id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-50829353
https://www.bbc.com/amharic/news-50829353
ሞዛምቢክ '1.5 ቶን ሄሮይን ሲያጓጉዙ' የነበሩ 12 ኢራናውያንን በቁጥጥር ሥር አዋለች
ሞዛምቢክ ሕንድ ውቅያኖስ ላይ ግምቱ ከ1.5 ቶን በላይ ሄሮይን ሲያጓጉዙ የነበሩ 12 የኢራን ዜጎችን በቁጥጥር ሥር አዋለች።
ሄሮይን የተሰኘውን አደገኛ አደንዛዥ ዕጽ ሲያጓጉዙ ነበሩ የተባሉት 12ቱ ኢራናውያን የተያዙት ከሞዛምቢክ ሰሜናዊ አቅጣጫ ሕንድ ውቅያኖስ ላይ ነበር። አደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎቹ ሲጓዙባት የነበረችው መካከለኛ ጀልባ በሞዛምቢክ ባህር ኃይል እና የሃገሪቱ ወንጀል ምርመራ ቡድን ስትከበብ ተጠርጣሪዎቹ ጀልባዋን በእሳት አጋይተው ወደ ውቅያኖሱ ዘለዋል። ወደ ሕንድ ውቅያኖስ ከዘዘሉት መካከል 3ቱ ህይወታቸው ሲያልፍ 12ቱ ደግሞ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። የሞዛምቢክ ፖሊስ እንደሚለው ከሆነ ተጠርጣሪ እጽ አዘዋዋሪዎቹ በጀልባዋ ላይ ተጭኖ የነበረ ወደ 1.5 ቶን የሚገመት ሄሮይን በእሳት አጋይተዋል። 12ቱ ኢራናውያን ፔምባ ወደምትሰኝ ከተማ ተወስደው በፖሊስ ምረመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል። የሞዛምቢክ መንግሥት ይህ ኦፕሬሽን ያካሄደው ከተለያዩ ምንጮች የደረሱት መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ እንደሆነ አሳውቋል።
news-56262378
https://www.bbc.com/amharic/news-56262378
ቢቲኤስ የሙዚቃ ቡድን በአልበም ሽያጭ ቴይለር ስዊፍትን እና ድሬክን በለጠ
የኮሪያው የወንዶች የሙዚቃ ቡድን ቢቲኤስ እአአ በ2020 በአልበም ሽያጭ ቴይለር ስዊፍትን መብለጡ ተነገረ።
የቢቲኤስ ቡድን አባላት እነዚህ የኮሪያ ፖፕ ሙዚቃ ኢንደስትሪ የከባድ ሚዛን ሻምፒዮና አሸናፊዎች፣ ተብለው የሚወደሱት የቡድኑ አባላት በአውሮፓና በአሜሪካ በአገራቸው ቋንቋ አቀንቅነው የበርካቶችን ልብ ማሸነፍ የቻሉ ናቸው። ቴይለር ስዊፍት በእአአ 2019 በምርጥ አልበም ሽያጭ ቀዳሚ የነበረች ሲሆን፣ በ2020 ቢቲኤስ የደረጃ ሰንጠረዡን በቀዳሚነት እንደመራ ተገልጿል። ቢቲኤስ በእንግሊዘኛ ያቀነቀኑት እና ዳይናማይት ሲሉ የጠሩት ነጠላ ዜማቸው አሜሪካውያን የሙዚቃ አድናቂዎችን ለሸመታ በገፍ ያስወጣ እነርሱንም ከእነ ሌዲ ጋጋ በአቻነት ለሽልማት ያሳጨ ነበር። እኤአ በ2019 በአልበም ሽያጭ ቀዳሚ የነበረችው ቴይለር ስዊፍት በ2020 የሁለተኛነት ደረጃ ላይ ወርዳለች። የዓለም አቀፉን የሙዚቃ ኢንደስትሪ ሽያጭ የሚመዘግበው ኤኤፍፒአይ፣ የኮሪያው የፖፕ ቡድን ቢቲኤስ በ2020 ምርጥ ሽያጭ ያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልጿል። ቢቲኤስ በ2020 ሁለት ምርጥ የሙዚቃ አልበሞችን ለአድናቂዎቻቸው አድርሷል። ማፕ ኦፍ ዘ ሶል፡7 እና ቢ የተሰኙት እነዚህ አልበሞች በአድናቂዎቻቸው ዘንድ ተወድውላቸዋል። 2020 በዓለማችን በሚገኙ 20 አገራት በአንደኝነት የተደመጠ ነጠላ ዜማ ያበረከቱበት ዓመትም ሆኖ ተመዝግቧል። ማፕ ኦፍ ዘ ሶል፡7 የተሰኘው አልበማቸውም ታትሞ ከመሰራጨቱ በፊት በብዛት በመታዘዝ ቀዳሚነቱን የያዘ አልበም ነው። ከሙዚቃ ስራዎቻቸው ጋር በተያያዘ ሰባቱም የቡድኑ አባላት ቢሊየነር ሆነው ተመዝግበዋል። የቢቲኤስ አባላት ዓለም አቀፍ የአልበም ሽያጩን በበላይነት ሲቆናጠጡ የመጀመሪያው ምዕራባውያን ያልሆኑ የሙዚቃ ቡድኖች ናቸው። ይህ ብቻ ሳይሆን ሙዚቃቸውም ሙሉ በሙሉ በእንግሊዘኛ ያልተዘፈነ መሆኑም ከሌሎች የደረጃ ሰንጠረዡን ከተቆጣጠሩ ድምጻውያኖች ለየት ያደርጋቸዋል። የዓለም አቀፍ ሽያጩ የሚሰላው በመላው ዓለም ያለው የሙዚቃው ሰንዱቅ ሽያጭ፣ ከኢንተርኔት ላይ ገዝተው የሚያወርዱና የሚያዳምጡ አድናቂዎች ቁጥር እንዲሁም በኦንላየን በቀጥታ እያጫውቱ የሚያዳምጡ አፍቃሪዎች ብዛት ተሰልቶ ሲሆን፣ እንዲሁም የእነርሱን ዘፈኖች ለመጫወት ፈቃድ ጠይቀው ክፍያ የሚፈጽሙ ሙዚቀኞችም ቀመሩ ውስጥ ይካተታሉ። በ2020 የምርጥ አልበሞች ሽያጭ ድሬክ ሶስተኛ፣ ዘዊኬንድ አራተኛ፣ ቢሊ ኤሊሽ ደግሞ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ቢቲኤስ በሌላ ስማቸው ባንግተን ቦይስ በመባል የሚጠሩ ሲሆን የተመሰረቱት እአአ በ2013 ላይ ነው። ሰባት አባላት ያሉት ይህ ቡድን ከመላው ደቡብ ኮሪያ የተወጣጡ ወጣት ወንዶችን አቅፎ ይዟል። ለኮሪያ የፖፕ የሙዚቃ ስልት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አልበሞችን እና የኮንሰርት ቲኬቶችን በመሸጥ፣ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎች በኦንላየን ቀጥታ ስራዎቻቸውን በማድመጥ የኮሪያን ፖፕ ኢንደስትሪ ሚዛን አክብደውታል፤ የደረጃ ልኬቱንም አርቀው ሰቅለውታል ተብሏል። ቡድኑን ከሃሳብ ጀምሮ ፀንሶ ያዋለደው ቀድሞ በኬፖፕ መዝናኛ ውስጥ የተለያዩ ቡድኖችን በማደራጀት እና በመምራት ልምድ የነበረው ፀኃፊ እና ፕሮዲውሰር ባንግ ሺ ሂውክ ነው። ባለፈው ዓመት ብቻ በኮርያ የአክስዮን ገበያ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ በማፍሰስ የቢቲኤስ አባላት 108 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት እንዲችሉ አድርጓል። ባለፈው ዓመት በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን በተለያዩ መድረኮችና ስታዲየሞች ማቅረብ እንዳይችሉ ያደረጋቸው ቢቲኤሶች ሁለተኛ አልበማቸውን ቀርፀው ለአድማጮቻቸው አቅርበዋል። ይህ አልበም ዳይናማይት የተሰኘ የሙዚቃ ስራቸው የተካተተበት ሲሆን፣ የመጀመሪያው በእንግሊዘኛ የተዘፈነና የተለቀቀ ነጠላ ዜማቸው ነበር። በአሜሪካ ይህ ስራ እንደተለቀቀ የደረጃ ሰንጠረዦችን መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን በኦንላየን በቀጥታ በብዛት በመደመጥም ቀዳሚ ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ ዳይናማይት የተሰኘው ስራቸው ቢቲኤሶችን ከነ ሌዲ ጋጋ እና ቴይለር ስዊፍት ተርታ ለግራሚ አሳጭቷቸው ነበር።
news-46479747
https://www.bbc.com/amharic/news-46479747
ዓይነ ስውሯ ሰዎችን ለመርዳት ስትል በርካታ ፈጠራዎችን አበርክታለች
በ14 ዓመቷ የዋና ገንዳ ውስጥ ባጋጠማት አደጋ ነበር ቺዬኮ አሳካዋ ዓይኖቿ የታወሩት። ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ደግሞ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንና 'አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ' በመፍጠር ማየት የተሳናቸውን ሰዎች ሕይወት ለማሻሻል እየጣረች ነው።
ቺዬኮ አሳካዋ በተደራሽነት ዙሪያ ለሠራችው ጥናትና ላደረገችው አስተዋጽዖ የጃፓን የክብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች የጃፓናዊቷ ዶ/ር ቺዬኮ "ስጀመር ምንም ዓይነት አጋዥ ቴክኖሎጂዎች አልነበሩም" ትላለች። "ብቻዬን ምንም ዓይነት መረጃ ማንበብ አልችልም ነበር። በተጨማሪም ብቻዬን መንቀሳቀስ አልችልም ነበር" • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት እነዚህ ተግዳሮቶች ነበሩ አሁን እየሰራች ወዳለው ነገር የመሯት። ለዓይነ ስውራን የተዘጋጀ የኮምፕዩተር ሳይንስ ትምህርቶችን ተከታትላ እንዳበቃች ወዲያው አይቢኤም በተሰኘው ድርጅት ውስጥ ሥራ አግኘች። ዶክትሬቷን እያጠናች ሥራዋን የጀመረችውም የመሥሪያ ቤቷን ለአካል ጉዳተኞች ምቹነት በማጥናት ነበር። የመጀመሪያዎቹ የብሬል ዲጂታል ፈጠራዎችና ከኢንተርኔት የድምጽ ፍለጋ በስተጀርባ ዶ/ር ቺዬኮ ትገኝበታለች። እነዚህ የፍለጋ ዘዴዎች በአሁኑ ዘመን በጣም የተስፋፉ ቢሆኑም እንኳን የዛሬ 20 ዓመታት በፊት ግን ለዓይነ ስውር ጃፓናውያን ከዚያ ቀደም የማያገኟቸውን መረጃዎች እንዲያገኙ ዕድል ፈጥራላቸዋለች። አሁን ከሌሎች ቴክኖሎጂስቶች ጋር በመሆን የተሌኣዩ 'አርቲፊሻል ኢንቴሌገንሶችን' በመጠቀም የተለያዩ መሣሪያዎችን ሊሠሩ ነው። ብሬል እና በድምጽ የሚታዘዙ ቱክኖሎጂዎች ለዓይነ ስውራን ዋና መሣሪያዎች ናቸው 'ማይክሮ ማፒንግ' ለምሳሌ ዶ/ር ቺዬኮ 'ናቭኮግ' የተሰኘውን በአስቸጋሪ ቦታዎች ላይ ለመንቀሳቀስ የሚያግዝ በድምጽ የሚታገዝ የዘመናዊ ስልክ መተግበሪያ ለዓይነ ስውራን ፈጥራለች። ይህም መለስተኛ ኃይል ያላቸው የብሉቱዝ የምልክት ምንጮች የቤት ውስጥ ካርታ ለመዘርጋት በየ10 ሜ.ር ርቀት ላይ ይቀመጣሉ። የቦታውንም ዱካ ማውጣት ናሙና መረጃዎች ይሰበሰባሉ። "ያለንበትን ቦታ ለማወቅ የናሙናውን ዱካ ካለንበት ጋር በማነፃፀር ለማወቅ ይረዳናል" ትላለች። የመንቀሳቀሻ መተግበሪያዎች ዓይነ ስውራን በትር መጠቀም ያቆማሉ ማለት ነው? ብዙ መረጃዎችን መሰብሰባችን በጉግል ማፕስ ላይ ካሉ ካርታዎች በበለጠ መረጃ ሊሰጥ ቢችልም ይህ በቤት ውስት ግን ብዙም ጠቃሚ አይደለም ምክንያቱም ለዓይነ ስውራን የሚያስፈልገውን መረጃ አይሰጥም። አምስት የኖቤል ተሸላሚዎችን ባበቃው አይቢኤም ውስጥ ተጋባዥ አጥኚ የሆነችው ዶ/ር ቺዬኮ "ጠቃሚ ቢሆንም በተገቢ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አይረዳንም" ትላለች። • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት 'ናቨኮግ' ገና ጅማሬው ላይ ቢሆንም በአሜሪካ የተለያዩ ቦታዎች ላይና በቶክዮ ደግሞ በአንድ ቦታ ላይ አለ። መተግበሪያው ለሕዝብ ግልጋሎት ሊቀርብ ትንሽ እንደቀረው አይቢኤም ገልጿል። "ቁጥጥር ሰጥቶኛል" የፒትስበርግ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የ70 ዓመቷ ክሪስቲን ሃሲንገርና የ65 ዓመት ባለቤታቸው ዳግላስ ሃሲንገር ለዓይነ ስውራን ተብሎ በተዘጋጀ ኮንፍረንስ ላይ ተገኝተው 'ናቭኮግ'ን ሞክረውታል። ለመንግሥት ለ40 ዓመታት አገልግለው ጡረታ የወጡት ክሪስቲን "ሁኔታዬ በእራሴ ቁጥጥር ውስጥ እንደነበር ነው የተሰማኝ" ይላሉ። ሌሎች መተግበሪያዎችን ለመንቀሳቀስ እንደሚጠቀሙና 'ናቭኮግ'ን ሲጠቀሙ በትር ይዘው ቢሆንም በማያውቁት ቦታ ላይ ለመንቀሳቀስ ይበለጥ ነፃነት እንደሰጣቸው ይናገራሉ። • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ ባለቤታቸው ዳግለስም በቤት ውስጥ ስንንቀሳቀስ "የምንገምተውን" ነው መተግበሪያው የቀነሰለን ይላሉ። "በእራሴ መንቀሳቀስ መቻሌ እፎይታ እንዲሰማን አድርጓል።" ዶ/ር ቺዬኮ ቀለማት ትውስታዋ ናቭኮግን ለመሥራትና ሌሎች ሥራዎቿም ላእ እንደጠቀማት ትናገራለች ቀለል ያለ ሻንጣ ሮቦት የዶ/ር ቺዬኮ ቀጣዩ ሥራ የ'አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ' ሻንጣ ነው ይህም ለእንቅስቃሴ የሚረዳ ሮቦት ነው። ዓይነ ስውር የሆነን ሰው እንደ ኤርፖርት ዓይነት ለእንቅስቃሴ የሚከብድ ቦታ ላይ አቅጣጫ፣ የበረራና የበር ለውጥ መረጃዎችን በመስጠት ይመራል። ሻንጣው በውስጡ ሞተር ያለው ሲሆን በእራሱ መንቀሳቀስና ዕቃዎችን ለመለየት የሚያስችለው ካሜራና 'ሊዳር' በተሰኘ ቴክኖሎጂ ብርሃንና ርቀትን እንዲለካ ታስቦ የተሠራ ነው። ደረጃ ሲኖር ሻንጣው በተጠቃሚው እንዲነሳ ያሳውቃል። "አብረን ብንሠራ ሮቦቱ አነስ፣ ቀለልና ርካሽ መሆን ይችላል" ትላለች ዶ/ር ቺዬኮ። ለሙከራ የተሠራው ሮቦት "በጣም ከባድ" ነው ትላለች። አይቢኤም ቀጣዩን ሮቦት ቀላል የማድረግና ቢያንስ የእጅ ኮምፕዩተር እንዲችል ተደርጎ ተሠርቶ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማድረስ ዕቅድ እንዳለው ተናገሯል። "ብቻዬን መጓዝ በጣም ነው የምፈልገው። ለዚያም ነው ምንም ያህል ጊዜ ቢፈጅም በአርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ የሮቦት ሻንጣ ላይ ማተኮር የምፈልገው" ትላለች። በአይቢኤም ለሙከራ የተሠራውን ሻንጣ አሳይተውኛል ግን ለሕዝብ ለማቅረብ ዝግጁ ባለመሆኑ ምስሉን እንኳን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደሉም። የማይክሮሶፍት ሠራተኛው ሳቂብ ሸይክ በድምጽ ትእዛዝ የሚቀበለውን ዘመናዊ ስልክ አሠራር ሲያሳይ አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስን ለማህበረሰቡ ጥቅም ምንም ፍላጎት ቢኖረው አይቢኤም ከማይክሮሶፍትና ከጉግል አንፃር በጣም ወደኋላ ቀርቷል። ማይክሮሶፍት 115 ሚሊዮን ፓውንድ 'አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ ፎር ጉድ' ለተሰኘው ፕሮግራም የመደበ ሲሆን 25 ሚሊዮን ፓውንድ ደግሞ ለ'አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ' ለተደራሽነት መድቧል። ለምሳሌ 'ሲዪንግ አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ' የተሰኘው በድምጽ ትዕዛዝ የሚቀበል ካሜራ ሲሆን በዋናነት የሚያተኩሩበት ሥራ ነው። በዚህ ዓመት መጨረሻ ደግሞ ጉግል ዓይነ ስውራንን ለመምራት ታስቦ የተሠራውን ሉካውት የተሰኘውን መተግበሪያ ለሕዝብ ያቀርባል። ለሲሲኤስ ኢንሳይት የአርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ ዋና ኃላፊ የሆነው ኒክ ማክዋየር "አካል ጉዳተኞች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ተረስተዋል" ይላል። በዚህ ዓመት ውስጥ ግን ብዙ ድርጅቶች ለአርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ ገንዘብ እየመደቡ በመሆኑ ነገሮች እየተቀየር እንደሆነ ይናገራል። ከሌሎች የተለያዩ ድርጅቶችም ብዙ የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚመጣ አልጠራጠርም ብሏል።
48362087
https://www.bbc.com/amharic/48362087
"የከተማ መስፋፋት የኢትዮጵያን ብዝሀ ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል" ዶ/ር መለሰ ማርዮ
ዛሬ የዓለም የብዝሀ ሕይወት ቀን 'Our Biodiversity, Our food, Our Health' በሚል መሪ ቃል ታስቦ ይውላል። ኢትዮጵያም ቀኑን 'ብዝሀ ሕይወት ሀብታችን፣ ምግባችን ጤናችን' በሚል ታከብራለች።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ "የሰው ልጆች ሕይወት መሰረት የሆነውን ብዝሀ ሕይወት እንጠብቅ" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? ብዝሀ ሕይወት የሰው ልጆች ምግብ፣ ጤና ባጠቃላይም የህልውና መሰረት እንደመሆኑ፤ ከፍተኛ ጥበቃ ሊደረግለት እንደሚገባ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በተለይም የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ የመላው ዓለም ስጋት መሆናቸውን ተከትሎ የብዝሀ ሕይወት ጥበቃ የዓለም መሪዎች መወያያ አጀንዳም ሆኗል። በኢትዮጵያ የብዝሀ ሕይወት ሀብት ላይ የተጋረጡ ፈተናዎች የትኞቹ ናቸው? ስንል የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ማርዮን ጠይቀናል። 1. የከተማ መስፋፋት ዶ/ር መለሰ እንደሚሉት፤ በዋነኛነት በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ያለው የከተማ መስፋፋት ነው። የከተማ መስፋፋት ብዝሀ ሕይወት የሚገኝባቸው አካባቢዎችን ከማጥፋቱ ባሻገር፤ የሕዝብ ቁጥር መጨመሩ ለእጽዋት መመናመን ምክንያት ሆኗል። "ሰዎች የሚመገቧቸው እጽዋት የሚገኙባቸው አካባቢዎች እየጠፉ መጥተዋል" የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከሁለት ዓመት በፊት የተሠራ ጥናት፤ በየዓመቱ 92ሺህ ሄክታር ደን እንደሚወድም ማሳየቱን ያጣቅሳሉ። • ጣና ሐይቅ የተጋረጡበት ፈተናዎች የሕዝብ ቁጥር መጨመር በተለያዩ ፓርኮች ለሚከሰቱ ሰደድ እሳቶች ምክንያትም ነው። በተያያዥም የከተማ መስፋፋት የእጽዋትና እንስሳትን ህልውና አደጋ ውስጥ ከትቷል ይላሉ። 2. መጤ ዝርያዎች 'ወራሪ' የሚባሉ ዝርያዎች የኢትዮጵያ የብዝሀ ሕይወት ሀብት እንዲመናመን ምክንያት ሆነዋል። "በምስራቅ ደቡብ ኢትዯጵያና በስምጥ ሸለቆ አካባቢ ወደ 1. 8 ሚሊየን ሄክታር ቦታ ይዘዋል። የውሀ አካላትን እያጠፋ ያለው የእምቦጭ አረምን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል" ይላሉ ዶ/ር መለሰ። መጤ ዝርያዎች፤ እጽዋትና አዝርእት የሚመረቱበት የእርሻ መሬትን ስለተቆጣጠሩ የቀድሞ ሀገር በቀል ምርቶች እየጠፉ ነው። "ነባር ዝርያዎችን እያጣን ነው። ለምሳሌ እኔ ያደግኩበት ደጋ አካባቢ የነበረው እንጀራ ጣዕምና ሽታም እየተቀየረ ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኙ የነበሩ መድሀኒትነት ያላቸው ምግቦችም አደጋ አንዣቦባቸዋል። እንደምሳሌ የሚጠቅሱት ላይዚን የሚባል አሚኖአሲድ የያዘ የገብስ ዝርያን ነው። እሳቸው እንደሚሉት ከ70 እስከ 90 የሚሆኑ ነባር ዝርያዎች ጠፍተዋል። • ''የተፈጥሮ ሃብታችንን ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ አንጠብቅም'' 3. የአየር ንብርት ለውጥ የመላው ዓለም ራስ ምታት የሆነው የአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያም ችግር ነው። ዛሬ ዛሬ ቆላ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ወደበረሀነት እየተቀየሩ ስለመጡ ቀድሞ የሚበቀሉ እጽዋት እየጠፉ መምጣታቸውን ዶ/ር መለሰ ይናገራሉ። የአየር ንብርት ለውጥ በቤትና በዱር እንስሳት ላይም ተጽእኖ ያሳድራል። 4. ብክለት ብክለት ስንል የብስና የውሀ አካላት ብክለትን ያጠቃልላል። ጸረ ተባይና ጸረ አረም ኬሚካሎች በሰውና በእንስሳት ላይ ተጽእኖ እያሳደሩ ነው። ዶ/ር መለሰ እንደሚናገሩት፤ ንቦችና ዘር የሚያሸጋግሩ ቢራቢሮዎች (ፖሊኔተር) እየጠፉ ነው። ይህም ድርቅ የሚቋቋሙና ቶሎ የሚበቅሉ ዘሮች በስፋት እንዳይሰራጩ ያደርጋል። የውሀ አካላት በፋብሪካ ፍሳሽና ቆሻሻ መበከላቸው ሌለው ችግር ነው። ምን ይደረግ? ዶ/ር መለሰ እንደሚሉት፤ የኢትዮጵያን ብዝሀ ሕይወት ለመታደግ በፖሊሲ የትኩረት አቅጣጫ ማስቀመጥ ያስፈልጋል። የእጽዋት፣ የእንስሳት፣ የውሀ ሀብትና ሌሎችም የተፈጥሮ ሀብቶችን የሚያስተዳድሩ ተቋሞች ውሳኔ ከማስተላለፋቸው በፊት መናበብ ይገባቸዋል። • ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ለምንስ ግድ ይሰጠናል? "የኢትዮጵያን ብዝሀ ሕይወት የሚጠብቀው ኢንስቲትዩቱ ብቻ ሳይሆን ማኅበረሰቡም ጭምር ነው። የአየር ንብረት ተጽእኖን መቋቋም የምንችለው ብዝሀ ሕይወትን በመጠበቅ ነው" ይላሉ ዋና ዳይሬክተሩ። በሽታ መከላከል፣ ከፍተኛ ምርት መስጠትና ድርቅ መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዮት ጂን ባንክ በመውሰድ መጠቀም እንደሚቻል ያስረዳሉ። ከዘመናዊነት ጋር ተያይዘው የመጡ የምግብ አይነቶች እንደካንሰር፣ ስኳርና ደም ግፊት ላሉ ተላለፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምክንያት በመሆናቸው ተፈጥሯዊ ምግብ ማዘውተርንም ይመክራሉ። የሕዝበ ቁጥር መጨመር ያመጣውን የምግብ እጥረት ችግር ለመፍታት 'አግሮፎረስተሪ' የተባለውን መንገድ መጠቀምን እንደ አማራጭ ያስቀምጣሉ። ይህ ደንና የፍራፍሬ ዛፍ በጥምረት የሚመረትበት ዘዴ ነው።
news-53588737
https://www.bbc.com/amharic/news-53588737
ጭምብል የማይለብሱ የአሜሪካ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት አባላት ይባረራሉ ተባለ
በአሜሪካ የሕግ መምሪያው ምክር ቤት እንደራሴዎች ጭምብል እንዲለብሱ ታዘዙ፡፡
እንደራሴዎቹ ብቻም ሳይሆን ሁሉም የምክር ቤቱ ሠራተኞችም ይህንኑ ደንብ ካልተከተሉ ሊባረሩ እንደሚችሉ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ናንሲ ፒሎሲ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ በአሜሪካ ጭምብል የመልበሱ ነገር ብዙ ሲያጨቃጭቅ ነው የሰነበተው፡፡ ግማሾች አለመልበስ መብታችን ነው ይላሉ፡፡ ትራምፕም ቢሆን ጭምብል ማጥለቅ ይቀፋቸዋል፡፡ እምብዛምም ይህን ሲያበረታቱ አይታዩም፡፡ አሁን በዚያ አገር በኮቪድ-19 ምክንያት የሟቾች ቁጥር 150ሺህ ማለፉን ተከትሎ ጠበቅ ያሉ መመሪያዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡ መመሪያዎቹ ከሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባላት የጀመሩ ይመስላል፡፡ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፒሎሲ ጭምብል የማይለብሱ እንደራሴዎችን ጭምር ከምክር ቤት ለማስወጣት የዛቱት የተከበሩ የምክር ቤቱ አባል ሪፐብሊካኑ ሉዊ ጎህመርት ትናንትና በኮሮና መያዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሉዊ ጎህመርት የቴክሳስ ተወካይ ሲሆኑ በካፒቶሎ ሂል (የሁለቱ ምክር ቤቶች መቀመጫ ግቢ) ያለ ጭምብል ሽር ጉድ ሲሉ ነበር ተብሏል፡፡ እንዲያውም ከትናንት በስቲያ የፌዴራል አቃቢ ሕግ ዊሊያም ባር በምክር ቤት ለብርቱ ጥያቄ በቀረቡበት ወቅት እርሳቸው ያለ ጭምብል ነበር ቁጭ ያሉት፡፡ የተከበሩ ሉዊ ጎህመርት ጭምብል አላጠልቅም፣ መብቴ ነው ሲሉ ያስቸግሩም ነበር፡፡ ትናንት ማምሻውን ‹‹ወገኖቼ፣ በዉሃን ቫይረስ ሳልያዝ አልቀረሁም› ሲሉ በቪዲዮ በቫይረሱ መለከፋቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከርሳቸው ጋር ወዲያ ወዲህ ሲሉ የነበሩ ሰዎች በሙሉ ወሸባ ይገባሉ ተብሏል፡፡ የፌዴራል አቃቢ ሕግ ዊሊያም ባር ከተከበሩ ሉዊ ጎህመርት ጋር በቅርብ ተነካክተው ይሆናል በሚል አስቸኳይ ምርመራ እንዲያደርጉ ተብሏል፡፡ የተከበሩ ሊዊ ጉህመርት ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ወደ ቴክሳስ ለመጓዝ ቀጠሮ ነበራቸው፡፡ ምርመራ ማድረጋቸው በጀ እንጂ ከትራምፕ ጋር በአንድ አውሮፕላን እንደ እቅዳቸው ተሳፍረው ቢሆን ኖሮ ትራምፕም ጭምብል ማጥለቅ ስለማይወዱ ፕሬዝዳንቱ በተህዋሲው ሊለከፉ ይችሉ ነበር ተብሏል፡፡ የካሊፎርኒያ ተወካይ አፈጉባኤ ወ/ሮ ናንሲ ፒሎሲ እንደተናገሩት እንደራሴዎች ተራቸው ደርሶ ንግግር ለማድረግ ሲፈልጉ ብቻ ጭምብላቸውን ዝቅ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ከዚያ ሌላ ያለ ጭምብል የታየ ሰው አባራለሁ ብለዋል፡፡ እስከዛሬ 10 የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት በኮቪድ ተህዋሲ ተይዘዋል፡፡ ከነዚህ መሀል ሦስቱ ዲሞክራቶች ሰባቱ ሪፐብሊካን ናቸው፡፡
news-47644473
https://www.bbc.com/amharic/news-47644473
ከክራይስትቸርች የመስጊድ ጥቃት በተአምር የተረፈው ኢትዮጵያዊ
በተለይ በኒውዚላንድ ዋነኛ ርዕስ ሆኖ እንዲህ አይነቱን አሰቃቂ ድርጊት ለመከላከል የሀገሪቱ መንግሥት በጦር መሳሪያ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ህግን እስከማውጣት የሚያደርስ ውሳኔ ላይ ደርሷል።
በዚህ ጥቃት የተገደሉትና ጉዳት የደረሰባቸው የተለያየ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሰዎች ሲሆኑ ሁለት ኢትዮጵያዊያንም ከባድ የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ለማረጋገጥ ችለናል። በእለቱ የአርብ የጸሎት ሥነ ሥርዓትን ለመካፈል ወደ መስጊዱ ሄደው ያሁሉ እልቂት በአንድ ታጣቂ ሲፈጸም በቅር የተመለከቱና ከጥቃቱ በተአምር የተረፉት ሌላው ኢትዮጵያዊ አቶ አብዱልቃድ አባቦራ በኒውዝላንድ የክራይስትቸርች ከተማ ነዋሪ ናቸው። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? ክስተቱንም ሲያስታውሱ " በዕለቱ የሳምንቱን አስተምሮ እየተከታተልን እያለን ከኋላችን በመግቢያው ኮሪደር በኩል ተኩስ ሰማን። ግን የሆነ ኤሌክትሪክ ኮንታክት ፈጥሮ ወይም ህጻናት በርችት የሚጫወቱ ነበር የመሰለን። ምክንያቱም ኒውዝላንድ ውስጥ በፍጹም እንደዚህ አይነት ነገር አንጠብቅም" ይላሉ። ከዚያም በድጋሚ የተኩስ ድምጽና እሳት ወደ ውስጥ ከኮሪደሩ ሲገባ እንደተመለከቱና ከፊለፊታቸውም ሰዎቹም ሲወድቁ ተመለከቱ። የተኩሱም ውርጅብኝ እሳቸው ወዳሉበት እቀረበ መጣ። በዚህ ጊዜ መስጊዱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በሙሉ መስኮቶቹንና በሮቹን ሰባብረው መውጣት ጀመሩ። ማምለጥ የሚችለው በሙሉ አመለጠ። ነገር ግን እሳቸው በነበሩበት ስፍራ በኩል በኩል ምንም አይነት በርም ሆነ መስኮት አልነበረም። ታጣቂው እየተኮሰ ወደ ክፍሉ ሲገባ የመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሰለነበሩ አቶ አብዱልቃድ ፊትለፊት ተመልክተውታል። የያዘው የጦር መሳሪያም አውቶማቲክ ጠመንጃ እንደነበረና ጥይት ሲያልቅበት ካርታውን እየቀየረ ''በግራም በቀኝም እየዞረ ማጨድ ነው በቃ፤ አጨደን አጨደን'' ይላሉ። ተኳሹ ማንንም ከማንም ሳይመርጥ ባገኘው ላይ እየተኮሰ ይጥላል። "በዙሪያው ያሉትን ሰዎቹን ረፍርፎ ከጨረሰ በኋላ ነብሱ ያልወጣውን፤ የሚተነፍሰውን ደግሞ እየዞረ አንድ በአንድ ገደላቸው። ወደ 15 ደቂቃ ሙሉ ነው ይተኩስ የነበረው።" • ከተገደሉት አንዱ የማዕድን ኩባንያው ባለቤት ነበር አቶ አብዱልቃድ ይህን ሁሉ ክስተት የሚመለከቱት በሞት ተከበው ባሉበት የመስጊዱ አንድ ጥግ ላይ ሆነው ነበር። "እኔ በአጋጣሚ ለመሮጥ ስላልቻልኩኝ ከፊቴ አንድ ቁርአን የሚቀመጥበት የመጽሃፍት መደርደሪያ ነበረ። እሱን ሳብኩትና እላዬ ላይ ጣልኩት። ከጭንቅላቴ እስከ ወገቤ ተሸፍኘኜ ስለነበረ ገዳዩ አላየኝም" ይላሉ። መስጊዱ ውስጥ የተኩስ ሩምታ ሲዘንብ መውጫ አጥተው ነፍሳቸውን ማትረፍ ካልቻሉት መካከል አቶ አብዱልቃድ እና የመስጊዱ ኢማም ብቻ ነበሩ ምንም ሳንነካ ከመአቱ የተረፉት። "ለአርብ ጸሎት ከመጡት አርባ ሰዎች ወዲያው ነው ህይወታቸው ያለፈው። ሌሎች አርባ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል።" በዚህ ሁሉ የጥይት ውርጂብኝ መካከል በዙሪያቸው የነበሩትን ሰዎች ህይወት የቀጠፈው ሞት እየቀረባቸው በመጣ ጊዜ አቶ አብዱልቃድ ከመጽሃፍ መደርደሪያው ስር ሆነው ይሰማቸው የነበረውን ሲያስታውሱ " በቃ ያው እየተገደልን መሆኑን ሳውቅ፤ ለካ ሰው እንደዚህ ነው የሚሞተው ብዬ አሰብኩ። አንዳንድ ጊዜ በዜና የምመለከተው ነገር እኔም ላይ እንደተፈጠረ ገባኝ" ይላሉ። ከሁሉ በላይ ግን የሁለት ሳምንት አራስ የሆነችው ባለቤታቸው እና ትመህርት ቤት ያሉት ሁለቱ ልጆቻቸው ደጋግመው በጭንቅላታቸው ይመላለሱ እንደነበር ገልጸው ምንም ማድረግ ስላልቻሉ "ትንፋሼን ዋጥ አድርጌ ወደ ጸሎት ገባሁ። ምክንያቱም እንደምሞት እርግጠኛ ነበርኩኝ።" ተኩሱ አልቆመም ከአጠገባቸው በግራም በቀኝም የሞቱ ሰዎች በደም ተነክረው ወድቀው ይታያቸዋል፤ የተኩሱ ድምጽ መስጊዱን አሁንም እያናወጠው ነው። ስለዚህ ይህ እጣ እሳቸውንም እንደሚደርሳቸው እርግጠኛ ነበሩ። ከጸሎቱ ጉን ለጎንም ወደሃገር ቤት ያስባሉ ስለእናታቸው፤ "እናቴም አለች፤ እሷንም አሰብኳት። እኔ ብቻ ነን የምረዳት፤ በቃ እንዴት ትሆናለች የሚልም ነገር አሰብኩኝ። ከሞት ጋር በተፋጠጥኩበት በመጨረሻው ደቂቃ ላይ" ይላሉ። ታጣቂው መጀመሪያ ላይ መስጊዱ ውስጥ ተኩስ የከፈተው በያዘው አውቶማቲክ ጠመንጃ ሦስት ጊዜ ካርታውን እየቀየረ ነበር። ከዚያ በኋላ ደግሞ ከፊል አውቶማቲክ መሳሪያ አውጥቶ የተረፉትን መግደል ቀጠለ። ከመስጊዱ አምልጠው እየሮጡ የነበሩት ላይ ሳይቀር "በመስኮት በኩል ወደ ውጪ ተኩሶ ይተኩስ ነበር። ከውስጥ ሁላችንንም ገድሎ የጨረሰ ሲመስለው ሮጦ ከመስጊዱ ወጣ። እሱ ወደ ውጪ ሲወጣ አርፍደው የሚመጡ የነበሩ ሌሎች ምዕመናንን አገኛቸው። እነሱንም እዛው መግቢያው ላይ ተኩሶ ገደላቸው።" • "የሠራዊቱ ሁኔታ ከፍተኛ የህሊና መረበሽ ውስጥ ከቶኛል" አቶ ነአምን ዘለቀ አቶ አብዱልቃድር አባቦራ ሃምሳ የሚደርሱ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው ገዳይ በቅርብ እርቀት ሆነው መትረፋቸውን እንደተአምር ነው የሚመለከቱት። በጥቃቱ ከሞቱት ባሻገር በርካቶች ቆስለዋል የሚያውቋቸው ሁለት ኢትዮጵያዊያንም ከባድ የመቁሰል ጉዳት እንደደተሰባቸው ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ሆስፒታል ውስጥ ህክምና ላይ ናቸው። በሁለቱ ኢትዮጵያዊያን ላይ ስለደረሰው የጉዳት መጠንም ሲናገሩ "አንደኛው ጀርባው ላይ ነው የተመታው። ጥይቱ በሳምባው ውስጥ አልፎ፤ በትከሻው ወጥቷል። እሱ በጣም አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነበረ" የሚተነፍሰውም በህክምና መሳሪያ ድጋፍ እንደነበረና አሁን በራሱ መተንፈስ ጀምሮ የጤንነቱ ሁኔታ እየተሻሻለ ነው።" ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ደግሞ እግሩን ነው በጥይት የተመታው። ቀዶ ህክምና እንደተደረገለትና አሁንም ሆስፒታል እንደሆ ተናግረዋል። ከጥቃቱ በኋላ አቶ አብዱልቃድር ቁጥሩን እንዴት አድርገው እንደመቱት ባያስታውሱም ቀድመው የደወሉት ወደ ባለቤታቸው ነበረ። በአጋጣሚም የሚያውቁት ታክሲ የሚነዳ ግለሰብና አግኝቷቸው ወደቤታቸው እንዳደረሳቸው ያስታውሳሉ። ኒውዚላንድ ውስጥ እንዲህ አይነቱ ጥቃት ተፈጽሞ ስለማያውቅ ፖሊሶች ጥቃቱ የተፈጸመው በሃገሬው ተወላጅ ይሆናል ብለው ስላላሰቡ አቶ አብዱልቃድር እና ጥቂት በመስጊዱ ዙሪያ የነበሩ ሰዎች ለምርመራ ከፖሊሶች ጋር ቆይተው ነበር። "እኛን ለተወሰነ ጊዜ አቆይተውን ነበር።እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ድረስ እዛው ቆየን። ፎቶ አነሱን፤ ሙሉ መረጃችንን ወሰዱና ለቀቁን" ብለዋል። • የትኞቹ ሃገራት ከፍተኛ ስደተኛ አላቸው? "ቤቴ ገብቼ ባለቤቴን ሳገኛት ምንም መናገር አልቻልኩም እንዲሁ ተቃቅፈን ማልቀስ ባቻ ነበር። እስከሚቀጥለው ቀን ድረስ አእምሮዬ ልክ አልነበረም። ይኸው እስካሁን ምንም እንቅልፍ አልተኛም። እስከዛሬ ድረስም ሥራ አልሄድኩም ሲሉ በጥቃቱ እለት ካሳለፉት ሰቆቃ እስካሁን መውጣት እንዳልቻሉ ይናገራሉ። ይህንን አሰቃቂ ክስተት መርሳት ከባድ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አብዱልቃድር በደም ተጨማልቁት ምንጣፎች የተሰባበሩት መስታወቶችና በሮች ደጋግመው በአይነ ህሊናቸው ይመላለሳሉ። "በዚህ ሳምንአርብ የት እንደምንሰገድ አላቀውቅም" ይላሉ። ነገር ግን ከዚያ ሁሉ መአት በመትረፋቸው ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ። "እኔ አሁን አዲስ ህይወት እንደምኖር ነው የምቆጥረው። እንደገና እንደተወለደ ሰው ነው የምቆጥረው። በዚህ ዓለም ሁለተኛ ዕድል እንዳገኘሁ ነው የምቆጥረው።"ባለፈው አርብ መጋቢት 6/2011 ዓ.ም ኒውዚላንድ ክራይስትቸርች ከተማ ውስጥ በሚገኝ መስጊድ ውስጥ አንድ ታጣቂ የፈጸመው ጥቃት የ50 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈ በኋላ ጉዳዩ እስከ ዛሬ ድረስ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።
news-56330503
https://www.bbc.com/amharic/news-56330503
ሠራተኞቹ 'የዘረኝነት ጥቃት ሲደርስባቸው' እረፍት እንዲወጡ የሚያስገድደው' ጉግል
ጉግል አሜሪካ ውስጥ ሠራተኞቹ የዘረኝነትና ፆታዊ ጥቃት ሲደርስባቸው የሕክምና እረፍት እንዲወስዱና የአእምሮ ጤና ሐኪም እንዲያማክሩ እንደሚያደርግ ተነገረ።
ይህንን የዘገበው ኤንቢሲ የተሰኘው ጣቢያ ነው። አንድ የጉግል ሠራተኛ ስለደረሰው ጥቃት የጉግል የሰው ኃይል የሕክምና እረፍት እንዲወስዱ ማስገደድን ልማድ እንዳደረገው ይናገራሉ። በቅርቡ ሁለት የጉግል 'አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኤቲክስ' [ሰው ሰራሽ ልህቀት ሥነ-ምግባር] አጥኚዎች ስለዘር ስብጥር በማንሳታቸው በኩባንያው መባረራቸውን አሳውቀው ነበር። ጉግል መሰል ድርጊቶችን አልፈፀምኩም ሲል አስተባብሎ፤ በተነሳው ክስ ላይ ምርመራ እንደሚያደርግ ተናግሯል። "ሠራተኞች የሚያነሱት ቅሬታ የሚታይበት ሥርዓት አለን። በጣም ግልፅ በሆነ መንገድ ነው ለመሥራት እንጥራለን" በሏል ኩባንያው በለቀቀው መግለጫ። "ፖሊሲዎቻችንን የሚጥሱ ሠራተኞች ላይ ከበድ ያለ እርምጃ እንወስዳለን" ብሏል ድርጅቱ። የቀድሞ የጉግል ሠራተኛ የሆነው ቤንጃሚን ክሩዝ የቆዳ ቀለሙን በተመለከተ አንድ ሌላ ሠራተኛ የሰጠውን አስተያየት በተመለከተ ለሰው ኃይል ቅሬታ ማቅረቡን ለኤንቢሲ ተናግሯል። "ቅሬታውን ካቀረብኩ በኋላ ሥራዎቼ ከእኔ ይነጠቁ ጀመር። ነገር ግን የቡድኔ አባላት ምን እንዳልተፈጠረ ነበር የሚሆኑት" ሲል ለጣቢያው ተናግሯል። "የሕክምና እረፍት እንድወስድ ከመከሩኝ በኋላ ሁሉን ነገር በፍጥነት ነበር ያስኬዱት" ይላል። ሌላ የቀድሞ የጉግል ሠራተኛ ደግሞ "ባለፈው ዓመት በደረሰባቸው ነገር ብቻ የአእምሮ ሕክምና እረፍረት እንዲወስዱ የተደረጉ በትንሹ 10 ሰዎች መጥቀስ እችላለሁ" ይላሉ። የኤንቢሲ የምርመራ ዘገባ አንድ ደርዘን የጉግል ሠራተኞች ሆነው ይህ ጉዳይ የደረሰባቸው ሰዎችን ታሪክ ይፋ አድርጓል። ከእነዚህ መካከል ባለፈው ዓመት [2020] ሥራቸውን ያጡት የሰው ሰራሽ ልህቀት ባለሙያዎቹ ትምኒት ገብሩና ማርጋሬት ሚቼል ይገኙበታል። ከጉግል መባረሯ ዓለም አቀፍ ማዕበል የፈጠረውና ጉግልን ያስተቸው ትምኒት ገብሩ [ዶ/ር] ከመባረሯ በፊት የስነ-ልቡና አማካሪ እንድታይ ምክር እንደተሰጣት ትናገራለች። ከሥራ ከመባረሯ በፊት በይፋ ትምኒትን የደገፈችው የሙያ አጋሯ ማርጋሬት ሚቼል [ዶ/ር] የኤንቢሲ የምርመራ ዘገባ የሷንም ሂደት የሚያንፀባርቅ እንደሆነ በትዊተር ገጿ ፅፋለች። ማርጋሬት አክላ ዘገባው በጣም ከባድ ቢሆንም 'የተደበቀ እውነታን ማጋለጡ' አስፈላጊ ነው ብላለች። ጉግል የተሰባጠረ የሰው ኃይል የለውም ተብሎ የሚተች ብቸኛው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አይደለም። ባለፈው ሳምንት አንድ የአሜሪካ ኤጀንሲ ፌስቡክ ሰው ሲቀጥር ሕቡዕ በሆነ መንገድ ዘረኝነት አለበት ሲል ምርመራ እያደረገበት እንደሆነ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ቅሬታውን ያቀረቡት ለሥራ ማመልከቻ ዶኪዩመንታቸውን የላኩ አራት ሰዎች ናቸው። የፌስቡክ አፈ ቀላጤ አንዲ ስቶን ስለጉዳዩ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
51636781
https://www.bbc.com/amharic/51636781
ሆስኒ ሙባረክ፡ የአዲስ አበባው የግድያ ሙከራ ሲታወስ
ሙባረክ የካቲት 17/2012 ዓ.ም አሸለቡ። በሰላም፤ ያውም በሆስፒታል ውስጥ፤ ያውም በተመቻቸ አልጋቸው ላይ ሆነው።
እኚህ ሰው ግን ከሞት ጋር ሲተናነቁ የአሁኑ የመጨረሻቸው ይሁን እንጂ የመጀመሪያቸው አልነበረም። በትንሹ 6 ጊዜ ሞት እየመጣ 'ዘይሯቸው' ይመለሳል። ሙባረክ በሳንጃ፣ በቢላ፣ በጥይትና በቦምብ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ከሞት መንጋጋ ያመለጡ ተአምረኛ ሰው ናቸው። ጥቂቶቹን ዛሬ ባናስታውስ ታሪክ ይታዘበናል። ጥቅምት 6፣1981። የዛሬ 41 ዓመት አካባቢ። አንዋር ሳዳት ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መናኺም ቤገን ጋር የካምፕ ዴቪድ ስምምነት ፈረሙ። ኖርዌይ ኖቤል ሸለመቻቸው፤ አረቡ ዓለም ግን ዓይንህን ላፈር አላቸው፤ "ከሀዲው ሳዳት" ተባሉ። ሞት ለሳዳት ተዘመረ። ያኔ የሳዳት ምክትል ሆስኒ ሙባረክ ነበሩ። በካይሮ አብዮት አደባባይ "ኦፕሬሽን ባድር" እየተዘከረ ነበር። ይህ ኦፕሬሽን ግብጽ እስራኤልን ድል ያደረገችበት ቀን ነው። ግብጾች የረመዳን ጦርነት ይሉታል። ታሪክ የዮም ኪፑር ጦርነት ይለዋል። ዮም ኪፑር በአይሁድ ዕምነት የቤዛና የንስሃ ቅዱስ ዕለት ነው። ግብጾች በዚህ ቅዱስ ቀን ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝረው ስዊዝ ካናልን ተሻግረው የሲናይ በረሃ አንድ ግዛትን ከእስራኤል ነጻ ያወጡበት ቀን ነው። ይህ ቀን በየዓመቱ ይዘከራል። ያን ዕለትም በካይሮ አብዮት አደባባይ ይኸው እየሆነ ነበር። ሙባረክና ሳዳት ተደላድለው ሰልፈኛውን ወታደር እያጨበጨቡ ይሸኛሉ። አንድ ወታደር በኮፍያው የእጅ ቦምብ ቀርቅሮ... ከኦራል መኪና ላይ በድንገት ወርዶ አንዋር ሳዳትን ተጠጋቸው፤ እርሳቸው ደግሞ ለመደበኛ ወታደራዊ ሰላምታ መስሏቸው ፈገግ ይሉለታል። የጥይት መአት አርከፈከፈባቸው። ሳዳት ሞቱ። ሙባረክ ቆሰሉ። ሆስኒ ሙባረክ የመጀመሪያውን የሞት ቀጠሮ ለጥቂት አመለጡት። መስከረም 7፣ 1999፤ ሙባረክ በኢንዱስትሪ የወደብ ከተማ ፖርት ሳይድ ጉብኝት ላይ ነበሩ። ሕዝቡ 'ሙባረክዬ' እያለ ይስማቸዋል። እርሳቸውም ከመኪናቸው በመስኮት ወጥተው አጸፋውን ይመልሳሉ። አንድ ቢላ በኪሱ የሸጎጠ የ40 ዓመት ጎልማሳ ሊከትፋቸው ሰነዘረ፤ የአየር ኃይል አብራሪ የነበሩት ሙባረክ ያን ለታ ከቢላም ከሞትም አመለጡ፤ እጃቸው ላይ ብቻ ቆሰሉ። ከብርሃን የፈጠኑት ጠባቂዎቻቸው ሰውየውን በዚያው ቅጽበት ከሕይወት ወደ ሞት ሸኙት። ሙባረክ በቦሌ ጎዳና ሆስኒ ሙባረክ ለሦስተኛ ጊዜ የሞት ቀጠሮ የነበራቸው በአዲስ አበባ ነበር። ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ፤ አንድ ሰማያዊ ቫን መኪና መንገዱን ዘግቶ ጥይት ማርከፍከፍ ጀመረ። ዕድሜ ለኢትዮጵያ ወታደሮች ሙባረክ ከሞት ተረፉ። እርሳቸው ግን የእኔ ደህንነቶች ናቸው ያተረፉኝ ብለዋል። ያኔ ካይሮ ላይ ተመልሰው አዲስ አበባ ላይ ስላጋጠቸው ነገር ለጋዜጠኞች እንዲህ ብለው ነበር። "ሊገድሉኝ የሞከሩት ሰዎች በትክክል የምን ዜጋ እንደሆኑ ልነግራችሁ አልችልም። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ አይመስሉም፤ ጥቁርም አይደሉም። 5 ወይም 6 ቢሆኑ ነው። የተወሰኑት ጣራ ላይ ነበሩ። ገና ከቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ እንደወጣሁ ነው። "አንድ ሰማያዊ መኪና መንገዱን ዘጋው፤ አንዱ ወርዶ መተኮስ ጀመረ። ሌሎች ከፎቅ ይተኩሱ ነበር። መኪናዬ ግን ጥይት አይበሳውም ነበር። ምንም አልደነገጥኩም። ሾፌሬ ግብጻዊ ነበር። መኪናውም የኛው ነበር። ቀኝ ወደ ኋላ ዞረህ ተመለስ አልኩት። ሦስቱን የገደሏቸው የኛ ደህንነቶች ናቸው።" የሙባረክ አጭር የሕይወት ታሪክ ሙባረክ የተወለዱት በሰሜን ግብጽ ካፍር አል መስለሃ ውስጥ ነው። ያን ጊዜ አንዋር ሳዳትን ሆኑ ገማል አብዱልናስር አልመጡም። በንጉሥ አህመድ ፉአድ ፓሻ ዘመን ነው የተወለዱት። ይህ ማለት ሙባረክ ተወልደው እስኪሞቱ ባሉ 91 ዓመታት ውስጥ 4 ፕሬዝዳንቶች ሲፈራረቁ አይተዋል። ሙባረክ ከ'ተራ' ቤተሰብ ይምጡ እንጂ ተራ ሰው አልነበሩም። ከዝነኛው የግብጽ ወታደራዊ አካዳሚ ተመርቀዋል። አየር ኃይል ገብተው፣ ትንንሽ የጦር አውሮፕላኖችን ለሁለት ዓመት አብርረው፤ ከዚያ የአብራሪዎች አስተማሪ ሆኑ። ሥራው ግን ሰለቻቸው። በዚህ መሀል ታላቁ ጄኔራል ጋማል አብዱልናስር ከሥልጣናቸው ሲፈነገሉ በአይነ ቁራኛ ተመለከቱ። ያን ቀን ሥልጣን ውልብ ሳትልባቸው አልቀረም። እንደ ጎርጎሮሶዊያኑ በ1959 ሙባረክ ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት አቀኑ። ያኔ ሶቭየት ኅብረት ለግብጽ ሁነኛ ረዳት ነበረች። እዚያ ሄደው ቦምብ ጣይ አውሮፕላን አብራሪነት ተማሩ። ከሶቪየት ኅብረት ሲመለሱ ሩሲያኛን አቀላጥፈው ነው። ወዲያው የአየር ኃይል አካዳሚው አለቃ ሆኑ፤ ወዲያውኑ የአየር ኃይል ዋና አዛዥነቱን ያዙ። ወዲያው መከላከያ ሚኒስትር ሆኑ። በሥልጣን ላይ ሥልጣን ደራረቡ። እርሳቸው ግን አሁንም ይበርደኛል ይሉ ነበር። ይህ ሁሉ ሥልጣን ታዲያ እንዲሁ አልመጣም። ከእስራኤል ጋር በነበረው የ6ቱ ቀን ጦርነት በአየር ኃይል አዛዥነታቸው ብሔራዊ ጀግና ተደርገው በመታየታቸው ነው ሥልጣን እግር በግር እያሳደደ የሚከተላቸው። ይህን የሙባረክን ዝና ያስተዋሉት ሳዳት በመጨረሻም ምክትላቸው አደረጓቸው። ሳዳት ሲገደሉ ሙባረክ አጠገባቸው ነበሩ። እርሳቸውን አስቀብረው፤ ቁስላቸውን አስጠግገው ወደ ቤተ መንግሥት ሰተት ብለው ገቡ። ከዚህ በኋላ ከሞቀው ቤተ መንግሥት ለመውጣት 3 ዐሥርታት አስፈልጓቸዋል። ከዚህ በኋላ ሙባረክ ከሀብታሟ ሳኡዲ አረቢያ ጋር ታረቁ። በሳዳት ምክንያት ከአረብ ሊግ የተባረረችው ግብጽም ወደ ህብረቱ ተመለሰች። እንዲያውም የአረብ ሊግ መቀመጫ ወደ ግብጽ ተመለሰ። ሙባረክ የተማሩት በሩሲያ ውስጥ ነው። በሩሲያኛ ቋንቋ ይቀኛሉ። ነገር ግን ከሶቭየት ኅብረት ይልቅ ምዕራቡ ጋር የሙጥኝ አሉ። እስራኤል ጋር አልቃረንም፤ ስምምነቱንም አላፈርስም በማለታቸው አሜሪካ ሙባረክን ወደደች። ቢሊዮን ዶላሮችን ማፍሰስ ጀመረች። ሙባረክ የጀመሩት የአሜሪካና የግብጽ ወታደራዊ ፍቅር ዛሬም ደረስ ቀጥሏል። ሙባረክ በተለይም በመጨረሻው የአንቀጥቅጠህ ግዛ ዘመናቸው ለይቶላቸው ነበር። እርሳቸው ላይ ብዕሩን ያነሳ የካይሮ ደራሲ ይቆነጠጣል፤ በሙባረክ ቤተሰብ የተሳለቀ ኮሜዲያን ይኮረኮማል፤ ሙባረክ ታፍረውና ተከብረው ነበር የኖሩት፤ በውድም በግድም። ከዕለታት ባንዱ ቀን የካይሮ "አብዯት አደባባይ" (ታህሪር) ተጥለቀለቀች። የአረቡ ጸደይ ከተፍ አለ። ተንቀጥቅጦ የተገዛላቸው የንስር ሕዝብ አንቀጠቀጣቸው። ታንክ ቢልኩ፤ ጥይት ቢያርከፈክፉ ወይ ፍንክች፤ እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ2011 ላይ ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲባል ሥልጣኔን ለቅቂያለሁ አሉ። ግብጾች ዘመናዊው ፈርኦን ሥልጣን ለቀቀ ብለው በደስታ እንባ ተራጩ። የፈርኦን መሸኘት ግን ሌላ ፈርኦንን እንዳይመጣ አላደረገም። ዛሬ ግብጻዊያን ለሙባረክ ያለቅሳሉ? ወይስ ማረን ሙባረክ ይላሉ? ሙባረክን የሸኘው የታታህሪር አደባባይ ሬሳቸውን ሲሸኝ ምን ይል ይሆን?
news-50499122
https://www.bbc.com/amharic/news-50499122
በዓለም ላይ ሔሮይን ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ያለው በሲሽልስ ነው
ምድረ ገነትነቷን ብዙዎች የሚመሰክሩላት ሲሽልስ በአደንዣዥ እፅ ወረርሽን ክፉኛ እየተሰቃየች እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ትላልቅ የዘንባባ ዛፎች ጥላ፣ ነጭ አሸዋማ የባህር ዳርቻዎች ውበት ወደ ሆኗት ሲሽልስ በየዓመቱ 360 ሺህ ቱሪስቶች ይጎርፋሉ።
ነገር ግን ከሲሽልስ የግል ደሴቶች፣ ሪዞርቶችና ምርጥ ምርጥ ሆቴሎች ጀርባ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝቧን የአደንዛዥ እፅ ሱሰኛ ባደረገ ወረርሽኝ የምትመሳቀል አገርን ያስተውላሉ። ከሲሽልስ አጠቃላይ 94 ሺህ ሕዝብ ከአምስት እስከ ስድስት ሺህ የሚደርሰው በአደንዣዥ እፅ ሱስ የተያዘ መሆኑን የአገሪቱ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መረጃ ያሳያል። ሲሽልስ በዓለም አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ የሄሮይ ሱስ የተመዘገበባት አገር ለመሆኗ መረጃዎች አሉ። የ34 ዓመቱ ጀድ ሊስፐራንስ ካናቢስ መጠቀም የጀመረው የ20 ዓመት ወጣት ሳለ ነበር። ከዚያ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ ሄሮይን መጠቀም ጀመረ። ሱሱን ለመሙላት ከአያቱ ገንዘብ ይሰርቅም እንደነበር ያስታውሳል። ከ115 ደሴቶች የተሰራችው ሲሽልስ ድንበሯ በዚህም በዛም ክፍት ነው። ሄሮይን ወደ ሲሽልስ የሚደርሰው ከማእከላዊ እስያ በተለይም ከአፍጋኒስታን ተነስቶ በምስራቅ አፍሪካ በማለፍ ረዥም ርቀት አቋርጦ ነው። በአደንዣዥ እፅ ሱስ የተያዙ ሰዎች በርካታ በመሆናቸው ጉዳዩን በወንጀል ከማየት ይልቅ እንደ በሽታ አይቶ ማከምን ነው የሲሽልስ ባለስልጣናት መፍትሄ ያሉት። በዚህም መሰረት የሄሮይን ተጠቃሚዎች ለመታከም ሁለት አማራጮች ያሏቸው ሲሆን የህክምናም የስነልቦናም ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። በአሁኑ ወቅት ሁለት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች የህክምና አገልግሎቱን ለማግኘት ተመዝግበዋል። ሁሌም ጠዋት ጠዋት ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ሆነው የሚገለግሉ አውቶቢሶች ደጃፍ ላይ ተካሚዎች ይሰለፋሉ። ነርስና የስነልቦና ባለሙያዎች በማገገም ላይ ላሉ የአደንዛዥ እፅ ሱሰኞች ተገቢ ያሉትን እና እንዲያገግሙ የሚረዳቸውን ሜታዶን የተሰኘ መድሃኒት ይሰጧቸዋል። ብዙዎች እንደሚሉት በሄሮይን ሱስ ወረርሽኝ ብዙ የሲሽልስ ጎጆዎች ተናግተዋል። በአገሪቱ የሱስ ማገገም ትልልቅ ፕሮግራሞች መዘርጋታቸውን ተከትሎ የሄሮይን ዋጋ እየቀነሰ እንዳለም መረጃዎች አሉ። • ላይቤሪያ የጦርና የኢኮኖሚ ወንጀሎች ፍርድ ቤት ልታቋቋም ነው • ሲሪላንካ የሞት ቅጣትን ለማስፈፀም ሁለት አናቂዎች ቀጠረች
48552481
https://www.bbc.com/amharic/48552481
የሞተር ብስክሌቶች እና ሕገወጥነት በአዲስ አበባ
ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ሲሆን ወ/ሮ ብሩክታዊት ጌታሁን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ስፋራው አውራሪስ ሆቴል አካባቢ ከሚገኘው የአብሲኒያ ባንክ 22 ቅርንጫፍ ገንዘብ ገቢ ለማድረግ እየሄዱ ነበር።
ወደ ባንኩ ከመድረሳቸው በፊት ግን በሞተር የታገዙ ዘራፊዎች የያዙትን ገንዘብ ነጠቋቸው። ግለሰቧ ገንዘቡን ይዘው የነበረው በፌስታል እንደነበር አብረዋቸው የነበሩት አቶ አለማየሁ ግርማ ለፖሊስ ተናግረዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሱዳን ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል • ኔይማር ደፍሮኛል ያለችው ሴት ቲቪ ላይ ቀርባለች • እግር ኳስ ተጫዋቹ ወንድወሰን ዮሐንስ እንዴት ተገደለ? የያዙትን ገንዘብ ለመንጠቅ ትግል ሲደረግም ገንዘቡ ይዘረገፋል። ያኔ በአካባቢው የነበሩ ሰዎችና የጥበቃ ሰራተኞች ዘራፊዎችን ለመከላከል የአቅማቸውን ጣሩ። ግለሰቧ በፌስታል ይዘውት ከነበረው 405 ሺህ ብር መካከልም ከ3 መቶ ሺህ ብር በላይ ማትረፍ እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ አክሎም ወንጀል ፈፃሚዎቹ ሲገለገሉበት የነበረ አንድ ሞተር ብስክሌት መያዙንም ገልጿል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ፋሲካው በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች በሞተር የታገዘ ዘረፋ እንደሚካሄድ ይሰማል። ነዋሪውም ምሬቱን ይገልፃል ብለን ስለጉዳዩ ላነሳንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የሞተር ብስክሌቶች በተለያዩ ወንጀሎች መሳተፍ ብቻ ሳይሆን በጣም በርካታ የሆነ የትራፊክ ደንብ መተላለፍ ላይም ይገኛሉ ብለዋል። የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አክለውም አንዳንድ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ሐሰተኛ የመንጃ ፈቃድ ይዘው እንደሚያሽከረክሩ፣ ሞተሩ ላይ የራሱ ያልሆነ ሰሌዳ በመለጠፍ እንደሚንቀሳቀሱ ይናገራሉ። ሰሌዳ ሳይኖራቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መጥተው አዲስ አበባ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መኖራቸውንም አልሸሸጉም። ሞተር ብስክሌቶቹ ሥርዓት ይዘው መስራት እንዳለባቸው ስለታመነ በመንግሥት ደረጃ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው የሚሉት ኮማንደር ፋሲካው ችግሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሔ ያገኛል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ቀምተው የሚሮጡ፣ በትራፊክ ደንብ መተላለፍ ጥፋት ላይ የተገኙ ከአስር ሺዎች በላይ ሞተር ብስክሌቶች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ኮማንደር ፋሲካው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በቅሚያ ተግባር ላይ የተሳተፉ ሞተር ብስክሌቶችንም ቢሆን ቀላል ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉትን በቁጥጥር ስር አውለናል ይላሉ። ኮማንደር ፋሲካው በአዲስ አበባና በኦሮሚያ የሞተር ብስክሌቶች ሰሌዳ አምስት ዲጂት አለመድረሱን አስታውሰው በሕገወጥ ተግባር ላይ የሚሰማሩ ሞተር ብስክሌቶች ሰሌዳቸውን ከሌላ መኪና ላይ ስለሚወስዱ ነዋሪው አጠራጣሪ ነገሮችን በሚመለከትበት ወቅት ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በአሳቻ ስፍራና ጊዜ የሚንቀሳቀሱ እና ሰሌዳ የሌላቸውንም ሞተር ብስክሌቶች መጠቀም አደገኛ ስለሚሆን ነዋሪዎች ጥንቃቄ አንዲያደርጉ አስታውሰዋል።
news-56213815
https://www.bbc.com/amharic/news-56213815
ህጻናት መብት፡ በናይጄሪያ ከ300 በላይ ተማሪዎች መታገታቸው ተሰማ
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ከ300 በላይ ሴት ተማሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተጠልፈው መወሰዳቸው ተገለፀ።
ፖሊስ ተማሪዎቹ አርብ ዕለት ጠዋት ዛምፋራ ግዛት ጃንገቤ ከሚገኘው አዳሪ ትምህርት ቤታቸው ከተጠለፉ በኋላ ወደ ጫካ እንደተወሰዱ እምነት አለው። ይህ በቅርብ ሳምንታት ከተፈፀሙ የተማሪዎች የጅምላ ጠለፋ መካከል በቅርቡ የሆነ ነው። በናይጀሪያ ታጣቂ ቡድኖች በገንዘብ ተደራድረው ለመልቀቅ ሲሉ ተማሪዎችን ያግታሉ። አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ ወደ ቅጥር ግቢው ሲገቡ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል የደንብ ልብስ ለብሰው እንደነበርና ሴት ተማሪዎቹን ተሽከርካሪ ላይ እንዲወጡ እንዳስገደዷቸው ተናግረዋል። ሌላ የዓይን እማኝ ደግሞ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ ታጣቂዎቹ ትምህርት ቤት ውስጥ የገቡት በእግራቸው ነው ብለዋል። የታጣቂዎቹ ቁጥርም 100 እንደሚሆን የዓይን እማኙ ምስክርነታቸው ሰጥተዋል። የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ፤ ድርጊቱን 'ጭካኔ የተሞላበት' እና 'የህጻናትን መብት የጣሰ' ሲል በተማሪዎቹ ጠለፋ ማዘኑን ገልጿል። ፕሬዚደንት ሙሃመዱ ቡሃሪ አሁን የተፈፀመውን የተማሪዎች እገታ " ኢ ሰብዓዊ እና ተቀባይነት የሌለው" ሲል አውግዘውታል። ፕሬዚደንቱ በሰጡት መግለጫ ፤ አስተዳደራቸው በርካታ ገንዘብ ለማግኘት ብለው ንጹሃን ተማሪዎችን በሚያግቱ አደገኛ ቡድኖች ተግባር አይሸነፍም ብለዋል። ዋነኛ ዓለማቸውም የታገቱ ተማሪዎች በሕይወትና ጉዳት ሳይደርስባቸው ማግኘት እንደሆነም ተናግረዋል። ቡሃሪ አክለውም ምንም እንኳን ባለሥልጣናት ከፍተኛ ኃይል ማሰማራት ቢችሉም፤ ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን እንደ ጋሻ ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ የሚል ስጋት መኖሩን ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በኒጀር ግዛት አጎራባች በምትገኘው ካጋራ ተጠልፈው የተወሰዱ 27 ተማሪዎችን ጨምሮ 42 ሰዎች እስካሁን ድረስ አልተለቀቁም። እአአ በ2014 በአገሪቷ ሰሜን ምስራቅ ከተማ ችቦክ 276 ተማሪዎች በእስላማዊ ታጣቂ ቡድኑ ቦኮ ሃራም ታግተው ነበር። ይህ በናይጀሪያ በትምህርት ቤቶች ላይ የደረሰው ጥቃት ዓለም አቀፋዊ ትኩረት አግኝቶ ነበር። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚፈፀሙ ጥቃቶች የሚፈፀሙት በአደገኛ ወንበዴዎች እንደሆነ ጥርጣሬ አለ። እስካሁን በጥቃቱ ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን የለም። በዛምፋራ ግዛት ታጣቂ ቡድኖች ብዙ ጊዜ ተማሪዎችን የሚያግቱት ጠቀም ባለ ገንዘብ ለመደራደር ሲሉ ነው። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር፤ ታጣቂዎች ከአጎራባች ሲና ግዛት ካንካራ ከ300 በላይ ወንድ ተማሪዎችን ሲወስዱ ከሰሜን ምስራቅ የአገሪቷ ክፍል በመቶዎች ማይሎች በሚርቅ ቦታ ላይ የሚንቀሳቀሰው ቦኮሃራም ከጥቃቱ ጀርባ እንዳለ የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተዋል። በኋላ ላይ በተደረገ ድርድርም ተማሪዎቹ መለቀቃቸው ይታወሳል።
news-48735459
https://www.bbc.com/amharic/news-48735459
በሃየሎም ይምሉ የነበሩት ጄነራል ሰዓረ መኮንን ማን ናቸው?
ትናንት በተሰነዘረባቸው ድንገተኛ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡት ጄነራል ሰዓረ መኮንን በልጅነታቸው ወደ ትግል ከተቀላቀሉ ጊዜ ጀምሮ ሙሉ ህይወታቸውን በወታደራዊ አገልግሎት ነበር ያሳለፉት።
በትግራይ ክልል ልዩ ስሙ ሽረ እንዳባጉና የተወለዱት ጄነራል ሰዓረ መኮነን፤ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን እዚያው ተከታትለዋል። ሆኖም የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ከተመሰረተ ሁለት ዓመት ሳይሞላው በ1968 ዓ.ም ነበር በ17 ዓመታቸው ትምህርታቸውን አቋርጠው ትግሉን የተቀላቀሉት። እዚያም ከተራ ታጋይነት ተነስተው በተለያዩ ወታደራዊ አመራር እርከን ላይ አገልግለዋል። • ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መገደላቸው ተነገረ • ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ያሉበት እንደማይታወቅ የአማራ ክልል ገለፀ በቀይ ኮከብ ዘመቻም ወደ ኤርትራ ለድጋፍ ከዘመተው የህወሓት ቡድን ጋር በአመራርነት ተጉዘው ለአንድ ዓመት ያህል እዚያው ቆይተዋል። "ከደርግ ሠራዊት ጋር በተደረገው ጦርነት ሰዓረ ያልተሳተፈበት ውጊያ የለም" ማለት ይቻላል - ይላሉ ጀግነታቸውን የሚያውሱት የትግል ጓዶቻቸው። በርካታ ታጋዮች በውሃ ጥም ያለቁበት ሰርዶ በተባለ የአፋር ክልል ውስጥ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገው በህይወት ከቀሩት ጥቂት ታጋዮች መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ በጄነራል ሓየሎም የክፍለ ጦር ኣዛዥነት ስር ከፍተኛ አመራር ሆነው በዘመቻው ተሳታፊ ነበሩ። በመጨረሻም በደብረ ታቦርና በሰሜን ሽዋ በተረደገው ከፍተኛ ውጊያ የብርጌድ አዛዥ በኋላም የክፍለ ጦር መሪ ሆነው ድል ማስመዝገባቸው የህይወት ታሪካቸው ያትታል። ከደርግ ውድቀት በኋላ ከደርግ ውድቀት በኋላ በተለይ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ሆነው የሰሩ ሲሆን፤ በኢትዮ ኤርትራ የድንበር ጦርነት ወቅት የቡሬ ግንባርን በመምራት የኢትዮጵያ ሠራዊት ከፍተኛ ድል እንዲቀዳጅ ካደረጉ የጦር ኣዛዦች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸው ይነገራል። • መፈንቅለ መንግሥቱና የግድያ ሙከራዎች ከጦርነቱ በኋላ በ2004 የአገር መከላለከያ ሠራዊት እንደ አዲስ ሲደራጅ፤ የሃገሪቱ ጦር ሠራዊት በሁለት ቦታዎች ተከፍሎ ሲዋቀር የአንዱን ዕዝ አዛዥ ሆነው ከፍተኛ አመራር ሰጥተዋል። ቀጥሎም አደረጃጀቱ ተተሻሽሎ አኣራት ዕዞች ሲዋቀር፤ በተለይ የኢትዮ ኤርትራ ድንበር አካባቢ ተሰማርቶ የነበረው የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ሆነው ረዘም ላለ ጊዜ መርተውታል። ከአራት ዓመት በፊት ግን ባልታወቀ ምክንያት ከዚሁ ኃላፊነታቸው ተነስተው የስልጠና ዋና መምርያ ከፍተኛ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ ነበር። • ስለመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውና ስለግድያው እስካሁን የምናውቀው ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የመከላከያ ሠራዊቱ መልሶ ሲዋቀር በርካት የህወሓት ነባር ተጋዮች ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ጄነራል ሰዓረ መኮንን ግን የቀድሞውን ኤታማዦር ሹም ጄነራለ ሳሞራ የኑስን ተክተው ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ለአንድ ዓመት ሲሰሩ የጦር ኃይሉን መርተዋል። "ሃየሎም ይሙት" ጄነራል ሰዓረ መኮንን የጄነራል ሃየሎም አርአያ የትግል ጓድ ከመሆናቸውም ባሻገር የቅርብ ጓደኞች እንደነበሩ ይነገራል። የሶርዶውን ጨምሮ በተለያዩ የውጊያ ውሎዎች አንድ ላይ ተሳትፈው እንደነበሩ ይነገራል። በነበራቸው ጥብቅ ግንኙነት የተነሳም ጄነራል ሃየሎም ከተገደሉ በኋላ "ሃሎም ይሙት" እያሉ ይምሉ እንደነበር በቅርብ የሚያውቋቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጨምረውም ጄነራል ሰዓረ በባህሪም ከጄነራል ሃየሎም ጋር በጣም እንደሚቀራረቡ ይመሰክራሉ። • የሰኔ 16ቱ ጥቃትና ብዙም ያልተነገረላቸው ክስተቶች ጄነራሉን በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚያውቋቸው ሰዎች እንደሚመሰክሩት፤ በቀላሉ ከሰው ጋር መግባባት የሚችሉ፣ ተጫዋችና ርህሩህ እንደነበሩ ይመሰክራሉ። ጄነራል ሰዓረ የሁለት ልጆች አባት ሲሆኑ የመጀመርያ ልጃቸው በትግል ላይ ሳሉ የተወለደች ሲሆን ሁለተኛው ልጃቸው ደግሞ ከደርግ መውደቅ በኋላ ነው የተወለደው።
news-53160666
https://www.bbc.com/amharic/news-53160666
ለ50 ዓመታት ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ እንቆቅልሽ በቀናት ውስጥ የፈታችው ተማሪ
አሜሪካዊቷ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለ50 ዓመት የበርካቶችን አእምሮ የፈተነውንና ሳይፈታ የቆየውን የሒሳብ ቀመር በቀላሉ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ በትርፍ ሰዓቷ ፈትታዋለች።
ሊሳ ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን በዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክሳስ እየሰራች ነው። ከዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሯ ካሜሮን ጎርደን ጋር እያወራች በነበረበት ወቅት እግረ መንገዷን ለወሬያቸው ማጣፈጫ በሚል የሰራችውን የሒሳብ ስሌት፣ ያቃለለችውን የሒሳብ ቀመር አነሳች። "መጮህ ጀመረ 'እንዴት በጣም ደስተኛ አልሆንሽም?'" እንዳላት ፒኪሪሎ በኳንታ ለሚታተመው የሳይንስ ዜናን የሚሰራጨው ድረገጽ ተናግራለች። "እብድ ነው የሆነው" በማለትም የነበረውን ሁኔታ ያስታወሰችው። ወይዘሪት ፒኪሪሎ ሦስተኛ ዲግሪዋን ሳትይዝ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያሰጣት የሒሳብ ቀመር 'ኮንዌይ ኖት ፕሮብሌም' ይሰኛል። ኮንዌይ ኖት ፕሮፕሌም (Conway knot problem) በብሪታንያዊው ሒሳብ ሊቅ ጆን ሆርቶን ኮንዌይ በ1970 የተቀመረ ነው። ፒካሪሎ ግን ስለዚህ መልመጃ የሰማችው ለመጀመሪያ ጊዜ እአአ በ2018 በአንድ ሴሚናር ላይ መሆኑን ታስታውሳለች። ፕሮፌሰር ጎርደን "ምን ያህል እድሜ ጠገብ ዝነኛ የሒሳብ መልመጃ መሆኑን ያወቀች አይመስለኝም" ብለዋል። የሒሳብ ጥልፍልፎሹ ከእውነታው የገመድ ጥልፍልፍ ጋር ተመሳሳይነት አለው የወይዘሪት ፒኪሪሎ ሥራ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የታተመ ሲሆን እርሷም ይህንን የጥያቄ ጎምቱ፣ የመልመጃዎች አውራ በመፍታቷ በማሳቹሴት ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝታለች። "የኮንዌይ ኖት መልመጃ ለረዥም ዓመታት በሒሳብ ሊቃውንት ሊፈታ ሳይችል ቆይቷል" ያሉት ስፔናዊው ተመራማሪ ያቬር አራማዮና ናቸው። ይህ የሒሳብ ቀመር እንደምን ያለ ነው? ሒሳባዊ ቋጠሮ (Mathematical knots) የአንድ የሒሳብ ዘርፍ ሲሆን የሚመደብበትም ክፍል ቶፖሎጂ ይሰኛል። የኮንዌይ ኖት የሂሳብ አዋቂዎችን ለአመታት ግራ ሰዒኣጋባ ነበር በቀላል ቋንቋ፣ ቶፖሎጂ የሚያጠናው ቁሶች ቅርጻቸውን ሲቀይሩ፣ ሲጎብጡ፣ ሲጠመዘዙ እና ሲወጠሩ-ነገር ግን ሳይሰበሩ እንዴት ያለ ጠባይ እንደሚያሳዩ ነው። ኖት ቲዎሪ (የጥልፍልልፎሽ ኀልዮት) የቶፖሎጂ አንዱ ዘርፍ ነው። ከእውኑ ዓለም ምሳሌዎች በተጻራሪው፣ ሒሳባዊ ቋጠሮ መጨረሻዎቹ የተሳሰረ ነው። በእርግጥ ቀላሉ ቋጠሮ የቀለበት ቅርጽ አለው፤ እናም ሊዋሃድ አይችልም። ነገር ግን የበለጠ ውስብስብ ይሆናል፤ ይህም አንዱ በአንዱ ላይ ሲጠላለፍና ሲቆላለፍ ነው። ይህንን በቀላሉ ለማስረዳት ገመድን ማሰብ በቂ ነው የሚሉት ማሪታኒያ ሲልቬሮ ናቸው። በሴቪሊ ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ሊቅ የሆኑት እኚህ ምሁር "የጥልፍልልፎሽ ኀልዮት በአንድ ገመድ ላይ የሚከሰትን ቅርጽ አልባነት ያጠናል" ሲሉ ያክላሉ። "በሌላ ቋንቋ፣ ገመዱን እንዴት አድርገን እንደምንጠመዝዝ፣ እንደምናጎብጠው፣ እንደምናጥፈው፣ እንደምንጨምቀው. . .ገመዱን ለመቁረጥ የማናደርገው ነገር ማለት ነው። ያ ክልክል ነው።" Just like in real life, the complexity of mathematical knots can also vary ቶፖሎጂ ታዲያ በተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች ውስጥ ቁልፍ ቦታ አለው። የምጣኔ ሃብት ገበያዎችን እንዲሁም የዲኤንኤ ሞሎኪውልስን ቅርጽ ለማጥናት ይውላል። የኮንዌይ ኖት ከኖት ፕሮብሌም ጀርባ ያለው ሰው ጆን ሆርቶን ኮንዌይ በሚያዚያ ወር በተወለደ በ82 ዓመቱ በኮሮናበቫይረስ ምክንያት ሞቷል። ሊቨርፑል የተወለደው ይህ የሒሳብ ሊቅ በዘርፉ ምሁራን ዘንድ ተወዳጅ እንደነበር ይነገርለታል። ወይዘሪት ፒኪሪሎ 11 ጊዜ የተጠላለፈን የኮንዌይ ኖት ነው ተመሳሳዩን በመስራት "አቻ ጥልፍልፍ" መፍታት የቻለችው። እርሷ በአቻነት የሰራችው ጥልፍልፎሽን የእውቁን የሒሳብ ሊቅ የ50 ዓመት ሚስጥር ለመፍታት ተጠቀመችበት። "ቀን ቀን ለመስራት አልፈልግም ነበር፤ ያ ለሒሳብ የሚመች አይመስለኝም. . . ልክ የቤት ሥራ እንደተሰጠኝ በማሰብ ቤት ወስጄ ነው የሰራሁት" ብላለች። ወይዘሪት ፒኪሪሎ በአሜሪካ ማይን በምትባል ገጠራማ ስፍራ ተወልዳ ያደገች ሲሆን ሒሳብን ያጠናችው በቦስተን ኮሌጅ ነው።
news-55169539
https://www.bbc.com/amharic/news-55169539
ኬንያ ለማበጣበጥ እያሴረችብኝ ነው ስትል ሶማሊያ ወነጀለች
ኬንያ ሶማሊያን ለማበጣበጥና መረጋጋት እንዳይሰፍን እያሴረች ነው ሲሉ የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ኦስማን አቡበከር ዱቤ ወቅሰዋል።
አገሪቷ ለምርጫ በምትዘጋጅበት ወቅትም ይህ እቅድ እየተከወነ እንደሆነም ሚኒስትሩ በአገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል። "ኬንያን እናከብራለን። በጉርብትና የተመሰረተ አብሮነትና መተጋገዝም እንዲኖር እንፈልጋለን። በኛ በኩል እነዚህን እሴቶች አጠንክረን ይዘናል። ከኬንያ በኩል ግን በማይገባ የቀን ህልም እየቃበዙ የሶማሊያን መሬትና ውሃ መቆጣጠር ይፈልጋሉ" በማለትም በብሄራዊ ቴሌቪዥኑ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ በተላለፈ ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ እንደ አባሪ ያነሱትም ከኬንያ በኩል ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና የሶማሊያ ተቃዋሚ መሪዎችን ናይሮቢ ማስተናገዷን በማንሳት ነው። ከደቡባዊ ሶማሊያ ጁባላንድ ግዛት የተውጣጡ ፖለቲከኞች በመጪው የሶማሊያ ምርጫ ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከዚህ ቀደምም እንዲሁ ፖለቲከኞቹ ውይይት አድርገዋል ተብሏል። "ሞቃዲሾ አንድም ቢሆን የኬንያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን አስተናግዳ አታውቅም። በጎረቤቶቻችን ላይ ውጥረት እንዲነግስም አንፈልግም ነገር ግን በሶማሊያ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች መነሻቸው ከናይሮቢ ሆኗል። በሶማሊያ የሚደረሱ ስምምነቶች የሚጣሱበትም ቦታ ኬንያ ሆኗል" ያሉት ሚኒስትሩ አክለውም "በአገሪቱ ያለውን አገዛዝ ላይ አለመረጋጋትና ፖለቲካዊ ውጥረቶች እንዲነግሱ እቅዶች የሚቆመሩበት ቦታ ሆኗል-ናይሮቢ። ለዚያም ነው ለምክክር አምባሳደራችንን ከናይሮቢ የጠራነው" በማለት የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ኬንያ በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል (አሚሶም) ስር በሶማሊያ ያሰማራቻቸውን ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ቁልፍ የሚባሉ ግዛቶቿ በአልሻበባብ ቁጥጥር ስር እንደዋሉም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። "በሶማሊያ የተሰማራው የኬንያ ኃይል ማንንም ሳያሳውቅ መውጣቱን ተከትሎ ግዛቶቹ በአልሻባብ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህንን ችላ የምንለው ጉዳይ ሊሆን ይገባል?" ብለውም ሚኒስትሩ ጠይቀዋል። ከቀናት በፊት የሶማሊያ መንግሥት አምባሳደሯን ከጠራች በኋላ በሞቃዲሾ የሚገኙትንም የኬንያ አምባሳደር ለምክክር አገራቸው እንዲሄዱ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል። የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩሉ በሶማሊያ የውስጥና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ጣልቃ ገብተዋል የሚለውን ጉዳይ አጣጥተለውታል። በኬንያና በሶማሊያ መካከል ያለው ግንኙነት በአመታት ውስጥ መሻከር አሳይቷል። ይህም በህንድ ውቅያኖስ ላይ የሚገኘው በተፈጥሮ ነዳጅና ዘይት የበለፀገው 150 ሺህ ካሬ ሜትር የሚሸፍነው ቦታ እሰጣገባ ጋር በተያያዘ ነው።
news-49737845
https://www.bbc.com/amharic/news-49737845
አሜሪካ፡ ''ሳዑዲን ያጠቁት ድሮን እና ሚሳዔሎች መነሻቸው ከኢራን ነው''
አሜሪካ ሳዑዲ ላይ የተቃጡትየድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች መነሻቸው ከኢራን ስለመሆኑ ደርሼበታለው አለች።
አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማትን ዒላማ አድርገው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱት ጥቃቶች መነሻቸው ከደቡባዊ ኢራን ነው። ኢራን በበኩሏ ከጥቃቶቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም ስትል ቆይታለች። በየመን የሚንቀሳቀሱት እና በኢራን ድጋፍ የሚደረግላቸው የሁቲ አማጽያን በሳዑዲ ጥቃቱን ያደረስነው እኛ ነን ቢሉም ሰሚ አላገኙም። • ሳዑዲ ላይ በተፈጸመው ጥቃት የኢራን እጅ እንዳለበት የአሜሪካ መረጃ ጠቆመ • አሜሪካ ለምን ከምድር በታች ነዳጅ ዘይት ትደብቃለች? የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ''የድሮን ጥቃቱ ከየመን ስለመነሳቱ የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ የለም። ሁሉም መንግሥታት ኢራን በዓለም የኢንርጂ ምንጭ ላይ የሰነዘረችውን ጥቃት ማውገዝ አለባቸው'' ለማለት ጊዜ አልወሰደባቸውም ነበር። ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ባለስልጣን ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ጥቃቱ የተሰነዘረበት አቅጣጫ እና ስፋት ከግምት ውስጥ ሲገባ የሁቲ አማጽያን ፈጽመውታል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል። የሁቲ አማጽያን ከዚህ ቀደም ወደ ሳዑዲ የድሮን ጥቃቶችን አድርሰዋል፤ ሚሳዔሎችንም አስወንጭፈዋል። የአሜሪካ ባለስልጣናት ይህን ጥቃት ግን የሁቲ አማጽያን መፈጸም የሚያስችል ቁመና የላቸውም፤ እንዲሁም ጥቃቶቹ የተሰነዘሩት በየመን የሁቲ አማጽያን ከሚቆጣጠሩት ስፍራም አይደለም። በሳዑዲ ላይ ጥቃቱ ከተሰነዘረ በኋላ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጨማሪ ማሳየቱ ይታወሳል። የሳዑዲ አረቢያ ኢነርጂ ሚንስትር ትናንት (ማክሰኞ) በነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ተጠግነው ወደ ቀደመ የማምረት አቅማቸው በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ይመለሳሉ ብለዋል። አሜሪካ ምን እያለች ነው? የአሜሪካ ባለስልጣናት የሳዑዲን ነዳጅ ማቀነባበሪያ ለመምታት ጥቅም ላይ የዋሉት የድሮን እና ሚሳዔል አይነቶችን ለይተናል ብለዋል። ጥቃቱ ከደረሰበት ስፍራ በሚሰበሰቡ ቁሶች ላይ የሚደረገው የፎረንሲክ ምርመራ ውጤት ኢራን እጇ እንዳለበት የማያወላውል መረጃ ማሳየታቸው አይቀሬ ነው እያሉ። ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ትናንት "አሜሪካ ሁሉንም መረጃዎች እየመረመረች ነው" ካሉ በኋላ የውጪ ጉዳይ ቢሮው ኃላፊ ማይክ ፖምፔዎ "ምላሻችን ምን መሆን አንዳለበት ለመወያየት" ወደ ሳዑዲ እያቀኑ ነው ብለዋል። • በሳዑዲ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ • በሳዑዲ የደረሰው ጥቃት እጅጉን እንዳሳሰባቸው የኔቶ ኃላፊ ገለፁ "ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የእራሷን እና የወዳጅ ሃገራትን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ከመውሰድ ወደኋላ አትልም። በዚህ እርግጠኛ ሁኑ" ሲሉ ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ተደምጠዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት ፕሬዝደንት ትራምፕ ለጥፋቱ ማን ተጠያቂ እንደሆነ ስለምናውቅ "አቀባብለን" የሳዑዲ መንግሥት ምክረ ሃሰብ ምን እንደሆነ እየጠበቅን ነው በማለት ወታደራዊ አማራጭ ከግምት ውስጥ እንደገባ አመላክተዋል። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጃቫድ ዛሪፍ በትዊተር ገጻቸው ላይ አሜሪካ እውነቱን አምና መቀበል አልፈለገችም ካሉ በኋላ ይህን ሁሉ እስጥ አገባ ማስቆም የሚቻለው በየመን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ማስቆም ሲቻል ነው ብለዋል።
news-47275502
https://www.bbc.com/amharic/news-47275502
እስራኤል ያሰናበተችው ኒጀራዊ ኑሮውን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ አድርጓል
እስራኤል ወደ ሀገሩ እንዲመለስ የላከችው ኒጀራዊ ሀገሩ አልቀበልም ስላለችው፣ ከኅዳር ወር ጀምሮ በቦሌ አየር ማረፊያ ተርሚናል ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል።
የ24 ዓመቱ ኢሳ ሙሃመድ ለቢቢሲ እንደተናገረው፣ "ይኸው እዚህ በአየር መንገዱ ውስጥ በመጥፎ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ። ምንም ነገር የለም፤ ምንም" ብሏል። የሙሐመድ ዕድለቢስነት የጀመረው ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ እስራኤል ውስጥ ያለሕጋዊ ፈቃድ ሲኖር ከተያዘ ጊዜ ጀምሮ ነው። ከ2011 ጀምሮ በእስራኤል ይኖር ነበር። የተሻለ ሕይወት አገኛለሁ በሚል ሀገሩን ለቅቆ የወጣው በ16 ዓመቱ እንደሆነ ይናገራል። እርሱ እንደሚለው እግሩ እስራኤልን ከመርገጡ በፊት ለሕገወጥ አዘዋዋሪዎች በግብፅና በሊቢያ አድርገው ወደ እስራኤል እንዲወስዱት ከፍሎ ነበር። አንድ ጊዜ እግሩ ቴል አቪቭን ከረገጠ በኋላ ያገኘውን ሥራ እየሠራ የዕለት ጉርሱን ያገኝ ነበር። በ2018 እስራኤል ውስጥ ያለሕጋዊ ወረቀት ነው የምትኖረው ተብሎ በቁጥጥር ሥር ሲውል በአንድ የከረሜላ ፋብሪካ ውስጥ ነበር የሚሠራው። • "ታከለ ኡማ አዲስ አበባን መምራት የለባቸውም" እስክንድር ነጋ ለበርካታ ወራት በማቆያ ሥፍራ ከተቀመጠ በኋላ፣ ኅዳር ወር ላይ እስራኤል በአስቸኳይ የጉዞ ሰነድ አዘጋጅታ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ አድርጎ ወደ ሀገሩ ኒጀር እንዲገባ አሳፈረችው። ነገር ግን ሀገሩ ሲደርስ የኒጀር መንግሥት የጉዞ ሰነድህ የተጭበረበረ ነው በማለት አላስገባም አሉት። "ኒጀር ውስጥ አልፈለጉኝም፣ ሊቀበሉኝ አልፈለጉም" ይላል መሐመድ። በኒጀር ለሳምንታት ታግቶ ከቆየ በኋላ 'በል ወደ መጣህበት እስራኤል' በማለት ላኩት። እስራኤል ግን በጭራሽ በማለት በድጋሚ ወደመጣህበት ብላ ላከችው። "እጅና እግሬን አስረው አልቀበልም ወዳለችኝ ሀገሬ ኒጀር በድጋሚ ላኩኝ" ይላል የ24 ዓመቱ ሙሀመድ። በዚህ መሀል ኒጀር ለሁለተኛ ጊዜ አላቅህም ብላ አላስገባም በማለት ስትመልሰው አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ እያለ እስራኤል የሰጠችው የጉዞ ሰነድ ጊዜው አለፈበት፤ ተቃጠለ። • እስራኤል አፍሪካዊያን ስደተኞች እንዲወጡ አዘዘች • እስራኤል ካገር አልወጣም ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞችን አሰረች ይህ የሆነው ባለፈው ኅዳር ወር ነው። ከዛን ጊዜ ጀምሮ መሄጃ ያጣ መፃተኛ፣ የሰው ሀገር ሰው፣ ሆኖ በቦሌ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ ይንከላወሳል። ቢቢሲ የኒጀር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ሰነዱ ሀሰተኛ ነው ያለውን ለማጣራት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ምላሽ ሊያገኝ አልቻለም። ሙሀመድ አሁን በመንገደኞች መውጫ በኩል ወዲያ ወዲህ ሲንገላወድ ይውላል። መንገደኞች አልያም ሠራተኞች የሚሰጡትን ምግብ እንደሚመገብም ይናገራል። "የአየር መንገዱ ሠራተኞች ምግብ ይሰጡኛል። ሁሉም ቀን ለኔ ተመሳሳይ ነው፤ ግን ሳላመሰግናቸው አላልፍም" ይላል። የሚተኛው ደግሞ በአየር መንገዱ ተርሚናል በሚገኘው የፀሎት ክፍል አንድ ጥግ ሻንጣውና አነስተኛ መስገጃውን በማንጠፍ ነው። "አየር መንገድ ውስጥ መቆየት አልፈልግም ምክንያቱም አየር መንገዱ ሀገሬ አይደለም" ይላል። የእስራኤል ኢሚግሬሽን ለቢቢሲ በጻፈው ደብዳቤ ሙሐመድ ከእስራኤል ለቅቆ እንዲወጣ የተደረገው በሀገሪቱ ውስጥ በሕገወጥ መልኩ ገብቶ በመገኘቱ እንደሆነ አረጋግጧል። ከሀገሩ ለቅቆ እንዲወጣ የሰጠውም ሰነድ ሕጋዊ እንደሆነ እና ለውጪ ሀገር ዜጎች የሚሰጥ ሕጋዊ 'ሊሴ ፓሴ' ወረቀት እንደሆነም አብራርቷል። ሙሐመድ ከኒጀር ከእስራኤልና ከኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊዎች ጋር የጠየቁትን ሁሉ በማድረግ መተባበሩን ይናገራል። ነገር ግን ጉዳዩ መቋጫ ሊገኝለት አልቻለም። • መባረር ወይም እስር የሚጠብቃቸው ስደተኞች በእስራኤል • ከእስራኤል የሚባረሩ ስደተኞች ለአደጋ እየተጋለጡ ነው ስደተኞችን እጇን ዘርግታ በመቀበል መልካም ስም ያተረፈችው ኢትዮጵያ የሙሀመድ ጉዳይ አጣብቂኝ ውስጥ የጣላት ይመስላል። ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ኃላፊ እንደሚሉት በመሀመድ ጉዳይ እጃቸውን ማስገባት የሚችሉት በኢትዮጵያ ለመቆየት ጥገኝነት ከጠየቀ ብቻ ነው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ መሀመድ ፈቃደኛ አይደለም። "ይህ የራሱ ጉዳይ ነው። ስለ ክብሩ እንጨነቃለን፤ ሐሳቡን ቀይሮ የጥገኝነት ጥያቄውን ለማቅረብ ፈቃደኛ ከሆነ ደግመን እንጠይቀዋለን፤ ይህንን ብቻ ነው ልናደርግ የምንችለው" ብለዋል። ሙሀመድ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ መቆየት አይፈልግም። ወደ ሀገሩ ኒጀር መመለስ ወይም ደግሞ እስራኤል መሄድ ነው የልቡ መሻት።
news-55932225
https://www.bbc.com/amharic/news-55932225
ጋዜጠኞች ከእነ ጃዋር መሐመድ ችሎት እንዲወጡ ተደረገ
በረሃብ አድማ ላይ ናቸው የተባሉት እነ ጃዋር መሃመድ በዛሬው ችሎት ሃሳባቸውን ማስረዳት እንደተሳናቸው ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ መሐመድ ጅማ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
ጃዋር መሐመድ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ አንደኛ ችሎት ዛሬ ማለዳ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ቀጠሮ ይዞ ነበር። በቀጠሮው መሰረት የቀረቡት አቶ ጃዋር መሃመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሃምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲ ጠሃ የረሃብ አድማ ላይ ከሆኑ ዛሬ 8ኛ ቀናቸው መሆናቸውን የተናገሩት አቶ መሀመድ፣ "ሰውነታቸው በጣም ስለተዳከመ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እነሱ ብዙ መናገር ስላልቻሉ እኛ ሃሳባቸውን አስረድተናል።" ብለዋል። ጠበቃቸው አቶ መሃመድ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ደንበኞቻቸው እነ አቶ ጃዋር መሀመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የረሃብ አድማ ከጀመሩ 8ኛ ቀናችው መሆኑን ጠቅሰው "በጣም ተዳክመን፣ ራሳችንን ስተን የህክምና እርዳታ የሚያስፈልገን ከሆነ እኛ በመረጥነው ሃኪም ብቻ የህክምና ርዳታ ይደረግልን' ሲሉ ፍርድ ቤቱን እንደጠየቁም አስረድተዋል። ፍርድ ቤቱም አቤቱታቸውን ካደመጠ በኋላ በግል ሃኪም እንዲታዩ ፈቅዷል። አቶ መሐመድ በረሃብ አድማ ላይ ያሉት እነ ጃዋር ስላሉበት ሁኔታ ተጠይቀው "እኔ በግሌ እንዳስተዋልኩት፣ በተለይ ጃዋር በጣም ተጎድቷል። በጣም ስለተዳከሙ ብዙ መናገር አልቻሉም። በጣም ተጎድተዋል።" ብለዋል። ፖለቲከኞቹ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የረሃብ አድማ እያደረጉ ያሉት የፖለቲከኞችን እስር እና በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚደርሰውን ጫና በመቃወም እንደሆነ ሌላኛው ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ትናንት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ጠበቃው ቱሊ ባይሳ ፖለቲከኞቹ እያደረጉት ያሉት የረሃብ አድማ እንዳደከማቸው ገልጸው፤ ደንበኞቻቸው ለማነጋገር በሄዱበት ወቅት ወጥተው ሊያነጋግሯቸው ስላልቻሉ "ተኝተው ባሉበት" ለማነጋገር ተገድደናል ሲሉ ለቢቢሲ ደንበኞቻቸው ያሉበትን ሁኔታ አብራርተዋል። የእነ ጃዋር የፍርድ ቤት ውሎ ምን ይመስላል? ማለዳ የተጀመረውን የችሎት ውሎውን ለመዘገብ እና ለመከታተል በችሎቱ የተገኙ ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ተቋም ሠራተኞች ተፈትሸው ወደ ችሎቱ ከገቡ በኋላ በጸጥታ አስከባሪዎች ከችሎቱ እንዲወጡ ተደርገዋል። የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የቢቢሲውን ሪፖርተር ጨምሮ 8 ጋዜጠኞችን እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባልደረባ ከችሎቱ በማስወጣት የፍርድ ሂደቱን እንዳይከታተሉ መከልከላቸውን የቢቢሲ ጋዜጠኛ ተናግሯል። ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደቱን እንዳይከታተሉ ከፍርድ ቤት እንዲወጡ የተደረገበት ምክንያት ባይገለጽላቸውም፤ አንዳንድ የፖሊስ አባላት ግን "ከላይ በመጣ ትዕዛዝ" ጋዜጠኞችን እንዳስወጡ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በመጀመሪያ ተከሳሾች እና ጠበቆች ችሎቱ ለህዝብ ክፍት መሆኑን መጠየቃቸውን የተናገሩት አቶ መሐመድ፣ ከዚህ በፊት በነበረው ቀጠሮ ላይ ቢጫ የለበሱ ሰዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱም መከልከላቸው ተገቢ አለመሆኑን መናገሩን አስረድተዋል። ጠበቆቹ ይህ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተከብሮ እንደሆነም ጠይቀዋል። አክለውም ፍርድ ቤት በተለየ ሁኔታ ችሎቱን ዝግ ካላደረገ በስተቀር ተከሳሽ በክፍት ችሎት የመዳኘት መብት አለው በማለት ለችሎቱ ማቅረባቸውን ገልፀዋል። የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ከአንድ ሳምንት በፊት ተይዞ የነበረው ቀጠሮ ቢጫ ቀለም ልብስ በለበሱ ግለሰቦች ችሎቱ ወደዛሬ እንዲሸጋገር መደረጉ የሚታወስ ነው። የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል ቢጫ ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የተገኙ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤቱ እንዳይገቡ በፖሊስ መከልከላቸውን ተከትሎ ተከሳሾች እና ጠበቆች ያሰሙትን አቤቱታ ተከትሎ ነው ተለዋጭ ቀጠሮ ለዛሬ የተሰጠው። በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶች ቢጫ ልብስ የመልበስ ዘመቻ ሲያከናውኑ የቆዩ ሲሆን ይህም ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እና ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚለብሱትን ባለ ቢጫ ቀለም ቱታ ለመወከል ነው። ፍርድ ቤቱ በእነጃዋር መሃመድ የችሎት ሂደት ላይ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን የሚያመላክቱ አልባሳትን ለብሶ መገኘት ከአመጽ ጋር ሊያያዝ ይችላል በማለት የድጋፍ ልብስ እንዳይለበስ ብሎ መወሰኑን አቶ መሐመድ ጅማ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ ማንኛውም በችሎት የሚታደም አካል አድማ የሚመስሉ ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን የሚያመላክቱ አልባሳትን ለብሶ ችሎት መታደም እንደማይችል ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ አቶ መሐመድ በዛሬው የእነ ጃዋር ችሎት ቤተሰቦች እና ጋዜጠኞች እንዳይገቡ ተደርገዋል ብለዋል። ፍርድ ቤቱ ከዚህ በኋላ ጋዜጠኞች እና የቤተሰብ አባላት በአቅራቢያው ካሉ ይግቡ ብሎ ነበር ማለቱን ጠቅሰው፣ አንዴ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ 'ካሉ ተመልሰው ይግቡ' መባሉ ትክክል አይደለም ማለታቸውን ገልፀዋል። ከችሎቱ እንዲወጡ የተገደዱት ጋዜጠኞች ችሎቱን እንዳይከታተሉ ለምን እንደተከለከሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት እና ምክትላቸውን የጠየቁ ሲሆን ኃላፊዎቹም ጉዳዩን አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጧቸው ተናግረዋል። በዛሬው ቀጠሮ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ ጋዜጠኞች ወደ ችሎት ብቻም ሳይሆን ወደ ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው እንዳይቀርቡ ተከልክለው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ መልኩ በርካታ የፖሊስ አባላት በፍርድ ቤቱ ዙሪያ ተሰማርተው ታይተዋል። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የወንጀል ችሎት፣ የተጠርጣሪዎቹን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለየካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉት እነ አቶ ጃዋር ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ፤ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 ጋር የተያያዙ ናቸው።
43906276
https://www.bbc.com/amharic/43906276
ካንዬ ትራምፕን በትዊተር በመደገፉ ዘለፋን እያስተናገደ ነው
አሜሪካዊውው ታዋቂ የሂፕ ሆፕ አቀንቃኝ ካንዬ ዌስት በቅርቡ በትዊተር ገፁ ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድጋፍ መስጠቱን ተከትሎ ብዙዎች ወቀሳቸውን እየሰነዘሩ ነው።
የ40 ዓመት እድሜ ያለው ካንዬ ትራምፕን በሚደግፉ በተከታታይ በትዊተር ካሰፈራቸው ፅሁፎቹ መካከል "አሜሪካን እንደገና ታላቅ ማድረግ" የሚለውን የፕሬዚዳንቱን መፈክርና በትራምፕ የተፈረመበት ቀይ ኮፍያም አጥልቆ ታይቷል። "ከትራምፕ ጋር መስማማት ማንም አይጠበቅበትም ነገር ግን፤ የህዝቡ ግፊት ግን ትራምፕን ሊያስጠላኝ አይችልም" በማለት በትዊተር ገፁ አስፍሯል። ትራምፕ በአፀፋ ምላሻቸው በትዊተር ላይ "ካንዬ አመሰግናለሁ! አሪፍ ነው" ብለዋል። ካንዬ በተለያዩ ድረ-ገፆች ዘለፋን ማስተናገዱን ተከትሎም ባለቤቱ ኪም ካርዳሽያን ዌስት በበኩሏ ደግፋው ተከራክራለች። "ባለቤቴን ጥላሸት ለመቀባት ለምትጣጣሩ የሚዲያ አካላት በሙሉ ካንዬ ቀውሷል እንዲሁም በትዊተር ገፁ ያሰፈረው ይረብሻል የሚለው አስተያየታችሁ አስፈሪ ነው። ሀሳቡን በነፃነት ስለገለፀና ራሱን ስለሆነ የአዕምሮ ጤንነት መጓደል ነው ብላችሁ ለመፈረጅ ወይ ፍጥነታችሁ! ትክክል አይደለም" ብላለች። ካንዬና ትራምፕ የተዋወቁት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ካሸነፉ በኋላ ሲሆን ባለፈው ረቡዕም ከትራምፕ ጋር "የድራጎንን ኃይል እንደሚጋሩ" እንዲሁም ትራምፕ "ወንድሙ እንደሆኑ" በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል። ካንዬ ቺካጎ ያደጉትን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፉት ስምንት ዓመት ስልጣን ላይ ቢቆዩም "ችካጎ ምንም አልተቀየረችም" በሚል ተችቷቸዋል። አስተያየቱም የትዊተር ድረ-ገፅ ተጠቃሚዎችን ያበሳጨ ሲሆን አንድ የትዊተር ተጠቃሚም የዘፋኙን "ዘ ላይፍ ኦፍ ፓውሎ" የሚለውን ዘፈኑን በመጥቀስ "የዱሮው ካንዬ ናፈቀኝ" ብላለች። ኪም ካርዳሽያን ትችቶቹን በማጣጣል" ካንዬ በመንጋዎች የሚንሸራሸር ሀሳብ አይደግፍም ለዚህም ነው የምወደው እንዲሁም የማከብረው። ከጥቂት ዓመታት በኋላ እንደሱ አይነት ተመሳሳይ አስተያየት የሚሰጡ እንደሱ አይፈረጁም እንዲያውም ይመሰገናሉ። ካንዬ ከጊዜው የቀደመ ነው" ብላለች። ከእሷም በተጨማሪ ቻንስ ተብሎ የሚታወቀው ራፐርም በትዊተር ላይ ባሰፈረው ምላሽ የአዕምሮም ሆነ አካላዊ ጤንነቱን ለሚጠራጠሩት "በደህና ሁኔታ ላይ ነው ያለው" በማለት የድጋፍ ምላሽ ሰጥቷል። ካንዬም በበኩሉ ከባለቤቱ ምክር በመስማት የሚስማማው ከራሱ ጋር ብቻ እንደሆነ ምላሽ ሰጥቷል።
45303599
https://www.bbc.com/amharic/45303599
አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታገዱ
የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦንን እና አቶ ታደሰ ካሳን ከማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ማገዱን ይፋ አደረገ።
የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ጉባኤ ላይ የነበረ ሲሆን፤ ጉባኤው ሲጠናቀቅ አቶ በረከትን እንዲሁም አቶ ታደሰን ማገዱን አስታውቋል። ኮሚቴው የሁለቱን አባላት እገዳ ባስተላለፈበት ጉባኤ ሌሎችም አዳዲስ ውሳኔዎች ላይ መደረሱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። • አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ የአቶ በረከት የአቶ ታደሰ እገዳ "በጥረት ኮርፖሬት ላይ ከሰሩት ጥፋት ጋር የተያያዘ ነው" ተብሏል። ስለዚህም እስከ ቀጣዩ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከኮሚቴው አባልነት መታገዳቸው ታውቋል። በጉባኤው ላይ ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከል፤ ነባር አመራሮች በማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያ መሻሩ ይገኝበታል።
news-45194494
https://www.bbc.com/amharic/news-45194494
የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊሲን ትጥቅ ለማስፈታት ዕቅድ የለም
የፌደራል መንግሥት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስን ትጥቅ ለማስፈታት ዕቅድ እንደሌለው በሃገር መከላከያ የኢንዶክትሬኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ተሰማ ለቢቢሲ ገለጹ።
ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ''የፌደራል የፀጥታ ኃይል የሶማሌ ክልልን የፀጥታ ኃይል ትጥቅ የማስፈታት ዓላማ ይዞ አልተንቀሳቀሰም። ልዩ ኃይሉ ቀድሞም እንዲሰለጠን እና እንዲታጠቅ ያደረገው የፌደራሉ መንግሥት ነው" ብለዋል። ጨምረውም ልዩ ኃይሉ ሰልጥኖና ታጥቆ ከክልሉ መንግሥት ጋር ብዙ ሥራ መስራቱንና አሁንም እየሰራ መሆኑን ተናግረው፤ "በአሁኑ ወቅትም ልዩ ኃይሉ ፀጥታ የማስፈኑ ሥራ አካል ሆኖ እንዲሰራ የማድግ ተግባር እየተከናወነ እንጂ ትጥቅ የማስፈታት ዓላማም ሆነ ዕቅድ የለም'' ብለዋል። • መቋጫ ያልተገኘለት የኦሮሚያ ሶማሌ ጉዳይ • በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ድንበር ግጭት የገዳ ስርዓት መፍትሔ ለምን አላመጣም? • አቶ አብዲ ስለተናገሩት ጉዳይ እንደማያውቅ ኢህአዴግ ገለፀ • ባለፉት ሦስት ቀናት በምሥራቅ ሐረርጌ በተፈፀመ ጥቃት 22 ሰዎች ተገደሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ተቺዎች የክልሉ ልዩ ፖሊስ አመሰራረት ምንም አይነት የህግ መሰረት የለውም ቢሉም፤ ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ሁሉም ክልሎች ውስጥ የልዩ ኃይል አደረጃጀት እንዳለ አመልክተዋል። "መደበኛ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻዎች አሉ። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልም እንደማንኛውም ክልል የልዩ ኃይል ፖሊሶችን አሰልጥኖ በማሰማራት ከፌደራል ኃይል ጋር የፀጥታ ማስከበር ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም በአካባቢው የተሻለ መረጋጋት ተፍጥሯል። ከሕጋዊ ዕውቅና ውጪ የተቋቋመ አልነበረም'' ብለዋል። ልዩ ፖሊስ የታጠቀው መሳሪያ የሌሎች ክልል ፖሊሶች ከሚታጠቁ መሳሪያ አንጻር ከባድ እና የዘመነ ነው እየተባለ ለሚነሳው ቅሬታም ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ በሶማሌ ክልል የፀጥታ ችግር እንደነበረና ይህን ችግር ለመቅረፍ ከፌደራል የፀጥታ ኃይል ጋር ልዩ ኃይሉን የማጠናከር እና የማዘጋጀት ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል። • ''ጫካ ውስጥ አስቀምጠው ለተከታታይ ቀናት ደፍረውኛል'' • መንግሥት ልዩ ፖሊስን እንዲበትን አምነስቲ ጠየቀ • ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ "በዚህም የፀጥታ ችግሩንም ለመቅረፍ ተችሏል። አሁን ምንድነው መስተካከል ያለበት በሚለው ላይ መንግሥት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሚከናወን ይሆናል። በወቅቱ ግን አስፈላጊ ነገር ስለሆነ የተደረገ ነገር ነው'' ብለዋል። የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በተደጋጋሚ በክልሉ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደሚፈጽም ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች እንዲሁም በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልል ድንበር አቅራቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ የሶማሌ ልዩ ኃይል አባላት ብዛት እና አደረጃጀት ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
news-48563241
https://www.bbc.com/amharic/news-48563241
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፊቱን ወደ ቻይና እያዞረ ይሆን?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መጋቢት 1/2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ሲበር አደጋ ካጋጠመው በኋላ ድርጅቱ አውሮፕላኖቹን ማገዱን አስታውቆ ነበር።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ ለቻይናው ዜና ወኪል ዢንዋ በሰጡት መረጃ ድርጅቱ ኮማክ የተባለው የቻይና አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የሚያመርታቸው 'ሲ 919' የተባሉትን አውሮፕላኖች ሁኔታ የሚከታተል ኮሚቴ አዋቅሯል። የአውሮፕላኖቹን አስተማማኝነት ለመቆጣጠርም ኢትዮጵያ አየር መንገድ መሀንዲሶች ከኮማክ ጋር በቅርበት እየሰሩ ስለመሆኑም ዢንዋ ዘግቧል። በቻይና የተሰራው የመጀመሪያው 'ሲ 919' መንገደኛ አመላላሽ አውሮፕላን በአውሮፓውያኑ 2017 ከሻንግሃይ ፑዶንግ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመነሳት ነበር የሙከራ በረራውን ያደረገው። • ቦይንግ "ችግሩ ተፈቷል" እያለ ነው • ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው የቻይናው ኩባንያ 'ሲ 919' ለተባሉት አውሮፕላኖች ከ300 በላይ ትዕዛዞችን የተቀበለ ሲሆን አውሮፕላኖቹን በአውሮፓውያኑ 2021 ማስረከብ እንደሚጀምር ገልጿል። ትእዛዙን የሰጡት አየር መንገዶች ደግሞ ሁሉም ከቻይና ናቸው። እውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፊቱን ወደ ቻይና እያዞረ ይሆን? የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ማኔጀር የሆኑት አቶ አስራት በጋሻው ቻይና ለኢትዮጵያም ሆነ በአጠቃላይ ለአፍሪካ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና ሌሎች ዘርፎች ላይ ትብብር እያደረገች እንደመሆኑ አየር መንገዱም በአቪዬሽን ዘርፍ ከቻይና ድርጅቶች ጋር ሲሰራ እንደቆየ ያስታውሳሉ። አያይዘውም አየር መንገዱ ወደ አምስት የቻይና መዳረሻዎች እንደሚበር በመጥቀስ ከቻይና ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ማድረጉ ከዚህ በፊትም የነበረ፣ ወደፊትም የሚቀጥልና የሁለቱ ሃገራት ግንኙት ላይ የተመሰረተ ነው ይላሉ። ''የቻይና ምርት የሆኑ አውሮፕላኖችን ኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊገዛ ነው የሚባለው ዜና ግን በታሳቢነት ደረጃ ያለ ነገር እንጂ ያለቀለትና ያበቃለት ጉዳይ አይደለም'' ብለዋል አቶ አስራት። አክለውም ድርጅታቸው ቦይንግ ማክስ አውሮፕላኖችን በመተው ፊቱን ወደ ቻይና አዙሯል የሚለው መረጃ የተሳሳተና ያልተረጋገጠ ስለመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ደጋግመው መግለጻቸውን አስታውሰዋል። በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረገው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ እንደሚቀጥል ግን ይናገራሉ አቶ አስራት። ኮማክ በተባለው የቻይና አውሮፕላን አምራችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ መካከል የተደረሰው ስምምነት ምን አይነት ነው? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ማኔጀሩ ሲመልሱ ንግግሩ ከተጀመረ ከሁለት ዓመት በላይ መሆኑን በማስታወስ ንግግሩ ገና ያላለቀና ወደፊትም የሚቀጥል ነው በማለት ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ቻይና ቦይንግና ኤርባስን የመገዳደር አቅም አላት? ቻይና ላለፉት አስር ዓመታት በቅርቡ የዓለምን የኤቪዬሽን ኢንዱስትሪ ለመቆጣጠር በማሰብ የራሷ የሆኑና ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ስታመርትና ስትሞክር ቆይታለች። በምጽሃረ ቃል ኮማክ በመባል የሚታወቀው የቻይና አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የሚያመርታቸው አውሮፕላኖች ብዙ ትችቶች እየተሰነዘሩበት ቢሆንም የሃገር ውስጥ አየር መንገዶች ግን ምርቶቹን ከመጠቀም ያገዳቸው የለም። • ቦይንግ ትርፋማነቴ ቀንሷል አለ • "አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ እንደ ዘርፉ ባለሙያዎች ትንበያ ከሆነ ግን በቅርብ ጊዜያት ቻይና ሰራሽ አውሮፕላኖች የቦይንግና ኤርባስን ምርቶች ገበያ መሻማት መጀመራቸው አይቀርም። በኤቪዬሽን ዘርፉ የማማከር ስራ የሚሰሩት ሹኮር ዮሱፍ እንደሚሉት የቻይናን ገበያ ሰብሮ የመግባት አቅም እንደ ቀላል መመለከት አይቻልም። ''የአቪዬሽን ዘርፉ በቅርቡ በአውሮፓና አሜሪካ አምራቾች ብቻ መዘወሩ ቀርቶ፣ ተጨማሪ ሶስተኛ አካል መግባቱ አይቀርም። ከቻይና የተሻለ አቅምና ቴክኖሎጂ ያለው ሃገር ማሰብ ደግሞ ዘበት ነው'' ብለዋል። በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድና ሌሎች ከቦይንግና ኤርባስ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ከዚህ በኋላ በምን አይነት መልኩ ያስቀጥላሉ የሚለው ጥያቄ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ማኔጀር የሆኑት አቶ አስራት በጋሻው ግን አየር መንገዱና ቦይንግ ያላቸው ግንኙነት የቆየና ከ70 ዓመታት ያላነሰ እንደሆነ ይናገራሉ። • የቦይንግ ኃላፊ የሟቾችን ቤተሰቦች በይፋ ይቅርታ ጠየቁ ''የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ ምርት የሆኑ ወደ 80 አካባቢ አውሮፕላኖች አሉት። አውሮፕላኖቹንም አሁንም እየተጠቀመባቸው ነው"ብለዋል። አክለውም አየር መንገዱም ከቦይንግ ጋር ያለው ግንኙነት ሰላማዊና ልክ እንደበፊቱ በንግድ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነ አቶ አስራት ገልጸዋል። በዓለም ላይ ያሉት 737 ማክስ አውሮፕላኖች 370 ሲሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድም አራቱን እየተጠቀመ ነበር። በመጋቢት ወር ይሄው አውሮፕላን ባጋጠመው አደጋ መከስከሱን ተከትሎ አየር መንገዱ አራቱንም አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ በማድረግ አስቀምጧቸዋል። ''አውሮፕላኖቹ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግቢ ውስጥ ደህንነታቸው ተጠብቆና ዓለማቀፍ ደረጃዎችን በጠበቀ መልኩ እንደቆሙ ነው የሚገኙት። አየር መንገዱም ወደፊት የሚሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ ተከትሎ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል።" ይላሉ አቶ አስራት። የቻይናው ኮማክ ኩባንያ የሚያመርታቸው አውሮፕላኖች የሃገሪቱን የደህንነትና ተያያዥ መስፈርቶች በማሟላታቸው በቻይና፣ አፍሪካ፣ ደቡብ አሜሪካና አንዳንድ የኢስያ ሃገራት መብረር የሚያስችል ፈቃድ አግኝተዋል። ነገር ግን አውሮፕላኖቹ የዓለማቀፉን ገበያ ለመስበርና ተወዳዳሪ ለመሆን አሁንም የአሜሪካና አውሮፓ ሃገራት የበረራ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል። ለነዚህ አውሮፕላኖች ከሃገራቱ ፈቃድ ማግኘት ደግሞ ቻይናን የሚጠብቃት ትልቁ ፈተና ነው።
news-53304140
https://www.bbc.com/amharic/news-53304140
ጥቁር ሞትን ዳግም ሊቀሰቅስ የሚችለው ወረርሽኝ በቻይና ታየ
የቻይና ባለስልጣናት ራስ ገዝ በሆነችው ኢነር ሞንጎሊያ ግዛት ውስጥ ቡቦኒክ የተሰኘ በሽታ በመከሰቱ ቅድመ ጥንቃቄ መውሰድ ጀመሩ።
እንደ ቻይና መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከዚህ በሽታ ጋር በተያያዘ በአንዲት የገጠር መንደር ውስጥ የሚኖር እረኛ በለይቶ ማቆያ የገባ ሲሆን አሁን በተሻለ ጤንንት ላይ ይገኛል ተብሏል። ባለስልጣናቱ ደረጃ 3 ያሉትን ማስጠንቀቂያ ያወጡ ሲሆን ይህም በሽታው ገና ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንዳለ እንደሚያሳይ ተገልጿል። የቡቦኒክ ወረርሽኝ በባክቴሪያ የሚከሰት ሲሆን በቀላሉ በአንቲባዮቲክ ማከም እንደሚቻል ነገር ግን ታማሚው ሕክምና ካላገኘ ግን በሽታው ሊገድል እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በቻይና የመጀመሪያው የቡቦኒክ ወረርሽኝ የተመዘገበው ቅዳሜ ዕለት ሲሆን ይህም በኡራድ ሚድል ባነር ሆስፒታል በባያኑር ከተማ ውስጥ ነው። እስካሁን ድረስ ታካሚው እንዴትና ለምን በበሽታው ሊያዝ እንደቻለ ፍንጭ አልተገኘም ተብሏል። ባለስልጣናቱ ያወጡት ደረጃ 3 ማስጠንቀቂያ እንስሳት ወረርሽኙን ሊሸከሙ ስለሚችሉ ማደንም ሆነ መመገብ የሚከለክል ሲሆን እንዲሁም በተመሳሳይ በሽታ መያዙን የሚጠረጥሩትን ሰው እንዲያሳውቁ ይጠይቃል። እስካሁን በዓለም ላይ በቡቦኒክ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች በተለያየ ጊዜ ተገኝተዋል። በ2017 ማዳጋስካር ውስጥ 300 ያህል ሰዎች በበሽታው ተይዘው ነበር። ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ሁለት ሰዎች በሞንጎሊያ በዚህ ወረርሽኝ የተነሳ ሲሞቱ የማርሞት (የአይጥ ጥዝርያ) ጥሬ ሥጋን በልተው መያዛቸው ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት በሞንጎሊያ ዋና ከተማ ኡላንባታር ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ በአካባቢው የማርሞት ጥሬ ሥጋና ኩላሊት ለመልካም ጤንነት ፍቱን ነው ተብሎ ይታመናል። የአይጥ ዝርያ የሆነችው ማርሞት ባክቴሪያውን ተሸካሚ ብቻ ሳትሆን በአገሪቱ የተከሰቱ ወረርሽኞችም መነሻ እንደሆነች ይታመናል። ቡቦኒክ ወረርሽኝ የሊምፍ ኖዶች (በአንገትና በብብት አካባቢ የሚገኙ) እብጠትን የሚያስከትል ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በቀላሉ ምልክቶቹን ለመለየት አስቸጋሪ ነው ተብሏል። የቡቦኒክ ወርረሽኝ ከዚህ ቀደም ጥቁር ሞት እየተባለ የሚታወቀው ወረርሽኝ ሲሆን በዚህም ወረርሽኝ የተነሳ በ14ኛው ክፍለ ዘመን 50 ሚሊዮን ሰዎች በመላው ዓለም ላይ መሞታቸው ይጠቀሳል። ወረርሽኝ ምንድን ነው? ዓለም እስካሁን ያስተናገደቻቸው ወረርሽኞችስ ምን ዓይነት ነበሩ?
news-47126798
https://www.bbc.com/amharic/news-47126798
አሳሳቢ እየሆኑ የመጡት አዳዲሶቹ የአባላዘር በሽታዎች
በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ጨምሮ በዓለማችን በተለያዩ ጊዜያት አዳዲስ በሽታዎች ይከሰታሉ።
አዳዲስ የአባላዘር በሽታዎች አሳሳቢ እየሆኑ ነው ለሕብረተሰብ ጤና እጅግ አደገኛ ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ ከሚባሉት መካከል በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉት በሽታዎች መካከል አዲስ ክስተት እየሆኑ ናቸው ስለሚባሉት አራት የጤና ችግሮች እንንገራችሁ። 1. ኔይሴሪያ ሜኒንጃይቲዲስ ኔይሴሪያ ሜኒንጃይቲዲስ አደገኛ ሲሆን በተለይ አንጎልንና የአከርካሪ ሽፋንን ያጠቃል ይህ ኔይሴሪያ ሜኒንጃይቲዲስ በአብዛኛው ሜኒንጎኮከስ እየተባለ የሚጠቀስ ሲሆን በቀላሉ የሚስፋፋ የማጅራት ገትር አይነት ነው። በሽታው አደገኛ ሲሆን በተለይ አንጎልንና የአከርካሪ ሽፋንን በማጥቃት እስከሞት ሊያደርስ ይችላል። • ጋናውያኑን ያስቆጣው የስነ ወሲብ ትምህርት • ስለ ወሲብ እንዲያስቡ የማይፈቀድላቸው ኢራናውያን በአብዛኛው እየታወቀ የመጣው የሽንት ቧንቧና የመራቢያ አካላት ኢንፌክሽን ተብሎ ነው። የበሽታው ባክቴሪያ በንክኪ ጭምር ሊተላለፍ የሚችል እንደሆነ ይነገራል። ከአምስት አስከ አስር በመቶ በሚጠጉ ጎልማሶች አፍንጫና ጉሮሮ ውስጥ የኔይሴሪያ ሜኒንጃይቲዲስ ባክቴሪያ ስለሚገኝ በግብረ ሥጋ ግንኙነት፣ በመሳሳም እንዲሁም በሽታውን ሊያስተላልፉ በሚችሉ ከሰውነት በሚወጡ ፈሳሾች አማካይነት ይተላለፋል። ከአራት ዓመት በፊት በበርካታ የአሜሪካ ከተሞች የተከሰተው ይህ በሽታ የቅርብ ተዛማጁ ከሆነው ጨብጥን ከሚያመጣው ባክቴሪያ የዘር ቅንጣት ጋር በመዋሃድ መከሰቱን ሳይንቲስቶች ገልጸዋል። ይህ ሽግግር በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፈውን ይህን በሽታ በአደገኛ ሁኔታ እንዲስፋፋ አድርጎታል። አምስት አይነት የኔይሴሪያ ሜኒንጃይቲዲስ በዓለም ዙሪያ እየተከሰቱ ላሉት አብዛኞቹ ወረርሽኞች ምክንያት ናቸው። ጥሩው ነገር ደግሞ አምስቱን የበሽታው አይነቶች የሚከላከሉ ሁለት ክትባቶች አሉ። 2. ማይኮፕላዝማ ጄኒታሊየም ማይኮፕላዝማ ጄኒታሊየም በሴቶች ላይ አደገኛ ነው በጣም ትንሽ ከሆኑት ባክቴሪያዎች መካከል የሚመደበው ማይኮፕላዝማ ጄኒታሊየም ከመጠኑ በላይ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ ሆኗል። በ1980ዎቹ የታወቀው ይህ በሽታ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ እስከ ሁለት በመቶ የሚሆኑ በተለይ ወጣቶችና ጎልማሶች ላይ በስፋት ይስተዋላል። ማይኮፕላዝማ ጄኒታሊየም በአብዛኛው የህመም ምልክቶች የማይታዩበት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ በሽንት ቧንቧ አካባቢ የሚሰማ የማይመች ስሜት ከሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ጋር ያመሳስለዋል። • ኃይል የተቀላቀለበት ወሲብ መፈጸም ''እየተለመደ መጥቷል'' በሽታው በመራቢያ ክፍሎች ላይ በሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት ምክንያት ከመሃንነት፣ ከጽንስ መቋረጥ፣ ከጊዜ በፊት የሚከሰት ወሊድ እና ከመሰል ችግሮች ጋር ይያያዛል። ኮንዶም መጠቀም በበሽታው ከመያዝ የሚከላከል ሲሆን፤ አጥኚዎች ይህ በሽታ አንቲባዮቲክ መድሃኒቶችን የመላመድ ባህሪን እያዳበረ በመሆኑ አሳሳቢ እንደሚሆን ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነው። "የሚያሳስበኝ ይህ በሽታ መድሃኒት የመቋቋም አቅሙ እየተጠናከረ መምጣቱና መስፋፋቱ ነው" ያሉት አሜሪካ ውስጥ የሚገኝ የአንድ የጤና ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ማቲው ጎልደን ናቸው። የከፋ ጉዳት ሊያደርስ የሚችልን የማይኮፕላዝማ ጄኒታሊየምን ተህዋስ አይነት መፈጠርን ለመከላከል ተጨማሪ ምርመራ በጣም አስፋለጊ እንደሆነም ተነግሯል። 3. ሺጌላ ፍሌክስኔሪ ሺጌላ የሆድ ቁርጠትና ደም የቀላቀለ አሰጨናቂ ተቅማጥን ያስከትላል ሺጌሎሲስ (ወይም የሺጌላ ተቅማጥ) በመባል የሚታወቀው በሽታ የሚተላለፈው ከሰው ልጅ አይነ ምድር ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሚኖር ንክኪ ነው። በሽታው ከባድ የሚባል የሆድ ቁርጠትና ደም የቀላቀለ አሰጨናቂ ተቅማጥን ያስከትላል፤ በዚህም በሽታው ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ እንዲተላለፍ እድል ያገኛል። ምንም እንኳን ይህ በሽታ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባለቸው አገራት ውስጥ ባሉ ተደጋጋሚ ጉዞ በሚያደርጉና በታዳጊ ልጆች ላይ በስፋት የሚስተዋል ቢሆንም፤ በ1970ዎቹ አጥኚዎች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይም እንደሚታይ መዝግበዋል። • ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን? በኒውዮርክ ከተማ የጤና ጉዳዮች ባለስልጣን ከሆኑት መካከል አንዱ ዲሜትሪ ዳስካላኪስ ስለሺጌሎሲስ አደገኛ እየሆነ መምጣት ሲናገሩ፤ ይህ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፈው በሽታ ጨብጥን ለማከም ጥቅም ላይ የሚውለውን አዚትሮማይሲን የተባለውን መድሃኒት እየተላመደው ነው። የሕዝብ ጤና ተቋማት ይህ በሽታ ከራሱ አልፎ አደገኛ አይነት ጨብጥ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። በብዙ ቦታዎችም ለየት ያለ የማከም ዘዴ እየተተገበረ መሆኑም ተነግሯል። 4. ሊምፎግራኑሎማ ቬኔሩም (ኤልጂቪ) አብዛኛዎቹን የአባላዘር በሽታዎች ኮንዶም በመጠቀም መከላከል ይቻላል ይህ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ የሚታወቀው በክላይሜዲያ ትራኮማሲስ ዝርያ አማካይነት የሚመጣ ሲሆን "እጅግ የከፋ ህመምን ሊያስከትል ይችላል" ሲሉ የሳን ፍራንሲስኮው ዶክተር ክሪስቶፈር ስኪዝል ይናገራሉ። በሽታው በመጀመሪያ ላይ በብልት አካባቢ ጊዜያዊ እብጠት፣ ውሃ መቋጠር ወይም መድማት ካጋጠመ በኋላ የሰውነታችንን የሊምፍ ሥርዓት በመውረር ያጠቃል። በሽታው ፊንጢጣንና የመጸዳጃ አካል ላይ እብጠትና የከፋ ህመምን በማስከተል ፊስቱላን የመሰለ ሌሎች ችግሮችንም ያመጣል። ባለፉት አስር ዓመታት ሊምፎግራኑሎማ ቬኔሩም በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ውስጥ በስፋት የሚታይ በሽታ ሲሆን፤ በተለይ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በሚፈጽሙ ሰዎች መካከል በሚከሰቱ የተለያዩ ወረርሽኞች ጋርም ሲዛመድ ቆይቷል። • ወንዶች፤ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒና ለመዋጥ ዝግጁ ናችሁ? ከክላይሜዲያ ጋር ተያይዞ እንደሚከሰተው ሊምፎግራኑሎማ ቬኔሩም የሰዎችን በኤችአይቪ የመያዝ አጋጣሚን ይጨምረዋል። ምንጊዜም በተገቢው ሁኔታ ኮንዶም መጠቀም በበሽታው የመያዝ ስጋትን የሚቀንስ ሲሆን፤ በሊምፎግራኑሎማ ቬኔሩም የተያዙ ሰዎች ታከመው ለመዳን ለሦስት ሳምንታት የሚሰጠውን የጸረ ተህዋያን መድሃኒትን መውሰድ ይኖርባቸዋል።
news-41144938
https://www.bbc.com/amharic/news-41144938
የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔና የሃገሪቱን የፍትሕ ሥርዓት ችግር አለበት ብለው ተናገሩ።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ወር የተካሄደውን የፕሬዚዳንት ምርጫ ካፈረሰ በኃላ የሃገሪቱ የፍትሕ ሥርዓት ችግር አለበት ብለው ተናገሩ።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስከትሎ ራይላ ኦዲንጋ ደስታቸውን ገለጹ በቴሌቪዥን የተላለፈውን የቀጥታ ሥርጭት ላይ ተመልሶ የሚመረጥ ከሆነ የሃገሪቱን የፍርድ ቤት አሠራር እንደሚያስተካክል ቃል ገባ። ይህ ውሳኔ ይፋ የተደገረገው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በተደረው የምርጫ ሥነ-ሥርዓት ላይ ያዩአቸውን ልዩነቶች በመግለጽ ነበር በተጨማሪም ከ60 ቀናት በኃላ ሌላ ምርጫ እንዲካሄድ አዘዙ። ፕሬዚዳንት ኬንያታ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብር ከተናገረ በኃላ በፍራቻና በውጥረት ወቅትም መረጋጋት እነዲኖር ጥሪ አቅርቧል። ሆኖም ግን ባለፈው አርብ ዕለት በተደረገው አድማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ዳኛዎች አጭበርባሪዎች በማለት ሰይሟቸዋል። ባለፈው 2 ነሐሴ 2009 የተደረገው የምርጫ ሥርዓት በብዙዎች ዘንድ እነደ ታሕሳስ 2000 ምርጫው ይታወካል የሚል ስጋትና ፍራቻ ፈጥሮ ነበር። ዊልያም ሩቶ ምክትል ፕሬዚዳንት የምርጫውን ኮሚሽን ቀን እነዲወስን በመግፋት ገዢው የጁቢሌ ፓረቲ ዝግጁ እነደሆነ አሳውቋል። የተቃዋሚው ፓርቲ ተወዳዳሪ ራይላ ኦዲንጋ ደግሞ ኮሚሽኑ እምነት እሚጣልበት ባለመሆኑ ከናካቴው እንዲቀየር ጥያቅ አቅርበዋል። "ይህን ጉዳይ መልሰን መመልከት ይኖርብናል ምክንያቱም የማይካድ ችግር ነው ያለው" በማለት የፍትሕ ሚኒስቴሩን ቅዳሜ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል። "ማን ሾማችሁ? ተሹማእኃልስ? ችግር ስላለ መጠገን አለበት" በማለትም ቀጥለው ተናግሯል። በዚህ ዓመት የነበረው የምርጫ ውጤት ውጥረት እንደ 2000 ዓ.ም ባይሆንም ቢያንስ 28 ሰዎች ሞተዋል። የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን አቶ ኬንያታን የምርጫው በ1.4 ሚልዮን ድምጽ ብልጫ አሸናፊ መሆናቸውን ባሳወቀ ከጥቂት ጊዜ በኃላ ነበር ተቃዋሚው ኦጊንጋ ወደ አቅራቢያ ፍርድ ቤት ክሳቸውን ያቀረቡት። ባለፈው እርብ ዕለት በተደረገው ውሳኔ የፍትሕ ኃላፊ የሆኑት ዴቪድ ማራጋ የዚህ ዓመት ምርጫ ሥርዓት ሕገ-መንግሥቱን ያልተከተለ ሂደት በመሆኑ ትክክል ያልሆነና የሚሻር ምርጫ ነው በማለት ተናግረዋል። ውሳኔው የፕሬዚዳንቱን ፓርቲ ወይንም ዘመቻ በምንም አይነት ወቀሳ አላቀረቡበትም። የ72 ዓመቱ አቶ ኦዲንጋ ይህን ውሳኔ "ለኬንያውያን በሙሉና ለመላው አፋሪካ የሚበቃ ታሪካዊ ክንውን ነው በማለት ተናግረዋል"። ይህንም ምርጫ አስከትሎ ከአውሮፓ ሕብረት ከአፍሪካ ሕብረትና ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የተውጣጡ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምንም አይነት ማጭበርበር እነዳልነበረና አቶ ኦዲንጋም በዕሺታ ውሳኔውን እንዲቀበሉ አበረታተውታል።
news-43454470
https://www.bbc.com/amharic/news-43454470
የሞያሌ ተፈናቃዮች ያሉበት አሳሳቢ ሁኔታ
ባለፉት ሁለት ቀናት ከኢትዮጵያ ሸሽተው በኬንያ ደምበላ ፈቻና እና ሶመሬ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ቢቢሲ ቃኝቷል፤ በርካታ ስደተኞችንም አነጋግረናል።
ከእነዚህ መካከል አንዱ የህክምና ባለሙያዎች ''እድለኛ'' ብለው የሚጠሩት ጉዮ ጃርሶ ነው። ጉዮ በሞያሌ ከተማ የተሽከርካሪ ጎማ የመጠገን ሥራ ላይ ነበር የተሰማራው። ''ሰዎች የተገደሉ ቀን እንደተለመደው ከጓደኞቼ ጋር በመሆን የተሽከርካሪ ጎማ የመጠገን ሥራ ላይ ነበርን። ምንም ሳናጠፋ በስራችን ላይ እያለን ተኩስ ከፈቱብን። እኔ በሁለት ጥይት ተመታሁ። ከሶስቱ ጓደኞቼ ሁለቱ የዛን ቀን ሲገደሉ አንዱ ደግሞ አሁንም ሆስፒታል ውስጥ ይገኛል'' ሲል በምሬት ይናገራል። ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው ሁለቱም ጥይቶች ሰውነቱን በስተው ነው ያለፉት። የመጀመሪያው ቀኝ እጁን ሁለተኛው ጥይት ደግሞ ከሆዱ በላይ ጎኑን በስቶት አልፏል። በስደተኛ ጣቢያው ውስጥ የነበሩ የቀይ መስቀል ማሕበር የጤና ባለሙያዎች የጎዮ ህይወት መትረፍ አስደናቂ እንደሆነ፤ ምናልባትም ከሁለቱ ጥይቶች አንዱ ጥቂት ወደ ግራ የሰውነቱ ክፍል ቢጠጋ ኖሮ ህይወቱ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችል እንደነበር ይናገራሉ። ጉዮ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች አምቡላንስ ጠርተው ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል እንደወሰዱት ይናገራል፤ ከትናንት በስትያ ከሆስፒታል አንደወጣ በቀጥታ ወደ ሶመሬ ስደተኞች ጣቢያ ነበር ያመራው። ከሃገር ሸሽተው ከወጡት ዜጎች መካከል ሌላኛዋ ወ/ሮ ከድጃ መሃመድ ነች። የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ከድጃ ሞያሌ ከተማ በሚገኘው አነስተኛ መደብሯ ውስጥ የተለያዩ ሸቀጦችን ትነግድ ነበር። ወ/ሮ ከድጃ በሞያሌ የነበረው ግድያ ''ለእኔ እና ለልጆቼ ስጋት ስለሆነብኝ ሸሽቼ ወጣሁ'' ትላለች። ወ/ሮ ከድጃ ''እኔ ተከራይቼ የምኖርበት ግቢ ውስጥ ፊት ለፊቴ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። በሬን ከፍቼ ስወጣ እኔም ላይ ተተኮሰብኝ። አላህ ጠብቆኝ ህይወቴ ተረፈች። ከዛም በሬን ዘግቼ እስኪያልፉ ጠብቄ ልጆቼን ይዤ በፍጥነት ከከተማው ሸሽቼ ወጣሁ'' በማለት የነበረውን ክስተት ታስታውሳለች። የእርሷ እንዲሁም የጎረቤቴ ናቸው ያለቻቸውን ልጆች ጨምሮ በርካታ ህጻናት ከድጃ በሰራችው የላስቲክ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ተመልክተናል። ራሄል የአክስቷን ልጅ አቅፋ ከህጻናቱ መካከል በወላጆቻቸው ፍቃድ የ15 ዓመት ዕድሜ ያላት ራሄልን እና የ10 ዓመቷ ኢቅራን አነጋግራናል። የአክስቷን ልጅ አቅፋ ያገኘናት ራሄል ''የጦርነቱ ቀን በጣም ብዙ ደም አየን። እኛንም ይገድሉናል ብለን ሸሽተን ወደ እዚህ መጣን። እዚህ ከመጣን ጀምሮ የበቆሎ ገንፎ ነው የምንበላው'' ትላለች። ራሄል የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ወደ ትምህር ቤት መመለስ ብትፈልግም ከፍተኛ ፍራቻ እንዳደረባት ግን አልደበቀችንም። ''ልጆች ሲገደሉ አይቻለሁ። ትምህርት ቤት ሄጄ መማር እፈልጋለው ግን ወደዛ መመለስ እፈራለው'' ያለችን ደግሞ ልክ እንደ ራሄል ሁሉ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ኢቅራ ናት። መንግሥት ከቀናት በፊት በሞያሌ የተፈጸመው ግድያው 'በስህተት የተፈፀመ ነው' ማለቱ አይዘነጋም። ይሁን እንጂ ወ/ሮ ከድጃን ጨምሮ በጣቢያዎቹ ውስጥ ያነጋገርናቸው ተፈናቃዮች በዚህ የሚስማሙ አይመስሉም። ድንበር ተሻግረው ኬንያ ከገቡ የሞያሌ ተፈናቃዮች መካከል አንዷ የሆኑት ወ/ሮ አዳነች ''እኔ በስህተት ነው ብዬ አላምንም። 'ሸሚዝ የለበሰውን ምታው' እያሉ እየተኮሱ በስህተት ነው ማለት አይቻልም። ሆነ ብለው ወጣቶችን ነበር ኢላማ ሲያደርጉ የነበረው። ከዛም በኋላ የ10 ዓመት ልጅ አባረው ነው የገደሉት ይህም በስህተት ነው?'' ስትል በምሬት ትጠይቃለች። የሞያሌ ከተማ እና የአጎራባቸ ቀበሌ ነዋሪዎች ለደህንነታቸው በመስጋት አሁንም ድንበር አቋርጠው ወደ ኬንያ እየተመሙ ነው። ባሳለፍነው ቅዳሜ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጂኔራል አሰፋ አብዩ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ዲና ሙፈቲም ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተመሳሳይ ነገር ነግረውናል። አምባሳደሩ ይህን ይበሉ እንጂ በኬንያ እና ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የታዘብነው አሁንም በርካቶች ድንበር አቋርጠው ወደ ስደተኛ ጣቢያዎች ሲተሙ ነው። አልፎም ካነጋገርናቸው ተፈናቃዮች መካከል በርካቶች ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ፍላጎት የላቸውም። ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ባገኘነው መረጃ መሰረት፤ ከአራት በላይ በሆኑ ጣቢያዎች ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች ቁጥር አስር ሺህ ይገመታል። ከወርልድ ቪዝን ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየን ደግሞ ከስደተኞቹ መካከል ሰማንያ በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው። ሶመሬ ተብሎ በሚጠራው የስደተኞች ጣቢያ ውስጥ ከ3500 በላይ ሰዎች ይገኛሉ። በጣቢያው በአንድ አነስተኛ ከላስቲክ በተሰራ ቤት ውስጥ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን ይዞ ይገኛል። በጣቢያው በርካታ ሰዎች በጠባብ ቦታዎች ላይ ተፋፍገው ስለሚገኙ እንዲሁም የመጸዳጃ እና በቂ የሆነ የህክምና አገልግሎት ባለመኖሩ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በጣቢያው የወርልድ ቪዥን ተወካይ የሆኑት ደንከን ኦዳዎ ለቢቢሲ ይናገራሉ። በጣቢያው ውስጥ በርካታ ህጻናት እና ነብሰ ጡር ሴቶች ስለሚገኙ የበሽታ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ እንደሆነ በማስታወስ የተቅማጥ በሽታ ምልክቶች መታየታቸውንም ድንከን ኦዳዎ ነግረውናል። ጨምረውም በኢትዮጵያ መረጋጋት ሰፍኖ የስደተኞች ቁጥር ካልቀነሰ በቀር ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስጠነቅቃሉ። የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለስደተኞቹ ከሚያደርጉት ድጋፍ በተጨማሪ በርካታ የኬንያ ዜጎች ሃገር ጥለው የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አስጠግተው እያኖሯቸው እንደሆነም ቢቢሲ ተገንዝቧል። ከዚህ በተጨማሪም በግል መኪኖቻቸው ልብስ እና ምግብ ጭነው ሲያድሉም ተመልክተናል።
news-55313819
https://www.bbc.com/amharic/news-55313819
ኮሮናቫይረስ፡ 'አዲስ አይነት የኮሮናቫይረስ ዝርያ' በእንግሊዝ መገኘቱ ተገለጸ
ከዚህ ቀደም ከነበረው የተለየ ዝርያ ያለው አዲስ የኮሮናቫይረስ በአንዳንድ የእንግሊዝ አካባቢዎች በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑ ተነገረ።
የዩናትድ ኪንግደም ጤና ሚንስትር ማት ሃንኮክ ለአገሪቱ ምክር ቤት አባላት እንደተናጉት፤ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ቢያንስ በተለያዩ 60 ስፍራዎች መገኘቱ ተመዝግቧል ብለዋል። ማት ሃንኮክ መንግሥታቸው ጉዳዩን ለዓለም ጤና ድርጅት ማሳወቁን እና የዩኬ ተመራማሪዎች በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ላይ ምርምር እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል። የጤና ሚንስትሩ እስካሁን ያሉት መረጃዎች ይህ ዝርያ ከዚህ ቀደም ከነበረው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በላይ አደገኛ ስለመሆኑ አልያም የበለጸጉት የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ስለመቋቋሙ አያመለክቱም ብለዋል። "በተለይ በደቡብ እንግሊዝ በርካታ በዚህ አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የተጠቁ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎችን አግኝተናል" ያሉት ማት ሃንኮክ፤ ክትባቶችን ለዜጎች በፍጥነት በማድረስ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል። የጤና ባለሙያው ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተለመደው የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንደሚለይ ተናግረዋል። ፕሮፌሰሩ ጨምረውም በደቡብ እንግሊዝ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በአዲሱ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አረጋግጠዋል። በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ውስጥ የቫይረሱ የፕሮቲን ብዛት እንደጨመረ የታወቀ ሲሆን፤ የቫይረሱ የፕሮቲን መጠን መጨመር በቫይረሱ ባህሪ ላይ የሚኖረው ለውጥ ምን ሊሆን እንደሚችል ግን ገና ግልጽ አይደለም። በበርሚንግሃም ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አለን ማክናሊ፤ "ብዙ መደናገጥ ያለብን አይመስለኝም። ይህ ማለት ቫይረሱ በፍጥነት የተላለፋል ማለት አይደለም ወይም አደገኛ ነው ማለት አይደለም" ብለዋል። በቅርብ ቀናት ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ፋይዘርና በባዮንቴክ የበለጸገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል። 95 በመቶ የኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ሆና ነበር።
news-42509573
https://www.bbc.com/amharic/news-42509573
አፕል ስልኮች በዝግታ እንዲሰሩ በማድረጉ ይቅርታ ጠየቀ
የቆዩ የአይፎን አይነቶችን ሆን ብሎ በዝግታ እንዲሰሩ በማድረጉ የደረሰበትን ወቀሳ ተከትሎ አፕል ይቅርታ ጠየቀ። ኩባንያው ባትሪዎችን እንደሚቀይርና እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ተጠቃሚዎች የስልካቸውን ባትሪ ደህንነት መከታተል የሚችሉበት ሶፍትዌር ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ኩባንያው በ2018 ተጠቃሚዎች የስልካቸውን ባትሪ ደህንነት መከታተል የሚችሉበት ሶፍትዌር ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል። የቆዩ አይፎኖችን የያዙ ብዙ ተጠቃሚዎች ወደ አዳዲሶቹ እንዲሸጋገሩ ኩባንያው ሆን ብሎ የድሮዎቹ ቀስ ብለው እንዲሰሩ ሳያደርግ እንዳልቀር ቀደም ሲል ብዙዎች ጠርጥረው ነበር። አፕልም የድሮ ባትሪዎች ያላቸውን ስልኮቹን ሆን ብሎ በዝግታ እንዲሰሩ ማድረጉን አምኗል። ይህን ያደረገው ግን የስልኮቹ ባትሪ እድሜ እንዲረዝም መሆኑን አስታውቋል። ኩባንያው ድረ ገፁ ላይ የዋስትና ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ባትሪዎች የሚቀይርበትን ሂሳብ ከ 79 ዶላር ወደ 29 ዶላር ዝቅ ማድረጉንም አስታውቋል። ኩባንያው በደንበኞቹ ዘንድ ምንም አይነት መጠራጠር እንዲፈጠር እንደማይፈልግና እምነታቸውን ለማግኘትም አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግም ተናግሯል። "በአፕል ኩባንያ የደንበኞች እምነት ማለት ሁሉም ነገር ነው። የደንበኞችን እምነት ለማግኘትና ለመጠበቅ መስራታችንን አናቋርጥም።" የሚል መልእክቱን ኩባንያው በድረ ገፁ ላይ አስፍሯል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አፕል አሜሪካ ውሰጥ ስምንት የተለያዩ ክሶች የተመሰረቱበት ሲሆን በእስራኤልና በፈረንሳይም ተመሳሳይ ክሶች ተመስርተውበታል። ኩባንያውም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ያረጁ አይፎኖችን ሆን ብሎ ቀስ ብለው እንዲሰሩ ማድረጉን እንዳመነ ይታወሳል። ስልኩ የሚሰራበትን የአሰራር ሥርዓት እንዴት ማሻሻል ይቻላል? የአይፎን ስልክ ተጠቃሚ ከሆኑ ይህን መንገድ መከተል ይችላሉ። በመጀመሪያ ሞባይልዎ የኢንተርኔት ግንኙነት እንዳለው ያረጋግጡ። ዋይፋይ ቢጠቀሙ ይመረጣል። በመጀመሪያ መቼየት (ሴቲንግ) ይግቡ፤ ከዚያም ጀነራል የሚለውን ሲጫኑ- ሶፍትዌር አፕዴት የሚል አማራጭን ያገኛሉ። ይህንኑ ሲጫኑ ለስልክዎ የተዘጋጀ አዲስ ስሪት ካለ ማሻሻል ይችላሉ። 'ዩር ሶፍትዌር ኢዝ እፕ ቱ ዴት' የሚል መልዕክት ከተመለከቱ ግን ስልክዎ የተሻሻለው አሰራር ስላለው መጠቀምዎን ይቀጥሉ። የአንድሮይድ ስልክ (ሳምሰንግ እና ሁዋዌ ስልኮችን ጨምሮ) ተጠቃሚ ከሆኑ ደግሞ ስልክዎ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳለው በማረጋገጥ፤ ወደ ሴቲንግ ይሂዱ ከዚያም አባውት ዲቫይስ የሚለውን ይጫኑ ከዚያም ሶፍትዌር አፕዴት የሚለውን ሲጫኑ ለስልክዎ አዲስ ስሪት ካለ ማሻሻል ይችላሉ። ''ዩር ሶፍትዌር ኢዝ እፕ ቱ ዴት'' የሚል መልዕክት ከተመለከቱ ግን ስልክዎ የተሻሻለው አሰራር ስላለው መጠቀምዎን ይቀጥሉ።
news-44061572
https://www.bbc.com/amharic/news-44061572
የኢትዮጵያ የዕዳ መጠን እየጨመረ ነው
አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ባወጣው የአፍሪካ ሃገራት ምጣኔ ሃብታዊ ዘገባ፤ የኢትዮጵያ የዕዳ ጫና መጠን ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርቷ 56.2 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝ ገለጸ።
ባሳለፍነው ዓመት የ10.9 በመቶ እድገት ያስመዘገበች ሃገር ይህን ያክል ዕዳ መሸከሟ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሆነች ያሳያል ብሏል መግለጫው። ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘውን ምጣኔ ሃብታቸውን ለማስቀጠል ሲሉ ከፍተኛ የሆነ ዕዳ ውስጥ እየገቡ እንደሆነ በየዓመቱ የሚወጣው ዘገባ ያትታል። 40 በመቶ የሚሆኑት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ የሚባል የዕዳ መጠን አስመዝግበዋል፤ ወይም ወደዚያ እየተጠጉ ነው የሚለው ዘገባው እነዚህ ሃገራት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የማይወጡት ችግር ይገጥማቸዋል ሲል ይተነብያል። ኢትዮጵያ እና ዛምቢያ ከአጠቃላይ ሃገራዊ ምርታቸው ጋር ያልተመጣጠነ ዕዳ እያስመዘገቡ መሆኑን የዓለም አቀፉ ተቋም ጥናት ያሳያል። በ2016 የኢትዮጵያ ዕዳ መጠን ከሃገራዊ አጠቃላይ ምርቷ 55 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 ደግሞ ቀላል የማይባል ለውጥ በማሳየት ወደ 56 በመቶ አድጓል። ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት አሁንም የመሠረተ ልማት ሥራዎቻቸውን ለማስቀጠልና ማሕበራዊ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወደ ብድር መግባታቸው አይቀርም የሚለው ዘገባው ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ካለባቸው ግን የብድር መጠናቸውን መቀነስ ግድ ይላል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ለመሠረታዊ ፍጆታ የሚውሉ እቃዎች ዋጋ ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ መጥቷል። በ2016 የሃገሪቱ አጠቃላይ የመሰረታዊ ፍጆታ ዋጋ በ6.7 በመቶ ብቻ ያደገ ሲሆን በ2017 ግን ከእጥፍ በላይ በመጨመር 13.6 በመቶ እድገት አሳይቷል።
news-44206677
https://www.bbc.com/amharic/news-44206677
ኢራን አሜሪካ ማዕቀብ እጥላለሁ ማለቷን አወገዘች
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዛሪፍ አሜሪካ በታሪኳ ከፍተኛ የሆነውን ማዕቀብ እጥላለሁ ማለቷን ነቅፈዋል።
በአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚያሳዩት አሜሪካ በተኮላሸው ፖለቲካዋ እስረኛ እንደሆነችና የሚመጣው መዘዝም ተቋዳሽ እንደምትሆን ተናግረዋል። የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ የሆኑት ፌደሪካ ሞገሪኒ በበኩላቸው አሜሪካን ተችተዋል። በአውሮፓውያኑ 2015 የተፈፀመውን የኒውክሌር ስምምነት መሰረዝ ለመካከለኛ ምስራቅ ያለውን ፋይዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማሳየት እንዳልቻሉም ገልፀዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ወር መጀመሪያ ስምምነቱን ለመተው መወሰናችውን ተከትሎ " በስምምነቱ ላይ ሌላ ምርጫ የለም በመሆኑም ኢራን ሃላፊነቷን የምትወጣ ከሆነ የአውሮፓ ህብረት በስምምነቱ ሊቀጥል ይችላል" ብለዋል። ከኢራን የኒውክሌር ስምምነት በኋላ አንዳንድ በአውሮፓ የሚገኙ ትልልቅ ድርጅቶች በኢራን መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ የቸኮሉ ቢሆንም፤ አሜሪካ ስምምነቱን መሰረዟን ተከትሎ ኢራን ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ አሊያም ከአሜሪካ ጋር ንግድ ለመጀመር ምርጫ ውስጥ እንዲገቡ ተገደዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ምን ተናገሩ? አሜሪካ አዲስ ማዕቀብ ልትጥል እንደምትችል የገለፁ ሲሆን አዲሱ አርምጃ ከዚህ ቀደም ያልተደረገ የገንዘብ ጫናን ሊጨምር ይችላል ብለዋል። ከኢራን ጋር አዲስ ስምምነትም የሚደረስ ከሆነ ወታደራዊ ሃይሏን ከሶሪያ እንድታስወጣና የየመን አማፂያንን ድጋፍ ማቆም እንዳለባት ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል። የቀደመው ማዕቀብ ከኢራን ጋር የሚኖረውን የንግድ ትስስር የሚከለክል ነበር። ማይክ ፖምፔዮ አዲሱ እርምጃ ምን ሊሆን እንደሚችል በዝርዝር አልተናገሩም ። ይሁን እንጂ ባለፈው ሳምንት በኢራን ማዕከላዊ ባንክ ላይ ማዕቀብ የተጣለ ሲሆን፤ ይህም የእርምጃው መጀመሪያ ነው ብለዋል። ኢራን በአለም ትልቋ ነዳጅ አምራች ስትሆን በየዓመቱ ወደ ውጭ የምትልከው የነዳጅ ዘይት በቢሊየን ዶላር ይገመታል። የአገሪቱ የነዳጅ ዘይት ምርትና ዕድገት በአለም አቀፉ ማዕቀብ ጫና ስር ነው። ማዕቀቡ በፍጥነት ተግባር ላይ እንደማይውል የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የወራት ማሳሰቢያ ቀነ-ገደብ አለው ብለዋል። የኢራን ምላሽ ምን ይመስላል? የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጃቫድ ዛሪፍ አሜሪካ ወደ "ጠብ አጫሪነቷ" መመለሷን ገልፀው ነገር ግን ኢራን ለኒውክሌር ስምምነቱ መፍትሄ ለማፈላለግ ከሌሎች አጋር አገራት ጋር እየሰራች እንደሆነ ተናግረዋል። የኢራኑ ፕሬዚደንት ሃሰን ሮሃኒ በበኩላቸው ማይክ ፖምፔዮ የቀድሞ የሲኤአይ ኤ ኃላፊ ከመሆናቸው አንፃር በኢራንንና በተቀረው አለም ላይ ይህን መወሰናቸው ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ግላዊ ትችታቸውን ሰንዝረዋል። የኒውክሌር ስምምነቱ ምን ነበር? ኢራን ኒውክሌርን ለመስራት የሚያገለግለውን ዩራኒየምን መጠን ለመቀነስ ተስማምታ ነበር። ይህም ለአስራ አምስት አመታት የሚሆን ለኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ጣቢያ ና ለኒውክሌር መሳሪያ እንዲውል የታሰበ ነበር። ፐሉቶኒየም የተሰኘ ለቦምብ መስሪያ የሚውል ኬሚካል አላመርትም በማለትም ተስማምታ ነበር። በዚህም ሳቢያ በተባበሩት መንግስታት ፣ አሜሪካና ፣ የአውሮፓ ህብረት የተጣለባት ማዕቀብ የኢራን ኢኮኖሚ እንዳያንሰራራ አድርጎታል። ስምምነቱ በኢራንንና በአምስት የፀጥታው ምክር ቤት አባል አገራት አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ ፣ ቻይናና ሩሲያ እንዲሁም ጀርመን ጋር የተደረገ ነበር።
news-46285854
https://www.bbc.com/amharic/news-46285854
ትራምፕ በካሾግጂ ግድያ ምክንያት ውግዘት ከደረሰባት ሳዑዲ ጎን ቆመዋል
ሳዑዲ አረቢያ ከጀማል ካሾግጂ ግድያ ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፍ ውግዘት ቢደርስባትም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሃገሪቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ትራምፕ በቢዝነስ እና ወታደራዊ ግንኙነቱ ላይ ትኩረት አድርገዋል ሳዑዲ ተባባሪ እና ከየትኛውም ሃገር በላይ በአሜሪካ መዋለ ንዋይዋን ያፈሰሰች ናት ሲሉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን በቅርቡ ህይወቱ ስላለፈው ካሾግጂ አሟሟት የማወቃቸው ዕድል ከፍተኛ ነው ብለዋል። "ሆኖም ግን የእኛ ግንኙነት ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ነው" ሲሉ ገልጸዋል። የሳዑዲ ዜግነት ያለው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ ቱርክ ኢስታንቡል ወደ ሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ገብቶ ህይወቱ ማለፉ ከተረጋገጠ ሳምንታት አልፈዋል። • የጀማል ኻሾግጂን ግድያ ለመሸፈን 'ባለሙያዎች ተልከዋል' • «ኻሾግጂ አደገኛ ሰው ነበር» የሳዑዲው ልዑል ሳዑዲ በቆንስላው ሠራተኞች ተገቢ ያልሆነ አያያዝ ጋዜጠኛው ህይወቱ ማለፉን በመግለጽ አልጋ ወራሹ ስለግድያው ያውቁ ነበር የሚለውን ዘገባ አጣጥለዋል። ሳዑዲ ከየትኛውም ሃገር በላይ በአሜሪካ መዋለ ንዋይዋን ያፈሰሰች ሃገር ናት - ትራምፕ ሲ አይ ኤ ግድያውን ሞሃመድ ቢን ሳልማን ማዘዛቸውን ያምናል ሲሉ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው "አልጋ ወራሹ ስለግድያው ሊያውቁም ላያውቁም ይችላሉ" ብለዋል። • የጋዜጠኛው አስክሬን 'በአሲድ እንዲሟሟ ተደርጓል' ሲ አይ ኤም ቢሆን ስለግድያው "100%" እርግጥኛ አይደለም ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። ባለፈው እሑድ ከቱርክ የቀረበላቸውንና ጋዜጠኛውን አገዳደል ያመላክታል ተባለለትን ድምጽ ለመስማት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን አስታውቀዋል።
news-57333182
https://www.bbc.com/amharic/news-57333182
የቻይናው ፕሬዚዳንት አገራቸው በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ እንድትከተል ጥሪ አቀረቡ
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ አገራቸው ወዳጆቿን ማብዛት እንደምትፈልግ አስታውቀዋል።
ለዚህም አገራቸው የገፅታ ግንባታ ያስፈልጋታል ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ከኮሙኒስት ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ አገራቸው "ታማኝ፣ ተወዳጅና ክብር ያላትን የቻይናን ገፅታ መፍጠር አስፈላጊ ነው ማለታቸውን የአገሪቱ የዜና ወኪል ሺኑዋ ዘግቧል። ቻይና ከምዕራባውያኑ ጋር ያላት ግንኙነት ከአመት አመት ወደ ባላንጣነት እንደተሸጋገረ የሚናገሩት ተንታኞች ቻይና ይህንን ማለቷ መሰረታዊ በሆነ መልኩ ዲፕሎማሲያዋን ልትቀይር መሆኑ አመላካች ነው። ቻይና በተለይም እንደ አሜሪካ ጋር ካሉ ታላላቅ ኃያላን አገራት ጋር የሻከረ ግንኙነት ነው ያላት። በአገሪቷ ባሉ ሙስሊም ህዝቦች ላይ በምታደርሰው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትና በሆንግ ኮንግ የዲሞክራሲ ደጋፊዎች በምታደርሰው እስሮችና እንግልቶች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ቻይና ከፍተኛ ውግዘቶችን አስተናግዳለች። በቅርቡም አሜሪካ የኮቪድ-19 መነሻ የቻይና ቤተ ሙከራዎች ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ምርመራ አደርጋለሁ ማለቷን ተከትሎ ቻይና በበኩሏ "የራሳቸውን ጥፋት ለመደበቅና ፖለቲካዊ ማጭበርበር" ነው በሚል አፀፋዊ ምላሽ ሰጥታለች። ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ሰኞ እለት ከባለስልጣኖቻቸው ጋር በመከሩበት ወቅት ቻይና ታሪኳን በአዎንታዊ መልኩ ልትናገር ይገባል ብለዋል። "አጋሮችና ወዳኞች ማፍራት አስፈላጊ ነው።በአለም አቀፉ ዘንድ ያለውን ዋነኛ የህዝብ አስተያየትን ለማስቀየር የወዳጆቻችንን ቁጥር መጨመር አስፈላጊ ነው" ማለታቸውንም ሺኑዋ ዘግቧል። አክለውም አገራቸው ከአለም ጋር በምታደርገው ግንኙነት "ግልፅና በራሷ የምትተማመን እንዲሁም ራሷን ከፍ የማታደርግ" ሆና መታየት እንዳለባት አስረድተዋል። ፖርቲው በሚሰራቸው የፕሮፖጋንዳ ስራዎችም መንግሥታቸው "ለቻይና ህዝብ ደስታና ብልፅግና የሚሰራ ነው" የሚለውን አፅንኦት መስጠት ይገባቸዋል ብለዋል። የፕሬዚዳንቱን ንግግር ያጤኑ ተንታኞች መሪው ለመጀመሪያ ጊዜ የቻይናን መገለልና ብቸኝነት ያመኑበት ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ የቻይና ፕሬዚዳንትነትን ስልጣን የጨበጡት በአውሮፓውያኑ 2012 ሲሆን በቁርጠኝነትና በጨቋኝነት ይተቻሉ። በአገሪቱ ላይ ለሚሰነዘሩ ማንኛውም አይነት ተቃውሞዎች የአገሪቱ ዲፕሎማቶች ምላሽ ማጣጣል ወይም ደግሞ በጠብ አጫሪነት ነበር።
news-57088295
https://www.bbc.com/amharic/news-57088295
"በደምቢ ዶሎ ከፍርድ ውጭ የተፈጸመው ግድያ አሳሳቢ ነው"- ኢሰመኮ
በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ በወንጀል የተጠረጠረውን አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን ያሳወቀው በዛሬው ዕለት ግንቦት 4፣ 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነው። ማክሰኞ ዕለት በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ተጠርጣሪ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት ኃይል መገደሉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአካባቢ የመንግሥት ባለስልጣናትም የወጣቱን መገደል አረጋግጠው፤ ወጣቱ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ "በአደባባይ አልተገደለም" ሲሉ አስተባብለዋል። የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ወጣት አማኑዔል 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በመሆኑ 'እርምጃ ተወስዶበታል' በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል። ኮሚሽኑ በመግለጫው ምን አለ? በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ በወንጀል ተጠርጥሯል የተባለው አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል፡፡ ኮሚሽኑ ማንኛውንም ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎችን የሚያወግዝ መሆኑን አስታውቆ ሁሉም የሕግ አስፈፃሚ አካላት ሕጋዊ መንገዶች ብቻ አንዲተገብሩ መልዕክቱን አስተላለፏል፡፡ "ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ ብሏል፡፡ ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ኮሚሽኑ ጠይቋል። ኮሚሽኑ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ ስለ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት ወጣት አማኑዔል 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በመሆኑ 'እርምጃ ተወስዶበታል' በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት በበኩሉ ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲል በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል። የከተማው ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ ላይም ወጣቱ ከመገደሉ በፊት የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል አትሟል። በአካባቢው በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የ"ሸኔ" ቡድን እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። በምዕራብ ኦሮሚያ በተለያዩ አካባቢዎች ቡድኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በማድረስ በተደጋጋሚ ይወነጅላል። በቪዲዮው ላይ ምን ይታያል? በዚህ የፌስቡክ ገጽ ላይ ወጣቱ ከመገደሉ በፊት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ ይታያል። ቪዲዮን እየቀረጸ የሚገኘው ሰው የወጣቱን ስም እና የትውልድ ስፍራውን ይጠይቀዋል። እጁ ወደ ኋላ የታሰረው ወጣት አንገቱ ላይ ሽጉጥ ተንጠልጥሎ ይታያል። በወጣቱ እግር ላይ እና በዙሪያው ደም የሚታይ ሲሆን ልብሱም በጭቃ ተለውሷል። አደባባይ ፊትለፊት የቆመው ወጣት ስሙ አማኑኤል ወንድሙ ከበደ እንደሚባል እና ትውልዱ ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። ወጣቱ ለምን ተገደለ? የከተማው ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ ይህ ወጣት የመንግሥት ባለስልጣናት በመግደል የሚታወቀው "አባ ቶርቤ' የተሰኘው ህቡዕ ቡድን አባል ነበር። ወጣቱ ትናንት በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊትም ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር "በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከቀናት በፊት በደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔትዎርክ ጋዜጠኛ የነበረውን ሲሳይ ፊዳ የገደለው የአባ ቶርቤ ቡድን ነው ሲል አክሏል።
news-56318087
https://www.bbc.com/amharic/news-56318087
የኢትዮጵያ ምርጫ 2013፡ ኦነግ ከምርጫው መውጣቱን ሲያሳውቅ ሌሎች አመራሮች ደግሞ የመሳተፍ ፍላጎት አለን አሉ
በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከጥቂት ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ እንደማይሳተፍ ባወጣው መግለጫ አሳወቀ።
በሌላ በኩል በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው ሌላኛው የግንባሩ ቡድን ግን በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ቢገልፅም ዕጩ ስለማስመዝገቡ ግን ምንም ያለው ነገር የለም። በአቶ ዳውድ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በምርጫው ለመሳተፍ የሚያስችሉት አመቺ ሁኔታዎች አለመኖራቸውን ገልጾ፤ በገዢው የብልጽግና ፓርቲ ዘንድ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ አስፈላጊ መስፈርቶች ለማሟላት ፍላጎት አለመኖሩ ከምርጫው ለመውጣቱ ምክንያት መሆኑን አመልክቷል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ግንቦት 28 2013 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ደግሞ ሰኔ 5 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ያስረዳል። በዚህ አገራዊ ምርጫ እስከ 50 ሚሊዮን መራጮች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳሉ። በበርካታ የአገሪቱ ክፍል ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን የዕጩዎች ምዝገባ በተራዘመባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ የካቲት 30/2013 ዓ.ም ያበቃል። ኦነግ በምርጫው ውስጥ እንደማይሳተፍ ባመለከተበት መግለጫው ላይ ለአገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ተግባራዊ ቢደረጉ ይጠቅማሉ ያላቸውን እርምጃዎችን ጠቅሷል። በዚህም መሠረት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉም የፓለቲካ እስረኞችን እንዲለቀቁ፣ የተዘጉና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጽ/ቤቶች እንዲከፈቱ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ሁሉም ጦርነቶች በማቆም ሁሉን ያካተተ ድርድር እንዲደረግ፣ የአገሪቱ ቁልፍ ተቋማት ገለልተኛና ከአድልዎ የፀዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን ለመፍታት ሁሉም ወገኖች የሚሳተፉበት የፓለቲካ ውይይት ሂደት እንዲጀመር ጠይቋል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ በመግለጫው በምርጫው እንደማይሳተፍ ይግለጽ እንጂ፤ ሌላኛው በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የግንባሩ አካል ግን በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ለቢቢሲ ገልጿል። ባለፈው ዓመት ጥር በኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ግንባሩ በሁለት ወገን በመሆን የተለያዩ አቋሞችን እያንጸባረቀ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም የረጅም ጊዜ የድርጅቱ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ በአንድ ወገን ሆነው ድርጅቱን እየመሩ ሲሆን፤ በሌላ ወገን ደግሞ በአቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመሩ ሌሎች የግንባሩ አመራር አባላት በግንባሩ ስም እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ አስገብተው የነበረ ሲሆን፣ ቦርዱም በግንባሩ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባትና ልዩነት ሁለቱም ወገኖች በሕገ ደንባቸው መሠረት ተነጋግረው እንዲፈቱ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። አቶ አራርሶ ቢቂላ እና አቶ ዳውድ ኢብሳ በአቶ አራርሶ የሚመራው የኦነግ አመራር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዳሉት ግንባሩ ከምርጫው መውጣትን በተመለከተ ውሳኔ ላይ አልደረሰም። "ሊቀ መንበሩ ማለት ድርጅቱ ማለት አይደለም" ያሉት አቶ ቀጀላ፣ ድርጅታቸው የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩበትም በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው አመልክተዋል። "በአሁኑ ጊዜ እንቅፋት የሆነብን የውስጣችን ችግር ነው። የፓርቲው ሊቀ መንበር የሚጠበቅባቸውን እያደረጉ አይደለም" በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ግንባሩ አሁን ባለበት ሁኔታ እንዴት በምርጫው እንደሚሳተፍ አቶ ቀጀላ ሲገልጹ "የድርጅቱን ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተን አዲስ አመራር ለመምረጥ እየሰራን ነው" በማለት ሊቀ መንበሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠሩ ግፊት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኦነግ ባወጣው መግለጫ ላይ ግንባሩ ተዘግተውብኛል ያላቸውን ጽህፈት ቤቶቻቸውን በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ቀጀላ አዲስ አበባ የሚገኘው ጽህፈት ቤቱ በግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር እጅ ስር መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ያሉት የግንባሩ ጽህፈት ቤቶች የተዘጉት በአቅም ማጣት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸውና አለ ባሉት የአስተዳደር ችግር ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል። "ችግር የለም ማለት አይደለም ነገር አብዛኞቹ የራሳችን የውስጥ ችግሮች ናቸው። እኛ የፈጠርናቸው የውስጥ ችግሮችና አመራሮች ተገቢውን አመራር ባለመስጠቱ ነው" በማለት ከምርጫው ተገፍተን ነው የወጣነው የሚለውን ሃሳብ አይቀበሉትም። በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍላጎቱ ውጪ በደረሱበት ጫናዎች ለመውጣት መገደዱን ማስታወቁ ይታወሳል። ኦፌኮ ይህን ውሳኔውን ያሳወቀው በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የሚገኙት ጽህፈት ቤቶቹ መዘጋትና የአመራርና የአባላቱ መታሰርን እንደምክንያት በማስቀመጥ ከመጪው ምርጫ ተገፍቼ ወጥቻለሁ በማለት ነው። ከምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን የገለጹ ፓርቲዎችን በተመለከተ በሚቀርቡ ቅሬታዎች ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ቢቢሲ ከቀናት በፊት የገዢው የብልጽግና ፓርቲ የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳን (ዶ/ር) ጠይቆ ነበር። ቢቂላ (ዶ/ር) እንደሚሉት በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመሳተፍ ታግሎ ከማሻሻል ይልቅ፣ በትንሹም በትልቁም ምክንያት ከምርጫ መውጣት ሕዝቡ የፖሊሲ አማራጭ እንዳያገኝ የሚያደርግ ውሳኔ ነው ብለዋል። በፖለቲካ ፓርቲዎቹ አባላትና ጽህፈት ቤቶች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተመለከተም "እነዚህን የቀረቡ ስሞታዎች በዝርዝር ቀርበው ማጣራት ተደርጎ አብዛኞቹ ክሶች መሰረተ ቢስ ሆነው ተገኝተዋል" ሲሉ ተናግረዋል። ችግሮች አያጋጥሙም ማለት እንደማይቻል የገለጹት ቢቂላ (ዶ/ር)፤ እነዚህንም ለማረምና ለማስተካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና የአስተዳደር መዋቅሩ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
news-46589154
https://www.bbc.com/amharic/news-46589154
ብሄራዊ ባንክ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር የግሉን ዘርፍ ለማገዝ ስምምነቶችን አደረገ
የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ፍሊፕ ለ ዌሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው የስድስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወቅት ብሄራዊ ባንክ ከኮርፖሬሹ ጋር የግሉን ዘርፍ ለማገዝ ስምምነቶችን አደረገ ነው።
የመጀመሪያው ስምምነት ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለተመረጡ የኢትዮጵያ ባንኮች በዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ መርኃ ግብር አማካይነት ድጋፍ የሚያደርግበት ሲሆን ሁለተኛው ስምምነት ደግሞ ኮርፖሬሽኑ ለኢትዮጵያ በብር ብድር የሚያቀርብበት ነው ተብሏል። "የዛሬው ስምምነት ኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ ዕድገት ያላትን ቁርጠኛነት ይጠቁማል" ሲሉ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተናገሩት የፋይናንስ እና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ናቸው።አቶ አህመድ ጨምረውም መንግሥት የፋይናንስ ዘርፉን ለማሳደግ ከፖሊሲ ምርመራ አንስቶ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ በበኩላቸው ስምምነቶቹ ኢትዮጵያ ላጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግር የመፍትሄ አካል ከመሆኑም በላይ ለግሉ ዘርፍ ፋይናንስ በማቅረብ ረገድ ከፍ ያለ ሚና አለው ብለዋል። • ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በቅዳሜው ውይይት ላይ ምን አሉ? • ከአፋር እስከ ዲሲ፤ በዚህ ሳምንት የሚጠበቁ ክስተቶች • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ለግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ምንጩን ማብዛት አለብን፤ ይህ የዚህ ስምምነት አንደኛው አካል ነው" ብለዋል ገዥው።ከዚህም በተጨማሪ "የግሉን ዘርፍ ባካተተ ሁኔታ የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ አውድ እንዴት ሊሠራ እንደሚችል ጥናት እያካሄድን ነው" ሲሉ የባንኩ ገዥ አክለው ተናግረዋል።ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) በዓለም ባንክ ሥር የግሉን ዘርፍ የሚመለከት ክንፍ ሆኖ የተቋቋመው እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ አጋማሽ ሲሆን በማደግ ላይ ባሉ አገራት የግሉን ዘርፍ ዕድገት የማበረታትን ሥራ ይከውናል። አይኤፍሲ አባል ሆነው በመሠረቱት አገራት ባለቤትነት የተያዘ እና የሚተዳደር ተቋም ነው። ፈረንሳይዊው ፍሊፕ ለ ዌሩ እ.ኤ.አ ከመጋቢት 2016 አንስቶ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።ሥራ አስኪያጁ በኢትዮጵያ የስድስት ቀናት ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር የተገናኙ ሲሆን የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክንም ጎብኝተዋል። ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ እርስ በእርስ እንዲተማመኑ እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የንግድ ሥራ ክንውን የሚያቀላጥፉ የማሻሻያ እርምጃዎችን ለመውሰድ በኮሚሽኑ እና በኮርፖሬሽኑ መካከል የትብብር ስምምነት ላይ መደረሱንም አቶ ፍፁም አክለው ገልፀዋል።ሥራ አስጂያጁ በልጅነታቸው ወቅት አዲስ አበባ በሚገኘው የሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከተታትለው የነበረ ሲሆን በቆይታችው ወቅት ትምህርት ቤቱን እንደጎበኙ ዛሬ ሰኞ ቀትር ላይ ለጋዜጠኞች ባደረጉት ገለፃ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ባንኮች ከተለያዩ የዓለም አገራት ባንኮች ጋር የብድር ስራን በሚያከናውኑበት ወቅቅ በቂ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ካልተገኘ በስራው ላይ ችግሮች እንደሚፈጠሩ ያስረዱት የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ፤ የዛሬው ስምምነት አይኤፍሲ ዋስትና እንደሚሰጥ የሚያረጋግጥ በመሆኑ፤ ይህም የኢትዮጵያ ባንኮች ከውጭ አገራት አቻዎቻቸው ጋር ያላቸውን ስራ የሚያቀል ነው ብለዋል። "ሲጠቃለሉ ሁለቱ ስምምነቶች ተጨማሪ ዶላር ላገሪቱ ያስገኛሉ፤ ለግሉ ዘርፍ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ያመጣል፤ ላገጠመን የውጭ ምንዛሬ ችግር ዋስትና ይሰጣል" ሲሉ ተናግረዋል።
news-53807025
https://www.bbc.com/amharic/news-53807025
በትግራይ መራጮችን ለመመዝገብ የሞባይል መተግበሪያ ጥቅም ላይ ይውላል ተባለ
በትግራይ መራጮችን ለመመዝገብ የሞባይል መተግበሪያ ጥቅም ላይ ይውላል ተባለ።
የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ‘ሃራ ስርዓት ምህዳር’ ከሚሰኝ ድርጅት ጋር መራጮች የሚመዘገቡበት እና ድምጻቸውን የሚሰጡበት መተግበሪያ በጋራ እያበለጸጉ ይገኛሉ። ይህ መተግበሪያ ለመጀመርያ ጊዜ ትናንት በመቀለ ሙከራ ተደርጎበታል። መራጮች ሞባይል ላይ በሚጫነው መተግበርያ [አፕ] የሚመዘገቡ ሲሆን፤ አንድ መራጭን ለመመዝገብ ከ30 እስከ 50 ሰከንዶች ብቻ በቂ መሆናቸውን የ‘ሃራ ስርዓት ምህዳር’ ወኪል ኃ/ስላሴ ሊላይ ተናግረዋል። መራጮችን ለመመዝገብ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደማያስፈልገው የተጠቀሰው መተግበሪያ፤ መራጮች ድምጽ እንዲሰጡ እንዲያስችል ተደርጎ የተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል። የመተግበሪያው የድምጽ አሰጣጥ ስርዓት ደግሞ በሚቀጥለው እሁድ ሙከራ ይደረግበታል ሲሉ አቶ ኃ/ስላሴ ሊላይ ተናግረዋል። ይህ መተግበሪያ በምርጫ ዕለት አንድ መራጭ ብቻውን ወደ ምስጢራዊ የድምጽ መስጫ ቦታ ገብቶ ከወረቀት ንክኪ ነጻ በሆነ መልኩ በታብሌት በመታገዝ ‘በዲጂታል ኮሮጆ’ ድምጹን እንዲሰጥ ያስችላል ሲሉ አቶ ኃ/ስላሴ ተናግረዋል። በትግራይ የሚካሄደው ክልላዊ ምርጫ ጳጉሜ 4 እንዲሆን መወሰኑን የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል። የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው የግዜ ሰሌዳ መሠረት የመራጮች ምዝገባ ከነሐሴ 15-22 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፤ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የምርጫ ቅስቀሳ ደግሞ ነሐሴ 29 ይጠናቀቃል ተብሏል።
news-44234740
https://www.bbc.com/amharic/news-44234740
ለረጅም ሰዓት ስክሪንን መጠቀም ለካንሰርና ለልብ ህመም ይዳርጋል
ረጅም ሰዓት ስክሪን ላይ እየተመለከቱ መቆየት ከካንሰርና ከልብ ህመም ግንኙነት እንዳለው አዲስ የወጣ ጥናት አመለከተ።
የግላስኮው ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እንዳሉት በትርፍ ሰዓታቸው ሳይቀር በቴሌቪዥንና በኮምፒዩተር ስክሪኖች ላይ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ 39 ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን መረጃ ተንትኗል። በጥናቱ መሰረትም በስክሪኖች ላይ ረጅም ሰዓት የሚያጠፉ ሰዎች አነስተኛ ቆይታ ካላቸው ሰዎች ጋር ሲነፃፀር የጤና ሁኔታቸው በእጥፍ የተዳከመ ሆኖ አግኝተውታል። ከጥናቱ መሪዎች አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ጃሰን ጊል እንዳሉት የጥናቱ ግኝት የህብረተሰብ ጤና መመሪያ ላይ ለውጥን ሊያስከትል ይችላል፤ ለልብ ህመም ሲዳርግ ሞትንም ያፋጥናል ብለዋል። "የየሰዉ ረጅም ሰዓት የመቀመጥ ልማድ ሊለያይ ይችላል፤ ነገር ግን ከስክሪን ላይ የምናሳልፈው ጊዜ ከመጠን ያለፈ ከሆነ በአጠቃላይ ጤናን እንደሚጎዳ አመላክቷል ብለዋል። የሰውነት አቋም፣ ጥንካሬና የሰውነት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። የጥናቱ ውጤትም ለተጠቀሱት የጤና እክሎች ከሚዳርጉ ሌሎች ምክንያቶች ማለትም ሲጋራ ማጨስ፣ የአመጋገብ ሥርዓት እንዲሁም ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ነፃ ሆኖ የተካሄደ ነው ። የጥናቱ ፀሃፊ ዶክተር ካርሎስ በበኩላቸው "ዝቅተኛ የሰውነት አቅም፣ ጥንካሬ፣ የሰውነት አቋምና የሰውነት እንቅስቃሴ ያላቸው ሰዎች ረጅም ሰዓት የመቀመጥ ልምዳቸውን በመቀነስ ቀድመው ሊከላከሉት ይችላሉ'' ሲሉ መክረዋል።
news-42162597
https://www.bbc.com/amharic/news-42162597
ጥበብን በወር-አበባና በአጽም
የወር አበባ ደም እንደ ፀያፍና ነውር ተደርጎ በሚታይበት ሀገር ታዋቂዋ ሰዓሊ ምህረት ከበደ በወር አበባዋ የሳለችው ስዕል አነጋጋሪና ጥያቄንም ፈጥሯል።
ይህ ፕሮጀክቷ ለሁለት አመታት እንደቆየ የምትናገረው ምህረት የወር አበባዋንም በመጠቀም ስዕሎቿን እንደሳለች ትናገራለች። የወር አበባ ከቆሻሻነትና እርግማን ጋር እንደሚያያዝ የምትናገረው ምህረት በአጠቃላይ መወገድ ያለበትና አላስፈላጊም ነገር ተደርጎ ይታያል ትላለች። " የወር አበባ ቆሻሻ ወይም እርግማን ከሆነ የሰው ልጅ እዚህ የመጣበትን ሂደት ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል" ትላለች። "ሀሳቤን ብቻ ሳይሆን እኔነቴም የሰፈነበት ስራ ነው" በማለት ምህረት ትናገራለች። በአጠቃላይ ፕሮጀክቷ አባታዊ ስርዓት (ፓትርያርካል) በሆነው አለም ላይ ሴት መሆን ምን ማለት ነው የሚል አንድምታ እንዳለው ትናገራለች። "የወር አበባ ደሜን መጠቀሜ በራሴ መልዕክት አለው" በማለት የምትናገረው ምህረት " ሴቶች በዚህ ስርአት ላይ እንዴት ነው የሚኖሩት፤ በምንስ መንገድ ነው የሚታዩት? ለሚሉት ጥያቄዎችም በታሪክ ውስጥ ምንም አይነት ሚና እንደሌለን ተደርገን ነው የምንታየው። ይሄም ስራየ ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ይሞክራል" ትላለች። በማህበረሰቡ ውስጥ የወር አበባ ደም የሚታይበትን መንገድም ለመቀየርም ስትነሳ ፈታኝ እንደሆነ ከመጀመሪያው ተሰምቷታል። "በሃገራችን የወር አበባ ደም የምታይ ሴት የዕምነት ቦታዎች ላይ መገኘት እንደሌለባት ማህበረሰቡ ያስባል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ደግሞ የወር አበባ ደም እያዩ ያሉ ሴቶች"ንፁህ" እስኪሆኑ ከማህበረሰቡ ተነጥለው ለብቻቸው የሚቆዩበት ሁኔታም አለ።" የምትለው ምህረት የሷም አስተዳደግ በዚህ ተፅእኖ ስር መሆኑ "ሴት ማለት ምንድን ናት" የሚለውን ጥያቄ በተደጋጋሚ እንድትጠይቅ አድርጓታል። "ወላድነት" (ፈርቲሊቲ) የሚለው ሀሳብ በዚህ ጥበብ ስራዋ ዋና ማዕከል ሲሆን የጥበብ ስራውም አቀራራረብ በትልቅ ሰሀን ውስጥ አፈር ሞልታ፣ እንቁላል እንዲሁም በወር አበባ ደም የተሳሉ 40 ስዕሎቿን አሳይታለች። ይህንንም ስራዋን በሞደርን አርት ሙዚየም ገብረ-ክርስቶስ ደስታ ማዕከል 'ፋና ወጊ' በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን በዚህ አውደ ርዕይም ላይ የሌሎችም አርቲስቶች ስራዎች አብሮ ቀርቧል። ይህ ስራዋ ቀለል ተደርጎ አልታየም ብዙ ያውቃሉ ብላ በምትጠብቃቸው ወንድ አርቲስቶች መካከል ራሱ "ለምን እጇን ትጨብጠዋለህ? የሚሉ አስተያየቶች መምጣታቸው ማህበረሰቡ ውስጥ ስር ሰዶ የገባውን "ንፁህ አለመሆን" የሚለውን ሃሳብ በግልፅ ያሳየኝ ነው" ትላለች። የምህረት ብቻ ሳይሆን በዚሁ አውደ-ርዕይ ላይ ስራዋን አቅርባ የነበረው ሄለን ዘሩም በእናቷ አፅም የሰራችው የጥበብ ስራ አነጋጋሪ ነበር። "ይከሰሱ" የሚሉ ወሬዎችም እንደነበሩ ሁለቱም ይናገራሉ። የሁለቱም ሰዓሊዎች ስራዎች የተከተሉት ዘይቤ በአለም ላይ በአሁኑ ዘንድ ታዋቂነትን እያተረፈ ያለውን 'ፐርፎርማንስ አርት' ወይም ሰውነትን ወይም የሰውነትን አካል እንደ አንድ የጥበብ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም ማለት ነው። ከተለመደው የስዕል ጥበብ በመውጣትም የማሀበረሰቡን እሳቤ፣የተለያዩ ርዕዮተ አለማትንም ሆነ ሌሎች ሀሳቦችን ማህበረሰቡንም በቀጥታ በሚያሳትፍ መልኩ በአርቲስቶች የሚሰራ የጥበብ አይነት ነው። ከነዚህም ውስጥ የሚያስደነግጡና የሚሰቀጥጡ ስራዎችም በዓለም ላይ ታይተዋል። ከጥቂት አመታት በፊት በሩሲያው አርቲስት ፔትር ፓቭልንስኪ ሩሲያ ውስጥ ያለውን ጭቆና ለማሳየት ብልቱን ከወለሉ ጋር ማጣበቁ ለብዙዎች ከሰቅጣጭም በላይ ነው። ከጥቂት አመታት በፊት ነበር አዲስ አበባን መልሶ በማልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን መቃብር የተቀበሩ ሰዎችንም ቆፍረው እንዲያወጡ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ትዕዛዝ የመጣው። ይሄም ሁኔታ በብዙዎች ዘንድ አሳዛኝ ትዝታዎችን እንዲሁም የተረሱ ሀዘኖችን ቀስቅሷል። በዚሁም አጋጣሚ ነው ሄለን ዘሩ የእናቷንም መቃብር አውጥታ ወደ ሌላ ቦታ እንድትቀብር የተነገራት። እናቷን በህፃንነቷ ብታጣም መቃብሯን እየተመላለሰች እንዳላየች ሄለን ትናገራለች። እናቷም ከሞተች ከአስራ አምስት አመታት በኋላ ወደ መቃብሯ መመለስ ብቻ ሳይሆን አፅሟን አውጥቶ መቅበር የሷ ኃላፊነት ነበር። ቁፋሮው ሲጀመር ቀላል እንዳልነበር የምትናገረው ሄለን " የየቀኑ ትግልም ነበር" ትላለች ሁኔታው ከአዕምሮዋ ከምታስበው በላይ ስለነበር መቀበልም ከብዷት ነበር። ሁኔታውንም ቀለል ለማድረግ ከቁፋሮው ጀምሮ መቅረፅ ጀመረች። በዚህም አጋጣሚ ነው ይህንን ማሰብ የሚከብድ ጉዳይ ወደ ጥበብ ስራዎች ለመቀየር ያሰበችው። የመጀመሪያው ከቁፋሮው ጀምሮ እስከተቀበሩበት ደብረ-ዳሞ ገዳም ያለውን ጉዞ በቪዲዮ የመቅረፅ ስራ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከልጅነት ትዝታዎቿ በመቀንጨብ ወደ ጥበብ ስራ የቀየረችው ነው። በዚህም ስራዋ እንደ ሬሳ ተገንዛ እናቷ ከ15 አመት በላይ በቆየችበት የመቃብር ስፍራ ውስጥ ትተተኛለች እንዲሁም ትንቀሳቀሳለች። የመቃብር ስፍራውም በቀይ ዣንጥላ ተከቦ ነበር። ቀይ ዣንጥላ እንደ ምልክትነት እንደተጠቀመችው የምትናገረው ሄለን "እናቴ ከመሞቷ በፊት ከሆስፒታል ስትመጣ ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁዋት ቀይ ዣንጥላ ይዛ ነበር" ትላለች። ይህ "የልብ ስብራት" የፈጠረባትን ሂደትም የጥበብ ስራዋ ቀለል እንዳደረገላት ትናገራለች። "የእናቴ መቃብር ሲከፈት ሀዘኑም እንደገና አገረሸ። በምን መንገድ ነው እንደገና የናቴን ቀብር ማየቱ ለኔ ብቻ ሳይሆን በጊዜው የሚወዷቸውን ሰዎች መቃብር አንሱ ለተባሉት የሚነካ ጉዳይ ነው" ትላለች። ይህንን ጥልቅ ስሜት በስዕልም ሆነ በተለመዱ የጥበብ አይነቶች ማሳየቱ በቂ ስላልነበር ይህንን ዘዴ እንደመረጠች ትናገራለች። በአውደ-ርዕዩ ላይም 15 ሜትር በከሰል የሳለችው ስዕል እንዲሁም 'ፐርፎርማንስ ጥበብ' (ትርኢት) ያሳየችበት ቪዲዮና፣ ሌላኛው እስከ ደብረዳሞ ቀብር ድረስ የነበረው ቪዲዮ ደግሞ በሬሳ ሳጥኑ መሰረት ዲዛይን የተደረገ ሳጥን ውስጥ ታይተዋል። በተለይ ሳጥኑ የመቃብር አይነት ዲዛይን ስለነበረው ለብዙዎች ከፍተኛ የስሜት መናወጥ እንደፈጠረ ሄለን አልደበቀችም። " በጣም የተደናገጡና ብዙዎችም አልቅሰዋል" ትላለች። ሁለቱም አርቲስቶች የጥበብ ገደብ የለውም ብለው የሚያምኑ ሲሆን የፐርፎርማንስ ጥበብም በቀጥታ ከተመልካቹ ጋር እንዲገናኙ ዕድል እንደሰጣቸው ይናገራሉ።
news-48552539
https://www.bbc.com/amharic/news-48552539
ኔይማር ደፍሮኛል ብላ የከሰሰችው ሴት ብራዚል ቲቪ ላይ ቀርባለች
ዓመቱ የኔይማር አይመስልም፤ ብዙዎችን እጅ በመዳፍ ባስያዘ ገንዘብ ከባርሴሎና ወደ ፒኤስጂ ያቀናው በጉዳት ምክንያት በርካታ ጨዋታዎችን መጫወት ሳይችል ቀርቷል።
አልፎም ማንቸስተር ዩናይትድ ክለቡ ፒኤስጂን ከቻምፒዮንስ ሊግ ሲያሰናብት ፍትሐዊ ያልሆነ ፍርድ ተሰጥቷል ብሎ በመቃወሙ በአውሮጳ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ቅጣት ተጥሎበታል። የብራዚል አሠልጣኝ የሆኑት ቲቶ አምበልነቱን ከ27 ዓመቱ ኔይማር ነጥቀው ለቡድን አጋሩ የሰጡት በያዝነው ወር ነው። • ኔይማር የቀረበበትን ወሲባዊ ትንኮሳ ክስ አጣጣለ ዕለተ ረቡዕ ሃገሩ ብራዚል ከኳታር ጋር በነበራት ጨዋታ ጉዳት ደርሶበት ከሜዳ ሲወጣ ለኮፓ አሜሪካ እንደማይደርስ ታውቋል። አሁን ደግሞ ኔይማር አስገድዶ ደፍሮኛል ያለች ሴት ብራዚል ውስጥ ቲቪ ላይ ቀርባ ደረሰብኝ ያለችውን በደል አሰምታለች። ናጂላ ትሪኒዳዴ የተሰኘችው ይህች ሴት ባለፈው አርብ ነበር ኔይማር አስገድዶ ደፍሮኛል ስትል ክስ ያሰማችው። ተጨዋቹ ክሱ ሃሰት ነው፤ እንደውም እነሆ በዋትስአፕ ያወራነው ሲል ከከሳሹ ጋር የተለዋወጠውን መልዕክት በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቹ ይፋ አድርጓል። ከሳሿ ኔይማር ፓሪስ የሚገኝ አንድ ሆቴል ጠርቶኝ ነው የደፈረኝ ትላለች። መጀመሪያ ግን በፈቃደኝት እርሱ ወደ ሚገኝበት ሆቴል እንደደሄደች በመጠቆም። • የሳዑዲውን ልዑል መስሎ ሲያጭበረብር የነበረው ግለሰብ ታሰረ የቴሌቪዥን ዝግጅቱ አቅራቢ 'የደረሰብሽ ጥቃት ነው ወይስ አስገድዶ መድፈር?' ሲል ለጠየቃት ምላሽ የሰጠችው ትሪኒዳዴ 'ጥቃትትም ደርሶብኛል፤ ተደፍሬያለሁም' ስትል መልሳለች። ኔይማር በፅሁፍ መልዕክት ልውውጣቸው ከምታውቀው በተለየ በጣም ግልፍተኛ ሆኖ እንደጠበቃት ተናግራለች። የጠባቸው መንስዔም 'በኮንዶም ወይስ ያለኮንዶም?' እንደሆነ አልሸሸገችም። ኔይማርም ሆነ ወኪሉ እንዲሁም አባቱ ውንጀላው ውሃ አያነሳም፤ ሃሰት ነው ሲሉ አጣጥለውታል። ኔይማር ከአስገድዶ መድፈሩ ክስ በተጨማሪ ከከሳሿ ጋር ያደረገውን የፅሁፍ ልውውጥ ያለፈቃዷ በመለጠፉ ሊከሰስ እንደሚችል ይጠበቃል። • የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት
news-55657687
https://www.bbc.com/amharic/news-55657687
ኮሮናቫይረስ፡ አፍሪካ 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' የኮቪድ-19 ክትባት አገኘች
አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ ተገለፀ።
አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል። ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም። በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው። በደቡብ አፍሪካ አዲሱ የኮቪድ -19 ዝርያ ስጋት የፈጠረ ሲሆን፤ በርካታ ሰዎችም በዚሁ ቫይረስ እየተያዙ ነው። "በዚህ ምክንያት በጥረታችን ለጊዜው 270 ሚሊየን ዶዝ [መጠን ] ክትባት ከሦስት የክትባት አቅራቢዎች ማለትም ፋይዘር፣ አስትራዜኔካ[ በሕንድ ሴረም ኢንስቲቲዩት በኩል] እና ከጆንሰን እና ጆንሰን አግኝተናል" ብለዋል ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ረቡዕ ዕለት በሰጡት መግለጫ። ቢያንስ 50 ሚሊዮን 'ዶዝ' [መጠን] ክትባቶችም ወሳኝ በሆኑት ከሚያዚያ እስከ ሰኔ ባሉት ወራት እንደሚቀርቡ ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል። በተጨማሪም ቀጠናው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት ክትባቱን ማዳረስ አላማ ካደረገው ግሎባል ኮቫክስ 600 ሚሊየን ዶዝ [መጠን] እንደሚጠብቅ ተገልጿል። ይሁን እንጂ በአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል የሳይንስ አማካሪ የሆኑት ኒካሴ ደምቢ "አማራጭ መፍትሔ ስላለን ደስተኞች ነን" በማለት ባለሥልጣናት አሁንም ዝርዝር ጉዳዮችን እየተጠባበቁ መሆኑን ለኤአፍፒ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ፕሬዚደንት ራማፎሳ እንዳሉት ባለሥልጣናት በኮቫክስ ጥረት በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት የመጀመሪያ ዓመት አጋማሽ የተለቀቀው ክትባት የጤና ባለሙያዎችን ለመከተብ ብቻ በቂ ነው የሚል ስጋት አላቸው። እያንዳንዱ ሰው ሁለት ዶዝ ክትባት መውሰድ ያለበት ሲሆን 1.3 ቢሊዮን ሕዝብ ያለውን አህጉር አፍሪካ ለመከተብ 2.6 ቢሊየን ክትባት ያስፈልጋል። "እነዚህ ጥረቶች፤ የኮቫክስ ጥረቶችን ለመደጎም እና ብዙ የክትባት ዶዞችን በተቻለ መጠንና ፍጥነት በመላው አፍሪካ እንዲዳረስ ለማረጋገጥ ነው" ሲሉ ፕሬዚደንቱ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አብራርተዋል። አፍሪካ እስካሁን ከ3 ሚሊዮን በላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡባት ሲሆን 75 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችም በበሽታው ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል። በአንጻሩ ደግሞ አሜሪካ 23 ሚሊዮን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችና ከ383 ሺህ በላይ ሞት ተመዝግቦባታል። የዓለም አገራት ክትባቱን ለመግዛትም ጥድፊያ ላይ ናቸው። ሃብታም አገራትም አብዛኛውን በክትባት አምራቾች የቀረበውን ክትባት በመግዛታቸው ክስ ይቀርብባቸዋል።
news-51082200
https://www.bbc.com/amharic/news-51082200
በስሪ ላንካ 361 ዝሆኖች ተገድለዋል ተባለ
ስሪ ላንካ በታሪኳ እጅግ ከፍተኛው በተባለ የዝሆኖች ሞት በፈረንጆቹ 2019 361ዱን እንዳጣች አንድ የአካባቢ ተቆርቋሪ ቡድን አስታወቀ።
ስሪ ላንካ ነጻነቷን ካገኘችበት የፈረንጆቹ 1948 ጀምሮ እንዲህ አይነት የዝሆኖች ሞት ታይቶ አይታወቅም ያለው ቡድኑ ለአብዛኛዎቹ የሞታቸው ምክንያት ሰዎች እንደሆኑ ገልጿል። በስሪ ላንካ እስከ 7500 ሚደርሱ ዝሆኖች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን እነሱን መግደል በሀገሪቱ ሕግ መሰረት ወንጀል ነው። ዝሆኖቹ ምግብና ውሀ ፍለጋ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወደ ሰዎች መኖሪያ አካባቢ ይገባሉ። • የምርምሩን ዝሆን የገደሉት አዳኞች ፈቃዳቸውን ተነጠቁ • የሩስያ ላሞች ጭንቀት መቀነሻ ቴክኖሎጂ ተገጠመላቸው በገጠራማዊቱ ስሪ ላንካ የሚኖሩ ዜጎች ደግሞ ዝሆኖቹ ሰብላቸውን ስለሚያበላሹባቸው እንደ ጠላት ነው የሚመለከቷቸው። 'ሳጂዋ ቻሚካራ' የተባለው የአካባቢ ተቆርቋሪ ቡድን ለቢቢሲ እንደገለጸው ባለፈው ዓመት ከሞቱት 361 ዝሆኖች መካከል እስከ 85 በመቶ የሚደርሱት የተደገሉት በሰዎች ነው። የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አጥሮችን፣ መርዝና ፈንጂዎችን በመጠቀም ዝሆኖቹን የሚገድሉ ሲሆን አንዳንዶቹም ለምግብነት እንደሚጠቀሟቸው ቡድኑ ገልጿል። ባለፈው መስከረም ወር ላይ የሀገሪቱ ሃላፊዎች እንደገለጹት ሰባት የሚሆኑ ዝሆኖች 'ምርት አበላሹ' በሚል ምክንያት በአካባቢው ነዋሪዎች ተመርዘው እንዲሞቱ ተደርገዋል። • ያልተፈላ ወተት ለጤና ጠቃሚ ነው ጎጂ? ቢቢሲ የዘርፉ ባለሙያዎችን አነጋግሮ ባገኘው መረጃ መሰረት በስሪ ላንካ ገጠራማ ክፍሎች ጫካዎች እየተመነጠሩ አዳዲስ የእርሻ ማሳዎች ስለሚዘጋጁ ዝሆኖቹ ተፈጥሯዊ መኖሪያቸውን ለቅቀው እንዲሄዱ እየተገደዱ ነው። በዚህም ምክንያት ለዝሆኖቹ ምግብና ውሃ ማግኘት እጅግ ከባድ ሆኖባቸዋል ተብሏል።
news-48545493
https://www.bbc.com/amharic/news-48545493
በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የተፈጠረው አለመረጋጋት ለቀናት መቀጠሉ ተሰማ
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ''በማንነታችን ምክንያት ጥቃት እየተሰነዘረብን ነው'' ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ብሄር ተኮር ጥቃቶች እየተሰነዘሩብን ነው የሚሉት ተማሪዎቹ፤ በዩኒቨርሲቲው የተከሰተው አለመረጋጋት ለቀናት መዝለቁን ተናግረዋል። ''ወንድ ተማሪዎች በአንድ ህንጻ ሴት ተማሪዎችም ደግሞ በሌላ ህንጻ ውስጥ ሆነን በአንድ ቦታ እንድንቆይ ተደርገናል። ምግብ እንኳን ከበላን ዛሬ ሦስተኛ ቀናችን ነው። ችግራችሁ ምንድነው ብሎ የጠየቀን አካል እንኳ የለም'' በማለት ስሟ እንዳይጠቀስ የጠየቀች የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለቢቢሲ ተናግራለች። በዩኒቨርሲቲው ተከስቶ በነበረ ግጭት ጉዳት የገጠማቸው ተማሪዎችም ከህንጻው እንዳይወጡ ስለመደረጋቸው ተማሪዎቹ ይናገራሉ። • የሕክምና ባለሙያው ታካሚዎችን በመግደል ዘብጥያ ወረደ • የአምልኮ ቦታ የተነፈጉት የአክሱም ሙስሊሞች • የቱሉ ፈራ ደጋግ ኢትዮጵያዊ ልቦች ከዩኒቨርሲቲው ሸሸቶ ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ የሚናገረው ሌላው ተማሪ፤ በዩኒቨርሲቲው የተሰማሩ የፌደራል ፖሊስ እና የአማራ ክልል ጸጥታ አስከባሪ ኃይሎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ በተማሪዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም አልቻሉም ይላል። ''እነሱ [የጸጥታ አስከባሪዎች] ምንም ማድረግ አልቻሉም። ተማሪዎችን እንደበድባለን ብለው ሲነሱ ይማጸኗቸዋል እንጂ ምንም አይነት እርምጃ አይወስዱም። በቁጥጥር ሥር ቢያውሏቸውም ወደ ህግ አካል አያቀርቧቸውም'' ይላል። በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አለመረጋጋት ከተከሰተ ሁለት ሳምንታት የተቆጠሩ ሲሆን ከባለፈው እሁድ ወዲህ ግን ግጭቱ እየጠነከረ እንደመጣ ተማሪዎቹ ያስረዳሉ። የግጭቱ መነሾ ይህ ነው ሊባል እንደማይችል የሚናገሩት ተማሪዎቹ፤ በአንድ ብሔር ተወላጅ ተማሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸም እንደተጀመረ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ያስረዳሉ። ''እየደረሰብን ያለውን ጥቃት ሊያስቆምልን የሚችል አካል ባለመገኘቱ ሰኞ ዕለት ምን ማድረግ እንደሚኖርብን ለመነጋገር ውይይት ማድረግ ጀመርን'' በማለት ኢላማ ሆነናል ካሉት ተማሪዎች አንዱ ያስረዳል። ስብሰባ እያደረጉ በሚገኙበት ወቅት የተደራጁ ተማሪዎች ድንጋይ መወርወር መጀመራቸውን ይሄው ተማሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። የደብረ ብርሃን ከተማ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ምክትል ኮማንደር ዘነበ ገብሩ በበኩላቸው ''በሁለት ሰዎች መካከል የተፈጠረ ግጭት ወደ ቡድን ጸብ ተሸጋገረ'' በማለት የግጭቱን መንስዔ ይገልጻሉ። የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች ካለባቸው ስጋት የተነሳ ምግብ ለመመገብ ወደ ካፍቴሪያ እየሄዱ አይደለም ሲሉም የተማሪዎቹን ሀሳብ ትክክለኛነት ይናገራሉ። ምክትል ኮማንደር ዘነበ በተማሪዎቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው እና የሚገኙባቸው ህንጻዎችን በጸጥታ ኃይሎች ተከቦ እንደሚገኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ''ድንጋይ ሲወረውሩ የተያዙ 10 ተማሪዎች ስማቸው በዩኒቨርሲቲው ከተመዘገበ በኋላ ምክር ተሰጥቷቸው ተለቀዋል። አሁን በእስር ላይ የሚገኝ ተማሪ የለም'' በማለት ያስረዱት ኮማንደሩ፤ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ከግቢው ውጪ ያሉ አንዳንድ አካላትም ጥቃት አድርሰውብናል የሚለውን የተማሪዎች ክስ በፍፁም ሲሉ ያጣጥላሉ። ''ከግቢ ውጪ መጥቶ ጥቃት የሰነዘረ በፍጹም የለም'' አክለውም ''በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ይገኛሉ። ከውጪ ገብቶ ችግር መፍጠር የሚፈልግ ሊኖር ይችላል። እስካሁን ግን በእኛ በኩል አልተረጋገጠም። የኦሮሞ እና የአማራ ብሄር ተወላጆች እንዲጋጩ የሚፈልግ አካል እንዳለ ይሰማናል'' በማለት ምክትል ኮማንደሩ ይናገራሉ። ያነጋገርናቸው ተማሪዎች በዚህ ሁኔታ ትምህርት መቀጠል እንደሚከብዳቸው ተናግረው ወደ ቀያቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች ስበሰባ ላይ ነን በማለታቸው ሃሳባቸውን ማካተት አልቻልንም። በዩኒቨርሲቲው በተፈጠረው ግጭትና ውጥረት ትምህርት የተቋረጠ ሲሆን አመሻሽ ላይ ባገኘነው መረጃ መሰረት ዛሬ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ሲያደረጉ መዋላቸውን ሰምተናል።
news-42602951
https://www.bbc.com/amharic/news-42602951
በታንዛንያ አርግዘው የተገኙ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ታሰሩ
በደቡባዊ ታንዛኒያ ታንዳሂምባ በተሰኘ አካባቢ አምስት ተማሪዎች አርግዘው በመገኘታቸው ከነቤተሰባቸው መታሰራቸውና በመጨረሻ ግን በዋስ መለቀቃቸው ተሰማ።
የህፃናት መብት ተከራካሪዎች ደግሞ እርምጃው ያልተገባ ነው በማለት ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ናቸው። ታዳጊዎቹ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ሊታሰሩ የቻሉት በአካባቢው ኮሚሽነር ትእዛዝ ነበር። የፆታ እኩልነትና የህፃናት መብት ተከራካሪዎች ህፃናቱ እንዲታሰሩ ትእዛዝ የሰጡ ሃላፊዎች ተጠያቂ መሆን አለባቸው እያሉ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ ሃላፊዎቹ ታዳጊዎቹን ያስረገዙ ወንዶችን ሳያስሩ ተጠቂዎቹን ለእስር መዳረጋቸው ነው። ሞሃመድ አዚዝ የተባሉ አንድ የአካባቢው የመንግሥት ሃላፊ እንደገለፁት ታዳጊዎቹን ያስረገዙ ወንዶች እየተፈለጉ ነው። ሃላፊው አዚዝ እንዳሉት ታዳጊዎቹ ከነወላጆቻቸው እንዲታሰሩ የተደረገው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢው እየጨመረ ያለውን የታዳጊ ሴቶች እርግዝናን የመከላከል እርምጃ አካል ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ባለፈው ሁለት ዓመት ብቻ በአካባቢው 55 ተማሪዎች አርግዘዋል። ችግሩ እየተባባሰ በመምጣቱ የፖለቲከኞችንም ትኩረት እየሳበ ነው። ባለፈው ዓመት የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ የወለዱ ተማሪዎች ዳግም ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ መፈቀድ የለበትም የሚል አስተያየት በመስጠታቸው ትችቶች ተሰንዝረውባቸው ነበር። የታዳጊዎች እርግዝና በደቡባዊ ታንዛኒያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ሲሆን የአገሪቱ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው በየዓመቱ በእርግዝና ምክንያት በርካታ ታዳጊዎች ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ። የደቡብ ታንዛኒያ ክልል ኮሚሽነር ጊላሲየስ ባያንክዋ ለቢቢሲ እንደገለፁት ታዳጊዎቹም ላይ ሆነ ወላጆቻቸው ላይ ምንም አይነት ክስ አይመሰረትም። በሌላ በኩል ደግሞ የታዳጊዎች እርግዝናን ለመከላከል ክልሎች ተገቢ ነው ያሉትን እርምጃ የመውሰድ ስልጣን እንዳላቸውም ሃላፊው ተናግረዋል።
news-53568625
https://www.bbc.com/amharic/news-53568625
ዩዌሪ ሙሴቪኒ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ ሆነው ቀረቡ
የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ፓርቲያቸው በመጪው የፈረንጆች ዓመት ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ በማድረግ እንደመረጣቸው አስታወቀ።
የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ ናሽናል ሪዚስታንስ ሙቭመንት ለ2021 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዩዌሪ ሙሴቪኒን እጩ አድረጎ ማቅረቡን ያስታወቀው ዛሬ ነው። እጩ ሆነው የቀረቡት ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ፤ ለውድድር የሚቀርቡት የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በህዳር ወር ላይ ሲያፀድቅ ነው። ለ34 ዓመታት ኡጋንዳን ያስተዳደሩት ፕሬዝዳንት ሙሴቪኒ፤ ተወዳድረው ካሸነፉ ለተጨማሪ አምስት ዓመት ስልጣን ላይ ይቆያሉ ማለት ነው። በሚቀጥለው ዓመት ታኅሳስ ወር ላይ ለሚካሄደው ምርጫ ሌሎች ፓርቲዎች እስካሁን ድረስ እጩዎቻቸውን አላሳወቁም። ነገር ግን የፕሬዝዳንቱ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ የሚገመተው ድምጻዊውና ፖለቲከኛው ሮበርት ኪያጉላኒ ወይንም በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን እንደሚሆን ይጠበቃል። ቦቢ ዋይን በአገሪቱ ወጣት መራጮች ዘንድ ትልቅ እድል አለው ተብሎ ከአሁኑ ግምት ተሰጥቶታል። በ2017 የአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ዘመን የሚገድበውን ሕግ ሽሮታል። የፕሬዝዳንቱ ተቺዎች እንደሚሉት ከሆነ ይህ የሥልጣን ዘመንን የሚገድበው ሕግ በመነሳቱ ዩዌሪ ሙሴቪኒ የእድሜ ልክ ፕሬዳንት እንዲሆኑ እድል ተሰጥቷቸዋል ይላሉ። ባለፈው ወር የአገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን የ2021 ምርጫ በታኅሳስ ወር እንደሚካሄድ የገለፀ ሲሆን፤ ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የምረጡኝ ዘመቻ ማካሄድ አይቻልም ሲል አስታውቋል። በኡጋንዳ በመጪው ዓመት ለሚካሄደው ምርጫ የምረጡኝ ዘመቻ ማድረግ የሚፈቀደው በሬዲዮ፣ ቲቪ እና በበይነ መረብ አማካእነት ብቻ ነው። በኡጋንዳ ሬዲዮ ከፍተኛ የሆነ ተቀባይነት ያለው መገናኛ ብዙሃን ነው። በአገሪቱ የሚገኙ አብዛኛው ሬዲዮ ጣቢዎች አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ ደጋፊ በመሆናቸው በምርጫ ዘመቻው ወቅት የበላይነት ሊኖረው ይችላሉ ተብሎ ይገመታል።
news-48574581
https://www.bbc.com/amharic/news-48574581
በዓመት 115 ሚሊዮን ህፃናት ወንዶች ያለዕድሜቸው ጋብቻ ያደርጋሉ
ያለዕድሜ ጋብቻ ሲባል አብዛኛውን ጊዜ ጭንቅላታችን ላይ የሚመጣው በዕድሜ ያልጠኑ ሴቶች ከትልልቅ ወንዶች ጋር የሚያደርጉት ጋብቻ ነው።
ነገር ግን ይህ በህፃናት ሴቶች ብቻ ሳይሆን በወንዶችም እንደሚከሰት በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የህፃነት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ያወጣው ሪፖርት ያሳያል። ምንም እንኳን ከወንዶች ልጆች ይልቅ ሴት ህፃናት በከፍተኛ ሁኔታ የሚጋለጡ ቢሆንም ወንዶች ልጆችም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳለው ሪፖርቱ በተጨማሪ ይፋ አድርጓል። "ምንም እንኳን በህፃንነታቸው የሚያገቡ ወንዶችና ሴቶች ባላቸው አካላዊና ማህበራዊ ልዩነት ለተመሳሳይ አደጋ ባይጋለጡም ይህ ልምድ ግን እድሜያቸው ያልደረሱ ህፃናትን መብት መጣስ ነው" በማለት በህፃናት ወንዶች ዘንድ ያለውን ያለዕድሜ ጋብቻ ሪፖርት የፃፉት ኮለን ሙሬይ ጋስተን፣ ክርስቲና ሚሱናስና ክላውዲያ ካባ ገልፀዋል። •የተነጠቀ ልጅነት •የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ •ድብቅ የህጻናት ጋብቻዎች ጥናቱም ያለዕድሜ ጋብቻ ያስከተለባቸውን የኑሮ ፈተና የዳሰሰ ሲሆን "ልክ እንደ ህፃናት ሴቶች ወንዶችም ህፃናት ዕድሜያቸው የማይፈቅደውን የትልቅ ሰው ኃላፊነት ለመሸከም እንደሚገደዱም" ያስረዳል። ጋብቻውም በልጅነት ወላጅነትን እንዲሁም የቤታቸውን ቀዳዳ ለመሙላት ሲባል ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫናና እንደሚሸከሙ የሚያስረዳው ሪፖርቱ እንዲሁም ትምህርትና ሌሎች ነገሮችንም በህፃንነታቸው ተነፍገው እንደሚያድጉ ሪፖርቱ ጨምሮ ያትታል። እንደ ዩኒሴፍ መረጃ በዓለም ላይ በሁለቱም ፆታዎች 765 ሚሊዮን ህፃናት ያለ ዕድሜያቸው የሚጋቡ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 115 ሚሊየኖቹ ህፃናት ወንዶች ናቸው። ምርምሩ የ82 ሃገራትን መረጃ የወሰደ ሲሆን፤ ከ20 እስከ 24 እድሜ ካሉ ወንዶች ውስጥ 4.5% ከ18 ዓመት በታች ያገቡ መሆናቸውን ያሳያል። በሪፖርቱ መሰረት የላቲን አሜሪካና የካሪቢያን ደሴቶች በ8.3% በአንደኛነት ሲቀመጡ፤ የእስያና ፓስፊክ ሃገራት በ5.9 % ሁለተኛውን ሲይዙ፤ የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ከ2% ባነሰ ቁጥር በትንሽነቱ ይጠቀሳሉ። በአንደኛነት የሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ በ27.9% ስትመራ፤ ኒካራጓ በ19.4%ና ማዳጋስካር በ12.9% ተከታትለው የሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ያለዕድሜ ጋብቻ ከሚፈፀምባቸው ቁጥራቸው ከፍተኛ ከሆኑት ሃያ ሃገራት መካከል ሰባቱ ላቲን አሜሪካ ይገኛሉ። •ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ ያሳየው የኢትዮጵያ በጀት ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሱት በባህሉ ሰርፀው የገቡ የፆታ ሚናዎች በህፃንነታቸው እንዲያገቡ ጫና እንደሚያደርግባቸው በኒካራጓ የሚገኘው የዩኒሴፍ ተወካይ ማሪያ ሊሊ ሮድሪገዝ ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ በማህበረሰቡ ለወንድነት የተሰጠው ትርጉም ህፃናት ወንዶችም ቢሆኑ "ወንድነታቸውን" ለማስመስከር ሴቶችን ማስረገዝ እንዳለባቸው እንዲያምኑ እንዳደረጋቸው ባለሙያው ይገልፃሉ። ድህነት፦ ሌላኛው ወንዶች በህፃንነታቸው ያገባሉ ተብሎ እንደ ምክንያት የተጠቀሰው የትምህርትና የግንዛቤ እጥረት ሲሆን " ትምህርት ቤት በህፃንነታቸው የሚገቡ ወንዶች ወደ ትዳር አይገቡም" የሚሉት ሮድሪገዝ በላቲን አሜሪካ ባሉ ሃገራት የትምህርት ስርአት ውስጥ የ ስነ ተዋልዶና ፆታዊ ግንኙነት በጥልቀት አለመሰጠት እንዲሁም በቤታቸው በነዚህ ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ንግግር ባለመኖሩ ክፍተትን እንሚፈጥር ይናገራሉ። •በአመት አንዴ ብቅ የምትለው ከውሃ በታች ያለችው መንደር ከዚህም በተጨማሪ ከደሃ ቤተሰብ የሚወለዱ ልጆች ነፃነታቸውን በቶሎ ለማረጋገጥ ወደ ትዳር እንደሚያመሩም ጥናቱ እንደሚያሳይ ማሪያ ገልፀዋል።
news-50883361
https://www.bbc.com/amharic/news-50883361
የኢትዮጵያና የአማራ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ወደ ሞጣ ሊያቀኑ ነው
ከትናት በስቲያ በአማራ ክልል፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ የሚገኘው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፣ ጀሚዑል ኸይራት ታላቁ መስጊድ እና አየር ማረፊያ መስጊድ ላይ ቃጠሎ መድረሱ አሳዛኝ መሆኑን የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታውቋል።
ጉባኤው በድርጊቱ ማዘኑን አስታውቆ ለወደፊትም እንዲህ አይነት ድርጊት እንዳይፈጸም ጥሪውን አስተላልፏል። የኢትዮጵያ ሐይማኖት ጉባኤ አባላትና የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ወደ ሞጣ በማቅናት ከነዋሪዎች ጋር እንደሚወያዩና የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል። • በሞጣ የተፈጠረው ምንድን ነው? ይህ የተገለጸው የአማራ ክልል ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሞጣ ከተማ በሐይማኖት ተቋማት ላይ በደረሰው ጉዳት ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። "የሠው ልጅ ሊደረግበት የማይገባውን ነገር ሌሎች ላይ ማድረጉ ተገቢ አይደለም" ያሉት የጉባኤው የቦርድ ሰብሳቢ መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም ናቸው። • የትግራይና የፌደራል መንግሥቱ ግንኙነት በጣም አሳሳቢ ነው- ዶ/ር አብረሃም ተከስተ • ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ "ሰው የሚያደርሰው ይህን መሰሉ ጥፋት በሰማይም በምድርም የሚያስጠይቀው ነው" ያሉት ሰብሳቢው የሐይማኖት ተቋማት እንክብካቤ ሊደረግላቸው ሲገባ መቃጠላቸው ግራ የሚያጋባ ነው ብለዋል ። "የአካባቢው ህብረተሰብ አብሮ የሚበላ እና የሚጠጣ እንጂ ለዘረፋ እና ለእሳት የሚዳረግ አይደለም፤ ክቡር የሆነውን ቤተ ዕምነት ማቃጠልም ተገቢ አይደለም" ብለዋል መንግሥትም ቢሆን በየጊዜው በተለይ በአማራ ክልል የሚፈጠሩ ችግሮችን ቀድሞ ፈጥኖ የመከላከል ሥራ መሥራት እንዳለበት አስታውሰው እንዲህ አይነት ጥፋት ከተፈጸመ በኋላ ሰዎችን ለህግ አቅርቦ ፍጻሜ ላይ ማድረስ እንደሚገባ አስምረዋል። ነገር ግን ህግ የጣሱ እርምት ማግኘት ሲገባቸው የተቀጡ ሰዎች ባለመኖራቸው ችግሩ እንደተስፋፋ ገልፀዋል። "እንዲህ ከሆነ ነው ሰው ነፍሱንም እጁንም የሚሰበሰብው" ብለዋል። ሁሉም ማህበረስብ ያገባኛል ብሎ መሥራት ያለበትን መሥራት እና ኃላፊነቱን መወጣት አለበትም ሲሉ ተናግረዋል። "ሁሉም የነበረውን አብሮነት እና መቻቻል ማጠናከር፤ የተሳተፉትንም ለህግ እንዲቀርቡ በመተባበር እና የተዘረፈውንም ሃብትም መተካት አለብን" ብለዋል የቦርዱ ሰብሳቢ መልአከ ሠላም ኤፍሬም ሙሉዓለም። በሞጣ ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተስፋዬን ጠቅሶ የአማራ መገናኛ ብዙን ዘግቧል።
47534782
https://www.bbc.com/amharic/47534782
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም እንኳ ከትናንት ወዲያ በደረሰው የቦይንግ 737-8 ማክስ ET302 አደጋ ችግር ውስጥ ቢሆንም ዛሬም የአፍሪካው ምርጥ በመሆን ነው የሚታወቀው።
አየር መንገዱ አፍሪካ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ጥቂት አየር መንገዶች ትልቁም ነው። በ2017/2018 በጀት ዓመት አየር መንገዱ 245 ሚሊዮን ዶላር ሲያተርፍ 10.6 ሚሊዮን መንገደኞችንም አመላልሷል። በአፄ ሃይለ ስላሴ አገሪቷን የማዘመን እርምጃ እንደ አውሮፓውያኑ በ1945 የተቋቋመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚያው ዓመት ማብቂያ የመጀመሪያ በረራውን ወደ ካይሮ አድርጓል። • ቻይና በቦይንግ 737 ማክስ 8 የሚደረጉ በረራዎችን አገደች ኢትዮጵያ አየር መንገድ በቁጥሮች አየር መንገዱ ማስፋፊያ ማድረጉን ተከትሎ 111 አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን አለም ዓቀፍ መዳረሻውን ወደ 106 ፤ የአገር ውስጡን ደግሞ 23 አድርሷል። ኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 787 ድሪምላይነርና 757 ትልልቅ ጫኝ አውሮፕላኖችን ለመጠቀም የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ ሲሆን በዚህም አዳዲስ አውሮፕላኖችን የሚጠቀም አየር መንገድ ሆኗል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አማካይ እድሜ 5.4 ዓመት ሲሆን በብሪቲሽ አየር መንገድ የአንድ አውሮፕላን አማካይ እድሜ 13.5 ዓመት፣ በዩናይትድ አየር መንገድ 15 ዓመት እንዲሁም በአሜሪካ አየር መንገድ 10.7 ዓመት ነው። ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደህንነት አስተማማኙ የአፍሪካ አየር መንገድም ነው። ቢሆንም እስከ አሁን አራት ከባድ አደጋዎችን አስተናግዷል። • ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው ከአሁኑ አደጋ በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ያጋጠመው እንደ አውሮፓውያኑ በ2010 ET 409 ከቤሩት አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ነድዶ ሜዲትራኒያን ላይ በመውደቁ ነበር። በአደጋው 89 መንገደኞችና የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ሞተዋል። የሊባኖስ የምርመራ ቡድን የበረራ ስህተት ለአደጋው ምክንያት ነው ቢልም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን አውሮፕላኑን ያጋጠመው ፍንዳታ ነው በማለት የቡድኑን ሪፖርት ውድቅ አድርጎታል። አውሮፕላኑ አደጋው እንዲያጋጥመው የተሰራ ሴራ ፣ መብረቅ ወይም እንዲወድቅ ተመትቷል የሚሉ ግምቶችም በኤክስፐርቶች ተቀምጠዋል። እንደ አውሮፓውያኑ በ1988 ደግሞ በባህር ዳር የአየር መንገዱ አውሮፕላን በማረፍ ላይ ሳለ ኤንጅኑ ውስጥ እርግቦች በመግባታቸው በተነሳ እሳት 35 ሰዎች ሞተዋል። በ1996 ደግሞ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ይበር በነበረው ቦይንግ 767 ላይ ጠለፋ በመደረጉ አውሮፕላኑ በኮሞሮስ ደሴት አቅራቢያ ህንድ ውቅያኖስ ላይ መውደቁ ይታወሳል። በዚህ አደጋ ከ 175 መንገደኞች 125ቱ ሞተዋል። የአፍሪካ መሪ አየር መንገዱ ከራሱ አልፎ የሌሎች አፍሪካ አገራት አየር መንገዶችን ይረዳል። በዚህ እርምጃው በማላዊ አየር መንገድ 49 በመቶ ፣ በዛምቢያ 45 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ያለው ሲሆን በሞዛምቢክም በአዲስ መልክ አየር መንገድ ስራ የማስጀመር ፕላን እንዳለው ቀደም ብሎ አስታውቋል። በተመሳሳይ ትንንሽ አካባቢያዊ ጣቢያዎችን በጅቡቲ፣ ቻድ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ለመክፈት ንግግር ላይ ነው። እንደ ማላዊና ቶጎ ባሉ አገራት አሁንም ማእከላት አሉት። በዚህ መልኩ ችግር ውስጥ የገቡ የአፍሪካ አየር መንገዶችን መታደግ ኢትዮጵያ አየር መንገድን በኢንዱስትሪው ትልቅ አድርጎል። ኢትዮጵያ አየር መንገድ በጥሩ የንግድ ስትራቴጂውም ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እየተደረገ ያለው ማስፋፊያ በአፍሪካ አቬሽን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ሌላ ከፍታ ይወስደዋል ተብሎም ይታመናል። ምንም እንኳ የአሁኑ አደጋ አየር መንገዱን ቢያንገጫግጨውም የረዥም ጊዜ ራዩን እንደሚያሳካ ይታመናል። • "የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ
news-53529882
https://www.bbc.com/amharic/news-53529882
ሩስያ ሕዋ ላይ የጦር መሣሪያ ሞክራለች ሲሉ አሜሪካ እና እንግሊዝ ወቀሱ
ዩናይትድ ስቴትስና ዩናይትድ ኪንግደም፤ ሩስያ ሕዋ ላይ የጦር መሣሪያ ባሕሪ ያለው ነገር ሞክራለች ሲሉ ወቅሰዋል።
ሁለቱ ሃገራት መሣሪያው ሕዋ ላይ ያሉ ሳተላይቶችን ለማውደም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። የአሜሪካ ሃገር ውስጥ ጉዳዮች መሥሪያ ቤት 'ሕዋ ላይ የታየው ፀረ-ሳተላይት መሣሪያ' አሳስቦኛል ብሏል። የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ሕዋ ላይ ያሉ የሩስያ ንብረቶች ላይ ምርመራ የሚያካሂድ አዲስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሊያውል መሆኑን አሳውቆ ነበር። አሜሪካ ሕዋ ላይ ይንቀሳቀሳል የተባለው የሩስያ ቴክኖሎጂ ላይ ጥርጣሬ ገብቶኛል ካለች ዘግየት ብትልም ዩናይት ኪንግደም ግን ቅሬታዋን ስታሰማ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የዩናይት ኪንግደም ሕዋ ዳይሬክተር ሃርቪ ስሚዝ፤ ሩስያ ሕዋ ላይ እያሳየችው ያለው ባሕሪ እንዳሰጋቸው አልሸሸጉም። "የሩስያ ድርጊት ሰላማዊውን የሕዋ ምህዳር የሚያውክ ነው። አልፎም ስብርባሪዎች ዓለም የሚጠቅማባቸው ሳተላይቶች አደጋ ሊያደርሱ ይችላሉ። ሩስያ ኃላፊነት ሊሰማት ይገባል።" ሩስያ፣ አሜሪካ፣ ዩኬ እና ቻይናን ጨምሮ ሌሎች ከ100 በላይ ሃገራት ሕዋን በሰላማዊ መንገድ በጋራ ለመጠቀም ስምምነት ገብተዋል። ስምምነቱ የጦር መሣሪያዎችን ሕዋ ላይ መጠቀም እንደማይቻል ያትታል። የአሜሪካ ሕዋ ቁጥጥር ኃላፊ ጄኔራል ጄይ ሬይመንድ፤ ሩስያ ሕዋ ላይ ፀረ-ሳተላይት መሣሪያ መሞከሯን የሚያሳይ ማስረጃ አለን ይላሉ። ሩስያ ከሳተለይት ጋር በተያያዘ ከአሜሪካ ወቀሳ ሲደርስባት ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ባለፈው የካቲት ሁለት የሩስያ ሳተላይቶች በአንድ የአሜሪካ ሳተላይት ዙሪያ ሲንያዣብቡ ነበር ስትል አሜሪካ መክሰሷ አይዘነጋም። ባለፈው ጥር ደግሞ ሩስያ ከመሬት ሕዋ ላይ ያለን ሳተላይት ሊያጠቃ የሚችል መሣሪያ ሙከራ አድርጋ ነበር። ባለፉት አስር ዓመታት ፀረ-ሳተላይት መሣሪያ ሙከራ ያደረጉ ሃገራት አራት ብቻ ናቸው። እኒህም ሩስያ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ እንደ ሕንድ ናቸው። ነገር ግን ሩስያ ሳተላይትን የሚያወድም ሳተላይት ሠርታለች ተብላ ነው የምትወቀሰው። ብዙዎች ሕዋ ቀጣዩ የጦርነት ቀጣና እየሆነ መጥቷል ይላሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት ምህዳሩ ለመረጃ መሰብሰቢያ፣ ለግንኙነት፣ ምርምርና ቅድመ-ማስጠንቀቂያ እየዋለ በመሆኑ ነው።
news-44924339
https://www.bbc.com/amharic/news-44924339
በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ተቃጠሉ
ባለፉት ሰባት ወራት ኬንያ ውስጥ የሚገኙ ከ50 የሚበልጡ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የእሳት አደጋ ሲገጥማቸው ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ደግሞ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ ነው ያጋጠሙት።
ትናንት ምሽት በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሚገኙ የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ሳቢያ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ ተደርጓል። እሁድ ዕለት በአንደኛው ትምህርት ቤት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 31 ተማሪዎች በጭስ በመታፈንና በሌሎች ጉዳቶች ሳቢያ ሆስፒታል ገብተዋል። • ጉግል ኢንተርኔትን በላስቲክ ከረጢት ይዞ ኬንያ ገብቷል • ኬንያ ሺሻን አገደች • ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው ይህ አደጋ በዚህ ዓመት ብቻ ካጋጠሙ በትምህርት ቤቶች ላይ እሳት የማስነሳት 50 ተከታታይ የቃጠሎ ጥቃቶች መካከል አንዱ ነው። በዚህም ምክንያት ቢያንስ 40 የሚሆኑ የተለያዩ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እሳት በማስነሳት ክስ ቀርቦባቸዋል። ተማሪዎቹ ትምህርት ቤታቸው ላይ እሳት እንዲያስነሱ ያደረጋቸው ምክንያት ምን እንደሆነ አከራካሪ ቢሆንም ለፈተና ያለቸው ፍርሃት፣ በኩረጃ ላይ ሚካሄድ ቁጥጥር፣ ጥብቅ የትምህርት ቤት ውስጥ ደንቦች ወይም በትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ላይ የሚደረጉ ለውጦች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይታመናል። በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ወላጆች ባጋጠሙ ውድመቶች ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠር ዶላሮች ቅጣት ይጠብቃቸዋል። በቃጠሎ የተጎዱትን ትምህርት ቤቶች ለመጠገን እያንዳንዱ ተማሪ 10 እና 50 ዶላር እንዲከፍሉ ተደርጓል። በአንድንድ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ቢጀመርም ወደ ትምህርት ቤት የተመለሱ ተማሪዎች እንደሚሉት ባልተሟሉ የመማሪያ፣ የመመገቢያና የማደሪ ክፍሎች ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ቀደም ባሉ ጊዜያት ተመሳሳይ ንብረት የማውደም ድርጊቶች ያጋጠሙ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት 100 የሚደርሱ ትምህርት ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ከደረሰባቸው በኋላ ድርጊቱ እንዳይደገም ለመከላከል ምርመራ ተደርጎ ነበር።
news-49463975
https://www.bbc.com/amharic/news-49463975
ደቡብ አፍሪቃ የታንዛኒያ አውሮፕላንን ጆሃንስበርግ ውስጥ በቁጥጥር ሥር አዋለች
የደቡብ አፍሪቃ ባለሥልጣናት የታንዛኒያ ብሔራዊ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በቁጥር ሥር ማዋላቸውን አስታውቀዋል።
የታንዛኒያ አየር መንገድ 2007 ዓ.ም. በአዲስ መልክ ሥራ ሲጀምር አንድ አውሮፕላን ብቻ ነበረው ኤዬር ባስ 220-300 የተሰኘው የታንዛኒያ አውሮፕላን ዓርብ ዕለት ከጆሃንስበርግ ወደ ዳሬሳላም ሊበር ሲሰናዳ ነበር። አውሮፕላኑ በቁጥጥር ሥር በዋለ ጊዜ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል የታወቀ ነገር አልነበረም። የደቡብ አፍሪቃ ባለሥልጣናትም 'በዚህ ምክንያት ነው' የሚል አስተያየት መስጠት አልሻቱም። አንድ ጡረታ የወጡ አርሶ አደር ግን አውሮፕላኑ ሊታገት የቻለው የታንዛኒያ መንግሥት ሊከፍላቸው የሚገባውን 33 ሚሊዮን ዶላር መክፈል ባለመቻሉ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ጠበቃ ሮጀር ዌክፊልድ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ገንዘቡ ለደቡብ አፍሪቃዊው አርሶ አደር በካሳ መልክ እንዲሰጥ ያስፈለገው የታንዛኒያ መንግሥት የገበሬውን መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ በመያዙ ነው። የታንዛኒያ መንግሥት አፈ-ቀላጤ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጉዳዩን የሚመረምሩ የሕግ ሰዎች ወደ ደቡብ አፍሪቃ እንዳቀኑ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አርብ ዕለት ከደቡብ ወደ ምስራቅ አፍሪቃ እንዲበር ቀጠሮ የተያዘለት አውሮፕላን ተጓዦች በሌሎች አውሮፕላኖች ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ መደረጉን የታንዛኒያ አየር መንገድ ኃላፊ አሳውቀዋል። የታንዛኒያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪቃ መብረር ከጀመረ በቅጡ ሁለት ወር አልሞሉትም። አየር መንገዱ ከፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ ሥልጣን መያዝ በኋላ ሥራ ሲጀምር አንድ አውሮፕላን ብቻ ነበረው። የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በተመሳሳይ የታንዛኒያ አውሮፕላን ካናዳ ውስጥ መያዟ አይዘነጋም። በወቅቱ አንድ የካናዳ የግንባታ ኩባንያ ካሳ አልተከፈለኝም ሲል አውሮፕላኗ እንድትታገት ያስደረገው።
news-55216842
https://www.bbc.com/amharic/news-55216842
ኮሮናቫይረስ ፡ በፓኪስታን በኦክስጅን እጥረት ሳቢያ ህሙማን ሞቱ
በፓኪስታን የኦክስጅን እጥረት ገጥሞ ስድስት የኮቪድ-19 ህሙማን ሕይወታቸው አለፈ።
ፐርሽዋር በምትባል ግዛት የሚገኝ የመንግሥት ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና ላይ የነበሩ ህሙማን ናቸው የሞቱት። የህሙማኑ ቤተሰቦች ነፍሳቸውን ለማዳን ሲማጸኑ እንደነበረም ተነግሯል። ኦክስጅን በመዘግየቱ ሳቢያ 200 ህሙማን የኦክስጅን መጠን ተቀንሶባቸዋል። የሆስፒታሉ አመራሮች ኦክስጅን አቅራቢውን ወቅሰዋል። ብዙ ሠራተኞችም ተባረዋል። ፓኪስታን ውስጥ ወረርሽኙ እንደ አዲስ አገርሽቷል። 400,000 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው 8,000 ሞተዋል። ካይበር ቲቺንግ በተባለው ሆስፒታል ቅዳሜ የሚጠበቀው ኦክስጅን ሳይደርስ በመቅረቱ ህሙማኑ ለሞት ተዳርገዋል። 300 መጠባበቂያ ሲሊንደሮች ቢኖሩም ቬንትሌተሮችን የማንቀሳቀስ ጉልበት አልነበራቸውም ተብሏል። እናቱ በኮሮናቫይረስ የተያዘችው ሙራድ አሊ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ሆስፒታሉ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ለማዳን ሲሯሯጡ ነበር። “ሀኪሞቹን ስንለምናቸው ነበር። አንዳንድ ህሙማን ወደ ድንገተኛ ክፍል ተዘዋወሩ” ብሏል። ድንገተኛ ክፍል ውስጥ የነበረው ኦክስጅን ሲገባደድ ግን ሰዎች እንደሞቱና ብዙዎች ህመማቸው እንደተባባሰባቸው ተናግሯል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች የህሙማን ቤተሰቦች ኦክስጅን እንዲገዙ ቢጠይቁም ሁሉም የመግዛት አቅም እንዳልነበራቸው ሙራድ ገልጿል። የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ከሞቱት ህሙማን አምስቱ ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ናቸው። አንዱ ታማሚ ደግሞ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ሲታከም ነበር። የሆስፒታሉ አመራሮች ኦክስጅን መዘግየቱ “በወንጀል የሚያስጠይቅ ቸልታ ነው” ብለዋል። ኦክስጅኑን ለሆስፒታሉ እንዲያደርስ የተመደበ ባለሙያ በቦታው እንዳልነበረ በምርመራ ተድርሶበታል። የሆስፒታሉን ዳይሬክተር ጨምሮ ሌሎችም ብዙ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ከሥራ ታግደዋል።
48597772
https://www.bbc.com/amharic/48597772
በአማራ ክልል በተከሰቱ ግጭቶች 224 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
በአማራ ክልል የተለያዩ ስፍራዎች ከተከሰቱ ግጭቶችን ጋር በተያያዘ 224 ሰዎች በቁጥጥር መዋላቸውን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ምግባሩ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ምግባሩ ከበደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በክልሉ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ጉዳይ ትልቁ የፖለቲካም የመልካም አስተዳደር ሥራ ነው ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ግጭት በተፈጸመባቸው 3 አካባቢዎች ጥፋት የፈጸሙ ሰዎችን ለሕግ ለማቅረብ የምርመራ ሥራ ተጀምሯል ብለዋል። አቃቤ ሕጉ በማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ኦሮሞ ማህበረሰብ አስተዳደር እና ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ ቦታዎች የምርመራ ሥራ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የፌደራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ፣ የፌደራል እና የክልሉ አቃቤ ሕግ እንዲሁም የዞን ፖሊስ የተካተቱበት የምርመራ ቡድን መመሥረቱንም አቃቤ ሕጉ ተናግረዋል። በማዕከላዊ እና ምእራብ ጎንደር ዞኖች 150 ሰዎች ጉዳያቸው እየተመረመረ በማረሚያ ቤት እንደሚገኙ አቶ ምግባሩ አስታውቀዋል። ሆኖም ተጠርጣሪዎች ገና በቁጥጥር ሥራ ያልዋሉ ሲሆን ይህም ከነበረው ግጭት ስፋትና ውስብስብነት የተነሳ መሆኑን ጠቁመዋል። • በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ታጣቂዎች አምስት ሰዎች ገደሉ • በካማሼ ዞን ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ በኦሮሞ ማህበረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን ደግሞ ላለፉት ሶስት ወራት በተሰራው የምርመራ ሥራ ማስረጃ የተገኘባቸው 50 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አቃቤ ሕጉ ተናግረዋል። በቤኔሻንጉል ጉሙዝ እና በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት 24 ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እየተከታተሉ ነው። "የአማራ ክልል በቅርቡ የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት እና ሠላም የሰፈነበት ክልል ማድረግ እንደምንችል አምነን እየሠራን ነው የምንገኘው" የሚሉት አቃቤ ሕጉ ምግባሩ ከበደ፤ ህበረተሰቡ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን ሳልፎ በመስጠት ሊተባበር ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።
news-52657885
https://www.bbc.com/amharic/news-52657885
ኮሮናቫይረስን እየተከላከልን በጥንቃቄ ምርጫ እናደርጋለን፡ ዶ/ር ደብረፅዮን
የትግራይ ክልል አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ የራሱን ምርጫ ማካሄድ እንደሚችል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካል ተናገሩ።
የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ሊቀ መንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካል ይህንን የተናገሩት በምርጫና በኮሮናቫይረስ ዙሪያ ትናንት መቀለ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ እንዳሉት "የፌዴራል መንግሥት ምርጫ ሊያካሂድ እንደማይችል በማስታወቁ በክልል ደረጃ ግን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን እየተከላከልን በጥንቃቄ ምርጫውን ማካሄድ እንችላለን" ብለዋል። ጨምረውም "በክልላችን ምርጫው በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ በክልሉ ካሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከማህበራትና ከሕዝብ ጋር በመመካከር የምርጫ ቦርድንም ባሳተፈ ሁኔታ ሕጋዊ አፈፃፀም እንዲኖረው ይደረጋል" ብለዋል። • አሜሪካ በዳሬሰላም በቫይረሱ የመያዝ እድል "ከፍተኛ" ነው አለች • የጥንት ምስሎችን ነፍስ የሚዘራባቸው ወጣት • የኮሮናቫይረስ ክራሞት በኢትዮጵያ፡ ከመጋቢት እስከ ግንቦት የትግራይ መንግሥት በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ሲወስን ለኮሮናቫይረስ ትኩረት ባለመስጠት ሳይሆን ለሕዝብ ውሳኔና ለሕገ መንግሥቱ ተገዥ በመሆናቸው እንደሆነም ተናግረዋል። ከመስከረም በኋላ በየትኛውም ደረጃ ሥልጣን ላይ ያለው የመንግሥት መዋቅር ሕጋዊነት ስለማይኖረው ምርጫ ሳይካሄድ ከቀረ አደገኛ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል ያስጠነቀቁት ዶ/ር ደብረፅዮን "ከመስከረም በኋላ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት ቅቡልነትም ሆነ ሕጋዊነት ስለማይኖራቸው በአገር ደረጃ ምርጫ አለመካሄዱ አደገኛ ነው" በማለት አስጠንቅቀዋል። ከመስከረም ወዲያ ሥልጣን ላይ መቆየት "ከሕዝብ ውሳኔና ፍላጎት መውጣት ነው፤ ከሕገ መንግሥትም ውጪ ነው" ብለዋል። "ወደ ውድድሩ እንገባለን፣ ልንመረጥም ላንመረጥም እንችላለን" የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን፤ "ወደ ውድድሩ እንገባለን፣ ልንመረጥም ላንመረጥም እንችላለን" ሲሉ ምርጫ ማካሄድ የግድ መሆኑን አስምረውበታል። አያይዘውም ምርጫ ማካሄድ አይቻልም ቢባል እንኳን፤ ቀጣይ እርምጃ ምን መሆን አለበት የሚለውን መወሰን የሚችው ሕዝብ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች መሆኑን ጠቁመው፤ "አገር አቀፍ ምክክር ያስፈልጋል" ብለዋል። ምርጫን ማካሄድ የሚያስፈልገው የዜጎችን የመምረጥና የመመረጥ መብትን እንዳይጣስ ለማድረግ ነው ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን "አሁን ያለው ሁኔታ ምርጫን የማራዘምና ያለማራዘም ብቻ ሳይሆን የሕዝብን ውሳኔ አለመተግበር፣ ሕገ መንግሥቱ ያለማክበር ነው" ብለዋል። "ምርጫ አይካሄድም እየተባለ ያለው በኮሮናቫይረስ ምክንያት አይደለም" ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ "ቀደም ሲል ፍላጎትና ዝግጅት ቢኖር ኖሮ በግንቦት ወር ላይ ማድረግ ይቻል ነበር" በማለት ቀድሞውኑም ምርጫ ለማድረግ ፍላጎት እንዳልነበረ አመልክተዋል። ለተፈጠረው ችግር በመንግሥት በኩል ቀርቦ የተወካዮች ምክር ቤት ያጸደቀውን ውሳኔንም በሚመለከት "ከምርጫ ጋር ተያይዞ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የሚተረጎም ነገር የለም፤ አምስት ዓመት ማለት አምስት ዓመት ነው" ሲሉ የትርጉም ጥያቄ የቀረበበትን ሁኔታ አጣጥለውታል። ከዚህ ይልቅም ሕገ መንግሥቱን በጣሰ መንገድ ስልጣንን ለማራዘም የተለያየ ሰበብ ከማቅረብ፣ ከሕዝብና ከፖለቲካ ፓርቲዎች እንደዚሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት መፍትሄ መሻት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ዶክተር ደብረ ፅዮን በሕገ መንግሥቱ በየአምስት ዓመቱ ምርጫ መካሄድ እንዳለበትና ከሕዝብ ምርጫ ውጪ ወደ ኃላፊነት መምጣት እንደሌለ በግልፅ የተቀመጠ መሆኑን አመልክተው "ከመስከረም በኋላ በፌዴራል ደረጃም ሆነ በክልሎች አሁን ያሉት መንግሥታት የስልጣን ጊዚያቸው ስለሚያበቃ። ህጋዊነት ስለማይኖራቸው ምርጫውን ማድረግ ወሳኝ ነው" ብለዋል። "ኮሮናቫይረስ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ምክንያት መሆን የለበትም" ሕወሓት በሕገ መንግሥቱ መሠረት ምርጫ ይካሄድ፣ አፈጻጸሙ ላይ ደግሞ ምክክር ይደረግ የሚል አቋም እንዳለውም አክለዋል። ምርጫ ቦርድና ምርጫውን የሚታዘብ ነፃ አካል ተሳትፎ፣ በሥርዓት ምርጫው እንዲካሄድ ፍላጎት እንዳላቸውም አያይዘው ጠቅሰዋል። "ምክንያት ደርድረን ወይም ለሕገ መንግሥት ትርጉም ሰጥተን ልንቀጥል አንችልም" ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ። ዶ/ር ደብረፅዮን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን፤ ኮሮናቫይረስ ሥልጣን ላይ ለመቆየት ምክንያት መሆን የለበትም" ሲሉ በመግለጫው ተናግረዋል። ኮሮናቫይረስ መቼ እንደሚወገድ ስለማይታወቅ፣ ጥንቃቄ እያደረጉ ምርጫ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ምርጫ እንደቀደሙት ጊዜያት ሳይሆን የቅስቀሳ ሂደት እና ድምፅ አሰጣጥ ጥንቃቄ የተሞላ ሆኖ ምርጫውን ማካሄድ ይቻላል ብለዋል። "ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ራሱ ሕዝቡ የሚፈልገው መንግሥት መሆን አለበት" ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ "ያልተመረጠ መንግሥትን ማስቀጠል ተቀባይነት የለውም። ወደ አምባገነንነት እየተቀየረ ነው ማለት ነው" ሲሉ በዛሬው መግለጫ ተናግረዋል። አያይዘውም "ምርጫ ይካሄድ ያለ መወቀጥ አለበት፤ የተባልከውን ስማ፣ ተግብር ካልሆነ ትወቀጣለህ የሚለው ነገር መፍትሔ አይሆንም፤ የባሰ ነገሩን ያቀጣጥለዋል፤ ችግሩን ያባብሰዋል። የኃይል እርምጃ የሚያስወስድ ነገር የለም" ሲሉም አቋማቸውን አስታውቀዋል። "ሕዝቡ ከፈለገ ይምረጠን ካልፈለገ ይወርውረን" ሲሉም ለምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
45899605
https://www.bbc.com/amharic/45899605
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በወታደሮቹ ድርጊት ተበሳጭተው እንደነበር ተናገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ለሃገሪቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ላይ የመንግሥታቸውን አቋም ሲያብራሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቆዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የዓመቱ መጀመሪያ የጋራ ስብሰባ ላይ መንግሥትን በዚህ ዓመት ከፍ ያለ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ላይ ጠቅላይ ሚኒስሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል። • የሰራዊት አባላቱ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይት • "ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው" ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን በማንሳት የመንግሥታቸውን ዓላማና ዕቅድ በማንሳት ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በደሞዝ ጥያቄ ሰበብ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ስለሄዱ ወታደሮችም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እንዳሉት ታጥቀው ወደ ጽህፈት ቤታቸው የመጡት የሠራዊቱ አባላት አካሄድ አደገኛ እንደነበረና በዚህ መሃል መንግሥት የኃይል እርምጃን በመውሰድ ቢሞከር ኖሮ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችል እንደነበር ተናግረው፤ ይህም ለውጡን ለማጨናገፍ ሊውል ይችል እነደነበር አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም ፍንጭ ባይሰጡም ከዚህ ክስተት ጋር ተያይዞ የለውጡን ሂደት ለማጨናገፍ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች በስተጀርባ መኖራቸውን ተናግረዋል። በድርጊቱ እጅጉን መበሳጨታቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቢሆንም ግን ሕዝቡን ለማረጋጋትና አላስፈላጊ ሁኔታዎች እንዳፈጠሩ በሚል በእርጋታና በፈገግታ ለጋዜጠኞች መግለጫ መስጠታቸውን ተናግረዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ "ሳንገድለው አመለጠን" የሚሉ ሰዎች እንደነበሩም ለምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ በሃገሪቱ እየመጣ ያለው ለውጥ ስኬታማ መሆን ካልቻለ የመጨንገፍ እድል ሊገጥመው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል። ለዚህ ደግሞ "ለውጡን ለማጨናገፍ እየሰሩ ያሉ አካላትን ማስቆም ያስፈልጋል። መንግሥትም ይህን ድርጊት በበላይነት የሚመሩትን አካላት በመለየት የማስቆም ሥራ የሚሰራበትን አካሄድ እየተከተለ ይገኛል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ላይ የካቢኔ ሚኒስተሮችን የመሰየሙ ሂደት ቀላል እንዳልነበረ አመልክተዋል። ሃያዎቹን ሚኒስትሮች ለመሾም የተደረገው ሥራ በርካታ ትግሎች የተካሄደበት በፈታኝ ሂደት ውስጥ ማለፉን ገልፀዋል።
news-52703739
https://www.bbc.com/amharic/news-52703739
በኢትዮጵያ ከባንኮች በሚወጣ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ተጣለ
ኢትዮጵያ ከባንኮችና ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በሚወጣ የጥሬ ገንዘብ ላይ ገደብ መጣሏን አስታወቀች።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዛሬ ይፋ ባደረገውና ተግባራዊ በሚሆነው መመሪያው መሰረት ተቋማትና ግለሰቦች ከባንኮች በቀንና በወር ውስጥ ከባንኮች በሚያወጡት የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ተጥሏል። በዚህም መሰረት አንድ ግለሰብ በቀን እስከ 200 ሺህ ብር እንዲሁም በወር እስከ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ከባንኮች ማውጣት የሚችል ሲሆን፤ ተቋማት ደግሞ በቀን እስከ 300 ሺህ ብር እና በወር እስከ 2.5 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ይህንን እርምጃ በተመለከተ እንደተናገሩት "የገንዘብ ዝውውርን ሥርዓት በማስያዝ ወንጀልንና የግብር ስወራን ለመከላከል ይረዳል" ማለታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በጥሬ ገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለውን የመጠን ገደብ በተመለከተ የወጣው መመሪያ እንዳመለከተው ግን ከተቀመጠው መጠን በላይ ለማንቀሳቀስ ለሚፈልጉ በገንዘብ ተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች በኩል የሚያቀርቡት ምክንያት ተመርምሮ እንደሚፈቀድላቸው ተገልጿል። በተጨማሪም የመጠን ገደብ ከተጣለበት በላይ ጥሬ ገንዘብ ለሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦችና ተቋማት ከአንድ ሒሳብ ወደ ሒሳብ፣ በቼክ፣ወይም በሲፒኦ ተጨማሪ ገንዘብ ማዘዋወር እንደሚችሉም ተመልክቷል። ከዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የተነገረው መመሪያን ተግባራዊነትን በተመለከተ ብሔራዊ ባንክ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፤ ባንኮችም በየሳምንቱ የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን ለማዕከላዊው ባንክ ሪፖርት እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል። ይህ መመሪያም በአገሪቱ ያሉትን ሁሉንም ባንኮችና አነስተኛና ጥቃቅን የገንዘብ ተቋማትንም የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል። ይህንን የብሔራዊ ባንኩን መመሪያ ተላልፈው የተገኙ የገንዘብ ተቋማት ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸውም ተመልክቷል።
news-41545298
https://www.bbc.com/amharic/news-41545298
ሜጀር ጄነራል፣ ርዕሰ-መስተዳድር፣ አፈ-ጉባኤ...ከዚያስ?
አቶ አባዱላ ገመዳ ከሁለት ሳምንታት በፊት ለዓመታት ከተቀመጡበት የአፈ ጉባኤነት መንበር ላይ ለመልቀቅ መጠየቃቸው ከባለፈው ሳምንት ማብቂያ ጀምሮ ዋነኛ ርዕስ ሆኖ ዘልቋል።
አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ ከፓርቲያቸው ኢህአዴግ/ኦህዴድ እንዲሁም ከእራሳቸው አንደበት ዜናውን ለማስተባበል የተሰማ ነገር ስለሌለ ሥልጣን ለመልቀቅ መጠየቃቸው ሃቅ ወደ መሆኑ ያመዘነ በነበረበት ጊዜ ጥያቄ የማቅረባቸውን እውነትነት እራሳቸው አረጋጥጠዋል። ወታደራዊው መንግሥት አባዱላ መስራችና አባል የሆኑበት ኦህዴድ በሚገኝበት ኢህአዴግ ተሸንፎ ከተወገደበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ የወታደራዊና የሲቪል ሃላፊነቶች ላይ ቆይተዋል። አባዱላ ከትግል በኋላ ፓርቲውን የተቀላቀሉ በርካታ አመራሮች ባሉበት ኦህዴድ ውስጥ ተቀባይነት ካላቸው ቀደምት ጥቂት መስራች አባላት ውስጥ ቀዳሚው እንደሆኑ ይነገራል። ለዚህም ይመስላል በርካታ የኦህዴድ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም በፓርቲውና በክልሉ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ ያሉ አመራሮች ዜናው እንደተሰማ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአፈጉባኤውን ምስል በስፋት የሚለጥፉትና የገጻቸው መለያ እያደረጉ ያሉት። ቅሬታ አባዱላ ገመዳን በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች፤ በተለይ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ብዙም ደስተኛ እንዳልነበሩ ይናገራሉ። እንደሚታወቀው የአዲስ አበባና የኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላንን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በክልሉ ውስጥ እስካሁን ለዘለቀው ቅሬታ መነሻ ነበር። አቶ አባዱላም ችግሩን ለማብረድና መረጋጋት ለማምጣት ከፊት ሆነው ሲሰሩ ከነበሩት ሰዎች መካከል ቀዳሚው ናቸው። የሥልጣን መልቀቂያ ማቅረባቸው ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ የጥያቄውን እውነትነት ከማረጋገጥ ጎን ለጎን የውሳኔያቸውን ትክክለኛ ምክንያት ማወቅ ለተቃዋሚዎቻቸው ብቻ ሳይሆን በዙሪያቸው ላሉትም ጥያቄ ሆኗል። ኦሮሚያ ከሶማሌ ክልል ጋር በሚዋሰንባቸው የድንበር አካባቢዎች የተቀሰቀሰው አሳሳቢ ግጭትና መፈናቀል የሚያስቆመው ጠፍቶ ለረጅም ጊዜ መዝለቁም ቅሬታ ሳይፈጥርባቸው እንዳልቀረ የቅርብ ሰዎቻቸው ይናገራሉ። ከሁሉ በላይ አቶ አባዱላ ወደ ባሌ ዞን በሄዱበት ጊዜ በግጭቱ የከፋ ችግር የደረሰባቸውን ሰዎች ባገኙበት ጊዜ የተሰማቸው ሃዘንና ተስፋ መቁረጥ ለዚህ ውሳኔያቸው አባባሽ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አብረዋቸው የነበሩ ሰዎች ይጠረጥራሉ። ከማዕከል ወደ ክልል ኦሮሚያ አርሲ ዞን የተወለዱት አባዱላ ገመዳ በመጪው ሰኔ 60ኛ ዓመታቸውን የሚድፍኑ ሲሆን የልጆች አባትም ናቸው። አቶ አባዱላ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በተለያዩ ሃላፊነቶች፤ በወታደራዊ መለዮ ስር እስከ የሜጀር ጄኔራልነት ማዕረግ ይዘው ስርተዋል። ደም ባፋሰሰውና እስካሁን እልባት ባላገኘው የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነትም ሚና ከነበራቸው የጦር መሪዎች ውስጥ ይጠቀሳሉ። ከጦርነቱ በኋላ በዋናነት በህወሃት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ በርካታ የኢህአዴግ አንጋፋ ባለሥልጣናት ከፓርቲና ከመንግሥት ሃላፊነቶች ሲነሱ የሌሎች ክልሎችን ጨምሮ አቶ ኩማ ደመቅሳ ከኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳደርነት እንዲለቁ ተደርገው ነበር። በወቅቱ የተፈጠረውን የሥልጣን ክፍተት ለመሙላትም አባዱላ ገመዳ ወታደራዊ ማዕርጋቸውን በአቶ ተክተው የኦሮሚያ ክልልን የርዕሰ መስተዳድር መንበር ያዙ። የክልሉ ፕሬዝዳንት በነበሩት ጊዜ ከፍተኛ ተቀባይነትና ድጋፍን ለማግኘት ከመቻላቸውም በላይ ስኬታማ ሥራዎችን ማከናወናቸውም ይነገርላቸዋል። ሌሎች ደግሞ የኦሮሚያ ክልልን መሬትን ያለአግባብ ለፈለጉት ሰው በብዛት ሲሰጡ ነበር በማለት ይወቅሷቸዋል። ለረጅም ጊዜ የዘለቀው ተቃውሞ ከክልል ወደ ማዕከል በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ ተመልሰው እንዲያገለግሉ ጥሪ በተደረጋላቸው ጊዜ በክልሉ ምክር ቤትና በኦህዴድ በኩል ጥያቄዎች ተነስተው ነበረ። በ2002 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሆነው ሲመጡ በክልሉ በርካታ የጀመሩዋቸው ሥራዎች እንደነበሩና አመራሩንም በከፍተኛ ደረጃ አንቀሳቅሰው እንደነበረ በመግለፅ ብዙ የድርጅቱ አባላት ቅር መሰኘታቸውን ገልፀው ነበር። አባዱላ ከኦሮሚያ ክልል ተነስተው የተወካዮች ምክር ቤትን በአፈ-ጉባኤነት ለአምስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ በ2008 በድጋሚ ለሁለተኛ ዙር በነበሩበት ቦታ እንዲቀጥሉ ተደርገዋል። አባዱላ በትምህርት በኩል በቀዳሚነት በቻይና የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ወታደራዊ አመራርን የተማሩ ሲሆን፤ ከዚያም በህዝብ አስተዳደር የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ እንዳላቸው ታሪካቸው ያሳያል። ወዴት? የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ከታወቀ በኋላ በማህበራዊው የመገናኛ ዘዴ በኩል የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። በተለይ የመልቀቃቸው ምክንያትና ቀጣይ እርምጃቸው ምን እንደሚሆን ማወቅ የብዙዎች ጉጉት ሆኗል። እሳቸውም በመጨረሻ ላይ በሰጡት ቃል ወደፊት ጥያቄያቸው ምላሽ ሲያገኝ የመልቀቃቸውን ምክንያት በዝርዝር እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። የምክር ቤት አባልነታቸውን፣ በኢህአዴግና በኦህዴድ ውስጥ ያላቸውን ኃላፊነቶች በሙሉ ይተዋሉ? ወይስ የአፈ-ጉባኤ ሥልጣናቸውን ብቻ ? የሚለው ጥያቄ የብዎዙች የነበረ ቢሆንም አባዱላ እንዳሉት፤ ''ጥያቄዬ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር አፈ-ጉባኤነት የመልቀቅ ቢሆንም፣ የመረጠኝን ሕዝብና ያስመረጠኝን ድርጅት ስለማከብር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነቴ እቀጥላለሁ'' ብለዋል። ነገር ግን መንግሥት ለባለሥልጣናት ከሚሰጠው ጥቅማ ጥቅም ውስጥ አንዱ የሆነውንና ለበርካታ ዓመታት ሲኖሩበት የቆዩትን ቤት እንደለቀቁ መነገሩ ደግሞ ውሳኔያቸው ከመንግሥት ሥራዎች መራቅን ሊጨምር ይችላል የሚል ጥርጣሬን አጭሮ ነበር።። ማግባባት ቢቢሲ ስለጉዳዩ ለማወቅ አቶ አባዱላን ጨምሮ በፌደራል መንግሥቱና በኦሮምያ ክልል ውስጥ ሰለጉዳዩ ያውቃሉ የሚላቸውን ከፍተኛ ኃላፊዎችን አግኝቶ ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ቢሆንም ግን የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል። ሁሉም ግን ምክር ቤቱ ሲከፈት የሚፈጠረውን ለማወቅ የጓጓ ይመስላል። አባዱላ ገመዳ ባቀረቡት የሥልጣን መልቀቅ ጥያቄ ፀንተው ከቦታቸው ከተነሱ በኦህዴድ ውስጥ በይፋ ''በቃኝ'' በማለት ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ቀጥለው ሁለተኛው የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን ይሆናሉ።
news-47939684
https://www.bbc.com/amharic/news-47939684
ሩሲያዊው የኦርቶዶክስ ቄስ በባለቤታቸው "ሀጥያት" ለቅጣት ራቅ ወዳለ ገጠር ተመድበዋል
በሩሲያ ኡራል በምትባል ግዛት የሚኖሩ አንድ የኦርቶዶክስ ቄስ ባለቤታቸው በፆም ወቅት በአካባቢው ቁንጅና ውድድር በመሳተፏ ለቅጣት ሲባል ራቅ ወዳለ ገጠር ተመድበዋል።
ኦክሳና ዞቶፋ የተባለችው ግለሰብ የቁንጅና ሳሎን ያላት ሲሆን ቁንጅና ውድድር ማሸነፏን ተከትሎ ባለቤቱ ያልታወቀው ፒካቡ የተባለ ድረ ገፅ አሸናፊዋ የቄስ ሚስት መሆኗን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ከፍተኛ ትችትን አስተናግዳለች። •“ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ የእምነቱ ኃላፊዎች ድርጊቷን ከሰሙ በኋላም ቄሱን ሰርጂ ዞቶፍን በማግኒቶጎርስክ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው የኢየሱስ እርገት ተብሎ ከሚጠራው ካቴድራል ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ አድርገዋቸዋል። ከማግኒቶጎርስክ 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኝ አንዲት መንደር የተመደቡ ሲሆን የህዝብ ቁጥሯም አራት ሺ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል። የቤተክርስቲያን አስተዳደርና ጉዳዮችን የሚመለከተው ፍርድ ቤት ኃላፊ የሆኑት ኤጲስ ቆጶስ ፌዮዶር ሳፕሪይክን እንደተናገሩት " የቄስ ሚስት ራሷን እንዲህ መገላለጧ ከፍተኛ ኃጥያት ነው" ብለዋል። •የስዊዘርላንድ መንግሥት ቡና ለህይወት አስፈላጊ እንዳልሆነ ገለፀ ባለቤታቸው ንስሀ እስከምትገባም ድረስ ወደ ኃላፊነት እንደማይመለሱም ውሳኔ አስተላልፈዋል። "ቤተሰቡን መቆጣጠር የማይችል ምን አይነት ቄስ ነው? እንዴትስ አድርጎ ነው ጉባኤውን የሚቆጣጠረው" የሚል ጥያቄም አንስተዋል። ፒካቡ የተባለው ይሄው ድረገፅም ያወጣው ፅሁፍ እንደሚያትተው ይህ የሚያስቆጣ ስራዋ የመጀመሪያዋ እንዳልሆነ ነው። ሌቭ ባክሊትስኪ የተባሉት ሌላኛው ቄስ በበኩላቸው በአንድ ወቅት በባህር ዳርቻ አጠገብ የዋና ልብስ ለብሳ ፎቶ ተነስታ በማህበራዊ ሚዲያ የለጠፈች ሲሆን ፎቶውንም ያጠፋችው ከተነገራት በኋላ መሆኑን ገልፀዋል። "ባህሪዋ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው" ነው ያሉት ቄስ ሌቭ ቄሱ ከስራቸው ተነስተው ወደ ሌላ አካባቢ መመደባቸው ጊዜያዊ እርምጃ እንደሆነና "ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ መልዕክት እንዲሆናቸው ነው" ብለዋል። ከስራቸው የተነሱት ቄስ በበኩላቸው ጥፋት እንደሰሩ ቢያምኑም ቅጣቱን ግን ምህረት አልባ ብለውታል። •በአዲስ አበባ ሊፈጸም የነበረ የሽብር ጥቃት መክሸፉ ተነገረ ከዚህም በተጨማሪም ባለቤታቸው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አፀያፊ አስተያየቶች እንደደረሰባት በመንገርም ምሬታቸውን አቅርበዋል። ዜናው የብዙ ሩሲያውንን ቀልብ የሳበ ሲሆን አንዳንዶችም ቄሱን ከመተቸት አልቦዘኑም " ስለ ቄሶች ባለቤቶችም ሆነ ቄሶችም ማወቅ የሚገባችሁ ይህንኑ ነው። የሚሰብኩትን በተግባር የማያውሉ ናቸው" በማለት አንድ አስተያየት ሰጭ ዘልፏቸዋል። • መንግሥት ከኦነግ ጋር ካገር ውጭ ሊወያይ ነው ሌሎች በበኩላቸው የቤተ ክርስቲያኗን ውሳኔ በማፌዝ ለባለትዳሮቹ ድጋፋቸውን ገልጸዋል። "ህይወቷን ተደስታ የማትኖረው ለምንድን ነው? ቄሶች ከሀጥያት ነፃ ናቸው ብለው የሚያምኑ አሁንም አሉ ማለት ነው። እነሱ እኮ ጥሩ ስራ ያላቸው ተራ ሰዎች ናቸው" የሚል አስተያየት በፒካቡ ድረገፅ ላይ ተነቧል •«ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) "ችግሩ ምንድን ነው? የሳትኩት ነገር ይሆን? በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የትኛው ቦታ ላይ ነው ቄሶች ቆንጆ ሚስት እንዳይኖራቸው የሚከለክለው" በማለት አስተያየቱን የሰነዘረም አለ። ከዚህም በተጨማሪ ቤተ ክርስቲያኗን በነገር ሸንቆጥ ያደረጉ አስተያየቶች አልታጡም "ከሁሉም የተቀደሱት እኒህ ሰዎች በፆም ወቅት የሌሎች አይን በሜካፕ ቢሸፈንም ጉድፍን ማየት ችለዋል" በማለት ነው።
53424331
https://www.bbc.com/amharic/53424331
ግብጽ በሕዳሴው ግድብ ውሃ ሙሌት ላይ ኢትዮጵያን ማብራሪያ ጠየቀች
ግብጽ የኢትዮጵያ መንግሥትን በአስቸኳይ ስለ ግድቡ ውሃ ሙሌት ማብራሪያ እንዲሰጣት መጠየቋ ተሰማ።
ግብጽ ማወቅ የምትፈልገው ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ኢትዮጵያ ሆን ብላ መሙላት መጀመር አለመጀመሯን ማወቅ እንደሆነ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብጽ እያደረጉት የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር መቋረጡ እንደተሰማ ነበር የግድቡ ውሃ መጠን እየጨመረ መሆኑን የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎች መውጣት የጀመሩት። ሱዳን በበኩሏ በታችኛው አገራት ያለው የውሃው ፍሰት በቀን 90 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትሮች መቀነሱን ገልፃለች። ኢትዮጵያ ግድቡን በይፋ መሙላት አለመጀመሯን ተናግራለች። 5 ቢሊየን ዶላር የይፈጃል የተባለው ይህ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል ድርድር እየተደረገበት ቆይቷል። በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ምዕራፍ ውሃ ሙሌት መጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ማስታወቁን የአገር ውስጥ ሚዲያዎች የዘገቡ ቢሆንም በይፋ አለመጀመሩን ሚኒስትሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ የግድቡ ሙሌት መጀመሩን አስመልክቶ ለቢቢሲ በሰጡት ምላሽ ዘገባው "በስህተት የወጣ ነው፤ የራስ ትርጉም ተጨምሮበታል። ግድቡ ግንባታው አሁን የደረሰበት ደርሷል፤ ግድቡ ውሃ ይይዛል እንጂ በይፋ የተጀመረ ነገር የለም" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሚኒስትሩ ለአሶሺየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት እነዚህ የሳተላይት ምስሎች የሚያሳዩት ከፍተኛ ዝናብ መኖሩንና ከግድቡ ከሚወጣው ይልቅ ግድቡ ውስጥ የሚገባው መጨመሩን ነው ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ስለሺ ለቢቢሲ እንደገለጹት ባለፈው ዓመት ውሃው ያልፍ የነበረው በ520 ከፍታ ላይ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት 560 ከፍታ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። ከ560 ከፍታ በታች ያለው ውሃ ግድቡ ውስጥ የሚቀር እንደሆነና ሙሌቱም ከግንባታው ሂደት ጋር የማይነጣጠል ነው ማለታቸውንም የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
news-54915504
https://www.bbc.com/amharic/news-54915504
የሰሜን ኮሪያና የሩሲያ የመረጃ መዝባሪዎች ጥቃት በክትባት ምርምሮች ላይ
በሰሜን ኮሮያና በሩሲያ መንግሥታት የሚደገፉ የመረጃ መረብ መዝባሪዎች (ሃከርስ) ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚሰሩ ተቋማትን ኢላማ እንዳደረጉ ማይክሮሶፍት ገለጸ።
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት እንዳለው በቅጽል ስም "ፋንሲ ቤር" የተባለው የሩሲያ ቡድንና "ዚንክ" እንዲሁም "ሲሪየም" የተባሉት ሁለት የሰሜን ኮሪያ የመረጃ መረብ ሰርሳሪ ቡድኖች በቅርቡ ከተደረሰባቸው ጥቃቶች ጀርባ እንዳሉ ተጠቁሟል። የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የመረጃ ደኅንነት ማዕከል ቀደም ሲል የሩሲያ የመረጃ መረብ መዝባሪዎች በክትባት ላይ በሚደረጉ ምርምሮች ላይ ትኩረት አድርገው ጥቃት ለመፈጸም እየሞከሩ መሆኑን አስታውቆ ነበር። ነገር ግን ሩሲያ በወቅቱ በድርጊቱ ውስጥ እጇ እንደሌለበት አሳውቃ ነበር። የመረጃ መረብ ደኅንነትን ለመጠበቅ የሚረዱ ሶፍትዌሮችን የሚሰራው ማይክሮሶፍት እንደገለጸው፤ የሰባት መድኃኒት አምራች ኩባንያዎችን የኮምፒውተር ሥርዓት ሰብሮ ለመግባት የተደረጉ ሙከራዎችን ተከላክሏል። በተጨማሪም ክትባት ለማግኘት በካናዳ፣ በፈረንሳይ፣ በህንድ፣ በደቡብ ኮሪያ እና በአሜሪካ ጥረት የሚያደርጉ የምርምር ተቋማትም ኢላማ መደረጋቸው ተጠቁሟል። ማይክሮሶፍት ጨምሮም መረጃዎችን ለመመዝበር እየጣረ ያለው የሩሲያው ቡድን ኢላማ የተደረጉትን ተቋማት አካውንቶች ሰብሮ ለመግባት በሚያደርገው ሙከራ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የይለፍ ቃሎችን በመጠቀም ከባድ የተባለውን ዘዴ እንደተጠቀመ ገልጿል። ከሰሜን ኮሪያ ናቸው ከተባሉት ሰርሳሪ ቡድኖች አንደኛው ከዓለም የጤና ድርጅት ባለስልጣናት ከአንዱ የተላከ የሚመስል ኢሜል በመላክ ኢላማ የተደረጉትን ተቋማት የኮምፒውተር ሥርዓት ሰብሮ ለመግባት የሚያስችል መረጃን ለማግኘት ሙከራ ማድረጉም ተደርሶበታል። ማይክሮሶፍት እንዳለው የተቋማት የኮምፒውተር ሥርዓት ሰብሮ ለመግባት ከተደረጉት ሙከራዎች መካከል አንዳንዶቹ ሳይሳኩ የቀሩ ቢሆንም፤ አንዳንዶቹ ግን ተሳክተዋል ብሎ አስጠንቅቋል። ሩሲያ ቀደም ሲል የክትባት ምርምሮችን ኢላማ አድርጋለች የተባለውን ክስ ማስተባበሏ ይታወሳል። በአሜሪካ ዋሽንግተን የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ለሮይተርስ በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ ላይ ከቀደመው የተለየ መረጃ እንደማይሰጥ ገልጿል።
news-52015116
https://www.bbc.com/amharic/news-52015116
ኮሮናቫይረስ፡ የአፍሪካ አገራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እየደነገጉ ነው
ሴኔጋልና አይቮሪኮስት በግዛቶቻቸው ውስጥ የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደንገግ ሌሎች የአፍሪካ አገራትን ተቀላቀሉ።
የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል እንዳስታወቁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ የሚሆነው ዛሬ ማክሰኞ ዕኩለ ሌሊት ላይ ሲሆን ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት የሚቆይ የሰዓት እላፊም ተጥሏል። የአገሪቱ ጦር ሠራዊትና ፖሊስ የተላለፉትን ውሳኔዎች እንዲያስፈጽምም ታዟል። ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ይህንን እርምጃ ያስታወቁት አገራቸው የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት ፈተና ውስጥ እንደሆነች ለሕዝባቸው ዛሬ ባደረጉት ንግግር ነው። "በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የመጀመሪያው ታማሚ ከተገኘ በኋላ መንግሥት ወረርሽኙን ለመግታት አስፈላጊውን ጥረት ያደረገ ቢሆንም፤ እስካሁን ያሰብነውን አላሳካንም" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ። በሴኔጋል እስካሁን በኮሮናቫይረስ አማካይነት በሚተላለፈውና ኮቪድ-19 በተባለው የመተንፈሻ አካላት ወረርሽኝ መያዛቸው የተረጋገጠ 79 ሲሆን ከእነዚህም መካከል 8ቱ ሰዎች ድነዋል። በአገሪቱ በሽታው ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ ከ1500 በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ለበሽታው መቆጣጠሪያ 1.5 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ደግሞ 80 ሚሊዮን ዶላር የተመደበ መሆኑንና ተናግረዋል። የአይቮሪኮስት ፕሬዝዳንት አሌሳኔ ኦታራ ደግሞ መንግሥታቸው ከዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋት 11 ሰዓት የሚቆይ ሰዓት እላፊ በማወጅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀስ በቀስ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር አሳውቀዋል። "በገጠመን የወረርሽኝ መስፋፋት ምክንያት በመላዋ አገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ወስኛለሁ" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በቴሌቪዥን ቀርበው መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል። ፕሬዝዳንት ኦታራ በተጨማሪም ከሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች ወደ ዋና ከተማዋ የሚደረጉ ያልተፈቀዱ እንቅስቃሴዎች እንዳይደረጉና መጠጥ ቤቶችም እንዲዘጉ አዘዋል። በበሽታው መስፋፋት ምክንያት ቀደም ብለው የአስቸኳይ ጊዜ ያወጁ ሌሎቹ የአፍሪካ አገራት ሱዳን፣ ግብጽና ሊቢያ ናቸው።
news-57011553
https://www.bbc.com/amharic/news-57011553
ኢሰመኮ፡ በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ እንደሚያሳስበው ገለፀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን [ኢሰመኮ] በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ ያሳስበኛል ብሏል።
ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው ፖሊስ ጣብያዎች ዕድሜያቸው ከ 9 እስከ 18 ዓመት የሚሆናቸው ሕጻናት አካለ መጠን ከደረሱ ሰዎች ጋር ተቀላቅለው በእስር ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል። በፖሊስ ጣቢያዎቹ ብዙ ሰዎች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ “በወቅታዊ ሁኔታ” የተጠረጠሩ ናቸው በሚል መታሰራቸውን፣ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ ምርመራ ሳይጀመርባቸው እና ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሕግ ከተቀመጠው ጊዜ በላይ ታስረው እንደቆዩ የሚያመላክቱ አሳማኝ መረጃዎች ቀርበዋል ይላል መግለጫው። በተጨማሪም በብዙ ፖሊስ ጣቢያዎች ዐቃቤ ሕግ በቂ መረጃ ባለመገኘቱ ምክንያት “የአያስከስስም ውሳኔ” የሰጠባቸው ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት መለቀቅ የነበረባቸው ተጠርጣሪዎች ዋና ተሳታፊ (ኮር) ናቸው ወይም በሌላ ወንጀል ይፈለጋሉ በሚል ያለ አግባብ ታስረው እንዲቆዩ የሚደረጉ መሆኑን ተረድቻለሁ ብሏል። በ21 ፖሊስ ጣብያዎች የተደረገ ክትትል የሰብአዊ መብት ተቋርቋሪው ኮሚሽን ከህዳር11 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በክልሉ ያለውን የእስረኞችን አያያዝ ሁኔታ በተመለከተ በ21 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ክትትል ማድረጉን በመግለጫው አትቷል። ኮሚሽኑ፤ በተለይም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቁጥጥር የዋሉ ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ ሌሎችም “በወቅታዊ ሁኔታ” የተያዙ የሚባሉ ብዛት ያላቸው እስረኞች የሚገኙባቸውና ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ከሚቀርቡባቸው መካከል የተመረጡ ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ክትትል አድርጊያለሁ ብሏል። በክትትሉም ከእስረኞች እና የፖሊስ ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን፣እንዲሁም የክትትሉን ግኝቶች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የክልሉ የሕግ አስከባሪ እና የአስተዳደር አካላት በማሳወቅ ምላሽ እንዲሰጥባቸው መጠየቁን ኮሚሽኑ አሳውቋል። ኢሰመኮ፤ በጎበኛቸው የፖሊስ ጣቢያዎች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው ይላል። በፖሊስ ጣቢያዎቹ ብዙ ሰዎች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ ተይዘው የታሰሩ፣፣ ከነዚህም አብዛኛዎቹ ምርመራ ሳይጀመርባቸው እና ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሕግ ከተቀመጠው ጊዜ በላይ የታሰሩ ስለመኖራቸው አሳማን ማስረጃ ማግኘቱን በመግለጫው ላእ አመልክቷል። በተጨማሪም በበርካታ ፖሊስ ጣቢያዎች ዐቃቤ ሕግ በቂ መረጃ ባለመገኘቱ ምክንያት “የአያስከስስም ውሳኔ” የሰጠባቸው ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሠረት መለቀቅ የነበረባቸው ተጠርጣሪዎች በሌላ ወንጀል ይፈለጋሉ በሚል ያለ አግባብ ታስረው እንዲቆዩ መደረጋቸውን መረዳቱንም በመግለጫው ላይ አስፍሯል። የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ኃላፊዎች “በወቅታዊ ሁኔታ” ተጠርጥረው የታሰሩ እስረኞች ጉዳያቸው የሚታየው በዞን እና በወረዳ ደረጃ በተቋቋሙ “የፀጥታ ምክር ቤቶች” መሆኑን ይገልጻሉ ይላል። ይህ አሰራር ብዛት ያላቸው ተጠርጣሪዎችን በሕግ ከመዳኘት ይልቅ የፖለቲካ (የአስተዳደራዊ) ውሳኔዎች ሰለባ እንዲሆኑ አድርጓል ሲል የኢሰመኮ መግለጫ ያትታል። ኢሰመኮ በጎበኛው ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ እስረኞች ድብደባ እንደተፈፀመባቸው እና ጉዳት እንደደረሰባቸው አይቻለሁ ብሏል። በተወሰኑ ቦታዎች “የኦነግ ሸኔ” አባል ወይም ደጋፊ ናቸው በሚል የሚፈለጉ “ልጆቻችሁን አቅርቡ” በማለት አባት ወይም እናትን የማሰር፤ “ባልሽን አቅርቢ” በማለት ሚስትን የማሰር ተግባር እንደሚፈጸም ከተለያዩ ታሳሪዎች አሳማኝ ምስክርነቶችን መቀበሉን በመግለጫው ገልጿል። ክትትሉ በተደረገባቸው በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች ሴት እስረኞች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የተወሰኑት እድሜያቸው ከ 5 ወር አስከ 10 ዓመት የሚሆናቸው ሕጻናት ልጆቻቸውን ይዘው የታሰሩ ናቸው ይላል የኮሚሽኑ ሪፖርት። አብዛኛዎቹ ፖሊስ ጣቢያዎች ንፅህናቸው ያልተጠበቀ፣ በጣም የተጨናነቁ እንዲሁም የምግብ፣ ውሃና መፀዳጃ አቅርቦት የሌላቸው መሆኑን ታዝቢያለሁ ብሏል ኮሚሽኑ። የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተጠቀሱትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በተመለከተ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር የምርመራ ቡድን በማዋቀር የማጣራት ሥራ መሥራቱን ጠቅሶ ግኝቶቹን በማስተባበል ዝርዝር ምላሽ ሰጥቷል ይላል የኢሰመኮ መለግጫ።
48729124
https://www.bbc.com/amharic/48729124
ለአፍሪካ ዋንጫ የሚፋለሙት ኃያላን እንስሳት
ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ግብጽ ብምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የ24 ሃገራት ቡድኖች ይሳተፋሉ። ቡድኖቹ ከነገቡት የሃገር ባንዲራና ስም ባሻገር መጠሪያ ቅጽል አላቸው።
በአፍሪካ እግር ኳስ ውስጥ ቅጽል ስሞች ጉልህ ቦታ አላቸው። እነዚህ ስሞች ለቡድኖቹ ደጋፊዎች መለያ ከመሆን በተጨማሪ ተጫዋቾችን በማነቃቃት በኩልም ይጠቅማሉ። የብሔራዊ ቡድኖች ቅጽል ስም፣ በቀለማት ካሸበረቁ ደጋፊዎችና የከበሮ ድምፅ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ መለያ ድምቀቶች ናቸው። ተምዘግዛጊዎቹ ንስሮች በሚቀጥሉት ሳምንታት ግብጽ ውስጥ ንስሮቹ ጎልተው ይታያሉ ተብለው ይጠበቃል። • የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ውጤት ይገምቱ • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በሚለብሰው አረንጓዴ ማሊያ ተለይቶ የሚታወቅ ቢሆንም ንስሮቹ የሚለው ስያሜያቸው ግን የበለጠ መለያቸው ነው። ብድኑ ይህን ስያሜ የወሰደው ከሃገሪቱ ብሔራዊ መለያ ላይ ነው። ቱኒዚያ ከካርቴጅ ሥልጣኔ ጋር በነበራት ግንኙነት የተነሳ ቡድኗ የካርቴጅ ንስር የሚል መጠሪያን አግኝቷል። ብሔራዊ መለያቸውም ንስር ነበረ። እዚህ ጋር የማሊ ንስሮችም ሊዘነጉ አይገባም። በተጨማሪም ኡጋንዳም የበራሪ አእዋፍ (ሽመላ) መለያ ነው ያላት። የጫካው ግብግብ እዚህ የእግር ኳስ ሜዳውም ውስጥ ልክ እንደጫካው ዓለም የበላይነት ለማግኘት የሚደረግ ፍልሚያ አለ። ከአንበሳ እስከ እባብ፣ ከአቦሸማኔ እስከ ዝሆን ያሉት የዱር እንስሳት በዚህ ዓመቱ የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ቦታ አላቸው። ነገሥታትና ጦረኞች መሪዎችን የማክበር ጠንካራ የአፍሪካዊያን ባህል መሠረት አንዳንድ ቡድኖች ስያሜያቸውን ከእነርሱ ወስደዋል። ሰባት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን በመውሰድ የውድድሩ ንጉሥ የሆኑት ግብጻዊያን ለውጤታቸው የሚመጥን ፈርዖኖቹ የሚለውን ስያሜ ከቀደምት ንገሥታቶቻቸው ወስደዋል። ፈርዖኖቹ የዚምባብዌ ጦረኞች ከተባሉት የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን አድርገው ድል ቀንቷቸዋል። • የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል የጨዋታዎቹን ዝርዝር እዚህ ያገኛሉ • የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ውጤት ይገምቱ የኬንያ ብሔራዊ ቡድን ስያሜያቸውን ከዱር እንስሳትና ከመሪዎች ውጪ ካደረጉ ቡድኖች መካከል ነው። የሃራምቤ ከዋክብት ይባላሉ፤ ሃራምቤ የሚለው የስዋሂሊ ቃል ሕብረት መፍጠር ሲሆን ጥሪው ከቡድኑ አልፎ በሃገር ደረጃ ለአንድ ዓላማ መሰባሰብን ያመለክታል። የዝነኞቹ የጋና ብሔራዊ ቡድን መጠሪያ ጥቋቁሮቹ ከዋክብት ሲሆን ይህም የተወሰደው ሃገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ካልው ጥቁር ኮከብ ነው። ይህም አንድነትን ለማመልከት እንደዋለ ይነገራል። ከሳምንታት በኋላ የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ሲጠናቀቅ ንስሮቹ ከሁሉ ከፍ ብለው መብረራቸው፤ አንበሶቹ ኃያልነታቸውን እንዳስከበሩ መቆየታቸውን ነገሥታቱም የበላይ ሆነው በመሪነት መዝለቃቸው የሚለይ ይሆናል። • ከእግር ኳስ ሜዳ ወደ ኮኛክ ጠመቃ
news-51838458
https://www.bbc.com/amharic/news-51838458
ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑ ታወጀ
የዓለም ጤና ድርጅት ዛሬ ምሽት ዓለምን እያስጨነቀ ያለውን የኮሮናቫይረስ በሽታ "ወረርሽኝ" መሆኑን አውጇል።
አንድ በሽታ ወረርሽኝ የሚባለው በዓለም ዙሪያ በተመሳሳይ ጊዜ በተለያዩ አገራት ውስጥ ሲሰራጭ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳሉት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከቻይና ውጪ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ13 እጥፍ ጨምሯል። • የኮሮናቫይረስ ንግዱንም ስፖርትንም መጉዳቱን ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናገረ • የማንችስተር ሲቲና የአርሰናል ጨዋታ በኮሮናቫይረስ ስጋት ተሰረዘ • ኮሮናቫይረስ ሰዎችን ከእምነታቸው እየለየ ይሆን? ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጨምረውም በሽታውን በተመለከተ እርምጃ ለመውሰድ የታየው ቸልተኝነት "በጣም እንዳሳሰባቸው" ተናግረዋል። በሽታው ወረርሽኝ ተብሎ መሰየሙ የዓለም የጤና ድርጅት በሽታውን በተመለከተ አገራት ማድረግ ይገባቸዋል ብሎ የመከራቸው ነገሮች ይቀየራሉ ማለት እንዳልሆነ አመልክተዋል። መንግሥታት የወረርሽኙን ፍጥነት ለመግታት የሚወስዱትን እርምጃ የበለጠ ቀልጣፋ በማድረግ "አስቸኳይና ፋታ የማይሰጥ" ሊያደርጉት ይገባል ብለዋል። "በርካታ አገራትም ይህ ቫይረስ ባለበት ለማስቆምና ለመቆጣጠር የሚቻል እንደሆነ አስመስክረዋል" ሲሉ ዶክተር ቴድሮስ ተናግረዋል። በሽታው በስፋት የሚተላለፍበት ሁኔታ ባጋጠማቸው አገራት ውስጥ ተመሳሳይ ነገርን ለማከናወን ይቻል እንደሆነ ማረጋገጥ ዋነኛው ፈተና መሆኑንም ገልጸዋል። ጨምረውም መንግሥታት "የዜጎችን ጤና በመጠበቅ፣ የአገልግሎት መቋረጥን በመቆጣጠርና ለሰዎች ሕይወት ክብር በመስጠት" መካከል ያለውን ሚዛን መጠበቅ ነበረባቸው ብለዋል። ከጥቂት ወራት በፊት ቻይና ውስጥ የተቀሰቀስው ይህ በሽታ በርካታ አገራትን በማዳረስ እስካሁን ድረስ ከ4366 በላይ ሰዎችን ሲገድል በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ደግሞ ከ122 ሺህ በላይ ሆኗል።
54617481
https://www.bbc.com/amharic/54617481
በቀለ ገርባ፡ የአቶ በቀለ ገርባ ቤተሰቦች ጤናቸው አሳስቦናል አሉ
የአቶ በቀለ ገርባ ቤተሰብ አባላት የአቶ በቀለ ጤና ሁኔታ እጅጉን አሳስቦናል አሉ።
የአቶ በቀለ ገርባ ባለቤት ወ/ሮ ሃና ረጋሳ ባለቤታቸው ዓይናቸው ላይ ሕመም ያጋጠማቸው ከዚህ ቀደም ለ7 ዓመታት ያክል እስር ቤት በቆዩበት ወቅት መሆኑን አስታውሰዋል። በአሁንም በቂ ሕክምና እያገኙ ስላልሆነ የግራ ዓይናቸው ሁኔታ አሳስቦናል ብለዋል። "ግራ ዓይኑን ነው የሚያመው። ሕመሙ የጀመረው እስር ቤት ሳለ ነው። በወቅቱ ከእስር ቤት እየተመላለሰ ይታከም ነበር" የሚሉት ወ/ሮ ሃና፤ አሁን ላይ አቶ በቀለ የሕክምና ክትትል እያገኙ ስላልሆነ ግራ ዓይናቸው የማየት አቅም 50 በመቶ ብቻ መሆኑን ይናገራሉ። አቶ በቀለ ሕክምና ማግኘት አለመቻላቸውም ትልቅ ስጋት እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ በወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሰው የጤና እክል ባጋጠመው ወቅት ሕክምና የማግኘት መብት አለው፤ መንግሥትም ይህን የማስፈጸም ግዴታ አለበት ይላል። የፌደራል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ፍቃዱ ጸጋ፤ አቶ በቀለ ገርባ ዓይናቸውን የመታመማቸውን ጉዳይ ከማህበራዊ ሚዲያዎች መስማታቸውን እንጂ በይፋዊ መንገድ ወደ መስሥሪያ ቤታቸው የመጣ መረጃ አለመኖሩን ይናገራሉ። "ስለዚህ ጉዳይ የማውቀው ነገር የለም። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ነው የተመለከትኩት። በመሥሪያ ቤታችን ውስጥ የተጠርጣሪዎች መብት መከበሩን የሚከታተሉ ጠበቆች አሉን። ስለዚህ ጉዳይ ከሰማን በኋላ ሁኔታዎችን አቀናጅተን ወደ ስፍራው ልከናቸዋል" ብለዋል። ወ/ሮ ሃና በበኩላቸው አቶ በቀለ ሕክምና እንዲያገኙ ፍርድ ቤት የፈቀደ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ‹‹አቶ በቀለ በግል ሕክምና ተቋም ሄደው ይታከሙ አይልም›› በሚል ምክንያት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሕክምናውን መከልከሉን ተናግረዋል። "ሐኪም ግራ ዓይኑ የማየት አቅሙ ከ50 በመቶ በታች እንደሆነ ነግሮታል። ስለዚህም በየወሩ ዓይኑ ላይ የሚወጋውን መርፌ ማቋረጥ እንደሌለበት ነበር የተነገረው" ይላሉ። ከአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ቱሊ ባይሳ፤ የአቶ በቀለ ጉዳይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እየታየ በነበረበት ወቅት ፍርድ ቤቱ ዓይናቸውን በግል የጤና ተቋም እንዲታከሙ ፈቅዶላቸው ነበር ይላሉ። አቶ በቀለ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከተዘዋወሩ በኋላ ግን የማረሚያ ቤቱ አስተዳዳሪዎች የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልደረሰንም በማለት ሕክምና እንዲያገኙ ፍቃድ መከልከሉን ይናገራሉ። አቶ ቱሊ "ፍርድ ቤት በግል የሕክምና ተቋም እንዲከታከሙ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ማረሚያ ቤቱ ይህን እየፈጸመ አይደለም። ስለዚህ አቤቱታችንን ጉዳያቸው እየታየ ባለቤት ፍርድ ቤት እናቀርባለን" ብለዋል። ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ፍቃዱ ጸጋ አንድ ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ሕክምና እንዲያገኝ ፈቅዶለት ተጠርጣሪው ሕክምና እንዳያገኝ መከልከል ወንጀል ነው ካሉ በኋላ የተጠርጣሪውን መብት የከለከለ አካል በሕግ ይጠየቃል ብለዋል።
news-52179255
https://www.bbc.com/amharic/news-52179255
ኮሮናቫይረስ፡ ሲንጋፖር ከ20ሺህ በላይ የውጪ አገር ሰራተኞችን በለይቶ ማቆያ ውስጥ አስቀመጠች
ሲንጋፖር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እየተስፋፋ በመምጣቱ 20 ሺህ የውጭ አገር ሠራተኞች በማደሪያ ክፍላቸው ውስጥ ለ14 ቀናት እንዲቆዩ አዘዘች።
እነዚህ ሠራተኞች የህንድ፣ የታይላንድ፣ የስሪላንካና የባንግላዲሽ ዜግነት ያላቸው እንደሆነ ተገልጿል። ሠራተኞቹ በሁለት የተለያዩ ህንፃዎች ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን 13 ሺህ ሠራተኞች ያሉበት አንዱ ማደሪያ ውስጥ ብቻ 63 በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 6800 ሠራተኞች ባሉበት የማደሪያ ሕንፃ ደግሞ 28 ታማሚዎች ተገኝተዋል። የሲንጋፖር መንግሥት ወደ እነዚህ ሁለት የመኖሪያ ህንፃዎች ማንም እንዳይገባና እንዳይወጣ ሲል የእንቅስቃሴ ገደብ አስቀምጧል። • በአዲሱ የሞባይል ቴክኖሎጂ ላይ የተነዛው ሐሰተኛ ወሬ ጉዳትን አስከተለ እነዚህ ህንጻዎች ከደቡብ እስያ ለሚመጡ የግንባታ ሠራተኞች ማደሪያ በመሆን የሚያገለግሉ ናቸው ተብሏል። ሠራተኞቹ በክፍላቸው ለአስራ አራት ቀን ሲቆዩ ክፍያቸው የማይቋረጥ ሲሆን በቀን ሦስቴ እንዲመገቡ ይደረጋል ተብሏል። የሠራተኞቹን ደሞዝ አሰሪያዎቻቸው የሚሸፍኑ ሲሆን የምግባቸውንም ወጪ እንዲችሉ ተደርጓል ተብሏል። ነገር ግን ክፍሎቹ በሰው ብዛት መጨናነቃቸውና ንጽህናቸው አለመጠበቁን አንስተው የሚተቹ አልጠፉም። ነዋሪዎቹም ቢሆኑ እነዚህ ማደሪያዎች የንጽህና ክፍላቸው የሚያፈስ፣ ምግብ ለማግኘት ረዣዥም ሰልፍ የሚደረግባቸውና በበረሮ የተሞሉ መሆኑን ይናገራሉ። በሲንጋፖር ፑንጎልና ዌስቲት የሚገኙት እነዚህ ማደሪያዎች ሙሉ በሙሉ መውጣትና መግባት ተከልክሎባቸዋል። መንግሥት እንዳለው በእነዚህ ማደሪያ ህንጻዎች የሚገኙ ታማሚዎች ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቷል። እናም ቤት የመቆየት ገደቡ "የሠራተኞቹን ደህንነት ለመጠበቅና ስርጭቱ ወደ ማኅበረሰቡ እንዳይስፋፋ ለመከላከል የተደረገ" ነው ብሏል። ሠራተኞቹ የሚኖሩበትን ፎቅ ለቅቀው መውጣት የማይችሉ ሲሆን በክፍላቸው አልያም በፎቃቸው ላይ ከማይኖሩ ሰዎች ጋርም እንዳይቀላቀሉ ተነግሯቸዋል። በአንድ ክፍል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ከክፍል ክፍል ይለያል ተብሏል። ቢቢሲ በ2015 ባደረገው ጉብኝት በአንድ ክፍል ውስጥ 12 ሰዎች እንደሚኖሩ ተመልክቷል። • ወሲብና ኮሮናቫይረስን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች ለሠራተኞቹ ከምግባቸው በተጨማሪ፣ የንጽህና መጠበቂያ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ሙቀታቸውን መለኪያ ቴርሞ ሜትር ይሰጣቸዋል ተብሏል። ሠራተኞቹ በቀን ሁለቴ ሙቀታቸውን መለካትና መመዝገብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በመኖሪያ ህንፃቸው አቅራቢያ የህክምና ቡድን እንደሚኖር ተገልጿል። ሲንጋፖር ከውጪ አገር መጥተው ለሚሰሩ ሠራተኞች ማደሪያ በግለሰቦች የሚዘጋጅ ሲሆን ከ1ሺህ በላይ ነዋሪዎች ካሉ በመንግሥት ተመዝግቦ ፍቃድ ማግኘት ይኖርበታል። በአጠቃላይ በአገሪቱ ከ40 በላይ የሠራተኞች ማደሪያዎች ይገኛሉ። በሲንጋፖር እስካሁን ድረስ 1300 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲታወቅ ስድስት ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በዚያች ትንሽዬ አገር ውስጥ 5.7 ሚሊዮን ሕዝብ ሲኖር ከዚህ ውስጥ ደግሞ 1.4 ሚሊዮኑ ከውጪ አገራት የመጡ ሠራተኞች ናቸው።
news-53929103
https://www.bbc.com/amharic/news-53929103
ትራምፕ፡ "ጆ ባይደን ከእኔ ጋር ክርክር ከመግጠምህ በፊት የአበረታች መድኃኒር ምርመራ አድርግ"
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ "ጆ ባይደን ከኔ ጋር ክርክር ከመግጠምህ በፊት ኮሮና ተመርመር" ሲሉ ተደምጠዋል።
በመጪው ምርጫ ይፋለማሉ ተብለው የሚጠበቁት ትራምፕና ባይደን በቀጣዩ ወር ክርክር ሊያደርጉ ቀጠሮ ይዘዋል። ዋሽንግተን ኤክዛሚነር ከተባለ ጣቢያ ጋር ቆይታ የነበራቸው ትራምፕ ጆ ባይደን አቅማቸው ጎልበት ብዬ አይቸዋለሁ። መድኃኒት እየተጠቀሙ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ተደምጠዋል። ትራምፕ ተቀናቃኛቸው መድኃኒት እየተጠቀሙ እንደሆነ መገመታቸውን ይናገሩ እንጂ ምንም ማስረጃ አላቀረቡም። እንዴት እርግጠኛ ሆኑ? ተብለው የተጠየቁት ዶናልድ፤ "እኔ እንዲህ ዓይነት ነገር በማስተዋል የተካንኩ ነኝ" የሚል ምላሽ ነው የሰጡት። ትራምፕና ጆ ኅዳር ላይ ከሚካሄደው የአሜሪካ ምርጫ በፊት ሶስት ጊዜ ተገናኝተው ክርክር ይገጥማሉ። ዶናልድ፤ ባለፈው ምርጫ ተቀናቃኛቸው የነበሩት ሂላሪ ክሊንተን ወደ ክርክር ከመምጣታቸው በፊት የሆነ አነቃቂ ነገር ይወስዳሉ፤ ይመርመሩልኝ ማለታቸው አይዘነጋም። የሂላሪ ክሊንተን ሰዎች በወቅቱ የትራምፕን ወቀሳ ውሃ የማያነሳ ሲሉ አጣጥለውት ነበር። ዕለተ ረቡዕ ቃለ መጠይቅ የነበራቸው ዶናልድ ለአሁኑ ተቀናቃኛቸውም ተመሳሳይ ጥሪ አቅርበዋል - 'እውነተኛ ነኝ ካልክ ተመርምረህ ና' የሚል። ትራምፕ፤ የቀድሞው ምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከዚህ ቀደም ቴሌቪዥን መስኮት ላይ ሲቀርቡ 'ቃላት የማይታዘዟቸው ነበሩ'፤ አሁን ግን ነቃ ነቃ ብለዋል ይላሉ። ፕሬዝደንቱ ተቃናቃኛቸው ጆ የዴሞክራት ፓርቲ ዕጩ ሆነው ከመቅረባቸው በፊት ከበርኒ ሳንደርስ ጋር በነበራቸው ክርክር ላይ 'ደርሰው እሳት የላሱ' መሆናቸው አልጣማቸውም። "ዕጩ ከመሆናቸው በፊት በነበሩ መድረኮች ላይ አቅም አልባ ሆነው ነበር የታዩት፤ ድንገት ከበርኒ ጋር በነበረው ክርክር ላይ ጎልብተው መታየታቸው እንዴት ሊሆን እንደቻለ አላውቅም' ብለዋል ፕሬዝደንቱ። "ክርክሩ እኮ ደባሪና እንዲሁ ፈዛዛ ነበረ። ምንም የተለየ ነገር አልታየበትም" ሲሉ የሁለቱን ዴሞክራቶች ክርክር አጣጥለውታል። "እኛ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ እናቀርባለን እንጂ ዝም ብለን አናይም።" ትራምፕ በሳቸውና በተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን መካከል የሚደረገው ክርክር የሞት የሽረት እንደሚሆን ይናገራሉ። "ትግሉ ቀላል አይሆንም። እኛ አፋችንና ጭንቅላታችንን ነው የምንጠቀመው። ደግሞ ቆመን ነው የምንከራከረው። እኔ ሁሉም እንዲቆም እፈልጋለሁ - እነሱ መቀመጠ ነው የሚፈልጉት።" የመጀመሪያ ክርክር ክሊቭላንድ፣ ኦሃዮ ውስጥ መስከረም ወር መገባደጃ ላይ ይደረጋል። ሁለተኛ ደግሞ በፍሎሪዳዋ ማያሚ ጥቅምት አጋማሽ ላይ ቀጠሮ ተይዞለታል። የመጨረሻው ክርክር ወርሃ ጥቅም ሲገባደድ ናሽቪል ቴኔሲ ውስጥ የሚደረግ ይሆናል። ትራምፕ ከጆ ባይደን ጋር አንድ ተጨማሪ ክርክር እንዲኖራቸው ቢጠይቁም የፕሬዝደንቶች ክርክር ኮሚሽን ጥያቀያቸውን ውድቅ አድርጎታል። የመጀመሪያ ክርክር ቀደም ብለው ለሚመርጡ ሰዎች ሲባል ከተያዘለት ቀጠሮ ቀድሞ ይካሄድ ብለው ጠይቀው ነበር ፕሬዝደንቱ። ኮሚሽኑ ይህንንም ውድቅ አድርጎታል። የ74 ዓመቱ ትራምፕና የ77 ዓመቱ ጆ ባይደን 'የአእምሮ ሕመም አለብህ' ተባብለው ተሰዳድበው ያውቃሉ።
news-48859253
https://www.bbc.com/amharic/news-48859253
ቦይንግ ለተጎጂ ቤተሰቦች መቶ ሚሊዮን ዶላር ሊሰጥ ነው
በኢንዶኔዥያና ኢትዮጵያ ለተከሰከሱት ሁለት የ737 ማክስ አውሮፕላን ተጎጂ ቤተሰቦች ቦይንግ መቶ ሚሊዮን ዶላር አቀረበ።
ይህ ገንዘብ በሁለቱ አውሮፕላኖች አደጋ ለሞቱ በድምሩ ለ346 ተጎጂ ቤተሰቦች የሚሰጥ ነው። ገንዘቡ የሟች ቤተሰቦችን የትምህርትና የኑሮ ወጪን የሚሸፍነው ነው ብሏል ቦይንግ። •"ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት •"ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም ይህ ገንዘብ የሟች ቤተሰቦች በፍርድ ቤት ለከሰሱት ክስ የቀረበ ሳይሆን ድርጅቱ ከፍርድ ሂደቱ ውጭ ያደረገው ክፍያ ነው። ቦይንግ ዛሬ ሰኔ 26፣ 2011 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "የሚሰጠው ገንዘብ ለትምህርት፣ ከችግር ለመውጣት እንዲሁም የችግሩ ገፈት ቀማሽ ለሆኑት ቤተሰቦች የዕለት ተዕለት ኑሮና ለኢኮኖሚ ልማት ይውላል። "ቦይንግ ከአካባቢው አስተዳዳሪዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ይተባበራል። ይሄ የመጀመሪያው ኢንቨስትመንትም በዓመታት ውስጥ የሚከፈል ይሆናል" ብሏል። •"እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የቦይንግ ሊቀ መንበርና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ሙይልንበርግ " ቦይንግ በሁለቱም አደጋዎች በተቀጠፈው ሕይወት በከፍተኛ ሁኔታ አዝኗል። የጠፋው ሕይወት በሚቀጥሉት ዓመታትም የሚረሳ አይሆንም" ሲሉ ተናግረዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም "ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ላጡት ከልባችን ሀዘናችንን እየገለፅን ይሄ የመጀመሪያ ገንዘብ መፅናናትን ይፈጥርላቸዋል ብለን እናስባለን" ብለዋል። በኢንዶኔዥያ ላየን ኤይርና በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ተጎጂ የሆኑት ቦይንግን የከሰሱት ሲሆን እስካሁንም ገና ውሳኔ ላይ አልተደረሰም። ኩባንያው በኢንዶኔዥያ ላየር ኤይር አደጋ ለተጎዱት ጉዳዩን በስምምነት ለመጨረስና ብር ለመክፈል እየተነጋገረ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ተጠቂዎችንም በስምምነት ለመፍታት ሀሳብ ቢያቀርብም በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡት ለመስማማት ዝግጁ እንዳልሆኑ አሳውቀዋል።
news-49457671
https://www.bbc.com/amharic/news-49457671
ናሳ ህዋ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጀል ተፈጸመ አለ
አን ማክሌን ጠፈርተኛ ናት። ከምድር ብዙ ርቀት ተጉዛ ህዋ ላይ የምትገኘው አን፤ በጠፈር ምርምር ታሪክ ህዋ ላይ ሳለች ወንጀል የሠራች የመጀመሪያዋ ግለሰብ መሆኗን ናሳ ይፋ አድርጓል።
ጠፈርተኛዋ ከፍቅር ጓደኛዋ ጋር ከተቃቃረች ቆየት ብሏል። ህዋ ላይ መሆኗ ታዲያ የቀድሞ ወዳጇን የባንክ አካውንት ከመፈተሽ አላገዳትም። አን የቀድሞ ወዳጇን የባንክ አካውንት መፈተሿን ብታምንም፤ "ምንም አላጠፋሁም" ማለቷን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። አን እና ስመር እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2014 ትዳር መስርተው፤ 2018 ላይ ተለያይተዋል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? የቀድሞ ወዳጇ ስምር ዎርደን ጉዳዩን ለንግድ ኮሚሽን ሪፖርት ካደረገ በኋላ፤ ጠፈርተኛዋ ወደ መሬት ተመልሳለች። አን በጠበቃዋ በኩል ለኒዮርክ ታይምስ እንደተናገረችው፤ የስመርን የባንክ አካውንት የፈተሸችው አብረው ሳሉ በጋራ ያሳድጉት የነበረውን የስምር ልጅ የሚያስተዳድርበት በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ ነበር። ጠበቃዋ ረስቲ ሀርዲን "አንዳችም ጥፋት የለባትም" ሲሉ ተደምጠዋል። • በ2024 እቃና ሰው ጫኝ መንኮራኩር ወደጨረቃ ይላካል ተባለ ናሳ ጉዳዩን ከሁለቱም ግለሰቦች እያጣራ እንደሚገኝ ለኒውዮርክ ታይምስ ገልጿል። አን 2013 ላይ ናሳን ከመቀላቀሏ በፊት ለ800 ሰዓታት የጦር አውሮፕላን ወደ ኢራቅ አብርራለች። ናሳ ሙሉ በሙሉ ሴቶች ያሳተፈ የህዋ ጉዞ ለማድረግ ባቀደበት ወቅት ከተካተቱ ጠፈርተኞች አንዷ ናት። ሆኖም ናሳ "ለጠፈርተኞቹ የሚሆን ልብስ አላዘጋጀሁም" ብሎ ጉዞው መሰረዙ ይታወሳል። ለመሆኑ ህዋ ላይ ሕግ የሚተገበረው እንዴት ነው? የህዋ ማዕከሉ ባለቤቶች አሜሪካ፣ ሩስያ፣ አውሮፓ፣ ጃፓን እና ካናዳ ናቸው። አንድ ሰው ወንጀል ቢፈጽም የሚጠየቀው በአገሩ ሕግ ነው። • ለመብረር የተዘጋጁት ልጃገረዶች አንድ አገር ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረውን ግለሰብ በሌላ አገር ሕግ ለመዳኘት ከወሰነች፤ ግለሰቡ ወደ ምድር እንዲመለስ ከተደረገ በኋላ ለፍርድ ይቀርባል። ከዚህ ቀደም ህዋ ላይ ወንጀል ተሠርቶ ስለማያውቅ የህዋ ሕግ ተግባራዊ የሚሆንበት እድል አልነበረም። ምናልባትም ቱሪስቶች ህዋን መጎብኘት ሲጀምሩ ሕጉን መተግበር ይጀመር ይሆናል።
news-52740282
https://www.bbc.com/amharic/news-52740282
ኮሮናቫይረስ፡ የኢትዮጵያ የአበባ ምርት ፍላጎት በአውሮፓ እያንሰራራ ነው ተባለ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ በመታት በአውሮፓ ውስጥ የበሽታው ጉዳት እየቀነሰ መምጣቱ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ የአበባ ምርት ተፈላጊነት እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ።
ከቻይና በመቀጠል የኮሮናቫይረስ በበርካታ የአውሮፓ አገራት ውስጥ ተዛምቶ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ በመያዛቸው በንግድና በእንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት ፈጥሮ ነበር። በሽታው በርካታ ሰዎችን የገደለባቸው አገራት በወረርሽኙ መስፋፋት ላይ ለውጥ በመታየቱ የእንቅስቃሴ ገደቦች ላልተው ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ለኢትዮጵያ አበቦች ያለው ፍላጎት እየተሻለ መምጣቱ ተነግሯል። አውሮፓ ውስጥ በበሽታው ምክንያት ተቀዛቅዞ በነበረው የአበባ ፍላጎት ላይ ጥሩ ለውጥ እንዳለ የተናገሩት የኢትዮጵያ አበባ አትክልት እና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴወድሮስ ዘውዴ ናቸው። ዋና ዳይሬክተሩ ከእንቅስቃሴ ገደቦች መላላት ጋር ተያይዞ በአውሮፓ ገበያ ላይ ለኢትዮጵያ አበቦች ያለው ፍላጎት ከማንሰራራቱ ጋር ተያይዞ በገበያም ሆነ በዋጋ በኩል ጭማሪ መኖሩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከየካቲት ወር ጀምሮ አስደንጋጭ የሚባል የገበያ እና ዋጋ መውደቅ እንደነበር የተናገሩት አቶ ቴወድሮስ በተያዘው የግንቦት ወር ላይ የፍላጎትና የዋጋ መሻሻል አለ ብለዋል። በተለይ ለኢትዮጵያ አበባ ትልቅ የገበያ መዳረሻ ናቸው የሚባሉት እንደጀርመን እና ስዊትዘርላንድ ያሉት አገራት ድንበሮቻቸውን መክፈታቸውና የእንቅስቃሴ ገደቦች መላላታቸው ለአበባ ገበያው ማንሰራራት ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አገራቱ ከወሰዷቸው እርምጃዎች በተጨማሪ "ከእናቶች ቀን መከበር ጋር ተዳምሮ ገበያው ላይ መነቃቃት ፈጥሯል" ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጨምረውም አሁን ካሉት ተስፋ ሰጪ ለውጦች በተጨማሪ ሌሎችም አገራት ድንበሮቻቸውን ሲከፍቱና የጣሉትን የእንቅስቃሴ ገደቦች ሲያላሉ የአበባ ፍላጎትና ዋጋው መሻሻሉን ይቀጥላል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአበባ ልማት ዘርፍ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ መንግሥት በብድር፣ በጉምሩክ እና በሌሎች ተያያዥ ዙሪያ ላቀረቡት ጥያቄ ፈጣን ምላሽና ድጋፍ እንደሰጣቸው ጠቁመዋል። አቶ ቴዎድሮስ እንዳሉት ባለፉት ወራት አምራቾች ቀላል የማይባል ፈተና ገጥሟቸው እንደነበር አስታውሰው፤ ነገር ግን በዚህ ሳቢያ የአበባ እርሻዎች ሰራተኞችን አለመቀነሳቸውን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት በምርቶች ፍላጎት ላይ መሻሻሎች እየታዩ በመሆናቸው የአበባ እርሻዎች ሙሉ ለሙሉ ወደ መደበኛ ሥራቸው እየገቡ መሆናቸውንም አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ተናግረዋል።
41263763
https://www.bbc.com/amharic/41263763
የመጀመሪያውን ፊደል በ60 ዓመቷ መቁጠር የጀመረችው ኬንያዊቷ ፍሎረንስ
ዕድሜ ስድሳ ከረገጠ በኋላ ማንበብ መጀመር ምን ይመስላል? ይህን ሁሉ ዕድሜ ሳናነብ ከተጓዝን በኋላ ማንበብ መጀመርስ ምን ዓይነት ለውጥ ያመጣል?
ማንበብ በመቻላችን ምክንያት በየሰዓቱ ምን ያህል መረጃ እንደምናጋብስ ብናስበው ሊገርመን ይችላል። ጋዜጣ አንብበን በአከባቢያችን ብሎም በዓለም ዙሪያ ምን እየተከናወነ እንዳለ ማወቅ ስንችል፤ ቢሯችን ገብተን በበይነ-መረብ 'ኢ-ሜይል' የተደረገልንን መልዕክት ስናጣራም ሆነ በተንቀሳቃሽ ስልካችን የተላከልንን መልዕክት ስናነብ ብዙ መረጃዎችን እንቃርማለን። ስራችንን ያለ እነዚህ ነገሮች መከወን እጅጉን አዳጋች ሊሆንብን ይችላል። ነገር ግን ማንበብ ባንችል ብለን ብናስብስ? ቼሶንጎች በተባለ የኬንያ ገጠራማ አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ፍሎረንስ ቼፕቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊደል የቆጠረችው በ60 ዓመቷ ነው። የፍሎረንስ የልጅ ልጅ ከትምህርት ቤት መፅሓፍ ይዛ ስትመጣ ነበር ሴት አያቷ ፊደል ለመጀመሪያ ጊዜ የገለጠችው። ቡክ ኤይድ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት ነበር የፍሎረንስ የልጅ ልጅ ለምትማርበት ትምህርት ቤት ቤተ-መፃሕፍት ከእንግሊዝ አታሚዎች ያመጣቸውን መፃሕፍት የለገሰው። ነገር ግን የአብዛኛዎቹ ልጆች ወላጆች እና አያቶች እራሳቸው ማንበብም ሆነ መፃፍ የሚችሉ ባለመሆናቸው አስተማሪዎቹ እነሱንም ለማስተማር ቆረጡ። "ፊደል መቁጠር የጀመርኩት በ60 ዓመቴ ነው" የምትለው ፍሎረንስ ስትናገር "ማንበብ ከቻልኩ ወዲህ የሰለጠነውን ዓለም የተቀላቀልኩ ሆኖ ተሰማኝ" ትላለች። "ልጅ እያለሁ ቤተሰቦቼ እኔ እንድማር ብዙ አያግዙኝም ነበር። አግብቼ፣ ለነሱም ጥሎሽ አምጥቼ ከብቶችን እየጠበኩ እንድኖር ነበር ፍላጎታቸው። ቤተሰቦቼ ትምህርት የነበረው ጥቅም ብዙ አልገባቸውም ነበር" ስትል ታክላለች ፍሎረንስ። ፍሎረንስ ፊርማ ማሳረፍም ሆነ ማንኛውንም ሕጋዊ ወረቀት አንብባ መረዳት አትችልም ነበር። ባለፈው ሕይወቷ ተጭበርብራም እንደሆን የምታውቀው ነገር የላትም። አሁን ግን ፍሎረንስ ማንበብ ችላለች። ማንበብ መቻሏ የሰጣትን ጥቅምም ዘርዝራ አትጨርስም። የታዘዘላት መድሓኒት ጥቅም እና የጎንዮሽ ጉዳት ከመረጃ መስጫ ወረቀቱ ላይ አንብባ በቀላሉ መረዳትም ትችላለች። ጋዜጣ አንብባ የውጭው ዓለም ላይ ምን እየተከናወነ እንዳለ እየተገነዘበችም ትገኛለች። ከሁሉም በላይ ግን ታሪክ አዘል መፃሕፍትን፤ ከቤተዘመድ የሚላክላትን ደብዳቤ እንዲሁም መፅሐፍ-ቅዱስን ማንበብ መቻሏ እጅግ ደስታ እንደሰጣት ትናገራለች። "በተጨማሪም የዓለም ካርታን እያየሁ ሌሎቻ ሀገራት የት እንዳሉ ማወቅ መቻሌ ትልቅ ደስታ ይሰጠኛል" ባይ ነች። "ሌላው ደግሞ ግብርና ላይ የተፃፉ መፃሕፍትን በማንበቤ እንዴት እርሻየን መንከባከብ እንዳለብኝም አውቄያለሁ" በማለት ታክላለች ፍሎረንስ። የልጅ ልጇን የትምሀርት ቤት ውጤትም ማጣራት ችላለች ፍሎረንስ። ማንበብ ከሚችሉም ሆነ ከማይችሉ ሰዎች ጋር ስትሆን ድሮ የነበረባት ዝምታ ተሽሮ አሁን በልበ ሙሉነት መጫወት ጀምራለች። "በማሕበረሰባችን ውስጥ ያሉ ጥሩ እና ጎጂ የሆኑ ህግጋት እና ባህሎች አሁን ተለይተው ተገልጠውልኛል" ትላለች ፍሎረንስ ስታስረዳ። ፍሎረንስ ብቻ ሳትሆን ሌሎችም ዕድሜያቸው የገፋ የማሕበረሰቡ አባላት የንባብ ትምህርቱን መውሰድ ጀምረዋል። በሰማንያዎቹ ዕድሜ መባቻ ላይ የሚገኙ አዛውንትም የትምህርቱ አካል ነበሩ። እርግጥ የአዛውንቱ ዓይን ደክሞ መፃፍ እና ማንበብ ቢያግዳቸውም ለወጡበት ማሕበረሰብ መልዕክት ለማስተላለፍ ሲሉ ወደ ትምህርት ቤት እንደሚመጡ ይናገራሉ። ቡክ ኤይድ ከተባለው ድርጅት የመጣችው ኤማ ቴይለር የነፍሎረንስን ትምህርት ቤት ቤተ-መፃሕፍት ከጎበኘች በኋላ መፃህፍቱ በዕድሜ የገፉ ሰዎችን ጭምር እንዲያነቡ በመገፋፋታቸው እጅግ መደሰቷን ትገልፃለች። "በኬንያ ገጠራማ ስፍራዎች ቤተ-መፃሕፍት ለታዳጊዎች ጥሩ ጊዜ ማሳለፊያ እየሆኑ ነው። እዚህ ሲመጡ ከለላ እንዳገኙ ይሰማቸዋል። መፃሕፍትን እንደ ጓደኞቻቸው መቁጠር ጀምረዋል" በማለት ኤማ ታስረዳለች።
51202805
https://www.bbc.com/amharic/51202805
ኤርትራን ጨምሮ አራት የአፍሪካ አገራት የአሜሪካ የጉዞ እገዳ ሊጣልባቸው ነው
ዶናልድ ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ አገራት ላይ የጉዞ ክልከላ ሊያደርጉ መሆኑ ተነገረ።
በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የጉዞ እገዳ ይጣልባቸዋል የተባሉ አገራት ዝርዝርን ተመልክተናል ያሉ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ፤ የጉዞ እገዳው ሰለባ ይሆናሉ የተባሉት የአፍሪካ አገራት ኤርትራ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን እና ታንዛኒያ መሆናቸውን ዘግበዋል። በስዊትዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ከ'ዎል ስተሪት ጆርናል' ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አራት የአፍሪካ አገራት ላይ የጉዞ እገዳ ለመጣል ማቀዳቸውን አረጋግጠው፤ የአገራቱን ዝርዝር ግን ከመናገር ተቆጥበዋል። ዘ ፖለቲኮ በበኩሉ የአገራቱ ዝርዝር የመጨረሻ ውሳኔ አለመሆኑን እና ለውጥ ሊደረግባቸው እንደሚችል አስነብቧል። ዘ ፖለቲኮ ከአራቱ የአፍሪካ አገራት በተጨማሪ ቤላሩስ፣ ምያንማር (በርማ) እና ክሪጊስታን የጉዞ እገዳ ሊጣልባቸው የሚችሉ አገራት መሆናቸውን ዘግቧል። ፕሬዝደንቱ ሊያጸድቁት እንደሚችሉ የተገመተው እና በረቂቅ ላይ የሚገኘው ሕግ፤ እገዳ የተጣለባቸውን አገራት ዜጎች ሙሉ በሙሉ ከጉዞ የሚገድብ እንዳልሆነ እና በተወሰኑ የቪዛ አይነቶች እና የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ ብቻ ገደብ እንደሚጥል ተነግሯል። የአሜሪካ መንግሥት የጉዞ እግዱን በየትኞቹ አገራት ላይ እና ምን አይነት እገዳ እንደጣለ በቀጣይ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። እነዚህ አገራት በምን መስፈርት ተመርጠው የጉዞ እገዳው እንደተጣለባቸው ግልጽ ባይደረግም፤ የአሜሪካ የስነ ሕዝብ እና ጤና ዳሰሳ ጥናት አሃዞች እንደሚያሳዩት የእነዚህ አገራት ዜጎች አሜሪካ ከደረሱ በኋላ ከተፈቀደላቸው ቀን በላይ ይቆያሉ። እ.አ.አ. 2018 ለጉብኝት ወይም ለሥራ ወደ አሜሪካ ከተጓዙ ኤርትራውያን መካከል 24 በመቶ የሚሆኑት በቪዛቸው ላይ ከተፈቀደላቸው ቀናት በላይ በአሜሪካ ቆይተዋል። 5 በመቶ የሚሆኑት ናይጄሪያውን እና 12 በመቶ የሚሆኑት ሱዳናውያን በተመሳሳይ መልኩ ከተፈቀደላቸው ቀናት በላይ በአሜሪካ ቆይተዋል። በአጠቃላይ ወደ አሜሪካ ለሥራ ወይም ለጉብኝት ተጉዘው ከተፈቀደላቸው በላይ የሚቆዩት 1.9 በመቶ የሚያህሉት መሆናቸውን አሃዞች ይጠቁማሉ። እ.አ.አ. 2017 ፕሬዝዳንት ትራምፕ አብዛኞቹ የሙስሊም አገራት ከሆኑት፤ ኢራን፣ ሶማሊያ፣ ሶሪያና የየመን ዜጎች ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ጉዞ ላይ እግድ መጣላቸው ይታወሳል። እገዳው በፍርድ ቤት ክርክር ተደርጎበት የነበር ቢሆንም፤ ሰኔ 2018 የአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን አጽንቶታል። ዲቪ ሎተሪ 'በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ ፕሮግራም' ተሳታፊ ከሆኑ ሃገራት መካከል የተወሰኑት ሃገራት በፕሮግራሙ እንዳይሳተፉ ሊደረግ እንደሚችል ጭምር ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል አስነብቧል። 'በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ ፕሮግራም' በአሜሪካ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ሃገራት ዜጎች፤ በእጣ አማካኝነት ወደ አሜሪካ መጥተው ግሪን ካርድ (የመኖሪያ ፍቃድ) የሚያሰጥ ፕሮግራም ነው። ይህ ፕሮግራም አሜሪካን የተለያዩ የዓለማችን ሃገራት ሰዎች የሚኖሩባት ልዩነቶቸን በውስጧ የያዘች ሃገር ያደርጋታል ተብሎ ሲተገበር ቆይቷል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ግን ይህ ፕሮግራም 'የማይፈለጉ' አይነት ሰዎችን ወደ አሜሪካ እያመጣ ስለሆነ መቅረት አለበት በማለት፤ በዲቪ ፕሮግራም ፈንታ ክህሎት ያላቸውን ሰዎች ለይቶ በተለየ ቪዛ ወደ አሜሪካ የማምጣት ፕሮግራም ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ይላሉ።
news-45168221
https://www.bbc.com/amharic/news-45168221
የጋሬዝ ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን፡ ሳላህ፣ ፖግባ፣ ዛሃ፣ ዎከር . . . ። ሌሎችስ እነማን ናቸው?
ያለፈው ዓመት ሻማፕዮኖች የዘንድሮውን የውድድር ዘመን አርሴናልን በማሸነፍ ጀምረዋል። የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በነበረው ማንቸስተር ዩናይትድ ሌስተር ሲቲን አሸንፏል።
ፖል ፖግባ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ጎል አስቆጥሯል። በሌሎች ጨዋታዎች ቨርፑል እና ቶተንሃምም አሸናፊ ለመሆን ችለዋል። ዎልቭሶች ሁለት ጊዜ ከኋላ በመነሳተር ከኤቨርተን ጋር አቻ ለመለያየት ችለዋል። በሳምንቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ እነማን ሊካተቱ ይችላሉ? እነሆ የጋሬዝ ክሩክስ ምርጥ 11። ግብ ጠባቂ- ዴቪድ ደ ሂያ ዴቪድ ደ ሂያ በፕሪሚር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ላይ ድንቅ ብቃቱን ማሳየት ጀምሯል። በእሱ ደረጃ ላለ ተጫዋች ከስፔን ጋር ያሳለፈው የዓለም ዋንጫ አስደንጋጭ ቢሆንም ከሌስተር ጋር ይህ አልተደገመም። ያዳናቸው ሁለት ኳሶች ማንቸሰተር ዩናይትድ ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሎታል። ይህን ያውቃሉ? ማንቸስትር በመጀመሪያ ጨዋታው ሌስተርን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሶስት ኳሶችን አድኗል። ተከላካዮች፡ አሮን ዋን-ቢሳካ፣ ካይል ዎከር፣ ቪጂል ቫን ዳይክ እና ሉክ ሾው አሮና ዋን-ቢሳካ፡ የ20 ዓመቱ ተጫዋች ድንቅ እንቅስቃሴ አሳይቷል። ዋን ቢሳካ ሪያን ሴሴኞን፥ አንድሬ ሹርለን እና አቡባከር ካማራን በፍጥነት ካለፈ በኋላ ከአሌክሳንደር ሚትሪቪችን በጉልበት በመብለጥ ለዊልፍሬድ ዛሃ ያቀበላት ኳስ ከመረብ አርፋለች። ፓላሶች አልማዝ ያገኙ ሲሆን እኔ ብሆን ለረዥም ጊዜ የሚያቆየውን ውል በፍጥነት አስፈርመው ነበር። ይህን ያውቃሉ? ዋን-ባሰካ ለጎል የሚሆን ኳስ ከማመቻቸቱም በላይ ጎል እንዳይቆጠርባቸው እገዛ አድርጓል። ካይል ዎከር፡ ዎከር ድንቅ ተጫወች እየመሰለ ነው። አርሰን ቬንግር አይሆነውም ባሉት የሶስት ተከላካይ መስመር ላይ በመሰለፍ በዓለም ዋንጫው ላይ ጥሩ ተንቀሳቅሷል። በፕሪሚየር ሊጉ መክፈቻ ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ ድንቅ ተከላካይ ሆኖ አምሽቷል። ይህን ያውቃሉ? ዎከር ከአርሴናል ጋር በነበረው ጨዋታ 23 ጊዜ በፍጥነት ሲምዘገዘግ ነበር። ይህ ደግሞ በመጀመሪያው ሳምንት በተከላካኦች ከተደረጉት ሁሉ የላቀው ነው። ቪጂል ቫን ዳይክ ፡ ሊቨርፑል ዌስት ሃምን 3 ለ 0 እየመራ ባለበት ወቅት እንኳን አብረውት ያሉትን ተከላካዮች ጎል ሳይቆጠርባቸው ጨዋታውን ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ሲያሳስብ ነበር። ይህ ቫን ዳይክ ወደ ቡድኑ ከመምጣቱ በፊት እና አሁን ያለው ሊቨርፑል ልዩነት ነው። ይህን ያውቃሉ? ከዌስት ሃም ጋር በነበረው ጨዋታ 98.4 በመቶ የተሳኩ ኳሶችን አቀብሏል። ሉክ ሾው ማንቸስተሮች ባሳዩት ጥሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ወደ አሰልጣኝነት የተቀየረው ማይክል ካሪክ ሚና እንደነበረው አምናለሁ። ሾው በጨዋታው ላየዕ ይሳተፋል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ሾው ከሁለት ዓመት በፊት ከቼልሲ ጋር በነበረ ጨዋታ ላይ ግራ ተጋብቶ እንደነበር አስታውሳለሁ። ከሌይስትር ጋር ግን ተከላካዩ ድንቅ ነበር። ይህን ያውቃሉ? ሾው በ134 ጫወታዎች የመጀመሪያ ጎሉን ነው ያስቆጠረው። አማካዮች ሮቤርቶ ፔሬራ፣ ሩበን ኔቬስ እና ፖል ፖግባ ሮቤርቶ ፔሬራ፡ ክሪስ ሃተን ጥሩ የቅድመ ውድድር ጊዜ ማሳለፋቸውን እና ለዋትፎርድ ዝግጁ መሆናቸውን ቢገልጹም ፔሬራ ነጥብ አሰጥሏቸዋል። ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረው ሮቤርቶ ፔሬራ በሊጉ አራት ተከታታይ ዓመታት የቆዩትን ዋትፎርዶችን ለሌላ ተጨማሪ ዓመት በሊጉ ለመቆየት የሚችሉ አይነት አስመስሏሰቸዋል። ይህን ያውቃሉ?ባለፉት ስድስት የዋትፎርድ የሊጉ ጎሎች ውስጥ ፔሬራ ተሳትፎ ነበረው። አምስት አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ በማቀበል። ሩበን ኔቬስ: ፖርቹጋላዊው ተጫዋች ገና በ 21 ዓመቱ ድንቅ መሆኑን አሳይቷል። ዎልቭሶችን በሊጉ ማቆት የሚችል ከሆነ ባርሴሎና ወይንም ሪያል ማድሪድ ሊወስዱት ማሰባቸው አይቀርም። ይህ ከሆነ የክለቡ ደጋፊዎችም ተጫዋቹ ስለመቆየቱ ጥርጣሬ ይገባቸዋል። ይህን ያውቃሉ? ካለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ ከእንግሊዝ አራት ከፍተኛ ሊጎች ውስጥ ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውጭ ሰባት ጎሎችን በማስቆተር ቀዳሚ ነው። ፖል ፖግባ፡ ጆሴ ሞውሪንሆ በውድድር ዓመቱ መክፈቻ ጨዋታ ላይ ፖል ፖግባን የቡድናቸው አምበል ያደረጉት ሲሆን ይህም ከየዓለም ዋንጫ አሸናፊው ከአሰልጣኙ የሚያገኘው ብቸኛ ማበረታቻ ሊሆን ይችላል። ተጫዋቹም ከሌስትር ጋር በነበረው ጨዋታ ድንቅ በመሆን ምላሹን ሰጥቷል። ይህን ያውቃሉ? ፖግባ በሶስተኛው ደቂቃ ኣስቆጠራት ጎል ማንቸስትር ዩናይትድ በውድድር መክፈቻ በፍጥነት ያስቆተራት ጎል ናት። ከዚህ በፊት ድዋይት ዮርክ በሰባተኛው ደቂቃ ላይኤቨርተን ላይ አስቆትሮ ክብረወሰኑን ይዞ ነበር። • አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ • የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ: የላውሮ ግምት አጥቂዎች- ሞሃመድ ሳላህ፣ ዊልፍሬድ ዛሃ እና ሪቻርልሰን ሞሃመድ ሳላህ: የተለመደው አገልግሎት ተጀምሯል። ሳላህ አንፊልድ ላይ ብቃቱን ማሳየቱን ቀጥሏል። ሊቨርፑሎች አሁን እያሳዩ ያሉትን አጨዋወት አደንቃለሁ። ኳስ በሚገርም ፍጥነት ወደ ተቀናቃኝ ሜዳ ይዘው ይሄዳሉ። ይህን ያውቃሉ? ሳላህ ሊቨርፑል በሊጉ ከዌስት ሃም ጋር ባደረጋቸው ሶስት ቸዋታዎች በአምስት ጎሎች ላይ በቀጥታ ተሳትፎ ነበረው። ዊልፍሬድ ዛሃ: ይህ ከዛሃ ያየሁት ምርት እንቅስቃሴ ባይሆንም ከሪያን ሴሴኞን የምጠብቀውን ነው ያደረገው። ስለፉልሃሙ ተጫዋች ብዙ የሰማሁ ሲሆን ይህን ለማየትም እየጠበቅኩ ነው። ፓላስ ውስጥ ጊዜው የዛሃ ሲሆን ሴሴኞን ግን ገና ታዳጊ ነው የሚመስለው። ይህን ያውቃሉ?ዛሃ ለክሪስታል ፓለስ በፕሪሚየር ሊጉ 23ኛ ጎሉን ነው ያስቆጠረው። ይህም ከክሪስ አርምስትሮንግ ጋር እኩል አድርጎታል። ሪቻርልሰን: ለተጫዋቹ ይህ ድንቅ አጀማመር ነው። ቡድኑ ዳኛው በወሰኑት ውሳኔ ባይጎዳ የሪቻርልሰንን ጎሎች ተጠቅሞ ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሶ ነበር። በአወዛጋቢ ውሳኔዎቻቸው ምክንያት የእንግሊዝ ዳኞች ተመራጭ አይደሉም። የሊጉ ዳኞች ለዓለም ዋንጫ ለምን እንደ፥ኣይመረጡ ለማወቅ ክሬግ ፓውሰን ፊል ጃጊኤልካን ከሜዳ ያሰናበቱበትን ሁኔታ ማየት በቂ ነው። ይህን ያውቃሉ? ለኤቨርተን ካደረጋቸው ሁለት ሙከራዎች ነው የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረው። ወዋትፎርድ እያለ 53 ጊዜ ሞክሮ ጎል ማስቆተር አልቻለም ነበር።
news-45545757
https://www.bbc.com/amharic/news-45545757
የምግብ ብክነትን ለማስቀረት መተግበሪያ በናይጄሪያ
"ለማንኛውም ሰው ለማንኛውም ልጅ ያለምግብ የማይታመን ነው። አቅልንም ያሳጣል።"
ኦስካር ኢፖኒሞ ከቾውቤሪ ጀርባ ያለ ስራ ፈጣሪ ነው "አስታውሳለሁ ልጅ እያለሁ ምግብ ስላልነበረ በቀን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነበር ጥሩ ምግብ የምበላው።" የኦስካር ኢፖኒሞ ጥረት የልጅነት ርሃብ ያቀጣጠለው ነው። አባቱ በህመም ምክንያት ሥራ መስራት ባለመቻሉ ቤተሰቡ በሙሉ ተርቦ ነበር። • የምግብ ብክነትን ለማስወገድ አዲስ ፈጠራ • አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው? አሁን ግን በናይጀሪያ ዋና ከተማ አቡጃ የሚገኘው ይህ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሥራ ፈጠሪ ለዚህ የምግብ አቅርቦት የኢፍትሃዊነት ችግር ምላሽ አለው። ቾውበሪ የተሰኘ እና ሰዎችን መጨረሻው የቆሻሻ ገንዳ ሊሆን ከሚችል ምግብ ጋር የሚያገናኝ መተግበሪያ ባለቤት ነው። እስካሁን መተግበሪያው 35 በሚሆኑ በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና በናይጄሪያ በሚገኙ ሌሎች ተቋማት ተቀባይነትን አግኝቷል። በአቡጃ በሚገኝ አንድ ሱፐር ማርኬት ውስጥ ያለ አንድ የሽያጭ ረዳት በስንዴ ዱቄት ከተሞላው መደርደሪያ ወደ ሱቁ ጋሪ እየጫነ ነው። የቾውበሪ መተግበሪያን በመጠቀም ምርቱን በቅናሽ ዋጋ ለገዛው ስሪፍቲ ስላየር ለተባለው ግብረሰናይ ድርጅት እያዘጋጀ ነው። ቅናሽ የተደረገባቸው ምርቶች በአንደኛው መተላለፊያ ቆመን እያለ ኦስካር ቴክኖሎጂው እንዴት እንደሚሰራ ሊያሳየኝ ታብሌቱን አወጣ። "በዚህ መተግበሪያ ውስጥ ነጋዴዎችን የአገልግሎት ጊዜያቸው ሊጠናቀቅ የተቃረቡ ምርቶቻቸውን በተመለከተ መረጃ እንዲያስቀምጡ የሚረዳቸው የአሰራር ሥርዓት ወይም ሲስተም አለን" በማለት ያብራራል ኦስካር። "እነዚህ ምርቶች የአገልግሎት ጊዜያቸው እየተገባደደ በመሆኑ በነጋዴዎቹ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ተደርጎባቸዋል። ምግቦቹ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሲያልፍ በነጋዴዎቹ እንደዋዛ ሊጣሉ ይችሉ የነበሩ ናቸው። በእኛ የአሰራር ሥርዓት ምክንያት ግን ኪሳራቸውን ሊያድኑ የሚችሉበት መንገድ አላቸው።" "በተመሳሳይ ሰዓት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ምግቡን በርካሽ ዋጋ በመውሰድ የሚያሰራጩት ተጨማሪ ምግብ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።" ሊጣሉ ይችሉ የነበሩ ቅናሽ የተደረገባቸው ምርቶች ለምግብ ዋስትና ችግሮች አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ይህ ሱፐር ማርኬት ቾውበሪ የተባለውን መተግበሪያ መጠቀም የጀመረው ያኔ የዛሬ ሁለት ዓመት ወደ ሥራ እንደገባ ነበር። "ከእኛ ጋር የሚሰሩት አንዳንድ ሱቆች ከዚህ በፊት ይጥሉት ከነበረው እስከ 80 በመቶ የሚደርስ ምግብ ማዳን እንደቻሉ ይናገራሉ" ይላል ኦስካር። በተባበሩት መንግሥታት የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው በመላው ዓለም ለምግብነት ከሚመረተው ምግብ አንድ ሦስተኛው ይጠፋል ወይም ይጣላል። • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ • የ15 ዓመቷ ታዳጊ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ቀልብ እየገዛች ነው ይህም በየዓመቱ 1ነጥብ 3 ቢሊዮን ቶን ይሆናል። የተባበሩት መንግሥታት አሃዝ አክሎም ምንም እንኳን በቂ ምግብ በዓለም ላይ ቢኖርም ከዘጠኝ ሰዎች አንዱ ጾሙን እንደሚያደር ይጠቁማል። የኦስካር ችግሩን የመገንዘብ አቅም በታችኛው ረድፍ ላይ የሚገኙትን እጅግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የመድረስ ተልዕኮው ማጠንጠኛ ነው። "እነዚህ ሰዎች ዘመናዊ ስልኮች ባይኖሯቸውም ከመተግበሪያው ተጠቃሚ እንዲሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ወሳኝ ናቸው" ይላል ኦስካር። መንግሥታዊ ያልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ፕያካሳን በመሳሰሉ ከተሞች ለሚኖሩ ሰዎች ምሳ በማቅረብ እያገዟቸው ነው ስሪፍቲ ስላየር የቾዉበሪ መተግበሪያን በመጠቀም ለምግብ ስርጭት መርሃ-ግብራቸው ቅናሽ የተደረገባቸውን ምርቶች ከሚገዙት በርካታ ግብረ ሰናይ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው። መርሃ ግብራችው የሚደገፈው የተለገሳቸውን ልባሽ ጨርቆች በመሸጥ ነው። ነገር ግን የስሪፍቲ ስላየር መስራች ልጅኦማ ንዊዙ እንደሚሉት ቾውቤሪ የድጋፍ መጠናቸውን ከፍ እንዲል አድርጎላቸዋል። "ምገባውን የጀመርነው በ40 ሰዎች ነበር፤ ነገር ግን የማህበረሰቡ ቁጥር ማሻቀቡን ቀጠለ። አሁን እነሱን እና በአቅራቢያው የሚገኙ ማህበረሶችን ጨምሮ ወደ 200 ያህል ሰዎች በየሳምንቱ እሁድ እንመግባለን" ይላሉ። • የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች • ከጋና የፈጠራ ሥራዎች ጀርባ ያለው ሥራ ፈጣሪ "የምንመግባቸው ሰዎች ቁጥር እያደገ ሲመጣ ወጪያችንን ለመቀነስ አማራጭ መንገዶችን መፈለግ ጀመርን። ከቾውበሪ ጋር አብሮ የመስራት መልካሙ ነገርም ምግብን በምንፈልገው ብዛት ማግኘት ማስቻሉ ነው።" የተባበሩት መንግሥታት አሃዝ እንደሚያሳየው በናይጀሪያ ከ14 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ችግር አለባቸው። የምግብ ዋስትናን የሚያቀነቅነው ሼሁ ሙሳ ያርአድዋ ፋውንዴሽን ውስጥ ዳይሬክተር አማራ ንዋንክፓ እንደሚሉት ርሃብ ዋነኛው ችግር ነው። "እኔ እንደማስበው በምግብ አቅርቦት እና ተደረሻነት የገጠመን ችግር ለፈጠራ ሰዎች መልካም አጋጣሚን ሆኖላቸዋል። ከችግሩ ለመውጣት ከፈጠራ ውጪ ምንም አማራጭ የለንም" ይላሉ አማራ። ኦስካር ኢፖኒሞ መተግበሪያውን የፈጠረው ከእራሱ የልጅነት ርሃብ በመነሳት ነው የምገባ መርሃ ግበር በሚካሄድባት ከአቡጃ ወጣ ብላ በምተገኘው ፕያካሳ በተሰኘችው አነስተኛ እና በተራሮች በተከበበችው ከተማ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት። "ብዙውን ጊዜ ጉዳዩን በተመለከተ ስሜታዊ እሆናለሁ። በቀላል ሀሳብ ሰዎችን በትክክለኛው መንገድ መድረስ እንደሚቻል ቀልቤ ይነግረኛል። ግን ስሜቴ የተደበላለቀ ነው" ብሏል። ከእርሱ ጋር ለጉብኝት በሄድንበት ወቅት በዋናነት ሴቶች እና ህጻናት የሆኑ 50 ያህል ሰዎች ለምሳ ተሰልፈው ነበር። እንደተነገረን ለአብዛኞቹ ይሄ የሳምንቱ ትልቁ የምግብ ጊዜያቸው ሊሆን ይችላል። ኦስካር እንደሚለው "ችግሩ ማስፋቱ ላይ ነው። ሥራችን ለመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ተቋርጦ የሚቆየው እዚያ ላይ ነው። በረጅሙ ጉዞ ውስጥ አለሁበት። የምግብ እሴት ሰንሰለት እስካለ ድረስ መቼውንም ቢሆን በአካባቢው የምግብ ዝውውሩ ይቀጥላል።" የምግብ ብክነት ከፍተኛ ችግር ነው፤ ይህ ሥራ ፈጣሪም ለዚህ ቀላል መፍትሄ ዓለም አቀፍ ምኞቶች አሉት። አንድ ጊዜ በናይጀሪያ እና በአህጉረ አፍሪካ ተጽዕኖ ማሳደር ከጀመረ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሰዎችን ህይወት መቀየሩን እንደሚቀጥል ተስፋ ሰንቋል። ይህ የቢቢሲ ተከታታይ መሰናዶ የተዘጋጀው ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው። #bbcinnovators
news-51440267
https://www.bbc.com/amharic/news-51440267
''የአሰብና ምፅዋ ወደቦችን አገልግሎት ለማሻሻል እየሰራን ነው'' ፕሬዚዳንት ኢሳያስ
የምፅዋና የአሰብ ወደቦች የሚሰጡትን አገልግሎት የማሻሻል ስራዎች እየሰሩ እንደሆነ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትናንትናው ዕለት ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ከኃገሪትዋ ውስጣዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት ከመንግስት መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው። የነዚህን ወደቦችን አገልግሎት ውጤታማነት ለመጨመር የማደስ፣ የማስፋትና የማሳደግ ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል። • "የኤርትራ መሬት ያልተመለሰው በህወሓት እምቢታ ነው" ፕ/ት ኢሳያስ • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? "ወደቦቹን ስናሻሽል ኢትዮጵያን ብቻ እያሰብን አይደለም፤ ዋነኛ ትኩረታችን ቀይባሕር በቀጠናው ላይ ያላትን ቦታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰፋ ያለ አገልግሎት እንዲሰጡ ያለመ እቅድ ነው" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ "ከተጋገዝን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ስለምንችል በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ውህደት መፍጠር" አንዱ የመንግስታቸው ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከወደቦች በተጨማሪ ከመንገድ ግንባታ ጋር የተያዙ እቅዶችም ላይ መረጃ የሰጡ ሲሆን፤ በዚህም ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኙ መንገዶችም የሚያስፈልጋቸውን ጥገናም ሆነ ግንባታ ለመስራት መንግሥታቸው አቅዷል ብለዋል። በዚህም መሰረት ከአሰብ በደባየሲማ ኢትዮጵያን የሚያገናኘውን መንገድ የማስፋት፤ ከምጽዋ በደቀመኃሪ አድርጎ ዛላምበሳ፤ ከአስመራ በመንደፈራ፣ ራማን የሚያገናኙት የአስፋልት መንገዶች ደግሞ የማሻሻል ስራዎች በዚህ አመት እንደሚጀመሩና፤ የተጀመሩትም እንደሚጠናቀቁ ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቱ በሃገሪቱ ውስጥ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን፣ ኢንቨስትመንት፣ የኑሮ ውድነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህም መካከል ለሁለት አስርት አመታት ሲንከባለል የመጣው የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ ማስተካከያ ጥያቄ ላይ ምላሽ የሰጡት ፕሬዚዳንቱ ሰራተኞች አስፈላጊውን የኑሮ ወጪ የሚሸፍንላቸው በቂ ደመወዝ እንዳልነበራቸው አምነዋል። መንግሥታቸው ይህንን ችግር ለመፍታት ከሁለት አመታት በፊት የደመወዝ ማስተካከያ ማድረግ መጀመሩን ጠቁመው፤ በደመወዝ ማስተካከያው ሂደት እስከ አሁን ጭማሪው ያልደረሳቸው የመንግስት ሰራተኞች የሁለት ዓመት ድምር እንደሚደርሳቸው ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል። መንግሥት የደመወዝ ማስተካከያ አሰራሩንም ለመተግበር እክሎች እንደገጠሙት የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ይህም በሃገሪትዋ "ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች" የሸቀጦች ዋጋ ንረት በመፈጠሩ ነው ብለዋል። "መንግሥት ይህ ኢ-ምክንያታዊ የሆነ የዋጋ ንረትን በቸልታ አያልፈውም ፤ እርምት ይወስዳል" በማለት አስጠንቅቀዋል ያለውን የዋጋ ንረት ለማስተካከልም ባለፉት ዓመታት መንግሥት የቤት ኪራይ፣ ስጋ እና የታሸገ ውሀ ላይ የዋጋ ተመን ማድረግ እንደጀመረ ምንጮች ይገልጻሉ። የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ዋነኛው የሀገሪትዋ ቁልፍ ችግር እንደሆነ ያወሱት ፕሬዚዳንቱ መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት ብሎ የጀመራቸው የቤቶች ግንባታ ቢጀምርም፤ ያላለቁ ቤቶች ግን በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች • ኤርትራ በዶይቼ ቬለ ዘገባ ሳቢያ የጀርመን አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀች በሂደትም መንግሥት ጥናት አካሂዶ አዋጪ ሆኖ ከተገኘ በቤቶች ግንባታ የውጪ ተቋራጮች ጭምር ለማሳተፍ ሀሳብ እንዳለ የገለጹት ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፤ ያላለቁ እቅዶች ስላሉ በዚህ አመት የሚሰሩ ስራዎችን ለማስቀመጥ ትንሽ ከባድ እንደሆነ በመጠቆም ዝርዝርም ሆነ ቀነ ገደብ ከማስቀመጥ ተቆጥበዋል። ፕሬዚዳንቱ አንዳንድ ሃገሪቷ ያሉባትን ችግሮች በግልፅ ከመናገር ወደኋላ ያላሉ ሲሆን በተለይም ባለፉት 20 ዓመታት "አክስሮናል" ያሉትን የትምህርት ዘርፍ ፖሊሲ ለሀገሪትዋ ኢኮኖሚ ዋነኛው ምሰሶ በመሆኑ ስር ነቀል ለውጥ ሊመጣ ይገባል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቀይ ባህር በዓመት እስከ 100 ሺ ቶን የአሳ ሀብት ማግኘት እየታቸለ ባለፉት 20 ዓመታት ግን አስር ሺ ቶን ብቻ እንደነበረ ገልጸዋል። ይህንን የአሳ ሀብት ለማሳደግም አስፈላጊውን የመሰረተ ልማት ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን አብራርተዋል። ፕሬዚዳንቱ መንግሥታቸው በዚህ አመት ከያዟቸው ሌሎች እቅዶች መካከል በአሰብ፣ ምጽዋ እና አስመራ ከተሞች 60 ሜጋ ዋት ኤሌትሪክ ከታዳሽ ኃይል ለማመንጨት የተለያየ መጠን ያላቸው የውሀ ግድቦች የሚገነቡ ሲሆን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ለማበረታት አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንደሚሰሩም አስረድተዋል።
news-55074075
https://www.bbc.com/amharic/news-55074075
አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና አረፈ
ከምድራችን የእግር ኳስ ኮከብ ተጫዋቾች መካከል ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የሚጠቀሰው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በ60 ዓመት ዕድሜው አረፈ።
የቀድሞው የአርጀንቲና ኮከብ ተጫዋች እና በኋላም የአገሩ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ያረፈው ቤቱ ውስጥ ሳለ በልብ ችግር እንደሆነ ተገልጿል። ማራዶና በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ በአንጎሉ ውስጥ ላጋጠመው የደም መርጋት የተሳካ ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት የነበረ ሲሆን በተከታይነትም ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ ሕክምና ይደረግለታል ተብሎ ነበር። የዓለማችን የምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች ከሚባሉት አንዱ የሆነው ማራዶና አርጀንቲና እአአ በ1986 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ስትሆን የቡድኑ አምበል የነበረ ሲሆን ድንቅ ችሎታውንና የታወቀባቸውን የኳስ ጥበቡን በማሳየት ዓለምን አስደምሞ ነበር። በተለይ በወቅቱ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ጋር ባደረገችው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ እሱ "የእግዜር እጅ" ያላትና ዳኞች ሳያዩ በእጁ ያስቆጠራት ግብ ዘወትር ትታወሳለች። በተጨማሪም ለስፔኑ ባርሴሎናና ለጣሊያኑ ናፖሊ ቡድኖች በአውሮፓ ውስጥ የተጫወተ ሲሆን፤ በጣሊያን ሴሪ አ ውስጥም ሁለት ጊዜ ዋንጫ ለማንሳት በቅቶ ነበር። የአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበር የማራዶና ሞት በተሰማ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ "በጀግናችን ሞት በጣሙን አዝነናል" በማለት "ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ ትኖራለህ" ብሏል። ማራዶና ለአገሩ አርጀንቲና በአራት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በተደረጉ 91 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 34 ግቦችን አስቆጥሯል። ማራዶና የተከለከሉ አበረታች መድኃኒቶችንና ዕጽ በመጠቀም ስሙ በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየ ሲሆን ከስፖርትም እገዳ ተጥሎበት ነበር። ማራዶና ፕሮፌሽናል እግር ኳስን ከዛሬ 23 ዓመት በፊት በ37 ዓመት ዕድሜው ያቆመ ሲሆን፤ በአርጀንቲና ውስጥ ያሉ ቡድኖችን በአሰልጣኝነት ከመራ በኋላ የአገሩን ብሔራዊ ቡድንንም በማሰልጠን ለዓለም ዋንጫ አብቅቷል። ከዚያም በኋላ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ እና በሜክሲኮ ውስጥ የሚገኙ ቡድኖችን በተለያዩ ጊዜያት አሰልጥኖ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ደግሞ የአገሩን አንድ ቡድን በማሰልጠን ላይ ነበር። የማራዶና አድናቂዎች ሐዘናቸውን ሲገልጹ
news-49658876
https://www.bbc.com/amharic/news-49658876
የጀማል ኻሾግጂ አገዳደል በዝርዝር ይፋ ሆነ
ቱርክ ውስጥ የሚገኝ አንድ ጋዜጣ ሳኡዲ አረቢያዊው ጃማል ኻሾግጂ ከመገደሉ በፊት የነበሩትን የመጨረሻ ሰዓታትና አገዳደሉን በዝርዝር የሚገልጽ መረጃ ይዞ ወጥቷል።
ጋዜጠኛ ጃማል ኻሾግጂ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ነበር ኢስታንቡል በሚገኘው የሳኡዲ አረቢያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ውስጥ የተገደለው። ከቱርክ መንግስት ጋር ግንኙነት ያለው ይህ ጋዜጣ እንዳስታወቀው በእጄ ገባ ያለው መረጃ ጃማል ከመገደሉ በፊትና አገዳደሉን የሚገልጽ የድምጽ ማስረጃ ሲሆን የቱርክ ደህንነት አባላት ነበሩ መጀመሪያ ላይ ያገኙት። • «ካሾግጂ ወዲያው ነበር የታነቀው» ቱርክ • ስለ ጀማል ኻሾግጂ አሟሟት እስካሁን የምናውቃቸው እውነታዎች ጋዜጣው ላይ የወጣው መረጃ ጋዜጠኛው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ምን እንደተናገረ ጭምር ይገልጻል። ኻሾግጂ ድንገት ከመሰወሩ በፊት አሜሪካ ውስጥ ሆኖ ዋሽንግተን ፖስት ለተባለው ጋዜጣ ይጽፍ ነበር። በጽሁፎቹም ሳኡዲ አረቢያ መንግስት ይፈጽማቸዋል ስለሚላቸው በደሎች በተደጋጋሚ ይጽፍ ነበር። ባሳለፍነው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ነበር ኻሾግጂ ቱርክ፥ ኢስታንቡል ውስጥ ወደሚገኘው የሳኡዲ አረቢያ ቆንስላ ጎራ ያለው እጮኛውን ለማግባት የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ለማግኘት ነበር። ነገር ግን ያላሰበው ነገር አጋጥሞት ከቅጥር ግቢው ሳይወጣ ቀርቷል። በቆንስላው ውስጥ የተገደለው ኻሾግጂ፣ ወደ ቅጥር ግቢው እንደገባ ነበር የታነቀው ስትል በወቅቱ ቱርክ መግለጫ ሰጥታ ነበር። ከዚያም የጋዜጠኛው በድን አካል ተቆራርጦ እንዲጠፋ ተደርጓል። ይሁ ሁሉ የተከናወነው ቀድሞ በተፃፈ ስክሪፕት መሠረት ነው። ሳባህ የተባለው ጋዜጣ ከኻሾግጂ ሞት ጋር በተያያዘ ሁለት ዘገባዎችን ይዞ የወጣ ሲሆን የዓለም መገናኛ ብዙሃንን ቀልብ መግዛት ችሏል። ጋዜጣው እንደሚያትተው ቀድመው የተዘጋጁ ነፍሰ ገዳዮች በቅጥር ግቢው እየተጠባበቁ ነበር። ኻሾግጂ ልክ ወደ ቆንፅላው ቅጥር ግቢ ሲገባ በእነዚህ ግለሰቦች ነው ታንቆ የተገደለው። እንደ ማስረጃም ጋዜጣው የተለያዩ የፖሊስ ምርመራ ውጤቶችን፣ ከሳኡዲ አረቢያ የመጣ የመርማሪዎች ቡድን አገኘሁት ያለውን መረጃ፣ እንዲሁም ሌሎች አባሪ ሰነዶችን ተጠቅሜያለው ብሏል። • የሳዑዲው ጋዜጠኛ ለመገደሉ ቱርክ አሳማኝ ማስረጃ እንድታቀርብ አሜሪካ ጠየቀች ኻሾግጂ ወደ ቆንስላው እንደገባ ሁኔታው ስላላማረው ለመመለስ ቢሞክርም በዓለማቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ስለሚፈለግ ወደ ሳኡዲ አረቢያ መመለስ እንዳለበት ተነግሮት ነበር። በሃሳቡ ያልተስማማው ኻሾግጂ ስለሁኔታው ለወንድ ልጁ የጽሁፍ መልእክት ልኮ ነበር። ከዚህ በኋላ ነበር እየተጎተተ ወደ አንድ ክፍል ውስጥ የተወሰደው። ለገዳዮቹም እባካችሁ አፌን አትሸፍኑኝ፤ የአተነፋፈስ ችግር አለብኝ ቢላቸውም ሊሰሙት ፈቃደኛ አልነበሩም። ልክ አፉን እንደሸፈኑት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ራሱን ስቷል። ተገኘ በተባለው የድምጽ ቅጂ መሰረት ከጭንቅላቱ እስከ አንገቱ ድረስ አየር በማያስገባ ጭንብል እንዲሸፈን ተደርጓል። ህይወቱ ካለፈ በኋላም የጋዜጠኛው በድን አካል ተቆራርጦ እንዲጠፋ ተደርጓል። ምንም እንኳን ኻሾግጂ ኢስታንቡል የሳኡዲ አረቢያ ቆንስላ ውስጥ መገደሉ ቢረጋገጥም እስካሁን ድረስ ሬሳው እምጥ ይገባ ስምጥ አይታወቅም።
news-51655541
https://www.bbc.com/amharic/news-51655541
ልዑልነት ይቅርብኝ ያለው የእንግሊዙ ልዑል 'ሃሪ ብቻ ብላችሁ ጥሩኝ' እያለ ነው.
የሰሴክስ ልዑሉ ሃሪ ለጋዜጠኞች "ሃሪ ብቻ ብላችሁ ጥሩኝ" ሲል ተናገረ።
ልዑሉ ይህን ያሉት በቱሪዝም ጉዳይ ላይ በስኮትላንድ መዲና ኤደንብራህ እየተሰጠ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። ከሳምንታት በኋላ የንግስቷ የልጅ ልጅ እና ባለቤቱ ሜጋን ከንጉሳዊ ስርዓት ሙሉ በሙሉ ኃላፊነት ይገለላሉ። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ልዑል ሃሪ የቱሪዝም እና የጉብኚዎች ቁጥር በፍጥነት ማደግ ውብ ለሆኑ የዓለማችን መተኪያ የሌላቸው ቅርሶች አደጋን ደቅኗል ብሏል። ልዑል ሃሪ በፍጥነት አስፈላጊው እርምጃ ካልተወሰደ መተኪያ የሌላቸው የዓለማችን መዳረሻዎች ይወድማሉ ወይም ይዘጋሉ ይላል። ልዑል ሃሪ ከንጉሳዊ ስርዓት ኃላፊነቱ ከመገለሉ በፊት ከሚከውናቸው የመጨረሻ ኃላፊነቶች መካከል አንዱ ወደ ስኮትላንድ የወሰደው የቱሪዝም ጉዳይ አንዱ ነው። ልዑል ሃሪ እና ባለቤቱ ሜጋን ህወታቸውን በሰሜን አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም እንደሚያደርጉ እና የንጉሳዊው ስርዓት ከሚጠይቀው ኃላፊነት እራሳቸውን እንደሚያገሉ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ከሁለት ዓመት በፊት ልዑል ሃሪ በወቅቱ እጮኛው ከነበረችው ሜጋን ጋር አሁን ወዳቀናበት ኤደንብራ በሄደ ጊዜ በርካቶች አደባባይ ወጥተው ፍቅራቸውን በመግለጽ አቀባበል አድረገውላቸው ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ ልዑሉ በተመሳሳይ ሥፍራ በተገኘበት ወቅት ግን የጠበቀው ድባብ የተለየ ነው። ሜጋን አብራው አልነበረችውም፤ እሱን ለመቀበል የወጣው ሰው ቁጥርም በጣም አነስተኛ ነበር። ልዑል ሃሪ ከትናንት በስቲያ ኤደንብራህ ባቡር ጣቢያ ሲደርስ ባርኔጣውን አድርጎ፣ ጄንስ ሱሪ ታጥቆ እና ቦርሳውን በጀርባ አዝሎ ነበር።
54874862
https://www.bbc.com/amharic/54874862
ኮሮናቫይረስ፡ የኬንያ ፖሊስ የኮቪድ-19 መመሪያን ተላልፈዋል ያላቸውን 1000 ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋለ
የኬንያ ፖሊስ የኮቪድ-19 ስርጭት ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያና ደንቦችን ተላልፈዋል ያላቸውን 1000 ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋለ።
የአገሪቱ ባለስልጣናት አብዛኞቹ ሰዎች በመጠጥ ቤቶች፣ ከመጋቢት ወር ጀምሮ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተቀመጠውን የሰዓት እላፊ ተላልፈው መያዛቸውን ተናግረዋል። ኬንያ 62000 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ሲረጋገጥ ከእነዚህም መካከል 1000 ያህሉ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ፖሊስ በመላ አገሪቱ በሚገኙ መጠጥ ቤቶችና መዝናኛ ስፍራዎች ድንገተኛ አሰሳ በማድረግ እና የተቀመጠውን መመሪያ መተግበሩን በማረጋገጥ የሁለተኛ ዙር የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ሙከራ እያደረገ ነው ተብሏል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ በመጠጥ ቤቶች በፌሽታ ላይ የነበሩ ሰዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተይዘዋል። ሰዎቹ ከምሽቱ 3፡00 በኋላ በመጠጥ ቤት ውስጥ የተገኙ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ናቸው ተብሏል። ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች በአጠቃላይ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡና 200 የአሜሪካ ዶላር (20000 ሽልንግ ገደማ)እንደሚቀጡ አስተውቋል። ከሰዓት እላፊ በኋላ ደንበኞቻቸውን ሲያስተናግዱ የነበሩ የመጠጥ ቤት ባለንብረቶች የንግድ ፈቃዳቸው እንደሚሰረዝ እና እንደማይታደስላቸው ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአንዳንድ የአገሪቱ የገጠር ክፍሎች መስፋፋቱን ተከትሎ ኮቪድ-19ን ለመከላከል ያስችላሉ ያሏቸውን መመሪያዎች በቅርቡ አስተላልፈው ነበር።
news-51964267
https://www.bbc.com/amharic/news-51964267
በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ ሥርዓት ውስን ሰዎች በሚገኙበት ሰኞ ይፈጸማል
ትናንት ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኞ እንደሚፈጸም ተነገረ።
ዶ/ር ካትሪን ሃምሊን የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ማናጀር ዶ/ር ተሾመ ታፈሰ ለቢቢሲ እንደገለጹት የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ሰኞ ቀትር 7 ሰዓት ላይ በጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል። ዶ/ር ተሾመ እንደተናገሩት ከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ አድናቂዎቻቸው፣ ደጋፊዎቻቸውና ከየማዕከላቱ የመጡ ሠራተኞች እየተገኙ የስንብት ፕሮግራም ይካሄዳል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሕዝብ ስብሰባዎችን መቀነስ ተገቢ ስለሆነም በሚደረገው የስንብትና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ላይ በአንድ ግዜ የሚገኙ የሰዎች ቁጥር ውስን እንዲሆን እንደሚደረግ ዶ/ር ተሾመ አክለዋል። ዶ/ር ካትሪንን "የእናቶች እናት ናቸው" ሲሉ የሚገልጿቸው ዶ/ር ተሾመ፤ "የፊስቱላ ችግር እንደነበረ ባልታወቀበት ሰዓት መጥተው ነው፤ ከ60 ሺህ በላይ እናቶችንና ወጣት ሴቶችን ጤንነትን የመለሱ ሴት ናቸው" ብለዋል። ከአጠቃላይ የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ሠራተኞች መካከል አዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ውስጥ የሚሠሩት ወደ 160 የሚሆኑት ሠራተኞች የቀድሞ ፊስቱላ ታካሚ የነበሩና ሕይታቸውን አሻሽለው ተቀጥረው የሚሠሩ መሆናቸውን ዶ/ር ተሾመ አስታውሰዋል። ለሦስት ሳምንታት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለ61 ዓመታት ስለመኖሩት ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የህይወት ታሪክ ለማንበብ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።
56186297
https://www.bbc.com/amharic/56186297
ባይደን በኢራን በሚደገፉ ሚሊሺያዎች ላይ የአየር ድብደባ እንዲፈጸም ፈቀዱ
የአሜሪካ ጦር በሶሪያ የሚገኙና በኢራን በሚደገፉ ሚሊሻዎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ድብደባ ማድረጉን ፔንታጎን ገለጸ።
በቅርቡ በአሜሪካ እና በአጋሮቿ ላይ በኢራቅ ለተፈፀሙ ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት ነው ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን የአየር ድብደባ እንዲደረግ ያዘዙት። በጥቃቱ "በርካታ በኢራን የሚደገፉ የታጣቂ ቡድኖች በሚጠቀሙበት የድንበር መቆጣጠሪያ ቦታ የሚገኙ በርካታ ተቋማትን ወድመዋል" ብሏል። በቅርቡ በአሜሪካ እና በአጋሮቿ ላይ በኢራቅ ለተፈፀሙ ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት ነው ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን የአየር ድብደባ እንዲደረግ ያዘዙት። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ኢራቅ ውስጥ አሜሪካ ላይ ባነጣጠረ የሮኬት ጥቃት አንድ ሲቪል ሠራተኛ ተገደሏል። በዚህ የሮኬት ጥቃት ኢርቢልን ጨምሮ በአሜሪካ የሚመራው ጥምረት በሚጠቀሙበት የጦር ሰፈር የሮኬት ጥቃት ተፈጽሞ አንድ የአሜሪካ ወታደራዊ አባል እና አምስት ሌሎች ሲቪል ሠራተኞች ቆስለዋል። የአሜሪካ ኤምባሲን እና የሌሎች ዲፕሎማቲክ መቀመጫ የሆነውን ግሪን ዞንን ጨምሮ በባግዳድ የሚገኙትን የአሜሪካን የጦር ሰፈሮችም በሮኬቶች ተመተዋል። እንደፔንታጎን ገለጻ ሐሙስ በምስራቅ ሶሪያ በተካሄደው ዘመቻ ኢላማ የተደረጉት ካታይብ ሄዝቦላህ እና ካታይብ ሳይድ አል-ሹሃዳ የተባሉ ሁለት የሚሊሻ ቡድኖችን ነው። ጥቃቱን "ተመጣጣኝ ወታደራዊ ምላሽ" ያለው ፔንታጎን ከ"ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች" ጎን ለጎን የጥምር ኃይሉን በማማከር የተወሰደ ነው ሲል ገልጿል። ፔንታጎን በመግለጫ "እርምጃው የማያሻማ መልዕክት ያስተላልፋል" ብሏል። "ፕሬዝዳንት ባይደን የአሜሪካ እና የጥምር ኃይሉን አባላት ለመጠበቅ እርምጃ ይወስዳሉ። በተመሳሳይም በምስራቃዊ ሶሪያም ሆነ በኢራቅ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ወደ የሚቀንስ እርምጃ ወስደናል" ሲል አጠናቋል።
news-55905196
https://www.bbc.com/amharic/news-55905196
ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ አፍሪካውያን አልኮል መጠጥ ላይ የተጣለባቸው ገደብ በመነሳቱ ተደስተዋል
በደቡብ አፍሪካ ወረርሽኙን ተከትሎ አልኮል መጠጦች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነሳ፡፡
የባሕር ዳርቻዎችም መከፈት ተጀምረዋል፡፡ ለመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት መሰባሰብም እንዲሁ በተወሰነ መልኩ ተፈቅዷል፡፡ ይህ ጥብቅ ገደብ የመላላቱ ዜና የተሰማው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የአስትራዜኒካ ክትባት አገራቸው መድረሱን ባበሰሩበት ማግስት ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ የመጀመርያውን 1 ሚሊዮን ጠብታ ክትባት ከአስትራዜኒካ አግኝታለች፡፡ ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ አገራት በሙሉ ብዙ ሰዎች በወርሽኙ የተያዙባት አገር ናት፡፡ በሟች ቁጥርም ከፍተኛውን የሰው ብዛት ነው ያስመዘገበችው፡፡ አንድ ሚሊዮን 400ሺ ዜጎቿ በተህዋሲው የተጠቁ ሲሆን 45ሺ የሚጠጉት ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በርካታ የዓለም አገራት ከደቡብ አፍሪካ የሚመጡ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዳይገቡ አግደዋል፡፡ ይህም የሆነው የኮቪድ አዲስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካ መኖሩ በመረጋገጡ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የተገኘው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ በፍጥነት የመዛመት ባህሪ ስላለው ለብዙ አገራት ስጋት ሆኗል፡፡ ይህ አዲሱ ዝርያ ለክትባት እጅ አይሰጥ ይሆን የሚል ፍርሃት በባለሙያዎች ዘንድ ይሰማል፡፡ አሁንም ደቡብ አፍሪካ ደረጃ 3 በሚባለው የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ ያለች ሲሆን ወሳኝ የሚባሉ ገደቦች ላይ ግን ማዕቀቦች እየላሉ ነው፡፡ መደብሮች አሁን አልኮል መጠጥ ከሰኞ እስከ ሐሙስ፣ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት መሸጥ ይችላሉ፡፡ በመጠጥ ቤቶች ደግሞ ከጠዋት 4፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 2፡00 ሰዓት ደንበኞች ቁጭ ብለው አልኮል መጠጥ መስተናገድ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ከዚህ በኋላ የሰዓት እላፊ የሚሆነው ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት እስከ ሌሊት 10፡00 ሰዓት ነው፡፡ ደቡብ አፍሪካ ወረርሽኙ ከተጀመረ ወዲህ ለ3ኛ ዙር አልኮል መጠጥ ላይ ገደብ መጣሏ ይታወቃል፡፡ በዚህ የተነሳ መጠጥ አምራቾች፣ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ሰራተኞቻቸውን ለመበተን እየተገደዱ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ ይህ በአልኮል መጠጥ ላይ የተጣለው ገደብ በብዙ ነዋሪዎች ዘንድም ቅሬታ ፈጥሮ ነበር፡፡ በአልኮል መጠጦች ላይ ከተጣለው ማዕቀብ መላላት ሌላ መስጊዶች ወይም አብያተ ክርስቲያናት ወይም ሌሎች የእምነት ተቋማት 50 ሰዎችን በውስጥ፣ እስከ 100 ምዕመናን በደጅ ማስተናገድ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ፓርኮችና የባሕር ዳርቻዎች ለተገልጋዮች ክፍት ሆነዋል፡፡ ራማፎሳ ከመድኃኒት አምራቾች ጋር ባደረግነው ድርድር 50 ሚሊዮን ጠብታዎችን ለማግኘት ተነጋግረናል ብለዋል፡፡ ደቡብ አፍሪካ በዚህ ዓመት 40 ሚሊዮን ዜጎችን ለመከተብ አቅዳለች፡፡ ይህም የሕዝቧን 2/3ኛ የሚሸፍን ነው፡፡
news-49534090
https://www.bbc.com/amharic/news-49534090
ደቡብ አፍሪካዊው 32 ሴቶችን በመድፈር 32 የተለያየ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2016 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት 32 ሴቶችን አስገድዶ በመድፈር የተከሰሰው ደቡብ አፍሪካዊ 32 የተለያየ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።
"ደርባን የፍጥነት መንገድ ላይ የሚደፍረው ግለሰብ" በሚል ስም የሚጠራው ግለሰቡ፤ ሥራ አጥ ሴቶችን 'ሥራ አገኝላችኋለሁ' በሚል ማታለያ በመቅረብ ጥቃት እንደፈጸመባቸው የፒንታውን ማጊስትሬት ፍርድ ቤት አስታውቋል። • ዝነኛው ድምጻዊ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ ተባለ • የታዳጊዋ ሬስቶራንት ውስጥ መደፈር ደቡብ አፍሪቃውያንን አስቆጥቷል • በምዕራብ ጎጃም ታራሚ አስገድዶ የደፈረው ፓሊስ የእስራት ጊዜ ተጨመረበት ሞሰስ ማቪላ የተባለው ግለሰብ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ሲፈረድ ፍርድ ቤት ውስጥ የነበሩ ግለሰቦች የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፤ 'እጅግ አስቀያሚ ነህ' ብለው የሰደቡትም ነበሩ። በፍርድ ቤቱ፤ "አንተ ያለርህራሄ ይህንን ሁሉ በደል ከፈጸምክ በኋላ ፍርድ ቤቱ እንዲምርህ አትጠብቅ" ተብሏል። ከእድሜ ልክ እስራቱ በተጨማሪ ሁለት ሴቶችን ለመድፈር በመሞከሩ 20 ዓመትና በስርቆት የ15 ዓመት እስር ተፈርዶበታል። ካሪንዳ ጃግሞሀን የተባለች ጋዜጠኛ በግለሰቡ ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች ጥቂቱ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተሰማቸውን ደስታ ሲገልጹ የሚያሳይ ቪድዮ ትዊት አድርጋለች።
news-41397352
https://www.bbc.com/amharic/news-41397352
ቻይና በኮሚኒስት ፓርቲው ስብስባ መባቻ ላይ 'ዋትስአፕን' ዘጋች
የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያው 'ዋትስአፕ' በቀጣይ ወር ከሚካሄደው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ስብሰባ በፊት ሀገሪቱ ላይ እንዳይሰራ ተደረገ።
ቻይናያውያን ተጠቃሚዎች ላለፉት ጥቂት ሳምንታት መተገብረያውን ለመጠቀም እጅጉን መቸገራቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል። መተግበሪያው ከዚህ በፊት በቻይና ተመሳሳይ እክል ሲያጋጥመው 'ቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትወርክ' (ቪፒኤን) የተሰኘን ስውር ማቋረጫ በመጠቀም ቻይናውያን ሲገለገሉ እንደነበረ ይታዋሳል። 'ዋትስአፕ' ከፌስቡክ ምርቶች ውስጥ ቻይና ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጥ የተፈቀደለት ብቸኛው መተግበሪያ ነው። የቢቢሲ የቻይና ዘጋቢ እንደገለፀው ችግሩ መከሰት ከጀመረ ሳምንት ሆኖታል። ተጠቃሚዎች ተንቀሳቃሽ ምስልም ሆነ ፎቶግራፍ ወደሌላ ሀገር መላክ ተስኗቸው ቆይቷል። ቻይና በቀጣይ ወር ከሚካሄደው የኮሚኒስት ፓርቲው ስበሰባ በፊት የፀጥታ ኃይሏን በተለያየ መልኩ እያጠናከረች ትገኛለች። 'ዋትስአፕ' የተሰኘውን መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያን መዝጋትም የዚህ ሂደት አንድ አካል እንደሆነ እየተዘገበ ነው። የቻይና መንግስት አንድ አማካሪ እንደገለፁት "ስብሰባው ፀጥታ በሰፈነበት መልኩ እንዲከናወንና ሕብረተሰባዊ ሰላም እንዲፈጠር መሰል ሂደቶች የግድ ናቸው" ብለዋል። ነገር ግን ሁኔታው እስከመቼ ሊዘልቅ እንደሚችል ግልፅ እንዳልሆነ ታውቋል። የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚናገሩት የቻይና መንግስት በ'ዋትስአፕ በኩል ሀሳብ የገባው፤ መተግበሪያው ከላኪው እና ከተቀባዩ ውጭ ሌሎች መልዕክቱን እንዳያዩት ስለሚያደርግ ነው። በቻይና መሰል ድርጊቶች የተለመዱ ናቸው። የቻይና መንግስት በይነ-መረብ እና የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎችን በየጊዜው እንዳይሰሩ በማድረግ ይታወቃል። ሰኞ ዕለት የቻይና መንግስት የሳይበር ደህንነት መስሪያ ቤት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ቴንሴንት፣ ባይዱ እና ዌይቦ የመሳሰሉ የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎች በሕጉ መሰረት የማይንቀሳቀሱ ከሆነ ከፍተኛ ቅጣት ሊተላልፋባቸው እንደሚችል ማስጠንቀቁ ይታወሳል። መተግበሪያዎቹ የሀሰት ዜናና ወሲብ ቀስቃሽ እንዲሁም የጎሳ እና የድንበር ግጭት የሚያስነሱ ይዘቶች ላይ ጥንቃቄ የማያደርጉ ከሆነ ዕገዳው ሊጣልባቸው እንደሚችል ተዘግቧል።
51030554
https://www.bbc.com/amharic/51030554
ኡጋንዳውያን ለፕሬዝደንት ሙሴቪኒ ሲንበረከኩ የሚያሳየው ምስል አነጋጋሪ ሆኗል
የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ለተንበረከኩላቸው አዛውንት ግራጫ ፖስታ ሲያድሉ የሚታይበት ተንቀሳቃሽ ምስል መነጋገሪያ ሆኗል።
ሙሴቪኒ ለአምስት ቀናት ጫካ ውስጥ ነው የምኖረው ብለው ዱር ከከተሙ ሶስት ቀናት ሆኗቸዋል። በዚህ የጫካ ኑሯቸው አብሯቸው የተሳተፈ አንድ ግለሰብ ነው ሙሴቪኒ በእንብርክክ ላሉ አዛውንቶች ግራጫ ፖስታ ሲያድሉ ቪድዮ ቀርፆ ማሕበራዊ ድር-አምባዎች ላይ የለቀቀው። ፕሬዝደንቱ ወደ ጫካ መመለስ ያስፈለጋቸው ሥልጣን ከመያዛቸው በፊት በታጣቂነት ዘመናቸው ያለፉበትን ለማስታወስ ነው ተብሏል። ሙሴቪኒ እና አጋሮቻቸው በ1978 ዓ.ም. ነው የኢዲ አሚን ዳዳን መንግሥት ገልብጠው ሥልጣን የያዙት። ከሰሞኑ በተለቀቀው ቪዲዮ ላይ ነዋሪዎች ዝማሬ እያሰሙ፤ ሙሴቪኒ ደግሞ ወንበር ላይ ተቀምጠው በእንብርክካቸው ወደ እሳቸው ለሚጠጉ አዛውንቶች በእርዳታ መልክ ግራጫ ፖስታ ሲያድሉ ይታያሉ። ሙሴቪኒ በግራጫ ፖስታ ውስጥ ገንዘብ እያደሉ እንደሆነ ተገምቷል እንደ ግሪጎሪ አቆጣጠር በ2021 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሙሴቪኒን ይገዳደራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተቀናቃኞች መካከል የሆኑት ኪዛ ቤስጊዬ ድርጊቱ አረጋውያንን የሚያሸማቅቅ ነው ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከተለቀቀ በኋላ በርካታ ኡጋንዳውያን ድርጊቱን አውግዘውታል። አንዳንዶች ፕሬዝደንቱ ይህን የሚያደርጉት በሚቀጥለው ምርጭ ሕዝቡ እንዲመርጣቸው በማሰብ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ሙሴቪኒ ስለ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ምንም ያሉት ነገር የለም። ይልቁንስ በጫካ ጉዟቸው አብረዋቸው የተሳተፉትን ምስጋና እንካኝ ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ታጣቂ በነበሩ ጊዜ ከያኔው የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ኦቦቴ ጦር ጋር የተዋጉበትን ቦታ ጎብኝተው በሚቀጥሉት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ መናገሻቸው ካምፓላ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
55883440
https://www.bbc.com/amharic/55883440
ኢትዮ ሱዳን: የሁለቱን ሃገራት ድንበር ጉዳይን ለመፍታት ሶስተኛ ወገን አያስፈልግም ተባለ
ኢትዮጵያ በሱዳን ድንበር ያለውን ውጥረት ለመፍታት የሶስተኛ አካል ጣልቃ ገብነትን እንደማትፈልግ አቶ ውሂብ ሙሉነህ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከድንበር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ቴክኒካል አማካሪና በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ኮሚሽን አባል ለቢቢሲ ገለፁ።
አቶ ውሂብ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር አለመግባባት ውዝግብ በውይይት ብቻ ለመፍታት ጥብቅ ፍላጎት እንዳላት ለቢቢሲ ገልፀዋል። ሱዳንም ብትሆን እስካሁን ድረስ በሁለትዮሽ ንግግር የሚል ሃሳብ ብቻ እንዳላቸው የሶስተኛ ወገን አደራዳሪነትን እንዲኖር አለማቅረባቸውን ተናግረዋል። ሁለቱን አገራት ለማስታረቅና ለማሸማገል የተለያዩ አካላትም ጥረት እያደረጉ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ጉዳዩ ያሳሰባት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኢትዮጵያና ሱዳን ያላቸውን የድንበር ላይ ውዝግብ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እንዲፈቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ ጠይቃለች። የሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪና ነዋሪዎች የሱዳን ሠራዊት ወረራ ፈጽሞበታል ወደ ሚባሉት ስፍራዎች ዘልቆ መግባት የጀመረው በአካባቢው የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ ከጀመረ በኋላ በጥቅምት 29 2013 ዓ.ም እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በድንበር አካባቢ ያለውን አለመግባባት በተመለከተ ጉዳዩ በሁለቱ አገራት መንግሥታት አማካይነት በሠላማዊ መንገድ እንደሚፈታና ለዚህም ጥረት እያደረገች እንደሆነ ኢትዮጵያ ስትገልጽ ብትቆይም ሱዳን ግን የያዘችውን መሬት ለቅቃ እንደማትወጣ ገልጻለች። ኢትዯጵያ በበኩሏ ሱዳን በኃይል የያዘችውን መሬት ለቅቃ እስካልወጣች እንድትወጣ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠች ሲሆን ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ድርድር እንደማይኖር መግለጿ ይታወሳል። የኢትዮጵያና ሱዳንን የድንበር ጉዳይ መፍታት የሚቻለው ሁለቱ ሀገሮች ባቋቋሟቸው መዋቅሮች ብቻ መሆኑን አቶ ውሂብ ገልፀዋል። የድንበሩ ሁኔታ እስኪፈታ ድረስ ግን ኢትዮጵያና ሱዳን የፈረሟቸው ስምምነቶች ተከብረው መቆየት እንዳለባቸው አቶ ውሂብ አፅንኦት ይሰጣሉ። "የኢትዮጵያን ሕልውና የሚጻረሩ ኃይሎች መኖራቸውን እናውቃለን" ያሉት አቶ ውሂብ " ሌላ ሶስተኛ አካል ሊኖር ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ በኩል ሶስተኛ አካል ሊኖር ይችላል የሚሉ ንግግሮች ቢሰሙም ሶስተኛ ወግን የተባለው እስካሁን በስም አልተጠቀሰም። ሆኖም እነዚህን ኃይላት በመጋበዝ በዚህ የድንበር ውዝግብ ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው ማድረግ ኢትዮጵያ እንደማትፈልግ አክለው ያስረዳሉ። በተለያዩ ጊዜያት በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት እኤአ 1972 የሀሳብ ልውውጥ ስምምነት ተፈራርመው ድንበራቸውን እንደገና ለማካለል መስማማታቸውን አቶ ውሂብ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ሀገራት የሚቀበሉት የመፍትሔ ሀሳብ ላይ እስኪደርሱ ድረስ የድንበር ነባራዊ ሁኔታው ባለበት ተከብሮ እንዲቆይ መስማማታቸውን አመልክተዋል። በ1972 ዓ.ም የተደረሰው ስምምነት በተባበሩት መንግሥታት የተመዘገበ መሆኑን በማንሳት፣ ይኸው ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆንና ጦርነት እንደማያስፈልግ ኢትዮጵያ ለሱዳን ማስረዳቷን ይገልጻሉ። "የጦር ፍላጎት በኢትዮጵያ ዘንድ የለም" የሚሉት አቶ ውሂብ ሁለቱ ሕዝቦች በተለያየ ነገር እንደሚተሳሰሩ ተናግረዋል። የትኛውም ጦርነት ሲያልቅ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንደሚመጣ በማስታወስ፣ ከጦርነት አማራጭ ይልቅ ልዩነቶችን በመነጋገር መፍትሔ መስጠት የተሻለ መሆኑን አክለዋል። በአፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላትን የድንበር ጉዳይ በጋራ መፍታቷን ያነሱት አቶ ውሂብ፣ የድንበሩን አለመግባባት ለመፍታት ሶስተኛ ወገን አስፈላጊ አይደለም ብለዋል። በድንበሩ አካባቢ አሁንም አልፎ አልፎ ተኩስ እንደሚሰማ የገለፁት አቶ ውሂብ፣ ይህ ጉዳይ እንዲቆም ኢትዮጵያ መናገሯን ገልፀዋል። አቶ ውሂብ ሁለቱ አገራት የሚያደርጉት ውይይት መች ሊቀጥል ይችላል ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ የሚያደርጉት ንግግር በማንኛውም ሰዓት ሊቀጥል ይችላል ብለዋል። ኢትዮጵያና ሱዳን የጋራ ድንበር ኮሚሽን፣ የጋራ ድንበር ቴክኒክ ኮሚቴ እና የጋራ ልዩ ኮሚቴ አቋቁመው ለድንበሩ ጉዳይ መፍትሔ ለመስጠት ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል "የሕግ ማስከበር ዘመቻ" ላይ በነበረችበት ወቅት የሱዳን መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቋን የገለፁት አቶ ውሂብ፣ በዚህም በመስማማት ድንበራቸውን እንደሚዘጉ መናገራቸውን ይገልጻሉ። ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር አልፋ እንድትጠብቅም ሆነ መሬት እንድትይዝ የተደረሰ ስምምነት እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከሰሞኑ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው ። "ድንበር አካባቢ የሁለቱን አገሮች ደህንነት የሚጎዳ እንቅስቃሴ እንዳይኖር በኛ አመራር ለሱዳን መንግሥት አደራ ተሰጥቷል" ያሉት ቃለ አቀባዩ አክለውም ሆኖም "ድንበሩን አልፈው አገራችን ግቡ መሬት ይዛችሁ ጠብቁልን የሚል አይነት ሊኖር የሚችል አይደለም፤ አልነበረም" ብለዋል። ከሰሞኑ የሱዳን ምክር ቤት ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ሱዳን ሰራዊቷን ወደ ድንበር ያስጠጋችው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብይ አህመድ ጥያቄና ፈቃድ ነው መባሉ ተዘግቧል። ድንበሩን የሚቆጣጣረው መካናይዝድ (የተቀናጀ) ጦር ወደ ትግራይ ሲሰማራ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር በማለፍ ሰባት የወታደራዊ ካምፖችን በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ወረራ መፈፀሙን አማካሪው ተናግረዋል። በወቅቱም ሰብሎችን ማቃጠል እንዲሁም ዘረፋ መፈፀሙን አክለዋል። ለዚህም ምላሽ የሰጡት ቃለ አቀባዩ "ቅዠት ነው" ካሉ በኋላም "አጥፊ ኃይሎች የናንተን ድንበር ተጠቅመው ወደኛ ድንበር እንዳይገቡ ማለት ኑና ገብታችሁ ጭራሽ ያልተከለለና መቶ አመት በዚሁ ሁኔታ ይሁን ተብሎ የቆየውን መሬት ድንበር የኛ ነው በሉ ማለትም አይደለም" ብለዋል። ማንም አገር የድንበር አለመግባባት ሲገጥመው የጋራ ኮሚሽን በማቋቋም ጉዳዮን ለመፍታት እንደሚሰራ በመግለጽ፣ ይህ አለማቀፍ አሰራር በሁለቱ አገራት መካከልም ይቀጥል በማለት ለሱዳን ከፍተኛ ኃላፊዎች ጥያቄ መቅረቡን ተናግረዋል። ከዓመታት በፊት ኢትዮጵያና ሱዳን ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረውን 744 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ድንበራቸውን ለይቶ ለማመላከት የሚያስችል ንግግርን መልሰው መጀመራቸው ይታወሳል። በዚህ መፍትሄ ለመስጠት አስቸጋሪ የሆነው አካባቢ ፋሽጋ የሚባለው ነበር። በ1902 እና በ1907 (እአአ) የነበረው የቅኝ ግዛት ስምምነት መሰረት ዓለም አቀፉ ድንበር ወደ ምሥራቅ ይዘልቃል። በዚህም ሳቢያ መሬቱ ወደ ሱዳን የሚካተት ይሆናል። ነገር ግን ቦታው ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ሲሆን የግብርና ሥራ በማከናወንም የሚጠበቅባቸውን ግብር ለኢትዮጵያ መንግሥት ሲከፍሉ ቆይተዋል።
news-47944655
https://www.bbc.com/amharic/news-47944655
ታሪካዊው የፈረንሳይ ካቴድራል ኖትረ ዳም በእሳት ጋየ
በፓሪስ እምብርት የሚገኘው ጥንታዊው እና ታሪካዊው ኖትረ ዳም ካቴድራል ትናንት ነበር በእሳት የጋየው። በእሳት ጉዳት ከደረሰበት በኋላ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑኤል ማክሮ ኖትረ ዳምን መልሰን እንገነባዋለን ሲሉ ተደምጠዋል።
የእሳት አደጋ ሠራተኞች በወሰዱት እርምጃ የካቴድራሉን ግንብ እና ሁለት ማማዎች ከነበልባሉ መታደግ የቻሉ ሲሆን ጣሪያው እና አናቱ ግን ፈርሷል። 850 ዓመታትን ያስቆጠረው ኖትረ ዳም ካቴድራል ፓሪስ መሃል ከተማ ይገኛል። የእሳት አደጋ ሠራተኞች እሳቱን መቆጣጠር የቻሉት እሳት መነሳቱ ሪፖርት ከተደረገ ከ9 ሰዓታት በኋላ ነበር። የእሳቱ መነሻ እስካሁን በግልፅ ባይነገርም የሃገሪቱ ባለስልጣናት ግን በካቴድራሉ እየተካሄደ ካለው እድሳት ጋር አገናኝተውታል። • በሰሜን ተራሮች ፓርክ በሄሊኮፕተር ውሃ እየተረጨ ነው • ሩሲያዊው ቄስ በባለቤታቸው "ሀጥያት" ለስደት ተዳረጉ • የምክር ቤቱ ስብሰባ ኢህአዴግን ወዴት ይመራው ይሆን? ፕሬዝደንት ማክሮ በአደጋው ስፍራ ተገኘተው በሁኔታው በጣም ማዘናቸውን ገልፀው የእሳት አደጋው እንዳይከስት ማድረግ እንደሚቻል በመጠቆም፤ ለኖትረ ዳም መልሶ ግንባታ ዓለም አቀፍ ጥሪ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል። ፕሬዝደንት ማክሮ ስሜታዊ ሆነው በሰጡት መግለጫ ''መልሰን እንገነባዋለን። ኖትረ ዳም የታሪካችን አካል ነው። የፈረንሳይ ሕዝብ የሚጠብቀውም ይህንኑ ነው'' ያሉ ሲሆን ከአሁኑ ኖትረ ዳምን መልሶ ለመገንባት በርካቶች ድጋፍ ማድረግ ጀምረዋል። የጉቺና የሌሎች ፋሽን ምርቶች ባለቤት የሆነው ፈረንሳዊው ቢሊየነር ፍራንሷ-ኦንሪ ፒኖ፤ ለኖትረ ዳም ግንባታ 100 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። ትናንት ሰኞ ምሽት 2፡30 ላይ የጀመረው እሳት በፍጥነት ወደ ጣሪያው በመዛመት ከመስተዋት የተሠሩ መስኮቶቹን፣ ከእንጨት የተሠሩ የውስጥ ንድፎቹን፣ ጣሪያውን እና ማማውን አውድሟል። እሳቱን ለመቆጣጠር 500 የሚሆኑ የእሳት አደጋ ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆኑ አንዱ በእሳቱ ጉዳት እንደደረሰበት ተዘግቧል። የእሳት አደጋ ሠራተኞቹ በኖትረ ዳም ካቴድራል ውስጥ የነበሩ ውድ የጥበብ ሥራዎች እና ኃይማኖታዊ ቁሶችን ማዳን መቻላቸውም ተነግሯል። ከእሳት ከተረፉት ኃይማኖታዊ ቁሶች መካከል ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ በፊት የተደረገለት የእሾህ አክሊል ይገኝበታል። ኖትረ ዳም ለፈረንሳዊያን ምናቸው ነው? ኖትረ ዳም ካቴድራል ለ9 ሰዓታት ሲቃጠል የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በቀጥታ እየዘገቡት ነበር። ይህን ሲመለከቱ የነበሩት የታሪክ ምሁር ካሚይ ፓስካል ለፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ሲናገሩ '' ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የዓለም ደስታ እና ሃዘን በኖትረ ዳም ደውል ታውጇል። እያየን ባለነው ነገር እጅግ በጣም ተደናግጠናል'' ብለዋል። ኖትረ ዳም ለፈረንሳውያን ሃገራዊ አርማቸው ተደርጎ ይወሰዳል። ኖትረ ዳም ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ መሃል ፓሪስ ላይ ቆሟል። በርካቶች የፈረንሳይ መለያ አድርገው የሚወስዱት የኤይፈል ማማ እንኳ ዕድሜው ከ100 ዓመት ፈቅ ቢል ነው። ኖትረ ዳም የመጀመሪያ እና ሁለተኛ የዓለም ጦርነት ጉዳት ሳያስተናግድ አልፏል። በፈረንሳይ ሥነ-ጽሑፍ ሥራዎች ውስጥም ስሙ ሳይጠቀስ አያልፍም። ኖትረ ዳም ለ9 ሰዓታት ያክል በእሳት ሲነድ በርካታ ፈረንሳውያን አደጋው ስፍራ በመገኘት ቆመው በዝምታ ይመለከቱ ነበር። ሌሎች ይዘምራሉ፤ የተቀሩት ደግሞ ፀሎት ያደርሳሉ። በፓሪስ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ ደውል ሲያሰሙ አመሹ። ኖትረ ዳም በዓመት 13 ሚሊዮን ሕዝብ ይጎበኛዋል። ዶናልድ ትራምፕ፣ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ፣ ዩኔስኮ፣ የጃፓን መንግሥት፣ የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚንስትር እና የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ሃዘናቸውን ከገለፁ ግለሰቦች እና ተቋማት መካከል ይገኙበታል።
news-57312692
https://www.bbc.com/amharic/news-57312692
ናኦሚ ኦሳካ ከፈረንሳይ ውድድር ራሷን አገለለች
የአለም ቁጥር ሁለት የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናኦሚ ኦሳካ ከፈረንሳይ ውድድር ራሷን እንዳገለለች አስታወቀች።
ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ለመናገር ፈቃደኛ ካልሆነች ትታገዳለች የሚል ውዝግብን ተከትሎ ነው በፈረንሳይ ኦፕን እንደማትወዳደር ያሳወቀችው። ይህንን ባሳወቀችበት የትዊተር መልዕክትም ናኦሚ በጭንቀት (ዲፕረሽን) ህመም እየተሰቃየች እንደሆነ አስፍራለች። ህመሟም የጀመረው ከሶስት አመት በፊት በሜዳ ቴኒስ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠውን የመጀመሪያዋን ግራንድ ስላም ካሸነፈች ጀምሮ ነው። የ23 አመቷ አትሌት የአዕምሮ ጤንነቷን ለመጠበቅ በሮላንድ ጋሮስ ጋዜጣዊ መግለጫ አልሳተፍም ያለችው ባለፈው ሳምንት ነበር። ባለፈው ሳምንት እሁድ ከሮማኒያዊቷ ፖትሪሺያ ማሪያ ቲግ ጋር በነበረው ውድድር በአሸናፊነት ያጠናቀቀችበት ጨዋታ ተከትሎ ከሚዲያዎች ጋር ቆይታ አላደርግም በማለቷ 15 ሺህ ዶላር ተቀጥታለች። በዚያኑ ቀን የግራንድ ስላም ውድድር አዘጋጆች ባወጡት የጋራ መግለጫ አትሌቷ ሚዲያ አላናግርም በሚል ባህርይዋ ከቀጠለች ከጨዋታዎች እንደምትታገድ አስጠንቅቀው ነበር። አትሌቷም በትናንትናው ዕለት ከፈረንሳይ ኦፕን ራሷን እንዳገለለች ገልፃ "ለተወሰነ ጊዜም ከሜዳ ራሴን አርቄያለሁ " ብላለች። "ትክክለኛው ወቅት ሲመጣ ከውድድር አዘጋጆች ጋር ለአትሌቶች፣ ለሚዲያዎችና ለተመልካቾች በምን መንገድ ውድድሮችን ማሻሻል እንችላለን የሚለው ላይ መወያየት እፈልጋለሁ' ብላለች። የፈረንሳይ ቴኒስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጊለስ ሞሬቴን የናኦሚን ራሷን ከውድድር ማግለል አስመልክቶ "አሳዛኝ" ብለውታል። "ናኦሚ በገጠማት ሁኔታ ሃዘን ተሰምቶናል። በፍጥነትም እንድታገግም ምኞታችንን እየገለፅን በሚቀጥለው አመት ውድድራችን እናያታለን ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል ። "ሁሉም የግራንድ ስላምስ ውድድሮች ማለት ደብልዩ ቲ ኤ፣ ኤቲፒና አይቲኤ ለአትሌቶች ጤና ቅድሚያ በመስጠት በሌሎችም ዘርፎች አትሌቶች የሚሻሻሉበትን መንገድ እንቀይሳለን። ከዚህም ጋር ተያይዞ አትሌቶች ከሚዲያዎች ጋር ያላቸው ግንኙነቶች እንዲሻሻሉ ስንሰራ ነበር። አሁንም እንሰራለን" በማለት አስረድተዋል።
news-46257710
https://www.bbc.com/amharic/news-46257710
የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት የሚሰጠው ሜሪ ስቶፕስ ኬንያ ውስጥ ታገደ
በዓለማቀፍ ደረጃ የጤና አገልግሎት የሚሰጠው ሜሪ ስቶፕስ ከጽንስ ማቋረጥ ጋር በተያያዘ የሚሰጠው አገልግሎት በኬንያ ባለስልጣናት ታገደ።
የጤና ባለሙያዎች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ድርጅቱ የጽንስ ማስወረድን የሚያበረታቱ ማስታወቂያዎችን ሰርቷል የሚሉ ከፍተኛ ቅሬታዎች ሲነሱበት ቆይቷል ብሏል። ኬንያ ውስጥ የእናትየው ጤና አደጋ ውስጥ እስካልገባ ድረስ ጽንስ ማቋረጥ በህግ ያስቀጣል። ሜሪ ስቶፕስ በበኩሉ እስካሁን ድረስ ስራውን በተገቢውና ህጉን በጠበቀ መልኩ ሲሰራ እንደነበር አስታውቋል። • በካማሺ ዞን የመንግሥት ስራ ተቋርጧል የኬንያ የማስታወቂያ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት አልፍሬድ ሙቱዋ እገዳው ተገቢ እንደሆነ በመግለጽ ጽንስ ማስወረድ በቀድሞ የአሜሪካ መንግስት አበረታችነት የመጣና ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠት ያስከተለ ተግባር ነው ብለዋል። አንዳንድ ኬንያውያን ግን እገዳው ህገወጥና ለጤና ጠንቅ የሆነ በየሰፈሩ የሚደረግ የጽንስ ማስወረድን አንዳያበረታታ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። የኬንያ የጤና ባለሙያዎች ምክር ቤት ለሜሪ ስቶፕስ በላከው ደብዳቤ መሰረት ድርጅቱ መልእክቱ ከደረሰው ዕለት ጀምሮ ማንኛውም አይነት የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎቶችን በአስቸኳይ እንዲያቆም አዝዟል። • በሃሰተኛ ዜናዎች "የሞቱ" የኪነጥበብ ሰዎች ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ ለሚቀጥሉት ስድሳ ቀናት የሚሰጣቸውን አገለግሎቶች የሚገልጽ ሙሉ ሪፖርት በየሳምንቱ ለምክር ቤቱ እንዲያስገባም ተጠይቋል። ሜሪ ስቶፕስ በቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚለቃቸው ማስታወቂያዎች በመስሪያ ቤታቸው ፍቃድ ያላገኙ እንደሆነና ጽንስ ማቋረጥ ጥሩ እንደሆነ የሚገልጹ ናቸው ሲሉ የማስታወቂያ ጉዳዮችን የሚቆጣጠሩት አልፍሬድ ሙቱዋ ተናግረዋል። ድርጅቱ የሃገሪቱን ህገመንግስት በጠበቀ መልኩ አግልግሎት ሲሰጥ እንደነበረ በኬንያ የሜሪ ስቶፕስ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዳና ቲልሰን ገልጸዋል። ሜሪ ስቶፕስ ኬንያ፤ በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር አገልግሎት መስጠት የጀመረው እ.አ.አ. በ1985 ሲሆን፤ 22 ክሊኒኮችና 15 ተንቀሳቃሽ አገልግሎት መስጫዎች አሉት። • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው
54798226
https://www.bbc.com/amharic/54798226
የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች ውጥረቱ እንዲረግብ ጠየቁ
የትግራይና የፌደራል መንግሥት የገቡበትን ውጥረት ሊያረግቡ እንደሚገባ የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግሥታት በኤምባሲዎቻቸው በኩል ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ሁለቱም ወገኖች የገቡበትን ውጥረት እንዲያረግቡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለሰላማዊ ሰዎች ደህንነትና ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባልም ብሏል። "ሁሉም ወገኖች ለሰላማዊ ሰዎች ደህንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ እናበረታታለን" ብሏል መግለጫው። የእንግሊዝ ኤምባሲም በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ክልል ያለው ውጥረት በአፋጣኝ እንዲረግብ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ስም የጠየቀ ሲሆን የሰላማዊ ዜጎቻቸውን ደህንነት ሁለቱም ወገኖች እንዲያስጠብቁ ጠይቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ህወሃት በትግራይ የሚገኘው የመከላካያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልፀው ጦርነት መከፈቱን አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው የመከላከያ ሠራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ "ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል" ብለዋል። የትግራይ ክልል መንግሥት በክልሉ የሚገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላትና አዛዦች ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን ለመሰለፍ ወስኗል በማለት መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው ከዛሬዋ እለት ጀምሮ ጥቅትም 25/ 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ውስጥና ድንበር አካባቢ ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ የተከለከለ እንደሆነ አትቷል።
49706314
https://www.bbc.com/amharic/49706314
የክልል እንሁን ጥያቄ ከከፋ ዞን ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ቀረበ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ወደ ቦንጋ አቅንተው ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ያቀኑት ከቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን እና ከመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ጋር በመሆን ነው። ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው እስከ ጅማ ድረስ በአውሮፕላን የተጓዙት ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ልዑካቸው ከጅማ እስከ ቦንጋ የ100 ኪሎ ሜትር መንገድን በመኪና ተጉዘዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በቦንጋ ከተማ እስታዲያም ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤ ከዚያም ወደ ከተማ አስተዳደሩ ቢሮ በማቅናት ከዞኑ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድረገዋል። ለጠቅላይ ሚንስትሩ ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል የክልል እንሁን የሚለው በተደጋጋሚ የቀረበ ነበር። • የደቡብ ክልል፡ ውስብስቡ የዐብይ ፈተና • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? "በየደረጃው ለሚገኙ የመንግሥት አካላት የክልል የመሆንን ጥያቄ አቅርበናል" ያሉት አንድ ተሳታፊ "ለፍርድ ቤት አገልግሎት ሃዋሳ ለመድረስ 800 ኪ.ሜትሮችን ነው የምንጓዘው። ይህ ብቻም ሳይሆን የዞኑ ባለስልጣናት ለስብሰባ ወደ ሃሳዋሳ ሲያቀኑ ብዙ ወጪ ነው የሚያወጡት" ብለዋል። "የከፋ ህዝብ ባለፉት ስርዓቶች ብዙ ጉዳቶችን ያስተናገደ ህዝብ ነው። የከፋ ዞን የክልል የመሆን ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ነው" ሲሉ አንድ ሌለኛው ተሳታፊ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በተደጋጋሚ ክልል እንሁን ለሚሉ ጥያቄዎች ሲመልሱ "ክልል ብትሆኑ ጥያቄዎቻችሁ ሁሉ ምላሽ ያገኛሉ ብላችሁ ካሰባችሁ ስህተት ነው" ብለዋል። "ለምሳሌ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ክልል ሆነው ሳለ እናንተ የምታነሱትን ጥያቄ እነሱም ያነሳሉ" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ "በአሁኑ ሰዓት የከፋን ህዝብ እየስተዳደረ ያለው ሌላ አይደለም። እራሳችሁን በራሳችሁ እያስተዳደራችሁ ትገኛላችሁ" ብለዋል። ይሁን እንጂ የክልል እንሁን ጥያቄው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና ከክልሉ መንግሥት ጋር ተመክሮ ወደ ፌደራል የሚመጣ ጉዳይ ከሆነ ምንም አሳሳቢ የሚሆን አይደለም ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ። የከፋ ህዝብ ያመነበት ጥያቄ ከሆነ ማንም ሊያስቆመው የሚችለው ጥያቄ አለመሆኑን ጠቅለይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። የቡና ብሔራዊ ሙዚያም በከፋ ዞን ከዚህ ቀደም በብዙ ወጪ ግንባታው የተከናወነው ብሔራዊ የቡና ሙዚያም እስካሁን ሥራ አለመጀመሩን በመጥቀስ ሙዚየሙ ሥራ እንዲጀምር ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል። • ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ በሙዚየሙ ጉዳይ ከባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር ጋር እንደሚነጋገሩ ቃል የገቡት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የቡና መገኛ ሥፍራ ጮጬ አይደለም ከፋ ነው የሚል ክርክር ከተነሳ፤ በጉዳዩ ላይ የፖለቲካ እሰጣ ገባ ማምጣት አያስፈልግም ብለዋል። የቡና መገኛ ስፍራ ይሄ ነው ለማለት "እውቀቱም ሆነ አቅሙ የለኝም" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ተመራማሪዎች በጉዳዩ ጥናት ማድረግ ይችላሉ ብለዋል። የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ሌላው ከተሳታፊዎች በብዛት ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የመሰረተ ልማት ጥያቄ ይጠቀሳል። በደቡብ ኢትዮጵያ የመንገድ ልማት አነስተኛ መሆኑን በመጥቀስ በዚህ ዓመት መንግሥት አዳዲስ የመንገድ ግንባታዎችን ለማከናወን ከፍተኛ በጀት መመደቡን ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረዋል። "የተነሱ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ከስር ከስር እየመለሰን እንሄዳለንም" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። "ከተግባባን ከፋን ማልማት ከባድ አይደለም" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ልማት እና እድገት በትዕግስት እና በድካም ነው የሚገኙት የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
news-54054561
https://www.bbc.com/amharic/news-54054561
ቻይና፡ አውስትራሊያዊቷ ጋዜጠኛ የቻይናን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ጥላለች ተባለ
አውስትራሊያዊቷ ጋዜጠኛ ለሳምንታት በቻይና በቁጥጥር ሥር ውላ እንድትቆይ የተደረገው የአገሪቱን ብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣሏ ነው ተባለ።
ጋዜጠኛ ቼንገፍ ሊ የቻይና ግሎባል ቴሌቪዥን ኔትዎርክ (ሲጂቲኤን) አቅራቢዋ ቼንግ ሊ "የቻይናን ብሔራዊ ደኅንነት አደጋ ላይ መጣል" በሚል ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር እንድትውል መደረጓን ቻይና ይፋ አድርጋለች። ቻይና ውስጥ በዚህ በመሰል ወንጀል በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው እስከ ስድስት ወራት ድረስ ምርመር ሊደርግለትና ከእሥር ላይወጣ ይችላል። ቼንግ ሊ ከነሐሴ 8 ጀምሮ በቻይና በቁጥጥር ሥር ውላ ትገኛለች። በቻይና እና አውስትራሊያ መካከል ያለው ውጥረት እያየለ መጥቷል። በዚህም የአውስትራሊያ መንግሥት ቻይና የሚገኙ ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከዚህ ቀደም ማሳሰቢያ አስተላልፎ ነበር። የቻይና እና የአውስትራሊያ ግነኙነት እየሻከረ የመጣው አውስትራሊያ የኮሮናቫይረስ መነሾ በይፋ ይጣራ ማለቷን ተከትሎ ነው። ቻይናም ለዚህ የአውስትራሊያ ተግባር ምላሽ ነው በተባለለት ውሳኔ ቻይና ከአውስትራሊያ ወደ አገሯ በሚገቡ ምርቶች ላይ እገዳዎችን ጥላለች። ከዚህ በተጨማሪም ቻይና ዜጎቿ ለከፍተኛ ትምህርት አውስትራሊያን መዳረሻቸው አድርገው ከመወሰናቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡበት ስታሳስብ ቆይታለች። ጋዜጠኛዋ ቼንግ ሊ በምትሰራበት የቴሌቪዥን ጣቢያ ውስጥ በበርካቶች ዘንድ የተከበረች እና በተመልካቾች ዘንድም የምትወደድ የቢዝነስ ዘጋቢ ነች። በቻይና መንግሥት በቁጥጥር ሥር መዋሏ ይፋ ከመሆኑ በፊት ከቤተሰብ እና ከጓደኞቿ ጋር የነበራትን ግነኙነት በድንገት አቋርጣ ነበር። ከዚያም የቻይና መንግሥት ጋዜጠኛዋ በቁጥጥር ሥር መዋሏን አስታወቀ። ቼንግ ሊ ከነሐሴ 8 ጀምሮ በቻይና በቁጥጥር ሥር ውላ ትገኛለች። ቼንግ ሊ በቁጥጥር ሥር መዋሏ በተገለጸበት ወቅት በየትኛው ወንጀል ተጠርጥራ እንደታሰረች በግልጽ አልተነገረም። ይሁን እንጂ በርካቶች በቤጂንግ እና ካንቤራ መካከል እየሻከረመ የመጣው ግነኙነት አውስትራሊያዊቷን ጋዜጠኛ ለእስር እንድትዳረግ ምክንያት ነው እያሉ ነው። ከቼንግ በተጨማሪ በቻይና ይሰሩ የነበሩ ሁለት የአውስትራሊያ ዜጋ የሆኑ ጋዜጠኞች ሰኞ ዕለት ቻይናን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል። ቼንግ ለሲጂቲኤን ለስምንት ዓመታት ያገለገለች ሲሆን 'ግሎባል ቢዝነስ' በተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ አቅራቢ ሆና ትሰራለች። ጋዜጠኛዋ በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ሥር ከዋለች ወዲህ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ድረ-ገፅ ላይ ስለእሷና ሥራዎቿ የሚያትተው ገፅ መነሳቱ ተነግሯል።
news-56073531
https://www.bbc.com/amharic/news-56073531
የተገደሉት የኢዜማ አባል "ማስፈራሪያ እና ዛቻ" ይደርስባቸው ነበር ተባለ
ባለፈው ዕሁድ በቢሾፍቱ ከተማ የተገደሉት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አባል ላይ ቀደም ሲል ዛቻና ማስፈራሪያ ተፈጽሞባቸው እንደነበር ተገለጸ።
የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኢዜማ የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ግርማ ሞገስ እሁድ ዕለት መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በጥይት ከመገደላቸው ቀደም ብሎ ማስፈራራሪያ ይደርሳቸው ነበር። የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ ትናንት ሰኞ በሰጡት መግለጫ፣ እሁድ በግምት ከምሽቱ 3፡00 ላይ መምህር ግርማ ሞገስ የተባሉ ግለሰብ "ለጊዜው ማንነቱ ባልታወቀ ተጠርጣሪ" በጥይት መገደላቸውን አረጋግጠዋል። የከተማው ፖሊስ ጥቃቱን የፈጸመውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ተናግሯል። የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንደገለፁት፣ "አቶ ግርማ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚያደርጉት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ማንነታቸውን ከማያውቋቸው ሰዎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይደርስባቸው እንደነበር ለፓርቲው ሪፖርት አቅርበው ነበር።" ፓርቲውም በቀረበው ሪፖርት መሰረት ክትትል ሲያደርግ እንደነበርም ተናግረዋል። ኮማንደር ታሪኩ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ከመምህር ግርማ ጋር ግጭት የነበራቸው ግለሰቦች ያስፈራሯቸው እና ይዝቱባቸው እንደነበር መረጃ መገኘቱን በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል። ማስፈራሪያ እና ዛቻ ያደርሱ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ገልፀዋል። እሁድ ምሽት የተፈፀመው ግድያ፣ ሲደርስባቸው ከነበረው ማስፈራሪያና ዛቻ ጋር ይያያዛል ወይስ አይያያዝም? የሚለውን ጉዳይ ማጣራት እንደሚያስፈልግው አቶ ናትናኤል ገልፀው፤ ኢዜማ ማጣራቱ ተደርጎ እንዳበቃ በይፋ እንደሚገልፅ አቶ ናትናኤል አሳውቀዋል። ኢዜማ ከግድያው ጋር በተያያዘ ከመንግሥት ኃላፊዎች እና ከአካባቢው የፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ንግግር እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።
news-50535120
https://www.bbc.com/amharic/news-50535120
ሲዳማ: 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል
የሲዳማ ዞን ቀጣይ ዕጣ ፈንታን ለመወሰን ረቡዕ ዕለት በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ዞኑ የአገሪቱ 10ኛው ክልል የመሆን ድምጽ ማግኘቱን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
በዚህም መሰረት በሕዝበ ውሳኔው በመሳተፍ ከተመዘገበው ህዝብ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት፤ ማለትም 98.51 በመቶው ዞኑ ክልል እንዲሆን የሚያስችለውን ድምጽ ሰጥተዋል። በሕዝበ ውሳኔው ውጤት መሰረትም እስካሁን ድረስ ዞኑን በስሩ አድርጎ ሲያስተዳድረው የቆየው የደቡብ ክልል ኃላፊነቱን አዲስ ለሚመሠረተው የሲዳማ ክልል ያስተላልፋል። ዋና መቀመጫውን በሲዳማ ዞን ውስጥ በምትገኘው በሐዋሳ ከተማ ያደረገው የደቡብ ክልል ለሁለት የምርጫ ዘመን ያህል መቀመጫውን ከአዲሱ የሲዳማ ክልል ጋር ተጋርቶ እንደሚቆይ ቀደም ሲል ተገልጿል። በሕዝበ ውሳኔው መሠረት አዲስ የሚመሠረተው የሲዳማ ክልል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አንድ አባል ይሆናል። የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 47 አንድ ክልል ክልልነቱ የሚረጋገጠው ሃሳቡ ለምክርት ቤት ቀርቦ በሕዝበ-ውሳኔ አብላጫ ድምፅ ሲያገኝ ነው። ረቡዕ [ኅዳር 10/2012] በተደረገው ሕዝበ-ውሳኔ ለመሳተፍ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ነበር ድምፅ ሰጭዎች ወደ ምርጫ ጣብያዎች መጉረፍ የጀመሩት። ውጤቱ ሐሙስ ቢበዛ አርብ ይታወቃል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻውን ኦፊሴላዊ ውጤት ትላንት፤ ቅዳሜ [ኅዳር 13/2012] ይፋ አድርጓል። ምርጫው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁ ቢነገርም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አባል የሆነ አንድ ግለሰብ ምርጫውን ሊያስተጓጉል ሲሞክር ይዤ ለፖሊስ አስረክቤያለሁ ሲል አሳውቆ ነበር። የምርጫውን ውጤት ተከትሎ ሌሎች ክልሎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በሲዳማ ሕዝበ-ውሳኔ ውጤት የተሰማቸውን ደስታ ሲገልፁ ነበር። ለሲዳማ ክልልነት ድምፃቸውን የሰጡ ሻፌታን፤ ሲዳማ ከደቡብ ክልል ጋር ይቆይ ያሉ ደግሞ ጎጆን በመረጡበት በዚህ ሕዝበ ውሳኔ የምርጫ ጣብያዎች አንሰዋል ተብሎ መጀመሪያ ተመድበው ከነበሩት 1692 የምርጫ ጣብያዎች ተጨማሪ 169 ጣብያዎች ተቋቁመው ነበር። ምንም እንኳ 99.8 በመቶ ሻፌታን ቢመርጡም 1.48 በመቶ ወይም 33463 ሰዎች ድምፃቸውን ለጎጆ ሰጥተዋል። 18351 የምርጫ ካርዶችን ደግሞ ዋጋ አልባ ሲል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል። ውጤቱን ተከትሎ በሐዋሳ እና በሌሎች የሲዳማ ዞን ሥፍራዎች ነዋሪዎች ደስታቸውን ሲገልፁ ነበር።
news-55516801
https://www.bbc.com/amharic/news-55516801
በአሜሪካ ምክር ቤት መሪዎች መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ
በአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የብዙሃን መሪው ሚች ማኮኔል መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ።
ሚች ማኮኔል እና ናንሲ ፔሎሲ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከሚገኘው የናንሲ ፔሎሲ ቤት ውጪ አንገቱ የተቆረጠ አሳማና ደም የሚመስል ቀለም የተገኘ ሲሆን ግድግዳውም በተለያየ ጽሁፍ ተበላሽቶ ተገኝቷል። ኬንተኪ ውስጥ በሚገኘው የሪፐብሊካኑ ማኮኔል ቤት ግድግዳ ላይ ደግሞ "ገንዘቤ የታለ" የሚል ጽሁፍና የስድብ ቃላት ተጽፈው ተገኝተዋል። ይህ በባለስልጣናቱ መኖሪያ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የተከሰተው በኮሮናቫይረስ ምክንያት ያጋጠመውን ችግር ለመቅረፍ በቀረበው የድጋፍ ዕቅድ ላይ በምክር ቤት ከባድ ፖለቲካዊ ውዝግብ መካሄዱን ተከትሎ ነው። ባለፈው ማክሰኞ በዲሞክራቶች በሚመራው የአሜሪካ ምክር ቤት የ40 ሪፐብሊካን አባላት ድጋፍን በማግኘት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገቢያቸው ለተጎዳ ዜጎች እንዲሰጥ ሐሳብ ቀርቦበት የነበረውን የ600 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ወደ 2000 ዶላር ከፍ እንዲል ተወስኖ ነበር። ምንም ችንኳን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ረቂው የምክር ቤት አባላቱ እንዲያጸድቁ ቢጠይቁም በሪፐብሊካኖች የሚመራው የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከፍተኛ የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀውን በጀት ሳይቀበለው ቀርቷል። ረቡዕ ዕለት ሚች ማኮኔል እንደተናገሩት በሚደረግ ማንኛውም ጫና "በብድር የሚገኘውን ገንዘብ ድጋፉ ለማያስፈልጋቸው ለዲሞክራት ሐብታም ወዳጆች በጥድፊያ እንዲሰጥ አናደርግም" ሲሉ ተደምጠው ነበር። ሚች ማኮኔል ቅዳሜ በቤታቸው ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ባወጡት መግለጫ ላይ "ቢስማሙም ባይስማሙም" በምክር ቤቱ የሥራ ሂደት ወቅት የተሳተፉትን በሙሉ አመስግነዋል። ጨምረውም "ይህ የተለየ ጉዳይ ነው" በማለት የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም "ንብረት ማውደምና ጉዳት ማድረስ እንዲሁም ፍርሃት ለመፍጠር የሚደረገው ፖለቲካም በማኅበረሰባችን ውስጥ ቦታ የለውም" ብለዋል። የሳንፍራንሲስኮ ፖሊስ በአፈጉባኤዋ ቤት ላይ በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ ምርመራ እያደረጉ ሲሆን ፔሎሲ ግን እስካሁን ምንም አስተያየት አልሰጡም። ባለፈው አርብ የአሜሪካ ምክር ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ የስልጣን ዘመን አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። በቅርቡ በተደረገው ምርጫ ለአሜሪካ ምክር ቤት አባልነት የተመረጡ የኮንግረስ አባላት ዛሬ እሁድ ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ።
49027427
https://www.bbc.com/amharic/49027427
በኦሮሚያና ትግራይ ሕገ-ወጥ ናቸው የተባሉ 2400 ቤቶች ፈረሱ
በመቀሌ ዙርያ የእንደርታ ወረዳ አስተዳደር ከ400 በላይ "ሕገ-ወጥ ናቸው" ያላቸውን ቤቶች 'በዶዘር በመታገዝ' ማፍረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለጹ።
በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ሸዋ፤ አዳማና ሞጆ አካባቢዎች 'በሕገ-ወጥ መሬት ወረራ የተገነቡ' የተባሉ ከ2000 በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የአካበቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ኦሮምኛ ክፍል ተናግረዋል። በትግራይ ክልል በእንደርታ ወረዳ አስተዳደር ሥር የሚገኘው 'ማሕበረ ገነት' ቀበሌ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጥዑማይ ፍጹም ጉዳዩን አስመልክተው ሲናገሩ "ከ4-10 የቤተሰብ አባሎች የሚኖሩባቸውና ከ1990 ዓ.ም ጀምረው ያስተዳደሩዋቸው ቤቶች ጨምሮ ህጋዊና ሕገ-ወጥ ቤት ሳይለይ ከ420 በላይ ቤቶች እንዲፈርሱ ተደርጓል" ይላሉ። • የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው? እሳቸው እንዳሉት ስለቤቶቹ መፍረስ የተሰጠ ቅድመ ማስጠንቀቂያ አልነበረም። ከክስተቱ በኋላ በድርጊቱ የተቆጡ ነዋሪዎች ወደ ርዕሰ-መስተዳድሩ ቢሮ በመሄድ ተቃውሟቸውን እንደገለጹ አቶ ጥዑማይ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የእንደርታ አካባቢ ነዋሪዎች እንዳሉት ከሆነ የወረዳው አስተዳደር በልዩ ኃይል እና በፖሊስ ታጅቦ ነው እርምጃውን የወሰደው። ክለውም "ሁኔታውን የተቃወሙ እና ፎቶ ያነሱ" ሰዎች መታሰራቸውም ነዋሪዎቹ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ቤታቸው የፈረሰባቸው የእንደርታ ከተማ አንድ ነዋሪ "ከሃያ ዓመት በፊትም ሆነ በቅርቡ የተሰሩ ቤቶች በአንድ ላይ ፈርሰዋል" ሲሉ ተናግረዋል። "ስለጉዳዩ መረጃ እስክናቀርብ እንኳ ግዜ አልተሰጠንም። ይፈርሳል አይፈርስም ስለሚለውም አናውቅም ነበር። ማታ 'ዶዘር' ይዘው መጥተው እቃዎቻችንን አውጡ አሉን" ይላሉ። ቤታቸው ከፈረሰባቸው አንዳንዶቹ 'አውላላ ሜዳ ላይ' ድንኳን ሰርተው ተጠልለው እንደሚገኙም ነዋሪዎች ተናግረዋል። • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? "ከአማራ ክልል ተፈናቅለው የመጡ አንዳንድ ሰዎች እዚህ መሬት ገዝተው ነበረ። አሁን ተመልሰው ለችግር ተዳርገዋል" ሲሉም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ሌሎች ነዋሪዎችም "ከነ ሙሉ ንብረታቸው ቤታቸው የፈረሰባቸው አሉ" ይላሉ። የትግራይ ክልልም ሆነ የወረዳው አስተዳደር ጉዳዩን በተመለከተ የሰጠው መግለጫ የለም። በምሥራቅ ሸዋ ዞን የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ክፍል ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙባረክ ዑስማን፤ በዞኑ ውስጥ ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ የተስፋፋ ሲሆን ሕገ-ወጥ ቤቶችን በተመለከተ የወጣውን ደንብ ቁጥር 182 ተከትሎ ከ2005 ዓ.ም ወዲህ የተሰሩ 5000 ያህል ቤቶች አንደሚፈርሱ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል [ዶ/ር] መንግሥታቸው የሕገወጥ ቤቶች ግንባታ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወስድ ቀደም ሲል ገልጸው ነበር። በመሬት ወረራ እና ሕገ-ወጥ የቤቶች ግንባታ ላይ የተሰማሩ ሰዎችም ከተግባራችው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀው ነበር። • መፈናቀል፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ዓመት ፈተናዎች አንዱ
news-55477833
https://www.bbc.com/amharic/news-55477833
ሙዚቃ ፡ በ2021 የሙዚቃ ድግሶች ወደ መድረክ ይመለሱ ይሆን?
የፈረንጆቹ 2020 ምን መልካም ነገር ትቶ አለፈ ቢባል ሙዚቃ ማለት ይቻላል።
እንግሊዛዊቷ ዱዋ ሊፓ እና ሌዲ ጋጋ ከቤታቸው ሆነው በበይነ መረብ አድናቂዎቻቸውን አስጨፍረዋል። በርካታ ተወዳጅ ሙዚቀኞች አልበሞቻቸውን ለአድናቂዎቻቸው አቅርበዋል። እርግጥ ነው ሰዎች በአካል ሄደው የሚታደሙበት የሙዚቃ ድግስ አልነበረም - ለኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት። ነገር ግን ይህ ለአርቲስቶች መነቃቃት ሆናቸው እንጂ ሥራ የለም ብለው እንዲቀመጡ አላደረጋቸውም። ቻርሊ ኤክስሲኤክስ የተሰኘችው ወጣት ዘፋኝ በስድስት ሳምንታት አገባዳ የለቀቀችው አልበም በሚሊዮኖች ተቸብችቦላታል። አንጋፋው ፖል ማካርቲኒ ከ50 ዓመት በፊት የጀመረውን አልበም ዘንድሮ አጠናቋል። ቴይለር ስዊፍት ደግሞ በአምስት ወራት ውስጥ ሁለት አልበም ለአድናቂዎቿ አበርክታለች። አሁን ጥያቄው እውን በሚቀጥለው በዚህ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት 2021 የሙዚቃ ድግስ [ኮንሰርት] ይመለስ ይሆን ወይ? የሚለው ነው። የኢንተርኔት ድግሶች 2021 የኢንተርኔት [በይነ መረብ] ድግሶች የሚደምቁበት እንደሚሆን ይገመታል። ኮሮናቫይረስ የአርቲስቶች ጓዳ ጎድጓዳ አድናቂዎቻቸው እንዲያዩ አድርጓል። አብዛኞቹ ሙዚቀኞች ድግሳቸውን ሲያቀርቡ የነበሩት ከመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ነው። እንደው የታዋቂ ሰዎች ኩሽና እንደኛው ይሆን? ብለው ይጠይቁ ለነበሩ 2020ን ያክል ለጋስ ዓመት የለም። የምርም ፈረስ የሚያስጋልብ መኖሪያ ቤት ያላቸው ዘፋኞች ከኩሽና እስከ መኝታና መታጠቢያ ቤታቸው እየተሽከረከሩ በእጃቸው በያዙት ድምፅ ማጉያ ሲቀኙ ነበር። ዱዋ ሊፓ የተሰኘችው አዲስ ሙዚቀኛ ባለፈው ኅዳር ከጓዳዋ ሆና ያስተላፈችው ድግስ በኢንተርኔት ዓለም ብዙ ሰዎች ያዩት ሆኗል። ሙዚቀኛዋ ከቤት ያስተላለፈችው ድግስ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ወጥቶበታል። ድግሱን በኢንተርኔት ለመከታተል በቻይናና ሕንድ ብቻ 284 ሺህ ሰዎች ቲኬት ገዝተዋል። ሙዚቀኛዋ እንዲህ በጉጉት የተጠበቀውን ድግስ እንደዋዛ አላየችውም። ከኋላዋ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ዳንሰኞች አሰልፋ ነበር። እንደ ኤልተን ጆን ያሉ ሙዚቀኞች ተጋባዥ ሆነው መጥተው አድምቀውታል። አሜሪካዊ ራፐር ትራቪስ ስኮት ደግሞ በሌላ ዓይነት ነው ብቅ ያለው። ራፐሩ 'ፎርትናይት' በተሰኘው የቪድዮ ጌም ነው የዘጠኝ ደቂቃ ሙዚቃውን ያስኮመኮመው። ለዚህም 20 ሚሊዮን ዶላር ተከፍሎታል። ትራቪስ በ2018/19 ለ58 ቀናት ተዘዋውሮ ከሠራው የሙዚቃ ድግስ ያገኘው ገንዘብ 53 ሚሊዮን ዶላር ነበር። የበይነ መረብ ሙዚቃ ድግስ ሌላኛው ጥቅም ተመልካቹ በፒጃማው ሆኖ ከቤቱ መከታተል መቻሉ ነው። የሚወዱትን ሙዚቀኛ ለማየት ወደ ትልቅ ከተማ መሄድ አይጠበቅብም ማለት ነው። ከዚህም አልፎ የኢንተርኔት ኮንሰርት ቦታ ሞልቷል አይል፤ ዕድሜዎ አልደረሰ አይል። [ለምሳሌ የዱዋ ኮንሰርት ዋጋው 7.50 ዩሮ ነበር።] ኮሮናቫይረስ በክትባት ተሸንፎ ቢጠፋ እንኳ ኮንሰርቶች ቶሎ ወደ መድረክ ይመለሳሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። ድግሶች ይመለሳሉ - ግን እንዴት? አንዳንዶች የሙዚቃ ድግስ በሚቀጥለው ፋሲካ ይመለሳል ይላሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ክረምት ላይ ሳይመለስ አይቀርም ባይ ናቸው። አንዳንድ ሙዚቀኞች ለሚቀጥለው ዓመት ከአሁኑ የድግሳቸውን መግቢያ በመሸጥ ላይ ናቸው። ሌሎች ደግሞ መጪው ዘመን አያስተማምንም በማለት እየሰረዙ ይገኛሉ። ኮሮናቫይረስ ቢቀንስ እንኳ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ ይሆናል። ወደ ድግስ ሲሄዱ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ደግሞ ሌላኛው የመጪው ዘመን እውነታ ነው። ይህን ሁሉ ከምናደርግ ለምን ታዳሚዎችን በፀረ-ተህዋስ ፈሳሽ አንረጫቸውም ያሉም አልጠፉም። አካላዊ ርቀት ሳይጠበቅ ሲቀር በጩኸት የሚያሳብቅ የእጅ አምባር ይገጠም የሚል ሐሳብም ተሰምቷል። 'ቲኬትማስተር' የተሰኘው የሙዚቃ ድግሶች አዘጋጅ ተቋም ሰዎች ኮቪድ-19 እንደሌለባቸው የሚያረጋግጥ ሠርቲፊኬት ከሌላቸው ቲኬት እንዳይገዙ መከልከል አለባቸው ይላል። ያም ሆነ ይህ ወደፊት የሙዚቃ ድግሶች ልክ እንደቀድሞው እየተፋፈጉ የሚታደሟቸው ይሆናሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ይመስላል። እና በአዲሱ ዓመት ከምዕራባዊያኑ ሙዚቀኞች ምን ይጠበቃል? ታዋቂዋ አሜሪካዊት ሶፍት ሮክና ካንትሪ ሙዚቀኛ ቴይለር ስዊፍት በተጠናቀቀው 2020 ባወጣችው አልበም ለግራሚ ሽልማት ታጭታለች። ሙዚቀኛዋ ከዚህ በፊት የሠራቻቸውን ሥራዎች ስቱዲዮ ገብታ ድጋሚ መቅረፅ ትፈልጋለች። ለምን ካሉ ነገሩ ወዲህ ነው። የሙዚቀኛዋ የቀድሞ ሥራዎች ባለቤት እሷ አይደለችም፤ የቀድሞ ድርጅቷ እንጂ። የቴይለር ሙዚቃዎች መብት ያለው ድርጅት የዘፋኟን ሥራዎች በ300 ሚሊዮን ዶላር እንደሸጠ ተዘግቦ ነበር። አሁን ድጋሚ መቅዳት ያሻትም የኮፒ ራይት መብቷን ድጋሚ ለመቆጣጠር ነው። አዴልና ሪሃና አዴልና ሪሃና አልበም አይለቁም? ተወዳጆቹ አዴልና ሪሃን ከዛሬ ነገ አልበም ይለቃሉ ተብሎ ቢጠበቅም በአድናቂዎቻቸው ላይ ጨክነዋል። በሚቀጥለው ዓመት ጠብቁን እያሉን ይሄው አዲስ የሙዚቃ ሥራ ካስደመጡ ሦስት ዓመት ሆናቸው። ሪሃና በሰባት ዓመት ሰባት አልበሞችን አከታትላ አድናቂዎቿን በተወዳጅ ሙዚቃዎቿ ፍቅር ካጨናነቀች በኋላ ትኩረቷን ወደ ፋሽን አዙራለች። በአድናቂዎቿ ዘንድ ሪሪ በተሰኘ ቅፅል ስሟ የምትቆላመጠው ሪሃና ለኮቪድ-19 እንዲሆን ብላ ሚሊዮን ዶላሮች ለግሳለች። አዴልም እንዲሁ የሙዚቃ አልበም የማውጣቷ ነገር አጠራጣሪ ነው። ነገር ግን ድሬክ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት ሙዚቃ ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።
news-55541616
https://www.bbc.com/amharic/news-55541616
የግራሚ ሽልማት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ተላለፈ
የ2021 የግራሚ ሽልማት ሥነ ሥርዓት በኮሮናቫይረስ ስጋት ሳቢያ ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉን የሽልማቱ አዘጋጆች አሳወቁ።
በዚህ ዓመት ለስድስት ሽልማቶች የታጨችው ዶዋ ሊፓ በዓለማችን የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ታላቅ ከሚባሉት ሽልማቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ሽልማት ከሦሰት ሳምንት በኋላ ነበር ሊካሄድ የታሰበው። ነገር ግን በአሜሪካዋ የሎስ አንጀለስ ከተማና በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ በኮሮረናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ሥነ ሥርዓቱ ከሁለት ወር በኋላ መጋቢት አጋማሽ ላይ እንዲደረግ ተወስኗል። በዚህ ዓመት ሊካሄድ ለታቀደው ሽልማት በኅዳር ወር ይፋ የተደረገው የዕጩዎች ዝርዝርን ቢዮንሴ፣ ቴይለር ስዊፍትና ዱዋ ሊፓ የቀዳሚነቱን እየመሩ ነው። "ከሙዚቃው ማኅበረሰብና ይህንን የሽልማት ሥነ ሥርዓት ለማዘጋጀት ያለድካም እየሰሩ ካሉት በመቶዎች ከሚቆጠሩ ሠራተኞች ጤናና ደኅንነት በላይ የሚያሳስበን ምንም ነገር የለም" ይላል የግራሚ ሽልማትን ከሚያዘጋጀው ተቋም የወጣው መግለጫ ያለውን የጤና ስጋት በማመለከት። የዚህን ዓመት የግራሚ ሽልማት መድረክ ይመራዋል ተብሎ የታሰበው ታዋቂው ኮሚዲያን ትሬቨር ኖዋ ይሳተፍ እንደሆነ አስካሁን ግልጽ አይደለም። ምንም እንኳን እንዴት እንደሚሆን ዝርዝሩ ባይገለጽም ቀደም ሲል የሽልማቱ አዘጋጅ ድርጅት የዚህ ዓመቱ የግራሚ ሥነ ሥርዓት በአብዛኛው በኢንተርኔት አማካይነት የሚካሄድ እንደሚሆን መግለጹን ኤኤፍፒ ዜና ወኪል ዘግቦ ነበር። ባለፈው ዓመት አሜሪካ ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ከግራሚ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሽልማቶች በኢንተርኔት አማካይነት ለመካሄድ ተገደዋል። የአሜሪካዋ የካሊፎርኒያ ግዛት በተለይ በወረርሽኙ መስፋፋት ክፉኛ በመመታቷ የአምቡላንስ ሠራተኞች የታመሙ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል እንዳያመጡ ታዘዋል።
news-53326847
https://www.bbc.com/amharic/news-53326847
የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮናቫይረስ በአየር ወለድ ብናኞች ሊተላለፍ እንደሚችል ተናገረ
የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ በአየር ላይ እየተንሳፈፉ በሚቆዩ ጥቃቅን ብናኞች ሊተላለፍ ይችላል የሚለውን መረጃ እውነታነት ሊኖረው ይችላል ሲል ተቀበለ።
በተለይ ይህ በአየር ላይ በሚቆዩ ጥቃቅን ብናኞች የመተላለፍ ሂደት ሰው ተጨናንቆ በሚገኝባቸው ስፍራዎች ውስጥ፣ ዝግ በሆኑና በቂ አየር በማይንቀሳቀስባቸው ቤቶች እና ቢሮዎች የመከሰት እድሉ እንዳለው ገልጿል። ይህ ግኝት ከተረጋገጠ በቤት ውስጥ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ ለውጥ ሊደረግ ይችላል ተብሏል። ለወራት የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 መተላለፊያ መንገዶችን ሲጠቅስ ቫይረሱ የሚተላለፈው ሰዎች በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ወቅት በሚወጡ ጥቃቅን ጠብታ ፈሳሾች ነው ሲል ነበር። እነዚህ ጠብታዎች አየር ላይ ተንሳፍፈው የሚቆዩ ሳይሆኑ ወደ ታች ወርደው በቁሶች አልያም መሬት ላይ ያርፋሉ። ለዚያም ነው እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ እንደ አንድ ቁልፍ መከላከለያ መንገድ ሲነገር የከረመው። ነገር ግን ከ32 አገራት የተሰባሰቡ 239 ሳይንቲስቶች በዚህ ሃሳብ እንደማይስማሙ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ተናግረዋል። የእነዚህ ተመራማሪዎች ሃሳብ ቫይረሱ በአየር ምክንያት ሊሰራጭም ይችላል የሚል ነው። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከሚተነፍሱት አየር የሚወጡ ጥቃቅን ብናኞች አየር ኣለይ እየተንሳፈፉ ለሰዓታት ይቆያሉ ባይ ናቸው። " መረጃውን እንዲቀበሉ እንፈልጋለን፣" ያሉት በኮሎራዶ ዩኒቨርስቲ የኬምስትሪ ምሁር የሆኑት ጆሴ ጂሜኔዝ ናቸው። "ይህ በዓለም ጤና ድርጅት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት አይደለም። ሳይንሳዊ ክርክር ነው፣ ወደ ህዝቡ መውጣት የፈለግነው ከእነርሱ ጋር በርካታ ውይይት ካደረግን በኋላ መረጃዎቻችንን ለመቀበል አሻፈረኝ በማለታቸው ነው" ብለዋል ለሮይተርስ የዜና ወኪል። የዓለም ጤና ድርጅት የእነዚህ ተመራማሪዎች ሃሳብ እውነት ሊሆን የሚችልባቸው እድሎች መኖራቸውን ተናግሯል። የጤና ድርጅቱ ይህ በተጨናነቁ ስፍራዎች ወይንም በተዘጉ ቦታዎች ሊከሰት እንደሚችል ተናግሯል። የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊዎች መረጃው የመጀመሪያ ደረጃ መሆኑንና ተጨማሪ ፍተሻ ሊካሄድበት እንደሚገባ መዘንጋት እንደሌለበት አሳስበዋል። ይህ መረጃ በሚገባ እንደሚፈተሽ የተገለፀ ሲሆን እውነታነቱ ከተረጋገጠ የኮሮናቫይረስ መከላከል መረጃዎች ላይ የተወሰነ ለውጥ መደረጉ እንዲሁም በሰፊው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ሊጀመር እንደሚችል እየተገለፀ ነው። ከዚህም ባሻገር የበለጠ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በተለይ ደግሞ በመጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች እንዲሁም በህዝብ ትራንስፖርቶች ውስጥ ይህ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
news-47898944
https://www.bbc.com/amharic/news-47898944
ኦማር አል-ሽር: የሱዳኑ ገዢ ከየት ወደየት?
የኦማር አል-በሽር አገዛዝ አልፋ እና ኦሜጋ ተመሳሳይ እና ድራማዊ ሆኗል። በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግሥት ተጀምሮ፤ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ፍፃሜውን አግኝቷል።
ፕሬዝደንት አል-ባሽር ሱዳንን ለ30 ዓመታት ያክል መርተዋል ምሳ ሰዓት ገደማ ነበር የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር አዋድ አብን በሃገሪቱ ቴሌቪዥን ጣብያ ብቅ ብለው፤ የኦማር አል-በሽር አገዛዝ አክትሟል፤ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ወታደራዊ መንግሥትም ተመሥርቷል፤ ሲሉ አዋጅ ያሰሙት። • የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች ሱዳን ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር እንደምትተዳደርም ነው ሚኒስትሩ ቆፍጠን ባለ ንግግራቸው ያሳወቁት። አክለውም፤ አል-ባሽር በቁጥጥር ሥር ውለዋል፤ «ደህንነቱ በተጠበቀ ሥፍራም ይቆያሉ» ሲሉ ዜናውን አሰሙ። የዓመታት ጦርነት የአል-ባሽር የፖለቲካ ሕይወት በጦርነት ዜማ የተቃኘ ነው። በአውሮፓውያኑ 1989 ነበር አል-ባሽር የያኔዋን የአፍሪቃ ግዙፍ ሃገር ለማስተዳደር መንበሩን የተቆናጠጡት። አል-ባሽር ሥልጣን ሲቆናጠጡ በደቡባዊ እና ሰሜናዊ ሱዳናውያን መካከል በተከሰተ የእርስ በርስ ጦርነት ሃገሪቱ ትታመስ የነበረበት ወቅት ነበር። ሱዳን በአል-ባሽር አገዛዝ መባቻ ግድም የተረጋጋች ብትመስልም ግጭቱ እንደ አዲስ አገረሸ፤ አል-ባሽርም ዳርፉር አካባቢ ከባድ የጦር ኃይል ተጠቅመዋል ተብለዋል ተወቀሱ። • ሱዳን ውስጥ የዳቦና የነዳጅ ዋጋ ንሮብናል ያሉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) አል-ባሽር የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋልና እፈልጋቸዋለሁ ሲል ለፈፈ። ጫና የበረታባቸው አል-ባሽር ግን በአውሮፓውያኑ 2010 እና 2015 የተደረጉ ምርጫዎችን በማሸነፍ መንበራቸው ላይ ተደላደሉ። በአይሲሲ የእሥር ማዘዣ የወጣባቸው አል-ባሽር ከሃገራቸው ውጭ በተገኙበት የካቴና ሲሳይ እንዲሆኑ ቢወሰንባቸውም ወደ ግብፅ፣ ሳዑዲ አራቢያ እና ደቡብ አፍሪቃ ከመሄድ ግን ያገዳቸው አልተገኘም። ወርሃ ሰኔ 2015 ላይ ግን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሳሉ ሊያዙ መሆናቸውን የሰሙት አል-ባሽር ሹልክ ብለው የወጡበት መንገድ ዓለምን ጉድ አሰኘ። የተዋሃደች ሱዳን አል-ባሽር ሥልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት ወታደራዊ አዛዥ ነበሩ፤ ኅላፊነታቸው ደግሞ በጆን ጋራንግ የሚመራውን በደቡብ በኩል የሚንቀሳሰቀሰውን አማፂ ቡድን መዋጋት። • የኢትዮጵያና አሜሪካ የተለየ ግንኙነት እስከምን ድረስ? ባሽር ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ ከጋራንግ ጋር እርቅ ቢያወርዱም ሙሉ ሰላም ሊሰፍን አልቻለም። አልፎም ደቡብ ሱዳናውያን 'የእንገንጠል' ጥያቄ አቀረቡ። 2011 ላይ በተካሄደ ሕዝበ-ውሳኔ 99 በመቶ ያክል ደቡበድ ሱዳናውያን 'የእንገንጠል' ጥያቄውን ደግፈው ድምፅ ሰጡ። ከስድስት ወራት በኋላ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን በይፋ ተለያዩ። ምንም እንኳ ደቡብ ሱዳን ተገንጥላ ራሷን ብትችልም አል-ባሽር በዳርፉር ጉዳይ አሁንም ጣልቃ እየገቡ ነው ተብለው መወቀሳቸው አልቀረም፤ ምንም እንኳ እርሳቸው ክሱን ቢክዱም። የአል-ባሽር ክስ መዝገብ ዘር ማጥፋት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የጦር ወንጀል በ1944 የተወለዱት ባሽር በለጋነታቸው ነበር ወደ ውትድርናው ዓለም የገቡት። ምንም ልጅ እንደሌላቸው የሚነገርላቸው ባሽር በ50ዎቹ ዕድሜ ላይ ሳሉ ሁለተኛ ሚስታቸውን አገቡ። ከዚህ ውጭ ስለ አል-ባሽር የግል ሕይወት ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። የካርቱም ቀውስ ባሽር በ30 ዓመት የሥልጣን ዕድሜያቸው የአሁኑን የመሰለ ተቃውሞ ገጥሟቸው አያውቅም። ባለፈው ዓመት ወርሃ ታህሳስ ላይ በዳቦ እና ነዳጅ ዋጋ መናር ሳቢያ የተጀመረው ተቃውሞ እነሆ ባሽርን ጠልፎ ሊጥል በቅቷል። ከደቡብ ሱዳን መገንጠል በኋላ የሱዳን ምጣኔ ሃብት ቀጥ ብሎ ሊቆም አልቻለም፤ ምክንያቱ ደግሞ የካርቱም ነዳጅ ሦስት አራተኛው ከጁባ ጋር በመሄዱ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ኑሮ መናርና ድህነት መስፋፋት ያዘ። የባሽር አገዛዝ ግን ችግሩን ከመቅረፍ ይልቅ ራሱን በሙስና ተጠልፎ አገኘው። • "ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት ፍየል ወዲህ የሆነባቸው ባሽር ወርሃ የካቲት ላይ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳወጁ፤ ካቢኒያቸውንም እንደ አዲስ ለማዋቀር ተገደዱ። በምርጫ ያወጣኝ ሕዝብ በምርጫ ያውርደኝ ያሉት ባሽር የሽግግር ጊዜ መንግሥት አላቋቁምም፤ የ2020 ምርጫ ላይ እንገናኝ ሲሉ ተደመጡ። ተቃውሞ ከተጀመረ ወዲህ ቢያንስ 28 ሰዎች እንደተገደሉ ዘገባዎች ያረጋግጣሉ፤ ምንም እንኳ 'ሂውማን ራይትስ ዎች' ቁጥሩ ከዚያ በላይ ነው ቢልም። አሁን ላይ ባሽር ለሰላሳ ዓመታት ከተቆናጠጡት መንበር በግዴታ ወርደዋል፤ ወታደራዊ የሽግግር መንግሥትም ተመሥርቷል። አንዳንዶች ግን ሁሉት ዓመት በወታደራዊ ኃይል መመራት ተገቢ አይደለም የሚል ምሬት ከአሁኑ ማሰማት ይዘዋል። የባሽር ሥልጣን ግብዓተ-መሬት ሱዳናውያንን ቢያስፈነድቅም ነገ ላይ ስለሚሆነው ነገር ግን ማንም እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይችልም። ሱዳን የቀድሞውን ፕሬዝደንት ኦማር አል-በሽርን ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፋ ልትሰጥ እንደሆነ የተነገረው ማክሰኞ የካቲት 3/2012 ነው። ሱዳን በበላይነት እየመራ ያለው የሽግግር ምክር ቤት ነው አል ባሽርን ለአይሲሲ አሳልፈ ለመስጠት መወሰኑን ያሳወቀው። አል-ባሽር፤ ወርሃ ሰኔ 2015 ላይ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሳሉ ሊያዙ መሆናቸውን ሰምተው ሹልክ ብለው የወጡበት መንገድ ዓለምን ጉድ አሰኝቶ ነበር።
news-50703907
https://www.bbc.com/amharic/news-50703907
ህንዳዊቷን ዶክተር በቡድን ደፍረው ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት በፖሊስ ተገደሉ
ከሰሞኑ በህንዷ ግዛት ሃይደራባድ አንዲት ዶክተር በቡድን ተደፍራ ተገድላ አስከሬኗ የተገኘ ሲሆን፤ ከግድያዋም ጋር ተያይዞ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ነበር።
እነዚህን ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ተኩሶ እንደገደላቸው ተዘግቧል። በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበሩት ተጠርጣሪዎች በዚሁ ሳምንት አርብ እለት ወንጀሉ ወደተፈፀመበት ቦታ ተወስደው ነበር። • የተነጠቀ ልጅነት • የታዳጊዋ ሬስቶራንት ውስጥ መደፈር ደቡብ አፍሪቃውያንን አስቆጥቷል በቦታው ላይ እያሉ የፖሊስ ኃላፊዎቹን ጠመንጃ ሰርቀው ሊያመልጡ ሲል እንደተኮሱባቸውም ፖሊስ ለቢቢሲ ገልጿል። ምንም እንኳን ፖሊስ ይህን ይበል እንጂ አምነስቲን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሆን ተብሎ የተፈፀመ ግድያ ሊሆን ስለሚችል ምርመራ ሊደረግበት እንደሚገባ የህንድን መንግሥትን እየጠየቁ ነው። "መደፈርን ለመከላከል መፍትሄው ግድያ አይደለም" በማለት በህንድ የአምነስቲ ስራ አስፈፃሚ አቪናሽ ኩማር ተናግረዋል። የሃያ ሰባት አመቷ ዶክተር አስከሬኗ ተጥሎ የገኘው ከሰሞኑ ነው፤ ይህም ሁኔታ በሃገሪቷ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱ የሚታወስ ነው። የተጠርጣሪዎቹ መገደል ከተሰማ በኋላ የሟች እናት ለቢቢሲ "በእውነቱ ፍትህን አግኝተናል" ያሉ ሲሆን፤ ጎረቤቶቻቸውም የተጠርጣሪዎችን መገደል ሲሰሙ በመንገድ ላይ ርችት በመተኮስ እንዲሁም ለፖሊስ ምስጋናቸውን በማሰማት ደስታቸውን ገልፀዋል። •የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት •"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" ተጠርጣሪዎቹ አስከሬኗ ወደተገኘበትና ወንጀሉ ወደተፈፀመበት ቦታ ሲወሰዱ በአስር ፖሊሶች ታጅበው የነበረ ሲሆን፤ በካቴናም አልታሰሩም ነበር ተብሏል። ተደፍራ የተገደለችበት አካባቢም ማይክሮሶፍትና ጉግልን ጨምሮ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ቢሯቸው የሚገኝበት ስፍራ ነው። የፖሊስ ኮሚሽነሩ እንደገለፁት በወቅቱም ጠፋ የተባለውን የሟቿን ስልክ እየፈለጉ በነበረበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ በድንጋይና በዱላ ፖሊሶች ላይ ጥቃት ሲጀምሩ፤ በአፀፋው ሁለቱ ፖሊሶች እንደተኮሱባቸው ነው። "ምንም እንኳን ፖሊሶቹ እጅ እንዲሰጡና ከጥቃቱ እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ ቢያሳስቧቸውም፤ ለአስራ አምስት ደቂቃ ያህልም ፖሊሶቹን በማዋከባቸው ተኩሰው ገድለዋቸዋል" ብለዋል። ሁለት ፖሊሶችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ሆስፒታል እየታከሙ እንደሆነ ኮሚሽነሩ አክለው ገልፀዋል። "እውነት ለመናገር፤ ሕግ የማስከበር ስራ ተሰርቷል" ብለዋል። የሟቿ ቤተሰቦች ልጃቸው ጠፍታ በነበረበት ወቅት ፖሊስ ፈጣን ምላሽ አልሰጠንም በማለት ተችቷቸው እንደነበር የሚታወስ ነው።
news-56648232
https://www.bbc.com/amharic/news-56648232
ኮሮናቫይረስ፡ በሩዋንዳ የኮቪድ-19 መመሪያን የጣሱ ሙሽሮች ውጭ እንዲያድሩ ተደረጉ
በሩዋንዳ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የወጡ መመሪያዎችን ጥሰዋል የተባሉ ሙሽሮችና ቤተሰቦቻቸው ውጭ እንዲያድሩ መገደዳቸው ተገልጿል።
መመሪያውን ጥሰው ሰርግ አድርገዋል የተባሉ ሙሽሮች በሰርጋቸው ምሽት ውጭ እንዲያድሩ መደረጉ ከፍተኛ ትችትን አስነስቷል፤ በርካታ ሩዋንዳውያንን አስቆጥቷል። ይህንንም የሚያሳየው ቪዲዮ በርካቶች ተጋርተውታል። ስሜ አይገለፅ ያለችው ሙሽሪት ለቢቢሲ እንደተናገረችው ምሽቱን በስታዲየም ማሳለፏን በተመለከተ "የሰርጌን ምሽት በእንደዚህ ሁኔታ ውጭ ማሳለፌ መቼም ቢሆን በህይወቴ የማልረሳው መጥፎ ትዝታ ነው" ብላለች። አክላም "በዚህ መንገድ ሰዎችን ማዋረድና ማሳፈር ኮሮናቫይረስን እንድንፈራ ወይም መመሪያዎቹን እንድናከብር አያደርገንም" በማለት አስረድታለች። በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ የፈረንጆቹን የትንሳኤ ክብረ በዓል አስመልክቶ ሊደረጉ የነበሩ ሶስት ሰርጎችን ፖሊስ አስቁሜያለሁ ብሏል። ለዚህም መመሪያው ከሚያዘው 20 ታዳሚዎች በላይ መሆኑ ጋር ተያይዞ ነው ተብሏል። የፖሊስ ቃለ አቀባይ ለሩዋንዳ ሚዲያ እንደተናገሩት "በርካቶች መመሪያዎችን በመጣስ ዝግጅቶችን እያደረጉ ነው" ፖሊስም እንዲህ አይነት ጥሰቶችን በዝምታ አይመለከትም ብለዋል። ሙሽሮቹ የሰርጋቸውን ምሽት በስታዲየም ማሳለፋቸውን በርካቶች በበይነ መረብ ያወገዙት ሲሆን ህግ አስከባሪዎች ያልተገባ ስራ ሰርተዋል ብለዋል። ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሰዎችን ይዘው ምሽቱን በስታዲየም እንዲያሳልፉ አድርገዋል በማለት የተቹ እንዳሉ ሁሉ ለህዝቡ ደህንነት ነው በማለት ያሞካሹት አልታጡም። ክላሪስ ካራሲራ የተባለች የሩዋንዳ ሙዚቀኛ በበኩሏ "ሰብዓዊነትን ያጣ እንዲሁም ለተጣማሪዎቹም ሆነ ለወደፊት ልጆቻቸው ከፍተኛ ህመምን" የሚፈጥር ነው በማለት በትዊተር ገጿ አስፍራለች። ሩዋንዳ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ያወጣቻቸው መመሪያዎች በአለም አቀፍ ደረጃ የተወደሰ ቢሆንም ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ተቃዋሚዎች በበኩላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው በማለት ይከራከራሉ። አገሪቷ ወረርሽኙ ከተከሰተባት ዕለት ጀምሮ 22 ሺህ የኮሮናቫይረስ ህመምተኞችን የመዘገበች ሲሆን እስካሁንም 311 ዜጎቿን አጥታለች።