id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
51686708
https://www.bbc.com/amharic/51686708
አሜሪካ፡ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት መፈረም አለበት
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በውሃ የመሙላትና የሙከራ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም እንዳለበት አሜሪካ አርብ ለሊት ባወጣችው መግለጫ ማመላከቷ ይታወሳል።
የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው ቀደም ሲል የነበረውና ግንባታው በታችኛው የተፋሰሱ አገራት ላይ ጉልህ ጉዳት እንዳይደርስ በሚለው የመርህ ስምምነት መሰረት "ግድቡን በውሃ የመሙላትና ሥራውን የመሞከር ሂደት ስምምነት ሳይደረግ መከናወን የለበትም" ብሏል። የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምኑቺን ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት ከዚህ በፊት በነበሩ ስምምነቶች መሰረት ግድቡን በውሃ የመሙላቱ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም አለበት። ትናንት የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ማንኛውም ነገር የኢትዮጵያን ፍላጎትና ጥቅም በሚጠብቅ መልኩ ብቻ እንደሚከናወንና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ድርድር እንደማይካሄድ አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒሰቴር የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር የታላቁን የህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲደረግ ከነበረው ድርድር አንጻር ያወጣውን መግለጫ ከፍተኛ ቅሬታ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል መፈጠሩን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ "የግድቡን የውሃ ሙሌት ከግንባታው ትይዩ በፍትሐዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም እንዲሁም ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርሆዎች መሰረት የምታከናውን ይሆናል" ተብሏል። አርብ ለሊት የወጣው የአሜሪካ መግለጫ በተፋሰሱ አገራት መካከል የተጀመረው ድርድር በቶሎ መጠናቀቅ እንዳለበት የሚኒስትሩ መግለጫ አመልክቶ፣ ግብጽ ስምምነቱን ለመፈረም ያሳየችውን ዝግጁነት አድንቋል። ጨምሮም በኢትዮጵያ በኩል በጉዳዩ ላይ እየተካሄደ ያለውን ብሔራዊ ምክክር መግለጫው እንደሚረዳ በማመልከት ምክክሩ በቶሎ ተጠናቅቆ የድርድር ሂደቱን በማጠናቀቅ በተቻለ ፍጥነት ስምምነቱ እንዲፈረም ፍላጎታቸው መሆኑን የአሜሪካው ባለስልጣን በመስሪያ ቤታቸው በኩል ያወጡት መግለጫ ጠቅሷል። ግድቡን በውሃ የመሙላት ሥራ ከመጀመሩ በፊት በዓለም አቀፍ ደረጃዎች መሰረት ሁሉም አስፈላጊ የደህንነት እርምጃዎች ተግባራዊ ከመደረጋቸው አንጻር በታችኞቹ ተፋሰስ አገራት ግብጽና ሱዳን ሕዝብ ዘንድ ያለውን ስጋት እንደሚገነዘቡ አመልክቷል። የካቲት 19 እና 20 ዋሽንግተን ላይ በሚደረግ ስምምነት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ውይይት ኢትዮጵያ እያደረኩት ያለው አገራዊ ውይይትን ስላላጠናቀቅኩ መሳተፍ አልችልም ስትል ረቡዕ ዕለት በማሳወቋ ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወሳል። • የግዙፉ ግድብ ግንባታ፡ የኢትዮጵያና ግብፅ ቅራኔ በመግለጫው ላይ የአሜሪካው የገንዝብ ሚኒስትር ቴቨን ምኑቺን ከግብጽና ከሱዳን የውጭ ጉዳይና የውሃ ሃብት ሚኒስትሮች ጋር የተናጠልና የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውም ተመልክቷል። ለወራት በኢትዮጵያ፣ በግብጽና በሱዳን መካከል በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው ድርድር በቶሎ መቋጫ እንዲያገኝ እንደምትፈልግ አሜሪካ በመግለጫው አጽንኦት አስታውቃች። አሜሪካ ሶስቱ አገራት ስምምነት እስኪፈራረሙ ድረስ ከህዳሴው ግድብ ድርድር ጋር በተያያዘ ተሳትፎዋ እንደሚቀጥልም ያረጋግጣል የገንዘብ ሚኒስቴሩ መግለጫ። አሜሪካ በሶስቱ አገራት የህግና የቴክኒክ ቡድኖች የቀረቡ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ የስምምነት ሰነዱ እንዲዘጋጅ ነገሮችን ስታሳልጥ እንደነበር ፤ ዓለም ባንክ ደግሞ በስምምነቱ ሰነድ የቴክኒክ ጉዳዮች ዙሪያ ግብአት ማድረጉንም መግለጫው ያትታል። ኢትዮጵያ ባልተሳተፈችበት የዋሽንግተኑ መድረክ ሱዳን እና ግብፅ በተናጠል ከአሜሪካና ዓለምባንክ ጋር ባደረጉት ውይይት ስምምነቱን በሚመለከት ሃሳባቸውን አንፀባርቀዋል። አሜሪካ ባለፉት አራት ወራት የተደረጉ ተግባራት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያሉ ሁሉንም ጉዳዮች የሚዳስስ ስምምነት እንዲደረግ የሚያስችል ውጤት አምጥተዋል ብላ እንደምታምንም በመግለጫው ተገልጿል። በአሜሪካ ዋሽንግትን ዲሲ ለሁለት ቀናት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ በሚደረገው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንደማትካፈል የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር። ሚኒስቴሩ የአሜሪካ መንግሥትና የአለም ባንክ በታዛቢነት በሚገኙበት የካቲት 19 እና 20/2012 ዓ.ም ከሱዳን እና ግብጽ ጋር ሊካሂድ በታቀደው ቀጣይ የሦስትዮሽ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ እንደማትገኝ ያስታወቀው፣ ተደራዳሪ ቡድኑ በአገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባለማጠናቀቁ መሆኑን በመግለጽ ነበር። ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙርያ የሚያደርጉትን ድርድር የአሜሪካ መንግሥት ቀደሞ በታዛቢነት አሁን ደግሞ በአደራዳሪነት መግባቱን በመቃወም በአሜሪካ፣ ዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወቃል።
news-54520002
https://www.bbc.com/amharic/news-54520002
ኢትዮ-ኤርትራ፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ጉብኝቶች ምን ፋይዳ አላቸው?
በድንበር ይገባኛል ምክንያት ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ተፋጠው የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሰላም መድረኩ መምጣታቸውን ተከትሎ የሁለቱ አገራት መሪዎች በርካታ የሥራ ጉብኝቶችን አካሂደዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መጥተው በአገራቱ መካከል ሰላም ከወረደ በኋላ ባሉት ጊዜያት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂቢያንስ ለአራት ጊዜያት ያህል ከልዑካኖቻቸው ጋር ወደ ኢትዯጵያ በመምጣት ይፋዊ ጉብኝትና ውይይቶችን አድርገዋል። እነዚህ ጉብኝቶች በተካሄዱባቸው ጊዜያት ሁሉ መሪዎቹ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ በደፈናው ከመጥቀስ በዘለለ የተደረጉ ውይይቶች ርእስና የደረሱባቸው ስምምነቶች እነዚህ ናቸው የሚሉ ዝርዝር መረጃዎች እስካሁን አልተሰጠም። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰኞ ጠዋት ለሦስት ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በቀጥታ ወደ ጅማ ያመሩ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም እዚያው በመገኘት ተቀብለዋቸዋል። የፕሬዝዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ከአካባቢያዊና አገራዊ ሁኔታዎች አንጻር ያለውን አንድምታ የዓለም አቀፍና የፖለቲካ ተንታኙ አቶ አብዱራሕማን አቡ ሀሽም "አዲስ ነገር የሌለው" ሲሉ ይገልፁታል። በአሜሪካ ጆርጂያ ጉኔት ኮሌጅ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት ዮሐንስ ገዳሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው "እንዲህ አይነት ጉብኝት ቢያንስ በከፍተኛ ባለስልጣናት እና በሁለቱ መሪዎች መካከል በሚገባ ታስቦበት የተደረገ ነው" ሲሉ ይሞግታሉ። አቶ አብዱርሃማን መጀመሪያ በሁለቱ አገራት መካከል የሰላም ስምምነት ሲደረስ በኤርትራውያን ዘንድ የተለያዩ ጥያቄዎች እንደነበሩ በማንሳት፤ አስተዳደራዊና ሕጋዊ መሰረት መያዝ የነበረባቸው ጉዳዮች ሳይዙ መቅረታቸውን ጠቅሰው ስምምነቱ ለኤርትራውያን ያመጣው ለውጥ እንደሌለ ያስረዳሉ። የሁለቱ አገራት ስምምነት ተስፋ አጭሮባቸው የነበሩ ወገኖችም ከዕለት ወደ ዕለት ተስፋቸው እየከሰመ መሄዱን የሚያነሱት አቶ አብዱርሃማን ስምምነቱ የሁለት አገራት ሳይሆን የሁለት ወዳጆች ይመስላል ሲሉ ተቋማዊ መልክ እንደሚጎድለው ይተቻሉ። እንዲህ አይነት ግንኙነት ደግሞ ከዚህ ቀደምም በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል እንደነበር የሚያስታውሱት ምሁሩ፤ ነገር ግን ለሁለቱም አገራት ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት እንደተሳነው በመግለጽ የሁለቱን አገራት ሰላም በሁለት ግለሰቦች መካከል ብቻ ማድረጉ "ትክክል አይደለም፤ ዘላቂ ሊሆን አይችልም" ሲሉ ይገልጻሉ። አቶ አብዱርሃማን "የአሁኑ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጉብኝት ምንም ልዩ የሚያደርገው ነገር የለም" በማለትም ይደመድማሉ። ዮሐንስ ገዳሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሁለቱ አገራት መሪዎች መገናኘት በአጋጣሚ የተደረገ፣ ግጥምጥሞሽ ተደርጎ የሚታይ ሳይሆን ታቅዶበት የሚደረግ መሆኑ መታየት አለበት ሲሉ ይገልጻሉ። ለዮሐንስ (ዶ/ር) የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጉብኝት በሁለቱ አገራት በከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም በርዕሳነ መንግሥታቱ መካከል ቢያንስ አስቀድሞ የታሰበ ሊሆን ይችላል። ሁለቱ አገራት የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ግንኙነታቸው ወደተሳለጠ የኢኮኖሚ፣ የንግድ ትስስር፣ ልዩ ወደ ሆነ ትብብር አድጎ ባይታይም የውስጥ ለውስጥ ንግግሮች እንደሚኖሩ በተዘዋዋሪ እንደሚሰማ ያነሳሉ። ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውንና ትብብራቸውን ወደዚያ ለማሳደግ መተማመን ማሳደግ እንደሚኖርባቸው የሚያነሱት ዮሐንስ (ዶ/ር)፤ ላለፉት 20 ዓመታት በግጭትና በፍጥጫ ውስጥ የነበሩ አገራት ከመሆናቸው አንጻር ብዙ መተማመን ብዙ መነጋገር የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አንዳሉ ያነሳሉ። የሁለቱ አገራት ተደጋጋሚ ጉብኝት ያመጣው ለውጥ በኤርትራ ዘንድ እንደሌለ የሚያነሱት አቶ አብዱርሃማን በበኩላቸው አሁንም የኤርትራ መንግሥት "አምባገነን ሆኖ እንደቀጠለ ነው" ሲሉ ይገልፃሉ። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ላለፉት 30 ዓመታት ተቃዋሚዎቻቸውን በማፈን፣ በማሰር ስልጣን ላይ መቆየታቸውን በመግለጽ ኢትዮጵያም ብትሆን ከኤርትራ ኢመደበኛ ጉብኝቶች ታተርፋለች ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። ግንኙነቱ የፓርቲ እንኳ ነው ብሎ ለመናገር እንደሚቸግር የሚገልፁት አቶ አብዱርሃማን በኤርትራ ፓርቲ አለ ለማለት እንደማያስደፍር ጠቅሰው፤ የአዲስ አበባው ብልጽግና ፓርቲም አንደኛ ጠቅላላ ጉባዔውን እንኳ አለማካሄዱን አንስተው የግለሰቦች ግንኙነት መሆኑን ያሰምሩበታል። ዮሐንስ (ዶ/ር) በበኩላቸው ይህ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ እንዲዳብር ሁለቱ ርዕሳነ መንግሥታት አንዳቸው በሌላኛቸው አገር እየተገኙ መወያየት የመረጡ ይመስላል ሲሉ አክለዋል። ሁለቱ አገራት የጋራ የሆነ ባህል ታሪክ የነበራቸው መሆኑን የሚያነሱት ዮሐንስ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰት ማንኛውም ነገር ኤርትራ ውስጥ የራሱ ተጽዕኖ እንዳለው ሁሉ፤ ኤርትራ ውስጥም የሚከሰት ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ የራሱ ተጽዕኖ አንደሚኖረው ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ችግር መኖሩን በማንሳትም የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሆነውን ጉዳይ በቅርበት ቢከታተል ሊያስደንቅ እንደማይገባም ይጠቅሳሉ። ኤርትራ ውስጥም ቢሆን በርካታ ችግሮች መኖራቸውን የሚያነሱት ዮሐንስ ገዳሙ (ዶ/ር)፤ ነገር ግን ውጥረቱ የሚታየው በዲያስፖራው ዘንድ ስለሆነ ለኢትዮጵያ በቀጥታ አስተያየት ለመስጠትም ሆነ ለመሳተፍ ከባድ መሆኑን ይገልጻሉ። እነዚህ ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸውን እያደሱ ባለበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት በቀጠናው ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ተመልክቶ እንዲሁም የአገራቸውን ጥቅም ከግንዛቤ በማስገባት ተጽዕኖ ቢፈጥሩ ተጠባቂ መሆኑን ይገልጻሉ። ጥያቄው መሆን ያለበት ከቀጠናው ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ገንቢ በሆነ መልኩ ተሳትፈዋል ወይ? የሚለው መሆን እንዳለበትም ያስረዳሉ። የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላም ስምምነት መካከል ተቋማዊ መልክ የያዘ ነገር ተሰምቶ እንማይታወቅ የሚተቹ ወገኖችን በተመለከተ ሲናገሩም "የሁለት መሪዎች መጨባበጥ ራሱ ተቋማዊ ቅርጽ አለው" ብለዋል። ተቋማት ሲባሉ ግዑዝ ሕንጻዎች ወይንም የተለያዩ ሕጋዊ ሰነዶች ላይ ያረፉ ነገሮች ብቻ አለመሆኑን በማንሳትም የሚሰጡትና የሚያሳዩት ምላሽ እንዲሁም መሪዎች አንዳቸው ሌላኛቸውን የሚያዩበት መንገድንም እንደሚጨምር ይገልጻሉ። በተደጋጋሚ የሚደረጉ ግንኙነቶች የሚመሰረቱ ተቋማት ላይ የራሳቸው የሆነ ተጽዕኖ እንደሚኖራቸው በማንሳትም፤ የዚህም ትልቁ ፋይዳ መተማመንን ማዳበር መሆኑን ጠቅሰው ቸል ሊባል የሚገባው አለመሆኑን ዮሐንስ (ዶ/ር) ያብራራሉ። የመሪዎቹ የአሁን ግንኙነት ተቋማዊ ቅርጽ እየያዘ በሚመጣበት ወቅት የሁለቱ አገራት ሕዝቦች ብዙ እምርታ እንደሚያሳዩም በመግለጽ ተስፋቸውን ያስቀምጣሉ። አገራዊ ነባራዊ ሐቆች በተለይ ደግሞ ኤርትራ ውስጥ ያለውን ሁኔታም በማንሳትም ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ዝግ መሆኗን ማስተዋል እንደሚገባ ይነገራሉ። ይህ ዝግ የነበረ የፖለቲካ ምህዳር በዚህ የሰላም ስምምነት ምክንያት ክፍት ወደ መሆን ሊሄድ መሆኑ ኤርትራውያኑ ራሳቸውንም ስጋት ውስጥ ሳይከታቸው እንዳልቀረም ያነሳሉ። ከዚያ አንጻር ደረጃ በደረጃ ኢኮኖሚያዊና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር እንዲሄድ መፈለጋቸውን በማንሳት ከፌሽታና ከሆይ ሆይታው ረጋ ባለ መልኩ ጉዳዮችን እንደገና ለማጤን መፈለግ በእነርሱ ስፍራ መታየቱን ይገልጻሉ። ሁለቱ አገራት የነበራቸውን ቁስል በአንድ ጊዜ አክመውና ረስተው ግንኙነታቸውን በፍጥነት ይጀምሩ ማለት አስቸጋሪ መሆኑን በማንሳትም የመረጡት መንገድ ተገቢ ነው ብለው እንደሚያስቡ ዮሐንስ ገዳሙ (ዶ/ር) ይናገራሉ።
news-51074354
https://www.bbc.com/amharic/news-51074354
በቡሌ ሆራና በሀዋሳ የኒቨርሲቲ የተፈጠረው ምን ነበር?
ትናንት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተቀሰቀሰ ግጭት የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው የዩኒቨርሲቲው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ሰይፉ ለቢቢሲ ገለጹ።
በተያያዘም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ተማሪዎች መካከል ተነሳ በተባለ ግጭት የአንድ ተማሪ ሕይወት አልፏል። በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈጠረው ምን ነበር? ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ተማሪዎች መካከል ተነሳ በተባለ ግጭት የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርማየ አሰፋ ገልፀዋል። ኃላፊዋ እንደገለፁልን እስካነጋገርናቸው ሰዓት ድረስ በዩኒቨርሲቲው ግጭት አለመኖሩን ገልፀው፤ ከትናንት በስቲያ አመሻሹ ላይ ሱራፌል ሳሙኤል የተባለ የአንደኛ ዓመት ተማሪ በተማሪዎች ማደሪያ ኮሪደር ላይ ወድቆ መገኘቱን ተናግረዋል። "ተማሪው በተገኘ ሰዓት ደም እየፈሰሰው ነበር። ወዲያውኑ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ተወሰደ፤ ነገር ግን በጣም አስጊ ሁኔታ ውስጥ ስለነበር ሕይወቱ ሊተርፍ አልቻለም" ብለዋል። ተማሪው በስለት የመወጋት አደጋ እንዳጋጠመው የገለፁት ኃላፊዋ፤ ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኑ ወደ ሚንሊክ ሆስፒታል መላኩን በትናንትናው ዕለት ነግረውናል። ከተማሪው ሞት ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ወደ 44 የሚደርሱ ተማሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም አስረድተዋል። ሟች ተማሪ፤ የእርሱ የዶርም ልጅ ከነበረና አሁን ተጠርጥሮ በተያዘ ተማሪ መካከል የግል ግጭት እንደነበራቸውም ኃላፊዋ አክለዋል። ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ያነጋገርነው የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በምዕራብ ኦሮሚያ ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ ወዲህ የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት መቋረጡን በማስመልከት ተማሪዎች ጠዋት 2፡30 አካባቢ ሰልፍ እንደወጡ ይናገራል። እርሱ እንደሚለው ሰልፉ ሰላማዊ ነበር። ይሁን እንጅ የዩኒቨርሲቲ ግቢ ፖሊሶች "ቀጠቀጡን" ይላል። በዚህም ስምንት ሰዎች በጥይት ሲመቱ የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን ገልፆልናል። ሕይወቱ ያለፈው ተማሪ በጥይት የተመታው በግቢው 'ዲኤስቲቪ' የሚባል አካባቢ ነው ይላል። "ተተኩሶብናል፤ የግቢው ፖሊስ መሳሪያ ይዞ ባይረብሽ በሰላም ወጥተን በሰላም እንገባ ነበር" የሚለው ተማሪው፤ በዱላ እና በጥይት ጉዳት የደረሰባቸውም በርካቶች እንደሆኑ ነግሮናል። ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የዩኒቨርሲቲው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ሰይፉ፤ በግጭቱ የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን እና አንድ ተማሪ በጥይት እግሩ ላይ ተመትቶ ወደ ሃዋሳ ሆስፒታል መላኩን አረጋግጠዋል። ተማሪዎቹ በአራቱ የወለጋ ዞኖች ለምን የኢንተርኔትና ስልክ አገልግሎት ተቋረጠ፣ ለምን በኮማንድ ፖስት ሥር ሆነ የሚሉ መፈክሮችን ይዘው እንደነበር አቶ ዳንኤል ገልፀውልናል። ዳይሬክተሩ እንዳሉት ተማሪዎች ሰላማዊ አካሄድ አልነበራቸውም፤ ድንጋይ መወርወር፣ መስታወቶችን መሰባበር ላይ ነበሩ። ይሁን እንጅ "ተማሪ ላይ አልተተኮሰም ፤ ወደ ላይ ነበር ሲተኮስ የነበረው፤ በተማሪ ጀርባ የገባ እና በተማሪዎች ውስጥ ሆኖ የሚተኩስ አካል እንደነበር ነው የፀጥታ አካላት እየገለፁ ያሉት" ሲሉም ገልፀውልናል። በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ፤ በምዕራብ ኦሮሚያ ያለውን ችግር በመቃወም ከትናንት በስቲያ ምሽት በተነሳ ግጭት በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። ይህንን ተከትሎ በዩኒቨርሲቲው ግጭት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ባላቸው 77 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል። እርምጃ ከተወሰደባቸው ተማሪዎች ሁለቱ ከትምህርታቸው ሲሰናበቱ፤ 75 ተማሪዎች ደግሞ ለሁለት ዓመታት ያህል ከትምህርታቸው ታግደዋል። በቅርቡ የጅማ፣ ወሎ፣ ጎንደር እና ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች በተከሰቱ ግጭቶችና አለመረጋጋት ተሳትፎ ነበራቸው ባሏቸው ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዳቸው ይታወሳል። አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች እርምጃ የወሰዱት በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት ወራት በተከሰቱት ግጭቶች ተሳትፎ ነበራቸው ባሏቸው ከ470 በላይ ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ ነበር።
news-53892020
https://www.bbc.com/amharic/news-53892020
እስራኤል፡ ወጣቶች ከአንድ ሺህ ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ የወርቅ ሳንቲሞች አገኙ
የቅሪተ አካል ምርምር በሚካሄድበት አካባቢ በበጎ ፍቃደኝነት የሚሠሩ የእስራኤል ወጣቶች 1,100 ዓመታት ያስቆጠሩ 425 የወርቅ ሳንቲሞች አገኙ።
በማዕከላዊ እስራኤል የተገኙት የወርቅ ሳንቲሞች በሸክላ ጆግ ውስጥ ተቀብረው ነበር። አብዛኞቹ ሳንቲሞች በጥንታዊ የእስልምና ዘመን ግዛቱ የአብሳድ ካሊፋት ክፍል ሳለ የነበሩ ሲሆኑ፤ 845 ግራም ይመዝናሉ። በተቀበሩበት ወቅት በከፍተኛ ገንዘብ የሚገመት ዋጋ ነበራቸው። የሳንቲሞቹ ዋጋ በዘመኑ አንድ ቅንጡ ቤት ያስገዛ ነበር። ሳንቲሙ የማን እንደነበረና ለምን ከተቀበረበት ሳይወጣ እንደቀረ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። በእስራኤል ጥንታዊ ቅርሶች ባለሥልጣን የሚሠሩት የቁፋሮው ኃላፊዎች ሊያት ናዳቭዚቭ እና ሌሊ ሃዳድ “ሳንቲሞቹን ከ1,100 ዓመታት በፊት የቀበራቸው ሰው ተመልሶ ሊወስዳቸው ሳያስብ አልቀረም። መያዣውን በቢስማር አጣብቀውት ነበር” ብለዋል። እንደዚህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሳንቲሞች አንድ ሥፍራ ተቀብረው ማግኘት ብዙም አልተለመደም። “ወርቅ እጅግ ውድ ከመሆኑ የተነሳ በቁፋሮ ወቅት የተቀበረ ወርቅ ብዙ ጊዜ አናገኝም። ወርቅ እየቀለጠ ከትውልድ ወደ ትውልድ በመሸጋገር ጥቅም ላይ ይውላል” ብለዋል ተመራማሪዎቹ። ወርቁን ካገኙ ወጣቶች አንዱ የሆነው ኦዝ ኮኸን “በጣም ድንቅ ነገር ነው የገጠመኝ። ስቆፍር ስስ ቅጠል የሚመስል ነገረ አየው። በድጋሚ ስመለከተው ግን የወርቅ ሳንቲሞች እንደሆኑ ገባኝ” ብሏል። የወርቅ ተመራማሪው ሮበርት ኩል እንደሚሉት፤ በቁፋሮ የተገኘው የወርቅ መገበያያ ሳንቲም ብቻ ሳይሆን 270 የወርቅ ቁርጥራጮች ጭምርም ናቸው። እነዚህ ቁርጥራጮች እንደ ዝርዝር ሳንቲም የሚያገለግሉ ነበሩ። ከወርቅ ቁርጥራጮቹ አንዱ የባዛንታይን ሥርወ መንግሥቱ ቲዎፍሎስ ምስል አለበት። ምስሉ ከኮንስታንቲሎፕ ምስል ጋር የተያያዘ ሲሆን፤ በወቅቱ ሁለቱ ተቀናቃኞች መካከል አንዳች ትስስር መኖሩን የሚጠቁምም ነው።
44326959
https://www.bbc.com/amharic/44326959
ሠዐሊ እያዩ ገነት "ሀገሬ ራሱ በድንቅ ተቃርኖ ውስጥ ተዛንቃ ስላለች ሥራዎቼም እንደዛ ናቸው"
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህሩ እያዩ ገነት ሥዕልን እንጀራዬ ብሎ ከመያዙ በፊት የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ነበር። ሥዕልን መሳል የጀመረው በተፈጥሯዊ ግፊት እንደሆነ የሚናገረው እያዩ በልጅነት እድሜው ''ነገሮችን ከጽሁፍ ይልቅ በምስል ስመለከት በቀላሉ እረዳ ነበር'' ይላል።
የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ሆኖ ተቀጥሮ ሥራ ቢጀምርም የውስጥ ስሜቱ ግን የሚነግረው ሠዐሊ መሆኑን ስለነበር ወደ አዲኢስ አበባ በመምጣት ዩኒቨርስቲ ገብቶ ስዕልን አጠና። ከዱርቤቴ አቅራቢያ በምትገኘው ጉራች ጊዮርጊስ የተወለደው እያዩ፤ አሁን ለሚገኝበት ደረጃ የአባቱ አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል እንዳልነበር ይገልፃል። አባቱ የልጅነት ፍላጎቱን ነገሮችን በምስል የመግለፅ ንሸጣውን እያዩ የማበረታቻ ሽልማት እየሰጡ ተሰጥኦውን መኮትኮታቸውን ያስታውሳል። እያዩ ነፃ እና ፍቅር በተሞላ ቤተሰብ እና ዘመድ መሀል ነው ያደግኩት በማለት ገጠር ማደጉ ለጥበብ ሕይወቱ ትልቁን አስተዋፅዖ እንዳደረገ ይናገራል። ''ማህበረሰቡ አንድን አርቲስት ጥሩ አርቲስት ነው ብሎ የሚያስበው የአንድን ነገር ተፈጥሯዊ ምስል ሳይቀይር ወይም ሳያዛባ ሲያስመስል ነው'' የሚለው እያዩ በልጅነት እድሜው ይህ አውንታዊ የአሳሳል ዘውግ ተቀባይነት ስለነበረው እሱም የታዋቂ ግለሰቦችን ፎቶግራፎች አስመስሎ በመስራት ከቤተሰቡ እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ሁሉ አድናቆትን ያገኘ እንደነበር ያስታውሳል። ሁነኛ ሃሳብ ገላጩ ጽሑፍ ወይስ ሥዕል? ለእያዩ ምስል ከየትኛውም የሃሳብ ማራመጃ መንገዶች መካከል ጉልበታሙ ነው። የምስልን ጉልበት ከተረዳን ሥዕል ከጽሑፍ በተሻለ ሁኔታ ሃሳባችንን ሊገልጽልን ይችላል ባይ ነው። እንደ እያዩ አተያይ በአንድ ሰው አዕምሮ ውስጥ አንድ ሃሳብ ሲፈልቅ፣ ሃሳቡ ቀድሞ በምስል መልክ በአዕምሮው ውስጥ ይቀረጻል። ''አንድ ደራሲ ድርሰቱን ሲጽፍ በድርሰቱ ውስጥ ያሉትን ገጸ-ባህሪያትን ቀድሞ በአዕምሮው ውስጥ ይስላቸዋል፤ ከዚያም በአዕምሮ ውስጥ የሳላቸውን በጽሑፍ ከወረቀት ጋር ያገናኛቸዋል'' ይላል። እያዩ ብሩሽን ከሸራ ጋር ሲያገናኝ መንፈሳዊ ሙዚቃዎችን እያደመጠ መሳል ይወዳል። ይህ ግን የውጭውን አለም ረብሻ ለማስቀረት እንጂ ነገሮች ፀጥ ካሉ በፀጥታው ውስጥ ተመስጥኦውን በመፈለግ መሳል ይመርጣል። ሥራዎቹን ያቀረበባቸው መድረኮች በሀገርም ውስጥ ሆነ ከሀገር ውጭ በርካታ አውደ ርዕዮችን ላይ የተሳተፈው እያዩ በሀገር ውስጥ በብሔራዊ ሙዚያም እና በርካታ መድረኮች ላይ በግልና በቡድን ሥራዎቹን አቅርቧል። ከኢትዮጵያም ውጪ በአሜሪካንና በኢኳዶር የሥዕል ሥራዎቹን ማሳየት ብቻ ሳይሆን አብሮ ለውይይት የሚሆኑ ፅሁፎችን ያቀረበባቸው መድረኮች እንዳሉም ያስታውሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊትም በጉራማይሌ የአርት ማዕከል ውስጥ ''ነቁጥ'' በሚል ርዕስ ሥራዎቹን ለህዝብ አሳይቷል። በእያዩ የሥዕል ሥራዎች ላይ ቆዳ ትልቅ ቦታ ይዞ ይታያል። በርካታ ሥዕሎቹም በቆዳ ላይ ነው የተሳሉት። ''እኔ ያደኩበት ማህበረሰብ የቆዳን ሥነ-ውበት ጠንቅቀው ያውቁታል። አንድን በሬ አርደው ስጋውን ከበሉ በኋላም ቢሆን ቆዳውን አለስልሰው ይሰቅሉታል። በዚህም ፍቅራቸውን እና ተፈጥሯዊ ግንኙነታቸውን ይገልጹበታል። እኔም ይህን ቁርኝነት በሥራዎቼ ላይ ግብአት አድርጌ እጠቀምበታለሁ" ይላል። የዓለም ህዝብ የራሱ የሆነ ባህል እና የሥነ-ጥብብ መገለጫ አለው የሚለው እያዩ የስዕል ሥራዎቹ በምዕራብውያን ተጽእኖ ስር እንዳይወድቁ ይጠነቀቃል። ለእያዩ ማህበረሰቡ በተለምዶ የሚሰራቸው የጥበብ ሥራዎች ተራ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች ብቻ አይደሉም ሲል ይሞግታል፤ ''እነዚህም ሥነ-ጥበብ ነው'' የሚባሉት ሲል ተራው ማህበረሰብ የሚሰራው እና የጥበብ እጁን ያሳረፈበት ምርጥ የጥበብ ሥራ እንደሆነ ያብራራል። አክሎም እኔም ሥራዎቼን ባለው እሴት ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ፣ ፖለቲካዊ ወይም ማህበራዊ ፍንጭ ሰጥቼና ጨምሬበት ነው የምሰራው ሲል ስለሥራዎቹ ያስረዳል። ኢትዮጵያውያን ወካይ አሳሳል ስልት እንከተላለን የሚለው እያዩ በሀገሪቱ ያሉ ጎብኚዎች የሚያዘወትሯቸው ስፍራዎች ላይ የሚገኙ የስዕል ውጤቶች ቢታዩ ይህ ነገር እንደሚጎላ ይናገራል። ''ታዲያ እኔም ኢትዮጵየያዊ ከሆንኩ እና ከዚህ ሰፊ ባህር ከተጨለፍኩ እንደምን ውክልናን ከስዕሌ ማስቀረት ይቻለኛል?'' በማለት በሬን እና ቀንዱን በስዕሎቹ ውስጥ ለውክልና ተጠቀሞበታል። ከበሬም ይላል እያዩ ግንባሩ፣ ፊት ለፊት የሚታየው አካሉ ላይ ያተኩራል። ይህ ሁለት ሀሳብ ይወክልልኛል የሚለው ሠዐሊ እያዩ ቀዳሚ ሀሳቡ የአሸናፊነት እና የተማፅኖ ድምፅን እንዲወክልልኝ አድርጌ ነው የምጠቀምበት ይላል። የአሳሳል ስልት እያዩ በአሳሳል ዘዬው ቅፅበቶችን በሸራ ላይ ማስቀረት እንደሚፈልግ ይናገራል። "በስዕሎቼ በቅፅበቶች ውስጥ የተሰማኝን ስሜት ለመግለፅ የትኛው መንገድ ይሻለኛል የሚለውን እመርጣለሁ።" በዓውደ ዓመት ወቅት እንደ ኪነ-ጥበብ ባለሙያ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊ እና እንደ ሐይማኖተኛ ሰው እውናዊው አሳሳል የሚገልፅልኝ ሆኖ ሳገኘው እርሱን እጠቀማለሁ ይላል። ''በእርግጥ አንዳንድ ሀሳቦች ሰወር ብለው በተመልካች ዘንድ ጥያቄና የአእምሮ ሙግት ቢፈጥሩ ብዬ ሳስብ ወደ አብስትራክት ቀረብ ያሉ ስዕሎችን መሳል እመርጣለሁ'' የሚለው እያዩ ''ለእኔ የሚመቸኝ ግን ዓለም ራሱ በአብስትራክት እና በእውነታ መካከል ስለሆነች ሁለቱን አዛንቆ መሳል ነው።'' ''የምናየውን እውነታ ሁሉ ጠጋ ብለን ስናየው አለ ያልነው ነገር በውስጡ የለም'' የሚለው እያዩ በከፊል እውናዊ የሆነውን አሳሳል መጠቀም ይመርጣል። በአሳሳል ረገድም ብዙ ነፃነት ይሰጠኛል ብሎ ያምናል። "ሀገሬ ራሱ በተቃርኖ ውስጥ ተዛንቃ ስላለች ሥራዎቼም እንደዛ ናቸው እላለሁ።" በሥራዎቼ ባህላዊ የሚባሉ ነገሮችን ወስጄ ከጀርባው ደግሞ በጣም ዘመናዊ ሃሳብን በማምጣት በሸራዬ ላይ ተዋደውና ተጋምደው እንዲቀመጡ አደርጋለሁ የሚለው እያዩ ይህ የአሳሳለ ዘይቤው በሥራዎቹ ውስጥ ሁሉ ዱካው እንደሚገኝ ይጠቅሳል። ጥበብን መረዳት ሥዕል ለአይን ብቻ ሊሰራ ይችላል የሚለው እያዩ ጠያቂ፣ ስልተምት ያለው ለተመልካቹ የማሰብና የመመርመር እድል የሚሰጥ መሆን እንዳለበት ያምናል። ሰዎች እንደኖሩበት ባህልና ማህበረሰብ አንድን ሥራ ሊረዱት ይገባልም ባይ ነው። አንድ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ሥራው ከእጁ ከወጣ በኋላ የእርሱ ሳይሆን የተመልካች የተርጓሚው ነው ሲል ሃሳቡንም ያጠናክራል። የአንድ ሥራ ታዳሚ ልጓም ሊበጅለት አይገባም ሲልም አፅንኦት ይሰጣል።
news-53133863
https://www.bbc.com/amharic/news-53133863
በኮሪያ ሙዚቀኞች ሰበብ የተመናመነው የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ
ፕሬዝደንት ትራምፕ ኦክላሆማን በአንድ እግሯ ለማቆም ሲዝቱ ነው የሰነበቱት። የምርጫ ቅስቀሳ ምን እንደሚመስል አሳያችኋለሁ ሲሉም ፎክረዋል። ነገር ግን እሳቸው ያሰቡት ወዲህ እውነታው ወዲያ ሆነባቸው።
ትራምፕ አሜሪካን ለሁለተኛ ክፍለ-ጊዜ ለመምራት ቅስቀሳ ጀምረዋል። አሜሪካን ታላቅ አደርጋለሁ ከሚለው መፈክራቸው የአሜሪካን ታላቅነት አስቀጥላለሁ ወደሚል ተሻግረዋል። ኦክላሆማ ግዛት፤ ተልሳ ከተማ ውስጥም ይህን ታሪክ በቀይ እፅፋለሁ ሲሉ መፎከር ከጀመሩ ሳምንታት ተቆጥረዋል። ልክ ሰዓቱ ደርሶ የትራምፕ ደጋፊዎች አዳራሹን ከአፍ እስከገደፉ ይሞሉታል ተብሎ ሲጠበቅ ግን ትራምፕ ያሰቡት ሳይሆን ጠላቶቻቸውን ያስፈገገ ታሪክ ተሰራ። ይህን ያስተዋሉ የትራምፕ ነቃፊዎች በየማሕበራዊ ድር-አምባዎቻቸው እየወጡ ሰውዬውን መዘባበቻ አደረጓቸው። የኮሪያ ሙዚቀኞችንም ያመሰግኑ ጀመር። • በብራዚል የሟቾች ቁጥር ከ50ሺህ ዘለለ • "እንደ ቆሻሻ ነው አውጥተው የወረወሩን" ኢትዮጵያውያኑ በሊባኖስ • በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ አህዮች ለቆዳቸው ሲባል በኬንያ እየታረዱ ነው ትራምፕና የኮሪያ ሙዚቀኞች ደግሞ ምን አገናኛቸው? ጥሩ ጥያቄ ነው። ነገሩ ወዲህ ነው። ኬፖፕ የተሰኘው የኮሪያ ሙዚቃ ዘውግ አሜሪካ ውስጥ ዝናው የናኘ ነው። ታዲያ እኒህ የኮሪያ ሙዚቀኞች ቲክ-ቶክ በተሰኘው ማሕበራዊ ድር-አምባ ለደጋፊዎቻቸው አንድ መልዕክት ይልካሉ። 'የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ እንሳተፋለን ብላችሁ ቲኬት ያዙ፤ በቅስቀሳው ላይ ግን እንዳትገኙ' የሚል። የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ሰዎች ይህ ሃሰት ነው ሲሉ ይከራከራሉ። አዳራሹ 19 ሺህ ሰው አቅፎ ደግፎ ይይዛል። የቅስቀሳው ሰዎች አዳራሹ መሙላቱ ስለማይቀር ከአዳራሹ ውጭ ያለውን ቦታ እንጠቀማለን የሚል ዕቅድ ነበራቸው። የተልሳ ከተማ እሳት አደጋ ሰዎች ብርጌድ ለቅስቀሳው የተገኙ ሰዎች ቁጥር ከ6 ሺህ አይበልጥም ሲሉ ተሰምቷል። የትራምፕ ሰዎች ግን ቁጥሩ ከዚያ በጣም ይልቃል ሲሉ ይሞግታሉ። የቅስቀሳ ኃላፊ ብራድ ፓርስካል እኛ ሰዎች ቲኬት ገዝተው ይቀራሉ የሚል እሳቤ የለንም፤ ምክንያቱም ወደ አዳራሹ ቀድሞ የመጣ መግባት ይፈቅደልታልና ሲሉ መግለጫ አውጥተዋል። "መገናኛ ብዙሃንና እና ተቃዋሚዎች ሰዎች ወደ ቅስቀሳው እንዳይሄዱ አድርገዋል" ሲሉም ወቅሰዋል። "ግራ ዘመሞች ቅስቀሳ እንዴት እንደሚከናወን አያውቁም። ሰዎች ቅስቀሳውን ለመታደም ሲመዘገቡ ስልክ ቁጥራቸውን እንመዝባለን፤ መገኘት መቻላቸውንም እናረጋግጣለን። ይህን የምናደርገው ሃሰተኛ ተመዝጋቢዎችን ለመመንጠር ነው።" የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የነበሩትና የትራምፕ ዋነኛ ነቃፊ የሆኑት ስትቭ ሽሚድት የ16 ዓመት ልጃቸውንና ጓደኞቿን ጨምሮ በርካታ ታዳጊ አሜሪካውያን ቲኬት ጠይቀው ነገር ግን ቅስቀሳውን አልታደሙም ሲሉ በትዊተር ግድግዳቸው ላይ ፅፈዋል። በርካታ ወላጆችም 'አዎ ልጆቻችን እንዲህ አድርገዋል' ሲሉ እየተደመጡ ነው። ወጣቷ ፖለቲከኛ አሌክሳንደር ኦስካዚዮ ኮርቴዝ ወጣቶችና የኬ-ፖፕ ለዚህ ድርጊታቸው አድናቂዎችን አንቆለጳጵሰዋል። • ቀለበታዊው የፀሐይ ግርዶሽ በላልይበላ • በእንግሊዝ ወደ መጠጥ ቤት ጎራ የሚሉ ሰዎች መመዝገብ ሊኖርባቸው ይችላል ተባለ ወጣቶቹ ምን ያክል ቲኬቶችን ሸምተን እንገኛለን ብለው እንደቆረጡ በውል የታወቀ ቁጥር ባይኖርም ከቀናት በፊት ቲክ ቶክ የተሰኘው ድር ላይ ታዳጊዎች ይህን እንዲያደርጉ ሲሰብክ የነበረ ወጣት 700 ሺህ 'ላይኮች' አግኝቷል። ትራምፕ፤ መጀመሪያ ቅስቀሳውን ማድረግ አስበው የነበረው በግሪጎሪ አቆጣጠር ሰኔ 19 ነበር። ይህ ቀን ደግሞ ጁንቲንዝ ይባላል። ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባርነት ሕገ-ወጥ እንዲሆን የተወሰነበት ነው። ትራምፕ በዚህ ቀን ቅስቀሳ ላካሂድ ማለታቸው ብዙዎችን አስከፍቶ ነበር። አልፎም ቅስቀሳው በአሜሪካ ታሪክ አስከፊው የዘር ጭፍጨፋ የተካሄደባት ተልሳ ውስጥ መሆኑ ቁጣን መጫሩ አልቀረም። ከዚህ በኋላ ነው የቅስቀሳው ቅዳሜ ሰኔ 20 እንዲሆን የተደረገው። ቅስቀሳው ላይ የተገኘው የቢቢሲው አንተኒ ዙርከር ምንም እንኳ ቲኬቶችን የቆረጡ ሰዎች ባይገኙም የትራምፕ ደጋፊዎች ቢመጡም ቦታ አያጡም ነበር ሲል ዘግቧል። ነገር ግን በርካታ ቲኪቶች መያዛቸው ደጋፊዎችን ሳያዘነጋ አልቀረም ይላል። ቅስቀሳው ላይ የተገኙ ሰዎች ቁጥር የተመናመነ መሆኑ ሲታወቅ ወጣቶችን ሲቀሰቅስ የነበረው ግለሰብ በተለይ ደግሞ ዕድሜያቸው ለምርጫ ያልደረሰ ታደጊዎችን ሲያመሰግንና ሲያደንቅ ታይቷል። የኬ-ፖፕ ሙዚቃ አድናቂዎች ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ሲያመጡ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። በቅርቡ አሜሪካን በተቃውሞ የናጣት የጆርጅ ፍሎይድ ግድያን ተከትሎ ብላክ ላይቭስ ማተር [የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት] ለተሰኘው ተቋም በርካታ ገንዘብ ማሰባሰብ ችለዋል። ኮሮናቫይረስ ቅስቀሳውን የሚታደሙ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ ቢጋለጡ የትራምፕ ቅስቀሳ ቡድን ተጠያቂ እንደማይሆን የሚያትት ቅፅ ፈርመው ነው ወደ አዳራሹ የገቡት። ቅስቀሳው ሊጀምር ሰዓታት ሲቀሩት ከአስተባባሪዎች መካከል 6 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተነግሮ ነበር። አብዛኛዎች የትራምፕ ደጋፊዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አልጣለቁም። የሪፐብሊካኖች ግዛት በሆነችው ኦክላሆማ ሁለት ሰዓት ገደማ የፈጀ ንግግር ያደረጉት ትራምፕ በርካታ ጉዳዮችን ሲያነሱ ሲጥሉ አምሽተዋል። ቅስቀሳው በዚህ የወረርሽኝ ወቅት እንዳይካሄድ ብዙዎች ቢወተውቱም ትራምፕ ሊሰሟቸው ፈቃደኛ አልነበሩም። አሜሪካ 2.2 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተይዘውባታል። 119 ሺህ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
news-53633983
https://www.bbc.com/amharic/news-53633983
ከሁለት ወራት በፊት ወደ ሕዋ የበረረችው ታክሲ ተመለሰች
ሁለት አሜሪካውያንን አሳፍራ ወደ ዓለም አቀፉ የሕዋ ጣቢያ ያመራችው ታክሲ በሰላም ወደ ምድር ተመልሳለች።
ስፔስኤክስ የተሰኘው የግል ኩባንያ ንብረት የሆነችው 'ድራገን ካፕሱል'፤ ዳግ ሃርሊ እና ቦብ ቤንከን የተሰኙ የጠፈር ተመራማሪዎችን ይዛ ነው ከሕዋ ወደ ምድር በመምዘግዘግ በሜክሲኮ ሰርጥ ፍሎሪዳ አካባቢ ያረፈችው። የሕዋ ተመራማሪዎች በሰላም ከጠፈር ወደ መሬት ሲመለሱ በአሜሪካ ታሪክ የዛሬ 45 ዓመት ከተከወነው የአፖሎ ተልዕኮ በኋላ የመጀመሪያው ነው። ሁለቱን ጠፈርተኞች ያሳፈረችው ታክሲ ውሃ ስትነካ በዙሪያዋ የግል ጀልባዎች ነበሩ። ባለሥልጣናት ታክሲዋ አደገኛ ኬሚካል እንዳትረጭ በሚል ጀልባዎች ራቅ እንዲሉ ሲያሳስቡ ነበር። የአሜሪካ የሕዋ ምርምር ተቋም ናሳ አለቃ ጂም ብራይደንስታይን 'በአካባቢው የግል ጀልባዎች ይኖራሉ ብለን አልገመትንም ነበር' ብለዋል። በርካቶች የሕዋ ታክሲዋ ስታርፍ በአካባቢው ጀልባዎች መታየታቸው ስላስደነቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በማሕበራዊ ድር-አምባዎች ሲጋሩ ነበር። ጠፈርተኛ ሃርሊ 'ኩራትና ክብር ተሰምቶናል' ሲል በተልዕኮው በመሳተፉ የተሰማውን ደስታ ገልጿል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት ወራት በፊት ታክሲዋ ስትመነጠቅ በቀጥታ ሲመለከቱ ነበር። ወደ ምድር በሰላም የተደረገው ጉዞም እንዳስደሰታቸው በትዊተር ገፃቸው አሳውቀዋል። ለሁለቱ ተመራማሪዎችም ምስጋና ችረዋል። የድራገን ተልዕኮ ለአሜሪካ ታሪካዊ ድል ነው። በግል መንኮራኩር ወደ ጠፈር የተደረገ የመጀመሪያው ጉዞ ሲሆን ከዚህ በኋላ የሚደረጉ ጉዞዎችንም ቀላል ያደርጋቸዋል ተብሏል። የባለሃብቱ ኢላን መስክ ንብረት የሆነችው ድራገን ለናሳ እንደምትሸጥም ታውቋል። ናሳ ለሕዋ ጉዞ ቢሊዮኖችን ከማፍሰስ ይልቅ ከግል ድርጅቶች መግዛት አዋጭ ነው ሲል አስታውቋል። ታክሲዋ በሚቀጥለው ዓመት እንደገና ወደ ጠፈር ጉዞ ታደርጋለች።
news-48926447
https://www.bbc.com/amharic/news-48926447
አምነስቲ በቅርቡ የታሰሩ ጋዜጠኞች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥትን ነቀፈ
ዓለምዓቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች መታሰር እንዳሳሰበው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ መንበሩ ከመጡ ወዲህ በሚዲያ ነጻነት ድንቅ እምርታን እየታየ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሁኔታዎች የመቀልበስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል። በባለፈው አመት በብዙዎች ዘንድ ጨቋኝ የተባለውን የበጎ አድራጎትና የሲቪል ማህበራት ህግ መሻሻሉን እንዲሁም በእስር ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችና ጦማሪዎች ተፈትተዋል ብሏል። •የባለአደራ ምክር ቤት አባላት ከ'መፈንቅለ መንግሥቱ' ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ቀረቡ •“በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ ባወጣውም መረጃ አንድም ጋዜጠኛ በእስር የለለበት ሁኔታ መፈጠሩንና በአለም አቀፉ የፕሬስ ነፃነት ደረጃም (ወርልድ ፕሬስ ፍሪደም ኢንዴክስ) መሰረት አርባኛ ሆናም ነበር በማለት መግለጫው አስታውሷል። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሁኔታዎች ወደነበሩበት መለወጣቸው አሳሳቢ ሆኗል ይላል አምነስቲ። በነዚህ ሳምንታት በአዲስ መልኩ ጋዜጠኞችን የማሸማቀቅና የማሰር ዘመቻ እንዳለ የገለፀው መግለጫው ተከትሎም በትናንትናው ዕለት የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የተቋሙንና የሰራዊቱን ስም እያጠፉ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ክስ ሊመሰርትም መሆኑንም አስታውቋል። "የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር በፕሬስ ነፃነት ላይ በታየው እመርታ ከፍተኛ ሙገሳን የተቀበሉ ሲሆን ኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንን ለማስተናገድም በቅታ ነበር።" በማለት በአፍሪካ ቀንድ፣ በምስራቅና የግሬት ሌክስ የአምነስቲ ዳይሬክተር ጆዋን ናንዩኪ ተናግረዋል። "ይህ በአዲስ መልኩ የተጀመረው ጋዜጠኞችን የማሰር ዘመቻ የታየውን የፕሬስ ነፃነት ወደ ኋላ የሚመልስ እርምጃ ነው።የኢትዮጵያ መንግሥት የታሰሩ ጋዜጠኞችን በቶሎ ይፍታ፤ ክሳቸውም አሁኑኑ ውደቅ ይደረግ" ብሏል አምነስቲ •"ብ/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ የአስራት ቴሌቪዥን ዋና አዘጋጅ በሪሁ አዳነ እንዲሁም ከህትመት የወጣችው የዕንቁ መጽሔት የቀድሞ ዋና አዘጋጅ ኤሊያስ ገብሩ በመግለጫው ከተጠቀሱ ጋዜጠኞች መካከል ይገኙበታል። ጋዜጠኞቹ የጸረ ሽብር ሕግ ተጠቅሶ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ይህ ሕግ ቀደም ያለው አስተዳደር የተቃውሞ ድምጽን ለማፈን ሲጠቀምበት የነበረ እንደሆነ መግለጫው አክሎ አትቷል። መግለጫው የሰኔ 15ቱን ክስተት ተከትሎ የአብን አባላትና ሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች መታሰራቸውንም ነቅፏል።
news-45205366
https://www.bbc.com/amharic/news-45205366
ጋዳፊ ከስልጣን እንዲወርዱ ሲደረግ በነበረ ግድያ የተሳተፉ 45 ሰዎች ላይ ሞት ተፈረደ
የሊቢያ ፍርድ ቤት 45 የሚሊሻ ታጣቂዎች በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ ወሰነ።
የሊቢያ አማፂያን በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን (ኔቶ) ታግዘው የጋዳፊን መንግሥት ከስልጣን ወርውረው ትሪፖሊን የተቆጣጠሩት ከ7 ዓመታት በፊት ነበር። የሊቢያ ፍትህ ሚኒስቴር እንዳለው 45ቱ ሚሊሻዎች የጋዳፊ መንግሥትን ለመጣል ብረት ያነገቡ አማጺያን ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካቶችን በመግደላቸው ነው የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው። ኤኤፍፒ እንደዘገበው ከጋዳፊ የስልጣን ዘመን በኋላ 45 ሰዎች ላይ በተመሳሳይ ጊዜ የሞት ፍርድ ሲተላለፍ ይህ ትልቁ ቁጥር ነው። • መንግሥትና ኦብነግ የጀመሩት ጉዞ የት ያደርሳል? • የመገንጠል መብት ለማን? መቼ? • የ"ይቻላል" መንፈስ የሰፈነበት የአዲስ አበባው ቴድኤክስ የንግግር መድረክ በሊቢያ ከተቀሰቀሰው ህዝባዊው አመጽ በኋላ አገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት ርቋት ቆይታለች። 45 ሰዎች ላይ ከተላለፈው የሞት ፍርድ በተጨማሪ 54 ሰዎች ላይ የአምስት ዓመት የእስር ፍርድ ተላልፏል። ሰይፍ አል-ኢስላም ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ወደ ፖለቲካው ዓለም ለመመለስ እየሰበ እንደሆነ ተናግሮ ነበር። የጋዳፊ ልጅ የሆነው ሰይፍ አል-ኢስላምን ጨምሮ በጋዳፊ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የነበሩት ላይ የሞት ፍርድ ተላልፎ ነበር። በሊቢያ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ፍርደኞች አብዛኛውን ጊዜ ፍርዱ ተፈጻሚ ሳይሆንባቸው እድሜ ልክ በእስር እንዲያሳልፉ ይደረጋል። ይሁን እንጂ ሰይፍ አል-ኢስላም ከአንድ ዓመት በፊት ከእስር ተለቋል። ሰይፍ አል-ኢስላም ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ከሬውተርስ ጋር ነበረው ቆይታ ወደ ፖለቲካው ዓለም ለመመለስ እየሰበ እንደሆነ ተናግሮ ነበር።
41303382
https://www.bbc.com/amharic/41303382
በሰሜን ጎንደር 4 ወረዳዎች በቅማንት አስተዳደር ስር ለመጠቃለል ወይንም በነበረው አስተዳደር ስር ለመቀጠል ሕዝበ ውሳኔ ተካሄደ
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በ4 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ የ8 ቀበሌ ነዋሪዎች በትናንትናው ዕለት ከማለዳ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሕዝበ ውሳኔ ሲያካሄዱ ውለዋል።
በሕዝበ ውሳኔው መሰረት የቀበሌዎቹ ኗሪዎች በቅማንት የራስ አስተዳደር ሥር ለመጠቃለል ወይንም እስካሁን በነበረው አስተዳደር ለመቀጠል የሚያስችላቸውን ውሳኔ አስተላልፈዋል። ከቅማንት ሕዝብ የማንነት እንዲሁም የራስ አስተዳደር ጥያቄ ጋር በተያያዘ በ2008 ዓ.ም በአካባቢው በተቀሰቀሱ ግጭቶች የፀጥታ አስከባሪ አካላትን ጨምሮ 95 ሰዎች መገደላቸውን መንግስታዊ የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት ይገልጻል። ሪፖርቱ አክሎም የክልሉ የጸጥታ አስከባሪ አካላት "ከመጠን ያለፈ ኃይል" ተጠቅመዋል ሲል ወንጅሏል። ባለፉት አምስት ዓመታት በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከተነሱ ተመሳሳይ የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄዎች በተለየ የቅማንትን ሕዝብ ጥያቄ የአማራ ክልል መንግሥት ተመልክቶ በመጋቢት 2007 ባደረገው ጉባኤ ዕውቅና ሰጥቶታል። የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄዎች በደቡብ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የኮንሶና የቁጫ እንዲሁም የወልቃይት አካባቢ ኗሪዎች ማንሳታቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት የቅማንት ተወላጆች በብዛት ይኖሩባቸዋል የተባሉ በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ 42 ቀበሌዎች በቅማንት የራስ አስተዳደኣር እንዲካተቱ ሲደረግ የአማራና የቅማንት ተወላጆች ተቀላቅለው የሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች ደግሞ በሕዝበ ውሳኔ ምርጫቸውን እንዲያሳውቁ ተወስኗል። በቅማንት ሕዝበ ውሳኔ 25000 ያህል ኗሪዎች በ34 የምርጫ ጣብያዎች ላይ ድምፃቸውን ያሰማሉ ተብሎ የነበረ ቢሆንም በሕዝበ ውሳኔው ላይ ለመሳተፍ ካርድ የወሰዱት በ8 ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ21 000 በላይ ሰዎች መሆናቸውን የክልሉ የብዙሃን መገናኛ ድርጅት ገልጿል። የምርጫ ጣብያዎቹም ቁጥር ቀድሞ ከታሰበው በአስር ያነሰ ነው። ጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር ቀበሌ አካባቢ ሲዘዋወር የነበረ ጋዜጠኛ በአንዳንድ የምርጫ ጣብያዎች የሕዝበ ውሳኔ ሒደቱ ዘግይቶ ከመጀመሩ በስተቀር እዚህ ግባ የሚባል ችግር አለማየቱን ለቢቢሲ ገልጿል። በአካባቢው ያነጋገራቸው አንድ አዛውንት ብዙዎቹ የአካባቢው ኗሪዎች እርስ በእርስ ተጋብተው ለረጅም ጊዜ መኖራቸውን ካስረዱት በኋላ የሕዝበ ውሳኔው መቃቃርን እንዳይፈጥር ስጋት የገባቸው መሆኑን እንደገለጹለትም ይናገራል። ከመራጮች መካከል በዛ ያሉ ዕድሜያቸው ያልደረሰ የሚመስሉ ድምጽ ሰጪዎችን መመልከቱንና ዕድሜያቸውን ሲጠይቅ ሁሉም "አስራ ስምንት" ሲሉ እንደመለሱለት ጋዜጠኛው ጨምሮ አስረድቷል። የሕዝበ ውሳኔው ውጤት ተቆጥሮ ከዛሬ መስከረም 8 ማለዳ አንድ ሰዓት ጀምሮ በየምርጫ ጣብያው እንደሚለጠፍ ይጠበቃል። ሂደቱን በበላይነት የሚቆጣጠረውና የሚያስፈፅመው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው የድምፁ ውጤት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መስከረም 15 ቀን ይላካል።
news-48363924
https://www.bbc.com/amharic/news-48363924
ታዋቂው ኬንያዊ ደራሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
እውቁ ኬኒያዊ ደራሲ ቢንያቫንጋ ዋይኒያና በ48 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ቤተሰበቦቹ አረጋገጡ።
ቢንያቫንጋ ዋይኒያና ደራሲው በ2002 የኬን ተሸላሚ የነበረ ሲሆን በ2014 ደግሞ ታይም መፅሔት ከዓለማችን 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከል አንዱ አድርጎ አካትቶት ነበር። ቢንያቫንጋ ዋይኒያና በዓለም ዙሪያ በተለይ የሚታወቀው 'ሃው ቱ ራይት አባውት አፍሪካ' በተሰኘው ምጸታዊ መጣጥፉ ነው። • 22 ኢትዮጵያዊያን ናይሮቢ ውስጥ ተያዙ • በናይሮቢ ወንዞች የአስከሬኖች መገኘት አሳሳቢ ሆኗል ቢንያቫንጋ ዋይኒያና በኬንያ በይፋ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ መሆኑን የተናገረ የመጀመሪያው ታዋቂ ግለሰብ ነው፤ ባለፈው ዓመትም ጋብቻ ሊፈጽም መሆኑን አሳውቆ ነበር። በዚህም የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ሕገ ወጥ በሆነባት ኬንያ የተለያዩ ሃሳቦች ተንጸባርቀው ነበረ። ቢንያቫንጋ ዋይኒያና ከአራት ዓመታት በፊት በጽኑ ታሞ እንደነበረ ተናግሯል። የማረፉ ዜና ከተሰማ በኋላ ወንድሙ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ቤተሰቡ የቢንያቫንጋ ዋይኒያና በሕይወት የቆየበትን የስኬት ዘመን እንደሚዘክሩ ተናግሯል። ዋይኒያና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት መብት ተከራካሪ በመሆን የሚታወቅ ሲሆን፤ በተለያዩ ጆርናሎች ላይ ባሳተማቸው ጥናታዊ ሥራዎቹ፣ በረዥምና አጫጭር ልቦለድ ድርሰቶቹ ይታወሳል።
news-47278602
https://www.bbc.com/amharic/news-47278602
«በስልክዎ ታካሚና አካሚ እናገናኛለን» ሥራ ፈጣሪው ወጣት መላኩ ኃይለማርያም
በሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ እና በሂውማን ኒውትሪሽን የትምህርት ዘርፎች ዲፕሎማ እና ዲግሪ አለው፤ የሕክምና ባለሙያው መላኩ ኃይለማርያም።
«ከላቦራቶሪ ቴክኒሺያንነት፣ የሽያጭ ባለሙያ እስከ ማርኬቲን ማኔጀርነት ለ10 ዓመታት ያክል ስሠራ ቆይቻለሁ» ይላል። ታድያ እነዚህ ያለፉት አሥር ዓመታት የሕክምና መስጫ ተቋማትንና የሚሠጡትን አገልግሎት በቅጡ እንዲረዳ አድርገውታል። «በተለይ ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች እና ላቦራቶሪዎች እንዴት እንደሚሠሩ እና ያለባቸውን ክፍተት ለመርዳት ያገዙኝ ዓመታት ናቸው።» ይላል። • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና የሕክምና ዕቃዎችን አስመጥቶ በማከፋፈል ሥራ በርካታ ጊዜያትን ያሳለፈው መላኩ «ያላዳረስኩት ሆስፒታልና ክሊኒክ የለም» ሲል የስራ ልምዱን ይናገራል። «በዚህ ሥራዬ ወቅትም በሕክምናው ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን ለማየት እሞክር ነበር፤ ይህ ነው ወደዚህ የሥራ ፈጠራ እንዳመራ የገፋፋኝ» ባይ ነው መላኩ። 'የመረጃ ኤግዚቢሽን' 'ኢትዮሜዶን.ኮም' ይሰኛል መላኩ የሰራው ድረ-ገፅና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ (አፕሊኬሽን)። የመላኩ ዓላማ አካሚና ታካሚን ማቀራረብ ነው፤ የሕክምና ዕቃ አስመጪዎችን ከገዢዎች ማገናኘት፤ ሰውን በጤና መረጃ ማርካት። አዲስ አበባ ውስጥ የሕክምና ዕቃዎች እንዲሁም ተፈላጊ መድሃኒቶችን በቀላሉ ማግኘት ዘበት ነው። እግር እስኪቀጥን ተፈልጎ ላይገኝ ይችላል። አሁን አሁን ተፈላጊ የሕክምና ባለሙያን ከማግኘት ተጨማሪ ፕላኔት ማግኘት ይቀላል በማለት የሚቀልዱ አሉ። የመላኩ ሃሳብ እነዚህን ችግሮች መቅረፍ ነው፤ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ላይ ብቻም ሳይሆን ክፍለ ሃገራትንም ጭምር። • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው «የሕክምና ዕቃዎችን በተመለከተ ከዚህ በፊት የተለመደው ኤግዚቢሽን ተዘጋጅቶ፤ አቅራቢዎችም ገዢዎችም በአካል ተገናኝተው መደራደር ነው። እኔ የሠራሁት ድረ-ገፅ ግን አቅራቢዎችና ገዢዎችን ሰዎች እጃቸው ላይ ባለ ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚያገናኝ ነው።» አያድርገውና ህመም ገጠመዎ እንበል። ለዚህ በሽታዎ የሚሹት ደግሞ 'ስፔሻሊስት' ሐኪም ነው። ይህ ሐኪም የት እንደሚገኝ አሊያም ለጤና ችግርዎን ትኩረት ሰጥቶ የሚያክም ሆስፒታል ወይም ክሊኒክ የቱ እንደሆነ ማወቅ ቢሹ ማድረግ ያለብዎና ትልቁ ነገር ተንቀሳቃሽ ስልክዎን መዘዝ አድርጎ በይነ-መረብን መቃኘት ነው። በድረ-ገፁ 'ሄልዝኬር' በተሰኘው ምዕራፍ ሥር አሁን ላይ በርካታ ሆስፒታሎች፤ ልዩ ክሊኒኮች እና ላቦራቶሪዎች ይገኛሉ። ተጠቃሚዎች ባሻቸው ጊዜ የሚፈልጉትን ዓይነት የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ጣቢያ የሚያገኙበት ገፅ ነው መላኩ የሠራው። የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያውን (አፕሊኬሽን) የሠራው መላኩ 'አፕሊኬሽኑ' ሊጠናቀቅ የቀረው ጥቂት ጊዜ እንደሆነ በመግለፅ በቅርቡ አንድሮይድ እና አይኦኤስ በተሰኙ የስልክ ዓይነቶች ላይ በቀላሉ እንደሚገኝ ያስረዳል። • ሴቶችን ከመንቀሳቀስ የሚያግደው መተግበሪያ ሊመረመር ነው «ማንኛውም ሰው ካለበት ሆኖ የፈለገውን የሕክምና ዕቃ ማዘዝ ይችላል። ጨረታ ተብሎ እየወጣ ነገሮች እንዳይሆን እንዳይሆን ሲሆኑ አይቻለሁ። ድረ-ገፁ ላይ ግን ትክክለኛው መረጃ ነው የሚቀመጠው።» አልፎም የመላኩ 'አፕሊኬሽን' የእያንዳንዱን የጤና መስጫ ተቋም ድረ-ገፅ ጋር (ካላቸው) ይይዛል። የሕክምና ዕቃ አስመጪዎችም ጭምር። ፈተና. . . መላኩ በበይነ መረብ እገዛ የሕክምና ዕቃ አቅራቢዎችን ከፈላጊዎች፤ ታካሚዎችን ከአካሚዎች ያገናኛል። ታድያ እኒህን ሰዎችን ማግኘትና ማገናኘት ቀላል እንዳልሆነ እሙን ነው። ለዚያውም ወጣ ገባ በሚል 'ኢንተርኔት' አገልግሎት። መላኩ «ትልቁ ፈተና የሕክምና ተቋማትንና የሕክምና ዕቃ አስመጪዎችን መመዝገብ ነው። አገልግሎት ሰጪዎቹ ምርትና አገልግሎታቸውን በድረ-ገፃችን እንዲያስተዋውቁ ማድረግ ትልቅ ፈተና ነው።» ይላል። ሆስፒታሎች እና የሕክምና ዕቃ አቅራቢዎች አሁንም እንደ ቴሌቪዥን ያሉ 'ባህላዊ' የማስታወቂያ ማስነገሪያ መንገዶችን እንደሚመርጡ መላኩ አይሸሽግም። • ቀዶ ህክምና በአፍሪካ ስጋት መሆኑ ከፍ ብሏል «እርግጥ ነው አሁን ላይ የኢንተርኔት አገልግሎቱ የተሻለ ነው። ቢሆንም ድርጅቶች ኢንተርኔት ቢቋረጥስ እያሉ ይጠይቁናል። ለዚህ ነው ውል ከምንፈፅማቸው ድርጅቶች ጋር የዋስትና ስምምነት ልንደርስ የሆነው። ይህ ማለት ኢንተርኔት ቢቋረጥ ድርጅቶቹ ለድረ-ገፁ ከሚከፍሉት ክፍያ ታስቦ ይመለስላቸዋል» ሲልም ያስረዳል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኢንተርኔት ጉዳይ እና የተቋማት ወደ ድረ-ገፅ እና አፕሊኬሽኖች ለመምጣት ማመንታት ችግር ቢሆንበትም የተጠቃሚዎች ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ መምጣት ተስፋ እንደሚሰጠው መላኩ ይናገራል። ምንም እንኳ የሕክምና አቅራቢ ድርጅቶች የሚከፍሉት የተወሰነ ክፍያ ቢኖርም፤ አገልግሎታቸውን ድረ-ገፁ ላይ ማስተዋወቅ የሚሹ የህክምና መስጫ ተቋማት ምንም ዓይነት ክፍያ እንደማይጠየቁ መላኩ ይናገራል። ምክንያቱን ሲገልጽ ደግሞ ድረ-ገፁ "በዋነኛነት ማሕበረሰቡን እንዲያገለግል ስለምንሻ ነው" ይላል። የኢንተርኔት ወጣ ገባ ማለት እየፈተነውም ቢሆን፤ የሕክምና መስጫ አገልግሎት ተቋማት ድረ-ገፁን ለመቀላቀል እያመነቱም ቢሆን፤ መላኩ በድረ-ገፅና 'አፕሊኬሽን' ታካሚና አካሚን ለማገናኘት አዲስ ነገር ይዞ ብቅ ብሏል።
news-45013308
https://www.bbc.com/amharic/news-45013308
በሰሜን ወሎ መርሳ የሚገኙ ባለሃብቶች የምርት ቦታቸው እንደወደመባቸው ገለፁ
በፍራፍሬ ምርቷ በምትታወቀው የሰሜን ወሎዋ መርሳ ከሰሞኑ በግብርና ዘርፍ በተሰማሩ ባለሃብቶችና በአካባቢው አርሶ አደሮች መካከል ግጭት ተፈጥሮ ነበር። ግጭቱን ተከትሎም የባለሃብቶቹ ይዞታ የሆኑ የደረሱ አትክልትና ፍራፍሬዎች እንዲሁም የከብት መኖ ወድሟል።
የወጣት ያሲን ደመቀ የልማት ቦታ ውድመቱ ከመድረሱ በፊትና ከደረሰ በሗላ በመርሳ ከተማ የቀበሌ 04 ነዋሪ የሆነው ወጣት ያሲን ደመቀ እንደተናገረው ጨቆርሳ ዳውጋ በሚባለው ቦታ ወጣቶች ተደራጅተው አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የከብት መኖ ያመርታሉ። የእርሱ ይዞታ ከዚህ አካባቢ አሻግሮ የሚገኝ ሲሆን መሬቱ ከቀድሞውም የግሉ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንዳለው ይናገራል። • ''አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት'' ከንቲባ ታከለ ኡማ • በደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት እሳት ተነሳ • በጎባው ግጭት የስድስት ሰዎች ሕይወት ጠፋ ይሁን እንጂ ለከብቶቻችን የግጦሽ መሬት አጣን በሚል በተደጋጋሚ አቤቱታቸውን ያሰሙ የነበሩ የአካባቢው አርሶ አደሮች ለጥያቄያችን ምላሽ አላገኘንም በሚል በመጥረቢያ አትክልቶቹን በመቆራረጥ፣ ቤቶችን በማፍረስና የሳር ክምሮችን በማቃጠል ውድመት ማድረሳቸውን ተናግሯል። "የደረሰ የማንጎ ዛፍ ከስሩ እየቆረጡና ፍሬውን እየለቀሙ በጆንያ እየከተቱ ወስደዋል። አፕል እንዲሁም በሰው ቁመት ልክ የሚሆን ኤለፋንት ግራስ የተባለ የከብት መኖ ሙሉ በሙሉ ወድሞብኛል" ይላል። ያሲን በግምት ቁጥራቸው 50 የሚደርሱ አርሶ አደሮች ወደ ቦታው በማምራት አትክልቶቹን ማውደም ሲጀምሩ "ሌት ከቀን የቆፈርኩበት አፈር የበላውንና ደም የቋጠረውን እጄን እዩት። እባካችሁ!" ብሎ ቢለምናቸውም ከተግባራቸው እንዳልተቆጠቡ ይናገራል። ሰሚ ሲያጣ ትቷቸው ወደ ቤቱ ከማምራት ውጪ አማራጭ አልነበረውም። በጥቃቱ ወደ 200 የሚጠጋ የማንጎ ዛፍ ፣ በዓመት እስከ 200,000 ብር የሚገመት በ 2.5 ሄክታር መሬት ላይ የበቀለ የከብት መኖ ወድሞብኛል ሲል ቅሬታውን ገልጿል። ስለጉዳዩን ያነጋገርናቸው የሀብሩ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ባለሙያ የሆኑት ስለሽ ማርዬ እንደሚሉት የወረዳው የአካባቢ ጥበቃ መሬቱ ነፃ መሆኑን አረጋግጦና የዞኑ ህግና ደንብ በሚያዘው መሰረት ጨረታ በማውጣት በግብርና ሙያ ላይ ላሉ ወጣቶች መሬቱን ሰጥቷል። አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው ከይዞታቸው ታልፎ የግጦሽ መሬታቸው እንደታጠረባቸው ይናገራሉ። ይህንንም ተከትሎ ሐምሌ 10፣ 2010 ዓ. ም. ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ከብቶቻቸውን ወረዳው አስተዳደር ድረስ ነድተው በመምጣት 'የምናበላቸው አጣን' ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተው እንደነበር አቶ ስለሽ ማርዬ ያስታውሳሉ። በወቅቱም የወረዳው አስተዳዳሪ ሰብስቦ ያነጋገራቸው ሲሆን አለመግባባቱ እልባት እስከሚያገኝ ድረስ ከባለሃብቶቹ ጋር ያላቸውን አምባጓሮ እንዲያቆሙ ጠይቋቸዋል። ለጊዜው ባላሃብቶቹ እንዲታገዱ የወረዳው አስተዳደር ለቀበሌው የእግድ ደብዳቤ ፅፎ ነበር። ነገር ግን ዞኑ ወረዳው ለባለሃብቶች በሚሰጥ ከ 10 ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ ስልጣን የለውም በማለት እግዱን አንስቶታል ይላሉ። በዚህ መሃል ውዝግቡ ያስቆጣቸው አርሶ አደሮችም ሃይል በመጠቀም ውድመት እንዳደረሱ አስረድተዋል። ወረዳው አርሶ አደሮችንና ልማታችን ወደመብን ያሉ ባለሃብቶችን የማረጋጋት ስራ እየሰራ ሲሆን የሁለቱን ወገኖች አለመግባባት ለመፍታት እየሰራ እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል።
news-44393962
https://www.bbc.com/amharic/news-44393962
ስፔን በሴት ሚኒስትሮች ቁጥር አዲስ ታሪክ አስመዘገበች
ሴቶችን በውሳኔ ሰጪነት ማሳተፍ ባልተለመደበት ዓለም ስፔን አዲስ ታሪክ አስመዝግባለች።
(ከግራ ወደ ቀኝ) የምጣኔ ሐብት ሚኒስትሯ ናዲያ ካልቪኖ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ካርመን ካልቮ እና የገንዘብ ሚኒስትሯ ማሪያ ጄሱስ ሞንቴሮ በስፔን ካቢኔ የሴት ሚኒስትሮች ቁጥር ከወንዶቹ መብለጡ መገናኛ ብዙኃንን አነጋግሯል። የሴት መብት ተቆርቋሪዎች ክስተቱን አወድሰውታል። የስፔን ሶሻሊስት ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንሼዝ ከ17 የሚኒስትር ወንበሮች ውስጥ አስራ አንዱን ለሴቶች ሰጥተዋል። ይህ ቁጥር ከየትኛውም የአውሮፓ አገር ካቢኔ የበለጠ ነው ተብሏል። የሴቶች መብት ተቆርቋሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሳንሼዝ በተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዘመን ወንዶች ተቆጣጥረውት የነበረውን ካቢኔ ፐውዘውታል። በአገሪቱ ሴት ሚኒስትሮች በቁጥር ከወንድ ሚኒስትሮች መብለጣቸው ብቻ ሳይሆን በካቢኔ ውስጥ እጅግ ቁልፍ የሚባሉትን እንደ መከላከያ፣ ምጣኔ ሐብት፣ ገንዘብና ፋይናንስ እንዲሁም የትምህርት ሚኒስትርነቱን ቦታ ሴቶች መያዛቸው በአገሪቱ አዲስ ዓይነት ተስፋን ጭሯል። ከዚህም ባሻገር የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርም ሴት ናቸው። አንዳንድ ሚዲያዎች ይህንን ካቢኔ "የሴቶች ካቢኔ" ሲሉ ጠርተውታል። የሴቶች ጉዳይ እጅጉኑ ግድ የሚላቸው ተራማጁ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳሉት በስፔን ማርች 8 የተደረገው ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍና ያነሳቸውን ቁልፍ የእኩልነት ጥያቄዎቸ አዲሶቹ ሚኒስትሮች ያሳኩታል ብለው ያምናሉ። የሴቶች ቀን በተከበረበት ማርች 8 በቁጥር ከ5 ሚሊዮን የሚልቁ ዜጎች ወደ አደባባይ በመውጣት የጾታ ጥቃትና ያልተመጣጠነ ክፍያን ተቃውመው ነበር።
news-56827451
https://www.bbc.com/amharic/news-56827451
ዓለም አቀፍ የወባ ቀን፡ በኢትዮጵያ መድኃኒት የሚቋቋም የወባ በሽታ ያሰጋ ይሆን?
መድኃኒት የተላመደ የወባ ፓራሳይት በእስያ ታይላንድና ካምቦዲያ ድንበር አቅራብያ እንዲሁም በአፍሪካ ደግሞ በሩዋንዳ መገኘቱ ይፋ ተደርጓል።
ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ በሽታውን ለመቆጣጠር የተለያዩ ፕሮግራሞችን ዘርግታ እየሰራች ባለችው ኢትዮጵያ ውስጥ መድኃኒቱን የተለማመደ ወባ ስለመኖሩ የሚያመለክት መረጃ የለም። በጤና ሚኒስቴር ብሔራዊ የወባ ማጥፋት ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ መብርሃቶም ኃይለ በኢትዮጵያ መድኃኒቱን የተለማመደ የወባ በሽታ አለመከሰቱን ለቢቢሲ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የወባ መድኃኒቶች ፍቱንነት ላይ በየሁለት ዓመቱ ጥናት እንደሚደረግ የገለጹት አስተባባሪው፣ በዚህም መሠረት የመድኃኒት 'ብግርነት' ወይንም መድኃኒቱን የሚቋቋም የወባ ዝርያ በኢትዮጵያ አለመኖሩን ተናግረዋል። በአርማወር ሃንሰን የምርምር ተቋም ወባ ላይ ጥናት የሚያደርጉት ዶ/ር ፍፁም ግርማ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን የወባ መድኃኒቶች ውጤታማነት ላይ ጥናት በየጊዜው እንደሚሰራ አመልክተው፤ እስካሁን ድረስ መድኃኒቱን የተለማመደ የወባ ዝርያ ስለመከሰቱ ምንም ዓይነት መረጃ አልተገኘም ይላሉ። ነገር ግን መድኃኒቱን የሚቋቋም ፓራሳይት መኖር አለመኖሩን ለመለየት የተሻለ የመመርመሪያ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። በፈረንጆች አቆጣጣር ከ2000 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የወባ ወረርሽኝ ስርጭት መቀነስ አሳይቶ ቆይቷል። ባለፉት አሥርት ዓመታት ውስጥ ለውጦች ቢመዘገቡም እ.አ.አ ከ2015 ወዲህ ግን ወደፊትም ወደ ኋላም እየሄድን አይደለም ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት በ2019 ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በዓለም ላይ የወባ ስርጭትን እየቀነሱ ከሄዱ አራት አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች። ወባ በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የወባ ስርጭት የሚከሰተው የዝናብ ወራቱን ተከትሎ ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ ድረስ ባሉት ወራት ውስጥ እንደሆነ አቶ መብርሃቶም ኃይለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የበልግ ዝናብን ተከትሎም በሚያዚያ እና በግንቦት ወራት በተወሰነ መልኩ ወረርሽኙ ጭማሪ እንደሚያሳይ አክለው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ወባ በወረርሽኝ መልክ የመከሰት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የለም ያሉት ኃላፊው፤ ይህንን ለማድረግ የተቻለውም የስርጭት ወቅቶችን ታሳቢ ያደረገ የመከላከል እና የመቆጣጠር እንዲሁም ወባን ማስወገድ የሚያስችል ስትራቴጂዎች ተነድፈው ላለፉት 15 ዓመታት በመሰራቱ እንደሆነ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ከአስር ዓመት በፊት በዓመት እስከ 5 ሚሊዮን በወባ የተያዙ ህሙማን ሪፖርት ይደረግ እንደነበር ገልፀው፤ በ2011 ዓ ም ደግሞ ከ1 ሚሊየን በታች የወባ ህሙማን ቁጥር ሪፖርት መደረጉን ያስታውሳሉ። በ2012 ዓ.ም ረዥም የዝናብ ወቅት እና ጎርፍ ከመኖር ጋር ተያይዞ ቁጥሩ በተወሰነ መልኩ ጨምሮ የነበረ በሆንም በ2013 ዓ.ም ቁጥሩ መቀነሱን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ላለፉት 50 ዓመታት ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጣር ጥረት ሲደረግ የቆየ ቢሆንም አሁን ግን ወባን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር 52 በመቶው ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች እንደሚኖር አቶ መብርሃቶም ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ከፍተኛ የወባ ስርጭት ያለባቸው ክልልች ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል መሆናቸውን አመልክተው፤ በሌሎች ክልሎች ግን የዝናብ ወቅትን ተከትሎ የመጨመር እና የመቀነስ ሁኔታ እንደሚታይ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም እና ፕላስሞዲየም ቫይቫክስ የሚባሉ ሁለት ዓይነት የወባ ፓራሳይቶች ይገኛሉ። ስለ ወባ ምን ማወቅ አለብዎት?
news-49372539
https://www.bbc.com/amharic/news-49372539
ሶልቭ አይቲ ኢኖቬሽን : የዘንድሮው የፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች ዛሬ ይታወቃሉ
በሶልቭ አይቲ ኢኖቬሽን (Solve IT Inovation) ሲካሄድ የነበረው የዘንድሮው ሃገር አቀፍ የወጣቶች የፈጠራ ሥራ ውድድር አሸናፊዎች ዛሬ ይፋ እንደሚደረጉ የአይኮግ ላብስ (iCog Labs) መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ ለቢቢሲ ገለፁ።
• ሶፊያ ከዐብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ሶልቭ አይቲ ኢኖቬሽን በተባለ ፋውንዴሽን [አይኮግ ላብስና ሌሎች ተባባሪ ድርጅቶች ተካተው የሚያዋቅሩት] በአገር አቀፍ ደረጃ ዕድሜያቸው ከ18-28 በሚደርሱ ወጣቶች መካከል የፈጠራ ውድድር ያካሂዳል። ዋነኛ ዓላማውም በአዲስ አበባ ላይ ብቻ ትኩረት ያላደረገና በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል የሚገኙ ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎችን ማውጣትና ሥራዎቻቸው ተግባር ላይ እንዲውሉ ማሰልጠን፣ መደገፍና ለውጤት ማብቃት ነው። ውድድሩ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የመጡ የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ወጣቶችን፤ ከተለያዩ ሃገራት ጋር ከሚገኙ እና በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ እንዲሁም ቴክኖሎጂ ላይ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ለማስተሳሰር አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ሥራ አስኪያጁ ገልፀውልናል። በባለፈው ዓመት የተካሄደውን ውድድር የአሜሪካ ኤምባሲና አይኮግ ላብስ በጋራ በመሆን ሲያዘጋጁት የዘንድሮውን ዓመት ውድድር ደግሞ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ ጃይካና አይኮግ ላብስ በጋራ በመሆን አዘጋጅተውታል። ዘንድሮም ከመላው ሃገሪቱ የተመዘገቡ ወጣቶች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ይዘው ለውድድር ቀርበዋል። • የወንድሙን ገዳይ ለመበቀል ወደ ፈጠራ ሥራ የገባው ኢትዮጵያዊ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ውድድር ላይ ወደ 1500 የሆኑ ተመዝጋቢዎች የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ውድድር ላይ ግን ቁጥሩ ጨምሮ ወደ 2800 የሚጠጉ ተወዳዳሪዎች ተመዝግበው ለመጨረሻው ዙር ውድድር የደረሱት 160 ወጣቶች መሆናቸውን ከአቶ ጌትነት ሰምተናል። 63 የፈጠራ ሥራዎችም ለውድድሩ እንደቀረቡ ገልፀውልናል። ከየክልሉ አዲስ አበባ የመጡ ተወዳዳሪዎች የካምፕ ቆይታ፣ ሥልጠና፣ የቴክኖሎጂ ተቋማትን የመጎብኘት አጋጣሚው ነበራቸው። ከሁሉም ክልሎች የተሳተፉ ተወዳዳሪዎች ቢኖሩም ከአዲስ አበባ የመጡት ግን ቁጥራቸው ከፍተኛ ነበር ብለዋል። የውድድር ማስታወቂያውን ያወጡትም በዲጂታል ቴክኖሎጂ [ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ቴሌግራምና የመሳሰሉት] ሲሆን በአይኮግ ላብስ ድረ-ገፅ ላይ ገብተው እንዲሞሉ ይደረጋል ፤ ይህም ወጣቶቹ ዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅመው እንዲሞሉ ለማስቻል ሲሆን በዚህ ዘዴ የተጠቀሙም አንድ ነጥብ ያገኛሉ። • አዲስ አበባ፡ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን እየጣረች ያለች ከተማ አብዛኛዎቹ ተወዳዳሪዎች በትምህርት፣ በሆቴልና ቱሪዝም በጤና እንዲሁም በግብርና ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሥራዎችን እንዳቀረቡ የሚናገሩት አቶ ጌትነት "በዚህ ዘመን እርሻ መታረስ የነበረበት በቴክኖሎጂ ነበር" ይላሉ። በተለይ በጤናው ዘርፍ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ ሥራዎች እንደሚበራከቱ ይናገራሉ። ከጋምቤላም እንዲሁ ያላቸውን ባህላዊ የሠርግ ሥነ ሥርዓት በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማድረግ የሠሩ ወጣቶች እንደቀረቡም ነግረውናል። ባለፈው ዓመት አንድ ኦክስጅን የሚያስፈልገው ታማሚ የሚወስደውን የኦክስጅን መጠን የሚቆጣጠር የፈጠራ ሥራ ያቀረበው ወጣት ያሸነፈ ሲሆን [ከጅማ] የ75 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኖ ነበር። በዚያው ውድድርም ሁለተኛ ደረጃን የያዘው [ከመቀሌ] የተለያዩ ግብዓቶችን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ሥራን ያቀረበ ሲሆን በሦስተኛው ደረጃ ላይ ደግሞ [ከባህር ዳር] 'Hello Reminder' የተባለ ዕቃና ህፃናት ቢጠፉ በሞባይል አማካኝነት ያሉበትን የሚያሳውቅ የፈጠራ ሥራ ቀርቦ ነበር። ለእነርሱም የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደተበረከተላቸው አቶ ጌትነት አስታውሰዋል። ውድድሮቹ በገለልተኛና ከድርጅቱ ውጭ ባሉ ባለሙያዎች እንደሚዳኝም አክለዋል። በዘንድሮው ውድድርም ለተሳተፉት በሙሉ የምስክር ወረቀትና ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለሚወጡት ፕሮጀክቶች የ100 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል። የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የአሜሪካና የጃፓን ኤምባሲ አምባሳደሮች፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና እንግዶች በተገኙበት በቃና አዳራሽ ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ አቶ ጌትነት ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-53155227
https://www.bbc.com/amharic/news-53155227
ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ?
ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት ሰኔ 16/2010 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ድጋፍ በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ በተሰነዘረው የቦንብ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።
ጥቃቱን በማቀነባበርና በመምራት አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክስ የተመሰረተ ሲሆን ሁለት ሰዎች ደግሞ አለመያዛቸውን በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የተደራጁ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ፍቃዱ ጸጋ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አምስቱ ግለሰቦች ላይ የቀረበው ክስ የሽብር ድርጊት የሚል ሲሆን የፀረ ሽብር አዋጁ 652/2001 አንቀጽ 3 ስር መከሰሳቸውን አብራርተዋል። የሰኔ 16 ተከሳሾች መዝገብ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ተከሳሾች የመጨረሻ ይቅረብል ያሉት ሰነድ እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ ፍቃዱ፣ እርሱ ላይ ብያኔ ለመስጠትና የፍርድ ውሳኔውን ለማዘጋጀት እን ሌሎች የሚያስፈልጉ ነገሮች መኖራቸውን ለመወሰን ቀጠሮ ተሰጥቶ እንደነበር ገልጸዋል። ከኮሮናወረርሽኝ ወዲህ ችሎቶች ሥራ በማቋረጣቸው የተከሳሾች ጉዳይ አለመንቀሳቀሱን አቶ ፈቃዱ ጸጋ አመልክተዋል። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩት አምስቱም ተከሳሾች ይከላከሉ ተብሏል ያሉት አቶ ፍቃዱ፣ እነርሱም መከላከያ ምስክር የሚሉትን አሰምተዋል ሲሉ ገአስታወስኣል። "ነገር ግን በምስክርነት የጠቀሷቸው አንዳንድ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎችን የመከላከያ ምስክሮቻችን ናቸው በሚል ስለጠየቁ፣ በወቅቱ መገናኛ ብዙሃን ላይ ቀርበው ስለተናገሩ ብቻ፣ ፍርድ ቤቱ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አለው ወይስ የለውም ተገቢ ነው፣ አይደለም የሚለውን ለመወሰን ቀጠሮ ሰጥቶ በነበረበት ወቅት ነው ወረርሽኙ ተከስቶ ችሎቱ የተቋረጠው።" ነገር ግን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አቃቤ ሕግ ማስረጃ የማሰማት ሂደት ማለቁን ጨምረው ተናግረዋል። በቁጥጥር ስላልዋሉት ሁለት ሰዎች ሲናገሩም አንደኛው የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ የነበሩትና ሌላኛዋ ይህንን ጉዳይ አቀናብራለች የተባለች ሴት በክሱ ላይ ተጠቅሰው ያልተያዙ መሆናቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቀድሞ የደኅንነት ኃላፊ በሌላ መዝገብም መከሰሳቸውን በማስታወስ፣ ክስ የቀረበባቸውና በፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋሉት አምስቱ ሰዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በአቃቤ ሕግ የቀረበባቸው ክስ ስለተረጋገጠ ተከላከሉ ተብሏል። ሁለቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎችን ለመያዝ ምን እየተደረገ ነው ተብለው የተጠየቁት አቶ ፍቃዱ፣ ምርመራ አይቆምም ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። ማስረጃዎች በተገኙና በተረጋገጡ ልክ ሂደቱ ይቀጥላል። በወቅቱ በቂ ጥርጣሬ የሚያጭሩ ነገሮች ነበሩ። በሌላ ወንጀል የተጠረጠረ ሰው በዚህ ጉዳይ ማስረጃ መሆን እችላለሁ ብሎ ቃሉን የሰጠ ሰው ነበር ሲሉም አክለዋል። "እርሱን በሌላ ጉዳይ ላይ ተጠርጣሪ ማድረግ ነው የሚሻለው ወይስ እዚህ ጉዳይ ላይ ምስክር ማድረግ ነው የሚሻለው የሚለውን መወሰን የሚፈልግ ነገር ሊሆን ይችላል" ሲሉም ያለውን ሁኔታ ያስረዳሉ። ግን ያልተያዙትን ሰዎች ወደ ሕግ የማቅረቡ ጥረት እንደሚቀጥል በተለይም ከአገር ውጪ ኬንያ ውስጥ አለች የተባለችውን ሴት መያዝ አንዱ አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል።
news-51631860
https://www.bbc.com/amharic/news-51631860
ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፡ የጤና ችግር ያለባቸውና ተሳትፏቸው ውስን የሆኑት ይለቀቃሉ
በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙ ሰዎች መካከል ስድሳ ሦስቱ የተመሰረተባቸው ክስ እንዲቋረጥና ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ።
እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው መካከል በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተከሰሱ ነገር ግን በአመራር ቦታዎች ላይ ያልነበሩ ሰዎች ይገኙበታል የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኃላፊዎች የሆኑት አቶ ፍቃዱ ፀጋና አቶ ዝናቡ ቱኑ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው መካከል በሙስናና በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተከሰሱ ነገር ግን በአመራር ቦታዎች ላይ ያልነበሩ ሰዎች ናቸው። በተጨማሪም በአዲስ አበባና በባሕር ዳር ከተሞች ውስጥ ሠኔ 15/2011 ዓ.ም ከተፈጸመው ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ግድያ እንዲሁም በሶማሌ፣ በሲዳማና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ውስጥ ካጋጠሙ ግጭቶች ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችም ይገኙበታል ተብሏል። በጠቅላይ አቃቤ ሕግ የፌስቡክ ገጽ ላይ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረጉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ ሌተናንት ኮሎኔል ቢንያም ተወልደ፣ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ይገኙበታል። በተጨማሪም ሌተናንት ኮሎኔል ሰላም ይሁን፣ ሌተናንት ኮሎኔል ጸጋዬ አንሙት፣ ሌተናንት ኮሎኔል ለተብርሀን ደሞዝ፣ ኮለኔል ሸጋው ሙሉጌታ፣ ወ/ሮ ራህማ አህመድ እና ወ/ሮ ዘምዘም ሀሰን ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተደረገው መካከል ይጠቀሳሉ። • በ30 የኢትዮጵያ ወረዳዎች የኩፍኝ ወረርሽኝ መከሰቱ ገለፀ • ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ሲቋረጥ ምን ይከሰታል? • አቶ ንዋይ ገብረአብ በሚያውቋቸው አንደበት የመረጃ መረብ ደኅንነት ተቋም ከፍተኛ ኃላፊ የነበሩት የሌተናንት ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ጠበቃ አቶ ኃይለሥላሴ ገብረመድህን፣ ሌተናነት ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደን ጨምሮ ሌሎች የሜቴክ ተከሳሾች ክሳቸው ይቋረጣል የሚል መረጃ እንዳላቸው ትናንት ለቢቢሲ መግለጻቸው ይታወሳል። በተጨማሪም አዲሱ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀ መንበር አቶ በለጠ ሞላ ለቢቢሲ እንደገለጹት ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ መንግሥት በእስር ላይ ያሉ አባሎቻቸውን እንዲፈታ መነጋገራቸውን አመልክተው ነበር። የድርጅቱ አመራር ከሆኑት መካከል በእስር ላይ ሳሉ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት እና ክሳቸው ከተቋረጡት አንዱ የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ናቸው። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በእስር ላይ የቆዩት ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ የተወሰነው "ምንም ስላላጠፉ እና ማስረጃ ስላልተገኘባቸው ሳይሆን የተወሰኑት የጤና ችግር ስላለባቸው ሌሎቹ ደግሞ የወንጀል ተሳትፏቸው አነስተኛ ስለሆነ ነው" ብሏል። በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በእስር ላይ የሚገኙ የቀድሞ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችና የፖለቲካ መሪዎች ጉዳያቸው በሕግ አግባብ ታይቶ ክሳቸው እንደሚቋረጥ ፍንጭ ሰጥተው ነበር። ይህንንም በተመለከተ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ትናንት ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ የሕግ አግባብን ተከትሎ በእስር ላይ ያሉ 60 ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንደሚለቀቁ አመልክቶ ነበር። በተጨማሪም የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ከተጠረጠሩ ከ3600 በላይ ግለሰቦች ውስጥ እስካሁን 1682ቱ ብቻ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
news-50414966
https://www.bbc.com/amharic/news-50414966
ጎርፍ በቀላቀለ ወጀብ ተወስደው የነበሩት ላሞች ውቅያኖስ ዳር በሕይወት ተገኙ
ሰሜን ካሊፎርኒያ ውስጥ ሃሪኬን ዶሪያን የተሰኘው ጎርፍ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ ባደረሰው ጥፋት ሞተዋል የተባሉ ላሞች ውቅያኖስ ዳር ሲንጎማለሉ ታይተዋል።
ቼዳር ደሴት ላይ ነዋሪ የነበሩት እኒህ ላሞች የተረፉት ውቅያኖስ ላይ ሲዋኙ ከከረሙ በኋላ ሳይሆን አልቀረም ተብሏል። ሳይሞቱ አልቀረም ተብለው የተገመቱት ላሞች አንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ካለ ፓርክ ውስጥ ሳር ሲግጡ ተገኝተዋል። ሦስቱ ላሞች 8 ኪሎ ሜትር ያህል የውቅያኖስ አካል በዋና ሳያካልሉ አልቀረም የሚሉት የፓርኩ ሰዎች ላሞቹን ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ለመመለስ ዕቅድ እየነደፉ ነው። አንድ የፓርኩ ሠራተኛ ነው ከላሞቹ አንዷ ፓርኩ ውስጥ ስትንጎማለል ባለፈው ወር ያያት። ላሚቱ ከተገኘች ቀናት በኋላ ደግሞ ወዳጆቿ ሣር ሲከረክሙ ተገኝተዋል። የፓርኩ ባለሙያ የሆኑት ሆርቫርት ላሞቹ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ጥልቅ ሥፍራ አለመጋባታቸው ዕድለኛ ናቸው ይላሉ። ባለፈው መስከረም ሃሪኬን ዶሪያን ጎርፍ የቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ ሲጥል በጎርፍ የተወሰዱ በርካታ ፈረሦች ነበሩ ተብሏል። የፓርኩ ባለሙያ ላሞቹ በ8 ኪሎ ሜትር ዋናቸው ስንቱን እንዳሳለፉ በመገመት «መቼም ብዙ የሚካፍሉን ታሪክ ይኖራል» ሲሉ ቀልድ ጣል አድርገዋል። ሃሪኬን ዶሪያን መስከረም ላይ ወጀቡን ሰሜን ካሊፎርኒያ ላይ ሲያሳርፍ ንብረት እና እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ይህ ወጀብ ወደ ባሃማስ ደሴት አቅንቶ የሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጥፋት እንዳደረሰ አይዘነጋም።
news-57222408
https://www.bbc.com/amharic/news-57222408
አሜሪካ በየትኞቹ አገራት ላይ ምን ዓይነት ዕቀባዎችን ጥላለች?
አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ኃያላን አገራት የምጣኔ ሀብት፣ የፖለቲካ ግንኙነት፣ የንግድ፣ ወታደራዊ፣ እርዳታ የማቆም እና ሌሎችም ማዕቀቦች በተለያየ ምክንያት ይጥላሉ።
የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል ሲባል፣ በአንድ አገር ውስጥ በተለያየ መንገድ አፈና ሲካሄድ ወይም ደግሞ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የሚተላለፍ ተግባር ተከናውኗል በሚባልባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ኃያላን አገራት ማዕቀብ ይጥላሉ። የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ባለሥልጣናት፣ በወታደራዊና የደኅንነት አባሎች፣ በአማራ ክልል ኃይሎች እንዲሁም በህወሓት አባላት ላይ የቪዛ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች። ለዚህም በምክንያትነት የቀረበው በትግራይ ክልል የሚካሄደው ጦርነት እንዲቆምና የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ እንዲወጡ፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል፣ የግጭቱ ተሳታፊ ኃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ያደረገችው ጥረት ተቀባይነት አለማግኘቱ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ አገራት በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ መግባታቸውን ጠቅሶ በማንኛውም መንገድ ጫና ለማሳደር መሞከሩን እንደማይቀበለው በተደጋጋሚ አስታውቋል። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ማዕቀብ ከጣለችባቸው አገሮች ጥቂቱን እንመልከት። ከተለያዩ ድረ ገጾች የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ አሜሪካ እስከ አውሮፓውያኑ 2020 ማዕቀብ ከጣለችባቸው አገሮች መካከል ቤላሩስ፣ ብሩንዲ፣ ሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሆንግ ኮንግ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ሊባኖስ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ኒካራግዋ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶርያ፣ ዩክሬን፣ ሩስያ፣ ቬንዝዌላ፣ የመን እና ዚምባብዌ ይጠቀሳሉ። የአሜሪካ እንዲሁም የሌሎችን አገራት ማዕቀብ መጣል በአሉታዊም በአወንታዊም መንገድ የሚተነትኑ አሉ። በእርግጥ ሁሉንም አይነት ማዕቀብ በአንድ መመዘኛ ለመለካት አይቻልም። ማዕቀቡ የተጣለበትን አገር እውነታ፣ ማዕቀቡ የተጣለበትን ምክንያት፣ ማዕቀቡን የጣለው አገር እና የተጣለበት አገር የሚያቀርቡትን መከራከሪያ እንዲሁም ማዕቀቡን በመጣል ለማግኘት የታለመው ነገር ከግምት መግባት አለበት። በአንድ በኩል አገራት ማዕቀብ በመጣል የአገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅና ኃያልነታቸው ጎልቶ እንዲታይ ማድረጋቸውን የሚተቹ አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አገራት ላይ በማዕቀብ ጫና በማሳደር የሰብዓዊ መብት እንዲከበር እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሕግጋት እንዳይጣሱ ማረቅ ይቻላል ብለው የሚከራከሩም አሉ። ማዕቀብ መጣል ምን ያህል ውጤት ያመጣል? የአገራትን ምጣኔ ሀብት እና የዲፕሎማሲ ተሰሚነት ማሽመድመድ ዋጋ አለው? ማዕቀብ የሚጥሉ አገራት የምጣኔ ሀብት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተሰሚነት ቢኖራቸውም ሌሎች አገራት ላይ ማዕቀብ የመጣል የሞራል ልዕልና አላቸው? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ይሰነዘራሉ። ዘለግ ላለ ጊዜ ማዕቀብ ከተጣለባቸው አገራት አንዷ ኩባ ስትሆን፤ ማዕቀቡ የተጣለው በአሜሪካ መንግሥት የሚደገፈው አስተዳደር በፊደል ካስትሮ ከተሸነፈ በኋላ ነው። አሜሪካ ኩባ ላይ የጣለችው የንግድ ማዕቀብ ነው። ሌላዋ አገር ኢራን ናት። እአአ ከ1979ቱ አብዮት በኋላ ከምዕራባውያን ጋር ወዳጅ የነበሩት የኢራኑ ሻህ ከሥልጣን ተወግደዋል። አሜሪካ ኢራን ላይ የጣለችው ማዕቀብ ዛሬም ድረስ በሁለቱ አገራት ለሚስተዋለው ውጥረት አስተዋጽኦ አበርክቷል። አሜሪካ ኢራንን "ሽብርን በመደገፍ" እንዲሁም ከዩራንየም ማበልጸግ ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ትወነጅላለች። ኢራንም ብትሆን አሜሪካን በበጎ አትመለከትም። በሁለቱ አገራት ያለው ውጥረት ዓመታትን ተሻግሮ ዛሬም ድረስ እንዳለ ነው። አሜሪካ ማዕቀብ ከጣለችባቸው አገሮች ሌላዋ ሰሜን ኮርያ ናት። እአአ በ1950 የተቀሰቀሰው የሁለቱ አገራት አለመግባባት እስከዛሬም ውጥረት አንግሶ ዘልቋል። የአሜሪካ የምጣኔ ሀብት ማዕቀብ ሰሜን ኮርያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ቢያሳድርም፤ ሰሜን ኮርያ በምዕራባውያን ዘንድ የሚሰጣት ስም እምብዛም የሚያሳስባት አይመስልም። ማዕቀብ የሚጥሉ አገራትን ያለፈ ታሪክ እንዲሁም በአገራቸው ውስጥ የሚገኝ ነባራዊ ሁኔታን በማጣቀስ ማዕቀብን የሚኮንኑ አሉ። አንዳንድ የመብት ተሟጋቾች ደግሞ መንግሥታት ለሚፈጽሙት ወንጀል ተጠያቂ ከሚደረጉበት መንገድ አንዱ ማዕቀብ ነው ይላሉ። አሜሪካ የምትጥላቸው ማዕቀቦች አገራት ላይ ብቻ ያነጣጠሩ አይደሉም። በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና የፖለቲካ ተቋማት ላይም እገዳ ይጣላል። ለምሳሌ እአአ በ2017 ሚያንማር ውስጥ ከተፈጠረው ውዝግብ ጋር ተያይዞ በተወሰኑ ሰዎች ላይ የቪዛ እገዳ ተጥሏል። የአሜሪካ ማዕቀብ ከሚያካትታቸው መካከል የጦር መሣሪያ ንግድ እገዳ፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እገዳ፣ የንግድ ዝውውር እገዳ ይገኙበታል። በተጨማሪም አገራት ብድር እንዳያገኙ ማድረግ፣ ማዕቀብ የተጣለባቸውን ግለሰቦች ቪዛ መከልከል እንዲሁም የገንዘብ ዝውውር ላይ እገዳ መጣልም ይጠቀሳሉ።
news-41480239
https://www.bbc.com/amharic/news-41480239
የገጠር ሴቶች በግብርና ስራ የተደቀነባቸውን ጋሬጣ እያለፉ ነው?
ባለፉት አስርት ዓመታት በታዳጊ ሀገራት በግብርና ተግባራት ላይ የሚሳተፉ ሴቶች ቁጥራቸው ጨምሯል።
የስራ ሁኔታዎቻቸውን ለማሻሻል የሚረዱ መርሃግብሮችም እየተተገበሩ ነው። ግን ይህ እርምጃ እውን በተጨባጭ እያበቃቸው ነው ? "ብዙ የስኳር ድንች ምርት አለን የምንፈልገው ገዢ ብቻ ነው።" ትላለች ሮዛሊና ባሌስቴሮስ በሰሜናዊ ኮሎምቢያ ዳርቻ የምትገኘው ኮረብታማዋ ሞንቴስ ዴ ማርያ ለሮዛሊና የመኖሪያም የመስሪያም ቦታዋ ናት። በዚህ ዓመት ደግሞ ጥሩ ምርት አግኝተዋል፤ ነገር ግን የግዢ ፍላጎቱ አነስተኛ ስለሆነ ምርቱ ከወዲሁ መበስበስ ጀምሯል። እናም ማህበረሰቡ ዩ ቲዩብ ባሉ ማህበራዊ ድረ-ገፆች የሽያጭ ጥሪ ማሰማት ጀምሯል። "ድንች ስኳራችንን በመሸመት እንድትረዱን እንጋብዛለን።" ትላለች አርሶ አደሯ በኮሎምቢያ ዝናን ባተረፈው የ40 ሰከንድ ቪዲዮ። '' ለመገጣጠሚያ ህመም ፣ለሆድ ድርቀትና በማረጫ ወቅት በጣም ጠቃሚ ምግብ ነው።" በማለት ሌሎች የስራ ባልደረቦቿም ምርቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ። የኮሎምቢያ ሴት አርሶአደሮች በዩቲዩብ ምርቶቻቸውን እያስተዋወቁ ነው የ32 ዓመቷና የ 5 ልጆች እናት የሆነችው አርሶአደር አይናጉል አብድራህማኖቫም በማዕከላዊ ኪርጊስተን በሚገኘው ተራራማ መንደር በሚገኝ የሴቶች ራስ አገዝ ቡድን ታቅፋለች። "በተከላውም ሆነ በጠብታ መስኖ አጠቃቀም ብዙ አግዘውኛል" ትላለች ። ከዚህ ቀደም በእርሻ መሬቷ እንደማይለሙ የምታስባቸውን ቲማቲም፣ ኪያርና ካሮት ታመርታለች። በሰሜናዊ ላኦስ ደግሞ ወይዘሪት ቪዬንግ በእንጉዳይ ምርት ገቢ ኑሮዋንም ትመራለች። ማህበረሰቡ የጫካ እንጉዳዮችን ለምግብ ፍጆታ የመሰብሰብ ልምድ ነበረው። ወይዘሪት ቪዬንግና ሌሎች ጎደኞቿ በአካባቢው ለገበያ የሚቀርብ እንጉዳይን የማልማት ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ግን ነገሮች መቀየር ጀመሩ። ቪንግ በግብርናና ብዝኃ ሕይወት ፕሮጀክት የእንጉዳይ ልማት ቲክኒኮችን ተምራለች የታዳጊ ሀገራት ሴቶች ከግብርና የሰው ኃይል በአማካይ 43 በመቶውን ይሸፍናሉ። ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ደግሞ ባለሙያዎች በግብርና ሴቶች ከዚህ በተሻለ የሚሳተፉበትን ሂደት አስተውለዋል። የግብርና ስራ ወደ ሴቶች እየተሸጋገረ ስለመሆኑ አሳማኝ ማስረጃዎች እንዳሉ በ2016 የወጣው የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ሪፖርት ያመለክታል። ምናልባትም ወንዶች ከግብርና ስራዎች እየወጡ ስለሆነ አሊያም ሴቶች በዘርፉ በሚገኙ ተግባራት እየተሳተፉ ስለሆነ ሊሆን ይችላል። ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት በ2015 በዓለማችን በኢኮኖሚ በንቃት ከሚሳተፉ ሴቶች አንድ አራተኛ የሚሆኑት በግብርና የተሰማሩ እንደነበሩ ይገልጻል። ይሁንና ይህ አሃዝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ እንደየአካባቢው ሁኔታ ልዩነት ያሳያል። አነስተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ግብርና ከፍተኛውን የስራ እድል ቢፈጥርም ከፍተኛ ገቢ ባላቸው ግን ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ወደ ኢንዱስትሪ ወይም ወደ አገልግሎት ዘርፍ ያመዝናሉ። ታዲያ ለውጡ የሚታየው የት ነው? ይህ የሴቶች የግብርና ተሳትፎ በሰሜናዊ አፍሪካ በይበልጥ ይስተዋላል ፤ በግብርና የተሰማሩ ሴቶች ቁጥር እአአ 1980 እስከ 2010 በነበሩት 30 ዓመታት ከ 30 በመቶ ወደ 43 በመቶ አድጓል። በምዕራብ እስያ በዚሁ ጊዜ ከ 35 ወደ 48 በመቶ ጨምሯል። የሴቶች የግብርና ተሳትፎ በምስራቅና በደቡብ ምስራቅ እስያ እንዲሁም በላቲን አሜሪካም ቢሆን ለውጡ በግልጽ የሚታይ ነው። ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ግን ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በሴቶች ተሳትፎ ብዙም ለውጥ አልታየም። በሴራሊዮን፣ በሌሴቶና በሞዛምቢክ ግን ተሳትፎው ከ 60 በመቶም በልጧል። የግብርና ባለሙያዎች በዚህ አካባቢ ከወዲሁ የግብርና ስራውን ሴቶች እንደተቆጣጠሩት አረጋግጠዋል። የወንዶች ስደት የፈጠረው ጫና የሴቶች የእርሻ ስራ ተሳትፎ መጨመር በራሱ ልማት ሊሆን ይችላል። አንዳንዶች እርሻን ጉሮሮን ከመሸፈኛ አልፈው እንደገቢ ምንጭ በመጠቀም ቤተሰባቸውንና ማሀበረሰባቸውን እየደጎሙ ነው። ሆኖም ይህ ሁልጊዜም የሴቶችን መብቃት ላያሳይ ይችላል። ለዚህ ከዋነኛ ምክንያቱ አንዱ የወንዶች ስደት የፈጠረው ጫና ነው። "የገጠር ወጣት ወንዶች ከሴቶቹ በበለጠ ወደ ከተማ ይሰደዳሉ'' ይላሉ የፋኦ የፖሊሲ ባለሙያው ሊበር ሰቶሉካል። '' የሴቶች ተሳትፎ በከፊል ወይም ካልታረሰ የእርሻ መሬት አቅርቦት ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፤ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች አዋጪ የስራ አማራጮች መኖራቸውና ግጭቶችና ጦርነቶች በወንዶች የህዝብ ብዛት ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥረዋል'' እናም ቤት የቀሩ ሴቶች የወንዶቹን እጥረት ለማካካስ የስራ ሰዓታቸውን መጨመር ግድ እንደሚላቸው ሞያተኞች ይናገራሉ። ሴቶች በግብርና የሰው ኃይል ትልቅ ድርሻ ቢኖራቸውም በገጠር ሊያገኙ የሚችሉት የስራ ዕድል ግን አሁንም በስጋት ላይ ነው። ብዙዎቹ ክፍያ የሌላቸው፣ በተወሰነ ወቅት ብቻ የሚኖሩና በትርፍ ጊዜ ሊሰሩ የሚችሉ ናቸው። ክፍያ ባላቸው ስራዎችም ቢሆን ትኩረታቸው በጉልበት ስራና ብዙም ክህሎት በማይጠይቁት ሲሆን የአስተዳደር ቦታዎች ግን በአብዛኛው የሚያዙት በወንዶች ነው። "ሴቶች ቢያርሱም የገበያ ስራውን የሚከውኑትና ገንዘቡን የሚቆጣጠሩት ወንዶች ናቸው። '' የምትለው ደግሞ የማህበራዊና የስነጾታ ባለሙያዋ ዲና ናጃር ናት። የክፍያ አለመመጣጠን ሴቶች ከወንዶች ጋር ተመሳሳይ ስራ ሲሰሩም የሚከፈላቸው ክፍያ ያነሰ ነው። በ14 ሀገራት የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ደሞዛቸው ከወንዶቹ በአማካይ በ28 በመቶ ይቀንሳል። የታዳጊ ሀገራት ሴት አርሶአደሮች ደግሞ ሌሎች ኃላፊነቶችም ስለሚበዙባቸው ከ 20-30 በመቶ የምርታማነት ከፍተት እንደሚታይባቸው ባለሙያዎች ያናገራሉ። ሆኖም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥም አልፎ የሴቶች የግብርና ሚና ተጨባጭ ጥቅሞችን አስገኝቷል። ''በተለይም በዘር ጊዜ ህይወት በጣም አስቸጋሪ ነበር'' አርሶአደር ሳኒሃን ''አሁን ምርት የመሰብሰቢያ ጊዜ ባይሆንም አልጨነቅም፤ በከባድ ጊዜም በሚያጠነክሩን አዳዲስ መስኮች እየተሳተፍን ነው።'' ባይ ናት በማዕከላዊ ማሊ የገጠር መንደር የምትኖረው የ4 ልጆች እናት ሳኒሃን ቴራ። በፋኦ እገዛ በተማሯቸው አዳዲስ ቴክኒኮች እሷና መሰል የማሊ ሴቶች ወንዶች ወደሌላ የስራ ዘርፎች ሲሰማሩ ቤተሰባቸውን የመመገብና ሙሉ መሬታቸው ላይ ተክሎችን የማልማት ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ። "በእርግጠኝነት የምናገኘው ምርት የምግብ ፍጆታችንን ለበርካታ ወራት እንደሚሸፍንልን አልጠራጠርም።'' ትላለች ሳኒሃን። ይሁንና የመሬት ባለቤትነት መብት ጉዳይ ለዚህ ማህበራዊ እድገት ትልቁ ማነቆ ሆኗል። ምክንያቱም ከታዳጊ ሀገራት በብዙሃኑ ሴቶች ከወንዶች እኩል የመሬት ባለቤት የመሆን መብት የላቸውም። 100 ሴቶች የተሰኘው ተከታታይ መሰናዶ አምስት ዓመት ሆነው። በዓለም ዙሪያ ያሉ ሴቶች ሊወያዩባቸው በሚፈልጓቸው ርዕሶች ላይ ያተኩራል። በዚህ ዓመትም ሴቶች ለአራት ዋና እንቅፋቶች የሚያቀርቡትን መፍትሔዎች ይዳሰሳሉ። እነሱም: ከባድ ፈተናዎች፣ የትምህርት እጦት፣ በሕዝብ መጓጓዣ ላይ ሚፈፀም ጥቃት እንዲሁም ፆታዊ ጭቆና በተከታታይ ከሚቀርቡት የ100 ሴቶች መሰናዶዎችን ይከታተሉ።
news-53255453
https://www.bbc.com/amharic/news-53255453
ኮሮናቫይረስ የሴቶችን ሕይወት እየቀየረው ይሆን?
ሴቶች በቤት ውስጥ ሲውሉ በአብዛኛው ልጆችን የመንከባከብና ቤትን የመቆጣጠር ኃላፊነት የሚጣልባቸው ሲሆን ከኮሮናቫይረስ በኋላ ደግሞ ሥራቸውንም ሊያጡ የሚችሉ ብዙዎች ናቸው።
ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ በርካቶች በቤት ውስጥ በመዋላቸው አስርት ዓመታት በሴቶች እኩልነትና ተጠቃሚነት ዙሪያ ሲሰሩ የነበሩ ሥራዎችን መና እንዳያስቀረው እየተሰጋ ነው። ስዊድናዊቷ አና ዣቪዬር የሁለት ልጆች እናት ስትሆን በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የስምንት ወር ነፍሰጡር ነች። ምንም እንኳን ባለፉት ወራት ከቤተሰቦቿ ቤት በመውጣት የራሷን ቤት በማፈላለግ የነበረች ቢሆንም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነገሮችን እንዳመሰቃቀለባት ትናገራለች። ከወረርሽኙ በፊትም ለብዙ ዓመታት የሰራችበትን የውበት መጠበቂያዎች አምራች ኩባንያ በመልቀቅ ስቶክሆልም ውስጥ የራሷን የህጻናት መገልገያዎች ማምረቻ ድርጅት ለመክፈት በዝግጅት ላይ ነበረች። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ እሷና ባለቤቷ ከቤት መስራት የጀመሩ ሲሆን፤ በቤት ውስጥ ያለው የሥራ ክፍፍል ግን የሥራ ሰዓቷን ጭምር እንደሚሻማባት ትናገራለች። ምንም እንኳን በቤት ውስጥ ለሚያስፈልጉ ነገሮች በየወሩ እኩል የሆነ ገንዘብ አዋጥተው የሚኖ ቢሆንም ፤ እሷ ከባለቤቷ በበለጠ መልኩ ልጆችን የመንከባከብ፣ ምግብ ማብሰልና ቤት የማጽዳት ኃላፊነት አለባት። "በውይይታችን ወቅት ባለቤቴ የህክምና መሳሪያዎችን ለሚያመርት ድርጅት ስለሚሰራና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚደገው ጥረት መንግሥትን ስለሚረዳ ሙሉ ጊዜውን መሰዋት እንዳለበት ተስማማን።" ነገር ግን ሥራውን ከጨረሰ በኋላ ያሉበትን ቀላል የሚባሉ ኃላፊነቶች እንኳን አሁንም ቢሆን ለመወጣት ፍላጎት አልነበረውም ትላለች አና። በዚህ ምክንያት መስማማት ባለመቻላቸው በየቀኑ የምትመላለስ ሠራተኛ ለመቅጠር ተገደዋል። ነፍሰጡርነት፣ የወረርሽኝ ስጋትና የቤት ውስጥ ሥራ ተደማምረው ሕይትን ከባድ እንዳደረጉባት የምትናገረው አና፤ ልጇን ከመውለዷ በፊት ለመጨረስ አስባቸው የነበሩ በራካታ ነገሮች እስካሁን እንዳልተጀመሩ ትገልጻለች። ልክ ኮሮናቫይረስ በመላው ዓለም መሰራጨት ሲጀምርና ተቋማት ሠራተኞቻቸው ከቤታቸው ሆነው ሥራቸውን አንዲያከናውኑ ማድረግ ሲጀምሩ ብዙዎች ምናልባት የቤት ውስጥ ሥራዎች እኩል በሆነ ሁኔታ ሊሰሩ ነው የሚል ግምታቸውን አስቀምጠው ነበር። ነገር ግን በበርካታ አገራት በተሰሩ ጥናቶች መሰረት እውነታው የተገላቢጦሽ ነበር። አና እና መሰል ሴቶች እንደውም ከሌላ ጊዜው በበለጠ ልጆቻቸውን የመንከባከብና ምግብ የማብሰል ኃላፊነት ተጭኖባቸዋል። ከአሜሪካ ቦስተን ተመራማሪዎች በ3000 ሰዎች ላይ ባደረጉት የዳሰሳ ጥናት በቤት ውስጥ ከሚውሉ ሰዎች ውስጥ ሴቶቹ ከወንዶች በበለጠ ሁኔታ በሳምንት ተጨማሪ 15 ሰዓታትን በቤት ውስጥ ሥራና ልጆችን በመንከባከብ ያሳልፋሉ። ምንም እንኳን በበርካታ አገራት በተለይም በአውሮፓ የእንቅስቃሴ ገደቦቹ እየላሉ ቢሆንም ኮረሮናቫይረስ ያስከተለው ጫና በቀላሉ የሚጠፋ እንዳልሆነ ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ። ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ላይ ‘የብሪቲሽ ጆርናል ኦፍ ፊሎሶፊ’ ምክትል አርታኢዋ ኤሊዛቤት ሃኖን በትዊተር ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ሴቶች ለመጽሔቱ የሚያቀርቧቸው ጽሁፎች ቁጥር በእጅጉ መቀነሱን ገልጻ ነበር። ይህም መልዕክት በመላው ዓለም በሚገኙ ሴቶች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። የተባበሩት መንግሥታት በቅርቡ ባወጣው አንድ ጥናት ላይ፤ የኮረሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲሰሩ የነበሩ ሴቶችን ወደ አመራርነት ስፍራ የማምጣትና እኩል እድል የመፍጠር ጥረቶችን ሊያደናቅፍ እንደሚችል ጠቁሟል። በሪፖርቱ መሰረት ከየካቲት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት ብቻ አሜሪካ ውስጥ 11.5 ሚሊየን ሴቶች ሥራቸውን ያጡ ሲሆን በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት ሥራቸውን ያጡ ወንዶች ቁጥር ግን 9 ሚሊየን ነው። ይህ ደግሞ መጀመሪያውኑ ከሴቶቹ በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ወንዶች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው መገኘታቸው ነገሮችን አሳሳቢ አድርጓል። በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ በፊት አብዛኛውን ሰዓታቸውን በሥራቸው ምክንያት ውጪ ያሳልፉ የነበሩ አባቶች የቤት ውስጥ ሥራዎችን በአግባቡ መስራት የጀመሩበትና ልጆቻቸውን መንከባከብ እያዘወተሩ ይገኛሉ። ምንም እንኳን አሁንም ቢሆንም ሴቶች ከቤት ውስጥ ሥራ የአንበሳውን ድርሻ ቢወስዱም ከነጭራሹ ምንም ነገር ሰርተው የማያውቁ አባቶች ወደ ኩሽናዎች ሲገቡ መታየታቸው እንደ ትልቅ የለውጥ ጉዞ መቆጠር አለበት የሚሉም አልጠፉም። አንድ ካናዳ ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት ደግሞ 40 በመቶ የሚሆኑ አባቶች ከዚህ በፊት ከሚያደርጉት በተሻለ ምግብ እያበሰሉና ልጆቻቸውን እየተንከባከቡ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን 30 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ልብስ ማጠብና ቤት ማጽዳት መጀመራቸውን ተናግረዋል።
news-42085718
https://www.bbc.com/amharic/news-42085718
ስንቶቻችን የኮሞሮሱን የአውሮፕላን አደጋ እናስታውሳለን?
በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ የምትገኘው የኮሞሮስ ደሴት ተመራጭ የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራ ነች።
ቦይንግ 767 የህንድ ውቅያኖስን ነክቶ ከመከስከሱ በፊት የነበረው ቅጽበት በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ሲዝናኑ የነበሩ ጎብኚዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ህዳር 14/1989 ዓ.ም ግን ያልተጠበቀ ነገር ተመለከቱ። ይህንን አሳዛኝ አጋጣሚም በካሜራቸው ቀርጸው ማቆየት የቻሉም ነበሩ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET961 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ 175 መንገደኞችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ ሳለ ሶስት ኢትዮጵያን ወደ አውሮፕላኑን መቆጣጠሪያ ክፍል(cockpit) በኃይል በመግባት አብራሪዎቹ የበረራ አቅጣጫቸውን ወደ አውስትራሊያ እንዲያደርጉ አስገደዱ። አቅጣጫውን እንዲቀይር የተደረገው አውሮፕላን ለአራት ሰዓታት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ ነዳጅ ጨርሶ በኮሞሮስ ደሴት ላይ ተከሰከሰ። ግዙፉ ቦይንግ 767 በሰዓት 324 ኪሎ ሜትር ፍጥነት በመብረር ላይ እያለ ነበር አካሉ ከውሃው ጋር የተጋጨው። ይህም የአውሮፕላኑ አካል ተሰባብሮ በርካቶች ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆኗል። ዋና አብራሪው ካፒቴን ልዑል አባተ እና ምክትል አብራሪ የነበሩት ካፕቴን ዮናስ መኩሪያ ሊደርስ የነበረውን ከፍተኛ የሰው ህይወት መጥፋት ባደረጉት ጥረት በማዳናቸው ከበርካቶች ሙገሳ ቀርቦላቸዋል። የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 125 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን 50 የሚሆኑት ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳት አስተናግደው በህይወት ተርፈዋል። በህይወት ከተረፉት መካከል አቶ አስመላሽ ስብሃቱ ይገኙበታል። ዛሬ ላይ አቶ አስመላሽ የ83 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ቢሆኑም የዛሬዋን ቀን 21ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው አድርገው ነው የሚያከብሩት። የአቶ አስመላሽ ልጅ ወ/ሮ ኤደን አስመላሽ ''አባታችን ከአደጋው በመትረፉ እንደገና እንደተወለደ አድርገን ነው የምናስበው'' ትላለች። ''በህይወት በመትረፉ ለእኛ ከፍተኛ ደስታ የነበር ቢሆም እሱ ግን የተደበላለቀ ስሜት ነው የተሰማው። ቀኑን ሲያስብ በአደጋው ህይወታቸውን ያጡትን ያስባል። በሌላ በኩል ደግሞ በህይወት መትረፉ ያስደስተዋል'' ስትል ታስረዳለች። ''በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ህጻናት በህይወት ቢኖሩ ይሄኔ ትምህርታቸውን ያጠናቅቁ ነበር'' እያለ ያብሰለስላል ትላለች ኤደን ስለ አባቷ ስትናገር። አቶ አስመላሽ በአውሮፕላኑ ክፍት ቦታ ባለመኖሩ መጓዝ እንደማይችሉ ተነግሯቸው ነበር። ሆኖም የአየር መንገዱ የረዥም ጊዜ ደንበኛ ስለሆኑ ወንበር ተፈልጎ እንደተገኘላቸው ትናገራለች። አቶ አስመላሽ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊትም የረዥም ጊዜ ጓደኛቸውን በአውሮፕላኑ ውስጥ አግኝተው ቦታ በመቀየር ጓደኛቸው ጋር እንደተቀመጡ ትናገራለች። የዕድል ነገር ሆኖ የአቶ አስመላሽ ጓደኛ በህይወት መትረፍ አልቻሉም። በሶስት ኢትዮጵያውያን የተጠለፈው አውሮፕላን ከአዲሰ አበባ የተነሳው ናይሮቢ የሚያደርሰውን ነዳጅ ብቻ ሞልቶ ነበር። ይሁን እንጂ ጠላፊዎቹ ወደ አውስትራሊያ እንዲበር በማስገደዳቸው ነዳጁ እስኪያልቅ በአየር ላይ ለአራት ሰዓታት ቆይቷል። አብራሪውና ረዳት አብራሪው ግን ጠላፊዎቹን "በቂ ነዳጅ የለንም ስለዚህ በአቅራቢያችን ባለ ቦታ አርፈን ነዳጅ መቅዳት አለብን" ቢሏቸውም ጠላፊዎቹ ግን አሻፈረኝ አሉ። ከዚያም የአውሮፕላኖቹ ሁለቱም ሞተሮች አገልግሎት መስጠት አቆሙ። አውሮፕላኑም ከፍታውን በከፍተኛ ፍጥነት በመቀነስ ወደታች መንደርደር ጀመረ። በመጨረሻም በኮሞሮስ ደሴት አካባቢ ህንድ ውቅያኖስ ላይ ከውሃ ጋር ተላተመ፤ የአውሮፕላኑ ክፍሎችም በግፊቱ ብዙ ቦታ ተበታተኑ። በአቅራቢያው የነበሩት የደሴቱ ነዋሪዎችና ጎብኚዎችም በፍጥነት ወደ አደጋው ቦታ በመሄድ የተረፉትንና የሞቱትን ሰዎች አስክሬን ከውሃ ውስጥ ማውጣት ችለዋል። ዋና አብራሪው ካፒቴን ልዑል አባተ የጠላፊዎቹን ከፍተኛ የአካልና የአዕምሮ ጥቃት ተቋቁመው ውሃ ላይ ማሳረፍ በመቻላቸው በብዙ መገናኛ ብዙሃንና ከአደጋው በተረፉ ተጓዦች "ጀግና" በማለት ተወድሰዋል። ዛሬ በናይሮቢ ኬንያ የሚኖሩት አቶ አስመላሽና ቤተሰባቸውም የሁለተኛውን የትውልድ ቀናቸውን 21ኛ ዓመት እያከበሩ ነው። ስለአደጋው ማወቅ ያሉባችሁ ነገሮች ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ጠላፊዎችም ከሞቱት መካከል ናቸው።
news-48524408
https://www.bbc.com/amharic/news-48524408
በአክሱም ዩኒቨርስቲ ግጭት አንድ ተማሪ ሲሞት በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል
በአክሱም ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መካከል የተከሰተን ግጭት ተከትሎ አንድ ተማሪ ሲገደል አስር ተማሪዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደረሰባቸው።
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ኪሮስ ግዑሽ ከግንቦት 19/2011 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው የብሄር መልክ ያለው ውጥረትና ድንጋይ መወራወር መኖሩን ያስታውሳሉ። ውጥረቱ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም በተፈጠረው ግጭት አንድ ተማሪ መሞቱ መነሻ ሳይሆን እንደማይቀር ጥርጣሬያቸውን ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ኃይሎችን በግቢው ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ለማረጋጋት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቢቆይም "አልፎ አልፎ የብሔር መልክ ያላቸው ትንንሽ ትንኮሳዎች ነበሩ" ይላሉ። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአክሱም ከፍተኛ ሆስፒታል ሰራተኛ አንድ ተማሪ እንደሞተ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ባለሙያው ጨምረውም በርካታ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸውንም ተናግረዋል። • በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰ ረብሻ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ ዶ/ር ኪሮስ እንዳሉት ሁኔታው ተረጋግቶ ለተማሪዎች ፈተና መሰጠት መጀመሩን ሰኞ ዕለትም ማጠቃለያ ፈተና መውሰዳቸውን ተናግረዋል። "ነገር ግን ትናንት የኢድ አል ፈጥር በዓል በመሆኑ ትምህርት አልነበረም" የሚሉት ዶክተር ኪሮስ፤ ቀን 4፡30 ገደማ የተወሰኑ ተማሪዎች ድንጋይ መወራወር ጀመሩ ይላሉ። ይህም ሰፋ ወዳለ ግጭት እንደተሻገረና በግጭቱም የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል። ሕይወቱ ያለፈው ተማሪ ዮሐንስ ማስረሻ በዩኒቨርሲቲው የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበር። "ፖሊስ ግጭቱን ለማረጋጋት ብሎ አስለቃሽ ጭስ የተኮሰ ሲሆን እርሱን ለመሸሽ ብለው አብዛኞቹ ተማሪዎች ከግቢው ወጥተው ነበር፤ ሟች ተማሪም ከግቢው ውጪ ወደ ቤተክርስቲያን መሄጃ መንገድ ሞቶ ነው የተገኘው። የተማሪውን አሟሟት ለማጣራት አስክሬኑን ወደ አዲስ አበበባ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተልኳል" ብለዋል። ዶ/ር ኪሮስ እንደሚሉት ሌሎች በግጭቱ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል ተኝተው የሚታከሙ ሦስት ተማሪዎች ያሉ ሲሆን ሌላ ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸው በርካታ ተማሪዎችም የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ተመልሰዋል። ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲውና በተለያዩ ጤና ጣቢያዎች ስለታከሙ ለጊዜው ትክክለኛ የቁጥር መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል። ቁጥሩ በትክክል ሲታወቅም መግለጫ እንደሚሰጡ አክለዋል። አስከ ጠዋት 2፡30 ድረስ በግጭቱ የተጠረጠሩ አራት ተማሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ከፖሊስ እንደሰሙ ነግረውናል፤ ከዚያም በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተማሪዎች እንዳሉም ሰምተዋል። ግጭቱን ለማረጋጋት ዛሬ የአክሱም ከተማ የአገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ከተማሪዎች ጋር ውይይት የተደረጉ ሲሆን ተማሪዎችን የማረጋጋት ሥራ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል። ትናንት ማታ ጀምሮ የመከላከያ ኃይልና የፌደራል ፖሊስም በግቢው ውስጥ መሰማራታቸውንም ነግረውናል። "አሁንም በስጋት ውስጥ ያሉና የተጨነቁ በርካታ ተማሪዎች ስላሉ ተማሪዎቹን ማረጋጋት ይቀረናል" ሲሉ ዶ/ር ኪሮስ ለቢቢሲ ገልፀዋል። • ዩኒቨርሲቲ ብሎ ለመጥራት የሚያስቸግሩ "ዩኒቨርሲቲዎች" በዚህ ድርጊት ውስጥ ተሳትፈዋል የተባሉ ተማሪዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት ላይ መሆኑን የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትናንት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ የገለፀ ሲሆን በተማሪው ሞት ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማውም አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት በመግለጫው ላይ ድርጊቱን አስነዋሪ ሲል የገለጸው ሲሆን፤ ግድያውን አጥብቆ እንደሚኮንነውና ፈጻሚዎቹን ወደ ህግ ለማቅረብ እየተደረገ ላለው ጥረት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያውን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አጥብቆ እንደሚያወግዝ ክልሉ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለተማሪ ዮሐንስ ማስረሻ ሞት ምክንያት የሆኑ ወንጀለኞች በአስቸኳይ ተለይተው ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማድረግ እና ወደፊትም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራው ነው ብሏል።
41365354
https://www.bbc.com/amharic/41365354
"በህገ መንግስቱም ብሔሬ እንዲጠቀስ የሚያስገድድ አንቀፅ የለም። "
ሰሞኑን ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች ግጭት ጋር ተያይዞ መታወቂያ ላይ ብሔር መስፈሩ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል። በተለይም መታወቂያ ላይ ያለ የብሔር ማንነት ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል በሚልም ጉዳዩ መከራከሪያ ሆኗል።
መታወቂያ ላይ" ብሔር" የሚለውን ለማስተካከል ረጅም ጉዞ የተጓዘው ያሬድ ሹመቴ ምንም እንኳን ብሔርን መታወቂያ ላይ መጥቀስ መንግሥት ከዘረጋው ማንነትን መሰረት ካደረገው ፌዴራሊዝም ጋር 26 ዓመታትን ቢያስቆጥርም አሁንም ጥያቄ የሚነሳበት ጉዳይ ሆኗል። ከሚነሱት አከራካሪ ጉዳዮች ውስጥ ከተለያዩ ብሔሮች የተወለዱ ሰዎች አንድ ብሔር ብቻ እንዲመርጡ መገደዳቸው፤ የብሔር ማንነት አይገልፀንም የሚሉ፤ ብሔር የሚለው ቃል አንድን ማሕበረሰብን አይገልፅም የሚሉት ይገኙበታል። ከዚህ በተቃራኒው ብሔር ማንነትን የሚገልፅ በመሆኑ መታወቂያ ላይ እንዲካተት አጥብቀው የሚከራከሩም አሉ። ብሔር መታወቂያ ላይ መካተቱን ከሚቃወሙት አንዱ የፊልም ባለሙያ የሆነው ያሬድ ሹመቴ ይህንን ለማስቀየር ብዙ እርቀት ተጉዟል። "ብሔር ለሚለው ሀሳብ ለኔ ኢትዮጵያ የምትለው ትበቃኛለች።" በማለትም ይናገራል። መጀመሪያ መታወቂያውን ሲያወጣ ብዙ ያላሰላሰለበት ያሬድ እንደ ብዙ ኢትዮጵያዊ በቅፅ በተሞላው መስፈርት መሰረት ነው መታወቂያ ያወጣው። ምንም እንኳን መታወቂያው ከወጣ ብዙ ዓመታት ቢያስቆጥርም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባንክ ቤት ብር ለማውጣት ወይም ለተለያዩ ጉዳዮች መታወቂያውን በሚጠቀምበት ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ይረበሽው እንደነበር ይናገራል ። ከዛም ለማምለጥ የሥራ መታወቂያን፣ መንጃ ፍቃድን እንዲሁም ፓስፖርቱን መጠቀም ጀመረ። በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት ሀገሪቱ ላይ ባለው ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭትና ውጥረቶች ጋር ተያይዞ የበለጠ መታወቂያው ላይ ብሔር ብሎ መስፈሩን ሊቀበለው አልቻለም። "በብሔር ምክንያት የወዳጆች ግንኙነት እየተበላሸ፤ ለብዙዎች በሰላም ከሚኖሩበት ቦታ ለመፈናቀል ምክንያት በመሆኑ አደገኛነቱ እየጎላ መጥቷል። " በማለት የሚናገረው ያሬድ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ብሔርን መተው ለሚፈልጉ መነሳሳትን ሊፈጥር እንደሚችል ያስረዳል። ብሔርና ሃገር በተጨማሪም "ብሔር የሚለውን ቃል ሃገር የሚለውን ሀሳብ የሚገልፅ እንጂ የተለየ መለያ ነው ብዬ አላስብም።" በማለት የሚናገረው ያሬድ ለማጣቀሻም ያህል የቀድሞ ፅሁፎችን ይጠቅሳል። በኢትዮጵያ የህትመት ታሪክ ቀዳሚ ሥፍራን የሚይዙት ተስፋገብረ ሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋን "ቡልጋ'' የሚባል ብሔር የለም። በዚህም ትርጉሙ ቦታን ማሳያ ሆኖ ነው የተጠቀሰው ይላል። "ከዚህም በተጨማሪ ፕሬዚዳንት የሚለውን ቃል በአማርኛ ለመጠቀም 'ርዕሰ-ብሔር' እንለዋለን፤ ስለዚህ ብሔር የሚለው ለአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ወይም በአንድ ወንዝ ብቻ ተከልሎ ለሚኖር በአመለካከት አንድ ለሆነ ቡድን የሚሰጥ አይደለም። " ይላል ያሬድ። ብሔርን መሰረት ያደረጉ ቡድኖች መጠናከር የኢትዮጵያ ብሔርተኝነትን አዳክሟል ብሎ የሚያምነው ያሬድ፤ ኢትዮጵያዊነትን ከማቀንቀን ይልቅ ብሔር ላይ ማተኮር የበለጠ ጎልቷል ብሎ ያምናል። በተቃራኒው ያሉት ደግሞ ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገር የሰሜኑን ባህል መሰረት ያደረገችና የሌሎችን ማህበረሰብ እምነት፣ ስርዓትና ወግን በመዋጥ እንዲሁም በመጨቆን የተመሰረተ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ የሚባለውን ማንነት ጥያቄ ውስጥ ይከቱታል። ከፍተኛ የሆነ የብሔር ጭቆና ነበር የሚሉት እንዳሉ ሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ የመደብ ጭቆና እንጂ የብሔር ጭቆና አልነበረም የሚሉም አሉ። ሆኖም ግን ያሬድ እንደሚለው "ብሔራቸውን መጥቀስ ለሚፈልጉ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ ተብሎ እንዲፃፍላቸው የሚፈልጉት ምርጫቸው ይተበቅ፤ ማንም ኢትዮጵያዊ ላይ ብሔር እንዳይፃፍ የሚል ጥያቄ የለኝም። ለኔ ግን የማይገልፀኝን ነገር፣ በህገ-መንግሥቱ የማልገደድበትን ማንነት ሊፃፍብኝ አይገባም። የኔም ጥያቄ ይመለስ መብቴ አይከልከል ነው እያልኩ ያለሁት። " ይላል ያሬድ። ብሔር የሚለውን ኢትዮጵያዊ እንዲባልለት ጉዳዩን ወደ ቀበሌ የወሰደውም ከስምንት ወራት በፊት ነው። መታወቂያው ላይ ብሔር በሚለው ቦታ ላይ 'ኢትዮጵያዊ' ተብሎ እንዲፃፍለት ጥያቄ ሲያቀርብ፤ የተሰጠው መልስ ግን ''ቅፁ ላይ ካለው ወይ ከአባትህ ወይ ከእናትህ ከአንዳቸው ብሔር መርጠህ መታወቂያ ይሰጥሀል እንጂ አንተ ላልከው መመሪያው አይፈቅድም። " የሚል ነው። የፊልም ባለሙያው ያሬድ ሹመቴ ያቀረበው ጥያቄ በቀበሌው ተቀባይነት ባለማግኘቱ ወደ ወረዳው ሥራ አስፈፃሚ ተመርቷል። በማህበራዊ ድረ-ገፁ ላይ እንደፃፈው ብዙዎች ጉዳዩን እንዳልተረዱት ያስረዳ ሲሆን "ብሔርህ በእናትህ ተፅፎ ነው?" እና "ብሔር ሳይር እንዴት ዜጋ መሆን ይቻላል። ብሔር የግድ ነው።" የሚሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡለት ሲሆን፤ መልሳቸው ግን ተመሳሳይ ነበር "መመሪያው አይፈቅድም!" የሚል ነው። መመሪያውን የሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነቶችና የነዋሪዎች አገልግሎት ፅህፈት ቤት የተባለው ተቋም ነው። በነዋሪዎች መታወቂያ አሰጣጥ መሟላት ካለባቸው ጉዳዮች ውስጥ ከብሔር በተጨማሪ ሀይማኖት ቢጠቀስም እንደ አስገዳጅ ሁኔታ አልተካተተም። ጉዳዩም ወደ ክፍለ-ከተማ ተመርቶ ብዙዎቹ በመገረምና በመሳቅ እንደተቀበሉት ያሬድ ይናገራል። ጥያቄያቸውም ተመሳሳይ ነው ለምን ብሔርህ እንዳይጠቀስ ፈለግክ? የእርሱ መልስም "በብሔር ስለማላምን ነው። ቤተሰቦቼም አንተ የዚህ ብሔር አባል ነህ ብለው ስላላሳደጉኝ፤ ስለብሔር ምንም አላውቅም። የማውቀው ኢትዮጵያዊ መሆኔን ብቻ ነው። በህገ-መንግሥቱም ብሔሬ እንዲጠቀስ የሚያስገድድ አንቀፅ የለም። " የሚል መልስም ይሰጣል። በመጨረሻም መመሪያው መሻር የሚቻለው በፍርድ ቤት ብቻ ስለሆነ፤ ፍርድ ቤት ሄዶ ብሔር የሚለው መታወቂያዬ ላይ አይስፈር በሚል እንዲያመለክት ነገሩት። ጉዳዩ በዚህ አላለቀም የክፍለ-ከተማው ፍርድ ቤት ወደ ሌላ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መራው። በምላሹም ጥያቄውን እንደተረዱት ይህ "የመብት ጥያቄ ነው። ህገ-መንግሥታዊ መብት ነው የምትጠይቀው። ነገር ግን ይህ ጥያቄ በእኛ ደረጃ የሚታይ አይደለም። አንተ መፍትሔ የምታገኘው ፌደራል ፍርድ ቤት በመሔድ ነው። " የሚል ነበር። ፌደራል ፍርድ ቤት ባመራበትም ወቅት ያገኘው ምላሽ "ጥያቄህ መመሪያው እራሱ ህገ-መንግሥቱን ይፃረራል የሚል ስለሆነ መመሪያውን ያወጣው አካል ህገ-መንግሥቱን አላከበረም በሚል ለህገ-መንግሥት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማለትም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው ክስህን በማመልከቻ ማቅረብ ያለብህ። " የሚል ነበር። ጉዳዩ አሁንም እልባት አላገኘም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ አቋርጦት የነበረ ሲሆን ክሱን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው።
news-56121970
https://www.bbc.com/amharic/news-56121970
የኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አገራት በድንበሩ ጉዳይ ሱዳንን እንዲመክሩ ጥሪ አቀረበች
የኢትዮጵያ መንግሥት ሱዳን በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የድንበር አለመግባባት በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ የአፍሪካ አገራት ሱዳንን በመምከር አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ሐሙስ ባወጣው በዚህ መግለጫ ላይ በድንበር ጉዳይ ሰበብ ሁለቱ አገራት ወደ ጦርነት እንዲገቡ የሱዳን የመከላከያ ኃይል ከፍተኛ ግፊት እያደረገ ነው ሲል ወንጅሏል። በተጨማሪም የሱዳን ሕዝብ መንግሥቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ሊያበላሽ በሚችል መልኩ ሦስተኛ ወገን ፍላጎት መጠቀሚያ እየሆነ እንዳለ እንዲያጣራም ጥሪ አቅርቧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሁለቱ አገራት መካከል ካለው የድንበር አለመግባባት አንጻር ሱዳን እየተከተለችው ያለውን ችግሩን አባባሽ ጸብ አጫሪ እርምጃን በጽኑ አውግዞታል። ኢትዮጵያ የትኛውም ግጭት የሁለቱን አገራት ደኅንነት የሚጎዳና ከባድ ጉዳትን የሚያስከትል መሆኑን እንደምትገነዘብ የጠቆመው መግለጫ፤ በሱዳን መንግሥት ወታደራዊ ክንፍ እየተበረታታ ያለው ግጭት "በሱዳን ሕዝብ ኪሳራ የሦስተኛ ወገንን ፍላጎት የሚያስፈጽም ነው" ብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው በዚህ ጠንካራ መግለጫው ላይ የድንበር ጥያቄው ሊስተናገድባቸው የሚችሉ በቂ መንገዶች ቢኖሩም "የሱዳን ሠራዊት ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመጣስ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ፈጽሟል" ብሏል። መግለጫው ጨምሮም በሁለቱ አገራት መካከል ካለው የትብብርና የወዳጅነት መንፈስ በተቃራኒ "የሱዳን ሠራዊት ንብረቶችን ዘርፏል፣ ካምፖችን አቃጥሏል፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በማጥቃት እንዲፈናቀሉ ያደረገ ሲሆን ባዷቸውን የነበሩ የኢትዮጵያ ሠራዊት ካምፖችን ተቆጣጥሯል" ሲል ከሷል። ባለፈው ሳምንት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሠራዊት በአንዳንድ የድንበር አካባቢዎች ላይ ጥቃት ፈጽሞ ወረራ አካሂዷል ሲል መክሱ ይታወሳል። ለዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጠው ምላሽ ሱዳን በመሬት ላይ እየተከሰተ ያለውን ሐቅ በመካድ የተሳሳተ መረጃ እያሰራጨች ነው በማለት፤ እራሷን ከፈጸመችው ወረራ በተቃራኒው ወረራ እንደተፈጸመባት እየገለጸች ነው ብሏል። "ይህም የጸብ አጫሪነት ድርጊቷንና ተጨማሪ ግዛቶችን ለመያዝ የምታደርገውን ሙከራ ለመሸፋፈን" እንደሆነ መግለጫው አመልክቷል። ኢትዮጵያ ባሉ አማራጮች ሁሉ ለችግሩ ሠላማዊ መፍትሔ እንዲገኝለት እንደመትፈልግ የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ "በሱዳን ሠራዊት በኩል ወዳጅ የሆነውን የኢትዮጵያንና የሱዳንን ሕዝብ ወዳልተፈለገ ጦርነት ለመግፋት የሚደረገው ሙከራ የአገራቱንና የአካባቢውን ሠላም፣ መረጋጋትና ልማት ያስተጓጉለዋል" ብሏል። ሱዳን ባለፈው ጥቅምት ወር ማብቂያ ለረጅም ጊዜ ይገባኛል ስትላቸው የነበሩትን በርካታ የድንበር አካባቢዎችን ሠራዊቷን በማሰማራት የተቆጣጠረች ሲሆን፤ ባለስልጣናቷም በቁጥጥራቸው ስር ያስገቡት ሕጋዊ ግዛታቸው መሆኑን በመግለጽ ይዞታቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። የሱዳንን እርምጃ ተከትሎ ኢትዮጵያ የድንበር አካባቢው ይዞታ ወደነበረበት እንዲመለስና ሁለቱ አገራት ችግሩን ቀደም ሲል ጀምረውት በነበረው የድንበር ኮሚሽን በኩል በውይይት እንዲፈቱት በተደጋጋሚ መጠየቋ ይታወሳል። ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ሁለት አገሮችን እያወዛገበ የሚገኘው ድንበር፤ አልፋሽቃ፣ ከፍ ያለ የእርሻ ልማትና ተያያዥ ኢንቨስትመንቶች ይካሄዱበታል። ባለፈው ሳምንት እሁድ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሠራዊት ድንበር አቋርጦ ወረራ ፈጽሞብኛል ማለቱን የአገሪቱ ዜና ወኪል ዘግቧል። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት በድንበሩ አካባቢ ያለው የሁለቱም ወገን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየጨመረ በመሄዱ አገራቱ ውዝግቡን ከዚህ በፊት በጀመሩት የውይይት መንገድ መፍታት ካልቻሉ ውጥረቱ ወደ ወታደራዊ ግጭት እንዳያመራ ተሰግቷል። በዚህ ሳምንትም ሱዳን በአዲስ አበባ የሚገኙትን ዲፕሎማቷን "ለምክክር" በሚል መጥራቷን የተለያዩ የዜና ምንጮች የዘገቡ ሲሆን ጥሪው ከድንበሩ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መሆኑ ግን አልተረጋገጠም። የሱዳን መንግሥት የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሳባቸውን የአል ፋሽቃ አካባቢን የተቆጣጠረው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በትግራይ ወደ ተቀሰቀሰው ግጭት መሰማራቱን ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው በዚህ መግለጫ የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ በውይይት ይፈታ ዘንድ ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጿል። ሁለቱም አገራት ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው በተደጋጋሚ የገለጹ ቢሆንም ኢትዮጵያ የድንበሩን ጉዳይ በንግግር ለመፍታት የሱዳን ጦር ቀድሞ ወደ ነበረበት ስፍራ መመለስ አለበት ስትል፣ ሱዳን ደግሞ ሠራዊቷ ከያዛቸው ቦታዎች እንደማይወጣ በተደጋጋሚ ገልጻለች። የኢትዮጰያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ወዳጅ የሆኑትን የኢትዮጵያ እና የሱዳን ሕዝቦች ወደ አላስፈላጊ ጦርነት ለማስገባት በሱዳን ጦር እየተደረገ ያለው ሙከራ የሁለቱን አገራት እንዲሁም በአጠቃላይ የቀጠናውን ሰላም፣ መረጋጋት እና እድገት የሚሸረሽር ከባድ ስህተት ነው ሲልም አስቀምጧል። የአፍሪካ አገራት የሱዳን መንግሥት የድንበሩን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ ጥረት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል። ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ጥልቅ ግንዛቤ ላለው እንዲሁም ከፍተኛ ትዕግስት ላሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢፌዴሪ መንግሥት ምስጋና አቅርቧል። ኢትዮጵያና ሱዳን የሚጋሩት ድንበር ርዝመት 750 ኪሎ ሜትር ያካልላል። ነገር ግን ይህ ድንበር አብዛኛው ርቀት ግልጽ በሆነ መንገድ መሬት ላይ አልተመላከተም። ይህን ለማሳካት ተደጋጋሚ ንግግሮች ተጀምረው በተደጋጋሚ ተቋርጠዋል። የአልፋሽቃ ማዕዘን ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በይገባኛል የምትወዛገብብት አካባቢ ረዥም የግዛት ድንበር ነው ያላት። ሁለቱም አገሮች ለም ነው የሚባለውን ፋሽቃ አካባቢን እጅጉኑ ይፈልጉታል። ይህ በሁለቱ አገሮች ዓይን ውስጥ ያለው አካባቢ የአልፋሽቃ ማዕዘን ወይም የአልፋሽቃ ጥግ ተብሎ ይጠራል። በዚህ ድንበር ሁለቱም አቅጣጫ የሚገኙ ገበሬዎች ባሻገራቸው ያሉ ለም መሬቶች ላይ ያማትራሉ። አልፋሽቃ ማዕዘን በደቡብ ምሥራቅ ሱዳን ምሥራቃዊ ገዳሪፍ የሚገኝ ለም መሬት ነው። አልፋሽቃ መሬት 250 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍንና 600 ሺህ ኤክር ለም መሬትን የሚሸፍን ነው። ለለምነቱ ምክንያት የሆኑት እንደ አትባራ፣ ሰቲት እና ባስላም ወንዞችም በቅርብ ይገኛሉ። የሱዳን ባለሥልጣናት አልፋሽቃ የሱዳን ግዛት ነው ይላሉ። አሁን በኢትዮጵያን እጅ ለምን ሆነ ሲባሉ፣ "የሱዳን መንግሥት ከአገሪቱ ጋር ባለው የትብብርና የመግባባት ስምምነት መንፈስ ነው የኢትዮጵያ ገበሬዎች ቦታውን አሁን እያለሙት ያሉት" ይላሉ። ሁለቱ መንግሥታት ከዚህ ቀደም ይህንን አወዛጋቢ ድንበር በድጋሚ ለማስመር፣ የጋራ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እና የአካባቢው ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር። ቀደም ካለው አስተዳደር ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሬው ሕዝብ ሉአላዊ መሬቱን ቆርሶ እየሰጠ ነው በሚል ተደጋጋሚ ወቀሳ ሲቀርብበት ነው የቆየው። እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2014 የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የወቅቱ ሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸውን ድንበሩ መሬት ላይ የሚመላከትበትን የመጨረሻ ቀን እንዲያሳውቁ መመርያ አስተላልፈውላቸው ነበር። ሆኖም አወዛጋቢውን ድንበር መሬት ላይ የማመላከቱ ሥራ እስከዛሬም አልተሳካም፡፡
news-53499194
https://www.bbc.com/amharic/news-53499194
አሜሪካ በቴክሳስ ሂዩስተን የሚገኘውን የቻይና ቆንስላ እንዲዘጋ አዘዘች
አሜሪካ በቴክሳስ ግዛት ሂውስተን ከተማ የሚገኘው የቻይና ቆንስላ እስከ ዓብር ድረስ እንዲዘጋ አዘዘች።
ቤጂንግ የአሜሪካ ውሳኔ “ፖለቲካዊ ፍላጎት የታየበት” ነው ብላለች። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ከዚህ ውሳኔ የተደረሰው “የአሜሪካን አዕምሯዊ ንብረት ለመጠበቅ ሲባል ነው” ብሏል። የቻይና የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን በበኩላቸው አሜሪካ ቆንስላው እንዲዘጋ መወሰኗ “እጅጉን የሚያስቆጣ ነው፤ ለውሳኔው ትክክለኛነት መከራከሪያ ማቅረብ እንኳ አያስችልም” ብለዋል። አሜሪካ ቆንስላው እንዲዘጋ ስለመወሰኗ የተነገረው፤ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በቆንስላው ቅጥር ግቢ ውስጥ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ ወረቀት ሲያቃጥሉ መታየታቸውን ተከትሎ ነው። በአሜሪካ እና ቻይና መካከል ያለው ውጥረት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እያየለ መጥቷል። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቤጂንግ መንግሥት ጋር በንግድ፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና በሆንግ ኮንግ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ሲነታረክ ይስተዋላል። ትናንት ድግሞ ቻይና የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር የሚያካሂዱ ቤተ ሙከራዎች ላይ ስለላ እያደረገች ነው ሲል የአሜሪካ የፍትህ ተቋም ከሷል። በኮሮናቫይረስ ላይ የሚደረግ ምርምርን ሰልለዋል የተባሉ ሁለት ቻይናውያን ላይም ክስ መስርቷል። በክሱ ላይ በስም የተጠቀሱት ሁለት ግለሰቦች በአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ስላላ ሲያካሂዱ፤ የቻይና መንግሥት የደህንነት ተቋም ድርጋፍ አድርጎላቸዋል ተብሏል። ቻይና በበኩሏ አሜሪካ ከመሰል ተግባሯ እንድትቆጠብ የጠየቀች ሲሆን፤ “ይህ ሳይሆን ቀርቶ አሜሪካ በዚህ መንገድ መቀጠልን የምትሻ ከሆነ፤ ቻይና ጠንካራ ምላሽ ትሰጣለች” ብላለች።
50245029
https://www.bbc.com/amharic/50245029
ትዊተር የትኛውንም የፖለቲካ ይዘት ያለው ማስታወቂያ ሊያግድ ነው
ትዊተር በመላው ዓለም የፖለቲካ ይዘት ያላችው ማስታወቂያዎችን ሊያግድ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ማስታወቂያዎቹ ከሚፈለገው ቦታ መድረስ እና ተደራሽ መሆን ያለባቸው በራሳቸው እንጂ በገንዘብ ተገፍተው መሆን እንደሌለበት አስታውቋ ኩባንያው።
"ለንግድ ተቋማት በበይነ መረብ ማስተዋወቅ አቻ የሌለው የማስታወቂያ ስልት ቢሆንም ፖለቲካ ላይ ሲመጣ ግን የራሱ አደጋዎች አሉት" ሲሉ የተናገሩት የድርጅቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ጃክ ዶርሴይ ናቸው። በቅርቡ ተቀናቃኛቸው ፌስ ቡክ የፖለቲካ ይዘት ያላቸው ማስታወቂያዎችን እንደማያግድ ገልጾ ነበር ። • አረቄ ከእንቁላል ደባልቆ በመጠጣት እውቅና ያተረፈው ቻይናዊ • ስለባለፈው ሳምንት ግጭቶችና ጥቃቶች አስካሁን የምናውቃቸው ነገሮች • ኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ሁከት 359 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ይህ ዜና በ2020 ምርጫ በሚወዳደሩ በአሜሪካውያን ፖለቲከኞች ዘንድ ጎራ ፈጥሯል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዳግም ምርጫ ዘመቻ አስተዳደር የሆኑት ብራድ ፓርስኬል ፣ እገዳው " ትራምፕንና ወግ አጥባቂዎችን ዝም ለማሰኘት በግራ ዘመሞች የተወሰደ ርምጃ" ሲሉ ገልፀውታል። ነገር ግን የጆ ባይደን የምርጫ ዘመቻ ቃል አቀባይ የሆኑት ቢል ሩሶ " በገንዘብና ለዲሞክራሲያችን ባለን ታማኝነት መካከል ምርጫ ሲደቀን ቢያንስ ለአንድ ጊዜ እንኳ ገንዘብ ማሸነፍ እንደማይችል ማወቅ አበረታች ነው" ብለዋል። እርምጃውን በተመለከተ የፌስ ቡክ መስራች የሆኑት ማርክ ዙከርበርግ የኩባንያውን ፖሊሲ ደግፎ ተናግሯል። " በዲሞክራሲ ውስጥ የግል ኩባንያዎች ፖለቲከኞችን ወይንም ዜናን ቅድመ ምርመራ ሊያደርጉ ይገባል ብዬ አላምንም" ሲል ከጋዜጠኞች ጋር በስልክ በነበረው ውይይት ላይ ገልጿል። የቲውተር እገዳ ከ22 ቀን በኋላ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ዝርዝሩ ህዳር ወር አጋማሽ ላይ ይወጣል ተብሏል። በበይነ መረብ የሚቀርቡ የፖለቲካ ማስታወቂያዎች "ሲቪክ ማሕበረሰቡ ለሚያደርገው ውይይት ፈተና" መሆኑን የትዊተር የበላይ ኃላፊ በትዊተራቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። ተጋርጠዋል ካሏቸው አደጋዎች መካከልም "መልዕክቶችን በማሽን በታገዘ ሁኔታ ለተወሰነ ሰዓት አቆይቶ መልቀቅ፣ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በትንንሹ ከፋፍሎ ሳይቀር ተደራሽ ማድረግ፣ በአግባቡ ያልተፈተሸ አሳሳች መረጃ፣ ሐሰተኛ ዜናዎች" ናቸው። " ታማኝ አይለም" ያሉ ሲሆን " ለኛ ሰዎች የተሳሳተ መረጃ እያስተላለፉ በስርዓታችን ላይ ሲጫወቱ፣ ሰዎች ማስታወቂያዎቻቸውን እንዲያዩላቸው ሲከፍሉን፣ የሚፈልጉትን ማለት ሲችሉ ጠንክረን እየሰራን ነው ማለት ከባድ ነው" ብለዋል። ይህ አዲስ ፖሊሲ በስልጣን ላይ ያሉ የምርጫ ተወዳዳሪዎችን እደግፋል የሚል ትችት የቀረበበት ሲሆን ለዚህም መልስ ሲሰጡ "በርካታ ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች ያለ ፖለቲካ ማስታወቂያዎች በሺዎች ለሚቆጠሩ ግለሰቦች ይደርሳሉ" ብለዋል። የመራጮች ምዝገባ ማስታወቂያዎች በዚህ እገዳ የተነሳ አይጎዱም ሲሉ አስታውቀዋል።
news-49027545
https://www.bbc.com/amharic/news-49027545
ዮአኪን ''ኤል ቻፖ'' ጉዝማን የዕድሜ ልክ እስራት ተበየነበት
የአሜሪካ ፍርድ ቤት ዕጽ አዘዋዋሪው ዮአኪን ''ኤል ቻፖ'' ጉዝማን ላይ የዕድሜ ልክ እስራት በየነ።
ዮአኪን ''ኤል ቻፖ'' ጉዝማን ከወራት በፊት በኒው ዮርክ የተሰየመው ፍርድ ቤት ኤል ቻፖ በዕጽ እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ጨምሮ በ10 ወንጀሎች ጥፋተኛ ሲል ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። ከዕድሜ ልክ እስሩ በተጨማሪ ኤል ቻፖ በሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ወንጀል በሚል ተጨማሪ የ30 ዓመት እስር የተላለፈበት ሲሆን፤ 12.6 ቢሊየን ዶላር መቀጮ እንዲከፍልም ተፈርዶበታል። አቃቤ ሕጎች ኤል ቻፖ የእስር ዘመኑን የሚያሳልፈው ከአርማታ ብረት ከሚወፍር ብረት በታጠረ እስር ቤት ውስጥ ነው በማለት ከአሜሪካ እስር ቤት ማምለጥ እንደማይችል ጠቁመዋል። ኤል ቻፖ ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሁለት የሜክሲኮ እስር ቤቶች ማምለጡ የሚታወስ ነው። • በችሎት አደባባይ የወጣው የኤል ቻፖ ገመና • ኢትዮጵያዊቷ የዕፅ ነጋዴው ኤል ቻፖን ጉዳይ ለመዳኘት ተመረጠች በድጋሚ ታህሣሥ 2008 በቁጥጥር ሥር የዋለው ኤል ቻፖ 2009 ላይ ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጥቷል። ኤል ቻፖ ይመራው የነበረው ሲናሎዋ የተባለው የእጽ አዘዋዋሪ ቡድን ወደ አሜሪካ ለሚገቡ ዕፆች ተጠያቂ ይደረጋል። ትናንት የፍርድ ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት ዮአኪን ኤል ቻፖ ጉዝማን የእስር ክፍል በፍጹም ምቹ አለመሆኑን እና ''ስቃይ'' እንደሆነበት ለፍርድ ቤቱ በአስተርጓሚ ተናግሯል። ''ኤል ቻፖ'' በሳምንት ለሁለት ሰዓታት ከእስር ክፍሉ ውጪ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ ከሳምንታት በፊት በኒው ዮርክ ፍርድ ቤት ዳኛ ውድቅ ተደርጎ ነበር። ዳኛው ኤል ቻፖ ይህን ምክንያት ያመጣው ከእስር ለማምለጥ አስቦ ነው ሲሉ ተከራክረዋል። • ኤል ቻፖ ከእስር ክፍሉ መውጣት አይችልም ትናንት ኤል ቻፖ ላይ የተላለፈውን የፍርድ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ እንደሚጠይቁ ጠበቆቹ ተናግረዋል። ጠበቃ ጄፈሪ ሊችትማን ዳኞቹ በመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ምክንያት ጫና ስር ወድቀው ነው ይህን አግባብ ያልሆነ ፍርድ የሰጡት ብለዋል። በጉዝማን (ቀኝ) እና የቀድሞ አጋሩ እድሜያቸው እስከ 13 ዓመት ድረስ የሚገመቱ ሴት ህጻናት ልጆችን በዕጽ ራሳቸውን እንዲስቱ ካደረገ በኋላ ደፈሯል የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን፤ አንድ የዓይን እማኝ ደግሞ ጉዝማን ሶስት ሰዎችን ተኩሶ ሲገድል አይቸዋለሁ ሲል መስክሯል። ተቀናቃኝ የዕጽ አዘዋዋሪ ቡድንን የተቀላቀሉ ሁለት የቀድሞ ባልደረቦቹን ከደበደበ በኋላ በጥይት መትቶ በመግደል አስክሬናቸው በእሳት እንዲቃጠል አድርጓል ሲል የቀድሞ የግል ጠባቂው ኤል ቻፖ ላይ መስክሯል። ዮአኪን ኤል ቻፖ ጉዝማን ትናንት ወደ ፍርድ ቤቱ ክፍል ሲገባ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ምን ሊሆን እንደሚችል ያወቀው ይመስላል ስትል የፍርድ ሂደቱን የተከታተለችው የቢቢሲዋ ጋዜጠኛ ናዳ ታዋፊክ ትናገራለች። ኤል ቻፖ የፍርድ ሂደቱን ከመከታተል ይልቅ ትኩረቱ የነበረው ባለቤቱ ላይ እና የቤተሰብ አባላቱ ላይ ነበር። ከተቀመጠበት ሆኖ ጣቶቹን እየሳመ ወደ ሚስቱ እና ቤተሰቡ የሰላምታ መልዕክት ያሳይ ነበር። የኤል ቻፖ ባለቤት ኤማ ኮርኔል የፍርድ ሂደቱን ተከታትላለች ኤል ቻፖ ጉዝማን ማነው? "ኤል ቻፖ'' ማለት ''አጭሩ'' እንደማለት ሲሆን በሰሜናዊ ሜክሲኮ ሲናሎአ የተሰኘ የዕፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ነበረ። ኤል ቻፖ የሚመራው ቡድን ወደ አሜሪካ ለሚላከው ዕፅ ትልቁን ድርሻ ይዞ ነበር። እአአ 2009 ፎርብስ ኤል ቻፖ ጉዝማን የተጣራ 1ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገበ ከበርቴ ነው በማለት የዓለማችን 701ኛው በማለት የሃብታሞች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል። የፍርድ ሂደቱ ተደብቆ የቆየውን የኤል ቻፖ ጉዝማን ህይወትን አደባባይ ያወጣ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። በፍርድ ሂደቱ ላይ የቀድሞ የቅርብ አጋሩ የነበሩ ሁሉ መስክረውበታል። ጉዝማን ለቀድሞው የሜክሲኮ ርዕሰ ብሔር ኤንሪክ ፔና ኒቶ በ2012 ስልጠን ከያዙ በኋላ እርሱ ላይ የሚደረገው ክትትል እንዲቆም በመጠየቅ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ጉቦ መክፈሉም የተሰማው ችሎት ላይ ነበር። ርዕሰ ብሔሩ ግን ይህ ውንጀላ እውነትነት የለውም ሲሉ አስተባብለዋል። ገድሎ ያቃጠላቸው የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴ ተፎካካሪዎች እንዳሉ ከዘመዶቹ መካከልም የገደላቸው እንዳሉ ተገምቷል። ችሎቱ ኤል ቻፖ በ2015 በሜክሲኮ እጅግ ጥብቅ ከሆነው እስር ቤት እንዴት እንዳመለጠም በዝርዝር አድምጧል። ልጁ በእስር ቤቱ አቅራቢያ የሚገኝ ቤት እንደገዛ እና ጂፒኤስ ያለው ሰዓት ወደ እስር ቤቱ በድብቅ ማስገባቱ ተመስክሯል። በሚስቱ እና በቅምጦቹ ላይ ለመሰለል በስልኩ ላይ ሶፍትዌር ይጠቀም እንደነበርም ተመስክሮ፤ ኤፍ ቢ አይ የተለዋወጣቸውን የፅሑፍ እንዲያቀርብ ተደርጓል። በአንድ የፅሁፍ መልዕክቱ ላይም ከነበረበት ቤት አሜሪካዊያንና ሜክሲኳዊያን ከከፈቱበት ድንገተኛ ዘመቻ እንዴት እንዳመለጠ የሚገልጽና ልብስ እና ጫማ እንዲመጣለት የጠየቀበት መልዕክቱም ተነቧል። ጉዝማን በአሜሪካ የፍትህ አደባባይ ለፍርድ ከቀረቡ የሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴዎች መካከል ትልቁ ነው።
43041312
https://www.bbc.com/amharic/43041312
በኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት ትምህርት የማቋረጥ አደጋ ላይ ናቸው ተባለ
በኢትዯጵያ ከረሃብና ግጭት ጋር በተያያዘ በአሁኑ ዓመት ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የማቋረጥ አደጋ ላይ እንደሆኑ ዓለም አቀፉ የሕፃናት ድርጅት አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ሕፃናት ድርጅት የሃገሪቱ ዳይሬክተር ኤኪን ኦጉቶጉላሪ እስካሁን ባለው ሁኔታም ወደ አራት መቶ ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንደተፈናቀሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የትምህርት ሚኒስቴር መረጃን ጠቁመው እንደተናገሩትም ከየካቲት 2009 ጀምሮ 623 ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን ይህም በየወሩ የሚዘጉ ትምህርት ቤቶችን ቁጥር 51 ያደርሰዋል። ይህ ድርቅም ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ እንዲሁም ኬንያ 90 ሺ ያህል ልጆች በየሳምንቱ ከትምህርት ገበታቸውም የመፈናቀል አደጋ ላይ እንደሆኑ ዓለም አቀፉ የሕፃናት ድርጅት ሰሞኑን ያወጣው ሪፖርት ያሳያል። ይህ ቁጥርም በዓመቱ 4.7 ሚሊዮን ያህል ሊሆን እንደሚችል ሪፖርቱ ያስረዳል። ልጆቹ ከትምህርት ቤት ውጭ ሲሆኑ ለተጓዳኝ ችግሮች እነዚህም ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ ሕገ-ወጥ የሕፃናት ዝውውር እንዲሁም ለሌሎች ጉዳዮች ተጋላጭ እንደሆኑ ሪፖርቱ የገለጸ ሲሆን በአስደንጋጭም ሁኔታ እስከ ስምንት ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሕፃናት ጀምሮ በአካባቢው ባሉ ወታደሮች እየተመለመሉም እንደሆነም ሪፖርቱ ጨምሮ ያስረዳል። ሕፃናት በድርቁም ሆነ በረሃቡ በክፍተኛ ሁኔታ እንደተጎዱ የሚናገሩት ኤኪን "ምንም ሆነ ምንም ትምህርት ቤቶቹ የማይዘጉበት ሁኔታ መፈጠር አለበት፤ ይህም ልጆቹንም በአንድ ቦታ ላይ በማድረግ መርዳት የሚፈልጉ ድርጅቶች እንዲረዱ እንዲሁም ከሚደርስባቸው ጥቃቶችም ለመከላከል ያስችላል" ይላሉ። የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፉ ሕፃናት አድን ድርጅት ተወካይ ዴቪድ ራይት ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል። "በየቀኑ 12ሺ የሚሆኑ ተማሪዎች በየዓመቱ የትምህርት ገበታቸው ላይ የማይገኙ ከሆነ በዚህ ቀጠና የሚገኙ ቀጣዩ ትውልድ ዕጣ ፈንታ ከፍተኛ አደጋ ላይ ይወድቃል። ማንኛውም ልጅ ቢሆን ከትምህርት ገበታው መፈናቀል የለበትም፤ የመማር መብታቸውም ሊጠበቅላቸው ይገባል። በድርቅም ሆነ በረሃብ ጊዜ ትምህርት ቤቶቹን ክፍት ማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው ምክንያቱም ትምህርት ቤቶቹ ምግብ፣ ውሃም ይሁን ክትባትም ማቅረብ አለባቸውም" ብለዋል። የዓለም አቀፉ ሕፃናት አድን ድርጅትም በዚህ ዓመት የያዘውም ዕቅድ ትምህርት ቤታቸውን ሳይለቁ እንደተጠበቁ ቤተሰቦቻቸው እንደገና መልሰው የሚያገግሙበትና ለወደፊቱም የሚያቅዱበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሆነም ሪፖርቱ ያትታል። የውሃ እንዲሁም የክትባት አቅርቦት ወይም ዘመቻዎች አደገኛ የሆኑ ወረርሽኞችን እንደ ኮሌራ ያሉትን ለመከላከል ያስችላል ያለው ሪፖርቱ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ልጆችም ባሉባቸው መጠለያዎች ዛፍም ስር ቢሆን የተለያዩ ትምህርቶችን ሊወስዱ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት ይገኙበታል። በአጠቃላይ በክልሉ 21 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በምግብ እጥረት እየተሰቃዩም እንደሆነ ሪፖርቱ ጨምሮ ያስረዳል። የኢትዮጵያ ቆላማውን ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃው ይህ ረሃብ በታሪክም ክፉ የሚባል ረሃብ እንደሆነ ኤኪን ይገልጻሉ። "በጣም አደገኛና ከ1970ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያ አስተናግዳው የማታውቀው ክፉ ረሃብም ነው" ይላሉ። ይህ ረሃብም የቀጠለ ሲሆን በዚህ ዓመትም ያለው ሁኔታ ጥሩ እንዳልሆነ ይናገራሉ። በተከታታይም የዝናብ እጥረት በማጋጠሙ ረሃቡ ሊቀጥል እንደቻለም አሁንም የአየር ሁኔታ ትንበያዎች እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል ኤኪን ለቢቢሲ ፍራቻቸውን ገልጸዋል። "ይሄ ማለት የድርቁም ሆነ የረሃቡ ሁኔታ በቆላማው የኢትዮጵያ ክፍል እንደሚቀጥል ነው"ይላሉ። በምላሹም ድርጅቱ ልጆችን የመመገብ ፕሮግራም እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁሶችን የለገሱ ሲሆን በዚህም 11ሺህ የሚሆኑ ሕፃናትም ተጠቃሚ እንደሆኑ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ልጆቹንም በየዓመቱ ትምህርት ቤት ለመመለስ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ገልጸው በአጠቃላይ ግን ለኢትዮጵያ ድርቅና ረሃብ ከለጋሾች የሚሰጠው ምላሽ እያሽቆለቆለ መሆኑንም ይገልጻሉ። የድርጅቱን ምሳሌም በማንሳት ከሁለት ዓመታት በፊት መቶ ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ግን በተሰጠው ምላሽ አምስት ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደሆነ ይገልጻሉ። "ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ ናት። ረሃቡን ለመቋቋም እየታገለች ነው፤ በዚህም ወቅት ኢትዮጵያ መደገፍ አለባት" ይላሉ።
news-52689428
https://www.bbc.com/amharic/news-52689428
በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተነስቶ የነበረው እሣት በቁጥጥር ስር ዋለ
ትላንት [አርብ] በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተነስቶ የነበረው እሣት በቁጥጥር ስር ዋለ።
እሳቱ ትላንት ሳንቃ በር በሚባለው የፓርኩ አካባቢ መከሰቱን የገለጹት የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ "አሁን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረነዋል" ሲሉ ለቢቢሲ በስልክ ተናግረዋል። እሳቱ የተነሳበትን ምክንያት ተጠይቀው አንድ የምርመራ ቡድን ወደ አካባቢው መላኩን እና ውጤቱ እንደታወቀ ይፋ እንደሚያደረግ አስታውቀዋል። "እሳቱ ሰፊ ጉዳት አድርሷል ተብሎ አይታሰብም" ያሉት ዋና አስተዳዳሪው "የተወሰነ ሄክታር የሳር መሬት ተቃጥሏል። መጀመሪያ እሳቱ ሲነሳ የአካባቢው ሰው ስለተቆጣጠረው ያን ያህል ጉዳት አደረሰ ለማለት አይቻልም። የኅብረተሰቡ ተከታትሎ ባያጠፋው ኖሮ ጉዳቱ ሰፊ ይሆን ነበር" ብለዋል። በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ባለፈው ዓመት በተደጋጋሚ እሳት መነሳቱ የሚታወስ ሲሆን፤ በሆሌኮፕተር እና ከእስራኤል በመጡ ባለሙያዎች ድጋፍ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። ከዚህ ልምድ በመወስድ በእያንዳንዱ ወረዳ የእሳት አደጋ መከላከል ብርጌድ መቋቋሙን ያስታወቁት አቶ ወርቁ እሳቱ በተለያየ ምክንያት እንደሚነሳ አስታውቀው "ቆላው ላይ በተፈጥሮ እሳት ሊነሳ ይችላል። ይህ ግን [የትላንቱ] ደጋ ስለሆነ በተፈጥሮ ነው የተነሳው ብሎ ለመደምደም አያስችልምም። ለማንኛውም እየተጠና ነው" ብለዋል። ከተቋቋመው የእሳት አደጋ መከላከል ብርጌድ በተጨማሪ የአካባቢው ማኅበረሰብ የባለቤትነት ስሜት እንዲኖረው በመደረጉ የዘንድሮው እንደ አምናው ጉዳት አለማድረሱን ገልጸዋል። በአውሮፓዊያኑ 1978 በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ባለፈው ዓመት እሳት ተነስቶ ሰፊ ጉዳት ካደረሰ በኋላ በጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። በዚህም ሳንቃ በር እና መስገጎ በሚባሉ ቦታዎች 330 ሄክታር በላይ ቦታ ተቃጥሎ ነበር።
news-49317092
https://www.bbc.com/amharic/news-49317092
በ10 ሰከንድ ውስጥ ለስርቆት የተጋለጡት ዘመናዊ መኪኖች
አዲስ ተመርተው ገበያ ላይ ከዋሉት እጅግ ዘመናዊ ታዋቂ መኪኖች መካከል አንዳንዶቹ ካለቁልፍ የመንቀሳቀስ ሥርዓታቸው ላይ በተገኘ ደካማ ጎን ሳቢያ ለስርቆት እየተጋለጡ መሆናቸው ብዙዎችን እያሳሰበ ነው።
የመኪኖቹ አሰራር አሽከርካሪው ምንም ቁልፍ ሳያስፈልገው መኪናውን ከፍቶ ለመግባት የሚያስችል ነው። በተሽከርካሪዎች ጉዳይ ላይ የሚያተኩር አንድ እንግሊዝ ውስጥ የሚታተም መጽሔት ካለ ቁልፍ በሚከፈቱና ሞተራቸው በሚነሳ ሰባት የተለያዩ መኪኖች ላይ ሙከራ አድርጎ ነበር። የተለያየ ስያሜ ያላቸው የአውዲ፣ የላንድሮቨርና የሌሎች መኪኖች ዘመናዊ ስሪቶች ከባለቤቶቻቸው ውጪ መኪኖቹን ለመስረቅ ከፍቶ ለመግባትና አስነስቶ ለመሄድ አስር ሰከንዶች ብቻ ናቸው የወሰዱት። • በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ • ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» • የህዋ ጣቢያዋ ዛሬ ማታ በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ትታያለች የተሽከርካሪ ደህንነት ባለሙያዎች ሙከራውን ያደረጉት የመኪና ሌቦች የሚጠቀሙትን ዘዴ ተግባራዊ በማድረግ ነው ሲል መጽሔቱ ዘግቧል። ባለሙያዎቹ ባደረጉት ሙከራ መኪኖቹን ከፍቶ ለመግባትና አስነስቶ ለመውሰድ የፈጀውን ጊዜ መዝግበው የያዙ ሲሆን፤ በውጤቱም ከሚጠበቀው በጣም አጭር በሚባል ጊዜ ሌቦቹ መኪኖቹን ለመስረቅ እንደሚችሉ ደርሰውበታል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የመኪና ስርቆት በኢንግላንድና ዌልስ ውስጥ ባለፉት ስምንት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጨምሯል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከ106 ሺህ በላይ መኪኖች ተሰርቀዋል። በዚህም ሳቢያ ባለንበት ዓመት መኪኖቻቸው የተሰረቁባቸው ሰዎች የጠየቁት የኢንሹራንስ ክፍያ መጠን በሰባት ዓመታት ውስጥ ከታየው ከፍተኛው መጠን እንደሆነም ተነግሯል። የኢንሹራንስ ኩባንያዎች እንደሚሉት በመኪኖች ስርቆት ምክንያት እየተጠየቁ ላሉት ክፍያዎች ማሻቀብ ቁልፍ አልባ ዘመናዊ መኪኖች ከፊል ምክንያቶች እንደሆኑ ያምናሉ። ለስርቆት የተጋለጡት መኪኖች አምራች ኩባንያዎች ሁኔታው እንዳሳሰባቸው ገልጸው፤ ምርቶቻቸውን ለስርቆት ተጋላጭ ያደረገውን ምክንያት ከፖሊስ ጋር በመተባባር ለይተው መፍትሄ በማግኘት የተሽከርካሪዎቻቸው ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም ተሽከርካሪዎችን በመሸጥ የሚታወቁ ድርጅቶች ለስርቆት የተጋለጠውን ዘመናዊውን የመኪኖች ቁልፍ አልባ ሥርዓት በባለቤቶቹ ፍላጎት መሰረት እንዳይሰራ ማድረግ እንዲችሉ እንደተፈቀደ ተገልጿል። ቁልፍ አልባ መኪኖቹ እንዴት ይሰረቃሉ? እንዲህ አይነት መኪኖችን የሚሰርቁ ሌቦች በተለምዶ ሁለት በመሆን ነው ለስርቆት የሚሰማሩት። በአብዛኛው ኢላማ የሚያደርጓቸው መኪኖች ደግሞ ከቤት ውጪ የቆሙ መኪኖችን ነው። አንደኛው ሌባ መኪናውን ለመክፈት የሚጠቀሙበትን ዘመናዊ መሳሪያ ይዞ ከመኪናው አቅራቢያ ይቆማል፤ ሌላኛው ደግሞ ሌላ ተመሳሳይ መሳሪያ ይዞ ከቤቱ አቅራቢያ ይቆማል። ከሁለቱ መሳሪያዎች የሚለቀቀው የጨረር መልዕክት የመኪናው ሥርዓት ላይ ግራ መጋባትን በመፍጠር እንዲከፈት ያደርገዋል። ሌቦቹ መኪናውን ከሰረቁ በኋላ ጠቃሚ አካላቱን ለያይተው እንደሚወስዱ ፖሊስ ይናገራል። ይህንን የቁልፍ አልባ መኪኖች ስርቆትን ለመከላከል መኪና አምራቾች እንቅስቃሴን የሚለይ ቴክኖሎጂን ጨምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ ጀምረዋል። በመኪኖቹ ላይ ሙከራ ያደረጉት ባለሙያዎች እንደሚሉት ስርቆትን ለመከላከል ሲባል እንቅስቃሴን የሚለየው ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸውን መኪኖች ለመክፈት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም። በዚህም ቴክኖሎጂው የመኪና ስርቆትን ለመከላከል አስተማማኝ መሆኑን ደርሰውበታል። ቢሆንም ግን ይህ ዘመናዊ የመኪና ስርቆት መከላከያ ቴክኖሎጂ በገበያው ላይ በስፋት አይገኝም።
47579804
https://www.bbc.com/amharic/47579804
በኒውዚላንዱ የመስጊዶች ጥቃት 50 ሰዎች ተገደሉ
ዛሬ በኒውዚላንድ ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስኪዶች ላይ በተከፈተ ተኩስ 49 ሰዎች ሲገደሉ ብዙዎች መጎዳታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ጥቃቱን ፈፅሟል የተባለ አንድ ታጣቂ ነገ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ እንደሚመሰረትበትም ተገልጿል። • ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል ግለሰቡ ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ በነበረው ካሜራ አልኑር በተባለው መስጊድ ሕፃን፣ ሴት ሳይል በመስጊዱ የነበሩ ሰዎች ላይ ሁሉ የተኩስ እሩምታ ሲከፍት በፌስቡክ ቀጥታ ማሰራጨቱም ተገልጿል። ቀደም ሲል በጥቃቱ እጃቸው አለበት ተብሎ የተጠረጠሩ ሦስት ወንዶችና አንዲት ሴት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ ገልፆ የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ ግን አንደኛው ግለሰብ ከጥቃቱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም በሚል ተለቋል። የቀሪዎቹ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ እያጣራ እንደሆነም ፖሊስ አስታውቋል። የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ጥቃቱ የተፈፀመበት ይህ ቀን የአገሪቱ "ጨለማ ቀን" ነው ብለዋል። የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ደግሞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት አንዳቸው አውስትራሊያዊ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ተጠርጣሪዎቹንም "ፅንፈኞች፣ ቀኝ ዘመም አሸባሪዎች" ብለዋቸዋል። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት
news-52526782
https://www.bbc.com/amharic/news-52526782
ኮሮናቫይረስ የአውሮፕላን ጉዞን ይለውጠዋል ተባለ፤ በምን መልኩ?
ተጓዦች ከጉዞ በፊት የደም ምርመራ እንዲያደርጉ ማስገደድ፤ በአየር ማረፊያዎች ሰዎች ሊጠጋጉ የሚችሉባቸውን ስፍራዎች በመስታውት መከፋፈል አልያም ከበረራ በፊት ሰዎች በሳኒታይዘር እጆቻቸውን እንዲያጸዱ ማድረግ ገፍተው የሄዱ እርምጃዎች ሊመስሉ ይችላሉ።
ከአገር አገር የሚደረግ ሽርሽር በእጅጉ ይቀንሳል ይሁን እንጂ ቀላል የማይባሉ አየር መንገዶች ተጓዦች ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ እያደረጉ እንደሆነ እንዲሰማቸው ለማድረግ ለመተግበር እያሰቡት ያሉ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች ናቸው። ምንም እንኳ በመላው ዓለም ከአገልግሎት ውጪ ቆመው የሚገኙት የመንገደኖች ማመላለሻ አውሮፕላኖች መቼ በረራ ማድረግ እንደሚጀምሩ ባናውቅም፤ ከኮረናቫይረስ ስርጭት በኋላ የሚኖረው ከአንድ አገር ወደ ሌላ የሚደረገው ጉዞ ምን መልክ እንደሚኖረው መገመት ይቻላል። በአየር ማረፊያዎች ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ በአየር መንደኞች ውስጥ 'ማኅብራዊ ርቀትን መጠበቅ' የሚለው የትንቃቄ እርምጃ መቀጠሉ አይቀርም። በፍተሻ ቦታዎችም ሆነ የጉዞ ቅድም ሁኔታዎችን ሲያሟሉ [ቼክ ኢን ሲያደርጉ] ከ1-2 ሜትር ርቀት መጠበቅ ግድ ይሆናል። በአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ አንዳንድ አየር ማረፊያዎች ከዚህ በተጨማሪ፤ ተጓዦች እጆቻቸውን ለ20 ሰከንድ በሳሙና እንዲታጠቡ እና በሳኒታይዘር እንዲያጸዱ እያደረጉ ይገኛሉ። የሆንግ ኮንግ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊ ሙሉ የሰውንት ክፍል ከጽረ-ተዋሲያንስ የሚያጸዳ ማሽን አስተክሏል። ማሽኑ ጸረ-ተዋሲያንን በመርጨት በ40 ሰከንድ ውስጥ በሰውነት እና ልብስ ላይ ያሉ ቫይረሶችን እና ባክቴሪያዎችን ይገድላል ተብሏል። ሙሉ የሰውንት ክፍል ከጽረ-ተዋሲያንስ የሚያጸዳ ማሽን በሆንግ ኮንግ አየር ማረፊ ከዚህ በተጨማሪም አየር ማረፊያው በጨረር አማካኝነት ቫይረሶችን እየተዘዋወረ የሚገድል ሮቦት በሥራ ላይ አንደሚያውል አስታውቋል። ሌሎች አየር ማረፊያዎች ደግሞ የሰውነት ሙቀት ልኬት ለሁሉም ተጓዦች ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ኢሚሬትስ አየር መንገድ ደገሞ ተጓዦች ከዱባይ ከመሳፈራቸው በፊት በደም ናሙና ውስጥ ኮቪድ-19 መኖር አለመኖሩን በ10 ደቂቃ ውስጥ ውጤት የሚለይ መሳሪያ ያድላል። አውሮፕላን ውስጥ ወደ አውሮፕላን ዘልቀው ሲገቡ የለመዱትን የበረራ አስተናጋጆች ፈገግታን ላትመለከቱ ትችላላችሁ። ምክንያቱም የበረራ አስተናጋጆቹ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ስለሚያጠልቁ። ምናልባት እርሰዎም የመረጡት አየር መንገድ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ሊሆን ይችላል። አየር መንገዶች ተጓዦች ከመሳፈራቸው በፈት የመመገቢያ ጠረጴዛዎች፣ የእቃ መጫኛ ሰንዱቆችን፣ መጸዳጃ ቤቶች እና መቀመጫ ወንበሮችን በጸረ-ተህዋሲያን እንዲጸዱ ይደረጋሉ። ከኮሮናቫይረስ በኋላም አንዳንድ አየር መንገዶች ጠበቅ ያለ ርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል። በኮሪያ አየር መንገድ ቢሳፈሩ ሙሉ ጋዋን፣ ጓንት እና የፊት ጭንብል ያደረጉ የበረራ አስተናጋጆች በረራዎች ምቹ እና ቀላል ለማድረግ ደፋ ቀና ሲሉ ይመለከታሉ። ከኮሮናቫይረስ በኋላ በሚኖሩት ጥቂት ወራት የአየር መንገድ ቲኬቶች ዋጋ የሚቀመሱ አይሆንም እየተባለ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ማኅበራዊ ርቀትን ለመጠበቅ ሲባል በመንገደኖች መካከል አንድ ክፍት ወንበር ስለሚተው ነው። የዚህን ወጪ ለማካካስ ደግሞ አየር መንዶች የቲኬት ዋጋዎች ላይ ማስተካከያ ስለሚያደርጉ ነው። ሌላ ምን አዲስ ነገር ይፈጠር ይሆን? ከኮሮናቫይረስ ዘመን በኋላ ለጉዞ ሻንጣቸውን የሚሸክፉ ሰዎች ቁጥር እንደሚቀንስ ይጠበቃል። ለዚህም 'ለቫይረሱ ተጋላጭ ልሆን እችላለሁ' ከሚለው ስጋት በተጨማሪ ሌሎች ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ። ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበራ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት ከተሳተፉ ሰዎች 60 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሌላ አገር ለሽርሽርም ሆነ ለሥራ የምጓዘው የኮሮናቫይረስ በቁጥጥር ሥር ከዋለ ከሁለት ወራት በኋላ ነው ብለዋል። ቦይንግ እንደሚለው ከሆነ አየር መንገዶችም ወደተለመደው የበረራ አገልግሎት በቀርቡ አይመለሱም። የኮሮናቫይረስ ተጽእኖም በኢንዱስትሪው ላይ እስከ 2023 ይዘልቃል።
55526500
https://www.bbc.com/amharic/55526500
ትራምፕ “ድምጽ አጭበርብሩልኝ” ሲሉ የተለማመጡበት የስልክ ንግግር ይፋ ሆነ
ትራምፕ ስልክ እየደወሉ ጆ ባይደንን እንዳሸንፈው ትንሽ ድምጽ እንዴትም ብላችሁ አሟሉልልኝ እያሉ የግዛት አስመራጮችን ይለምኑ እንደነበር ዋሺንግተን ፖስት አጋለጠ።
ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደንን እንዳሸንፍ ድምጽ ከየትም ብላችሁ ፈልጉ እያሉ ከደወሉባቸው የግዛት የምርጫ ኃላፊዎች አንዱ የጆርጂያ ግዛት ምርጫ አስፈጻሚ ብራድ ራፍነስፐርግ ናቸው። ዋሺንግተን ፖስት ይፋ ባደረገው የስልክ ቅጂ ንግግር ትራምፕ ለብራድ እባክህ 11ሺ 780 ድምጽ ከየትም ብለህ ፈልግ እያሉ ሲለምኑ እንደነበር ያጋልጣል። ብራድ በበኩላቸው የጆርጂያ ግዛት ቆጠራው በትክክል ተቆጥሮ መጠናቀቁን ለትራምፕ ሲናገሩ ይሰማሉ። ሆኖም ትራምፕ ሰውየውን በማባበልና በማግባባት ትንሽ የተጭበረበሩ ድምጾችን ካገኘ እሳቸው አሸናፊ እንደሚሆኑ በማስረዳት እንደምንም ተባባሪ እንዲሆን ሲያበረታቱት ይሰማል። ሚስተር ብራድን በማግባባቱ የስልክ ንግግር ውስጥ ትራምፕ እንዲህ ሲሉ ይሰማል "እንደምንም ብለህ ድምጽ ቆጠራው ላይ ስህተት ሰርተናል ብትልልኝ እኔን በቀላሉ አሸናፊ ያደርገኛል፤ ያን ብትል ምንድነው ችግሩ" ሚስተር ብራድ በበኩላቸው "የተከበሩ ፕሬዝዳንት፣ ቆጠራው ስህተት ነው ብለው የያዙት መረጃ ስህተት መሆኑ ነው ችግሩ" ብለው ይመልሱላቸዋል። ትራምፕ ምርጫ ኃላፊው ማባበያቸውን አልቀበል ሲሏቸው ቆጣ ብለው "ምርጫ ሲጭበረበር እያየህ ዝም ማለት ወንጀል እንደሆነ አታውቅም? ይሄ አንተንም ሆነ ጠበቃህን ብዙ ችግር ውስጥ የሚከትህ ነው የሚሆነው" እያሉ ለማስፈራራት ሞክረዋል። ትራምፕ የጆርጂያ ግዛት ምርጫ አስፈጻሚን ለማግባባት የሞከሩት 11ሺ 780 ድምጽ ቢያገኙ አሸናፊ ሊያደርጋቸው ይችል እንደነበረ ስለተረዱ ነው። ትራምፕ የተለማመጡትን የመራጭ ድምጽ ቢያገኙ በጆርጂያ ግዛት 2 ሚሊዮን 473ሺህ 634 ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ያደርጋቸው ነበር። ጆ ባይደን ያገኙት ድምጽ 2 ሚሊዮን 473ሺህ 633 ስለነበር በትንሽ ድምጽ ልዩነት ግዛቲቱን ማሸነፍ ነበር የትራምፕ ግብ። ጆ ባይደን ጆርጂያ ግዛትን ማሸነፋቸው አይዘነጋም። ጆርጂያ ትራምፕ ያሸንፉበታል ተብሎ የሚጠበቅ ግዛት ስለነበር ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ግዛት ከፍተኛ የማሸነፍ ፍላጎት ነበራቸው። አሁን 50ዎቹም ግዛቶች ማን አሸናፊ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ያተሙ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ግን ውጤቱን ለማስቀልበስ ቢያንስ 60 የሚሆኑ የክስ ፋይሎችን ከፍተው ነበር። የአሜሪካ ፍርድ ቤቶች 60ውን ክስ በተለያዩ ግዛቶች ውድቅ አድርገዋቸዋል። ከነገ በስቲያ በጃንዋሪ 6 ኮንግረስ ተሰብስቦ የምርጫ ውጤቱን በይፋ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚያ በኋላ በጃንዋሪ 20 ጆ ባይደን ቃለ መሀላ ፈጽመው ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት ይገባሉ። በጆርጂያ ግዛት ሁለት የሴናተር ወኪሎች ምርጫ ከሰሞኑ ይደረጋል። ውጤቱን የላይኛውን ምክር ቤት ለመቆጣጠር እጅግ ወሳኝ ይሆናል። ለምሳሌ በምርጫው ዲሞክራቶች ቢያሸንፉ በሴኔቱ የሪፐብሊካንና የዲሞክራቶች ቁጥር አቻ ይሆናል። ይህም ማለት ምክር ቤቱን የሚመሩት ምክትል ፕሬዝዳንት የሚሆኑት ካማላ ሐሪስ ስለሚሆኑ እርሳቸው በሚሰጡት አንዲት ድምጽ የዲሞክራቶች ፍላጎት ተፈጻሚ መሆን ይችላል። የታችኛው ምክር ቤት ግን አሁንም በዲሞክራት ወኪሎች የበላይነት የተያዘ ነው። ናንሲ ፒሎሲም በድጋሚ ለሌላ 4 ዓመት የታችኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል።
49862568
https://www.bbc.com/amharic/49862568
የመስቀል ደመራ አከባበር ውዝግብ በቢሺፍቱ ከተማ
ትናንት ከኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተነስተው፤ ወደ ደመራ ለመሄድ መንገድ ላይ ሳሉ፤ "ያልተፈቀደ ሰንደቅ አላማ ይዛችኋል" በሚል ማለፍ መከልከላቸውን የቢሾፍቱ ኪዳነ ምሕረት አገልጋዮችና ምዕመናን ለቢቢሲ ተናገሩ።
የደብረ መፅሔት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን- ቢሾፍቱ የዓደአ ወረዳ ቤተክህነት ጸሀፊ መጋቤ ጥበብ እውነቱ ጥላሁን፤ ከደመራው ዕለት ቀደም ብለው ከከተማው አስተዳደር ጋር በበዓሉ አከባበር ዙሪያ ለመነጋገር ስብሰባ ቢያደርጉም ባለመግባባት እንደተለያዩ ያስታውሳሉ። የኢሬቻ እና የመስቀል በዓል በሰላም እንዲያልፍ ከአድባራት ኃላፊዎች፣ ከምንጣፍ አንጣፊ ማኅበራት እና ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ጋር በመሆን ውይይት ተካሂዶ እንደነበር የሚያስታውሱት ጸሀፊው፤ "ልሙጥ ባንዲራ መያዝ ትችላላችሁ፣ አትችሉም" የሚለው ውይይት ላይ የሌሎች እምነት ተከታይ ኃላፊዎች መሳተፋቸው እንዳላስደሰታቸው ይናገራሉ። • በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ • መሐመድ አሊ፡ የአልሲሲን ገመና አደባባይ ያሰጣው ግብጻዊ ከዚህ ስብሰባ በኋላ ግን፤ የከተማው ከንቲባ ጠርተዋቸው ይቅርታ እንደጠየቋቸውና በሰንደቅ አላማ ጉዳይ ተነጋግረው፤ ልሙጥ (ኮከብ የሌለው) ባንዲራ መያዝ በሕግ ስለማይፈቀድ፤ ይዘው መውጣት እንደሌለባቸው መስማማታቸውን ይናገራሉ። የበዓል ማድመቂያ ሪቫኖችን ግን በአደባባይ ላይ አስረው በዓሉ በድምቀት እንዲከበር እንደተስማሙ ያክላሉ። መላከ ሰላም አባ ሩፋኤል በቢሾፍቱ የደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ፤ የመስቀል በዓልን ለማክበር በቢሾፍቱ የሚገኙ አድባራት በአጠቃላይ ወደ መስቀል አደባባይ እንደሚወጡ አስታውሰው፤ ሁሉም ቤተክርስቲያናት በወጣላቸው መርሃ ግብር መሰረት ወደ መስቀል አደባባይ መምጣታቸውን ይገልፃሉ። ሆኖም ግን የደብረ መፅሔት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያንን የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የለበሱት ልብስ ላይ "ልሙጥ ባንዲራ አለበት" ያሉ የአካባቢው ወጣቶች፤ ዝማሬ የሚያሰሙትን የዕምነቱን ተከታዮች አታልፉም ብለው እንደከለከሏቸውና ወደ መስቀል አደባባይ መሄድ አንዳልቻሉ መላከ ሰላም አባ ሩፋኤል ይናገራሉ። የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባል የሆኑ አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ እንዳረጋገጠው፤ ትናንት ከኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተነስተው ወደ ቢሾፍቱ መስቀል አደባባይ መሄድ የጀመሩት ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ነው። በግምት ከቤተክርስቲያኒቱ 500 ሜትር እንደራቁ፤ የተወሰኑ ወጣቶች "የለበሳችሁት ባንዲራ የተከለከለው ነው" በሚል እንዳስቆሟቸው ይናገራል። "በመጀመሪያ እነዚህን ወጣቶች እየዘመርን አልፈናቸው ነበር" የሚለው የሰንበት ትምህርት ቤቱ አገልጋይ፤ በኋላ ግን የቀበሌ 5 አስተዳደር ፖሊስ ይዘው ሄደው መንገዱን እንደዘጉትና ለሰዓታት ቆመው መከራከራቸውን ይናገራል። "የለበስነው የመዘምራን ልብስ ድሮም እንጠቀምበት የነበረ፣ ቆቡም ድግድጋቱም አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው። ይህንን ካላወለቃችሁ አታልፉም አሉን" ሲል በወቅቱ የነበረውን ይናገራል። ቤተክርስተያን ቀለሙን ለዘመናት ስትጠቀምበት መኖሯን የሚገልፁትና "ይህ ምልክት የቀስተ ደመና ምልክት፣ ከመስቀሉ በፊት ነበረ፣ የኖህ ቃል ኪዳን የዳግመኛ አለመጥፋት ምልክት ነው" የሚሉት ደግሞ የወረዳው ቤተ ክህነት ጸሀፊ ናቸው። • ሁሌም አብሮን ያለው 'የመስቀል ወፍ' • ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ አትሄዱም ብለው ያስቆሟቸው የፀጥታ አካላት፤ ሰንደቅ አላማውን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በማዛመድ "የአብን ነው፣ የኢዜማ ነው" ብለው እንዳንገላቷቸው የሚናገረው የሰንበት ትመህርት ቤቱ አገልጋይ፤ እነርሱም አናወልቅም በማለት መስቀል አደባባይ መሄዳቸውን ትተው ወደ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን መመለሳቸውን ይናገራል። ይህ አገልጋይ "27 ዓመት በቤተክርስቲያኒቱ ሳገለግል ተከልክለን አናውቅም ዘንድሮ መከልከላችን አዲስ ነው" ይላል። የኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን መዘምራንና ምዕመናን አለመምጣታቸውን ያስተዋሉ ወደ መስቀል አዳባባይ የሄዱት ሰዎች፤ "አንድ ደብር ጎሎ ደመራ አናበራም" ብለው ወደ ኪዳነ ምሕረት መሄዳቸውን የሚናገሩት ደግሞ መላከ ሰላም አባ ሩፋኤል ናቸው። በዚህም የተነሳ በቢሾፍቱ መስቀል አደባባይ ደመራውን ሳያበሩ መቅረታቸውን ተናግረዋል። የፖሊስ ኃላፊው አናግረው "ምዕመኑ ይመጣሉ" መባላቸውን የሚያስታውሱት መላከ ሰላም አባ ሩፋኤል፤ ሳይመጡ ሲቀሩ የተወሰኑ አድባራት አስተዳዳሪዎች ከመስቀል አደባባይ ተነስተው ወደ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ምዕመናኑን ለማምጣት ማምራታቸውን አስታውሰዋል። የአድባራቱ አስተዳዳሪዎች የኪዳነ ምሕረት ምዕመናንን አሳምነውም ወደ መስቀል አደባባይ ለመውሰድና ደመራው እንዲበራ ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም ስላልተሳካ፤ ወደ መስቀል አደባባይ በመመለስ ትምህርተ ወንጌል ተሰብኮ፣ ፀሎት ተደርጎ፣ ወደ ቡራኬ ሊኬድ በሚባልበት ሰዓት፤ በመስቀል አደባባይ የተገኘው ምዕመን "ኪዳነ ምሕረቶች ሳይመጡ ዳመራው አይለኮስም" በማለቱ ምክንያት ፀሎት ተደርጎ፣ ደመራው ሳይለኮስ ትተው እንደሄዱ የዓደአ ወረዳ የቤተክህነት ፀሀፊ እና የደብረ ገነት ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ኃላፊዎቹ አክለውም ፤ "ዛሬ ማለዳ እንዳየነው ግን ደመራው ተቃጥሏል፤ ማን እንዳደረገው አናውቅም" ብለዋል። የወረዳው የቤተክህነት ጸሀፊ አክለውም፤ ትናንት እንዲህ አይነት ችግር የታየው በኪዳነ ምሕርት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ቢሾፍቱ አፋፍ ደብረ ስብሃት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲይን ጭምር መሆኑንም ይገልፃሉ። • በኢትዮጵያውያን ተሰርቶ የአውሮፓውያንን ድጋፍ የሻተው ላሊበላ የአካባቢው የምንጣፍ አንጣፊ ማኅበራት፤ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ላይ የሥላሴና የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ያለበት ካናቴራ እንዲያወልቁ መደረጋቸውን ይናገራሉ። ይህንን ካናቴራ አምና ወጣቶቹ ለጥምቀት በዓልም ተጠቅመውበታል የሚሉት ፀሀፊው፤ ትናንት ግን በፀጥታ አካላት በመከልከላቸው ነጠላ ለብሰው ወደ መስቀል አደባባይ መምጠታቸውን ይናገራሉ። ዛሬ ማለዳ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተፈጠረውን ሰምተው፤ ወደ ቢሾፍቱ ደብረ መዊ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሄደው ምዕመናኑን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላቶችን እና የሀይማኖት አባቶችን በማነጋገር እያረጋጉ መሆኑን በስፍራው የተገኙት ኃላፊዎቹ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ደመራው ትናንት መለኮሱን አረጋግጦ፤ ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ግን መረጃ መሰብሰብ እንዳለበት ገልጾልናል። የከተማዋ ከንቲባ ስልክ ባለመስራቱ በጉዳዮ ላይ ምላሻቸውን ማግኘት አልቻልንም።
news-51401848
https://www.bbc.com/amharic/news-51401848
የኮሮናቫይረስን መከሰት ያጋለጠው ዶክተር በበሽታው ህይወቱ አለፈ
ገዳዩ ኮሮናባይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ለማሳወቅ ጥረት ያደረገው ቻይናዊው ዶክተር በቫይረሱ ህይወቱ በማለፉ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ቁጣና ሃዘንን ቀሰቀሰ።
ዶክተር ሊ ዌንሊያንግ የዶክተሩ ሞት ከተሰማ በኋላ የቻይና የማህበራዊ ትስስር መድረክ በሆነው ዌቦ ላይ ዜጎች ከፍተኛ ሐዘናቸውን ሲገልጹ ቆይተው ሁኔታው ወደ ቁጣ ለመቀየር ጊዜ አልፈጀበትም። በዚህም ምክንያት መንግሥት መጀመሪያ ላይ በሽታውን ለመደበቅ በመሞከርና የወረርሽኙን አስከፊነት በማቃለል ክስ እየተሰነዘረበት ነው። በዶክትር ሊ ሞት የተፈጠረው ቁጣ እየተባባሰ በቻይና ውስጥ የመናገር ነጻነት ስላለበት ሁኔታ ውይይት እንዲጀመር አድርጓል። የአገሪቱ ጸረ ሙስና ተቋምም "ከዶክተሩ ጉዳይ ጋር በተያያዘ" ምርመራ ማድረግ እንደሚጀምር አሳውቋል። አንድ የቻይና ድረ ገጽ እንዳለው የሟቹ ዶክተር ባለቤት እርጉዝ ስትሆን ሰኔ ላእ እንደምትወልድ ይጠበቃል። ኮሮናቫይረስ እስካሁን 636 ሰዎችን የገደለ ሲሆን ከ31 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቻይና ብቻ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ዶክተር ሊ ዌንሊያንግ ወረርሽኙ በተከሰተበት ዉሃን ከተማ ዉሃን ሴንትራል ሆስፒታል ውስጥ ይሰራ ነበር። ዶክተር ሊ በሆስፒታሉ ውስጥ ይሰራ በነበረበት ወቅት በአንድ እንግዳ ቫይረስ ተጠቅተው የመጡ ሰባት ሰዎችን ያገኛል። ከዚያም በሽታው ከ15 ዓመታት በፊት ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ሆኖ የነበረው 'ሳርስ' ሳይሆን እንደማይቀር ገምቶ ነበር። • ኢትዮጵያውያን፡ የአስወጡን ድምጽ በጎሉባት የቻይናዋ ዉሃን • ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ስም ለማውጣት ያስቸገረው አዲሱ ቫይረስ የበሽታውን መከሰት በተመለከተ ለሰዎች በመንገር እንዲጠነቀቁ ምክር የለገሰ ሲሆን ፖሊሶች ቤቱ ድረስ መጥተው ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አስጠንቅቀውታል። ፖሊሶቹ በወቅቱ 'ሃሰተኛ መረጃን እያሰራጨህ ህብረተሰቡን እያሸበርክ ነው' ሲሉ ነበር ማስጠንቀቂያውን የሰጡት። ዶክተር ሊ ይህን ማስጠንቀቂያ ከደረሰው ከአንድ ወር በኋላ ግን በሽታው በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ዓለምን ማስጨነቅ ሲጀምር፤ ዶክተር ሊም የበሽታው ሰለባ ሆኖ የሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ ነበር። ሊ ከሃኪም ቤት ተኝቶ ታሪኩን ይፋ ሲያደርግ ጀግና ተብሎ ተወድሷል። "ጤና ይስጥልኝ፤ ሊ ዌንሊያንግ እባላለሁ፣ በዉሃን ማዕከላዊ ሆስፒታል የዓይን ሃኪም ነኝ" በማላት ይጀምራል የዶክተሩ መልዕክት። ዶክተሩ ይፋ ያደረገው መልዕክት የኮሮናቫይረስ በተከሰተባቸው የመጀመሪያ ሳምንታት ዉሃን ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት በሽታውን ለመሸፋፈን ያደረጉትን ጥረት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ተብሏል። ታህሳስ ወር ላይ ወረርሽኙ በተከሰተበት ማዕከል ውስጥ ይሰራ የነበረው ዶክተር ሊ በአንድ እንግዳ ቫይረስ ተጠቅተው የመጡ ሰባት ሰዎችን አግኝቶ ነበር ተናግሯል። • የኮሮናቫይረስ ስጋትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደ አውሮፓዊያኑ ታህሳስ 30 ላይ ዶክተሩ በአንድ የቡድን መልዕክት መለዋወጫ መድረክ ላይ ለሙያ አጋሮቹ ዶክተሮች ስለወረርሽኙ መከሰትና እራሳቸውን ለመጠበቅ የመከላከያ አልባሳትን እንዲጠቀሙ የሚመክር መልዕክት አስተላልፎ ነበር። ከአራት ቀናት በኋላ ከሕዝብ ደህንንት ቢሮ ባለስልጣናት መጥተው አንድ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርም ነገሩት። ወረቀቱም ዶክተሩን "ሐሰተኛ አስተያየቶችን በመስጠት" ይህም "በከፍተኛ ሁኔታ ማኅበራዊ ሥርዓትን የሚያናጋ" መሆኑን በመግለጽ ጥፋተኛ አድርጎ የሚከስ ነበር። ለዶክተሩ የተጻፈው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ "በጥብቅ የምናሳስብህ ነገር ቢኖር፡ በዚህ ድርጊትህ በግትርነት የምትገፋ ከሆነና ሕግን ባለማክበር በሕገወጥ ተግባርህ የምትቀጥል ከሆነ ለፍርድ ትቀርባለህ። ገብቶሃል?" ይላል የቀረበለት ወረቀት። ከስርም ዶክተር ሊ በእጅ ጽሑፉ "አዎ፤ ተረድቻለሁ" የሚል ጽሑፍ ሰፍሯል። "ሐሰተኛ አሉቧልታዎችን በማሰራጨት" በሚል ተጠርጥረው ምርመራ ከተደረገባቸው ስምንት ሰዎች ዶክተሩ አንዱ ነው። በጥር ወር ማብቂያ ላይም ዶክተር ሊ ከባለስልጣናት የተሰጠውን የዚህን ደብዳቤ ቅጂ 'ዌቦ' በተባለው የቻይናዊያን ማህበራዊ የትስስር መድረክ ላይ በማውጣት ምን አጋጥሞት እንደነበረ ይፋ አደረገ። ይህንን ተከትሎም የአካባቢው ባለስልጣናት የበሽታው ወረርሽኝ ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ በኋላ ዶክተሩን ይቅርታ ቢጠይቁትም፤ ይቀርታው የዘገየ ነበር። • ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ስም ለማውጣት ያስቸገረው አዲሱ ቫይረስ በጥር ወር መጀመሪያ ሳምንታት ላይ ዉሃን ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት በቫይረሱ የሚያዙት ሰዎች በሽታው ካለባቸው እንስሳት ጋር የቀረበ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ብቻ እንደሆኑ በመግለጻቸው፤ ሐኪሞችን ለመከላከል ምንም መመሪያ አልተሰጠም ነበር። ፖሊሶች ዶክትር ሊን ካናገሩት ከሳምንት በኋላ አንዲት የግላኮማ ችግር ያለባትን ሴት እያከመ ነበር። ታካሚዋም አዲሱ የኮሮናቫይረስ እንዳለባት አላወቀም። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈረው ጽሑፉ ዶክትር ሊ በጥር ወር ሁለተኛ ሳምንት ላይ ሳል እንደጀመረው፣ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ትኩሳት እንዳጋጠመውና ከሁለት ቀናት በኋላም ብሶበት ሆስፒታል እንደገባ ገልጿል። ቤተሰቦቹም መታመማቸውንና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንም አመልክቷል። ዶክትር ሊ ላይ የመጀመሪያው የበሽታው ምልክት ከታየ ከ10 ቀናት በኋላ ቻይና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን አወጀች። ዶክትር ሊ እንዳለው የኮሮናቫይረስ ምርመራ በተደጋጋሚ ቢደረግለትም የተገኘው ውጤት ግን ነጻ እንደሆነ ነበር። ነገር ግን በጥር ወር መጨረሻ ላይ የተደረገለት ምርመራ በበሽታው መያዙን አመለከተ። ይህንንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይፋ በማድረጉ አድናቆትና ድጋፍን ከበርካታ ሰዎች አግኝቷል።
news-42221277
https://www.bbc.com/amharic/news-42221277
የእንግሊዝ የእርዳታ ገንዘብ በሶሪያ ለሚገኙ አክራሪዎች ውሏል ተባለ
የቢቢሲ ፓናሮማ ፕሮግራም የምርምር ዘገባን ተከትሎ የእንግሊዝ ታክስ ከፋዮች ገንዘብ ሶሪያ ለሚገኝ አክራሪ ቡድን ውሏል በሚል የእንግሊዝ መንግሥት አንድ የእርዳታ ፕሮጀክትን አግዷል።
በእንግሊዝ የሚደገፍ የሶሪያ ፖሊስ ሃይል በፍርድ ቤቶች ጣልቃ በመግባት አሰቃቂ የሚባሉ ፍርዶችንም እንደሰጡና ጫና ማድረጉንም ዘገባው ጨምሮ ያስረዳል። ይህንን ዘገባ ተከትሎ የእንግሊዝ መንግሥት ቃል አቀባይ ለአሸባሪዎች የሚደረግ ትብብርን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያየው ተናግረዋል። የታገደውን ፕሮጀክት እየሰራ እየተገበረ የነበረው አዳም ስሚዝ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት በበኩሉ ውንጀላውን ክዶታል። ዘ ፍሪ ሲሪያን ፖሊስ ( የሶሪያ ፖሊስ ነፃ አውጪ) የተቋቋመው የሶሪያ አመፅን ተከትሎ ሲሆን አላማውም በተቃሚው ኃይል ቁጥጥር ስር የነበሩ ግዛቶች ላይ ህግና ስርአትን ማስፈን ነው። አዳም ስሚዝ ኢንተርናሽናል ደግሞ ከአውሮፓውያኑ 2014 ጀምሮ ይህንን ፕሮጀክት ሲቆጣጠር ነበር። እንግሊዝን ጨምሮ ስድስት ሀገራት ለዚህ ፕሮጀክት የሚለግሱ ሲሆን አማፂያን በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች አሌፖ፣ኢድሊብና ዳራ ግዛቶች ላይ በፕሮጀክቱ አማካኝነት የማህበረሰብ ፓሊስ ስራ ይሰራል። ዋና አላማው የነበረውም የሲቪል ፖሊስ ሃይልን ማሰማራትና ከአክራሪ ቡድን ጋር አለመተባባር የሚል ቢሆንም የቢቢሲ ፓናሮማ ዘገባ ግን ፕሮጀክቱ በተቃራኒው ከአክራሪ ቡድኑ ጋር ግንኙነት እንደነበረው አሳይቷል። ዘገባው ፕሮጀክቱን ከወነጀለበት ምክንያቶች አንዳንዶቹም የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ፀሐፊ ቦሪስ ጆንሰን በባለፈው ሚያዝያ የእንግሊዝ መንግስት የሶሪያ ፖሊስ ነፃ አውጪ ለሚደግፈው 'አክሰስ ቱ ጀስቲስ ኤንድ ኮሚዩኒቲ ሴኩሪቲ' አራት ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚለግሱ አስታውቀው ነበር። 'አክሰስ ቱ ጀስቲስ ኤንድ ኮሚዩኒቲ ሴኩሪቲ' እንደሚለው ከሆነ የሶሪያ ፖሊስ ነፃ አውጪ መሳሪያን የማይታጠቅ ከማህበረሰቡ የተውጣጣ የፖሊስ ኃይል ሲሆን በጦርነት ፍርስርሷ ለወጣው ሃገር የህግ የበላይነትንና ለሚሊዮኖች ደግሞ ደህንነትን ለማስፈን በሚል የተቋቋመ ነው። የዚሁ ድርጅት ቃል አቀባይም " የቢቢሲ ፓኖራማ ውንጀላን በፍፁም አንቀበለውም ፤ የታክስ ከፋዮችን ገንዘብ ሽብርን ለመከላከል፣ በጦር ዞን ውስጥ ለሚገኙ ማህበረሰቦች የደህንነት ከለላን ለመስጠት ነው ያዋልነው" ብለዋል። "ድርጅቱ በፕሮጀክቱ ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን በጣም ፈታኝና ከፍተኛ አደጋ ባለባቸው አካባቢዎች መድረስ የቻለ ሲሆን ፕሮጀክቱ በውጭ ጉዳይ፣ በኮመንዌልዝ ቢሮና አምስት መንግስታት ትብብር የሚደገፍ ነው" በማለት ጨምረውም ገንዘብ ለፖሊስ የሚለግሱት አማራጭ ስላልነበርና የእንግሊዝ መንግሥትም ስለ ክፍያዎቹ እንደሚያውቁ ይገልፃሉ።
news-54129007
https://www.bbc.com/amharic/news-54129007
ታሊባን እና የአፍጋን መንግሥት ለሰላም ድርድር ኳታር ገቡ
ለወራት ዘግይቶ የቆየው በአፍጋኒስታን መንግሥት እና በታሊባን መካከል የሚደረገው የሰላም ድርድር በባህረ ሰላጤዋ አገር ኳታር ዛሬ ይጀመራል።
የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ደግሞ የሰላም ድርድሩ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ለመታደም ወደ ዶሃ ጎዞ ጀምረዋል። ፖምፔዮ የሰላም ድርድሩን “ታሪካዊ” ሲሉ ጠርተውታል። አሜሪካ ከወራት በፊት ከታሊባን ጋር የደህንነት ስምምነት ከደረሰች በኋላ ነው በአፍጋን መንግሥት እና በታሊባን መካከል የሰላም ድርድር እንደሚካሄድ የተገለጸው። የአፍንጋኒስታን መንግሥትን የሚወክለው ልዑክ ትናንት ምሽት ወደ ዶሃ ያቀና ሲሆን የልዑኩ መሪ አብዱላህ አብዱል “ሰላምን ለማግኘት ነው የምንጓዘው” ብለዋል። ከአፍጋኒስታን መንግሥት ልዑክ ጋር የሴቶችን መብት እና ፍላጎት መከበሩን የሚያረጋግጡ ስድስት ሴቶች ወደ ዶሃ መጓዛቸው ተነገሯል። ታሊባን በበኩሉ ከትናንት በስቲያ ስድስት እሰረኞች መለቀቃቸውን እንዳረጋገጥን በሰላም ድርድሩ ላይ እንሳተፋለን ብሏል። እነዚህ ስድስት የታሊባን እስረኞች እንዳይለቀቁ ፈረንሳይ እና አውስትራሊያ ጥያቄ አቅርበዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው እኚህ የታሊባን እስረኞች በዜጎቻቸው ግድያ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው በሚል ነው። ይህ በታሊባን እና በአፍንጋኒስታን መንግሥት መካከል የሚደረግ የመጀመሪያ የፊት ለፊት ውይይት እንደሆነ ይታመናል። ታሊባኖች የአፍጋን መንግሥት “ደካማ” እና “የአሜሪካ አሻንጉሊት ነው” በሚል ለድርድር ለመቀመጥ ፍላጎት ሳያሳዩ ቆይተዋል። እአአ 1979 የሶቪየት ወረራን ተከትሎ የተጀመረውን ግጭት ለማስቆም ሁለቱም ወገን ተስፋ ሰንቀዋል። ይህ ውይይት ለወራት ዘግይቶ ነው የሚካሄደው። ለዚህ ደግሞ ምንክያቱ አሜሪካ እና ታሊባን ከወራት በፊት በደረሱት የሰላም ስምምነት ላይ የእሰረኞች ልውውጥ እንዲካሄድ የደረሱት ስምምነት እስካሁን ተፈጻሚ ሳይሆን በመቅረቱ ነው። በዛ ስምምነት መሰረት ታሊባን ይዞ የሚገኘውን 1 ሺህ የአፍጋኒስታን ወታደሮችን ለመፍታት የተስማማ ሲሆን የአፍጋኒስታን መንግሥት ደግሞ 5 ሺህ የታሊባን ወታደሮችን እንደሚፈታ አሜሪካ ማረጋገጫ ሰጥታለች። በአሜሪካ እና ታሊባን ስምምነት ላይ አሜሪካ እና የሰሜን አትላንቲክ የቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አጋሮች ሁሉንም ወታደሮቻቸውን በ14 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ተስማምተዋል። አሜሪካ ጨምራ በታሊባን ላይ ጥላ የሚገኘውን ማዕቀብ ታነሳለች። የተባበሩት መንግሥታትም በታሊባን ላይ ጥሎት የሚገኘው ማዕቀብ እንዲነሳ አሜሪካ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር አብራ ለመስራት ተስማምታለች። በምላሹ ደግሞ ታሊባን በሚቆጣጠራቸው አከባቢዎች አል-ቃኢዳ ወይም የትኛው ጽንፈኛ ቡድን እንዲንቀሳቀስ አይፈቅድም።
news-48250847
https://www.bbc.com/amharic/news-48250847
በቡርኪናፋሶ ቤተ ክርስቲያን በደረሰ ጥቃት ስድስት ምዕመናን ተገደሉ
ትናንት በሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ አምልኮ ላይ የነበሩ ክርስቲያኖች ላይ ተኩስ ተከፍቶ የቤተክርስቲያኒቱን ቄስ ጨምሮ ስድስት ምዕመናን መገደላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ።
ምዕመናኑ የካቶሊክ ቤተክርስትያን አባላት ሲሆኑ የጠዋት አምልኮ ስርዓት ላይ ነበሩ ተብሏል። ጥቃቱ የደረሰባት ዳብሎ ከተማ ከንቲባ ኦስማኔ ዞንጎ "የታጠቁ አካላት ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ዘለው በመግባት ለማምለጥ የሚሞክሩት ላይ መተኮስ ጀመሩ" ብለዋል። ጥቃቱን ያደረሱት አካላት 20 እና 30 ይሆናሉ የተባለ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑንም አቃጥለዋል። • "ይህንን ሐውልት የኢትዮጵያ ሕዝብ አሠሩላቸው" • "ሊወልዱ እያማጡም የእናታቸውን ስም ነው የሚጠሩት" ሚዲዋይፍ • "አመራር ስንመድብ መስፈርታችን ብቃትና ችሎታ ነው" ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የከተማው ከንቲባ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደገለፁት ሌሎች ሕንፃዎች ሲቃጠሉና ጤና ጣቢያው ላይ ዘረፋ ሲፈፀም መደናገጥ ተፈጥሯል። ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ የከተማው ነዋሪዎች በፍርሃት ተውጠው ከቤታቸው ሳይወጡ ውለዋል ተብሏል። የደህንነት ምንጮች ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንዳረጋገጡት ለከተማዋ ተጨማሪ ወታደራዊ ኃይል አቅራቢያ ከሚገኝ ከተማ ተልኳል። በአካባቢው የሚኖር ጋዜጠኛ ለቢቢሲ እንደተናገረው ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ክርስቲያኖች በከተማቸው የሚገኘው የወታደሮች ኃይል ወዲያውኑ ስላልደረሰላቸው ተበሳጭተዋል። በቡርኪናፋሶ ጂሃዲስቶች በአምስት ሳምንት ውስጥ ጥቃት ሲፈፅሙ ይህ ሶስተኛቸው ሲሆን ከ2016 ጀምሮም ጥቃት በፈፀም ይታወቃሉ።
news-46969293
https://www.bbc.com/amharic/news-46969293
የዚምባብዌ ወታደሮች ሰልፈኞችን በተለያየ መንገድ ሲያሰቃዩ ነበር ተባለ
በዚምባብዌ መንግሥት የተቋቋመው የሰብአዊ መብት ቡድን የሃገሪቱ ወታደሮች በግልጽ የማይስተዋሉ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም የተቃውሞ ሰልፎችን ሲበትኑና አዘጋጆቹን ሲያፍኑ እንደነበረ ገለጸ።
የዚምባብዌው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንዳስታወቀው ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን ለመበተን መንግሥት ወታደሮችን መጠቀሙ የተሳሳተ እርምጃ ነበር ብሏል። የተቃውሞ ሰልፎቹ የጀመሩት ባለፈው ሳምንት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መናሩ ነበር። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የአውሮፓ ጉብኝት • ቀብሩን አዘጋጅቶ ራሱን ያጠፋው አርሶ አደር ከወደ ሃራሬ የሚሰሙ ዜናዎች እንደሚዘግቡት ወታደሮቹ ሰልፈኞች ላይ ያልታሰቡና ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ጥቃቶችን በተደጋጋሚ ፈጽመዋል። አንድ ቢቢሲ ያነጋገረው የዋና ከተማዋ ነዋሪ እንደገለጸው ወደ 30 የሚጠጉ ሰልፈኞች በድንገት በወታደሮች ተከበው ከፍተኛ ድብደባ ሲደርስባቸው ተመልክቷል። ከ14 ወራት በፊት በወታደሮች እርዳታ ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሙሉ ወታደራዊ ስልጣን መያዛቸው ደግሞ በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬን ፈጥሯል። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመውን የኃይል እርምጃ እንደማይታገሱ ገልጸዋል። የሰብአዊ መብት ኮሚሽኑ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እስካሁን 8 ሰዎች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን የሞታቸው ምክንያት ደግሞ በተፈጸመባቸው ጥቃት ነው። የተቃውሞ ሰልፎቹ በተካሄዱባቸው አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ዜጎች ደግሞ ዋነኛ ሰለባዎች ነበሩ ብሏል ሪፖርቱ። • መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች • ሱዳን ሁለት የውጪ ሃገር ጋዜጠኞችን አገደች የዚምባብዌ መከላከያ ኃይል አባላትና የሪፐብሊኩ ፖሊስ ሃይል አባላት አንድ ላይ በመሆን በፈጸሙት የማሰቃየት ተግባር እድሜያቸው እስከ 11 ዓመት የሚደርሱ ህጻናትም ጭምር በሌሊት ከቤታቸው ተወስደው መሬት ላይ እንዲተኙ በማድረግ ድበደባና ማሰቃየት ደርሶባቸዋል ሲል ኮሚሽኑ አገኘሁት ያለውን መረጃ ይፋ አድርጓል። ምንም እንኳን የሰብአዊ መብት ኮሚሸኑ የሟቾች ቁጥር 8 ነው ቢልም አንዳንድ ሰዎች ግን በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 12 ይደርሳል በማለት ይከራከራሉ።
news-46834060
https://www.bbc.com/amharic/news-46834060
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ከቀረበበት የመድፈር ክስ ጋር በተያያዘ የዘረመል ናሙና እንዲያቀርብ በፖሊስ ታዘዘ
የላስ ቬጋስ ፖሊስ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ከቀረበበት የመድፈር ክስ ጋር በተያያዘ የዘረመል ናሙና እንዲያቀርብ የሚያዝ ደብዳቤ ከፍርድ ቤት ማህተም ጋር አያይዞ እንዳስገባ ተገለጸ።
የ33 ዓመቱ ጠበቃ የሆኑ ፒተር ክሪስቲያንሰን እንደገለጹት የፖሊስ ጥያቄ የተለመደና በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች የሚያገለግል የህግ አሰራር ነው ብለዋል። 'ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል' የተባለ ጋዜጣ እንደዘገበው የላስ ቬጋስ ፖሊስ ጥያቄ እሱ በሚጫወትበት ሃገር ጣልያን ለሚገኝ ፍርድ ቤት ተልኳል። በጎርጎሳውያኑ 2009 ዓ.ም. ፈጽሞታል ተብሎ የቀረበበትን ክስ የጁቬንቱሱ የፊት መስመር ተጫዋች ጉዳዩ ሀሰት ነው በማለት ተከራክሯል። • ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘች • የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ • ሞርጋን ፍሪማን በፆታዊ ትንኮሳ ለቀረበባቸው ውንጀላ ይቅርታ ጠየቁ በ2009 የተከሰተው ጉዳይ በሁለቱም መካከል በመፈቃቀድ ነው እንጂ ደንበኛዬ ምንም አይነት አስገድዶ ያደረገው ነገር የለም ብሏል ጠበቃው። 'ዴር ስፒግል' የተባለ የጀርመን ጋዜጣ ነበር ማዮርጋ የተባለችው ሴት ለላስ ቬጋስ ፖሊስ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ክስ መመስረቷን ለመጀመሪያ ጊዜ የዘገበው። እንደ ጋዜጣው ከሆነም ማዮርጋ በጎርጎሳውያኑ 2010 ክሪስቲያኖ ሮናልዶ 375 ሺ ዶላር እንዲከፍላት ተስማምታ ነበር። የሮናልዶ ጠበቃ እንደሚለው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ የቀረቡት ማስረጃዎች በሙሉ የውሸትና የተቀነባበሩ ናቸው። ወይዘሪት ማዮርጋና ሮናልዶ በ2009 በላስቬጋስ ፓልም ሆቴልና ቁማር ቤት በሚገኘው ሬይን የምሽት ጭፈራ ቤት ይገናኛሉ። ከዚያም ጨዋታ ሲደራ ሮናልዶ ወደ ራሱ ማደሪያ እንደወሰዳትና እንደደፈራት ገልጻ ነበር።
news-47565534
https://www.bbc.com/amharic/news-47565534
ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን በሙሉ አገደ
የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ አሰቃቂው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተከሰከሰበት ቦታ ላይ አዳዲስ መረጃዎች በመገኘቱ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን በሙሉ አግዷል።
ኩባንያው እንዳሳወቀው ያሉትን 371 አውሮፕላኖቹን አግዷል። የአሜሪካ ፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር እንደገለፀው አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ የተገኙ አዳዲስ መረጃዎችና የተጣሩ የሳተላይት ምስሎች አስተዳደሩ በጊዜያዊነት የእግድ ውሳኔውን እንዲያስተላልፍ አድርጎታል። •እንግሊዝ ቦይንግን ከበረራ ካገዱት ሃገራት ተቀላቀለች በርካታ ቁጥር ያላቸው ሀገራት ቦይንግ 737-8 ማክስን ሲያግዱ አስተዳደሩ እምቢተኝነት ማሳየቱ የሚታወስ ነው። እለተ እሁድ መጋቢት 1 ቀን ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ሲበር የነበረው ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ለ157 ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት ሆኗል። •ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው ከአምስት ወራት በፊት የኢንዶኔዥያ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737-8 ማክስ ተከስክሶ 189 ሰዎች ከሞቱበት አደጋ ቀጥሎ አስከፊው ነው ተብሏል። የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ያገኘው መረጃ ምንድን ነው? አስተዳደሩ ከብሔራዊ የትራንስፖርት ጥበቃ ቦርድ ጋር በመተባበር አደጋውን የሚመረምር ቡድን የላኩ ሲሆን፤ የድርጅቱ ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ዳን ኤልዌል በትናንትናው ዕለት በሰጡት መግለጫ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራው ዱካ ከላየን አየር መንገድ ጋር ተመሳሳይ ነው" በተጨማሪም የመከስከስ አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ የተገኙት መረጃዎች በላየን አየር መንገድ ከደረሰው ዕጣ ፈንታ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አሳይ ነው ብለዋል። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው አስተዳደሩ በአደጋው ስፍራ ላይ ባገኘው አዳዲስ እንዲሁም ቁሳዊ መረጃዎችን፤ ከሌሎች ቦታዎችም የተገኙ መረጃዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት አስቸኳይ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፍ ተናግረው ነበር። ቦይንግ 737-8 ማክስን በማገድ አሜሪካና ብራዚል የእንግሊዝ፣ ቻይና፣ ህንድና አውስትራሊያን ፈለግ ተከትለዋል። በትላንትናው እለት የካናዳ ትራንስፖርት ሚኒስትር ስለ አደጋው አዲስ መረጃ አግኝቻለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖቹን አግዳለች። እንደ መረጃውም በቅርቡ የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8ና ካናዳ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ያሉት 737 ማክስ አውሮፕላኖች ተመሳሳይ የበረራ ሁኔታን ማሳየታቸውን ይፋ አድርገዋል።
54308134
https://www.bbc.com/amharic/54308134
ትራምፕ በአሜሪካ ጽንስ ማቋረጥ ወንጀል ሊሆን እንደሚችል ጠቆሙ
ፕሬዝደንት ትራምፕ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እአአ 1973 ላይ ጽንስ ማቋረጥን ሕጋዊ ያደረገውን ውሳኔ ተመልሶ ሊያጤነው እንደሚችል ጠቆሙ።
ትራምፕ በእሳቸው እጩነት የቀረቡት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የጽንስ ማቋረጥ ሕጋዊነትን ፍርድ ቤቱ ደግሞ እንዲያይ በማድረጉ ላይ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ኤሚ ባሬት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አድርገው ሲመርጡ ስለ ጽንስ ማቋረጥ ሕግ ዙሪያ ቀድመው እንዳልተወያዩ ተናግረዋል። ኤሚ ባሬት "በአመለካከቷ ወግ አጥባቂ ነች" ብለዋል ትራምፕ። በትራምፕ እጩ ሆነው የቀረቡት ወግ አጥባቂዋ ኤሚ ባሬት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እአአ 1973 ላይ ጽንስ ማቋረጥ ሕጋዊ ነው ብሎ የወሰነውን ውሳኔ እንዳያሽሩት ስጋት እንዳላቸው የሴቶች መብት ተከራካሪ ዴሞክራቶች ይናገራሉ። የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 9 የሕይወት ዘመን ዳኞች ያሉት ሲሆን የኤሚ ባሬት ሹመት የሚረጋገጥ ከሆነ ከአጠቃላይ 9 የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች መካከል የወግ አጥባቂ ዳኞች ብዛት ወደ 6 ከፍ ይላል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ ሆነው የሚሾሙ ዳኞች ሙሉ የዕድሜ ዘመናቸውን ማገልገል ይችላሉ። በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚያስተላለፉት ውሳኔም በአገሪቱ ፖሊስ እና ስትራቴጂዎች ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ነው። ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቅርቡ ካስተላለፋቸው ውሳኔዎች መካከል በሁሉም 50 የአሜሪካ ግዛቶች የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን መፍቀድ እና ትራምፕ አስተላልፈው የነበረውን የጉዞ ገደብ ማስቆም ተጠቃሽ ናቸው። እአአ 1973 ላይ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጽንስ ማቋረጥ ሕጋዊ ነው ሲል 7 ለ2 በሆነ ድምጽ ወሰኗል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ ውሳኔ የደረሰው ሴቶች እርግዝናን የማቋረጥ መብታቸው ከግል የፍላጎት ነጻነት የሚመነጭ መሆኑ እና ይህም በአሜሪካ ሕገ-መንግሥት ውስጥ የተንጸባረቀ ነው በማለት ነው። ኤሚ ባሬት ኤሚ ኮሬት ባሬት ማን ናቸው? የ48 ዓመቷ ዳኛ ጠንካራ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ናቸው። ጽንስ ማቋረጥን አጥብቀው ይቃወማሉ። ከዚህ ቀደም በጻፉት ጽሑፍ ላይ የሰው ልጅ ሕይወት የሚጀምረው ከተጸነሰበት ቅጽበት ጀምሮ ነው ብለዋል። ስለዚህ ጽንስ ማቋረጥ ከንፍስ ማጥፋት አይተናነስም ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ የዳኛዋ አቋም በአሜሪካ ጽንስ ማቋረጥ ሕጋዊ መሆኑ እንዲቀር በሚሹ ሰዎች ዘንድ ደስታን ፈጥሯል። ኢንዲያና ግዛት ውስጥ ከሚገኘው ኖተር ዳም ዩኒቨርሲቲ በሕግ የተመረቁት ዳኛ የትራምፕ ጠንካራ የጸረ- ስደተኞች ፖሊስ ደጋፊ መሆናቸው ይነገራል። አሜሪካውያን የጦር መሳሪያ የመታጠቅ መብት አላቸው የሚል ጽኑ አቋም እንዳላቸውም ይገለጻል። የ7 ልጆች እናት የሆኑት ኤሚ ቤሬት በተማሩበት ዩኒቨርሲቲም ለ15 ዓመታት አስተምረዋል።
news-53237139
https://www.bbc.com/amharic/news-53237139
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ከአዲስ አበባ ወደ ትውልድ ቦታው አምቦ ተመለሰ
በፖለቲካዊ ግጥሞቹ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ በትናንትናው ዕለት በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ ተቃውሞዎች ተከስተዋል።
የአርቲስቱ አስከሬን በበርካታ አድናቂዎቹ ታጅቦ ወደ አምቦ ሲያመራ የነበረ ቢሆንም በተገደለባት አዲስ አበባ አስከሬኑ ማረፍ አለበት የሚሉ ተቃውሞዎችም ነበሩ። አስከሬኑ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ኦሮሞ ባህል ማዕከል መወሰዱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰቦች አረጋግጠዋል። በአሁኑ ሰዓት ወደ ትውልድ ቦታው አምቦ ተወስዶ ወላጆቹ ቤትም ይገኛል። በተያያዘ ዜናም የፌዴራል ፖሊስ የ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦኤምኤን) አዲስ አበባ ስቱዲዮ "ጥሶ በመግባት ሠራተኞቹን እንዳሰረበት" የቴሌቪዥን ጣቢያው ይፋዊ በሆነው ፌስቡክ ገጹ ገልጿል። ድምጻዊ ሃጫሉ በጥይት ተመትቶ መገደሉ ከተሰማ በኋላ በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን በመላው አገሪቱም የኢንተርኔት መቋረጥ ተከስቷል። የተቃውሞ ሰልፍ ከተካሄደባው ከተሞች መካከል አዳማ አንዷ ስትሆን በከተማዋ አንዳንድ የመንግሥት ህንጻዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው የዓይን ምስክሮች ለቢቢሲ ሪፖርተሮች ገልጸዋል። የአዳማ የሆስፒታል ምንጮች ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንዳረጋገጡት ወደ ሆስፒታል በጥይት ተመትተው የመጡ ሰዎች ሲኖሩ የሶስት ሰዎችም ህይወት አልፏል። በተጨማሪም በአዳማ ከተማ ለተቃውሞ ወደ ኦቢኤን የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲያመሩ የነበሩ ሰልፈኞች በጸጥታ ኃይሎች የተበተኑ ሲሆን፤ አንድ ሰው መቁሰሉን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። ቢቢሲ ከጭሮ ማረጋገጥ እንደቻለው ሁለት ተቃዋሚ ሰልፈኞ በጥይት ተመትተው ሲሞቱ የመንግሥት ሕንጻዎችም ተቃጥለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የትውልድ አካባቢ በሆነው ጅማ ውስጥም ሰልፎች የተደረጉ መሆኑን ከቦታው ያናገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
news-51353306
https://www.bbc.com/amharic/news-51353306
ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን የገነባችውን ሆስፒታል ልትከፍት ነው
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት መዛመትን ተከትሎ ቻይና ለኮሮና ቫይረስ በብቸኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ገንብታ ጨርሳለች።
ሆስፒታሉን የገነባችው የቫይረሱ መነሻ በሆነችው ዉሃን ከተማ ሲሆን የግንባታው ስራን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ስምንት ቀናት ብቻ ነው ያስፈለጉት። ሆዎሸንሻን የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሆስፒታል አንድ ሺ የህሙማን አልጋዎች አሉት። ቻይና ከዚህ ሆስፒታል በተጨማሪ ለኮሮናቫይረስ ህሙማንን ብቻ የሚያክሙ ሆስፒታሎችን በመገንባት ላይ ናት። በመላው ቻይና በተስፋፋው ኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እስካሁን 17 ሺ የደረሰ ሲሆን ለ361 ህይወት መቀጠፍም ምክንያት ሆኗል። ኮሮናቫይረስ ለቻይና ብቻ ሳይሆን ለዓለም ስጋት መሆኑ ቀጥሎ ፊሊፒንስ ውስጥ አንድ ግለሰብ በቫይረሱ ህይወቱ ማለፏ ተረጋግጧል። ከቻይና ውጪ በቫይረሱ ሰው ሲሞት ይህ የመጀመሪያው ነው። የ44 ዓመቱ ቻይናዊ ግለሰብ ከዉሃን የመጣ ሲሆን፤ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው ግለሰቡ ፊሊፒንስ ከመድረሱ በፊት በቫይረሱ ተይዞ ነበር። ይህንንም ተከተሎ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ሌሎች በርካታ አገራት ከቻይና የሚመጡ በረራዎችን አግደዋል። ነገር ግን የአለም ጤና ድርጅት በረራዎችን ማገድ ከሚጠቅመው በላይ ሊጎዳ እንደሚችል ምክሮችን እየለገሰ ነው። መረጃዎች እንዳይተላለፉ እንቅፋት ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የህክምና ቁሳቀሱሶች በቀላሉ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፤ እንዲሁን አጠቃላይ የአገራትን ኢኮኖሚ ይጎዳል። ከዚህ በተጨማሪም ተጓዦች በህገወጥ መንገድ ድንበሮችን እንዲያቋርጡ በር ስለሚከፍት የቫይረሱን በፍጥነት የመዛመቱን ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻቅበው ይችላል ይላል ከአለም ጤና ድርጅት የተገኘው መረጃ። አለም አቀፍ በረራ እግዶችን ተከትሎ ቻይና የአለም ጤና ድርጅትን ምክር የተላለፈ ነው በማለት ተችታዋለች። ከቻይና የጤና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እንዲሁም ከቻይና ውጭም 150 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውም ተረጋግጧል። በሁቤ ግዛት በምትገኘው ዉሃን ከተማም ሆስፒታሎች በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ የመጣውን የህሙማንን ቁጥር ለማከም ከአቅማቸው በላይ ነውም ተብሏል። ከሰሞኑም የሆንግ ኮንግ ዶክተሮች ቻይናን የሚያገናኘው ድንበር ሊዘጋ ይገባልም በሚል አድማ መትተዋል። የቻይና ባለስልጣናት ግን በአለም ጤና ድርጅት ምክር መሰረት ድንበሩ እንደማይዘጋና መመርመሪያ ቦታዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ነገር ግን የቻይና ባለስልጣናትን ምላሽ አጥጋቢ አይደለም ያሉት እነዚህ ዶክተሮች ቻይና የጠየቁትን የማታደርግ ከሆነ ከነገ ጀምሮ ዶክተሮችም ሆነ ነርሶች የህክምና አገልግሎት ለመስጠት በቦታቸው ላይ እንደማይገኙ ነው። ከሰሞኑም የዓለም የጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ የወቅቱ አሳሳቢ የምድራችን የጤና ስጋት ነው ሲል አውጇል። • በኮሮናቫይረስ ሳይያዙ አይቀሩም ተብለው የተጠረጠሩ 4 ሰዎች በአዲስ አበባ ተገኙ •ኤርትራ አሜሪካ የጣለችው የቪዛ እገዳ አግባብነት የለውም አለች የድርጅቱ ዋና ዳይሬክትር ዶክትር ቴድሮስ አድሃኖም ይፋ እንዳደረጉት ለዚህ ውሳኔ ዋነኛው ምክንያት "በቻይና የተከሰተው ነገር ሳይሆን በሌሎች አገሮች እየሆነ ያለው ነው" ብለዋል። የዓለም የጤና ድርጅት የበሽታ ወረርሽኝ ተከስቶ ከዚህ አይነት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ይህ ስድስተኛው ሲሆን ከዚህ ቀደም ኤችዋን ኤን ዋን የተባለው ኢንፍሉዌንዛ፣ ኢቦላ፣ ፖሊዮ፣ ዚካና በድጋሚ የተከሰተው ኢቦላ ምክንያት ነበሩ። በሽታው ሲጀምር በትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ተከትሎት ይከሰታል፤ ከዚያም ከሳምንት በኋላ የትንፋሽ ማጠርን በማስከተል አንዳንድ ህሙማንን የሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያስፈልጋቸው ሊያደርግ ይችላል። በአራት ሰዎች ላይ ከሚከሰተው ይህ በሽታ አንዱ እጅግ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ። በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ማስነጠስና የአፍንጫ ፈሳሽ ላይታይበት ይችላል። የኮሮናቫይረስ ቀለል ካለ የጉንፋን ምልክቶች አንስቶ እየከፋ ሲሄድ እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። በሽታው የተያዙ ሰዎችን ለሞት እስከሚዳርጋቸው የተወሰነ ጊዜን ስለሚወስድ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል የተወሰኑት እስካሁንም ሊሞቱ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል። በተጨማሪም ምን ያህል እስካሁን ያልተመዘገቡ በበሽታው የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ማወቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።
news-51052196
https://www.bbc.com/amharic/news-51052196
ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያለው ከውሃ የሚሰራው ምግብ
የፊንላንድ ተመራማሪዎች ከምንም ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያለው ምግብ በማምረት ላይ ናቸው።
ምርቱም በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ከአኩሪአተር ከሚሰሩ ምግቦች ጋር በዋጋ መፎካከር እንደሚጀምር ይጠበቃል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ለዚህ ፕሮቲን ምርት ጥቅም ላይ የሚውለው ኤሌክትሪክ ከጸሀይ ብርሀን አልያም ከንፋስ ኃይል የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ምንም አይነት ጎጂ ንጥረ ነገሮችን ወደ ከባቢ አየር ሳይለቁ ማምረት ይቻላል። የእነዚህ ተመራማሪዎች ስራ ሙሉ በሙሉ ውጤታማ የሚሆን ከሆነ ከግብርና ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት ሁነኛ አማራጭ እንደሚሆን ይታሰባል። በአሁኑ ሰዓት ተመራማሪዎቹ የምርምር ስራቸውን ለማከናወን 5.5 ሚሊየን ዩሮ የሚደርስ ገንዘብ ፈሰስ ለማድረግ የተስማሙ ባለሃበቶች ያሉ ሲሆን በኤሌክትሪክ ዋጋ ላይ ተመስርተው ደግሞ ከአኩሪ አተር የሚሰሩ ምግቦችን የመተካት ዓላማ ሰንቀዋል። ከምንም ማለት በሚቻል መልኩ የሚሰራው የፕሮቲን ዱቄት ምንም አይነት ጣእም የሌለው ሲሆን ተመራማሪዎቹም ቢሆኑ ሆነ ብለን ነው ምላስ ላይ ሊስተዋል የሚችል ጣእም እንዳይኖረው ያደረግነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ በትልልቅ የእርሻ ማሳዎች ውስጥ የሚመረቱ እንደ አኩሪ አተር ያሉ ተክሎችን ፍሬዎች የሚመገቡ ከብቶችም ቢሆኑ ይህንን የፕሮቲን ዱቄት መኗቸው ቢያደርጉ ላቅ ያለ ውጤት እንደሚገኝበት ተመራማሪዎቹ ያስረዳሉ። ምናልባት ይህ ፕሮቲን በከፍተኛ ደረጃ ተመርቶ የዓለማችንን የምግብ ፍላጎት የመቅረፍ እድሉ ዝቅተኛ ቢሆንም ዓለማችን ወዴት እየሄደች እንደሆነ ማሳያ ሊሆን የሚችል እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል። ሙሉ በሙሉ በቤተ ሙከራዎች ውስጥ ምንም አይነት አፈርም ሆነ ተፈጥሯዊ ሂደቶችን ያልተከተሉ የምግብ ምርቶች የወደፊቱ ተስፋችን ሊሆኑ እንደሚችሉ ይሄ ምርት ጠቋሚ ነው ብለዋል። እ.አ.አ. በ 1960ዎቹ ወደ ጠፈር ለሚጓዙ ባለሙያዎች ተብሎ ምርምሩ የተጀመረው ይህ የምግብ አማራጭ በ 2022 ሙሉ በሙሉ ለምግብነት ብዙ ሆኖ ለገበያ እንደሚቀርብ ይጠበቃል። ነገሮች ሁሉ በታሰበላቸው የሚሄዱ ከሆነና የምርቱ ፍላጎት ከፍተኛ ከሆነ ደግሞ በ 2025 ትልቅ ማቀነባበሪያ ለመክፈት ታስቧል። 'ሶሌይን' የሚል ስያሜ የተሰጠው የፕሮቲን ዱቄት የማምረት ሂደት ኤሌክትሮሊሲስ የሚባል ሂደትን በመከተል ውሃን ለሁለት በመክፈል ይጀምራል። በዚህ ጊዜ ሄይድሮጂኑ ከውሃው ተለይቶ ይወጣል። በመቀጠልም ሃይድሮጂኑን፣ ከአየር የሚገኘውን ካርቦን ዳይኦክሳይድና ሌሎች ንጥረ ነገሮች አፈር ውስጥ የሚኖሩት ባክቴሪያዎች እንዲመገቡት ይደረጋል። ታዲያ መጨረሻ ላይ ባክቴሪያዎቹ የፕሮቲን ዱቄቱን ያመርታሉ። ይህን ምርት ለማምረት ከፍተኛ ግልጋሎት የሚሰጠው ኤሌክትሪክ ደግሞ ዋጋው በቀነሰና ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ መገኘት ሲጀምር የፕሮቲን ዱቄቱ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ተመራማሪዎቹ ይገልጻሉ። ግብርና እና አሳ ማጥመድ ዓለማችንን በከፍተኛ ሁኔታ እየበዘበዙ ነው ብለው የሚያምኑት ተመራማሪዎቹ ይህ ምርት ብዙ ነገሮችን ቀላል እንደሚያደርግ ተስፋ ሰንቀዋል። ''የምግብ ምርት ዓለማችንን በአስፈሪ ሁኔታ እያራቆታት ነው። በፍጥት እየተቀየረ የመጣው የአየር ጸባይም ቢሆን ለግብርና ተብሎ ከሚጨፈጨፈው ደን ጋር በቀጥታ ይገናኛል'' ብሏል ከተመራማሪዎቹ አንዱ። አክሎም ''ምድራችን ወደፊት ለሰዎች መኖሪያነት ምቹ ሆና ትቀጥላለች ብዬ አላስብም። ይህን መሰል ግኝቶች ግን ተስፋ ይሰጡኛል'' ብሏል።
news-48101931
https://www.bbc.com/amharic/news-48101931
የአይ ኤስ መሪ ከአምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ታየ
የኢስላማዊ ታጣቂ (አይ ኤስ) ቡድን መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ ድምጹን ካጠፋ ከአምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክቱን አስተላልፏል። ቡድኑ ለተነጠቃቸው ይዞታዎችም የበቀል እርምጃ እንደሚወስድ ዝቷል።
በአውሮፓውያኑ 2014 ሞሱል በተባለችው የሶሪያ ከተማ ውስጥ ሆኖ በሶሪያና ኢራቅ ላይ እስላማዊ ካሊፌት መመስረቱን ካወጀ በኋላ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ቀርቶ ነበር። • በኢራቅ እስላማዊ ቡድኑ 200 የጅምላ መቃብሮችን ትቶ መሄዱን የተባበሩት መንግሥታት ተናገረ • የአይኤስ ታጣቂዎች ኢትዮጵያዊያንን ገደሉ በተንቀሳቃሽ ምስሉ በቅርቡ በባጉዝ ያጋጠማቸውን ሽንፈት ያመነ ሲሆን መልዕክቱ መቼ እንደተቀረጸ ግን እርግጠኛ መሆን አልተቻለም። ቡድኑ በበኩሉ ተንቀሳቃሽ ምስሉ በያዝነው ሚያዚያ ወር ላይ የተቀረጸ እንደሆነ አስታውቋል። አልባግዳዲ በመልዕክቱ ከሁለት ሳምንት በፊት በስሪላንካ የፋሲካ በዓል ዕለት ለደረሰው የቦምብ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን ባጉዝ ላይ ላጋጠማቸው ሽንፈት ምላሽ እንደሆነ አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም አልባግዳዲ የሚመራው ቡድን በቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ፣ ሱዳንና አልጄሪያ ባሉ የአፍሪካ ሃገራት ስላለው ወታደራዊ ግንኙነትና መታወጅ ስላለበት ኢስላማዊ ጂሃድ መልዕክቱን አስተላልፏል። ቡድኑ ምንም እንኳን በተለያዩ ግዛቶች ሽንፈትን ቢቀምስም የዚህኛው ተንቀሳቃሽ ምስል ዋነኛ ግቡ ሽንፈቶቹን ለመቀበል ሳይሆን አልባግዳዲን ለገደለ 25 ሚሊየን ዶላር ሽልማት ከመኖሩ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ሳይሞት አይቀርም ማለታቸውን ለማስተባበል ይመስላል።
42503301
https://www.bbc.com/amharic/42503301
በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት አንዳንድ ስልኮች ዋትስአፕን አያስጠቅሙም
በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት መልዕክት መላላኪያው ዋትስአፕ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ዕለት (ታህሣሥ 23) ጀምሮ በተወሰኑ የእጅ ስልኮች ላይ መስራት እንደሚያቆም እየተነገረ ነው።
እንደ ዋትስፕ ይፋዊ ድረ-ገጽ ከሆነ፤ ብላክቤሪ ስሪት ሆነው ስልኩ የሚሰራበት ሥርዓት (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) 10 እና የዊንዶውስ ስልክ ስሪት ሆነው ስልኩ የሚሰራበት ሥርዓት 8.0 ከሆነ ስልኮቹ ከዋትስፕ መተግበሪያ ጋር መጣጣም አይችሉም። ከእነዚህ በተጨማሪም የሚከተሉት የሞባይል ስልኮች ላይ ዋትስአፕ እንደማይሰራ ተነግሯል፤ አንድሮይድ 2.3.3 በፊት የነበሩ ስሪቶች፣ ዊንዶውስ ፎን 7፣ አይፎን 3GS ወይም አይፎን ስልክ ሆኖ ስልኩ የሚሰራበት ሥርዓት 6 ከሆነ እንዲሁም ኖኪያ ሲይምቢያን S60 ዋትስአፕን ማስጠቀም አይችሉም። ኩባንያው ኖኪያ S40፣ እንዲሁም አንድሮይድ የአሰራር ሥርዓት 2.3.7 የሚጠቀሙ ስልኮች ዋትስአፕን ተግባራዊ ለማድረግ እንደማይቻላቸው አስታውቋል። ይህም ማለት ምንም እንኳ እነኚህን ስልኮች የሚጠቀሙ ሰዎች መልዕክት መላክና መቀበል ቢችሉም አንዳንድ የመተግበሪያዎችን መጠቀም አይቻላቸውም። ለምሳሌ መተግበሪያው (አፕሊኬሽን) አንድ ጊዜ ስልኩ ላይ ከተጫነ በኋላ አዲስ አካውንት መክፈትም ሆነ ለውጥ ማድረግ አይቻልም። ኩባንያው ተጠቃሚዎች አንድሮይድ 4.0፣ ዊንዶውስ ፎን 8 እንዲሁም ኤይኦኤስ 7 እና ከዚያ በላይ የአሰራር ሥርዓትን የሚጠቀሙ ስልኮችን እንዲገዙ ያበረታታል። የኩባንያው መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ዋትስአፕን በተገቢው ሁኔታ ይጠቀማሉ። ቴሌግራምና ስናፕቻትን የመሳሰሉ ሌሎች የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎች ገበያው ላይ ቢኖሩም ዋትስአፕ በዓለማችን በጣም ታዋቂው የመልዕክት መላላኪያ መሣሪያ እንደሆነ ይታመናል። ኩባንያው በየጊዜው ለመተግበሪያው ማሻሻያ በማድረግ ተጠቃሚዎችን ከጊዜው ጋር ለማራመድ ይሞክራል ተብሏል።
news-44718735
https://www.bbc.com/amharic/news-44718735
"መንግሥት የሚደግፈው የሙስሊሙን ሕብረተሠብ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የሚወክል ትልቁ የአስተዳደር እርከን ተደርጎ ይታሰባል። ሆኖም ይህ መጅሊስ ለዓመታት የፖለቲካ ገለልተኛንትና የውክል ጥያቄ ሲነሳበት ነው የኖረው።
ይህንንና በርካታ ሌሎች የመብት ጥያቄዎችን ለመመለስ በሕዝበ ሙስሊሙ ተቋቁሞ የነበረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ከዓመታት በፊት ከመንግሥት ጋር ንግግር ጀምሮ የነበረ ሲሆን ወደ ኋላ ላይ ግን በሽብር ክስ አባላቱ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን እና ከቅርብ ወራት በፊት ከእስር የተፈቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በጽሕፈት ቤታቸው ጠርተው አወያይተዋል። ዶክተር ዐብይ በሁለት ፈረቃ ነበር ሁለቱን አካላት ያነጋገሩት። "በውይይቱ ወቅት ይዛችሁ የገባችኋቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች ምን ነበሩ?" በማለት የኢትዮጵያ ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባልና የኮሚቴው ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ አህመዲን ጀበልን ቢቢሲ ጠይቋቸው ነበር። እሳቸውም ሲመልሱ፣" መጅሊስ የሕዝበ ሙስሊሙ ተቋም ቢሆንም፤ በተግባር ደረጃ ግን ላለፉት ዓመታት የማኅበረሰቡ የቅሬታ ምንጭ ሆኖ መዝለቁን" ካብራሩ በኋላ "ይህም የሆነው ተቋሙ ህዝቡ እንደሚፈልገውና ሕጉ እንደሚፈቅደው ምርጫ አለማካሄዱ፤ የመንግስት ጣልቃ ገብነት መኖሩ ነበር" ብለዋል። በተለይም ከዐብይ አሕመድ በፊት የነበረው የመንግሥት አስተዳደር በተለያዩ ጊዜያትና በተደጋጋሚ የደህንነት አካላቱ ዛቻ፣ ማስፈራሪያና ሁሉን አቀፍ ጣልቃ ገብነት ተለይቷቸው እንደማያውቅ አቶ አሕመዲን ያስረዳሉ። የፌዴራል ጉዳዮችም ተመሳሳይ ችግር ይፈጥር እንደነበር አስታውሰዋል። የዛሬ 10 ዓመት በዶክተር ጀይላን ከድርና ሙፍቲህ ሀጅ ዑመር ኢድሪስ መሪነት ልዩነቶችን ለመቅረፍ ውይይት ተደርጎ በደኅንነት ሰዎች እንዲመክን መደረጉንም አውስተዋል። ሀጂ ዑመር ኢድሪስ ያኔ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮችና የኢትዮጵያ ኡለማ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት መሆናቸውን ተናግረው "በነአባይ ጸሐዬና በደህንነቶች ተገምግመው ነው በወቅቱ አርፈህ ተቀመጥ የተባሉት" ይላሉ አቶ አሕመዲን፣ በወቅቱ የደህንነቱ ጣልቃ ገብነት እስከምን ደረጃ ድረስ እንደነበር ሲያስረዱ። አዲሱ መጅሊስ እንዴት ይዋቀር? በትናንቱ ውይይት በርካታ ጉዳዮች ቢነሱም በዋናነት ግን የውይይቱ ትኩረት የነበረው የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የመጅሊሱ ጉዳይ ነበር ብለዋል። እንደ አቶ አሕመዲን ገለጻ በመጅሊሱ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ያስፈለገው አንድ ጊዜ ጠንካራ መጅሊስ ከተቋቋመ ሌሎች የሙስሊሙ ጥያቄዎች በዚያው እንደሚመለሱ ታሳቢ በመደረጉ ነው። "ሁሉንም የሚያስማማ መጅሊስ ካለ፤ መንግስትም ለራሱ ሲል ይመልሰዋል፤ የሙስሊሙንም ጥያቄ እናንተ ትመልሱታላችሁ ወደሚለው ሃሳብ ስለተደረሰ ትኩረታችንን ወደ መጅሊሱ አድርገን ነበር" ይላሉ አቶ አሕመዲን። በውይይቱ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አንድ ቀን ቀደም ብለው ከመጅሊሱ አመራሮች ጋር ውይይት እንዳደረጉና ችግሩ በተግባር እንዳለ ጠቅሰው ነበር። በውይይቱ ወቅት አንዳንድ የመጅሊሱ አባላት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴውን ለማጥላላት ሙከራ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል። "የፖለቲካ ዓላማ አላቸው፤ አክራሪዎች ናቸው ሲሉ" ከሰውን ነበር ያሉት አቶ አሕመዲን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን "አሁን እንዲህ ዓይነት ወሬ የምናወራበት ጊዜ አይደለም" ሲሉ የመወቃቀስ አዝማሚያውን ተችተዋል። "እናንተ ላይ ጥያቄ የሚያነሳ የህብረተሰብ ክፍል አለ፤ ስለዚህ ኮሚቴው ሌላ አላማ አለው ብላችሁ መነሳት አትችሉም። ሌላ አላማ ቢኖራቸውም፤ እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው ተደራጅተው መጠየቅ መብታቸው ነው" በማለት ጠንካራ ወቀሳ በመጅሊሱ አመራሮች ላይ መሰንዘራቸውን ገልጸዋል። ዶክተር ዐብይ በጉዳዩ ላይ የመንግሥትን ገለልተኝነት አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውንም ከአቶ አሕመዲን ጀበል ሰምተናል። "መንግስት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ላይ ያላችሁትን መሪዎች አይደግፍም፤ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴውንም አይደግፍም፤ መንግሥት የሚደግፈው የሙስሊሙን ህብረተሰብ ነው" ማለታቸውን አቶ አሕመዲን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚመጥን ተቋም መፈጠር አለበት" ማለታቸውን አቶ አህመዲን ጨምረው ነግረውናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቀደም ብሎ መጅሊሱን ሲደግፉ የነበሩ የመንግስት አካላትን ክፉኛ ከወቀሱ በኋላ "መንግሥት እንዲህ አይነት ጉዳዮች ላይ እጁን አስገብቶ አንዱን የሃይማኖት ተቋም ደግፎ ሌላውን ነቅፎ መቆየቱ ስህተት ነበር" ብለዋል። "እኔ እስካለሁ ድረስ እንዲህ ዓይነት ነገሮች አይኖሩም" ሲሉም ማረጋገጫ ሰጥተዋል። በውይይቱ ማጠናቀቂያ "አሁን ያሉት የመጅሊሱ አባላት በህጋዊ መንገድ ሳይሆን በመንግስት ፈቃድ ነው የተመረጡት፤ ስለዚህ የሽግግር መጅሊስ ይቋቋም" ብለን ሃሳብ አቅርበን ነበር ያሉት አቶ አህመዲን፤ ሃሳባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳልወደዱትና ከዚያ ይልቅ ለሁሉም ችግሮች የመፍትሄ ሐሳብ የሚያቀርብ አዲስ ጊዜያዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ የመፍትሄ ሃሳብ ይዞ እንዲቀርብ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል። የዚህ ኮሚቴ ዋና ሥራ ምንድነው በሚል ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄም አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። "አዲሱ ኮሚቴ የኢትዮጰያ እስልምና ጉዳዮች እንዴት ቢዋቀር የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ችግር መፍታት ይችላል? ሁሉም ሰው የሚወደውና የሚፈልገው ዓይነት መጅሊስ እንዴት ማቋቋም ይቻላል? የመጅሊስ ምርጫ የትና እንዴት ይደረግ? የሚሉትን ትያቄዎች አጥንቶ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ነው የተቋቋመው።" አዲሱ ኮሚቴ በአገር ውስጥና ከኢትዮጵያ ውጪም ቢሆን በመንቀሳቀስ የሌሎች አገሮችን የመጅሊስ አወቃቀር ልምድ በማየት ያለቀለት ነገር ይዞ ማቅረብ ነው ስራው የሚሆነው ሲሉም አክለዋል። አቶ አሕመዲን ጀበል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቀደም ብሎ የተቋቋመው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አዲስ በሚመሠረተው መጅሊስ ምንም ዓይነት የሥልጣን ፍላጎት የለውም።
news-47952556
https://www.bbc.com/amharic/news-47952556
ባህሬን የ138 ሰዎችን ዜግነት ነጠቀች
በባህሬን የሚገኝ ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 139 ሰዎችን ወደ ማረሚያቤት እንዲገቡ በመወሰን 138ቱ ደግሞ የባህሬን ዜግነታቸውን ነጥቋል።
69 ሰዎች የሞት ፍርድ ሲበየንባቸው ቀሪዎቹ ደግሞ ከሶስት እስከ ሰባት ዓመት ድረስ ተፈርዶባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። የሱኒ እስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆነችው ባህሬን፣ የሺያ ተከታይ የሆነችው ኢራንን ከመሰሎቿ ጋር በመሆን በባህሬን መረጋጋትና ሰላም እንዳይኖር እየሠራች ነው የሚል ውንጀላ አቅርባ ነበር። • ኬንያዊቷ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሞታ ተገኘች • መንግሥትን ተሳድቧል የተባለው ደራሲ ተከሰሰ 58 ተጠርጣሪዎች በሌሉበት የፍርድ ሂደቱ የተከናወነ ሲሆን የባህሬን ዜግነታቸውን የተነጠቁት ሰዎች መጨረሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም። ባሳላፍነው መስከረም ነበር የባህሬን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ''የባህሬን ሂዝቦላህ'' ከተባለው አሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 169 ሰዎች የክስ ሂደት እየተከታተለ እንደሆነ ያስታወቀው። ተጠርጣሪዎቹም ፈንጂዎችን በመቅበር፣ የግድያ ሙከራ በማድረግ፣ ንብረት በማውደምና ህገወጥ የጦር መሳሪያ በማዘዋወር ክሶች ቀርበውባቸዋል። ማክሰኞ ዕለትም ፍርድ ቤቱ ለመጨረሻ ክስ የቀረቡት 139 ተጠርጣሪዎች ላይ የእስር ፍርድ የበየነ ሲሆን 96 ተጠርጣሪዎች ደግሞ እያንዳንዳቸው ከ700 ሺ ብር በላይ እንዲከፍሉ ተፈርዶባቸዋል። ለፍርድ ከቀረቡት 138ቱ ያለምንም ይግባኝ የባህሬን ዜግነታቸው ሙሉ በሙሉ የተገፈፈ ሲሆን አንድ ግለሰብ ግን የእስር ፍርድ ብቻ ተበይኖበታል። • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የዓለማቀፉ ሰብአዊ መብት አዋጅ መሰረት ግን ማንኛውም ግለሰብ ዜግነት የማግኘት ሙሉ መብት ያለው ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ዜግነቱን መነጠቅም ሆነ ወደ ሃገሩ መግባት እንደሚችል ተደንግጓል። በአውሮፓውያኑ 2018 የባህሬን መንግስት በተመሳሳይ መልኩ ስምንት ዜጎቹን ዜግነታቸውን በመንጠቅ ወደ ኢራን አባሯቸው ነበር።
41548753
https://www.bbc.com/amharic/41548753
ትራምፕ ስደተኞችን ለማባረር አዲስ ዕቅድ እያቀዱ ነው
የትራምፕ አስተዳደር በሜክሲኮ እና በአሜሪካ መካከል ሊገነባ ከታሰበው አጨቃጫቂ አጥር ግንባታ ጀምሮ ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ታዳጊ ስደተኞችን ከሃገሪቱ ለማስወጣት የሚያስችል ሰነድ በማርቀቅ ላይ ይገኛል።
ትራምፕ ሕጋዊ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውን ስደተኞች የማስወጣት ዕቅዳቸው ይሰምር ዘንድ በሺህ የሚቆጠሩ የስደተኛ ጉዳይ ሠራተኞችን ለመቅጠር አስበዋል። ባለፈው ወር ፕሬዝደንቱ 'ዳካ' የተሰኘውን ለስደተኛ ታዳጊዎች ድጋፍ የሚሰጠውንና 800ሺህ ስደተኞች አስጠልሏል የሚባልለትን ዕቅድ እንዲቋረጥ ማድረጋቸው ይታወሳል። የዕቅዱ ይዘቶች • በሜክሲኮ እና በአሜሪካ መካከል ስደተኞች እንዳይገቡ የሚያግድ አጥር ግንባታ • 10ሺህ የስደተኛ ጉዳይ ሠራተኞችን እንዲሁም 1ሺህ የሕግ ባለሙያዎችን መቅጠር • ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን ወደ አሜሪካ እንዳያመጡ ማገድ • በኮምፕዩተር በታገዘ ዘዴ ኩባንያዎች ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞችን እንዳይቀጥሩ ማድረግ. . . የሚሉ አንቀፆችን አቅፏል። 'ዳካ' የተሰኘው ለስደተኛ ታዳጊዎች ድጋፍ የሚሰጠው ዕቅድ በቀድሞው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ዘመን 2012 ላይ በተለይ ደግሞ ከደቡብ አሜሪካ የሚመጡ ሕፃናት ለመጠበቅ ሲባል የፀደቀ ሰነድ ነበር። በሕጉ ስር የተጠለሉ ታዳጊዎች የትምህርት እና የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደርጋሉ። ወርሃ መስከረም ላይ ፕሬዝደንት ትራምፕ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ኮንግረሳቸው አዲስ ተለዋጭ ዕቅድ ካላመጣ የታዳጊዎች ሕልም አደጋ ላይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። አዲሱን የትራምፕ ዕቅድ ቀዳሚ ተሠላፊ ዴሞክራቶች በጽኑ ተቃውመውታል። ዴሞክራቷ ናንሲ ፔሎሲ እና አጋራቸው ቻክ ሹመር "አመራሮች ሕልመኛ ታዳጊዎችን የሚታደግ ዕቅድ በማርቀቅ ፈንታ ግድ የሌሽነትን የሚንያንጸባርቁ ሕጎችን ማርቀቅ ከጀመሩ፤ እኔ ከልባቸው ነው ብዬ አላስብም" ሲሉ ትችታቸውን አሰምተዋል። ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መረጃዎቻቸውን ለሃገር ውስጥ ደህንነት እና ለኤፍ.ቢ.አይ በማስረከብ በሕጉ ለመጠለል ብቁ መሆን አለመሆናቸውን ያረጋግጣሉ።
news-50178708
https://www.bbc.com/amharic/news-50178708
በርካታ ኤርትራዊያን ታዳጊዎች ሰሜን አየርላንድ ውስጥ ተገኙ
ከምሥራቅ አፍሪካ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሰሜን አየርላንድ የመጡ ናቸው የተባሉ በርካታ ታዳጊዎች ቤልፋስት ውስጥ ወደሚገኝ የህጻናት መንከባከቢያ መግባታቸው ተነገረ።
ታዳጊዎቹ ከሰሜን አፍሪካ ሀገራትና ከኤርትራ የመጡ መሆኑ የተነገረ ሲሆን አብሯቸው አንድም አዋቂ እንደሌለ ፖሊስ ገልጿል። ወደ አየርላንድ ገብተው የተገኙት እነዚህ ታዳጊዎች የተገኙት በተለያዩ ጊዜያት መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል። • ". . . ጦርነት ታውጆብን ነበር" ደብረጽዮን ገብረሚካኤል • በባንግላዴሽ ተማሪዋን አቃጥለው የገደሉ 16 ግለሰቦች ሞት ተበየነባቸው • በሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚሆን የስፖርት እንቅስቃሴ ተጀመረ ታዳጊዎች በምን መንገድ ወደ ሰሜን አየርላንድ እንደገቡ ግልጽ ያልሆነ ሲሆን፣ ምናልባትም በመርከቦች የእቃ መጫኛ ኮንቴይነር ውስጥ ተጭነው እንደመጡ ይገመታል። ፖሊስ ግን በኮንቴይነር ነው የገቡት የሚለውን በማስተባበል ታዳጊዎቹ በምን መንገድ እንደመጡ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ታዳጊዎቹ ከተገኙበት ጊዜ ጀምሮም ቤልፋስት ውስጥ በሚገኝ የጤናና ማህበራዊ እንክብካቤ በሚያደርግ ማዕከል ውስጥ እንዲቆዩ መደረጋቸው ተጠቅሷል። የሰሜን አየርላንድ ፖሊስ እንዳለው "ከተለያዩ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ጋር በመተባበር በእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ያሉት ታዳጊዎች እንዴት ያለ አዋቂ ሰው ድጋፍ እዚህ ሊደርሱ እንደቻሉ ለማወቅ እየሰራን ነው" ብሏል። "ነገር ግን ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ የታዳጊዎቹ ደህንነትን ነው" ሲል አክሏል።
news-52302705
https://www.bbc.com/amharic/news-52302705
አሰቃቂው የኢራን አስክሬን ማቆያ ክፍል ገጽታ
ይህ ቪዲዮ በመንግሥት የአስክሬን ማቆያ ክፍል የተቀረጸ ነው። በቪዲዮ ላይ ሠራተኞች በበርካታ አስክሬኖች ተከበው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ይታያሉ።
ኮሮናቫይረስ፡ በኢራን አስክሬን ማቆያ ክፍል ውስጥ ገሚሱ አስክሬን በነጭ ጨርቅ ተጠቅልሏል። ሌላው በጥቁር ላስቲክ ተከቷል። ቪዲዮን እየቀረጸ ያለው ሰው በነጭ ጨርቅ የተጠቀለሉት ዛሬ ጠዋት "የተሠሩ" ናቸው ይላል። ከዛ ደግሞ በጥቁር የአስክሬን ላስቲክ ውስጥ የተጠቀለሉ እስክሬኖችን እያሳየ፤ "እነዚህ ደግሞ ቀብራቸው ከመፈጸሙ በፊት ገና ለቀብር ዝግጁ የሚደረጉ ናቸው" ሲል ይናገራል። ከዚያ የስልኩን ካሜራ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላው እየወሰደ በተመሳሳይ መልኩ ተደርድረው የሚታዩ በርካታ አስክሬኖችን ያስቃኛል። ይህ ቪዲዮ የተቀረጸው በኢራን ቆም በምትባል ከተማ ውስጥ ነው። ኮሮናቫይረስ በኢራን መሰራጨት የጀመረው ከዚች ከተማ እንደሆነ ይታመናል። ቪዲዮን የሚቀርጸው ግለሰብ ሁሉም በኮሮናቫይረስ ምክንይት እንደሞቱ ይናገራል። ቢቢሲ ግን ይህን አላረጋገጠም። ቪዲዮን የሚቀርጸው ሰው፤ አስክሬኖቹ በዛ ስፍራ ከአምስት እስከ ስድስት ቀናት እንደቆዩ መናገሩ ግን የበርካቶችን ቀልብ ስቧል። ይህ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከታየ በኋላ ኢራን ካመነችው በላይ በርካቶች በቫይረሱ ሳይሞቱ እና ሳይያዙ እንዳልቀሩ ያረጋገጠ ነው እየተባለ ነው። ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ አገራት በኮሮና ክፉኛ የተጠቃች አገር ናት። በአገሪቱ ምን ያክሉ በቫይረሱ እንደተያዙ አልያም እንደሞቱ ማወቅ እጅጉን ከባድ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአገሪቱ የሚገኙ መንግሥታዊ አስክሬን ማቆያዎችን እና ቀብር አስፈጻሚዎች በአስክሬን ብዛት ተጥለቅልቀዋል። ለዚህም እንደምክንያት ከሚጠቀሱት መካከል የግል ተቋማት ቫይረሱ ከሞቱ ሰዎች ወደ ሠራተኞቻችን ሊተላለፍ ይችላል በማለት በኮቪድ-19 ምክንያት ሞቱ ሰዎችን አስክሬን እንቀበልም ማለታቸው ይገኝበታል። በአንዳንድ የመንግሥት አስክሬን ማቆያ ስፍራዎች በእስላማዊ ስርዓት አስክሬኖችን ለቀብር ዝግጁ እያደረጉ የሚገኙት በጎ ፍቃደኞች ናቸው። የዓለም ጤና ድርጅት በኮቪድ-19 ከሞተ ሰው ቫይረሱ ስለመተላለፉ ማረጋገጫ ባይረኖርም ሰዎች በቫይረሱ የሞተ ሰው አስክሬን ጋር የሚኖራቸው ንክኪ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት ሲል ይመክራል። ለቪዲዮው የኢራን ባለስልጣናት ምላሻቸው ምን ነበረ? በአስክሬን ማቆያ የተቀረጸውን ቪዲዮ በርካቶች ከተጋሩት በኋላ ቪዲዮን የቀረጸው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ባለስልጣናት ለሟች ቤተሰቦች ሁሉም አስክሬን በእስላማዊ ስርዓት በክብር እንደተያዙ ሲናገሩ ቆይተዋል። የሟች ቤተሰቦች የዘመዶቻቸው አስክሬን እንዴት እንደተያዘ ማወቅ ቀርቶ የዘመዶቻቸው አስክሬን የት እንዳለ እንኳ እንደማያውቁ ይናገራሉ። መንግሥት ይህ ወረርሽኝ ካለፈ በኋላ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች የቀብር ስፍራዎችን ለዘመድ ወዳጅ እንደሚያሳውቅ ተናግሯል። በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቀብር በኢራን አንድ የኢራን መንግሥት ይፋዊ አሃዝ መሠረት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ60ሺህ በላይ ሲሆን በቫይረሱ ተይዘው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ4ሺህ በላይ ነው። ይሁን እንጂ በአሜሪካ የሚገኙ ኢራናዊያን ተመራማሪዎች ባቨይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር መንግሥት ከሚለው ቁጥር እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን ይናገራሉ። ከማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት እና ቨርጅን ቴክ የሆኑት ኢራናውያን ተመራማሪዎች መንግሥት የሚሰጠው አሃዝ ትክክለኛነትን በመጠራጠራቸው ትክክለኛውን ቁጥር ያሳያል ያሉትን አንድ ስርዓት ፈጥረዋል። ይህ ሰርዓት መነሻቸው ከኢራን ሆኖ በሌላ መዳረሻ አገር በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች እና ከበርካታ ኢራን ውስጥ ከሚገኙ የህክምና ተቋማት መረጃዎችን በመሰብሰብ በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎችን ቁጥር አስልተዋል። በዚህም መሠረት ከፈረንጆቹ ማርች 20 ወዲህ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 15ሺህ እንዲሁም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን ደግሞ 1ሚሊዮን አድርሰውታል። ይህ ቁጥር ግን መንግሥት ከሚለው ከ10 እጥፍ በላይ ከፍ ያለ ነው። የኢራን ባለስልጣናት ከማርች 20 ወዲህ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1433 እንዲሁም የሞቱት ደግሞ 20ሺህ ብቻ እንደሆነ አመላክተዋል።
news-52089668
https://www.bbc.com/amharic/news-52089668
ኮሮናቫይረስ፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ እስከ ሠኔ ድረስ ከኮሮና ታገገምላች አሉ
በፌደራል የኮሮናቫይረስ መመሪያ መሰረት የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የሚያስችሉት አካላዊ እርቀትን መጠበቅን የመሳሰሉ እርምጃዎች እስከ ሚያዚያ ወር ድረስ እንደሚቆዩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
ቀደም ሲል ፕሬዝዳንቱ እነዚህ እርምጃዎች በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር አጋማሽ ላይ በሚከበረው የፋሲካ በዓል ሰሞን ሊላሉ እንደሚችሉ ገልጸው ነበር። ነገር ግን አሁን ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት "በሁለት ሳምንት ውስጥ በበሽታው ምክንያት የሚያጋጥመው ሞት ከፍተኛው ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችልበት እድል አለ" ብለዋል። ትራምፕ ትናንት ዋይት ሐውስ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ግብረ ኃይል ሥራዎችን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ አካላዊ እርቀትን መጠበቅን የመሳሰሉት በሽታውን የመከላከያ መንገዶች "በአሸናፊነት ለመውጣት ዘዴ ነው" ብለዋል። • የህክምና ባለሙያዎቻቸውን ለመከላከል የሚተጉት ቱኒዚያውያን አክለውም አሜሪካ ሠኔ ወር ላይ "ከበሽታው ለማገገም ጉዞ ላይ ትሆናለች" ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። በአሜሪካ ውስጥ በሁለት ሳማንት ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጠር ከፍተኛው መጠን ላይ ይደርሳል ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ "ድል ከመገኘቱ በፊት ድልን ከማወጅ የከፋ ነገር የለም፤ ይህም ከሁሉ የባሰ ሽንፈት ነው" ብለዋል። ተንታኞች እንዳሉት ግን ፕሬዝዳንቱ ስለከፍተኛው የወረርሽኙ "የሞት መጠንን" የጠቀሱበት ሁኔታ በአገሪቱ የሚከሰተውን አጠቃላይ በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን አሃዝ ለማመልከት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረስ ሆስፒታሎች በታማሚዎች ሊጥለቀለቁ ይችላሉ የሚለው የበርካቶች ስጋት ትራምፕን ሳያሳስባቸው አልቀረም። ቀደም ሲልም የዋይት ሐውስ የህክምና አማካሪ የሆኑት ዶክተር አንተኒ ፋውቺ ቫይረሱ እስከ 200 ሺህ የሚደርሱ አሜሪካዊያንን ሊገድል እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸው ነበር። ዶክተሩ ጨምረውም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአገሪቱ ዜጎች በኮሮናቫይረስ ሊያዙበት የሚችል ዕድል እንዳለ ተናግረዋል። • የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የኢትዮጵያ ዝግጁነት ምን ይመስላል? በአሁኑ ጊዜ አሜሪካ ውስጥ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ከ140,000 ሺህ በላይ ህሙማን ይገኛሉ። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ በተጠናቀረው አሃዝ መሰረት እስከ ትናንት እሁድ ምሽት ድረስም 2,493 ሰዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። አሜሪካ በበሽታው በተያዙ ሰዎች ብዛት ቀደም ብሎ በሽታው ተከስቶባቸው ከነበሩት ከቻይናና ጣሊያን መብለጧን ባለፈው ሳምንት የወጡ የበሽታው መስፋፋት ዘገባዎች አመልክተዋል።
news-51617825
https://www.bbc.com/amharic/news-51617825
አቶ ንዋይ ገብረአብ በሚያውቋቸው አንደበት
ለረዥም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የየቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊና አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ንዋይ ገብረአብ ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ከ1970ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕላን ኮሚሽን ውስጥም ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል። ከኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪነታቸው ባለፈ የኢትዮጵያ የልማት ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል። በተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ድርጅቶች ውስጥም በአማካሪነት ሰርተዋል። አቶ ንዋይ ከአዲስ አበባ እና ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። " በአገሪቱ ይመዘገቡ ለነበሩ የኢኮኖሚ እድገቶች መንግስትንና አቶ መለስን በማማከር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል" ዶ/ር አብረሃም ተከስተ የቀድሞው የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስትር ዶ/ር አብረሃም ተከስተ አሁን የትግራይ ክልል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊእንደሚያስታውሱት የኢትዯጵያ ኢኮኖሚ በደርግ ጊዜ በ80ዎቹ መጀመርያ በተለይ ኢኮኖሚው የተሽመደመደበትና ቀውስ ውስጥ የወደቀበት ጊዜ ነበር። ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ሲመጣና እርሳቸው በአማካሪነት ሥራ ሲጀምሩ አንዱ ትልቁ ፈተና ኢኮኖመሚውን ማረጋጋት ነበር። የወጪ ንግድ፣ የመንግሥት በጀት የነበረውን ክፍተት፣ ትልልቅ የአገሪቱ የኢኮኖሚው ችግሮችን፤ የውጭ እዳን ጭምር ሥርዓት እንዲይዝ ያደረጉት አቶ ንዋይ መሆናቸውን ይናገራሉ። በዚህ ረገድ አቶ ንዋይ የተጫወቱት ሚና ትልቅ ነበርም ይላሉ። እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጀት አይኤም ኤፍ፣ ዓለም ባንክ ጋር በነበረ ድርድር ከፊት ሆነው ይደራደሩ የነበሩት እርሳቸው እንደነበሩና የኢትዯጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ ብዙ መጣራቸውንም ያስታውሳሉ ዶ/ር አብረሃም። "አቶ ነዋይ አገሩቱን የሚጠቅሙ ወሳኝ ፖሊሲዎችን ተከላክለዋል። በአጠቃላይ በአገሪቱ ይመዘገቡ ለነበሩ የኢኮኖሚ እድገቶች መንግስትንና አቶ መለስን በማማከር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል"ይላሉ። ከሰው ጋር ተረዳድቶ መስራት የሚችሉ ፣ ይህ ሁሉ እውቀት ይህንን ሁሉ ልምድ ይዘው እጅግ ትሁት፣ ሰው እንዲማር ሰው እንዲያድግ የሚወዱ ቀና ሰው ናቸው ሲሉም ይገልጿቸዋል አቶ ንዋይን። መንግሥት የራሱ የፖሊሲ ነፃነት እንዲኖረው ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውንም ይጠቅሳሉ። "እጅግ ረጋ ያሉ፣ ለምንም ነገር የማይቸኩሉ፣ በጥሞና አስተውለው የሚናገሩ ሰው ናቸው" ዶ/ር ግሩም አበበ ዶ/ር ግሩም አበበ በኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት (EDRI) መሪ ተመራማሪ ነበሩ። አቶ ንዋይን ላለፉት 13 ዓመታት ያውቋቸዋል። መጀመሪያ ሲተዋወቁ ያስተዋሉት "እጅግ ረጋ ያሉ፣ ለምንም ነገር የማይቸኩሉ፣ በጥሞና አስተውለው የሚናገሩ ሰው እንደሆኑ ነው" ይላሉ። የሚናገሩት ነገር ጠንካራ፣ ፍሬያማና አስተማሪ እንደነበረ ያስታውሳሉ። "ጠንከር ያለ መልዕክት ማስተላለፍ እንኳን ሲፈልጉ ረጋ ብለው፣ የተመረጡ ቃላት ተጠቅመው፣ መልዕክቱ ሌላ ይዘት እንዳይሮረው አድርገው ነበር" ሲሉም ይገልጿቸዋል። አንድ ወቅት ለልምድ ልውውጥ ወደ ደቡብ ኮርያ አንድ ላይ አቅንተው ነበር። አብዛኛው ግንኙነታቸው ሥራ ተኮር ቢሆንም፤ የደቡብ ኮርያው አጋጣሚ ከሥራ ውጪ የመነጋገር እድል ሰጥቷቸው ነበር። "የብዙ አገር ልምድ ያላቸው፣ በጣም ብዙ ያነበቡ፣ ያነበቡትን ለአገሬ በምን መልኩ ይጠቅማል የሚለው የሚያስጨንቃቸው ሰው እንደሆኑ ተረዳሁ" ሲሉ በወቅቱ ስለ አቶ ንዋይ የተሰማቸውን ዶ/ር ግሩም ይናገራሉ። በደቡብ ኮርያው መድረክ፤ ስለ ምሥራቅ እስያ አገራት ምጣኔ ኃብት የተለያዩ ምሁራን ንግግር ያደርጉ ነበር። "አቶ ንዋይ ያደሩትን ንግግር፣ ለሚጠየቁት ጥያቄ የሰጡት መልስ ሁላችንንም አስገርሞን ነበር" ሲሉም ትውስታቸውን ለቢቢሲ አካፍለዋል። በመሰረቱት የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት አጥኚዎችን ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምረው መልምለው፣ ትምህርት እንዲማሩ፣ በአግባቡ ከተማሩ እገዛ ማድረግ እንደሚችሉ የሳስቡ እንደነበርም ያስታውሳሉ። "ኢንስቲትዩቱን ሲያቋቁሙት አላማዬ ብለው የያዙት ጠንካራ የሰው ኃይል መፍጠርና ያንን የሰው ኃይል ተጠቅሞ አገሪቷን በፖሊሲ፣ በምርምር መርዳት የሚችል ተቋም እንዲሆን ነው።" ኢንስቲትዩቱ ዓለም አቀፍ ተቋሞች በጥናትና ምርምር ዘርፍ በሚያወጡት የደረጃ ሰንጠረዥ ከኢትዮጵያ አንደኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ከአንድ እስከ አስር ደረጃ እንደሚያገኝም ይናገራሉ። በአጭር ጊዜ ኢንስቲትዩቱን እዚህ ደረጃ ማድረስን እንደ ትልቅ ስኬትም ያዩታል። "ወጣት ሆነው የመለመሏቸው የሳቸው ፍሬ የሆኑ ልጆች የተለያየ ቦታ አሉ። በዚህ በጣም ደስ እንደሚላች እሰማለሁ።" በአህጉሪቱ በአጠቃላይ ጠንካራ የምጣኔ ኃብት ፖሊሲ እንዲኖር እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የሚካሄዱ ድርድሮችን በበቂ ሁኔታ ለመምራት (እኩል ተደራዳሪ ለመሆን) በቂ አገር በቀል የተማረ ኃይል ሊኖር እንደሚገባ ያምናሉ። አቶ ንዋይ ከሥራ ውጪ ባለ ሕይወታቸው መጻሕፍት ከማንበብ ባሻገር ሂልተን ሆቴል አካባቢ ቅዳሜና እሑድ ጋዜጣ ማንበብ ያዘወትሩ እንደነበር ዶ/ር ግሩም ይናገራሉ። ከተለያዩ አገራት ልምድ ለመቅሰም ስለሚሹ ዓለም አቀፍ የውይይት መድረኮችን መከታተልም ይወዱ ነበር። ዶ/ር ግሩም እንደሚሉት ለመጨረሻ ጊዜ የተነጋገሩት ከስድስት ወር በፊት ነበር። በወቅቱ አቶ ንዋይ ጡረታ ወጥተው መጽሐፍ እየጻፉ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ግሩም "መጽሐፍዎ በእጄ እስከሚገባ እጓጓለሁ" እንዳሏቸው ያስታውሳሉ። በወቅቱ አቶ ንዋይም "መጽሐፉን እየሠራሁበት ነው" ብለው ምላሽ ሰጥተዋቸው ነበር። "በጣም ለስላሳ ሰው፣ ረጋ ያሉ፣ ባለራዕይ፣ ነገሮችን ራቅ ብለው ማየት የሚችሉ"ዶ/ር ፍሬው በቀለ ትውውቃቸው የጀመረው ተመርቀው የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩትን ሲቀላቀሉ ሲሆን በወቅቱም አቶ ንዋይ የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ነበሩ። በወቅቱ ለትምህርት ተልከው ስለነበር፤ የመስሪያ ቤቱ ድጋፍም አልተለያቸውም ግንኙነታቸውም የቀጠለው በዚያ መልኩ ነው። ተምረው ከመጡ ከ2013 በኋላ በጡረታ እስከተገለሉበት ድረስ አብረው ሰርተዋል። አብዛኛውን ጊዜ ከስራ ጋር በተገናኘ ሁኔታ በተለይም ከምጣኔ ኃብት ጋር በተያያዘ ውይይትም አድርገዋል። አቶ ንዋይን እንዴት ይገልጿቸዋል ሲባሉም "በጣም ለስላሳ ሰው፣ ረጋ ያሉ፣ ባለራዕይ፣ ነገሮችን ራቅ ብለው ማየት የሚችሉ" ይሏቸዋል። ለአምስት አመታትም ያህል ከአቶ ንዋይ ጋር በቅርበት የመስራት እድሉን አግኝተዋል። ለዚህም የሚያነሱት ተማሪዎችን በሚመለምሉበት ወቅት አስር፣ ሃያ አመት ወደፊት የሚሆነውንም በማሰብ ነበር። በተለይም ለምርምሮች ከፍተኛ ቦታንም ይሰጡ እንደነበር ያስታውሳሉ። "ለውይይቶች ክፍት ነበሩ፤" የሚሏቸው አቶ ንዋይ በተደጋጋሚ አፍሪካውያን ከውጭ የሚመጡ ጫናዎችን ተቋቁመው የራሳቸውን የምጣኔ ኃብትም ሆነ ሌሎች ፖሊሲዎቻቸውን ለነሱ በሚመጥን መልኩ ሊቀርፁ ይገባል በማለት በተደጋጋሚ ይሟገቱ ነበርም ያስታውሳሉ። "ባለ ራዕይ ናቸው ስል ለፖሊሲ አውጭ ዛሬ የገጠመ ችግር ብቻ አይደለም ምርምር የወደፊቱንም ያለመ ነው። ለታዳጊ ሃገር እንደዚህ አይነት ነገሮች ብዙ ላይታሰቡ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ትኩረት የሚደረገው የእለት ተእለትና አጣዳፊ ለሆኑ ጉዳዮች ነው።" የሚሉት ዶ/ር ፍሬው ከዛ ባለፈ ግን የወደፊቱን የሚሆነውንም የሚቀይሱ ናቸው ይሏቸዋል አቶ ንዋይን።
news-56882027
https://www.bbc.com/amharic/news-56882027
በቅርቡ ባጋጠመው 'ግጭት 200 ያህል ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ' ተነገረ
ከሳምንት በፊት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ውስጥ በተከሰተ "ግጭት እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች" ሳይሞቱ እንዳልቀረ ሮይተርስ የዜና ወኪል አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ዘገበ።
በአጣዬ ከተማ ከደረሰው ጉዳት መካከል ነዋሪዎችና የአካባቢው ባለሥልጣናት ባለፉት ቀናት እንደተናገሩት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት መውደሙንና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ኃላፊ አቶ እንዳለ ኃይሌ ለሮይተርስ እንደተናገሩት "ከተፈናቀሉ ሰዎች ያገኘነውን መረጃ መሠረት አድርገን እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች ከሁለቱም ዞኖች ሳይሞቱ አይቀሩም" ብለዋል። ኃላፊ ጨምረውም ይህ የተጠቀሰው የሞቱ ሰዎች አሃዝን የበለጠ ማረጋገጥ እንደሚፈልግም አመልክተዋል። በቅርብ ጊዜ በተከሰተው ጥቃት ክፉኛ ከተጎዱት አካባቢዎች መካከል ዋነኛዋ በሆነችው በአጣዬ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ ከ20 እስከ 25 በመቶ የሚሆኑት በእሳት መጋየታቸውን አቶ እንዳለ ተናግረዋል። በተጨማሪም ከሰሜን ሸዋ ዞን 250 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እንዲሁም 78 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ከኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ የምትገኝ አንዲት ትንሽ ከተማ በመጋቢት ወር ሙሉ ለሙሉ መውደሟን አቶ እንዳለ እንደተናገሩ ጠቅሶ ነገር ግን ስለደረሰው ጉዳት ተጨማሪ ዝርዝር እንዳልሰጡ አመልክቷል። ጥቃቱን ተከትሎ የክልሉና የዞኖቹ ባለሥልጣናት ለተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን፤ ትክክለኛ አሃዝ እንደሌላቸው ነገር ግን በሰውና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን መረዳታቸውን ገልጸው ነበር። ባለፈው ሳምንት በጥቃቱ በሰው ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ከሰሜን ሸዋ ዞኑ አስተዳደር መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ በሞከረበት ጊዜ የአካባቢው ኃላፊዎች በቀዳሚነት የተፈናቀሉትን በመርዳት ወደመኖሪያቸው ለመመለስ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው ጎን ለጎንም መረጃ እያሰባሰቡ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው መጋቢት ወር በአካባቢው በተከሰተ ጥቃትና ግጭት ተመሳሳይ ከባድ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በክስተቱ ከ300 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ኤኤፍፒ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋምን ባለስልጣንን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ሰሜን ሸዋ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ ቀደም ሲል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ አርብ ሚያዝያ 08/2013 ዓ.ም በተፈጸሙ ጥቃቶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። በወቅቱ የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ኃላፊ አቶ አበራ መኮንን ለቢቢሲ እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈፀመው በዞኑ ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ላይ ሲሆን "በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የታጠቀ ኃይል ወረራ" ፈጽሞ ጉዳት አድርሷል ብለው ነበር። በጥቃቱ ወቅት የታጣቂው ኃይል በሰዎችና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አመልክተው ክስተቱ በአካባቢው ከነበረው የፌደራልና የክልሉ የጸጥታ ኃይል "አቅም በላይ" መሆኑንና በጸጥታ አካላት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን ተቋም እንደተናገሩት በጥቃቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰና ለጥቃቱም "ኦነግ-ሸኔ እና ሌላ ተከታይ" ያሉትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኙት አጣዬ፣ አንጾኪያና በኤፍራታ የሚባሉት ሲሆኑ፤ የአጣዬ ከተማ ከሁሉም በከፋ ሁኔታ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባት ከጥቃቱ በኋላ የሚወጡ ምስሎች አመልክተዋል። በወቅቱ በታጠቁ ኃይሎች የተፈጸመውን ጥቃት በመሸሽ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያቸውን በመተው ወደ ገጠር መንደሮችና በዙሪያቸው ወዳሉ ከተሞች መሄዳቸው መነገሩ ይታወሳል። የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ተሰማርቶ ችግሩን ከተቆጣጠረ በኋላ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች የእለት ደራሽ እርዳታ ለማቅረና ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት እያደረገ መሆኑን ባለፈው ሳምንት ተገልጾ ነበር። ከሦስት ሳምንታት በፊት በአካባቢዎቹ በተፈፀመ ጥቃትና ግጭት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልከላ በሰሜን ሸዋ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና በደቡብ ወሎ ውስጥ በሚገኙ የጸጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስን መከልከሉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቋል። በአማራ ክልል ምሥራቃዊ ክፍል ውስጥ የተከሰተውን የሠላም መደፍረስ ለመቆጣጠር የዕዝ ማዕከል [ኮማንድ ፖስት] መመስረቱን የገለጸው መከላከያ ሚኒስቴር ፤ በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብ ወሎ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ውስጥ በታጠቁ ኃይሎች የሚፈጸሙ ጥቃትን ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ መሆኑም ገልጿል። በዚህም መሠረት የዕዝ ማዕከሉ ከደብረ ሲና እስከ ኮምቦልቻ ባለው መስመር አዋሳኝ ወረዳዎች ከመንገድ ግራና ቀኝ ባለው 20 ኪሎ ሜትር ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል አሳውቋል። በተጨማሪም በአካባቢዎቹ መንገድ መዝጋት፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ የመንግሥት ተቋማት፣ የግለሰብ መኖሪያና ንብረት ማውደም ወይም "ለዚህ ተግባር በተናጠልም ይሁን በቡድን መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ" መሆኑን ገልጿል። ጥቃት በተፈጸመባቸውና የተቋቋመው የዕዝ ማዕከል መረጋጋትን ለማስፈን በሚንቀሳቀስባቸው በእነዚህ አካባቢዎች የተጣሉትን ክልከላዎች ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም አካል ላይ "ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት" ጨምሮ አስታውቋል። በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶችና ጥቃቶች ሲፈጸሙ የቆዩ ሲሆን አሁን የተፈጸመው ግን እስካሁን ካጋጠሙት መካከል ሰፊ ቦታዎችን ከማዳረሱ በተጨማሪ ባስከተለው ጉዳት ቀደም ካሉት የከፋ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የአካባቢው ባለስልጣናት በአሁኑ ጊዜ የተፈናቀሉትን ወደ መኖሪያቸው ለመመለስና ቀሪውን ነዋሪ ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ባለፉት ቀናት በተፈጸመው ጥቃት በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት ዝርዝር ለማወቅ አለመቻላቸውን ገልጸዋል። የተቃውሞ ሰልፎች በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ ከተሞች የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ይህንን ጥቃት በመቃወምና መንግሥት በሌሎች ክልሎች በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችናና ማፈናቀሎችን እንዲያስቆም የሚጠይቁ ሰልፎች ሲካሄዱ ሰንበተዋል። ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞችና በተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ መስተዳደርና የፌደራል መንግሥቱ በአማራ ብሔር አባላት ላይ ባለፉት ዓመታት እየተፈጸሙ ናቸው ያሏቸውን ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲያስቆሙ ጠይቀዋል። የተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በርካታ ሕዝብ የተሳተፈባቸው ሲሆኑ በተለያዩ ቀናት ሲካሄዱ ቆይተዋል። በተጨማሪም በአንዳንድ ከተሞች ውስጥ በተለያዩ ቀናት በተደጋጋሚ ተካሂደዋል። ሰልፉ በሰሜን ሸዋ ውስጥ የተፈጸመውን ጥቃት መነሻ ያደረገ ቢሆንም በተለያየ ጊዜያት በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀመውን ጥቃትም የሚያወግዝ እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሰልፉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
news-51956832
https://www.bbc.com/amharic/news-51956832
ኬንያዊው ኮሮናቫይረስ አለብህ በሚል ጥርጣሬ ተደብድቦ ተገደለ
በሰሜን ምስራቅ ኬንያ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ይዞታል ብለው የጠረጠሩትን አንድ ግለሰብ ደብድበው መግደላቸውን የአካባቢው ፖሊስ ለቢቢሲ አስታወቀ።
የፖሊስ አዛዡ ነህሚያ ቢቶክ እንዳሉት እስካሁን በግለሰቡ ግድያ ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው የሌለ ሲሆን ምርመራ ግን እየተካሄደ ነው። ግድያው የተፈፀመው በኬንያዋ ክዋሌ ግዛት በአሳ ምርት በምትታወቀውና ምሳምብዌኒ በተባለች መንደር ነው። ቦታው በባህር ዳርቻውና በነጭ አሸዋው ውበት በቱሪስቶችም በእጅጉ የሚዘወተር ነው። • የኮሮናቫይረስ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ላይ ያጠላው ስጋት • በኬንያ ስለኮሮናቫይረስ ሃሰተኛ መረጃ ያሰራጨው ግለሰብ ታሰረ • 'ኮሮናቫይረስ አለብህ' በሚል ቡጢ የቀመሰው የኦክስፎርድ ተማሪ ግለሰቡ የተገደለው ማክሰኞ ምሽት ሶስት ሰዓት ገደማ ወደ ቤቱ በማምራት ላይ ሳለ እንደሆነ ተገልጿል። የኬንያ መንግሥት እስካሁን በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሰባት ደርሷል። መንግሥት ወደ ኬንያ የሚገቡ የውጭ አገር ዜጎች ላይ ጥብቅ የጉዞ እገዳ የጣለ ሲሆን የትምህርት ተቋማትን ዘግቷል፤ ህዝባዊ ስብሰባዎችንም አግዷል።
news-56073530
https://www.bbc.com/amharic/news-56073530
ኮሮናቫይረስ: እስራኤል የፋይዘር ክትባት ውጤታማ ሆኖ ማግኘቷን ገለፀች
ከእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፋይዘር ክትባት የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን 94 በመቶ የመከላከል አቅም አለው።
ይህም ክትባቱ በክሊኒክ ውስጥ በተደረጉለት ሙከራዎች ወቅት የነበረውን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ህዝብ ውስጥም ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ውጤታማነት እያስገኘ መሆኑን የማህበረሰብ ጤና ሐኪሙ ፕሮፌሰር ሀጋይ ሌቪን ተናግረዋል። "በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ቡድኖች ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መስጠት ወሳኝ" ነበር ብለዋል፡፡ የእስራኤል ትልቁ የጤና ፈንድ ክላሊት በተመሳሰይ ዕድሜ እና የጤና ሁኔታ በሚገኙ 600,000 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ መልካም የሚባል ውጤት መገኘቱን፣ ክትባት ካልወሰዱ ሰዎች አንጻር እንደታየባቸው አመልክቷል፡፡ ክትባቱን በወሰዱት ዘንድ 94% ያነሰ ኢንፌክሽኖችን አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም ክትባቱ ሁሉንም ማለት በሚቻል ሁኔታ ከባድ ህመሞችን ተከላክሏል፡፡ ውጤቱ ከ70 ዎቹ በላይ የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ቡድኖች ውስጥ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ "እንደ እንግሊዝ ላሉት ሌሎች ሀገሮች" ስለ ክትባቱ ጠቃሚ መልዕክት ከማስተላለፉም በተጨማሪ፣ በቫይረሱ በጣም ሊታመሙ የሚችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች "በከፍተኛ" ሁኔታ ክትባቱን እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል ፕሮፌሰር ሌቪን፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም የእንቅስቃሴ ገደቦችን ከማላላት በፊት ምን ያህል ቁጥር መከተብ እንደሚያስፈልግ መናገር አልችልም ብለዋል፡፡ "በመተላለፍ ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም" ብለዋል፡፡ ሆኖም ቢያንስ "ክትባቱ ግለሰብን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው" ሲሉም አክለዋል፡፡ የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃን በመተንተን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ኤራን ሴጋል በበኩላቸው ክትባቱ በኮቪድ -19 ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመረዳት ሃገሪቱ ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ ከሆኑት መካከል 80 በመቶውን መከተብ እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ እስራኤል የክትባት መርሃግብሩ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመመልከት በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ሀገር ብትሆንም፣ ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ የሆነ ህዝብን ማዳረስ እና በርካታ ሳምንታትን ሊፈጅባት ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ክትባት በተወሰዱ እና ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ በሆናቸው እና ከዚያ ቀደም ነዋሪዎቻቸውን ባስከተቡ ከተሞች ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ሲቀንስ ታይቷል። ይህም ቀደም ባሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ወቅት ያልታየ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ከእገዳው ይልቅ ክትባቱ ለቁጥሩ መቀነስ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠንካራ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ ፕሮፌሰር ሴጋል እንደሚያስጠነቀቁት ከሆነ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ በዝግታ የቀነሰ ሲሆን ምናልባትም በእስራኤል ውስጥ ዋነኛው የቫይረሱ ዝርያ በሆነው እና በብሪታንያ በተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ "በጣም ፈጣን" በሆነው በእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር እንኳን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊከላከሉት የማይችሉ ሲሆን በበሽታው ከተያዙም በጠና ሊታመሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ "አሁንም ቢሆን ከእንቅስቃሴ እገዳው ለመውጣት በጥንቃቄ መውጣት አለብን" ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሆስፒታል መተኛት ሊገደዱ ይችላሉ ይላሉ፡ እስራኤል ከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን ማዕበል እያጋጠማት እና በጥብቅ እገዳዎች ውስጥ ብትቆይም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ የመከተብ መብት ስላላቸው ትምህርት ቤቶች የመከፈት ተስፋ አላቸው ተብሏል፡፡ በፍልስጤም ግዛቶች ክትባቱን ማን መስጠት አለበት በሚለው ጥያቄ ሃገሪቱ ትችት ደርሶባታል፡፡ ለጤና ሠራተኞች እንዲደርስ እስራኤል በዌስት ባንክ እና በጋዛ ላሉት ፍልስጤሞች የተወሰነ መጠን ያለው ክትባት ማሳለፍ የጀመረችው ገና አሁን ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከነዋሪዎቿ ለሩብ ያህሉ ሁለቱንም ዙር ክትባት ሰጥታለች፡፡
news-51764787
https://www.bbc.com/amharic/news-51764787
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ ግብጽን በመደገፍ ያወጣውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አደረገች
የአረብ ሊግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትላንት ካይሮ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ግብጽን በመደገፍ ያወጣውን የውሳኔ ሃሳብ ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበለው የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ሊጉ በግድቡ ዙሪያ እየተደረገ ያለውን ድርድር ቁልፍ እውነታዎችን ሳያገናዝብ በውሳኔ ሃሳቡ የሰጠው ጭፍን ድጋፍ እንዳሳዘነው አመልክቷል። መግለጫው በተጨማሪም የውሳኔ ሃሳቡን እንደማትቀበል አሳውቃለች የተባለችውን የሱዳንን አቋም ያደነቀ ሲሆን፤ ከግድቡ አንጻር በተቀነባበረው የአረብ ሊግ አቋም ላይ "ሱዳን በድጋሚ ለምክንያታዊነትና ለፍትህ ያላትን አቋም አሳይታለች" ሲል አወድሷታል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ እንዳለው ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ይዛው የቆየችውን "የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት የአባይ ውሃ ሃብቷን የመጠቀም መብቷን" ታስከብራለች። አባይ ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ እንደመሆኑ ውሃውን ከሚጋሩ አገራት ጋር በመተባበር መርህ ጉልህ የሆነ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ ፍትሃዊና ተቀባይነት ባለው መንገድ መጠቀምን ትደግፋለች። በተጨማሪም በግልጽ በሚደረግ ውይይት ሁሉንም የሚጠቅም ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻል ኢትዮጵያ እንደምታምን መግለጫው አመልክቷል። የበላይነት ለመያዝ የሚደረግ ጥረት ውጤት የማያመጣ ከመሆኑ በተጨማሪ አሁን ባለው አገራት እርስ በርስ ተሳስረው በሚኖሩበት ዘመን ቦታ የለውም ሲል የጋራ ተጠቃሚነትን አስፈላጊነት ጠቅሷል። ግድቡን በውሃ ለመሙላትና የውሃ አለቃቀቅን በተመለከተ መሰረት ለሆነውና ቀደም ሲል ለተደረሰው የመርህ ድንጋጌ ስምምነት ኢትዮጵያ ተገዢ መሆኗን እንደምታረጋግጥና በዚህ ስምምነትም የመጀመሪያ ደረጃ የግድቡ የውሃ ሙሌት ከግድቡ የግንባታ ሂደት ጋር ጎን ለጎን ይካሄዳል እንደሚልም መግለጫው አመልክቷል። በመጨረሻም መግለጫው የአረብ ሊግ ከኢትዮጵያ ጋር ለረጅም ዘመናት በነበረው ግንኙነትና የጋራ ዕሴቶች አንጻር ከእውነት ጋር እንደሚቆም እምነት እንዳለው ጠቅሶ ወደፊትም ለጋራ ግብ በቅርበት ለመስራት እንደሚፈልግ ገልጿል። በተያያዘ ዜና ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አንጻር አገራዊ ክብርን አሳልፎ የሚስጥ ስምምነት ውስጥ መንግሥታቸው እንደማይገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ትናንት መናገራቸው ተዘግቦ ነበር። የብልፅግና ፓርቲ የአመራሮች ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት "ከውጭ ለምናገኘው ሀብት ብለን አገራዊ ክብራችንን አሳልፈን አንሰጥም" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም በመልዕክታቸው ግድቡ የሌሎችንም ሀገራት ጥቅምን በማይጋፋ መልኩ አጠናቀን ጥቅም ላይ እናውለዋልን ሲሉም አምልክተዋል። ጨምረውም "ምንም እንኳ ቀደም ብለን ማጠናቀቅ ቢኖርብንም፤ በባለፈው ሳንቆጭ የያዝነውን ሳንለቅ ግድቡን አጠናቀን የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መስራት ያስፈልጋል" ብለዋል። የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ባለፈው ቅዳሜ ያወጡት መግለጫ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናትና ከህዝቡ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን በሂደቱ የአሜሪካ ገለልተኝነት ላይ ከተለያዩ ወገኖች ጥያቄን አስነስቷ። የአሜሪካ መግለጫ የድርድር ሰነዱ ሳይፈረም በዚህ ዓመት መገባደጃ ላይ ይጀመራል ይተባለው የውሃ ሙሌት ሥራ መካሄድ እንደሌለበት በአጽንኦት ቢያስቀምጥም ኢትዮጵያ በዚህ እንደማትስማማ አሳውቃለች።
news-54143719
https://www.bbc.com/amharic/news-54143719
በሎስ አንጀለስ ሁለት ፖሊሶች ላይ የተኮሰውን ሰው ማንነት የጠቆመ መቶ ሺ ዶላር ይሸለማል
በሎስ አንጀለስ ሁለት ፖሊሶች ላይ የተኮሰውን ሰው ማንነት የጠቆመ መቶ ሺ ዶላር እንደሚሸለም ተገለፀ።
አንድ ማንነቱ ለገዜው ያልተለየ ግለሰብ አገር ሰላም ነው ብለው ፖሊስ መኪናቸው ውስጥ ቁጭ ብለው በነበሩ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች ላይ አከታትሎ ከተኮሰባቸው በኋላ ለጊዜው ተሰውሯል፡፡ ይህ የሆነው ባለፈው ቅዳሜ ማታ በሎሳንጀለስ ነው፡፡ ሁለቱም ፖሊሶች እስካሁን ሕይወታቸው ባታልፍም በጽኑ ሕምሙና ክፍል በአደገኛ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ተብሏል፡፡ የደቂቅ የጎዳና ካሜራ (ሲሲቲቪ) ምሥሎች እንደሚያሳዩት ግለሰቡ ወደ ፖሊሶቹ መኪና ሽጉጥ ደግኖ የተጠጋው በተሳፋሪ ወንበር በኩል ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ አከታትሎ ተኩሶ ሲሸሽ ይታያል፡፡ ምሥሉ ግን የሰውየውን ማንነት ለመለየት የሚያስችል አልሆነም፡፡የሎስ አንጀለስ የፖሊስ አለቃ አሌክስ ቪላኑቫ ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡ የሎስ አንጀለስና አካባቢዋ አስተዳደር ይህንን ወንጀለኛ ያለበትን የሚያውቅ ይጠቁመን እኛ መቶ ሺህ ዶላር ወዲያውኑ እንሸልመዋለን ብሏል፡፡ በአገሬው አቆጣጠር በ2020 ዓ.ም ብቻ 40 ፖሊሶች በሥራ ገበታቸው ላይ ሳሉ ተገድለዋል፡፡ ሁለቱ ፖሊሶች ላይ ጉዳት ቢደርስም በሆስፒታሉ የድንገተኛ ታማሚዎች በር ላይ ጥቂት ሰልፈኞች ፖሊስን የሚያወግዝ መፈክሮችን ሲያሰሙ ነበር፡፡ ‹‹የተተኮሰባቸው የፖሊስ መኮንኖች እንዲሞቱ ነው ምኞታችን›› እያሉ ሲቃወሙም ተሰምተዋል፡፡ ለጊዜው ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን አንዷ ግን ጋዜጠኛ ሆና በመገኘቷ ተለቃለች፡፡ ሆኖም ያየችው ሰው እንዳለና እጇ ላይም መረጃ እንደሚገኝ ጠቁማለች፡፡ ጥይት የተተኮሰባቸው ሁለቱ የፖሊስ መኮንኖች ስማቸው ለጊዜው ይፋ ባይሆንም የ31 ዓመት ሴት እና የ24 ዓመት ወጣት ወንድ ፖሊስ እንደሆኑ ግን ተነግሯል፡፡ ከፖሊስ አካዳሚ ከተመረቁና ሥራ ከጀመሩ ገና 14 ወራቸው ነበር፡፡በኅዳር ወር ለመፋለም በምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ያሉት ባይደንና ትራምፕ ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡ዶናልድ ትራምፕ ‹‹ይህ አውሬነት ነው›› ሲሉ ባይደን በበኩላቸው ማንኛውም የኃይል ጥቃት ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
news-42476581
https://www.bbc.com/amharic/news-42476581
ከአይኤስ በኋላ የመጀመሪያው ገና በሞሱል እየተከበረ ነው
አይ ኤስ ከከተማዋ ተጠራርጎ ከወጣ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የገና ሥነ-ሥርዓት በኢራቋ ሞሱል ከተማ ተከበረ።
አይ ኤስ ከተማዋን በተቆጣጠረበት ወቅት ማንኛውም ዓይነት ክርስትያናዊ በዓላትን ማክበርም ሆነ ዝግጅቶችን ማካሄድ ለሕይወት አስጊ እንደነበረ አይዘነጋም። አይ ኤስ በከተማዋ የሚገኙ ክርስትያኖችን ወደ እስልምና እምነት እንዲቀየሩ፣ ግብር እንዲከፍሉ ካለሆነ ደግሞ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ካወጀ በኋላ በርካታ የክርስትና እምነት ተከታዮች አከባባቢውን ለቀው ለመውጣት ተገደው ነበር። በያዝነው ወር መባቻ የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል-አባዲ አይ ኤስን ከኢራቅ ለማስወጣት የተካሄደው የሶስት ወር ተልዕኮ በድል መጠናቀቁን አውጀው ነበር። የሞሱል ከተማ ነዋሪዎች የገና በዓልን በቅዱስ ጳውሎስ ቤተ-ክርስትያን ባከበረቡት ወቅት አካባቢው በታጠቁ ወታደሮች ሲጠበቅ ነበር። የኢራቅ የካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ፓትሪያርክ ሉዊስ ራፋኤል ሳኮ የእምነቱ ተከታዮች በሞሱል፣ በኢራቅ እና በመላው ዓለም ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲጸልዩ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፋርካድ ማልኮ አይኤስ ከተሸነፈ በኋላ ወደ ከተማዋ የተመለሰ ክርስትያን ሲሆን የክርስትና እምነትን አንደገና ለማስጀመር ይህ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብሏል። በበጎ ፍቃደኞች የተከፈተው ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ-ክርስትያን ለምዕመናን አገልግሎት የሚሰጥ ብቸኛው በሞሱል ከተማ የሚገኝ የክርስቲያኖች ቤተ-እምነት ነው። አይ ኤስ እአአ በ2014 ሞሱልን ከመቆጣጠሩ በፊት በከተማዋ ውስጥ 35ሺ የሚጠጉ ክርስትያኖች ይኖሩባት ነበር።
news-56530284
https://www.bbc.com/amharic/news-56530284
ባለፉት ሁለት ሳምንት ፓርኮችንና ጥብቅ ደኖችን እያወደመ ያለው እሳት
በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ከባድ ጉዳትን ያደረሱ የእሳት አደጋዎች በተደጋጋሚ ሲከሰቱ ቆይተዋል።
በወፍ ዋሻ ላይ የደረሰው እሳት አደጋ ከጥቂት ወራት በፊት በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የገበያ ስፍራዎችና የመኖሪያ አካባቢዎች ላይ በተከታታይ በደረሱ የእሳት አደጋዎች በሚሊዮኖች ብር የሚገመት ንብረት ለውድመት መዳረጉ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ባለንበት የመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮችና ጥብቅ ደኖች ላይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ከባድ ውድመትን አድርሷል። በእነዚህ የተፈጥሮ ደኖች ላይ ያጋጠመውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ሲሆን በስሜን ብሔራዊ ፓርክ ላይ የደረሰው ቃጠሎ መጥፋቱ የተነገረ ቢሆንም በሌሎቹ አካባቢዎች ግን እሳቱ ለቀናት ቀጥሏል። መጋቢት 2/2013፡ በሃላይደጌ አሰቦት ዕጩ ብሔራዊ ፓርክ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተው የእሳት አደጋ በተከሰተ የእሳት አደጋ እስካሁን ከ100 ኪሎ ሜትር ስኩየር በላይ የሚገመት ሳርና ቁጥቋጦ መውደሙ ተገልጿል። በደረቅ የአየር ሁኔታና በአካባቢው ባለው ከፍተኛ ንፋስና ምክንያት ቃጠሎው በፍጥነት እየተስፋፋ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንደሆነ ተነግሯል። መጋቢት 5/2013፡ የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አካል በሆነው የጭላሎ ጋለማ ደን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ረጅም እድሜ ያላቸው የዛፍ አይነቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል። ለቀናት የቆየው የእሳት አደጋው ሰፊ ቦታን የሸፈነ ሲሆን ፓርኩ ከሚያካትታቸው ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ በሰባቱ የእሳት አደጋው ውድምትን አድርሷል። የእሳቱ መንስኤ ለግጦሽና የዱር እንስሳትን ለመከላከል በሚል በተለኮሰ እሳት ሳቢያ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የጭላሎ ተራራ በተለያዩ ጊዜያት ተመሳሳይ የእሳት አደጋዎች አጋጥሞታል። መጋቢት 12/2013፡ በግዙፉ የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ላይ የእሳት ቃጠሎ ተከስቶ ከባድ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል። ምክንያቱ ያልታወቀው በፓርኩ ገደላማ አካባቢዎች የተነሳው ይህ የእሳት አደጋ በሳርና በአንዳንድ ዛፎች ላይ የተወሰነ ጉዳት አድርሶ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን በፓርኩ ውስጥ በሚገኙ የዱር እንሰሳት ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተነግሯል። ከዚህ ቀደምም የፓርኩን ሰፊ ቦታ ያዳረሰና ከፍተኛ የተፈጥሮ ሃብት ውድመትን ያስከተለ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር የሚታወስ ነው። መጋቢት 13/2013፡ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው ወፍ ዋሻ በተባለው ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ተከስቶ በፍጥነት መስፋፋቱ ተነግሯል። እሳቱ በአንኮበር ወረዳ በኩል በሚገኘው የደኑ ክፍል ላይ ተነስቶ ሦስት ቀበሌዎችን ላይ በሚገኝ ደን ላይ ውድመትን አድርሷል። ከባድ ጉዳትን ያደረሰው ይህ የእሳት ቃጠሎ ከግለሰብ ማሳ የተነሳ እሳት ወደ ደኑ በመዛመቱ መሆኑ ተገልጿል። መጋቢት 14/2013፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን የሚገኘውና ጅባት ተብሎ የሚታወቀው ደን ላይ ካለፈው ማክሰኞ የጀመረ የአሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ነዋሪዎችና ባለስልጣናት የተናገሩ ሲሆን፤ አደጋው እስካሁን 1 ሺህ ሄክታር የሚሸፍን ደን ማውደሙን ተገልጿል። የእሳቱ ምክንያት ምን እንደሆነ በትክክል የታወቀ ነገር ባይኖርም አደጋው ግን እጅግ የከፋ በመሆኑ በአካባቢው ነዋሪ ጥረት ብቻ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንደሆነ ተነገሯል። የጅባት ጥብቅ ደን 27 ሺህ ሄክታር መሬትን የሚሸፍን ሲሆን በውስጡም በርካታ የአእዋፋት ዝርያና የተለያዩ የዱር እንስሳት መኖሪያ ነው። በአሰቦት የደረሰው የእሳት አደጋ የእሳቱ መንስኤ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን መኮንን እንደሚሉት፤ እነዚህ ስፍራዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ደን ያለባቸውና በረሃማ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ሰደድ እሣት በራሱ ጊዜ የሚነሳበት ወቅት አለ። ሌላኛው ደግሞ ሰዎች በጫካዎቹ ውስጥ ያለውን ማር ለመቁረጥ ወይም ከሰል ለማክሰል ሲሉ የሚለኩሱት እሳት ከቁጥጥር ውጪ በመሆን ወደ ፓርኮቹ በመዛመት ከባድ ውድመትን ሊያስከትሉ ይችላል ብለዋል። በተጨማሪም አብዛኞቹ ፓርኮች የግጦሽ መሬት ስላላቸው አሁን ወቅቱ በጋ በመሆኑ ለከብቶቻቸው የማይሆነውን የደረቀ ሳር እዚያው መስክ ላይ እንዳለ በማቃጠል አዲስ ሳር እንዲበቅል ለማድረግ በሚል በሚለኮስ እሳት ውድመት ሊከሰት ይችላል ሲሉ አቶ ሰለሞን ምክንያቶቹን አስቀምጠዋል። ስለዚህ በደኖች ውስጥ ካለው በጣም ደረቅ የአየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ እሳት የሚነሳበት ሁኔታ እንዳለው ሁሉ በሰዎች አማካይነት የሚፈጠሩ የእሳት አደጋዎች ስላሉ "መነሻዎቹ ተፈጥራዊና ሰው ሠራሽ ናቸው" ይላሉ።
news-52564126
https://www.bbc.com/amharic/news-52564126
አል ሲሲን ተችቶ ለእስር የተዳረገው የፊልም ባለሙያ 'ሳኒታይዘር ጠጥቶ ህይወቱ አለፈ'
በሙዚቃ ቪዲዮ የግብጹን ፕሬዝደንት የተቸው የፊልም ባለሙያው ሻዲይ ሐባሽ በተመረዘ አልኮል ህይወቱ አለፈ ሲሉ የግብጽ ባለስልጣናት አስታወቁ።
የ24 ዓመቱ የፊልም ባለሙያ ካይሮ በሚገኘው እርስ ቤት፤ ከቀናት በፊት ውሃ መስሎት ሳኒታይዘር በመጠጣቱ ነው ህይወቱ ያለፈው ሲል አቃቤ ሕግ ተናግረዋል። አቃቤ ሕጉ ጨምረውም የኮቪድ-19 ወረርሽኘን ለመከላከል ሳኒታይዘር በእስር ለሚገኙ ታራሚዎች ተከፋፍሏል ብለዋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን ለሻዲይ ሐባሽ ሞት ምክያቱ በቂ የህክምና ክትትል ማጣት ነው ሲሉ ይኮንናሉ። ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ላለፉት ሁለት ዓመት በእስር ላይ የቆየ ሲሆን፤ "ሐሰተኛ ዜናዎችን ማሰራጨት" እና "የሕገ-ወጥ ድርጅት አባል መሆን" የሚሉ ክሶች ተመስርተውበት ነበር። ሻዲይ ሐባሽ ለአስር የተዳረገው ከአገር ውጪ በስደት የሚገኘውን የራሚይ ኢሳም 'ባላህ' የተሰኘ ሙዚቃ ዳይሬክት [ካዘጋጀ] ካደረገ በኋላ ነበር። 'ባላህ' የሚለው ቃል በግብጽ ዝነኛ ፊልም ላይ ውሸታም ገጸ ባህሪን ወክሎ የሚተውንን ሰው ይወክላል። የፕሬዝደንት አል-ሲሲ ተቺዎችም ፕሬዝደንቱን 'ባላህ' ሲሉ ይጠሯቸዋል። የዘፈኑን ግጥም የጻፈው ጋላል ኤል-ቤሃይሪ ከሁለት ዓመት በፊት የሶስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። ሻዲይ ሐባሽ ለሁለት ዓመታት በእስር ላይ ሲቆይ ለፍርድ አለመቀርቡ የፈጠረበትን ተስፋ ቢስነት በአንድ ደብዳቤ ላይ ገልጾ ነበር። ሻዲይ ሐባሽ "መቼ እና እንዴት እንደምወጣ ሳላውቅ በብቸኝነት ወደ አንደ ክፍል ከተወረወርኩ ሁለት ዓመታት አለፉ" ያለ ሲሆን ጨምሮም፤ "እስር አይደለም የሚገድለው፤ ብቸኝነት ነው" ብሎ ነበር። ጠበቃ አህመድ አል-ካህዋጋ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል እንደተናገሩት፤ ኮቪድ-19 ወደ እስር ቤት እንዳይዛመት በማሰብ የግብጽ መንግሥት በማረሚያ ቤት ያሉ ሰዎች መጠየቅን መከልከሉን ተከትሎ በቅርቡ ሻዲይ ሐባሽን የጎበኘ ሰው የለም። ጠበቃው እንዳሉት ሻዲይ ሐባሽ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ወደ ማረሚያ ቤቱ ከተመለሰ በኋላ ዓርብ ምሽት ህይወቱ አልፏል። ማክሰኞ ዕለት አቃቢ ሕጉ በበኩላቸው ሐበሻ ወደ ሆስፒታል ባመራበት ወቅት ከመሞቱ አንድ ቀን በፊት ከፍተኛ መጠን ያለው እጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር መጠጣቱን ተናግሯል ብሏል። ሻዲይ ሐባሽ ሳኒታይዘሩን የጠጣው ከውሃ ጋር ተመሳስሎበት መሆኑን እና ከፍተኛ የሆድ ህመም ሲሰማው እንደነበረ ለሃኪሞች መናገሩን አቃቤ ሕጉ ጨምረው ተናግረዋል። ይህን የሻዲይ ሐባሽን ሞት ምክንያት የሚጠራጠሩ በርካቶች ናቸው። መንግሥት ለወጣቱ ፊልም ባለሙያ ሞት እንደምክንያት ያቀረበው ብዙ አጠራጣሪ ነገሮች አሉበት ይላሉ። ከፍተኛ ህመም ላይ ከነበረ ለምን በቂ ህክምና አልተደረገለትም፣ ሕግን በተጻረረ መልኩ ለምን ክስ ሳይመሰረትበት ለሁለት ዓመታት በእስር ላይ እንዲቆይ ተደረገ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።
news-53967067
https://www.bbc.com/amharic/news-53967067
ኢትዮጵያ፡ አምባሳደር ፍፁም አሜሪካ እንዳይሰጥ ያገደችው ገንዘብ 'ጊዜያዊ' ነው አሉ
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ አሜሪካ ቀደም ሲል ለኢትዮጵያ ልትሰጥ አቅዳው የነበረው ገንዘብ ድጋፍ እንዳይሰጥ የተደረገው "በጊዜያዊነት" ነው ሲሉ ገለጹ።
አምባሳደሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የገንዘብ ድጋፉ የተያዘው ለአጭር ጊዜ መሆኑን ከሚመለከታቸው የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊዎች እንደተረዱ ጠቅሰዋል። አምባሳደር ፍጹም አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመደበችው 130 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዳይሰጥ መወሰኗ ከተሰማ በኋላ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ገልጸው የነበረ ሲሆን በዚሁ መሰረት ነው ገንዘቡ በጊዜያዊነት እንዳይሰጥ መደረጉን እንደተረዱ ያመለከቱት። በመጀመሪያ ላይ ይህንን የአሜሪካ መንግሥትን ውሳኔ በተመለከተ ይፋ ያደረገው 'ፎሬይን ፖሊሲ' የተባለው መጽሔት ሲሆን፤ መጽሔቱ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠጥ የመደበችውን 130 ሚሊዮን ዶላር ላለመስጠጥ መወሰኗል የውስጥ ምንጮቹን ጠቅሶ ከቀናት በፊት ዘግቦ ነበረ። መጽሔቱ አሜሪካ ለደረሰችበት ለዚህ የእርዳታ ገንዘቡ እገዳ ውሳኔ ምክንያቱ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ካለው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ እንደሆነ በዘገባው አስነብቧል። አምባሳደር ፍጹም አረጋም በገጻቸው ላይ የ130 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዳይሰጥ መወሰኑን እንደሰሙና ከአሜሪካ መንግሥት በኩል ማብራሪያ መጠየቃቸውን ጠቅሰው "ጉዳዩ በሕዝባችን ጥሪት እየገነባነው ካለው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር እንደሚያያዝ ሰምተናል" ብለዋል። አምባሳደር ፍጹም በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚመለከታቸው የአሜሪካ ባለስልጣናት በኩል ማብራሪያ ጠይቀው ቀጠሮ ተሰጥቷቸው እንደነበረ ገልጸው የነበረ ሲሆን ትናንት "በቀጠሮአችን መሠረት ተገናኝተን ማብራሪያውን አግኝተናል። ጉዳዩ 'Temporary Pause' [በጊዜያዊነት እንዲቆም የተደረገ] እንደሆነ ተረድተናል" ሲሉ በገጻቸው ላይ አስፍረዋል። አምባሳደር ፍጹም ከየትኞቹ የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር እንደተወያዩና "የገንዘቡ ድጋፍ በጊዜያዊነት እንዲቆም ስለመደረጉ ተረድተናል" ከማለት ውጪ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ አልሰጡም። አምባሳደሩ ጨምረውም "ግድቡ የኛ ነው! ተባብረን እንጨርሰዋለን! በጥረታችን ኢትዮጵያችን በብርሃን ትደምቃለች!" ሲሉም በማኅበራዊ ገጾቻቸው ላይ አስፍረዋል። አሜሪካ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ዋሽንግተን ውስጥ ሲደረግ የነበረውን ድርድር ስታስተናግድ የነበረች ሲሆን ኢትዮጵያ በመጨረሻ ላይ የቀረበው የስምምነት ሰነድ ሳትቀበለው ፊርማዋን ሳታኖር መቅረቷ ይታውሳል። በአገራቱ መካከል በሚደረገው ድርድር ውስጥ ተጽእኖ ለማሳደር ሙከራ አድርጋለች ስትባል የቆየችው አሜሪካ፤ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ያቀደችውን የ130 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መያዟ በአገሪቱ ላይ ጫና ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ አንዳንዶች ይናገራሉ። አሜሪካ፤ ኢትዮጵያ በቢሊዮኖች ዶላር አውጥታ ለዓመታት ስትገነባው የቆየችውና ወደ መጠናቀቁ እየተቃረባ ባለው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ሲካሄድ በቆየው ድርድር ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሸማጋይነት ብትቆይም ጥረቷ ሳይሳካ ቀርቷል። ፎሬይን ፖሊሲ ወደ 130 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የእርዳታ ገንዘብ ታገደ ባለው ዘገባው፤ የገንዘቡን እግድ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፔዮ ፊርማቸውን ማኖራቸውን ጠቅሷል። ፎሬን ፖሊሲ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ በሰራው ዘገባ ገንዘቡ የታገደው ለደኅንነት፣ ለጸረ-ሽብር፣ ለወታደራዊ ትምህርት እና ስልጠና እንዲሁም የሰው ልጆች ዝውውርን ለመግታት ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፈ አካል ነው እንጂ ይህ የእርዳታ ገንዘቡ እግድ የጤና እና የምግብ እርዳታ የመሳሰሉ ድጋፎችን አይመለከትም ብሏል።
news-50279537
https://www.bbc.com/amharic/news-50279537
ኃይሌ ገብረሥላሴ ለ78 ሰዎች ሞት ፌስቡክን ወቀሰ
በፌስቡክ ላይ የተሰራጩ ሐሰተኛ ዜናዎች ከሳምንት በፊት በአገሪቱ ተከስቶ ለ78 ሰዎች ሞት ሰበብ ለሆነው ግጭትና ጥቃት ምክንያት እንደሆነ ኢትዮጵያዊው ስመጥር ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ ለቢቢሲ ተናገረ።
ችግሩ የተቀሰቀሰው ከፍተኛ ተጽእኖና ተደማጭነት ያለው የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተርና አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ የመንግሥት ባለስልጣናት የተመደቡለትን የግል ጠባቂዎቹን በማንሳት ህይወቱን ለአደጋ ለማጋለጥ ሞክረዋል በማለት ያሰራጨውን የማህበራዊ መገናኛ መድረክ መልዕክት ተከትሎ ነው። • "በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ተቀባይነት ማሳጣት የሚሹ ግጭቱን አባብሰውታል" ቢልለኔ ስዩም መንግሥትና የተለያዩ ወገኖች ለሰዎች ህይወት መጥፋትና ለንብረት ውድመት ምክንያት የሆነው ችግር ሃይማኖታዊና የብሔር ገጽታ እንደነበረው አመልክተዋል። ማህበራዊ የመገናኛ መድረኮች ለችግሩ መባባስ ምክንያት እንደሆኑ የሚያምነው ኃይሌ ገብረሥላሴ አንዳንድ መልዕክቶችን ከገጹ ላይ እንዲነሱ ካላደረገ ፌስቡክን ሊከስ እንደሚችል ተናግሯል። ከዚህ አንጻር የትኞቹ የፌስቡክ መልዕክቶች እንዲነሱ እንደሚጠይቅ በግልጽ ባይናገርም፤ አዲስ አበባ ውስጥ ለቢቢሲ "ሐሰተኛ ዜናዎች በቀላሉ መሰራጨት ይችላሉ" ሲል ገልጿል። • "በመንግሥት መዋቅር ሥር ሆነውም ግጭቶችን የሚያባብሱ እንዳሉ እናውቃለን" ኢዜማ ሰማኒያ ለሚጠጉ ሰዎች መገደል ዋነኛ ምክንያቱ "ፌስቡክ ነበር ብዬ አምናለሁ" ሲል የ46 ዓመቱ ኃይሌ የወቀሳ ጣቱን በፌስ ቡክ ላይ ጠቁሟል። ጃዋር መሐመድ በፌስቡክ ላይ ያሰፈረውን መልዕክት ተከትሎ በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ሳቢያ በኦሮሚያና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለቀናት በዘለቀው ሁከት፤ የሞትና የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ከቤት ንብረታቸው ሸሽተው በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የጃዋርን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ነገር እንዲፈጠር አለማድረጋቸውን በመግለጽ፤ ለክስተቱ መፈጠር የጃዋርን ጥበቃ በማንሳት በኩል የተሳተፉ ሰዎች ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ እርምጃ እንደሚወስዱ ገልጸዋል። ከተከሰተው ሁከት ጋር የተያያዙ ናቸው በሚል በሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚያሳዩ አሰቃቂ ፎቶና ቪዲዮዎች በማህበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ ሲታዩ ሰንብተዋል። • ኦሮሚያ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ሁከት 359 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ኃይሌ እንደሚያምነው ምስሎቹ የሚያሳዩት በኢትዮጽያዊያን የተፈጸሙ ድርጊቶች አይደሉም ብሎ ነው። "ወገኖቼን አውቃቸዋለሁ፤ እንዲህ አይነት አስቀያሚ ድርጊቶችን አይፈጽሙም" ብሏል። አለመረጋጋቱ በተከሰተበት ጊዜ አንድ የአካባቢ ባለስልጣን ወጣቶችን አስታጥቃለሁ አለ የተባለበትን ጨምሮ ሌሎች ሐስተኛ ቪዲዮዎች በማህበራዊ መድረኮች ላይ ተሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል። የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡባት እለት አንስቶ ስለአንድነት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ጥሪ ከማቅረብ ባይቆጠቡም በአገሪቱ የሚታየው የብሔር ውጥረት ከቁጥጥር ውጪ እንዳይወጣ ስጋት አለ። ከሩጫው ባሻገር ስኬታማ የንግድ ሰው የሆነው ኃይሌ ገብረሥላሴ፤ በሩዋንዳ የተከሰተው የዘር ፍጅት ካጋጠመ ረጅም ጊዜ አለመሆኑን በማስታወስ "ኢትዮጵያ ልትጠነቀቅ ይገባል" በማለት አሳስቧል። • "ክስተቱ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ ነው የምረዳው" ጀዋር መሐመድ ኃይሌ ጨምሮም ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ከሆኑ በኋላ ምን ሊከሰት እንደሚችል ለማሳየት ሊቢያ፣ ሶሪያና የመን የገቡበትን ችግር እንደ ምሳሌ ጠቅሷል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ካጋጠመው ግጭትና ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ የአገሪቱ ባለስልጣናት ከ400 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው የተነገረ ሲሆን ችግሩ የገጠማቸው አካባቢዎችም ወደ መረጋጋት እየተመለሱ መሆኑ እየተነገረ ነው። ፌስቡክ ኃይሌ ገብረሥላሴ ላቀረበው ክስ ምላሽ ያልሰጠ ቢሆንም፤ ድርጅቱ ግን "የሐሰተኛ ዜናዎችን ስርጭት ለመግታት" እንደሚሰራ የሚያመለክት ፖሊሲ አለው።
news-45167730
https://www.bbc.com/amharic/news-45167730
የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች እንዴት ሥራ ያገኛሉ?
ክረምት አዳዲስ ምሩቃን ከትምህርት ዓለም ወደ ሥራ ፍለጋ የሚሸጋገሩበት ነው።
በሚሊኒየም አዳራሽ የተካሄደው ስራ ማፈላለጊያ መድረክ በርካቶች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም መመረቅ የሚሰጠውን ደስታ አጣጥመው ሳይጨርሱ ሥራ አገኝ ይሆን? በሚል ስጋት ይዋጣሉ። ሥራ ማፈላለጊያ የትምህርት ማስረጃ ከማሰናዳት አንስቶ በየማስታወቂያ መለጠፊያው ማማተር፣ እድለኛ ከሆኑ ደግሞ ለሥራ ቅጥር ግምገማ የጽሁፍና የቃል ፈተና መዘጋጀትም ይጠበቅባቸዋል። ምሩቃን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ አሟልተውም ሥራ ለማግኘት ሲቸገሩ ይታያል። • ለተመራቂ ተማሪዎች አምስት ጠቃሚ ነጥቦች • መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ፕሮግራም የተመረቁ ተማሪዎች መምህር ለመሆን "ብቁ አይደሉም" ሥራ ፍለጋን ለማቅለል እንዲሁም ቀጣሪና ተቀጣሪን በአንድ መድረክ ለማገናኘት ያለመ መርሀ-ግብር ያሳለፍነው አርብና ቅዳሜ ሚሊኒየም አዳራሽ ውስጥ ተካሂዶ ነበር። መድረኩ አዳዲስ ምሩቃን የትምህርት ማስረጃቸውን ሊቀጥሯቸው ለሚችሉ ድርጅቶች እንዲሰጡ እድል አመቻችቷል። የትምህርት ማስረጃቸው በቀጣሪዎች ለማስገምገም በቦታው ከተገኙት መካከል ኬነሳ ሒካ ገምቴሳ እና ፌነት ማስረሻ ይገኙበታል። ኬነሳ የአካውንቲንግና ፋይናንስ ምሩቅ ፌነት ደግሞ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ተመራቂ ናቸው። ኬነሳ ከዚህ ቀደም በዋነኛነት ሥራ የሚፈልገው ጋዜጣ ላይ ነበር። ስለ መርሀ-ግብሩ ከሰማ በኋላ በደረጃ ዶት ኮም ድረ ገጽ ተመዝግቦ ተሳታፊ ሆኗል። "ፍላጎቴ የትኛውም ድርጅት ሲቪዬን ተመልክቶ ቢቀጥረኝ ነው" ይላል። ተመራቂዎች የትምህርት ማስረጃቸውን ለቀጣሪዎች ሰጥተዋል ፌነት በበኩሏ "መድረኩ አዳዲስ ተመራቂዎች ሥራ እንዲያገኙ ያግዛል" ስትል በመርሀ ግብሩ የተገኙት ተቋሞች የትምህርት ማስረጃዋን ገምግመው ብቁ ከሆነች ሥራ እንደምታገኝ ተስፋዋን ትናገራለች። መርሀ ግብሩ ቀጣሪዎች በተለያየ መስርያ ቤት ልምድ ላካበቱ ሰራተኞች ብቻ ሳይሆን ለአዳዲስ ምሩቃንም የቅጥር እድል እንዲሰጡ ለማሳሰብ ያለመመም ነበር። የኢትዮ ጆብስ ወይም ኢንፎ ማይድስን ሶሉሽንስ ሪጅናል ዳይሬክተር ህሊና ለገሰ እንደምትናገረው መሰናዶው ዋነኛ አላማው በተመራቂዎችና ቀጣሪዎች መካከል ድልድይ መፍጠር ነው። አብዛኛውን ጊዜ ተመራቂዎች የት ተቋም ማመልከት እንዳለባቸው አያውቁም። ቀጣሪዎች በአንጻሩ አዳዲስ ተመራቂዎችን ለመቅጠር ተነሳሽነት አያሳዩም። ክፍተቱን ለመሙላት በሚል ኢትዮ ጆብስ፤ ደረጃ ዶት ኮም ከተሰኘ ድረ ገጽ እንዲሁም ከትምህርት ሚንስቴር ጋር በመተባበር የሥራ ማፈላለጊያ መድረክ (ጆብ ፌር) አዘጋጅቷል። በመድረኩ 250 ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ ከሦስት ሺህ በላይ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ለተመራቂዎቹ አቅርበዋል። በ2010 ዓ. ም የተመረቁ ተማሪዎች በኢትዮ ጆብስ ድረ ገጽ ካመለከቱ በኋላ የመድረኩ ታሳታፊ ሆነዋል። ተመራቂዎቹ ስራ የማግኘት ተስፋ ሰንቀዋል በዚህ መድረክ ላይ ተሳታፊ ለሆኑት በዳይሬክተሯ አማካይነት ተማሪዎቹ ሥራ ለመፈለግ የትምህርት ማስረጃ (ካሪኩለም ቪቴ ወይም ሲቪ) ስለሚጽፉበት መንገድ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። "ብዙ ድርጅቶች ልምድ ያላቸው ሰራተኞች መቅጠር ይፈልጋሉ። ሆኖም አዳዲስ ምሩቃንም ስልጠና ከተሰጣቸው የመቀጠርና የማደግ አቅም እንዳላቸው ማሳየት እንፈልጋለን" ትላለለች። በመድረኩ ወደ 20 ሺህ ተማሪዎች ከመሳተፋቸው ባሻገር ሰባት ዩኒቨርስቲዎች ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር እንዲገናኙ ተደርጓል። በየዓመቱ ከ160 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ይመረቃሉ። ተመራቂዎቹ ሥራ በሚፈልጉበት ወቅት ምን እንደሚጠበቅባቸው ስልጠና መውሰድ እንዳለባቸው ህሊና ታምናለች። ለተወሰነ ጊዜ በአንድ ድርጅት ተቀጥረው የሙከራ ሥራ (ኢንተርንሺፕ) እንዲሰሩ ማድረግም ከተመረቁ በኋላ ለሚጠብቃቸው የሥራ ዓለም ያግዛል ትላለች። "ተማሪዎች የተሻለ ክህሎትና የመቀጠር ብቃት እንዲኖራቸው ተደርገው መመረቅ አለባቸው" ትላለች። መርሀ ግብሩን ዓመታዊ የማድረግ እቅድ አለ።
news-49816454
https://www.bbc.com/amharic/news-49816454
የ40 ሺህ ብር ጉቦ አልቀበልም ያለው ዋና ሳጅን ሲራጅ ምን ይላል?
ዋና ሳጅን ሲራጅ አብደላ በአፋር ክልል ዞን አንድ፤ ኤሊዳአር ወረዳ ማንዳ ቀበሌ በፖሊስነት ሙያ ላይ ተሰማርቶ ይሰራል። ሳጅን ሲራጅ በፖሊስነት መሥራት ከጀመረ ገና አንድ ዓመት ተኩል አካባቢ እንደሆነው ይናገራል።
አካባቢው ድንበር በመሆኑ ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውሮችና ኮንትሮባንዶች የሚበዙበት አካባቢ እንደሆነ በቆይታው ተገንዝቧል። ታዲያ ባለፈው ሐሙስ መስከረም 8 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ አምስት ሰዓት ገደማ አንድ ተሽከርካሪ ባዶውን ለማለፍ ሲሞክር ይመለከታል። በወቅቱ በሥራ ላይ እሱን ጨምሮ አራት የፖሊስ አባላት የነበሩ ቢሆንም በወቅቱ ወደ መንገዱ ያመራው ግን እርሱ ብቻ ነበር። መንገድ በመዝጋት ተሽከርካሪው እንዲቆም ትዕዛዝ ሰጠ። ትዕዛዝ በተሰጠው መሠረት አሽከርካሪው መኪናውን አቆመ። ምንም የጫነው ነገር አልነበረም። ጋቢና ውስጥ ግን ሹፌሩ፣ ረዳቱና ሌላ ባለቤት እንደሆኑ የተነገረው አንድ ሰው ነበሩ። በዚህ ሌሊት ምንም ጭነት ሳይዝ ምን ያስጉዛቸዋል? ሲል ሲራጅ ጥርጣሬ ያድርበታል። "ቦታው ግንባር በመሆኑ ከመከላከያ መኪና በስተቀር ሌሎች መኪናዎች እምብዛም አያልፉም" ሲል በዋናነት ወደ ጥርጣሬ የከተተውን ምክንያት ይናገራል። ከዚህም ባሻገር ቀደም ብሎ ከሕብረተሰቡ ጥቆማ ደርሶት እንደነበርም ያክላል። ከዚያም ተሽከርካሪውን የእጅ ባትሪ አብርቶ መፈተሽ ይጀምራል። ጥርጣሬው እውነት ሆኖም ከተሽከርካሪው ጎማ በላይ የታሰረ ጆንያ ያያል። • ፖሊስ አንድን ወጣት ሲደበድብ በተንቀሳቃሽ ምስል ያስቀረው የዐይን እማኝ • በጎንደር ከ3ሺህ በላይ የመትረየስ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ "ይህ ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል። ግለሰቦቹ "እኛ የምናውቀው ነገር የለም" የሚል መልስ ቢሰጡትም በፍተሻው 29 ክላሽንኮቭ የጦር መሣሪያ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያመሩ ትዕዛዝ ይሰጣል። እነርሱ ግን አንድ መሣሪያና አርባ ሺህ ብር በመስጠት መደራደር ጀመሩ። ከዚያም አርባ ሺህ ብሩን በመያዝ ከእነመሣሪያቸው በቁጥጥር ሥር ሊያውላቸው ችሏል። "አርባ ሺህ ብር እና አንድ መሳሪያ ከአገር ደህንነት አይበልጥም" ይላል ምክንያቱንም ሲያስረዳ። ሳጅን ሲራጅ ከዚህ ቀደም በነበረው አጭር የሥራ ልምድ እንዲህ ዓይነት ጉዳይ አጋጥሞት እንደማያውቅ ይናገራል። ይህ ዜና ከተሰማ በኋላ ግን ዝናው ናኘ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድም ይህንን የፖሊስ አባል ጽህፈት ቤታቸው ድረስ ጠርተው የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክትውለታል። እንኳንስ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ከማንም ሽልማት ይበረከትልኛል ብሎ ያላሰበው ዋና ሳጅን ሲራጅ፤ ሽልማቱ ደስታንና መበረታታትን እንደፈጠረለት ይናገራል። "ወደፊትም እንደዚህ ዓይነት ሕገ ወጥ ተግባር ብናይ ማለፍ እንደሌለብን በሥልጠናችን ወቅት አስቀድመን ቃል የገባንበት ጉዳይ ነው" ሲል የሙያ ግዴታው እና ኃላፊነቱ የሕዝብንና የአገር ደህንነትን ማስጠበቅ እንደሆነ ያስረዳል። የክልሉ መንግሥትም ለፖሊስ አባሉ የ50 ሺህ ብር ሽልማት አበርክቶለታል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንም የዋና ሳጅንነት ማዕረግ እንደሰጠው የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ቢኒ ለቢቢሲ ገልፀዋል። " '40 ሺህ ብር ሊሰጡት ነበር 'እምቢ' ብሎ ነው' ብለን ለክልሉ ፕሬዚደንት ስንነግራቸው፤ ከእነርሱ የበለጠ ነው የምንሸልመው ብለው ነው 50 ሺህ ብር የሸለሙት" ሲሉ የክልሉ ፕሬዚዳንት በወቅቱ የተሰማቸውን ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል። እርሳቸው እንደሚሉት መሣሪያው በቁጥጥር ሥር የዋለበት ቡሬ ግንባር፤ ድንበር በመሆኑ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የኮንትሮባንድ ንግድና ሕገ ወጥ የመሣሪያ ዝውውር ያጋጥማል። • በአዲስ አበባ ሊፈጸም የነበረ የሽብር ጥቃት መክሸፉ ተነገረ • ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዙት የአል ሸባብና የአይ ኤስ አባላት ማንነት ይፋ ሆነ በዚህም ምክንያት የፖሊስ አባላቶቻቸው ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ግንዛቤ መስጠት ዝንፍ የማይሉበት ተግባራቸው ነው። በመሆኑም ሲራጅ ከሕብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በገንዘብ ሳይደለል ሕገወጥ የመሣሪያ አዘዋዋሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋል ችሏል ይላሉ። ለዚህም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የፖሊስ አባሉ ለሕግ የበላይነት ላበረከተው አስተዋፅኦ የእውቅና የምስክር ወረቀት እና ሜዳሊያ አበርክተውለታል። የፌደራል ፖሊስም የምስክር ወረቀትና ሞባይል ስልክ ሸልሞታል። ኮሚሽነሩ አክለውም ዋና ሳጅን ሲራጅ ሲሠራበት የነበረበት ቦታ ላይ ዳግም ድል እንደሚያስመዘግብ ተስፋ እንዳላቸው ነግረውናል። "የተሽከርካሪውን ሹፌር ባነጋገርኩበት ወቅት፤ 'መኪናው ባዶ በመሆኑ ጠለቅ ያለ ፍተሻ አይደረግብንም' በማለት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሲሰጣቸው እንደቆሙ ነግሮኛል" ሲሉ የማምለጥ ሙከራ እንዳላደረጉ ኮሚሽነሩ ገልፀውልናል። ወዲያው ጥበቃ ላይ የነበሩ ሌሎች ፖሊሶችና የአካባቢው ማኅበረሰብ ትብብር እንዳደረጉለት በመጥቀስ። ሕገወጥ መሣሪያ በማዘዋወር የተጠረጠሩት ግለሰቦች እና ተሽከርካሪው በአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በእስር ላይ ሆነው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። ከአንድ ወር በፊት፤ አንድ ተሽከርካሪ በዚያው ክልል 'ሰርዶ' የተባለ ኬላ ጥሶ በማለፍ ሎግያ መግቢያ ላይ የጦር መሣሪያና በርካታ ጥይቶችን እንደጫነ መያዙን አስታውሰዋል። ምንም እንኳን እስካሁን ጉቦ በመቀበል ተጠርጥረው የተያዙ የፖሊስ አባላት ባይኖሩም፤ ሕገ ወጦች የፀጥታ አባላትን በተለያየ መንገድ በማማለል የማይሰሩት ሥራ ስለሌለ ሙስና ይኖራል ብለው ያስባሉ- ኮሚሽነሩ። ይሁን እንጅ በክልሉ ጉቦ ሲቀበሉ በቁጥጥር ሥር የዋሉ የፖሊስ አባላት አለመኖራቸውን ገልፀውልናል።
54920175
https://www.bbc.com/amharic/54920175
ትግራይ፡ በኢትዮጵያ የተከሰተው ግጭት ጎረቤት አገራትን ያሰጋ ይሆን?
በኢትዮጵያ በፌደራል መንግሥቱና እና በትግራይ ክልል መስተዳደር መካከል የሚደረገው ውጊያ በአገሪቱ መጻዒ ዕጣ ላይ ከሚደቅነው ፈተና በተጨማሪ የጎረቤት አገራትንም በእጅጉ ይጎዳል።
ጦርነቱ በተጀመረ በቀናት ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ "የኢትዮጵያ የተረጋጋች አገር መሆን ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና በአጠቃላይ አስፈላጊ ነው" ብለው ነበር። ኢትዮጵያ ከ110 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ያላት ሲሆን ምጣኔ ሃብቷም በአህጉሪቱ ካሉ ሌሎች አገራት ጋር ሲነጻፀር በፍጥት እያደገ መሆኑ ጦርነቱ በአገሪቱ ላይም ተጽዕኖው ቀላል እንዳይሆን ያደርገዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መንግሥት ከትግራይ ክልል ጋር ያለውን ልዩነት በድርድር እንዲፈቱ ከተለያዩ የዓለም መንግሥታት የቀረበላቸውን ጥሪ "የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይከበሩ" በሚል ችላ ብሏቸዋል። መንግሥት ግጭቱን በኢትዮጵያ ያለውን የሕገ መንግሥት ሥርዓት ለማፍረስ ከሚጥር አካል ጋር የሚደረግ "የሕግ ማስከበር" ተግባር መሆኑን ይገልጻል። ይህ ጦርነት በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል ለረዥም ጊዜ የነበረን ውጥረት ተከትሎ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች የአየር ድብደባውን እና ውጊያውን ሽሽት ወደ ጎረቤት ሱዳን ሸሽተዋል። "ተጽዕኖው ከፍተኛ ነው" የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ራሺድ አብዲ "ጦርነቱ ቀጠናዊ ነው" ሲሉ ይሞግታሉ። "ሱዳናውያን ተሳተፈዋል እንዲሁም ሌሎች አገራትም አንድ ቦታ ላይ መሳተፋቸው አይቀርም፤ ምክንያቱም ስትራቴጂካዊ አገር [ኢትዮጵያ] ናት። ስለዚህ ተጽዕኖው ከፍተኛ ነው" ብለዋል። እንደ ራሺድ ከሆነ ከትግራይ ክልል ጋር ረዥሙን ድንበር የምትጋራው ኤርትራም ወደ ጦርነቱ መጎተቷ አይቀርም። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደግሞ የትግራይን ክልል ከሚያስተዳድረው ፓርቲ ህወሓት ጋር ያላቸው ግንኙነት የሻከረ ነው። በተቃራኒው ፕሬዝዳንቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ደግሞ የቅርብ አጋር ናቸው። እስካሁን ግን የኤርትራ መንግሥት በፌደራል እና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል ባለው ጦርነት ውስጥ እጁ እንደሌለበት ገልጿል። በሌላ ወገን የፌደራል መንግሥቱ ትኩረቱን ሁሉ በትግራይ ክልል ላይ ማድረጉ በሶማሊያ የአልሸባብ አማፂያንን ለመከላከል የሚያደርገው ተሳትፎን እንደሚያዳክመው ራሺድ አብዲ ይገልጻሉ። አክለውም ኢትዮጵያ ምንም እንኳ የአፍሪካ ሕብረት ያሰማራቸው የአሚሶም ጦር አባላት ባይሆኑም፣ ከሶማሊያ ምዕራባዊ ድንበር 600 ወታደሮቿን አስወጠታለች። "ሁኔታዎች ከዚህ በላይ እየከፉ የሚሄዱ ከሆነ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከአሚሶምም ሊወጡ ይችላሉ፣ ያ ደግሞ ከባድ ቀውስ ነው. . . አልሸባብ ዳግም እንዲጠናከርና እንዲሰባሰብ ያደርገዋል" ይላሉ። ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕም ግጭቱ በፍጥነት ካልቆመ "ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድን በአጠቃላይ ቀውስ ውስጥ ይጥላል" በማለት በዚህ ሃሳብ ይስማማል። ኢትዮጵያስ እንደ አገር? የሁለቱ መንግሥታት ጦርነት የኢትዮጵያ ጎረቤት አገራት ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ እንዳለ ሆኖ ጦርነቱ ኢትዮጵያንም እንደ አገር ያዳክማታል የሚሉ ወገኖች አሉ። ያ ደግሞ ኢትዮጵያ በቀጠናው ላይ ባላት ተሳትፎ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ሌሎች በአገሪቱ የሚገኙና ነፍጥ አንስተው ለመታገል የወሰኑ ወገኖች በማዕከላዊ መንግሥቱ ላይ እንዲያምፁ ያደርጋቸዋል። አብዲ ረሺድ ይህንን ሲያስረዱ "እያየነው ያለነው ምንድን ነው ተጽዕኖው ከማዕከል እየራቀ ማዕከላዊው መንግሥት ደግሞ እየተዳከመ መሆኑን ነው" ይላሉ። ይሀ ግን መቀመጫውን ናይሮቢ ላደረገው የአፍሪካ ቀንድ ቲንክ ታንክ ተቋም ባልደረባ ሃሰን ካህናንጄ አልተዋጠለትም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሁን እየወሰዱት ያለው እርምጃ የትግራይ ክልል መንግሥትን ወደ ሕጋዊ መስመር ለማምጣትና ሌሎችም እንደ ምሳሌ ወስደው እንዳይከተሉት የማድረግ ነው ሲል ይሞግታል። "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ይህንን የሚያየው ለሌሎች ክልሎች መጥፎ ምሳሌ እንደሆነ ነው. . . ወደ መገንጠል የሚያመራ የተናጠል ውሳኔ ለኢትዮጵያ መነጣጠል ነው፤ ያ ደግሞ ኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠሏ ያበቃል ማለት ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግሯል። "የመጨረሻው ግብ ክልሉን ወደ ፌደራላዊ ሥርዓቱ በማምጣት እንደ አንድ አገር ምርጫ ማካሄድ ነው። በተግባር ሲታሰብ በጣም ከባድ ቢሆንም የማይቻል ግን አይደለም።" በዚህ መካከል ቀውሱን በመፍራትም ሆነ በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቤታቸውንና ቀያቸው ጥለው ይሰደዳሉ ሲሉ ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባይ አርብ ዕለት ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት፣ በአካባቢው እየመጡ ያሉ የስደተኞች ቁጥር ከፍተኛ ሲሆን "አሁን እርዳታ ማቅረብ ከምንችለው በላይ ነው" ብለዋል። የሱዳን መንግሥትም 20ሺህ ሰዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ የሚችል የስደተኞች መጠለያ ከድንበሩ በ80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ለመገንባት ፈቃደኛ መሆኑ እና ሌሎች አካባቢዎችም መለየታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። አካባቢው በበረሃ አንበጣ የተጎዳ መሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ የምግብ እጥረት እንዲከሰት ማድረጉን የጠቀሰው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ሌላ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ዳግም ሊከሰት እንደሚችል ተንብይዋል። ትግራይ ክልል ከአጠቃላይ ሕዝቡ 10 በመቶ ያህሉ፣ 600ሺህ ያህሉ የምግብ እህል እርዳታ የሚጠብቅ ሲሆን፣ በመላ አገሪቱ ደግሞም ሰባት ሚሊዮን ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋላጭ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ይገልጻል። ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት ይጨምራል። ኢትዮጵያ ያላት ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥርና ስትራቴጂካዊ ስፍራነቷ በኢትዮጵያ የሚከሰት ጦርነትም፣ የሰብዓዊ ቀውስ ሆነ ማንኛውንም ነገር ወደ ሌሎች አይዛመትም ብሎ መደምደም አይቻልም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ግን ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ለመቋጨትና ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው በሚል አቋማቸው እንደፀኑ ናቸው። ነገር ግን ይህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ባይሳካና ለረዥም ጊዜ አገሪቱ ጦርነት ውስጥ የምትቆይ ከሆነ ጦሱ ለጎረቤት አገራትም መትረፉ አይቀሬ ነው።
news-52983709
https://www.bbc.com/amharic/news-52983709
በህዳሴው ግድብ ድርድር በታዛቢዎች ሚና ላይ ስምምነት አለመደረሱ ተነገረ
ለወራት ተቋርጦ የነበረው በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል የህዳሴው ግድብን በተመለከተ የሚደረገው ድርድር በደቡብ አፍሪካ፣ በአውሮፓ ሕብረትና በአሜሪካ ታዛቢነት ተጀመረ።
ይሁን እንጂ በድርድሩ በታዛቢነት የሚሳተፉት አገራት ሚናን በተመለከተ ምን መሆን ይገባዋል በሚለው ሃሳብ ላይ በተደራዳሪ አገራቱ መካከል መግባባት ላይ እንዳልተደረሰ ተነግሯል። ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለውና ከሱዳንና ከግብጽ ጋር የተራዘመ ድርድርና ውይይት ሲደረግበት የቆየው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የተመለከተው ድርድር መጀመሩን የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። አክሎም ይህ በሦስቱ አገራት መካከል የሚደረገው ድርድር የግድቡ የመጀመሪያ ሙሌትና ዓመታዊ አለቃቅ ላይ ብቻ የተወሰነ እንደሚሆን ተመልክቷል። ድርድሩ ማክሰኞ ሰኔ 2/2012 ዓ.ም በበይነ-መረብ የቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካይነት ቀደም ሲል ተሳታፊ ከነበረችው አሜሪካ በተጨማሪ ደቡብ አፍሪካናና የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ በታዛቢነት በተገኙበት በአገራቱ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ነው የተካሄደው። በዚህ ከወራት በኋላ በተካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባ ተሳታፊ አገራቱ ስለድርድሩ የአካሄድ ሥነ ሥርዓት፣ ስለታዛቢዎችና ሌሎች ዋና ዋና ያልተቋጩ ጉዳዮችን በተመለከተ መወያየታቸው ተገልጿል። በተጨማሪም ተደራዳሪ አገራቱ ቁልፍ የድርድር ጉዳዮች ናቸው ያሏቸውን ሃሳቦች በዝርዝር አቅርበው በቀጣይ ቀናት ተከታታይ ውይይቶችን ለማድረግ ከስምምነት ደርሰዋል ተብሏል። ስምምነት ባልተደረሰበት የድርድሩ ታዛቢዎች ሚናን በሚመለከት ያለውን ልዩነት ላይ መፍትሄ ለማግኘትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ስብሰባው በዛሬው ዕለት [ረቡዕ]ም የሚቀጥል ይሆናል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ እንዳለው "የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ልዩነቶችን በድርድር ለመፍታት ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ዝግጁ ናት" ብሏል።
news-52514029
https://www.bbc.com/amharic/news-52514029
የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በገለልተኛ ሜዳ ሊጠናቀቅ ይሆን?
የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል። የሊጉ ክለቦች ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈለጋሉ ነው የሚሉት።
ሊጉን በ25 ነጥብ እየመሩ ያሉት የሊቨርፑሎች አልፎም ተጫዋቾችና ወደ ሜዳ የሚገቡ ሌሎች ባለሙያዎችን ለመመርመር 40 ሺህ መመርመሪያ መሣሪያዎች ያስፈልጋሉ። የ2019/20 ወድድር ዘመን 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። እነዚህን ጨዋታዎች እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች የቪድዮ ስብሰባ አድርገው ነበር። በስብሰባው ላይ እንደ ሕክምና ባለሙያዎች ያሉ ያገባቸዋል የተባሉ ሰዎችም ተገኝተው ነበር። ክለቦች ሊጉ በቀላሉ ወደ ውድድር እንደማይመለስ መግባባት ላይ ደርሰዋል። የፕሪሚዬር ሊጉ አስተዳዳሪ አካል መንግሥት ይሁንታ ሲሰጥ ብቻ ነው ወደ ሜዳ የምንመለሰው ብሏል። ገለልተኛ ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው ተብሏል። አልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው ተብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው። ሁሉም የሊጉ ክለቦች የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ተስማምተዋል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ተብሏል። የእንግሊዝ መንግሥት እንቅስቃሴዎች ቀስ በቀስ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ካደረገ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በዝግ ሜዳ ወደ ውድድር እንደሚመለስ ይጠበቃል። ተጨዋቾች በሳምንት ሁለት ጊዜ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይደርግላቸዋል። በየቀኑ ደግሞ የበሽታው ምልክት ታየባቸው አልታየባቸው የሚለው ይለካል። አልፎም ሜዳዎች በየጊዜው ንፅህናቸው ይጣራል ተብሏል። ተጫዎቾች ከጨዋታ ውጪ ባሉት ጊዜያት ሁሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ አለባቸው። በውድድር ስፍራዎች ውስጥም ምግብ መብላትም ሆነ ገላን መታጠብ አይችሉም።
news-53831242
https://www.bbc.com/amharic/news-53831242
ኮሮናቫይረስ፡ አውስትራሊያ የኮሮና ክትባት በነጻ እሰጣለሁ አለች
አውስትራሊያ ኮቪድ-19 ክትባትን ለአገሬ ሕዝብ ሽራፊ ሳንቲም ሳልቀበል አድላለሁ ብላለች፡፡
አውትራሊያ 25 ሚሊዮን ለሚሆነው ሕዝቧ የምታድለውን ክትባት የምታገኘው ከእንግሊዝ ነው፡፡ አሁን በሙከራ ላይ ካሉ የክትባት ዜናዎች ሁሉ ላቅ ያለ ተስፋ የተጣለበት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ክትባት ነው፡፡ ኦክስፎርድ ክትባቱን ከታዋቂው የመድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ጋር በመቀናጀት እያዳበረው ይገኛል፡፡ ይህ ክትባት በቀጣይ የሚደረጉ የመጨረሻ ምዕራፍ የክሊኒካል ሙከራዎች ስኬታማ ሆነው ከተጠናቀቁ አውስራሊያ ክትባቱን ለመግዛት ቀዳሚ አገር ሆና ተሰልፋለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን፡፡ ሞሪሰን እንደሚሉት ክትባቱን እያንዳንዱ ዜጋ እንዲወስድ ግዴታ ይጣልበታል፡፡ በአውስትራሊያ የሟቾች ቁጥር 450 አልፏል፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰውም በቪክቶሪያ ግዛት ነው፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ አካባቢ ቪክቶሪያ የአስቸኳይ ጊዜ በመደንገግ ሰዎች ቤታቸው እንዲቀመጡ አስገድዳ ነበር፡፡ ይህም በሽታው ሥርጭት ከፍ ብሎ በመታየቱ ነው፡፡ አሁን በአውስራሊያ 7ሺ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ እንደተነኩ ይገመታል፡፡ ሆኖም አሁን በየቀኑ አዳዲስ ታማሚዎቸ ቁጥር እየጨመረ ሳይሆን እየቀነሰ ነው ያለው፡፡ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲና የአስትራዜኔካ ጥምረት እየተሞከረ ያለው ክትባት በዓለም ላይ አሁን ተስፋ ከተጣለባቸው አምስት ሙከራዎች በዋነኛነት የሚጠቀስ ነው፡፡ አገራት ይህን ክትባት ወደ ገበያ ሲወጣ ቅድሚያ አግኝተው ለሕዝባቸው ለማድረስ ከፍተኛ ፉክክር ላይ ናቸው፡፡ የመጨረሻው የሙከራ ምዕራፍ ስኬታማ ሲሆን አውስራሊያ መድኃኒቱን በአገሯ ለማምረት ተዘጋጅታ ከወዲሁ ስምምነት ፈጽማለች፡፡ ሞሪስ እንደሚሉት ‹‹ወዲያው አምርተን ወዲያው 25 ሚሊዮን ሕዝባችንን እንከትባለን፡፡›› አንድ አገር ሙሉ ሕዝቧን ለመክተብ ምን ያህል ወጪ ያስወጣታል የሚለው ገና አልተሰላም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አውስትራሊያ ሌላ ስምምነት አድርጋለች፡፡ ይህ ስምምነት 25 ሚሊዮን ዶላር አስከፍሏታል፡፡ ስምምነቱ ከአሜሪካ የመድኃኒት ቁሳቁስ አምራች ቤክተን ዲኪንሰን ጋር ሲሆን 100 ሚሊዮን መርፌና ስሪንጆችን ለማቅረብ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ አውስትራሊያ ከአስትራዜኔካ ጋር ያደረገቸው የክትባት ስምምነት በታሪኳ የመጀመርያው ነው፡፡ የአውስትራሊያ ሕዝብ መቼ ይከተባል ለሚለው ሚስተር ሞሪሰን ‹‹ክትባቱ የመጨረሻው ሙከራ ከተሳካ በመጪው ዓመት የመጀመርያዎቹ ወራት አውስትራሊያዊያን ይከተቡታል›› ብለዋል፡፡ ክትባት መከተብ ግዴታ ነው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁሉም ዜጋ የመከተብ ግዴታ ይጣልበታል ቢሉም ይህ አከራካሪ ጉዳይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ሞሪሰን መንግስታቸው በዚህ ረገድ ገና ፖሊሲ እየቀረጸ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለአንድ የአገሬው ራዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሚስተር ሞሪሰን ‹‹በተለየ የጤና ምክንያት መድኃኒቱን ለመከተብ የማይገደዱ›› እንደሚኖሩ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹እያወራን ያለነው የዓለምን ምጣኔ ሀብት ስላንኮታኮተ ወረርሽኝ ነው፡፡ ሺዎችን ሕይወት ስለቀጠፈ ወረርሽኝ ነው፤ ክትባቱ አማራጭ ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም›› ብለዋል አስገዳጅነቱ አይቀሬ መሆኑን ሲያስገነዝቡ፡፡ ሚስተር ሞሪሰን በትንሹ 95 ከመቶ አውስትራሊያዊያንን ለመከተብ እንደታሰበ አልሸሸጉም፡፡
news-57222405
https://www.bbc.com/amharic/news-57222405
አነፍናፊ ውሾች ኮሮናቫይረስ ያለባቸውን እንደሚለዩ ተጠቆመ
አነፍናፊ ውሾች የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ የሳይንስ ሊቃውንት አስታወቁ፡፡
በተካሄደ አንድ ሙከራ መሠረት ውሾች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚያመነጩትን ልዩ የሆነ ሽታ እንዲለዩ ሰልጥነዋል። የሰው አፍንጫ ግን ይህን ሽታ መለየት አይችልም። ይህም በአውሮፕላን ማረፊያዎች ወይም ብዙ ሰዎች በሚገኙበት ዝግጅቶች ቫይረሱ ያለባቸውን ለመለየት ሊረዳ ይችላል፡፡ ውሾቹ የሚለዩዋቸው ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው በቤተ ሙከራ ምርመራ መረጋገጥ አለት ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡ ውሾቹ 88 በመቶ የኮሮናቫይረስን በትክክል ቢለዩምም 14 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ኮቪድ-19 ሳይኖርባቸው ቫይረሱ እንዳለባቸው በስህተት በውሾቹ ተለይወተዋል። የውሾች የማሽተት ችሎታ ከሰዎች እስከ 100,000 እጥፍ ይበልጣል። ለረዥም ጊዜም አደንዛዥ እጽና ፈንጂዎችን ሲለዩ ኖረዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ምርምሮች አንዳንድ የውሻ ዝርያዎች ካንሰር፣ ፓርኪንሰን እና ወባን ጨምሮ የተለያዩ በሽታዎችን በጠረን መለየት እንደሚችሉ አሳይተዋል፡፡ ስድስት ውሾች ኮሮናቫይረስ ያለባቸው ሰዎች የለበሷቸውን ካልሲዎች፣ የአፍና አፍንጫ ጭንብሎች እና የተለያዩ ቲሸርቶችን ሽታ እንዲገነዘቡ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡ ውጤቱን በትክክል ሲገምቱም ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ውሾቹ ከለዩዋቸው እና ቫይረሱ ከሌለባቸው ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ጉንፋን ያለባቸው ሲሆን ይህም የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች መለየት መቻላቸውን ለማረጋገጥ ነው ተብሏል፡፡ ውሾቹ የተለያዩ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎችን ከመለየት ባሻገር ምንም ምልክቶች የሌላቸውን እና በጣም አነስተኛ ቫይረስ በሰውነታቸው ውስጥ ያለባቸውንም ሰዎች ለይተዋል። እንስሳቱን ያሠለጠኑት የሜዲካል ዲቴክሽን ዶግስ ዋና ሳይንቲስት የሆኑት ዶ/ር ክሌር ገስት፤ "ውጤቱ ውሾች የሰውን ልጅ ህመሞችን በማሽተት ለመለየት በጣም አስተማማኝ ከሆኑት የባዮሴንሰሮች አንዱ ስለመሆናቸው ተጨማሪ ማስረጃ ነው" ብለዋል፡፡ ውሾቹ 88 በመቶ የሚሆኑትን ቫይረሱ ያለባቸውን መለየት ችለዋል። ይህም 100 ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች 12ቱን ብቻ መለየት አልቻሉም ማለት ነው፡፡ ኮቪድ-19 ከሌለባቸው 100 ሰዎች መካከል አነፍናፊ ውሾቹ 14ቱ ቫይረሱ አለባቸው ሲሉ በስህተት ለይተዋል። 300 ተሳፋሪዎችን በጫነ አውሮፕላን ውስጥ አንድ ሰው ኮቪድ-19 ካለበት ውሾቹ ግለሰቡን በትክክል ለይተው ማወቅ ይችላሉ። ሆኖም በስህተት 42 መንገደኞች ቫይረሱ አለባቸው ሲሉም ይለያሉ። ይህ ማለት አንዳንድ ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች የማይለዩ ሲሆን ቫይረሱ የሌለባቸው አንዳንድ ሰዎችም በውሾቹ አለባቸው ሊባሉ ይችላሉ፡፡ የተለያዩ መርመሪያ ዘዴዎች ተመሳሳይ ስህተት ይፈጽማሉ። ከተለመደው የአፍንጫ ወይንም የጉሮሮ ፈሳሽን በመጠቀም ከሚደረገው ምርመራ አንጻር ውሾቹ ብዙ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው በተሳሳተ መንገድ ያሳያሉ። በመሆኑም የምርምር ቡድኑ ውሾችን ብቻ በመጠቀም ቫይረሱን ለመለየት መሞከርን አይመክርም፡፡ ውሾቹ ከተለመዱት መርመሪያዎች ጎን ለጎን ተጨማሪ የማጣሪያ መመርመሪያ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው ተመርማሪዎቹ ያምናሉ። የውሻ ምርመራን ከተለመደው የአፍና የአፍንጫ ምርመራ ጋር በማጣመር እስከ 91 በመቶ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ይለያሉ ይላሉ፡፡ ዋነኛው ጠቀሜታ ግን ፍጥነት ነው። በጣም ፈጣን በሚባሉት መመርመሪያዎች ውጤቱን ለማግኘት 15 ደቂቃዎችን ሲወስዱ፤ ውሾች ግን በሰከንዶች ውስጥ በማሽተት ቫይረሱን ሊለዩ ይችላሉ፡፡ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ሁለት ውሾች 300 ሰዎችን በግማሽ ሰዓት ውስጥ መመርመር ይችላሉ፡፡ ጥናቱን ከዱራም ዩኒቨርስቲ ጎን ለጎን ባካሄደው የሎንዶን የንፅህና እና ትሮፒካል ሜዲካል ትምህርት ቤት ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሎጋን ዘዴው "የጅምላ ምርመራ ለማድረግ ተስማሚ ሊሆን ይችላል" ብለዋል፡፡ ሰዎች ለበረራ ወይም ለአንድ ዝግጅት በተሰለፉበት ውሾቹን በመጠቀም መመርመር እና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተለዩትን በመደበኛው የፒ.ሲ.አር. ምርመራ በድጋሚ እንዲመረመሩ ማድረግ ይቻላል። ይህም ወደ ሆቴሎች ለይቶ ማቆያ የሚገቡትን ሰዎች ቁጥር ለመቀነስ ያስችላል፡፡ ብዙ ምርመራ በማይደረግባቸው እንደ ባቡር ጣቢያ ባሉ አካባቢዎች ከፍተኛ የቫይረሱ አሰራጭ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ውሾችን በመጠቀም መለየት ይቻላል ተብሏል፡፡ ጥናቱ ገና በመጀመርያ ምዕራፍ ላይ የሚገኝ ነው። በሳይንስ መጽሔቶች ላይ ከመታተሙ በፊት በሌሎች ሳይንቲስቶች መገምገም እና በመቀጠልም ከልብስ ይልቅ ቫይረሱ ባለባቸው ሰዎች ላይ ሙከራ ማድረግን ይጠይቃል፡፡
50429563
https://www.bbc.com/amharic/50429563
"ቦይንግ እኔ በሌለሁበት አባቴን ቀበረው" በአደጋው አባቷን ያጣችው ዚፓራ
በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ሳቢያ ሕይወታቸውን ካጡት አንዱ የዚፖራ ኩሪያ አባት ናቸው።
ዚፖራ ኩሪያ ባለፈው ሐሙስ በአደጋው የሞቱና አስክሬናቸውን ለመለየት ያልተቻለ ተሳፋሪዎች በተመሳሳይ ሬሳ ሳጥን፣ በመደዳ ተቀብረዋል። ዚፓራ ይህ ሲከናወን በሥፍራው አልተገኘችም ነበር። በዕለቱ የቦይንግና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦታው እንደተገኙ ቢነገርም፤ ዚፓራና ቤተሰቦቿ ስለ ክንውኑ የሰሙት ዘግይተው ስለነበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ አልተኙም። በአደጋው ከሞቱ ተሳፋሪዎች የሦስቱ ቤተሰቦች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ስለ ሥነ ሥርዓቱ የተነገራቸው ከቀናት በፊት ነበር። ስለዚህም በዕለቱ መገኘት የቻሉት ከ157 የሟቾች ቤተሰቦች ሁለቱ ብቻ ናቸው። • በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው • ኬንያውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድንና ቦይንግን ሊከሱ ነው "ቦይንግና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአባቴ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን ሳስበው ያንዘፈዝፈኛል" ስትል ዚፓራ ሀዘኗን ትገልጻለች። እስካለፈው ሳምንት ድረስ አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ሥፍራ የሰዎች አስክሬን እንዲሁም የአውሮፕላኑ ስብርባሪም ይገኝ ነበር። በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ባለፈው ወር አካባቢውን ሲጎበኙ፤ የሰዎች ቅሪተ አካል እና ቁሳቁሶችም ማየታቸው እንዳስደነገጣቸው ተናገረው ነበር። በአደጋው የሞቱና አስክሬናቸውን ለመለየት ያልተቻለ ተሳፋሪዎች በተመሳሳይ ሬሳ ሳጥን፣ በመደዳ ተቀብረዋል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ 302 ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ መዲና ናይሮቢ በረራ በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መከስከሱ ይታወሳል። የሰዎች አስክሬን እና የአውሮፕላኑ የመረጃ ቋትም ተሰብስቦ ነበር። አደጋው የደረሰው በአውሮፕላኑ የበረራ መቆጣጠሪያ እክል ምክንያት ሲሆን፤ ከዓመት በፊት ኢንዶኔዥያ ውስጥም በተመሳሳይ ሁኔታ 737 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሷል። ማክስ 737 ላለፉት ዘጠኝ ወራት ከበረራ ታግዷል። • "ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም • ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ የቢቢሲ ባልደረቦች አደጋው የደረሰበትን ሥፍራ በጎበኙበት ወቅት የአውሮፕላኑ የተለያዩ ክፍሎች ወዳድቀው አግኝተዋል። አካባቢው እየተጠበቀ ስላልነበረ እንስሳት በተከለለው ሥፍራ ገብተው ነበር። በአካባቢው ዝናብ ሲበረታ ችግሩ መባባሱን ያስተዋሉ በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሰዎች አንዳች እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀው ነበር። ሳምያ ሮዝ ልጇ ሳምያ ሮዝን በአደጋው ያጣችው ናዲያ ሚሊሮን፤ "በአካባቢው በግልጽ የሚታየውን የሰዎች አጥንት ነዋሪዎች ይሸፍኑት ነበር፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎችን ቅሪተ አካል እንዲሸፍን እንፈልጋለን" ብላለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ችግሩ መኖሩን አምኖ፤ በኢንሹራንስ ምክንያት እርምጃ መውሰድ አለመቻሉን ለሟቾች ቤተሰቦች አስታውቆ ነበር። ሆኖም ከቤተሰቦች ጫና ሲበረታበት እና የቢቢሲን ምርመራ ተከትሎ ችግሩ ተቀርፏል። ከዚህ ቀደም ለፎረንሲክ ምርመራ የተነሱ የአጽም ቅሪቶች ተሰባስበው በሬሳ ሳጥን ተከተዋል። አካባቢው የቀብር ሥፍራም ተደርጓል። • የቦይንግ ኃላፊ የሟቾችን ቤተሰቦች በይፋ ይቅርታ ጠየቁ • «ሙሉ ቤተሰቤን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ» የሟቾች ቤተሰቦች፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከመካሄዱ አስቀድሞ ሊያሳውቃቸው ይገባ እንደነበር ገልጸዋል። ቦይንግ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። ሆኖም "በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በላየን ኤር አደጋ ሳቢያ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሰዎች መጽናናቱን እንመኛለን፤ ድጋፍ በማድረግም እንቀጥላለን" የሚል መግለጫ አውጥቷል። ዚፓራ ኩሪያ ባለፈው ወር ወደ ኢትዮጵያ ተጉዛ የአባቷን አስክሬን ለመውሰድ ጥረት ብታደርግም የደረሰችው ዘግይታ ነበር። "ቦታው ላይ በጊዜው አለመገኘቴ ልብ ይሰብራል" ስትልም የተሰማትን ሃዘን ገልጻለች። የአባቷ ሥርዓተ ቀብር የሚካሄድበትን ቀን ብታውቅ እንደማትቀር ገልጻም፤ "አባቴን እንዳልሰናበተው አደረጉኝ" ብላለች።
news-52088101
https://www.bbc.com/amharic/news-52088101
ኮሮናቫይረስ፡ አለም ከኢቦላ እልህ አስጨራሽ ትግል ሊማር ይገባል
የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ላይቤሪያን ለአስራ ሁለት ዓመታት መርተዋል። በእነዚህ ዓመታትም ውስጥ በአገሪቷ ታሪክ ፈታኝ የሚባለውና ለአምስት ሺህ ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነው የኢቦላ ወርርሽኝ ወቅትም በአመራር ላይ ነበሩ።
ቢቢሲ የኖቤል አሸናፊ የሆኑትን የቀድሞ የላይቤሪያ መሪ በኮሮናቫይረስ ላይ ያላቸውን አስተያት ጠይቋቸዋል። የቀድሞዋ ፕሬዚዳንትም ለዓለም ሕዝብ ያላቸውን መልዕክትም አስተላልፈዋል። እንደ ጎርጎሳውያኑ 2014 የኢቦላ ወረርሽኝ 2ሺህ የሚሆኑ ዜጎቻችን የቀጠፈበት ወቅት ሲሆን፤ ወረርሽኙም ባልተጠበቀ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተም ነበር። በዚያ ወቅት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ባለሙያዎችን እንዲሁም ቁሳቁሶችን በማስተባበር እንዲልኩልን በመማፀን ደብዳቤ ፃፍኩላቸው። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሲተባበር የምንፈራውን ወረርሽኝም ሊቀንስ እንደሚችል አስረዳሁ። አሁንም ቢሆን ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም መናገር የምፈልገው መተባበር እንደሚያስፈልግ ነው። • የኮሮናቫይረስ መነሻ የነበረችው ዉሃን ከተማ በከፊል ለእንቅስቃሴ ክፍት ሆነች በሁለት ዓመታት ውስጥ 11 ሺህ 325 ሰዎች በምዕራብ አፍሪካ ላይቤሪያን ጨምሮ፣ በሴራሊዮን፣ በጊኒ በበሽታው ሞተዋል። ከስድስት ዓመታት በፊት በጦርነት ተዳክማ የነበረችው የላይቤሪያ ኢኮኖሚ የበሽታውን መዛመት መሸከም እንደማይችል፣ ያለው የጤና ሥርዓትም ያሽቆለቆለ ከመሆኑ አንፃር ለበሽታው እንድንጋለጥና እንዲዛመትም ምክንያት ሆኗል። ዓለም አቀፍፍ ማኅበረሰብም ለምዕራብ አፍሪካ ያሳየው ምላሽም አጠቃላይ ያለንን የጋራ የጤና ደህንነት የሚያሳይ ነው። ይህንንም ተላላፊ በሽታ በዚሁ መግታት ካልቻልን የትኛውም አገርም ሆነ ቦታ ላለ ማንኛውም የሰው ዘር ጠንቅ ነው በማለት ተከራከርኩ። ይህንም ተከትሎ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በጎ ምላሽ ሰጠ፤ ምላሹም ጥሩ ነበር። በተባበሩት መንግሥታትና በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት አስተባባሪነትም የተለያዩ እርዳታዎችም ተሰባሰቡ። አሜሪካም ቀጥላ ይህንኑ መንገድ ተከተለች። አብረንም ይህንን እልህ አስጨራሽ ትግል ተወጣነው። የዚያን ወቅት በተሰራው አመርቂ ሥራ ምክንያት ውጤታማ የሆኑ ክትባቶች እንዲሁም ሌሎች መድሃኒቶች በዓለም ላይ ምጡቅ በሚባሉ ሳይንቲስቶች አማካኝነት ተሰራ። አሁንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የምናገረው ቢኖር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተመሳሳይ የሆነ ትብብር እንዲያደርግ ነው። ምንም እንኳን አፍሪካ እንደ አህጉር ቫይረሱ ሲመጣ ቢዘገይም፤ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መዛመቱን ለመታገል ምንም ዝግጅት ያላደረገችውን አህጉር ክፉኛ እንደሚመታት ሳይታለም የተፈታ ነው። መዛመቱን ለመቀነስ አብረን፣ ተደጋግፈን ልንሰራ ይገባል። ለቫይረሱ መዛመት የተሰጠው ምላሽ ከእስያ ወደ አውሮፓ እንዲሁም ወደ አሜሪካ ስህተቶች ተፈፅመዋል። ጊዜ ባክኗል፣ መረጃ ተደብቋል እንዲሁም በማይሆን መንገድ ተላልፏል። እምነትም ተሰብሯል። "እኔም ተመሳሳይ ስህተት ሰርቻለሁ" ፍራቻ፣ መደበቅ፣ መረጃዎችንም አለመግለፅ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ለመደበቅ መሯሯጥ ነበር፤ እናም መፍትሄው ከማኅበረሰቡ ውስጥ ነበር። እኔም አውቃለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ስህተቶች ከስድስት ዓመታት በፊት ፈፅሜያቸዋለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ዓለም አቀፍ ድጋፍ የሚሰጡትም ይህንኑ ሰርተዋል። ስህተታችንም አስተካክለናል፤ ከማኅበረሰቡም ጋር አብረን እየሰራን ነው። የመዛመቱን ሁኔታ ለመቀነስ ብዙዎች ድንበሮቻቸውን እየዘጉ ነው። ይህ ማለት ግን ብቻችንን ነን ማለት አይደለም፤ እያንዳንዱ አገርም በራሱ ተነጥሎ ቆሟል ማለት አይደለም። በተቃራኒው ይሄ የማኅበረሰቡ የጋራ ምላሽ ነው፤ ድንበሮችን መዝጋት ልዩነት ያመጣል። • የህክምና ባለሙያዎቻቸውን ለመከላከል የሚተጉት ቱኒዚያውያን ሁሉም ዜጎች፣ ሁሉም አገራት የራሳቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል። "አሸናፊ ሆነን ወጥተናል" በላይቤሪያ ኢቦላ ወረርሽኝ አሸናፊ ሆነን መውጣታችን እንደ ማኅበረሰብ ጠንካራ አድርጎናል። በኢቦላ ወረርሸኝ ወቅት የተዘረጉ የጤና ሥርዓቶች ኮቪድ-19ን ለመከላከል ረድቶናል። ዋናው የማምንበት ነገር በግለሰቦች መንፈስ አምናለሁ፣ በጋራ መፀለይ እንዲሁም በአምላክ ያለን ተስፋ ትልቅ ነገር ነው። በዓለም ላለው ማኅበረሰብ ደህንነትም እፀልያለሁ።
news-46563273
https://www.bbc.com/amharic/news-46563273
ሙሉ ጥርሷን ያስነቀለችው ሴት ህይወቷ አለፈ
እንግሊዝ ውስጥ ሙሉ ጥርሷን ያስነቀለች አንዲት የአእምሮ ህመምተኛ ሴት ከቀናት በኋላ ህይወቷ ማለፉ ተገለጸ።
ሬቸል ጆንሰን ሙሉ ጥርሷ በመበስበሱ በአካባቢው የሚገኝ የጥርስ ህክምና ባለሙያ ሁሉም ጥርሶቿ እንዲነቀሉ ካደረገ በኋላ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ለቤተሰቦቿ ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ከሰአታት ቆይታ በኋላ ሬቸል ራሷን ስታ በመውደቋ በድጋሚ ወደ ሆስፒታል ተወስዳ፤ ለቀናት በሞትና በህይወት መካከል ስትታገል ከቆች በኋላ በመጨረሻ ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል። በአካባቢው የሚኖሩ ሌሎች ቤተሰቦችም ተመሳሳይ ክስተት እንዳጋጠማቸው ተናግረዋል። ምንም እንኳን ልጆቻቸው ባይሞቱም፤ ለትንሽ የጥርስ ህክምና ሄደው ሙሉ ጥርሳቸው ተነቅሎባቸው እንደተለመሱ ገልጸዋል። • የሜቴክ የህዳሴ ግድብ ውል ለፈረንሳይና ጀርመን ኩባንያዎች ሊሰጥ ነው • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች • በበረራ ላይ ሴት የተነኮሰው ህንዳዊ ዘብጥያ ወረደ የሬቸል ቤተሰቦችም ልጃችን ሙሉ ጥርሷ እንዲነቀል አልጠየቅንም ነበር፤ እሷ የአእምሮ ህመምተኛ ስለሆነች ሁሉንም ነገር በራሷ መወሰን አትችልም ሲሉ በሃዘን ተውጠው ሁኔታው ያስረዳሉ። የጥርስ ህክምና ባለሙያውም የቤተሰቦቿን አስተያየት ሳይጠይቅና ይሁንታ ሳያገኝ ሙሉ ጥርሷን መንቀሉ ተገቢ አይደለም በማለት የእንግሊዝ የጤናና ክብካቤ ቢሮ ጉዳዩን እየመረመረው ነው። ህክምናው ከተደረገላት አንድ ቀን በኋላ በቤት ውስጥ የምትንከባከባት ነርስ ለእናትየው ደውላ ልጇ ደህና እንዳልሆነችና ምላሷ ማበጡን እንዲሁም ከአፏ አካባቢ ደም እየፈሰሳት እንደሆነ ተናግራ ነበር። በቀጣዩ ቀን ሁኔታው ሲባባስ እናትየው ወደ ሆስፒታል ብታመጣትም እዛው ሆስፒታል ውስጥ ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።
news-53696685
https://www.bbc.com/amharic/news-53696685
ኮሮናቫይረስ፡ በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ
በድሬዳዋ 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋገጠ።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ወይዘሮ ስንታየሁ ለጤና ባለሙያዎቹ በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን በተመለከተም አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል በድንገተኛ እና በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚሰሩ ነርሶችና ዶክተሮች እንደሚገኙበት በመጥቀስ፤ በዚህ ክፍል የሚሰሩት ባለሙያዎች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ተጋላጭ መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ እስካሁን ድረስ ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረገላቸው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ከ500 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውንና 17 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማገገማቸውን የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ስንታየሁ ደበሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 66 ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ተካ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጊኒር ከተማ እና በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ በተደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ እነዚህ ታራሚዎች ኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታራሚዎች ለህክምና ወደ ሮቤ ሆስፒታል መላካቸውንም ቢቢሲ ከኃላፊው መረዳት ችሏል። ኃላፊው በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ታራሚዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ በማያስችላቸው እና ያለ ምንም ጥንቃቄ መልኩ መታሰራቸው በሽታው እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች የፀረ ተህዋሲ ርጭት ተደርጓል። በቀላል ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑንም ተናግረዋል። ታራሚዎቹን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦችም በሽታውን ወደ ኅብረተሰቡ ይዘው በመሄድ ስርጭቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ከተጠረጠሩት ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 470 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ 21 ሺህ 452 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህም መካከል በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 380 ደርሷል።
news-56108178
https://www.bbc.com/amharic/news-56108178
በኒው ዚላንድ ትምህርት ቤቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በነጻ ሊሰጥ ነው
በኒው ዚላንድ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ባጠቃላይ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በነጻ ሊያቀርቡ ነው።
ከቀጣዩ ሰኔ አንስቶ ትምህርት ቤቶቹ የንጽህና መጠበቂያ እንደሚሰጡ ተገልጿል። ሴቶች የወር አበባቸው ሲመጣ የንጽህና መጠበቂያ ለመግዛት አቅም ሲያጡ ትምህርት ቤት ይቀራሉ። የአገሪቱ አመራሮች በወር አበባ ምክንያት ማንኛዋም ሴት ከትምህርት ቤት እንዳትቀር በሚል ይህን ውሳኔ እንዳስተላለፉ ተገልጿል። አምና በ15 ትምህርት ቤቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በነጻ ለመስጠት ሙከራ ተደርጎ ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን "ታዳጊ ሴቶች ተፈጥሯዊ በሆነው የወር አበባ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው መቅረት የለባቸውም" ብለዋል። ኒው ዚላንድ ውስጥ ከ12 ሴቶች አንዷ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በማጣት ከትምህርት ቤት እንደምትቀርም ጠቅላይ ሚንስትሯ ተናግረዋል። ዝቅተኛ ገቢ ካለው ቤተሰብ የተገኙና አቅመ ደካማ ታዳጊዎች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ለመግዛት ስለማይችሉ በየወሩ ከትምህርት ገበታቸው ይሰናከላሉ። የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ መስጠት መንግሥት ድህነትን ከሚዋጋባቸው መንገዶች አንዱ እንደሆ ጠቅላይ ሚንስትሯ አስረድተዋል። መንግሥት በዚህ መንገድ ታዳጊዎች ከትምህርት እንዳይስተጓጎሉና ጤናቸው እንዲጠበቅም እንደሚያደርግ አያይዘው ጠቅሰዋል። በትምህርት ቤቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በነጻ ለመስጠት ኒው ዚላንድ እስከ አውሮፓውያኑ 2024 ድረስ 25 ሚሊዮን ዶላር ታወጣለች። ባለፈው ጥቅምት ስኮትላንድ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በነጻ በማደል የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። እንግሊዝ ውስጥ ለመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በነጻ ይሰጣል። በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ በነጻ እንዲሰጥ የሚያዘውን ሕግ አጽድቀዋል። በኢትዮጵያም በመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል። ይህም የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ገበያ ላይ የሚቀርብበትን ዋጋ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል። የሴቶችና የህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ተመርተው ሲገቡ ቀደም ሲል ተጥሎባቸው የነበረው የ30 በመቶ ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን መደረጉንም ሚኒስቴሩ ማስታወቁ ይታወሳል።
news-55391887
https://www.bbc.com/amharic/news-55391887
እስራኤል ወደ ሞሮኮ ‘ታሪካዊ’ የተባለ ቀጥታ የንግድ በረራ ጀመረች
የእስራኤል አውሮፕላን በእስራኤልና በሞሮኮ መካከል የተደረገውን የመጀመሪያ ቀጥታ የንግድ በረራ አደረገ።
ይህ የሆነው ሁለቱ አገራት በቅርቡ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ ከተስማሙ በኋላ ነው። አውሮፕላኑ በአረብኛ፣ በዕብራይስጥ እና በእንግሊዝኛ 'ሰላም' በሚል ቃል ያሸበረቀ ሲሆን ስለ ዲፕሎማሲያዊው ስምምነት ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር የሚሄዱ ከፍተኛ የእስራኤል ልዑካንን አሳፍሯል። ሁለቱ አገራት ስምምነት ላይ የደረሱበት ድርድር የተካሄደው በዋሽንግተን ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አማች እና የመካከለኛው ምሥራቅ መልዕክተኛ ጄራረድ ኩሽነር ከእስራኤል ከተላከ ቡድን ጋር በመሆን ነበር። ስምምነቱ የአረብ አገራት ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ ሲያካሂዷቸው የነበሩ ተከታታይ ስምምነቶች አካል ነው። ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር ከተስማሙ የአረብ አገራት ዝርዝር ውስጥ መካተቷ የሚታወስ ነው። ሞሮኮ ከነሐሴ ወር ወዲህ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማሻሻል ከስምምነት የደረሰች አራተኛዋ አገር ናት። ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ከስምምነት መድረሷን ተከትሎ በምዕራብ ሳሃራ ግዛት ለምታነሳው የይገባኛል ጥያቄ አሜሪካ እውቅና ለመስጠት መስማማቷ ይታወሳል። በአልጄሪያ የሚደገፉ ፖሊሳሪዮ ግንባር በምዕራብ ሰሃራ የራስ ገዝ አስተዳደር ለመመስረት ከሞሮኮ ጋር ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ አለመግባባት ውስጥ ነበሩ። በቅርቡ የትራምፕ አስተዳደር ሱዳን፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዲያወርዱ ያደራደረ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የፈረሙት ግብጽ እና ዮርዳኖስ ሲደመሩ፤ ከአረብ ሊግ አባል አገራት ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የደረሱት አገራት ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ይላል። ዋይት ሃውስ ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደምትጀምር፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትብብሮችን ለመጀመር መስማማቷን በወቅቱ አስታውቆ ነበር። በራባት እና ቴል አቪዝ የላይዘን ቢሮዎች በፍጥነት ሥራ ለማስጀምር፤ ከዚያም ኤምባሲዎች ለመክፈት ተስማምተዋል ተብሏል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግራቸው ስምምነቱን "ታሪካዊ" ያሉት ሲሆን፤ ለሞሮኮ ንጉስ ሞሐመድ ስድስተኛ ምስጋናቸውን አቅርበው ነበር። ሞሮኮም ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር መስማማቷን የንጉሡ ቤተ-መንግሥት አረጋግጧል። ግብጽ፣ ዩኤኢ እና ባህሬን፤ ሁለቱ አገራት የደረሱትን ስምምነት በደስታ ተቀብለነዋል ብለዋል። የፍልስጤም መሪዎች ግን ስምምነቱን አጥላልተውት ነበር። ፍልስጤማውያን የአረብ ሊግ አባላት ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት ማድረጋቸውን ሲቃወሙ ቆይተዋል። የፍልስጤም መሪዎች እስራኤል ከአረብ አገራት ጋር ዲፕሊማሲያዊ ግንኙነት እንድትጀምር መፈቀዱ መብታችንን እንድትጋፋ የሚያበረታታ ነው ማለታቸው ይታወሳል።
news-56898070
https://www.bbc.com/amharic/news-56898070
ኮሮናቫይረስ፡ አሜሪካ 60 ሚሊዮን የሚጠጋ የኮቪድ-19 ክትባት ለተለያዩ አገራት ልትሰጥ ነው
አሜሪካ ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጋ የአስትራዜኒካ ክትባት ለሌሎች አገራት ልትሰጥ እንደሆነ ዋይት ሐውስ አስታወቀ።
ክትባቶቹ አስተማማኝነታቸው ተረጋግጦ በቀጣይ ወራት ወደተለያዩ አገራት እንደሚላኩ ተገልጿል። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ገና ፍቃድ ያልሰጣቸው በርካታ ክትባቶች አሜሪካ ውስጥ ተከማችተው ይገኛሉ። የተለያዩ አገራት በቂ ክትባት ማግኘት ባይችሉም የአሜሪካ መንግሥት ግን ከሚያስፈልገው በላይ ክትባት እያከማቸ ነው በሚል ሲተች ቆይቷል። ባለፈው ወር ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አራት ሚሊዮን የአስትራዜኒካ ክትባት ለሜክሲኮ እና ለካናዳ ለመስጠት ቃል ገብተው ነበር። በሕንድ የኮሮናቫይረስ ስርጭት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ፤ አሜሪካ ያከማቸችውን ክትባት እንድትለግስ ጫና እየተደረገባት ነው። አሜሪካ ለክትባት ምርት የሚውሉ ግብዓቶችን ለሕንድ ለመለገስም ቃል ገብታለች። ከጠቅላይ ሚንስትር ንሬንድራ ሞዲ ጋር የስልክ ውይይት ያደረጉት ፕሬዝዳንት ባይደን፤ ኦክስጅን፣ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ መሣሪያ፣ ክትባትና ሌሎችም ምርቶችን ለመስጠት ቃል ገብተዋል። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር በቀጣይ ሳምንታት የክትባቶቹን ደኅንነት ፈትሾ ፍቃድ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዋይት ሐውስ መግለጫ ይጠቁማል። ከዚያም ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ የአስትራዜኒካ ክትባት ወደተለያዩ አገራት ይላካል። ለአገራት ይከፋፈላል የተባለው የተቀረው 50 ሚሊዮን ክትባት በተለያየ የምርት ደረጃ ላይ ነው። የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ እንዳሉት የትኞቹ አገራት ክትባቱን እንደሚያገኙ በቀጣይ ይገለጻል። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ተቆጣጣሪ እስካሁን ፍቃድ የሰጠው ለፋይዘር ባዮንቴክ፣ ለሞደርና እና ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ነው። እነዚህ ክትባቶች ለአገሪቱ ዜጎች በቂ ስለሚሆኑ ተጨማሪ የአስትራዜኒካ ክትባት እንደማያስፈልግ ተንታኞች ይናገራሉ። እስካሁን በአሜሪካ ከ53 በመቶ በላይ የሚሆኑ አዋቂዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት አግኝተዋል። የባይደን አስተዳደር ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጋ ክትባት ለመለገስ ውሳኔ ማሳለፉ "የክትባት ዲፕሎማሲ" ሲሉ ተንታኞች ገልጸውታል።
sport-51425052
https://www.bbc.com/amharic/sport-51425052
ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ይቆያል፡ ፔፕ ጋርዲዮላ
በርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ሰሞኑን አንድ ነገር ላይ ስምምነት ነበራቸው። የስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ሰሞኑን የፈጠረው ቅራኔ መዳረሻውን ማንችስተር ሲቲ ያደርጋል የሚል።
ሊዮኔል ሜሲ "ሜሲ የእግር ኳስ ዘመኑን በባርሳ የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል፤ የማምነውም እንደዚያ እንደሚሆን ነው" በማለት የማንቺስትር ሲቲው አለቃና የቀድሞው የሜሲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ግን የበርካቶችን ግምት ከግምት እንዳያልፍ አድርጎታል። የ32 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የኮከብ የእግር ኳስ ሕይወቱን ያሳለፈው ከባርሴሎና ጋር ነው። ነገር ግን በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ ክለቡን በነጻ ዝውውር መልቀቅ የሚያስችል ስምምነት አለው። የአሁኑ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከ2008 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ 2012 ድረስ ለአራት ዓመታት ያክል ሜሲን አሰልጥኖታል። በአራት ዓመት ጊዜውም ሦስት የላሊጋና ሁለት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በአንድ ወቅትም "እኔ በጣም እድለኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ቢያንስ የዓለማችንን ምርጡን ተጫዋች ሌዮኔል ሜሲን አሰልጥኜዋለሁ" በማለት ጋርዲዮላ ለሜሲ ያለውን አድናቆት ገልጿል። ይህ ወደጅነታቸውም አሁን እንደገና ሊያገናኛቸው ይችላል የሚለውን ግምት በበርካቶች ዘንድ አሳድሯል። ነገር ግን ጋርዲዮላ የማይታሰብ ነው ብሏል። "እዚያው [ባርሴሎና] ይቆያል፤ የእኔ ፍላጎት ይህ ነው" በማለት። ጋርዲዮላ ባርሴሎናን ለቆ ወደ ባየር ሙኒክ ሲያመራ ባርሴሎናን በዋንጫ አንበሽብሾት ነበር። የክለቡም በጣም ስኬታማው አሰልጣኝ የነበረ ሲሆን በአራት ዓመት ቆይታው 14 ዋንጫዎችን ለስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ገቢ አድርጓል። ከዚያም ወደ ጀርመን አቅንቶ ጋርዲዮላ ከባየር ሙኒክ ጋር ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የቡንደስ ሊጋውን ዋንጫ ማሸነፍ ችሏዋል። ወደ እንግሊዝ በማምራትም ማንችስተር ሲቲን በማሰልጠን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ የውድድር ጊዜያት በበላይነት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አሸፏል። በዚህኛው የውድድር ዘመን ግን ጋርዲዮላ የሚደግመው አይመስልም፤ አንድም ጨዋታ ያልተሸነፈው ሊቨርፑል 13 ጨዋታዎች ብቻ እየቀሩት ማንችስተር ሲቲን በ22 ነጥብ ርቆ ሊጉን እየመራ ይገኛል። ፔፕ ጋርዲዮላ የባርሴሎናው የምንጊዜም ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊ በመሆን የምድራችን ብቸኛ ተጫዋች ሲሆን በባርሳ ቆይታው 10 የላሊጋና አራት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አሸንፏል። እስከ ፈረንጆቹ 2021 በባርሳ የሚያቆየው ኮንትራትም አለው። ነገር ግን የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤሪክ አቢዳል ተጫዋቾች በቀድሞው የክለቡ አሰልጣኝ ኧርኔስቶ ቫልቨርዴ ጊዜ "ጠንክረው አይሰሩም ነበር" የሚል ክስ ማንሳቱን ተከትሎ ሜሲ የአጸፋ መልስ ሰጥቷል። በእንደዚህ አይነት ጠንካራ ንግግሩ ለዓመታት የማይታወቀው ሜሲ አሁን መልስ መስጠቱ ክለቡ ጋር መለያየትን ስለመረጠ ሊሆን ይችላል በማለት ተንታኞች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። አሁን በአቢዳልና በሜሲ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ጋርዲዮላ ማራገብ አልፈለገም። ሁለቱንም በአንድ ወቅት ባርሳ ውስጥ ያሰለጠኑት ጋርዲዮላ "ስለሌላ ክለብ ተጫዋቾች ማውራት አልፈልግም፤ ሜሲ ግን የእግር ኳስ ዘመኑን እዚያው ባርሴሎና ውስጥ የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል" ብሏል።
news-53328680
https://www.bbc.com/amharic/news-53328680
ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች አገራት ከኮቪድ-19 በባሰ በረሃብ በርካቶች ሊሞቱ ይችላሉ ተባለ
በኮሮናቫይረስ ሰበብ በተከሰቱ ቀውሶች ሳቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት ውስጥ በወረርሽኙ ከሚሞቱ ሰዎች ቁጥር የሚበልጡ በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ ኦክስፋም አስታወቀ።
ኦክስፋም እንዳለው ኮቪድ-19 ለወትሮው በረሃብ እየተሰቃየ ባለው ዓለም ላይ የከፋ ረሃብን አስከትሏል። በዚህም በተለይ አስር አገራት ክፉኛ ችግር እንደሚገጥማቸው የገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያም አንዷ እንደሆነች አመልክቷል። ድርጅቱ ባወጣው የአስር አገራት ዝርዝር ውስጥ አብዛኞቹ የሚገኙት በአፍሪካና በእስያ አህጉር ሲሆን እነሱም ኢትዮጵያ ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ የመን፣ ሶሪያ፣ አፍጋኒስታን፣ ቬንዝዌላ፣ ምዕራብ ሳህል እና ሄይቲ ናቸው። ኦክስፋም ጉዳዩን በሚመለከት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ኮሮናቫይረስ በዓለም ላይ የነበረውን የረሃብ ቀውስ ከማባባሱም በላይ ረሃብ ተከስቶባቸው የማያውቁ አዳዲስ አካባቢዎችን እየፈጠረ ነው ብሏል። በዚህም መሰረት ከወራት በኋላ በየቀኑ ከ6ሺህ እስከ 12 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት በሚከሰት ረሃብ ሳቢያ በዓለም ዙሪያ ለሞት ሊዳረጉ ይችላሉ ብሏል። ይህም አሃዝ የኮሮናቫይረስ ከሚገድላቸው ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ የሚልቅ እንደሚሆን ኦክስፋም አስጠንቅቋል። የተራድኦ ድርጅቱ እንዳለው፤ ሥራ አጥነት፣ ምግብ አምራቾች በእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት መሥራት አለመቻላቸው እንዲሁም እርዳታ ለማከፋፈል አዳጋች መሆኑ ረሃቡን ያባብሰዋል። መንግሥታት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መስፋፋት ለመግታት ከሚያደርጉት ጥረት ጎን ለጎን የተጋረጠውን የረሃብ ቀውስ ለመቆጣጠር አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱም ጠይቋል። ድርጅቱ እንዳለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ላይ እየጨመረ በነበረው የረሃብ ችግር ላይ አባባሽ ምክንያት ሆኗል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት በዓለም ዙሪያ 821 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና ችግር ያጋጠማቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በከባድ ወይም በከፋ ረሃብ ለስቃይ የተዳረጉት 149 ሚሊዮን ሰዎች ይሆናሉ። በአሁኑ ወቅትም ኮሮናቫይረስ በየአካባቢው ከሚከሰቱ ግጭቶች፣ እየጨመረ ከመጣው የኑሮ ልዩነትና እየተባባሰ ካለው የአየር ጸባይ ለወጥ ጋር ተዳምሮ የተዳከመውን የዓለም የምግብ አቅርቦት ሥርዓት በመጉዳት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ድሆችን ወደ ረሃብ አፋፍ አድርሷቸዋል ብሏል።
48669408
https://www.bbc.com/amharic/48669408
ሞሐመድ ሙርሲ ፍርድ ቤት ውስጥ ሞቱ
የቀድሞው የግብጽ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ሙርሲ ዛሬ ፍርድ ቤት ውስጥ በድንገት ተዝለፍልፈው ከወደቁ በኋላ መሞታቸው እየተዘገበ ነው።
ሙርሲ እንደ አውሮፓዊያኑ በ2013 ነበር በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን የተነጠቁት። በግብጽ ታሪክ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይሁንታን ያገኙ የመጀመርያው ርዕሰ ብሔር ነበሩ። ያም ሆኖ አገሪቱን መምራት የቻሉት ለአንድ ዓመት ብቻ ነበር። የሕዝብ ተቃውሞን ተከትሎ በአልሲሲ የተመራ ወታደራዊ ኃይል ሥልጣናቸውን ነጥቋቸዋል። • ግብጽ 40 ታጣቂዎችን ገደለች • አሜሪካ የግብፁ ሙስሊም ብራዘርሁድን በአሸባሪነት ልትፈርጅ ነው ሙሐመድ ሙርሲ ለከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ነው። ሟቹ ሞሐመድ ሙርሲ ማን ነበሩ? ሞሐመድ ሙርሲ የተለወዱት ኢል አድዋህ ሸርቂያ በምትባል አውራጃ እንደ አውሮፓያዊያኑ በ1951 ነበር። በ1970ዎቹ በካይሮ ዩኒቨርስቲ ምህንድስና ካጠኑ በኋላ የፒኤች ዲ ጥናታቸውን ለማድረግ ወደ አሜሪካ አቀኑ። ትምህርታቸውን በአሜሪካ ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ግብጽ በመመለስ በዛግዚግ ዩኒቨርስቲ በፕሮፌሰርነት ማገልገል ጀመሩ። የፖለቲካ ሕይወታቸውን የጀመሩት በሙስሊም ብራዘርሁድ የጋይዳንስ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ነበር። ፕሬዝዳንት እስኪሆኑ ድረስም የነጻነትና ፍትህ ፓርቲ መሪ ነበሩ። በአውሮፓዊያን ከ2000 እስከ 2005 ድረስ በግል የምክር ቤት ተመራጭ ነበሩ። በምክር ቤት እንደራሴ በሆኑባቸው ጊዜያት መንግሥትን በመተቸት ዝና አትርፈዋል። በአውሮፓዊያን 2012 የሙስሊም ብራዘርሁድ እጩ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሚሊየነሩ ካይራት አልሻተር ከፓርቲው ገለል ከተደረጉ በኋላ ነበር። በግብጽ ታሪክ በሕዝብ ዲሞክራሲ የተመረጡ የመጀመርያው መሪ የሆኑት ሞሐመድ ሙርሲ፤ በተመረጡ ማግስት ሁሉን ግብጻዊ ለማገልገል፣ ሕገ መንግሥቱን ለማስጠበቅ ቃል ቢገቡም ተቺዎቻቸው ግን ሥልጣኑን ለፓርቲያቸው ሰዎች አድርገውታል ሲሉ ይተቿቸዋል። • ግብጽ በመካከለኛው ምስራቅ ትልቁን ካቴድራል ከፈተች • 'የሴቶች ቫያግራ' በአፍሪካዊቷ ሃገር ሞሐመድ ሙርሲ በሥልጣን መቆየት የቻሉት ለአንድ ዓመት ብቻ ነበር። ሕዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ ሙርሲ ሥልጣን እንዲለቁ ግፊት በረታባቸው። ሆኖም በጄ አላሉም። የተቃውሞውን ያህልም ድጋፍ ነበራቸው። በአውሮፓውያኑ 2013 የያኔው የጦሩ መሪ አብዱል ፈታህ አልሲሲ በአልሲሲ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መሀል ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት ካልበረደ አገሪቱ ወደከፋ ቀውስ ልታመራ እንደምትችል አሳሰቡ። በዚያው ዓመት ሐምሌ ወር ሙርሲ ነገሮች በ48 ሰዓታት ውስጥ መልክ የማይዙ ከሆነ ሕግና ሥርዓት ለማስፈን ወታደሩ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል ጠቆሙ። በሐምሌ 3 ምሽት አልሲሲ ሕገ መንግሥቱ መታገዱን፣ ግብጽም በቴክኖክራቶች በተዋቀረ ጊዜያዊ ኮሚቴ እንደምትመራ አስታወቁ። ከዚያች ምሽት ወዲህ ሙርሲ ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደው ታሰሩ። የሙርሲ ደጋፊዎች ዘለግ ያለ ተቃውሞ በማድረጋቸው ወታደሩ በወሰደው እርምጃ ከአንድ ሺ የሚልቁ ዜጎች ተገደሉ። ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ሙርሲ በአገር ክህደት ተከሰሱ። የሙርሲ የበኩር ልጅ አባቱ እስር ቤት የተያዙበት ሁኔታ ለጤናቸው አስጊ እንደሆነ ሲናገር ቆይቷል። ይኸው ልጃቸው አባቱ የደም ግፊትና ስኳር ታማሚ እንደነበሩም አመላክቷል። መሰረታዊ የጤና ክትትልና የመድኃኒት አቅርቦት እንደተነፈጋቸውም ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናግሮ ነበር። ከአምስት ወራት በፊት ይህ ልጃቸው በዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ በጻፈው አስተያየት የግብጽ ባለሥልጣናት አባቱ ሙርሲ በሚፈለገው ፍጥነት እንዲሞቱ እንደሚፈልጉ ተናግሮ ነበር። ሙሐመድ ሙርሲ የአራት ልጆች አባት ነበሩ።
news-50371705
https://www.bbc.com/amharic/news-50371705
አየር መንገዶች "ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸውን ያስቀድማሉ" የሚል ክስ ቀረበባቸው
በብሪቲሽ አየር መንደገድ ውስጥ የሚሰራ አንድ የዘርፉ ባለሙያ እንዳጋለጠው፤ በአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሆነ ተብሎ አውሮፕላኖች ብዙ ነዳጀ ጭነው እንዲጓዙ ይደረጋል።
ይህም አውሮፕላኑ በሚይዘው ክብደት ልክ ብዙ ነዳጅ ተቃጥሎ አየር እንዲበከል እየተደረገ ነው ተብሏል። አየር መንገዶች አውሮፕላኖቻቸው ከመነሻቸው ብዙ ነዳጅ ጭነው የሚነሱት በመዳረሻ አየር መንገዶች ለነዳጅ የሚጠየቁትን ብዙ የነዳጅ ገንዘብ ለማስቀረት ነው። ብሪቲሽ አየር መንገድ "ለደህንነት እና ከዋጋ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች" ተጨማሪ ነዳጅ ይዞ መብረር የተለመደ ነው ብሏል። ቢቢሲ ፓኖራማ የተሰኘው የቢቢሲ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ባለፈው ዓመት የብሪቲሽ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ተጨማሪ ነዳጅ ይዘው በመብረራቸው ተጨማሪ 18ሺህ ቶን ካርበን ዳይኦክሳይድ አመንጭተዋል ሲል መዘገቡ ይታወሳል። አንድ ጥናት እንዳረጋገጠው ደግሞ አውሮፓ ውስጥ ከሚደረጉ ከአምስት በረራዎች ቢያንስ በአንዱ አውሮፕላኑ ተጨማሪ ነዳጅ ይዞ ወደ መዳረሻው ይበራል። ተቺዎች እንደሚሉት ይህ ተግባር አየር መንገዶች የአየር ብክለትን ለመቀነስ እንሰራለን የሚሉትን ቃል ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው። ከተቺዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት ጆህን ሳኡቨን አየር መንገዶች "ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸወን ያስቀድማሉ" ለምንለው ይህ ትክክለኛ ማሳያ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
news-50805245
https://www.bbc.com/amharic/news-50805245
ቦትስዋና፡ የምርምሩን ዝሆን የገደሉት አዳኞች ፈቃዳቸውን ተነጠቁ
በቦትስዋና ሁለት አዳኞች የምርምር ዝሆን መግደላቸውን ተከትሎ ፈቃዳቸው ተነጥቋል።
ሚሸል ሊ ፖተርና ኬቪን ሻርፕ የተባሉት አዳኞችም በሃገሪቱ መንግሥት ትዕዛዝ መሰረት የአደን ፈቃዳቸውን አስረክበዋል። ለረዥም ጊዜያት የዝሆን አደንን ከልክላ የነበረችው ቦትስዋና ከጥቂት ወራት በፊት ነበር እንደገና የፈቀደችው። •"ማርታ፣ ለምን ለምን ሞተች?" •ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ ዝሆኖች በመንደሮች ውስጥ ባሉ እርሻዎች ውስጥ በመግባት እህሎችን በማበላሸት እንዲሁም ሰዎችን እየገደሉ ስላስቸገሩም ነው አደኑ እንደገና ፈቃድ ያገኘው። ነገር ግን አሁን የተገደለው ይህ ዝሆን የምርምር በሚል ጥበቃ እንዲደረግለት ተወስኖ ነበር። በቦትስዋና የሚገኙ ዝሆኖች ቁጥር ወደ 130ሺ ይጠጋል። ዝሆኑ መገደሉን ተከትሎ ቅዳሜ እለትም የቦትስዋና መንግሥት ባወጣው መግለጫ "ሚሼል ሊ ፖተር እስከ መጨረሻው ድረስ የአደን ፈቃዱ የማይመለስለት ሲሆን የሌላኛው አዳኝ ኬቪን ሻርፕም ለሶስት አመት የሚወሰድበት ይሆናል" ተብሏል። •የአብዲሳ አጋ ጀብዱ በሥዕል መጽሐፍ የሁለቱ አዳኞች ዜግነት ያልተገለፀ ሲሆን፤ ግለሰቦቹም ለቢቢሲ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ከዚህም በተጨማሪ ዝሆኑ አንገቱ ላይ አድርጎት የነበረውን ቀበቶ እንዲተኩ የተጠየቁ ሲሆን አንገቱ ላይ አጥልቆት የነበረው ቀበቶ እንዴት እንደተበላሸ የተገለፀ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም መንግሥት ባወጣው መግለጫ ዝሆኑ ፊት ለፊት ቆሞ ስለነበር አጥልቆት የነበረውን ቀበቶ ማየት እንዳልቻሉ አዳኞቹ መናገራቸውን አትቷል። "ዝሆኑ ከወደቀ በኋላ ግን ቀበቶውን ማየት እንደቻሉና የምርምርም መሆኑን መረዳታቸውንም መናገራቸው" በመግለጫው ተካትቷል። ነገር ግን ይህ አሳማኝ እንዳልሆነ የካላሃሪ የጥበቃ ማህበር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል አሳውቋል፤ ለዚህም እንደምክንያትነት የሰጡትም የዝሆን ቀበቶ በጣም ትልቅና ከየትም አቅጣጫ እንደሚታይ በመግለፅ ነው። ሮይተርስ በበኩሉ እንደዘገበው ሁለቱ አዳኞች ቀበቶውን ያበላሹት ማስረጃ ለመደበቅ ሲሞክሩ እንደሆነ ነው። አብዛኛዎቹ ዝሆኖች በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ ሲሆን በናሚቢያ፣ ዛምቢያና ዚምባብዌን በሚያዋስነው ድንበር በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ። በአፍሪካ ውስጥ 415ሺ የሚገመቱ ዝሆኖች የሚገኙ ቢሆንም ባለው የህገወጥ አደን ምክንያት ቁጥራቸው እያሽቆለቆለ ነው ተብሏል።
50900206
https://www.bbc.com/amharic/50900206
ቦይንግ ዋና ስራ አስፈፃሚውን ቢያሰናብትም በ737 ማክስ ላይ ስጋቶቹ እንዳሉ ናቸው
ቦይንግ ዋና ስራ አስፈጻሚውን፣ዴኒስ ሚሌንበርግ፣ በድርጅቱ ላይ ያለውን እምነት ለመመለስ በሚል ከስራ ማባረሩ ይታወሳል። ኩባንያው ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው ሁለት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ ከተከሰከሱ እና ከ340 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ ነው።
ከእነዚህ አውሮፕላኖች መከስከስ በኋላ ቦይንግ ከደህንነት ይልቅ ትርፍን አስቀድሟል በሚል ወቀሳዎች ሲቀርቡበት ነበር። ቤተሰቦቻቸውን በአውሮፕላን አደጋው ያጡ ሰዎች የስራ አስፈጻሚውን ከስራ መሰናበት ቢዘገይም ትክክለኛ እርምጃ ነው ብለዋል። • ቦይንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚውን አባረረ • ቦይንግ "ከእንግዲህ የሚታመን ድርጅት አይደለም" ነገር ግን ቦይንግ የተሰናበቱትን ዋና ስራ አስፈጻሚ ረዥም ጊዜ ባገለገሉት የቦርድ አባሉ ለመተካት መወሰኑ አሁንም ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል። አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ ዴቪድ ካልሆን፣ ኩባንያውን በቦርድ አባልነት ከ2009 ጀምሮ ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የዋና ሥራ አስፈፃሚ ኃላፊነቱን እና ፕሬዚደንት ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው ታውቋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ሚስቱን ያጣው ፓል እንጆሮጌ " የስራ አስፈፃሚው ሚሌንበርግ መባረር የሚያስደስት ቢሆንም አሁን ግን ድርጅቱ አስተዳዳሪዎቹን የሚመርጥበትን መስፈርት መለስ ብሎ መመልከት አለበት" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። አክሎም " ካልሆን ለቦታው የሚመጥን ሰው አይደለም" ብሏል። ሌላኛዋ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ አባቷን ያጣችው ዚፖራ ኩሪያ ደግሞ ሚሌንበርግ መተካት የነበረበት "ከረዥም ጊዜ በፊት" መሆኑን ተናግራ፤ ነገር ግን ለአውሮፕላኖቹ መከስከስ ኃላፊነት የሚወስዱ ሌሎች ሰዎችም መኖር አለባቸው ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች። አክላም "አሁን የድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መልቀቅ እንዳለባቸው ይሰማኛል" ብላለች። የተደረጉ ለውጦች ቦይንግ ሁለት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ በአምስት ወራት ልዩነት ከተከሰከሱ በኋላ ከግራም ከቀኝም ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገበት ነው። የቦይንግ ምርት የሆኑት ሁለት 737 ማክስ 800 አውሮፕላኖች መከስከሳቸውን ተከትሎ ለዘጠኝ ወራት ያህል ሞዴሉ እገዳ ተጥሎበትም ቆይቷል። ኩባንያው በዚህ እያለቀ ባለው የፈረንጆች ዓመት በሽያጭም በብቃትም ምርጡ የተባለውን አውሮፕላን አየር ላይ ለማዋል እቅድ የነበረው ቢሆንም የአሜሪካ ተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት በፍጥነት ወደ በረራ እንዲገባ ምስክርነቱን እንደማይሰጠው አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት ቦይንግ ምርቶቹን እንደሚያቋርጥ ማስታወቁ ይታወሳል። • «ሙሉ ቤተሰቤን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ» • "የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ ድርጅቱ አርብ እለት ወደ ዓለም አቀፉ የሕዋ ማዕከል ሊያመጥቀው የነበረው መንኮራኩር የቴክኒክ ችግር ገጥሞት ሌላ ፈተና ውስጥ ወድቆም ነበር። በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ እያለ የተሾሙት ዴቪድ ካልሆን የዋና ሥራ አስፈፃሚ ኃላፊነቱን ይዘውና ፕሬዚደንት ሆነው ከፈረንጆቹ ጥር 13 ጀምሮ ማገልገል ይጀምራሉ። ላውረንስ ኬልነር ደግሞ የድርጅቱ የቦርድ ኃላፊ ሆነው ሊያገለግሉ እንደሚችሉም ተነግሯል። "የዳይሬክተሮች ቦርድ፤ በካምፓኒው ላይ በራስ መተማመንን ለመመለስ፣ ወደፊት ተጠናክሮ ለመቀጠል እንዲሁም ከደንበኞች፣ ተቆጣጣሪዎች እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር፤ አመራር መቀየር አስፈላጊ እንደሆነ ወስኗል" ሲል ቦይንግ በመግለጫው ምክንያቱን አስቀምጧል። • የቱሉ ፈራ ደጋግ ኢትዮጵያዊ ልቦች • "አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ በድርጅቱ አዲስ አመራር ሥር፤ ቦይንግ ከፌደራል አቪየሽን ባለሥልጣን [FAA] እንዲሁም ከተቆጣጣሪዎች እና ደንበኞች ጋር ግልፅ የሆነ፣ ውጤታማና የተቀላጠፈ ኮሚዩኒኬሽን እንዲኖረው የሚያስችል አሰራርም እንደሚያሻሽል አክሏል። ድርጅቱ ይህንን ለውጥ ቢያደርግም በዋሺንግተን የሚገኙ የድርጅቱ ቀንደኛ ተቺዎች ግን አሁንም ኩባንያው ለለውጥ ባለው ቁርጠኝነት ላይ ጥያቄ አለን እያሉ ነው። ማይክል ስቱሞ በኢትዮጲያ አውሮፕላን አደጋ ሴት ልጁን አጥቷል፤ ማይክል በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ግለሰቦች ቦይንግን እንዲገዳደሩት በሚል አሰባስቧቸዋል። የዋና ስራ አስፈጻሚውን ከስራ መነሳትም አስመልክቶ " ቦይንግን ያክል ኩባንያ ወደ ደህንነትና ፈጠራ የሚያንደረድር አንድ መልካም እርምጃ" ብሎታል። ቀጣዩ እርምጃ መሆን ያለበት ደግሞ " ከአቅማቸው በታች የሚሰሩ ወይንም ችሎታ የሌላቸውን በረካታ የቦርድ አባላቱን እንዲለቅቁ ማድረግ ነው" ሲል ይናገራል። "የሶፍት ዌር ችግር" ኤምካስ (ማኑቨሪንግ ካራክተርስቲክስ ኦግመንቴሽን ሲስተም) ለሚለው ምህጻረ ቃል ነው። ይህ ሲስተም አውሮፕላኑን የሞተሩ ክብደትና የተቀመጠበትን ቦታ ምክንያት አድርጎ እንዳይቆምና እንዳያጋድል ያደርገዋል። ይህም አውሮፕላኑ ሽቅብ በሚወጣ ጊዜ የሚያሳየውን ዝማሜ ተከትሎ ሚዛኑን እንዲያስጠብቀው ለማድረግ የተሠራ ነበር። • ቦይንግ 737 ማክስ የአውሮፕላን ምርቱን ለጊዜው ሊያቋርጥ ነው ነገር ግን የኢንዶኒዢያው ላየን አውሮፕላን ምርመራ ውጤት እንዳመላከተው ይህ ሴንሰር አውሮፕላኑ በአፍጢሙ እንዲደፋ የሚያደርግበት ሁኔታ አለ። ይህም የሚሆነው ሚዛኑን ለመጠበቅ የሚልከው መልዕክት (ሲግናል) እርስበርሱ የሚጣረስ በመሆኑ ነው። ይህም ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጭ የሚሆን ነገር ነው። የተከሰከሰው የኢንዶኒዢያ አየር መንገድ ከ20 ጊዜ በላይ የአውሮፕላኑ አፍንጫ ቁልቁል እንዲያዘምና እንዲምዘገዘግ አድርጎታል። አሁን ቦይንግ አድሼዋለሁ የሚለው ሶፍትዌር በአውሮፕላኑ አፍንጫ የምትገኘው ሴንሰር እርስበርሱ የሚጣረስ ምልእክት ካስተላለፈ ኤምካስ የተሰኘውን መቆጣጠሪያ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ ባልቦላ ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ የሚያደርግ ነው።
news-55614496
https://www.bbc.com/amharic/news-55614496
ሕዳሴ ግድብ፡ ሱዳን በሕዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት ላይ ሳትስማማ ቀረች
ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲያደርጉት የነበረው ውይይት በሳምንቱ ማብቂያ ላይ የተሰበሰበ ሲሆን ድርድሩን ለማስቀጠል በቀረበ ሃሳብ ላይ ሱዳን ሳትስማማ መቅረቷን ተገለጸ።
ድርድሩን ለማስቀጠል እንዲያግዝ አገራቱ ከአፍረካ ሕብረት ባለሙያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ ውጤቱ ለሕብረቱ ምክር ቤት ሊቀመንበር እንዲቀርብ በሚለው ሃሳብ ላይ ኢትዮጵያና ግብጽ ሲስማሙ ሱዳን እንዳልተቀበለችው ስለሚኒስትሮቹ የሦስትዮሽ ስብሰባ የወጣው መግለጫ አመላክቷል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት ምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ እየገነባችው ያለው ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታው 78 በመቶ ያህል መድረሱ የተነገረ ሲሆን ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ማካሄዱ ይታወሳል። ቀደም ሲል ተጀምሮ ሲካሄድ የነበረው በግድቡ የውሃ ሙሌትና ቀጣይ ሥራ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በአፍሪካ ሕብረት አሸማጋይነት የሚካሄደው ውይይት፤ እሁድ ዕለት በሦስቱ አጋራት ሚኒስትሮች መካከል በበይነ መረብ የተካሄደ ሲሆን መግባባት ላይ ሳይደረስ መጠናቀቁ ተገልጿል። ይህ ስብሰባ የአፍሪካን ሕብረት በመወከል በደቡብ አፍሪካ የዓለምአቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ሕብረት አስፈጻሚ ምከር ቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢ ናሌዲ ፓንዶር የሚመራ ሲሆን፣ እርሳቸውም ስብሰባው ያለስምምነት በመጠናቀቁ ማዘናቸውን እና ጉዳዩን ወደ ፕሬዝዳንት ራማፎሳ እንደሚመሩት ማስታወቃቸውን የሱዳን የዜና ወኪል ዘግቧል። ሱዳን በበኩሏ የሕዳሴ ግድብ ስምነቱ መቋጫ ሳያገኝ ሁለተኛ ዙር ሙሌት የሚካሄድ ከሆነ በሮዚየር ግድብ ላይ አደጋ መደቀኑን በማንሳት ተቃውማለች። ሮዚየር ግድብ ውሃ የመያዝ አቅሙ ከሕዳሴ ግድብ በ10 በመቶ ያነሰ ነው ተብሏል። የሱዳን ዜና ወኪል የአገሪቱን የመስኖና ውሃ ሀብቶች ሚኒስትርን ፕሮፌሰር ያሲር አባስን ጠቅሶ እንደዘገበው አገራቸው የሕዳሴ ግድብ አደራዳሪዎቹ ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንዲችሉ ሚናቸው እንዲሰፋ እንደምትፈልግ መግለጻቸውን ዘግቧል። ግብጽ በተደጋጋሚ ግድቡ የውሃውን መጠን ይቀንሰዋል ስትል ቅሬታ ስታሰማ ቆይታለች። ትናንት የተካሄደው ስብሰባ ባለፈው ሳምንት እንዲካሄድ ስምምነት ተደርሶበት የነበረው የሦስትዮሽ ስብሰባ ቀደም ባለው ውይይት ላይ ሱዳን ሳትገኝ በመቅረቷ ምክንያት ሳይካሄድ ከቀረ በኋላ የተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ድርድሩን ለማስቀጠል ይረዳል በሚል አገራቱ ለሦስት ቀናት ከአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ እንዲያካሂዱ፣ በማስከተል የሦስትዮሽ ስብሰባ እንዲካሄድ እና ውጤቱ ለሊቀመንበሯ እንዲገለጥ ሃሳብ አቅርበው እንደነበር የወጣው መግለጫ ያሳያል። "ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ይህን ተቀብለው በውይይቱ ለመቀጠል የተስማሙ ሲሆን ሱዳን ሃሳቡን ባለመቀበሏ ስብሰባው በዚሁ ተጠናቋል" ይላል መግለጫው። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ስብሰባ ሱዳን የሦስትዮሽ ስብሰባ እንዳይካሄድ እና ስብሰባዎች ከአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች ጋር ብቻ እንዲደረጉ አቋም መያዟ ይታወሳል። ሆኖም በአሁኑ ስብሰባ አገራቱ ከአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ ያድርጉ የሚለው ሃሳብ ሲቀርብ፣ ሱዳን የባለሙያዎቹ የተጨማሪ ኃላፊነት መመሪያ (ቢጋር) ካልተዘጋጀ በቀር መካሄድ አይችልም የሚል አቋም መያዟን በመግለጫው ላይ ገልጿል። ኢትዮጵያ የሱዳንን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል በግድብ ደኅንነት፣ በመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በሌሎች ቴከኒካዊ ጉዳዮች ላይ መፍትሄ ለመስጠት ዝግጁነቷን መግለጿን አስታውቃለች። ሲጠናቀቅ የአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ይሆናል የተባለው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ዙሪያ ሱዳንና ግብጽ ቅሬታ በማንሳታቸው ይህንኑ በውይይት ለመፍታት ተከታታይ ድርድሮች ሲደረጉ ቆይተዋል። ምንም እንኳን ሁለቱ አገራት የውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ስምምነት መደረስ አለበት በማለት ግፊት ቢያደርጉም ኢትዮጵያ ባለፈው የክረምት ወር የግድቡን የመጀመሪያ ደረጃ የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ ማከናወኗን መግለጿ ይታወሳል። ግብጽ ከአባይ ወንዝ ላይ በማገኘው የውሃ መጠን ላይ መቀነስን ያስከትላል በሚል ጥያቄ በምታነሳበት በዚህ ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ፣ በካርቱም፣ በካይሮና በዋሽንግተን ውስጥ አገራቱ ተከታታይ ድርድሮች ቢካሄዱም አስካሁን መደምደሚያ ላይ አልተደረሰም። በተለይ በአሜሪካ አሸማጋይነት ዋሽንግተን ላይ ሲካሄድ የነበረው ድርድር መቋጫ ላይ ይደርሳል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም በመጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ ጥቅሜን የሚያስጠብቅ አይደለም በማለት ራሷን ከስምምነቱ ውጪ ማድረጓ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት የተጀመረው ውይይት እየተካሄደ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች እየተቋረጠ መልሶ ሲጀመር እዚህ ላይ ደርሷል።
50093604
https://www.bbc.com/amharic/50093604
የምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ጉዳይ ሐሰተኛ ዜና ወይስ የተቀለበሰ ውሳኔ?
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መወሰኑና በምትካቸው ሌላ ሰው ሊሾም መሆኑ ተሰምቶ ነበር።
ይህ ወሬ ግን ሐሙስ ዕለት የከንቲባው ጽህፈት ቤት "ከንቲባው በሥራ ላይ ናቸው" በማለት ከሥልጣን አለመነሳታቸውን በመግለጽ ወሬውን 'ሐሰት ነው' ሲል አጣጥሎታል። ባለፉት ቀናት የተለያዩ መገናኛ ብዙኀን ከዚህ ጉዳይ ጋር ቅርበት አለን የሚሉ አካላትን አናገርን በማለት ሲዘግቡ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ግን ምንም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቦ ቆይቶ ነበር። ቢቢሲ ኦሮምኛ በዚህ ጉዳይ ላይ በቂ መረጃ ካላቸው ሰዎች አጣርቶ ምክትል ከንቲባው ከኃላፊነታቸው ሊነሱ መሆኑ "እውነተኛ እንደሆነ" ዘግቦ ነበር። • "አዲስ አበባ የምንወዛገብባት ሳትሆን በጋራ የምንኖርባት ከተማ ናት" ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በወቅቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ያሉ መረጃዎችን መሰረት አድርጎ ለሚናገር ማንኛውም ግለሰብ፤ የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባውን እስከ አጠናቀቀበት ድረስ ጉዳዩ ያለቀለት ይመስል ነበር። ሐሙስ ዕለት አመሻሽ ላይ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ማጠናቀቁ በተገለፀ በጥቂት ሰዓት ውስጥ የከተማ አስተዳደሩ ዝምታውን በመስበር "ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሥራ ላይ ናቸው፣ ከሥልጠጣናቸው ተነስተዋል ተብሎ የወጣው ወሬ ስህተት ነው" በማለት በማህበራዊ መገናኛ ገፁ ላይ አስፍሯል። ይህ መረጃ የወጣው የኦዲፒ ስብሰባ መጠናቀቁን ተከትሎ የኦዲፒ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ የስብሰባውን መጠናቀቅ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ከገለጹ ከአንድ ሰዓት በኋላ ነው። ቢቢሲ ኦሮምኛ ያገኛቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት ምክትል ከንቲባው ከስልጣናቸው እንዲነሱ ከሳምንት ቀደም ብሎ ከበላይ ኃላፊዎች ጋር በመነገሩ ምክትል ከንቲባው አስቀድመው ይዘዋቸው የነበሩ ፕሮግራሞቻቸውን ሰርዘው ነበር። ከኃላፊነታቸው ሊነሱ እንደነበር የሚያሳዩ መረጃዎች ለአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከሥልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ምንም አይነት ደብዳቤ እጃቸው ላይ እንዳልደረሰ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን በመጠየቅ ለማረጋገጥ ችለናል። ይሁን እንጂ ጥቅምት 8 በፊት ምክትል ከንቲባው "በእጆችህ ላይ ያሉትን ሥራዎች አጠናቅቀህ ጨርስ፤ ሌላ ሠው ያንተን ቦታ ይተካል" ተብሎ ተነግሯቸው እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ካነጋገርናቸው ሰዎች መካከል አንዱ ይገልጻሉ። • ''አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት'' ከንቲባ ታከለ ኡማ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከኃላፊነታቸው መነሳት እንደማይፈልጉና ይህም ጉዳይ ለእርሳቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ደስተኛ እንዳልነበሩ፣ በሥራቸውም ላይ ጫና ፈጥሮ እንደነበር በሥራ አጋጣሚ ለእርሳቸው ቅርበት ያላቸው ሰዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፈው ማክሰኞ የአድዋ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች ሥራዎችን እያስመረቁና እያስጀመሩ መቆየታቸው ለዚህ ሌላው ማሳያ ነው የሚሉት እኚህ ግለሰብ የተለያዩ አካላት 'በአንድ ጊዜ ይህንን ሁሉ ሥራዎች ለመስራት ለምን ተጣደፉ?' ብለው ሲጠይቁ እንደነበር መረዳት ችለናል። ምክትል ከንቲባው ማክሰኞ ዕለት ቢሯቸው ቆይተው እንደወጡና የከንቲባው ጽሕፈት ቤትና ሌሎች የከተማው አስተዳደር ቢሮዎች አካባቢ የነበሩ ሰራተኞች ላይ ይታዩ የነበሩ ስሜቶችም ከንቲባው ይለቃሉ በሚል የሀዘን ድባብ ያጠላበት እንደነበር እኚሁ ግለሰብ ያስታውሳሉ። ከንቲባው በመጨረሻ የከተማ አስተዳደሩ ፕሮግራም ላይ የተናገሩት መልዕክት የስንብት መሆኑን እንደተረዱ በስፍራው የነበሩና ቢቢሲ ያናገራቸው ሰዎች ይገልጻሉ። • በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም የተቀሰቀሰው ውዝግብ "እርሳቸውን የማንሳት ውሳኔ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጣ ነው ብለን እንጠረጥራለን" የሚሉት እኚህ ግለሰብ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በእርግጠኝነት ከአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባነታቸው ሊነሱ እንደነበር ተጨማሪ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ያስረዳሉ። ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም የከንቲባው ጽህፈት ቤት በፌስ ቡክ ገፁ ላይ እደገለፀው ኢንጂነር ታከለ በኮፐንሀገን በተዘጋጀው የዓለም አቀፍ ከንቲባዎች ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘው ነበር። ይህ ጉባኤ ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት1/2012 ዓ.ም ድረስ ይካሄድ ለነበረው ጉባኤ ላይ ኢንጂነሩ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን ለመሳተፍ ይዘውት የነበረውን ዝግጅት እንዲቀርና የአየር ቲኬታቸውም መሰረዙን ምንጮቻችን ሰምተናል። በተመሳሳይ ደግሞ የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ ለምክትል ከንቲባው ባደረጉት ግብዣ ወደዚያው ለማቅናት ይዘውት የነበረው ፕሮግራምም መሰረዙን ከምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል። የምክትል ከንቲባው ከሥልጣን የመነሳት ምክንያት ምንድን ነው? የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ መጀመሪያ ወደ ስልጣን ሲመጡ ሁሉም በደስታ ስሜት አልተቀበላቸውም ነበር። በከተማዋ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ አካላት የእርሳቸውን ሹመት ተከትሎ የተለያዩ የተቃውሞ ድምጾችን ሲያሰሙ እንደነበር ይታወሳል። ምክትል ከንቲባው ግን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማስጀመር የከተማዋ ነዋሪዎችን ቀልብ ለመሳብ የሚያስችሉ ሥራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል። ከእነዚህ መካከል ለከተማው ተማሪዎች ደብተርና የደንብ ልብስ በነጻ እንዲሰጥ ማድረጋቸው በተለይ ደግሞ ለ300 ሺህ ተማሪዎች የዘወትር ምሳና ቁርስ ምገባ እንዲጀመር ማድረጋቸውም የከተማዋ ነዋሪዎችን ልብ ካሸነፉበት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። • "ታከለ ኡማ አዲስ አበባን መምራት የለባቸውም" እስክንድር ነጋ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ምክትል ከንቲባው ላይ ቅሬታ የነበራቸው አካላት መግለጫ ከማውጣት ባለፈ በግልፅ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ተደምጧል። በከንቲባው ላይ ከውጪ ከሚሰማው ተቃውሞ በተጨማሪ በዙሪያቸው ካሉ የገዢው ፓርቲ አባላት ጭምር ለዚህ ቦታ ሲታጩ ጀምሮ መሾማቸውን የሚቃወሙ ግለሰቦች ስለነበሩ የሥልጣን ጊዜያቸው የተደላደለ እንዳልሆነ ይነገራል። በአዲስ አበባ መስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ደግሞ ሐሙስ ወደማታ አካባቢ በከንቲባው ጽህፈት ቤት ሰራተኞች መካከል የነበረውን ስሜት ሲገልፁ "እንኳን ደስ አላችሁ፤ ውሳኔው ተቀልብሷል" እየተባባሉ እንደነበር በመግለፅ ከንቲባው ተመልሰው በሥራቸው ላይ አንዲቆዩ መደረጉ የፈጠረውነ ስሜት ይናገራሉ። አርብ ዕለት ጠዋት የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ በስብሰባው ላይ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በተመለከተ በመግለጫው ስለምክትል ከንቲባው ጉዳይ ምንም ነገር አላለም። • የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት የፓርላማውን ውሳኔ ተቃወመ ቢቢሲም ይህ የውሳኔ ሃሳብ በኦዲፒ ስብሰባ ላይ ቀርቦ መቀየር አለመቀየሩን ለማጣራት ያደረግው ሙከራም አልተሳካም። ምክትል ከንቲባው በሥራ ላይ ናቸው የሚለው መረጃ የኦዲፒ ስብሰባ መጠናቀቁ ከተገለጸ ከአንድ ሰዓት በኋላ መውጣቱ ግን ጉዳዩ ተገጣጥሞ ነው ለማለት ግን እንደሚያስቸግር ጉዳዩን ያነሳንላቸው ምንጮቻችን ይናገራሉ። ከተለያዩ ወገኖች መነሳታቸውን በተመለከተ የተሰማው መረጃ ተከትሎ የቀረበው ተቃውሞ ውሳኔው እንዲቀለበስ ድርሻ እንደነበረው እንደሚያምኑ እኚሁ ግለሰብ አክለው ተናግረዋል።
news-52977238
https://www.bbc.com/amharic/news-52977238
የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከ97 ዓመት በኋላ ዜጎቿን በማርስ ለማስፈር አቅዳለች
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንኩራኩር ወደ ማርስ ለመላክ ጫፍ የደረሰች ሲሆን በዚህም ወደ ማርስ የምታመጥቀው የጠፈር መርከብ ከአረቡ ዓለም ቀዳሚ ያደርጋታል።
ይህ ጉዞ የተባበሩት አረብ ኤምሬትን በዘርፉ በአረቡ ዓለም ቀዳሚ ያደርጋታል የዚህ የጠፈር ጉዞ 7 ወራት ይወስዳል። በጠፈር መርከብ ከመሬት ወደ ማርስ ምህዋር ጉዞ 500 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ይጠጋል። የሰው አልባ መንኩራኮሯ ተልዕኮ የማርስን ምህዋር በመሾር የአየር ንብረትና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ለቃቅሞ ወደ ምድር ማቀበል ነው። እነዚህን እጅግ አስፈላጊ የተባሉ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለመሰብሰብ 687 ቀናትን በዚያው ትቆያለች። አንድ ጊዜ የማርስን ምህዋር ለመዞር በአማካይ 55 ሰዓት ይወስድባታል። ትናንት ሰኞ የዚህ ፕሮጀክት አስተባባሪ ሰላህ አል አሚሪ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ይህ ጉዞ ሲሳካ ለወጣት አረብ ሳይንቲስቶች ትልቅ መነቃቃት ይፈጥራል። "ለህዋ ምሕንድስናም አዲስ ምዕራፍ ይሆናል" ብለዋል። የዚህች ተልዕኮ ስም "አማል" ሲሆን ትርጉሙም ተስፋ እንደማለት ነው። የጠፈር መርከቧ የምትነሳው በሩቅ ምሥራቅ ከምትገኝ ታኔጋሺማ ከምትባል የጃፓን ደሴት ሲሆን በሐምሌ 14 ጉዞዋን ትጀምራለች ተብሎ ይጠበቃል። የምትመጥቅበት ሮኬት የጃፓን ስሪት ሲሆን ሮኬቷ ሦስት ሙቀት መቆጣጠርያና መረጃ መቀበያ መሣሪያዎች ተገጥመውላታል። የያዘችው ከፍተኛ ጥራት ያለው ካሜራ ብናኝና የኦዞን አየርን ጭምር እንዲለካና ቀርጾ እንዲያስቀር ያስችላታል። ሁለተኛው መሣሪያ ደግሞ የኢንፍራሬድ ስፔክትረም ሲሆን የህዋን የላይኛውና የታችኛውን ሽፋን ይለካል። ይህ መሣሪያ የተሰራውም በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ ነው። ሦስተኛው የተገጠመው መሣሪያ አልትራቫዮሌት ስፔክትሮሜትር ሲሆን የኦክሲጂንና የሀይድሮጂን መጠንን ይለካል። የዚህ ተልዕኮ አንዱ ዓላማ ለውሃ እጅግ አስፈላጊ የሆኑት የኦክሲጅናና የሀይድሮጂን ምጣኔዎች ከፕላኔት እንዴት እየሸሹ እየሄዱ እንደሆነ መረዳት ነው። ሰር ኢያን ብላችፎርድ በእንግሊዝ ሳይንስ ሙዚየም ግሩፕ ዳይሬክተር ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት አብዛኞቹ እስከዛሬ ወደ ማርስ የተደረጉ የምርምር ጉዞዎች ዓላማ የከርሰ ምድር ጥናት (ጂኦሎጂ ተኮር) የነበረ ሲሆን ይቺ የአረብ ኢምሬቶች መንኮራኩር ጉዞ ግን ለአየር ንብረት ጥናት መሆኑ ልዩ ያደርጋታል። ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የህዋ ጉዞ ስታደርግ ይህ የመጀመርያዋ አይደለም። በተለይ ወደ ምድር ምህዋር ሮኬቶችን ልካ ታውቃለች። አንድ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዋንም ከዚህ ቀደም ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ ልካ ነበር። በዓረቡ ዓለም ወደ ሕዋ በመጓዝ የመጀርያው ሰው የሳኡዲው ልዑል ሱልጣን ቢን ሳልማን አል ሱኡድ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ1985 በአሜሪካ የህዋ መጓጓዣ ነበር ልዑሉ ጉዞውን ያደረጉት። ይህ ተልዕኮ ግን ከልዑሉ ጋር የሚስተካከል አይደለም። አንደኛው ይህ የህዋ መጓጓዣ የተገነባው በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የራሷ አቅም ሲሆን ወደ ጃፓን ደሴት ከተጓጓዘ በኋላ የሥነ ፈለክ ሳይንቲስቶች ለጤና ሲባል ለይቶ ማቆያ ውስጥ ገብተው እንዲቆዩ ይደረጋል። በብሪታኒያ ኦፕን ዩኒቨርስቲ የህዋ ጥናት ፕሮፌሰር የሆኑት ሞኒካ ግራዲ እንደሚሉት የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የምታደርገው ይህ ጉዞ በዓለም ኃያላን መንግሥታት ብቻ ተይዞ የነበረውን ዘርፍ የሚቀይር ይሆናል። "ይሳካል ብዬ አስባለሁ፤ የማርስ ጉዞ ብዙውን ጊዜ እክል አያጣውም፤ ዞሮ ዞሮ ይህ ጉዞ በናሳና በአውሮፓ ስፔስ ኤጀንሲ መዳፍ ሥር የወደቀውን ዘርፍ ሌሎችም አገራት እንዲገቡበት የሚያደፋፍር ይሆናል።" ዩናይትር አረብ ኢምሬትስ በዚህ ጉዞ ለዓለም ማሳየት የፈለገችው ከ8 ዓመታት በፊት የአረብ ምሁራን እና ተመራማሪዎች በሳይንሳዊ ምርምር ቀዳሚ እንደነበሩ ነው። የዱባይ ገዥ በዚህ ሕልማቸው በነበረው የህዋ ጉዞን እጅግ ተደስተዋል ተብሏል። አንዱ ዓላማ የአረቡን ዓለም በነዳጅ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ ያለውን ምጣኔ ሀብት ለመቀያየጥ ያደርጋል። ይህ የህዋ ጉዞ ስኬታማ ከሆነ ለአረቡ ዓለም ኩራትን የሚፈጥር ነው ተብሏል። ይቺ መንኩራኩር በለስ ቀንቷት ቀይዋ ፕላኔት ጋር ከደረሰች፣ እዚያ መድረሷ የሚበሰርበት ዕለት ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ 50ኛ ዓመት ብሔራዊ በዓል ጋር ይገጣጠማል። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እንደ አገር የተመሠረተችው እንደ አውሮፓዊያኑ በ1971 ዓ.ም ነበር። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በ2117 ዓ.ም በማርስ ዜጎቿን የማስፈር እቅድ አላት። ይህም የሚሆነው ከ97 ዓመታት በኋላ ነው።
news-55930521
https://www.bbc.com/amharic/news-55930521
በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ ነበሩ የተባሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበሩየተባሉ 15 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።
ይህ የተባለው የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ነው። የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በኤምባሲው ላይ ጥቃት በመፈጸም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም የአዲስ አበባን ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ የነበሩ ናቸው ያላቸውን 15 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። ሬውተርስ በጉዳዩ ላይ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስተያየት ቢጠይቅም ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል። አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ በህቡዕ የተደራጀው ቡድን ጥቃቱን ለመፈጸም ተልዕኳቸውን ከውጭ መቀበላቸውን እና ለጥቃት ሊጠቀሙባቸው ያዘጋጇቸው ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችና ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች እና ሰነዶች መገኘታቸውን አመልክቷል። ጥቃቱን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቡድኑን አባላት ሲመራ ነበር የተባለው የ35 ዓመት ግለሰብ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመር ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫውአመልክቷል። ይህ ጥቃት ለማድረስ የተሰማሩ ቡድን አባላትን ሲመራ ነበር የተባለው ግለሰብ ለጥቃቱ ማቀነባበሪያነት እንዲውል በአሥር ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር ከውጪ እንደተላከለት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ማረጋገጥ እንደቻለ የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል። ሌላ ተመሳሳይ ተልዕኮ የተሠጠው ህቡዕ ቡድንም በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የጠቆመው መግለጫው፤ መረጃውን ቀድሞ ያገኘውና ክትትል ሲያደርግ የቆየው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የግንኙነት መረቡን ለመበጣጠስ እንዲሁም ተጠርጣሪዎችን አድኖ ለመያዝም ከሱዳን የመረጃና የደህንነት ተቋም ጋር በቅንጅት መሰራቱን ጠቁሟል። በህቡዕ የተደራጀው ቡድኑ መሪ ኑሮውን በስዊዲን ያደረገው ግለሰብ መሆኑን እና ግለሰቡም በስዊዲን አገር በቁጥጥርሥር እንዲውል መደረጉን የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ገልጿል። ሌሎች ከሴራው ጋር ግንኙነት ያለቸውና በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ 21 ተጠርጣሪ ግለሰቦችንም በቁጥጥር ሥርየማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫአመልክቷል።
news-56156444
https://www.bbc.com/amharic/news-56156444
ምርጫ 2013፡ ኢሰመኮ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ በመጪው ምርጫ አጀንዳ እንዲሆን ጠየቀ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በግንቦት ወር በሚካሄደው ምርጫ 2013 የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ የምርጫ አጀንዳ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረበ።
ኮሚሽኑ ይህንን ያለው ለምርጫ 2013 ሊከበሩና ሊፈጸሙ የሚገባቸው ያላቸውን "ባለ 6 ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ" ባስተዋወቀበት ወቅት ነው። ከዚህ ቀደም የኢሰማኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) "የዚህ ምርጫ ቅስቀሳዎች አካል መሆን አለበት ብለን የምናስበው የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው" በማለት ኢትዮጵያ ውስጥ "በጣም ውስብስብ እና ጥልቅ የሆነ" የሰብዓዊ መብት ቀውስ መኖሩን ገልፀው ነበር። ኮሚሽኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቢመረጡ በሰብዓዊ መብቶች ረገድ ምን ቃል እንደሚገቡ ማድመጥ እንደሚፈልጉም በወቅቱ ተናግረው ነበር። ግንቦት 28 እና ሰኔ 15 ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ ለሚካሄደው ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን እያስመዘገቡ ይገኛሉ። የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳዎቻቸውን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ላይም በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሠልፎች ተካሂደዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በግንቦት ወር 2013 ዓ.ም በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊያከብሯቸው፣ ሊፈጽሟችው እና ሊያስፈጽሟቸው ይገባል ያላቸውን ባለ 6 ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ይፋ አደረጓል። ኮሚሽኑ በተለይም የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግሥት አካላት፣ የሲቪል ማኅበራት እና የሚዲያ ተቋማት እነዚህን ስድስት ነጥቦች ሊያፈጽሟቸውና ሊያስፈጽሟቸው ይገባል ሲል ገልጿል። ባለ ስድስት ነጥቦቹ የሰብዓዊ መብቶች አጀንዳዎች ሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ በተመለከተ የሚወስዱትን ተጨባጭ እርምጃዎች ማሳወቅ፣ ለሰብአዊ መብቶች በቁርጠኝነት እንዲቆሙ፣ ለሥርዓተ-ጾታ ምላሽ ሰጪ የሆነ የምርጫ ሂደት እንዲኖር ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚሉትን ጠቅሷል። ጨምሮም ለሰብአዊ መብት መሻሻል የሚያግዙ የሕግና ፖሊሲዎች ማሻሻያ ቃል ኪዳን መግባት፣ የመንቀሳቀስ፣ የመደራጀት፣ መረጃ የማግኘትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዲረጋገጥ እና ከግጭት ቀስቃሽ፣ የጥላቻ ንግግር እንዲሁም ከኃይል እርምጃዎች ሙሉ በሙሉ መቆጠብ መሆናቸው ላይ በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ለእነዚህም አጀንዳዎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ባለድርሻ አካላት በይፋ ቃል እንዲገቡና እንዲሁም በገቡት ቃል መሰረት እንዲተገብሩ ጥሪውን አቅርቧል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) "የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ በአገራዊ ምርጫው አጀንዳ እንዲሆን ማድረግ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት በኮሚሽኑ የተቀመጡትን የሰብአዊ መብት አጀንዳ ነጥቦች አትኩሮት ሰጥተው እንዲመለከቷቸው፣ ቃል እንዲገቡ በጠየቅናቸው ጉዳዮች ላይ የሚገቡትን ቃልኪዳን እንዲያሳውቁ እና በአጀንዳው በተቀመጠው መሰረት ሰብአዊ መብቶችን በማክበር እንዲቀሳቀሱ" በማለት ጥሪ አቅርበዋል። በ2012 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ በተከሰተው የኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት ወደ 2013 ዓ.ም የተሸጋገረው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት በተለየ ከፍ ያለ ፉክክር ይካሄድበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ መንግሥትና ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን የበኩሉን እንደሚወጣ በተደጋጋሚ ቃል መግባቱ ይታወሳል።
43972248
https://www.bbc.com/amharic/43972248
ኮዴይን፦ ገዳዩ 'ሽሮፕ'
በሰሜን ናይጄሪያ በምትገኘው ካኖ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ በቡድን ቡድን የሆኑ ወጣቶች፤ ቡናማ የመድሃኒት ብልቃጥ ጨብጠው ወፍራም ጣፋጭ ፈሳሽ እየተጎነጩ ነው።
ወጣቶቹ የሚጠጡት ለሳል ተብሎ የሚሰጠውን በተለምዶ 'ሽሮፕ' ተብሎ የሚጠራውን (የsyrup እና codeine ንጥረ ነገሮች ቅይጥ ) ፈሳሽ ነው። ጣፋጩን የእንጆሪ ጣዕም ያለውን መድሃኒት የሚጠጡ ወጣቶች ይሰክሩና እንዲናውዛሉ። ይሄ ትዕይንት በአስጨናቂ ሁኔታ በመላዋ ናይጄሪያ የተንሰራፋ ነው። የዚህ ኃይለኛ መድሃኒት ሱሰኞች ቁጥር ባልተጠበቀ ሁኔታ እጅጉን ከፍ ብሏል። እንደ ናይጄሪያ መንግሥት ቆጠራ በሰሜን ናይጄሪያ ሁለት ክልሎች ብቻ 3 ሚሊዮን ብልቃጥ ሽሮፕ በየቀኑ ይጠጣል። ውጤቱም እጅግ አሳዛኝ ነው። በመንግሥት በሚተዳደረው የሱስ የማገገሚያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ሶሰኞች ሌላ ሰው ያጠቃሉ በሚል ፍርሃት ከመሬት ጋር በሰንሰለት ተጠፍረዋል ይታያሉ። "ይሄ ጉዳይ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ሁሉንም ሰው እየለከፈ ነው" የሚለው ሳኒ ችግሩ ከአንደኛው ቤት ወደ አንደኛው እየተዛመተ መሆኑን ይናገራል። የኮዲን ሽሮፕን ከሚገባው መጠን በላይ መውሰድ አንጎል ላይ ጫና ይፈጥራል ወደ እብደትም ይወስዳል። በማገገሚያ ማዕከሉ ካሉት ታካሚዎች መካከል የ16 ዓመቷ ወጣት ለዕድሜ አቻዎቿ ስለ ችግሩ ግልፅ መልዕክት አላት።"እውነት ለመናገር እስከአሁን አልሄዱ እንደሁ ወደ ሱሰኝነቱ እንዳይሄዱ እመክራቸዋለሁ። ህይወታቸውን ያበላሸዋልና" ትላለች። በየሳምንቱ ህገ-ወጥ የኮዴን ሽሮፕ ቅይጥን ለመያዝ እንደሚሰማራው በካኖ የሚገኘው ብሄራዊ የመድሃኒት ህግ አስፈፃሚ አጄንሲ ዕምነት ከሆነ፤ በጎዳናዎቹ ላይ ከተንሰራፋው ቅይጥ ለመያዝ የቻሉት አንድ አስረኛውን ብቻ ነው። "እነዚህ መድሃኒቶች ከጨረቃ የመጡ አይደሉም። ከባህርም የወጡ አይደሉም። የሆነ ቦታ ተመርተው፣ ከአንድ ስፍራ ወደ አንድ ስፍራ የሚጓጓዙ ናቸው። ለማወቅ አንፈልግም እያልን ነው" በማላት የናይጄሪያ መንግሥት አስፈላጊውን ቁጥጥር እንዳላደረገ የሚናገሩት ደግም የህክምና ባለሙያዋ ዶክተር ማይሮ ማንዳራ ናቸው። የቢቢሲ የአፍሪቃ ዐይን ልዩ የ5 ወራት ህቡዕ ምርመራ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሯል። የምርመራ ጋዜጠኞቹ እራሳቸውን የሳል ሽሮፑን ካለ ህጋዊ የማዘዣ ወረቀት እንደሚገዛ የንግድ ሰው በማቅረብ፤ ህገ-ወጡን የሽሮፕ ቅይጥ የሽያጭ ስምምነትን ምስል ለመቅረፅ ችለዋል። ለአብነትም በኢሎሪን ናይጀሪያ ዋነኛ የሳል ሽሮፕ አምራች ከሆኑት መካካል አንዱ የሆነው የባዮራጅ ፋብሪካ ይጠቀሳል። የሽያጭ ተወካይ የሆኑት አልመንሰሩ እንዲሁም የመጋዘን አስተዳዳሪው ባባ አይቢጄ ለህቡዕ የምርመራ ቡድኑ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የኮዴን ምርትንና ሌላ ውህድን ለመሸጥ ፈቅደዋል። ባባ ኢቢጂ እንደሚለው ህፃናት ሱስ የሚሆነውን የኦፒዮድ ቅይጥን አንዴ ከቀመሱ ተጨማሪ ለማግኘት ተመልሰው ይመጣሉ። ባዮራጅ ፋብሪካ ባዮሊን የተባለውን ፈሳሽ ከኮዴን ጋር እንደማይሸጥ አል መንሱሩም ከሁለት ዓመት ነፊት ፋብሪካው እንደለቀቁ ተናግረዋል። ባባ ኢቢጂም ሆነ አልመንሱሩ ጥፋት መፈፀማቸውን ክደዋል። እኒህ ግለሰቦች መሰል ንግድ ለመስራት ነፃ ቢሆኑም በዚህ ውጥንቅጥ በእጅጉ የተጎዱት የናይጄሪያ ወጣቶች ናቸው። ቢቢሲ ይህን መርማሪ ዘገባ ከሰራ በኋላ የናይጄሪያ መንግሥት ይህ ገዳይ እና ሱስ አስያዥ መድሃኒት በሃገሪቱ እንዳይሸጥ ማዘዙ ተሰምቷል።
news-44278218
https://www.bbc.com/amharic/news-44278218
"ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው'' አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ
በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በልዩ ይቅርታ እንደሚፈቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቅዳሜ እለት መግለፁን ተከትሎ ከትንናት ሰኞ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መፈታታቸውን ሲጠብቁ ቆይተው ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ተለቀዋል።
በቤተሰባቸው ቤት ከቅዳሜ ጀምረው ሲጠባበቁ ለነበሩት ወዳጆቻቸው ባደረጉት ንግግር አቶ አንዳርጋቸው ''እኔ ተፈትቻለሁ ኢትዮጵያ ግን ያልተፈቱ ብዙ ችግሮች አሉባት'' ብለዋል። ከእስር ተፈተው ቤታቸው ሲደርሱ የተመለከቱት ነገር ያልጠበቁት እንደሆነ የተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው። "ምንም መረጃ ባይኖረኝም ኢትዮጵያዊያን እኔን ለማስፈታት ጥረት እንደሚያደርጉ ይሰማኝ ነበር" ብለዋል። ለዚህ ቀን መምጣት ለደከሙ ለሁሉም ሰዎች ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ "የኢትዮጵያ ሕዝብ ገብቶበት ካለው አስቸጋሪ ሁኔታ አንፃር፤ እንዲህ አይነት ሃገር ከማየት ፍርድ ቤታችሁ የወሰነውን የሞት ቅጣት ተግባራዊ አድርጉ'' በማለት ለመርማሪዎች መናገራቸውን ገልፀዋል። ከዚህ በፊት በቴሌቪዥን ተቆራርጦ ነው የቀረበው ያሉትን ምስል እንዳዩት የተናገሩት አቶ አንዳርጋቸው "ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው፤ ነገር ግን ቆራርጠው ነው ያቀረቡት።" ጨምረውም "ፍቱኝ ብዬ አልጠይቃችሁም አብሬያችሁ የሰራሁበትን ጊዜ እንደውለታ ቆጥራችሁ የሞት ፍርዱን ተግባራዊ አድርጉ ብዬ ጠይቄያቸዋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርግ የቆየው ሪፕሪቭ የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም እንዳለው አቶ አንዳርጋቸው ለንደን ከሚገኙት የህይወት አጋራቸው የሚ ኃይለማሪያም ጋር ከአራት ዓመት በኋላ ለአጭር ጊዜ በስልክ ተነጋግረዋል። የሪፕራይቭ ዳይሬክተር ማያ ፎአ ስለአንዳርጋቸው መፈታት በሰጡት አስተያየት "ቤተሰቡ፣ ልጆቹና ደጋፊዎቹ የሚደሰቱበት አስደሳች ዜና ነው። በቅርቡም ወደ ለንደን መጥቶ ለረጅም ጊዜ ተለይቷቸው የቆዩትን ልጆቹን ያገኛቸዋል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ" ብለዋል። ሰኞ ጠዋት የእንግሊዝ ኤምባሲ መኪኖች በማረሚያ ቤት አካባቢ ተገኝተው ነበር፤ የአቶ አንዳርጋቸው እህት በስፍራው ከኤምባሲ ሰዎች ጋር የነበረች ሲሆን ለቤተሰቦቿ ደውላ ማለዳ እንዳገኘችውና ወደቤት እንደሚመጣ ነግራቸው ነበር። ከሰኞ እለት ጀምሮ አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ የሚገኘው የቤተሰቦቹ ቤትና አካባቢው በመፈታቱ የተሰማቸውን ደስታ በሚገልጡ መልዕክቶችና በፎቶዎቹ አሸብርቆ ውሏል። የአንዳርጋቸው ደጋፊዎች የእርሱን ምስል የታተመበት ቲሸርት ለብሰው በአካባቢው ተገኝተው ሲጨፍሩ እና ደስታቸውን ሲገልጡ እንደነበር ተመልክተናል። በለንደን የምትኖረው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህይወት አጋር ወ/ሮ የምስራች ኃይለማርያም (የሚ) በባለቤቷ ሊፈታ በመሆኑ እጅግ መደሰቷን እና እስካሁንም የተፈጠረውን እንዳላመነች ለቢቢሲ ተናግራለች። ''ከአንድ ሰው ህይወት 4 አመት የሚሆነውን በእስር ማሳለፍ ምን አይነት ተጽዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል መገመት ይከብዳል። ነገር ግን ባለቤቴ ከዚህ በኋላ ወደ ፀሃፊነት ያዘነብላል ብዬ አስባለሁ'' ትላለች ወ/ሮ የሚ። ለልጆቼ ዜናውን ስትነግራቸው በደስታ አልቅሰው ነበር የምትለው የሚ፤ እስካሁን አንዳርጋቸውን ለማነጋገር እየጠበቁ እንደሆነ ገልጻለች። ባለቤቷ በሽብርተኝነት በተፈረጀው ግንቦት ሰባት ድርጅት ስለነበረው ኃላፊነት እና ስለቤተሰቡ ሁኔታ የተጠየቀችው የሚ፤ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ሰዎች ከመንግሥት ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ይታወቃል፤ ስለዚህ ሁሌም ቢሆን የሆነ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል እገምት ነበር ብላለች። የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ አንዳርጋቸው፣ በሽብር ወንጀል ሁለት ጊዜ ክስ ተመሥርቶባቸው በዕድሜ ልክና በሞት እንዲቀጡ እንደተፈረደባቸው ይታወሳል።
42869443
https://www.bbc.com/amharic/42869443
ካለሁበት 20፡ አንዳንድ ቦታዎች ጀጎልን ያስታውሱኛል
ሚካኤል ባሕሩ እባላለሁ። ተወልጄ ያደግሁት ሐረር ከተማ ሲሆን፤ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቴን የተከታተልኩት አዲስ አበባ ነው። አሁን ያለሁት ደግሞ ሆላንድ ውስጥ አምስተርዳም ከተማ ነው።
ወደ እዚህ ሃገር የመጣሁት መጀመሪያ ሀገር ቤት በህክምና ትምህርት ከተመረቅሁ በኋላ ነው። ትምህርቴን ለመቀጠል በነበረኝ ፍላጎት ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት አመልክቼ ነበር። በመጨረሻም አሁን ያለሁበት ከተማ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ተቀብሎኝ ሁለተኛ ዲግሪ ለመስራት ነው የመጣሁት። አምስተርዳምን ኢትዮጵያ ውስጥ ከኖርኩባቸው ከተሞች የተለየ የሚያደርገው በቀዳሚነት ቅዝቃዜዋ ነው። በተጨማሪ ሆላንድ ሜዳማ ስለሆነች እንደ ኢትዮጵያ ተራራ የመመለከት እድልህ ጠባብ ነው። አምስተርዳም ውስጥ ከፎቆቹ ባሻገር የምታይ ተራራ የለም ዙሪያው በህንፃዎች የተከበበ ነው። ወደ ሆላንድ ከመጠሁ በኋላ አዘውትሬ የምመገበውና የምወደው በሳልመን ዓሳ የተዘጋጀ መግብ ነው። ከቤት ውጪ ምግብ ቤት እየሄድኩ መመገብን ስለማልመርጥ ብዙ ጊዜ እራሴ እየሰራሁ ነው የምመገበው። ስለዚህም ከዓሳ የሚዘጋጀውን ምግብ እመርጠዋለሁ። ከሃገሬ ከወጣሁ አጭር ጊዜ ቢሆንም ስለሃገር ቤት ሳስብ ዘወትር የሚናፍቀኝ የሀገሬ ሰው ነው። ከሀገር ውጪ የተለየ ባህል ካላቸው ሰዎች ጋር በቀላሉ ተዋህዶ መኖር አስቸጋሪ በመሆኑ የማውቃቸው ሰዎች ይናፍቃሉ። በህይወቴ ውስጥ የማውቃቸው ሰዎች በሙሉ ያሉት ሃገር ቤት ነው። ስለዚህ ከቤተሰቤ ጀምሮ ሁሉም ሰዎች ዘወትር ይናፍቁኛል። ከቤቴ በመስኮት በኩል ወደውጪ ስመለከት በተለይ ጠዋት የማየው በበጋ ጊዜ ሲሆን ከምሥራቅ የምትወጣውን ፀሃይ ነው። አምስተርዳም ውስጥ አብዛኛው ሰው ለጤናውም ሲል ብስክሌት ተጠቃሚ ነው። በተለይ ጠዋት በጣም ብዙ ብስክሌቶች ተደርድረው ቆመው በመስኮቴ በኩል እመለከታለሁ። እናም ጠዋት ላይ ቡናዬን እየጠጣሁ በመስኮት የምትገባውን ፀሃይ እየሞቅኩ ውጪውን መመልከት ደስ ያሰኘኛል። አምስተርዳም ብዙ ነገሮች አሏት፤ ግን ቢኖራት ወይም ቢጨመርላት የምለው ነገር ተራራ ነው። ከተማዋ ሜዳማ ስለሆነች ተራራ ለማየት ይቸግራል ስለዚህ ለከተማዋ ብቻ ሳይሆን ሃገሪተወ ተራራ ቢኖራት የበለጠ የተሟላ ትሆናለች ብዬ አስባለሁ። ወንዞችና የሚያምሩ መስኮች በከተማዋ ውስጥ አሉ። በብስክሌትም ሆነ በእግሬ ስጓዝ አንድ ከፍ ያለቦታ ቢኖራቸው ወደዚያ ሄጄ የከተማዋን ዙሪያ ገባ ብመለከት ደስ ይለኛል። እናም ይህ እድል ቢኖር ጥሩ ስሜትን ይሰጣል ብዬ ስለማስብ ከተማዋ ተራራ ቢኖራት እላለሁ። አሁን ግን በምታምረው ከተማ ውስጥ ዞር ዞር ብዬ ስትመለከት የተወሰነ ነገር ብቻ ነው ማየት የምችለው። እናም ከዛፎች ወይም ከህንፃዎች ጀርባ ምን እንዳለ ለማየት ያስቸግራል። በተለይ በከተማዋ ውስጥ ስትቆይ የመታፈን አይነት ስሜትን ይፈጥራል። ስለዚህ አምስተርዳም ውስጥ ከፍ ብለው የሚታዩ ተራሮች ቢኖሩ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። አንዳንድ የአምስተርዳም አካባቢዎች ከትውልድ ከተማዬ ከሐረር ጋር ይመሳሰሉብኛል። በተለይ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ተቃራርበው የተሰሩ ቤቶችና በተጠረቡ ድንጋዮች የተገነቡ የውስጥ ለውስጥ የከተማዋ መንገዶች ትንሽም ቢሆን ጀጎልን ያስታውሱኛል። በተለይ በመጣሁበት ወቅት ወደ እነዚህ አካባቢዎች ስሄድ ድንቅ ይለኝ ነበር። ነገር ግን ከዚህ ውጪ አብዛኛው የከተማው ክፍል እኔ ከማውቃቸው የሃገራችን አካባቢዎች ጋር ብዙም የሚያመሳስል ነገር የለውም። እስካሁን እንደተማሪ አምስተርዳም ውስጥ በቆየሁበት ጊዜ የጎላ አስቸጋሪ ነገር አልገጠመኝም። ነገር ግን ለሃገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ስለነበርኩ ሰዎችን ለመቅረብና ተዋውቆ ማህበራዊ ግንኙነትን ለመመስረት መጀመሪያ ላይ ተቸግሬ ነበር። ይህም ከሃገርና ከቤተሰብ ናፍቆት እንዲሁም ከትምህርቱ ጫና ጋር ተያይዞ ከብዶኝ ነበር። ለሁለት ወራት ያህልም በዚህ ምክንያት ተቸግሬ ነበር። ከዚህ ውጪ ግን ፈጣሪ ይመስገን አሁን ለምጄ ሁሉ ነገር ጥሩ እየተሄደልኝ ነው። አሁን ባለሁበት ሁኔታ ድንገት ብድግ ብዬ ወደ አንድ ቦታ መሄድ ብችል የምመርጠው ቦታ ሐረርን ነው። ቀጥታ ወደ ሐረር በመሄድ ጀጎል ውስጥ በመሆን ጣፋጭ ፍራፍሬዎቿንና ምግቦቿን እየበላሁ እራሴን ባገኝ ደስ ይለኛል። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍል ለማግኘት ፦ ካለሁበት 21፡በእንግሊዝ ሰው ወደየግል ጉዳዩ ነው የሚሯሯጠው ካለሁበት 22፡ የተወለድኩባት፣ የቤተሰብ ፍቅርና ህይወት ያሞቃት ቤቴ ትናፍቀኛለች
news-54198845
https://www.bbc.com/amharic/news-54198845
ኢትዯጵያ፡ አገራዊ ምርጫው በዚህ ዓመት መካሄድ እንደሚችል ተገለጸ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ስድስተኛው ዙር አገራዊ መርጫ ሊካሄድ እንደሚችል የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ አስታወቁ።
በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት አስከ አንድ ዓመት ለሚደርስ ጊዜ እንዲሸጋገር የተወሰነው ምርጫ እንዲካሄድ የወረርሽኙ ሁኔታን በተመለከተ ከጤና ባለስልጣናት የሚሰጡ ምክሮችን መሰረት እንደሚያደርግ ተገልጾ ነበር። በዚህም መሰረት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአገሪቱ ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታን በተመለከተ የመስሪያ ቤታቸውን ግምገማ ለሕዝብ ተወካዮች ምከክር ቤት ባቀረቡበት ጊዜ ነው አገራዊ ምርጫን ለማካሄድ እንደሚቻል አመልክተዋል። ካለው የወረርሽኝ ስጋት አንጻር የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን ከግምት ውስጥ የሚያስገባ የምርጫ ሥነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ሚኒስትሯ ገልጸዋል። አክለውም ምርጫውን ለማካሄድ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ካጋጠመ "ይህ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል" ሲሉ ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ላይ ጠቅሰዋል። ሚኒስትሯ እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ወረርሽኙ በሁሉም ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን፤ በዚህም የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት የታወቀ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። እስካሁንም በተደረገው ምርመራ ከ66 ሺህ 200 ሰዎች በላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 1 ሺህ 45 ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት መሞታቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነሰ ባይሆንም የቅድመ መከላከልና ስርጭቱን በመግታት ሂደት ውስጥ በሁሉም ደረጃ አቅም ማሳደግ መቻሉን አመልክተዋል። በዚህም የአገሪቱ የመመርመርም ሆነ የክትትል አቅም በማደጉ በከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ጋር መድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር ከበሽታው መከላከልና ሕክምና አንጻር የተሰሩ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለምክር ቤቱ ዝርዝር የሆነ ሪፖርት አቅርበዋል። በአገሪቱ ካለው የወረርሽኝ መስፋፋት ሁኔታ አኳያ አገራዊ ምርጫን ከማካሄድ አንጻር የበርካታ አገራት ተሞክሮዎች ላይ ምልከታ የተደረገባቸው ሲሆን፣ በአንዳንዶቹ በወረርሽኝ ወቅት ምርጫ ተካሂዷል፤ በአብዛኞቹ ደግሞ እንዲተላለፍ ተደርጓል። በኢትዮጵያም በሽታውን የመከላከልም ሆነ የመቆጣጠር ዝግጅነቱ ዝቅተኛ በነበረበት ወቅት ምርጫን ማከናወን ስጋቱ የበለጠ የሚያሳድገው በመሆኑ በተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል። ስለዚህም ወረርሽኙ የጤና ስጋት መሆኑ እንዳለ ቢሆንም ቀደም ሲል ከነበረው ልምድ እንፃር ከፍተኛ አለመሆኑ፣ በሽታው ከዚህም በኋላ ረዘም ላለ ጊዜ ስጋት ሆኖ ሊቆይ ሰለሚችል፤ ምርጫው ሲራዘም ከነበርንበት ሁኔታ አንጻር ስለስርጭቱ የተሻለ መረጃ መኖሩ ተገልጿል። እንዲሁም አስፈላጊውን የበሽታው ምርመራ፣ ክትትል፣ ሕክምናና ጥንቃቄን በተመለከተ የተሻለ አቅምና ግንዛቤ በመኖሩ፤ በተጨማሪም የተለያዩ አገራትን የምርጫ ተሞክሮን በማየት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ እንዳለ ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጣዩን አገራዊ ምርጫን በተመለከተ በቀረበውን የጤና ሚኒስቴር ሪፖር ላይ በመወያየት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ሳቢያ እንዲራዘምና በክልሎችና በፌደራል ደረጃ ያሉት ምክር ቤቶች ቀጣዩ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ በሥራቸው ላይ እንዲቀጥሉ መወሰኑ ይታወሳል።
news-49671843
https://www.bbc.com/amharic/news-49671843
የአእምሮ ጤና ሰባኪው ፓስተር ራሱን አጠፋ
የአእምሮ ጤና አስተማሪ እና ብዙ አባላት ያላት ቤተክርስቲያን ፓስተር ራሱን አጠፋ።
የ30 ዓመቱ ጃሪድ ዊልሰን 15 ሺህ በላይ ተከታዮች ባላት ቤተክርስቲያን ውስጥ እየሰበከ ከ18 ወራት በላይ አገልግሎ ነበር። ጃሪድ ከባለቤቱ ጋር በመሆን በድብርት ለሚሰቃዩ ሰዎች ድጋፍ የሚያደርግ ፕሮግራም ቀርጸው ይፋ አድርገው ነበር። የሁለት ልጆች አባት የነበረው ጃሪድ ባለቤት በሞቱ መላው ቤተሰቡ ከባድ ሃዘን ውስጥ እንደገቡ ተናግራለች። • በምሥራቅ ወለጋ የአራት ቀን ሬሳ አስነሳለሁ ብሎ መቃብር ያስቆፈረው 'ነብይ' በቁጥጥር ሥር ዋለ • በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው በአዞ ተገደሉ • ወንዶች ከሴቶች በበለጠ ለምን እራሳቸውን ያጠፋሉ? የፓስተሩን መሞት ይፋ ያደረጉት ግሬግ ሎውሪ የተባሉ ፓስተር ናቸው። "ጃሪድ ፈጣሪን የሚወድ እና የአገልጋይ ልብ የነበረው ሰው ነው። ሁሌም ንቁ፣ መልካም እና ሰዎችን ለማገልገል የሚጥር ሰው ነበር" ሲሉ ስለቀድሞ አገልጋይ ጃሪድ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። "ጃሪድ በተደጋጋሚ በድብርት ይጠቃ ነው። ይህንንም በግልጽ ይናገር ነበር" ያሉት ፓስተር ግሬግ፤ "ድብርት ተጫጭኗቸው ራሳቸውን ስለማጥፋት የሚያስቡ ሰዎችን መርዳት ይፈልግ ነበር" ሲሉም አክለዋል። የመሞቱ ዜና ከመሰማቱ በፊት፤ ጃሪድ በትዊተር ገጹ ላይ "ኢየሱሰን ትወድ የነበረች እና ራሷን ስላጠፋች ሴት" የቀብር ስርዓት በተመለከተ በአሰፈረው ጽሁፍ፤ "ኢየሱስን መውደድ ራስን ስለ ማጥፋት ከማሰብ አያስቆምም። ኢየሱስን መውደድ ከድብርት አያድንም። ይህ ማለት ግን ኢየሱስ መጽናኛ እና ድጋፍ አይሆነንም ማለት አይደለም'' ሲል ጽፎ ነበር። የጃሪድን ቤተሰብ ለመደገፍ እየተዋጣ ባለው ገንዘብ እስካሁን ከ42ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር መሰብሰብ ተችሏል።
news-47823866
https://www.bbc.com/amharic/news-47823866
ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ
የኢቲ 302 የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ የቦይንግ ከፍተኛ ኃላፊዎች መግለጫ ሰጥተዋል።
ዴኒስ ሚሌንበርግ የቦይንግ ኩባንያ ሊቀመንበር፣ ፕሬዚደንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ መግለጫ ያወጡት ሁለቱ ከፍተኛ የቦይንግ ኃላፊዎች ዴኒስ ሚሌንበርግ የቦይንግ ኩባንያ ሊቀመንበር፣ ፕሬዚደንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የቦይንግ የመንገደኞች አውሮፕላን ፕሬዝደንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኬቪን ማካሊስተር ናቸው። ዴኒስ ሚሌንበርግ በ737 ማክስ አውሮፕላኖች ምክንያት ለጠፋው የሰው ህይወት አዝነናል ብለዋል። የኩባንያው ሊቀመንበር '' . . . የኢቲ 302 የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት እንዳሳየው እንደ ከዚህ ቀደሙ [ላየን ኤየር] ኤምካስ የተሰኘው ሶፍትዌር በተሳሳተ መረጃ 'አክቲቬትድ' (ሥራውን ጀምሯል) ሆኖ ነበር'' ብለዋል። • ''አብራሪዎቹ ትክክለኛው መመሪያ ተከትለዋል'' ''አደጋን ሊያስከትል የሚችል ሁኔታን የመቅረፍ ሥራ የእኛ ነው። አውሮፕላኑ የእኛ ስሪት ነው። እንዴት እንደሚስተካከልም የምናውቀው እኛው ነን። . . . ለኤምካስ ሶፍትዌር ማስተካከያ ከተደረገለት በኋላ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ ሲመለስ በበረራ ደህንነታቸው አስተማማኝ ከሆኑ አውሮፕላኖች መካከል አንዱ ይሆናል'' ሲሉም ተደምጠዋል በቪዲዮ በተደገፈው መግለጫቸው። የቦይንግ የመንገደኞች አውሮፕላን ፕሬዝደንት እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ኬቪን ማካሊስተር በበኩላቸው ''የኢትዮጵያ የአደጋ መርማሪ ቡድን ላልተቋረጠው ትጋታቸው እናመሰግናቸዋለን። የበረራ ደህንነትን ለማረጋገጥ የአደጋው መንስዔ ምን እንደሆነ መረዳት ቁልፍ ጉዳይ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን በአጽንኦት ተመልክተን የአውሮፕላናችንን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን'' ብለዋል። • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? ኬቪን ማካሊስተር ጨምረውም ''በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ የበረራ መረጃ መቅጃው የያዘው መረጃ እንዳሳየው አውሮፕላኑ የተሳሳተ ማዕዘን ጠቋሚ (አንግለ ኦፍ አታክ ሴንሰር) ግብዓት ስለነበረው የደህንነት መቆጣጠሪያ ሥርዓቱ (ኤምካስ) ሥራውን እንዲያከናውን አድረጎታል" ሲል መግለጫው ኢቲ 302 ከኢንዶኔዢያው አውሮፕላን ጋር ተመሳሳይ አደጋ እንደገጠመው ገልጿል። ቦይንግ ጨምሮም በተሳሳተ መረጃ ኤምካስ (ማኑቬሪንግ ክራክተሪስቲክስ ኦጉመንቴሽን ሲስተም) አክቲቬት እንዳይሆን የተሻሻለ ሶፍትዌር እያዘጋጀ እንደሆነ፣ ለአብራሪዎች ስልጠና እና 737 ማክስን በተመለከተ የሥልጠና ፕሮግራሞችን እየቀረጸ እንደሆነ ገልጿል። የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ መውጣቱን ተከትሎ ቢቢሲ ካነጋገራቸው ኢትዮጵያዊያን መካከል ሳራ ቢረዳ "ሁኔታው ለኢትዮጵያውያን በጣም አሳዛኝ ነው። አሁን ስህተቱ የአየር መንገዱ እንዳልሆነ ተረድተናል። ይህ ዜና አስደሳች ነው ማለት ባልችልም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስም እና ዝና አስጠብቆ የሚያቆይ ነው። ችግሩ የሶፍትዌሩ መሆኑን እና አብራሪዎቹም አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር እንደሞከሩ አውቀናል" ብላለች። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? ሌላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እስራኤል ተፈራ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ከወጣ በኋላ እንዲህ ሲል አስተያየቱን ለቢቢሲ ሰጥቷል። ''አብራሪዎቹ ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል፤ ጀግኖች ናቸው። ችግሩ የአውሮፕላኑ ነው። አደጋው በጣም ቢያሳዝነኝም አሁን ባለው መረጃ ግን አብራሪዎቹ ጀግኖች ናቸው። በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊደነቅ ይገባዋል። በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ መጽናናትን እመኛለሁ።'' የአደጋው መንስኤ ከአውሮፕላኑ የደህንነት መጠበቂያ ሥርዓት ጋር የተያያዘ እንደሆነ መታወቁና የአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ ቦይንግም የምርመራውን ውጤት መቀበሉ ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ትልቅ እፎይታ እንደሆነ የአየር ትራንስፖርት ባለሙያዎች ተናግረዋል።
news-51313698
https://www.bbc.com/amharic/news-51313698
ኃይለኛ ንፋስ ትራምፕ በሜክሲኮ ድንበር እያስገነቡ ያሉትን አጥር አፈረሰ
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና ሜክሲኮ ድንበር ላይ እያስገነቡ ያሉት አጥር በኃይለኛ ንፋስ መፍረሱን የአሜሪካ ባለስልጣናት አስታወቁ።
በሜክሲኮዋ ካሌክሲኮ እና በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ከተሞች መካከል እየተገነባ የነበረው የአጥሩ አካል ረቡዕ ጠዋት አካባቢ በኃይለኛ ንፋስ መውደቁ ተነግሯል። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ የሚሻገሩ ስደተኞችን ለማስቆም በማሰብ በሁለቱ አገራት መካከል አጨቃጫቂ የሆነውን ረዥም የብረት አጥር እየስገነቡ እንደሆነ ይታወቃለ። ከፍታው 9 ሜትር የሚረዝመውን የብረት አጥር ለማቆም የተገነባው ኮንክሪት አለመድረቁ ለአጥሩ በንፋስ መውደቅ እንደምክንያት ተጠቅሷል። የአሜሪካ ብሔራዊ ሜትሪዮሎጂ አገልግሎት እንዳስታወቀው በወቅቱ የነበረው የንፋስ ፍጥነት በሰዓት 48 ኪ.ሜትር ይደርስ ነበር። ትራምፕ ስድተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ይረዳኛል ያሉት የአጥር ግንባታ 3145 ኪሎ ሜትር በላይ ይረዝማል። ከትናንት በስቲያ ፕሬዝደንት ትራምፕ በኒው ጀርሲ ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያስገነቡት ያሉት የአጥር ግንባታ "ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት" ግንባታው እየተካሄድ እንደሆነ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረው ነበር። ትራምፕ ይህን ባሉ በአንድ ቀን ልዩነት የአጥሩ ክፍል በንፋስ ወድቋል። የአሜሪካ ድንበር ጥበቃ ለኤልኤ ታይምስ እንደተናገሩት አጥሩ በንፋስ መውደቁን ተከትሎ በሰው እና በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም። በንፋሱ የወደቀ እና የተወላገደ የአጥሩን ክፍል ለማቃናት ጥረት የሚያደርጉ ክሬኖች ታይተዋል። ትራምፕ ለፕሬዝደንትነት ሲወዳደሩ ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል በሜክሲኮ እና በአሜሪካ መካከል የግንብ አጥር መገንባት አንዱና አጨቃጫቂው ሃሳባቸው ነበር። ትራምፕ በወቅቱ ለአጥሩ ግንባታ ወጪውን የምትሸፍነው ሜክሲኮ ነች ሲሉም መደመጣቸው ይታወሳል። ሜክሲኮ ግን ለአጥሩ ግንባታ ስባሪ ሳንቲም እንደማታወጣ ካስታወቀች በኋላ፤ ትራምፕ ከፔንታጎን ጨምሮ ከተለያዩ አካላት ለአጥሩ ወጪ መሸፈኛ ፈንድ አስባስበዋል። ፔንታጎን በአሜሪካ እና በሜክሲኮ ድንበር ላይ ለሚገነባው አጥር 3.4 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።
55407745
https://www.bbc.com/amharic/55407745
ኮሮናቫይረስ ፡ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቲቪ እየታዩ ተከተቡ
የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት ጆ ባይደን በቴሌቭዥን እየታዩ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ተከተቡ።
ባይደን የመጀመሪያውን የክትባት ጠብታ ሲወስዱ፤ አሜሪካውን ክትባቱን መውሰድ "አስተማማኝ መሆኑን እንዲያውቁ እፈልጋለሁ" ብለዋል። ባለፈው ሳምንት የፕሬዘዳንት ትራምፕ ምክትል የሆኑት ማይክ ፔንስ፣ አፈ ጉባኤዋ ናንሲ ፔሎሲ እና ሌሎችም የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በቴሌቪዥን እየታዩ ተከትበዋል። ሞደርና ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ውስጥ ፍቃድ ከተሰጠው ወዲህ ክትባቱ መሰጠት ተጀምሯል። ከ500 ሺህ በላይ አሜሪካውያን መከተባቸውም ተገልጿል። ባይደን ሲከተቡ "ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ማሳሳብ እፈልጋለሁ። ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም" ብለዋል። የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ክትባት በማስጀመሩ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። የባይደን ባለቤት ጂል የመጀመሪያ የክትባት ጠብታ ወስደዋል። የባይደን ምክትል ሆነው የተመረጡት ካምላ ሀሪስ እና ባለቤታቸውም በመጪው ሳምንት ክትባት ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባይደን ዋይት ሀውስ ከገቡ በኋላ ባሉት 100 ቀናት ውስጥ 100 ሚሊዮን ክትባት የመስጠት እቅድ አላቸው። አሜሪካ ውስጥ ከ18 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 319 ሺህ ያህል ሰዎች ሞተዋል። ቫይረሱ ይዟቸው 3 ቀን ሆስፒታል ያሳለፉት ትራምፕ ክትባቱን ስለመውሰዳቸው ያሉት ነገር የለም። ሆኖም ግን "ክትባቱን ለመውሰድ መርሀ ግብር አልያዝኩም። በትክክለኛው ጊዜ ክትባቱን ለመውሰድ ግን እጠባበቃለሁ" ሲሉ ትዊት አድርገዋል። ክትባቱ መጀመሪያ ለማን ይሰጣል? ፋይዘር 3 ሚሊዮን ጠብታ አሜሪካ ልኳል። 6 ሚሊዮን የሞደርና ክትባትም ወደ አሜሪካ ለመግባት ዝግጅቱ ተጠናቋል። በአሜሪካ በሦስት ደረጃ ክትባቱ ለእነማን እንደሚሰጥ መረጃ ወጥቷል። ደረጃ 1ሀ- ክትባቱ ለ21 ሚሊዮን የጤና ባለሙያዎች ይሰጣል። በተጨማሪም 3 ሚሊዮን አረጋውያን ክትባቱን ያገኛሉ። ደረጃ 1ለ- ከ75 ዓመት በላይ የሆኑ አሜሪካውያን ይከተባሉ። ፖስታ አድራሾች፣ መምህራን፣ ነጋዴዎችን ጨምሮ 30 ሚሊዮን እጅግ አስፈላጊ አገልግሎት ሰጪዎችም ይከተባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ደረጃ 1ሐ- ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎች ክትባቱ ይሰጣቸዋል። እነዚህ ለኮቪድ-19 የሚያጋልጥ ቀደም ያለ ህመም ያለባቸው 129 ሚሊዮን ሰዎች ናቸው።
news-54422254
https://www.bbc.com/amharic/news-54422254
ህወሓት ፡ በ5ኛው ዘመን የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት የተገኙት ብቸኛዋ የህወሓት አባል
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ያሉና በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ላይ የሚገኙ አባላቱ የተወከሉበትን ምክር ቤትና ኃላፊነት ለቅቀው እንዲወጡ አዝዟል።
በመሆኑም መስከረም 25/2013 ዓ.ም በተካሄደው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የትግራይ ክልል ተወካዮች እንደማይሳተፉ ተገልጾ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ህወሓት ካሉት 38 የትግራይ ክልልን እና አምስት አዲስ አበባን ወክለው በምክር ቤቱ ከሚገኙት እንደራሴዎች መካከል 42ቱ ሳይገኙ ቀርተዋል። በስብሰባ ላይ የተገኙት አንድ ተወካይ ብቻ ነበሩ። እርሳቸውም ወ/ሮ ያየሽ ተስፋሁነይ ናቸው። ወ/ሮ ያየሽ በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ህወሓትን (ኢህአዴግ) ወክለው ነበር ከአምስት ዓመት በፊት በተካሄደው ምርጫ ላይ በመሳተፍ የምክር ቤት አባል የሆኑት። ቢቢሲ ከእርሳቸው ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል። የምክር ቤቱን ስብሰባ እንዳትሳተፉ ከህወሓት የመጣውን ትዕዛዝ እንዴት ነበር የሰሙት? ወ/ሮ ያየሽ፡ ለእኔ በደብዳቤም ሆነ በስልክ የደረሰኝ ነገር የለም። ከመገናኛ ብዙሃን ነው የሰማሁት። በጉዳዩ ላይ የተደረገ ውይይት ነበር? ወ/ሮ ያየሽ፡ እኔ አልተወያየሁም። ሌሎችን ወክዬ መናገር አልችልም። ስለሌሎቹ ግን አላውቅም። ከእርስዎ በስተቀር በምክር ቤቱ ያሉ ሁሉም የህወሓት ተወካዮች በስብሰባው ላይ አልተገኙም። እርስዎ ለመገኘት እንዴት ወሰኑ? ወ/ሮ ያየሽ፡ እንደሚታወቀው የተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን በአምስት ዓመት ነው የሚያበቃው፤ ይሁን እንጂ በአገራችን በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ከተፈጠረው ስጋት፣ ፍርሃትና ችግር አንፃር ምርጫ ቦርድ ምርጫ ለማካሄድ የተቸገረ መሆኑን ገልጾ፤ በሕገ መንግሥቱ አግባብ መሰረት ወደ ተወካዮች ምክር ቤት መጥቶ፤ ከዚያም የፌደሬሽን ምክር ቤት ባደረገው ውሳኔ መሰረት ምርጫው እንዲራዘም ሆኗል። ይህ አካሄድ ሕገ-መንግሥታዊ ስለሆነ፣ መርህን የተከተለ እና ለሕዝብ የሚጠቅም በመሆኑ፤ እኔ የመረጥኩት ይህንን ሕጋዊ አግባብን ተከትሎ የተሰጠ ውሳኔ ስለሆነ ነው በስብሰባው ላይ ልገኝ የቻልኩት። እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከቤተሰብም ሆነ ከሌላ አካል የደረሰበዎት ጫና አለ? ወ/ሮ ያየሽ፡ በማንም የደረሰብኝ ጫና ወይም ተፅዕኖ የለም። መታወቅ ያለበት ነገር እኔ ራሴን የቻልኩኝ አዋቂ ሰው ነኝ። ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው በራሱ መወሰን እንዳለበት በአፅንኦት የማምን ሰው ነኝ። እንደዚህ ዓይነት ሃሳቦች መምጣታቸው ባይገርምም፤ ሰው በራሱ አመለካከት እና እይታ የሚወስን ፍጡሩ መሆኑ መታወቅ አለበት። አንድ ሚዲያም ይህንኑ ሲጠይቀኝ በምሳሌ ነበር ያስረዳሁት። ምን ብለው? ወ/ሮ ያየሽ፡ የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን አንድ ጊዜ 'ልጅዎ እንደዚህ ያደርጋል፣ እንደዚህ ያጠፋል፣ ምናምን እያሉ ጋዜጠኞች ጠየቋቸው። ጥያቄያቸው የልጃቸውን ጥፋት ከእርሳቸው ጋር ለማገናኘት ነበር። እናም እርሳቸው 'He is an adult! He is a man' ብለው ነበር የመለሱት። እኔም እንደዚያ ነው የማስበው። እኔ ራሴን የቻልኩ ሴት፣ ራሴን የቻልኩ ብቁ ሰው ነኝ ብዬ ነው የማስበውና በራሴ እምነት የመሰለኝን ለማድረግ ብቁ ሰው ነኝ ብዬ ነው የማምነው። ከቤተሰብ ጋር ተመሳሳይ ወይም የተለያየ ሃሳብ ሊኖረኝ ይችላል። እምነቴ ግን የራሴ ነው። የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አባል ነዎት? ወ/ሮ ያየሽ፡ አይደለሁም። ታዲያ ምርጫ እስከሚካሄድ ማንን ወክለው ነው በምክር ቤቱ የሚቀጥሉት? ህወሓትን? ወይስ . . . ? ወ/ሮ ያየሽ፡ ምክር ቤት ውስጥ ስንወከል የሕዝብ ውክልና ይዘን እንጂ ለፓርቲ ውክልና በሚል አግባብ አይደለም። ስለዚህ እኔ የሕዝብ ውክልና ይዤ ነው የምቀጥለው። በምክር ቤቱ ህወሓት ይህን ያህል መቀመጫ አለው ብሎ የሚወስድ ካለም መውሰድ ይችላል። በዚህ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ የመወዳደር ሃሳብ አለዎት? ወ/ሮ ያየሽ፡ አልወሰንኩም። ቢወዳደሩ ግን ማንን ወክለው የሚወዳደሩ ይመስልዎታል? ወ/ሮ ያየሽ፡ እሱንም አልወሰንኩም። ከዚህ ቀደም የክልል ምክር ቤት ወይም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው ያውቃሉ? ወ/ሮ ያየሽ፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው። የክልል ምክር ቤት አባል ሆኜም አላውቅም። አንድ ወቅት ግን በ1992 ዓ.ም የመቀሌ ከተማ ምክር ቤት አባል ሆኜ አውቃለሁ። በፌደራልና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል ፖለቲካዊ መካረሮች እንዳሉ ይታወቃል። እርስዎ ይህንን ጉዳይ እንዴት ነው የሚያዩት? ወ/ሮ ያየሽ፡ ለሕዝብ ችግር መፍትሔ ለመስጠት፣ ሕዝብ የተቸገረበትን ጉዳይ ፍትሃዊ የሆነ ውሳኔ ለመስጠት፤ ሁላችንም መቆም አለብን ብዬ ነው የማስበው። ግለሰቦች ወይም ፓርቲዎች በተለያዩ ሃሳቦች ሊጠላለፉ ይችላሉ፤ ነገር ግን አሁን በሰለጠነ ጊዜ ላይ ነው ያለነው። በመሆኑም የሕዝብ ጥቅምን መሰረት በማድረግ በጋራ ቁጭ ብሎ በመነጋገርና ውሳኔ በመስጠት በጋራ ችግሮችን መቅረፍ አለብን የሚል አስተያየት ነው ያለኝ። በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የተገኙ ብቸኛ የህወሓትን አባል ኖት። ይህን መወሰንዎ ምን ውጤት ይኖረዋል ብለው ያስባሉ? ወ/ሮ ያየሽ፡ እኔ ህወሓትን ወክዬ የተወዳደርኩት በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ነው። አዲስ አበባ ላይ አምስት የህወሓት ተወካዮች ነን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገባነው። እኔ ፓርላማ ስገባ ድምፁን የሰጠኝን ሕዝብ አክብሬ፤ የሕዝብ ጥያቄ ማስተናገድና ግዴታና ኃላፊነት የጣለብኝን ሕዝብ ማገልገል አለብኝ ብዬ ነው። መታየት ያለበትም ከዚህ አንፃር ነው። ፓርላማ ስንገባ የህወሓትን ወይም የኢሕአዴግ ሃሳብን ብቻ ለማራመድ አይደለም፤ የሕዝብ ጥያቄንም ለመመለስ ነው የገባሁት። ይህንን ውሳኔዎን ተከትሎ ያጋጠመዎ ነገር አለ? ወ/ሮ ያየሽ፡ በቀጥታ የመጣ ጥያቄም ሆነ የደረሰብኝ ነገር የለም። አሁን ወጣቱም ሆነ ሕዝቡም በሰፊው የሚጠቀመው ማኅበራዊ ሚዲያ አለ። በዚያ ላይ ለሕዝብ በመወገኔ ምክንያት ድጋፉን የሚገልጽልኝ ብዙ ነው። ይሁን እንጂ የህወሓትን ሃሳብ የሚያራምዱ ጽንፈኛ የሆነ አመለካከል ያላቸው ሰዎች፣ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚጽፉ ሰዎች፤ ተገቢ ያልሆነና የሰው ሃሳብ የማያከብር ስድብና ማስፈራሪያዎችን እያየሁ ነው ያለሁት። ሁላችንም የተለያየ ሃሳብና አመለካከት ነው ያለን። ሃሳብና ተቃውሟቸውን ማቅረባቸውን አከብራለሁ፤ አደንቃለሁ። መሆንም አለበት። በዚያም ቅር አይለኝም፤ ነገር ግን በግል መሳደብ፣ አላስፈላጊ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ለማንም ስለማያስተምር ባይሆን ብዬ አስባለሁ። ከዚህ ውጪ በቀጥታ የመጣ ጥያቄ የለም። ውሳኔዎን ተከትሎ ከህወሓት በኩል የደረሰዎ ነገር አለ? ወ/ሮ ያየሽ፡ በቀጥታ የመጣ ነገር የለም፤ ነገር ግን ጽንፍ ይዘው በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል የሚፅፉ በርካታ ሰዎች አሉ። በተዘዋዋሪ ግን የእነርሱ ወገን የሆኑ፣ የእነሱን ሃሳብ የሚያራምዱ ሰዎች የሚፅፉትን እያየሁ ነው። ይህም ከዚያ በኩል የመጣ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ። እዚህ ውሳኔ ላይ በመድረስዎ ምክንያት ችግር ሊገጥመኝ ይችላል ብለው ይሰጋሉ? ወ/ሮ ያየሽ፡ ለሕዝብ ለምን ወገንሽ ብሎ ስጋት ላይ ሊጥለኝ የሚችል አካል መኖር አለበት ብዬ አላስብም፤ ነገር ግን የሚመጣውን ነገር ሁሉ ከሕዝብ ጋር ሆነን ችግሮችን በጋራ እንፈታለን ብዬ ነው የማስበው።