንድ ባትሪ የዕድሜ ዘመኑ በዚህን ያህል ረዘመ ማለት ንፋስ ባይኖርም ተርባይኑ ኃይሉን በባትሪ ያጠራቅማል። የፀሐይ ኃይል ያጠራቀመው ፓኔል ፀሐይ ባትወጣም ጉልበቱን በባትሪው ያጠራቅማል። ባትሪው ደግሞ ሙሉኝ ሳይል አገልግሎት ይሰጣል ማለት ነው። ግዙፎቹን ነገሮች ትተን ስለ ስልካችንና ባትሪዎቹ ብናወራ ራሱ ከዚህ ወዲያ ስልካችን ቻርጅ መደረግ ላያሻው ይችል ይሆናል። አንድ የማይንቀሳቀስ ግዙፍ ባትሪ ቤታችን በማስቀመጥ ከፀሐይም ይሁን ከኤሌክትሪክ ኃይልን እንዲሰበስብ ካደረግነው በኋላ ከዚያ ወዲያ ስለ መብራት መጥፋት ጭራሽ ላናስብ እንችላለን ማለት ነው። ቻይና ውስጥ ያለው አዲሱ የቴስላ ፋብሪካ ርካሹ አማራጭ? በቀጣይ ዘመን የሚመረቱ ባትሪዎች ርካሽ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም። ለምሳሌ ለኤሌክትሪክ መኪና የሚሆን የባትሪ ዋጋ ውድድር በመኖሩ አሁን ከ100 ዶላር በታች ገብቷል። ርካሽ ባትሪዎች ደግሞ ብዙ ነገሮችን ያቀላሉ። ደንበኞች ዝሆኔ ባትሪዎችን መኪናዎቻቸው ላይ ለመግጠም አያቅማሙም። ሁለት ጥቅምን ያስገኛሉና። አንዱ ጥቅም ዝሆኔ ባትሪዎች አንድ ጊዜ ቻርጅ ከተደረጉ ረዥም ርቀት ስለሚወስዱን ነው። ለምሳሌ ከዚህ በኋላ አንድ የአሌክትሪክ መኪና አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ በትንሹ 800 ኪሎ ሜትር ሊነዳ ይችላል። ሁለተኛው ደግሞ ዝሆኔ ባትሪዎች ጥቂት ደቂቃ ቻርጅ ቢደረጉ በርካታ ጉልበት መያዝ ስለሚችሉ ነው። ለምሳሌ 10 ደቂቃ ቻርጅ የተደረገ የኤሌክትሪክ መኪና 300 ማይል ሊጓዝ ይችላል። ይሄ ማለት ማደያ ገብተው ነዳጅ ቀድተው የሚወጡበት ሰዓት እንደማለት ነው። በቅርብ ቀን የቴስላ መኪናዎች ፈጣሪ ኢለን መስክ ኤስ እና ኤክስ ለሚባሉት ወደ እኛ አገር ገና ላልገቡት መኪናዎች ይህን አዲስ ባትሪ ገጥሞ አዲስ የብስራት ዜና ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል። የባትሪ ቴክኖሎጂው በአየር ንብረት ለውጥ ላይም አውንታዊ ሚና ይኖረዋል እነዚህ ባትሪዎች የት ይመረታሉ ? እነዚህ እጅግ አጓጊ፣ ዋጋና ጉልበት ቆጣቢ ባትሪዎች በየት ሊመረቱ ይሆን? የዚህ የቴክኖሎጂ ጥንቅር ዘጋቢ በለንደን እንደሚሆን ይገምታል። ሰሞኑን ኢሎን መስክ በእንግሊዝ ሉተን አየር መንገድ የግል ጄቱ አርፋ ነበር። ምናልባት የመስክ ትልቁ የዝሆኔ ባትሪ ፋብሪካ በዚህች ትንሽዬ ከተማ ውስጥ ሊሆን እንደሚችል ተጠርጥሯል። ሌላኛው እነዚህን ባትሪዎች አምራች ፋብሪካ በሂውስተን ቴክሳስ ሊሆን ይችላል የሚከፈተው። እነዚህ ጊጋ ፋብሪካዎች የሚል ስም የተሰጣቸው ያለምክንያት አይደለም። በቢሊዮን ዋት ጉልበት መቋጠር የሚችሉ ባትሪዎችን ስለሚያመርቱ ነው። ጥሬ እቃዎች ከቻይናው ካትል ኩባንያ እንደሚመጡ ይጠበቃል። ከኮባልት ነጻ የሆኑ ባትሪዎችን ለማምረት ዘዴው ተገኝቷል። ኮባልት አንደኛ ውድ ማዕድን ነው። ሁለተኛ በዋናነት የሚመረተው ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ነው። የሚመረተው ደግሞ የልጆችን ጉልበት በመበዝበዝ ጭምር ነው። በዚህ የባትሪ ምርት ዋናው ማዕድን ሊትየም ነው የሚሆነው። ያንን ደግሞ ከደቡብ አሜሪካ በርካሽ ለማውጣት መንገዱ ተይዟል። አዲሱ ባትሪ ሕይወታችንን በምን መንገድ ይቀይራል? ይህንን ጽሑፍ ስጀምር ከኢሎን መስክ ፈጠራዎች ሁሉ ይህ የባትሪ ፈጠራ ዓለምን ይቀይራል ብያችሁ ነበር። ይህ እምነቴ አሁንም አልተቀየረም። የማቱሳላን እድሜ የሚይዙ ባትሪዎች ሲፈጠሩ ኃይል የምናገኝበት መንገድ ሙሉ በሙሉ ይቀየራል። ከዚያ በኋላ ማንም ሰው ከቤንዚንና ከናፍጣ መኪና ጋር አይንደፋደፍም። ይህን የምናደርገው ባትሪ በሚፈጥረው ምቾት ነው። የኤሌክትሪክ መኪናዎች ጉልበት ለመቋጠር ምቹ ከሆኑ፣ በዋጋ ርካሽ ከሆኑ ማን ወደ ናፍጣ ይሄዳል? ሌላም ትልቅ ምክንያት አለን፤ ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ፊታችንን ለማዞር… የአየር ንብረት ለውጥ። የካርበን ልቀትን በአያሌው ለመቀነስ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ተመራጭ መሆናቸው እሙን ነው። በአጭር ሰዓት የሚሞሉ ባትሪዎች መፈጠራቸው ደግሞ የኃይል ቁጠባን በእጥፍ ይጨምራል። ለዚህም ነው ነገ የባትሪ ዘመን ነው የምንለው።
news-47798992
https://www.bbc.com/amharic/news-47798992
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት መግለጫ ምን ይላል?
በጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ የባለአደራ ምክርቤት ባሳለፍነው ቅዳሜ መጋቢት 21/2011 ዓ.ም ለጋዜጠኞች ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መከልከሉ ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎ የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ክልከላው የተደረገው የፀጥታ ስጋት በመኖሩ ለደህንነት ሲባል እንደሆነ አስታውቋል።
• "በሰላማዊ ትግል እስከመጨረሻው በፅናት እንታገላለን" እስክንድር ነጋ በመሆኑም ከእስክንድር ነጋ ጋር በመነጋጋር በሚፈልገው ቦታና ጊዜ መስጠት እንደሚችል በገለፀው መሰረት ዛሬ መጋቢት 25/2011 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል በሚል አራት ኪሎ በሚገኘው የእስክንድር ነጋ ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። የምክርቤቱ አመራር አባላትም ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት 'የከፋፍለህ ግዛ' ዓላማ ባነገቡ አምባገነኖች መዳፍ ወድቃ ብዙ ፈተናዎችን እንዳለፈች የሚያነሳው መግለጫው ለዚህ ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ የሚያፋጁ የልዩ ጥቅም ፈሊጥ አንደኛው ወጥመድ እንደሆነም ተጠቅሷል። በዚህም የገዥ ፓርቲው አካል የሆነው ኦዴፓ አንዱ መሆኑ በእጅጉ እንደሚያሳስበው የገለፀው ምክር ቤቱ "ማንኛውም ሂደት ፍፁም ሊሆን ስለማይችል በሂሳዊ ድጋፍ እየሞረዱና እያስተካከሉ መሄዱ የግድ ነው" ሲል ያክላል። ምንም እንኳን የሀገሪቷ አበይት የትኩረት አቅጣጫ የምርጫ ጉዳይ ቢሆንም የአዲስ አበባን ጉዳይ በጎንዮሽ ለማንሳት መገደዳቸውን ገልፀዋል። • ''አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት'' ከንቲባ ታከለ ኡማ በዲሞክራሲ መንገድ የተመረጠ አስተዳደር አለመኖር ዋናው ጥያቄ መሆኑን የሚያነሳው ምክርቤቱ ይህም በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ ክስተት ነው ብለዋል። "በሌሎች የሃገሪቷ ክልሎችና ከተሞች ባልታየ መልኩ የነዋሪዎቿ ጥቅምም እየተገፋ ይገኛል" ሲል መግለጫው አትቷል። በቦሌ ክፍለ ከተማ የታደሉት በሺዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ መታወቂያዎች፣ ከተማዋ ወኪሎች ባልመረጠችበት ሁኔታ ከኦሮሚያ ጋር ያለው የአስተዳደር ወሰን ድርድር እንዲደረግ መወሰኑ፣ የከተማዋን የብሔር ስብጥር ለመቀየር ዒላማ ያደረገው መንግስታዊ ሰፈራ እቅድ እና ኦዴፓ ስለ አዲስ አበባ በተደጋጋሚ ያወጣቸው መግለጫዎችን በምሳሌነት ጠቅሰዋል። እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ የሚቻለው በሰላማዊ መሆኑን እንደተገነዘበ የሚገልፀው ምክር ቤቱ "ከመሰረታዊ መርህ ፍንክች እንደማይል በአደባባይ ቃል ገብቷል፤ ይህንን ቃልኪዳን ሰምቶና አይቶ እንዳልሰማና እንዳላየ በመሆን በህዝብ በተወከለው ምክርቤታችን ሰላማዊ አካሄድና ህጋዊነት ላይ ከባለስልጣን የሚነሱ ጥያቄዎች ፈፅሞ አግባብነት የላቸውም" ሲልም አስታውቋል። እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎችም መልስ ላለመስጠት ሰበብ ፍለጋ ነው የሚል ጥርጣሬ እንዳሳደረባቸውም ገልፀዋል። • ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና ሚካኤል መላክ እንዲለቀቁ አምነስቲ ጠየቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በአንድ መድረክ ላይ ግልጽ ጦርነት ውስጥ እንገባለን ብለው ስለሰጡት አስተያየት የተጠየቀው እስክንድር መልስ ሲሰጥ "እንቅስቃሴያችን ሰላማዊና ሕጋዊ እንዲሆን ውክልና የሰጠን ሕዝብ ቃልኪዳን አስገብቶናል። ጦርነት ቢከፈትብን እንኳን ምላሻችን ሰላማዊ ነው። የሃሳብ ጦርነት ግን ልንፋለም እንችላለን" ብሏል። "ባልደራስ የተሰባሰበው በአስር ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ውክልና ስላለን ሞራላዊና ፖለቲካዊ ሕጋዊነት አለን፤ የከተማው ምክር ቤት ከንቲባውን ጨምሮ ይህ የለውም" ሲልም ጨምሮ ተናግሯል። በመጨረሻም በአዲስ አበባባና በኦሮሚያ መካከል ሊደረግ የታሰበ የአስተዳደር ወሰን ድርድር በሁለቱም ክልል በህዝብ የተመረጡ መስተዳድሮች እስኪሰየሙ ድረስ እንዲቆይ፣ የከተሞች የብሔር ስብጥር ለመለወጥ ሲባል የተጀመረው የሰፈራ መርሃ ግብር በህዝብ የተመረጡ መስተዳድሮች እስከሚሰየሙ እንዲቆም የሚሉ ሁለት ጥያቄዎችን ለመንግስት አቅርበዋል። እነዚህን ጥያቄዎችም ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፣ ለኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ፕሬዚደንት ለማ መገርሳ፣ ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ማድረሳቸውም በመግለጫው ተጠቅሷል። የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት መጋቢት 1/2011 ዓ.ም ኢትዮጵያዊነትን፣ አንድነትን፣ እኩልነትን፣ ወንድማማችነትን፣ ሰላማዊነትን የእንቅስቃሴው መሰረት አድርጎ በባልደራስ አዳራሽ በተስብሳቢው ድምፅ እንደተቋቋመ ምክርቤቱ አስታውሷል።
news-54588934
https://www.bbc.com/amharic/news-54588934
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የቀጠናው ኃያልነት ጉዞ
የባለፈው አመት ለበርካታ አገራት ፈታኝ ቢሆንም ለትንሿ ነገር ግን ሃብታሟ አረብ ኤምሬትስ ኃያልነቷን እያስመሰከረችበት ያለፈችበት አመት ሆኗል።
የገልፍ አገሯ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ወደ ማርስ መንኮራኩሯን አምጥቃለች፤ ከእስራኤል ጋር ታሪካዊ የሚባል ሰላማዊ ስምምነትን ፈፅማለች፤ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝንም በመግታት ምስጋና ከተቸራቸውም መካከል አንዷ ሆናለች። ከዚያም አልፎ ፋብሪካዎቿ ያመረቱትን የኮሮናቫይረስ የህክምና መከላከያ ቁሳቁሶችን በበላይነት ስታስተዳደራት ለነበረው የዩናይትድ ኪንግደምም ልካለች። በሊቢያ፣ የመንና ሶማሊያ ላይ ያላትን የበላይነቷንን ለማስመስከርም ከቱርክም ጋር ፉክክር ውስጥ ገብታለች። አምሳኛ አመት የነፃነት በዓሏን ከወራት በኋላ ልታከብር በዝግጅት ያለችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በአለም አቀፉ ላይ ኃያልነቷን ለማስፈን እያደረገች ያለችው ምንድን ነው? ማን ነውስ እየመራው ያለው? የቢቢሲው ዘጋቢ ፍራንክ ጋረድነር እንዲህ ቃኝቶታል ወቅቱ በጎሮጎሳውያኑ 1999 ነው። የኮሶቮ ጦርነትም ለአንድ አመት ያህል የተጧጧፈበት ጊዜ። በአልባንያና በኮሶቮ ድንበር አካባቢ ባለ ድንኳን አካባቢም ቆሜ ነበር። ቦታው በኮሶቮ ስደተኞች ተሞልቷል። የስደተኞቹ መጠለያ ካምፕ የተቋቋመው በኤምሬትስ ቀይ ጨረቃ ማህበረሰብ ሲሆን፤ የሚያስፈልገውንም ቁሳቁሶች ሞልተውት ነበር። ምግብ አብሳዮች፣ ሃላል ስጋ፣ የቴሌኮም ኢንጂነሮች (መሃንዲሶች)፣ ኢማሞችና ከአፍ ገደፋቸው የታጠቁ ወታደሮችም በአካባቢው ይታያሉ። ስፍራው የደረስነውም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የአየር ኃይል ነበር። አጠገቤም ሆኖ አንድ ረዘም ያለ፣ ጢማም ሰው ጥርሱን እየፋቀ ነበር። የብሪታንያ ሮያል ወታደራዊ ማሰልጠኛ ምሩቁና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ጦርንም ላቅ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ እየሞከረ የነበረው ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ነው። ለቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ ጠየቅኩት ብዙም ፍላጎት ባይኖረውም ተስማማ። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከፈረንሳይ ጋር ስላካሄዱት የሁለትዮሽ ስምምነትም ይነግረኝ ጀመር። አገሩ 400 የፈረንሳይ ታንኮችን እንድትገዛና በለውጡም ፈረንሳይ የኤምሬትስ ወታደሮችን እንድታሰለጥንና በኮሶቮም ጦርነት ላይ እንዲሰማሩ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር። ምንም እንኳን ጦርነቱ የሚካሄድበት የባልካን ግዛት ከመዲናዋ አቡዳቢ የ3 ሺህ 200 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ያለ ቢሆንም የአረብ ኤምሬትስ ከገልፍ ውጭ አገራት ባሉት አገራትም ቦታ እንዲኖራትም እየሞከረች የነበረበት ወቅት ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ)ን ደግፎ በአውሮፓ ላይ ወታደሮች ስታሰማራ የመጀሪያዋ አረብ አገርም ሆናለች። 'ትንንሾቹ ስፓርታ' በቀጣይነትም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኢላማ አፍጋኒስታን ነበረች። በርካታ የአገሪቷ ዜጎች ባያውቁም የተባበሩት ኤምሬትስ ኔቶን በመደገፍ ወታደሮቿን አሰማርታለች። ከታሊባን መውደቅ በኋላም የኤምሬትሱ አልጋወራሽ የሆኑት ሼክ መሐመድ ቢንዛይድ የኔቶን በአፍጋኒስታን መሰማራት ተቃውመውታል። በባግራም የጦር ሰፈር የሰፈሩትን የኤምሬትስ ልዩ ኃይል ለማየትም እድል አግኝቼ ነበር- በጎሮጎሳውያኑ 2008። በደቡብ አሜሪካ በተለይም ብራዚል በተሰሩ የጦር መኪኖች ተጭነው ራቅ ወዳሉ የአፍጋኒስታን መንደሮች ውስጥ ገብተው ቁርአን ይሰጡ ነበር፤ ጣፋጭም እንዲሁ። በዕድሜ ባለፀጋ ከሆኑት አፍጋኒስታውያንም ጋር ቁጭ ብለው ጊዜ በመውሰድ ይወያያሉ። ምን ትፈልጋላችሁ? ወታደሮቹ ይጠይቃሉ። "መስጂድ፣ ትምህርት ቤት፣ ንፁህ ውሃ?" ትፈልጋላችሁ ይሏቸዋል። ገንዘብም ያመጡና ለአካባቢው ኮንትራክተሮች በመስጠት የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ያሰራሉ። በወቅቱ የአረብ ኤምሬትስ አሻራ ከፍተኛ የማይባል ሊሆን ይችላል ነገር ግን ገንዘብና ሃይማኖትን በመጠቀም የአካባቢው ማህበረሰብ ኔቶ ላይ የነበረውን ጥርጣሬም ለመቀነስ ተጠቅመውበታል። በሄልማንድ በመሳሰሉ የአፍጋኒስታን ግዛቶችም ከብሪታንያ ሃይሎች ጋር በመጣመር እልህ አስጨራሽ የሚባሉ ጦርነቶችን አካሂደዋል። የቀድሞው የአሜሪካ የመከላከያ ኃይል ዋና ፀሃፊ ጂም ማቲስ ኤምሬቶችን 'ትንንሾቹ ስፓርታ' ሲል ጠርተዋቸዋል። ይህም አገሪቷ ትንሽ ከመሆኗ አንፃር፤ የህዝብ ቁጥሯም አስር ሚሊዮን ባይሆንም እያደረሰች ያለቸውን ተፅእኖ ለመግለፅ ነበር። አሸናፊ የሌለበት የየመን ጦርነት በከፍተኛ ችግሮች የተሞላው የየመን የጦር ዘመቻ ቀጠለ። የሳዑዲ አረቢያው ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን በየመን የርስበርስ ጦርነት ላይ እጃቸውን ሲያስገቡ ኤምሬቶችም በ2015 ተቀላቀሉ። ኤፍ-16 የተባሉ የጦር ጄቶችንም በመላክ የሁቲ አማፂያንን መደብደብ ጀመሩ። ወታደሮቿንም በደቡባዊ የመን አሰፈረች። ከሁለት አመታት በፊትም በየመን ቁልፍ የምትባለውን የሶኮርታ ደሴት ላይ ጦሯን አሰፈረች። በዚህም አልተገታችም በኤርትራዋም አሰብ የጦር ሰፈር በመከራየት ጦሯን በቀይ ባህር ላይ አዘመተች። ይህም የሁዳይዳህን ወደብ ከሁቲዎች ለመንጠቅ ነበር። የየመን ጦርነት ለስድስት አመታት ያህልም ቀጥሏል። አሸናፊ የሚባልም አካል የለም። ሁቲዎችም ቢሆን መዲናዋን ሰንዓን ጨምሮ በርካታ የአገሪቷ ግዛቲቷን እንደተቆጣጠሩ ነው። ኤምሬቶች ባደረሱት ጥቃትም የበርካታ ሰዎችን ህይወት ቀጥፈዋል። በአንድ የሚሳይል ጥቃት አምሳ የመናውያንም መሞታቸውንም ተከትሎ ኤምሬቶች የሶስት ቀናት ኃዘን አውጀው ነበር። ከአንዳንድ የአካባቢው ታጣቂዎች ጋር ባላቸው ግንኙነትም የኤምሬቶች ስም ጠልሽቷል። ታጣቂዎቹ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ናቸው። ለሞት በሚያደርስ ሙቀት በመጋዘንም ውስጥ በርካታ እስረኞችን በማጎርም በርካታ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይወቅሷታል አረብ ኤምሬትስን እስራኤል- አዲሱ ጥምረት በየመን ያላትን ተሳትፎ ብትቀንስም በቀጠናው ላይ ያላትን ተፅእኖ ለመጨመር አወዛጋቢ በሚባል ሁኔታ ከቱርክ ጋር ፉክክር ላይ ናት። ቱርክ በሶማሊያዋ መዲና ሞቃዲሾ ተሰማርታ የምትገኝ ስትሆን ኤምሬትስ በበኩሏ ሶማሊላንድን ትደግፋለች እንዲሁም በበርበራና ወደብና በኤደን ገልፍም የጦር ሰፈር አቋቁማለች። በጦርነት በተጎሳቆለችው ሊቢያም ኤምሬቶች የሩሲያና ግብፅን ጦር ጋር በመሆን የምስራቁን ካሊፋ ሃፍጣርን ኃይልን እየደገፉ ሲሆን በሌላኛው ጎራ ደግሞ የምዕራቡን ጎን ደግሞ በቱርክ፣ ኳታርና ሌሎች ኃይሎች በመደገፍ ተሰልፈዋል። መስከረም ወር ላይም ግሪክን ለማገዝ ወደ ክሬት ደሴት ተዋጊ ጄቶችን የላከች ሲሆን ይህም በምስራቅ ሜድትራንያን ነዳጅ የማውጣት መብት ጋር በተያያዘ ከቱርክ ጋር በመጋተራቸው ነው። ከዚህ ሌላ ባልተጠበቀ ሁኔታም ከእስራኤል ጋር ስምምነት ፈፅማለች። ለአመታትም በሚስጥራዊ ሁኔታ ሲያካሂዱት የነበረውን ጥምረትም ይፋ አድርገውታል። እንደ ሳዑዲ አረቢያ ኤምሬት ብትሆን እስራኤል ሰራሽ የደህንነት መሳሪያዎችን በመጠቀም ዜጎቿን ትሰልል ነበር። የአሁኑ ጥምረት የጤና፣ ባዮ ቴክኖሎጂ፣ ባህላዊና የንግድ ሽርኮች በተጨማሪ የጦርና የደህንነት ግንኙነታቸውንም በበለጠ ያጠናክራሉ ተብሎም ይታሰባል። የሁለቱም አገራት ጠላት የሆነችው ኢራን የእስራኤልና የኤምሬቶችን ስምምነት አውግዛለች። ኢራን ብቻ አይደለችም፣ ቱርክ እንዲሁም ፍልስጥኤማውያን ቢሆኑም አውግዘውታል። ፍልስጥኤም ራሷን የቻለች ግዛት ለመሆን የምታደርገውን ትግል ያጨለመና ኤምሬትም ፍልስጥኤማውያንን ክዳለች ተብሏል። የአቡዳቢ ፍላጎት በዚህ አይገታም። በአሜሪካ እርዳታም መንኮራኩር በማምጠቅና ወደ ማርስ በመላክ የመጀመሪያዋ አረብ አገር ሆናለች። 200 ሚሊዮን ዶላር በወጣበትና ተስፋ ተብሎ በተሰየመው የመንኮራኩር የማምጠቅ ጉዞም የተነሳው ከጃፓን ደሴት ነው። በጠፈርም ላይ 126 ሺህ ኪሎሜትር በሰዓት ይጓዛልም ተብሏል። 495 ሚሊዮን ኪሎሜትር ርቀት ያለውን መዳረሻዋም የካቲት አካባቢ ትደርሳለች ተብሏል። የሰው አልባ መንኩራኮሯ ተልዕኮ የማርስን ምህዋር በመሾር የአየር ንብረትና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ለቃቅሞ ወደ ምድር ማቀበል ነው። በአለም አቀፉ ላይ ስፍራ እንዲኖረን እንፈልጋለን ያሉት የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንዋር ጋርጋሽ ናቸው። "የትኞቹንም ጋሬጣዎች ማለፍ እንፈልጋለን። ለዚህም ቁልፍ የሚባሉ አካሄዶችን በመከተል እንሻገራቸዋለን" ብለዋል።
news-45520905
https://www.bbc.com/amharic/news-45520905
ኦፌኮና ሰማያዊ ፓርቲ መንግሥት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ
ሰሞኑን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በአርማ እየተመካኘ እየተፈጠረ ያለው አምባጓሮ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖው ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከማምራቱ በፊት መንግሥት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠየቁ።
ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመግለጫቸው ላይ "ትናንት አስከፊውን አገዛዝ ከጫንቃችን አሽቀንጥረን ለመጣል ያደረግነው ብርቱ ተጋድሎ በጎመራ ማግሥት የለውጡን ሂደት መደገፍና አገሪቱን እንደ አገር የማስቀጠሉ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ሲገባ በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ የሚታዩት ግጭቶችና ሥርዓት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ብለዋል። • አዲስ አበባ ብትረጋጋም የሚሰጉ አሉ ፓርቲዎቹ በተለይ ሰሞኑን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው እሰጣገባ በብርቱ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል። ቢዚህም ሳቢያ በተፈጠረ ፉክክር "ትውልዱን ለግጭት ማነሳሳት ፍፁም ሊወገዝ የሚገባው እኩይ ተግባር ነው" ሲሉ አውግዘዋል። ኦፌኮና ሰማያዊ በመግለጫቸው ላይ ጨምረውም "እያንዳንዳችን ፍላጎታችንንና ድጋፋችንን ለምንሻው አካል እየሰጠን አንዳችን የአንዳችንን ሃሳብም ሆነ መልካም ድርጊትን እያከበርን የተጀመረውን ለውጥና ሽግግር መደገፍ ወሳኝ ነው" ብለዋል። ፓርቲዎቹ በአርማ እየተመካኘ የሚፈጠር አምባጓሮ ባስቸኳይ እንዲቆምና ወጣቱ ትውልድ በፍቅርና በመቻቻል ዘመኑን እንዲዋጅ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአባገዳ መሪዎች ወጣቶችን እንዲያረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል።
47442572
https://www.bbc.com/amharic/47442572
የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ሊመለስ ነው
የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ከ150 ዓመታት በኋላ ሊመለስ ነው።
ከአጼ ቴዎድሮስ ቁንድላ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ቅርሶችም ተዘርፈዋል በመቅደላ ጦርነት ወቅት ለእንግሊዞች እጅ አልሰጥም ብለው ራሳቸውን ያጠፉት የአፄ ቴዎድሮስን ቁንዳላ ከ150 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ መሆኑን በእንግሊዝ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል። • "ፍቃዱ ተክለማርያም የሀገር ቅርስ ነው" • ኢትዮጵያዊው ጀማል ይመር በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ በእንግሊዝ ሀገር በሚገኘው የብሔራዊ ጦር ሙዝየም በይዞታው ሥር የቆየውን የአፄ ቴዎድሮስ (መይሳው ካሳ) ቁንዳላ ለመመለስ መስማማቱን የተገለፀ ሲሆን በመጪው ሐሙስም ከኤምባሲው ጋር ውይይት ሊያደርግ ቀጠሮ ተይዟል። አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ በ1868 ዓ. ም. ከእንግሊዝ አገር ከመጡ 32 ሺ ወታደሮች ጋር ተዋግተው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ተከትሎ በሀገሪቷ ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እንደተፈፀመ የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ። ምንም እንኳን የእንግሊዝ ጦር አዛዦች አፄ ቴዎድሮስ ይዘዋቸው የነበሩ እስረኞችን ለማስፈታት ነው ቢሉም የንጉሡን ቁንዳላ ከመሸለት በተጨማሪ መስቀልና የጣት ቀለበታቸውን፤ ሸሚዛቸውንና ሽጉጣቸውን ዘርፈዋል። • አሜሪካ ለላሊበላ ቤተክርስትያን ጥበቃ ፕሮጀክት 13.7 ሚሊዮን ብር ሰጠች • 900 ዓመታትን ያስቆጠሩ የወርቅ ሳንቲሞች ተገኙ ከዚህም በተጨማሪ መጻሕፍት፣ የተለያዩ ከወርቅ የተሠሩ ቅርሶችን፣ መንፈሳዊ ሥዕሎችን፣ ታቦታት፣ ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች ሳይቀሩ ተዘርፈዋል፤ ቅርሶች ተቃጥለዋል፤ መጻሕፍትንም ቀዳደዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የጀግና ተምሳሌት የኾኑት የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ወደ ሀገራቸው መመለስ ከፍተኛ ደስታን እንደፈጠረም ኤምባሲው በመግለጫው አስታውቋል። በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ተመስገን ገበየሁ "የአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ በመሆኑ ደስ ብሎኛል" ብለዋል። በርካታ የአጼ ቴዎድሮስ የግል ንብረቶች በመቅደላው መዘረፋቸውን ገልጸው፣ የንጉሡ ቁንዳላ ሊመለስ መኾኑን በጎ ጅማሮ ነው ብለዋል። "ይህ ጅማሮ ነው። ብዙ መመለስ ያለባቸው ቅርሶች አሉ፤ ይመለሳሉ ብዬ አምናለሁ" የአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ መመለስ ጎብኚዎችን ስለሚስብ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደሚኖረው መምህሩ ተናግረዋል።
news-53699944
https://www.bbc.com/amharic/news-53699944
ኮሮናቫይረስ፡ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህር በቫይረሱ ሕይወታቸው አለፈ
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በኮሮናቫይረስ ተይዘው የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው ዛሬ ሕይወታቸው ማለፉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ለቢቢሲ ገለፁ።
ሕክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት የመቀለ የኮሮና ታማሚዎች ማገገሚያ ማዕከል ሕይወታቸው ማለፉንም የገለፁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፤ ከእርሳቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላት አንድ ግለሰብም በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጦ ሕክምና እየተደረገላት እንደሚገኝ አክለዋል። በዩኒቨርስቲው የተለያዩ ግቢዎች በሚገኙ ለይቶ ማቆያዎች የሚሰሩ 1 ሹፌር፣ 2 የፀረ ተህዋስ ኬሚካል ርጭት ባለሙያዎች፣ 23 የፅዳት ሰራተኞች እና 10 የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት ኮሚኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ዘ ሚካኤል ገልፀውልናል። ዶ/ር ፍሰሃየ ከመምህርነት ባሻገር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮናቫይረስ ፈጣን ግብረ መልስ ቡድን መሪ በመሆን እንዲሁም በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ በኮሮናቫይረስ መረጃ ትንተና እና ትንበያ ክፍል እየሰሩ እንደነበር ዶ/ር ኪሮስ ገልፀውልናል። ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በሙያ አማካሪነት ለ17 ዓመታት አገልግለዋል። ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በመዛወር በዩኒቨርሲቲው የሕብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ፍሰሃየ በእናቶችና ህፃናት ህክምና፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች፣ በስነ-ምግብ፣ በወባ፣ በኤች አይቪ ኤድስና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ጨምሮ በሌሎች የሕብረተሰብ ጤና ዘርፎች ከ50 በላይ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በታዋቂ ጆርናሎች ማሳተማቸውን አክለዋል። የቀብር ሥነ ስርዓታቸውም ነገ በመቀለ ከተማ እንደሚፈፀም ዶ/ር ኪሮስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በትግራይ ክልል እስካሁን በተደረገ 25 ሺህ 579 ናሙናዎች ተመርምረው 1016 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
50336849
https://www.bbc.com/amharic/50336849
"ስምምነቱ ከመጠላለፍ የሚያወጣን ነው" አዴፓ
ከሰሞኑ የአማራን ህዝብ ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) እና አቶ ተተካ በቀለ የጋራ መድረክም በመፍጠር በሚያስሟሟቸው አጀንዳዎች ላይ አብረው ለመስራት የተስማሙት ፓርቲዎች አዴፓ፣ አብን፣ አዴኃን፣ መአህድ፣ መላው አማራ ህዝብ ፓርቲና ነፀብራቅ አማራ ናቸው። ፖለቲካ ፓርቲዎቹ የተለያዩ ፕሮግራሞች፣ ርዕዮተ ዓለም ከመከተላቸው አንፃር እንዲሁም የአማራን ህዝብ ጥቅም አልወከሉም በሚል ከመወነጃጀላቸው ጋር ተያይዞ በምን አይነት ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሱ የሚለው ጥያቄን የሚያስነሳ ነው። •"እስሩ አብንን ለማዳከም ያለመ ነው" ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) •"ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ለተመሳሳይ ህዝብ እንደመስራታቸው መጠን ምንም እንኳን ፕሮግራማቸውም ሆነ ሌሎች የሚለያዩዋቸው ጉዳዮች ቢኖርም አብሮ ለመስራቱም መሰረቱ እንወክለዋለን የሚሉት ህዝብ ልማትና ብልፅግና እንደሆነ የአብን ሊቀመንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ይናገራሉ። ይህንንም መሰረት በማድረግ በዋነኝነት የአማራን ህዝብ ጥቅም እንዲሁም ደህነነት ማስጠበቅ አጀንዳዎች ላይ ስምምነት መደረሱን ደሳለኝ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። ይህም መሰረታዊ ለውጥ ለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው በተለይም ሲወነጃጀሉ ለነበሩ ፓርቲዎች አዙሪቱን የሰበረ ጉዳይ መሆኑንም ይናገራሉ። "ከመጠላለፍ ወጥተን ወደ መተባበሩ እንድናተኩር፤ የምናደርጋቸውም ውድድሮች በሰለጠነና በሰከነ መንገድ እንዲሆን ስምምነት ላይ ደርሰናል" ብለዋል። የአዴፓ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተተካ በቀለም ሃሳብ ከዚህ የተለየ አይደለም። •“የኢህአፓና መኢሶን ነገር አማራ ክልል ላይ ሊከሰት ይችላል ብዬ ነበር” •«ዶ/ር ዐብይ ተገዳዳሪያቸውን ስልታዊ በሆነ መልኩ እያገለሉ ነው» ዶ/ር ደሣለኝ ጫኔ "መድረኩ የሚለየው ከመጠላለፍ ወጥቶ በሰከነ ፖለቲካዊ ትግል ውስጥ ለማለፍ እና በአማራ ህዝብ ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች የሚያደርጉት ሥራ በትብብር ላይ የተመሰረተ ሆኖ ህዝቡ በላቀ ደረጃ የሚጠቀምበት እና በአማራ የጋራ አጀንዳዎች ላይ በጋራ መስራት ነው። በዚህም ሁሉንም በአማራ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች የተሰባሰቡበት እና ልብ ለልብ የተግባባንበት ነው ማለት ይቻላል" ብለዋል። ፖለቲካ ፓርቲዎቹ የጋራ አቅጣጫ ለመቀየስ የተስማሙ ሲሆን ይህም የህዝቡን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በጠራ መልኩ ማስቀመጥ፣ የአጭር፣ የመካከለኛና ረዥም ጊዜ ግብ በመንደፍ አብረው ለመስራትም ስምምነት ላይ እንደደረሱ ይናገራሉ። በፖለቲካው ዘርፍ ስምምነት ላይ ከደረሱባቸው መካከል የተወሰኑትን ደሳለኝ (ዶ/ር) እንደጠቀሱት ፓርቲዎቹ በማንኛውም እንቅሴያቸው ላይ ስም ከማጠልሸት፣ ከመወነጃጀልና ከመጠላለፍ መታቀብ፤ ወጣቱን በጋራ አቅጣጫ ማስያዝ፤ ቀጣዩ ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን አብሮ መስራት ናቸው። "ለዘመናት የነበረውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የመጠላለፍና የመገዳደል ባህልንም የሚያስቀር ነው። አሁን ባለው ሁኔታ አማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ይህ ነው የሚባል ልዩነት የለንም" በማለትም አቶ ተተካ ይናገራሉ። የአማራን ህዝብና ፍላጎት በዘላቂነት ለማረጋገጥ፤ ከጥቃት ለመከላከል እና ከችግር ለመጠበቅ በአማራ ህዝብ ስም የተደራጁ ኃይሎች ማዶ ለማዶ ሆነው ከሚጠላለፉ ተቀራርበው መስራት በሚችሉበት ላይ አብረው ህዝቡን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ መጣር አለባቸው የሚል ጽኑ እምነት አዴፓ አለው ብለዋል ኃላፊው። •የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? •ሦስቱ ሃገራት በዋሽንግተን ምን ተስማሙ? በክልሉ ብቻ ሳይሆን ከክልሉ ውጭ ለሚኖሩ ሚሊዮን አማሮችም ድምፃቸው የሚሰማበትን መንገድ መቀየስ፣ ህዝቡ በቋንቋው የመጠቀም፣ ባህሉን የማዳበር እንዲሁም የፖለቲካ ውክልና የሚያገኙበት መንገድ ላይ ለመስራትም ፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተስማምተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የህይወት ደህንነቱ፣ የንብረት ዋስትና የማግኘት እሱንም የማስጠበቅም ሥራ ለመስራት ማቀዳቸውንም ፓርቲዎቹ ያስረዳሉ። ከፖለቲካው በተጨማሪ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊና የወጣቱንም የፖለቲካ ተሳትፎ በመጨመር ረገድም አብረው ለመስራት ከተስማሙባቸው ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። ምንም እንኳን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ስምምነት በአንዳንድ አካላት ዘንድ እንደ ውህደት ወይም ግንባር የመፍጠር አድርገው የተመለከቱት ቢኖሩም ደሳለኝም (ዶ/ር) ሆነ አቶ ተተካ ይህ እንዳልሆነ አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። "በሚያስማሙን እና በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ አብረን እንሥራ፤ በማያግባቡን ደግሞ እንተባበር ነው። በጋራ የመስራት ፍላጎት ሰነድ እንጂ አስገዳጅ ህግም ሰነድም አይደለም " ሲሉ አቶ ተተካ ያስረዳሉ። ወደፊት በግንባር ደረጃ ወይንም በመዋሃድ ዕቅድ ይኖር ይሆን ወይ በሚል ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ዓላማ እና አጀንዳ እየጠበበ ከሄደ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ ድርጅቶች መካከል እስከ ውህደት ልናመራበት የምንችልበት አጋጣሚ ዝግ ላይሆን ይችላል" ሲሉ አቶ ተተካ መልሰዋል። በትብብር መድረኩ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆኑ ምሁራን የሃይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሰው በየጊዜው በመገናኘት ሥራዎች እየተገመገሙ አቅጣጫ በማስያዝ በቀጣይነት እንደሚሰራም ያስረዳሉ። "ለዓመታት የጨቋኝና ተጨቋኝ ታሪክ በመፍጠር የአማራን ህዝብ የባይተዋርነት ስሜት እንዲሰማው ለረዥም ጊዜ ተሰርቷል፤ ይሄ በጥናትና በዕውቀት ተመስርቶ መቀልበስ አለበት የሚል ፅኑ እምነት አዴፓ አለው፤ ይህንን ከሞላ ጎደል ሌሎች ፓርቲዎችም ይስማሙበታል" ይላሉ አቶ ተተካ። ለረዥም ጊዜያት አብን፤ አዴፓን ወይም የቀድሞውን ብአዴን ለአማራ ህዝብ ጥቅም እየሰራ አልነበረም፤ የአማራ ህዝብ ውክልና የለውም ሲሉ በተደጋጋሚ ይሰማ ነበር፤ ይህንን ሃሳባቸውን ያስቀየራቸው ጉዳይም አዴፓ ካደረገው የአመራር ለውጥ ጋር እንደሚገናኝም ሊቀመንበሩ ያስረዳሉ። የቀደመ የአዴፓ ታሪክ "የአማራን ህዝብ አጀንዳ አሳልፎ የሚሰጥ ነበር" የሚሉት ደሳለኝ (ዶ/ር) ካለፈው ዓመት ጀምሮ ግን ድርጅቱ ውስጥ "ለአማራ ጥቅም አልታመኑም" የተባሉ አመራሮችን ያጠራበት፤ የተሻለ የአማራ ወገንተኝነት የሚያሳይና ለአማራ ህዝብ የሚቆረቆሩ አመራሮችን ወደፊት ያመጣበት ሁኔታ ተፈጥሯል ይላሉ። "ሙሉ በሙሉ ባይሆንም አብሮ በመስራት ደረጃ የሚያስችለውን ማስተካከል አምጥቷል" ይላሉ። በተለይም ከሕገ መንግሥቱ ጋር ተያይዞ አማራ ህዝብ አልተወከለበትም የሚሉ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ከአብን ይሰማ ነበር። አዴፓ ደግሞ ሕገ መንግሥቱን ካረቀቁት ድርጅቶች አንዱ ከመሆኑ አንፃር ተቃርኖ የለውም ወይ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ደሳለኝ (ዶ/ር) ምላሻቸው አሁን ያለው የአዴፓ አቋም ነው። አብን ሕገ መንግሥቱ የአማራ ህዝብ ስላልተወከለበት ሊሻሻል ይገባል ብሎ ከማመኑ አንፃር አዴፓም ይህንን መቀበሉ አብሮ ለመስራት እንዳስቻላቸው ይናገራሉ። ከአዴፓ ጋር ከነበራቸው ቅራኔ በተጨማሪ ህወሓትን ጋር ያላቸውን የከፋ ቅሬታም በተደጋጋሚ ከመናገራቸው አንፃር፤ አብረው ሊሰሩት ያቀዱት አዴፓ ደግሞ ከህወሓት ጋር በአንድ ግንባር ስር ነው፤ ይህ እንዴት ይታያል? ቢቢሲ ለደሳለኝ (ዶ/ር) ያቀረበላቸው ጥያቄ ነው። ምንም እንኳን ህወሓትና አዴፓ ከአስርት ዓመታት በላይ በእህትማማችነት በኢህአዴግ ውስጥ ሲሰሩ የቆዩ ቢሆንም በቅርብ ጊዜያት ግን በግልፅ ተቃርኗቸው እየታየ ነው ይላሉ። በቅርብ ጊዜያት ፓርቲዎቹ ባወጧቸው መግለጫዎችም ያላቸውን የሻከረ ግንኙነት ያሳየ ሲሆን፤ ይህንንም በማየት በአሁኑ ሰዓት ያላቸው ግንኙነት የይምሰል አይነት ነው በማለት ደሳለኝ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። •2011፡ በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት •"ፍቅር እስከ መቃብርን አልረሳውም" ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ይህንንም በመታዘብ በቀጣይ ሊፈጠር በሚችለው አዲሱ የውህድ ፓርቲ ህወሓት ሊገባ የማይችልበት እድል ሰፊ መሆኑን ያስረዳሉ። የዚህ አንድምታውም "አዴፓ ወደ አማራ ህዝብ ጥያቄ እየቀረበ መሔዱን የሚያሳይ ነው፤ እሱንም የሚያረጋግጥልን ነው። ከአዴፓም ጋር እያደረግናቸው ያሉ ግንኙነቶች ወደፊት የሚያስኬደን መሆኑን የሚያሳይ ነው። ከህወሓት ጋር በአንድ ግንባር ውስጥ ስላለ አማራዊ የሆነውን አዴፓን ገፍተን አብረን አንሰራም የምንልበት ምክንያት ሊኖር አይችልም" ይላሉ። ምንም እንኳን ህወሓት ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ቢኖራቸውም ህወሓትም ቢሆን ሥርዓት ወዳለው የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲገባ እንፈልጋለን ይላሉ።
news-50309164
https://www.bbc.com/amharic/news-50309164
ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ፡ 'ማህበረሰብን እንደ መሀይም መቁጠር የለብንም ይሉ ነበር'
በልጅነታቸው በግርዛት ምክንያት ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል። ሦስት ጊዜ ያህል ከተደረገባቸው የጠለፋ ሙከራ አምልጠዋል። ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቱ በእርሳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በእህቶቻቸውም ላይ ደርሶ ሁለቱን እህቶቻቸውን በግርዛት ምክንያት በሞት አጥተዋል።
መከራቸው ይህ ብቻም አልነበረም "ሴት ልጅ አትማርም" በሚለው የአገሬው ልማድ የትምህርት ዕድል ማግኘት አልቻሉም ነበር። በወቅቱም አባታቸው ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ ሲከለክሉ እናታቸው ደብቀው ትምህርት ቤት ይልኳቸው ነበር። • የሴት ልጅ ግርዛት በከፍተኛ ደረጃ ቀነሰ • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? ትምህርት ቤት ለመሄድ በጠዋት ይነሱና ውሃ ለመቅዳት ወንዝ ይወርዳሉ። ከዚያም የቀዱትን ውሃ ሳር ውስጥ ደብቀው ለመማር ክፍል ውስጥ ይቀመጣሉ። አጎታቸው በመጠኑም ቢሆን ያሉባቸውን ኃላፊነቶች ይጋሯቸው ነበር። በኋላም በሚስጢር የያዙት ትምህርት ተጋለጠ - ማንበብ መቻላቸው ታውቆ ጉድ ተባለ። በወቅቱ በአካባቢው ከአራተኛ ክፍል በላይ የተማሩ ብቸኛዋ ሴት እንደነበሩም ይነገራል - ዶክተር ቦጋለች ገብሬ፤ በብዙዎቹ አጠራር 'ቦጌ'። በእናታቸው ድጋፍ በድብቅ የጀመሩት ትምህርት አሜሪካ ድረስ ወስዷቸዋል። በእስራኤል አገር በሂብሪው ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የትምህርት ዕድል አግኝተው 'ማይክሮ ባዮሎጂ' እና 'ፊዚዮሎጂ' አጥንተዋል። ከዚያም በአሜሪካ አገር በማሳቹሴትስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲም በ'ኢፒዲሚዎሎጂ' ሦስተኛ ድግሪያቸውን አግኝተዋል። በ1989 ዓ.ም ወደ አገራቸው በመመለስ በእርሳቸው ላይ ሲደርስ የነበረው በደል በሌሎች ላይ እንዳይደርስ ለመሞገት ከምባታ ጠንባሮ ዞን የተጀመረውን እና 'ከምባቲ ሜንቲ ጌዝማ' [ኬ ኤም ጂ] ወይንም የከምባታ ሴቶች ራስ አገዝ በመባል የሚታወቀውን አገር በቀል ድርጅት መስርተዋል። ድርጅቱ በአካባቢው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን ከግርዛት እንደታደገ ይነገራል። "ያልተገረዘች ሴት ባል አታገኝም" የሚለውን የአካባቢውን የቆየ ልማድ ታግሎ፤ የነበረውን የግርዛት ሽፋን 3 በመቶ እንዲወርድ ያደረገ ታላቅ ተግባር ማከናዎናቸውን ብዙዎች ይናገሩታል። እኝህ በኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቀረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ተመራማሪ ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። በአሜሪካን አገር በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከትናንት በስቲያ ሌሊት ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል። ሕልፈታቸው ለብዙዎች ዱብዳ ነበር። ሕመም ሳይጠናባቸው ሥራ ላይ እያሉ ነበር ወደ አሜሪካ አገር የሄዱት በመሆኑም ሕልፈታቸውን ሲሰማ ማመን እንዳልቻለ የድርጅቱ ሠራተኛ የሆነው አቶ በላይ አድማሱ ይናገራል። አቶ በላይ፤ ዶ/ር ቦጋለች በጎጂ ልማዳዊ ድርጊት እና በሴቶች አቅም ማጎልበት ላይ እንደሚሠሩ ያወቀው ገና ተማሪ ሳለ ነበር - በተለያዩ መድረኮች ላይ ተሞክሯቸውን ሲያካፍሉ። "በአካባቢው ቀዳሚ የትምህርት እድል ያገኙ ሴት እንደነበሩ ልምዳቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ያካፍሉ ነበር" ይላል። በአካባቢው ያለው ባህል ሴቶች ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ስለሚያውቁ በሴቶች ደህንነትና መብት ላይ የሚሠሩት በሙሉ አቅማቸው ነበር። "'ማህበረሰብ መሀይም አይደለም፤ ዕውቀት አለው። ከእነሱ የምንማረው ብዙ ነገር አለ። እነሱን አንደ አላዋቂ መቁጠር የለብንም' የሚለው አቋማቸው ያስገርመኛል" ይላል። በዚህም ምክንያት ከማህበረሰቡ ጋር ጠጋ ብሎ መወያየት እንደሚያስፈልግ እና ማህበረሰቡ የራሱን ችግር መፍታት እንዳለበት ያላቸው እምነት ከእርሱ ጋር የቀረው ሃሳባቸው ነው። • “በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማርን ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም የምከራከርበት ነው” ገነት ዘውዴ [ዶ/ር] በፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር የኢትዮጵያ ተወካይ የነበሩት ዶክተር ንጉሴ ተፈራም ከዶ/ር ቦጋለች ጋር የሥራ ትውውቅ ነበራቸው። እርሳቸውም ዶ/ር ቦጋለች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ በተደረገው ጥረት ውስጥ የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ እንደነበር ይመሰክራሉ። ከእርሳቸው ጋር በአገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን ከአገር ውጭ በተደረጉ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ የመገናኘት ዕድል የነበራቸው ዶ/ር ንጉሴ፤ በአሜሪካ 'ውመን ደሊቨር' ባዘጋጀው ስብሰባም ላይ ሽልማት ሲበረከትላቸው በሥፍራው እንደነበሩ ያስታውሳሉ። ይህ ብቻም ሳይሆን ለጊዜው በውል አያስታውሱት እንጂ ሌሎች ሽልማቶችም እንደተበረከተላቸው ይናገራሉ። "ጎጂ ልማዳዊ ድርጊትን ለማስወገድ በተደረገው ጥረት ሁሉ ማንን ማንሳት እንችላለን? ሲባል በመጀመሪያው መስመር መምጣት ያለባት ዶክተር ቦጋለች ትመስለኛለች" ይላሉ። ዶ/ር ንጉሴ እንደሚሉት ዶ/ር ቦጋለች የጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ነገር ያንገበግባቸዋል። ሲናገሩም ሆነ ሲፅፉ ልባቸው የሚጨነቅበት፣ እልህ ውስጥ የሚገቡበት ሙሉ በሙሉ የተሰጡበት ነበር። ጥረታቸውም በለሆሳስ ሳይሆን ለመልካም ነገር እልኸኛ ነበሩ። "ልቧ ውስጥ የሚነድ እሳት፣ በጣም ቁጭትና ሀዘን ያለባት፣ የበለጠ ለመሥራት ብዙ የምታስብ እንደነበር አውቃለሁ፤ ለሁላችንም ጥሩ ምሳሌ የሆነች ሴት ነበረች" ይላሉ። ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች 70/80 በመቶ ሕፃናትን እና ሴቶችን ነው በአገራችን የሚያጠቃው የሚሉት ዶ/ር ንጉሴ፤ ይህንን ለመግታት ላደረጉት አስተዋፅኦ ሥራቸው ራሱ እንደሚመሰክር ይገልጻሉ። "የሴቶች መብት በተሻለ መልኩ የሚከበርበት አገር ኖራ፤ የትምህርት እድል አግኝታ ከፍ ባለችበት ሰዓት በሕዝቡ ላይ ተስፋ ሳትቆርጥ መምጣቷ በጣም ይገርመኛል፤ የጥንካሬ ምልክት ናት" የምትለው ደግሞ የሕግ ባለሙያዋ ህሊና ብርሃኑ ናት። ለሴቶች መብት እንደሚቆረቆር ሰው በጣም ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች አሉ የምትለው ህሊና፤ ብዙ ጊዜ በተሻለ ማህበረሰብ ውስጥ መኖር ሲጀመር ወደታች መመልከት የተለመደ አለመሆኑን በመግለፅ ዶ/ር ቦጋለች ግን ይህንን ልማድ የሰበሩ ሴት እንደሆኑ ትናገራለች። "ወደ ኢትዮጵያ ከመጣች በኋላም የአንድ ሰው ሳይሆን፤ የሺህ ሰው ጥንካሬ ነው ይዛ የመጣችው" ትላለች። ህሊና እንደምትለው ጥንካሬያቸው፣ መሥራት የሚፈልጉትን በትክክል አስቀምጠው መምጣታቸው ለእርሷም ሆነ ለሌሎች መልካም ነገር መሥራት ለሚፈልጉት ተምሳሌት ናቸው። "እምቢታ፣ መጋፈጥ የተለመደም አይደለም፤ ህብረተሰቡን ያስደነግጣል፤ ያንን ሁሉ ጥሳ ማህበረሰቡን ለመለወጥ መሞከሯ በጣም ጥንካሬዋን ያሳየናል" ስትል ታስታውሳቸዋለች። "በመልካም ነገር ፅንፍ [ራዲካል] ሃሳብ ሲኖር፣ የማህበረሰቡን ልማድ ላለመቀበል ወደ ታች የሚጎትትሽን ነገር እንዳታይ ምሳሌ ናት" በማለት ታክላለች። ህሊና እንደምትለው በጠለፋ ማግባት እስከ 2005 ድረስ በሕግ የተከለከለ አልነበረም። ግርዛት፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻ በማህበረሰባዊ ደረጃ እንደ መጥፎ ባህል ብቻ ሳይሆን ኢ- ሰብዓዊ ድርጊትም እንደሆነ በሕግም እንደሚያስጠይቅ አይወራም። ብዙ ጊዜ ጎጂ ባህል በሚል ተሸፋፍኖ ነበር የሚነገረው። ዶ/ር ቦጋለች ግን ጎጂ ልማድ በሚለው ሸፋፍነው አላስቀመጡትም፤ ይልቁኑ ሕገ-ወጥነት ብለው ነበር የተጋፈጡት። ዶ/ር ቦጋለች በዚህ በጎ ተግባራቸው በአፍሪካ በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመከላከል በአውሮፓዊያኑ 2007 የተበረከተላቸውን 'ላሪሳ' ሽልማት ጨምሮ በዓለም አቀፍና በአገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችንም አግኝተዋል። ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ በ2008 ዓ.ም የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚም ነበሩ። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በተወለዱበት ከምባታ ጠንባሮ ዞን ለማድረግ የድርጅቱ ቦርድ አባላት ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ጋር በመሆን እየተነጋገሩ እንዳሉ በዚያው ዞን የኬ ኤም ጂ ሠራተኛ የሆኑት አቶ በላይ አድማሱ ገልፀውልናል።
47972745
https://www.bbc.com/amharic/47972745
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከቃጠሎው በኋላ
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተደጋጋሚ የእሳት ቃጠሎ አጋጥሞት ያውቃል። እንዲህ እንዳሁኑ ያለ ሲገጥመው ግን የመጀመሪያው ነው። እሳቱ ከአንድ ሺህ ሔክታር በላይ የሆነውን የፓርኩን ክፍል አውድሟል።
ፓርኩ 43 ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን አንዱ ቀበሌ ላይ ብቻ ቃጠሎው እንደደረሰ የአካባቢው ኃላፊዎች ይናገራሉ። ይህ በአለም የቅርስ መዝገብ ስሙ የሰፈረ፣ የእነ ዋሊያ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ እና ቀይ ቀበሮ መኖሪያ ብሔራዊ ፓርክ እየተቃጠለ ነውን የሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን እሳቱን ለማጥፋት የአቅማቸውን ሲያደርጉ ነበር። በመጨረሻም ከኬኒያ በተገኘ የእሳት ማጥፊያ ሂሊኮፕተርና፣ ከእስራኤል በመጡ ባለሙያዎች ድጋፍ እሳቱ መጥፋቱ ተነግሯል። • ኢትዮጵያ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት እንዴት ትውጣ? • ስለ እንቅልፍ የተሳሳቱ አመለካከቶች • የጌዲዮ ተፈናቃዮች የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል የአሁኑ እሳት በምን ተለየ? በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ላቀው መብራት በተደጋጋሚ በፓርኩ ውስጥ እሳት ሲነሳ በማጥፋቱ ሥራ ላይ ተሳትፈዋል። የአሁኑ "ገደል ውስጥ ነው" ሲል ልዩነቱን ያስረዳሉ። ቀደም ሲል የሚነሱ እሳቶችን በአፈርና በውሃ ማጥፋት በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ የተለመደ ነው። ይኼኛው ግን የአካባቢው ነዋሪዎች በቀላሉ ከሚደርሱበት ቦታ አልነበረም ሲነድ የነበረው። "አብዛኛው ሰው ገደላማው የፓርኩ ክፍል የመግባት ልምድ የለውም" የሚሉት አቶ ላቀው ሜዳማውን ክፍል መቆጣጠር መቻላቸውን ግን ይገልጻሉ። አቶ ደሴ ብርሃን ደግሞ ሌላም ምክንያት ያነሳሉ፤ የስልክ ኔትዎርክ አለመኖርን። "እሳቱ በጀመረባቸው ሁለት ቀናት የስልክ ኔትዎርክ አለመኖሩ እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል" ይላሉ። ከዚህ ቀደም በፓርኩ እሳት ሲነሳ ሰዎች ስልክ ደውለው ህብረተሰቡን በማስተባበር የማጥፋቱ ሥራ ይከናወናል። "እሳቱ ለሶስት ቀናት ከፍተኛ ነበር" የሚሉት ደግሞ የፓርኩ ህብረተሰብና ቱሪዝም ኃላፊ አቶ ታደሠ ይግዛው ናቸው። እሳቱ የተነሳበት አካባቢ ከፍታ ያለው በመሆኑ እና ንፋሱም ከፍተኛ መሆኑ በፍጥነት እንዲስፋፋ እና ወደ ገደላማው አካባቢ እንዲዛመት ምክኒያት ነበር ብለዋል። በእንስሳቱ ላይ ምን ያህል ጉዳት ደረሰ? እንደኃላፊው ከሆነ ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው የፓርኩ ክፍል በእሳቱ ምክንያት ተቃጥሏል። ከ90 በመቶ በላይ በእሳቱ ጉዳት የደረሰበት ክፍል ደግሞ ጓሳ የተባለው የሳር ዓይነት ነው። አነስተኛ መጠን ያለው የፓርኩ ደንም ከጉዳት አላመለጠም። በፓርኩ እሳት ለማጥፋት የተሰበሰቡ ሰዎች በአደጋው የፓርኩ መለያ የሆኑት እንደጭላዳ ዝንጀሮ እና ዋሊያ ያሉት የዱር እንስሳት አለመሞታቸውን በእፎይታ ያነሳሉ። ይህ ግን ለሁሉም እፎይታን የሚሰጥ አይደለም። • የውሃ አጣጭ ለማግኘት የሚረዱ ሰባት ነጥቦች ስጋት ካለባቸው መካከል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የዱር እንስሳት ባለሙያ የሆኑት አቶ ደርቤ ለቅሲዮስ አንዱ ናቸው። "በተዘዋዋሪም ቢሆን በእንስሳቱ ላይ ጉዳት ደርሷል" ይላሉ። በእሳቱ ምክንያት የጓሳ ሳር እና አይጦች መቃጠላቸው ተረጋግጧል። እነዚህ ደግሞ በዋነኝነት የቀይ ቀበሮ እና የዋሊያ ምግቦች ናቸው። ለዚህም ነው አቶ ደርቤ እንስሳቱ በተዘዋዋሪም ቢሆን በእሳቱ ተጎድተዋል የሚሉት። እንስሳቱ ወደሌላኛው የፓርኩ ክፍል እንዲሸሹም ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። እሳቱስ በጎ ጎን አለው? በእንስሳቱ ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተጽዕኖ ብቻ መታየት የለበትም የሚሉ ግን አሉ። እነዚህ ወገኖች እሳት መኖሩ ጥቅምም አለው ሲሉ ይከራከራሉ። "እሳት በራሱ አንድ የአስተዳደር (ማኔጅመንት) ዘዴ ነው" ይላሉ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ ቲመር። የፓርኩ ሳር በእሳት ቢቃጠል ለብዝሃ ህይወቱ ጠቀሜታው ከፍ ያለ እንደሆነ በመግለጽ። ይህንን ሲያስረዱም "ሣሩ በየጊዜው እየተቃጠለ አዲስ ሣር እንዲበቅል ቢደረግ በምግብ የበለጸገ እና ምርታማ ሣር ለእንስሳቱ ይኖራል" ይላሉ። ይህ ግን የሚሆነው በቁጥጥር ስር መዋል የሚችል፤ በብዝሃ ህይወቱ እና በእንስሳት ላይ ጉዳት የማያደርስ መሆኑ በጥናት ሲረጋገጥ መሆኑን ያስረዳሉ። የአሁኑም እሳት አስቸጋሪ የሆነው ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ነው ይላሉ አቶ ግርማ። የአካባቢው ህብረተሰብ ይህንን ዕውቀት ያውቀዋል። ደረቁ ሳር ተቃጥሎ ለከብቶቻቸው አዲስ እና የበለጸገ ሳር ለማግኘት ሲሉ ያስጀመሩት ቃጠሎ ለዚህ አደጋ ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምታቸውንም ያስቀምጣሉ። በዚህ ረገድ ፓርኩም ሆነ ባለስልጣኑ በተቀናጀ፤ ከቁጥጥር ውጭ ባልሆነ እና ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ ሳሩን በየጊዜው ቢያቃጥሉ ለዱር እንስሳቱም ሆነ ለብዝሃ ህይወቱ ከፍ ያለ ጥቅም ያስገኛል ሲሉ ሃሳባቸውን ያስቀምጣሉ። የውጭ ሃገር ባለሙያዎቹ ምን አከናወኑ? እሳት፣ ተፈጥሮ ራሱን እንዲያድስ የሚያግዝ ዘዴ ነው ሲሉ እሳቱን ለመከላከል ከእስራኤል የመጡት ባለሙያዎችም ያስረዳሉ። ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ከእስራኤል የእሳት አደጋ መከላከል ከመጡት ዘጠኝ ባለሙያዎች መካከል አንዱ ኤሪያል ናቸው። "በሰዎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት እስካላደረሰ ድረስ" እሳት ጠቀሜታም አለው ሲሉ ይገልጻሉ። እንደባለሙያው ከሆነ እሳቱን ለመቆጣጠር በተከናወነው ሥራ ውስጥ ቡድኑ የቴክኒክ ድጋፍ አድርጓል። "በቀረቡት የእሳት አደጋ መከላከያ መሣሪዎች እንዴት መስራት አንደሚቻል አሳይተናል" ብለዋል። በደቡብ አፍሪካ የተመዘገበችው እና ባለቤትነትዋ የኬንያ የሆነችው የእሳት መከላከያ ሄሊኮፕተርም በሙሉ አቅሟ እንድትሠራ የእስራኤላውያኑ ድጋፍ ትልቅ ነበር። ሄሊኮፕተሯ ቀደም ሲል እሳት ለማጥፋት ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ውሃ ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በማምጣት ወደ አደጋው ቦታ ለመድረስ 30 ደቂቃ ይፈጅባት ነበር። ውሃ በቦቴ አደጋው በደረሰበት አቅራቢያ በማስመጣት የሄሊኮፕተሯን ምልልስ ከአስር ደቂቃ በታች ከማድረግ ባለፈ ነዳጅ ለመቆጠብም ባለሙያዎቹ አግዘዋል። "ሁለት ባለሙያዎቻችን እሳቱ ያለበት ጉድጓድ ውስጥ በመግባት ሄሊኮፕተሯ ውሃ በትክክለኛው ቦታ እንድትደፋ አድርገናል" ሲሉ አሪየል ያስረዳሉ። እሳቱ ጠፍቷል ለማለት ለምን አስቸገረ? ይህ ሁሉ ሥራ ተከናውኖ ግን እሳቱ ጠፍቷል ለማለት ብዙዎች ሲቸገሩ ተስተውሏል። 'እሳቱ ጠፍቷል' የሚለውን መረጃ ለመስጠት መገናኛ ብዙሃን፤ ትልቁን ዜና ለመካፈል ደግሞ ህብረተሰቡ በጉጉት ሲጠብቅ ቆይቷል። በተለይ ደግሞ ከማክሰኞ ጀምሮ እሳቱ ጠፋ የሚል መረጃ ለማግኘት በጉጉት የሚጠብቁት መገናኛ ብዙሃን የሚፈልጉትን አላገኙም። "እሳቱ ጉዳት በማያደርስበት በከፍተኛ ሁኔታ ከመቀነስ ባለፈ በቁጥጥር ስር መዋል በሚችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል" ሲሉ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ገልጸዋል። ይህ አገላለጽ የዋና አስተዳዳሪው ብቻ አይደለም፤ የሌሎችም ስለፓርኩ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጭምር እንጂ። ለዚህ ደግሞ ምክንያት የሆነው ከማክሰኞ ጀምሮ በፓርኩ ውስጥ የእሳት ነበልባል ባይታይም በጣም አነስተኛ የሚባል ጭስ መኖሩ ነው። ይህ ደግሞ የመሬት ውስጥ (ሰርፌስ ፋየር) የሚባለው ዓይነት እሳት በመሆኑ ነው። ይህ ዓይነቱ እሳት በጊዜ ሂደት ሊጠፋ ወይም ደግሞ በነበልባል መልክ በመነሳት ድጋሚ አካባቢውን ሊያቃጥል የሚችል ነው። ይህ ዓይነቱ እሳቱ በገደላማው የፓርኩ ክፍል በመከሰቱ አለ እንዳይባል የሚታይ ነበልባል አለመኖሩ ጠፍቷል እንዳይባል ደግሞ ጭስ እየታየ በመሆኑ በግልጽ ስለጉዳዩ ለመናገር አዳጋች አድርጎታል። ይህንን ለመወሰን ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ ነው፤ ባለሙያዎችም ሆኑ የፓርኩ ኃላፊዎች እሳቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል እንዳይሉ ያደረጋቸው። እንደኤሪያል ከሆነ እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ላለመግባት ዋነኛው መፍትሔ የዓለም ቅርስ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የእሳት መከላከል ቡድን ማቋቋም ነው። እንደባለሙያው ከሆነ "የእሳት መከላከል ቡድን መቋቋም አደጋ ቢፈጠር እንኳን ስጋት ከማስከተሉ በፊት በፍጥነት ለመከላከል ያስችላል።" ለእነአቶ ላቀውም የገቢ ምንጭ ከመሆን ባለፈ ለአካባቢው ስነምህዳር መጠበቅ የሚረዳቸው ፓርክ ተመሳሳይ ችግር አንዳይከሰትበት ቀድሞ መሥራቱ ለነገ የማይባል ነው ።
news-41157840
https://www.bbc.com/amharic/news-41157840
በድጋሚ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ኡሁሩና ራይላ ብቻ ይሳተፋሉ
ነሓሴ 8 ተካሂዶ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ያሸነፉበት የምርጫ ውጤት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከሰረዘው በህኃላ ቀጣይ ምርጫ ጥቅምት 17 እንዲካሄድ ቀን መቆረጡን የኬንያ ገለልተኛ የምርጫና የድንበር ኮሚሽን አሰታውቆዋል።
ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ (በስተግራ) ነሓሴ 8 ተካሂዶ በነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቢያሸንፉም ኦዲንጋ ባሰሙት አቤቱታ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምርጫውን ውጤት 'ህገምንግስታዊ ያልሆነ' ብሎ ሸሮታል የገለልተኛው የምርጫና የድንበር ኮሚሽን አዲስ መሪ ሆነው የተመረጡት ዋፉሉ ቼቡካቲ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ ብቻ እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል። ነሓሴ 8 ተካሂዶ በነበረው ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ማሸነፋቸው ይታወሳል ይሁን እንጂ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋን ኤቤቱታ ሰምቶ ከመረመረ በኃዋላ የምረጫውን ውጤት 'ህገ-ምንግስታዊ አይደለም' በማለት ሽሮታል። ይህ አይነት ውሳኔ በአፍሪቃ ታሪክ የመጀመሪያው ነው። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ውሳኔውን ሲያስተላልፉ የተወሰኑ የገለልተኛው የምርጫና የድንበር ኮሚሽን አባላት ''አግባብነት የሌለው እና የተዛባ ነገር'' ፈጽመዋል ብለዋል።
43087725
https://www.bbc.com/amharic/43087725
በሻሸመኔ እስር ቤት በተነሳ እሳት የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ
ዛሬ ጠዋት በሻሸመኔ በሚገኘው እስር ቤት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን፣ ሶስት ሰዎች መቁሰላቸውንና የእስረኞች ማደሪያ የነበረው ቤት በቃጠሎ መውደሙን የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የእስር ቤቱ ኃላፊ የሆኑት ከፍተኛ ኢንስፔክተር ፈይሳ ትክሴ እንደተናገሩት እሳቱ ከተነሳ በኋላ ለማምለጥ የሞከረ አንድ ታራሚ በጥይት ተገድሏል። ከማለዳው አንድ ሰአት ተኩል ላይ የተነሳው ቃጠሎ ምክንያት "እስረኞቹ ሆን ብለው የኤሌትሪክ ገመዶችን በማያያዝ ያስጀመሩት ነው"ብለዋል። በዚህ ማረሚያ ቤት ውስጥ በአጠቃላይ ወደ 2000 የሚጠጉ እስረኞች የሚገኙ ሲሆን ይጠቀሙበት ከነበረው አምስት ብሎኮች ሶስቱ በቃጠሎው ሙሉ በሙሉ መውደሙንም ከፍተኛ ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል። በአሁኑ ሰአት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን እሳቱ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና አሁን ለእስረኞቹ ማደሪያ በማመቻቸት ላይ መሆናቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል የአይን እማኝ ለቢቢሲ እንደተናገረው የማረሚያ ቤቱ አካባቢ በመካለከያ እና በኦሮሚያ ፖሊስ ጥበቃ እየተደረገለት ይገኛል። እንዲሁም ማለዳ ተዘግቶ የነበረው ከሻሸመኔ ወደ ሐዋሳ የሚወስደው ዋና መንገድ አሁን ተከፍቶ አገልግሎት መጀመሩን እና ከተማዋ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ መሆኗንም ይህው የአይን እማኝ ተናግሯል።
news-56041932
https://www.bbc.com/amharic/news-56041932
"ጀዋር መሐመድ እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊያውቃቸው አልቻለም" ኦፌኮ
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እነ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ አሐምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጾ መንግሥት "በአስቸኳይ ሕይወታቸውን አድኖ ግዴታውን ይወጣ" ሲል መግለጫ አውጥቷል።
ጀዋር መሐመድ "ለሚጠፋው የዜጎቻችንና አባሎቻችን ሕይወት መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል" በማለት ሕዝቡ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድርም ፓርቲው አሳስቧል። የኦፌኮ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ የረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እስረኞች "ታመዋል። ከዚያም በላይ ሰው መለየት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ሕይወታቸው አስጊ ደረጃ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፊርማ በማሰባሰብ፣ አቤቱታ በማሰማት፣ ሰልፍ በማድረግ ወይም መንግሥታቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር በማድረግ የእስረኞቹን ሕይወት እንዲያድን ጠይቀዋል። ያሳለፍነው ሰኞ፣ የካቲት 1/2013 ዓ.ም እስረኞቹን እንደጎበኟቸው የጠቀሱት አቶ ጥሩነህ፤ "ምንም ቃል ማውጣት አይችሉም። የሕክምና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል። አያይዘውም አቶ ጀዋር መሐመድን ሊጠይቋቸው የሄዱ እናታቸውን መለየት እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ሰኞ እለት አይቻቸዋለሁ። ቃል ማውጣት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ጀዋር መሐመድን እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊለያቸው አልቻለም። ጀዋር መሬት ይዞ እየዳኸ ነው ወደ እስር ክፍሉ የሄደው። አልቅሼ ነው የተለየሁት" በማለት ሁኔታውን ገልጸዋል። አቶ ጥሩነህ ዐቃቤ ሕግ፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶችና ሌሎችም አካላት እስር ቤት ሄደው እነ አቶ ጀዋርን እንዲያዩና መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድሩም ጠይቀዋል። "በኢትዮጵያ ታሪክም ጥቁር ነጥብ መሆኑን በመገንዘብ ለመንግሥት አስፈላጊውን ማስጠንቀቂያ ምክርም መስጠት ይችላሉ" ብለዋል። የኦፌኮ አባላት በጅማ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን፣ በምዕራብ ወለጋ፣ በምሥራቅ ወለጋ እና በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እንደሚታሰሩ፣ ታስረውም ፍርድ ቤት ያልቀረቡ እንዲሁም እንግልት የደረሰባቸው እንዳሉ ተናግረዋል። "ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ አባሎቻችንና ሌላው ሕዝብም መታሰሩ ያሳስበናል። ነገሮች ካልተሻሻሉ በሚደርስብን ጫና፣በግድያና በማስፈራሪያው ሳቢያ ኦፌኮ ሊዳረከም ሊፈርስም ይችላል" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። እነ አቶ ጀዋር በረሃብ አድማ ላይ ለረዥም ቀናት በመቆየታቸው የተነሳ የጤና ችግር እየተስተዋለባቸው መሆኑን የጤና ክትትል ከሚያደርጉላቸው ሐኪሞች መካከል አንዷ የሆኑት ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ለቢቢሲ መግለጻቸው አይዘነጋም። የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነና ከ15 ቀናት በላይ እንዳለፋቸው ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። እነ አቶ ጃዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፣ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሣሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ ሲሆኑ በወቅቱ ውሳኔ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ መሆናቸውም የሚታወስ ነው። የቀሩት አራት ክሶች "በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ"፣ የፀረ ሽብር አዋጅ 1176/2012 እና የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅን 7061/2004 የሚመለከቱ ናቸው።
news-56547522
https://www.bbc.com/amharic/news-56547522
ኪነጥበብ፡ ከቤተመንግሥት እስከ ሕዝቡ የወረደው ቴአትር በ100 ዓመታት
ቴአትር በአገራችን መድረክ ጅማሬውን ያገኘው ፖለቲካዊ ጭብጥን በመምዘዝና ንግሥቲቱንና ከፍተኛ ሹማምንቶቿን የክብር ታዳሚው በማድረግ ነው።
እንደውም የቤተ መንግሥትን ዐይን ብቻ ለመሳብ የተሰናዳ እስኪመስል ድረስ ተራውን ማኅበረሰብ እዩልኝ ወይንም ድግሴን ቅመሱልኝ የማለት ልምድ አልነበረውም። በጊዜ ሒደት ግን ቴአትር ከዚህ ብቸኛ ዐውድ ወጥቶ፣ ሰውኛ በሆኑ ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ ይጻፍም ይተወንም ጀመር። ይኸው ዛሬ ላይ ደግሞ ስለ ፍቅር እያለቀስንም እየሳቅንም፣ ስለ ፖለቲካችን እየተሳለቅን፣ ረቂቅ የሰው መልኮች ግዘፍ ነስተው እየተመለከትንም፣ በተለያዩ የተውኔት ዘውጎች የስሜት መፈራረቆችን እያስተናገድን ከማዕዱ እየተካፈልን ነው። ጷጉሜ 3/1913 ዓ. ም ሆቴል ውስጥ መታየት የጀመረው የአማርኛ ዘመናዊ ተውኔት፤ ዘንድሮ 100 ዓመት ሞልቶት በባለሙያዎቹ ሽር ጉድ እየተባለለት ነው። ታሪክን የኋሊት የኢትዮጵያ የአማርኛ ዘመናዊ ቴአትርን በ1913 ዓ. ም ያዋለዱት ፊታውራሪ ተክለሀዋርያት ተክለማርያም ናቸው። እኚህ የአማርኛ ዘመናዊ ተውኔት ፈር ቀዳጅ የጻፉት እና ያዘጋጁት የመጀመሪያው ተውኔት "የአውሬዎች ኮሜዲያ መሳለቂያ" ነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበባት መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ወርቁ፤ ቴአትሩ ለዕይታ የበቃው በወቅቱ አገሪቱን ያስተዳድሩ ለነበሩ ከፍተኛ ሹማምንት ነበር ይላሉ። "የአውሬዎች ኮሜዲያ መሳለቂያ" የዕይታ እድሜው አንድ ቀን ብቻ እንደነበርም ያስረዳሉ። ይህ ተውኔት የቤት እና የዱር እንስሳትን ገጸ ባህሪ በማድረግ የተሠራ ነው። እነዚህ ገጸ ባህሪያት በዘመኑ የነበሩ ፖለቲከኞችን ይወክላሉ በሚል በአንዳንድ ሹማምንት ዘንድ የተለጠጠ ትርጉም ተሰጥቶት ነበር። "የአውሬዎች ኮሜዲያ መሳለቂያ" ለእነዚህ ከፍተኛ ሹማምንቶች ከቀረበ በኋላ ዳግም ለተመልካች እይታ ያልቀረበበት ምክንያት በወቅቱ ተውኔቱን ከተመለከቱ ሹማምንቶች መካከል ንግሥት ዘውዲቱ ፊት እየቀረቡ ተውኔቱ እኮ ሥርዓትሽን የሚሰድብ፣ የሚዘልፍ፣ የሚያናንቅ፣ የሚያዋርድ ነው በማለት ሹክ በማለታቸው ነው። የበግ ገጸ ባህሪ ልጅ እያሱን፣ ተኩላው ደግሞ ራስ ተፈሪ መኮንንን ይወክላል ያሉ እና ወገን ለይተው የተከራከሩ ነበሩ። በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ራስ ተፈሪ መኮንን ተብለው እየተጠሩ አልጋ ወራሽ ነበሩ። ንጉሠ ነገሥታት ዘውዲቱ ደግሞ የአገሪቱ ንግሥት በመሆን ኢትዮጵያን ያስተዳድሩ ነበር። ከዚያ በኋላ ቴአትሩ ታገደ። የብሔራዊ ቴአትር ዳይሬክተር የሆነው ደራሲና አዘጋጅ ማንያዘዋል እንደሻው ይህንን ታሪክ በመጥቀስ፤ የኢትዮጵያ ቴአትር ጉዞ የተጀመረው "በመከልከል ነው" ይላል። ይህ ቴአትር ዳግም ለእይታ የበቃው አጼ ኃይለሥላሴ ከነገሡ ከሁለት ዓመት በኋላ በ1925 ዓ. ም ነው። ለእይታ በሚበቃበት ወቅት እንደዛሬው ግርማ ሞገሥ የሞላቸው ቴአትር ቤቶች፣ በብርሃን የሚንቆጠቆጡ መድረኮች አልነበሩም። በወቅቱ ቴራስ በሚባል ሆቴል ውስጥ መታየቱን ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ይናገራሉ። ያኔ ታድያ ተውኔት በማሳየት ስማቸው የሚጠቀሰው ግራንድ፣ ሮያል፣ ግሌዝ እና ማጀስቲክ የተሰኙት ሆቴሎች ነበሩ። የኢትዮጵያ ተውኔት ሲጀምር ፖለቲካዊ ተውኔቶችን በማቅረብ እንደሆነ ፕሮፌሰሩ ይናገራሉ። የዘመኑን የሥርዓት ብልሹነት፣ የባለሥልጣናቱን ደካማነት እና አላዋቂነት በማሳየት ነው የጀመረው። ይህ በማኅበረሰቡ ዘንድ የታዩ ጉድለቶችን በመንቀስ የጀመረው የኢትዮጵያ ተውኔት ጉዞ ቀጣይ መዳረሻ ተፈሪ መኮንን እና ዳግማዊ ትምህርት ቤት ሆነ። ቴአትር በ1919 ዓ. ም ትምህርት ቤት የገባው፤ በሆቴል ቤቶች ውስጥ ያሳዩ በነበሩት ዶ/ር ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ፣ ባለቤታቸው ቀፀላወርቅ ቱሉ፣ የጊዮርጊስ ትምህርት ቤት መምህር በነበሩት መስፍን ቀለመወርቅ የሚባሉ መምህራን አማካይነት ነው። እነዚህ በኢትዮጵያ ቴአትር ታሪክ ውስጥ የሚጠቀሱ ግለሰቦች የፍቅር እና የአገልግሎት ማኅበር የሚል አቋቁመው ማኅበሩ ለሚደግፋቸው ታዳጊዎች የሚሆን ገቢ ለማሰባሰብ ቴአትርን እንደመሣሪያነት መጠቀማቸው ይጠቀሳል። ከዚህ በኋላ ከሆቴል ቤት ወጥቶ ቀስ በቀስ ለቋንቋ ማስተማሪያነት ወደ ትምህርት ቤት ገባ። በ1996 በብሔራዊ ትያትር የተመደረከው ኪሊዎፓትራ ተውኔት ላይ ዓለማየሁ ታደሰ እና ሙሉዓለም ታደሰ ሲተውኑ። ተውኔቱ በጆን ድራይደን ተደርሶ በአዶኒስ የተተረጎመ ሲሆን ኣዘጋጀው ደግሞ ተስፋዬ ገብረማርያም ነበር። "ድርሰትና ዝግጅት በወንዶች ቁጥጥር ሥር የወደቀ ሙያ ነው" ተውኔት ሲጀመር በወንዶች ነው የተጀመረው የምትለው ደራሲና አዘጋጅ መዓዛ ወርቁ ቴአትር በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለቋንቋ ማስተማሪያነት ሲውል፤ በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ዮፍታሄ ንጉሤ፣ በመነን ትምህርት ቤት ደግሞ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ እንደነበሩ ታነሳለች። በእርግጥ በትወናው ላይ ቀድሞውም ቢሆን ሴቶች እንደነበሩ የምታነሳው መዓዛ፤ በድርሰቱ እና ዝግጅቱ ፋና ወጊ በመሆን ግን ከፊት የነበሩት ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ መሆናቸውን ትናገራለች። መነን ትምህርት ቤት በወቅቱ የሴቶች ትምህርት ቤት ሲሆን፤ ወ/ሮ ስንዱ ደግሞ በማስተዳደር ኃላፊነታቸውን ይወጡ ነበር። ወ/ሮ ስንዱ ደርሰውና አዘጋጅተው ለቋንቋ ማስተማርያነት የሚያቀርቧቸው ተውኔቶች ላይ የወንድ ገጸ ባህሪንም ሴቶቹ በመተወን ይሳተፉ እንደነበር ትናገራለች። ወ/ሮ ስንዱ በመራሔ ተውኔትነት (አዘጋጅነት) በመደረኳቸው ሥራዎች ላይ እህታቸው የውብዳር ገብሩን (እማሆይ ጽጌ ማርያም) በፒያኖ የማጀቢያ ሙዚቃ ያሠሩ እንደነበርም ትናገራለች። ወ/ሮ ስንዱ ቴአትሮች መጻፍ ብቻ ሳይሆን በማሳተምም ስማቸው ጎልቶ እንደሚነሳ በመጥቀስ "የየካቲት እልቂት" የሚባል መጽሐፋቸውን ትጠቅሳለች። ወ/ሮስንዱ ተውኔቶቻቸው በተለያዩ ሆቴሎች እንዲሁም በአገር ፍቅር ታይተዋል። የአማርኛ ዘመናዊ ቴአትር የ100 ዓመት ጉዞን ወደኋላ መለስ ብሎ በሴታዊነት መነጽር ለሚመለከት፤ እንዲህ እንደ ወ/ሮ ስንዱ ሰንደቃቸው ከፍ ብሎ የሚውለበለብ በርካታ ሴቶችን በድርሰትና በዝግጅት ሙያ ውስጥ አያገኝም። "ድርሰትና ዝግጅት በጣም በወንዶች ቁጥጥር ሥር የወደቀ ሙያ ነው" የምትለው መዓዛ፤ እንደማንኛውም ሙያ በጥበቡ ዓለም ውስጥም ጎልቶ እንደሚታይ ታነሳለች። በቴአትር ጥበባት ውስጥ ድርሰትና ዝግጅት ማለት የውሳኔ ሰጪነት ሚና መሆኑን በማንሳትም፤ በዚህ የአመራር ሰጪነት ቦታ ላይ በጣት የሚቆጠሩ ሴቶች ብቻ እንደሚገኙ ትናገራለች። በድርሰት የሚታወቁ ሴቶች በጣም ጥቂት መሆናቸውን በመጥቀስ የሚሠሩትም ከወንዶች ጋር በመተባበር መሆኑን ትናገራለች። ሴቶች በድርሰትና በዝግጅቱ በብዛት መምጣት የጀመሩት ከኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣት በኋላ የግል ቴአትር ፕሮዳክሽኖች መስፋፋታቸውን ተከትሎ መሆኑን ትገልጻለች። የግል ቴአትር ፕሮዳክሽኖች ሴቶች በግላቸው እንዲጽፉ፣ እንዲያዘጋጁና ፕሮዲውስ እንዲያደርጉ እድል መፍጠራቸውን ከራሷ ልምድ በመነሳት ትናገራለች። በዚህም አዜብ ወርቁ፣ ገነት አጥላው፣ ባዩሽ ዓለማየሁ፣ ዓለምፀሀይ በቀለ እንዲሁም ትዕግሥት ዓለሙን በአስረጅነት ትጠቅሳለች። የቴአትር ውጣ ውረድ ደራሲና አዘጋጅ ማንያዘዋል ቴአትር ከመነሻው ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በጥርጣሬ የሚታይ ዘረፍ መሆኑን ይጠቅሳል። አንዳንዴ የሳንሱር ገመዱ ጠበቅ ሲል ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲላላ 100 ዓመት እንደሞላው በመግለጽ፤ በዚህ ምክንያት እድገቱ የ100 ዓመት እድሜው ያህል አለመሆኑን ያነሳል። እንደ ማንያዘዋል ገለጻ የቴአትር ፈታኝ ጊዜያት ወታደራዊው የደርግ አገዛዝ ሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ነበር። ወቅቱ ጠንካራ ሳንሱር የነበረበት፣ ሥራዎች በአብዛኛው የፕሮፓጋንዳ የነበሩበት እንደሆነ ይጠቅሳል። ይህንንም ሲገልጸው ቴአትር "ታንቆ ተይዞ ነበር ማለት ይቻላል" ይላል። በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ ዘመን ቴአትር እንዲስፋፋ፣ በበርካታ ተመልካቾች ዘንድ እንዲታይም የተሠሩ መልካም ነገሮች እነደነበሩ ያነሳል። በደርግ ጊዜ በየተቋማቱ ሰኞ ከሰዓት የሚካሄድ የውይይት ክበብ ውስጥ ውይይት ይካሄድ ነበር። ይህንን አሰልቺ የሆነ የፖለቲካና የፕሮፓጋንዳ ውይይት ለማለዘብ አብዮታዊ ተውኔቶች ሲወጡ እነርሱን የውይይት ክበብ አባላት እንዲያዩት ይደረግ ነበር። እነዚህ ተውኔቶች በቅናሽ ለፋብሪካ እና ለመንግሥት ሠራተኞች ይቀርቡ ስለነበር ቴአትር ቤቶች በበርካታ ሰዎች እንዲጎበኙ እድል ፈጥሯል። ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ሲመጣ በአንጻራዊነት ነጻነት ስለተገኘ በሳምንት በየቴአትር ቤቶቹ አምስት እና ስድስት ቴአትሮች መታየት መጀመራቸውን ይጠቅሳል። ነገር ግን እየቆየ ሲሄድ በግልጽ ሳንሱር ባይካሄድም በተለያየ መልኩ ተጽዕኖ ማሳደር መጀመሩን ይናገራል። ይህንንም ሲያስረዳ በብሔራዊ ቴአትር የጌትነት እንየው "ወይ አዲስ አበባ" የተሰኘው ሙዚቃዊ ቴአትር ድርሰት በካድሬዎች ፖለቲካዊ ትርጉም ተሰጥቶት ከመውጣቱ በፊት መታገዱን ይጠቅሳል። የኢትዮጵያ ቴአትር ለወደፊትስ? ለደራሲና አዘጋጅ ማንያዘዋል በአሁኑ ሰዓት በርካታ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ከፍተው ተማሪዎችን ማስመረቃቸው ለአገሪቱ የቴአትር እድገት አንዱ መልካም እድል ነው። ነገር ግን አሁንም በአገሪቱ ያሉት ቴአትር ቤቶች ጥቂትና በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰኑ በመሆናቸው እነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የሚያስመርቋቸው ተማሪዎች የት ይቀጠራሉ? የሚለው ያስጨንቃቸዋል። በቅርቡ ትምህርት ሚኒስቴር ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ኪነ ጥበብን በሥርዓተ ትምህርቱ ሊያካትት መሆኑን ሰምቻለሁ በማለትም ይህን ጭንቀታቸውን በተወሰነ መልኩ እንደሚቀንስላቸው ያምናል። የኪነ ጥበብ ትምህርት በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ መካተቱ መሠረታዊ የጥበብ እውቀት ይዞ የሚያድግ ትውልድ እንዲሁም በሳል ተመልካች ለማፍራት አሌ የማይባል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አያይዞ ያነሳል። የኢትዮጵያ ቴአትርን ወደ ፊት ሲያስበው በአዲስ አበባ እና በአማርኛ ቋንቋ ብቻ ታጥሮ ባይቀር ደስ ይለዋል። በተለያዩ የአገሪቱ ቋንቋዎች ቴአትሮች በብዛት አለመሠራታቸው ለእድገቱ እንቅፋት መሆኑንም ያክላል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ቴአትርን በመደበኛነት የሚያሳዩ ቢኖሩ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለዓለም የጥበብ እድገት እንደሚጠቅም ያሰምርበታል። መዓዛ የሴቶች ተሳትፎን በቴአትር ውስጥ ከማየታችን በፊት ጥበቡ መቀጠል አለበት ትላለች። ቴአትር ሲጻፍ ሲመደረክ እስትንፋሱ ሲቀጥል የሴቶች ተሳትፎ እየደረጀ እና እየሰፋ ይመጣል ባይ ናት። እርሷ እና ባልደረቦቿ የቴአትርን መቶኛ ዓመት ለማሰብ በሚያደርጉት ውይይት ውስጥ የሴቶች ሚና ከፍ እንዲል እንደሚጥሩም ትገልጻለች።
news-56801398
https://www.bbc.com/amharic/news-56801398
በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጸመው ጥቃትና ያስከተለው ቀውስ
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት መውደሙን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አጣዬ በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ሞላሌ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አበይ ኃብተማርያም የተፈጠረው ጥቃት የእነርሱ ቀበሌ ላይም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል። "ጥቃቱ ከተጀመረ አንድ ወር ሆኖታል" ያሉት አቶ አበይ፣ መጋቢት 12/2013 ዓ.ም የመጀመሪያው ግጭት መቀስቀሱን እና በወቅቱ ግን ግጭቱ በአጎራባች ቀበሌዎች እንጂ እነርሱ ወዳሉበት አካባቢ አለመድረሱን ያስታውሳሉ። በአሁኑ ጥቃት እርሳቸው በሚኖሩበት ሞላሌ ቀበሌ ብቻ ቢያንስ 250 የመኖሪያ ቤቶች ከነንብረታቸው በእሳት መውደማቸውንና ነዋሪዎችም ነፍሳቸውን ለማትረፍ አካባቢያቸውን ለቀው መሰደዳቸውን ተናግረዋል። በጥቃቱ በዚሁ ቀበሌ ብቻ ከ10 ያላነሱ ሰዎች እንደሞቱ የተናገሩት አቶ አበይ ስምንት ሰዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል። ከእሁድ ጀምሮ የመከላከያ ሠራዊትና ፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ከተሰማራ በኋላ መረጋጋት እተመለሰ ቢሆንም፤ አቶ አበይ አሁን ያሉበትን ሁኔታ ሲናገሩም "ቤታቸው ተቃጥሎ አባት እና እናቶቻቸው የሞቱባቸው ልጆችን ይዘን ምን እንደምናደርጋቸው ጨንቆናል" ይላሉ። ቀደም ሲል መጋቢት 12 ላይ የነበረውን ጥቃት ተከትሎ ከሞላሌ አቅራቢያ በምትገኘው ነጌሳ ቀበሌ ውስጥ የነበሩ ነዋሪዎች ቤት በመቃጠሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሸሽተው በቀበሌዋ ተጠልለው እንደነበር ያስታውሳሉ። ከዚህ በኋላ ባለፈው ሳምንት ዳግመኛ ያገረሸው ግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ወዳሉበት ወደሞላሌ ቀበሌ መስፋፋቱን ተናግረዋል። አቶ አበይ እንደሚሉት በወቅቱ የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው ተሰማርቶ የነበረ ቢሆንም በስፍራው ብዙም ባለመቆየቱ የታጠቁት ኃይሎች ደወ ሞላሌ ቀበሌ በመምጣት ቤት ንብረት ማቃጠላቸውን ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ [ሰኞ ከሰዓት በኋላ] በአካባቢው ምንም አይነት የተኩስ ድምጽ ባይኖርም ቤት ንበረታቸው የወደመባቸው ተፈናቃዮች ግን ምንም ዓይነት እርዳታ እያገኙ አለመሆኑን ተናግረዋል። እርሳቸው እንደሚገምቱት በቀበሌዋ ብቻ ከአምስት ሺህ በላይ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን "መጠለያም ሆነ ምግብ ለማቅረብ ያነጋገረን የመንግሥት አካልም የለም" ብለዋል። ". . . ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው" አቶ አህመድ እንድሪስ ሲሆኑ የኩሪብሪ ቀበሌ ነዋሪ ነው። ኩሪብሪ ቀወት ወረዳ ውስጥ የምትገኝ ቀበሌ ስትሆን ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ጥቃት ከደረሰባቸው መካከል አንዷ ነች። በቀበሌዋ ጥቃቱ የተፈጸመው አርብ ጠዋት እንደነበር የሚናገሩት አቶ አህመድ ሁኔታው በጣም አስቸጋሪ እንደነበር በማስረዳት "የሞተውን ሰው ለመቅበር ምቹ ሁኔታ አጥተን ማታ ከሦስት ሰዓት በኋላ ሾልከን በመሄድ ነው አውጥተን የቀበርነው" ይላሉ። አቶ አህመድ አጎቱን ጨምሮ በጥቃቱ 11 ሰዎች እንደተገደሉ ማረጋገጣቸውን ይናገራሉ። ከአካባቢው ነዋሪ ውጪ የመጡ ሰዎች ናቸው ጥቃቱን በመፈጸም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱት ታጣቂዎች የሚሉት አቶ አህመድ በከባድ መሣሪያ በመታገዝ ጥቃት መፈጸሙን ገልጾ ለጥቃቱ መንግሥትን ተጠያቂ አድርገዋል። በቀበሌዋ የሚገኙ ነዋሪዎች ከጥቃቱ ለማምለጥ መኖሪያቸውን ለቅቀው ወደ አጎራባች የመንዝ ወረዳዎች ሸሽተዋል። በአንጻሩ በእዚህኛው ቀበሌ የሰው ሕይወት ቢጠፋም እንደሌሎች ቀበሌዎች ቤት አለመቃጠሉን አቶ አህመድ ይናገራሉ። አካባቢው ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ጋር ተጎራብቶ የሚገኝ በመሆኑ በሠርግም፣ በሐዘኑም አብረን ነው የምንኖረው፣ ተጋብተናል የሚሉት አቶ አህመድ፣ "ጥቃቱን የሚፈጽሙት ታጣቂዎች ግን ከሌላ ቦታ የሚመጡ ናቸው" ሲሉ ሁኔታውን ያስረዳሉ። ስምንት ቤተሰብ ይዘው የሸሹት አባወራ ሌላኛው ቢቢሲ ያነጋገራቸው አቶ መላኬ የሸዋሮቢት ነዋሪ ሲሆኑ የጥቃቱን መጀመር ተከትሎ ስምንት የቤተሰባቸውን አባላት ይዘው ወደ ደብረሲና ተሰድደዋል። እርሳቸው እንደሚሉት በሸዋ ሮቢት ችግሩ የተከሰተው ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ሲሆን ይህንን በመስጋትም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች አካባቢውን አስቀድመው ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ይናገራሉ። በወቅቱ ጥቃቱ ከሸዋ ሮቢት ከተማ ቀበሌዎች አንዷ በሆነችው ዙጢ ላይ ብቻ ተወስኖ ወደመሃል ከተማ አለመግባቱን ያስታውሳሉ። አቶ መላኬ እንደሚሉት መከላከያ ሚኒስቴር ግጭቱ የተቀሰቀሰባቸው ስፍራዎች በዕዝ ማዕከል [ኮማንድ ፖስት] ስር እንዲሆኑ መወሰኑን ተከትሎ ልጆቻቸውን ደብረሲና ትተው እርሳቸው አሁን ወደቤታቸው መመለሳቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ወቅት በሸዋሮቢት አንጻራዊ ሰላም መኖሩን የሚገልጹት አቶ መልኬ፣ እንደከዚህ ቀደሙ ባይሆንም በአብዛኛው ሰው እንቅስቃሴ እያደረገ እና ወደ መደበኛ ሕይወት እየተመለሰ መሆኑን ገልጸዋል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ቀወት ወረዳ፣ ኤፍራታና ግድም ወረዳ፣ ሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር፣ ወደ ክልሉ ኮምዩኒኬሽ እንዲሁም ወደ አማራ ብልጽግና ፓርቲ በተደጋጋሚ ቢደውልም ቢያደርግም ስልካቸው ባለመነሳቱ ጥረቱ አልተሳካም። እሁድ አመሻሹ ላይ የመከላከያ ሠራዊት ከሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ሲና ጀምሮ እስከ ደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ድረስ ያሉት አካባቢዎች በኮማንድ ፖስት ውስጥ መሆናቸውን ገልጿል። በእነዚህ አካባቢዎችም ከዋናው መንገድ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት ዙሪያ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተደንግጓል። በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ግችቶችና ጥቃቶች ሲፈጸሙ የቆዩ ሲሆን አሁን የተፈጸመው ግን እስካሁን ካጋጠሙት መካከል ሰፊ ቦታዎችን ከማዳረሱ በተጨማሪ ባስከተለው ጉዳት ቀደም ካሉት የከፋ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የአካባቢው ባለስልጣናት በአሁኑ ጊዜ የተፈናቀሉትን ወደ መኖሪያቸው ለመመለስና ቀሪውን ነዋሪ ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ባለፉት ቀናት በተፈጸመው ጥቃት በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት ዝርዝር ለማወቅ አለመቻላቸውን ገልጸዋል። ባለፈው መጋቢት ወር በአካባቢው በነበረ ጥቃትና ግጭት በተመሳሳይ ከባድ የሚባል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በክስተቱ ከ300 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ኤኤፍፒ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋምን ባለስልጣንን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ማን ምን አለ? የአማራ ክልል የሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በቀጠናው ከፍተኛ ጉዳት ማጋጠሙን ገልጸው ይህንን ጥፋት ያደረሰውም 'ኦነግ ሸኔ' መሆኑን ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን መግለጻቸው ይታወሳል። አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ጥቃት ካደረሰው ቡድን ነጻ ለማድረግ በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ሲሳይ የመኖሪያ ቀየውን ለቆ ወደ ደብረሲናና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሸሹ ነዋሪዎችን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በአማራ ክልል ውስጥ በሚገኘው የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የጅሌ ድሙጋ ወረዳ አስተዳዳሪ አሮ ሰይድ ጀማል ሐሰን ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት አርብ ዕለት ግጭቱ የተቀሰቀሰው "የአማራ ክልል ጸጥታ ኃይሎች አንድ ባለሱቅን መግደላቸውን ተከትሎ ነው።" ጨምረውም "በአንድ ጤና ኬላ ውስጥ ብቻ 53 የቆሰሉና 18 የሞቱ ሰዎችን አይቻለሁ። ሁሉም ኦሮሞዎች ናቸው" ሲሉ አስተዳዳሪው ተናግረዋል። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ያለችው የቀወት ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኤሊያስ አበበ እንዳሉት ውጊያው የተጀመረው ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር በተለየው ኦነግ-ሸኔ በተባለው ታጣቂ ቡድን እንደሆነ ለሮይተርስ ገልጸዋል። እንዲሁም በአካባቢያቸው ስለደረሰው ጉዳት መረጃ እያሰባሰቡ መሆኑን ነገር ግን "በርካታ ሰዎች ሞተዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀሩ ተቃጥለዋል" ሲሉም ተናግረዋል። ሮይተርስ ከአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልጿል። በአማራ ክልል በስፋት የሚንቀሳቀሰው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ ለችግሩ ዋነኛ ተጠያቂ ጠቅላይ ሚንስትሩ እና እርሳቸው የሚመሩት ብልጽግና ፓርቲ ናቸው ሲል መግለጫ አውጥቷል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ፤ ኢዜማ ደግሞ ጥቃቱን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ መንግሥት በአካባቢው በተደጋጋሚ የተከሰተውን ችግር "መነሻውን መርምሮ ከምንጩ ከማድረቅ ይልቅ ችግር በተፈጠረ ቁጥር ሠራዊት ሲያዘምት እና የተረጋገ ሲመስለው ሠራዊት ሲያሰወጣ ተመልክተናል" ብሏል። ጨምሮም እንዲህ አይነቱ እርምጃ ትክክለኛ መፍትሄ አይደለም በማለት "መንግሥት የአስተዳደራዊና የጸጥታ መዋቅሩን መመርመር እንዳለበት" አሳስቧል። የተቃውሞ ሰልፍ በደሴ ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ከተሞች የተፈፀመውን ጥቃት በመቃወም ዛሬ በደሴ ከተማ በርካታ ሰዎች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ በተፈጸሙ ተከታታይ ጥቃቶች ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ ሰላማዊ ሰዎችና የፀጥታ አካላት መገደላቸው የተነገረ ሲሆን በንብረትም ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ሰልፉ የሰሞኑን ጥቃት መነሻ ያደረገ ቢሆንም በተለያየ ጊዜያት በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃትም የሚያወግዝ እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሰልፉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል። የደሴ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ማዘንጊያ አበበ ስለ ሰልፉ ሲናገሩ የሰልፉ መንፈስ "በየቦታው በአማራ ላይ የሚፈፀመው ግድያ መቆም አለበት የሚል እንደነበር" ተናግረው፤ መንግሥት ይህንን ጥቃት እንዲያስቆም መጠየቁንም አመልክተዋል። ሌላኛው ስሜ አይጠቀስ ያለ የሰልፉ ተሳታፊም በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው መፈናቀልና ግድያ እንዲቆም የጠየቀ መሆኑን አመልክቶ "የማንም ፓርቲ አባል ሆነን ሳይሆን በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ግድያ እና መፈናቀል ተቃውመን ነው የወጣነው" ብሏል። መንግሥት ብሔር ተኮር መፈናቀል እና ግድያን እንዲያስቆም፣ በሰልፉ ላይ መጠየቁን የሚናገረው ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቀው ይህ ግለሰብ፣ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ እንዲያደርግ መጠየቁ ተናግሯል። ይህ ሰልፍ ማኅበረሰቡ በራሱ ተነሳሽነት ያካሄደው ሰልፍ እንደሆነ የተናገሩት ሌላኛው የደሴ ከተማ ነዋሪ አቶ ጋሻው ጉግሳ ተናግረዋል። የደሴ ከተማ የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንሰፔክተር ሐሰን መሐመድ ሰልፉ መካሄዱን አረጋግጠው በሰላም መጠናቀቁን ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ለልፉ የወጡ ግለሰቦች አስፈቅደው ሳይሆን በራሳቸው ተነሳሽነት የወጡ ናቸው" ያሉት ኢንስፔክተር ሐሰን የትኛውም የከተማው አስተዳደር ተወካይ አለመገኘቱን ጨምረው ተናግረዋል።
news-52733716
https://www.bbc.com/amharic/news-52733716
ኮሮናቫይረስ፡ በወረርሽኙ ወቅት ጀርመኖችን በሙያዋ የምታግዘው ኢትዮጵያዊት
በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሰው የሚያውቀኝ በዶክተር ምፅላል ነው። ባለቤቴ ጀርመን ስለነበርና በባሕላቸው ስም መቀላቀል የተለመደ ስለሆነ ያባቴንም እንዳላጣ በማሰብ ምፅላል ክፈለየሱስ ማቺ ሆንኩኝ። ልጅ እያለሁ ጦርነት ማስቆም እመኝ ነበር። በ21 ዓመቴ በተባበሩት መንግሥታት የጦር መሳሪያ ቁጥጥርና ቅነሳ ላይ ላይ መሥራት ጀመርኩ።
በተባበሩት መንግሥታት ስትራቴጂስት ሆኜ በምሠራበት ወቅት የኬሚካል ጦር መሳሪያ ጉባዔ በተባበሩት መንግሥታት ዋና አጀንዳዎች መካከል እንዲሆን ከሠሩት ሰዎች መካከል ነበርኩኝ። ያስፈልጉ ከነበሩት የ76 አገራት ፊርማዎች 23 አገራት እንዲፈርሙ ያደረኩት እኔ ነበርኩኝ። የኛም ቡድን ይህን ራቲፋይ በማስደረጉ የኖቤል የሰላም ተሻላሚ ሆነን ነበር። በዚያን ጊዜ ብቸኛዋ ሴት ኢትዮጵያዊት ነበርኩኝ። አሁንም ቢሆን የምታገለው ኬሚካልና ባዮሎጂካል የሆኑ መሣሪያዎች እንዲጠፉ አልያም እንዳይስፋፉ በማድረግ ነው። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን ኢላማዬን ትንሽ ዞር አድርጌ ትኩረቴን በእርሻ ሰብል ላይ አድርጌያለሁ። በአገር ቤት ሳይንስን ተጠቅሞ ከአርሶ አደሮች ጋር በመሥራት ኢትዮጵያ የሚበቅሉ ሰብሎች ለመጀመሪያ ጊዜ በጀርመንና በጃፓን ተቀባይነት እንዲኖራቸው አድርጊያለሁ። • ከዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሳይንቲስቶች መካከል አንዷ የሆኑት ኢትዮጵያዊት • በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን አሁን ደግሞ የኮሮናቫይረስ ወረርሺኝ ከተነሳ ጀምሮ 'ሳይንስና ቴክኖሎጂ በኮሮናቫይረስ' እና 'ኢነር ጀርኒ' የተሰኙ ሁለት የተለያዩ የዩትዩብ የነፃ የመረጃ አገልግሎቶችን መስጠት ጀምሬያለሁ። ወደዚህ ግን የገባሁት ከመሬት ተነስቼ አልነበረም። እዚህ፣ ጀርመን የነበሩ ዶክተሮች እና ነርሶች፣ ጣሊያን የተፈጠረውን ዓለም ካየ በኋላ፣ በጣም ከባድ የአዕምሮ ረብሻ ገጥሟቸው ነበር። ከዚህ ቀደም ደግሞ እኔ በተለያዩ መድረኮች ላይ በሳይንስ የተደገፉ የውስጣዊ ሰላም ንግግሮችን አድርጌ ስለነበር እርዳታ እንዳቀርብ ጥያቄ ቀረበልኝ። ለቀረበልኝ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ብዬ ለሁሉም ይጠቅማል ብዬ በማሰብ የዩትዩብ ቻናል ከፍቼ ንግግሩን በበይነ መረብ ማስተላለፍ ጀመርኩኝ። የመጀመሪያው ንግግሬንም በፍርሃት ዙሪያ 'ፍርሃትን ማሸነፍ' በሚል ርዕስ አቀረብኩኝ። ሳይንስና መንፈሳዊነት አንድ ላይ የሚሄዱ የአንድ አካል ሁለት ጎኖች ናቸው ብዬ አምናለሁ። እንዲያውም ብዙ መንፈሳዊ ተብለው የሚታሰቡ ሃሳቦች በሳይንስ ማስረዳት ይቻላል ባይ ነኝ። አይንስታይንም ለልጁ በፃፈላት ደብዳቤ እንደሚለው ፍርሃትን ማሸነፍ የሚቻለው በፍቅር ነው፤ ስለዚህ ከፍርሃት ለመላቀቅ የፍቅርን ጉዞ በዩትዩብ አስጀመርኩኝ። ይህን ጉዞ ስጀምርም ብዙ ስዎች የምሥጋና መልዕክት አድርሰውኛል። ስለ ፍቅር እና ስለዚህ ውስጣዊ ጉዞ በማወራበት ጊዜ ብዙ ሰዎች፣ በተለይ ደግሞ አገር ቤት ያሉ ሰዎች፣ ስለ ሃይማኖታዊ ጉዞ የማወሳ ይመስላቸዋል። ምንም ቢመሳሰል ግን እኔ ስለ ሳይንስ ነው የማወራው። ማለትም ስለ ኤፒጄኔቲክስ፣ ኒዩሮሲኖፕሲስና ኒዩሮሚረሪንግ ነው የማወራው። አያቶቻችን ድሮ አንዳንድ ሰው ሲታመም 'ይህ ነገር ከዘር የመጣ ነው' ይሉ ነበር። ይህ ደግሞ ኤፒጄኔቲክስ ይባላል። በዘረመል (ዲኤንኤ) የመጡ በሽታዎች ቢሆኑም እንኳን አሁን በሳይንስ እገዛ ማሸነፍ፣ መዳን፣ መለወጥ ይቻላል ነው እያልን ያለነው። የዩትዩብ ቻናሉም ዋናው ዓላማ በሃይማኖታዊ ሳይሆን በመንፈሳዊው እና በሳይንስ መካከል ያለውን የመረዳት ክፍተት ለመዝጋት ነው። • በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለምን ተስፋፋ? • የኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ያጠላበት የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ደም ብዛት ወይንም የስኳር በሽታ አብዛኛውን ጊዜ በዘር የሚመጡ መሆናቸውን ሰዎች ይረዳሉ። የአዕምሮ ችግሮችም ልክ እንደዚያው በዘር ሊመጡ እንድሚችሉ ለማስረዳት እጥራለሁ። አንዳንዴ በዘር የሚመጡት የአዕምሮ ችግሮችም ሆኑ አካል ላይ የሚፈጠሩ በሽታዎች ከመወለዳችን ሊታዩ ይችላሉ። አንዳንዴ ደግሞ ቢኖሩም እንኳን ሁኔታዎች ካልተመቻቹላቸው ላይታዩ ይችላሉ። እናም ብዙ ጊዜ በውጥረት በጭንቀት መካከል ወይንም በአካባቢው ያሉ ሁኔታዎች ሊቀሰቅሷቸው ይችላሉ። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ላይ ለሚገኝ ሰው ደግሞ መፍትሔውን ለማግኘት እርዳታ ማቅረብ ያስፈልጋል። የሚቀርበውን መፍትሔ የሚቀበል ሰው ደግሞ ከችግሩ የመላቀቅ አጋጣሚው ሰፊ ይሆናል። እርዳታ መጠየቅ ያለበት ደግሞ ከአቅም በላይ ሲሆን ሳይሆን ከመጀመሪያው ነው። በባህላችን በተለይ የአዕምሮ ችግሮችን ለመቀበል ስለሚያቅተን የመሸፋፈን ልማድ አለ። ይህ ብዙ ጠቃሚ አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ የሚታዩ ችግሮች ከሌሉ በስተቀር ራስን የመቀየር ሃሳብ 'ትራንስፎርሜሽን' አይመጣልንም። ፆም፣ ፀሎትና ፀበልም ሆነ መንፈሳዊ ጉዞዎች የሚደረጉት ጭንቀት ሲኖር ወይንም መፍትሔ ፍለጋ ነው። እነዚህ መጥፎ ናቸው ሳይሆን እያልኩኝ ያለሁት፣ ልክ በችግር ጊዜ መንፈሳዊነትን እንደምንፈልገው ሁሉ በሌላም ጊዜ ልናዘወትረው ይገባል ነው የምለው። ይህም ሳይንሳዊ ነው። በተለይ አሁን ደግሞ ዓለም ያለችበት ሁኔታ ሁላችንንም የሚያሳስብ በመሆኑ ውስጣዊ ጉዞ ከምንጊዜም በላይ ጠቃሚ ነው። በአገራችን ለምሳሌ የተለያዩ መንፈሳዊና ባህላዊ የሆኑ የመንፈስ እርጋታ የሚሰጡ መፍትሔዎች አሉ። እነዚህን ባህላዊ የሆኑ መንፈሳዊ እርካታና እርጋታ የሚሰጡ መፍትሔዎች በሳይንሱ ዓለም 'ትራንስፎርሜሽን' የምለው ውስጣዊ የጉዞ ዓይነት ነው። ሳይንስ 'ትራንስፎርሜሽን' የሚለው ራስን ከማዳመጥ የሚመጣ መፍትሔ ሲሆን በቀላሉ ለማስረዳት ያህል ከሕፃንነታችን አንስቶ ነፍስ አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የተማርናቸው ብዙ ነገሮችን መቀየር ማለት ነው። እነዚህም ትምህርቶች ማንነታችን ያዋቀሩ ዋና ባህሪያችን ምሰሶዎች ሆነዋል። የምንፈራቸው፣ የምንወዳቸው ብሎም የምናስባቸውና የምንመኛቸው ነገሮች ሁሉ ሳይቀር በዘረ መልና በአካባቢያችን ማንነታችንን ያቋቋሙ ናቸው። የሚገኙትም በኒዩሮኖቻችን ነው። እነዚህን ነው ማንም ሰው መቀየር ይችላል እያልኩ ያለኹት። ለመቀየር ደግሞ ሥራ ይጠይቃል። የትራንስፎርሜሽን ሥራ ማለት ነው። • እሷ ማናት፡ "አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ"- ሐና ተክሌ • የኮቪድ-19 ክትባት ለድሃ አገራት እንዲደርስ የ2 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈረመ ይህንን በኒዩሮኖቻችን የተፃፈ መረጃ በውስጣዊ ጉዞ መቀየር አቅም የሌላቸው ደግሞ በመድሃኒት እርዳታ ሊቀይሩት ይችላሉ። እሱ ግን ሌላ ጉዳይ ነውና እኔም የማተኩረው በፈቃደኝነት ራሳቸውን ከተለያዩ በዘር የመጡም ሆኑ ከአካባቢ የተወረሱ ልማዶችን ለማላቀቅ እርዳታ እየሰጠኹ እገኛለሁ። በጀርመን የጦርነቱ ትውስታ በብዙዎች ዘር መረጃ ውስጥ ስላለ ይህ የኮሮና ወረርሽኝ ብዙ ጭንቀቶችን ቀስቅሷል። ሁኔታው እስኪረጋጋ ደግሞ ውስጣዊ እርጋታ እንዲያገኙ ስረዳቸው ቆይቻለሁ። ኮሮና ከመምጣቱ በፊት ብዙ ጀርመኖችን እንደዚሁ እረዳ ነበር ። እንደውም በሳይንሱ አንዳንዴ ከተለመደ አካባቢ መውጣትና መንፈሳዊ የሆኑ ነገሮችን ማድረግ ከራስ ጋር ለመነጋገር ጥቅም ስላለው ኢትዮጵያ ድረስ ይዥያቸው የሄድኩት ብዙ ጀርመኖች አሉ። አሁን መጓዝ ባይቻልም የተለያዩ መፍትሔዎችን በመጠቀም አግዛቸዋለሁ። ለምሳሌ በኮሮና ንብረት ያጡ፣ ዕዳ ያለባቸው፣ ከሥራ የተባረሩ ብዙ ሰዎች አሉ። እነርሱም ጉድጓድ ውስጥ ያሉ ያህል ስሜት ሊሰማቸው እንደሚችል ይገባኛል። ብመክራቸው በአሁን ሰዓት ከጉድጓዱ ለመውጣት መጣር እንደሌለባቸው ነው። ምክንያቱም ባለው እውነታ ምክንያት ያንን ማድረግ በጣም ከባድ ይሆንባቸዋል። ከዚህ ይልቅ የነበሩበትን እንዲያስቡ፣ ተመልሰው ወደነበሩበት መመለስ እንደማያቅታቸው እንዲያስቡ፣በተጨማሪም ሕልሞቻቸውን፣ መሆን የሚፈልጉትንና ማድረግ የሚመኟቸው ነገሮች ላይ እንዲያተኩሩ አበረታታቸዋለሁ።
news-54759328
https://www.bbc.com/amharic/news-54759328
የአሜሪካ ምርጫ፡ መምረጥ እንደሚችሉ ያልታወቁት 750 ሺዎቹ የአሜሪካ ታራሚዎች
ከእስር በኋላ ሌላ እድል በህይወት ላይ ይኖር ይሆን?
ከሶስት አስር አመታት በላይ በእስር የቆየው ሬናልዶ ሁድሰን በማረሚያ ቤት ህይወቱን ቀይሮ፣ የነገን ተስፋ ሰንቆ ነበር የወጣው። ገና በታዳጊነቱ ከፍተኛ ጥቃት ያስተናገደው ሬናልዶ በነፍስ ግድያ ወንጀል ክስ ነው 37 በእስር የቆየው። በአስራዎቹ እድሜውም አደንዛዥ እፅን ይጠቀም የነበረ ሲሆን በዚህም ወቅት ነው ለእስር የተዳረገው። መላ ህይወቱን በእስር ያሳለፈው ሬናልዶ በማረሚያ ቤትም ውስጥ እያለ ታራሚዎችን በማስተማርም ያግዝም ነበር፤ ከውጭው ካለው አለምም ጋር በምን መንገድ ግንኙነታቸውን መቀጠል ይችላሉ የሚለውም ዋናው ትኩረቱ ነበር። የ56 አመቱ ሬናልዶ በዚህ አመት በተለይም በዚህ ወቅት ሚሊዮኖች መምረጥ አለባቸውም እያለ ነው። ምርጫ ለምን? በእስር ቤት ያሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን መምረጥ እንደሚችሉም ሆነ እንደማይችሉ ግንዛቤው የሌላቸው ሲሆን ይህም በዲሞክራሲያዊ ሂደት ተሳታፊ እንዳይሆኑና ማህበረሰቦቻቸውን ተፅእኖ ከሚያመጡ ፖሊሲዎችም እንዲገለሉ ሆነዋል። ሬናልዶም ከ750 ሺህ በላይ ታራሚዎችን የሚገለሉበትን መዋቅራዊ ስርአትም ከሚታገሉት አንዱ ነው። በአሜሪካ ምርጫ ህግ መሰረት ከበድ ያለ ወንጀል የፈፀሙና ረዘም ያለ የእስር ጊዜ የተፈረደባቸው ታራሚዎች በአብዛኛዎቹ ግዛት መምረጥ አይችሉም። መምረጥ የሚችሉት በሜይን፣ ቬርሞንትና ዋሽንግተን ዲሲ ብቻ ነው። ነገር ግን የፍርድ ጊዜያቸውን እየተጠባበቁ ያሉ፣ ወይም ቀለል ባሉ ወንጀሎች አጠር ላለ ጊዜ በእስር ያሉ ታራሚዎች መምረጥ ይችላሉ። በአሜሪካም ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች ውስጥ ክስ ያልተመሰረተባቸው ነገር ግን የተጠየቁትን 500 ዶላር የዋስ ገንዘብ መክፈል ባለመቻላቸው በእስር ላይ ያሉ በርካቶች ናቸው። በቅርብ አመታት ውስጥ የዲሞክራሲ ደጋፊ ቡድኖች በጎ ፈቃደኞችን በተለያዩ የአሜሪካ እስር ቤቶች ውስጥ በመላክ መሰረታዊ ህገ መንግሥታዊ መብታቸውን እያስተማሩ ይገኛሉ። በሂውስተን የሚገኘው የሃሪስ ማረሚያ ቤት አንድ ሺህ የሚሆኑ መምረጥ የሚችሉ ታራሚዎች መዝግበዋል። ሳንዲያጎ ባሉ እስር ቤቶች ደግሞ በጥቁር ሙስሊሞች የሚመራና ለፍትህ የሚታገል ቡድን በእስር ቤት ያሉ ታራሚዎችን 17 ዶላር በሰዓት በመክፈል ድምፅ ለማሰባሰብም እየሞከሩ ነው። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያትም በርካታ ተሟጋቾች በየማረሚያ ቤቱ በመሄድ መምረጥ የሚችሉ እስረኞችን ስለ መብታቸው ማሳወቅ ተስኗቸዋል ተብሏል። ስፕሬድ ዘ ቮት የሚባል ተሟጋች ቡድንም በበኩሉ ታራሚዎች በፖስታ እንዲመርጡ ለማድረግም አንድ ፕሮግራምም ጀምሯል። ይህም ፕሮግራም በ20 ግዛቶች የሚገኙ 52 እስር ቤቶችን የሚሸፍን ነው። የቡድኑ መስራች ካት ካልቪን እንደሚናገሩት ይህንን ፕሮግራም በመጠቀም በርካታ ታራሚዎች መምረጥ መጀመራቸውን ነው። ከፕሬዚዳንታዊው ምርጫ፣ ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም በፊትም የሚሰሩባቸው እስር ቤቶች ታራሚዎች በፖስታ ድምፃቸውን እንዲልኩ እየሰሩ ነው። ሆኖም የመራጮች መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ከእስር ቤት ምርጫን በፖስታ መምረጥ ቀላል እንዳልሆነ ነው። ቺካጎ ቮትስ የተሰኛ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ጄን ዲን እንደሚሉት ወረቀቶቹን ሲሞሉ በርካታ ስህተቶች እየተፈፀሙ መሆናቸውን ነው። ከእስር ቤት ውጭ ያሉ በፖስታ የሚመርጡ ሰዎች ለምርጫ ከመመዝገብ ጀምሮ፣ ለምርጫ ቦርዱ መላክ፣ መርጦ መላክ የመሳሰሉ የተወሳሰቡ ሂደቶች ያጋጥማቸዋል። በዚህም ሁኔታ በማረሚያ ቤቶች የአቅርቦትና የገንዘብ ችግርም አጋጥሟል ተብሏል፥። ቺካጎ ቮትስ በአንድ ጊዜ 5 ሺህ እስረኞችን መያዝ ከሚችለው ሲቲ ኩክ እስር ቤት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው ሲሆን ከ2017 ጀምሮም 5 ሺህ ታራሚዎች ድምፃቸውን እንዲሰጡ ለማስቻልም መመዝገብ ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ በዚህ እስር ቤት የሚገኙ ታራሚዎችም አሜሪካ በዘንድሮው በምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በአካል ድምፃቸውን መስጠት እንዲያስችላቸው አዋጁ እንዲቀየር ግፊት አድርጓል። ታራሚዎች ባሉበት መምረጥ የሚያስችላቸው ማሽንም በእስር ቤቱ ተገጥሞም በተሳካ ሁኔታ መምረጣቸውንም ዲን ይናገራሉ። ሆኖም ሁሉም እስር ቤቶች እንደ ኩክ እስር ቤት ከተሟጋቾች ጋር በመቀናጀት አይሰሩም። በማረሚያ ቤቶችም የሚያጋጥሙ እክሎች በርካታ ናቸው። በርካታ ግዛቶች በመራጭነት ለመመዝገብ ብሔራዊ መታወቂያና ቋሚ አድራሻ ይፈልጋሉ። ነገር ግን በርካታ እስር ቤቶች ታራሚዎች ገና ሲገቡ መታወቂያቸውንም ሆነ የመንጃ ፈቃዳቸውን ይነጥቋቸዋል። ብዙዎቹ ታራሚዎች ቋሚ የሆነ አድራሻ የላቸውም። ምንም እንኳን ድምፃቸውን መስጠት የሚችሉ ታራሚዎች ቢኖሩም በባለስልጣናትና በማረሚያ ቤቶች አስተዳዳሪዎች "እብሪተኝነት" ከመምረጥ ይሰናከላሉ። ከዚህም በተጨማሪ የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ታራሚዎች መምረጥ እንደሚችሉም ከግምት ውስጥ አያስገቡትም ወይም መብታቸውን ለማክበርና ለመተባበር ፈቃደኛ አይደሉም። በሌላ መልኩ ስናየው በርካታ አሜሪካውያን ለመምረጥ ፍላጎቱ የላቸውም። በ2016 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተመዘገቡት 61.4 በመቶ ናቸው የመረጡት። ለተሻለ ፍትሃዊ ስርአት የሚሰራው ሴንቴንሲንግ ፕሮጀክት ድርጅት ከፍተኛ አማካሪ ማርክ ማውየር እንደሚሉት ከበርካታ አስርት አመታትም ጥናት በኋላም ቢሆንም በእስር ቤት ያሉ ታራሚዎች ምርጫው ቢኖራቸው ምን ያህሉ ድምፃቸውን መስጠት ይፈልጋሉ ለሚለው ግልፅ ያለ መረጃ የለም። እሳቸው ቁጥሩ ዝቅ ያለና 10 በመቶ ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። ጄን ዲን በበኩላቸው ከእስር ቤቶች የሚመጣው የመራጮች ቁጥር ዝቅተኛ መሆን ታራሚዎች ግድ አይሰጣቸውም ወይም ፍላጎት የላቸውም የሚለውን አያሳይም ይላሉ። በሚሰሩበት ኩክ ማረሚያ ቤት የመራጮች ማሽን ከመገጠማቸው በፊትም በርካታ የሴት ታራሚዎች መምረጥ እንደሚፈልጉ መረዳታቸውን ይናገራሉ። "በሴቶች ማረሚያ ቤት ውስጥ ካሉት 74 በመቶዎቹ መምረጥ እንደሚፈልጉ ነግረውኛል" ይላሉ። ጊዜውም ሲደርስ አንዳንዶች በጊዜ በመለቀቃቸው፣ አዳዲስ ታራሚዎች በመምጣታቸው፣ የመራጮች የምዝገባ ፎርሞች መጥፋት ወይንም በትክክል አለመሞላት ጋር ተያይዞም የተጠበቀውን ያህል ሳይሆን 20-40 የሚሆኑ ብቻ ናቸው መሞላት የቻሉት። ይህንንም በማየት በርካቶች መምረጥ ቢፈልጉም በሚፈጠሩት ተደራራቢ እክሎች ምክንያት ለታራሚዎች መምረጥ ፈታኝ እንዳደረገው ነው። ሂደቱንም ማቅለል እንደሚቻልም ኩክ እስር ቤት ማሽኖችን በመግጠም ምሳሌ መሆኑን ይናገራሉ። በተለይም በርካታ እስረኞች ጥቁርና ላቲን አሜሪካውያን ወይም ደግሞ ከነጩ ውጭ ያለው ማህበረሰብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞም ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረሰ ነው። በአሜሪካ ያሉ ጥቁር አሜሪካውያንም ሆነ ላቲን አሜሪካውያን የህዝብ ቁጥር አነስተኛ ቢሆንም ግማሽ የሚሆነውን የማረሚያ ቤት ቁጥር ይዘዋል። የአገሪቱ የፍትህ ስርአት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ፖሊስ በማሰማራት፣ በቀላልና ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ለእስር በመዳረግና በሌሎች ምክንያቶች ጥቁር አሜሪካውያንና ላቲን አሜሪካውያን እንዳይመርጡ ሆነዋልም ተብሏል። ሆኖም በርካታ ተሟጋቾች እንደሚሉት በማህበረሰቡ ዘንድ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው ዳኞች፣ የፖሊስ ኃላፊዎችና አቃቤያነ ህጎች በተመራጭነት ከመቅረባቸውም አንፃር በቀጥታ መታገል የሚቻለው በማንኛውም መንገድ ድምፅ ሲሰጥ ብቻ ነው። ድምፅ በመስጠት ብቻ ነው ኢ-ፍትሃዊነትንም ሆነ ለቦታው ትክክለኛ ያልሆኑ ሰዎችን መታገል የሚቻለው ይላሉ። ሬናልዶም በራሱ ተነሳሽነት መራጮችን እየቀሰቀሰ ይገኛል። "ባገኘሁትም አጋጣሚ የመራጭነት እድል አግኝታችሁ እንዴት አትመርጡም እላለሁ?" በማለት ይጠይቃል። ሬናልዶም በመራጭነት ሲሳተፍ ለሁለተኛ ጊዜው ነው። በመጀመሪያው ምርጫ ወቅት ገና የፍርድ ሂደቱን እየጠበቀ የነበረበት 1980ዎቹ ሲሆን በወቅቱም ቺካጎ የመጀመሪያውን ጥቁር ከንቲባ ሃሮልድ ዋሽንግተን የመረጠችበት ወቅት ነው። "በእስር ላይ ናችሁ፤ እስር ቤት መራር እንደሆነ እናውቃለን። አስተዳደሩ ወደዳችሁም አልወደዳችሁም በህገ መንግሥቱ የተሰጣችሁ መብት ስለሆነ እንመርጣለን በሉ። ይህ ማህበራዊ ግዴታችሁ ነው" በማለት ለታራሚዎች መልእክቱን አስተላልፏል።
news-50922555
https://www.bbc.com/amharic/news-50922555
የባህር ዳር ጫት ከገበያ ሊጠፋ ነው?
ከባህር ዳር 25 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ዘጌ ነዋሪ የሆነው ሙላት ኢብራሂም ለ12 ዓመታት የመከላከያ ሠራዊት አባል ሆኖ አገሩን ሲያገለግል ቆይቷል። ከ1991 እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ።
ከዚያ በኋላም ማረሻ እና ሞፈር ይዞ እርሻ ላይ በመሠማራት ሌላኛውን የህይወቱን ምዕራፍ ጀመረ። ጫት ማምረት ደግሞ ቀዳሚ ሥራው ሆነ። ካለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እና ሌሎች ሲሠሩት መመልከቱ ከሌሎች የግብርና ዘርፎች ይልቅ ወደ ጫት እንዲያዘነብል አድርጎታል። "ከውትድርና ስመጣ ህብረተሰቡ ጫት ነበር የሚተክለው። እኔም ከዚህ በኋላ ነበር ወደ ጫት ማምረት የገባሁት" ሲል ያስታውሳል። • ቴህራን ጥቃት ከፈፀመች በሚል አሜሪካ 52 የኢራን ተቋማት ላይ መሳሪያዋን አነጣጥራለች ባለፉት ዓመታት ጫት እያመረተ ቢቆይም ያሰበውን ያህል ውጤታማ መሆን ግን አልቻለም። የሥራው አድካሚነት፣ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሄድ እንዲሁም በኅብረተሰቡ ዘንድ የጫት ሱስ መስፋፋቱ ሌሎች አማራጮችን እንዲያይ ግድ አለው። "ጓሮውን ጨምሮ ሁሉም አካባቢ በጫት የተሸፈነ ነው። ሌላ የተተከለ ነገር የለም። ጫት ተሽጦም ለኅብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት የለም- ከሱስ ባለፈ ማለት ነው። ከጫት የሚገኘው ገንዘብ ጎጂ ባይሆን አዋጭም አይደለም። ሆኖም ጫት ማምረት ላይ ከተሠማራህ ሌላ ለመስራት ያስቸግራል። ሁሌም ተከታተሉኝ ይላል" ሲል ሙላቱ ያስረዳል። • ጫት የአእምሮ ጤናን እንደሚጎዳ ጥናት አመለከተ በአካባቢው በግብርና ሥራ ከተሠማሩት አንዱ የሆነው ኡመር አልቃድርም በዚህ ሃሳብ ይስማማል። ከቤተሶቼ ባገኘሁት ማሳ ላይ ጫት በማምረት ወደ ግብርና እንደገባ በመጥቀስ፤ ለስምንት ወይም ለአስር ዓመታት አካባቢ ጫት ለማምረት ደክሟል። ጫት "ብዙም ዋጋ የለውም። ታገኛለህ፤ ሠራተኛ ላይ ታወጣለህ። ብዙ ልፋት እና ወጪ አለው። ትል የሚበላው አለ። ሌላ ሥራ መሥራት አይቻልም። ልፋት ብቻ ነው። ወጣቱም ወደዚህ ሱስ ገብቷል" ይላል። ጫትን በሙዝ አሁን አሁን ግን ሙላትና ኡመርን የመሳሳሉ ጫትን የሚያመርቱ ሰዎች ፊታቸውን ወደሌሎች ምርቶች እያዞሩ ነው። በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የግብርና መምሪያ የዘጌ 01 ቀበሌ የግብርና ጽህፈት ቤት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አድማሱ ተካ እንደሚሉት ጫቱን በሌላ ተክል የመቀየር ሃሳብ በአብዛኛው ከአካባቢው ፍላጎት የመነጨ ነው። "ጫት ሥራ በማስፈታት ያቦዝናል፣ ህይወትንና ጤናን ያቃውሳል። የአካባቢው ነዋሪዎች ጫት ለወጣቶች ጠንቅ በመሆኑ መጥፋት አለበት እያሉ ነው። ጫት አይጠቅምም ለዚህ መጥፋት አለበት" ማለታቸውን ያስታውሳሉ። ለዚህ ደግሞ የተመራጭ ተደርጎ የታሰበው አካባቢው ላይ የተሻለ ምርታማ ሆነው ኅብረተሰቡን የሚጠቅሙ እንደሙዝ፣ አቮካዶ፣ ቡና እና የመሳሰሉትን ማምረት ሆነ። • ጫትን መቆጣጠር ወይስ ማገድ? ይህንን ለማድረግ ደግሞ የግብርና ባለሙያዎች እና አርሶ አደሮች አርባ ምንጭ ድረስ በመሄድ በአካባቢው ውጤታማ ስለሆነው የሙዝ እርሻ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል። "አርባ ምንጭ ድረስ አርሶ አደሮችን ጭምር ይዘን ሄድን ነበር። የሙዝ ምርቱ በጣም የተለየ ነው። መኪና እየገባ ምርቱን ለገበያ ያቀርባል" የሚሉት አቶ አድማሱ ተካ ይህንን በአርዓያነት በመከተል በአካባቢያቸው ተግባራዊ ለማድረግ እንደወሰኑ ይናገራሉ። በዘጌ 01 ቀበሌ በርካታ አርሶ አደሮች በጫት ተሸፍነው የነበሩ ማሳዎቻቸውን ሱስ ከሚያስዝ ወደ ሚጠቅም ተክል በመቀየር ላይ ናቸው። አሁን ሙዙ አድጎ ለፍሬ ሲያፈራ ጫቱን በማስወገድ ከሙዙ በመጠቀም ላይ ናቸው። አርባ ምንጭ ሄደው እንደተመለከቱት ማሳቸው ድረስ መኪና ገብቶ ምርታቸውን ለገበያ የሚቀርብበት መንገድን እየፈለጉ ነው። "እኛም ማሳው አፍርቶ ሁለት ጎጥ ሙሉ ሙዝ ሆኖ በመኪና በመጫን አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን ነው የምንፈልገው። ጫት ለልጅ ማታለያ አይሆንም። ሙዝ ግን ለሰውነትም ገንቢ ነው" ይላሉ አቶ አድማሱ። ጫትን ቀስ በቀስ ማስወጣት አቶ ሙላት ኢብራሒም በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ የአትክልት እና ፍራፍሬ ባለሙያ ናቸው። የጫት ማሳን በአትክልትና ፍራፍሬ የመቀየር ሥራ በሁለት መንገድ እየተሠራ ነው ይላሉ። "አንደናው የጫት ማሳ የሌላቸው ሙሉ ለሙሉ ወደዚያ ሳይገቡ ወደ ሌሎች አትክልት እና ፍራፍሬዎች እንዲያመሩ ማድረግ ነው። ሁለተኛው፤ የተከሉት ደግሞ ከጫቱ ወጥተው አትክልት እና ፍራፍሬ እንዲያመርቱ ለማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ ስልጠና ይሰጣል" ይላሉ። አቶ አድማሱ እንደሚሉት ጫትን በጊዜ ሂደት ወደ ሙዝ መቀየር ጥረት እየተደረገ ነው። ለዚህም መጀመሪያ ጫቱን ሙሉ ለሙሉ ሳያጠፉ አልፎ አልፎ ሙዝ እንዲተክሉ በማድረግ ቀስ በቀስ ለውጥ እየተደረገ ነው። • "ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም" ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ በዚህ ዘዴ ወደ ሥራው የሚገቡ አርሶ አደሮች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል። "ይሄንን ከሞከርን አንድ አመት ሊሆነን ነው" የሚሉት አቶ አቶ አድማሱ "ሰባት አርሶ አደሮች ሙሉ ለሙሉ ጫት አጥፍተው በሙዝ ተክተዋል። በርካቶች ደግሞ ጫት መሃል ሙዝ የተከሉ አሉ። ወደፊት ጫት ይጠፋ እና ሙዝ ቦታውን ይይዛል።" ሌሎች ደግሞ ሙዝን በጫት ተክል መሃል የተከሉ ሲሆኑ ከሁለት ዓመት በኋላ አየር ንብረቱም ስለሚመች ሙሉ ለሙሉ በሙዝ የሚተካ ይሆናል። በዚህ ሂደትም ጫት ለሙዝ ቦታ እየለቀቀ ይሄዳል ይላሉ። ጫቱ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋም ከፍተኛ ለውጥ በአካባቢው እየታየ መሆኑን በመጥቀስ "በቀበሌው ከአምስት እስከ ስድስት ሔክታር የሚሆን የጫት ማሳ ነበር። ከሁለት እስከ ሦስት ሔክታር የሚሆነው አሁን ከጫት ነጻ ሆኖ ሙዝ ብቻ ለምቶበታል" ሲሉ አቶ አድማሱ ያስረዳሉ። የሙዝ ገቢ ከጫት ይበልጣል? ጫቱን በሙዝ ተክል በመቀየራቸው ሙላትና እሱን የመሰሉ አርሶ አደሮች የተለያየ ጥቅም በማግኘት ላይ እንደሆኑ ይጠቅሳሉ።"አሁን ምርት እያገኘን ለገበያ እያቀረብን ነው። ምርቱም ጥሩ ነው" ይላል ሙላት። ኡመርም በበኩሉ "ወደ ሥራ ከገባን ሁለት ዓመት ሆነን። ለማልማት አንድ ዓመት ፈጀብን። በሁለተኛው ዓመት አፍርቷል። አሁን ጥሩ ነው። ለህብረተሰቡ እዚሁ እናቀርባለን። ሙዝ ከቀጸደቀ እና ካደገ በኋላ አልፎ አልፎ መንከባከብ እንጂ አድካሚ አይደለም" ይላል። ብዙዎች ከጫት የሚገኘው ገቢ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ወደ ሥራው እንደሚገቡ ቢጠቅሱም እነሙላት ግን ከሙዝም ጥሩ ገቢ ማግኘት እንደሚቻል ይናገራሉ። "ከጫት አንጻር በየሳምንቱ ወይም ሁለት ሳምንት የተወሰነ የምታገኘው ነገር አለ። ወጪውም በዚያው ልክ ነው። ሆኖም ግን ሙዙ ሁሉም አፍርቷል። ተረካቢ ስናገኝ ቆንጆ ገቢ አለው። እስካሁን እዚሁ እየሸጠን ነው። የበለጠ ገበያ ቢኖር ደግሞ አዋጪ ነው" በማለት የሙዝ ምርት ሥራው ስለማይበዛ ሌላ ነገርም ለመስራት እድል እንደሚሰጥ ሙላት ይገልጻል ። ኡመር አልቃድር በበኩሉ "እዚህ አካባቢ የገበያ ትስስር አልተፈጠረም። [ሙዝ በኪሎ] ባህር ዳር ላይ 30 እና 40 ብር ሆኖ እዚህ ከ20-25 ብር እንሸጣለን። ትስስር ከተፈጠረ እኛም እንጠቀማለን። ሰዉም ከእኛ ልምድ ይወስዳል" ሲል የገበያ ዕድሉ ከተሻሻለ የሚገኘው ገቢም እንደሚጨምር ያምናል። ከሙዝ ምርቱ ባሻገር የሙዝ ችግኝ ማዘጋጀቱም ሌላ የገቢ እድልን እንደሚፈጥር አቶ አድማሱ ይናገራሉ፤ "አርሶ አደሮቹ ባለፈው ሁለት መኪና ችግኝ ሸጠዋል። በአግባቡ ከተሠራ በኢኮኖሚ ረገድ ሙዝ አዋጪ ተክል ነው። የጫት እና የሙዝን ማሳ ብናይ ከአንድ የሙዝ ተክል እንኳን ከ200 እስከ 250 ፍሬ ሙዝ ይገኛል። ይኼንን ወደ ሂሳብ ስንቀይረው ሰፊ ልዩነት አለው።" ከውትድርና ወደ ግብርና የገባው ሙላት፤ ጥሩ ገቢ አገኝበታለሁ ያለው የጫት ተክል ከአድካሚነቱ ባሻገር የጠበቀውን ያህል ገንዘብ ካለማስገኘቱ ባሻገር ወታቶችን በሱስ እንዲጠመዱ ምክንያት መሆኑ ስላሳሰበው ፊቱን ወደ ሙዝ ምርት በማዞር በአካባቢው ላሉ አርሶ አደሮች አርዓያ ለመሆን እየተጋ ነው። "ከዚህ በኋላ ጫት ካለው ጎጂነት አንጻር በሌላ አትክልት ሙሉ ለሙሉ መቀየር አለበት። ጥቅሙም ለራስ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው ኅብረተሰብ ና ለአገርም ነው" በማለት ሙዝ ማንም ለጉዳት ሳይዳርግ አምራቹንም የሚጠቅም ምርት እንደሆነ ካገኘው ጥቅም ተነስቶ ሙላት ይናገራል። "የጫት ማሳዬን ወደ ሙዝ ሙዝ መቀየሬ የተሻለ ነገር ለማግኘት አስችሎኛል። ጫት በብዙ ሥራን የሚጠይቅና አድካሚ ነው። ሙዝ ግን ሥራው ቀለል ያለ ስለሆነ ሌላ ሥራን ለመስራት እድልን ይሰጣል" ሲል ያገኘውን ጠቀሜታ በመጥቀስ ያጠቃልላል። ጫት ሁሉ ነገሯ የሆነችው ከተማ
42999950
https://www.bbc.com/amharic/42999950
በኢትዮጵያ የአዕምሮ ህሙማን ሰብዓዊ መብት እየተጣሰ ይሆን?
በኢትዮጵያ ውስጥ የአእምሮ ህመምተኝነት በባህሉም ሆነ በእምነት ከሰይጣን ወይም መጥፎ መናፍስት ጋር የተቆራኘ ነው ተብሎ ይታመናል።
በተለይም ከበድ ያለ የአዕምሮ ህመም ያለባቸው ብዙዎችም መደብደብ፣ መንገላታት፣ መታሰር እንዲሁም በአጠቃላይ ከማህበረሰቡ መገለል ይደርስባቸዋል። ብዙዎች ሲታመሙም ሃይማኖታዊ ፈውሶችን እንደ ፀበል፣ ፀሎት እንዲሁም ማህበረሰቡ አዋቂ ብሎ የሚፈርጃቸው ጋር ይሄዳሉ። ወደ አዕምሮ የህክምና ማእከላት የሚመጡትም በነዚህ ቦታዎች ፈውስ ካላገኙ እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሳይካትሪ ትምህርት ዘርፍ ክፍል አሶሺየት ፕሮፌሰር እንዲሁም አማኑኤል ሆስፒታል ለ12 ዓመታት ሀኪም ሆነው ያገለገሉት ዶክተር ዮናስ ባህረ-ጥበብ ይናገራሉ። ምንም እንኳን ከ360 በላይ የአዕምሮ ህመም እንዳለ የሚናገሩት ዶክተር ዮናስ ማህበረሰቡ የአዕምሮ ህመም ብሎ የሚጠራው በራሳቸው ወይም በሰዎች ላይ ጠንቅ ማድረስ ሲጀምሩ እንደሆነ ይናገራሉ። ህመማቸው ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ሰዎችም ማህበረሰቡ ራሳቸውም ላይ ሆነ ሌላው ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸውም በሚል ይታሰራሉ፣ ይደበደባሉ። ይሄም የሚሆነው ለአዕምሮ ህሙማኑ ኃላፊነት የሚወስዱ ተቋማት እንዲሁም የመንግሥት አካላት ስለሌሉ እንደሆነ ዶክተር ዮናስ ይናገራሉ። "በነዚህ ሂደቶች የአዕምሮ ህሙማኑ ጉዳት ይደርስባቸዋል፤ ይራባሉ፣ ይጠማሉ፣ የሚታሰሩበት የእግር ሰንሰለት ከርክሯቸው ኢንፌክሽን ሊፈጥር ይችላል። መደብደብም ይኖራል" ይላሉ። ይህ በማህበረሰቡ ያለው የአዕምሮ ህሙማን አያያዝም በአዕምሮ ህሙማን ማዕከላትም እየተደገመ እንደሆነ የህግ ባለሙያው አይተነው ደበበ "ቢሀይንድ ክሎዝድ ዶርስ ዘ ሂውማን ራይት ኮንዲሽንስ ኦፍ ፐርሰንስ ዊዝ ሜንታል ዲስኤብሊቲ ኢን ኢትዮጵያን ሳይካትሪክ ፋሲሊቲስ" በሚለው የድህረ ምረቃ መመረቂያ ፅሁፉ ውስጥ ይጠቅሳል። የአእምሮ ህሙማን ምንም አይነት የህግ ከለላ የላቸውም የሚለው አቶ አይተነው የጤና ማእከላት ውስጥ የሚገቡት ጥቂቶቹ የአዕምሮ ህሙማን ታስረው እንዲሁም የህክምና አሰጣጡም ሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነው ይላል። ጥናቱ አማኑኤል ሆስፒታልና የገፈርሳ የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከልንም አካቷል። አከራካሪው ኤሌክትሮ ኮንቨልሲቭ ቴራፒ ምንም እንኳን አንዳንድ የአዕምሮ ህሙማን ራሳቸውን የሚያውቁ እንዳሉ ሁሉ ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን የማያውቁ የአዕምሮ ህመምተኞች አሉ። እነዚህ ህሙማን መድሀኒት፣ምግብም ሆነ መጠጥ የማይወስዱበት ደረጃ ላይ በሚደርሱበት ወቅት በጤና ማዕከላት ውስጥ ከማደንዘዣ ጋር የኤሌክትሪክ ሾክ ይሰጣቸዋል። የኤሌክትሪክ ሾኩ ከተሰጣቸው በኋላ እንደሚነቁም ምግብ ሊመገቡ እንደሚችሉ አይተነው ይናገራል። ማደንዘዣ ተጨምሮ ኤሌክትሪክ ሾክ በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ኤሌክትሪክ ስለሚተላለፍ ዘላቂ የሆነ የማስታወስ ችግር እንደሚገጥማቸው አቶ አይተነው ይናገራል። የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናቶችን የሚጠቅሰው አይተነው "1/3 የሚሆኑት በኤሌክትሪካል ኮንቨልሲቭ ቴራፒ የታከሙ ሰዎች ዘላቂ የሆነ የመርሳት ችግር እንዲሁም የጭንቅላት ጉዳት ደርሶባቸዋል" ይላል። በተቃራኒው ዶክተር ዮናስ "ኤሌክትሮ ኮንቨልሲቭ ቴራፒ ህይወትን ሊታደግ የሚችል ህክምና ነው፤ ያለሱ መስራት በጣም አስቸጋሪና ፈታኝ ነው፤ ምክንያቱም ህመምተኛው ለወራት አልበላም አልጠጣም ይላል፤ ካልጋም ላይወርድ ይችላል፤ የሰውነት አቅም እየደከመ ደሙም እየወረደ ይመጣል። ሊሞትም ይችላል" ይላሉ። ዶክተር ዮናስ እንደሚናገሩት የተለያዩ የምርምር ውጤቶች ይህ ህክምና ስለ አዳኝነቱ ብዙ እንደተባለለት ነው "ሁለት ወይም ሶስት ቴራፒ ሲሰጠው ህመምተኛው መብላት እንዲሁም መናገር ይጀምራል" ይላሉ። ይህ ቴራፒ ከማደንዘዣ ጋር እንደሚሰጥ የሚናገሩት ዶክተር ዮናስ ያለማደንዘዣ ከሆነ ግን የአጥንት መሰንጠቅ እንዲሁም ከፍተኛ የራስ ህመምም እንደሚያስከትል ይገልፃሉ። ከማደንዘዣም ጋርም ሆነ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የማስታወስ ችግር እንዲሁም የራስ ህመም የጎንዮሽ ጉዳቶቹ እንደሆኑ ዶክተር ዮናስ ይናገራሉ። "ጉዳቱንና ጥቅሙን አመዛዝነን ነው እነዚህን ህክምናዎችን የምናዘው፤ ሰውየው አይበላም አይጠጣም ህይወቱ አደጋ ላይ ነው፤ ስለዚህ ስለ ራስ ሀመም ሆነ ጊዜያዊ መዘንጋትን አናስታውስም የሞት አፋፍ ላይ ላለ ሰው ዋናው ነገር ህይወትን ማዳን ነው" ይላሉ። በኤሌክትሮ ኮንቨልሲቭ ቴራፒ የታከሙ ኢትዮጵያውያን የአዕምሮ ህሙማንን ጥናቱ ያላካተተ ሲሆን በኢትዮጵያ ያሉ የአዕምሮ ህሙማን ህክምና ማዕከላት ዶክተሮች ግን የጎንዮሽ ጉዳቱን ቢረዱትም ምንም አይነት የማቆም ዕቅድ እንደሌላቸው አይተነው ይናገራል። የተለያዩ ምርምሮችን ያካተተው ጥናቱ የናቷን ሞት ማስታወስ የማትችል ህመምተኛና በከፍተኛ ሁኔታ የአዕምሮ ጉዳት የደረሰባቸውና ዘላቂ የሆነ የመርሳት ችግር ያጋጠማቸው ብዙ እንደሆኑ ይናገራል። በአጠቃላይም ይህንን ህክምናን "በሰው ልጅ ላይ ኢሰብአዊ የሆነ ስቃይና እንግልት" በማለት ይገልፀዋል። በአለም አቀፍ ህክምናው ዘርፍ ቴራፒውን በመጠቀም ላይ ያለው አቋም የተከፋፈለ ሲሆን የሚቃወሙትም እንዳሉ በተቃራኒው የሞት አፋፍ ላይ የደረሱ የአዕምሮ ህሙማን የሞትና የህይወት ጉዳይ ስለሆነ ከሞት ይህንን ህክምና በመጠቀም ማዳንን ይመርጣሉ። ከዚህ በተቃራኒው የሰብአዊ መብት ተሟጋⶇች ስቃይና እንግልት ስለሆነ መቆም አለበት ይላሉ። "በስቃይና እንግልት መታከም ኢሰብአዊ ነው፤ ህመምተኞቹም ፈቃድ መስጠት የማይችሉበት ሁኔታ ላይ በመሆናቸው የማስታወስ ችግር ወይም የአዕምሮ ጉዳት እንደሚደርስባቸው አያውቁም"ይላል አይተነው። ምንም እንኳን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው ብለው ይህንን ቢያወግዙትም ምርጫው ግን ሞት ወይም ይህንን ህክምና ተጠቅሞ ማዳን እንደሆነ ዶክተር ዮናስ ይናገራሉ። "ይሄ የሞራል ክርክር ነው። አንድን ሰው ቢሞት ይሻላል ወይስ ተሰቃይቶና ተንገላቶ በየትኛውም መንገድ ማትረፍ ይሻላል?" በማለት አይተነው ይጠይቃል። መታሰርና ስቃይ በተለያዩ የጤና ማዕከላት የሚገኙ የአዕምሮ ህሙማንን ሁኔታን እንደመታሰር የሚቆጥረው አይተነው "ህሙማኑ በቤተሰብና በዘመድ ታስረው ወደ ማዕከሉ ቢመጡና ደህና ነኝ ቢሉ ተገደው ይታከማሉ ወይስ? በየጊዜው ስላለው ህክምናና ስለሚደረግላቸው ህክምና የጎንዮሽ ጉዳትስ ምን ያህል ይነገራቸዋል የሚለውን ጥያቄ ይጠይቃል? ምንም እንኳን ፈቃድ መስጠት የማይችሉ ህመምተኞች ቢኖሩም ፈቃድ መስጠት የሚችሉ ግን መጠየቅ አለባቸው ይላል። " ሁሉንም የአዕምሮ ህመምተኞች ዞሬ አነጋግሬቸዋለሁ ሁሉም የሚሉት ፈቃድም እንዳልተጠየቁና ስለ ህክምናቸው እንደማይነገራቸው ነው" ይላል። በአማኑኤልም ሆስፒታልም ሆነ በገፈርሳ እጃቸውንና እግራቸውን ታስረው የሚንቀሳቀሱ ሰዎች እንዳየ የሚናገረው አይተነው ""ኢ-ሰብአዊ ድርጊትም ነው" ይላል። በገፈርሳ ከ20-30 የሚሆኑ ህሙማን በአንድ ክፍል ውስጥ የሚያድሩ ሲሆን በሚጮሁበት ጊዜ "ሌሎች ሻል ያሉ ህመምተኞች" በአንሶላ ያስሩዋቸዋል ወይ ከበር አስወጥተው እንደሚያባርሩዋቸው አቶ አይተነው ይገልፃል። " የአዕምሮ ህሙማኑ ሌሊት ነርስም ሆነ ሀኪምም መጥራት አይችሉም፤ ስለዚህ በሚጮሁበት ጊዜ ከነሱ ሻል ያሉ የአዕምሮ ህሙማን ያስሩዋቸዋል ወይም በሌሊትም ቢሆን እንደሚያባርሩዋቸው ተመልክቻለሁ። ይሄ ሁኔታ ደግሞ አደጋ ላይ ይጥላቸዋል።" ይላል። ዋናው ነገር ደህንነት ነው የሚሉት ዶክተር ዮናስ "በአንዳንድ አጋጣሚዎች ህመምተኞች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው በሚደባደቡበት ወቅትና ሰው በሚያጠቁበት ወቅት ሰዎች ተቆጣጥረው ቢጥሏቸው ወይ ቢታሰሩ የአዕምሮ ህከምና ዕውቀቱ ለሌለው ሰው ስቃይና እንግልት ሊመስል ይችላል" ይላሉ። "ደህንነት መፍጠር የማይቻል ከሆነ አስቸጋሪ ነው፤ ደህንነቱ ግን ከድህነቱና ኢኮኖሚው አንፃር ድብደባና ጥቃት ሊመስል ይችላል። ህመምተኞቹ እስከሚረጋጉ ድረስም ሊታሰሩ ይችላል። ካለበለዚያ በአካባቢው ጉዳት እንዲያደርሱ መፍቀድ ነው" ይላሉ። በመጀመሪያም ህመምተኛውን ለማረጋጋት የሚወሰደው እርምጃ መርፌ መውጋት እንደሆነ የሚገልፁት ዶክተር ዮናስ መድሀኒቱ እስኪሰራ ሶስት ሰዓትም እንደሚወስድ ይገልፃሉ። " በነዛ ሰዓታት ውስጥ ጉዳት ሊደርስ ይችላል። ራሳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ መደረግ አለበት።" ይላሉ ዶክተር ዮናስ ከዚያም በተጨማሪ የግል ህይወታቸው ሙሉ በሙሉ የተጋለጠና እንደነ ገፈርሳ ያሉት ማዕከላት ላይ ሽንት ቤት ሳይቀር በቁጥጥር ነው የሚለው አይተነው። በገፈርሳ ማዕከል 20፣ 30 አመት የቆዩና ከማህበረሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበትም መንገድ አልተመቻቸም ይላል። በገፈርሳ ማዕከል በተለይም ብቻቸውን መንገድ ላይ ሲሄዱ መኪና የተገጩበት፣ጫት ሲገዙም አይተነው እንደተመለከተ ይናገራል። ክፍተት እንዳለ የሚናገሩት ዶክተር ዮናስ ይሄም መንግሥት ቅድሚያ የሚሰጠው ለተላላፊ በሽታዎች እንደ ወባና ኤችአይቪ ኤድስ ስለሆነ ነው። በጤና ማእከላት ብቻም ችግሩ ስለማይፈታ በፀበል ቦታዎች ድብደባዎች እንዲቀሩና በጥምረትም መድሃኒት እንዲሰጣቸውና የምክር አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት እንዲሰጣቸው ማድረግ አስችሏል። "በምዕራባውያን ሞዴል ሳይሆን በአገር በቀል ሁኔታ ህክምናው እንዲሻሻል መደረግ አለበት"ይላሉ። ጨምረውም "በምእራባውያን አይን ሀገሪቷ መተቸት የለበትም፤ ድህነቱ ከግምት ውስጥ መግባት አለበት፤ በመንገድ ላይ ቆሻሻ አጥንት የሚለቅሙ አሉ እነሱን አስሮ መመገብ ምንም ችግር የለውም" ይላሉ ዶክተር ዮናስ። ድህነትም ቢኖር የሰብአዊ መብት መጣስ ድርድር ውስጥ መግባት የለበትም የሚለው አይተነው የአዕምሮ ጤና ህግ ባለመኖሩ ክፍተትን ፈጥሯል የሚለው አይተነው በአዕምሮ ህሙማን ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅ የህግ ማዕቀፍም ሊኖርም ይገባል ይላል።
news-46669934
https://www.bbc.com/amharic/news-46669934
የኤርትራውን ሚኒስትር በጥይት ያቆሰለው መያዙ ተነገረ
የኤርትራ ኃይልና ማዕድን ሚኒስትር ጄነራል ስብሐት ኤፍሬም ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በጥይት ተመትተው እንደቆሰሉና ለከፍተኛ ህክምና ከአገር እንደወጡም ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገለፅ ነበር።
•የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? የኤርትራ መንግሥት በጄኔራሉ ላይ ስለደረሰው ጥቃት ይፋዊ መግለጫ ባይሰጥም በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር አቶ እስጢፋኖስ አፈወርቅ ግን የደረሰውን ጥቃት አውግዘው ሚኒስትሩ እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸው በትዊተር ገፃቸው አስተላልፈዋል። •የኤርትራው ፕሬዚዳንት የሞቃዲሾ ጉብኝት "ስብሐት ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግም እመኛለሁ፤ ይህንን የፈሪዎች ሥራም አወግዛለሁ" ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ቢቢሲ ከኤርትራ መንግሥት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ግን አልተሳካም። •ኤርትራ ካሳ ጠየቀች ደረሰ የተባለው ጥቃት በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ አድብቶ በነበረ አንድ ግለሰብ መፈፀሙንና ግለሰቡም በቁጥጥር ስር እንደዋለ ለቢቢሲ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ከአስመራ አሳውቀዋል። ጄኔራል ስብሐት ለ19 ዓመታት የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን ፤ በመጀመሪያዎቹ የኤርትራ የነጻነት ዓመታት ደግሞ የአሥመራ ከተማ አስተዳደርና የጤና ሚኒስትር ነበሩ። ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም ከሕዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ከፍተኛ አመራሮች አንዱ ሲሆኑ የፖለቲካ ጽህፈት ቤት አባልም ናቸው።
news-41665169
https://www.bbc.com/amharic/news-41665169
የቻይና የዕርዳታ ሚስጢር ሲገለጥ
ቻይና ብዙ ሃገራዊ ጉዳዮችን በሚስጥር በመያዝ ትታወቃለች። አሁን ግን አጥኚዎች ከሃገሪቱ ሚስጥሮች መካከል አንዱ የሆነውን እና ቤጂንግ ለሌሎች ሃገራት በእርዳታ የምትሰጠውን የገንዘብ መጠን ማወቅ ችለዋል።
እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ቻይና የውጭ እርዳታ ተቀባይ ሃገር ነበረች። አሁን ግን ዕርዳታ እና ብድር በመስጠት የረዥም ጊዜ ታሪክ ካላት አሜሪካ ጋር በመፎካከር ላይ ትገኛለች። ለመጀመሪያ ጊዜም ከቻይና ውጭ ያሉ የአጥኚዎች ቡድን አባላት ቻይና ለተለያዩ ሃገራት የሰጠችውን የገንዘብ ድጋፍ የሚያሳይ መረጃ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ማሰባሰብ ችለዋል። በ140 ሃገራት የሚገኙ አምስት ሺህ ፕሮጀክቶች ላይ በማተኮርም፤ ቻይና እና አሜሪካ ለሃገራት በሚሰጡት ድጋፍ በመፎካከር ላይ ይገኛሉ ብለዋል። ሆኖም "በጀቱን በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ እያዋሉት ይገኛሉ። የእነዚህን ሰነዶች ስብስብ የተለያዩ ውጤቶች አላቸው" ሲል የፕሮጀክቱ ዋና አጥኚ ብራድ ፓርክስ ይገልጻል። ብራድ የሚመራውና በቨርጂኒያ ዊሊያምና ሜሪ ኮሌጅ የሚገኘው ኤይድዳታ የምርምር ቡድን፤ ከሃርቫርድ እና ከጀርመኑ ሄደልበርግ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በመሆን ነው ጥናቱን ያጠናቀቀው። የቻይና ሠራተኞች የኢትዮ-ጅቡቲን የባቡር መስመር ሲሰሩ ሚስጥሩን እንዴት ሊደርሱበት ቻሉ? በቻይና መንግሥት ምላሽ ያልተሰጣቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ ኤይድዳታ የራሱን ዘዴ ተግባራዊ አድርጓል። ይፋዊ የኤምባሲ ማስረጃዎችን፤ የቻይናን የእርዳታና የእዳ መረጃዎችን እና ከቻይና ወደ ዕርዳታ ተቀባይ ሃገራት የሚደረገውን የገንዘብ ፍሰት ተጠቅመው ነው ጥናታቸውን ያካሄዱት። አንድ በአንድ የተሰባሰበው መረጃ ሙሉ ቅርጽ ሲይዝ፤ የቻይና መንግሥት ድጋፍ የት እንደደረሰ እና ያመጣውን ለውጥ ሊያሳይ የሚችል ምስል ፈጥሯል። "ዘዴው የማይታወቀውን ዓለም ይበልጥ ይፋ አድርጓል" ይላል ፓርክስ። "የቻይና መንግሥት አንድ ነገርን ለመደበቅ ከፈለገ እኛ አናገኘውም። ሆኖም ቻይና ወደ እርዳታ ተቀባዩ ሃገር የምትለከው ገንዘብ ከፍተኛ ከሆነ መረጃ መውጣት ይጀምራል" ይላል። ቻይና ገንዘብ እንዴት ትሰጣለች? መረጃው በተገኘባቸው ዓመታት ከፍተኛ እርዳታ በመስጠት የሚታወቁት አሜሪካ እና ቻይና ተመሳሳይ መጠን ያለው ገንዘብ ለተለያዩ ሃገራት መስጠታቸው ከጥናቱ ዋነኛ ግኝቶች አንዱ ነው። ገንዘቡን ያከፋፈሉበት መንገድ ግን በጣም የተለያየ ነው። አብዛኛው (93%) የአሜሪካ የፋይናንስ ድጋፍ አሰጣጥ ቀደም ሲል በተለመደው እና በምዕራባዊያን ሃገራት የድጋፍ ስምምነት ትርጉም ውስጥ የሚጠቃለል ነው። የድጋፉ ዋና ዓላማ የተቀባይ ሃገራትን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል የሚሰጥ ነው። ከዚህ ውስጥ አንድ አራተኛ የሚሆነው ቀጥታ ድጋፍ እንጂ ተመላሽ በሚሆን ብድር መልክ የሚሰጥ አይደለም። በተቃራኒው ቻይና ከምትሰጠው ድጋፍ ትንሽ መጠን (21%) ያለው ነው በተለመደው የእርዳታ አሰጣጥ መሠረት ሌሎች ሃገራት ጋር የሚደርሰው። ሌላውስ? "የአንበሳውን ድርሻ" የሚይዘው ገንዘብ ግን በንግድ ድጋፍ መልክ ከወለድ ጋር ለቤጂንግ እንዲመለስ ተደርጎ የሚሰጥ ነው። "ቻይና ከገንዘቧ ላይ ጥሩ ኢኮኖሚያዊ ትርፍ ማግኘት ትፍልጋለች" ሲል ብራድ ፓርክስ ይገልጻል። ገንዘቡስ ምን ውጤት አስገኘ? ሌላኛው የምርምር ቡድኑ ትልቅ ውጤት እንደሚያሳየው ቻይና በተለመደው የእርዳታ አሰጣጥ መንገድ የምትሰጠው ገንዘብ፤ በተቀባይ ሃገራት ዘንድ አስደሳች የኢኮኖሚ ውጤት አስገኝቷል። ለረዥም ጊዜ በቻይና እርዳታ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ለቻይናዊያን ሠራተኞች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እና ለሃገራቸው ትርፍ የቆሙ እንደሆኑ ይታሰብ ነበር። በተጨማሪም በአካባቢው ያሉ ሰዎችን ህይወት በመቀየር በኩል ያላቸው ድርሻ አነስተኛ እንደሆነ ይታመን ነበር። እንደ ጥናቱ ከሆነ ግን ቻይና እንደ ሌሎች ምዕራባዊያን ሃገራት ለልማት የሚረዱ ዕርዳታዎችን ማቅረብ ችላለች። የትኞቹ ሃገራት የቻይናን ገንዘብ እያገኙ ነው? እ.አ.አ ከ2000 ጀምሮ የአፍሪካ ሃገራት ከቻይና ድጋፍ ከፍተኛውን ድርሻ ለማግኘት ችለዋል። ከሴኔጋል ሆስፒታል ጀምሮ እስከ ፓኪስታን እና ሲሪላንካ ወደብ ግንባታ ድረስ ድጋፉ በመላው ዓለም ተከፋፍሏል። እ.አ.አ በ2014 ከቻይና ድጋፍ በማግኘት ሩሲያ ቀዳሚ ስትሆን ፓኪስታንና ናይጄሪያ ተከታዩን ደረጃ መያዛቸውን የኤይድዳታ መረጃ ያሳያል። በተቃራኒው አሜሪካ በቀዳሚነት ድጋፍ የሰጠችው ለኢራቅ፣ አፍጋኒስታንና ፓኪስታን ነው። በቻይና ፋይናንስ ፓኪስታን ወደብ ገንብታለች ቻይና እና አሜሪካ ለሃገራት የሚሰጡት እርዳታ በአብዛኛው ፖለቲካቸውን መሠረት በማድረግ ነው። ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሁለቱም ሃገራት እርዳታ በብዛት የሚሰጡት በተበበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ከጎናቸው ለቆሙ ሃገራት ነው። ለቻይና ቁልፉን ቦታ የሚይዘው ኢኮኖሚ ነው። የኤይድዳታ ጥናት እንደሚያሳየው ቻይና ብድሩ ከነወለዱ እንደሚለስላት በምትፈልግባቸው ሃገራት የወጪ ንግድንና የገበያ ብድርን በማስተዋወቅ ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ሰሜን ኮሪያ የኢኮኖሚ ቀውስ ያጋጠማት ሰሜን ኮሪያ እንድትቋቋም በመርዳት በኩል ቻይና ቀዳሚዋ ሃገር መሆኗ ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። ነገር ግን እንደ ኤይድዳታ አጥኚዎች ከሆነ ባለፉት 14 ዓመታት 210 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ 17 የቻይና ፕሮጀክቶች በሰሜን ኮሪያ መኖራቸውን አስታውቀዋል። ከሰሜን ኮሪያ መረጃ ለማግኘት ከባድ እንደሆነች ብራድ ፓርክስ ይጠቅሳል። ቻይና በገንዘብም ሆነ በተለያየ መንገዶች ለሰሜን ኮሪያ የምታደርገው ድጋፍ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ መረብ ውጭ ነው። የቻይና ገንዘብ ለምን የሚያጓጓ ሆነ? ከ1960ዎቹ እስከ 1990ዎቹ ድረስ ምዕራባዊያን ሃገራት ከፍተኛ የወለድ መጠን ያለው ብድር ለሃገራት ይሰጡ ነበር። ሆኖም ተበዳሪ ሃገራት የተበደሩትን ገንዘብ መክፈል አለመቻላቸው ስትራቴጂው ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል። አስደንጋጭ የሆነው የምዕራባውያን እርዳታ ሞዴል አሁን ተሻሽሏል። "ለታዳጊ ሃገራት ዓላማውን ትርፍ ያደረገ፤ ወለድ ያለው ብድር መስጠት አያስፈለግም የሚል የጋራ መግባቢያ አለ" ይላል ብራድ ፓርክስ። "ቻይና ይህንን የተተው መድረክ ለመሙላት ብቅ ብላለች። መግባቢያው ላይም አልደረሰችም። በዚህም በዝቅተኛ ወይንም በከፍተኛ ወለድ ብድር ትሰጣለች" ብሏል። "ሃገራትም የኢኮኖሚ መቃወስ ሲያጋጥማቸው ወደ ዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም ከማቅናት ይልቅ ቻይናን እየመረጡ ነው" ሲል ያስረዳል። ቻይና ገንዘብ ማበደሯን ትቀጥላለች? ቻይና ከከፍተኛ ወለድ ጋር በምታበድረው ገንዘብ ምክንያት የተበዳሪ ሃገራት ኢኮኖሚ አልተጎዳም። ሃገራቱ የኢኮኖሚ ዕድገትም እያስመዘገቡ አይደለም። አጥኚዎቹ በቀጣዮቹ 10 እና 15 ዓመታት ተበዳሪ ሃገራት ብድሩን መመለስ ስለሚከብዳቸው ይህ ሁኔታ ሊቀየር ይችላል የሚል ፍራቻ አላቸው። ይህ ካጋጠመ ቻይና ስለሁኔታው በድጋሚ ልታስብ ትችላለች። "ምዕራባዊያን እርዳታ ሰጪዎችና አበዳሪዎች የብድራቸው አለመመለስ የፈጠረባቸው አይነት ችግር ከ10 ወይንም 15 ዓመታት በኋላ ሊያጋጥም ይችላል። ይህ ካጋጠመ ደግሞ ቻይና ብድር የምትሰጥበትን ዘዴ ልትቀይር ትችላለች" ይላል ብራድ ፓርክስ። የብሪትሽ ኮሎምቢያ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪው ዢአኦጁን ሊ እንደሚለው ቻይና ብድር የምትሰጥብት መንገድ እየተቀየረ ነው ይላል። ሃገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደ ኤሽያ ኢንፍራስትራክቸር ኢንቨስትመንት ባንክ ባሉ ተቋማት በኩል በማበደር ለዓለም ባንክ ምላሽ እየሰጠች ነው። ቻይና የዓለማችን ቁጥር አንድ አበዳሪ ብትሆን ምን ችግር አለው? ቻይና የምትሰጠው ብድር በመላው ዓለም ተጽዕኖ እንዳለው እሙን ነው። በተለይ ደግሞ ቀደም ሲል አበዳሪ የነበሩ ሃገራት ገንዘብ ከመፍቀዳቸው በፊት ያስቀምጧቸው የነበሩትን መሥፈርቶች እንዲያቆሙ እያስገደደ ነው። ቻይና ከዋና ዋናዎቹ አበዳሪ ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗ ቀደም ሲል አበዳሪ በሆኑት ሃገራት መካከል ያለውን ፉክክር አጠናክሯል ይላል የኢኮኖሚ ባለሙያው ዲዬጎ ሄርናንዴዝ። "አንድ የአፍሪካ ሃገርም በቻይና ስትደገፍ የዓለም ባንክ ለብድሩ የሚያስቀምጠውን መስፈርት ይቀንሳል" ሲል ይገልጻል። ቻይና ድጋፏን በአንድ በመቶ ባሳደገች ቁጥር፤ የዓለም ባንክ ብድር ለመስጠት እንደነጻ ገበያንና የኢኮኖሚ ግልጽነትን ያሉ መሥፈርቶቹን በ15 በመቶ ቀንሷል። አንዳንድ ሃገራት የቻይና መንግሥት ብድርን በመተማመን የዴሞክራሲ ሥርዓታቸው ላይ ለውጥ እያመጡ አይደሉም ሲሉ ይተቻሉ። በተለይ ቀደም ሲል ከምዕራባዊያን ብድር ለማግኘት የሚቀመጡ መስፈርቶች እየቀነሱ መሆናቸውን በመጠቆም። ካምቦዲያ ለዚህ ምሳሌ ናት፤ ዋሽንግተን የምትፈልገውን ነጻ ምርጫ ወደ ጎን በመተው ከቻይና ጋር ጠንካራ ግንኙነት ከፈጠረች በኋላ ነጻ መገናኛ ብዙሃንና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ዘግታለች። የቻይና ድጋፍ የአፍሪካ ሃገራትን ምን ያህል እንደለወጠ ዢአኦጁን ሊ አጥንቷል። ታዳጊ ሃገራቱ በምዕራባዊያኑ እንደመስፈርት የሚቀመጠውን የዴሞክራሲ ማሻሻያ ወደ ጎን በመተው ፊታቸውን ወደ ቻይና አዙረዋል። በዚህም የዴሞክራሲ ለውጥ አዝጋሚ ሆኗል። "ቀደምት አበዳሪ ሃገራት የቻይናን የብድር አካሄድ ይተቻሉ። የአፍሪካ ሃገራት በበኩላቸው ብድሩን በጸጋ ተቀብለዋል ወይንም አዲስ አማራጭ ስላላቸው ደስተኞች ናቸው" ይላል ሊ።
news-55584060
https://www.bbc.com/amharic/news-55584060
አሜሪካ ፡ 228 ዓመት ያስቆጠረው የካፒቶል ሒል ኪነ ሕንጻ አጭር የሕይወት ታሪክ
አሜሪካኖች ዲሞክራሲያችሁን በቃላት ሳይሆን በሕንጻ ግለጹበት ብትሏቸው ዋሺንግተን ዲሲ ይዘዋችሁ ይሄዳሉ፤ ካፒቶል ሒል ይዘዋችሁ ይገባሉ።
ያለ ምክንያት አይደለም። ካፒቶል ሒል የዲሞክራሲ ጽንሰ ሐሳብ በግብርም በሐሳብም የያዘ ሕንጻ ስለሆነ ነው። አንዳንድ ጸሐፊዎች ካፒቶል ሒልን "የዲሞክራሲ ቤተ መቅደስ" ብለው የሚጠሩት ለዚሁ ነው። ዲሲ የመንግሥት መቀመጫ ከተማ ናት። አሜሪካ በመንግሥታዊ ቅርጽ ስትወለድ ከፊላደልፊያ ወደ ዲሲ ዞረች። የአሜሪካ የመንግሥት መቀመጫን በአንድ ሕንጻ ማመላከት ግን ከባድ ነው። ምናልባት ለዚህ ቀረብ የሚለው ካፒቶል ሒል ነው። ካፒቶል ሒል ለአሜሪካ 4 ኪሎ እንደማለት ነው፤ በግርድፉ። የላዕላይና የታህታይ ምክር ቤቶች ፓርላማ ሕንጻ የሚገኘው እዚህ ነው። የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚገኘውም በዚሁ ግቢ ነው። ኮንግረስ ላይብረሪ እዚህ ኮረብታ ላይ ነው። ዝርዝሩ ብዙ ነው። ይህ ሕንጻ ብዙ ታሪክ የተሸከመ ነው። ለዚህም ነው በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚጎበኙት። ለዚህ ነው የፖለቲካ ብቻ ሳይሆን የቱሪዝም መዳረሻም የሆነው። ከሕንጻዎቹ ንጣትና ምስስሎሽ የተነሳ ዋይት ሐውስና ካፒቶል ሒል አንድ የሚመስሏቸው ብዙ ናቸው። በሁለቱ ሕንጻዎች መሀል ግን የሁለት ማይል ወይም የ3.2 ኪሎ ሜትር ርቀት አለ። የግብርም ልዩነት አለ። ዋይት ሐውስ የአስፈጻሚው መሥሪያና ማደርያ ነው ብንል ይሻላል። በካፒቶል ሒል ግን ሕግ አውጪዎች ይበዙበታል። ዋይት ሐውስ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መኖርያ ቤትና ጽሕፈት ቤትን አጣምሮ የያዘ ነው። ከፕሬዝዳንቱና ከ15ቱ የካቢኔ አባላት ጋር የተያያዙ፣ ረዳቶችና የረዳት ረዳቶችን ጨምሮ በርካታ የአስፈጻሚው አካላት አሉበት። ምዕራብና ምሥራቅ ክንፍን ይዞ የኦቫል ቢሮን አቅፎ 400 የሚሆኑ ሠራተኞች ፕሬዝዳንቱን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለማገዝ በ6 ወለል ውስጥ የተቀመጡ 132 ክፍሎች ያሉት ሕንጻ ነው - ዋይት ሐውስ። ካፒቶል ሒልና ዋይት ሐውስን በመጠን ማነጻጸር ትክክል አይደለም። ካፒቶል ሒል እጅግ ግዙፍ ሕንጻ ነው። በውስጡ የሚገኘው ኮንግረስ ቤተመጻሕፍት የተሸከመው 38 ሚሊዮን መጻሕፍት ብቻ ስለ ካፒቶል ሒል ግቢ ግዝፈት አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ካፒቶል ሒል መቼ ተገነባ? ይህን ሕንጻ ጆርጅ ዋሺንግተን ነው አምጠው ያዋለዱት። ለመንግሥት መቀመጫነት ዋሺንግተን ዲሲን መረጡ። የመጀመርያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዋሺንግተን የመንግሥት መቀመጫ ዲሲ ውስጥ እንዲሆን ሲወስኑ አንድ ኮረብታ ታያቸው። የጀንኪንስን ኮረብታ። በዚያች አነስተኛ ኮረብታ ላይ የሚቀመጥ ግዙፍ ሕንጻ አሰቡ። በርከት ያሉ ንድፎች ቀርበው ነበር። የዶ/ር ዊሊያም ቶርተን ንድፍ ቀልባቸውን ሳበው። ለኪነ ሕንጻው መጀመሪያ የተጨነቀው ሰው ዶ/ር ዊሊያም ቶርተን ይባላል። የእሱ አእምሮ የፈጠረው ንድፍ ነው የጆርጅ ዋሺንግተንን ቀልብ የገዛው። በመስከረም 18/1793 (እአአ) ጆርጅ ዋሺንግተን እዚህ ኮረብታ ላይ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ። ሆኖም ግንባታው በግንባታ እቃዎች አቅርቦት አለመኖርና በሰለጠነ የሰው ኃይል ማነስ ምክንያት በታሰበው ጊዜ ሊጀመር አልቻለም። ስለዚህ ለጊዜው አንድ ክንፍ ሕንጻ ብቻ ቢገነባ ይሻላል በሚል የሰሜን ክንፍ ሕንጻ ሥራው ተጀመረ። ይህም መሠረት ድንጋዩ በተጣለ በ3ኛ ዓመቱ መሆኑ ነው። ይህ የሰሜን ክንፉ ሕንጻ ሲገባበት 3ኛው ወለል ጭራሽ ያልተጠናቀቁ ብዙ ክፍሎች ይቀሩት ነበር። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የኮንግረስ ላይብረሪ ወለል፣ የዲስትሪክ ኦፍ ኮሎምቢያ ፍርድ ቤት ወለል በ1800 አካባቢ ተገባበት። በ1803 ኮንግረስ የካፒቶል ሒል ግንባታ እንዲጠናቀቅ የሚያስችል በጀት አጸደቀ። በ1811 የደቡብ ክንፍ ሕንጻ ተጠናቀቀ። ደቡባዊ ሕንጻው የሕግ አውጪዎችን አዳራሽ አጠናቆ አገልግሎት ጀመረ። ሆኖም በ1012 ጦርነት ነበር። የቀሩትን ሕንጻዎች ለመገንባትም በጦርነቱ የተነሳ ገንዘብ ጠፋ። ጦርነቱ ቀጠለና በነሐሴ ወር 1814 የብሪታኒያ ወታደሮች ሕንጻውን እሳት ለቀቁበት። በአጋጣሚ ከፍተኛ ዝናብ በመዝነቡ እሳቱ ጠፍቶ የተወነሰው የሕንጻው ክፍል ተረፈ። ከዚያ በኋላ አዲሱ አርክቴክት ቻርለስ ቡልፊች በአዲስ ጉልበት ካፒቶል ሒልን ማስፋት ጀመረ። በ1819 ካፒቶል ሒልን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለሕግ መምሪያው ምክር ቤትና ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አዳራሾችና ቢሮዎች ምቹ አድርጎ አጠናቀቀው። የኪነ ሕንጻ አዋቂው ቻርለስ ቡልፊች እነዚህን ሦስት ክንፎች ካጠናቀቀ በኋላ መሀል ላይ የሚገኘውን በመዳብ የተለበጠውን አሁን ጉልላት ያለበትን ሕንጻ ጀመረ። በ1826 በመዳብ የተለበጠው የሕንጻውን ጉልላት የተሸከመው ሕንጻ ተጠናቀቀ። ከዚህ በኋላ ግቢውንና ሕንጻውን በማሳመር ረዥም ዓመታትን አጠፋ። ሆኖም በ1850 በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ወኪሎቻቸውን እየላኩ አሜሪካ በመጠንና በውክልና እየሰፋች ስትመጣ ይህ የሕዝብ እንደራሴዎች፣ የሕግ አውጪዎችና የሕግ ተርጓሚዎች የሚርመሰመሱበት ሕንጻ እየጠበበ መጣ። በዚያን ጊዜ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሚራልድ ፊልሞር በቃ አዲስ ማስፋፊያ ይጀመር አሉ። ቶማስ ዋልተር የሚባል የኪነ ሕንጻ አዋቂ ከፊላደልፊያ አስመጡና ሥራ አስጀመሩት። ይህ ሰው በካፒቶል ሒል የሰሜንና የደቡብ ተጨማሪ ክንፎችን እገነባለሁ ብሎ ተነሳ። በሰሜን አቅጣጫ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ግዙፍ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ በደቡብ አቅጣጫ ደግሞ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አዳራሽን ገነባ። እነዚህ በካፒቶል ሒል ክንፍ ላይ ግራና ቀኝ ተጨማሪ ክንፍ ሆነው የተጨመሩት አዳራሾች ካፒቶል ሒልን እጅግ ግዙፍ አደረጉት። ሕንጻው ሲገዝፍ ደግሞ ላዩ ላይ የተከመረበት በመዳብ የተለበጠው ጉልላት ኮሳሳ እየሆነ መጣ። ስለዚህ የሕንጻውን ግዝፈት የሚመጥን አዲስ ጉልላት ያስፈልጋል ተባለ። በ1855 የመዳቡ ጉልላት ፈርሶ ሌላ በብረት ጥልፍልፎሽ የሚደገፍ የግዙፍ ጉልላት ግንባታ ተጀመረ። ይሄ ጉልላት የዋዛ አይደለም፤ በጣም ግዙፍና 108 መስኮቶች ያሉት ነው። በ1863 (እአአ) 19 ጫማ ወይም 6 ሜትር የሚረዝመው የነጻነት ሐውልት በነሐስ ተለብጦ በተጠናቀቀው የሕንጻው ጉልላት ላይ እንዲቀመጥ ተደረገ። ይህ ዝነኛ ሐውልት ሄልሜት ያጠለቀች የሴት ምሥል ሲሆን 15ሺህ ፓውንድ ወይም 6ሺህ 800 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጅግ ግዙፍ ሐውልት ነው። ይህ ሕንጻ 200 ዓመታትን በፈጀው ዘመኑ በጣም በርካታ ማሻሻያዎች የተደረጉለት ሲሆን መጨረሻ ላይ የተጨመረለት የጎብኚዎች ምድር ቤት ነው። ይህ የጎብኚዎች ምድር ቤት ግዙፍና ሙሉ በሙሉ ከወለል በታች ሆኖ የተገነባ ዘመናዊ አዳራሽ ነው። በየዓመቱ በዚህ አዳራሽ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች የሕንጻዎቹን አገልግሎቶች ሳያውኩ፣ የሕዝብ እንደራሴዎችን ሳይረብሹ ጉብኝት አድርገው ይወጣሉ። አሁን አሜሪካ ከ50 ግዛቶቿ ሁለት ሁለት እንደራሴዎችን ወደ ካፒቶል ሒል አምጥታ ታከራክራቸዋለች። 100 ሆነው የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ ይከራከራሉ። በግራ በኩል ደግሞ ናንሲ ፔሎሲ ቆፍጠን ብለው የሚመሩት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አዳራሽ አለ። እዚያ ደግሞ 50ዎቹ ግዛቶች እንደ ሕዝብ ብዛታቸው በቁጥር የተለያዩ የሕዝብ እንደራሴዎችን ይልኩና ሕግ በማውጣት ይጠመዳሉ። እነዚህ የታችኛው ምክር ቤት የሚሰበሰቡት እንደራሴዎች ቁጥር 435 ነው። ድምጽ መስጠት የሚችሉት እነዚህ ናቸው። ብዙዎቹ ቢሯቸው እዚህ ካፒቶል ሒል ነው። ዋና ዋና ቢሮዎች ብቻ ቢቆጠሩ 540 ይሆናሉ። የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች የካፒቶል ሒልን የፊተኛውን ክፍል ጥሰው ገብተው ነው ይህ ሕንጻ በድጋሚ የሕይወት ታሪኩ እንዲጻፍ፣ የዓለም ሚዲያ እንዲያወራለት ያደረጉት። ምክንያቱም ይህ ሕንጻ ተራ ሕንጻ አይደለም። የዲሞክራሲ ቤተ መቅደስ እያሉ ነው የሚጠሩት። ለማንኛውም የትራምፕ ደጋፊዎች ሌላ ነውጥ ካላስነሱ ከ13 ቀናት በኋላ ጆ ባይደን ካፒቶል ሒል ፊት ለፊት 46ኛው ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ይፈጽማሉ። 228 ዓመት ያስቆጠረው ካፒቶል ሒል እሳቸውንም ታሪክ እስኪያደርጋቸው ድረስ። ታሪክ የማይሆን ማን አለ?
news-55496900
https://www.bbc.com/amharic/news-55496900
የስደተኞች ተቆርቋሪና የስኬት ተምሳሌቷ አጊቱ ጉደታ ማን ነበረች?
ማክሰኞ ዕለት በሰሜናዊ ጣሊያን ትሬንቲኖ ግዛት ውስጥ ነዋሪ የነበረችው ታዋቂዋ ኢትዮጵያዊት የአጊቱ ጉደታ ግድያን ተከትሎ በጣሊያን የኢትጵያ ተወካይ የሆኑት አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ ጉዳዩን በቅርበት ለመከታተል ከባልደረቦቻቸው ጋር ወደ ስፍራው መሄዳቸውን ቢቢሲ ለማወቅ ችሏል።
አጊቱ ከፍየሎቿ ጋር ኤምባሲው የአጊቱ ግድያ ከተሰማ በኋላ ተሰማውን ሐዘን ገልጾ ወንጀሉን በተመለከተም ከጣሊያን መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንደሚያደርግ መግለጹ ይታወሳል። በጣሊያን ውስጥ ከፍየል ወተት በምታዘጋጀው አይብ [ቺዝ] ታዋቂነት ያተረፈችው የስደተኛዋ ኢትዮጵያዊት የአጊቱ ጉደታ ግድያ በጣልያን ከባድ ድንጋጤን ከመፍጠሩ ባሻገር የዓለም መገናኛ ብዙሃን ዋነኛ ርዕስ ሆኗል። በተለይም ለስደተኞች መብት በመቆም የምትታወቀው የአጊቱ መገደል ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ልብ ሰብሯል። በርካቶች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሀዘናቸውን እየገለጹም ነው። በጣልያኗ ትሬንቲኖ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ፍራሲሎንጎ ትኖር የነበረው አጊቱ ቤቷ ውስጥ ነበር ተገድላ የተገኘችው። ምርመራ እያደረገ እንደሆነ የገለጸው ፖሊስ እንዳለው፤ መኖሪያ ቤቷ ውስጥ ጭንቅላቷ ላይ ክፉኛ ተመትታ ጉዳት ደርሶባት አስከሬኗ የተገኘው ባለፈው ማከሰኞ ነበር። የሞተችው ጭንቅላቷ ላይ በመዶሻ ተመታ ሊሆን እንደሚችልና በግድያው ተጠርጥሮ የተያዘ ጋናዊ ስደተኛ ለፖሊስ በሰጠው ቃል ወንጀሉን መፈጸሙን ማመኑም ተገልጿል። የጣልያኑ ጋዜጣ ኮርየር ዴላ ሴራ እንደዘገበው አጊቱን የገደላት ሠራተኛዋ ጋናዊው ሱሌይማን አዳምስ 32 ዓመቱ ነው። የግድያው ምክንያት ከክፍያ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ አለመግባባት ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል። የትሬንቲኖ ግዛት የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሚካኤሌ ካፑርሶ "በአጊቱ እና ሱሌይማን መካከል ጸብ መኖሩን አናውቅም። ከዚህ ቀደም ቀጥራው አብሯት ሠርተዋል" ብለዋል። ጨምረውም አጊቱ ከሁለት ወር በፊት በግድያው የተጠረጠረውን ሱሌይማን አብሯት እንዲሠራ እንደጠራችው ገልጸው፤ የአንድ ወር ደሞዝ አልተከፈለኝም በሚል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር አስረድተዋል። የግድያው ተጠርጣሪ አጊቱን ቢያንስ ሦስት ጊዜ በመዶሻ እንደተመታችና ወሲባዊ ጥቃት እንዳደረሰባት ማመኑንም ኮሎኔል ሚካኤሌ ገልጸዋል። አጊቱ ማን ነበረች? አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው አጊቱ ከአስር ዓመት በፊት ነበር በስደት ወደ ጣሊያን የሄደችው። ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ስትጨርስ ነጻ የትምህርት እድል አግኝታ በትሬንቲኖ ዩኒቨርስቲ ማኅበረሰብ ሳይንስን አጥንታ በዲግሪ ተመርቃለች። ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳ ለጥቂት ጊዜ ከቆየች በኋላ እአአ 2010 ላይ ወደ ጣልያን ተመልሳ ሄዳ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቀች። ትላልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያካሄዱትን የመሬት ነጠቃ በመቃሟ የግድያ ዛቻ ይደርስባት ስለነበር ኢትዮጵያን ጥላ ለመሄዷ ምክንያት ነበር። ከፍየል ወተት አይብ የማምረት ሐሳብን የወጠነችውም ወደ ጣልያን ካቀናች በኋላ ነው። ከኢትዮጵያ ሸሽታ ጣልያን ውስጥ ጥገኝነት ከጠየቀች በኋላ የስደት ኑሮዋን የምትገፋበት መተዳደሪያ መፍጠር ነበረባት። በዚህም በትሬንቲኖ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ፍየሎችን ማርባትና ልዩ ልዩ የወተት ተዋጽኦ ማምረት ከጀመረችም ዓመታት ተቆጥረዋል። በምትኖርበት አካባቢ ባሉ ጣልያናውያን እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት በስደት ወደ ጣልያን በሄዱ ሰዎች ዘንድም ታዋቂና ተወዳጅ ነበረች - አጊቱ። አጊቱና የፍየል እርባታ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረገችው ቆይታ እንስሳትን ማርባት በቤተሰቧ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሸጋገረ ልማድ እንደሆነ ተናግራለች። በተጨማሪም ቀደም ሲል ዋነኛ ትኩረታቸውን በአርብቶ አደሮች ላይ ባደረጉ በዘላቂ ግብርና ፕሮጀክቶች ላይ በመስራት ልምድ የነበራት አጊቱ በእንስሳት እርባታ ሥራዋ ስኬት የእራሱ የሆነ አስተዋጽኦ እንደነበረው ከዚህ በፊት ተናግራ ነበር። ጣልያን ውስጥ ከፍየል ወተት አይብ ማምረት ስትጀምር ለበርካታ አፍሪካውያን የሥራ እድል ፈጥራለች። ከዚህ ባሻገርም ዘረኛነትን በመጋፈጥ እንዲሁም ለስደተኞች መብት በመቆም ትታወቃለች። ፍየሎች ላይ አተኩሮ መሥራት እንደሚያስደስታት በተለያዩ ቃለ መጠይቆች ተናግራለች። ጣልያን ውስጥ ጥቅም ላይ ያልዋለ የእርባታ መሬት ስታገኝ አገር በቀል ፍየሎችን ለማርባት ወሰነች። ፔታታሞኒኪና የሚል መጠሪያ ያላቸው እና ዝርያቸው ሊጠፋ የነበሩ ፍየሎችን ማርባት የጀመረቸው አጊቱ በመነሻዋ ላይ 15 ፍየሎች ብቻ ነበሯት። በጊዜ ሂደት ወደ 180 የሚደርሱ ፍየሎችን ማርባት ስትችል፤ የፍሎቹን ወተት በመጠቀም ታዋቂነትን ያተረፈላትን ተወዳጅ አይብ ማምረት ጀመረች። በምትኖርበት አካባቢ ፍየሎቹን ለማሳደግ ስለሚመችና አገር በቀል ስለሆኑ እንደመረጠቻቸው ተናግራ ነበር። በፍየል እርባታዋና በአይብ ምርት ሥራዋ ውስጥ ከምትቀጥራቸው ሠራተኞች መካከል አብዛኞቹ የሥራ ዕድል ያላነኙ ስደተኞች ናቸው። ጣልያን ውስጥ ስለተማረች ከመኖሪያ ፍቃድ ጋር የተያያዙ ሰነዶች እንዲሁም ትሬንቲኖ ውስጥ ጓደኞችም ነበሯት። ተወዳጁ የአይብ ምርት ከፍየል ወተት ስለሚሠራ አይብ ለመማርና አብረዋት ለመሥራት የሚሄዱም ብዙ ናቸው። እሷም የምትወደውን ሙያ ለሠራተኞቿ ከማስተማር ወደኋላ አትልም። ሙያውን ለማዳበር በፍየል አይብ ወደምትታወቀው ፈረንሳይ ሄዳ ስለ አይብ አሠራር ተምራለች። ወደ 15 የሚደርሱ የአይብ አይነቶች ለደንበኞቿ ታቀርባለች። በሥራዋ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክተውላታል። በሚላን ኤክስፖ ላይ የምትኖርበትን ግዛት ወክሎ የቀረበውም የእሷ የአይብ ምርት ነበር። በምትኖርበት ግዛት ከፍየል ወተት የሚሠራ አይብ ሙያ ውስጥ ማንም አልነበረም ማለት ይቻላል። አጊቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያየ አካባቢ ለሚሄዱም ለዓመታት አይብ አቅርባለች። ከፍየል ወተት የሚሠራ ተፈጥሯዊ መዋዋቢያ ታመርታለች። ቱሪስቶችን የፍየል መንጋም ታስጎበኛለች። የዘረኝነት ፈተና ጣሊያን ከጀርመን ጋር በምትዋሰንበት ተራራማዋ ትሬንቲኖ ውስጥ ለዓመታት የኖረችው አጊቱ፤ ዘረኛነት ላይ የተመሠረቱ ጥቃቶች ያጋጥሟት እንደነበር ለፖሊስ አመልክታለች። "አስቀያሚ ጥቁር እያሉ ይሰድቡኛል፤ ያለሁበትም ቦታ አገሬ እንዳልሆነ ይነግሩኛል" በማለት ያገጠሟትን የዘረኛነት ጥቃቶች ስትገልጽ ነበር። አጊቱ የሚገጥማትን የዘረኝነት ጥቃት ይፋ ባወጣችበት ጊዜ የግዛቲቱ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኡጎ ሮሲ ድርጊቱን ተቃውመው ከጎኗ ቆመው ነበር። ፕሬዝዳንቱ በወቅቱ "አጊቱ ስደተኛ ሆና የእንስሳት እርባታ ሥራዋን በግዛታችን ውስጥ ማከናወን መጀመሯ የትሬንቲኖን እንግዳ ተቀባይነትና ደጋፊነትን ያሳያል" ብለው ነበር። አጊቱ በተለይም ለስደተኞች የአዲስ ሕይወት ተስፋና ተምሳሌት ነበረች። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት [ጃንዋሪ 1/2021] አርብ ዕለት 43 ዓመት ይሆናት ነበር።
news-48332383
https://www.bbc.com/amharic/news-48332383
ገበታ ለሸገር፡ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ሰዎች ምን ይላሉ?
አቶ ዮሐንስ መኮንን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ-ሕንፃና የቅርስ ጥበቃ መምህር ናቸው። የዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ የቤተ መንግሥት የግብር አዳራሽ እድሳት ሥራው ከተሰራለት በኋላ እያንዳንዱን ቦታ ለማስጎብኘት በበጎ ፈቃደኝነት ከተመረጡና ከተሳተፉ ስምንት ባለሙያዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን አጫውተውናል። በእራቱም ላይ ተጋብዘው ከጠቅላዩ ጋር አብረው ገበታ ቆርሰዋል።
• የ5 ሚሊዮን ብር እራት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር • "እራት ለመመገብ አይደለም የምንሄደው" በላይነህ ክንዴ ተጋባዥ እንግዶችን በማስጎብኘት ሂደት እርሳቸው ብቻቸውን ከ40 በላይ ቻይናውያን ማስጎብኘታቸውን የጠቀሱት አቶ ዮሐንስ አንድ ሰው በአማካይ 30 ሰው በአንዴ ያስጎበኝ ነበር በማለት የነበረውን ሁናቴ ያስታውሳሉ። ከእንግዶቹ መካከልም በጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም ዘመን ቤተ መንግሥቱን ለማየት እድል ያገኙ የውጪ እንግዶች ሲኖሩበት በወቅቱ የነበራቸውን ትዝታ በማጋራት መደመማቸውን እንዳጫወቷቸው ይናገራሉ። አጤ ኃይለ ሥላሴ የተቀበሩበትን ስፍራ፣ ከላይ የጓድ መንግሥቱ ቢሮ ከታች የእርሳቸው መቃብር፣ ስድሳዎቹ ሰዎች የተረሸኑበት፣ ጄነራሎቹ የታሰሩበትን ሁሉ ማስጎብኘታቸውን አጫውተውናል። "ቤተ መንግሥቱ ያረፈው 40 ሔክታር ላይ ነው" የሚሉት ባለሙያው ከዚህ ሁሉ ሥፍራ ለጎብኚ ክፍት ሆኖ በትናንትናው እለት የመታየት ወግ የደረሰው አንድ አራተኛው ነው ሲሉ ግምታቸውን ያሰፍራሉ። አቶ ይትባረክ ዘገዬ የዋርካ ትሬዲንግ ሃውስ ኃ/የተ/የግ/ማ ባለቤት ሲሆኑ ትናንት በተካሄደው 'ገበታ ለሸገር' የእራት ግብዣ ላይ ከተሳተፉት አንዱ ናቸው። ፕሮጀክቱን መደገፍ አለብኝ፤ መሰራትም አለበት ብለው 5 ሚሊየን ብር በመክፍል ገበታ ለሸገር እራትን ተጋብዘዋል፤ ፕሮጀክቱንም ደግፈዋል። " ዋናው እራቱ ሳይሆን ዓላማው ነው፤ እራቱም በጣም ጥሩ ነበር" የሚሉት አቶ ይትባረክ 'ገበታ ለሸገር'ን ከጠበቁት በላይ እንዳገኙት ይናገራሉ። ገና ወደ ቤተመንግሥት ሲገቡም ጉብኝት እንዳዳረጉና ታሪካቸውን በማወቃቸው እርካታ እንደተሰማቸው ይገልፃሉ። ለወደፊቱ ፊልም ይሰራበታል እንዲሁም ከመጭው መስከረም ወር ጀምሮ ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል የተባለውን ቤተ መንግሥት ጎብኝተዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ቤተ መንግሥቱን ሲጎበኙ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው። በዚህም ከአጤ ሚንሊክ ጀምሮ፤ አጤ ኃይለ ሥላሴ እንዲሁም ጠቅላይ ሚንስትሮችና ፕሬዚዳንቶች ሲኖሩበት የነበረውን ቦታ በማየታቸው ደስታ ተሰምቷቸዋል። ቤተ መንግሥቱ በተለይ በደርግ ዘመን ብዙ ታሪክ የተሰራበት በመሆኑ ቦታውን መጎብኘታቸው የረኩበት እንደሆነ ይናገራሉ። ለሌላው ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል ታሪክና ቅርስ ነው ሲሉም ያክላሉ። የሥነ-ሕንፃ ባለሙያው አቶ ዮሐንስ ለእራቱ ከታደሙት 300 የሚሆኑ እንግዶች መካከል ገሚሱ ኢትዮጵያን ገሚሱ ደግሞ የውጭ ሀገር ዜጎች ነበሩ ብለውናል። • "ቻይና በአፍሪካ ውስጥ የታይታ ፕሮጀክት የላትም" ፕሬዚዳንት ሺ ዢፒንግ ተጋባዥ እንግዶች በአጠቃላይ እኩል ስላልደረሱ ቀድመው የመጡት የአጤውን ቤተመንግሥትና ተያያዥ ቅርሶች ከጎበኙ በኋላ የኮክቴል ግብዣ እንደተደረገላቸው አቶ ዮሐንስ ጨምረው ያስረዳሉ። እግረመንገዳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከእንግዶች ጋር በተናጠልም በቡድንም በአጤ ሚኒሊክ የግብር አዳራሽ በር ላይ ፎቶ ሲነሱ ነበር ብለዋል። አቶ ይትባረክ ዘገዬም " ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ፎቶ ግራፍ መነሳትና መጨባበጥ ብቻም ሳይሆን እንደ ቅርብ ዘመድ ተሳስመናል" ይላሉ። የኮክቴሉን መሰናዶና መስተንግዶ የተወጣው ሸራተን እንደሆነም አቶ ዩሃንስ ይናገራሉ። እምቢልታ ይነፋ ነጋሪት ይጎሰም እንግዶች ተጠቃልለው ሲመጡ በጥንቱ ወግና ባህል መሰረት ነጋሪት እየተጎሰመ፣ ግራና ቀኝ የቆሙ የሀገር ባህል ልብስ የለበሱ ሰዎች እምቢልታ እየነፉ ተጋባዥ እንግዶች ወደ ምግብ አዳራሹ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሁሉም እንግዶች ተጠቃልለው እስኪገቡ ድረስ ደጅ በመሆን እንግዶቹን እጅ እየነሱ እንዲገቡ ይጋብዙ ነበር ብለዋል አቶ ዮሐንስ። አቶ ይትባረክ ከዚህ ቀደም ከነበሩ ጠቅላይ ሚንስትሮች ጋር የመገናኘትና የመጨባበጥ እድሉ ቢኖራቸውም ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ግን ለየት ይላሉ ብለዋል። • የላሙ ፕሮጀክት ቦርድ አባላት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው ምክንያታቸውንም " እርሳቸው የሰው ቀረቤታና ያለ መሰልቸት ቀርበው የማነጋጋር ችሎታ አላቸው" ሲሉ ያስቀምጣሉ። በአዳራሹ ሲገኙም " ፍቅር እስከ መቃብርን መፅሐፍ ስላነበብኩ ፊታውራሪ መሸሻ ግብር የሚያበሉበት እልፍኝ ነው የታወሰኝ" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም እንግዶች ከገቡ በኋላ ወደ አዳራሹ ገብተው ፕሮጀክታቸውን በሚመለከት ገለፃ አድርገዋል። በእያንዳንዱ ተጋባዥ ጠረጴዛ በመምጣትም እየጨበጡ ከየትኛው ተቋም እንደመጡ ይጠይቁ እንደነበርና 'ሸገርን በማስዋብ ፕሮጀክት ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን' አጫውተውናል። የአብርሐም ወልዴ 'ባላገሩ የባህል ኦርኬስትራ' አስደናቂ ዝግጅት አቅርቧል ያሉት አቶ ዮሐንስ ጠቅላይ ሚንስትሩም አብርሐምን በአደባባይ አመስግነውታል። እንደ ማህሙድ አህመድ ያሉ ሌሎች አንጋፋ ድምፃውያንም ዝግጅታቸውን አቅርበዋል። ምን ተወራ? ዶክተር አብይ በትናንትናው የእራት ግብዣ ላይ ለእንግዶቻቸው ስለ አዲስ አበባ የወንዞች ልማት ፕሮጀክት እና ሌሎች አዲስ አበባ ውስጥ የሚተገበሩ ፕሮጄክቶች ንግግር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያሉ ረዳቶቻቸውም ቤተመንግሥት አካባቢ ሊሰራ ስለታሰበውና 20 ሺህ ሰው ያስተናግዳል ስለተባለው ቤተ መፃህፍትም ገለፃ በማድረግ ምን ሊመስል እንደሚችል የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ቀርቧል። ቤተመፃህፍቱ የሚሰራው ፓርላማው አካባቢ በሚገኝ ሰፊ ቦታ ላይ ይሆናል። የታችኛው ኢዮ ቤሊዮ ቤተመንግስት ዲዛይንም መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ከፈረንሳይ መንግሥት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ማለታቸውንም አክለውልናል። ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ የሚደረግበት የለገሃሩ ፕሮጄክት በቅርቡ እንደሚጀመርም ተናግረዋል- ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ከሳር ቤት እስከ ጎተራ ማሳለጫ ያለውን የትራፊክ ፍሰት የሚያሳልጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትም ተነስቷል እንደ አቶ ዮሐንስ። "በአጠቃላይ ስድስት ፕሮጀክቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ውስጥ ተካትተዋል።" ይላሉ የሥነ ሕንፃ ባለሙያው። • ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት ከንግግራቸው እንደ ቁልፍ መልዕክት የወሰድኩት ይላሉ አቶ ዮሐንስ 'አቧራ ከማስነሳት አሻራ ማስቀመጥ' የሚለውን ነው በማለት በተለያየ ምክንያት ግጭቶች ቀስቅሶ አቧራ ማስነሳት ቀላል ነገር ነው። ለትውልድ የሚቆይ አሻራ ማቆየት ግን በጣም ጠቃሚ ሥራ ነው የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ነግረውናል። በንግግራቸው መጨረሻም ላይ የዝግጅቱ ታዳሚዎች በሙሉ ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ እንዲያነሱ በመጠየቅ፣ በኋላም አውራጣታቸውን እንዲያሳይዋቸው ካደረጉ በኋላ፣ አውራ ጣታቸውን ፊት ለፊታቸው ያለ ገበታ ላይ እንዲያሳርፉ አድርገው ቃል አስገብተዋቸዋል። እንግዶቹ ገበታቸው ላይ አውራ ጣታቸውን ካኖሩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሉትን ደግመው በማለት ቃል ገብተዋል። በተባበረ ድምፅ "አሻራዬን አኖራለሁ፤ ሀገራዊ ግዴታዬን እወጣለሁ" በማለት ቃል እንደገቡም ያስታውሳሉ። ከዚህ ሁሉ በኋላ የእራት ግብዣ ተካሂዷል። ሻኛውን ከዳቢት፣ ቀዮን ከጮማ ማወራረድ ለፈለገ ቁርጥ ስጋ በታዳሚው ዙሪያ እየዞረ፣ ጠጅ በብርሌ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ለውጪ ዜጎቹም የፈረንጅ ምግቦች ቀርበው ተስተናግደዋል። "በታሪክ መፃህፍት እንዳነበብኩት የመሳፍንቶቹ አይነት ግብዣ ነው የተደረገልን" ይላሉ አቶ ዮሐንስ። • ኢትዮጵያ ለሱዳንና ለጅቡቲ ኃይል ማቅረብ ማቋረጧ ተገለፀ ቻይናውያን ለብቻቸው ለ65 ሰው መክፈላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል ያሉት አቶ ዮሐንስ ከውጪ ዜጎቹ በብዛት ቻይናውያን እንደነበሩ ነግረውናል። በርካታ ሴቶችም በአስተናጋጅም በተስተናጋጅነትም መገኘታቸውን ይጠቅሳሉ። "የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዐዛ አሸናፊ፣ የሸገር ሬዲዮ መስራችና ባለቤት ወ/ሮ መዐዛ ብሩ ነበሩ።" እንግዶች ማዕድ የቆረሱበት አዳራሽ ፈረስ የሚያስጋልብ ስለነበር እንግዶች እንደልባቸው ለመንቀሳቀስ እድል ነበራቸው ያሉት አቶ ዮሐንስ ሰዎች ከፕሮጀክቱ ጋር የተገናኘ ወሬ፣ ቤተመንግሥቱ በመጎብኘታቸው የደስታ ባህር ውስጥ ነበሩ በማለት የታዘቡትን አጫውተውናል። "ቤተመንግሥቱ ውስጥ መግባት፣ በአጤ ሚኒሊክ የግብር አዳራሽ ውስጥ በመገኘት መመገብ፣ ለመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያለው ስሜት በራሱ ቀለል ያለ እንዲሆን አድርጎታል።" አቶ ዮሐንስ በሙያቸው የሥነ ሕንፃ ባለሙያ ስለሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን ሲያገኟቸው "የተጀመረው ሥራ ጥሩ ነው፤ ግን ብዙ ባለሙያዎች ተሳትፈው ልናዳብረው እንችላለን" ብለው እንደነገሯቸውም ያስታውሳሉ። አቶ ይትባረክ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ያዩትን ለውጥ በማንሳት ይህ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተተግብሮ ሥራ ላይ ይውላል የሚል እምነት አላቸው። ሲጠናቀቅም የቱሪስት መዳረሻ በመሆን ለድሃው የአገሪቱ ሕዝቦች ጠቀሜታ ይኖረዋል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል። "በተለይ በአገር ውስጥ ያሉት መዝናኛዎች ሆቴሎች ናቸው፤ በሆቴል ደግሞ መጠጥና ምግብ ብቻ ነው ያለው" የሚሉት አቶ ይትባረክ ይህኛው ከእነዚህ የመዝናኛ ሥፍራዎች ለየት ስለሚል ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ አገር ዜጎች ጠቀሜታ እንደሚኖረው አክለዋል። በቀጣይ ገንዘብ ስለማሰባሰብ በግብዣ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተባለ ባይኖርም፤ አገርን ለማልማትና ለማሳደግ በምንጠየቅበት ማዋጣትና መስራታችን አይቀርም ብለዋል። ቢቢሲ፡ ተመሳሳይ የ5 ሚሊየን እራት ቢዘጋጅ ይሳተፋሉ? አቶ ይትባረክ፡ አቅሜ ከቻለ አስር ጊዜም ቢሆን እሳተፋለሁ። እግረ መንገድ የሚነሱ ነጥቦች በእርግጥ አዲስ አበባ ዓመቱን ሙሉ ኩልል ብሎ የሚፈስ ወንዝ አላት ይሆን? የሚለው ጥያቄ ከፕሮጀክቱ መፀነስ ጀምሮ በባለሙያዎች እንደሚነሳ የሚናገሩት አቶ ዮሀንስ ይህንን ሀሳብ የሚያነሱ ባለሙያዎች እነ አምስተርዳምን ምሳሌ አድርገው ይጠቅሳሉ ይላሉ። አቶ ዮሐንስ ግን እንደዚህ አይነት መናፈሻ፣ መልከዓ ምድሩ አዲስ አበባ ውስጥ መሰራቱ በራሱ እንደ በጎ ጅምር በመውሰድ እርሱ ላይ ማደርጀት የምንችል ይመስለኛል በማለት በፕሮጀክቱ ላይ ያላቸውን እምነት ይገልጣሉ። አክለውም የዲዛይን ሀሳቡ ላይ ሀገርኛ የሆኑ ነገሮች እንዲጨመሩ ጥረት ተደርጓል፤ በጥሩ ሁኔታ ዲዛይን ተደርጓል የሚያስመሰግንም ተግባር ነው በማለት ሀሳባቸውን ይቋጫሉ። የእለቱ መርሀ ግብር ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ ከምሽቱ 3፡50 ላይ ተጠናቋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬተርያት ብለኔ ሥዩም ለቢቢሲ እንደተናገሩት የእራት ግብዣው የተካሄደበት የአጤ ሚኒሊክ የግብር አዳራሽ ከአጤ ኃይለ ሥላሴ ጀምሮ ተዘግቶ የቆየ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ነው።
news-48741588
https://www.bbc.com/amharic/news-48741588
በቅዳሜው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ምግባሩ ከበደ አረፉ
ቅዳሜ ዕለት በአማራ ክልል በተፈፀመው ጥቃት የመቁሰል ጉዳት ከደረሰባቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አንዱ የሆኑት የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ምግባሩ ከበደ በዛሬው ዕለት ህይወታቸው አልፏል።
አቶ ምግባሩ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም አማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር ውስጥ ተሞከረ በተባለው "መፈንቅለ መንግሥት" ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ዛሬ ህይወታቸው ማለፉን የአማራ ቴሌቪዥን በሰበር ዜናው ገልጿል። •ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ •ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው •የሥራ ኃላፊነታቸውን "ከባድና የሚያስጨንቅ... ነው" ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ? በአማራ ክልል ተሞከረ የተባለውን "መፈንቅለ መንግሥት" ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴ እንዲሁም የሃገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮነን ጄኔራል ገዛኢ አበራ ተገድለዋል።
news-57101751
https://www.bbc.com/amharic/news-57101751
ትግራይ፡ በገርዓልታ ተራሮችና ሐውዜን ከተማ ዙርያ የሆነው ምንድን ነው?
በቅርቡ በሽብር የተፈረጀው ህወሐት ሲመራው በነበረው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት እና በፌዴራል መንግሥት መካከል ጥቅምት 24 2013 ዓ.ም የተጀመረው ወታደራዊ ግጭት ሰባተኛ ወሩን ይዟል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፣ በሕዳር ወር መጀመርያ ላይ የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌዴራል ሰራዊት ቁጥጥር ስር መዋሏን ተከትሎ፣ ጦርነቱ እንደተጠናቀቀ ቢናገሩም፣ አሁንም በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች ውጊያዎች መቀጠላቸው ሪፖርቶች ያመላክታሉ። እንደ ዓለም አቀፍ መንግሥታት ሪፖርት ከሆነ በክልሉ የቀጠለው ግጭት ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ አስከትሏል። በሌላ በኩል ሰሞኑን በሐውዜን ወረዳና በተለይ ደግሞ በገርዓልታ ተራሮች ዙርያ ውግያ መካሄዱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሚያዝያ 25 2013 ጀምሮ በሶስት ግንባሮች ውጊያ መካሄዱን እነዚህ ነዋሪዎች ጨምረው ተናግረዋል። ከአንድ ቤት ተቆፍረው የወጡ ሰባት ህጻናት ሃፍቶም የተባለው የሐውዜን ከተማ ነዋሪ፣ ከጥቅምት 24 2013 ጀምሮ ሐውዜን "የውጊያ መናሃርያ ሆናለች ቢባል ማጋነን አይሆንም" ይላል። በአከባቢው ቢያንስ ለስድስተኛ ግዜ ውግያ መሰማቱንና፤ የበርካታች ሰላማዊ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ይናገራል። የዓይን ምስክሮች እንደሚሉት፤ ሚያዝያ 29 2013 ዓ.ም ላይ ሐውዜን በከባድ መሳርያ ድብደባ ተፈጽሞባታል። በከተማዋ በ02 ቀበሌ የሚገኘው፤ የአቶ ብሩ በላይ መኖርያ ቤት ጥቃት ከደረሰባቸው መካከል አንዱ ነው። "ከባድ መሳርያ ከመውደቁ በፊት በከተማዋ ምንም ነገር አልነበረም። በመጋብና ድጉም አቅጣጫ ግን ከርቀት የውግያ ድምጽ ይሰማ ነበር። ቤቱ ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ሲደርስ በርከት ያሉ ሴቶች ነበሩ። በተለይ በአንድ ክፍል ደግሞ የጎረቤት ልጆችን ጨምሮ ሰባት ህጻናት ነበሩ" ትላለች ከአደጋው የተረፈችው ግደይ። በህይወት የተረፉት ህጻናት ለህክምና ወደ መቀለ አይደር ሆስፒታል የወሰደችው ግደይን ሁኔታውን ስታስረዳ፣ "በ16 [ሚያዝያ] የከባድ መሳርያ ድብደባ ነበር። የአሁኑ የሚያዝያ 29 ግን የከፋ ነው" ትላለች። እንደ ግደይ ገለጻ የተተኮሰው የከባድ መሳሪያ መካከል አንዱ በከተማዋ 02 ቀበሌ በሚገኘው የአቶ ብሩ በላይ መኖርያ ቤት ላይ ወድቆቤቱ ሙሉ በሙሉ ተደርምሷል። ግደይ አምስቱን ልጆች በመያዝ በቅድሚያ ወደ ውቅሮ ሆስፒታል ያመራች ሲሆን አንዷ ተሽሏት ወደ ቤተሰቦቿ ስትሄድ ቀሪዎቹን ወደ አይደር ሆስፒታል ወስዳ ህክምናቸውን እየተከታተለች መሆኑን ትናገራለች። የሞቱት ሕጻናት ዕድሜያቸው ሁለት ዓመት መሆኑን የምትናገረው ግደይ በህይወት ተርፈው በህክምና ላይ የሚገኙት ደግሞ ከ7 እስከ የ12 ዓመት ያሉ ልጆች መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግራለች። የሁለተኛ ዓመት የመቀለ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪ የሆነው ተክለብርሃን ከአራቱ ህጻናት መካከል ሶስቱን በሆስፒታሉ ውስጥ ማየቱን ይናገራል። ህጻናቱ ስብራት፣ የመቁሰልና የቆዳ መሰንጠቅ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለቢቢሲ ገልጿል። "በከባድ መሳርያ የተመታ ቤት ፈራርሶ፤ እዛው ተደፍነው ተቆፍረው እንደወጡ ነው የነገሩን፤ የፈራረሰው ድንጋዩም ጭምር ጉዳት አድርሶባቸዋል ብለን ነው የምናስበው።" የመከላከያ ሰራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮለኔል ጌትነት አዳነ፤ በሐውዜን ከተማና አካባቢው በህጻናት ላይ ደረሰ ስለተባለው ጉዳት ተጠይቀው በከባድ መሳርያ ድብደባ የግለሰብ ቤት ወደመ የሚባል ነገር ስህተት ነው ብለዋል። "በሽብር የተፈረጀው ከባድ መሳርያ የለውም፤ ከባድ መሳርያ ያለው እኛ ጋር በመከላከያ ሰራዊት እጅ ነው። የት ቦታ ላይ መተኮስ እንዳለበት ያውቃል። . . . በከባድ መሳርያ ድብደባ የግለሰብ ቤት ወደመ የሚባል ነገር ስህተት ነው። እንደዛ የሚሆንበት ዕድል በጣም ውሱን ነው። የደረሰ ጉዳትም ካለ ወደፊት ታይቶ ይታረማል ፤ ይፋ የሚደረግም ይሆናል ብዬ አስባለሁ። እስካአሁን ባለው መረጃ ግን በከባድ መሳርያ ይህን ያህል ጥቃት ደረሰ የሚል በመከላከያ ሰራዊት በፍጹም የለም። እንደው አንደኛ ነገር የሚባለው፤ እሱ ውግያ የተመራበት አግባብ በጣም በጣም ጥንቃቄ የተሞላበት መሆኑ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ግደይ ሚያዝያ 17 2013 ዓ.ም የመንግሥት ወታደሮች ተኩሰው የገደሉዋቸው የአንድ ቤተ ሰብ አባላትን ታስታውሳለች። ወታደሮቹ አማርኛም ትግርኛም የሚናገሩ ነበሩ ስትልም ትናገራለች። ግደይ መጋቢት 28 ደግሞ ሁለት የቅርብ ዘመዶችዋ የሚገኙባቸው አራት የገጠር ነዋሪዎች በከተማ ውስጥ እንደቀበረች ትናገራለች። አርሶ አደር ግርማይ በበኩሉ ሚያዚያ 17 2013 ዓ.ም የመንግሥት ወታደሮች ሊገድሉት እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል። በዕለቱ በቤቱ ውስጥ ድግስ እንደነበር የሚናገረው ግርማይ፤ 'ጠላ ለጁንታ ነው የጠመቅከው' ብለው ሊገድሉኝ መሳርያ አቀባብለውብኝ ነበር" ይላል። በአካባቢው ሚያዝያ 16 2013 ዓ.ም ከባድ ጦርነት መካሄዱን የሚያስታውሰው ግርማይ "ከቀኑ ጀምረን ፈርተን ከቤት አልወጣንም። 'ጧት ተነስተው ማነው ሲዋጋን ያደረው' ብለው ጠየቁን። 'እኔ ከቤት አልወጣሁም፤ አላየሁም' ስላቸው አላመኑኝም" ይላል። "ትልቁ ነገር በሕይወት መትረፌ ነው" የሚለው ግርማይ፣ የልጁ ወርቅና የባለቤቱን ብርና ልብስ፤ ሽልማት በሙሉ፤ ሴቶቹ ወታደሮች እንደወሰዱበት ይናገራል። አንደኛዋ ሴት ልጁ በቅርቡ ያገባች እንደሆነች የሚያስረዳው ግርማይ በስጋት፤ ዕቃዋን ጠቅልላ ወደ መቀለ ለመሄድ ተዘጋጅታ ባለችበት እንዲህ አይነት ሁኔታ ማጋጠሙን ለቢቢሲ አስረድቷል። ኮሎኔል ጌትነት ግን ሰራዊቱ ከገበሬ አብራክ የወጣ ህዝባዊ ነው በማለት "በፍጹም ተዓማኒነት የሌለው" በማለት አጣጥለውታል። "ሰራዊቱ፤ አንዱ ስልጣን ላይ ሲቆይ ህዝባዊ ሌላ ሰው ስልጣን ላይ ሲወጣ ገዳይ እንዲሆን ሆኖ አይደለም የተገነባው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህዝባዊነቱ ነው የሚታወቀው።" ከሚያዝያ 25 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሶስት ግንባሮች ውጊያዎች መካሄዳቸው ይነገራል። ራሱን 'የትግራይ መከላከያ ሰራዊት' [TDF] ብሎ የሚጠራው ኃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ገብረ ገብረጻዲቅ፤ ለህወሓት ቅርበት ባለው ድምፀ ወያነ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ በሰጠው መግለጫ፤ በሶስቱ ግንባሮች በአጠቃላይ 1 ሺሕ 896 የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውን ከ1800 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውንና መማረካቸውን ይናገራሉ። የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት በበኩላቸው ሰራዊቱ በአካባቢው የአሰሳ እንቅስቃሴ ማድረጉን ሆኖም የደረሰበት ጉዳት እንደሌለ፤ በህወሓት የተሰራጨው መረጃ ውሸት እንደሆነ ተናግረዋል። ኃላፊው ገርዓልታ አካባቢ ውጊያ መካሄዱን ተናግረው ወደፊት የተሟላ መግለጫ እንደሚሰጥበት አክለዋል። በህወሓት የተሰጡ መግለጫዎችን በተመለከተ ግን፡ "እነሱ ያልገደሉት ምን ነገር አለ፤ እነሱ 'ገደልን' በሚሉት ልክ ቢሆን በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ሰራዊት አይኖራትም ነበረ" በማለት ውሸት መሆኑ እና ድርጅቱ በሌላ አካባቢ በተለይ ደግሞ በሑመራ ደረሰበት ያሉትን ጉዳት ለመሸፈን መሆኑን ተናግሯል። አክለውም "ህወሐት በአሁኑ ወቅት ሰራዊት ይዞ መከላከያን ደምስሶ የሚገፋበት አቅም የለውም። እውነታው ይሄ ነው። አሁን ያለው የድብብቆሽ ጨዋታ ነው። መደበቅ፤ አመራሮቹን መሸሸግ። በተለያየ ነገር አመሳስሎ ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ካልሆነ በስተቀር"። "ቢያንስ ቢያንስ እንኳን ተአማኒነት እንዲኖረው፤ ደፈጣ አድርገን መታን ቢባል ያስኬዳል፤ ደፈጣ ግለሰቦችንም ሊያደርጉት ስለሚችሉ። ውግያ ገጥሞ ግን የሚገፋ ኃይል አለ ተብሎ የሚባለው የውሸት ፕሮፖጋንዳቸው አካል ነው" ብለዋል።
54828908
https://www.bbc.com/amharic/54828908
ሶማሊያዊቷን ታዳጊ ደፍረው የገደሉት በሞት ተቀጡ
በሶማሊያዋ ራስ መር ፑንት ላንድ ግዛት የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት ታዳጊዋን ደፍረው ገድለዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች የሞት ቅጣት በይኖባቸዋል።
ታዳጊዋ የአስራ አራት አመት ልጅ ነበረች ተብሏል። የመድፈርና ግድያ ወንጀሉን የፈፀሙት መሃመድ አብዲ ፋራይና አብደራህማን መሃመድ አይዛክ የሚባሉ ግለሰቦች ናቸው። በባለፈው አመት በቦሳሶ ከተማ አግተው እንደወሰዷትና ወንጀሉንም እንደፈፀሙ ተናዘዋል። በሶማሊያ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መጨመር በርካቶችን ስጋት ላይ ጥሏል። በተለይም በቅርብ ወራት ውስጥ እንዲህ አይነት ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መሆኑንም መረጃዎች ያሳያሉ። ፖሊስም በርካታ የመደፈር ወንጀሎችንና መገደሎችንም እየመረመረ ይገኛል። ባለፈው ወር በሶማሊያዋ መዲና ሞቃዲሾ የ19 አመት ግለሰብ በቡድን ተደፍራ ተገድላለች። ግለሰቧ ከስድስት ፎቅ ላይ ወርውረዋት ነው ህይወቷ የጠፋው። ፖሊስም ይህንን ወንጀልም እየመረመረም እንዳለ ተገልጿል።
news-47317091
https://www.bbc.com/amharic/news-47317091
ኦዲፒ 'በፌዴራሊዝም አልደራደርም' ሲል ምን ማለቱ ነው?
የሰሞኑ የኦዲፓ መግለጫ እንደዋዛ አልታለፈም፤ ለሰፊ የማኅበራዊ ውይይት በር ከፍተ እንጂ። 'በፌዴራሊዝሙ አንደራደርም' የሚለው ሐሳብ በተለይም በአሓዳዊ ፖለቲካ አቀንቃኞች ላይ ቀዝቃዛ ውኃን የቸለሰ ይመስላል።
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ኾኖም መግለጫው ለተከፈተ ዘመቻ ምላሽ እንደሆነ በኦዲፒ ተገልጿል፤ ዘመቻው በማን፣ መቼና የት እንደተከፈተ ለይቶ ባይጠቅስም። ይህ በፌዴራሊዝም ላይ ተከፈተ የተባለው የሐሰት ዘመቻ ሁለት ግብ እንደነበረው የኦዲፒ መግለጫ ጨምሮ ያወሳል። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? 'የፌዴራል ሥርዓቱ ከዛሬ ነገ መፍረሱ ነው በሚል ብሔር ብሔረሰቦች በጥርጣሬ እንዲመለከቱት ማድረግ ሲሆን ሌላው ደግሞ' ተጨማሪ መብት እንደሚያገኝ እየጠበቀ ያለውን የኦሮሞን ሕዝብ' እንኳንስ ተጨማሪ መብት ይቅርና 'ከዚህ ቀደም ያገኘኸውንም ልታጣ ነው' በሚል ማደናገር ነው ሲል የዘመቻውን ግብ ያትታል። ለመኾኑ መግለጫዉ ባለፉት ቀናት በሕዝብ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ለምን ኾነ? በዚህ ወቅት ይህን መግለጫ ማውጣትስ ለምን አስፈለገ? በተገዳዳሪ ፓርቲዎች ዘንድ መግለጫው ምን ስሜት ፈጠረ? ቢቢሲ የአርበኞች ግንቦት 7 እና የኢሀን አመራሮችን አነጋግሯል። 'ሕዝቡ በምኞት ቀውስ ውስጥ ነው' ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት መግለጫው አነጋጋሪ የሆነው በርካታ ሕዝብ ዶ/ር ዐቢይ አገሩን አንድ አደርጋለሁ የሚሉትን ነገር እንደ ትግል አጀንዳ የምር በመቁጠሩ ይህን ተከትሎ የመጣ "የምኞትና የፍላጎት ቀውስ" ነው ይላሉ። • የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማስጠንቀቂያ ምን ያህል ተጨባጭ ነው? ዶ/ር ዐቢይ የሚናገሩትን ብቻ በማየት ብዙ ሰው ለውጡ ሥር ነቀል ነው ብሎ አምኖ ነበር። ነገር ግን አሁን የኦዲፒ ትክክለኛ አቋም በተለየም በፌዴራሊዝም ዙርያ የቱ ጋር እንደሆነ ሲታወቅ በሕዝቡ ዘንድ የምኞት ቀውስን እንዳስከተለ ይገምታሉ። ''እንደ ሕዝብ ከደረቅ ሐቅ ይልቅ ምኞታችንን የማመን ደዌ ተጸናውቶናል'' ይላሉ። "ኢትዮጵያ የሁላችንንም አቋም የምንተገብርባት የሙከራ ቦታ አይደለችም" መግለጫው በዚህ ደረጃ ለምን አነጋገረ? ምን አዲስ ነገርስ ኖሮት ነው? እንደ ኢንጅነር ይልቃል አመለካከት በኦዲፒ ዉስጥ አዲስ ነገር አልተፈጠረም። መግለጫውም ቢኾን አዲስ ነገር የለውም። በኢህአዴግ ዉስጥ እያለም ኦዲፒ የዉስጥ ትግል ሲያደርግ ይህንን ሐሳብ እያራመደ ነው የመጣዉ። ሲጀመርም ኦዲፒ ከህወሓት የሞግዚት አስተዳደር ከመውጣት ውጭ ወትሮም የተለየ ፍላጎት አልነበረዉም። "እንዲያዉም እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ ይሄ ሕገ መንግሥት እንዲሻሻል ከማይፈልጉ ድርጅቶች መካከል ከህወሓትም በላይ ግንባር ቀደሙ ኦዲፒ ነዉ" ይላሉ ኢንጂነር ጌትነት። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በበኩላቸው ፖለቲካዊ ትንቢት መስጠት እንደማይፈልጉ ገልጸው ኾኖም ግን ማንም ቢሆን ለድርድር ዝግ መሆን እንደሌለበት ያስገነዝባሉ። "አንደራደርም ሲሉ አሁን ያለው የቋንቋ ፌዴራሊዝም ይቀጥል ነው? ወይስ ኢትዮጵያን ከዚህ ፌዴራሊዝም ውጭ ማስተዳደር አይቻልም ማለት ነው? ይህን የማስረዳት የኦዲፒ ዕዳ ነው" ይላሉ። አቶ ኤፍሬም አክለዉም ኢትዮጵያ ዉስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የየራሳችን አቋም አለን። እና ኢትዮጵያ የሁላችንንም አቋም የምንተገብርባት የሙከራ ቦታ አይደለችም። ስለዚህ አንድን ሐሳብ አንስቶ አንደራደርም የሚለዉ ነገር ለእኔ ትክክለኛ ሐሳብ ነዉ ብዬ አላምንም ብለዋል። የመግለጫው መቼት? ሌላው ውይይትን ያጫረው መግለጫው የወጣበት ጊዜና በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው ነባራዊ ሁኔታ ነው። ከዚህ አንጻር በዚህ ወቅት ይህ መግለጫ ለመውጣቱ ገፊ ምክንያቶች ሲሉ የሚጠቅሷቸው ሦስት መላምቶች አሏቸው፤ ኢንጂነር ይልቃል። ''ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጅማዉን ጨምሮ በተለያዩ ጉባኤዎች ከጠላት ጋር እያበራችሁ ኦሮሞ አገር መምራት አይችልም እያስባለችሁን ነው በማለት ከኦነግ በላይ ለኦሮሞ ተቆርቋሪ እንደሆኑ ለማሳየትና አሁን ያለውን መንግሥት የኦሮሞ መንግሥት መሆኑን ለመግለጽ ጥረት አድርገዋል'' ይላሉ። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' ምናልባት በንንግራቸው አሀዳዊ የሚመስሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፌዴራሊዝም እያፈገፈጉ ናቸው በሚል ከኦነግ ደጋፊዎች ሊያርቃቸው ይችላል። አንደኛው የመግለጫው አንድምታ ይህንን ድጋፍ መልሶ ማጠናከሪያ ይመስላል። ሁለተኛዉ ህወሓት በ44ኛ የምሥረታ በዓሉ የብሔር ብሔረሰቦች መብትና ሕገ መንግሥቱን የምትደግፉ ሰዎች ከጎኔ ኾኑ፣ ፌዴራሊዝሙን እናድን ብሎ ያወጣው ጥሪ የፈጠረው ግፊት ነው ይላሉ ኢንጂነሩ። ''ሦስተኛው ምክንያት ከግንቦት 7 ሰዎች ጋር ያለውን መቀራረብ በማየት የኦሮሞ አክቲቪስቶች ሥልጣን አስወሰዳችሁብን ሲሏቸዉ ስለነበር ለዚያ ምላሸ ለመስጠት ይመስላል።'' መግለጫው አርበኞች ግንቦት 7 ላይ ያነጣጠረ ነው? መግለጫው አርበኞች ግንቦት 7 ላይ ያነጣጠረ ይሆን? በሚል የተጠየቁት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ መግለጫው የእሳቸዉን ፓርቲ እንደማይመለከት፤ አርበኞች ግንቦት 7ም የፌዴራሊዝም ጸር ሳሆን ደጋፊ መሆኑን አውስተዋል። "ኦዲፒ እኛ ላይ የሚያነጣጥርበት ምንም ምክንያት የለም። ይልቅ እኛና ኦዲፒ የምናነጣጥረው ወደ ጋራ ጠላት ነው" ሲሉ በመግለጫው አለመደናገጣቸውንም ጭምር ገልጸዋል። በአንድም ሆነ በሌላ ቅርጹ ፌዴራሊዝምንና ያልተማከለ አስተዳደርን የማይደግፍ ጉልህ ፓርቲ በአገሪቱ በሌለበት ሁኔታ ኦዲፒ ይህን መግለጫ ሲያወጣ ማንን ታሳቢ አድርጎ እንደሆነ አለመገለጹ አንዱ መነጋገሪያ ነው። • ውክልናን በቪድዮ ከዚህም በላይ ኦዲፒ አልደራደርበትም የሚለው ፌዴራሊዝም አሁን ያለውን የቋንቋ ፌዴራሊዝም ነው ወይስ ሌላ ማንኛውንም አማራጭ የፌዴራሊዝም ቅርጽ የሚለውም ሌላው ያልተመለሰ ጥያቄ ነው። አሁን ያለው ፌደራሊዝምን ቅርጽ መቀየር ያስፈልጋል ብለው የሚያምኑት ኢንጂነር ይልቃልም የኦዲፒ መግለጫ ግን የቋንቋ ፌዴራሊዝምን ባለው ሁኔታ ለማስቀጠል ያለመ ስለመሆኑ አይጠራጠሩም። "ደጋግመን ስለወደቅን በሕዝቡ ዘንድ እውነታውን ከመውሰድ ይልቅ ምኞታችንን የማመን አዝማሚያ አለ። ጥሬ ሐቁ ግን ኦዴፒ በፌዴራል ሥርዓቱ አንደራደርም ሲል ይህን ቋንቋን መሠረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አሁን ባለው ቅርጽ እንዲቀጥል አደርጋለሁ ማለት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም" ይላሉ። ምክንያቱን ሲያስረዱም "ኦዲፒ አሁን ባለው የፌዴራሊዝም ቅርጽ መቀጠልን የሚሻውና ይህ ነገር ያለቀለት አድርጎ የሚያየው ወደ 'ኦቶኖሚ'፣ ወደ ኮንፌዴራሽን መሄድ ብሎም ወደ መገንጠለም ለመሄድ ሁለተኛ አጀንዳ ይዞ ስለሚንቀሳቀስ ይህን ፌደራሊዝም ማስቀጠል ይፈልጋል" ይላሉ ኢንጅነር ይልቃል። "የዜግነት ፖለቲካና ፌዴራሊዝም አይጣሉም" ብዙውን ጊዜ የአሐዳዊነት ጠበቃና ከፌዴራሊዝሙ በተጻራሪ እንደቆመ ፓርቲ ተደርጎ የሚታሰበው ግንቦት 7 ከቋንቋ ፌዴራሊዝም እንጂ ካልተማከለ የአስተዳደር አወቃቀር ጋር ጥል የለኝም ይላል። ብዙዎች ግን ፓርቲውን በዚያ መንገድ ለማየት ይቸገራሉ ወይም አይፈልጉም። ቃል አቀባዩ አቶ ኤፍሬም እንደዚያ የሚያስቡን "የሐሳብ ድሀዎች" ናቸው ይላሉ። "የዜግነት ፖለቲካ በአሐዳዊ ሥርዓት ውስጥ ሊገለጽ ይችላል፤ ፌዴራል በሆነ ሥርዓት ውስጥም ሊገለጽ ይችላል። የዜግነት ፖለቲካ በፌዴራል ሥርዓት ውስጥ አይኖርም ብሎ ማሰብ ግን ስህተት ነው።" • አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ አበክረን ከተናገርናቸው ነገሮች ውስጥ ኢትዮጵያን ከአሁን በኋላ ካልተማከለ ሥርዓት ውጭ መምራት እንደማይቻል ነው። ነገር ግን ብዙ ዓይነት ያልተማከሉ ሥርዓቶች አሉ። ከነዚያ ውስጥ እኛ ለኢትዮጵያ የሚበጃት ፌዴራሊዝም ነው ብለን እናምናለን። "በፌዴራሊዝም አያምኑም የሚሉን ሰዎች የመጨረሻ ቃላችን አሁንም ሙሉ በሙሉ እናምናለን ነው" ብለዋል፤ አቶ ኤፍሬም። "ኢትዮጵያን ከቋንቋ ይልቅ ወደ ኅብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ብንለውጣት ጥሩ ነው ብለን በጥቅሉ እናምናለን፤ እንዴት ይሄ ተግባራዊ ይሆናል የሚለው ግን ከእኛም በላይ ነው፤ በእኛ ድርጅት ብቻ የሚፈጸም ነው ብዬም አላምንም" ይላሉ። በቅርቡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በደብረማርቆስ ፌዴራሊዝሙ መፍረስ እንዳለበት የሚያሳስብ አስተያየት መስጠታቸውን በተመለከተ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ኤፍሬም ሁኔታውን አስተባብለዋል። "እኔና አንዳርጋቸው አንድ ድርጅት ውስጥ ነን፤ በፌዴራሊዝም ላይ የተለያየ አቋም ሊኖረን አይችልም። [እሱ] ፌዴራሊዝሙ ይፍረስ አላለም። አሁን ያለው የዘርና የቋንቋ አደረጃጀት ይፍረስ ነው ያለው" ብለዋል። 'አንደራደርምን' ምን አመጣው? የኦዲፒ መግለጫ የቆሰቆሳቸው ሐሳቦች በፌዴራሊዝም ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያጠነጥኑ አይመስልም። ከመግለጫው ይዘት ይልቅ "ለድርድር ዝግ ነኝ" ማለቱ ይበልጥ ያሰጋቸው ጥቂት አይደሉም። ለየትኛውም አማራጭ ሐሳብ በሩ ክፍት መሆኑ የሚታሰበው የዐቢይ አስተዳደር "አንደራደርም" የሚል ጠጣር ቃል፣ ያውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚመሩት መሪ- ፓርቲ መስማት ብዙዎችን ሳይጎረብጣቸው አልቀረም።
news-55486853
https://www.bbc.com/amharic/news-55486853
አዲስ የተመረጡት አሜሪካዊ ሕግ አውጪ በኮቪድ-19 ሞቱ
አዲስ የተመረጡት የሪፐብሊካን ሕግ አውጪ ሉክ ሌቶው በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው አለፈ። የ41 ዓመቱ ሉክ፤ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ የመጀመሪያው የኮንግረስ አባል ናቸው።
የፊታችን እሑድ በይፋ ቃለ መሀላ ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። የተመረጡት የሉዊዝያና ወኪል ሆነው ነበር። በበሽታው መያዛቸውን ታህሳስ 18 አስታውቀው ሆስፒታል ገብተውም ነበር። የሉዊዝያና አገረ ገዢ ጆን ቤል ኤድዋርድስ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ እለት ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አዘዋል። “እኔና ባለቤቴ በሉክ ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። ለቤተሰቡ መጽናናትንም እንመኛለን” ብለዋል አገረ ገዢው። ገዢው የግዛቲቱ ተወካይ ሆነው አገራቸውን ሳያገለግሉ ሕይወታቸው በማለፉ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። ሉክ የሁለት ልጆች አባት ነበሩ። ታህሳስ 19 ሆስፒታል ገብተው ከአራት ቀን በኋላ የጤና ሁኔታቸው አስጊ ስለሆነ የጽኑ ህሙማን ማቆያ ገብተዋል። በማቆያው ሳሉ ትላንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። “ቤተሰባችን በፀሎት እና በተለያየ መንገድ የደገፉንን ሰዎች ያመሰግናል። በዚህ ከባድ ወቅት ግላዊነታችን እንዲጠበቅም እንጠይቃለን” ሲል ቤተሰባቸው መግለጫ አውጥቷል።
news-53196000
https://www.bbc.com/amharic/news-53196000
የህዳሴ ግድብ ድርድርና ለፀጥታው ምክር ቤት የተላኩት ደብዳቤዎች
በህዳሴ ግድብ ላይ ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ድርድር መቋጫ ሳያገኝ ግብፅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ ጠይቃለች።
ግብፅ ባስገባችው ባለስድሳ ሦስት ገፅ ደብዳቤ ላይ ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ኢትዮጵያ ውሃ ከመሙላት እንድትታቀብና ምክር ቤቱ ጣልቃ በመግባት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብላለች። ግብፅ ኢትዮጵያ የግድቡን ሙሌት የምትጀምር ከሆነ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት ስጋት ስለሚሆን ምክር ቤቱ ይህንን ጉዳይ ቸል እንዳይል እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲያሳድርም ጠይቃለች። ለዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ የሰጠ ሲሆን፤ ግብፅ ኢትዮጵያ ግድቡን ውሃ የመሙላት ተግባር በቀጠናው እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ሰላምና ደኅንነት ጠንቅ ነው ማለቷ እንዳሳዘነውም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ሪቬሬ በላኩት ደብዳቤ ገልፀዋል። የሦስትዮሽ ስምምነቱ ሳይጠናቀቅ ግብፅ ምክር ቤቱን ጣልቃ እንዲገባ መጠየቋ ግራ የሚያጋባ ቢሆንም "ድርድሩ ፍሬ አልባ እንዲሆን እየሰራች ከነበረችው ግብፅ" የሚጠበቅ ነው ብሏል። የሦስትዮሽ ስምምነት ከመደረሱ በፊት የግድቡ ሙሌት መጀመር የለበትም በማለት ተቃውሞዋን ያሰማችው ግብፅ ብቻ ሳትሆን ጉዳዩ በመሪዎች ደረጃ እንዲፈታ ያቀረበችው ሱዳን ናት። ሱዳን ለፀጥታው ምክር ቤት ባስገባችው የአቤቱታ ደብዳቤ ኢትዮጵያ የሦስትዮሽ ስምምነት ከመደረሱ በፊት በሚቀጥለው ወር ግድቡን የምትሞላ ከሆነ በታችኛው ተፋሰስ አገራት የሚኖሩ ሚሊዮኖች አደጋ ውስጥ ይወድቃሉ ብላለች። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤትም የህዳሴ ግድብ ላይ ያሉ ቅራኔዎችን ለማየት በመጪው ሰኞ ቀጠሮ መያዙን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ አንድ ዲፕሎማትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። የቪዲዮ ኮንፈረንሱ የተጠራው ግብፅን በመወከል ከአሜሪካ መሆኑንም ዲፕሎማቱ መናገራቸው ተጠቅሷል። በግብፅ ጥያቄ መሰረት ምክር ቤቱ የዝግ ስብሰባ አድርጎ የነበረ ሲሆን ሦስቱ አገራት የላኳቸውንም ደብዳቤዎች ላይ ይፋዊ ያልሆነ ውይይት አድርገዋል ተብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ቃለ አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ ሦስቱ አገራት ያሏቸውን ቅራኔዎች ፈትተው፤ በሰላማዊ መንገድ ድርድሩንም እንዲቋጩ ጥሪ አድርገዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም ሃገራቱ በተፈራረሙት የትብብር መርህ መግለጫ ስምምነት መሠረት ድርድሩን በሰላም እንዲቋጩ መልዕክት ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው። በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይም በመገኘት ጉዳዪን ማስረዳት እንደምትፈልግ በቅርቡ የገለፀችው ግብፅ ሦስቱ አገራት በድርድሩ እንዲቀጥሉና ፍትሃዊና ሚዛናዊ ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ምክር ቤቱ ጣልቃ በመግባት እንዲያረጋግጥ ጠይቃለች። ከዚህ ቀደም የህዳሴ ግድብን በይፋ ስትደግፍ የነበረችው ሱዳን፣ በአሁኑ ሰዓት የአቋም ለውጥ እንዳደረገች ለመንግሥታቱ ድርጅት የላከችው ደብዳቤ እንደሚጠቁም አንዳንዶች ይናገራሉ። ኢትዮጵያ የግድቡን ሙሌት ያለ ታችኛው ተፋሰስ አገራት መሙላት የምትጀምር ከሆነ የሱዳንን ሮዚየርስ ግድብ ደኅንነት እንዲሁም በታችኛው ተፋሰስ አገራትም ላይ አደጋ ይደቅናል ብላለች ሱዳን። ሱዳን ከህዳሴ ግድብ የሚለቀቀው ውሃ የሮዚየርስ ግድብን በጎርፍ የመጥለቅለቅ አደጋ እንዳያጋጥመውም ስጋት አለኝ ብላለች። መለቀቅ የሚገባውንም የውሃ መጠንንም አስቀምጣለች። በሦስቱ አገራት በኩል በድርድሩ ላይ ያለው የፖለቲካ ፈቃደኝነት ተመሳሳይ አይደለም ያለችው ሱዳን፤ የፀጥታው ምክር ቤትም የአገራቱን መሪዎች በመጋበዝ ፖለቲካዊ ፈቃደኝነታቸውንና የቀሩትን ህጋዊ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ እንዲያደርግ ጠይቃለች። ከሰኔ 2 እስከ 10 ድረስ የተካሄደው የህዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቀቅን በተመለከተው ድርድርም ለአገራቱ መሪዎች እንዲተላለፍ ሱዳን ሃሳብ አቅርባ ነበር። የሱዳን የውሃ እና መስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስ ለሪፖርተሮች እንደተናገሩት ከ90-95 በመቶ የሚሆኑ የቴክኒካል ጉዳዮች ላይ መስማማት እንደተቻለ፤ ነገር ግን ሕጋዊ ጉዳዮችና የውሃ ክፍፍል ጋር ተያይዞ አሁንም ቢሆን ምንም ስምምነት አለመደረሱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ ድርድሩ ከህዳሴው ግድብ ውሃ አሞላልና አለቃቀቅ አልፎ በውሃ ድርሻና አጠቃቀም ላይም እንዲሆንና የኢትዮጵያን የወደፊት በአባይ ውሃ የመጠቀም መብትን የሚገድብ ዓይነት ስምምነት ላይ እንዲደረስ ፍላጎቶች ያሉ በመሆናቸው ድርድሩ ወደፊት ሊሄድ አልቻለም ብላለች። ግብጽ በጎርጎሳውያኑ 1959 የተፈረመውና፣ የአብዛኛውን የውሃውን ድርሻ የሚሰጣትን የቅኝ ግዛት ስምምነት አጥብቃ በመያዝ ታሪካዊ ተጠቃሚነት በሚል መርህ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት እንዳላት ደብዳቤው ጠቅሷል። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ያላካተተ ከመሆኑ በተጨማሪ ግብጽ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንዲሁም ሱዳን 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንድታገኝና 86 በመቶ የናይልን ውሃ የምትገብረውን ኢትዮጵያ ያለ ውሃ የሚያስቀር አግላይና ኢፍትሃዊ ስምምነት ነው፤ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊነትንም ይጥሳል ብሏል። ደብዳቤውም ላይ እንደተጠቀሰው ግብጽ በተደጋጋሚ የውሃ ክፍፍል ድርድር ነው በማለት በላይኛው ተፋሰስ አገራት የሚሰሩ ልማቶችን ለማገድ ብትሞክርም በአንፃራዊው ይህ ድርድር የህዳሴ ግድብ ውሃ አለቃቀቅና የግድቡ አሰራርን በተመለከተ እንደሆነ ደብዳቤው ገልጿል። ደብዳቤው ጨምሮም ግብፅ የውሃ ክፍፍል እንዲካተተት በመጠየቋ ድርድሩ እንዲሰናከል ምክንያት ሆኗል ብሏል ሲል ለድርድሩ አለማሳካት ግብፅን ተጠያቂ አድርጓል። "የውሃ ክፍፍል ከሆነ ሌሎች የተፋሰሱ አገራትም ሊሳተፉ ይገባ ነበር፤ እነሱም ተጠቃሚዎች ከመሆናቸው አንፃር በውሃ ክፍፍሉ ሦስቱ አገራት ብቻ ሊወስኑላቸው አይችሉምም" ሲልም የግብፅን አካሄድ አግላይ ነው ሲል ተችቷል። ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና በመፍጠር ለማንበርከክና ምክር ቤቱንም በተሳሳተ መንገድ ለመውሰድ እየሞከረች ነው ያለችው፤ ከሰሞኑ አገራቱ የደረሱባቸው ስምምነቶችም ኢትዮጵያ ምን ያህል ግድቧም ቢሆን ልዩነቶችን ለማጥበብ እየሰራች መሆኑን ማሳያ እንደሆነ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በላከችው ደብዳቤ ላይ ጠቅሳለች። ሦስቱ አገራት ለፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ሲያስገቡ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ግብፅ ከወር በፊት የምክር ቤቱን መተዳደሪያ አንቀፅ 35 በመጥቀስ ያለው ሁኔታ የዓለምን ደኅንነትና ሰላም የሚያደፈርስ ነው ብላ ነበር። ግብፅ በዓመታት ውስጥ ሲደረግ የነበረው ድርድር ፍሬ አለማፍራቱንና ዋሽንግተን ውስጥ በአሜሪካና በዓለም ባንክ አሸማጋይነት ሲካሄድ የነበረው ድርድርም የሦስቱን አገራት ጥቅም ያማከለ ቢሆንም ኢትዮጵያ ውድቅ እንዳደረገው ጠቅሳለች።በቅርቡም የነበረው ድርድር የፈረሰው ከኢትዮጵያ በኩል ፖለቲካዊ ፈቃደኝነት ባለመገኘቱ እንደሆነም ደብዳቤው አትቷል። ኢትዮጵያ ያለሦስትዮሽ ስምምነት የግድቡን ሙሌት እጀምራለሁ ማለቷም ከአምስት ዓመታት በፊት የተፈራረሙትን የህዳሴ ግድብ የትብብር መግለጫ ስምምነትም የሚጥስና የታችኛው ተፋሰስ ሃገራትንም የሚጎዳ ነው ብላለች። የግድቡ ሙሌት መጀመር ለግብፅ ህዝብ አደጋ እንደሚጋረጥም ደብዳቤው ጠቅሷል። ኢትዮጵያ የግድቡን ሙሌት መጀመር የለባትም የሚል አቋም የያዘው ደብዳቤው በይዘትም በቅርቡ ከተላከው ጋር ተመሳሳይ ያለው ሲሆን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ የትብብር መግለጫ ስምምነቱን እንድታከብርና ወደ ድርድሩም እንድትመለስ እንዲያደርጉ የሚጠይቅ ነው። ቀደም ያለው ባለአስራ ሰባቱ ገፅ የግብፅ አቤቱታ ኢትዮጵያ ከግድቡ ሙሌትም እንድትታቀብ ይጠይቃል። ኢስቶኒያ የፀጥታ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር ከመሆኗም ጋር ተያይዞ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳሜህ ሹክሪህ የኢስቶኒያ አቻቸውንም ኡርማስ ሬይንሳሉን ደውለው እንዳነጋገሩ ዘገባዎች አመልክተዋል። ኢትዮጵያም በበኩሏ ለዚህ ምላሽ የሰጠች ሲሆን የግድቡን ውሃ ሙሌት ለመጀመር የግብፅ አዎንታዊ ሁኔታን ማግኘት አስገዳጅ እንዳልሆነ በላከችው ደብዳቤ ጠቅሳለች። ለድርድሩ መቆም እንዲሁም መጓተት ግብፅ ምክንያት እንደሆነች አመልክታለች። ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ ሙሌት በማካሄድም እንደምትጸና አስታውቃለች። ሚያዝያ መጀመሪያ ላይ ባቀረበችውም ዕቅድ መሰረት በመጀመሪያው ዓመት 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትርና፣ በሁለተኛው ዓመትም 13.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃም ለመሙላት ማሰቧንም በደብዳቤው ላይ አካታለች። ይህም ውሃ በታችኛው ተፋሰሰስ አገራት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንደማያደርስና የመጀመሪያ ደረጃ የግድቡ የውሃ ሙሌት መመሪያም የተወሰደው ሦስቱ አገራት ከተስማሙበት የግድብ ትብብር መግለጫ ስምምነት መሆኑንም አፅንኦት ሰጥቷል። ኢትዮጵያ የግብፅን ፈቃድ የማግኘት ህጋዊ ግዴታ እንደሌለበት ያሰመረው ደብዳቤው ግብፅ የግድቡን ድርድር ለማሰናክለ እንደምትሰራ ተጠቅሷል። ደብዳቤው አክሎም ኢትዮጵያ የአባይን ውሃን በፍትሐዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት መርህ የመጠቀም እንጂ የታችኞቹ ተፋሰስ አገራትን በፍጹም የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላትም አረጋግጧል። የግብፅ ለዘመናት የዘለቀ ተጠቃሚነቷን የጠቀሰው ደብዳቤው የአስዋንን ግድብ ስትገነባ ኢትዮጵያን ሳታማክር ሲሆን ግብፅ ይህንኑ አካሄድ በመቀጠል የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት እንዳለም አፅንኦት ሰጥቷል። ይህ ታሪካዊ ስህተት መስተካከል አለበት ያለው ደብዳቤው በተለይም ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ያለ መብራት እንዲሁም በድህነት ውስጥ ላሉባት ኢትዮጵያ ግድቡ ያለውን ጠቀሜታም በዝርዝር ተጠቀምጧል። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢትዮጵያ የግድቡን ወሃ ሙሌት ለማካሄድ ያላትን አቋም እንዲደግፉም ደብዳቤው ጥሪ ቀርቧል። ግብፅ ከምታነሳቸው ቅሬታዎች መካከል ኢትዮጵያ ግድቡን ሙሉ አቅም እየተጠቀመች ድርቅ ቢያጋጥም ችግሩ የሦስቱም አገራት ጉዳይ ነው የሚል አቋም ላይ መድረሷን ነው። ረዘም ላለ ጊዜ ድርቅ የሚከሰት ከሆነ ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ጥቅምን ለመጠበቅ ዋስትና ልትሰጠን ይገባል በማለትም ግብፅ ትከራከራለች። ኢትዮጵያ በበኩሏ የግብፅ ሃሳብ በአባይ ወንዝ ላይ ተፈጥሯዊ መብት እንዳይኖራት ወይም ምንም ዓይነት የውሃ ልማት ያልተገነባበት ፍሰት እንዲኖር የሚጠብቅ ነው በማለትም ተችታለች።
news-50905758
https://www.bbc.com/amharic/news-50905758
አቶ ለማ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው የወጡባቸው አጋጣሚዎች
'ዘ ኢኮኖሚስት' የተሰኘው መጽሄት በ2018 በኢትዮጵያ ''እጅግት ታዋቂው ፖለቲከኛ'' ሲል ለማ መገርሳን መርጦ ነበር። ዛሬም የቀድሞ የጨፌ አፈ-ጉባኤና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት የአሁኑ የመከላከያ ሚንስትሩ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተጽህኖ ፈጣሪነታቸው እንደጎላ እና መነጋገሪያ እንደሆኑ ነው።
ከሦስት ሳምንታት በፊት አቶ ለማ መገርሳ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የኢህአዴግ መዋሃድ እና ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የመደመር ፍልስፍና ጋር እንደማይስማሙ መናገራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ እና አቶ ለማ መገርሳ በተለያዩ መድረኮች ላይ የሚያደርጉት ንግግር እና አንዱ ለአንዱ የሚያሳዩት ተግባራት ሁለቱ ፖለቲከኞች ከትግል አጋርነታቸው በላይ የእርስ በእርስ ቅርርባቸው ከፍ ያለ እንደሆነ የሚያሳይ ነበር። • በመንግሥት መኪና የጦር መሳሪያ ሲዘዋወር ተያዘ • "የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ይኖራሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ ታዲያ አቶ ለማ በመገናኛ ብዙሃን ቀርበው በጠቅላይ ሚንስትሩ የመደመር ፍልስፍና እንደማይስማሙ ሲናገሩ በተለይ በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ድንጋጤን የፈጠረ ክስተት ነበር። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደግሞ ከፍተኛ የፓርቲ አባላቶቻቸው አቶ ለማ ያላቸውን የሃሳብ ልዩነት በማጥበብ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር አብሮ ለመስራት መግባባታቸውን ተናግረዋል። በወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪነታቸው የማይካደው አቶ ለማ፤ ከፍ ሲልም "ለመውደቅና ለመበታተን ከጫፍ ደርሳ የነበረችውን ኢትዮጵያ በአንድነቷ እንድትቀጥል ያደረጉ ሰው ናቸው" ተብለው እስከ መወደስ ይደርሳሉ። ለመሆኑ ትውልድ እና እድገታቸው ምሥራቅ ወለጋ የሆኑት የ44 ዓመቱ አቶ ለማ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጎልተው እንዲወጡ ያስቻሏቸው አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው? "ማስተር ፕላን" 2008 ዓ.ም የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተሰኘውን እቅድ በመቃወም በኦሮሚያ ሕዝባዊ ተቃውሞ የተቀጣጠለበት ዓመት ነበር። ታዲያ የሕዝቡን ተቃውሞ ለማርገብ ከፍተኛ የክልሉ መንግሥት ባለስልጣናት ወደተለያዩ ስፍራዎች በመጓዝ ሕዝቡን የማወያየት ሥራዎችን ሲያከናውኑ ነበር። በወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ወይም ጨፌ አፈ-ጉባኤ የነበሩት አቶ ለማም ወደ ቡራዩ ከተማ በመጓዝ ከከተማው እና ከአካባቢዋ ከተወጣጡ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድረገዋል። በውይይታቸው ወቅት ማስተር ፕላኑ ሕዝብ የማይፈልገው ከሆነ ሊቀር የሚችል እቅድ ስለመሆኑ ተናግረው ነበር። • በሞጣ የተፈጠረው ምንድን ነው? የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ማስተር ፕላኑ መተግበሩ እንደማይቀር በሚናገሩበት ወቅት፤ የክልሉ ባለስልጣናት ማስተር ፕላኑን ለሕዝብ ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም በማስረዳት በተወጠሩበት በዚያን ጊዜ ነበር አቶ ለማ "ማስተር ፕላኑ ሕዝብ ካልፈለገው ይቀራል፤ ከሰማይ የሚወርድ ነገር የለም" የሚል ይዘት ያለው ንግግር ያደረጉት። በኦሮሚያ "የኢኮኖሚ አብዮት" የሚል እንቅስቃሴ በስፋት አስጀምረው ነበር። ጥር 2008 ላይ የቀድሞ ኦህዴድ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሙሉ በሙሉ ኦሮሚያ ላይ ተግባራዊ እንደማይደረግ ወሰነ። ከዚያም አቶ ለማ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት ሆነው ተሾሙ። የለማ ቡድን "ቲም ለማ" አቶ ለማ የኦህዴድ ሊቀ መንበር እና የክልሉ ፕሬዝደንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ እርሳቸው የመረጧቸውን አባላት በመመልመል 'ቲም ለማ' የተሰኘ ቡድን እንዳቋቋሙ ይነገራል። ይህ ቡድን ሕዝቡ በወቅቱ ያነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎችን የክልሉ መንግሥት ጥያቄ በማድረግ ምላሸ ለመስጠት ጥረት ያደርግ ነበረ። • የሐኪሞች እጅ ጽሑፍ የማይነበበው ለምንድን ነው? በዚያን ወቅትም የክልሉ ገዢ ፓርቲ ኦህዴድ በታሪኩ 'ኦሮምኛ የፌደራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እታገላለሁ" ያለው። ተከትሎም በሺህዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ከእስር መልቀቁ ፓርቲው በኦሮሚያ ያለው ድጋፍ እንዲጨምር አድርጎለት ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በ'ቲም ለማ' ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክቱ ነበር ለውጡ በተቃረበበት ጊዜ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል ድንበር አቅራቢያ ላይ ተከስቶ የነበረው ግጭት በኦህዴድ ላይ ከፍተኛ ጫና ከፈጠሩ ክስተቶች መካከል የሚጠቀስ ነው። በዚህም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በጨለንቆ አካባቢ 16 ሰዎች መገደላቸውን በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ወጥተው መቃወማቸው ከፍተኛ ድጋፍን አስገኝቶላቸዋል። አቶ ለማ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከክልሉ እውቅና ውጪ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በመግባት በንጹሃን ላያ አድርሷል የተባለውን ጥቃትና ግድያን በግልጽ ነቅፈው ነበር። 'ጌታችን ሕዝባችን' ጥር 4/2008 የኦህዴድ 27ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓልን በማስመልከት በአዳማ ከተማ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ አቶ ለማ ለፓርቲያቸው አባላት ". . . ጌታችን ሕዝባችን ነው። የክልላችን ሕዝብ ነው። ለሌላ ጌታ መስገድ የለብንም" በማለት ተናግረው ነበር። ይህ የአቶ ለማ ንግግር ህውሓት በኦህዴድ ላይ የነበረውን የበላይነት የሰበረ ነው በማለት አንዳንድ ድርጅቱንና የአገሪቱን ፖለቲካ በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። • የኦሮሞና የሶማሌ ግጭት የወለደው የቴሌቭዥን ጣቢያ ዶ/ር ሄኖክ ገቢሳ "ህዝብ ተስፋ ቆርጦበት የነበረው ኦህዴድ ተስፋ እንዲዘራበት ያደረገ ንግግር ነው" ሲሉ ያክላሉ። "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" ከለውጡ ማግስት ጀምሮና በተከታይ በነበሩት ጊዜያት አቶ ለማ በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙበት ወቅት ነበር። ከዚህ ቀጥሎ ያደረጉት ንግግር ከክልላቸው አልፎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የመንግሥት ባለስልጣናትን፣ አባ ገዳዎችን፣ አርቲስቶችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን ይዘው ወደ ባህር ዳር አቀኑ። ይህ የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ ወንድማማችነትን ለማጠናከር ባለመው መድረክ ላይ "ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው" በማለት ያደረጉት ንግግር በበርካቶች ተወዳጅነትን አስገኘቶላቸዋል። በወቅቱ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ባስገቡበበት ወቅት፤ ተሰናባቹን ጠቅላይ ሚንስትር ሊተኩ ይችላሉ ተብለው በስፋት ስማቸው ሲነሱ ከነበሩት መካከል አቶ ለማ መገርሳ አንዱ ነበሩ። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሊያድኑት የነበረው ለገሰ ወጊ ማን ነበረ? ሸገር ታይምስ የተሰኘው መጽሄት በአንድ ዕትሙ አቶ ለማ ኢትዮጵያን በችግር ግዜ ሊያሻግሯት የሚችሉት "ሙሴ" ሲል በፊት ገጹ ላይ ይዟቸው ወጥቶም ነበር። ስልጣን አሳልፎ መስጠት ጥር 2010 ዓ.ም ላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ብዙ ያልተለመደ ክስተት በኦህዴድ ውስጥ ተፈጸሟል። ነገሮች ከቁጥጥራቸው ውጪ እየሆኑና አገሪቱም ወደ አሳሳቢ አቅጣጫ እያመራች መሆኑን ተገነዘቡት የወቅቱ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሥራ መልቀቂያ አስገቡ። ይህንንም ተከትሎ ምንም እንኳን የፌደራሉ ምክር ቤት አባል ባይሆኑም ብዙዎች አቶ ለማ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ ሊይዙ ይችላሉ ብለው ግምት ሰጥተው ነበር። ነገር ግን የፌደራሉ ፓርላማ አባልና የፓርቲያቸው ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ዶ/ር ዐብይ ወደፊት እንዲመጡ መንገድ ለማመቻቸት ሲሉ የኦህዴድ ሊቀ መንበርነት ቦታቸውን እንዲይዙ ማድረጋቸው በርካቶችን አስደንቋል። ይህም ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበርነት ቦታን እንዲይዙና በተለመደው አሰራራም የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር እንዲሆኑ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ይስማሙበታል። ወደ መድረኩ መመለስ አቶ ለማ በመላው አገሪቱ ትኩረትን ያገኙ ፖለቲከኛ መሆን በመቻላቸው ተግባራቸውን ንግግራቸውን በርካቶች በቅርበት ይከታተኩት ነበር። በዚህም በሌሎች ሰዎች ጥቆማ በየዓመቱ በጎ ሥራ ለፈጸሙ የሚሰጠው "የበጎ ሰው ሽልማት" ለአቶ ለማ በ2010 ዓ.ም ተበርክቶላቸዋል። አቶ ለማ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትነትን ለቀው የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትርነት ቦታን ከያዙ በኋላ በፖለቲካው መድረክ ላይ ብዙም አይታዩም ነበር። ይህም በርካታ መላምቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲሰነዘሩ ምክንያት ሆኖ ነበር። ለረጅም ጊዜ ድምጻቸው ጠፍቶ የነበሩት አቶ ለማ ዋና የመነጋገሪያ ርዕስ ሆነው የተከሰቱት የኢህአዴግን መክሰም ተከትሎ አዲሱ 'ብልጽግና ፓርቲ' እውን ሲሆን ነበር። አቶ ለማ በውህደቱና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር እሳቤ ላይ ልዩነት እንዳላቸውን በፓርቲያቸው ውስጥ ተሰሚነት እንደሌላቸው በይፋ ሲገልጹ ግራ መጋባትን ፈጥሮ ነበር። ይህም የአገሪቱን ፖለቲካ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሚመሩት መንግሥት ላይ ከባድ ቀውስ ያስከትላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ እንዲፈጠር አድርጎ ነበር። አቶ ለማ ያሉበትን ሁኔታ ይፋ ካደረጉ በኋላ በመከላከያ ሚኒስትርነታቸው ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ለሥራ ወደ አሜሪካ ደርሰው ከተመለሱ በኋላ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለእሳቸው ቅርብ በሆኑ የተለያዩ ሰዎች አማካይነት የሽምግልናና የማቀራረብ ጥረት ሲደረግ መቆየቱ ለጉዳዩ ቅርበት ያለቸው ሲገልጹ ቆይተዋል። በመጨረሻም አቶ ለማ ራሳቸው ወጥተው ባያረጋግጡም ወይም ባያስተባብሉም ፓርቲያቸውና አንዳንድ የፓርቲው ከፍተኛ ባለስልጣናት የተፈጠረው ልዩነት ላይ ውይይት ተደርጎ ከመግባባት ላይ መደረሱንና ከአዲሱ ፓርቲ አብረው ለመስራት መስማማታቸው ተነግሯል።
51555780
https://www.bbc.com/amharic/51555780
አዲሱ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ፈንታ በሹመታቸው ዙሪያ ምን ይላሉ?
ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልልም የምሁራን መማክርት ጉባኤ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው።
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥራ አመራርና አስተዳደር፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በቀጠናዊና አካባቢያዊ ልማት ጥናት (ሪጂናል ኤንድ ሎካል ዴቨሎፕመንት ስተዲስ) ዘርፍ አግኝተዋል። ሦስተኛ ዲግሪያቸውንም በልማት ጥናት (ዴቨሎፕመንት ስተዲስ) ኔዘርላንድስ ዘሄግ ከሚገኘው ኢንስቲትዩት ኦፍ ሶሻል ስተዲስ ማግኘታቸውን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ገልፀዋል። ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ የአማራ ክልል ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል። ቢቢሲ ትናንት አመሻሹን ደውሎ ለዶ/ር ፈንታ የተወሰኑ ጥያቄዎች አቅርቧል። ምን አስተዋፅኦ አደርጋለሁ ብለው ነው ሹመቱን የተቀበሉት? ዶ/ር ፈንታ፡ ብዙ ነገር አበረክታለሁ ብዬ አስባለሁ። እንደገና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት ለግማሽ ክፍለ ዘመን የሚሆን የኢትዮጵያ ገበሬ ከኪሱ፣ እናቶች ከመቀነታቸው ፈተው ያስተማሩት ኢንተሌክችዋል [ምሁር] ቡድን ተገልሎ ቆይቷል፤ በገጠመው የታሪክ አጋጣሚ ምክንያት። በመሆኑም ጉዟችን አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን አዳጋች እየሆነ መጥቷል። ስለዚህ እኔ በግሌ ከእንግዲህ በኋላ ከውጪ በመሆን፣ ፖለቲካውን በመተቸት የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ማስተካከል አይቻልም [ብዬ አምናለሁ]። ገብቶ የምንችለውን ሁሉ፣ ፖለቲከኞችንም በማገዝ መለወጥ ይቻላል የሚል ትልቅ እምነት አለኝ። • እነ አቶ በረከት የጤና ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ አጭር ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠየቁ ሙያዬ ሕዝብ አስተዳደርና ልማትና አመራር ነው። ከመጀመሪያ ጀምሮ በሕዝብ አስተዳደር ነው የተመረቅኩት። ሁለተኛ ዲግሪየዬን የጨረስኩት በአካባቢና ክልላዊ ልማት (ሪጂናል ኤንድ ሎካል ዴቬሎፕመንት ስተዲስ) ነው። ሦስተኛ ዲግሪዬ ልማት ጥናት (ዴቬሎፕመንት ስተዲስ) ነው። በመሰረታዊነት ደግሞ ዴቬሎፕመንት ስተዲስ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ነው። ስለዚህ የምርምር ጽሑፎቼ፣ የማስተማር ሥራዬ፣ አጠቃላይ ሕይወት ዘመኔ ከሕዝብ አስተዳደር ጋር ቁርኝት ያለው በመሆኑ እጅግ አስተዋጽኦ ማድረግ እችላለሁ ብዬ እገምታለሁ። ግምት ብቻ ሳይሆን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደምችል እምነት አለኝ። ፖለቲከኛ መሆንና በተማሩበት ዘርፍ ማገልገል [academician] መሆን ይለያያል ለሚሉ ሰዎች ምን አስተያየት አለዎት? ዶ/ር ፈንታ፡ እኔ የመጣሁት በተማርኩበት ሙያ ለማገልገል ነው። ዝም ብሎ የፖለቲካ ፖዚሽን [ሥልጣን] ለመውሰድ አይደለም። በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በኢትዮጵያ በሚደረገው የሕዝብ አገልግሎትም መሰረታዊ የፖለቲካ እንቅፋቶቻችንና ድክመቶቻችን ወደኋላ መለስ ብለን በምናይበት ጊዜ የሕዝብ የአገልግሎት እርካታ ማነስ [አንዱ] ነው። መሠረታዊ ችግራቸው ይህ ነው። ይህንን ለማገዝ ደግሞ ፖለቲከኞች ብቻቸውን አይደለም። በዚህ ሙያ ላይ የተማሩ ሰዎች ትልቅ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ ብቻ ሳይሆን ያበረክታሉ። ሌላኛው ፖለቲከኛነትና አካዳሚሺያን መሆን [ምሁርነት] በፖዚሽን [በሥልጣን] የተለያየ ነው። አካዳሚክስ ፖለቲካን አያውቁም ማለት ግን አይደለም። • "በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር የተከሰተው ለመላው ሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት ነው" የአማራ ክልል ደኀንነትና ጸጥታ ካውንስል እኔ በመጀመሪያ ዲግሪዬ ማይነሬ ፖለቲካል ሳይንስ ነው፤ ይህንን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ፖለቲከኛ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲካ ራሱ ምንድን ነው? የሚሉትን ጠንቅቄ አውቃለሁ። አንድ ይኼ ነው። ሁለተኛ እኔንና መሠሎቼ ያደግነው በዚህ ማህበረሰብ ውስብስብ በሆነ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ ነው። ስለዚህ የየቀን ኑሯችን፣ የዕለት ተዕለት ኑሯችን፣ የፖለቲካ ኃላፊነት መውሰድና አለመውሰድ ካልሆነ በስተቀር ልዩነቱ፣ እያንዳንዱ ሰው፣ እንኳን እኔ በሙያው ቅርብ የሆንኩትና ያለፍኩበት ሰው ይቅርና ከሙያውም ሩቅ የሆነ ሰው ስለ ፖለቲካ የራሱ ግንዛቤ ብቻ ሳይሆን አቋም አለው። ስለዚህ ወደፊትም መታረም ያለበት ኢንቴሌክችዋልን ቴክኖክራት አድርጎ ብቻ መሳል ተገቢ አይደለም። የሕዝብን ፍላጎት ለማርካት ነው እዚያ ያሉት። የሕዝብን ፍላጎት ለማርካት ደግሞ አንዱ ትልቅ ጎዳና እንዲህ አይነትን አገልግሎት መስጠት ነው። ስለዚህ እኔ አሁን አንድ የፖለቲካ ሥልጣን እንዲሁ ወሰድኩ ብዬ ሳይሆን ሕዝብን በሰፊው ላገለግልበት ከምችልባቸው አጋጣሚዎች አንዱ ትልቁ አጋጣሚ ነው የሚል የግል እምነት ነው ያለኝ። ስለዚህ ፖለቲካውን ምሁራን አያውቁም ብለው የሚደመድሙ ሰዎች ካሉ እኔ ትክክል አይደለም ብዬ ነው የማምነው። በብዙ አገሮችም ቢሆን የፖለቲካ ፖዚሽን [ሥልጣን] አያውቁም እንጂ ፖለቲካው የሚመራው በምሁራን ነው። ስለዚህ እምነቴ ይህ ነው። እርግጠኛ ነኝ የፖለቲካ ግንዛቤየም በቂ ነው። ከሕዝብ ጋር ኖረናል። የሕዝብ የፖለቲካ ጥያቄዎችን ጠንቅቀን እናውቃለን። የፖለቲካ አመራሩ ደግሞ በእንዲህ አይነት ቢታገዝ የበለጠ ውጤታማ፣ አሁን ካለንበት ደግሞ ወደፊት ለመራመድ ይጠቅማል ብዬ ነው የማምነው። የተካሄደውን ሹም ሽር በተመለከተ የምክርቤት አባላት ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ከቀረቡት ቅሬታዎች መካከል ሹመቱ (ከክልል ተነስተው ወደ ፌደራል የሄዱ) "ክልሉን ለማዳከም የተሠራ ነው፤ ጊዜውን የጠበቀም አይደለም" የሚሉት ይገኙበታል። እዚህ ላይ የግል አስተያየትዎ ምንድን ነው?በርግጥ የሚያሰጋ ነገር አለ? ዶ/ር ፈንታ፡ እኔ የሚያሰጋ ነገር አይታየኝም። እነዚያ ወንድሞቻችን ወደ ፌደራል ኃላፊነት የሄዱት በዚህ ክልል ተወልደው፣ በዚህ ክልል ሕዝብ ውስጥ ያገለገሉ ናቸው። አሁንም ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። በአገር አቀፍ ደረጃ ሄዱ ማለት የዚህን ክልል ፖለቲካ ጭራሹኑ ዘንግተው ጥለውት ሄዱ ማለት አይደለም። የክልሉ ፖለቲካ በማዕከላዊ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ ውክልና እንዲኖረው፣ የክልሉ መሠረታዊ የሆኑ ጥቅሞች በማዕከላዊ ደረጃ፣ የፖለቲካ ጥቅሞች፣ የኢኮኖሚ ጥቅሞች፣ የማህበራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ የሚያደርጉ ናቸው። እኛ ደግሞ ከእነዚህ ሰዎች ጋራ በተለያየ የቴክኖክራት ወይንም ደግሞ የሙያ አገልግሎት ስንደግፍ እንዲሁ ዛሬ ከሰማይ የተወለድን ወይንም ዱብ ያልን ሰዎች አይደለንም። በመሰረቱ የሌሎቹ እንደተጠበቀ ሆኖ ሁለት ሰው እኮ ነው አዲስ የመጣው። እኔና ዶ/ር ሰዒድ ነን። ዶ/ር ሙሉነሽ የቢሮ ኃላፊ ሆና ያገለገለች ናት። ሁለት ሰው መጣና ያኛው እንዲህ ሆነ የሚለው ነገር እኔ እንደግል ብዙም አይታየኝም። • የማንነት ጥያቄዎች የጎሉበት የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ ከአማራ ክልል ተነስተው ፌደራል ስለሄዱ የፖለቲካ ሥርዓቱን ይዘነጋሉ የሚለውን ብዙም አልጋራም። "ሴራ ነው" የሚሉ ግለሰቦች የራሳቸው መብት ነው። ወደ ፖለቲካ ዓለም ስትመጪ ልትማሪ የሚገባው ትልቅ ነገር ግለሰቦች የሚመስላቸውን ሃሳብ ያራምዳሉ። ብዙኃኑን የገዛው ወደፊት ይኼዳል ማለት ነው። ዛሬም የሆነው ይህ ነው። ሃሳባቸውን የሰጡ ሰዎችን ከመጥፎነት፣ ከተለያየ ችግር ነው ብዬ አልፈርጅም። እንደውም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደፊት እንዲራመድ ከተፈለገ ከፍረጃ መውጣት መቻል አለብን። እያንዳንዱ ሃሳብ በራሱ ሜሪት [ባለው ዋጋ] ቆሞ መሄድ አለበት። ለሕዝቡ ወይንም ደግሞ ውሳኔ ለሚሰጠው አካል እንደዛሬው የምክር ቤት አባላት የጉዳዩን ምንነት ቁልጭ አድርጎ በማውጣት ብዙኃኑ የሚገዙት አድርጎ ነው መሸጥ ያለብን እንጂ እንዲሁ ገና ከመጀመሪያው ላይ የሆነ ነገር ለጥፈንለት ይኼ ነው ካልን [አስቸጋሪ ነው]። አንዱ ፖለቲካችን ወደፊት እንዳይንቀሳቀስ ቸንክሮ የያዘው ችግር ፍረጃ ነው። ይህ የግል ሃሳቤ ነው። ሰዎቹን ግን አፕሪሺየት የማደርገው [የማደንቀው] ፣ ያመኑበትን ነገር በቀጥታ፣ በግልጽ ማንፀባረቃቸውን ነው። መለመድ ያለበትም፣ ኢትዮጵያ ወደፊት ልትራመድ የምትችለውም እንዲህ ዓይነት ሀሳቦችን አንሸራሽሮ በመጨረሻ ላይ ሕዝብ ያመነበትን ወይንም የሕዝብ ወኪሎች ያመኑበትን ሲያሳልፉት ነው። ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለምናደርገው ጉዞም ራሱን የቻለ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብዬ አምናለሁ። በክልሉ ሕዝብ የሚነሱ በርካታ ጥያቄዎች አሉ። በግልዎ ሕዝቡን ለማገልገል ምን ላይ ትኩረት ለማድረግ አስበዋል? ዶ/ር ፈንታ፡ እንዳልሽው ብዙ ጥያቄዎች አሉ። የዚህ ክልል፣ የሕዝቡ ትልቁ ጥያቄ መጀመሪያ የሚፈታው ጥያቄዎቹን ጊዜ ሰጥቶ በሰከነ፣ በተናበበ፣ በተረጋጋ መንፈስ፣ አገራዊ አንድነታችንን አባቶቻችን ዋጋ የከፈሉባትን አገር ሊያስቀጥል በሚችል፣ የአማራ ሕዝብ ጥቅም የሚያስከብር ፖለቲካ ለመሥራት መደማመጥ ያስፈልጋል። መስከን ያስፈልጋል። ስለዚህ እነዚህ በሰከነ መንፈስ ጊዜ ወስደን የምንፈታቸው ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ለጠየቅሽኝ ጥያቄ በአስቸኳይ መጀመር አለበት ብዬ የማምነው የአማራ ሕዝብ የሕዝብ አገልግሎት በበቂ ሁኔታ እንዲዳረሰው ከማድረግ ነው። • የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሞጣ የደረሰውን የቤተ እምነት ተቋማት ቃጠሎ አወገዘ በፍርድ ቤቶች ዜጎች ሄደው ያለመጉላላት፣ በጤና ተቋማት ሄደው ያለመጉላላት፣ ባለን ሀብት ሙሉ ጊዜያችንን መስዋዕት አድርገን ለዜጎች ጥቅምና ፍላጎት የሚቆጭ የመንግሥት ሠራተኛ እንዲኖር ማገዝና ማበረታታት፣ አብሮ መሥራት [እንዲሁም] አርዓያ ሆኖ ማሳየት የሚሉት ለኔ የመጀመሪያዎቹ ናቸው። ምክንያቱም ለዜጎች ባለን አቅም፣ ባለን ሃብት አገልግሎት ከሰጠናቸው ሌሎቹን በመደማመጥ ወደፊት መሄድ እንችላለን። ስለዚህ የእኔ የመጀመሪያ ትልቁ ሥራዬ የሚሆነው ሲቪል ሰርቪሱ ወይንም የመንግሥት ሠራተኛው በራሳችን ብዙ የምንለውጠው ነገር እንዳለ አምነን እንድንሠራ ጉልበት መሆን፣ ማበረታታት፣ ማነቃቃት ለሕዝባችን የማናደርገው ነገር ሊኖር እንደማይገባ፣ ሌሎች የምንጠይቃቸውን ጥያቄዎች እኛ በአቅማችን በእጃችን ውስጥ ያለውን ነገር አሟጠን ተጠቅመን ከዚያ በኋላ ይህ ይገባናል ብለን እንድንጠይቅ የሚያስችል አስተሳሰብና ሥነ ልቦና እንዲኖረን ማድረግ ነው። ሕዝቡ ከሚያነሳቸው ጥያቄዎች መካከል በቅርቡ በሰላማዊ ሰልፍም ሲጠይቅ የነበረው እና የታገቱ ተማሪዎችን የተመለከተው ጉዳይ ነው። እርሱን በተመለከተ ለመሥራት ያሰቡት አለ? ዶ/ር ፈንታ፡ ዛሬ እዚህ ቦታ ላይ ስለመጣሁ ሳይሆን ቀድሜ በነበርኩበትም ቦታ ላይ፣ በመማክርት ጉባኤም ሆነን ይህ ጉዳይ እጅግ የሚያሳስብ፣ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄም ነው መሆን ያለበት። ምክንያቱም የታገቱ ልጆች የአማራ ልጆች ስለሆኑ ብቻ ሌላው ተኝቶ የሚያድርበት አገር ከተፈጠረ ለነገ ምንም ዓይነት ዋስትና ሊኖረን ስለማይችል። ነገር ግን ለዚህ ጥያቄ የአማራ ክልል መንግሥት ከማዕከላዊ መንግሥት ጋራ የማይቋረጥ፣ ያላሰለሰ፣ ቀጣይነት ያለው፣ ድምዳሜው የሚታወቅበትና የሚቋጭበት ሥራ ወጥ በሆነ መንገድ ሠርቶ፣ እየተሰቃዩ ላሉ ቤተሰቦቻቸውና ለሕዝቡም ባጠቃላይ ምላሽ መሰጠት መቻል አለበት። ምላሽ የሚሰጥበትን ስርዓት እንዲሁ በሚዲያ ላይ ወጥቶ በመናገር ሳይሆን ያላሰለሰ ሥራ መሥራትና ይህንን ጉዳይ መቋጨት አለበት። • "የሰኔ 15 ግድያ በጄነራል አሳምነውና ለክልሉ ተቆርቋሪ ነን በሚሉ አክቲቪስቶች የተጠነሰሰ ነው" የታገቱት ወገኖቻችን ማንኛውም ሥራ ተሰርቶ ወደቤተሰቦቻቸው የሚቀላቀሉበትና ሁኔታዎቹ በግልጽ የሚታወቁበትን ሂደት ማወቅ፣ ምክንያቱም ከእንግዲህ በኋላ እንዲሁ ዝም ብለን ብንቀጥል እያንዳንዳችን መረዳት ያለብን ከታገቱት ውስጥ የእኔ ልጅ ብትሆን፣ የኔ እህት ብትሆን፣ የኔ ወንድም ቢሆን ብሎ ነው ሁሉም ማሰብ ያለበት። በሃገር መሪም ደረጃ ያሉ በክልልም አመራር ደረጃ ያለው፣ እያንዳንዱ ዜጋ ማሰብ ያለበት በዚህ ደረጃ ነው ብዬ ነው የማምነው። ይኼ ሥራ ይሰራል። ለዚህ ስራ እንዲሰራ ደግሞ የበኩሌን ያላሰለሰ ጥረት አደርጋለሁ ብዬ አምናለሁ። ምን ተግዳሮት ይገጥመኛል ብለው ያስባሉ? ዶ/ር ፈንታ፡ አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ይቅርና፣ በማንኛውም የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታቸው የተረጋጋ በሆኑ አገሮችም ቢሆን አዲስ ቢሮ ስትመጪ የተለያየ ኃሳቦች አሉ። እነዚያን ሀሳቦች እንደ ፎቶ ኮፒ ማሽን ኮፒ እያደረግሽ የምትልኪበት አይደለም። ሀሳብሽን ለመሸጥ ጊዜ ይጠይቃል። ሀሳብሽን አሳምነሽ ሌሎቹ ገዝተውት፣ ገበያ ላይ እንዲያውሉት ለማድረግ ጊዜ ይጠይቃል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ደግሞ እንደሚታየው ራሱን የቻለ ፈተና ስለገጠመው እነዚህን ነገሮች በቀላሉ ነገ ጠዋት ሸጬ ዋጋ አውጥተው አገኛለሁ የሚለው ፈታኝ ነው። እነዚህን ሀሳቦች ለሕዝብ፣ ለመንግሥት ሠራተኛው፣ ለፖለቲካ ኃላፊዎች፣ በበቂ ሁኔታ ማስረጽ ጊዜ ይወስዳል። እነዚህን ሥራዎች በመጣደፍ ሳይሆን በተረጋጋ ሥራ ካልሠራናቸው ራሳቸውን የቻሉ ፈተናዎችም ይሆናሉ። • የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ ይኼ ካልሆነ፤ በአንድ ምሽት ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ምናልባትም ከስበት ተቃራኒ የሚሄድ ይሆናል። በቃ የሚቀበል ሕዝብ የለም፣ የሚቀበል አመራር የለም፣ ብለን ቶሎ ተስፋ እንዳንቆርጥ የሥነ ልቦና ዝግጅት ስላለኝ ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችም በዚህ መንገድ እንወጣለን ብዬ ነው ተስፋ የማደርገው።
50612204
https://www.bbc.com/amharic/50612204
“ኦዲፒ ዋጋ የተከፈለባቸውን ጥያቄዎች ወደ ጎን መተው አይገባውም” ፕ/ር መረራ ጉዲና
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትርና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ፤ የኢሕአዴግን ውህደት እንደማያምኑበት ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ገልፀዋል።
"የሀገሪቱን ፖለቲካ በሚፈለገው ፍጥነት ወደፊት ለማስኬድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና በመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መካከል ያለው መግባባት ወሳኝ ነው" "መዋሀዱ ትክክል አይደለም። ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም፤ ወቅቱም አይደለም" ያሉት አቶ ለማ፤ በመደመር ፍልስፍናም እንደማይስማሙ ከራድዮ ጣቢያው ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ መናገራቸው ተዘግቧል። አቶ ለማ፤ የኢሕአዴግ ምክር ቤት የፓርቲዎችን ውህደት ባፀደቀ ጊዜ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንደነበር አስታውቀው ስለ ሂደቱ ግን ለጣቢያው ከማብራራት ተቆጥበዋል። አቶ ለማ መደመርን የተቃወሙበትን ምክንያት ለቪኦኤ ሲያስረዱም፤ በአጠቃላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ድረስ የፓርቲዎች ውህደትን በተመለከተ የተለየ ሀሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል። • የ31 ዓመቱ ኢሕአዴግ ማን ነው? • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "መደመር" መጽሐፍ ተመረቀ • የጠቅላይ ሚኒስትሩ መጽሐፍ ምን ይዟል? ይህንንም ለሥራ አስፈጻሚውና ለሁሉም መናገራቸውን መግለፃቸው በጣቢያው ላይ ተላልፏል። አቶ ታየ ደንደኣ ስለ ብልፅግና ፓርቲ አመሠራረት ሂደት፣ ፋይዳዎቹና የአቶ ለማ በውህደቱ አላምንም ማለትን አስመልክተው ከኤስቢኤስ አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ማድረጋቸውን በፌስቡክ ገፁ ላይ አስነብቧል። ሬዲዮው አክሎም አቶ ታዬ፣ "አቶ ለማ በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ውህደቱ አስፈላጊ እንደሆነና የመደመር ዕሳቤ ከኢትዮጵያ ዐልፎ ለምሥራቅ አፍሪካም ጠቃሚ ሃሳብ እንደሆነ ተስማምተው ነው ያጸደቁት፤ የልዩነት ሃሳብ አልሰማንም። ከዚያም አልፎ በኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴና ጉባኤ፣ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ ሁሉ የተለየ አቋም አላንጸባረቁም። በዚህ መሄድ አለብን የሚል የተለየ አማራጭ ሃሳብም አላቀረቡም" ማለታቸውን አስታውቋል። ይህንን የአቶ ለማ አቋም አስመልክተን ያነጋገርናቸው በዋሺንግተንና ሊ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር የሆኑት ሔኖክ ገቢሳ (ዶ/ር) ውህደት ብለን የምንናገር ከሆነ ለዚች አገር ከፍተኛ ውለታ ዋሉ እንደ አቶ ለማ መገርሳ ያሉትን ሰዎች እየቀነስን ውህደቱን እውን ማድረግ አስቸጋሪ ነው ብለውናል። ዶ/ር ሔኖክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎችን፣ ሀሳባቸውንና እምነታቸውን ሳያካትቱ ውህደቱን ማካሄድ ከባድ ይሆናል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ፣ ዶ/ር አቢይ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት 'ለዐቢይ ትልቁ ተግዳሮት የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝቦችን መርቶ ማሻገር ሳይሆን ኢህአዴግን እንደ ኢህአዴግ መርቶ መሻገር መቻልና አለመቻል ላይ ይመሰረታል' ማለታቸውን በማስታወስ፣ በአሁኑ ሰዓትም በግንባሩ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች መጠላለፍ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ትልቁ ተግዳሮት ሆኖበታል ብለው እንደሚያምኑ ይገልጻሉ። "ከዚህም የተነሳ እንደሚፈለገው አብሮ ወደፊት መሄድ አልቻሉም" በማለት የእርሳቸው ፓርቲ ኢህአዴግ ተዋሀደም አልተዋሀደም የሚጠብቅበት ነገር እንዳለ አጽንኦት ሰጥተው ያስረዳሉ። በውህደቱ ላይ አቶ ለማ እንደማይስማሙ በተባራሪ ወሬ ሲሰሙ መቆየታቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ሔኖክ ደግሞ፤ እንዲህ ዓይነት መከፋፈል በአሁኑ ሰዓት መፈጠር አልነበረበትም ብለው እንደሚያምኑ ያስረዳሉ። ለዚህም ምክንያት ነው ያሉትን ሲጠቅሱም፤ "በእነርሱ መካከል በሚፈጠር አለመግባባት የኦሮሞ ትግል መከፋፈል የለበትም ብዬ ስለማምን ነው" ብለዋል። "አቶ ለማም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ትልቅ ውለታ የዋሉ ሰዎች ስለሆኑ ሃሳባቸውን ወደ አንድ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል" በማለትም፤ "የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ እንመልሳለን ብለው ካመኑ፤ የኦሮሞ ሕዝብ መሪዎች ነን ብለው ካሉ፤ መደማመጥ አስፈላጊ ነው" ሲሉ መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ያሰምሩበታል። የኢትዮጵያ መሪዎች ዲሞክራሲን አንገነባለን ሲሉ ተቃራኒ ሀሳቦችንም ማስታገድ አለባቸው ብዬ አምናለሁ የሚሉት ዶ/ር ሔኖክ፤ አሁንም ያለመግባባት መንስዔ የሆነው የውህደት ውሳኔ እንደገና መታየት አለበት ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ ገልፀዋል። • "ውስኪ ጠጪ ኢህአዴጎች እባካችሁ ውሃ የናፈቀው ሕዝብ እንዳለ አትርሱ" ጠ/ሚ ዐብይ አቶ ለማ ኦዲፒን ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር በማስታረቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም በማንሳት፤ የእርሳቸው አቋም የደጋፊዎቻቸውንም አቋም እንደሚለውጠው ዶ/ር ሔኖክ ይገልጻሉ። ከዚህም በመነሳት የአቶ ለማ አስተያየት ወደኋላ ከተተወ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ተናግረዋል። ዶ/ር ሔኖክ "ለማ መገርሳን የቀነሰ መደመር፣ መደመር አይሆንም" ሲሉም አስረድተዋል። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ዶ/ር ዐቢይ ይህንን የሚቀበሉ አይመስሉም የሚሉት የሕግ ባለሙያው፤ የኦሮሞና ሌሎች የአገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ እንዲመለስ የሚፈልጉ ከሆነ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይና አቶ ለማ የግድ በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ያሰምሩበታል። 'ፖለቲካ የሰጥቶ መቀበል ጥበብ ነው' "ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይና አቶ ለማ አንድ ባህል እና አንድ ቋንቋ ኖሯቸው፣ ለተመሳሳይ ሕዝብ እየታገሉ፣ በመግባባት አብሮ መሥራት ካቃታቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ አስቸጋሪ ነው ብዬ አምናለሁ" ብለዋል ዶ/ር ሔኖክ። ይህ ትግል እዚህ የደረሰው በኦሮሞ ልጆች ደምና በሕዝቦች መስዋዕትነት ነው ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ ፓርቲው ዋጋ የተከፈለባቸውን ጥያቄዎችን ወደ ጎን መተው አይገባውም ይላሉ። ፖለቲካ በራሱ የሰጥቶ መቀበል ጥበብ ነው የሚሉት ዶ/ር ሔኖክ በበኩላቸው፤ በፖለቲካ አካሄድ ውስጥ መደማመጥና ሚዛን ለሚደፋ ተፎካካሪ ሀሳብ መሸነፍ ወሳኝ መሆኑን ያስረዳሉ። ውህደት የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ የሚመልስ እስከሆነ ድረስ ምንም ችግር የለበትም የሚሉት ዶ/ር ሔኖክ፤ ይሁን እንጂ አዲሱ መዋቅር እንደ ሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ይሰጣል መባሉ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ይናገራሉ። በመሆኑም ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በዚህ ጉዳይ ላይ መግባባትን ለማምጣት፣ ቆም ብለው ግልፅና ፍትሀዊ የሆነ ምክክር ከአቶ ለማ ጋር ቢያደርጉ የበለጠ ጠቀሜታ አለው ብለው እንደሚያምኑ አብራርተዋል። አለመግባባቱ ቢቀጥል ምን ሊፈጠር ይችላል? በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና በመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መካከል በተከሰተው አለመግባባት፣ ስለወደፊቱ የሀገሪቱ ሁኔታ ፓርቲያቸው ስጋት እንዳለው የተጠየቁት ፕሮፌሰር መረራ፣ "እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ፌደራሊዝም ሰፍኖ፣ ሕዝቦች በቀያቸው እኩል ባለቤትነት ኖሯቸው ትግላችንን ግብ እስኪመታ ድረስ መስጋታችን አይቀርም" ብለዋል። የአገሪቱን ፖለቲካ በሚፈለገው ፍጥነት ወደፊት ለማስኬድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና በመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መካከል ያለው መግባባት ወሳኝ ነው የሚሉት ዶ/ር ሔኖክ፤ ይህንንም መግባባት ለማምጣት ትልቁ ሚና የሚጠበቀው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑን ይናገራሉ። በመካከላቸው መግባባት ባይፈጠር ግን የአገሪቱ ፖለቲካ ወዳልተፈለገ ጎዳና ሊሄድ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አልሸሸጉም። ይህንንም ሲያብራሩም፤ "ምናልባትም አቶ ለማ ሥልጣን ወደ መልቀቅ እርምጃ ሊያመሩ ይችላሉ" በማለት፤ ይህ ሆነ ማለት ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትሩ ወደ ተቃዋሚነት ተሸጋገሩ ማለት ነው ሲሉ ያብራራሉ። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "መደመር" መጽሐፍ ተመረቀ ከዚህም በተጨማሪ አቶ ለማ የተቃዋሚነትን አቋም የሚከተሉ ከሆነ በእርሳቸው አመራር የሚያምኑ አካላት ስላሉ ትልቅ የፖለቲካ ክፍፍል ይፈጥራል ብለዋል። ይህም በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ላይ የራሱ ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። በተለይም በመጪው ምርጫ ላይ የሕዝብ ድምጽ መከፋፈልን ሊያስከትል ይችላል ብለዋል። ፕሮፌሰር መረራ በበኩላቸው በዚህ ወሳኝ ሰዓት ሁሉም የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ቄሮ በተረጋጋ መንፈስ አብሮ ሊቆም ይገባል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊዎች በወቅታዊ የፓርቲው ሁኔታ ላይ እየመከሩ መሆኑን የኢህአዴግ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጽፏል። የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ እንዲሁም የኦዲፒ አመራሮች በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን ደጋግመን የሞከርን ቢሆንም ለጊዜው ምላሽ ማግኘት አልቻልንም፤ ነገር ግን ምላሻቸውን እንዳገኘን የምናካትት መሆንን መግለፅ እንወዳለን።
48406931
https://www.bbc.com/amharic/48406931
ፌስቡክ የአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው?
ፌስቡክ ወቀሳ በዝቶበታል። በተለይም ከአህጉረ አፍሪካ።
በማኅበራዊ ሚዲያው የሚሰራጨውን ሀሰተኛ መረጃ መግታት እንዳልቻለ ተንታኞች ይናገራሉ። የአህጉሪቷን የዴሞክራሲ ሥርዓት አደጋ ውስጥ ከቷልም ተብሏል። • "የአደገኛ ግለሰቦች" የፌስቡክ ገጽ መዘጋት ጀመረ ሀሰተኛ ዜናዎች አፍሪካ ውስጥ በተካሄዱ ስምንት ምርጫዎች ላይ ተጽዕኖ ማድረጋቸው የተነገረ ሲሆን፤ ፌስቡክ ከዜናው ጀርባ ነበረ ያለውን የእስራኤል ተቋም ገጽ መዝጋቱ ይታወሳል። 'አርኪሜይድ ግሩፕስ' የተባለው የእስራኤል ተቋምን ጨምሮ 256 የፌስቡክና ኢንስታግራም ገጾች ታግደዋል። በእነዚህ ገጾች ይሰራጭ የነበረው መረጃ በዋነኛነት ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ አንጎላ፣ ኒጀርና ቱኒዚያ ላይ ያነጣጠረ እንደነበረ ፌስቡክ ይፋ አድርጓል። • ፌስቡክ ሦስት ቢሊዮን አካውንቶችን አገደ የ 'ወርልድ ዋይድ ዌብ ፋውንዴሽን' ሠራተኛ ናኒንጃ ሳምቡሪ፤ ፌስቡክ እርምጃውን ለመውሰድ ዘግይቷል ይላሉ። "የአህጉሪቷ የዴሞክራሲ ሥርዓት አደጋ ውስጥ ነው። ጥብቅ የመረጃ ደህንነት መቆጣጠሪያ አለመኖሩ አንዱ ችግር ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። አፍሪካና ፌስቡክ የካሜሩን የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሬቤካ ኤኖንችሆን እንደሚናገሩት ፌስቡክ አፍሪካ ውስጥ ያለው አሠራር ከተቀረው ዓለም የተለየ ነው። ለምሳሌ፤ ፌስቡክ በ 'ካምብሪጅ አናሊቲካ'ው አጋጣሚ አፍሪካ ውስጥ እምብዛም አልተወቀሰም። እንደ ጎርጎራሳውያኑ አቆጣጠር 2018 ላይ ከ230 ሚሊየን በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የግል መረጃ ተመዝብሮ፤ የምርጫ ሂደት ውጤት ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር መዋሉ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ምርጫ ከተካሄደባቸው አገሮች መካከል ናይጄሪያና ኬንያ ይገኙበታል። • ፌስቡክ ግላዊ መረጃን አሳልፎ በመስጠት ተከሰሰ ፌስቡክ አፍሪካ ላይ የተቃጡ ገጾችን መዝጋቱን ሲያሳውቅ፤ የኮንጎው ጦማሪ ሳይመን ንኮላ ማታምባ አንድ ጥያቄ ሰንዝሮ ነበር። "ፌስቡክ በሌሎች አህጉሮች ላይ ለማድረግ የማይደፍረውን ነገር አፍሪካ ውስጥ የሚያደርገው ለምንድን ነው?" የሚል። መነሻቸው ከእስራኤል ነበር የተባሉት ገጾች ሥራቸውን ለማከናወን ከ2012 እስከ 2019 812,000 ዶላር አወጥተዋል። 2.8 ሚለየን ተከታዮች አፍርተውመ ነበር። ቢቢሲ 'አርኪሜይድ ግሩፕስ' ከተባለው ተቋም ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። በገጹ ላይ የነበሩ መረጃዎችንም ሙሉ በሙሉ አስወግዷል። ከተወገዱት መረጃዎች ውስጥ የናይጄሪያ ምርጫ ላይ ያተኮሩት ይጠቀሳሉ። • ፌስቡክ አፍሪካ ላይ የተቃጡ ገጾችን ዘጋ የአሜሪካው የምርምር ተቋም 'ዘ አትላንቲክ ካውስል ዲጂታል ፎረንሲክ ሪሰርች ላብ' በሠራው ጥናት እንደተመለከተው፤ የቀድው የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዘዳንት አቲኩ አቡበከርን ስም የሚያጠለሽ ምስል ተሰራጭቷል። 'ሴንተር ፎር ዴሞክራሲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት' የተባለው አቡጃ የሚገኝ ተቋም ውስጥ የሚሠሩት ኢዳት ሀሰን እንዳሉት፤ ምስሎቹ ከየት እንደመነጩ ማወቅ አልተቻለም። ፌስቡክ ከዘጋቸው ገጾች አንዱ 'ጋና 24' ይባላል። የዜና ማሰራጫ ገጽ ቢመስለም መረጃው ይተላለፍ የነበረው ከእስራኤልና እንግሊዝ ነበር። በዴሞክራቲክ ኮንጎ ብሔራዊ ምርጫ ወቅት ፌሊክስ ተሺስኬይዲን የሚደግፍ መረጃ የሚሰራጫበት ገጽም ነበር። • እነ ፌስቡክ ግላዊ መረጃዎትን ያለአግባብ እንደሚጠቀሙበት ያውቃሉ? በእርግጥ በነዚህ ገጾች የሚሰራጨው ሀሰተኛ ዜና በመንግሥት ለውጥ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን የሚያሳይ መረጃ የለም። እንዲያውም የአፍሪካ መሪዎች የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቱን ሳይጠቀሙበት አልቀሩም። አደገኛውን የሀሰተኛ መረጃ ሥርጭት ለመግታት አፍሪካ ውስጥ ከ139 ሚሊየን በላይ ሰዎች ፌስቡክን በዋነኛነት በስልክ ይጠቀማሉ። አብላጫውን ቁጥር የያዙት ደግሞ ወጣት አፍሪካውያን ናቸው። በምርጫ ወቅት ድምጽ ከሚሰጡ ዜጎች ብዙዎች ወጣቶች እንደመሆናቸው በፌስቡክ የሚሠራጭ መረጃ በቀላሉ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል። የካሜሩኗ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሬቤካ እንደሚናገሩት፤ እነዚህ ወጣቶች የሚያገኙት መረጃ ምንጩ ፌስቡክ እንደሆነ ያምናሉ። ፌስቡክን በመጠቀም ሦስተኛ ወገን መረጃ ሊያሠራጭ እንሚችል አይገምቱም። ባለሙያዋ "ፌስቡክ ኃላፊነት ተሰምቶት በማኅበራዊ ሚዲያው የሚሰራጨውን መረጃ መቆጠጠር ግዴታው ነው" ይላሉ። • ፌስቡክ የትራምፕን ክስ ውድቅ አደረገ አፍሪካ ውስጥ ያሉ ያሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ማኅበራዊ ሚድያውን እንዴት ይገለገሉበታል? የሚለውን ጉዳይ ፌስቡክ በአንክሮ እንዲመለከት ባለሙያዋ ያሳስባሉ። ቢቢሲ ይህንን አስተያየት ለፌስቡክ ቢሰጥም ተቀባይነት አላገኘም። ፌስቡክ እንዳለው፤ ተቋሙ አፍሪካን 'እንደ ቤተ ሙከራ' አድርጓታል የሚለው ክስ ተቀባይነት የለውም። በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት አፍሪካ ላይ ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሰ በመሆኑን ያክላል። ፌስቡክ የየአገራቱ ቋንቋ የሚችሉ ባለሙያዎች ከመቅጠር ባሻገር ፓሊሲ ማውጣቱን ይገልጻል። የሀሰተኛ ዜና ሥርጭትን ለመገደብ፤ በፌስቡክ የሚሰራጪ መረጃዎችን የሚገመግም ተቋም በኬንያ መዲና ናይሮቢ እንደሚያቋቁምም አክሏል። በተቋሙ ውስጥ የኦሮምኛ፣ ሶማልኛ፣ ስዋሂሊና ሀውሳ ተናጋሪዎች ይቀጠራሉ። • ግጭትን ለማባባስ ፌስቡክ ጥቅም ላይ ውሏል ተባለ በተጨማሪም ካሜሩን፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካና ሴኔጋል ውስጥ መረጃ ከሚያጣሩ ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ እንደሚሠራ ተመልክቷል። ፌስቡክ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ስለሰተኛ መረጃ አደገኛነት ያዘጋጃቸውን ጽሁፎች በጋዜጣ አስነብቧል። ጥያቄው ፌስቡክ የሚጠበቅበትን ሁሉ አድርጓል ወይ? ነው። አፍሪካ ውስጥ ምርጫ በተካሄደ ቁጥር ዜጎች ማኅበራዊ ሚድያ እንዳይቋረጥባቸው ይሰጋሉ። በፌስቡክና በዋትስአፕ የሚሰራጭ ሀሰተኛ መረጃ ለማስቆም የሚወሰድ እርምጃ እንደሆነም ይነገራል። ጋናዊው የቴክኖጂ ምሁር ኩዋቤና አኩማኦህ-ቦቴንግ እንደሚናገሩት፤ ፌስቡክን ማገድ ብቻውን ለውጥ አያመጣም። "ስለአንድ ተቋም ብቻ የምናወራ ከሆነ ውጤታማ አንሆንም። መንግሥትና የደህንነት ተቋሞን ሚናም ማየት አለብን" ይላሉ ባለንበት የመረጃ ዘመን የሀሰተኛ ዜና ስርጭትን ለመግታት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎችም የሚመለከታቸው ተቋሞች መተባበር እንዳለባቸውም ያስረዳሉ።
news-52965330
https://www.bbc.com/amharic/news-52965330
ለ34 ዓመታት ምስጢር ሆኖ የቆየው የስዊዲኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ግድያ
"ተራ ሕዝብ" ብሎ አጉል ቋንቋ አለ፡፡ "ተራ ጠቅላይ ሚኒስትርስ?"
ሕዝብ በሚበዛበት ጎዳና ላይ የተገደሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ኦሉፍ ፓልማ እንዲያ ብሎ ነገር ካለ የስዊድኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሉፍ ፓልማን ማንም አይቀድማቸውም፡፡ ከሕዝብ ጋር እየተጋፉ ጉሊት ወርዶ ቲማቲም መግዛት ተራ ካስባለ፣ ፓልማ ተራ ነበሩ፡፡ ብስክሌት እየጋለቡ ቤተ መንግሥት መሄድ ተራ ካስባለ ፓልማ ተራ ነበሩ፡፡ ሲኒማ መሰለፍ ተራ ካስባለ ፓልማ ተራ ሰውም፣ ተራ ጠቅላይ ሚኒስትርም ነበሩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ግን፣ በአንድ ተራ ምሽት ‹‹ተራው ጠቅላይ ሚኒስትር›› ሲኒማ ቤት ሄደው አንድ 'ተራ' ኮሜዲ ተመልከተው ሲወጡ በአንድ ጥቁር ኮት በለበሰ "ተራ" ነፍሰ ገዳይ ተገደሉ፡፡ ማን ገደላቸው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ "እንጃ!" የሚል ነው፡፡ ፖሊስንም፣ አባዲናንም፣ ወንጀል ምርመራንም፣ አቃቢ ሕግንም ብትጠይቁት ይህንኑ ነው የሚላችሁ፡፡ "እኔንጃ!"…. "እኛንጃ!" ወደው አይደለም ታዲያ፡፡ ወንጀለኛው ተነነና ነው…ቢፈለግ ቢፈለግ ዱካው ጠፋና ነው…፡፡ ለ34 ዓመታት! የፓልማ ኑሮ ተራ ቢመስልም ሞታቸው ተራ ሊሆን ያልቻለውም ለዚሁ ነው፡፡ ጉዳዩ ተዳፈነ ሲባል ድንጋይ ፈንቅሎ ይነሳል…፡፡ አበቃለት ሲባል…አንዱ ደውሎ…'እኔ ነኝ የገደልኳቸው፤ እባካችሁ እሰሩኝ' ይላል፡፡ ነገሩ እኛ ለበዓሉ ግርማ ሞት እንደምንብሰለሰለው መሆኑ ነው፡፡ ለስዊድኖች የጠቅላይ ሚኒስትር ፓልማ ሞት እንዲያ ያለ ነው፤ እንቆቅልሽ…ሁልጊዜም የሚከነክን፣ የሚያብከነክን…፡፡ ዶ/ር ጃን ቦንደርሰን በግድያው ዙርያ መጽሐፍ የጻፉ ዝነኛ ደራሲ ናቸው፡፡ "Blood on the Snow, The killing of Olof Palme" የተሰኘ ወፍራም ሥራ አላቸው፡፡ በዚሁ የግድያ እንቆቅልሽ ላይ ለቢቢሲ ሰሞኑን ሲናገሩ፣ "…ምን ማለት መሰለህ፣ እንዴት ብዬ ላስረዳህ? ነገሩ እኮ ማርጋሬታ ታቸር በዝነኛው የሎንዶን አደባባይ (ፒካዲሊ ሰርከስ) በሽጉጥ ተደብድባ ተገድላ፣ ገዳይዋ ተንጎማሎ ያላንዳች ስጋት ባቡር ተሳፍሮ ሲሰወር ማለት ነው…ይህ ነው'ኮ የሆነው፤ የዛሬ 34 ዓመት በስቶክኾልም"፡፡ ይልቅ ጊዜ አናጥፋ! "ማን ገደላቸው?"ን ትተን "እንዴት ተገደሉ"ን እናስቀድም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሉፍ ፓልማ የተለያዩ አገራት መሪዎችንና ሥርዓታቸውን ይተቹ ነበር እንዴት ተገደሉ? ወሩ ጥቅምት ነበር፤ ምሽቱ አርብ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓልማ የሕዝብ ሲኒማ ቤት ሄዶ ፊልም ማየት አማራቸው፡፡ ለነገሩ ሐሳቡ መጀመርያ የባለቤታቸው የወ/ሮ ሊዝቤት ነበር፡፡ ‹‹ለምን ሲኒማ አንገባም አሏቸው፡፡ ተስማሙ፡፡ ልጃቸውን ማርቲንን ጠርተው "እስኪ የኔ ልጅ ሮጥ ብለህ ለኔና ላባትህ የሲኒማ ቤት ትኬት ገዝተህ ጠብቀን፤ ጎሽ ተባረክ" አሉት፡፡ ልጃቸው ሄደ፡፡ ሲኒማ ቤት በር ሊገናኙ ተቃጠሩ፡፡ ባልና ሚስት እንደነገሩ ለባብሰው ወጡ፡፡ ሁለቱም አጀብ አይወዱም፤ ሪፐብሊካን ጋርድ የላቸውም፡፡ እስካፍንጫው የታጠቀ ልዩ ኮማንዶ አያሰልፉም፡፡ ያን ምሽትም እንደ ሁልጊዜው ማንንም ሳያስከትሉ ነበር ወደ ሲኒማ ቤት ያመሩት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማንም መንገድ ላይ ነበር የሚያገኛቸው፤ ብርቅ አልነረም እርሳቸውን ማየት፡፡ ‹‹ በቃ አንድ ተራ ዜጋ ነኝ፤ ጠ/ሚኒስትር ስለሆንኩ ልዩ ክብካቤ አይገባኝም›› ይሉ ነበር፡፡ ዜጋውም በፈለገው ሰዓት መንገድ ላይ አስቁሞ ያናግራቸው ነበር፡፡ በነገራችሁ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓልማ ሁሌም አወዛጋቢ ፖለቲከኛ ነበሩ፡፡ በአገራቸው ብቻም ሳይሆን በዓለም አቀፍ መድረክ ጭምር የሚናገሩት አቧራ ያስነሳል፡፡ የሚሰጡት አስተያየት ሚዲያ ያንጫጫል፡፡ እጅግ ተወዳጅ ስነበሩ ሊሆን ይችላል ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠው አገራቸው ስዊድንን እያስተዳደሯት የነበረው፡፡ የተቀናጣ ሕይወት ያልነበራቸው ፓልማ፣ ለዓለም ጭቁኖች ድምጽ እሆናለው ያሉት ባለጸጋው ፓልማ ያን ቀፋፊ ምሽት ያለ አንዳች አጀብ ሲኒማ ገብተው ኮሜዲ አይተው ወጡ፡፡ ምን ዋጋ አለው ደጅ ላይ ትራጀዲ ገጠማቸው፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው… የሚወዷቸውን ባለቤታቸውን ወ/ሮ ሊዝቤትን ከጎናቸው ሸጎጥ አድርገው ከሲኒማ ቤት ወጡና በእግር መጓዝ ጀመሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሉፍ ፓልማን ከባለቤታቸው ሊዝቤት ጋር መሽቷል'ኮ፡፡ ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ21 ደቀቃ ሆኗል፡፡ ኾኖም ዕለቱ አርብ ስለነበር በርካታ ስዊድናዊያን በየመሸታ ቤቱ ሽር ብትን እያሉ ነበር፤ አርብ ለስዊድኖች የአሸሼ ገዳሜ ሌሊት ናት፡፡ ባልና ሚስት ከሲኒማ ቤት ወጥተው ትንሽ እንደተጓዙ አንድ ረዥም ሰውዬ፣ ጥቁር ጃኬት የለበሰ፣ ደንዳና፣ ትከሻው የሚከብድ…በሰፊ መዳፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ትከሻ ከኋላ መጥቶ መታ መታ አደረገ፡፡ ፓልማ ዞር ሲሉ ከመቅጽበት በጥይት ደበደባቸው፡፡ አንድ ጥይት በቂ ነበረች፡፡ ጥይቷን ከቅርብ ርቀት በጀርባቸው ነው የለቀቀው፡፡ አንድ ሰው በዚህ ርቀት ሲተኮስበት ሞቱ ቅጽበታዊ ነው የሚሆነው፡፡ እርሳቸውም ተዘልፍልፈው መሬት ከመንካታቸው በፊት ነፍሳቸው ወጣች፡፡ የሞታቸው ፍጥነት የብርሃን ነበር፡፡ ጥቁር ኮት የለበሰው ነፍሰ ገዳይ ቀጥሎ ባለቤታቸው ላይ ተኮሰና…ምንም እንዳልተፈጠረ ነገር ቀብረር ብሎ…ትንሽ ዱብ ዱብ እንደማለትም እየቃጣው መንገዱን ተሻገረና የሆነች የኛን "70 ደረጃ" የምትመስል መወጣጫ ተሻግሮ ሄደ፡፡ እነሱ ‹‹89 ደረጃ›› ይሏታል፡፡ ያኔ ለተመለከተው'ኮ ፍቅረኛውን ተቃጥሮ ያረፈደ ጅንን ቀብራራ ጎረምሳ እንጂ ነብሰ ገዳይ ሊመስል? በጭራሽ፡፡ ደግሞ ገድሎ ሲሄድ በርካታ ሰዎች ዐይተውታል፡፡ በትንሹ 20 ሰዎች ተመልክተውታል፡፡ ቢኾንም አልተከተሉትም፡፡ ለምን አልተከተሉትም ግን? ብቻ በሶምሶማ ሄደና ተሰወረ፡፡ ይኸው ስንት ዘመን፡፡ እምጥ ይግባ ስምጥ….የሚያውቅ የለም፡፡ 34 ዓመታት…ዝም ጭጭ፡፡ ረዥሙ ነፍሰ ገዳይ እንዴት "አጎንብሶ"አመለጠ? ጠቅላይ ሚኒስትርን የሚያህል ነገር ገድሎ እየተንጎማለሉ መሄድ አለ አንዴ? እሺ መሄዱንስ ይሂድ? ግን ወዴት ሄደ? ስዊድናዊያን ይጠይቃሉ፡፡ እስከዛሬ መልስ የለም፡፡ የሚገርመው ይህ ግድያ የተፈጸመው በስቶክሆልም ግርግር በሚበዛበት ቁጥር-1 ጎዳና ላይ መሆኑ ነው፤ በስቪየቫገን፡፡ ደርዘን የሚሆኑ ሰዎች ያን ረዥሙን ነፍሰ ገዳይ ዐይተውታል፤ በስካር መንፈስም ይሁን በሞቅታ…፡፡ውሃ የያዙትም ይሁን ዊስኪ የጨበጡ…፣ የሚሳሳሙትም ይሁን የሚጨቃጨቁት…፡፡ 20 ሰዎች ዐይተውታል፡፡ ኾኖም አልተከተሉትም፡፡ ለምን አልተከተሉትም? ያ ረዥሙ ነፍሰ ገዳይ ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን በጥይት ደብድቦ ሲሄድ እነዚያ ሁሉ ሰዎች ያን ምሽት ተመልክተውታል፤ በሁለት ምክንያት፡-አንደኛ ምሽቱ አርብ ነበር፤ "ፍራይዴይ ናይት!" ሁለተኛ ሰው የሚርመሰመስበት ጎዳና ነበር ግድያው የተፈጸመው፡፡ግን ለምን አልተከተሉትም? ምናልባት ትኩረታቸው ሟችን ለማዳን ስለነበረ ይሆን? በአካባቢው ይዝናኑ የነበሩ ሰዎች በ6ደቂቃ ውስጥ የሚወዷቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆስፒታል ወስደዋቸዋል፡፡ ኾኖም ያ ሁሉ ከንቱ ነበር፡፡ ገዳዩ እጅግ አደገኛ መሣሪያ ነበር የተኮሰባቸው፡፡ "ስሚዝ ኤንድ ዌሰን-575 ሪቮልቨር" የሚባል ክፉ መሣሪያ ፡፡ በብዛት ፊልም ላይ ነፍሰ ገዳዮች ይዘውት በምናየው መጥፎ መሣሪያ፡፡ ለዚያም ነው ፓልማ በሰከንዶች ሽርፍራፊ የሞቱት፡፡ በተተኮሱበት ቅጽበት፤ ተዝለፍልፈው መሬት ላይ ከመውደደቃቸው በፊት ነው የሞቱት፡፡ ያን ያህል ኃያል መሣሪያ ነበር የተተኮሰባቸው፡፡ ጥይት መከላከያ ደርበው ቢለብሱ እንኳ አይተርፉም ነበር፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ኦሉፍ ፓልማ ግድያ በአገሪቱ ድንጋጤንና መላምቶችን አስፋፋ 10 ሺህ ሰዎች በፖሊስ ተመርምረዋል ከዚያች ምሽት ጀምሮ ላለፉት 34 ዓመታት ፖሊስ እንቅልፍ አልተኛም፡፡ ወይም እንቅልፉን ለጥጦታል፡፡ ሁለቱም ዓረፍተ ነገሮች ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ፖሊስ እንቅልፉን ባይለጥጥ እንዴት በአደባባይ የአንድ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር የገደለ ሰው በቁጥጥር ሥር ማዋል ያቅተዋል? "አልተኛንም" የሚለውም ትክክል ይመስላል፡፡ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች ተመርምረዋል፡፡ እንቅልፍ በዐይኔ ሳይዞር ላለፉት 34 ዓመታት መርምሬ የደረስኩበትን አሳውቃለሁ ብሏል ፖሊስ፡፡ ከነገ በስቲያ ነው ይህ ቀን፡፡ረቡዕ፡፡ የክፍለ ዘመኑ ጋዜጣዊ መግለጫ ቢባል አያንሰውም፡፡ ዋና አቃቢ ሕግ ክሪስተር ፒተርሰን ባለፈው ጥቅምት ለስዊድን ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲናገሩ ‹‹ያን ምሽት ምን እንደተፈጠረና ጠ/ሚኒስትራችንን ማን እንደገደላቸው በቅርቡ የጠራ መረጃ ይን እንቀርባለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል፡፡ መቼስ የሆነ ነገር ባያገኙ እንዲህ የሚያጓጓ ተስፋን አይሰጡም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተገደሉ በኋላ በስዊድን ምን ሆነ? ስዊድኖች ድምጻቸው ከፍ ብሎ የሚሰማ ሕዝቦች አይደሉም፡፡ አርምሞ ላይ ያሉ ሰዎች ነው የሚመስሉት፡፡ አገራቸውም እንደዚያ ናት፡፡ ኮሽታ ይናፍቃል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድያ እጅጉን ደንግጠው ነበር፤ ያኔ፡፡ ቻርሎታ ዋልስተን ለምሳሌ ያን ጊዜ 12 ዓመቷ ነበር፡፡ ኾኖም ይህ ክስተት ሲከሰት በደንብ ታስታውሳለች፡፡ አባቷ የሆነው ነገር አስደንግጦት ነበር፡፡ ‹‹ቤታችን ቲቪ ተከፈተ፡፡ በመላው ስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለተገደሉበት ሁኔታ እንጂ ስለሌላ ነገር የሚያወራ ሰው ጠፋ፡፡›› ብላለች ለቢቢሲ፡፡ አሁን 46 ዓመቷ ነው ታርሎታ፡፡ ያን ጊዜ እጅግ ልባቸው በሐዘን ተነክቶ ስለነበር ትምህርት ቤት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ማድረጋቸው ትዝ ይላታል፡፡ ‹‹በስዊድን እንደዚህ ዓይነት ነገር ተከስቶ የሚያውቅ አይመስለኝም ነበር፡፡ ሁሉም ፖለቲካ ተረሳ፤ ሁሉም ጉዳይ ተረሳ፤ የርሱ ሞት አገሩን ሁሉ በሐዘን ዋጠው፡፡ ›› ከግድያው በኋላ ተራው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የስዊድን ፖሊስም ግራ ተጋብቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም መርማሪዎች ወደ ወንጀል ቦታ መጥተው አካባቢውን በፍጥነት መከለል ሲገባቸው የተወሰኑ ቦታዎችን ብቻ ነው ያጠሩት፡፡ ድንበር ቶሎ መዝጋት ሲገባቸው ያ አልተደረገም፡፡ ይባስ ብሎ በክስተቱ የደነገጡ ዜጎች ወደ ቦታው በብዛት ይጎርፉ ነበር፡፡ ይህ ነገር የአሻራ ምርመራ እንዲደረግ ዕድል አልሰጠም፡፡ የጠ/ሚኒስትር ፓልማ ደም የፈሰሰበት ቦታ ሳይደርቅ እንኳ ሰዎች በአጠገቡ ይቆሙም ይመለቱም ነበር፡፡ በነገታው መጥተው አበባ የሚያስቀምጡም ነበሩ፡፡ ነገሩ ሁሉ ትርምስምስ ብሎ ነበር፡፡ ምናልባት ስዊድኖች ለወንጀል አዲስ ስለሆኑ ይሆን? እንዴት ፖሊስ ሥራውን በአግባቡ አይሠራም? ለምሳሌ የዓይን እማኞች ወዲያው ቃላቸው እንዲሰጡ እንኳ ሳይደረግ ወደ ቤታቸው ሄደዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለቤታቸው ላይ ከተኮሱት አንደኛዋ ጥይት በወቅቱ ሳትገኘት ቀርታ ከቀናት በኋላ ነው አንድ መንገደኛ መሬት ላይ አግኝቷት ለፖሊስ የሰጠው፡፡ ይህ ሁሉ መዝረክረክ የሚናገረው ፖሊስ ያን ጊዜ ሥራውን በአግባቡ አለማከናወኑን ነው፡፡ ለማንኛውም ቀናት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን እየተኩ ሄዱ፡፡ ገዳይ የለም! በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ጥቆማ ይሰጣሉ፡፡ ገዳይ ግን የለም፡፡ ነፍሰ ገዳዩ ለዘመናት አለመታወቁ ስዊድናዊያኑን ይበልጥ ግራ አጋባቸው፡፡ ነገሩ ከትኩስ ደረቅ የግድያ ወንጀል አልፎ ተረትና ፊልም ወደ መሆኑ ያመዘነውም ለዚሁ ይሆናል፡፡ በጊዜ ሂደት ይህ ነገር እንደ ቅዠት እያደረገ የሚያባንናቸው ዜጎች ተፈጠሩ፡፡ ግድያውን መርምረን ደረስንበት የሚሉ አማተር ጀብደኛ መርማሪዎች ተወለዱ፡፡ privatspanarna ይሏቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ጤነኞች ናቸው፤ ሌሎች ግን ዘብረቅ ያደርጋሉ፡፡ ግድያውን ተከትሎ ባለፉት 30 ዓመታት ራሱን የቻለ በሽታ ተፈጥሯል፤ በስዊድን፡፡ ፓልማኒያ የሚባል፤ እንዲሁም ፓልማሲክ የሚባል፡፡ የዚህ በሽታ ምልክቶች በሰውየው አሟሟት መብሰልሰል ነው፤ ያለማቋረጥ፡፡ በራስ ተነሳሽነት ምርመራ መጀመርንም ያካትታል፣ አንዳንዴም ገዳዩ እኔ ነኝ ብሎ ለፖሊስ እጅ መስጠትን ይጨምራል፡፡ በዚህ መንገድ 130 ሰዎች እኛ ነን ገዳዮቹ ብለው ለፖሊስ እጅ ሰጥተዋል ቢባል አሁን ማን ያምናል? አነርሱ ገዳይ እንደሆኑ ይመኑ እንጂ አንዳቸውም ግን ወንጀለኛ ኾነው አልተገኙም፡፡ የ"ፓልማሲክ" ተጠቂዎች ናቸው፡፡ ይህ ግድያ እንደ ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ እንደ ወንድማቸው እንደ ሮበርት ኬነዲ፣ እንደ በዓሉ ግርማ፣ እንደ ቱፓክ ሻኩር ምስጢር ነው፡፡ኾኖም ምስጢሩ አልተፈታም፡፡ በ34 ዓመት ምርመራ ከ10ሺ ሰዎች በቅጡ ተመርምረዋል፡፡ በስዊድን ዋና ቢሮ የሚገኘው የምርመራ ዶሴ ፋይል 250 ሜትር ሼልፍ ቢሰራ አይበቃውም፡፡ በምድር ላይ እስከዛሬ ካልተፈቱ የግድያ እንቆቅልሾች አንዱና ትልቁ የተባለውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህን ግድያ ተንተርሶ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፊልሞች፣ መጽሐፎች፣ የመድረክ ተውኔቶች፣ የጋዜጣ መጣጥፎት ተጽፈዋል፣ ተደርሰዋል፣ታትመዋል፣ ተሰራጭተዋል፡፡ በፓልማ ግድያ ብቻ ላይ ያተኮረ ፖድካስት ሥርጭትም በስዊድን ውስጥ አለ፡፡ ፓልሜሞርዴት ይባላል፡፡ 173 ክፍል ድረስ ተሰራጭቷል፡፡ የቀን ቅኝት በሉት፡፡ ሌላ ቡድን ደግሞ አለ፡፡ ሟቹን ለመዘከር ሲል ሲኒማ ገብቶ ፊልም አይቶ፣ በዚያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሄዱበት ጎዳና በሌሊት ሄዶ ልክ በተገደሉባት ሰዓት 05፡21 የተገደሉባት ቦታ የመቆም ሥነ ሥርዓት የሚያካሄድ ቡድን፡፡ ሌላ ማኅበርም ተፈጥሯል፡፡ እውነት አፈላላጊ የሚባል፡፡ Sanningskommission የሚባል፡፡ የዚህ ማኅበር ዓላማ ደግሞ በሰውየው ዙርያ የራሱን ምርመራ እያደረገ መረጃን ለጋዜጠኞና መርማሪዎች ማቀበል ነው፡፡ የተቋቋመበት ዓላማ ገዳዩ ወይም ምስክሮች ፖሊስ ጋር መሄድ ከፈሩ እኛ ጋ ሊመጡ ይችላሉ በሚል ነው፡፡ በአጭሩ አገሩ በዚህ ግድያ የስዊድን ሕዝቦ አብዶ ነው የኖረው ማለት ይቻላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሉፍ ፓልማ የተገደሉበት ስፍራ የሴራ ትብታቦ በእርሳቸው ዙርያ ዝም ተብሎ ወደ ሴራ ትብታቦ (conspiracy theory) አልተገባም፡፡ ፖሊስ ተጨባጭ ነገር ሲያጣ ነው ነገሩ ሁሉ የአሉባልታና ሴራ መፈንጫ የኾነው፡፡ የመጀመርያው መርማሪ ሀንስ ሆልሜር ይባል ነበር፡፡ እንዲህ ውስብስብ ጉዳይ እንኳ ይዞ አያውቅም፣ ከዚያ በፊት፡፡ ኾኖም ምስጢሩን ፈትቼ የስዊድን ጀግና እኾናለው ብሎ የተነሳ ሰው ነበር ይሉታል፡፡ ቢለው ቢለው አልሆነለትም፡፡ መርማሪ ሆልሜር የመጀመርያ ተጠርጣሪ ያደረጋቸው ከቱርክ መንግሥት ጋር ለነጻነት የሚዋጉትን ፒኬኬዎችን ነበር፡፡ ያን ዘመን ፒኬኬ ጽንፈኛ ነው በሚል በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ተወግዞ ነበር፡፡ የሆነ ቀን እንዲያውም ተጠርጣሪውን ለመያዝ ተቃርቢያለሁ አለና፤ የፒኬኬ አባላት ይሰበሰቡበታል የሚባል ቤተ መጻሕፍትን ድንገቴ ወረራ በማድረግ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ፡፡ አንዳች ነገር ጠብ አላለትም፡፡ የስዊድን ሕዝብ በዚህ መርማሪ ተናደደበት፡፡ የሆልሜር ምርመራ ፍሬ ሳያፈራ ሲቀር የሴራ መላምት ቦታውን ያዘ፡፡ የገዛ ሚስቱ ናት ያስገደለችው የሚል አለ፡፡ ለምን ቢባል እየማጋጠ አስቸግሯት፡፡ ጆን ኤፍ ኬኔዲን የገደለው ምስጢራዊ የሰይጣን አምላኪዎች ቡድን ነው ያስገደለው የሚሉም አሉ፡፡ ለምን ቢባል መልስ የለም፡፡ የገዛ ወንድ ልጁ ማርተን ነው የስገደለው ተባለ፡፡ ለምን ቢባል…አባቱ ላይ ቂያሜ ነበረው፡፡ ጨርሶውኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓልማ አልሞቱም፣ ሁሉም ነገር ድራማ ነው ተባለ፤ ለምን ቢባል ጀግና አይሞትም፡፡ በእርግጥም በስዊድን ‹‹የፓልማ ደዌ›› የሚባል ነገር ተፈጥሮ ነበር፤ ብዙ ሰዎች በዚህ ደዌ ታመዋል፡፡ ታማሚዎች ይዘባርቃሉ፤ ሴራ ይጎነጉናሉ፡፡ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ በአንድ ወቅት ለኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ እንደተናገረው ‹‹በሽታው የእውነት ነው፤ ሰዎች ከዚህ አባዜ ከተሰቃዩ በኋላ ድነው እየደወሉ ይቅርታ ይጠይቁኛል›› ብሏል፡፡ ለማንኛውም መርማሪ ሆልሜር ውግዘት ደርሶበት ሥራውን ለቀቀ፡፡ በኋላ ላይ ነገሩን ዳር ሳላደርስ አልሞትም ብሎ በግሉ እንደ ተራ ዜጋ ምርመራውን ገፋበት፡፡ አንድ ቀን በድብቅ ሕገ ወጥ የስልክ ግንኙነት መጥለፊያ መሣሪያ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገባ ተያዘ፡፡ ሌላ ቅሌት! አወዛጋቢው ፓልማ ማን ነበሩ? ፓልማ ለ16 ዓመታት ግራ ዘመሙን ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ መርተዋል፡፡ ይህ ፓርቲ ስዊድንን በ20ኛው ክፍለ ዘመን በአመዛኙ የመራ አውራ ፓርቲ ነበር፡፡ ስዊድንን ስዊድን ያደረጋት ይህ ፓርቲ ነው፡፡ የናጠጠ ሀብታም ግብር እየተጫነበት ድሀን እንዲደጉም፤ የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ እንዲሆን ያስቻለ ፓርቲ ይህ ፓርቲ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ፓልማ ይህን ፓርቲ ነው የመሩት፡፡ የተወለዱት እንደነርሱ አቆጣጠር በ1927 ሲሆን ከመሳፍንት ቤተሰብ ነበር የተገኙት፡፡ በ1949 የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ አባል ሆኑ፡፡ በ1969 የፓርቲውን መሪነት ከመልማያቸው ከታግ ኤርላንደር ተረከቡ፡፡ ታግ ኤርላንደር የስዊድን የ"ዌልፌር ሲስተም" አባት ይባላሉ፡፡ ስዊድን ዓለም የሚቀናባት አገር ያደረጉ ሰው ናቸው፡፡ ዌልፌር ሲስተም ሀብታምን በግብር ተጭኖ ድሀን ከፍ የማድረግ፣ የማመጣጠን ምጣኔ ሀብታዊ-ወ-ፖለቲካዊ የአስተዳር ስልት ነው፡፡ ኦሉፍ ፓልማ ታዲያ ፖለቲካን የተማሩት ይህን ዘዴ በስዊድን ከዘረጉት ከኚህ ጎምቱ ፖለቲከኛ ነበር፡፡ ወደበኋላም ፓልማ የታግ ኤርላንድን ፖሊሲና ሌጋሲ ያስቀጠሉ ሁነኛ ሰው ነበሩ፡፡ ጠ/ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ የሠራተኛ ማኅበራትን አቅምና ጉልበት እንዲጠነክር አድገዋል፡፡ የጤና መድኅን እንዲስፋፋ ተግተዋል፤ ከንጉሣዊ አስተዳደር ጋር የተሳሰሩ የፖለቲካ ሥልጣኖችን መንግለዋል፤ በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ እንዲፈስ አስችለዋል፡፡ በርሳቸው ጊዜ መዋዕለ ሕጻናት እንደ አሸን ፈሉ፡፡ የትምህርት ጥራት ጨመረ፡፡ ሴቶች የቢሮ ሥራ ተሳትፏቸው ተመነደገ፡፡ የጾታ እኩልነት በሚደንቅ ፍጥነት በመላው ስዊድን ባሕል እየሆነ መጣ፡፡ ኦሎፍ ፓልማ የአገር ውስጥ አንበሳ ብቻ አልነበሩም ታዲያ፡፡ በዓለም አቀፍ ጉዳዮችም ድምጻቸው ኃያል ነበር፡፡ ጭቆናን ይጠላሉ፤ ጨቋኝ ያወግዛሉ፤ ተጨቋኝ ይረዳሉ፡፡ በስፔን የጄኔራል ፍራንኮን ፋሽስታዊ አገዛዝ ክፉኛ ያወግዙ ነበር፡፡ "እነዚህ እርኩስ ገዳዮች" ይሏቸው ነበር፣ የጄኔራል ፍራንኮን ሰዎች፡፡ ለአሜሪካም ሆነ ለታላቋ ሶቪየት ኅብረት አይመለሱም፡፡ በ1968 ሶቪየት ኅብረት ቼኮዝላቫኪያን ስትወር ፓልሜ ከፍተኛ ተቃውሞን አሰምተዋል፡፡ በ1972 አሜሪካ ሰሜን ቬትናምን በቦምብ ስትደበድብ ፓልማ ‹‹ይሄማ በ2ኛ የዓለም ጦርነት ጊዜ ናዚዎች አይሁዶች ላይ ከፈጸሙት ጥፋት በምን ተለየ?" ብለው ሂስ ሂሰዋል፡፡ በዚህን ጊዜ አሜሪካ ክፉኛ ተቀየመቻቸው፡፡ በስቶክሆልምና በዋሺንግተን መሀል የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትም ተቋረጠ፤ ለአጭር ጊዜም ቢሆን፡፡ ‹‹በተናገርኩት ነገር አልጸጸትም፤ ምክንያቱም ፍትህ ሲጓደል ስታይ ዝም ማለት የለብህም፤ የትም ቢሆን፣ መቼም ቢሆን፡፡›› ብለው ነበር ድሮ ያኔ፣ ለኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ፡፡ ፓልማ ተናጋሪ ብቻም ሳይሆን አስታራቂም ነበሩ፡፡ የ1980ዎቹን የኢራቅና ኢራን ጦርነትን የሸመገሉ ሰው ናቸው፡፡ ሰንድስቶርም የተባሉ ሰው ስለ ፓልማ አስተያየት ሲሰጡ፤ ‹‹ሰውየው ወይ በጣም የምትወደው፣ ወይ በጣም የምትጠላው ዓይነት ሰው ነበር›› ብለዋል፡፡ ‹‹እጅግ እጅግ የሚወዱት ሰዎች ነበሩ፡፡ እጅግ እጅግ የተቆጡበት መንግሥታትም ነበሩ፡፡›› ለማንኛውም ፓልማ በጣም ተወዳጁ የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚባሉት ውስጥ ይመደባሉ፡፡ ከ34 ዓመታት በኋላ ዛሬም የተገደሉበት ጎዳና ላይ የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጡ ሰዎች ያሉትም ለዚህ ይሆናል፡፡ ክሪስ ፒተርሰን ደቡብ አፍሪካ ትሆን ያስገደለቻቸው? ፓልማ ዝም አልልም ባይነታቸው በርካታ ወዳጅ እንዳፈራላቸው ሁሉ ጠላትም ገዝቶላቸው ነበር፡፡ የስዊድን የቢዝነስ ሰዎችና ሊበራሎች እንደርሳቸው የተመቿቸው ባይኖርም የዓለም ኃያላን መንግሥታት ግን ጥርስ ነክሰውባቸዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒሰትር ፓልማ ግድያ ከፍተኛው ተጠርጣሪ የዚያ ዘመኑ የደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ መንግሥት ነው፡፡ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ፓልማ ከመገደላቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ለጸረ አፓርታይድ ታጋዮች ንግግር አድርገው ነበር፡፡ ‹‹የአፓርታይድ ሥርዓት ድምጥማጡ ሊጠፋ እንጂ ሊሻሻል አይገባም፡፡ አስቀያሚና መጥፎ ሥርዓት ነው›› ብለው በግልጽ አውግዛውታል፡፡ ግራ ዘመሙ ፓልማ ይህን ወሬ አውርተው ብቻ አልሄዱም፡፡ በአፓርታይድ ሥርዓት ላይ ማዕቀብ የሚጣልበትን መንገድ ያሰላስሉ ጀመር፡፡ ለነ ማንዴላ፣ ለኤኤንሲ የገንዘብ እርዳታም ማድረግ ጀመሩ፡፡ሚሊዮኖችን ለገሱ፡፡ ለአፓርታድ አፍቃሪ ነጭ ደቡብ አፍሪካዊያን ፓልማ መወገድ ያለባቸው ሰው ነበሩ፡፡አውሮጳዊ ሆነው የነጭን የበላይነት እንዴት ይቃወማሉ ሲሉ ጥርስ የነከሱባቸው የአፓርታይድ አፍቃሪ ነጮች ጥቂት አልነበሩም፡፡ ይህ በቅ ምናልባት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያስገደለቻቸው ደቡብ አፍሪካ ትሆን የሚል ጥያቄን አጫረ፡፡ ከፍተኛ ምርመራም ተጀመረ፡፡ ስዊድን ነገሩ ከአቅሟ በላይ ሲሆንባት እንግሊዝን እርጂኝ አለቻት፡፡ ኤምአይ-16 የዩናይትድ ኪንግደም የስለላ ተቋም በጉዳዩ ገባበት፡፡ የሚያውቀውን ለስዊድን አቀበለ፡፡ በእርግጥም ጠ/ሚኒስትሩ በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ መሪዎች ጥርስ ተነክሶባቸው ነበር አለ፡፡ እንዲገደሉም ፍላጎት ነበር ሲል አጋለጠ፡፡ እንግሊዝ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ሥርዓት ውስጥ ከነበረ አንድ ታማኝ ምንጭ ሰውየውን ለመግደል እቅድ ተይዞ እንደነበር መረጃ አግኝታ ይህንኑ ለስዊድን አቀብላለች፡፡ ክሬግ ዊሊየምሰን የሚባል የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ሥርዓት ውስጥ የነበረ ሰው ደግሞ ግድያውን እንዲያቀነባበር ተነግሮት ነበር፡፡ ይህ ሰው ደግሞ በርቲል ዌዲን ከሚባል ስዊድናዊው የቀኝ አክራሪ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበረው፡፡ ዌዲን ዛሬም ድረስ በሕይወት አለ፡፡ ዋዲን ተይዞ ተመረመረ፡፡ አላመነም፡፡ ዌዲን በወቅቱ ቀኝ አክራሪ ብቻም ሳይሆን የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ሥርዓት ደጋፊና በስለላ መረብ ውስጥ ቁልፍ ሰው ነበር፡፡ ግድያውን እሱ ባይፈጽምም አቀነባብሮት ይሆን? ማን ገድሏቸው ይሆን? ምንም እንኳ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የገደላቸውን ሰው ያን ምሽት ጣጣውን ጨርሶ መንገድ ተሻግሮ ሲሄድ ብዙዎች ቢያዩትም ፖሊስ ግን ሰውየው ያለበትን ፍንጭ ማግኘት ተቸግሮ ነበር፡፡ ኋላ ላይ የተገኘችው ጥይት እንዳሳበቀችው ገዳዩ የተጠቀመው እጅግ አደገኛ የሆነውን "357 ማግነም" የእጅ ጦር መሣሪያ ነው፡፡ ዶ/ር ቦንደርሰን ለቢቢሲ እንደተናገሩት በዚህ መሣሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጥይት መከላከያ እንኳ ደራርበው ቢለብሱ ከመሞት አይድኑም ነበር፡፡ ይህ የሚያሳየው ግድያው በጣም አስተማማኝና የማያዳግም እንዲሆን ታቅዶና ተወጥኖ የተገባበት ስለመሆኑ ነው፡፡ የመጀመርያው መርማሪ ሆልሜር በ1987 በቅሌት ሥራውን መልቀቁን ጠቅሰናል፡፡ በኋላ እሱ ራሱ ልቦለድ ጸሐፊ ኾነ፡፡ ከልቦለዱ በኋላ ግን አንድ ያልጨረሰው መጽሐፍ ነበር፡፡ በግድያው ዙርያ መሆኑ ይታወቃል፤ በዚያው ሳይጨርሰው ሞተ፡፡ ከርሱ በኋላ የመጣው መርማሪ ክሪስተር ፒተርሰን የሚባል ወንጀለኛን አሰረ፡፡ ሰውየው በ1970ዎቹ በስቶክሆለም ጎዳና አንድን መንገደኛ በጩቤ ወግቶ መግደሉ ይታወቃል፡፡ ሰውየውን የገደለበት ምንም በቂ ምክንያት አልነበረውም፡፡ፍርዱን ጨርሶ የወጣ ሰው ነበር፡፡ የሚደደንቀው የዚህ ወንጀለኛ የሰውነት ቁመና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ገድሏል ከተባለው ቀውላላው ሰውዬ ጋር ምስስሎሽ ያለው ነው፡፡ ፖሊሶችና ወንጀለኛው በአንድ እንዲሰለፉ ተደርጎ የጠቅላይ ሚኒስትር ፓልማ ሚስት ተጠርጣሪውን በቲቪ እንድታየው ተደርጎ ‹‹ገዳዩ የትኛው ይመስልሻል?›› ተባለች፡፡ ፒተርሰንን ነጥላ አወጣችው፡፡ ተከሰሰና በ1989 ዕድሜ ልክ ተፈረደበት፡፡ ነገር ግን ጠበቃው ወዲያው ይግባኝ አለ፡፡ የእድሜ ልክ የተፈረደበት ሰው ከሦስት ቀን በኋላ ፍርድ ቤት በነጻ ለቀቀው፡፡ ምክንያቱም ሰውየው ላይ በቂ መረጃ ሊገኝ ቀርቶ አንዳችም አሳማኝ ነገር አልተገኘበትም፡፡ በዚያ ላይ ፖሊስ ለሴትዮዋ ለይታ እንድታወጣው ከመጠየቁ በፊት ስለ ሰካራምነቱ ነግሯት ነበር፡፡ ሰካራም መለየት ደግሞ ቀላል ነው፡፡ ለካንስ ያ የሰካራም ፊቱ ነው ተጽእኖ አድርጎባት ‹‹እሱ ነው ገዳዩ›› ያስባላት፡፡ ሰካራሙ ሰውዬ ሲፈታ ለተንገላታበት 50ሺ ዶላር ካሳ ተከፍሎት ነው፡፡ ወደቤቱ ቀብረር ብሎ ሲሄድ ታዲያ በአንድ እጁ ቮድካ በሌላ እጁ ቤይሌይ የአይሪሽ መጠጥ ይዞ ነበር፡፡ ያ ክስተት በጋዜጠኞች ካሜራ ተቀርጾ ቀርቶ ስለነበር እርሱ ያን ጊዜ ይዞት የነበረውን መጠጥ ቅልቅል ዛሬም ድረስ ስዊድናዊን ‹‹ዘ ኪለር›› እያሉ ይጠሩታል፡፡ ፒተርሰን ቮድካውን እየጠጣ ኖረ፡፡ ኖሮ ኖሮ በ2004 ሞተ፡፡ ከመሞቱ በፊት ግን ጋዜጠኞች ጋር ይደውልና ገዳዩ እርሱ ስለመሆኑ መጠነኛ ፍንጭ ይሰጣቸውና በጉጉት ልባቸውን ያንጠለጥላል፡፡ ሞቅ ብሏቸው ሲጽፉ ደግሞ በስም ማጥፋት ይከሰቸዋል፡፡ በዚህ ሂደት ብዙ ብር ካሳ ይፈረድለታል፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ነው ኖሮ ኖሮ አንድም ፍንጭ ሳይተው የሞተው፡፡ ከዚህ ሰውዬ ሞት በኋላ ስዊድን በተወዳጁ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሞት ምላሽ በማጣቷ የሴራ ትብታቦ ውስጥ ተዘፍቃ ኖራለች፡፡ በግድያው ዙርያ ብዙ ሴራ ነዳፊዎች ያልፈተፈቱት አሉባልታ የለም፡፡ አንዲያውም ይህ ነገር በስዊድን የሥነ ልቦና ሞያዊ ስም ሁሉ ተሰጥቶታል፡፡ Palmes sjukdom ይሉታል፡፡ የፓልማ ደዌ እንደማት ነው፡፡ በ1996 አንድ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ የተገደሉት አፓርታይድን በመቃወማቸውና ለኤኤንሲ ፓርቲ ድጋፍ በመስጠታቸው ነው የሚል መረጃ አወጣ፡፡ ጉድ ተባለ፡፡ ሰውየው ይህን ባለ በስንተኛው ቀን ሞተ፡፡ የስዊድን ፖሊስ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሄዶ ምርመራ ጀምሮ ነበር፡፡ ምንም ያገኘው ነገር አልነበረም፡፡ ስቴግ ላርሰን ደራሲ ነው፡፡ "Girl with the Dragon Tattoo" መጽሐፍ የጻፈው እርሱ ነው፡፡ ይህን ግድያ በተመለከተ እስከ ሞቱ ድረስ ሲመራመር ነው የኖረው፡፡ እርሱ የሚምነው የአፓርታይድ ሰዎች ናቸው ፓልማን ያስገደሉት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገደሉበት ቦታ ላይ የተቀመጠ ማስታወሻ የጦር መሣሪያ ደላሎች ይሆኑ? ዶ/ር ቦንድሰን በበኩላቸው ግድያው ከሕንድ የጦር መሣሪያ ንግድ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ እንዴት ሲባሉ፣ ቦፎርስ የተባለ የስዊድን ኩባንያ ለሕንድ የጦር መሣሪያ ለመሸጥ በ80ዎቹ እና 90ዎቹ ስምምነት አድርጎ ነበር፡፡ ኩባንያው ይህንን ለመሳካት በርካታ ክፍያዎችን ለሚሊየነር ደላሎች ፈጽሟል፡፡ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትረ ራጂቭ ጋንዲ ሳይቀሩ በነገሩ ተነክረውበት ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስትር ፓልማ ይህን የጦር መሣሪያ ሻጭ ኩባንያ ጋር የተያያዘውን ሙስና ደርሰውበት ነበር፡፡ ስለዚህ ከዚህ ኩባንያ ትርፍ ለማጋበስ ያሰፈሰፉ ሚሊየነር ደላሎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ነፍሰ ገዳይ ቀጥረው አስገድለዋቸዋል፡፡ ይህ የዶ/ር ሐሳብ ግን ፖሊስ ችላ ብለውታል፡፡ የማይመስል ነገር ሆኖባቸው፡፡ ከዐይን እማኞቹ አንዱ ለምን ራሱን አጠፋ? ሌላው ጥርጣሬ ስካንዲያ ከተባለ ኡንሹራንስ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ከሚሰራ ሰውዬ ጋር ይያያዛል፡፡ ይህ ኩባንያ ዋና መሥሪያ ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚያች ምሽት ከተገደሉበት ጎዳና አጠገብ ነው የሚገኘው፡፡ በዚህ ዋና መሥሪያ ቤቱ የሚሠራ ስካንዲያ ማን የሚባል ሰው ነበር፡፡ ግድያውን ከተመለከቱ 20 ሰዎች አንዱ ነበር፡፡ በ2000 ዓ. ም ራሱን አጠፋ፡፡ ለምን ራሱን ሊያጠፋ ቻለ? የሚያውቀው ነገር ይኖር ይሆን? በዚህ ሰው ላይ ትኩረት አድርጎ ለ12 ዓመታት ምርመራ ሲያደርግ የነበረ ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ነበር፡፡ ቶማ ፒተርሰን ይባላል፡፡ እርሱ ነው የጠቅላይ ሚኒስትራችን ገዳዩ ይህ ሰው ሲል ጥርጣሬ የጀመረው፡፡ መነሻ ምክንያት ነበረው፡፡ ይህ ራሱን ያጠፋው ሰው አንደኛ የጦር መሣሪያ ስልጠና ወስዷል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ የጦር መሣሪያ መሰብሰብ ሆቢው ያደረገ አንድ ወዳጅ ነበረው፡፡ ይህ ወዳጁ ሰውየው የተገደሉበት ዓይነት መሣሪያ ነበረው፡፡ በዚያ ላይ ተጠርጣሪው ማግነም ከሚባለው ተሸከርካሪ ጦር መሣሪያ ትልቅ ፍቅር ነበረው፡፡ በዚያ ላይ ሰውየው ቃል ሲሰጥ ‹‹እዛ ቦታ የተገኘሁት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ነፍሳቸው አልወጣች እንደሆን ለማትረፍ ነበር›› ብሎ ዋሽቷል፡፡ ብዙ ሰዊድናዊያን ይህ ሰው አንድ ቡድን ነገሩን ለማዘናጋት እየተጠቀመበት እንደሆነ ያምናሉ እንጂ ገዳይ ነው አይሉም፡፡ ምክንያቱም ገዳዩ እጅግ ግዙፍና ረዥም መሆኑ እየታወቀ ይህ ተጠርጣሪ ግን አጭርና ደቃቃ ሰው ነበር፡፡ በዚያ ላይ ይህ ሰው ከዚያ ክስተት ወዲህም ይሁን ወዲያ ሰው ገድሎ አያውቅም፡፡ እንዲሁ ነው ራሱን ያጠፋው፡፡ ማርቴን ፓልማ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ወንድ ልጅ ነው፡፡ አባቱ ከመገደላቸው ቀደም ብሎ እርሳቸውን ለመጨረሻ ጊዜ ካገኟቸው ሰዎችም አንዱ ነው፡፡ ‹‹ፖሊስ ገዳዩ ማን እንደሆነ ያውቃል፤ መግለጽ ነው ያልደረፈው›› ብሏል፡፡ ፖሊስ ምን ያስፈራዋል? ልጁ ምን ማለቱ ይሆን? ፖሊስ ገዳዩን የሚያውቅ ከነበረ ታዲያ ይህን ሁሉ ሰዎች ለምን መረመረ? እነዚህ ሁሉ ሰዎች ገዳይ ከልሆኑ ደግሞ ማን ነው ገዳዩ? ምናለበት ቢናዘዝ… ረቡዕ በጉጉት እየተጠበቀች ያለችው ያለምክንያት አይደለም፡፡ ዶ/ር ቦንደሰን ግን ጨለምተኛ ሆነዋል፡፡ ‹‹ እሮብ አዲስ ነገር ከፖሊስ አልጠብቅም፤ አዲስ መረጃም አይኖራቸውም፡፡ ያም ሆኖ ጉዳዩን መዝጋት ፈልገዋል፡፡ ደግሞም መዘጋት አለበት፤ መልስ የለኝም ማለትም አንድ መልስ ነው እኮ፡፡" ሌላ ያልነገርናችሁ ምስጢርም አለ፡፡ ባለፈው ሚያዚያ ፖሊስ አንድ ዎኪቶኪ ስልክ አገኘ፡፡ ስልኩን የሆነ ሰውዬ ነው ለፖሊስ የሰጠው፡፡ ይሄ ዎኪ ቶኪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገደሉ ማግስት ነበር አንድ ሰውዬ አግኝቶት የደበቀው? ለምን ደበቀው? ለስዊድናዊያን ረቡዕ የሩቅ ቅርብ የሆነችው ያለምክንያት አይደለም፡፡ በስዊድን አቆጣጠር ነገ መቼ ነው?
50443855
https://www.bbc.com/amharic/50443855
በደረቀ ቆራጣ ጣት መጠጥ የሚቀምመው ካናዳዊ ሞተ
የአልኮል መጠጦችን ቀላቅሎ፣ ቅጠላ ቅጠል ጠብ አድርጎ በመቀመም የተካኑ ብዙ ናቸው። ካናዳዊው ካፒቴን ዲክ ስቴቨንሰን የሚታወቀው ግን መዐዛማ ቅጠሎችን ከጠንካራ የአልኮል መጠጦች ጋር ደባልቆ፣ በመዐዛ እያወዱ በመጠጥ ጉልበት በማስከር ብቻ አይደለም። "ሶርቶ ኮክቴል" በተሰኘው መጠጥ እንጂ።
ካፒቴን ዲክ ስቴቨንሰን ለራሱ መጠጥ ሲቀዳ የዚህ መጠጥ ስም ወደ አማርኛ ሲመለስ፤ ወዙ ቢመጠጥም፣ በአጭር ቃል ግን 'ቆራጣ ጣት ጣል ያለበት መጠጥ' ማለት ነው። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና እንዳይበላሽ ሆኖ የደረቀው ጣት፤ እውነተኛ የሰው ልጅ ጣት ነው። ሲጠጡት ደግሞ ሕግ አለው። ግጥም፤ ጭልጥ አልያም ፉት ሊያደርጉት ይችላሉ፤ ነገር ግን ውስጡ ያለው ጣት ከንፈርዎን ሊነካ ግድ ነው። የዚህ መጠጥ ፈጣሪ ካፒቴን ዲክ በ89 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ተሰናብቷል። ካፒቴኑ ማስከር ሥራው ነበር። ከማስከርም በላይ ግን በደረቀ ቆራጣ ጣት የተከሸነ መጠጥ በመቀመም የተካነ ነበር። እኤአ ከ1973 ጀምሮ ከመቶ ሺህ ሰዎች በላይ የሶርቶ ኮክቴል ክለብን ተቀላቅለዋል የዚህ መጠጥ ሃሳብ እንዴት ተገኘ? ይህ የ89 ዓመት አዛውንት መጠጡን ለደንበኞቹ መቸብቸብ የጀመረው እኤአ በ1970ዎቹ ነበር። በ1973 ግድም እርሱና ጓደኞቹ በአንድ የተረሳ የልብስ ሳጥን ውስጥ ቆራጣ ጣት ያገኛሉ። • አረቄ ከእንቁላል ደባልቆ በመጠጣት እውቅና ያተረፈው ቻይናዊ ጣቱ እንዳይበላሽ ሆኖ የደረቀ ነበር። ያኔ ታዲያ ከሚጠጡት የአልኮል መጠጥ ጋር እንዴት አድርገው ሊቀምሙት እንደሚችሉት አወጡ አወረዱና የሶርቶ ኮክቴልን ሃሳብ አመነጩ። ከዚህ ሃሳብ መጠንሰስ አንስቶ፤ መጠጡ የሚሸጥበት ግሮሰሪ ከ 10 በላይ የሰው እጅ ጣቶችን በስጦታ አግኝቷል። እኤአ ከ1973 ጀምሮ ከመቶ ሺህ ሰዎች በላይ የሶርቶ ኮክቴል ክለብን ተቀላቅለዋል። ግሮሰሪው የሚገኝባት የካናዳዋ ዳውሰን ከተማ ነዋሪዎች፤ ስቴቨንሰንን "ጀግናችን" ሲሉ በሞቱ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጠዋል። የከተማዋ አስተዳደሮችም በትዊተር ገፃቸው ላይ "ከተማችን አትረሳዎትም" ሲሉ ውለታውን አንቆለጳጵሰዋል። • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች በከተማዋ የሚገኝ ሆቴልም "የከተማችን አምባሳደር" ብሎታል ልጁ ዲክሲ ስቴቨንሰንም፤ የአባቴ የመጨረሻ ቃል ጣቶቹ ተጠብቀው ለሶርቶ ኮክቴል ክለብ እንዲሰጡለት ነው ስትል ለሲቢኤስ የዜና ወኪል ተናግራለች። ሆቴሉም ከቤተሰቡ ጋር በመሆን በደረቀ ጣት የተከሸነ መጠጥ ቀማሚውን ለማሰብ እቅድ እዟል።
49463977
https://www.bbc.com/amharic/49463977
ለኃይማኖት እኩልነት እና ማሕበራዊ ፍትህ የሚታገሉት የሰይጣን አምላኪዎች
'ስለ ሰይጣናዊ አምልኮ የምታውቁት ሁሉ ስህተት ነው።'
ስለ ሰይጣናዊ ቤተ-መቅደስ [ሳታኒክ ቴምፕል] የሚያትት አንድ ዘጋቢ ፊልም የሚለው ይህንን ነው። ስሙ ይመሳሰል እንጂ በ96 [እ.አ.አ.] ከተመሠረተው የሰይጣን ቤተ-አምልኮ ጋር ልዩነት አለው። የሰው ነብስ መገበር?. . . የለም። ደም መጠጣት?. . . የለም። ጥቁር የለበሱ ሰዎች. . . ይሄስ ይኖረዋል። ቤተ-እምነቱ የተመሠረተው 2013 [እ.አ.አ.] ላይ ነው። ሃሳባችን ቅንነትና እና ሩህሩህነት ለማበረታታት ነው ይላሉ። አልፎም ጨቛኝ አስተዳደርን ለመቃወም፣ ፍትሕን ለማስፈን እና ግለሰባዊ ፈቃድን ለማጠንከር እንደተቋቋመ መሥራቾቹ ይናገራሉ። 'ሰይጣንን ማመስገን?' በሚል ርዕስ በፔኒ ሊን የተሠራው ዘጋቢ ፊልም የቤተ-እምነቱን ሃሳብ ይዳስሳል። አማኞቹ ክርስትና የአሜሪካውያን ግላዊ ሕይወት ውስጥ በእጅጉ ጣልቃ ይገባል ሲሉ ይተቻሉ። ለአስሩ ትዕዛዛት ኦክላሆማ ከተማ ላይ ሃውልት እንደተሠራ ሁላ ለእነሱም የሰይጣንን አምሳያ ሃውልት በትልቁ የምናቆምበት ሥፍራ ይሰጠን ሲሉ ይከራከራሉ። ትግላችን የኃይማኖት እኩልነት እንዲሰፍን ነው፤ ማሕበራዊ ፍትህ እና ሰብዓዊ መብትን እናከብራለንም ባይ ናቸው። «ሰዎች ቆም ብለው እውን አሜሪካ የክርስትያን ሃገር ናት ወይ ብለው እንዲያስቡ እንፈልጋለን። ምክንያቱም አይደለችም» ይላል የቤተ-እምነቱ ቃል አቀባይ ሉሲዬን ግሪቭስ። 50 ሺህ ገደማ አባላት እንዳለው የሚነገርለት 'ሳታኒክ ቴምፕል' አማኞች እየዞሩ ሰዎች ደም እንዲለግሱ ሲያበረታቱ፣ ቤት ለሌላቸው ካልሲ ሲሰበስቡ እና የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችን ሲያፀዱ ፊልሙ ላይ ይታያሉ። ትያትር ውስጥ 'ሆረር' ፊልሞችን እያዩ በጥቋቁር ልብሶች ሆነው ሰይጣንን የሚዘክሩ ድርጊቶች ቢያከናውኑም አንዳቸውም በሰይጣን እናምናለን አይሉም። 'የምናምነው በሂብሩ ቋንቋ በተገለፀው ሰይጣን እንጂ' ይላሉ፤ ትርጉሙ ደግሞ ባላጋራ። ፊልሙ አማኞቹ እንዲተከልላቸው የሚሸቱት ባፎሜት [ባሮሜት] ላይ አትኩሮቱን አድርጓል፤ ሁለት ጣቶቹን ወደሰማይ የቀሰረው ባለፍየል ቀንዱ ሰው መሳይ የነሃስ ሃውልት። ቃል አቀባዩ ግሪቭስ [ለራሱና ለቤተሰቡ ደህንነት ሲል በተለያዩ ስሞች ይጠራል፤ ትክክለኛ ስሙም አይታወቅም] በየሥፍራው እየሄደ ባፎሜቱን ይሰቅላል። ነገር ግን ይህንን ማድረግ ለእርሱ ቀላል እንዳልሆነ ፊልሙ ላይ ሲናገር ይደመጣል። ሃውልት ለማስመረቅ ወደ ተለያዩ ሥፍራዎች ሲጓዝ ጥይት መከላከያ ያለው ጃኬት እንደሚታለብስ እና ከብዙ ሰዎች 'የእንገልሃለን' ማስፈራሪያ እንደሚደርሰው አይደብቅም። 'ሳታኒክ ቴምፕል' ወይንም ሰይጣናዊ ቤተ-መቅደስ የተሰኘው እንቅስቃሴ በሰፊው ከሚታወቀው የሰይጣን ቤተ-እምነት [ሳታኒክ ቸርች] በላይ ተወዳጅነትን እያተረፈ ይመስላል። በየሄዱበት ሥፍራም የሚሰበኩትን ቆመው የሚሰሙ በርካቶች ናቸው። ጨርቄን ማቄን ሳይሉ የሚከተሏቸውም አልጠፉም።
49859429
https://www.bbc.com/amharic/49859429
በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ
በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ።
•የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ሁለት ፓትሪያርክ ይኖራታል መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን በቁጥጥር ስር የዋሉት ቤተክርስትያኗ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት እንዲቆም የሚያወግዝ ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሰው በመገኘታቸው ነበር።ምእመናኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆኑት ቲሸርቶች 'የቤተክርስትያን ጉዳይ ያገባኛል'፣ የቤተክርስትያን መቃጠልና ጥቃት ይቁም' የሚሉ ፅሁፎች ያለባቸው እንደነበሩ አባ ወልደየሱስ አስረድተዋል። •የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ አካሄዱ አራቱ ደግሞ የሌላ ሰው ባጅ አድርገው በመገኘታቸው በቁጥጥር ሲውሉ ቀሪዎቹ 12 የሚሆኑት ደግሞ ስለት ይዘው ተገኝተዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስረዳሉ። •ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም ጠየቀ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የተወሰዱት ካዛንችዝ ከሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደነበርና በኋላ እሳቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሃላፊዎች ከነጋገሩ በኋላ 37 በዋስ መለቀቃቸውን መላከሕይወት አባ ወልደየሱስ ተናግረዋል።
news-52343684
https://www.bbc.com/amharic/news-52343684
ኮሮናቫይረስ፦ በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሻለ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት?
በኒውዚላንድ፣ ጀርመን፣ ታይዋንና ኖርዌይ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው የተነጠቁ ሰዎች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ነው።
እነዚህን አገራት የሚያመሳስላቸው ይህ ብቻ ሳይሆን መሪዎቻቸም ሴቶች መሆናቸው ነው። እኚሁ ሴት መሪዎች በዚህ ዓለም አቀፍ የጤና ቀውስ ወቅት የቫይረሱን መዛመት እንዲሁም የሟቾችን ቁጥር መቆጣጠር በመቻላቸው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ሙገሳን እያገኙ ይገኛሉ። •"ያስጨነቀኝ ከእኔ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ጤንነት ነበር" የኮሮናቫይረስ ታማሚዋ ከባህር ዳር •"መደብር ሄጄ የውጪ አገር ሰው አንቀበልም አሉኝ" ኢትዮጵያዊቷ በቻይና በመገናኛ ብዙሀን ዘንድም 'ምሳሌ መሆን የሚገባቸውም' በሚል እየተሞካሹ ነው። በቅርቡ ፎርብስ ባወጣው አንድ ፅሁፍ "የእውነተኛ መሪነት ተምሳሌት" ብሏቸዋል። "ሴት መሪዎች በዚህ ቀውስ ወቅት እንዴት አድርገን የሰውን ልጅ ህይወት መታደግ እንደሚቻል ለዓለም እያስተማሩ ነው" በማለት የፎርብስ ጽሁፍ አትቷል። አገራት እየወሰዷቸው ባሉ እርምጃዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠትና፣ የሰውን ልጅ ህይወት እየታደጉ ያሉ መሪዎች በሴት የሚመሩ አገራት ቢሆኑም፤ በዓለማችን ያሉ ሴት መሪዎች ሰባት በመቶ ብቻ ናቸው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመታገል ሴት መሪዎች እንዴት ሊሳካላቸው ቻለ? የቀደመ ምላሽ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት መሆኑን ተከትሎ የአይስላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ካትሪን ጃኮብስዶቲር በፍጥነት ተግባራዊ ያደረጉት እርምጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሕዝባቸውን መመርመር ነው። ሦስት መቶ ስድሳ ሺህ ብቻ የሕዝብ ቁጥር ባላት አገራቸው ውስጥ በሽታውን ችላ ያሉት ጉዳይ አልነበረም። እርምጃ መውሰድ የጀመሩት ጥር ወር መጨረሻ አካባቢ ነው። በአገሪቷ በቫይረሱ የተያዘ ሰው መኖሩ ከመረጋገጡ በፊት ሃያና ከዚያ በላይ ሰዎች ሆኖ መሰብሰብ ተከለከለ። በአይስላንድ በቫይረሱ የተያዘ ሰው መኖሩ ከመረጋገጡ በፊት ሃያና ከዚያ በላይ ሰዎች ስብሰባ ተከለከለ። እነዚህንም እርምጃዎች ተከትሎ አስከ ትናንትና ሚያዝያ 13፣ 2012 ዓ.ም በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ ብቻ ነው። በታይዋንም ፕሬዚዳንት ሳይ ኢንግ ዌን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የወረርሽኝ መቆጣጠሪያ ማዕከል ያቋቋሙት ቀድመው ነው። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ወይም ግንኙነት አለባቸው የተባሉ ሰዎችንም ክትትል ማጠናከርም በከፍተኛ ሁኔታ ሰርተውበታል። በሽታውም ከሰው ወደ ሰው እንዳይዛመት የሚያገለግሉ ፊት ጭምብልን የመሳሰሉ የመከላከያ ቁሳቁሶችንም ማምረቱንና ማሰራጨቱን በእሳቸው መሪነት የተከናወነ ነው። ሃያ አራት ሚሊዮን የሕዝብ ቁጥር ባላትና የቻይና አካል በሆነችው ታይዋን የሞተው ሰው ቁጥር ስድስት ብቻ ሆኖ ዓለምን አስደምሟል። •ለኮሮናቫይረስ፤ መቼ ነው ሐኪም ቤት መሄድ ያለብኝ? •"የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም" ዶ/ር ፅዮን ፍሬው የታይዋን መሪ ብቻ አይደሉም የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደንም ኮሮናቫይረስን ለመግታት ፈታኝ የሚባለውን ውሳኔ በማስተላለፍ አገራቸውን ከወረርሽኙ ታድገዋታል። የተለያዩ አገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየወሰዱት ባለው እርምጃ፣ ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ደረጃ ላይ ደርሶ እንዲመለስ የሚያደርግ ውሳኔ ላይ ቢደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትሯ ግን ወረርሽኙን ሙሉ በሙሉ የማስቆም ሥራ ላይ ነበር ያተኮሩት። አገራት ሙሉ በሙሉ የመዝጋትም ሆነ አስገዳጅ የቤት መቀመጥ ውሳኔ የሚወስኑት በኮሮናቫይረስ የተያዘው ሰው ቁጥር ከፍ ሲል ነው። እኚህ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን ከሌሎች አገራት በተለየ ሁኔታ የሟቾች ቁጥር ስድስት ሲደርስ ሙሉ በሙሉ አገሪቷን ዘጉ፤ ዜጎች ቤታቸው እንዲቀመጡ ተወሰነ። እስከ ትናንትና ሚያዝያ 13፣ 2012 ዓ.ም ድረስ የተመዘገበው የሟች ቁጥርም 12 ነው። የታይዋኗ ፕሬዚዳንት ሳይ ኢንግ ዌን ከባለስልጣኖቻቸውና ከወታደሮቻቸው ጋር የፊት ጭምብል አጥልቀው ከኮሮና ቀውስ ጋር ተያይዞ በፍጥነትና፣ በተሳካ ሁኔታ ምላሽ የሰጡ አገራት በሴቶች ከመመራታቸው በተጨማሪ ሌላም ተመሳሳይ ሁኔታዎችን ይጋራሉ። አገራቱ ያደገ የምጣኔ ሃብት ባለቤት ሲሆኑ ለዜጎቻቸውም የደኅንነትና ማኅበራዊ ድጋፍ ሥርዓት ዘርግተው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። በዓለም ላይ ባሉ አገራትም ዘንድ ማኅራዊ ልማት ተብሎ በሚጠራው ዘርፍ ከፍተኛ ነጥብን ማስመዝገብ ችለዋል። ለኮሮናቫይረስ ቀውስ የይድረስ ይድረስ ሳይሆን ከዚህ ቀደምም ጠንካራ የጤና ሥርዓት ዘርግተው ድንገተኛ ሁኔታዎችንም የማከም ብቃት ያላቸው ከመሆናቸው አንፃር የኮሮናቫይረስ ትግል አልከበዳቸውም። •የመጀመሪያውን ኮሮናቫይረስ ስላገኘችው ሴት ያውቃሉ? እናም ነገሩ ከመሪዎቹ ነው፤ ሴት መሪዎች መሆናቸው ነው ቁም ነገሩ። ስለዚህም አንዲት አገር ሴት መሪ ሲኖራት ስለአገሪቱ ሁኔታ የሚጠቁመው ነገር ይኖር ይሆን? ሴቶች ተመርጠው በፖለቲካው ውስጥ የሚሳተፉበት መንገድ የራሱን ሚና እንደሚጫወት ተንታኞች ይናገራሉ። "ሴቶች ከወንዶች የተለየ አይነት አመራር አላቸው ብዬ አላስብም። ነገር ግን ሴቶች በመሪነት ቦታ ሲቀመጡ ውሳኔ ላይ ለየት ያለ ሁኔታ ሊያመጡ ይችላሉ" የሚሉት በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ በታዳጊና በሴቶች ላይ የሚያጠነጥነው 3ዲ ተብሎ የሚጠራው ፕሮጀክት ሥራ አስፈፃሚ ናቸው። "ሴቶችን እንዲሁም ወንዶችንም ማሳተፍ ስለሚችል ጥሩ ውሳኔ ላይ መድረስ ይቻላል" በማለት ለቢቢሲ አስረድተዋል። በተቃራኒው ደግሞ ዓለማችን የሳይንስን እውነታ የካዱ፣ እንዲሁም በማን አለብኝነት በተወጠሩ እንደ አሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የብራዚሉ ጄይር ቦልሶናሮ አይነት መሪዎችንም አይታለች። የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ኮሮናቫይረስ ጉንፋን ነው በማለት አጣጥለው አካላዊ ርቀት አያስፈልግም እስከ ማለት ደርሰዋል። የእነዚህ መሪዎች ሁኔታ ከወንድነታቸው ጋር የተያያዘ ጉዳይ ይኖረው ይሆን? በለንደን ኮሌጅ የሴቶች አመራር ተቋም ዳይሬክተር ሮዚ ካምቤል፤ አመራር ከሴትነት እንዲሁም ከወንድነት ጋር የሚያይዘው ጉዳይ የለም ይላሉ "የአመራር ብቃት አብሮ የሚወለድ ጉዳይ አይደለም። ነገር ግን ማኅበራዊ አኗኗራችን የሚፈጥረው የራሱ ተፅእኖ አለው። ሴቶች ሃዘኔታ ሲኖራቸው እንዲሁም በመተባበር መመራት ተቀባይነት አለው። ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አብዛኞቹ ወንድ መሪዎች ብልጣብልጥ፣ ራስ ወዳድ፣ ማን አለብኝ ባይ ናቸው።" ይህም እንዴት ሆነ ለሚለውም ምሁሯ ምላሽ አላቸው "በፖለቲካው ዓለም ውስጥ ባለው የወንዶች አመራር እነዚህ ባህርያት ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘታቸው እወደድ ባይ መሪዎች በዝተዋል።" እወደድ ባይ መሪዎች ያንን ሕዝብ ለማስደሰት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፤ የሚሉት ፕሮፌሰር ሮዚ ወረርሽኙንም የመቆጣጠሩንም ሂደት ዋጋ አስከፍሏቸዋል ይላሉ። •የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኛ የኮቪድ-19 ናሙና ሲሰበስቡ ተገደሉ ለመጥቀስም ያህል የአሜሪካ፣ የብራዚል፣ የእስራኤልና የሃንጋሪ መሪዎች ችግሮቻቸውን ከመቅረፍ ይልቅ ጥፋታቸውን በሌሎች ላይ ለማላከክ ሲሯሯጡ ተሰምተዋል። በተደጋጋሚም የውጭ አገራት ዜጎች ቫይረሱን እንዳስገቡት እንዲሁም አገራትን ጥፋተኛ አድርገዋል። "ለምሳሌ ያህል ትራምፕና ቦልሶናሮን እንውሰድ የማን አለብኝነት ባህርይ ያሳያሉ። ምንም ከአፈጣጠራቸው ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ የለም። እንዲህ ለመታበይ መርጠው ነው" ይላሉ። "አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች በሕዝብ እወደድ ባይ የመሆን እንዲሁም ፅንፈኛና ወግ አጥባቂ አክራሪ መሪዎች አይሆኑም። ግን ሆኖም አንዳንድ አይታጡም ለምሳሌ የፈረንሳይዋ መሪ ማሪን ለ ፔን" በማለት ያስረዳሉ። ኮሮናቫይረስን ለመግታት አገራት እየወሰዱት ያለው እርምጃ የተለያየ ነው፤ ምክንያቱም የየአገራቱ ማኅበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ እውነታ መለያየቱ ለወረርሽኙ የሚሰጡትም ምላሽም ተመሳሳይ እንዳይሆን አድርጎታል። እዚህ ላይ ፆታ ብቻውን የሚጫወተው ሚና ላይኖር ይችላል። ምንም እንኳን ትራምፕና ቦልሶናሮ ከእወደድ ባይነታቸው አንፃር የማን አለብኝነትና ራስ ወዳድ ቢሆኑም እንዲህ አይነት ባህርይ ያልተላበሱ ወንዶች ፕሬዚዳንቶችም በአገሮቻቸው ከፍተኛ እመርታን ማሳየታቸውን ፕሮፌሰር ሮዚ ይናገራሉ። ለምሳሌነት ከሚጠቅሷቸው መካከል ጥቂት ሞት የተመዘገበባትን የደቡብ ኮሪያ መሪ ሙን ጄን ነው። ፕሬዚዳንቱ በአገራቸው ላሳዩትም የአመራር ብቃት በቅርቡ በተደረገው ምርጫ ተቀናቃኞቻቸውን በከፍተኛ ድምፅ ልዩነት ማሸነፍ ችለዋል። •ከሚስታቸውና ከልጃቸው ጋር ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የአዳማ ነዋሪ ወደ ቤታቸው ተመለሱ የግሪኩም ጠቅላይ ሚኒስትር ክይሪያኖስ ሚትሶታኪስ ሌላኛው ፕሮፌሰሯ በምሳሌነት የሚጠቅሷቸው መሪ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወረርሽኙ እንዳይዛመት ከፍተኛ ሚናን በመጫወት እንዲሁም የሟቾች ቁጥርም እስከ ሚያዝያ 13/2012 ዓ.ም ድረስ በ114 እንዲገታ የላቀ ጥረት አድርገዋል ተብሏል። አገሪቷ 11 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን በተቃራኒው 60 ሚሊዮን ህዝብ ባላት ጣልያን 22 ሺ ሞት ተመዝግቧል። ግሪክ በወረርሽኙ መነሻ ወቅት የታወቁ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት አካላዊ ርቀትን አስገዳጅ እንዲሆን ውሳኔ ያሳለፈችው የመጀመሪያው ሞት ከመመዝገቡ በፊት ነበር። ሴቶች ከወንዶች በበለጠ በኮሮና ቫይረስ በማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ጫና ያርፍባቸዋል። ሁሉም በሴቶች የሚመሩ አገራት አይደሉም ወረርሽኙን መግታት የቻሉት አንዳንድ ሴት መሪዎች አሁንም ያላሰለሰ ትግል ላይ ናቸው። ለምሳሌም ያክል የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሃሲና ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ባለባት አገራቸው የቫይረሱን መዛመት መግታት ችለዋል። ሆኖም አገሪቷ ባላት የመመርመር ብቃት ማነስ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ባለባቸው የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት የተነሳ ስጋቶች አልተቀረፉም። አስቸጋሪ ውሳኔዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት አገራት ፈታኝ የሚባሉ ውሳኔዎችን ማሳለፍ አለባቸው። ወረርሽኙ ገና ከመዛመቱ በፊት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ ማገድ ወይም መዝጋትን አስገዳጅ ሊያደርጉ ይገባል። እነዚህ ውሳኔዎች አጠር ላለ ጊዜ ምናልባት ፖለቲካዊ ዋጋ ሊያስከፍሏቸው እንደሚችሉ ፕሮፌሰሯ ይናገራሉ "የእወደድ ባይ መሪ ተቃራኒ ይህ ነው። መሪዎችም ተግባራዊ ሊያደርጉት የሚገባ ነው።" በተቃራኒው ሴቶች መሪዎች ግልፅነት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት በተሞላበት መልኩ ለዜጎቻቸው የወረርሽኙን ስጋት በማሳወቅና አገሮቻቸው የገጠሟቸውን ፈተናዎችንም በመወያየት በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችለዋል። •በኮቪድ - 19 የሞተ ሰው የቀብር ሥነ- ሥርዓት እንዴት መፈጸም አለበት? የጀርመኗ መራሔተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ኮቪድ-19 "ከባድ ስጋት" መሆኑን ያሳወቁት በፍጥነት ነው። ይህንንም ተከትሎ አገራቸው በከፍተኛ ሁኔታ የምርመራ ጣቢያዎችን አቋቋመች፣ ከአውሮፓ የሚመጡም ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደረጉ። በሌሎች አውሮፓ አገራት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሲያልቁ 83 ሚሊዮን ባላት ጀርመን የሟቾች ቁጥር 4600 ሆኗል። የስካንድኔቪያኖቹ ኖርዌይና ዴንማርክ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትሮቻቸውም በማን አለብኝነት ሲንጠራሩ ከነበሩ አቻ ወንድ መሪዎቻቸው በበለጠ ቫይረሱን መቆጣጠር ችለዋል። የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልድበርግና የዴንማርኳ ሜት ፍሬዴሪክሰን የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልድበርግና አቻቸው የዴንማርኳ ሜት ፍሬዴሪክሰን ትልልቅ ሰዎች እንዳይገቡ በማድረግ ለህፃናት ብቻ የጥያቄና መልስ ፕሮግራም አዘጋጅተው ነበር። የኒውዚላንድ መሪ ጃሰንዳ አርደንም እንዳቻዎቻቸው ሁሉ ህፃናትን ችላ አላሉም፤ በአገራቸው እንደተለመደው የትንሳኤ በዓል ላይ በሚደረገው ባህል መሰረት ኮሮናቫይረስ እንደማያቋርጠው አሳውቀው በየቤታቸውም የቸኮሌት እንቁላል እንዲደርሳቸው አድርገዋል። •"ቀብር ከሩቁ እናይ ነበር" የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር ነዋሪዎች ታሪክ ሴት መሪዎች የሚያደርጉትንም በማስተዋል ከዚህ ቀደም እንደ ቀልድ ወይም ችላ ተብለው የነበሩ ጉዳዮችን በማንሳት ፖለቲካ በህፃናት ላይ የሚያደርገውን ጫና ቦታ መስጠት እንደቻሉ ፕሮፌሰሯ ያስረዳሉ። በተለይም የግል ጉዳይ ተብለው ወደ ጎን የተተዉ እንደ የቤት ውስጥ ጥቃቶችንና የህፃናት እንክብካቤ መሰረታዊ ጉዳዮች መሆናቸውን እንዳሳዩ ፕሮፌሰሯ አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። የተሻሉ ውሳኔዎች በዓለም ላይ 70 በመቶ የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ሴቶች ቢሆኑም፤ በመሪነት ቦታ ላይ ከሚገኙት 153ቱ መካከል ግን አስሩ ብቻ ሴቶች መሆናቸውን ከሁለት ዓመት በፊት የወጣ መረጃ ጠቁሟል። ከዚህም በተጨማሪ የፓርላማ አባላትን በምናይበት ወቅት ሴቶች ሩብ ብቻ ናቸው። በአለም ላይ 70 በመቶ የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ሴቶች ቢሆኑም፤ በአለማችን ካሉ 153 መሪዎች መካከል አስሩ ብቻ ሴቶች መሆናቸውን ከሁለት አመት በፊት የወጣ መረጃ ጠቁሟል። በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በጤናው ዘርፍ የሴቶች አመራር ሚናን ለመጨመር የሚሰራውን ውሜን ሊፍት ሄልዝ ቦርድን የሚመሩት ዶ/ር ጉፕታ በአመራር ላይ የሚገኙ ሴቶች ቁጥር መጨመር የተሻለ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይ መድረስ እንደሚያስችል ይናገራሉ። •ከኮሮናቫይረስ በኋላ ኢኮኖሚያቸው በቶሎ ሊያገግም የሚችል አምስት አገራት "ለጥቂቶች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎች የሚጠቅሙ ፖሊሲዎችንም ሆነ ውሳኔዎችን መስጠት ይችላሉ" በማለት ያስረዳሉ። "ምክንያቱም ሴት መሪዎች በተለያየ የሥራ ድርሻ እንዲሁም የመሪነት ቦታ ሆነው ህይወትን ያውቁታል። አብዛኛውንም ጊዜ የሚሰጣቸው የሥራ ድርሻ በማኅበረሰቡ ዘንድ ለሴቶች ተብለው የተተው ናቸው። በመሪነት ቦታም ሲመጡ ያካበቱትን ልምድ፣ ያለውንም ክፍተት ስለሚረዱ የተሻለ ፖሊሲ እንዲሁም ውሳኔ ላይ መድረስ ይችላሉ" ይላሉ። ዶ/ር ጉፕታ አክለውም ኮቪድ-19 ሊያስከትለው የሚችለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ልብ ሊባል እንደሚገባ አስታውሰው፤ በተለይም የቤት ውስት ጥቃት መጨመር እንዲሁም በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለው ክፍያ ልዩነት እንዳያንሰራራ ባለድርሻ አካላት ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባም መክረዋል።
48672478
https://www.bbc.com/amharic/48672478
"ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል" ደበበ እሸቱ
በ1936 ዓ. ም. ነው የተወለደው፤ ደበበ እሸቱ። በሀገር ፍቅርና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (የአሁኑ ብሔራዊ ቴአትር) መድረክ ላይ ለረዥም ዓመታት በተዋናይነትና በአዘጋጅነት ነግሷል። በተለያዩ ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት ተሳትፏል። ሆሊውድ በተሠራው 'ሻፍት ኢን አፍሪካ' በተሰኘው ፊልም ላይ በመሳተፍም ስሙን በደማቁ ፅፏል።
ከጋዜጠኛነት በተጨማሪ በራድዮና በቴሌቪዥን ሥራዎችም ላይ ተሳትፏል። 'ያላቻ ጋብቻ'፣ 'ሮሚዎና ዡልየት' እና 'ዳንዴው ጨቡዴ' ከተወነባቸው ሥራዎች ጥቂቶቹ ናቸው። በእንግሊዘኛ ከሠራቸው ፊልሞች መካከል 'ዘ ሴይለር ፍሮም ጂብራልታር'፣ 'ጉማ'፣ 'ዘ አፍሪካን ስፓይ'፣ 'ዜልዳ'፣ 'ዘ ግሬቭ ዲገር' እና 'ዘ ግሬት ሪቤሊየን ' ይጠቀሳሉ። ደበበ በአማርኛ ብቻ ሳይሆን በእንግሊዘኛ የተፃፉ ተውኔቶች ላይም ተሳትፏል። 'ዘ ጌም ኦፍ ቼዝ' ላይ በትወና ፣ 'ኦቴሎ' ላይ በመተወንና በማዘጋጀትም አሻራውን አኑሯል። • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች ደበበ በ1995 ቀስተ ደመና ፓርቲን ተቀላቅሎ፤ በኋላም ቅንጅት ውስጥ የሕዝብ ግንኙነት ነበር። በዚህ የፖለቲካ ተሳትፎው ከአንድ ዓመት በላይ ታስሯል። ይህ ጎሙቱ የሙያ ሰው ኬንያ፣ ናይሮቢ የሚገኘው ቢሯችን መጥቶ ነበር። እኛም ቀጣዮቹን ጥያቄዎች አቅርበንለታል። ቢቢሲ፡ ጤናህ እንዴት ነው? ደበበ እሸቱ፡ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። አላማርርም። 'ባዶ እግር'ቴአትር ላይ ትሳተፋለህ ተብሎ ነበር፤ ግን አላየንህም። ለምን ነበር? ደበበ እሸቱ፡ አንድ ጊዜ አሞኝ ሆስፒታል ገብቼ ነበር። እና ለጊዜው አቋርጬ ነበር። እየደከመኝም፣ አንዳንድ ጊዜ ከእድሜ አንፃር እያየሁት እንጂ በተቻለ መጠን እየሠራሁ ነው። ከእስር ቤት ከወጣህ በኋላ እንደ አዲስ በተለያዩ ሥራዎች ወደ አድናቂዎችህ መጥተሀል። መጽሐፍም ተርጉመሀል። መጽሐፉ ምን ያህል ተነቧል? ደበበ እሸቱ፡ ተነባቢነቱ ምን ያህል እንደሆነ መረጃው የለኝም። ነገር ግን ገበያ ላይ አልቋል። ስንት ኮፒ ታትሞ ነው ያለቀው? ደበበ እሸቱ፡አገር ውስጥ ወደ አስር ሺህ ኮፒ ሲሆን፤ በውጪም ታትሞ ለገበያ የቀረበው እንደዚሁ ተሸጦ አልቋል። ስለዚህ አገር ውስጥ በድጋሚ ሊታተም ነው። ሌላ እየጻፍክ ወይም እየተረጎምክ ያለኸው መጽሐፍ አለ? ደበበ እሸቱ፡ በቅርብ ጊዜ ለህትመት የሚበቃ ተርጉሜ የጨረስኩት መጽሐፍ አለ። መጽሐፉ ወደ ኢትዮጵያ ስለመጡት የመጀመሪያው የካቶሊክ ጳጳስ አቡነ ዣርሶ ነው። ስለእርሳቸው ብዙ አይነገርም። ጃንሆይን ፈረንሳይኛ ያስተማሩት አቡነ ዣርሶ ናቸው ይባላል። ነገር ግን አይደሉም። አቡነ ዣርሶ መርጠው ያሳደጓቸው አቶ አለማየሁ የሚባሉ ሰው ናቸው። ጃንሆይ በስደት በሄዱበት ጊዜ ሊግ ኦፍ ኔሽን ውስጥ ገብተው እንዲናገሩ ያደፋፈሯቸው፣ ያስገደዷቸው፤ እንደውም ከፈረንሳይና ከሌሎችም አገሮች አብረዋቸው የሚሄዱ ሰዎች እንደሚኖሩና ይህንን ካላደረጉ ግን የጣሊያን መንግሥት ያለምንም ተቃውሞ ኢትዮጵያን ቅኝ ስለሚገዛ ሄደው ንግግር ያድርጉ ያሉ ትልቅ ሰው ናቸው። • በብርሃን ታስሰው የማይገኙት ሴት ኮሜዲያን ንግሥቲቱ ባያቆሟቸው ኖሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመላ ካቶሊክ ይሆን ነበር፤ ካለህበት ቦታ እንዳንትንቀሳቀስ በማለት የገደቧቸው። ታሪካቸውን በፈረንሳይኛ ነው የጻፉት። እኔ ወደ እንግሊዘኛ ተመልሶ የታተመውን መጽሐፍ ከአንድ ወዳጄ ጋር አግኝቼ ነው አንብቤ የተረጎምኩት። መቼ ነው ገበያ ላይ የሚውለው? ደበበ እሸቱ፡ ገና ወደ ማተሚያ ቤት አልሄደም፤ ምናልባት ከሁለት ወር በኋላ ታትሞ ገበያ ላይ ይውል ይሆናል። ከእስራኤላውያን ጋር 'ቀያይ ቀምበጦች' የሚል አንድ ፊልም እየሠራህ እንደነበር ሰምቻለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ታየ? ደበበ እሸቱ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም። አሁንም ገና ፌስቲቫሎች ላይ እየቀረበ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ካናዳ፣ ቫንክሁቨር ላይ ዓለም አቀፍ የፊልምና የቴሌቪዥን ፌስቲቫል ላይ ታይቶ በምርጥ መሪ ተዋናይ ዘርፍ ተሸላሚ ሆኛለሁ። በመሪ ተዋናይነት ብቻ ነው የተሳተፍከው? ደበበ እሸቱ፡ በትርጉምም ተሳትፌያለሁ። ስክሪፕቱን (ፅሁፉን) ከእንግሊዝኛ በመመለስና ዳይሬክተሩን በማገዝም ተሳትፌያለሁ። ከምናውቃቸው ሰዎች ማን ማን ተሳትፎበታል? ደበበ እሸቱ፡ (ሳቅ) ከምታውቃቸው መካከል እኔ ብቻ ነኝ የተሳተፍኩበት። ፈረንጆቹን አታውቃቸውም እያልከኝ ነው? ደበበ እሸቱ፡(ሳቅ) አይደለም፤ ቤተ እስራኤሎቹን አታውቃቸውም ለማለት ነው። ደራሲውና ጸሐፊው ቤተ እስራኤላዊ ነው። ፊልም ሥራ ተምሯል። ሁለት ዘጋቢ ፊልሞች ሰርቷል። አንደኛው ተሸልሟል። ፕሮፌሽናል ኤዲተር ነው። የአይ ቲ ኤክስፐርት (ባለሙያ) ነው። በዳይሬክቲንግና በአክቲንግ (በተዋናይነት) ሁለት ዲግሪ አለው። አሁን ኢትዮጵያዊ ነኝ ነው የሚለው። ከእኔ ጋር ከተገናኘ በኋላ ሁለት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። ደበበ እሸቱ እ.አ.አ. በ1973 'ሻፍት ኢን አፍሪካ' የተሰኘው ፊልም ላይ ከኔዳ አርነሪክ ጋር ሲተውን • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች ማን ይባላል ስሙ? ደበበ እሸቱ፡ባዚ ጌቴ ይባላል። በሕፃንነቱ ነው ወደ እስራኤል የሄደው። ከራሱ ሕይወት በመነሳት ነው ፊልሙን የፃፈው። በፊልሙ የሚያሳው የባህል ልዩነት በቤተሰብ ውስጥ የሚያመጣውን መለያየት ነው። ፊልሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ቴልአቪቭ ውስጥ በዘጠኝ ሲኒማ ቤቶችና በዘጠኝ ቴሌቪዥኖች አንዴ ነው ለእይታ የበቃው። የመክፈቻ ፕሮግራሙ መዝጊያ ላይ ቡና ሻይ እያልን ከእንግዶች ጋር ስንወያይ አንዲት ሁለተኛ ዲግሪዋን አጠናቅቃ ሦስተኛ ዲግሪዋን እየሠራች ያለች ቤተ እስራኤላዊት ወጣት መጥታ ከሚገባኝ በላይ አጥብቃ አመሰገነችኝ። እኔም 'ምነው እንዲህ ምስጋናውን አጠነከርሽው?' ብዬ ስጠይቃት 'ፊልሙ ላይ ከአባቷ ጋር የተጣላችውን ልጅ ስመለከት የኔ ታሪክ መስሎኝ ነው' ብላ ነገረችኝ። 'ከአባቴ ጋር ሳንነጋገር ብዙ ዓመት ሆኖናል' አለች። 'አባትሽ ዛሬ አልመጡም?'ስላት፤ 'መጥተዋል' ብላ በርቀት ጠቆመችኝ። • ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር ሄጄ አባትየውን 'ፊልሙን እንዴት አዩት?' ስላቸው 'ልጄንና እኔን አየሁበት፤ እግዚአብሔር ይስጥህ አስለቀስከኝ' አሉኝ። 'ታዲያ ለምን ልጅዎትን አያናግሯትም?' ብላቸው 'ከሷ ጋርማ በቃ ተለያየን' አሉኝ። 'አሁን ብትመጣስ?' ስላቸው 'ልጄ ነች አቅፌ እስማታለሁ' አሉ ከዚያ አገናኘኋቸውና ተላቀሱ። እና ሌሎች ሰዎችም እንዲህ እንዲያደርጉ ያስቻለ ፊልም ነው። ባዚ ጌቴ ይህንን እድል ስለሰጠኝ በጣም አመሰግነዋለሁ። ከፊልሙ በፊት ትተዋወቁ ነበር? ደበበ እሸቱ፡ አንተዋወቅም። ሲፈልገኝና የተለያዩ ሰዎችን ሲጠይቅ (ሳቅ) ቃሊቲ ነበርኩ። ትምህርት ቤት ነበርኩ። ስለዚህ አላገኘኝም። ከቃሊቲ ከወጣሁ በኋላም ሰዎች አታገኘውም ብለውት ተስፋ አስቆርጠውት እንደነበር አጫውቶኛል። በኋላ ግን ቺካጎ የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ልጄን ፌስቡክ ላይ አግኝቷት 'የደበበ እሸቱ ልጅ ነሽ?' ብሎ ይጠይቃታል። እርሷም ሌላ ነገር ስለመሰላት 'ምን አገባህ?' ብላ ትመልስለታለች። በኋላ ላይ 'አባትሽን እስራኤላውያን ለሥራ እየፈለጉት ነው' ብሎ ዝርዝሩን ሲያጫውታት 'ልጠይቀውና እሺ ካለኝ ስልኩን እሰጣችኋለሁ' ብላቸው አናገረችኝ። ከዚያ በኋላ ነው የደወሉልኝ። በንግግራችን መካከል እሺም እምቢም ከማለቴ በፊት ጽሁፉን ማየት አለብኝ አልኩ። ሲኖፕሲሱን (የፅሁፉን ጭብጥ) ላኩልኝ። እኔ በሲኖፕስስ አላምንም። ምክንያቱም በመካከል በርካታ ነገር ሊካተትበት ይችላል። ስለዚህ ሙሉ ጽሑፉን ላኩልኝ አልኳቸው፤ ላኩልኝ። • የፈረሰው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ቤት ጠባቂ ምን ይላል? ከዚያ ትንሽ ፊልም ተቀርፀህ ላክልን አሉኝ። ላኩላቸው። ከዚያ በኋላ ግን ጠፉ። እኔም ትተውታል ብዬ ተቀምጬ ባለሁበት ካናዳ ልጄን ለመጠየቅ ከባለቤቴ ጋር በሄድኩበት ደወሉልኝ። ከዛም 'ኮንትራት ለመፈራረም ለንደን ና እኛም ለንደን እንመጣለን' አሉ። አልመጣም አልኩ። ኮንትራቱን ከተፈራረምኩ ወይ ኢትዮጵያ አልያም እስራኤል ነው መሆን ያለበት ብያቸው በዚያ ተስማምተን እስራኤል ሄጄ ተፈራረምን። ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው እዚያ ነው። ከኢትዮጵያ በብዛት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሠሩ ፊልሞች ላይ ስትሳተፍ የማውቀው አንተን ነው። ከአንተ ውጪ በዓለም አቀፍ ፊልሞች ላይ የሚሳተፉ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አሉ? ደበበ እሸቱ፡ዘውዴ አርዓያ የምትባል ጣሊያን አገር ከፍተኛ እድል አግኝታ ፊልም የምትሠራ ኤርትራዊት አውቃለሁ። ከኤርትራዊቷ ውጪ እዚህ አገር ያለኸው አንተ ነህ? (ሳቅ) ደበበ እሸቱ፡ (ሳቅ) አይደለሁም። ሌሎችም ሊኖሩ ይችላሉ። ቅድምስለቃሊቲ ስታነሳ 'ትምህርት ቤት ነበርኩ' አልክ። በርግጥ የቃሊቲ ቆይታህን እንደ ትምህርት ቤት ነው የምታየው? ደበበ እሸቱ፡አዎ እንደ ትምህርት ቤት ነው የወሰድኩት። ምን ተማርክበት? ደበበ እሸቱ፡ ትዕግስትን ተምሬበታለሁ። ሲጋራ ከብዙ ዓመታት በኋላ ማቆም የቻልኩት ቃሊቲ ነው። ሰዎች እስር ቤት ሲጋራ ይለመዳል እንጂ ሲጋራ አይተውም ሲሉ ሞገቱኝ። እኔ ግን ማቆም እችላለሁ ብዬ አቆምኩኝ። አንድ ሰው በሚታሰርበት ጊዜ ሰው መሆኑ እንደሚጠፋ ተምሬበታለሁ። እስር ላይ ያለ ሰው የራሱ ሰው አይደለም። ሰዎች ናቸው እንዲቀመጥ እንዲነሳ፣ እንዲበላ፣ እንዲጠጣ፣ እንዲሄድ፣ እንዲቆምና እንዲያዘግም የሚነግሩት። የሚቆጣጠሩትም ከበላይ ያሉት ሰዎች ናቸው። እኛን ያጋጠሙን ደግሞ ክፉዎች ናቸው። ሊጎዱን ይሞክሩ ነበር። ግን ሳይደግስ አይጣላም ሆኖ ፖሊሶቹን በፍቅር አሸንፈናቸው ነበር። • ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ በወቅቱ የነበሩት ኃላፊዎች ፖሊሶቹን በየወሩ ይቀይሯቸው ነበር። እኛ ጋር በተመደቡ ማግስት ደግሞ ከእኛ ጋር ወዳጅ ይሆናሉ። እኛ እንነግራቸው የነበረው እነሱ እንዳላሰሩን፣ እነሱ የኛ ጠባቂዎች ብቻ መሆናቸውንና የሚጠብቁንም ለኛ ደህንነት እንደሆነ ነበር። ስለዚህም በጠላትነት ከመፈራረጅ ይልቅ በኢትዮጵያዊነት ለመግባባት እንሞክር ነበር። ስለዚህ እኔ ትምህርት ቤት ነው ብዬ ነው የማየው። በርካቶች አሁንም ድረስ አንተ ያለህበትን ተውኔት ለማየት ይጓጓሉ።ልክ እንዳንተ ሰፍ የምንልለት ወጣት ተዋናይ ማየት ያልቻልነውለምንድን ነው? ደበበ እሸቱ፡ መጀመሪያ እኔን አያችሁና ወደዳችኋ (ሳቅ) [ሌሎችም ተዋንያን] ግን አሉ። ቢኖሩ አናያቸውም ነበር? ደበበ እሸቱ፡ አሉ፤ በቴአትሩም በፊልሙም ላይ አሉ። ከነሙሉዓለም ታደሰ እና ዓለማየሁ ታደሰ ወዲያ በቴአትሩ ላይ ስማቸው የሚነሳ ተዋናዮችአሉ? ደበበ እሸቱ፡እነሱም እኮ የኔ እድሜ አይደሉም። ነገር ግን ተተኪወጣትየምንላቸውም አይደሉም። ደበበ እሸቱ፡ በእርግጥ ወጣት አይደሉም። ችግሩን ግን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። እነዚህ ልጆች የሚያገኙት የወር ደመወዝ አነስተኛ በመሆኑ ከቴአትር ይልቅ ወደ ፊልም ያደላሉ። ክፍያው ቢስተካከልና ለመኖር የሚያስችላቸው ገቢ ቢያገኙ መድረክ ላይ ይቆዩ ነበር። በርካታ ባለሙያ መድረክ ላይ መታየት፣ መሥራት ይፈልጋል። አሁን በቅርብ የተከፈተው 'መንታ መንገድ' አለ። ማንያዘዋል የተረጎመው 'እምዬ ብረቷ' ቴአትርም አለ። እዚያም ላይ ብዙ ልጆች አሉ። ግን ብዙ ፈተና አለው። ደሞዛቸው ቢስተካከልላቸውና ለመኖር የሚችሉበት ገቢ ቢያገኙ በርካታ ወጣት ተዋንያንን መድረኩ ላይ እናያለን። ደግሞ ወጣቶቹ ሀሳብ አላቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባዘጋጁት 'ገበታ ለሸገር' የእራት ግብዣ ላይ እነሰለሞን ዓለሙ በሕንድ ተይዞ የነበረውን በመላ አገሪቱ ዛፍ የመትከል ክብረ ወሰን ሐምሌ 21 መስበር የሚያስችል ዘመቻ ለማካሄድ አስበዋል። • በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ? ስንት ችግኝ ነው ለመትከል ያሰባችሁት? ደበበ እሸቱ፡ሕንድ 100 ሚሊየን ዛፍ በመትከል ክብረ ወሰኑን ይዛለች። እኛ በመላ አገሪቱ ሁለት መቶ ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ነው ያሰብነው። በቅርብ ጊዜ ውስጥ በትወና ወይምበዝግጅት መድረክ ላይ እናይሀለን? ደበበ እሸቱ፡በቴሌቪዥን አላየኸኝም? አዎ፤ 'ደርሶ መልስ' ላይ። ደበበ እሸቱ፡አንድ ሰውም ቴአትር ትሠራልኛለህ ብሎኝ ጽሁፉን ለማየት እየጠበኩ ነው። ከወደድኩት እሠራዋለሁ። ካልወደድኩት አልሠራውም። ስሙን የምናውቀው ደራሲ ነው? ደበበ እሸቱ፡ እኔም አላውቀውም። (ሳቅ) አንድ ጥሩ ድርሰት አለኝ ብሎኛል፤ በኩራት። እኔም የምኮራበት ደራሲ ነው። ድርሰቱን ያምጣውና እንተያያለን። ከአሁን በኋላ ከዚህ ሰው ጋር ሰርቼ በቃኝ የምትለው ሰው አለ? ደበበ እሸቱ፡እኔ ቴአትር አይበቃኝም። መዐዛ ወርቁ እግዜር ይስጣት 'ደርሶ መልስ' ላይ ከማከብረው ዓለማየሁ ታደሰ ጋር እንድገናኝ አድርጋኛለች። ገና ከእስር ቤት እንደወጣሁ 'ጋሽ ደበበ አብረን እንሥራ ብሎኝ' ከሰለሞን ቦጋለ ጋርም ሠርተናል። ከሌሎቹም ጋር ብሠራ ደስ ይለኛል። እና ከእንግዲህ በኋላ ከእከሌ ጋር ብሠራ የምለው ሰው የለም። ደበበ በጣምወደ መንግሥት እየተጠጋ ነው ብለው የሚተቹህ ሰዎች ገጥመውኛል። ደበበ እሸቱ፡ደግ አደረኩ! ለምን? ደበበ እሸቱ፡ ነፃነቴን የሰጠኝ [ጠቅላይ ሚንስትር] ዐቢይ ነው። ሌላ ማን ሰጠኝ? ዶ/ር ዐቢይ ነው በነፃነት የመናገር መብቴን የመለሰልኝ። ዶ/ር ዐቢይ ነው ቤተ መንግሥት ያስገባኝ። ዶ/ር ዐቢይ ነው ፕሮግራም ምራልኝ ያለኝ። ከመሸማቀቅና ማን አየኝ ከሚል መሳቀቅና መገላመጥ ያወጣኝ ዶ/ር ዐቢይ ነው። ስለዚህ ያደላሁት ወደ መንግሥት ሳይሆን ወደ ዶ/ር ዐቢይ ነው። ለእሱ ደግሞ መልሴ ደግ አደረኩ ነው። በርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በዚህ መልክ የምትደግፋቸው ከሆነ ስህተት ሲሰሩ ብትመለከት ለመናገር ድፍረቱ ይኖርሀል? ደበበ እሸቱ፡ መንገድ ፈልጌ እነግረዋለሁ። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እነግረዋለሁ እንጂ ከጀርባ አላማውም። ምክንያቱም በአንድ ቀን ሁሉንም ነገር መሥራት እንደማይችልና አንድ ሰው መሆኑን አውቃለሁ። በፊት ካሉት ሰዎች እሱ እያበላሸ ቢቀጥል ይሻለኛል። ሌላው ቢቀር ትንሽ የዲሞክራሲ ጭላንጭል አሳይቶኛል። እነዚያ 'ደበበ ከመንግሥት ጋር ገጥሟል' የሚሉ ከዚያኛው መንግሥት ጋር ገጥመው ይሆናል ስለዚህ ይናደዳሉ። የዶ/ር ዐቢይ ደጋፊ ሲያዩ አይናቸው ደም ይለብሳል።
news-55198052
https://www.bbc.com/amharic/news-55198052
ኮሮናቫይረስ ፡ ሩሲያ የኮቪድ-19 ክትባትን በመዲናዋ ሞስኮ መስጠት ጀመረች
በሩሲያ መዲና ሞስኮ የኮቪድ-19 ክትባት መስጠት ተጀመረ።
ሞስኮ የሚገኙ የሕክምና መስጫዎች ለበሽታው በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጀምሮ ክትባቱን እንደሚሰጡ ተገልጿል። ሩሲያ ባለፈው ነሐሴ ላይ ይፋ ያደረገችው ስፑትኒክ 5 የተባለው ክትባት፤ 95 በመቶ ውጤታማ እንደሆነና ጉልህ የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለው ተነግሯል። በእርግጥ ክትባቱ አሁንም ሰዎች ላይ እየተሞከረ ነው። የመጀመሪያውን ዙር ክትባቱን ለመውሰድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተመዝግበዋል። ሩሲያ ምን ያህል ክትባት ማምረት እንደምትችል ግልጽ ባይሆንም፤ አምራቾች እስከ ዓመቱ መገባደጃ ሁለት ሚሊዮን ጠብታ እንዲያዘጋጁ ይጠበቃል። ክትባቱ ለማን ይሰጣል? 13 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያን እንዳሉት፤ ክትባቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለጤና ባለሙያዎች እና ለትምህርት ቤት ሠራተኞች ይሰጣል። ተጨማሪ ክትባቶች ሲመረቱ ለተቀረው ማኅበረሰብ እንደሚዳረስ ከንቲባው ጠቁመዋል። ከላይ በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች የተሰማሩና እድሜያቸው ከ18 እስከ 60 የሆኑ ዜጎች በድረ ገጽ ተመዝግበዋል። በሞስኮ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የክትባቱን አገልግሎት የሚሠጡ 70 ማዕከሎች ተከፍተዋል። ክትባቱ የተሰጣቸው ባለፉት 30 ቀናት የመተንፈሻ አካል ህመም የገጠማቸው፣ የከፋ የጤና እክል ያለባቸው፣ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንደሚለዩ ተገልጿል። ሕዝቡ ምን አለ? ክትባቱን በተመለከት የሕዝቡ ስሜት የተደበላለቀ ነው። የከተማው ነዋሪ ኢጎር ኪቮቦኮቭ "የበሽታውን ስርጭት ሊቀንስ ስለሚችል ደስ ብሎኛል" ሲል ለሮይተርስ ተናግሯል። ሌላው ነዋሪ ሰርጌ ጊሻን ግን ክትባቱን ለመውሰድ አላሰብኩም ብሏል። "ሂደቱ ረዥም ጊዜ ነው የሚወስደው። ያለው ክትባት ደግሞ ጥቂት ነው። ሌላው ሰው ይከተብ። እኔ እንኳን እተርፋለሁ ብዬ አስባለሁ።" ሩሲያ ውስጥ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ2.3 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ሲሆኑ፤ 41,730 ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ሞተዋል። ሞስኮ ቫይረሱ በስፋት ከተሰራጨባቸው ከተሞች አንዷ ናት። በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ በቫይረሱ የሚያዙና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ይመዘገባሉ። በመላው ሩስያ የሚገኙ ሆስፒታሎች የሚያስተናግዱት ህሙማን ቁጥር ከአቅማቸው በላይ ሆኗል። ይሁን እንጂ ሩሲያ አገር አቀፍ የእንቅስቃሴ ገደብ እንደማትጥል አስታውቃለች። የሞስኮ ከንቲባ ግን ባለፈው ወር ለመጠጥ ቤቶች የመክፈቻና የመዝጊያ ሰዓት ገድበዋል። የከፍተኛ ትምህርት በርቀት እንዲሰጥና የስፖርት ክንውኖች እንዲቀነሱም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
54159837
https://www.bbc.com/amharic/54159837
ኢኮኖሚ ፡ የኢትዮጵያ የብር ኖት መቀየር የሚኖረው አንድምታ
ኢትዮጵያ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እናየ100 የገንዘብ ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች ይፋ አድርጋለች።
ከአዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች ውስጥም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜም የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶቹን ለመቀየር ሌላ ወጪ ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊዮን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታውቀዋል። አገሪቱ የገንዘብ ኖቶችን ለመቀየር በኢ-መደበኛ መልኩ ገንዘብ ከባንክ ውጭ በከፍተኛ ሁኔታ መንቀሳቀሱ፣ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚሉ ምክንያቶችን አስቀምጣለች። ከዚህ ቀደም አገሪቷ ከፋይናንስ ዘርፍ (ከባንክ) ውጭ ያለው ገንዘብ ከመደበኛው ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ በመሆኑም እንዴት ይሰብሰብ የሚሉ ጥያቄዎች የባንኮች ዋና ማዕከል ሆነውም ነበር። በኢ-መደበኛ ሁኔታ ያለውን የገንዘብ ፍሰት ወደ መደበኛ ለማምጣትም ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን በተለያየ ጊዜም የወጡ መመሪያዎችም ለዚህ ማመላከቻዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ከባንክ ውጭ ያለው ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ከዚህ ቀደም በፋይናንስ ዘርፉ የተሰራ ጥናት የሚያሳይ ሲሆን በባለፈው ዓመትም አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ እጥረት (ሊኩዊዲቲ) አጋጥሟት ነበር። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም ይህንንም ችግር ለመፍታት አንዳንድ ጊዜያዊ መፍትሄዎችን መውሰዱ የሚታወስ ነው። የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የዋጋ ግሽበት የለውጡ ዋነኛ መሰናክል ሆነው ቆይተዋል በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምጣኔ ሀብቱ መዳከም ምክንያት ያሉትን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት የገንዘብ ኖት ለውጥ ማድረጓም በከፍተኛ ሁኔታ ከዘርፉ ውጭ ያለውን ገንዘብ ወደ መደበኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ሂደት ለማምጣትም ይረዳታል በማለት የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ በበኩላቸው መንግሥት የገንዘብ ለውጥ ማድረግ ካስፈለገው ምክንያቶች መካከል ዋነኛው ከገንዘብ ጋር የተገናኙ ሕገ-ወጥ ዝውውሮችን ለመግታት እንደሆነ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው አስረድተዋል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ በብዛት በጥሬ ገንዘብ ግብይት የሚካሄድበት መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ይናገር ከባንኮች ውጭ ያለው ጥሬ ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። "አብዛኛው ኅብረተሰባችን ከባንክ ውጭ ነው ግብይት የሚያደርገው በዚህ ምክንያት ብዙ ጥሬ ገንዘብ ከባንክ ውጭ ይገኛል ማለት ነው። በዚህም የጥሬ ገንዘብ እጥረት ባንኮች ላይ ማጋጠም እድሉ ሰፊ ነው።ለ ገቢ አሰባሰብ አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል የሚል እምነት ነው ያለን፤ ለአጠቃቀም የተሻለ አገልግሎት ይሰጣል፤ የህትመት ወጪንም በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል" ብለዋል። ከባንክ ውጭ ያለው ጥሬ ገንዘብ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት አገራት ጭምር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። "ከባንክ ውጭ የሚገኝ ገንዘብ ደግሞ ለሕገ-ወጥ ተግባራት ሲውል ነው የሚታየው፤ በተለይ በኮንትሮባንድ [ሕገ-ወጥ ንግድ] የተሰማሩ ግለሰቦች ይጠቀሙበታል" ብለዋል። ዶ/ር ይናገር ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቦች ግብር ላለመክፈል ሲሉ ገንዘባቸውን ከባንክ ውጭ የማስቀመጥ ልማድም እየሰፋ መምጣቱን ጠቁመው አሁን ያለውን የገንዘብ ኖት መቀየር አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት አስረድተዋል። ከባንክ ውጭ የተጠራቀመ ገንዘብ ጥቅም የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላም በአውሮፕላን ጣቢያዎችና ድንበሮች እንዲሁም በባንኮች አካባቢ ከፍተኛ ቁጥጥርም ይደረጋል ተብሏል። የፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ ገንዝብ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ በሕገ ወጥ መንገድ የሚሰበሰብ ገንዘብ ካገኙ እንደሚወርሱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከባንኮች ውጭ ያለው ገንዘብ ወደ ባንኮች ሲመለስም የሂሳብ ደብተር ተከፍቶ ባንኮች ውስጥ እንዲቀመጥ ይደረጋል። ለመሆኑ የብር ኖትን መቀየር እንደ ኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንዴት ሊያስቆም ይችላል? የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባንክ ሥርዓት ውጭ የሚንቀሳቀስ ከ113 ቢሊየን ብር በላይ መኖሩን ይናገራሉ። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን የዋጋ ንረት ከፍተኛ በመሆኑና ባንክ ቤቶች ብር ለሚያስቀምጥ የሚሰጡት ወለድ ዝቅተኛ በመሆኑ ሰዎች ገንዘቤን በእጄ እይዛለሁ የሚል አስተሳሰብ መኖሩን እንደ አንድ ምክንያት ያነሳሉ። በሌላ በኩል በሙስናና በሌሎች ምክንያቶች "ተቋማትም ግለሰቦችም ሲዘርፉ ስለነበር ነው" ይላሉ። ለዚህ ንግግራቸውም ከለውጡ በኋላ የተከማቹ በርካታ ገንዘቦች በጆንያ እየታጨቁ እና በመኪና እየተጫኑ ሲዘዋወሩ መያዛቸውን እንደ ምሳሌም ይጠቅሳሉ። የገንዘብ ኖቶቹ ላይ ለውጥ መደረጉም ሰዎች ገንዘባቸውን ለመቀየር ባንክ በሚሄዱበት ጊዜ፤ በጤናማ የግብይት ሥርዓት ገንዘቡን ማግኘት አለማግኘታቸውን ለማረጋገጥ እድል ይሰጣል ብለዋል ባለሙያው። በመሆኑም እስካሁን የተሰሩ የሙስና ምንጮችን ለማወቅም ሆነ ከአሁን በኋላ የሚሰሩ ሙስናዎች ላይ ፍራቻ እንዲፈጥር ሊያደርግ እንደሚችልም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ረዳት ፐሮፌሰር ጉቱ ለገስ ደግሞ ከገንዘብ ጋር ተያይዞ ያሉ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የብር ኖቶች መቀየር አንዱ እንጂ፤ ብቸኛው መፍትሔ አለመሆኑን ያሰምሩበታል። ረዳት ፕሮፌሰር ጉቱ "አንድ ነገር ሲተዋወቅ ውጤታማ ለመሆን አለመሆኑ አንዱ ወሳኙ ነገር፤ ተቋማዊ አደረጃጃትና የመተግበር አቅም ነው። ይህ ካልሆነ ግን አዙሪት ነው የሚሆነው" ብለዋል። መንግሥት ገንዘቡን ከቀየረ በኋላ ሕገ-ወጥ ገንዘብ ይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የየራሳቸውን እርምጃ መውሰዳቸው እንደማይቀር የጠቆሙት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ መንግሥት ተቋማዊ አደረጃጀቱ ጠንካራ ሆኖ ይሄን ነገር ልብ ብሎ መከታተል እንዳለበት መክረዋል። አሁን የተወሰደው እርምጃ ቀደም ብለው የተሰሩ ሥራዎች ስላሉ ውጤታማ ይሆናል ተብሎ ይገመታልም ብለዋል። ነገር ግን "ቀድሞ የነበረው የውጭ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ ያለው ሙስናና ደካማ አስተዳደር ካልተስተካከለ ተመልሶ ያው ነው የሚሆነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አዲስ የ200 ብር ኖት ማስገባት ለምን ተፈለገ? በኢትዮጵያ በቅርብ አመታት ውስጥ የገንዘብ የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ያሽቆለቆለ ሲሆን ከዚህም አንፃር ባለ ሁለት መቶ ኖቶች ወደ ገበያው ውስጥ መግባት አስፈላጊ እንደሆነም የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ። ረዳት ፕሮፌሰር ጉቱ የዋጋ ንረቱ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በተለያየ ግብይት ሂደት ውስጥ የሚሳተፈው ኅብረተሰብ ብዙ ብር ለመያዝ እየተገደደ መሆኑን በመጥቀስ ያንን ሊያስቀርላቸው እንደሚችል ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ወደ ኤሌክትሮኒክስ የግብይት ሥርዓት እንዲገቡም እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። ኢኮኖሚው ሲያድግ ወደዚያ መግባቱ እንደማይቀር በመግለፅ። አቶ ዋሲሁን በበኩላቸው የገንዘብ ኖት ከፍ እያለ ሲመጣ ገንዘቦች መግዛት አቅማቸው መዳከሙን የሚያመላክት መሆኑን ይናገራሉ። በምሳሌ ሲያስረዱም "አሁን 5 ብር ዝቅተኛው ገንዘብ እየሆነ ነው። አንድ ብርና ሁለት ብር የሚገዛቸው ነገሮች እየጠፉ ነው። ሰዎች መቶ ብርም ይዘው በፊት የሚገዙትን ያህል እቃ መግዛት አይችሉም፤ በመሆኑም ሰዎች ብዙ የወረቀት ገንዘብ ይዘው ከሚሄድ ያድናቸዋል" ይላሉ። ነገር ግን ከ20 በመቶ በላይ የዋጋ ንረት በሚመዘገብበት ሁኔታና የ100 ብርና የ200 ብር ልዩነት ብዙም ባለመሆኑ መሆን የነበረት የ500 ወይም የ1000 ብር ኖት ወደገበያው መግባት እንደነበር አቶ ዋሲሁን ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የገንዘብ መቀየሩን ተከትሎ ምን ሊፈጠር ይችላል? መንግሥት አሮጌ የብር ኖቶቹን ለመቀየር የሦስት ወር የጊዜ ገደብ አስቀምጧል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው እንደሚሉት ከሆነ አዲሱ መገበያያ ገንዘብ ይፋ መደረጉን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ ባልተለመደ መልኩ የገንዘብ ዝውውር ሊስተዋል ይችላል። "ሰዎች አዳዲስ የሒሳብ ቁጥር እየከፈቱም ሊያስቀምጡ ይችላሉ። ጥሬ ገንዘቡን ወደ ባንክ ላለማስገባትም የንብረት ግዥ ሊጧጧፍ ይችላል። መኪና፣ ቤት መግዛት ሊኖር ይችላል" ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በሌላ በኩል በሙስና የተከማቸ አሊያም ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ገንዘብ በእጃቸው የያዙ ግለሰቦች፤ የሚመጣባቸውን ጥያቄን በመፍራት በዘመድ አዝማዶቻቸው ስም በርካታ የሒሳብ ቁጥሮችን ሊከፍቱ እንደሚችሉም አመላክተዋል።
news-52226198
https://www.bbc.com/amharic/news-52226198
ኮሮናቫይረስ፡ ድብደባ፣ ግድያ፣ ስለላ በአፍሪካ
ኮሮናቫይረስ መላው ዓለምን አስጨንቋል። መንግሥታት በረራ በማቆም፣ እንቅስቃሴ በመግታትም ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው።
የኡጋንዳ ፖሊሶች የጎዳና ቸርቻሪዎችን ደብድበዋል አፍሪካ ውስጥ እነዚህን እርምጃዎች የሚያስፈጽሙት ፖሊሶች ዜጎችን ሲዘልፉ፣ ሲደበድቡ ገፋ ሲልም ሲገድሉ ታይቷል። ይህ የጸጥታ ኃይሎች ድርጊት፤ ማኅበረሰቡን ከኮሮናቫይረስ ለመጠበቅ የሚደረገው ጥረት የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ወደመጋፋት እያመራ ይሆን? የሚል ጥያቄ አጭሯል። በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሺህ በልጧል። መንግሥታት ወረርሽኙን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እየደነገጉ፣ የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ እየሰለሉም ነው። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፤ እነዚህ እርምጃዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት መሆኑን ካቆመ በኋላም ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ይሰጋሉ። መንግሥታት የሰዓት እላፊ ገደብ መጣልና እንቅስቃሴ መግታት የሰዎችን ሕይወት ይታደጋል ይላሉ። ነገር ግን ተገቢ ያልሆነ ኃይል መጠቀምም የሰውን ሕይወት ይቀጥፋል። • ፋሲካና ረመዳን በኮሮናቫይረስ ጊዜ እንዴት ሊከበሩ ይሆን? • የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአምስት ወራት በመላው አገሪቱ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ የኬንያ ፖሊሶች በምሽት ሲጓዝ ያገኙትን ወጣት ሲያስቆሙ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለአምስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተደነገገው ትላንት ነበር። ነሐሴ ላይ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው አገራዊ ምርጫም ተራዝሟል። ሆኖም ግን ምርጫው እንዲራዘም ከመወሰኑ በፊት ከተቃዋሚዎች ጋር ውይይት መደረግ ነበረበት ሲሉ የተቹ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ነበሩ። የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያላግባብ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል የሚል ፍርሀት እንዳለው አስታውቋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በተመለከተ ከተቃዋሚዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። • "ደስ ብሎኛል፤ የ98 ዓመቷ እናቴ ከኮሮናቫይረስ ድናለች" • በሽታውን ለመግታት ከዚህም በላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተገለጸ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄው አቶ ጣሂር መሐመድ፤ አዋጁ ዝርዝር መረጃ የለውም ብለዋል። "ዜጎች ምን እንደሚፈቀድና ምን እንደተከለከለ የማወቅ መብት አላቸው" ሲሉም አስረድተዋል። የሚተላፉት ውሳኔዎች ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ያለሙ ናቸው ሲሉም አቶ ጣሂር ተችተዋል። ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጋለች ኬንያ ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ በቤቱ በረንዳ ላይ ይጫወት የነበረ የ13 ዓመት ታዳጊ 'በባረቀ' የፖሊስ ጥይት ሕይወቱ አልፏል። በፖሊስ ተደብድቦ የሞተ የሞተር ሳይክል ነጂን ጨምሮ ሦስት ሌሎች ሰዎችም ሕይወታቸውን ማጣታቸውም ተዘግቧል። ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ስለተፈጠረው ነገር ኬንያውያንን ይቅርታ ጠይቀው፤ ማኅበረሰቡ ከፖሊስ ጋር እንዲተባበር ጠይቀዋል። ኡጋንዳ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ 'ሂውማን ራይትስ ዋች' በኡጋንዳ ፖሊሶች አላስፈላጊ ኃይል እየተጠቀሙ ነው ሲል ወንጅሏል። ፖሊሶች አትክልት ቸርቻሪዎችን እና የታክሲ ሾፌሮችንም ደብድበዋል ተብሏል። በተጨማሪም ለቤት አልባ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የተዘጋጀ መጠለያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 23 ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏል። በተጨማሪም፤ እንቅስቃሴ መግታት በኡጋንዳ ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖ ዘገባ የሠሩ አስር ጋዜጠኞች በፖሊስ መደብደባቸውን የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው 'ሂውማን ራይትስ ኔትወርክ ፎር ጆርናሊስትስ' ለቢቢሲ ገልጿል። • የአፍሪካ መሪዎች ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖምን ከትራምፕ እየተከላከሉ ነው • ኮሮናቫይረስን ለመቆጣጠር የፈጠራ ሥራዎቹን ያበረከተው ወጣት የደቡብ አፍሪካ ፖሊሶች የፕላስቲክ ጥይት ተኩሰዋል መንግሥት፤ ቤት የሌላቸው ሰዎችን፣ የጎዳና ቸርቻሪዎችን እንዲሁም ሌሎችም ተጋላጭ የማኅበረሰቡ አባላትን መጠበቅ እንደሚገባው 'ሂውማን ራይትስ ዋች' ተናግሯል። ባለፈው ማክሰኞ አስር የኡጋንዳ ፖሊሶች 38 ሴቶችን በለአንጋ በመግረፍና ጭቃ ውስጥ እንዲዋኙ በማስገደድ ተከሰዋል። ደቡብ አፍሪካ ደቡብ አፍሪካ ከመላው አህጉሪቱ በበለጠ በኮሮናቫይረስ የተያዙ በርካታ ሰዎች ያሉባት አገር ናት። በአገሪቱ እንቅስቃሴ እንዲገደብ ከተወሰነ በኋላ ቢያንስ ስምንት ሰዎች እንደተገደሉ የደቡብ አፍሪካው ገለልተኛ መርማሪ ቡድን 'ኢንዲፔንደንት ፖሊስ ኢንቨስትጌቲቭ ዳይሬክቶሬት' አስታውቋል። ኮሮናቫይረስ በተለይም ጠንካራ የጤና ሥርዓት ለሌላት አፍሪካ እጅግ አስጊ ነው። ሆኖም ግን ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች 'ፍሪደም ሀውስ' የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ሰብዓዊ መብትን እንዳይጋፉ እሰጋለሁ ብሏል። • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ ባንክ እያዘጋጀሁ ነው አለ • 'ባሌ ፀጉሬን ይዞ ከግድግዳ ጋር ያጋጨኛል . . . ' ጋና የጋና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፤ ለአገሪቱ ፕሬዘዳንት እንቅስቃሴን መግታት የሚያስችለው አዲስ ሕግ እንደሚያሰጋቸው ተናግረዋል። ተቃዋሚ ፖለቲከኛው ራስ ሙባረክ "ፕሬዘዳንቱ ሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ ድንጋጌ ተጠቅመው፤ በየሦስት ወሩ ፓርላማ እየመጡ፤ የድንጋጌውን አስፈላጊነት ለሕዝብ እንደራሴዎች እንዲያቀርቡ ነበር የምንፈልገው" ብለዋል። አዲሱ ሕግ ግን ፕሬዝዳንቱ የሰዎችን እንቅስቃሴ እንዳሻቸው እንዲገድቡ ይፈቅዳል። የአገሪቱ የፍትሕ ሚንስትር በበኩላቸው ሕጉ የዜጎችን ጤና እንደሚያስጠብቅ ይገልጻሉ። ማላዊ የማላዊ ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሪካ፤ ኮሮናቫይረስን "በፖለቲካው የሠሯቸውን ስህተቶች ለማረም" እየተጠቀሙበት ነው የሚል ትችት ቀርቦባቸዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች መሪው ጊፍት ትራፔንስ እንደሚሉት፤ "መንግሥት ኮሮናቫይረስን ሥልጣኑን ለማራዘም ሊጠቀምበት ይፈልጋል።" የአገሪቱ የመረጃ ሚንስትር ማርክ ቦቶሚኒ ግን ክሱን አጣጥለዋል። ከወራት በኋላ ምርጫ የሚጠብቃቸው ፕሬዝዳንቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግገዋል። ታንዛንያ ሦስት የታንዛንያ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መንግሥት ኮሮናቫይስን ለመከላከለ እየወሰደ ስላለው እርምጃ "ሐሰተኛና የተሳሳተ መረጃ አስተላልፋችኋል" በሚል ተቀጥተዋል። ስለቅጣቱ ዝርዝር መረጃ በመንግሥት ባይሰጥም፤ ጣቢያዎቹ ፕሬዘዳንት ጆን ማጉፉሊን ስለተቹ እንደተቀጡ እየተነገረ ነው። ፕሬዝዳንቱ "ኮሮናቫይረስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አይኖርም" ብለው ከተናገሩ በኋላ ቤተ ክርስቲያኖች አይዘጉ ማለታቸው ይታወሳል። የስልክ ስለላ ሌላው የመብት ተሟጋቾች ስጋት መንግሥት ዜጎችን የመሰለሉ ጉዳይ ነው። የኬንያ መንግሥት ኮሮናቫይረስ አለባቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎችን በስልካቸው እየተከታተለ ነው። ቃል አቀባዩ ሳይረስ ኦጉና ክትትሉ ለ14 ቀን በለይቶ ማቆያ መሆን ያለባቸውን ሰዎች ለመጠበቅ የሚደረግ ነው ብለዋል። ጠበቃና የግል መረጃ ጥበቃ ባለሙያ ሙጋምቢ ላይቡታ በበኩላቸው፤ ዜጎች ክትትል እየተደረገባቸው ስለመሆኑ መረጃ ሊሰጣቸው ይገባል ይላሉ። ደቡብ አፍሪካ ከቴሌኮም ድርጅቶች ጋር በመተባበር ኮሮናቫይረስ ካለባቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ዜጎች የት እንደሄዱ ለማወቅ መረጃ እየሰበሰበሰች ነው። በተባበሩት መንግሥታት የነፃነትና መብት ወኪል ዴቪድ ካይ እንደሚሉት፤ መሰል የጤና ቀውሶች ሲከሰቱ፤ መንግሥታት የተለያዩ የአደጋ ጊዜ እርምጃዎች መውሰዳቸው የተለመደ ነው። "ከህክምና ጋር የተያያዘ ስለላ (ሜዲካል ሰርቬለንስ) እንደሚካሄድ እርግጥ ነው" ይላሉ። ሆኖም ግን እርምጃዎቹ ሕግ ወጥ እንዳይሆኑ ቁጥጥር ሊደረግ እንደሚገባ ያስረዳሉ። ኮሮናቫይረስ ስጋት መሆኑ ሲቆም፤ እርምጃዎቹም መቆም እንዳለባቸውም ይገልጻሉ። በዚህ ረገድ፤ ደቡብ አፍሪካ አንድ የቀድሞ ዳኛ መረጃ የመሰብሰብ ሂደቱን እንዲከታተሉና ሊስተካከል ይገባዋል የሚሉትን እንዲጠቁሙ መሾሟን የመብት ተሟጋቾች አወድሰዋል።
news-47932762
https://www.bbc.com/amharic/news-47932762
የምክር ቤቱ ስብሰባ ኢህአዴግን ወዴት ይመራው ይሆን?
የገዢው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ከጠቅላላው ጉባኤ ቀጥሎ ወሳኝ የሆነውን መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን ከዛሬ ጀምሮ በማካሄድ ባለፉት ወራት ስለተከናወኑ ተግባራትና በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ግምገማ በማድረግ ውሳኔዎችን እንደሚሰጥ ተነግሯል።
ይህ የምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን መጥተው በድርጅቱ የተወሰኑ እርምጃዎችን በመውሰድ ድፍን አንድ አመት ከሞላቸው በኋላ የሚደርግ ከመሆኑ በተጨማሪ ሃገሪቱ ውስጥ የተለያዩ አሳሳቢ ችግሮች እየተከሰቱ ባሉበት ወቅት ነው። በተጨማሪም ቀደም ሲል የገዢው ግንባር መስራችና ዋነኛ አካል የነበረው ህወሓት በማዕከላዊው መንግሥት ውስጥ የነበረው ወሳኝነትና ተሳትፎ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመጡ በኋላ እየቀነሰና ከግንባሩ ጋር ያለው ትስስር ላልቶ ባለበት ጊዜ የሚካሄድ መሆኑ ምናልባትም የጥምረቱን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን ሊሆን ይችላል። • ኢህአዴግ እዋሃዳለሁ ሲል የምሩን ነው? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር በመሆን የሃገሪቱን የመሪነት መንበር ከያዙ በኋላ የህወሓት ተሳትፎ በእጅጉ የቀነሰ ሲመስል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲ ኦህዴድ (የአሁኑ ኦዲፒ) ከብአዴን (ከአሁኑ አዴፓ) ጋር የጠነከራ ጉድኝት አጠናክረዋል። የደቡቡ ደኢህዴንም የሁለቱን ያህል ባይሆንም ከጥምረቱ ጋር ያለው ዝምድና በነበረበት የዘለቀ ነበር። ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከህወሓት እንደ ድርጅት የሚወጡ መግለጫዎችና አመራሩ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚናገሯቸው ነገሮች በገዢው ፓርቲ ውስጥ ከዚህ በፊት የነበረው ጥብቅ ትስስርና ማዕከላዊነት እየላላ አንዳንድ ጊዜም የሚቃረኑ ተጻራሪ ነገሮች ሲቀርቡ ተስተውሏል። በተለይ ዛሬ ከሚጀመረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ቀደም ብሎ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ካደረገው ስብሰባ ተከትሎ የወጣው የድርጅቱ መግለጫ ማዕከላዊው መንግሥት የሚጠበቅበትን እንዳልተወጣና የድርጅቱ የተሃድሶ ውሳኔ ከታሰበለት አቅጣጫ መውጣቱን በመጥቀስ ጠንካራ ትችትን ሰንዝሯል። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ በሃገሪቱ እየተከሰተ ያለው ችግር እየተባባሰ መሆኑንና ወደማያባራ አደጋ የሚያስገቡ ችግሮች በመጠንም በስፋትም እየጨመሩ መሆናቸውን አመልክቶ ባለፉት ዓመታት የተገኙ ለውጦችን ስጋት ላይ መውደቃቸውን አመልክቷል። የኢህአዴግ በጥልቀት የመታደስ እርምጃ "ተኮላሸቷል" ብሎ የሚያምነው ህወሓት በሃገሪቱ "የሰላም እጦት መስፋፋቱን፣ መረጋጋት እየጠፋ ሁከትና ግርግሮች በስፋት እየጨመረ መምጣቱ፣ ሕግና ሥርዓት ማስከበር እንዳልተቻለ. . ." በመጥቀስ ግምገማ ማድረጉን ገልጿል። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጨምሮም ለዚህ እንደዋና ምክንያት ያስቀመጠው አመራሩ ከኢህአዴግ መሰረታዊ እምነቶች ማፈንገጡና "ቅጥ ባጣ ደባል አመለካከት" ተበርዟል በማለት የሕገ መንግሥት ጥሰት እየፈፀመ እንዲሁም የፌዴራል ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል አስተሳሰብና ድርጊት መንሰራፋቱን በመጥቀስ ያለውን የድርጅቱን አመራር ከሷል። ይህ ከኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በፊት የወጣው የህወሓት መረር ያለ መግለጫ የድርጅቱን ስብሰባ ጠንከር ያሉ ጉዳዮች የሚነሱበትና የአባል ድርጅቶቹ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚወስን ውጤትን ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል። ነገር ግን ከድርጅቱ የቆየ ባሕል አንጻር በውስጥ የሚደረጉ ንግግሮች ከውጪ እንደሚታዩት የጎላ ለውጥ በሚያመጣ ሁኔታ ሳይሆን የእርስ በርስ ግምገማ በሚመስል ሁኔታ ውይይት ተደርጎባቸው በእዚያው ተዳፍነው ይቀራሉ የሚሉ በርካታ ሰዎች አሉ። የቀድሞው የአዴፓ አባል አቶ ቹቹ አለባቸው እንደሚሉት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በስብሰባቸው ላይ ብዙ ነገሮች አንስተው "እስከ ጥጋቸው" ድረስ እንደሚገማገሙ ነገር ግን አንዳችም ነገር ወደ ውጪ አይወጣም። የህወሓትና ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ለድምጺ ወያኔ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ግን ድርጅቱን የገጠሙት ፈተናዎች ከበድ ያሉ በመሆናቸው ፊት ለፊት ያሉ ችግሮችን ከመነጋገር ውጪ ምንም አማራጭ እንደሌለ የድርጅታቸው እምነት መሆኑን አመልክተዋል። • አምስት ጉዳዮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲነሱ የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች ቀደም ብሎ በመግለጫው ላይ ይፋ ያደረገው ህወሓት ብቻ ሲሆን በዋናነት የእርሱ አጀንዳ የውይይት መድረኩን ይይዘዋል ተብሎ ይታመናል። ጉዳዮቹም ያለውን አመራርና የድርጅቱን ቀጣይነት የሚመለከቱ በመሆናቸው ውይይቱ ከዚህ በፊት ከነበሩት አንጻር ጠንከር ያለ ሊሆን ይችላል። የድርጅቱን የወደፊት ዕጣን በተመለከተ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ የተነሳው አባል ድርጅቶችን በማዋሃድ ኢህአዴግን አንድ ወጥ ፓርቲ የማድረጉ ፍላጎት ክፉኛ በህወሓት ከተብጠለጠሉት ጉዳዮች አንዱ ነው። መግለጫው ጉዳዩ የተነሳው "ኢህአዴግ ጤናማ በነበረበት ወቅት" እንደሆነ በመግለጽ ችግሮች እንዳሉ አመልክቷል። "ጉባኤው ከፍተኛ ፍትጊያ ይኖረዋል" የሚሉት አቶ ቹቹ፤ በተለይ ወደ ውህደት የመሄዱ ጉዳይ ከፍተኛ የሃሳብ ፍጭት እንደሚያስተናግድ ይህም ከህወሓት በኩል እንደሚሆን ያምናሉ። ምክንያታቸውንም ሲያስቀምጡ "ህወሓት እያለ ያለው ከአንድነት በፊት አንድ ሊያደርጉን የሚገቡት የመርህ ጉዳዮች ላይ እንስማማ ነው። ከዚህ አንጻር የፓርቲዎቹ ጉልበት እያበጠ የኢህአዴግ አቅም እየተዳከመ ስለመጣ ውህደቱ እውን ይሆናል ብዬ አላምንም፤ ከሆነም ለይስሙላ እንጂ ትርጉም አይኖረውም" ይላሉ። ይህንን ሃሳብ የሚያራምዱት ኦዲፒ፣ አዴፓ እና ደኢህዴንም ቢሆኑ በየክልሎቻቸው የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች ድርጅቱን በማዋሃድ ሊወጡት ያሰቡ እንደሚመስላቸው የሚናገሩት አቶ ቹቹ ሦስቱ ከደገፉት ወደፊት የመሄድ ዕድል እንዳለው ይገምታሉ። "ኦዴፓ በክልሉ በኦነግ ና በሌሎች ፖለቲከኞች የበላይነት እየተወሰደበት ስለሆነ በመጣበት ለመሄድ ስለሚቸገር ውህደቱን ተጠቅሞ በመድረኩ ላይ አስፈላጊ ሆኖ መቀጠል ይፈልጋል፤ ደኢህዴን በክልሉ በሚነሱ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች የተነሳ እየተፍረከረከ ከማንም በላይ ውህደቱን ይፈልገዋል። አዴፓ መንታ መንገድ ላይ ይቆማል፤ ምክንያቱም ውህደቱን ይፈልገዋል ነገር ግን በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ ብሄርተኛ ድርጅት ስለመጣበት ለመምረጥ ይቸገራል። እንደዚያም ሆኖ መምረጥ ካለበት ውህደቱን ይመርጣል" ሲሉ አቶ ቹቹ ይተነትናሉ። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የሀዋሳውን ጉባኤ ይታደማሉ? አሁን አሁን ፓርቲዎቹ ባሉበት ሁኔታ ውህደት ይፈጸማል የሚል ግምት የለኝም የሚሉት የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉት አቶ ገረሱ ቱፋ ናቸው። ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ "መጀመሪያ በውስጣቸው ያለው አብሮ የመቀጠልን ችግር መፍታት አለባቸው። አብረው ከቀጠሉ ምን አሻሽለው ነው የሚቀጥሉት? አጋር ተብለው ሲጠሩ የነበሩት ድርጅቶችስ እንዴት ነው የሚሆኑት?" የሚለውን ወስነው ለህዝብ ግልጽ ማድረግ እንዳለባቸው ያምናሉ። የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ህወሓት እየተፈጠሩ ላሉ ችግሮች ያለውን አመራር ተጠያቂ ነው ማለቱ እንደ ክርክር ሊቀርብ የሚችል ቢሆንም አሁን ያለው አመራር ሲመረጥ ህወሓቶችም እንደነበሩ ይጠቅሳሉ። ስለዚህ የኢህአዴግ ውድቀት የህወሓትም ውድቀት ነው ይላሉ። እንደ አቶ ሙሉጌታ "ፓርቲዎቹ አሁን የያዙት አንዱ አንዱን መክሰስና መወንጀል ነው። እንደ ኢህአዴግ አንድ ሆነን በአንድ መመሪያ ለመገዛት በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት ቃል የምንገባበት ውሳኔ ማስተላለፍ አለብን የሚሉ አይደሉም። ሌላው ቀርቶ በርዕዮተ ዓለም እንኳን ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው።" አክለውም ያላቸውን ልዩነቶች በአንድ ስብሰባ አስታርቀው አንድ የሚያደርጋቸው ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ብለው እንደማይጠብቁና "እንደዚያ ብሎ ማሰብ ተአምር እንደመጠበቅ ነው" ይላሉ። አቶ ቹቹ አለባቸውም ከስብሰባው ብዙ አዲስ ነገር ይመጣል ብለው አይጠብቁም። "በውህደቱ በኩል ግን ምናልባት አገሪቱ አስፈሪ ደረጃ ላይ እየደረሰች ስለሆነ፤ ቢስማሙም ባይስማሙም ወደ አንድነት የመምጣቱን ጉዳይ ሊያጣጥሙት ይችላሉ። ይህ የሆነው ደግሞ የብሄር ፖለቲካው ጫፍ ላይ በመድረሱ ነው የሚል ድምዳሜ ስላለ በዚህ ላይ ጠንከር ያለ አቋም ይወስዳሉ" በማለት በድምጽ ብልጫ ውሳኔ ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ ይገምታሉ። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በርካታ አወንታዊ ለውጦች እንደመጡ የሚናገሩት አቶ ቹቹ "ኢህአዴግ ግን ተዳክሟል" ይላሉ። በለውጡ ሂደት የማዕከላዊ መንግሥት ሕግ የማስከበር አቅም መዳከም አመራሩ ወደሚፈለገው አቅጣጫ እንዳይሄድ እንዳገደው ጠቅሰው መፈናቀሎች፣ በአዲስ አበባ ላይ የተወሰደው አቋም፣ ሹመት አስጣጦች ተደማምረው "ከህወሓት የባሰ እንጅ የተሻለ አልመጣም ወደሚል ተስፋ የመቁረጥ አዝማሚያ ህዝቡን ወሰዶታል" ይላሉ አቶ ቹቹ። • በአዲስ አበባ ሊፈጸም የነበረ የሽብር ጥቃት መክሸፉ ተነገረ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከሚያካሂደው ስብሰባ ሃገርን ወደ ጤነኛና ወደ ተረጋጋ መንገድ ሊወስድ የሚችል የመፍትሄ ሀሳብ አልጠብቅም ብለዋል አቶ ቹቹ አለባቸው። ምክንያታቸውንም "አራት ድርጅቶች እንደ ድርጅት እና እንደ ግለሰብ በመሃከላቸው ያለው ግንኙነት ጤነኛ አይደለም። እየተወያዩ ሳይሆን አንዱ አንዱን ሲያወግዝና ሲከስ ነው የቆዩት። በዚህም ሳቢያ የድርጅቶቹ መሪዎች ተገናኝተው ሲወያዩ በተቻለ መጠን አንዱ ሌላኛውን እየወቀሰ የራሱን የፖለቲካና የበላይነት ለማረጋገጥ የሚጥሩ ነው የሚመስለኝ።" ሲሉ ያስቀምጣሉ። ፖለቲከኞች ዋና አላማቸው ስልጣን ነው የሚሉት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ "ከዚህ ቀውስ ምን አተርፋለሁ? የሚለው ይመስለኛል የመጀመሪያው እሳቤያቸው" ይላሉ። በዚህ ምክንያት አሁን ያለው ከባድ አገራዊ ችግር ከባድ ፈተና የደቀነ ቢሆንም ለፖለቲከኞች ግን ችግሩ አልታያቸውም ይላሉ። "በአንድ ስብሰባ ተገናኝተው መሰረታዊውን የአገራችን ችግር ፈትሸው፤ የራሳቸውን የስልጣን ፍላጎት ወደ ጎን በመተው የአገር ፍላጎት አስቀድመው ሊያረጋጋ የሚችል ውሳኔ ያሳልፋሉ ብዬ አላስብም" ይላሉ አቶ ሙሉጌታ። ባለፈው አንድ ዓመት በርካታ አዎንታዊ እርምጃዎች ቢታዩም ፈታኝ ሁኔታዎችም እንዳሉ የሚያስታውሱት አቶ ገረሱ ቱፋ አሁን በሚያደርጉት የምክር ቤት ጉባኤም "ድርጅቶቹ በውስጣቸው ያለውን ችግር ፈትተው፤ ለወደፊቱም ግልፅ የሆነ ራዕይ በማስቀመጥ አገሪቷ አሁን ካለችበት አሳሳቢ ሁኔታ ወዴት እንደሚወስዱ፣ እየተነሱ ያሉ ግጭቶች እንዴት እንደሚፈቱ ወስነው ይወጣሉ" ብለው እንደማያስቡ አቶ ገረሱ ይናገራሉ። በርካቶች ከገዢው ኢህአዴግ ውስጥ ተለይቶ ለመውጣት ፍላጎት እንደማይኖር ቢያምኑም፤ ምናልባት የመለያየት ነገር ቢከሰት አሳሳቢ ሁኔታ እንደሚፈጠር አቶ ገረሱ ይናገራሉ። መለያየቱ ከመጣ "አገሩን በማስተዳደር ላይ ችግር ይገጥማቸዋል። ግጭቶች በየቦታው ይከፈታሉ። ይህ ሁኔታ ለተቃዋሚዎች አማራጭ ሆነው ሊመጡ የሚያስችላቸው ቢሆንም ዝግጅት እያደረጉ አይደሉም። እስካሁንም ምን አይነት አማራጭ እንደሚያመጡ ያሳዩበት ሁኔታ የለም። በዚህ ምክንያት በቂ ሚና ይጫወታሉ የሚል እምነት የለኝም" ሲሉ አስረድተዋል።
news-56506562
https://www.bbc.com/amharic/news-56506562
ኢትዮ-ኤርትራ፡ ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት ተስማማች
ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ያስገባቻቸውን ወታደሮቿን ለማስወጣት ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።
ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ሲሸኙ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ፣ አርብ ጠዋት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሐሙስ ዕለት አሥመራ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባደረጉት ውይይት ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማማታለች። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የድንበር አካባቢዎቹን ተረክቦ ጥበቃውን ወዲያውኑ እንደሚጀምር ሁለቱ መሪዎች ከስምምነት ደርሰዋል። በሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ተፈጽሞ ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ የህወሓት ኃይሎች ወደ አሥመራ ሮኬቶችን መተኮሳቸው የኤርትራ መንግሥት ተጨማሪ ጥቃቶችን ለማስቆምና ብሔራዊ ደኅንነቱን ለማስከበር ድንበር መሻገሩ ተገልጿል። የኤርትራ ሠራዊት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት በግጭቱ ውስጥ እየተሳተፈ እንደሆነ የተለያዩ ሪፖርቶች ቢገልጹም እስካሁን ድረስ ከኤርትራ መንግሥት በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም። መግለጫው በተጨማሪም ሁለቱ አገራት በመተማመንና በመልካም ጉርብትና ላይ በተመሰረተ መንፈስ የጀመሩትን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ምጣኔ ሃብታዊ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ ባለው ሕዝብና ከድንበር ባሻገር ኤርትራ ውስጥ በሚገኘው ሕዝብ መካከል መተማመንን መሰረተ ባደረገው መልኩ ግንኙነቱ እንዲሻሻሻል ማድረግ አስፈላጊ ነው ብሏል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በኤርትራ ያደረጉት ጉብኝት መጠናቀቅን በማስመለክት የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚንስቴር መግለጫ አውጥቷል። ሚንስቴሩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሥመራ ቆይታ ወቅት መሪዎቹ በአገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይና በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ባለፉት 5 ወራት "የተሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን በጥልቀት ገምግመዋል" ብሏል። በቀጣይነትም ሁለቱ መሪዎች አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው ለመመክር መስማማታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ ከተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ጋር ተያይዞ የኤርትራ መንግሥትና ሕዝብ ሠራዊታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በገባበት ጊዜ ላደረገለት ድጋፍ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ ሲያመሰግኑ ቆይተዋል። ማክሰኞ ዕለት ከአገሪቱ ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስና ማብራሪያ ወቅት ይህንኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ጥቅምት መጨረሻ ላይ የህወሓት ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ የኤርትራ ሠራዊት በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ እንደሆነ በተለያዩ ወገኖች ሲገለጽ ቆይቷል። ነገር ግን ሁለቱ አገራት የኤርትራን ሚና ሲያስተባብሉ ቆይተው ከቀናት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በድንበር አካባቢ ባሉ ቦታዎች ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ሠራዊት ከጀርባው ጥቃት እየተፈጸመበት የድንበር አካባቢውን መጠበቅ አስቸጋሪ ስለሆነበት የኤርትራ ጦር ድንበር አልፎ መግባቱን በማብራሪያቸው ላይ ተናግረዋል። አክለውም ሠራዊቱ የህወሓት ኃይሎችን ለመዋጋት ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች በመንቀሳቀሱ ክፍተት እንደተፈጠረና የኤርትራ መንግሥትም በዚህ ክፍተት ጥቃት እንዳይፈጸምበት በመስጋቱ ወደ ስፍራዎቹ መግባቱን ገልጸዋል። ቢሆንም ግን የኢትዮጵያ ሠራዊት ሌላውን ተልዕኮ ሲያጠናቅቅና አካባቢዎቹን መቆጣጠር ሲችል የኤርትራ ኃይሎች ከስፍራው እንደሚወጡ ተናግረው ነበር። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾችና ድርጅቶች በተደጋጋሚ ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ክልል ውስጥ ከድንበር አካባቢዎች ባሻገር በሚገኙ ስፍራዎች ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ግድያና ዘረፋዎችን መፈጸሙ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን ኤርትራ ግን ይህንን ክስ ውድቅ አድርጋዋለች። የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ውስጥ ተፈጸሙ ከተባሉ ግድያዎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ አሜሪካንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ አገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሠራዊቱ ከክልሉ እንዲወጣ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው የሚያደርሱትን ጥፋቶች መንግሥታቸው ፈጽሞ እንደማይቀበለው አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ሠራዊት መቀለን ተቆጣጥሮ የህወሓት አመራሮችን ከሥልጣናቸው ከማስወገዱ በፊት የህወሓት ኃይሎች በአሥመራና በሌሎች የኤርትራ ከተሞች ላይ የሮኬት ጥቃቶች ማድረሳቸውን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም በከተሞቹ ነዋሪዎችና በዲፕሎማቶች ቢረጋገጥም በወቅቱ ከኤርትራ ባለሥልጣናት በኩል የተሰጠ ምላሽ አልነበረም። በትግይ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለተኛ ጉዞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሐሙስ ከሰዓት በኋላ ወደ አሥመራ ተጉዘው በኤርትራ ወታደሮች መውጣትና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ አርብ ረፋድ ላይ ወደ አዲስ አበባ የተመለሱበት ይህ ጉብኝት፤ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ በኋላ የተደረገ ሁለተኛው ጉዟቸው ነው። የመጀመሪያ ግጭቱ በተጀመረበት ወቅት ጥቃት ተሰንዝሮበት ወደ ኤርትራ የተሻገረውን የኢትዮጵያን ሠራዊት ለመጎብኘትና መልሶ ለማደራጀት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጦር ጄነራሎቻቸው ጋር ወደ ኤርትራ የተጓዙበት ነበረ። ይህ ይፋዊ ያልበረ ጉዞ በወቅቱ ያልተነገረ ሲሆን የፌደራሉ ሠራዊት ከሦስት ሳምንታት ዘመቻ በኋላ የክልሉን ዋና ከተማ ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአገሪቱ ምክር ቤት ስለግጭቱ አጠቃላይ ሁኔታ ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ መግለጻቸው ይታወሳል። የአሁኑ ጉብኝት ግን የኤርትራ ስም በተደጋጋሚ የተነሳበት ትግራይ ውስጥ የተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ከተከሰተ በኋላ የተደረገ ይፋዊ ጉዞ ነው። የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና አብሯቸው የተጓዘው ልዑክ አሥመራ ሲደርስ የአገሪቱ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ኤርትራ ያመሩት ከመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀንዓ ያደታ እንዲሁም ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ጋር መሆኑ ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እና በቀጠናው ልማት ዙሪያ እንደሚነጋገሩ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገልጸዋል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሁለት አስርት ዓመታት የቆየውን ፍጥጫቸውን ፈትተው ሠላም ካወረዱ በኋላ የሁለቱ አገራት መሪዎች ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ጉብኝቶችን አድርገዋል። በትግራይ ውስጥ የተከሰተው ግጭት ከመቀስቀሱ ጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ የመጨረሻውን ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሲሆኑ በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል የተለያዩ ቦታዎችን ጎብኝተው እንደነበር ይታወሳል። በትግራይ ውስጥ ጥቅምት መጨረሻ ላይ በትግራይ ውስጥ በተከሰተው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ህይወት ማለፉ ሲነገር፤ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ሸሽተዋል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት ደግሞ ግጭቱን በመሸሽ ተፈናቅለው በክልሉ ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።
news-55541614
https://www.bbc.com/amharic/news-55541614
የአሜሪካ ምርጫ 2020፡ የጆርጂያ ግዛት ምርጫ ለምን አሜሪካውያንን አስጨነቀ?
በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከየግዛቱ እኩል 2 እንደራሴዎች የሚሞሉት የመቶ ወኪሎች ሸንጎ ነው። ይህ ምክር ቤት የፕሬዝዳንቱ ልጓም ነው ማለት ይቻላል። ባለ ትልቅ ሥልጣን ነው። ፕሬዝዳንቱ አገሪቱን ባሻቸው አቅጣጫ እንዳይጋልቧት ያደርጋል።
ትራምፕ በምርጫው ዋዜማ ለዕጩዎቻቸው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሃምሳዎቹ የአሜሪካ ግዛቶች እያንዳንዳቸው ሁለት ወኪሎችን አስመርጠው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱን ይሞሉታል። ድምሩ ድፍን 100 ይመጣል። ለታችኛው ምክር ቤት ግን የግዛቶች ውክልና በሕዝብ ቁጥር ነው። በአሁኑ ጊዜ 50ዎቹ እንደራሴዎች የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ናቸው። 48ቱ ደግሞ የዲሞክራት ፓርቲ አባላት ናቸው። ሁለቱ ገለልተኛ ነን የሚሉ እንደራሴዎች ሲሆኑ አንገስ ኪንግ ከሜይን ግዛት እና በርኒ ሳንደርስ ከቬርሞንት ግዛት የተወከሉ ናቸው። የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የሚያጸድቀው ቁልፍ ጉዳይ ሲኖር ብዙዉን ጊዜ ሁለቱ ገለልተኛ የሸንጎው አባላት ከዲሞክራቶች ጋር ይወግኑና ድምጽ ሲሰጥ 50 ለ 50 እኩል ይሆናል። ፍጥጫ! በዚህ ጊዜ ወሳኙ የመለያ ድምጽ ከየት ነው የሚመጣው? ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ማይክ ፔንስ። በሕግ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ሰብሳቢ ነው። ስለዚህ የፔንስ ድምጽ ቁልፍ ሚና የሚኖረው ለዚህ ነው። ከ15 ቀናት በኋላ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስን ካምላ ሐሪስ ትታካቸዋለች። የካምላ ድምጽ እጅግ ቁልፍ እንዲሆን ከጆርጂያ ሁለት ወኪሎች ሸንጎውን መቀላቀል አለባቸው። ቢያንስ እኩሌታዎቹ ዲሞክራቶች እንዲሆኑ። የዲሞክራቶች የበላይነት በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ውስጥ እንዳይኖር ለማድረግ ዲሞክራቶች ሁለት ወኪሎችን እዚህ ሸንጎ ውስጥ ማስገባት ስላለባቸው ነው አሁን ጭንቅ የተፈጠረው። ይህ ዛሬ እየተደረገ ያለው የጆርጂያ ምርጫ ለዲሞክራቶችና ለሪፐብሊካን ፓርቲዎች የሞት ሽረት ትግል የሆነውም ለዚሁ ነው። የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ወሳኝ ፖሊሲዎችን ለማጸደቅ፣ የሕግ ማዕቀፎችን በድምጽ ለማሳለፍ፣ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ሹመቶችን ለማጸደቅ፣ ፕሬዝዳንቱን አስፈላጊ ሲሆን ለመክከሰስ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት ለማጽደቅ ወሳኙ ይህ የላዕላዩ ሸንጎ ነው። ባይደን ለፓርቲያቸው ዕጩዎች ሲቀሰቅሱ ሪፐብሊካኖች ይህን ሸንጎ ከ2014 ጀምሮ እንደተቆጣጠሩት ነው ያሉት። ልክ ዲሞክራቶች ታችኛውን ምክር ቤት እንደተቆጣጠሩት ሁሉ ላይኛው ምክር ቤት የሪፐብሊካኖች መፈንጫ አዳራሽ ሆኖ ነው የቆየው። ይህ ሁኔታ ቢቀየር ዲሞክራቶች፣ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት፣ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤትና ነጩን ቤተመንግሥት የግላቸው አደረጉት እንደማለት ነው። ይህ ጆ ባይደንን እጅግ ጉልበተኛው ፕሬዝዳንት ሊያደርጋቸው ይችላል። ጆ ባይደን ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ሕይወታቸው ቀላል ይሆንላቸዋል። ነገሩን ገልብጠን ብናስበው ደግሞ ሪፐብሊካኖች የላዕላይ ምክር ቤቱን ብልጫ ይዘው፣ የአብላጫ መቀመጫ ወኪሉ ሚች ማኮኔል በሚመሩት ሸንጎ ውስጥ ሁለት ዓመት እንዲቀመጡ ቢፈቀድ ባይደን የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት የጭንቅ ዓመታት ይሆኑባቸዋል። ምክንያቱም ሪፐብሊካኖች የጆ ባይደን አጀንዳዎች ከሕግ መምሪያ ምክር ቤት አልፈው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሲደርሱ ሊታነቁባቸው ይችላሉና ነው። ለዚህ ነው የዛሬው የጆርጂያ ግዛት የእንደራሴ ምርጫ ጭንቅ የሆነው። ለምሳሌ በጆርጂያ ሁለቱ ተወካዮች ከሪፐብሊካን ቢሆኑ ባይደን ከዚያ በኋላ እያንዳንዱን አጀንዳ በምክር ቤቱ በኩል አጸድቆ ለማሳለፍ ሲሹ ሁልጊዜም ሁለት ሦስት ሪፐብሊካን እንደራሴዎችን ማባበልና መለማመጥ ሊኖርባቸው ይችላል። ይህን የፖለቲካ ልምምጥ ለማስቀረት የዛሬው የጆርጂያ ምርጫ ወሳኝ ሆኗል። አሁን ሁለቱም ፓርቲዎች የጆርጂያን ውጤት በጭንቀት እየጠበቁ ያሉት ከዚህ አንጻር ነው። ሁለቱም ፓርቲዎች በሙሉ ጉልበት እየቀሰቀሱ ሰንብተዋል። እንዲያውም ሪፐብሊካኖች ለማስታወቂያ ብቻ እስከ 400 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ አድርገዋል ነው የሚባለው። የዲሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩዎች ራፋኤል ዋርኖክ እና ጆን ኦሶፍ በጆርጂያ እየተፎካከሩ ያሉት እነማን ናቸው? ጆርጂያ ግዛት የሪፐብሊካን ታማኝ ይዞታ ሆና ነው የቆየችው። ባይደን ናቸው ታሪኩን የቀየሩት። አትላንታ የሚገኙት ተመራጩ ፕሬዝዳንት መራጮችን "ዲሞክራቶቹን እጩዎች መርጣችሁ ታሪክ ሥሩ" እያሉ ሲቀሰቅሱ ነበር። ተመራጯ ምክትል ፕሬዝዳንት ካምላ ሐሪስም ጆርጂያ ነው ያሉት። ከፍተኛ ቅስቀሳ ይዘዋል። ጆርጂያ ለሕግ መወሰኛውም ምክር ቤት የወከለቻቸው ሁለት እጩዎች ሪፐብሊካን ነበሩ። አሁን በሚደረገው ምርጫ ላይ ወንበራቸውን ለማስጠበቅ እየተፋለሙ ነው ያሉት። አንደኛው ዴቪድ ፐርዲዩ ናቸው። ከ2015 ጀምሮ በሸንጎው ውስጥ ቆይተዋል። እሳቸውን አስወጥቶ ለመግባት እየሞከረ ያለው ወጣቱ ጆን ኦሶፍ ነው። ቀድሞው ጋዜጠኛ ጆን 33 ዓመቱ ነው። ሁለቱ እጮዎች በቅስቀሳ ላይ መዘላለፍ አብዝተዋል። የዲሞክራቱ እጩ ጆን ሚስተር ዴቪድን በሕገ ወጥ ንግድ ይከሳቸዋል። እሳቸው የቀድሞ የሪቡክ ብራንድ ሥራ አስፈጻሚ ነበሩ። ሁለቱ እጩዎች የቴሌቪዥን የቀጥታ ክርክር ለማድረግ ተቀጣጥረው አልተሳካላቸውም። የሪፐብሊካኑ ዴቪድ ሊገኝ አልቻለም። ሌሎቹ ሁለቱ ተፎካካሪዎች የሪፐብሊካኑ ኬሪ እና የዲሞክራቱ ሬፍ ራፋኤል ዋርኖክ ናቸው። ኬሪ እውቅ ሀብታም ሴት ናት። የቅርጫት ኳስ ቡድንን በባለቤትነት የምታስተዳድር አዱኛ የበዛላት ባለሀብት ናት። ዋርኖክ በበኩሉ በጆርጂያ የመጀመሪያው ጥቁር እንደራሴ ለመሆን ነው እየተፎካከረ ያለው። ዋርኖክ በአትላንታ የአቤኔዘር ቤተክርስቲያን ሰባኪ ሲሆን፤ እንደ ታላቁ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ሁሉ እሱም እውቅናው ከቤተክርስቲያን የሚነሳ ነው። በነገራችሁ ላይ ማርቲን ሉተር ኪንግ ድሮ በዚህ የአቤኔዘር ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው መስበክ የጀመረው። አባቱም የዚህ ቤተክርስቲያን መሥራች ነበሩ። ራፋኤል ዋርኖክ ልክ እንደ ማርቲን ሁሉ እውቅ የጥቁሮች መብት ተቆርቋሪ ከመሆኑም በላይ "የብላክ ላይቭስ ማተር" ንቅናቄ ንቁ ደጋፊ ነው። ከአነጋገሩ ጀምሮ ብዙ ነገሮቹ ከዝነኛ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ጋር ይመሳሰላል ይላሉ የአሜሪካ ሚዲያዎች። ሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩዎች ሴናተር ኬሊ ሊዮፍለር እና ዴቪድ ፕርዱዩ በጆርጂያ ለምን ድጋሚ ምርጫ ይደረጋል? በጆርጂያ ግዛት የምርጫ መተዳደርያ ሕግ ዕጩዎች ከ50 በመቶ በታች የነዋሪ ድምጽ ካገኙ ምርጫው ይደገማል ይላል። ባለፈው ኅዳር ወደ ውድድር የገቡት ዕጩዎች ታዲያ አንዳቸውም 50 ከመቶ ድምጽ ሊያገኙ አልቻሉም። ሊዮፍለር እና ዋርኖክ እየተወዳደሩ ያሉት ግን በጤና ምክንያት አንድ የጆርጂያ እንደራሴ በገዛ ፈቃዳቸው ውክልናቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው። ባለፈው ምርጫ ዲሞክራቱ ዋርኖክ ያገኙት ድምጽ 32.9 በመቶ ሲሆን ኬሊ ሊዮፍለር 25.9 በመቶ ድምጽ በማግኘት 2ኛ ሆናለች። በሌላኛው ውድድር ደግሞ ዴቪድ ፕርዱዩ 49.3 በመቶ ሲያገኝ ጆን ኦሶፍ 47.95 ከመቶ ድምጽ ማግኘት ችለው ነበር። ሁሉም ያገኙት ድምጽ ከ50 ከመቶ በታች በመሆኑ ድጋሚ ምርጫው ዛሬ ሊሆን ችሏል። ላለፉት 20 ዓመታት በጆርጂያ አንድም እንደራሴ ከዲሞክራቲክ ፓርቲ ወጥቶ ያሸነፈና ወደ ላዕላይ ምክር ቤት መግባት የቻለ የለም። እንኳንስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ይቅርና ለፕሬዝዳንቶችም ደቡባዊ አሜሪካ ጆርጂያ ፈተና ሆና ነው የኖረችው። ጆ ባይደን በጆርጂያ ሲያሸንፉ ከ30 ዓመት በኋላ መሆኑ ስለ ግዛቱ ምንነትና ማንነት ብዙ ይነግረናል። ጆ ባይደንም ሆኑ ትራምፕ የጆርጂያ ውጤት ለሚቀጥሉት ረዥም ዓመታት አሜሪካ ምን እንደምትመስል የሚወስን ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ጽሑፍ እስኪጠናቀር ድረስ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ጆርጂያዊያን ድምጽ ሰጥተዋል። ይህም ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገበው ሕዝብ 40 እጁ ይሆናል። ሪፐብሊካኑ ኬሊና ዴቪድ አሁን የሸንጎው አባል ናቸው። ከሸንጎው ሊፈነቅሏቸው እየተጉ ያሉት ጆን እና ጥቁሩ ዋርኖክ ናቸው። ትናንት ሰኞ ጆ ባይደን በጆርጂያ ዋና ከተማ አትላንታ ቅስቀሳ ሲያደርጉ "ጆርጂያ መላው አሜሪካ አንቺን እየተመለከተ ነው። በረዥም የፖለቲካ ሕይወቴ አንድ ግዛት 4 ዓመትን ብቻ ሳይሆን የመላው አሜሪካንን የፖለቲካ እጣ ፈንታ ሲወስን አይቼ አላውቅም፤ ጆርጂያ አንቺ የመጀመሪያዋ ነሽ" ሲሉ ሕዝቡ ድምጽ እንዲሰጣቸው ተማጽነዋል። ይህን ሲናገሩ የዲሞክራቶቹ እጩዎች ጆን እና ዋርኖክ በግራና ቀኝ አብረዋቸው ቆመው ነበር። ዶናልድ ትራምፕም ወደ ጆርጂያ ወርደዋል። በቅስቀሳ ወቅት ባደረጉት ንግግር "ጆርጂያ የመጨረሻዋ የሪፐብሊካኑ ምሽግ" ሲሉ ነገሩን ከጦርነት ጋር አነጻጽረውታል። የሪፐብሊካን እና የዲሞክራቶች የአሁኑ ጊዜያዊ የሸንጎ ቁጥር 52 ለ 48 ነው። ዛሬ ማታ ወይም ነገ በሚታወቀው ውጤት ሁለቱም የዲሞክራቲክ እጩዎች ድል ቢቀናቸው አሜሪካ የዲሞክራቶች አገር ሆነች የማለት ያህል ነው።
news-51772334
https://www.bbc.com/amharic/news-51772334
አሚን ዳንኤል፣ ቀና ዘመድኩንና ዳንኤል ለማ፡ ማወቅ የሚገባችሁ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ ሙዚቀኞች
የተወለዱበትን ቀዬ ለቆ፣ ባህልና አኗኗር ዘዬ፣ ዘመድና ቤተሰብ ትቶ መሰደድ ምን አይነት ስሜት ይኖረው ይሆን?
አገራቸው በጦርነት ፈራርሶ፣ ቤታቸው በጦርነት ወድሞ፣ በፖለቲካ እምነታቸው ተሳዳጅ ሆነው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ነገን በማለም የነጎዱትን ታሪክ ይቁጠረው። ኢትዮጵያውያን ወደ ሌላ አገራት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ያጠኑ ሰዎች እንደሚሉት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህዝብ ስደት የተጀመረው በደርግ ወቅት ነው። የተለያዩ አፍሪካ አገራት በተለይም ሱዳን የብዙዎች መቀመጫ ነበረች፤ ከዚያም ነገን ተስፋ ወደ ፈነጠቁላቸውም ምዕራቡ ዓለም። ምንም እንኳን ካደጉበት አገር፣ ባህል መነቀል ቀላል ባይሆንም በህይወት የተረፉ ስደተኞች ከዜሮ ጀምረው ኑሮን መስርተዋል፤ ልጆቻቸውን አሳድገዋል፣ ለቁም ነገር አብቅተዋል። ይህ ሁኔታ የጃማይካዊቷ ፀሀፊ ኤድዊጅ ዳንቲካትን "ሁሉም ስደተኞች አርቲስቶች ናቸው" የሚለውን አባባል ያስታውሳል። ፀሃፊዋ ይህንን የምትልበት ምክንያት አላት ይህም ስደተኞች ከስር መሰረታቸው ተነቅለው፣ ከዜሮ ጀምረው፣ አዲስ ህይወት መስርተው ቤትን አገርን በሚመስላቸው መልኩ ስለሚቀርፁት ነው። ይሄ የኢትዮጵያውን ስደተኞች ብቻ እውነታ ሳይሆን የብዙ አገራት ስደተኞች ነው። የእነዚህ ስደተኞች ልጆችስ ኑሮ ምን ይመስላል፤ እስቲ በሌላው አለም እያንፀባረቁ ያሉ መኖሪያቸውን በምዕራቡ አለም ያደረጉ ሙዚቀኞችን ታሪክ በትንሹ እናጋራችሁ። አሚኔ ዳንኤል አሚኔ ዳንኤል- እምቢተኛው በዓለማችን ውስጥ በቀለም፣ በማንነት በዘር እንዲሁም በተለያዩ እምነቶች ጭቆና እንደሚደርስበት ለማወቅ ምናልባት በሚጨቆኑ ሰዎች መንገድ ማለፍ ይጠበቅ ይሆን? ከታሪክ፣ ከመፃህፍትና ከተጨቆነ የማኅበረሰብ ክፍል አንደበት መረዳት አይቻል ይሆን? ለብዙዎች እልቂት ከሆነው ጦርነቶች፣ ህመሙ ለትውልድ ትውልድ ከተረፈው የባርነት ታሪክ፣ ጠባሳው ካልሻረው ቅኝ ግዛት ምን ያህል ተምረን ይሆን? የዓለማችንን ነባራዊ ሁኔታ ስናይ ሌላ አይነት ጭቆና እልቂት እንደቀጠለ ነው። ለዛም ነው ብዙዎች በጥበባቸው፣ በፅሁፎቻቸው፣ በሰልፎች እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለማሰማት የመረጡት። ኢትዮጵያዊው አሜሪካዊ ራፐር አሚኔ ዳንኤል ቀልድ በተዋዛበት መልኩ ያወጣው 'ሬድ መርሰዲስ' ጥቁሮች የሚደርስባቸውን መገለልና ዘረኝነት በቀልድ መልኩ ጠቆም ያደርጋል። እስቲ የኃይል አሰላለፉ ተገለባብጦ ነጮች አሁን ያሉበትን የጥቁሮች ቦታ ሲይዙና አድልዎና ዘረኝነቱን በመገልበጥ ያሳያል። በቪዲዮውም ላይ ነጭ የቆዳ ቀለም አድርጎ መታየቱም አወዛጋቢም አድርጎት ነበር፤ የተናደዱበትም ነበሩ መልእከቱንም የተረዱ እንዲሁ። 'ሬድ መርሰዲስ'ም በቢልቦርድ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ በመቶዎች ዝርዝር አስራ አንደኛ ሆኖ ለ28 ሳምንታት ያህል የቆየ ሲሆን፤ 221 ሚሊዮን ተመልካቾችም ቪዲዮውን አይተውታል። በራፕ ሙዚቃ መድረክ ውስጥ ስም እያተረፈ ያለው አሚኔ የሚያምንበትን ነገር ከመዝፈንም ሆነ ከመናገር ወደ ኋላ አይልም። በቅርቡ ጂሚ ፋለን የሚያቀርበው ታዋቂው ፕሮግራም "ዘ ቱ ናይት ሾው" ላይ ትራምፕን ወርፏቸዋል። "አሜሪካን ታላቅ አታደርጋትም፤ ያደረከው በሙሉ ጥላቻን ማስፈን ነው፤ ትራምፕ የሚሰራውን የማያውቅ ግለሰብ ነው፤ ምንድን ነው የሚለው? ይህቺ አገር እኮ የስደተኞች ናት" ብሏል። ለአሚኔ ስደተኝነት በቅርቡ የሚያውቀው ነው፤ ብዙ ሳይርቅ የቤተሰቦቹ ታሪክ ነው፤ እናቱ እፀ ህይወትና ዳንኤል ከኢትዮጵያ ተሰደው ነው ፖርትላንድ የከተሙት፣ ኑሮን በባዕድ አገር 'ሀ' ብለው የጀመሩት፤ ቤትን የመሰረቱት። እናቱ የሚሰሩት ፖስታ ቤት ሲሆን አባቱ ደግሞ መምህርና አስተርጓሚ ናቸው። አሚኔ ነጭ ተማሪዎች በብዛት ባሉበት ትምህርት ቤት ነው የተማረው፤ ገና በልጅነቱ ጥቁር መሆኑን የሚያስታውሱት ጨቅላ ህፃናት ከቤተሰባቸው የወረሱትን ጥላቻን በማንፀባረቅ 'ኒገር፣ ኒገር' ሲሉት ነው ያደገው። "ሁሌም ቢሆን የባዳነት ስሜት እንደተሰማኝ ነው፤ ያ ወቅት ለእኔ አሰቃቂ ነበር" ይላል። ከትምህርት ቤት ሲወጣ ግን ጥላቻውንም ሁሉንም ይረሳዋል፤ ቤት ውስጥ ቤተሰቦቹ አማርኛ ያወራሉ። የኢትዮጵያ ሙዚቃም ያደምጣሉ። ከኢትዮጵያ ሙዚቃ በተጨማሪ እናቱ ደግሞ ቱፓክ ሻኩርን፣ ማይክል ጃክሰን፣ ጆን ሜየርና ካንዬ ዌስትን የመሳሰሉ ሙዚቃ አስተዋወቀችው። ሙዚቃው እንዲሁም የቤተሰቡ ታሪክ ውስጥ ራሱን ይከታል፤ የትምህርት ቤት ዓለምንም ይረሳዋል። አንደኛ ደረጃ በገጠመው ከፍተኛ ጥላቻ በብዙ መልክ የተቀየረው ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሌላ ትምህርት ቤት በመቀየሩ ነው፤ ጓደኞችም አፈራ። በትምህርቱም ጎበዝ ነበር። ወደ ሙዚቃው ዓለምም የገባው በዚህ ወቅት ነው። አሚኔ ዳንኤል በሙዚቃው ቀጠለበት ፖርትላንድ ስቴት ዩኒቨርስቲ ማርኬቲንግ እያጠናም ሙዚቃውን ተደብቆ ይሰራ ነበር። ነገር ግን ቀላል አልሆነለትም፤ ሙዚቀኞችም ሆነ አቀናባሪዎች ከእሱ ጋር ተጣምረው መስራት አልፈለጉም፤ ለስቱዲዮ ከፍሎ መስራት ደግሞ በተማሪ አቅም ገንዘብ ከየት ይምጣ፤ የማይታሰብም ሆነ። ለዚያም ነው አሜሪካ ውስጥ ዘረኝነት ቢኖርም "የደቡቡ ክፍል ዘረኝነት ይለያል" የሚለው። ጥቁር በመሆን ብቻ ሥራ፣ መኖሪያ ቤት አለማግኘት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች የብዙዎችን ጥቁሮች ህይወት ያከበዱ ናቸው። ነገር ግን ለራሱ መላ በመዘየድ ከአምስት ዓመታት በፊት ራሱ ላፕቶፑ ላይ የቀዳውና ያቀናበረው 'ካሮላይን' የተሰኘ ሙዚቃው ብዙዎችን ያስደነቀ ነጠላ ዘፈን ሆነ። በዚህ ሙዚቃውም ከሚታገል ኮሌጅ ተማሪ የሂፕ ሆፕ ኮከብም ሆነ። ቪዲዮውንም 175 ሚሊዮን ተመልካች አየው። ከዚህም በተጨማሪ ካሮሊን ሶስት ጊዜ የፕላቲኒየም ደረጃ ላይ ደርሷል። የመጀመሪያው አልበሙ "ጉድ ፎር ዩ" ከሦስት ዓመት በፊት የወጣ ሲሆን ራፕ፣ ኢንዲ ሮክንና ሌሎችንም ስልቶች አጣምሮ ይዟል፤ በዚህም አልበም ከፍተኛ ተቀባይነትን ማግኘት ችሏል። ኒውዮርክ ታይምስ "የራሱን ስልት የፈጠረ" በማለት ያንቆለጳጰሰው አሚኔ ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት የራሳቸውን ድምፅ መፍጠር የቻሉትን ካንዬ ዌስት፣ አንድሬ 3000፣ ፋረል ዊልያምስን በአንድ ላይ ማምጣት የቻለ ነው ብሎታል። ከኤርትራዊና ኢትዮጵያዊ ስደተኞች የተወለደው የ25 ዓመቱ ራፐር ቅርጫት ኳስ የመጫወት ህልም ነበረው፤ ህይወት የራሷ ሌላ እቅድ ስላላት ወደ ሙዚቃው ዓለም ወሰደችው። ቀና ዘመድኩን ቀና ዘመድኩን - የማህበራዊ ፍትህ ታጋዩ በኢትዮጵያ አንድ አባባል አለ፤ "ስምን መልአክ ያወጣዋል" የሚል፤ አባባሉ ሰምና ወርቅ አለው። ሰሙ ስም ዝም ብሎ በዘፈቀደ አይወጣም የሚል ሲሆን ወርቁ ግን የአንድ ሰው ተግባሩ ከስሙ ጋር በጥሩም ይሁን በመጥፎ ሲገናኝ ሁሉን የሚያውቁ አወጡት ለማለት ነው። •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቀና ዘመድኩንም ይሄንን አባባል የወረሰ ይመስላል። ስሙን የሰጠው አባቱ ሲሆን ስሙም በህይወቱ ትልቅ ትርጉም አለው፤ ለቀናነትም ትልቅ ቦታ ይሰጣል። ቤተሰቦቹ እንዳወረሱት ስምም መኖር ይፈልጋል። ብዙዎች በዚያው መንገድ እየኖረ መሆኑንንም ተግባሩን በማየት ይመሰክሩለታል። የ41 ዓመቱ ቀና ዘመድኩን ሙዚቀኛ፣ ፀሃፊ፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪ እንዲሁም የማህበራዊ ፍትህ ታጋይም ነው። ሙዚቃው ለግራሚ፣ ኤሚ እንዲሁም ቪኤምኤ ታጭቷል። ቀና ከሙዚቀኝነቱ በተጨማሪ በዓለም አቀፉ ውስጥ ያለውን የውሃ እጥረት፣ አቅርቦት ችግርም ለመፍታት በብዙ ሚሊዮኖች ዶላርም ለማሰባሰብ ችሏል። "ገንዘብና እውቅና ሳይሆን ሥራዎቼ ለሌሎች ህይወት አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ እፈልጋለሁ፤ እንደ አርቲስትም የመረጥኩትም መንገድ እሱን ነው" ብሏል በአንድ ወቅት በሰጠው ቃለ መጠይቅ። ለምሳሌ "ሌትስ ስታርት ኤ ሪቮሉሽን' የሚለውን ሙዚቃውን ብንወስድ በአጠቃላይ ነገሮችን ከስር መሰረት መቀየር የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ ይዟል። ቀና ሙዚቃዬ ምን ያህል ተፅእኖ አለው? የተሻለ ሰው መሆንን አነሳስቷችኋል? በጎ ነገር እንድታደርጉ ገፋፍቷችኋል? ከዚህ በፊት ስለ ራሳችሁ የማታውቁትን ነገር እንድታውቁ አድርጓችኋል ወይ ብሎ ይጠይቃል። የተለያዩ የሙዚቃ ስልቶችን በማጣመር የሚመራመረው ዳንኤል ኤሌክትሮኒካ፣ ሲንተቲክ ፖፕ፣ ፖስት ሮክ እንዲሁም ሃውስ የሚጫወተው ቀና 'ሰይ ጉድባይ ቱ ላቭ' የሚለውም ሙዚቃው ምርጥ የከተማ (ኧርባን) አማራጭ በሚልም ለ2009 ግራሚ ታጭቷል። ሙዚቃዎቹ ሲወጡ የአሜሪካ የሙዚቃ ሰንጠረዥን የሚቆጣጠሩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 'ፍሪ ታይም' አልበሙን መጥቀስ ይቻላል። አንደኛው አልበሙም 'ሂት ሲከርስ' በሚባለው የአሜሪካ የሙዚቃ ሰንጠረዥ አንደኛ ሆኖ ነበር። በሙዚቃው ውስጥ ሳም ኩክ፣ ናት ኪንግስ፣ ፍራንክ ሴናትራ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው ሲሆን ልክ እንደነሱም መንፈስን ሰርስሮ የሚሰርፅ፣ ወደሌላ ዓለም የሚያመጥቅ ሙዚቃን መስራት ይፈልጋል። ቀና የተወለደው ኢትዮጵያ ሲሆን እስከ ሦስት ዓመቱም ያደገው በአያቱ ቤት ነው። ወላጅ አባትና እናቱ የደርግን መንግሥት ሸሽተው ወደ እንግሊዝ ከዚያም ወደ አሜሪካ አቀኑ፤ ቀናም ወላጆቹን የተቀላቀለው በዚህ ወቅት ነበር። ገና በታዳጊነቱ ወደ ሙዚቃው ዓለም የመጣው ቀና፤ ራሱን ፒያኖ በማስተማርም ስቲቪ ወንደር፣ ማርቪን ጌይ እንዲሁም ዘ ኪውርና ዱራን ዱራን ቡድኖችን ሙዚቃ አጥንቷል። ቀና በተለያዩ አልበሞቹ ከፋረል ዊልያምስ እንዲሁም ከራፐሩ ቸንጅ ጋር በመጣመር ሙዚቃዎችን የሰራ ሲሆን፤ ከሙዚቃው በተጨማሪ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች አገራትን የውሃ ችግር ለመፍታት በሚል ከሙዚቀኛ ጓደኛው ሉፔ ፊያስኮ እንዲሁም ከሌሎች ታዋቂ ሰዎች ጋር በመሆን የኪሊማንጀሮ ተራራን በ2010 ወጥተዋል። 'ተርን' የሚለውም የዘፈኑም ሽያጭ ለዚህ ፕሮጀክት ውሏል። ዳንኤል ለማ ዳንኤል ለማ- ለአገሩ ባዳ ከኢትዮጵያ በሺዎች ኪሎ ሜትር ርቆ በአውሮፓዊቷ አገር በስዊድን ታዋቂ የሆነውን ዳንኤል ለማን ያውቁት ይሆን? ምናልባት ኑሯችሁ በስካንድኔቪያን አገራት በአንዱ ከሆነ በተለያዩ ፌስቲቫሎች ላይ ጊታሩን ይዞ ለስለስ ያለ ሙዚቃውን ሲጫወት አይታችሁት ይሆናል። እነ 'ማይ ቨርዥን'፣ 'ሪባውንድ'፣ 'ድሪመርስና ፉልስ'፣ 'ሳም በዲ ኦን ዩር ሳይድ' የመሳሰሉ ዘፈኖቹን ካወቃችሁት ደግሞ አብሮ አለመዝፈን ከባድ ነው። ፌስቲቫሉ ቀርቶ ድንገት ሥራ ላይ ሆናችሁ 'ኢፍ አይ ዩዝድ ቱ ላቭ ዩ'ን እየሰማችሁ 'ላይክ ኤ ሬይንቦው ራይት ናው' የሚለውን ሃረግ አለመደጋገም አይቻልም። የ48 ዓመቱ ዳንኤል የተወለደው ኢትዮጵያ ነው። ወደ ስዊድን ደግሞ ያቀናው ገና ነፍስም ሳያውቅ በጨቅላነቱ ቤተሰቦቹ የተሻለ ህይወት ይኖራል በሚል በጉዲፈቻ ሰጥተውት ነው። •"ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ ለዳንኤል ሙዚቃው ያለፈበት ጉዞን፣ ህልሙ ተስፋውና ፀፀቱ፣ የተደራረቡ ማንነቶች መግለጫው ነው። ሙዚቃው ከብዙ ነገር ማምለጫም ሆነ መግለጫም ሆኖታል። ምናልባት የአውሮፓ ኑሮ ምቹ ከመሆኑ አንፃር ስዊድን ማደግ ቀላል ሊመስል ይችላል፤ ለዳንኤል ግን ከባድ ነበር። ምክንያቱም ብቸኛው ጥቁር ልጅ በክፍሉ ውስጥ እሱ ስለነበር። የዳንኤል ሙዚቃ ጉዞ የሚጀምረው ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ነው፤ ባንድም መሰረቱ ። ከመዝፈን በተጨማሪም ከበሮም ይጫወት ነበር። ባንዱም እያደገ መጣ፣ ዳንኤልም ሙዚቃ ወደ መፃፉ ጠልቆ ገባ። በመጀመሪያ አካባቢ ቀላል አልነበረም፤ መድረክ ላይ ብዙ ሰዎች ፊት መዝፈን፤ የመድረክ ፍራቻውም እንዲሁ እስኪለምደው ድረስ። መጀመሪያ አካባቢ የራሱ ባይሆንም የታዋቂው አሜሪካዊ ሙዚቃ ቦብ ዲለንን ይጫወት ነበር እንዲሁም የምንጊዜም ጀግናዬ የሚለውን የሬጌውን ንጉሥ ቦብ ማርሌንም ይጫወት ነበር፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የኖረውም አልበም የቦብ ማርሌይ ነው። በተለይም በነጭ አገር ውስጥ እሱን የሚመስል ሰው በሚዲያው ላይም ሆነ በአካባቢው አለመኖር የቦብ ማርሌ ሙዚቃ ሊኖርበት የሚችል ሌላ ዓለም ፈጠረለት። ቦብ ማርሌን ሙዚቃውን ብቻ ሳይሆን ለዳንኤል ፀጉሩን ድሬድ ለማድረግ መነሻ ሆነው። ከቦብ ማርሌ በተጨማሪ የታዋቂዋን ጥቁር አሜሪካዊ ፀሐፊና የከለር ፐርፕል ደራሲ አሊስ ዋከርን 'ኦፕረስድ ሄይር' (የተጨቆነው ፀጉር)ን ማንበቡ ነፃነት ከፀጉር እንደሚጀምር ለመረዳት እንዳስቻለው በአንድ ወቅት ተናግሯል። ዳንኤል ለማ ሙዚቃውንም በጎን እየተጫወተ ሥነ መለኮትና ታሪክን በደቡብ ስዊድን ከሚገኘው ሉንድ ዩኒቨርስቲ አጥንቷል። ከዚያም ኑሮውን ለሦስት ዓመታት ያህል በኒውዮርክ ያደረገው ዳንኤል የመጀመሪያ አልበሙን ቢያጠናቅቅም በአንዳንድ እክሎች ምክንያት ሳይለቀቅ ቀረ። ቢሆንም የኒውዮርክ የተለያዩ የሙዚቃ መድረኮችን እንዲያይ እድሉን ሰጥቶታል፤ በተለያዩ ክለቦችም ተጫውቷል። ወደ ስዊድንም ተመልሶ በዓመታት ውስጥ ስድስት አልበሞችን ሰርቷል፤ በተለይም 'ያላ ያላ' ለሚለው ፊልም የሰራው ማጀቢያ 'ኢፍ አይ ዩዝድ ቱ ላቭ ዩ' ለግራሚ እንዲታጭ አድርጎታል። ፊልሙ በስዊድን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በስካንድኔቪያን አገሮች ታዋቂነትን አትርፏል። ምንም እንኳን ስዊድን ውስጥ በራሳቸው ቋንቋ የሆኑ ሙዚቃዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተደማጭነት ቢኖራቸውም፤ ዳንኤል በእንግሊዝኛ በሚዘፍናቸው ሙዚቃዎቹ በሙዚቃው መድረክ ላይ ጎልቶ ለመታየት ችሏል። ሆኖም ግን ጥቁር መሆኑ ያለውን ተፅእኖ አይደብቅም። ዳንኤል ለማ ከሬጌም በተጨማሪ ብሉዝ፣ ሶውል፣ ጎስፔል፣ ሮክ፣ ሐገረሰብ ሪትም ኤንድ ብሉዝን በመቀላቀል ይጫወታል። "ሙዚቃዎቼ ለሰዎች በህይወታቸው ትርጉም እንዲሰጣቸው እፈልጋለሁ። ጠዋት ለምን ይነሳሉ? የሚሰሯቸውንስ ሥራዎችስ ለምን ይሰራሉ? የህይወትስ ትርጉሙስ ምንድን ነው የሚለውን በሙዚቃዎቼ በተወሰነ መልኩ መመለስ እፈልጋለሁ" ይላል። •ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን የማደጎ ቤተሰቦቹ ማንነቱንም ሆነ ስለቤተሰቦቹ እየነገሩ ነው ያሳደጉት በዚያም ምክንያት ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ከአዕምሮው እንደማትጠፋ ይናገራል። በሃያዎቹ ዕድሜ መጨረሻም ቤተሰቦቹ ጋር ሊገናኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጣ። ቤተሰቦቹ ጋር መገናኘት ቀላል አልነበረም ነጭ አገር ለምን ሰደዱኝ የሚሉ ያልተመለሱ ጥያቄዎች፣ የማንነትን መቀማት ፀፀት እንዲሁም ወላጆቹን መቀበልም አዳግቶት እንደነበር በአንድ ወቅት ተናግሯል። ቢሆንም ቤተሰቦቹንም ሆነ ተቀማሁ የሚለውን ማንነት ለማጥናት ቁርጠኛ ነበረ። ከቤተሰቦቹ ጋር ከመገናኘት በተጨማሪ ስለ አገሩ ሙዚቃ አንደ አዲስም መማር ጀመረ። ከዚያ በኋላ መመላለስ የጀመረው ዳንኤል በተለያዩ መድረኮች በዓመታዊ የሰላም ፌስቲቫል በግዮን እንዲሁም በኮፊ ሃውስ ለኢትዮጵያውያን አድማጮች የመጫወት እድሉን አግኝቷል።
news-55663240
https://www.bbc.com/amharic/news-55663240
ትግራይ- በፌደራል መንግሥቱና ሕወሓት መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ኤርትራውያን ስደተኞች ያሉበት ሁኔታ
የተባበሩት መንግሥታትና የአውሮፓ ሕብረት በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት ኃይሎች መካከል የተካሄደውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በክልሉ የሰብዓዊ ቀውስ ሊባባስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ትናንት ማምሻውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ኃላፊ ፊሊፖ ግራንዲ፣ በትግራይ ክልል ባለው ሁኔታና በንፁሃን ዜጎች ላይ ባለው ተጽዕኖ በተለይ ደግሞ በክልሉ ተጠልለው የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ሁኔታ እጅጉን እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል። በትግራይ ክልል ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በአገር ውስጥ ተፈናቅለዋል የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ወደ አዲስ አበባና ሌሎች የአገሪቱ ክልሎች መሸሻቸው ተገልጿል። የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ በገባበት በትግራይ ክልል ውስጥ፣ በመቶ ሺህ የሚደርሱ የኤርትራ ስደተኞች የሚኖሩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥትና የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት (ዩኤንኤችሲአር) ከለላ ያደርጉላቸው ነበር። በክልሉ ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ የበርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅት ሠራተኞች፣ የዩኤንኤችሲአርን ጨምሮ፣ ስደተኞቹን ከአነስተኛ ድጋፍ ጋር በአንዳንድ ስፍራም ያለምንም ድጋፍ ትተዋቸው አካባቢውን ለቅቀው መውጣታቸውን ቢቢሲ መረዳት ችሏል። በጥቅምት ወር ላይ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞቸ ድርጅት ኤጀንሲ ኃላፊዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በአካባቢው ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ድርጅቱ ወደ ስደተኞች መጠለያዎች መድረስ እንዲሁም ሠራተኞቻቸውን ማግኘት አለመቻላቸውን ገልፀው ነበር። "ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ ለእኛ ከባድ ነው። ከዚህ የግንኙነት መስመር ሙሉ በሙሉ መቋረጥ በፊትም የነበረን የግንኙነት መስመር በጣም ውሱን ነበር። በሽመልባ የስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ስደተኞች ለደኅንነታቸው ሲሉ ወደ ህጻጽ መጠለያ ጣብያ እያመሩ ነው።" የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በህወሓት ታጣቂዎች ላይ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ የጀመረው እርምጃ፣ በክልሉ የተለያዩ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የለውም ሲል ተናግሮ ነበር። ባለስልጣናት በትግራይ የሚገኙት የስደተኛ መጠለያዎች ደኅንነታቸው የተጠበቀ በመሆኑ ስጋት ገብቷቸው ለቅቀው የወጡ እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ መንግሥት በታኅሣስ ወር ላይ "በርካታ ቁጥር ያላቸውና የተሳሳተ መረጃ የደረሳቸው ስደተኞች ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ መጠለያውን ለቀው ወጥተዋል" ሲል ተናግሯል። "መንግሥት እነዚህን ስደተኞች ወደ መጡበት መጠለያ ጣቢያ ደኅንታቸው ተጠብቆ እንዲመለሱ እያደረገ ነው" በማለት ምግብ ወደ መጠለያ ጣብያዎቹ እየተጓጓዘ መሆኑን አስታውቋል። በማይ አይኒ የስደተኞች መጠለያ ጣብያ ይኖር የነበረና አሁን ወደ ሌላ የአገሪቱ ክፍል የሄደ ስደተኛ ለቢቢሲ እንደገለፀው መጠለያውን ለቀው የወጡበት ምክንያት ሁለት መሆኑን አብራርቷል። "የመጀመሪያው ምክንያት እንደ ምግብ፣ ውሃ፣ መድኃኒት ያሉ መሠረታዊ አቅርቦቶች አለመኖራቸው ነው። የዩኤንኤችሲአር ሠራተኞች መጠለያ ጣቢያውን ጥለው ከሄዱ በኋላ ስደተኞቹ ለረሃብ ብቻ ሳይሆን ለአደጋም ተጋልጠናል።" ለደኅንነቱ ሲባል ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቀው ይህ ስደተኛ ሁለተኛ ያለውን ምክንያት ሲያስረዳም የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ጎን በመሰለፍ እየተዋጉ መሆናቸውን መስማታቸው ለአደጋ እንደተጋለጡ እንዲሰማቸው ማድረጉን ያስረዳል። "የኤርትራ ወታደሮች በሽመልባና ህጻጽ የስደተኛ ካምፖች አደረጉ የተባለውን ስንሰማ በመጠለያ ውስጥ ያለን ሁሉ በፍርሃት ተናጥንና ወዲያውኑ ካምፑን ለቅቀን ወጣን።" በአዲ ሀሪሽ ይኖር የነበረ ሌላ ስደተኛ በበኩሉ ". . . ጦርነቱ መጠለያ ጣቢያው ወደ ሚገኝበት አካባቢ በደረሰ ሰዓት፣ ለደኅንነታችን ስንል ከለላ ፍለጋ ሸሸን። ምግብና ውሃ እያለቀ ሲመጣም ስደተኛው ያለውን እየተጋራ ሲቃመስ ነበር። መጠለያ ጣብያውን ለቅቀን የወጣነው በረሃብና በጥማት ምክንያት ነው" ሲል ለቢቢሲ የነበረውን ሁኔታ አስረድቷል። አንድ ስደተኛ እንደሚገልፀው "አዲ ሃሪሽ የስደተኞች መጠለያን ለቅቄ ወደ አዲ አርቃይ ሄድኩ። ከአዲ አርቃይ በሰው 95 ብር በመክፈል ወደ ጎንደር አቀናን። በኬላዎች አካባቢ ቢያስቆሙንም ኤርትራዊነቴን የሚገልጽ መታወቂያ ስላለኝ ችግር አልገጠመኝም" ብሏል። ከዚያም ከጎንደር ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ለአንድ ሰው 900 ብር በመክፈል መሄዱን ተናግሯል። እርሱ እንደሚለው ከሆነ ከጎንደር አዲስ አበባ ለመድረስ 13 ሰዓት ያህል ወስዶባቸዋል። በሽመልባ የስደተኞች ጣቢያ ይኖር የነበረ ስደተኛ ማንነቱ እንዳይገለጽ በመጠየቅ ለቢቢሲ እንደተናገረው፣ በኅዳር 2/2013 ዓ.ም የኤርትራ ወታደሮች ወደ ሽመልባና ህጻጽ መጠለያዎች መምጣታቸውን ገልጿል። "የኤርትራ ወታደር ደንብ ልብስን የለበሱ ሰዎች በአንድ ስፍራ እንድንሰባሰብ ካደረጉ በኋላ የመጡት ከትግራይ ሚሊሻዎች ሊከላከሉን መሆኑን ነገሩን።" "እዚህ ሊከላከልላችሁ የሚችል ማንም የዩኤንኤችሲአር ባለስልጣን የለም፤ ሁሉም ሄደዋል አይመለሱም" አሉን። ግሰለቡ እንዳለው ከሆነ ወታደሮቹ "በረሃብ ከምትሞቱ" በማለት፣ ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ እንዳግባቧቸውና የኤርትራ መንግሥት ይቅርታ እንዳደረገላቸው እንደነገሯቸው ያስታውሳል። በሚቀጥለው ቀን ከጋሽ ባርካ ክልል የኤርትራ ባለሥልጣናት መጥተው የስደተኞቹን ተወካይ፣ "የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ባለሥልጣን ሠራተኞች" በመሰብሰብ ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ እንዲያሳምኗቸው መናገራቸውን ይገልጻል። ነገር ግን ስደተኞቹ ለተወካያቸው ጥያቄያቸው እስኪመለስ ድረስ መመለስ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል። ይህ ኤርትራዊ ስደተኛ እንደሚገልፀው፣ ከሁለት ቀናት በኋላ የኤርትራ ብሔራዊ ደኅንነት አባላት የሆኑ ሰዎች ወደ መጠለያው በመምጣት፣ በጉልበት ስደተኞቹን በመክበብ የተወሰኑትን ወደ ኤርትራ ወስደዋቸዋል። ከተወሰዱት ስደተኞች መካከል በርካቶቹ ለአስር ዓመት ያህል በመጠለያ ጣቢያው የኖሩ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ የስደተኛ ማኅበረሰቡ ተወካይ ናቸው። ይህ ግለሰብ ለቢቢሲ እንደገለፀው በኃይል ታፍነው ከተወሰዱት መካከል አንዲት ኤርትራዊ እናት ያለችበት ሲሆን፣ ጨቅላ ልጅ መታቀፏን ያስታውሳል። "ባለፈው ዓመት በመጠለያ ውስጥ ትዳር ከመሰረተች በኋላ ነበር የወለደችው። ከትዳር አጋሯና ከጨቅላ ልጇ ጋር በጉልበት እንድትመለስ ተደርጓል።" ሽመልባና ህጻጽ የስደተኞች መጠለያዎችን በተመለከተ ዩኤንኤችሲአር እስካሁን እንዳልጎበኛቸው ተናግሯል። "ወደ እዚያ ለመሄድ ፈቃድ የለንም። የምናውቀው ነገር ቢኖር ለሁለት ወራት ያህል ከየትኛውም አቅርቦት ተቋርጠው ነው ያሉት።" ከሽመልባና ህጻጽ የስደተኛ ጣብያዎች ታፍነው ስለተወሰዱ ኤርትራውያን የተጠየቀው ድርጅቱ፣ "በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን አናግረናል። በእርግጥም በሰሜን መጠለያ ጣቢያዎች ስደተኞች ታፍነው መወሰዳችውን ሰምተናል። ማረጋገጥ የምንችልበት መንገድ የለም፤ ነገር ግን እውነት ከሆነ በአስከፊ ሁኔታ የዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነው" ሲል ምላሽን ሰጥቷል። የስደተኞች ድርጅቱ በድጋሚ የኢትዮጵያ መንግሥትን መጠለያ ጣቢያዎቹ የተለመደውን አገልግሎት መስጠት እንዲቀጥሉ እንዲደረግ ጠይቋል። የኤርትራ ስደተኞች በትግራይ በትግራይ በሚገኙ አራት የስደተኛ መጠለያ ጣብያዎች 100 ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች ይኖራሉ። ኤርትራውያኑ አገራቸውን ጥለው የተሰደዱት ፖለቲካዊ እስርንና የግዴታ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎትን በመሸሽ ነው። ባለፈው ወር የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች ኤጀንሲ የበላይ ኃላፊ በትግራይ ክልል የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች በግዴታ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ስለመደረጉ፣ ስለ መታገታቸውንና መገደላቸው መስማታቸው በመግለጽ "እጅጉን ስጋት እንደፈጠረባቸው" ተናግረው ነበር። ፊሊፖ ግራንዴ እንዳሉት እንዲህ አይነት ድርጊት ከተረጋገጠ፣ ዋነኛ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ነው ብለዋል። ግራንዴ አክለውም የተባበሩት መንግሥታት በትግራይ የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎችን ለመጎብኘት ያለምንም ገደብ እንዲፈቀድ ጠይቀዋል። በፈረንጆቹ ገና የተባበሩት መንግሥታት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጥምረት በማይ አይኒ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ለ13 ሺህ ኤርትራውያን ስደተኞች የምግብ እርዳታ አድርሷል። 240 ሜትሪክ ቶን ምግብ ደግሞ በአዲ ሃሩሽ የስደተኞች መጠለያ ለሚገኙ 12 ሺህ 170 ስደተኞች መሰጠቱን የተባበሩት መንግሥታት ያወጣው መግለጫ ያሳያል። ድርጅቱ ትናንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለስደተኞቹ ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እየተሰራ ቢሆንም በትግራይ ክልል ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ጊዜ አንስቶ ሽመልባና ህጻጽ የስደተኛ መጠለያ ጣብያዎችን መመልከት እንዳልቻለ ገልጿል። ፊሊፖ ግራንዴም በእነዚህ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኤርትራውያን ደኅንነት እንደሚያሳስባቸው በመግለጫቸው ላይ ገልፀዋል። በእነዚህ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ስደተኞች ለሳምንታት ያለምንም እርዳታ መቆየታቸውን በመግለጽ የሁኔታውን አሳሳቢነት ጠቅሰዋል። አክለውም እነዚህ ጣቢያዎች ስላሉበት ሁኔታ የተለያዩ ተጨባጭ ያልሆኑ መረጃዎች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ሕግና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚያሳዩ ውድመቶች መድረሳቸውን የሚያስረዱ የሳተላይት ምስሎች መመልከታቸውንም አብራርተዋል።
news-47399590
https://www.bbc.com/amharic/news-47399590
ጎንደር፡ የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥትን አደጋ ላይ የጣለው ምንድን ነው?
ጎንደር በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ፋሲለደስ እንደተቆረቆረች ይነገራል። ይሁን እንጂ ከአፄ ፋሲለደስ ንግሥና 300 ዓመታት ቀድማ በምንጮችና በተራሮች የተከበበች መንደር ነበረች ሲሉ የሚሞግቱም የታሪክ አዋቂዎች አሉ።
ጎንደር ለ200 ዓመታት የኢትዮጵያ መናገሻ ሆና አገልግላለች። ባሏት ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ቅርሶች፣ ታሪካዊ ቦታዎች እንዲሁም ኃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶች ትታወቃለች። የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ ከሆኑ አካባቢዎች መካከል በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈረው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ጎንደርን ከፋሲል ግንብ ነጥሎ ማየት ይከብዳል። ስለ ጎንደር የተዜሙ ሙዚቃዎች የሚነግሩንም ይህንኑ ነው። ዛሬ ዛሬ ግን የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ስም የሚነሳው በአስደናቂነቱ፣ በታሪካዊነቱና የኪነ ህንፃ ጥበቡ ብቻ ሳይሆን አደጋ የተጋረጠበት ቅርስ በመሆኑ ነው። በስፍራው ያገኘናቸው ጎብኚዎችም የፋሲል ግንብ ህልውና እንዳሳሰባቸው ገልፀውልናል። • የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር መቆየት ፋሲልን ሲጎበኝ የመጀመሪያው ነው። "በጣም የሚገርም ጥበብ ነው ያየሁት። ታሪካዊ ቦታ ነው። ታሪካዊ በመሆኑ ደግሞ ለትውልድ የሚተላለፍ መሆን ነበረበት" ይላል። መቆየት ቤተ መንግሥቱን ተሰነጣጥቆና ተሰባብሮ ሲያየው ስሜቱ እንደተነካ ገልጿል። "ለምን ጥገና አይደረግለትም?" ሲል የሁሉም የሆነውን ጥያቄ ይጠይቃል። መንግሥትና የሚመለከተው የቅርስ ጥበቃ አካል ምን እየሠራ እንደሆነ ማወቅና መከታተል ያስፈልጋል ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷል። ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የሄደው ሌላው ጎብኝ ሳሙኤል በለጠም "ቤተ መንግሥቱን ሳየው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማኝ" ይላል። ጥበብ የተሞላበትን ኪነ ህንፃ ሲያይ በኢትዮጵያዊነቱ ኩራት ተሰምቶታል። በሌላ በኩል ደግሞ ቅርሱ ጥበቃና እንክብካቤ መነፈጉ አሳፍሮታል። ሳሙኤል ይህን የተደበላለቀ ስሜት ውጦ ዝም አላለም። በጉዳዩ ላይ ከሥራ አስኪያጁ ጋር ተወያይተዋል። "ለምን ዝም እንዳሉ አልገባኝም፤ ለምን ከተማ ላይ ብቻ ትኩረት ይደረጋል?" ሲል እንዲመለስለት የሚፈልገውን ጥያቄ ይሰነዝራል። ከዚህ ቀደም ላሊበላን መጎብኘታቸውን የሚናገሩት ምትኩ እንዳለ የአፄ ፋሲለደስን ግንብ ሲጎበኙ የመጀመሪያቸው ነው። በጉብኝታቸው ብዙ ጠብቀው ነበር። ይሁን እንጂ ያዩት ነገር አስደንግጧቸዋል። "ኢትዮጵያዊነትን እያጣን ነው" ሲሉ በአጭሩ ይገልፁታል። "ጥናት ተደርጎ በባለሙያ መጠገን አለበት፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የራሱን አስተዋፅኦ ማድረግ አለበት" ይላሉ። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? በጎንደር አስጎብኚዎች ማህበር አስጎብኚ የሆነችው ቁምነገር ቢምረው የፋሲል ግንብ ያን ያህል እየተጎበኘ አይደለም የሚል አቋም አላት። እሷ ዘወትር ስታየው የተለየ ስሜት እንደሚሰማትና እንደምትኮራ ትናገራለች። "ሳየው እኮራለሁ፤ ማንነቴን አገኘዋለሁ፤ ደስታ ይሰማኛል፤ በማያቸው ነገሮች እገረማለሁ፤ ትልቅ ታሪክ ያላቸው ሕዝቦች እንደነበሩና፤ እኔም የዚያ ታሪክ አባል እንደሆንኩ ይሰማኛል። " ቢሆንም ግን እንደ ዓለም ቅርስነቱና ታሪካዊነቱ በመንግሥትም ሆነ በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም) ትኩረት ተሰጥቶት የሚያስፈልገው ጥገናም ሆነ እንክብካቤ እየተደረገለት አይደለም ትላለች። የአደጋው ምክንያት? ቁምነገር እንደምትለው፣ በፋሲል ግንብ ቅጥር ግቢ ውስጥ በርካታ የሰርግ ሥነ ሥርዓቶች ይካሄዳሉ። ማህበረሰቡ ስለ ቅርስ በቂ ግንዛቤ ስለሌለው ብዙዎች ፎቶ ለመነሳት ግንቦቹ ላይ ይወጣሉ። ሰርጉን ምክንያት በማድረግም ይጨፍራሉ። ይህ ቅርሱን አደጋ ላይ የጣለው አንድ ምክንያት እንደሆነ ታስረዳለች። ለቅርሱ ደህንነት ሲባል ማንኛውም የሰርግ እንቅስቃሴ መቆም አለበት ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች። • "ቤቶቹ በማንኛውም ሰዓት ሊደረመሱ ይችላሉ" የሥነ ሕንፃ ባለሙያ የሆኑት አቶ ማሞ ጌታሁን ተማሪ ሳሉ ጀምረው የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥትን (የፋሲል ግንብን) ለማየት ጉጉት እንደነበራቸው ያስታውሳሉ። ሥራ ሲይዙ ባህልና ቅርሶችን የሚከታተል መሥሪያ ቤት ተመድበው በቀጥታ ወደ ቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ሥራ ገቡ። ከ1980ዎቹ ጀምሮ የፕሮጀክት ጥናቶችን አዘጋጅተዋል። በተጨማሪም ከሌሎች ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በአፄ ፋሲል፣ በእቴጌ ምንትዋብ ቤተ መንግሥት፣ በደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን፣ በአፄ ፋሲል መዋኛና ሌሎች በርካታ ቅርሶች ላይ ከሙሉ የጥገና ሥራ እስከ መለስተኛ እንክብካቤ ድረስ ሰርተዋል። አቶ ጌታሁን ቅርሱ የሚገኝበትን ሁኔታ ለማየት ጥናት መሥራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ፋሲልን በተደጋጋሚ ጎብኝተውታል፤ የወዳጅ ያህል ያውቁታል። በዚህ ልምዳቸው የከተማ መስፋፋትና ያለ በቂ ጥናት የሚሰሩ ጥገናዎች በቅርሱ ላይ ችግር ሲያስከትሉ ተመልክተዋል። ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት የሚሰጠው ትኩረት ማነስ፣ የበጀት እጥረት፣ የእንክብካቤና ጥገና ጊዜ መዘግየትንም እንደ ምክንያት ይጠቅሳሉ። የፋሲለደስ ግንብ የአሁን ይዞታ የሥነ ህንፃ ባለሙያው እንደሚሉት፣ በቅርሱ ጣራያ ላይ ከሚታዩ ችግሮች በተጨማሪ ግድግዳዎች ተሰነጣጥቀዋል፤ በቅርፁ የመንሸራተትና የመዝመም እክሎችም ገጥመውታል። በአእዋፋትና በእፅዋት እንዲሁም በሌላ ንክኪ መብዛት የተነሳ ተሸርሽሯል፤ ካቦቹም ወዳድቀዋል። የጎንደር ዓለም አቀፍ ቅርስ አስተዳደር አስተዳደሪ አቶ ጌታሁን ሥዩም በበኩላቸው "የፍቅር ቤተ መንግሥት ከተዘጋ ከ10 ዓመት በላይ ሆኖታል፤ የዮሐንስ ቤተ መንግሥትም እንዲሁ ተዘግቶ ነው ያለው፤ የታላቁ እያሱ ቤተ መንግሥትም ከፈረሰ በኋላ ጥገና አልተደረገለትም" ብለዋል። የዳዊት ቤተ መንግሥትና የአፄ በካፋ ቤተ መንግሥትም እንዲሁ አደጋ ላይ እንደሚገኙ ሌሎቹም በርካታ ስንጥቆች እንዳሉባቸው ገልፀዋል። በአንድና በሁለት ሴንቲ ሜትር ይለካ የነበረው ስንጥቅ አሁን ወደ 5 ሴንቲ ሜትር ሰፍቷል። በምስጥና በፈንገስ ምክንያት የእንጨት አካሎቻቸው እየተበሉና እየበሰበሱ ይገኛሉ። አስፈላጊው ጥገና ካልተደረገ የመውደቅ ወይም የመደርመስ አደጋ ማጋጠሙ ጥርጥር የለውም። የመኪና ንዝረትና ግጭትም ቅርሶቹን ይፈታተኗቸዋል። መፍትሔው ምንድን ነው? ጎብኚዎች፣ አስጎብኚዎች እንዲሁም ባለሙያዎች ያስቀመጧቸው የመፍትሔ ሀሳቦች ተመሳሳይ ናቸው። ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ቅርሱን የማዳንና የማቆየት ሥራ ሊሠሩ እንደሚገባ ይናገራሉ። ቅድሚያ የሚሰጠውን መለየት፣ ለቅርሱ ኃላፊነት ወስዶ የሚሠራን ሰው መመደብ፣ መገምገምና ክትክክል ማድረግ ይገባል። በቂ በጀት መመደብም ከመንግሥት ይጠበቃል ይላሉ። የቅርሶቹ የጉዳት መጠን በጥናት ታውቆ በቅርሱ አካባቢ የከባድ መኪኖችን እንቅስቃሴ መቆጣጠርም ያሰመሩበት ጉዳይ ነው። ምን እየተሠራ ነው? ለቅርሱ ጥበቃ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩ የሚናገሩት የጎንደር ዓለም አቀፍ ቅርስ አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ጌታሁን ሥዩም ናቸው። በከተማ አስተዳደሩ አቅም የሚቻሉ የጥገና ሥራዎች ተከናውነዋል ይላሉ። ከሁለት ዓመታት በፊት በነበረው ሀገራዊ ተቃውሞ ምክንያት የቱሪስት መቀዛቀዝ የታየ ቢሆንም አሁን ላይ በተሻለ ሁኔታ ጎብኚዎች ይመጣሉ። ይሁን እንጂ የቱሪስቶች የቆይታ ጊዜ አናሳ ነው። "የግማሽ ቀን ጉዞ የሚያደርጉ ጎብኚዎች በዝተዋል፤ ይህም ከመሰረተ ልማት ጋር የተገናኘ ነው" ይላሉ። • ከኢትዯጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት ሊመለሱ ነው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በየዓመቱ ከ1 ሚሊዮን ብር ያላነሰ በጀት ይመድባል። ከሌሎች ድጋፍ አድራጊዎች ጋር በጋራ በመሆንም ቅርሱን ከአደጋ ለመጠበቅ እየተሠራ እንደሆነ አቶ ጌታሁን ገልፀዋል። ቤተ መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን በውስጡ ያሉት ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ምን ያህል ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው? ንጽህናቸውስ ይጠበቃል? የሚሉ ጥያቄዎችም ይነሳሉ። አቶ ጌታሁን፣ እነዚህና ሌሎችም በርካታ መዋቅራዊ ችግሮች ካልተፈቱ ቅርሱ "አደጋ ላይ ነው" የሚለው ቃል አይገልፀውም ይላሉ። የአፄ ፋሲለደስ ቤተመንግሥት የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት በ1979 ዓ. ም. በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል። ቤተ መዛግብት፣ የአፄ ፋሲል መዋኛ፣ ቁስቋም ማርያም ራስ ግምብና ደረስጌ ማርያምን ያቀፈ ነው። በአፄ ፋሲለደስ ግንብ ውስጥ ያሉት ቤተ መንግሥቶች ከ100 በላይ ክፍሎች አሏቸው። ባለ ሦስትና ባለ አራት ፎቅ ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ 7 ሄክታር (70 ሺህ ስኩየር ሜትር) ይሸፍናሉ። ግንቡ የተሠራው ከ300-400 ዓመታት በላይ በኖረ የድንጋይ ካብ ሲሆን በዋናነት ድንጋይ፣ ኖራና እንጨት ጥቅም ላይ ውለዋል። በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች መሠራቱም ይነገርለታል። በአፄ ፋሲለደስ ግንብ ውስጥ ያሉት ቤተ መንግሥቶችን ልዩ የሚያደርጋቸው እያንዳንዱ ነገሥታት የራሳቸውን አሻራና ታሪክ ለትውልድ ትተው ማለፋቸው ነው። ቤተ መንግሥቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦ 1. የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት፡- ይህ ቀደምቱ ነው። ንጉሡ ቤተ መንግሥቱን ለማሳነፅ 10 ዓመታት ፈጅቶባቸዋል። 2. የአፄ ዮሐንስ ቤተ መንግሥት፡- አፄ ፋሲለደስ ለ36 ዓመታት ከነገሱ በኋላ ልጃቸው እሳቸውን ተክተው ወደ ስልጣን መጥተው ከ1667-1682 ዓ. ም. ሲነግሡ የተሠራ ነው። 3. የታላቁ አዲያም ሰገድ እያሱ ቤተመንግስት፦ የነገሡት ከ1682-1706 ዓ. ም. ነበር። ንጉሡ ጥሩ ፈረሰኛ ነበሩና በኮርቻ ቅርፅ የተሠራ ውብ ቤተ መንግሥት እንደተሰራ ታሪክ ያወሳራል። 4. የአፄ ዳዊት ቤተመንግስት፦ ለአምስት ዓመታት (ከ1716-1721 ዓ. ም.) ሲነግሡ ያሳነፁት ህንፃ ነው። ትልቅ የሙዚቃ ግንብ ያለው ሲሆን፣ ግንባር ቀደሙ የኪነ ጥበብ ማሳያ ህንፃ እንደሆነ ይነገራል። ጥቁር አንበሳ የሚባሉት አንበሶች መኖሪያ ይገኝ የነበረውም በዚህ ነበር። 5. የንጉሥ መሲሰገድ በካፋ ቤተ መንግሥት፦ ለዘጠኝ ዓመታት (ከ1721-1730) የነገሡ ሲሆን፣ የሳቸው ፍላጎት የነበረው ሕዝቡን ግብር የሚያበሉበት ትልቅ ሕንፃ መሥራት ነበር። ስለዚህም ከ250 በላይ ሰዎች መያዝ የሚችልና ፈረሶች የሚቆሙበት ቦታ ያለው ትልቅ የግብር አዳራሽ አሳነጹ። 6. የእቴጌ ምንትዋብ ቤተ መንግሥት፦ ከ1730-1755 ዓ. ም. የነገሡ ሲሆን፣ በጣና ገዳማት ላይም አሻራቸውን አሳርፈዋል።
news-41011744
https://www.bbc.com/amharic/news-41011744
ቡናን መጠጣት ካሉት ሌሎች ጠቀሜታዎች በተጨማሪ እድሜን ያረዝማል ይባላል
በእንግሊዝ አገር የሚገኝ አንድ የጥናት አሳታሚ ተቋም አዲስ የወጣ ጥናት መሰረት አድርጎ እንደጠቆመው በቀን ውስጥ ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት የጠጪውን እድሜ ላይ ለውጥ ያመጣል ይላል። በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ግን ጥናቱ አላስደሰታቸውም። የአንድ ግለሰብን ሌላ የህይወት ልምምድ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ፤ በቀን ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት ብቻውን እድሜን ያራዝማል ብሎ መደምደሙ ተቺዎቹ ጥናቱን በጥርጣሬ እንዲመለከቱት አድርጓቸዋል። ጥናቱ ምን አለ?
በኢንተርናሽናል የካንሰር ምርምር ኤጀንሲና በኢምፔሪያል ለንደን ኮሌጅ ጥምረት የተሰራው ይህ አዲስ ጥናት እንደገለጸው በቀን ውስጥ ቡናን በርከት አድርጎ መጠጣት በተለይ ከልብ እና ከአንጀት ጋር ተያይዞ የሚመጣን ሞት በእጅጉ ለመቀነስ ያስችላል። እዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እድሜያቸው ከሰላሳ አምስት ዓመት በላይ በሆኑ ከአስር የተለያዩ የአወሮፓ ሃገሮች የተወጣጡ ሰዎችን እንደናሙና መውሰድ አስፈልጓል። ተመራማሪዎቹ በጥናቱ ጅማሬ ላይ ለናሙና የተወሰዱትን ሰዎች የቡና አወሳሰድ መጠን ካጠኑ በኋላ በ16 ዓመት ሂደት አማካኝ የሞት መጠኑን ተከታትለዋል። አንድ ስኒ ቡና ምን ያህል እድሜ ይጨምራል? በዚህ አዲስ ጥናት ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ዴቪድ ስፒጌልሃልተር ሲያስረዱ በቀን አንድ ተጨማሪ ስኒ ቡና የሚጠጣ ወንድ እድሜው ላይ በአማካኝ በሶስት ወራት ያህል ሲጨምር ሴት ደግሞ በአንድ ወር ታራዝማለች። ምንም እንኳን ይህ አዲስ ጥናት በርካታ ባለሙያዎችን ያሳተፈና ዓመታት ፈጅቶ የተሰራ ቢሆንም ቡና እድሜን ማስረዘም አለማስረዘሙ ግን ሁሉንም ተመራማሪዎች እንዲስማሙበት አድርጎ አላቀረበም። እርስዎ የቡና አፍቃሪ ከሆኑ ከዚህ የሚቀጥለው ላያስደስቶት ይችላል። ጥናቱ አሻሚ መሆኑና ሌሎችን ከግምት ውስጥ መግባት የነበረባቸውን ማህበራዊና የጤና ጉዳዮችን ከግንዛቤ አለማስገባቱ የቡና ወዳጆችን ማደናገሩ አልቀረም። ለምሳሌ፤ ቡናን አብዝተው የሚጠጡ ሰዎች ገቢ ቡና ከማያዘወትሩት አንጻር ከፍተኛ ከሆነና የገቢያቸው ከፍ ማለት ለእድሜያቸው መጨመር አስተዋጽኦ ማበርከት አለማበርከቱ ጥናቱ ከግንዛቤ ያለመውሰዱ አንዱ ነው። በቀን አንድ ስኒ ተጨማሪ ቡና መጠጣት አድሜን በሶት ወር ያስረዝማል ሌላው ደግሞ ምናልባት ቡና አብዝተው የሚጠጡ በርካታዎች ጊዜያቸውን ከሰዎች ጋር በማሳለፋቸው ምክንያት ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነት ፈጥረው እድሜያቸውን ረዝሞ መሆን አለመሆኑን ጥናቱ ከግንዛቤ አላስገባም። በተጨማሪም ቡና እድሜን ከመጨመሩ ባሻገር ተጓዳኝ የጤና እክሎችን መፍጠር አለመፍጠሩ ጥናቱ አለማካተቱ ተቀባይነቱን ጥያቄ ውስጥ ከቶታል። ምክንያቱም በቅርቡ ሌሎች ተመራማሪዎች ቡና መጠጣትን ከሴቶች የማህፀን ካንሰር ጋር አያይዘውት እንደነበር አይዘነጋም። ከሁሉ በላይ ደግሞ የጥናት ወረቀቱ የስኳር እና የልብ ህመምተኞችን በናሙናነት አለመጠቀሙ፤ ቡና በመጠጣት ብቻውን እድሜ ይጨምራል ብሎ ለመደምደም እንዳንችል ያደርገናል ተብሏል። እውን ቡና ጠቃሚ ነው? ከዚህ ጥናት በፊት በቡና መጠጣት ላይ የተሰሩ ጥናቶች በሙሉ እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ናቸው። የቡና የማነቃቃት ሃይል የብዙ ቡና አፍቃሪዎች ልክፍተኛ መሆን ምክንያት እንደሆነ እሙን ነው። ነገር ግን በቡና ውስጥ ያለው ካፌይን የተባለው ንጥረ ነገር የማናቃቃት ሃይሉ ከሰው ሰው ይለያያል። የእንግሊዝ የጤና ባለሙያዎች ለአጠቃላይ ቡና ተጠቃሚዎች ቡና የመጠጣት ልኬት ባያወጡም ለነፍሰ ጡር ሴት ግን በቀን ከ200 ሚሊ ግራም በላይ የካፌይን መጠን በቀን እንዳትወስድ ያስጠነቅቃሉ። ምክንያቱንም ሲያስረዱ የሚወለደው ጨቅላ የክብደት መጠን ከሚጠበቀው በታች ከማድረግ አልፎ አንዳንዴም ጭንገፋን ሊያስከትል ይችላል ይላሉ። ካፌይን የተባለው ንጥረ ነገር ግን ከቡና አልፎ በሌሎችን መጠጦች ውስጥ መገኘቱ ጉዳዩን አከራካሪ ያደርገዋል። ለምሳሌ 200 ሚ.ግ ካፌይንን በሁለት ማግ የሻይ ብርጭቆ ውስጥ እና አንድ ጠርሙስ ኮላ መጠጥ ውስጥ በቀላሉ ይገኛል። አሜካዊቷ ታዳጊ በተከታታይ የካፌይን ንጥረ ነገር ያለውን መጠጥ በመውሰዷ ህይወቷ ማለፉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ታዲያ ቡና እድሜ እንደሚጨምር በምን እርግጠኛ መሆን እንችላለን? ቡና እድሜ መጨመር አለመጨመሩን በሳይናሳዊ ምርምር እርግጠኛ ለመሆን የናሙና መጠኑን ማብዛት ጥሩ አማራጭ ነው። ይህም ከሁሉም የዓለም ክፍሎች የተወጣጡ በሚሊዩን የሚቆጠሩ ሰዎችን በናሙናነት በማሳተፍ እያንዳንዷን የህይወታቸው ክፍል ማጥናት የግድ ይላል። ይህም የሚበሉትና የሚጠጡትን፥ የገቢያቸውን ሁኔታ እንዲሁም ስፖርታዊ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ እና አለማድረጋቸውን ሁሉ ግምት ውስጥ አስገብቶ ማጥናት ማለት ነው።እንደዚህ አይነት ጥናት አይታሰብ ከተባለ ደግሞ አዋጭ እና ሁሉም ተመራማሪወች የተስማሙበት እድሜን መጨመሪያ ዘዴ መፈጸም ግድ ይልል። በቀን ለ20 ደቂቃ ያህል የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ።
50922448
https://www.bbc.com/amharic/50922448
በምሥራቅ ሐረርጌ የቢላል መስጂድንና ራጉዔል ቤተ ክርስትያንን የሚያሰሩት ካህን
መላዕከ ሕይወት ቆሞስ አባ አክሊለ ማርያም፣ በምሥራቅ ሐረርጌ በቀርሳ ወረዳ የላንጌ ቅዱስ ራጉዔል ቤተ ክርስትያንና የቢላል መስጂድን ያሰራሉ።
"ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ብሆንም ለአንድ ሐይማኖት ብቻ ብቆም እግዚአብሔርን ራሱ ያሳፍረዋል" የአገልግሎት ስፍራቸው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንዳፋ በኬ ማርያም መሆኑን የሚናገሩት ካህን በምሥራቅ ሐረርጌ የሚገኝ መስጂድንና ቤተ ክርስቲያንን በእኩል ቆመው ያሳንጻሉ። የሚያገኛቸውን ሙስሊምና ክርስቲያን በእኩል ለቤተ እምነቶቹ ማሰሪያ ሲጠይቁ ግር ይል ይሆናል። እርሳቸው ግን ታሪክ አጣቅሰው ከቅዱሳት መጻህፍት አመሳክረው ኃላፊነታቸው የሁሉም ምዕመናን፤ በሙስሊሙም በክርስቲያኑም ወገን፤ መሆን እንዳለበት ያስተምራሉ። ከምሥራቅ ሐረርጌ መምጣታቸውን የሚሰማ የመጀመሪያ ጥያቄው በአካባቢው የሚገኙ ክርስትያኖችና አብያተ ክርስትያናት ሁኔታን ነው። እርሳቸው ደግሞ የላንጌ አካባቢ ሕዝብን ፍቅር ተናግረው አይጠግቡም። • በመስጅዶች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሄዱ • 'ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ' በ2007 ዓ.ም ሐረር የቁልቢ ገብርዔል ገዳምን ለመሳለም በሄዱበት ወቅት ከቁልቢ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የላንጌ ቅዱስ ራጉዔል ቤተ ክርስትያንን መመልከታቸውን ያስተውላሉ። በአካባቢው ያሉ ክርስትያኖች ኑሯቸው ከእጅ ወዳፍ መሆኑን አካባቢው ዝናብ አጠር በመሆኑ የዓመት ቀለባቸውን በዓመት አንዴ የሚጥለውን ዝናብ ጠብቀው እንደሚያመርቱ ይረዳሉ። • "በጎጃም ማርያም ቤተክርስቲያን ለመስጊድ 3ሺ ብር ረድታለች' ተባልኩኝ" ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የአካባቢው ክርስትያኖች የሚያመልኩበት ቤተ ክርስትያን ደግሞ እርጅና ተጭኖት እየፈረሰ ነው። ስለዚህ እዚያው ቆይተው ለማሰራት ይወስናሉ። በዚያ ቆይታቸው በከተማዋ ውስጥ የሚገኘውን ላንጌ ቢላል መስጂድ ተመለከቱ። የቤተ ክርስቲያኑም ሆነ የመስጂዱ መልክ የአካባቢው ማህበረሰብን ይመስላል። የገንዘብ አቅም በሌለበት አካበባቢ ቤተ እምነቶችም ድሃ ናቸው። ሲፈርሱ የሚያስጠግን ቢያዘሙ የሚያቀና ይቸግራል። አባ አክሊለ ማርያም የላንጌ ቅዱስ ራጉዔል ቤተክርስትያንን አዲስ አበባና አካባቢዋ ከሚገኙ ክርስትያን ወገኖች ገንዘብ በመጠየቅ እያሰሩ ግንባታውም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን አስተዋሉ። በምሥራቅ ሐረርጌ ለሚገኘው የላንጌ ቢላል መስጂድ አንድ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ በ500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የቤተ ክርስትያን ሕንጻ እንዲሁም በቅጽር ግቢው ውስጥ ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንጻዎች ተሰርተዋል። ይህንን እያሰሩ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቢላል መስጂድን ተመለከቱ። መስጂዱ በሚገባ አልታነጸም፤ እድሳት ይፈልጋል። በአካባቢው የሚገኙ ሙስሊሞችን አገኙ። በአካባቢው ያሉ ሙስሊም ወገኖች ኑሮ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ተመሳሳይ ነው። ክርስትያኖችና ሙስሊሞች በአካባቢው በተመሳሳይ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ነው የሚኖሩት። ሁለቱም ሰማይ ቀና ብለው አይተው፣ መሬት የሰጠቻቸውን ለቅመው የሚኖሩ አርሶ አደሮች ናቸው። አባ አክሊለ ማርያም ሰዎች ለእናንተ እንዲያደርጉላችሁ የምትሹትን፣ እናንተም አድርጉላቸው የሚለውን መንፈሳዊ ቃል በመከተል እርሳቸውም መስጂዱን ለማሰራት መወሰናቸው ይናገራሉ። የቅዱስ ራጉዔል ቤተ ክርስቲያን በእምነበረድ ታንጾ ከጎኑ የቢላል መስጂድ በእድሳት እጦት አዝሞ ማየት አልሆነላቸውም። በእምነት ክርስትያን ቢሆኑም ከክርስትና አስተምህሮ መካከል አንዱ የሆነው የሰው ልጅን በሙሉ በእኩል ማገልገል በመሆኑ መስጂዱንም ለማሰራት መወሰናቸው ይናገራሉ። • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች በዚህም የተነሳ ለእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ማመልከቻ በመጻፍ ለሙስሊም ወንድሞችም መስጂድ ለማሰራት እንደሚፈልጉ ጠየቁ። የእስልምና ጉዳዮችም እንዲህ አይነቱ ተግባር በኢትዮጵያ ውስጥ እስልምና በገባ ወቅት የነበረ መሆኑን በማስታወስና በማድነቅ የድጋፍ ደብዳቤ ለአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች እንደጻፉላቸው ይናገራሉ። የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች በበኩሉ በአዲስ አበባ ለሚገኙ መስጂዶች በአጠቃላይ የድጋፍ ደብዳቤ ከጻፈላቸው በኋላ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ገንዘብ ማሰባሰባቸውን ይናገራሉ። በምስራቅ ሐረርጌ የሚገኘው ቅዱስ ራጉዔል ቤተክርስትያን አባ አክሊለ እንደሚናገሩት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከአዲስ አበባ የሙስሊም ማህበረሰብ በተሰበሰበ ገንዘብ በላንጌ የሚገኘው መስጂድን መሰረት የማስገንባት ሥራ ተከናውኗል። ይህንን ተግባራቸውን ማከናወን የጀመሩት መስከረም 2011 ዓ.ም ላይ ሲሆን ደብዳቤ ተጽፎላቸው ወደ ሥራ የገቡት ደግሞ ጥቅምት 2/2011 ዓ.ም መሆኑን ያስታውሳሉ። እርዳታ የማሰባሰብ ሥራውን የጀመሩት ፒያሳ ከሚገኘው ኑር መስጂድ መሆኑን የሚናገሩት አባ አክሊለ፤ የመስጂዱ የበላይ ጠባቂና አስተዳዳሪ ኡስታዝ መንሱር ከፍተኛ ድጋፍ እንዳደረጉላቸው ይገልፃሉ። አባ አክሊለ በላንጌ የሚገኘውን መስጂድ ሲያሰሩም ሆነ ቤተ ክርስቲያኑ ሲያስገነቡ በእኩል ክትትል እንደሚያደርጉ ገልፀው ቤተ ክርስቲያኑ ፎቅ ስለሆነ መስጂዱም ፎቅ መሆን አለበት በሚል ሀሳብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። • በሞጣ የተፈጠረው ምንድን ነው? መስጂዱ የምድር ቤት ግንባታው ተሰርቶ መጠናቀቁንና የላይኛውን ክፍል ግንባታ ለማስጀመር ገንዘብ አጥሮ በድጋሚ የእርዳታ ድጋፍ ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ከሚገኙ የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ገንዘብ እያሰባስቡ እንደሆነ ይናገራሉ። እርሳቸው ክርስቲያን ሆነው መስጂዱን ለማስገንባት በእምነት ገንዘባቸውን የሚሰጡ ሙስሊሞች መኖራቸው የሚያሳየው ምን እንደሆነ አባ አክሊለ ሲናገሩ፣ ዛሬም በሕዝቦች መካከል ያለ መተሳሰብና አብሮ የመኖር ባህል ጠንካራ መሆኑን ነው ይላሉ። ለሰሚም ሆነ ለተመልካች የእርሳቸው ድርጊት ኢትዮጵያና እስልምና ያላቸውን ግንኙነት እንደሚያሳይ በመግለጽ፣ ሙስሊሞች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት የተደረገላቸው መልካም አቀባበል ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ በርካታ ትምህርት እንደሚሰጥ ያስረዳሉ። መላዕከ ሕይወት ቆሞስ አባ አክሊለ ማርያም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በቀርሳ ወረዳ ላንጌ ከተማ ለሚያሰሩት ቢላል መስጂድ ገንዘብ ለማሰባሰብ የድጋፍ ደብዳቤ ተጽፎላቸዋል በኃይማኖትም መጻህፍት ያለው መንፈሳዊ ቃል ብቻ ሳይሆን ሕብረተሰቡ በመኖር የገነባነው መዋደድና አብሮ የመኖር ባህል ለዚህ ተግባር ጠንካራ አጋዥ እንደሆናቸው ይናገራሉ። በድርጊታቸው የሚያገኟቸው ሰዎች ደስተኛ መሆናቸውን በማንሳትም እርሳቸውም በሙስሊም ወንድሞቻቸው ተግባር ልባቸው መነካቱን ይገልጻሉ። "ሰው ሊደሰት የሚችለው ሰውን ሲያገለግል ነው" በማለት በመስጂድ የሚያደርጉትም አገልግሎት ደስታን እንደሚሰጣቸው ያስረዳሉ። "ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ብሆንም ለአንድ ሐይማኖት ብቻ ብቆም እግዚአብሔርን ራሱ ያሳፍረዋል" በማለት ሁሉን በእኩል ማገልገል ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አባል የሆኑት ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ስለመላዕከ ሕይወት ቆሞስ አባ አክሊለ ማርያም ሲናገሩ "በካህኑ ጥያቄ መሰረት የድጋፍ ደብዳቤ ጽፈንላቸዋል። እስካሁንም ከመቶ ሺህ ብር በላይ ለመስጂዱ ግንባታ ተሰብስቧል" ሲሉ መስክረዋል። የእርሳቸውንም ተግባር በተመለከተ ሲያስረዱ "ይህ በጎ ድርጊት የሚያሳየን ሁሌም ሕዝቡ አንድ መሆኑንና ሳይለያይ ለመደጋገፍና ለመረዳዳት ያለውን ጽኑ ፍላጎት ነው" ብለውናል። በምሥራቅ ሐረርጌ በቀርሳ ወረዳ የላንጌ ቅዱስ ራጉዔል ቤተ ክርስቲያን ባለሁለት ፎቅ ሕንፃው ማለቁን፣ ቤተክርስቲያኑም ጉልላቱ ላይ መድረሱን አጥሩም መሰራቱን ይናገራሉ። መስጂዱም አልቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ጠንክረው እንደሚሰሩ ይገልፃሉ። ምሥራቅ ሐረርጌ በቀርሳ ወረዳ እና በኩርፋ ጨለኬ ወረዳዎች የነበሩ ግጭቶችንና ስጋቶችን በማንሳትም በላንጌ ህዝበ ሙስሊሙ ከክርስቲያኑ ጎን በመቆም አብሮ የመኖር ባህሉንና ትስስሩን ጠብቆ ይህንን ወቅት ማለፉን ያስረዳሉ። በከተማው የሚገኙ ነዋሪዎችና ቤተ ክርስቲያናትን በጽኑ ተጋድሎ ከጥቃት መከላከላቸውን ይመሰክራሉ። በምሥራቅ ሐረርጌ በቀርሳ ወረዳ የላንጌ ራጉዔል ቤተ ክርስትያንና የቢላል መስጂድን በአንድነት የሚያሰሩት ካህን
news-56859880
https://www.bbc.com/amharic/news-56859880
የዘር ጭፍጨፋ ወይም ጄኖሳይድ ምንድን ነው?
የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) ድርጊት እጅግ ከፍተኛው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ነው። አንድ ቡድን ላይ አነጣጥሮ በርካታ አባላቱን መፍጀት በሰው ልጆች ታሪክ አሰቃቂ ጠባሳ ትቶ ያለፈባቸው ወቅቶች በክፉ ይታወሳሉ።
በ1940ዎቹ (እአአ) ናዚዎች አይሁዳውያንን በጅምላ የጨፈጨፉበት ወቅት ይጠቀሳል። ከሕግ ትርጓሜ አንጻር የዘር ማጥፋት የሚባሉት ምን አይነት ጭፍጨፋዎች ናቸው? የሚል ጥያቄ ይሰነዘራል። የዘር ማጥፋት የሚለው አገላለጽ የሚሠራው በየትኞቹ ሁኔታዎች ነው? የሚለውም እንዲሁ። የዘር ጭፍጨፋ ወይም በእንግሊዘኛው ጄኖሳይድ [Genocide] የሚለው ቃል፤ እንደ አውሮፓውያኑ በ1943 በአይሁድ ፓላንዳዊው ጠበቃ ዶ/ር ራፋኤል ለምኪን ነው ጥቅም ላይ የዋለው። ቃሉ የግሪኩ ጄኖስ [Genos] እና የላቲኑ ሳይድ [Cide] ቃላት ጥምረት ነው። ጄኖስ ዘር ወይም ብሔር ማለት ሲሆን ሳይድ ደግሞ ግድያን ያመለክታል። ከአንድ ወንድሙ ውጪ መላ ቤተሰቡን በአይሁዳውያን ላይ በተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ (ሆሎኮስት) ወቅት ያጣው ዶ/ር ራፋኤል፤ የዘር ጭፍጨፋ በዓለም አቀፍ ሕግ ወንጀል ተብሎ እንዲመዘገብ ንቅናቄ አድርጓል። ንቅናቄው፤ የተባበሩት መንግሥታት የዘር ጭፍጨፋን በሚመለከት ስምምነት ላይ እንዲደርስ አስችሏል። ይህ የሆነው በአውሮፓውያኑ በ1948 ሲሆን፤ ስምምነቱ መተግበር የጀመረው ከሰኔ 1951 ወዲህ ነው። የስምምነቱ ሁለተኛ አንቀጽ የዘር ጭፍጨፋን የሚተረጉመው "የአንድ አገር፣ ብሔር፣ ዘር ወይም ሐይማኖት አባላትን ሙሉ በሙሉም ይሁን በከፊል ለማጥፋት የተቃጣ" ብሎ ነው። ይህም የአንድ ቡድን አባላትን መግደል፣ ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እንዲሁም ሥነ ልቦናዊ ጥቃት ማድረስን ያካትታል። በተጨማሪም የቡድኑ አባላት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ማሴር፣ የቡድኑ አባላት ልጆች እንዳይወልዱ ማድረግ እና ልጆችን በግዳጅ ወደ ሌላ ቡድን መውሰድን ያካትታል። የተባበሩት መንግሥታት ስምምነትን የተቀበሉ አገራት የዘር ጭፍጨፋን የመግታት እና የዘር ጭፍጨፋ ሲፈጸም የመቅጣት ግዴታ አለባቸው። በእርግጥ ይህ የተባበሩት መንግሥታት ስምምነት ከጸደቀ በኋላ የተለያዩ ትችቶች ተሰንዝረውበታል። በዋነኛነት የቀረበው ቅሬታ ስምምነቱን በልዩ ሁኔታዎች ውስጥ ለመተግበር አስቸጋሪ መሆኑ ነው። የዘር ጭፍጨፋ ትርጓሜ ጠባብ ነው ብለው የሚተቹ አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የዘር ጭፍጨፋ የሚለው ገለጻ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ መዋሉ ቃሉ ዋጋ እንዲያጣ አድርጎታል የሚል መከራከሪያ ይነሳል። ሴሬብሬኒሳ ውስጥ የተገደሉ ከሰባት ሺህ በላይ ሙስሊሞች ስም ዝርዝር ይህንን ስምምነት በተመለከተ የሚነሱ ትችቶችን በዝርዝር እንመልከት፦ ከላይ የተሰነዘሩት ትችቶች እንዳሉ ሆነው፤ የዘር ጭፍጨፋ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው የሚል ነጥብ የሚያነሱ አሉ። ስለ ሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ መጽሐፍ ያሳተሙት አለን ደስታቼ "የዘር ጭፍጨፋ ከሌሎች ወንጀሎች የሚለየው በኢላማው ነው" ይላሉ። የዘር ጭፍጨፋ ከሌሎች ሰብዓዊ መብትን የሚጥሱ ወንጀሎች የሚለየው አንድን ቡድን ለማጥፋት ታስቦ የሚደረግ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። "የዘር ጭፍጨፋ እጅግ የከፋ ወንጀል ነው" በማለትም ያክላሉ። ቃሉ ጥቅም ላይ የሚውልባቸው ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው? የሚለው ላይ ግን ጥያቄ አላቸው። በተመሳሳይ ጥያቄ የሚነሳበት ቃል "ፋሺስት" ነው። በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሰብዓዊ መብት ፖሊሲ ማዕከል የቀድሞ ዳይሬክተር ማይክል ኢግናቲፍ ቃሉ ሁሉንም አይነት ጥቃቶች ለመግለጽ ሲውል እንደሚስተዋል ይናገራሉ። "ለምሳሌ ባርነት የዘር ጭፍጨፋ ነው ይባላል። ባርነት የሚኮነን ድርጊት ሲሆን፤ ሰዎችን የማጥፋት ሳይሆን የመበዝበዝ ሥርዓት ነበር" ይላሉ። ምን ያህል የዘር ጭፍጨፋዎች ተፈጽመዋል? የዘር ጭፍጨፋን የተመለከቱ የተለያዩ ትርጓሜዎች አሉ። ይህ ልዩነት በ20ኛው ክፍለ ዘመን ምን ያህል የዘር ጭፍጨፋ ተፈጽሟል? የሚለው ላይ አለመስማማትን ፈጥሯል። ባለፈው ምዕተ ዓመት የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ ሆሎኮስት ብቻ ነው የሚሉ አሉ። በሌላ በኩል የ1948ቱን የተባበሩት መንግሥታት ስምምነት በመጥቀስ ሦስት የዘር ጭፍጨፋዎች ተፈጽመዋል ይባላል። እነዚህ ሦስት የዘር ጭፍጨፋዎች ከ1915 እስከ 1920 በኦቶማን ቱርክ፤ አርመናውያን ላይ የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ፣ ከስድስት ሚሊዮን በላይ አይሁዳውያን የተፈጁበት ሆሎኮስት እና ወደ 800,000 ቱትሲዎችና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተፈጁበት የ1994ቱ የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ናቸው። በቅርቡ የዘር ጭፍጨፋ ተብለው የተመዘገቡም አሉ። አንደኛው በ1995 በቦስንያ የተፈጸመው ነው። የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ ዓለም አቀፍ የወንጀል ልዩ ፍርድ ቤት ነው የዘር ጭፍጨፋ ብሎ የፈረጀው። ሌላው በዩክሬን ከ1932 እስከ 1933 በሶቭየት አማካይነት የተከሰተው ሰው ሠራሽ ረሀብ ነው። የ1975ቱ ኢንዶኔዥያ በምሥራቅ ቲሞር ላይ የጸፈመችው ወረራ፣ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች በግድያ፣ በረሀብና በጉልበት ብዝበዛ ያለቁበት የ1970ዎቹ የካምቦዲያ በኬምር ሩዥ የተፈጸመው ግድያ ይጠቀሳሉ። እነዚህ ካምቦዲያውያን ኢላማ የተደረጉት በፖለቲካዊ አቋማቸው ወይም ማኅበረሰቡ ውስጥ ባላቸው ቦታ ነው የሚለው ብዙዎችን ያከራክራል። ይህ ማለት ደግሞ ግድያውን ከተባበሩት መንግሥታት የዘር ጭፍጨፋ ትርጓሜ ውጪ ያደርገዋል ማለት ነው። ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንደ በአውሮፓውያኑ 2010 በቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። ሰባት ዓመታት በፈጀ ውጊያ በአገሪቱ የዳርፉር ግዛት ውስት 300,000 ሰዎች መሞታቸውና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በመፈናቀላቸው ሳቢያ አልበሽር በዘር ጭፍጨፋ ተከሰዋል። በ2016 አሜሪካ፤ ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) በኢራቅ እና ኢራን ባሉ ክርስቲያኖች፣ ያዚዲዎችና የሺአ ማኅበረሰብ አባላት ላይ የዘር ጭፍጨፋ ፈጽሟል ስትል ከሳለች። የዚያን ጊዜው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ "አይኤስ በመርህ፣ በተግባርና ለራሱ በሰጠው ስም መሠረት ዘር አጥፊ ነው" ብለዋል። በ2017 ጋምቢያ ለዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት ያስገባችው ክስ ሚያንማር፤ በሮሂንጋ ሙስሊሞች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ፈጽማለች ይላል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሮሂንጋ ሙስሊሞች ከሚያንማር ሸሽተው ባንግላዲሽና ሌሎችም አገሮች ተጠልለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ መገደላቸውም ተዘግቧል። በ2021 አሜሪካ፣ ካናዳ እና ኔዘርላንድስ በአንድነት ቻይና፤ በዢንዣንግ ውስጥ የዊጋ ማኅበረሰብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ ፈጽማለች ሲሉ ከሰዋል። ሌሎች አገራትም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤታቸው አማካይነት ተመሳሳይ ክስ አሰምተዋል። ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት ቻይና፤ የዊጋ ማኅበረሰብን በግዳጅ በማምከን፣ በጅምላ በማገት፣ ጉልበት በመበዝበዝ፣ በመድፈርና በማሰቃየት ጥቃት አድርሳለች። እነዚህ ጥቃቶች የዘር ጭፍጨፋ የሚባሉ ቢሆንም ቻይና ክሱን አጣጥላለች። በኬምር ሩዥ የተገደሉ ሰዎች መታሰቢያ ሙዚየም የዘር ጭፍጨፋ የፍርድ ሂደት በዘር ጭፍጨፋ በግንባር ቀደምነት ፍርድ ቤት የቀረበው ሁቱ እና የሩዋንዳዋ ታባ ከተማ ከንቲባ የነበረው ዣን ፖል አካይሱ ነበር። ጉዳዩን የዳኘው ልዩ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መስከረም 2/1998 ግለሰቡን በዘር ጭፍጨፋና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች ፈርዶበታል። ፍርድ ቤቱ በሩዋንዳ ጉዳይ ፍርድ ያሳለፈው 85 ሰዎች ላይ ሲሆን፤ ከእነዚህ 29ኙ የተፈረደባቸው በዘር ጭፍጨፋ ነው። 2010 ነሐሴ ላይ ሾልኮ የወጣ የተባበሩት መንግሥታት ሰነድ እንደሚያሳየው፤ ጥቃት ፈጻሚዎቹ የሩዋንዳ ሁቱዎች ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶባቸዋል። በ2001 የቀድሞው የቦሲኒያ ጄነራል ራዲስላቭ ክርስቲች በዓለም አቀፉ ልዩ የወንጀል ችሎት የተፈረደበት የመጀመሪያው ሰው ሆኗል። ጄነራሉ አቤቱታ ያሰማው "የሞቱት ሰዎች ቁጥር 8,000 ነው። ይህም የዘር ጭፍጨፋ አያስብለውም" ብሎ ነበር። 2004 ላይ ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን ውድቅ አድርጎታል። በ2007 የቀድሞው የቦሲኒያ ሰርብ ኮማንደር ራትኮ ምላዲች በዘር ጭፍጨፋ፣ በጦር ወንጀል እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከሶ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል። ይህ ግለሰብ "የቦሲኒያው ጨፍጫፊ" በሚል ይጠራል። በ2018 ከኬምእ ሩዥ ግድያ ጋር በተያያዘ የ92 ዓመቱ ኑዎን ቺያ እና የ87 ዓመቱ ኪው ሳምፒን በዘር ጭፍጨፋና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከሰው የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል።
news-48242586
https://www.bbc.com/amharic/news-48242586
የእናቶች ቀን፡ ያለ እናት የመጀመሪያው የእናቶች ቀን
ስለ እናት ፍቅር ለመግለፅ ቃላት ያጥረናል የሚሉት በርካቶች ናቸው። የእናትን ፍቅር ግዝፈቱንና በቃላት የማይገለፅ መሆኑን ለማሳየት። ስለ እናት ብዙ ተዚሟል፤ ተገጥሟል፤ ተነግሯል። ወደፊትም ይቀጥላል ... ዛሬ የእናቶች ቀን ነው። ይህ ቀን እናታቸው ከጎናቸው ላሉት ደስታ፤ በሕይወት ለተለየቻቸው ደግሞ ሃዘን ፈጥሮ ያልፋል።
ሻረን እናቷን ያጣችው በቅርቡ ነው • የልጃቸውን ደፋሪ የገደሉት እናት ነጻ ወጡ ለመሆኑ እናታቸው በሞት ከተለየቻቸው በኋላ የእናቶችን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ያከብሩታል? ምንስ ይሰማቸዋል? "የእናቶች ቀን ባይመጣ ደስ ይለኛል" የምትለው የለንደኗ ነዋሪ ሻረን ዱሳርድ ናት። ሻረን እናቷን ሎሬንን በሞት ካጣች ገና አስር ሳምንታት ብቻ ናቸው የተቆጠሩት። በመሆኑም የእናቶች ቀን ደንታም አይሰጣት። እናቱን ላጣ ሰው የእናቶች ቀን የተለየ ትርጉም አለውም ትላለች። "ሃዘናችሁን ለመቋቋም ስትታገሉ፤ ቀኑን አስመልክቶ በየማሕበራዊ ሚዲያው ላይ የሚለጠፉ ፎቶግራፎችና የሚተላለፉ መልዕክቶች ይጎርፋሉ፤ ይህንን ምንም ማስወገድ አይቻልም።" ትላለች። እርሷ እንደምትለው ይህ ብቻም ሳይሆን በየሱቆቹ የሚሸጡ የስጦታ ካርዶች፣ አበቦች እና ስጦታዎች አብራችሁ ስለሌለች እናት እንድታስቡና እንደታከብሩ ይገፋፋል። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ "ይህ ቀን መምጣቱን ሳስብ በጣም ይጨንቀኛል፤ ምን እንደማደርግ ይጠፋኛል ፤ ማሕበራዊ ገፄን ለመዝጋትም አስባለሁ" ትላለች ሻረን። የ28 ዓመቷ ሻረን እንደምትለው በርካታ ሰዎች ስሜቷን ለመጠበቅ ሲሉ ከእርሷ ጋር ስለ እናቶች ቀን ማውራታቸውን ትተዋል። ነገር ግን ለአንድ የራዲዮ ጣቢያ በሰጠችው ቃለ-መጠይቅ ሰዎች ቀኑን በማሰብ ብቻ መልዕክት ቢልኩላት እንደማይከፋት ተናግራለች። "ዋናው ነገር ሰዎች መጠየቀቻውና ደህንነቴን ማረጋገጣቸው ነው፤ እርሱን ደግሞ እፈልገዋለሁ" ስትልም አክላለች። "እናቴ የተጠበሰ ሥጋ ትወዳለች፤ እርሱን እንሠራለን፤ እርሷን የምናስብበትና ፍቅራችንን የምንገልፅበት ቀን ነው ፤ ላለማልቀስ እሞክራለሁ" ስትል ቀኑን እንዴት ልታሳልፈው እንዳሰበች ገልፃለች። ክሪስቲ እና እናቷ ማንዲ ሌላኛዋ ቢቢሲ ያነጋገራት ክሪስቲ ናት። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የክሪስቲ እናት ከዚህ ዓለም የተለየችው በድንገት ነበር። እርሷ እንደምትለው በዚህ ቀን በስጦታዎችና በስጦታ ካርዶች መከበብ ለእርሷ በጣም ከባድ ነው።" በየዓመቱ የስጦታ ካርድ እሰጣታለሁ፤ ካርዶቹ የሚያስቁ ነበሩ፤ ሌላ ስጦታ ገዝቼላት አላውቅም" ስትል ታስታውሳለች። ክሪስቲ የማህበራዊ ሚዲያው እንደረዳት ትናገራለች ምክንያቱም እናታቸውን በቅርቡ ያጡ ሰዎች እዚያ ላይ አሉ፤ እነርሱን ስታይም ብቻዋን እንዳልሆነች ይሰማታል። እርሷ እንደምትለው አንዳንድ ሰዎች በእርሷ ሃዘን ምክንያት ደስታቸውን ለመደበቅ ይሞክራሉ። እርሷ ግን ይህንን አትፈልገውም። • ካለሁበት 16 ፡ 'ጭራሹኑ መጥፎ ነገሮች እንዳይከሰቱ ማድረግ ብችል ደስታዬ ወደር የለውም' "ርዕሱን አትለውጡት ምክንያቱም እናንተ የእራሳችሁ እናት አለች ፤ እራሳችሁን ደስተኛ አድርጉ" ስትል በእርሷ ምክንያት ሌሎች ሰዎች በስሜት ሲመሰቃቀሉ ማየት እንደማትወድ ገልፃልናለች። ሳራ ቤኔት በሃዘን ላይ ያሉ ሕፃናት፣ ወጣቶችንና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዳ ግብረሰናይ ድርጅት ውስጥ ትሠራለች። እርሷ እንደምትለው "እናታችሁን ካጣችሁ የመጀመሪያው የእናቶች ቀን ከሆነ ሁሉም ነገር ይቀየራል፤ እናት ስትሞት ቀሪው ቤተሰብ በዚህ ቀን ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም፤ ምንስ ሊያደርጉስ ይችላሉ?" ጥያቄዋ ነው። እርሷ እንደምትለው አንዳንዶች በሕይወት የሌለች እናታቸውን በማስታወስ ያከብሩታል፤ ሌሎች ግን ጭራሽኑ ስለ ቀኑ ማሰብ አይፈልጉም። በመሆኑም ትላለች ሳራ "በጣም ከባድ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፤ ለቤተሰብና ለወዳጅ ዘመድም ስለ እሷ ማሰብ ምን ያህል ፈታኝ እንደሚሆን መገንዘብ ይጠይቃል" ቁጭ ብላችሁ እራሳችሁን አዳምጡ። እናትን ማጣት ምን ያህል አንገብጋቢ እንደሚሆን ማሰብ ቀላል ነው ስትል ስሜቷን አጋርታለች።
46683639
https://www.bbc.com/amharic/46683639
"ህልም ያላቸው ወጣቶች ድህነትን ከላያቸው ላይ ነቅለው መጣል ይችላሉ" የጠብታ አምቡላንስ ባለቤት
ከ20 ዓመት በላይ ከባሌ- ጊኒር እስከ ጥቁር አንበሳ በመንግሥት ሥራ ተቀጥረው ሠርተዋል፤ ከነርስነት እስከ አኔስቴዢያ ባለሙያነት (የማደንዘዣ ህክምና) አገልግለዋል። አቶ ክብረት አበበ የሥራ ሕይወት የጀመረው እንዲህ ነው።
አቶ ክብረት የመጀመሪያው የግል አምቡላንስ ጠብታን የመሰረቱ ግለሰብ ናቸው። ለ17 ዓመታት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በማደንዘዣ ህክምና ክፍል ውስጥ ሲሰሩ ያዩት ነገር ጠብታን በውስጣቸው እንዲፀንሱ አደረገ። ይሰሩበት የነበረው ጥቁር አንበሳ በአዲስ አበባ መሃል ላይ የሚገኝ ትልቅ ሆስፒታል ነው፤ ማንም ሰው ታሞ ከጥቁር አንበሳ የሚቀር አይመስልም ነበር። • «ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ ወደዚህ ስሙም አገልግሎቱም የገዘፈ ሆስፒታል መኪና የገጨው፣ ደም የሚፈሰው፣ መተንፈስ የተቸገረ ወዘተርፈ ሁሉ ይመጣል። "ማንም ሰው አጠገቡ ሌላ ሆስፒታል ቢኖር እንኳ ጥቁር አንበሳ የመጀመሪያ ምርጫው ይመስል ነበር" ይላሉ የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውሱ። በ2001 ዓ. ም. የወጣ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በየ10 ሺህ መኪናው 194 ሞት ይከሰታል። የመኪና ፈጣሪና ፈብራኪዎች ጃፓኖች ጋር ግን በ20 ሺህ መኪኖች አንድ ሰው ብቻ በመኪና አደጋ ይሞታል። ከሁሉም የከፋው ይላሉ አቶ ክብረት፤ "የተገጨው ግለሰብ በታክሲ ወይም በገጨው መኪና ወንበር ላይ የወሳንሳ አንስተው ጭነውት እያርገፈገፉ መማምጣታቸው ነው"። ሕክምና የሚጀመረው ሆስፒታል አይደለም መኪኖቹን አምርተው የላኩት ሳይሞቱ የእኛ የተቀባዮቹ ሞት የሚያሳየው ጥንቃቄ እንደጎደለን ነው የሚሉት አቶ ክብረት፤ እንዴት መኪና አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ማትረፍ እችላለሁ? የሚለው ጥያቄ ለሥራቸው መነሻ እንደነበር አይዘነጉም። በድንገተኛ አደጋ ወደ ሆስፒታል የሚሄድ ሰው በቀጠሮ ወደ ሆስፒታል እንደሚሄድ ሰው አይደለም የሚሉት አቶ ክብረት፤ የድንገተኛ ህክምና አሰጣጥ ችግርን ዓለም እንዴት ፈታው? ብለው ማጥናት ጀመሩ። • ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ የሚመጡ የሙያ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው? ማኅበረሰቡ ድንገተኛ አደጋ የደረሰበትን ሰው ደም ለማቆም፣ ትንፋሽ ለመስጠትና የበለጠ ሳይጎዳና ህይወቱ አደጋ ላይ ሳይወድቅ ወደ ሆስፒታል ማድረስ ያለበት እንዴት ነው? የሚለውን ሲያሰላስሉ የጠብታ አምቡላንስ ሀሳብ መጣላቸው። ይህንን ሀሳባቸውን ከባልደረቦቻቸው ጋር ሲያወሩ፤ ሁልጊዜም የሚነግሯቸው በድንገተኛ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን ህይወት ለማዳን መሥራት ያለበት መንግሥት እንደሆነ ነው። እሳቸው ግን፤ መንግሥት ሲባትል የሚውልበት ነገር ብዙ ነው፤ ይህንን ስራዬ ብሎ ላያየው ይችላል። ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብለው ተነሱ። "ከመላ ሀገሪቷ ትንፋሽ ያጡ ሰዎች ወደ ጥቁር አንበሳ ሲመጡ፤ እኛ የሞት ሰርተፊኬት እንደፃፍን መኖር የለብንም፤ ለውጥ መምጣት አለበት" የመልካም አጋጣሚና እድል ቀጠሮ በዚህ መካከል ከለንደን ለሥራ የመጡ አንድ ሰው የመተንፈስና የደም ዝውውር ችግር ገጥሟቸው ወደ ለንደን በፍጥነት ሄደው መታከም እንዳለባቸው ተነገረ። ያኔ አቶ ክብረትንና ለድንገተኛ አደጋ ህክምና ያላቸውን ፍላጎትና ዝግጁነት የሚያውቁ እርሳቸው ከታካሚው ጋር አብረው እንዲሄዱ ጠቆሙ። • የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም • ከወንበርና ከሲጋራ የቱ ይገድላል? ከዛም ወደ ለንደን ታካሚውን ይዘው ሄዱ፤ ለንደን አየር ማረፊያ ሲደርሱ ታካሚውን ለመቀበል የጠበቃቸውን ሲያዩ "አንድ አገር አንድ ሰው ነው" አሉ ለራሳቸው። ኢንቨስተር መሆን ይፈልጉ ስለነበር አንድ ቀን አምቡላንስ የምገዛበት በማለት የቁጠባ ሂሳብ ከፍተው ለሰባት ዓመት ይቆጥቡ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ክብረት፤ የቆጠቡት ገንዘብ እንኳን አምቡላንስ ጎማውን የሚገዛ እንዳልነበር ያስታውሳሉ። በሆስፒታል ሲሠሩ የተመለከቱትን የድንገተኛ አደጋ ህክምና ክፍተት ለመሙላት የራሳቸውን ጠብታ ጠብ ማድረግ የፈለጉት አቶ ክብረት የባንኮችን ደጃፍ መቆርቆር ጀመሩ። የጠብታ አምቡላንስ ባለቤት ምክር ለስራ ፈጣሪ ወጣቶች የትኛውም ባንክ ሊጀምሩ የፈለጉትን ሃሳብ ከሶስት ደቂቃ በላይ ለመስማት አለመፈለጉን የሚናገሩት አቶ ክብረት፤ "እንዴት ገንዘብ እንደምታመጣና እንዴት እንደምትከፍለን በሚገባ አላስረዳህም" ስለተባሉ ሌላ አማራጭ መፈለግ ጀመሩ። የቀራቸው አማራጭ አራስ ልጅ ታቅፈው ጥሪቴ ሀብቴ ብለው የሚኖሩበትን ቤት መሸጥ ነበር። ከባለቤታቸው ጋር ተነጋግረው የዛሬን ሳይሆን የነገን አስበው ሸጡት። ወዲያውኑ ወደ ዱባይ አቅንተው ሶስት አሮጌ መኪኖችን በመግዛት ወደ አምቡላንስ አስቀይረው መጡ። አምቡላንሶቹ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ቢሆንም ለትራንስፖርት ሚኒስቴርና ለጉሙሩክ የሚከፈለውን ገንዘብ መክፈል ስለነበረባቸው መኪናቸውን ጨምረው ሸጠዋል። ሁሌም በተግዳሮት ውስጥ መኖር አቶ ክብረት ፈተናው ግን አምቡላንስ መግዛቱ ብቻ አልነበረም ይላሉ። ከለንደን እንደተመለሱ ሥራቸውን በመልቀቅ የአምቡላንስ አገልግሎት መጀመር እንደሚፈልጉ ተናገሩ። ሆኖም የወቅቱ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሰዎች "በጎ አድራጎት ድርጅት ብትሆን እንደ ቀይ መስቀል አይነት ፈቃድ መስጠት ይቻላል። ካልሆነ የግል ክሊኒክ ወይንም ሆስፒታል ነው መክፈት ያለብህ እንጂ፤ ለግል አምቡላንስ ተቀመጠ ምንም አይነት መስፈርት የለም" አሏቸው። ስድስት ወር መሉ በየቢሮው በመግባትና ሀሳቡን በማስረዳት የራሳቸው 17 ገፅ ስታንደርድ በመፃፍ እና በማስገባት ፈቃድ ማግኘት ቻሉ። "የድንገተኛ አገልግሎት ልቡ የጥሪ ማዕከሉ ነው" የሚሉት አቶ ክብረት፤ ሥራ ሲጀምሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያጓጓዙት አብራቸው ትሰራ የነበረች አንዲት ነርስ እናት ታመው ወደ ቤተ-ዛታ እንደሆነ ያስታውሳሉ። "ስለሥራችን የሚያውቅ ማንም አልነበረም። የግል ስልኬን ነበር እንደ ጥሪ ማዕከል የምጠቀመው" በግል ዘርፉ ነጋዴው በየሰከንዱ ከተግዳሮት ጋር ነው የሚሰራው የሚሉት አቶ ክብረት፤ "የግሉ ዘርፍ ነጋዴ ነው። ነጋዴ ደግሞ ሌባ ነው የሚል አመለካከት ተንሰራፍቶና ተስፋፍቶ በሚገኝበት ማኅበረሰብ ውስጥ መሥራት ፈተናውን ያከብደዋል" ይላሉ። በአስር ዓመት የስራ ህይወታቸው የገጠሟቸው ተግዳሮቶች ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ናቸው ይላሉ። ሆኖም በብርታት ያቆሟቸውን ሦስት ነገሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ለመጀመር ለሚያስቡ ሰዎች ያካፍላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብ ያለው ሰው በፍፁም ትርፍ አላገኝበትም በማለት በጎ አድራጎት ድርጅት ይከፍታል ወይም ሀሳቤ ሁሉ ትርፍ በትርፍ ያደርገኛል በማለት ንግድ ያቋቁማል የሚሉት አቶ ክብረት፤ በዚህ መካከል ተፅዕኖ ፈጥሮ የሚገኝ ትርፍ ላይ ሕግም ማበረታቻም የለም በማለት በመንግስት በኩል ካሉት ተግዳሮቶች መካከል አንዱን ያነሳሉ። ጠብታ ዛሬ "እያንዳንዳችን በምናየውና በምናዋጣው ጠብታ ልክ የኢትዮጵያን ችግር ብሎም የአፍሪካን እንደፍናለን" የሚሉት አቶ ክብረት ጠብታ ከተቋቋመ ጀምሮ ከ 65 ሺህ በላይ ሰዎች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማመላለሱን ይናገራሉ። "ተፅዕኖ አምጥተን፤ ችግራችን ፈተን ትርፍ ማግኘት ነው ምንፈልገው" የሚሉት አቶ ክብረት፤ ጠብታ ድርጅታቸው ብቻ ሳይሆን የሕይወታቸው ፍልስፍናም እንደሆነ ያስረዳሉ። ለ10 ዓመት ያህልም የራሳቸውን ጠብታ በዚህ ፍልስፍና መሰረት መወጣታቸውን በኩራት ይናገራሉ። በሦስት አምቡላንሰ የተጀመረው የጠብታ አምቡላንስ ጉዞ ዛሬ 13 አምቡላንስ ደርሷል። ሦስቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያሟሉ እንደሆኑ የነገሩን አቶ ክብረት፤ በውስጣቸው የልብ ምት ማስነሻ ያላቸው፣ ኦክስጅን አቅርቦት የተሟላላቸው፣ ከኤር ላይ ኦክስጅንን ተቀብሎ ማዘዋወር የሚችሉ ናቸው ይላሉ። በቅርቡም አስመራ ድረስ ታካሚ እንዳጓጓዙ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ ጠረፍ ድረስ ህሙማንን አጓጉዘው እንደሚያውቁ ይናገራሉ። አቶ ክብረት "ህልማችን በምስራቅ አፍሪካ በድንገተኛ ህክምና የልቀት ማዕከል መሆን ነው" ብለዋል። በ10 ዓመታት የጠብታ አምቡላንስ አገልግሎት ውስጥ ከ45 ሺህ በላይ ሰዎችን በድንገተኛ ህክምና አሰጣጥን አሰልጥነዋል። 20ሺዎቹ የትራፊክ ፖሊሶች ሹፌሮች ሲሆኑ የመጀመሪያውን ፓራ ሜዲክ ኮሌጅም ከፍተዋል። "የማኅበራዊ ሥራ ፈጣሪ እንደመሆኔ መፍታት የምፈልገው ማኅበራዊ ችግርን ነው" የሚሉት አቶ ክብረት፤ በኮሌጃቸው ገንዘብ ከፍለው መማር የሚችሉ ሳይሆን የመማር አቅም እያላቸው ነገር ግን መክፈል የማይችሉትን ወጣቶች እንደሚያስተምሩ ይናገራሉ። ለዚህም ከሌሎች ገንዘብ ካላቸው ወገኖች ጋር በመሆን እና እነዚህን ወጣቶች አስተምሮ ሥራ ሲይዙ እንዲከፍሉ በማድረግ የእነርሱ ክፍያ ቀጣይ ተማሪዎችን እንዲያስተምር የሚያስችል እቅድ ነድፈው እየሰሩ መሆኑን ያስረዳሉ። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት • ደስታን አጥብቀን ስለፈለግ ለምን አናገኘውም? አሁን ከአንድ የኖርዌይ ድርጅት ባገኙት የገንዘብ ድገፍ 15 ልጆች ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ነግረውናል። በተመረጡ አምስት ክልሎች የአምቡላንስ አገልግሎት ለመጀመርናና ኮሌጁን ለማስፋት እቅድ መያዛቸውን የገለፁት አቶ ክብረት፤ ከተለያዩ የባህር ማዶ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመነጋገር በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ 5ሺህ የሚሆኑ ወጣት ፓራ ሜዲኮችን ለማሰልጠን አቅደዋል። እነዚህ ወጣቶች መክፈል የማይችሉ ግን ተምረው ስራ ይዘው የሚከፍሉ እንደሚሆኑም ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ወደ 24 ሺህ ፓራ ሜዲኮች ትፈልጋለች በማለትም ሀሳባቸውን ይቋጫሉ።
news-53216689
https://www.bbc.com/amharic/news-53216689
ቻይና ዜጎቿን ለኮሮናቫይረስ የባሕል መድኃኒት እንዲወስዱ ለምን ታበረታታለች?
በመላው ዓለም የሚገኙ ሳይንቲስቶች ለኮቪድ-19 ፈውስ የሚሆን መድኃኒት ለመቀመም ሩጫ ላይ ናቸው።
ቤይጂንግ በበኩሏ በዚህ ፈታኝ ሰዓት የባሕል መድኃኒቶቿን ከፍ ከፍ ማድረግ ሥራዬ ብላ ተያይዛዋለች። ሰሞኑን በቻይና መንግሥት የተሰራጨ አንድ መረጃ እንደሚያትተው "በወረርሽኙ ከተያዙት 92 እጅ የሚሆኑት ቻይናዊያን በአንድም ሆነ በሌላ ሁኔታ ሊፈወሱ የቻሉት የቻይና ባሕላዊ ሕክምና ረድቷቸው ነው" ይላል። የቻይና የባሕል ሕክምና በዓለም ላይ ረዥም ክፍለ ዘመን ያስቆጠረና ውስብስብ ታሪክ ያለው ነው። ከሥራ ሥርና ከቅጠላ ቅጠል ቅመማ ጀምሮ እስከ ቻይና ደረቅ መርፌ ሕክምና (አኩፓንቸር) እንዲሁም ታይ ቺ (ከማርሻል አርት ጋር የተያያዘ በባሕላዊ ስፖርት እንቅስቃሴ ፈውስ የማግኘት ሂደት)፤ እነዚህ ሁሉ የቻይና ባሕላዊ ሕክምና ውስጥ የሚካተቱ ናቸው። ታይ ቺ አእምሮንና ሰውነትን የማዋሀድና የማናበብ እንቅስቃሴ ነው። በቻይና ኅብረተሰብ ውስጥ የባሕል ሕክምና ሰፊ ተቀባይነት ያለው ሲሆን፤ ከአባት ወደ ልጅ ከትውልድ ትውልድ ሲወርድ ሲወራረድ የመጣና በቻይናዊያን ባሕል ውስጥ ሰፊ ቦታ የሚሰጠው ነው። አሁን አሁን ግን ነገሩ ተቃውሞም እየገጠመው ይመስላል። በተለይ የባሕል ሕክምናው ሳይንስን ገሸሽ ማድረግ ሲጀምር ነገሩ ደስ ያላሰኛቸው የአዲሱ ትውልድ አባላት "ኧረ ይሄ ነገር መስመር ሳተ" ማለታቸው አልቀረም። ቻይና የአሁኑን የወረርሽ ዘመን አስታካ ዘመናት ያስቆጠረውን ይህን የባሕል ሕክምና በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ገናና እንዲሆንላት ጥርሷን ነክሳ፣ መቀነቷን ሸብ አድርጋ በመስራት ላይ ያለች ትመስላለች። የቻይናው ፕሬዝዳንት ባሕላዊ መድኃኒቶችን ይደግፋሉ የቻይና የብሔራዊ ጤና ኮሚሽን ለምሳሌ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ባሳተመው የጤና መመርያ መጽሐፍ ላይ የባሕል ሕክምና አንድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ እንዲይዝ አድርጎታል። የአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ በበኩሉ የቻይና የባሕል ሕክምና ከዚህ ቀደም የሳርስ ወረርሽኝ በተቀሰቀሰበት በ2003 አካባቢ እንዴት ቻይናዊያንን እንደታደገ አበክሮ ማስገንዘብ ይዟል። በጤና መመርያው ላይ ለምሳሌ ወረርሽኙን ለመታደግ ስድስት የባሕል ሕክምና ዘዴዎች እንዳሉ ያብራራል። ከእነዚህ መካከል ሁለቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው ነበር። የመጀመሪያው ሉዋንሁዋን ኪንጉዌን የተሰኘው የባሕል ሕክምና ነው። ይህ መድኃኒት የሚዘጋጀው ከ13 የሥራ ሥርና የቅጠላ ቅጠል ጭማቂ ነው። በተለይም ፎርቴሲያ የተሰኘው ባለ ቢጫ ቀለም ተክል እና ሮዲዮላ ሮዝ ቅጠል ፍቱንነታቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ይነገራል። ሌላው ደግሞ ጂንሁዋ ኪንጋን ነው። ይህ በ2009 ለተቀሰቀሰው ሌላ ወረርሽኝ ፈውስ ሆኖ ነው የቆየው። የሚዘጋጀው ከቀረፋ፣ ሀኒሳክል ከተሰኘ ቅጠል፣ ከሱፍ እና ከተልባ ነው። የቻይና የባሕል ሕክምና ደጋፊዎች እነዚህን የተቀመሙ መድኃኒቶች ለኮሮናቫይረስ ማስታገሻ መጠቀም ፈውስ ያስገኛል ሲሉ፤ ሌሎች በበኩላቸው መድኃኒቶቹ በእርግጥም ፈውስ ስለማስገኘታቸው ሳይንስ በቤተ ሙከራ ሊያረጋግጣቸው ይገባል ይላሉ። የአሜሪካ ብሔራዊ የጤና ኢንስቲትዩት በበኩሉ እነዚህ የባሕል መድኃኒቶች የበሽታ ምልክቶችን በማስታገስ ረገድ ምጥን ሚና ቢኖራቸውም ኮሮናቫይረስን ይፈውሳሉ ወይ የሚለው ግን ገና የሚጣራ ነው ብሏል። በጉዳዩ ላይ በኔቸር የሳይንስ ጆርናል ላይ ኤዲዛርድ ኤርነስት የተባሉ የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪ እንደጻፉት ደግሞ የቻይና የባሕል ሕክምና ፈውስ ማምጣቱ ይቅርና አደገኛ ነው፤ ሊወሰድም አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል። ተመራማሪዋ ይህን ይበሉ እንጂ የቻይና ሕክምና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቻይና አገር ብቻም ሳይሆን በመላው ዓለም ተፈላጊነቱ በእጥፍ ጨምሯል። የቻይና ስቴት ካውንስል ባለፈው ዓመት ባወጣው አንድ መረጃ የቻይና ባሕላዊ ሕክምና ኢንዱስትሪ 420 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገመት ይፋ አድርጎ ነበር። የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ደግሞ በቻይና ሕክምና ዙርያ ጠንካራ የደጋፊነት መንፈስ እንዳላቸው ይነገራል። እንዲያውም በአንድ ወቅት "የቻይና ባሕላዊ ሕክምና የቻይና ሥልጣኔ ሕያው ቅርስ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። ቻይና በርካሽ ምርቶቿም ሆነ በብድር ቀፍድዳ ታዳጊ አገራትን በጉያዋ አድርጋ የድጋፍ መሰረቶቿ እንዲሆኑ እንደምትሞክረው ሁሉ፤ ይህን የባሕል ሕክምና በመላው ዓለም በማስተዋወቅ አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ግንባር፣ አዲስ እቅድ ይዛ ተነስታለች። ቤይጂንግ ይህን ባሕላዊ ሕክምና በተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ብዙ ብትጥርም ሰምሮላታል ለማለት ግን ይከብዳል። በቢሊዮን የሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች አሁንም ቢሆን የቻይና የባሕል ሕክምና ምን እንደሆነ አያውቁም። እንኳንስ ሊሞክሩት በጭራሽ ሰምተውት የማያውቁ ብዙ ናቸው። ቻይና ይህን ወረርሽኝ ከለላ በማድረግ ባሕላዊ ሕክምናዋን ለማስተዋወቅ መሞከሯን ብዙዎች አልወደዱላትም። በችግር ውስጥ ፖለቲካዊና ባሕላዊ ትርፍ እንደማጋበስ አድርገው ነው የተመለከቱት። ቻይና ግን ይህን ታስተባብላለች። ለባሕላዊ መድኃኒቶች መስሪያ በርካታ በርካታ ብርቅዬ እንስሳት ተገድለዋል ቻይና በአሁኑ ሰዓት በድጋፍ ስም ከዘመናዊ የሕክምና ቁሳቁሶች ጋር ቀላቅላ የባሕል መድኃኒቶቿን ከባሕል ሐኪሞቿ ጋር አጣምራ ወደ ታዳጊ የእስያ፣ የአፍሪካና የምሥራቅ አውሮፓ አገራት እየላከች ትገኛለች። "የቻይናን ልምድ ማካፈል እንፈልጋለን፣ ለኮቪድ-19 የቻይናን መፍትሄ ለዓለም ማጋራት እንፈልጋለን፣ በዚህም የተቀረው ዓለም የቻይናን መድኃኒቶች እንዲሞክቸው እንሻለን" ብለዋል የቻይና ብሔራዊ የባሕልም ሕክምና አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ዩ ያንሆንግ። ሚስተር ዮንግ ቻይና የባሕል መድኃኒቶቿን የእጅ አዙር ኃያልነት ማሳያና ተጽእኖ መፍጠሪያ እያደረገቻቸው እንደሆነ አይክዱም። "በወረርሽኙ ቁጥጥር የቻይናን አካሄድ ውጤታማነት፣ የምዕራቡን ዓለምን ደግሞ ውጤት አልባነት አስታከን የቻይና የባሕል ሕክምና እንዲታወቅ እየሰራን ነው" ይላሉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ። የቻይና የባሕል ሕክምና በዓለም ጤና ድርጅት ዘንድ ባለፈው ዓመት አድናቆት ማግኘቱ ለሌላ እውቅና አብቅቶታል። ብዙዎች የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይና የባሕል ሕክምና የሰጠውን አድናቆት አሳሳች ሲሉ ተችተውት ነበር። የዓለም ጤና ድርጀት በዓለም ዙርያ በነበሩ የባሕል ሕክምናዎች ላይ የ"ተጠንቀቁ" መልዕክት ሲያሰራጭ በቻይና የባሕል ሕክምና ዙርያ ግን ይህንኑ ተመሳሳይ መልዕክቱን ከእንግሊዝኛና ከቻይንኛ ቋንቋዎች ላይ ማንሳቱ ትዝብት ውስጥ ጥሎት እንደነበር ይታወሳል። አንዳንዶች ድርጅቱ በቻይና ተጽዕኖ ሥር ወድቋል ሲሉ ይህንኑ እንደማስረጃ ያቀርባሉ፤ ይተቹታልም። የቻይና ባሕል ሕክምና ጥብቅ ሳይንሳዊ የቤተ ሙከራ ሂደቶችን ያላለፈ በመሆኑ በዓለም ዙርያ ተቀባይነቱ እንደልብ እንዳይሆን አድርጎታል። ባሳለፍነው ግንቦት የስዊድን ቤተ ሙከራ ሊንሁዋ ኪንግዌን የተሰኘውን የቻይና የባሕል መድኃኒት በቤተ ሙከራ በማስገባት ምርምር ያደረገበት ሲሆን፤ ከዚህ ውህድ ውስጥ ማግኘት የቻለው ሜንቶል የተባለን የቀረፋ ሽታ ያለው ንጥረ ነገር ብቻ ነው። ለመድኃኒትነት የሚያበቃ ምንም ነገር ሳያገኝበት ቀርቷል። የቻይና የባሕል ሕክምና በብዝኃ ሕይወት ለይ አደጋ እንደቀነ የሚናገሩም አልጠፉም። ከቻይና ሕዝብ ብዛት አንጻር አንዳንድ የባሕል መድኃኒቶችን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ለማግኘት በብርቅዬ እንሰሳት ላይ የሚፈጸም አደን እንዲበራከት አድርጓል። ለምሳሌ የቻይና ብሔራዊ ጤና ኮሚሽን የድብ ሐሞት ፈሳሽን የያዘ ውህድ መወጋት የኮሮናቫይረስን መከላከል ጥሩ ነው በማለቱ፤ እንዲሁም ከፓንጎሊን ተራማጅ እንሰሳ ቅርፊት መድኃኒት ይሰራል የሚል እምነት በመንሰራፋቱ በእነዚህ ላይ አደን በርክቶ ነበር። መድኃኒትን በፕሮፓጋንዳ? ይህ በእንዲህ እንዳለ የቻይና መንግሥትና የቻይና መገናኛ ብዙሃን ባሕላዊ ሕክምናቸውን በማስተዋወቅ ረገድ ከመጠን ያለፈ ዘመቻ መክፈታቸው ሌላ ያልታሰበ ጣጣ ይዞባቸው መጥቷል። ለምሳሌ በዩናን አውራጃ በወረርሽኙ ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት ዝር እንዳይሉ የተነገራቸው ተማሪዎች ወረርሽኙ ጋብ ሲል ወደ ትምህርት ገበታ ሊመለሱ ሲሉ የባሕላዊ መድኃኒት ካልተጋታችሁ ትምህርት ቤት መግባት አትችሉም ተብለው ነበር። በቤይጂንግ የከተማ አስተዳደር ደግሞ አንድ ሕግ ረቂቅ ላይ ደርሶ ነበር። ረቂቅ ሕጉ የቻይና የባሕል ሕክምናን የሚያጥላላ ማንኛውም ቻይናዊ ለፍርድ እንዲቀርብ የሚጠይቅ ነው። እነዚህ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች የቻይና የባሕል ሕክምና ጉዳይ በዚያች አገር አዲስ የውይይትና የክርክር ምዕራፍ እንዲከፈት ምክንያት ሆኗል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም 'የቻይና ባሕል ሕክምና ሳይንስ ነው ወይስ አይደለም?' የሚለው ሙግት ማኅበራዊ የመገናኛ መድረኮችን አጥለቅልቆታል። "ሳይንስ ለተጠየቅ ክፍት ነው፤ የቻይና ባሕል ሕክምና ለተጠየቅ ዝግ ነው። ስለዚህ የቻይና የባሕል ሕክምና ሳይንስ አይደለም" ይላል አንድ የዌቦ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ። ዶ/ር ሊዮ በበኩላቸው በዚህ መንገድ ሙግቱን ይዘጉታል። "አንድ መድኃኒት በሳይንስ እንጂ በፕሮፓጋንዳ ኃይል ፈዋሽነቱ አይረጋገጥም።"
news-52557463
https://www.bbc.com/amharic/news-52557463
ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበራቸውን ለማስመር ተስማሙ
ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ እና አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ ያለውን ውጥረት አስመልክቶ ማዕክሰኞ እለት በስልክ መወያየታቸውን ሱዳን ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
ሁለቱ መሪዎችም በውይይታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ድንበር ለመወሰን የባለሙያዎች ቡድን ለማቋቋም ተስማምተዋል ተብሏል፡፡ በቅርቡ ሱዳን ኢትዮጵያ በሱዳን ድንበር በኩል የሚገኘውና በአገሪቷ ትልቁ የእርሻ አካባቢ አል ፋሻጋ የሚገኙ ወታደሮቿን እንድታስወጣ ጥሪ አቅርባለች፡፡ • በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ምክንያት የመናገር ነፃነት አደጋ ላይ ነው- ሂዩማን ራይትስ ዎች • ኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ የዘረ-መል ለውጥ የተደረገባቸው የእህል ዘሮችን ለማምረትና ለመጠቀም አልተስማማችም • አቅመ ደካሞችን እያማለለ የሚገኘው የማፊያዎች ገንዘብ አካባቢው ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር የነበረ ነው፡፡ ከ12 ቀናት በፊት በኢትዮጵያ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት አንድ የሱዳን ወታደር ሲገደል፤ ሌሎች ሦስት የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡ ይሁን እንጅ ፕሬዚደንት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ በሁለቱ አገራት መካካል ያለው ግንኙነት እየተሸሻለ መጥቷል፡፡
news-54296033
https://www.bbc.com/amharic/news-54296033
እምቦጭ፡ ተገኘ የተባለው ፀረ እምቦጭ አረም "መድኃኒት" እና የተከተለው ውዝግብ
የአንቦጭ አረም የኢትዮጵያን ትልቁን ሐይቅ ጣና ላይ ተንሰራፍቶበት የሐይቁንና በዙሪያው የሚገኙ ነዋሪዎችን ህልውና ስጋት ውስጥ ከከተተው ዓመታት ተቆጥረዋል። አረሙ ያለመፍትሔ ከዓመት ዓመት በሐይቁ ላይ እየተስፋፋ ለሌሎች በአገሪቱ ለሚገኙ የውሃ አካላት ሊተርፍ እንደሚችል እየተነገረ ቆይቷል።
ውሃው ለተለያዩ አገልግሎቶች ስለሚውል ኬሚካል ደግሞ ተመራጭ አይደልም በየጊዜው የሰው ጉልበትን በመጠቀም ከተወሰነው ሐይቁ ክፍል ላይ አረሙን ለማስወገድ ከሚደረገው ጥረት ባሻገር የተለያዩ ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኞች ለወራሪው አረም የሚሆን መፍትሄ ለማግኘት ይሆናል ያሉትን የበኩላቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል። በሰው ጉልበትም በቴክኖሎጂም የተደረጉት ጥረቶች ውጤት ስላላስገኙ የአረሙ መስፋፋት እየጨመረ ይገኛል። ሰሞኑን ግን መሪጌታ በላይ አዳሙ የተባሉ ግለሰብ ለዚህ አሳሳቢ አረም መፍትሔ የሚሆን መድኃኒት እንዳገኙ ሲናገሩ ተሰምቷል። ይህ ከዕጸዋት ተዘጋጅቶ ለሰባት ዓመታት ሙከራ ሲያደርጉበት እንደቆ የሚናገሩለት መፍትሔ እምቦጭ አረምን ድራሹን የሚያጠፋ "መድኃኒት ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መሪጌታ በላይ እንደሚሉት "መድኃኒቱ" እንቦጩ ላይ ከተረጨ ከ24 ሰዓታት በኋላ አረሙን እንደሚያደርቀው ይናገራሉ። ይህንን ሥራቸውንም "በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች አሳይቼ ማረጋገጫ አግኝቻለሁ" ይላሉ። "መድኃኒቱን"ላይ የተደረገው ሙከራ መሪጌታ በላይ የቀመሙትን መድኃኒት ወደ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በመውሰድ ለባለሙያዎች አሳይተዋል። የተግባር ሙከራም እንደተደረገበት ይናገራሉ። ይህንንም ሙከራ በቅርበት የተከታተሉት በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ መምህር የሆኑት ወ/ሮ ፍትፍቴ መለሰ ናቸው። መምህርቷ የዶክትሬት [ሦስተኛ] ዲግሪያቸውን በእምቦጭ አረም ላይ እየሰሩ ይገኛሉ። መሪጌታ በላይ ለእምቦጭ አረም ማስወገጃነት ያገለግላል ያሉትን መድኃኒት በዩንቨርሲቲው አማካይነት ሙከራ እንዲደረግበት ሲጠይቁ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወ/ሮ ፍትፍቴ በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጅ ኢንስቲቲዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር እንደተመደቡ ተገልጸወል። ይህንንም ተከትሎ በግለሰቡ ተዘጋጅቶ የቀረበውን መድኃኒት በእምቦጭ አረም ላይ በማድረግ ያሳየውን ለውጥ የተመለከተ ሪፖርት አዘጋጅተው ለሚመለከተው የትምህርት ተቋሙ ክፍል ማቅረባቸውን ወ/ሮ ፍትፍቴ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ሙከራው በአረሙ ላይ ከመጀመሩ በፊት መድኃኒቱን ያቀረቡት መሪጌታ በላይ የተዘጋጀው መድኃኒት ሌሎች የውሃ ውስጥ እጸዋትንና ነፍሳትን የሚጎዳ ኬሚካል መሆን አለመሆኑን ለማሳት "መድኃኒቱን" እንደጠጡት መምህርቷ ተናግረዋል። ከዚያም በኋላ ምርምር በሚደረግበት የሙከራ ኩሬ ላይ "መድኃኒቱ" ተደርጎ "በ24 ሰዓት በኋላ በስፍራው ከነበረው የእንቦጭ አረም ውስጥ ቢያንስ 70 ከመቶ የሚሆነው ደርቆ አገኘነው" ያሉት ወ/ሮ ፍትፍቴ፤ አረሙ መቶ በመቶ ስላልደረቀ ድጋሚ እንዲረጭ ተደርጎ ሙሉ በሙሉ መድረቁን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል። ሙከራው በዚህ ሳያበቃ በመጀመሪያ የተገኘውን ውጤት ለማረጋገጥ ተደጋጋሚ መሞከራ አስፈላጊ ስለነበረ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ጊዜ ተሞክሮ ተመሳሳይ ውጤት መታየቱን ወ/ሮ ፍትፍቴ አረጋግጠዋል። ነገር ግን በውሃ አካላት ላይ የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው መሆኑን ለማረጋገጥ መድኃኒቱ ሌላ ቦታ ላይ መሞከር ነበረበት። በመሆኑም አሳዎች ላይ ጉዳት አለማምጣቱን ለማረጋገጥ በባሕርዳር አሳ ምርምር ተቋም ውስጥ ተሞክሮ "በአሳዎቹ ላይ በተደረገ ክትትል ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም" በማለት መስክረዋል። "በአሳዎች ላይ የተሞከረውን መድኃኒት ግማሹን በመውሰድም እራሴ ምርምር በማደርግበት ማዕከል ውስጥ ባለ እንቦጭ ላይ ስሞክረውም አረሙን አድርቆታል" በማለት ለአራተኛ ጊዜ ውጤቱን ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል። መድኃኒቱ ከምን እንደተቀመመ አላውቅም፤ አረሙን ግን እንዳደርቀው አረጋግጫለሁ ያሉት ወ/ሮ ፍትፍቴ "ያየሁትን አረጋግጬ ለትምህርት ክፍሌ ሪፖርት ጽፌያለሁ።" ጥያቄ በ"መድኃኒቱ" ላይ ይህንን ተከትሎም የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክትር ለመሪጌታ በላይ አዳሙ ስለሥራቸው ውጤት የማረጋገጫ ደብዳቤ መጻፉንም ገልጸዋል። ነገር ግን በአማራ ክልል የጣናና የሌሎች የውሃ አካላት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አያሌው ወንዴ (ዶ/ር) ግን ይህንን የማረጋገጫ ደብዳቤ አይቀበሉትም። "ይህ በግለሰብ ደረጃ የተሰጠ አስተያየት እንጂ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ተካተው እና ሳይንሳዊ መንገድን ተከትሎ የተረጋገጠ ነገር አይደለም" ይላሉ። ቀደም ሲል መሪጌታ በላይ መድኃኒቱን እንዳገኙ ወደ እርሳቸው ቢሮ እንደሄዱ የሚገልጹት አያሌው ወንዴ (ዶ/ር)፤ የተባለውን መድኃኒትም "ከአንድ ዓመት በፊት ሙከራ አድርገንበት ውጤት አላየንበትም" ብለዋል። መሪርጌታ በላይ ይህንን በተመለከተ "ሙከራውን ብናደርግም በተቋሙ ውስጥ ባሉ ኃላፊዎች የተሰጠኝ ምላሽ አንድ ጊዜ አይሰራም፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይሰራል የሚል ነበር። በመሆኑም ሁኔታው ስላላስደሰተኝ ግንኙነቴ ተቋርቷል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በተጨማሪም መሪጌታ በላይ የሚያነሱት ጉዳይ ሥራቸውን ባቀረቡበት ጊዜ የጣናና ሌሎች የውሃ አካላት ባለስልጣን መድኃኒቱ የተቀመመበትን የእጽዋት ዝርዝር ካላወቅን አንሞክረውም መባላቸውን አንስተዋል። ይህንንም በተመለከተ አያሌው (ዶ/ር) ትክክል መሆኑን ጠቅሰው፤ እንዳሉትም መድኃኒቱ ከዕጽዋት እንደተሰራ በቃል መነገሩ ብቻ ብቁ አያደርገውም በማለት "በውሃ አካላት ላይም ሆነ በራሱ በሐይቁ ላይ ጉዳት የማያደርስ መሆኑን አይተን ማረጋገጥ ስለነበረብን ምንነቱን ጠይቀናል" ብለዋል። በወቅቱ እርሳቸውም ዕጽዋቱን ለማሳየት ፍቃደኛ እንዳልነበሩ የገለጹት መሪጌታ በላይ፣ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ "በአሁኑ ወቅት የአዕምሯዊ መብት ባለቤትነቴን ስላረጋገጥኩ በማንኛውም ሰዓትና ቦታ ለመሞከርም ሆነ መድኃኒቱ የተቀመመበትን እጽዋት ለማሳየት ፈቃደኛ ነኝ" ብለዋል። አያሌውም (ዶ/ር) ማንም ቢሆን መፍትሄ አለኝ የሚል ካለ ለመቀበል ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸው፤ መሪጌታ በላይም "የተለየና መፍትሔ የሚያመጣ ነገር ሰርተው ከሆነ እናስተናግዳቸዋለን" ብለዋል። እምቦጭ አረም በጣና ሐይቅ ላይ ምን ያህል እየተስፋፋ ነው? ሙከራና ውዝግብ በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም መርጌታ በላይ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ጋር ለመስራት "መድኃኒቱን" ይዘው በመሄድ በዩኒቨርስቲው የሐዲስ አለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው አንዳርጌ ገልጸዋል። እሳቸው እንደሚሉት መሪጌታ በላይ አዳሙ አረሙን ያስወግዳል ያሉት "መድኃኒት" እንዲሞከርላቸው ዩንቨርሲቲውን በደብዳቤ ጠይቀው፤ የሐዲስ አለማየሁ የባሕል ጥናት ተቋም የተለያዩ ሙያተኞችን በማዋቀር ሙከራውን መሪጌታ በላይ ባሉበት ማካሄዱን አስታውሰዋል። ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 6/2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት አካባቢ በተመረጠ አንድ ስፍራ በሚገኝ የእንቦጭ አረም ላይ ግለሰቡ ያዘጋጁት 25 ሊትር "መድኃኒት" በመርጨት መከራ መደረጉን አቶ ግዛቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጊዜም ሙከራው የተደረገበት ቦታ ከምንም ነገር ንክኪ ነጻ መሆን ስለነበረበት ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ስፍራውን የሚከታተል ጥበቃ ተመድቦ እንደነበና ከሙከራው በኋላ የተገኘ ውጤት ካለ ለመመልከት ወደ ቦታው ሲኬድ ግን "ምንም ለውጥ አላየንም" ሲሉ ገልጸዋል። "መድኃኒቱ" በተሞከረበት ወቅት የነበሩት መሪጌታ በላይ ግን የተገኘውን ውጤት ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር እንዲመለከቱ ቢጋበዙም ሳይሳተፉ መቅረታቸውን አቶ ግዛቸው ጠቅሰው፤ በቀጣይም ከዩኒቨርሲቲው ጋር ግንኙነታቸው ሙሉ ለሙሉ አቋርተዋል ብለዋል። መሪጌታ በላይ ግን ከዩንቨርሲቲው ሙያተኞች ጋር ወደ ሙከራው ስፍራ ማምራታቸውን ቢገልጹም በተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ "የመድኃኒቱን" ሙከራ ግን እንዳላካሄዱ ገልጸዋል። "ወደ ስፍራው ሂደናል፤ ነገር ግን የመሞከሪያ ገንዳ፣ አጥር እና ጥበቃ የተደረገለት ቦታ ባለመኖሩ መድኃኒቴን አላስሞክርም ብዬ ትቼ ተመልሻለሁ" በማለት የአቶ ግዛቸውን ማብራሪያ አስተባብለዋል። ተሞክሮ ውጤት አልተገኘበትም ስለተባለው መድኃኒትም "የራሳቸውን መድኃኒት ካልሆነ በስተቀር የእኔን አልሞከርንም" ብለዋል። እምቦጭን የሚያጠፋ መፍትሔ ለማግኘት ምርምር በሚያደርጉበትና ደረስኩበት ያሉን ውጤትም በሚያዘጋጁበት ጊዜ "ለመድኃኒቱ የሚሆን እጽዋት በበቂ ሁኔታ በአገር ውስጥ መኖሩን የዳሰሳ ጥናት አድርጌያለሁ" በማለት በቂ ግብአት እንዳለ መሪጌታ በላይ ይናገራሉ። ስለዚህም ባዘጋጁት "መድኃኒት" እና ባለው የእጽዋትም ግብአት የጣና ሐይቅን ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ባለ ጊዜ ውስጥ ከእንቦጭ አረም ማጽዳት ይቻላል ብለው ያምናሉ። ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን ሌሎች ሐይቆችን ደግሞ እጽዋቱን በማልማት "መድኃኒቱን" በመቀመም ማጽዳት ይቻላል ብለዋል። ጣና ሐይቅ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ፈተናዎች እየገጠሙት ነው የተመዘገበው "መድኃኒት" ይህ ያዘጋጁት ጸረ እምቦጭ "መድኃኒት" በፈሳሽና በዱቄት መልክ የተዘጋጀ መሆኑን የሚጠቅሱት መሪጌታ በላይ፤ ፈሳሹን በሊትር ከ30 እስከ 50 ብር ለመሸጥ እንዳቀዱና አንድ ሊትሩ 3 ሜትር በ3 ሜትር የሆነ በአረም የተወረረር ቦታን ሊሸፍን እንደሚችል ይገምታሉ። "የመድኃኒቱን ሙከራ ለሰባት ዓመታት ያህል በአባይ፣ ቆቃ እና ጣና አካባቢዎች አስፈላጊውን ሂደት ጠብቄ አከናውኛለሁ" የሚሉት መሪታጌ በላይ "የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነት መብት የተሰጠኝ እኔ ያቀረብኩትን መረጃ በመቀበልና በሌላ አካል ያልተሰራ አዲስ ግኝት መሆኑን በማረጋገጥ ነው" ነው ሲሉ ሥራቸው በስማቸው መመዝገቡን ይናገራሉ። በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት የፓተንት መርማሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ጣፋ ለቢቢሲ እንደገለጹት የመሪጌታ አዳሙን የእምቦጭ አረም ማጥፊያ "መፈድኃኒትን" በአነስተኛ የፈጠራ ዘርፍ ማረጋገጫ እንደተሰጠ ገልጸው፤ ይህም "በኢትዮጵያ ደረጃ አዲስ መሆኑን እና ጥቅም ሰጪ መሆኑን የሚያረጋገጥ" ነው ብለውናል። ከዚህ በፊት የቀረበ ተመሳሳይ የምርምር ውጤት አለመኖሩን በማረጋገጥ ለመሪጌታ በላይ ማረጋገጫውን እንደሰጡ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፤ ይህም "የቅድመ ምርምር ማረጋገጫ ነው" ብለውታል። የተሰጠው ማረጋገጫም "መድኃኒቱ" በቀጥታ ውሃ ላይ ወይም የትም ቦታ ላይ እንዲሞከር የማያረጋግጥ መሆኑን አስረድተዋል። ጽህፈት ቤቱ "መድኃኒቱን" በተመለከተ ቀደም ሲል በባሕርዳርና በሌሎች ቦታዎች ላይ የተደረገውን ምርምር የያዘ ጥቅል የጽሁፍ ሰነድ እና በምርምሩ ወቅት የተከተሉትን ሂደት በመገምገም ማረጋገጫውን እንደሰጠ አቶ ጌታቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ነገር ግን "ይህ ማረጋገጫ የተሰጠው ምርምሩ የእርሳቸው ንብረት መሆኑን ለማረጋገጥ እንጂ፣ አገልግሎት ላይ እንዲውል እውቅ የሚሰጥ አይደለም" ያሉት አቶ ጌታቸው፤ በቀጣይነት "የመድኃኒቱን" አጠቃቀም እና የጎንዮሽ ጉዳት ሊያረጋግጡ የሚችሉት የአካባቢ ጥበቃ እና ጤና ጥበቃን የመሳሰሉት ተቋማት መሆናቸውን አስረድተዋል። ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ከቀናት በፊት "መድኃኒቱን" በሚመለከት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በመሪጌታ በላይ አዳሙ ለሙከራ የተዘጋጀው የእምቦጭ አረም ማጥፊያ "መድኃኒት" ላይ የውሳኔ ሐሳብ እንዳልሰጠ አመልክቷል። ጨምሮም "መድኃኒቱ በአነስተኛ ደረጃ አረሙን ማጥፋት ቢችልም የጎንዮሽ ጉዳቱ በሳይንስናዊ ምርመራ አልተረጋገጠም" በማለት "በመድኃኒቱ" ላይ የቤተሙከራ ሥራ ለማከናወን መሪጌታ በላይ ተቀራርቦ ለመሥራት የሚያስችል ዕድል አልሰጡም ሲል ገልጿል።
news-46543353
https://www.bbc.com/amharic/news-46543353
ፈረንሳይ 'አላሁ አክበር' ብሎ ተኩስ የከፈተውን ግለሰብ በማደን ላይ ናት
በምስራቃዊ ፈረንሳይ ከተማ ስትራስበርግ የአውሮፓውያንን ገና በዓል ምክንያት በማድረግ ማክሰኞ ምሽት ላይ እየተዝናኑ የነበሩ ሰዎች ላይ 'አላሁ አክበር ' ብሎ ተኩስ በመክፈት ሁለት ሰዎችን ገድሎ አስራ አንድ የሚሆኑትን ያቆሰለውን ግለሰብ ለመያዝ ፈረንሳይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን አሰማርታለች።
በመገናኛ ብዙሃን ቸሪፍ ቺካት ተብሎ በመጠራት ላይ ያለው ይህ ግለሰብ እስር ቤት በነበረበት ወቅት አክራሪ እንደሆነ ተገልጿል። የፓሪስ ከተማ አቃቤ ህግ የሆኑት ሪሚ ሄትዝ እንደገለፁት ደግሞ ግለሰቡ የ29 ዓመት ወጣት ሲሆን ጥቃቱን የፈፀመበት ቦታ ላይ መሳሪያና ስለት ይዞ የነበረ ሲሆን ጥቃቱን ከፈፀመ በኋላ በታክሲ ከአካባቢው ተሰውሯል። የታክሲ ሾፌሩም ግለሰቡ አስር ሰዎችን እንደገደለና ከወታደሮች ጋር ሲታኮስ መቁሰሉንም በኩራት እንደነገረው ለፖሊስ ቃሉን ሰጥቷል። • በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃና ግፍ ለተፈጸመባቸው ካሳ ሊጠየቅ ነው • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ • ኻሾግጂ የዓመቱ ምርጥ ሰው ዝርዝር ውስጥ ተካተተ ጥቃቱ በተፈፀመ ምሽት ከግለሰቡ ጋር ግንኙት እንዳላቸው የተጠረጠሩ አራት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቃቤ ህጉ አስታውቀዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ የፀጥታ ሃይሎችን አሰማርተው ፍለጋውን እያካሄዱ ቢሆንም ምናልባትም ግለሰቡ ከፈረንሳይ ሳይወጣ እንዳልቀረ የፈረንሳይ ምክትል አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ሎረን ኑንዝ ቀደም ሲል ተናግረዋል። የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ክሪስቶፍ ካስታነር በበኩላቸው ደግሞ የገና በዓል ዝግጅቶች በሚካሄድባቸው ቦታዎች እንዲሁም ድንበሮች ላይ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ እንዳለ ገልፀዋል። የስትራስበርግ ከተማ ከንቲባ ሮናልድ ሪስ ዛሬ በገና በዓል የገበያ ስፍራዎች ዝግ እንደሚሆኑና በከተማዋ የስብሰባ ማዕከሎችም ሰንደቅ አላማ ዝቅ እንደሚል ተናግረው ነበር።
news-49174787
https://www.bbc.com/amharic/news-49174787
ኢትዮጵያ፡ የዛፍ ችግኝ የመትከል ዘመቻ ታሪካዊ ዳራ ምን ያሳያል?
ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም 'አረንጓዴ አሻራ' በሚል ዘመቻ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ችግኝ ተክለዋል።
በዚህ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻም በአንድ ጀምበር ከ350 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በሕንድ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ኢትዮጵያ መስበሯ ተዘግቧል። ለመሆኑ ችግኝን በዘመቻ መትከል መቼ፣ እንዴት እና በማን ተጀመረ? • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች • የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ? ችግኝን በዘመቻ መትከል በሕዝቡ ነው የተጀመረው የሚሉት በአካባቢ ጥበቃ ላይ በርካታ ምርምሮችን ያደሩት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሔር ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት ከአንድ ሺህ ዓመታት በፊት ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የዛፍ ችግኞችን የመትከል ልማድ ነበረው። "የዛፍ ጠቃሚነትን ከማንም በላይ ሕዝቡ ይረዳ ነበር" የሚሉት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ከዚያ በኋላ የዛፎች መቆረጥ በመብዛቱ እነርሱን የመተካት ጥረት ተጀመረ ይላሉ። ያ- ጥረትም እየተፋፋመ መጥቶ ዘንድሮ በስፋት የችግኝ ተከላ መካሄዱን ይገልጻሉ። "ሕዝቡ አካባቢውን ያውቃል፤ ተነግሮት አይደለም አካባቢውን እንዲያውቅ የሚማረው፤ የአካባቢ እንክብካቤ ለዘመናዊው ትውልድ የተላለፈው ከሕዝቡ ነው። በመሆኑም ሕዝቡ ድሮም ቢሆን መትከል ባያስፈልገው ዛፎችን ይንከባከብ ነበር፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲታየውም ችግኞችን ይተክል ነበር። መሬቱ እንዳይሸረሸርም እርከኖችን ይሰራ ነበር፤ ይህም አዲስ ነገር አይደለም" ብለዋል። ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ይኸው ባህል በዘመናዊነት ምክንያት መዳከሙን ገልፀው ወደፊት ወደ ነበረው ባህል የመመለስ ጥረት መጀመሩን ይናገራሉ። በሺህዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የቆየን ባህል በዚህ ጊዜ ተጀመረ ማለት ባይቻልም በተለያየ ጊዜ እና ዘመናት ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ ዘመቻዎች ይካሄዱ እንደነበር ግን ያስታውሳሉ- ዶ/ር ተወልደ ብርሃን። • ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር "ከሺህዎች ዓመታት በፊት ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ነበር የሚተክለው ዘመቻውም ከታች ወደ ላይ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን ዘመቻው ከላይ ወደታች ሆኗል" ይላሉ። በዘመነ መሳፍንት ከነበረው የሥልጣን ሽኩቻ በኋላ ማዕከላዊ መንግሥት የጥንቱ የዛፍ ችግኞችን የመትከል ባህል እየተዳከመ ሲመጣ ወደነበረበት ለመመለስ ከላይ ወደታች ትዕዛዝ ማስተላለፍ እንደተጀመረ ያወሳሉ። የተለያዩ ጥናታዊና ታሪካዊ ፅሁፎች ችግኝን በዘመቻ መትከል የተጀመረው በ14ኛው ክፍለ ዘመን በንጉስ ዘረ ያዕቆብ ዘመን እንደሆነ ያስረዳሉ። ከሁለት ዓመታት በፊት Status, Challenge and Opportunities of environmental Management in Ethiopia በሚል በታተመ ጆርናል ላይ በንጉስ ዘረ ያዕቆብ ዘመን በዘመቻ ከተተከሉና ተጠብቀው ከቆዩ ደኖች ወፍ ዋሻ፣ ጅባት፣ መናገሻ እና የየረር ተራሮች ጥብቅ ደኖች ተጠቅሰዋል። ከዚያም በኋላ አፄ ምንሊክ "ዘመናዊ" እፅዋትን ለኢትዮጵያ እንዳስተዋወቁ ይነገራል። በአገሪቱ ያለውን የማገዶና የቤት መሥሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለመቀነስ የባህር ዛፍ ተክልን ከአውስትራሊያ እንዳስመጡ ይነገራል። በወቅቱም የደን መጨፍጨፍን ለመከላከል "ሁሉም በግለሰብ መሬት ላይ ያሉ ዛፎች የመንግሥት ንብረት ናቸው" ሲሉ አውጀው እንደነበር በዚሁ ጆርናል ላይ ተጠቅሷል። ይህም ደኖች የህዝብ ሐብት እንደሆኑ በሕብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ለመፍጠር አስችሏል። ከዚያም በኋላ ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ መሪዎች የተለያዩ ስልቶችን እየተጠቀሙ ችግኞችን በዘመቻ ያስተክሉ ነበር። "ቤተክርስቲያንና መስጊዶች ምን ጊዜም ዛፎችን የመጠበቅና የመንከባከብ ልማድ አላቸው፤ በእርሻና በተለያየ መልኩ ቦታው ቢፈለግም ዛፎችን ጠብቆ ማቆየት የተለመደ ነው" የሚሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የአካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ ናቸው። በመንግሥት ደረጃ ችግኞችን አፍልቶ መትከል የተጀመረው ግን በአጼ ልብነ ድንግል ዘመን ነው ይላሉ ። በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጼ ልብነ ድንግል ከወፍ ዋሻ ዘርና ችግኞችን ወስደው ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በሚገኝ መናገሻ ሱባ የሚባል ሥፍራ የሃበሻ ጽድ መትከላቸውን ያነሳሉ። ከዚያ በኋላ አፄ ምንሊክ ባህርዛፍን ከአውስትራሊያ በማስመጣት ተክለዋል ሲሉ ያወሳሉ። "ምን አልባት አጼ ሚንሊክ ባህር ዛፍን አዲስ አበባ ባያስመጡ ኖሮ አዲስ አበባ አሁን ያለችበት ቦታ ልትገኝ አትችልም ነበር የሚል እምነት አለኝ" ይላሉ። በወቅቱ የአፄ ሚንሊክ ሠራዊትና በዙሪያቸው የነበሩት ሠራተኞች የማገዶና የቤት መሥሪያ ግብዓት እጥረት ይገጥማቸው ነበር። ይህንንም ለመፍታት ንጉሡ ባህርዛፍ አስመጥተው ባያስተክሉ አዲስ አበባ ባለችበት ላትቀጥል ትችል ነበር ሲሉ ምክንያታቸውን ያስረዳሉ- በዘመኑ ነገሥታት በተለያዩ ምክንያቶች መናገሻቸውን ይለዋውጡ እንደነበር በማስታወስ። አፄ ምንሊክ በፍጥነት ማደግ የሚችልና ራሱን በፍጥነት የሚተካውን ባህርዛፍን በአማካሪያቸው አማካኝነት እንደመረጡትም ይነገራል። በዛፍ ችግኝ ተከላ ታሪካዊ ዳራ ላይ የተሰሩ ጥናቶችን የሚጠቅሱት ዶ/ር አብዮት አፄ ኃይለ ሥላሴ ችግኝን ለመትከልና ለመንከባከብ የደን አዋጅን በማውጣት በርካታ ሥራዎች ማከናወናቸውን ያስረዳሉ። "አጼ ኃይለ ሥላሴ ችግኝ መትከልን እንደ አንድ የመንግሥት ሥራ አድርገው ይወስዱት ነበር" ይላሉ ዶ/ር አብዮት። አፄ ኃይለሥላሴ ከእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ በጢስ አባይ ፏፏቴ ስር-1950ዎቹ • የአየር ንብረት ለውጥ፤ የት ደረስን? እርሳቸው እንደሚሉት አጼ ኃይለ ሥላሴ ደን መጠበቅና ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ፓርኮች እንዲቋቋሙ ምክንያት ሆነዋል። አዋሽ ብሔራዊ ፓርክን በምሳሌነት ያጣቅሳሉ። በደርግ ዘመነ መንግሥትም የአካባቢ ጥበቃን የተመለከቱ ፖሊሲዎች ተቀርፀዋል። ዋነኛ ትኩረታቸው ግን የዱር እንስሳት ጥበቃ ላይ እንደነበር ጥናቶች ያትታሉ። በተለይ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1973/74 (1966 ዓ.ም) በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተከሰተው ርሃብና ድርቅ፤ አካባቢ ጥበቃ ላይ ጠንክሮ ለመስራት ካነሳሱት ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። በአጠቃላይ ደን ሥራ ላይ ከፍተኛና የተቀናጀ ስራ ለመስራት ዝግጅት ተደርጎ፣ ቦታዎች ተመርጠው፣ ችግኞች ተፈልተው፣ ለማህበረሰቡ አነስተኛ ድጎማ በማድረግ፤ በተራቆቱ ቦታዎች ችግኞች እንዲተከሉ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ዶ/ር አብዮትም ያረጋግጣሉ። በተራሮች ላይ በብዛት የሚታዩት ደኖችም በዚያ ዘመን የተተከሉ ናቸው ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት የችግኝ መትከል ዘመቻዎችን ለማካሄድም በዋነኛነት ለሰዎች ማበረታቻዎችን በመስጠት፤ ለምሳሌ እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች የእርዳታ እህል ለመስጠት ችግኝ እንዲተክሉ ይደረግ ነበር። "ለትምህርት ቤት ደብተር መግዣ ችግኝ ተክለን ገንዘብ ይከፈለን ነበር" ሲሉ የራሳቸውን ተሞክሮ ያነሳሉ። በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጊዜ በተለይ ዋናው የትኩረት አቅጣጫ የአየር ንብረት ለውጥ በመሆኑ ችግኝ መትከልና አካባቢን መንከባከብ እንደ አንድ ትልቅ ሥራ እንዲወሰድ በርካታ ሥራዎች ይከናወኑ ነበር። ይህ ወቅት የልማትና የአካባቢ ጥበቃ ተቋማት የተመሠረቱበትም ነው። በፖሊሲ ደረጃም ሥነ ምህዳርን፣ አካባቢን፣ የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃን በሚመለከት ግብ ተቀምጦለት እንቅስቃሴ የተጀመረበት ነው። በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን እየመሩ ያሉት ዶክተር ዐብይ አሕመድም 'አረንጓዴ አሻራ' በሚል የተደረገው አገር አቀፍ የችግኝ መትከል ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ዘመቻው በፍላጎት ላይ የተመሠረተ እና በስፋት በርካታ ችግኞች መተከላቸው ቀደም ካሉት ዘመናት ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ዶ/ር አብዮት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። በጥንታዊው ዘመን በሕዝቡ ተነሳሽነት የሚደረገው ችግኝ የመትከል ዘመቻ አሁን ላይ በመንግሥት አነሳሽነት መካሄዱ ብዙዎችን ያነጋግራል። ሕዝቡ ራሱ አውቆ ነው መትከል ያለበት፤ ዘመቻ አያስፈልግም በሚል። ይህንኑ ያነሳንላቸው ዶ/ር አብዮት "ከከተሞች መስፋፋትና ሥልጣኔ ጋር ተያይዞ ችግሮቹ እየገነኑ ሲመጡ ማህበረሰቡ የባህርይ ለውጥ ማሳየቱ የሚፈረድበት አይደለም" ሲሉ ይመልሳሉ። በመሆኑም ማህበረሰቡን ማነሳሳትና ወደ ቀደመው ባህሉ ማሻገር እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ። ባሳለፍነው ሰኞ በአንድ ጀንበር የተተከሉት ከ350 ሚሊየን በላይ ችግኞች በእርሳቸው ሙያዊ ስሌት 80 ሺህ ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን በዚህ ዓመት ሊተከል የታቀደው አራት ቢሊየን ችግኝ ደግሞ አንድ ሚሊየን ሄክታር መሬት ሊሸፍን እንደሚችል ለቢቢሲ ገልፀዋል። ችግኙ ፀድቆ ደን መሆን ሲችል የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በአንድ በመቶ ሊያድግ እንደሚችል ይገምታሉ- አንድ በመቶ በደን ሽፋን ሂሳብ ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ። የደን ሽፋን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የሚናገሩት ዶ/ር አብዮት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ባለፉት አምስት ዓመታት 15.5 በመቶ እንደሆነ ያስረዳሉ። በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በአውሮፓውያኑ 2020 የደን ሽፋንን 20 በመቶ ለማድረስ መታቀዱን አስታውሰዋል። ከ80 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 40 በመቶ እንደነበር ጥናቶች እንደሚያሳዩ የሚናገሩት ዶ/ር አብዮት ምን ያህል የደን ሽፋን እንደሚያስፈልግ ጣራ ሊሰራለት እንደማይገባ ይናገራሉ። በኢትዯጵያ በአጠቃላይ 6027 የእፅዋት ዝርያዎች እንደሚገኙም ዶ/ር አብዮት ነግረውናል።
55300624
https://www.bbc.com/amharic/55300624
ትግራይ ፡ በሳምንቱ ማብቂያ መቀለ ያስተናገደቻቸው አበይት ክንውኖች
ባለፈው ጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የፌደሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል አስተዳደር እንዲፈርስ ከወሰነ በኋላ የተሰየመው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሥራው እንደሚጀምር ተነግሯል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉ ነጋ (ዶ/ር) ጠቅሶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ በክልሉ በነበረው ግጭት ምክንያት ከአንድ ወር በላይ ሥራ አቁመው የሚገኙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ቅድመ ዝግጅቶች ተደርጓል። በዚህም ለሳምንታት ሥራ ያቆሙ የመንግሥት ሠራተኞች ከዛሬ ሰኞ ታህሳስ 05/2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የማይመለሱ ሠራተኞች ግን በገዛ ፍቃዳቸው ሥራቸውን እንደለቀቁ ተደርጎ እንደሚቆጠር ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል። በክልሉ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶችም ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለስ አለባቸው ያሉት ሙሉ ነጋ (ዶ/ር)፤ ይህን በማያደርጉ የንግድ ድርጅቶች ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል ብለዋል። ጦር መሳሪያ ማስረከብ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ውስጥ መደበኛ እንቅስቃሴዎችን ከማስጀመር በተጨማሪ "በሕጋዊም ሆነ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የጦር መሳሪያ ታጥቆ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ እስከ ማክሰኞ ታህሳስ 6 ድረስ ትጥቁን በአቅራቢያው ለሚገኝ የጸጥታ አካል እንዲያስረክብ" መታዘዙን ዶክተር ሙሉን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪም የጦር መሳሪያዎችን በፈቃደኝነት የማስረከቢያ ጊዜው ሲጠናቀቅ የጸጥታ አካላት ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ለመያዝ የቤት ለቤት ፍተሻ እንደሚያደረጉ ተገልጿል። በዚህም ጊዜ የጦር መሳሪያዎች የሚገኙባቸው ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የጊዜያዊ አስተዳዳሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙሉ ነጋ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ሞባይል እና ኤሌክትሪክ በመቀለ የወታደራዊ ግጭቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል የኤልክትሪክ፣ የስልክና የኢንተርኔት አግልግሎት ለሳምንታት ተቋርጦ ቆይቷል። ከሳምንት በፊት በአንዳንድ አካባቢዎች አገልግሎቶቹ መልሰው ቢጀምሩም በክልሉ ዋና ከተማ ግን አስከ ቅዳሜ ድረስ ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህም በርካቶች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው የሞባይል ድምጽ አገልግሎት በመቀለ እና በማይጨው ከተሞች መጀመሩን ኢትዮቴሌኮም ያስታወቀው ቅዳሜ ታህሳስ 3/2013 ዓ.ም ነበር። ከመቀለ ውጪ ያሉ ሰዎች ወዳጅ ዘመዶቻቸን ከ40 ቀናት በኋላ በስልክ ስለማግኘታቸው በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየጻፉ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለሳምንታት ተቋርጦ የቆየባት መቀለ የአሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀምራለች። በክልሉ በበርካታ ስፍራዎች በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ላይ በደረሰው ጉዳት የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ መቆየቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቆ ነበር። የደረሰውን ጉዳት ጠግኖ ነዋሪዎች የአሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሲሰራ መቆየቱን አስታውቋል። በዚህም መቀለ፣ አላማጣ፣ ማይጨው፣ መሆኒ፣ ሰቆጣ፣ ኲዊሀ እና አዲጉዶም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ማድረግ እንደተቻለም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ በመቀለ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ ትናንት በመቀለ ከተማ ተገኝተው ከአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በመቀለ በነበራቸው ወይይት ጦርነቱን ለመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና ሠራዊት አባላት ምስጋና አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ባደረጉት ወይይት የህወሓት ኃይሎች የሉት የሠራዊት ብዛት ወደ 80 ሺህ ይገመት እንደነበር ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከመቀለ እየሸሹ በነበሩ የህወሓት ኃይሎች ላይ ብቻ ሠራዊቱ ሮኬት መተኮሱን በንግግራቸው መካከል ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከጉብኝታቸው በኋላ "በመቀሌ ተገኝቼ ከብሔራዊ መከላከያ ሠራዊታችን አዛዦች እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት አድርጌያለሁ። የቴሌኮም እና የኤሌክትሪክ ኃይል መሠረታዊ አገልግሎቶች ከጥገና ሥራ በኋላ ተመልሰው እየቀጠሉ ነው። "የመሠረተ ልማት መልሶ ግንባታ እየተከናወነ ሲሆን፣ ሰብዓዊ እርዳታም እየቀረበ ነው። ወንጀለኛውን ቡድን ለሕግ የማቅረብ ሥራችን ይቀጥላል" ብለዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር ጉብኝት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ (ዶ/ር) የሥራ ጉብኝነት ለማድረግ ትናንት በኢትዮጵያ ተገኝተው ነበር። ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንሰትር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት መሆኑን ቢጠቅሱም አብደላ ሀምዶክ ግን ከሠዓታት በኋላ በመጡበት ዕለት ወደ ሱዳን ተመልሰዋል። ሱዳን ትሪቢዩን የአብደላ ሀምዶክ ፕሬስ ሴክሬታሪ፤ "የጠቅላይ ሚንሰትሩ የኢትዮጵያ ጉብኝት ፍሬያማ እና የጉብኝቱን ዓላማ ሙሉ በሙሉ ያሳካ ነበረ" እንዳሉት ዘግቧል። መነሻ ለዓመታት የቆውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ያጋጠመውን ቀውስ ተከትሎ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ከወሰኑ በኋላ የለውጥ ፍላጎቱ በገዢው ፓርቲ ውስጥ መንጸባረቅ ጀምሮ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በህወሓት የበላይነት ሲመራ ነበረው ኢህአዴግ በሕዝቡ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ለማብረድና የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለማድረግ መወሰኑ ይታወሳል። በለውጡ ሂደት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በፓርቲው የተወሰነውን የለውጥ እርምጃ በፍጥነት በመተግበር ከአብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አድናቆትን ለማግኘት ችለዋል። በእርማጃቸው የገፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአራት ብሔራዊ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው ኢህአዴግ በማክሰም አንድ ወጥ አገራዊ ፓርቲ ለመመስረት ጥረት በሚያደርጉበት ጊዜ የገዢው ፓርቲ ዋነኛ መስራችና በአገሪቱ አጠቃላይ ፖለቲካ ውስጥ ሰፊ ተጽእኖ የነበረው ህወሓት ቅሬታና ተቃውሞ ማሰማት ጀመረ። "ብልጽግና" የተባለው ተለያዩ የክልል ፓርቲዎችን በማሳተፍ ከኢህአዴግ ሰፋ ያለ ፓርቲ ሲመሰረት ህወሓት ከፓርቲው እራሱን በማግለሉ መካሰስና ውዝግብ መከሰት ጀመረ። ከዚህም በኋላ የህወሓት አመራሮች ማዕከላቸውን መቀለ በማድረግ የተቃዋሚ ፓርቲነትን ሚና ይዘው ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። ህወሓት የገዢነት መንበሩን ከኢህአዴግ ከተረከበው ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ልዩነት በማንሳት ሲወዛገቡ የቆዩ ሲሆን፤ በተለይ ባለፈው ዓመት መካሄድ የነበረበትና በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈው ምርጫ ነገሮችን በከፍተኛ ደረጃ እንዲካረሩ ማድረጉ ይታወሳል። በበሽታው ምክንያት የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች የስልጣን ዘመን ምርጫው አስኪደረግ ድረስ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ሲወሰን ህወሓት ግን "ሕገወጥ እርምጃ ነው" በማለት ተቃውሞውን አሰምቶ በትግራይ ክልል ግን የተናጠል ምርጫ እንደሚያካሄድ አሳውቆ ነበር። ይህ የህወሓት ውሳኔ ከምርጫ ቦርድ፣ ከፌደራል መንግሥቱና ከፌዴሬሽን ምክር ቤት "ተቀባይነት የለውም" በሚል ተቃውሞ ቢገጥመውም በክልሉ የምርጫ አስፈጻሚ አካል በማዋቀር ባለፈው ዓመት ጳጉሜ ወር ላይ መርጫው ተካሂዶ ህወሓት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ውጤት ማሸነፉ ተነግሮ ነበር። ይህ የምርጫ ሂደት ቀድሞውንም ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር የነበረውን ውዝግብ እንዲካረር አደረገው። መጀመሪያም ምርጫው ተቀባይነት የለውም በማለት ሲያስጠነቅቅ የነበረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግሥቱ ከክልሉ መስተዳደር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳያደርግ በማዘዘዝ በጀት የማቀብ እርምጃ ወሰደ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነበር ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በትግራይ ክልል የሚገኘውን ከአገሪቱ ሠራዊት ትልቁ ክፍል የሚባለውን የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው የተነገረው። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በህወሓት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ በምድርና በአየር ለሦስት ሳምንታት ያህል የዘለቀ ዘመቻ ተካሂዶ የክልሉ ዋና ከተማ በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት እጅ ስትገባ መንግሥት ሕግ የማስከበር ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ማብቃቱን ማሳወቁ ይታወሳል።
news-48183236
https://www.bbc.com/amharic/news-48183236
በረመዳን ፆም ቴምር ለምን ይዘወተራል?
የረመዳን ወር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ወር ነው። የረመዳን ፆም ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ይፀናል። አማኞቹ ከወትሮው በተለየ ኃይማኖታዊ ሥርዓት በፆምና በዱዓ ፈጣሪያቸውን እየተማፀኑ የሚያሳልፉበትም ቅዱስ ወር ነው። የዘንድሮው 1440ኛው የረመዳን ፆምም ሰኞ ዕለት ተጀምሯል።
ታዲያ በረመዳን ወቅት በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ብቻ ሳይሆን የእምነቱ ተከታይ ወዳጅ ዘመድ ባላቸው የሌላ እምነት ተከታዮች የሚዘወተሩ ምግቦች አሉ። ሾርባ፣ ሳምቡሳ፣ ጣፋጭ ብስኩቶችና ቴምር የረመዳን ምግባዊ ትዕምርቶች ናቸው ማለት ይቻላል። • "ወሎዬው" መንዙማ በአንድ ጉዳይ ምክንያት ለማፍጠር ቤቱ መድረስ ያልቻለ፤ መንገድ ላይ ቴምር ገዝቶ ፆምን መግደፍ በዚህ ወቅት እንግዳ ነገር አይደለም። በዚህ የረመዳን ወር ማስቲካና ብስኩት ሲሸጡ የነበሩ የጎዳና ላይ ነጋዴዎችም ወሳኝ ቦታዎችን እየመረጡ ቴምርን መሸጣቸው የተለመደ ነው። ለመሆኑ ቴምር በረመዳን ወር ለምን ይዘወተራል? ቴምር ኃይማኖታዊም ሆነ የጤና ፋይዳ አለው የሚሉት ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ናቸው። "በእስልምና ኃይማኖት ግን በቴምር ማፍጠር ሱና ነው" ይላሉ። እርሳቸው እንደገለፁልን 'ሱና' ማለት ነብዩ መሐመድ የሰሩት፣ የተገበሩት፣ የተናገሩት አሊያም ሌሎች ሲሰሩት አይተው ያፀደቁት ነው። ኡስታዝ እንደገለፁልን ነብዩ መሐመድም በሚያፈጥሩበት ጊዜ ቴምርን ይመገቡ ስለነበርና በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እርሳቸው የተናገሩትን፣ የተገበሩትን አሊያም ያፀደቁትን መከተል 'ምንዳ' ያስገኛል ተብሎ ስለሚታመን ቴምር ለማፍጠሪያ ተመራጭ ሆኗል። ቴምር መመገብ ብቻ ሳይሆን የቴምር ፍሬዎቹ ቁጥር ሳይቀር ኃይማኖታዊ ይዘት አለው። ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ምክንያቱን ሲያስረዱም " ነብዩ መሐመድ 'አላህ ኢተጋማሽ ቁጥሮችን ይወዳል (3፣ 5፣ 7፣ 9...) የምትመገቧቸው ቴምሮችም ኢተጋማሽ የሆኑ ቁጥሮች መሆን አለበት' ሲሉ ተናግረዋል፤ ይህም አላህ ኢተጋማሽ መሆኑንና አንድ መሆኑን ያሳዩበት ነው" ይላሉ። አንድ ሰው የተመገባቸውን የቴምር ቁጥሮች ኢተጋማሽ ማድረጉ ሌላ መንፈሳዊ 'ምንዳ' ያስገኝለታል ሲሉም ያክላሉ። በመሆኑም በቴምር ማፍጠሩና የፍሬውን ቁጥር ኢተጋማሽ አድርጎ መመገቡ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚባለው ምንዳን ለማብዛት እንደሚረዳ ያስረዳሉ። የቴምር እርሻ "ነብዩ መሐመድ ቴምር በሌለበት ጊዜም በውሃ ፆማቸውን ይፈቱ ነበር" የሚሉት ኡስታዝ ሀሰን፤ በእስልምና እምነት በፍጥሪያ ሰዓት ቴምርን በቅርበት ማግኘት ካልተቻለ በውሃ ፆማቸውን እንዲፈቱ ታዟል ይላሉ። ይህም የእርሳቸውን ድርጊትና ቃል ለማክበር ህዝበ ሙስሊሙ ፆሙን በቴምር አሊያም በውሃ ይገድፋል። እርሳቸው ያንን የሚያደርጉበት ምክንያት ጤንነታዊ አሊያም ማህበራዊ ፋይዳ ሊሆን እንደሚችልም ኡስታዝ ያክላሉ። ኡስታዝ እንደነገሩን ቴምርን በተመለከተ ብዙ የተነገሩ ሐዲሶች (የነብዩ መሐመድ ንግግሮች) አሉ። ነብዩ መሐመድ ከአትክልት ውስጥ ሁሉም ነገሩ (ሥሩም፣ ግንዱም፣ ቅጠሉም፣ ፍሬውም ) ጥቅም ላይ የሚውለው ቴምር ነው የሚል ተናግረዋል፤ በጎ በጎ ነገሮችንና ባህሪያትንም በቴምር እየመሰሉ የሚናገሩበት ሁኔታም እንዳለ በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። • የቢላል አዛን የናፈቃቸው ሀበሾች "በቅዱስ ቁርዓን ውስጥ እያንዳንዱ ሕይወት የተመሠረተው በውሃ ላይ ነው ተብሎ በግልፅ ተቀምጧል፤ በዚህም ምክንያት በቴምር አሊያም በውሃ ይፈጠራል።" ይላሉ- ኡስታዝ ሀሰን ታጁ። ነገር ግን በረመዳን ወቅት የምንመገባቸው ሌሎች ምግቦች እንደየአካባቢው ባህል የሚወሰን ነው። በእኛ አገር ሳምቡሳ፣ ሾርባ እንዲሁም ሌሎች ምግቦች ይዘወተራሉ። በሌሎች ሙስሊም አገራትም የተለያየ የአመጋገብ ሥርዓትና ምግቦች ቢኖርም ውሃና ቴምር ግን ሁሉንም የሚያመሳስሉ ናቸው ብለውናል። ቴምር በሥነ ምግብ ባለሙያ በኢትዮጵያ ሥነ ምግብ ሶሳይቲ የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑት አቶ አብነት ተክሌ ቴምር ሙቀትን መቋቋም ከሚችሉ ፍራፍሬዎች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን ከሚበቅልበት ቦታ አንፃር ታሪካዊ አመጣጦች ሊኖሩት ይችላል ሲሉ ይጀምራሉ። በአብዛኛው የአረብ አገራት ሞቃት በመሆናቸው ቴምር አብቃይም ናቸው። በመሆኑም እዚያ አካባቢ ከመብቀሉ የተነሳ እንደ ልምድ የሚመገቡት ፍራፍሬ በመሆኑ ሊሆን ይችላል ሲሉ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። በሥነ ምግብ ሳይንስ ግን ቴምር እንደማንኛውም ፍራፍሬ የቫይታሚን ይዘቱ ጠቃሚ እንደሆነ ይገልፃሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ፍራፍሬዎች በቫይታሚን ይዘታቸው አንዱ ካንዱ ቢበላለጡ እንጂ ይዘታቸው ለጤንነት ጠቃሚ ነው። ጠቃሚ የሆኑበትን ምክንያት ሲያስረዱም ደረቅ የሆነ ካሎሪ ስለማይሰጡ ነው። ለምሳሌ ሙዝ፣ ቴምር ሌሎችም እንደ ስኳር ጣፋጭነታቸውን ብቻ ሳይሆን አብረው ተያይዘው የሚመጡ ንጥረነገሮች በውስጣቸው ይዘዋል። • በፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል? "እነርሱ ባይኖሩ እንደ የቆዳ በሽታ፣ የደም መርጋት የተለያዩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ ዕድላችን ሰፊ ይሆን ነበር" የሚሉት ባለሙያው ጠቃሚ ከሚባሉት ፍራፍሬዎች ውስጥ ደግሞ አንዱ ቴምር መሆኑን ይጠቅሳሉ። ቴምር እንደ ሌሎች ፍራፍሬዎች በውስጡ ጣፋጭነት ያለው ሲሆን የስኳሩ ዓይነት በተለይ ሰውነታችን በፍጥነት አቃጥሎት ደማችን ውስጥ ያለውን ግሉኮስ (የስኳር መጠን) የሚጨምር ስለሆነ ተመራጭ ፍሬ ነው ይላሉ። በተጨማሪም ቴምር በውስጡ ከፍተኛ አሰር (Fiber) ያለው በመሆኑ በቀጥታ ወደ ሰውነታችን ከመግባቱ በፊት የመፈጨት ሂደት ላይ የመቆየት ባህሪም አለው ይላሉ። በመሆኑም በረመዳን ወቅት ሰውነታችን ምንም ምግብ ሳያገኝ ስለሚውል ቀኑን ሙሉ የምናደርገው እንቅስቃሴ እንደ ጉልበት የምንጠቀምበት ንጥረ ነገር ከደም ውስጥ ወጥቶ ወደ ሴሎቻችን የሚዘዋወረውን ግሉኮስ ነው። በመሆኑም ቀኑን ሙሉ ምግብ ሳንመገብ ስለምንቆይ ፆሙን ስንጨርሰ ይህ ንጥረ ነገር አንሶ ይገኛል። ይህንንም ለመመለስ ጣፋጭ ነገሮች ይወሰዳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ጣፋጭ የሆኑ ምግቦች በቀጥታ ወደ ግሉኮስ ተቀይረው ደማችን ውስጥ ገብተው ለእኛ ጉልበትን እና ማነቃቃትን የሚወስዱት ጊዜ ይለያያል። "ቴምር አንድም ስኳርነት ያለው ሲሆን፤ መጠናዊ የሆነ የግሉኮስ አጨማመርን ይፈጥራል ፤ ይህም ተመራጭ ፍራፍሬ ያደርገዋል" ሲሉ ያክላሉ። ከሥነ ምግብ አንፃር የተጠባበሱና ጣፋጭነት ያላቸው ኬኮችና ብስኩቶች ከመውሰድ ቴምር መመገብ ለጤና ጥሩ በመሆኑ በማንኛውም ጊዜ ቢወሰድ ሲሉ ይመክራሉ- ባለሙያው። አክለውም በማንኛውም ጊዜ የምንመገባቸው ምግቦች ተመጣጣኝ እንዲሆኑ ይመከራሉ። "ለዚህም ደግሞ ትልቁ ግብዓት አትክልትና ፍራፍሬዎች ናቸው" ሲሉም ይገልፃሉ። • ከረመዳን ፆም ጋር የተያያዙ የተሳሳቱ እሳቤዎች በአገር አቀፍ ደረጃ በአውሮፓውያኑ 2013 ሰዎች ምን ይመገባሉ? (Food Consumption Survey) በሚል የተጠና ጥናት እንደሚያመላክተው የኢትዮጵያ ህዝብ አትክልትና ፍራፍሬ አጠቃቀሙ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል ብለዋል። አቶ አብነት እንደሚሉት የዓለም ጤና ድርጅት አንድ ሰው በቀን ውስጥ 400 ግራምና ከዚያ በላይ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲመገብ የሚመክር ቢሆንም የኢትዮጵያ ግን ዝቅተኛ ሆኖ ነው የተገኘው። በመሆኑም ቴምርን ጨምሮ ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎች የኢትዮጵያ ህዝብ በአግባቡ እየተመገበ አይደለም። ጥናቱ አቅርቦትን በተመለከተ ያለው ነገር ባይኖርም የተመረተው እየተሸጠ ፤ ምርት የለም ወይም ከምርት በኋላ በአቀማመጥ ችግር እየጠፋ ነው የሚል ሦስት ግምቶችን ያስቀምጣሉ። በጥናቱ የኢትዮጵያ ህዝብ በአብዛኛው የሚመገበው የእህል ዘሮችን፤ እንደ ስንዴ፣ በቆሎ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ሥራ ሥሮች እንደ ድንችና ካሳቫ የመጠቀም ልምዶችን ያሳያል ብለውናል። ይሁን እንጂ የእንስሳት ተዋፅኦ ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ የጥራጥሬ አጠቃቀም ዝቅተኛ ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን ትልቅ ለውጥም የሚፈልግ ነው ሲሉ አክለዋል።
news-54179474
https://www.bbc.com/amharic/news-54179474
ዜና ማየት ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል!
እኛ ራሳችን ዜና አቅራቢ ሆነን ይህን ማለታችን ወለፈንዲ ሊሆን ይችላል። ትዝብት ላይ ሊጥለንም ይችላል። ያም ሆኖ ግን ነገሩ አሳሳቢ ነው።
ቀኑን ሙሉ የዜና ቆሎ መቆርጠም ቢቀርብንስ? ሌላው ቢቀር ለአእምሯችን ጤና ስንል። መረጃ ትንፋሽ አሳጣን እኮ፡፡ የመረጃ ሱናሚ ጠራርጎ ወሰደን እኮ… በኮቪድ ዘመን ደግሞ ቤት ተዘግቶ መዋል የዜና ሸመታችንን ሰማይ አድርሶታል፡፡ በብዙ ዓለም ይህ ነገር እውነት ነው፡፡ እስኪ አስቡት… እጃችሁ ላይ የቲቪ ትዕይንት መዘርዝር መዘወርያ አለ እንበል፡፡ ሪሞት! ሌላኛው እጃችሁ ላይ ደግሞ ስልካችሁ ይኖራል፤ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በዚህ ዘመን ከስልካችን ከራቅን ጭንቅ ነው የሚሆንብን፡፡ ምናልባትም ይህን ጽሑፍ በስልካችሁ እያነበባችሁት ይሆናል፡፡ ከንባብ የሚያናጥቡ ተከታታይ መልእክቶች እየደረሷችሁም ይሆናል፡፡ በፌስቡክ…በቴሌግራም…በዋትስአፕ…በትዊተር… በዚያ ላይ ‹ይቺን አንብባትማ በሞቴ!› የሚለው ሰው ብዛቱ… "ጉርሻ ይመስል!" ለምን እንደሆነ ባይታወቅም ሁሉም ሰው የያዘውን ንባብ እንኳ ሳይጨርስ የማጋራት ሱስ አለበት፡፡ አንዳንዱ አጭሬ የቧልት ቪዲዮ ዓይቶ፣ ስቆ እንኳ ሳይጨርስ አጋርቶ ይጨርሳል፡፡ ጊዜ የለም፡፡ የመረጃ ግሽበት አለ፡፡ ስለዚህ ወደሚቀጥለው፡፡ ሳቅን ለማጣጣም ቀርቶ ፈገግታን ለመጨረስ የሚሆን ጊዜ የለም፡፡ እጃችሁ ላይ የቲቪ 'ሪሞት' አለ ብለናል፡፡ ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ ሰበር ዜና እየላኩ የአእምሮ ጫና ይፈጥራሉ፡፡ ፈነዳ፣ አፈነዳ፣ ፈነዱ….ገደለ፣ ገደሉ…ተገደለ፣ አስገደለ፣ ሞቱ፣ ቆሰሉ…አቆሰለ…ቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቅብርጥሶ… ሪሞቱን ይዛችሁታል ብለናል….፡፡ እንዳትለቁት፡፡ ዓለምን በቲቪ መስኮት እየሾፈራችኋት ነው፡፡ በቲቪ የትእይንቶች መዘርዝር ውስጥ 300 ቻናሎች አሉ፡፡ 300 ምርጫዎች አሏችሁ ማለት ነው፡፡ የትኛውን ማየት ይሻላል? ይህ የምርጫ መብዛት ራሱ ለአእምሮ ጤና መልካም አይደለም፡፡ ከቲቪ መዘርዝሩ ጎን የራዲዮ መዘርዝር አለ፡፡ ከሱ ጎን ላፕቶፕ አለ፡፡ ላፕቶፑ ውስጥ እልፍ ፊልሞች አሉበት፡፡ በዚህ ላይ ከጎረቤት የሆነ ራዲዮ ጣቢያው ላንቃው እስኪሰነጠቅ ይጮኻል፡፡ ከወዲያ በኩል ሼልፍ ላይ ያላነበቧችኋቸው መጻሕፍት እያዛጉ ነው፡፡ ዓለም ትጨንቃለች፡፡ መረጃ ይንዠቀዠቃል፡፡ ሰቆቃ…ዜና…ሰቆቃ…መረጃ…ገደሉ፣ ተገደለ፣ ቆሰሉ አቆሰለ፡፡ ጂኒ ጃንካ ቁልቋል…. በዚሁ ሁሉ መሀል ሌላ መልእክት ይመጣል፡፡ ከወዳጅ፣ ከቴሌ፣ ከቴሌግራም ጉጅሌ፣ ከፌስቡክ ክበብ… መረጃውን እንቀበላለን፤ እንጎርሳለን፡፡ ደግሞ መረጃውን አላምጠን አይደለም የምንጎርሰው፡፡ ምኑ ይላመጥና፡፡ ማስቲካ…ይላመጣል? ይዋጣል? መረጃ ማስቲካ ላንቲካ ሆኗል፡፡ ማመንዠግ ነው እንጂ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ዝምብሎ ማቀበል ነው፣ የሰማው ላልሰማው፡፡ የሰማው ለሰማው፡፡ ወዘተ፡፡ ወዘተ ራሱ ድሮ አጭር ቃል ነበር፡፡ አሁን ወዘተ ረዥም ቃል ሆኗል፡፡ መረጃ ያታክታል፡፡ የዚህ ጽሑፍ እንደ አንጀት መርዘም ራሱ አታካች ነው፡፡ ለምን እዚህ ጋ አናቆመውም፡፡ ምክንያቱም ጸሐፊው ተስፋ ያደርጋላ…ጠቃሚ መረጃ እያቀበለ እንደሆነ ይሰማዋላ፡፡ ስለዚህ አያቆምም ይቀጥላል፡፡ ማንም ደንታው ባይሆንም ይቀጥላል፡፡ ለመረጃ ግሽበት የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት፡፡ በዓይንና ጆሮ የምንሸምተው ዜና ካሎሪ ቢሆን እኮ አለመጠን ወፍረን ፈንድተናል፣ ይሄኔ፡፡ ስኳር፣ ጨጓራ፣ ደም ብዛት፣ ደም ግፊት ነበረብን እኮ ይሄኔ፡፡ ሽንታችን ቀለሙ ቢጫ፣ ሽታው ዜና ዜና የሚል ይሆን ነበር ይሄኔ፡፡ ደግነቱ ዜና ካሎሪ የለውም፡፡ ካሎሪ የለውም ማለት ግን ጭንቅላታችን ላይ አይወጣም ማለት ነው እንዴ? አይደለም፡፡ ልክ እንደ ቢጫ ወባ ዘሎ ጭንቅላታችን ላይ ይወጣል፡፡ ይህን የምንረዳው ግን ዘግይተን ነው፡፡ ፓሮል ጎሽ የ32 ዓመት ወጣት ናት፡፡ በዜና ጎርፍ ተወሰደች፡፡ እንደ ቀልድ ሪሞቱን ታነሳዋለች፡፡ አንዱ ዜና ለሌላው ሲያቀብላት፣ ሌላው ለሌላ ሲያሻግራት እንዲሁ እንደ ቅሪላ እየተለጋች ቀኑ መሽቶ ይነጋል፣ ነግቶ ይመሻል፡፡ ‹‹ወንድ ልጅ ቆረጠ፣ ሴት ልጅ ወሰነች›› አልኩ በሆዴ ትላለች ፓሮል፣ የሆነ ቀን፡፡ ፓሮል ቤተሰቦቿ ሕንድ ናቸው፡፡ እሷ ስዊድን ነው የምትኖረው፡፡ ስዊድን ነው የምኖረው ትበል እንጂ እውነተኛ ሕይወቷ ቲቪ ውስጥ ነው፤ ኢንተርኔት ውስጥ ነው፡፡ ስለ ሕንድ አንዱን ዜና ጀምራ ሌላውን ስትገልጥ በሕንድ የወጣች ፀሐይ በስዊድን ትጠልቃለች፡፡ ይህ ሁልጊዜ የሚሆን ነው፡፡ በቀን በቀን፡፡ በመጨረሻ ካሮል ጭንቅላቷ መደንዘዝ ጀመረ፡፡ ‹‹ሕንድ እየሆነ ያለው ነገር ቤተሰቤን የሚጨርስ ስለሚመስለኝ ለተደጋጋሚ ጭንቀት ተዳረኩ›› ብላለች ካሮል፣ ለቢቢሲ፡፡ ክሪስ ክላንሲ ደግሞ አለ፡፡ 33 ዓመቱ ነው፡፡ በአውስትራሊያ፣ ቪክቶሪያ ነው የሚኖረው፡፡ የርሱ ሱስ ጫት አይደለም፡፡ ዜና ነው፡፡ ዜና-ሱስ የሚባል ነገር ታሟል፡፡ ዜና ማየት ብቻ አይደለም ችግሩ፡፡ የዓለም ጋዜጠኞችን ልቅም አድርጎ ይከተላል፡፡ በትዊተር፣ በፌስቡክ እግር በእግር ይከተላቸዋል፡፡ አንዲት ቅንጣት ዜና አታልፈውም፡፡ ከዜና በፊት ዜና ያገኛል፡፡ በቀኑ መጨረሻ ግን ይደነዝዛል፡፡ ይታክታል፡፡ ለካንስ ሳያስበው ዓለም ላይ የተፈጠረ ክፉ ነገሮችን በሙሉ በዐይኑ በኩል ሲጠጣቸው ነው የዋለው፡፡ ልክ ማታ ላይ ጭንቅላቱን ሲወቅረው ነው ይህን የሚረዳው፡፡ ቲቪውንና ስልኩን ሲዘጋ ነው የሚታወቀው፡፡ ወደ መኝታው ሲሄድ ሕልሙ ዜና በዜና፡፡ ሽብር በሽብር፡፡ ደግሞ አያስችለውም፣ ጠዋት መልሶ ይከፍተዋል፡፡ ዜናው ደግሞ አይቀየርም፡፡ መልሶ መላልሶ ያው ጉዳይ ይታኘካል፣ ይመነዠጋል፡፡ ማስቲካ ላንቲካ፡፡ ‹‹ለጤናዬ ሰጋሁ፤ እየታመምኩ መጣሁ፤ እርምጃ ወሰድኩ፡፡ ዜና በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ማየት ጀመርኩ፡፡›› ይላል ክሪስ ጤናው እንዴት እንደተመለሰለት ሲናገር፡፡ ጎሽ እና ክሪስ ብቻቸውን አይደሉም ይላል ስታትስቲክስ፡፡ ሚሊዮኖች እንደነሱ እየተሰቃዩ ነው፡፡ ምናልባትም ቢሊዮኖች፡፡ ምንም እንኳ በዚህ ክፉ የወረርሽኝ ዘመን ቤት ተዘግቶ መዋል የቲቪ ተጠቃሚዎችን ቁጥር እንዲያሻቅብ ቢያደርግም፤ በብዙ አገራት ግን የዜና ግሽበት ተከስቷል፡፡ ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በከፍተኛ ሁኔታ የተመልካቾቻቸው ቁጥር ቀንሷል፡፡ በአውስራሊያ ደግሞ ከዜና ቻናሎች ይልቅ መዝናኛዎች የተሻለ ተመልካች ቁጥር አስመዝግበዋል፡፡ ፒው የሪሰርች ሴንተር በሰራው አንድ ጥናት ደግሞ በርካታ ሰዎች ስለ ኮሮና ዜና በጭራሽ መስማት አይፈልጉም፡፡ ለምን? አታክቷቸዋላ፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ ከ10 ሰዎች ሰባቱ ስለ ኮሮና ምንም ዓይነት ዜና መስማት ጠላን ብለዋል፡፡ መጥፎ ዜና እንዴት ነው የሚጎዳን? የአእምሮ ጤና አዋቂዎች ሁለት ነገር ያነሳሉ፡፡ አንዱ የበዛ መረጃ ወደ ታዳሚዎች እየተወነጨፈ የሰዎችን አእምሮ ቀስ በቀስ እየበጠበጠ መሆኑን፡፡ ሁለተኛው ዜና ምን ያህል እንደሚጎዳን አለመገንዘባችን፡፡ ለምሳሌ ስለ ኮሮና ቢጠራቀም አንድ ሜጋ ባይት የሚወጣው ዜና በቀን በቀን ሰምተን ይሆናል፡፡ ግንዛቢያችን ግን በአንድ ኪሎ ባይት እንኳ ጨምሯል? አልጨመረም፡፡ እንደ መረጃው ብዛቱ የመረጃ ጥራት አለን ማለት አይደለም፡፡ የሚመስለን ግን ብዙ በሰማን፣ ባየን፣ ባነበብን ቁጥር ብዙ ማወቃችን ነው፡፡ ለምሳሌ የኮሮና ዜና ዕለታዊ ቢሆንም የሰዎች በበሽታው ላይ ያላቸው ግንዛቤ ግን ተቀራራቢ ነው፡፡ ብዙ ዜና በመስማታቸው ከበሽታው የተፈወሱ የሉም፡፡ ብዙ የዜና እንጀራ በመመገባቸው የተህዋሲውን ክትባት ያገኙ የሉም፡፡ ዛሬ በዚህ አገር እንዲህ ያህል ሰዎች ተያዙ፣ ተመረዙ የሚል ዜና እየወቀረን ስንውል ግን አእምሯችን ላይ ጉዳት እያደረስን ነው፤ እንወቀውም አንወቀውም፡፡ ለምሳሌ ሰዎች ጭምብል ማጥለቅ አለባቸው ተብሏል፣ 2 ሜትር መራራቅ አለባቸው ተብሏል፤ እጃቸውን መታጠብ አለባቸው ተብሏል፡፡ ይህንኑ መረጃ በተለያየ መንገድ ለመቶ ሺ ጊዜ መስማት ትርፉ ምንድነው? ጆን ፖል ዴቪስ ሳይኮቴራፒስት ናቸው፡፡ ደንበኞቻቸው በመረጃ ሱናሚ ምክንያት ብቻ ለድብታ እና ለጭንቀት እንደተዳረጉ ደርሰውበታል፡፡ ጆን ፖል እንደሚሉት ከሆነ በሌላ የዓለም ጥግ የደረሰ አደጋ በዜና መልክ አእምሯችን ከቀሰመው በኋላ የዘነጋነው ይመስለናል፡፡ አእምሮ ግን ውስብስብ ነው፡፡ ባይታወቀንም የሰማነው መጥፎ ዜና ቀናችንን ያገረጣዋል፡፡ በፌስቡክ ሸርተቴ ሲንሸራተቱ፣ በመረጃ ሲንከላወሱ የሚውሉ ሰዎች አሉታዊነት እንደሚያጠቃቸው ብዙ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ እነሱ የድብታ መጫወቻዎች ነው የሚሆኑት፡፡ ዱካክ ከነ ሠራዊቱ እላያቸው ላይ ይሰፍራል፡፡ ባለማየትና በማየት መሀል ሚዛኑ የቱ ጋ ነው? ሰዎች ነን፤ የመረጃ ዘመን ላይ ነን፡፡ ያለ መረጃ መኖር አንችል ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መረጃ የአእምሮ ጤናን ያውካል እየተባልን ነው፡፡ ስለዚህ ምን ተሻለ? ፕሮፌሰር ዴቪስ የአእምሮ ጤና ተመራማሪ ናቸው፡፡ በቀን አንድ ጊዜ ዋና ዋና ዜናዎችን አለፍ አለፍ እያሉ ማየት በቂ ነው ይላሉ፡፡ በዜና ሱስ ለሚሰቃዩ ሰዎች ግን ሚዲያ ቅኝት በሳምንት አንድ ጊዜ በቂ ነው ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር ዴቪስ ሌላው ምክራቸው ዜናን ብቻ ሳይሆን ዜና ጣቢያን ማጋበስ አደገኛ እንደሆነ ነው፡፡ የዜና ምንጫችን ከሚታመኑ አንድ ወይም ሁለት ሚዲያዎች ብቻ ብናደርግ ለአእምሯችን ውለታ ዋልንለት ማለት ነው፡፡ ሚዲያዎች ሁሉ መጥፎ አይደሉም፤ ሁሉም ደግሞ ለጤናዎ በጎ አይደሉም፡፡ በረብ የለሽ የመረጃ ጥይት የማያቆስልዎትን ሚዲያዎች መምረጥ የርስዎ ፋንታ ነው፡፡ አሰስ ገሰሱን የሚያቀርብልዎት ማኅበራዊ ሚዲያ ለአእምሮ መቃወስ ሊዳርግ ይችላል፡፡ ፕሮፌሰር ጆን ፖል ዴቪስ ለሁሉም ነገር ድንበር ማበጀት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ ለምሳሌ በቀን ውስጥ ጠዋት ወይም ምሳ ሰዓት ላይ አንድ ጊዜ ብቻ ለ15 ደቂቃዎች መረጃ ቃርመን ከዚያ ግን በምንም መልኩ አለመመለስ፡፡ ይህ ግን ይቻላል? እንደሚባለው ቀላል ነው? በዲጂታል ዓለም ችግሩ የሚጀምረው የመጀመርያዋን ዜና ከማየቱ ላይ ነው፡፡ ከዚያማ እያሳሳቀ ይወስደናል፡፡ በመጨረሻ የጥፋተኝነት ስሜቱ አእምሯችን ይቀውራል፡፡ ምናልባት ራስን በጊዜ የሽቦ አጥር ማጠር አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ ስልክን አንድ ጊዜ አይቼ እዘጋዋለሁ ብለው የሚከፍቱ የዋሆች ናቸው፡፡ በመረጃ ሱናሚ ተጥረግርገው የማይወሰዱት ስንቶቹ ናቸው? ፓራል ጎሽ ሰዎችን በሰዓት ገድቦ መረጃን መቆጣጠር እንደሚችሉ መንገር ቀልድ ነው ትላለች፡፡ እሷ ሞክራው አልተሳካላትም፡፡ ለእሷ መፍትሄ የሆነላት መረጃን ከሰዎች አፍ መቀበልን ነው፡፡ ለሻይ ከሰዎች ጋ ስትገናኝ ሰዎች ያወሩላታል፡፡ መረጃ ከአፍ አፋቸው ትቀልባለች፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው መንገድ አልሰራላትም፡፡ አንድ ጊዜ ወደ ስልኬ ከገባሁማ መውጫ የለኝም ትላለች፡፡ የሷ ታሪክ የሚሊዮኖች ታሪክ ነው፡፡ ‹‹አሁን ነጻ ወጥቻለሁ፤ በዕለታዊ ቅራቅንቦ ዜና አልታለልም፤ ልቦለድ ማንበብ ነው የምወደው፤ ለሱ ጊዜ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ትላለች፡፡›› ይስመርላት!
48572251
https://www.bbc.com/amharic/48572251
የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ ወዲያና ወዲህ
የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ እድሜው ቢቆጠር ገና የአንድ ወጣት እድሜን እንኳ በቅጡ አይሞላም። በእርግጥ ጉማን በእማኝነት ጠርቶ ለሚሞግት ምላሹ የፊልም ኢንዱስትሪው ያንሰራራበትን 1990ዎቹን ብቻ ማስላታችንን መጥቀስ ነው።
የቴዎድሮስ ተሾመ ቀዝቀቃዛ ወላፈን፣ የዮናስ ብርሃነ መዋ ሔርሜላና ጉዲፈቻ የተሰኙ ፊልሞች በየሲኒማ ቤቶች ሸራ ላይ የነገሱበት ዘመን ነበር፡፡ ሺዎች ተሰልፈው ያዩት፤ የከተማው መነጋገሪያ፤ የመገናኛ ብዙኃን ርዕስ ሆነው ነበር። በ1990ዎቹ ማንሰራራት የጀመረው የኢትዮጵያ ሲኒማ ነገሬ ብሎ የሚያነሳው አጀንዳ፤ በአብይነት አጋፋሪ ሆነው የሚከውኑት ባለሙያዎች፤ ገንዘባቸውንም ላባቸውንም የሚያፈሱለት ጠቢባን ሁሉም ወጣቶች ናቸው። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም የኢትዮጵያ ፊልም በወጣቶች ተደራጅቶ፤ ለወጣቶች የእንጀራ ገመድ መሆን ብቻ አይደለም ለጋነቱን የሚያሳየው የሚመደብለትም በጀት ገና ልጅ ነው። በከተማው ለዕይታ የበቁ ፊልሞችን የገመገመ አንድ ባለሙያ እንደሚለው በአማካይ አንድ ፊልም ተሰርቶ ለእይታ እስኪበቃ ድረስ ስድስት መቶ ሺህ ብር ገደማ ይፈጃል። እርግጥ ነው እንደ ቁራኛ ያሉ ከአለፍ ገደም እስከ 4 ሚሊየን ብር የወጣባቸው ፊልሞች አይታጡም። ግን ከአማካይ ወጪው አልፎ መበጀት የቻለ ደፋር ፕሮዲውሰር፣ ብዙ ገንዘብ የሚጠይቁ ፊልሞችንም የጻፈ ደራሲ፤ ገና የፊልም ኢንዱስትሪው ማህጸን አላፈራም። ቢያፈራም እኔ አለሁ ብሎ ወደፊት አልመጣም። እንደው ለመሆኑ በዓመት ስንት ፊልሞች ታመርታላችሁ ብለን የጠየቅናቸው የፊልም ባለሙያዎች በትንሹ ሰማኒያ በትልቁ ደግሞ መቶ መልሳቸው ነው። ይህንን መልስ እንደመጨረሻ ወስደን የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶችን ካሰስን በሳምንት አንድ ወይንም ሁለት ፊልም የሚያስመርቁ አዳራሾችን እናገኛለን። በፊልም ኢንዱስትሪው መነቃቃት በርካታ የሕንጻ ባለቤቶች እየተበረታቱ ለመሆኑ እማኝ የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችም አሉ። እንደ ጋትስ ኢንተርቴይመንት ለአንድ ፊልም 400 ብር ድረስ የሚስከፍሉ የሲኒማ አዳራሾች እንዳሉ ሁሉ በድምጽ ጥራት በምቾትና በሌሎች ግብአቶች ራሳቸውን ብቁ አድርገው ያሉ ሲኒማ ቤቶች በአዲስ አበባ አራቱም አቅጣጫ ይገኛሉ። • "ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ ፊልም መመለክት የፈለገ ከአስኮ እስከ መገናኛ፣ ከአየር ጤና እስከ አዲሱ ገበያ፣ ከአቃቂ እስከ ስድስት ኪሎ በአቅራቢያው የሲኒማ አዳራሽ ያገኛል። ቦሌ የመጣ ኤድናሞል፣ ሳርቤት ያቀና አዶት ሲኒማ ይዝናናል። ጉርድ ሾላ ነኝ ያለ ሴንቸሪ ሲኒማ፣ ፒያሳ የመጣ አምፔርና ሲኒማ ኢትዮጵያ ገብቶ ያሻውን ይኮመኩማል። ይህ እንደ ዋርካ እየሰፋ እና እየገዘፈ የሚሄድ የፊልም ኢንዱስትሪ ብርታትና ድክመቱ ምንድን ነው? አንድ ወደፊት የፊልም ኢንዱስትሪው ራሳቸውን ባስተማሩ ወጣት ባለሙያዎች የተገነባ ነው የሚለው የፊልም ፕሮዲውሰሮች ማህበር ሰብሳቢው ቢንያም አለማየሁ ነው። ለእርሱ ብቁ ባለሙያዎች እየተፈጠሩ ናቸው። ይህ ግን በግለሰብ ደረጃ የሚታይ ለፊልሙ እድገት በተናጠል አስተዋፅኦ የሚያበረክት ጉዳይ ነው። ይህንን የግለሰቦች አቅምና ልክ ወደ ፊልም ኢንዱስትሪው ቋት ሲወሰድ ክፍተት እናያለን ይላል ቢኒያም። ለፊልም ባለሙያው ድርብ ድል ደግሞ የፊልም እድገትን ለመለካት አንዱ መንገድ የምርት ብዛቱ ነው። የሚዲያው ቴክኖሎጂ በተሻሻለ ቁጥር ፊልምን በቀላሉ በመስራት ለገበያ ማቅረብ ስላስቻለ የምርት መጠኑ ጨምሯል ይላሉ። ሌላው ደግሞ እንደ አንድ የጥበብ ሥራ በፌስቲቫል ደረጃ ዓለም ላይ ሄዶ በመወዳደር፣ ሀገሪቱንና ባለሙያውን በመወከል ረገድ ያለው እድል ከታየ ግን አሁንም የኢትዮጵያ ፊልም አንካሳ ነው ይላል ድርብ ድል። ለሲኒማቶግራፈርና ፕሮዲውሰሩ ታምራት መኮንን ግን የፊልም እድገት ላይ የምስል ጥራቱን አይቶ እድል አለ ብሎ ማውራት እንደማይቻል ይናገራል። ለፊልም ጥራቱ አስተዋጽኦ ያደረገው ቴክኖሎጂው ነው፤ በማለት ከዚህ ይልቅ መነሳት ያለባቸው ሌሎች ነገሮች መሆናቸውን ይዘረዝራል። • “አንቺሆዬ”፡ የኢትዮጵያዊያት ታሪክን መናገር የፊልም ባለሙያው ሔኖክ አየለ ተሰማ በኢትዮጵያዊያን ተመልካቾችና ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ባህሎችና ታሪኮች እጅጉን ይተማመናል። የሀገር ውስጥ ሥራን የመመልከት ባህሉ ለፊልም ሰሪው ተስፋ ሰጪ ነው በማለትም ሥራው ዝቅ ያለ በሆነ ጊዜ እንኳ ተመልካች ከሲኒማ ቤት አለመራቁ እድል ነው ይላል። ሌላው የተለያዩ ታሪክ ለመተረክ የሚያስችሉ ባህሎች መኖራቸው ለኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስሪ የተቸሩ ጸጋዎ ናቸው ባይ ነው ሔኖክ። ችግሮቹ ምንድን ናቸው? አቶ ድርብ ድል ፊልም በቀላሉ ዘው የሚባልበት፣ ትንሽ ሰርቶ ብዙ የሚገኝበት ዘርፍ ነው ብሎ ማሰብ ስህተት መሆኑን ጠቅሶ ባለሙያው ራሱን በየጊዜው የሚያሳድግበት የሙያ ሥነ ምግባሩን የሚያከብርበት ዘርፍ ከሆነ የወደፊት ጉዞው የተሳካ ይሆናል ሲል ይናገራል። ለኢትዮጵያ ተብሎ ፊልም የሚለካበት የተለየ መሥፈርት ሊዘረጋ አይችልም የሚለው ድርብ ድል፤ የሲኒማ ጥበብ ዓለም አቀፋዊነትን እንደ አስረጅ ያነሳል። የሲኒማ ጥበብ ለዘመናት የራሱ የሆነ የታሪክ መንገሪያ ቅርጽ ያበጀ፣ የራሱን የተለያዩ ዘውጎች ያዳበረ በመሆኑ የእኛ ፊልሞች መንጠራራት ያለባቸው እነዚያ ዓለም አቀፍ የሆኑ መለኪያዎችን ለማሟላት መሆኑን ያስታውሳሉ። እነዚህን ዓለም አቀፋዊነት ተቀባይነት ያላቸው የፊልም መንገሪያ መዋቅሮችን በማሟላት ደረጃ ደካማ በመሆናችን ግን ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰርተን ከዓለም የዘርፉ ጠቢባን ጎን ለመቆም አቅቶናል ይላሉ። እርግጥ በቁጥር አነስተኛም ቢሆኑ እዚህም እዚያ የኢትዮጵያዊያንንና የፊልም ባለሙያውን ስም ያስጠሩ ሥራዎች ተሰርተው በአውሮፓና በአሜሪካ ፌስቲቫሎች ላይ ዋንጫ ያመጡ ቢኖሩም ፊልሞቻችን ዓለም አቀፍ አቀራረቦችን፤ በቴክኒክ፣ በምስል፣ በድምጽ፣ በትወና ማሳየት ችለዋል የሚለው መመለስ አለበት ይላሉ። ይህንን ሀሳባቸውን ሲቋጩም ፊልሞቻችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ አልሰራናቸውም በማለት ነው። ለፊልም ባለሙያው ሔኖክ ከሚሊኒየም በኋላ የነበሩት አምስትና ስድስ ዓመታት የፊልም ዘርፉ ወርቃማ ዓመታት ናቸው። እነ እቴጌ ቁጥር ሁለት፣ የሎሚ ሽታ፣ ረቡኒን በመጥቀስ ወቅቱ አዳዲስ ነገሮች የተሞከሩበት በቅርጽም በስልትም የተሻሉ ነገሮች የቀረቡበት ነበር ሲል ይገልጸዋል። እነዚህን ፊልሞች በኢኮኖሚ ስኬት፣ በሥራ ጥራት ያመጡትን መሻሻል አለማድነቅና አለማበረታታት ሌሎች ተመሳሳይና የተሻሻሉ ሥራዎች እንዳናይ አድርጎናል ይላል ሔኖክ። • "በሰው ሃገር አገኘሁ የምለው ነገር ስደተኛ በሚል ስም መጠራትን ብቻ ነው።" የፊልም ባለሙያው የትምህርት ውስንነት አለበት ያለው ሔኖክ የአቅም ችግር፣ የክህሎት ማጣት በዘርፉ ውስጥ የሚታይና በፍጥነት ሊሞላ የሚገባው ክፍተት ነው ለእርሱ። በእርግጥ የገንዘብ ተግዳሮትም የፊልም ሥራውን ፈትሮ የያዘ ጉዳይ ነው። የሙያ ሥነ ምግባር ጉዳይም የማይታለፍ ነው ሲልም ያክላል። ያነጋገርናቸው ባለሙያዎች በአጠቃላይ በሙያ ሥነ ምግባር ላይ ዘርፉ ያለበትን ጉድለት ይጋራሉ። በጀትም ቢሆን በአንድ አንደበት የሚናሩለት ችግር ነው። ለሲኒማቶግራፈሩ ታምራት ደግሞ ለኢትዮጵያ ፊልም እድገት ዋነኛ እንቅፋቱ ባለቤት ማጣቱ ነው። የኢትዮያ ፊልም ኢንዱስትሪ ማነህ? ወዴት ነህ? ብሎ የሚመራው ጠንካራ ተቋም ዛሬም አላገኘም። የፖሊሲ አለመኖር፣ መመሪያ ማጣትም ሌላው እንከኖቹ ናቸው። "የፊልሙ ኢንዱስትሪ እንደ አንድ ዘርፍ አልታየም" የሚለው ታምራት ዛሬም ሀገሪቱ እየተገለገለችበት ያለው በ1967 ዓ.ም የወጣ ህግን ነው ሲል ዘርፉ ለገጠመው ፈተና አስተዋጽኦ ያደረጉ ነጥቦችን ያነሳል። ዘርፉ ጠንካራ ሀሳቦችን ሳይሆኑ ቧልት ብቻ የሚታይበት እየሆነ ነው በማለት የፊልም ጽሑፎች ክፍተትንም ይነቅሳል። "በካሜራ ቴክኖሎጂ መሻሻል ቢታይም በታሪክ ነገራ ዛሬም ድረስ የጀመርንበት ዘመን ላይ ነው ያለነው" የሚለው አቶ ታምራት ዘርፉ የበርካታ ሙያዎች ጥምረት በመሆኑ የእነዚህ ባለመያዎች በበቂ ብዛትና ብቃት አለማግኘት ፈተና መሆኑን ይናገራል። በወሲብ ፊልሞች ሱሰኛ የሆኑ ወጣት ሴቶች ዘርፉ ውድ ነው የሚለው ታምራት ጠንካራ ኢትዮጵያዊ የታሪክ ሀሳብ አምጥቶ፣ በፊልም ለመስራት ዋጋው የማይቀመስ ስለሆነ ባለሀብቶች በዚህ ዘርፍ ላይ ኢንቨስት እንዳያደርጉ አድርቸዋል ይላል። ሲኒማ ቤቶች የሚያስከፍሉት ክፍያ፣ መንግሥት የሚወስደው ታክስ የፊልም ባለሙያው የሰራበትን ዋጋ እንዳይመልስ አድርጎታል የሚለው አቶ ታምራት ፊልም ሰሪ በመሆኑ የሌሎች መጠቀሚያ ከመሆን ባሻገር የፊልም ባለሙያውን የላቡን ውጤት እንዳያገኝ አድርጎታል ሲል ያክላል። "በእርግጥ አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር የሚፈልግ ባለሙያ የገበያ ፈተና ይገጥመዋል" የሚለው ሔኖክ በበቂ ሁኔታ በመምህራንና ቁሳቁስ የተሟሉና የተደራጁ የፊልም ትምህርት ቤቶች አለመገኘት ክፍተቶቹ የበለጠ እንዲሰፉ ማድረጉን ይጠቅሳል። ምን ይደረግ? የፊልም ኢንዱስትሪው እንዲያድግና፤ በኢኮኖሚው ላይ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የመንግሥትን ድጋፍ ይሻል ያሉት ሔኖክና ታምራት ናቸው። ከእነርሱ የተለየ ሀሳብ ያለው ድርብ ድል ደግሞ መጀመሪያ ባለሙያው ራሱን መመዘንና ያሉበትን ድክመቶች ማሻሻል አለበት ይላል። ባለሙያዎቹ ፊልሙ የሃገሪቱን ባህል በማስተዋወቅ ረገድ ለበርካቶች የሥራ እድል በመፍጠር በኩል በሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቢስማሙም መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ግን የየራሳቸውን ሀሳብ ያዋጣሉ። ታምራት መንግሥት የፊልም ኮሚሽን አቋቁሞ ሀገሪቱን የሚያስተዋውቁ ሥራዎችን ማበረታታትና የፊልም ወርክሾፖችንና ትምህርት ቤቶችን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን ይጠቅሳሉ። መንግሥት ይንን ዘርፍ ይፈልገዋል የሚለው ታምራት ለሥራ እድል ፈጠራ፣ የሀገሪቱን ባህል ለሌሎች ለማስተዋወቅ፣ የውጪ ምንዛሪ ለማግኘት መንግሥት ሥራዬ ብሎ መስራት አለበት ሲል ሀሳቡን ያጠናክራል። ለዚህ ደግሞ የደቡብ አፍሪካንና የናይጄሪያን ልምድ ማየት በቂ ነው ባይ ነው። የፊልም ቁሳቁስ ላይ የሚጣሉ ቀረጦች ላይ ማስተካከያ ቢደረግ የሀገር ውስጥ ፊልም ሰሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የውጭ ባለሙያዎችም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሰሩ በማበረታታት የውጪ ምንዛሪ ያስገኛል፤ የሚለው ታምራት መገንባት የምንፈልገውን ነገር ሁሉ አንደ ሀገር መገንባት የምንችለው ማንቀሳቀስ የምንፈልገውን የምናንቀሳቅሰው ዘርፉ በተገቢው መንገድ ሲደገፍ መሆኑን አጽንኦት ይሰጠዋል። ድርብ ድል ደግሞ "በፈጠራና በቴክኒክ እውቀት ባለሙያው ራሱን ብቁ ማድረግ አለበት" ይላል። አንድ የፊልም ባለሙያ መናገር የሚፈልገውን ታሪክ፣ ማሳየት የሚፈልገውን ጉዳይ በብስለትና በጥበብ ለማቅረብ ከጽሁፍ ጀምሮ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ የላቀ ሥራ ለማቅረብ ሲጥር አይስተዋልም የሚለው ድርብ ድል "ፊልም መስራትን እንደ ቀላል የመውሰድ አዝማሚያ ስላለ ፊልሞቻችን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ሳንችል ቀርተናል" ይላል። የእኛን ፊልም ከሌላው ዓለም ነጥሎ ማየት ተገቢ አይደለም የሚለው ድርብ ድል ፊልም ሰሪው የራሱን አቅም ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ አለመስራቱ ክፍተቱን እንዳይደፍን ማድረጉን ይጠቅሳል። ለፊልም ፕሮዲውሰሮች ማህበር አመራሩ ቢኒያም የፊልሙን ዘርፍ የሚመራው ባህልና ቱሪዝም ፖሊሲ ካወጣ አንድ ዓመት ከሰባት ወር ቢሆነውም በተግባር ላይ ለማዋል ግን ፈጣን እንቅስቃሴ እያደረገ አለመሆኑ ሊሻሻል የሚገባው ጉዳይ ነው። • "የናንዬ ሕይወት" የአይዳ ዕደማርያም ምስል ከሳች መፀሐፍ ፖሊሲው ይላል ቢኒያም "ያሉብንን የትምህርት፣ የመሰረተ ልማትና የስርጭት ችግሮችን ይፈታል፤ የስርጭት ችግራችን ብዙ ነው" የሚለው ቢኒያም አንድ ፊልም ለኢንተርኔት፣ ለቴሌቪዥን፣ ለሲኒማ ቤቶች ደጋግሞ የሚሸጥ በመሆኑ ፖሊሲው ወደ ሥራ ቢገባ ያየናቸውን የስርጭት ችግር እንደሚፈታ ያምናል። አክሎም "ዛሬም እንደ ቅንጦት እቃ ውስኪና ሲጋራ ተደራራቢ ታክስ እንከፍላለን ይህ መስተካከል አለበት" ይላል። መንግሥት የሚፈታቸው ችግሮች እንዳሉ ሆነው የፕሮዲውሰር ማህበሩ በራሱ ያሉበትን ችግሮች ለመፍታትም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ቢኒያም ይናገራ። ይህም ከዚህ በፊት ፊልሞች የእይታ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ይሰረቁ እንደነበር በማስታወስ ያንን ለማስቀረት በሁሉም ሲኒማ ቤቶች አዲስ እስከ 4ኬ የሚያጫውት ኢንክሪፕቲቭ ቪዲዮ ዲስፕሌይ ማስገጠማቸውንና የፊልሞችን ደህንትና ጥራት ማስጠበቃቸውን ይገልጻል። ሌላው ቢኒያም የጠቀሰው ፊልሞቹ የውጭ ምዛሬ እንዲያመጡ በኦንላይን መሸጥ እንዲያስችላቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል የዲያስፖራ አካውንት ለመክፈት እየሰሩ መሆኑን ነው። ሔኖክ መንግሥትና የፊልም ሰሪው የሚግባቡበት ፖሊሲ ቀርጸው ማስጸደቃቸውን በማስታወስ ፖሊሲው በቶሎ ሥራ ላይ ይዋል በሚለው የቢኒያም ሀሳብ ይስማማል። እንደፊልም ባለሙያ ግን የግል ብቃትን ማሳደግ፣ የዘርፉን እድገት ለማሻሻል በሚሰሩ ማህበራት ላይ መሳተፍ አስፈላጊ መሆኑንም ይጠቅሳል። በአሁኑ ጊዜ በርከት ያሉ የፊልም ትምህርት ቤቶች አለመኖራቸውን በማንሳትወደፊት የሚከፈቱት በጥራት ማስተማር እንዲጀመሩ ለማድረግ ሥራዎች ከአሁኑ መሰራት እንዳለባቸው ያስታውሳል። ጥሩ የተሰሩ ፊልሞችን ማበረታታት ተገቢ ነው የሚለው ሔኖክ ምሳሌ ስለሚሆኑ ሥራዎች አብዝቶ ማውራት ችግር ያለባቸውን ፊልሞች ያክማል ብሎ እንደሚምን በመግለጽ በዘርፉ ገንቢ አስተያየት መለዋወጥ ሚዳብርበት መድረክ እንዲመቻች ያለውን ፍላጎት ይገልጻል። አክሎም በአፍሪካ ውስጥም ሆነ ከአፍሪካ ውጭ ፊልም ሰሪው በትብብር ከሌሎች ጋር ለመስራት ክፍት መሆን እንደሚያስፈልገው ጠቅሶ ይህን እድል ፊልም ሰሪውም አጥብቆ መፈለግ እንዳለበት ይመክራል። በማንተጋፍቶት ስለሺ ተፅፎ የተሰናዳው ግርታ ፊልም በቅርቡ በቤልጂየም በተዘጋጀ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ላይ አሸናፊ ሆኗል። ሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለፊልም የዛሬ አርባ ዓመት በሚሼል ፓፓ ታኪስ የተሰራው ባለቀለም ፊልም ጉማ ይሰኛል። ጉማ ስያሜውን ብቻ ሳይሆን ከኦሮምኛ ቋንቋ የወሰደው በኦሮሞ ማህበረሰብ ውስጥ ባለው የግጭት አፈታት ባህል ላይ በማጠንጠን የተሰራ ዘጋቢ ፊልም እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የኢትዮጵያ ፊልም በአማርኛ ቋንቋ የተሰሩ ፊልሞችን በሳምንት ሁለት ወይንም ሦስት ሲያስመርቅ በዓመት በአማካይ ከ 80 በላይ ሲያመርት በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለመስራት ለምን ወኔ ከዳው? ባለሙያዎቹ መልስ አላቸው። ሁሉም ግን መልሳቸውን የሚጀምሩት ኢትዮጵያ በባህል፣ በታሪክ፣ በቋንቋ ብዝሃነት የታደለች መሆኗን በመጥቀስ ነው። ነገር ግን ይላል ታምራት ፊልም ቢዝነስ መሆኑ መረሳት የለበትም። በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ፊልም ሰርቶ ለገበያ ለማቅረብ ገበያ አለ ወይ? የሚለው መታየት አለበት ሲል ምክንያቱን ያስቀምጣል። ሌላው ዘርፉን የሚያውቅ፣ ከባህሉ የወጣ ብቁ ባለሙያ አለመኖር ችግር ነው። መንግሥት በተለያዩ ቋንቋዎች ለሚሰሩ ፊልሞችን የሚሰጠው ማበረታቻ ምን ያህል ነው? የሚለው መታየት አለበት ይላሉ ባለሙያዎቹ። አቶ ድርብ ድል በበኩሉ "በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አለመስራታችን አቢይ ምክንያቱ ለፊልም ትምህርት፣ ለሙያው ያለን ተጋልጦ ማነስ አስተዋጽኦ አድርጓል" ይላል። ፊልም ለመስራት ሀሳብና ይዘት ይዞ የሚመጣው ሰው ዳራ ወሳኝ ነው በማለት፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ፊልም ሰሪዎች እንዳይመጡ የአቅም እና የሙያ ክህሎት ክፍተት መኖሩ ላይ ይስማማል። ሌላው ደግሞ የፊልም ሰሪው ምርጫ ወሳኝ ነው ይላል። ለሔኖክ በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለመስራት የበጀት ውስንነት እንደልብ እንዳይዘረጉ በማድረግ ምርጫቸውን በመገደብ አሉታዊ ሚና መጫወቱን ይጠቅሳል። አንድ ፊልም ለመስራት ፍላጎት ቢኖር እንኳ የገንዘብ አቅም ውሱን መሆን በቀላሉ በቅርብ አካባቢ ያሉታሪኮች ላይ ለማተኮር ፊልም ሰሪው ይገደዳል ሲል ያሰስረዳል። በጣም ጥቂት ሰዎች የሚጠየቀውን በጀት መድበው ፊልሞችን ቢሰሩ እንኳ የገበያ ውስንነት ካለ ፊልሙ የወጣበትን ወጪ ስለማይመልስ የፊልም ፕሮዲውሰሮች በትንሽ ዋጋ ሰርተው ማትረፍ ወደ ሚያስችላቸው ፊልሞች ያዘነብላሉ ይላል። የፕሮዲውሰሮች ማህበር አመራሩ ቢኒያም በቀጣይ ዓመት በመላ ሀገሪቱ አዳዲስ ደረጃቸውን የጠበቁ 150 ሲኒማ ቤቶች ወደ ሥራ እንደሚገቡ አስታውሶ በየክልሉ ያሉ ፊልም አፍቃሪያንን ለመድረስ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በአማርኛ የሚሰሩ ፊልሞቸን ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተርጉሞ ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑን ተናግሯል።
news-50198594
https://www.bbc.com/amharic/news-50198594
በኦሮሚያ፣ በድሬዳዋና በሐረር ባለፈው ሳምንት ስላጋጠሙ ግጭቶችና ጥቃቶች አስካሁን የምናውቃቸው ነገሮች
ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ እኩለ ሌሊት ላይ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሀመድ በመንግሥት ተመድበውለት የነበሩት የደህንነት ጥበቃ አባላት 'በዚህ ለሊት እንዲነሱብኝ ታዘዋል' በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መልዕከት አሰፈረ።
ጃዋር እንደሚለው ማክሰኞ ዕኩለ ሌሊት አቅራቢያ ሁለት መኪኖች ወደሚኖርበት ቤት አካባቢ በመምጣት ጥበቃዎቹን እርሱ ሳያውቅ "እቃቸውን ይዘው ቤቱን ለቀው እንዲወጡ" እንደተነገራቸው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል። አክሎም ጥበቃዎቹ ለምን እንዲወጡ እንደጠየቁና ለስልጠና እንደሆነ እንደተነገራቸው እነሱም እንዳልተቀበሉ፣ ከዚያም ስልክ ተደውሎላቸው በአስቸኳይ ቤቱን ለቀው ካልወጡ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ጠቅሷል። • በተለያዩ ሥፍራዎች ባጋጠሙ ግጭቶች የሟቾች ቁጥር 67 ደርሷል • "ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው" አርቲስት ታማኝ በየነ ይህንንም ተከትሎ ደጋፊዎቹና የአገሪቱን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች ጃዋር ያሰፍራቸው የነበሩ አጫጭር መልዕክቶችን በመከታተል፣ ምን ሊከሰት እንደሚችል ግምታቸውንና በጉዳዩ ላይ አስተያየት በመስጠት መልዕክት ሲለዋወጡ እስከ ንጋት ቆዩ። ሌሎች የጃዋር አድናቂዎችና ተከታዮች ደግሞ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል በሚል ስጋት ከተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ቦሌ አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በማቅናት መሰባሰብ ጀመሩ። በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ደግሞ ጃዋር ገጠመው የተባለውን ነገር በመቃወም ሰልፎች ሲካሄዱ በአንዳንድ ቦታዎችም መንገዶች ተዘጉ፤ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተገታ። ረቡዕ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽር እንደሻው ጣሰው በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ላይ ቀርበው ጃዋር መሀመድ ለተከታዮቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው ጥቃት ሊደርስብኝ ነበር በማለት ያስተላለፉት መልዕክት ስህተት መሆኑን ገለጹ። አክለውም "በመንግሥትም በፖሊስም በኩል ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደም" በማለት ፖሊስ እንደወትሮው የየዕለት ተግባሩን እያከናወነ እንደሚገኝም አመልክተዋል። ኮሚሽነሩ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱና መደበኛ እንቅስቃሴዎች እንዲቀጥሉ ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን ፖሊስ የሕግ ማስከበር ሥራውን እንደሚቀጥል አመለከቱ። ጃዋር ረቡዕ ዕለት ለቢቢሲ እንደተናገረው "በውድቅት ለሊት በጣም አጠራጣሪ በሆነ መልኩ የተሞከረው ምን እንደሆነ አልገባኝም። የእስርም አይመስለኝም። በዱርዬዎች ቤቴ ላይ ጥቃት በማድረስ ለማሳበብ እንደታሰበ ነው ያሉኝ መረጃዎች የሚያሰዩት" በማለት በመኖሪያ ቤቱ የተፈጸመው ክስተት በእርሱ ላይ የተደረገ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ መደምደሚያ ላይ መድረሱን ተናግሯል። • "ያለን አማራጭ ውይይት ብቻ ነው" ጀዋር መሐመድ • ወደ ኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለፀ ከሰዓት በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተቀሰቀሱት ሰልፎች ግጭትና ጥቃቶችን በማስከተል በሰዎች ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች መውጣት ጀመሩ። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው በሰጡት መግለጫ ክስተቱ "መሆን ያልነበረበት ትልቅ ስህተት ነው" በማለት የክልሉ መንግሥትም ሆነ የፌደራል መንግሥት የጃዋርን ደህንነት እንደሚያስጠብቁ ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዝደንቱ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ስህተት ሲሉ የገለጹት ክስተት በማን እንደተፈጸመና፣ ለምን እኩለ ለሊት ላይ ማድረግ እንደታሰበ እንደሚጣራ አመለከቱ። ሐሙስ ሐሙስ ዕለት ግጭትና ጥቃቱ በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ፣ ከእነዚህ ቦታዎች የሚወጡ መረጃዎች ዳግሞ ክስተቶቹ የብሔርና የሃይማኖት ገጽታን መያዛቸውና ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም ከአስር በላይ መሆኑን ቢቢሲ ያረጋገጠ ሲሆን ቁጥሩም ከፍ እያለ መጥቶ ከ20 በላይ ሆነ። በሚፈጸሙ ጥቃቶች ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የአካል ጉዳትና ከፍ ያለ የንብረት ውድመትም አጋጥሟል። በዚህም በእሳት ከተቃጠሉ ተሽከርካሪዎች፣ የንግድ ተቋማትና መኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ የእምነት ተቋማትም ላይ ጉዳት ደርሷል። ሐሙስ ከሰዓት በኋላ የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎችና ፖለቲከኞች በአክቲቪስት ጃዋር መኖሪያ ቤት ተገኝተው በሰጡት የጋራ መግለጫ ወጣቶች ከሰሞኑ ከተከሰተው ግጭት ራሳቸውን እዲቆጥቡ ጥሪ አቅርበው ነበር። በዚህ ወቅት ጃዋር "ጉልበተኞች በጉልበታቸው ከቀጠሉ ግን ልክ እንደ ትላንቱ መፍትሄ ፈልግ እንልሃለን። .... አሁን ወደ ማረጋጋት ተመለሱ። ግን ሁል ጊዜም እንደምላችሁ ንቁ ሁኑ። አንድ ዓይናችሁን ብቻ ዘግታችሁ ተኙ" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። • የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስት ቀናት ጸሎት እና ምሕላ አወጀ • ወደ ኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለፀ ሐሙስ ዕለት ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ለማካሄድ ተሰብስቦ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአገሪቱ እየተከሰተ ያለውን ግጭትና ጥቃትን መሰረት አድርጎ ባወጣው የሰላም ጥሪ "አገሪቷ እንኳንስ ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰቡ የማይገባቸው ጎሳንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ መጠነ ሰፊ ግጭቶች በተለያዩ አካባቢዎች መስፋፋታቸው እንዳሳሰበው" ገልጾ ለሦስት ቀናት የጸሎትና ምሕላ አውጇል። አርብ ግጭቱና ጥቃቱ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኙትን ቢሾፍቱ፣ አዳማና አምቦ ውስጥ ለሁለት ቀናት ቆይቶ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ከእነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ ኮፈሌ፣ ዶዶላ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋና ባሌ ሮቤ ውስጥ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ግጭትና ጥቃቶች መፈጸማቸው የተሰማ ሲሆን የሞቱና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍ እንዲል አድርጓል። ቢቢሲ ከሆስፒታል ምንጮች፣ ከመንግሥት አካላትና ከሟች ቤተሰቦች ባሰባሰበው መረጃ መሰረት በሁለቱ ቀናት ግጭት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 44 መድረሱን ያረጋገጠ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህ የላቀ እንደሚሆን ስጋት እንዳለ አመልክቶ ነበር። አርብ ረፋድ ላይ፣ ረቡዕና ሐሙስ ዕለት የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሰረት የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ተናገሩ። የመከላከያ ሠራዊት በፍጥነት ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ጉዳት ማጋጠሙን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ በወቅቱ ጠቁመዋል። በዚሁ ቀን 10፡00 ሰዓት ገደማ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ከመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ፣ ከሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል እና ከፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሸነር ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ላይ የቤተክርስቲያኗ ተወካዮች በቤተክርስቲያን ላይ የሚቃጣው ጥቃት እንዲቆም እና መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን እንዲያከናውን ጠይቀዋል። አርብ ምሽት ሮይተርስ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው በግጭቱና በጥቃቶቹ ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች 67 መድረሱን አመልክቶ፤ ከሟቾቹ አስራ ሦስቱ በጥይት ቀሪዎቹ 54ቱ ደግሞ በድንጋይና በዱላ ተደብድበው እንደሞቱ ገልጿል። የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥርም ከሁለት መቶ በላይ መሆኑም ተነግሯል። ቅዳሜ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር በአገሪቱ የተከሰተው ግጭትን በተመለከተ በኤምባሲው የፌስቡክ ገጽ ላይ በስማቸው በወጣ መልዕክት ላይ "ሰሞኑን በታዩት የጥላቻና ጠብ አጫሪ ንግግሮችና ጥቃቶች" በእጅጉ መረበሻቸውን አመልክተው፤ "የጥቃቶቹ ተሳታፊዎችንና ጥቃቶቹን የሚያነሳሱትን አጥብቀን እናወግዛለን። እንዲህ አይነቱ ድርጊትም ምንም አይነት ማሳመኛ ሊቀርብለት አይችልም" ብለዋል። አገራቸው በኢትዮጵያን ሰላም፣ ብልጽግናና አካታች የሆነ የፖለቲካ ሁኔታ እንዲፈጠር እንደምትሰራና ያልተቆጠበ ድጋፍ እንደምትሰጥ አመልክተው፤ ለዚህም አላማ ከሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቅሰዋል። አምባሳደሩ ሲያጠቃልሉ "ሁሉም ለሚፈጽመው ድርጊትና ውሳኔ ኃላፊነት አለበት። ስለዚህም ጥቃቶችን ማነሳሳትም ሆነ ድርጊቱን አለማውገዝ ተቀባይነት የለውም። ሁላችንም ሰላምን፣ አንድነትንና መቻቻልን የመምረጥ ነጻነት እንዲሁም ኃላፊነት አለብን" ብለዋል አምባሳደር ራይነር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ በሩሲያና በአፍሪካ መሪዎች መካከል ለሁለት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ በነበረበት ወቅት የተከሰተውን ይህን ግጭት በተመለከተ ከጉባኤው እንደተመለሱ ስለጉዳዩ አንዳች ነገር ይላሉ ተብለው የተጠበቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ቅዳሜ ምሽት ነበር መግለጫ የሰጡት። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ተብሎ ከጽህፈት ቤታቸው የወጣው የጽሁፍ መግለጫ በተከሠተው እጅግ አሳዛኝ ግጭት፣ በዜጎችና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት፣ ማዘናቸውን ገልጸው "የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና አጥፊዎች በሕግ ፊት ቀርበው ተገቢው ሁሉ እንዲያገኙ ያለማወላወል እንሠራለን" ማለታቸው በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ አክሎም "ይህ ሁሉ ለምን እንደመጣብን እናውቃለን። ከዚህ የበለጠ ፈተና ቢያጋጥመንም እንኳን የጀመርነውን ጉዞ አናቋርጥም። አረሙን እየነቀልን፤ ስንዴውን እየተከባከብን እንሄዳለን እንጂ ለአረሙ ስንል ስንዴውን አንተወውም" ብለዋል። ረቡዕና ሐሙስ በነበረው ግጭት ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በድሬዳዋ 110፣ በአዳማ ደግሞ ከ60 ሰዎች በላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
news-52726230
https://www.bbc.com/amharic/news-52726230
ኮሮናቫይረስ፡ በህመሙ ለመጠቃት ምን ያህል የቫይረስ ቅንጣት መጠን ያስፈልጋል?
የሰው ልጅ ደሴት አይደለም፤ ብቻችንንም ልንኖር አልተፈጠርንም። ያንንም በመገንዘብ ለሺዎች ዓመታት ሰዎች በአንድነት ኖረዋል።
በዓለም ታሪክ ውስጥ በዚህ ወቅት እየሆነ እንዳለው ማኅበራዊ ህይወት ጠንቅ ውስጥ ገብቶ አያውቅም። የኢትዮጵያ እናቶች እንደሚሉት "ከሰው የማያገናኝ፤ ማኅበራዊ ህይወት የሚጠላበት ክፉ ወቅት" ሰው ሰውን እንደሌባ የሚጠራጠርበት ዘመን። አውቶብስ ውስጥ ለመግባት ተሰልፈን ተራችንን እየጠበቅን ድንገት የሚያስነጥስ ሰው ስናይ፣ ይሄ ሰውዬ ያስተላልፍብኝ ይሆን? አውቶብስ ውስጥ ልግባ ወይስ ዝም ብዬ ልሂድ? ብለን ራሳችንን እንጠይቃለን። ምግብ ከቤት ውጭ መመገብ የከተሜነት ባህል በሆነባት ዓለም ወደ ምግብ ቤቶች መሄድ አለመሄድ በአሁኑ ወቅት ፈታኝ ሆኗል። ከዚህ ሁሉ በላይ የየእለት ጉዳያችንን ለማከናወን የሕዝብ ትራንስፖርት መጠቀም ለብዙዎች የሚፈሩትም ጉዳይ ከሆነ ከራረመ። በተለይም በአሁኑ ጊዜ የኮሮናቫይረስን መዛመትን ለመግታት አገራት የወሰዷቸውን እርምጃዎች እያላሉ ባሉበት ሁኔታ ሕዝቡ ወደቀደመ ህይወቱ እየተመለሰ ነው። የተለያዩ ማኅበራዊ ህይወታቸውንም ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ቢሆንም፤ ሠርግ፣ ቀብር፣ ተሰባስቦ መመገብና የመሳሰሉት የቫይረሱን መዛመት ሊጨምሩት ይችላሉ የሚል ስጋትን አዝለዋል። በተለይም ሁለተኛ ዙር ወረርሽኙኝ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ፍራቻን አንግሷል። የሰውነትን በሽታዎችን የመከላከል አቅም ላይ ጥናትን ያደረጉት የሥነ ህይወት (ባዮሎጂ) ረዳት ፕሮፌሰር ኤሪን ብሮሜጅ የኮሮናቫይረስ ስጋትን ልንቀንስ የምንችልበት እንዲሁም እንዳይዘን የምናደርግበት ሁኔታን በተመለከተ ቢቢሲ ምክር እንዲለግሱ ጠይቋቸዋል። በማሳቹሴትስ ዳርት ማውዝ ዪኒቨርስቲ ስለ ወረርሽኝና ተላላፊ በሽታ የሚያስተምሩት ፕሮፌሰር ኤሪን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በቅርበት ተከታትለውታል። ራሳቸውን በበሽታዎች ላይ ልሂቅ አድርገው የማይቆጥሩት ፕሮፌሰሩ በአንፃሩ ራሳቸውን ሳይንሳዊ መረጃዎችን አቀባይ ብለው ነው የሚጠሩት። በኮሮናቫይረስ ስጋቶች ላይ የፅሁፍ ስራዎችን ያበረከቱ ሲሆን አንደኛው ፅሁፋቸውም 16 ሚሊዮን ጊዜ ተነቧል። ወደቀደመ ህይወታችን ለመመለስ በምናደርገው ጥረት ውስጥ እንዴት ደኅንነታችንን መጠበቅ እንደምንችል የለገሷቸው ምክር እነሆ። ሰዎች የት ነው የሚታመሙት? ፕሮፌሰር ኤሪን እንደሚሉት አብዛኛው ሰው በቫይረሱ የሚጠቃው በቤቱ ውስጥ ሲሆን፤ ይህም ከሩቅ ሰው ሳይሆን ከቤተሰብ አባላት ጋር በሚደረግ ንክኪና ግንኙነት ነው። ከቤታችን ውጭ ስንሆንስ? በየቀኑ አየር ለመቀበል በምንራመድበት ወቅት? ወደፓርኮች በምንሄድበት ወቅትስ? አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያለ ፊት ጭምብል የሚሮጡ ሰዎች ቫይረሱን ሊያስተላልፉብን ይችሉ ይሆን? የሚሉት በርካታ ጥያቄዎች በአእምሯችን ይመላለሳሉ። ፕሮፌሰሩ ለዚህ ምላሽ አላቸው የሚተላለፍበት አጋጣሚ ትንሽ ነው ይላሉ። "ከቤት ውጭ ባሉ ቦታዎች በምንተነፍስበት ወቅት ትንፋሻችን በአጭር ጊዜ ነው በንኖ የሚጠፋው። በአየር ላይ የመቆየት እድል የለውም" ይላሉ። ይህ ማለት በቫይረሱ ለመያዝ ረዘም ያለ ጊዜ አይኖርም ማለት ነው። "በቫይረሱ ለመያዝ ማጥቃት የሚችል የቫይረሱ መጠን መኖር አለበት። ከዚህ ቀደም በመርስና ሳርስ ተላላፊ በሽታዎች ላይ በተደረገ ጥናት 1 ሺህ መጠን ያለው የቫይረስ ቅንጣቶች ያስፈልጋሉ። ከዚህም በመውሰድ ለኮሮናቫይረስም አንድ ሺህ የቫይረስ ቅንጣቶች እንደሚያስፈልጉ ተረድተናል" በማለት በፅሁፋቸው ላይ አትተዋል። ይህ ቁጥር አሁንም ቢሆን አከራካሪ ሲሆን በተለያዩ ሙከራዎችም የሚወሰን አይደለም። ሆኖም ግን ቫይረሱ እንዴት እንደሚተላለፍ ጠቃሚ መረጃን ይሰጣል። ዋናው ጉዳይ የተጠቀሱት የቫይረሱ ቅንጣቶች ቁጥር ላይ በተለያየ መንገድ ከተጠቀሰው አንድ ሺህ ቅንጣቶች መድረስ ይችላል። "በአንድ ትንፋሽ አንድ ሺህ የቫይረሱን ቅንጣቶች ሊቀበሉ ይችላሉ ወይም በአስር ትንፋሽ መቶ የቫይረሱን ቅንጣቶች እንዲሁም ሌላ አማራጭ በመቶ ትንፋሾች አስር የቫይረሱን ቅንጣቶች ሊሆን ይችላል። እያንዳንዷ አጋጣሚ ግን በቫይረሱ ወደመጠቃት የሚያመሩን ናቸው" በማለት ያስረዳሉ። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር አጭር ጊዜ ካሳለፍን ወይም ያለ ጭምብል አካላዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ያገኘናቸው ሰዎች በቫይረሱ የምንጠቃበትን የቫይረስ ቅንጣት መጠን ማስተላለፍ አይችሉም። ስለዚህ መጠንቀቅ ያለብን ከምን አይነት ጉዳዮች ነው? የበሽታውን ምልክት የሚያሳዩ ሳልም ሆነ ማስነጠስ በተለያየ ደረጃ በሽታውን በከፍተኛ ሁኔታ ያስተላልፋሉ። እንደ ፕሮፌሰሩ ከሆን አንዴ በሚሳልበት ወቅት በአማካኝ ሦስት ሺህ ጠብታዎች የይረጫሉ። ጠብታዎች ከበድ ያሉ ሲሆኑ በአንዴም ወደ መሬት ይንጠባጠባሉ፤ የተወሰኑት ደግሞ በአየር ላይ ይቀሩና በነፋስ አማካኝነት የመጓዝን እድል ያገኛሉ። ነገር ግን ድንገት በአሳንሰር (ሊፍት) ውስጥ ሆነው አንድ ግለሰብ ከመሳል ይልቅ ቢያነጥስ በቫይረሱ የመያዝ እድልዎ አስር እጥፍ ይጨምራል። በአንድ ማስነጠስ በአማካኝ ሰላሳ ሺህ ጠብታዎች ይወጣሉ፤ በክብደታቸውም ቀላል ስለሆኑ ረዥም ርቀትን የመጓዝ አቅማቸውም በጣም ከፍተኛ የሚባል ርቀትን መሸፈን የሚችሉ እንደሆነ ፕሮፌሰሩ ይናገራሉ። "በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ቢያነጥስ ከሰውየው የሚወጣው የቫይረሱ ቅንጣት ሁለት መቶ ሚሊዮን ይደርሳልም" በማለትም ምሁሩ በፅሁፋቸው ላይ አስፍረዋል። "እናም በቫይረሱ የተያዘ ሰው ጋር አንድ ላይ ተቀምጠው እያወሩ ፊት ለፊት ቢያነጥስብዎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቫይረሱ ቅንጣቶች ከመለቀቃቸው አንፃር የሚጠቁበትም ዕድል ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችሉ ማወቅ ይገባዎታል።" ድንገት እንኳን በቫይረሱ የተጠቃው ሰው አስነጥሶ ወደ ሌላ ቦታ ቢሄድ እንኳን ከመጠቃት አምልጠዋል ማለት አይደለም፤ አንዳንድ ጠብታዎች በአየር ላይ ለደቂቃዎች የመቆየት እድል አላቸው። እዚያ ክፍል ሰውየው በሌለበት ወቅት ቢገቡ ሊጠቁ ይችላሉ። ምልክት የማያሳዩ አስተላላፊዎች በቫይረሱ የተጠቁ ህሙማን ምልክቶቹን ለአምስት ቀናት ላያሳዩ ይችላሉ፤ ሆኖም በሽታውን ያስተላልፋሉ። አንዳንዶቹም ጭራሽ ምልክት እስከ መጨረሻው ላይታይባቸው ይችላል። ከዚህም በላይ በትንፋሽም ቫይረሱ ወደ ከባቢው ይለቀቃል። ግን ምን ያህል? በአንዴ የምንተነፍሰው ከ50 አስከ 5000 ጠብታዎች ይኖሩታል። አብዛኛዎቹ ጠብታዎች በፍጥነት መሬት ላይ ያርፋሉ። በተለይም በአፍንጫችን በምንተነፍስበት ወቅት የጠብታዎቹ መጠን ይቀንሳሉ። "በምንተነፍስበት ወቅት ተጣርቶ ስለሆነ የሚወጣው የቫይረሱም ቅንጣቶች ይቀንሳሉ። ከዚህም በተጨማሪ በምንተነፍስበት ወቅት ወደውጭ መግፋት የሚያስችለን ከፍተኛ ኃይል ስለሚያጥረን፤ ከታችኛው የመተንፈሻ አካላችን የቫይረሱ ቅንጣቶች አይወጡም" በማለት ለቢቢሲ አስረድተዋል። ይሄ ጉዳይ በጣም ጠቃሚ ግኝት ነው፤ ምክንያቱም የኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠራቅሞ የሚገኘው በታችኛው የመተንፈሻ አካላችን ውስጥ በሚገኙ ህብረ ህዋሳት ነው። ሆኖም አንድ ሰው በሚተነፍስበት ወቅት ምን ያህል የኮሮናቫይረስ ቅንጣቶች እንደሚለቀቁ መረጃ የለም፤ ሆኖም ፕሮፌሰሩ በጉንፋን ላይ የተደረገ ጥናትን ጠቅሰው ከ3 እስከ 20 ሊሆን ይችላል ይላሉ። ለኮሮናቫይረስም በተመሳሳይ መልኩ የሚሰራ ከሆነ አንድ ህመምተኛ ሃያ የቫይረስ ቅንጣቶችን የሚተነፍስ ከሆነ በቫይረሱ ለመያዝ ሰውየው ያለማቋረጥ ለአምሳ ደቂቃ ሊተነፍስብን ይገባል። በዚህ መሰረት ነው አንድ ሺህ ያህል የቫይረሱ ቅንጣቶች ላይ መድረስ የሚቻለው። ስለዚህ ምልክት የማያሳዩ ሰዎች ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ መሆን በሽታው ላይተላለፍ ይችላል። መናገር የጠብታዎቹን መጠን በአስር መጠን የሚጨምረው ሲሆን በደቂቃም 200 ያደርሰዋል። መዝፈን እንዲሁም ባልተገባ መንገድ እየተወናጨፉ መጮህ በአየር ላይ የሚፈናጠሩትን የጠብታዎች መጠን እየጨመረው ይሄዳል። "በመድረክ ላይ ሆነው በሚጮሁበት እንዲሁም በሚዘፍኑበት ወቅት ጠብታዎቹ በቀጥታ ወደ ሳንባ ነው የሚገቡት" በማለት ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ እነዚህም ጠብታዎች የሚወጡት በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ ከተጠቁ ህብረ ህዋሳት ነው። "ለመጮህ ከፍተኛ የሆነ ኃይል ስንጠቀም፤ ጠብታዎቹም የሚወጡት በከፍተኛ ሁኔታ የቫይረሱን መጠን ከያዙት ህብረ ህዋሳት ነው" ይላሉ። ምንም እንኳን በዚህ መንገድ የቫይረሱ የመተላለፍ ሁኔታ በጣም ዝቅተኛ ቢሆንም፤ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከቤት ውጭ ቫይረሱን የሚያዛምቱት የኮሮናቫይረስን ምልክቶች የማያሳዩ ናቸው። የትኞቹ አካባቢዎች የበለጠ አስጊ ናቸው? ግልፅ በሆነ መንገድ ከቫይረሱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው የጤና ባለሙያዎች በስጋት የአንበሳ ድርሻውን ይይዛሉ። አንዳንድ አካባቢዎችም እንዲሁ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ ተይዘውበታል። በተለያዩ መርከቦች፣ የቢሮ ስብሰባዎች፣ ስፖርታዊ ዝግጅቶች፣ የልደት ድግሶች እንዲሁም የቀብር ሥርዓቶች ፕሮፌሰሩ ከሚጠቅሷቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው። በእነዚህ አጋጣሚዎች ድንገት የታመመ ሰው ካለ በርካታ ሰዎች ተሰባስበው ረዘም ያለ ጊዜን ማሳለፋቸው በቫይረሱ የመጋለጣቸውን ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምረዋል። "ምንም እንኳን አስራ አምስት ሜትር ርቀት ላይ ቢገኙም፣ በአየር ላይ የሚገኘው ቫይረስ ካሉበት ለመድረስ ሩቅ ቢሆንም፤ ረዘም ያለ ጊዜ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቫይረሱ የመጠቃት ሁኔታዎን ይጨምረዋል" ይላሉ። ወደ ሥራም በምንመለስበት ጊዜ አንዳንድ የሥራ አይነቶችም በተለየ መንገድ ስጋት ይኖራቸዋል። የተለያየ ክፍል የሌላቸው፣ አዳራሽ በሚመስል ሁኔታ የተሰሩና አየር መተላለፍ የማይችልባቸው ቢሮዎች የሚሰሩ ሰዎች ፈታኝ ሁኔታ ይገጥማቸዋል። ፕሮፌሰሩ እንደ ምሳሌ የሚጠቅሱትም በደቡብ ኮሪያ በአንድ ቢሮ ውስጥ ከሚሰሩ 216 ሠራተኞች መካከል 94ቱ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ነው። በቫይረሱ የተጠቁትም አብዛኛው አንድ ሰፋ ያለ ቢሮን የሚጋሩ ናቸው። የጥርስ ሐኪሞች ብዙ ባይባሉም ለኮሮናቫይረስ ስጋት የተጋለጡ ናቸው። "የጥርስ ሐኪሞች የሥራቸውን ቦታ እንደገና ሊያጤኑት ይገባል። በዋነኝነት የሚጎዱት የጥርስ ሐኪሞቹ ናቸው፤ ህመምተኞቹ አይደሉም። ህመምተኞቹ በቀላሉ ወደ ሐኪሞቹ ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ምክንያቱም ሃኪሞቹ ተጠግተው ጥርስ ይቦረቡራሉ፣ ከአፍ የሚወጣውን ፈሳሽ ሁሉ ያጸዳሉ። ዶክተሮቹ የራሳቸውን ጤንነት ቢጠብቁም የህመምተኞቻቸውን ሁኔታ ማወቅ ግን አይችሉም" ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ መምህራንም በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ናቸው። "በእድሜያቸው ጠና ያሉ መምህራንና ፕሮፌሰሮች በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች በአንድ ክፍል ውስጥ ያስተምራሉ። እነዚህን የሥራ አይነቶች ደኅንነታቸውን የተጠበቀ ለማድረግ ኮሮናቫይረስን ከግምት ውስጥ በማስገባት መከለስ ያስፈልጋል" ብለዋል። ከቤት ውጭና በቤት ውስጥ እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ከቤት ውጭ የተያዙት በቁጥር በጣም ትንሽ ናቸው። ነፋስ፣ አየር፣ የፀሐይ ብርሃን፣ ሙቀትና እርጥበት ቫይረሱን በአየር ላይ ላያቆዩት ይችላሉ። ስለዚህ አካላዊ ርቀታችንን ጠብቀን፣ ከሰዎች ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ በመቀነስ ስጋቱንም ልንቀንስ እንችላለን። ሆኖም አንዳንድ ከቤት ውጭ የሚደረጉ መስተጋብሮች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ሰዎች ተሰብስበው የሚያወሩበት፣ የሚዘፍኑበት እንዲሁም የሚጮሁበት አጋጣሚ ከሆነ ስጋቶች ይጨምራሉ። በቤት ውስጥ የሚደረጉ አካላዊ ርቀቶች ከጊዜ በኋላ እየቀሩ ይመጣሉ። በዚህም ሁኔታ ዝቅተኛ አየር የሚዘዋወርበት ሁኔታ ካለ ደግሞ ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል። ሆኖም የተለያዩ እቃዎችን ለመሸመት በምንወጣበት ጊዜ ብዙ በመደብሮች ላይ የምናሳልፈው ጊዜ የተወሰነ ከሆነ ስጋቱም በጣም ዝቅተኛ ይሆናል። ስጋቶችን መገምገም የኮሮናቫይረስ መመሪያዎች እየላሉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት እንቅስቃሴዎቻችን ምን አይነት ስጋት ሊያስከትሉ ይችላሉ የሚለውን መገምገም አለብን። የትኛውም ቢሮም ይሁን ቤት ውስጥ በምትሆኑበት ወቅት ቦታው ያለውን ስፋት፣ ያሉትን ሰዎች ብዛት እንዲሁም ምን ያህል ጊዜ በዚያ ቦታ እንደምናሳልፍ ልናስብበት ይገባል። "አየር የሚተላለፍበትና፣ ጥቂት ሰዎች ያሉበት ቦታ ከሆነ ስጋቱ ዝቅተኛ ነው። ግን ቢሮው ሰፊና ብዙዎች የሚጋሩት ከሆነ ስጋቱን እንደገና ልናጤን ይገባል። ከዚህም በተጨማሪ የሥራዎ ሁኔታ ፊት ለፊት መነጋገር እንዲሁም ጮክ ብሎ መነጋገር ያለበት ከሆነ ስጋቱ ስለሚልቅ በከፍተኛ ሁኔታ ልናስብበት ይገባል።" "ምንም እንኳን ያተኮርኩት ትንፋሽ፣ ማስነጠስና ሳል ላይ ቢሆንም ሌላ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያለብን ጠብታዎቹ የሚያርፉበትን ቦታ ነው። ሁልጊዜም ቢሆን እጃችንን በተደጋጋሚ መታጠብ፣ ፊታችንን መንካት ማቆም አለብን" በማለት ጽፈዋል። በመጨረሻም ለልደታችን ተብሎ የተዘጋጀው ኬክ ላይም ሻማ ማጥፋት እንድናቆምም መክረዋል።
48701096
https://www.bbc.com/amharic/48701096
"ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር )
ፀደቀ ይሁኔ ወልዱ (ኢንጂነር ) የፍሊንት ስቶን ኢንጂነሪንግ መስራችና ባለ አክሲዮን ናቸው። በዚህ ዓመትም በ29 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያስገነቡትና በአባታቸው ስም የሰየሙት አዳሪ ትምህርት ቤት በደሴ ሥራውን ጀምሯል። በቅርቡም "ሾተል" የሚል መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል። በመጽሐፉና በሙያቸው ዙሪያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። መጽሐፍዎት ምን ላይ የሚያተኩር ነው?
ፀደቀ ይሁኔ፦ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ ነው የፃፍኩት። የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ባለ ሁለት ስለት ቢላ ነው። በአግባቡ ካልተያዘ በአንድ በኩል ሰውን ይጎዳል በአንድ በኩል ሊያለማ ይችላል የሚል ነገር ነው ያለው። በመጽሐፉ ውስጥ አምስቱ ቁልፍ ችግሮቻች ያልኳቸው የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን፣ ንግድ፣ ትራንስፖርት እና ፋይናንስን በሚገባ ለማየት ሞክሬያለሁ። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት አሁን ያለነው ሁለተኛው የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ ነው። ይህ የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ምርመራ ያስፈልገዋል በማለት ለመፃፍ የተነሱት መቼ ነው? ፀደቀ ይሁኔ፦ መጀመሪያ ላይ ያሰብኩት በበራሪ ወረቀት መልኩ ሀሳቤን ለማካፈል ነበር። ከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን፣ ንግድ፣ ትራንስፖርትና ፋይናንስ እነዚህን አምስቱ ጉዳዮችን በማንሳት ውይይት እናድርግ በሚል ለሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች በኢሜል እየላኩ ብቆይም ብዙም ሀሳቤን አልቀለቡትም። ከዚያ ግራ ተጋባሁ፤ በኋላ ላይ ደግሞ አንድ ሰው ሌሎቹንም ጨምራቸው ሲለኝ ኢንዱስትሪንና ግብርናን ጨምሬ እንደገና ላኩላቸው። በዚህ ሂደት ላይ እያለሁ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመጡት። እርሳቸው እንደተመረጡ የእድገትና የትራንስፎርሜሽኑ ግምገማ ህዝባዊ መድረኮች መካሄድ ጀመሩ። ሕዝባዊ መድረኮቹ ላይ ህዝቡ የሚያነሳቸውና አመራሩ የሚረዳበት መንገድ አልገጠመልኝም። • "ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም ሕብረተሰቡ እሮሮውን በግልፅ ነው የሚያስረዳው። አመራሩ ግን በእሮሮ ውስጥ ችግሮቹንና መፍትሄዎቹን የመቅለብ አቅሙ ዝቅተኛ ሆነብኝ። እና አሁንም ሌላ ጠበብ ያለ መድረክ እናዘጋጅ ብዬ ፋና ብሮድካስቲንግና ብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን አንድ ላይ ሆነው እኔ ትንሽ እገዛ አድርጌ የዛሬ ዓመት ገደማ አንድ መድረክ አዘጋጀን። እዚያ መድረክ ላይም የተነሱት ነገሮችን ስመለከታቸው ብዙ ሰው የታየው ነገር የለም። ስለዚህ ይህንን ነገር በደንብ ባየው ይሻላል በማለት ትንሽ ጽፌበት በመጽሀፍ መልክ ቀላል መረዳት (ኮመን ሴንስ) የሚጠይቁትን ነገሮች ባሰፍር፤ በዚህ በለውጥ ወቅት ብዙ ሰው ትራንስፎርሜሽንን ተገንዝቦ አዲሱን የለውጥ አመራር ያግዛል ብዬ በዚያ መልክ ጀመርኩት። በኋላ ግን ሳየው፤ መረጃዎችን ስሰበስብ ውስጡ ብዙ ችግሮች አሉት። እና ይኼ በ100 ገፅ በራሪ ወረቀት ሊሆን አይችልም አልኩ። ምክንያቱም ፋይናንስ ብቻ 200 ገፅ ሆነብኝ። ለዚያውም ቆራርጨው ነው አንጂ የሰራሁት አጠቃላይ ወደ 800 ገፅ ነበር። ከዚያ ለሕትመት እንዲሆን በማለት ወደ 500 ገጽ አሳጠርኩት። • የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው 'ሞባይል' እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን? የኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ መስመር ህፀጾች አሉበት። በነፃነትና በእኩልነት የሚያምን ድርጅት ነፃነትና እኩልነትን አላራመደም። በገበያውና በፖለቲካ ውስጥ ነፃ ገበያንና ነፃ ፖለቲካን ዋና ምሰሶዎቼ ናቸው ብሎ የተነሳ ድርጅት ነፃ ገበያም አላካሄደም ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም። ገና በ97 ዓ.ም ነፃነት ፖለቲካው ላይ ትንሽ ብቅ ሲል ደነገጠና ዝግት አደረገው። ልክ የፖለቲካውን ነፃነት ሲዘጋው ነፃ ገበያውም በነፃ ፖለቲካው ማፈኛ ሥርዓት ነፃ ገበያውን የሚቆጣጠሩ ኃይሎች መጡና የነበረውን እንዳልነበር አደረጉት። ያንን ነው በማስረጃ አስደግፌ ከንድፈ ሃሳባዊ መነሻ ጋር ለማየት የሞከርኩት። ለምሳሌ የኢትዮጵያ መንግሥት ስለታይዋን በጣም ነው አድንቆ የሚያወራው። ታይዋን ማለት ግን የነዋሪውን ብዛት የቆዳውንም ስፋት ስታየው ከአዲስ አበባ የማይተልቅ ኢኮኖሚ ያላት ሀገር ነች። በዚህ ብዝኀነት በበዛበት ሀገር የታይዋንን ሞዴል እጭናለሁ ማለት ከዲሞክራሲ ጋር የሚሄድ አይደለም። ማነሷ ብቻ አይደለም መሪዎቿ የደሴቲቱን ነዋሪዎች እንደ ሁለተኛ ዜጋ ጨቁነው ያሳደጓት ሀገር ናት። እንደዛ ተጨቁኖ ሊያድግ የሚፈልግ የኢትዮጵያ ሕዝብ የለም። ጭቆናውን የሚፈቅድ ሕዝብ ባለበት የታይዋን ሞዴል ሊሰራ ይችላል። ጭቆናውን የማይፈቅድ ማህበረሰብ ባለበት ግን መጀመሪያ ላይ የዛሬ 19 ዓመት መለስ ዜናዊ ዲሞክራሲ፣ ነፃ ገበያ አማራጭ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው ብሎ ጽፎታል። መንገድም ግብም ነው ብሎ ነው የሚጀምረው። ፈጣን እድገት ሁሉንም አሳታፊ የሆነ፣ ከተመፅዋችነትና ከፖሊሲ ተጽዕኖ የራቀ ብሎ ያስቀመጠ ድርጅት በኋላ ግን የሁሉም መጫወቻ ነው የሆነው። አሁን ያንን መመለስ ይቻላል። የተጻፈ ነገር ስለሆነ ያንን ተከትሎ መሄድ ይቻላል። የሰው ሀሳብ ነው ገጣጥሜ የጻፍኩት የራሴ ሀሳብ የለበትም። በእርስዎ ሀሳብ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ መሬት ላይ ወርዷል? ስኬታማ ነበር? ፀደቀ ይሁኔ፦ የመጀመሪያው አምስት ዓመት መለስ በሕይወት ስለነበር በደንብ ነው የሄደው። በተለይ ደግሞ እስከ 97 ዓ.ም ድረስ የነበረውን ነፃ አካሄድ ከዐዕቅዱም በፊት በድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ውስጥ ነበረው እንቅስቃሴ ውስጥ የነበረው ነፃ አስተሳሰብ መልሶ ማምጣት ይቻል ነበር። ያንን ማድረግ አልቻለም። እንደሚመስለኝ ከ2002 በኋላ በጂቲፒ 2 የበለጠ ነፃ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ለማካሄድ ታስቦ፣ እንኳን ከውጪ ነፃነት ሊኖር በዛው በኢህአዴግ ውስጥም ነፃ ወስጠ ድርጅት ዲሞክራሲ ጠፋ። በዚያ ዲሞክራሲ በጠፋበት ጊዜ ደግሞ ኃያል የሆኑ ሰዎች በፈቀዱት መንገድ መሩት። ለሕዝብ ያልወገነ ሁሉም ለየራሱ የቆመበት አካሄድ ስለሆነ የሄደው መጨረሻው እንደምናየው ታሪክ ነው የሆነው። አንድ ቀን ያ እንዴት እንደሆነ ከእኔ የበለጠ የሚያውቁ ሰዎች መፃፋቸው አይቀርም። • ኢሳያስን ለመጣል ያለመው'#ይበቃል' የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ አሁን ግን የታቀደው ምን ነበር? ወዴት ነው የምንሄደው? ካልክ ዘጠና በመቶ በሥራ ላይ የዋለው ህብረተሰብ 41 በመቶው ለራሱ ሥራ የፈጠረ ነው። 39 በመቶ በግብርና 11 በመቶው በግሉና በመንግሥት ተቀጥሮ ነው ያለው። ብዙ ጊዜ የምንሟገተው በግሉና በመንግሥት ተቀጥሮ ስላለው 11 በመቶው ነው። 89 በመቶውን ሕብረተሰብ የሚያስተናግድ ሥራ ሳንሰራ፣ ስለእርሱ ሳናወራ ትራንስፎርሜሽን ማምጣት አንችልም። መጽሐፉ ውስጥ ዝርዝር ነገሮች ተቀምተዋል። ብዙ ስህተቶች ሊኖሩት ይችላሉ። የዓላማ ስህተት ግን እንደሌለው አረጋግጥልሀለው። ጂቲፒው ተመልሶ መስመር ውስጥ መግባት አለበት። መንግሥት የተለያዩ የሕዝብ ንብረቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወር እየተንቀሳቀሰ ነው፤ እርስዎ በዚህ እርምጃ ላይ ያለዎት አቋም ምንድን ነው? ፀደቀ ይሁኔ፦ ልማት ምርጫ አይደለም። ልማታዊ መንግሥት ያልሆነ የለም። መንግሥት ነው ካልን ልማት አለ። ያልለማ ሀገር ላይ አለመልማት ጭራሽ የሚታሰብም ነገር አይደለም። ልማት ምን ጊዜም ቢሆን የፖለቲካ አጀንዳ ከመሆን አይቆምም፤ በበለፀጉት ሀገሮችም እንኳ ቢሆን። ጥያቄው ልማትን ማን ያልማ የሚል ነው። መንግሥት ያልማ ወይስ የግሉ ዘርፍ። በእርሱም ደግሞ ሙግት የለም። መንግሥት ሊያለማ አይችልም። መንግሥት መሠረተ ልማት ነው የሚያለማው ሌላውን ነገር የግሉ ዘርፍ ያለማል። ገንዘብን የሚያውቀው፣ ለገንዘብ የሚቆመው የግሉ ዘርፍ ነው። የሕዝብ ሀብት (ስቴት ካፒታል) በማን ስር ይሁን? ካፒታሉን ማን ይቆጣጠረው ቢባል፣ የስቴት ካፒታሉ ይብዛ ቢባል፣ እንደ አሜሪካ ግዙፍ ስቴት ካፒታል ያለበት ሀገር የለም። በአሜሪካ በቢሊየን የሚቆጠሩ ሀብቶች የሚያንቀሳቅሰው ጦር ሠራዊቱ ያለው ኢንደስትሪ ነው፤ የወደብ አስተዳደሩ ትልቁ ነገራቸው ነው። ትራንስፖርት ዘርፉ እንዳለ የእነርሱ ነው። ስለዚህ ብዙ ካፒታል የስቴት ካፒተታል ነው አሁንም ቢሆን። መንግሥት ካፒታል አይኑረው ከሆነ በሎሌነት ለሌሎች ሀገሮች ወይ ለሌሎች ካፒታሊስቶች እንደር ካልሆነ በስተቀር፤ በሀገር ጉዳይ ላይ ስቴት ካፒታል አይኑረን የሚል መንግሥት አይመጣም። ሊመጣም አይችልም። ቢመጣም አሁን ባለው የንቃተ ህሊና ደረጃ በአጭር ጊዜ ከሥልጣን ይወርዳል። ዲሞክራሲ ስር ባልሰደደበት ሀገር ሁለት መንገድ ብቻ ነው ያለው። አንዱ ምንድን ነው የኢኮኖሚ ተሳታፊዎቹ ድንበር ዘለል ወደ ሆነ ወደ ድብቅ ኮንትሮባንድ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ይገቡና መንግሥትን ያንቁታል። ብር ሲያጣ ይወድቃል። ሌላው ኢኮኖሚውን ይተውና ኢኮኖሚ ውስጥ ያልተሳተፉ ሰዎች አማፂ ይሆናሉ። በዚህም ያፈርሱታል። ዲሞክራሲ ስር ቢሰድ ኖሮ ግን በምርጫ ብቻ ነበር ከስልጣን የሚወርደው። አሁን ግን ዲሞክራሲው ስር ስላልሰደደ መጀመሪያ ዲሞክራሲውን ስር የማስያዝ ሥራ መስራት አለብን። የመጀመሪያው የመንግሥት ሥራ ምን ልሽጥና ምን አልሽጥ ሳይሆን እንዴት አድርጌ ዲሞክራሲውን መሰረት ላስይዝ ነው መሆን ያለበት። ለምሳሌ የአካባቢ ምርጫ 2010 ላይ መካሄድ ሲኖርበት አልተካሄደም። ስለዚህ ይህ ምርጫ 2012 ድረስ ዘግይቶ ከሀገራዊ ምርጫ ጋር የሚካሄድበት ምክንያት የለም። ድሮም ሕገ መንግሥቱ በአንድ ጊዜ የሕዝብ ሥርዓቱ አንዳይፈርስ ለማድረግ የአካባቢና ሀገራዊ ምርጫ የሚካሄዱበትን ነገሮች እንዲንገጫገጩ አድርጓቸዋል። • ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ? ስለዚህ መጀመሪያ በአካባቢ ምርጫ መሰረት ላይ የቆሙ ክልሎችና አካባቢዎች መኖር አለባቸው። ያ ሕዝባዊ ተቋም በአግባቡ ሳይቆም ሀገራዊ ምርጫ ማካሄድም አይቻልም። ድርጅቶቹን የሚገዙትስ ቢሆኑ በድርድር ሰዓት ቀጣይነት በሌለው መንግሥት ምንድን ነው የሚደራደሩት? የአንድ ነገር እሴት እኮ የረዥም ግዜ ትርፉ ነው። ስለዚህ የሚቀጥለው ምርጫ ውጤቱ ምን እንደሆነ ሳያውቁ ምንድን ነው የሚገዙት? ያለንን የሕዝብ ሀብት ወደ ግል ለማዘዋወር ብቻ ካልሆነ በስተቀር የምንሸጠው ውጤታማ የሆነ ዘርፍ ለማምጣት ከሆነ መጀመሪያ መደረግ ያለበት የመቀመጫዬን ነው። መጀመሪያ ዲሞክራሲው መስፈን አለበት። በእርግጥ ዲሞክራሲ እስኪሰፍን ድረስ ተብሎ ስለ ኢኮኖሚው ሳይወራ አይቀርም። ግን ቢያንስ ቢያንስ የአካባቢ ምርጫ ተካሂዶ ህብረተሰቡ በራሱ ጉዳይ፣ በእለታዊ አጀንዳዎቹ የሚጠመድበትን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ምህዳር ማደላደል አለብን። ያንን ሳናደርግ ቴሌንና መብራት ኃይልን መሸጥ የሚባለው ነገር አያስኬድም። እነዚህ አገልግሎቶች የሚተሳሳሩት ከወረዳና ከቀበሌዎች ከከተሞች ጋር ነው። የገበያ ሁኔታን ሳታረጋጋ ቴሌን የምትሸጥበት መንገድ ምንድን ነው? የገንዘብ፣ የኢኮኖሚም ሆነ የፖለቲካ ትርጉም አይሰጥም። ከነበሩት አለመረጋጋቶች ጋር በተያያዘ የኮንስትራክሽን ዘርፉ መቀዛቀዝ ይታይበታል ይባላል፤ እርስዎ በዘርፉ ላይ እንደተሰማራ አንድ ግለሰብ ሁኔታውን እንዴት ነው የሚገመግሙት? ፀደቀ ይሁኔ፦ እኔ ኮንስራክሽኑን የማየው እንደ ሁለት ነገሮች ነው። አንዱ ኪራይ (ሬንት) ነው። መሸሸጊያ ነው። የመንግሥት በጀት ላይ ጥገኛ ስለሆንን ከአንዱ ነጥቄ ወደ አንደኛው እንዴት ላምጣው በሚለው ሙግት ውስጥ ነው ያለነው። ሁለተኛው ግን ማንኛውም ባለሀብት የሚበዘብዘው በምንድን ነው? ባለሀብት ማለት በዝባዥ ማለት ነው፣ ሳትበዘብዝ ካፒታል አታጠራቅምም (ሳቅ)። የሚበዘበዘው ጉልበት ነው። የሚበዘበዝ ጉልበት በጣም በብዛት ያለው ደግሞ ገጠር ውስጥ ነው። የገጠሩ አርሶ አደር የገፋውን አምራች ኃይል ሥራ ፍለጋ መንገድ ላይ ይቆማል። ከዚያ ደግሞ አልፎ ወደ ከተማ ይመጣል። ስለዚህ ኮንስትራክሽን ላይ ይህ የሰው ኃይል ነው ያለው። • "ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል" ደበበ እሸቱ ለሰራተኛው ደህንነት ግድ ሳይሰጠን ከፎቅ ላይ ሰው እየፈጠፈጥን፣ ሚስማር አየወጋው፣ ከተገቢው በታች እየከፈልነው ነው የምናተርፈው። ስለዚህ ይኼ ከአርሶ አደሩ በተበዘበዘ ገንዘብ በመንግሥት በጀት ጥገኛ የሆነ ዘርፍን እንዴት እናስተካከለው የሚለው ነው የመጀመሪያ ጥያቄ። የትኛውም መንግሥት ቢመጣ ይኼንን ሳያስተካክል የመንግሥት ግዢ ስላለበት፤ መንግሥት የመሰረተ ልማት ግዢ ውስጥ ያለውን ግፍና ሌብነት ሳያስተካክል የመደብ ለውጥ አይመጣም። የመደብ ለውጥ ሳያመጣ እንዲሁ አርሶ አደር እንደሆነ መቀጠል የለበትም፤ መቼም። ያንን ለማምጣት ከፈለገ የሕብረተሰቡን ገንዘብ የሚበላውን ነገር ማስተካከል አለበት። ከተሞችና ኮንስትራክሽን አብረው አርሶ አደሮቹን መበዝበዣዎች ናቸው፤ እርሱን መጀመሪያ ማስተካከል አለብን። ይኼ መሰረታዊ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ሀሳብ ነው። አሁን ግን ሌሎች ሌብነቶችም ወደ ኮንስትራክሽን ዘርፉ እየገቡ ነው። ለምሳሌ ብረትን ብትወስድ ብዙ አስመጪዎች ሲያስመጡ ታክስ የለባቸውም ነገር ግን ዶላሩ በእጃቸው ስለማይገባ ብዙ ፐርሰንት ይወስድባቸዋል። (30 ፐርሰንት ይመስለኛል) ዶላሩንም ቢሆን እንደፈለጉ ስለማይገዙ የአርማታ ብረት ብዙ አስመጪዎች የውጪ ምንዛሬ የሚመነዝሩበት ሆኗል። የውጪ ምንዛሬ እጥረት ተፈጠረ ከተባለ በኋላ የብረት ዋጋ በ300 ፐርሰንት ጨምሯል። በኪሎ ከ18 ብር የነበረው 54 ብር ነው የገባው። ብሄራዊ ባንክ የሚያወጣውን መረጃ ብናይ ብር ተገቢ ያልሆነውን ዋጋ እንደተሰጠው ያሳያል። ላኪው ይህንን የብርን ያልተገባ ዋጋ የሚያካክሰው ቡናውንም ሰሊጡንም በርካሽ ዋጋ ይሸጥና ከውጪ የሚመጣውን ብረት ውድ ያደርገዋል። ስለዚህ ብረት አሁን ወርቅ ሆነ፤ የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚቆጣጠሩት ብሔራዊ ባንክንና የውጪውን ንግድ የሚቆጣጠሩት ኃይሎች ናቸው። ስለዚህ እኛ ዝም ብለን አስተላላፊ ነን። የውጪ ምንዛሬ እናገላብጣለን እንጂ ሥራ አንሰራም። • ኢትዮጵያ እና ኤርትራ - ከሰኔ እስከ ሰኔ ይኼ ቢከፈት ግን ቀጥታ ማስመጣት ብንችል ላኪውም ያ መንገድ ስለሌለው ወደ አገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ወይንም ወደ ካፒታል ኢንቨስትመንት ይሄዳል። ወደ ኮንስትራክሽን ዘርፉ መግባት ለሚፈልጉ ወጣቶች ምን ትመክራቸዋለህ? ኮንስትራክሽን በእኔ ግምት በየትኛውም ሀገር ውስጥ በቀላሉ የሌብነት ጫካ መሆን የሚችል ዘርፍ ነው። የመሰረተ ልማት ግዢ ግዙፍ ስለሆነ በርካታ ነገሮች በቀላሉ አይታወቁም። አንድ የሽንት ቤት መቀመጫ አምስት ሺህ ዶላርም አምስት ዶላርም ሊሆን እችላል። በእነዚህ ነገሮች ውስጥ አንዱን ዋጋ ሰጥተህ አንደኛውን ማቀበል ዋናው የትርፍ ምንጭ ነው። ሌላው የትርፍ ምንጭ ደግሞ በወዛደሩ ጉዳት ማትረፍ ነው። እነዚህ ነገሮች መስተካከል አለባቸው። አዳዲስ ወደ ገበያው የሚገቡ ወጣቶች የዋህነታቸው ሳይጠፋ የሀገር ተልእኳቸውን እንዲጨምሩበት ማስቻል አለብን። ይህ ለየትኛውም ዘርፍ ይሰራል። ኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ደግሞ ለሰው ልጆች ብሎ የቆመ ከሁሉም የላቀ ውጤት ያገኛል ብዬ አምናለሁ። እኔ እንደዛ ነው እዚህ የደረስኩት። መጥፎ ሳልሆን ቀርቼ ሳይሆን መጥፎዋን መንገድ ቀድሜ ስለተውኩት ነው።
44653057
https://www.bbc.com/amharic/44653057
"በትግራይ ስም እንደራጅ እንጂ የኛ አመለካከት ቀድሞውንም ኢትዮጵያዊ ነው" ዶክተር አረጋዊ በርሔ
የህወሐት መስራችና የቀድሞ አመራር የነበሩት አቶ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) በሀገሪቱ ካለው ለውጥና የተቃዋሚዎችና ተፎካካሪዎች ወደ ሀገራችሁ ጥሪ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለሱ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ዶክተር አረጋዊ በርሔ ወደ አገር ውስጥ ስለመመለስ ውሳኔያቸው፣ ከህወሐት ጋር ያላቸውን ልዩነትና ቀጣዩ የትግል መስመራቸውን በማስመልከት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱት ከረዥም ጊዜ በኋላ ነው፤ አሁን ለመመለስ የፈለጋችሁት ለምንድነው? በመግለጫችን ላይ እንዳስታወቅነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ለውጥ እየመጣ ነው። እስከዛሬ ከነበረው አገዛዝ ለየት ያለና ተቃዋሚዎችን እንደ ተፎካካሪ የሚያይ፤ መብታቸውን የሚጠብቅ ሆኖ አግኝተነዋል። እንዲሁም አብሮ ሊያሰሩ የሚችሉ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው፤ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን የኛን ራዕይና አላማ ለህዝቡ ለማሳወቅና ካለው ለውጥ ጋርም አብረን እንድንጓዝ አስተዋጽኦ ለማድረግ ወስነን ነው ለመግባት እየተዘጋጀን ያለነው። ከዚህ ቀደም ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ጠይቃችሁ በጎ ምላሽ እንዳላገኛችሁ ይታወቃል። እስኪ ስለሁኔታው ይንገሩን? አዎ! ብዙ ግዜ ሞክረናል። በተናጥል እንደ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር፤ የተለያዩ ህብረቶች አባል እንደመሆናችን በቡድንም በተደጋጋሚ ሙከራዎች አድርገናል። ነገር ግን የነበረው መንግስት አምባገነናዊ የሆነ ባህሪ ስለነበረው፤ እስካሁን የኛን ጥያቄዎች ውድቅ እያደረገ ነው የመጣው። አሁን ግን ውድቅ የሚያደርግ ሳይሆን ወደ ሃገራችን እንድንገባ የሚወተውት፤ እንድንገባ የሚተባበር አዲስ ሃይል ስለተፈጠረ፤ እኛም ለመግባት ወስነናል። የአዲሱ ለውጥ አራማጆች አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የእነ ዶክተር ዐብይ አህመድ ቡድን፤ ተቃዋሚዎችን ከውጪ እየሰበሰበ፣ እየጠራ፣ እየተቀበለና እያስተናገደ ነው። ይህ አይነት ጸባይ ባለፈው መንግስት አልነበረም። አመቺ ሁኔታ እንዳልነበር ሁሉም ሰው ያውቀዋል። የእስረኞች መፈታትና የማዕከላዊ መዘጋት ውሳኔ አንድምታዎች መንግስት ጥሪ ከማድረግ ባለፈ በሃገሪቷ ፖለቲካዊ ሁኔታ የናንተን አስተዋጽኦ ለመቀበል መንገዶች ተመቻችተዋል ብለው ያምናሉ? አንደኛ አያያዛቸውን ስናየው ለጋራ ተሳትፎ የሚተባበሩ መስሎ ነው የታየን። ለምን እንደዚህ አልክ ብባል፤ ተቃዋሚ የነበሩ ሃይሎችን ሲቀበሉ አይተናል። እንደውም በትጥቅ ትግል ተሰማርተው የነበሩትን ሳይቀርም እየተቀበሉ ነው። ሁለተኛ፤ አፍነው ይዘዋቸው የነበሩና ታስረው የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ሲፈቱ አይተናል። ለብዙ አመታት ታስረው የነበሩ የሚዲያ ሰዎችም በአንድ ጊዜ ሲፈቱ አይተናል። ስለዚህ፤ እነዚህ ተጨባጭ እርምጃዎች ናቸው። ከንግግር ባለፈ በተቃዋሚ ወይም በተፎካካሪዎች ላይ ምንም መጥፎ አመለካከት እንደሌለ በተጨባጭ ያመለካክታሉ። ስለዚህ ይሄ ሁሉ ለኛ ትልቅ ተስፋ አሳድሮብናል። ይህ ትንሽ ነው ካልን ደግሞ ራሳችን ገብተን ሰፋ እንዲል፤ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲዳረስ የማድረጉ ኃላፊነት የኛ ነው። ነገር ግን ከውጪ ሆነን እንደዚህ ካላገደረጋችሁ አንገባም የምንልበት ምክንያት ወደ ኃላ መሸሽ መስሎ ነው የሚታየኝ። ወደሃገር ውስጥ ከተመለሳችሁ በኋላ በምን መንገድ ነው ተሳትፎ ለማድረግ ያሰባችሁት? በተጨባጭ የያዛችኋቸው ዕቅዶች አሉ? ዕቅዶች አሉን። በሁለት አቅጣጫ ነው የምንታገለው። የመጀመሪያው የትግራይ ህዝብን ወገኑ፤ እህቱ፤ ወንድሙ ከሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋራ አንድነት፣ ሰላም ፍቅር ስለሚፈልግ ይህን እናስተጋባለን። ይህ እንዲሆንም እንታገላለን። እስካሁን ድረስ የመለያየት ፖለቲካ ነበር የሚራመደው። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተዋደቀ እንደመሆኑ ኢትዮጵያዊነቱን አስረግጦ ከወገኑ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ወደ እድገት ጎዳና፣ ሰላም፣ ፍቅርና አንድነት እንዲጓዝ ለመስራት ነው እቅዳችን። ሁለተኛው ደግሞ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የመጣው ለውጥ መልክ ባለው መንገድ እንዲቀጥልና የጋራ ስርአት እንዲመሰረት ለማድረግ ከለውጥ አራማጆቹ ጋር ለመስራት ነው። የአንዱ ሃይል ሌላውን የሚያሸንፍበት አይነት ጉዳይ ሳይሆን በጋራ ለሁላችንም የሚጠቅም ስርአት እንዲመሰረት ለማመቻቸት ነው። ለሁላችንም የሚበጅ ስርአት ከተመሰረተ በሰላም ለመወዳደር ነው የምናስበው። እያንዳንዱ ፓርቲ የሚፈልገውን ለህዝብ እያሰማ የህዝብ አመኔታና ድጋፍ እያገኘ ለተወሰኑ አመታት ሊመራ ይችላል። እዛ ለመድረስ የጋራ ስምምነትና ስርዓት መመስረት ያስፈልጋል። አሁን ያሉት ሁኔታዎች ደግሞ አመቺ ስለሆኑ እንደሚሳካልን ተስፋ አደርጋለሁ። ከህዝባችን የኢትዮጵያ ህዝብ መሃል ገብተን፣ ድጋፋቸውን አግኝተን ሃገሪቱ ከነበረችበት ችግር ወጥታ እንደሌሎቹ የበለጸጉና የተከበሩ ሃገራት እንደምትሆን እርግጠኞች ነን። በትውስታ ወደኋላ እንመልስዎትና በህወሀት አመራር ላይ ሳሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አንድ ጥፋት አጥፍተው እንደቀጧቸው ይነገራል። ስለጉዳዪ ሊያብራሩልን ይችላሉ? (ሳቅ) ያለፈ ነገር ምን ያደርጋል? የወደፊቱ ላይ ብናተኩር የሚሻል ይመስለኛል። ሁኔታዎች ሲረጋጉ ቀስ ብለን በሰፊው እናወራዋለን፤ እንተነትነዋለን። ከህወሐት ተገንጥሎ ወጥቶ እንደገና በተቃዋሚነት ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ተስፋ ምን አይነት ስሜት አለው? በመጀመሪያ ከህወሃት ጋር አልተስማማንም። ህዝቡና ታጋዩ ሌላ ነው። ሁሌም ቢሆን ህዝቡ ግን እኛ የምንለውን ሃሳብ የሚደግፍ ነበር። በጊዜው የነበሩት አመራሮች ግን እኛን ለማግለል ውስጥ ውስጡን ይሰሩ ነበር። በዚህ ምክንያት አላማ መቃወስ ስለመጣ በዚያ ሁኔታ መቀጠል አልቻልንም። የኛ አመለካከት ድሮውንም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ነው። በትግራይ ስም እንደራጅ እንጂ የኛ አመለካከት ቀድሞውንም ኢትዮጵያዊ ነው። እቅዳችን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትኖር ለማድረግ ነበር። እነሱ ወደ መገንጠሉ የሚያዘሙ ነበሩ። እኛ ከወጣን በኋላ ቀናቸውና ስልጣን ያዙ። ኢትዮጵያውያን መስለውም እስካሁን ድረስ ሲመሩ ቆይተዋል። ይህንን ውጭ ወጥተን መቃወም፣ ማጋለጥና ትግሉ ፈር እንዲይዝ ለማድረግ እስካሁን ተንቀሳቅሰናል። ውጭ ሆነን አላረፍንም። እስካሁን ድረስ እኛን ከሚመስሉ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትኖር ከሚመኙ ደርጅቶች ጋር ያላሰለሰ ትግል አድርገናል። እውነት ነው በውጭ ሀገር ለመታገል የተገደድነው ሀገር ውስጥ አምባገነን ስርዓት ስላለ ነው። ይህ ስርዓት እስካለ ድረስ ጠብ የማይል ነገር ሊኖር እንደማይችል ይገባኛል። ኢህአዴግን ህወሐት እየመራው ቢቆይም ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ግጭቱ ስለበረከተ እየተዳከመ ሄዶ ከውስጥ በነዶክተር አብይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳ የሚመራው ኃይል ተፈጠረ። ኢህአዴግን ከውስጥ ስላዳከመው የድሮውን መስመር ሊይዝ አልቻለም። ስለዚህ የአሁኑ መስመር ድሮ እኛ የምንለው፣ የምንደግፈው ስለሆነ ነው ለመግባት የወሰንነው። ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) ወደ 23 ዓመታት የቆየ ፓርቲ ቢሆንም ብዙም አይታወቅም። ለምን? አፈና ነዋ! የታፈነ ሁኔታ ነበር ያለው። በተለይ የድሮ የህወሃት መሪዎች ትግራይ ውስጥ ማንም የፖቲካ ድርጅት ዝር እንዳይል፤ ጋዜጣ ለማንበብ እንኳን ምንም እድል እንዳይከፈት አድርገዋል። ከዛም ባሻገር እስከ አሁን ድረስ ህወሃትና የትግራይ ህዝብ አንድ ሳይሆኑ፤ አንድ ናቸው እያለ፤ እነሱ በኢትዮጰያ ህዝብ ላይ የሚሰሯቸው በደሎች ለህዝቡ እየተረፈ ነው። በዚህ ምክንያት ህዝብ፤ ህዝብ እየተጋጨ ነው። አሁን በትግራይ ህዝብ ላይ እየወረደ ያለው ግፍ ሰርቶ የሚያድር ህዝብ በየአካባቢው እንደ ጠላት መታየቱ ነው። ይሄ የተሳሳተ አመለካከት ነው። ለዚህ ተጠያቂዎቹ የድሮዎቹ የህወሃት መሪዎች እንጂ ህዝቡ ሊሆን አይችልም። ህዝቡ አይደግፋቸውም። ህዝቡ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ታፍኖ እየኖረ ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ አልቻልንም። አፈናው በርትቶብን ነበር። ህዝቡን ልናነጋግር ይቅርና፤ የምንጽፈው ጽሁፍ ወደዚያ እንዳይገባና የምንናገረው ንግግር እንዳይሰማ ሙሉ በሙል ተቆጣጥረውት ነበር። በዚህ ምክንያት እንቅስቃሴያችን ብዙ ሳይታወቅ ቆይቷል። ይህንን የአፈና አጥር እየሰበረ መከታተል የሚፈልግ ሰው ያውቀናል። በእርግጥ ከሃገር ውጪ ከተቃዋሚ ሀይሎች ጋር እየተሰባሰብን የምናደርገው እንቅስቃሴ በስፋት ይታወቃል። ሀገር ቤት ግን በብሄር ደረጃም ሆነ በሀገር ደረጃ እነሱ የሚቆጣጠሩት ሚዲያ ነው ያለው። ወደ ሃገር ውስጥ የመመለሳችሁን ጉዳይ ከመንግስት ጋር ተወያይታችኋል ወይ? የመመለሳቸሁ ሂደትስ እንዴት ነው የሚከናወነው? ከመንግስት ጋር በደንብ ተወያይተናል። የነሱንም ይሁንታ አግኝተናል። ምን ያህል የፓርቲው አባላት ወደ ሃገር ቤት እንደሚመለሱ ለጊዜው መናገር ባንችልም፤ አንድ ቡድን ግን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይሄዳል።
53013910
https://www.bbc.com/amharic/53013910
በኮቪድ-19 ምክንያት በአሜሪካ በኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ላይ የተባባሰው ጾታዊ ጥቃት
ዱንያ መኮንን ኑሮዋን በአሜሪካ ያደረገች የሕግ ባለሙያ ናት። በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘችው ኢትዮጵያ ሲሆን በተባበሩት መንግሥታትና መንግሥታዊ ባልሆኑም ድርጅቶች ውስጥ በሰብዓዊ መብት ባለሙያነቷ አገልግላለች። በሥራ ዓለም ከተሠማራችበት ጊዜ አንስቶ ትኩረቷን በሴቶችና በሕፃናት መብት ጥሰት ዙሪያ ላይ በማድረግ ሠርታለች።
በሴቶች ላይ በሚደረጉ የመብት ጥሰቶች ላይ በኢትዮጵያም ትሠራ እንደነበር የምትናገረው ዱንያ፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ውስጥ የነፃ ሕግ አገልግሎት ትሰጥ ነበር። በወቅቱ በአገሪቱ ለሴቶች መብት ጥሰት እምብዛም ትኩረት ስላልነበረና ጥቃቶቹም በብዛትና በተደጋጋሚ ያጋጥሙ ስለነበር በይመለከተኛል ስሜትና የሕግን ሚና በማስተዋል ሥራውን ለመቀላቀል መገፋፋቷን ታስረዳለች። ዱንያ በተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ክፍል ውስጥ በሴቶች ጥቃት ላይ አተኩራ ትሠራ በነበረበት ወቅት በደረሰችባቸው ግኝቶች ምክንያት ሥራው በይበልጥ ትኩረት እንደሚያስፈልገው ተረዳች። ከዚያም በዚሁ ዘርፍ ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝታ በአፍሪካውያን ሴቶች መብት አድቮከሲ ሁለተኛ ዲግሪዋን ከአሜሪካ ጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ በብሔራዊ ደህንነት የተመረቀች ሲሆን፣ አሁንም እዚያው በአሜሪካ በሴቶች መብት ላይ ተቀጥራ እየሠራች ሲሆን የነጻ አገልግሎትም ትሰጣለች። በአሁን ሰዓት በአሜሪካ ካሉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሕብረተሰብ ጋር በይበልጥ እየሠራች ያለችው ዱንያ " ያለው ሁኔታ ልክ አገር ቤት እንዳለው ነው። እንደውም፣ እዚህ ያለው የባሰ ነው። የተማረው የሕብረተሰብ ክፍል ከአገር ቤት አንፃር ቢበዛም እንኳን በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ግን ይበልጥ የከፋ ነው" ትላለች። በተለይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከመጣ አንስቶ ብዙ ጥንዶች ከቤታቸው ሳይወጡ በመቆየታቸው የተነሳ ጥቃቶቹ መባባሳቸውን ትገልፃለች። ከወረርሽኙ በፊት የነበረው የጥቃት መጠን በማህበረሰቡ ውስጥ በጣም ከፍተኛ የነበረ ሲሆን ጭራሽ ወረርሽኙን ተከትሎ ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ ደግሞ አብሮ ጭንቀት ይዞ በመምጣቱ ብዙ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውን ትጠቁማለች። "በእንደዚህ ዓይነት ጊዜ በተለይ በትንሽ በትልቁ ሰዎች እየተጋጩ ነው። ምክንያቱም የአብዛኛዎቹ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ በመሆኑ ውጥረትና ጭንቀት ላይ ናቸው። በአሁን ሰዓት አብዛኛው ሕብረተሰባችን ኪራይ መክፈል አቅቶት ነው የሚገኘው። በዚያም ምክንያት ብዙ ጉዳዮች እስከ ፍቺ ደርሰው ወደ ሕግ ቢሮ እየመጡ ይገኛሉ" በማለት ከወረርሽኙ ወዲህ በአሜሪካ ያለውን ሁኔታ ታስረዳለች። ዱንያ የመሥሪያ ቤታቸውን ደጃፍ የሚጠኑት ጥንዶች ቁጥር ቢበዛም፣ "ቢያንስ እርዳታ የትና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ የሚያውቁት ናቸው ወደኛ የሚመጡት። የሚያሳስበው፣መረጃ የማይደርሳቸው የሕብረተሰባችን ክፍሎች ብዙ መሆናቸው ነው" ትላለች። በአሁን ሰዓት ዋናው የሥራቸው ትኩረት ዱንያ ከፍ ብሎ የጠቀሰቻቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በመሆናቸው ርዳታው እንዴት እንዲደርሳቸው ማድረግ እንደሚቻል እርሷ እና የሥራ ባልደረቦቿ ጠንቅቀው ማጤን እንደነበረባቸውም ታስረዳለች። " (የአስቸኳይ ጊዜ) አዋጁ ሲወጣ ሁሉም ነገር የተዘጋ የመሰላቸው ሰዎች ነበሩ። አብዛኛው መረጃ በእንግሊዝኛ ወይንም ገፋ ቢል በስፓኒሽ ነው የሚሰጠው። ይህም ደግሞ ከተለያዩ የአገራችን ከተሞች የመጡትን ያካተተ አይሆንም። ስለዚህ እነርሱ በሚረዷቸው ቋንቋዎች መድረሳችን ሙያዊ ግዴታችን ነበር" ትላለች። ዱንያና ባልደረቦቿ ችግሩን ከተገነዘቡ በኋላ የማህበራዊ ድረ ገፆችን በመጠቀም የውይይትና የመረጃ መስጫ መስመር ከፈቱ። ይህም የተጠቁስት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አስፈላጊው መረጃ እንዲደርሳቸው በማሰብ መሆኑንም ጠቅሳለች። "ሰው እንዲያውቅና እንዲረዳ የምንፈልገው ነገር በአሁን ሰዓት የሕግ አገልግሎት ለሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ የሕግ ባለሙያዎችም ሆንን አግልግሎቱ ክፍት መሆናቸውን ነው። የጥበቃ ጥያቄ፣ ፍቺም ሆነ ማንኛውንም ርዳታ ማግኘት ለሚፈልጉ ወንድም እህቶቻችን በተቻለን መጠን በቋንቋቸው አገልግሎት ለመስጠት ቆርጠን ተነሳን" በማለት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ታፔላ፣ ፓምፍሌቶችና በራሪ ወረቀቶችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መዘጋጀታቸውንም ጭምር ትናገራለች። በመቀጠልም "ከሁሉም በላይ ለግሪን ካርድ ባሎቻቸው ወይም ሚስቶቻቸው አመልክተውላቸው በመጠበቅ ላይ ያሉት በይበልጥ ለጥቃት ተጋላጭ ሆነው ይገኛሉ። አሜሪካ የሚገኙበት ሁኔታው እርግጠኛ ባለመሆኑ ምክንያት ጥቃቱን በፀጥታ እየተቀበሉ እየተጎዱ የሚኖሩት ብዙ ናቸው" እያለች መኖሪያ ፈቃድ ለሌላቸው እንኳን ሕጉ እንደሚያገለግላቸው ማሳወቅ ግዴታ ነው ትላለች። "ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወደ ሕግ ቢጮኹ በሂደት ላይ ያለው የመኖሪያ ፈቃድ ሰነዳቸው ላይ ምንም ዓይነት እንቅፋት እንዳማይገጥማቸው እንዲያውቁ እንፈልጋለን። ምክንያቱም በ'ቫዮለንስ አጌንስት ዊሜን አክት' ሕግ መሠረት አስፈላጊው 'ፕሮቴክቲቭ ኦርደር' ተወስኖላቸው ተገቢው ጥበቃ ይደረግላቸዋል።" ዱንያ ሥራው ይጀመር እንጂ ገና ብዙ እንደሚቀራቸው በማስረዳት ኮቪድ-19 በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ጭራሽ አባብሶታል ትላለች። መሄጃ የሌላቸው ስለሚምስላቸው በሞት አፋፍ ላይ እያሉም ርዳታ ፍለጋ ወደ ሕግም ሆነ ወደ ዘመድ ጓደኛ ለመምጣት መቸገራቸውን ታስረዳለች። "ሌላ ጊዜ የሴቶች ጥቃት ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነበር። ቢያንስ ለቡናም ሆነ በምክንያት ከሰዎች ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ችግራቸውን የሚያጋሩት ሰው አያጡም ነበር። አሁን ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ስለተደረጉ፣ ችግር ላይ መሆናቸውን ራሱ ለማወቅ ተቸግረናል" የምትለው ዱንያ እስካሁን ያለው የጥቃት ቁጥር ባይታወቅም እንኳን እየተባባሰ መሆኑ የማይካድ ነው ትላለች። "ባለው ፆታዊ ጥቃት ላይ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እክሎች ሲደረቡበት ከዚህ ቀደም ተመዝግቦ ከምናውቀውና ከነበሩት የጥቃት ቁጥሮች ወረርሽኙ ሲያበቃ እጥፍ ወይም ከዚያም በላይ ይሆናሉ ብለን እንገምታለን" በማለት ያንን ቀደም ብሎ ለመግታት በማሰብ ከወዲሁ የሚያስፈልገውን መረጃ ለማህበረሰቡ ማደርስን ቅድሚያ መስጠታቸውን ታስረዳለች። "ማንም ሰው ጥቃትን የኑሮው አካል ሊያደርገው አይገባም። ማንም ሰው ሌላን ሰው ማጥቃት መብት የለውም። አንድ ሰው ጥቃት ከደረሰበት ወንጀል ተፈፅሞብኛል ብሎ ማሰብ አለበት። በዘልማድ ቻይው የሚባለው ነገር አይሠራም ምክንያቱም የሕይወት ህልፈት ሊከሰት ይችላል" በማለት ማንም ሰው የወንጀል ተባባሪ መሆን የለበትም በማለት ምክር ትሰጣለች።
42305548
https://www.bbc.com/amharic/42305548
እየሩሳሌም ለምን የኢትዮጵያዊያን ህልም ሆነች?
በተለይም ከንግስት ሳባ ታሪካዊው የእየሩሳሌም ጉብኝትና በእየሩሳሌም ከሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ገዳማት ጋር በተያያዘ ብዙዎች እየሩሳሌምን ያውቋታል።
ደጋግመውመም በአእምሯቸው ይስሏታል። ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በቡድን በቡድን እየሆኑ ወደ እየሩሳሌም ይሄዱ እነደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ዛሬ ደግሞ በተለያዩ የጉዞ ወኪሎች አማካኝነት በርካቶች ወደ እየሩሳሌም እየሄዱ ነው። እየሩሳሌም የብዙ እናቶች አባቶችና ወጣቶች ህልም ነች። "ህይወቷን ሙሉ ስለ እየሩሳሌም እየሰማች ስለኖረች እየሩሳሌምን ማየት ለእናቴ ትልቅ ነገር ነበር።ይህን ህልሟን ማሳካት ደግሞ ለእኔም እነደዚያው ነው" የሚለው ሄኖክ ፀሀዬ ኑሮውን በአሜሪካ ካደረገ ጥቂት አመታት ተቆጥረዋል። ወደ አሜሪካ ሲሄድ ይህን ፍላጎታቸውን እንደሚያሳካ ለእናቱ ቃል ገብቶላቸው ነበር። ነገር ግን እሱ ቃሉን ጠብቆ ባለፈው አመት እናቱ ወደ እየሩሳሌም ሊሄዱ ባሉበት ወቅት አባቱ ከዚህ ዓለም በመለየታቸው እቅዱ ሳይሳካ ቀረ። ሀዘን ውስጥ ቢሆኑም የእናቱ እየሩሳሌምን የመጎብኘት ህልም ግን ያው እንዳለ ነበር። ስለዚህም እናቱን ለመጭው ገና ወደ እየሩሳሌም ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው። እናቱም ጉዞውን በጉጉት እየጠበቁ መሆኑን፤ ለእናቱ ይህን በማድረጉ ደግሞ እሱም ከመጠን ባለፈ መልኩ መደሰቱን ይናገራል። የአሜሪካ ለእየሩሳሌም በእስራኤል ዋና ከተማነት እውቅና መስጠትን በሚመለከት ያለውን አስተያየትም ሰንዝሯል። እንደ አውሮፓውያኑ በ1917 የተደረገውንና ለእስራኤል መፈጠር መሰረት የሆነውን የባልፎር ስምምነት በመጥቀስ ያ ለዘመናት ያከራከረ ምድር ከመጀመሪያውም የፍልስጤም ነው ብሎ እንደሚያምን ይናገራል። ስለዚህም ዛሬ ላይ "ምእራብ እየሩሳሌም ለእስራኤል ፤ምስራቅ ደግሞ ለፍልስጤም መሆን እንዳለበት አምናለሁ"ይላል። ጋዜጠኛና በመንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር የሆነው ሄኖክ ያሬድ ደግሞ "ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከሃይማኖት፣ ከታሪክ፣ ከባህልና ከቅርስ አንፃር ለኔ ልዩ ቦታና ትርጉም አላት፡፡ አንድም በባሕረ ሐሳባችን (ዘመን አቆጣጠራችን) የምንጠቀምበት ዓመተ ምሕረት እንዲሁም ዓመተ ዓለም መነሻውና መድረሻው ከቅድስት ሀገር ጋር ይያያዛል፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጽንሰቱ እስከ ዕርገቱ የተመላለሰባት ናትና" ይላል። ከአባቱ ጋር ወደ እየሩሳሌም የሄደው ከአምስት ዓመት በፊት ለኢትዮጵያዊያንም ሆነ ለቤተ እስራኤሎቹ የዐዲስ ዓመት መጀመሩያ በሆነው በወርኃ መስከረም ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በታሪክ ትምህርቶችና በምስል፤ በመስማትም ጭምር የሚያውቃትንና የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ሕልም እየሩሳሌምን ማየት ልዩ ስሜት እንዳሳደረበት ያስታውሳል፡፡ "ወሬ ባይን ይገባል እንዲሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ከምስልና ከንባብ ባሻገር ታሪካዊ ኩነቶች የተፈጸሙበት ሥፍራ ላይ መገኘት ምንኛ ደስ ይላል! ዕፁብን ዕፁብ ትለዋለህ እንጂ ምን ሌላ ቃል ታበጅለታለህ! እንዲል ያገሬ ሰው"ይላል ሄኖክ። ከክርስቶስ ልደት በፊት የንግስት ሳባና ንጉስ ሶሎሞን ታሪክን እንዲሁም የቀዳማዊ ምኒሊክ መወለድን በማስታወስ እነዚህ ነገሮች ኢትዮጵያን ከእየሩሳሌም ጋር እንደሚያቆራኝ ይናገራል። በተጨማሪም በእስራኤል የሚገኙት የኢትዮጵያ ገዳማት ኢትዮጵያውያንን ከእየሩሳሌም ያስተሳሰረ ሌላ ጉዳይ መሆኑን ያስረዳል። ተጓዦችን ወደ እየሩሳሌም ከሚወስዱ የጉዞ ወኪሎች መካከል ቀራኒዮ በእየሩሳሌም አንዱ ነው። ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ የድርጅቱ መስራችና ስራ እስኪያጅ ናቸው። ድርጅቱ 2002 ዓ ም ላይ እነዴት ተመሰረተ? በቀዳማዊ ሐይለስላሴ ስልጣን ዘመን የተመሰረተና ወደ እየሩሳሌም ለኢትዮጵያዊያን ጉዞ የሚያመቻች ማህበር አባል ነበሩ ወ/ሮ እጅጋየሁ። አሁንም የዚሁ ማህበር አባል ናቸው። በዚህ ማህበር ወደ እየሩሳሌም ጉዞ ሲያደርጉ በነበረበት ጊዜ የኢትዮጵያዊያን ወደ እየሩሳሌም የመሄድ ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን ማስተዋላቸው ድርጅቱን ለማቋቋም መነሻ እንደሆናቸው ይናገራሉ። ምንም እንኳ ዛሬ ላይ የተለያዩ የጉዞ ወኪሎች ቢኖሩም ፍላጎቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተጨማሪ የጉዞ ወኪሎች ወደ ስራው ሊገቡ እንደሚችሉ እምነታቸውን ይገልፃሉ። "ዓላማዬ ትርፍ አይደለም።ብዙዎች ያችን ምድር ረግጠው እንዲመለሱ እፈልጋለሁ።እንጀራ ሸጣ ያሳደገች እናትን እንዴት ላስደስት የሚሉ ልጆች ለእናቶቻቸው የሚያደርጉት ነገር ነው"ይላሉ። ቀራኒዮ በእየሩሳሌም ስራ ሲጀምር ወደ እየሩሳሌም የወሰደው 180 ሰዎችን ነበር። ያኔ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ነበር ጉዞ የሚያዘጋጀው አሁን ግን በዓመት አራት ጉዞዎችን የሚያዘጋጅ ሲሆን ለምሳሌ ለገና በአል 122 ሰዎችን ለመውሰድ መዝግቧል። እስከ 430 ተጓዦችን የወሰዱበት ጊዜም እንዳለ ወ/ሮ እጅጋየሁ ይናገራሉ። መሄድ የማይፈቀድላቸው ሄደው ይቀራሉ ብለው የሚገምቷቸውን ወጣቶች አይወስዱም። መጓዝ እንፈልጋለን ብለው ወደ ቢሯቸው የሚሄዱ ወጣቶችን የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዲሁም ማስረጃ እንዲያቀርቡ በመጠየቅ እንደማይቀሩ ካላረጋገጡ እንደማይወስዱ ወ/ሮ እጅጋሁ ይናገራሉ። "የወጣቶች እዚያ ሄዶ መቅረት በእስራኤልና በኢትዮጵያ መንግስትም ተጠያቂ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት የተዘጉ የጉዞ ወኪሎችም አሉ።"የሚሉት ወ/ሮ እጅጋየሁ ብዙ ጊዜ የሚሄዱት ሴቶች እንደሆኑ ይናገራሉ። በተመሳሳይ የትምህርትና የስልጠና እድል አግኝተውም ይሁን ለጉብኝት ቪዛ ለማግኘት የተለያዩ ኤምባሲዎች የሚገቡ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ሄደው ይቀራሉ ተብሎ ስለሚገመት ቪዛ ለማግኘት ይቸገራሉ። በዚህ መልኩ ካገኙት የትምህርትና የስልጠና እድል የተስተጓጎሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ጥቂት አይደሉም። ጥሩ የሚባል የትምህርትና የስራ ደረጃ ላይ ያሉ ሆነው በተለያዩ ኤምባሲዎች የጉብኝት ቪዛ የተከለከሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ ጥቂት አይደሉም። የኢትዮጵያ ገዳሞች በእየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእየሩሳሌም ሰባት ገዳማት አሏት። እነዚህም ዴር ሱልጣን ፣ኪዳነ ምሕረት፣ቅዱስ ፊሊጶስ፣ ቅድስት ሥላሴ፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ አልዓዛርና ቤተልሔም ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የሆነው ዴር ሡልጣን ገዳም በግዕዝ ደብረ ሥልጣን የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ከጌታ ቅዱስ መቃብር ቤተመቅደስ በስተምሥራቅ ይገኛል። ሄኖክ እንደሚለው ዴር ሡልጣን ጥንት ንጉስ ሰሎሞን ከኢትዮጵያ ለተለያዩ በዓላት ወደ እስራኤል የሚሄዱ ጎብኚዎችና መልዕክተኞች ማረፊያ ይሆን ዘንድ ለንግስት ሳባ የሰጣት እነደሆነ የቤተ ክርስትያን ታሪክን በመጥቀስ ይናገራል። ኋላም ገዳም ተመስርቶበት በኢትዮጵያ ነገስታት ሲረዳ መቆየቱን ይገልፃል። ከቀራንዮ በእየሩሳሌም የጉዞ ወኪል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እጅጋየሁ ንግግር መረዳት የሚቻለው ዛሬም ኢትዮጵያዊያን ገዳሙን እንደሚረዱ ነው። የመውደቅ ችግር ለተጋረጠበት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ኢትዮጵውያን እርዳታ ማድረጋቸውን ወ/ሮ እጅጋሁ ይናገራሉ። ለዘመናት ያወዛገበች ከተማ ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንም መዲናችን ነች እንደሚሏት እየሩሳሌም በመካከለኛው ምስራቅ ለዘመናት አወዛጋቢ የሆነ ጉዳይ የለም። እየሩሳሌም በአለም ዓቀፍ ደረጃም በተመሳሳይ መልኩ አወዛጋቢ ናት። አሁን ደግሞ የአሜሪካ እየሩሳሌምን በእስራኤል መዲናነት እውቅና መስጠትን ተከትሎ የእየሩሳሌም አወዛጋቢነት አይሏል። እየሩሳሌም በተለያዩ ምክንያቶች ለክርስትና፣ለአይሁድና ለሙስሊሙ የተቀደሰች ምድር ናት። በዚህ መልኩ የሶስቱም እምነቶች ትኩረት መሆኗም ለዘመናት እየሩሳሌም አከራካሪ ሆና እንድትዘልቅ አድርጓል። እስራኤል እንደ አውሮፓውያኑ በ1980 እየሩሳሌም መዲናዋ መሆኗን ማወጇን ተከትሎ ፍልስጤማውያንም ምስራቅ እየሩሳሌምን ወደፊት የምትመሰርተው ፍልስጤም መቀመጫ ትሆናለች በማለት የይገባናል ጥያቄአቸውን አንስተዋል።
news-50122885
https://www.bbc.com/amharic/news-50122885
#3 እሷ ማናት?፡ ማየትና መስማት የተሳናት የመብት ተሟጋችና የሕግ ባለሞያዋ ሃበን ግርማ
ዛሬም ድረስ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው እኩል ተምረው የሚያድጉ፣ ሠርተው የሚቀየሩ የማይመስላቸው አይታጡም። ከዚህ የማህበረሰብ ጎምቱ አመለካከት ጋር ታግለው፣ የእለት ኑሯቸውን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ለሌላው አርአያ የሆኑ በርካታ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎችም አሉ።
"አታድግም፣ መማር፣ መስራት አትችልም፤ አታገባም የሚሉኝ ብዙ ሰዎች ነበሩ" ከሩቅ ዘመን ሔለን ኬለርን ብንጠቅስ ከቅርብ ደግሞ ሊ ሪድሊይ እማኛችን ነው። የኛዋን የትነበርሽ ንጉሤንም ሳንረሳ ማለት ነው። 'ሎስት ቮይስ' በሚል የሚታውቀው እንግሊዛዊው ሊ ሪድሊይ ለ39 ዓመታት ድምፅ ያልነበረው ኮሜዲያን ነው። ሰዎች ለአካል ጉዳት ያላቸውን አመለካከትና አገላለፅ ለማረም ሊ፣ እ.ኤ.አ በ2018 በተካሄደው ታዋቂው ልዩ የክህሎት ውድድር 'ብሪቴይን ጋት-ታለንት' ላይ የራሱ አካላዊ ጉዳትን እያነሳ በመቀለድ አሸንፏል። • የኢትዩጵያውያን አካል ጉዳተኞች ፈተናዎች ምን ድረስ? • ኢትዮጵያዊው የ100 ሜትር ክብረወሰን ባለቤት ይህ መናገር የማይችለው፣ ነገር ግን በሳቅ ጎርፍ የሚያጥለቀልቀው ኮሜዲያን፣ በጋዜጠኝነት ሁለት ዲግሪ ሲኖረው ለቢቢሲ እና ለሌሎች የሃገሪቷ ጋዜጦች በመሥራትም በርካታ ሽልማቶች የተጎናፀፈ ነው። ለዛሬው የእሷ ማናት ዝግጅታችን የመረጥናት ሐበንም አካል ጉዳት ሞራሏን ሳይበግረው፣ ለራሷም ለሌሎችም አርዓያ መሆን የቻለች ግለሰብ ናት። ሌላኛዋ ሄለን ኬለር ስወለድ ጀምሮ የመስማትም ሆነ የማየትም ችግር አብሮኝ ነበር የተወለደው። ለሆነ ነገር 'ገደብ' በማስቀመጥ አላምንም፤ 31 ዓመቴ ነው። ሐበን ግርማ እባላለሁ። ሁሌም አካላዊ ጉዳት ያላቸው ሰዎች መሥራት የሚችሉት ነገር የተገደበ ነው የሚሉ አስተሳሰቦችን ስታገል ኖሬያለሁ፤ አሁንም በዚሁ የትግል ሜዳ ውስጥ ነኝ። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪዬን አግኝቻለሁ። በዚህም በዩኒቨርስቲው ታሪክ የመጀመሪያዋ ማየትና መስማት የተሳናት የሕግ ምሩቅ ሆኛለሁ። በ2019 ደግሞ ''The Deaf blind Woman who Conquered Harvard Law'' የሚል መጽሐፍ ለንባብ አብቅቻለሁ። ይህን መጽሀፍ በስሜ የተሰየመ ሲሆን፣ የህይወት ተሞኩሮዬን፤ ውጣ ውረዴንና ስኬቴን ያሰፈርኩበት ነው። • በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት በመላው ዓለም እየዞርኩ 'የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች፣ እኩል ተደራሽና ተጠቃሚ መሆን አለባቸው' የሚል ዘመቻ የማደርግ ሲሆን፣ ለዚህ የአካል ጉዳተኞች መብት እንዲከበር ለማደርገው ጥረት ዓለማችን መሪዎችና የተለያዩ አካሎች የማበረታቻ ቃላቸውን፣ እውቅናና አድናቆታቸውን ሰጥተውኝ ያውቃሉ። ከእነዚህም መካከል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የነበሩት ባራክ ኦባማና ቢል ክሊንተን፣ የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ይገኙበታል። ተወልጄ ያደግኩት በኦክላንድ ካሊፎርኒያ ነው። እናትና አባቴ ግን ከኤርትራ እና ከኢትዮጵያ ናቸው። መጀመሪያ ላይ በትንሹም ቢሆን ማየትና መስማት እችል ነበር፤ በኋላ ላይ ግን ዓይኖቼም ሆኑ ጆሮዎቼ የማየትና የመስማት አቅማቸው እየደከመ በመምጣቱ በመሳሪያ በመታገዝ ወደ መግባባት ተሸጋግሬያለሁ። አሁን ድምጽ ቀድቶ በሚይዝ መሣሪያ በመናገር ከሰዎች ጋር እግባባለሁ። የፈለግኩትን ማይል ብጓዝ የማይለየኝ ማይሎ ነው፤ ማይሎ ውሻዬ ነው፤ የቀኝ እጄ! "ዓለምን እዞራለሁ። ማይሎ የሚባል የሦስት ዓመት ዕድሜ ያለው የ'ጀርመን ሼፐርድ' ዝርያ ያለው ውሻዬ፣ እኔን መንገድ መምራት የሚያስችለው የሁለት ዓመት ትምህርት ተሰጥቶታል። አሁን ሁሉንም ነገር ማየት የሚችል ውሻ አለኝ። ደረጃዎች ላይ መቆም፣ አስቸጋሪ ቦታዎችን መለየት፣ መሻገሪያ መንገድ ስንደርስ መቆም እና ሌሎችንም ክህሎቶች ተምሯል። ሁለታችን አብረን እንጓዛለን፤ በአውሮፕላን ይሁን በእግር ጉዟችን አንድ ላይ ነው። ማይሎ ድንቅ የመንገድ መሪ ነው።" • ዐይነ ስውሩ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ሕንፃ ከሰባተኛ ፎቅ የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ሞተ በመጪው ጊዜ በመላው ዓለም ላይ ላሉ 1.3 ቢሊየን የአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሚሆን የመኪና ቴክኖሎጂ ቢፈበረክ ምኞቴ ነው። ምክንያቴ ደግሞ የአካል ጉዳተኞች እኩል ዕድል አግኝተው በነፃነት እንዲማሩ፣ እንዲሠሩና እንዲንቀሳቀሱ የሚፈጥረው ፀጋ በቀላሉ የሚታይ ስላልሆነ ነው። መደነስ፣ ብስክሌት መጋለብ፣ ተራራ መውጣት እና ሌሎች የአካል እንቅስቃሴዎችን አደርጋለሁ። የፈለግኩትን ማይል ብጓዝ የማይለየኝ ማይሎ ነው፤ ማይሎ ውሻዬ ነው፤ የቀኝ እጄ! ብዙ ቤተሰቦችም ሆኑ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ከሌላኛው የሕብረሰተብ ክፍል ያነሱ ወይም የተለዩ መሆናቸው እንዳይሰማቸው አሊያም ወላጆቻቸው እንዳያፍሩባቸው ችግራቸውን ይደብቃሉ፤ ይደበቃሉም። "እኔም በዚህ አልፌያለሁ፤ ከሌሎች ሰዎች የተለየሁ እንደሆንኩኝ እንዳይሰማኝ ያለኝን የአካል ጉዳት የደበቅኩበት ጊዜ ነበር።" የአካል ጉዳት ማንኛውም ሰው የሕይወት ተግዳሮች እንዳለው እንዲቀበል እንጂ እንዲያፍርበት መሆን የለበትም፤ ተግዳሮቶቹን መቀበል ደግሞ መፍትሄዎች ለማምጣት መሥራት እንዳለብህ እንድታምን ያደርጋል። "እኔም የአካል ጉዳተኛ መሆኔን ተቀበልኩት። አላይም፣ አልሰማም። ግን ደግሞ ብዙ ክህሎት አለኝ። የአካል ጉዳት አለብህ ማለት ጥንካሬ የለህም ማለት አይደለም"። በመጽሐፌም ውስጥ ማስረጽ የፈለግኩትና ጎልቶ እንዲታይ የፈለግሁት መልዕክት ይህ ነው። ሐበን ማለት በትግርኛ ኩራት ማለት ነው። ብዙ የአካል ጉዳት ያላቸው ሰዎች ያፍራሉ፣ ችግራቸውንም ይደብቃሉ። በዚህ መጽሐፍ የአካል ጉዳት ኩራት መሆኑን ተቀብለው ያላቸውን ፀጋ ተጠቅመው የተለየ ነገር መሥራት እንደሚችሉ ነው የማስተምረው። ማየት የሚችሉ ሰዎች የዓይን ብርሃናቸውን ተጠቅመው ማንበብ መቻላቸው ለእነሱ የተሰጠ ፀጋ ሲሆን፣ እኔ ብሬይልንና ጣቶቼን በመጠቀም አነባለሁ። ይህ ለእኔ የተሰጠ ፀጋ ስለሆነ ከዓይን ስራ ጋር እኩል ነው። • ኢትዮጵያን ጨምሮ 130 አገራትን የጎበኘው ዓይነ ስውር በኢኮኖሚ ደረጃ የተሻሉ፣ በትምህርትና በሌሎች አገልግሎቶች ተደራሽ የሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ተወልጄ ባድግም የአካል ጉዳትን እንደ ነውር የሚቆጥሩ አንዳንድ ሰዎች ስለማእጠፉ ከባድ የልጅነት ጊዜ አሳልፌያለሁ። "አታድግም፣ ትምህርት ቤት አትሄድም፣ አትሰራም፣ አታገባም የሚሉኝ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ወላጆቼ እኚህ አስተሳሰቦች ይታገሉ ነበር፣ እኔም እነዚህ መልዕክቶች ሲደርሱኝ መታገል ግድ ይለኝ ነበር።" የአካል ጉዳት፣ ሰዎች በህይወት ሲኖሩ የሚገጥማቸው ነገር ነው። የአካል ጉዳት 'ሃበን ነው' [ኩራት ነው] በማለት ነው የማምነው። የአካል ጉዳት ኖሮብን በተለያዩ ውጣ ውረዶች የምናልፍ ሰዎች ሊኖረን የሚገባው አማራጭ፣ ተቀብሎን የሚሄድ ማህበረሰብ ስላለ የአካል ጉዳታችን ልንኮራበት እንጂ ልናፍርበት አይገባም። "አትዘኑልኝ፤ ሌሎች አማራጮች ተጠቅሜ መንቀሳቀስ እችላለሁ። እኛ ደግሞ ክብር ይገባናል፤ በሁሉም መልኩ ተጠቃሚዎች መሆን አለብን" የሚል ዘመቻ የጀመርኩት ለዚህ ነው። "የአካል ጉዳት ያለብኝ ሰው ነኝ፤ ሴትም ነኝ። እስከ አሁን በባህላችን፣ ሴት ልጅ ላይ የሚደርስ መድልዎ አለ። በተለይ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ላይ የሚደርስ 'ኢቦሊዝም' የሚባል መድልዎ አለ። ይህም የአካል ጉዳተኞች፣ ከሌላው የህብረሰተብ ክፍል የበታች ናቸው የሚል አመለካከት ያለ በመሆኑ ነው፤ ልንታገለው ይገባል።" "ማየት የተሳናቸው ሰዎች ምርጫ የላቸውም የሚሉ ሰዎች ቢኖሩም፣ ቤተሰቦቼ ጠንክረሽ ስትሰሪ ታሸኒፊያለሽ ብላው ስላሳደጉኝ ትምህርቴን ጠንክሬ ነው የተማርኩት።" • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" ነገር ግን ለእኔ ስራ መስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ የቀሩ ነበሩ። የዩኒቨርሰቲ ትምህርቴን ካጠናቀኩ በኋላ ስራ መፈለግ ግድ ነበር፤ ግን የትምህርት ማስረጃዬንና ልምዴን የሚገልጽ ወረቀቴን አይተው ለቃለ መጠይቅ የሚጠሩኝ ተቋማት፣ የአካል ጉዳት እንዳለብኝ ሲያዩ 'ስራውን' ለመስጠት አይደፍሩም ነበር። "ለቃለ መጠይቅ ስቀርብ፡ የአካል ጉዳተኛ መሆኔን ሲያውቁ ይቅርታ ይሉኛል። ስራውን ሊሰጡኝ ፍቃደኞች አይሆኑም። የአካል ጉዳተኞች ይህንን ስራ መስራት አይችሉም የሚል የተሳሳተ አመለካከት አለ። ብዙ ተቋማት ስራ መስራት እንደማልችል በማሰብ ብዙ እድል ነፍገውኛል" ማንኛውም ዓይነት የአካል ጉዳት ያለበት ሰው፣ በተለይ ደግሞ ማየት የተሳነው ከሆነ፣ ሌሎች ክህሎቶችን ለማሳደግ መንገድ የሚከፍት ስለሆነ፣ 'የቤት ስራ' ተብለው የሚወሰዱ ስራዎች ተምሮ ማደግ አለበት። ሴቶች አቅማቸው በማሳደግ በህይወታቸው ብዙ አማራጮች እንዳሉ መገንዘብ አለባቸው። አካል ጉዳተኛ ሴቶች ደግሞ፣ ልዩ ክህሎታቸውን ማዳበር ላይ ትኩረት መስጠት አለባቸው። የሴቶች ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ጾታዊ መድልዎ አሁንም ትልቁ ፈተና ነው። ሁል ግዜ መሰናክል ሆኖ የሚቀጥል ጉዳይ በመሆኑ አሁን የምናደርገው ትግል ለመጪው ትውልድ ሊያግዝ ይችላል። "እኔ ራሴን፣ ልዩ ነሽ፤ ልዩ ፍጡር ለመሆን አትፈሪ እላታለሁ። አብዛኛዎቻችን ልዩ የሆንንበት ምክንያት ለመደበቅ ስለ ምንሞክር፡ ልዩነታችን ደብቀን ለመመሳሰል እንፈልጋለን። ይህ ልክ አይደለም፤ ራሴን መምሰል ነው የምፈለገው። የአካል ጉዳት ያለባችሁ ከሆናችሁም ኩራት ነውና አክብሩት።" እሷ ማናት? የሚለው ጥንቅራችን ያሰቡበትን ዓላማ ለማሳካት ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፉ ሴቶችን ታሪክ የምናስቃኝበት ነው።
news-42242663
https://www.bbc.com/amharic/news-42242663
''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ በደጋፊዎች መካከል ለሚቀስቀስ ግጭት እና እርሱን ተከትሎ ለሚፈጠር ኹከት ባይተዋር ባይሆንም የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ግን ከስፖርትም በዘለለ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ነባራዊ መልክ የሚያንፀባርቁ መሆናቸውን ማስተዋል ይቻላል።
ትግራይ ስታዲየም በ2009 ዓ.ም በርካታ ቁጥር ያለው የስቴዲየም ብጥብጥ በተለይም በላይኛው ፕሪሚየር ሊግ ቢዘገብም ከብጥብጦቹ ጀርባ እግር ኳስን የሚሻገሩ ገፊ ምክንያቶች እምብዛም እንዳልነበሩ ይጠቀሳል። በያዝነው ዓመት በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚለኮሱ ግጭቶች እና ረብሻዎች ቁጥር አይሏል። ከተጀመረ ጥቂት ሳምንታትን ብቻ ባስቆጠረው የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር ከረብሻዎች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ክለቦች ላይ የጣለው ቅጣት ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደደረሰ ጉዳዩን የሚከታተሉ ባለሞያዎች ያስረዳሉ። መጠናቸው ይለያይ እንጅ ባለፉት ሁለት ወራት ሃዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ አዲግራት፣ ጅማ እና በቅርቡ ደግሞ ወልዲያ ከተሞች ውስጥ ግጭቶች እና ረብሻዎችን አስተናግደዋል። ባለፈው እሁድ በወልዲያ ስፖርት ክለብ እና በመቀሌ ከተማ መካከል ሊደረግ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት በሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወት የጠፋ ሲሆን ንብረት ላይ ዘረፋና ወድመት ተከስቷል። በዕለቱ ማገባደጃ ላይ በመቀሌ ከተማ መንገዶች ላይም ክስተቱን ለመቃወም በርካታ ሰዎች ወጥተው ነበር። ጨዋታው ካለመካሄዱ በተጨማሪ የግጭቱ አሻራ እስከቀጣይ ቀናት ቀጥሏል። የትግራይ ክልል የእግር ኳስ ፈዴሬሽንም ክስተቱን በማውገዝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈደሬሽን ጉዳዩን ኣጣርቶ በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ በደብዳቤ ጠይቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ የወልዲያው ክስተት ከእግር ኳስ የሚሻገር ገፅታ እንዳለው ይገልፃሉ። በሴካፋ ውድድር ከሚሳተፈው የወንድ አዋቂዎች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ጋር ናይሮቢ የሚገኙት አቶ ጁነዲን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ግጭቱ ከስፖርት ሜዳ ውጭ መቀስቀሱን አስታውሰው "ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ይዘት ያለው ነገር ነው። ሜዳ ውስጥ ቢሆን ከኳስ ድጋፍ ጋር ይያያዝ ነበር፤ ሌላ ትኩሳት ያለበት ነው የሚመስለኝ፤ እግር ኳስ ብቻውን አይመስለኝም" ሲሉ ተናግረዋል። ከማኅበረሰባዊነት እስከ ብሔረተኛነት በስፖርቱ ዓለም የተመልካቾች ነውጠኛነት ምክንያቶች ብዙ ናቸው ሲል የሚያስረዳው የስፖርት ተንታኙ መንሱር አብዱልቀኒ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ወይንም ምጣኔ ኃብታዊ ብሶቶች ስቴዲየም ላይ ሊያጠሉ እንደሚችሉ ይናገራል። በኢትዮጵያ እግር ኳስን የታከከ ብጥብጥ ሲከሰት "የመጀመሪያው ባይሆንም እየተባባሰ ግን ሄዷል። የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ስናጤን ደግሞ ከእግር ኳስ ባሻገር ሌሎች የጀርባ ምክንያቶች እንዳሉ ግልፅ ነው"ይላል። እግር ኳስ ማኅበረሰባዊ መሰረት ከሌለው በስተቀር የጠነከረ የእኔነት ስሜት ሊፈጥር አይቻለውም የሚለው መንሱር፤ ይሁንና ክለቦች ከማኅበረሰባዊ መሰረታቸው በዘለለ ብሔር ተኮር መልክን እየተላበሱ የመምጣታቸውን አዝማሚያ "አደገኛ ነው" ይለዋል። "ከአንዳንድ በጥባጭነት እጅግ ወደተደራጀ ነውጠኛነት ሊሄድ ይችላል። ቀስ በቀስ ወደመቧደን እየተሄደ ነው። ራሳችንን መከላከል እና ማዘጋጀት አለብን በሚል ደጋፊዎች ራሳቸውን ማደራጀት ከጀመሩ የሚያሰጋ ዓይነት እውነታ ሊፈጠር ይችላል።" ላለፉት ሁለት ዓመታት መቀሌ ከተማ የእግር ኳስ ክለብን የደገፈውና ባለፈው እሁድ ማለዳ የወልዲያ አመሻሹን ደግሞ የመቀሌ ኹከቶችን የታዘበው ገብረመድህን ኃይለስላሴ በዚህ አስተያየት ይስማማል። "የእኔነቱ መንፈስ ከርሮ ከኳስ ወዳጅነት ወደብሔርተኝነት ነው እየሄደ ያለው፤ ከዚህ ቀደም ብጥብጡ ተጀምሮ የሚያልቀው ስቴዲየም ነው፤ ከዚያ አያልፍም። አሁን አሁን እየታየ ያለው ግን የባሰ ነው" ሲል ለቢቢሲ አስተያየቱን ሰጥቷል። የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለብን የሚደግፈውና የድጋፍ እንቅስቃሴዎችን በማስተባበር ተሳትፎ ያለው እሸቱ ቢያድጎ በአንፃሩ ስለ ክለብ ድጋፍ ፖለቲካዊ አንድምታዎች የሚሰጡ አስተያየቶች የተጋነኑ ናቸው ባይ ነው። "ሰዎችን ወደሜዳ የሚስባቸው በዋናነት ኳሱ ነው" በማለት እሸቱ ይናገራል። የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ሆኖም ክለቦች የማንነት ማግነኛ እና የራስ ኩራት መገለጫ መድረኮች እየሆኑ የመምጣታቸውን ሃቅ በየአካባቢው እየጎመራ ከመጣው የዘውግ ብሔርተኛነት ጋር የሚያስተሳስሩት አልጠፉም። እሸቱ የሚደግፈው ፋሲል ከነማ ለምሳሌ ስያሜውን ከክለቡ መናገሻ ጎንደር ከተማ መስራች አፄ ፋሲል ጋር ሲያሰናስል በአርማው ደግሞ በአፄ ቴዎድሮስ ምስል አሸብርቋል። ፋሲል ከነማ ከአካባቢው የአለባበስ ልማድ እንደሆነ ከሚነገርለት ጃኖ የማልያ እሳቤውን እንደተዋሰ የሚናገረው እሸቱ ከደጋፊ አመራሮች ጋር በመሆን በመሰንቆ የሚታጀብ የአደጋገፍ ስልትን ተግባራዊ ለማድረግ በመሥራት ላይ መሆኑንንም ይገልፃል። ይህ ታሪክን የማጣቀስ ሁኔታም በጅማም ታይቷል። ከዚህ ቀደም ጅማ ከነማ ይባል የነበረው የእግር ኳስ ክለብ በአዲስ መልክ ሲዋቀር በታሪካዊው ንጉሥ ስም ጅማ አባጅፋር የተሰኘ አዲስ መጠሪያን ተላብሷል። ክለቡን ለበርካታ ዓመታት የደገፈውና በአካባቢው ተወልዶ በጅማ ከተማ ያደገው ገዛኸኝ ከበደ ይህ እርምጃ ከከተማዋ ነዋሪዎች ባሻገር ከሌሎች በርካታ የአካባቢው ወረዳዎች ደጋፊዎችን ለመሰብሰብ ታልሞ የተከናወነ ነው ይላል። የአባ ጅፋር ደጋፊዎች ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሀዋሳ ከነማ ጋር በነበረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ረብሻ አስነስተዋል በሚል ክለቡ አንድ ጨዋታን ያለደጋፊ እንዲያከናውን፤ እንዲሁም 150 ሺህ ብር እንዲከፍል ቅጣት ተላልፎበታል። ገዛኸኝ እንደሚለው ለረብሻው መንስዔ የሆነው ሌላኛው የከተማዋ ክለብ ጅማ አባ ቡና ላይ ያልተገባ በደል እንደደረሰበት በመታመኑ ነው። "የፌዴሬሽን ሰዎች ለኦሮሚያ ክልል ክለቦች ጥሩ አመለካከት የላቸውም ይባላል" ሲል ገዛኸኝ ተናግሯል። በኦሮሚያ ውስጥ የፌዴራል ስፖርት ተቋማትን በጥርጣሬ መመልከት በእግር ኳስ ብቻ ሳይገደብ አትሌቲክስ ላይም ይስተዋል እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ከዚህ በኋላስ? አቶ ጁነዲን የሚመሩት ፌዴሬሽን ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲኖር ከክልል መንግሥታት እና ከተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራ ይናገራሉ። "እግር ኳስ ከፖለቲካ፣ ከኃይማኖትና ከዘር የፀዳ መሆን እንዳለበት የሚያስረዳውን ዓለም አቀፍ መርኅ መተግበር እንዳለበት እናምናለን" ብለዋል። በእግር ኳስ ተመልካቾች ነውጠኝነት ላይ ጥናትን ላከናወነው መንሱር ግን ፌዴሬሽኑ ከውይይት የዘለለ ፋይዳ ያለው ነገር እየሰራ አይደለም። ክለቦች ሲቋቋሙ ወይንም ሲዋቀሩ አካባቢያዊ መገለጫ ወይንም ከተማዊ ስያሜ ሊኖራቸው ቢችልም ከብሔር፣ ከዘር ወይንም ከኃይማኖት ጋር በተቆራኘ መልኩ መደራጀት ክልክል መሆኑን የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ማኅበራት ማደራጃ መመሪያ አንቀፅ 50 ቁጥር 2 ይገልፃል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ብቻ ፌዴሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ሊጎች የብሔር ስም የተቀጠላላቸው 14 ክለቦች ውድድር ያደርጉ ነበር። ከእነዚህ ክለቦች መካከል ሐድያ ሆሳዕና የእግር ኳስ ክለብ፣ ወላይታ ድቻ፣ ጎፋ ባሬንቼ፣ ካብዳባ አፋር የመሳሰሉ ክለቦች እንዳሉ መንሱር ይገልፃል። ከዚህም በተጨማሪ ክለቦች የተለያዩ የአገሪቱን ክልሎች እንደሚወክሉ መታሰቡ፤ ክልሎች ብሔርን መሰረት አድርገው እንደመዋቀራቸው ብሄርን እንደሚወክሉ ወደመታሰብ አድጓል። መጠሪያው ባይኖርም እንኳን ከሚመጡበት ክልል ጋር ተያይዞ የእገሌ ብሔር ነው የሚል እምነት አሳድረዋል። እግር ኳስ ይብቃን? ገብረመድህን አደጋገፍ አሁን ባለው መልኩ የሚቀጥል ከሆነ እግር ኳሱ ከናካቴው ቢቀር ይሻላል ባይ ነው። "ያው እንደለመድነው የአውሮፓ እግር ኳስን ብንከታተል ይሻለናል" ይላል። መንሱር የእግር ኳሱን ሊጎችን ሙሉ በሙሉ ማቆም ችግሮች አልፈታ ካሉ ሊደረስበት የሚችል እርምጃ እንደሆነ ይናገራል። ለአሁኑ ግን ሁሉም ጨዋታዎች እኩል እንዳልሆኑ ግንዛቤ ተወስዶ የስጋት መጠን ልኬት ሊወጣላቸው ይገባል በማለት ምክሩን ይለግሳል። በዚህም መሰረት አደጋ የመፈጠር ዕድላቸው ከፍ ያሉባቸው ጨዋታዎችን በባዶ ሜዳ ከማጫወት በሌላ ሜዳ እስከማጫወት ድረስ የሚሄድ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል መንሱር ይጠቁማል። ለዘለቄታው መፍትሄ ለማበጀት ግን ሊጎች በተለይም ፕሪሚየር ሊጉ የሚካሄድበትን መዋቅር ከአገሪቱ ነባራዊ እውነታ ጋር በተናበበ መልኩ ማስተካከል ያሻል ባይ ነው። እግር ኳስ ብቻውን አገርን ለመበታተን የሚያበቃ አቅም የለውም ሲል የሚሟገተው መንሱር በአግባቡ ከተያዘ የአንድነትን፣ የወንድማማችነትን ስሜት እንደሚያዳብር አፅንዖት ሰጥቶ ይናገራል። "ነገር ግን ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ የባሕርይ ለውጦች፣ ችግሮች እና ክፉ አስተሳሰቦች ሁሉ በስቴዲየም ይገለፃሉ" ይላል።
news-42617049
https://www.bbc.com/amharic/news-42617049
ቁርጡ ያልታወቀው የታሳሪ ቤተሰቦች ጥበቃ
ዕለተ ረቡዕ ታህሳስ 25/2010 ዓ.ም የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት "ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ በአቃቢ ሕግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙና የተፈረደባቸው አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና ሌሎች ግለሰቦች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በምህረት ሕግና ሕገ-መንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ እንዲፈቱ ተወስኗል" ሲል መግለጫ ያወጣው።
መግለጫው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰለቸን ሳይሉ በተለይ ደግሞ ቂሊንጦ፣ ዝዋይ እና ማዕከላዊ እስር ቤቶች አቅራቢያ እየዋሉ በር በሩን እያዩ ነው። አመፅና አድማ በማስነሳት ወንጀል ተፈርዶበት እስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዮናታን ተስፋዬ ቤተሰብ ዜናው ከተሰማበት ዕለት ጀምሮ መፈታቱን እየጠበቁ ነው። "ከገና በዓል ጋር በተያያዘ ልጃችን ሊለቀቅ ይችላል ብለን በጉጉት ስንጠብቅ ብንቆይም እስካሁን ምንም ዓይነት ፍንጭ የለም" ይላሉ ልጃቸው ዮናታን ተስፋዬ በዝዋይ እስር ቤት የሚገኘው፤ አቶ ተስፋዬ ረጋሳ። በፍርድ ሂደት ላይ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆዩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ልጅ ቦንቱ በቀለ ግን ውሳኔው ተግባራዊ ሆኖ ካላየች ለማመን እንደምትቸገር ትናገራለች። "መንግሥት ጠዋት የተናገረውን ከሰዓት ስለማይደግመው ከእስር ወጥቶ እንደ ቀድሞው አብረን ቁርስ ስንበላ ብቻ ነው የማምነው" ትላለች። የዮናታን አባት የመንግሥት ውሳኔ ከተሰማ በኋላ ልጃቸውን ባያገኙትም ሌሎች ወዳጅ ዘመዶቹ ሄደው ጎብኝተውታል። ''ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ በመግለጫው መሠረት እኔም ከእስር ልለቀቅ እችላለሁ ብሎ እየጠበቀ እንደሆነም አጫውቷቸዋል" ይላሉ አቶ ተስፋዬ። ቢቢሲ ይህንን ዜና በሚያሰናዳበት ወቅት አቶ በቀለ ገርባ ለሕክምና እርዳታ ከእስር ቤት ውጭ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። ልጃቸው ቦንቱ ለቢቢሲ እንደተናገረችው "እኔስ ለምጄዋለሁ፤ ታናናሽ ወንድሞቼ ግን ትምህርታቸውን መከታተል ተስኗቸዋል" ትላለች። በነበቀለ ገርባ የክስ መዝገብ ውስጥ የሚካተቱት የኦፌኮ አባላቱ አዲሱ ቡላላ እና ደጀኔ ጣፋ መግለጫውን በተመለከተ እስካሁን ምንም ዓይነት ነገር እንዳልሰሙ እንደነገሯትም ገልፃለች። በጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ መሠረት ከእስረኞች መፈታት በተጨማሪ የተለያዩ ሰቆቃዎች በእስረኞች ላይ እንደሚፈፀምበት ሲነገር የቆው ማእከላዊ የምርመራ ማእከል እንዲዘጋ ተወስኗል ብለዋል። 'አምነስቲ ኢንተርናሽናል' የተሰኘው የመብት ተሟጋች ቡድን የእስረኞች መፈታትና የማዕከላዊ መዘጋት ዜና እንደተሰማ ''የአስከፊው የጭቆና ዘመን ማብቃት ምልክት ሊሆን ይችላል'' ብሎ እንደዘገበ አይዘነጋም። ነገር ግን ከመንግሥት በኩል ስለሂደቱም ሆነ የትኞቹ ግለሰቦች ከእስር ሊለቀቁ እንደሚችሉ የተሰጠ ፍንጭ የለም። "ምንም እንኳ በይግባኙ መሠረት የዮናታን የእስር ጊዜ ከስድስት ዓመት ተኩል ወደ ሦስት ዓመት ተኩል ቢቀነስም ሙሉ በሙሉ ከእስር ተለቆ ደግሞ ብናዬው ቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹ ከምንም በላይ ደስተኛ ልንሆን እንደምንችል ጥርጥር የለውም" ይላሉ አቶ ተስፋዬ። አክለውም "መግለጫው ከድርጊቱ በፊት መጥቶ የእኛን ቤተሰብም ሆነ ሌሎች ወዳጅ ዘመዶቻቸው በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን አጉል ጉጉት ላይ ከሚጥል ተግባሩ ቢቀድም የተሻለ ነበር" በማለት ውሳኔውን ተከትሎ የተከሰተውን ጉጉት ይጠቅሳሉ። ስለ ጉዳዩ የሚያውቁት ነገር ካለ በሚል ፌዴራል ማረሚያ ቤትን ጠይቀን "እስካሁን ከጠቅላይ ሚንስቴር ጽህፈት ቤትም ሆነ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ የደረሰን ምንም ዓይነት ደብዳቤ የለም። እንደደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል" ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው ምክትል ሳጅን ሳህለገብርዔል ይትባረክ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የፌዴራል አቃቤ ሕግም በተመሳሳይ ምንም ዓይነት ደብዳቤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እንዳልደረሰው አሳውቋል። ቦንቱ በቀለ ለቢቢሲ እንደተናገረችው ከትናንት በስትያ ቂሊንጦ እስር ቤት አካባቢ በርካታ ሰዎች ወዳጅ ዘመዶቻቸው በመግለጫው መሰረት ከእስር ይፈቱ እንደሆን በጉጉት ሲጠብቁ ነበር። ሁኔታዎች መስመር ይዘው ማን ከእስር እንደሚፈታ ወይም ምህረት እንደሚደረግለት እስከሚታወቅ ድረስ ግን የታሳሪ ቤተሰብ እንዲሁም የወዳጅ ዘመድ ጉጉትና ጥበቃ ይቀጥላል።
news-49753182
https://www.bbc.com/amharic/news-49753182
ኤርትራ፡ እንቅስቃሴ አልባዋ የወደብ ከተማ -ምጽዋ
ከሦስት ሳምንታት በፊት የቢቢሲ ጋዜጠኞች በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ15 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን እንድንዘግብ ፍቃድ ተሰጥቶን ወደ ኤርትራ እቅንተን ነበር።
በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሶስት ክፍሎች አሰናድተናል። አራተኛው እና የመጨረሻው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። ከዚህ በፊት የነበሩ ጽሑፎችን ለመመልከት ከዚህ በታች ያሉትን ማስፈንጠሪያዎችን ይጫኑ። ማሳሰቢያ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ። በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ነው። • የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው • የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ ከአሥመራ ወደ መጽዋ ሲያቀኑ አስደናቂ እይታን የሚፈጥረውን ተራራማውን እና ጠመዝማዛውን መንገድ ያቆራርጣሉ። ምጽዋ ወይም በኤርትራዊያን አጠራር ምጽዋዕ ከመዲናዋ አሥመራ በስተምራቅ በኩል 115 ኪ.ሜትሮችን ርቃ ትገኛለች። ከአሥመራ ወደ ምጽዋ ሲያቀኑ አስደናቂ እይታን የሚፈጥረውን ተራራማውን እና ጠመዝማዛውን መንገድ ያቆራርጣሉ። በወራሪው ጣሊያን የተሰራው ይህ መንገድ ድንጋያማ ተራሮችን እያቆራረጠ ያልፋል። ሐምሌ 2010 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በፕሬዝደንት ኢሳያስ ግብዣ ወደ አሥመራ ባቀኑበት ወቅት በለስ የተመገቡበትን አካባቢ አልፈው ነው ምጽዋ የሚደርሱት። ሃሊማ ሞሐመድ አንድ ፍሬ በለስ በአንድ ናቅፋ ትሸጣለች። ሁለቱ መሪዎች በለሱን የተመገቡበት አካባቢ ''ድርፎ'' ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፤ በቦታው ብዙ በለስ የሚሸጡ ወጣት ሴቶች ይገኛሉ። በእዚህ ስፍራ አንድ ፍሬ በለስ በአንድ ናቅፋ ይሸጣል። በስፍራው በለስ ስትሸጥ ያገኘናት ሃሊማ ሞሐመድ ሁለቱ መሪዎች ይህን አካባቢ ከጎበኙ በኋላ ቦታው የበለስ ንግድ የሚዘወተርበት ቦታ እንደሆነ ነግራናለች። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ወደ ስፍራው ባቀኑበት ወቅት ነበር በሁለቱ ሃገራት ኤምባሲዎች እንዲከፈቱ፣ አየር መንገዶች በረራ እንዲጀምሩ እና ወደቦችም ሥራ እንዲጀምሩ የተስማሙት። • "ተጨማሪ የፌደራል የሥራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ እየተሠራ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ በጣሊያ የቅኝ ግዛት ወቅት ተዘርግቶ የነበረውን እና ግዙፍ ድንጋያማ ተራራን አቆራርጦ ያልፍ የነበረው ባቡር አሁን ላይ ቅሪተ አካሉ ብቻ ነው የቀረው። ጉዞውን በምስራቅ አቅጣጫ ወደ ምጽዋ ባደረጉ ቁጥር የባህር ወለል ከፍታ እየቀነሰ፤ ሙቀቱም እየጨመረ ይሄዳል። በጉዞው ላይ በጣሊያን የቅኝ ግዛት ወቅት ተዘርግቶ የነበረውን እና ግዙፍ ድንጋያማ ተራራን አቆራርጦ የሚያልፈውን የባቡር መስመር ማስተዋልዎ አይቀርም። ከበርካታ አስረተ ዓመታት በፊት የተዘረጋው የባቡር መስመር የሚያልፈበትን መልከዓ ምድር ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህን የባቡር ሃዲድ ለመዘርጋት ምን ያክል ትልቅ ድካም እና ገንዘብ ፈሰስ እንደተደረገበት መገንዘብ ይቻላል። አሁን ላይ ጭው ባለው በረሃ መካከል ቅሪተ አካሉ ብቻ የቀረው የባቡር አካል እና ሃዲድ በዛ በደጉ ዘመን ሰው እና ሸቀጦችን ከወደብ ከተማዋ ምጽዋ ወደ አሥመራ፣ ከረን እና ኡደት ወደሚሰኙ ከተሞች ያመላልስ ነበር። ''የሙት ከተማዋ ምጽዋዕ'' በወደብ ከተማዋ ምጸዋ ሲደርሱ የባህር ወለል ከፍታው ዜሮ መሆኑን ያስታውላሉ። በዚህ ወቅት ላይ የሙቀት መጠኑ እስከ 52 ዲግሪ ሴንቲገሬድ ሊሆን ይችላል። በስፍራው በነበርንበት ወቅት እኩለ ቀን ላይ የሙቀት መጠኑ 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነበር። ምጽዋዕ በአንድ ወቅት ላይ ቅንጡ በነበሩ አሁን ላይ ግን ፈራርሰው ብቻቸውን በተተዉ ህንጻዎች ተሞልታለች። ከቀይ ባህር ዳርቻ ላይ የምትገኛዋን ጥንታዊ ከተማ ሁኔታዋ የወደብ ከተማ አይነት አይደለም። ምጽዋን "እንቅስቀሴ የማይስተዋልባት የሙት ከተማ" ብሎ መግለጽ ማጋነን ላይሆን ይችላል። ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በአንድ ወቅት ላይ ቅንጡ በነበሩ አሁን ላይ ግን ፈራርሰው ብቻቸውን በተተዉ ህንጻዎች ተሞልታለች። በወደብ ከተሞች ላይ ፈጣን የሆነ የሰዎች እና የከባድ መኪኖች እንቅስቃሴዎችን ማስተዋል የተለመደ ነው። ይህ ግን በምጽዋ የለም። በአንድ ስፍራ ተሰባስበው ከቆሙ ጥቂት የደረቅ ጭነት መኪኖች ውጪ ለጥ ባለው ጎዳና ላይ የሚሸከረከር መኪና አይታይም። ከተማዋ እንዲህ በጸጥታ መንፈስ የተመታችበት ሁኔታ ጤናማ አይመስልም። በጣት በሚቆጠሩት ምግብ ቤቶች ውስጥ እንኳ ሰው አይታይም። ወደ አንዱ ሬስቶራንት ዘልቀው ቢገቡ ከአናትዎ በላይ የሚሽከረከረው የአየር ማቀዝቀዣ ድምጽን ብቻ ነው የሚሰሙት። ወደ ሥፍራው ይዞን እንዲሄድ የተላከው ሰው፤ "አሁን ሙቀት ስለሆነ ነው። ማታ ላይ ሰዎች ከቤታቸው ይወጣሉ" ብሎናል። እሱ ይህን ይበል እንጂ ከተማዋ እንዲህ በጸጥታ መንፈስ የተመታችበት ሁኔታ ጤናማ አይመስልም። ምጽዋ ወደብ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከደረሱት የሰላም ስምምንት በኋላ ለምጽዋ ወደብ አንዳንድ ለውጦች እንደተደረጉለት ሰምተናል። ይሁን እንጂ እኛ ወደ ሥፍራው በሄድንበት ወቅት ወደ ወደቡ መጠጋት እስከሚቻለው ስፍራ ድረስ ቀርበን እንደተመለከትነው በወደቡ ዙሪያ የተመለከትነው እንቅስቃሴ የለም። ግዙፍ መርከቦች ቆመዋል። ክሬኖችም እንዲሁ። የመጫን እና የማውረድ ሥራዎች ግን የሉም። በምጽዋ ወደብ ግዙፍ መርከቦች ክሬኖችም ይታያሉ የመጫን እና የማውረድ እንቅስቃሴዎች ግን አይታዩም ቀይ ባህር ከኤርትራም አልፎ ለጎረቤት ሃገራት ትልቅ የተፈጥሮ ጸጋ ነው። የቀይ ባህር ዳርቻ በዛ ሞቃታማ ስፍራ በዋና ራስን ቀዝቀዝ እና ዘና ለማድረግ ምቹ ስፍራ ነው። ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ሰዎች ከባህር ዳርቸው ሰፍራ ላይ ይዝናናሉ። የቀይ ባህር ዳርቻን ሲዋኙ የተመለከትናቸው ሰዎች ቁጥር በከተማዋ ካስተዋልናቸው ሰዎች ቁጥር በላይ ስለመሆናቸው ጥርጥር የለውም። ባህር ዳርቻው ላይ የሚገኙት ጥቂት ሆቴሎች አስርት ዓመታትን ያስቆጠሩ ናቸው። ቀይ ባህር ላይ የሚዝናኑ ሰዎች ሌተናል ኮሎኔል ጌታቸው መርሃ ጽዮን (ኢንጅነር) የፕሬዝደንቱ አማካሪ እና የመረጃ እና ካርታ ኃላፊ ናቸው። ኃላፊው በወደብ ከተማዋ ምጽዋ የሚፈለገው አይነት የንግድ እንቅስቃሴ እንደሌለ ይስማማሉ። • የመይሳው ካሳ የልጅ ልጆች "እንደ ጦርነት የከፋ ነገር የለም። ከልማት ይልቅ ሉዓላዊነታችንን የማስከበር ሥራ ላይ ተጠምደን ነው የቆየነው። አሁን ሁሉም ነገር ተቀይሯል" ይላሉ። ኃላፊው ከዚህ በተጨማሪ ኤርትራ ማዕቀብ ተጥሎባት የቆየች ሃገር መሆኗን በማስታወስ በወደብ ከተሞች የወጪ ገቢ እንቅስቃሴ በስፋት የማይስተዋልበትን ምክንያት ይህ መሆኑን ያስረዳሉ። ኤርትራ መቀመጫውን ሶማሊያ ላደረገው አል-ሸባብ የቁሳቁስና የስልጠና ድጋፍ ታደርጋለች በሚል እአአ በ2009 ላይ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ማዕቀብ ተጥሎባት ነበር። ማዕቀቡ የጦር መሳሪያ ዝውውርን እና ንብረት ማንቀሳቀስ እገዳን ጨምሮ የባለስልጣናት ጉዞ ላይ ጭምር አሉታዊ ተጽእኖን ፈጥሮ ቆይቷል። ከአል-ሸባብ ጋር ምንም አይነት ግነኙነት እንደሌላት በተደጋጋሚ ስታስተባብል የቆየችው ኤርትራ፤ ተጥሎበት የቆየው ማዕቀብ ላደረሰባት የምጣኔ ሃብት ቀውስ ካሳ እንደምትጠይቅ መሪዎቿ ተናግረው ነበር። • ኤርትራ ካሳ ጠየቀች እንደ የመረጃ እና ካርታ ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ጌታቸው ከሆነ፤ ከዓመት በፊት ማዕቀቡ መነሳቱ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር የሰላም ስምምነት መደረሱን ተከትሎ ኤርትራ በምጽዋ ብዙ የልማት መረሃ-ግብሮች እንደተያዙ እና ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ በረከቶችን ይዘው እንደሚመጡ ተስፋ ሰንቀዋል። ተስፋ ከተጣለባቸው ፕሮጅከቶች መካከል ደግሞ አንዱ ደግሞ ከ20-30 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የጸሃይ ኃይል ማመንጫ ነው።
news-55367982
https://www.bbc.com/amharic/news-55367982
ትግራይ፡ "ከመቀለ ድብደባ የተረፍንበት መንገድ"
ቤተሰቦቹን ያጣ ጨቅላ ህፃን፣ ራሷን ስታ ያለች ታዳጊ፣ የተገደሉ አዛውንት ሴት- እነዚህ ክስተቶች የመከላከያ ሠራዊት መቀለን ለመቆጣጠርና የትግራይ ክልል አስተዳደሪ የነበረውን ህወሓትን ለመጣል በተደረገው ውጊያ ከታዩ አደጋዎችና ሞቶች መካከል የተወሰኑት ናቸው።
እነዚህ ሕዳር 19/ 2013 ዓ.ም መቀለን ለመቆጣጠር በደረሰው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከተረፉ ነዋሪዎችና ዶክተር የተሰሙም ታሪኮች ናቸው። ከ500 ሺህ በላይ ሕዝብ ነዋሪ ባለባት የትግራይ ክልሏ መዲና መቀለ ስለተፈጠረው ነገር ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎችና ዶክተሮቹ የሚናገሩት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ካሉት ጋር ይቃረናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወቅታዊ ሁኔታን አስመልከቶ በተናገሩበት ወቅት መካላከያ ሠራዊት ባደረገው ወታደራዊ ዘመቻ አንድ ንፁህ ዜጋም አልተገደለም ማለታቸው የሚታወስ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ሻክሮ የነበረው የፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልል አስተዳደር ግንኙነት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ አምርቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘውን የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀሙ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ይህም የምድር ውጊያና የአየር ጥቃቶችን ያካተተ ነበር። ግጭቱ ከተነሳ በኋላ የኮሚዩኒኬሽን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ መረጃ ማግኘት አዳጋች የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የስልክ አገልግሎት በመመለሱ ቢቢሲ በርካታ ነዋሪዎችን ማናገር ችሏል። ስማቸው ለደኅንነታቸው ሲባል አልተጠቀሰም። ማስጠንቀቂያ፡ በፅሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ሁኔታዎች አንዳንድ አንባቢያንን ሊረብሹ ስለሚችሉ ከወዲሁ እንዲጠነቀቁ እናሳስበለን። በአይደር የሚገኙ የቤት አከራይ እለቱ ቅዳሜ ሕዳር 19/2013 ዓ.ም ነበር። በግቢያችን ውስጥ በደረሰ የከባድ መሳሪያ ድብደባ አራት ቤቶች በሙሉ ወደሙ። በአንደኛው ቤት ውስጥ ሙሉ ቤተሰቡ አልቆ አንድ ታዳጊ ልጅ ብቻ በህይወት ተረፈ። አባቱ፣ እናቱና ሁለት እህቶቹ ወዲያው ነበር የሞቱት። አስከሬናቸውም ተቆራርጦ ነበር። ለስድስት ዓመታት ያህል ተከራይተው ነው የኖሩት። የደረሰባቸውም ሁኔታ በጣም አሳዛኝና ልብ የሚሰብር ነው። ባለቤቴም ብትጎዳም ይህን ያህል ለክፉ የሚሰጥ አይደለም። እኔም ደረቴ ላይ ጉዳት የደረሰብኝ ሲሆን እስካሁንም አላገገምኩም። በመቀሌ ከሚገኘው ዋነኛው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የወጣነው ከቀናት በፊት ነው። በሆስፒታሉ ባለው የመድኃኒት፣ የህክምና ቁሳቁሶች እንዲሁም የዶክተሮች እጥረት ምክንያት ተገቢ ህክምና ማግኘት አልቻልንም። በርካታ ጉዳት ደርሶባቸው የመጡም ስለነበሩ የሆስፒታሉ ዋነኛ ትኩረት ክፉኛ በቆሰሉት ላይ ነው። ለኔእና ለባለቤቴ ሆስፒታሉ የታዘዘልንን መድኃኒት ከውጭ በሚገኝ ፋርማሲ እንድንገዛ በተነገረን መሰረት ብንፈልግም መድኃኒት እንዳለቀ ተነገረን። ጨርሰናል፤ በክምችት ክፍላችን የለም ተባልን። ሕይወት አዳጋች ሆናብናለች። ለአርባ ቀናት ያህል ዋና ዋና ገበያዎች እንደተዘጉ ናቸው። መሰረታዊ የሚባሉ ቁሳቁሶችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ምግብ ማግኘት ራሱ ፈታኝ ነው። ህይወታቸውን ለማዳን እግሬ አውጭኝ ብለው ከመቀሌ የሸሹ ነዋሪዎችም እስካሁንም አልተመለሱም። ደብዛቸው እንደጠፋ ነው። ያሉበትንም አናውቅም። የሁለት ልጆች እናቷ በሃወልቲ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የከባድ ጦር መሳሪያ ጥቃትና የአየር ድብደባዎች ከሕዳር 19/2013 ዓ.ም በፊትም በመቀለ ላይ ነበር።ሕዳር 19 ግን በመኖሪያዬ አካባቢ ተከሰተ። ጠዋት የጀመረ እሰከ ምሽት ድረስ አላባራም። በቤታችንም ላይ የከባድ ጦር መሳሪያ ድምፆች እያፏጨ ያልፍ ነበር። በከፍተኛ ፍርሐት ውስጥ ስለነበርን ልጆቼ ያለቅሱ ነበር። በአካባቢው በሚገኝ ቤትም የከባድ ጦር መሳሪያ በማረፉ ቤቱ ሙሉ በሙሉ ወደመ። አንዲት አዛውንት ተገደሉ፤ ልጃቸውም ከፉኛ ቆሰለች። በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል በሞትና በሕይወት መካከል በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ትገኛለች። አብዛኛዎቹ ጎረቤቶቻችን መቀለ ላይ ከደረሰው ከባድ ጥቃት ከተፈጸመበት ከሕዳር 19 በፊት ነው፤ ለህይወታቸው ፈርተው የሸሹት። እኔም፣ ልጆቼም እንዲሁም በቤታችን ተከራይተው የሚኖሩ ሰዎች ሳንሸሽ ቀረን። በቤታችን አካል ጉዳተኛና መሮጥ የማትችል ሰውም ስለነበረች ነበር ሁኔታውን የጠበቅነው። ነገር ግን በዚያች ዕለት የከባድ መሳሪያ ጥቃቱና ድብደባው በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስጨንቀን በአቅራቢያችን ወደሚገኝ በግንባታ ላይ ወዳለ ህንፃ ስር ገብተን ምሽቱን እዚያ አሳለፍን። የተራቡ የሠራዊቱ አባላት ምግብ አንድንሰጣቸው እየጠየቁን ነበር በነገታው ጠዋት የሰዎች ድምፅ መስማት ጀመርን፤ ነገር ግን ሁሉ ነገር እስኪረጋጋ ከተደበቅንበት ለመውጣት አልደፈርንም። ወደ በኋላ ላይ ስንወጣ ግን ከተማዋን የተቆጣጠሯትን የፌደራል መከላከያ ሠራዊት አባላትን ማየት ጀመርን። ገበያዎቹና ሱቆቹ በመዘጋታቸው ምክንያት የሚበላ ምግብና ውሃ እንድንሰጣቸው ጠየቁን። እርስ በርስ የምንጋራት ትንሽ ምግብ ብትኖረንም ካለችን የተወሰነ ሰጠኋቸው። በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ገበያዎች ቢከፈቱም ዋጋቸው ከመወደዱ የተነሳ የሚቀመስ አልሆነም። ካለው የሸቀጦች እጥረትም ጋር ተያይዞ ዋጋቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እያናሩት ነው። በመቀለ በአንዳንድ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው ውሃ፣ ኤሌክትሪክ ቢመለስም እኔ ግን የምኖርበት አካባቢ አልተመለሰም። ምግብም ለማብሰል በእንጨትና በምድጃ ነው የምንጠቀመው። እንጀራም የምንጋግረው በእንጨት ነው። ጎረቤቶቼም መጥተው ይጠቀሙበታል። የውሃ አገልግሎትም ባለመኖሩ ከመቀለ ወጣ ብሎ ከሚገኙ ጉድጓዶች ውሃ እየቀዳን ነው የምንጠቀመው። የፌደራል መከላከያ ሠራዊት አባላት ከተማውን እየዞሩ ቅኝት ያደርጋሉ። ነዋሪዎች ፊት ለፊት ወታደሮቹን ሲያዩ በከፍተኛ ሁኔታ ይደነግጣሉ። በአንዳንድ የትግራይ አካባቢዎች ወታደሮቹ ነዋሪዎችን እንደገደሉና ንብረትም እንደዘረፉ ቢሰማም በመቀሌ ይህንን አላየሁም። በአንዳንድ የከተማዋ ሰፈሮች ተፈላጊ ሰዎችን ለመያዝ የቤት ለቤት አሰሳ ቢያደርጉም እኔ በምኖርበት ሰፈር ይኼ አላጋጠመኝም። ነፃ የወጡ እስረኞች ከተማዋን መዘበሩ በሰዓት እላፊ አዋጁ ምክንያት አሁንም ቢሆን ከማታ እስከ ጠዋት በከተማዋ መንቀሳቀስ አይቻልም። እሰከ ቅርብ ቀናትም ድረስ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እየሰማን ነበር። ወታደሮቹ የከተማዋን ወጣቶች እንደገደሉ ሰምተናል። በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ ዝርፊያም ስለነበር ወጣቶቹ የሰዓት እላፊ አዋጁን ተላልፈው ከተማዋን እየጠበቁ ነበር። ወታደሮቹም የሰዓት እላፊውን ተላልፋችኋል በሚል በሚጠይቋቸውም ወቅት በተፈጠረ ፍጥጫ ተኩሰውባቸዋል። በክልሉ አስተዳደር የነበሩትና በከተማዋ ተሰማርተው የነበሩት ፖሊሶች በጎዳናው ላይ አይታዩም። በከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ ዝርፊያ ተፈፅሟል። በተለይም የክልሉ አስተዳዳሪ በከተማዋ ላይ ቁጥጥሩን ካጣ በኋላ የከተማዋ ዝርፊያው ቀላል የሚባል አልነበረም። አብዛኞቹ ዘረፋዎች የተፈፀሙት በቅርቡ ከእስር ቤት በወጡ ታራሚዎች ነው። ታራሚዎቹ ከእስር ቤት በነፃ ይለቀቁ ወይም ያምልጡ የምናውቀው ነገር የለም። የከተማዋ ነዋሪዎችም በዝርፊያው ተሳትፈዋል። ነገር ግን አሁን ይኼ በአብዛኛው ቆሟል። ዶክተር-በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል አሰቃቂ የሚባለውን ጊዜ አልፈን ይኸው በህይወት አለን። እኔ ከቤተሰቤ ጋር ደህና ነኝ። ነገር ግን በሆስፒታሉ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በከባድ መሳሪያ ጥቃቱ ተገድለዋል። ሕዳር 19/2013 ዓ.ም አራት ሰዓት አካባቢ የመከላከያ ኃይል መድፎችን ጨምሮ ከባድ መሳሪያ በከተማዋ ላይ መተኮስ ጀመረ፤ ይህም እስከ ምሽት ድረስ ሳያባራ ቀጠለ። እኔ ራሱ የ22 ሰዎች አስከሬን ቆጥሬያለሁ። ሰባት ሟቾች ጥዋት እንዲሁም 15 ሰዎች ወደ አመሻሹ አካባቢ። ሁሉም ሰላማዊ ዜጎች ናቸው። የአንዳንዶቹ አስከሬኖች በጥቃቱ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ በመጎዳታቸው ምክንያት ማንነታቸውንም ማወቅ አልተቻለም። ማወቅ ከቻልነውም ሰዎች ውስጥ አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊ ልጅ አስከሬን እንዲሁም የ70 ዓመት አዛውንት ይገኙበታል። ሟቾቹ ከከተማዋ ከተለያዩ ሰፈሮች የመጡ ናቸው፤ ቀበሌ 15፣ እንዳገብርኤል፣ መናኸሪያና ቀበሌ 12 ይገኙበታል። የአንድ ዓመት ተኩል ጨቅላ ህፃንን ጨምሮ 70 ቁስለኞችን ተቀብለናል። የመከላከያ ሠራዊት የመቀለ ከተማን ከመቆጣጠሩ ሁለት ሳምንት በፊት የአየር ጥቃት ነበር። በጥቃቱም አንደኛው የመቀለ ዩኒቨርስቲ ካምፓስ ተመትቷል። በአየር ጥቃቱም የተጎዱ 22 ተማሪዎችን አክመናል። በሚያሳዝን ሁኔታም አንድ የሶሺዮሎጂ ተማሪ ህይወት አልፏል። እንደርታ አካባቢ በደረሰም ሌላ የአየር ጥቃት አንዲት እናትና የሰባት ዓመት ልጇ ተገድለዋል። እናቲቱ ወዲያው ህይወቷ ሲያልፍ፤ ልጇ ግን ጭንቅላቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት እንዲሁም አንድ አይኗ ጠፍቶ ነበር የመጣችው። ህይወቷን ለማትረፍ የሚቻለንን ነገር ሁሉ ብናደርግም አልተሳካልንም። በከፍተኛ ደረጃ የህሙማን አልጋ፣ የመድኃኒትና እንዲሁም የህክምና ቁሳቁሶች ግብአት እጥረት አጋጥሞ ነበር። በአሁኑ ወቅት የፌደራል መንግሥቱ በተወሰነ መልኩ የህክምና ግብአቶችን ቢልክም ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ እየሰራ አይደለም።
46698816
https://www.bbc.com/amharic/46698816
ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች
የኩኩ ሰብስቤ "ነገሩ እንዴት ነው" የሚለውን ሙዚቃ ሰምቶ ያጣጣመ አድናቂ፣ ዘፈኑ በአዲስ ጣዕም በኅብረ ዝማሬ ቡድን ቀርቦ ሰምቶታል። የግርማ በየነን "ፅጌረዳ" ያንጎራጎረ የሙዚቃ አፍቃሪ፣ በአዲስ ድምፃውያን ኅብረ ዝማሬ፣ በአዲስ ቅንብር ደግሞ አጣጥሞታል።
የመረዋ ኀብረ ዝማሬ ቡድን አባላት እነዚህን ነባር ሙዚቃዎች በአዲስ መልኩ ሠርቶ ለሙዚቃ አፍቃሪያን የሚያደርሰው ቡድን "መረዋ" ይሰኛል። የመረዋ የኅብረ ዝማሬ ቡድን በጋራ መሥራት የጀመሩት 2005 ዓ. ም. መስከረም ላይ ነው። ያሰባሰባቸው ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ነው። የ "መረዋ" ወጣቶች ጆሯቸውም ነፍሳቸውም ከለመዱት ውጪ፣ አዲስ ነገር የመሞከር ፍላጎት ወደ ሙዚቃ ስልቱ እንደገፋቸው ይናገራሉ። • የኤርትራ ዘፈኖች በኢትዮጵያዊ አቀናባሪ • የሙዚቃ ሕክምና በኢትዮጵያ • በአማርኛ የሚያንጎራጉረው ፈረንሳያዊ ሁሉም የቡድኑ አባላት የሙዚቃ መሳሪያ መጫወት ብቻ ሳይሆን ያቀነቅናሉ። እያንዳንዱ የቡድኑ አባል ደግሞ የየራሱ ቀለም አለው። የወንድ ወፍራም ድምፅ፣ የወንድ ቀጭን ድምፅ፣ የሴት ወፍራም ድምፅ፣ የሴት ቀጭን ድምፅ አንድ ላይ ተዋህዶ ለጆሮ ሲስማማ፣ የበለጠ መግለፅ የሚችለው ሲሰዘፍነው፣ በላቀ ሁኔታ የሚያሳምረው ሲያጅበው፣ ሁሉም ድምፀ መረዋ፣ ሁሉም የኅብሩ አንድ አካል ይሆናሉ። አስራ አንድ እንደ አንድ፣ አንድ እንደ አስራ አንድ 11 አባላት ያሉት መረዋ ከተመሰረተ ጀምሮ የተለያዩ አባላት ተፈራርቀዋል። ስም ካላቸው እስከ አዳዲስ ሙዚቀኞች ድረስ መረዋን ተቀላቅለው ለቅቀዋል። አባላቱ ይህ የሆነው "ሙዚቃ የቡድን ሥራ በመሆኑ ነው" ይላሉ። መረዋዎች እንደሚሉት ቡድኑ ውስጥ የተለያዩ ሰዎች መግባትና መውጣታቸው ሁለት ነገሮች ያሳያል። "አንደኛውና ቀዳሚው፣ ሥራው ተደጋጋሚ ጥናት መጠየቁ ነው። መሰጠት፣ ቁርጠኝነት ስለሚፈልግ ነው።" ሲሉ ምክንያቱን ያስረዳሉ። ሌላው ምክንያት ቡድኑ እንደሌሎች ባንዶች ክፍያ የሌለው መሆኑ ነው። በሳምንት የተወሰኑ ቀናት ሰርተው የሚያገኙት ቋሚ ገቢ የለም። ስለዚህ ሙዚቀኞች ገንዘብ ወደሚያስገኙ ሥራዎች ፊታቸውን ያዞራሉ። "የሥራ ስነ ምግባርም የሚጠቀስ ምክንያት ነው።" በማለት ያክላሉ። በዚህ ምክንያትም ከመረዋ ምስረታ ጀምሮ የተለያዩ አባላት ሲቀያየሩ ነው እዚህ የደረሱት። ከቡድኑ ጋር የተለያዩ ሙዚቃዎች ያጠኑ ሰዎች ጣጥለው ሲሄዱ መጉዳቱ እንደማይቀር የሚናገሩት የቡድኑ አባላት፤ ዘወትር አዲስ ሰው በማምጣት ማስጠናት ፈታኝ ነው ይላሉ። • የባህታ ትውስታዎች • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ • "ሀገሬ ራሱ በድንቅ ተቃርኖ ውስጥ ተዛንቃ ስላለች ሥራዎቼም እንደዛ ናቸው" "በርግጥ አንድ ሰው ሙዚቃ አጥንቶ በትንንሽ ምክንያቶች ቡድኑን ጥሎ ሲወጣ ቡድኑ የሚያጣው ነገር ይኖራል። ማስጠናት ሥራ ይፈልጋል። ግን የማይቻል ሥራ አይደለም።" የቡድኑ አባላት የተሰባሰቡት ከሙዚቃ ትምህርት ቤቶች መሆኑ ለድምፅ መረጣና ቅንጅቱ እንደረዳቸው ይመሰክራሉ። "አንድ ትምህርት ቤት ስለተማርን አንድ ክበብ ውስጥ ነን" ድምፃዊ ማግኘት ለኛ ከባድ አይደለም" የሙዚቃ መሳሪያ አልወጣም መረዋዎች ድምፃቸው እየተስረቀረቀ ብቻ አይደለም ዜማ የሚያቀብሉን። የሙዚቃ መሳሪያዎችንም በድምፃቸው ይጫወታሉ። ታዲያ የያሬድ ተማሪ ሆናችሁ፣ የሙዚቃ መሳሪያ አጥንታችሁ፣ ተክናችሁበት፣ ዲግሪ ከጨበጣችሁ በኋላ ምነው እርግፍ አድርጋችሁ ተዋችሁት? ስንል ጠየቅናቸው። "በፍፁም ከሥራችን ውስጥ የሙዚቃ መሳሪያን ማስወገድ አልፈለግንም። እንደዛ የሚያስገድድም ትምህርት አልተማርንም፤ የለምም።" ያለ ቆምጨጭ ያለ መልስ አገኘን። መረዋዎች፤ አዲስ ነገር ለመሞከር ስንል ነው ይህንን የጀመርነው ይላሉ። ከኢትዮጵያ ውጪ የሚሰሩ መሰል ሙዚቃዎች ላይ ከሙዚቃ መሳሪያ በተለየ ድምፅ ላይ ብቻ አተኩረው መካናቸውን እንደ ማስረጃ ይጠቅሳሉ። "ይህንንም በዩኒቨርስቲ ደረጃ ስልጠና መስጠት ጀምረዋል። የኛ ስርዓተ ትምህርት እዚህ ደረጃ ባይደርስም አሁን ከስር በሚመጡ ወጣቶች፣ ይህ ነገር ቢታይ፣ ቢሞከር፣ ክፋት የለውም። እኛም እሴት መጨመር ስለፈለግን ነው።" ለሙዚቃ መሳሪያ መነሻው የሰው ልጅ ድምፅ ነው የሚሉት መረዋዎች፣ የሙዚቃ መሳሪያ ቀስ እያለ እግሩን እየሳበና እየዘመነ መጥቶ እንጂ የሰው ልጅ ድምፅ ብቻውን ውብ ተስረቅራቂ፣ ለጆሮ ጥዑም ነው ሲሉ ይከራከራሉ። "የሙዚቃ መሳሪያዎች ስራ ላይ የዋሉት ድምፅን ወክለው ለመጫወት (ኢሚቴት) ለማድረግ ነው ተብለን ተምረናል። የሰው ልጅ በድምፅ ምንም አይነት ነገር ማድረግ ይችላል።" በማለት መሳሪያዎችን በድምፃቸው የተኩት ለዚህ እንደሆነ ያስረዳሉ። ከዚህ በተጨማሪም ይላሉ አባላቱ፤ "በድምፅ ብቻ የሚጫወት የኅብረ ዝማሬ ቡድን አይደለንም።" በማለት በኅብረ ዝማሬ ቡድኑ ውስጥ በድምፅ ብቻ መጫወት አንዱ ዘርፍ መሆኑን ይጠቅሳሉ። በመሳሪያ ታጅቦ መጫወት ሌላው ዘርፍ በማለት "በሚቀጥሉት ሥራዎቻችን ላይ በማንኛውም ሰአት ከሙዚቃ መሳሪያ ጋር ልንጫወት እንችላለን" ራሳቸውን ያለ ሙዚቃ መሳሪያ የሚጫወት የኅብረ ዝማሬ ቡድን ብቻ ብለው አይፈርጁም። በአጋጣሚ በዩቲዩብ ላይ የተለቀቁት ሁለት ሥራዎቻቸው እንደዛ ቢሆኑም፤ መሳሪያ ተጠቅመውም ይጫወታሉ። ለምሳሌ በቅርቡ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ከሚያስተምረው ድራመር ተፈሪ ጋር በሠሩት ሙዚቃ ላይ በመሳሪያ ታጅበው እናያቸዋለን። የቡድን አባላቱ ቁጥር መብዛት ዕድል ወይስ ተግዳሮት መረዋ የኅብረ ዝማሬ ቡድን ያለ ሙዚቃ መሳሪያ ሙዚቃ በመጫወት እየታወቁ መጥተዋል። መነሻ የሆኗቸው የደቡብ አፍሪካ ''Black Mambazo'' ናቸው። ከደቡብ አፍሪካ ውጪ በማዳጋስካርና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ባህል ውስጥ ኅብረ ዝማሬ በርከት ባሉ ሰዎች ሲቀነቀን ማስተዋላቸውን ይጠቅሳሉ። "መብዛታችን የኅብረ ዝማሬውን ውበት ለመጨመር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። የኅብረ ዝማሬ ቡድንም አወቃቀርም እንደዛ ነው" ምዕራባውያን በአነስተኛ ሰው ስብስብ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ተደግፈው ቡድን ያዋቅራሉ የሚሉት መረዋዎች፤ ይህ ግን በአፍሪካ ባህላዊ የህብረ ዝማሬ ሙዚቃ ላይ እንደማይታይ ያስረዳሉ። ምንም አይነት መሳሪያ ድምፃቸውንና ቅኝታቸውን ለማረቅ አይጠቀሙም። "ቡድኑ ተፈጥሮን ተጠቅሞ፣ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ነው የሚሰራው" የሚሉት መረዋዎች፤ በሙዚቃ ስቱዲዮ ውስጥም ሆነ መድረክ ላይም ሢሰሩ አንድ አይነት መሆኑን ይናገራሉ። መረዋዎች በጣሊያን ባህል ማዕከል ትልቅ ኮንሰርት አዘጋጅተው ነበር። በዚያ ኮንሰርት ከ20 በላይ ሙዚቃዎች ተጫውተዋል። በሙዚቃ መሳሪያም ታጅበውም የምርምር (ኤክስፐርመንታል) ሙዚቃ ሠርተዋል። ያኔ ያውቋቸው የነበሩት በሙዚቃ ህይወት ውስጥ ያሉ ሰዎች ብቻ እንደነበሩ ያስታውሳሉ። ሙዚቃ ሲያቀርቡ ይታደሙ የነበሩትም ሙዚቀኞች እና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ነበሩ። ሆኖም የመጀመሪያ ሥራቸው በዩቲዩብ ላይ ከወተለቀቀ በኋላ ግን የአድናቂዎቻቸውና የተከታዮቻቸው ብዛት እንደጨመረ ይገልጻሉ። የሙዚቃ ቡድኑ 11 አባላት መንገድ ላይ ሲሄዱ እስከመለየት ያደረሳቸውን እውቅና ያገኙት የ"ነገሩ እንዴት ነው" የሙዚቃ ቪዲዮ ከወጣ በኋላ ነው። በቡድን ሲንቀሳቀሱም አድናቂዎች በቀላሉ ይለይዋቸዋል። "ያንን ኮንሰርት ዛሬ ብንሠራው የሚገኘው ሰው ቁጥር ከፍተኛ ይሆን ነበር" ይላሉ መለስ ብለው ጊዜውን በማስታወስ። በተለያየ ጊዜ የተለያዩ መሪ ድምጻውያን እንደሚጠቀሙ የሚናገሩት የመረዋ ቡድን አባላት ምክንያቱን እንዲህ ያብራሩታል። "መጀመሪያ የምንሠራቸውን ሙዚቃዎች እንለያለን። የምንሠራው ቅኝት ላይ ከሆነ ቅኝቱን በሚገባ ተረድቶ የሚዘፍን ብቃት ያለው ሰው ያስፈልገናል። ዳያቶኒክ ሙዚቃዎች የምንሠራ ከሆነ እዛ ውስጥ ያሉትን ቴክኒኮች የበለጠ የሚገልፅ ሰው ያስፈልጋል። ሰው ለመምረጥ የምንሰራው ሙዚቃ ወሳኝነት አለው" ስለዚህም ዛሬ ከፊት ሆነው ሲያቀነቅኑ ያየናቸውን ሙዚቀኞች ከኋላ፣ ከጀርባ ሆነው ሲያጅቡ የነበሩ ደግሞ ከፊት ሆነው ሲያዜሙ እናያለን። የተለመደውን ባልተለመደው መንገድ ሙዚቃ ስናደምጥ ጆሯችን የሰለጠነበት መንገድ አንድ አይነት ማለትም ድምጽ በሙዚቃ ታጅቦ መስማት ነው። የከበሮ ድምፅ ከጊታር ተዋህዶ፣ ኪቦርድ ከሳክስፎን አብሮና ውበት ፈጥሮ መስማት የለመድነው ነው። ይህንን የተለመደ የጥበብ ስራ ወስዶ በአዲስ መልክ መስራት ለመረዋዎች ቀላል እንደነበር ትምህርታቸውን በመጥቀስ ያስረዳሉ። ". . . ቅንብር የሙዚቃ ትምህርት አንድ አካል ነው። ያሬድ እንደ አንድ ትምህርት ይሰጣል። የቡድኑ አባላት የተለያዩ ቅንብሮችን ይሠራሉ። ምዕራፍ ተክሌ ያቀናበራቸውን ሙዚቃዎችም በተለያዩ መድረኮች ላይ ተጫውተናል። የ"ፅጌረዳ"ን ቅንብር የሰራው ደግሞ እስራኤል ጥላሁን ነው" በአንድ ወቅት የሚሠውራን ቅንብር በሌላ ወቅት ሌላ ሰው መልሶ ሊሠራ እንደሚችል፤ ካልሆነም መነሻ ሀሳቡን አንድ ሰው ከሠራ በኋላ የቡድኑ አባላት ቅንብሩን ሊያዳብሩት እንደሚችሉ ይናገራሉ። በ"አካፔላ" የኅብረ ዝማሬ ቡድን ውስጥ የተለመደው የድምጻውያንን ሥራ ድጋሚ ማቀናበር መሆኑን የሚናገሩት መረዋዎች፤ መጀመሪያ ላይ ድምፃዊያኑ ከሌሎች አካላት ፈቃድ ማግኘት ይቸገሩ እንደነበር ያስታውሳሉ። ለዘርፉ አዲስ ሆኖ ድምፃዊ፣ ገጣሚ፣ ዜማ ደራሲ ለየብቻ ማናገር ፈታኝ ነበር የሚሉት መረዋዎች፤ ቀጣዩ ሥራዎቻቸው የመጀመሪያውን ያህል እንዳልከበደባቸው ይናገራሉ። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን ዛሬ ዛሬ ሥራቸውን ያዩ ባለሙያዎች "የኔንም ሙዚቃ ብትሠሩ" ብለው እንደሚጠይቋቸው ይገልፃሉ። ለወደፊት የራሳቸውን አልበሞች አሳትመው በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ትልልቅ የሙዚቃ ትርዒቶች መሥራት እንዲሁም፤ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች መጫወትም ይፈልጋሉ። በ"አካፔላ" ዘርፍ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ የራሳቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት ይሻሉ። በተለያዩ ክልሎች በመዘዋወር የየአካባቢውን ሙዚቃ በማጥናት በኅብረ ዝማሬ መግፋትም ይፈልጋሉ። የወደፊት እቅዳቸው ላይ በደማቅ ቀለም ከተፃፉት መካከል በዓለም አቀፍ ፌስትቫሎችና ውድድሮች ላይ መሳተፍም ይገኝበታል።
49174746
https://www.bbc.com/amharic/49174746
የበጎ ሰው ሽልማት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ሀገር ውስጥ ባበረከቱት አስተዋፅኦ ሊሸልም ነው
በየዓመቱ የተለያዩ ግለሰቦችን እውቅና በመስጠት የሚታወቀው የበጎ ሰው ሽልማት ዘንድሮ በሚያካሄደው ሥነ-ሥርዓት ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሸልማት ዘርፎች በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎችን ሀገር ውስጥ ባበረከቱት አስተዋፅኦ መሸለም የሚያስችል ዘርፍ መጨመሩን የሽልማት ኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ቀለምወርቅ ሚደቅሳ ለቢቢሲ ገለፁ።
ፀሐፊው አክለውም የበጎ ሰው ሽልማት ራሱን የቻለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሆኖ መመዝገቡንም ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በተደጋጋሚ ለመመዝገብ ጥያቄ ቢያቀርቡም አለመቻላቸውን የተናገሩት አቶ ቀለምወርቅ አሁን ግን አዋጁ በመሻሻሉና የኤጀንሲውም አወቃቀር ስለተቀየረ መመዝገባቸውን ገልጸዋል። • የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫ ተራዘመ ከዚህ በኋላ እቅድ በማውጣትና የተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ውስጥ በመንቀሳቀስ በጎነትን እና በጎ ማድረግን የሚያበረታታ ሥራ እንደሚሰሩ ጨምረው አስረድተዋል። ዲያስፖራውን መሸለም ለምን? አቶ ቀለምወርቅ እንደሚሉት ከሆነ በዚህ ዓመት የሚካሄደው የበጎ ሰው ሽልማት ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዘርፎች በተለየ ዲያስፖራውን የሚያካትት ዘርፍ ተካትቶበታል። ከዚህ ቀደም ምንም እንኳ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት ለሀገራቸው የተለያየ ነገር ቢያበረክቱም ከእነርሱ ጋር በመቀራረብ መስራትና ማበረታታት አዳጋች ነበር ያሉት አቶ ቀለምወርቅ፤ አሁን ግን ሀገሪቱ ላይ ያለው ለውጥ ይህንን የሚያበረታታ በመሆኑ ዘርፉ መጨመሩን ገልጸዋል። የዳያስፖራ ማህበረሰብ ለሀገሩ የተለያየ ነገር ሲያበረክት መቆየቱን ያስታወሱት ፀሐፊው ይህንን እንደ በጎ ሰው ለማበረታታት በማሰብ ዘርፉ መጨመሩን ተናግረዋል። የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በዚህ ዓመት አበርክቷቸው የሚመዘነው በማንኛውም ዘርፍ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው ዳያስፖራውም ልክ እንደ ሌሎች ዘርፎች ሁሉ በዲያስፖራው አባላትና በሌሎች ተጠቁመው ዕጩ እንደሆኑ ገልፀዋል። • የዱባዩ መሪና ጥላቸው የኮበለለችው ባለቤታቸው ወደ ፍርድ ቤት ሊያመሩ ነው የበጎ ሰው ሽልማት በየዓመቱ እጩ የሚያደርጋቸውን ግለሰቦች ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በስልክ፣ በኢሜል፣ በፖስታ፣ በማህበራዊ ትስስር ገፆች እና በኦንላይን ጥቆማ የሚቀበል ሲሆን አንዳንዴ ጥቆማ የሚሳሳበት ዘርፍ ካለ ሊጠቁሙ የሚችሉ አካላትን ኮሚቴው እንደሚያነጋግር አስታውሰዋል። ዘንድሮ በሁሉም ዘርፍ በቂ ሰው መጠቆሙን እና የዳያስፖራው ዘርፍም በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በርካታ ጥቆማ መቀበላቸውን ጨምረው ተናግረዋል። እጩ የሚሆን ሰው የመጠቆሚያ ጊዜው አንድ ወር እንደነበር ያስታወሱት አቶ ቀለምወርቅ አሁን በመጠናቀቁ እጩዎቹን ነገ በሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። ከዳያስፖራ ውጪ በሳይንስ፣ በመምህርነት፣ በበጎ አድራጎት፣ በቅርስና ባህል፣ መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት በመወጣት፣ በንግድና የሥራ ፈጠራ፣ በማህበራዊ ጥናትና ኪነጥበብ ዘርፍ እጩዎች መኖራቸውን አስታውሰው የኪነጥበብ ዘርፍ በርካታ ንዑስ ዘርፎች ስላሉት ዘንድሮ በፎቶ ግራፍ ጥበብ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ብቻ በእጩነት እንደሚቀርቡ ተናግረዋል። • የታዋቂዋ ወጣት አስክሬን ሻንጣ ውስጥ ተገኘ አስር ዘርፎች ያሉት የበጎ ሰው ሽልማት በኮሚቴው ውሳኔ አንድ ልዩ ተሸላሚ እንደሚኖረውም ጨምረው አስታውቀዋል። ሽልማቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች የበጎ ሰው ሽልማት በዓመት አንዴ የሚካሄድ መርሀ ግብር መሆኑን በማስታወስ እስከዛሬ እውቅና የተሰጣቸው ግለሰቦች ሕይወት ላይም ሆነ ሌሎች ላይ ስራችሁ ለውጥ ማምጣቱን እንዴት ታረጋግጣላችሁ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ቀለምወርቅ ተሸላሚዎቹ ራሳቸው ላይ የሚፈጥረው ለውጥ ቀዳሚው መሆኑን አስረድተዋል። ለሀገር በርካታ ነገር አድርገው የሚሰሩት ነገር 'ትውልዱ ከቁብ አይጥፈውም' የሚል ስሜት የነበራቸው ተሸላሚዎች፣ ከሽልማቱ በኋላ መንፈሳቸው ተነቃቅቶ የተሻለ ስራ መስራታቸውን አምባሳደር ዘውዴ ረታን በምሳሌነት በመጥቀስ አስረድተዋል። ሕብረተሰቡ ለተሸላሚዎቹ የሚሰጠው ክብርና አመለካከት ራሱ እንደሚቀየር ሲናገሩም የሐረሩን ሼህ አብዱላሂ ሸሪፍን በማንሳት በተቋም ደረጃ ቢገነባ እንኳ ፈታኝ የሚሆነውን የተለያዩ ኃይማኖቶችና ዘርፎች ቅርስ አሰባስበው ሙዚየም ያደራጁ መሆናቸውን ገልፀው ከሽልማቱ በኋላ ክልሉ የተለያየ ድጋፍ እንዳደረገላቸው አስረድተዋል። • ብሔራዊ አገልግሎት መንፈሳዊ ህይወቱን የነጠቀው ኤርትራዊው ዲያቆን በመንግሥት የሥራ ዘርፍም አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስን በመጥቀስ በዲፕሎማሲው ጎምቱ መሆናቸውን ካስረዱ በኋላ ተገቢውን እውቅና አግኝተው እንደማያውቁ ነገር ግን ከበጎ ሰው ሽልማት በኋላ የተለያዩ እውቅናዎችን ማግኘታቸውን ይናገራሉ። አብዛኞቹ ተሸላሚዎች ታሪካቸው እንኳ በአግባቡ ተሰንዶ አይገኝም የሚሉት አቶ ቀለምወርቅ ሽልማት ከተቀበሉ በኋላ ያለፉ ግለሰቦች የሽኝት ስነስርዓታቸው ላይ የሚነበበው የበጎ ሰው ያዘጋጀው የሕይወት ታሪክ መግለጫ እንደሆነ ያስታውሳሉ። አንዳንድ ተቋማት ለእነዚህ ግለሰቦች ኃላፊነት በመውሰድ በስማቸው የተለያዩ ነገሮች ማድረጋቸውን የሚናገሩት አቶ ቀለምወርቅ ለዚህም የአቢሲኒያ ባንክን በማንሳት፣ ፊት አውራሪ አመዴ ለማ፣ ቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረስላሴ ዘብሔረ ቡልጋን የመሳሰሉ ሰዎች በስማቸው ቅርንጫፍ ተከፍቶላቸው እንደሚገኝ በመግለፅ፣ በተለያዩ የበጎ ሰው ተሸላሚዎች ስም ቅርንጫፎች መሰየሙን ይጠቅሳሉ። መልካምነት በኮሚቴ የመልካምነት ሚዛን ከሰው ሰው እንደሚለያይ በማንሳት ለመሆኑ ለእናንተ በጎ ሰው የሚለውን በኮሚቴ መበየን አይከብድም ተብለው የተጠየቁት አቶ ቀለም ወርቅ ሲመልሱ የበጎ ሰው ሽልማት የራሱ የሆነ ቦርድ እንዳለው ገልፀው የምርጫ ሂደቱም እንዲሁ ራሱን በቻለ መንገድ እንደሚታይ ያስረዳሉ። • አምባሳደር ሬድዋን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለምን ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አላቀረቡም? ድርጅቱ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጥቆማዎችን ከተቀበለ በኋላ ባለሙያዎችን በመቅጠር የሕይወት ታሪካቸው እንዲፃፍ ማድረግ ቀዳሚው ስራው መሆኑን የሚናገሩት አቶ ቀለምወርቅ ግለሰቦቹ ያበረከቱት አስተዋፅኦ አንድ ሁለት ተብሎ ተቆጥሮ፣ ቅርብ የሆኑ ሰዎቻቸው፣ አብረዋቸው የሰሩ፣ የአካባቢያቸው ሰዎችን በማናገር ታሪካቸው እንደሚጻፍ ይገልጣሉ። ከዚህ ሁሉ በኋላ የበጎ ሰው ሽልማት ኮሚቴ ተሰብስቦ በተፃፈው ታሪካቸው መሰረት የሰሩትን ስራ መዝኖ ሶስት እጩዎችን እንደሚመርጥ ገልፀዋል። ከዚህ በኋላ አምስት ሌሎች ባለሙያዎች፣ በዚህ ጉዳይም ላይ ዳኝነት እየሰጡ እንደሆነ የማይተዋወቁ፣ ታሪክ ተልኮላቸው ከአንድ እስከ ሶስት ደረጃ በመስጠት ይለያሉ በማለት ሂደቱን ያብራራሉ። "እነዚህ ዳኞች በሰጡት ነጥብ ነው፥ እኛ የዓመቱ የበጎ ሰው ብለን የምንሸልመው።" አንዳንድ ጊዜ እጩዎችን ይፋ ካደረግን በኋላ የተጠቆሙ ሰዎች ላይ የተለያዩ ቅሬታዎች ይመጣሉ ያሉት አቶ ቀለምወርቅ እርሱንም ከግምት ውስጥ እንደሚያስገቡ ተናግረዋል። • ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው የዚህ ዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ነሐሴ 26 ከ7፡30 ጀምሮ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል የሽልማት መስጠት ስነስርዓቱ እንደሚኖር አቶ ቀለምወርቅ ሚደቅሳ ተናግረዋል።
news-47731664
https://www.bbc.com/amharic/news-47731664
ዐቢይ እና የኢትዮጵያ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን መጥተው በተለያዩ ፈተናዎች የተተበተበውን የሀገሪቱን ፖለቲካ ለማስተካከል የሚያስችሉ ቁልፍ የሚባሉ እርምጃዎችን ቢወስዱም ከአንድ ዓመት በኋላ አሁንም ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ናት የሚሉ በርካቶች ናቸው።
የዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን መምጣትን ተከትሎ ኢትዮጵያ ላለፈው አንድ ዓመት በለውጥ መንገድ ስትጓዝ ቆይታለች። ይህ የለውጥ ጉዞ አሁንም እንደቀጠለ ቢሆንም የጉዞው በተደጋጋሚ መንገራገጭ በርካታ ጥያቄዎችን እያስነሳ፣ ስጋት እያጫረና ፍርሃትንም እያነገሰ ነው። ከጥቂት ቀናት በፊትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠንከርና መረር ያለ ንግግር ማድረጋቸውም ከዚሁ ጋር የሚያያዝ ነው የሚሉ አሉ። • የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ ከእነዚህ ነገሮች በመነሳት ለውጡን በሚመለከት ፅንፍ ለፅንፍ የሆኑ አስተያየቶች እየተንፀባረቁ ሲሆን የለውጡ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይንም መተቸትና ማብጠልጠልም ተጀምሯል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው የለውጥ እርምጃ ከአንድ ዓመት በኋላ የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ የአገሪቱ የፖለቲካ ሽግግር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፖለቲካ ተንታኞች የየራሳቸውን ምልከታ ያስቀምጣሉ። "አዲስ አበባ እንደ እየሩሳሌም" የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በአሁኑ ወቅት ተስፋ ሰጪና ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ጎን ለጎን እየሄዱ እንደሆነ፤ ይህ ደግሞ ለውጡን መስቀለኛ መንገድ ላይ እንዳቆመው ያስረዳሉ። "ስለዚህ ከሁለቱም ነገሮች ጋር ወደፊት እየገፋን ነው" ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሃገሪቱ ውስጥ ላሉ በርካታና ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች ምላሽ የሆንኑ ዘንድ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስደዋል። ከእነዚህም መካከል እንደ ምርጫ ቦርድ ማሻሻያ፣ የፀረ ሽብርና የሲቪል ማህበራትን የተመለከቱ ሕጎችን ለማሻሻል የተወሰዱ እርምጃዎች ፕሮፌሰር መረራ ተስፋ ሰጪዎች ከሚሏቸው ውስጥ ይጠቀሳሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያነጋገሩ መሆናቸውም ሌላው የሚጠቅሱት ነገር ነው። • በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዚህ ሂደት ውስጥ የለውጡ እንከን ወይም ተስፋ አስቆራጭ ከሚሏቸው ውስጥ የመጀመሪያው የኢህአዴግ አቋም ላይ የሚያነጣጥር ነው። "ገዥው ፓርቲ ራሱ ለውጡን ለማንበብም ሆነ ወደ ፊት ለመግፋት አንድ ላይ ነው ወይ? የተወሰነው ለውጡን ሲገፋ የተወሰኑት ወደ ኋላ የሚጎትቱ ይመስላል።" አክለውም ሽግግሩን መስቀለኛ መንገድ ላይ እንዲሆን ያደረጉ ከሚሏቸው ያልተመለሱ የታሪክ ፈተናዎችን በሁለተኛ ደረጃ ያስቀምጣሉ። ያላለፍናቸው የታሪክ ፈተናዎች ከሚሏቸው የአዲስ አበባ ጉዳይ አንዱ ሲሆን "አዲስ አበባም እየሩሳሌም እንዳትሆን አንዳንድ ቦታዎች ስጋቶች እየተፈጠሩ ነው" ይላሉ። የለውጡ የሚመራበት ፍኖተ ካርታ አልባ መሆንም ለእሳቸው ሌላው ከባድ ችግር ነው። እየተደረጉ ባሉ ነገሮች ማለትም ምን አይነት ኢትዮጵያ? ምን አይነት ለውጥ? በምን ደረጃ ወዴት? የሚሉ ነገሮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ላይ ተደርሶ የተቀመጠ ፍኖተ ካርታ ሊኖር ይገባል የሚል አቋም አላቸው፤ ፕሮፌሰር መረራ። • ዶ/ር ዐብይ በግላቸው ለውጥ ያመጣሉ? ከገዢው ፓርቲ በተጨማሪም በፖለቲካው መድረክ ላይ ያሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ በሆኑ አጀንዳዎች አብሮ ለመስራት አለመሞከርም ሌላው የለውጡ እንከን እንደሆኑ ያምናሉ። በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተገኝተው 'ለውጡ እዚህ አልደረሰም' የሚል ነገር ከህዝቡ መስማታቸውን የሚናገሩት ፕሮፌሰር መረራ "በዚህ መንገድ ከቀጠልን ህዝቡ በለውጡ ተስፋ እንዳይቆርጥ እሰጋለሁ" ይላሉ። በተጨባጭ በህዝቡ ፖለቲካዊም ሆነ ሁለንተናዊ ህይወት ውስጥ መሬት ላይ የሚታይ ነገር ከሌለ ለውጥ ለውጥ የሚባለው ነገር የልሂቃን ጨዋታ ሆኖ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል የሚል ስጋትም አላቸው። ፕሮፌሰር መረራ ጨምረውም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች እተከሰቱ ለሰዎች መፈናቀልና መጎዳት ምክንያት እየሆኑ ለሚታዩት ግጭቶች መፍትሄ መፈለግም በጣም ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ይጠቁናሉ። ኦዴፓና አዴፓ እየተገፋፉ ነው? በኬል ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት የፖለቲካ ተንታኙ ዶ/ር አወል አሎ ስለለውጥ ሲወራ እንደ አገር የነበርንበት ሁኔታ ምንድን ነው? ከየት ወደ የት ነው የምንሻገረው? የሚለውን ማየት ያስፈልጋል ይላሉ። የአገሪቷ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ተቃርኖዎች ምንድን ናቸው? ትልልቆቹ የፖለቲካ ጥያቄዎችስ? እነዚህ ጥያቄዎች አብዛኛው የፖለቲካ ኃይል እንደሚፈልገው ይፈቱ ቢባል በምን መልኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፈታል? የሚለው ነገር ለዶ/ር አወል ወሳኝ መነሻ ነው። • ለየት ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ደብዳቤ ለየመኖች ከዚህ ነጥብ በመነሳት ምንም እንኳ ፈታኝና የሚያሰጉ ነገሮችን እየተመለከቱ ቢሆንም አሁን ያለው ሽግግር መጥፎ ደረጃ ላይ ነው ብለው አያስቡም። እሳቸው እንደሚሉት እየታዩ ያሉ ነገሮች ይገጥማሉ ተብሎ መታሰብ ነበረበት። "ምክንያቱም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙ መከፋፈሎች፣ ከሚስማሙበት ይልቅ የማይስማሙበት ነገር የሚበዛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያሉበት፤ በጥቅሉ ብዙ ቀይ መስመሮች ያሉበት" ይላሉ። ስለዚህም ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ አሁን የለውጥ ሂደቱን ያጋጠሙ ችግሮች እንዳይፈጠሩ፤ ከተፈጠሩም በጊዜ ለመፍታት መስራት ነበረበት ብለው ያምናሉ ዶ/ር አወል። መንግሥት ያን አድርጎ ቢሆን ኖሮ አሁን ያለው ከመስመር የወጡ ነገሮችን፤ ሥርዓት አልበኝነትን ማስቀረት ይቻል ነበር ብለው ያስባሉ። ነገር ግን በለውጡ ሂደት ውስጥ ፈታኝ ነገሮች ቢኖሩም "ተስፋ ልንቆርጥ የምንችልበት ቦታ ላይ በጭራሽ አልደረስንም" በማለት ነገሮችን ወደ መስመር ለማስገባት አሁንም እንዳልረፈደ ይገልፃሉ። የተወሳሰበ ታሪክ ባለው እንደ ኢትዮጵያ ባለ አገር የፖለቲካ ሽግግር ቀላል እንደማይሆን ግልፅ ቢሆንም መንግሥት ሊሰራቸው ሲገባ ያልሰራቸው የቤት ሥራዎች መኖራቸው ዶ/ር አወልን ጨምሮ ለብዙዎች አከራካሪ ጉዳይ አይደለም። ለህይወታቸውና ለንብረታቸው ዋስትና ላጡ ሰዎች የዲሞክራሲና የህግ የበላይነት ጉዳይ ሁለተኛ ስለሚሆን መንግሥት በአሁኑ ወቅት ለህግ የበላይነት ትልቅ ትኩረት መስጠት እንዳለበት ያሳስባሉ። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወታደሮቹ ድርጊት ተበሳጭተው እንደነበር ተናገሩ በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ብሔረተኝነትን በሚያራምዱ ኃይሎች መካከል እየተካሄዱ ያሉ ክርክሮችና መበሻሸቆች አገሪቱን ወደ ትልቅ አደጋ ሊመራ ይችላል የሚል ስጋትም አላቸው። የብሔርን መሰረት ያደረጉ ብሔረተኞች የድሮውን ሥርዓት እኛ ላይ ለመጫን እየተንቀሳቀሰ ነው፤ የኢትዮጵያ ብሔረተኞች ደግሞ ስለኢትዮጵያ ጥሩ ጥሩ ነገር ቢናገሩም በተግባር ግን የብሔረተኞቹን አላማ ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እየወቀሱ ያሉበት ሁኔታን በማሳያነት ይጠቅሳሉ ዶ/ር አወል። የእነዚህ ሁለት ኃይሎች ክርክር ከገዥው ፓርቲ ዘንድ ጭምር ደርሶ መከፋፈልን እየፈጠረ ነውም ይላሉ። በተለይም የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በጎራቸው ውስጥ ያሉ ብሔረተኛዎችን የመከተል ግልፅ አዝማሚያ ታይቷል ይላሉ። እነዚህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ስበትን የሚቆጣጠሩ ፓርቲዎች በየበኩላቸው ባሉ ብሔርተኛ ቡድኖች ተፅእኖ ስር ከወደቁ ለአገሪቱ ከባድ አደጋ እንደሚሆን ጨምረው ያስረግጣሉ። "ፓርቲዎቹ መግባባት ሳይችሉ ቀርተው የሚፈጠረው ንትርክ ገዥውን ፓርቲ እንደ ፓርቲ እንዳይቀጥል የሚያደርግ ከሆነ ይህች ሃገር ከፍተኛ ችግር ውስጥ ትወድቃለች ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ስጋታቸውን ያስቀምታሉ። ትልቅ ተፅዕኖ የነበረው ህወሓት ወደ ዳር መውጣት ራሱን የቻለ ችግር በሆነበት ሁኔታ በኦዴፓና በአዴፓ መካከል ያለው ሁኔታ ለገዥው ፓርቲ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሊሆን እንደሚችልም ይገልጻሉ። ፖለቲካ ሁሌም ሰጥቶ መቀበል ስለሆነ እንደ ወጣት በስሜትና በኃይል ከመሄድ ይልቅ ማመቻመችን ምርጫቸውን ማድረግ እንዳለባቸውም ይመክራሉ። ነጥብ ማስቆጠር በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ አብርሃ ሃይለዝጊ ወቅታዊው የአገሪቱ ሁኔታ የፖለቲካ ኃይሎች ባለመደማመጥ እየተወነጃጀሉ ነጥብ ለማስቆጠር ብቻ የሚሮጡበት በመሆኑ አገሪቷ ትልቅ አደጋ ላይ ነች የሚል ስጋት አላቸው። ስለዚህም የሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ቆም ብለው አገሪቷ እንዴት ትዳን? ብሎ በማሰብ ሃላፊነት በተሞላ መንፈስ መወያየት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ጊዜ ላይ ተደርሷል ይላሉ። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እንደ ዶ/ር አወል ሁሉ ከመቼውም በላይ የአገሪቱ ፖለቲከኞች ለ'አንተም ተው አንቺም ተይ' ሰጥቶ የመቀበል ፖለቲካ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም ያሳስባሉ። ጽንፍ የወጡትን የፖለቲካ አመለካከቶችና ፍላጎቶችን ለማቀራረብና ፍጥጫን ለማስቀረት ደግሞ ሳይዘገይ ከስሜታዊነት የራቁ ሃቀኛና ግልጽ ውይይቶች የሚደረጉባቸው የፖለቲካ መድረኮች ያስፈልጋሉ ይላሉ። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በ100 የሥራ ቀናት የት የት ሄዱ? ምን ምን ሠሩ?
news-52760651
https://www.bbc.com/amharic/news-52760651
"ለአባታችን ገዳዮች ይቅርታ አድርገንላቸዋል" የሳዑዲው ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ልጅ
ከሁለት አመታት በፊት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለው የሳዑዲው ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ልጅ ለአባቱ ገዳዮች ይቅርታ እንዳደረጉላቸው የሚገልፅ መግለጫ በዛሬው ዕለት አውጥቷል። በሰላ ትችቱ የሚታወቀው ጋዜጠኛ በቱርክ መዲና በሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ውስጥ የተገደለው በጎርጎሳውያኑ 2018 ነበር።
የሳዑዲ ባለስልጣናት አሟሟቱን በተመለከተ ከሃገሪቱ መንግሥት በመጣ ትእዛዝ እንዳልሆነ ቢናገሩም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ በደህንነት አካላትና በተባበሩት መንግሥታት ዘንድ አመኔታን አላገኙም። ጀማል ኻሾግጂ ከመሞቱ በፊት ነዋሪነቱን አሜሪካ ያደረገ ሲሆን ለዋሽንግተን ፖስትም ይፅፍ ነበር። ጋዜጠኛው ቆንስላ ውስጥ ከገባ በኋላ መጥፋቱን ተከትሎ የሳዑዲ ባለስልጣናት እርስ በርስ የሚጣረሱ መረጃዎች ይሰጡ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ወደ ሳዑዲ እንዲያመጣው የታዘዘው ቡድን ተልዕኮው ወዳልሆነ አቅጣጫ አምርቶ መገደሉን አምነዋል። በጎርጎሳውያኑ ታህሳስ 2019ም በጋዜጠኛው ግድያ እጃቸው አለበት የተባሉ አምስት ግለሰቦችን በሪያድ በተደረገ ሚስጥራዊ የፍርድ ሂደት ሞት ተፈርዶባቸዋል። የተባባሩት መንግሥታት ልዩ ተወካይ አግነስ ካላማርድ የፍርድ ሂደቱን "የፍትህ ተቃራኒ" ሲሉ የጠሩት ሲሆን ነፃ ምርመራ መደረግም እንዳለበት አሳስበዋል። የጀማል ኻሾግጂ ቤተሰቦች ምን አሉ? መግለጫው በጋዜጠኛው ልጅ ሳላህ ሻሾግጂ ትዊተር ገፅ ላይ በዛሬው ዕለት የወጣ ሲሆን "በዚች በተቀደሰች የረመዳን ወር አምላክ ያለንን እናስታውሳለን። የሰው ልጅ ይቅር ካለና እርቅ ማውረድ ከቻለ ሽልማቱ የሚገኘው ከአላህ ነው" በማለት ኑሮውን በሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ያደረገው ሳላህ ፅፏል። "ስለዚህም የሰማዕቱ ጀማል ኻሾግጂ ቤተሰቦች አባታችንን የገደሉትን ይቅርታ አድርገንላቸዋል፤ ሽልማቱንም ከአምላካችን እናገኘዋለን" በማለት በትዊተር ገፁ አስፍሯል። የጋዜጠኛው ጀማል ልጅ ሳላህ ሻሾግጂ ከአልጋ ወራሽ ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ጋር ከአባቱ ግድያ በኋላ በእስልምና ህግ መሰረት ቤተሰብም ይቅርታ ቢያደርግም የሞት ቅጣቱ ተፈፃሚ ይሆናል። በዚህ ሁኔታ ግን የሞት ቅጣቱ ተፈፃሚ ይሁን የታወቀ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም ሳላህ ሳዑዲ በምታደርገው ምርመራ እንደሚተማመንና ድጋፉንም እንደሚቸር ገልፆ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የአባቱን ሞት በመጠቀም የሃገሪቱን አመራር ሊያዳክሙ ይፈልጋሉ ያላቸውን "ተቃዋሚዎችና ጠላቶች" በማለትም ተችቷል። የጀማል ኻሾግጂ ልጆች የአባታቸውን ሞት ተከትሎ ቤት፣ የወር ክፍያ በካሳነት እየተሰጣቸው እንደሆነ ባለፈው አመት ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። ከጋዜጠኛው ልጆችም መካከል የመጀመሪያ ልጁ ሳላህ ኻሾግጂ ብቻ ሳዑዲ አረቢያ በመኖር መቀጠሉንም ጋዜጣው አስነብቧል። ጀማል ኻሾግጂ ላይ ምን ተከሰተ? ጋዜጠኛው ጀማል ኻሾግጂ ከጎርጎሳውያኑ 2017 ጀምሮ በግዞት በአሜሪካ እየኖረ ነበር። በጎርጎሳውያኑ ጥቅምት 2018 በኢስታንቡል በሚገኘው የሳኡዲ ቆንስላ ያመራውም እጮኛው ሃቲስ ሴንጊዝን ለማግባት የሚያስፈልጉትን መረጃዎች ለመውሰድ ነበር። መርማሪዎች እንደሚያምኑት እዛው ገድለው አካሉንም እንደ ቆራረጡት ነው። አስከሬኑም ሆነ የተረፈ ነገር አልተገኘም። እጮኛው በወቅቱ ውጭ እየጠበቀች ነበር። የሳዑዲ ባለስልጣናት በመጀመሪያ ከሳዑዲ ቆንስላ እንደወጣ የተናገሩ ሲሆን ከዚያ በኋላም በርካታ የሚጣረሱ መረጃዎች ሰጥተዋል። ከዚያ በኋላ የወጣው የጋዜጠኛው አሰቃቂ አገዳደል ዝርዝር መረጃ አለምን አስደንግጧል። የተባበሩት መንግሥታትም የሳዑዲው ልዑል ቢን ሳልማንና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በግድያው እጃቸው እንዳለበት የታመነ መረጃ እንዳለው ገልፆ ሪፖርት አወጣ። ልዑሉ በግድያው ላይ እጄ የለበትም ብለው የካዱ ሲሆን ሆኖም " እንደ ሳዑዲ አረቢያ መሪነቴ ሙሉ ሃላፊነቱን እወስዳለሁ። በተለይም ገዳዮቹ ለሳዑዲ መንግሥት የሚሰሩ ከመሆናቸው አንፃር" ብለዋል።
45873594
https://www.bbc.com/amharic/45873594
ከብ/ጄኔራል ከማል ገልቹና ብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ሹመት ጀርባ?
ከዓመታት በፊት መቶ ሃምሳ የሚሆኑ ወታደሮችን ይዘው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግን) የተቀላቀሉት፣ ከዚያም ከኦነግ ወጥተው የራሳቸውን ፓርቲ ያቋቋሙትና በቅርቡ ወደ አገራቸው የተመለሱት ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የመሾማቸው ነገር የተሰማው ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ነበር።
ብ/ጄኔራል ከማል ገልቹና ብ/ጄኔራል አሳምነው ፅጌ በሌላ በኩል በመፈንቅለ መንግሥት ተከስሰው ዘጠኝ ዓመታትን በእስር ያሳለፉትና በቅርቡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ የአማራ ክልል ፅጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው የተሰማው በተመሳሳይ ጊዜ ነበር። የሹመቱን ዜና ተከትሎ ብዙ መላምቶች መሰንዘራቸው አልቀረም። የጄኔራል ከማል ገልቹን ሹመት እሾህን በሾህ ነው የሚሉ አንዳንዶች ከኦነግ አብራክ የወጡት ከማል ገልቹን እዚህ ኃላፊነት ላይ ማስቀመጥ ትጥቅ ለመፍታት አንገራግሯል የተባለውን ኦነግን ቀስ በቀስ ለመግራት ሁነኛ ዘዴ ነው ያሉም አሉ። በእንግሊዙ ኪል ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት እንደ ዶ/ር አወል ቃሲል አሎ ያሉ ፖለቲካ ተንታኞች ደግሞ በዚህ ሐሳብ አይስማሙም።እንዲያውም ሹመቱ ከኦነግ ትጥቅ መፍታትና አለመፍታት ጋር የሚያያዘው ምንም ነገር የለም ይላሉ። "...ስለ ኦነግ ሌላ ሰው የሌለው እሳቸው ብቻ ያላቸው ዕውቀት ይኖራል ብዬ አላስብም"በማለት ሹመቱን ለኦነግ የተሰጠ አጸፋ አድርገው እንደማያዩት ያስቀምጣሉ። ሹመቱ አስገርሟቸው ከሆነ የተጠየቁት ዶ/ር አወል "ከዚህ ሥርዓት ጋር ትልቅ ተቃርኖ የነበረው፣ የራሱን ፓርቲ አቋቁሞ በውጭ አገር ይንቀሳቀስ የነበረና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም እንደ ጠላት ይታይ የነበረ ግለሰብ ወደ አገር ቤት ተመልሶ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአንድ ክልል መንግሥት የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ መሆን" በተወሰነ መልኩ ሊያስገርም እንደሚችል ይገልፃሉ። በአንጻሩ ደግሞ የአገሪቱ የፖለቲካ ሁለንተና እየተቀየረ ያለበት ፍጥነት ሲታይ ነገሩ ብዙም የሚገርም እንዳልሆነ ያወሳሉ። የብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ ሹመት ምን ዓይነት ትርጉም ነው የሚሰጥዎት? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ዶ/ር አወል "ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኦዴፓ) እምብዛምም የተለየ ፕሮግራም ከሌላቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር አንድ ሆኖ የመሥራት ነገር በብዙ ሰዎች ሲነገር ነበር።" ካሉ በኋላ በፓርቲዎቹም መካከል ንግግር ተጀምሮ እንደነበር በግል እንደሚያውቁ ጠቅሰዋል። ስለዚህም ሹመቱ ለሳቸው የሁለቱ ፓርቲዎች ንግግርና አብሮነት የወለደው እና የጄኔራሉ ልምድና ብቃት ላይ የተመሠረተ ነው። . "ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው" . የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ . የሰኔ 16ቱ ጥቃት ተጠርጣሪ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተሰጠ በሌላ በኩል ምንም እንኳ የፕሮግራም ልዩነት ባይኖራቸውም ኦሮሚያ ላይ የተለያዩ ፓርቲዎች በተናጥል መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ በፓርቲዎቹ ላይ ሥርዓቱ የኔ ነው የሚል የባለቤትነት መንፈስ ለመፍጠርና ወደ አንድ ለማምጣት ታስቦበት የተደረግ ሊሆን እንደሚችልም ይገምታሉ። ኦሮሚያ ላይ የሚንቀሳቀሱና ሰፊ ደጋፍ ያላቸው እንደ ኦነግ እና ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ለሹመት ባልተጋበዙበት ሁኔታ የብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ ሹመት ምን ያሳያል? ዶ/ር አወል እንደሚያምኑት ነገሩ የሚያሳየው ከኦዴፓ ጋር ንግግር ላይ ከነበሩትና ለመቀላቀል ከተስማሙት መካከል የብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ ፓርቲ መግባባት ላይ መድረሱ ነው። ሹመቱም በዚሁ አንፃር የሄደ ነው። በጆርጂያ ጉኔት ኮሌጅ የፖለቲካ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ዮሐንስ ገዳሙም የጄኔራል ከማል ገልቹ ሹመት አጠቃላይ በአገሪቱ ያለው የለውጥ መንፈስ የወለደው ነው ብለው ያምናሉ። የ"ባላንጣዎች ጥምረት" በምዕራቡ ዓለምም ያለ አሠራር እንደሆነ የጠቀሱት ዶ/ር ዮሐንስ ሹመቱ "በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለውን ማኅበረሰብ ፍላጎት ለማሟላት በጋራ የምንሠራና ጥያቄዎቻችሁን ለመመለስ የምንሞክር ነን" የሚል መልእክት ያለው ነውይላሉ። በተለይም ኦሮሚያ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኃይል ክፍፍል አለ እየተባለ የሚነገረውን ነገር ለማስተካከል የተወሰደ እርምጃ ሊሆን እንደሚችልም ይገምታሉ፤ ዶ/ር ዮሐንስ። የብ/ጄኔራል ከማል ገልቹም ሆነ የብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ የፀጥታ ተቋማትን እንዲመሩ መሾም የፀጥታ ተቋማትን ከፓርቲ ፖለቲካ ነፃ የማድረግ የመንግሥት ፍላጎትን ጥያቄ ውስጥ አይከተውም ወይ የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው ዶ/ር ዮሐንስ "የኢትዮጵያ የፀጥታም ሆነ ማንኛውም አስተዳደራዊ ጉዳይ ከፖለቲካ ፓርቲ ተፅእኖ በፍፁም ሊወጣ አይችልም" በማለት ይመልሳሉ። ይህ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው የርዕዮተ ዓለም ለውጥን ተከትሎ ነው ባይ ናቸው። "ዛሬም ሥልጣን ላይ ያለው ኢህአዴግ ነው።ምንም እንኳ አሳማኝ የሚባሉ ለውጦችን እያደረገ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ባህሪውን ይቀይራል ብዬ አላምንም" በከፍተኛ አመራር ደረጃ የፓርቲና የመንግሥት አስተዳደር መስምርን እንለያያለን ብለው ቃል ቢገቡም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ይህን እንዲያደርጉ የሚፈቅድ አይደለም የሚሉት ዶ/ር ዮሐንስ ዞሮ ዞሮ ተሿሚዎቹ የፓርቲያቸውን ፍላጎት እንደሚያስፈፅሙና ከፓርቲያቸው ተጽእኖ ሊላቀቁ የሚችሉበት ዕድል እንደሌለ ይደመድማሉ።
news-51355846
https://www.bbc.com/amharic/news-51355846
"የደባ ፖለቲካውን ማስቆም ፈተና ሆኗል፤ ግን ኢትዮጵያን የምናስቀጥል መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ"
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እየተነሱላቸው ላሉ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ለጠቅላይ ሚንስትሩ ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል። ስለ ታገቱት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተማሪዎቹን ያገተው ማነው?፣ የታገቱት ተማሪዎች ተለቀዋል ተብሏል፤ የት ነው የሚገኙት? ማነው ያገታቸው? የሚለው ጥያቄ ይገኝበታል። ሕግ ወጥ የመሬት ወረራ፣ ታዳጊዎችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ታዳጊዎችን አግቶ ገንዘብ የመጠየቅ እና ገንዘቡ የማይከፈል ከሆነ የመግደል እርምጃ ተስተውሏል። ይህን አይነት ሕገ-ወጥነት ለመግታት ምን እየተደረገ ነው? የጸጥታ ችግር በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ጉጂ እና ቦረና አካባቢ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን መንግሥት እንዴት ተዘጋጅቷል? ምርጫ 2012 ምርጫ በነሐሴ፤ በክረምት ወር እንዲካሄድ መወሰኑ ምን ያህል ትክክለኛ ነው? የ'ክልል እንሁን' ጥያቄ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች መካከል በርካታ ብሄረሰቦች የክልል እንሁን ጥያቄ እያነሱ እንደሆነ በማስታወስ፤ የብሄረሰቦች ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ያለበት በሕገ-መንግሥቱ መሠረት እንጂ ሌላ ጥናት ማድረግ አስፋለጊነት የለውም። የትግራይ ተወላጆችን ማግለል ወደ ትግራይ ክልል ሊያመሩ የነበረ የቻይና ልዑካን ቡድን ወደ ትግራይ እንዳይሄድ ተከልክሏል፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የትግራይ ክልል ተወላጆችም ከሥራ ተገለዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት ከሰሞኑ የተደረገው ውይይት ይዘት ምን እንደሆነ እና የተደረሰበትን ደረጃ ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዲያብራሩ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ከመስጠታቸው በፊት፤ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ መንግሥታቸው ምን አይነት ችግር ገጥሞት እንደነበረ እና ችግሮቹን ለመፍታት እየመጣበት ያለውን መንገድ አስረድተዋል። ከእርሳቸው በፊት የነበረው መንግሥት በውስብስብ 'ኔትወርክ'' ተይዞ እንደነበረ እና እርሳቸውም ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ይህን 'ኔትወርክ ለመበጣጠስ' ጥረት ሲደረግ መቆየቱን፤ ይሁን እንጂ ይህ ለመንግሥት ከፍተኛ ፈተና ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል። "እስከታችኛው የመንግሥት እርከን ድረስ የተዘረጋው ይህ ኔትወርክ፤ ሲፈለግ ማንም እንዳይንቀሳቀስ የማድረግ አቅም አለው" ብለዋል። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም • የግዙፉ ግድብ ግንባታ፡ የኢትዮጵያና ግብፅ ቅራኔ "ይህ ውስብስብ እና ጥልፍልፍ ኔትወርክን መገንዘብ ችግር ነበር። ኔትወርኩን መበጣጠስ መከራ ነው። ይህን ኔትወርክ ማግኘት እና መበጠስ ስንጀምር ደግሞ ኔትወርኩ እስከ ታችኛው የመንግሥት እርከን ድረስ ትስስር እንዳለው ተረድተናል" ብለዋል። "ሕዝቡ እንዲረዳ የምፈልገው አሁን ያለንበት ጊዜ የመጨረሻ ከፍተኛ ፈተና የተሞላ ወቅት መሆኑን ነው።" ሲሉ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የሴራ ፤ የደባ ፖለቲካውን ማስቆም ፈተና ሆኗል፤ ነገር ግን ኢትዮጵያን የምናስቀጥል መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ይህ የሚታለፍ ፈተና ነው።" ሲሉም ተደምጠዋል። የደምቢ ዶሎ እገታ "ቦኮ ሃራም ሰው ሲያግት ኃላፊነት እወስዳለሁ ብሎ ያውጃል፤ እዚህ ግን እስካሁን ኃላፊነት እወስዳለሁ ያለ የለም" በማለት እገታውን ማን እንዳከናወነ እንደማይታወቅ ግልፅ አድርገዋል። በውል የማይታወቁ ግለሰቦች አሉ። ተጎድተዋል እንዳይባል በእገታው የተጎዳ የለም። ተማሪ ያልሆኑ፤ መኖሪያቸው ሌላ ቦታ የሆኑ ተቀላቅለው አሉ። ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር፣ የሰላም ሚንስትር እንዲሁም ከሁሉም የጸጥታ አካላት የተውጣጣ ኮሚቴ ምርመራ ላይ ነው፤ ምርመራ ሲጨርሱ የሚደርሱበትን ግልጽ ያደርጋል። • የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀንና የመንግሥት ዝምታ "ባልተሟላ መረጃ መግለጫ መስጠት ስላልነበረብን ነው መረጃ ሳንሰጥ የቆየነው" በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ምንም ሳይል የቆየበትን ምክንያት ለማብራራት ሞክረዋል። በምዕራብ ወለጋ እና በጉጂ ስላለው የጸጥታ ችግር በጉጂ ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር እየተቀረፈ እንደሚገኝ በመግለጽ ያለው የጸጥታ ችግር አስጊ የሚባል እንዳልሆነ ገልፀዋል። በምዕራብ ወለጋ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ግን ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል። "ሁሌም መፍትሄው ሰላማዊ ነው። ነገር ግን ለዲሞክራሲ እጇን በከፈተች አንድ አገር ሁለት የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም" ያሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "አሁን ላይ መንግሥትን በሁለቱም ጫፍ ጫና ውስጥ የሚስገባ ሥራ ነው እየተሠራ ያለው" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአንድ በኩል መንግሥት ሰላም የማስከበር ሥራን ለመስራት ጸጥታ አስከባሪ ወደ ሥፍራው ሲያሰማራ "'ኦፕሬሽን ወሰዳችሁ' እንባላለን"፤ በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት በምዕራብ ወለጋ ሕግ የማስከበር ሥራን እየሰራ አይደለም እየተባለ ይወቀሳል ብለዋል። በትግራይ እና በፌደራል መንግሥት መካከል ስላለው ግነኙነት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የትግራይ ክልል ተወላጆች በማንነታቸው እየተለዩ ከሥልጣን እንዲነሱ ተደርገዋል የተባለው ስህተት ነው ብለዋል። "ከ10 በላይ ሚንስትር ዲኤታዎች አሉ፤ አንድም አልተነሳም፤ ሌላ ሚንስትር እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤም አልተነሱም። . . . የትግራይን ሕዝብ ያገለለ መንግሥት በኢትዮጵያ ሊኖር አይችልም። እኛም እንዲሆን አንፈቅድም" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም፤ "ብልጽግና የፈለገውን ማድረግ ይችላል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የራሱን ካቢኔ መርጦ ማቋቋም ይችላል። ስትፈልጉ ጠቅላይ ሚንስትሩን አንሱ" ብለዋል። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች ህወሃት በፌደራል መንግሥቱ ተገፍቷል መባሉን ያስተባበሉት ጠቅላይ ሚንስትር "ህውሃት አልተገፋም፤ ወደፊት አብረን ልንሰራ እንችላለን" ብለዋል። ምርጫ 2012 ምርጫው በክረምት መካሄዱ ትክክል አይደለም ለሚለው ቅሬታ፤ ምክር ቤቱ "ምርጫ ቦርድ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ እንደመሆኑ ቦርዱን ጠርታችሁ አናግሩ" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል። "መንግሥት ከመመስረቱ አንድ ወር ቀድሞ ምርጫ መካሄድ አለበት። ይህ ሕገ-መንግሥታዊ ነው። ግንቦት ወይስ ነሐሴ የሚለውን ምርጫ ቦርድን ጠይቁ። ሥልጣኑ የእናንተ ስለሆነ" ያሉ ሲሆን፤ መንግሥት ከመመስረቱ አንድ ወር ቀደም ብሎ ምርጫ መካሄድ አለበት ብለዋል። የክልል እና የዞን እንሁን ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ክልል የመሆን እና የልማት ጥያቄ አብሮ የሚሄዱ ጥያቄዎች አይደሉም ብለዋል። "ክልል፣ ዞን እና ወረዳ በበዛ ቁጥር ደሞዝተኛ ነው የሚበዛው እንጂ የሕዝብ የልማት ጥያቄ አይደለም የሚመለሰው" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨምረውም የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 47 በመጥቀስ ሕገ-መንግሥቱ በራሱ ይህን በማስፈጸም ረገድ ክፍተት መኖሩን ጠቁመዋል። በተጨማሪም ክልል እንሁን ጥያቄዎችን በአሁኑ ሰዓት ምርጫ ቦርድ እንዲያስፈጽም መጠበቅ ስህተት ነው ብለዋል። "ምርጫ ቦርድ አሁን ላይ ይህን ሁሉ ማስፈጸም ይችላል ብሎ መጠበቁ ትክክል አይሆንም" በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ኢቲዮ ቴሌኮም፣ መብራት ኃይል እና ሌሎች የመንግሥት ተቋማት ያስመዘገቡትን ውጤት ተናግረዋል። ኢትዮ ቴሌኮም 8 ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን መመዝገቡ እና ለመንግሥት ከፍተኛ ገቢ ማስገኘቱን ጠቅሰዋል። መብራት ኃይልም ብዙ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በመብራት ኃይል እጥረት ለተጠቃሚዎች በፈረቃ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውሰው ዘንድሮ ግን ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በሌለበት የኤሌክትሪክ ኃይል "በአስተዳደር ብቃት ነው ያለ ፈረቃ እንዲሠራጭ እየተደረገ ያለው" ብለዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ባለፉት 8 ዓመታት በሦስቱ አገራት መካከል ድርድር ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሰዋል። የአሜሪካ መንግሥት እና ዓለም ባንክ 'ለማደራደር' ጥያቄ አቅርበው 'ሲያደራድሩ' ቆይተዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ። "ለአሜሪካ እና ዓለም ባንክ ምስጋና ማቅረብ የሚያስፈልገው፤ በሚያውቁን እና አቅም ባላቸው ፊት ስንነጋገር መስማማት ጀምረናል" ብለዋል። ሦስቱም አገራት የመጨረሻ የተባለለትን ስምምነት ለመፈረም ከተዘጋጁ በኋላ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊት "ዝርዝር ዕይታ እና ውይይት ስለሚያስፈልገው [እንዳይፈረም] የሚል አቅጣጫ በመስጠቴ ፊርማው ቆይቷል" ማለታቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረዋል። በዚህም ፕሬዝደንት ትራምፕ፣ የዓለም ባንክ እና የአሜሪካ ፋይናንስ ሚንስትሩ ጋር በስልክ ተገናኝተው ረዘም ላለ ጊዜ መነጋገራቸውን ተናግረዋል። "እስካሁን የነበርነው ጠቅላይ ሚንስትሮች በግድቡ ዙሪያ የአቋም ልዩነት አላሳየንም" ያሉ ሲሆን፤ "ግብጽን ሳይጎዳ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ በሚያደርግ መንገድ እንሄዳለን። በዚህ ላይ የአሜሪካም ሆነ የዓለም ባንክ አቋም ይሄ ነው። ይህ የሚሆን ከሆነ ብዙ እርዳታ ቃል ተገብቷል" ብለዋል። "የግድቡ መጠን ሳይሆን አሁን ላይ አሞላል እና እንዴት ይለቀቅ የሚባለው ጉዳይ ላይ ተደርሷል። ሁለቱ ሚንስትሮች [የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጅ ሚንስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር] ያደረጉትን ማድነቅ እፈልጋለሁ" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። "ከየትኛውም መንግሥታት ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ስንወያይ ቀድሞ የሚመጣው የአባይ ጉዳይ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ድርድሩ በአጭር ጊዜ ይቋጫል ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።
news-45910979
https://www.bbc.com/amharic/news-45910979
የአብን ሊቀ መንበር ዶ/ር ደሣለኝ ጫኔ አዲሱ ካቢኔ አማራን ያገለለ ነው ይላሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አዲሱን ካቢኔያቸውን አዋቅረዋል፤ የተመጣጠነ የብሔርም ሆነ የፆታ ተዋጽዖ እንዲኖረው ብዙ መለፋቱንም ሐሙስ ዕለት በነበረው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ጉባዔ ፊት ቀርበው ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያዋቀሩት ኢዲሱ ካቢኔ ካልተዋጠላቸው ግለሰቦች መካከል በቅርቡ የተመሠረተው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር የሆኑት ዶ/ር ደሣለኝ ጫኔ ናቸው። ሊቀ መንበሩ አሁን ስላለው የፖለቲካ 'ጨዋታ ሕግም' የሚሉት አላቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያዋቀሩት ካቢኔ የተስማማዎት አይመስልም. . . ዶ/ር ደሣለኝ፦ በጥንካሬ ደረጃ ከዚህ በፊት ከነበረው ባልተለመደ መልኩ ከሴቶች ሹመት አንጻር የተሻለ ነው። ብሔርን እና የብሔራዊ ፓርቲዎች ተዋጽኦ ላይ ግን ችግር እንዳለበት ታዝቢያለው። • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ • ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች ምን ጎደለ? በግልጽ እንዳየነው ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሾሙት ሰዎች የፖለቲካ ካፒታል የሌላቸው እና የፓርቲውም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ያልሆኑ ጭምር ናቸው። እነኚህ ሰዎች የአማራን ሕዝብ ፍላጎቶች እና ጥያቄዎች ማስከበር የሚችሉ መሆናቸው እርግጠኛ የማይኮንባቸው ግለሰቦች ናቸው። ከዚህ ቀደምም የማይታወቁ እና የፖለቲካ ዕውቅና የሌላቸው ሰዎች ናቸው። እኔም እንደ አንድ የአማራ ብሔርተኛ ድርጅት መሪ፤ ዐብይ አሕመድ አማራውን ከወሳኝ የፌደራል መንግሥት የሥልጣን ቦታዎች እንዲገለል እያደረገ እንደሆነ ነው የምረዳው። ሁለተኛ ድክመቱ ወሳኝ የሚባሉ የፋይናንስ፣ የዲፕሎማሲ፣ የመከላከያ፣ የደኅንነት፣ የውጭ ጉዳይ ውስጥ አንድም አማራ አለመካተቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገዳዳሪያቸውን ስልታዊ በሆነ መልኩ እያገለሉ እንደሆነ ያሳያል። አምባገነን መንግሥታት የሚያደርጉት የሥልጣን ማደላደል እና ሥልጣን ጠቅልሎ የመያዝ እርምጃ ነው እያየሁ ያለሁት። ከላይ የሴቶች ተዋጽኦን አድንቀው አልፈዋል። በዚህ ውስጥ የጾታ ተዋጽኦን ነው የሚያዩት ወይስ ምን ያህል አማራ አለ የሚለውን ነው የሚመለከቱት? ማለት ቅድሚያ የታየዎት ጾታቸው ነው ወይስ ብሔራቸው? ኢህዴግ የተመሠረተው በብሔራዊ ፓርቲዎች ጥምረት ነው። ከነዚህም መካከል አንዱ አዴፓ ነው። አዴፓን በፌደራል መንግሥት ወክለው ከፍተኛ ሥልጣን ላይ የሚሰየሙ ሰዎች የአማራን ሕዝብ ወርድ እና ቁመቱን የሚመጥኑ መሆን አለባቸው። ሴቶች የሚገባቸውን የካቢኔ ቁጥር ማግኘታቸው ትክክል ቢሆንም። እርሶ የጠቅላይ ሚንስትሩን ካቢኔ እንዲያዋቅሩ ዕድሉ ቢሰጥዎ ምን ያህል የአማራ ተወላጅ ሚኒስትር አድርገው ይሾማሉ? በቅድሚያ እኔ ያነሳሁት ጥያቄ ቁጥሩ በዛ ወይም አነሰ የሚል አይደለም። ከ20 ካቢኔ አባላት 4 ወይም 5 አማራዎች አሉ። ይህም ብዙ የሚያስከፋ አይደለም። ያነሳሁት ጥያቄ ሆነ ተብሎ ጠንካራ የአዴፓ ተወካዮች ቦታ አልተሰጣቸውም ነው። ለምሳሌ በአዴፓ የማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ ላይ ከፍተኛ ድምጽ አግኝተው የተመረጡት ዶ/ር አምባቸው መኮንን ናቸው። ዶ/ር አምባቸውን እዚህ ካቢኔ ውስጥ አለማካተት ማለት ተሰሚነት ያላቸውን አዴፓዎች ሆነ ተብሎ ገሸሽ የማድረግ ስልት ነው። እርስዎ በጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኔ ውስጥ የአማራ ውክልና እንዲጎላ የሚፈልጉትን ያክል በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ሁሉም ብሔሮች ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ? 80 የሚኒስትር ቦታ የለም። ይህን የሁሉንም ፍላጎት እንዴት ማጣጣም ይቻላል? ሁሉንም ብሔር ለመወከል 80 የሚኒስትር ቦታዎችን መፍጠር አትችልም። ብቃት እና የሕዝብ አገልጋይነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሕዝብ ቁጥር ብዛት መሠረት ቦታዎች መሰጠት አለባቸው። በዚህ ስሌት ከሄድን፤ ኦሮሞ በርካታ ቁጥር አለው። ስለዚህ በርካታዎቹ ከኦሮሞ መሆን አለባቸው ብለው ያምናሉ ማለት ነው? ለምን እንደዛ ይሆናል? ውክልናው በሕዝብ ብዛት መሆን አለበት ስላሉኝ።ኢህአዴግ የተዋቀረው ከአራት ብሔራዊ ፓርቲዎች ስለሆነ፤ ከእነዚህ ፓርቲዎች የተሻለ አቅም እና ዕውቀት ያለው ሰው ነው ሊወጣ የሚችለው። አሁንም ቢሆን [በእርስዎ ስሌት ከሄድን] አንድ አፋር ወይም ሶማሌ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን ዕድል ላይኖረው ነው. . . ? አሁን ባለን የፖለቲካ አደረጃጀት መሠረት ከአፋር ወይም ከሶማሌ ወደ ከፍተኛ ሥልጣን ሊመጣ የሚችልበት ዕድል የጠበበ ነው። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወታደሮቹ ድርጊት ተበሳጭተው እንደነበር ተናገሩ ስለዚህ በእርስዎ ስሌት አንድ የአፋር ሕጻን ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን ማለም የለበትም? እየተከተልን ባለነው የጎሳ ፌደራሊዝም ሥርዓት ውስጥ የብሔር ቁጥርን መሠረት ያደረገ አሠራር ነው ያለው። ያ ማለት ግን የሌሎች ብሔር ተወካዮችም ወደ ሥልጣን መምጣት የለባቸውም ማለት አይደለም። ብሔርን ብቻ መሠረት ያደረገ ሹመት ተገደን የገባንበት ሥርዓት ሆኖ እንጂ ብቃትን መሠረት ያደረግ ሥርዓት የአማራ ሕዝብ የረዥም ጊዜ ፍላጎት ነበር። አሁን ደግሞ ተገደን የገባንበት ሥርዓት ነው ወደሚል ሐሳብ እየመጡ ነው። ቀደም ብዬ ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ ስላዋቀሩት ካቢኔ ስጠይቀዎ የአማራ ውክልና በተገቢው ሁኔታ የተሟላ እንዳልሆነ ሲያስረዱኝ ነበር። ቁጥሩ አነሰ አላልኩም። መቼም በጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኔ ውስጥ አንድ ወይም ሁለት አማራ ብቻ ቢሆኑ ቅር ይልዎታል አይደል? አዎ ቅር ይለኛል። አሁን ያለው ፖለቲካ በዜግነት ላይ የተመሠረት ፖለቲካ አይደለም። ሕገ-መንግሥቱ የሚለው እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እንጂ የኢትዮጵያ ዜጎች አይልም። በብሔር ተደራጅቶ ፍላጎትን ማስጠበቅ በሚቻልበት ሥርዓት ውስጥ አማራውም በብሔሩ ተደራጅቶ ጥቅሙን እና ፍላጎቱን መጠየቅ አለበት። • ከጄኔራሎቹ ሹመት ጀርባ? አሁን ከሰጡኝ አስተየየት በመነሳት እርስዎ ወደፊት አሁን ከሚያራምዱት የብሔራዊ ፖለቲካ ወጥተው የዜግነት ፖለቲካ የሚያራምዱበት ዕድል እንዳለ ይሰማኛል። እወጣለሁ ብዬ አላስብም (ከብሔር ፖለቲካ)። ምክንያቴን ላስረዳ። የዜግነት ፖለቲካ ወደ መድረኩ ቢመጣ እንኳ በአማራው ላይ ከዚህ ቀደም የደረሰበት ግፍ እና መከራ ተመልሶ እንዳይመጣበት በብሔሩ ተደራጅቶ እራሱን መጠበቅ እንዳለበት አስባለሁ። አማራ ሁሌም አማራዊ አደረጃጀቱን ይዞ መቀጠል አለበት። በፌስቡክ ገጽዎ ላይ ካሰፈሩት ጽሑፍ ውስጥ «የፌደራል ወሳኝ ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኦሮሞ መውረርና መቆጣጠር ለአማራው ሕዝብ ዓይን ያወጣ ክህደት እና ሸፍጥ ነው» ይላል። ቀደም ብሎ ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኔ ውስጥ የተካተቱት ሰዎች የአማራን ሕዝብ ፍላጎት ያስጠብቃሉ ብለው እንደማያምኑ እንጂ ከቁጥር ጋር የተገናኘ ቅሬታ እንደሌሎት ነው የነገሩኝ። ሐሳቡ የሚጋጭ ይመስላል። የኦሮሞ ውክልና በዝቷል ማለት ሳይሆን፤ ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የሰጧቸው ሹመቶች በኦሮሞዎች የማሲያዝ እና አማራን የመግፍት አዝማሚያዎች አሉት የሚል ነው። ለዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣት አማራ ከፍተኛ ድጋፍ እና አስተዋጽኦ አድርጓል። ወደ ሥልጣን ከመጣም በኋላ የመጀመሪያውን ድጋፍ ያገኘው ከአማራ ሕዝብ ነው። አሁን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአማራ ሕዝብ ላይ በግልጽ እየፈጸመ ካለው ክህደት መቆጠብ አለበት። እያወራ ያለው ሌላ ነው፣ የሚሠራው ሌላ ነው። ሰው መሾም ያለበት በብቃቱ መሆን አለበት እያሉ የምናየው ነገር ግን ብቃት ያላቸውን አማራ እያገለሉ ከእሳቸው ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት ባላቸው ሰዎች የመውረር ሁኔታ እየታዘብን ነው። ህወሓት ፈጽሞታል እያልን ስንቃወም የነበረውን ጉዳይ አሁን በኦሮሞው ሲደገም የማንቃወምበት ምክንያት የለም። ከብሔር በተጨማሪ ደግሞ የሃይማኖት ውክልና ጥያቄም አለ። አሁን ያለው የሚኒስትሮች ብዛት 19 ነው። መቼም ለብሔር እና ሃይማኖት ውክልና ተብሎ 80 እና ከዚያ በላይ ሚንስትር መሥሪያ ቤቶች አይመሰረቱም። ከዚህ ዓይነቱሁኔታ በቀላሉ መውጣት ይቻላል? በአጭር ጊዜ ውስጥ ከዚህ ዓይነት ችግር እንላቀቃለን ብዬ አላስብም። ለዚያም ነው የእኛም ፓርቲ በተጻፈ የጨዋታ ሕግ የአማራን ሕዝብ መብት እና ፍላጎት ማስከበር አለብን የምንለው። የጨዋታው ሕግ የሚቀየር ከሆነ ደግሞ ወደፊት የምንመለከተው ጉዳይ ይሆናል። • "ካሜራ ፊት ስቀመጥ ዘርም፣ ዘመድም ፓርቲም የለኝም " ቤተልሔም ታፈሰ ታዲያ እንደሱ ከሆነ የጨዋታውን ሕግ ለመቀየር መታገሉ አይሻልም? እሱን እኮ ሞክረነዋል። የአማራ ሕዝብ በዜግነት ፖለቲካ የሚያምን የፖለቲካ ፓርቲ በመመሥረቱ ብዙ ዋጋ ከፍሏል። ይህም ውጤት አላመጣም። አማራው ብቻውን ይህን ለመቀየር የሚታገልበት እና ሌላው በራሱ ጊዜ በብሔሩ የሚደራጅበት ጥቅሙን እና ፍላጎቱን የሚያስከብርበት እና ከዚያም አልፎ አማራውን የሚያጠቃበት ሥርዓት በመፈጠሩ እኮ ነው አማራ ተገፍቶ ወደዚህ የገባው። የጠቅላይ ሚንስትሩን የካቢኔ ሹመት በመቃወም የአዴፓ ተሿሚዎች ከካቢኔ ጥለው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። አዴፓ ይህን የሚያደርገው ይመስልዎታል? አዴፓ መገንዘብ ያለበት ጉዳይ ትልቁን የአማራ ሕዝብ ወክሎ ነው እዚያ የሚገኘው። ትልቅ ጉልበት አለው። የማስገደድ አቅም አለው። ይህንን ማድረግ የማይችል ከሆነ ደግሞ ሕዝባችን ከዚህ ቀደም አምባገነን መንግሥቶችን ከትከሻው አንስቶ ሲፈጠፍጥ አንደነበረ ሁሉ ዛሬም ታግሎ ራሱን ነጻ ያወጣል። ሕዝባችን ጥቅም እና መብቱን ማስከበሩን ይቀጥላል። የዐብይ አሕመድ መንግሥት ያዋቀረው ካቢኔ የአማራን ሕዝብ የሚመጥን አይደለም። ተስፋ አለኝ አዴፓም ይህን የካቢኔ ሹመት የሚመለከት መግለጫ ያወጣል የሚል፤ እምነት አለኝ። ይህን አቋም በፓርቲ ደረጃ ትወስዳላችሁ? ይህ ትልቅ የፖለቲካ ክስተት ስለሆነ የአብን ሥራ አስፈጻሚ ሁኔታውን ይገመግማል ብዬ አስባለሁ። ምን አቋም እንደሚወስድ ግን ከስብሰባው በኋላ የሚታወቅ ነው የሚሆነው። እስካሁን የገለጽኩልህም የግል ምልከታዬን ነው።
news-50080376
https://www.bbc.com/amharic/news-50080376
አቦይ ስብሃት ነጋ፡ "ህወሓትን የሚተካ የፖለቲካ ኃይል የለም"
አቶ ስብሃት ነጋ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ከተራ ታጋይ እስከ ከፍተኛ የህወሓት አመራር የደረሱ ግለሰብ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ፤ 'በክብር' ከተሰናበቱት ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ናቸው።
በትጥቅ ትግሉ ወቅት ስለነበራቸው ሚና እንዲሁም ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካዊ ሁኔታ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፡ ህወሓት ከተመሠረተበት ግዜ አንስቶ በክብር እስከተሰናበቱበት ድረስ አመራር ላይ ነበሩ። ከልምድዎ እጅግ የሚኮሩበት ወይም እንዲህ ባደርግ ኑሮ ብለው በግል ወይም እንደ ድርጅት የሚቆጩበት ነገር አለ? አቦይ ስብሃት፡ እንደ ድርጅት ድክመት አልነበረብንም አልልም፤ ብዙ ድክመቶች ነበሩብን። በግልም ስህተቶችን አልፈፀምንም አልልም። እኔም በግሌ አንዳንድ ስህተቶችን ፈጽሜያለሁ፤ ሆኖም በቅጽበት ይታረም ነበር። የሓኽፈን ውጊያ የኔ ስህተት ነበር ውጊያው ድል አልነበረም። ግን በፍጥነት ተምረን በፍጥነት ነበር የምናርመው። ከድክመት እንማር ነበር፤ በድልም የመርካት ሁኔታ እንዳይኖር እንማርበት ነበር። በድል መስከር አይገባም። የኢትዮጵያ መጻኢ ታሪክ ተጽፏል፤ ፕሮግራም ላይ ሰፍሯል። ከዚሁ በመነሳት ነው 'ትግሉ ረጅምና መራራ ነው፤ ድል ግን አይቀሬ ነው' ነው የተባለው። • ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም" ቢቢሲ፡ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ሥርዓቱ በሙስና በስብሷል ይሉ ነበር። እርስዎና ቤተሰብዎ ግን በሙስና ትታማላችሁ ምን አስተያየት አለዎት? አቦይ ስብሃት፡ ሙስና ቀስ እያለ የሚመጣ ችግር ነው። ሙስና አለ በሚለው ላይ 'መጠኑ ትንሽ ነው፤ አይደለም መጠነ ሰፊ ነው' የሚል ክርክር ነበር። ይብዛም ይነስም ምልክቱ ሲታይ ቶሎ መታረም ነበረበት። ኋላ ላይ እያደገ መጥቶ ሙስናን መጸየፍ እየደከመ መጣ። ሙስና የሥርዓታችን ዋነኛው ጠላት ነው እየተባለም ጥንቃቄያችን ግን እየቀነሰ መጣ። በ2008 እናጽዳው ተብሎ ታወጀ። ጸረ ዴሞክራሲያዊ ጠባብ ብሔረተኝነት (ጠባብነትና ትምክህት ማለት ነው)፣ የሃይማኖት አክራሪነት ጠላቶቻችን ናቸው ብለን ለይተን አስቀመጥን። ዋናው ተጠያቂ ደግሞ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ነው፤ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ምክትሉ ናቸው ብለን አስቀመጥን። ስለዚህ በፍጥነት መታደስ አለብን ብለን ወሰንን። ዶክተር ዐብይ ከተመረጠ በኋላም አሁንም በፍጥነትና በጥልቀት መታደስ አለብን ካልሆነ ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ ነው ያለችው አልን። ይህ ሳይተገበር ቀረ፤ እንዴት ቀረ? ማን አስቀረው? ተአምር ነው። አንድን ነገር ሊሆን አይገባውም ካላልክ በስተቀር ይለመዳላ፤ አሁን እየተለመደ ነው። ይህ ጉዳይ እንዴት ጠፋ ስትል፤ እኔ ጠፍታ ዳናዋ ካልተገኘው የማሌዥያ አውሮፕላን ጋር ነው የማመሳስለው። ቢቢሲ፡ እርስዎን በተመለከተ ሰለሚነገረውስ? አቦይ ስብሃት፡ የዚያው አካል ነው። መጣራት አለበት እሱ እንዲሆን እኮ ነው እየተጠየቀ ያለው። ሙሰኛ ማነው? አቶ እገሌ ወይስ ወይዘሮ እገሊት? ደፍሮ የሚያወጣው ነው የታጣው። ወኔ የለም፤ ድፍረት እኮ ነው የታጣው። የአገር ውስጥ ሙያተኞች ከውጭ ባለሞያዎች ጋር ሆነው እንዲሠሩ 'ፕሮፖዛል' ለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ደመቀ መኰንንና አቶ አባይ ወልዱ ቀርቦ ነበር። እንገባበታለን ተብሎ ቀረ። ነጻና ገለልተኛ በሆነ አካል መጣራት ነበረበት። አንተስ ብትለኝ እዚያው ውስጥ መጣራት አለብኝ። • "ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደትን ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" አቶ ጌታቸው ረዳ ቢቢሲ፡ አቦይ ስብሃት በአሁኑ ሰዓት ምን ዓይነት ሚናና ኃላፊነት አለዎት? አቦይ ስብሃት፡ የእኔ እምነት የህወሓት/ኢህአዴግ ፖለቲካዊ ፕሮግራም ነው። አሁን አለ ወይስ የለም የሚለውን ቆይቼ እገልጸዋለሁ። በግል የህወሓት ደጋፊ ነኝ። ትግራይ ውስጥ ትግራይን፤ ከትግራይ ደግሞ ለኢትዮጵያ፤ ህወሓትን የሚተካ የፖለቲካ ኃይል የለም። በመተዳደሪያ ሕጉ መሰረት [የህወሓት] አባል አይደለሁም። እየተናገርኩ ያለሁትም ህወሓትን ወክዬ ሳልሆን እራሴን ወክዬ ነው። የህዋስ አባልም አይደለሁም፤ የአባልነት ክፍያም አልከፍልም። ነገር ግን የህወሓት ደጋፊ ነኝ። ህወሓት ለትግራይ ህዝብ አማራጭ የለውም። የትግራይ ህዝብ ሀገርን እንዲጠቅም ካስፈለገ ህወሓት መተኪያ የለውም። ቢቢሲ፡ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው የሚለው ሃሳብ እያከራከረ ነው። በአንድ ወገን፣ ህወሓት እንደ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች አዳራሽ ውስጥ የተመሠረተ ሳይሆን ከትግራይ ሕዝብ አብራክ የተገኘ ነው። ይህን የሚቃወሙ ድርጅቶችና ግለሰቦች በበኩላቸው፣ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ከሆኑ ታድያ ለምን አማራጭ ኃይል ያስፈልጋል? ምርጫስ ለምን ያስፈልጋል? በማለት የሚከራከሩ አሉ። እዚህ ላይ ያለዎትን አቋም ይንገሩኝ? አቦይ ስብሃት፡ አሁን ባለው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ህወሓት መተኪያ የለውም። በሌላ የፖለቲካ ድርጅት ሊተካ አይችልም። ህወሓት ደግሞ መጥፋት አለበት። መጥፋት አለብኝ ነው የሚለው፤ መጥፋትም አለበት። ህወሓት የትግራይን እና የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመለወጥ ሚናዬን መጫወት አለብኝ ሲል፤ ራሱን ህወሓትን እና ኢህአዴግን ለማጥፋት ነው። ይህ ምን ማለት ነው? የህወሓትን ሕዝባዊ መሠረት ካየነው ገበሬው፣ ወዛደሩ፣ ንዑስ ባለሃብቱና አብዮታዊ ምሁሩ ናቸው። ዋነኞቹ ደግሞ ገበሬውና ወዛደሩ ናቸው። ገበሬው ከተለወጠ ህወሓት የእኔ መጥፋት ጸጋ ነው ብሎ ይቀበላል። ትግራይ የወዛደር እና የልማታዊ ባለሃብት መሆን አለባት። ገበሬው ቢበዛ ከሦስት እስከ አራት በመቶ ነው መሆን ያለበት። ገበሬው ባለሃብት መሆን ይኖርበታል። ሰለዚህ የወዛደር ድርጅት በግራ፤ የሃብታም ባለሃብት ድርጅት ደግሞ በቀኝ፤ የህወሓት ወራሾች ሆነው መምጣት አለባቸው። እነዚህ ድርጅቶች ገና አልተወለዱም። በትግራይ ተተኪ ድርጅት መምጣቱ ጸጋ ነው። ዛሬ ካልተወለደ ነገ መወረስ አይችልም። ሰለዚህ ወዛደሩን ወይም ባለሃብቱን መሠረት ያደረገ ድርጅት መምጣት አለበት። መደብ መሠረት ያላደረገ የፖለቲካ ድርጅት ጫጫታ ነው። አቶ ተወልደ ወልደማሪያም እና አቦይ ስብሃት ነጋ ቢቢሲ፡ ስለዚህ ተተኪው ድርጅት እስኪመጣ ድረስ ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ናቸው እያልን ነው? አቦይ ስብሃት፡ አዎ አንድ ናቸው። ወያኔ ይህ ድክመት አለበት ተብሎ ድርጅት ይመሠረታል እንዴ? ፖለቲካዊ ድርጅት ማለት ፖለቲካ ማለት ነው፤ ፖለቲካ ደግሞ መደብ ነው። ወያኔ ወዛደሩን እና ባለሃብቱን መሠረት ያደረጉትን የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ ጸጋ ነው የሚያያቸው፤ ልጆቹ ናቸው። ቢቢሲ፡ ትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አራት የፖለቲካ ፖርቲዎች አሉ። እነዚህን ፓርቲዎች እንዴት ነው የሚያዩዋቸው? አቦይ ስብሃት፡ እኔ የፖለቲካ ፓርቲዎች አልላቸውም። እየነገርኩህ ነው፤ መደብ መሠረት ያደረገ ነው የፖለቲካ ፓርቲ የሚባለው። ይህ አውሮፓ ውስጥም ቢሆን ረዥም ዓመታት ያስቆጠረ ትርጓሜ ነው። ይህ መደብ ይህን ሥራ እየሠራ ነው ብሎ የሚመሠረት መሆን አለበት። ማህበራዊ መሠረት ከሌለው ፖለቲካዊ ፓርቲ አይደለም። ገዢ መደብን ተጠቃሚ ያደረገ ፓርቲ ነው። ራሳችንን አናሞኝ። • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች ቢቢሲ፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ደርግን አሸንፎ ፌደራላዊ ሥርዓትን በመመሥረቱ የሚያደንቁት ወገኖች እንዳሉ ሁሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያን አንድነት ከፋፍሏል ብለው የሚወቅሱት አሉ። የእርስዎ ዕይታ ምንድን ነው? አቦይ ስብሃት፡ መመዘኛ መቀመጥ አለበት። ስሜታዊ ሳትሆን መስፈርት አስቀምጠህ መመዘንና መስፈርት ሳይኖርህ አስተያየት መስጠት ይለያያል። መስፈርት ሳታስቀምጥ አስተያየት መስጠት መፈረጅ ይባላል። ስለዚህ መመዘን እና መፈረጅ ይለያያሉ። ደርግን ሲታገሉ የነበሩ አብዛኞቹ ብሔራዊ ፓርቲዎች ከኢትዮጵያ የከፋ አገር የለም ይሉ ነበር፤ ልክ ናቸው። ፈታኙ ትግል የነበረው ኢትዮጵያ ውስጥ አብሮ መኖር አይቻልም የሚለው ነው። ህወሓት አብሮ መኖር ይቻላል፤ የሽግግር መንግሥቱ ላይ ቁጭ ብለን እንየው ብሎ ነው የታገለው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ መንግሥት ለማጽደቅ የነበረው ችግር ለማመን የሚከብድ ነበር። አብሮ መኖር ማለት ተአምር ማለት ነው ተባለ፤ አብዛኞቹ ፓርቲዎች ከኢትዮጵያ ለመነጠል ነበር ሲታገሉ የነበረው። ህወሓት ተአምር ይሠራል፤ አብረን እንኖራለን ብሎ ታገለ። ስለዚህ ኢህአዴግ እዚህ ላይ አጥብቆ ባይዝ ኑሮ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም ነበር። ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንድትኖር ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የማይተካ ሚና ተጫውተዋል። ህወሓት ወደ ስብሰባ አዳራሽ ከመግባቱ በፊት ይለምናቸው ነበር። በሕገ መንግሥት ላይ የተመሠረተች ሀገር ኢትዮጵያን በመፍጠር ወያኔን የሚደርስበት የለም። • "አገሪቷ አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት ህወሓት ተጠያቂ ነው" አዴፓ ቢቢሲ፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት እንደነበር እና መፈንቅለ መንግሥት እንደተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ ተናግረው ነበር። በለውጡ ሂደት ህወሓት የኢህአዴግ አባል እና አካል አልነበረም ወይ? አቦይ ስብሃት፡ አሜሪካ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እንደማትፈልግ የታወቀ ነው። የትኛውንም ሉዓላዊ ሀገር እንደማትወድም ይታወቃል። ልማታዊት ኢትዮጵያ እንደማትወድም የታወጀ ጉዳይ ነው። አሜሪካዊያን እገሌን አቅርቡት፤ እገሌን ደግሞ አርቁት ነው የሚሉት። የእኛ አቋም ደግሞ ሉዓላዊት ኢትዮጵያ እናንተ እንደምትፈልጓት አትሆንም የሚል ነበር። በዚህ አቋማችን ኢህአዴግን በጣም ይጠሉታል። ሁለተኛ ልማታዊ መንግሥትን አይወዱም። ልማታዊ መንግሥት ማለት ገበያ ላይ ድክመት ሲኖር ጣልቃ የሚገባ ማለት ነው። እነሱ ደግሞ እሱን ተዉት፤ እኛ እንገባበታለን ይላሉ። ቤታችሁን ክፍት አድርጉት፤ እናንተ ያቃታችሁን ነገር እኛ እናደርገዋለን ይላሉ። ጥላቻቸውን ለረጅም ጊዜ ሲገልጹ ነበር። 'ሶሪያ ሂጂ ብለናት የማትሄድ ኢትዮጵያ፤ ቻይናን የምታስገባ ኢትዮጵያ ምን እናደርጋታለን' ይሉ ነበር። ይህ አያስደስታቸውም። ከዚያ በኋላ መሃል አዲስ አበባ ያለውን መንግሥት ብቻ ገልብጠህ ወዳጅ አታፈራም ብለው ስላሰቡ፤ ራሳቸውን የቻሉትን የክልል መንግሥታት ለመገልበጥ ተነሳሱ። በኋላም ከአሜሪካ ሲቀሰሩ የነበሩ እጆች ገቡ። እኛ ላይ ጣታቸው ይቀስሩ እንደነበር እናውቃለን። ኢህአዴግን አፍርሱ ነበር የሚሉት፤ ነገር ግን ትዕዛዝ ከሰጡት በላይ የፌደራሊዝም ሥርዓቱንም ሕገ መንግሥቱንም አፈረሰ። ቢቢሲ፡ ማን? አቦይ ስብሃት፡ አዲስ አበባ ላይ ያለው መንግሥት። ቢቢሲ፡ እና ይህ ተግባር ህወሓትንስ አይመለከተውም? • አቶ ጌታቸው አሰፋ በሚያውቋቸው አንደበት አቦይ ስብሃት፡ ከደከምን በኋላ እኮ ነው የገቡት። አሜሪካ ላይም እኮ ማልቀስ የለብንም፤ ተጠቀሙበት እንጂ ዋናው ችግር የራሳችን ውስጣዊ ድክመት ነው። ስለዚህ ውስጣዊው ድክመት ላይ ህወሓትም አለበት። ሁላችንም ድርሻችን እንውሰድ ነው እያልኩ ያለሁት። ውስጣዊ ድክመት ባይኖረን የውጭ ጠላት አይረብሸንም ነበር። ቢቢሲ፡ እድሜዎት ከ80 በላይ ሆኗል። ከሥልጣን በመነሳትዎ ደስ እንዳላለዎትና ቅር እንደተሰኙ ይነገራል። ለምን ማረፍ አልፈለጉም? አቦይ ስብሃት፡ ከፓርቲው መሪነት ከተተካሁ በኋላ አንድ ሁለት ሳምንት ሳልመደብ ቆየሁ። ከዚያ በኋላ ስዩም መስፍን ''ሳንመድብህ ዘገየን'' አለኝ። እኔ አሁን መጦሪያዬ ነው፤ ምን ዓይነት ሥራ ትሰጡኛላችሁ? አልኩት። ጡረታ ከወጣሁ በኋላም ዶክተር ዐብይ አግኝቶኝ ነበር። ''ጡረታ በመውጣትህ ቅር ይልህ ይሆን?'' አለኝ። እኔ ከ23 ዓመት በፊት ጡረታ መውጣት ይገባኝ ነበር። 84 ዓመት ሆኖኝ ለምን በመንግሥት እጦራለሁ? ፖለቲካ ላይ ጡረታ የሚባል ነገር የለም። ልታጠፋም ልታለማም ትችላለህ። ስለዚህ ከ23 ዓመት በፊት ጡረታ መውጣት የነበረብኝ ሰው እንዴት ጡረታ ወጣሁ ብዬ ቅር ይለኛል? ይህን አንተ እንጂ ሌላ ሰው እንደዚያ አይለኝም...አልኩት (ሳቅ) ቢቢሲ፡ በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ከኢትዮጵያ ጋር ተከባብረን መኖር ካልቻልን ተገንጥለን 'ሀገረ ትግራይን' መመስረት አለብን የሚል አሰተያየት ሲሰጡ ይሰማል። እንደ ነባር ታጋይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው? አቦይ ስብሃት፡ መገንጠል ሕገ መንግሥታዊ መብት ነው። ሆኖም መቅደም ያለበት፣ ለመገንጠል ምክንያት እየሆነ ያለውን ኃይል መታገልን ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ችግር እየፈጠረ ያለው ጠባብና ትምክህተኛ የልሂቅ ኃይል ነው። ይህን ኃይል አሸንፎ አብሮ የመኖር እድል ይሰፋል። ደግሞም በቀላሉ ተሸናፊ ነው። መገንጠል ከባድ ነው። ይህንን ኃይል ማሸነፍ ግን ቀላል ነው። የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ዴሞክራሲያዊ ልማታዊት ኢትዮጵያን ማየት ነው። የአማራና የኦሮሞ እንዲሁም የሌሎች ሕዝቦች ፍላጎትም ተመሳሳይ ነው። ይህንን የሚያግተው ትምክህተኛና ጠባብ ኃይል ነው። ከመገንጠል ይህን ኃይል መታገል ይቀላል። መገንጠል ብትፈልግም፤ ይህንን የጥፋት ኃይል ካላሸነፍክ አትችልም፤ ወደ ጦርነት ነው የምትገባው። • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? ቢቢሲ፡ ቀደም ሲል በይፋም ሆነ በድብቅ ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ [ኤርትራ መንግሥት] ጋር ለመነጋገር ሞክራችሁ ነበር ይባላል። ምንድን ነው አስተያየትዎ? አቦይ ስብሃት፡ እኔ አልሞከርኩም፤ ሞኝ አይደለሁም። ኤርትራ ውስጥ ከማን ጋር ነው የምትነጋገረው? ብቸኛው የተደራጀው ኃይል ያለው፤ ህግዴፍ [በሥልጣን ያለው ፓርቲ] ነው። እሱ ደግሞ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ የሚመራ ነው። ኢሳያስ "በአፍሪካ ቀንድ የጎበዝ አለቃ መሆን ይችል ነበር። ላለፉት 27 ዓመታት፤ የወያኔ ሥርዓት ነው እንቅፋት የሆነብኝ" ነው የሚለው። ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ፤ ኢትዮጵያ የመላው የአፍሪካ ቀንድ በር ነች፤ ቀይ ባህር ደግሞ ሜዳው ነው። ለእንዲህ ላለውና የጎበዝ አለቃ መሆን ለሚያምረው ሰው፤ 'እባክህን የጎበዝ አለቃ መሆን አምሮህ ነበር፤ እንቅፋት ሆንብህ፤ ይቅርታ አርግልን፤ እንክፈትልህ' ብዬ ነው የምለምነው? ቢቢሲ፡ ስለ ዕርቅና ሰላምስ . . . አቦይ ስብሃት፡ 'እኔ የጎበዝ አለቃ ነኝ፤ በሩን ክፈቱልኝ ልግባ' አለ፤ ተዘጋበት። አንዳች የሚያነጋግር ጉዳይ የለንም። • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ ቢቢሲ፡ ታዲያ የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ግንኙነት እንዴት የሚሻሻል ይመስልዎታል? አቦይ ስብሃት፡ መጀመርያ የኤርትራ ሕዝብ ነው ቤቱን ማስተካከል ያለበት። ለራሱ ያልሆነ መሪ ለሌላ ሆኖ መነጋገር አይችልም። ለዚህ ደግሞ መጀመሪያ ኤርትራ ውስጥ ያለው ነገር መስተካከል አለበት። ይሄንን የማድረግ ብቸኛው ኃላፊነት ደግሞ የኤርትራ ሕዝብ ነው። ሁለተኛ፤ የእኛም ቤት መጠበቅ አለበት። ችግሩ በዚህ መንገድ ነው መፈታት የሚችለው። ቢቢሲ፡ ህወሓትን መውቀስ የሚፈልጉ ሰዎች ስብሃትን ነው ቀድመው የሚያነሱት። ህውሓት ዘረኛ ድርጅት ነውም ይላሉ። እስቲ የሚሰማዎትን በግልጽ ይንገሩኝ? አቦይ ስብሃት፡ ይሄን እነሱን ብትጠይቃቸው ይሻላል ነው የምለው። እንደሱ የሚሉ ሰዎች እንዳሉ በስሚ ስሚ እሰማለሁ፤ በእርግጠኝነት ባለማወቅ የሚሳሳት ሰው አለ። ይሄ ሆን ተብሎ ነው ወይስ ባለማወቅ የሚደርግ ስህተት ነው- መታየት አለበት። መሳሳት ማለት፤ እውነተኛ መረጃ ያለማግኘት ነው። ሆን ብሎ የሚያስወራው ግን፤ አንድም የጨነቀው ጠላት ነው፤ አልያም የሌላ ተላላኪ ነው። ሰለዚህ ተሳስተው ነው እንደሱ የሚሉት ወይስ ተልከው፤ የሚለውን እኔ ማወቅ አልችልም። እነሱ ናቸው የሚያውቁት። • በአንድ የጦር አውድማ ላይ ከወላጅ አባቷ ጋር የተፋለመችው ታጋይ ቢቢሲ፡ 'መቀሌ የሌቦች መደበቂያ ሆናለች፤ ህወሓት እውነት ካላት ለምን በሕግ የሚፈለጉትን ለሕግ አታቀርብም?' 'እርሶን ጨምሮ ከፍተኛ የህወሓት አመራር መቀሌ ሂዶው ተሰብስበዋል'- የሚል ነገር ተደጋግሞ ይሰማል። ምንድን ነው ምላሽዎ? አቦይ ስብሃት፡ ትግራይ ውስጥ ወንጀለኛ ተደብቋል የሚባለውን አልቀበለውም። የተከሰሰ ሰው እዚህ እንደሚኖርም አላውቅም። ዋናው ቁም ነገር ቅድም እንዳልኩህ ነው። በግምገማ ያስቀመጥናቸው ድክመቶች ነበሩ። ሌባና ንጹሕ እንዲጣራ፤ ግፈኛና ፍትሃዊ ማን እንደሆነ እንዲታወቅ። 'የሌብነት መንገድስ እንዴት መጣ?' የሚለው እንዲጣራ ነበር የተባለው። ከማለቃቀስ የተሻለው መፍትሄ ይሄው ነው። ትግራይ ውስጥ እኔን ጨምሮ፤ በአገር ድህንነትና በመከላከያ የነበሩ በርካታ ሰዎች አሉ። ሲቪል የነበሩም እንዲሁ። እነዚህ ስለ አገራቸው ስለ ኢትዮጵያ ሲሠሩና ሲጨነቁ ነው የማውቀው። እየከሰሱ ያሉ ሰዎች፤ ስለ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጨነቁ ከሆነ፤ ኢትዮጵያ ወደ አርማጌድዮን ያስገባታል የተባለው ችግር፤ እንደመጣ ያውቃሉ? ሌብነት፣ ግድያና እስራት፤ ኢህአዴግ ከዚህ በፊት አጥፍቻለሁ ካለው በላይ እየቀጠለ እንደሆነ አያወቁምን? በክልሎች የመፈንቅለ መንግሥት ሲደረግ ምን ይሰማቸዋል? መሰረታዊ የአገሪቱ ችግር አውቀው ወደዚህ ቢመጡም እሺ እናጣራው ባልን። እውነት ካለቸው፤ በአንድ ዓመት ከአምስት ወር ውስጥ የተካሄደው እስራት፣ የወደመ ንብረት፣ የጠፋው ብርና የተካሄደው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መጣራት አለባቸው። ቢቢሲ፡ የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን የሚሆን ይመስልዎታል? አቦይ ስብሃት፡ አሁን ባለው መንገድ የምንቀጥል ከሆነ አደገኛ ነው፤ ፌዴራላዊ ሥርዓቱን የማዳን ሥራ መሰራት አለበት። ቀጥሎ ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት፤ ምን እንደሆነ እንዲፈተሽ መደረግ አለበት። አሁን ሥልጣን ላይ ያለው እንደሆነ በሕዝብ ተቀባይነት የለውም። ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው። ይሄ ሳይንሳዊ አባባል ነው፤ ደስተኛ ያልሆነ፤ ሆኖም መብቱን የሚያውቅ ህብረተሰብ ይዘህ፤ በክልሎች ውስጥና በክልሎች መካከል የማይቀር እልቂት ይኖራል። ያልተደሰተ ህብረተሰብ አቅፈኽው ይተኛል እንዴ? አይተኛም።
news-57312697
https://www.bbc.com/amharic/news-57312697
በባንግላዴሽ 70 ነብሮችን 'የገደለው' አዳኝ ከ20 ዓመት ፍለጋ በኋላ ተያዘ
ሀቢብ ታሉክዳር ይባላል። ሀቢብ ነብር ተብሎም ይጠራል።
ይህንን ስያሜ ያሰጠው ነብር በማደን መታወቁ ነው። 70 ነብሮችን የገደለው አዳኙን ሀቢብን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሶስት የእስር ማዘዣ ወጥቶበት ከ20 ዓመታት አሰሳ በኋላ በፖሊስ እጅ ገብቷል። ሀቢብ በህንድና በባንግላዴሽ ድንበር መካከል በሚገኝ በሰንዳርባንስ ማንግሮቭ ደን ውስጥ ነበር አደኑን ሲያከናውን የነበረው። የደን ስፍራው ቤንጋል የተሰኘውን የነብር ዝርያ ከየትኛውም የዓለም ክፍል በላቀ የሚገኝበት ሲሆን ቁጥራቸው እየተመናመነ መጥቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ነብሮች ቀርተውበታል። በዓለም ዙሪያ ህገ ወጥ በሆነ መልኩ የቤንጋል ነብሮች ስጋና አጥንት ሳይቀር ንግድ መጧጧፍ ለቁጥራቸው መመናመን ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል። ታዲያ ነብር አዳኙ ሀቢብ "ለረጅም ጊዜ ሲሸሽ ነበር" ሲሉ የፖሊስ አዛዡ ሳይደር ራህማን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። የ50 ዓመቱ ሀቢብ ነብር ገዳይ ከመሆኑ በፊት ማር በማምረት ነበር ስራውን በደን ውስጥ የጀመረው። አብዱስ ሰላም የተባለ ማር ቆራጭ ነብር አዳኙ ሀቢብ "በአከባቢው ሰው በእኩል የሚከበርና የሚፈራ ነበር" ሲል አስተያየቱን ለኤ ኤፍ ፒ ሰጥቷል። " ደን ውስጥ ብቻውን ከነብር ጋር የሚጋፈጥ አደጋኛ ሰው ነው" ሲልም አክሏል። የፖሊስ መኮነኑ አብድልመናን ለመገኛ ብዙኃን በሰጠው አስተያየት ፖሊስና የደኑ አስተዳደር ሀቢብን ለዓመታት ሲያድኑት መቆየታቸውን ገልጸዋል። "ከአመታት በፊት የተቀመጠውን ወደ ደኑ የመግባት ክልከላ እየተላለፍ የዱር እንስሳትን ሲገል ነበር። ክስ እያለበት እንኳን ድርጊቱን አላቆመም ነበር። ይህንን ወንጀል የሚፈጽመው ከወሮ በላ ቡድን አባላት ጋር በመሆን ነው" ሲል አስረድቷል። ከሀያ ዓመታት አሰሳ በኃላ የተያዘው ነብር አዳኙ ሀቢብ ባለፈው ቅዳሜ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።
56993240
https://www.bbc.com/amharic/56993240
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ህወሓት" እና "ሸኔ"ን በሽብርተኝነት ፈረጀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ህወሓት" እና "ሸኔ" በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ህወሓት" እና "ሸኔ" በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የቀረበለትን ሀሳብ በአንድ ድምፀ ተዐቅቦ አጽድቋል። 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ባሳላፍነው ሳምንት የሚንስትሮች ምክር ቤት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ እና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሃሳብ አስተላልፎ እንደነበረ ይታወሳል። ዛሬ ስብሰባውን እያደረገ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለቱ ቡድኖች በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ ማጽደቁን ምክር ቤቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ አስታውቋል። በአሸባሪነት የተፈረጁት 'ሸኔ' እና ህወሓት ማን ናቸው? ሸኔ የሚንስትሮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ እንዲፈረጅ ሃሳብ ያቀረበው "ሸኔ" ቡድንን ነው። በአሁኑ ወቅት በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ በስፋት ስለሚንቀሳቀሰው እና የመንግሥት ባለስልጣናት፤ 'ኦነግ ሸኔ' ብለው ስለሚጠሩት ታጣቂ ቡድን የሚታወቀው የሚከተለውን ነው። መንግሥት በተለይ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት 'ኦነግ ሸኔ' በሚል የሚጠሩት ታጣቂ ኃይል ራሱን "የኦሮሞ ነጻነት ጦር" በማለት ይጠራል። 'የኦሮሞ ነጻነት ጦር' ለበርካታ አስርት ዓመታት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ የጦር ክንፍ ሆኖ ቆይቷል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህምድ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ከገቡ በኋላ የኦሮሞ ነጻነት ጦር (መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለው ቡድን) ከፓርቲው ተገንጥሎ በትጥቅ ትግሉ እንደሚቀጥል ይፋ አደረገ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ-መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የኦሮሞ ነጻነት ጦር (ኦነግ ሸኔ) በእርሳቸው እንደማይታዘዝ ይፋ አድርገው ነበር። ስለ 'ሸኔ' መንግሥት የሰጠው ማብራሪያ ከውሳኔው በኋላ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጌድዮን ጢሞቲዮስ [ፒኤችዲ] ሸኔ ስለተሰኘው ስያሜ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል። "በተለምዶ 'ሸኔ' የሚባለው እራሱን ደግሞ 'የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት' ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ ፣ በሌሎችም ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚያደርስ ድርጅት ነው። እራሱ ለእራሱ የሰጠውን ስያሜ ግን እኛ የምናፀድቅበት ምክንያት የለንም ፤ ተገቢም አይሆንም ብለን እናምናለን" ብለዋል አቃቤ ሕጉ። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ አክለው ይህ ቡድን ከዚህ በፊት እንደ 'ህወሓት' ተመዝግቦ ፣ ህጋዊ እውቅና ፣ ህጋዊ ሰውነት እና ሰርተፊኬት ኖሮት የሚያውቅ አይደለም። እሱ እራሱን በአንድ ስያሜ ይሰይማል ፤ አንዳንዶች በሌላ ስም ይጠሩታል በተለምዶ 'ኦነግ ሸኔ' ይባል ነበር ስለዚህ በተለምዶ ከሚጠራበት 'ኦነግ ሸኔ' ወይም 'ሸኔ' ከሚባለው 'ሸኔ' የሚለውን መርጠናል" ብለዋል። "እዚህ ጋር ግልፅ መሆን ያለበት በአዋጁ አንቀፅ 23 መሰረት ስያሜውን ብትለዋውጥ ያው ቡድን ያው ስብስብ እስከሆነ ድረስ በውሳኔ ሀሳቡ የተገለፀው ስብስብ እስከሆነ ድረስ ስያሜ መለዋወጥ የሚያመጣው ለውጥ የለም፤ ውሳኔ ሀሳቡ ተፈፃሚ ይሆንበታል። አይ እኔ እራሴን የምጠራው እንዲህ ብዬ ነው ፤ እንዲያ ብዬ ነው የሚለው ማምለጫ ሊሆን አይችልም" ሲሉም አብራርተዋል። ጠቅላይ አቃቤ አክለው "ሕጉ ኦነግ የሚባል በምርጫ ቦርድ የተመዘገበ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጀት አለ። ስለዚህ ከሱ ጋር ማምታታት ሊፈጥር ይችላል። ሸኜ የሚለው ብዙ ሰውም ስለሚያውቀው በዚያ እንዲሰየም ተደርጓል" ብለዋል. ሸኔ የሚለው መጠሪያ ከየት መጣ? ሸኔ- ማለት 'ሸን' ከሚለው የኦሮምኛ ቃል የመጣ ነው። 'ሸን' ማለት አምስት ማለት ነው። 'ሸኔ' ማለት ደግሞ አምስቱ እንደማለት ነው። በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ አምስት አባላት ያሉት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 'ጉሚ ሸኔ' ተብሎ ይጠራል። ጉሚ ሸኔ ማለት 'አምስት አባላት ያሉት ጉባኤ' እንደማለት ነው። ፓርቲው ግን ከ5 በላይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አባላት ሊኖረው ይችላል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን መሪ እንደሆነ የሚታመነው ኩምሳ ድሪባ በትግል ስሙ በስፋት የሚታወቀው ጃል [ጓድ] መሮ፤ ለኦሮሞ ነጻነት እንታገላለን ይላል። በተለያዩ ወቅቶች መንግሥት በዚህ ቡድን ላይ በሳምንታት ውስጥ 'እርምጃ' እወስዳለሁ ቢልም፤ በቡድኑ አባላት ተፈጽመዋል በሚባሉ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ተገድለዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል። መንግሥት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ቡድን በርካታ የመንግሥት ባለስልጣናት እና የፖሊስ አባላት ላይ ግድያ እና የባንክ ዝርፊያ መፈጸሙን ይገልጻል። መንግሥት ከዚህ ቀደም ይህ ቡድን በህወሓት ድጋፍ እንደሚደረግለት እና በትግራዩ ግጭትም ለህወሓት ወግነው ሲዋጉ ነበሩ ያላቸውን 'የኦነግ ሸኔ' ታጣቂዎችን መማረኩን አስታውቆ ነበር። ኦነግ-ሸኔ የሕዝብ 'ጠላት ነው' የቦረና አባ ገዳ የሆኑት ኩራ ጃርሶ ኦነግ-ሸኔን የሕዝብ ጠላት ነው ሲሉ ቡድኑን ማውገዛቸው ይታወሳል። አባ ገዳ ኩራ በታጣቂ ቡድኑ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ሠላማዊ ሰዎች በመገደላቸው ቡድኑን ጠላት ብሎ መፈረጁ እንዳስፈለጋቸው ተናግረዋል። የቦረና አባ ገዳ በማኅበረሰባቸው ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው ሲሆኑ የሚያስተላልፉትም መልዕክት ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው። ህወሓት ህወሓት በሽምቅ ውጊያ ወደ አገር መሪነት ከዛም ወደ የክልል አስተዳዳሪነት በመጨረሻም ወደ ሽምቅ ወጊያ ተመልሷል። ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ዋነኛው ተዋናይ ሆኖ የቆየው ህወሓት ባለፈው ጥቅምት ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ሰውነቱን አጥቶ እንዲሰረዝ ተደርጓል። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የንጉሡ አስተዳደር ወድቆ ወታደራዊው መንግሥት ወደሥልጣን መውጣቱን ተከትሎ ነበር የካቲት 11/1967 ዓ.ም የትጥቅ ትግል መጀመሩን ያስታወቀው። ለህወሓት የትጥቅ ትግል መነሻ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያቋቋሙት ማገብት (ማህበረ ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ) የተባለው መደበኛ ያልሆነ ቡድን ነበር። ማገብት በስምንት አባላት የተመሠረተ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በሪሁ በርሀ (አረጋዊ በርሄ ዶ/ር)፣ አምባዬ መስፍን (ስዩም መስፍን) እና አመሃ ፀሃዬ (አባይ ፀሃዬ) ተጠቃሽ ናቸው። ከደርግ ጋር የሚደረገው ጦርነት ወደ ሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ሲሸጋገር በየአካባቢዎቹ ያሉትን ሕዝቦች ይወክላሉ የተባሉ ድርጅቶችን ማቀፍ እንዲሁም ሊወክሉ ይችላሉ የሚባሉ እንዲቋቋሙ ህወሓት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። ይህንንም ተከትሎ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን)፣ ከኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ጋር በመጣመር ኢሕአዴግ የተባለውን ግንባር ፈጠረ። በህወሓት የበላይነት ይመራ የነበረው ኢሕአዴግ የደርግ መንግሥትን ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ ለ27 ዓመታት አገር መምራት ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን በግንባሩ ውስጥ ለዓመታት የቆየው ቅሬታ ስር እየሰደደና እየጎላ መጣ። በመጨረሻም ኢህአዴግ ከስሞ የብልጽግና ፓርቲ ሲተካው ህወሓት በአዲሱ ስብስብ ውስጥ ላለመግባት ከመወሰኑ ባሻገር "ውህደቱ ሕጋዊ አደለም'' በማለት ተቃውሞውን አስምቶ ነበር። ህወሓት ከፍተኛ አመራሮቹን ይዞ ወደ ትግራይ ካቀና በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የነበረው ግንኙነት ከመሻከር አልፎ ወደ ግጭት አምርቷል። ከ6 ወራት በፊት በተጀመረው ጦርነት የፌደራሉ መንግሥት 'ህወሓት አብቅቶለታል' ሲል አውጇል። የቡድኑ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች ተጠርጥረው የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ወራት ተቆጥረዋል። በርካታ የህወሓት አመራሮች በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውና ሌሎች ደግሞ መገደላቸው የአገሪቱ ሠራዊት መገለጹ ይታወሳል።
news-54915502
https://www.bbc.com/amharic/news-54915502
ትግራይ ፡ "መቀለ ያለው ትንሹ ወንድሜ መድኃኒቱ እያለቀ ነው" ሐና ዘርኣጽዮን
ትንሽ ወንድም አለኝ። ገና 11 ዓመቱ ነው። የሚጥል በሽታ አለበት። በዚያ ላይ የህብለ ሠረሠር በሽተኛ ነው። ቆሞ መራመድ አይችልም። በተከታታይ የሚወስደው መድኃኒት አለ። ተጨንቄያለሁ። ምክንያቱም መድኃኒቱ በቀላሉ አይገኝም። መድኃኒት ቤቶች ዝግ ናቸው። መድኃኒት ሳልክለትም ጦርነቱ ተቀሰቀሰ።
ትንሹ ወንድሜ መቀለ ነው የሚኖረው። ከቤተሰቦቼ ጋር። የሚገርመው ልክ ጦርነቱ ሊጀመር ዋዜማ በቪዲዮ አውርቼው ነበር። መድኃኒቱን እንደምልክለት ቃል ገብቼለትም ነበር። ወንድሜ የሚወስዳቸው መድኃኒቶች ውድ ናቸው። በዚያ ላይ ብዙውን ጊዜ መቀለ ያሉ መድኃኒት ቤቶች እነሱን መድኃኒቶች አይዟቸውም። ለቤተሰብ ብር ልኬ መድኃኒቱን አዲስ አበባ ሲሄዱ በዚያው እንዲገዙለት ቃል ገባሁላቸሁ። ገንዘቡን ቶሎ ብዬ ከዚህ ከምኖርበት ናይሮቢ ላኩላቸው። ሆኖም የላኩትን ገንዘብ ሳያወጡት ባንክ ቤቶች ተዘጉ። ብሔራዊ ባንክ በትግራይ የሚገኙ ከ600 በላይ የባንክ ቅርንጫፎች በሙሉ እንዲዘጉ ወሰነ። ቤተሰቦቼ ገንዘቡ አልደረሳቸውም። ወንድሜ መድኃኒቱ አልተገዛለትም። ተጨንቄያለሁ። ለነገሩ ገንዘቡ ቢደርሳቸው ኖሮም መድኃኒቱን አያገኙትም ነበር እያልኩ በግድ እጽናናለሁ። ምክንያቱም ወደ ትግራይ ማንኛውም በረራ ቆሟል። ይህ ማለት መድኃኒቱን ከአዲስ አበባ ለወንድሜ ሊያመጣለት የሚችል ሰው የለም። የመንገደኞች በረራ ሙሉ በሙሉ ቆሞ አሁን የአየር ክልሉ የወታደራዊ ጄቶች መናኸሪያ ነው የሆነው። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኖቤል ሎውሬት ዐብይ አሕመድ በትግራይ ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች እንዳይገኙ አስጠንቅቀዋል። የጦር ጄቶች ትግራይ ክልል የሚገኙ የስንቅና ትጥቅ ማከመቻዎችን እንዲደበድብ ትእዛዝ ሰጥተዋል። የትግራይ ክልል በበኩሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሰዎችን በእጅጉ ገድቧል። ገደቡ በአካባቢው ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ተከትሎ የመጣ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው በትግራይ ቢያንስ በስምንት ቦታዎች ጦርነት እየተደረገ ነው። ከእነዚህም አንዱ ሰሊጥ በማብቀል የሚታወቀው ሑመራ ነው። በዚህ የአጨዳና ምርት የመሰብሰቢያ ጊዜ ከአጎራባች ክልል አማራ የሚመጡ በርከት ያሉ ዜጎች ይሳተፋሉ። አንዳንዴ ሑመራ የሰሊጥ ሥራውን ሳስብ የኢትዮጵያ በብሔር ብሔረሰቦች እጣ ፈንታ እንዴት እንደተሳሰረ ማሳያ ሆኖ ይታየኛል። አሁን ግን እርስ በርስ ጥርጣሬውና ፍርሃቱ እንዳየለ ነው የምሰማው። በፌዴራል ፖሊስ እና በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች እንደሚነግሩኝ ከሆነ መሣሪያዎቻቸውን አስረክበው የግዳጅ እረፍት እንዲወስዱ እየተደረጉ ነው። ውሃ በፈረቃ ከ10 ቀናት በፊት ጦርነቱ ሲታወጅ የዓለም ትኩረት ሁሉ በአሜሪካ ምርጫ ላይ ሆኖ ነበር። ደንገት ከወዳጄ አንድ መልዕክት ደረሰኝ። "ሰማሽ የተፈጠረውን? ቤተሰቦችሽ ጋ ደውለሻል ለመሆኑ?" የሚል ይዘት ያለው መልዕክት። ወዲያውኑ መደዋወል ጀመርኩ። ቤተሰቦቼ የአንዳቸውም ስልክ አይሰራም። ኢንተርኔቱን ብለው የለም። ለካስ አኔን ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ትግራይ ውስጥ ከሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻችን ጋር ተቆራርጠናል። ይህ እንዴት አስጨናቂ እንደሆነ ላልደረሰበት ሰው እንዴት ማስረዳት ይቻላል? አሁን እጅግ እየናፈቀኝ ያለው ትንሹ ወንድሜ ነው። መናገር ስለማይችል በቤተሰቦቼ እገዛ በቪዲዮ እንዲሁ እያየሁ አዋራው ነበር። ላጫውተው እሞክር ነበር። አሁን በጣም ናፈቀኝ። ምንም ማድረግ አልቻልኩም። በናፈቀኝ ቁጥር ስልኬ ላይ ያለውን ፎቶውን አውጥቼ እያየሁ መቋቋም ያልቻልኩት ናፍቆቴን አስታግሳለሁ። የትንሹ ወንድሜን ፎቶ እያየሁ መጽናናት አልችልም። ምክንያቱም በሽታው አለ። ሕመሙን እያሰብኩ ምነው ይህ ጦርነት ቶሎ በቆመ ስል እቆዝማለሁ። ምነው ጦርነቱ ቶሎ በቆመና ትንሹ ወንድሜ መድኃኒቱን መውሰድ በቻለ። በዚያ ላይ ስንት ነገር አስቤ ነበር! ወደዚህ ወደ ናይሮቢ አስመጥቼው የተሻለ ሕክምና ማግኘት የሚችልበትን ዕድል እንዴት እንደማመቻች ሁሉ አስብ ነበር። በሕመሙ ምክንያት መራመድ ስለማይችል ዊልቸር ልገዛለትም እያሰበኩ ነበር። አሁን ሁሉም ሐሳቤ መና ቀርቷል። ቢያንስ ጦርነቱ እስኪቆም ድረስ ለወንድሜ ያለኝ ህልም እንዲቆም ሆኗል። ከዚህ የባሰው አስጨናቂ የሆነብኝ ግን ጦርነቱ ቢራዘምስ የሚለው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀረቡላቸውን የድርድር ሐሳቦች ገሸሽ አድርገዋቸዋል። ህወሓትም ቢሆን ጦርነቱን እስከመጨረሻው ከማካሄድ ላይመለስ ይችላል። ነገሩ እንዲያ ከሆነ ታዲያ ትንሹ ወንድሜ ምን ሊውጠው ነው? ቤተሰቦቼስ? በቀጣይ ቀናት የምግብ ዋጋ ይጨምር ይሆን? ከናካቴው የምግብ እጥረት ያጋጥም ይሆን? ቤተሰቦች እንዴት ነው ገንዘብ በእጃቸው ሳይኖራቸው መኖር የሚችሉት? ለምን ያህል ጊዜ? እንዴት ነው ሌላውስ ቤተሰቡ ከውጭ በሚልክለት ገንዘብ ኑሮውን ሚገፉ ቤተሰብ በቀጣይ ኑሮውን የሚገፋው? ገና ከአሁኑ የስንዴ ዱቄትና የነዳጅ እጥረት እያጋጠመ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ይህ ያስጨንቀኛል። ከዚህ ሁሉ የባሰው ደግሞ ውሃ ያለመኖሩ ነው። መቀለ ከአራት እስከ አምስት መቶ ሺህ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ ናት። ሆኖም የባንቧ ውሃ የምትመጣው በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ይህም ብርቅ ሆኖ የፈረቃ ሥርጭት አሁን ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። የውሃ ክፍፍል ሲቋረጥ ነዋሪዎች ስልክ ደውለው በጋሪ ውሃ ያስመጡ ነበር። አሁን ግን የስልክ ግንኙነት በመቋረጡ እሱም አገልግሎት ተቋርጧል። ያለ ውሃ ስንት ቀናት ማሳለፍ ይቻላል? ይህ አልበቃ ብሎ ደግሞ ሐሙስ ለታ ኤሌክትሪክ የሚያመነጨው ግድብ በጦር ጄት ተመቷል እየተባለ ነው። ይህም ነዋሪውን በጨለማ የሚያስቀር ነው የሚሆነው። ነገሩ ሁሉ አስጨንቆኛል። "ነጭ እንዳትለብሺ" እነዚህ ጭንቀቶቼ በቂ እንዳልሆኑት ሁሉ ሌላም ነገር ያስጨንቀኛል። ቤተሰቦቼ በሚኖሩበት ከተማ አደጋ ቢደርስስ? አይበለውና የአየር ጥቃት ቢዘንብስ? ልጅ እያለሁ የኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ሲካሄድ ትዝ ይለኛል። እናቴ ስትደብቀን። የጦር ጄቶች በመጡ ቁጥር በእሷ ቀሚስ ስንከለል ትዝ ይለኛል። እናቴ ነጭ ልብስ እንዳንለበስ ስትነግረን፤ በሰፈሩ ነጠላ አትልበሱ ሲባል ልጅ ብሆንም በደንብ አስታውሳለው። ነጠላ አትልበሱ ይባል የነበረው ቦምብ ጣይ ጄቶች በቀላሉ አይተው አደጋ ሊጥሉ ይችላሉ በሚል ነበር። የሚገርመው ይሄ ነጭ አትልበሱ የሚለው ነገር አእምሮዬ ላይ ተቀርጾ ከመቅረቱ የተነሳ እስካድግ ድረስ ፍርሃት ይሰማኝ ነበር። ካደግኩ በኋላ ነው አእምሮዬ "ኧረ ችግር የለውም" ብሎ ተደፋፍሬ መልበስ የጀመርኩት። የጦርነት ጠባሳ አእምሯዊ ጉዳቱ ከባድ መሆኑን የተረዳሁበት አጋጣሚ ነበር። ይሄ ታዲያ የእኔ ብቻ ጠባሳ አይደለም፤ ጓደኞቼ ትምህርት ቤታቸው ውስጥ ምሽግ ሲሰራ ያስታውሳሉ። ምሽጉ ይሰራ የነበረው በሌላ ትምህርት ቤት የኤርትራ አውሮፕላን ቦምብ ጥሎ ልጆች ላይ አደጋ በመድረሱ ነበር። ያኔ ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ይህንን መጥፎ ትዝታ እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ ማስታወስ አንሻም። ላይመለስ ጥሎን የሄደ፣ ከላያችን ላይ የተራገፈም መስሎን ነበር። ጦርነት እንዲህ ቅርብ ነው እንዴ? እኔና ጓደኞቼ ብቻ አይደለንም በዚህ ውስጥ ያለፍነው። የእኛ ወላጆችም ሆነ የእኛ አያቶች የሌላ የእነሱ ዘመን የጦርነት ትዝታ አላቸው። የመንግሥቱ ኃይለማርያም ጦርነት፣ የኃይለሥላሴ ጦርነት። ከጦርነት ወደ ጦርነት። የእኔ ከተማ መቀለ ብዙ ታሪኳና ትዝታዋ ከጦርነት ብዙም አይርቅም። ማብቂያ የሌለው ጦርነት፤ መቋጫ የሌለው አዙሪት። ያለፈው ዓመት የገና በዓል በመቀለ "እጮኛዬን ላገባው ቀጠሮ ነበረኝ" የሚገርመው በሚቀጥለው ወር ገና በዓልን ከቤተሰቦቼ ጋር ለማክበር ቀጠሮ ነበረኝ። በዚያውም ከእጮኛዬ ጋር ለመጋባት እያቀድን ነበር። እኔ ከዓመታት በፊት ወደ ናይሮቢ ስመጣ እሱ እዚያው መቀለ ቆየ። አሁን ጦርነቱ ድንገት መሀላችን ገባ። በእኔና በትንሹ ወንድሜ መሀል፣ በእኔና በቤተሰቦቼ መሀል፣ በእኔና በፍቅረኛዬ መሀል። ጦርነት ህልም ነጣቂ ነው። ይህንን ስል አባቴን አስታወሰኝ። አባቴ አናጺ ነው። እሱም እንደኔው ጦርነት ቆርጦታል። ሕልሙን። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲጀመር ድንገት ነበር ከእህቱ ጋር የተቆራረጠው። ኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበራቸውን ዘጉ። ለ20 ዓመት እህቱን እንዴት እንደሚናፍቃት ሲናገር ሰምቼዋለው። ለድፍን 20 ዓመት። ከ2 ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ሰላም ፈጥረው ለጊዜውም ቢሆን ድንበር ሲከፈት አባቴ እህቱን ሊያገኛት ጓጓ። ጉጉቱ እጅግ ከፍተኛ ነበር። መሞቷ ተነገረው። ሕልሙ ሟሸሸ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማስፈን ላደረጉት ጥረት ታላቁን የኖቤል ሽልማት በኦስሎ ሲቀበል እንዲህ ብለው ነበር። "ጦርነትን ለመቀስቀስ ጥቂት ሰዎች ይበቃሉ። ሰላም ለመፍጠር ግን መንደር፣ አገር መሰለፍ አለበት። ለእኔ ሰላም ማምጣት ልክ እንደ ችግኝ ነው የምመለከተው። ችግኝ እንዲጸድቅና ዛፍ እንዲሆን ውሃ ማጠጣትና አፈር መኮትኮት እንደሚሻው ሰላምም የማያወላዳ ቁርጠኝነት፣ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት እና ቀናነትን ይሻል።" እንደ አብዛኛው ሕዝብ እኔም ዐቢይ አሕመድና ደብረጽዮን ሰላም እንዲያመጡ እመኛለሁ። አለበለዚያ የጥላቻ ችግኝ ይጸድቃል። ያ ደግሞ አገር ያሳጣናል። ከዚህ ሁሉ የሐሳብ መኳተን በኋላ ታዲያ አሁንም ወደ አእምሮዬ የሚመጣው ትንሹ ወንድሜ ነው። መድኃኒቱን ማግኘት አለበት። ዶ/ር ዐቢይ፣ ዶ/ር ደብረጺዮን፤ ለትንሹ ወንደሜ መድኃኒቱን ስጡት።
54343330
https://www.bbc.com/amharic/54343330
ሕግ ፡ አዲሱ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ምን ይዞ ይመጣል?
ለ60 ዓመታት ገደማ በሥራ ላይ የቆየው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ እንዲሻሻል ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ የሚንስትሮች ምክር ቤት መስከረም 16/2013 ባካሄደው ስብሰባ መወሰኑ ይታወሳል።
ይህን ሕግ የማሻሻሉ ሥራ ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ሲከናወን የቆየ መሆኑን በዚሁ ሥራ ላይ ለአስር ዓመታት ከተሳተፉት ባለሙያዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሙሉወርቅ ሚደቅሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሕጉንማሻሻል ለምን አስፈለገ? ከ1954 ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውን ይህንን ለማሻሻል አስፈላጉ ከሆኑባቸው ምክንያቶች መካከል የተወሰኑትን የሕግ ባለሙያው አቶ ሙሉወርቅ ሚደቅሳ ለቢቢሲ አብራርተዋል። በ1987 ዓ.ም የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥተ ከጸደቀ በኋላ "ነባር ሕጎችን ከሕገ-መንግሥቱ ጋር ማጣጣም" የሚል ፕሮጅክት መጀመሩን የሕግ ባለሙያው ያስታውሳሉ። በዚህ ፕሮጅክትም የወንጀል ሕጉን እና የቤተሰብ ሕግን ጨምሮ በርካታ ሕጎች ተሻሽለዋል። የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግን የማሻሻሉ ሥራም የዚሁ ፕሮጅክት አካል መሆኑን ይጠቅሳሉ። በሕግ ሥርዓት ውስጥ ሁለት አይነት ሕጎች እንዳሉ የሚናገሩት አቶ ሙሉወርቅ፤ እነዚህም መሠረታዊ ሕግ እና የሥነ ሥርዓት ሕግጋት ይባላሉ። የእነዚህን ሕጎች ምንነት በተመለከተም "መሠረታዊ ሕግ መብት እና ግዴታን የሚደነግግ ሲሆን፤ የሥነ ሥርዓታ ሕግጋት ደግሞ የተደነገጉ ሕጎች ተግባራዊ የሚደረጉበት ነው" እንደይላሉ የሕግ ባለሙያው አቶ ሙሉወርቅ። ይህ እንዲሻሻል እየተደረገ ያለው ሕግም የሥነ-ስርዓት ሕግ መሆኑን ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ የወንጀል ሕጓን ያሻሻለችው በ1996 ዓ.ም ሲሆን አሁን የሚሻሻለው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ እና የማስረጃ ሕግጋት የወንጀል ሕጉ ማስፈጸሚያ መሆናቸውን ባለሙያው ይናገራሉ። "እናት ሕጉ ስለተሻሻለ የሥነ ሥርዓት ሕጉም መሻሻል አለበት። እንዲያውም ዘግይቷል። እስካሁን አገሪቱ ስትጠቀምበት የነበረው በ1954 የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ን ነው።" በቅርብ ዓመታት የወጡ አዋጆች የራሳቸውን የሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች ይዘው መውጣታቸውን የሚገልጹት አቶ ሙሉወርቅ፤ ለምሳሌም የጸረ-ሙስና አዋጁ እና የጸረ-ሽብር አዋጁ የየራሳቸውን የሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች እንዳሏቸው ጠቅሰዋል። ከዚህ አንጻርም "አዲስ የወንጀል ድንጋጌዎች በመጡ ቁጥር ዋናው የሥነ-ሥርዓት ሕግ ሊሻሻል ባለመቻሉ የራሳቸውን ሥነ ሥርዓት እየያዙ ወጡ። በዚህም የሥነ ሥርዓት ሕጉ ተበታተነ" በማለት አሁን የታሰበው ተግባር ይህንን ለማስቀረት ያለለመ መሆኑን ይናገራሉ። ያለውን የሥነ ሥርዓት ሕግ ማሻሻል አስፈላጊ ከሆኑባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ እነዚህን የተበታተኑትን የሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች አንድ ቦታ የመሰብሰበው እና የተጠቃለለ የሥነ ሥርዓት ሕግ እንዲኖር ማድረግ እንደሆነ ያስረዳሉ። "በአጠቃለይ ረቂቅ ሕጉ ሲተገበር አብዛኛውን ሥራ ለፖሊስ እና ለዐቃቤ ሕግ በመስጠት ፍርድ ቤት ላይ የሚኖረውን ጫና ይቀንሳል፣ ተጠርጣሪዎች እና ተከሳሾች ረዥም ጊዜ ፍትሕ ሳያገኙ የሚቆዩበትን ጊዜ ያስጥራል፣ በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን አስሮ ከመመርመር ይልቅ ምርመራ አከናውኖ ወደ መያዝ እንዲቀየር ያደርጋል" ይላሉ። ምን አዲስ ነገር ይዞ ይመጣል? የጥፋተኝነት ድርድር በዚህ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከዚህ ቀደም በአገሪቱ ሕግጋቶች ውስጥ የሌሉ አዳዲስ አሰራሮች መካተታቸውን አቶ ቀለምወርቅ ይናገራሉ። ከእነዚም መካከል አንዱ የጥፋተኝነት ድርድር (plea bargaining) ነው። የጥፋተኝነት ድርድር በዳበሩ የፍትሕ ሥርዓቶች ውስጥ በስፋት ይተገበራል የሚሉት የሕግ ባለሙያው፤ አንድ ግለሰብ ክስ ተመስርቶበት ዐቃቤ ሕግ ግለሰቡ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካለው ተጠርጣሪውን "ጥፋትህን እመን ይህን ያክል ፍርድ የወሰንብሃል" በሚል ያስማማል። ለምሳሌ በርካታ ክሶች የሚመሰረቱባቸው ተከሳሾች ይኖራሉ፤ ከእነርሱ ጋር ዐቃቤ ሕግ ሊደራደር ይችላል። በዚህም መሠረት ይህን ያህል ወንጀል ፈጽመሃል፤ በዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ማስረጃ አለኝ። ይህንን ይዘን ወደ ፍርድ ቤት ብንሄድ ክርክሩ እና የፍርድ ቤት ውጣ ውረዱ ብዙ ዓመት ይፈጃል፤ ስለዚህ የቀረቡብህን ክሶች እመን ዝቅ ያለ ቅጣት ይተላለፍብሃል የሚል ድርድር ሊካሄድ የሚችልብት ዕድል አለ። "ይህ ግን በፍርድ ቤት ስር የሚያልፍ ነው። ዐቃቤ ሕግ ድርድሩን ካካሄደ በኋላ ፍርድ ቤት ወስዶ ነው የሚያጸድቀው። ምክንያቱም አንድ ሰው ጥፋተኛ የሚባለው እና ቅጣት የሚጣልበት በፍርድ ቤት ብቻ ስለሆነ ድርድሩ ከዐቃቤ ሕግ ጋር ቢደረግም፤ ሂደቱ የጥፋተኝነት ድርድር ሥነ ሥርዓቱን ተከትሎ መካሄዱ በፍርድ ቤት መረጋገጥ አለበት" ይላሉ። ረቂቁ ተከሳሹ የጥፋተኝነት ድርድር ሲያደርግ የሕግ ባለሙያ ይዞ መሆኑ እንዳለበትም አስቀምጧል። ይህ የሚደረገው በፍርድ ቤት ላይ የሚኖረውን ጫና እና የክርክር ጊዜ ለመቀነስ መሆኑን የሕግ ባለሙያው ይናገራሉ። ተከሳሹም ጉዳዩ ፍርድ ቤት ከደረሰ ሊወሰንበት ከሚችለው ቅጣት ያነሰ ቅጣት ይሰጠዋል። ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶች ቦታ ያገኛሉ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተካተቱት አዳዲስ ጉዳዮች መካከል ሌላኛው ባህላዊ የፍትሕ ሥርዓቶች ወደ ወንጀል ፍትሕ ሥርዓቱ መካተታቸው ነው። "ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚያወጣቸው መመሪያዎች አንዳንድ ጉዳዮች በባህላዊ የፍትሕ ስርዓቶች ሊታዩ እንደሚችሉ አዲሱ የሥነ ሥርዓት ሕግ ያስቀምጣል" ይላሉ የሕግ ባለሙያው። ለምሳሌ በአንዳንድ ማህበረሰቦች ውስጥ አንድ ሰው ግድያ ፈጽሞ ፍርድ ቤት ሄዶ ተፈርዶበት ፍርዱን ጨርሶ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላም እርቅ ካልተፈጸመ ተበዳይ ፍትህ አልተሰጠኝም ብሎ ያስባል። በዚህም ፍትሕ መሰጠቱን ማረጋገጥ ስለማይቻል መሠረታዊ የሚባሉ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን የማይጻረሩ እስከሆነ ድረስ ከመደበኛ የፍትሕ ሥርዓቱ ውጪ በባህላዊ ሥርዓት ጉዳዮች መፍትሄ የሚያገኙበት አዲስ አሰራርን ያስተዋውቃል። ምን ይቀየራል? ሕጉን በማርቀቅ ሂደት ለረጅም ጊዜ የተሳተፉት አቶ ሙሉወርቅ እንደሚሉት፤ በረቂቅ አዋጁ የሚቀየሩ ጉዳዮች መኖራቸውን ይገልጻሉ። ከእነዚህም መካከል የዋስትና መብት፣ የጊዜ ቀጠሮ እና የቅጣት አፈጻጸሞች ላይ ለውጦች እንደሚኖር ጠቁመዋል። ብዙ ጊዜ ጠበቆች 'ድንበኛዬ ተጠርጥሮ የታሰረበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል አይለደም' ሲሉ ዐቃቤ ሕግ በተቃራኒው 'የዋስትና መብት መሰጠት የለበትም' የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ መስማት የተለመደ ነገር ነው። የሕግ ባለሙያው አቶ ቀለምወርቅ ሚደቅሳም የዋስትና መብት ብዙ አጨቃጫቂ ነገሮች እንደሉት ይናገራሉ። ይህ ረቂቅ አዋጅም አጨቃጫቂ የሚባሉ የዋስትና መብት ጉዳዮችን ግልጽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ይጠቅሳሉ። በኢትዮጵያ እስካሁን የተለመደው የገንዘብ ዋትስና መሆኑን በማስታወስም፤ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተጠርጣሪው በየቀኑ ወይም በየሳምንቱ ወደ መንግሥት ተቋም እየቀረበ ሪፖርት እያደረገ ከዚያ ውጪ ሥራውን እንዲሰራ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ይናገራሉ። መርማሪ ፖሊስ በያዘው ተጠርጣሪ ላይ ምርመራ ለማደረግ ፍርድ ቤትን በተደጋጋሚ የምርመራ ጊዜ ሲጠይቅ ይስተዋላል። ነባሩ የሥነ ሥርዓት ሕግ መደበኛው በሚባለው ወንጀል የ14 ቀን በጸረ-ሽብር ደግሞ የ28 የምርመራ ጊዜ ሊፈቀድ እንሚችል ያስቀምጣል። ይሁን እንጂ ነባሩ ሕግ ገደብ አያስቀምጥም። "ለምን ያክል ጊዜ ነው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ያሚያስቀምጠው የሚለው ላይ ገደብ የለም" ይላሉ። አዲሱ ሕግ ግን ለወንጀሎቹ ዝቅተኛ ወንጀል፣ መካከለኛ ወንጀል እና ከፍተኛ ወንጀል የሚል ደረጃ በማውጣት የምርመራ ቀን ብዛት እና ገደብ ላይ ጣራ ማውጣቱን ይናገራሉ። "ይሄ ከተከሳሾች መብት አንጻራ ጠቃሚ ድንጋጌ ነው። ለምሳሌ መካከለኛ ለሚባሉ ወንጀሎች መርማሪ ፖሊስ ከሁለት ጊዜ በላይ የምረመራ ጊዜ መጠየቅ አይችልም።" በተቻለ መጠን አንድ ተጠርጣሪ ከመያዙ በፊት ፖሊስ ማስረጃ እንዲሰበሰብ ጥረት የሚያደርግ ሕግ ነው ይላሉ አቶ ሙሉወርቅ። "ተጠርጣሪው ምርመራ እየተደገበት እንደሆነ አውቆ አራሱን ለመሰወር እና ማስረጃ ለማጥፋት የሚሞክርበት ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ ፖሊስ የምረመራ ሰራውን ጨርሶ ነው መያዝ ያለበት። ተጠርጣሪን ይዞ ማስረጃ የመፈለግ ሂደት መቀየር አለበት የሚል አካሄደን ይፈጥራል።" ነባሩ የሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ የቅጣት አፈጻጸም ዝርዝር ነገሮች የሉትም። ለምሳሌ ብዙ ጊዜ ተፈጻሚ ባይሆንም የሞት ቅጣትን ፍርድ ቤቶች እንደሚያስተላልፉ የሕግ ባለሙያው ይናገራሉ። ይህ የሞት ቅጣት በምን መንገድ ነው መፈጸም ያለበት? የሞት ቅጣት የተበየነበት ሰው የሞት ፍርዱ ወደ የእድሜ ልክ እስራት ሳይቀየርለት ወይም የሞት ቅጣቱ ተፈጻሚ ሳይሆንበት ለምን ያህለ ጊዜ ይቆያል? በሚሉት ጉዳዮች ላይ አዲሱ ሕግ ዝርዝር የአፈጻጸም ድንጋጌዎች ይዟል። ከሞት ቅጣት በተጨማሪ ዝርዝር የሆነ የገንዘብ ቅጣት እና የእስራት ቅጣት ላይ ዝርዝር የአፈጻጸም ድንጋጌዎችን መያዙን አቶ ቀለምወርቅ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
52933474
https://www.bbc.com/amharic/52933474
አዲስ አበባ፡ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለምን ተስፋፋ?
በኢትዮጵያ ያለውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለሚከታተል ሰው ባለፉት ጥቂት ቀናት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ ይችላል። አብዛኛው ቁጥር እየተመዘገበ የሚገኘው ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ነው።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በትናንትናው ዕለት ካወጣው መግለጫ መረዳት እንደተቻለው በመዲናዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1205 ደርሷል። በዚሁ ሪፖርት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡባቸው ክፍለ ከተሞች አዲስ ከተማ እና ልደታ ክፍለ ከተሞች ናቸው። ሁለቱ ክፍለ ከተሞች ባለፉት ጥቂት ቀናት በከተማው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን በፈረቃ ሲመሩ ቆይተዋል። አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአዲስ ከተማ እንብርት አካባቢ በልደታ፣ አራዳ፣ ጉለሌ እና ኮልፌ-ቀራንዮ ክፍለ ከተማዎች ይዋሰናል። ክፍለ ከተማው በአፍሪካ ጭምር ትልቅ ነው የሚባልለትን ገበያ መርካቶን ጨምሮ ትልቁ የአገሪቱ የአውቶብስ መናኃሪያም በዚሁ አካባቢ ይገኛል። "የአገር አቋራጭ አውቶብስ ተራ በክፍለ ከተማው አለ። ጠዋት ብቻ 4 ሺህ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ይሳፈሩበታል" ሲሉ የክፍለ ከተማው የበሽታው መከላከል እና መቆጣጠር አስተባባሪ አቶ ለበን ጸጋዬ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ስርጭት ለቫይረሱ በክፍለ ከተማው በፍጥነት መሰራጨት የተለያዩ መላምቶች ከዚህም ከዚያም ይወረወራሉ። ቀዳሚው አካባቢው የንግድ ማዕከል በመሆኑ የውጭ ሃር ጉዞዎች ሳይቋረጡ በፊት ብዙዎች ለንግድ ወደ ቻይና እና መካከለኛው ምስራቅ መመላለሳቸው ነው። ኑሯቸውን ለማሸነፍ ወደ መካከለኛው ምስራቅ በቤት ሠራተኛነት ሄደው የሚመለሱ ሰዎችም ቁጥር ቀላል አይደለም። በክፍለ ከተማው ወረዳ ሁለት የሚኖረው መስፍን ቀደም ሲል በልደታ ክፍለ ከተማ በከፍተኛ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ የተመዘገበበት አካባቢ "ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጋር የሚዋሰን እና ያለው የነዋሪው አኗኗር እና ትስስር ጥብቅ" መሆኑን ያነሳል። አቶ ለበን በበኩላቸው ኮሮናቫይረስ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ባለበት እና የሰዎች ንክኪ በሚበዛበት አካባቢ የመስፋፋት ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን በማስታወስ ክፍለ ከተማው ቀደም ሲል እንደ ኮሌራ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች በተደጋጋሚ መከሰቱን በምሳሌነት ያስታውሳሉ። ወደ አራቱም የአገሪቱ አቅጣጫዎች ለመሄድ ወደ ትልቁ አውቶብስ መናኃሪያ የሚያቀናው ህዝብ ቁጥር መጠን ከፍተኛ መሆን፤ በመርካቶ ያለው የሰዎች እንቅስቃሴ እና የንግድ ልውውጥ እንዲሁም በትንሽ ቆዳ ስፋት ብዙ ሰው የሚኖርበት አካባቢ መሆኑን በተጨማሪም በምክንያትነት ያነሳሉ። "ምንም የጉዞ ታሪክ እና ከታማሚ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች እንዲሁም በቫይረሱ ስለመያዛቸው ምንም ምልክት የሌላቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆን" ስርጭቱ እንዲስፋፋ ያደርጋል ያለን የአካባቢው ነዋሪ ፍቃዱ ደረጀ ነው። መሳለሚያ፣ መርካቶ፣ እና አውቶብስ ተራን የመሳሰሉ ሰዎች በብዛት በሚጎበኟቸው ቦታዎች እና ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የንግድ ልውውጡ በጥሬ ገንዘብ መሆኑንም ለስርጭቱ በምክንያትነት የሚያስቀምጡ አሉ። ጥንቃቄ "አሁን አሁን 99.9 በመቶው" የአዲስ አበባ ነዋሪ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል አድርጎ ከቤት ይወጣል ያለን መስፍን በሌላ በኩል "አንዳንዴ [ኮሮና] ያለም አይመስልም። ለወረርሽኙ መስፋፋት ስጋት ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ መርካቶ ነው። ሁሉም ነገር ከዚህ ቀደም እንደተለመደው ዓይነት ከመሆኑ የተነሳ ኮሮና ያለ አይመስልም" ብሏል። በዚህ ሃሳብ በንግድ ሥራ የተሠማራው ፍቃዱም ይስማማል። "እኔ መርካቶ ፖሊስ እየመታ ማስክ ያስደርጋል እንጂ ግፊያው እንደዚያው ነው። እንደውም ባለፈው [ቫይረሱ] መጣ የተባለ ጊዜ ማለት ነው። ሰዉ መንገዱ ሁላ ጭር እያለልን ነበር፤ አሁን አሁን ግን ኮሮና ምን ያመጣል እንየው እያሉ ነው። [. . .] ብዙም ሰው ኢትዮጵያዊያንን እየገደለ አይደለም በማለት ሰዉ ተዘናግቷል" ቫይረሱ ወደ አትዮጵያ በገባበት ሰሞን ህብረተሰቡ የነበረው ጥንቃቄ አሁን የለም። በየአካባቢው በበጎ ፈቃድ እጅ በማስታጠብ እና ትምህርት በመስጠት ሲሠሩ የነበሩ ሰዎች አሁን አይታዩም። በታክሲ ሰልፍ፣ በንግድ ማዕከላት፣ በሃይማኖት ተቋማት እና በሌሎች አካባቢዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እየተቀዛቀዘ ይገኛል። መላመድ እና ሥራቸውን አቋርጠው የነበሩ ሰዎች ወደ መደበኛ ሥራቸው እየተመለሱ መሆኑን ፍቃዱ አጫውቶናል። ስጋት ቫይረሱ በኢትዮጵያ ተገኘ ሲባል ዝግ የነበሩ ሱቆች መከፈት፤ ሰዎች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው መመለስ መጀመራቸው ስጋት እንደጫረበትም ፍቃዱ ይናገራል። ይህ ግን በአካባቢው የቫይረሱ ስርጭት ይጨምራል በሚል ብቻ አይደለም። ለሌሎች አካባቢዎችም ይተርፋል በሚል እንጂ። ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ጉዞ ለማድረግ አውቶብስ ተራን በየዕለቱ የሚረግጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እና ለመዲናዋ አዲስ አበባም ሆነ ለአገሪቱ የንግድ ማዕከል ወደ ሆነቸው መርካቶ የሚመላለሱ ሰዎች ስርጭቱን እንዳይጨምሩት ይሰጋል። "[በክፍለ ከተማው ቫይረሱ መጨመሩ] ስጋት አለው። አንደኛ መርካቶ ለሃገሪቱ የንግድ ማዕከል ናት ማለት ይቻላል። ወደ ተለያዩ ክልሎች ለመሄድም አውቶብስ ተራን መርገጥ ሊኖር ይችላል" ይላል ለበን። የእለት ገቢያቸውን በአካባቢው አግኝተው ወደ ሌሎች የከተማዋ ክፍሎች የሚያመሩትንም ቤቱ ይቁጠራቸው። ስለዚህ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ያለው የኮሮናቫይረስ መስፋፋት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለሌሎች የአዲስ አበባ አካባቢዎችም ሆነ ለመላው አገሪቱ ስጋት መሆኑን ያነጋገርናቸው ሰዎች በሙሉ የሚስማሙበት ነው። እርምጃዎች ካለው ስጋት ጎን ለጎን በአካባቢው በተደጋጋሚ ከሚሰማው አምቡላንስ ደምጽ በተጨማሪ የህክምና ባለሙያዎች ትምህርትም በስፋት እየተካሄደ ነው ብሎናል መስፍን። እያነጋገርነው ባለንበት ወቅት እንኳን በአካባቢው ህይወት ቢያልፍ ሳይመረመር ግብዓተ መሬቱ እንዳይፈጸም ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ነግሮናል፤ እኛም ትምህርቱ ሲሰጥ በስልክ እየሰማን ነበር። "ሰፈር ይደብራል። ፈጣሪ ይጠብቀን ትላለህ እንጂ ምንም አታደርግም። አሁን እናቶች [የምንነግራቸውን] እየሰሙ ነው። እኛም እያስተባበርን ነው። ፈጣሪ ይጠብቀን" ያለን መኖሪያው አብነት የሆነውና በአካበቢው ያሉ ሰዎችን እያስተባረ የሚገኘው ፍቃዱ ነው። • ቢል ጌትስ በክትባት ስም ክንዳችን ውስጥ ሊቀብሩት ያሰቡት ነገር አለ? በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ቫይረሱ በዝቶባቸዋል የሚባሉ አራት አካባቢዎች ተለይተዋል። ወረዳ 1 (በተለምዶ አብነት የሚባለው አካባቢ)፣ ወረዳ 2 (በተለምዶ መርካቶ የሚባለው አካባቢ በከፊል)፣ ወረዳ 7 (በተለምዶ አውቶብስ ተራ የሚባለው አካባቢ) እና ወረዳ 8 (በተለምዶ መርካቶ የሚባለው አካባቢ በከፊል) ናቸው። [መርካቶ በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ያርፋል።] ቫይረሱ ኢትዮጵያ ገባ ከተባለበት ከመጋቢት 5/2012 ጀምሮ ማህበረሰቡን እያስተማሩ እንደሚገኙ የሚገልጹት አቶ ለበን "ቤት ለቤት የሙቀት ልኬታ አሁን ሁለተኛ ዙር ጀምረናል። ሳል እና ሙቀት ያለባቸው እየተመረመሩ ነው። ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱ እና ሳል እና ትኩሳት ያላቸው ሰዎችም በተመሳሳይ ምርመራ እየተደረገላቸው ይገኛል" ብሎናል። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ጤና ቢሮ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳር የጤና ቢሮ ኃላፊ ናቸው። ". . .ከመላ አገሪቱ ከ60 እስከ 70 በመቶ ኬዝ አዲስ አበባ ይሆናል ተብሎ ነው" በማለት በከተማው ሊኖር የሚችለውን የቫይረሱ ስርጭት መጠን ግምት ያስቀምጣሉ። በኢትዮጵያ እስካሁን ከተመዘገቡት 1636 የኮሮናቫይረስ ህሙማን 74 በመቶ ወይንም 1205 ያህሉ ከአዲስ አበባ ናቸው። ግን ይህ ቁጥር የቫይረሱ ስርጭት ትልቁ መጠን ነው ተብሎ እንደማይገመት ዶክተር ዮሀንስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ቁጥሩ ገና የመስፋፋቱ ጫፍ ላይ አልደረሰም። ገና ነው ብለን ነው የምንጠብቀው። ጫፍ ይደርሳል የሚባልበትን ወቅት ለመለየት የተሰሩ ሞዴሎች አሉ። ይሄን ወር [ግንቦት] ጨርሰን ሰኔ መጨረሻ አካባቢ ዕድገቱ ጫፍ ላይ ሊደርስ ይችላል" ብለዋል። መጀመሪያ አካባቢ የነበረው እጅን መታጠብ እና መጠንቀቅን የመሳሰሉ ነገሮች ቢቀዛቀዙም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ ደግሞ ጨምሯል ብለዋል። ". . . እንደዚህ አይነት ወረርሽኝ ሲመጣ ረዥም ጊዜ ስለሚቆይ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖውን በማጤን ብዙ ነገሮች እንደስርጭቱ የሚቀየሩ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ሁሉም መጠንቀቅ እና ሌሎችንም መጠበቅ ያስፈልጋል" ይላሉ። አንዳንዶች በአዲስ አበባ የእንቅስቃሴ ገደብ ለምን አይጣልም ሲሉ ይጠይቃሉ። ዶክተር ዮሐንስ "በርካታ የአዲስ አበባ ህዝብ የዕለት ጉርሱን ሰርቶ የሚገባ ነው። የበለጸጉት ሃገራት ሞክረውት ያቃታቸው ነገር ነው። . . . የከተማውን እንቅስቃሴ ማቆም ማለት ሌላ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ነው የሚከተው።" በማለት እንደዚህ አይነት ነገር በእኛ አገር ሁኔታ የማይቻል መሆኑን ያብራራሉ። • አሜሪካ ሕግን በመጠቀም ጥቁር ዜጎቿ ላይ ግፍ ትፈፅማለች? ከዚህ ይልቅ እንደአማራጭ የተያዘው ቫይረሱ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች በወረዳ ወይንም በቀጠና ጠበብ ያለ ቦታ ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣል ስርጭቱን መቆጣጠር መሆኑን ኃላፊው ይገልጻሉ። "በሚከሰቱበት ብሎክ እና ቀጠና እንቅስቃሴዎችን በመግታት የአካባቢው ነዋሪዎች የሚያስፈልጋቸውን የዕለት ጉርስ የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው ብሎክ ቤዝድ የምግብ ባንክ እያቀረብን ልየታ እያደረግን ነው። አሁንም በዚያ እንቀጥላለን።" ሲሉ በልደታ ክፍለከተማ ለሁለት ሳምንት የተደረገውን የእንቅስቃሴ ገደብ ዓይነት እንደሚመርጡ ገልጸዋል። አሁን ቫይረሱ እየተስፋፋባቸው በሚገኝባቸው አካባቢዎች ካላቸው ባህሪ አንጻር ሊስፋፋ እንደሚችል ግምት እንደነበር ተናግረው "በአካባቢዎቹ በርካታ ናሙና እየወሰድን እንመረምራለን" ሲሉ ሃሳባቸውን ይደመድማሉ።
news-50191989
https://www.bbc.com/amharic/news-50191989
ግሬታ ተንበርግ፡ አዲስ የጥንዚዛ ዝርያ በአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ስም ተሰየመች
አዲስ የተገኘችው የጥንዚዛ ዝርያ በአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተምንበርግ ስም ተሰየመች። ግሬታ ተንበርግ የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ሰልፍ በመጥራት ያስተባበረች ታዳጊ ስትሆን፤ ሰልፉ ከአውስትራሊያ እስከ ኒውዮርክ፣ ከእስያ እስከ አፍሪካ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንደተሳተፉበት ተነግሯል።
ይህ ሰልፍ፤ የሠው ልጅ ያስከተለውን የዓለም ሙቀት መጨመር በመቃወም የተደረገ ትልቁ ሠልፍ ነው ተብሏል። የተመራውም በታዳጊዋ ግሬታ ተንበርግ ነበር። የ16 ዓመቷ ግሬታ በዘንድሮው የኖቤል የሠላም ሽልማትም ያሸንፋሉ ተብለው ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ነበረች። • በመላው ዓለም ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያሳተፈው ሰላማዊ ሰልፍ • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ በአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ስም የተሰየመችው 'ኒሎፕቶድስ ግሬቴ' የተሰኘችው ጥንዚዛ ቁመቷ ከአንድ ሚሊ ሜትር ያነሰች ስትሆን፤ ክንፍም ሆነ ዐይን የላትም። እንደ አንቴና ያሉ ሁለት ረጅም የአሳማ ዓይነት ጅራቶች አሏት። ተመራማሪው ዶክተር ማይክል ዳርቢይ ስያሜውን ለምን እንደመረጡት ሲናገሩ፤ በስዊድናዊቷ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች በጣም ከመደነቃቸው የተነሳ እንደሆነ ተናግረዋል። በአጭሩ 'ኤን ግሬቴ' የተባለችው ነፍሳት ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓዊያኑ 1960 በዊሊያም ብሎክ በኬንያ የተገኘች ሲሆን፤ ናሙናዎቹንም እአአ በ1978 በለንደን ለሚገኝ የተፈጥሯዊ ታሪክ ሙዚየም ለግሰዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሙዚየሙ ውስጥ ተቀምጣ ትገኛለች። ዶክተር ማይክል ስም ያልተሰጣቸው [ስም የለሽ] የሆኑ ዝርያዎችን በሚያጠኑበት ወቅት የእነዚህንም ነፍሳቶች ዝርያ ስብስብ ሲያጠኑ ነበር። ግሬታ ተንበርግ የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ የተቃውሞ እንቅስቀሴን መርታለች አዲስ የተገኘችውን ጥንዚዛ በታዳጊዋ ግሬታ ስም በመሰየም አካባቢን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ያደረገችውን አስደናቂ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት እንደፈለጉ ተመራማሪው አስረድተዋል። አሁን ጥንዚዛዋ በ'ኢንቶሞሎጅስቶች' [የነፍሳት ተመራማሪዎች] ወርሃዊ መፅሔት ላይ ስሟ በይፋ ሰፍሯል። ሙዚየሙ ውስጥ ያሉትን ጥንዚዛዎች ላይ ክትትል የሚያደርጉት ዶክተር ባርክሌይ በበኩላቸው፤ የተሰጠው ስም ተገቢ ነው ይላሉ። ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም "ያልተለዩ ዝርያዎች ሁል ጊዜ የመጥፋት እድላቸው የሰፋ ነው ፤ የሚጠፉትም ተመራማሪዎች ለእነሱ ስም ከመስጠታቸው በፊት ነው" ምክንያቱም የብዝሃነት እጦት ነው" ብለዋል። በመሆኑም ይላሉ ዶክተር ባርክሌይ "አዲስ ግኝቱ ለአደጋ የተጋለጡ ዝርያዎችን ለመጠበቅ ለአየር ንብረት ለውጥ ተግታ በሠራችው ታዳጊ ስም መሰየሙ ተገቢ ነው" ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል። ስማቸው ለእንስሳት መጠሪያ የዋለ ዝነኞች እነማን ናቸው? ለተመራማሪዎች አዲስ የተገኙ ዝርያዎችን ስያሜ መስጠት ቀላል አይደለም ፤ አዲስ ፈጣሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል። "አንድ ጥገኛ ተህዋስ የእውቁን ጃማይካዊ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኝ የቦብ ማርሌን ስያሜ አግኝቷል 'ግናሺያ ማርሌይ' በሚል። ሌላ የአሳ ዝርያም ከእንግሊዛዊው የእንስሳት ባህርይ፣ ዝግመተ ለውጥ እና የሥነ ሕይወት ተመራማሪ ሪቻርድ ዳውኪንስ ስም 'ዳውኪንሺያ' ተብሎ ይጠራል። በአንድ አነስተኛ ፓርክ የሚገኙ በሕይወት የሚገኙና የጠፉ ዝርያዎችም በእንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ዴቪድ አቶንቦሮው ተሰይመዋል። • የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዴቪድ አቶንቦሮው ተከታታይ በሆኑትና የተፈጥሮ ታሪኮችን በተመለከቱ ዘጋቢ ፊልሞች ይታወቃሉ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ተመራማሪዎቹ በሚያደንቋቸው ዝነኞችን እና እውቅ ሰዎች እንስሳትን ይሰይማሉ። ለምሳሌ በአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ እንደተሰየመችው 'ኤን ግሬቴ' የተሰኘች ይህችን ጥንዚዛ ወይም በእውቁ አሜሪካዊ ተዋናይና የአካባቢ ጥበቃ አምበሳደር ሊኦናርዶዲካርፒዮ ስም 'ስፒንታረስ ሊኦናርዶዲካርፒዮ' እንደተባለው ሸረሪት። በሌላ ጊዜ ደግሞ ዝነኞች በተለየ ከሚወዷቸው እንስሳት ጋር በማያያዝ ስያሜው ይሰጣሉ። 'ሌሙር' ተብለው የሚታወቁት እንስሳት በእንግሊዛዊው ተዋናይ እና ኮሜዲያን ጆን ክሊስ ስም 'አቫሂ ክሊሲ' ተብለው ይጠራሉ። ሌላኛው ደግሞ የእንስሳቶቹ መልክ ከዝነኞቹ ጋር ተቀራራቢነት ካለው በዚያ ሰው ስም ይሰየማሉ። ለምሳሌ ወርቃማ ፀጉር ያለው ዝንብ በአሜሪካዊቷ ድምፃዊና ተዋናይት ቢዮንሴ 'ስካፕሺያ ቢዮንሴ' ተብሎ ተሰይሟል። 'ኒኦፓልፓ ዶናልድ ትራምፒ' ም ተብሎ በአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ስም የተሰየመ የእሳት እራት አለ። ስያሜው በሥነ ሕይወት ተመራማሪው ቫዝሪክ ናዛሪ ከሁለት ዓመታት በፊት የተሰጠ ነው። የእሳት እራቱ ወርቃማ ጭንቅላት ያለው ሲሆን በአንፃራዊነት ትንሽ የመራቢያ አካል ያለው ነው። ባሳለፍነው ዓመት ሌላ እንስሳም በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ስም ተሰይሟል። እንስሳው በአሸዋ ውስጥ ጭንቅላቱን በመቅበር የሚታወቀው የውሃ ውስጥ እንስሳ ነው። 'ዘ ደርሞፊስ ዶናልድ ትራምፒ' የተባለው እንስሳ ይህንን ስያሜ ያገኘው ፕሬዚደንቱ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ነው። •የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል? የቤት እንስሳትም ቢሆኑ የራሳችሁን ስም ካለወጣችሁላቸው በስተቀር በሳይንሳዊ መንገድ የተሰጣቸውን ስም ይዘው መቀጠላቸው እሙን ነው። ታዲያ አንዳንዴ እንዲህ ዓይነት ስያሜ መስጠት አደገኛ ሊሆን ይችላል። ዐይነ ስውር የዋሻ ጥንዚዛ 'አኖፍታልመስ ሂትለሪ' ተብሎ በአውሮፓዊያኑ 1933 በጀርመናዊ አድናቂው አማካኝነት በናዚ ፓርቲ መሪና ፖለቲከኛ በነበረው አዶሊፍ ሂትለር ስም ከተሰየመ በኋላ ስሙን ይዞ ቀጥሏል።
43946081
https://www.bbc.com/amharic/43946081
ያልተነገረላቸው ትዝታዎችን ከዛኙ -"ቪንቴጅ አዲስ''
ከ1960ዎቹ መጨረሻ እስከ 1970ዎቹ አጋማሽ የነበረውን የኢትዮጵያን ገጽታ የሰነዱ መዝገቦች ጨለም ያሉ ትዕይንቶች ይበዛባቸዋል፡፡ ቀይ ሽብር፣ ነጭ ሽብር፣ ጅምላ እስር፣ ጅምላ ርሸና እያለ የሚከታተል ትርክት፡፡
መዝጋቢዎች ትልቅ ቦታ በሰጧቸው በእኒህ የታሪክ ጋራዎች የተከለሉ ወርቃማ ቤተሰባዊ ትዝታዎች፣ የፍቅርና መስዋዕትነት ታሪኮች፣ የጓደኝነትና አብሮነት ሁነቶችም ግን ነበሩ፡፡ ለእኒህ ሁነቶች ማስረጃ የሚሆኑ ፎቶዎች በብዙ ኢትዮጵያን እልፍኞች ውስጥ አሉ፡፡ ፎቶዎቹ ወደ አደባባይ እንዲወጡ እና ብዙሃን እንዲነጋገሩባቸው ለማድረግ "ቪንቴጅ አዲስ" - የአዲስ አበባ ትዝታ ድረ-ገጽ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፡፡ የአዲስ አበባ ትዝታ -ጽንሰት "ቪንቴጅ - አዲስ" -የአዲስ አበባ ትዝታ ፡- ዕድሜቸው 30 እና ከዚያ በላይ ያስቆጠሩ፣ በአብዛኛው በጥቁርና ነጭ ቀለም የተነሱ፣ ትናንትን ነጋሪ ፎቶዎች የተከዘኑበት ድረ-ገጽ ነው፡፡ የድረ-ገጹ መስራቾች ናፍቆት ገበየሁ፣ ፊሊፕ ሹትዝ እና ወንጌል አበበ የሚሰኙ ዕድሜያቸው በ20ዎቹ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው፡፡ እኒህ ወጣቶች ያልኖሩበትን ዘመን የሚያሳዩ ምስሎችን ለመሰብሰብ የተነሳሱት ከጎረቤት ሀገር ተሞክሮ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ከሁለት ዓመታት በፊት በእጃቸው የገባው የፎቶ መጽሃፍ የዐይን ገላጭነት ሚናን ተጫውቷል፡፡ የአዲስ አበባ ትዝታ መሥራቾች ከቀኝ ወደግራ ናፍቆት ገበየሁ፣ ፊሊፕ ሹትዝ እና ወንጌል አበበ። "መጀመሪያ ያየነው "ቪንቴጅ ዩጋንዳ" የሚባል መጽሃፍ ነው፤ በዚያ መጽሃፍ ላይ የቀደመውን ትውልድ የህይወት መልክ ለማሳየት በጥቁርና ነጭ የተነሱ ፎቶዎች ታትመዋል፡፡ እኛም ይሄንን ባየን ጊዜ 'ለምንድነው ይሄን የመሰለ ነገር አዲስ አበባ ላይ የማንሰራው?' ስንል ጠይቅን፣›› ስትል ጅማሮውን የምታስታውሰው ከመስራቾች አንዷ ናፍቆት ገበየሁ፣ 1960ዎቹና 70ዎቹ ከሚታወቁበት የውጥንቅጥ ትዝታ ወዲያ ያሉ መልካም ትዝታዎችን መዘከር ዋነኛ ግባቸው እንደነበረ ታወሳለች፣ ‹‹ያ ችግር በነበረበት ዘመንም ቢሆን ሰዎች ይጋቡ ነበር፣ ይማሩ ነበር፣ ሀገር ይጎበኙ ነበር፣ ጥሩና የደስታ ጊዜ ነበራቸው፤›› ስትል ታክላለች፡፡ ሌላኛው የድረ-ገጹ መስራች ስዊዘርላንዳዊው የንድፍ እና የፎቶ ጥበብ ባለሙያው ፊሊፕ ሹትዝ የናፍቆትን ሀሳብ በሚደግፍ መልኩ ፎቶዎቹ ለሱም ሆነ ለጎብኝዎች ያለፈውን ዘመን ሌላ ገጽታ ለማሳየት ያላቸውን ሃይል ሲገልጽ ‹‹በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የተነሱ ፎቶዎች አሉን፡፡ ሙሽሮችና ሚዜዎቻቸውን፣ ሰዎች ወደ ፎቶ ቤቶች ሄደው የተነሷቸው ዓይነት የሚያሳዩ ዓይነት ፎቶዎች፡፡ሁላችንም በዚያ ወቅት ስለነበረው ቀይ ሽብር ክስተት እናውቃለን፡፡ ቀይሽብር ጫፍ በነካበት በዚያ ወቅትም ቢሆን ሰዎች እየተደሰቱና እየሳቁ የተነሷቸውን ፎቶዎችን ማየት ስለዘመኑ የነበረኝን ዕይታ እንድቀይር የሚያደርግ ነው፣›› ይላል፡፡ ፊሊፕ የተናገረውን የሚደግፈው ፎቶ የዐይናለም እና ገነት ሰርግ በሚል በአራት ክፍል የተተረከው የፍቅር ታሪክ ነው። ያኔ ወጣቶቹ ዐይናለም እና ገነት የተጋቡት ቀይ ሸብር በበረታበት በ1971 ዓ.ም. ነው። ከዚያ በፊት ከ1966-1971 ዓ.ም. ባሉት ዓመታት ገነት እስረኛ ነበረች። ፎቶዎቹ ሁለት የፍቅር ወፎች ያሳለፉትን ፈተና፣ በጭንቅ ዘመንም ቢሆን ያለሙትን ጋብቻ ለማስፈፀም ያሳዩት ቆራጥነት ማሳያ ዐይነት ናቸው። ጥቁርና ነጭ መልካም ቀናት ‹የአዲስ አበባ ትዝታዎች› ድረ-ገጽ ከ1000 በላይ አዲስ አበቤዎች በአዘቦትና በልዩ ቀናት የተነሷቸው ፎቶዎች በአምድ በአምድ ተከፋፍለው ቀርበውበታል(ከ56 ቤተሰቦች የተገኙ ናቸው) ፡፡ከፎቶዎቹ የበረከቱቱ በ1960ዎቹና 70ዎቹ የተነሱ ቢሆንም እስከ 1920ዎቹ የሚወርዱ እስከ 1980 መጀመሪያ የሚዘልቁም አሉ፡፡ ከፎቶዎቹ ጀርባ ያሉ ታሪኮችን ጎብኝዎች እንዲረዱ የግርጌ ማስታወሻዎች ተካትተዋል፡፡ የአንዳንዶቹ የግርጌ ማስታወሻ ፈገግታን የሚደቅን፣ መደመምን የሚያጭር ዓይነት ነው፤ ለአብነት እኒህን ይመልከቱ፡፡ ስለወንድምና የአባቱ ሽጉጥ የዓይናለም እና ገነት ሰርግ የበቀለች ኪሮሽ ኢትዮጵያዊያን ጎብኝዎች ከፎቶዎቹ ጋር መንፈሳቸውን ለማዛመድ ቶሎ ይቀናቸዋል፡፡ ሆኖም ለሀገሪቱ እንግዳ ለህዝቡ ባዳ የሆነ ሰውም ቢሆን ፎቶዎቹን አይቶ ከመቼታቸው ጋር ከመቆራኘት የሚድን አይመስልም፡፡ ፊሊፕ ሹትዝ ይሄ የሆነው ከፎቶዎች ቀልብን የሚስብ ምስላዊ ይዘት፤ ትዝታ ቀስቃሽ ተፈጥሮ አንጻር እንደሆነ ይናገራል፡፡ የጥቁር እና ነጭ ፎቶች መናኸሪያ የሆነው የአዲስ አበባ ትዝታ ድረ-ገጽ ከዋናው ገጽ ጎብኝዎች በተጨማሪ ከ44ሺ በላይ የፌስቡክ ተከታዮች ከ2ሺ በላይ የኢንስታግራም ወዳጆች አሉት፡፡ አሰናጆቹ ከዚህ በላይ ጎብኝዎች እንደሚገኙ ተስፋ አላቸው፡፡ ሆኖም ገጹ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ የታለፉ መሰናክሎችንም አይዘነጉም፡፡ "የፎቶ ያለህ!"- ደጅ ጥናት ከአዲስ አበባ ትዝታዎች ገጽ ፊታውራሪዎች አንዷ የሆነችው ወንጌል አበበ፣ ፎቶ ግራፍ ታሪክን አትሞ ለማስቀመጥ ያለውን ሃይል ቀድማ እንደተረዳች ሚያሳብቁ ስራዎችን ከዚህ በፊት አቅርባለች፡፡ ከባልደረባዋ ናፍቆት ገበየሁ ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን መልክዐ ህይወት የሚሳይ የፎቶግራፍ ስብስብ ከዚህ በፊት አቅርበዋል፡፡ የቀደመ ልምድ ቢኖርም ቅሉ "ቪንቴጅ አዲስ አበባ"ን ለማዘጋጀት በሚጥሩበት ወቅት እልህ አስጨራሽ መሰናክሎችን ማለፍ ግድ ሆኖባቸዋል፤" አንዳንድ ሰዎች መጀመሪያ ላይ አያምኑንም፡፡ እነዚህን ፎቶዎች ወስዳችሁ ምን ልታደርጉ ነው? ሲሉ (በጥርጣሬ) ይጠይቃሉ፡፡ (አንዳንዶቹ) ዓላማችንና ዕቅዳችንን ስንነግራቸው በደስታ ሊረዱን ይስማማሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ፎቶ ሊሰጡን ከተስማሙ በኃላ ስለሚጠፉብን፣ እነሱን ማሳሳብ ግዴታ ይሆንብናል፡፡ በማሳሰብ እና መጨቅጨቅ መካከል ያለውን ስሜት ለማስታረቅ እየሞከርን ስራችንን ቀጥለናል፡፡ ከመሬት ተነስቶ ፎቶ ስጡኝ ብሎ መጠየቅ ከባድ ነው›› ትላለች ወንጌል፡፡ ሰዎችን ከማግባባት በተጨማሪ፣ የተገኙ ፎቶዎችን ወደ ዲጂታል ቀይሮ ለመሰነድ ያለው ሌላ ልፋትም እንደማይዘነጋ አሰናጆቹ ይናገራሉ፡፡ በዚህ ሂደት ያለፉ ፎቶዎች የሰዎች መነጋገሪያ እና መማሪያ ሲሆኑ ማየት የአሰናጆቹ እርካታ ምንጭ እንደሆነ ይታመናል፡፡ አንዳንዴ ራሳቸው 'የአዲስ አበባ ትዝታ' አዘጋጆችን የሚመስጡ፣ ዘመንን በማወዳዳር ጥያቄ እንዲጭሩ የሚያደርጓቸውን ፎቶዎች የሚያገኙባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ወንጌል አበበ፣ በደርግ ጊዜ ወደ ሆላንድ ሀገር ተሰደው የኢትዮጵያዊነት ዜግነታቸውን ሳይፈልጉ የቀየሩበትን አፍታ እያነሱ ዛሬም ድረስ በዐይናቸው ዕምባ ስለሚቋጥረው ጋሽ ስማቸው ስለሚባሉ የመርከብ ካፒቴን ስታስብ የተገለጸላትን እውነታ እንዲህ ትገልጸዋለች፣ "ዜግነቴን እንድቀይር ጊዜው አስገደደኝ እያሉ ዕምባ ሲተናነቃቸው ሳይ ገረመኝ፡፡ አሁን ያለው ጊዜ ተገላባጭ ነው፡፡ በዚህ ዘመን ያለ ወጣት መሄድ ፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያዊነታችን ያለን ኩራት ቀንሷል፡፡ (ጋሽ ስማቸው) እምባ እየተናነቃቸው ይሄንን ሲናገሩ የተማርኩት ይሄንን ነው፡፡" "የአዲስ አበባ ትዝታ" ራዕይ በተመሰረተ በሁለት ዓመታት ውስጥ የበርካቶችን ቀልብ የሳበው ድረ-ገጽ መስራቾች፣ ተጨማሪ ወዳጆችን ለማፍራት ዕቅዶችን ሰንቀዋል፡፡ ናፍቆት ገበየሁ የሰበሰቧቸው ፎቶዎች የብዙሃንን ዐይን እንዲያገኙ መላ እየዘየዱ መሆኑን ስታጋራ ‹‹በቀጣይ ዓመት ኅዳር 100 ፎቶዎችን የያዘ መጽሃፍ ለማሳተም አቅደናል፡፡ መጽሃፉ የዚያን ዘመን ሁኔታዎች ሚገልጹ አንቀጾች አብሮ ይይዛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ሀገራት እየዞርን የልምድ ማካፈል ስራ እንሰራለን፣›› ትላለች፡፡ ፊሊፕ በበኩሉ አሁን ትኩረቱን በአዲስ አበባ ላይ ብቻ የሆነው ድረ-ገጽ የሌሎች ከተሞችን ትዝታዎች በሚካትት መልኩ ለማወቃር ስለታሰበ ውጥን አጫውቶን ሆኖም ስራው ጉልበትና ጊዜን የሚወስድ ከመሆኑ አንጻር የበጎ ፈቃደኞችን ትብብር እና የለጋሾችን ተሳትፎም እንደሚፈለግ አልሸሸገም፡፡ "ቪንቴጅ -አዲስ" የትዝታ ጥግ ብቻ አይደለም። ያልታየ ገፅን ገላጭ፣ ከጭንቅ ዘመን ጀርባ ያሉ ብሩህ አፍታዎችን የሚያሳይ ሶስተኛ ዓይንም ጭምር እንጂ። በሁላችንም ቤት ግድግዳ ላይ እነኝህ ብርሃናማ ትዝታዎችን የመዘገቡ ጥቁር እና ነጭ ፎቶዎች እንደሚኖሩ እሙን ነው። ታሪክ እንደ ፎቶዎቹ ሁሉ ጥቁር እና ነጭ ነው። የጠቆሩ ክስተቶችን እንደመመዝገቡ የፈኩ ግለሰባዊ ትዝታዎችንም አትሟል-የኃለኞቹ በተራቸው ለዓይን እንዲበቁ ግን "የቪንቴጅ አዲስ አበባ" ዓይነቶቹ የትዝታ ካዝናዎች በእጅጉ ሳያስፈልጉን አይቀርም።
news-55421932
https://www.bbc.com/amharic/news-55421932
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በተፈጸመው ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ገለፁ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ማክሰኞ ሌሊት ለረቡዕ አጥቢያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና አምንስቲ ኢንተርናሽናል ገለፁ።
ቢቢሲ በተጨማሪ በጥቃቱ አካባቢ የነበሩ የዓይን እማኞችንና በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችን በማናገር ለመረዳት እንደቻለው 120 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ በጥቃቱ በትክክል ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ ለመግለጽ ባይችሉም ቁጥሩ "በጣም ከፍተኛ" እንደሆ ለቢቢሲ አረጋገጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ዛሬ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ላይ በመተከል ስለደረሰው ግድያ "እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል። በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ" ያሉ ሲሆን፣ መንግሥት ችግሩን ከሥሩ ለመፍታት " አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ አድርጓል" ብለዋል። ይህ ጥቃት በቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዳከመ መሄዱን እንደሚያሳይም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል። የአምንስቲ ኢንተርናሽናል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተገደሉትን ሰዎች አስመልክቶ ባወጣው መለግጫ "እጅግ አሰቃቂው ግድያ በክልሉ የሚኖሩ አማራዎች፣ ኦሮሞዎችና ሺናሻዎች ላይ ያነጣጠረ ነው። ይህ መንግሥት ብሔር ተኮር የሆነ ግድያን ለማስቆም በፍጥነት ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ የሚያሳይ ነው" ብሏል። ኮሚሽኑ ጥቃቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የታጠቁ ኃይሎች በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ በተባለው ቀበሌ ውስጥ ጥቃቱን ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ላይ መሆኑንና ጠቅሷል። ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ሞት ምክንያት የሆነው ጥቃት የተፈጸመው የጥቃቱ ሰለባዎች በእንቅልፍ ላይ በነበሩበት ወቅት ቤቶችን በማቃጠልና በተኩስ መሆኑም ተገልጿል። አምንስቲ ከጥቃቱ ከተረፉ መካከል አምስት ሰዎች እንዳነጋገረና ከእነዚህ ሰዎች አንዱ የቡለት ዞን ነዋሪ እንደሆኑ አሳውቋል። በተጨማሪም ሁሉም ድርጅቱ ያነጋገራቸው ሰዎች የታጠቁ የጉሙዝ ብሔር ተወላጆች የአማራ፣ ኦሮሞና ሺናሻ ብሔር ተወላጆችን ቤት እየነጠሉ ጥቃት እንዳደረሱ ተናግረዋል። ጥፋተኞች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አምስት አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ሥር ማዋሉን ትናንት ምሽት በክልሉ የመገናኛ ብዙኀን ላይ ይፋ አድርጓል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ቶማስ ኩዊ፣ የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አድጎ አምሳያ፣ አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፣ የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር፣ የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባንዲንግ ማራ፣እንዲሁም አቶ አረጋ ባልቢድ የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል። ኢሰመኮ ጥቃቱን በተመለከተ ተጎጂዎችንና ሌሎችንም በማነጋገር ባደረገው ማጣራት ጥቃቱ ለተፈጸመበት ቀበሌ የተመደበ የፖሊስ ወይም የፀጥታ ኃይል አለመኖሩን መረዳቱን አመልክቷል። ጥቃቱ የተፈጸመባት በኩጂ ቀበሌ ከወረዳው መቀመጫ ቡለን ከተማ 90 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኝ መሆኗን ጠቅሶ፤ በቀበሌው የሺናሻ፣ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ይኖሩባታል። አምነስቲ እንዳነጋገራቸው አምስት ሰዎች ምስክርነት ከሆነ ደግሞ ጥቃት አድራሾቹ ቤቶችን አቃጥለዋል፤ ሰዎችን በስለትና በጥይት ገድለዋል። እስካሁን ድረስ ቢያንስ 100 ሰዎች እንደተገደሉ ተዘግቧል። የሞት ቁጥሩ አሁንም ሊጨምር እንደሚችል አምነስቲ ያሳስባል። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚከታተለው ድርጅት መንግሥት ይህን 'አሰቃቂ ግድያ' እንዲመረምር ጥሪ አቅርቧል።"ጥቃት አድራሾቹ ለፍትህ መቅረብ አለባቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት መሰል ድርጊቶች ድጋሚ እንዳይከሰቱ ሊከላከል ይገባል" ብለዋል የድርጅቱ ኃላፊ። "አምነስቲ ኢንተርናሽናል በግሉ የአጥቂዎችን ማንነት ማረጋገጥ ባይችልም፤ ጥቃቱ በሥፍራው የሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ይገመታል። ከመስከረም ወር ጀምሮ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የሚኖሩ አማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ሺናሻዎችና አገዎች ላይ ያነጣጠረ ተከታታይ ጥቃት እየተፈፀመ ነው።" ኮሚሽኑ በበኩሉ በቡለን ሆስፒታል 36 ተጎጂዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑና ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ በጥይት ሌሎቹ በቀስት የቆሰሉ መሆናቸውን አረጋግጧል። "በተጨማሪም ጥቃት የደረሰባቸውን ሰዎች ሰዎች ሁኔታ የሚያሳዩና የሚረብሹ የፎቶግራፍ ማስረጃዎች ደርሰውኛል" ሲል ገልጿል። በጥቃቱ በሰው ሕይወትና በአካል ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የደረሱና የተሰበሰቡ ሰብሎች በእሳት እንዲወድሙ መደረጋቸውን ኢሰመኮ አመልክቶ፤ ቢያንስ 18 ያህል የእህል ክምሮች ሲቃጠሉ የተመለከቱ አንድ ተጎጂን በእማኝነት ጠቅሷል። ጥቃቱ ከበኩጂ ቀበሌ በተጨማሪ በጨላንቆና ዶሼ ቀበሌዎችም ቤቶች እየተቃጠሉ እንደሆነ ለኮሚሽኑ የተላኩ መረጃዎች እንዳሉ በመግለጽ፤ በድባጤ ወረዳ ዶንበን ቀበሌ ስጋት የገባቸው ነዋሪዎች ከጥቃቱ በኋላ ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆናቸው መረዳቱን አመልክቷል። ኢሰመኮ እንዳለው አካባቢው የተመደበው የመከላከያ ሠራዊት ከጥቃቱ ቀደም ብሎ የፌዴራልና የክልሉ አመራሮችን ለማጀብ ስፍራውን ለቆ መሄዱ ተከትሎ ጥቃት መፈጸሙናን እስከ እኩለ ቀን መቆየቱ ተነግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ታህሳስ 13/2013 በመተከል በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር በአካባቢው ሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ተነጋግረው ነበር ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ተጎጂዎች እንደሚሉት በጥቃቱ ከሞቱ ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ የሺናሻ ተወላጆች ናቸው። ነዋሪዎቹ ጨምረውም በጥቃቱ በስምና በመልክ የሚያውቋቸው የበኩጂ ቀበሌ ነዋሪዎች ጭምር መሳተፋቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጂዎች ገልጸዋል። ኢሰመኮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚከሰቱ ጥቃቶችን በተመለከተ የፌዴራሉና የክልሉን መንግሥታት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንዲያደርጉ ሲያሳስብ መቆየቱን ጠቅሶ "ይሁንና ጥቃቶቹ በመልክና በስፋት እየተባባሱ መጥተዋል" ብሏል። ኮሚሽኑ በጥቃቱ ላይ ተገቢው ማጣራትና ጥቃቱን ባለመከላከልም ሆነ በሌላ መልኩ ጥቃቱን የፈጸሙና ያባባሱ ሰዎችን ሕግ ፊት የማቅረብ ሂደት ከወዲሁ እንዲጀመር አሳስቧል። ጨምሮም በአካባቢው የሚገኘውን የፀጥታ ኃይልና መዋቅር የሰዎችን ደኅንነት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በከፍተኛ ደረጃ በአፋጣኝ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርቧል። የአካባቢው ባለስልጣናት ጥቃቱን የሚፈጽሙት ኃይሎችን "ጸረ ሠላም" ከማለት ውጪ ማንነታቸውና የጥቃቱ አላማ በግልጽ አይታወቅም። በተለያዩ ጊዜዎች በጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች የተለያየ ቁጥር ያላቸው በጥቃቶቹ ተሳትፈዋል የተባሉ ታጣቂዎች መገደላቸው ሲዘገብ ቆይቷል። የግድያውን እውነተኛ መንስዔ የሚያጣራ ኮሚቴ ይቋቋም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ፣ ኢዜማ በመተከል የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ ባወጣው የሀዘን መግለጫ ላይ ክልሉ የዜጎች መሰረታዊ መብት የሆነውን በሕይወት የመቆየት መብት ማስከበር ባለመቻሉ እና ድርጊቱ እየተደጋገመ በመምጣቱ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እስካሁን የተፈጸሙት አሰቃቂ ወንጀሎችን ክልሉ ለምን ማስቆም እንዳልቻለ እውነተኛ መንስዔ የሚያጣራ ኮሚቴ አቋቁሞ በአፋጣኝ ተጠያቂነትን እንዲያሰፍን ጠይቋል። አክሎም የፌደራል መንግሥት በሕግ አግባብ ጣልቃ በመግባት የዜጎቹን ሕይወት የመጠበቅ እና ሕግ የማስከበር ሥራውን ከማስጠበቅ በተጨማሪ አጥፊዎችን እና በክልሉ ያሉ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮችን ተጠያቂ እንዲያደርግ አሳስቧል። በአካባቢው ለወራት በዘለቀው ጥቃት ሳቢያ ጸጥታውን ለመቆጠጠርና በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጸሙትን ጥቃቶች ለማስቆም ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ የፌደራል መንግሥት ጦር ሠራዊትና የክልሉ የጸጥታ አካላት የተካተቱበት ኮማንድ ፖስት ተደጋጋሚ ጥቃት በሚፈጸምባቸው አካባቢዎች መዋቀሩ ይታወሳል። ነገር ግን አሁንም ድረስ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፉ ተከታታይ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ነው። አሁን የተፈጸመውና ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ጥቃት በአካባቢው ከተፈጸሙት ሁሉ የከፋው እንደሆነ ይነገራል።
news-48735774
https://www.bbc.com/amharic/news-48735774
ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የአማራ ክልል ገለፀ
በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ከተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ግድያ ጀርባ አሉ ተብለው የተጠረጠሩት ብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የክልሉ የሰላም ግንባታና ህዝብ ደኅንነት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገደቤ ኃይሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በትናንትናው ዕለት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ብርጋዲየር ጄኔራሉ በልዩ ኃይሎች ታጅበው እንደመጡና በመጀመሪያም የርዕሰ መስተዳደሩ አጃቢዎች ላይ ተኩስ እንደከፈቱ፤ ቀጥለውም የክልሉ አመራሮች ላይ የተኮሱ ሲሆን በዚህም ሦስቱ እንደተመቱ አቶ ገደቤ ይናገራሉ። • ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው •ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ •መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች "ጥቃቱ በከፍተኛ ደረጃ የተቀነባበረ ነው" ያሉት አቶ ገደቤ የፀጥታ ቢሮ፣ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮና የአዴፓ ጽህፈት ቤት ላይም ጥቃት እንደደረሰ ገልፀዋል። "ጥቃቱ ያልተጠበቀ ነው" የሚሉት አቶ ገደቤ በወቅቱም የክልሉ ፀጥታ ኃይል አካባቢውን ለመቆጣጠር ጥረት ባደረገበት ወቅት ብርጋዲየር ጄኔራሉ እንዳመለጡ ገልፀው፤ ከርዕሰ መስተዳድሩና ከአማካሪያቸው በተጨማሪ አጃቢዎቻቸው የተገደሉ ሲሆን እስካሁን ባለው ሁኔታ የሟቾች ቁጥር እንደማይታወቅ ገልፀዋል። በባህርዳር ሁኔታዎች ቢረጋጉም የርዕሰ መስተዳድሩን ሞት ተከትሎ ከተማዋ በድንጋጤ መዋጧን አቶ ገደቤ ተናግረዋል። "ርዕሰ መስተዳድሩ ለክልሉ ህዝብ ሌት ተቀን የሚሰራ ሰው ነበር፤ እንዲህ ባለ ሁኔታ መሰዋቱ በጣም አስደንጋጭና አሳዛኝ ነው" በማለት አቶ ገደቤ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-50909604
https://www.bbc.com/amharic/news-50909604
#8 እሷ ማናት፡ "አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ"- ሐና ተክሌ
ሐና ተክሌ እባላለሁ። አዲስ አበባ አብነት፣ ቀበሌ 28 አካበቢ ነው ተወልጄ ያደግሁት። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ግን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄጄ ኑሮዬን በዚያ አድርጌያለሁ። ባለትዳርና የሦስት ልጆች እናት ነኝ።
አትችይም የሚሉኝ ሰዎች ሁሌም ለሌላ ተጋድሎ ያነሳሱኛል። በ2004* ሂልኮ የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነበርኩ። ሁሌም የራሴን ሥራ መስራት እፈልግ ስለነበር በርካታ መጽሐፍትን ሳነብ የሕይወቴን መስመር ቀየርኩ። የሕይወት መስመሬ በትምህርት ብቻ አለመሆኑን ስረዳ የተለያዩ ነገሮችን በአማራጭነት መመልከት ጀመርኩ። ያኔ እጄ ላይ ከወደቀው እድል አንዱ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ነው። በተለይ እናቴ ያሳደገችኝ ብቻዋን መሆኑ ወደዚህ ሥራ እንድገባ ምክንያት ሆኖኛል። • "የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ላይ የሚለወጡ ነገሮች ይኖራሉ" የጠ/ሚ የኢኮኖሚ አማካሪ እናቴ ስድስት ልጆች ነበሯት እኔ ከሦስቱ ጋር ነው ያደግሁት። አምስተኛ ልጇ ነኝ። ልጆቿን ለማኖር ለረዥም ጊዜ በሥራ የኖረችው ዱባይ ነበር። ሁሌም የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ከትምህርት መልስ እናቶቻቸው ምሳ አዘጋጅተው፣ ቡና አጫጭሰው ሲጠብቋቸው እናታችን አጠገባችን ስለሌለችና ይህንን ማየት ባለመቻሌ አዝን ነበር። እንደ ሌሎች ልጆች እናቶች ቤት ቡና ቀራርቦ እናቴ እንድትጠብቀን የማድረግ የልጅነት ሕልሜ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ስሰማ ልቤ ውስጥ የነበረው ሰርቼ ውጤታማ ብሆን እናቴን ከዱባይ አምጥቼ ቤት ስገባ ዘወትር ባገኛት የሚለው ሀሳብ ነው ያነሳሳኝ። ከዚያም በዚሁ ሥራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጓዝኩ፤ ደቡብ አፍሪካ የሄድኩት በአጋጣሚ ነው። ለሁለት ሳምንት ለሥራ በሄድኩበት ነው እዚያው የቀረሁት። የመጀመሪያውን አንድ ዓመት ወጣ ገባ እያልኩ ቆየሁ። ከዚያ በኋላ ግን ጠቅልዬ እዚያው መኖር ጀመርኩ። ወደ ደቡብ አፍሪካም የተጓዝኩት እዚያ ደንበኞችን ለማፈፍራት ነበር። በመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ጉዞዬ ቢዝነሱ ስኬታማ ሆኖ ሰፍቶ ነበር። እስከ 2009 ድረስም ስሰራ ቆይቻለሁ። በኔትወርክ ማርኬቲንግ ውስጥ ከገንዘብ በተጨማሪም የአመራር፣ የተግባቦት፣ የሽያጭና አስተዳደር ክህሎቶችን አግኝቼበታለሁ። ኔትወርክ ማርኬቲንግ ብዙ አስተምሮኛል። ማግኘትና ማጣት ብዙ አስተምሮኛል። • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት በራስ መተማመኔን የጨመረውም እርሱን እየሰራሁ ነው። ይህ የሥራ ሕይወት የተለያዩ በሮች እንዳሉትና በየትኛውም መንገድ ብጓዝ ስኬታማ እንደምሆን ያየሁበትም ነው። 2009 ላይ ግን ይህንን ሥራ አቁሜ ሌሎች ሥራዎችን ጀመርኩ። ከሕንድ እቃዎችን እያስመጣሁ ለቸርቻሪዎች መስጠት ጀመርኩ። በእርግጥ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥራዎችንም ሰርቻለሁ። ትርፍና ኪሳራውን አይቼ በ2015 ላይ አቆምኩት። በእርግጥ ሥራውን ያቆምኩት ስለከሰርኩ ነው ብል ይሻላል። ትዳርና ሐና 2013 ላይ ትዳር መስርቼ ወዲያው የመጀመሪያ ልጄን ወለድኩ። ልጆች ስወልድ ለልጆቼ የተሻለ ጥሪት የመቋጠር ፍላጎት በብርቱ ፈተነኝ። ባለቤቴ ጋቦናዊ ሲሆን የህይወት እቅዱ በሙሉ ተምሮ ስኬታማ መሆን ነው። የሒሳብ ትምህርት ያጠና ሲሆን ያን ጊዜ ሦስተኛ ዲግሪውን እየሰራ ነበር። ስንጋባ 35 ዓመቱ ነበር። እሱም 40 ዓመት ሳይሞላው ፕሮፌሰር ለመሆን በማለም እየጣረ ነበር። የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ክፍያ ደሞዙን ሳሰላው ባሌ በሚያገኘው ገንዘብ ልኖረው የምፈልገው ህይወት ሩቅ መሆኑ ተሰማኝ። ስለዚህ ከ2013 ጀምሮ የልቤን ፍላጎት ይዤ በየቀኑ አዳዲስ የንግድ ሀሳቦችን እመለከት ጀመር። ከዚያ እርሱ ከሥራ ወደቤት ሲመለስ ያገኘኋቸውን የንግድ ሀሳቦች እንመካከርባቸዋለን። ሁለተኛ ልጄን ከወለድኩ በኋላ ቢትኮይንን ተዋወቅሁ። 2015 ነሐሴ ወር ላይ ስለቢትኮይን ሰምቼ ለባለቤቴ ብነግረውም ሊቀበለኝ አልቻለም። • ስድስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በጣና እምቦጭ ዙሪያ ስለቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ ልታስረዳኝ የሞከረችውን ልጅ ለስድስት ዓመት ልጅ እንደምታስረጂ አድርገሽ አስረጂኝ ብያት ብታስረዳኝም አልገባኝም ነበር። ጎግል ላይ በቀላሉ መረዳት የሚቻልበት መንገድን ጠይቄ ያገኘሁት መረጃ ግን ረዳኝ። ባለቤቴ የዘወትር ውትወታዬ ሲበረታበት አንድ ለሊት ቁጭ ብሎ ማንበብ ጀመረ። ባነበባቸው ጥናቶች ውስጥ የተሳተፉ ዩኒቨርስቲዎች፣ የተደረጉ ጥናቶች ቢዝነሱ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ አሳዩት። በኋላ ትኩረት ልሰጠው እንደሚገባ ነገረኝ። ከዚህ በኋላ ነው ቀላል የምለውንና አቅሜ የሚችለው ላይ የተሳተፍኩት። ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ 'ማይኒንግ' [በቢትኮይን ውስጥ ያለ ሥራ] ላይ መስራት ጀመርኩ። በዚህ ሥራ ላይ ተሰማርቼ ገና መስመር ሳይዝ ባለቤቴ በካናዳ ኦንታሪዮ ሪሰርች ኢንስቲትዩት የተመራማሪነት እድል አግኝቶ እኔና ልጆቼ ደቡብ አፍሪካ ቀርተን እርሱ ብቻውን እንዲሄድ ተስማማን። በዚህ ተስማምተን እርሱ ካናዳ ሄዶ ቤተሰቡን ለማስተዳደር ከሚያገኘው ገቢ ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካ መላክ ነበረበት። ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቢትኮይን ገንዘብ ማግኘት ጀመርኩ። በስድስት ወር ውስጥ የእርሱን የዓመት ደሞዝ ያህል ማግኘት ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ወደ ካናዳ የመሄድ ሀሳቤን ተውኩት። ከስድስት ወር በኋላ ሊጠይቀን ሲመጣ ያለውን ለውጥ ተመለከተና ከሦስት ወር ቆይታ በኋላ የካናዳ ሥራውን ጥሎ እኔን ለመደገፍ መጣ። • ዓለም ሁሉ የሚያወራለት ክሪይፕቶከረንሲ ምንድነው? በዚህ ሥራ ውስጥ ከተሰማራሁ በኋላ በአንድ ዓመት ከግማሽ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ችያለሁ። ከዚያ በኋላም ቢዝነሱ እየሰፋ እና እየተጠቀምኩ ነው። ሚሊየነር መሆን ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው መንገዱ ክፍት ነው። ልጅ ወልደው ተደራራቢ ኃላፊነት ላለባቸው በቀላሉ ሊሰሩት የሚችሉት ሥራ ነው። እኔ በሰው አገር እየኖርኩ፣ ሦስት ልጆች እያሉኝ፤ ሁሉም ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ፤ መስራት ከቻልኩ ሌሎችም መስራት ይችላሉ። ለዚህ ሥራ ኢንተርኔትና ሀብታም የመሆን ፍላጎት እስካለ ድረስ መስራት ይቻላል። አትችይም የሚሉኝ ሰዎች ሁሌም ለሌላ ተጋድሎ ያነሳሱኛል። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሀገሩን ቋንቋ አትናገሪም ያሉኝ፣ ሴት መሆኔን ያስታወሱኝ ሰዎች በአጠቃላይ ዛሬ ለደረስኩበት አነሳስተውኛል። ባለቤቴ ቤት ውስጥ ከማርገዝና ከማጥባት ውጪ ሁሉንም ነገር ያግዘኛል፤ ይደግፈኛል። በዚህም እድለኛ ነኝ። ገንዘብ ለሁሉም ነገር መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ገንዘብ ሁሉንም ነገር ያቀላል። ስለዚህ ገንዘብ ሁሌም ለማግኘት ጠንክሬ እሰራለሁ። እንደ አፍሪካዊ የእኔ ሕይወት ሲቀየር የሌሎችም ሕይወት ስለሚቀየር የአንድን ሰው ሕይወት ለመለወጥ ጠንክሬ ነው የምሰራው። ብዙ አፍሪካዊያንን ሚሊየነር ለማድረግ አስባለሁ። ቢትኮይን ምንድን ነው? ቢትኮይን ልክ እንደ ዶላር እንደ ዩሮ ሁሉ ገንዘብ ነው። ሌላው ቢትኮይንን ከአንድ ሰው ወደ ሌላው በቀላሉ ዋጋው ሳይሸራረፍ ማስተላለፍ ይቻላል። ቢትኮይን ለመላክ የሦስተኛ አካል ጣልቃ ገብነትን አስወግዷል። እኔ ቢትኮይን ማይኒንግ ላይ ከተሰማራሁ በኋላ ሁሌም ለሌሎች የምነግረው ቢትኮይንን ገዝተው ማስቀመጥ እንደሚችሉ፣ ቢትኮይን ንግድ ላይ የመሰማራት እድል መኖሩን አልያም ንግዳቸውን በቢትኮይን መገበያየት እንደሚችሉ ነው። ይህ ለሁሉም ሰው ያለ እድል ነው። ግን በጥንቃቄ መስራት ያስፈልጋል። በዓለም ላይ በርካታ አጭበርባሪዎች ስላሉ በሚገባ አጥንቶ መግባት ያስፈልጋል። ሚሊየነር መሆን ይቻላል ስል በአንድ ጀምበር መሆን ይቻላል እያልኩ አይደለም። ጠንክሮ መስራትን ይጠይቃል። እኔ የተሰማራሁበት ቢትኮይን ማይኒንግ ይባላል። ቢትኮይን ማይኒንግ ገንዘብ ማተም እንደማለት ነው፤ ቢትኮይን ማተም ነው። ለዚህ ሁሉ ግን ጠንከር ያለ ገንዘብ እንዲሁም ታማኝ አጋር ማግኘት ያስፈልጋል። • የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ 'ሊብራ' ጥያቄን አስነሳ • አዲሱ የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ አፍሪካን ያጥለቀልቅ ይሆን? እኔና ባለቤቴ 2015 ላይ 'አቺቨርስ ክለብ አካዳሚ' የተሰኘ ተቋም አቋቁመን ክሪፕቶከረንሲ አካዳሚ እና ኔትወርክ ማስተማር ጀመርን። ይህንንም ከፕሪቶሪያ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር ነው የምንሰራው። በአካዳሚያችን ፋንዳሜንታል ኦፍ ብሎክ ቼይን፣ ክሪፕቶከረንሲ ኤንድ ክሪፕቶ ፋይናንስ፣ ብሎክ ቼይን ፎር ቢዝነስን የተሰኙ ኮርሶች እናስተምራለን። እኔ ደግሞ በአቺቨርስ ኔትወርክ በኩል ወደ ተለያዩ አገራት እየሄድኩ ልምዴን አካፍላለሁ። ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እንሰራለን። የምንሰራው በአፍሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን 33 አገራት ውስጥ ነው። እስካሁን 30 የሚሆኑ ሰዎች በሥራቸው ሚሊየን ዶላር እንዲያገኙ አድርገናል። ከእነዚህ ሰዎች መካከልም በሥራ ገበታቸው ላይ ሆነው የሚሰሩ አንዳንዶቹም የለቀቁ ይገኙበታል። በአፍሪካ ውስጥ በዚህ ትምህርት ሰፊውን ሥራ እየሰራን ነው። አሁን መቀመጫውን ፖላንድ ካደረገ ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርመን እየሰራን ነው። እኔ ሰዎችን አስተምራለሁ፤ አፍሪካ ውስጥ ላለ ሰው ትልቅ እድል ነው። ማንም ሰው ቢሰማራበት ውጤታማ ሊሆን ይችላል። *ሁሉም የዘመን አቆጣጠሮች በአውሮፓዊያን ነው እሷ ማናት? የሚለው ጥንቅራችን ያሰቡበትን ዓላማ ለማሳካት ብዙ ውጣውረዶችን ያሳለፉ ሴቶችን ታሪክ የምናስቃኝበት ነው።
news-54703890
https://www.bbc.com/amharic/news-54703890
በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ድንበር አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው
በሶማሌ እና በአፋር ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላም ለማውረድ ሁለቱ ክልሎች በመንግሥትና በሕዝብ ለሕዝብ ደረጃም መነጋገር እንደሚቀጥሉ በሶማሌ ክልል ምክትል የኮምንኬሽን ኃላፊ የሆኑት ዲባ አሕመድ ለቢቢሲ ገለጹ።
በሁለቱ ክልሎች ድንበር አካባቢ በተከሰተው ግጭት ሳቢያ ማክሰኞ እለት 10 ሰዎች እንደተገደሉና ከሰኞ ጀምሮ የሞቱት ሰዎች ባጠቃላይ 27 እንደሆኑ ተናግረዋል። በትናንትናው ዕለት የአፋር ክልል ኮሚዩኔኬሽን ኃላፊ አቶ አሕመድ ካሎይታ በድንበር አካባቢ በነበረው ግጭት 10 ሰዎች መሞታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከእነዚህም መካከል ሁለቱ የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች መሆናቸው ተዘግቧል። "በሁለቱ ክልሎች ድንበር አካባቢ ያለው ግጭት ቆይቷል። ከሁለት ዓመት በላይ ብዙ ሰው የሞተበት የድንበር ግጭት ነው" ያሉት ምክትል ኃላፊዋ፤ የዚህ ሳምንት ክስተት ግን ከቀደሙት የተለየ እንደሆነ ገልጸዋል። ጥቃቱን በተመለከተ ምርመራ እየተካሄ እንደሚገኝ ጠቁመው "አሸባሪ ቡድን በሚል ያስቀመጡበት ሁኔታ አልተመቸንም። አሸባሪ ቡድን የሚባል እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አላየንም። በእርግጥ የሽብር ጥቃት ነው። የተገደሉት አስሩም ንጹሀን ዜጎች ናቸው" ብለዋል። ከዚህ ቀደምም በአፋር እና በሶማሌ ክልሎች መካከል ንግግር እየተደረገ እንደሆነ አስታውሰው፤ "እኛ በመነጋገር እናምናለን። የአፋር ወንድሞቻችንም ያምናሉ ብዬ ነው የማስበው። ንግግሩ ይቀጥላል" ሲሉ አስረድተዋል። ምክትል የኮምንኬሽን ኃላፊ የሆኑት ዲባ፤ ጥቃቱን ማን እንዳደረሰ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጸው፤ "ሕዝቦቹ ወንድማማች ናቸው። ሁከት የሚፈጥር ሦስተኛ አካል አለ ብዬ ነው የምገምተው። ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን የሚያደረግ አካል አለ። መጀመሪያም ክስተቱ እንዲፈጠር እቅዱን ዘርግተው አሁንም ሰላም እንዳይኖር ንቅናቄ እያደረጉ ነው" ብለዋል። የሁለቱ ክልሎች ሕዝቦች ተመሳሳይ ባህል እንዳላቸው እንዲሁም በጋብቻም ተሳስረው እንደሚኖሩ በማጣቀስ፤ "ለፖለቲካ ፍጆታ ብለው በልቶ ጠጥቶ ያላደረ ሕዝብ ማጫረስን በምን እንደምገልጸው ራሱ አላውቅም" ሲሉ ተናግረዋል። አሁን በአካባቢው ሰላም እንሰፈነና በፌደራልና በክልል ደረጃም ንግግር እንዳለ ገልጸዋል። አያይዘውም ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ400 ያላነሱ ሰዎች እንደተገደሉ እና ንብረትም እንደወደመም ተናግረዋል። የአፋር ክልል ስለ ግጭቱ ምን አለ? በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 17፣ 2013 ዓ.ም በአፋር ክልል ገዳማይቱ በምትባል አካባቢ በትምህርት ቤት ውስጥ የተገደሉት የትምህርት ሚኒስቴር ሁለት ሰራተኞች "አሸባሪ በሚባሉ ኃይሎች" እንደሆነ የአፋር ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አህመድ ካሎይታ አስታውቀዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሁኔታ ለመቆጣጠር የተሰማሩት የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች አቶ ሙላት ፀጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህን ጨምሮ በክልሉ በደረሰ ጥቃት አስር ሰዎች ተገድለዋል። በክልሉ ዞን ሶስት ገለአሎ በምትባል ወረዳ፣ ሰርከሞና ቴሌ ቀበሌ በሚባል መንደር የሚገኙ የአርብቶ አደር ማሕበረሰብ ላይ ጥቅምት 16፣ 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት በተፈፀመ ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገድለዋል። አቶ አህመድ "የሽብር ጥቃት" ያሉትም ሴቶችና ህፃናት ላይ እንዳነጣጠረም ጠቅሰዋል። የትምህርት ሚኒስቴርም ሰራተኞች በጥይት መገደልም ከዚህ "የሽብር ጥቃት ብለው" ከሚጠሩት ጋርም የተያያዘ ነው ይላሉ። በክልሉ የተለያዩ ግጭቶች እንደሚያጋጥሙ የሚናገሩት አቶ አህመድ እንዲህ አይነት "መሰል የሽብር ጥቃት" ሲያጋጥም ግን ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ይናገራሉ። ከዚህ ቀደምም በባለፈው አመት በአፋምቦ ወረዳ ኦግኖ ቀበሌ በተመሳሳይ መልኩ ሌሊት ላይ ሴቶችና ህፃናት ላይ ያነጣጠረ "የሽብር ጥቃት ተፈፅሞ ቁጥራቸውን ያልጠቀሱት ሰዎች መገደላቸውን ያስታውሳሉ። ጥቃት የደረሰበት አካባቢ የኢትዮ-ጂቡቲ አውራ ጎዳናና አለም አቀፍ መተላለፊያ ድንበር እንደሆነም ይገልፃሉ። ጥቃቱን ያደረሱት አካላት ማንነትን በተመለከተ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄም፤ በህገ ወጥ ንግድ (ኮንትሮባንድ) ተሰማርተው የነበሩና ያ እንቅስቃሴያቸው የተገታባቸው ኃይሎች "በአካባቢው የሚኖሩ የሶማሌ ኢሳ ጎሳ ማህበረሰቦችንም ከለላ በማድረግ" ህዝቡን እያጠቁ ይገኛሉ ብለዋል። "አሸባሪ ለየትኛውም አይወግንም እነሱን ከለላ አድርጎ ከመጣ የነሱን ሰላም ሊያውክ የሚችል ኃይል እንደሆነ ታውቆ እነሱም በነሱ ውስጥ አቋርጠው እዛ ቦታ ላይ ሽብር ሊፈጥሩ የሚችሉ ኃይሎችን ቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር መቻል አለባቸው" ይላሉ። በአካባቢው የሽብር ጥቃት እየተደጋገመ መምጣቱን የሚናገሩት አቶ አህመድ በቅርቡም በክልሉ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ድጋፍ ለማድረግ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ልዑካኖችም ላይ በደረሰ ጥቃት የአንድ ፀጥታ ኃይል ህይወት ያለፈ ሲሆን አንዱም ተጎድቷል። ልዑካኖቹ ድጋፋቸውን አድርሰው ሲመለሱ በፀጥታ ኃይሎቹ ላይ ባነጣጠረ ጥቃትም ህይወት መጥፋቱን አስታውሰዋል። "አገሪቷ ላይ የመጣውን ለውጥ የማይደግፉና የሚፃረሩ ከውጭም የራሳቸው የሆነ ተልእኮ ያላቸው ኃይሎች አገሪቷ የጀመረችውን የብልፅግናና የአንድነት ጉዞም ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ናቸው" የሚሏቸው ኃይሎችም በክልሉም የሚፈፀመው ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃትም ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው ይላሉ። እነዚህ ኃይሎች በድንገተኛ ሁኔታ ጥቃት እያደረሱ የሚገኙ ሲሆን በከባድ መኪና አሽከርካሪዎችም እንዲሁ ጥቃቱ እየተፈፀመ ይገኛሉ ብለዋል። ይሄ መስመር አለም አቀፍ መተላለፊያ ድንበር እንደመሆኑ መጠን የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት መጠበቅም ኃላፊነት የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ኃይል በመሆኑም እነሱም የሚችሉትን እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል። "የኮንትሮባንድ ንግድ የተቋረጠባቸው ሊኖሩ ይችላሉ እነዚሁ ኃይሎች ናቸው ተደራጅተው የሽብር ጥቃት ፈፅመው የሚመለሱት።" የሚሉት ኃላፊው እንደዚህ ጥቃት የሚፈፅሙ ኃይሎችን የሶማሌ ክልልም ይሁን ሁሉም ሊያወግዝ ይገባል ይላሉ ። "የኢሳ ማህበረሰብ በተለይም ገዳማይቱ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦችም ከውስጣቸው ወጥቶ ሌሎች ላይ ጉዳት አድርሶ የሚመለሱ ኃይሎችን መታገል አለባቸው። ሽፋን ከመሆን ይልቅ መከላከል ይገባል።" ብለዋል በባለፈው አመትም እንዲሁ ተመሳሳይ ችግር አጋጥሞ ከአገሪቱ ሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም ከሶማሌ ክልልም ጋር ችግሩን ለመፍታትና ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም የተናገሩት ኃላፊው ክልሉም የማጣራት ሰራውን እንደሚቀጥልና የህዝብ ለህዝብ ውይይትም ይቀጥላል ብለዋል። በተለይም ክልሉ በጎርፍ ክፉኛ ተጠቅቶ ኃብቱና ንብረቱን ባጣበት ወቅት ማጋጠሙም አሳዛኝ እንደሆነ የሚገልፁት ኃላፊው ጥቃቱ የደረሰባቸው አርብቶ አደር ማህበረሰብ እንዲሁ በጎርፉ ኃብትና ንብረቱን የተቀማ ነው ይላሉ። የትምህርት ሚኒስቴር ስለተገደሉት ባልደረቦቹ የሰጠው ምላሽ በክልሉም በሰራ ላይ እያሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን ላጡት ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በዛሬው ዕለት ሽኝት መደረጉን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። ሰራተኞቹ ወደ አፋር የተንቀሳቀሱት ጥቅምት 13፣ 2013 ዓ.ም ሲሆን በትናንትናው ዕለትም ወደሚሰሩበት ቦታ ገዳማይቱ በምትባል ቦታም ትምህርት ቤት ውስጥ ስራ እየሰሩ እያለ ነው ባልታወቁ ሰዎች በጥይት መመታታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚዩኒኬሸን ጉዳዮች ዳይሬክተር ሐረጓ ማሞ ይናገራሉ። ሰራተኞቹም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ከማስቀጠልም በተጨማሪ በልጅነታቸው በመዳራቸውና በሌሎች ምክንያቶች ወደ ኋላ እየቀሩ ያሉ ሴቶችንም አትኩሮት በመስጠት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግም ነው ወደ ቦታው ያመሩት። ጂቡቲ መስመር ላይ አንዳንድ አለመረጋጋቶች በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ እለት፣ ጥቅምት 16፣ 2013 ዓ.ም ተከስቷል የሚሉ መረጃዎች መውጣታቸውን በማስመልከት የትምህርት ሚኒስቴሩ መረጃ አልነበረውም ወይ? ተብሎ ዳይሬክተሯ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሰራተኞቹ ከተባለው ቀን በፊት ቀደም ብለው እንደወጡና ከሰኞ በፊት በነበረውም ሁኔታ ሰላም የነበረ መሆኑን ይናገራሉ። ከሄዱበት እለትም ጀምሮ የተለያዩ አካባቢዎችም ስራ መስራትም ችለው እንደነበርም ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞቹን በቡድን ወደተለያዩ ቦታዎች የላከ ሲሆን እነዚህ ሰራተኞችም በአጋጣሚ እንደተገደሉም ሐረጓ አስታውቀዋል። የሰራተኞቹ አስከሬን ከአፋር ክልል በዛሬው ዕለት፣ጥቅምት 18 2013 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባም ገብቷል። የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞችም ለሰራተኞቹ አስከሬን ወደየአካካቢያቸው ሽኝት ማድረጋቸውንም መረጃው ጠቁሟል። በወቅቱም ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) የአበባ ጉንጉን ከማኖር በተጨማሪ በሰራተኞቹ እልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ኃዘንም ገልፀው ለወዳጅ፣ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል። ሁለቱ ሰራተኞች በተገደሉበት ወቅት የመቁሰል አደጋ ያጋጠመው ሌላኛው የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኛ አቶ ደምሴ ታምሬ የቀዶ ህክምናውን በክልሉ አድርጎ እያገገመ መሆኑንም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነውን መረጃ ያስረዳል።