id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
51485031
https://www.bbc.com/amharic/51485031
ሥጋት ያጫረው የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ሕግ ጸደቀ
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርን እና ሐሰተኛ መረጃን ለመቆጣጠር የወጣውንና የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጆችን ዛሬ ባደረገው ልዩ ስብሰባው አጽድቋል።
የጥላቻ ንግግርን እና ሐሰተኛ መረጃን ለመቆጣጠር የረቀቀው ሕግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ከወትሮው የተሻለ ይዞታ ላይ ይገኛል የሚባልለትን ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት ላይ አደጋን ይጋርጣል በሚል ስጋታቸውን የሚሰነዝሩ የመኖራቸውን ያህል፤ ሕጉ ምን ያህል ሊተገበር ይችላል በሚለው ጉዳይ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው የሚገልፁም አልጠፉም። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድጋፍ ሠልፍ እና የኦፌኮ ስብሰባ መከልከል በጅማ • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ የመንግሥት አካላት ደጋግመው አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በአገሪቱ ውስጥ ሰርክ የሚነሱ የብሔርም የኃይማኖትም መልክ ያላቸው ግጭቶች እና ግርግሮች በተለይ በማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛ ዘዴዎች በሚሰራጩ እና ጥላቻ በሚታጨቅባቸው መልዕክቶች የሚባባሱ ምናልባትም የሚያነሳሱ ናቸው ሲሉ ይደመጣሉ። ሕጉን ማን አረቀቀው? በኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት እየተከናወኑ ካሉ ሥራዎች መካከል፣ትልቁ የሕግ እና የፍትህ ማሻሻያ ነው ይላሉ የፅሕፈቱ ቃል አቀባይ አቶ ዝናቡ ቱኑ የሕጉን አረቃቅ ሒደት ለቢቢሲ ሲያስረዱ፤ "የሕግ እና የፍትሕ ማሻሻያ ሥራ ድሮ በተለመደው መንገድ እንዲሄድ ታሳቢ የተደረገ አይደለም።" ዋነኛ ሥራው ህግን ማርቀቅ እንዲሁም ማስረፅን ያደረገ ራሱን የቻለ መምርያ በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፅሕፈት ውስጥ ይገኛል። መምርያውን በተግባራቱ ሊያግዝ የሚችል አቶ ዝናቡ "ፍፁም ገለልተኛ ነው" የሚሉት የሕግ እና የፍትሕ አማካሪ ምክር ቤት አለ። ምክር ቤቱ በተለይ ትላልቅ የሚባሉ ሕግጋትን በማርቀቅ ረገድ የጠቅላይ አቃቤ ሕግን ያማክራል እንደቃል አቀባዩ ገለፃ። "ከመንግስት ባሻገር በዘርፉ ውስጥ ሰፊ ልምድ ያላቸው ዕውቀትም ያላቸው ፣ ክህሎትም ያላቸው፣ ልምድ ዕውቀት እና ክህሎታቸውን ለሕዝባቸው አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ያሉበት" ነው ምክር ቤቱ ይላሉ አቶ ዝናቡ። • አቶ ታዬ ደንደአ 2 ሚሊዮን ብር ተዘረፍኩ አሉ • ትዊተር የትኛውንም የፖለቲካ ይዘት ያለው ማስታወቂያ ሊያግድ ነው አማካሪ ምክር ቤቱ ሦስት ዋና ዋና ሥራዎችን እንዲሰራ ነው የተፈለገው እንደ አቶ ዝናቡ። አንዱ እርሳቸው "ጨቋኝ ናቸው የሚባሉና የሚያፍኑ" ነበሩ ያሏቸውን ሕግጋት ማሻሻል ነው። ሁለተኛው አሁን የተደረሰበትን ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ የሚያንፀባርቁ አዳዲስ ሕግጋትን ማርቀቅን፤ ሦስተኛው ደግሞ እነዚህ ሕግጋትን ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ በመገምገም ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ለመንግሥት እንዲቀርብ ማድረግ ነው። ሆኖም ይህ ምክር ቤት "የሚያግዘን አንድ ቡድን ነው። በዋናነት ግን የጥላቻ እና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀው በተቋማችን አቅም፣ የሌሎችንም ባለድርሻ አካላትን ድጋፍ ወስዶ ነው" ይላሉ አቶ ዝናቡ። ሕጉ ስጋትን ለምን አጫረ? የጥላቻ ንግግርን እና ጉዳት አድራሽ የሐሰተኛ መረጃዎችን ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው ሕግ መረቀቁ ከተሰማበት እና ረቂቅ ሕጉ ለውይይት ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ ነው ስጋት እንደገባቸው የሚናገሩ አካላት ድምፅ መሰማት የጀመረው። የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው ቡድን ሂውማን ራይትስ ዎች በወርሃ ታህሳስ ባወጣው ሪፖርት ሕጉ ከፍተኛ ማሻሻያ የማይደረግበት ከሆነ የመናገር ነፃነትን የመደፍጠጥ አቅም እንዳለው ፍራቻውን አሳውቋል። በወቅቱ በሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ላይቲቲያ ባደር "የኢትዮጵያ መንግስት አንዳንድ ጊዜ በበይነ መረብ የሚሰራጩ ንግግርች እና አስተያየቶች ላባባሷቸው ማኅበረሰባዊ ግጭቶች ምላሽ አንዲሰጥ የሚደርስበት ጫና እየጨመረ ነው" ብለው ነበር። • ጠብ አጫሪና ጥቃት አድራሽ የፌስቡክ ፖስቶችን እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል? • ፌስቡክ ሐሰተኛ ዜናዎችን መለየት ሊጀምር ነው ሆኖም "ሕግ አስከባሪ መኮንኖች ኃሳብን በነፃነት የመግለፅን መብቶች እንዲጥሱ በር የሚከፍት ሕግ" መፍትሔ አይሆንም ብለዋል ባደር። ግጭትን መቀስቀስን እና ማነሳሳት ቀደም ሲል በፀደቁ የኢትዮጵያ ሕግጋትም የተከለከለ መሆኑን በማስታወስ የጥላቻ ሕግን እና ጉዳት አድራሽ ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨትን ብቻ የሚመለከት ሕግ ማርቀቅ የተለየ ኃሳብን ያላቸው ሰዎች ላይ የፍርሃትን ቆፈን በመፍጠር ፀጥ የማሰኘት ዓላማ ሊኖረው ይችላል ሲል የሚሟገተው ደግሞ ጋዜጠኛ እና ጦማሪው በፍቃዱ ኃይሉ ነው። "መንግሥት ራሱ እኮ ከጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃን ከማሰራጨት የነፃ አይደለም" ይላል በፍቃዱ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። "የክልል መንግሥታት የሚያስተዳደሯቸውን የብዙሃን መገናኛዎች ተመልከቱ። በፕሮፓጋንዳ ጦርነት ተጠምደዋል። ይህ ጦርነትም አንዳንዴ በጥላቻ ይዘት ባላቸው ንግግሮች እና በሐሰተኛ መረጃዎች የተደገፈ ነው።" ለበፍቃዱ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተቀሰቀሱ የብሔር እና የኃይማኖት ግጭቶች የበይነ መረብ ስርጭት ተደራሽነት ዝቅ ባለባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ጭምር የተከሰቱ መሆናቸው መንግሥት አንደሚለው የማኅበራዊ ብዙሃን መገናኛዎች ሚና ከፍ ያለ እንዳልነበር ያሳያል። ሕጉ ቢወጣም እንኳ በማኅበራዊ የብዙሃን መገናኘዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግር እና ጉዳት አድራሽ ሐሰተኛ መረጃዎችን መቆጣጠርም የሚታሰበውን ያህል ቀላል አይደለም ባይ ነው በፍቃዱ። • ምርጫ ቦርድ የጃዋር ዜግነትን አስመልክቶ ኢሚግሬሽንን ማብራሪያ ጠየቀ ከጥላቻ እና ሐሰተኛ ንግግሮች ጀርባ ያሉ የማኅበራዊ ብዙሃን መገናኛ አካላት "አንዳንዶቹ ማን እንደሆኑ አይታወቅም። በድብቅ የሚፅፉ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ በጣም ዝነኛ ከመሆናቸው የተነሳ እነርሱ ላይ እርምጃ መውሰድ፣ ንግግራቸው ሊያደርስ ከሚችለው የበለጠ ነውጥን የሚቀሰቅስ ሊሆን ይችላል።" የተገደበ ነፃነት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ አቶ ዝናቡ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የንግግር መብት ፍፁማዊ ያለመሆኑን አስረግጠው ይናገራሉ፤ ይህም ለአገር እና ለሕዝቦች ደህንነት ስጋት በሚሆንበት ጊዜ ኃሳብን የመግለፅ መብት ይገደባል። ነገር ግን አሁን እየተሰነዘሩ ያሉ ስጋቶች እና ጥርጣሬዎች ኢትዮጵያ ካለፈችባቸው ነባራዊ ሃቆች የሚቀዱ እንደመሆናቸው መነሻቸውን እንገነዘባለን ይላሉ ቃል አቀባዩ። ሆኖም "ብሔሮች እየተጠቁ ነው፤ ግለሰቦች ስማቸው ጭምር እየተጠቀሰ፣ አደጋን እንዲጋፈጡ እየሆኑ ነው። ይህ ሁኔታ እየጨመረ ነው። ወጣቶች ሆ ብለው በደቦ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ውስጥ እየተሳተፉ ነው። ይህ መቆም አለበት" ይላሉ። • ከሞት የታደገው ጎሽ ከቤት አልወጣም ብሎት የተቸገረው ኢትዮጵያዊ "መንግሥት የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት ስላለበት እንደነዚህ ዓይነት አዋጆች አስፈላጊነታቸው ላቅ ያለ ነው። መነሻችን እርሱ ነው።" ሆኖም ይህ የመንግሥት ሙግት በትክክልም የተችዎችን ስጋት የሚቀርፍ መሆን ያለመሆኑ ከሕግ አተገባበር ጋር በተያያዘ ጊዜ ብቻ የሚመልሰው ይመስላል።
news-53885867
https://www.bbc.com/amharic/news-53885867
ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ገደብ ተላልፈው ሲጨፍሩ የነበሩ 13 ወጣቶች ሞቱ
በላቲን አሜሪካዋ አገር ፔሩ ነው ይህ አሳዛኝ ክስተት የተፈጸመው፡፡
በአንድ መሸታ ቤት በር ዘግተው የልደት ድግስ አሰናድተው፣ "አስረሽ ምቺው" ላይ የነበሩ ወጣቶች ፖሊስ ይደርስባቸዋል፡፡ በፖሊስ መከበባቸውን ሲያውቁ በመሸታ ቤቱ አንዲት ቀጭን በር በኩል ለማምለጥ ሩጫ ይጀመራል፡፡ በዚህ ጊዜ ነው መረጋገጥና መተፋፈግ ተፈጥሮ ለሳቅ ለጨዋታ እንዲሁም ለደስታ የመጡ 13 ሰዎች ሕይወት እንዲህ እንደዋዛ ያለፈው፡፡ ፖሊስ ድንገተኛ ወረራ ያደረገው ጥቆማ ደርሶት ነው፡፡ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰዎች ተሰብስበው እንዳይጨፍሩ የፔሩ መንግሥት እገዳ ከጣለ ሰነባብቷል፡፡ በሊማ፤ ሎስ ኦሊቮስ በሚባለው ሰፈር ቶማስ ሬስቶባር ናይት ክለብ ነው ይህ አሳዛኝ አደጋ የደረሰው፡፡ የአይን እማኞች እንደሚሉት ፖሊስ አስለቃስ ጭስ ተጠቅሟል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ እኔ አልተኮስኩም ሲል ተከራክሯል፡፡ ፕሬዝዳንት ማርቲን ቪዝካራ እንደተናገሩት በመሸታ ቤቱ ውስጥ አሸሼ ገዳሜ ሲሉ ከነበሩና ምርመራ ከተደረገላቸው 23 ወጣቶች ውስጥ 15ቱ ተህዋሲው ተገኝቶባቸዋል፡፡ ፔሩ ከደቡብ አሜሪካ አገሮች ውስጥ ኮቪድ ክፉኛ ካጠቃቸው ተርታ ትመደባለች፡፡ ግማሽ ሚሊዮን ሰዎች ተህዋሲው የያዛቸው ሲሆን 27ሺ ሰዎች ሞተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ነው ካለፈው መጋቢት አጋማሽ ጀምሮ ሰአት እላፊ የታወጀው፡፡ የፔሩ የአገር ውስጥ ሚኒስትር እንዳሉት የቅዳሜውን የልደት ድግስ 120 ሰዎች ታድመውበት ነበር፡፡ በጭፈራ ላይ የነበሩት ወጣቶች ፖሊስ መምጣቱን ሲያውቁ በደረጃው ላይ ቀድመው ለማምለጥ ሙከራ ላይ በነበሩበት ጊዜ ነው መጨፈላለቁ ተፈጥሮ አደጋው ሊደርስ የቻለው፡፡ ከ13ቱ ሟቾች ውስጥ ሁለቱ ሴቶች ናቸው፡፡ የመሸታ ቤቱ ባለቤት የሆኑት ባልና ሚስት ለጊዜው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
news-41841322
https://www.bbc.com/amharic/news-41841322
ለብዙዎች ወርቃማ እድል የሆነው የዲቪ ሎተሪ
በየዓመቱ 14 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በወርሃ ጥቅምት ላይ የሚጀመረውን የዲቪ ሎተሪ ተጠቅመው ህጋዊ የአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ይመዘገባሉ።
ግሪን ካርድ ሎተሪ የሚባለውን ፕሮግራም ተጠቅመው እ.አ.አ ከ1995 ጀምሮ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ቪዛ አግኝተዋል። ትላንት በኒው ዮርክ ጥቃት ያደረሰው ግለሰብ በ2010 የግሪን ካርድ ፕሮግራም ባለዕጣ ሆኖ ወደ አሜሪካ መግባቱን ተከትሎ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፕሮግራሙን አጣጥለዋል። ባለፈው ጥር የግሪን ካርድ ሎተሪ በችሎታ፣ በትምህርት እና በመሰል የመምረጫ ሂደቶች መሰረትነት ወደሚሰጥ ዘዴ እንዲቀየር ሪፐብሊካኖች ያቀረቡትን ዕቅድ ፕሬዝዳንቱ ደግፈዋል። የዲቪ ሎተሪው ምንድን ነው? የዲቪ ሎተሪ ፕሮግራሙ በአሜሪካ በስደተኝነት በቂ ድርሻን ላላገኙ ሃገራት ዜጎች በየዓመቱ 50 ሺህ ቪዛዎችን ይሰጣል። ይህ ደግሞ የአሜሪካ ዜግነትን ለማግኘትም በር ከፋች ነው። የምርጫው ሂደት በኮምፒውተር ሲሆን ቪዛ ተቀባዮች አሜሪካ ውስጥ ስፖንሰር፣ ሥራ ወይም ደግሞ ቤተሰብ እንዲኖራቸው አይጠበቅባቸውም። እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ህንድ እና ቻይናን ጨምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት50 ሺህ የግሪን ካርድ የዲቪ ሎተሪ አሸናፊዎች ያሏቸው ሃገራት ዜጎች በእድሉ መሳተፍ አይችሉም። በሎተሪው ላይ ለመሳተፍ ብቸኛው መስፈርት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅ ወይም ከዚህ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የትምህርት ደረጃ መያዝ ነው። አሸናፊዎች የትዳር አጋሮቻቸውን እና ታዳጊ ልጆቻቸውን ይዘው ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የሚፈቀድላቸው ሲሆን ይህ ግን በፕሬዝዳንት ትራምፕ ድጋፍ አልተሰጠውም። የዲቪ ሎተሪ ዕጩዎች በአሜሪካ ኤምባሲ በመገኘት ፊት ለፊት ቃለ መጠየቅ ማድረግ ይኖርባቸዋ። ከሽብር ጋር በተያያዘ ሪከርድ ያለባችወ አመልካቾች ዕድሉ የማይሰጣቸው ይሆናል። በዕድሉ ማን ተጠቀመ? ህጉ መጀመሪያ ላይ የአውሮፓ ስደተኞችን ቁጥር ለማብዛት ተብሎ ቢጀመርም የስደተኞችን ቁጥር ከመጨመሩም በላይ በተለይ ከአፍሪካ ወደ አሜሪካ የሚገቡትን ሰዎች ቁጥር አሳድጎታል። እንደፒው ሪሰርች ሴንተር ጥናት ከሆነ የሎተሪ ፕሮግራሙን በመጠቀም ከሰሃራ በታች ያሉ አፍሪካ ሃገራት ወደ አሜሪካ ለመግባት ችለዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ዕገዳ እንዲጣልባቸው ከሚፈልጓቸው ሃገራትም ፕሮግራሙን ተጠቅመው ወደ አሜሪካ የገቡ አሉ። እንደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከሆነ እ.አ.አ በ2015 ኋይት ሃውስ በጥቁር መዝገብ እንዲሰፍሩ ከሚፈልጋቸው ስድስት የሙስሊም ሃገራት ብቻ 10,500 ሰዎች ለዲቪ ቪዛ ሎተሪ ተመርጠዋል። ትራምፕ የግሪን ካርድ ሎተሪን ያስቀራሉ? ፕሬዝዳንቱ በራሳቸው ፕሮግራሙን የማስቀረት ስልጣን የሌላቸው ሲሆን የአሜሪካ ኮንግረስ አዲስ የስደተኞች ህግ እስኪያወጣ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ትራምፕ በሃገሪቱ ሴኔት ውስጥ በወግ አጥባቂዎች ድጋፍ ያገኘውና ግሪን ካርድን ለማስቀረት የቀረበውን ዕቅድ ይደግፋሉ። ዕቅዱ የስደተኞችን ቁጥር በግማሽ ይቀንሳል ተብሏል። ሪፎርሚንግ አሜሪካን ኢሚግሬሽን ፎር ስትሮንግ ኢምፕሎይመንት አክት የተባለው ዕቅድ እ.አ.አ. ጥር 2017 ይፋ የተደረገ እና በፕሬዝዳንት ትራምፕ ድጋፍ የተሰጠው ቢሆንም በሴኔቱ ማግኘት የሚገባውን ያህል ድምጽ አላገኝም። የኮንግረሱ አባላት ስደተኞች ፕሮግራሙን መቀየር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም በሚል ትኩረታቸውን በጤና እና በግብር ጉዳዮች ላይ አድርገዋል።
news-44798075
https://www.bbc.com/amharic/news-44798075
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከኤርትራ ጋር የጀመሩትን የአብሮነት እርምጃ ምን ይፈትነዋል?
የኢትዮጵያ መንግሥት ለሁለት አሰርት አመታት በኢትዮጵያና ኤርትራ ሰፍኖ የዘለቀዉን ሞት አልባ ጦርነት ለመቋጨት የአልጀርስ ስምምነትን ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ ካሳወቀ ከ18 ቀናት በኋላ የኤርትራ መንግስት ጥሪውን ለመቀበል ዝግጁ እንደሆነ ማሳወቁ ይታወሳል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የተመራውን የልኡካን ቡድን እራት በጋበዙበት ምሽት ባለፉት 25 አመታት የተፈጠሩ ሰላም የማስፈን እድሎች በሁለቱ አገራት መሪዎች እምቢተኝነት ምክንያት ለፍሬ አለመብቃታቸውን ገልፀው ያለፈው ጊዜ እንዳይደገም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አብረው ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በበኩላቸው "የዜጎችን ተጠቃሚነት እንዳናረጋግጥ የተጋረጠብንን የመለያየት ግድግዳ አፍርሰን፣ ላለፉት 20 አመታት ከባድ ኪሳራ ያደረሰብንን ሞት አልባ ጦርነት ቋጭተን፣ ወደ አዲስ ምዕራፍ ለመሸጋገር የጀመርነዉ ጉዞ እንደሚሳካ አልጠራጠርም" ብለዋል። ከ1998 ዓ. ም. ጀምሮ የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ተቋርጦ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የአገራቱ መንግስታት ለሰላም ያሳዩት ተነሳሽነት ለሁለቱ አገራት እንዲሁም ለቀጠናውም ሰላምና ልማት መንገድ እንደሚከፍት በርካቶች ይስማሙበታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም የሁለቱ አገራት ሰላም ለቀጠናዉ መረጋጋትና ልማት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው በዚህ ትውልድ 'አለመግባባት' የሚባል መሰናክል መኖር እንደሌለበት ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? በኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ስምምነት ሦስተኛ ወገን አልተሳተፈበትም ተባለ መሰረታዊ ግንኙነቶችን ያኮላሸ ጦርነት በካናዳ ኩዊንስ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህሩ ኤርትራዊ ዓወት ተወልደ ወልደሚካኤል (ዶ/ር) በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀከል የተካሄደዉ ጦርነት የማይተመንና የማይተካ የሰው ህይወትና አቅም እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ኪሳራም ማስከተሉን ይናገራሉ። ጦርነቱ በተለይም በድንበር አካባቢ የሚኖሩ የሁለቱንም አገር ዜጎች ኪሳራ አሸክሟል ይላሉ። "ጦርነቱ ካቆመበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን 'ጦርነት በሌላ ስልት' ተብሎ የሚታወቀው ሞት አልባ ጦርነት መሰረታዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን አኮላሽቷል" ሲሉ የጦርነቱን ጠባሳ ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ታራምድ የነበረው የማዳከም ስትራቴጂና ኤርትራ ከቀጠናዉ ተሳትፎ ርቃ በሌላ የፖለቲካ አለም ዉስጥ መዋተትዋ፤ የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ እንዳይረጋጋ ምክንያት መሆኑን መምህሩ ያወሳሉ። "ምስራቅ አፍሪካ ከኢትዮጵያና ኤርትራ ባሻገር ለአለም አገራትም በጣም ስትራቴጂያዊ ቀጠና ነው። ቀጠናው አሜሪካ ውስጥ ከደረሰዉ 9/11 የሽብር ጥቃት በኋላ የሽብር ተግባርን ለማጥፋት የተጀመረዉ ትግል ዋነኛ የቴአትር ቦታ ሆኗል። የሁለቱ ሀገራት አለመረጋጋት ሶማሊያን የሽብርተኞች መንደር እንድትሆን አድርጓታል" ይላሉ። የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ጦስ በሶማሊያ? ኤርትራ ኢትዮጵያ ስትከተለዉ ከነበረዉ የማዳከም ስትራቴጂ ለመውጣትና የራስዋን ጥቅም ለማስከበር የወሰደችው እርምጃ የአረብ ሀገሮች ወታደራዊ መቀመጫ እንድትሆን አድርጓታል። አሁን ሁለቱንም አገራት የከፈቱት የሰላም በር ላለፉት 20 አመታት የነበረውን ጦርነት የሸበበው ሸካራ ግንኙነት ከማደሱ ባለፈ በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ተስፋ ተጥሎበታል። ዶክተር ዓወት ተቀራራቢ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ገጽታ ያላቸው የአፍሪካ ቀንድ አገሮች የተቀናጀ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል አቅም እንደሚገነቡ ያምናሉ። ሁለቱንም አገራት በዚህ ቀጠና ትልቅ ሚና መጫወት የሚያስችል አቅም አላቸው። በጎረቤቶቻቸዉ በሶማሊያና ደቡብ ሱዳን የታየውን ጦርነትና አለመረጋጋት እንዲያረግቡ ተጥሎባቸዉ የነበረው ተስፋ ዳግም እንደሚያንሰራራ መምህሩ ይናገራል። ከዚህ ባሻገር ባለፉት ሦስት ወራት ኢትዮጵያ ዉስጥ የተስተዋሉ ለውጦች ኤርትራ ውስጣዊ ፖለቲካዊ ለውጥ እንድታደርግ በቀጥታም በተዘዋዋሪም እንደሚያስገድዱ ዶክተር ዓወት ይናገራሉ። ሁለቱ አገራት በሰብአዊ መብትና ሁለገብ ለውጥ ረገድ ይነሱባቸው ለነበሩ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሰጡ ያላቸውን ተስፋም ያክላሉ። ለሁለት አስርት ዓመታት ተፋጠው የነበሩት ኤርትራና ኢትዮጵያ ጉዟቸው ምን ይመስላል? ተስፋ መሰል መሰናክሎች ዶክተር ዓወት እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሰት የአልጀርስ ስምምነትን ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ እንደሚተገብር መግለጹ የሚደነቅ እርምጃ ቢሆንም የማንነትና ህልውና ጥያቄ ያነገቡ የድንበር አካባቢ ነዋሪዎች ከውሳኔው በፊት መወያየት ነበረብን የሚል ጥያቄ ማንሳቸውን ቸል ማለት አይቻልም ። "ሆኖም ግን ህዝብ ለውይይት የሚቀርበው ወይም የሚጠራዉ አሁን አይደለም" ይላሉ። እንደ መምህሩ ገለጻ ህዝብ ሳይወያይ ከውሳኔ በመደረሱ ቅሬታ አለ። "ይሁን እንጂ ድሮም ህዝቡን ቢያወያዩት ኖሮ ጦርነቱም ባልተጀመረ ነበር" ብለው አንድ መንግስት አለም አቀፋዊ ስምምነት ሲፈርም ስምምነቱን ለመተግበር እንደሚገደድም ያስረዳሉ። ሁለቱም አገራት ስምምነቱን ሲፈርሙ የየራሳቸውን ጥቅም የሚያስጠብቁ የማንነት ጥያቄዎች በማንሳት ውሳኔዉን እንዳያደናቅፉት የድንበር ጥያቄዎቻቸው ተፈትሸው ውሳኔ መሰጠቱን ያጣቅሳሉ። ዶክተር ዓወት ስለወደፊቱ ሲጠየቁ "የወደፊት ግንኙነታችን በሰው ሰራሽ ድንበር መደናቀፍ የለበትም። የውስጥ አስተዳደራዊ ችግሮችን በመፍታት መፍትሄ ማበጀት ይቻላል" ይላሉ። "ሁለቱ መንግስታት የጀመሩት የሰላም መንገድ መረጋጋትና ጥሞና ይሻል" መምህሩ በሁለቱ አገሮች መካከል አለመተማመንና አለመግባባት አሁንም መኖሩን ይገልጻሉ። ሁለቱ አገራት በቅድሚያ ውስጣዊ አስተዳደራዊ ችግሮቻቸውን መፍታት እንዳለባቸውም ይጠቁማሉ። "ሁለቱ መንግስታት የጀመሩት የሰላም መንገድ መረጋጋትና ጥሞና ይሻል" ሲሉም ሰከን ብሎ መጓዝን ይመክራሉ። የኢትዮጵያ መንግስት አካሄድ የሰዎችን ስሜትና ፍላጎት እየኮረኮረ ሁኔታዎች የሚያንጸባርቅ መሆኑን ይገልጻሉ። ይህን መሰረት በማድረግም ውሳኔዎች መዋቅራዊ ቅርጽ ይዘው በስርዓት መተግበር ካልጀሩ ችግሮች መፈጠራቸው አይቀርም ይላሉ። በተጨማሪም ሁለቱንም መንግስታት ድንበር ላይ ያላቸው ግጭት ለመፍታት ከመሯሯጣቸው አስቀድሞ የኤርትራ መንግስት የህዝቡን ጥያቄና ፍላጎት በማያሻማ መልኩ መመለስ መቻል አለበት ይላሉ። መምህሩ በኤርትራ በኩል እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጡት "መንግስት ከባድ ዋጋ ተከፍሎበት የተኮላሸውን የኤርትራ ሰላም መመለስና የውስጥ ተቋማትን ማደራጀት አለበት" በማለት ነው። ቅድመ ሁኔታዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያና ኤርትራ ስምምነት ላይ ቢደርሱም ዘላቂ ሰላም ስለማይኖር ቆም ብሎ ማሰብ ያዋጣል ይላሉ።
news-47194870
https://www.bbc.com/amharic/news-47194870
ሀንጋሪ የሕዝብ ቁጥሯን ለማሳደግ እናቶችን ከግብርና ከዕዳ ነፃ ልታደርግ ነው
የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚንስትር አራት አሊያም ከዚያ በላይ ልጆች ያሏት ሀንጋሪያዊ እናት ግብር ከመክፈል ነፃ እንደምትሆን አስታውቀዋል፤ የውልደት መጠንን ለመጨመርም እቅድ ተይዟል።
የሀንጋሪ የህዝብ ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን አሁን የሚወሰደው ርምጃ ችግሩን ያቃልለዋል ተብሎ ይታመናል። • የሰው ልጅ ዘር እየመነመነ ነው ጠቅላይ ሚኒስተር ቪክተር ኦርባን እንደተናገሩት እርምጃው በስደተኞች ላይ ጥገኛ ከመሆን የሚያድንና የአገሪቷን መፃኢ ዕድል የሚያሻሽል ነው ብለዋል። የሀንጋሪ የህዝብ ብዛት በዓመት በ32 ሺህ ይቀንሳል፤ በአውሮፓ ኅብረት በአማካይ ከተቀመጠው የውልደት መጠን ሀንጋሪያን ሴቶች ያላቸው የልጆች ቁጥር ዝቅተኛ እንደሆነም ተነግሯል። ይህንንም ለማስተካከል ከሚወሰዱ የመፍትሔ ሃሳቦች ከወለድ ነፃ የሆነ 36 ሺህ ዶላር (1 ሚሊየን ብር) ብድር የሚያገኙ ሲሆን ሦስት ልጅ ከወለዱ በኋላም ይህ ብድር ሙሉ በሙሉ ይሰረዝላቸዋል። ለምዕራባዊያኑ የውልደት መጠን መቀነስ ምክንያቱ በአገር ውስጥ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር ሲሆን፤ ለአንድ ቁጥሩ ለቀነሰ ህፃን በሌላ ስደተኛ ህፃን ስለሚተካ ቁጥሩ ያን ያህል አሳሳቢ አይሆንም ሲሉ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የሃንጋሪ ህዝቦች የተለየ አስተሳሰብ ነው ያላቸው የሚሉት ሚኒስትሩ "ቁጥር አንፈልግም፤ የምንፈልገው ሀንጋሪያዊያን ህፃናትን ነው" ብለዋል። • «የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፦ ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ቢሆንም ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ኦርባን ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት መንግሥት የሚያወጣቸውን አዳዲስ ህጎች በመቃወም በቡዳፔስት ህዝባዊ ተቃውሞ ተደርጎ ነበር። ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችም በሚኒስትሩ ቢሮ አቅራቢያ በመሰባሰብ እንዲሁም ሌሎች በዳንዩብ ወንዝ ላይ የተገነባውንና በአገሪቱ ትልቅ የሚባለውን ድልድይ በመዝጋት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የውልደት መጠንን ለመጨመር የሚያስችል ሰባት የእቅድ ዝርዝሮችን አንስተው ነበር።ከእነዚህም መካከል • በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት 21 ሺህ የሚሆኑ የህፃናት ማቆያ ቦታዎችን ማዘጋጀት • ለአገሪቱ የጤና ክብካቤ የሚውል ተጨማሪ 2.5 ቢሊየን ዶላር ማዋል • ሰባት የተሳፋሪዎች ወንበር ያለው ተሽከርካሪ ለመግዛት መንግስት ድጋፍ ማድረግ የሚሉትን ነጥቦች የዘረዘሩ ሲሆን ንግግራቸውንም "ረጂም እድሜ ለሀንጋሪና ለህዝቦቿ" ሲሉ ተደምጠዋል። • መቀመጫቸውን ለማስተለቅ የሚታትሩ ሴቶች እየሞቱ ነው አንዲት ሀንጋሪያዊት ሴት በሕይወት ዘመኗ የውልደት መጠኗ በአማካይ 1.45 ሲሆን ይህም የአውሮፓ ህብረት ከተቀመጠው አማካይ የውልደት መጠን 1.58 ያነሰ ነው። ፈረንሳይ ከአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ከፍተኛ የውልደት መጠን ያላት ሲሆን በአማካይ 1.96 ነው፤ በተቃራኒው ስፔን 1.33 አሃዝ በዝቅተኛ ደረጃ ተመዝግባለች። አፍሪካዊቷ ኒጀር ደግሞ በዓለማችን ከፍተኛ የውልደት መጠን ያለባት አገር ተደርጋ ተመዝግባለች ፤ ይህም አንዲት እናት በአማካይ 7.24 ልጆች ሊኖሯት ይችላሉ ማለት ነው።
news-47194996
https://www.bbc.com/amharic/news-47194996
ጃንሆይና ራስ ተፈሪያን
ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ጉልህ ሚና ከነበራቸው መሪዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የመታስቢያ ሃውልት በአፍሪካ ሕብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተመርቆ ይፋ ሆኗል።
አፄ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ጉልህ ሚና ከመጫወታቸውም በላይ 1955 ዓ.ም የተካሄደው የህብረቱ የመጀመሪያው ስብሰባ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ከፍተኛ ጥረት አድረገዋል። ምንም እንኳ በ1994 ላይ የአፍሪካ እንድነት ድርጅት ወደ የአፍሪካ ህብረት የተቀየረ ቢሆንም የአንድነት ድርጅቱን በማቋቋም ላበረከቱት ሚና ሃውልቱ እንዲቆምላቸው ሆኗል። • ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ • የጌታቸው ረዳ ዕይታ፤ ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ • ጤፏን ለማስመለስ እየተውተረተረች ያለችው ኢትዮጵያ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቋቋም ጋር ብቻ ሳይሆን ከራስተፈረያን ጋር ተያይዞ ስማቸው ይነሳል። አጼ ኃይለ ሥላሴ በሌላኛው የዓለም ክፍል በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ ይህን ያክል ተቀባይነት ያላቸው ለምን ይሆን? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው። የአፄ ኃይለ ሥላሴ ንግስናን እና የጥቁሮች የመብት ተሟጋች የነበረውን የጃማይካዊውን ማርከስ ጋርቬይ ትንቢት የሚያገናኙት ብዙዎች ናቸው። ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ንግስናን 10 ዓመታት በፊት ጃማይካዊው የመብት ተሟጋች ማርከስ ጋርቬይ ተከታዮቹን ''ወደ አፍሪካ ተመልከቱ፤ ጥቁር ንጉስ ይነግሳል፤ የመሰጠት ዓመትም ይመጣል'' ሲል ነገራቸው። ከትንቢቱ 10 ዓመታት በኋላ ራስ ተፈሪ መኮንን የተሰኙ በኢትዮጵያ ሲነግሱ በርካቶች ትንቢቱ እውነት የመሆኑ ምልክት ነው አሉ። ከ10ሺህ ኪ.ሜ በላይ ርቀው የሚገኙት ሰዎች፤ አፄ ኃይለ ስላሴን እንደ ፈጣሪ ኢትዮጵያንም የቃል-ኪዳኗ ምድር አድርገው ወሰዱ። አፄ ኃይለ ስላሴ 1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጃማይካን ጎብኝተው ነበር። በጉብኝታቸው ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ጃማይካውያን የደመቀ አቀባበል አድረገውላቸዋል። • "ኮሜዲ፣የጤፍ ዝናብ ነው" ቤቲ ዋኖስ • ጣልያን በተሸነፈችበት አድዋ ቆንስላዋን ለምን ከፈተች? ከ1940ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በርካታ ራስተፈሪያኖች ወደ ኢትዮጵያ መትመም ጀምረው ነበር። የጃንሆይ ጉብኝትን ተከትሎም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ጃማይካውያን ቁጥር ጨምሮ ነበር። አፄ ኃይለ ስላሴ በ1967 ዓ.ም ህይወታቸው ሲያልፍ በተከታዮቻቸው ዘንድ ግራ መጋባት ተፈጥሮ ነበር። ከዚያም ያረፈው የምድር አካላቸው ነው ተብሎ በተከታዮቻቸው ዘንድ ታመነ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ''ወደ አፍሪካ ተመልከቱ፤ ጥቁር ንጉስ ይነግሳል፤ የመሰጠት ዓመትም ይመጣል'' ብሎ የተንበየው ጋርቬይ የአፄ ኃይለ ስላሴ ተቺ ነበር። አሁንም ቢሆን አፄ ኃይለ ስላሴ ለኢትዮጵያ መልካም ነበሩ፤ አይደለም ኢትዮጵያን በድለዋል የሚሉ የሃሳብ ክፍፍሎች እንዳሉ ናቸው። የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት በኢትዮጵያ 1966 ተከስቶ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው እና ወደ 200ሺህ ህዝብ ላለቀበት ረሃብ አፄ ኃይለ ስላሴ ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት አላሳዩም ሲል ይወቅሳቸዋል። በስልጣን ዘመናቸውም በተቀናቃኞቻቸው ላይ በሚወስዷቸው የማያዳግም እርምጃ ይታወቃሉ። የጣሊያን ወረራ ተከትሎ አፄ ኃይለ ስላሴ ሃገር ጥለው መሸሻቸው በማርከስ ጋርቬይ ጭምር አስወቅሷቸዋል። አፄ ኃይለ ስላሴ ከቀድሞ የጋና ፕሬዚዳንት ኩዋሜ ኑኩሩማ የአፍሪካ እንድነት ድርጅት በተቋቋመት ወቅት አዲስ አበባ ላይ። መምህሩ ዮሃንስ ወልደማሪያም (ዶ/ር) አፄ ኃይለ ስላሴ እንደ አምባገነን ነው መታሰብ ያለባቸው ሲሉ ይሞግታሉ። አፄ ኃይለ ስላሴ አርቅቀው ያጸደቁት ሕገ-መንግሥት ስልጣኑን በሙሉ በእሳቸው ቁጥጥር ሥር ያደረገ መሆኑ ይወሳል። በተቃራኒው የጃንሆይ ደጋፊዎች አፄ ኃይለ ስላሴ ድንቅ መሪ መሆናቸውን እና ኢትዮጵያን ለማዘመን የታተሩ መሪ መሆናቸውን ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ በጣሊያን ከተወረረች በኋላ በሊግ ኦፍ ኔሽን ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ያቀረቡት አቤቱታ አሁንም ድረስ ይታሰባል። በአዲስ አበባ የቆመውም ሃውልት በርካቶችን አፄ ኃይለ ስላሴ ለፓን አፍሪካኒዝም ትብብር ለማጠንከር የነበራቸውን ህልም ለተቀረው የአህጉሪቱ ህዝብ አስታዋሽ ሆኖ ይቆያል የሚል እምነት አሳድሮባቸዋል።
news-52796481
https://www.bbc.com/amharic/news-52796481
ናይጄሪያ ምግብ ከውጪ ለማስገባት ገንዘብ የለኝም አለች
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሐሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፈጠረው ችግር የተነሳ አገራቸው ምግብ ከውጪ ለማስገባት "ገንዘብ የላትም" አሉ።
በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ከኢትዮጵያ ቀድማ የመጀመሪያውን የሆነችው ናይጄሪያ የውጪ ምንዛሪ ችግር ስላጋጠማት የአገሪቱ አርሶ አደሮች ሕዝቡን መቀልብ የሚችል መጠን ያለው ምግብ እንዲያመርቱ ፕሬዝዳንቱ ጠይቀዋል። ቡሐሪ ይህንን የተናገሩት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሚከሰትን የምግብ ዋስትና ችግር በተመለከተ ስጋቶች በመፈጠራቸውና በአገሪቱም በምግብ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ተከትሎ ነው። እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት የአገሪቱ አርሶ አደሮች እንኳን በዚህ በወረርሽኙ ወቅት ይቅርና ከዚያ በፊትም 200 ሚሊዮን የሚደርሰውን ሕዝብ የምግብ ፍላጎት ማሟላት አይችሉም ነበር። ምንም እንኳን የናይጄሪያ የግብርና ዘርፍ በርካታ ሰዎች የተሰማሩበት ዋነኛ መስክ ቢሆንም፤ ከነዳጅ ዘይት በሚገኝ ገቢ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጥገኛ በሆነው የአገሪቱ መዕተዓኘየ ሐዓዕጠዕ ተነሳ ትኩረት ተነፍጎት ቆይቷል። ናይጄሪያ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በድንበሮቿ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ከታይላንድ በሕገ ወጥ መንገድ የሚገባውን የሩዝ ምርት በመግታት በአገር ውስጥ ለሚመረተውን ሩዝ ገበያ ለማመቻቸት ጥረት ስታደርግ ነበር። ናይጄሪያ ከውጪ የሚመጣ የሩዝ ምርት ላይ ክልከላ ከመጣሏ ቀደም ብሎ በየዓመቱ ከአንድ ሚሊየን ቶን በላይ ሩዝ ከታይላንድ ታስገባ ነበር። አገሪቱን በሚያዋስኗት አገራት ድንበር በኩል የሚገባው ሩዝ የተከለከለ በመሆኑ በወደብ በኩል ብቻ ነው ሩዝ ወደ ናይጄሪያ እየገባ ያለው። በዚህም ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣሉ ዋጋውን አስወድዶታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ በኋላ ናይጄሪያ ውስጥ የምግብ ዋጋ ላይ ጭማሪ የተከሰተ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዘይት ዋዳ በመውደቁ ምክንያት ደግሞ መንግሥት ያገኘው የነበረው በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እንደተነበየው በአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላት ናይጄሪያ በዚህ ዓመት ኢኮኖሚዋ በ1.5 በመቶ ያሽቆለቁላል።
news-56183557
https://www.bbc.com/amharic/news-56183557
ኮሮናቫይረስ ፡ ለኢትዮጵያና ለሌሎች አገራት ይሆናል የተባለው የኮቪድ-19 ክትባት መሠራጨት ጀመረ
ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች አገራት የኮቪድ-19 ክትባትን ያቀርባል የተባለው የኮቫክስ የክትባት አቅርቦት ፕሮግራም በአፍሪካ ውስጥ መሰራጨት ጀመረ።
ክትባቱ ጋና ዋና ከተማ ሲደርስ በዚህም መሠረት የመጀመሪያው የኮቫክስ ክትባት ጋና በመቀበል የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። በዓለም ጤና ድርጅት መሪነት የተዘረጋው ይህ ሥርዓት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ለሁሉም የዓለም አገራት በፍትሃዊ መንገድ እንዲከፋፈሉ ለማድረግ ያለመ ነው። ኮቫክስ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ሁለት ቢሊየን የኮቪድ-19 ክትባቶችን በዓለም ዙሪያ የማሠራጨት ዕቅድ አለው። በአስትራዜኔካና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተመረቱ 600 ሺህ ብልቃጥ ክትባቶች ዛሬ ረቡዕ የጋና ዋና ከተማ አክራ ደርሰዋል። የዓለም ጤና ድርጅትና የተባበሩት መንግሥት የሕፃናት መርጃ [ዩኒሴፍ] ባወጡት መግለጫ "እጅግ ጠቃሚ እርምጃ ነው" ብለዋል። "የኮቪድ-19 ክትባቶች ጋና መድረሳቸው ወረርሽኙን ለማጥፋት አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ ነው" ብለዋል ድርጅቶቹ። ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጋና ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት 580 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ነገር ግን ጋና የምትመረምረው ሰው ብዛት አናሳ በመሆኑ ነው እንጂ ቁጥሩ ከዚህ በላይ ነው ተብሎ ይታመናል። ኮቫክስ ምንድነው? የኮሮናቫይረስ ክትባት ሥራ ላይ መዋል ከጀመረ ወዲህ ሃብታም የሚባሉቱ አገራት ናቸው ክትባቱን በገፍ እየገዙ ዜጎቻቸውን እየከተቡ ያሉት። በዶክተር ቴድሮስ መሥሪያ ቤት አማካይነት የተዘረጋው ኮቫክስ የተሰኘው ማዕቀፍ ደሃ አገራት ክትባቱን ለማግኘት ብዙ እንዳይጠብቁ ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል። በዚህ ማዕቀፍ መሠረት ሃብታሞቹ አገራት አቅም የሌላቸውን አገራት በገንዘብ እንዲያግዙ ይደረጋሉ። በአንድ ዓመት ብቻ በ190 አገራት ሁለት ቢሊዮን ክትባቶችን ለማሠራጨት ታልሟል። በተለይ ደግሞ 92 ደሃ የሚባሉ አገራት ከሌሎች 98 አቅም ካላቸው አገራት እኩል ክትባቱን እንዲቀበሉ ይደረጋል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ናቸው። ነገር ግን እንደ ሴኔጋል ያሉ ጥቂት አገራት ከዚህ ማዕቀፍ ውጭ ክትባት ማግኘት ችለዋል። ፕሮግራሙ እስካሁን ድረስ ለክትባት የሚሆን 6 በሊየን ዶላር ማሳበሳብ ችሏል። ቢሆንም ተጨማሪ 2 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል እየተባለ ነው። ምንም እንኳ ፕሮግራሙ ቀርፋፋ ነው እየተባለ ቢተችም የዓለም ጤና ድርጅትና ዩኒሴፍ አሁን ጋና የደረሰው ክትባት የመጀመሪያው ዙር ነው ብለዋል።
news-52367655
https://www.bbc.com/amharic/news-52367655
ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ በጣለ ከባድ ዝናብ የሰው ህይወት አለፈ
በከባድ ዝናብ ምክንያት በኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ጨምሮ በሌሎች ምሥራቅ አፍሪካ አገራት የጎረፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ተባለ።
የኬንያ ሜትዮሮሎጂ ክፍል ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ ጎርፍ ሊያጋጥም እንደሚችል አሰጠንቅቋል። ተቋሙ እንዳስታወቀው በዋና መዲናዋ ናይሮቢና በምዕራብና ምሥራቅ የአገሪቷ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ብሏል። ከትናንት በስቲያ በጋሞ ዞን የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፋና መዘገቡ ይታወሳል። በምዕራብ ኬንያ እየጣለ ያለውን ከባድ ዝናብም ተከትሎ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት ቢያንስ ከ10 ሰዎች በላይ ሕይወታቸው አልፏል። በተመሳሳይ በኡጋንዳም ከባድ ዝናብ እየጣለ መሆኑን ተከትሎ የቪክቶሪያ ሐይቅ መጠን በመጨመሩ በሐይቁ ዳርቻ የሚኖሩ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ባለፈው እሁድ አሳስበዋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሥራቃዊ ክፍልም በጎርፍ ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ከ10 በላይ ሰዎች ድግሞ ሞተዋል። ባለፈው ዓመት በህዳርና ታህሳስ ወር ባልተጠበቀ መልኩ የጣለው ከባድ ዝናብ ጎርፍ ማስከተሉ ይታወሳል። በመሆኑም አሁን እየጣለ ያለው ዝናብም ባልተጠበቀ መልኩ ከባድ እንደሚሆን ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።
news-49108558
https://www.bbc.com/amharic/news-49108558
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ማምረት ላቆም እችላለሁ ሲል አስጠነቀቀ
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ወደ በረራ የሚመለሱበት ጊዜ የሚጓተት ከሆነ አውሮፕላኖቹን ማምረቴን አቆማለሁ ሲል አስጠነቀቀ።
ትናንት በ737 ማክስ አውሮፕላኖቹ መዘዝ በሩብ ዓመት ውስጥ ብቻ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የ3.4 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠመው ይፋ አድርጓል። በተለያዩ ቀጠናዎች ከሚገኙ አየር ተቆጣጣሪዎች ጋር የሚደረገው ትንቅንቅ የሚቀጥል ከሆነ እና አውሮፕላኖቹን በአጭር ግዜ ውስጥ ወደ በረራ መመለስ ካልቻልኩ ማክስ 737 አውሮፕላኖችን ማምረቴን ሙሉ በሙሉ አቆማለሁም ብሏል። • ቦይንግ ለተጎጂ ቤተሰቦች 100ሚ. ዶላር ሊሰጥ ነው • ቦይንግ በ 737 ማክስ ምክንያት አምስት ቢልየን ዶላር ማውጣቱ ተገለጸ ይሁን እንጂ የቦይንግ ኃላፊ ዴኒስ ሙለንበርግ በጥቅምት ወር አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንደሚመለሱ ባለሙሉ ተስፋ ናቸው። ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 ከተከሰከሰ በኋላ በመላው ዓለም አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ እገዳ ተጥሎባቸዋል። የኢትዮጵያው አየር መንገዱ አውሮፕላን ከመከስከሱ አምስት ወራት ቀደም ብሎ የኢንዶኔዢያው ቦይንግ 737 ማክስ መከስከሱ ይታወሳል። ለሁለቱ አውሮፕለኖች መከስከስ ምክንያት ዝርዝር ምረመራ እየተካሄ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቶች እንዲሁም የአየር በረራ ደህንነት ባለስልጣናት አውሮፕላኖቹ ኤምካስ ተብሎ የሚጠራው መተግበሪያቸው ላይ እክል መኖሩን ጠቁመዋል። ቦይንግ በኤምካስ ስርዓቱ ላይ ችግር እንዳለ አምኖ እሱን ለማስተካከል እየሰራ ይገኛል። • አቶ ተወልደ አየር መንገዶች ሁሉ ለጊዜው ቦይንግ 737-8 ማክስን እንዳይጠቀሙ ጠየቁ • "ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት ከወራት በፊት ኩባንያ ሊቀመንበር ዴኒስ ሙለንበርግ ''. . . ለኤምካስ ሶፍትዌር ማስተካከያ ከተደረገለት በኋላ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ ሲመለስ በበረራ ደህንነታቸው አስተማማኝ ከሆኑ አውሮፕላኖች መካከል አንዱ ይሆናል'' ሲሉ ተናግረው ነበር። ቦይንግ የኤምካስ ስርዓቱ እያሻሻለ እንደሚገኝ እና እስካሁንም 225 የፍተሻ ምስለ በረራዎችን ማድረጉን ገልጿል። ሁለቱ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከተከሰከሱ በኋላ ቦይንግ በወር ያመርት የነበረውን 737 ማክስ ከ52 ወደ 42 መቀነሱን የኩባንያው ሊቀመንበር ለባለሀብቶች ተናግረዋል። ኩባንያው የሚያመርተው አውሮፕላን ቁጥር በመቀነሱ፤ ግብዓት የሚሆኑ ቁሶች ዋጋ አብሮ ጨምሯል። 737 ማክስ አውሮፕላኖችም ከበረራ በመታገዳቸውና ለደንበኞቹ ማስረከብ ባለመቻሉ ላመረተው ምርት ገቢ መሰብሰብ አልቻለም። በእነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች ኩባንያው በሶስት ወራት ውስጥ 3.4 ቢሊየን ዶላር ከስሯል።ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው
news-54920170
https://www.bbc.com/amharic/news-54920170
ሐይማኖት፡ ቤልጂየም ቅዱስ ቁርዓንን ሊያቃጥሉ የነበሩ የዴንማርክ ዜጎችን አባረረች
ቤልጂየም ቅዱስ ቁርዓንን ሊያቃጥሉ የነበሩ አምስት የዴንማርክ ዜግነት ያለቸው የቀኝ አክራሪ ቡድን አባላትን ከአገሯ አባራለች። ለአንድ ዓመትም ተመልሰው ወደ ቤልጂየም እንዳይገቡ እግድ ጥላባቸዋለች።
ለዚህ ቅጣት የተዳረጉት አምስቱ ዴንማርካዊያን ቤልጂየም ውስጥ ቅዱስ ቁርዓንን የማቃጠል ሥነ ሥርዓት ለማከናወን መዶለታቸውን ስለደረሰችበት ነው። አምስቱ ዴንማርካዊያን ይህን ድርጊት ሊፈጽሙ የነበረው በቤልጂየም ሙስሊሞች በሚበዙበት ሰፈር ነበር። በቤልጂየም የስደተኛ ጉዳዮች ዋና ጸሐፊ ሳሚ ማሕዲ ድርጊቱን ሊፈጽሙ የነበሩትን ዶላቾች "ለሰላምና መረጋጋት አደገኛ ፍጡሮች" ሲሉ ገልጸዋቸዋል። አምስቱ አክራሪ ቀኝ ዘመም ዴንማርካዊያን የመጤ_ጠል ፓርቲ መሪ የዴንማርካዊው የሚስተር ራስመስ ፓሉዳን ወዳጆች ናቸው። ራስመስ ፓሉዳን በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ጥቁሮችና ሙስሊሞች በሕጋዊነት መኖራቸው ትክክል አይደለም፣ ወደመጡበት መመለስም አለባቸው፣ አውሮፓ የአውሮፓዊያን ናት የሚል ትግል የያዘ ቀኝ አክራሪ ዴንማርካዊ ግለሰብ ነው። ፓሉዳን ባለፈው ረቡዕ በፓሪስ ቅዱስ ቁርዓንን የማቃጠል ሥነ ሥርዓት ለማከናወን ፍላጎት እንዳለው በመታወቁ በአስቸኳይ ከፈረንሳይ እንዲወጣ መደረጉ ይታወሳል። በዚህ የፈረንጆች ዓመት መጀመርያ ደግሞ ራስመስ ፓሉዳን በአገሩ ዴንማርክ የአንድ ወር እስር ተፈርዶበት ነበር። ለእስር የተዳረገውም በማኅበራዊ ሚዲያው ጸረ ኢስላም ይዘት ያላቸው ቪዲዮዎችን በማሰራጨቱ ነበር። ራስመስ ሁሉም ሙስሊሞች ከአውሮፓ ሊወጡ ይገባል የሚል አቋም የሚያራምድ ፓርቲ መሪ ነው። አምስቱ ቤልጂየም ያባረረቻቸው ዴንማርካዊያን የፓሉዳን አጋሮች የነበሩ ሲሆን፤ በርካታ ሞሮኳዊያን ይኖሩበታል በሚባለው በብራስልስ ከተማ ሞልነቢክ ሴይን ዣን ሰፈር ቅዱስ ቁርዓንን ለማቃጠል ሲዶልቱ ነበር ተብሏል። የቤልጂየም የስደተኞች ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ "አሁን እኛ ጥላቻን የሚነዛ ሰው አንፈልግም" ብለዋል። ባለፈው ነሐሴ የሚስተር ራስመስ ፓሉዳን ደጋፊዎች ከኮፐንሐገን በቅርብ ርቀት በምትገኘውና ስደተኞች በሚበዙባት የስዊድን ሦስተኛ ከተማ ማልሞ፣ ቅዱስ ቁርዓን ለማቃጠል በመሞከራቸው ረብሻ ተቀስቅሶ ብዙ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
news-44281318
https://www.bbc.com/amharic/news-44281318
ብሩንዲ በፈረንሳይ ኤምባሲ ለእርዳታ የተበረከቱላትን አህዮች ስድብ ነው በማለት አጣጣለች
የፈረንሳይ ኤምባሲ በብሩንዲ ጊቴጋ መንደር ለሚኖሩ ሰዎች አስር አህዮችን በእርዳታ መለገሱን ተከትሎ፤ የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ፒኤሬ ንኩሩንዚዛ አማካሪ ዘለፋ ነው ሲሉ ለ ኤ ኤፍ ፒ ገለፁ።
የግብርና ሚኒስቴር ሴቶችና ህፃናት ላይ የሚሰራ አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅትን ወክሎ አህዮቹ ከጎረቤት አገር ታንዛኒያ እንዲገዙ ጠይቋል። ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በሴቶችና ህፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን፤ ሴቶችና ህፃናት የግብርና ውጤቶችን፣ ውሃ ፣ እንጨትና ሌሎች ቁሳቁሶችን እንዲያመላልሱበት በማድረግ ሸክማቸውን ለማቅለል በማለም ነበር አህዮቹን ለመግዛት እቅድ ውስጥ የገባው። የግብርና ሚንስትርሩ ዲዮ ጋይድ ሩሬማ ያለ ምንም ሂደት አህዮቹ ከተሰጡበት አካባቢ በአስቸኳይ ተሰብስበው እንዲመጡ የአካባቢው አስተዳዳሪ እንዲያስተባብሩ ጠይቀዋል። የብሩንዲ ምክርቤቱ ፕሬዚዳንት ቃለ አቀባይ የሆኑት ጋቢይ ቡጋጋ በበኩላቸው "ፈረንሳይ ወደ አህያ ደረጃ አውርዳናለች ፤እውነት ለመናገር አህያ የምን ምልክት ነው?" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል። የፈረንሳይ አምባሳደር ሎረንት ደላሆውሴ በበኩላቸው "እያንዳንዱ ሒደት የታወቀ ነበር ፤ ይህም አዲስ ነገር እንዳልሆነና ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ፕሮጀክት ከቤልጂየም በተገኘም እርዳታ በምስራቅ ሩይሂ ግዛት ተመሳሳይ ድጋፍ ተደርጓል ፤ነገር ግን ምንም ዓይነት ምላሽ አልተሰጣቸውም" ብለዋል። አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአውሮፓ ዲፕሎማት ፈረንሳይ ከወራት በፊት በብሩንዲ ህገ መንግስቱን ለማሻሻል በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ ትችት በመሰንዘሯ ምክንያት ለእርሱ የተሰጣት አፀፋዊ ምላሽ ነው ሲሉ ለ ኤ ኤፍ ፒ ተናግረዋል። ፈረንሳይ በህዝበ ውሳኔው ላይ ህገ መንግስቱ የፕሬዚዳንቱን የስልጣን ቆይታን በማራዘም እስከ አውሮፓውያኑ 2034 ድረስ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችላቸው ነው በማለት መተቸቷ የሚታወስ ነው።
47399820
https://www.bbc.com/amharic/47399820
የ5 ሚሊዮን ብር እራት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር
በቅርቡ ይፋ የተደረገውን የአዲስ አበባ ወንዞችና ዳርቻዎቻቸውን የማልማት ሥራን እውን ለማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት አማካይነት በነፍስ ወከፍ አምስት ሚሊዮን ብር ተከፍሎ የሚታደሙበት የእራት ድግስ ተዘጋጅቷል።
'ገበታ ለሸገር' በሚል ስያሜ የተዘጋጀው የእራት ዝግጅት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሚታደሙበት ሲሆን አምስት ሚሊዮን ብር ከፍለው የዝግጅቱ ተሳታፊ ለሚሆኑ ሰዎች የተለያዩ መታሰቢያ ተዘጋጅቷል። • የማትተነፍሰው ከተማ: አዲስ አበባ • ፓሪስን፣ ኒዮርክን፣ ዱባይን ... ወደ አዲስ አበባ ይህ የልማት ሥራ ሲጠናቀቅ በተለያዩ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻዎች ላይ የእራት ዝግጅቱ ታዳሚዎቹ ስም በተናጠል ተጽፎ የሚቀመጥ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋርም የአንድ ለአንድ ፎቶ የመነሳት እድልን ያገኛሉ ተብሏል። ይህም ፎቶግራፍ የአዲስ አበባን ገጽታ የቀየሩ ግለሰቦች በሚል ተሰባስቦ በአንድ ጥራዝ ላይ እንዲቀርብ ይደረጋል ተብሏል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ዛሬ ባቀረበው የግብዣ ጥሪም የንግድ ተቋማት ባለቤቶችና አመራሮች እንዲሁም የዓለም አቀፍና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በዚሁ የእራት ዝግጅት ላይ እንዲታደሙ ጋብዟል። በቫርኔሮ ኩባንያ የሚከናወነው የአዲስ አበባን ገጽታ በከፍተኛ ደረጃ ይለውጣል ተብሎ የታሰበው ፕሮጀክት በ29 ቢሊየን ብር ወጪ የሚከናወን ሲሆን በሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተነግሮለታል። • በሃገሪቱ የተከሰቱት ቀውሶችና አዲስ አበባ ሥራው የአዲስ አበባ ከተማን ለሁለት ከፍለው የሚያልፉ ወንዞችን መሰረት ያደረገ ሲሆን ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እርቀት የሚሸፍን ነው። የአዲስ አበባ ወንዞችና ዳርቻዎች ልማት ሥራ ሲጠናቀቅ 4 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ የተነገረ ሲሆን፤ በውስጡም አስፈላጊው ነገር የተሟላላቸው የመዝናኛ፣ የመጓጓዣ፣ የንግድ ማዕከላትና አረንጓዴ ስፍራዎች ይኖሩታል ተብሏል።
news-52273877
https://www.bbc.com/amharic/news-52273877
ኮሮናቫይረስ የዓለም የምግብ አቅርቦት ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ
ብዙ አገራት እንቅስቃሴ ገተዋል። ይህን ተከትሎም በመደብሮች የምግብ እጥረት መከሰቱ እየተነገረ ነው።
በሌላ በኩል ሬስቶራንቶችና ሌሎችም የመስተንገዶ አገልግሎት ሰጪዎች በመዘጋታቸው፤ ምግብ አምራቾች ክምችታቸው ሊበላሽ እንደሆነ ገልጸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ በምግብ አቅርቦት ዘርፍ ላይ በተለያየ መንገድ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው። ከነዚህ አምስቱን እንመልከት። 1. ወተት ተትረፍርፏል አንዳንድ አገራት ካፌዎቻቸውን ዘግተዋል። ቡና እተሸጠ አለመሆኑ ደግሞ የወተት ምርት እንዲትረፈረፍ ምክንያት ሆኗል። የአሜሪካ የወተት ተዋጽኦ አምራቾች እንደሚሉት፤ ከገዢዎች ጋር እየተገናኙ ስላልሆነ በየቀኑ ወደ 14 ሚሊዮን ሊትር ወተት ለመድፋት ተገደዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የወተት ተዋጽኦ አምራቾች ማኅበር ኃላፊ ፒተር ኤሊቪስ፤ በየሳምንቱ አምስት ሚሊዮን ሊትር ወተት ከጥቅም ውጪ ሊሆን ይችላል ብለዋል። አርሶ አደሮች ምርታቸውን መሸጥ አለመቻላቸው ገቢያቸውን እንደሚያናጋውም ኃላፊው ይናገራሉ። የስኮትላንድ አርሶ አደሮች የወተት ምርታቸውን እንዲቀንሱ ተነግሯቸዋል። 2. ሰብል እየባከነ ነው አንዳንድ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በቀጥታ ለመደብሮች ለማስረከብ ቢሞክሩም፤ የገበያ ፍላጎት በመቀየሩና ምርት ከመጠን በላይ በመከማቸቱ ውጤታማ አልሆኑም። ኒው ዮርክ ታይምስ ያነጋገረው ዶሮ አምራች፤ በየሳምንቱ 750,000 እንቁላል ለማሶገድ ተገድጃለሁ ይላል። አንድ አርሶ አደር ደግሞ የሽንኩርት ምርታቸው ባለበት በስብሶ ወደ ማዳበሪያነት እንዲለወጥ ትተውታል። የሕንድ ሻይ አምራቾችም የገፈቱ ቀማሽ ሆነዋል። 3. በቂ ሠራተኞች የሉም ከምርት መትረፍረፍና ለገበያ ማቅረብ አለመቻል በተጨማሪ፤ ሠራተኞች አለማግኘትም አርሶ አደሮችን እየፈተነ ነው። አገር አቀፍ እንቅስቃሴ የማቆም ውሳኔና ማኅበራዊ ርቀትን የመጠበቅ ሕግ ብዙዎች ሥራ እንዲያቆሙ ምክንያት ሆኗል። ባለፈው ሳምንት፤ ጀርመን በሺዎች የሚቆጠሩ የሮማንያ እና ፖላንድ ሠራተኞች ሰብል እንዲሰበስቡ ፍቃድ ሰጥታ ነበር። 4. የሸማቾች ባህሪ ተቀይሯል በወረርሽኙ ሳቢያ ሸማቾች የሚገዟቸው የሸቀጥ አይነቶች ተቀይረዋል። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም ብዙዎች ቤት እያበሰሉ ስለሆነ የዱቄት ፍላጎት ጨምሯል። ፈረንሳውያን በበኩላቸው የፋብሪካ ውጤት የሆኑ ምግቦችን ቀንሰዋል። ይህም ጤናማ አመጋገብ ማዘውተር በመጀመራቸው አልያም ከአነስተኛ ቸርቻሪዎች መግዛት ስለጀመሩም ሊሆን ይችላል። የፈረንሳይ የግብርና ሚንስትር የምግብ መደብሮች እንዲከፈቱ ጠይቀዋል። ቀድሞ የተዘጉት ማኅበራዊ ርቀትን ለማስጠበቅ አይቻልም በሚል ፍራቻ ነበር። 5. የተከማቸው ምግብ ጥቅም ላይ አልዋለም የመስተንግዶ ዘርፎች መዘጋት የተከማቹ ምግቦች እና መጠጦች ጥቅም አልባ ለመሆናቸው ምክንያት ነው። በእርግጥ የአንዳንድ ምግቦች ሽያጭ ጭማሪ አሳይቷል። ለአብነት ያህል በ38 በመቶ ቀንሶ የነበረው የአሜሪካ የብርቱካን ጭማቂ ገበያ አሁን ላይ መሻሻል አሳይቷል። የ ‘አግዚክሮፕ’ የገበያ ጥናት ባለሙያ ስቴፈን ኢንስ እንደሚሉት፤ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም የሚያሳድጉ ምግቦች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። ነገር ግን በረራዎች መታገዳቸው የብርቱካን ጭማቂ የመሰሉ ምርቶች በስፋት እንዳይከፋፈሉ አድርጓል።
news-55421936
https://www.bbc.com/amharic/news-55421936
ፍርድ ቤት በጣሊያን ኤምባሲ ላሉት የቀድሞ ባለስልጣናት አመክሮ ፈቀደ
ለሠላሳ ዓመታት በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት የቆዩት ሁለት የቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከኤምባሲው እንዲወጡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአብላጫ ድምጽ ወሰነ።
ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ ሠላሳ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት የቆዩት እነዚህ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ ናቸው። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ሁለቱን ግለሰቦች በተመለከተ የቀረበውን የአመክሮ አቤቱታ ከመረመረ በኋላ በኤምባሲው ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት የቆዩት የቀድሞ ባለስልጣናት ካሉበት ቦታ ነጻ ሊወጡ ይገባል ሲል በአብላጫ ድምጽ ወስኗል። ጉዳዩን ለመመልከት ከተሰየሙት ዳኞች መካከል አንደኛው ግለሰቦቹ ፍርድ አግኝተው ቅጣታቸውን በማረሚያ ቤት ያልተቀበሉ በመሆናቸው "ከመደበኛው የአመክሮ ሥርዓት ውጪ የአመክሮ ጊዜያቸው እንደደረሰ በመቁጠር እንዲለቀቁ ከውሳኔ መደረሱ" ላይ ልዩነት እንደላቸው ማሳወቃቸውን ፋና ዘግቧል። በደርግ የስልጣን ዘመን ተፈጽመዋል በተባሉ ከፍተኛ ወንጀሎች ከሌሎች የወቅቱ ከፍተኛ ባለስልጠናት ጋር በሌሉበት ተከሰው የነበሩት ሁለቱ ግለሰቦች የሞት ፍርድ ተበይኖባቸው ነበር። የኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባን ከመያዙ አንድ ቀን ቀደም ብለው በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ከተጠለሉት አራት የወቅቱ ከፍተኛ ባለስልጣንት መካከል የነበሩት ብርሃኑ ባይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ የሠራዊቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ነበሩ። ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ ከእስር ቤት ውጪ ለ30 ዓመታት ያህል በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ከቆዩ በኋላ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በግለሰቦቹ ላይ የተላለፈው የሞት ቅጣት ውሳኔ ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲቀየር ለአገሪቱ ፕሬዝደንት ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር የዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪ ለቢቢሲ ባለፈው ሳምንት መግለጻቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሞት ቅጣቱ ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲሻሻል መፍቀዳቸው ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ይፋ ተደርጓል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን ለቢቢሲ እንደገለጹት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለቱ የቀድሞ ባለስልጣናት፤ የሞት ፍርዳቸው ወደ እድሜ ልክ እስራት በርዕሰ ብሔሯ ተቀንሶላቸዋል። ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደርግ መንግሥት ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ነው የሞት ቅጣት የተበየነባቸው። ዐቃቤ ሕግም በተመሳሳይ የተላለፈባቸው የሞት ፍርድ ወደ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀነስ በይቅርታ እና የምህርት ቦርድ በኩል ለርዕሰ ብሔሯ ጥያቄ ማቅረቡ ተነግሯል። ሁለቱ የቀድሞ ባለስልጠናት ለዓመታት ተጠግተውበት ከነበረው ኤምባሲ እንዲወጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተሰጠው በዐቃቤ ሕግ ጥያቄ መሠረት ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የሞት ቅጣቱን ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲቀነስ ካደረጉ በኋላ በዐቃቤ ሕግ በአመክሮ እንዲለቀቁ በቀረበ ጥያቄ ነው። የኢህአዴግ ኃይሎች አዲስ አበባን ለመያዝ አንድ ሳምንት ሲቀራቸው የወቅቱ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም ስልጣናቸውንና አገራቸውን ለቀው አስካሁን ድረስ በጥገኝነት ወደሚገኙባት ዚምባብዌ ካቀኑ ከሳምንት በኋላ ነበር ባለስልጣናቱ ወደ ጣሊያን ኤምባሲ የገቡት። ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እንዲሁም ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ በውቅቱ ተይዘው ከነበሩ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በስልጣን ዘመናቸው ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸው በሌሉበት የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው ነበር። መንግሥትም የጣሊያን መንግሥት ተፈላጊዎቹን አሳልፎ እንዲሰጠው በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ጣሊያን ጥያቄውን ሳትቀበለው ግለሰቦቹን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኤምባሲዋ ውስጥ አስጠግታ 30 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ለቀሩት ጊዜ አቆይታቸዋለች። በወቅቱ በኤምባሲው ውስጥ ጥገኝነት በመጠየቅ ገብተው የነበሩት ከፍተኛ ባለስልጣናት ስምንት የነበሩ ሲሆን አራቱ በእራሳቸው ፈቃድ ኤምባሲውን ለቀው መውጣታቸው ይነገራል። አሁን ኤምባሲው ውስጥ ከሚገኙት ከኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ በተጨማሪ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም አገር ለቀው ሲሄዱ ለቀናት የመሪነት ቦታውን ይዘው የነበሩት ሌ/ጀኔራል ተስፋዬ ገብረኪዳን እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኃይሉ ይመኑ ይገኙ ነበር። እነዚህ ከፍተኛ የቀድሞ ባለስልጣናት በኤምባሲው ውስጥ ጥገኝነት አግኝተው ለተለያዩ ጊዜያት ከቆዩ በኋላ እዚያው እንዳሉ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው እንዳለፈ ይታወቃል። ዚምባብዌ የሚገኙትንና በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ በወቅቱ እጃቸውን ሰጥተው በነበሩ የቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ጥፋቶች የከባድ ክስ ተመስርቶባቸው የፍርድ ሂደቱ ለዓመታት ከተካሄደ በኋላ አብዛኞቹ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። ነገር ግን በእስር ላይ ሳሉ ህይወታቸው ካለፈው ውጪ ያሉት ባለስልጣናት ከ20 ዓመታት እስር በኋላ በምህረት ነጻ መውጣታቸው ይታወቃል።
news-56372138
https://www.bbc.com/amharic/news-56372138
ተዋናይቷ ተቃውሞዋን ለመግለፅ በፈረንሳይ የፊልም ሽልማት ላይ እርቃኗን ወጣች
ፈረንሳዊቷ ተዋናይት ሴዛር ተብሎ በሚታወቀው የአገሪቷ የፊልም ሽልማት ላይ ተቃውሞዋን ለመግለፅ እርቃኗን ወጥታለች።
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የአገሪቱ መንግሥት ለባህል ዘርፍ የሚሰጠውን ድጋፍ ችላ ብሎታል። ከፍተኛ ድጋፍ ያስፈልጋልም በማለት ነው ለተቃውሞ ይህንን ያደረገችው። የ57 አመቷ ኮሪን ማሲየሮ በመጀመሪያ ላይ አህያ የሚመስል ኮትና በደም የተነከረ ቀሚስ ለብሳ የነበረ ሲሆን መድረክ ላይ ከወጣች በኋላ ግን እርቃኗን ቀርታለች። ማሲየሮ በያዝነው ሳምንት አርብ በተካሄደው የአካል ርቀትን በጠበቀው በዚህ ዝግጅት ላይ በምርጥ አልባሳት ዘርፍ የተዘጋጀውን ሽልማት ለመሸለም ነበር ወደ መድረክ የወጣችው። ነገር ግን በሰውነቷ ፊት ለፊት ክፍል ላይ "ባህል ከሌለ የወደፊት የለም" የሚለውን ፅሁፍ ለማሳየት እርቃኗን መውጣቷ በርካቶችን አስደንግጧል። በጀርባዋም እንዲሁ " ጥበባችንን መልሱልን፤ ገንዛባችንን መልሱልን" የሚል ጠቅላይ ሚኒስትር ጂን ካስቴክስን የሚጠይቅ መፈክርም ፅፋ ነበር። በወረርሸኙ ምክንያት ሲኒማ ቤቶች ለሶስት ወራት ያህል ተዘግተዋል። አንዳንድ ተዋናዮችና ዳይሬክተሮችም እንዲሁ በዝግጅቱ ላይ መንግሥት በባህሉ ዘርፍ ሊያደርግ የሚገባውን ድጋፍ ተናግረዋል። በታህሳስ ወር ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋናዮች፣ የፊልም ዳይሬክተሮች፣ ሙዚቀኞች፣ ተችዎችና በጥበቡ ዘርፍ አሉ የሚባሉ ፈረንሳውያን ፓሪስን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች ላይ የተቃውሞ ሰልፎችን አካሂደዋል። ሰልፎቹ መንግሥት የጥበብ ማሳያ ቦታዎችን መዝጋቱን በመተቸት የተደረጉ ናቸው። በዚህ የሽልማት ወቅት የአልበርት ዶፖንቴል ፊልም የሆነው አዲየው ሌ ኮን ወይም (ደህና ሰንብቱ ጅሎች) የሚለው ፊልም በምርጥነት ተሸልሟል። አንዲት ህመምተኛ ሴት የጠፋ ልጇን ለመፈለግ የምታደርገውን ፈታኝ ጉዞ የሚያሳየው ሌላኛው ፊልም ሰባት የሴዛር ሽልማቶችን ያሸነፈ ሲሆን በምርጥ ዳይሬክተርነትም ዘርፍ አንዱ ተሸላሚ ሆኗል። በምርጥ ውጭ አገር ፊልም ዘርፍ የዴንማርኩ 'አናዘር ራውንድ' አሸናፊ ሆኗል።
news-46551604
https://www.bbc.com/amharic/news-46551604
የኤርትራው ፕሬዚዳንት የሞቃዲሾ ጉብኝት
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ዛሬ ወደ ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ማቅናታቸውን ቢቢሲ ሶማሊኛ ዘግቧል።
በሁለት ቀን ቆይታቸውም ከሶማሊያው አቻቸው መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ። ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ የህዝባዊ ግንባር ኃርነት ኤርትራ ታጋይ በነበሩበት ወቅት ሶማሊያ ይመላለሱ የነበረ ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ግን የመጀመሪያ ጉብኝታቸው እንደሆነ ተዘግቧል። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ ሁለቱ ኃገራት የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚል አቋም ያራምዱ የነበረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት በወቅቱ ስልጣን የነበረው የሶማሊያ ፌደራላዊ የሽግግር መንግሥት ግብዣ ተከትሎ ወደ አካባቢው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ያካሄደ ሲሆን፤ ሁለቱም ባላንጣዎች በሶማልያ ተቃራኒ ቡድኖችን ሲደግፉ ነበር። •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •ሴት እስረኞችና የማዕከላዊ ምርመራ •ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? የኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስታት በአካባቢው የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት፤ በብዙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደ የውክልና ጦርነት ተደርጎ ነበር የተወሰደው። ይህንንም ተከትሎ የኤርትራ መንግሥት አልሸባብን እንደሚደግፍ የተባበሩት መንግስታት አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት፣ የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ማዕቀብ የጣለ ሲሆን፣ ማዕቀቡን ለሁለተኛና ለሦስተኛ ጊዜ ማራዘሙም ይታወሳል፡፡ ኤርትራ የሚቀርብባትን ውንጀላ ያልተቀበለች ሲሆን፤ የተጣለባትን ማዕቀብም መሰረት አልባ ስትል አጣጥላው ነበር። ከአስር ዓመት በላይ የሶማሊያና የኤርትራ ግንኙነት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ በቅርብ ጊዜያትም የሁለቱ ኃገራት ግንኙነት በመሻሻል ላይ መሆኑ ተዘግቧል። የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ኤርትራ ሁለት ጊዜ በመሔድ ከኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ሲገናኙ፤ በባህርዳርም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ የሶስትዮሽ ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ የሶማሊያ ጉብኝታቸውን ካጠናቁ በኋላ ወደ ኬንያዋ መዲና ናይሮቢ እንደሚያቀኑም ተገልጿል ።
news-54950897
https://www.bbc.com/amharic/news-54950897
ፔሩ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ሶስት ፕሬዚዳንቶችን አየች
የፔሩ ምክር ቤት አዲስ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት መርጧል- ይህም ከሳምንት ባነሰ ወቅት የመጡ ሶስተኛ ፕሬዚዳንት ናቸው።
የ76 አመት ዕድሜ ባለፀጋው የምክር ቤት አባል ፍራንቺስኮ ሳጋስቲ አገሪቷ ልታደርገው ካቀደችው የመጪው አመት ምርጫም ድረስ ይመራሉ ተብሏል። ግለሰቡ መሃንዲስና ምሁር ናቸው። ባለፈው ሳምንት የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ማርቲን ቪዝካራ በሙስና ወንጀል ተዘፍቀዋል በሚል ከስልጣናቸው ተነስተዋል። ፕሬዚዳንቱ ወንጀሉን አልፈፀምኩም ብለው ቢክዱም በመላው አገሪቷ ተቃውሞ እንዲቀጣጠል ሆኗል። በዚህም ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ተጎድተዋል። አዲሱ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ፍራንቺስኮ ሳጋስቲ የተመረጡት ከሚያስፈልጋቸው ውስጥ ትንሹን 60 ድምፅ ማግኘታቸውን ተከትሎ ነው። ፓርቲያቸው ባለፈው ሳምንት ከስልጣናቸው የተነሱትን ፕሬዚዳንት በመቃወም ድምፅ የሰጠው ብቸኛው ፓርቲ አባል ናቸው። "በአሁኑ ወቅት ለፔሩ ዋነኛው ነገር መረጋጋት እንዲፈጠርና ይህ ቀውስም እንዲቆም ነው" በማለት የፓርላማ አባሉ አልበርቶ ደ ቤላውንዴ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ድምፅ ከመሰጠቱ በፊት ተናግረዋል። ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ፍራንቺስኮ ሳጋስቲ ከመሾማቸው በፊት ፔሩ የፓርላማውን የቀድሞ አፈ ጉባኤ ማኑኤል ሜሪኖን በፕሬዚዳንትነት መርጣ ነበር። በሙስና ተዘፍቀዋል የተባሉትን ፕሬዚዳንት ማርቲን ቪዝካራን ከስልጣን መውረድ ተከትሎ አገሪቷን እንዲመሩ ቢመረጡም በስልጣን የቆዩት ከሳምንት ያነሰ ጊዜ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ግለሰቡ ቀውሱን ለማረጋጋት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ፖለቲከኞች ከስልጣን እንዲወርድ በመጠየቃቸው ነው። በርካታ ወጣቶችን ያካተተ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ፕሬዚዳንት ቪዝካራ ከስልጣን እንዲወርዱ ተከታታይ ሰልፎችን አድርገዋል። በተለይም ቅዳሜ እለት በሊማ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ሰላማዊ ቢሆንም ከአመሻሹ በፖሊስና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ተፈጥሯል ተብሏል። ፖሊስ አስለቃሸ ጋዝ በመርጨትም ሰልፈኞቹን ለመበተን ሞክሯል። በዚህም ግጭት ሁለት ተቃዋሚዎች ተገድለዋል። ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ የመጡት ፕሬዚዳንትም ቀውሱን ከማረጋጋትና ከፖሊስ ጭካኔ ጋር በተያያዘ በተነሳባቸው ተቃውሞ እሁድ እለት ከስልጣን ተነስተዋል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት የምጣኔ ኃብቷ የተዳከመው ፔሩ የማትወጣበት የፖለቲካዊ ቀውስ እንዳትገባ ፍራቻ አለ።
51813107
https://www.bbc.com/amharic/51813107
የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ፎቶ አንሺ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የአፄ ኃይለ ሥላሴ ፎቶ ግራፍ አንሺ በመሆን ያገለገሉት ሰር ሞሂንድራ ዲሎን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ሞሂንድራ በአፄ ኃይለሥላሴ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ላይ አብረዋቸው በመጓዝ ምስሎችን ያስቀሩ እንደነበር በህይወት ድርሳናቸው ላይ ሰፍሮ ይገኛል። የ85 ዓመቱ ሞሂንድራ የ1977ቱን የኢትዮጵያ ድርቅ በምስል በማስቀረትም ይታወቃሉ። • ለአባልነት ዲግሪ ሲጠይቅ የነበረው ፓርቲ ለምርጫው ምን እያደረገ ነው? • ዚምባብዌ ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎች ወላጆችን ልታስር ነው • ከኮሮናቫይረስ ጋር የሚደረገውን ፍልሚያ የሚመሩት ሰው ሞሂንድራ በሙያቸው ስማቸውን የተከሉበትና አሻራውን ያኖሩበት ይህ ስራቸው መሆኑን የሚናገሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ረሃቡ በተከሰተበት ገጠራማ አካባቢዎች ለ13 ወራት በመቀመጥ ዕለት በዕለት በረሃብ የተጎዱ ጨቅላ ሕፃናት ዓይናቸው ስር ሲሞቱ መመልከታቸው በአንድ ወቅት ገልፀው ነበር። ሞሂንዲራ ከመሐመድ አሚን ጋር በመሆን የቀረፁትና 'አፍሪካን ካላቫሪ' በሚል ርዕስ የተሰራው የ30 ደቂቃ ዘጋቢ ፊልም በወቅቱ ተፈጥሮ የነበረውን ረሃብ ለዓለም ሕዝብ በማሳየት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ከዚህ ዘጋቢ ፊልም ተከትሎ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፣ የዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የተለያዩ እርዳታዎችን በመጫን ወደ ኢትዮጵያ ያመሩ ሲሆን እማሆይ ቴሬሳን የመሰሉ ታላላቅ ሰዎች ፊልሙ ያሳደረባቸውን ስሜት ገልፀው ነበር። ሞሂንድራ፣ እማሆይ ቴሬሳ እጃቸውን ይዘው " ልጄ፣ ፈጣሪ ይህንን ፊልም አንድትቀርጸው መርጦሃል" እንዳሏቸው በአንድ ወቅት ተናግረው ነበር። ሞሂንድራ ለአፄ ኃይለሥላሴና ለኢትዮጵያ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በልጅ ልጃቸው ዘረያዕቆብ አስፋወሰን ኃይለስላሴ በኩል "ናይት ኮማንደር" የሚል ዕውቅና ተቀብለዋል። ራሳቸውን በራሳቸው የፎቶግራፍ ማንሳት ጥበብን ማስተማራቸውን የሚናገሩት ሞሂንድራ፣ ከአጼ ኃይለስላሴ ሌላ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ጆሞ ኬኒያታ፣ የኡጋንዳውን ኢዲያምን ዳዳ፣ ሮበርት ሙጋቤ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎችን እንቅስቃሴ በምስል ማስቀረት ችለዋል። ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር መስራት በጀመርኩበት ወቅት " የአፍሪካ መሪ" ተደርገው ይታሰቡ ነበር የሚሉት ሰር ሞሂንድራ፣ በወቅቱ ተከስቶ የነበረው ረሃብ የነበራቸውን ሞገስና ተቀባይነት እንደጎዳው በአንድ ወቅት በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ ተናግረዋል። ሰር ሞሂንድራ ዲሎን የተወለዱት በሕንድ ፑንጃብ በምትገኝ አነስተኛ መንደር ሲሆን መብራት፣ ንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲሁም መፀዳጃ በሌለበት ቤት ውስጥ ልጅነታቸውን እንዳሳለፉ ተናግረዋል።
49996604
https://www.bbc.com/amharic/49996604
ቱርክ ሶሪያ ላይ ጥቃት እንድትፈፅም ይኹንታዋን እንዳልሰጠች አሜሪካ ገለፀች
አሜሪካ ለቱርክ ሰሜናዊ ሶሪያ ላይ ጥቃት እንድትፈፅም 'ይኹንታዋን' እንዳልሰጠች የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ ማይክ ፖምፒዮ ገለፁ።
ቱርክ የአሜሪካ ጦር መውጣቱን ተከትሎ በድንበር አካባቢ በሚገኙና በኩርዶች የሚመራ ጦር ላይ ጥቃት ከፍታለች። ፖምፒዮ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቱርክ የድንበር አካባቢ ጦራቸው እንዲወጣ ማድረጋቸውንም ደግፈዋል። ይህ እርምጃ ግን በአሜሪካ ባሉ ፓለቲከኞችም ሆነ በሌሎች ወገኖች ዘንድ ድጋፍ አላገኘም። • ግብጽ በአባይ ውሃ ላይ ያለኝን መብት ለመከላከል ኃይሉም ቁርጠኝነቱም አለኝ አለች • እየበረታ በመሄድ ላይ ያለው የዋጋ ንረት አዙሪት • "ትግላችን ከጨቋኝ ገዥዎች ጋር እንጂ ከሕዝቡ ጋር አልነበረም" ኦዴፓ ቱርክ የአሜሪካ ጦር መውጣቱን ተከትሎ በድንበር አካባቢ በሚገኙና በኩርዶች የሚመራ ጦር ላይ ጥቃት ከፍታለች። የቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን እንዳሉት ጥቃቱ "ድንበር አካባቢ የሚፈጠር የሽብር ተግባርን መከላከል" ነው። የቱርክ ጦር ድንበር አካባቢ በከፈተው ጦርነት ኢላማ ያደረገው የኩርድ ወታደሮችን አስወግዶ " ደህንነቱ የተጠበቀ ዞን" መፍጠር ሲሆን ስፍራው ላይ የሶሪያ ስደተኞችም ይኖሩበታል። የአውሮፓ ሕብረት ግን ይህ ቱርክ ያቀረበችውን ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ መፍጠር የሚል ሀሳብ መሳካቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳለው ተናግሯል። አክሎም ስደተኞች ሊኖሩበት የሚችሉትና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ መስፈርት ያሟላ ይሆናል የሚለውም ላይ ስጋት እንዳለው አስታውቋል። ዩ ኬ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ቤልጂየምና ፖላንድ ከተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ጋር በቀጣይ ስለሚወሰዱ ርምጃዎች ለመነጋገር ጥያቄ አቅርበዋል። የአረብ ሊግም አስቸኳይ ስብሰባ የጠራ ሲሆን ስብሰባው ቅዳሜ ዕለት በካይሮ ይካሄዳል ተብሏል። በኩርዶች የሚመራው ጦር የቱርክ ጦርን ለመመከት ቃል የገባ ሲሆን ለሚፈፀምበትም ጥቃት ምላሽ መስጠት ጀምሯል። ኩርዶች አሜሪካ አይ ኤስን ለማሸነፍ ባደረገችው ጦርነት ውስጥ ዋነኛ አጋር የነበሩ ሲሆን በርካታ የአይ ኤስ ተዋጊዎችና ቤተሰቦቻቸውን በእስር ቤትና በመጠለያ ካምፖች በማቆየት እየጠበቁ ይገኛሉ። ጦርነቱ ከቀጠለ ይህንን ተግባራቸውን ስለመቀጠል አለመቀጠላቸው የታወቀ ነገር የለም። የአሜሪካ ጦር በሰሜን ሶሪያ የነበሩ ሁለት ከ30 በላይ ምዕራባውያን ገድለዋል በሚል ክስ የቀረበባቸውን የብሪቴይን ዜጎች እንደወሰደ ተናግሯል። ሁለቱ ሰዎች ኤል ሻፌ ኤልሻኪህ እና አሌክሳንዳ ኮቴይ የሚባሉ ሲሆን 'ዘ ቢትልስ' በሚል ቅፅል ስምም ይታወቁ ነበር። የቱርክ ጦር ከትናንት ጀምሮ በበርካታ መንደሮች ላይ የአየር ጥቃት ፈፅሟል። በዚህም የተነሳ በርካታ ሰዎች ከመኖሪያ ሠፈራቸውን ጥለው መሸሽ ጀምረዋል። የኩርድ ጦር ቢያንስ አምስት ንፁኃን ዜጎች በጥቃቱ መሞታቸውን ተናግሮ 25 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። የቱርክ መከላከያ ሚኒስትርም ጦሩ ወደ ድንበር ከተሞቹ መግባቱን ተናግሯል። የቱርክ መከላከያ ኃይል በትዊተር ገፁ ላይ 181 "አሸባሪዎች" ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሙን ተናግሯል።
news-51306276
https://www.bbc.com/amharic/news-51306276
ኮሮናቫይረስ በመላዋ ቻይና መዛመቱ ተነገረ፤ የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ ነው
በቻይና አንድ ግዛት ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሮናቫይረስ መላዋን ቻይናን ማዳረሱንና በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥርም 170 መድረሱ ተነገረ።
የቻይና የጤና ባለስልጣናት እንዳስታወቁት እስከ ትላንት ድረስ በአገሪቱ ውስጥ 7711 በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች አሉ። በሽታው ከቻይና ባሻገር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ቢያንስ 16 አገራት ውስጥ መዛመቱም ተገልጿል። • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ የዓለም የጤና ድርጅትም ዛሬ ተሰብስቦ በወረርሽኙ ላይ እንደሚመክርና በሽታው ያለበት ደረጃ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆን አለሚሆኑን ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ትናንት እንደተናገሩት "ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ በተለይም በአንዳንድ አገራት ውስጥ በዋናነት ከሰው ወደ ሰው የታየው የበሽታው ስርጭት አሳስቦናል" ብለዋል በተለይም ጀርመንን፣ ቬትናምንና ጃፓንን ከዚህ አንጻር ጠቅሰዋል። ዳይሬክተሩ ጨምረውም "ከቻይና ውጪ ያለው የበሽታው ስርጭት በአንጻራዊነት ትንሽ ቢሆንም፤ ከፍተኛ ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችል ዕድል አለ" ብለዋል። • ኮሮናቫይረስ፡ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ምንም እንኳን እስካሁን በሽታውን የሚፈውስ መድሃኒትም ሆነ የሚከላከል ክትባት የለም። ኮሮና ቫይረስ የከፋ የመተንፈሻ አካላት ህመምን በማስከተል እስከ ሞት የሚያደርስ ሲሆን በተለይም በሽታው ቀደም ሲል ህመም በነበረባቸው በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ እንደሚጸና ባለሙያዎች ይናገራሉ። እስካሁን ድረስ ቻይና ውስጥ በበሽታው መያዛቸውና መሞታቸው የተረጋገጠው አብዛኞቹ ሰዎች ሁቤይ የምትባለው ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ወረርሽኙ በተቀሰቀሰባት የዉሃን ከተማ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ተብሏል። በአሁኑ ጊዜ በከተማዋ ያሉ ሰዎች እንዳይወጡ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን ቻይና የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት በግዛቶቿ ውስጥም በርካታ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን ጥላለች። በሁቤይ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ከቤታቸው መውጣት ምንም ስጋት እንደሌለው እኪረጋገጥ ድረስ የዕት ከዕለት ሥራቸውን ከቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ በአሰሪዎቻቸው ተነግሯቸዋል። በቻይና በተከሰተው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተዘጉ ከተሞች ጭር ብለዋል
news-53610862
https://www.bbc.com/amharic/news-53610862
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ በረራዎች እየተጀመሩ ነው
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት አገራት አስተላልፈዋቸው ከነበሩ መመሪያዎች መካከል ዓለም አቀፍ በረራዎችን ማቆም፣ አየር ማረፊያዎቻቸውንና ድንበሮቻቸውን መዝጋት ይገኙበታል።
በአሁኑ ወቅት እነዚህ መመሪያዎች እየተሻሻሉ ሲሆን ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች በረራቸውን እንደገና የጀመሩ ሲሆን በርካቶችም ከሐምሌ 25/2012 ዓ.ም ጀምሮ በረራዎችን እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል። ከእነዚህም ውስጥ ኬንያ ትገኝበታለች። በወረርሽኙ ምክንያት ዘግታው የነበረውን አየር ማረፊያዋን እንዲሁም በረራዎች በነገው ዕለት እንደሚጀመሩ የኬንያው የጤና ሚኒስትር ሙታይ ካግዌ ገልፀዋል። ምንም እንኳን በረራ ይጀመራል ቢባልም የጤና ሚኒስትሩ እንዳሳወቁት ከጥብቅ ቁጥጥርና መመሪያዎች ጋር መሆኑን እንዲሁም ተጓዦች ሁኔታዎች ሊቀየሩና በነዚህም ምክንያቶች መጉላላት ሊያጋጥም እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። በመጀመሪያው ዙር ከሁሉም አገራት የሚመጡ ተጓዦች ሳይሆኑ ወደ አገሯ እንዲገቡ የፈቀደችው ለይታ አስራ የአንድ አገራትን ዝርዝር አውጥታለች። እነዚህም አስራ አንድ አገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ካናዳ፣ ዚምባብዌ፣ ፈረንሳይ፣ ኡጋንዳ፣ ናሚቢያ፣ ሞሮኮና ሩዋንዳ ናቸው። አገሪቷ የኮሮናቫይረስ የማኅበረሰብ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ያሳወቀች ሲሆን በዛሬው ዕለት 723 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 636 ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪም ኬንያ እስካሁን 341 ዜጎቿንም በቫይረሱ አጥታለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቋርጧቸው የነበሩ በርካታ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ፣ የአውሮፓና የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በረራዎቹን በዚህ ወር መልሶ መጀመሩንና ወደ ተቀሩትንም መዳረሻዎቹ በተከታይነት በረራዎችን ማካሄድ እንደሚጀምር አስታውቋል። በአፍሪካ ውስጥ ወደ ምዕራብ አፍሪካዋ ካሜሩን ሁለት ከተሞች በረራ ማድረግ የጀመረ ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ ጂቡቲ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ዘግታው የነበረውን አየር ማረፊያዋን ክፍት ማድረጓን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ወር ወደ ጂቡቲ የሚያደርገውን በረራ ጀምሯል። ከአፍሪካ ግዙፉ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስካሁንድ ድረስ ከአርባ አገራት በላይ ዓለም አቀፍ በረራዎችን እያደረገም ይገኛል። የምርመራ ውጤት አገራት አየር ማረፊያቸውን መክፈት እንዲሁም በረራዎችን ቢጀምሩም ኢትዮጵያን ጨምሮ አገራቱ መንገደኞቹ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የኮቪድ- 19 ሰርቲፊኬት ይዘው እንዲመጡ ያስገድዳሉ። ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ከአምስት ቀናት በፊት የተደረገ 'አርቲ ፒሲአር' የተባለውን የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርገው የነፃ ሰርቲፊኬት መያዝ የሚጠበቅብዎ ሲሆን፤ ከደረሱም በኋላ ሙቀትዎት ተለክቶ፣ መረጃዎት ተወስዶ በቤትዎ ለአስራ አራት ቀናት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቀመጡ ይጠየቃሉ። በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን አገሪቷ አትቀበልም። የነፃ ሰርቲፊኬት ካልያዙ አገሪቷ በመረጠቻቸው ለይቶ ማቆያዎች ውስጥ ለሰባት ቀናት እንዲገቡ ይደረጋሉ፤ ምርመራም ይደረጋል። ወደ ኬንያም ለመግባት የሚያስቡ መንገደኞች ከተመረመሩ 96 ሰዓታት በታች የሆነውና ነፃ መሆንዎትን የሚያሳይ የኮቪድ-19 ሰርቲፊኬት ማሳየት አለብዎት። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች የሆኑትን ሳል፣ ከ37.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሙቀት በላይ ሊያሳዩ አይገባም።
news-44763380
https://www.bbc.com/amharic/news-44763380
"ዛሬ ትግርኛ የለ፣ አማርኛ የለ! ቋንቋው ጠፍቶብኛል" ዐብይ አሕመድ
ሁለቱ መሪዎች በትናንቱ የእራት ግብዣ ላይ አብሮ ለመሥራት መስማማታቸውን፣ አዲስ የወዳጅነት ምዕራፍ መከፈቱን የሚያበስሩ ንግግሮችን አሰምተዋል። ታዳሚውም በተደጋጋሚ የሁለቱን መሪዎች ንግግሮችን በጭብጨባ ሲያጅብ ነበር።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጋር ከአስመራ ወጣ ብሎ በሚገኝ "ድርፎ" በተሰኘ ሥፍራ በመዝናናት ላይ ሳሉ የፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ንግግር በአጭሩ "ዛሬ በአስመራ ሕዝቡ ወጥቶ ያሳየው ትዕይንት ሌላ ተጨማሪ ንግግር አያስፈልገውም። የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ብቻ አይደለም፤ ከልቡ የቆየውን እምቅ ፍላጎት ነው በይፋ የገለፀው። በዚህ አጋጣሚ ሁለቱንም ሕዝቦች እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። የዚችን ሀገር እውነተኛ ስሜት ምን እንደሚመስል አይታችሁታል። ዶክተር ዐብይ የወሰደው ምርጫ ቀላል ምርጫ አይደለም። ለ25 ዓመታት ያጠፋነው ግዜ፣ ያከሰርነው ዕድል በምንም መለኪያ መስፈር የሚቻል አይደለም። አሁን ግን አልከሰርንም። ከዚህ በኋላ ባለው ጉዟችን ከዶክተር ዐብይ ጋር አብረን ነን። የሚገጥመንን ፈተናም ሆነ መልካም ዕድል አብረን እንወጣዋለን።" • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ምዕራፍ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ንግግር ባጭሩ "ዛሬ ትግርኛ የለ፥ አማርኛ የለ! ቋንቋው ጠፍቶብኛል። ደስታዬን ግን ፊቴ ላይ ዕዩት።...ክቡር ኢሳያስ፣ (በኤርትራኛ ወዲ አፎም)፣ለኤርትራ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ፣ አለን። ብዙ ሕዝብ ካለቀ በኋላም ቢሆን አሁን የጀመርነው ጉዞ አልረፈደም። እናንተ ኤርትራዊያን ሠላም ሀዋርያት የሆናችሁ፤ ከሠላም ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም ....። ሠላም አይደለም ለሠው ለሠማይ አእዋፍ እንኳን አስፈላጊ ነው። አሁን ሁላችሁም ኢትዮጵያዊ ናችሁ። የኤርትራ ጳጳሳትና ሸሆች የኢትዮጵያም ናችሁ። ለልጆቻችሁ ሠላምና ፍቅር መፀለይ አለባችሁ።...ልጆቻችን እኛ ያሠርነውን ገመድ ፣ ያጠርነውን አጥር....እንዲያፈርሱ እናድርግ...። የኤርትራ ሕዝብ ሆይ! የሰለጠንክና ሥራ ወዳጅ ነህ ። ግን ሰላም ከሌለ ፍሬያማ አትሆንም...። ለናንተ ሠላም ይገባችኋል። ስለ ውጊያ መስማት ይበቃናል። እኛ ሰላም ከሆንን ምሥራቅ አፍሪካም ሰላም ትሆናለች ።...በሌላ አገር ያሉ የሁለታችንም ዜጎች እንደ ዕቃ ሣይሆን በክብር እንቀበላቸዋለን ። በውቅያኖስ ሣይሆን በክብር እንልካቸዋለን። አስመራ ብዙ አማርኛ የሚችሉ ሕዝቦች ስላሉ በአማርኛም ልናገር...ዛሬ..." • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? ስምምነቶች ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ትናንት ምሽት የኤርትራው ፕሬዝደንት የእራት ግብዣ ባደረጉላቸው ወቅት የተናገሩት፥ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ለተደረገላቸው አቀባበል እና ለተሰጣቸው ፍቅር ፕሬዝደንት ኢሳያስን እና የኤርትራን ሕዝብን ያመሰገኑ ሲሆን፤ በፍጥነት በመሥራት የሁለቱን አገራት ሕዝብ እንክሳለን ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር በነበራቸው ውይይት ሦስት ዋና ዋና የሚባሉ ስምምነቶችን ፈጽመዋል። 1ኛ-በሁለቱም አገራት ኤምባሲዎች እንዲከፈቱ 2ኛ- አየር መንገዶች ሥራ እንዲጀምሩ 3ኛ- ወደቦች ሥራ እንዲጀምሩ መስማማታቸውን ተናግረዋል። • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ?
49835640
https://www.bbc.com/amharic/49835640
የትራምፕ የስልክ ጥሪ ሲተነተን
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ አቻቸው ጋር ያደረጉት የስልክ ልውውጥ ይፋ ሆኗል። ዲሞክራቶች ዛሬም እርሳቸውን ከስሶ ተጠያቂ ለማድረግ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ይፋ ከሆነው የስልክ ጥሪ ምን ነገሮች ጎልተው ወጡ?
ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና የዩክሬኑ አቻቸው ዜሌንስኪ በወርሃ ሐምሌ ያደረጉት የስልክ ልውውጥ በተቺዎቻቸው እንዲብጠለጠሉ አድርጓቸዋል። የምርጫ 2020 ዋነኛ ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደንን ጥላሸት ለመቀባት የውጪ ኃይል እርዳታ ጠይቀዋል ሲሉም ይከስሷቸዋል። ከስልክ ምልልሶቹ ውስጥ ጎልተው የወጡት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው። 1. ጆ ባይደን ሦስቴ ተጠቅሰዋል ትራምፕ በስልክ ልውውጡ ወቅት "ስለ ባይደን ልጅ በርካታ የምንነጋገረው ነገር አለ። ባይደን ልጁ እንዳይጠየቅ አቃቤ ሕጉ ማድረጉን በርካቶች ማወቅ ይፈልጋሉ። ስለዚህ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጋር ማንኛውንም ነገር ብታደርግና ጉዳዩ ቢታይ መልካም ነው። ባይደን ልጁን ከተጣያቂነት ስለማስመለጡ በአደባባይ ጉራውን ይቸረችራል፤ ስለዚህ ጉዳዩን ብታየው. . . ለኔ መቼም እንዲህ አይነት ነገር ዘግናኝ ነው" ብለዋል። • ትራምፕ 'ሐውልት' ቆመላቸው • ዶናልድ ትራምፕ ተከሰሱ ይህ ትራምፕ ዩክሬን የባይደንን ጉዳይ እንድትመለከተው እየተጫኗት መሆኑን ያሳያል ይላሉ ተንታኞች። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ሕግን ጄነራል ቢል ባርን እንዲያናግሯቸው ነግረዋቸዋል። ነገር ግን የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በዚህ ጉዳይ እጃቸውን እንዳላስገቡ ጠቅሷል። 2. የትራምፕ እከክልኝ ልከክልህ ጥያቄ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ "በመከላከያ ረገድ እያደረጉት ስላለው ድጋፍ ላመሰግን እወዳለሁ። በቀጣዮቹ እርምጃዎች ላይ ለመተባበር ዝግጁ ነን። ለመከላከያ ኃይላችን ተጨማሪ ፀረ ታንክ ለመግዛት ዝግጁ ነን" ብለዋል። ትራምፕ በምላሹም "አንድ ውለታ እንድትውልልኝ ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። ምክንያቱም አገራችን በበርካታ ውጣ ውረዶች ውስጥ ማለፏን ዩክሬንን መቼም አይጠፋትም" ብለዋል። በዚህ የስልክ ምልልስ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በግልፅ የሌላ አገር ፕሬዝዳንትን ውለታ ጠይቀዋል ይላሉ ተንታኞች። ነገር ግን በምላሹ ምን እንደሚሰጡ ግልፅ አይደለም በማለትም ከዚህ የስልክ ምልልስ ቀደም ብሎ የተከናወነ ድርጊትን ያጣቅሳሉ። • "ትራምፕ ከሩስያ ጋር አልዶለቱም" • "ለወጣቶች አስፈሪ ጊዜ ነው" ትራምፕ ከዚህ የስልክ ምልልስ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ትራምፕ ኮንግረስ ለዩክሬን ያፀደቀውን የ250 ሚሊየን ዶላር የወታደራዊ እርዳታ እስከ መስከረም አጋማሽ በሚል አዘግይተውት ነበር። ለዚህም ግልፅ ማብራሪያ በወቅቱ አለመቅረቡ ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እያለ ነው የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ከአሜሪካ ፀረ ታንክ ለመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው የገለፁት። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ንግግራቸውን እንደጨረሱ ትራምፕ "ውለታ" ያሉትን ጠየቁ፤ ከዚህ በኋላ ነው የጆ ባይደን ስም የተነሳው። ዲሞክራቶች፤ ይህ የስልክ ቃለ ምልልስ ይፋ ከመሆኑ በፊት ትራምፕ የያዙትን የዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ፤ ዩክሬን ዋነኛ የምርጫ ተቀናቃኛቸው ላይ ምርመራ ከጀመረች ለመልቀቅ ጠይቀዋል ሲሉ ወንጅለዋቸው ነበር። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ግልፅ ያለ ጥያቄ ሲያቀርቡ የሚያሳይ የስልክ ምልልስ አልተገኘም። ዲሞክራቶች ግን ቢሆንም እዚህና እዚያ ያሉ ነጥቦችን አገናኝቶ የነገሩን ዳር ዳርታ ማወቅ ቀላል ነው ሲሉ ይናገራሉ። 3. አውሮፓውያንን ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል ትራምፕ በዚህ የስልክ ምልልሳቸው ወቅት "ለዩክሬን በርካታ ነገር አድርገናል። የአውሮፓ አገራት ከሚያደርጉት በላይ በርካታ ጉልበትና ጊዜ አፍስሰናል። ድጋፍ ሊያደርጉላችሁ ይገባል። ጀርመን ምንም ነገር አላደረገችላችሁም። ያደረጉት ነገር ቢኖር ወሬ ብቻ ነው። እኔ እንደሚመስለኝ ልትጠይቋቸው ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል። ሪፐብሊካን ከዚህ ንግግር ተነስተው ትራምፕ ወታደራዊ እርዳታውን የያዙት ለዚህ ነው እያሉ ነው። ይህ ደግሞ ለትራምፕ ጥሩ መከላከያ ሆኗል። • ኢንተርኔት በሚቋረጥበት አገር የኢንተርኔት ነፃነት ጉባኤ? • ኢትዮጵያን ጨምሮ 130 አገራትን የጎበኘው ዓይነ ስውር ከዚህ በፊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ እርዳታው ለምን እንደዘገየ ሲናገሩ ከዚህ ቀደም በሶቪየት አገራት ያለውን ሙስና አንስተው ነበር። ከማክሰኞ እለት ወዲህ ግን ይህንን ነጥባቸውን ትተው አሜሪካ ለዩክሬን በርካታ ድጋፍ በማድረጓ የአውሮፓ አገራት ላይ ግፊት ለማሳደር ነው ሲሉ ተደምጠዋል። በጉዳዩ ላይ ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካን ቢከራከሩበትም ፍርዱን ግን የሚሰጠው የአሜሪካ ሕዝብ ይሆናል። 4. ትራምፕ በአቅም ማነስ የተባረረን የዩክሬን አቃቤ ሕግ ደጋፈዋል "ጎበዝ የሆነ አቃቤ ሕግ እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ መታገዱ አግባብ አይመስለኝም። በርካታ ሰዎች ይህ ጎበዝ አቃቤ ሕግ ከሥራው የታገደበት ምክንያት አግባብ አለመሆኑንና አንዳንድ መጥፎ ሰዎች ከእርሱ መታገድ ጀርባ እንዳሉ እያወሩ ነው። ሚስተር ጊዩላኒ በጣም የተከነበረ ሰው ነው። የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ነው። እንዲደውልልህ አደርጋለሁ። ከጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጋር ሆኖ እንዲደውልልህ አደርጋለሁ" ይህ ትራምፕ የጠቀሱት የዩክሬን አቃቤ ሕግ ከሥራው የተሰናበተው ብቁ አይደለም ተብሎ ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን በአግባቡ እንዳልተስተናገደ ጠቅሰዋል። አቃቤ ሕጉ ቪክቶር ሾኪን የሚባል ሲሆን በዩክሬን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከስራው የተባረረው በ2016 ነበር። ጆ ባይደን እና ሌሎች የአሜሪካ ባለስልጣናት፤ የአውሮፓ አጋሮቻቸው እና የዩክሬን የለውጥ ኃይሎች የሚባሉት ግለሰቡን ሙሰኛ ነው ሲሉ ይገልፁታል። እዚህ ላይ ስማቸው የተጠቀሰው የቀድሞ የኒውዮርኩ ከንቲባ የትራምፕ የግል ጠበቃ ናቸው። ጠበቃው የፕሬዝዳንቱን የዩክሬን ጉዳይ እንዲይዙላቸው መጠቀሳቸው መነጋገሪያ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ነው።
54777156
https://www.bbc.com/amharic/54777156
“የፈረንሳይ ምርቶችን አንገዛም”
ከቱርክ እስከ ባንግላዲሽ፤ ከጆርዳን እስከ ማሌዥያ የፈረንሳይ ምርቶች እንዲታገዱ ንቅነቄ እየተካሄነ ነው።
አንዳንድ መደብሮች የፈረንሳይ ምርቶችን ከመደርደሪያቸው አውርደዋል። የፈረንሳይ ምርቶች እንዲታገዱ የሚያበረታታው ሀሽታግ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከ100,000 ጊዜ በላይ ታይቷል። ንቅናቄው የተጀመረው የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ ነው። ስለ ንግግር ነጻነት ሲያስተምር የነብዩ መሐመድን ካርቱን ለተማሪዎቹ ያሳየ የታሪክ መምህር መገደሉን ተከትሎ፤ ፕሬዘዳንቱ "የተገደለው የነጋችንን መውሰድ በሚፈልጉ ኢስላሚስቶች ነው። ካርቱን ከመሥራት አንቆጠብም" ብለዋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2006 ላይ ቻርሊ ሄብዶ የተባለው የስላቅ መጽሔት የነብዩ መሐመድን ምሥል ማተሙ ይታወሳል። ይህም በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞችን አስቆጥቷል። . ቱርክ ፕሬዚዳንቷን አዋርዷል ያለችውን የፈረንሳይ መፅሄት ልትከስ ነው . ፈረንሳይ ምርቶቿ ላይ ማዕቀብ እንዳይጣል የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን ጠየቀች . በሶማሊያ ፀረ-ፈረንሳይ ሰልፍ ተካሄደ ማክሮን ከሃይማኖት ነጻ የሆነ ምልከታ እና የንግግር ነጻነትን መደገፋቸው ተገቢ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። ባለፈው ሳምንት ኒስ ከተማ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ፤ ማክሮን "እስላማዊ የሽብር ጥቃት ነው" ብለዋል። ንግግራቸውን በርካታ የሙስሊም አገራትን ኮንነዋል። ባንግላዲሽ ውስጥ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የፈረንሳይ ምርቶች እንዲታገዱ የሚጠይቅ ሰልፍ አካሂደዋል። ቢቢሲ ሦስት አገሮች የሚኖሩ፣ የፈረንሳይ ምርቶችን መግዛት ለማቆም የወሰኑ ሰዎችን አነጋግሯል። የፓኪስታኗ ተዋናይት- ሚሺ ካሀን የፈረንሳይ መዋዋቢያ እጠቀም ነበር። በተለይ ሎሬል ፓኪስታን ውስጥ በቀላሉ ይገኛል። አሁን ግን ምግብ እና ቁሳቁስ ስገዛ ፈረንሳይ አለመሠራቱን አረጋግጬ ነው። የፈረንሳይ ምርቶችን በፓኪስታን ምርቶች እየተካሁ ነው። ምክንያቱም የአገሪቱ ፕሬዘዳንት መላው የሙስሊም ማኅበረሰብን አዋርዷል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የፈረንሳይ ምርቶችን ማንም እንዳይገዛ እየቀሰቀስኩ ነው። ሃይማኖቴን እየተከላከልኩ ስለሆነ ህሊናዬ ንጹህ ነው። ከእንግዲህ ሰዎች ሃይማኖታችን እና ነብያችን ላይ እንዲቀልዱ መፍቀድ የለብንም። በቃን። እስካሁን ሃይማኖቱ ላይ የተሳለቁ ሰዎችን ይቅር ብለናል። ከእንግዲህ ግን እርምጃ እንወስዳለን። ማክሮን ሆነ ብለው ሊጎዱን እንደፈለጉ ይሰማኛል። ሰውን ከቆነጠጡ በኋላ "አመመህ?" ብሎ የመጠየቅ ያህል ነው። ጥላቻን እየዘሩ ነው። ሰዎችን እየተነኮሱ፣ እየከፋፈሉ ነው። ንግግራቸው ሙስሊም ጠል ድርጊት ያነሳሳል። የአገራቸውን ዜጎች አንድ ማድረግ እና እኩል ማየት ነው የሚጠበቅባቸው። መጀመሪያ ላይ የቻርሊ ሄድቦ መጽሔትን ስመለከት የምናገረው ጠፋኝ። ለረዥም ጊዜ ላለማየት ሞክሬያለሁ። ሳየው ግን ደነገጥኩ። አለቀስኩ። ፈጣሪዬ ሆይ ለምን ይሄን ተመለከትኩ? አልኩ። ቱርካዊቷ ተማሪ- ላቲፍ ኦዝደሚር እንደ ላንኮም ያሉ ምርቶችን በየቀኑ እጠቀም ነበር። ከዚ በኋላ ግን አልገዛም። የፈረንሳይ ምርቶችን የማልገዛው ከዚህ በኋላ ትዕግስት እንደሌለን ለማሳየት ነው። የፈረንሳይን ሙስሊም ጠል አካሄድ መታገል እፈልጋለሁ። እኛ ሙስሊሞች ድምጻችንን ማሰማት አለብን። ለዘመናት ታፍነናል። አሁን ማድረግ የምንችለው ምርቶቹን አለመግዛት ብቻ ነው። ቻርሊ ሄብዶ አስጸያፊ ነገር አትሟል። በፊት ገጹ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ካናቴራ ያለ ሱሪ ለብሰው፣ ቢራ ሲጠጡና ሂጃብ የለበሰች ሙስሊም ሴት ቀሚስ ሲገልቡ ያሳያል። ሂጃብ እንደሚለብስ ሰው ሳስበው ይህ ሙስሊም ሴቶችን የሚያስከፋ ነው። እንደኔ ያሉ ሙስሊም ሴቶች ሃይማኖቱ በበጎ እንዲታይ እና በማኅበረሰቡ ዘንድ እኩል እንድንታይ እንታገላለን። ይህ ካርቱን ግን ትግላችንን ዋጋ ያሳጣዋል። አውሮፓ ሙስሊም ሴቶችን ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች እኩል መቼም እንደማታይ ያሳያል። ካርቱንም ይሁን ስላቅ መፍጠር ያለበት የበሰለ አስተሳሰብ እና ክርክር ነው። አውሮፓ ግን ከዚህ በተቃራኒው ሙስሊሞችን ለማግለል ትጠቀምበታለች። በተደጋጋሚ እነዚህን ካርቱኖች መሳል እሳቱ ላይ ቤንዚን መጨመር ማለት ነው። ይሄን ነው የምንፈልገው? በንግግር ነጻነት ስም እርስ በራሳችን የምንዘላለፍበት እና የምንጠላላበት ዓለም ነው የምንሻው? ሀይማ መሐመድ ሞሳ- የሞሪታኒያ ተማሪ የፈረንሳይን ድርጊት ለመኮነን በተጠራው ሰልፍ ላይ ከቤተሰቦቼና ከጓደኞቼ ጋር ተሳትፌያለሁ። የፈረንሳይ ምጣኔ ሀብት ተንኮታኩቶ ማክሮን በጥላቻ ንግግራቸው ያስቀየሟቸውን ሁለት ቢሊዮን ሙስሊሞች ይቅርታ እስካልጠየቁ ድረስ የፈረንሳይ ምርቶችን ባጠቃላይ አንገዛም። በፈረንሳይ አይብ ፋንታ የቱርክ ምርቶችን እየተጠቀምን ነው። እንደ ላኮስቴ ያሉ የፈረንሳይ ሽቶዎች አሉኝ። ከጨረስኳቸው በኋላ ከእንግዲህ በድጋሚ አልገዛም። ማክሮን ይቅርታ እንዲጠይቁ ደብዳቤ ጽፌያለሁ። እሳቸው የታሪክ መምህሩ ክብር ይገባቸዋል ብለዋል። የኛ ነቢይስ ክብር አይገባቸውም? በሙስሊም ጠል ንግግራቸው ሃይማኖቱን ከኋላ ቀርነት ጋር ማገናኘታቸው በጣም አስቆጥቶናል። ይህንን ኢ ፍትሐዊ ንግግር መታገስ የለብንም። የፈረንሳዩ መሪ አንድ ማኅበረሰብን የሚያስቀይም ምስልን የንግግር ነጻነት መገለጫ ማለታቸው ሃይማኖቱን ማጥቃት ነው። በፖለቲካ ውድድር ነጥብ ለማስቆጠር ነው የሞከሩት። የነብዩ መሐመድ ካርቱን ቻርሊ ሄብዶ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲታተም ልጅ ነበርኩ። በመጽሔቱ ቢሮ የደረሰው ጥቃት ትዝ ይለኛል። እስከዛሬ ካርቱኑን ላለማየት ስሞክር ነበር። ባለፈው ግን ትዊተር ላይ ተመለከትኩት። እንደተዋረድኩ ተሰማኝ። እስልምና ልክ እንደ ክርስትና እና የአይሁድ ሃይማኖት ለምን አይከበርም?
44037506
https://www.bbc.com/amharic/44037506
"ዳንስ እንደተወዛዋዡ ነው" ምንተስኖት ጌታቸው
የምንተስኖት የትውልድ ከተማ አዳማ ናት። በአዳማ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቅቆ ወደ አዲስ አበባ መጣ። ወደ አዲስ አበባ የመጣው በዊንጌት የቴክንክና ሙያ ትምህርት ቤት ለመማር ነው። ከዚያ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ወደ ዳንስ ህይወት መግባቱን ይናገራል።
ዳንስ የልጅነት ህልሙ አልነበረም። ''መሆን የምፈልገው አባቴ አትሌት ስለነበር የማርሻል አርት ባለሙያ ነበር'' ይላል። በፊልም ላይ የሚያያቸውን የቻይና ማርሻል ጥበቦች እካንበታለሁ ብሎ ያስብ ነበር። ''ቤተሰቦቼ እንደማንኛውም ልጅ ሕክምና አልያም ምህንድስና ባጠና ደስ ይላቸው ነበር'' የሚለው ምንተስኖት ''እኔ ግን ዳንስን መረጥኩና ልቤንም ቀልቤንም ሳበው'' ይላል። ቤተሰቦቹም በዚህ ሙያ ራስህን የምትችልና በአግባቡ የምትኖር ከሆነ በማለት እንደፈቀዱለት ያስታውሳል። ምንተስኖት ውዝዋዜን የጀመረው በአዳማ ሰርከስ ውስጥ ነው። በቡድኑ ውስጥ የጅምናስቲክ ስፖርትና የተለያዩ ጥበቦች የነበሩ ቢሆንም በተጨማሪም የባህላዊ ውዝዋዜዎች ይሰሩ ነበር። ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላም ይህንን የውዝዋዜ ተሰጥኦውንና ትንሽ ልምዱን ይዞ ወደ መኩሪያ የቲያትር ስቱዲዮ አመራ። የተውኔት ባለሙያው አቶ አባተ መኩሪያ በቲያትር ስቱዲዮ ውስጥ መኩሪያ የዳንስ ቡድን ነበረው ይላል ምንተስኖት። በዚያ ውስጥ በመታቀፍ የዳንስ ትርኢቶችን ያቀርብ እንደነበር ያስታውሳል። በተለይ የአቶ አባተ መኩሪያ ልጅ ውቢት ይህንን ኃላፊነት ወስዳ ታሰለጥናቸው እንደነበር የሚያስታውሰው ምንተስኖት አሁን ላለበት የዘመናዊ ዳንስ ስልት መነሻ እንደሆነው ይናገራል። ኮንተምፐረሪ ዳንስ አዲስ አበባ ለዚህ የውዝዋዜ ስልት አፍቃሪዎች የበለጠ የተመቸች ነች የሚለው ምንተስኖት፤ ምክንያቱም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫቸውን በከተማዋ ማድረጋቸው ነው። የእነዚህ ተቋማት በአዲስ አበባ መኖር ለእርሱ የተለያዩ ትርኢቶችን ለማዘጋጀትና ለማቅረብ እድሉን እንዳሰፋለት ያስታውሳል። ምንተስኖት ከጀርመን ባህል ማዕከል ጎተ ኢንስቲቲዩት፣ ከአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ፣ ከኖርዌይ፣ ደቡብ አፍሪካ ኢምባሲዎች ጋር በመሆን ዝግጅቶች አቅርቧል። ሌላው በሀገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የዳንስ ቡድኖች ጋር በመሆን ትርኢቶችን ማቅረቡንም ይናገራል። ከአዱኛ የዳንስ ቡድን ሌላ ከዴስትኖ፣ ከሀሁ፣ ከጃቤዛ፣ ከወንዳታ የዳንስ ቡድኖች ጋር የተለያዩ ስራዎች መስራቱን ያስታውሳል። በአዲስ አበባ የዳንስ ጥበብ አሁን ጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንም ከዚህ የበለጠ መሰራት እንዳለበት ይናገራል። ከሰላምታ ጋር ምንተስኖት የመአዛ ወርቁ ድርሰት የሆነው 'ከሰላምታ ጋር' በተሰኘው ተውኔት ላይ በዳንስ ተሳትፏል። ዳንሱንም ያቀናበረውም እርሱ ነበር። ከተውኔቱ ደራሲ መዓዛ ጋር መኩሪያ ስቱዲዮ እያለ እንደሚተዋወቁ የሚናገረው ምንተስኖት ተውኔቱን ይዛ ስትመጣ ሃሳቡን እንደወደደው ይናገራል። ተውኔቱ ላይ በየትዕይንቱ በዳንስ እንዲገለፅ የምትፈልገውን ሃሳብን ፅፋ መምጣቷን የሚያስታውሰው ምንተስኖት "በተውኔቱ ላይ ሁለት ተወዛዋዦች እንዲኖሩ ትፈልግ ስለነበር እኔ ሃሳቧን ወስጄ ቅንብሩን ሰራሁት" ይላል። መአዛ በተውኔቱ ላይ እንዲቀርብ ያደረገችው ዳንስ በሌሎች ቲያትር ቤቶች ከሚቀርቡ ሙዚቃዊ ተውኔት የተለየ መሆኑን የሚናገረው ምንተስኖት በተውኔቱ ላይ የኮንተምፐረሪ ዳንስ በአብስትራክት መልኩ እንደቀረበበት ይናገራል። በተውኔቱ ላይ ስመጥር የሆኑት ኤልሳቤጥ መላኩ እና አለማየሁ ታደሰ በሚተውኑበት መድረክ ውስጥ ተቀናጅቶ መስራት የበለጠ ደስታውን ከፍ አድርጎለት እንደነበር የሚገልፀው ምንተስኖት "እድለኛ ነኝ ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ብዙ ልምድ ያላቸው ምሳሌ የሆኑ ሰዎች ናቸው። ከእነርሱ ጋር አንድ መድረክ ላይ መሳተፌ ለእኔ ትልቅ መነሳሳት፣ ትልቅ ድጋፍና ጥንካሬ ነበር የሆነኝ። ወደዚህ ዘርፍ ገብቼ እንድማርም ምክንያት የሆነኝም አንዱ ይህ ነው" ይላል። ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ጋር ስትሰራ ራስህን ወደተሻለ ቦታ ማድረስ እንዳለብህ ትረዳለህ የሚለው ምንተስኖት የዳንስ ትምህርቱን በአውሮፓ ውስጥ በአየርላንድ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሊምሬ ተከታትሏል። ዳንስን በዲግሪ ዳንስን በተሰጥኦ ብቻ ሳይሆን በትምህርት ማሳደግ እንደሚቻል ካሳዩት ሰዎች መካከል መአዛ ወርቁ እና ውቢት መኩሪያ መሆናቸውን በቀዳሚነት ይጠቅሳል። ያኔ ነው ዳንስን ዩኒቨርስቲ ገብቼ ለመማር የነሸጠኝ ይላል። ከዚያ በኋላ አይኑን ወደ ተለየዩ ተቋማት አማተረ፤ ተሳክቶለትም በአየርላንድ የሚገኘው እድል ሰጠው።በተቋሙ ደብተር ይዞ ክፍል ውስጥ ከመማር ጀምሮ የተለያዩ ተግባራዊ ስልጠናዎችን አግኝቷል። ትምህርቱ በተለያየ ዘርፍ ብቁ ሆኜ እንድወጣ ያለመ ነበር የሚለው ምንተስኖት፤ ከትምህርቱ ባሻገር ከዳንስ ባለሙያዎችና ድርጅቶች ጋር በመገናኘት የዳንስ ትርኢቶችን ያቀርብም ነበር። ይህ ደግሞ ሀገሩንም ሆነ ባህሉንም ለማስተዋወቅ ረድቶታል። በመቀጠል ደግሞ በሦስተኛ ዲግሪ ደረጃ ትምህርቱን ለመቀጠል የተለያዩ ነገሮችን እየሞከረ እንደሆነ ይገልፃል። ዳንስና ዓለምአቀፍ ጉዞ አባተ ሙኩሪያ እያለ በአብዛኛው ከአፍሪካ ከሚመጡ ባለሙያዎች ጋር ሥራውን አቅርቦ ያውቃል። ከአሜሪካ፣ ኖርዌይና ስዊዲን ባለሙያዎች ጋር አንድ መድረክ ተጋርቷል። እነዚህ ባለሙያዎች ስመጥር ከመሆናቸው በተጨማሪ ትላልቅ መድረኮች ላይም አብሯቸው የመሳተፍ እድል ነበረው። ከተሳተፈባቸው ትላልቅ መድረኮች መካከል አንደኛው ቻይና ሆንግ ኮንግ የተካሄደ ፌስቲቫል ሲሆን "በሴኔጋልና ታንዛኒያ የተካሄዱት ፌስቲቫሎች ራሴንም ሥራዬንም ለማስተዋወቅ መሰረት የሆነኝ ናቸው" ይላል።
50709585
https://www.bbc.com/amharic/50709585
ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ ሊጠበቁ ነው-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቢቢሲ ገልጿል።
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ዩኒቨርስቲዎች ወደ ሰላማዊ የመማር ማስተማር መመለስ የሚቻለው ጥበቃዎቹን ማጠናከር ሲቻል መሆኑ በመታመኑና ተቋማቱ የፌደራል ተቋማት በመሆናቸው በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑን ተናግረዋል። አቶ ደቻሳ አክለውም "ከተማሪዎች ጋር በተደጋጋሚ በተደረገ ውይይት የቀረበው ቅሬታ የግቢው የጥበቃ አካላት ላይ መሆኑን በማንሳት በተጨማሪም ተማሪዎች የፌደራል ፖሊስ በገለልተኝነት እያገለገሉን ነው" በማለታቸው እዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱን አብራርተዋል። • የጌዲዮ ዞን የክልል እንሁን ጥያቄ ምን ደረሰ? • ገንዘብ ያለው ሊገዛው የሚችለው 'ወርቃማው' ፓስፖርት ለምን ተፈላጊ ሆነ? • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . በትናንትናው ዕለት በወልዲያ ዩኒቨርስቲ ዛሬ ደግሞ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች መሞታቸውን የየዩኒቨርስቲዎቹ አስተዳደሮች በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል። በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የፔዳጎጂ ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረው አዲ ዋቆ የሞተው በወልዲያ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዳ ከቆየ በኋላ እንደሆነም ታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ጓደኞቹ እንደተናገሩት ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ዕለት አዲናን ጨምሮ ሌሎች ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው የጥበቃ አካላት ድብደባ ደርሶባቸው እንደነበር ገልጸው ከዚህ ድብደባ በኋላ አዲ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት የጎንደር ዩኒቨርስቲ በፌስቡክ ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ማሾ ዑመር የተባለ የእንስሳት ህክምና ተማሪ ትናንት ማታ ባልታወቁ ሰዎች በደረሰበት ጥቃት ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ቢወሰድም ሊተርፍ አልቻለም። ጉዳቱን በማድረስ የተጠረጠሩት ከሟቹ ዶርም ፊት ለፊት የሚገኙ ተማሪዎች ናቸው ያለው ዩኒቨርስቲው፣ ፖሊስ ምርመራ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን የምርመራ ውጤቱም እንደ ተጠናቀቀ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች ዛቻ እንደሚደርስባቸው የማስፈራሪያ ወረቀቶችም እንደሚለጠፉ መረጃ እንዳላቸው አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ለዚህም መፍትሔ ነው ያሉት የግቢዎቹ ጥበቃ እንዲጠናከር ማድረግ በመሆኑ በፌደራል ፖሊስ ይጠበቁ መባሉን አቶ ደቻሳ ተናግረዋል። ተቋማቱን ወደ ሰላማዊ መማር ማስተማር ለመመለስ የዩኒቨርስቲዎቹ አስተዳደሮች የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው ያሉት አቶ ደቻሳ፣ ዩኒቨርስቲዎች የፌደራል ተቋማት ስለሆኑ ጥበቃዎቻቸውንና ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ለማጠናከር "በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ እያመቻቸን ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ መቼ ይሆናል የሚለውን ሲያብራሩም ጠንከር ያለ የጥበቃ ሁኔታ እንዲኖር ፤ በሚቀጥለው አንድ ሳምንት ውስጥ ፌደራል ፖሊስ ይገባል ሲሉ አረጋግጠዋል። በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ባለው የደህንነት ሁኔታ፣ ስጋት የገባቸው ተማሪዎች ለቅቀው የሄዱ ተማሪዎች መኖራቸው ይታወቃል። ይህንንም አስመልክተው ሲናገሩ፣ ከየክልሎቹ ጋር በመነጋገር፣ ትራንስፖርት አመቻችተው ለመመለስ ግብረ ኃይል አቋቁመው እየሰሩም እንደሆነ ተናግረዋል። በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በአንጻራዊነት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት አለ የሚሉት አቶ ደቻሳ፣ ክፍተት ሆኖ የሚታየው ለቅቀው የሄዱ ተማሪዎች ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ማካካሻ ትምህርት በመስጠት ያመለጣቸውን ለማስተማር ወደ መደበኛ የመማር ማስተማሩ ስርዓት እንዲገቡ ከክልሎች ጋር እየሰሩም መሆኑን አክለው ገልፀዋል። አቶ ደቻሳ በመላው አገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል የጸጥታ አካላት የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
news-55241928
https://www.bbc.com/amharic/news-55241928
ትግራይ ፡ በተባበሩት መንግሥታት ሰራተኞች ላይ እንደተተኮሰባቸው ኢትዮጵያ አረጋገጠች
ትግራይ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች የፍተሻ ጣቢያ በጣሱ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች ላይ እንደተኮሱና በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን አረጋገጡ።
የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ባለፈው ሳምንት እሁድ ኅዳር 27/2013 ዓ.ም የኤርትራ ስደተኞች የሚገኙበትን ማዕከልን ለመጎብኘት ሲያቀኑ የነበሩና ፍተሻ ጣቢያዎችን ጥሰው አልፈዋል ተብሏል። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንዳሉት የድርጅቱ ሠራተኞ መሄድ ወዳልተፈቀደላቸው አካባቢ በመግባት የመንግሥትን መመሪያ በመተለለፋቸው ነው የተተኮሰባቸውና የተያዙት። "የተወሰኑ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል የተተኮሰባቸውም አሉ" ማለታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። "ሁለት የፍተሻ ጣቢያዎችን በመጣስ ነድተው ነው ያልተፈቀደላቸው ቦታ የገቡት። እንዳይሄዱም ተነግሯቸዋል። ሦስተኛውን የፍተሻ ጣቢያም ሊጥሱ ሲሉ ነው የተተኮሰባቸው እንዲሁም በቁጥጥር ስር የዋሉት" በማለት ሬድዋን መናገራቸውን ኤኤፍፒ በዘገባው አመልክቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስለ ክስተቱ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠም። ሮይተርስም በዘገባው የተባበሩት መንግሥታት በፀጥታ አባላት ባለፈው ሳምንት እሁድ የተተኮሰባቸው ሠራተኞች ሽመልባ የተባለውን የኤርትራ ስደተኞች ማዕከል ሊጎበኙ የነበሩና ሁለት የፍተሻ ጣቢያዎችም ላይ ሳያቆሙ ጥሰው ሄደዋል ብሏል። ቡድኑ በአካባቢው እርዳታ ለማቅረብ የመንገዶችን ሁኔታ ለመገምገም የተላኩ አራት አባላትን ይዟል በማለትም ሮይተርስ የተባበሩት መንግሥታት ቃለ አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በፌደራል መንግሥትና በህወሓት መካከል ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት መቋጫ አላገኘም። በክልሉም የኤርትራ ስደተኞች ጉዳይ አሳሳቢም እንደሆነም እየተገለፀ ነው። በተለይም ያልተረጋገጡ ቢሆኑም የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ገብተው ስደተኞቹን ወደ ኤርትራ እየመለሷቸው ነው የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውም ስጋትን አጭረዋል። የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግሥታት የኤርትራ ወታደሮች ህወሓትን ለመውጋት ተሳትፈዋል የሚባለውን አይቀበሉትም። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማድረስ አስተማማኝ መተላለፊያ መንገድ ሊመቻች ይገባልም እያለ ነው። የእርዳታ ድርጅቶች ከስምንት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ባሏት ትግራይ ክልል የምግብና የህክምና ቁሳቁሶች ግብአት እጥረትም አጋጥሟል እያሉ ነው። በኢትዮጵያ ያሉ የስደተኞች ሁኔታ በኤርትራ ያለውን አስገዳጅ ብሔራዊ ውትድርናና ፖለቲካዊ ጭቆና ለማምለጥ በርካታ ኤርትራውያን ስደተኞች ድንበር አቋርጠው ወደ ትግራይ ክልል ገብተዋል። ኤርትራ ነፃነቷን ካገኘችበት ጀምሮ በአንድ ፓርቲ ስር በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እየተመራች ያለች አገር ናት። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ሁለቱ አገራት ሰላምና ጦርነት በሌለበት ሁኔታ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ተፋጥጠው ነበር። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይና በፕሬዚዳንት ኢሳያስ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ፍጥጫውም የቆመ ሲሆን ለዚሁ ተግባራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም የኖቤል ሽልማት ማግኘታቸው ይታወሳል። ሆኖም በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረሰው ስምምነት ግን "ወታደራዊ ትብብር" ሆኗል በማለት እየተቹ ሲሆን ለዚህም የሚያቀርቡት በሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ወታደሮች ህወሓትን ለመውጋት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል የሚል ነው። ሁለቱም መንግሥታት የኤርትራ ሰራዊት በጦርነቱ መሳተፉን ቢክዱም የሮይተርስ ዜና አገልግሎት የአሜሪካ መንግሥትን ምንጭ በመጥቀስ የኤርትራ ኃይል በትግራይ ውጊያ መሳተፋቸውን ማረጋጋጣቸውን ዘግቧል። "በዚህ ጉዳይ ምንም መጠራጠር የለም" በማለት ስማቸው ያልተጠቀሰው ምንጭ መናገራቸውን ሮይተርስ አስነብቧል። ከዚሀም በተጨማሪ ግጭቱ ከተጀመረ በኋላ ህወሃት ወደ ኤርትራ ሮኬቶችን አስወንጭፏል። ወታደራዊው ውጊያ ተቋጭቷል? የመከላከያ ሠራዊት የትግራይ ክልል መቀመጫን መቀለን ህዳር 19/2013 ዓ.ም ቢቆጣጠርም ውጊያዎች ግን በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ ሌሎች ምንጮች ይጠቁማሉ። ለዚህም "ያልተቆጣጠርናቸው የቀሩ የሚሊሺያ ወይም የልዩ ኃይል አባላት አሉ" በማለትም አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ስልጣን ላይ መምጣታቸውን ተከትሎ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ግንኙነት እየሻከረ የመጣ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጓቸው ማሻሻያዎችም ላይ ልዩነቶች የነበሯቸው ሲሆን ኋላ ላይ እጅጉን ተካሮ ቆይቶ ነበር። ይህንንም ተከትሎ በትግራይ ክልል ከአንድ ወር በፊት የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘውን የመከላከያ ሰሜን ዕዝ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ከገለጹ በኋላ መሆኑ ይታወሳል። በዚህ ግጭትም ከ40 ሺህ በላይ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ሲሆን በርካቶችም እንዲሁ ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተነግሯል።
53046822
https://www.bbc.com/amharic/53046822
ፈረንሳይ ኮሮናቫይረስን ድል ነሳሁት አለች
ኢማኑኤል ማክሮን ለሕዝባቸው ባደረጉት ንግግር ከኮሮናቫይረስ ጋር የነበረውን ጦርነት ፈረንሳይ በድል አጠናቃለች ብለዋል፡፡ ሆኖም ጦርነቱ የመጀመርያ ዙር እንጂ አልተጠናቀቀም፡፡
በዚህም የተነሳ በእንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ እንዲነሳ ፈረንሳይ ወስናለች፡፡ ይህን ተከትሎ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ በየካፌው፣ በየሬስቶራንቱ ዘና ማለት ተፈቅዷል፡፡ በመላው ፈረንሳይ የሚገኙ አገልግሎት መስጫዎችም ለደንበኞች ክፍት ተደርገዋል፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ ወደ ሌላ የአውሮፓ አገራት መጓዝም ተፈቅዷል፡፡ መጦሪያና የእንክብካቤ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ አዛውንቶችን መጎብኘትም ይቻላል ብላለች ፈረንሳይ፡፡ እነዚህ የመጦሪያ ማዕከላት ውስጥ በርካታ የዕድሜ ባለጸጋ ፈረንሳዊያን በቫይረሱ ተይዘው መሞታቸው ይታወሳል፡፡ ዛሬ ሰኞ ፈረንሳይ ብቻ ሳትሆን በርካታ የአውሮፓ አገራትም ድንበሮቻቸውን መከፋፈት ጀምረዋል፡፡ ለሕዝባቸው በቴሌቪዥን ንግግር ያደረጉት ማክሮን ቫይረሱን ድል ብናደርገውም ተመልሶ አይመጣም ማለት ግን አይደለም ሲሉ መዘናጋት እንደማያስፈልግ አስጠንቅቀዋል፡፡ ፈረንሳይ ትምህርት ቤቶች ከሰኔ 22 ጀምሮ ወደ መማር ማስተማሩ እንዲገቡ ብላለች፡፡ ይህ መመሪያ ግን የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን አይመለከትም፡፡ አሁን ገደቦችን ብናነሳም ቫይረሱ በድጋሚ ከመጣ ግን በፍጥነት በራችንን ዘግተን ለመፋለም ተዘጋጅተናል ብለዋል ማክሮን በንግግራቸው፡፡ የትኞቹ የአውሮፓ አገራት ድንበራቸውን ከፈቱ? የአውሮፓ ኅብረት ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ አባል አገራት ድንበራቸውን እንዲከፋፍቱ እያበረታታ ቢሆንም ሁሉም አባላት ግን ተቀብለውታል ማለት አይደለም፡፡ ለጊዜው ዛሬ ሰኞ ድንበር ሙሉ በሙሉ እንከፍታለን ካሉት መካከል ቤልጂየም፣ ክሮሺያ፣ ስዊዘርላንድና ጀርመን ይገኙበታል፡፡ ቼክ ሪፐብሊክ ድንበሬ ለ26 አገራት ክፍት ነው፣ ሆኖም ግን ለስዊድን፣ ለዩናይትድ ኪንግደም፣ ለፖርቹጋልና ለቤልጅየም አልፈቀድኩም ብላለች፡፡ ግሪክ በበኩሏ እንኳንስ ከዚህ ከአውሮፓ ይቅርና እንደ አውስራሊያ፣ ኒውዚላንድ፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ካሉ ሩቅ አገራት ጭምር ለሚመጡ ድንበሬ ክፍት ነው ብላለች፡፡ ጣሊያንና ሆላንድ ቀደም ብለው ድንበራቸውን የከፈቱ አገራት ናቸው፡፡ ስፔንና ሉክዘምበርግ ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ ድንበራቸውን ያልዘጉ ብቸኛ አገራት ናቸው፡፡ ፈረንሳይ የአካባቢ ምርጫን አራዝማለች ፈረንሳይ 2ኛ ዙር የአካባቢ ምርጫ መርኅ ግብር ለጊዜው እንዲራዘም ወስናለች፡፡ መጋቢት ላይ ይደረጋል የተባለው ይህ ምርጫ ወደ ሰኔ 28 ተገፍቷል፡፡ ሆኖም ምርጫው የሚካሄደው ተገቢው ርቀት ተጠብቆ በከፍተኛ ጥንቃቄ ይሆናል ተብሏል፡፡ ፈረንሳይ 29 ሺህ 400 ዜጎቿን ቫይረሱ ገድሎባታል፡፡ አሁንም ድረስ በቫይረሱ የተያዙት ደግሞ 194 ሺህ ደርሰዋል፡፡ ሆኖም አዲስ የሚያዙት ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡
news-56442847
https://www.bbc.com/amharic/news-56442847
አንዳንድ የእስር ቅጣቶች ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ዓመት ለምን ይረዝማሉ?
ሰዎች ለሚፈጽሟቸው የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች በፍርድ ቤት የተለያዩ ቅጣቶች ይወሰንባቸዋል። በተለይ የእስር ፍርድ የተለመደው አይነት ቅጣት ሲሆን ይህም ከጥቂት ቀናት አስከ ዓመታት ሊደርስ ይችላል።
አንዳንድ ጊዜ ጥፋተኞች ሰው በየትኛውም ሁኔታ በዚህ ዓለም በህይወት ሊቆይበት ከሚችለው ዓመት በላይ ፍርድ ሲሰጥ ለብዙዎች ግራ ያጋባል። ለምሳሌ አንድ ጥፋተኛ ለፈጸመው ወንጀል "የሁለት መቶ ዓመት የእስር ቅጣት ተወሰነበት" የሚል ዜና ሲሰሙ ምን አይነት የቅጣት ውሳኔ ነው? በማለት መጠየቅዎ አይቀርም። እንደዚህ ዓይነት ዜናዎችን በተደጋጋሚ እንሰማለን። በፈረንጆቹ የካቲት ወር መጀመሪያ አካባቢ በአሜሪካ ሆዜ አልቫሬዝ ፈርናንዴዝ የተባለ ሰው የሁለት መቶ ዓመት የእስር ቅጣት ተፈርዶበታል። ይህ የ58 ዓመት ጎልማሳ አንዲት የስድስት ዓመት ሕጻንን ዘጠኝ ዓመት እስኪሞላት ድረስ ባደረሰባት ተደጋጋሚ ጾታዊ ጥቃት ነበር የ200 ዓመት እስር የተፈረደበት። በዚህ ቅጣት መሰረት ታዲያ ይህ ሰው የእስር ቅጣቱን ሲጨርስ እድሜው ሁለት መቶ ሃምሳ ስምንት ይሆነዋል ማለት ነው። ይኹን እንጂ በዓለም ላይ የሰው ልጅ የእድሜ ጣርያ እንኳን ሁለት መቶ ሊሞላ 100 የሞላቸው ቢቆጠሩ ከሁለት እጅ ጣት በላይ አይሆኑም። ታዲያ የሰው ልጅ ኖረ ከተባለ ቢበዛ ቢበዛ 100 እና 120 ዓመት ነው። ስለዚህ ጥፋት የተገኘበትን ሰው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓመታት ወይንም አንዳንዴ በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታት ይፈርድባቸዋል። ታዲያ ለዚህ ነው ብዙዎች፤ ሰዎች ለፈጸሙት ከባድ ወንጀል ሊፈጽመት የማይችሉትን ቅጣት መወሰን ውጤቱ አልታይ ሲላቸው በአስፈላጊነቱ ላይ ጥያቄ የሚያነሱትል። ይግባኝ የሌለው እድሜ ልክ ቅጣት ቢፈርዱባቸው በቂ አይደለምን? የቅጣት ዓይነቶች በተለያዩ አገራት ልዩነት አላቸው። አንዳንዱ የሞት ቅጣት ሌላው ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት እንዲሁም ሌሎች የቅጣት አይነቶች በጥፋት ፈጻሚዎች ላይ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ፍርድ ይሰጣሉ። የረዥም ዓመታት እስር ፍርድ ግን በብዛት የሚሰማው ከአሜሪካን ነው። በዚህች አገር በአንድ ሰው የተሰሩ የተለያዩ ወንጀሎች ክብደት እንዲያገኙ ለማድረግ ሲባል የረዥም ዓመታት የቅጣት ውሳኔ በፍርድ ቤት ይሰጣል። ይህ ምን ማለት ነው? በአጭር እና ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ ጥፋት የተገኘበት ግለሰብ ለፈጸማቸው የተለያዩ ተደራራቢ ወንጀሎች ለእያንዳንዱ ወንጀል በተናጠል ቅጣት ስለሚጣልበት ነው የቅጣት ዓመታቱ ግለሰቡ በምንም ዓይነት ሁኔታ በህይወት ከሚቆይበት በላይ በጣሙን የተጋነነ የሚሆነው። በምሳሌ እንየው፡ ሆዜ አልቫሬዝ በሕጻኗ ላይ ተደጋጋሚ ጾታዊ ጥቃት በመፈፀም ወንጀል ቅጣት የተፈረደበትን ግለሰብ ነው። ይህ ግለሰብ የስድስት ዓመቷን ሕጻን ዘጠኝ ዓመት እስኪሞላት ድረስ ጾታዊ በደል አድርሶባታል። በዚህም የተከሰሰበባቸው የተለያዩ ወንጀሎች አስራ ዘጠኝ ነበሩ። ስለዚህ ይህ ሰው በአስራ ዘጠኙም ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ለእያንዳንዱ ክሶች ለየብቻ የቅጣት ዓመታት ተፈርዶበት እነዚህ የወንጀል ቅጣቶች ሲደማመሩ ሁለት መቶ ዓመት ሊሆኑ በመቻላቸው ነው ከፍተኛው የእስር ቅጣት የተበየነበት። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በተደራራቢ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ፍርድ የተሰጠው ግለሰብ ቅጣቱን በተመሳሳይ ጊዜ እንዲጨርስ ይደረጋል። ይህም ማለት አንድ ግለሰብ በአምስት የተለያዩ ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቶ እያንዳንዱ ጥፋት ሃያ ዓመት ካስፈረደበት ሁሉንም ቅጣቶች በአንድ ጊዜ የሚፈጽም ይሆናል። ይህም ማለት የእስር ቅጣቱ የአምስቱ ጥፋቶች 20 ዓመታት እስር ተደምሮ አንድ መቶ ዓመት ሳይሆን፤ የሁሉም የእስር ቅጣቶች በአንድ ጊዜ ስለሚፈጸሙ በሃያ ዓመት የእስር ቅጣት ብቻ ፍርዱን ሊፈጽም ይችላል። "የሚተላለፉ የፍርድ ውሳኔዎች አንድ ሰው እስር ቤት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ማሳለፍ እንዳለበት ብቻ አይደለም፤ ውሳኔው ለማስተማሪያነት ነው"ይላሉ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሕግ ፕሮፌሰር የሆኑት ፍራንክሊን ዚም ሪንግ። በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አዲ ደቀቦ በበኩላቸው አገራት እንደዚህ ዓይነት የእስር ቅጣቶችን የሚያስተላልፉት ከተፈጸመው ወንጀል አንጻር የቅጣት ወሰን የሌላቸው ሲሆኑ ነው ይላል። "የቅጣት ጣርያ ስላልተቀመጠ ሰዎች መኖር ከሚችሉበት እድሜ በላይ ይፈረድባቸዋል" በማለት የሚከተለውን አስረጅ ይጠቅሳሉ። ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት የ191 ሰዎችን ሕይወት በቀጠፈው እና በስፔን በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ላይ የተሳተፉ ወንጀለኞችን 43000 በሚደርስ ዓመት እስር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል ሲል ይጠቅሳል። ከዚህ በተቃራኒ ሌሎች አገራት ደግሞ በጣም አጭር የሆነ የእስር ቅጣት አላቸው። ለምሳሌ በኖርዌይ 77 ሰዎችን ሆን ብሎ የገደለው አንደሬስ ብሬቪክ የተባለው ግለሰብ 21 ዓመት ብቻ ነው የተፈረደበት። የኢትዮጵያ ሕግስ ምን ይላል? አቶ አዲ ደቀቦ እንደሚሉት በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ከፍተኛው የእስር ቅጣት 25 ዓመት ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ከ25 ዓመት በላይ በእስራት አይቀጣም። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው በስድስት የተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥሮ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ ለፈጸማቸው ወንጀሎች እያንዳንዱ ተደምሮ ቅጣቱ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይናገራል። ቢሆንም ግን የእነዚህ ወንጀሎች ድምር ከ25 ዓመት እስካልበለጠ ድረስ ነው። ድምሩ ከ25 ዓመት በልጦ ሃምሳ ወይም ስድሳ ዓመት ቢደርስ ግን ታራሚው ግለሰብ የእስር ጊዜውን እንዲፈጽም የሚደረገው ለ25 ዓመታት ብቻ መሆኑን የሕግ ባለሙያው ያስረዳሉ። ሌሎች አገሮች ግን ድምሩ የቱንም ያክል ቢሆን እና ከግለሰቡ እድሜ ቢበልጥ እንኳ ቅጣቱን እንዲፈጽም ሊፈረድበት ይችላል። እንደ ሕግ ባለሙያው ገለጻ አንድ ግለሰብ ይህን ያክል ረዥም ዓመት ሊፈረድበት የሚችለው ሌላኛው ምክንያት ይህ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ታራሚ ከእስር ቤት በይቅርታ ወጥቶ ወደ ኅብረተሰቡ እንዳይቀላቀል ለማድረግ ነው።
news-49274470
https://www.bbc.com/amharic/news-49274470
ቶርፖት ናያሪክጎር፡ ወባን በቀላሉ የሚለይ የፈጠራ ሥራ የሠራው ኢትዮጵያዊ
ቶርፖት ናያሪክጎር ሮምዶር ተወልዶ ያደገው ጋምቤላ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን አሶሳም አዲስ አበባም እያለ የተማረ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በኩየራ አድቬንቲስት ሚሽን ተምሮ አስራ ሁለተኛ ክፍልን ጋምቤላ መሰናዶ ትምህርት ቤት አጠናቋል።
ቶርፖት በአሁኑ ሰዓት በዲላ ዩኒቨርስቲ የሦስተኛ ዓመት የኤክትሪካልና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነው። ቶርፖት ወንድሙን ያጣው በወባ ምክንያት እንደነበር ያስታውሳል። ወንድሙ ብቻ ሳይሆን፤ በአጠቃላይ በክልሉ በወባ የሚያዙና የሚሰቃዩ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ቤተሰቦቹ ጋር በቆየበት ጊዜ ሁሉ ታዝቧል። • የብስክሌት ጀልባ የሠራው ወጣት • ወባ አጥፊው ክትባት ሙከራ ላይ ሊውል ነው ይህቺን የቀዬውን ነዋሪ ሁሉ አቅም ነስታ ከአልጋ የምታውል በሽታ እንዴት በቀላሉ ማከም አልተቻለም? በቶርፖት የልጅነት አዕምሮው ውስጥ የሚመላለስ ጥያቄ ነበር። "በክልሉ ውስጥ ወንድሜ በሞተበት ጊዜ በርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ወባን ለማጥፋት አጎበር ያከፋፍሉ ነበር" ሲል የሚያስታውሰው ቶርፖት ጤና ጣቢያው ከቤተሰቦቹ ቤት የአንድ ሰዓት የእግር ጉዞ ያህል እንደሚርቅ ይናገራል። በዚህም ምክንያት ሕክምናን በቶሎ ለማግኘት አዳጋች ነበር። ወንድሙ በወባ ምክንያት ሲሞት፣ ወባን ከምድረ ገፅ ማጥፋት እንዳለበት አሰበ፤ እንዴት? ምንም እውቀቱ አልነበረውም። ብቻ ዳግመኛ ወባ ቤተሰቡ ውስጥ ገብታ አንዱን የቤተሰቡን አባል በሞት ስትነጥቅ ማሰብ አልፈለገም። ቶርፖት በዲላ ዩኒቨርስቲ ዩኒቨርስቲ ገብቶ ራሱን በእውቀት ሲያደረጅ፣ በቴክኖሎጂው መስክ ወባን የመከላከል ብልሀት ብልጭ አለለት። በዚህ መካከል ደግሞ ሁዋዌ ወደ ዲላ ዩኒቨርስቲ ጎራ አለ። • አደገኛ የተባለ የወባ በሽታ በበርካታ ሀገራት ስጋት ፈጥሯል። በኢትዮጵያስ? የሁዋዌ ዲላ ዩኒቨርስቲ መምጣት ለተማሪዎቹ የአንድ ወር ሥልጠና ለመስጠት ነበር። ከሁዋዌ አይሲቲ አካዳሚ ሥልጠናው ከወሰደ በኋላ እስቲ እውቀቱ ይመዘን ተብሎ ለፈተና ተቀመጠ። ፈተናው ለቶርፖት ከባድ አልነበረም፤ አለፈ፤ እነርሱ ደግሞ በምላሹ አዲስ አበባ ወሰዱት። ውድድሩ በዚህ አላበቃም። አዲስ አበባ ሄዶ ደግሞ ከሌሎች ጋር ለውድድር ተቀመጠ፤ ይህንንም በድል አጠናቀቀ። ያኔ ወደ ቻይና መጓዝ የሚያስችለው ቲኬት ተቆረጠለት። ቻይና የሁዋዌ ዋና መናገሻ ወደ ሆነው ሼንዘን በማምራት በዚህ ግዙፍ ተቋም ውስጥ የአይሲቲን ቴክኖሎጂ ያያሉ፤ ይዳስሳሉ፤ ይጨብጣሉ። ወደ ቻይና የሄደው ከሦስት ኢትዮጵያዊያን ጋር እንደነበር የሚያስታውሰው ቶርፖት ውድድራቸው ፈጠራ ላይ ሳይሆን ኔት ወርኪንግ ላይ እንደነበር ይናገራል። • የወባ ትንኝን 99 በመቶ የሚገድል ፈንገስ ተገኘ በዚህ የሁዋዌ ግብዣ ላይ የታደሙ በርካታ አፍሪካውያንም ነበሩ። በሁዋዌ ዋና ጽህፈት ቤት ሆኖ የ5ጂ ቴክኖሎጂን ምጥቀት እና ከተማዋ እንዴት በኔትወርክ እንደተሳሰረች ተመለከተ፤ ተደመመ። እናም ዘወትር በልቡ ያለውን ሀሳብ 'ወባን መከላከል' እውን ለማድረግ ቆረጠ። ከቻይና ሲመለስ ስለ አይኮግ ላብስ ሰማ። የአይኮግ ላብስ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ እንደሚናገሩት፣ ድርጅታቸው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማስፋፋት ይሰራሉ። ይህ ቶርፖት የተሳተፈበት ውድድርም አይኮግ ሶልቭ አይቲ (i Cog Solve IT) የሚሰኝ ሲሆን የቶርፖትን የልጅነት ሕልም ለማሳካት መንገድ የጠረገ ነበር። ፈጠራና ቴክኖሎጂ ቶርፖት ወባን የማጥፋት ሕልሙን ለማሳካት ቴክኖሎጂን ቀኝ እጁ አድሮጎ ተነሳ። ይህንን የፈጠራ ሥራም 'ቶር ማላሪያ ዲቴክቲንግ ዲቫይስ' ሲል ሰየመው። "ቴክኖሎጂው ከደም ንክኪ የራቀ ነው" ይላል ስለ ስራው ሲያስረዳ። የሕመምተኛውን እጅ ስካን [በማንሳት] በማድረግ ብቻ በወባ መያዝ አለመያዙን ማወቅ እንዲያስችል አድርጎ እንደሰራው ይናገራል። እንዴት? ግራ ለገባው ሰው መልስ አለው። "በወባ የተያዘ ሰው ቀይ የደም ህዋስ 'ባይ ኮንኬቭ' የሆነው የሴሉ ቅርፅ በፕላስሞዲየሙ አማካኝነት ቅርፁ ይቀየራል። በዚህ ወቅት በወባ ያልተያዘና የተያዘን ሰው ሌዘር ሴንሰር ተጠቅሞ መለየት እንዲችል ማድረግ ይቻላል" ይላል ቶርፖት። • ሶፊያ ከዐብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች ይህ የሌዘር ሴንሰር የታማሚውን የጣት ምስል በመውሰድ ቀይ የደም ህዋስን የላይት ኢንቴንሲቲ ይለካል። የተለያየ ቅርፅ ያላቸው ህዋሶች የተለያየ የብርሃን ኢንቴንሲቲ ይወስዳሉ። አንድ ሰው ወባ ካለበት ፖዘቲቭ፤ ከሌለበት ደግሞ ኔጋቲቭ ላይት ኢንቴንሲቲ ያሳያል ሲል በአጭሩ ያብራራል። ምንም ደም መውሰድ ሳያስፈልግ በጨረር ምርመራ ብቻ ተጠቅሞ እጅን ስካን በማድረግ መመርመር የሚያስችለው ይህ መሳሪያ በስልክ ላይ ተጭኖ ይሰራል ብሏል ቶርፖት። በስልክ የተወሰደውን ምስል ወደ መመርመሪያው በኔትወርክ ወስዶ አንድ ሰው ወባ አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን በተቀመጠው ዳታ መሰረት መለየት ያስችላል ሲል ያክላል። ይህንን የፈጠራ ሥራ በሚሰራበት ወቅትም የሦስተኛ ዓመት የኮምፒዩተር ሳይንስ ተማሪ የሆነው ሮቤል ከበደ ከጎኑ በመሆን እንደደገፈው ሳይገልፅ አላለፈም። "መሳሪያውን ለመጠቀም የተራቀቀ የቴክኖሎጂ እውቀት የግድ አያስፈልግም" የሚለው ቶርፖት ማንም ሰው በቀላሉ ወባ እንዳለበትና እንደሌለበት ማወቅ እንዲያስችል ተደርጎ መሰራቱን አስረግጦ ይናገራል። ይህ መመርመሪያ መሳሪያ ሙሉ በሙሉ ተሰርቶ አለመጠናቀቁን የሚያስረዳው ቶርፖት ከግማሽ በላይ መጠናቀቁን ያብራራል። ይህ መሳሪያ ገና የመጀመሪያ ደረጃ ሥራው ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ወባን 70 በመቶ መለየት ይችላል ሲል የሚናገረው ቶርፖት፣ ይህም የሆነበት ምክንያትም በሀገራችን በስፋት የሚገኙት የወባ ዓይነቶች ሁለት በመሆናቸው ነው ሲል ያክላል። የሁለቱንም ወባ መረጃዎች በሚገባ አስገብቶ መመርመሪያውን ዳግም የማሻሻል ሥራው ደግሞ እየተሰራ ነው። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ የአይኮግ ላብ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት በ2010 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ውድድር ተጠናቅቆ ወደ ሁለተኛ ዙር ያለፉት መለየታቸውን ይናገራሉ። ውድድሩ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል የመጡ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ወጣቶችን፤ ከተለያዩ ሃገራት ጋር ከሚገኙ እና በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ለማስተሳሰር አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል። ይህ ቶርፖት እየተወዳደረበት ያለው i Cog Solve IT የሁለተኛ ዙር ተሳታፊዎች የፈጠራ ሥራ ከድርጅቱ ውጪ በሚመጡ ባለሙያዎች ተመዝኖ ለአሸናፊው በቅርቡ ሽልማት እና እውቅና እንደሚሰጠው ጨምረው አስረድተዋል። ቶርፖት ይህን መሳሪያ ሙሉ በሙሉ አጠናቅቆ ወደ ሥራ ከገባ የወንድሙን ገዳይ 'ወባ'ን እንደተበቀለ ያህል ይሰማዋል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ሌሎች የማህበረሰቡን ችግር የሚቀርፉ ፈጠራዎች ላይ መሰማራት፣ በጋምቤላ ክልል ያሉ ወጣቶችና ታዳጊዎችን የኮምፒውተርና አይሲቲ እውቀት ከፍ ለማድረግ ለማስተማር ሕልም ሰንቋል።
news-56380693
https://www.bbc.com/amharic/news-56380693
ምርጫ 2013፡ ስድስተኛው ክልላዊና አገራዊ ምርጫ በኦሮሚያ ክልል
የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የቀሩት ከሦስት ወራት ያነሱ ጊዜያት ብቻ ናቸው።
በኦሮምያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እና በዚህ ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከተጠበቁት መካከል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) "ተገፍተናል" በሚል በምርጫው እንደማይሳተፉ ተናግረዋል። እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ላለመሳተፍ ካቀረቧቸው ምክንያቶች መካከል የአባላቶቻቸው እና የአመራሮቻቸው መታሰር እንደዚሁም ደግሞ የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ኦፌኮም ሆነ ኦነግ በኢትዮጵያ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የቆዩ እና በርካታ ደጋፊዎች እና አባላት አሏቸው የሚባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው። ኦፌኮ በ2004 ዓ.ም በኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዲን) እና በኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ (ኦሕኮ) ፓርቲዎች ውህደት የተመሰረተ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በ1968 ዓ.ም ነጻ የወጣች እና ራሷን የቻለች የኦሮሚያ ሪፐብሊክን ለመፍጠር በማቀድ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት ው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የትጥቅ ትግል በማካሄድ ረዥም ዓመታትን ያሳለፈው ይህ ፓርቲ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለመሳተፍ በመወሰን ወደ አገር ውስጥ ከገቡ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። በኦሮሚያ ለመወዳደር ዕጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ዕጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ዝርዝር ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በኦሮሚያ ለመወዳደር አራት ዕጩዎቹን ያስመዘገበው የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ (ኦነን) ይገኝበታል። በሌላ በኩል ብልጽግና በኦሮሚያ ውስጥ ባሉ የምርጫ ወረዳዎች በሙሉ እንደሚወዳደር ይጠበቃል። ኢዜማ በበኩሉ በኦሮሚያ ውስጥ በ70 የምርጫ ወረዳዎች ላይ ዕጩዎቹን ያስመዘገበ ሲሆን ባጋጠመው ችግር ምክንያት ፓርቲው በሃያ አምስት የምርጫ ወረዳዎች ዕጩዎችን እንዳላስመዘገበ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይም ከምርጫ ቦርድ ጋር እየተወያዩ መሆኑንም ጨምረው አመልክተዋል። ከዚህም ውጪ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና እናት ፓርቲ በኦሮሚያ ለመወዳደር እጩዎቻቸውን ካስመዘገቡ ፓርቲዎች መካከል ናቸው። የኦነግ እና የኦፌኮ በምርጫ አለመሳተፍ በምርጫ ቦርድ እና በብልጽግና ዓይን የብልጽግና ፓርቲ ሕዝብ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) "ኦነግ እና ኦፌኮ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖሩ እንኳ ተቋቁመው መታገል አለባቸው እንጂ እንዲሁ በቀላሉ ወጥተናል ብለው መወሰናቸው ትክክል አይደለም" በማለት ይናገራሉ። በተጨማሪም ቢቂላ (ዶ/ር) ፓርቲዎቹ መንግሥት ጫና ያደርስብናል፣ አባላቶቻችንን ያስራል፣ ጽህፈት ቤታችንን ዘግቷል ሲሉ የሚያቀርቡትን ውንጀላ "መሰረት የሌለው" ሲሉ አጣጥለውታል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ባለፈው ሳምንት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት የአባላትን መታሰር አስመልክቶ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታሰሩት እንዲፈቱ እየሰሩ መቆየታናቸውን እና በተወሰነ መልኩም መፍትሔ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ከጽህፈት ቤቶች መዘጋት ጋርም ተያይዞ ኦነግና ኦፌኮ የተዘጉባቸውን ጽህፈት ቤቶችን ተመለከተ መረጃ እንዲያቀርቡ ተጠይቀው ሁለቱም ፓርቲዎች መልስ ሳይሰጡ መቅረታቸውን የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቀሳ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ሁሎቱም ፓርቲዎች ባለመሳተፋቸው ሊያጋጥም ይችላል ብሎ የተዘጋጀበት ችግር እንደሌለ ተናግሯል። የምርጫ እንቅስቃሴ በነዋሪዎች ዓይን የምርጫ ዝግጅት እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ በተመለከተ፣ ቢቢሲ የተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ነዋሪዎችን አነጋግሯል። የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪ የሆኑት አቶ ሃብታሙ ያደቴ አካባቢያቸው እያስተዳደረ ካለው ብልጽግና ፓርቲ ውጪ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ እንደሌለ ይናገራሉ። ውድድር ደግሞ ከአንድ በላይ በሆኑ አካላት መካከል የሚደረግ መሆኑን የሚናገሩት እኚህ ነዋሪ "በአሁኑ ጊዜ ግን የምርጫ ፉክክር እየተካሄደ መሆኑን የሚያሳይ ነገር እነደሌለ" ይናገራሉ። በሌላ በኩል የቦረና ዞን ነዋሪ የሆኑት አቶ ገልገሎ ዋቆ እነዚህ ፓርቲዎች ያጋጠማቸውን ችግሮች ከመንግሥት ጋር በመሆን በመፍታት ምርጫ ላይ መሳተፋቸው መልካም እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ "ኦነግ እና ኦፌኮ የማይሳተፉበት ምርጫ የሕዝብ ተቀባይነት ይኖረዋል የሚለው ላይ ጥርጣሬ አለኝ" የሚለው የምሥራቅ ወለጋ ነዋሪ የሆነው ወጣት ናትናኤል ጳውሎስ ነው። "ምርጫው አሳታፊ አይደለም" የሚለው ይህ ወጣት "በዚህም ከጥቅሙ ይልቅ አሉታዊ ተጽዕኖው ትልቅ ሊሆን እንደሚችል" ያለውን ስጋት ይናገራል/ ናትናኤል የፓርቲው አመራሮችና አባላት መታሰነርንም በማንሳት "...የክልላችን ሕዝብ የሚወክል ፓርቲ እና በዚህ ምርጫ ተሳትፎ ያለው የትኛው ፓርቲ ነው?" በማለት ይጠይቃል። ከዚህም በተጨማሪ በአራቱም የወለጋ ዞኖች፣ በኢሊአባ ቦራ እና ጉጂ ውስጥ የሰላም ስጋት መኖሩን የሚናገረው ናትናኤል፣ "አሁን እኔ ለምሳሌ ሄጄ በሰልፍ ላይ ወረቀት ወስጄ ለመምረጥ ፍላጎት የለኝም፤ ምክንያቱም ለደህንነቴ እሰጋለሁ' በማለት ይናገራል። ሲጠበቅ የነበረው አለመግባባት በአምቦ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ሰለሞን ተፈራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫ መውጣት ዋነኛ ምክንያት ኦነግ እና ኦፌኮ አገር እያስተዳደር ካለው ድርጅት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ይናገራሉ። "የሁለቱ ፓርቲዎች ከምርጫ መውጣትም በአጋጣሚ የሆነ ሳይሆን ሲጠበቅ የነበረ ነው" የሚሉት እኚህ ምሁር የሁለቱ ፓርቲዎቹ በምርጫ አለመሳተፍ የመራጮችን ቁጥር ይቀንሰዋል ሲሉ ያስረዳሉ። ፓርቲዎቹ ሰፊ ተቀባይነት ባላቸው አካባቢዎች የሚደረግ ምርጫ የሚገኘው ውጤት የሕዝብ ተቀባይነት እንዳእኖረው ሊያደርግ እንደሚችል ስጋታቸውን ይናገራሉ። ስለዚህ በዚህ ምክንያት ሊያጋጥም የሚችል ችግር ከኦሮሚያ እና ከአገሪቷ አልፎ የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል መምህር ሰለሞን ተፈራ አስረድተዋል። አክለውም "እነዚህ አለመግባባቶች በአብዛኛው ከምርጫ በኋላ የሚቀጥሉና የአገሪቷን ሰላምና አንድነት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ። ስለዚህ ይህ በትኩረት መታየት አለበት" ሲሉ ምክራቸውን ያቀርባሉ።
news-53524253
https://www.bbc.com/amharic/news-53524253
ሃሪ እና ሜጋን ልጃቸውን በድሮን ፎቶ ያነሳው ግለሰብ ላይ ክስ መሰረቱ
የሰሴክሱ መስፍን ሃሪ እና ባለቤቱ ሜጋን በድሮን አማካኝነት ጨቅላ ልጃቸው አርቺን ፎቶ ያነሳው ግለሰብ ላይ ክስ መሰረቱ።
በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ የተከፈተው ክስ፤ በስም ያልተጠቀሰው ግለሰብ የ14 ወራት ጨቅላ የሆነውን የሃሪ እና ሜጋን ልጅ አርቺን በመኖሪያ ቤታቸው በድሮን አማካኝነት ፎቶግራፍ አንስቷል ይላል። ጥንዶቹ ፎቶግራፎቹ የተነሱት የልጃቸውን እና የእነሱን ግላዊነት በተላለፈ መልኩ ነው ይላሉ። ሃሪ እና ሜጋን ከዚህ ቀደም በድብቅ ፎቶ የሚያነሷቸውን ሰዎች አስጠንቅቀው ነበር። ሜጋን፤ ካናዳ ውስጥ ልጇኝ ከፊት አዝላ ሁለት ውሾች በገመድ እያንሸራሸረች የምትታይበት ፎቶ ሾልኮ ከወጣ በኋላ ነበር ጥንዶቹ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክታቸውን ያሰሙት። ሃሪ እና ሜጋን ከወራት በፊት ከእንግሊዝ ንጉሳዊያን ስርዓት እራሳቸውን ማግለላቸው የሚታወስ ሲሆን፤ አሁን መቀመጫቸውን በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ አድርገዋል። የጥንዶቹ ጠበቃ የሆኑት ማይክል ኩምፕ፤ “በካሊፎርኒያ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባላት በመኖሪያ ቤታቸው የግላዊነት መብታቸው የተጠበቀ ነው። ድሮንም፣ ሄሊኮፍተር ወይም ፎቶግራፎች ይህን መብት መተላለፍ አይችሉም” ብለዋል። ጠበቃው ጨምረው እንደተናገሩት፤ ሃሪ እና ሜጋን በተደጋጋሚ ፎቶግራፍ ተደብቀው በሚያነሱ ፓፓራዚዎች ምክንያት ግላዊ መብታቸው በተደጋጋሚ እየተጣሰ ነው። በመኖሪያ ቤታቸው ላይም ሄሊኮፍተር ፎቶግራፍ ለማንሳት በተደጋጋሚ እንደሚበር እና ፎቶግራፍ አንሺዎችም አጥራቸውን እየሰረሰሩ ፎቶግራፍ ማንሻ ሌንሶችን አስርገው እንደሚያስገቡ ጠበቃው ተናግረዋል። የልዑል ሃሪ እናት የሆነችው ልዕልት ዳያና በሞተርብስክሌት ሲከታተሏት ከነበሩ 'ፓፓራዚዎች' ስታመልጥ ሳለች ባጋጠማት የመኪና አደጋ ህይወቷ ማለፉ አይዘነጋም።
news-54210656
https://www.bbc.com/amharic/news-54210656
ጃዋር መሐመድ ፡ ዐቃቤ ሕግ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች በውጭ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ክስ መሰረተ
በአስር ላይ የሚገኙትን አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሀምዛ አድነን ጨምሮ ሌሎች ከአገር ውጪ በሚገኙ 24 ሰዎች ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መመስረቱን ዛሬ [ቅዳሜ] አስታወቀ።
ጃዋር መሐመድ፣ ብርሃነመስቀል አበበ፣ በቀለ ገርባ በእነአቶ ጃዋር ላይ ትናንት የክስ መዝገብ ይከፈትባቸዋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ክስ አለመመስረቱን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ዛሬ ከፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ሌሎችንም ሰዎች ጨምሮ ክስ መመስረቱን ገልጿል። በዚህም መሠረት ከአቶ ጃዋር መሐመድ፣ ከአቶ በቀለ ገርባና ከአቶ ሀምዛ አድናን በተጨማሪ በሌሉበት የኦሮሚያ ሜዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) ኃላፊ አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ከወራት በፊት በአሜሪካ በሚገኝ የኢትዮጵያ ቆንስላ ዲፕሎማት የነበሩት ብርሃነመስቀል አበበ (ዶ/ር)፣ ነዋሪነታቸው አውስትራሊያ የሆነው አቶ ፀጋዬ ረጋሳን ጨምሮ በአጠቃላይ 24 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱ ታውቋል። ከግለሰቦቹ በተጨማሪም ከወራት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ የነበረው ቢሮው የተዘጋው የኦሮሚያ ሜዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) በተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይም ክስ ተመስርቷል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዳከለው ክሱ የተመሠረተባቸው ተቋምና ግለሰቦች "እንደየተሳትፏቸው በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርንና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ፣ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድግ" የሚሉ ክሶች የቀረቡባቸው መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2004 እና የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በመተላለፍ በፈፀሙት ወንጀልም ክስ መስርቷል። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዳለው መስከረም 6/2013 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 260215፤ በአጠቃላይ አስር ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ጠቅሶ ተከሳሾቹም ሰኞ መስከረም 11/2013 ዓ.ም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የተመሠረተባቸው ክስ ዝርዝር እንደሚደርሳቸው አመልክቷል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ትናንት ክስ የሚመሰርትበት ቀን የመጨረሻ ቀን እንደነበረና በዚሁ መሠረትም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ ይመሰረታል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ነገር ግን ክሱ ሳይመሰረት በመቅረቱ የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ በደንበኞቻቸው ላይ ክስ ስላልተመሰረተ "አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ [ሃቢየስኮርፐስ] የፊታችን ሰኞ ለፍርድ ቤት እናቀርባለን" ብለው ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ነገር ግን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ እንዳስታወቀው በእስር ላይ ያሉትን ተጠርጣሪዎች ጨምሮ በውጪ አገራት በሚገኙ 24 ሰዎች ላይ አስር ተደራራቢ ክሶችን መስርቷል። ክሱም ሰኞ ዕለት ለተከሳሾቹ እንደሚቀርብ አሳውቋል። ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደመሰረተባቸው ሰዎች መካከል አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባና አቶ ሀምዛ አድናን በአስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን በውጪ አገር የሚኖሩት ተከሳሾች ዝርዝር ይፋ የተደረገው ዛሬ ነው። ታዋቂው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሠኔ 22/2012 ዓ.ም መገደልን ተከትሎ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በርካታ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑ ይታወቃል።
news-52550439
https://www.bbc.com/amharic/news-52550439
ኮሮናቫይረስ፡ “ያልተፈተነ መድኃኒት አትውሰዱ” የአለም ጤና ድርጅት
የአለም ጤና ድርጅት ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ መድኃኒቶችን ለኮሮናቫይረስ በማለት ሰዎች እንዳይወስዱ አስጠነቀቀ።
ምንም እንኳን በአፍሪካ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ ፈውስ ተብለው የቀረቡት ከአገር በቀል የተቀመሙ መድኃኒቶች ቢሆኑም እንኳን፤ ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶች መሆን አለባቸው። አፍሪካውያንም ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶች አቅርቦትን የማግኘት መብት አላቸው ተብሏል። የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት ከዕፅዋት የተቀመመ የኮቪድ19 መድኃኒት ተገኝቷል በማለትም እያስተዋወቁ ባለበት ወቅት ነው ይህ መግለጫ የወጣው። የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ መድኃኒቱ “ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑና አዳኝነቱን” በተመለከተ ሳይንሳዊ ድጋፎችን እንዲቀርቡለት ጠይቋል። ከተለያዩ እፅዋት የተቀመመው መድኃኒት በባለፉት ሶስት ሳምንታት በሃያ ሰዎች ላይ ሙከራ መደረጉን የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህም የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ካወጣው መመሪያ ጋር ይጣረሳል ተብሏል። • በስልጤ ዞን ኮቪድ-19 ያለባቸው ሴት እንዴት ሊገኙ ቻሉ? • በጂቡቲ የኮቪድ-19 መጨመር ለአፋር ክልል ስጋት መሆኑ ተነገረ መድኃኒትም ለማግኘት ረዘም ያለ ጊዜና የተለያዩ ደረጃዎችንም ማለፍ እንዳለበት ተጠቁሟል። ህዝቡ መድኃኒቱን እንዲወስደው ከመደረጉም በፊት በጥቂት ሰዎች ላይ ተሞክሮ ፈዋሽነቱ መረጋገጥ ይኖርበታል። ይሁን እንጂ ጊኒ ቢሳው፣ ኢኳቶሪያል ጊኒና ላይቤሪያ ከዕፅዋት የተቀመመውን መድኃኒት ወደ ሃገራቸው እንዲመጣ አዘዋል። መድኃኒቱ የተሰራው የወባ በሽታንና ለሌሎችም በሽታዎች መድኃኒት ከሆነው የአሪቲ ቅጠል (አርቲሚዥያ)ና ሌሎችም ዕፅዋት መሆኑ ተነግሯል። ባለፈው ሳምንት የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት አንድሬ ራጆይሊና ስለ መድኃኒቱም ለማስረዳት ከተለያዩ አፍሪካ መሪዎች ጋር በ’አንላይን’ ስብሰባቸውን አድርገዋል። ከስብሰባውም በኋላ የአፍሪካ ህብረት ስለ መድኃኒቱ ዝርዝር የጠየቀ ሲሆን ይህም በአፍሪካ የበሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል ማዕከል ግምገማ የሚደረግበት ይሆናል። የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት እንዲህ አይነት አገር በቀል መድኃኒቶችን ለመድኃኒትነት የማዋል ግኝት “ይበል የሚያሰኝ ነው” ካለ በኋላ ሆኖም “ የጎንዮሽ ጉዳትና አዳኝነቱን” በተመለከተ ምርመራ ያስፈልጋል ብሏል። “አፍሪካውያን እንደተቀረው አለም ደረጃውን የጠበቀ መድኃኒት መውሰድ ይገባቸዋል” ብሏል በመግለጫው ለኮሮናቫይረስ የክትባት ሙከራ፣ ምርምር ስራዎች፣ እንዲሁም መድኃኒት ለማግኘትና ለእንክብካቤ ስምንት ቢሊዮን ዶላር በዚሁ ሳምንት ተመድቧል። በአለም ላይ የተጀመሩ የክትባት ሙከራዎችም ቁጥር በርካታ ነው። ሆኖም በርካታ በዘርፉ ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ክትባቱ እስከ ጎርጎሳውያኑ 2021 አጋማሽ ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ይናገራሉ። የኮሮናቫይረስ በተከሰተ ማግስት የቤት መቀመጥ እንዲሁም የሰአት እላፊ አዋጆችን አስተላልፈው የነበሩ ሃገራት ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ጋር ለማጣጣም ህጎቻቸውን አላልተዋል። ህጎቹን ማላቱን ተከትሎ የመድኃኒቱን ፍለጋ ጥያቄዎችም በርትተዋል። በማዳጋስካር 151 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ሞት አልተከሰተም። ፕሬዚዳንቱ በትላልቅ ሶስት ከተሞች ጥለዋቸው የነበሩ የቤት መቀመጥ አዋጆችን ማላላታቸውንም አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
news-53025970
https://www.bbc.com/amharic/news-53025970
"ስለተደፈርኩበት ሁኔታ መፃፌ እፎይታን ፈጥሮልኛል" የፊልም ፀሐፊዋ ሚኬላ
ሚኬላ ኮኤል ተዋናይት፣ ፀሐፊ እንዲሁም የፊልም አዘጋጅ ናት። 'ቺዊንግ ገም' በሚለው ተከታታይ ፊልሟም ከፍተኛ አድናቆትን ተጎናፅፋለች።
ጊዜው ሁለተኛውን ሲዝን (ክፍል) 'ቺዊንግ ገም' እየፃፈች የነበረችበት ወቅት ነበር። በአንደኛው ቀን መሃል ላይ ከመፃፏ እረፍት ወሰደችና ከጓደኛዋ ጋር አንድ ሁለት ሊሉ ሄዱ። ከዚያም ብዙ ነገሮች ጨለማ ሆኑ። በነገታው ጥዋት ስትነሳ አንዳንድ ነገሮች እንደ ህልም ትዝ ይሏት ጀመር። መጠጧ ላይ የሚያደነዝዝ ነገር እንደተጨመረበትና እንደተደፈረችም ተረዳች። ይህ ጨለማና ፈታኝ የሆነው አጋጣሚዋን 'አይ ሜይ ዲስትሮይ ዩ' (ላጠፋህ(ሽ) እችላለሁ) በሚልም ፃፈችው። ከመፃፍ በተጨማሪ ወደ ፊልም ቀየረችው፤ ራሷም ተውናበታለች፣ ከሌላ ባለሙያም ጋር በመሆን ያዘጋጀችው እሷ ናት። በቢቢሲም ላይ የቀረበው ክፍል ብቻዋን የምትተውንበት ነው። "ለመፃፍ ሁለት ዓመት ተኩል ወስዶብኛል። በወቅቱም ተጨማሪ ሥራ እየሰራሁ አልነበረም" በማለት ለሬድዮ ኒውስ ቢት ተናግራለች። "በጣም ፈታኝና አስቸጋሪ ወቅት ብቻ ሳይሆን ጥቃቱ በአሁኑ ወቅትም እየተፈፀመብኝ እንዳለ ተሰምቶኝ ነበር፤ ነገር ግን መፃፌ እፎይታን ሰጥቶኛል" ብላለች። ሬፕ ክራይሲስ የተባለው ድርጅት ባወጣው መረጃ ከአስራ ስድስት ዓመት በላይ የሆኑ 20 በመቶ ሴቶችና 4 በመቶ ወንዶች እንደሚደፈሩ ነው። ይህ መረጃ በእንግሊዝና በዌልስ ያለውን ነው የሚያሳየው። ቢቢሲ ባደረገው የማጣራት ሥራ በጎርጎሳውያኑ 2015 እና 2019 2 ሺህ 600 የሚሆኑ ሰዎች መጠጣቸው ላይ የሚያደነዝዝ ነገር በመጨመር እንደተደፈሩ ነው። ከእነዚህም ውስጥ 72 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። መረጃው የተጠናቀረው ከእንግሊዝና ከዌልስ ነው። "ራሳችንን ጥፋተኛ ማድረህ ማንንም አይጠቅምም" በፊልሙ ላይ ያለችው የሚኬላ ገፀ ባህርይ አራቤላ በተለያዩ የስሜት ምስቅልቅሎች ውስጥ ትመላለሳለች። በተቻለም መጠን ከደረሰባት አደጋም ለማምለጥ ትቀልዳለች፣ ትስቃለች። ፊልሙ ላይ ያለችው ገፀ ባህርይ አራቤላ የሚኬላ የእውነተኛ ህይወቷም ነፀብራቅ ናት። "እንዲህ አይነት አሰቃቂ ክስተተቶች ሲፈጠሩብን እንዲሁም የሚያስታውሱን ነገሮች ሲበዙ በተለያየ መንገድ ለማለፍ እንሞክራለን፤ እንታገላለን። አንዳንድ ጊዜም በማዘን ብቻ አይደለም" ብላለች። "አንዳንድ ጊዜም የደረሰብንን ነገር ለመካድም እንሞክራለን። ሰዎች እንዲያምኑን እየለመንን አይደለም ነገር ግን ሰዎች ስለደረሰብን ነገር በመንገር እንድናምናቸው ይፈልጋሉ" ትላለች። በፊልሙ ላይ ያለችው አራቤላ በጓደኞቿ እርዳታ የት እንደተደፈረችና በማን እንደሆነ ትደርስበታለች። በፊልሙ ላይ የተሳሉት የጓደኞቿ ገፀ ባህርያትም በፍቅር ግንኙነት ወቅት የሚፈልጉትንና የማይፈልጉትን ነገር ለማለት ድምፃቸውን ከማሰማት ጋር ተያይዞ የራሳቸው የተወሳሰበ ታሪክ አላቸው። "አጠቃላይ ፊልሙ በወሲብ ግንኙነት ወቅት ፈቃድ ጠቃሚ እንደሆነ ያስረዳል። ምን ያህል ፈቃዳችን እንዴት በሰዎች ጉልበት ሲነጠቅ፤ በራሳችን መወሰን አለመቻላችን የሚፈጥረውን ስሜት ነው የሚያሳየው" ትላለች ሚኬላ። "በደረሰብን ነገር ወደ ራሳችን መጠቆምና ራሳችንን ጥፋተኛ ማድረግ ማንንም አይጠቅምም" የምትለው ሚኬላ "ለራሳችን ደግ ልንሆን ይገባል። በማንፈልግበት ወቅት ጮክ ብለን 'አይሆንም' ባለማለታችን ልንፀፀት አይገባም። ለራሳችን ይቅርታ ልናደርግ ይገባል።" ከዚህ ፊልምም ብዙዎችም እንደሚማሩ ተስፋ አላት። በተውኔቱ ላይ ያለችው አራቤላ በሰላሳዎቹ እድሜ የምትገኝ ሲሆን በትዊተር አማካኝነት ከፍተኛ እውቅናን አተረፈች። መፅሀፍም ለማሳተም ስምምነት ላይ ደረሰች። እንዲህ እውቅና ላይ ብትደርስም ግራ መጋባቷም የበዛ ነው። "የሚሊኒየሙ የዓለም ገፅታ ነው። በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን ሰዎች ህይወታቸውን እንዴት በጥሩ መልኩ እየኖሩ እንደሆነ ማሳየት ይፈልጋሉ።" "ከስልኩ ወይም ከላፕቶፑ ጀርባ ያለነው ሰዎች ግን ህይወታቸውን የተስተካከለ መልክ ላይኖረው ይችላል። በርካታው የዚህ ዘመን ወጣት በተመሳሳይ መልኩ ነው እየኖረ ያለው፤ እናም ጤነኛ አካሄድም አይመስለኝም። ሁላችንም ቢሆን ህይወታችን ምስቅልቅል ውስጥ እንዳለ ይሰማናል። የተስተካከለ ህይወት አለን ብለን አናስብም" ትላለች። 'አይ ሜይ ዲስትሮይ ዩ' (ላጠፋህ (ሽ) እችላለሁ) የሚለው ፊልሟም ከፍተኛ አደናቆትም እየተቸረው ይገኛል። አንዲት ሴት ጥቃት ከደረሰባት በኋላ የምታልፍበትን መንገድ በተለየ መልኩ በማቅረቧ ብቻ ሳይሆን መሪ ተዋናይቷ ከተለመደው አሰልቺ ባህርይም ወጣ ማድረግ በመቻሏ ነው። "የትኛውንም የህይወት ዘዬ ስንመርጥ የራሱ ጥቅምና ጉዳት አለው። ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ የሆነበት የአኗኗር ዘዬ የለም። በተውኔቱ ውስጥ ያሉት ገፀ ባህርያት ደፋር፣ ጠንካራና ጎበዝ ተደርገው ነው የተሳሉት። በራሳቸው ነፃነትን መርጠው ለማንነታቸው ታማኝ ሆነው መኖርን የመረጡ ናቸው" በማለት ሚኬላ ትገልጻቸዋልች። "ምንም ቢሆን ፍራቻ ህይወቴን እንዲቆጣጠረው አልፈልግም። በእኔ እድሜ የሚገኙ ሰዎችም ጋር የሚያመሳስለንም አንዱ በፍራቻ አለመሸበብን በመምረጣችን ነው" ብላለች።
news-57146501
https://www.bbc.com/amharic/news-57146501
በምዕራብ ኦሮሚያ 'ሦስት ቻይናውያን ታግተዋል የተባለው ሐሰት ነው'
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ሦስት ቻይናውያን የማዕድን አውጪ ኩባንያ ሠራተኞች በታጣቂዎች ታግተዋል መባሉን ሐሰት ነው ሲሉ የዞኑ ባለሥልጣን አስተባበሉ።
እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራ ቡድን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ አቅራቢያ ሦስት የቻይና ዜጋ የሆኑ የማዕድን ሠራተኞችን አግቼ ይዣለሁ ብሎ ነበር። ይሁን እንጂ የምዕራብ ወላጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በዞኑ ውስጥ ታግቶ የሚገኝ የውጭ ዜጋ የለም በማለት ቡድኑ ያወጣው መግለጫ ሐሰት ነው ብለዋል። አቶ ኤልያስ ጨምረውም "በዞኑ ውስጥ ታግቶ የሚገኝ ቻይናዊ አለመኖሩን አረጋግጫለሁ" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ ጥቃቶችን እንደሚፈጽም የሚነገረውና መንግሥት 'ሸኔ' እያለ የሚጠራው ቡድን በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተብሎ መፈረጁ ይታወሳል። ይህ ቡድን ባለፈው ቅዳሜ በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ አቅራቢያ በማዕድን ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሦስት የቻይና ዜጎችን አግቼ ይዣላሁ ማለቱ ይታወሳል። በመግለጫው ተፈጸመ ላለው እገታ ምክንያቱ "በመንግሥት እና በማዕድን አውጪዎቹ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ሕጋዊ አይደለም" የሚል ነው። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተገንጥሎ የትጥቅ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን የሚገልጸው ይህ ቡድን በአካባቢው የሚደረገው የማዕድን ቁፋሮ በርካቶችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፣ በአካባቢያዊ ላይም ጉዳት እያስከተለ ነው ብሏል። ይህ ቡድን ሦስት ቻይናውያን ማዕድን አውጪ ሠራተኞችን አግቼ ያዝኩ ይበል እንጂ ሦስቱ ቻይናውያን የሚሰሩበት ድርጅት ማንነት፣ በየትኛው የማዕድን ማውጣት ተግባራት ላይ ተሰማርተው እንደነበረና የቻይናውያኑ ኃላፊነት ምን እንደሆነ ያለው ነገር የለም። የታጣቂ ቡድኑ ነው ከተባለው መግለጫ ጋር ታግተዋል የተባሉ የሦስት ሰዎች ፎቶግራፍ የተሰራጨ ቢሆንም ስለግለሰቦቹ ማንነት የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ ግን አልተገኘም። ጉዳዩን በተመለከተ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ አዲስ አበባ ከሚገኘው የቻይና ኤምባሲ የተባለ ነገር የለም። የአካባቢው ባለስልጣናት ምን ይላሉ? በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የምዕራብ ወላጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ፤ እገታውን በተመለከተ "በማኅበራዊ ሚዲያ የተባለውን አንብበናል፤ ውሸት ነው። አረጋግጠናል" ብለዋል። "በወረዳችን፣ በቀበሌያችን መሰል ነገር አለመከሰቱን አረጋግጠናል" ያሉት አቶ ኤልያስ፤ ጨምረውም በአካባቢው የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱ ቻይናውያን አለመታገታቸውን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል። መንዲ ከተማ የቱርክ እና የሕንድ ዜጎች ማዕድን የማውጣት ሥራ ተሰማርተው እንደሚገኙ የሚናገሩት አቶ ኤልያስ፤ በአካባቢው ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ዘወትር በሥራ ገበታቸው እንደማይገኙ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የመነ ሲቡ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ ታመነ ይህ ክስተት እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ አለመከሰቱን ተናግረው፤ "በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኦዳ ቢልዲጊሉ ወረዳ እገታው ተፈጽሟል" የሚል መረጃ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህን በተመለከተ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው ነገር የለም። የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው ስለ ጉዳዩ የማውቀው የለም ብለዋል። "ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የውጭ አገር ዜጎች ታፍነዋል የሚል መረጃ የለኝም። ኦሮሚያ ውስጥ ቢሆን ኖሮ መረጃው ይደርሰን ነበር" ብለዋል። ከሁለት ዓመት በፊት መንዲ ከተማ አቅራቢያ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ሁለት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ አምስት ማዕድን አውጪዎች መገደላቸው ይታወሳል። በምዕራብ እና ደቡብ የኦሮሚያ አካባቢዎች ባለፉት ጥቂት ዓመታት በታጣቂዎች በሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች በርካታ የመንግሥት ባለስልጣናት እና ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም ለረጅም ዓመታት በትጥቅ ትግል ላይ ከነበረው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ተለይቶ የወጣውና እራሱን 'የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት' ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት ደግሞ 'ሸኔ' የተባለው ቡድን ስም በተደጋጋሚ ሲነሳ ቆይቷል። የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቡድኑን የሽብር ቡድን አድርጎ ከጥቂት ሳምንታት በፊት መሰየሙ ይታወሳል። በኦሮሚያ ክልል በዚህ ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 18 የመንግሥት ባለስልጣናት፣ 112 የፖሊስ አባላት እና 42 የሚሊሻ አባላት በታጣቂዎች መገደላቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል።
48173887
https://www.bbc.com/amharic/48173887
በሞስኮ አውሮፕላን ተከስክሶ የሰው ሕይወት ጠፋ
በሞስኮ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር ገጥሞት በረራውን አቋርጦ እንዲያርፍ ከተደረገ በኋላ በእሳት ተያይዞ 41 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ።
• ቻይና ሙስሊም ዜጎቿን እየሰለለች ነው ተባለ ይህ የሆነው በሞስኮ ሼሬሜትይቮ አየር ማረፊያ ሲሆን አውሮፕላኑም ኤሮፍሎት የተሰኘ ኤር መንገድ ነው ተብሏል። በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ እየተዘዋወረ ያለ ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው መንገደኞች በእሳት ከሚንቀለቀለው አውሮፕላን ለማምለጥ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮችን ሲጠቀሙ ይታያል። በአደጋው ከሞቱት መካከል ሁለት ሕፃናት እና አንድ የበረራ አስተናጋጅ እንደሚገኙበት የራሺያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። አውሮፕላኑ 73 መንገደኞችን እና አምስት የአውሮፕላኑን ባልደረቦች አሳፍሮ ነበር። • ቦይንግ 737 ወንዝ ውስጥ ገባ አንድ የአይን ምስክር እንደተናገረው ከአውሮፕላኑ በሕይወት ሰዎች መውጣታቸውን "ተአምር" ብሎታል። "37 ሰዎች ከአደጋው ተርፈዋል፤ ከእነዚህ መካከል 33ቱ መንገደኞች ሲሆኑ አራቱ የአየር መንገዱ ሠራተኞች ናቸው።" ብለዋል የአደጋውን መንስዔ እየመረመሩ ያሉት ባለሙያ። አምስት ሰዎች በሆስፒታል ተኝተው የሕክምና ክትትል እያገኙ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። • ኢትዮጵያዊው የኡጋንዳ አየር ኃይል ፊታውራሪ አውሮፕላኑ በረራ በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ተመልሶ ለማረፍ ተገድዷል። ነገር ግን ተመልሶ ለማረፍ እየተንደረደረ ሳለ ሞተሩ በእሳት መያያዙን አየር መንገዱ በመግለጫው ላይ ተናግሯል። መግለጫው አክሎም የአውሮፕላኑ አብራሪዎች የተሳፋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል ይላል። "መንገደኞቹ በ55 ሰከንድ ውስጥ አውሮፕላኑን ለቅቀው እንዲወጡ አድርገዋል" ሲል በመጥቀስ።
news-46956205
https://www.bbc.com/amharic/news-46956205
ጣልያን አፍሪካን በተመለከተ የሰጠችው አስተያየት ፈረንሳይን አስቆጣ
የጣሊያን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ፈረንሳይ አፍሪካን ትበዘብዛለች፤ ስደትንም ታበረታታለች ማለታቸውን ተከትሎ ፈረንሳይ የጣሊያን አምባሳደርን ለጥያቄ ጠረርታለች።
የጣሊያን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሉዊጂ ዲ ማኢኦ እሁድ ምሽት የጣሊያን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሉዊጂ ዲ ማኢኦ ፈረንሳይ በአፍሪካ ላይ ያላትን ፖሊሲ በመቃወም የአውሮፓ ህብረት ፈርንሳይ ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ጥሪ አቅረበው ነበር። • ባለፉት አስር ዓመታት ያልተቀየሩ እውነታዎች • ቀብሩን አዘጋጅቶ ራሱን ያጠፋው አርሶ አደር ''ፈረንሳይ ከአስር በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራትን ቅኝ መግዛት አላቆመችም'' ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ። ጣሊያን እና ፈረንሳይ ከዚህ ቀደም ስደትን የሚመለከቱ ጉዳዮች አጋጭቷቸው ነበረ። ጣሊያን ኑሯቸውን በአውሮፓ ለመመስራት ለሚጓዙ አፍሪካውያን ስደተኞች የመጀመሪያ መዳረሻቸው ነች። ባለፈው ዓመት ፈረንሳይ ሜዲትራኒያን ባህር ላይ ጀልባቸው ችግር ላጋጠማው አፍሪካውያን ስደተኞች እርዳታ አላደረገችም በማለት ጣሊያንን ከሳ ነበረ። ጣሊያን በበኩሏ ፈረንሳይ ስደተኞችን የመቀበል ፍላጎት የላትም ብላ ነበር። ''የአውሮፓ ህብረት ፈረንሳይን እና እንደ ፈረንሳይ ያሉ አፍሪካን የሚያደኅዩ ሃገራት ላይ ማዕቀብ መጣል ይኖርበታል። ምክንያቱም አፍሪካውያን አፍሪካ ውስጥ እንጂ ከሜዲትራኒያን ባህር በታች ሆነው መገኘት የለባቸውም።'' በአውሮፓውያኑ 2019 የመጀመሪያዎቹ 16 ቀናት ብቻ ከ4200 በላይ ስደተኞች አውሮፓ ደርሰዋል ''አፍሪካውያን አሁንም የሚሰደዱት አውሮፓዊያን ሃገራት በተለይም ፈረንሳይ በርካታ የአፍሪካ ሃገራትን ቅኝ እየገዙ ስለሆነ ነው'' ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ተደምጠዋል። • 'የሴቶች ቫያግራ' በአፍሪካዊቷ ሃገር የምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር ተከትሎ በፈረንሳይ የጣሊያን አምባሳደር የሆኑት ቴሬሳ ካስታልዶ ለጥያቄ የፈረንሳይ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ተጠርተዋል። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም እንደሚለው ከሆነ በመጀመሪያዎቹ የ2019 16 ቀናት ብቻ ከአራት ሺህ በላይ ስደተኞች በባህር ተጉዘው አውሮፓ ደርሰዋል። ይህም አሃዝ ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጨምሯል ብሏል ተቋሙ።
news-56153791
https://www.bbc.com/amharic/news-56153791
ትግራይ ውስጥ በአውቶብስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 6 ተማሪዎች ተገደሉ
ተመራቂ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አሳፍሮ ከመቀለ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘ በነበረ አውቶብስ ላይ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ ስድስቱ ሲገደሉ ሌሎች መቁሰላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞች እና የሆስፒታል ምንጮች ለቢቢሲ ገለፁ።
መቀለ ዩኒቨርስቲ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የካቲት 11/2013 ዓ.ም አርባ አንድ ወጣት ሴቶችና ወንዶችን አሳፍሮ ይጓዝ በነበረው አውቶቡስ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው አዲ መስኖ በምትባል ቦታ ላይ መሆኑም ተገልጿል። ይህንን በተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ከክልሉም ሆነ ከፌደራል መንግሥቱ አስካሁን የተሰጠ ማብራሪያም ሆነ ስለጥቃቱ ፈጻሚዎች በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። በአውቶብሱ ውስጥ ተሳፍሮ የነበረና ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ትምህርት ተመራቂ ተማሪ፤ በጥቃቱ ስድስት ተማሪዎች ሞተው መመልከቱን እና በሰባት ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ለቢቢሲ ገልጿል። ተማሪው ጨምሮም በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል መሆኑን በመግለጽ "እኔም ውስጥ እግሬ ላይ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞኛል" ብሏል። ቢያንስ ለስድስት ሰዎች መሞትና ከ10 በላይ በሚሆኑት ላይ ለደረሰው ጉዳት ምክንያት የሆነው ጥቃት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ገደማ በትግራይ ክልል ሒዋነ ከተማ፤ ልዩ ስሙ አዲ መስኖ የሚባል አካባቢ መድረሱን በአውቶብሱ ተሳፍረው የነበሩ ተማሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የመቀለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ፕሬዚደንት እና የአገር አቀፍ የተማሪዎች ሕብረት ምክትል ፕሬዚደንት አብረሃለይ አረፋይኔ ከተማሪዎቹ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ለቢቢሲ እንደገለጸው ሒዋነ ከተማ አካባቢ የሰባት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉንና ከ10 በላይ የሚሆኑት ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል። በጥቃቱ ተማሪዎቹን አጅበው ሲጓዙ የነበሩ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት አባላትም መገደላቸውን መስማቱን አብረሃለይ ጠቅሶ፤ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች የህክምና ድጋፍ እንዲያገኙ ወደ ወልዲያ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ጨምሮ ተናግሯል። ከጥቃቱ የተረፉ ተማሪዎች ለህክምና ከተወሰዱባቸው ሆስፒታሎች አንዱ የሆነው የቆቦ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሳሁን አዲሱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ አርብ ምሽት 35 ተማሪዎች ወደ ሆስፒታላቸው መምጣታቸውን አመልክተው ከመካከላቸው 12ቱ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ። በጥቃቱ ከተጎዱት መካከል ሴቶችም እንደሚገኙበት የገለፁት አቶ ካሳሁን፤ እጃቸው፣ ጭናቸው እና መቀመጫቸው ላይ በጥይት የተመቱ ተማሪዎች መመልከታቸውን ጠቅሰው፤ ነገር ግን የደረሰባቸው ጉዳት ለክፉ የሚሰጥ አይደለም ብለዋል። ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሉ ሕክምና የተደርጎላቸው ተማሪዎች ትናንት እሁድ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አማካይነት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሸኘት እንደተወሰዱ ጨምረው ተናግረዋል። አቶ ካሳሁን በጥቃቱ ህይወታቸው አልፏል የተባሉት ሰዎች አስከሬን ወደ ሆስፒታላቸው አለመምጣቱን ገልጸው፤ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ከመጡት ውስጥም በሕክምና ላይ ሕይወቱ ያለፈ አለመኖሩን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ተማሪዎች ከሳምንት በፊት በመቀለ ከተማ በተከናወነው የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ተሳትፈው ወደ የመጡባቸው አካባቢዎች እተመለሱ የነበሩ ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈንቅል የተባለው ስብስብ የሆነውና ህወሓትን በመቃወም የሚታወቀው ቡድን አመራር የነበረው አቶ የማነ ንጉሠ በተመሳሳይ ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈጸመበት ጥቃት ቅዳሜ ዕለት ተገድሏል። መንግሥት ለአቶ የማነ ግድያ "የህወሓት ርዝራዥ" ያላቸውን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን፤ ከግድያው ጋር ተያያዘ ኃላፊነት የወሰደም ሆነ በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ ስለመኖሩ ተባለ ነገር የለም። በአውቶብሱ ላይ ምን ነበር የተፈጸመው? በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት ተስተጓጉሎ በነበረው ትምህርት ምክንያት ሳይመረቁ የቆዩ ተማሪዎች ከሳምንት በፊት በመቀለ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት መመረቃቸው ይታወሳል። ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል አንዱ የሆነውና በአውቶብሱ ተሳፍሮ ነበረው ተማሪ ለቢቢሲ እንደተናገረው እሱና ሌሎች ተማሪዎች ከምረቃቸው በኋላ አስከ ረቡዕ ዕለት ባሉት ቀናት የትምህርት ማስረጃቸውን ተቀብለው ነበር ወደየመጡበት ለመመለስ ጉዞ የጀመሩት። ሐሙስ ዕለት ጉዟቸውን ሲጀምሩ በሁለት መከላከያ ሠራዊት አባላት ታጅበው የነበረ ሲሆን፤ በመንገዳቸው ላይ 'አዲጉዶም’ የተባለ ቦታ ሲደርሱ መንገድ ዝግ ነው የሚል ወሬ መሰማቱን ተማሪው ያስታውሳል። ወደ ሥፍራው ሲደርሱም ወጣቶች መንገድ ዘግተው እንዳገኙና የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ መንገዱን አስከፍተው ጉዟቸውን እንደቀጠሉ ይናገራል። ተማሪው ጨምሮ እንደሚለው ዕለቱ የየካቲት 11 በዓል ስለነበር በአካባቢው ብዙም እንቅስቃሴ አይታይም ነበር። ከዚያ በኋላም ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ 'አዲ መስኖ’ የተባለች ቦታ ላይ ታጣቂዎች እንዳስቆሟቸውና የመከላከያ ሠራዊት አባላቱም ሊያነጋግሯቸው ከአውቶብሱ ሲወርዱ ተኩስ መከፈቱን ገልጿል። "ጥይቱ ከብዙ አቅጣጫ ነው የሚመጣው፤ ምንም የምናውቀው ነገር የለም፤ ብቻ ዝቅ በሉ ነው የተባልነው" ይላል። "በጥቃቱ ዓይናችን እያየ ስድስት ተማሪ ነው ሕይወቱ ያለፈው" የሚለው ተማሪው፤ በአውቶብሱና በሌሎች የተማሪዎቹ መረጃዎችና ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱንም ለቢቢሲ ተናግሯል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ የታጣቂዎች ቁጥር ከ30 እስከ 50 ይደርሳል የሚለው ከጥቃቱ የተረፈው ተማሪ፤ ታጣቂዎቹ "የተረፍነውን ተማሪዎች ናቸሁ" በሚል እንደለቀቋቸው ጠቅሷል። ከጥቃቱ በኋላም ሌላ መኪና ተሳፍረው ወደ አላማጣ መሄዳቸውንና ከዚያም በመከላካያ ሠራዊት እርዳታ ወደ ቆቦ ሆስፒታል መሄድ መቻላቸውን ተማሪው ለቢቢሲ አስረድቷል። ባለፈው ሳምንት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ላይ ክልሉ እንዳይረጋጋ ለማድረግ የሚሞክሩ "የተበተኑ የህወሓት ኃይሎችን" መኖራቸውን መጥቀሱ የሚታወስ ሲሆን ሕዝቡም መጠጊያ እንዳይሰጣቸው ጥሪ አቅርቦ ነበር። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጨምሮም "የተበተኑ" ያላቸው የህወሓት ኃይሎች በሕዝቡ ውስጥ መሸሸጋቸውን ገልጾ "የጥፋት ኃይሎች በመንደሮች እና በከተሞች ውስጥ ተሰማርተው የሕዝቡን ሠላም በማናጋት ወደ ሌላ የከፋ ቀውስ እንዲገባ እየሰሩ ነው" ብሏል። በትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ላይ በቀረበውና ከጊዜያዊው አስተዳደር የወጣው ይህ መግለጫ እንዳስጠነቀቀው ፣ ሊወሰድ በሚችለው እርምጃ ሕዝቡ እንዳይጎዳ "የጥፋት ኃይሎቹን አሳልፎ እንዲሰጥ ወይም ለደኅንነቱ ሲል ራሱን ከእነዚህ ኃይሎች እንዲያርቅ" አሳስቧል።በተጨማሪ የክልሉ ነዋሪዎች ከምሽት 12:00 ሰዓት እስከ ንጋት 12:00 ሰዓት የተደነገገውን ሰዓት እላፊ ጨምሮ ሌሎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውሳኔዎችን እንዲያከብሩም አሳስቧል። ባለፈው ማክሰኞ የካቲት 09/2013 ዓ.ም ለትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል በሚያስተላልፉ መስመሮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በመላው የትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዳግም መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መስታወቁ ይታወሳል። ድርጅቱ በክልሉ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የተቋረጠው "የህወሓት ርዝራዦች" ያላቸው ኃይሎች በክልሉ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በፈፀሙት ጥቃት መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ የፌደራል መንግሥት በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ የክልሉ አስተዳዳሪ የነበረው የህወሓት አመራሮችን ከስልጣን መወገዳቸው የሚታወስ ሲሆን፤ መንግሥት በተለያዩ ጊዜያት ለሚፈጸሙ ጥቃቶች የተበታተኑ የሚላቸውን የቡድኑን ታጣቂዎች ተጠያቂ ያደርጋል።
news-55435035
https://www.bbc.com/amharic/news-55435035
ኮሮናቫይረስ ፡ ወደ ታይዋን ኮቪድ-19 ቫይረስ አስገብቷል የተባለው አብራሪ ከሥራ ተባረረ
የኮሮናቫይረስን ወደ ታይዋን ይዞ ገብቷል የባለ ኒው ዚላንዳዊው የአውሮፕላን አብራሪ ከሥራ ተሰናብቷል።
ሰውዬው ታይዋን ውስጥ ከወራት በኋላ ለተከሰተው የኮሮናቫይረስ የማኅበረሰብ ሥርጭት ተጠያቂ ነው ተብሎ ነው ከሥራው የተባረረው። አብራሪው ኢቫ ኤይር ለተሰኘው የታይዋን አየር መንገድ ይሰራ የነበረ ሲሆን፤ ባለፈው ማክሰኞ ከአብራሪው ጋር ግንኙነት የነበረው ግለሰብ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት ተገልጿል። ታይዋን ለ253 ቀናት አንድም በአገር ውስጥ ያለ ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘባትም ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ ወዲህ መንግሥት ሕዝቡ የገና በዓል ግርግሩን ገታ እንዲያደርገው አሳስቧል። ከገና ተከትሎ የሚከበረው የአዲስ ዓመት ዋዜማ ቀንም ሰዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ ተነግሯቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ማናወጥ ከጀመረ ወዲህ ታይዋን 777 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን ሰባት ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን አሳውቃለች። የአውሮፕላን አብራሪው በቫይረሱ የተያዘው በያዝነው የታኅሣሥ ወር መግቢያ ላይ ቢሆንም ምንም የበሽታው ምልክት ግን አልነበረውም ተብሏል። አብራሪዎች ወደ ታይዋን ሲመጡ ለሦስት ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ የሚገደዱ ቢሆንም ምልክት ካላሳዩ ምርመራ እንዲያደርጉ አይመከሩም። ሰውዬው ምልክት ባይኖረውም ከዩናይትስ ስቴትስ አውሮፕላኑን እያበረረ ሲመጣ ግን ሲያስል ነበር ተብሏል። ይህንንም ተከትሎ አብራሪው መሬት እንዳረፈ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ እንዳለበት ተደርሶበታል። የታይዋን ባለሥልጣናት አንድ ሰው ቫይረሱ እንደተገኘበት ካረጋገጡ በኋላ ከየት ነው የመጣውን የሚለውን ሲያጣሩ ነበር አብራሪው ላይ የደረሱበት። ኒው ዚላንዳዊው አብራሪ ከመመርመሩ በፊት ከማን ጋር ግንኙነት እንደነበረው ባለማሳወቁ ነው ሥራውን ያጣው። ሰውዬው በዚህ ጥፋቱ 300 ሺህ የታይዋን ዶላር [415 ሺህ ብር ገደማ] እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ኢቫ ኤይር አብራሪው ከሥራው የተሰናበተው የአየር መንገዱን ደንብ ባለማክበሩና የአውሮፕላኑ ጋቢና [ኮክፒት] ውስጥ ሳለ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጉ ነው ብሏል። ሰውዬው ከአንዲት ሴት በተጨማሪ ሁሉት የሥራ አጋሮቹንም በበሽታው እንዲያዙ አድርጓል ተብሎ ተወቅሷል። ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ አብራሪ "ወረርሽኙን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት" ችላ ብሏል የሚል ትችት ገጥሞታል። ታይዋን ኮሮናቫይረስ በአውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ አገሯ መግባቱን ከሰማች ወዲህ ጥብቅ የመከላከያ መንገዶች እንደ አዲስ ለመዘርጋት አቅዳለች። ቫይረሱን ከአብራሪው ተላልፎባታል ከተባለችው ሴት ጋር በአንድም ሆነ በሌላም መንገድ ግንኙት አላቸው የተባሉ 170 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው። የቻይና ጎረቤት የሆነችው ታይዋን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ጥብቅ እርምጃ ከወሰዱና ከተሳካላቸው ጥቂት የዓለማችን ግዛቶች መካከል ናት። የታይዋን 23 ሚሊዮን ነዋሪዎችም በሽታውን ለመከላከል ከባለሥልጣናት የሚሰጡ መመሪያዎችን በማክበር አስተዋፅዖ አበርክተዋል ተብለው ይመሰገናሉ።
news-56262377
https://www.bbc.com/amharic/news-56262377
መቀለ ውስጥ ታስሮ የነበረው የቢቢሲ ዘጋቢ ግርማይ ገብሩ ተለቀቀ
በኢትዮጵያ ሠራዊት መቀለ ውሰጥ በቁጥጥር ሥር ውሎ የቆየው የቢቢሲ ሪፖርተር ግርማይ ገብሩ ከእስር ተለቀቀ።
ጋዜጠኛ ግርማይ ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር የተለቀቀው ለሁለት ቀናት በእስር ከቆየ በኋላ ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትበት ነው። ቢቢሲም ጋዜጠኛው በምን ምክያት እንደታሰረ መረጃ አላገኘም። ግርማይ ከተያዘ በኋላ መጀመሪያ ላይ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የቆ ሲሆን በኋላ ላይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተዘዋውሮ ነበር። ግጭት በተካሄደበት የሰሜናዊ ኢትዮጵያዋ የትግራይ ክልል የቢቢሲ ትግርኛ ቋንቋ ዘጋቢ የሆነው ግርማይ ገብሩ በኢትዮጵያ ወታደሮች መታሰሩን ተከትሎ ቢቢሲ ስጋቱን ግልጾ ነበር። የቢቢሲ ቃል አቀባይ እስሩን በተመለከተ "ስጋታችንን ለኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ገልጸን ምላሻቸውን እየተጠባበቅን ነው" ብለው ነበር። ትግራይ ውስጥ ከግርማይ በተጨማሪ ታስረው ነበሩ የኤኤፍፒ ዜና ወኪልና የፋይናንሻል ታይምስ ዘጋቢና አስተርጓሚዎችም ከእስር መለቀቃቸው ተገልጿል። ለቢቢሲ የትግርኛ ቋንቋ አገልግሎት የሚሰራው ግርማይ ገብሩ ሰኞ የካቲት 22 የተያዘው በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ ውስጥ በሚገኝ ካፍቴሪያ ውስጥ ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር ነበር። የዓይን እማኞች ለቢቢሲ እንደተናገሩት አምሰቱ ሰዎች የተያዙት ወታደራዊ የደንብ ልብስ በለበሱ ግለሰቦች ሲሆን፤ በሁለት የወታደር ተሽከርካሪዎች በታጀበ መኪና መወሰዳቸውን ገልጸው ነበር። ግርማይን ጨምሮ አምሰት ሰዎች ለምን ተይዘው እንደተወሰዱ ግልጽ አይደለም። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ሪፖርተሩ መቀለ ውስጥ ወደሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል። ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ወደ ትግራይ ለወራት እንዳይገቡ ከተከለከለ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ አገር ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ገብተው እንዲዘግቡ ባለፈው ሳምንት መፍቀዱ ይታወሳል። የቢቢሲው ዘጋቢ ታስሮ የነበረው ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) እና ለፋይናንሻል ታይምስ የሚያግዙ ባለሙያዎች (ፊክሰር) መታሰራቸው ከተነገረ ከቀናት በኋላ ነው። ህወሓትን ለማስወገድ በተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ የፌደራል መንግሥቱ ኃይሎች የትግራይ ክልልን መቆጣጠራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ካስታወቁ በኋላ ካለፈው ኅዳር ጀምሮ ክልሉ በወታደራዊ ዕዝ ስር ይገኛል። ወታደራዊ ግጭቱ የተባባሰው የህወሓት ኃይሎች ትግራይ ውስጥ በሚገኘው የሠሜን ዕዝ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ ነበር። በውጊያው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለመፈናቀል ተዳርገዋል፤ በተጨማሪም በክልሉ ተፈጽመዋል የተባሉ ግድያዎችና የሰብአዊ ቀውስ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ ነው።
news-51701973
https://www.bbc.com/amharic/news-51701973
ሶማሊያን የጎበኙ 11 የኬንያ ምክር ቤት አባላት በፖሊስ ምርመራ ተደረገባቸው
አስራ አንድ የኬንያ ፓርላማ የሕዝብ እንደራሴዎች ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ሶማሊያ ውስጥ ካደረጉት ጉብኝት ጋር በተያያዘ በፖሊስ ምርመራ ተደረገባቸው።
በኬንያ የሚገኘው ኤንቲቪ እንደዘገበው የምክር ቤት አባላቱ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ጋር ተገናኝተው አስላማዊውን ታጣቂ ቡድን መቆጣጠር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል። ነገር ግን የአገሪቱ የደኅንነት ኃላፊ ሙሪቲ ካንጊ እንዳሉት የምክር ቤት እንደራሴዎቹ ጉብኝት በመንግሥት ይሁንታን ያገኘ አይደለም። አስራ አንዱ የኬንያ ምክር ቤት አባላት ስለጉዟቸው ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ወደ ሶማሊያ ያቀኑት በግል ፍላጎታቸው እንደሆነ አመልክተዋል። የቴሌቪዥን ጣቢያው የሕግ አውጪው ምክር ቤት አባላት ከሶማሊያ ጉዟቸው መልስ ናይሮቢ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል በዩቲዩብ ገጹ ላይ አስቀምጧል። የፓርላማው አባላት ወደ መዲናዋ ናይሮቢ ዋነኛ አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ "ከፖሊስ ጋር ለነበረ ውይይት" ለአጭር ጊዜ ተይዘው የነበረ ሲሆን ነገር ግን ወዲያው ተለቀዋል። በተጨማሪም በቀጣይነት ምንም አይነት ክስ እንደማይመሰረትባቸው ተነግሯል። ወደ ሶማሊያ በተደረገው ጉዞ ላይ ከተሳተፉት አስራ አንዱ የሕዝብ እንደራሴዎች መካከል አብዛኞቹ ሶማሊያን ከሚያዋስነውና በተደጋጋሚ አልሻባብ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ከሚፈጽምበት የኬንያ ሰሜን ምሥራቅ ግዛት የተወከሉ ናቸው። በአካባቢው በቅርቡ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን ከሌሎች የኬንያ ግዛቶች በመምጣት በመንግሥት ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰዎች ስፍራውን ጥለው ሸሸተዋል።
news-42025205
https://www.bbc.com/amharic/news-42025205
ጦሩ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ሙጋቤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ታዩ
የሃገሪቱ ጦር ከሶስት ቀናት በፊት ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ሮበርት ሙጋቤ በአደባባይ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የታዩት።
ሙጋቤ በተማሪዎች የምረቃት ፕሮግራም ላይ በዚምባብዌ መዲና በሆነችው ሃራሬ በተማሪዎች የምረቃት ፕሮግራም ላይ ለህዝብ የታዩት። ላለፉት ጥቂት ቀናት ሙጋቤ በቁም እስር ላይ መቆየታቸው ይታወቃል። አርብ ጠዋት የዚምባብዌው ሄራልድ ጋዜጣ ሙጋቤ የጦሩን መሪ ጀነራል ኮንስታኒቲኖ ቺዌንጋንና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ(ሳድክ) ተወካዮች ጋር በቤተመንግሥት ሲነጋግሩ የሚያሳዩ ፎቶዎችን አውጥቶ ነበር። ሙጋቤ ከሥልጣን አልወርድም እያሉ ነው ሬውተርስ የዓይን እማኝን ጠቅሶ እንደዘገበው ሙጋቤ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከተመራቂዎች ሞቅ ያለ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ሙጋቤ በቀይ ምንጣፍ ላይ በዝግታ እየተራመዱ ወደ መድረኩ ሲወጡ ሞቅ ያለ ድጋፍ እና ጭብጨባ ሲደረግላቸው ነበር ሲል የቢቢሲው ሪፖርተር አንድሪው ሃርዲንግ ከሃራሬ ዘግቧል። የሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤም ሆኑ የትምህርት ሚንስትሩ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ አልተገኙም። ሙጋቤ በየዓመቱ በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ መገኘትን ልምድ ያደረጉ ቢሆንም በቁም እስር ላይ እንደመቆየታቸው በፕሮግራሙ ላይ ይገኛሉ ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። ሙጋቤ እስከቀጣዩ ምርጫ ሥልጣኔን አልለቅም ማለታቸውን የመረጃ ምንጮች እየገለጹ ነው።
news-53974986
https://www.bbc.com/amharic/news-53974986
ፈረንሳይ፡ እንደራሴውን 'ባሪያ' አድርጎ የሳለው ጋዜጣ ትችት ገጥሞታል
አንድ ቀኝ ዘመም የፈረንሳይ ጋዜጣ የሕዝብ እንደራሴዋን 'ባሪያ' አድርጎ በመሳሉ ከወዲህም ከወዲያም ነቀፋ እያስተናገደ ነው።
ቫለር አክችዌል የተሰኘው ጋዜጣ ሶሻሊስት የሆኑትን የፈረንሳይ እንደራሴ ዳኒዬሌ ኦቦኖ ልክ እንደ ባሪያ አንገታቸው ላይ የብረት ሰንሰለት የታሰረባቸው በማስመሰል ነው ያተመው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዦ ካስቴክስ 'በጣም ቀፋፊ እትም' ሲሉ የጋዜጣውን ሥራ ኮንነዋል። ጋዜጣው እትሙ ላይ ለለጠፈው ስዕል ይቅርታ ቢጠይቅም በይዘቱ እንደማይደራደር አስታውቋል። ጋቦን የተወለዱት እንደራሴ ኦቦኖ የፈረንሳይ ግራ ዘመም ፓርቲ ፍራንስ አንባውድ ብሔራዊ ጉባዔ ምክትል ኃላፊ ሲሆኑ ፓሪስን ወክለው ነው በሕዝብ እንደራሴነት የሚያገለግሉት። እንደራሴዋ "ቀኝ ዘመሞች - እኩይ፣ የዘቀጠና ጨካኝ ተግባር" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል። "ይህ ምስል ለኔም ሆነ ለአያት ቅድመ አያቶቼ፤ ለቤተሰቤና ለማራምደው ፖለቲካ ስድብ ነው" ያሉት እንደራሴዋ "ከመቼውም ጊዜ በላይ ዘረኝነትን ለመዋጋት ቆርጨ ተነስቻለሁ" ሲሉ አክለዋል። ኦቦኖ፤ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ታዋቂውን የፈረንሳይ አብዮት መፈክር ተጠቅመው "ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለአብሮነት" መታገላቸውን እንደማያቆሙ አስታውቀዋል። የፈረንሳይ ፕሬዝደንታዊ ፅ/ቤት ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማክሮን ለእንደራሴዋ ደውለው "ለየትኛውም ዓይነት ዘረኝነት ቦታ የለኝም" ሲሉ ነግረዋቸዋል ብሏል። የቀኝ ዘመሙ ፓርቲ፤ ናሽናል ራሊ ነባር አባል የሆኑት ዋሌራንድ ደ ሴይንት-ጀስት፤ እትሙ ለአንደራሴዋ ምንም ዓይነት ክብር አላሳየም በማለት የጋዜጣውን ድርጊት ኮንነዋል። አሜሪካ ውስጥ ጥቁሩ ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ የተቀጣጠለው የፀረ-ዘረኝነት ዘመቻ ፈረንሳይ ደርሶ ባለፈው ሰኔና ሐምሌ በርካታ ተቃውሞዎች ሲደረጉ እንደነበር ይታወሳል። ተቃዋሚዎች የቅኝ ግዛት ዘመን የዘረኝነት ትርክት አሁንም ይስተዋላል ሲሉ ይወቅሳሉ። ፕሬዝደንት ማክሮን ፈረንሳይ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት ለማስወገድ መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ ቢናገሩም ሃገራቸው የቅኝ ገዥዎችን ኃውልት እንደማታፈርስ አስረግጠዋል። ዩናይትድ ስቴትስና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የበርካታ ሰዎች ኃውልት መፍረሱና የሌሎችም እንዲፈርስ ጥያቄ መቅረቡ አይዘነጋም። ጋዜጣው በ18ኛው ክፍለ ዘመን ይፈፀመው ከነበረው ባርነት ጋር በተያያዘ ለሠራው ዘገባ ነው የእንደራሴዋን ፎቶ የተጠቀመው።
41968943
https://www.bbc.com/amharic/41968943
በኢትዮጵያ ብሔር ተኮር ግጭቶችና ጥቃቶች አሳሳቢ ሆነዋል
በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ለዜጎች ሞት እና መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ብሔር ተኮር ጥቃቶች እና ግጭቶች አፋጣኝ የፖሊሲ እና የአፈጻጸም መፍትሄ ያሻቸዋል ሲል የመብት ተሟጋቹ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ገልጿል።
በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብቶችን መከበር ለማረጋገጥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስልጣን ተሰጥቶት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ብሄር ተኮር ግጭቶችን ለማጣራት ዝግጅቴን እያጠናቀቅኩ ነው ብሏል። ኮሚሽኑ ከድንበር ይገባኛል ጋር በተገናኘ በተለይም በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት መንስዔ እንዲሁም የደረሱ ጉዳቶችን በማጣራት ላይ መሆኑንም ለቢቢሲ አስረድቷል። ሰመጉ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ጌዲኦ ዞን፤ እንዲሁም በሐረሪ ክልል ሐረር ከተማ ባለፈው ዓመት ተፈፅመዋል ያላቸውን የመብት ጥሰቶች አስመልክቶ በቅርቡ ባወጣው ልዩ መግለጫ ለብሔር ተኮር ጥቃቶች እና ግጭቶች በቂ ትኩረት አልተሰጠም፤ አስፈላጊው የህግ እና ተቋማዊ ስራም አልተከወነም የሚሉ ነቀፌታዎችን ማቅረቡ ይታወሳል። የጉባዔው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብፅዐተ ተረፈ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መግለጫው ሲወጣ በአንድ በኩል በተጠቀሱት ስፍራዎች ላይ የተነሱት ችግሮች በራሳቸው መፍትሄ የሚያሻቸው መሆኑን በመጠቆም፤ በሌላ በኩል ደግሞ እየተባባሱ የመጡትን ግጭቶች እና ጥቃቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አፅንዖት መስጠትን ታሳቢ አድርጓል። "ሁለት ወገኖች እኩል የሚሳተፉባቸው በድንበር ይገባኛል፣ በግጦሽ መሬት እና በመሳሰሉት ምክንያቶች የሚቀሰቀሱ ግጭቶች አሉ፤ በፊትም ነበሩ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ራሳቸውን የሚከላከሉበት ምንም ዓይነት ፖለቲካዊም ሆነ ሌላ አቋም የሌላቸው አናሳ ብሔሮች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መበራከት ይዘዋል" ብለዋል አቶ ብፅዓተ። በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል ድንበር አቅራቢያ ተፈናቅለው በሐማሬሳ መጠለያ ውስጥ የነበሩ (ከአንድ ወር በፊት የተነሳ ፎቶ) ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተነሱ ግጭቶች በርካቶች ሕይወታቸውን ባጡበትና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከሶማሌ ክልል በተፈናቀሉ በጥቂት ጊዜ ውስጥ፤ በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን እንዲሁም በቤንሻንጉል ክልል ካማሺ ዞን የተከሰቱ ግጭቶች እና የተፈፀሙ ጥቃቶች ለሞት እና ለመፈናቀል ምክንያት መሆናቸው ይታወሳል። "ሕይወቴን ብቻ ይዤ መውጣት ነው የምፈልገው" ከዚህም በተጨማሪ በወርሃ መስከረም 2009 ዓ.ም በጌዲኦ ዞን እንዲሁም በሰኔ ወር 2009 ዓ.ም በሐረር ከተማ ብሔር ላይ ያነጣጠሩ የመብት ረገጣዎች ተፈፅመዋል የሚለው የሰመጉ መግለጫ፤ የብሔር ተኮር ግጭቶች እና ጥቃቶች "እየከፉና በአደገኛ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ ለመገኘታቸው አንድ ማሳያ ሊሆን ይችላል" ይላል። በኢሰመኮ የሰብዓዊ መብቶች ምርመራ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርሃኑ አባዲ በበኩላቸው ከተለያዩ ስፍራዎች የመጡ ጥቆማዎችን በመከተል ብሔር ተኮር ግጭቶችን የሚያጣራ ቡድን በቅርቡ ይንቀሳቀሳል ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል፤ ቡድኑ ከሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች መካከል የኦሮሚያ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል እንደሚገኙባቸውም ጨምረው ገልፀዋል። አቶ ብርሃኑ "ከድንበር ጥያቄ ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የደረሰውን ችግር የሚያጣራ ቡድን ግን ወደቦታዎች አምርቶ ስራውን በማከናወን ላይ ይገኛል" ብለዋል። የሰመጉ መግለጫ በቀጥታ ተጎጅዎችን እና የተጎጂ ቤተሰቦች በማነጋገር፤ የምስክሮችን ቃል በመቀበል እና ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉትን አካባቢዎች በአካል በመጎብኘት ባደረግኩት ማጣራት በመስከረም ወር 2009 ዓ.ም በደረሰ ብሔር ተኮር ጥቃት የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን ደርሼበታለሁ ይላል። መግለጫው ጨምሮም በ2009 ዓ.ም የሰኔ ወር መገባደጃ ላይ የአፍረን ቀሎ የባህልና የታሪክ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ መጣል ጋር ተያይዞ ብሔር ላይ ያነጣጣረ ማዋከብ፣ እስራት እና ድብደባ ተፈፅሟል ይላል። መንግስት ለመሰል ግጭቶች እና ጥቃቶች መንስዔ የሆኑት "ጥቅማቸው የተነካባቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች" እና "የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች" ናቸው ሲል ይወነጅላል። በቅርቡም የብሔር ይዘት ያላቸውን ግጭቶችን የማባባስ ሚና ያላቸው የአመራር አባላት እንዳሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የተናገሩ ሲሆን፤ እነዚህ አባላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ መናገራቸው ይታወሳል። "በድንበር ይገባኛል ሰበብ የከፉ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት መንግስት ከሕብረተሰቡ ጋርም በመመካከር አስቸኳይ መፍትሄ ይስጥ" በሚል ርዕስ ኢሰመጉ ባለፈው ጳጉሜ መግለጫ አውጥቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ መንግሥት ለጥቃት እና ግጭቶቹ የሚሰጠውን ምላሽ "የዘገየ" ከመሆኑም ባሻገር ችግሮቹን ከስር መርምሮ ሲቀርፍ አይስተዋልም ሲል ይወቅሳል። እንደ አምቦ ዩኒቨርስቲ መምህርና ጦማሪው ስዩም ተሾመ ግን የጥቃቶቹ እና ግጭቶቹ መሰረታዊ መነሻ ላለፈው ሩብ ምዕተ ዓመት ስራ ላይ ካለው ብሔር ተኮር የፌዴራሊዝም ስርዓት የሚዘል አይደለም። መንግሥት ላይ የሚቀርቡ ተቃውሞዎች፣ ሕዝባዊ ሰልፎች እና አድማዎች ብሔር ተኮር ብሔርተኝነት ካልተጨመረባቸው በስተቀር ወደ ብሔር ግጭትነት አይቀየሩም ሲል የሚከራከረው ስዩም "የብሔር ተኮር ስርዓት መጥፎ መልክ የሚገለጠው የብሔር ልዩነቶችን በሚያገን ስርዓት ያለመተማመን የተዘራበት ማሕበረሰብ በፖለቲካዊ ያለመረጋጋት ሲናጥ ነው" ይላል። "ያኔ የዘር ግጭት ተባብሶ የዘር ማጥፋት ሊከሰት ይችላል" ሲል ስዩም ለቢቢሲ ያስረዳል። ባለፉት 26 ዓመታት ኢሰመጉ ካወጣቸው ወደ አንድ መቶ ሰማንያ የሚጠጉ በመብት ጥሰት ዙርያ የሚያጠነጥኑ መግለጫዎች መካከል ከአርባ በላይ የሚሆኑት የብሔር ጥቃቶችን ወይንም የብሔር ተኮር ግጭቶችን ተከትሎ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን የሚመለከቱ ናቸው። አቶ ብፅዓተ የግጭቶቹና ጥቃቶቹ መደጋገም በተመለከተ "አንድም ትምህርት እንዳልተወሰደ ያሳያል፤ ከዚህ በባሰም የታጠቁ አካላት ጭምር ወዲያና ወዲህ ተቧድነው ወገኔ ከሚሉት ጋር አብረው በግጭት እና ጥቃቶች መሳተፋቸው የችግሩን መጠንከር ያሳያል" ሲሉ ይደመድማሉ።
news-55017452
https://www.bbc.com/amharic/news-55017452
አፍጋኒስታን ፡ "የአውስትራሊያ ወታደሮች 'ደም እንዲለምዱ' የአፍጋኒስታን እስረኞችን እንዲገድሉ ይደረግ ነበር" ሪፖርት
የአውስትራሊያ መከላከያ አካል የነበረው ልዩ ኃይል አፍጋኒስታን በነበረ ጊዜ ወታደሮቹ ደም እንዲለምዱ የአፍጋኒስታን እስረኞችን ተኩሰው እንዲገድሉ ያበረታታ እንደነበር አንድ ሪፖርት አጋለጠ።
በአውስትራሊያ መንግሥት ተቀባይነት ባገኘው በዚህ ሪፖርት ላይ ወታደሮች 39 አፍጋኒስታዊያንን በዚሁ መንገድ እንደገደሉ ምርመራው አመልክቷል። አፍጋኒስታን ሰላም ለማስከበር ዘምቶ የነበረው የአውስትራሊያ መከላከያ ሠራዊት ይህንን የጦር ወንጀል መፈጸሙን አስረግጦ ለመናገር ላለፉት አራት ወራት ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቷል። የምርመራ ውጤቱም በመላው ዓለም በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። በትንሹ 19 የሚሆኑ የቀድሞና የአሁን ወታደሮች በዚህ የጦር ወንጀል በቀጥታ ሊጠየቁ ይችላሉ ተብሏል። ይህ አሰቃቂ "የጦር ወንጀል" የተፈጸመው በጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ2009 እስከ 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ነው። በግፍ የተገደሉት ደግሞ የአፍጋን ገበሬዎች፣ ንጹሐንና እና አስረኞች ናቸው። ይህ ዓመታትን የወሰደው የምርመራ ሪፖርትን የመሩትና ይፋ ያደረጉት ሜጀር ጄኔራል ጀስቲስ ፖል እዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ጉዳዩ ጋር በቀጥታና በተዘዋዋሪ ግንኙነት የነበራቸው 400 ሰዎችን ቃለ ምልልስ አድርገዋል። በመጨረሻ ያገኙት የምርመራ ውጤታቸው እንደሚያሳየው ከሆነ ጦሩ አፍጋኒስታን በቆየባቸው ወቅት ልምድ የሌላቸው ወጣት ወታደሮች ደም እንዲለምዱና ሰው የመግደል ድፍረትና ወኔ እንዲያገኙ ለማስቻል በእስር ላይ የነበሩ አፍጋኒስታዊያንን ተኩሰው እንዲገድሉ ይበረታቱ ነበር። ይህን ድርጊትም በተደጋጋሚ አድርገውታል። ከዚህ በተጨማሪ በግፍ የተገደሉ አፍጋኒስታዊያን በተለይም ገበሬዎች በውጊያ የሞቱ ለማስመሰል ሲባልም የጦር መሣሪያ የሚከማቹበትና የጦር አውድማ ላይ ወስዶ ሬሳቸውን የመጣል ተግባር ይፈጸም ነበር ይላል ሪፖርቱ። ሰላማዊ በሆኑ ዜጎች ላይም ሰቅጣጭ የሚባል ግፍ ይፈጸም እንደነበር ተብራርቷል በሪፖርቱ። በጥናቱ የመጀመርያ ምዕራፍ ተሳትፎ የነበራቸው ሳማንታ ክሮምቮትስ ለቢቢሲ ስለተፈጸመው ግፍ ሲናገሩ "ድርጊቱ ይፈጸም የነበረው በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ ነበር" ብለዋል። በዚህ ድርጊት ላይ ምናልባትም 25 የሚሆኑ የአውስትራሊያ ልዩ ኃይል አባላት በቀጥታ ተሳትፈውበታል። የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን ባለፈው ሳምንት ለዜጎቻቸው "አስቸጋሪና ለማመን የሚከብድ ሪፖርት" በዚህ ሳምንት ሊሰሙ እንደሚችሉ ከወዲሁ ጥቆማ ሰጥተው ነበር። ሪፖርቱ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ጠ/ሚኒስትር ሞሪሰን ለአፍጋኑ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ደውለው ይህ ሪፖርት ስላጋለጠው ሀቅና ስለተፈጸመው አሳፋሪ ተግባር "ጥልቅ ሐዘን" እንደተሰማቸው በስልክ ነግረዋቸዋል። አፍጋኒስታን በሪፖርቱ ላይ እስካሁን ያለችው ነገር የለም። ሞሪሰን ጥፋተኞቹ ላይ ክስ የሚመሰረት ልዩ መርማሪ ቡድን እንደሚቋቋም ይፋ አድርገዋል። ሆኖም ጥፋተኞቹ የእጃቸውን እስኪያገኙ ዓመታት ሊወስድ ይችላል ብለዋል የአውስትራሊያ ሚዲያዎች። የፍርድ ሒደቱም ቢሆን ሌላ በርካታ ዓመታትን እንደሚወስድ ይጠበቃል። አውስትራሊያ በአሁኑ ሰዓት 400 የሚሆኑ ወታደሮቿ ከአሜሪካን ወታደሮች ጋር በመሆን በአፍጋኒስታን የሰላም ማስከበር ውስጥ ይገኛሉ። በዚህ ዓመት መጀመርያ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በአፍጋኒስታን የጦር ወንጀል ተፈጽሞ ከሆነ በሚል አሜሪካንና ሌሎች ጦራቸውን ያስገቡ አገራት ላይ ምርመራ መጀመሩ ይታወሳል።
56170354
https://www.bbc.com/amharic/56170354
ታይገር ዉድስ ባጋጠመው የመኪና አደጋ እግሮቹ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል ተባለ
እውቁ የጎልፍ ስፖርት ተጫዋጭ ታይገር ዉድስ በሎስ አንጀለስ የመኪና አደጋ አጋጥሞት ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።
ውድስ "እግሮቹ ላይ ብዙ ጉዳት ስለደረሰበት" የቀዶ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል ተብሏል።፡ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ እንዳስታወቀው ታይገር ዉድስ የነበረበት ተሽከርካሪው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። የ15 ጊዜ የጎልፍ ሻምፒዮኑ እና የ45 ዓመቱ ዉድስ አደጋ ከደረሰበት መኪና በእሳት አደጋ ሰራተኞች እና በሕኪሞች ርብርብ ሊወጣ ችሏል። ፖሊስ እንዳለው በአደጋው ስፍራ ዉድስ "እራሱን ያውቅ" ነበር ብሏል። አሜሪካዊው በአምቡላንስ ዌስት ካርሰን ካሊፎርኒያ ወደሚገኘው ሃርበር-ዩሲኤልኤ የህክምና ማዕከል ተወሰዷል። የዉድስ ወኪል ማርክ ስቲንበርግ ማክሰኞ ዕለት አደጋውን መድረሱን አረጋግጦ ቀዶ ጥገና እየተደረገለት እና ጉዳቱን በተመለከተ ዝርዝሩን ገልጿል። የሎስ አንጀለስ የእሳት አደጋ መከላከያ ክፍል ኃላፊ ዳሪል ኦስቢ እንዳሉት "በሁለቱም እግሮች ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ተረድቻለሁ። ህይወቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ጉዳቶች አይደሉም" ብለዋል። ቪላኑቫ እንዳሉት የውድስ መኪና "የመንገድ ማካፈያውን አቋርጦ ብዙ መቶ ሜትሮች ርቆ ሄዷል። ይህም ከመደበኛው ፍጥነት በላይ ይጓዝ እንደነበር ያመላክታል" ብለዋል። አክለውም "አካባቢው ቁልቁል፣ ተዳፋት እና ጠመዝማዛ ስለሆነ ተደጋጋሚ አደጋዎች ይደጋገሙበታል" ሲሉ ገልጸዋል። ታይገር ዉድስ ያሽከረክራት የነበረችው መኪና ዉድስ ያሽከረክረው የነበረው ቅንጡ መኪና የመንገድ ጠርዝ እና ዛፍ መግጨቱን እና ብዙ ጊዜ መገልበጡን ተናግረዋል። የሎስ አንጀለስ ፖሊስ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ካርሎስ ጎንዛሌዝ ቀድመው በቦታው ተገኝተው እንደነበር እና ዉድስ የደህንነት ቀበቶውን አጥልቆ እንደነበረና ስሙን ሲናገር "ረጋ ያለ እና ጥሩ ሁኔታ ላይ" ነበር ብለዋል። አክለውም ዉድስ ከዚህ አደጋ በሕይወት ለመውጣት መቻሉ በጣም ዕድለኛ ነው ብለዋል። በርካቶች ታይገር ዉድስ በፍጥነት ከደረሰበት ጉዳት እንዲያገግም ምኞታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ዉድስ በጎርጎሮሳዊያኑ በ 2009 የመኪና አደጋ የደረሰበት ሲሆን በትዳሩ ላይ ታማኝ አለመሆኑን በማመኑ ትዳሩ ፈርሷል። ከጎልፍ ውድድር እረፍት ቢወስድም ብዙም ሳይቆይ ወደ ስፖርቱ ተመልሷል። በ2013 ያስመዘገባቸው አምስት ድሎችን ተከትሎም ዉድስ በቀጣዮቹ አራት ዓመታት ውስጥ በጀርባ ህመም እና በከባድ ቀዶ ጥገናዎች ምክንያት 24 ውድድሮች ላይ ብቻ ተሳትፏል። ዉድስ እአአ በ2017 ተሽከርካሪው ውስጥ ተኝቶ የተገኘ ሲሆን በዕጽ ተፅዕኖ ስር ሆኖ በማሽከርከር ተጠርጥሮ ነበር። በኋላም በግዴለሽነት ማሽከርከር ወንጀል ጥፋተኛ ተባሏል። ዉድስ አምስተኛ የጀርባ ቀዶ ጥገናውን ተከትሎ በሚያዝያ ወር በሚካሄደው የማስተርስ ውድድር ለመሳተፍ ተስፋ እንዳደረገ ተናግሮ ነበር። በ2019 በጎልፍ የዓለም ደረጃ ስድስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ዉድስ አሁን ግን 50ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
51922334
https://www.bbc.com/amharic/51922334
መዓዛ መላኩ፤ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ስለኮሮናቫይረስ መረጃ የምታቀብለዋ በጎ ፍቃደኛ
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ሕብረተሰቡን ለመርዳት በበጎ ፈቃደኝነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው።
ከእነዚህም መካከል ሰለ ኮሮናቫይረሰ ጠቃሚ መረጃዎችን መስማት ለተሳናቸው ዜጎች በፌስቡክ አማካኝነት በምልክት ቋንቋ የምታሰራጨው መዓዛ መላኩ ትገኝበታለች። ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች እንደዚህ ያሉ ወሳኝ እና ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያገኙበት ዕድል በጣም ጠባብ እንደሆነ መዓዛ ትናገራለች። • አሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ጀመረች ለዚህም "ኃላፊነቴን መወጣት ስላለብኝ ይህን ተግባር ለመፈጸም ተነሳሳሁኝ" ስትል መዓዛ ለቢቢሲ ተናግራለች። መዓዛ በፌስቡክ ገጿ ቫይረሱን በተመለከተ ከመንግሥት እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎችን መስማት ለተሳናቸው ዜጎች በምልክት ቋንቋ እያስተላለፈች ትገኛለች። በአገሪቱ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች አጥጋቢ መረጃ መስጠት እስኪጀምሩ ድረስ ፌስቡክን በመጠቀም መልዕክት የማድረስ ጥረቴን እቀጥላለሁ ብላለች። መዓዛ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምልክት ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪዋን፤ ሁለተኛ ዲግሪዋን ደግሞ ከኦስሎ ዩኒቨርሲቲ በልዩ ፍላጎት ትምህርት አጠናቃለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትናንትናው ዕለት አምስት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው መገኘታቸውን ተከትሎ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትልልቅ ስብሰባዎች ለቀጣዮቹ 15 ቀናት እንደሚዘጉ አስታውቀዋል። • በኮሮናቫይረስ የተያዙት ቶም ሃንክስና ሪታ ዊልሰን ከሆስፒታል ወጡ • አምቡላንስ ሰብሮ ያመለጠው ከቫይረሱ ነጻ ሆኖ ተገኘ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደ አስፈላጊነቱ በያሉበት ዩኒቨርሲቲ ክትትል የሚደረግላቸው መሆኑን ገልፀው እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ አነስተኛ ስብሰባዎችም በጤና ሚኒስቴር እውቅና ሊካሄዱ እንደሚችሉም አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ወቅት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ እንደ አልኮልና ሳሙና ያሉ በስፋት የሚሰራጩም ይሆናል ብለዋል። እህንን ተከትሎም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አንበሳ እና ሸገር አውቶብሶች ለተሳፋሪዎቻቸው የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር እንደሚያቀርቡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) አስታወቀዋል። ተሳፋሪዎች ወደ አውቶብሶቹ ሲገቡ እጃቸውን በሳኒታይዘር እንዲያጸዱ ይሆናል ያሉት ምክትል ከንቲባው ፤ የአውቶብሶቹ አሽከርካሪዎችም የእጅ ጓንት ያደርጋሉ ብለዋል።
49862566
https://www.bbc.com/amharic/49862566
በዶሃ የሴቶች ማራቶን 28 ሯጮች አቋርጠው ወጡ
ትናንት እኩለ ለሊት በኳታር፣ ዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካሄደው የማራቶን ሩጫ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ማቋረጣቸው ተሰማ።
በመካከል አቋርጠው ከወጡት መካከል ኢትዮጵያውያኖች ይገኙበታል ሩጫውን በበላይነት ኬኒያዊቷ ሩት ቼፔንጌቲች ያሸነፈች ሲሆን፤ ከ68 ተወዳዳሪዎች 28ቱ በሙቀቱ ከባድነት ምክንያት አቋርጠው መውጣታቸው ተዘግቧል። እኩለ ለሊት ላይ የተደረገውን ይህ የሴቶች የማራቶን ውድድር ካቋረጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋ አንዷ ነች። የውድድሩ አዘጋጆች ከዋናው ውድድር ቀድመው የማራቶን ውድድሩ እንዲካሄድ ያደረጉት የአየር ጠባዩ ለማራቶን ምቹ ላይሆን ይችላል በሚል እንደሆነ ተነግሯል። • በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ • ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ስለአባይ አጠቃቀም ምላሽ ሰጡ • ፌስቡክ 'የላይክ' ቁጥርን ማሳየት ሊያቆም ነው የሴቶች ማራቶን ሲካሄድ፤ የሙቀት መጠኑ 32 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ወበቁ ደግሞ ከ70 በመቶ በላይ ነበር ተብሏል። የኢትዮጵያ ማራቶን አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ ሮባ፤ የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊዋ ሩቲ ነጋን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተወዳዳሪዎች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል። "በአገራችን ማራቶንን በዚህ የአየር ጠባይ መሮጥ የሚታሰብ አይደለም" ካሉ በኋላ "ምን ያህሎቹ እንደሚጨርሱ ለማየት ጓጉቻለሁ" ብለዋል። የ23 ዓመቷ ቼፔንጌቲች ሩጫውን በ2 ሰዓት ከ32 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ በማጠናቀቅ ወርቅ ስታገኝ፤ የባህሬን ዜግነት ያላት ሯጭ ሁለተኛ፣ ናሚቢያዊቷ ሯጭ ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል። ቼፔንጌቲች፤ "በእንዲህ አይነት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አሸንፋለሁ ብዬ አልጠበቅኩም" በማለት ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ተናግራለች። የብሪታኒያ ፈጣን የማራቶን ሯጭ ቻርሎቴ ፑርዱኤ እና ሌሎች ታዋቂ ሯጮችም አቋርጠው ከወጡት መካከል ናቸው።
51956835
https://www.bbc.com/amharic/51956835
በኮሮናቫይረስ ስጋት ሰዎች እቃዎችን በገፍ እየገዙ እንዳያጠራቅሙ ምን ይደረግ?.
በተለያዩ አገራት የኮሮናቫይረስ ሕሙማን ሪፖርት መደረግን ተከትሎ የድንጋጤ የገፍ ግዥ (panic buying) በስፋት ተስተውሏል።
ይህንን የድንጋጤ የጥድፊያ ገበያ መቆጣጠር ይቻላል? በሱፐር ማርኬቶች፣ በሰፈር መደብሮች እና ማከፋፈያዎች የተወሰኑ አስፈላጊ የሆኑ እንደ ምግብ፣ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙናና ሶፍት እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ እቃዎችን በገፍ ገዝተው ሌሎች ሰዎች ጥቂት እንኳ እንዳያገኙ ሆኗል። ባለፈው ሳምንት አርብ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በኢትዮጵያም በኬንያም መገኘታቸው መገለፁን ተከትሎ አዲስ አበባ እና ናይሮቢ ላይም በየሱፐርማርኬቶች የገፍ ሸመታ በከፍተኛ ሁኔታ ተስተውሏል። • ለሶስት ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው 61 ዓመት የኖሩት ዶክተር ሃምሊን ካትሪን ማን ናቸው? • የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ቅድመ ዝግጁነትና ምላሽ ቡድን ምን እየሰራ ነው? • በጣሊያን በኮሮናቫይረስ በአንድ ቀን ብቻ 475 ሰዎች ሞቱ ይህ ከጥቂት ቀናት በፊት እንደ አውስትራሊያ፣ አሜሪካ፣ ደቡብ አፍሪካና ጃፓን ባሉ አገራትም ታይቷል። ዜናው በተሰማ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ አዲስ አበባ ውስጥ ዲቶል ሳሙና፣ አልኮል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲሁም ሳኒታይዘር ማግኘት የማይታሰብ ሆኗል። ፓስታ፣ ሩዝ፣ ረዥም ቀን ያላቸው ወተቶች የህመም ማስታገሻዎችን ጭምር ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ ነበር። በማግስቱም የተለያዩ የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች፣ የህፃናት የታሸጉ ምግቦች በሱፐርማርኬት መደርደሪያዎች ላይ አልነበሩም። በሌላ በኩል በቀላሉ በወፍጮ ቤቶች ጤፍ ማግኘት አለመቻላቸውን የሚገልፁም አልታጡም። ሰዎች ይኼና ያኛው ሳይሉና ምን ያህል ያስፈልገኛል ሳይሉ ያገኙትን ነገር ሁሉ እያፈሱ ገዝተዋል። ይህን የሚያሳዩ ፎቶዎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎችም በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭተዋል። ሰዎች መሰረታዊ ፍጆታዎችን በገፍ እየገዙ በመሆናቸው እጥረት እንዳይፈጠር ሱፐር ማርኬቶች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? በእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዜጎቻቸው እቃዎችን ሲሸምቱ ምክንያታዊ እንዲሆኑ ጠይቀዋል። ሱፐርማርኬቶችም ደንበኞቻቸውን ተመሳሳይ ጥያቄ ጠይቀዋል። በእንግሊዝ ታዋቂ ሱፐርማርኬቶች ሰዎች ከአንድ ምርት ምን ያህል መግዛት እንደሚችሉ ገደብ ለማስቀመጥ ተገድደዋል። በኢንተርኔት ገበያም ቢሆን ሰዎች የሚገዙት የእቃ ብዛት ላይ ገደብ ይጥላሉ ሱፐርማርኬቶቹ። የድንጋጤ የገፍ ግዥ በትክክልም እጥረት በሌለበት የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች እጥረት ከማስከተሉ ባሻገር ለግዥ የሚደረገው ያልተገባ ግርግርና መገፋፋት ለቫይረሱ ስርጭት መንገድ ይከፍታል። በትናንትናው እለት አዲስ አበባ ፋርማሲዎች ደጃፍ ላይ ሳኒታይዘር ለመግዛት የነበረው ግርግርም የዚሁ ማሳያ ነው። በዚህ ረገድ በእንግሊዝ ያሉ ሱፐርማርኬቶች ደንበኞች በሱፐርማርከኬቶች እንቅስቃሴአቸው በምን ያህል ርቀት መሆን አለበት የሚሉና ሌሎችንም ጉዳዮች በማስመልከት መመሪያ አውጥተዋል። ለምሳሌ በእድሜ የገፉ እንዲሁም አካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ለብቻቸው መስተናገድ የሚችሉበት የተለየ ሰዓትንም ጭምር ይፋ አድርገዋል ሱፐርማርኬቶቹ። የሰዎችን ማህበራዊ መስተጋብር ለመቀነስ በማሰብ እዚያው ሱፐርማርኬት ውስጥ የሚገኙ ካፍቴሪያዎችንም ዘግተዋል። በሌላ በኩል በእንግሊዝ መንግሥት በበኩሉ ዜጎች እቃዎችን እየገዙ የሚያጠራቅሙበት ምንም ምክንያት እንደሌለ ለዜጎቹ ገልጿል።
48782466
https://www.bbc.com/amharic/48782466
በቤንሻንጉል ክልል በሽፍቶች በደረሰ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ የታጠቁ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ ከ30 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲል ሀሰን ለቢቢሲ ገለፁ።
ጥቃቱ የደረሰው እሁድ ለሰኞ አጥቢያ 11 ሰዓት ላይ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ በጥቃቱ ወደ 16 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልፀው ወደ 66 ቤቶች በቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተናግረዋል። • "ከጄ/ል አሳምነው ጋ በምንም ጉዳይ ያወራሁበት አጋጣሚ የለም" እስክንድር ነጋ • የጋምቢያ መንግሥት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን ከዚህ በፊት በአማራ ክልል የሚኖሩ የጉሙዝ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ያኔም ለቁጥር መግለፅ ከባድ ያሉት ሰው መሞቱን ተናግረዋል። ጥቃት አድራሾቹ 'ከአማራ ክልል መምጣታቸውን' የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በቁጥጥር የዋለ መሳሪያና ሰው ቢኖርም ምን ያህል እንደሆነ ግን የተጠናከረ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል። በስፍራው አሁንም ስጋት መኖሩን የተናገሩት አቶ አሻድሊ ሀሰን ጉዳዩን ለመፍታት ከመከላከያና ከፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር እየሰሩ መሆኑን ጨምረው አስረድተዋል። በጉዳቱ የቆሰሉ ሰዎች በፓዊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው ገልፀዋል።
news-56495523
https://www.bbc.com/amharic/news-56495523
የግጭቱ መነሻ "ጽንፈኝነት እና የፖለቲካ አሻጥር ነው"- የኦሮሚያ ብልጽግና
የገዢው ፓርቲ አንድ አካል የሆነው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተከሰተው ግጭት መነሻው "ጽንፈኝነት እና የፖለቲካ አሻጥር ነው" አለ።
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ሰኞ ማታ ባወጣው መግለጫ በአካባቢው ከአርብ ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት በንፁሃን ዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲል አስታውቋል። የአማራ ክልል መስተዳደር ክስተቱን አስመልክቶ ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ የሰዎች ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን ጠቁሞ "በንጹሐን ላይ የተፈፀሙው ይህ ጥቃት በፍጹም ተቀባይነት የሌለው አደገኛና ከባድ ወንጀል ነው" ብሎ ነበር። የአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬና በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ አካባቢዎች በንጹሐን ላይ የተፈጸመው ጥቃት አደገኛና ከባድ ወንጀል ነው ማለቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ብልጽግና በመግለጫው ላይ "የአማራ ክልል መንግሥት ታጣቂዎች፤ ያልታጠቁ ሰዎችን፣ እርቅ ሲሰብኩ የነበሩ ሽማግሌዎችን ሴቶችንና ሕጻናትን እንዲሁም ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየሄዱ የነበሩ ንፁሃንን በመግደል የወሎ ኦሮሞ ላይ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል" ሲል ወንጅሏል። ፓርቲው አክሎም ጥፋተኞቹ "ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን፤ ጉዳዩንም እንከታተላለን" ሲል አስታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የኦሮሚያ የፀጥታና አስተዳደር ኃላፊ አቶ ጅብሪል መሐመድ በበኩላቸው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተፈጠረው "ትክክል ነው ብለን አናምን" ሲሉ ተናግረዋል። የቢሮው ኃላፊ ለቢቢሲ "የግጭቱ መነሻ ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨት ሥልጣን ለመያዝ የሚደረግ ጥረት ነው" ብለዋል። ጉዳዩ ምንም እንኳ በአማራ ክልል ውስጥ የተፈፀመ ቢሆንም "ብሔር ተኮር ስለሆነ እኛንም ይመለከተናል" ሲሉ ተናግረዋል። "የጋራ አገር ነው ያለን፣ ሕግ ተጥሶ ንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ዝም ብለን ልንምለከት አንችልም፤ እናም ጉዳዩ ላይ እየሰሩ ካሉ አካላት ጋር በመሆን እየተከታተልነው ነው" ሲሉም አክለዋል። በቅድሚያ ግጭቱ መቆም አለበት ያሉት አቶ ጅብሪል "ከዚያ በመቀጠል ደግሞ ምንጩ ተጣርቶ ማስተካከያ መደረግ አለበት። የአማራ ክልል መንግሥትም ይህንን ያደርጋል ብዬ አምናለሁ" ብለዋል። የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ላይ ለግጭቱ መነሻ በማለት ስሙን ያልገለፀው አንድን ፓርቲ "ጽንፈኛ" በማለት ወነጀለ ሲሆን፣ "የክልሉ አንዳንድ የመንግሥት ኃላፊዎችም ለሥልጣን ብለው የሰሩት አሻጥር ነው" ሲልም አክሏል። በተጨማሪም በደረሰው ጉዳት ውስጥ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ፓርቲው አመልክቷል። የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በዚህ መግለጫው ላይ የግጭቱ መነሻ በኦሮሚያ ክልል ሁከት ለመቀስቀስ እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሞ ሕዝቦች መካከል ግጭት ማስነሳት እንደሆነ ይዘረዝራል። የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የአማራ መንግሥት ታጣቂዎች በንፁሃን ዜጎች ሕይወት እና ንብረት ላይ ያደረሱትን ጉዳት አምርሮ እንደሚያወግዝ አስታውቋል። በዚሁ መግለጫ ላይ በዞኑ ውስጥ ኦነግ ሸኔ እንደማይንቀሳቀስ ገልጾ፣ "በንፁሃን ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመደበቅ ሲባል ሕዝቡን በኦነግ ሸኔነት መፈረጅ ተቀባይነት የለውም" ብሏል። የፖለቲከኞች አሻጥር ምክንያት በሕዝቦች መካከል ያለ ወንድማማችነት እንዳይጎዳ እና የአገር አንድነት እንዳይፈርስ ዜጎችን በንቃት መጠበቅ አለባቸው ሲልም አሳስቧል። የተከሰተው ምንድን ነው? ባለፈው አርብ ምሽት ከሦስት ሰዓት ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፤ ኤፍራታና ግድም ወረዳና አጣዬ ከተማ ውስጥ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሰላማዊ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎችና የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። የኤፍራታና ግድም ወረዳ የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን አልታየ እስከ ቅዳሜ ረፋድ ድረስ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን መመልከታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚህም ከፍ እንደሚል እያመለከቱ ነው። የጅሌ ጥሙጋ አስተዳዳሪ አቶ ጀማል ሃሰን በበኩላቸው አጣዬና ጅሌ ጥሙጋ እንዲህ አይነት ግጭት ሲፈጠር የመጀመሪያ አይደለም በማለት ከባለፈው ግጭት በኋላ ሰላም ወርዶ እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን ግን የአንድ ግለሰብ መገደልን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት የክልሉ ልዩ ኃይል ለአንድ ወገን ሲያደላ ይታያል ሲሉ ይከሳሉ። የክልሉ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ለተፈጠረው ግጭት ምክንያቱ ሐሙስ መጋቢት 9/2013 ዓ.ም ምሽት "ጅሌ ጥሙጋ ውስጥ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ጠብ ምክንያት አንድ ሰው ህይወት መጥፋት" ለው ብሏል። ይህንንም ተከትሎ በአገር ሽማግሌዎችና በሐይማኖት አባቶች አማካይነት እርቅ ተፈጽሞ እንደነበር ጠቅሶ ነገር ግን "የኦነግ ቡድንና እሱን መሰል ተባባሪ የሆኑ አካላት እርቀ ሰላም ወርዶ መፍትሔ ያገኘውን ክስተት ምክንያት በማድረግ" ጥቃቱ መፈጸሙን ገልጿል። በዚህም ከአርብ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ጀምሮ "አርሶ አደር ይይዘዋል ተብሎ በማይጠበቅ ከባድና የቡድን መሣሪያ በመታገዝ የተደራጀና ብዛት ያለው የታጠቀ ኃይል በአጎራባቹ የሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ ከተማና አካባቢው ሰላማዊ ዜጎች ላይ ነውረኛ የሆነ ጥቃት ተፈጽሟል" ብሏል። የአማራ ክልል እሁድ እለት ባወጣው መግለጫ ላይ በክስተቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች መጠን አልገለጸም። በአማራ ክልል ውስጥ በሚገኙት በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬና በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ አካባቢዎች ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የተከሰተን ግድያ ተከትሎ ከአርብ በምሽት ጀምሮ ከባድ የተኩስ ድምጽ በአካባቢው መከሰቱንና በዚህም በርካታ ሰዎች እንደሞቱ ተነግሯል። ግጭቱ ለተከታታይ ቀናት የቆየ ሲሆን በሰው ላይ ከደረሰው ቁጥሩ እስካሁን በውል ካልታወቀው ጉዳት ባሻገር በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአካባቢው የአማራና የኦሮሞ ማኅበረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ግጭቶች አጋጥመው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
56977452
https://www.bbc.com/amharic/56977452
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ በቀጠናው ጉብኝት ማድረግ ጀመሩ
በቅርቡ የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ አድርጎ የሾማቸው ጄፈሪ ፌልትማን በቀጠናው ወዳሉ አገራት ጉዞ ማድረግ መጀመራቸውን የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።
ጄፍሪ ፌልትማን ልዩ መልዕከተኛው ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 5 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ወደ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ያቀናሉ ተብሏል። ልዩ መልዕክተኛው ጄፈሪ ፌልትማን በሚያደርጉት ጉዞ የየአገራቱን ባለስልጣናት ጨምሮ ከተባበሩት መንግሥት እና የአፍሪካ ሕብረት ተወካዮች ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪም ጄፈሪ ከፖለቲከኞች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር እንደሚገናኙ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ቢሮ አስታውቋል። የውጪ ጉዳይ ቢሮው በመግለጫው የልዩ መልዕክተኛው ጉዞ የጆ ባይደን አስተዳደር በአፍሪካ ቀንድ ያለው ፖለቲካ እና የደህንነት ችግር እንዲሁም የሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብሏል። ፌልትማን ማን ናቸው? ጄፍሪ ፌልትማን በሹመታቸው ወቅት በተለይ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ስላሉ ሁኔታዎች የተለየ ትኩረት እንደሚሰጡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አስታውቆ ነበር። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ዋና ጸሐፊዎች ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅትም በልዩ መልዕክተኝነት አገልግለዋል፤ በተጨማሪም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ፌልትማን በሊባኖስ፣ በኢራቅ፣ በእስራኤል፣ በቱኒዚያ፣ በሃንጋሪና በሄይቲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል። ቀጣዩ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ 'ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም' ጄፈሪ ፌልትማን ወደ ቀጠናው ጉዞ ከማድረጋቸው በፊት አምስት የአሜሪካ ሴናተሮች የተጻፈ ደብዳቤ ደርሷቸው ነበር። ለልዩ መልዕክተኛው በጻፉት ደብዳቤ ኢትዮጵያ ከሳምንታት በኋላ ስለምታደርገው አገራዊ ምርጫ፣ ስለትግራይ እና በሌሎች የአገሪቱ ስፍራዎች ስላሉ ግጭቶች ለተሿሚው ልዩ መልዕክተኛ መልዕከታቸውን አጋርተዋል። ሴናተሮቹ በደብዳቤያቸው አገራዊው ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ነጻ፣ ሚዛናዊ እና ግልጽ ሆኖ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አያሟላም ብለዋል።
news-51942027
https://www.bbc.com/amharic/news-51942027
ኮሮናቫይረስ፡ ስለወረርሽኙ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ ካሉ አገራት መካከል ከ150 በላይ በሚሆኑት ውስጥ መከሰቱ ተረጋግጧል። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች ስለበሽታው ለማወቅ የተለያዩ ጥያቄዎችን እየጠየቁ ነው።
እኛም ታዳሚዎቻችንን በኮሮናቫይረስ ዙሪያ ማወቅ ስለሚፈልጓቸው ነገሮች ጠይቀናቸው የብዙዎች ጥያቄ የሆኑትን መርጠን አቅርበናል። የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ቫይረሱን ለመካላከል ይጠቅማል? በሽታውን በመከላከል በኩል የፊት ጭንብል የሚኖረውን አስተዋጽኦን በተመለከተ በጣም ውስን መረጃ ብቻ ነው ያለው። • ሕንድ በስልክ ጥሪ ስለኮሮናቫይረስ መረጃ እየሰጠች ነው የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ወረርሽኙን ለመከላከል የግል ንጽህናን በአግባቡ መጠበቅ ወሳኝ ነው። በተለይ ደግሞ እጃችንን ወደ አፋችን፣ አፍንጫችንና ዓይናችን ከማስጠጋታችን በፊት በአግባቡ መታጠብ ከሁሉ የላቀ ውጤታማ መከላከያ ነው። ቫይረሱ በበር እጀታዎች አማካይነት ሊተላለፍ ይችላል፤ ለምን ያህልስ ጊዜ በእጀታዎች ላይ ሊቆይ ይችላል? ቫይረሱ ያለበት ሰው እጁ ላይ አስሎ ወይም አስነጥሶ የበር እጀታዎችንና ሌሎች ነገሮችን ከነካ ቫይረሱን ወደ ተነካው እቃ ሊያሸጋግር ይችላል። የበር እጀታዎች በተለያዩ ሰዎች ስለሚነኩ በሽታውን በማስተላለፍ በኩል አንድ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ። ባለሙያዎች እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ በተለያዩ ቁሶች ላይ ለቀናት በህይወት በመቆየት ወደ ሰዎች ሊተላለፍ ይችላል። • ኮሮናቫይረስና የአእምሮ ጤና ምን አገናኛቸው? ስለዚህም በበሽታው ላለመያዝና ስርጭቱን ለመግታት እጅን በመደበኛነት መታጠብ ወሳኙ የመከላከያ መንገድ ነው። የኮሮናቫይረስ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ይተላለፋል? በሽታው በግብረ ሥጋ ግንኙነት ይተላለፍ እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም። በአሁኑ ወቅት ለበሽታው መተላላፊያ ተብለው የሚጠቀሱት ማሳል፣ ማስነጠስና በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን መንካት ናቸው። በጉንፋንና በኮሮናቫይረስ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? የኮሮናቫይረስና ጉንፋን የሚጋሯቸው ተመሳሳይ የበሽታ ምልክቶች ስላሏቸው ለመለየትና ለመመርመር አስቸጋሪ ሆኗል። የኮሮናቫይረስን ለመለየት በዋናነት ማተኮር ያለብን ምልክቶች ትኩሳትና ጠንካራ ሳል ናቸው። ጉንፋን ግን የጉሮሮ ህመምን ጨምሮ ሌሎች ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን ኮሮናቫይረስ ደግሞ የትንፋሽ ማጠር ያስከትላል። የኮሮናቫይረስ ከጉንፋን የበለጠ ተላላፊ ነው? በጉንፍንና በኮሮናቫይረስ መካከል ቀጥተኛ ንጽጽር ለማድረግ ጊዜው ገና ቢሆንም ነገር ግን ሁለቱም ቫይረሶች በከፍተኛ ደረጃ የሚተላለፉ ናቸው። • ተመራማሪዎች ሰውነታችን የኮሮናቫይረስን የሚከላከልበትን መንገድ መለየት ቻሉ በኮሮናቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው በአማካይ ከሁለት እስከ ሦስት ወደ የሚደርሱ ሰዎች የሚያስተላልፉ ሲሆን፤ ጉንፋን የያዘው ሰው ግን በሽታውን ወደ አንድ ሊያጋባ ይችላል። ሁለቱም በሽታዎች ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ሊተላለፉ ይችላሉ። የኮሮናቫይረስ በሽታው ያለበት ሰው ባዘጋጀው ምግብ በኩል ሊተላለፍ ይችላል? የኮሮናቫይረስ በሽታ ያለበት ሰው ምግቡን በሚያዘጋጅበት ወቅት ተገቢውን የንጽህና ጥንቃቄ ካላደረገ ወደ ተመጋቢው ሊተላለፍ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። የኮሮናቫይረስ በሳልና በማስነጠስ በሚከሰቱ ብናኝ ጠብታዎች በእጅ አማካይነት ወደ ሰዎች ሊተላለፍ ይችላል። የቫይረሱ መስፋፋትን ለመግታት ምግብን ከመንካታችንና ከመመገባችን በፊት እጃችንን በደንብ አድርጎ መታጠብ ይመከራል። የግልና የአካባቢ ንጽህናን መጠበቅ በሽታውን ለመከላከል ወሳኝ ነው በሽታው በተከሰተባቸው ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው? በሽታው መኖሩ በተረጋገጠባቸው አገራት የሚኖሩ ሰዎች በወረርሽኙ የመያዝ ዕድላቸውን ለመቀነስ መከተል ያለባቸው የተለያዩ እርምጃዎች አሉ። ቫይረሱ በሳልና በማስነጠስ ጊዜ የሚፈጠሩ ጥቃቅን ጠብታዎች በሰዎች መካከል በሚኖር ንክኪ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። ስለዚህም የተለያዩ ሰዎች የሚነኳቸውን ነገሮችን ከመንካት መቆጠብ እንዲሁም አዘውትሮ እጅን በውሃና በሳሙና መታጠብ ወይም ተህዋሲያንን በሚገድሉ የንጽህና መጠበቂያ ፈሳሾች [ሳኒታይዘር] እጅን ማጽዳት ያስፈልጋል። • በየደቂቃው በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርን የሚያሳይ ካርታ በተጨማሪም ከሚያስሉ፣ ከሚያስነጥሱና ትኩሳት ካለባቸው ሰዎች ጋር ቅርበትና ንክኪን ማስወገድ በቫይረሱ መያዝን ሊያስወግድ ይችላል። በኮሮናቫይረስ ተይዣለሁ ተብሎ የሚታሰብ ከሆነም ከበሽታው ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ለመጠየቅ ወደ ተዘጋጁ የስልክ መስመሮች በመደወል ማሳወቅና ማድረግ ያለብንን መፈጸም ይኖርብናል። የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት አለ? እስካሁን ድረስ በኮሮናቫይረስ እንዳንያዝ የሚያስችል ክትባት የሌለ ቢሆንም ተመራማሪዎች ክትባትና መድሃኒት ለማግኘት ከፍተኛ ትረት እያደረጉ ይገኛሉ። የወረርሽኙ ቫይረስ ዝርያ ከዚህ በፊት በሰዎች ላይ ታይቶ የማይታወቅ አይነት በመሆኑ ሃኪሞችና ተመራማሪዎች ስለቫይረሱ በዝርዝር ለማወቅ ጊዜ ሳያስፈልጋቸው አይቀርም። የአየር ሁኔታና ሙቀት በበሽታው መስፋፋት ላይ ተጽእኖ ይኖረው ይሆን? በየወቅቱ የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለውጥ በበሽታው መስፋፋት ላይ የሚኖረውን ውጤት በተመለከተ አስካሁን ድረስ የታወቀ ነገር የለም። ምንም እንኳን ጉንፋንን የመሳሰሉ አንዳንድ ቫይረሶች ወቅታዊ የአየር ሁኔታን እየተከተሉ የሚከሰቱና የሚስፋፉ ቢሆንም ከኮሮናቫይረስ አንጻር እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም። የኮሮናቫይረስ ዝርያ ቤተሰብ በሆነው 'መርስ' ተብሎ በሚታወቀው ቫይረስ ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው፤ በሽታው ሞቃት በሆነ ጊዜ በስፋት የመከሰት ባህሪይ እንዳለው ተገልጿል።
50249069
https://www.bbc.com/amharic/50249069
ኡጋንዳ የጠፉት ኤርትራውያን ኳስ ተጫዋቾች ስጋት ላይ ነን አሉ
ኡጋንዳ ውስጥ የጠፉት አራት ኤርትራውያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ስጋት ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለፈው ወር በደቡብ ምዕራብ ኡጋንዳ ጂንጋ ከተማ ከሆቴላቸው የጠፉት የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን አባላት ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦብናልም ብለዋል።
የእግር ኳስ ቡድኑን ትተው ኡጋንዳ ውስጥ በመጥፋታቸው ድረ ገጽ ላይ ማስፈራሪያዎች እየደረሷቸው እንደሆነ ተጫዋቾቹ ገልጸዋል። የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ ውድድር ግማሽ ፍጻሜ ላይ መሰናበቱ ይታወሳል። • አራት የኤርትራ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አባላት ኡጋንዳ ውስጥ ጠፉ • ኢትዮጵያና ግብፅ በአሜሪካ ለውይይት እንጂ ለድርድር አይገናኙም ተባለ • የአማራ ክልል ረዳት ፖሊስ ኮሚሽነር ሰይድ አህመድ በዋስትና እንዲለቀቁ ተወሰነ ተጫዋቾቹ ታፍነው ወደ ኤርትራ ሊወሰዱ እንደሚችሉ ስጋት እንደገባቸው ገልጸው፤ ከኡጋንዳ አስወጡን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ከተጫዋቾቹ አንዱ፤ "ስለኛ ግድ የሚሰጠው አካል ካለ ከዚህ አገር እንዲያወጣን እንለምናለን። በየሳምንቱ ከቤት ቤት እየቀየርን፣ እየተሽሎኮሎክን እየኖርን ነው" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ተጫዋቾቹ ወደ ኤርትራ ከተመለሱ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ገልጸዋል። አሜሪካዊ ጠበቃቸው ኪምበርሊ ሞተሊ እንዳሉት፤ ተጫዋቾቹ ኡጋንዳ ውስጥ እየተፈለጉ እንደሆነ ሰምተዋል። በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተራድኦ ድርጅት (ዩኤንኤችሲአር) ጥገኝነት ቢጠይቁም እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙም ጠበቃዋ ተናግረዋል። ተጫዋቾቹ እንዳሉት፤ ሰዎች ስለሚያውቋቸውና ሊለይዋቸው ስለሚችሉ ከቦታ ቦታ በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻሉም። ሕይወታቸውን እየገፉ ያሉትም ከበጎ ፍቃደኞች በሚያገኙት እርዳታ ነው። ኤርትራ በተሳተፈችባቸው ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ኤርትራውያን ተጫዋቾች ሲጠፉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም።
news-49133155
https://www.bbc.com/amharic/news-49133155
በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ለሀምሌ 29 ተቀጠሩ
ሰኔ 15 በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው 'መፈንቅለ መንግስት' ጋር በተያያዘ የጸጥታ ኃላፊዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩና በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች ጉዳይ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ታይቷል።
ፖሊስ በአጠቃላይ የ90 ሰዎችን ቃል መስማቱን ገልጾ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ለዚህ ደግሞ ተጨማሪ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ማስፈለጉን በምክንያትነት አስቀምጧል። •"እናቴ ካልመጣች አልመረቅም" ኢዛና ሐዲስ ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ •በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን በእለቱ ጥቃት የደረሰባቸውና ጥቃቱን ለመመከት የሠሩ መኖራቸውን እና ማስረጃ የሚያስቀርብ በቂ ፍንጭ አለመኖሩን በመጥቀስ የተወሰኑት ተጠርጣሪዎች ጠበቃ የጊዜ ቀጠሮውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቋል። ከወንጀሉ ጋር የሚያያዝ ምንም ፍንጭ እንዳልተገኘባቸው የገለጹት ኮሎኔል አለበል አማረ ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። "ድርጊቱን ያስቆምኩት እኔ ነኝ" ያሉት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በበከሉላቸው ምንም ማስረጃ ስላልተገኘባቸው የጊዜ ቀጠሮውን ፍርድ ቤቱ አንዳይቀበል ጠይቀዋል። ሌሎች ተጠርጣሪዎችም የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ እንዲሆን ጠይቀዋል። ከወንጀሉ አፈጻጸም አንጻር ጊዜ እንደሚያስፈልግ የገለጸው ፖሊስ በበኩሉ የሰው እና የቴክኒክ መረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋል ብሏል። ግራ ቀኙን ያዳመጠው ፍርድ ቤት የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታታሉ ለሐምሌ 29/2011 ቀጠሮ ሰጥቷል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 218 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው መታየት ከጀመረ በኋላ 103 መፈታታቸው ይታወቃል። ከዛሬው ችሎት በኋላ ደግሞ 57 ይለቀቃሉ ተብሏል። የሚለቀቁት ግለሰቦች እነማን እንደሆኑ ግን የተገለጸ ነገር የለም።ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በሰጠው መሠረት ህክምና እንዳላገኙ የገለጹ ሲሆን ፖሊስ ግን ህክምና እያገኙ ነው ብሏል። •ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት እንዲከናወን ብሏል። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አብዛኛዎቹ ደሞዝ ማግኘታቸውን የጠቀሱት ተጠርጣሪዎች ደሞዝ ያልተከፈላቸው እንዲከፈላቸው በጠየቁት መሠረት እንዲፈጸም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ማረሚያ ቤት መሄድ የሚፈልጉ እና በፖሊስ ጣቢያ መቆየት የሚፈልጉ በመኖራቸው ተለይተው እንዲቀርቡም ተጠይቋል። በተጠርጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ስሜ ለሁለተኛ ቀን አልተጠራም ሲል አንድ ተጠርጣሪ የጠየቀ ቢሆንም ስሙ መኖሩን ፍርድ ቤቱ አረጋግጧል። ለጋዜጠኞች ብቻ ክፍት በነበረው ሂደት ከተጠርጣሪዎች ብዛት አንጻር ክፍሉ ተጣቦ ነበር።በፍርድ ቤቱ እና በአካባቢው ከፍተኛ የጸጥታ ሃይል ተሰማርቶ ነበር።
news-48761080
https://www.bbc.com/amharic/news-48761080
የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው አስክሬን ላሊበላ ገባ
የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን አስክሬን ላሊበላ አየር ማረፊያ እንደደረሰ በሥፍራው የሚገኙት የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ለቢቢሲ ገለፁ።
• ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ • ስለ'መፈንቅለ መንግሥት' ሙከራው እስካሁን የማናውቃቸው ነገሮች ትናንት የብ/ጄነራል አሳምነው መገደል ከተሰማ በኋላ ቤተሰቦቻቸው አስክሬናቸው በክብር እንዲሰጣቸው ለወረዳው ጥያቄ በማቅረባቸው መንግሥት ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አስክሬናቸውን እንደሸኘ አቶ ማንደፍሮ ተናግረዋል። ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት አካባቢ የብ/ጀኔራሉ አስክሬን ከባህር ዳር ወደ ትውልድ ቀያቸው እንደሚላክ በስልክ እንደተነገራቸው የገለፁት ምክትል ከንቲባው አስክሬናቸውን በክብር ለመቀበል በአየር ማረፊያ እንደተገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጄነራሉ ቤተሰቦች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የአካባቢው የመንግሥት አመራር አካላት፣ የፀጥታ ኃይሎችና የቤተክርስቲያን ቀሳውስት በአውሮፕላን ማረፊያው ተገኝተዋል። ከቤተሰቦቻቸው ጋር ገና ስላልተነጋገሩ የብ/ጄነራሉ የቀብር ሥነ ሥርዓት የትና መቼ እንደሚፈፀም በእርግጠኝነት መግለፅ እንደማይችሉ የገለፁልን ምክትል ከንቲባው፤ ሕብረተሰቡ ኃዘኑን የሚገልፅበት በከተማ አደባባይ ትልቅ ድንኳን የተዘጋጀ መሆኑንና አስክሬናቸውም በዚሁ ድንኳን ውስጥ እንደሚያርፍ አስረድተዋል። በዚያው ሥፍራ ሌሊቱን የፀሎተ ፍትሃት ሥነ ሥርዓት እየተደረገ እንደሚያድር መረጃ እንዳላቸው ገልፀውልናል። ምክትል ከንቲባው ብ/ጄነራል አሳምነው ለአገር ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በደማቅ ሁኔታ ለመፈፀም ኮሚቴ መዋቀሩን አክለዋል። በዚህም መሠረት የቀብር ሥነ ሥርዓቱን በዲስፕሊንና በፕሮቶኮል ለመምራት የክብር ተመላሽ ጄነራሎች በአካባቢው ላይ በመኖራቸው በእነርሱ ይመራል ብለዋል። በሌላ በኩልም የፀጥታ ሂደቱን የሚመራ ቡድን፣ የወጣቱ ሰላምና ደህንነት የሚከታተል ሌላ በወጣቶች የሚመራ ቡድን እንዲሁም የሃይማኖት ሥነ ሥርዓቱን የሚመራ ኮሚቴም ተዋቅሯል። • ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ አቶ ማንደፍሮ እንደገለፁልን ትናንት ብ/ጄነራሉ መገደላቸውን ከተሰማ አንስቶ በሕብረተሰቡ ዘንድ የተዘበራራቀ ስሜት እንደሚታይ እንዲሁም በክልሉ አመራሮች ሞት ምክንያት ድንጋጤ ውስጥ መሆናቸውን ነግረውናል። የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት አመራርና የፀጥታ አካላት ከህዝቡ ጎን በመሆን ቤተሰባቸውን በማፅናናትና ህዝቡንም በማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ አስረድተዋል። ቅዳሜ ሰኔ 15፣ 2011 ዓ.ም ባህር ዳር ውስጥ ተሞክሯል የተባለውን "መፈንቅለ መንግሥት" መርተዋል ተብለው ሰማቸው የተጠቀሰው የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋድየር ጄነራል አሳምነው ጽጌ መገደላቸው ይታወሳል።
news-53619554
https://www.bbc.com/amharic/news-53619554
ሕንድ፡ ሳኒታይዘር የጠጡ ቢያንስ 10 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ
በሕንድ ውስጥ በምትገኘው አንድራ ፕራዴሽ ግዛት የመጠጥ መሸጫ ሱቆች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርከት ባለ አልኮል የተሰራ ሳኒታይዘር የጠጡ ቢያንስ አስር ግለሰቦች ሕይወታቸው ማለፉ ተዘገበ።
የአካባቢው ፖሊስ ኃላፊ ሲዳርት ኩሻል እንደተናገሩት ሰዎቹ ሕይወታቸው ሊያልፍ የቻለው ሳኒታይዘሩን ከውሃ እና ከለስላስ መጠጦች ጋር ቀላቅለው በመጠጣታቸው ነው። አክለውም ''ሁሉም አልኮል ላይ ጥገኛ ነበሩ" ያሉት የፖሊስ ኃላፊው፤ የሳኒታይዘር፣ ውሃ እና ለስላስ መጠጦች ቅልቅሉን መጠጣት የጀመሩት ከመሞታቸው አስር ቀናት በፊት እንደሆነ ተናግረዋል። ''ሳኒታይዘሩ ለጤና ጎጂ የሆነ መርዛማ ንጥረነገር በውስጡ ስለመኖሩና አለመኖሩ ምርመራ እያካሄድን እንገኛለን'' ካሉ በኋላ ከሳኒታይዘሩ የተወሰዱ ናሙናዎች ለኬሚካል ምርመራ መላካቸውን አስታውቀዋል። አንዳንድ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል ሱሰኛ የሆኑ ሰዎች አልኮል ማግኘት ሳይችሉ ሲቀሩ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘሮችን እንደ አማራጭ እየተጠቀሙ እንደሆነ ኃላፊው ለሮይተርስ የዜና ወኪል ገልጸዋል። ኩሪቼዱ በተባለችው መንደር በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። ''በእንቅስቃሴ ገደቡ ምክንያት አልኮል አይሸጥም፤ ነገር ግን ሳኒታይዘሮቹ በቀላሉ መገኘት የሚችሉ ናቸው'' ብለዋል። የሕንድ ፌደራል መንግሥት ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በማሰብ አንዳንድ የንግድ ተቋማት መልሰው እንዲከፈቱ መወሰኑ የሚታወስ ነው። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይም እንደ ዮጋ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተሪያዎች እንዲከፈቱና የሰዎች እንቂስቃሴ እንዲጀመር ተደርጓል። ነገር ግን በርካታ የአገሪቱ ግዛቶች ቫይረሱ እየጨመረ በመጣባቸው አንዳንድ አካባቢዎች የእንቅስቃሴ ገደቦችን አስቀምጠዋል። በደቡባዊ ሕንድ በምትገኘው አንድራ ፕራዴሽ ግዛት ባለፈው ወር ብቻ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከእጥፍ በላይ መጨመሩን የግዛቲቱ መንግሥት አስታውቆ ነበር። ሕንድ ውስጥ በየቀኑ እስካሁን ከ55 ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ37 ሺ በላይ ደርሷል።
51513395
https://www.bbc.com/amharic/51513395
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን መልቀቅ ሲታወስ
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት የዛሬ ሁለት ዓመት ነበር።
"የመፍትሔ አካል ለመሆን በማሰብ በፍቃዴ ሥልጣኔን ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርቤያለሁ" ኃይለማርያም ደሳለኝ የካቲት 8/2010 ዓ.ም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነታቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ለመልቀቅ ነበር ጥያቄ ያቀረቡት። በወቅቱ ከድርጅት መሪነትና ከሥልጣናቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት "የሀገሪቱ ችግር የመፍትሄ አካል ለመሆን" ስለፈለጉ መሆኑንም ገልፀው ነበር። • የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ • በጠምባሮ ወረዳ ከሰማይ ወረደ የተባለው እሳት ወይስ ሚትዮራይትስ? • ኦነግና ኦፌኮ አባሎቻችን እየታሰሩብን ነው አሉ ኃይለማርያም ደሳለኝ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ሊቀመንበርነት ለመነሳት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን በመናገር ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ጥያቄም ተቀባይነት ያገኛል ብለው እንደሚያምኑ አስታውቀው ነበር። "የኢህአዴግ ምክር ቤት ፍፁም ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የሚተካኝን የኢህአዴግ ሊቀ-መንበር ይመርጣል ብየ አምናለሁ። በተመሳሳይ መንገድ ድርጅቱና መንግሥት ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በማድረግ በአገራችን ዳግም ታሪክ የሚሰራበት ወቅት ነው ብዬ አምናለሁ" ነበር ያሉት። በወቅቱ ያስገቧቸው የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤዎች ውሳኔ እስከሚያገኙ በኃላፊነታቸው እንደሚቆዩም ተናግረዋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም በመግለጫቸው ለሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች መፍትሄ ፍለጋ ህዝቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ አስተላልፈው ነበር። "ይህንን አሳሳቢ ሁኔታ ለመቅረፍ መላው የአገራችን ህዝቦች ከዚህ በፊት የተለመደው ኢትዮጵያዊ የመቻቻል እና የመከባበር ሁኔታ እንዲቀጥል መስራት አለብን።" ጨምረውም "በአገራችን ደኅህንት ዋስትና እኔም በበኩሌ የድርሻዬን ለማበርከት ዝግጁ ነኝ" ብለው ነበር። ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ከወረዱ በኋላም የዚምባብዌ ምርጫን እንዲታዘብ የተላከውን የአፍሪካ ሕብረት ልዑካን ቡድን በመምራት ወደ ወደዚያው በማቅናት ከቀድሞውን ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ጋር ተገናኝተው ፎቶ በመነሳታቸው የማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆነው ነበር። • ምርጫው ይደረጋል የተባለበት ቀን ወደፊት ተገፋ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ ቆይተው በሞት የተለዩት አቶ መለስ ዜናዊን በመተካት ሥልጣን የተረከቡት በመስከረም ወር 2005 ዓ. ም. ነበር። የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆነንም ለስድስት ዓመታት ያህል አገልግለዋል። እርሳቸውንም በመተካት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፓርቲውንም ሆነ የአገሪቱን ሥልጣን መረከባቸው ይታወሳል። አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ በአገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ያለቸው ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰ ሲሆን በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መሪነት ከኤርትራ ጋር ለዓመታት የነበረው ፍጥጫ ሲያበቃ ወደ አሥመራ ካመራው የኢትዮጵያ ቡድን ጋር ወደ ኤርትራ ተጉዘው ነበር። አቶ ኃይለማሪያም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከአገር ውጪ ባሉ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የቦርድ አባል እንዲሆኑም ተመርጠዋል። በዚህም መሰረት ከሚጠቀሱት ተቋማት መካከል በአፍሪካ የአረንጓዴ ልማት ጥረት ውስጥ ተሳትፎ የሚያደርገውና በአስራ አንድ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የሚገኙ 30 ሚሊዮን የሚሆኑ አርሶ አደሮችን የምግብ ዋስትና ለማሻሻል በሚሰራው 'አሊያንስ ፎረ ኤ ግሪን ሪቮሉሽን ኢን አፍሪካ' የተባለው ድርጅት የቦርድ አባል ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ የሚከሰቱና ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን የሚከታተለው መንግሥታዊ ያልሆነው 'ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ'ም የቡድኑ የቦርድ አባል እንዲሆኑ በቅርቡ መርጧቸዋል።
news-42621970
https://www.bbc.com/amharic/news-42621970
የኤርትራ ዘፈኖች በኢትዮጵያዊ አቀናባሪ
በረከት ወልዱ ወደ ሙዚቃ የገባበትን አጋጣሚ ሲያስታውስ "ከነጋዴ ቤተሰብ ስለተወለድኩ እኔም ነጋዴ ነበርኩኝ ሙዚቃ የኔ እኔ ደሞ የሙዚቃ አልነበርንም" ይላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ነበር ተወልዶ ባደገባት አክሱም ከተማ ከሙዚቃ ጋር የተዋወቀው።
ለሁለት ወራት የሚቆይ የሙዚቃ ስልጥና የመሳተፍ ዕድልን ካገኘ በኋላ ነበር የበረከትና የሙዚቃ አብሮነት ተጠነሰሰ። የኑሮው አቅጣጫ ግን ከንግድ ወደ ጥበብ ሙሉ ለሙሉ አልተሽጋገረም። ሙሉ ጊዜውን ለሙዚቃ ሳይሰጥ የንግድ ሥራውን ቀጠለ። በረከት ኑሮውን ከአክሱም ወደ አዲስ አበባ ሲቀይር ንግድና ሙዚቃም አብረውት ነበሩ። ለሙዚቃ ያለው ፍቅር ከፍ እያለ ሄዶ ጃዝ አምባ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ገብቶ የሙዚቃ መሳርያ በመማር የተሻለ እውቀትና ችሎታ አገኘ። በረከትና ኤርትራውያን ድምፃውያን በረከት በ2005 ዓ.ም የራሱን ስቱድዮ በመክፈት የዘፋኖችን ድምፅ ከሙዚቃ መሳርያዎች ጋር ማቀናበር ጀመረ። አጭር በሚባል ጊዜ በርካታ ሥራዎችን በመስራት በሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ እውቅናና ተቀባይነት ለማግኘት በቃ። "በመድረክ የምሰራቸው ሥራዎችም ከሙዚቃ አፍቃሪዎች ጋር እንድተዋወቅ ረድተውኛል" የሚለው በረከት፤ አብሮ ለመስራት ይመኝ ከነበሩት ድምፃውያን ጋር የመሥራት እድልን እንዳገኘም ይናገራል። ለአብርሃም ገብረመድህንና ለሰለሞን ባይረ ተወዳጅ የዘፈን ቅንብሮች ለመስራትም ችሏል። በትግርኛ ቋንቋ ከሚዘፍኑ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ከታዋቂ ኤርትራዊያን ጋርም አብሮ እየሰራ ይገኛል። "ድምፃዊ ተስፋአለም ቆርጫጭ በቅርቡ 'አስመራ ወይ ዲሲ' በሚል ርዕስ ለህዝብ ያቀረበውን ሥራ አብረን ነው የሰራነው" ይላል በረከት። ከእነዑስማን አብራር፣ ሮቤል ሚኪኤለ፣ ምሕረትአብ፣ ፍፁም ባራኪና ሌሎች በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ተወዳጅ የኤርትራ ድምፃውያን ጋር የሰራችው ሥራዎች እንዳሉም ያስረዳል። ያቀናበራቸውን ዘፈኖች አጠናቆ ለባለቤቶቹ ሲያስረክብ ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰማው ይሚናገረው በረከት፤ በውጭ ሃገር ሆነው የሚልኩለት ያላለቁ ማሳያ ሥራዎች ድምፃውያኑ በሚፈልጉትና በሚወዱት መንገድ አዘጋጅቶ ሲልክላችው ከድምፃውያኑም ሆነ ከሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ አድናቆት እንደሚቀርብለት ይገልፃል። ድምፃዊ ሮቤል ሚኪኤለ ከበረከት ጋር አብረው ከሰሩ ኤርትራዊ ድምፃዊያን አንዱ ነው። "ከበረከት ጋር የተገናኘው ሙዚቃዬን የሚያቀናብርልኝ ሰው በምፈልግበት ጊዜ ነበር። በሥራው የሚደነቅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ከገንዘብ ይልቅ ለሙዚቃ የሚጨነቅ ባለሙያ ነው" ሲል ያሞግሰዋል። ለረጅም ጊዜ ከበረከት ጋር አብሮ የሰራው ድምፃዊ ሃይለ ገዙም "በረከት ለሞያው እንጂ ለገንዘብ የሚኖር አይደለም። በርካታ ቆንጆ ሥራዎች አብረን ሰርተናል። ሁሉም አንድ አይነት ቋንቋ በሚናገሩ ሁለት ህዝቦች ይደመጣሉ" ይላል። ኢትዮጵያና ኤርትራ "በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው ሁኔታ ከሥራችን አላስተጓጎለንም" የሚለው በረከት በሁለቱም ሃገራት ያለው የትግርኛ ሙዚቃ ምትና ጣዕም ልዩነት እንደሌለው ያምናል። "በጥንቃቄና ሙያዊ በሆነ ብቃት ከተሰራ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ ትግርኛና ኤርትራ ውስጥ የሚሰራ የትግርኛ ዘፈን ልዩነት አይኖረውም" ይላል። ከኤርትራዊያኑ ድምፃውያን ጋር በጥሩ መግባባትና መከባበር የሚሰራው በረከት "በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ቢፈታ ሙዚቃውን የበለጠ ለማሳደግ እድል ሊፈጥር ይችላል" ይላል። በረከት አንድ ቀን በአካል ተቀራርቦ እየተወያዩ የትግርኛ ሙዚቃዎችን የመስራት ዕድል እንደሚኖር እምነት አለው።
news-47744592
https://www.bbc.com/amharic/news-47744592
ቦይንግ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ጋር በተያያዘ ተከሰሰ
በኢትዮጵያው አየር መንገድ አደጋ ህይወቱን ያጣ አንድ ግለሰብ ቤተሰቦች በአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ ቦይንግ ላይ በአሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት ክስ መሰረቱ።
ከሁለት ሳምንት በፊት በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩት 157 መንገደኞች በሙሉ በአዳጋው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። • ቦይንግ "ችግሩ ተፈቷል" እያለ ነው • "በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት በአደጋው ህይወቱ ያለፈው ሩዋንዳዊ ግለሰብ ጃክሰን ሙሶኒ ዘመዶች በክሳቸው ላይ አደጋው የደረሰበት አውሮፕላን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በአውቶማቲክ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓቱ ላይ የዲዛይን ችግር አለበት ሲሉ አመልክተዋል። ከአምስት ወራት በፊት ከተከሰከሰው ተመሳሳይ የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን በኋላ በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ አደጋው ሲደገም ቦይንግ 737 ማክስ የተባለው አይነት ስሪት ያላቸው አውሮፕላኖች በሙሉ ከበረራ ታግደዋል። • "አደጋውን ስሰማ ክው ነበር ያልኩት..." አቶ ተወልደ ገ/ማርያም አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ በቀረበበት ክስ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። ረቡዕ እለት ቦይንግ ከአደጋዎቹ ጋር ግንኙነት አለው የተባለው በአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ላይ ያለው ችግር መፍትሄ እንደተበጀለት አስታውቋል። የአደጋው መርማሪዎች ምክንያቱ ምን እንደሆነ ገና በምርመራ ላይ ናቸው። በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ የሚመረምሩ ባለሙያዎች የአውሮፕላኑ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት ከአደጋው በፊት እንዲሰራ ተደርጎ እንደነበር በመጀመሪያ ደረጃ ውጤታቸው እንደደረሱበት ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገበ። • ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው ጋዜጣው ስማቸው ያልተገለጹ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ውጤቱ ትናንት ሐሙስ ለአሜሪካ ፌደራል የአየር ትራንስፖርት አስተዳደር በተሰጠ ማብራሪያ ወቅት መቅረቡ ተነግሯል። የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓቱ አውሮፕላኑ እንዳይቆም ለመከላከል የሚረዳ ነው። ይህንን በተመለከተ ቦይንግ ምላሽ ካለው ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ስለአደጋው የሚደረገው ምርመራ ከመጠናቀቁ በፊት ምንም ዓይነት አስተያየት እንደማይሰጥ ገልጿል። ጨምሮም ስለጉዳዩ ያሉ ጥያቄዎች በሙሉ መቅረብ ያለባቸው ምርመራውን እያደረጉ ላሉ ባለስልጣናት እንደሆነም ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል ያወጣውን ዘገባ እንደተመለከተውና በቅርቡ ምላሸ እንደሚሰጥ ተናግሯል።
48224206
https://www.bbc.com/amharic/48224206
በ2024 እቃና ሰው ጫኝ መንኮራኩር ወደጨረቃ ይላካል ተባለ
የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ ሰዎችን እንዲሁም ቁሳቁስ ይዞ ጨረቃ ላይ የሚያርፍ 'ስፔስክራፍት' (መንኮራኩር) አስተዋውቋል።
የአማዞን መስራች እና የዋሽግተን ፖስት ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ጄፍ ቤዞስ ወደ ጨረቃ የሚያቀናው መንኮራኩር ምን ሊመስል እንደሚችል ይፋ ያደረገ ሲሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2024 መንኮራኩሩ እውን ይሆናል ተብሏል። ይህ ወደጨረቃ ለመጓጓዝ የሚውለው መሣሪያ የጠፈር ተመራማሪዎችንና የተለያዩ መገልገያዎችን ይጭናል። • ጄፍ ቤዞስ በ35 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ ትዳሩን ለማፍረስ ተስማማ 'ብሉ ኦሪጅን' የተባለ ህዋ አሳሽ ድርጅት ያለው ጄፍ "ጨረቃ ላይ ተመልሰን መሄድ አለብን፤ አሁን ከሄድን መመለስም አያስፈልግም" ሲል ተናግሯል። አዲሱን መንኮራኩር በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ያስተዋወቀው የናሳ አመራሮች በተገኙበት ነበር። • ለመብረር የተዘጋጁት ልጃገረዶች መንኮራኩሩ ከመሬት ወደጨረቃ በቀጥታ ለመመንጠቅ በቂ ነዳጅ እንዳለው ተገልጿል። ከመሬት ሲነሳ 14,968 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን፤ ጨረቃ ላይ ሊያርፍ ሲቃረብ ወደ 3,175 ኪሎ ይቀንሳል። መንኮራኩሩን በጨረቃ ደቡባዊ ክፍል ለማሳረፍ እቅድ ተይዟል። • ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው በጨረቃ ደቡባዊ ክፍል የበረዶ ቅንጣቶች እንደተገኙና፤ ከበረዶው ውሀ በማውጣት ከዛም ወደ ሀይድሮጅን በመቀየር መንኮራኩሩን በድጋሚ በነዳጅ መሙላት እንደሚቻል ተመላክቷል። ነዳጁ መሞላቱ መንኮራኩሩ በፀሀይ ዙሪያ ተጨማሪ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ያስችለዋል ተብሏል። የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ጠፈርተኞችን በ2024 ወደጨረቃ የመላክ እቅድ እንዳለ ተናግረው ነበር። ጄፍ ይህንን እቅድ እንደሚያሳኩትም ገልጿል። መንኮራኩሩ ከ2016 አንስቶ ግንባታው መጀመሩ እቅዳቸውን ለማሳካት እንደሚያግዛቸውም ጄፍ ተናግሯል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? ጄፍ የሰው ልጅ በጠፈር ላይ የሚኖርበትና የሚሠራበት ዘመን ቅርብ ይሆን ዘንድ ከሚያደርገው ጥረት አንዱ ወደጨረቃ መጓዝን ቀላል ማድረግ ነው።
news-45705849
https://www.bbc.com/amharic/news-45705849
ትግል ለተሻለ የአካል ጉዳተኞች ማገገሚያ በሰሜን አፍሪካ
አሚና ስላኦዊይ ከባለቤቷ ጋር በእረፍት ሽርሽር ላይ እያለች ነበር ከብስክሌት ወድቃ መጨረሻዋ ተሽከርካሪ ወንበር (ዊልቼር) ላይ የሆነው፡፡
ከሞሮኮው ትልቁ የአካል ጉዳተኛ ማዕከል ጀርባ ያለችው አሚና ስላኦዊይ ናት አደጋው የእሷን ብቻ ሳይሆን በሞሮኮ እና ሌሎች ሃገራት የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አካል ጉዳተኞችን ህይወት የቀየረ ነበር፡፡ አሚና ከሀብታም ቤተሰብ የመጣች በመሆኗ የምትፈልገውን ህክምና የማግኘት አቅም ነበራት፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ሞሮኳውያን ጓደኞቿ ይህን ማድረግ እንደማይችሉ አሰበች፡፡ • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ • አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው? ከጥቂት ጓደኞቿ ጋር በመሆን የመሰረተችው የማገገሚያ ማዕከል ከ25 ዓመታት በኋላ 26ሺህ አካል ጉዳተኞች ህክምና፣ መገልገያ መሳሪያዎች እና ድጋፍ እንዲያገኙ አግዟል፡፡ "በመጀመሪያ ሁሉም ይስቁ ነበር፤ እብድ ናችሁ፡፡ የተሰባሰባችሁት መራመድ እንኳ የማትችሉ ናችሁ፤ በዛ ላይ ገንዘብም የላችሁ፡፡ ይባስ ብሎ የማገገሚያ ማዕከል ለመገንባት ታስባላችሁ? ይሉናል። እኛም መልሳችን አዎ ነበር" ትላለች አሚና። ራስን በገንዘብ መቻል ከአሚና ጋር እያወራን የድርጅቷ ግሩፕ ኤ.ኤም.ኤች ዋና መለያ በሆነው እና በካዛብላንካ በሚገኘው ኑር ማገገሚያ ማዕከል ኮሪዶር ወደ ታች እየተጓዝን ነው። በኮሪዶሩ ሁለቱም አቅጣጫ ህሙማን ክብደት የሚያነሱባቸው ከፍ ያለ ሙዚቃ የሚሰሙባቸው ሰፋፊ ክፍሎች አሉ፡፡ "የመድህን ዋስትና ያላቸው ወይም የሚከፍሉት ያላቸው ሰዎች ለአቅመ ደካማዎች ይከፍላሉ" ትላለች ድርጅቱ የመክፈል አቅም የሌላቸውን ሰዎች የሚያስተናግድበትን ፈጠራ የተሞላበት ዘዴ ስታብራራ። ባለጸጋ ህሙማን ለራሳቸው መክፈል ለማይችሉ ታካሚዎች ድጎማ ያደርጋሉ "አምስት ሰዎች በክፍያ በታከሙ ቁጥር አንድ ሰው በነጻ አገልግሎት ያገኛል፡፡ እናም ይህ የአሰራር ዘዴ ከአራት ወይም ከአምስት ዓመት በኋላ እራሳችንን እንድንችል አደረገን። የምናፈሰው መዋዕለ ንዋይ ተጨማሪ ትርፍ ስለሚያስገኝልን፤ ሰዎችን መርዳት አስችሎናል። በነጻ ህክምና ከሚያገኙት ሰዎች መካከል ደግሞ ፈቲሃ ኤት ሞሃመድ አንዷ ናት። የቤቷን ደረጃዎች እያጸዳች እያለ ወድቃ ነበር የአካል ጉዳት ያጋጠማት። ቡድኑ የማገገሚያዋን 80 በመቶ ውጪ ሸፍኖላታል፡፡ በልዩ ሁኔታ የተሰራ ሞተር ሳይክልም ገዝቶላታል፡፡ • ለመብረር የተዘጋጁት ልጃገረዶች • የምግብ ብክነትን ለማስወገድ አዲስ ፈጠራ ሞተር ሳይክሉን መንገድ ዳር ባላት መሸጫ ላይ የምትቸረችራቸውን የመዋቢያ እቃዎች ለመግዛት በየቀኑ ትጠቀምበታለች። "አልጋ ውስጥ እያለሁና እናቴ ሁሉንም ነገር ስትሰራልኝ በተለየ አለም ውስጥ የምኖር ያክል ይሰማኝ ነበር፡፡ ሰውነቴ አይታዘዘኝም፤ በህይወት እንዳለሁ እንኳን አይሰማኝም ነበር፡፡" "ሞተር ሳይክሌን መጋለብ እወዳለሁ:: አሁን ነጻነት ይሰማኛል" ትላለች፡፡ ከማገገሚያ ባሻገር በየቀኑ 120 ያህል አካል ጉዳተኛ ሰዎች ከማገገሚያ እስከ ሰው ሰራሽ ተገጣሚ የሰውነት ክፍሎች እና የስነ ልቦና ድጋፍ ፍለጋ ወደ አሚና ቢሮዎች ይመጣሉ፡፡ "የግሩፕ ኤ.ኤም.ኤችን ለየት የሚያደርገው የማገገሚያ ወጪ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ነገር ለመሸፈን መሞከራቸው ነው" ይላሉ በሞሮኮ የአጋርነት፤ ሴቶች፤ ቤተሰብ እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር የማህበራዊ ውህደት ዳይሬክተር አህመድ አይት ብራሂም፡፡ "አካል ጉዳተኞች ተመልሰው ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀላቸውን ማረጋገጥ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ በመላው አፍሪካ በእርግጥም ለየት ያለ ነው፡፡" ከነርቭ ችግር ጋር በተያያዘ አካል ጉዳተኛ የሆነችው ከድጃ ከአሚና ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላታል የአሚና ግሩፕ አሁን አካል ጉዳተኛ ህጻናትን ለመቀላቀል የሚያስችል ይበልጥ አካታች የሆነ አደረጃጀት ያለው ት/ቤት ከፍቷል፡፡ ይህ ደግሞ ከአካል ጉዳተኛ ህጻናት ከግማሽ በታቹ ብቻ ወደ ት/ቤት ለሚሄዱባት ሀገር እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ የስምንት ዓመቷ ከድጃ ከነርቭ ችግር ጋር በተገናኘ አካል ጉዳተኛ ስትሆን ትምህርቷን በመከታተል ላይ ትገኛለች፡፡ የምትኖረውም ከክሊኒኩ አጠገብ ወላጆቿ በተከራዩት ጠባብ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ልጃቸው የሚያስፈልጋትን ድጋፍ እንድታገኝ ለማድረግ ማራካሽ ከምትባል ከተማ ወደዚህ የመጡት ከዓመት በፊት ነበር፡፡ • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ • የ15 ዓመቷ ታዳጊ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ቀልብ እየገዛች ነው "ማራካሽ እያለሁ ጓደኞች አልነበሩኝም፡፡ እዚህ ከመጣሁ በኋላ ነው ጓደኞች ማፍራት የጀመርኩት፡፡ እየተሻለኝ ሲመጣ የሆነ በጣም ደስ የሚያሰኘኝ ስሜት ይሰማኝ አብዛኛውን የከድጃን የማገገሚያ ወጪ የሚሸፍነው የአሚና ግሩፕ ነው፡፡ ቤተሰቦቿ ከድጃ እንዴት ትበሳጭ እንደነበር እና አብዛኛውን ጊዜዋን አልጋ ላይ በጀርባዋ ተኝታ ታሳልፍ እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ አሁን ግን ስዕል መሳል፤ ከሌሎች ልጆች ጋር መጫወት ብሎም ራሷን ችላ እስከመቆም ሳይቀር ደርሳለች፡፡ በእድገት ጎዳና ለመቀጠል ክሊኒኩ ከመላው አፍሪካ ሀብታም ህሙማንን ለመሳብ ጥረት እያደረገ ነው አዳዲስ ተግዳሮቶች ወደ ክሊንኩ ስንመለስ አሚናን ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስበሰባ ውስጥ ሆና አገኘናት፡፡ ምንም እንኳ ስኬታማ ቢሆኑም የግሩፑ ፈጠራ የታከለበት የገንዘብ አያያዝ ሞዴል አደጋ ስለተጋረጠበት የወደፊት ስልቶች ላይ እየተወያዩ ነው። ችግር እየሆነ የመጣው የግል ክሊኒኮች ለሀብታም አካል ጉዳተኞች የሚሆን ተወዳዳሪ እና ቅንጡ የማገገሚያ ማዕከል ለመገንባት እያቀዱ መሆኑ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ እንደ ፈቲሃ እና ከድጃን ለመሳሰሉ መክፈል ለማይችሉ አካል ጉዳተኞች የህክምና ወጪ የሚሸፍኑት ሃብታሞቹ ናቸው፡፡ ነገር ግን ችግሩ ያ ብቻ አይደለም፡፡ "የበጀታችንን አንድ አስረኛ የምናወጣው መክፈል ለማይችሉ ህሙማን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን የመግዛት አቅማችን በየጊዜው እየቀነሰ ሲሆን ከመንግስትም ምንም አይነት ድጋፍ አናገኝም፡፡ በመሆኑም የገንዘብ ድጋፍ በምናገኝበት ዘዴ ላይ የበለጠ ፈጠራ ያስፈልገናል" ትላለች አሚና:: • የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች • ከጋና የፈጠራ ሥራዎች ጀርባ ያለው ሥራ ፈጣሪ በቅርቡ ክሊኒኩ ለሀብታም ህሙማን የሚሆን 20 ራሳቸውን የቻሉ ክፍሎች ያለው አዲስ ቅርንጫፍ ከፍቷል፡፡ የማገገሚያ አማራጮች ውስን በሆኑባቸው እንዲሁም ከነጭራሹ በሌሉባቸው በመላው አፍሪካ የሚገኙ ብዙ ባለጸጋ አካል ጉዳተኞችን ቀልብም እየሳበ ነው፡፡ በዋናነት የሚመጡት ከሴኔጋል፤ ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከጊኒ ሲሆን፤ የሚመጡበትም ምክንያት ቅርበቱ እንዲሁም ዋጋው ከፈረንሳይም ሆነ ከሌሎች አውሮፓ ሀገራት በአስር እጥፍ ስለሚረክስ ነው፡፡ "ጊዜው ይሮጣል አሁን 25 ዓመት ሞላን፡፡ ቡድኑ እዚሁ እንዳለ ነው፡፡ ግን እስከመቼ?" ትላለች አሚና፡፡ "ግባችን እኛ ከዚህ ስንሄድ የሰራነው እንደማይጠፋ ማረጋገጥ ነው፡፡ ካዛብላንካ አጠገብ ሌላ ሆስፒታል ልንከፍት ነው፡፡ ከተሳካም ሌሎች በርካታ የማገገሚያ ማዕከላትን እንከፍታለን፡፡ በአፍሪካ የማገገሚያ መሪዎች መሆን እንፈልጋለን፡፡" ይህ የቢቢሲ ተከታታይ ክፍል የተዘጋጀው ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡ #bbcinnovators
news-50122411
https://www.bbc.com/amharic/news-50122411
የሮማ ክለብ ደጋፊዎች በሮናልዶ ቬይራ ላይ የዘረኝነት ጥቃት አደረሱበት
የጣልያኑ ክለብ ሳምፕዶሪያና የእንግሊዙ ከሃያ አንድ ዓመት በታች ተጫዋች ሮናልዶ ቬይራ ከሮማ ክለብ ደጋፊዎች የዘረኝነት ጥቃት ደርሶበታል።
የዝንጀሮ ድምፆችን በማውጣት ተጫዋቹ ላይ የዘረኝነት ጥቃት እንዳደረሱበትም ተገልጿል። ይኸው ሁኔታ የተፈጠረው የጣልያኑ ሴሪያ ጨዋታ ሲካሄድ በነበረበት በሳምፕዶሪያ ሉይጂ ስታዲየም ሲሆን ክለቦቹ ያለግብ ተለያይተዋል። •ደቡብ አፍሪካዊቷ የፓርላማ አባል የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባት •ዘረኝነት ሽሽት - ከአሜሪካ ወደ ጋና የሮማ ደጋፊዎች የዝንጀሮ ድምፅ በማስመሰል ተጫዋቾቹ ላይ መጮሃቸውን ተከትሎ ክለቡ በትዊተር ገፁ ይቅርታን አስፍሯል። "ሰምቻቸዋለሁ ግን ስለዚህ ጉዳይ ማውራት አልፈልግም" በማለት የ21 ዓመቱ ቬይራ ለጣልያን ቴሌቪዥን የተናገረ ሲሆን "እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ብዙ ጊዜ ይፈጠራል፤ እንዲህም መሆን የለበትም" ብሏል። ጊኒ ቢሳው የተወለደው ተጫዋች ወደ እንግሊዝ የሄደው ገና በህፃንነቱ ሲሆን፤ ከሊድስ ክለብ ወደ ሳምፕዶሪያ የተዛወረው ባለፈው ዓመት ነው። •አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" ከዚህ ቀደምም በእግር ኳስ ሜዳዎች የዘረኝነት ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን ባለፈውም የፊዮረንቲናው ክለብ ተከላካይ ብራዚላዊው ዳልበርት በአትላንታ ደጋፊዎች የዘረኝነት ጥቃት ደርሶብኛል ማለቱን ተከትሎም ጨዋታው ተቋርጦ ነበር። ሮማ ክለብም ለተከላካያቸው ጁዋን ጂሰስ በማህበራዊ ሚዲያ የዘረኝነት ዘለፋን ልኳል ያለውን ግለሰብም ምንም ጨዋታ እንዳይመለከት አግዶታል። በኢንተር ሚላን አጥቂ ሮሜሉ ሉካሉ የዘረኝነት ድምፆችን አሰምቷል ተብሎ የነበረው ካሊጋሪ ክለብ ነፃ ተደርገዋል። ይህ ክለብ በባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የዘረኝነት ጥቃቶች ጋር በተያያዘ ሦስት ጊዜ ምርመራ ተከፍቶበት ነበር።
news-56480599
https://www.bbc.com/amharic/news-56480599
የዩናይትድ ኪንግደም ቤተ-መንግሥት ከቀረበበት ወቀሳ በኋላ ‘የብዝሃነት’ ፖሊሲዬን እየመረመርኩ ነው አለ
የንግስት ኤሊዛቤት ይፋዊ መኖሪያ የሆነው ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት በንጉሳውያን መኖሪያዎች ውስጥ የብዝሃነት ፖሊሲዎችን እየመረመርኩ ነው አለ።
ንግስት ኤሊዛቤት ይህ ምርመራ የሚካሄደው የንጉሳዊያኑ ቤተሰብ መኖሪያ በሆኑት በባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት፣ ክሌሬንስ ሃውስ እና ኪንግስተን ቤተ-መንግሥቶች ውስጥ ብዝሃነትን ለማሻሻል ነው ተብሏል። ምንጮች እንደሚሉት ቤተ-መንግሥቱ ከዚህ ቀደምም ቢሆን ብዝሃነትን ለማስፋት ፖሊሲዎች፣ አሰራሮች እና ፕሮግራሞች ቢኖሩትም በሚፈለገው መጠን ለውጥ አልመጣም። ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት የብዝሃነት ፖሊሲዬን ላጤን ነው ያለው፤ ልዑል ሃሪ እና ባለቤቱ ሜጋን በቤተ-መንግሥቱ ውስጥ ዘረኝነት አለ የሚል ቅሬታ ካሰሙ በኋላ ነው። ልዑል ሃሪ እና ከጥቁር እናት የተገኘችው ባለቤቱ ሜጋን ከኦፕራ ዊንፍሬይ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ የተረገዘው ልጅ ሲወለድ የቆዳ ቀለሙ ምን ያክል ጥቁር ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ቀርቦላቸው እንደነበረ ተናግረዋል። ጥንዶቹ ይህን እስተያየት ማን እንደሰጠ ያሉት ነገር ባይኖርም ልዑል ሃሪ ግን ንግስት ኤሊዛቤት ወይም የንግስቷ ባለቤት ልዑል ፊሊፕ ይህን አስተያየት አለመስጠታቸውን ለኦፕራ አረጋግጧል። የጥንዶቹ ቃል-መጠይቅ ለንጉሳዊያኑ ቤተሰብ አስቸጋሪ ሁኔታን የፈጠረ ነበር ተብሏል። ለዚህም ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት ጉዳዩን በአጽንኦት ተመልክቶ እና ‘ቤተሰቡ በግል መፍትሄ ይሰጥበታል’ ብሎ ነበር። ይህ የብዛህነት ምርምራ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ማህበረሰብ አባላት፣ አካል ጉዳተኞች እና የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን የቤተ-መንግሥቱ አካል እንዲሆኑ ይጥራል ተብሏል። የብዝሃነት ጉዳይንም ለመመርመር ቤተ-መንግሥቱ ገለልተኛ የሆነ አካል አመለካከትን የምርመራው አካል ለማደረግ ቁርጠኛ ነውም ተብሏል። ይህ የብዝሃነት ምርመራ “የብዝሃነት አለቃ” የሚል ማዕረግ ያለው ግለሰብ ቅጥርንም ሊያስተዋውቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።
54183501
https://www.bbc.com/amharic/54183501
የኬንያ ፖሊሶች የደንብ ልብሳችሁን ገዝታችሁ ልበሱ ተባሉ
በኬንያዋ መዲና የሚገኙ ፖሊሶች የደንብ ልብሳቸውን በራሳቸው ወጪ በመግዛት ላይ ናቸው።
ፖሊሶቹ ከሰኞ ጀምሮ የተቀየረውን የመለዮ ልብስ (ዩኒፎርም) መልበስ እንዳለባቸው የተነገራቸው ሲሆን በገበያውም ላይ የአቅርቦት ችግር እንደተፈጠረም የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል። አንዳንድ ፖሊሶች አዲሱን የደንብ ልብስ ሳይለብሱ በቀድሞው መምጣታቸውን ተከትሎ ወደቤታቸው እንዲመለሱ መደረጋቸውንም የአገሪቱ ጋዜጦች ደይሊ ኔሽንና ስታንዳርድ በዘገባቸው አስነብበዋል። ብሄራዊ የፖሊስ አገልግሎት እንዲሁም የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ለሪፖርቱ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። በዘገባው ላይ ዋቢ የተደረጉት ፖሊሶች እንደተናገሩት ልብስ ሰፊዎች ጋር ሄደው እንዲያሰፉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። መንግሥት ለአዲሱ ደንብ ልብሳቸው ወጪያቸውን ሳይሸፍን የቀረ ሲሆን ልብስ ሰፊዎቹም ወደ 2 ሺህ ብር ገደማ እንዳስወጣቸውም ደይሊ ኔሽን ዘግቧል። አዲሱን መመሪያ ተከትሎም አንዳንድ ፖሊሶች የደንብ ልብሱን ለመግዛት አቅም ያጥረናል በሚልም ቤታቸው ቀርተዋል። አዲሱ ሰማያዊ መለዮ ልብስ ከሁለት አመት በፊት ነበር የፖሊስ እንዲሆን የተወሰነው።
news-52357581
https://www.bbc.com/amharic/news-52357581
ኮሮናቫይረስ፡ ፖለቲካዊ አለመግባባት የሰውን ህይወት ለማዳን የሚደረገን ጥረት እንዳያደናቅፍ ዶ/ር ቴድሮስ አስጠነቀቁ
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር ዶክትር ቴድሮስ አድኃኖም በፖለቲካዊ አለመግባባት ሳቢያ የሰውን ህይወት ለማዳን የሚደረገው ጥረት ሊደናቅፍ እንደሚችልም አስጠነቀቁ።
ከአሜሪካ ጋር አለምግባባት ውስጥ ስለገባው ድርጅታቸው በተመለከተ ዶክተር ቴድሮስ በስሜት ተሞልተው በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት "በዓለም የጤና ድርጅት ውስጥ ምንም ምስጢር የለንም፤ የህይወት ጉዳይ በመሆኑ መረጃን ባገኘን ጊዜ ሁሉ እናጋራለን" ሲሉ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረውም "ከየት እንደመጣሁ ታውቃላችሁ፤ ስለጦርነት አውቃለሁ። ድህነትንም አውቃለሁ። ሰዎችን ለስቃይ ስለሚዳርጉ ነገሮች አውቃለሁ። ሰዎች እንዴት በድህነት ምክንያት ለሞት እንደሚዳረጉ አውቃለሁ" ሲሉ በስሜት ተናግረዋል። "ይህን ሁሉ የማያውቁ ይኖራሉ. . . በቀላል የህይወት ጎዳና ላይ አልፈው ይሆናል። ምናልባትም ጦርነት ማለት፤ ድህነት ማለት ምን እንደሆኑ ላያውቁ ይችላሉ። ለዚህም ነው ስሜታዊ የሆንኩት" ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ድርጅታቸው የኮሮናቫይረስን የተመለከተ ምንም አይነት መረጃ ከየትኛውም አገር አለመደበቁን በዘርዝር አብራርተዋል። ዶክትር ቴድሮስ በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው ላይ እንዳሉት ከአሜሪካ የበሽታ መቆጠጠሪያና መከላከያ ማዕከል የተወከሉ 15 ባለሙያዎች ከጥር ወር ጀምሮ ስለበሽታው ያሉ መረጃዎችን በሙሉ እንዲያውቁ ሲደረጉ ቆይተዋል ብለዋል። ትራምፕ ድርጅቱን በግልጽ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በአግባቡ አልያዘውም ከማለታቸው በተጨማሩ ለቻይና ወገንተኛ ሆኗል በማለት ሲተቹ ቆይተዋል። የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አያያዙን በተመለከተ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተደጋጋሚ ሲተች የቆየ ሲሆን፤ ባላፈው ሳምንትም አሜሪካ ለድርጅቱ ታበረክት የነበረውን የገንዘብ አስተዋጽኦ ማገዳቸው ይታወሳል።
44223275
https://www.bbc.com/amharic/44223275
የዳቦና የወተት እጥረት በአዲስ አበባ
ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአዲስ አበባ የዳቦ መጋጋሪያና ማከፋፈያ ደጃፎች ረጃጅም ሰልፎችን ሲያስተናግዱ ሰንብተዋል።
በሌላ በኩል የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ መደብሮችም ከሁለት በላይ የታሸጉ ወተቶችን እንደማይሸጡ የሚደነግጉ ማስታወቂያዎችን ለጥፈው ተስተውለዋል፥ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ችግሩ ባለፈው ሚያዝያ ወር ቢስተዋልም በያዝነው ግንቦት ወር ግን ተቀርፏል ባይ ነው። በመዲናይቱምና በሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎችም የትንሳዔ በዐልን ተከትሎ የሚፈጠረውን ከፍተኛ ፍላጎት ማስተናገድ የሚችል ምርት ማቅረብ ካለመቻሉ ጋር በተያያዘ፤ የወተት እጥረት ማጋጠሙ እንግዳ እንዳልሆነ በአንድ ወተት ማቀነባበር እና ማሰራጨት ስራ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ኃላፊ ይናገራሉ። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኤልያስ በየነ ችግሩን ያባበሰ ሌላ ምክንያትን ጨምረው ያነሳሉ፤ የስንዴ አቅርቦት እጥረት። የአቅርቦት እጥረቱ ከመንግስት የድጎማ ስንዴ የሚያገኙ ዳቦ መጋገሪያዎችን ከምርታቸው እስከ ግማሽ የሚደርስ ያህሉን እንዲቀንስ ከማስገደዱም በተጨማሪ በእንስሳት መኖ ምርት ላይም ጫና አሳርፏልም ይላሉ። "ባለፈው ሚያዚያ ወር በመንግስት ድጎማ ከሚቀርቡ የሸቀጦች አንዱ የሆነው የስንዴ ምርት፤ መንግሥት በሚያቀርበው ልክ በተሟላ መልኩ ባለመቅረቡ ችግር ተከስቷል" ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩት አቶ ኤልያስ እጥረቱ "በተወሰኑ በድጎማ ላይ በተመሰረቱ ፋብሪካዎች ላይ" ጫና ማሳደሩንና ይህም በዳቦ ከገበያ መጥፋት መተርጎሙን ያስረዳሉ። ዳቦው በሚገኝበት ጊዜ ዋጋው ጨምሮ እና መጠኑ አንሶ እንደሚገኝ አስሩን ክፍላተ ከተማዎቹ ተዟዙሮ ያጠናው የንግድ ቢሮው ግብረ ኃይል እንደደረሰበትም አቶ ኤልያስ ይገልፃሉ። "መንግስት የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ህይወት ለማቅለል እና የኑሮ ውድነቱን ለማስታገስ የሚያቀርበው የድጎማ ምርት ጊዜን ጠብቆ መድረስ ነበረበት። ከግዥ ጋር ተያይዞ ትንሽ የመዘግየት ሁኔታ ሲከሰት፥ ችግሩ እንደሚፈጠር ይታወቃል" ይላሉ አቶ ኤልያስ። እርሳቸው የስንዴ አቅርቦት እጥረቱ ከግዥ ስርዓት ጋር እንደሚያያዝ ይናገሩ እንጅ፤ የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አገልገሎት ዋና ዳይሬክቶር የሆኑት አቶ ይገዙ ዳባ ግን የአቅርቦት ችግር ለዳቦ እጥረት ምክንያት ሆኗል በሚለው አስተያየት አይስማሙም። አቶ ይገዙ መስሪያ ቤታቸው ግዥውን ያከናወነበት አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ጅቡቲ ወደብ ላይ ይገኝ እንደነበርና የስንዴ እጥረት ተከስቶ ቢሆን ኖሮ ፤ እርሱን በአስቸኳይ ወደአገር ውስጥ ማስገባት ይቻል እንደነበር ይከራከራሉ። "ችግሩ ቢኖር ኖሮ ይህንን በአስቸኳይ ወደ አገር ውስጥ አስገብቶ ችግሩን በአስቸኳይ ለመፍታት የሚቻልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችል ነበር። ተገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ አለን" ሲሉ ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ተጨማሪ ግዥዎች መኖራቸውን አይደብቁም። "ያም ሆነ ይህ የስንዴ ችግርን በአስቸኳይ ለመፍታት ከዚህ በፊት አራት መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን ገዝተን ነበር፤ ከዚህ በተጨማሪ ሁለት መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን (ሁለት ሚሊየን ኩንታል) በአስቸኳይ እንዲገባ ፕሮሚሲንግ ከሚባል ድርጅት ጋር ውል ተፈራርመናል" ይላሉ አቶ ይገዙ። የፊታችን አርብ በሚከፈት ሌላ ጨረታ የሁለት መቶ ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሚፈለገውን ምርት ስርጭት ተግባራዊ ከማድረግም በዘለለ ከዱቄት እና ዳቦ አምራቾች ጋር ውይይት አድርጌያለሁ ይላል። የስርጭት ችግር፣ የዳቦ እጥረቱን ዘለግ ላለ ጊዜ እንዲቆይ ሳያደርገው እንዳልቀረ የሚገምቱት አቶ ኤልያስ፤ "አጋጣሚውን ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት" ተጠቅመውበታል የተባሉ አምራቾች እና ነጋዴዎች መደብሮች መታሸጋቸውን ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሌላ በኩል መንግሥት ስንዴ ከውጭ እየገዛ ድጎማ ያስፈልጋቸዋል በሚል በርካሽ ዋጋ ማቅረቡ የአገር ውስጥ ምርታማነትን አያበረታታም ሲሉ የሚከራከሩት በጉዳዩ ላይ ጥናት ያካሄዱት የምጣኔ ኃብት ባለሞያው ዶክተር ደምስ ጫንያለው ናቸው። በተፈጥሯዊ የአየር ሁኔታ ምክንያቶች በአገር ውስጥ ምርት ፍላጎትን ሙሉ በሙሉ መሸፈን የማይቻልበት አጋጣሚ ሲፈጠር፤ የአገሪቱን የምግብ ዋስትናን ለማስጠበቅ ከውጭ ሃገራት ግዥን መፈፀሙ የሚጠበቅ ብሎም የሚወደስ ተግባር መሆኑን የሚያነሱት ዶክተር ጫንያለው፥፤ ለዚህም ከሦስት ዓመት ገደማ በፊት አንስቶ ኤል ኒኖ የሚል ስያሜ በተሰጠው ተፈጥሯዊ የአየር መዛባት ምክንያት የተከታታይ ወቅቶች የዝናብ እጥረት ባጋጠመበት ወቅት የተወሰደውን መንግስታዊ የግዥ እርምጃ በአብነት ያነሳሉ። ሆኖም ይህ ነው የተባለ መሰል የምርታማነት ችግር በሌለበት ጊዜ ሁሉ ስንዴን ከውጭ የማስገባት እንቅስቃሴ እንደፖሊሲ የሚያዝ መሆን የለበትም ባይ ናቸው። "መደጎምም ካለበት ከእኛው ገበሬዎች ነው መገዛት ያለበት" ሲሉ ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት፤ ከውጭ በሚገዙ ምርቶች ዘንድ የአስፈላጊነት ቅደም ተከተል እንዲፈጥር አድርጎታል። ስንዴ እንደሌሎች ስኳርን እንደመሳሰሉ መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶች ሁሉ ቅድሚያን ማግኘቱ የሚጠበቅ መሆኑን የምጣኔ ኃብት ባለሞያው ዶክተር ደምስ ይገልፃሉ። ስንዴን ከውጭ ከመግዛት ጋር በተያያዘ አሁን በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ደንቃራ ፈጥሮ እንደሁ የተጠየቁት የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኃላፊው አቶ ይገዙ በአሉታ ይመልሳሉ። "ምክንያቱም ስንዴውን በምንገዛበት ወቅት የስድስት ወር የዱቤ አገልግሎት አለ። ገንዘቡን የምንከፍለው ስንዴው ከገባ ከስድስት ወር በኋላ ነው። ስንዴው ከገባ በኋላ ክፍያ ላይ የሚያጋጥም ነገር ካለ ያኔ የሚታይ ነው የሚሆነው። " ብለዋል።
news-57298244
https://www.bbc.com/amharic/news-57298244
በካናዳ የተገኘው የ215 ህፃናት ጅምላ መቃብር ቁጣን አስነሳ
ከሰሞኑ የ215 ህፃናትን አፅም የያዘ የጅምላ መቃብር መገኘቱን ተከትሎ በካናዳ የሚገኙ የቀደምት ህዝቦች ማህበራት አገር አቀፍ ፍለጋው እንዲጀመር ጠይቀዋል፤ ቁጣቸውንም እየገለፁ ነው።
የቴኬኤምሉስፕ ቴ ሴክዌፑምክ ቀደምት ህዝቦች መሪ በያዝነው ሳምንት እንዳሳወቁት የህፃናቱ አፅም የተገኘበት ስፍራ የቀድሞ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲሆን የተቋቋመውም ቀደምት ህዝቦችን ወደ ነጭ ባህል ለማላመድ በሚል አላማ ነው። የህፃናቱ አፅም የተገኘው ካምሎፕስ ኢንዲያን በተባለ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲሆን ትምህርት ቤቱ በአውሮፓውያኑ 1978 ተዘግቷል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች የቀደምት ህዝቦች ልጆች በአዳሪነት ይማሩባቸው የነበሩ ናቸው። ከአውሮፖውያኑ 1863-1998 150 ሺህ የሚሆኑት እነዚህ ህፃናት ከቤተሰቦቻቸው በአስገዳጅ ሁኔታ ተወስደው በነዚህ ትምህርት ቤቶች ይማሩ ነበር። በራሳቸው ቋንቋ መናገርም ሆነ ባህላቸውን እንዲከተሉ አይፈቀድላቸውም ነበር፤ ከፍተኛ ጥቃቶችንም አስተናግደዋል። የጅምላ መቃብር መገኘቱ በርካቶችን ያስቆጣ ሲሆን ብዙዎችም በጊዜያዊነት በተሰራው የህፃናቱ መታሰቢያ ላይ ትንንሽ ጫማዎችን በማስቀመጥ ለማስታወስም ሞክረዋል። የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እንደሚረዱ ቃል ቢገቡም ዝርዝር ከመስጠት ተቆጥበዋል። "እንደ አባት ልጆቼ በአስገዳጅ ሁኔታ መወሰድን ማሰብ ይከብዳል" በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። አክለውም "እንደ ጠቅላይ ሚኒስትርም የቀደምት ህዝቦችን ህፃናትን ከማህበረሰቡ በመስረቅ ላይ የተመሰረተው ይህ የማላመድ ፖሊስ ምን ያህል አሳፋሪ እንደሆነ ልገልፅ እፈልጋለሁ" ብለዋል። ጀስቲን ትሩዶ ከሪፖርተሮች መንግሥታቸው ምን ያደርጋል? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ጠንከር ያለ እርምጃ እወስዳለሁ ቢሉም ዘርዘር ያለ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የቀደምት ህዝቦች ጉባኤ ብሔራዊ መሪ ፔሪ ቤልግሬድ ባወጡት መግለጫ ቤተሰቦች እውነታውን ማወቅ እንደሚገባቸውና ከሃዘናቸውም ለማገገም እድሉን ሊያገኙ ይገባል ብለዋል። "በቀድሞ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ ምርመራዎች ቢካሄዱ በህዝቦቻችን ላይ የደረሱ በርካታ የዘር ጭፍጨፋዎችን እውነታ እንረዳለን" በማለት ፔሪ ገልፀዋል። የህፃናቱን የጅምላ መቃብር መገኘት ተከትሎ በቻርሎቴ ታውን በተባለችው ግዛት የመጀመሪያ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆን ኤ ማክዶናልድ ሃውልት ተገርስሷል። ማክዶናልድ በነዚህ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ በነበራቸው ከፍተኛ ሚናም ነው ተቃዋሚዎች ሃውልቱን ኢላማ ያደረጉት። ካምሉፕስ ኢንዲያን አዳሪ ትምህርት ቤት የነጮችን ባህል ለማላመድ ከተከፈቱ ትምህርት ቤቶች መካከል ትልቁ ነው። በሮማን ካቶሊክ አስተዳደር የበላይነትም ሲሆን የተከፈተው ወቅቱም በአውሮፓውያኑ 1890 ነው። የተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው በተባለበት በአውሮፓውያኑ 1950ዎቹ 500 ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግድ ነበር። ማዕከላዊው መንግሥት በአውሮፓውያኑ 1969 የማስተዳደሩን ሁኔታ ከተቀበለ በኋላ ለአካባቢው ተማሪዎች እንደ አዳሪ ትምህርት ቤት ይገለገሉበት የነበረ ሲሆን በ1978ም ተዘግቷል።
54769256
https://www.bbc.com/amharic/54769256
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ
የኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ለስድስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።
የኢፌድሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ፣ ጥቅምት 25/2013 ባደረገው አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ መንግሥት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93/1/ሀ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን አስታውቋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት መግለጫ አክሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ እንደሚሆን አስታውቆ ይህንን አዋጅ የሚያስፈፅም በኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉት ግብረኃይል መቋቋሙን ገልጿል። ግብረኃይሉ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረሀይል" ተብሎ ይጠራልም ተብሏል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መደንገግ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዳም የሀገርን ሰላምና ሕልውና፣ የሕዝብንና የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ እና ሀገሪቷን ወደ ሁከትና ብጥብጥ የሚወስዱ ማናቸውንም ድርጊቶችን የመከላከል ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጿል። አክሎም በትግራይ ብሔራዊ ክልል ውስጥ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን እንዲሁም የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ አደጋ ላይ የሚጥሉ በተለይም የአገርን ሉዐላዊነት የሚገዳደሩ፣ የፌደራል መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት በክልሉ እንዳይወጣ እና ሀገሪቷን የጦር አውድማ የሚያደርጉ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎችን ጭምር በመጣስ በርካታ ሕገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀሙ ናቸው ብሏል። ይህን ሁኔታ በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የማይቻልበት ደረጃ ላይ መደረሱን የገለፀው መግለጫው በሕገ መንግሥቱ በተደነገገው መሠረት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ ልዩ እርምጃዎችን መውሰድ የሚያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደንገግ እና ተግባራዊ በማድረግ ሁኔታውን መቆጣጠር በማስፈለጉ አዋጁ መታወጁን ገልጿል። አዋጁ በመላው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ተፈፃሚ የሚደረግ ሲሆን፣ እንደያስፈላጊነቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚ ወይም ቀሪ የሚሆንባቸውን ተጨማሪ አካባቢዎችነ ግብረኃይሉ በሚያወጣው በመመሪያ ይወስናል ተብሏል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በ2/3ኛ ድምፅ መፅደቅ አለበት።
news-54748700
https://www.bbc.com/amharic/news-54748700
ቱርክና ግሪክ በከፍተኛ ርዕደ መሬት ተመቱ
ቱርክና ግሪክ ክፉኛ በሚባል ርዕደ መሬት ተመቱ። ርዕደ መሬቱ የተከሰተው በቱርክ አጊያን የባህር ዳርቻ በኩልና፣ በሰሜናዊዋ የግሪኳ ሳሞስ ደሴት ነው ተብሏል።
በቱርኳ ኢዝሚር ግዛት 7 ሬክተር ስኬል የርዕደ መሬቱን መለካቱን የአሜሪካው የስነ ምድር ጥናት አስታውቋል። ቱርክ በበኩሏ ርዕደ መሬቱ 6.6 ሬክተር ስኬል መሆኑን ያሳወቀች ሲሆን በዚህም አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 120 ሰዎችም ተጎድተዋል። በዚችው ግዛት 20 ህንፃዎች ፈራርሰዋል። ርዕደ መሬቱ በተወሰነ መልኩ ጎርፍና የሱናሚ አውሎ ንፋስንም አስከትሎ ኢዝሚርና ሳሞስ ደሴትን አጥለቅልቋቸዋል። ርዕደ መሬቱ በከተሞቹ መዲኖች አቴንስና ኢስታንቡል ድረስ የዘለቀ ሲሆን ጥልቁቱም 10ኪሎሜትር ነው ተብሏል። ቱርክ በበኩሏ ወደታች 16 ኪሎሜትር የዘለቀ ነው ብላለች። ለርዕደ መሬት ተጋላጭ በሆኑት ቱርክና ግሪክ በርካታ ጊዜ የሚያጋጥም የተፈጥሮ ክስተት ነው። በቱርኳ ሶስተኛ ታላቅ ከተማ ኢዝሚር በተፈጠረውም ርዕደ መሬት በርካቶች ደንግጠው በጎዳናዎች ላይ ሲሮጡ ታይተዋል። በርካታ ፎቆች ያሉት ህንፃም ተደረማምሶ ሲፈርስ የሚያሳይ ቪዲዮም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መውጣቱን የቢቢሲ ጋዜጠኛ ኦርላ ጉሪን ከቤይሩት ዘግባለች። በሌላኛው ቪዲዮ ላይ ደግሞ የከተማይቱ ነዋሪ ዘመድ ወዳጆቻቸውን በፍርስራሾች ውስጥ ሲፈልጉ ያሳያል። ከዚህም በተጨማሪ ርዕደ መሬቱ ባስከተለው ጎርፍ የተነሳ ባህሩ ከፍ በማለቱም አሳ አጥማጆች በባህር መጥፋታቸው ተነግሯል። በግሪክ ሱናሚ ባስከተለው ጎርፍ በሳሞስ ደሴት የሚገኙ በርካታ ህንፃዎች ፈርሰዋል ወይም ለጉዳት ተደርገዋል። የደሴቲቷ ነዋሪዎች ከባህር ዳርቻዎች ራቅ እንዲሉም ተነግሯቸው ነበር። በዛሬው እለት የተከሰተው ርዕደ መሬት በሌላኛው የግሪክ ደሴት ክሬት ደርሷል ተብሏል። በተደረማመሱና በፈራረሱ ህንፃዎችም ውስጥ የጠፉ ሰዎችን ሲፈልጉ የሚያሳዩ ቪዲየዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ወጥተዋል። በጥር ወርም በቱርኳ ምስራቃዊ ግዛት ኤላዚግ በደረሰ ርዕደ መሬት 30 ሰዎች ሲሞቱ 1 ሺህ 600 ተጎድተዋል። በ2019 የግሪኳ መዲና አቴንስ በደረሰ ርዕደ መሬት ከተማይቷ ተናውጣ ነበር። በ1999 በቱርኳ ኢዝሚት በደረሰው ርዕደ መሬት 17 ሺህ ሰዎች ሞተዋል።
news-54231259
https://www.bbc.com/amharic/news-54231259
ሱዳን ከአሜሪካ ጋር ለመደራደር ልዑኮቿን ወደ ዱባይ ላከች
ሱዳን ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ለመደራደር ከፍተኛ ልዑኮች ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መላኳን አስታወቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮና የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ። [ፖምፔዮ ወደ ሱዳን በመጡበት ወቅት] በአሜሪካ ለሽብር ድጋፍ የሚያደርጉ አገራት ዝርዝር ውስጥ ለመውጣት ሱዳን ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። ከዚህ ቀደም የነበረው የአል-በሽር መንግሥት ከአሜሪካ ጋር የነበረው ግንኙነት መልካም የሚባል አልነበረም። አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት አሜሪካ ሸብርን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውስጥ ትፍቀኛለች ብሎ ተስፋ አድርጓል። ይህ ማለት ሱዳን እጅግ የተጠማችውን ዓለም አቀፍ ብደር እና የውጭ ኢንቨስትመንት ማግኘት ትችላለች። የሱዳን ልዑክ በሽግግር ምክር ቤቱ ሊቀ-መንበር እና የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ በሆኑት ሉቴናንት ጄነራል አብዱል ፋታህ አል-ቡርሃን የሚመራ ሲሆን ልዑኩ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በምን ጉዳዮች ሊያወራ እንደሚችል በይፋ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ የሱዳን እና የአሜሪካ ልዑኮች በዩናይትድ አረብ ኤሜሬቶች በሁለት ጉዳዮች ላይ ሊነጋገሩ እንደሚችሉ ይታመናል። ሱዳንን ለአሸባሪዎች ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት ዝርዝር ውስጥ ለመፋቅ ሱዳን መክፈል ስላለባት ካሳ እንዲሁም ከእስራኤል ጋር ግንኙነትን ማሻሻል የሚሉት አይቀሬ አጀንዳዎች ናቸው የሚሉት በርካቶች ናቸው። አሜሪካ ከዚህ ለሽብር ድጋፍ የሚያደርጉ አገራት ከሚለው ዝርዝር ውስጥ ሱዳንን የማስወጣው ሱዳን በሽብር ጥቃቶች ጉዳት ለደረሰባቸው አሜሪካውያን 330 ሚሊዮን ዶላር መክፈል ስትችል ነው ትላለች። ከዚህ በተጨማሪ የትራምፕ አስተዳደር ለመካከለኛው ምስራቅ ስላምን ለማምጣት እስራኤል ከአረቡ ዓለም ጋር ያላትን ግነኙነት የምታሻሽልበት ስምምነት ማምጣት ትልቁ አጀንዳቸው ነው። በትራምፕ እቅድ ውስጥ ሱዳን የዚህ አንድ አካል እንደምትሆን ይገመታል። ባለቤትነቱ የሱዳን መንግሥት የሆነው ሱና የዜና ወኪል በሉቴናንት ጄነራል አብዱል ፋታህ የሚመራው ልዑክ ወደ ኤሜሬቶች የመራው ሱዳን ለሽብር ድጋፍ ከሚያደርጉ አገራት ዝርዝር ስለምትወጣበት መንገድ ለመምከር ነው ሲል ዘግቧል። የአሜሪካው አክሲዎ በበኩሉ በኢሚሬቶች መዲና አቡ ዳቢ የሚደረገው ድርድር ዋነኛ አጀንዳ በእስራኤል እና ሱዳን መካከል ግነኙነትን ማሻሻል ላይ ያተኮረ ነው ሲል ዘግቧል። የአሜሪካው ልዑክም በመካከለኛው ምስራቅ የብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀነራል ሚጉኤል ኮሬአ የሚመራ መሆኑን አክሲዮ ጠቅሷል። በበርካታ ሱዳናውያን ዘንድ ከእስራኤል ጋር ግነኙነት የማሻሻል ሃሳብ አጨቃጫቂ ነው። ቀደም ሲል ሉቴናንት ጄነራል አብዱል ፋታህ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ጋር በኡጋንዳ መገናኘታቸው በሱዳን እስላማዊ ሚሊሻዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር። ከሳምንታት በፊት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ወደ ካርቱም ማቅናታቸው ይታወሳል። ይህም ፖምፔዮን ከረዥም ዓመታት በኋላ አሜሪካን የጎበኙ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ያደርጋቸዋል። በፖምፔዮ ጉብኝት ወቅት የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አበደላ ሃምዶክ የሚመሩት የሽግግር መንግሥት ከእስራኤል ጋር ግንኙነትን በማሻሻል ጉዳይ ላይ ለመወያየት ሕጋዊ ስልጣን የለውም ብለው ነበር። አሜሪካ ሱዳንን በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያካተተችው እአአ 1993 ሲሆን ለዚህም ከምክንያቶች መካከል አንዱ የቀድሞ የአል-ቃኢዳ መሪ ኦሳማ ቢን ላደን በሱዳን ለአምስት ዓመታት መኖሩ ነው።
48565780
https://www.bbc.com/amharic/48565780
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የእግር ኳስ ተጫዋቹ ኦዚል ሚዜ ሆኑ
ጀርመናዊው የእግር ኳስ ኮከብን የቱርኩ ፕሬዝዳንት ጣይጵ ረሲፕ ኤርዶጋን ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው፣ ጎንበስ ቀና በማለት ሚዜ ሆነው ሞሸሩውታል።
ፕሬዝዳንት ኤርዶጋ እና ባለቤታቸው ኤሚኔ ከአዲስ ተጋቢዎቹ ጋር ቆመው ባለፈው ዓመት የዓለም ዋንጫ ከመካሄዱ በፊት ቱርካዊው ኦዚል ከፕሬዝዳንቱ ጋር ፎቶ ተነስቶ በመታየቱ የጀርመን መገናኛ ብዙኀን አፍ ማሟሻ ሆኖ ነበር። የ30 አመቱ የአርሴናል የመሃል ተጫዋች ከቀድሞዋ የቱርክ ሞዴል ጋር በቦሰፎረስ የባህር ዳርቻ በሚገኝ ቅንጡ ሆቴል ነው ትናንት የተሞሸረው። ጥንዶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በ2017 ሲሆን የእነርሱን ፍቅር ዓለም የሰማውና ፀሐይ የሞቀው ግን በ2018 ነበር። የኦዚል የፍቅር ግንኙነት ሰምሮ በትዳር እንዲታሰር ሲወስኑ ደግሞ ለሚዜነት ያሰቡት ለሀገርም ለዓለምም የገዘፉትን ሰው ነበር። እኚህ ሰው የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ናቸው። • «ሳሸንፍ ጀርመናዊ ስሸነፍ ስደተኛ» ኦዚል • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ኦዚል 'ሚዜ ሆነው ከጎኔ ይቁሙ' ሲላቸው ይሁንታቸውን የሰጡት ያለማቅማማት ነበር። ጀርመናዊው የአርሴናል እግር ኳስ ተጫዋች ሜሱት ኦዚል ከቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በአካል መገናኘቱ በጀርመን ግርግር ማስነሳቱን ቢያውቅም ባለፈው መጋቢት ወር ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ሚዜ እንዲሆኑት ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል። የቻንስለር አንጌላ ሜርኬል ዋና ጸሃፊ ሄልግ ብራውን ባለፈው አመት ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በተመለከተ ለቢልድ ጋዜጣ ሲናገሩ ኦዚል የመምረጥ መብት ቢኖረውም አሳዛኝ ነገር ግን ፈጥሯል ብለው ነበር። ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የታዋቂ ሰዎች ዝግጅት ላይ በተደጋጋሚ ይገኛሉ። በተለይ የምርጫ ዘመቻ ሲኖራቸው ቀዳሚ ምርጫቸው ነው። የኦዚል ሚዜ የሆኑትም ለኢስታንቡል የከንቲባ ምርጫ ሊደረግ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት ነው። ምክንያቱም ፓርቲያቸው ኤኬፒ በጠባብ ውጤት ያሸነፈበት ምርጫ ዓለም አቀፍ ውግዘት ስለደረሰበት ተሰርዟል። ባለፈው አመት ምንድን ነው የሆነው? ከቱርካዊ እናትና አባቱ ጀርመን ውስጥ የተወለደው ኦዚል ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ በተጫወተበት በ2014ቱ የዓለም ዋንጫን ጀርመን እንድታነሳ ጉልህ ድርሻ አበርክቷል። ከ2011 ጀምሮም የብሔራዊ ቡድኑ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች በማለትም ለአምስት ተከታታይ አመታት ደጋፊዎቹ መርጠውታል። • እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ? ነገር ግን ባለፈው አመት የሩሲያው አለም ዋንጫ ከመካሄዱ በፊት ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ጋር ፎቶ ተነስቶ በመታየቱ "የዚህ ልጅ ታማኝነት ለየትኛዋ ሃገር ነው" በማለት በጀርመን ትልቅ ውዝግብ አስነስቶ ነበር። በተለይ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ዙር ከአለም ዋንጫው ሲሰናበት ትችቱ በርትቶበት ነበር። ከዚህ በኋላም ኦዚል ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን የሚገልጽ ረጅም ሃተታ ጽፎ ተሰናብቷል። ዛቻና ስም ማጥፋት የተቀላቀለ ኢሜይል ደርሶኛል ያለው ኦዚል ከዓለም ዋንጫው ለመባረራቸውም ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ መቆጠሩ እንዳበሳጨው ተናግሯል። • ትኩረት እየሳበ የመጣው የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫ "ስናሸንፍ ጀርመናዊ ፣ ስንሸነፍ ደግሞ ስደተኛ እሆናለሁ" በማለት ምሬቱን የገለጸው ኦዚል ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ስኬታማ ጉዞ ቢኖረውም በደጋፊዎቹ ዘንድ የተሰጠው አስተያየት ግን ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር እስከመጨረሻው እንዲለያይ አድርጎታል።
news-48029400
https://www.bbc.com/amharic/news-48029400
ከ27 ዓመታት በኋላ ከ'ኮማ' የነቃችው ሴት
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዜግነት ያላት አንዲት ሴት በአውሮፓውያኑ 1991 ላይ ባጋጠማት የመኪና አደጋ ኮማ ውስጥ ገብታ (ዘለግ ላለ ጊዜ አእምሮን ስቶ መቆየት) ቢሆንም ተአምራዊ በተባለ ሁኔታ ከ27 ዓመታት በኋላ መንቃቷ ተሰምቷል።
ሙኒራ አብደላ የመኪና አደጋው ሲያጋጥማት የ32 ዓመት ወጣት የነበረች ሲሆን በወቅቱ እሷ ትጓዝበት የነበረው ተሽከርካሪ ከሕዝብ ማመላለሻ መኪና ጋር ተጋጭቶ ከባድ የጭንቅላት ጉዳት አጋጥሟት ነበር። አደጋው ሲደርስ ወንድ ልጇን ከትምህርት ቤት ለመቀበል እየሄደች ነበር። • በህክምና ስህተት የመከነው ህፃን • የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች ኦማር ዊቤር እናቱ የመኪና አደጋ አጋጥሟት ኮማ ውስጥ ስትገባ ገና የአራት ዓመት ጨቅላ ነበር። ተሽከርካሪው ውስጥ አብሯት ተቀምጦም ነበር። ነገር ግን እሱ በአደጋው ምንም ጉዳት ሳይደርስበት መትረፍ ችሏል። ''እስከዛሬ ድረስ ተስፋ አልቆረጥኩም። አንድ ቀን እንደምትነቃ አስብ ነበር። የእናቴን ታሪክ ማጋራት የፈለግኩትም ሰዎች በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባቸው ለማስተማር በማሰብ ነው'' ይላል ኦማር። ''እናቴ አደጋው በደረሰበት ወቅት እኔን ከአደጋው ለመከላከል በማሰብ ጥብቅ አድርጋ አቅፋኝ ነበር'' ሲልም ተናግሯል። ሙኒራ አብደላ የደረሰባት ጉዳት እጅግ ከፍተኛ ስለነበር የተሻለ ህክምና እንድታገኝ በሚል ወደ እንግሊዝ መዲና ለንደን ተወስዳ ነበር። ነገር ግን ምንም አይነት ለውጥ ማሳየት ስላልቻለች ወደ ሀገሯ እንድትመለስ ተደረገ። በመጨረሻም በ2017 ከአቡዳቢ መንግሥት በተገኘ ድጋፍ ወደ ጀርመን ሄዳ ህክምናዋን እንድትከታተል ተደረገ። ጀርመን በነበረችበት ወቅትም የተለያዩ ህክናዎችን ብታደርግም ይሄ ነው የሚባል መሻሻል ሳይታይበት ቀርቷል። ወደ ጀርመን ከተወሰደች ከአንድ ዓመት በኋላ ኦማር ከህክምና ባለሙያዎች ጋር አለመግባባት ውስጥ ይገባና ጭቅጭቅ ይነሳል። በዚህ መሃል እናቱ አንዳንድ የእንቅስቃሴ ምልክቶችን አሳየች። • ከሶስት ሰዎች የተወለደው ህጻን • የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም '' ከህክምና ባለሙያዎቹ ጋር አለመግባባት ሲፈጠር እኔ አደጋ ውስጥ እንደሆንኩ ተሰምቷታል። ለእዛም ነው እንቅስቃሴ ያደረገችው'' ሲል ኦማር ይናገራል። የነቃችበትን ቅጽበት ሲያስታውስም፤ ''ከሦስት ቀናት በኋላ የሆነ ሰው ስሜን ሲጠራ ከእንቅልፌ ነቃሁ። እናቴ ነበረች ስሜን የጠራችው። በደስታ ያደረግኩትን አላውቅም። ያንን ቀን ለብዙ ዓመታት ስጠብቀው ነበር። መጀመሪያ ያወጣችው ቃል ደግሞ የእኔ ስም ነው።'' ሙኒራ አብደላ አሁን 59 ዓመቷ ነው። ወደትውልድ ከተማዋ አቡዳቢ የተመለሰች ሲሆን፤ የማገገሚያና የአጥንት እንዲሁም የሙሉ ሰውነት ማጠንከሪያ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ትገኛለች።
46675440
https://www.bbc.com/amharic/46675440
ዐቢይ አሕመድ ለምን ወደ አምቦ አቀኑ?
ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን የያዘች ሄሊኮፕተር አምቦ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሳይተሰብ አረፈች። የጠቅላይ ሚንስተሩን ጉብኝት ያልተጠበቀ እንደመሆኑ ተማሪዎቹን እጅጉን አስደንቋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በአምቦ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽሕፈት ቤትም ዐቢይ አሕመድ ከተማሪዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተማሪዎቹ እምቅ ችሎታቸውና የወደፊት ዕድሎቻቸውን በመገንዘብ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የሚያነቃቃ መልእክት አስተላልፈዋል ብሏል። • "ሕዝብ እንዲጠይቅ አድርገናል" ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ • በምዕራብ ኦሮሚያ በታጠቁ ኃይሎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተገለፀ በዚህ የዐቢይ አሕመድ አጭር የአምቦ ቆይታ የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው የሮስ ሄዪ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ የማቅረብ ዕድሉን አግኘቶ ነበር። የማለዳውን ጉብኝት በተመለከተም ለቢቢሲ እንደተናገረው ''የጉብኝት በጭራሽ ያልጠበቅነው ነበር" ብሏል። "...እንደተለመደው ከጠዋት ሰልፍ በኋላ ወደ ክፍል ገባን፤ የመጀመሪያውን ክፍለ ጊዜ ከጨረስን በኋላ ጠቅላይ ሚንስትሩ እየመጡ መሆኑን ተነግሮን ሰልፍ የሚወጣበት ሜዳ ላይ ሆነን ጠበቅናቸው።'' ይላል። ጠቅላይ ሚስትሩ ለተማሪዎች ያደረጉት ንግግር ጠቅላል ሲደረግ 'እናንተ [ተማሪዎች] ትምህርታችሁ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጉ፤ ፖለቲካውን ለእኛ ተዉት' የሚል ይመስላል ይላል፣ የሮስ። ተማሪ የሮስ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያነሳላቸው ጥያቄ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርሱ ዕድሜ የሚገኙ እኩዯቹ ላይ የሚብሰለሰል አንኳር ጥያቄን አዝሏል። "ለምን ትከፋፈላላችሁ?" የተማሪውን ፍላጎት ያንጸባረቅኩበት ጥያቄ ነው ያነሳሁላቸው የሚለው የሮስ የጥያቄው ጭብጥ የሚከተለው ነበር፤ ''ለአንድ ሕዝብ የምትታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነታችሁ ለምን ሰፋ? በእናንተ የፖለቲካ ፍላጎት ልዩነት ሳቢያ የኦሮሞ ሕዝብ እየተጎዳ እና እየሞተ ነው ያለው። ይህን ለውጥ እንድንመለከተው የአምቦ ተማሪ ብዙ መስዕዋትነት ከፍሏል። በመንግሥት እና በኦነግ መካከል አሥመራ ላይ የተደረስውን ስምምነት ዝርዝር እንዲሁም አሁን የተፈጠረውን ልዩነት በግልጽ ማወቅ አለብን፤ ብዙዎች መስዋእት የሆኑት እውነትን ፍላጋ ነው፤ አሁንም እውነትን ነው የምንሻው'' ሲል ነበር ጥያቄውን የቋጨው። ይህ የተማሪ የሮስ ጥያቄ የአምቦ ተማሪዎች አእምሮ ላይ ብቻ የሚንከላስ አይደለም። የአካባቢው ነዋሪም ከመጋረጃ ጀርባ እየሆነ ስላለው ፖለቲካዊ ሽኩቻ ፍንጭ እንዲኖረው ይሻል። ዐቢይ አሕመድ አምቦ መሄድ ለምን አስፈለጋቸው? ቢቢሲ ከአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ባገኘው መረጃ እንዳረጋገጠው፤ በከተማዋ ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ተጠርቶ ነበር። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ከዛሬ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ እንዲዘልቅ የታሰበው በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ የተጠራው በከተማዋ ውስጥ በስፋት ተበትኖ በነበረ በራሪ ወረቀት ነው። ዓላማውም ከሰሞኑ በመንግሥትና በኦነግ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት መቃወም ነበር። ኾኖም ስማቸውን የማንጠቅሳቸው አንድ የከተማዋ ነዋሪ የአድማውን ጥሪ አልሰመረም፤ "ሁሉም ወደ ሥራው ወጥቷል'' ይላሉ። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአምቦ በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ሲከናወን ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ የመንግሥት እና የንግድ ተቋማት አገልግሎት አይሰጡም ነበር። ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፍ ተሽከርከሪም እምብዛምም አይስተዋልም። ይህን ጠንቅቆ የሚገነዘበው የከተማዋ ነዋሪ እንዲህ ዓይነት አድማዎች ከመታወጃቸው በፊት ባሉ ቀናት የሚያስፈልገውን መሠረታዊ ፍጆታ ሽምቶ ከቤቱ የማኖር ልማድን አዳብሯል። በዚህኛው የአድማ ጥሪ ግን ይህ እምብዛምም አልተስተዋለም። ምናልባት ክስተቱ ይህ የአድማው ጥሪ በብዙኃኑ ቅቡልነቱ ዝቅተኛ እንደነበር አንድ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ለቢቢሲ አስተያየቱን የሰጠ የአምቦ ከተማ ነዋሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአምቦ ጉብኝት ከተጠራው አድማና ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ያገናኘዋል። ''ጠቅላይ ሚንስትሩ ተቃውሞ ሳይነሳ በፍጥነት ነገሩን ለማብረድ በማሰብ እንደመጡ እናምናለን'' ይላሉ። ተማሪ የሮስንም ከዚሁ የተለየ ግምት የለውም። "እንዲሁ የጠቅላይ ሚንስትሩን ያልተጠበቀው ጉብኝት በአምቦ ሊነሳ የሚችለውን ተቃውሞ ለማምከን ያሰበ ይመስለኛል" ይላል። ''የተማሪው ጥያቄ በመንግሥት እና በኦነግ መካከል ያለው ልዩነት አንድም ጥይት ሳይተኮስ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል የሚል ነው።'' የሚለው የሮስ ''ጠቅላይ ሚንስትሩ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ የማይሰጡ ከሆነ የአምቦ ተማሪ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል ማለት ግን አይደለም።'' ይላል።
news-56417945
https://www.bbc.com/amharic/news-56417945
ቅርስ፡ እስራኤል ውስጥ 'ታሪካዊ' የተባለ ጥንታዊ የብራና ጥቅልና ቅርስ ተገኘ
በእስራኤል በርሃ ውስጥ በሚገኝ ዋሻ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የብራና ጥቅል ስብርባሪዎችና የሌላ ቅርስ ቅሪት መገኘቱን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ባለሥልጣናቱ ግኝቱን "ታሪካዊ" ብለውታል። እነዚህ የተገኙት በርካታ የብራናው ቁርጥራጮች በግሪክ የተጻፈባቸው ሲሆን የእግዚአብሔር ሥም ብቻ በእብራይስጥ ቋንቋ ተጽፎበታል። ይህ የብራና ጥቅል የአይሁድ አማጺያን ሳይሆን እንደማይቀር ይታመናል። የአይሁድ አማጺያን በሁለተኛው ክፍለ ዘመን በሮማ አገዛዝ ላይ ያካሄዱት አመፅ አለመሳካቱን ተከትሎ ወደ ተራሮች ተሰደው ነበር። እነዚህ የብራና ጥቅሎች የተገኙት በአካባቢው ያሉ ዋሻዎችን ከዘረፋ ለመከላከል በተካሄደ ዘመቻ ወቅት ነው። ከአውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ መጀመሪያ ወዲህ እንዲህ ዓይነት ቅርስ ሲገኝ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። የፈጣሪ ሥም የተጻፈበት የብራና ቁራጭ በ1960ዎቹ መጀመሪያ 'አስፈሪ ዋሻ' በመባል በሚታወቀው በዚያው አካባቢ ተመሳሳይ የብራና ቁርጥራጮችና 40 አፅሞች ተገኝተው ነበር። አሁን የተገኘው አዲስ ቅሪት የዘካሪያስና የናሆም መፅሐፍ ጥቅሶችን የያዙ ሲሆን ጥቅሶቹ የ12ቱ ንዑሳን ነብያት በመባል የሚታወቁት መጽሐፍ አካል ናቸው። ቅሪቱ በግሪክ የተጻፈ ሲሆን ቋንቋው የተወሰደው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራተኛው ክፍለ ዘመን ታላቁ እስክንድር የእስራኤሎችን ምድር ከወረረ በኋላ ነው። ይሁን እንጅ የእግዚአብሔር ሥም በእብራይስጥ ቋንቋ በግልጽ ተጽፎ ይገኛል። የእስራኤል የቅርስ ባለሥልጣን ዳሬክተር እስራኤል ሀሰን "ጥቅሉና ሌሎች በሥፍራው የተገኙ ቅርሶች ዋጋቸው የማይተመን ነው" ብለዋል። ከአይሁዶች ሽንፈት ወዲህ እምብዛም ያልተለመዱ ሳንቲሞች፣ 6 ሺህ ዓመታት ያስቆጠረ እንዳይፈርስ የተደረገ የህጻን አጽም እና 10 ሺህ 500 ዓመታት የተቀመጠ ትልቅ ቅርጫትም በቦታው ተገኝቷል። ይህ ዋሻ 80 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። ወደ ዋሻው በቀላሉ መሄድ ግን የማይታሰብ ነው። ወደዚያ መድረስ የሚቻለው ተራራውን እየቧጠጠ መውጣትም ሆነ መውረድ ኢሊያም በገመድ ታስሮ መውረድ መቻልን ይጠይቃል። ጉዞው የአገሪቷ የቅርስ ባለሥልጣን "በጣም ውስብስብና ፈታኝ" ያለው የዋሻዎቹን ስብስብ ከቅርስ ዘራፊዎች ለመጠበቅ የተደረገ ዘመቻ አካል ነበር። በጁዳን በርሃ ተራራዎችና ዋሻዎች በተደረገ ፍለጋ ከአስርተ ዓመታት ወዲህ በዓለማችን የታወቀው የአይሁድ መጽሐፍ [የሙት ባህር ጥቅሎች] እና የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥንታዊ ቅርሶችን የያዘ ግምጃ ቤቶች ተገኝቷል።
news-50954421
https://www.bbc.com/amharic/news-50954421
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ የታገቱት ስድስት ታዳጊዎች ለምን ተገደሉ?
ከጠገዴ ወረዳ ታግተው ከተወሰዱ ስምንት ታዳጊዎች መካከል ስድስቱ መገደላቸውን የጠገዴ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ እሸቴ አረጋዊ ለቢቢሲ አረጋገጡ።
ታዳጊዎቹ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግተው የተወሰዱት ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት አካባቢ ማይዳራ በሚባል ወንዝ አካባቢ ከብት በመጠበቅ ላይ ሳሉ እንደነበረ አቶ እሸቴ ይናገራሉ። እድሜያቸው ከ10-16 የሚሆኑት ታዳጊዎች፤ ከተያዙ በኋላ አጎራባች ወደሆነው ታች አርማጭሆ ወረዳ ተወስደዋል። ታዳጊዎቹ በታች አርማጭሆ ለ9 ተከታታይ ቀናት ታግተው ከቆዩ በኋላ፤ ታህሳስ 19 በጥንድ ታስረው ከስምንቱ ስድስቱ በጥይት ተመተው ተገድለዋል። ከሟች ታዳጊዎቹ መካከል አንደኛው ቤተሰቡን ለመርዳት ሰው ቤት በእረኝነት ተቀጥሮ የሚሰራ ነበር። በሕይወት ከተረፉት ታዳጊዎቹ አንዱ በጥይት ቆስሎ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ወደ ገደል በመንከባለሉ ከአጋቾቹ ማምለጥ ችሏል። መረጃውን ለሚመለከተው አካል የተናገረውም ይሄው ወደ ገደል ተንከባሎ ያመለጠው ታዳጊ መሆኑን አቶ እሸቴ ገልፀውልናል። የጠገዴ እና ታች አርማጭሆ ወረዳ የፀጥታ አካላት የታዳጊዎቹ መጥፋት ጥቆማ ከደረሳቸው በኋላ ፍለጋ ሲያካሂዱ መቆየታቸውን አቶ እሸቴ ያስታውሳሉ። ልጆቹ የተወሰዱት ከጠገዴ ወረዳ በመሆኑ የፀጥታ ኃይሉ ትኩረትም እዚያው አካባቢ ላይ ስለነበር የፀጥታ አካላት በወረዳው ያሉ ቀበሌዎች ሲያስሱ ነበር የቆዩት። "ቦታው ዘወር ያለ ነበር፤ ኮከራ ቀበሌ የሚባል ድሮም 'የሽፍታ መጠጊያ' ይባላል። እዚያ ወስደው ነው የገደሏቸው" ይላሉ አቶ እሸቴ። በመጨረሻም የመገደላቸውን መረጃ የሰሙት፤ ጓደኞቹ ሲገደሉ ወደ ገደል ተንከባሎ በመውደቁ ከግድያው ከተረፈው ታዳጊ ነው። በታዳጊው ላይ ተኩስ ቢከፍቱበትም ማምለጥ በመቻሉ ለፀጥታ ኃይሉ ጥቆማ ሰጥቷል። አቶ እሸቴ ከሞት ከተረፈው ታዳጊ አገኘሁት ያሉትን መረጃ አጣቅሰው፤ ግለሰቦቹ ታዳጊዎቹን ያገቷቸው ወደ ወላጆቻቸው ስልክ እየደወሉ ገንዘብ አምጡ እያሉ በማስፈራራት ገንዘብ ለመቀበል አልመው ነበር። አጋቾቹ አንድ ታዳጊን ለመልቀቅ ከ100 ሺህ ብር በላይ ጠይቀው የነበረ ሲሆን፤ በድርድር 50 ሺህ ድረስ ወርደው እንደነበር መስማታቸውን ኃላፊው ይናገራሉ። በአጠቃላይ ወላጆች ለስምንቱ ህፃናት ከ500 ሺህ እስከ 700 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀው ነበር። ወላጆች ድምጻቸውን ለመንግሥት አካል ከማሰማት በቀር የተጠየቁትን ገንዘብ መክፈል ባለመቻላቸው ልጆቻቸው ተገድለዋል። የ6ቱ ሕፃናት አስክሬን ከሞት ያመለጠው ታዳጊ በሰጠው ጥቆማ መሠረት፤ በፀጥታ አካሉና በማህበረሰቡ ትብብር አስክሬናቸው ከሥፍራው እንዲነሳ የተደረገ ሲሆን፤ ዛሬ በጠገዴ ገብርዔል ቀበሌ፣ ገብርዔል ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ተፈፅሟል። ግድያውን የፈሙትን ግለሰቦች በተመለከተ የጠየቅናቸው አቶ እሸቴ፤ "የወረዳው አሊያም የታች አርማጭሆ ሽፍታ ይባላል፤ እስካሁን ግን እገሌ ተብሎ የታወቀ ነገር የለም፤ እየተጣራ ነው" ብለዋል። በአሁኑ ሰዓት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ተጠርጣሪዎቹን አድኖ ለመያዝ ፍለጋ ላይ እንዳለም አክለዋል። ተደጋጋሚ እየሆነ የመጣው እገታ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር በሚገኙ ሥፍራዎች ውስጥ በተደጋጋሚ ስለሚታገቱ ሰዎች ዜና መስማት የተለመደ ይመስላል። ለዚሁ የእገታ ወንጀል በብዛት ሰለባ ከሚሆኑት መካከል ደግሞ አሽከርካሪዎች ይገኙበታል። አህመድ ይማም የአይሱዙ የጭነት መኪና አሽከርካሪ ነው። አህመድ ከመተማ-ሽንፋ-ፎገራ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሸቀጣ ሸቀጥና ሰሊጥ ያመላልስ እንደነበር ይናገራል። ከሁለት ሳምንት በፊት ከመተማ ተነስቶ ወደ ፎገራ ሸቀጣ ሸቀጥና ሰው ጭኖ ሲጓዝ ስድስት ታጣቂዎች መኪናውን በማስቆም እሱን፣ ረዳቱንና ሁለት ተሳፋሪዎች ሽንፋ ቀበሌ ላይ ማገታቸውን ይናገራል። አህመድ በታጣቂዎቹ እጅ ሦስት ቀን መቆየቱን የተናገረ ሲሆን፤ ታጣቂዎቹ እንደታገተ የወሰዱት አሞሃ ተራራ ወደሚባል ከፍ ያለ ተራራማ ሥፍራ ላይ መሆኑን ያስታውሳል። አህመድ እንደሚለው እነሱ ከታገቱበት ሥፍራ በሁለት ሰዓት የእግር መንገድ ርቀት ላይ የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ቢኖርም ማንም የደረሰላቸው እንደሌለ ለቢቢሲ ገልጿል። ከዚያም መታገታቸውን ለቤተሰቦቹና ጓደኞቹ መናገሩን ይናገራል። ታጣቂዎቹ እገታውን የፈፀሙት ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ መሆኑን የሚናገረው አህመድ፤ ወደ ተራራው ከወሰዷቸው በኋላ ሌሎች ሦስት ያልታጠቁ ባልደረቦቻቸውን መመልከቱን ይገልጻል። መንገድ ላይ እንዳስቆሟቸው መኪናውንና እነርሱን መፈተሻቸውን ይሁን እንጂ በቂ ገንዘብ አለማግኘታቸውን ተናግረው ወደ ተራራው ከወሰዷቸው በኋላ በነፍስ ወከፍ ሦስት መቶ ሺህ ብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን ይናገራል። ከብዙ ልመና እና ድርድር በኋላ 120 ሺህ ብር ከፍሎ መለቀቁን ገልጿል። ድርድሩ ሲካሄድ የነበረው እና ገንዘቡን የሰጣችሁት በምን ሁኔታ ነው ተብሎ ሲጠየቅ፤ "ከቤተሰቦቻችን ጋር ለመነጋገር ሞባይል ኔት ወርክ ወዳለበት አካባቢ ይዘውን ይሄዳሉ" ብሏል። የከፈለውን ገንዘብም ወንድሙ ጫካ ድረስ በመሄድ በጥሬ ገንዘብ መክፈሉን ያስረዳል። "ፖሊስ ወይንም ሌላ ሰው ይዞ ቢመጣ እንደሚገሉኝ ስለነገሩት፤ ብቻውን ጫካ ድረስ መጥቶ ከእነርሱ ለአንዱ ከፍሏል" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። አህመድ ለረዳቱ 15ሺህ ለአንዱ ተሳፋሪ ደግሞ 70ሺህ ብር መከፈሉንና መለቀቃቸውን እንደሚያስታውስ ጨምሮ አስረድቷል። በእስር ላይ በቆዩበት ወቅት ትንሽ ቆሎና አንድ ኩባያ ውሃ እየተሰጣቸው መቆየታቸውን በመናገር፤ ከእርሱ ሌላ 250ሺህ ብር ከፍለው የወጡ፣ ከሽንፋ ማዶ ቋራ የሚባል አካባቢ ደግሞ ታግተው ከነበሩ 10 ሰዎች፤ ሁለቱ ከሁለት ቀን በፊት 400 ሺህ ብር ከፍለው መውጣታቸውን እንደሚያውቅ ነግሮናል። በሕፃናት ላይ እንዲህ ዓይነት ድርጊት ሲፈፀም በአካባቢው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ያሉት የጠገዴ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ እሸቴ አረጋዊ፤ በሌሎች አዋቂዎች ላይ ግን "ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች" ሲሉ በገለጿቸው ግለሰቦች ገንዘብ አምጡ እየተባሉ መታገታቸው አዲስ ነገር አይደለም ብለዋል። "ግድያው የመጀመሪያ ቢሆንም፤ አግቶ ገንዘብ መቀበሉ ግን አዲስ ክስተት አይደለም" በማለትም ከዚህ ቀደም እገታ በመፈፀም ገንዘብ የሚጠይቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው እስከ 25 ዓመት እስር የተፈረደባቸው እንዳሉም ያስታውሳሉ። አቶ እሸቴ እንደሚሉት ከዚህ ቀደም በቁጥጥር ሥር ውለው የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባው ወንጀለኞች 'ሽፋታ' በመሆን በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታወቁ ናቸው ብለዋል። በአካባቢው የተለየ የፀጥታ ቁጥጥር ይደረጋል የሚሉት አቶ እሸቴ፤ መከላከያ፣ ልዩ ኃይል እና የቀበሌ ሚሊሻ ወደ በርሃ ድረስ በመግባት በየቀበሌው ተሰማርቶ እንደሚገኝ ገፀውልናል። በተመሳሳይ ከአንድ ሳምንት በፊት ከቋራ ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ነፍስ ገበያ ተብላ በምተጠራ አካባቢ ማንነታቸው በማይታወቅ ሰዎች ታገቶ ስድስት ሰዎች መወሰዳቸው ተነግሮ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ ለአካባቢው አስተዳደር በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ለጊዜው ምርመራ ላይ ነን በሚል ምክንያት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
news-54039327
https://www.bbc.com/amharic/news-54039327
ስድስት የኮንግረስ አባላት ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ መቋረጡን ተቃወሙ
ስድስት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉን በመቃወም ለአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ እና ለግምጃ ቤት ኃላፊው ስቲቭ ሙንሽን ደብሳቤ ጻፉ።
ደብዳቤውን ከጻፉት ስድስት የኮንግረስ አባላት መካከል ሶስቱ። ከግራ ወደ ቀኝ ኢልሃን ኦማር፣ ጄሰን ክሮው እና ጆይስ ቤቲ የኮንግረስ አባላቱ በጻፉት ደብዳቤ ላይ "አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉ እጅጉ አሳስቦናል" ብለዋል። "ይህ የውጪ ድጋፍ እንዲቀነስ መደረጉ ታማኝ ከሆነች አጋራችን ጋር ያለንን ግንኙነት ከማሻከሩም በተጨማሪ አሜሪካ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን መካከል በሚደረገው ድርድር ላይ የሚኖራትን ተሳትፎና ገለልተኝነትን ጥያቄ ውስጥ ይጥላል" ብለዋል የኮንግረስ አባላቱ። ቀደም ሲል የሲአይኤ ኃላፊ ለነበሩት የአሁኑ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ደብዳቤውን የጻፉት የኮንግስ አባላት ጄሰን ክሮው፣ ኢልሃን ኦማር፣ ኮኒን አልሬድ፣ ጆህን ግራሜንዲ፣ ጆይስ ቤቲ እና ጄራልድ ኮንሊይ ናቸው። አሜሪካ ኢትዮጵያ ግንባታውን በማካሄድ ላይ ባለችውና ከሱዳንና ከግብጽ ጋር የሚደረገው ድርድር መቋጫ ባላገኘው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ምክንያት ለኢትዮጵያ ለመስጠት አቅዳ የነበረውን ወደ 130 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የእርዳታ ገንዘብ ልትከለክል መሆኑ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል። በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ ከአሜሪካ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ጠይቀው ባገኙት ምላሽ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ ከታቀደው የገንዘብ ድጋፍ የታገደው "በጊዜያዊነት" ነው በማለት መግለጻቸው ይታወሳል። ደብዳቤውን የጻፉት ስድስቱ የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት "የህዳሴው ግድብ እየተገነባ ያለው በኢትዮጵያውያን የገንዘብ መዋጮ ነው።. . . ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ኩራት ነው በቀጠናውም ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማፋጠን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይሆናል" ብለዋል። የኮንግረስ አባላቱ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ መሆኑን ያስታወሱ ሲሆን፤ በአሜሪካም ከሩብ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን እንደሚኖሩ ጠቅሰዋል። የኮንግረስ አባላቱ ኢትዮጵያ በምሥራተቅ አፍኢካ የአሜሪካ ቁልፍ የደኅንነት አጋር መሆኗን ጠቅሰው፤ በሶማሊያ ለተሰማራው የአፍሪካ ሕብረት ተልዕኮ ውስጥ ቁልፍ ሚና የምትጫወትና በተለይም እንደ አል-ሸባብ ያሉ አሸባሪ ቡድኖችን ለመዋጋት ቁልፍ አጋር ናት ብለዋል። ጨምረውም "ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ እንዲቀንስ ማድረጉ በቀጠናው ከአሜሪካ ፍላጎት አንጻር ተጻራሪ ነው፤ በሁለቱ አገራት መካከል ለክፍለ ዘመን የዘለቀውን መልካም ግንኙነት ላይም አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል።" የኮንግረስ አባላቱ በደብዳቤያቸው "የጉዳዩን ውስብስብነት እንረዳለን" ካሉ በኋላ፤ ድጋፉ እንዲቀነስ መደረጉ አሜሪካ ለአንድ ወገን መወገኗን ያሳያል ካሉ በኋላ፤ በሁሉም ወገን ተቀባይነት ያለው መፍትሄ ለማምጣት ዩናይትድ ስቴትስ ገለልተኛ አሸማጋይ መሆን ይኖርባታል ብለዋል። "ስለዚህም ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ መቋረጥ እንደሌለበት እና ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት አሜሪካ ገለልተኛ አደራዳሪ እንድትሆን እንጠይቃለን" በማለት ስድስቱ የኮንግረስ አባለት ጠይቀዋል። ከሳምንት በፊት 'ፎሬይን ፖሊሲ' የተባለው መጽሔት የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ ከመደበው ድጋፍ ውስጥ 130 ሚሊዮን ዶላር ላለመስጠጥ መወሰኑን የውስጥ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቦ ነበረ። ይህንንም ተከትሎ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ገልጸው የነበረ ሲሆን በዚሁ መሰረት ነው ገንዘቡ በጊዜያዊነት እንዳይሰጥ መደረጉን ገልጸው ነበር። ሮይተርስ የዜና ወኪል ከቀናት በፊት ባወጠው ዘገባ አንድ የአሜሪካ መንግሥት ምንጭን ጠቅሶ አገሪቱ ለኢትዮጵያ ለመስጠት አቅዳ ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ወደ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የእርዳታ ገንዘብ ልትከለክል መሆኑ አመልክቷል።
news-53629395
https://www.bbc.com/amharic/news-53629395
በዩናይትድ ኪንግደም የፓርላማ አባሉ በመድፈር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው
በዩናይትድ ኪንግደም በመድፈር ወንጀል ተጠርጥረው የወግ አጥባቂው የፓርላማ አባል ታስረው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በዋስ መለቀቃቸው ተገልጿል።
ዘ ሰንደይ ታይምስ እንደዘገበው የፓርላማ አባሉ ላይ ክስ የተመሰረተባቸው በቀድሞ የፓርላማው ሰራተኛ ነው። ግለሰቡ ላይ የቀረበባቸው ክስ በባለፈው ሐምሌና በተያዘው ዓመት ጥር ወር መካከል ባሉት ጊዜያት ከተፈፀሙ አራት የተለያዩ ድርጊቶች ጋር የተያያዘ መሆኑንም የከተማው ፖሊስ አስረድቷል። ወግ አጥባቂው ፓርቲ በበኩሉ እንዲህ ዓይነት ክሶችን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚያየው ገልጿል። ዜናውን ቀድሞ የዘገበው ጋዜጣው፤ ግለሰቧ ትንኮሳ እንደደረሰባትና ወሲብ እንድትፈፅም እንደተገደደች እና በዚህም ሳቢያ በደረሰባት የአእምሮ ጉዳት ሆስፒታል ለመሄድ መገደዷን አትቷል። የከተማው ፖሊስም በክሱ ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት አርብ ዕለት ፖሊስ ከወሲባዊ ጥቃት ጋር የተያያዙ አራት የተለያዩ ተጨማሪ ክሶች መቀበሉንም በመግለጫው አስታውቋል። እነዚህ ጥቃቶች የተፈፀሙት በዌስትሚኒስተር ላምቤዝ እና ሃክኒይ በተባሉ ቦታዎች ሲሆን ድርጊቱም በባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር እና በተያዘው ዓመት ጥር ወር መካከል ባሉት ጊዜያት የተፈፀሙ ናቸው ብሏል። በ50ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙት ግለሰቡ በመድፈር ወንጀል ተጠርጥረው ትናንት በቁጥጥር ሥር የዋሉ ቢሆንም ከሳምንታት በኋላ እንዲቀርቡ ታዝዘው በዋስ ተለቀዋል። የወግ አጥባቂው ፓርቲ ቃል አቀባይም "እንደዚህ ዓይነት ክሶችን በትኩረት ነው የምናየው ፤ አሁን ጉዳዩ በፖሊስ የተያዘ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ሃሳብ መስጠት ትክክል አይሆንም" ሲሉ ዝርዝር ሃሳብ ከመስጠት ተቆጥበዋል። በሌላ በኩል የወግ አጥባቂው ፓርቲ አፈ ጉባኤ ማርክ ስፔንሰር በግለሰቧ የቀረበውን ክስ ያውቁ እንደነበርና ከዚህ ቀደም ተጎጅዋን አነጋግረው እንደነበር ተዘግቧል። ይሁን እንጂ አፈ ጉባዔው የክሱን መጠን ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እንደማያውቁ የቢቢሲ ምንጮች ተናግረዋል። ቃል አቀባዩም "አፈጉባዔው ሁሉንም የትንኮሳና ጥቃት ክሶች በትኩረት እንዳዩት ገልፀው፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ያነጋገሯቸውን ግለሰቦች የሚመለከታቸውን አካላት እንዲያነጋግሩ ሲያበረታቱ ነበር" ብለዋል።
news-50910372
https://www.bbc.com/amharic/news-50910372
ብዙም ያልታወቁት ከወር አበባ ጋር የሚከሰቱ የባህሪ ለውጦችና አደገኛ ውጤታቸው
'ፒኤምዲዲ' ይባላል፤ ብዙዎች እንዳለባቸው እንኳን አያውቁትም። ለወር አበባ ከደረሱ ሴቶች መካከል 8 በመቶዎቹን የሚያጠቃ ሲሆን ቁጡ መሆንና እረፍት አልባነት ይስዋልባቸዋል። ነገር ግን ስለዚህ የጤና እክል ብዙ ሰዎች በተለይም ሴቶች ግንዛቤ የላቸውም።
ካሮላይን ሄናጋን የ30 ዓመት ሴት ነች። በሥራዋ በጣም የተወጠረች ስትሆን ለእንግሊዙ የአገር ውስጥ ጉዳይ መስሪያ ቤት ነው የምትሰራው። በተደጋጋሚ የሚያጋጥማት ጭንቀትና ያልተለመዱ ባህሪያት ምናልባት ከሥራ ጫና ጋር የተያያዙ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነበር የምትገምተው። ''ማቆሚያ የሌለው አስጨናቂ ጉዞ'' ብላ ነው የምትገልጸው የሚሰማትን ስሜት። • ለዓመቱ ምርጥ የታጨችው ኢትዮጵያዊት • የወር አበባ ለምን በአንዳንድ ሴቶች ላይ ህመም ያስከትላል? አስጨናቂው ስሜት ምናልባት የሚለቀን ከሆነ ብላ አጠር ያለ እረፍትም እስከ መውሰድ ደርሳ ነበር። ነገር ግን ምንም የተለወጠ ነገር እንዳልነበረ ታስታውሳለች ካሮላይን። በእያንዳንዱ ጠዋት ከመጥፎ ስሜት ጋር ከመናሳት ባለፈ ከሰዎች ጋር ያላትን ማኅበራዊ ህይወትንም ጭምር አስቸጋሪ አድርጎታል። የሆድ በከፍተኛ ሁኔታ መነፋት፣ ከባድ ድካም፣ ጭንቀት፣ ከሰዎች ጋር በትንሽ በትልቁ መጣላት፣ ከአልጋ አለመውረድ፣ ሥራ አካባቢ ግድ የለሽ መሆን ካሮላይን ካጋጠሟት መካከል ዋናዎቹ ናቸው። በመጨረሻ ግን እነዚህ ነገሮች በሙሉ ከወር አበባዋ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ደረሰችበት። የሄደችባቸው ዶክተሮች (ሁሉም ወንዶች ነበሩ) ከወር አበባ በፊትና በወር አበባ ወቅት የሚከሰተው 'ፕሪማኑስትሪያል ሲንድረም ወይም 'ፒኤምኤስ' የሚባለው ተፈጥሮአዊ ሂደት እንደሆነ ቢነግሯትም "ለምን እኔ ላይ እንደዚህ በረታ?" የሚል ጥያቄ ፈጠረባት። በግሏ ሌሎች ባለሙያዎችን በማማከርና በይነ መረብ ላይ ያሉ መረጃዎችን በመጠቀም ችግሯ ላይ ደረሰችበት። 'ፕሪማኑስትሪያል ዲስፎሪክ ዲስኦርደር' ወይንም በአጭሩ 'ፒኤምዲዲ' ይባላል። በማላዊ የንፅህና መጠበቂያ ፓድ ዋጋ ውድ ነው። በዚህም የተነሳ ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ይቀራሉ። በዚህ ችግር የሚጠቁ ሴቶች የማይቋረጥ የድካም ስሜት፣ ከባድ የራስ ምታት፣ የባህሪ ቶሎ ቶሎ መለዋወጥ የሚያጋጥማቸው ሲሆን ሲብስ ደግሞ እራሳቸውን እስከማጥፋት ሊያደርሳቸው ይችላል። በቅርቡ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት 'ፒኤምዲዲ' ካለባቸው ሴቶች 15 በመቶ የሚሆኑት እራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ አድርገዋል። ካሮላይንም ከእነዚህ ሴቶች መካከል አንዷ ናት። በመጨረሻ ግን ከብዙ ጊዜ በኋላ የዘርፉን ባለሙያ አግኝታ ህክምና መከታተል ችላለች። ነገር ግን ህክምናው ጊዜያዊ እንጂ ሙሉ መፍትሄ ሊያስገኝላት አልቻለም ነበር። • በወር አበባ ምክንያት መምህሯ ያንጓጠጣት ተማሪ ራሷን አጠፋች • ከማህጸን ስለሚወጣ ፈሳሽ ምን ያህል ያውቃሉ? በዚህም ምክንያት ከዶክተሯ ጋር በመማከር እ.አ.አ. በ 2015 በ36 ዓመቷ ማህጸኗን በቀዶ ህክምና በማስወጣት አስባው የማታውቀውን ነገር በወጣትነቷ ለማድረግ መገደዷን ትናገራለች። 'ፕሪማኑስትሪያል ሲንድረም ወይም 'ፒኤምኤስ' የተለመደውና ከወር አበባ አንድ ወይም ሁለት ሳምንት በፊት የሚጀምር ሲሆን በርካታ ሴቶች የሚያጋጥማቸው አይነት ችግር ነው። ነገር ግን 'ፕሪማኑስትሪያል ዲስፎሪክ ዲስኦርደር' ወይንም 'ፒኤምዲዲ' ያለባቸው ሴቶች በቀላሉ ሊገላገሉት የሚችሉት ነገር አይደለም። ልክ እንደ ማንኛውም አይነት በሽታ የህክምና ክትትል የሚያስፈልገው ነው። ''ይህ ችግር በቀላሉ ሊታይ የማይገባውና ከፍተኛ የሥነ ልቦና ጫና ሊያስከትል የሚችል ነው'' ይላሉ በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችን ሥነ ልቦናን የሚያጠኑት ቶሪ ኢሰንሎር። አንዳንድ ባለሙያዎች ደግሞ ሴቶች በዚህ ችግር የሚጠቁ መሆኑ እስካልታወቀ ድረስ ባህሪያቸው በተቀያየረና ቁጡ በሆኑ ቁጥር በሥራ ቦታ፣ ከጓደኞቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ከባድ አደጋ ላይ ይወድቃል ይላሉ። ጥናቶች እንደሚጠቁት በመላው ዓለም ከሚገኙና ለአቅመ ሄዋን ከደረሱ ሴቶች መካከል ከ3 እስከ 8 በመቶ የሚሆኑት በዚሁ 'ፒኤምዲዲ' የሚጠቁ ሲሆን ይህም በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሴቶች የሚመለከት መሆኑን ያሳያል። • 'የወር አበባ ላይ ስለነበርኩ ለአያቴ ሐዘን መቀመጥ አልቻልኩም' • ለሁለት ዓመታት ልጁን በጓደኞቹ ያስደፈረው አባት ህንድን አስቆጣ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ በዘርፉ የተሰማሩ የህክምና ባለሙያዎች ዘንድ እንኳን ስለ 'ፒኤምዲዲ' ብዙም እውቀት አለመኖሩ ነው። በችግሩ ከሚያጋጥማቸው ሴቶች ጋር በተያያዘ ከታዩ ክስተቶች መካከል በእንግሊዝ አንዲት ሴት የመጠጥ ቤት አስተናጋጅን በስለት ወግታ የገደለችበትና በአሜሪካ ደግሞ ከፍጥነት በላይ በማሽከርከሯ ያስቆማት ፖሊስ ላይ ጥቃት ያደረሰችው ሴት ጉዳይ የሚጠቀስ ነው። በህክምና ባለሙያዎች እንደተረጋገጠው ሁለቱም ሴቶች በ'ፒኤምዲዲ' የሚሰቃዩ ነበሩ። ካሮላይን ሄናጋን ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች ስለችግሩ በቂ እውቀት ኖሯቸው በዚሁ ምክንያት ለሚሰቃዩ ሴቶች መፍትሄ እንደሚያገኙ ተስፋ ታደርጋለች። ''የትኛዋም ሴት በዚህ ምክንያት በፍርሀትና በጭንቀት መኖር የለባትም'' ትላለች።
news-48092091
https://www.bbc.com/amharic/news-48092091
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈፀመ ጥቃት 17 ሰዎች ሞቱ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ መተከል ዞን፤ ዳንዱር ወረዳ ላይ በተፈፀመ ጥቃት 17 ሰዎች መገደላቸውን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ለቢቢሲ አስታወቁ።
• «በስልክዎ ታካሚና አካሚ እናገናኛለን» ሥራ ፈጣሪው ወጣት ግጭቱ ሚያዚያ 17 /2011 ዓ.ም የተፈጠረ ሲሆን በጫኝና አውራጅ ሥራ በተሰማሩ ሁለት ግለሰቦች ግላዊ ጠብ ሰበብ እንደሆነ ተናግረዋል። ኃላፊው እንደሚሉት በጊዜው የነበረው ፌደራል ፖሊስ የሁለቱን ግለሰቦች ግጭት ለማረጋጋት ሲሞክር በመካከል አለመግባባት ተፈጥሮ በተተኮሰ ጥይት አንድ የጉሙዝ ተወላጅ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። ከዚህ በኋላ ግጭቱ እንደተባባሰ ኃላፊው ያስረዳሉ። "በክልሉ አንድ ጉሙዝ ከተገደለ፤ የቆዳ ቀለማቸው ቀላ ያሉ ሰዎችን የመግደልና የመበቀል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አለ" የሚሉት አቶ አሰማኸኝ፤ በዚህም ምክንያት በየቦታው ያሉ የአማራ ክልል ተወላጆች ላይ ግድያና ንብረቶቻቸውን የመዝረፍ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። አቶ አሰማኸኝ 17ቱ ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ ተገደሉ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ በአከባቢው በቀስት እና በጥይት ሰዎችን የመግደል ልማድ አለ። ይሁን እንጂ እኚህ ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ እንደተገደሉ የሚያሳይ ዝርዝር መረጃ የለኝም ብለዋል። ግጭቱ ለተከታታይ አራት ቀናት የዘለቀ ሲሆን የ17 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል። ከእነዚህ መካከል አስራ አንዱ የአማራ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ ስድስቱ የእዚያው አካባቢ ተወላጆች መሆናቸውን አቶ አሰማኸኝ ተናግረዋል። ለጊዜው ጉዳት ያጋጠማቸው ግለሰቦችን ቁጥር በእጃቸው ባይገኝም ጥቃቱ በተበታተነና በተለያየ አካባቢ በመፈፀሙ የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር ይችላል ብለዋል። • «አቶ ገዱም ሆነ ደመቀ እኛም ብንፈተሽ ግድፈት አለብን ማለታቸውን አስታውሳለሁ» የአቶ ታደሰ (ጥንቅሹ) ባለቤት በግጭቱ ስጋት ያደረባቸው ሰዎች እንጂ የተፈናቀሉ ሰዎች አለመኖራቸውም አክለዋል። በአካባቢው የፌደራልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች እንዲገቡ የተደረገ ቢሆንም አካባቢው ጫካና የተበታተነ የአኗኗር ስርዓት በመኖሩ ለማረጋጋት ቀናት ሊወስድ ችሏል ብለዋል አቶ አሰማኸኝ። ትናንት ሌሊት ፓዊ ወረዳ፤ አባውርኛ ቀበሌ ላይ 25 የሚሆኑ የአካባቢው ተወላጅ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ዛሬ ሌሊት በአንፃሩ መረጋጋት እንደታየ ነግረውናል። • የካቢኔው ሽግሽግ ምን ያመላክታል? የአማራ ክልል ከሚደግፋቸው ታዳጊ ክልሎች መካከል አንዱ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መሆኑን የሚጠቅሱት ኃፊው በአካባቢው ባለ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ምክንያት በአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን ኃላፊው ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ ይህንንም ለመከላከል የሁለቱ ክልል አመራሮች በቅርቡ በእንጂባራ ከተማ ተገናኝተው የመከሩ ሲሆን በጋራም እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል። በዚህ ግጭት ሳቢያም በስጋት የሚፈናቀሉ ሰዎች እንዳይኖሩ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ልዑካን ወደ አሶሳ እያመሩ መሆናቸውን ገልፀውልናል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።
50253440
https://www.bbc.com/amharic/50253440
"በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ተቀባይነት ማሳጣት የሚሹ ግጭቱን አባብሰውታል" ቢልለኔ ስዩም
በአንድ ጭብጥ ላይ ብቻ ያተኮረው የትናንቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መግለጫ ከሰሞኑ በኦሮሚያ፣ ሐረሪ ክልሎችና እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ተከስተው በነበሩ አለመረጋጋቶች፣ መፈናቀልና ጥቃቶች ጋር በተያያዘ 78 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሪታሪ ጽሕፈት ቤትን ወክለው መግለጫውን የሰጡት ቢልለኔ ስዩም ከግጭቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 409 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ብለዋል። የተጠርጣሪዎች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የወጣው መግለጫ የሟቾቹን ቁጥር 67 እንደሆነ የሚገልጽ ነበር። • ኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ሁከት 359 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ • ስለባለፈው ሳምንት ግጭቶችና ጥቃቶች አስካሁን የምናውቃቸው ነገሮች ቢልለኔ ስዩም ግጭቱ የሃይማኖትና የብሔር ገጽታ እንደነበረው አውስተው ለግጭቱ መባባስ በስም ያልጠቀሷቸው አካላትን ተጠያቂ አድርገዋል። እርሳቸው በስም ያልጠቀሷቸው እነዚህ አካላት አሁን እየተደረገ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ ይፈልጋሉ ሲሉም ከሰዋል። "እነዚህ ኃይሎች አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ተቀባይነት ማሳጣት የሚሹና በአገሪቱ ፍርሃት እንዲያረብ ፍላጎቱ የነበራቸው ናቸው" እንደ ቢልለኔ ገለጻ። በመግለጫቸው እነዚህ በስም ያልተጠቀሱት አካላት አጋጣሚውን ተጠቅመውበታል፤ አባብሰውታልም ብለዋል። ግጭቱ የገዢው ፓርቲ አሁን ለመዋሃድ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ የመጣ አጸፋዊ ምላሽ እንደሆነም ጠቆም አድርገዋል። ቢልለኔ ስዩም ከጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መሀል "ጀዋር መሐመድ ጠባቂዎቼ ሊነሱ ነበር ባለበት ምሽት በትክክል የሆነው ምንድነው?" የሚል ይገኝበታል። ከዚህ ቀደም በዚህ ረገድ እርስ በእርሳቸው የማይስማሙ መግለጫዎች ከፌዴራል መንግሥትና ከኦሮሚያ ክልል መውጣታቸው የሚታወስ ነው። • በግጭት ለተፈናቀሉት የተሰበሰበው አስቸኳይ እርዳታ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ •"በመንግሥት መዋቅር ሥር ሆነውም ግጭቶችን የሚያባብሱ እንዳሉ እናውቃለን" ኢዜማ ቢልለኔ ስዩም ሲመልሱ በዚያ ምሽት ስለሆነው ነገር በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ማብራሪያ ስለተሰጠ እርሳቸው አሁን የሚጨምሩት እንደሌለ ተናግረዋል። እርስ በርስ የሚጣረሱ መግለጫዎች ይወጡ እንደነበረ ግን እርሳቸውም መታዘባቸውን አውስተዋል። ይህም የሆነው ምናልባት በተለያየ ፍጥነት መረጃዎች መውጣታቸው የፈጠረው ሊሆን ይችላል ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹን በተመለከተ በመንግሥት በኩል ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ገብቶ ጉዳዩን እንዲያጣራ ፍላጎት ይኖራል ወይ? ተብለው የተጠየቁት ቢልለኔ "አሁን ያለው ምርመራ ሂደት ላይ ስለሆነ እሱ የሚኖረውን ውጤት አይተን የሚያስፈልግ ከሆነ ወደፊት የምናየው ይሆናል" ብለዋል።
55183182
https://www.bbc.com/amharic/55183182
ናሳ ከጨረቃ ላይ የአፈር ናሙና ለሚያመጣለት ኩባንያ 1 ዶላር ብቻ ሊከፍል ነው
ናሳ የአፈርና የዓለት ናሙና ከጨረቃ ላይ ለሚያመጣልኝ ኩባንያ ጠቀም ያለ ገንዘብ እከፍላለሁ ባለው መሰረት በርካታ ግዙፍ ኩባንያዎች ተወዳድረው ነበር።
ጨረታውን ያሸነፈው ኩባንያ ተለይቷል። ይህን ግዙፍና ውስብስብ ሥራ ሲያጠናቅቅ የሚከፈለው ግን አንድ ዶላር ብቻ ነው። በዚህ በርካቶች በተሳተፉበት ውድድር ዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ ያሸነፈው "ሉናር አውትፖስት" የተባለ ኩባንያ ነው። ይህ ኩባንያ ለአሜሪካው የሕዋ ኤጀንሲ ሥራውን ለመሥራት በ1 ዶላር ዋጋ ነው ስምምነት የተፈራረመው። ናሳ ከዚህ ስምምነት ጋር ሌሎች አራት ተመሳሳይ ኮንትራቶችን ያስፈረመ ሲሆን አራቱም እጅግ ዝቅ ባለ ዋጋ የተሰጡ ኮንትራቶች ናቸው ተብሏል። ዓላማውም በዝቅተኛ ዋጋ ጨረቃ ላይ ያሉ ነገሮችን ናሙና ማስቀለቀም ነው ተብሏል። ከአራቱ ጨረታዎች አንዱን ያሸነፈው ሌላኛው ኩባንያ መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው "ማስተን ስፔስ ሲስተም" ሲሆን ሦስተኛው ኩባንያ ደግሞ ቶክዮ የሚገኘው "አይስፔስ" ነው። ናሳ ለነዚህ ኩባንያዎች አገልግሎት ለእያንዳዳቸው አንድ አንድ ዶላር ይከፍላቸዋል። ሥራቸው የሚሆነው ጨረቃ ሄደው ከ50 እስከ 500 ግራም የሚመዝኑ ሪጎሊስ ወይም የጨረቃ አፈር (ዐለቶችን) ጭኖ ማምጣት ነው። የጨረቃ ዐለቶች በቢሊዮን ዓመታት ዕድሜ ያላቸው ናቸው። "እነዚህ ኩባንያዎች የጨረቃ አፈር ናሙና ለቅሞ ማምጣት ብቻ ሳይሆን ያን ስለማድረጋቸው በቪዲዮ የተደገፉ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው" ብለዋል የናሳ ቃል አቀባይ። ይህ ሥራ የሚከናወነው በ2023 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ነው። መቀመጫውን ኮሎራዶ ያደረገው ሉናር አውትፖስት የሮቦት ድርጅት ሲሆን ከደቡባዊ የጨረቃ ዋልታ አፈር ሰብስቦ ለማምጣት የአንድ ዶላር ኮንትራት ማሸነፉ እጅጉኑ አስደስቶታል። ይህ ድርጅት በዚህ ሥራ ለመሰማራት ዋና ዓላማው ገንዘብ አይደለም። ኩባንያዎቹ ይህንን ሥራ ካሳኩ በኋላ በርከት ያሉ ሳይንሳዊ ትርፎችን ያገኛሉ። አንዱ ተስፋቸው ከጨረቃ ወለል የሚገኙ ማዕድናትን እንዲያወጡ ዕድል ስለሚሰጣቸው ነው። ይህ ነው በ1 ዶላር ክፍያ እንዲህ ዓይነት ውስብስብ ኮንትራት ውስጥ ለመግባት የሚያበረታታቸው። ኩባንያው አሁን "ብሉ ኦሪጅን" ከተባለ ሌላ ግዙፍ ኩባንያ ጋር እየተነጋገረ ነው። ንግግሩ ያተኮረው ወደ ጨረቃ የሚያሳፍር የሕዋ ታክሲ ለመኮናተር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው። "ብሉ ኦሪጅን" የምድራችን የናጠጠው ቁጥር አንድ ሀብታም የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ኩባንያ ነው። ዋና ሥራው ሰዎችን ህዋ አሳፍሮ መመለስ ነው። ከናሳ ጋር ርካሽ የሥራ ውል ካደረጉት ድርጅቶች መካከል የጃፓኑ "አይስፔስ" ይገኝበታል። አይስፔስ በሰሜን ምሥራቅ ዋልታ በ2020 ዓ ም ለሚሰበስበው የጨረቃ ዐለት 5ሺ ዶላር ቁርጥ ክፍያ ያገኛል። የሐዋ ጉዳዮች ተንታኝ ሲኒየድ ኦ ሱሊቫን እንደሚሉት ለዚህ የሥራ ሥምምነት 1 ዶላር ቀላል ገንዘብ አይደለም። ምክንያቱም ይላሉ ተንታኙ፤ ኩባንያዎቹ በዚህ የሥራ ውል ስምምነት የሚገቡት ገንዘቡን ብለው አይደለም። ወደፊት የሚፈጥርላቸውን ዕድል ታሳቢ በማድረግ ነው። ይህ ኮንትራት ገዢና ሻጭ ከመሬት ውጭ ባለ ነገር ላይ እየተፈራረሙ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ብለዋል። የሚደንቀው አንድ ዶላር መከፈሉ ብቻ አይደለም። ኩባንያው ከጨረቃ የአፈር ናሙና ለማምጣት 1 ዶላሩ የሚከፈለው በሦስት ዙር መሆኑ ነው። መጀመርያ ውሉን ሲያስር የአንድ ዶላር 10 በመቶ ይከፈለዋል፤ ይሄ ተከፍሎታል። ቀጥሎ ደግሞ መንኩራኩር ተሳፍሮ ሲሄድ ነው። ሦስተኛውና ትልቁ ክፍያ ናሙናዎቹን ከጨረቃ ጭኖ አምጥቶ ሲያስረክብ ነው። ያን ጊዜ የአንድ ዶላር 80 ከመቶ ይከፈለዋል። "አዎ ይህ ቀልድ ሊመስል ይችላል፤ 1 ዶላር የሚከፈለው በአንድ ጊዜ አይደለም። በ3 ዙር ነው። መጀመርያ $0.10, ከዚያ ደግሞ $0.10, በመጨረሻም $0.80 ክፍያ ይፈጸማል ብለዋል" ቃል አቀባዩ ሳይረስ። ይህ ስምምነት የተፈረመው ቻይና የጨረቃ ናሙና ለማምጣት መንኩራኩር በላከች ማግስት ነው። የቻይናው ቼንጅ5 የጨረቃ መንኩራኩር አሁን በዚህ ሰዓት ናሙናዎቹን ጭኖ ወደመሬት በመምጣት ላይ ይገኛል።
50612491
https://www.bbc.com/amharic/50612491
ከፍየል ለምድ በሚሠራ ክር ሳቢያ የተቧቀሱት የሌሴቶ እንደራሴዎች
የሌሴቶ ፓርላማ ውስጥ የሕዝብ እንደራሴዎች መደባደባቸው፣ ሰነዶችና ሌላም ቁሳ ቁስ እርስ በእርስ መወራወራቸውም ተሰምቷል።
የሌሴቶ ፓርላማ ውስጥ የሕዝብ እንደራሴዎች መደባደባቸው፣ ሰነዶችና ሌላም ቁሳ ቁስ እርስ በእርስ መወራወራቸውም ተሰምቷል ግብግቡ የተነሳው ከፍየል ለምድ የሚሠራ ክር (ሞሂር) ንግድ ሕግን በተመለከተ ነው። ሞሂር በመባል የሚታወቀው ክር የሚሠራው ከፍየል ለምድ ሲሆን፤ ለስላሳ ስለሆነና ቅንጡ ምርት መሆኑ ስለሚታመን ውድ ነው። እንዲያውም አንዳንዶች 'እንቁ ክር' ይሉታል። ሞሂር የሌሴቶ ቀዳሚ ምርት፤ የብዙ ነዋሪዎቿ ቋሚ የገቢ ምንጭም ነው። • "ዕፀ ፋርስ በመሸጥ ልጆቼን አሳድጋለሁ" የሌሴቶዋ አምራች • በስህተት 12 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ አለብሽ የተባለችው ሃገር • ብሩንዲ መጠጥ ቤቶች በጊዜ እንዲዘጉ አዘዘች በያዝነው ዓመት መባቻ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች፤ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2018 ላይ የተላለፈ ድንጋጌን ተቃውመው ፓርላማ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር። ድንጋጌው አርሶ አደሮቹ የሞሂር ምርታቸውን ለቻይናዊ ደላላ (ጉዎሂ ሺ የተባለው ግለሰብ ለከፈተው ሌሴቶ ውል ሴንተር የተባለ ድርጅት) እንዲሸጡ የሚያስገድድ ነበር። አርሶ አደሮቹ እንዳሉት፤ ደላላው ለምርታቸው እየከፈለ አልነበረም። ይህን ተከትⶀ የተነሳው ቀውስ ወደ 48,000 አርሶ አደሮች ከአንድ ዓመት በላይ ገቢ እንዲያጡ ማድረጉን የደቡብ አፍሪካው ቢዝነስ ላይቭ መጽሔት ዘግቧል። በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች ከተካሄዱ በኋላ አወዛጋቢው ድንጋጌ በጠቅላይ ሚንስትር ቶም ታባኔ ተሽሮ ነበር። ሆኖም ግን አርሶ አደሮቹ ደስተኛ አልሆኑም። ለቻይናዊ ደላላ የመሸጥ ግዴታ የጣለው ሕግ ቢሻርም፤ ሞሂር ለጨረታ የሚቀርበው ከሌሴቶ ሳይሆን ከአጎራባቿ ደቡብ አፍሪካ እንዲሆን መወሰኑ ሌላ ችግር ፈጥሯል። የሌሴቶ አርሶ አደሮችም ፍትሀዊ ገበያ ባለማግኘታቸው ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ጥቅምት ላይ ይህ ሕግ ተሽሮ በሌላ እንዲተካ ቢወሰንም፤ የአዲሱ ድንጋጌ ረቂቅ አልተጠናቀቀም። የሌሴቶ አርሶ አደሮች እና ተቃዋሚዎች፤ ምርታቸውን ከአገራቸው ብቻ ከሸጡ፤ ገዢዎች የመጓጓዣ ወጪ ለመቀነስ ሲሉ ወደሌላ አካባቢ ይዘዋወራሉ የሚል ስጋት አላቸው። ፓርላማ ውስጥ የአነስተኛ ንግድ ክፍል ተቃውሞ እንደማያሰማ ያወቁት ተቀናቃኞች በነገሩ ተቆጥተዋል፤ የፓርላማው አፈ ጉባኤም ውይይቱ እንዲቆም አድርገዋል። አንጎራ በመባል የሚታወቀው የፍየል አይነት፤ ከ12 እስከ 15 ኢንች የሚደርስ ለምድ ስለሚያበቅል በአመት ሁለቴ ይሸለታል። ሌሴቶ ከአንጎራ ፍየል በሚገኘው ሞሂር ምርት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃ ይዛለች። ደቡብ አፍሪካ ከዓለም 53 በመቶ የሚሆነውን ሞሂር ታመርታለች። 75 በመቶ የሚሆነው የሌሴቶ ነዋሪ የሚኖረው በገጠር ሲሆን፤ አብዛኛው ቤተሰብ የሚተዳደረው በሞሂር ምርት ነው። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2018 ዘርፉ መቶ ሚሊዮን ዶላር ተገምቶ ነበር።
news-54368875
https://www.bbc.com/amharic/news-54368875
የእንግሊዙ ቤተ መፃህፍት በውሰት የተወሰዱ መፅሃፎቹ ከ48 ዓመታት በኋላ ተመለሱለት
ከቤተ መፃህፍት መፅሃፍ ተውሰው ምን ያህል ጊዜ ያቆያሉ? ሳምንታት፣ ወራት? ሳይመልሱስ ቀርተው ያውቃሉ።
በእንግሊዟ ሃምፕሻየር የሚገኝ አንድ ቤተ መፃህፍት ሁለት የህፃናት መፃህፍት ከአርባ ስምንት ዓመታት በኋላ ተመልሰውለታል። መፅሃፎቹም ላይ መፅሃፉን በልጅነቱ የተዋሰው አንዲ የተባለው ግለሰብ "ህፃናት ሆነን ወደ ሌላ ከተማ ሄድን እናም በ1972 የተዋስነውን መፅሃፍ ሳንመልስ ቀረን፤ ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን" ከሚል የይቅርታ ደብዳቤ ጋር ነው የመለሰው። የሃምሻየር ግዛት ምክር ቤት በበኩሉ መፅሃፉ የተመለሱበት መንገድ ልብ የሚነካ ነው ያለ ሲሆን መፅሃፎቹን ለመመለስ ይህንን ያህል የዘገየበትንም ጊዜ ቅጣት እንደማይቀጡ አስታውቋል። ምክር ቤቱ አክሎም መፅሃፎቹ በመመለሳቸው መደሰታቸውንና "የአንዲ አድራሻ ስለሌለን በቀጥታ መመለስ አልቻልንም፤ አንዲ ማወቅ ያለብህ ግን መፅሃፎቹን የመለስክበት መንገድ የቤተ መፃህፍቱን ሰራተኞች ያስደሰተና ልብ የሚነካ ድርጊት ነው" ብሏል። መፅሃፎቹ በውሰት የዘገዩበት ጊዜ ቅጣት ይቀጡ ቢባል 8 ሺህ ፓውንድ ያህል ያስቀጣም ነበር ተብሏል። መፅሃፎቹ ለህፃናት ቀለም አቀባብን የሚያስተምርና የባቡር መንገዶችን ታሪክ የያዘ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ለቤተ መፃህፍቱም ባለፈው ወር በፖስታ ነው የደረሱት።
news-41529112
https://www.bbc.com/amharic/news-41529112
ኢትዮጵያ፡ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ወረርሽኝ አዲስ ስጋት ፈጥሯል
ከአስር ዓመት በፊት የበርካታ ወጣቶችን ህይወት የቀጠፈው፣ ልጆችን ያለወላጅ የስቀረው እና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያስከተለው ኤች.አይ.ቪ ኤድስ አሁንም አንደ ወረርሽኝ ተከስቶ ስጋትን ፍጥሯል።
የፌደራል ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት መረጃ እንደሚያሳየው በሃገር ደረጃ የቫይረሱ ስርጭት 1.18 በመቶ ደርሷል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት ከአንድ በመቶ በላይ ከሆነ በአንድ ሃገር ውስጥ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ወረርሸን ተከስቷል ይባላል። በ1978 ዓ.ም በሁለት ሰዎች ደም ውስጥ ብቻ ይገኝ የነበረው ቫይረስ ዛሬ ላይ ከ700ሺ በላይ ዜጎች ደም ውስጥ ይገኛል ይላል፤ ከፌደራል ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የተገኝው መረጃ። የኤች አይ.ቪ.ኤድስ ወረርሽኝ ቀንሷል የሚለው በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው አመለካከት፤ በሽታው በድብቅ እንዲስፋፋ አስችሎታል። በ2009 ዓ.ም ብቻ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ27ሺ በላይ ነው፤ ይላል የፌደራል ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጸ/ቤት። ከፍተኛ ተጋላጭነት የቫይረሱ ስርጭት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ነው የተባለ ሲሆን፤ የስርጭት መጠኑም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በሚካሄዱባቸው ቦታቸው፣ አዲስ በሚመሰረቱ ከተሞች እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የስርጭት መጠኑ ከፍተኛ ነው ተብሏል። በገጠር አካባቢ የሚኖሩና በአበባ እርሻ ሥራ ላይ ተቀጥረው ከሚሰሩ ሴቶች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ-ሥጋ ግኑኝነት በመፈፀማቸው ፅንስ ለማቋረጥ ተዳርገዋል፤ ይላል የፌደራል ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት። ለቫይረሱ ተጋላጭነት የፆታ፣ የሥራ አይነት እና የኑሮ ደረጃ አስተዋፅኦ አንደሚያደርጉ የጽ/ቤቱ መረጃ ያሳያል። በሴቶች ላይ የለው የኢኮኖሚ እና ህብረተሰቡ የሚያደርስባቸው ጫና ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው መረጃው ያትታል። ከዚህም በተጨማሪ ሴተኛ አዳሪዎች ለቫይረሱ ተጋላጭነታቸው ጨምሯል። ጫት ቤቶች፣ ሺሻ ቤቶች እና ማሳጅ ቤቶች ለቫይረሱ ስርጭት መጨመር አስተዋፅኦ አበርክተዋል፤ ሲሉ አቶ ክፍሌ ምትኩ የፌደራል ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የዘርፈ ብዙ ምላሸ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር ተናግረዋል። ሃገሪቷ በ2030 የኤች.አይ.ቪ ቫይረስን ስርጭት ለመግታት የያዘችው እቅድ በዚህ አካሄድ መሳካቱ አጠራጣሪ ሆኗል። ኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ ስርጭትን መቀነስ ለምን ተሳናት? ከጥቂት ዓመታት በፊት መንግሥት አና ምንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባከናወኗቸው ተግባራት በቫይረሱ ምክንያት ይከሰት የነበረን ሞት በ70 በመቶ መቀነስ ተችሎ ነበር። በዚህ ስኬት ምክንያትም መንግሥትምና መንግሥታዊ የልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ህበረተሰቡ በአጠቃላይ ለኤች.አይ.ቪ ኤድስ ይሰጡ የነበረው ትኩረት እንዲቀንስ ሆኗል። አቶ ክፍሌ እንደሚሉት በኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስን ስርጭት ለመቀነስ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ የተመዘገበውን ስኬት ከግምት ውስጥ አስገብተው ሃገሪቷ በሽታውን በራሷ አቅም መቆጣጠር ትችላለች በማለት የደርጉ የነበረውን ድጋፍ ሙሉ በሙሉ አቁመዋል። ጽ/ቤታቸውም መንግሥት በመደበው በጀት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችሉ ተግባራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይናገራሉ።
news-55976634
https://www.bbc.com/amharic/news-55976634
ሴኔቱ ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ የመመስረቱ ሂደት ሕገ መንግሥታዊ ነው አለ
የአሜሪካ ሴኔት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ መመስረቱ ሕገ መንግሥታዊ ነው በማለት የክስ ሂደቱን አስቀጠለ።
የትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሃውስን ከለቀቁ በኋላ መሰል ክስ ሊቀርብባቸው አይችልም ሲሉ ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ 56-44 በሆነ የድምጽ ብልጫ የቀድሞ ፕሬዝደንት ላይ ክስ የመመስረቱ ሂደት ድጋፍ አግኝቷል። ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ወር ደጋፊዎቻቸው በካፒቶል ሂላ ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ አመጽ ቀስቅሰዋል በሚል እየተወነጀሉ ነው። ትራምፕ ምንም አይነት ማረጋገጫ ሳያቀርቡ ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ መቆየታቸው ይታወሳል። ትራምፕን እየከሰሱ የሚገኙት ዲሞክራቶች ሂድቱን በኤግዚቢትነት ያቀረቧቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማሳየት ጀምረዋል። በተንቀሳቃሽ ምሰሉ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ወደ ካፒቶል ሂል እንዲሄዱ 'ሲያነሳሱ' እና በሺዎች የሚቆጠሩ የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂልን ሰብረው ሲገቡ፤ በንብረት እና በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ያሳያል። ዴሞክራቶች ባቀረቡት ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው 'እስከመጨረሻው እንዲታገሉ' መልዕክት ሲያስተላልፉ፤ ይህን ተከትሎም በካፒቶል ሂል ላይ ጉዳት ሲደርስ አስመልክተዋል። ዲሞክራቱ ጄሚ ራስኪን፤ ይህ ተግባር ትራምፕን በወንጀል ማስጠየቅ አለበት ብለው ተከራክረዋል። "ይህ የአሜሪካ የወደፊት እጣ መሆን የለበት። በመንግሥታችን ላይ አመጽ የሚቀሰቅስ ፕሬዝደንት ሊኖረን አይገባም" ብለዋል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ትራምፕ ጠበቆች በበኩላቸው፤ ዶናልድ ትራምፕን በዚህ ሂደት ውስጥ ማሳለፍ ሕገ መንግሥታዊ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። ዲሞክራቶችም ይህን እያደረጉ ያሉት ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ነው ብለዋል። 56-44 የሚለው የድምጽ ውጤት ስድስት የትራምፕ ፓርቲ አባላት የሆኑ ሪፐብሊካኖች ከዲሞክራቶች ጎን በመሆን ድምጽ መስጠታቸውን ያመላክታል። በትራምፕ ላይ ክስ ለመመስረት 100 መቀመጫ ባሉት ሴኔት ውስጥ 2/3ኛ ድጋፍ ያስፈልጋል። ትራምፕ ላይ ክስ እንዲመሰረት ከተወሰነ ዶናልድ ትራምፕ ወደፊት የፖለቲካ ተሳትፎ አድርገው ስልጣን እንዳይዙ ሊደረጉ ይችላሉ። በካፒቶል ሂል የነበረው አመጽ በቀጣይ ምን ይፈጠራል? በትራምፕ ላይ ክስ እንዲመሰረት የሚጠይቁት ዴሞክራቶችም ሆኑ የትራምፕ ጠበቆች ለአንድ ተጨማሪ ቀን መከራከሪያ ነጥቦቻቸውን ማቅረባቸውን ይቀጥላሉ። በሴናተሮች በኩል ለሚነሱ ጥያቄዎች ዴሞክራቶች እና የትራምፕ ጠበቆች ምላሽ ይሰጣሉ። ዴሞክራቶቹ የዓይን ምስክሮችንም ቃል ሊያሰሙ ይችላሉ። እስከ መጪው ሰኞ ድረስ ትራምፕ ክስ እንዲመሰረትባቸው አልያም ነጻ እንዲወጡ ሴኔቱ ውሳኔ ማስተላለፉ አይቀርም ተብሏል።
news-54408180
https://www.bbc.com/amharic/news-54408180
"የቻይናን ኃያልነት ለመግታት ረፍዷል"
በቻይና መንግሥት ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቀው አርቲስትና የፊልም ባለሙያ አይ ዌይዌይ ቻይና በአለም አቀፉ ያላት ኃያልነት ከፍተኛ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት መግታት አይቻልም ብሏል።
አርቲስትና የፊልም ባለሙያ አይዌይዌይ "የምዕራቡ አለም ስለ ቻይና መጨነቅ የነበረበት ከአስርት አመታት በፊት ነበር። በአሁኑ ሰዓትም ግን ረፍዷል። ምክንያቱም ምዕራባውያን ከቻይና ጋር ጠንካራ ስርአት ዘርግተዋል ዝም ብለው ቢያቋርጡትም በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳሉ። ለዚያም ነው ቻይና የእብሪተኛ ባህርይ የምታሳየው" ብሏል። በ2008ቱ የቤጂንግ ኦሎምፒክስ የወፍ ጎጆ ስታዲየምን ዲዛይን ያደረገው አርቲስቱ የቻይናን መንግሥት መተቸቱንም ተከትሎ ነው ከባለስልጣናቱ ጋር ችግሮች መፈጠር የጀመሩት። በ2015ም ቻይናን ለቆ በበርሊን ኑሮውን አድርጎም ነበር። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ መኖሪያውን ካምብሪጅ አድርጓል። አይ ዌይዌይ እንደሚለው በአሁኑ ወቅት ቻይና ያላትን የምጣኔ ኃብት ኃያልነት ለፖለቲካዋ ተፅእኖም ትጠቀምበታለች። በቅርብ አመታት የቻይና የፖለቲካ ተፅእኖ በጉልህ መታየት ጀምሯል። እየጨመረ የመጣው ተፅእኖ ከአስር አመታት በፊት የነበረችው ቻይና ልታይ ልታይ የማትልና፣ ድምጿም በአለም ጎልቶ አይሰማም ነበር። የመንግሥት ባለስልጣናቷም ይዘውት የነበረው መፈክርም "ብርሃንን ደብቆ ጊዜን መግዛት" የሚል ነበር። በርካታ ሚኒስትሮቿም ቻይና አሁንም ቢሆን ታዳጊ አገር ናት ከምዕራቡ አለምም ብዙ መማርን ትሻለች ሲሉም ይሰሙ ነበር። ሆኖም የዢ ሺንፒንግ ወደ ስልጣን መምጣት ቻይና በአለም ታሳየው የነበረውን ባህርይ ሙሉ በሙሉ ቀየረው። በ2012 ዢ ሺንፒንግ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ሆኑ፣ በቀጣዩ አመት ፕሬዚዳንት ዢ ሺንፒንግ ቻይና በአለም ላይ ያላትን ቦታም ሆነ ገፅታ በአዲስ መልክ ያዋቀሩ ናቸው ይባልላቸዋል። የአገሪቷም መፈክር "ለስኬት እንስራ" በሚል ተተካ። በሆነ መንገድ ቻይና አሁንም ቢሆን ታዳጊ አገር ናት ምክንያቱ 250 ሚሊዮን ህዝቦቿ ከድህነት ወለል በታች ስለሚገኙ። በአለም ላይ ሁለተኛ ታላቅ የምጣኔ ኃብት ባለቤት ናት። በአሁኑም ወቅት አሜሪካን የምትገዳደራትና በቀጣዩ አመታትም ትቀድማታለችም ተብሎ የምትጠበቅም ሃገር ናት፣ ቻይና። ቻይና በአለም ላይ ያላት ተፅእኖ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ እየታየ ነው። በተቃራኒው ኃያሏ አገር አሜሪካም በሚታይ መልኩ ተፅእኖዋ እያሽቆለቆለ ነው። የቻይና ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ አዘጋጅ ሁ ሺን ቻይና በፖለቲካው ላይ ያላት ተፅእኖና ጫና በመላው አለምም እየተንሰራፋ ነው። ከጫፍ ጫፍ በሚባል ሁኔታ ከግሪላንድ፣ ካሪቢያን ደሴቶች፣ ፔሩ፣ አርጀንቲና፣ ፓኪስታን፣ ሞንጎሊያ የቻይና እጅ የሌለበት የለም። በቅርቡም የካሪቢያኗ ባርቤዶስ ደሴት የእንግሊዟን ንግሥት በርዕሰ ብሄርነት አንፈልጋቸውም ማለቷን ተከትሎ የእንግሊዙ የፓርላመንት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ቻይና ናት ሃሳቡን ያመጣችው በማለት ወቅሰዋታል። ቻይና በአለም ላይ ያላት ተፅእኖ በዚህ ተመለስ የሚባል አይደለም፤ በብሄራዊ ፍላጎቷ የሚመጣንም አገር ዝም ብላ አታልፈውም። የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ በቅርቡ ለንደንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ የእንግሊዝና የቻይና ግንኙነት በተወሰነ መልኩ ሻክሮ ነበር። በቅርቡም የቼክ ሪፐብሊክ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ታይዋንን መጎብኘታቸውን ተከትሎ፣ ከፍተኛ ዲፕሎማት አስጠንቅቀዋል። ግልፅ በሆነ መልኩ ቻይናን ለመተንኮስም ሆነ ከጀርባቸው ሆነው የሚያሴሩ የፀረ- ቻይና ኃይሎችን አገራቸው እንደማትታገስና የሚከተለው ነገር ክፉ ይሆናል ብለዋል። የቻይናና የሌሎች አገራት ፍጥጫ ምንም እንኳን አንዳንዶች ቻይና ያላትን ምጣኔ ኃብት በመጠቀም ከፍተኛ ተፅእኖም ታሳርፋለች ቢሉም ተናጋሪውና ተፅእኖ ፈጣሪው የቻይና ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ አዘጋጅ ሁ ሺን አይስማማም። ቻይና አገራትን እያብረከረከች ነው የሚለውም ተቀባይነት የለውምም ይላል። "አንድ መጠየቅ የምፈልገው ነገር ቢኖር ቻይና መቼ ነው አንድን አገር ያለ ፈቃዷ ምንም ነገር ለማድረግ ግፊት ወይም ጫና ያደረገችው?። በአለም ላይ አሁንም ቢሆን አሜሪካ ናት እቀባ በተለይም ኢኮኖሚያዊ እቀባ በመጣል ከፍተኛ ጫና ለማሳረፍ እየሞከረች ያለችው። ቻይና የትኛዋ አገር ላይ ነው ማዕቀብ የጣለችው?" በማለትም ይጠይቃል። አክሎም "ማዕቀብ ጥለን እናውቃለን። እንደ ሃገር አንዳንድ የማንስማማባቸው ጉዳዮች ላይ ስሜታችንን እናፀባርቃለን ይህም ብዙ ጊዜ የሚፈጠረው የአገራችን ብሄራዊ ጥቅም ሲነካ ነው" ይላል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ቻይና ከታይዋን አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ካናዳና ህንድ በሆነ መልኩ ተፋጣለች። በተለይም ከህንድ ጋር በድንበር ከተማዋ ስከርሚሽ ጋር በተያያዘ መሳሪያም ተማዘዋል። ከእንግሊዝና ከአሜሪካም ጋር ያለው መፋጠጥም እንደቀጠለ ነው። በግሎባል ታይምስ ላይ ያሉት ርዕሰ አንቀፆች የማኦ ዜዶንግን አገዛዝም ያስታውሳሉ ይባላል። በቅርቡ ርዕሰ አንቀፁ ላይ አውስትራሊያን አስመልክቶም "ከቻይና ጫማ ስር ያለች ማስቲካ" በሚልም አንድ ፅሁፍ አውጥቷል። አዘጋጁም አውስትራሊያ በተደጋጋሚ በቻይና ላይ ለምታደርገው ጥቃት ምላሽ ነው ብሏል። "አሁንም ቢሆን የሚሰማኝ በጫማዬ ላይ የተለጠፈች ማስቲካ ነው እንደሆነች ነው። ላራግፈው የማልችል ነገር ግን መጣበቁ ደስ የማይል ስሜት ነው የሚሰማኝ። ይህንን እንደ አገላለፅ ነው የተጠቀምኩበት፤ ይህንን ደግሞ እንደ አስተያየት መስጠት መብቴ ነው" ብሏል። ለአዘጋጁ በዋናነት የቻይና ፍጥጫ ከአሜሪካ ጋር ነው። በመጪው ህዳር የሚደረገው የአሜሪካ ምርጫን ለማሸነፍ በሚልም ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው ይላል። መጪው ምርጫም አሜሪካ ከቻይና ጋር ሊኖራት የሚችለውን ግንኙነት የሚወስን ይሆናል። ሆነም ቀረም በአለም ላይ ኃያሏንና ታላቋን አገር ቻይና አሜሪካም ሆነ ሌሎች አገራት በጠላትነት ሊመለከቷት አይገባም። አይ ዌይዌይ እንዳለው ለምዕራቡ አለምም ሆነ በአለም ላይ ቻይና ያላትን ተፅእኖ ለመግታት ጊዜው ረፍዷል።
42728942
https://www.bbc.com/amharic/42728942
የኢህአዲግ ፖለቲከኞችን የመፍታት አንድምታ
እንደ ኢትዮ ትራያል ትራከር ድረገፅ መረጃ ከሆነ በአሁን ሰአት በፀረ ሽብር ሕጉ ተከሰው ጉዳያቸው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተለያዩ ችሎቶች እየታየ ያለ ከ900 በላይ ሰዎች ይገኛሉ።
ዶ/ር መረራ ጉዲና እነዚህ ግለሰቦች ከግንቦት 7፣ ከኦነግ እና ሌሎች በኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር አብራችኋል በሚል የተከሰሱ መሆናቸውን ድረገፁ ላይ የሰፈረው መረጃ ያሳያል። በሀገሪቱ ከሶስት አመት በላይ በዘለቀው ተቃውሞ ምክንያት መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ ቃል ከገባ በኋላ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ አቶ ጌታቸው አምባዬ 115 በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሥር የሚገኙ 413 ደግሞ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ስር ያሉ እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ይለቀቃሉ ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል። ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ክሳቸው የሚቋረጠው እና ይቅርታ የሚደረግለቸው በጸረ-ሽብር ህጉ የተከሰሱትንም ይጨምራል ብለው ነበር። ይህንን ተከትሎም ዶ/ር መረራን ጨምሮ ሌሎች እስረኞች ተለቀዋል። የእነዚህ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት መለቀቅ በርግጥ ኢህአዴግ እንዳለው የፖለቲካውን ምህዳር ያሰፋል? የተሻለ መግባባትስ ይፈጥራል ስንል ምሁራንን አረናግረናል። ዶ/ር አሰፋ ፍሰሃ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። ይህ የመንግስት ውሳኔ ያለውን አንድምታ ሲያስረዱ፤ ለበርካታ ዓመታት ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን ለመመለስ መሪዎቹ እስር ቤት ተቀምጠው የተሻለ መግባባት መፍጠር እና ከህዝብም ጋር ለመነጋገር አስቸጋሪ መሆኑን መንግሥት ተረድቷል ይላሉ። "መንግሥት አሁን የወሰደው እርምጃ ባለፈው ሃያ አምስት አመታት ውስጥ የመድብለ ፓርቲ ስርአት በኢትዮጵያ የሚፈልገውን ያክል ስላልሄደ ነው። በተቃዋሚዎችም ሆነ በመንግስት በራሱ ችግር ውጤቱ አስደሳች አልነበረም።" ስለዚህ የተሻለ የመድብለ ስርአት እና የተሻለ መግባባት መፍጠር እንዲቻል እነዚህን መሪዎች መፍታት የግድ ነው ብለዋል። ላለፉት ሶስት ዓመታት ሕዝቡ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ሲጠይቁ ነበር የሚለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪ የሆነው ኩማ በቀለ፤ ''መንግሥት እስረኞቹን የፈታው ለታሳሪዎቹ ፍቅር ኖሮት ሳይሆን ህዝቡ ከፍተኛ ጫና ስላሳደረበት ነው' ይላል። ከባለፉት 26 ዓመታት ጀምሮ በተለያዩ ፖለቲካዊ ምክንያቶች የታሰሩት ዜጎች ቁጥር ወደ አንድ መቶ ሺህ ይጠጋል የሚሉት ደግሞ የህግ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ብርሃነ መስቀል ሰኚ ናቸው። ዶ/ር ብርሃነ፤ ይህን ያክል የፖለቲካ እስረኛ በሃገሪቱ ውስጥ እያለ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን መፍታት ''በህዝብ እንደ መቀለድ ነው'' ይላሉ። የፖለቲካ አመራሮችን እና አባላትን በመፍታት ብቻ የኢትዮጵያን ችግር ይፈታል ብለው የማያምኑት ዶ/ር አሰፋ ፍሰሃ ቀሪዎቹን ችግሮች ለመፍታት ግን የመጀመሪያ ጥሩ እርምጃ ነው ብለዋል። አቶ ነፃነት በላይ በአምንስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ የጥናት እና አድቮኬሲ ዳይሬክተር ናቸው። ድርጅታቸው የእነዶ/ር መረራን መለቀቅ ተከትሎ መግለጫ አውጥቷል። አቶ ነፃነት ስለመግለጫው ይዘት ሲያብረሩ "የተወሰኑ እስረኞች መፈታት ጥሩ እርምጃ ነው። ነገር ግን በርካታ የሕሊና እስረኞች አሁንም በእስር ቤት ታስረው፣ ተፈርዶባቸው አልያም የፍርድ ሂደታቸውን የሚከታተሉ አሉ፤ ስለዚህ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መለቀቅ አለባቸው የሚል መልዕክት በመግለጫው ላይ ተላልፏል ብለዋል። አቶ ነፃነት የመንግስት ባለስልጣናትም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ በተለያየ ፖለቲካዊ ምክንያት ሰዎች እንዳይታሰሩ የማረጋገጫ መፍትሔ መውሰድ አለባቸውም ይላሉ። እንደ አቶ ነፃነት ለዚህም የሚረዳው ደግሞ እንደ ፀረ ሽብር ሕጉ ያሉ ለበርካታ ሰዎች መታሰር ምክንያት የሆኑ ሕጎች በአስቸኳይ በሕዝብ እንደራሴው ቀርበው አስፈላጊው ማሻሻያ ሲደረግባቸው ነው። ምህዳሩን ማስፋት ''በመጀመሪያ ደረጃ የህዝቡ ጥያቄ የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት ሳይሆን ስልጣንን ከመንግሥት ወደ ህዝብ ይሸጋገር ነው። መንግሥት የህዝቡን ጥያቄ የተረዳበት ሁኔታ በራሱ ትክክል አይደለም'' ሲሉ ዶ/ር ብርሃነ ያስረዳሉ። ዜጎችን ያለአግባብ ለእስር የሚዳርጉ ህግ እና ስርዓቶች እስካልተሻሻሉ ድረስ፣ የመንግሥት ስራ አስፋጻሚ አካላት ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እስካልተወጡ ድረስ እና የፍትህ አካላትም በራሳቸው የሚመሩ እስካልሆኑ ድረስ እስረኞችን በመፍታት ብቻ መንግሥት እንደሚለው የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት አይቻልም ሲሉ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል ይሞግታሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሰዎች ሃሰባቸውን በነፃ በመግለፃቸው፣ በፖለቲካ ምህዳር ውስጥ በመሳተፋቸው ብቻ እስርና እንግልት እየደረሰባቸው ይገኛል የሚሉት አቶ ነፃነት ደግሞ ይህንን በቃ ብሎ ማቆም ለሃገሪቷ መረጋጋት፣ ለዲሞክራሲ መጎልበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ሲሉ ያስረዳሉ። ዋናው ነገር ግን ይህ እርምጃ ብዙዎችን ያጠቃለለ ነው ወይ የሚለው ነው የሚሉት አቶ ነፃነት "አሁንም ድረስ በእስር ቤቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ያለአግባብ የታሰሩ ዜጎች አሉ፤ ስለዚህ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታት ይገባቸዋል" ብለዋል። "ከዚህም በተጨማሪ መንግስት አስፈላጊ የሆኑ የሕግ ማሻሻያዎችን መውሰድ ይገባዋል። እንዲህ አይነት መዋቅራዊ ለውጦች ካልተወሰዱ ይህ ብቻውን በቂ ላይሆን ይችላል።" ሰዎች በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፈው በነፃነት ሃሳባቸውን መግለፅ የሚችሉት እና የፖለቲካው ምህዳርም የሚሰፋው የዜጎች ሰብአዊ መብት ሲጠበቅ ነው የሚሉት አቶ ነፃነት እነዚህን የሰብዓዊ መብቶች ደግሞ ኢትዮጵያ መፈረሟን ያስታወሳሉ። አቶ ነፃነት ኢትዮጵያ ይህንን ባላከበረችበት ዜጎች እታሰራለሁ እገደላለሁ ከሚል ፍራቻ ተላቀው ሃሳባቸውን በነፃነት ባልሰጡበት የፖለቲካ ምህዳሩ ይሰፋል ብሎ መናገር ያስቸግራል ሲሉ ይሰጋሉ። ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ከፖለቲካ ፓርቲዎችም ይሁን ከግለሰቦች ጋር ለሚኖረው ውይይት እና ንግግር እነዚህ መብቶች መጠበቅ አለባቸው ሲሉ ይመክራሉ።
news-55610111
https://www.bbc.com/amharic/news-55610111
አሜሪካ ፡ ዶናልድ ትራምፕ ከሥልጣን እንዲባረሩ ዲሞክራቶች ምክትላቸው ላይ ጫና እያሳደሩ ነው
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና ዲሞክራቶች ባለፈው ሳምንት ኮንግረስ ሲወረር ዶናልድ ትራምፕ የነበራቸውን ሚና ተከትሎ ከስልጣን እንዲያነሷቸው በምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ላይ ጫናቸውን አበርትተዋል።
አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የሕግ አውጪዎቹ ፔንስ ፕሬዝዳንቱን ለቢሮው ብቁ አለመሆናቸውን በማሳወቅ 25ኛ የሚባለውን የሕግ ማሻሻያ [አሜንድመንት] ተግባራዊ እንዲሆን እንዲጠይቁ ሃሳብ እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል። ምክትል ፕሬዝዳንት ፔንስ ግን ሀሳቡን ይቃወማሉ ተብሏል። ፕሬዝዳንት ፔንስ ፈቃደኛ ካልሆኑ፣ ደጋፊዎቻቸውን ወደ ካፒቶል እንዲወጡ ጥሪ ያቀረቡት ትራምፕ እንዲከሰሱ ምክር ቤቱ ድምጽ ይሰጣል። ሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድምጽ ተጭበርብሯል የሚሉ ያልተረጋገጡ ክሶችን በመደጋገም የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በዴሞክራቶችና ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሄደ ሪፐብሊካኖች ዘንድ አመጽ አነሳስተዋል በሚል ክስ እየቀረበባቸው ነው። በጥቃቱ የካፒቶል ሂል ፖሊስ መኮንንን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሞተዋል። ትራምፕ ትዊተርን ጨምሮ ከበርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ታግደው ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ምንም ዓይነት ይፋዊ መግለጫ አልሰጡም። ዲሞክራቱ ጆ ባይደን ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣኑን ለመረከብና ትራምፕ ዋይት ሐውስ ለመልቀቅ ቀናት ብቻ ቀርቷቸዋል። ትራምፕ ቀናት በኋላ በሚደረገው የባይደን በዓለ ሲመት ላይ እንደማይገኙም ተናግረዋል። ፔሎሲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላኩት ደብዳቤ እንዳሉት ፔንስ በሕገ-መንግሥቱ 25ኛ ማሻሻያ መሠረት ትራምፕን ከዋይት ሐውስ አስወግደው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ይጠይቃሉ። ምክር ቤቱ ማክሰኞ ዕለት በውሳኔው ላይ ድምጽ ሊሰጥ ይችላል። ከዚያ በኋላ ፔንስና ካቢኔው ምክር ቤቱ ወደ ክስ ከመግባቱ በፊት እርምጃ እንዲወስዱ 24 ሰዓታት ይሰጣቸዋል። "በፍጥነትነት እርምጃ እንወስዳለን ምክንያቱም ፕሬዝደንቱ ለሁሉም ስጋት ናቸው። በፕሬዝዳንቱ በዲሞክራሲያችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት በዘግናኝ ሁኔታ ተጠናክሮ በመቀጠሉ እርምጃው አስቸኳይ ሊሆን ይገባል" ብለዋል። ምንም እንኳን ፔንስ እሁድ ዕለት የባይደን በዓለ ሲመት ላይ ለመሳተፍ ማቀዳቸውን በመግለጽ ራሳቸውን ከፕሬዚዳንቱ ያራቁ ቢመስሉም ከስልጣን እንዲነሱ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው የሚያሳይ ምልክት ግን የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለተኛው የሪፐብሊካኑ ሴናተር ፓት ቶሜይ ፕሬዚዳንቱ "ስልጣናቸውን መልቀቅና በተቻለ ፍጥነት መሄድ አለባቸው" በማለት የአላስካውን ሊዛ ሙርኮቭስኪን ተቀላቅለዋል። ፔንስ በሃሳቡ ካልተስማሙስ? የምክር ቤቱ ዴሞክራቶች በክሱ ለመግፋት ቃል ገብተዋል። ዲሞክራቶች በትራምፕ ላይ "አመፅን የማስነሳትን" ክስ ሊመሠርቱ ይችላሉ ብለዋል ፔሎሲ። የአሜሪካ ከፍተኛ የሕግ አውጪዎች ትራምፕን በምክር ቤቱ ለመክሰስ የሚሰጠው ድምጽ እስከ ሳምንቱ አጋማሽ ድረስ ሊከናወን እንደሚችል ይናገራሉ። በዚህም ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ ሁለት ጊዜ ክስ የተመሠረተባቸው ብቸኛው ፕሬዝዳንት ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚያ ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲወገዱ ጉዳዩ የሁለት ሦስተኛ ድምጽ አስፈላጊ ወደ ሚሆንበት ሴኔት ይመራል። ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙም ሴኔቱ ትራምፕ እንደገና የመንግሥት ስልጣን እንዳይዙ ለማድረግ ድምጽ ሊሰጥ ይችላል። እስካሁን የትኛውም የሪፐብሊካን ሴናተር ትራምፕን በፈጸሙት ጥፋት ለመወንጀል ድምጽ እንሰጣለን አላለም። ዋይት ሐውስ እና ከፍተኛ ሪፐብሊካኖች ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲነሱ መፈለጉ "ፖለቲካዊ እርምጃ ነው" ያሉ ሲሆን "ታላቋን አገራችንን የበለጠ ለመለያየት ብቻ የሚያገለግል ነው" ሲሉም አጣጥለውታል። ባይደን "ለረጅም ጊዜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሥራውን ብቁ አይደሉም" ብለው እንደሚያስቡ ቢገልጹም ከሥልጣን መነሳታቸው ጉዳይ ግን የኮንግረሱ ውሳኔ ነው ብለዋል።
48065372
https://www.bbc.com/amharic/48065372
በአሜሪካ በግድያ የሚፈለገው ዮሃንስ ነሲቡ ተላልፎ ተሰጠ
በአሜሪካን ሃገር በሁለት ሰዎች ግድያ ክስ የተመሰረተበት እና በኢትዮጵያ ተሸሽጎ የነበረው ዮሃንስ ነሲቡ ለአሜሪካ መንግሥት ተላልፎ ተሰጠ።
ዮሃንስ ነሲቡ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የፌርፋክስ ፖሊስ ዮሃንስ ነሲቡ ትናንት አሜሪካ መድረሱን በድረ-ገጹ አስታውቋል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቨርጂኒያ ግዛት ፌርፋክስ ካውንቲ ፍርድ ቤት በሁለት ሰዎች ግድያ እና ያለ አግባብ የጦር መሳሪያ መጠቀም በሚሉ ወንጀሎች ክስ የተመሰረተበትን ዮሃንስ ነሲቡን አሳልፎ ለመስጠጥ ስለመወሰኑ መዘገቡ ይታወሳል። • አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ ተመሰረተ • ኢትዮጵያ ውስጥ የተሸለሙት ጋዜጠኞች ከእስር ተለቀቁ • ጠቅላይ ሚንስትሩ እንቁላል ተወረወረባቸው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና የአሜሪካ ፖሊስ እንደሚሉት ዮሃንስ ነሲቡ በዛብህ የተባለው ግለሰብ፤ ከሁለት ዓመታት በፊት በአሜሪካን ሃገር ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ገድሎ ወደ ኢትዮጵያ በማምለጥ ተጠርጥሯል። ''ዮሃንስ ነሲቡ በዛብህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የአሜሪካ ዜግነት አለው። የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ ተጠርጣሪው ከጥቂት ዓመታት በፊት በአሜሪካ ፈጽሞታል ተብሎ ለተጠረጠረበት የሁለት ሰዎች ግድያ እና በሁለት ያለ አግባብ የጦር መሳሪያ መጠቀም በሚሉ ወንጀሎች፤ በድምሩ በአራት ወንጀሎች እንደሚፈለግ ጠቁመው ተጠርጣሪው ተላልፎ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ጥያቄ ባቀረቡበት ሰነድ ላይ ወደፊት ኢትዮጵያ ለሚኖራት ተመሳሳይ ጥያቄ አሜሪካ ተባባሪ እንደምትሆን ገልጸዋል።'' በማለት ዮሃንስ ነሲቡ ተላልፎ እንዲሰጥ ስለመወሰኑ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግነኙነት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ ያብራራሉ። ሄኖክ ዮሃንስ እና ቅድስት ስሜነህ የፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት እንደሚለው ከሆነ የ24 ዓመቱ ዮሃንስ ነሲቡ ታህሳስ 7/2009 ዓ.ም. እና ታህሳስ 8/2009 ዓ.ም. ባሉት ተከታታይ ቀናት ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የ22 ዓመት ወጣቶች ሄኖክ ዮሃንስ እና ቅድስት ስሜነህን በጥይት መትቶ በመግደል ተጠርጥሯል ይላል። የአሜሪካ ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ መረጃዎች ወደ ተጠርጣሪው ከመጠቆማቸው በፊት ዮሃንስ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ሸሽቷል። ተጠርጣሪው ዮሃንስ ነሲቡ ለአሜሪካ መንግሥት ተላልፎ በመሰጠቱ ''የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን የደህንነት ቢሮ፣ ፌደራል ፖሊስ እና የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግን ለትብብሩ እና ሙያዊ ተግባር ያመሰግናል'' ያለው የፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ነው።
51102386
https://www.bbc.com/amharic/51102386
ናሳ፡ ከአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የመነጨው ጭስ ዓለምን ይዞራል
የአሜሪካው የጠፈር ሳይንስ ተቋም ናሳ ከአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የተነሳው ጭስ ዓለምን ዞሮ ወደ መጣበት ይመለሳል ሲል ተንብየዋል።
የአውስትራሊያ ምስራቃዊ ክፍልን ለወራት ሲያቃጥል የነበረው ሰደድ እሣት ጭስ የፓሲፊክ ውቅያኖስ ጣሪያ ላይ ተንሳፎ ይገኛል። ናሳ እንደሚለው በአውⶂጳውያኑ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ቀን ከአውስትራሊያ የተነሳው ጭስ የደቡብ አሜሪካ ሰማይ ላይ ታይቷል፤ በሳምንቱ ደግሞ የዓለምን ግማሽ ተንሸራሽሯል። ጭሱ ዓለምን ቢያንስ አንድ ጊዜ ሊዞራት እንደሚችል ናሳ አሳውቋል። የአውስትራሊያ ሰደድ እሣት ከ10 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ያቃጠለ ሲሆን 27 ሰዎችን ገድሏል፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዱር እንሳስትም ሰለባ ሆነዋል። 2 ሺህ ገደማ መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ዶጋ አመድ ሆነዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች የአውስትራሊያ ሰደድ እሣት የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ማሳያ ነው ይላሉ። ናሳ የሰደድ እሣቱ ጭስ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ከእሣት የሚፈጠር መብረቅ መሥራት ችሏል ይላል። ጭስ በጣም ኃያል ከመሆኑ የተነሳ ከመሬት ወደ ሰማይ 17̌ ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ተጉዞ ስትራቶስፌር የተሰኘው የሰማይ ክፍል ላይ መስፈር ችሏል። ተቋሙ፤ ጭሱ ወደ ሰማይ ከተመዝገዘገ በኋላ ሙቀት ወይስ ቅዝቃዜ ፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ጥናት ላይ መሆኑንም አሳውቋል። የደቡብ አሜሪካ ሃገራትና የአህጉረ-አውስትራሊያ አካል የሆነችው ኒው ዚላንድ በአውስትራሊያ ሰደድ እሣት ምክንያት ሰማያቸው ታፍኖ እንደነበር የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች የማሕበራዊ ድር-አምባ ተጠቃሚያዎች አጋርተዋል። ኒው ዚላንድን ጨምሮ ሲድኒ፣ ሜልቦርን፣ ካንቤራ እና አደላይድን የመሳሰሉ ትላልቅ የአውስትራሊያ ከተሞች በሰደድ እሣቱ ምክንያት ንፁህ አየር መተንፈስ ተስኗቸው ሰንብተዋል። አውስትራሊያ አሁንም እየተቃጠለች ነው። 100 ገደማ ጫካዎች አሁን እሣት ይዟቸዋል። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጣለ ያለው ዝናብ ሁኔታዎችን ቀዝቀዝ አድርጓቸዋል። ጭሱ ግን መጓዙን እንደሚቀጥል ናሳ አሳውቋል። አፍሪቃን ጨምሮ ሁሉንም የዓለማችን አህጉሮች ሊነካ ይችላልም ተብሏል። የአውስትራሊያን ጭስ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እናየው ይሆን?
news-52494919
https://www.bbc.com/amharic/news-52494919
ኮሮናቫይረስ፡ "የቱሪዝም እንቅስቃሴው ልክ መብራትን የማጥፋት ያህል በቅጽበት ቆሟል"
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርስኝ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጽዕኖው በከፍተኛ ሁኔታ እየታየ ይገኛል።
ተጽዕኖው ክንዱን ካበረታባቸው ዘርፎች መካከል የቱሪዝም ዘርፉ አንዱ ነው። በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ባለበት አማራ ክልል ተመራጭ መዳረሻ በሆኑት በላል ይበላ እና በጎንደር እያሳደረ የሚገኘውን ተጽዕኖ ለመመልከት ሞክረናል። በላል ይበላ ከተማ በቱሪስት አስጎብኚነት የሚያገለግሉት ዲያቆን ፈንታ ታደሰ ለቢቢሲ እንደገለጹት ምንም ቱሪስት በአካባቢው የለም። "ቤተክርስቲያኖች ተዘግተዋል። ከቤተክርስቲያን ካለው መንፈሳዊ አገልግሎት ውጪ የጉብኝት ሥራ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል" ብለዋል። "የቅዱስ ላልበላ አብያተክርስቲያናት ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ባሻገር በጣም ብዙ ቁጥር ላላቸው ወጣቶችም ሆነ ለአካባቢው ማኅበረሰብ የገቢ ምንጭ ናቸው። አሁን ግን ጎብኚ ስለሌለ ሥራ ቆሟል" ሲሉ ያስረዳሉ። በላል ይበላ ከተማ ምንም የቱሪስት እንቅስቀሴ እንደሌለ የገለጹት ዲያቆን ፈንታ "የስጦታ ዕቃዎችን የሚሸጡ ብዙ ሰዎች አሉ። ለቱሪስት የሚቀርቡ ብዙ ነገሮችንም ገዝተው ቢይዙም እነዚህን ለቱሪስቱ እንጂ ሕዝቡ የሚገዛቸው አይደሉም። የነበረው እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል፥ አቁሟል። ምንም የለም" ብለዋል። ላል ይበላ ከከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች ህይወት የተመረኮዘው በእርሻ ሲሆን በተጨማሪም የቅዱስ ላሊበላ አብያተክርስቲያናትን ለመጎብኘት በሚመጡ ቱሪስቶች ላይ መሆኑን በላሊበላ ከተማ አስተዳደር የባህል ቱሪዝም ጽህፈት በቤት ኃላፊ የሆኑት መሪ ጌታ መልካሙ አለሙ ገልጸዋል። የግብርና ምርቶችን ለሆቴሎች የሚያቀርቡ፣ በቅሎ አከራዮች፣ የታክሲ ማኅበራ፣ የስጦታ ዕቃ አምራቾች እና ሻጮች፣ የአካባቢ አስጎብኚዎች፣ሆቴሎች፣ ሪዞርት እና ሎጆች በሙሉ ከሺህዎች ከሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸው ጋር ሥራ ማቆማቸውን ገልጸዋል። ኃላፊው ወረርሽኙ "ላል ይበላ ላይ ያስከተለውረ ጉዳት በመሞት እና በመኖር መካከል ያህል ነው ማለት ይቻላል። ይሄ ምንም የተጋነነ አይደለም" ብለዋል። እንደ ኃላፊው ከሆነ ችግሩን ለመቀነስ ከመንግሥት ጋር እየተነጋገሩ ነው። በተለይም ከባንኮች ብድር ወስደው መኪና የገዙ እና ሆቴሎችን ለገዙ ሰዎች የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘም ግፊት እያደረጉ መሆኑን እና "መንግሥትም ያሰበበት ይመስለናል። እንደላል ይበላ ጥቅል መረጃ ስጡን ብለው ሰጥተናል። ምላሹን እየጠበቅን ነው" ብለዋል። ጎንደር ሌላኛዋ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የቱሪዝም እንቅስቃሴው የተቋረጠባት ታሪካዊቷ ጎንደር ናት። በከተማዋ የሚገኘው የጎሃ ሆቴል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አማራ አጥናፉ ከኮሮናቫይረስ መከሰት ጋር ተያይዞ ለቱሪስቶች አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ሆቴላቸው ሥራውን ተቋርጦ መዘጋቱን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተጨማሪም "ጉዳቱ በአሁኑ ወቅት የምንሰራው ሥራ መቋረጡ ብቻ ሳይሆን፤ ለወደፊት በደንበኞች ቀድመው ተይዘው የነበሩ ሥራዎችም በሙሉ ተሰርዘዋል" ሲሉ ያለውን ጫና አስረድተዋል። ነገር ግን ሆቴሉ ያለ አገልግሎት እንዳይቀመጥ ኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኃላፊነቱን ወደመወጣት ፊቱን ማዞሩን ሥራ አስኪያጁ አመልክተዋል። "ቫይረሱ በከተማዋ ቢከሰት የህክምና መስጫ ቦታዎች ተዘጋጅተዋል። የጎደላቸው ህክምና ለሚሰጡ ባለሙያዎች መኖሪያ በመሆኑ፤ እኛ ክፍሎቻችንን ሰጥተን ያለምንም ክፍያ እንዲገለገሉበት አድርገናል።" በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገቡትን የጎንደር አብያተ መንግስታት ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶች እንቅስቃሴ መቆሙን የጎንደር ከተማ ዓለም አቀፍ ቅርስ አስተዳዳር ኃላፊ አቶ ጌታሁን ስዩም ገልጸዋል። ይንንም "በአጭር ቃል ለመግለጽ የኮሮና ወረርሽን ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የጎንደር ቱሪዝም እንቅስቃሴ ልክ መብራትን የማጥፋት ያህል በቅጽበት የቆመ ጉዳይ ነው። ሙሉ ለሙሉ ነው የቆመው" ሲሉ ያስረዳሉ። ኃላፊው አክለውም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የአገር ውስጥም ሆነ የውጭም ቱሪስቶች እንቅስቃሴ አንድ ላይ በመቆሙ ሥራውን ሙሉ ለሙሉ እንዲቆም አድርጎታል። ነገር ግን ይህንን ሁኔታ በመጠቀም ቀደም ሲል በዕቅድ ተይዞ የነበረውን አብያተ መንግሥታቱ ላይ የቅርስ ጥገና እተከናወነ ነው። ጥገናው እና የእንክብካቤ ሥራው ቀደም ሲል ከጎብኚዎች በተገኘ ገንዘብት ቀደም እየተካሄደ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ በአገር ደረጃ ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ወደነበረው የአማራ ክልል ያለው እንቅስቃሴ መቆሙን የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ለቢበሲ ገልጸዋል። በዚህ ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ154 ሺህ በላይ የውጭ አገር ዜጎች ክልሉን የገበኙ ቢሆንም የኮሮናቫይረስ ክስተትን ተከትሎ በአሁኑ ጊዜ አጠቃላይ ቱሪስቶች እንቅስቃሴው መቆሙን አቶ እነድሪስ በማስረጃነት አንስተዋል። "በዚህም ምክንያት ዘርፉ የተሰማሩ ብዙ አካላት ከሥራ ውጪ ሆነዋል" ያሉት ኃላፊው የደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ሙሉ መረጃ እየተጠናቀረ መሆኑን ጠቅሰው "ሰሜን ተራራን ብቻ በአጭሩ ብንወስድ በኢኮ-ቱሪዝም የተደራጁ እና ሥራ ላይ የነበሩ 8300 የሚሆኑ ሰዎች አሁን ከሥራ ውጪ ሆነዋል" ብለዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በአገር አቀፍም ሆነ በክልልለ ደረጃ የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት እና ወደ ነበረበት ለመመለስ የስትራቴጂክ ፕላን ተዘጋጅቷል። "በዘርፉ ብዙ ተዋናዮች አሉ። ዘርፉ ብዙ የሥራ ዕድል የሚፈጥር እና የሚይዝ በመሆኑ የመጀመሪያው የጉዳት መጠን ልየታ ነው። ምን ያህል ሰው ከሥራ ውጪ ነው በሚል የመለየት ሥራ እየተከናወነ ነው። የጉዳቱን መጠን በማየት ከፌደራሉ ፕላን ላይ በመነሳት የክልሉን ስትራቴጂ በማዘጋጀትእና ከዘርፉ ተዋናዮች ጋር ተወያይተን ወደ ሥራ እንገባለን" ሲሉ አስረድተዋል።
news-55495601
https://www.bbc.com/amharic/news-55495601
አዲሱን የየመን ካቢኔ አባላት የያዘ አውሮፕላን ሲያርፍ በተፈጸመ ጥቃት 22 ሰዎች ተገደሉ
በደቡባዊ የመን ኤደን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ቢያንስ 22 ሰዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አዲስ የተመሠረተውን የየመን ካቢኔ ባለሥልጣናት የያዘ አውሮፕላን ከሳዑዲ ወደ የመን ሲመለስ ነው ፍንዳታው የተከሰተው። የመንግሥት ባለሥልጣኖች እና እርዳታ ሰጪዎች ጉዳት የደረሰበቸው ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንስትሩና የካቢኔ አባላቱ ግን እንዳልተጎዱ ተገልጿል። የመረጃ ሚንስትሩ ለጥቃቱ ተጠያቂ ያደረጉት የሁቲ አማጽያንን ነው። ከ2015 ወዲህ የመን በግጭት እየተናጠች የምትገኝ ሲሆን በሳዑዲ የሚመራ የአረብ አገራት ጥምር ኃይል የሁቲ አማጽያንን አሸንፎ ፕሬዘዳንት አብድራቡህ መንሱር ሀዲን ወደ ሥልጣን መመለስ ይፈልጋል። በግጭቱ ሳቢያ ከ110,000 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከዓለም የከፋው ሰብአዊ ቀውስ በተከሰተባት የመን፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ለረሀብ ተጋልጠዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ነገሮችን የበለጠ አባብሷል። አዲሱን የየመን ካቢኔ ወደ የመን የወሰደው አውሮፕላን ካረፈ በኋላ ተሳፋሪዎቹ እየወረዱ ሳለ ከፍተኛ ፍንዳታ ተከስቷል። ሚንስትሮቹን ለመቀበል አውሮፕላን ማረፊያ የተገኙ ሰዎችም ፍንዳታውን ሽሽት ሲበታተኑ ታይተዋል። ብዙም ሳይቆይ መሣሪያ ሲተኮስ ነበር። የኤኤፍፒ ጋዜጠኛና የዓለም አቀፍ ትብብር ሚንስትሩ ናጂብ አልአውጅ ቢያንስ ሁለት ፍንዳታ እንደሰሙ ተናግረዋል። የጥቃቱ መነሻ ገና ባይታወቅም የሮይተርስ የደህንነት ምንጭ ሦስት መሣሪያ በአውሮፕላን ማረፊያው እንደተገኘ ጠቁመዋል። የሳዑዲው አል-ሀዲት የቴሌቭዥን ጣቢያ ሚሳኤል ተተኩሶ ፍንዳታ ሲከሰት የሚያሳይ ቪድዮ ለቋል። እአአ በነሐሴ 2019 ኤደን ውስጥ ወታደራዊ ትእይንት ሲቀርብ በሁቲ የሚሳኤል ጥቃት ሳቢያ 36 ሰዎች ተገድለው ነበር። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በተሰነዘረው ጥቃት አንድ አባሉ መገደሉን፣ ሦስት አባላቱ መጎዳታቸውንና ሌሎች ሁለት ድጋፍ ሰጪዎች የት እንደደረሱ እንደማያውቅ ይፋ አድርጓል። የየመኑ አል-ማስዳር ድረ ገጽ እንዳለው፤ የሠራተኞች ሚንስቴር ጸሐፊ ያስሚን አል-አዋዲ፣ የወጣቶችና ስፖርት ምክትል ሚንስትር ሙነር አል-ዋጄህ፣ ምክትል የትራንስፖርት ሚንስትር ናስር ሸሪፍ ከተጎዱት መካከል ይጠቀሳሉ። ከጥቃቱ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትር ማን አብዱልማሊክ እና የካቢኔ አባላቱ ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ ተዘዋውረዋል። “ሁላችንም ደህና ነን። አውሮፕላን ማረፊያው ላይ የተሰነዘረው የሽብር ጥቃት በየመንና በሕዝቧ የተቃጣው ጦርነት አካል ነው። ኃላፊነታችንን እንድንወጣ የሚያበረታታ ነው” ብለዋል። የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዑክ ማርቲክ ግሪፍትስ በበኩላቸው ጥቃቱን በጽኑ አውግዘዋል። “የካቢኔ አባላቱ ከዚህ በኋላም ከባድ ጊዜ ይጠብቃቸዋል። ብርታቱን ይስጣቸው። ይህ ጥቃት የመንን በአፋጣኝ ሰላማዊ ማድረግ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው የሚጠቁም ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ከኤደኑ የአውሮፕላን ማረፊያ ጥቃት በኋላ ጠቅላይ ሚንስትሩ በነበሩበት የፕሬዘዳንት ቤተ መንግሥት አካባቢም ፍንዳታ ነበር። ሳዑዲ የምታስተዳድረው አል አረቢያ የቴሌቭዥን ጣቢያ ፈንጂ የጫነ ድሮን ተተኩሶበት መውደቁን ዘግቧል። የየመኑ አዲሱ ካቢኔ “የአንድነት ካቢኔ” ይባላል። ውጣ ውረድ ሊገጥመው እንደሚችልም ተጠባቂ ነው። ሆኖም ግን እንዲህ ያለ ጥቃት ይሰነዘራል ተብሎ አልተገመተም። በደቡባዊ የመን የሚኖሩ ዜጎች ለዓመታት ያለፉበትን ስቃይ የሚቀርፍ አስተዳደር እንደተሾመ ለመጠቆም አውሮፕላን ማረፊያው በቀይ ምንጣፍ ተውቦ ነበር። ሆኖም ግን ጥቃቱ የነገሮችን አቅጣጫ ለውጧል።
55255847
https://www.bbc.com/amharic/55255847
አርሜኒያ እና አዘርባጃን ዳግም ወደ ጦርነት እንዳይገቡ ስጋት ተፈጠረ
በሩሲያ አደራዳሪነት ሰላም ያወረዱት አዘርባጃንና አርሜኒያ ዳግም ወደለየለት ጦርነት እንዳይገቡ ተፈርቷል።
አዘርባጃን 4 ወታደሮቼ በአርሜኒያ ተገድለውብኛል ማለቷን ተከትሎ ነው ፍርሃት የነገሰው። ወታደሮቹ የተገደሉት ለጦርነቱ ምክንያት በሆነው የናጎሮኖ ካራባህ ክልል ነው ብለዋል የአዘርባጃን መከላከያ ሚኒስትር። አርሜኒያ በበኩሏ ከሠራዊቷ 6 የሚሆኑት ቆስለውብኛል ይህም የሆነው አዘርባጃን ተኩሳባቸው ነው ስትል ከሳለች። ሁለቱ አገራት ለ6 ሳምንታት የቆየ ከባድ የሚባል ጦርነት አድርገው በሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮች በሁለቱም ወገን ካለቁ በኋላ በሩሲያ ሸምጋይነት የተኩስ አቁም ማድረጋቸው አይዘነጋም። ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸውም መፈናቀል ደርሶባቸዋል። የሁለቱ አገራት ግጭት ናጎርኖ ካራባህ የተሰኘው ክልል ለኔ ይገባል በሚል የተደረገ ነበር። ይህ ክልል የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሕጋዊ የአዘርባጃን ክልል ነው ቢልም በአርሜኒያ የሚደገፉ የአርመን ዜጎች የሚኖሩበትና የሚያስተዳድሩበት ክልል ሆኖ ለዓመታት ቆይቷል። ይህም ከእአአ 1994 ጀምሮ እስከ 2020 የቆየ ነው። ሁለቱ አገራት ከእአአ 1994 ቀደም ብሎ ከባድ የሚባል ጦርነት ቢያደርጉም ያለ ሰላም ስምምነት ጦርነቱ በማብቃቱ ለረዥም ጊዜ በጠላትነት ሲተያዩ ነው የኖሩት። ከሳምንታት በፊት ሩሲያ በአወዛጋቢ ግዛቶቿ ሰላም አስከባሪ ማስፈሯ ይታወሳል። አርሜኒያ በቱርክ የሚደገፈውን የአዘርባጃንን ወታደራዊ ጥቃት መቋቋም ባለመቻሏ የሰላም ስምምነት ማድረጓ ይታወሳል። በኖቬምበር 9 የተፈረመው የሰላም ስምምነት አዘርባጃን በጦርነቱ በጉልበት የተቆጣጠረቻቸውን ግዛቶቿን ይዛ እንድትቀጥል የሚያደርግ ነው። የአወዛጋቢውን ክልል ሁለተኛዋን ትልቋን ከተማ ሹሻን የሚያካትት ነው። አርሜኒያ በዚህ ስምምነት መሠረት ከሌሎች 3 ግዛቶች ጦሯን በማስወጣት ቦታዎችን ለአዘርባጃን ማስረከብ ይኖርባታል። 2ሺህ የሩሲያ ወታደሮች ሰላም ለማስከበር በክልሉ እንዲሰማሩም ስምምነቱ ያዛል። በዚህ ስምምነት አዘርባጃን ከቱርክ ጋር የሚያገናኛትን ቁልፍ መንገድ እንዲሁም የኢራንና ቱርክ ድንበር ስፍራ አግኝታለች። በአጠቃላይ የሰላም ስምምነቱ ለአርሜኒያ ከፍተኛ ሽንፈት በመሆኑ አርሜኒያዊያን ቁጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። በዚህ ጦርነት በትንሹ 5ሺ ወታደሮች መገደላቸው ይገመታል። አሁን አገረሸ በተባለው ግጭት ሁለቱ አገራት አንዱ ሌላውን በመካሰስ ላይ ናቸው። አርሜኒያ ጦርነቱን መቋቋም ባለመቻሏ የፈረመችውን የሰላም ስምምነት የአርሜኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን "ለኔም ለሕዝቤም እጅግ የሚያም ስምምነት ነው የፈረምኩት" ሲሉ ገልጸውት ነበር።
news-45867173
https://www.bbc.com/amharic/news-45867173
የቪንሰንት ኮምፓኒ ወላጅ አባት የመጀመሪያው ጥቁር ከንቲባ ሆነው ተመረጡ
የማንችስተር ሲቲ እና የቤልጄም ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ቪንሰንት ኮምፓኒ ወላጅ አባት በቤልጂየም የመጀመሪያው ጥቁር ከንቲባ በመሆን ተመረጡ።
ፒየር ቪንሰንት ብራስልስ ውስጥ በምትገኝ ጋንሾሬን በምትባል ምርጫ ጣቢያ ላይ በርካታ ድምጽ በማግኘታቸው ከንቲባ ለመባል በቅተዋል። ኮምፓኒ እአአ በ1975 ነበር ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ ወደ ቤልጄም የመጡት። ሰውዬው ከ2006 ጀምሮ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ በማድረግ በብራሰልስ ግዛት ውስጥ የህዝብ ተወካይ በመሆን ከአራት ዓመታት በፊት የምክር ቤት ወንበር ማሸነፍ ችለው ነበር። • ረጅሙ የአውሮፕላን በረራ ስንት ሰዓት ይፈጅ ይሆን? • አፍሪካዊያን ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትን መጎብኘት ለምን ይከብዳቸዋል? የማንችስትር ሲቲ እግር ኳሰኛ በሆነው ዝነኛው ልጃቸው በርካቶች ያውቋቸዋል። የቪንሰንት ኮምፓኒ ወንድም ፍራንኮኢስ ደግሞ ቤልጄም ውስጥ ለሚገኝ ክለብ ይጫወታል። ወንድማማቾቹ ወላጅ አባታቸውን በጋራ በመሆን የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በቪንሰንት ኮምፓኒ ኢንስታግራም ገጽ ላይ የተለጠፈው የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት፤ ወንድማማቾቹ ''ታሪክ ተሰራ! አባታችን በጣም ኮርተንብሃል'' ይላል። • ሙሽሪት እጮኛዋ መቃብር ላይ ድል ባለ ሠርግ ተሞሸረች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ትውልዳቸው ከቤልጄም ውጪ የሆኑ ስደተኞች በሃገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ እየጨመረ መጥቷል። የቱርክ ስደተኞች ልጅ የሆነው ኢሚር ኪር 2012 ላይ የሴንት-ጆስ ከንቲባ በመሆን ተመርጦ ነበር። ወላጅ አባቷ ከሞሮኮ የሆኑት ናዲያ ሳሚኔት ደግሞ የሎንደርዘል መሪ በመሆን 2016 ላይ ተመርጣ ነበር።
news-47743564
https://www.bbc.com/amharic/news-47743564
ለመጀመሪያ ጊዜ ከኤች አይቪ በሽተኛ ኩላሊት ተለገሰ
በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ኤች አይቪ ኤድስ በሽተኛ ወደ ሌላ የኩላሊት ልገሳ ተደረገ።
ኒና ማርቲኔዝ [መሀል] ቀዶ ጥገናው የተደረገው በአሜሪካ ሜሪላንድ ጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል ሲሆን ሁለቱም ታካሚዎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል። "በዓለማችን ኤች አይቪ ያለበት ሰው ኩላሊቱን ሲለግስ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው" በማለት ዶ/ር ዶሪ ሴጄቭ ትናገራለች። ከዚህ በፊት በሚለግሰው ሰው ላይ ኤች አይቪ ከፍተኛ የኩላሊት በሽታ የመፍጠር ዕድል አለው ተብሎ ይታሰብ ነበር። ነገር ግን አዲስ የመጡት መድኃኒቶች በኩላሊት ላይ ጉዳት እንደማያደርሱ ተረጋግጧል። ጆን ሆፕኪንስ የምትሠራው ዶ/ር ክርስቲን ዱራንድ ቀዶ ጥገናው "ኅብረተሰው ኤች አይቪን የሚያይበትን መንገድ ይፈትናል፤ ከዚም አልፎ መድኃኒቶች እንዲሻሻሉ ያደርጋል" ብለዋል። ታካሚዎቹ "በዚህ ልዩ ዕድል በጣም ደስተኛ ናቸው፤ አሁን የረጅም ጊዜ ውጤቱን ነው የምንጠባበቀው" በማለት ዶ/ር ዱራንድ ጨምረዋል። ቀዶ ጥገናው የተካሄደው ሰኞ ሲሆን ኩላሊት የለገሰችው የ35 ዓመቷ ኒና ማረቲኔዝ "በጣም ደህና ነኝ" በማለት ለጋዜጠኞች ተናግራለች። ኩላሊቷን ለመለገስ ያነሳሳት የ"ግሬይስ አናቶሚ" ተከታታይ ፊልም አንድ ክፍል እንደሆነ ተናግራ በዓይነቱ የመጀመሪያው የሆነውን ቀዶ ጥገና ማድረጓ እንዳስደሰታትም ተናግራለች። "ዶክተሮቹ እኔን እየጠበቁ እንደነበር አውቃለው፤ ይህን የማድረግ ፍላጎት ያለው ማንም ሰው ቢሆን እንደሚቻል አሳይቻለው፤ ስለዚህ ቀጣዩን ሰው ለማየት ጓጉቻለው" ትላለች ኒና። ኩላሊት የተቀበለው ሰው እራሱን ለመግለፅ ያልፈለገ ቢሆንም ጤናው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሆነ ዶ/ር ዱራንድ ተናግረዋል። በዓለማችን ወደ 37 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከኤች አይቪ ጋር ይኖራሉ። • ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ • ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች
47876869
https://www.bbc.com/amharic/47876869
የሱዳን ፖሊስ አባላት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ እንዳይወስድ ታዘዙ
የሱዳን ፖሊስ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወስድ አባላቱን አዘዘ። ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ከአርብ ዕለት ጀምሮ በጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።
ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሺር ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ ናቸው። ቀደም ብሎ ከዋና መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውጪ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ የተሰማ ሲሆን ይህ የሆነውም ወታደሮች ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ላይ የመንግሥት የደህንነት ኃይሎች እንዳይተኩሱባቸው ሲከላከሉ እንደሆነ ተሰምቷል። የፖሊስ ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ "ሁሉንም አባላቱን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንዳይተኩሱ ታዟል።" ብሏል። • የዓለማችን ሃብታም ሴቶች • በሰሜን ሸዋ ዞኖች የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዘ • በሊቢያ በስራ ላይ ያለ ብቸኛው አየር መንገድ ጥቃት ደረሰበት "ፈጣሪ ሀገራችንን እንዲያረጋጋ እና ደህንነታችን እንዲጠብቅ .... ሱዳናውያን አንድ እንዲያደርገን....ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር መግባባት ላይ እንድንደርስ እንፀልያለን"ብለዋል በመግለጫቸው። ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ለመበተን የሞከሩ የብሄራዊ ፀጥታና ደህንነት አባላት ከወታደሩ ጋር መጋጨታቸው ተዘግቧል። የተቃውሞ ሰልፉ ከተጀመረ ቢያንስ ሁለት ወታደሮች ከዋና መስሪያ ቤቱ ውጪ መሞታቸው ተዘግቧል። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰባት ተቃዋሚ ሰልፈኞች መሞታቸውን 15 መጎዳታቸውን እና 42 የደህንነት ኃይሎች መጎዳታቸውን ገልፀው ነበር። 2ሺህ አምስት መቶ ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል። ከተቃዋሚ ሰልፈኞቹ አንዱ ለቢቢሲ እንደገለፀው ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ፣ ጥይት በደህንነት ኃይሎች ተተኩሷል። ወታደሮችም ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በግቢያቸው እንዲደበቁ እንደረዷቸው ተናግሯል። አክሎም "ኦማር አል በሺር ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ከአደባባዮች ላይ ዞር እንዲሉ ለማድረግ መሞከራቸው እርባና ቢስ ነው ምክንያቱም የትም አንሄድም " ብሏል። ሌላ ተቃዋሚ ሰልፈኛ በበኩሉ ሁሉም የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን እንደማይደግፉ ገልጧል። ከፍተኛ ሹማምንቶቹ አሁንም ፕሬዝዳንቱን የሚደግፉ ሲሆን አነስተኛ ማዕረግ ያላቸውና ተራው ወታደርና አባል ግን ከሕዝቡ ጋር ነው ሲል ለቢቢሲ አስረድቷል። አሜሪካ፣ እንግሊዝና ናርዌይ ሱዳን የፖለቲካ ሽግግር ለማድረግ መዘጋጀት እንዳለበት ገልፀዋል።
50387864
https://www.bbc.com/amharic/50387864
አሜሪካዊቷ ራፐር ካርዲ ቢ ወደ አፍሪካ ልትመጣ ነው
አሜሪካዊቷ ራፐር ካርዲ ቢ ወደ አፍሪካ ልትመጣ መሆኑን የሰሙ አፍሪካውያን አድናቂዎች በደስታና በቅናት ውስጥ ናቸው ተባለ።
ካርዲ ቢ በሚቀጥለው ወር ናይጄሪያና ጋና መጥታ ልትዘፍን መሆኑ ተሰምቷል ካርዲ ቢ በሚቀጥለው ወር ናይጄሪያና ጋና መጥቼ አቀነቅናለሁ ማለቷ ከተሰማ ወዲህ በናይጄሪያና በጋና የሚገኙ አድናቂዎቿ በደስታ ሲፈነጥዙ በሌላ የአህጉሪቷ ክፍል የሚገኙ አድናቂዎች በቅናት 'ቅጥል' ማለታቸው ተሰምቷል። ካርዲ ቢ ባለፈው ሳምንት አርብ በኢንስታግራም ገጿ ላይ "አፍሪካ መጣሁልሽ" ስትል የአፍሪካ ጉዞዋን ዜና አብስራለች። • የሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶች በደህንት ስጋት ተዘጉ • "ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው" • ሂላሪ ክሊንተን የሩስያ እጅ በእንግሊዝ ፖለቲካ ውስጥ ገብቷል አሉ ከዚያ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቿ ምላሻቸውን አስፍረዋል። አንድ የድምጻዊቷ አድናቂ "ወደ ናይጄሪያ እንኳን በደህና መጣሽ" ያለ ሲሆን ሌላ ደግሞ "ካርዲ በጉጉት እንጠብቅሻለን" ሲል መልዕክቱን አስፍሯል። አንድ ኬኒያዊ ግን "ናይሮቢስ? በሺዎች የምንቆጠር አድናቂዎችሽ እዚህም አለን" ሲል የተማጽኖ የሚመስል መልዕክት ጽፏል። ደቡብ አፍሪካውያንም ተመሳሳይ መልዕክታቸውን በገጿ ስር አኑረዋል። ድምጻዊቷ ከዚህ ቀደም ስትሪፐር [የራቁት ዳንሰኛ] የነበረች ሲሆን በዚህ ስራዋ ላይ እያለች ከእርሷ ጋር ወሲብ መፈፀም ይፈልጉ የነበሩ ግለሰቦችን በመድሃኒት በማደንዘዝ ትዘርፋቸው እንደነበር የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ወጥቶ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብታ ነበር። ካርዲ ቢ የአንድ ልጅ እናት ስትሆን ከራፐር ኒኪ ሚናጅ ጋር ተጋጭተው በገጠሙት ቡጢም የመገናኛ ብዙኀን አጀንዳ ሆና ከርማ ታውቃለች። ካርዲ ቢ ከድምጻዊነቱ ባሻገር 'ሃስለርስ' በተሰኘውና ጄኔፈር ሎፔዝ በመሪ ተዋናይነት ላይ በተሳተፈችበት ፊልም ላይ የተወነች ሲሆን ከዚህ ቀጥሎም በ'ፋስት ኤንድ ፉሪየስ 9' ላይም እንደምትተውን ተነግሯል። ካርዲ ቢ ሙሉ ስሟ ቤልሳሊስ ማርሌኒስ አልማንዘር ሲሆን በ2019 ምርጥ የራፕ አልበም ግራሚን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት ራፐር ሆናለች።