id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-47703114
https://www.bbc.com/amharic/news-47703114
አፕል ቲቪ፡ አዲሱ የበይነ መረብ ሥርጭቱን ይፋ አደረገ
ዝነኛ ሰዎች በተካፈሉበት ካሊፎረኒያ ውስጥ በተደረገ ደማቅ ዝግጅት አፕል 'አፕል ቲቪ' የተሰኘውን አዲስ የቴሌቪዥን ስርጭት መጀመሩን ይፋ አደረገ።
ጄኒፈር አኒስተን፣ ስቲቨን ስፒልበርግና ኦፕራ ዊንፍሪ በአፕል ዋና መሥሪያ ቤት አዲሱን ቴሌቭዥን ለማስመረቅ መድረኩን ካደመቁት ታዋቂ ሰዎች መካከል የተሰወሰኑት ነበሩ። • አዲስ አበባ፡ የፈጠራ ማዕከል ለመሆን እየጣረች ያለች ከተማ ቴሌቪዥኑ ነባር የኤችቢኦ እና ሁሉ የቴሌቪዥን ይዘቶችን ይዞ እንደሚመጣም ለሕዝብ አሳውቃዋል። ከቴሌቪዥኑ በተጨማሪ አፕል የክሬዲት ካርድ፣ የጌም መድረክና የተለያዩ መተግበሪያዎችንም ጭምር ለሕዝብ አገልግሎት ይዘው እንደሚመጡ ተነግሯል። • የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃል ደህንነት አስተማማኝ አይደለም ተባለ ዝግጅቱ በካሊፎረኒያ ግዛት የተደረገ ሲሆን የአፕል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቲም ኩክ ከመጀመሪያው ጀምረው ጥሪው አዲስ ዕቃ ይፋ ለማድረግ ሳይሆን አዲስ አገልግሎት ለሕዝብ ለማሳወቅ እንደሆነ ተናግረዋል። 42 ዓመታትን ላስቆጠረው ድርጅት አዲስ አቅጣጫ መሆኑ አይካድም ተብሏል። ስቲቭ ካሬል፣ ሪስ ዊተርስፑን እና ጄኒፈር አኒስተን አፕል ቲቪ አፕል ቆይቶም ሆነ ዘግይቶ ኔትፍሊክስ እና አማዞን ወደ ተቆጣጠሩት የበይነ መረብ ስርጭት ይገባል ተብሎ ይጠበቅ ነበረ። የአፕል ቲቪ መተግበሪያ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ስቲቨን ስፒልበርግ ቀደም ብሎ ፍንጭ ሰጥቶ ነበር። • የጉግል አጠቃቀምዎን የሚቀይሩ ሰባት እውነታዎች ስፒልበርግ እራሱ ለእዲሱ የቴሌቪዥን መድረክ አንዳንድ ፕሮግራሞችን እንደሚሠራም ተናግሯል። በዝግጅቱ መድረክ ላይ እራሳቸውን ካሳዩት መካከል ሪስ ዊተርስፑን፣ ስቲቭ ካሬል፣ ጄሶን ሞሞዋ፣ አልፍሬ ዉዳርድ እና ኮሜዲያን ኩሜል ናንጂያኒ ደግሞም ከሴሰሚ ስትሪት ቢግ በርድ ነበሩ። • ሴቶችን ከመንቀሳቀስ የሚያግደው መተግበሪያ ሊመረመር ነው መተግበሪያው እንደ ሳመሰንግ፣ ኤልጂ፣ ቪዚዮ፣ አማዞን፣ ሮኩ እና ሶኒ የተሰኙት የተወዳዳሪ መገልገያዎች ላይ ግልጋሎት እንደሚሰጥ ይፋ ተደርጓል። ኦፕራ ዊንፍሪ በአፕል ቲቪ የመጽሐፍ ቡድኗን የማስተላለፍ አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥታለች ከመጀመሪያው በአፕል ቲቪ ይዘት ውስጥ እንደማይካተት ያሳወቀው ኔትፍሊክስ ያልተገኘበት ዝግጅት ላይ ወርሃዊው ክፍያ አልተነገረም ነበር። "የአፕል ፈተና አዲሱን አገልግሎት ከተወዳዳሪ አቅራቢዎች ለየት ባለ እና በአዲስ መልኩ ለተገልጋዮች እንደ የኔትፍሊክስ 'ስትሬንጀር ቲንግስ' ማቅረብ እንደሚችል ነው" በኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የፊልም ፕሮዳክሽንና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ኤድ ብራማን ተናግረዋል። የአፕል ካርድ (የብድር አገልግሎት) ካርዱ እራሱ ከቲታንየም የተሠራ ሲሆን ለፊርማ እና ለቁጥር ቦታ አልተተወለትም በተጨማሪም በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት የአፕል ክሬዲት ካርድ በአሜሪካ ለሕዝብ አገልግሎት ይቀርባል። በአይፎን ስልክ ሊገለገሉበት የሚችሉትና እራሱን የቻለ ክሬዲት ካርድ የሚያዘጋጅ ሲሆን እያንዳንዱ ግዢ ላይ በጥሬ ገንዘብ መልስ መቀበል እንዲችሉ ይደረጋል። • ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም የሌለብዎት ሰአት መቼ ነው? "የክሬዲት ካርዱ ክፍያ በሚደረግበት ጊዜ ቀኑ ቢያልፍ የማርፈድ ቅጣት ክፍያ ወይም ዓመታዊ እና ዓለም አቀፍ ክፍያዎች አይኖሩትምም" ይላሉ የአፕል ቲቪ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኒፈር ቤይሊ። ጎልድመን ሳክስና እና ማስተር ካርድ በእንድ ላይ በመሆን ካርዱን እንደሠሩትም ታውቋል። የዜና አገልግሎት አፕል ኒውስ የሚል ሌላ አገልግሎትም ለሕዝብ እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል። አፕል ኒውስ እነ ማሪ ክሌር፣ ቮግ፣ ኒው ዮርከር፣ ኤስክዋየር፣ ናሽናል ጄዮግራፊክና ሮሊንግ ስቶንን የመሳሰሉ ከ300 በላይ መጽሔቶችን እንደሚይዝ ተነግሯል። ኤል ኤ ታይመስ እና ዎል ስትሪት ጁርናልም እንደሚካተቱ አሳውቀዋል። • እነ ፌስቡክ ግላዊ መረጃዎትን ያለአግባብ እንደሚጠቀሙበት ያውቃሉ? አክለውም አንባቢያን የሚያነቡትን እራሱ አፕል እንደማይከታተልና ለማስተዋወቂያ ድርጅቶች አሳልፎ እንደማይሰጥ ይፋ አድርጓል። አፕል ኒውስ በወር 9.99 ዶላር (በዛሬው ምንዛሬ 285 ብር ገደማ) የሚያወጣ ሲሆን ለአሜሪካና ለካናዳ ተገልጋዮች ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ክፍት እንደሆነ አሳውቀዋል። ይህ የፈረንጆቹ ዓመት ሳያልቅ ደግሞ ወደ አውሮፓም እንደሚሸጋገር ተናግረዋል። ከአፕል ቲቪ ለየት የሚያደርገው ይህ አገልግሎት በአፕል መገልገያ መሣሪያዎች ላይ ብቻ መኖሩ ነው። ጨዋታዎች (ጌሚንግ) አፕል አርኬድ ሌላ ቦታ የማይገኙ ከ100 በላይ ጨዋታዎችን (ጌሞችን) ያቀርባል ከመተግበሪያ ገበያው አፕል አርኬድ ከ100 በላይ ጨዋታዎችን ለሕዝብ ግልጋሎት የሚያቀርቡ ሲሆን እነዚህም ጨዋታዎች ያለ በይነ መረብ መጫወት እንደሚቻልም ተናግረዋል። አገልግሎቱ ለ150 ሃገራት በቅርብ የሚደርሱ ሲሆን የመመዝገቢያው ዋጋ ግን ይፋ አልተደረገም። • ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ የሚመጡ የሙያ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው? እ.አ.አ. በ2018 አይኤችኤስ ማርኬት የተሰኘው ድርጅት አይኦኤስ ማለትም የአፕል የአሠራር ሂደት በጨዋታ ገበያ የ33.5 ቢሊየን ዶላር ገበያ መሆኑን ተናግሯል። እንደ አፕል አርኬድ ያሉ የጨዋታ መድረኮች በውስጣዊ መተግበሪያ የሚገዙ ወይም ማስተዋወቂያ እንዲይዙ ባለማድረጋቸው ገና ትርፋማ ለመሆን ብዙ ዕድሎችን ሊፈጥር ይችላል በማለት የጨዋታ (ጌም) ተመራማሪና የአይኤችኤስ ዳይሬክተር ፒርስ ሃርዲንፍ ሮልስ ይናገራሉ። • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? አክሎም "ጨዋታዎቹን ለየት ባለ መልኩ በተጠና ወርሃዊ ክፍያና ለአፕል አርኬድ ብቻ የታሰቡ ጨዋታዎችን ለሕዝብ የማቅረቡ ውሳኔ ለጨዋታው ገበያ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው" በለዋል። አክለውም "አፕል እንደ ማይክሮሶፍት፣ ፌስቡክ፣ ጉግልና አማዞን ያሉ ድርጅቶች ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ የጨዋታውን ገበያ ሊቀላቀል ነው" ይላሉ።
news-48704462
https://www.bbc.com/amharic/news-48704462
ኢራን የአሜሪካ የቅኝት ድሮንን መትታ ጣለች
የአሜሪካ ወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በአወዛጋቢው የሆርሙዝ ሰርጥ ላይ በሚገኝ ዓለም አቀፍ የአየር ክልል ውስጥ ከምድር ወደ አየር በተተኮሰ የኢራን ሚሳዔል ተመትቶ መውደቁን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናገሩ።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ግን ድሮኗን መትቶ የጣለው ሆርሞዝጋን በተባለው የሃገሪቱ ደቡባዊ ግዛት ውስጥ በሚገኝ የአየር ክልል ውስጥ መሆኑን ገልጿል። • አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ወታደር ልትልክ ነው • ትራምፕ በነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ለተፈፀሙት ጥቃቶች ኢራንን ከሰሱ የአብዮታዊው ዘብ አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄነራል ሆሲን ሳላሚ ለሃገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ክስተቱ "ለአሜሪካ ግልጽ መልዕክት" አስተላልፏል ብለዋል። ይፋዊው የኢራን ዜና ወኪል ኢርና እንደዘገበው እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ የአሜሪካንን የቅኝት ድሮን መትቶ የጣለው ትናንት ጠዋት ላይ የኢራንን አየር ክልል ጥሶ ከገባ በኋላ ነው ብሏል። አብዮታዊ ዘብ ጨምሮም ተመትቶ የወደቀው የአሜሪካ ድሮን አርኪው-4 ግሎባል ሃውክ የተባለ እንደሆነ የገለጸ ሲሆን አንድ የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣን ግን ድሮኑ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ኤምኪው-4ሲ ትሪተን የተባለ እንደሆነ ለሮይተርስ ገልጿል። ይህ ሁኔታ የተከሰተው በኢራንና በአሜሪካ መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ ባለበት ጊዜ ነው። ሰኞ እለት የአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት የኢራን ኃይሎች በባሕረ ሰላጤው አካባቢ እያሳዩ ላለው "የጠብ አጫሪነት ባህሪ" ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 1ሺህ ወታደሮችን እያሰማራ መሆኑን ገልጾ ነበር። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት በኦማን ባሕረ ሰላጤ ውስጥ በሚገኘው የሆርሙዝ ሰርጥ ላይ በፈንጂ ለተመቱት ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ኢራንን ተጠያቂ በማደረግ ብትከስም ኢራን ውድቅ አድርጋዋለች። የዓለም የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት የሆነው አሜሪካና ኢራን የተፋጠጡበት የሆርሙዝ ሰርጥ
news-48509998
https://www.bbc.com/amharic/news-48509998
በርካታ የኬንያ መንግሥት ድረ ገጾች ጥቃት ደረሰባቸው
የኬንያ መንግሥት የመረጃ መረብ ደኅንነት ባለሙያዎች በበርካታ የሃገሪቱ መንግሥት ተቋማት ድረ ገጾች ላይ ሰኞ እለት የተፈጸመውን ጥቃት ለመቆጣጠር ጥረት እያደርጉ ነው።
በዚህም የተወሰኑት ድረ ገጾች ወደ መደበኛ ሥራቸው የተመለሱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ችግር እንደገጠማቸው ምልክት እየሰጡ ነው። በመረጃ መረብ ሰርሳሪዎች 18 የሚደርሱ በኬንያ መንግሥት የሚተዳደሩ ድረ ገጾች ኢላማ ሆነው መጠለፋቸውና ገጽታቸው እንዲለወጥ መደረጉ ተነግሯል። • ፌስቡክ የአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው? የተጠለፉት ድረ ገጾች ሲከፈቱ ኩርድ ኤሌክትሮኒክ ግሩፕ የተባለው የጥቃት ፈጻሚዎቹ አርማ በትልቁ የሚታይ ሲሆን የድረ ገጹ ጽሁፎችም በፍጹም አይነበቡም። ጥቃት ከተፈጸመባቸው ድረ ገጾች መካከል የመንግሥት ክፍያዎችን የሚያከናውነው እና የኬንያ መንግሥት ገቢዎች ባለስልጣን ይገኙበታል። የመንግሥት ቃል አቀባይ የሆኑት ሳይረስ ኦጉና ጥቃቱን ተከትሎ እንደተናገሩት የሃገሪቱ የመረጃ መረብ ሥርዓት ደኅንነቱ እንደተጠበቀ መሆኑን ተናግረው፤ የማንኛውም ግለሰብ መረጃም ለጥቃት እንዳልተጋለጠ አረጋግጠዋል። • ጉግል ስለእርስዎ የያዘውን መረጃ መሰረዝ እንደሚችሉ ያውቃሉ? ጥቃቱ ከተፈጸመ ከ24 ሠዓታት በኋላ አንዳንዶቹ ድረ ገጾች ወደ መደበኛ ሥራቸው የተመለሱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በመንግሥት የመረጃ መረብ ደኅንነት ባለሙያዎች ቡድን አስፈላጊው የደኅንነት ሥራ እየተሰራላቸው መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍን እያሳዩ ነው። ጥቃቱን እንደፈጸመ የተነገረለት የመረጃ መረብ ሰርሳሪ ቡድን 'ኩርድ ኤሌክትሮኒክ ግሩፕ' ድረ ገጽ ላይ እንደሰፈረው የቡድኑ ተግባር ጥቃት የሚፈጸምባቸውን ድረ ገጾች በመጥለፍ በቀዳሚ ገጾቻቸው የሚታዩ መረጃዎችን ማበላሸትና በሌላ መቀየር ነው። ይህንን ጥቃት በተመለከተ ቡድኑ ምን ዓላማ ይዞ እንደፈጸመው ግልጽ የሆነ ነገር የለም። ይህ በኬንያ መንግሥት ተቋማት ላይ የተፈጸመው የመረጃ መረብ ጥቃት የኬንያ መንግሥት ከዜጎቹ አስፈላጊ መረጃዎች በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ የማሰባሰብ ሥራ እያከናወነ ባለበት ወቅት ነው። • ፌስቡክ የአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው? ይህንን ተከትሎም በኬንያዊያን ዘንድ ግላዊ መረጃቸው ምን ያህል በመንግሥት ደኅንነቱ ተጠብቆ ይቆያል የሚለው ስጋት ተፈጥሮባቸዋል። ሴሪያኑ የተባለው በኬንያ የሚገኝ የመረጃ መረብ ደኅንነት በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው ባለፈው ዓመት የመጨረሻ አራት ወራት ውስጥ ብቻ ከ10 ሚሊዮን የሚበልጡ የመረጃ መረብ ስጋቶች በኬንያ ውስጥ ተለይተዋል። ሪፖርቱ አክሎም ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ የመረጃ መረብ ስጋቶች ኬንያን 286 ሚሊዮን ዶላርን አስወጥቷታል።
news-44000233
https://www.bbc.com/amharic/news-44000233
"400 ሚሊዮን ዶላር ካሳ" ለወርቅ ቆፋሪዎች
የደቡብ አፍሪካ ብልጽግና በወርቅ ማዕድን የተለበጠ ነው። የሚያብረቀርቀው ወርቅ የጥቁር አፍሪካዊያን ጨለማ ሕይወት ሳይጋርደው አልቀረም።
ወርቅ ቆፋሪ የጉልበት ሠራተኞች ለምዕተ ዓመት ያህል ለከፋ የጤና ችግር ሲጋለጡ፣ በማይድኑ በሽታዎች ሲያጣጥሩ የወርቅ ኩባንያዎቹ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ቆይተዋል። ሰሞኑን ግን ያልተጠበቀ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰምቷል። ኩባንያዎቹ ካሳ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ዉሳኔ። በደቡብ አፍሪካ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወርቅ ቆፋሪ የጉልበት ሠራተኞች እጅግ አደገኛ ለሆነ የሳንባ በሽታ ይጋለጣሉ። ይህ 'ሲሊኮሲስ' የተባለው የሳንባ ነቀርሳ ከማይድኑ በሽታዎች ይመደባል። በሽታው ከወርቅ ዐለቶች የሚወጣን ብናኝ በትንፋሽ በመሳብ የሚመጣ ነው። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ታዲያ ለነዚህ ታማሚዎችና የሟች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈል የሚያስገድድ ነው። ይህ ውሳኔ አራት ዐስርታት ከፈጀና እጅግ ከተራዘመ የፍርድ ቤት ሙግት በኋላ መሆኑ ትልቅ ትኩረትን ስቧል። ከዚህ ወዲህ ለሚከፈቱ ተመሳሳይ የፍርድ ቤት ክሶችም ጥሩ አብነት ሆኖ የተሳለጠ የፍርድ ሂደት እንዲኖር ምክንያት ይሆናልም ተብሏል። ግዙፎቹ ኩባንያዎች ለታማሚ ወርቅ ቆፋሪዎች በካሳ መልክ ለመክፈል የተስማሙት አምስት ቢሊዮን የደቡብ አፍሪካ ራንድ ነው። ይህ በዶላር ሲሰላ አራት መቶ ሚሊዮን ይደርሳል። የካሳ ተከፋዮቹ በዐስር ሺዎች የሚቆጠሩ የጉልበት ሠራተኞች ናቸው። ይህ ረዥም ዓመታትን የወሰደው የፍርድ ውሳኔ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በደቡብ አፍሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መጽደቅ ይጠበቅበታል። እጅግ ለከፋ የጤና ቀውስ የተጋለጡ የጉልበት ሠራተኞቻቸውን ለመካስ ከተስማሙት የወርቅ አምራች ኩባንያዎች ውስጥ ሀርመኒ ጎልድ፣ ጎልድ ፊልድስ፣ አፍሪካን ሬይንቦው ሚነራልስ፣ ሲባኒ ስቲል ዎተር፣ አንግሎ ጎልድ አሻንቲ እና አንግሎ አሜሪካን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
news-44525928
https://www.bbc.com/amharic/news-44525928
"ሽብር ምንድን ነው ፣ አሸባሪ ማን ነው?" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተውላቸው ነበር።
ከእነዚህ መካከል የአገሪቱን የሽብር ህግ የሚፃረሩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ስለመሆኑ የተነሳው ጥያቄ አንዱ ነበር። ይህን ጥያቄ ሲመልሱ ሽብር ምንድን ነው ፣አሸባሪስ ማን ነው? የሚል ጥያቄ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገሩን ሰፋ አድርጎ መመልከት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። "ሽብር ሲባል ስልጣን ላይ ለመቆየት፣ ስልጣን ለመያዝም አላግባብ ሃይል መጠቀምንም ይጨምራል" ብለዋል። ህገ-መንግስቱ የመከላከያና ደህንነት ተቋማት ከፓርቲ ገለልተኛ እንዲሆኑ ቢያስገድድም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ሌላ መሆኑን ተናግረዋል።ይህ ማለት ደግሞ መንግስት ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ተቋማትን ፈጥሯል ማለት እንደሆነ አመላክተዋል። "ህገመንግስቱ በፍርድ ቤት የታሰረ ሰውን ጨለማ ቤት አስቀምጡ፣ ግረፉ ይላል እንዴ?አይልም። መግረፍ ጨለማ ቤት ማስቀመጥና አካል ማጉደል የኛ የአሸባሪነት ተግባር ነው" በማለት ጣታቸውን መንግስት ላይ ቀስረዋል። "በሌብነት፣ በመግደልና በመግረፍ የኢትዮጵያ ህዝብ እኛን እስር ቤት ለማስገባት ምክንያት ነበረው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝቡ በይቅርታ ለመንግስት ሁለተኛ እድል ሰጥቷልም ብለዋል። የመንግስት የአልጀርሱን ስምምነት ተግባራዊ የማድረግ እንዲሁም የልማት ድርጅቶችን የተወሰነ ድርሻ ወደ ግል ይዞታ የማዘዋወር ውሳኔዎች የማብራሪያው ዋነኛ ትኩረት ነበሩ። በሌላ በኩል በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ ግጭቶችና የባለስልጣናት ሙስናም የንግግራቸው አብየት ጉዳዮች ነበሩ። አገሪቱ የገጠማትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመፍታት ዋነኛው መፍትሄ ኤክስፖርትን ማበረታታት ቢሆንም ሌሎች የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችም የሚደረጉ ሲሆን ፕራይቬታይዜሽን አንዱ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህ መሰረት በግል እንዲያዙ የተወሰኑት ኩባንያዎች የገበያ ውድድር ሳይኖርባቸው እንኳ ማደግ ያልቻሉ መሆናቸው ከግንዛቤ ሊገባ እንደሚገባ አስረድተዋል። የአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊነትን በተመለከተ የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ያፀደቀው ምክር ቤቱ የራሱን የወቅቱ ቃለ ጉባኤ ተመልሶ ይፈትሽ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። "የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ የፌደራል ካቢኔ አፅድቆት በወቅቱ የነበሩት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለተከበረው ምክር ቤት ሪፖርት አቅርበው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል ይህ ምክር ቤት። ተመልሶ ቃለ ጉባኤ መፈተሽ ይችላል።የፌደራል ካቢኔ ተነጋግሮና አፅድቆ ለአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን መቀበሉን በደብዳቤ አሳውቋል።እኔ ቢሮ አለ ቃለ ጉባኤው።አዲስ ውሳኔ አዲስ ሃሳብ የለም የሚለውን ይህ ፓርላማ ከማንም በላይ መገንዘብና ማስገንዘብ ይኖርበታል"ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ምክንያት ጥላቻ እንደሆነና በግጭቶቹ እጃቸው ያለ ባለስልጣናትም ሆኑ ከስልጣን ውጭ የሆኑ እጃቸውን እንዲሰበስቡ አስጠንቅቀዋል። በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሙስና ጋር በተያያዘ የመንግስት ባለስልጣናትን ዳግም አስጠንቅቀዋል።
45974840
https://www.bbc.com/amharic/45974840
በአስገዳይነት የሚጠረጠሩት የሳዑዲው ልዑል፣ የኻሾግጂን ገዳዮች ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ዛቱ
ሳዑዲ አረቢያን ሰቅዞ የያዘው የጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ጉዳይ በሦስተኛ ሳምንቱም ዓለምን ማነጋገሩ አላበቃም።
አባቱን አስገድለዋል የሚባሉት ልዑሉ የሟችን ልጅ፥ ሳላህ ቢን ኻሾግጂን አስጠርተው ሲያጽናኑት የሚያሳየው ምስል ቁጣን ቀስቅሷል ከሕዝብ ዕይታ ጠፍተው የከረሙት የሳኡዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን "የበረሃው ዳቮስ" በሚሰኘው የሪያድ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ብቅ ብለው ንግግር አድርገዋል። "እኔን አያድርገኝ፤ ጥፋተኞችን ካልቀጣሁ" ሲሉም ዝተዋል። • “የኻሾግጂን ሬሳ ለማን እንደሰጣችሁት ንገሩን” • የሳዑዲው ጋዜጠኛ ለመገደሉ ቱርክ አሳማኝ ማስረጃ እንድታቀርብ አሜሪካ ጠየቀች • በመጨረሻም ጀማል ኻሾጂ መገደሉን ሳዑዲ አመነች "ይህ ወንጀል ሳኡዳዊያን አንገት ያስደፋ ነው" ያሉት ልዑሉ በጋዜጠኛው ግድያ እጃቸውን ያስገቡ ሁሉ የስራቸውን ያገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል። በዚህ የተነሳ ግን ከቱርክ ጋር ያላቸው ግንኙነት ሊሻክር እንደማይገባም አስገንዝበዋል። ጋዜጠኛው እንዲገደል ትዕዛዝ ሰጥተዋል የሚባሉት ልዑል ባለፉት ቀናት የሟቹን ልጅ ሳላሕ ቢን ኻሹግጂን ወደ እልፍኛቸው አስጠርተው አጽናንተውታል። ይህንኑ የሚያሳየው ምሥል ከቀረበ ወዲህ ብዙዎች ቁጣቸውን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሲገልጹ ነበር። ሳዑድ አረቢያ በጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ጉዳይ ዙርያ እርስ በርሱ የሚጣረስ መረጃን ለዓለም ስታቀብል ሰንብታለች። ልዑሉ ሳያውቁት ይህ ወንጀል ሊፈጸም ይችላል? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው በመጀመርያዎቹ ቀናት ጋዜጠኛው ጀማል ቆንጽላችን ከገባ በኋላ በጓሮ በር ሾልኮ ወጥቷል ስትል የነበረችው ሳዑዲ አፍታም ሳትቆይ ጋዜጠኛው በኤምባሲዋ ውስጥ መገደሉን አምናለች። ኾኖም ከደህንነት ሰዎች ጋር አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ ገብቶ ቡጢ አርፎበት ነው የሞተው ብላ ነበር። ጣኢብ ራሲብ ኤርዶዋን ከትናንት በስቲያ ሸንጎ ቀርበው ባደረጉት ንግግር ሳኡዲዎችን "የሻኾግጂን ሬሳ የት አደረሳችሁት?" ሲሉ ጠይቀዋቸዋል። አንካራ ቀስ በቀስ ለመገናኛ ብዙኃን ያሾለከቻቸው መረጃዎች የሳኡዲ ንጉሣዊ ቤተሰብ በወንጀሉ ስለመሳተፉ የሚጠቁሙ ኾነዋል። የአሜሪካ የስለላ መሥሪያ ቤት ኃላፊም ዘለግ ላለ ሰዓት በቱርክ ቆይታ እንዳደረጉና ምናልባትም ቱርክ ጋዜጠኛው በአሰቃቂ ሁኔታ ስለመገደሉ ያስረዳሉ ያለቻቸውን የድምጽ መረጃዎች እንዲያዳምጡ እንዳደረገቻቸው ይገመታል። ግድያውን ተከትሎ የሪያዱ የኢንቨስትምነት ጉባኤ ስመ ጥር የሆኑ ባለሐብቶችና ርዕሰ ብሔሮች ላለመገኘት ወስነዋል። የኢፌድሪው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጉባኤውን ለመታደም ከቀናት በፊት ወደ ሪያድ ማምራታቸው ይታወሳል።
news-48250908
https://www.bbc.com/amharic/news-48250908
ማይናማር፡ አብራሪው አውሮፕላኑን ያለ ፊት ጎማው አሳርፎታል
በማይናማር የፊት ጎማዎች የመዘርጋት ችግር ያጋጠመውን አውሮፕላን ያለ ፊት ጎማው በሠላም እንዲያርፍ የያደረገው አብራሪ አድናቆት እየተቸረው ነው።
አብራሪው አውሮፕላኑን በሠላም በማሳረፉ አድናቆት ተችሮታል። ባለቤትነቱ የማይናማር ብሔራዊ አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላኑ በማንዳላይ አየር ማረፊያ ችግር ካጋጠመው በኋላ በማኮብኮቢያው መም ላይ በዝግታ ነበር ያረፈው። የዚህ ኢምብሬር 190 የተሰኘው አውሮፕላን አብራሪ፤ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ 89 ተሳፋሪዎች አንዳችም ጉዳት ሳያጋጥማቸው አውሮፕላኑን በሠላም በማሳረፉ አድናቆት ተችሮታል። ከያንጎን የተነሳው ይህ አውሮፕላን ወደ ማንዳላይ መቃረቢያ ሲደርስ ነበር የአውሮፕላኑ የፊት ጎማዎች አልዘረጋም ያሉት። በዚህ ጊዜ ታዲያ አብራሪው እያንዳንዱን የአደጋ ጊዜ ጥንቃቄዎችን የወሰደ ሲሆን የአውሮፕላኑን ክብደት ለመቀነስም ብዙ ነዳጅ እንዳቃጠለ አየር መንገዱ አስታውቋል። አብራሪው ምያት ሞ ኡንግ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎቹ የሚያርፍበትን ቦታ እስከሚወስኑለት ድረስም አየር ማረፊያውን ሁለት ጊዜ ዞሮታል ሲል አየር መንገዱ አክሏል። • ከአዲስ አበባ ናይሮቢ በመብረር ላይ የነበረው ET302 ተከሰከሰ • ቦይንግ የአደጋውን የምርመራ ውጤት ተቀበለ አውሮፕላኑ ሲያርፍ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል አውሮፕላኑ አፍንጫው መሬት እስከሚነካ ድረስ በኋላ ጎማው ነበር ያረፈው። አውሮፕላኑም እስከሚቆም ድረስ ለ25 ሰከንዶች በመሬት ላይ በቀስታ ተንሸራቷል። የማይናማር የትራንስፖርት ሚንስትር ዊነ ሃንት ለሮይተርስ የዜና ወኪል " አብራሪው በጣም ትልቅ ሥራ ነው የሠራው " ሲሉ አሞካሽተውታል። • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? በማይናማር በዚህ ሳምንት ብቻ እንዲህ ዓይነት ችግር ሲያጋጥም ለሁለተኛ ጊዜ ነው ተብሏል። ባለፈው ረቡዕ ቢማን የባንግላዲሽ አየር መንገድ አውሮፕላን ባጋጠመው መጥፎ የአየር ሁኔታ በያንጎነ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በሚሞክርበት ጊዜ ማኮብኮቢያ መሙን ስቶ ተንሸራቶ ነበር። በአደጋውም በትንሹ 17 ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።
news-56235748
https://www.bbc.com/amharic/news-56235748
ጃዋር መሐመድ፡ እነ አቶ ጃዋር ወደ ግል ሆስፒታል ተወሰዱ
አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አደነ ወደ መረጡት የግል ሆስፒታል ዛሬ ረፋዱ ላይ ተወሰዱ።
አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ከ30 ቀናት በላይ በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የተነገራለቸው ተከሳሾች፤ የተወሰዱት ላንድማርክ ተብሎ ወደሚጠራው ሆስፒታል መሆኑን ቢቢሲ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች እና የቤሰተብ አባላት መረዳት ችሏል። ተከሳሾቹ ታሰረው ይገኙበት ከነበረው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በአምቡላንስ ተጭነው በጸጥታ ኃይሎች ታጅበው ወደ ሆስፒታሉ ተወሰደዋል። የቤተሰብ አባላት እና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ እንደሚሉት፤ የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት ወደ ሆስፒታሉ እንዳይገቡ መከልከላቸውን እና ተከሳሾቹ ስለሚገኙበት የጤና ሁኔታ ማወቅ እንዳልተቻለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሾቹ ከግል ሃኪሞቻቸው ጋር እንደሚገኙ የቤተሰብ አባላቱ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በሆስፒታሉ ዙሪያም በርካታ የጸጥታ አካላት ተሰማርተው እንደሚገኙ ምንጮቹ ተናግረዋል። የተከሳሽ ጠበቆች እና የቤተሰብ አባላት እንደሚሉት ከሆነ፤ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ እና ሐምዛ አዳነ የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ ዛሬ 34ኛ ቀናቸው ላይ ይገኛሉ። ተከሳሾቹ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰው ወከባ ይቁም እንዲሁም የቤተሰብ አባላት ችሎት እና ማረሚያ ቤት ለጥየቃ ሲመጡ የሚደርስባቸው ወከባ ይቁም በማለት የረሃብ አድማውን እያደረጉ እንደሆነ ጠበቆቻቸው ይናገራሉ። በሆስፒታሉ ዙሪያ በርካታ የጸጥታ አካላት ተሰማርተው እንደሚገኙ ምንጮች ተናግረዋል። ተከሳሾች እንዴት ወደመረጡት ሆስፒታል ሊወሰዱ ቻሉ? በተከሳሽ ጠበቆች አቤቱታ የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሾች በመረጡት የጤና ተቋም እና ሆስፒታል ይታከሙ ሲል ፈቅዶ ነበር። ይሁን እንጂ ከአንድ ሳምንት በፊት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ይግባኝ ተከትሎ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የላንድማርክ ሆስፒታል ሃኪሞች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝተው ለተከሳሾች ሕክምና እንዲሰጥ በይኖ ነበር። ጠበቆች በበኩላቸው የሆስፒታሉ ሠራተኞች በቃሊቲ ማረሚያ የህክምና አገልግሎት ይስጡ መባሉ አግባብ አይደለም በሚል ተከራክረው ነበር። ጠበቆች ደንበኞቻቸው የ24 የህክምና ክትትል አልያም የሕክምና ማሽን ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው፤ አገልግሎቱን በማረሚያ ቤቱ ማግኘት አይችሉም በማለት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብለዋል። ሰበር ሰሚ ችሎቱም ትናንት በዋለው ችሎት ተከሳሾች በሆስፒታሉ ተገኝተው የሕክምና አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ በይኗል። ሰበር ሰሚ ችሎቱ ይህን ብይን ትናንት ከሰዓት የሰጠው፤ ትናንት ረፋድ ላይ ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የነበራቸው ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ከተሰጠበት በኋላ ነው። ትናንት ረፋድ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ሰዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ቀጠሮ ይዞ ነበር። ከእነዚህ መካከል እነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና በቀለ ገርባን ጨምሮ 21 ሰዎች በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር። ይኹን እንጂ ጠበቆች ደንበኞቻቸው እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ደጀኔ ጣፋ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ለፍርድ ቤት ተናግረው፤ ደንበኞቻቸው አሁን ባሉበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠት አይችሉም በማለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ዐቃቤ ሕግም ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥ እንደማይቃወም ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። በዚህም ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች አንደኛ ችሎት የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለመጋቢት 6/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በዚህ ችሎት ላይ የተገኘው የቢቢሲ ሪፖርተር፤ ተከሳሾች አካላቸው ደክሞ እና ከስተው ተመልክቷል። አንዳንድ ተከሳሾች በሰዎች ድጋፍ ወደ ችሎቱ ሲገቡ እና የተከሳሽ ቤተሰብ አባላት መካከል አንዳንዶቹ በችሎት ውስጥ ሲያለቅሱ ሪፖርተራችን ተመልክቷል። እነ አቶ ጃዋር መሐመድ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። እነ አቶ ጃዋር ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ መወሰኑ ይታወሳል።
54635974
https://www.bbc.com/amharic/54635974
የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በተከሰተው አለመረጋጋት ለወደሙ ኢንቨስትመንቶች መንግሥት የሚከፍለው ካሳ እንደሌለ ተገለፀ
የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተ አለመረጋጋት ለወደሙ ኢንቨስትመንቶች የሚከፍለው ካሳ አለመኖሩን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
የድምጻዊ ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች 89 የኢንቨስትመንት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል መውደማቸው ኮሚሽኑ ለቢቢሲ ገልጿል። ከወራት በፊት በክልሉ በተስተዋለው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ከተሞች መካከል ሻሸመኔ ፤ ዝዋይ የሚገኙበት ሲሆን የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ደርሷል። የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዋሲሁን ጎልጋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የአርቲስት ሃጫሉን ግድያን ተከትሎ በኢንቨስትመንት ድርጅቶች ላይ የደረሰው ጉዳት በገንዘብ ሲሰላ ከ3 ቢሊዮን በር በላይ እንደሚሆን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ጉዳቱ ከደረሰ በኋላ የተለያዩ ድርጅቶችን ለማገዝ የተለያዩ እርምጃዎች መውሰዱንም ገልፀዋል። "የደረሰው ጉዳት ከተለየ በኋላ ከፌደራል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመወያየት ከዚህ በፊት መኪና እና ማሽኖችን ከቀረጥ ነጻ ያስገቡ አሁንም በድጋሚ በነጻ እንዲያስገቡ፣ የባንክ ብድር ያለባቸው ደግሞ የእፎይታ ጊዜ እንዲሰጣቸው ተወስኗል" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው እነዚህ የኢንቨስትመንት ድርጅቶች ከዚህ በፊት የመሬት ጥያቄ አቅርበው ከነበረ በፍጥነት ምላሽ እንዲያገኙ መወሰኑን ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል። እነዚህ ድርጅቶች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ከማገዝ ውጪ ለደረሰው ጉዳት መንግሥት የሚከፍለው ምንም ዓይነት ካሳ እንደሌለ፣ እንዲሁም ለመክፈል ቃል የሚገባው ነገር አለመኖሩን አቶ ዋሲሁን ገልፀዋል። በአሁኑ ሰዓትም ጉዳት ከደረሰባቸው 89 ድርጅቶች መካከል ጥቂቶቹ ወደ ሥራ እየተመለሱ መሆኑን ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ጊዜያት በሚፈጠረው አለመረጋጋት የተነሳ፣ በኢንቨስትመንት ድርጅቶች ላይ በሚደርሰው ጉዳት ሥራ ላይ ያሉ ኢንቨስትመንቶች በሙሉ አቅማቸው እንዳይሰሩ ጫና እያሳደረባቸው እንደሆነም ገልፀዋል። " ኢንቨስትመንት የተረጋጋ ሰላም ይፈልጋል። የሰላም ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ኢንቨስተሮች በሙሉ አቅማቸው ለመስራት ስጋት ያድርባቸዋል። ይህም አንድ ጫና ነው፤ በቅርቡ የደረሰው አለመረጋጋትም እንደዚህ አይነት ጫና ፈጥሯል" ብለዋል። ሥራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙት ላይም ፍርሃት ቢታይም የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት መስህብ ጭማሬ እያሳየ መሆኑንና ያለው ፍላጎትም ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከ12 ሺህ በላይ የኢንቨስትመሰንት ድርጅቶች ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።
news-43409082
https://www.bbc.com/amharic/news-43409082
ሥራቸውን የጨረሱ መንኮራኩሮች መጨረሻቸው የት ነው?
የቻይናው ቲያንጎንግ - 1 የጠፈር ጣቢያ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሲሆን እንደ ቀድሞ መንኮራኩሮች ራቅ ያለ ስፍራ ሳይሆን በያዝነው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት ወደ ምድር ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ከምድር 2700 ኪሜ ርቆ በጥልቅ ውቅያኖስ ላይ በአውትራሊያ፣ ኒው ዚላንድ እና ደቡብ አሜሪካ መካከል የሚገኝ አንድ ሥፍራ አለ። ይህ ሰው በማይደርስበት የውቅያኖስ ጥግ የሚገኝ ሥፍራ ታዲያ የሳተላይት ባለሙያዎችም ትልቅ ትኩረት ስቧል። ምክንያቱም በምድር ዙሪያ የሚዞሩት ሳተላይቶች የሚያርፉት በዚያ ቦታ ነውና። ከጠፈር የሚመለሱ አነስተኛ መጠን ያላቸው ሳተላይቶች የሚቃጠሉ ሲሆን ትልልቆቹ ግን ስብርባሪያቸውም ቢሆን መሬት ሊደርስ ይችላል። ሰው በሚኖርባቸው አካባቢዎች ተከስክሰው ጉዳት እንዳያደርሱ በሚል ሰው የማይደርስበት የውቅያኖስ ክፍል ላይ እንዲወደቁ ይደረጋል። የይህ ቦታ ከጠፈር ለሚመለሱ ሳተላይቶቹ የቀብር ስፍራቸው ነው። እስካሁን ከ260 በላይ የሚሆኑ ሳተላይቶች ቀብራቸውን እዚህ ሥፍራ የፈፀሙ ሲሆን አብዛኛዎቹ ደግሞ የሩሲያ ንብረት ናቸው። በአውሮፓውያኑ 2001 በአካባቢው የተበታተነ አንድ 120 ቶን የሚመዝን ሳተላይትን ስብርባሪ አንዳንድ አሳ አስጋሪዎች ሰማይ ላይ እንዳዩት ተናግረው ነበር። በዓመት ውስጥ ብዙ ጊዜ ወደ ዓለም አቀፍ የጠፈር ምርምር ጣቢያ ዕቃዎችን የሚያጓጉዝ ሳተላይት የጣቢያውን ቆሻሻ ይዞ በዚህ ቦታ ይቃጥላል። ቁጥጥር ስለሚደረግበትም በዚህ ምክንያት ማንም ላይ ጉዳት አይደርስም። በአካባቢው ያለው ውሃ ለአሳ የሚሆን ምግብ ስለማይዝ የአሳ ማስገር ስራ አይከናወንም። ይህንን ማንም ያልደረሰበትን ቦታ ወደ ፊት በዓለም አቀፉ የስፔስ ጣቢያ የሚጎበኝ ነው። አሁን ያለው ዕቅድ በውቅያኖስ የማይደረስበት ሥፍራ ላይ ሳተላይቶችን በተጠና መልኩ ከስራ ውጭ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። አንዳንድ ጊዜ ከምድር ያሉ ተቆጣጣሪዎች ከሳተላይቶቹ ጋር ግንኙነታቸው ከተቋረጠ ሳተላይቱን ወይንም የጠፈር ጣቢያውን በደቡባዊ ፓስፊክ እንዲወድቅ ማድረግ አይቻልም። ይህ ነገር 36 ቶን በምትመዝነዋና በደቡብ አፍሪካ በአውሮፓውያኑ 1991 የተከሰከሰችው 'ሳልየት 7' እና በ1979 አውስትራሊያ የወደቀችው 'አሜሪካን ስካይ ላብ' ላይ አጋጥሟል። እስከሚታወቀው ድረስ ምድር ላይ ያለ ሰው በሳተላይት ስብርባሪ ስለመጎዳቱ ምንም መረጃ የለም። ከመስከረም 2018 ጀምሮ ባሉት አራት ወራት የቻይናዋ ቲያንጎንግ - 1 ወደ ምድር ትመለሳለች። ይህች የመጀመሪያዋ የቻይና ሳተላይት በ2011 ነነበር እንድትመነጠቅ የተደረገው። የቲያንጎንግ - 1 በድጋሚ ወደ ዑደቱ ከመግባቷ በፊት ከጥቅም ውጭ እየሆነች ነው። ሆኖም ከቻይና መሃንዲሶች ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ አቃጥለው በደቡባዊ ፓስፊክ እንዲከሰከስ ለማደረግ አልቻሉም። ሰሳተላይቷ ከመቃጠሉ ጥቂት ሰዓታቶች በፊት በእርግጠኝነት የምትወድቅበትን ቦታ መለየት ባይቻልም ቦታው ከሰሜናዊ ስፔን እስከደቡባዊ አውስትራሊያ ያለውን ቀጠና ያካልላል።
news-56401687
https://www.bbc.com/amharic/news-56401687
'በትግራይ የሕክምና ተቋማት ሆን ተብሎ ጥቃትና ዘረፋ ተፈጽሞባቸዋል'-ኤምኤስኤፍ
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) የተሰኘው በሕክምና ላይ የተሰማራው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በትግራይ ክልል በሚገኙ የሕክምና ተቋማት ላይ ሆን ተብሎ ዘረፋ እና ጥቃት ተፈጽሟል ሲል ገለፀ።
ድርጅቱ ዛሬ ሰኞ፣ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በተፈጸመው ዘረፋ የተነሳ በጣም ውሱን ሠራተኞች ብቻ የሥራ ገበታቸው ላይ እንደሚገኙ፣ እንዲሁም አንዳንድ ቦታም ምንም ዓይነት ባለሙያ አለመኖሩን አስታውቋል። ኤምኤስኤፍ ካለፈው ታኅሣስ ጀምሮ ከመቶ በላይ የሕክምና ተቋማትን መጎብኘቱን ገልፆ ሦስት አራተኛዎቹ ዘረፋ እንደተፈፀመባቸው ገልጿል። ድርጅቱ በዚሁ መግለጫው አንዳንዶቹ ዘረፋዎች የተፈፀሙት በወታደሮች ጭምር ነው ያለ ሲሆን 13 በመቶ የሚሆኑ የጤና ተቋማት ብቻ በአግባቡ እየሰሩ ነው ብሏል። የሠላም ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ሆስፒታሎች ውስጥ 75 በመቶዎቹ ሙሉ በሙሉ ሥራ መጀመራቸውን አስታወቋል። ሚኒስቴሩ በዚሁ መግለጫው ላይ 10 በመቶ የሚሆኑት በግማሽ አቅም አገልግሎት እየሰጡ ነው ብሏል። አገልግሎት በመስጠት ላይ በሚገኙ የጤና ተቋማት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ላይ ይገኛሉም ሲል አክሏል። በትግራይ ክልል ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ግጭት መቀስቃሱ ይታወሳል። ከሦስት ሳምንት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፌደራል መንግሥቱ ኃይሎች መቀለን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ "ሕግ የማስከበር ዘመቻው" መጠናቀቁን ቢገልፁም አሁንም በአንዳንድ ስፍራዎች ግጭቶች እንዳሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ይናገራሉ። በዚህ ግጭት የተነሳም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ጠባቂ ሲሆኑ፣ ከ60ሺህ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ወደ ሱዳን ተሰድደዋል። ኤምኤስኤፍ በመግለጫው በርካቶቹ የጤና ተቋማት በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች ተይዘው እንደሚገኙም ገልጿል። አክሎም ከአምስት የጤና ተቋማት አንዱ በወታደሮች ተይዞ ይገኛል ያለ ሲሆን ከኢትጵያ መንግሥት በኩል በዚህ ጉዳይ ላይ ተባለ ነገር የለም። ኤምኤስኤፍ በመግለጫው ላይ በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የጤና ተቋማት አምቡላንሶች እንዳላቸው አመልክቷል። የሠላም ሚኒስቴር በበኩሉ 54 አምቡላንሶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቅሶ በቀጣይ ጊዜያትም ተጨማሪ 52 አምቡላንሶች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብሏል። በኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊትና በህወሓት አማፂያን መካከል በተደረገው ወታደራዊ ግጭት የተነሳ በርካታ መሰረተ ልማቶች መውደማቸው የተነገረ ሲሆን መንግሥትም ጥገና በማድረግ ወደ ሥራ እየመለሳቸው መሆኑን እየገለፀ ይገኛል።
news-54240691
https://www.bbc.com/amharic/news-54240691
የደመራ በዓል አከባበር፡ የመስቀል ደመራ በዓል ሙሉ ኃይማኖታዊ እሴቱና ስርዓቱ ሳይጓደል ይከበራል- ቤተክርስቲያኒቱ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የ2013 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ሙሉ ሐይማኖታዊ እሴቱና ሥርዓቱ ሳይጓደል እንደሚከበር አስታወቀች።
የቤተክርስቲያኒቱ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዐብይ ኮሚቴ አባል የሆኑት መጋቤ ሰላም ሰለሞን ቶልቻ፤ በአዲስ አበባ በርካታ ምዕመናን ተገኝተው የሚያከብሩበት የመስቀል አደባባይ በግንባታ ላይ መሆኑ የበዓሉን ሐይማኖታዊ እሴቱና ሥርዓቱ እንደማያጓድለው ጠቅሰዋል። በዓሉን ለማክበር የሚታደሙ ምዕመናን ቁጥር በተወሰነ መልኩ መቀነሳቸውን የገለፁት መጋቤ ሰላም ሰለሞን፤ አካባቢው ግንባታ ላይ መሆኑ እና የግንባታ ቁሳቁስ በስፍራው ላይ መኖር እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለዚህ ምክንያት መሆናቸውን አንስተዋል። መስከረም 16 በመስቀል አደባባይ በመገኘት በዓሉን የሚታደሙና የሚያከብሩ ሰዎች ቁጥር ከ5000 እንደማይበልጥ የተናገሩት መጋቢ ሰላም ሰለሞን፤ የመግቢያ ባጆች ከ3000 እስከ 5000 እንደሚታተሙ ተናግረዋል። ቤተክርስትያኒቱ ከፀጥታ አካል ጋር በመተባበር በበዓሉ ላይ ለሚታደሙ የክብር እንግዶች እንዲሁም ምዕመናን፣ መዘምራንና ቀሳውስት ባጆችን እንደምታዘጋጅ አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌልና የሐዋሪያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት መጋቢ ሰላም ሰለሞን ለቢቢሲ አንደገለፁት፤ የ2013 የመስቀል በዓልን ለማክበር ያሉት ተግዳሮቶች ሦስት ናቸው። አንዱና ቀዳሚው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ነው ያሉ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት በዓሉን ምዕመናኑ በነቂስ ወጥተው አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው ማክበር እንደማይችሉ ተናግረዋል። ሁለተኛው የፀጥታ ጉዳይ ነው ያሉት ኃላፊው፤ የመንግስት የፀጥታ አካል በዓሉ ያለ ችግር እንዲከበር ከቤተክርስቲያኒቱ የበዓል አከባበር ኮሚቴ ጋር በጥምረት እንደሚሰራ ገልፀዋል። ሦስተኛው የመስቀል አደባባይ በግንባታ ሂደት ላይ መሆኑን በማስታወስ፤ የበዓሉ ታዳሚያን ቁጥር ይቀንሳል እንጂ ሐይማኖታዊ ሥርዓቱ ሳይጓደል ይከበራል ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በበዓሉ ላይ የሚቀርቡ ያሬዳዊ ዝማሬዎች፣ በሊቃውንቱ መካከል የተዘጋጁ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን መዝሙሮችና የሙሉ ትርዒቱ ዝግጅት መጠናቀቃቸውንና እንደሚቀርቡም አመልክተዋል። የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ቅዱስ ፓርቲያሪኩን ጨምሮ ይገኛሉ ያሉት መጋቢ ሰላም ሰለሞን፤ ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላላ ሊቃውንትና ካህናቱ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በሚመለከት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚሰጠው ምክር ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚናገሩት ኃላፊው፤ አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ በበዓሉ አከባበር ወቅት የሚተገበሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከዚህ በፊት የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች፣ ከምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤና ከፀጥታ አካል ጋር በመሆን በመስቀል አደባባይ ጉብኝት ማድረጋቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ በዚህም ምልከታ እንግዶች በየት በኩል እንደሚስተናገዱ፣ መዘምራን በየት በኩል ዝማሬ እንደሚያቀርቡ እንዲሁም ደመራ እንዴት እንደሚደመር ጥናት መደረጉን ገለፀዋል። በርካታ ቱሪስቶችና የውጭ አገራት ዜጎች ይታደሙበት የነበረው የመስቀል ደመራ በዓል በኮሮናቫይረስ ምክንያት የቱሪስቶች እንቅስቃሴ በዓለም ዙሪያ በመስተጓጎሉ በዚህ ዓመት እንደከዚህ ቀደሙ ብዙ ጎብኚዎች ላይገኑ ይችላሉ። የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ በርካታ ሕዝብ ታድሞባቸው ከሚከናወኑ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርትና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት እንደተመዘገበም ይታወቃል።
news-42048605
https://www.bbc.com/amharic/news-42048605
ያለአብራሪ በሚበረው የሰማይ ታክሲ ይጠቀማሉ?
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በሰውም ሆነ ያለሰው የሚበር የሰማይ ላይ ታክሲ ለገበያ ለማቅረብ እየተሯሯጡ ነው። ምን ያህል ይሳካላቸው ይሆን? እርስዎስ የሰማይ ላይ ታክሲዎቹን አምነው ይሳፈራሉ?
ዱባይ ደግሞ የሰማይ ላይ ታክሲዎቹን በመጠቀም ቀዳሚዋ ለመሆን እየሰራች ነው። ኡሃንግ 184 ሰማይ ላይ ችግር ከገጠመው ወዲያው መሬት ላይ ያርፋል ባለፈው ሰኔ የዱባይ መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ቮሎኮፕተር ከተሰኘው የጀርመን ኩባንያ ጋር ሰው አልባ የሰማይ ላይ ታክሲዎችን ለመሞከር ከስምምነት ደርሷል። ኩባንያው ሁለት ሰዎችን ማጓጓዝ የሚያስችል የሰማይ ላይ ታክሲ የመስራት ዕቅዱን እንዲያሳካ 25 ሚሊዮን ዩሮ ከባለሃብቶች አግኝቷል። እንደድርጅቱ ከሆነ ታክሲው በሰዓት 100 ኪሎሜትር ይጓዛል። በሰማይ ላይ ለ30 ደቂቃ መቆየት የሚችል ሲሆን ለዚህም የሚረዱት ዘጠኝ ባትሪዎች ተገጥመውለታል። "በአደጋ ወቅት የሚያስፈልገው ፓራሹት አስፈላጊ አይደለም" ሲል ቮሎኮፕተር ዋስትና ይሰጣል። የዱባይ መንገድና ትራንስፐፖርት ባለስልጣን ከቻይናው ኤሃንግ ኩባንያ ጋር በመሆንም አንድ ሰው ማጓጓዝ የሚያስችለውን ኤሃንግ 184 የተሰኘ ድሮን (ሰው አልባ አነስተኛ አወሮፕላን) በመሞከር ላይ ይገኛል። ሆኖም ዱባይ ያለሰው ከሚበሩት የሰማይ ላይ ታክሲዎችን ለመተግበር ከብዙ የዓለማችን ትልልቅ ከተሞች ጋር ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ ገብታለች። ኡበር የተሰኘው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋም የናሳውን ዋና የቴክኖሎጂ ባለሙያ ማርክ ሙርን ወደ ተቋሙ በመቀላቀል ፕሮጀክት ኢልቬት በተሸኘውና ወደፊት ለከተሞች በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የትራንስፖርት ጥያቄን በሚፈታው ስራ ላይ መድቦታል። የፈረንሳዩ አውሮፕላን አምራች ድርጅት ኤርባስ ከአውሮፕላኖቹ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቫሃና የተሰኘ የሰማይ ላይ ታክሲ በ2017 መጨረሻ ላይ የሚሞከር ሲሆን በ2020 ደግሞ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል። ተቋማቱ የመንገድ መዘጋጋት እየበዛ በመምጣቱ ፊታቸውን ወደ አየር ላይ እያዞሩ ነው። ለምሳሌ እንኳን በዓለማችን 10ኛዋ ሃብታም ከተማ ሳኦፖሎ በተለይ አርብ ዕለት መንገዶች ከ180 እስከ 295 ኪሎ ሜትር ድረስ ይዘጋጋሉ። ኤሃንግ አንድ ተጓዥ፤ ቮሎኮፕተር ሁለት ሲቲ ኤርባስ ደግሞ ከአራት እስከ ስድስት ሰው የሚጭኑ የሰማይ ላይ ታክሲዎችን ለመስራት እያቀዱ ነው። ኩባንያዎቹ ታክሲዎቹን በኤሌክትሪክ እንዲሰሩ በማድረግ አካባቢ ላይ ጉዳት የማያደርሱ ለማድረግ እየጣሩ ነው። ለመሆኑ እንዴት ይሰራሉ? በቀላሉስ ለመግዛት ይቻላል? ሶስት ወይም አራት ሰው የሚይዘው የሰማይ ላይ ታክሲ ዋጋ 'ኡበር ኤክስ' ከተሰኘው የመኪና ዋጋ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ሙር ይገልጻል። ያለውን ክብደትና ሃይል ከግምት በማስገባት እነዚህ ታክሲዎች ምን ያህል በአየር ላይ ይቆያሉ? ሞባይልዎ ባትሪው እንዳይጨርስ የሚፈልጉትን ያህል የሰማይ በላይ ታክሲ ቢኖርዎትም ባትሪው እንዳያልቅ ይፈልጋሉ። የቻይናው ኤሃንግ ድሮን ለ23 ደቂቃ መብረር ይችላል። ሆኖም የአሜሪካ አቪየሽን አስተዳደር ህግ አንድ አውሮፕላን ቢያንስ ለተጨማሪ 20 ደቂቃ የሚያቆውን ነዳጅ መያዝ አለበት። ይህ ማለት ደግሞ የኤሃንግ ድሮን መብረር የሚችለው ለሶስት ደቂቃ ብቻ ነው። ኡበር 50 የሚሆኑ የሰማይ ላይ ታክሲዎቹን ለማውጣት ባቀደበት በ2023 ባትሪው ላይ ማሻሻያ በማድረግ ችግሩ ይፈታል ይላል ሙር። የሳኦ ፖሎ ከተማ የትራፊክ መጨናነቅ ናሳ ያሻሻለው ቴክኖሎጂ ድሮኖች እርስ በእርስ የሚግባቡበትና ግጭት እንዳይኖር የሚረዳ ነው ተብሏል። ዘርፉን ይበልጥ ወደ ኋላ የሚጎትተው የህግ ጉዳይ ነው ተብሏል። በራሳቸው ተነስተው፥ በረው የሚያርፉ የንግድ አውሮፕላኖች ተግባራዊ ለመሆን ከጫፍ ቢደርሱም የአሜሪካ እና አውሮፓ የአቪየሺን ህጎች አውሮፕላኖች ያለአብራሪ እንዳይበሩ ያስገድዳሉ ሲሉ ፍራንኬል ዮኤል ይገልጻሉ። ስለዚህ እነዚህ ድሮኖች ህግ የአውጪዎችን እምነት ለማግኘት ረዥም ጊዜ የሚወስድባቸው ይመስላል። ይህ አውቶብስ ነው? ወይስ አውሮፕላን? ዘርፉን ዱባይ እየመራቸው ሲሆን እንደ አስተዳዳሪዋ ሼክ መሃመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም ገለጻ ከሆነ በ2020 ከህዝብ ትራንስፖርት ውስጥ 25 በመቶው በራሱ የሚንቀሳቀስ የትራንስፖርት ዓይነት ይሆናል። እንደአቪየሺን አማካሪው ማርክ ማርቲን ከሆነ ደግሞ "ንፋሳማው፥ አሸዋማውና ጉም ያለው የዱባይ አየር" ለድሮኖች አስቸጋሪ ነው። ዱባይ በዘርፉ ላይ በፍጥነት እየሰራች ቢሆንም ከአሜሪካና አውሮፓ ህግ አውጪዎች ጋር ተቀራርባ መስራት ይጠበቅባታል ይላል። "አንድ አደጋ ከደረሰ ከዛ በኋላ ማን አምኖ ድሮን ይጠቀማል?" ሲል ይጠይቃል።
news-51306280
https://www.bbc.com/amharic/news-51306280
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከስምምነት ሳይደረስ ቀረ
በኢትየጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ከምን ላይ እንደደረሰ ከተሳታፊዎቹ አልተሰማም።
የሶስቱ አገራት የውጪ ጉዳይ እና የውሃ ሚንስትሮች በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተው የመከሩ ሲሆን፤ ቀድሞ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ሦስቱ አገራት የደረሱትን ስምምነት ትናንት ይፋ እንደሚያደርጉ ተጠብቆ ነበር። ከሁለት ሳምንታት በፊት ሦስቱ አገራት እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ በሕዳሴው ግድብ ሙሊት እና ሌሎች መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት በሚያደርሱ ነጥቦች ላይ ተግባብተናል ብለው ነበር። በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ እንደሆነ በተነገረለት የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል ዙሪያ የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ በተከታታይ ዋሽንግተንን ጨምሮ በሦስቱ አገራት መዲናዎች ሲካሄድ ቆይቷል። የሦስቱ አገራት የውጪ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች ግድቡ ውሃ የሚሞላበትን እና ሥራ የሚያከናውነትን ሁኔታ ላይ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለፉት ሁለት ቀናት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴርና በዓለም ባንክ በታዛቢነት በተገኙበት የቀረበው ረቂቅ የስምምነት ሰነድ እንደሚያመለክተው በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ግድብ በዝናብ ወቅት በተለያዩ ደረጃዎች በውሃ እንዲሞላ የሚመክር ነው። ነገር ግን የውሃ ሙሌቱ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን አይጠቅስም፤ ይህም አገራቱ በሚያደርጉት ውይይት ዝርዝሩ ሂደት በመጨረሻው ስምምነት ላይ ይደርሳል ተብሎ ነበር። የግድቡ ውሃ አሞላል በተመለከተ ያለው ጉዳይ ለረጅም ጊዜ አጨቃቂ ሆኖ ቆይቷል። ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ለሚያስፈልጋት የኃይል አቅርቦት በጣም ወሳኝ እንደሆነና ለዚህም ግድቡ በተቻለ ፍጥነት የውሃ ሙሌቱ በቶሎ እንዲጀምር ፍላጎት አላት። ዘጠና በመቶ የሚሆነውን የውሃ ፍላጎቷን ከአባይ የምታገኘው ግብጽ ግን ግድቡ በፍጥነት የሚሞላ ከሆነ የምታገኘው የውሃ አቅርቦቷን ሊጎዳው እንደሚችል ስጋቷን እየገለጸች ነው። ከዓመታት በፊት ግንባታው ለተጀመረውና 4 ቢሊዮን ዶላር ወጪን ለሚጠይቀው በአባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው ግድብ፤ ኢትዮጵያ 85 በመቶ የሚደርሰውን ውሃ የምታበረክት ሲሆን፤ ግድቡ በስድስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በውሃ እንዲሞላ ፍላጎት አላት። ግብጽ ግን ከአባይ ወንዝ የምታገኘው የውሃ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይቀንስባት የውሃ ሙሌቱ ከ10 እስከ 20 ዓመታት በሚደርስ ጊዜ ውስጥ እንዲሞላ ትፈልጋለች።
news-55746584
https://www.bbc.com/amharic/news-55746584
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባት እንደማትፈልግ ገለጸች
የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ሌፍተናንት ጀነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን ሱዳን ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌላ ጎረቤት አገር ጋር ጦርነት ወስጥ መግባት እንደማትፈልግ ነገር ግን ስንዝር መሬት እንደማትሰጥ ገለጹ።
ሌፍተናንት ጀነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሱዳን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ሌፍተናንት ጀነራል አል ቡርሐን ይህንን የተናገሩት ከአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ሲሆን፤ ጨምረውም አገራቸው ሕጋዊ መብቷን በሚያስከብር መንገድ አሁን በሱዳን ሠራዊት የተያዙት ቦታዎች በይዞታዋ ውስጥ ከሚያደርግ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የሱዳን ሠራዊት የተሰማራበት አካባቢ የአገሪቱ ግዛት መሆኑን ያመለከቱት ጀነራሉ ጦር ሠራዊታቸው ይህንን እርምጃ የወሰደው በሱዳን መንግሥት ውስጥ ካለው ፖለቲካዊ አካል ጋር በተደረገ ሙሉ ቅንጅት መሆኑን አመልክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት መንግሥታቸው ከሱዳን ጋር ያጋጠመውን የድንበር ችግር በሰላም መፍታት እንጂ ወደ ጦርነት መግባት ፍላጎት እንደሌለው አመላክተዋል። ጨምረውም በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል በቅርቡ የተከሰተውን የድንበር ላይ ወታደራዊ ፍጥጫን በተመለከተ በቅርቡ በሁለቱ አገራት ወታደራዊ ተቋማት ደረጃ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ገልጸዋል። ጀነራል ብርሃኑ ሁለቱ አገራት ከዚህ ቀደም በድንበር አካባቢዎች የሚፈጠሩ ችግሮችን በሰላም ሲፈቱ መቆየታቸውን ገልጸው የአሁኑ ግን በክስተቱ ውስጥ "የሦስተኛ ወገን እጅ ስላለበት ችግሩ ጎላ ብሎ ወጥቷል" ሲሉ በስም ያልጠቀሱት ወገን በጉዳዩ ውስጥ አለ ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት በህወሓት ኃይሎች ላይ "የሕግ ማስከበር እርምጃ እየወሰደ ባለበት ወቅት የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበር ጥሶ ገብቷል" ያሉት ጀነራል ብርሃኑ ይህ ድርጊት ሁለቱ አገራት ካለቸው ወዳጅነት አንጻር "ከሱዳን የማይጠበቅ አሳዛኝ ተግባር ነው" በማለት ገልፀውታል። አክለውም የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበር ጥሶ ከመግባቱ ጀርባ የግድቡን ድርድርና ግንባታ ማስተጓጎልን ያለመ በስም ያልጠቀሱት ሶስተኛ አካል መኖሩን ለኢዜአ ተናግረዋል። "ሱዳን በሦስተኛ ወገን የተደገሰላትን የጦርነት ወጥመድ ወደ ጎን በመተው" የድንበሩን ጉዳይ በድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆን እንዳለባት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄነራል ብርሃኑ ጁላ አፅንኦት በመስጠት መልዕክታቸውን አስተልፈዋል። ኢትዮጵያና ሱዳን 750 ኪሊ ሜትሮች ያህል የጋራ ድንበር ሲኖራቸው፣ ለዓመታት በድንበር አካባቢ ግጭት ሲያጋጥም ነበር። በተለይ አል ፋሽቃ በሚባለው ለም የእርሻ መሬት ባለበት አካባቢ ግጭቶች በተለያዩ ጊዜያት መከሰታቸው ይነገራል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሱዳን ባለስልጣናት እንደከሰሱት በአካባቢው የኢትዮጵያ ኃይሎች ባካሄዱት ጥቃት አንዲት ሴትና ህጻንን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል። በድንበር አካካቢ ተከስቶ ሳምንታት ያስቆጠረው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሲሆን፣ በሠላማዊ ሰዎችና በወታደሮች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለመፈናቀል ተዳርገዋል። ውጥረቱን ለማርገብ በሁለቱ አገራት ጠቅላይ ሚኒስትርና በሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት አማካይነት ንግግር ቢደረግም እስካሁን ለቀውሱ መፍትሄ አላስገኘም። የኢትዮጵያና የሱዳን መንግሥታት ከድንበር ውዝግቡ ባሻገር ኢትዮጵያ ወደ ማጠናቀቁ እያደረሰችው ባለው ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ግብጽን ጨምሮ እያደረጉት የነበረው ድርድር በሱዳን ቅሬታ ምክንያት ወደፊት መራመድ ሳይችል መቋረጡ ተገልጿል።
news-46908582
https://www.bbc.com/amharic/news-46908582
የአፍሪካን የእግርኳስ ሙስና ቅሌት ያጋለጠው ጋናዊው ጋዜጠኛ አህመድ ሁሴን ተገደለ
የአፍሪካን የእግርኳስ የሙስና ቅሌት ያጋለጠው ጋናዊው የምርምር ጋዜጠኛ በጥይት ተገደለ።
ዘገባውን ተከትሎም አንድ ፖለቲከኛ ጋዜጠኛው ላደረሰው ጥፋት እንዲቀጣ ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ዛሬ ወደቤቱ እየነዳ በሚሄድበት ወቅት ተተኩሶበት ሞቷል። በሃገሪቱ ሚዲያ ዘገባ መሰረት ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በሞተርሳይክል ተከትለው አህመድ ሁሴን ሱዋሌን ሶስት ጊዜ ተኩሰው መትተውታል። ታይገር አይ (የነብር አይን) የሚባል የምርመራ ድርጅት አባል የነበረው ጋዜጠኛ የአፍሪካ የሙስና ቅሌት ያለበትን ሁኔታ አጋልጧል። •የአፍሪካ እግር ኳስ ቅሌት •''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ ይህ በስውር የተሰራው የምርመራ ዘገባ የእግር ኳስ ሃላፊዎች የገንዘብ ስጦታ ሲቀበሉ የሚያሳይ ሲሆን፤ ዘገባውም የቀድሞው የጋና እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት የህይወት ጊዜ እገዳ እንዲጣልባቸው አድርጓል። ቢቢሲ አፍሪካ የተባለው ፕሮግራም የሙስና ቅሌቱን ጥናታዊ ዘገባ የሰራበት ሲሆን፤ ቢቢሲ የማሳየቱን ፍቃድ ያገኘው ታይገር አይ የተባለውን ድርጅት የሚመራው አወዛጋቢው ጋዜጠኛ አናስ አረማየው መፍቀዱን ተከትሎ ነው። ቢቢሲ የጥናት ፊልሙን ካሳየ በኋላ የጋና ፓርላማ አባል የሆኑት ኬኔዲ አግያቦንግ በአንድ የጋና ዜና ማሰራጫ ድረገፅ ላይ በተለጠፈ ቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት የጋዜጠኛውን ፎቶ በማሳየት " በሚገኝበት ቦታ ደብድቡት፤ የሆነውን ይሁን እኔ እከፍላለሁ" ብለዋል። ጋዜጠኛው መገደሉን ተከትሎ አናስ በድፍረት በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቱ አባላቸው መገደሉ መቼም ቢሆን ዝም እንደማያሰኛቸው ተናግሯል። ትናንትና ሌሊት አክራ ውስጥ በሚገኝ ማዲና በሚባል ሰፈር አህመድ ሁሴን ሱዋሌ በደረቱ አካባቢ ሁለት ጊዜ በጥይት፣ አንገቱ ላይ ደግሞ አንድ ጊዜ እንደተመታ ተዘግቧል። በፖሊስ ሆስፒታል ወደሚገኝ መመርመሪያ አስከሬኑ የተላከ ሲሆን በቅርቡም የቀብር ስነ ስርአቱ ይፈፀማል። የምርምራ ጋዜጠኛው አህመድ በተለያዩ ዘገባዎች ላይ ከቢቢሲ ጋር በመጣመር ፕሮግራም የሰራ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በማላዊ በሚደረጉ አንዳንድ ስርአቶች ላይ የሰው አካል እንዴት እንደሚሸጥ የሚያሳየው ዘገባ ይገኝበታል። •ኬንያዊው እግር ኳስ ተጫዋች በመብረቅ ተመትቶ ሞተ በጋና ጋዜጠኞች ላይ የሚደርስ ጥቃት ያልተለመደ ሲሆን፤ በአለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን መረጃ መሰረት ከአራት አመት በፊት አንድ ጋዜጠኛ ተገድሏል። ከሁለት አመት በፊት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ በአጠቃላይ በአፍሪካ ውስጥ ስምንት ጋዜጠኞች ተገድለዋል።
news-49464135
https://www.bbc.com/amharic/news-49464135
ኬንያ በህዝብና በቤት ቆጠራው ምክንያት መጠጥ ቤቶችና የምሸት ክበቦች አገልግሎት እንዲያቋርጡ አደረገች
የኬንያ ሃገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ በትናንትናው ዕለት ነሐሴ 18፣ 2011ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፤ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅም 140ሺ ፖሊሶችን አሰማርታለች።
በትናንትናው እለት በተጀመረው የህዝብና የቤት ቆጠራው ምክንያት መጠጥ ቤቶች፣ ሬስቶራንቶችና የምሽት ክበቦች ለሁለት ቀናት ያህልም አመሻሹ ላይ ምንም አይነት አገልግሎት እንዳይሰጡም ትእዛዝ ተላልፎባቸዋል። •የሕዝብ ቆጠራው መራዘም ያስከተለው ቅሬታና የኮሚሽኑ ምላሽ •አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ኬንያ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነፃነቷን ከተጎናፀፈች በኋላ የተደረገው ስድስተኛ ቆጠራ ሲሆን ለሳምንት ያህልም እንደሚቀጥልም ተገልጿል። በመላው አገሪቱ በሚካሄደው በዚህ የህዝብና ቤት ቆጠራም ለማሳለጥ የተቀጠሩ ሰራተኞች ታብሌቶቻቸውን ይዘው በየቤቱ በማንኳኳት ቆጠራቸውን በማከናወን ላይ ናቸው። የሃገሪቱ ሚዲያዎች እንደዘገቡት በዚህ ቆጠራም ያልተለመዱ ጥያቄዎች ለምሳሌም ያህል በወር ለውሃና ለመብራት አገልግሎት የሚያወጡት ገንዘብ መጠን፣ ባጃጅ እንዲሁም የቤት እንስሶች አላችሁ ወይ የሚል ጥያቄን እንደተጠየቁ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከዚህም በተጨማሪ በባለፉት አስራ አምስት አመታት ከሃገር ውጭ ተጉዘው እንደሆነ፣ በባለፈው አመት ልጅ ሞቶባቸው ከሆነ፣ ምን ያህል ወንድ ልጆች አላችሁ የሚሉና ብዙዎችን ግራ ያጋቡ ጥያቄን እንደተጠየቁ ተዘግቧል። •የሌሉት 350 ሚሊዮን ሠዎች ቆጠራው በተጀመረበት እለትም የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰጡት መግለጫ የህዝብና ቤት ቆጠራው ሃገሪቷ ላቀደችው የልማት ፕሮግራሞች ግብዓት ስለሆነ ህዝቡ ትክክለኛውን መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሚቀጥለው ምርጫ ተፅእኖ ለመፍጠርና የመራጮቻቸውን ቁጥር ለመጨመር በሚል ፖለቲከኞች ህዝቡን ወደሚወክሉት አካባቢ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት እንዳያጓጉዙ ቀጠን ያለ ትእዛዝ ባለስልጣኖቿ አስተላልፈዋል። •ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ በዚህ የህዝብና የቤት ቆጠራም ላይ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለቱ የፆታ ምድብ ውስጥ የማይካተቱ 'ኢንተርሴክስ' የማህበረሰቡ አካላት ብሄራዊ የህዝብ ቁጥር ውስጥ ይካተታሉ። ይህም ለሰብዓዊ መብት ታጋዮች ትልቅ ድል ነው ተብሏል። በከፍተኛ ሙስና ቅሌቶች በምትታማው ኬንያ ለህዝብ ቆጠራው የተያዘው 180 ሚሊዮን ዶላር ጥያቄዎችንም አጭሯል። ከዚህም በተጨማሪ በኬንያ መረጃን የመጠበቅ ህግ ይህንን ያህል የጠበቀ ስላልሆነ ግላዊ መረጃዎች ሊጋለጡ ይችላሉ የሚልም ስጋት ሞልተውታል።
news-56411442
https://www.bbc.com/amharic/news-56411442
ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ በፍጹም እንዳታበሳጫት አስጠነቀቀች
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን እህት አሜሪካን በጠንካራ ቃላት አስጠነቀቀች፡፡
እጅግ ኃያል ናት የምትባለው የኪም ታናሽ እህት ኪም ዮ ጆንግ፣ አሜሪካ በዚህ ሰዓት አገሯን ሰሜን ኮሪያን የምታበሳጭ ተግባር ከፈጸመች ‹ወዮላት› ብላለች፡፡ እህት ኪም ጆንግ በተለይ ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ መጀመራቸውን ክፉኛ ተችታለች፡፡ የእህት ኪም ጆንግ አስተያየት በብሔራዊ ቴሌቪዥን የተላለፈው አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለመጀመር ደፋ ቀና በምትልበት ሰዓት መሆኑ አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቅርብ ቀናት የደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሶል ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ የጉብኝታቸው ዓላማም በአካባቢው እንዴት ዘላቂ ሰላም ማምጣት ይቻላል በሚለው ዙርያ ለመነጋገር ነው፡፡ አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር ፍላጎት ቢኖራትም ፒዮንግ ያንግ ግን ገና ጆ ባይደንን በፕሬዝዳንትነት ስለመቀበሏ እንኳ በይፋ ያለችው ነገር የለም፡፡ ሁለቱ አገሮች በኒውክሊየር እና ባሊስቲክ ሚሳይል ጉዳይ ላይ ሁልጊዜም ጠብ ላይ ናቸው፡፡ የፕሬዝዳንት ኪም እህት ኪም ዮ ጆንግ በዕለታዊው ሮዶንግ ሱሙን ጋዜጣ ላይ እንዲህ ብለዋል፣ ‹ለአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ምክር አለኝ፣ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት ከፈለጉ አገሬን ሰሜን ኮሪያን ከሚያስቆጣ ተግባር ይታቀቡ፡፡› ከዚህ ንግግር በተጨማሪ የኪም እህት ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ በጋራ የወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ መሆናቸው እልም ያለ ጠብ አጫሪነት ነው ብላለች፡፡ ‹እኔ ይህን የጠብ አጫሪነት ተግባር ሰሜን ኮሪያን ለመውረር ከመዘጋጀት ለይቼ አላየውም› ስትል ቁጣዋን ገልጻለች፡፡ ኪም ዮ ጆንግ የኃያሉ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ታናሽ እህት ስትሆን አሁን በሰሜን ኮሪያ ሁለተኛዋ ከፍተኛ ባለሥልጣን ተደርጋ ትወሰዳለች፡፡
news-54581071
https://www.bbc.com/amharic/news-54581071
ማክሮን፡ "ፈረንሳያዊው አንገቱን የተቀላው በሽብር ጥቃት ነው"
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ከመዲናዋ ፓሪስ አቅራቢያ አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው መምህር "በእስላማዊ የሽብር ጥቃት ነው" አሉ።
ፕሬዝደንት ማክሮን በጥቃቱ የተገደለው መምህር አወዛጋቢ የሆኑ የነብዩ መሐመድን ካርቱን ምስሎች ለተማሪዎቹ ያሳይ ነበር ተብሏል። ጥቃት አድራሹ በፖሊስ ተመትቶ ተገድሏል። ፕሬዝደንት ማክሮን በስም ያልተገለጸው መምህር የተገደለው "ሃሳብን በነጻነት መግለጽን በማስተማሩ ነው" ብለዋል። ጥቃቱ የተፈጸመበት ስፍራ ተገኝተው፤ "አያሸንፉም. . . ፈጣን እርምጃ እንወስዳለን" ብለዋል ፕሬዝደንት ማክሮን። ስለጥቃቱ እስካሁን የሚታወቁ ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት አከባቢ ትምህርት ቤት አቅራቢያ ነበር። ጥቃት አድራሹ በመንገድ ላይ በትልቅ ቢላዋ የመምህሩን አንገት ቆርጧል። ፖሊስ እንደሚለው ማንነቱ ይፋ ያልተደረገው ጥቃት አድራሽ ጥቃቱን ሲያደርስ "አላሁ አክበር" ሲል የአይን እማኞች ሰምተውታል። . 17 ታካሚዎችን የመረዘው ዶክተር . ፈረንሳይ ኮሮናቫይረስን ድል ነሳሁት አለች . ፈረንሳይ "ድንግልና" የሚመረምሩ ዶክተሮችን እቀጣለሁ አለች ግለሰቡ ጥቃቱን ካደረሰ በኋላ ከስፍራው ለመሰወር ቢጥርም ጥሪ የደረሰው ፖሊስ በፍጥነት በስፍራው ተገኝቷል። ፖሊስ ጥቃት አድራሹ እጁን እንዲሰጥ ቢጠይቀውም ዛቻ በማድረሱ ከፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ አራት ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች ከጥቃት አድራሹ ጋር ዝምድና ሳይኖራቸው አይቀርም ተብሏል። ምንም እንኳ ፖሊስ የጥቃት አድራሹን ማንነት ይፋ ባያደርግም፤ ቢኤፍኤምቲቪ የተሰኝ የፈረንሳይ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጥቃት አድራሹ ሩሲያ ሞስኮ ውስጥ የተወለደ የ18 ዓመት ወጣት ነው ሲል ዘግቧል። አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው መምህር ማነው? እንደ ሌሞንድ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ የታሪክ መምህሩ በክፍል ውስጥ ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽ ጋር በተያያዘ አወዛጋቢ የነብዩ መሐመድ የካርቱን ስዕሎችን በመጠቀም ያስተምራል። መምህሩ በዚህ ደስተኛ የማይሆኑ ተማሪዎች ካሉ ክፍሉን ለቀው መውጣት እንደሚችሉ ይናገር ነበር ብሏል ዘገባው። ከሳምንታት በፊት ሙስሊም ወላጆች የመምህሩን ተግባር በመቃወም ለትምህር ቤቱ ቅሬታ አቅርበውም ነበር። በፈረንሳይ መሰል ጥቃት ሲፈጸም ይህ መጀመሪያው አይደለም። ከሶስት ሳምንት በፊት ትውልደ ፓኪስታናዊ የ18 ዓመት ወጣት በስጋ መከትከቻ ትልቅ ቢላ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር። እአአ 2015 ላይ ሁለት ሙስሊም የፈረንሳይ ዜጎች የቻርሊ ሄብዶ መጽሔት ቢሮን ሰብረው በመግባት በሰራተኞቹ ላይ ተኩስ ከፍተው ሰራተኞቹን ጨምሮ በጠቅላላው 12 ሰዎች ገድለው ነበር።
news-57056788
https://www.bbc.com/amharic/news-57056788
እስራኤል በሎድ ከተማ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አወጀች
የእስራኤል መንግሥት በእስራኤላዊያን እና አረቦች መካከል ከፍተኛ አመፅ መነሳቱን ተከትሎ በሎድ ከተማ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጇል።
በእስራኤል የፀጥታ ሃይሎች እና በፍልስጤም ተቃዋሚዎች መካከል ያለው ግጭትም ተባብሶ ቀጥሏል። በሎድ ከተማ በተነሳው አመፅ መኪኖች ጋይተዋል እንዲሁም 12 ሰዎች ተጎድታል። የከተማው ከንቲባም ስማቸው ከእርስ በእርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ እየተነሳ ይገኛል። ማክሰኞ ምሽት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በሎድ ከተማ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጁን ይፋ አድርገዋል። የእስራኤል የድንበር ጠባቂ ፖሊሶችም ከዌስት ባንክ እንዲመጡ ተደርጓል። በቴል አቪቭ አቅራቢያ ባለችው የሎድ ከተማ የሚኖሩ እስራኤላዊያን፤ አረቦች የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ ወደ ረብሻ ተቀይሮ ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወሩ ፖሊስ ከፍተኛ ድምፅ በሚያሰሙ ፍንዳታዎች ምላሽ ሰጥቷል። ሰልፈኞቹ ከአንድ ቀን በፊት በረብሻው ህይወቱ ያለፈ ሰውን አስክሬን በበርካታ ቁጥር ተገኝተው ሸኝተዋል። የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በሎድ ከተማ በርካታ የንግድ ሱቆች እና ምኩራቦች በእሳት ተያይዘዋል። ሮይተርስ እንደዘገበው አንድ አረብ እየነዳ በነበረበት ወቅት አይሁዶች መኪናውን በድንጋይ አጥቅተዋል። የፍልስጤም ተዋጊዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል የተኮሱ ሲሆን እስራኤል በበኩሏ ከባድ የአየር ድብደባ በጋዛ ላይ አካሂዳለች። ባለፉት አመታታት በነበሩ ተመሳሳይ ግጭቶች ቢያንስ 40 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። የፍልስጤም ተዋጊዎች በበኩላቸው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ባካሄደችው የአየር ጥቃት አንድ ህንፃ ሙሉ ለሙሉ መውደሙን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን ወደ ቴል አቪቭ ተኩሰናል ብለዋል። የእስራኤል መከላከያ በጋዛ እያካሄደ ያለው የአየር ድብደባ የጋዛ ተዋጊዎች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ገልፆ ይህም በእየሩሳሌም እና ሌሎች አካባቢዎች ለተሰነዘሩ ጥቃቶች ምላሽ ነው ሲል ተደምጧል። ለሳምንታት የቆየው ይህ ውጥረት ለሙስሊሞችም ሆነ ለአይሁዶች ቅዱስ በሆነቸው እየሩሳሌም የእስራኤል ፖሊስ እና ፍልስጤማዊያን ሰልፈኞች መካከል በነበረው ግጭት ተባብሶ ለውጊያው መነሻ መሆኑ ተነግሯል። የዓለማ አቀፉ ህብረተሰብም ሁለቱም ወገኖች ውጥረቱን ለማርገብ እንዲሰሩ እየጠየቀ ይገኛል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመካከለኛው ምስራቅ ተወካይ ቶር ዌንስላድ ‹‹ሁለቱም ጎራዎች ነገሩ ወደ ለየለት ጦርነት እንዲገባ እያባባሱት ነው›› ሲሉ ተደምጠዋል። እስካሁን ድረስ 10 ህፃናትን ጨምሮ 35 ፍልስጤማዊያን እና አምስት እስራኤላዊያን በዚህ ግጭት ተገድለዋል ሲሉ የጤና ባለሞያዎች ገልፀዋል፡፡
41524130
https://www.bbc.com/amharic/41524130
የሩስያ ወታደሮች 'ሰልፊ' እንዳይነሱ ሊታገዱ ነው
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ወታደሮቹ 'ሰልፊ' በሥራ ላይ ሳሉ እንዳይነሱ የሚያዝ ሕግ አርቅቋል።
ረቂቁ ፎቶዎች፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንዲሁም ማንኛውም ወታደራዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች በይነ-መረብ ላይ እንዳይጫኑ ያዛል። አቅጣጫ ጠቋሚ ቴክኖሎጂዎች ወታደሮቹ ያሉበትን ቦታ ለጠላት አሳልፈው ሊሰጡ ይችላል ሲል ረቂቁ አፅንኦት ይሰጣል። የሩሲያ ወታደሮች ፎቶ ተነስተው በተለያዩ መንገዶች ካሰራጯቸው ምስሎች በመነሳት ሃገሪቱ በዩክሬይን እና በሶርያ ጦር ማዝመቷን ማወቅ ተችሏል። ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2014 አንድ የሩሲያ ወታደር፤ ሮኬቶችን በሩሲያ ለሚደገፈው የዩክሬይን አማፂ ቡድን አድርሶ መምጣቱን የሚጠቁም ፎቶ ለጥፎ ነበር። ይህንንም የቢቢሲዋ ሚሮስላቫ ፔትሳ በትዊተር ገጿ ላይ አስፍራዋለች። መጋቢት 2014 ላይ ሩሲያ ክሬሚያን ከወረረች ከጥቂት ወራት በኋላ የዩክሬይን አማፂ ቡድን የሃገሪቱን ምሥራቃዊ ክፍል መቆጣጠሩ የሚታወስ ነው። ምዕራባዊያን ሩሲያን የዩክሬይን አማፂ ቡድንን ከባድ የጦር መሣሪያ በማቅረብ ትደግፋለች በማለት ይወቅሱ እንደነበር ይታወሳል። ሩሲያም አንዳንድ ወዶ ገቦች ያግዙ ይሆናል እንጂ ከባድ የጦር መሣሪያ አላስታጠኳቸውም ስትል አስተባብላ እንደነበርም አይዘነጋም። የቫይስ ኒውስ ጋዜጠኛ ሳይመን ኦስትሮቭስኪ በዩትዩብ ገጹ፤ የሩሲያ ወታደሮች በይነ-መረብ ላይ የሚለጥፉትን ፎቶ በመከታተል የሩሲያን በዩክሬይን ያላትን ቀጥታ ጣልቃ ገብነት ማረጋገጥ መቻሉን የሚያሳይ ምሰል ጭኖ ነበር። በነሐሴ 2014 ደግሞ ሌላ ጋዜጠኛ የሩሲያ ወታደሮችን የማህበራዊ ድረ-ገጽ ፎቶዎች በመከታተል 76ኛው የሩሲያ አየር ኃይል ክፍል ጉዳት እንደደረሰበት እና ፒስኮቭ በምትባለው የምዕራብ ሩሲያ ክፍል እንደሚገኝ ማረጋጥ ችሏል። ከሩሲያ የጦር ክፍል ውስጥ ሁለት ክፍሎች ወታደሮቻቸው በይነ-መረብ ላይ ማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል ፎቶ እንዳይለጥፉ ሙሉ በሙሉ አግዷል። አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ከጥር 2018 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ይጠበቃል።
56201582
https://www.bbc.com/amharic/56201582
ቻይና የከፋ ድህነትን ከግዛቷ ማስወገዷን አወጀች
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አገራቸውን "በተዓምርዊ" ሁኔታ ከከፋ ድህነት መውጣቷን ተናገሩ።
ፕሬዝዳንቱ መንግሥታቸው ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ100 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት መቻሉን ገልፀዋል። ዢ ጂንፒንግ ቤይጂንግ ውስጥ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት "የተሟላ ድል" በማለት ስኬቱን አንቆለጳጵሰው "በታሪክ ውስጥ የሚመዘገብ" ብለውታል። ነገር ግን ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር ያልተዋጠላቸው ባለሙያዎች ድህነት በቻይና እንዴት እንደተለካ ጠይቀዋል። በቻይና የከፋ ድህነት ተብሎ የሚገለፀው በዓመት ገቢው ከ620 ዶላር በታች የሆነ ግለሰብ ነው። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው "የከፋ ድህነትን የማስወገድ ተግባሩ ተጠናቅቋል" ብለዋል። አሁን ባለው መስፈርት በገጠራማ የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ 98.99 ሚሊዮን ድሆች በሙሉ ከድህነት ወጥተዋል፤ 832 በድህነት የተጎዱ አካባቢዎች እና 128 ሺህ መንደሮች ደግሞ ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ተፍቋል" ሲሉ አክለዋል። ዢ ጂንፒንግ ወደ ስልጣን ከመጡበት 2012 (እኤአ) ጀምሮ በገጠር ያለን ድህነትን ማስወገድ ቁልፍ ተግባራቸው አድርገው ሲሰሩ ነበር። ቻይና ባለፈው ዓመት የመጨረሻዎቹን ድሃ የተሰኙ አካባቢዎችን ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ስማቸውን አንስታለች። በዚህም የተነሳ ቻይና በ2020 የከፋ ድህነትን ማስወገድ ችላለች። ዛሬ፣ ሐሙስ በተካሄደ ክብረ በዓል ላይ ዢ ጂንፒንግ ድህነትን በመዋጋት ተግባር ውስጥ ለተሳተፉ አካላት ሜዳሊያ ሸልመዋል። ነገር ግን ባለሙያዎች ቻይና ድህነትን የምትበይንበትን መስፈርት ዝቅ አድርጋ አስቀምጣለች፤ አሁንም በድሃ አካባቢዎች ተጨማሪ ሃብት ማፍሰስ ያስፈልጋል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በቻይና አንድ ሰው የከፋ ድህነት ውስጥ ይኖራል ለመባል የቀን ገቢው 1.69 ዶላር መሆን አለበት። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የዓለም ባንክ ግን 1.90 ዶላር የሚያገኝን ሰው የከፋ ድህነት ውስጥ ይገኛል ሲል ይበይናል። በቻይና አሁንም በዜጎች መካከል የሰፋ የሃብት ልዩነት ይታያል።
news-52164474
https://www.bbc.com/amharic/news-52164474
ኮሮናቫይረስ፡ "መኖር የሚፈልግ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት" ቀነኒሳ በቀለ
የኦሎምፒክ አሸናፊውና የአምስት ሺህና የአስር ሺህ ክብረወሰን ባለቤት የሆነው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ማኅበረሰቡ ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክሮች በሥራ ላይ እያዋለ አይደለም ሲል ስጋቱን ለቢቢሲ ተናገረ።
የዓለም ሕዝብ እንደ ቅጠል እየረገፈ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ሕዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሱን ከወረርሽኙ መጠበቅ ቢኖርበትም ይህ እየተተገበረ አለመሆኑ እንዳሳሰበው አትሌት ቀነኒሳ ገልጿል። • ወሲብና ኮሮናቫይረስን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች ጨምሮም "ሕዝቡ በባለሙያዎች የሚሰጠውን ምክር ተቀብሎ ራሱን የማይጠብቅ ከሆነ አገሪቱ ትልቅ ፈተና ሊገጥማት ይችላል" በማለት አሳስቧል። ቀነኒሳ እንዳለው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጤና መሰረተ ልማት እምብዛም ጠንካራ አለመሆኑን በመገንዘብ ሕዝቡ የሚሰጠውን ምክር በተግባር መተርጎም ይጠበቅበታል ሊል መክሯል። "ነገን በማሰብ መኖርን ያለመ ሰው፤ በዚህ ወቅት ለራሱና ለቤተሰቡ ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል" በማለት ጤንነት ካለ ወደ ፊት ብዙ ነገር መሥራት ይቻላል ሲል ቀነኒሳ ለጥንቃቄ ትኩርት እንዲሰጥ መክሯል። የበሽታው መስፋፋት ያሳሰበው ቀነኒሳ የግል ንብረቱ የሆነውንና በሱሉልታ የሚገኘውን የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ መንደር በኮሮናቫይረስ ለተጠረጠሩ ሰዎች ለይቶ ማቆያነት እንዲውል መስጠቱንም ገልጿል። ቀነኒሳ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከመምከር ባሻገር እሱም ድሃን ከሃብታም ከማይለየው በሽታ እራሱንና ቤተሰቡን ለመጠበቅ ጥንቃቄ እያደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል። በዚህም መሰረት ኮሮናቫይረስ ወደ አገር ውስጥ መግባቱን ከሰማ ጀምሮ ልምምድ የሚያደርገው ብቻውን እንደሆነ በመግለጽ "እያንዳንዱ ሠው የሚጠበቅበትን ጥንቃቄ ካደረገ ይህንን በሽታው መቆጣጠር ይቻላል" ብሏል። ነገር ግን "ብዙ ሰው እየተነገረ ያለውን እየሰማ አይመስልም፤ ይህንን ጉዳይ እንደ ቀላል የሚመለከተው ይመስለኛል" በማለት ቀነኒሳ ያጋጠመውን ይናገራል። በዚህ ወቅት "ለመጨበጥና አብሮ ፎቶ ለመነሳት የሚጠጉ ሰዎች ያገጥማሉ።. . . አይሆንም ስትላቸው ደግሞ የሚናደዱ ሰዎች አሉ" በማለት የዓለም ጤና ድርጀት የኮቪድ-19 ወረርሽን ስርጭትን ለመከላከል ይረዳሉ በማለት ያስቀመጣቸውን ምክሮች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያስታውሳል። • ልንቀበላቸው የማንችላቸውን ነገሮች እንድንቀበል ግፊት ሲደረግ ነበር ፡ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሌላ በኩል ደግሞ ከኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በጃፓን ሊካሄድ የነበረው የኦሊምፒክ ውድድርን አስመልክቶ የተጠየቀው ቀነኒሳ በአሁኑ ወቅት 38 ዓመት ሊሞላው እንደሆነ በመናገር፤ ውድድሩ በአንድ ዓመት መራዘሙ ምንም ተጽዕኖ እንደማያመጣበት ገልጿል። "አንድ እና ሁለት ዓመት ምንም ለውጥ አያመጣም። እደርሳለሁ፤ እሄዳለሁ እቅዴንም በተግባር ለማዋል እችላለሁ" ብሏል። በተጨማሪም ውድድሩ ቢሳተፍ ደስተኛ እንደሚሆን ገልጾ "ሁልጊዜም ፈጣሪ ያለው እንጂ ሠው ያለው አይሆንም" በማለት ዓለምን እያስጨነቀ ያለው በሽታ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ሕዝቡ የሚነገረውን ተግባራዊ እያደረገ መፀለይ እንዳለበት መክሯል።
news-49960038
https://www.bbc.com/amharic/news-49960038
ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት
ከመቶ አመት በፊት እንዲያውም ብዙ ሳንርቅ ኧረ ከሃያ አመታት በፊት ያለ መሬትና አርሶ አደሮች ግብርናን ማካሄድ ይቻላል ብሎ ማሰብ ሩቅ ህልም ነበር።
በጃፓን ግን እውን ሆኗል። በጃፓን ነዋሪ የሆነው ዩቺ ሞሪ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ቢያበቅልም፤ መሬትም ሆነ አፈር ለሱ አስፈላጊ አይደለም። በአማራጩ የጃፓን ሳይንቲስቶች የሰውን ልጅ ኩላሊት ለማከም የተሰራውን በግልፅ የሚያሳይና ፈሳሽም ሆነ አየር ማሳለፍ የሚችል 'ፖሊመር ፊልም' የተባለውን ፕላስቲክ መሳይ ነገር ለግብርና መጠቀም ከጀማመሩ ሰነባበቱ። •ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው አዝርዕቱ 'ፖሊመር ፊልሙ' ላይ የሚበቅሉ ሲሆን ፈሳሽም ሆነ ንጥረ ነገሮችን ለማጠራቀምም ይረዳል። አትክልቶችን የትኛውም ከባቢ እንዲበቅሉ ከማስቻል በተጨማሪ ከባህላዊው ግብርና 90 ፐርሰንት ያነሰን ውሃን በመጠቀም ፀረ ተባይ መድሃኒቶችንም ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል። ምክንያቱም ፖሊመሩ ቫይረስንም ሆነ ባክቴሪያን ማገድ ስለሚያስችለው ነው። •"የረሃብ አድማን የመረጥነው ከራሳችን የምንጀምረው ተቃውሞ ስለሆነ ነው" አቶ ገረሱ ገሳ በጥቂት የሰው ኃይልና ያለምንም መሬት የግብርናን አብዮት የፈጠረችበት አንዱ መንገድ ነው። ሳይንቲስቱ ዩይቺ ሞሪ 'ፖሊመር ፊልምን' በመጠቀም የግብርና ስራ ሲያከናውኑ "በኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲስ) ወቅት ደምን ለማጣራት የሚጠቅመውን እቃ በመውሰድ ነው መጠቀም የጀመርኩት" በማለት ሳይንቲስቱ ዩይቺ ሞሪ ለቢቢሲ ተናግሯል። ኩባንያው ሜቢኦል ይሄንን ፈጠራውን በ120 ሃገራት ማስመዝገብ ችሏል። •''ለሴቶች ቦክስ ምን ያደርጋል እያሉ ያንቋሽሹናል'' በጃፓን እየተካሄደ ባለው የግብርና አብዮት የእርሻ መሬቶች ወደ ቴክኖሎጂ ማዕከላት እየተቀየሩ ሲሆን ለዚህም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስና የመጠቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተግባራዊ በመሆን ላይ ናቸው። የዚህ አመት የተባበሩት መንግሥታት የውሃ ሃብትና ልማትን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርቱ ያለው የከባቢ መሸርሸርና የውሃ ሃብት መመናመን በዚህ ከቀጠለ በ2050 40 % የሚሆነው የአዝርዕት ምርቶችና 45% የሚሆነው የአለም ምርት ቀውስ ውስጥ እንደሚወድቅ ነው። ዩቺ ሞሪ የፈጠረው የአበቃቀል ዘዴ በጃፓን ከ150 በላይ ቦታዎች ተግባራዊ ሲሆን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አገራትም ተጠቃሚ ሆነዋል። በተለይም ይህ ዘዴ በጎርጎሮሳውያኑ 2011 የተፈጠረውን የኒውክለር ቀውስ ተከትሎ በተፈጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ጨረሮች ባስከተሉት የእርሻ መሬቶችን ብክለትን ለማስተካከልም ይረዳሉ ተብሏል። • ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን እንደማትቀበል አሳወቀች ሮቦት ትራክተሮች በ2050 የአለም አቀፉ የህዝብ ቁጥር ከ7.7 ቢሊዮን ወደ 9.8 ቢሊዮን ያድጋል ተብሎ እየተገመተ ባለበት ወቅት፤ የተለያዩ ኩባንያዎች ሊመጣ የሚችለውን የምግብ ፍላጎትን ለሟሟላት የተለያዩ የቢዝነስ አማራጮችን በመፈተሽ ላይ ናቸው። የጃፓን መንግሥት በአሁኑ ሰዓት በግብርና ስራዎች ከመዝራት እስከ ማረም ባለው ሂደት ላይ ሊያግዙ የሚችሉ 20 አይነት ሮቦቶች መመረት ላይ ከፍተኛ እርዳታ እያደረገ ነው። ከሆካይዶ ዩኒቨርስቲ ጋር በመጣመር ያንመር የተባለው አምራች ድርጅት አንድ ሮቦት አምርቶ በእርሻ መሬቶች ላይ እየተሞከረ ነው። ሮቦት ትራክተሮች መሬት ላይ ያሉ ቁሶችን ለመለየትም የሚያስችል መሳሪያ ስለተገጠማላቸው አንድ ሰው ሁለት ትራክተሮችን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ሊያሰራቸው ይችላል። በዚህ አመትም ኒሳን በፀሐይ ጉልበት የሚሰሩ፣ አቅጣጫን የሚያመላክቱና የዋይፋይ አገልግሎት የተገጠመላቸው ሮቦት አምርቷል። •"የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ ዳክየ (ደክ) የሚል ስያሜ የተሰጠውና ሳጥን የሚመስለው ሮቦት በሩዝ እርሻዎች ውስጥ በመመላለስ ውሃው ውስጥ ያለውን የኦክስጅን መጠን በመጨመር፣ የፀረተባይ መድሃኒቶችን መጠን መቀነስ አስችሏል። እርሻ በጥቂት ሰዎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ የእርሻ መሬት ላይ በቀጥታ መስራት የማይፈልጉና በቴክኖሎጂውም ብዙ ዕውቀት የሌላቸው ወጣቶችን ለመሳብ የጃፓን መንግሥት አቅዷል። በጥቂት የሰው ኃይልም የግብርና ዘርፉንና የምጣኔ ኃብቱን ለማሳደግ ይረዳልም ተብሏል። በባለፉት አስር አመታት በግብርና ዘርፍ የተሰማራው የሰው ኃይል ከ2.2ሚሊዮን ወደ 1.7 ሚሊዮን አሽቆልቁሏል። •በአሜሪካዊቷ ፖሊስ የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ ከዚህ በከፋ ሁኔታም በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩት ሰዎች አማካኝ እድሜ 67 አመት ሲሆን፤ ብዙ አርሶ አደሮችም በትርፍ ጊዜያቸው ነው የሚሰሩት። ሌላኛው የጃፓንን ግብርና የሚገድበው የሃገሪቷ መልክዓ ምድር አቀማመጥ ሲሆን በዚህም ምክንያት 40% የሚሆነውን የሃገሪቷን ምርት ብቻ ነው ማምረት የተቻለው። 85% የሚሆነው የሃገሪቷ የእርሻ ቦታ ተራራማ ሲሆን ቀሪው ደግሞ የሚያበቅለው ሩዝ ብቻ ነው። ሩዝ የጃፓናውያን ዋነኛ ምግብ ሲሆን ለሩዝ አምራች ገበሬዎች የመንግሥታቸው ድጋፍ አልተለያቸውም። በግብርና ላይ የሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ጥቅም ምንም እንኳን ለዘመናት ሩዝ ዋነኛ ምግብ ሆኖ ቢቆይም የአበላል ባህል በመቀየሩ በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1962 በአማካኝ በአመት አንድ ሰው 118ኪ.ግ ሩዝ ተጠቃሚነት በ2006 ወደ 60ኪ.ግራም ቀንሷል። ይህንንም በማየት ጃፓን የተለያዩ አዝርዕቶችን የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን እያበረታታች ነው። የሰው እርዳታ ዝቅተኛ በመሆኑም አርሶ አደሮች ወደተለያዩ ማሽኖችና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ፊታቸውን አዙረዋል። በከፍተኛ ሁኔታም ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ጥቅም ላይ እየዋሉ ሲሆን፤ አንድ ሰው ሙሉ ቀን የሚፈጅበትንም ስራ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ማጠናቀቅ ችለዋል። የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀም ከመሬት ይልቅ ውሃ ውስጥ የሚያድጉ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ለማምረት ችለዋል። ሚራይ የተባለው ቡድንም በመደርደሪያዎች ላይ በመትከል 10ሺ የሚሆኑ የሰላጣ ራሶችን በቀን ማብቀል ችለዋል። ያለ አፈር በውሃ ውስጥ የሚበቅለው ሰላጣ በተገጠመለት መሳሪያ፤ የአርቲፊሻል ብርሃን፣ የእርጥበት መጠን፣ ካርቦንዳይኦክሳይና የሙቀትን መጠን ይቆጣጠራል። አርቲፊሻል ብርሃን አትክልቶችን በከፍተኛ ፍጥነት ለማደግ የሚረዳቸው ሲሆን በበሽታ የመጠቃት እድላቸውንም ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል። ምርታማነት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት አትክልት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ቁጥር በሶስት እጥፍ አድጓል። በውሃ ውስጥ የሚመረተው (ሃይድሮኒክስ) ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ቢዝነስን የያዘ ሲሆን፤ በ2023 6.4 ቢሊዮን ይደርሳልም ተብሏል። የቴክኖሎጂ ሸግግር ጃፓን ከራሷ አልፋ፣ የአፍሪካ ሃገራት የሩዝ ምርታቸውን በማሳደግ በ2030፣ 50ሚሊዮን ቶን እንዲያመርቱ ለማስቻል ፕሮጀክቶችን ቀርፃለች። በአንዳንድ ቦታዎችም ለምሳሌ በሴኔጋል ጃፓን በግብርና ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ስልጠና ከመስጠት በተጨማሪ በመስኖ ስራ ላይም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እየተገበሩ ነው። ይህንንም ተከትሎ በሄክታር አራት ቶን ይመረት የነበረውን ወደ ሰባት በማሳደግ የአምራቾቹም ገቢ በ20% እንዲጨምር ሆኗል። በቪየትናም፣ በማይናማር፣ እንዲሁም በብራዚል ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን ቀርፃ እየሰራች ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የጃፓን አላማ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሀገሯን የምግብ ደህንነት ማረጋገጥ ነው።
45060061
https://www.bbc.com/amharic/45060061
በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል
ባለፉት ሁለት ሦስት ቀናት ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተሰነዘሩ ጥቃቶች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እንዲሁም የመንጋ ፍትህ ከህግ የበላይነት አንፃር ምን አይነት አደጋዎች እንደተጋረጡ አመላካች ነው።
በምስራቅ ወለጋ ወሊጋልቴ ገጠር ቀበሌም ቅዳሜ እለት ማምሻውን ሁለት ግለሰቦች በቡድን በድንጋይ ተደብድበው መሞታቸው ተሰምቷል። እሁድ ደግሞ በሻሸመኔ ቦምብ ይዟል በሚል አንድ ሰውን ወጣቶች የስልክ እንጨት ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለዋል። ትላንት ጀዋር መሀመድን ለመቀበል በርካቶች በሻሸመኔ ከተማ ስታዲየም ተገኝተው ነበር። በህዝብ መጨናነቅ ሳቢያ በተከሰተው መገፋፋት ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉም አሉ። የብዙሀኑ መነጋገሪያ የነበረው ግን ተደብዶቦ ህይወቱ ያለፈና ልብሱ ተገፎ፣ ተዘቅዝቆ የተሰቀለው ሰው ነው። ግለሰቡ ማንም ቢሆን፣ ምንም አይነት ተግባር ቢፈጽምም የደረሰበት አሰቃቂ ጥቃት ኢ-ፍትሀዊ ነው የሚሉ አስተያየቶች ተደምጠዋል። አንድን ሰው በአንድ ወንጀል ከሶ፣ ራስ ምስክር፣ ራስ ፈራጅ፣ ቀጪም ራስ የሆነበት የደቦ ፍትህ በሻሸመኔ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አካባቢዎችም እየተስተዋለ ነው። በሻሸመኔ ከተማ ጀዋርን ለመቀበል ወደ ስታዲየሙ አቅንተው ከነበሩ መካከል ስሜ አይጠቀስ ብሎ አስተያየቱን የሰጠን ግለሰብ ግርግር ካየ በኃላ ነበር ስለ ክስተቱ የሰማው። "ቦንብ ይዟል" የተባለው ሰው ተሰቅሎ የተመለከተ ሲሆን ተግባሩን "ትልቅ ስህተት" ይለዋል። ህብረተሰቡ ተረጋግቶ ማሰብና ከመሰል እርምጃ መቆጠብ እንዳለበትም ይናገራል። ሰው ተሰቅሎ ማየቱ እጅግ የዘገነነው ግለሰብ "አስጸያፊ ነው። በሀገራችን በባህላችንም የለም። ፍትሀዊም አይደደለም" ብሏል። የሻሸመኔ ከተማ የፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር መኮንን ታደሰ እንደሚሉት ከድርጊቱ ጀርባ ያሉትን ግለሰቦችና ምክንያታቸውን በመጣራት ላይ ነው። ግለሰቡ "ሳንጃ ይዟል" የሚል ወሬ ተሰራጭቶ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ምንም መሳሪያ እንዳላገኘም ገልጸዋል። ቅዳሜ እህል ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል ይጓዝ የነበረ ተሳቢ አማራ ክልል ውስጥ በወጣቶች እንዲቆም ተደርጎ ጭነቱ መዘረፉም ተሰምቷል። አሁን ነገሩ አስከፊ ደረጃ ላይ ቢደርስም ባለፉት የተወሰኑ ሳምንታትም በመንጋ ሰዎችን ማጥቃት እንዲሁም ንብረት ማውደም በተለያዩ አካባቢዎች የተስተዋለ እውነታ ነው። ከተወሰኑ ቀናት በፊት በአማራ ክልል አዊ ዞን በጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት አቅራቢያ በምትገኘው ፈንድቃ ከተማ ጥቃት ደርሶባቸው የሞቱትን የትግራይ ተወላጆች መጥቀስ ይቻላል። ከዚያም በደሴ ከተማ ወጣቶች የተፈረደበትንና በህግ አስከባሪዎች ጥበቃ ስር መንገድ ላይ የነበረን ወንጀለኛ የቡድን ጥቃት በመሰንዘር ማስመለጣቸውን የአንደኛ ፓሊስ ጣቢያ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጌታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በጣና በለስ ጥቃት ደርሶባቸው የሞቱት ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፀመ • ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ በኦሮሚያ እንዲሁም በሶማሌ ክልል ብሔርን መሰረት ባደረገ ጥቃት ህይወት ሲጠፋ በርካቶች የእኛ ያሉት መኖሪያቸውን ጥለው ሊሰደዱ ግድ ሆኗል። የሚራራ ልብ ጠፍቶ ህፃናት እንኳ የዚህ ጥቃት ሰለባ ሲሆኑ ታይቷል። በሃዋሳ እንዲሁም በአሶሳ በተመሳሳይ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡም ጥቂት አይደሉም። ሰዎች በደቦ በድንጋይ ተወግረው፣ በዱላና በብረት ተቀጥቅጠው ህይወታቸውን ሲያጡ አጋጥሟል። የዚህ ወገን የዚያኛው ወገን እየተባሉ በተለያዩ ቦታዎች መኪኖች ተቃጥለዋል ህንፃዎች በደቦ ወድመዋል። መንገዶችም በተደጋጋሚ ተዘግተዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ሰዎች በቡድን ተነስተው በሚወስዱት እርምጃ ህይወት እየጠፋ ንብረት እየወደመ ያለበት ሁኔታ ወደ አስከፊነት እየተሸጋገረ ነው የሚሉም አለ። የማህበራዊ ሳይንስና የህግ ባለሙያዎች በዚህ ሁኔታ ሰዎች ራሳቸው ከሳሽ እራሳቸው ፈራጅም የሆኑበት ነው ይላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ትምህርት ክፍል ለ36 ዓመታት ያስተማሩት ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ የመንጋ ፍትህ በእንግሊዝኛው 'ሞብ' የሚባለው ታፍኖ የነበረ ወይም ታፍኜ ነበር ብሎ የሚያስብ ማህበረሰብ አሁን ነፃ ነኝ ምንም የምሰራው ነገር አያስጠይቀኝም ብሎ ሲያስብ የሚገባበት ሁኔታ እንደሆነ ያስረዳሉ። ስለዚህም ሰዎች በግለሰብ አስተሳሰባቸው ሳይሆን በመንጋ ህሊና እየተመሩ ነው ይላሉ። "አንድ ሰው በ'ሞብ' ሲሳፈር የሚመራው በራሱ ህሊና ሳይሆን በመንጋ ነው። መንጋው የራሱ ህሊና ይፈጥራል" የሚሉት ዶ/ር የራስ ወርቅ በመንጋ ህሊና ከፍተኛ ጥፋት ካደረሱ በኋላ ሰዎች ከመንጋው ተነጥለው ወደ ቤታቸው ሲሄዱና ወደ ህሊናቸው ሲመለሱ ያደረጉትን ማመን ሁሉ እንደሚከብዳቸውና ፀፀት እንደሚገባቸው በጥናት መመልከቱን ይናገራሉ። በሌላ በኩል ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ትልቅ ተፅዕኖ እንዳለው የሚነገርለት ጀዋር መሃመድ፤ በአሁኑ ወቅት እዚም እዚያም እየታየ ያለው ጥቃትና ግጭት ከአምባገነን ወደ ደሞክራሲያዊ ሥርዓት በሚደረግ ሽግግር ወቅት ክፍተት የሚፈጠር እንደሆነ ያመለክታል። ጀዋር እንደሚለው ጊዜው የሽግግርና ክፍተት ያለበት ነው። ሰዎች ጠመንጃ የሚፈሩበት አይደለም የሕግ ሥርዓት ደግሞ እንደሚገባው እየሄደ አይደለም። ይህ ክፍተት ደግሞ "ሥርዓትና ህግ አልበኝነትን ይፈጥራል" ይላል። • በወልዲያ እና ፍኖተ-ሰላም ማረሚያ ቤቶች የእሳት አደጋ ደረሰ • የመርሳ ባለሃብቶች የምርት ቦታችን ወደመብን አሉ ይህ ክፍተት በአፋጣኝ የማይሞላ ከሆነ ሽግግሩ በርግጥም ወደ ዲሞክራሲ ያመራል ወይ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። ጥያቄ ብቻም ሳይሆን በዚህ የሽግግር በሚባለው ጊዜ የሚታዩ የደቦ ጥቃትና ንብረት ማውደሞች በጥቅሉ ሥርዓት አልበኝነትን በማጤን ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው በሚል ስጋት ያደረባቸውም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። በሌላ በኩል የአስቸኳይ ጊዜ ማወጅ ሁሉ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ እንደሆነ ሃሳባቸውን የሚሰነዝሩም አሉ። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ነገሮች ከባድ እንደሚሆኑና እስካሁን የተከፈለውም ዋጋ ከባድ እንደሆነ ዶ/ር የራስ ወርቅ ይናገራሉ። "የሆነው ሆኗል ለወደፊት እንዳይሆን ብንል እንኳ እስካሁን የተደረገው የራሱ ጠባሳ ይኖረዋል። በተለይም በሃይማኖትና በብሔር የሚደረጉ ጥቃቶች የሚያገረሹ ናቸው" ብለዋል። ዶ/ር የራስ ወርቅ ሕግና ሥርዓትን በማስከበር ችግሩን መፍታት እንደሚያስፈልግ ሲገልፁ ጀዋር ደግሞ ችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ ይፈልጋል በማለት ሃሳብ ይሰነዝራል። በደቦ በመንቀሳቀስ ሳይሆን ህብረተሰቡ በአካባቢው ከፖሊስና ከአካባቢ ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ነገሮችን ማረጋጋት እንደሚገባ በብሔራዊ ደረጃም ግን አፋጣኝ እርምጃ እንደሚያስፈልግ ጀዋር ይናገራል። "ችግሩ ፈጣን የሆነ የፖለቲካ መፍትሄ ያስፈልገዋል። ይህ ማለት ገዥው ፓርቲና ተቃዋሚዎች በመቀራረብ ህዝብን ሊያሳምን የሚችል ህግጋትን ማውጣት አለባቸው" በማለት ይደመድማል።
45988504
https://www.bbc.com/amharic/45988504
ከኤልን ጆንሰን ሰርሊፍ እስከ ሣህለወርቅ ዘውዴ - የዓለማችን ሴት መሪዎች
ኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝደንት አግኝታለች፤ በፕሬዝደንትነት ማዕረግ ሲሆን በሃገሪቱ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግሥት ከ20 የካቢኔ አባላት አስሩን ሴቶች አድርጎ በመሾም መነጋገሪያ የሆነው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ነበር። በያዝነው ሳምንት ደግሞ አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴ የሃገሪቱ ርዕሰ ብሔር አድርጎ በመሾም አፍሪካና የተቀረውን ዓለም ማነጋገር ችለዋል። ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝደንቷ የላቀ ሥልጣን ቢኖውም አሁን ላይ አፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የመንግሥት ቦታ በመያዝ ሣህለወርቅን የሚስተካከላቸው የለም። የላይቤሪያ ፕሬዝደንት የነበሩት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ አህጉረ አፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን በመጨበጥ ሃገራቸውን ለበርካታ ዓመታት መርተዋል። ነገር ግን በቅርቡ ለታዋቂው እግር ኳሰኛ ጆርጅ ዊሀ ቦታውን በሰላማዊ መንገድ በመልቀቅ ተሰናብተዋል። • ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡ በሚያውቋቸው ሰዎች አንደበት •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ •2010 ለታምራት ላይኔ፣ ለእስክንድር ነጋ፣ ለሃጫሉ ሁንዴሳ . . . የብራዚሏ ዲልማ ሩሴፍም ስማቸው የሚነሳ ነው፤ ምንም እንኳ ሙስና ስማቸው ተብጥልጥሎ ሥልጣን ቢለቁም። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተሰኘው የዜና ወኪል ከሆነ አሁን ላይ 17 ሴቶች በርዕሰ-ብሔርነት አሊያም በርዕሰ መንግሥትነት ያገለግላሉ። አዲሷ ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ይህን መዝገብ የተቀላቀሉ ግለሰብ ሲሆኑ ቁጥሩን ወደ 18 ከፍ አድርገውታል። በምጣኔ ሃብት ከፈረጠሙቱ መካከል የጀርመኗ መራሄ መንግሥት ኤንግላ ሜርክል እና የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ይጠቀሳሉ። ዓለማችን ካሏት ሴት መሪዎች መካከል 10 ያህሉ የመወሰን መብት ያለውን ሥልጣን የጨበጡ ሲሆን ይህም ከጠቅላላው 5.6 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል። • እነሆ አሁን በሥልጣን ላይ ያሉ ሴት የሃገራት መሪዎች፤ (የዘመናቱ አቆጣጠር በአውሮፓውያን መሆኑ ልብ ይባል) • ሸይክ ሃሲና - የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ • ከርስቲ ካሊጁሌድ - የኢስቶኒያ ፕሬዝደንት፤ ከፈረንጆቹ ጥቅምት 2016 ጀምሮ • ካትሪን ጃኮብስዶቲር - የአይስላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከፈረንጆቹ ህዳር 2017 ጀምሮ • ዳሊያ ግሪባውስካይት - የሉቴኒያ ፕሬዝደንት፤ ከግንቦት 2009 ጀምሮ • ማሪ-ሉዊ ኮሌይሮ ፕሬካ - የማልታ ፕሬዝደንት፤ ከነሃሴ 2014 • የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ ብሔር- አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ • ሂልዳ ሄይን - የማርሻል ደሴቶች ፕሬዝደንት፤ ከጥር 2016 ጀምሮ • ሳራ ኩጎንጌልዋ - የናሚቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከመጋቢት 2015 ጀምሮ • ቢዲያ ባንዳሪ - የኔፓል ፕሬዝደንት፤ ከጥቅምት 2015 ጀምሮ • ጃሲንዳ አርደርን - የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከጥቅምት 2017 ጀምሮ • ኤርና ሶልበርግ - የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከመስከረም 2013 ጀምሮ • መርሰዲስ አራዎዝ - የፔሩ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከመስከረም 2017 ጀምሮ • ቪዮሪካ ዳንሲላ - የሮማንያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከጥር 2018 ጀምሮ • አና ብራንቢች - የሰርቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ከሰኔ 2017 ጀምሮ • ሳይ ኢንግ-ዌን - የታይዋን ፕሬዝደንት፤ ከግንቦት 2016 ጀምሮ አማርኛ፤ ፈረንሳይኛ እና እንግሊዝኛ አቀላጥፈው የሚናገሩት የሶስት ልጆች እናት የሆኑት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ያለግዜያቸው ሥልጣን ከለቀቁት ፕሬዝደንት ሙላቱ ተሾመ ነው መንበሩን የተረከቡት። ምንም እንኳ የአዲሷ ፕሬዝደንት የመወሰን መብት ውሱን ቢሆንም ሃገሪቱ ውስጥ እየታየ ባለው የለውጥ ሂደት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና ቀላል የሚባል አይደለም። ኢትዮጵያና ሩዋንዳ አፍሪቃ ውስጥ በርካታ ሴት የካቢኔ አባላትን በማካተት እየመሩ ይገኛሉ፤ በፕሬዝደንትነት ደግሞ ኢትዯጵያ ቁንጮ ሆናለች። ወደፊት እንደ ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ያሉ የመወሰን ሥልጣን ያላቸው ሴት መሪዎች እና ሳህለወርቅ ዘውዴን የመሰሉ ርዕሰ-ብሔራት በርክተው እናይ ይሆን? ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። • አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው?
news-46478737
https://www.bbc.com/amharic/news-46478737
የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር፡ ከሁዋዌ ባልደረባ እስር ጀርባ ፖለቲካ የለም
የካናዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ ከሁዋዌ ባልደረባ እስር ጋር በተያያዘ የመንግሥታቸው እጅ እንደሌለበት አሳታወቁ።
የቻይናው ቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ ባለቤት ልጅ እና ምክትል ኃላፊ ሜንግ ዋንዦ ካናዳ ቫንኮቨር አየር ማረፊያ ውስጥ ለእሥር መዳረጓ ይታወሳል። ቻይና ሜንግ ዋንዦ በፍጥነት ከእስር እንድትለቀቅ የጠየቀች ሲሆን እስሩም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው ብላለች። የሥራ ኃላፊዋ ተጠርጥረው የታሰሩበት ጉዳይ ምን እንደሆነ ለህዝብ ይፋ አልተደረገም። ሁዋዌም ''ሜንግ አንዳች ስለ ፈጸመችው ስህተት የማውቀው ነገር የለም'' ብሏል። ዛሬ አርብ ፍርድ ቤት ትቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል። • የሁዋዌ ባለቤት ልጅ ካናዳ ውስጥ ታሠረች • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ • የኦሮሞ ፓርቲዎች የጋራ ፎረም ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደረሱ የቻይና እና አሜሪካ የንግድ ጦርነት በተጧጧፈበት ወቅት የሜንግ እሥር ተከትሏል። አርጀንቲና ላይ የጂ-20 ስብሰባ ወቅት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ሺፒንግ በተገናኙበት በዕለተ ቅዳሜ ነበረ ሜንግ ቫንኩቨር ካናዳ ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋለችው። የሜንግ እስር ቻይናን ያስቆጠ ሲሆን በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ጦርነት እንዳያባብሰው ተሰግቷል። ሜንግ በተሳረችበት ወቅት ሲወጡ የነበሩት ሪፖርቶች የእስሩ ምክንያት ምናልባትም ሁዋዌ አሜሪካ ኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ሳይተላለፍ አልቀረም። የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደህንነት አማካሪው ጆን ቦልት ከእስሩ ጋር በተያያዘ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሳይሰጡበት ቀርተዋል። ሜንግ የኩባንያው የፋይናንስ ኃላፊ እና የሁዋዌ መስራች ልጅ ነች። ሜንግ የኩባንያው የፋይናንስ ኃላፊ እና የሁዋዌ መስራች ልጅ ነች ሁዋዌ በዓለማችን ከሚገኙ ግዙፍ የቴሌኮም እቃዎች አቅራቢ ድርጅቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች መካከል አንደኛው ነው። በቅርቡም ከሳምሰንግ ቀጥሎ ትልቁ ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች መሆን ችሏል። የምዕራቡ ዓለም መንግሥታት ቻይና ሁዋዌን ተጠቅማ የስለላ አቅሟን ታዳብራለች ብለው ይሰጋሉ። ሁዋዌ ግን የመንግሥት ጣልቃ ገብነት የለም ይላል። የአሜሪካ ሕግ አርቃቂዎች በተደጋጋሚ ሁዋዌ የአሜሪካ ደህንነት ስጋት ነው እያሉ ይከሳሉ። የጃፓን መንግሥት የቻይና ኩባንያ የሆኑትን ሁዋዌ እና ዜድቲኢ (ZTE) በመረጃ መረብ ደህንነት ስጋት ምክንያት በአገሪቱ ውስጥ አገልግሎት እንዳይሰጡ እገዳ ልታደርግ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ኒው ዚላንድ እና አውስትራሊያ ሁዋዌን ካገዱ ሰነባብተዋል።
news-54554537
https://www.bbc.com/amharic/news-54554537
ቴክኖሎጂ፡ ጉግል ማሳዎችን መከታተል የሚችሉ ሮቦቶችን እየሰራ ነው
የጉግል አባት ድርጅት የሆነው አልፋቤት በማሳ ላይ በመሰማራት የእያንዳንዱን ተክል ሁኔታ መከታተል የሚችሉና የገበሬዎችን ሕይወት ማቅለል የሚችሉ ሮቦቶችን ለሙከራ ማቅረቡ ተሰምቷል።
ሮቦቶቹ ከላይ ሆነው ተክሎቹን መከታተል የሚችሉ ሲሆኑ የተክሎቹን ተፈጥሮአዊ እድገትና ሁኔታ በማይነካ መልኩ ስራቸውን መስራት እንደሚችሉ ተገልጿል። ድርጅቱ እንዳስታወቀው ዋነኛው አላማቸው ተክሎችን በተመለከተ በቂና አስተማማኝ መረጃ መሰብሰብ ነው። የፕሮጀክቱ መሪ የሆኑት ኤሊየት ግራንት ሲናገሩ '' እነዚህ ሮቦቶች የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ወደፊት የሚኖረንን የግብርናዘዴ ዘመናዊ እንደሚያደርገው እምነታችን ነው'' ብለዋል። የምርምር ቡድኑ እንደገለጸው እነዚህን ሮቦቶች ወደ ሙከራ ማሰገባት ያስፈለገው በዓለም ላይ ያለውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍና ዘላቂ በሆነ መልኩ የግብርና ውጤቶችን ለማዳረስ ነው። ነገር ግን አሁን ላይ ገበሬዎችና ትልልቅ የግብርና ድርጅቶች ያሏቸው መሳሪያዎች ይህንን ለማድረግ አላስቻሏቸውም። "እያንዳንዱ ተክል ምን ያክል ውሃና ንጥረነገር እንደሚያስፈልገው ማወቅ ከቻልንና የትኛው የተክል አይነት በየትኛው ቦታ ተመችቶች ያድጋል አልያም ይባዛል የሚለውን ጥያቄ መመለስ ከቻልን ግብርናችንን ውጤታማ በሆነ መልኩ ቀየርነው ማለት ነው'' ይላሉ የፕሮጀክቱ መሪ። ከዚህ በተጨማረም ሮቦቶቹ ስለ አፈርና በአፈር ውስጥ ስላሉ አስፈላጊ ንጥረነገሮች በቂ መረጃ መስጠት የሚችሉ ሲሆን ተክሎቹም ቢሆኑ በምን ያክል ፍጥነት እያደጉ እንደሆነ ማሳየት ይችላሉ። '' ባለፉት ጥቂት ዓመታት በካሊፎርኒያ እና ሶይቢን በሚገኙ የእንጆሪ ማሳዎች ላይ የተሞከሩ ሲሆን ሮቦቶቹ በጣም ጥርት ያለ ምስል ስለተክሎቹ ማግኘት እንድንችል አድርገውናል። ምን ያክል ንጥረነገር እንደተጠቀሙና የጸሀይ ብርሃን ምን ያክል እንደሚያስፈልጋቸውም ጭምር መረጃ ማግነት ችለናል'' ብለዋል። ከነዚህ ሮቦቶች ጋር የሚነሳው አንድ የጎንዮሽ ጉዳት የበይነ መረብ መረጃ ደህንነት ነው። መንግሥታት መረጃው እንዴት እንደሚሰበሰብና ጥቅም ላይ እንደሚውል ማወቅና መቆጠጠር መፈለጋቸው አይቀርም። ድርጅቱ እንደሚለው ከአሁኑ ከአርጀንቲና፣ ካናዳ፣ ደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ ገበሬዎችና ዘር ማዳቀል ላይ ከተሰማሩ ሰዎች ጋር መስራት እንደጀመረም አስታውቋል።
44478995
https://www.bbc.com/amharic/44478995
በሳንፍራንሲስኮ የመጀመሪያዋ ጥቁር ከንቲባ በጠባብ ድምፅ አሸነፈች
ለንደን ብሪድ፣ በሳንፍራሲስኮ የመጀመሪያዋ ጥቁር ከንቲባ ሆነች።
በዚህች ከተማ አፍሪካዊ አሜሪካውያን ቁጥራቸው በጣም አናሳ ነው። አያቷ በድህነት ያሳደጓት ለንደን ብሪድ ለከንቲባነት ለመብቃት በርካታ ኣውጣ ውረዶችን አልፋለች፤ ትልቅም ስኬት ነው ተብሎላታል። የ 43 ዓመቷ ብሪድ በጠባብ የድምፅ ብልጫ በማለፏና ባገኘችው የምርጫ ውጤት ደስተኛ እንደሆነች ገልፃለች። በአሜሪካ ከሚገኙ 15 ትላልቅ ከተሞች ብሪድ ብቸኛዋ ሴት ከንቲባ ነች። ሳንፍራንሲስኮ ቤት አልባ ምንዱባኖች የበዙባት፣ ከድሃ አገራት ጎዳናዎች ጋር የሚስተካከሉ በቆሻሻ የተሞሉ አውራ ጎዳናዎች ያሉባት፣ የቤት ዋጋ ውድነት የሰራተኛውን ክፍል በኑሮ ውድነት ፈትሮ የያዘባት ከተማ ነች። አዲሷ ተመራጭ ከንቲባ ከዚህ በፊት ከተማዋን ያስተዳድሩ የነበሩት ኢድ ሊ ከዚህ አለም በሞት ሲለዩ ተጠባባቂ በመሆን ለአጭር ጊዜ ሰርተዋል፤ ከዛ በኋላ ነው ለቦታው ራሳቸውን በእጩነት ያቀረቡት። ምርጫው ከተደረገ ሳምንት ያለፈው ሲሆን ውጤቱ የዘገየው ተወዳዳሪዎች ያገኙት የድምፅ ልዩነት ጠባብ በመሆኑ የከተማው የምርጫ ቦርድ በሺዎች የሚቆጠሩ የምርጫ ድምፆችን በድጋሚ ለመቁጠር በመገደዱ ነው። የከተማዋ የመጀመሪያ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ከንቲባ የነበሩትና ለምርጫው የተወዳደሩት ማርክ ሌኖ ከ ለንደን ብሪድ ጋር አንገት ለአንገት ተያይዘው የተሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ተቀብለውታል። ሳንፍራንሲስኮን በ1978 ሴት ከንቲባ አስተዳድረዋት የሚያውቁ ሲሆን እኚህ ሴት በአሁን ሰአት የካሊፎርኒያ ሴናተር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።
50298755
https://www.bbc.com/amharic/50298755
ማይክሮሶፍት በሳምንት አራት ቀን ብቻ መሥራት ውጤታማ ያደርጋል አለ
የጃፓኑ የማይክሮሶፍት ቅርንጫፍ ሠራተኞቹ በሳምት አራት ቀን ብቻ እንዲሠሩ ማድረጉን ተከትሎ ሽያጭ በ40 በመቶ ማደጉን ይፋ አድርጓል።
ቶክዮ ውስጥ ሠራተኞች እረፍት ሲወስዱ ሠራተኞች ከወርሀዊ ደሞዛቸው ሳይቀነስባቸው በሳምት አራት ቀን ብቻ ቢሠሩ ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆኑ ለማወቅ ጥናት እየሠራ የነበረው ማይክሮሶፍት፤ ተቀጣሪዎቹ በየሳምንቱ አርብ ቢሮ እንዳይገቡ አድርጎ ነበር። • ሥራ የማዘግየት ልማድን ለመቅረፍ የሚረዱ 8 ነጥቦች • የዘንድሮ ተመራቂዎች እንዴት ሥራ ያገኛሉ? ድርጅቱ የሙሉ ጊዜ ሠራተኞቹን ደሞዝ እየከፈላቸው እረፍት እንዲወስዱም ውሳኔ አሳልፏል። ከዚህ በተጨማሪም ስብሰባ ለ30 ደቂቃ ብቻ እንዲካሄድ፣ ፊት ለፊት ተገናኝቶ ከመወያየት ይልቅ በድረ ገጽ መነጋገር እንዲዘወተርም አድርጓል። ጃፓን በረዥም የሥራ ሰዓት ከሚታወቁ አገሮች አንዷ ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2017 ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው፤ ከጃፓን ተቋሞች አንድ አራተኛው ሠራተኞቻቸውን በወር ከ80 ሰዓት በላይ ያለ ተጨማሪ ክፍያ ያሠራሉ። ማይክሮሶፍት ዘንድሮ የሠራው ጥናት፤ 92 በመቶ ያህል ተቀጣሪዎቹን ያሳተፈ ነበር። • ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት • የዘንድሮው የፈጠራ ሥራ ውድድር አሸናፊዎች ዛሬ ይታወቃሉ ድርጅቱ እንዳለው፤ ጥናቱ ሲካሄድ፤ የኤሌክትሪክ ፍጆታ 23 በመቶ የቀነሰ ሲሆን፤ የወረቀት ህትመት ደግሞ 59 በመቶ አሽቆልቁሏል። ማይክሮሶፍት በቀጣይ ሠራተኞቹ በአግባቡ እረፍት የሚወስዱበት አሠራር የመዘርጋት እቅድ አለው። ከዚህ በተቃራኒው፤ የእንግሊዙ ሌበር ፓርቲ ያሠራው ጥናት በሳምንት አራት ቀን ብቻ መሥራት አዋጭ እንዳልሆነ ያሳያል። የድረ ገጽ መገበያያ አሊባባን የመሰረተው ጃክ ማ፤ "996" የተባለ አሠራር መዘርጋቱ ይታወሳል። ሠራተኞች በቀን ለ12 ሰዓት፣ ለስድስት ቀናት ይሠራሉ።
54136781
https://www.bbc.com/amharic/54136781
ስደት፡ ከአንድ ወር በላይ በባህር ላይ የቆዩ ስደተኞች ጣሊያን እንዲያርፉ ተፈቀደላቸው
ስደተኞቹ ሕይወታችንን እንለውጣለን ብለው ከሊቢያ የተነሱት ከአንድ ወር ከ10 ቀን ገደማ በፊት ነበር።
ታዲያ ሜዲትራኒያን ባህርን ለማቋረጥ የተሳፈሩባት ጀልባ ካሰበችበት ሳትደርስ መስጠም ጀመረች። ይህን ጊዜ ነበር የዴንማርክ የነዳጅ መርከብ 'ማእርስክ ኢቴኔ' ደርሳ ከሞት የታደገቻቸው። የመርከብ ድርጅቱ ስደተኞቹን ካሉበት ሁኔታ እንድናወጣቸው የጠየቁን የማልታ ባለሥልጣናት ናቸው ብለዋል። ማልታ ግን "እኔ ይህንን አላልኩም ፤ ጭራሽ ስደተኞቹንም የታደጓቸው ከእኔ የውሃ ክልል ውጭ ነው" ብላለች። ጣሊያንም ሆነች ሊቢያ ስደተኞቹን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ስደተኞቹ በባህሩ ላይ እንዲቆዩ ተገደዋል ብላለች ማእርስክ። መርከቧ በየትኛውም አገር እንዳያርፍ ፈቃድ ሳታገኝ በመቅረቷም፤ አንድ ነፍሰጡር ሴትን ጨምሮ 27ቱ ስደተኞች 40 ቀናትን በዚያው በባህር ላይ እንዲያሳልፉ ተገደዋል። በመጨረሻም ስደተኞቹ ጣሊያን እንዲያርፉ ተፈቅዶላቸው፤ ቅዳሜ ዕለት ምሽት በሜዲትራኒያን ዳርቻ በምትገኘው ሲሲሊ ደሴት እንዲያርፉ ተደርገዋል ። ሲሲሊ ከጣሊያን 20 ግዛቶች አንዷ ናት። ስደተኞቹ አርብ ዕለት ወደ ሜድትራንያን ሴቪንግ ሂዩማንስ በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጀልባ እንዲዛወሩ ሆኖ ወደ ፖዛሎ ወደብ ተወስደዋል። ስደተኞቹ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ገልጿል። ይህ የሆነውም ግሪክ የሞሪያ የስደተኞች ካምፕ በእሳት መውደሙን ተከትሎ ከ12 ሺህ በላይ ስደተኞችን ለመታደግ እየጣረች ባለችበት ሰዓት ነው። ባለፈው ሳምንት ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅትና ዓለም አቀፉ የመርከቦች ድርጅት ስደተኞቹ እንዲያርፉ ጥሪ አቅርበው ነበር። በተመሳሳይ ባለፈው ወርም ድርጅቶቹ ባደረጉት ጥሪ 353 ስደተኞች በሲሲሊ ደሴት እንዲያርፉ መደረጋቸው ይታወሳል። ሮይተርስ የዜና ወኪል ጠቅሶ በዘገበው መረጃ መሰረት በዚህ ዓመት ብቻ 19 ሺህ 400 ስደተኞች በጣሊያን ወደቦች ላይ እንዲያርፉ የተደረገ ሲሆን፤ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 5 ሺህ 200 ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ ነው። በተያዘው ዓመት ከሰሜን አፍሪካ 40 ሺህ ስደተኞች ባህር አቋርጠው አውሮፓ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስታውቋል። ከ400 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሞተዋል አሊያም የገቡበት አልታወቀም።
news-52977085
https://www.bbc.com/amharic/news-52977085
"የምር በጆርጅ ፍሎይድ ሞት ታዝናላችሁ እንዴ?" የክሮስፊት ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ
ክሮስፊት ዓለም አቀፍ የስፖርት ትጥቆችና ቁሶችን አምራችና ቸርቻሪ ኩባንያ ነው፡፡ ከሰውነት ማጎልመሻ ጋር የተያያዙ ንግዶች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡
የዚህ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ሰው በጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ላይ ተሳልቀዋል፡፡ ሥራ አስፈጻሚው ሚስተር ግሬግ ግላስማን ይባላሉ፡፡ በዚህ መረን በለቀቀ ድርጊታቸው ውግዘት ከደረሰባቸው በኋላ ነው ሥራቸውን ለመልቀቅ የተገደዱት፡፡ እኚህ ሰው በጆርጅ ፍሎይድ ሞት ላይ ከተዘባባቱ ወዲህ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያወጣል የሚባልለት ኩባንያቸው ጋር የሥራ ግንኙነት ያቋረጡ በርካታ ዓለም አቀፍ መደብሮች ናቸው፡፡ ሰውየው ሥራቸውን የለቀቁት በቴክሳስ የፍሎይድ ቀብር ሥነ ሥርዓት በተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ እኚህ ሰው መልቀቂያ ባስገቡበት ደብዳቤያቸው "ሳት ብሎኝ በተናገርኩት ነገር ብዙ ሰዎችን አስቀይሚያለሁ፤ የኔ ንግግር ቢዝነሱን እንዲጎዳ ስለማልሻ ጡረታ ለመውጣት ወስኛለሁ "ብለዋል፡፡ እርሳቸውን የተካው ዴቭ ካስትሮ፣ ድርጅታችን ክሮስፊት "ራሱን አንድ ጥላ ሥር የተሰባሰበ ቤተሰብ የሚመለከት፣ ብዝኃነኃነትን የሚቀበል የብዙኃን ድርጅት ነው፤ አባሎቻችንን አስቀይመናል›› ብሏል፡፡ ሚስተር ግላስማን ይህን እጅግ ሀብታም ኩባንያቸውን የመሰረቱት በካሊፎርኒያ የ2ኛ ደረጃ ተማሪ ሳሉ በወላጆቻቸው መኪና ማቆምያ ውስጥ ምርት በመጀመር ነበር፡፡ አሁን ኩባንያቸው ሰፈርቶና ጎምርቶ 13ሺህ ከሚሆኑ አለማቀፍ መደብሮች ጋር ይሰራል፡፡ ሚስተር ግላስማን ቅዳሜ ለታ በትዊተር ሰሌዳቸው የጻፉት ነገር ነው ቁጣን የቀሰቀሰባቸው፡፤ አሜሪካ ዘረኝነት የኅብረተሰብ ጤና ቀውስ ነው የሚባለውን አባባል ተንተርስው በትዊተር ሰሌዳቸው "ኮቪድ-19" የሚለውን "ፍሎይድ-19" ብለው በሟቹ ጥቁር አሜሪካዊ ላይ ለማሾፍ መሞከራቸው ነው መጀመርያ ችግር የፈጠረው፡፡ ከዚያም አልፈው ከርሳቸው ጋር በሽርክና የሚሰሩ ኩባንያዎች ስለምን ክሮስፊት በዚህ ግድያ ላይ ዝምታን መረጠ ብለው ሲጠይቋቸው " ለዚህ ለጆርጅ ፍሎይድ ሞት የምር ታዝናላችሁ እንዴ? እኔም ሆንኩ የኔ ባልደረቦች ግን በጭራሽ ግድ አልሰጠንም" ብለው ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ከርሳቸው ድርጅት ጋር የሚሰሩ ኩባንያዎች የሥራ ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል፡፡ ይህን እርምጃ ከወሰዱት ውስጥ ዝነኛውን የስፖርት ትጥቅ፣ ሪቡክን (Reebok) የሚያመርተው አዲዳስ (Adidas) ይገኝበታል፡፡
50084810
https://www.bbc.com/amharic/50084810
በፍራሹ ስር 137ሺ ብር ያስቀመጠው ኬንያዊ ገንዘብ ከመቀየሩ ጋር ተያይዞ ከሰረ
ኬንያ የመገበያያ ገንዘብ መቀየሯን ተከትሎ አንድ ግለሰብ 137 ሺ ብር (4ሺ 800 ዶላር) ከጥቅም ውጭ ሆኖበታል።
ጁሊየስ ኦዲንጋ ምቦጋ የተባለው ግለሰብ 137 ሺ ብር የሚገመት ባለ አንድ ሺ የኬንያ ሺልንግ ገንዘብ ፍራሹ ስር አስቀምጦ የነበረ ሲሆን ገንዘብ ለመቀየር የተቀመጠበት ቀነ ገደብም በማለፉ ነው ለዓመታት ያጠራቀመው ገንዘብ ከጥቅም ውጪ የሆነበት። •ኬንያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከሰባት ቢሊዮን ሺልንግ በላይ ጥቅም አልባ ሆነ •ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት የገንዘብ ቅየራው በሃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስቀረትና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንም ለመቆጣጠር እንዲያስችል እንደሆነ ተገልጿል። ግለሰቡ ከመንደሩ ሲያያ ግዛት ስልሳ ኪ.ሜትር ርቀት በሚገኘው የማዕከላዊ ባንክ በመገኘት አሮጌ የመገበያያ ገንዘቡን በአዲስ መልኩ ለመቀየር ሙከራ ቢያደርግም የገንዘብ መቀየሪያ ቀነ ገደቡ መጠናቀቁን ተከትሎ ለኪሳራ ተዳርጓል። •"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመካኒክነት ስራ ሲተዳደር የነበረው ግለሰብ ለጡረታ ብሎ ያጠራቀመው ገንዘብ እንደሆነም ለደይሊ ኔሽን ተናግሯል። የማዕከላዊ ባንክ አስተዳደር እንዳሳወቁት አዲስ የመገበያያ ገንዘብ የታወጀው ሰኔ አንድ ቀን ሲሆን ከመስከረም ሃያ ጀምሮ አሮጌው የመገበያያ ገንዘብ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። •"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ አፍሪካ ታክስ ጀስቲስ ኔትወርክ የተባለ ድርጅት እንዳሳወቀው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ኬንያ በየአመቱ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደምታጣ አስታውቋል። ባንኩ እንዳስታወቀውም የገንዘብ ቅይይሩ መሳካቱንና ከዚህ በኋላ ስርአት ባለው መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው።
news-51894636
https://www.bbc.com/amharic/news-51894636
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮናቫይረስ ነጻ ሆነው ተገኙ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ በተደረገላቸው ምርመራ ከበሽታው ነጻ ሆነው እንደተገኙ የጽህፈት ቤታቸው ሐኪም አስታወቁ።
ሾን ኮንሊይ ከሰዓታት በፊት ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት "ነጻ መሆናቸውን የሚያመለክተውን የፕሬዝዳናቱን የምርመራ ውጤት ቅዳሜ ምሽት ተቀብያለሁ" ሲሉ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምርመራ የተደረረገላቸው ከመካከላቸው የተወሰኑት የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ከብራዚል ልኡካን ጋር ፍሎሪዳ ውስጥ ከተገናኙ በኋላ ነው። በሽታው ከተገኘባቸው የልኡኩ አባላት መካከል የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ረዳት የሆኑ ግለሰብም ይገኙበታል ተብሏል። "ትራምፕ ከብራዚል የልኡካን ቡድን ጋር ከነበራቸው የዕራት ፕሮግራም ከሳምንት በኋላ በተደረገላቸው ምርመራ ከበሽታውና ከበሽታው ምክልቶች ነጻ ሆነው ተገኝተዋል" ሾን ኮንሊይ ተናገረዋል። የ73 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከልኡካን ቡድኑ ጋር ከተገናኙ በኋላ ምንም አይነት የበሽታው ምልክት አልታየብኝም በማለት እራሳቸውን ከሌሎች ለይተው አላቆዩም ነበር። ነገር ግን ዋይት ሐውስ ውስጥ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቀረበላቸውን ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ተከትሎ ምርመራ እንደሚያደርጉ ተናግረው ነበር። የአሜሪካ መንግሥት እንደሚያዘው ከሆነ በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ለ14 ቀናት እራሳቸውን ለይተው በቤታቸው ውስጥ መቆየት አለባቸው። አሜሪካ ውስጥ እስካሁን ከ2,700 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 54 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ህይወታቸውን አጥተዋል። አርብ ዕለት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሽታውን ለመዋጋት የሚያስችል የ50 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ለመፍቀድ የሚያስችላቸውን ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግገዋል። በዓለም ዙሪያ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት በተጨማሪ ሌሎች መሪዎችና ፖለቲከኞችም በበሽታው ተይዘዋል የሚል ጥርጣሬ በመፈጠሩ ምርመራና እራስን ለይቶ የማቆየት እርምጃ እየወሰዱ ነው። ባለፈው ሳምንት የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ባለቤታቸው በበሽታው ተይዘው በመገኘታቸው እራሳቸውን ለሁለት ሳምንታት ለይተው እንደሚያቆዩ አሳውቀዋል። ስፔን ውስጥ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፔድሮ ሳንቼዝ ባለቤት በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል። ባልና ሚስቱ ማድሪድ ውስጥ በሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት ውስጥ በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል። ስፔን ከጣሊያን በመቀጠል አውሮፓ ውስጥ በሽታው ክፉኛ ያጠቃት አገር ናት። በተጨማሪም የታላቋ ብሪታኒያ የጤና ሚኒሰትርና የወግ አጥባቂው ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑት ናዲን ዶሪስ በተደረገላቸው ምርመራ ኮሮናቫይረሱ ስለተገኘባቸው በቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን ለይተው ይገኛሉ። ቀደም ሲልም የኢራን ምክትል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የሆኑት ኢራጅ ሐሪርቺ በበሽታው እንደተያዙ ተረጋግጧል። ኢራን በቫይረሱ ክፉኛ ከተጠቁት አገራት መካከል የምትጠቀስ ስትሆን እስካሁን ከ600 በላይ ሰዎች በበሽታው ለሞት ተዳርገዋል።
51625625
https://www.bbc.com/amharic/51625625
በ30 የኢትዮጵያ ወረዳዎች የኩፍኝ ወረርሽኝ መከሰቱ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በ30 የኢትዮጵያ ወረዳዎች የኩፍኝ ወረርሽኝ መከሰቱን ገለፀ። እስካሁን ድረስ አምስት ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል።
ሦስቱ የሞቱት ሰዎች ወረርሽኙ በተከሰተባቸው 30 ወረዳዎች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝት እና ምላሽ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ 30ዎቹ ወረዳዎች በስድስት ክልሎች የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል። እነዚህም ክልሎች ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ አፋር፣ ሶማሊ እና ትግራይ መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል። ኃላፊው ለቢቢሲ እንደገለፁት፤ ወረርሽኙ የተከሰተባቸው ወረዳዎች የሚገኙት በገጠራማ የክልሎቹ አካባቢ ነው። • የኮቢ ብራያንት ባለቤት የተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ባለቤትን ከሰሰች • ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ሲቋረጥ ምን ይከሰታል? • የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝደንት ሆስኒ ሙባረክ ሞቱ በወረርሽኙ የተጎዱት አብዛኛዎቹ ወረዳዎች የሚገኙት ደግሞ በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልል መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል። አቶ መስፍን ጨምረው እንዳሉት፤ ወረርሽኙ የተከሰተባቸው አካባቢዎች የክትባት ስርጭቱ ደካማ የሆነባቸው ናቸው። እንደ ዳይሬክተሩ ከሆነ በዚህ ሳምንት ብቻ 228 በኩፍኝ የተያዙ ሰዎች መመዝገባቸው ታውቋል። የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኩፍኝ ወረርሽኝ የተከሰተው ባለፈው ሕዳር ወር ላይ ነው። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች በኩፍኝ ምክንያት የሰዎች ሕይወት ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል። በወቅቱ በርካቶች በወረርሽኙ መያዛቸውንና በአንዳንድ ቦታዎች መቀስቀሱን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር በየነ ሞገስ ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። እርሳቸው እንደሚሉት በሶማሌ ክልል ላይ በዋናነት ሸበሌ፣ ሊበንና ጃረር የሚባሉ ዞኖች ላይ ወረርሽኙ መከሰቱን ገልፀው በኦሮሚያ ክልል ደግሞ ባሌ ላይ መዛመቱን ገልፀው ነበር። በዓለም ዙሪያ በኩፍኝ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በ2018 ብቻ ከ140 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን የተደረገ ጥናት አመልክቶ ነበር። ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት መሆናቸውም ተነግሯል። የጤና ባለሙያዎች ስለዚህ ክስተት ሲገልጹ፤ በቀላሉ በክትባት መከላከል የሚቻል በሽታ የሰዎችን ሕይወት መቅጠፍ መጀመሩ በጣም አስደንጋጭና አሳሳቢ ነው ብለውታል።
news-45328013
https://www.bbc.com/amharic/news-45328013
ኮሌራን የሚቆጣጠር ኮምፕዩተር ተሰራ
በቅርቡ የተሰራው የፈጠራ ውጤት በየመን የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቆጣጠር አስችሏል። ይህም የሆነው ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት መተንበይ በመቻሉ ነው።
ባለፈው ዓመት ብቻ በየመን 50 ሺህ ሰዎች በኮሌራ በሽታ ተጠቅተው ነበር። በዚህ ዓመት፤ ኮምፕዩተሩ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ ግን ቁጥሩ ወደ 2500 ዝቅ ብሏል። አዲሱ የመተንበያ ኮምፕዩተር የእርዳታ ሰጪ ሰራተኞችን ስራ በእጅጉ ያቀለለ ሲሆን፤ የዝናብ ሂደትን በመከታተል ወረርሽኙ ከመከሰቱ ከሳምንታት በፊት መረጃው እንዲደርሳቸው ይረዳል። የቅድመ መከላከል ስራዎችን በአፋጣኝ ለማከናወን እጅግ ወሳኝ ፈጠራም ነው ተብሎለታል። ባለፈው ዓመት በየመን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከውሃ ወለድ በሽታዎች ጋር በተያያዘ ታመው ነበር። ከእነዚህ ውስጥ ከሁለት ሺ በላይ የሞቱ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ ደግሞ ህጻናት ናቸው። • የመዋቢያ ምርቶች ውስጥ መርዛማ ንጥረ-ነገሮች ተገኙ ቁጥሩ በአለማችን ከፍተኛው ተብሎ የተመዘገበ ሲሆን፤ በየመን የተከሰተው የእርስ በእርስ ጦርነት የውሃ ፍሳሽና የንጽህና አገልግሎት መስጫዎችን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ አድርጓቸዋል። ትንበያው እንዴት ይሰራል? የዝናብና የአየር ንብረት ትንበያ ባለሙያዎች በመጀመሪያ እጅግ የተራቀቀ የተባለውን ኮምፕዩተር በመጠቀም እስከ 10 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ባሉ ቦታዎች ምን ያክል ዝናብ የትኞች ላይ እንደሚዘንብ ይተነብያሉ። እነዚህ ቁጥሮች የውሃ መውረጃዎች ውስጥ የሚገባው ውሃ ምን ያክል እንደሆነ ለማወቅና የወረርሽኙን መነሻ ለመለየት እጅግ ጠቃሚ ናቸው። • አፍሪካዊው ወጣት ለወባ በሽታ መፍትሄ ይዞ መጥቷል • ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል የሚረዱ ዘጠኝ ሚስጥሮች ከትንበያው የተገኙትን መረጃዎች በአካባቢው ካለው የህዝብ ቁጥር፤ የንጹህ ውሃ አቅርቦትና የአየር ጸባይ ጋር በማወዳደር የትኞች አካባቢዎች ላይ የኮሌራ ወረርሽኝ ሊነሳ እንደሚችል ማወቅ ይቻላል። በመቀጠል የሚወሰደው እርምጃ የንጽህና አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችን፤ መድሃኒትና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ቀድሞ ወደ ቦታው ሟጓጓዝ ነው። ለአካባቢው ነዋሪዎችም የቅድመ ጥንቃቄ ስልጠና መስጠትና እንዲዘጋጁ ማድረግ ደግሞ ይቀጥላል። ውጤቱም ገና ከአሁኑ እየታየ ነው፤ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከወረርሽኙ መከላከል የተቻለ ሲሆን፤ በየመን እየተሰራ ያለውን ስራም ወደ ሌሎች ቦታዎች ለማዳረስ እየታሰበ ነው። በመላው ዓለም እስከ 30 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በየዓመቱ በኮሌራ ምክንያት ይሞታሉ። በዋነኛነት በወረርሺኙ የሚጠቁቱ ደግሞ አፍሪካውያንና ደቡብ እስያ አካባቢ የሚገኙ ሃገራት ናቸው። • ለአንድ ወር ከአልኮል መታቀብ የሚኖረው አስደናቂ ውጤት
news-56356816
https://www.bbc.com/amharic/news-56356816
ትግራይ፡ አሜሪካ ትግራይ ውስጥ "የዘር ማፅዳት ወንጀል" ተፈጽሟል አለች
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ሕዝብ "የዘር ማፅዳት ወንጀል" (ኤትኒክ ክሊንሲንግ) መፈጸሙን ተናገሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን በትናንትናው ዕለት ለአገሪቱ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ቀርበው ማብራሪያ ባቀረቡበት ወቅት ትግራይ ውስጥ እየተፈፀመ ነው ያሉትን "የዘር ማፅዳት ወንጀል ከማውገዝ" በተጨማሪ "ሙሉ ተጠያቂነት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል። በክልሉ እየደረሰ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎች ላይ ተዓማኒ መረጃዎች አሉ ያሉት አንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን ከማስቆም በተጨማሪ የጎረቤት አገር ኤርትራ ወታደሮችና የአጎራባቹ ክልል አማራ ሚሊሺያ እንዲወጡም ጠይቀዋል። "በትግራይ ክልል ውስጥ ከኤርትራ የመጡ የውጭ አገር ሠራዊት አባላት አሉ እንዲሁም ከአጎራባቹ ክልል አማራ ክልል የገቡ ወታደሮች አሉ። እነዚህ ኃይሎች ሊወጡ ይገባል" በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተጠቀሱት ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡና ተኩስ አቁም እንዲደረግ በመጠየቅ መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በሰጠው ምላሽ "እንደ ሉዓላዊት አገር ይህ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ኃላፊነት ነው" ያለ ሲሆን፤ "ኢትዮጵያ በግዛቷ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የትኛውንም የጸጥታ መዋቅር ማሰማራት የመንግሥት ኃላፊነት ነው" ብሏል በመግለጫው። በትናንትናው ዕለት ከምክር ቤቱ ኮሚቴ በክልሉ "የሰላም አስከባሪዎች ሊሰማሩ ይችላሉ" ተብሎ በቀረበላቸውም ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአካባቢው ሊኖር የሚገባ የፀጥታ ኃይል ኃይል ምን መምሰል እንደሚገባው አስረድተዋል። "በአካባቢው መሰማራት ያለበት የፀጥታ ኃይል የትግራይ ነዋሪዎችን ሰብዓዊ መብት የማይጥስ መሆን አለበት። ወይም በምዕራብ ትግራይ እንዳየነው የዘር ማፅዳት ወንጀል የማይፈፅም ሊሆን ይገባዋል። ይህም ሊቆም ይገባል" ብለዋል። "በአካባቢው የተፈፀሙትን ጥሰቶች ለማጣራት ነፃ የሆነ ምርመራ እንዲደረግ" ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም "አገሪቱ በፖለቲካው ወደፊት እንድትራመድ ለማስቻል የእርቅ ሂደትን አስፈላጊነትም" ጠቅሰዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር በተደጋጋሚ በስልክ መወያየታቸውን የጠቀሱት ብሊንከን "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በህወሓት ላይ ያላቸውን ስጋት እጋራለሁ፤ ነገር ግን በትግራይ ላይ እየተፈፀመ ያለው ነገር ተቀባይነት የለውም ሊቀየር ይገባል" ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተያየት ባይሰጥም ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ "ተፈፅመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር እርምጃዎችን መንግሥታቸው መውሰዱን" ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። በመግለጫቸው ምርመራ ለማካሄድም አስፈላጊ ናቸው ከተባሉ የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ መሆናቸውን ጠቁመዋል። አምነስቲና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ጨምሮ እንዲሁም የአይን እማኞች የኤርትራ ሠራዊት በክልሉ ላይ የዘፈቀደ ግድያዎችን፣ መደፈሮችንና ሌሎች ጥሰቶችን እያካሄደ መሆኑን ይናገራሉ ። ይህንን ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ የኤርትራ መንግሥት አይቀበሉትም። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ሚሼል ባሽሌት ባለፈው ሳምንት በክልሉ እየተፈፀመ ያለው ጥሰት "የጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል" ተደርጎ ሊቆጠር እንደሚችል መናገራቸው የሚታወስ ነው። በዚህም የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጸሙ የተባሉትንና እንደ ጦር ወንጀል ሊቆጠሩ የሚችሉ ሪፖርት የተደረጉ የጅምላ ግድያዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ወሲባዊ ጥቃቶችን ለመመርመር እንዲችል ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል። ከሰሞኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከትግራይ ክልል ግጭት ጋር በተያያዘ የተነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንና ግድያዎችን በተመለከተም መንግሥት ከፌደራል ፖሊስ፣ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመጣመር ይመረምራል ብለዋል። ጨምረውም የእነዚህን አካላት ምርመራ መሰረት በማድረግም መንግሥታቸው በድርጊቱ ውስጥ እጃቸው ያለበትን አካላት ወደ ፍትህ እንደሚያቀርብ አፅንኦት ሰጥተው፤ በምርመራው ላይ ተጨማሪ እርዳታ ካስፈለገ መንግሥት የውጭ አካል ሊጋብዝ እንደሚችል ጠቆም አድርገዋል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት በመፈፀሙ መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ወታደራዊ ዘመቻን ማካሄዱን ገልጿል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን ቢገልጽም በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከፍተኛ ኮሚሽነሯም በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ትግራይ ጦርነቱ መቀጠሉንም መረጃ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።
news-53915678
https://www.bbc.com/amharic/news-53915678
ሩሲያ፡ "ቭላድሚር ፑቲን ተቃዋሚያቸው አሌክሴ ናቫልኒን አላስመረዙትም"
ቭላድሚር ፑቲን ተቃዋሚያቸው አሌክሴ ናቫልኒን አስመርዘውታል የሚለውን ክስ የክሬምሊን ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ 'መሰረተ ቢስ' ብለውታል፡፡
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ክሱ ከእውነት የራቀ ከመሆኑም በላይ ከጉዳይ የምንጽፈውም እንኳን አይደለም ብለዋል፡፡ የጀርመን ሐኪሞች አሌክሴ እንደተመረዘ ፍንጭ መስጠታቸውን ተከትሎ ቃል አቀባዩ ለምን ለድምዳሜ አስቸኮላቸው ብለዋል፡፡ አሌክሴ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ነበር ከቶምስክ ወደ ሞስኮ በአውሮፕላን በመብረር ላይ ሳለ ታሞ ራሱን የሳተው፡፡ በኋላ እሱ የተሳፈረበት አውሮፕላን ኦምስክ የተሰኘች የሩስያ ከተማ እንዲያርፍ ተደርጎ በሳይቤሪያ ሆስፒታል የሕክምና እርዳታ ሲያገኝ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ጀርመንና ፈረንሳይ የተሻለ ሕክምና እንደሚያደርጉለት በመሪዎቻቸው በኩል መግለጻቸውን ተከትሎ አሌክሴ ወደ በርሊን በአውሮፕላን አምቡላንስ ተወስዷል፡፡ አሁን ሕክምናውን እየተከታተለ የሚገኘውም በዕውቁ ሻርሌት ሆስፒታል ነው፡፡ አሁንም ድረስ ራሱን ስቶ የሚገኝ ቢሆንም ሐኪሞች ያለበት ሁኔታ ለስጋት አይሰጥም ብለዋል፡፡ የአሌክሴ ደጋፊዎች እንደሚገምቱት አውሮፕላን ከመሳፈሩ በፊት በዚያው በአየር ጣቢያ አንድ ካፌ ውስጥ ሻይ ሲጠጣ ነበር፤ የተመረዘውም ያን ጊዜ ነው፡፡ የሻርሌት ሆስፒታል ሐኪሞች አሌክሴ ሕይወቱ እንደሚተርፍ ቢናገሩም የጤና ጉዳት ከፍ ያለ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ መመረዙንም አረጋግጠዋል፡፡ የሩሲያ የታችችኛው ምክር ቤት አፈ ኡባኤ ቪያቼስላቭ ቮሎሲን አንድ ኮሚቴ የአሌክሴን ጉዳይ እንዲመረምር አዘዋል፡፡ ጉዳዩን እንዲመረመር ያዘዙት ግን ፑቲን አድርገውታል ወይ የሚለውን ለማጣራት ሳይሆን የውጭ ኃይሎች በሩሲያ ብጥብጥና አመጽ ለመቀስቀስ ያደረጉት ሳይሆን አይቀርም ከሚል ጠንካራ እሳቤ ተነስተው ነው፡፡ አሌክሴ አሁን 44 ዓመቱ ነው፡፡ በሩሲያ ገናና እየሆነ የመጣው የፑቲን ሰዎችን ሙስና በማጋለጡና አይነኬ የሚባሉትን ቭላድሚር ፑቲንን በመጋፈጡ ነበር፡፡ አሌክሴ ቭላድሚር ፑቲን የሚመሩትን ዩናይትድ ፓርቲ የተሰኘውን ገዥ ፓርቲ 'የሌቦችና ቀጣፊዎች መሸሸጊያ' ሲል ይጠራዋል፡፡ ለበርካታ ጊዜ ለእስር የተዳረገው አሌክሴ ፑቲንን ገፍቶ መቃወሙ ለሕይወቱ አስጊ እንደሚሆን ሲጠበቅ ነበር፡፡ በሩሲያ ተቃዋሚዎችን፣ የምርመራ ጋዜጠኞችን እና የሰብአዊ መብት አቀንቃኞችን የማፈን፣ የማሰር እንዲሁም የመመረዝ ሁኔታ በተደጋጋሚ ተከስቶ ያውቃል፡፡ ክሬምሊን በተለይም ከፍተኛ ድጋፍ ያገኙ ተቃዋሚዎችንና የቀድሞ ሰላዮችን፣ እንዲሁም ወደ ምዕራብ አገራት የከዱ ቁልፍ ዜጎቿን በመርዝ ኤጀንት እንደምትመርዝ የቅርብ ጊዜ ታሪኮች ይመሰክራሉ፡፡ የክሬምሊን ቃል አቀባይ በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ተጠይቀው፣ ‹ይሄ ቀልድ ነው፤ እኛ የምር አድርገንም አንወስደውም› ሲሉ መልሰዋል፡፡ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንግላ ሜርክል ባለፈው ሰኞ ሩሲያ የአሌክሴን ጉዳይ በገለልተኛ አካል እንድታጣራ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ ዩናይትድ ኪንግደምም በተመሳሳይ ግልጽና ተአማኒ ምርመራ ይደረግ ብላለች፡፡ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ሚስተር ፔስኮቭ ግን ምርመራ የምንጀምረው መጀመርያ አሌክሴ መመረዙን ስናረጋግጥ ነው፡፡ መቼ ተመረዘና ? ብለዋል፡፡
news-53511868
https://www.bbc.com/amharic/news-53511868
የኮሮናቫይረስ መድኃኒትን ከአፍሪካ ባሕላዊ መድኃኒቶች ለመፈለግ ቡድን ተቋቋመ
ለኮሮናቫይረስ የሚሆን መድኃኒትን ከባሕላዊ መድኃኒቶች ለማግኘት የሚደረግ ጥረትን የሚደግፍና የሚያማክር ኮሚቴ በዓለም ጤና ድርጅት እና በአፍሪካ የበሽታ መከላከያ ማዕከል አማካይነት ተቋቋመ።
በአፍሪካ ውስጥ የተለያዩ ባሕላዊ የኮቪድ-19 መድኃኒቶች እንዳሉ ቢነገርም ፈዋሽነታቸው ግን አልተረጋገጠም በኮሚቴው ውስጥ የሚሳተፉት ባለሙያዎች የአፍሪካ አገራት ባሏቸው ባሕላዊ መድኃኒቶች ዙሪያ በሳይንስ፣ ደኅንነታቸውን የተጠበቀ በማድረግና በጥራት በኩል እንደሚያማክሩ ተገልጿል። ይህ ባሕላዊ መድኃኒቶችን ለኮሮናቫይረስ ለማዋል የሚደረገውን ጥረት የሚደግፈው ኮሚቴ አገራት በመድኃኒቶቹ ላይ በሚያደርጉት ሙከራ ወቅት አስፈላጊውን ዓለም አቀፋዊ የጥራት ደረጃዎችን የጠበቁ እንዲሆኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከዓለም ጤና ድርጅት የወጣው መግለጫ ገልጿል። "ዓለም ለኮሮናቫይረስ የሚሆን የመከላከያ ክትባት እና የፈውስ መድኃኒት ለማግኘት በምትጥርበት ወቅት፤ በባሕላዊ ህክምናው ዘርፍ ያለውን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም የሚደረገው ጥረት ሳይንስን መሰረት ያደረገ መሆን ይገባዋል" ሲሉ የአፍሪካ አካባቢ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ማሲዲሶ ሞይቲ መናገራቸውን መግለጫው አመልክቷል። ይህ የባለሙያዎች ኮሚቴ የተመሰረተው ከተለያዩ እጸዋት ተዘጋጀውን የኮቪድ-19 መድኃኒት ነው በማለት በስፋት ስታስተዋውቅ የነበረችው ማዳጋስካር በበሽታው የተያዙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህሙማን ማግኘቷን ተከትሎ ነው። በዚህ በማዳጋስካር ተገኘ በተባለው የኮሮናቫይረስ መድኃኒት ላይ የናይጄሪያ ተመራማሪዎች ፍተሻ አድርገው በእርግጥ ወረርሽኙን የመፈወስ ይዘት ማግኘት እንዳልቻሉ በዚህ ሳምንት አሳውቀዋል። የማዳጋስካሩ ፕሬዝደናት ሳይቀሩ ስለመድኃኒቱ ፈዋሽነት በመገናኛ ብዙሃን ላይ ቀርበው ተደጋጋሚ ማብራሪያ የሰጡ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ የአገሪቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች በበሽታው መያዛቸውና ሁለት ደግሞ መሞታቸው የመድኃኒቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ ከቶታል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ደግሞ ወረርሽኙ በሕዝቡ ውስጥ ተዛምቶ በየዕለቱ በርካታ ማዳጋስካራዊያን በበሽታው መያዛቸው ከመነገሩ በተጨማሪ የህክምና ተቋማት እየጨመረ በሚሄድ ከአቅማቸው በላይ በሆነ የህሙማን ቁጥር እየተጨናነቁ ነው ተብሏል።
45328930
https://www.bbc.com/amharic/45328930
በዓመቱ ፖለቲካዊ ያለመረጋጋት ለኢንስቨትመንት ደንቃራ ሆኖ ነበር ተባለ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር በላቸው መኩሪያ ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ በፅሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ከአንድ ወር በፊት የተጠናቀቀው የ2010 የበጀት ዓመት ለኮሚሽኑ በብዙ ረገድ "በጣም ፈታኝ ግን ደግሞ ውጤታማ ነበር" ብለዋል።
በ2010 የበጀት ዓመት በኢንቨስትመንት ፍሰት 4.6 ቢሊዮን ለማምጣት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ማሳካት የተቻለው መጠን ግን 3.75 ቢሊዮን ዶላር ነው እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተስተዋሉ ያለመረጋጋቶች በኢንቨስትመንት ላይ "ከፍተኛ ጫና አሳድረዋል።" የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ዕቃን ወደ አገር ውስጥ ከማስገባት እና ማስወጣት ጋር በተያያዘ ያለው የማጓጓዣ ፍጥነት (ሎጅስቲክስ) ችግር ሌሎች ፈተናዎች ነበሩም ተብለው በኮሚሽነሩ ተጠቅሰዋል። • በሰኔ 16ቱ ፍንዳታ ጥቅም ላይ ከዋለው ቦምብ ጋር የሚመሳሰል ቦምብ በተጠርጣሪ ቤት ተገኘተፅዕኖው በኢንቨስትመንት ፍሰት ረገድ በቀዳሚው የ2009 የበጀት ዓመት ከነበረው በታየው መጠነኛ መቀነስ ይገለፃል የሚሉት ኮሚሽነሩ በተጠቀሰው ዓመት የነበረው የኢንቨስትመንት ፍሰት መጠን 4.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደነበረ ያስታውሳሉ። በ2010 የበጀት ዓመት በኢንቨስትመንት ፍሰት 4.6 ቢሊዮን ለማምጣት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ማሳካት የተቻለው መጠን ግን 3.75 ቢሊዮን ዶላር ነው።እንደዚያም ቢሆን እንደኮሚሽነር በላቸው በዓመቱ ውስጥ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፤ በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ሥራ እንዲቀጥሉ በማገዝ እና መተማመንን በመፍጠር ረገድ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል። በበጀት ዓመቱ ከ270 በላይ የውጭ ባለሃብቶች ፈቃድ የተሰጠ ሲሆን ባለሃብቶቹ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ኢንቨስት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዓመቱ ኮምቦልቻ እና መቀሌ ፓርኮች ሥራ መጀመራቸው ከኮሚሽኑ ስኬቶች መካከል እንደሚጠቀሱ ያወሱት ኮሚሽነር በላቸው አሁን በአገሪቱ ውስጥ ስራ በጀመሩ ስድስት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሃምሳ ሃምስት ሺህ ለሚጠጉ ሠራተኞች ስራ ተፈጥሯል ብለዋል። • እነ አንዷለም አራጌ ህይወት እንደገና ኮሚሽኑ የማምረቻ ዘርፍ እ.ኤ.አ በ2025 ከአገሪቱ ዓመታዊ ጠቅላላ ምርት ሃያ በመቶ ድርሻ እንዲኖረው ዕቅድ ያለው ሲሆን የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ይሄንን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ያግዘኛል ብሎ ያስባል። በአሁኑ ወቅት ዘርፉ በዓመታዊ አጠቃላይ ምርት ውስጥ ያለው ድርሻ አምስት በመቶ አይሞላም። ከኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ምርቶችን ወደ ውጭ አገር በመላክ ወደ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል።በአዲሱ የ2011 የበጀት ዓመት የኢንቨስትመንት አዋጁን የማሻሻል ዕቅድ እንዳለ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ማሻሻያዎቹ በአንድ በኩል ኢትዮጵያ መንግስታዊ የልማት ተቋማትን ወደ ግል ለማዛወር ከያዘችው ውጥን ጋር የሚያያዙ ሲሆኑ በሌላ በኩል ለባለሃብቶች የሚሰጡ ማትጊያዎች አፈፃፀምን መሠረት ያደረጉ ናቸው። እየተሻሻለ ባለው የአሰሪና ሠራተኛ ህግ የዝቅተኛ ደሞዝ ወለል ጉዳይ እንደሚካተት የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ ይህ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ከኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ክፍያ ዝቅተኛነት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ቅሬታዎች መፍትሄ ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ አክለው ተናግረዋል። • የውጪ ሀገር ጥሪዎች ለምን በኢትዮጵያ ቁጥር ይወጣሉ?
news-49943843
https://www.bbc.com/amharic/news-49943843
የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚና የዜማ ደራሲ ኤልያስ መልካ አረፈ
የኤሊያስ መልካ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኞ እንደሚፈፀም የሙዚቃ ባለሙያው አቶ ዳዊት ይፍሩ ለቢቢሲ ተናገሩ። የቀብር ሥነ ሥርዓቱንም ለማስፈፀም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
አቶ ዳዊት እንዳሉት ቀብሩ የሚፈፀመው ሰኞ 9 ሰዓት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን በቅድሚያ ግን አስክሬኑ ኤልያስ ሙዚቃን ወዳጠናበት የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተወስዶ የክብር ሽንት ይደረግለታል ብለዋል። የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት ሰርፀ ፍሬ ስብኀት የሚመሩት ኮሚቴ በመንግሥት በኩል ያሉ ቀብሩን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ለማስፈፀም እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት በቀብሩ ላይ ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል። • ከነፍስ የተጠለሉ የዘሪቱ ከበደ ዜማዎች የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ጊታሪስት የሆነው ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ የተሰማው ዛሬ ማለዳ ነበር። ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስኳር እና ኩላሊት ህመም ገጥሞት ህክምናውን ሲከታተል መቆየቱን የቅርብ ጓደኞቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አዲስ አበባ ውስጥ አዲስ ከተማ ተብሎ በሚጠራውና ልዩ ስሙ አብነት በሚባለው ሰፈር የተወለደው ኤልያስ መልካ በልጅነቱ ጥሩ እግር ኳስ ተጫዋች እንደነበር ወዳጆቹ ይናገራሉ። በልጅነቱ አብረው የሰንበት ትምህርት በወንጌላውያን አማኞች ቤተ ክርስቲያን እየተማሩ ማደጋቸውን የሚናገረው ገጣሚ ዳዊት ፀጋዬ፣ ፒያኖ እና ጊታር ቤታቸው እየመጣ ይጫወት እንደነበር ያስታውሳል። ኤልያስ መልካ በአዲስ ከተማ ገነት ወንጌላውያን አማኞች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያገለግል እንደነበር የሚናገረው ዳዊት፣ ኤሊያስ መልካ በጣም ተጫዋች፣ የዋህና ቅን እንደነበር ያስታውሳል። አቶ ዳዊት ይፍሩ በበኩላቸው ኤሊያስን በቅርበት ያወቁት ከሦስት ዓመት ወዲህ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ከዚያ በፊት በሥራዎቹ ብቻ ነበር የማውቀው የሚሉት አቶ ዳዊት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ "የሙዚቃ ባለሙያዎች መብት አልተከበረም፣ ሥራቸው አላግባብ እየተነገደበት ነው፣ ጥቅም አላገኙም" በሚል እንቅስቃሴን በመጀመር ሲመራ እንደነበር ይናገራሉ። "ኤልያስ ለራሱ ሳይሆን ለሌሎች መኖር የታገለ ነበር" ሲሉም ይገልፁታል። ሥራዎቹ ዝም ተብለው የሚተዉ አይሆንም የሚሉት አቶ ዳዊት ይፍሩ፣ ተሰብስበው እንዲጠኑና በክብር እንዲቀመጡ ለእርሱም ቋሚ መታሰቢያ ለማኖር ሙዚቀኛው እንደሚሰራ ተናግረዋል። ኤሊያስ መልካ ዕድሜው በአርባዎቹ መጀመሪያ ላይ የነበረ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ኃይሉ ተስፋዬ የሚባል ትምህርት ቤት ከዚያም ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ ከፍተኛ 7 ትምህርት ቤት ተምሯል። ኤልያስ ወደ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በ1987 ዓ.ም ገብቶ የተማረ ሲሆን በዋናነት ቼሎ አጥንቷል። ኤሊያስ ሙዚቃን ማቀናበር የጀመረው 'በገና ስቱዲዩ'ን አቋቁሞ ሲሆን በሙያው ታታሪና ጎበዝ እንደነበር አብረውት የሰሩ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ኤልያስ መልካ በዋናነት ሊድ ጊታር ከመጫወት ባለፈ የሙዚቃና የዜማ ደራሲ እንዲሁም አቀናባሪ ነበር። • አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ ኤሊያስ በመዲና፣ ዜማ ላስታስ እና አፍሮ ሳውንድ ባንዶች ውስጥ ተጫውቷል። ኤሊያስ መልካ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ውስጥ እያለ በኦሮምኛ ሙዚቃ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የድምፅና የቅኝት አደራደሮች ላይ የሰራው አነስተኛ ጥናት በዘርፉ ተጠቃሽ መሆኑን መምህራኖቹ ይናገራሉ። በቅርቡም ከሙያ አጋሮቹ ጋር በመሆን አውታር የተሰኘ የሙዚቃ መሸጫ መተግበሪያ ሰርቶ ማስተዋወቁ ይታወሳል። ኤልያስ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ አሻራቸውን ካሳረፉ ወጣት ባለሙያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎችና ለሙዚቃ ቅርብ የሆኑ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የመሰከሩለት ከያኒ ነበር። • ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ "ሙዚቃ ከነሙሉ ክብሯ በኤሊያስ በኩል ታልፋለች" ሲሉ የሚመሰክሩለት ባለሙያዎች፣ የድምፃዊ ቴዲ አፍሮን "አቦጊዳ" ፤ የሚካኤል በላይነህን በ"አንተ ጎዳና" የዘሪቱ ከበደን የሙዚቃ ሰንዱቆች ያቀናበረው ኤሊያስ መልካ ነው። የሚኪያ በኃይሉን "ሸማመተው" የእዮብ መኮንንን "እንደ ቃል"፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ ኃይሌ ሩት፣ አረጋኽኝ ወራሽ፣ ኩኩ ሰብስቤን፣ ትዕግስት በቀለ፣ የትግርኛ ዘፋኝዋ ማህሌት ገብረ ጊዮርጊስ፣ ጌቴ አንለይ፣ ቼሊና የኤሊያስ ሥራዎች ካረፈባቸው ሥራዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። ኤሊያስ መልካ በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሕብረ ዝማሬዎችን ያቀናበረ ሲሆን ከእነዚህም መካከል መላ መላ፣ ማለባበስ ይቅር፣ ለአፍሪካ ሕብረት፣ በትራፊክ አደጋ መከላከል ላይ ያተኮሩት ተጠቃሽ ናቸው። ሁለገብ የሙዚቃ ባለሙያው ኤሊያስ መልካ ትዳር ያልመሰረተ ሲሆን፣ በተለያዩ ሥራዎቹ የተለያዩ ሽልማቶችንና እውቅናን ከተለያዩ ወገኖች አግኝቷል። ኤልያስ መልካ እስከ ባለፈው ቅዳሜ ድረስ በፋና የድምፃውያን ተሰጥኦ ውድድር ላይ በዳኝነት ሲያገለግል መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል።
news-45550766
https://www.bbc.com/amharic/news-45550766
ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው
የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱበት ቀን መቃረቡን ተከትሎ አመራሮቹን ለመቀበል በርካቶች ከተለያዩ የኦሮሚያ ሥፍራዎች ወደ አዲስ አበባ መትመም ጀምሩ።
ባለፈው ረቡዕ የኦነግ ደጋፊዎች በአንዳንድ አካባቢዎች የአዲስ አበባ አደባባዮችን እና የመንገድ ጠርዞችን በኦነግ ባንዲራ ማቅለም ጀመሩ። ይህን ተግባራቸውን ከተቃወሙ የከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ግጭት ተከሰተ። በግጭቱም የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። • የቡራዩ ተፈናቃዮች በምስል • አቶ ዳውድ ኢብሳ ማናቸው? ሐሙስ መስከረም 10 በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ውጥረት ሰፍኖ ዋለ። በዳውድ ኢብሳ የሚመራውን የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ለመቀበል በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ። በቡራዩ በኩል ወደ ከተማዋ ዘልቀው ለመግባት ጥረት ያደረጉ ወጣቶች ቡራዩ ከተማ ላይ በፖሊስ አማካኝነት ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ታገዱ። የፖሊስን እርምጃ ተከትሎም በፖሊስ እና በወጣቶቹ መከከል ከፍተኛ ውጥረት ተከሰተ። በዕለቱ ሁለት ወጣቶች መሞታቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ ዓርብ መስከረም 11 የተከሰተውን ወንጀል የአዲስ አበባ ፖሊስ የያዘው ስለሆነ ዝርዝር የጉዳቱን መጠን አላውቀውም ብለዋል። ከብዙ ፍጥጫ በኋላ በቡራዩ በኩል ወደ ከተማዋ ለመግባት ሙከራ ያደረጉት ወጣቶቸ ተፈቅዶላቸው ወደ ከተማዋ እንዲገቡ ሆነ። ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ የገቡት ወጣቶች አርብ ምሽትን በመስቀል አደባባይ አሳለፉ። አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በመስቀል አደባባይ ለሚገኙ ወጣቶች ምግብ እና ውሃ በመውሰድ እራት ሲመግቧቸው የሚያሳዩ ምስሎች በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር። • ሞትና መፈናቀል በአዲስ አበባ ዙሪያ • ከ2000 በላይ ሰልጣኝ ፖሊሶች የጤና እክል ገጥሟቸው ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ ቅዳሜ ረፋዱ ላይ በዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ቡደን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረሰ። የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ በመስቀል አደባባይ ይጠብቋቸው ለነበሩ ደጋፊዎቻቸው ንግግር አደረጉ። በመስቀል አደባባይ የነበረው ሥነ-ሥርዓት የለምንም የጸጥታ ችግር ተጠናቀቀ። ፌደራል ፖሊስም በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከ4 ሚሊዮን ህዝብ በላይ መሳተፉን አስታወቀ። መስከረም 12 ቅዳሜ ምሽት ብሔራ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው የተባሉ ጥቃቶች እና ዘርፊያዎች በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች ተፈጸሙ። በጥቃቱ ከ23 ሰዎች በላይ መሞታቸው ተዘገበ። ጉዳት የደረሰባቸውም በርካቶች መሆናቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ለደህንነታቸው በመስጋት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች የሟቾች እና የተጎጂዎችን ቁጥር ከፍ ያደርጋሉ። ጥቃት በመሸሽ በርካታ ዜጎች በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የእምነት ተቋማት ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። ሰኞ መስከረም 14 በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም በአዲስ አበባ ለተቃውሞ ሰልፍ በርካቶች አደባባይ ወጡ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል በሰጡት መግለጫ ''በርካቶቹ ድምጻቸውን አሰምተው ተበትነዋል። የተወሰነው ኃይል ግን አዝማሚያቸው ሌላ ነበር፤ ህብረተሰቡን ለማሸበር እና ግጭቱን ለማስፋፋት ቦንብ ይዘው የወጡ ነበሩ'' ያሉ ሲሆን ሰልፈኞቹ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታወቀዋል። የቡራዩ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ቅዳሜ ምሽት የተፈጸመውን ጥቃት በማውገዝ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አአቶ ለማ መገርሳም በቡራዩና አካባቢዋ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል። አቶ ለማ ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው ለመመለስና መልሶ ለመቋቋም የክልሉ መንግስት ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ይሰራል ብለዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ)፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ፣ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር፣ የኦሮሞ አንድነት ለነጻነት፣ የኦሮሞ አንድነት ግንባር እና ሰማያዊ ፓርቲ ሰሞኑን በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን አወግዘዋል። 7ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግጭቶች አሳሳቢና አሳዛኝ ናቸው ብለዋል። ፓርቲዎቹ የመንሥስት ይህ አይነቱ ግጭት ከመከሰቱ በፊት የመከላከል እርምጃ እንዲወስድ እና ወንጀለኞችን በአስቸኳይ ከህግ ፊት እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ በቡራዩና አካባቢው የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጣራ ቡድን ላሰማራ ነው ብሏል። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጉዳቱ መንስዔ፣ ጉዳት እና ስፋት አጣርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሪፖርት እንደሚያደርግ ኮሚሽነረር አዲሱ ገ/እግዚአብሄራ ተናግረዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከአሁን በኃላ የህግ ጥሰት እና የስርዓት አልበኝነት ባህሪ ያላቸው ድርጊቶችን መንግሥት አይታገስም ሱሉ መግለጫ ሰጥተዋል። ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ተጎጅዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ መቀጠል ባለበት ሁኔታ ላይ እራሱን የቻለ ኮሚቴ ተዋቅሮ ጉዳዩን በፍጥነት ለመቅረፍና መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ ነው ብለዋል።
52996554
https://www.bbc.com/amharic/52996554
"ከሴቶችና ህፃናት ጥቃት ጋር በተያያዘ 94 መዝገቦች በፖሊስ ምርመራ ላይ ናቸው" ጠቅላይ አቃቤ ህግ
በባለፉት ወራት ከመቶ በላይ ህፃናት መደፈራቸው ጋር በተያያዘ 94 መዝገቦች በፖሊስ ምርመራ ላይ መሆናቸውን እና 23 ክሶች መመስረታቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገፃቸው አስታውቀዋል።
ከዚሁም ጋር ተያይዞ በአራት መዝገቦች ላይ የፍርድ ውሳኔ መሰጠቱንም ጠቁመዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭት መዛመትን ለመግታት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ የተደፈሩ ህፃናት ቁጥር ማሻቀቡንና ከመቶ በላይ ህፃናት ሴቶችና ወንዶች መደፈራቸውን የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከሰሞኑ መግለፁ የሚታወስ ነው። በተቃራኒው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የሚፃረር መረጃን ሰጥተዋል። ህፃናቱ ከተፈፀመባቸው ወንጀል ጋር ተያይዞ ክስ አለመጀመሩን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ባለፈው ሳምንት አርብ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። "ከአዲስ አበባ ህፃናትና ሴቶች ቢሮ ሮ በህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃትን በተመለከተ ለህዝብ የተገለፀውን መረጃ መሠረት በማድረግ ባለፉት 2 ወራት የተከፈቱ የክስ መዝገቦችን ለመከታተል ባደረግነው የመረጃ ዳሰሳ ባለፉት 2 ወራት የተከፈቱ መዝገቦች እንደሌሉ አውቀናል" በማለት ፕሬዚዳንቷ መዓዛ አሸናፊ በትዊተር ገልፀዋል። በሃገሪቷም እየተከሰተ ያለውን የሴቶች እና የህፃናት ጥቃትን በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማ ማድረጋቸውን ያስታወቁት ጠቅላይ አቃቤ ህጓ ከኮቪድ 19 መከላከል ጋር ተያይዞጥቃቶች መጨመራቸውን አስረድተዋል። ወ/ሮ አዳነች በፌስቡክ ገፃቸው እንዳሳወቁት በዚህ ግምገማ ላይ የተሳተፉት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣ ጠቅላይ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ አዲስ አበባ ፖሊስ አዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ግምገማቸውም እንደሚያሳየው ወረርሽኙን ተከትሎ ጥቃቶች መጨመራቸውን፣ ወደ ፍትህ አካላት መምጣት መቀነሱን እና በተጨማሪም መረጃ አያያዞች ላይ ባለው ክፍተት ላይ ከባለድርሻ አካላቱ ጋር መነጋገራቸውን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ባለፉት ወራት ከመቶ በላይ ከ15 አመት በታች የሆኑ ህፃናት በወላጅ አባቶታቻቸውና የቤተሰብ አባላት ጭምር መደፈራቸውም ከፍተኛ ቁጣና ውግዘት ያስከተለ ሲሆን ቤቶችም ቢሆኑ ምን ያህል ለህፃናት ደህንነታቸው ያልተጠበቁ የመሆናቸውንም እውነታ አጋልጧል። የትምህርት ቤቶች መዘጋትና ልጆች ቤት መዋላቸውንም ተከትሎ የሚደፈሩ ህፃናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የተለያዩ ሆስፒታሎችን ዋቢ በማድረግ የጠቀሰ ሲሆን፤ ጥቃት የደረሰባቸው ህፃናት በተለያዩ የጤና ማእከላት ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ አምሳ ሴቶች የቤት ውስጥ ጥቃት እንደደረሰባቸውም ሪፖርት አድርገዋል። በፌደራል ፍ/ቤቶች የህፃናትና ሴቶች ጉዳይን የሚያዩ ችሎቶች በኮቪድ19 ምክንያት ያልተዘጉ መሆናቸውንም ወይዘሮ መዓዛ እንዲሁም ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።
news-53619868
https://www.bbc.com/amharic/news-53619868
ፌስቡክ እና ጉግል ለሚያወጡት ዜና እንዲከፍሉ ሊገደዱ ነው
የአውስትራሊያ መንግሥት ፌስቡክ እና ጉግል ለዜና እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ረቂቅ ሐሳብ አቀረበ።
የግምጃ ቤት ኃላፊው ጆሽ ፍራይደርንበርግ እንዳሉት "በዓለም ግንባር ቀደም የሆነው ይህ ረቂቅ፤ አሳታሚዎች እኩል የመወዳደርያ ሜዳ እንዲያገኙ ያግዛል።" ዘንድሮ በርካታ የዜና ተቋሞች ገቢያቸው በመቀነሱ ሳቢያ ተዘግተዋል፤ ሠራተኛ ለመቀነስ የተገደዱም አሉ። ፌስቡክ እና ጉግል ረቂቁን አጥብቀው ተቃውመውታል። በዚህም ሳቢያ ከአውስትራሊያ ገበያ ሊወጡ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። የግምጃ ቤት ኃላፊው በበኩላቸው፤ ረቂቁ ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ብለዋል። ረቂቁ ከጸደቀ፤ ለዜና የማይከፍሉ የቴክኖሎጂ ተቋሞች በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ረቂቁ ምን ይዟል? የአውስትራሊያው የውድድር እና ሸማቾች ኮሚሽን፤ የቴክኖሎጂ ተቋሞች ለዜና እንዲከፍሉ ሐሳብ ቢያቀርብም መጠኑን አልወሰነም። የዜና ተቋሞች ተጣምረው ከቴክኖሎጂ ድርጅቶች ጋር ዋጋውን እንዲደራደሩ ነው የሚፈልገው። በዚህም አንድ ዜና በጉግል ወይም በፌስቡክ ገጽ ሲወጣ ይከፈልበታል ማለት ነው። በድርድር ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ የውድድርና ሸማቾች ኮሚሽን እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃን ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ጣልቃ ይገባሉ። የቴክኖሎጂ ተቋሞች ለአልጎሪዝም የሚያስከፍሉትን ለመገናኛ ብዙሃን ማስታወቅ እንዳለባቸውም ረቂቁ ይጠቁማል። አንድ የቴክኖሎጂ ተቋም ለሚፈጽመው ጥሰት የሚጣልበት ቅጣት እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ ይችላል። ረቂቁ አሁን ያተኮረው ፌስቡክ እና ጉግል ላይ ቢሆንም፤ ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋሞች ላይም ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል። ባለ ድርሻ አካላት ምን አሉ? የግምጃ ቤት ኃላፊው “ለአውስትራሊያ መገናኛ ብዙሃን የወደፊት እጣ ፈንታ ሲባል ለውጥ ያስፈልጋል” ብለዋል። ረቂቅ ሕጉ፤ በመላው ዓለም ያሉ መንግሥታት የሕግ አውጪዎችን ትኩረት እንደሚያገኝም ተስፋ አላቸው። የአገሪቱ ግዙፍ መገናኛ ብዙሃን ረቂቁን ይደግፋሉ። ኒውስ ክሮፕ የተባለው ሚዲያ ዋና ኃላፊ ማይክል ሚለር እንዳሉት፤ የቴክኖሎጂ ተቋሞች “በነጻ የሚበሉበት” ጊዜ ሊያከትም ነው። የጉግል የአገር ውስጥ ኃላፊ ሜል ሲልቪያ "ድርጅታችን በረቂቁ በጣም ተበሳጭቷል" ብለው፤ ሐሳቡ ፈጠራ ላይ ጫና እንደሚያሳድርም ተናግረዋል። "የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ለአውስትራሊያ ዲጂታል ምጣኔ ሐብት ስጋት ነው። ለአውስትራሊያውን የምንሰጠው አገልግሎት ላይም ጫና ያሳድራል” ብለዋል። ፌስቡክ ለዜና እንዲከፍል የሚጠየቅ ከሆነ ከገጹ ላይ የአውስትራሊያ ዜናዎችን እንደሚያስወግድ ገልጿል። ረቂቁ ምክር ቤት ከመቅረቡ በፊት ለአንድ ወር የምክክር ጊዜ ክፍት ነው። ከነሐሴ በኋላ ለምክር ቤት እንደሚቀርብ የግምጃ ቤት ኃላፊው ተናግረዋል። ረቂቅ ሕጉ ከጸደቀ፤ በድጋሚ የሚከለሰው ከዓመት በኋላ ይሆናል።
news-42348624
https://www.bbc.com/amharic/news-42348624
በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የፓርላማ አባሉና አጋሮቹ በመደፈር ወንጀል ተቀጡ
ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ውስጥ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ 11 ሰዎች አንድ ጨቅላን ጨምሮ 40 ሕፃናትን በመድፈር ተከሰው ወንጀለኛ ሆነው በመገኘታቸው በእሥራት ተቀጥተዋል።
ወንጀሉን የፈፀሙት በአውሮፓውያኑ ከ2013 እስክ 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን ወንጀሉ የተፈፀመባቸው ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ8 ወር እስከ 12 ዓመት ያለ መሆኑንም ማወቅ ተችሏል። የቡድኑ መሪ ፍሬድሪክ ባቱሚኬ የተባለ የፓርላማ አባል የሆነ ግለሰብ ሲሆን በእሥራት ወንጀል እንዲቀጣም ተወስኖበታል። "የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የፈፀሙ መሰል ግለሰቦች ላይ የተሰጠው ብይን ለሌሎች መስተማሪያ ይሆናል ብለን እናስባለን" ሲሉ የተከሳሾቹ ጠበቃ ቻርልስ ቹባካ ይናገራሉ። 'ጄሺ ያ የሱ' ወይንም 'የእየሱስ ወታደር' በማለት የሚጠሩት እኚህ ግለሰቦች ሕፃናት አስገድዶ ከመድፈር በተጨማሪ በግድያ ወንጀል በመከሰሳቸው እስከ ዕድሜ ልክ እሥራት የሚደርስ ቅጣት እንደተበየነባቸው ለማወቅ ተችሏል። በጠቅላላው 18 ግለሰቦች የተከሰሱ ሲሆን ሁለቱ በአንድ ዓመት እሥራት እንዲቀጡ አምስት ደግሞ ነፃ ሆነው የተገኙ ሲሆን የተቀሩት 11 ሰዎች በከባድ ወንጅል ቅጣት ተበይኖባቸዋል። አብዛኛው ወንጀል የተፈፀመው በምሽት እንደሆነ የታወቀ ሲሆን ግለሰቦቹ 'የልጃገረድ ደም መንፈሳዊ ኃይል እና ከለላ ያጎናፅፈናል' ብለው በማመን ወንጀሉን እንደፈፀሙም ታውቋል። አንድ የመብት ጥሰት ተቋም እንዳሳወቀው ወንጀሉ ለተፈፀመባቸው ሕፃናት ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ ዶላር በካሳ መልክ የተከፈለ ሲሆን ለሟች ቤተሰቦች ደግሞ 15 ሺህ ዶላር ካሳ ተከፍሏል። ጋርዲያን የተሰኘው ጋዜጣ በ2016 ባወጣው ዘገባ መሠረት አንድ የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ባለስልጣን ኮንጎ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማስቆም አልቻለም በሚል መንበራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀዋል። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በሃገሪቱ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተጠቂ የሆኑ ሴቶች ድርጊቱን ካጋለጡ በገዛ ቤተሰቦቻቸው እና ዘመድ አዝማድ መገለል እንዳይደርስባቸው በመስጋት ሁኔታውን ለማንም አይናገሩም። ከ20 ዓመታት በላይ በእርስ በርስ ግጭት ስታተመስ የቆየችው ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በተለይ በምስራቁ ክፍል በሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ምክንያት ዜጎቿ ሰላምና መረጋጋት ማግኘት አልቻሉም።
news-53796980
https://www.bbc.com/amharic/news-53796980
አሜሪካ፡ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታናሽ ወንድም ሞቱ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "የልብ ወዳጄ" የሚሉት ታናሽ ወንድማቸው ህይወቱ በማለፉ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
"በተሰበረ ልብ ነው የምወደው ወንድሜ ሮበርት ዛሬ ምሽት ህይወቱ ማለፉን የምናገረው" በማለት በትናንትናው ዕለት ባወጡት መግለጫ አስፍረዋል። የ71 አመቱ ሮበርት በኒውዮርክ ሆስፒታል ውስጥ በነበሩበት ወቅትም ፕሬዚዳንቱ የጎበኟቸው ሲሆን ለጋዜጠኞችም "ፈታኝ ጊዜ ላይ ነው ያለው" ብለው ነበር። ሮበርት ትራምፕ የሞቱበት ምክንያት አልተገለፀም። በርካታ የአገሪቱ ሚዲያዎች በጠና ታመው እንደነበር ዘግበዋል። "ወንድሜ ብቻ አልነበረም፤ ሁሉን ነገር የማዋየው የልብ ጓደኛዬ ነበር" ፕሬዚዳንቱ ማለታቸውን የትናንትናው መግለጫ አስነብቧል። "ጥሎልልን ያለፈው ትዝታው ሁሌም አብሮን ይኖራል" ብለዋል። የፕሬዚዳንት ትራምፕ ልጅ ኤሪክ አጎቱን "ድንቅ፣ ጠንካራ፣ ቀና፣ ሩህሩህና በጣም ታማኝ ሰው ነበር" ሲል ገልጿቸዋል። አክሎም ቤተሰቡ ሁሉ እንደሚናፍቃቸው በትዊተር ገፁ አስፍሯል። ሮበርት ከፕሬዚዳንቱ በሁለት አመት የሚያንሱ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ በአጠቃላይ የቤተሰቦቹም ልጆች አምስት ናቸው። ሮበርት ትራምፕ ሙሉ የስራ ዘመናቸውን የቤተሰቡን የቤቶች ግንባታ ኢንዱስትሪ በበላይነት ሲቆጣጠሩ የነበረ ሲሆን እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ነበሩ። ከወንድማቸው ዶናልድ ትራምፕ በተለየ መልኩ የሚዲያ አትኩሮትና ዝናን የማይወዱ፣ ኑሯቸውንም በኒውዮርክ ገለል ባለ ስፍራ የነበረ ነበር። በቅርቡም የወንድማቸው ልጅ ሜሪ ትራምፕ ስለ ትራምፕ "ቤተሰባችን አደገኛ ሰው እንዴት ፈጠረ" የሚል የፕሬዚዳንቱን ጉድ የሚዘከዝክ መፅሃፍ ከማሳተም ለማስቆምም ፍርድ ቤት ሄደው ነበር። ኒውዮርክ ፖስት ባሳተመው ፅሁፍ ሮበርት በማንሃተን በሚገኘው ሲናይ ሆስፒታል ከሳምንት በላይም በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ነበሩ ብሏል።
news-52000941
https://www.bbc.com/amharic/news-52000941
ኮሮናቫይረስ፡ ሩዋንዳ ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴዎችን አገደች
ሩዋንዳ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል ዜጎቿ ከቤት እንዳይወጡ አዛለች። ክልከላው በመላ አገሪቱ የሚጸና ነው ተብሏል።
ሩዋንዳዊያን የመጠቀሚያ አቅርቦቶችን ወደ ቤት በመውሰድ ላይ ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነውን ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴን የማገድ እርምጃ ማስፈጸም ጀምራለች። ይህ የአሀሪቱ እርምጃ በሁለት መልኩ አስተያየት እየተሰጣት ነው። ትናንት በተጀመረው በዚህ እርምጃ መሰረት አገሪቱ በሁሉም አቅጣጫ የምትገናኝባቸው ድንበሮች ተዘጋግተዋል፤ ከቤት ውጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን፤ ሱቆች፣ ገበያና መጠጥ ቤቶችም በራቸውን ዘግተዋል። የመንግሥት ሰራተኞች ሥራቸውን ከቤታቸው ሆነው እንዲያከናውኑ መመሪያ ተላልፏል። ከውጭ አገራት የሚመጡ ሩዋንዳዊያንም ለ14 ቀናት መንግሥት ባዘጋጀው የለይቶ ማቆያ ቦታ የመቆየት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ሩዋንዳ እስካሁን 19 የኮሮናቫይረስ ታማሚ ዜጎችን መለየት የቻለች ሲሆን ከምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛውን ቁጥር ይዛለች። ሩዋንዳ የወሰደችውን እርምጃ ተከትሎ በማሕበራዊ ሚዲያ አንዳንዶቹ እርምጃው ቫይረሱን ለመከላከል ተገቢ መሆኑን በመደገፍ አሞካሽተዋል። በሌላ በኩል ገሚሶቹ ደግሞ እርምጃው በድንገት የተወሰደ በመሆኑ በሰዎች ሕይወት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል እያሉ ነው። በዚህ በቤት ውስጥ የመቆየት እርምጃ በቀን ሥራ ተሰማርተው ኑሯቸውን የሚገፉ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሩዋንዳዊያን ላይ በተለየ ሁኔታ ችግር ሊደርስባቸው እንደሚችል ተገምቷል። በቤት ውስጥ የመቀመጥ እርምጃው ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን እንደ ሁኔታው ሊከለስ እንደሚችል ከሩዋንዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የወጣው መረጃ ያመለክታል።
news-46464308
https://www.bbc.com/amharic/news-46464308
ፑቲን፡ አሜሪካ ስምምነቱን ጥላ ከወጣች ሩሲያ ሚሳዬል ትገነባለች
አሜሪካ ከሶቪየት ሕብረት ጋር በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሚሳዬል ላለመገንባት የተደረሰውን ስምምነት ጥላ የምትወጣ ከሆነ ሩሲያ ሚሳዬል መገንባት እንደምትጀምር ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስጠነቀቁ።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እአአ 1987 በአሜሪካ እና በቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት መካከል የተደረሰው ስምምነት አጭርም ይሁን መካከልኛ ርቀት የሚምዘገዘጉ ሚሳኤሎችን መገንባት የሚከለክል ነው። ባሳለፍነው ማክሰኞ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ሩሲያ ስምምነቱን ጥሳለች ብሎ ወቀሳ ከሰነዘረ በኋላ ነው፤ ፕሬዚዳንት ፑቲን ሩሲያ ከስምምነቱ ልትወጣ እንደምትችል ያስጠነቀቁት። • ሩሲያ 60 የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አባረረች ፑቲን እንደሚሉት ከሆነ የኔቶ ወቀሳ አሜሪካ ከስምምነቱ እንድትወጣ ምክንያት ለመሆን ነው። ፑቲን ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በሰጡት መግለጫ በርካታ ሃገራት በአሜሪካ እና ሶቪየት ሕብረት መካከል የተፈረመውን ስምምነት በመጣስ የተለያዩ አይነት ሚሳኤሎችን አበልጽገዋል። ''በርካታ ሃገራት የጦር መሳሪያው ስላላቸው አሜሪካውያን አጋሮቻችንም እነሱ ሊኖራቸው እንደሚገባ ያስባሉ'' ያሉ ሲሆን ጨምረውም ''የእኛ ምላሽስ ምንድነው የሚሆነው? ቀላል ነው- እኛም ይኖረናል'' ብለዋል። • ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤል ወደ ጃፓን አስወነጨፈች ከዚህ ቀደም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ ተግባራት ምክንያት አሜሪካ ስምምነቱን ጥላ ልትወጣ እንደምትችል ተናግረው ነበር። የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ለሩሲያ ይህ መሳሪያ ከሌሎች አማራጮች ብዙ ወጪ የማያስወጣት ነው። የኔቶ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ባወጡት መግለጫ ''የኔቶ አባል አገራት ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር የደረሰችውን ስምምነት ወደጎን በመተው 9ኤም729 ተብሎ የሚጠራውን የሚሳኤል ሥርዓት ገንብታ ሙከራ አካሂዳለች'' ብሏል። ሩሲያ ስምምነቱን በመጣስ የሚሳኤል ግንባታ አካሂዳለች የሚለውን ወቀሳ አትቀበልም። ኔቶ ይህን መግለጫ ይዞ ከወጣ በኋላ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ሩሲያ ለስምምነቱ ተገዢ ለመሆን የ60 ቀናት ገደብ ተቀምጦላታል፤ ያሉ ሲሆን ሩሲያ ወደ ስምምነቱ የማትመለስ ከሆነ አሜሪካም ምንም አይነት ግዴታ አይኖርባትም ብለዋል። ሩሲያ በበኩሏ በተደጋጋሚ የቀዝቃዛው ጦርነት ስምምነትን የጣሰ ምንም አይነት ተግባር እንዳልፈጸመች ተናገራለች። • ትራምፕ ፑቲን አሜሪካን እንዲጎበኙ ጋበዟቸው • ትራምፕ ከፑቲን ጋር በተያያዘ ወቀሳ እየዘነበባቸው ነው እአአ 1987 በአሜሪካ እና በቀድሞዋ ሶቪየት ዩኒየን መካከል የተፈረመው እና የመካከለኛ ርቀት ኒውክለር ኃይል ስምምነት እየተባለው የሚጠራው ሰነድ ሁለቱ ሃገራት ከባህር ላይ ከሚወነጨፉ መሳሪያዎች ውጪ ምንም አይነት የኒውክለር ይዘት ያላቸውንም ሆነ የሌላቸውን ሚሳኤል ባለቤትነትን ይከለክላል። በወቅቱ የሶቪየት ሕብረት መሪ የነበሩት ሚካኤል ጎርቫቾቨ እና የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሮናልድ ሬገን ስምምነቱን እአአ 1987 ላይ ሲፈርሙ። በስምምነቱ መሰረት እስከ አውሮፓዊያኑ 1991 ድረስ 2700 ሚሳኤሎች ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ ተደርገው ነበር። በተጨማሪም ይህ ስምምነት አንዳቸው የአንዳቸውን ጣቢይ እንዲፈትሹ ፍቃድ ይሰጣል። 2017 ላይ ቭላድሚር ፑቲን ስምምነቱ የሩሲያን ፍላጎት ያማከለ አይደለም ብለው ነበር።
44963161
https://www.bbc.com/amharic/44963161
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የመደመር ጉዞ ወደ አሜሪካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዛሬ ሐምሌ 18 ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ። በቆይታቸውም ከኢትዮጵያውያንና ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
እንደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ቢሮ ከሆነ ይሀ ጉብኝት የተሳካ እንዲሆን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዋሽንግተን ከሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ እና ሎስ አንጀለስ ከሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስል ጄኔራል ጽ/ቤት ጋር ተባብረው እየሰሩ ነው፡፡ ለዚህ ዝግጅትም የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን፣ አርቲስቶች፣ ባለሃብቶች በአጠቃላይ የተለያዩ የዳያስፖራ የህብረተሰብ ክፍሎች ደድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ቢሮው በፌስቡክ ገፁላይ አስፍሯል። • ወሳኝ ምጣኔ ሃብታዊ እርምጃዎች በ100 ቀናት • የዐብይ ቀጣይ ፈተናዎች • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት 63 የሚሆኑ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ከአዲስ አበባ የሄዱ የመገናኛ ብዙሃን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ሽፋን ለመስጠት ዝግጅት መማድረጋቸው ተገልጿል። በዋሺንግተን ዲሲ ነዋሪ የሆኑትና የዲሲው ግብረ ኃይል አባል የሆኑትን አቶ ቴዎድሮስ ካብት ይመር ዝግጅቱ መጠናቀቁን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከዋሺንግተን ብቻ ሳይሆን ከዲሲ ሩቅ ከሆኑ ስፍራዎች በርካታ ቻርተርድ ባሶችን እየሞሉ ለመምጣት ያቀዱ እንዳሉም አስረድተዋል። የሚመጣውን ሰው ማስተናገድ የሚችል ትልቅ አዳራሽም መዘጋጀቱን ጨምረው ተናግረዋል። አቶ ቴዎድሮስ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይነሳሉ ብለው ከጠቀሷቸው ጥያቄዎች መካከል ብሔርተኝነትን በተለይም ኢትዮጵያን በብሄር ከፋፍሎ ለመግዛት የሚደረገው ስልት ዛሬም ይቀጥላል ወይስ ያበቃል የሚሉ የሰንደቅ አላማ ጉዳይ ከጥያቄዎቹ መካከል ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስረዳሉ። አሉላ ሰለሞን የዚህ ዝግጅት ኮሚቴ አባል ነው። አጠቃላይ ህዝቡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለውን ክብርና ድጋፍ የሚገልፅበት መድረክ ይሆናል ብሎ ያምናል። ውይይቱ በቀጣይም የሚኖረው ፋይዳን የተጠየቁት አቶ አሉላ ብዙ መፈታት ያለባቸው ውስብስብ ጥያቄዎች አሉ ዲሞክራሲን ከማስፋት፣ የህዝብ ተሳትፎን ከማስፋት፣ ፍትሃዊ ምርጫን ከማካሄድ ጋር የተያያዙ እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን የሚያነሱ የዳያስፖራ ክፍሎች አሉ ሲሉ ያስረዳሉ። በተለያየ የመገናኛ ብዙሃንም በአክቲቪስትነት የሚታወቁ ብዙ ሰዎች ይህንን ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልፀው የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ ትክክለኛ የሆነ ለሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች መወዳደሪያ እና መዘጋጃ እድል እንዲኖር የሚጠይቁ ኃይሎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል መንግስት ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰተው ምላሽ ወደፊት የሚታእ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ እስከ ሃምሌ 24 ድረስ በአሜሪካ ቆይታ ያደርጋሉ ተብሏል። • የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ?
news-54368869
https://www.bbc.com/amharic/news-54368869
ጃዋር መሐመድ፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተጠየቀ
እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ላይ ነጻ ሆነን የመታየት መብታችንን የሚቃረን አስተያየት በመስጠታቸው ፍርድ ቤቱ እንዲጠይቅላቸው አቤቱታ አቀረቡ።
አቶ በቀለ ገርባና ጀዋር መሐመድ የጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት በመገኘት ለጋዜጠኞች የሰጡት መግለጫ ነጻ ሆኖ የመታየት መብታቸውን የሚጻረር መሆኑን እና ለህይወታቸው አስጊ እንደሆነ ዛሬ ለተሰየመው ፍርድ ቤቱ ገልፀዋል። "እኛ ላይ ምስክሮች እንኳ ሳይሰሙ፣ የፖለቲካ ባለስልጣናት፣ በተለይም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ፍርድ ቤቱ እኛ ላይ ውሳኔ እንዳስተላለፈ አድርገው ነበር የተናገሩት" ያሉት አቶ ጃዋር መሐመድ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መግለጫ ለህይወታቸው አስጊ መሆኑን ተናግረዋል። "ጽንፈኞች ተብለናል፤ እንዲሁም ግርግር እንደፈጠርን እና ሰው እንደገደልን ወስነዋል" በማለት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲጠየቁ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። አቶ በቀለ ገርባም " ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ እኛ መከላከል በማንችልበት ሁኔታ ለውጪ አገር ሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል። ይህም የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገለልተኛ መሆን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው" በማለት ዶ/ር ጌዲዮን ፍርድ ቤት ቀርበው መጠየቅ አለባቸው ሲሉ ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም በበኩሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በሚቀጥለው ቀጠሮ ላይ በጽሑፍ ምላሽ እንዲሰጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የዛሬ ችሎት ውሎ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ በ24 ሰዎች ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የከፈተውን ክስ ለተከሳሾች አንብቧል። ፍርድ ቤቱም ከተራ ቁጥር 1 እስከ 15 ድረስ ያሉ ተከሳሾችን ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ ሁከት በመፍጠር በአዲስ አበባ ከተማ የ13፣ በኦሮሚያ ክልል ደግሞ 167 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ 360 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እና 4.6 ቢሊዮን ብር በላይ የተገመተ ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን አንብቧል። ከዚህም ውጪ ያለፈቃድ የጦር መሳሪያዎችን ይዘው በመገኘትና የቴሌኮም ማጭበርበርን መፈፀም የሚሉ ጉዳዮች ክሱ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮች ናቸው። 18ኛ ፣ 21ኛ፣ 6ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ፣20፣7ኛ ተከሳሾች አማርኛ የማይሰሙ መሆናቸው ተገልጾ እነርሱ ላይ የቀረበውን ክስ አለመረዳታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል። ጠበቆቻቸው ደግሞ በደንበኞቻቸው ላይ የተከፈተውን ክስ ማረሚያ ቤት በመገኘት ማሳወቅ እንደሚችሉ ለፍርድ ቤቱ ገልፀዋል። ፍርድ ቤቱም የተከሳሽ ጠበቆችን ሁሉንም በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ አግኝተዋቸው እንዲወያዩ ማረሚያ ቤት ሁኔታውን እንዲያመቻች ትዕዛዝ ሰትቷል። አቤቱታና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው እንዲሁም ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤት በማቅረብ ፍርድ ቤቱም ትዕዛዝ ሰጥቶባቸዋል። ተከሳሾች እጃቸው በካቴና ታስሮ ረዥም ሰዓት መቆየታቸውንና እንዲፈታ ጠይቀው እምቢ መባላቸውን፤ እንዲሁም ጠዋት ቁርስ ሳይበሉ ወደ ፍርድ ቤት መወሰዳቸውን በመግለጽ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ለምን በካቴና እንደታሰሩ ማረሚያ ቤቱ በጽሁፍ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከዚህ በተጨማሪ ተከሳሾች ማለዳ ወደ ፍርድ ቤት ሲወሰዱ እስር ቤቱ ቁርስ እንዲያቀርበላቸው ፍርድ ቤቱ አዟል። የተከሳሽ ጠበቆች ሸምሰዲን ጠሃ የኢሬቻ በዓል ላይ እንዲገኝ ያቀረበውን ጥያቄ ትዕዛዝ ይሰጥልን በማለት ጠይቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ተከሳሾች የባህል ልብስ እንዲገባላቸውና የኢሬቻን በዓል እስር ቤት በጋራ እንድናከብር ይፈቀድልን ሲሉ ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም ሸምሰዲን ጠሃ ኢሬቻ ላይ ተገኝቶ በዓሉን እንዲያከብር ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ተከሳሾች ግን የባህል ልብስ ገብቶላቸው ከዚህ በፊት የተለያዩ የእምነት በዓላት ሲከበሩ እንደቆየው እንዲያከብሩ ሁኔታዎች እንዲመቻችላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል። በተጨማሪም ባህር ማዶ ቤተሰብ ያላቸው እስረኞች ቤተሰቦቻቸውን በግል ስልካቸው እንዲያገኟቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ሸምሰዲን ጠሃ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ድብደባ ስለደረሰባቸው ጆሯቸው መጎዳቱንና የሕክምና አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑን ጠበቆቹ ጨምረው ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱም አገልግሎቱን ለምን እንዳላገኙ ማረሚያ ቤቱ እንዲገልጽና ዛሬውኑ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል ደግሞ የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸው የገለፁት የኦፌኮ አመራሩ ደጀኔ ጣፋ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን በዚህ ጉዳይም ማረሚያ ቤቱ በጽሁፍ ምላሸ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል። አቶ ደጀኔ ጣፋ ከዚህ በፊት ሌላ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ያ ክስ መቋረጡን ዳኞች በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ላይ ገልፀዋል። በተጨማሪም እነ ደጀኔ ጉተማ፣ ዶ/ር ብርሃነ መስቀል አበበ፣ ፀጋዬ ረጋሳ ላይ ዐቃቤ ሕግ በጋዜጣ እንዲጠሩ ትዕዛዝ እንዲሰጥ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የጋዜጣ ጥሪ እንዲደርግ አዟል። በስተመጨረሻም ተከሳሾች፣ ጠበቆቻቸው የክስ መቃወሚያ ጥቅምት 23/2013 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ ሬጂስትራር እንዲያቀርቡና እና ዐቃቤ ሕግ ምላሹን ለኅዳር 18/2013 ችሎት ይዞ እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
news-55183383
https://www.bbc.com/amharic/news-55183383
ኦባማ፣ ቡሽና ክሊንተን በቲቪ መስኮት እየታዩ ሊከተቡ ነው
የቀድሞዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንቶች ባራክ ኦባማ፣ ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ እና ቢል ክሊንተን በቴሌቪዥን መስኮት እየታዩ የኮቪድ-19 ክትባት ለመወጋት ቃል ገብተዋል።
ሶስቱ የቀድሞ መራሄ መንግሥታት ክትባቱ በአሜሪካ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ፈቃድ ካገኘ በኋላ ክንዳችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል ብለዋል። ሁለቱ ዴሞክራቶች ኦባማና ክሊንተን እንደሁም ሪፐብሊካኑ ቡሽ በጤና ሙያ ጥርሳቸውን የነቀሉ ሰዎችን ይሁንታ ካገኙ በኋላ ነው የሚከተቡት። የቀድሞዎቹ መሪዎች ይህን ለማድረግ የቆረጡት ሕዝቡ በክትባት ላይ ያለው እምነት እንዲፀና በማሰብ ነው። ከዚህ ቀደም የተሰበሰቡ የሕዝብ አስተያየቶች እንደሚያመክቱት አሜሪካዊካዊያን በክትባት ጉዳይ ልግምታም ናቸው። ብዙዎቹ ክትባት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፤ ሲቀጥል ምን እንደሚሰጠን በምን እናውቃለን የሚል ጥርጣሬ አላቸው። ለምሳሌ ባለፈው ጥቅምት የተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት እንደሚጠቁመው ከ10 አሜሪካውያን ስድስቱ ክትባት ለመውሰድ ፈቃደኛ ናቸው። ይህ አስተያየት የተሰበሰበው ፋይዘርና ሞደርና የተባሉት ክትባት አምራቾች የሙከራ ውጤታቸውን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ነው። አሜሪካ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ክትባት ለገበያ እንዲውል አልፈቀደችም። ነገር ግን በሚቀጥሉት ሳምንታት ሞደርና እንዲሁም ፋይዘር የተባሉትን ክትባቶች መርምራ ውሳኔ ታሳልፋለች ተብሎ ይጠበቃል። "ቃል እገባላችኃለሁ፤ ክትባቱ ለእንደኔ ዓይነት ሰዎች ሲሰራ እከተባለሁ" ብለዋል ባራክ ከአንድ ራድዮ ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ። "በቴሌቪዥን መስኮት ቀርቤ ነው ደግሞ የምከተበው። ሰዎች ሳይንስ እንደማምን እንዲያውቁልኝ እፈልጋለሁ። ከተከተብኩ ደግሞ ኮቪድ-19 አይዘኝም ብዬ አምናለሁ።" የቡሽና ክሊንተን ተወካዮች ሲኤንኤን ለተሰኘው ጣቢያ እንደተናገሩት ሁለቱ ፕሬዝደንቶች ክትባቱ ለሕዝብ ይፋ ሲሆን ለመከተብ ዝግጁ ናቸው። ሕዝቡም እንዲከተብ አሳስበዋል ሲሉ ተናግረዋል የፕሬዝደንቶቹ ወኪሎች። የሕብረተሰብ ጤና ሙያተኞች በርካታ ሰዎች ከተከተቡ ሕዝቡ ቫይረሱን ሊላመደው ይችላል ብለው ያምናሉ። ይህ ደግሞ በሙያው 'ኸርድ ኢሚዩኒቲ' ይባላል። ወረርሽኙን ለመግታት ወሳኙ ምዕራፍ ተደርጎም ይቆጠራል። የአሜሪካ መድኃኒት ቁጥጥር ሰዎች ቫይረሱ ጥቅም ላይ እንዲውል ካፀደቁ በኋላ ሰፊ ማስታወቂያ ይሰራል ተብሏል። ዩናይትድ ኪንግደም ፋይዘር የተሰኘውን ክትባት ለመጠቀም ወስናለች። የቦሪስ ጆንሰን ፕሬስ ዋና ፀሐፊ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቲቪ እየታዩ ይወጉ ይሆናል የሚል ፍንጭ ሰጥተዋል።
news-53762650
https://www.bbc.com/amharic/news-53762650
በቻይና ተጠቃሚዎች የሚያዙት የምግብ መጠን ላይ ገደብ ሊበጅ ነው
ቻይና የምግብ ብክነትን ለማስቀረት ቆርጣ እንደተነሳችና በርካታ እርምጃዎችን ለመውሰድ መዘጋጀቷን አስታውቃለች። ፕሬዝዳንት ሺ ዢን ፒንግ በአገሪቱ የሚስተዋለውን የምግብ ብክነት '' አስደንጋጭና አሳዛኝ'' ሲሉ ገልጸውታል።
'ክሊን ፕሌት ካምፔይን' ወይም በአማርኛ ንፁህ የምግብ ሰሀን እንቅስቃሴ የተጀመረው ፐሬዝዳንቱ ከኮቪድ-19 በኋላ የምግብ ብክነት ቁልጭ ብሎ ታይቷል ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ፕሬዝዳንቱ አክለውም '' የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ይህንን ጉዳይ ልንከታተለው ይገባል'' ብለዋል። በተጨማሪም በቻይና ለሳምንታት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በርካታ የደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በጎርፍ መመታታቸውን ተከትሎ በቶኖች የሚቆጠር የገበሬዎች ምርት እንዳልንበር ሆኗል። ነገር ግን የቻይናው ብሄራዊ የዜና ተቋም 'ግሎባል ታይምስ' እነዚህ ምክንያቶች የምግብ እጥረት የሚያስከትሉ አይደሉም ካለ በኋላ የምግብ ብክነት በራሱ ግን እንደ ትልቅ ጉዳይ ሊታይ እንደሚገባው ገልጿል። የቴሌቪዥን ጣቢያው በበይነ መረብ አማካይነት በርካታ ምግቦችን ሲመገቡ በቀጥታ የሚያስተላልፉ ሰዎች ላይም ወቀሳ መሰል አስተያየት ሰጥቷል። የሺ ዢን ፒንግን ንግግር ተከትሎም የዉሃን የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሩ ማህበር ምግብ ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡት የምግብ ቁጥር ላይ ገደብ እንዲያስቀምጡ እየወተወተ ነው። በዚህም መሰረት በቡድን የሚመጡ ሰዎች ካላቸው ቁጥር በአንድ ያነሰ የምግብ አይነት ብቻ ነው ማዘዝ የሚችሉት። አራት ሰዎች ወደ አንድ ምግብ ቤት ጎራ ብለው አራት ምግብ ማዘዝ አይችሉም ማለት ነው። ስለዚህ አዝዘው መመገብ የሚችሉት ሶስት ምግብ ብቻ ይሆናል። ነገር ግን ይህ አሰራር ወደ ማህበረሰቡ ዘልቆ እስከሚገባ ብዙ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ተገምቷል። በቻይናውያን ባህል መሰረት ደግሞ ከሚመገቡት ምግብ በላይ ማዘዝ እንደ ጥሩ ነገር የሚቆጠር ነው። ሰዎች በቡድን ሆነው ሲመገቡ ሰሀኖችና ትሪዎች ባዶ ሆነው ከታዩ አስተናጋጁ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንደ መጥፎ እንግዳ ተቀባይ ነው የሚቆጠረው። 'ኤን-1' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሀሳብ በበርካቶች ትችትን አስተናግዷል። "በጣም አስጨናቂ ነገር ነው" ብለው የተከራከሩም አልጠፉም። '' አንድ ሰው ብቻውን ወደ ምግብ ቤት ቢሄድስ? ምን ያክል ምግብ ነው ማዘዝ የሚችለው? ምንም?'' ሲል አንድ ግለሰብ በአንድ የቻይና ማህበራዊ ሚዲያ በኩል ሀሳቡን አስፍሯል። ሌሎች ደግሞ አብዛኛዎቹ ምግብ ቤቶች ምግብ እንዲባክን አያደርጉም፤ እንደውም በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ናቸው በየአጋጣሚው ምግብ እንዲባክን የሚያደርጉት ብለዋል። የቻይናው የዜና ወኪል ሲሲቲቪ በበኩሉ በቀጥታ ስርጭት በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ በአፍ የመጉረስ ትእይንት የሚያሳዩ ግለሰቦችም ለዚህ ብክነት አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሆነ ገልጿል። ''ሙክባንግ' በመባል የሚታወቁት እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች በብዙ የቻይና አካባቢዎችና እስያ አገራት ተወዳጅ ናቸው። ቻይና ይህን መሰል የምግብ ብክንትን የመከላከል እንቅስቃሴ ስትጀምር ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። በአውሮፓውያኑ 2013 እጅግ የተጋነኑ የምግብ ድግሶችን እና የባለስልጣናት ግብዣዎችን ለማስቀረት ስራዎችን አከናውና ነበር። አንድ ቻይና ውስጥ የሚንቀሳቀስና አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራ ድርጅት እንዳስታወቀው በአውሮፓውያኑ 2015 በአገሪቱ ከ17 እስከ 18 ሚሊዮን ቶን ምግብ ተርፎ ተደፍቷል።
news-47038300
https://www.bbc.com/amharic/news-47038300
አሜሪካ ሁዋዌ ኩባንያን እና የፋይናንስ ኃላፊዋን በማጭበርበር ከሰሰች
የአሜሪካ የፍትህ መስሪያ ቤት በቻይናው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሁዋዌ እና የኩባንያው የፋይናንስ ኃላፊ ሜንግ ዋንዡ ላይ ክስ መሰረተ።
የአሜሪካ ተጠባባቂ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማቲው ዊትኬር፣ የንግድ ቢሮ ኃላፊው ዊልበር ሮስ (ግራ) እና የሃገር ውስጥ ደህንንት ጽኃፊዋ ክርስተጄን ኒልሰን እና የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክርስቶፈር ዌሪይ። በዓለማችን ቁጥር ሁለት የተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች ኩባንያ ላይ ከተመሰረቱት ክሶች መካከል የባንክ ማጭበርበር፣ ፍትህን ማደናቀፍ እና የቴክኖሎጂ ስርቆት የሚሉ ይገኙበታል። አሜሪካ በሁዋዌ ላይ የመሰረተችው ክስ ከቻይና ጋር የገጠመችውን የንግድ ጦርነት ወደለየት ደረጃ ከፍ ያደርገዋል፤ ሁዋዌም በመላው ዓለም ምርት እና አገልግሎቱን ለማስፋፋት የሚያደርገውን ጥረት ይገታዋል ተብሏል። ኩባንያውም ሆነ የፋይናንስ ኃላፊዋ ሜንግ ክሶቹን ያጣጥላሉ። የኩባንያው ባለቤት ልጅ እና የፋይናንስ ኃላፊ የሆኑት ሜንግ ዋንዡ በአሜሪካ ጥያቄ መሰረት ባሳለፍነው ወር ካናዳ ቫንኩቨር ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉ ይታወሳል። በወቅቱ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ሲደረግ የቀረበው ምክንያት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ኩባንያው ተላልፏል የሚል ነበር። • የሁዋዌ ባለቤት ልጅ ካናዳ ውስጥ ታሠረች • ትሩዶ፡ ከሁዋዌ ባልደረባ እስር ጀርባ ፖለቲካ የለም ''ለዓመታት የቻይና ኩባንያዎች ምርቶችን ወደ ውጪ በሚልኩበት ወቅት የአሜሪካ ሕጎችን ይጥሳሉ፤ ለማዕቀቦች ደንታ ቢስ ናቸው። ይህን ሁሉ ሕገ-ወጥ ተግባራት የሚፈጽሙት የአሜሪካንን የፋይናንስ ሥርዓት በመጠቀም ነው። ይህ መቆም አለበት'' ሲሉ የአሜሪካ የንግድ ቢሮ ኃላፊው ዊልበረ ሮስ ተናግረዋል። ሁዋዌ የባንክ ማጭበርበር፣ ፍትህን ማደናቀፍ ከሚሉ ክሶች በተጨማሪ ቲ-ሞባይል ከተሰኘ የሞባይል ኩባንያ የሞባይ ስልኮች ዕድሜ ማራዘም የሚቻልበትን ቴክኖሎጂ ሰርቋል የሚል ከስ ተመስርቶበታል። በጠቅላላው ሁዋዌ በአሜሪካ መንግሥት 23 ክሶች ተመስርቶበታል። የአሜሪካው ኤፍቢአይ ዳይሬክተር ክርስቶፌር ዋሪይ ሁዋዌ የሃገራችንን እና የዓለምን የንግድ ሥርዓት ጥሷል ያሉ ሲሆን፤ ጨምረውም ''ሁዋዌ ለአሜሪካ ምጣኔ ሃብት እና ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ደቅኗል'' ሲሉ ተደምጠዋል። ሁዋዌ ከሳምሰንግ በመቀጠል በዓለማችን የቴሌኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች አማራች እና አገልግሎት ሰጪ የሆነ ግዙፍ ኩባንያ ነው። የሁዋዌ ኩባንያ ባለቤት ልጅ እና የፋይንስ ኃላፊዋ ሜንግ ዋንዡ አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች ምዕራባውያን ሃገራት የቻይና መንግሥት ሁዋዌን ተጠቅሞ የስለላ አቅሙን ያሳድጋል ብለው ይሰጋሉ። ሁዋዌ ግን ከቻይና መንግሥት ጋር ምንም አይነት ግነኙነት የለኝም ይላል። • ትሩዶ፡ ከሁዋዌ ባልደረባ እስር ጀርባ ፖለቲካ የለም • የአሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት ዓለምን ሊያደኽይ ይችላል • ቻይና ከአሜሪካ በሚመጡ ምርቶች ላይ የሶስት ቢሊዮን ዶላር ቀረጥ ጫነች የሁዋዌ ኩባንያ ባለቤት ልጅ እና የፋይንስ ኃላፊዋ እስር ግን የቻይና መንግሥትን እጅጉን አስቆጥቷል። ከሳምንታት በፊት በአሜሪካ ጥያቄ በካናዳ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የፋይናንስ ኃላፊዋ ለጥቂት ቀናት በእስር ካሳለፉ በኋላ የ10 ሚሊዮን የካናዳ ዶላር ዋስ በመጥረት ከእስር ተለቀዋል። ይሁን እንጂ የፋይናንስ ኃላፊዋ ለ24 ሰዓታት በክትትል ስር የሚገኙ ሲሆን ሙሉ እንቅስቃሴያቸውን የሚጠቁም ቁርጪምጪት ላይ የሚታሰር ኤሌክትሮኒክ መሳሪያ ማሰር ግድ ሆኖባቸዋል።
news-54451116
https://www.bbc.com/amharic/news-54451116
የሴቶች መብት፡ ፈረንሳይ "ድንግልና" የሚመረምሩ ዶክተሮችን እቀጣለሁ አለች
ፈረንሳይ አወዛጋቢ የሚባለውን "የድንግልና ምርመራና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት" የሚሰጡ ዶክተሮችን በእስር እቀጣለሁ ብላለች።
"የድንግልና ሰርቲፊኬት" አብዛኛውን ጊዜ የሚጠየቀው ጋብቻቸውን በባህላዊ መንገድ ለሚያከናውኑ ነው። ህጉ ገና በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን ከሰሞኑ ከእምነት ነፃ የሆነ የፈረንሳይ እሴቶችን መመለስ በሚል ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "ኢስላማዊ ተገንጣይነትን" መዋጋት ብለው ካቀረቡት ኃሳብ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል። የፈረንሳይ የፅንስ ማቋረጥ ቡድን በበኩሉ "የድንግልና ምርምራ" እንዲህ ዝም ብሎ ማስቀረት የማይቻል ሲሆን ሰፋ ያለ ትምህርትም ያስፈልገዋል ብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ቢሆን ይህንን ምርመራ በፅኑ ይቃወማዋል። ረቂቅ ህጉ ገና ፓርላመንቱ ተወያይቶ ሊያፀድቀው የሚገባ ሲሆን በዚሁ ደረጃ ግን "የድንግልና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት" ለሰጠ ማንኛውም የጤና ባለሙያ አንድ አመት እስርና 15 ሺህ ፓውንድ ቅጣት ይጠብቀዋል። የፈረንሳይ 3 ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሰሞኑ እንደዘገበው 30 በመቶ የሚሆኑ ዶክተሮች "የድንግልና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት" እንደሚጠየቁና አብዛኛዎቹም በእምቢተኝነታቸው ይፀናሉ ብሏል። የአለም ጤና ድርጅት የሴቶችንና ታዳጊዎችን ወሲብ መፈፀም አለመፈፀማቸውን በእይታም ሆነ በጣት ለማረጋገጥ መሞከር አንዲት ሴት ወሲብ ፈፅማለች የሚለውን አያረጋግጥም። የሰብዓዊ መብታቸውንም የሚጥስና የሚገረስስ ነው በማለትም ያወግዛል። የማህፀን ሃኪም የሆኑት ዶክተር ጋዳ ለፈረንሳዩ ኢንተር ኒውስ እንደተናገሩት "በፈረንሳይ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ላይ ተፅእኖ አያደርስም። በየአመቱ ቢያንስ ሶስት ሴቶች "የድንግልና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት" የሚጠይቁኝ ሲሆን አብዛኛዎቹም ከሰሜን አፍሪካ የሚመጡ ናቸው" ብለዋል። ሴቶቹ የቤተሰብ ክብር አዋርዳችኋል በሚል አካላዊ ጥቃት ይደርስብናል በሚል ፍራቻ ዶክተሯ ጋር የሚመጡ ሲሆን እሳቸውም ቢሆን "የድንግልና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬቱን" ይሰጣሉ። "ወንድሜ ይደበድበኛል፤ አባቴ ያንቀኛል። አማቾቼ ስሜን ያጠፉታል ይህንን ሰርቲፊኬት ካላገኘሁ ይሉኛል። ላለማመን ምክንያት የለኝም" በማለትም ተናግረዋል። "የድንግልና ምርመራ" በበርካታ አገራት እንደሚፈፀም የተባበሩት መንግሥታትና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ሪፖርት ያሳያል። ምርመራው የሚፈፀመው ከእምነት ጋር በተገናኘ ብቻ ሳይሆን ከመደፈር ምርመራ እንዲሁም የፀጥታ ኃይሎችን ምልመላም ጋር በተያያዘም እንደሚከናወንም መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተለይም በሰሜን አፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ አገራት፣ ህንድ፣ አፍጋኒስታን፣ ባንግላዴሽና ደቡብ አፍሪካ ይሄ ተግባር ተንሰራፍቶ ይገኛል። ከሁለት አመት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መንግሥታት ይህንን ኢሰብዓዊ ተግባር እንዲያግዱት ጥሪ አድርጓል። ከዚህም በተጨማሪ "የድንግልና ምርመራና" ኋላ ቀር የስርዓተ ፆታ ልምዶችም ምን ያህል የሴቶችንና ታዳጊዎችን ማንነትም ሆነ ሰውነት መቆጣጠሪያነትም እንደሚውሉ ተመልክቶም ሰፋ ያለ ዘመቻና ትምህርት አስፈላጊ ነው ብሏል። ረቂቅ ህጉ በያዝነው አመት ታህሳስ ወር የሚቀርብ ሲሆን የጤና ባለሙያዎችን ብቻ ሳይሆን "የድንግልና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት" የሚጠይቁ ቤተሰቦችን ወይም እጮኛዎችንም የሚቀጣ ህግ ማካተት አለበትም ተብሏል። በርካታ ሙስሊም ሴቶች ከጋብቻ በፊት ወሲብ በመፈፀማቸው መገደልን ጨምሮ በርካታ ጥቃቶች ይደርስባቸዋል።
news-53536096
https://www.bbc.com/amharic/news-53536096
የሲንጋፖር ዜጋ በአሜሪካ ለቻይና ሲሰልል እንደነበረ አመነ
የሲንጋፖር ዜጋ የሆነው ግለሰብ በአሜሪካ ለቻይና ሲሰልል እንደነበረ አመነ።
ጁን ዌይ ዬኦ የተባለው ግለሰብ የፖለቲካ አማካሪ ድርጅቱን ተጠቅሞ በአሜሪካ ለቻይና የደህንነት ተቋም ሲሰራ እንበረ አምኗል ሲሉ የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ከሰሞኑ በአሜሪካ እና ቻይና መካከል ያለው እሰጣ ገባ አይሏል። አሜሪካ በሂውስተን የሚገኘውን የቻይና ቆንስላ መዝጋቷን ተከትሎ ለዚሁ ምላሽ እንዲሆን ቻይናም በቼንግዱ የሚገኘውን የአሜሪካ ቆንስላ እንዲዘጋ ትዕዛዝ አስተላልፋለች። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፔዮ ቆንስላውን ለመዝጋት የተወሰነው ቻይና የአሜሪካን አዕምሯዊ ንብረት ‘እየሰረቀች’ ስለሆነ ነው ብለዋል። የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ግን ይህ ሁሉ የአሜሪካ እርምጃ የሚመነጨው ‘ከቻይና ጠል ውሸቶች ነው’ ብለዋል። አሜሪካ በሂውስተን የሚገኘው የቻይና ቆንስላ እንዲዘጋ የሰጠችው ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ የአሜሪካ ጸጥታ ኃይሎች የቆንስላውን በር ከፍተው ወደ ቆንስላው ቅጥር ግቢ ሲገቡ ታይተዋል። የቆንስላው ሰራተኞች እቃቸውን ሸክፈው ሲወጡም ተስተውሏል። ቆንስላው በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ ተዘግቧል። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከቻይና መንግሥት ጋር በንግድ፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እና በሆንግ ኮንግ ጉዳዮች በተደጋጋሚ ሲጋጭ ይስተዋላል። ስለ ሲንጋፖሩ ዜጋ የሚታወቀው ምንድን ነው? ጁን ዌይ ዬኦ ወይም ዲክሰን ዩኦ ተብሎ የሚታወቀው ግለሰብ ትናንት በአሜሪካው የፌደራል ፍርድ ቤት ለቻይና መሰለሉን አምኖ ጥፋተኛ ነኝ ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል። እአአ 2019 ላይ በቁጥጥር ሥር የዋለው ጁን ዌይ ዬኦ ከእአአ 2015 እስከ 2019 ድረስ ለቻይና መንግሥት ሲሰልል መቆየቱን ማመኑን የአሜሪካ ፍትህ ተቋም አስታውቋል። ግለሰቡ በቀላሉ ማግኘት የማይቻሉ መረጃዎችን እየሰበሰበ ለቻይና ሲያቀብል ነበር ተብሏል። በሌላ በኩል የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ባመለከተችበት ወቅት ከቻይና ጦር ጋር ግነኙነት የለኝም ብላ ዋሽታ የነበረችው ቻይናዊት ተመራማሪ በቁጥጥር ሥር መዋሏን የአገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ጁዓን ታነግ የተባለችው የ37 ዓመት ተመራማሪ ቪዛ ማጭበርበር በሚል ወንጀል በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ክስ ከተመሰረተባቸው አራት ቻይናውያን መካከል አንዷ ናት። በጁዓን ላይ የቀረበው ክስ በቻይና ህዝቦች ነጻነት ጦር ውስጥ የነበራትን ተሳትፎ የአሜሪካ ቪዛ ለማግኘት ባመለከተችበት ወቅት ደብቃለች የሚል ነው። የአሜሪካው ኤፍቢአይ ጁዓን የወታደር ዩኒፎርም ለብሳ የሚያሳይ ምስል አግኝቷል።
news-55313818
https://www.bbc.com/amharic/news-55313818
ሶማሊያ ከኬንያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች
የሶማሊያ መንግሥት ከጎረቤት አገር ኬንያ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲ ግንኙነት ማቋረጡን ዛሬ አስታወቀ።
ይህንንም ተከትሎ የሶማሊያ መንግሥት ናይሮቢ የሚገኙ ሁሉም ዲፕሎማቶቹ ኬንያ ለቀው እንዲወጡ ጥሪ ያደረገ ሲሆን፤ በተመሳሳይም በሞቃዲሹ የሚገኙ የኬንያ ዲፕሎማቶችም አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሰባት ቀናት ቀነ ገደብ ሰጥቷል። ይህ የተገለፀው የሶማሊያው የማስታወቂያ ሚኒስትር ኦስማን አቡካር ዱቤ ለመንግሥት ሚዲያ በሰጡት መግለጫ ነው። ሚኒስትሩ "የሶማሊያ መንግሥት በዓለም አቀፍ ሕግና ሥርዓት በተረጋገጠው ብሔራዊ ሉዓላዊነቱ ላይ በመመስረት የአገሪቱን ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና መረጋጋት የማስጠበቅ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታውን በመወጣት ከኬንያ መንግሥት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማቋረጥ ወስኗል" ብለዋል። ውሳኔው የመጣው ሶማሊያ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሆኑትና የወቅቱ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ተቋም [ኢጋድ] ሊቀመንበር ለአብደላ ሃምዶክ በኬንያ ላይ የተቃውሞ ደብዳቤ ካስገባች በኋላ ነው። በቅርቡ ኬንያ ሶማሊያን ለማበጣበጥና መረጋጋት እንዳይሰፍን እያሴረች ነው ሲሉ የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ኦስማን አቡበከር ዱቤ ከሰው ነበር። ሚኒስትሩ "ኬንያን እናከብራለን። በጉርብትና ላይ የተመሠረተ አብሮነትና መተጋገዝም እንዲኖር እንፈልጋለን። በእኛ በኩል እነዚህን እሴቶች አጠንክረን ይዘናል። ከኬንያ በኩል ግን በማይገባ የቀን ህልም የሶማሊያን መሬትና ውሃ መቆጣጠር ይፈልጋሉ" በማለት ነበር በብሔራዊ ቴሌቪዥኑ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ በተላለፈ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት። ሚኒስትሩ እንደ ማስረጃ ያነሱትም ከኬንያ በኩል ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና የሶማሊያ ተቃዋሚ መሪዎችን ናይሮቢ ማስተናገዷን ነው። ከዚህ ቀደም ከደቡባዊ ሶማሊያ ጁባላንድ ግዛት የተወጣጡ ፖለቲከኞች በመጪው የሶማሊያ ምርጫ ላይ ውይይት አድርገዋል ተብሏል። "ሞቃዲሾ አንድም ቢሆን የኬንያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን አስተናግዳ አታውቅም። በጎረቤቶቻችን ላይ ውጥረት እንዲነግስም አንፈልግም ነገር ግን በሶማሊያ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች መነሻቸው ከናይሮቢ ሆኗል። በሶማሊያ የሚደረሱ ስምምነቶች የሚጣሱበትም ቦታ ኬንያ ሆኗል" ነበር ያሉት ሚኒስትሩ በወቅቱ በሰጡት መግለጫቸው። ከዚህም በተጨማሪ ኬንያ በአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል (አሚሶም) ስር በሶማሊያ ያሰማራቻቸውን ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ቁልፍ የሚባሉ ግዛቶቿ በአልሻበባብ ቁጥጥር ሥር እንደወደቁ ሚኒስትሩ መጥቀሳቸው አይዘነጋም። የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩሉ በሶማሊያ የውስጥና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ጣልቃ ገብተዋል የሚለውን ጉዳይ ማጣጣላቸው ይታወሳል።
49822031
https://www.bbc.com/amharic/49822031
ኢንተርኔት በሚቋረጥበት አገር የኢንተርኔት ነፃነት ጉባኤ?
የኢንተርኔት ነፃነትን የተመለከተ 'ፎረም ኦን ኢንተርኔት ፍሪደም ኢን አፍሪካ' የተሰኘ አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች በመዲናዋ ተሰባስበው ጉባኤውን እየተካፈሉ ነው።
ለቀናት የኢንተርኔት አገልግሎት በሚዘጋበት አልያም በሚቆራረጥባት አገር፤ የኢንተርኔት ነፃነት ቀንን የማክበር ተቃርኖ ያልተዋጠላቸው ብዙዎች ናቸው። በአንድ በኩል ጉባኤው ኢትዮጵያ ውስጥ መካሄዱ፤ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ላይ ውይይት እንዲካሄድ መንገድ እንደሚጠርግ የሚያምኑ አካላት አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጥ የንግግር ነፃነት የሚገደብበት አገር ላይ ጉባኤው መካሄዱን የሚተቹም ብዙ ናቸው። • የኢንተርኔቱን ባልቦላ ማን አጠፋው? • በሞባይል ኢንተርኔት መቋረጥ የተገደቡ እንቅስቃሴዎች • መንግሥት በምን የሕግ አግባብ ኢንተርኔት ይዘጋል? ከወራት በፊት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እየተካሄደ ሳለ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል። በአማራ ክልል "የመፈንቅለ መንግሥት" ሙከራ ተደርጓል መባሉን ተከትሎም ለቀናት ኢንተርኔት ተዘግቶ ነበር። በመላው ዓለም የኢንተርኔት አገልግሎትን የሚቃኘው 'ኔትብሎክስ' ባወጣው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ስታቋርጥ በየዕለቱ ወደ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምትከስር አስታውቋል። ጉባኤውን ኢትዮጵያ ውስጥ ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ? ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ሲቋረጥ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ጦማሪያን፣ የሕግ ባለሙያዎችና ሌሎችም መንግሥትን ይተቻሉ። በብሔራዊ ደረጃ ከ15 በመቶ የማይዘለው የኢንተርኔት ዝርጋታ ሲቋረጥ ማኅበረሰቡም እሮሮ ማሰማቱ አይቀረም። ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ የመብት ተቆርቋሪዎች መንግሥትን ከሚነቅፉበት ምክንያት አንዱም የኢንተርኔት መቋረጥ ነው። እነዚህን ነጥቦች በማስረጃነት በማንሳት ኮንፍረንሱን ለምን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማካሄድ እንደተወሰነ አዘጋጆችን ጠይቀን ነበር። የ 'ፎረም ኦን ኢንተርኔት ፍሪደም ኢን አፍሪካ' የፕሮግራም ኃላፊ አስናህ ካልሜራ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ የዜጎችን ኢንተርኔት የማግኘት መብት በመግፈፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ አገር በመሆን ትታወቅ የነበረ ቢሆንም፤ ባለፈው አንድ ዓመት አንጻራዊ ለውጥ መጥቷል። ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች፣ የመብት ተሟጋቾችና ጦማሪያን ከእሥር መለቀቃቸው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃ እንዳያሰራጩ ተደርገው ከነበሩ ድረ-ገጾች ላይ እገዳው መነሳቱ እንዲሁም ለወራት ኢንተርኔት ተቋርጦባቸው የነበሩ አካባቢዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ መደረጉን ያጣቅሳሉ። ሆኖም ግን ከ "መፈንቅለ መንግሥት" ሙከራው ጋር በተያያዘ ኢንተርኔት ተቋርጦ እንደነበርና ከዚሁ የ "መፈንቅለ መንግሥት" ሙከራ ጋር ይገናኛል በተባለ ክስ ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች መታሠራቸውን ይናገራሉ። "ቢሆንም ኢትዮጵያ ለለውጥ ቁርጠኛ አገር መሆኗን አይተናል። በኢንተርኔት ነፃነት ረገድና በሌችም ጉዳዮች ላይ ከሚሠሩ የመብት ተሟጋቾች ጋር በጋራ የመሥራት እንቅስቃሴም አስተውለናል" ሲሉ ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የታየው አንጻራዊ ለውጥ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች ተምሳሌት ቢሆንም፤ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማስፋትና መረጃ የማግኘት ነፃነትን በማክበር ረገድ ብዙ የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን በኢንተርኔት መረጃ የማግኘት መብት እንዲያከብር የሚያሳስብ የጋራ ስምምነት ሰነድ ለመፈራረም መወጠናቸውንም አስናህ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች በሚገኙበት ኮንፍረንስ ስለ ዴሞክራሲ መስፈን እና የሰብአዊ መብት መከበር በመነጋገር፤ የመብት ተሟጋቾችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚገፉበትም አክለዋል። 'ፎረም ኦን ኢንተርኔት ፍሪደም ኢን አፍሪካ' ከዚህ ቀደም በኡጋንዳ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በጋና እና ሌሎችም የአፍሪካ አገሮች ተካሂዷል። ኮንፍረሱ አፍሪካ ውስጥ የኢንተርኔት የመረጃ ስርጭት እንዳይገደብ እንዲሁም የመናገር ነፃነት እንዲከበር ንቅናቄ በማድረግ ይታወቃል። ምሕረት ዩሃንስ የኢንተርኔት መቋረጥ በነጋዴዎች ላይ የሚያሳድረው ጫና በመላው ዓለም የኢንተርኔት አገልግሎትን የሚቃኘው 'ኔትብሎክስ' እንደሚለው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ሲቋረጥ በየዕለቱ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ታጣለች። የኢንተርኔት መቋረጥ በአገር ደረጃ የሚያደርሰውን ቀውስ በግል ከሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች አንጻር ለመመልከት ያነጋገርናት ምሕረት ዮሐንስ አዲስ አበባ ውስጥ ጉር ሾላ አካባቢ በሚገኝ የኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ትሠራለች። ካፌው ሥራ ላይ በቆየባቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት የኢንተርኔት አገልገሎት መቆራረጥ እና ሲከፋም ተዘግቶ መቆየት ፈተና እንደሆነባት ትናገራለች። በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመልቀቂያ ፈተና ምክንያትም ሆነ ከተለያዩ ፖለቲካዊ ክስተቶች ጋር በተያያዘ የኢንተርኔት ግልጋሎት መቋረጥ ሲያጋጥም አብሮ የሚዘጋው ሥራችንም ነው ትላለች። በእነዚህ ጊዜያት "ሥራ የለም ማለት ይቻላል። እስኪከፈት ከመጠበቅ ውጭ ምንም ማድረግ የምንችለው ነገር የለም" ስትል ለቢቢሲ ታስረዳለች።"ኢንተርኔት ባይቆራረጥ፣ መዘጋቱ ቢቀር ጥሩ ነው" የምትለው ምሕረት የምትሠራበት ካፌ ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ የጽሕፈት መሣሪያዎችን በጎን የሚሸጥ ሲሆን፤ ከእነዚሀ ሽያጮች በሚያገኘው ገቢ ወጪዎቹን ለመሽፈን ይጥራል። "እኛ ሌላ ሌላ ገቢ ስላለን ነው እንጅ [ኢንተርኔት በማስጠቀም] የምናገኘው ገቢ በጣም ዝቅ ያለ ነው" ትላለች። • ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋቷ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጣች • ኢትዮቴሌኮም ኢንተርኔት ለምን እንደተቋረጠ መግለፅ እንደማይችል አስታወቀ የመደብር ኪራይን ከመሳሰሉ ወጪዎች በተጨማሪ ለኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢው ኢትዮ-ቴሌኮም መፈፀም ያለባቸው ክፍያዎች አገልግሎቱ በሚቋረጥባቸው ጊዜያትም እንደሚቀጥሉ ምሕረት ትናገራለች።"የምንከፍለው በወር ነው፤ አገልግሎቱ ቢኖርም ባይኖርም መክፈላችንን እንቀጥላለን" ትላለች ምሕረት ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ።
news-44920704
https://www.bbc.com/amharic/news-44920704
ከ60 ዓመት በኋላ የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ይሁንታ አገኘ
ከ 60 ዓመት በኋላ ወባን ለማከም የሚረዳ ኪኒን በአሜሪካ ባለስልጣናት ፈቃድ አገኘ። መድሃኒቱ በየአመቱ 8 ሚሊየን ሰዎች ላይ የሚያገረሸውን የወባ አይነት ለማከም የሚረዳ ነው።
ይህ አይነት የወባ በሽታ በጉበት ውስጥ ለረጅም ዓመት ተደብቆ የመቆየት ባህሪ አለው። ተመራማሪዎች ይህንን "ድንቅ ስኬት ሲሉ አሞካሽተውታል"። በአለም ዙሪያ የሚገኙ አስፈፃሚዎች አሁን መድኃኒቱን ለዜጎቻቸው ማዘዝ ይችሉ አይችሉ እንደሆን ይመለከቱታል። ደጋግሞ የሚያገረሽ የወባ በሽታ ፕላስሞዲየም ቪቫክስ በሚሰኝ ጥገኛ ተዋህሲያን የሚከሰት ሲሆን በአፍሪካ በዋናነት ከሚጠቀሱ የበሽታ አይነቶች መካከል አንዱ ነው። • የወባ በሽታን በትንፋሽ ማወቅ ተቻለ • አደገኛ የተባለ የወባ በሽታ በበርካታ ሀገራት ስጋት ፈጥሯል። በኢትዮጵያስ? • የወባ ትንኝ አደገኛ የሆነችው በሂደት ነው በወባ ትንኝ አንዴ መነደፍ ብቻ ለህመሙ የሚያጋልጥ ሲሆን በተለይ ህፃናት ይበልጥ ተጠቂ ናቸው። በዚህም የተነሳ ባመማቸው ቁጥር አቅማቸው ከእለት በዕለት እየቀነሰ የሚሄድ ሲሆን ከትምህርት ገበታቸውም ላይ ለመቅረት ይገደዳሉ። በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ባመማቸው ቁጥር የወባ ትንኟ ጥገኛ ተዋስህያኑን ከእነርሱ ወደሌሎች በማዛመት እነሱን መነሻ ታደርጋቸዋለች። ይህም በሽታውን ከምድረገፅ ለማጥፋት አስቸጋሪ አድርጎታል። አሁን የአሜሪካው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ታፌኖኪውይን ለተሰኘው መድሃኒት እውቅና ሰጥቷል። መድሃኒቱ በሽታዋ ከተደበቀበችበት ጉበት አውጥቶ በመግደል ሰዎች በህመሙ ዳግመኛ እንዳይሰቃዩ ያደርጋል። መድሃኒቱ ተጓዳኝ ህመሞችን ለማከም ከሚያግዙ ሌሎች መድሃኒቶች ጋር የሚሰጥ ይሆናል። በአሁን ሰዓት ጉበት ውስጥ የተደበቀች ወባን ለማከም የሚረዳ ፕሪማኪውን የተሰኘ መድሃኒት አለ። ነገር ግን አንድ ታፌንኪውንን ወስዶ ከሚገኘው ፈውስ ጋር ሲነፃፀር ፕሪማኪውንን ለ 14 ቀን መውሰድ ይጠይቃል። • በሀሰተኛ መድሃኒት ሰዎች እየሞቱ ነው አንዳንድ ባለሙያዎች ግን ሰዎች ይህንን መድሃኒት መውሰድ ከጀመሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለውጥ በማየታቸው ብቻ አቋርጠውት ዳግመኛ እንዳያገረሽባቸው ይሰጋሉ። የአሜሪካው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መድሃኒቱ በአሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላየ እንዲውል የፈቀደ ሲሆን መታወቅ ያለባቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዳሉትም አልሸሸገም።
news-55175302
https://www.bbc.com/amharic/news-55175302
ኮሮናቫይረስ ፡ አሜሪካ ውስጥ በአንድ ቀን ብቻ 195 ሺህ ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኘባቸው
አሜሪካ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከጀመረ ወዲህ በአንድ ቀን ብቻ ከፍተኛ የተባለውን ቁጥር አስመዝግባለች። ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ ታማሚዎች ቁጥርም ጣራ ነክቷል።
በኮቪድ-19 ምክንያት የአሜሪካ ሆስፒታሎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ከ100 በላይ ሆኗል። ይህም ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር እጥፍ ማለት ነው። ረቡዕ ዕለት የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ 195 ሺህ 695 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። 2 ሺህ 733 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት በአንድ ቀን ሕይወታቸው አልፏል። የሎስ አንጀለስ ከተማ ወረርሽኙ እንደ አዲስ በማገርሸቱ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ አዛለች። በአሜሪካ በጠቅላላው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 14 ሚሊዮን ገደማ ሆኗል። የሟቾች ቁጥር ደግሞ 254 ሺህ ነው። በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መጥቷል። ባለፈው ወር በየሳምንቱ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ እንደሆነ ተዘግቧል። ይህን ተከትሎ የሃገሪቱ የጤና ሥርዓት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል የጤና ሙያተኞች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው ካሊፎርኒያ፣ ቴክሳስና ፍሎሪዳ ግዛቶች በቫይረሱ እጅጉን ከተጠቁ መካከል ናቸው። የሎስ አንጀለስ ከተማ ከንቲባ ኤሪክ ግራሴቲ ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚደረግ የቤት ውስጥ ተቀመጡ አዋጅ ከተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካውያን ለገና እና ተያያዥ በዓላት ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩበት ወቅት ስለሆነ የወረርሽኙ መስፋፋት ቢጨምርም እንጂ አይቀንስም የሚል ስጋት አላቸው። የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠር ማዕከል ነዋሪዎች በገና በዓል ሲሉ ከመጓጓዝ እንዲቆጠቡ አሳስቧል። ነገር ግን ማዕከሉ ከዚህ በፊት ሰዎች ኮሮናቫይረስ ካለበት ሰው ጋር ግንኙት ካላቸው 14 ቀናት ራሳቸውን ያገላሉ ሲል ያወጣውን ጥብቅ ትዕዛዝ በማላላት ወደ 7 ዝቅ አድርጎታል። የአሜሪካ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣናት ሞደርና የተባለው ክትባት ለተጠቃሚዎች መሰራጨት ይችላል ወይስ ገና ነው የሚለውን ለመወሰን ለታህሳስ 10 ቀጠሮ ይዘዋል። ታህሳስ 17 ደግሞ ፋይዘር የተባለው ተቋም ያመረተውን ክትባት ለመፈተሽ ይገናኛሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ፋይዘር የተሰኘው ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀድ ከዓለም ቀዳሚዋ ሆናለች። በአሜሪካም ክትባቶቹ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቃድ ከተገኘ 21 ሚሊዮን የሚሆኑ የጤና ተቋማት ሠራተኞች ክትባቱ ቀድሞ ይደርሳቸዋል ተብሏል። በመቀጠል ደግሞ 3 ሚሊዮን የዕድሜ ባለፀጋዎች ማቆያ የሚኖሩ አዛውንት ክትባቱን ያገኛሉ የሚል ተስፋ አለ። የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ያሳሰባቸው ሌላው ጉዳይ ምን ያክል አሜሪካውያን ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ይሆናሉ የሚለው ጉዳይ ነው። በቅርቡ የተሰበሰበ አንድ ጥናት 58 በመቶ ሰዎች ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆናቸውን ያሳያል።
news-54094325
https://www.bbc.com/amharic/news-54094325
ሳይንቲስቶች የዓለም የዱር እንስሳት ቁጥር "በሰው ልጅ ጥፋት የተነሳ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ" መሆኑን አስጠነቀቁ
የዓለማችን የዱር እንስሳት ቁጥር ከሃምሳ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በሁለት ሶስተኛ ቁጥራቸው መቀነሱን የዓለም አቀፉ የአካባቢ ጥበቃ ቡድን (WWF) ያወጣው የጥናት ሪፖርት ገለፀ።
የዱር እንስሳት በደን ምንጣሮና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ እየጠፉ ነው ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው የዱር እንስሳቱ ቁጥር "በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ" ሲሆን ምንም አይነት መረጋጋትም ሆነ መቆም እንደማይታይበትም ተገልጿል። ይህ ጥናት ተፈጥሮ በሰው ልጆች ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እየወደመች መሆኑን በማንሳትም አስጠንቅቋል። የዱር እንስሳት ደኖች ሲቃጠሉ፣ የባህር ዓሳዎችን ከተገቢው በላይ ስንጠቀም እንዲሁም መኖሪያቸውን ስናወድም "በአስደንጋጭ ሁኔታ ቁጥራቸው እየቀነሰ ነው" ያሉት የድርጅቱ የበላይ ኃላፊ ታንያ ስቴሌ ናቸው። "አለማችንን እያናጋናት ነው፤ ቤታችን ብለን የምንጠራትን፤ ጤናችንን፣ ደህንነታችንን እንዲሁም ምድር ላይ ለመቆየት የሚረዳንን ነገር። አሁን ተፈጥሮ መልዕክቷን የላከችልን ሲሆን፣ ጊዜ ደግሞ ከእኛ ጋር አይደለም" ብለዋል። የድርጅቱ ጥናት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአካባቢ ጥበቃ ሳይንቲስቶች በዓለም ላይ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የዱር እንስሳት ዝርያዎችን በቅርበረት ከተከታተሉ በኋላ የቀረበ ነው። እኤአ ከ1970 ወዲህ ጀምሮ ከ 20 ሺህ በላይ አጥቢዎች፣ አእዋፋት፣ የአሳ ዝርያዎች፣ ተሳቢ እንስሳት፣ እንዲሁም 'አምፊቢያንሶችን' ተመልክቶ በአማካይ በ68 በመቶ ቁጥራቸው መቀነሱን አስቀምጧል። የእንስሳቱ ቁጥር መቀነስ በሰው ልጅ በሚያደርሰው ውድመት የተነሳ መከሰቱን ግልጽ ማስረጃ ነው የሚሉት በለንደን ዞሎጂካል ሶሳይቲ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አንድሪው ቴሪ ናቸው። "ምንም የሚለወጥ ነገር ከሌለ፣ ቁጥራቸው እየቀነሰ መምጣቱ አይቀርም። ይህ ደግሞ የዱር እንስሳቱ እንዲጠፉ እንደሚያደርግ እና የምንኖርበት ስነ ምህዳር አደጋ ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው" ሲሉ አክለዋል። ጥናቱ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን የሰው ልጅና ተፈጥሮ ምን ያህል የተጋመዱ መሆናቸውን ለማስታወስ በቂ ነው ሲል ያትታል። ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ መቀስቀስ ምክንያት እንደሆኑ ከሚታመኑ ነገሮች መካከል አንዱ የዱር እንስሳት ንግድ ሲሆን ይህ ደግሞ ለቁጥራቸው መቀነስም ሌላኛው አስረጅ ነው ተብሏል።
news-42430985
https://www.bbc.com/amharic/news-42430985
ደዳብ፡ በዓለም በትልቅነቱ ሁለተኛ የሆነው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ፈተና ውስጥ ወድቋል
አቶ ኢድሪስ መሐመድ ይባላሉ። ወደ ደዳብ የስደተኞች መጠለያ የመጡት እኤአ በ2007 መሆኑን ይናገራሉ።
የደዳብ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በመጀመሪያ ገና የ15 ዓመት ወጣት እያሉ ወደ ሶማሊያ መሰደዳቸውን የሚናገሩት አቶ ኢድሪስ በኬንያ በሚገኘው በዚሁ የመጠለያ ጣቢያ ከ 10 ዓመታት በላይ መቆየታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። እርሳቸው እንደሚሉት በተወለዱበት ባሌ አጋርፋ ከተማ አባታቸው ፊት ለፊታቸው ሲገደሉ እሳቸው እና እናታቸው እግራቸው ወደመራቸው አቅጣጫ አቀኑ፤ ይህ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ዋነኛ ምክንያት ሆናቸው። ከዚያም ካገኙት ሰው ጋር ሶማሊያ በመግባት ኑሯቸውን መሰረቱ። ባጋጠማቸው ችግር ከስድስት ልጆቻቸው እና ከሶማሊያዊት ሚስታቸው ጋር ወደ ደዳብ የስደተኞች መጠለያ መጥተው መኖር ጀመሩ። "ሕይወት በመጠለያ ጣቢያው በጣም ከባድ ነው። ይሁን እንጂ ሀገራችን ውስጥ የሚሰማው ወሬ እንድንመለስ የሚጋብዝ ሆኖ አላገኘነውም። ከሰውም ሆነ ከሚዲያ በምንሰማው ነገር ውስጣችን ያዝናል" በማለት ተናግረዋል። አቶ ኢድሪስ ልጆቻቸው የተወለዱት በባዕድ ሀገር በመሆኑ ሀገራቸውን፣ ባህላቸውን እና ቋንቋቸውን ለማወቅ አልታደሉም። ልጆቹ ሁልጊዜ ወደ ኢትዮጵያ እንዲወስዷቸው ቢጎተጉቷቸውም ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ በመፍራት ጥያቄያቸውን ለመመለስ አለመቻላቸውን ይናገራሉ። የአቶ ኢድሪስ ስጋት ወደ ሀገር መመለስ አለማቻል ብቻ ሳይሆን ተጠልለው የሚገኙበት እና ቀንን እገፋበታለሁ ያሉት ደዳብ የስደተኞች መጠለያ የመዘጋት ወሬ ጭምር ነው። "ይህ ሥፍራ ሕይወታችንን ለማዳን የተሸሸግንበት ነው፤ ይዘጋል ሲባል ትልቅ ሐዘን ነው የተሰማን፤ የምንለው ነገር የለም፤ ግራ የገባው ሰው ነን " በማለት የተሰማቸውን ስጋት ገልፀዋል። አቶ ኢድሪስ መሐመድ በደዳብ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አቶ አለማየሁ ወርዶፋም ከ2006 ጀምሮ በመጠለያው መኖር መጀመራቸውን ይናገራሉ። በአጠቃላይ ላለፉት 25 ዓመታት በየመን፣ ሶማሊያ እና ሱዳን በስደት መኖራቸውን የሚናገሩት አቶ አለማየሁ በፖለቲካ ምክንያት በደረሰባቸው ጫና እና ወከባ ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ከሀገር መውጣታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሽምግልና ዕድሜያቸው በስደት ሀገር የሚኖሩት አቶ አለማየሁ ልጆቻቸውም በተለያየ ሀገር ተበትነው እንደሚገኙ ይገልፃሉ። "ቤተሰቦቼን ጥዬ በስደት ዕድሜዬን እየጨረስኩ ነው" "የዚህ መጠለያ ኑሮ ከባድ ነው። ወደ ሶስተኛ ሀገር የመሄድ እድል እንኳ ከሌሎች እኩል አይሰጠንም። ለምሳሌ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ ከኛ መካከል አንድም ሰው የመሄድ እድል አላገኘም። መጠለያ ለማግኘት ራሱ በእኩል አይን አንታይም፤ ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ከሌሎች ሀገር የተለየ ነው በሚል ሰበብ ነፃ የትምህርት እድል እንኳ ተነፍገናል"በማለት በመጠለየዓው የሚደርስባቸውን ችግር ዘርዝረዋል። ከዚህም በተጨማሪ አለም አቀፉ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃለመጠይቅን ያላለፉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከአስር ዓመት በላይ በድርጅቱ ሳይመዘገቡ አልያም ወደ ሀገራቸው ሳይመለሱ የሚበሉት እስከማጣት ድረስ ተቸግረው በመጠለያው ኑሯቸውን በመግፋት ላይ እንዳሉ ተናግረዋል። የደህንነት ጉዳይ ሌላኛው አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የተናገሩት አቶ አለማየሁ በቅርቡ አራት ኢትዮጵያውያን በጩቤ ተወግተው ህይወታቸው ማለፉን ያስረዳሉ። ፖሊሶች በርቀት ስለሚገኙ በመሳሪያ አስፈራርተው ንብረታቸውን እንደሚዘረፉ ተናግረዋል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በቅርቡ የደዳብ ስደተኞች መጠለያ መዘጋትን ወሬ ሲሰሙ ቀኑ ጨልሞባቸዋል። በዚህ መጠለያ ጣቢያ ከሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መካከል ደግሞ ካርሎስ ተስፋዬ ሌላኛው ነው። "ስመጣ ብቻዬን ብሆንም አሁን ግን ትዳር መስርቼ አራት ልጆችን አፍርቻለሁ" ይላል ካርሎስ። ካርሎስ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲላ አካባቢ ይኖር የነበረ ሲሆን በሱና በቤተሰቡ ላይ በደረሰው ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ሀገር ለቆ ለመውጣት መገደዱን ይናገራል። አቶ ካርሎስ ተስፋዬ በደዳብ ስደተኞች መጠለያ ጣብያ ወደዚህ መጠለያ ጣቢያ ስመጣ የደህንነት ስጋቱ ከፍተኛ ነበር። የመሣሪያ ተኩስ በየጊዜው ይሰማ ነበር የሚለው ካርሎስ ሁለት ጊዜ ዝርፊያ እንዳገጠመው ተናግሯል። "ሃያ ዓመት በስደተኝነት በርካታ ነገሮችን አልፌ ብኖርም አሁን ግን መቋቋም የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ። ልጆቼን ትምህርት ቤት መላክ አልቻልኩም። ስለዚህ በዚህ ሁኔታ እዚህ ለመኖር በጣም ከብዶኛል።" በልጆቼ ምክንያት ወደ ሀገሬ መመለስ አልችልም የሚለው ካርሎስ "ወደ እዚህ ከመጣ ጀምሮ ይዘጋል የሚል ወሬ ሁሌ ስለምሰማ ፈጣሪዬን ብቻ ተስፋ አድርጌ ነው የምኖረው" ሲል ይናገራል። የደዳብ የስደተኞች መጠለያ የወደፊት እጣፈንታ ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዲ የስደተኞቹን አኗኗር ለመጎብኘት ወደ መጠለያው ያቀኑት የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዲ የመጠለያው የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለማስኬድ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመ ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደርጉ የነበሩ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች እርዳታቸውን ማቋረጠቸውን ተከትሎ የበጀት እጥረቱ እንደተፈጠረ አስታውቀዋል። ኮሚሽነሩ በደዳብ ያለውን ችግር ለመፍታት ኮሚሽኑ ከኬንያ እና ከሶማሊያ መንግስታት ጋር በጥምረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። "እስካሁን 32 ሺ የሶማሊያ ስደተኞች ወደ ኪስማዮ ተመልሰዋል። በቅርቡም ደግሞ 20 ቤተሰቦች ወደ አገራቸው ይመለሳሉ" ይላሉ ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዲ። የኬኒያ መንግስት መጠለያ ጣብያው እንዲቀጥል ፍላጎት ባይኖረዉም አሁን ግን መግባባት ላይ ደርሰናል ያሉት ግራንዲ የመጠሊያውን ችግር ለመፍታት የዓለም ባንክ እና ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶችን ተማፅነዋል። ስደተኞቹንም "ታጋሽ ሆኜ አብረን እስከሰራን ድረስ አይዘጋም፤ አትስጉ። እዚሁ መቀጠላችን ጥያቄ የለውም" ሲሉ አፅናንተዋል። በደዳብ መጠለያ ጣብያ የሚገኙ ስደተኞች ከሚሰጣቸው የምግብ እርዳታ በተጨማሪ ኣቅማቸዉ ያሳድጉ ዘንድ የተለያየ ስልጠና እየተሰጣቸዉ ይገኛል። በመጠለያ ጣብያው ሴቶችና ህጻናት በብዛት የሚገኙ ሲሆን ጾታዊ ጥቃት ደርሶባቸዉ የተሰደዱ ሴቶች በመጠለያው የምክር ኣገልግሎት ያገኛሉ። ለ26 አመታት አገልግሎት የሰጠው ደዳብ በአሁኑ ሰአት ከ200 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ስደተኞችን ይገኙበታል።
48975201
https://www.bbc.com/amharic/48975201
ኒውዝላንዳውያን "ጦር መሣሪያ አንፈልግም" እያሉ ነው
ከኒውዝላንድ ክራይስርቸርች ጥቃት በኋላ መሣሪያ መታገዱን ተከትሎ፤ ኒውዝላንዳውያን ከፊል አውቶማቲክ መሣሪያቸውን ማስረከብ ጀምረዋል።
መሣሪያ የታጠቀ ግለሰብ መስጅድ ውስጥ በሰነዘረው ጥቃት 51 ሰዎች መግደሉ ይታወሳል። ኒውዝላንዳውያን መሣሪያቸውን እያስረከቡ ያሉት ክራይስትቸርች መስጅድ ውስጥ ሲሆን፤ በቀጣይ በመላው አገሪቱ 250 የመሣሪያ መሰብሰቢያ ይኖራል። • ከክራይስትቸርች የመስጊድ ጥቃት በተአምር የተረፈው ኢትዮጵያዊ እስካሁን 224 መሣሪያ ላስረከቡ 169 የመሣሪያ ባለቤቶች 230,000 ዩሮ ካሳ ተከፍሏል። መሣሪያዎቹ እንዲወድሙም ተደርጓል። የፖሊስ ኮማንደር ማይክ ጆንሰን እንደተናገሩት፤ ዜጎች በጎ ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ። 900 የመሣሪያ ባለቤቶች 1,415 ሽጉጥ ለመመለስ መመዝገባቸውንም አክለዋል። • የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው አንድ የመሣሪያ ባለቤት ለአደን ይጠቀሙበት የነበረውን ሽጉጥ አስረክበው 6,900 ዩሮ ካሳ ተሰጥቷቸዋል። በሂደቱ ደስተኛ እንደሁኑም ተናግረዋል። በእርግጥ መሣሪያ የመሰብሰቡ ነገር ሁሉንም የህብረተሰቡ ክፍል አላስደሰተም። ቪንሰንት ሳንደርስ የተባሉ ግለሰብ መቶ ዓመት እጃቸው ላይ የቆየና የአያታቸው ንብረት የነበረ መሣሪያ አላቸው። መንግሥት መሣሪያ ለመሰብሰብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሰጠው ለሁለት ቀናት ብቻ እንደሆነና ሂደቱ እንደተጣደፈ ይናገራሉ። የኒውዝላንድ መንግሥት ለመሣሪያ መላሾች በአጠቃላይ 110 ሚሊየን ዩሮ ካሳ መድቧል። ወታደራዊ ከፊል አውቶማቲክ መሣሪያዎች እንዲሁም መሣሪያ ለመገጣጠም የሚውሉ ቁሳቁሶች የታገዱት ሚያዝያ ላይ ነበር። በወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጃሲንዳ አርደን በሕዝብ እንደራሴዎች ፊት በስሜት ተሞልተው "እርምጃው መወሰድ ያለበት ትክክለኛ ጊዜ አሁን ነው" ማለታቸው ይታወሳል።
44150424
https://www.bbc.com/amharic/44150424
በዳንጎቴ ሰራተኞች ግድያ ከ15 በላይ ጥይቶች ተተኩሰዋል
የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ሰዎች በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አለፈ።
የዲፕ ካማራ እና የሹፌራቸው አስክሬን (ግራ) እና ሲጓዙበት የነበረው መኪና (ቀኝ) ትናንት ማምሻውን ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ መኖሪያቸው አዲስ አበባ ከተማ እየተጓዙ ሳሉ ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ሁለት ግለሰቦች በመኪናው ላይ ተኩስ በመከፈቱ ስራ አስኪያጁን ጨምሮ አብረዋቸው ሲጓዙ የነበሩት ጸሃፊያቸውን እና ሹፌሩ ተገድለዋል። የዓይን እማኞች እንደነገሩን ከሆነ ህንዳዊ ዜግነት ያለቸው ዲፕ ካማራ ሲጓዙበት የነበረው ቶዮታ ላንድክሩዘር መኪና አካባቢ ወደ 17 የሚሆኑ የጥይት ቀለሃዎች አይተዋል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ በቦታው ላይ የተገኙ የዓይን እማኞቹ እንደሚሉት ከሆነ ሲጓዙበት የነበረው መኪናው ተጋጭቶ እንደቆመ ምልክቶች ያሳያሉ። ጥቃት አድራሾቹ ዲፕ ካማራን በ7 ጥይት በመምታት ገድለዋል። የአድዓ በርጋ የኦህዴድ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ድሪርሳ ታደሰ ደግሞ በስራ አስኪያጁ እና በሁለቱ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው ጋቲራ ተብሎ በሚጠራ ቦታ እንደሆነ ጠቅሰው ግለሰቦቹን ለመግደል ቢያንስ 15 ጥይቶች ተተኩሷል ብለዋል። አቶ ድሪርሳ ''የድርጅቱ ሹፌሮች ከአስተዳደሩ ጋር አለመግባባት ውስጥ ቆይተው ላለፉት ወራት ስራ ላይ አልነበሩም። ከዚህ በተጨማሪም ከፋብሪካው ጋር አብረው ከሚሰሩ ኤጀንሲዎች ጋርም የተለመዱ የሚባሉ አይነት አለመጋባባቶች እንደነበሩ እናውቃለን።'' ብለዋል። ዲፕ ካማራ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካን ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ አስተዳድረዋል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የፋብሪካው ሰራተኛ ለቢቢሲ እንዳሉት፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከባድ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ እንደነበር አስታውሰው፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዲፕ ካማራን ጨምሮ የፋብሪካው ሃላፊዎች ከአካባቢው ማህበረሰበ ጋር ባካሄዱት ተደጋጋሚ ውይይት በፋብሪካው እና በአካባቢው ማህብረሰብ ዘንድ መልካም የሚባል ግንኙነት ተፍጥሮ ነበር። የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ያስተዳደሩት ዲፕ ካማራ በአከባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፤ የቅጽል ስምም ወጥቶላቸው ነበር ሲሉ የፋብሪካው ሰራተኛ ነግረውናል። በተያያዘ ዘገባ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በግለሰቦቹ ላይ በተፈፀመው ግድያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እጅግ ማዘናቸውንና መንግሥታቸው በወንጀሉ ፈፃሚዎች ላይ ምርመራ በማድረግ ጉዳዩን ለፍትህ እንደሚያቀርቡ አስታወቀዋል።
news-50953724
https://www.bbc.com/amharic/news-50953724
የአውስትራሊያ እሳት፡ በሺዎች የሚቆጠሩት እሳት ሽሽት ወደ ውሃ ዳርቻዎች ተሰደዱ
በአውስትራሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተነሳውን የሰደድ እሳት ለማምለጥ ወደ ባህር ዳርቻዎች ተሰደዋል።
እሳቱ ወደ የቪክቶሪያ ባህር ዳርቻ ከተማ ወደ ሆነችው ማላኮታ የተዛመተ ሲሆን ፤ ወደ መኖሪያ ቤቶችም እየገሰገሰ ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ደም በለበሰው ሰማይ ሥር በውሃ ዳርቻዎች ላይ መጠለልና ጀልባዎች ላይ ተሳፍሮ መቆየት "በጣም ፈታኝ ነው" ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልፀውታል። • በእሳትና ከባድ በሙቀት እየተለበለበች የምትገኘው አውስትራሊያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች • በአውስትራሊያ ከባድ ድርቅ አጋጠመ • ከኢትዮጵያ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እስከ አውስትራሊያ ሰደድ እሳት በደቡብ ዌልስ ሌላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውንም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል። እስካሁን በአገሪቷ ከተከሰተው ሰደድ እሳት ጋር ተያይዞ 12 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። በሲድኒና ሜልቦርን መካከል በርካታ በዓል ወደ ሚከበርባቸው ቦታዎች የሚወስዱ መንገዶች በእሳት አደጋው ምክንያት ተቋርጠዋል። በሁለት አውስትራሊያ ግዛቶች፤ ከደቡብ ዌልስ ባቴማስ ቤይ፤ ወደ ቪክቶሪያ ቤርንስዳሌ በ500 ኪሎ ሜትር በአደገኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው። የአባት እና ልጅ እንደሆነ የተነገረ የሁለት ሰዎች አስክሬን በኒው ደቡባዊ ዌልስ ኮባርጎ ከተማም ተገኝቷል። የደቡብ ዌልስ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጋሪይ ወርቦይስ " በጣም አሳዛኝ አጋጣሚ ነው፤ እሳቱ ወደ እነርሱ ከመዛመቱ በፊት ግለሰቦቹ የሚቻላቸውን አድርገዋል"ብለዋል። ባለሥልጣናት እንዳሉት በአካባቢው ሌሎች አምስት ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። ከእነዚህ መካከል አራቱ ከቪክቶሪያ፤ ሌላው ደግሞ ከኒው ደቡባዊ ዌልስ ነው። የቪክቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ዳንኤል አንድሪውስ እንዳሉት በአካባቢው ዋና አውራ ጎዳና በመዘጋቱ፤ አገልግሎት ለተቋረጠባቸው አካባቢዎች ምግብ፣ ውሃ እና ኃይል ለማድረስ መርከብ ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። "እነዚህ ተነጥለው ያሉ ማህበረሰቦች የባህር ኃይልን በመጠቀም መድረስ ይቻላል" ሲሉም አክለዋል። ባለሥልጣናት በአብዛኛው ጎብኝዎች የሆኑና በአካባቢው ያሉ ሰዎች አሁን አካባቢውን ለቆ ለመውጣት ስለረፈደና አደገኛ ስለሚሆን ባሉበት እንዲቆዩ አሳስበዋል። እነዚህ ማህበረሰቦች በሚኖሩበት ሰሜናዊ ግዛት፤ እሳቱ በአካባቢው ባለው ሙቀት ፣ ንፋስና ደረቅ መብረቅ የአየር ጠባይ ሳቢያ እየተስፋፋ መሆኑም ተነግሯል።
news-54695065
https://www.bbc.com/amharic/news-54695065
ኤርዶጋን ዜጎቻቸውን የፈረንሳይ ምርትን አትጠቀሙ አሉ
የቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ቱርካውያን የፈረንሳይ ምርትን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ ጥሪ አቀረቡ። በቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው በፈረንሳይ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ ጫና እየደረሰ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ኤርዶጋን የፈረንሳዩን ፕሬዝደንት የአዕምሮ ጤና ምርመራ ያስፈልጋቸዋል ማለታቸው ይታወሳል። ኤርዶጋን ይህን ያሉት ፕሬዝደንት ማክሮን ጽንፈኛ እስላማዊነትን ለመዋጋት ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። ፈረንሳያዊው መምህር አወዛጋቢውን የነብዩ መሐመድን የካርቱን ምስሎች ክፍል ውስጥ በማሳየቱ አንገቱ ተቀልቶ መገደሉን ተከትሎ ፕሬዝደንት ማክሮን በጉዳዩ ላይ ጠንከር ያለ አቋም እየንጸባረቁ ይገኛሉ። የፈረንሳይ መንግሥትም የአንድን ማህበረሰብ ወይም እምነት ተከታዮችን ስሜት ለመጠበቅ ሲባል የሰዎች የመናገር መብት ሊገደብ አይደባም የሚል ጠንካራ አቋም ይዟል። ፈረንሳይ በያዘችው አቋም ማክሮን ላይ የሰላ ትችት የሰነዘሩት ኤርዶጋን ብቻ አይደሉም። የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትር ''ማክሮን እስልምናን እያጠቁ ነው'' ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረው ነበር። እንደ ኩዌት፣ ኳታር እና ጆርዳን ባሉ አገራት የፈረንሳይ ምርቶች ከመደብር መደርደሪያዎች ላይ ተነስተዋል። የቱርኩ ፕሬዝደንት “ማክሮን የሚባለው ግለሰብ ከእስልምና እና ሙስሊም ጋር ያለው ችግር ምንድነው?” ማለታቸውን ተከትሎ በቱርክ የፈረንሳይ አምባሳደር ወደ ፓሪስ መጠራታቸውን ተዘግቧል። ይህ የኤርዶጋን አስተያየት በፈረንሳይ እና ቱርክ መካከል ያሉ ልዩነቶች እየሰፉ ስለመምጣታቸው አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል። ሁለቱም የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል አገራት ይሁኑ እንጂ የማይሰማሙባቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። በሊቢያ እና ሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ሁለቱ አገራት በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው ይገኛሉ። በአርሜኒያ እና አዘርባጃን ግጭት ውስጥም የሁለቱ አገራት ፍላጎት የተለያየ ነው።
news-53364761
https://www.bbc.com/amharic/news-53364761
ኢትዮጵያ ውስጥ ታስሯል የተባለው ኬንያዊ ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ
ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በርካታ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ኬንያዊው ጋዜጠና ያሲን ጁማ አንዱ ነው።
በአገሪቱ ውስጥ ፖለቲከኞችና የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዳሉ የተነገ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንዱ ኬንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ ይገኝበታል። ያሲን በፖሊሶች ቁጥጥር ስር የዋለው ከሳምንት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የአቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ተግለጿል። ኬንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ አዲስ አበባ ከመያዙ በፊት ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን ከሰዓት በኋላ ከጓደኛው ጋር ሲያደርግ በነበረው የጽሑፍ መልዕክት ልውውጥ ላይ፤ በአቶ ጃዋር መሐመድ ቤት እንደሚገኝና ቤቱም በጸጥታ ኃይሎች እንደተከበበ ጽፎለት እንደነበረ ለቢቢሲ ተናግሯል። የጋዜጠኛው በአቶ ጃዋር መሐመድ ቤት ውስጥ መያዙን በተመለከተ ለማጣራት ቢቢሲ በቤቱ ውስጥ ነዋሪ የሆኑና ከጃዋር የቤተሰብ አባል እንደተረዳው ያሲን ጁማ ከዚያው ቤት በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን አረጋግጧል። ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በቁጥጥር ስር የዋለው አቶ ጃዋር ሐሙስ ዕለት ፖሊሶች ቤቱን ለመፈተሽ ይዘውት በመጡበት ቀን ነው ያሲን የተያዘው። የቤተሰቡ አባል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ፖሊሶች "ያሲንን ጨምሮ ሌሎች ሦስት ሰዎችን ይዘው ሄደዋል።" የጋዜጠኛ ያሲን ጁማ ቤተሰብና ጓደኞቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የመታሰሩን ዜና ይስሙ እንጂ ወደ የት እንደተወሰደና የት እንዳለ እስካሁን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል። የያሲን ባለቤት የሆነችው አሻ መሐመድ እንደምትለው፤ ባለቤቷ የት እንደሚገኝ የምታውቀው ነገር የለም። ለመጨረሻ ጊዜ ያነጋገረችውም ታሰረ በተባለበት ዕለት እንደሆነና የመታሰሩን ዜና የሰማችው 'ሲቲዝን' የተባለው የኬንያ ቴሌቪዥን ጣቢያ እስሩን በዘገበበት ወቅት ነው። በመጨረሻ በተያዘበት ዕለት በዋትስአፕ መልዕክት ሲለዋወጡ እንደነበር ገልጻ፤ በመጨረሻም የጸጥታ ሰዎች አብረውት እንዳሉ ገልጾ መደወል እንዳቆም እንደነገራት ለቢቢሲ ተናግራለች። የጋዜጠኛው ባለቤት አሻ መሐመድ፤ በአሁኑ ጊዜ ባሏ የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ምንም መረጃ እንደሌላት ገልጻ፤ ባለቤቷ የት እና ለምን እንደታሰረ ለማጣራት ጥረት ብታደርግም እስካሁን ምላሽ ማግኘት እንዳልቻለች ትናገራለች። ጉዳዩን በሚመለከትም "ለኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ኢሜይል ጽፌ ነበር፤ አልመለሱልኝም። ስልክ ስደውልም ስልካቸው አይሰራም። ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ብፈልግም በኮሮናቫይረስ ምክንያት መሄድ አይቻልም ተባልኩ" ትላለች። በአዲስ አበባ የሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ በበኩሉ ታስሯል ስለተባለው ጋዜጠኛ ባወጣው መግለጫ፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኬንያውያንን መዝግቦ እንደሚይዝ ጠቅሶ ያሲን ጁማ የሚባል ኬንያዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለመኖሩ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ አመልክቷል። ኤምባሲው ጨምሮም የተነሳውን ጉዳይ ተከትሎ ያሲን ጁማ በመባል የተገለጸው ግለሰብ በእስር ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ደብዳቤ መጻፉን ገልጿል። ቢቢሲ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ ታሰረ ስለተባለው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ እስካሁን ባላቸው መረጃ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንደሌላ ተናግረው፤ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ ኃይል አካላት ጋር አጣራለሁ ብለዋል።
news-54536598
https://www.bbc.com/amharic/news-54536598
የግብርና ሚኒስቴር የትግራይ ክልል መረጃ ባለመስጠቱ የኬሚካል ርጭት ማካሄድ አልተቻለም አለ
የትግራይ ክልል ግብርና ቢሮ የአንበጣ መንጋው ላይ የኬሚካል ርጭት ለማድረግ አስፈላጊ መረጃዎችን ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኑ በትግራይ ክልል በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል እርጭት ማካሄድ አለመቻሉን የግብርና ሚንስቴር አስታወቀ።
በግብርና ሚንስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበራ ለማ ለቢቢሲ እንደገጹት፤ የአንበጣ መንጋውን ለመዋጋት ሚኒስቴሩ አውሮፕላኖችን ጨምሮ የአንበጣ መከላከያ መሳሪያዎችን ቢያዘጋጅም "የትግራይ ክልል ግብርና ቢሮም ይሁን እስከ ወረዳ ያሉት መዋቅሮች የአንበጣውን መገኛ አሳውቆ እርጭት እንዲደረግ የፍቃደኝነት ችግር ስላለ እስካሁን ርጭት አልተካሄደም" ሲሉ ትናንት ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ አበራ አሁንም ቢሆን ከክልሉ ወረዳዎች ጋር በስልክ እየተገናኙ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የአንበጣ መንጋው የተከሰተበትን ቦታ ለይተው የሚያሳወቁ ከሆነ በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ማድረግ እንደሚቻል ጠቁመዋል። የገበሬው ምርት ከፖለቲካ የተለየ ነገር ነው ያሉት የሕዝብ ግነኙነት ዳይሬክተሩ "ፋይዳውን አይተው፤ ለሕብረተሰቡ አስበው" መረጃውን የሚሰጡ ከሆነ የፌደራል መንግሥት የኬሚካል ርጭቱን ለማካሄድ ዝግጅቱም ሆነ ፍላጎቱ አለው ብለዋል። የትግራይ ክልል በበኩሉ ከግብርና ሚኒስቴር የኬሚካል እርጭት የሚካሄድባቸውን ስፍራዎች ለይተው እንዲያሳውቁ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ለቢቢሲ አረጋግጧል። በትግራይ ክልል የእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ የተምች መከላከልና ቁጥጥር፣ የዕፅዋት ኳራንታይን ዳይሬክተር አቶ መብራህቶም ገብረኪዳን "የግብርና ሚንስቴር በአውሮፕላን አማካኝነት የኬሚካል እርጭት ለማካሄድ እንደሚረዱን ገልጸውልናል" ይላሉ። አቶ መብራህቶም "አውሮፕላን እንዲልኩና የሚረጭበት አካባቢ እንድናሳውቃቸው በነገሩን መሠረት ስምምነት ላይ ደርሰናል፤ ቢሆንም ግን እምነት የለንም" ይላሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ "ከዚህ ቀደም በአውሮፕላን የኬሚካል እርጭት እናካሂዳለን ተብሎ ከግብርና ሚንስቴር እንድንዘጋጅ ተነግሮን ብንጠብቅም ዋጃ አጠገብ ድንበር ላይ ረጭተው ተምልሰዋል" በማለት ቀደም ሲል የነበረውን ሁኔታ ጠቅሰዋል። አቶ መብራህቶም እንደሚሉት ከሆነ "አውሮፕላን የትም ቦታ ኬሚካል አይረጭም። ለምሳሌ በመንደር ውስጥ፣ ውሃ ላይ እንዲሁም ተራራማና ሸለቆ ውስጥ መርጨት የለበትም ወይም ለመርጨት አይመቸውም።" አቶ መብራህቶም ጨምረውም "የግብር ሚኒስቴር ቢያግዘን ጥሩ ነው ካልሆነም በራሳችን እንሰራዋለን" ይላሉ። የግብርና ሚንስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበራ ለማ በበኩላቸው "መጠንቀቅ ያለባቸው ለአርሶ አደሩ ሰብል ነው። ለአርሶ አደሩ ካሰቡ ኮኦርዲኔቶቹን [የአንበጣ መንጋው ሚገኝበት ትክክለኛ ስፍራን በካርታ ላይ የሚገኙ አመላካቾች] ሰጥተው ለርጭት ቢያዘጋጁ ጥሩ ነው" ብለዋል። "ለትግራይ፣ ለአማራ፣ ለአፋር ብለን አንለይም። የየትኛውንም አርሶ አደር ምርት ከበረሃ አንበጣ የመለየት ግዴታ ስላለብን ለሁሉም ክልል የሚሆን በጀት መድበናል። ይህን መጠቀም አለመጠቀም ጉዳይ ደግሞ የክልሎች ነው" ብለዋል። "የአርሶ አደሩ ማሳና የአርሶ አደሩ ምርት ከፖለቲካ የተለየ ነገር ነውና ከፖለቲካው ስሜት ወጥተው መረጃዎችን ይስጡን" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ወረዳዎች በተከሰተው የአንበጣ መንጋ ሰፊ ቦታን የሚሸፍን ማሳ ላይ ያለ ሰብል ጉዳት እደረሰበት መሆኑን አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። የአገሪቱ መንግሥትም የአንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንበጣውን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዲኤታው ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ባለፈው ሳምንት መናገራቸው ይታወሳል።
50555749
https://www.bbc.com/amharic/50555749
አባ ሳሙዔል ብርሃኑ፤ “የጃዋር መሐመድ አቀባበል ላይ ስለተገኘሁ ነው የታገድኩት”
ባለፈው ሳምንት አርብ ጃዋር መሀመድ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ውስጥ ከህዝብ ጋር ለመወያየት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ላይ ተገኝተው የነበሩት ቀሲስ ሳሙኤል ብርኃኑ ጃዋርን ለመቀበል በመውጣቴ ከስራ ታግጃለሁ ማለታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።
በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የምትገኘው የደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ክፍል አስተባባሪ የሆኑት ቀሲስ ሳሙኤል ብርኃኑ ከቤተክርስቲያኗ ኃላፊ መልዕክት እንደደረሳቸውም ለቢቢሲ ገልፀዋል። የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ የሆኑት ዶ/ር አማረ ካሳዬ በበኩላቸው "አባ ሳሙዔል አልተባረሩም" ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አባ ሳሙዔል ስብሰባው ላይ የተገኙት በኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት ተጋብዘው እንደሆነ በመግለጽ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ ራሳቸው በወቅቱ ጃዋርን በሚቃወመው ሠልፍ ላይ ታድመው ነበር ብለዋል። ዶ/ር አማረ በበኩላቸው አባ ሳሙዔል የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በትርፍ ሰዓታቸው አነስተኛ ክፍያ እየተከፈላቸው የሚያገለግሉ ካህን ናቸው እንጂ የእኛ ቋሚ ተቀጣሪ አይደሉም ሲሉ ሁኔታውን ያስረዳሉ። • ታዳጊዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረጋቸው ሊያስጨንቀን ይገባል? • እቴጌ፡ የጡት ካንሰርን በቀላሉ በስልክዎ መለየት እንደሚችሉ ያውቃሉ? • ህወሓት ከኢህአዴግ ለመፋታት ቆርጧል? አባ ሳሙዔል እኔ ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም አይደለም የወጣሁት በማለት "ፀሎት በኦሮምኛ እንዳደርግ በማህበረሰቡ ተጋብዤ ስብሰባውንም ተካፍያለሁ" ካሉ በኋላ ስብሰባውን ጨርሰው ከወጡ በኋላ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ ቀሲስ አማረ ካሳዬ መልዕክት እንደደረሳቸው ይናገራሉ። ቀሲስ አማረ እንዲሁ የኦሮሞ ማህበረሰብ ለአባ ሳሙዔል ያቀረበላቸውን ጥሪ አንደነገሯቸው አስታውሰው እንዲሄዱ እንደፈቀዱላቸው፣ የጃዋርን መገኘት ግን እንዳላነሱላቸው ያስታውሳሉ። የጃዋርን መገኘት ቢነግሯቸውም ኖሮ "ሃሳብ እሰጠዋለሁ እንጂ አልከለክለውም... መገኘት መብቱ ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። አባ ሳሙዔል በበኩላቸው የጃዋር መሐመድ አቀባበል ላይ ዋና ተዋናይ ነበርክ፤ በማለት ድርጊታቸው ሥራ አስኪያጁንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ምዕመናንን ማስቆጣቱን በመግለጽ "የእኔ ልጅ፣ ላንተም ለቤተ ክርስቲያኒቷም ደህንነት ሁኔታውን እስክናጣራ ድረስ አገልግሎት ላይ እንዳትገኝ ታግደሃል" የሚል ደብዳቤ እንደደረሳቸው ነግረውናል። እኔ የተገኘሁት ጸሎት ለማድረግ ነው ያሉት አባ ሳሙዔል ደብዳቤውን የጻፉት ቀሲስ አማረ ራሳቸው በስብሰባው ላይ ተገኝተው እንደነበር ተናግረዋል። ቀሲስ አማረ በበኩላቸው ሰልፉ ላይ መገኘታቸውን አረጋግጠው፤ ከሠልፉ በኋላ በርካታ ምዕመናን እየደወሉ ቅሬታ ማቅረባቸውን ያስረዳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ሊያነጋግሯቸው ፈልገው ወደ ግል ስልካቸው ደጋግመው የደወሉ ቢሆንም ሊያገኟቸው አለመቻላቸውን በመጥቀስ ይህ የተፈፀመው ቅዳሜ በመሆኑ እሁድ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቷ ቢመጣ ሊፈጠር የሚችለውን ግርግር ለማስቀረት በሚል "የእኔ ልጅ ጃዋር ስብሰባ ላይ መገኘትህ እኔንም ሕብረተሰቡንም አሳዝኗል፤ በዚህ ምክንያት ላንተም ደህንነት ለቤተ ክርስቲያኒቷም ሲባል በነገው ዕለት እንዳትመጣ ወደፊት የሚደረገውን እንወስናለን" ብለው በስልክ መልዕክት መላካቸውን ያስረዳሉ። ሕዝቡ በጃዋር ላይ ተቃውሞውን ያሰማው "ኦሮሞ ስለሆነ ወይንም ሙስሊም ስለሆነ ሳይሆን በድርጊቱ ነው" የሚሉት ቀሲስ አማረ እርሳቸውም ማዘናቸውን ይናገራሉ። አባ ሳሙዔል፤ የቤተክርስቲያኒቷ ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ አማረ 'ጃዋር ቤተ ክርስቲያን እንዲቃጠል ሲያደርግ ነበር፤ የቤተ እምነቱ ተከታዮችንም ሲያስገድላቸው ነበር' በማለት ተቃውሞ ለማሰማት ከወጡ ሰዎች ጋር ነበሩ ያሉ ሲሆን ቀሲስ አማረ ይህንን ማድረጋቸውን አምነዋል። ይህንን ያደረግኩት ግን "ነገሩ በጣም ስለከነከነኝና ስላሳዘነኝ እንጂ" መውጣትም አልነበረብኝም፤ መውጣትም አልፈልግም ነበር ሲሉ ያብራራሉ። ቀሲስ አማረ አክለውም ይህ የቤተ ክርስቲያናችን አቋምም ነው በማለት "ክርስቲያን በመሆን ብቻ መገደልን መገፋትን" እንደሚቃወሙ ይናገራሉ። አባ ሳሙዔል በበኩላቸው ጃዋር በሚመራው ስብሰባ ላይ ተገኝተው የሚቀርብበትን ክስና ወቀሳ በመጠየቅ መልስ ለማግኘት መሄዳቸውን ይናገራሉ። ቀሲስ አማረ በበኩላቸው "አባ ሳሙዔልን ያስመጣኋቸው እኔ ራሴ ነኝ፤ የተቀበልኳቸውምና አገልግል ያልኩት እኔ ራሴ ነኝ። ኦሮሞ በመሆናቸው ምንም የተፈጠረ ነገር የለም" ሲሉ ያስረዳሉ። እንዲህ አይነት ስብሰባ ለእኔ አዲስ አይደለም የሚሉት አባ ሳሙዔል በበኩላቸው ከዚህ በፊትም አንዱዓለም አራጌ ወደ አሜሪካ በሄደበት ወቅት በቤተ ክርስቲያን ተጋብዞ ፀሎት ማድረጋቸውን ያስታውሳሉ። • "ክስተቱ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ ነው የምረዳው" ጀዋር መሐመድ • ወደ ኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለፀ "ከጃዋር ጋርም የተለየ ነገር አላደረግንም" የሚሉት አባ ሳሙዔል፤ "በተመሳሳይ የሀገሪቷን ሁኔታ ተነጋግረን እኛም በአገራችን ጉዳይ ለመወያየትና ለመካፈል መብት ስላለን ገብተን ተወያይተን ወጣን" ብለዋል። የትላንትናው ደብዳቤ እንዴት እንደተጻፈ ባላውቅም ከዚህ በፊት ግን በተመሳሳይ መድረክ ላይ ተገኝቼ ፀሎት አድርጌ አውቃለሁ የሚሉት አባ ሳሙዔል፤ ከስብሰባው በኋላ ጃዋር 'ፀልዩልን ቤተክርስቲያንም ይሁን መስጂድ የሚጠብቁት ቄሮና ቀሬ ናቸው፤ ስለዚህ እናንተም በፀሎት ከጎናችን እንዳትለዩን' በማለት ተነጋግረን በሰላም ተለያየን ይላሉ። አክለውም ከስብሰባው እንደወጡ ከሥራ መታገዳቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ሲደርሳቸው ሀዘን እንደተሰማቸው ይናገራሉ። ቀሲስ አማረ በበኩላቸው "የማከብረው የምወደው ልጄ ነው፤ መልዕክቱንም ስልክለት ልጄ ብዬ ነው የላኩት። አሁንም ልጄ ነው የምለው እርሱ እንደዚህ ሆኖ በመጥፋቱ በጣም ነው ያዘንኩት" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-49143887
https://www.bbc.com/amharic/news-49143887
ብጉርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
በዓለማችን ከሚገኙ ዕድሜያቸው 11-30 ዓመት የሆናቸው ሰዎች መካከል 80 በመቶ የሚያህሉ ቢያንስ አንዴ በሰውነት ክፍላቸው ላይ ብጉር ይወጣባቸዋል።
ብጉር በዘር ሊተላለፍ የሚችል የቆዳ ችግር ነው። አብዛኛውን ጊዜ ብጉር ፊት ላይ እንዲወጣ የሚያደርገው ቅባት መሳይ ነገር የሚያመነጭ እጢ እና ከቆዳ ስር የሚገኝ ባክቴሪያ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቆዳ እና የአባላዘር በሽታ ትምህርት ክፍል መምህር እና ሃኪም የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ዳኛቸው ሺበሺ ናቸው። በዕጢ አማካኝነት የሚመነጨው ይህ ቅባት መሳይ ፈሳሽ በቆዳችን ላይ ቀዳዳ በመፍጠር ከቆዳ ሥር ወደ ሚገኘው ባክቴሪያ በመግባት ብጉር እንዲፈጠር ያደርጋል። • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች፤ በተለይም ደግሞ ቅባታማ ምግቦች ፊት ላይ ለሚወጣ ብጉር ምክንያት ናቸው ተብሎ የሚታመነው ስህተት መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው ይናገራሉ። ከቢቢሲ ኧርዝ ላብ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ ደግሞ ቅባታማ ይዘት ካላቸው ምግቦች ይልቅ ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸው ምግቦች እና መጠጦች በፊት ላይ ብጉር እንዲወጣ ያደርጋሉ። ለምሳሌ ለውዝ ከመብላት ይልቅ የለስላሳ መጠጦችን መጠቀም ለብጉር ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል። ዶ/ር ዳኛቸው "ብጉር በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ከሚኖሩ ሰዎች ይልቅ ብዙውን ጊዜ የተሻለ ህይወት በሚመሩ ሰዎች ላይ ይከሰታል። የወር አበባ ሊመጣ ሲል ብጉርም ፊት ላይ ሊወጣ ይችላል" ይላሉ። ብጉር ብዙውን ጊዜ በታዳጊዎች እና ወጣቶች ላይ ይስተዋል አንጂ በአዋቂዎች ላይም ይወጣል። ፊታቸው ላይ ብጉር መውጣቱ የሚያስጨንቃቸው ወጣቶች የህክምና እርዳታ ፍለጋ ወደ ሆስፒታሎች እንደሚመጣጡ ዶ/ር ዳኛቸው ይናገራሉ። ህክምናውም ከሶስት እስከ ስድስት ወራት ሊፈጅ እንደሚችል የሚያስረዱት ዶ/ር ዳኛቸው፤ ብጉር ፊት ላይ የሚጥለውን ምልክት ማስወገድ ግን ቀላል እንደማይሆን ይናገራሉ። • ጤና የራቀው የፈለገ ህይወት ሆስፒታል ብጉርን መከላከል ይቻላል? ብጉር እንዳይወጣ ማድረግ አይቻልም። ብጉር ከወጣ በኋላ ግን በእጅ ለማፍረጥ መሞከሩ በፊታችን ላይ አላስፈላጊ ምልክቶችን ጥሎ እንዲያልፍ የሚያደርግ ስለሆነ ከዚህ መሰሉ ተግባር መቆጠብ እንደሚገባ ዶ/ር ዳኛቸው ይናገራሉ። ዶ/ር ዳኛቸው እንደሚሉት በጸሃይ ጨረር ምክንያት ብጉር የሚወጣባቸው ሰዎች አሉ። እንደዚህ አይነት ሰዎች በተቻላቸው መጠን የጸሃይ ጨረር መካላከያ ክሬሞችን በመጠቀም ብጉር መከላከል ይችላሉ ይላሉ። የቢቢሲ ኧርዝ ላብ መረጃ እንደሚያመላክተው ደግሞ የስኳር መጠናቸው ከፍተና የሆኑ መግቦችን እና መጠጦችን ማቆም፣ በሶስት ወር እንዴ 30ሚሊ ግራም የዚንክ እንክብል መውሰድ ብጉር ሊከሰት የሚችልበትን አጋጣሚ በ15 በመቶ እንደሚቀንስ ያትታል። መረጃው በተጨማሪም ፊትን አብዝቶ አለመኳኳል፣ ጽጉር እና ሙሉ ሰውነትን ዘወትር መታጠብ ብጉር እንዳይከሰት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። • በየቀኑ አንድ ሚሊየን ሰው በአባላዘር በሽታ ይያዛል
44570372
https://www.bbc.com/amharic/44570372
የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ?
ኢትዮጵያ ለኤርትራ ላደረገችው የሰላም ጥሪ ኤርትራ ልዑካን ወደ አዲስ አበባ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ የሁለቱ አገራት ቀጣይ ግንኙነትን በሚመለከት የተለያዩ ሃሳቦች እየተሰነዘሩ ነው።
አዲስ አበባ እና አስመራ የሁለቱ ሃገራት ህዝቦች ባህል፣ቋንቋንና በርካታ እሴቶችን የሚጋሩና በብዙ መልኩ የሚተሳሰሩ ናቸው። አገራቱ ወደ ጦርነት ከመግባታቸው በፊት ጠንካራ ግንኙነት እንደነበራቸው የሚታወስ ነው። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሁለቱ አገራት መካከል በትክክልም ሰላም ማውረድ ከተፈለገ ስምምነቱ በመሪዎች ደረጃ የሚደረግ ፖለቲካዊ ስምምነት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን ከግንዛቤ ያስገባ መሆን እንዳለበት እየተገለፀ ነው። ሁለቱ አገራት ተሳክቶላቸው ግንኙነታቸውን ወደ ቀድሞ መመለስ ከቻሉ አገራቱ በተለይም ከኢኮኖሚ አንፃር ከግንኙነቱ ምን ያተርፋሉ?ህዝቡስ ምን ያገኛል? እንዲሁም ግንኙነቱ ዳግም እንዳይደናቀፍ ምን ማድረግ ይቻላል ?የሚሉና መሰል ጥያቄዎች ይነሳሉ። መቀመጫቸውን ለንደን ያደረጉት የአለም አቀፍ ግንኙነትና ኢኮኖሚ ትብብር ኤክስፐርት አቶ አብዱራህማን ሰኢድ የሁለቱ አገራት መልካም ግንኙነት መፍጠር ለሁለቱም ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አለው ይላሉ። ከአንድ መቶ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላት ኢትዮጵያ ለኤርትራ ሰፊ ገበያ መሆን መቻሏ፣ኤርትራ ወርቅን የመሰሉ ማእድናት ያሉባት መሆኗ፣ኤርትራ በምግብ ምርት ራሷን የቻለች አለመሆኗና ኢትዮጵያ ይህን ክፍተት መሙላት፤እንዲሁም ኢትዮጵያ የኤርትራ ወደቦችን መጠቀም መቻሏና ይህ ደግሞ ለኤርትራ ትልቅ ጥቅም እንደሚሆን በመጠቃቀስ ነጥባቸውን ያስረዳሉ። የግንኙነቱን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማረጋገጥ ግን በሁለቱም አገራት በኩል መልካም አስተዳደርን ማስፈንና ተቋማዊ ስርአት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ ያስረዳሉ። በአሁኑ ወቅት እየተደረጉ ባሉ መሻሻሎች ምክንያት በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ በኩል ምንም ችግር ባይኖርም በኤርትራ በኩል ግን ብዙ ስራ እንደሚቀር ያስረዳሉ። "በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት መጠበቅ እንዲሁም የፖለቲካ ነፃነት አለ።በተቃራኒው በኤርትራ የአንድ ሰው አገዛዝ ስርአት ነው ያለው''የሚሉት አቶ አብዱራህማን በአገራቱ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና ዲሞክራሲያዊ ስርአት እስካልተገነባ ድረስ ለአገራቱ ሰላም ኢኮኖሚያዊ ግንም ዋስትና የሚሆን ነገር እንደማይኖር ይገልፃሉ። በጦርነቱ ዋዜማ የሁለቱ አገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙት ምን ይመስል አንደነበር የሚያስታውሱት የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖትም የአቶ አብዱራህማንን ሃሳብ ይጋራሉ። እሳቸው እንደሚሉት ቀድሞ በሁለቱ አገራት መካከል መልካም ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት ይኖራል የሚል እምነት ነበር።ነገር ግን በወቅቱ የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ባልተገባ መልኩ ሊጠቀም መፈለጉ ችግር ፈጥሯል። "በተለይም ኤርትራ የራሷን ገንዘብ ናቅፋን ማተሟን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሁሉም ግብይቶች በዶላር እንዲሆኑ መወሰኗን ኤርትራ እንደ ትልቅ የኢኮኖሚ እንቅፋት በመቁጠር ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ተነሳች"ይላሉ። ያ የኢኮኖሚ ግንነኙነት እንከንም በድንበር ስም ለሁለቱ አገራት ጦርነት ውስጥ መግባት ምክንያት እንደሆነ ይገልፃሉ። አቶ አብዱራህማንም በሁለቱ አገራት ዋስትና የሚሰጥ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እስከሌለ ድረስ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶቹ መቀጠል ቢችሉ እንኳን ሃይል ላላቸው ቡድኖች እንጂ ለህዝቡ ወርዶ ጠብ የሚል ነገር እንደማይኖር ያስረዳሉ። ከዚህ ሲያልፍም ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቱ ዳግም የግጭት ምክንያት የመሆን ሰፊ እድል እንደሚኖረው አቶ አብዱራህማን ያሳስባሉ። ነገር ግን ለኢኮኖሚ ግንኙነቱ የሚሉት አይነት ዋስትና የሚሰጥ ስርአት መዘርጋት ከተቻለ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ብቻ ሳይሆን ሰፊ ማህበራዊና ባህላዊ እሴት የሚጋሩት እንደ ጅቡቲና ሶማሊያ ያሉ አገራትን ጨምሮ ጠንካራ አካባቢያዊ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት መዘርጋት እንደሚቻል አቶ አብዱራህማን ትልቅ ተስፋ አላቸው።
news-53803589
https://www.bbc.com/amharic/news-53803589
በሰርጋቸው ዕለት ለደረሰ ጥቃት ተጠያቂ የተደረጉት ጥንዶች
በሕይወታቸው በእጅጉ የሚደሰቱበት ቀን መሆን ነበረበት፤ ነገር ግን እጅግ ዘግናኙ ቀን ሆኖ አልፏል።
ሚርዋስ እና ሪሃና ባሳለፍነው ዓመት በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ሰርጋቸውን በሚያካሂዱበት ስነ-ስርዓት ላይ አንድ የአይኤስ ታጣቂ ባደረሰው የቦምብ ጥቃት 90 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። ጥንዶቹ በደረሰው ፍንዳት በርካታ የቤተሰብ አባሎቻቸውን፣ ጓደኛና ወዳጅ ያጡ ሲሆን በወቅቱ የደረሰባቸው የስነ አእምሮአዊ ጫናም ቀላል የሚባል አልነበረም። በዚህ ሳምንት ደግሞ ጥቃቱ ከደረስ አንድ ዓመት ይሞላዋል። የ18 ዓመቷ ሪሃና በዛች ዕለት ምን እንደተፈጠረ በይፋ ለማውራት ለመጀመሪያ ጊዜ ፈቃደኛ ሆናለች። ''በየቀኑ ሌሊት ላይ ቅዠት ይቀሰቅሰኛል፤ ሁሌም ስለማለቅስ እንቅልፍ አይወስደኝም'' ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። እሷ እንደምትገልጸው በርከት ያሉ ሰዎች የተሰበሰቡቡት ቦታ ስትገኝ ጭንቀት የሚይዛት ሲሆን በመኪና መንቀሳቀስም በእጅጉ ትፈራለች። ''በማንኛውም አጋጣሚ ተኩስ ወይም የፍንዳታ ድምጽ ስሰማ በሰርጌ ዕለት የተፈጸመውን ነገር ያስታውሰኛል፤ ነገሮቹ ሁሉ በድጋሚ የሚፈጠሩ እየመሰለኝ በጣም እፈራለው" ብላለች። ጥቃቱ ከተፈጸመ አንደኛ ዓመቱን ለማስታወስ ዘመዶቻቸውና ወዳጆቻቸው ሰርጉ ከተካሄደበት አዳራሽ ፊትለፊት በመሰብሰብ ቦምቡን ያፈነዳው አካል ለፍርድ እንዲቀርብ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ሚርዋስ ግን በቦታው አልተገኘም ነበር። ስለፍንዳተው ማሰብ በራሱ ሰውነቱን እንደሚያንቀጠቅጠው ይናገራል። ''ከፍንዳታው በፊት ሁላችን በደስታ ተውጠን ነበር። ነገር ግን በድንገት ሁላችን ከሰማይ ወደ ምድር የወደቅን አይነት ስሜት ተሰማኝ። በቅጽበት ውስጥ ደስታችን ወደ ሀዘንና ዋይታ ተቀየረች።'' የጥንዶቹ የሰርግ ስነ-ሰርዓት ላይ አይኤስ የተባለው አክራሪ እስላማዊ ቡድን ጥቃት የፈጸመው አፍጋኒስታን ውስጥ እንደ አናሳ ከሚቆጠሩት ሺአዎች አባል ስለሆኑ ነው። አይኤስም ሺአዎች እስልምናን ሙሉ በሙሉ አይቀበሉም በማለት ባለፉት ዓመታት ተደጋጋሚ ጥቃት ይፈጽማል። ለሪሀና እና ሚርዋስ የሰርጋቸው ዕለት የደረሰው ጥቃት አልበቃ ብሎ አንደንድ ዘመዶችና ጓደኞች ለፈሰሰው ደም እናንተ ናችሁ ተጠያቂዎች በማለት ወንጅለዋለቸዋል። ''አንድ ቀን አስቤዛ ለመግዛት ስንቀሳቀስ አንዲት በሰርጋችን ዕለት ዘመዷን የተነጠቀች ሴት አገኘሁ። አንተ ነብሰ በላ ነህ አለችኝ'' በማለት ያጋጠመውን ነገር ሚርዋስ ያስታውሳል። ሪሃናም ብትሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰዎች ጥፋተኛ እንደሆነች ነግረዋታል። ''አንቺና ባለቤትሽ በዛች በተረገመች ዕለት ሰርጋችሁን ባታካሂዱ ኖሮ ይሄ ሁሉ አይከሰትም ነበር'' የሚሏት በርካቶች ናቸው። ምንም እንኳን አይኤስ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ቢወስድም በአፍጋኒስታን በኃይልም በተቀባይነትም ጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኘው ታሊባን ነው። ታሊባንም ከአይኤስ ሲነጻጸር አነስተኛ ቁጥር ያለው ጥቃት ነው የሰነዘረው። እስካሁንም በአስርታት የሚቆጠሩ ጥቃቶችን በአፍጋኒስታን ፈጽሟል። ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ቡድኑ በዋና ከተማዋ ካቡል በአንድ ሆስፒታል ወላዶች ክፍል ውስጥ ፈጽሞታል በተባለው ጥቃት 24 ሴቶች፣ ህጻናትና አዲስ የተወለዱ ልጆች ተገድለዋል። ሪሃና እና ሚርዋስ በተፈጠረው ነገር አሁንም ድረስ ስነ-ልቦናዊ ጫና ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በነሱ ምክንያት እነዚያ ሁሉ ሰዎች መሞታቸው ደግሞ የጥፋተኝነት ስሜት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። ነገር ግን ጥንዶቹ የደረሰባቸውን የአእምሮ መታወክ ለማስታገስ በማሰብ የስነ-ልቦና ባለሙያ ጋር እስከመሄድ ደርሰዋል። በአሁኑ ሰአትም ትልቅ መሻሻል እያሳዩ እንደሆነ እራሳቸው መስክረዋል።
news-42262006
https://www.bbc.com/amharic/news-42262006
የኮንጎ ቀውስ ከመካከለኛው ምስራቅ እንደሚያይል እየተነገረ ነው
በአህጉረ አፍሪካዋ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከሰተው የእረስ በርስ ግጭት መፈናቀልን ካስከተሉ ግጭቶች ሁሉ የከፋ ነው ሲሉ የእርዳታ ድርጅቶች አሳሰቡ።
ሃገሪቱ ታጣቂዎች መንግሥትን ከሥልጣን ለማውረድ ትግል ከጀመሩ ወዲህ ሰላም አጥታ ቆይታለች። በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ባለፈው ዓመት ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካ በመቅረቱ ወደ ከፋ አረንቋ እንድትገባ አድርጓታል። "በመካከለኛው ምሥራቅ በተለይ ደግሞ በኢራቅ፣ የመንና ሶሪያ ግጭትን ሸሽተው ከሚሰደዱ ሰዎች በላይ በኮንጎ መኖሪያቸውን ጥለው የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እጅግ እያየለ ነው" ይላሉ የኖርዌይ እርዳታ ድርጅት የኮንጎ ኃላፊ ኡልሪካ ብሎም። በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት እንደሚየሳየው በያዝነው ዓመት ብቻ ቢያንስ በየቀኑ 5 ሺህ ሰዎች መኖሪያቸውን ጥለው ይሰደዳሉ። ለዚህም እንደ ዋነኛ ምክንያት እየተጠቀሱ ያሉት አዳዲስ ግጭቶች፣ የነባር ግጭቶች ማገርሸትና ምርጫው ባለመካሄዱ ምክንያት የተከሰተው ፖለቲካዊ ሽኩቻ ነው። እስካሁን 4 ሚሊዮን ሰዎች ከመኖሪያቸው ከመፈናቀላቸውም በላይ 7 ሚሊዮን የሚሆኑ የኮንጎ ዜጎች የምግብ እርዳታ እንደሚያሻቸው ነው ኃላፊዋ የሚያስረግጡት። "አሁኑኑ ፈጥነን ምላሽ መስጠት ካልቻልን የከፋ ረሃብ ተነስቶ የሰው ሕይወት እንደ ቅጠል መርገፉ አይቀሬ ነው" ሲሉም ያስጠነቅቃሉ። የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የማስታወቂያ ሚኒስትር ላምበርት ሜንዴ ግን የእርዳታ ድርጅቶቹን ስጋት ችላ በማለት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በታች ነው ይላሉ። ሚኒስትሩ ለቢቢሲ 'ፎከስ ኦን አፍሪካ' ዝግጅት እንደተናገሩት "እየወጡ ያሉ ዘገባዎች ሃሰት ናቸው፤ ይልቁንም ዜጎች ከተሰደዱበት እየተመለሱ ናቸው" ብለዋል። ዓለም የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን ጉዳይ ፊት ነስቶታል ይላል የቢቢሲው ጄምስ ኮፕናል። ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ይላል. . ."ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ያለውን ቀውስ የሚዘግቡ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሃገሪቱ ውስጥ የሉም።" "ወጣም ወረደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እንደ ሶሪያ ያለ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትም ሆነ ተፈላጊነት የላትም፤ ለዛም ነው ዓለም ፊት የነሳት" ሲልም ይከራከራል። ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የሰፊ ግዛት ባለቤትና በርካታ የተፈጥሮ ሃብት ያላት ሃገር ብትሆንም ለተከታታይ ዓመታት በሃገሪቱ የተከሰተው ግጭት ሰዎች በድህነት እንዲማቅቁና መሰረት ልማቶች እንዳይስፋፉ አድርጓል። በአውሮፓውያኑ 2001 ላይ በተገደሉት አባታቸው ሎረንት ካቢላ ቦታ ተተክተው ሥልጣን የያዙት ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ ሁለት ጊዜ ምርጫ ቢያሸንፉም ለሦስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ሕገ-መንግስቱ አይፈቅላቸውም። ተቺዎች ምርጫው የተጓተተው ካቢላ በሥልጣን እንዲቆዩ ታስቦ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ። የመንግሥት ተቃዋሚዎች ይበዙበታል ተብሎ በሚታሰበው ማዕከላዊ ካሳይ በተከሰተ ግጭት እስካሁን 400 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
news-42135372
https://www.bbc.com/amharic/news-42135372
የዱቄት ወተት እና የእናት ጡት ወተት ምንና ምን ናቸው?
መርዛማ ጋዝ እና የቀለጠ አለት ተቀላቅለው ከ ታምቦራ ተራራ በንፋስ ፍጥነት ሺዎችን እየገደሉ ይንደረደራሉ። ግዙፉ የታምቦራ ተራራ በ 1220 ሜትር አጥሯል።
ይህ የሆነው በ1815 ነበር። ቀስ በቀስ የአመድ እሳተገሞራ ወደ ሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ በማምራት ፀሀይን ጋረዳት። በ1816 አውሮጳ ያለ ክረምት ያለፈ ዓመት ሆነ ፤ ሰብሎች ደረቁ። ረሃብ የጠናባቸው ሰዎች አይጦችን፣ድመቶችን እና ሳር ተመገቡ። በጀርመኗ ዳርምስታድት ከተማ የዚህ ጉስቁልና ጥልቀት ለ 13 ዓመቱ የፈጠራ ሃሳብ ፈነጠቀለት። ጀስተስ ቮን ሊይቢግ አባቱን በስራ ቦታው ቀለም በመቀባት፣ በመወልወል እና በማቀራረብ ማገዝ ይወድ ነበር። ጥልቅ ጥናት ሊይቢግ ርሃብን የመከላከል ምኞትን ሰንቆ ምርጥ የኬሚስትሪ ባለሙያ ሆኖ አደገ። በማደበሪያ ላይ የተደረጉ የቀደሙ ምርምሮችን ሰርቷል። የስነምግብ ሳይንስ ምርምርም ፈርቀዳጅ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ሌላም ነገር ፈጥሯል፡ የዱቄት ወተትን። ሊይቢግ በ1865 ያስተዋወቀው ለህፃናት ያዘጋጀው ሟሚ ምግብ ከላም ወተት፣ከስንዴና ከብቅል ዱቄት እንዲሁም ከ ፖታሺየም ካርቦኔት የተዘጋጀ ነበር። ይህ የእናት ጡት ወተትን ተክቶ ለገበያ የቀረበ የመጀመሪያው የምርምር ውጤት ነበር። ሊይቢግ እንዳስተዋለው ሁሉም ህፃን ጡት የሚያጠባው እናት የለውም። ዘመናዊ ህክምና ሳይስፋፋ በፊት ከ100 ነፍሰጡር እናቶች መካከል አንዷ በወሊድ ምክንያት ትሞት ነበር። ዛሬ ይህ ቁጥር በድሃ አገራት በመጠኑ የተሻሻለ ነው። አንዳንድ እናቶች ደግሞ ጡታቸው ወተት አያግቱምም፤ ቁጥሩ አከራካሪ ቢሆንም ከሃያ እናቶች መካከል አንዷ ይህ አይነት ነገር እንደሚገጥማት ይገመታል። ታዲያ የዱቄት ወተት ከመፈብረኩ በፊት እነዚህ ህፃናት ምን ይውጣቸው ነበር? አቅሙ ያላቸው ወላጆች ልጃቸውን የሚያጠባላቸው ነርስ ይቀጥሩ ነበር፤ ከሊይቢግ ፈጠራ በፊት ጥሩ ገቢ የሚገኝበት ስራ ነበር። አንዳንዶች ደግሞ ፍየል ወይም አህያን ይጠቀሙ ነበር። ጀስተስ ቮን ሊይቢግ የፈጠራ ሃሳቡ የመጣለት አዳጊ እያለ የተመለከተው ረሃብ ነበር ጥሩ ግጥምጥሞሽ በርካቶች ለጨቅላዎቻቸው ዳቦ በውሃ አላቁጠው ይመግቡ ነበር፤ ይህ ደግሞ የመመገቢያ እቃው በቀላሉ በባክቴሪያ ስለሚበከል የጨቅላው ጤና አደጋ ላይ ይወድቃል። በ1800ዎቹ የመጀመሪያ አመታት የእናታቸውን ጡት ወተት ማግኘት ካልቻሉ ሶስት ህፃናት መካከል ሁለቱ ብቻ ነበሩ በህይወት መኖር የሚችሉት። የሊይቢግ የዱቄት ወተት በዚህ ወሳኝ ወቅት ነበር ገበያውን የተቀላቀለው። የጀርም ቲየሪ በሚገባ ተዋውቆ ነበር፤ የጡጦ ጫፍም ተፈብርኮ ነበር። በዚህ ወቅት የዱቄት ወተትም ጡት ማጥባት ካልቻሉ እናቶች በላይ ፈጥኖ ተሰራጨ። የሊይቢግ ለህፃናት የተዘጋጀ ሟሚ ምግብ ቀደም ሲል ጥሩ የኑሮ ዘይቤ ለሚመሩ ብቻ የነበረው አስቀርቶ ለሁሉም መድረስ ቻለ። አሁን ደግሞ ዘመናዊ የስራ ቦታን መልክ ለመስያዝ የሚመረጥ ሆኗል። ከወለዱ በሗላ ወደ ስራ መመለስ ለሚፈልጉ በርካታ እናቶች የዱቄት ወተት የፈጣሪ በረከት ሆኖ ቀረበ። የገቢ ክፍተት በቅርቡ የቺካጎ ዩኒቨርስቲ ከማስተርስ ዲግሪ መርሃ ግብር ወጥተው በማማከር እና በፋይናንስ አለም ወደስራ የገቡ ከፍተኛ ሃላፊነት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ላይ ጥናት አድርጎ ነበር። መጀመሪያ ላይ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው የገቢ መጠን ተመሳሳይ ይመስል ነበር። ከጊዜ በሗላ ላይ ግን ከፍተኛ የሆነ የገቢ ልዩነት መታየት ጀመረ። ይህ ደግሞ የሆነው በወሊድ ጊዜ ነው። ሴቶች ሲወልዱ ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ከስራ እረፍት ይወስዳሉ በምላሹ ቀጣሪዎች አነስተኛ ክፍያ ይከፍሏቸዋል። በተገላቢጦሽ ከሴቶች የበለጠ ልጅ ያላቸው ደግሞ ወንዶች ናቸው። ነገር ግን የስራ ጊዜያቸውን አይቀይሩም። ሴቶች ብቻ አምጠው መውለድ የመቻላቸውን ሀቅ ልንቀይረው አንችልም፤ነገር ግን የስራ ቦታ ባህሉን ልናስተካክለው እንችላለን። አንዲት ወላድ እናት ከወሊድ በሗላ ወደ ስራዋ ስትመለስ አባቶች ልጃቸውን ለመንከባከብ የዱቄት ወተት ቀላል ያደርግላቸዋል። በርግጥ የጡት ማለቢያ አማራጭ አለ። ነገር ግን ለአንዳንዶች ይህ ከዱቄት ወተት በላይ ጥረት የሚጠይቅ ነገር ነው። በ2016 በህክምና የጥናት መፅሄቶች ላይ የዱቄት ወተት የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያሳዩ በርካታ ጥናቶች ታትመዋል። የዱቄት ወተት የሚጠጡ ህፃናት የእናታቸውን ጡት ከሚጠቡ ህፃናት በበለጠ ይታመማሉ፤ በዚህም የተነሳ ወላጆች የህክምና ወጪያቸው ይጨምራል፤ እንዲሁም ከስራ ገበታቸው ላይ በተደጋጋሚ ይቀራሉ። ጡት በማጥባት ብቻ ግማሽ ያህል የህፃናት ተቅማጥን እና ሶስት እጅ የሚሆነውን ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዘ ኢንፌክሽንን መከላከል እንደሚቻል ይታመናል። በዚህ ጥናት መሰረት የእናት ጡት ወተት በአመት 800 000 ያህል የህፃናት ሞትን መከላከል ያስችላል። ታዲያ ሕይወት ለመታደግ ለፈለገው ጀስተስ ቮን ሊይቢግ ይህ አስደንጋጭ ነው። ጨቅላ ህፃናትን የእናት ጡት ማጥባት በአመት ከ 800,000በላይ የህፃናት ሞትን እንደሚከላከል አጥኒዎች ያምናሉ ኢኮኖሚያዊ አንድምታው እርግጥ ነው ባደጉት ሃገራት የተበከለ ወተት እና ውሃ ጉዳይ ያን ያህል ራስ ምታት አይደለም። የዱቄት ወተት ግን ሌላ ኢኮኖሚያዊ ገፅታ አለው። በላንሰንት ጥናት መሰረት የእናታቸውን ጡት እየጠቡ ያደጉ ልጆች የአይ ኪው (IQ)መጠናቸው ከሌሎቹ በሶስት ነጥብ ከፍ ያለ ነው። ይህ ታዲያ ትውልዱን ሁሉ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ለማድረግ ምን ያህል ይሆናል? ጥናቱ ይህንንም አስልቶታል። በአመት 300 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ያህል ያስወጣል። ይህ ደግሞ የአለም የዱቄት ወተት ገበያ ያህልን ይሆናል። ሊይቢግ ራሱ ለህፃናት ያዘጋጀው ሟሚ ምግብ ከእናት ጡት ወተት ይበልጣል ብሎ ተወራርዶ አያውቅም፤ በተቻለ መጠን በንጥረ ነገር ተመሳሳይ የሆነ ነገር እንደፈጠረ ግን ተናግሯል።
news-55919904
https://www.bbc.com/amharic/news-55919904
ሚየንማር፡ በመፈንቅለ መንግሥት የተፈነገሉት የሚየንማሯ ፕሬዝዳንት ሳን ሱ ቺ ተከሰሱ
በመፈንቅለ መንግሥት የተፈነገሉት የሚየንማሯ ፕሬዝዳንት ክስ ተመሰረተባቸው።
ሰኞ ዕለት መፈንቅለ መንግሥት በተደረገባቸው የሚየንማር ፕሬዝዳንት ሳን ሱ ቺ ላይ ፖሊስ በርከት ያሉ የክስ መዝገቦችን ከፍቶባቸዋል። የፖሊስ መዝገብ እንደሚያሳየው ከሆነ ፕሬዝዳንቷ እስከ የካቲት ስምንት ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ይቆያሉ ተብሏል። ሕጋዊ ያልሆኑ የወጭ እና ገቢ ንግዶችን እንዲሁም በሕገ ወጥ መንገድ የኮሚዩኒኬሽን ንብረቶች ባለቤት መሆን የሚሉት ከክሶቹ መካከል ናቸው። እስካሁን ፕሬዝዳንቷ የት እንዳሉ አይታወቅም፤ ነገር ግን በመዲናዋ ናይ ፒይ ታው ውስጥ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ተገምቷል። ከስልጣን የተወገዱት ፕሬዝዳንት ዊን ሚንትም ተከሰዋል። እርሳቸው የተከሰሱበት ወንጀል ደግሞ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተጣለውን የመሰብሰብ እገዳ በመተላለፍ ነው ተብሏል። በመሆኑም ለሁለት ሳምንታት ያክል በፖሊስ ቁጥጥር ውስጥ ይቆያሉ ብሏል። ሁለታቸውም ግን መፈንቅለ መንግሥቱ ከተካሄደ ጊዜ ጀምሮ ድምጻቸው አልተሰማም። በሚን አውንግ ህላይንግ የተመራው ወታደራዊው መፈንቅለ መንግሥቱ 11 አባላትን በማዋቀር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የአስተዳደር ሥራውን ጀምሯል። ወታደራዊው ጁንታ ባለፈው ህዳር ወር የተካሄደውን ምርጫ የተጭበረበረ ነው በማለት መፈንቅለ መንግሥቱን ተቀባይነት ለማስገኘት እየጣረ ነው። አሁን ላይ በፖሊስ የቀረቡት የክስ ዝርዝሮች የመጀመሪያና ለፍርድ ቤት የቀረቡ ሪፖርቶች ናቸው ተብሏል። በእዚህም የኮሚዩኒኬሽን መሳሪያዎችን በሕገ ወጥ መልኩ አስገብተው በቤታቸው ተገኝቷል የሚል ክስ በሳን ሱ ቺ ላይ ቀርቦባቸዋል። እማኞችን ለመጠየቅ፣ መረጃ ለመጠየቅ እና ተከሳሿን ጠይቆ የሕግ ምክር ለማግኘት ሲባል በቁጥጥር ሥር መቆየታቸውን የክስ መዝገቡ አስረድቷል። ዊን ሚይንት ደግሞ በብሔራዊ 'ዲዛስተር ማኔጅመንት' ሕግ የተከሰሱ ሲሆን፣ የቀረበባቸው ክስ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተጣለውን እገዳ በመጣስ ለምርጫ ቅስቀሳ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ስብሰባ አካሂደዋል የሚል ነው።
news-55383942
https://www.bbc.com/amharic/news-55383942
ኮቪድ-19፡ የዓለም ጤና ድርጅት በዩኬ የተከሰተውን አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በቅርበት እየተከታተልኩ ነው አለ
የዓለም ጤና ድርጅት በዩናይትድ ኪንግደም የተከሰተውን አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከአገሪቷ ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ መሆኑን አስታወቀ።
የአገሪቷ ባለሥልጣናት እንዳሉት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ቀድሞ ከነበረው በበለጠ በስፋት እየተዛመተ ሲሆን፤ የበለጠ ገዳይ ነው ተብሎ ግን አይታመንም። ለንደንን ጨምሮ የደቡብ ምስራቅ እንግሊዝ ሰፊው ክፍል የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት አዲስ እና ጥብቅ ገደብ ውስጥ ናቸው። ኔዘርላንድስ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ መከሰትን ተከትሎ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚደረጉ በረራዎችን ማገዷን አስታውቃለች። እገዳው ከእሁድ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን እስከ አውሮፓውያኑ ጥር አንድ ድረስ እንደሚቆይ የደች መንግሥት ገልጿል። እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በዩናይትድ ኪንግደም ከተገኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ናሙና በመገኘቱ እንደሆነ ተነግሯል። በዩኬ የተከሰተውን ሁኔታ የበለጠ ግልፅ እንዲሆን እየተጠባበቁ መሆኑን የገለፀው የአገሪቷ መንግሥት፤ "አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ወደ ኔዘርላንድስ ሊገባ የሚችልበትን ሁኔታ በተቻለ መጠን መገደብ አለበት" ብሏል። የደች መንግሥት አክሎም በቀጣዮቹ ቀናት በዩኬ የተገኘውን የአዲሱን ቫይረስ አደጋ ባለበት ለመቆጣጠር ስለሚያስችለው ሁኔታ ከሌሎች የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ጋር አብሮ እንደሚሰራ አስታውቋል። ስለአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የምናውቀው የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩኬ ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ድርጅቱ እንዳለው ዩኬ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ በተመለከተ እየተካሄዱ ስላሉ ጥናቶች መረጃዎችን ስታጋራ እንደነበር ጠቅሶ፤ ድርጅቱ ስለአዲሱ ቫይረስ ባሕርይ እና አደጋው የደረሰበትን ለአባል አገራቱ እና ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው እስከ 70 በመቶ ያህል የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከፍተኛ ሞት ስለማስከተሉ አሊያም በበለጸጉት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች እና ሕክምናዎች ሊበገር ስለመቻሉ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ፋይዘርና በባዮንቴክ የበለጸገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል። 95 በመቶ ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ሆና ነበር።
news-57307687
https://www.bbc.com/amharic/news-57307687
ቻይና ዜጎቿ እስከ ሦስት ልጆች መውለድ እንዲችሉ ፈቀደች
ጥንዶች በሚወልዷቸው ልጆች ቁጥር ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ስታደርግ የቆየችው ቻይና ዜጎቿ እስከ ሦስት ልጆች ድረስ መውለድ እንዲችሉ ፈቀደች።
ውሳኔው የተላለፈው በአገሪቱ የሕዝብ ቆጠራ ሲደረግ የወሊድ መጠን መቀነሱ ከታወቀ በኋላ ነው። ቻይና አንድ ልጅ ብቻ መውለድ የሚፈቅደውን ፖሊሲ የሰረዘችው እአአ በ2016 ነበር። ጥንዶች ሁለት ልጆች እንዲወለዱ ከፈቀደች በኋላም ግን የወሊድ ቁጥር አላደገም። በቻይና ከተሞች ልጆችን ለማሳደግ የሚወጣው ከፍተኛ ገንዘብ ብዙ ጥንዶች እንዳይወልዱ አድርጓል። እስከ ሦስት ልጆች ድረስ እንዲወለድ ፕሬዘዳንት ዢ ዢፒንግ መፍቀዳቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የዢንዋ ዘገባ እንደሚያሳየው፤ የአገሪቱን የሕዝብ ቁጥር ከመጨመር ባሻገር የእድሜ ባለጸጎችን ለመንከባከብ እቅድ ይነደፋል። የፖሊሲ ለውጡ ምን ያህል ለውጥ ያመጣል? ሲሉ ከጠየቁ ተንታኞች አንዱ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ሃዎ ዘሁ ነው። "የልጅ ቁጥርን የመጨመር ፖሊሲ ውጤታማ ቢሆን ኖሮ ሁለት ልጆች እንዲወለዱ ሲፈቀድ ለውጥ ይታይ ነበር" ብሏል። ጥንዶች ከሁለት ልጆች በላይ መውለድ እንደማይፈልጉና ምክንያቱም የኑሮ ውድነት እንደሆነ አስረድቷል። ሁለት ልጆች መውለድ ሲፈቀድ ነገሮች ካልተለወጡ አሁን ምን አዲስ ነገር ይፈጠራል? ብለው የሚጠይቁ ብዙ ናቸው። ለዘመናት ቻይናውያን ያለ እህት ወይም ወንድም መኖርን ስለለመዱ ትንሽ ቁጥር ያለው ቤተሰብ አያሳስባቸውም። በርካታ ጥንዶች ብዙ ልጆች ከመውለድ ይልቅ አንድ ልጅ ወልዶ የሚያስፈልገውን ነገር በአጠቃላይ አሟልቶ በማሳደግ ያምናሉ። በዚህ ወር የወጣው የቻይና ሕዝብ ቆጠራ የሚያሳየው አምና 12 ሚሊዮን ልጆች እንደተወለዱ ነው። 2016 ላይ የተወለዱት 18 ሚሊዮን ልጆች ሲሆኑ፤ ዝቅተኛ የልጆች ቁጥር የተመዘገበው በ1960ዎቹ ነበር። በርካታ የቻይና መገናኛ ብዙሃን ሦስት ልጆች መውለድ መፈቀዱን መነጋገሪያ አድርገውታል። በቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ዌቦ ላይም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አስተያየት እየሰጡበት ነው። አብዛኞቹ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ቻይናውያን ጥንዶች ብዙ ጫና ስላለባቸው ተጨማሪ ልጆች የመውለድ እቅድ የላቸውም። ጥንዶች ሲወልዱ ከሥራ ቦታቸው ተገቢው ማበረታቻ እንደሌለ አጣቅሰዋል። ዘለግ ላለ ሰዓት የሚሠሩ፣ ከአንድ በላይ ሥራ የሚይዙ ወይም የተለያየ ትምህርት የሚማሩም መኖራቸው እንደ ምክንያት ተነስተዋል። ቻይና ሁለት ልጆች መውለድ ስትፈቅድ ለተወሰነ ጊዜ የወሊድ መጠን ቢጨምርም እንዳልዘለቀ የኢኮኖሚስት ዋና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዩ ሱ ይናገራሉ። እአአ በ1979 አንድ ልጅ ብቻ የውለድ ፖሊሲ ከወጣ በኋላ የቻይና ቤተሰብ መዋቅር የተቀረጸው በዚህ መርህ ነው። ከአንድ በላይ ልጅ የወለዱ ጥንዶች ከሥራ መባረር፣ ጽንስ እንዲያቋርጡ መገደድ እናም ሌላ ቅጣት ደርሶባቸዋል። የአንድ ልጅ ፖሊሲ ትዳር ላይም ጫና አሳድሯል። በተለምዶ ለወንድ በሚያደላው የቻይና ማኅበረሰብ ወንዶች የተሻለ ማኅበራዊና የምጣኔ ሀብት ደረጃ እንዲኖራቸውም አድርጓል። በሌላ በኩል አዲሱ ፖሊሲ የከተማና የገጠር የኑሮ ሁኔታን እንደሚለውጥ የሚገምቱ ተንታኞች አሉ። እንደ ቤጂንግ ባሉ ከተሞች የሚኖሩ ሴቶች ልጅ ሳይወልዱ ሲቆዩ ከከተማ ውጪ ያሉት ግን ሰፊ ቤተሰብ የመመስረት ፍላጎት እንደሚኖራቸው ይገመታል። በዊስኮንሰን ማዲሰን ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ዶ/ር ይ ፉሺን እንደሚሉት፤ ብዙ ኢንዱስትሪዎች ቻይና ተኮር እየሆኑ በመምጣታቸው የቻይና የሕዝብ ቁጥር መቀነስ አሳሳቢ ይሆናል።
news-55120403
https://www.bbc.com/amharic/news-55120403
ካናዳ በገፍ የሚደረግ የመድኃኒት ወጪ ንግድን አገደች
ካናዳ በገፍ የሚደረግ የመድኃኒት ወጪ ንግድን ማገዷ ተሰምቷል። በአገሪቷ እጥረት ያጋጥማል በሚልም ፍራቻ ነው በጤና ባለሙያዎች ማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶች ላይ እገዳ የጣለችው።
አሜሪካ በቅርቡ መድኃኒቶችን ከካናዳ በማስመጣት በቅናሽ ዋጋ ለመሸጥ ማቀዷን ተከትሎ ነው ይህ ውሳኔ የተላለፈው። ምንም እንኳን በካናዳ ከሌሎች አገራት ጋር ሲወዳደር በጤና ባለሙያዎች ማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶች ዋጋ ውድ ቢሆንም፤ በአሜሪካ ካለው ግን የቀነሰ ነው። ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ ለመግዛት ያሰቡት መድኃኒት ክምችትም በአገሪቷ ከፍተኛ እጥረትም እንደሚያስከስትልም የካናዳ መድኃኒት አቅራቢዎችም ሲያስጠነቅቁ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝን ተከትሎም በአንዳንድ መድኃኒቶች ላይ ያለው የገበያ ፍላጎትም በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረ የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያሳያል። ካናዳ 68 በመቶ የሚሆነውን የመድኃኒት ክምችቷን ከአገር ውጭ የምታስገባ ሲሆን በመድኃኒት አቅርቦትም ላይ ችግር ምንም አይነት እክል እንዳያጋጥም መስራት እንደሚገባ የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል። "ኩባንያዎች እጥረት ተከስቷል ወይም ይከሰታል የሚል ስጋት ካላቸው ለመንግሥት ማሳወቅ አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሊያስከትለው የሚችለውን የጤና ስጋት ገምግመው ሪፖርት ማድረግ አለባቸው" ብሏል የጤና ሚኒስቴሩ መግለጫ። ዶናልድ ትራምፕ ረከስ ያለ መድኃኒት ከካናዳ እንዲገባ የሚያስችል ትዕዛዝ የፈረሙት በሐምሌ ወር ነበር። ይህንንም ተከትሎ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሌሎች አገራትን የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት ለማቅረብ ያላቸውን ፈቃደኝነት ጠቅሰው ተቀዳሚው ነገር ግን የአገራቸውን ሕዝብ ፍላጎት መጠበቅ ነው ብለው ነበር። በአሜሪካ ያሉ የመድኃኒት አምራች ፋብሪካዎች በአዳዲስ መድኃኒቶች ላይ ያለው ውድ ዋጋን እንዲሁም በቀደሙ መድኃኒቶች ላይ የዋጋ ጭማሪን አስመልክቶ ትችቶችን እያስተናገዱ ነው። እነዚህ ወቀሳዎች በዋነኝነት የመጡት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ከፖለቲከኞች፣ ከኢንሹራንስ ኩባንያዎችና ከህመምተኞች ቡድን በኩል ነው። ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንም የመድኃኒት ዋጋዎችን ለማውረድ ከሌላ አገር ለማስመጣት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።
news-53900465
https://www.bbc.com/amharic/news-53900465
ሱዳን: ሕገወጥ ወርቅ ፈላጊዎች ጥንታዊ ቅርስ አወደሙ
ሕገወጥ ወርቅ ፈላጊዎች 2000 ዓመት እድሜ እንዳለው የሚታመነውን የቅርስ ስፍራ ማውደማቸው ተገለፀ።
የሰሃራ በረሃ አካል በሆነው የሱዳን ምሥራቃዊ አካባቢ የሚገኘው ይህ የቅርስ ስፍራ ሙሉ በሙሉ መፈራረሱም ተገልጿል። ጃባል ማራግሃ የሚሰኘው ይህ የቅርስ ስፍራ በታሪክና ቅርስ አጥኚዎች ዘንድ እድሜው ከክርስቶስ ልደት በፊት 350 ዓመት በፊት፤ እንዲሁም ከክርስቶስ ልደት በኋላ 350 ባሉት ዓመታት መካከል በነበረው የሜሮይቲክ ዘመን ውስጥ የተገነባ አነስተኛ መንደር እንደሆነ ይታመናል። የሱዳን ቅርስና ሙዚየም ባለስልጣናት ባለፈው ወር ከዋና ከተማዋ 270 ኪሎ ሜትር የሚርቀውን ይህንን ታሪካዊ ስፍራ በጎበኙበት ወቅት ሁለት መቆፈሪያ ማሽኖችና አምስት ሰዎች በቁፋሮ ላይ ተሰማርተው ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ግለሰቦቹ 17 ሜትር ጥልቀትና 20 ሜትር ስፋት ያለው ጉድጓድ ቆፍረው ነበር ብለዋል። ሃባብ እድሪስ አህመድ አርኪዮሎጂስት ሲሆኑ በተፈጠረው ነገር ደንግጠዋል። በስፍራው እአአ ከ1999 ጀምሮ እንደሰሩ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል በመናገር "እዚህ ስፍራ ቁፋሮ ሲያካሄዱ የነበሩ ሰዎች ያላቸው ዓላማ አንድ ብቻ ነው፤ ወርቅ መፈለግ። የሆነ የእብድ ሥራ ነው የሰሩት። በፍጥነት ወርቅ ለማግኘት ከባድ የቁፋሮ መሳርያ ተጠቅመዋል" ብለዋል። ምንም እንኳ እንደ ግብጽ እጅጉን ስማቸው የገነነና በበርካቶች ዘንድ የሚታወቁ አይሁኑ እንጂ ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ፒራሚዶችና ጥንታዊ ስፍራዎች የሚገኙባት አገር ናት። የሱዳን አርኪዮሎጂስቶች እንዲህ ያለ ችግር አዲስ አለመሆኑን በመጥቀስ እያደገ የመጣ ነው ሲሉ አሳሳቢ መሆኑን ይገልጻሉ። በአባይ ወንዝ ዳርቻ በሚገኘውና ሳይ በሚሰኘው ደሴት ላይ በፈርኦን ዘመን እንደነበሩ የሚታመኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመቃብር ስፍራዎች በመዝባሪዎች ወድመዋል፤ ተዘርፈዋል። "በሱዳን ከሚገኙ በሺዎች ከሚቆጠሩና በሚገባ ከሚታወቁ ታሪካዊ ስፍራዎች ቢያንስ ቢያንስ በመቶዎች የሚቆጠሩት ወድመዋል አልያም ፈርሰዋል" ይላሉ የሱዳን ቅርስና ሙዚየሞች ዳይሬክተሩ ሃተም አል ኑር። አክለውም ለቅርሶቹ የሚደረግ ጥበቃ አለመኖር ለዘራፊዎች በቀላሉ እንዲጋለጡ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል። ሱዳን በአፍሪካ በወርቅ አምራችነት ከደቡብ አፍሪካና ከጋና በመቀጠል በሦስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ወርቅ ለአገሪቱ ባለፈው ዓመት 1.2 ቢሊየን ዶላር ያስገኘው በሕጋዊ መልኩ በማውጣት ለዓለም አቀፍ ገበያ የተሸጠው መሆኑን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ገልጿል። አንዳንድ የአካባቢ ባለስልጣናትና ነጋዴዎች ለሕገወጥ ማዕድን አውጪዎች ማሽን በመስጠት እንደሚያበረታቷቸው ይነገራል። የማዕድን ቆፋሪዎችም በቁጥጥር ስር በሚውሉበት ወቅት የሚጣልባቸው ቅጣት እምብዛም መሆኑ ግለሰቦቹ ከድርጊታቸው እንዳይታቀቡ ማድረጉን ይገልፃሉ። የጃባል ማራግሃን ታሪካዊ ስፍራን ያወደሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ቢውሉም በነጻ መለቀቃቸው ተሰምቷል። "በእስር መቆየት ነበረባቸው። ማሽናቸውም ቢሆን መያዝ ነበረበት። ሕጉ አለ" ብለዋል በሱዳን የቅርስ ክፍል ሰርተው የሚያውቁት መሃሙድ አል ታይብ። እነዚህን የታሪክ ስፍራዎች በዘላቂነት ለመከላከል መፍትሄው ወጣቶችን ስለአገሪቱ ታሪክ ማስተማር መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ። ያኔ ታሪካቸውንና ቅርሳቸውን ይጠብቁታል ሲሉ የሚመክሩት ደግሞ ፕሮፌሰር ሃባብ ኢድሪስ ሙሃመድ ናቸው።
news-45036020
https://www.bbc.com/amharic/news-45036020
በጣና በለስ ግድያ ፈፅመዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ
በአማራ ክልል አዊ ዞን በጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት አቅራቢያ በምትገኘው ፈንድቃ ከተማ ጥቃት ደርሶባቸው ከሞቱት አንዱ የ24 ዓመት ወጣት ሃብቶም ሃይለ ነው።
ቤተሰቦቹ አስከሬኑን ለመቀበል ከሐውዜን አላማጣ ድረስ ተጉዘው ነበር። አስከሬኑን ተቀብለው መቐለ በደረሱበት ወቅት ወንድሙን መብራህቶም ሃይለን ቢቢሲ አናግሮታል። "እኔ ምን ማለት እችላለሁ እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ነገር ነው። ሰው ሰርቼ እበላለሁ ብሎ ሄዶ ይሄ መፈፀሙ አሳዛኝ ነው። ይህ ሊቆም ነው የሚገባው።" ብሏል። ሌላኛው የጥቃቱ ሰለባ ሮቤል ያዕቆብ ትውልዱና እድገቱ አስመራ ከተማ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ 6 ዓመታትን አስቆጥሯል። •የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ •40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ •ዶክተር ብርሃኑ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ምን ተወያዩ? ወይዘሮ ይርጋለም ኪሮስ የሮቤል ያዕቆብ ዘመድ ሲሆኑ የሟቹ እናት እና እህቶቹ አሁንም አስመራ እንደሆኑም ይናገራሉ። ሮቤል የክሬን ሰራተኛ ሆኖ በጣና በለስ ፕሮጀክት ውስጥ ይሰራ እንደነበር ወይዘሮ ይርጋለም ይናገራሉ። "ይህን ምን ማለት ይቻላል? አምላክ እራሱ ያብረደው። ይህን ዘር እየለዩ መግደል፤ መንግስት አንድ ነገር እንዲያደርግ ነው የምንጠብቀው። ልጆቻችን ነገ ምንድነው እጣፈንታቸው? አይታወቅም! ልጆቻችን ለስራ በየቦታው ተበትነው ነው ያሉት። ሀገራችን ነው ብለው ነው የሚሄዱት? ከሃገራቸው ውጪስ የትስ መሄድ ይችላሉ?" በማለት ለቢቢሲ ገልፀዋል። የሮቤል ያዕቆብና ሶስተኛው ተጠቂ የሆኑት አቶ ሐድጉ ካሳ ፤ የቀብር ስነስርዓት በትውልድ ቀያቸው መቐለ ዛሬ ተፈፅሟል። •ሰመጉ በኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች የፀጥታ አካላት የመብት ጥሰቶችን መፈፀማቸውን በሪፖርቱ ገለፀ ለሞት የተዳረጉት ሆን ተብሎ የኤክትሪክ ሃይል ተቋርጦብናል በሚል በተቆጡ የከተማዋ ወጣቶች በደረሰ ጥቃት እንደሆነ ተዘግቧል። የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጥቃቱ ብሄርን መሰረት ያደረገ ነው ሲል ያወገዘ ሲሆን አጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው እልካለሁ ብሏል። በዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ምርመራ መጀመሩን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ማስታወቃቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
news-47156017
https://www.bbc.com/amharic/news-47156017
አሮን ሰናይ: "አክሱምና ላሊበላ ለፈጠራ እና ለዲዛይን ሥራዎቼ የመስፈርቴ ጣሪያ ናቸው"
አሮን ሰናይ ሕግንና ኢኮኖሚክስን አጣምሮ አጥንቶ ዲግሪውን ጨብጧል። የተመረቀበት ሙያ ግን አሁን እንጀራ ይሁነኝ ብሎ፣ አልባሳትንና ቦርሳዎችን ዲዛይን እያደረገ ከሚሰራው ሥራ ጋር አይገናኝም። ።
"ዲዛይን ማድረግ በሁሉም ሰው ውስጥ ያለ ሙያ ይመስለኛል" ይላል አሮን። ባለሙያዎቹ ከሌሎቹ የሚለዩት ውስጣቸው ያለውን የሃሳብ ድርና ማግ መልክ አስይዘው፣ ወረቀትና ጨርቅ ላይ ስለሚያሰፍሩት እንደሆነ ይመሰክራል። • "ኮሜዲ፣የጤፍ ዝናብ ነው" ቤቲ ዋኖስ • ቀራፂው ስለ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት ይናገራል ከፋሽን ጥበብ ጋር ያወዳጀውን ነገር ሲያስታውስ "ቤተሰቦቼ፣ ከአያቴ ከወይዘሮ ንግሥቲ ጀምሮ፣ ወንዱም ሴቱም አለባበስ አዋቂ፣ ሽቅርቅር ነበሩ" ይላል፤ "በተለይ ሴቶቹ ዘናጭ ናቸው" ሲል ያሞካሻቸዋል። አያቱ ወይዘሮ ንግሥቲ ነርስ ነበሩ፤ ዘመናቸውን ሁሉ የሃገር ባህል ልብስ ነበር የለበሱት። ይኖሩበት በነበረው አዳማ (ናዝሬት) የሚያያቸው ሁሉ የሚያስታውሳቸው እንደ ወተት ነጭ በሆነ ቀሚሳቸውና በሹሩባቸው ነው። "ዘወትር ይሳለሟት በነበረችው የማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ይቀመጡበት በነበረው ስፍራ ሰው ሁሉ ያውቃቸዋል" የሚለው አሮን ሁሉም ሰው በመልካምነታቸው የሚያውቃቸው አያቱ ወ/ሮ ንግሥቲን አርዓያ በማድረግ እ.ኤ.አ በ2014 በስማቸው የፋሽኑን ሃሳብ እውን አደረገ። • ከወንጀልነት ወደቀዳሚ መዋቢያነት የተሸጋገረው የከንፈር ቀለም ሁሌም ይህንን የሕይወት ድግግሞሽ ያለማዛነፍ ለዓመታት ኖረውበታል ይላል ስለአያቱ ሲናገር። "ይህንን የእማዬን የአለባበስ ዘዬ ሳስብ ከእራሷ አለመጣላቷ ይታሰበኛል። ሌሎችን ለማስደሰትና ለመመሳሰል ተብሎ የሚቀየር ነገር አልነበራትም። አሁንም እኔ በዲዛይኔ የሌሎችን ዱካ የማይከተል፣ የእራሴን ደማቅ መስመር ለማስመር፣ የእራሴን የፋሽን ዓለም ለመፍጠር እየሠራሁ ነው" ይላል። ንግሥቲን የሰባት ዓመት ልጅ እያለሁ ነው የጀመርኩት ያለን አሮን "ያኔ ግን ስም አልነበራትም፤ ዝም ብዬ የተለያዩ ነገሮችን እነድፍ ነበር" ይላል። ከአስተዳደጉ ባሻገር ስምንት ዓመት የኖረባት ፈረንሳይ ስለፋሽን የአቅሟን ማዋጣቷንም ይመሰክራል። ጅማሮ እ.አ.አ በ2014 ፈረንሳይ ሃገር የሬስቶራንት ባለቤት የሆነች አንዲት ግለሰብ በየዓመቱ የምታዘጋጀው የፋሽን ትርዒት ላይ ልታካትተው እንደምትፈልግ ነገረችው። ፈቃደኛ ሆነና ከሃገሩ ሲወጣ ቢበርደኝ የምደርበው ብሎ የያዘውን ጋቢ ተጠቅሞ የፋሽን ትርዒቱን ተቀላቀለ። 5 ሴት ጓደኞቹን ጠርቶ በጋቢው የተለየዩ የፈጠራ ሥራዎቹን አሳየ። "አያቴ ሰነፍ ሆና አታውቅም፤ የምመርጣቸውም ሞዴሎች ሰነፍ አይደሉም፤ እኔም ሰነፍ አይደለሁም። ስለዚህ የምሠራው ሥራ በስንፍና የታጀበ የአረም እርሻ እንዲሆን አልፈልግም። ዘመን የሚሻገር፣ ዘመኑን የሚከተል በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ ነው የምሠራው" ይላል አሮን ስለሥራዎቹ ሲናገር። • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? በመቀጠልም "እኔ የምሠራው ሴቶችን የበለጠ ውብ የሚያደርጉና ደጀን የሚሆኑ ቦርሳዎችን ነው" ይላል። ወደ ሃገሩ ሲመለስ፣ የዛሬ ዓመት ቮግ ኢታሊያ፣ ጎተ ኢኒስቲትዩትና ኤፍ ኤ ቱ ፋይቭ ፎር፣ የሚባሉ ማህበራት ባዘጋጁት ውድድር ላይ ሰዎች እንዲወዳደር ጋበዙት። ግብዣውን ተቀብሎ ለውድድር ንግሥቲን ይዞ ቀረበ እናም ለፍፃሜ ደረሰ። ንግሥቲ የሴቶች ፋሽን አብዮት ንግሥቲ የምታተኩረው ሴቶች ላይ ነው። የወንድ ፋሽን ያስቸግረኛል ይላል፤ ቲሸርትና ሸሚዝ ብዙም ጥበብ የማይታይባቸው ፈጠራን የሚያመክኑ ነገሮች ይመስሉታል። "የሴቶች ነገር ለፈጠራ የሚያነሳሳኝ ሲሆን የወንዶች ምርጫ ግን በትንሽ ነገር ስለታጠረ ስሜት አይሰጠኝም።" አሮን ቀልቡንና ሃሳቡን አዋህዶ የሚጠበብባቸው የፋሽን ሥራዎች ዘመናዊነትን ግለሰባዊ ማንነትን እንዲያሳዩ ይጥራል። የሚሠራቸው ሥራዎች የሴቶች ቦርሳዎች ብቻ አይደሉም፤ አልባሳትም ዲዛይን ያደርጋል። • ኢትዮጵያዊያን ለምን ሥጋ አይመገቡም? በእራስ መተማመን ያላቸው፣ እራሳቸውን በሃሳብም በቀለምም መግለፅ የሚፈልጉ ሴቶች፤ ችምችም ካለው የሰው ነዶ መካከል ተለይተው መታየት የሚፈልጉ የፋሽን ተከታዮች የእርሱ የገበያ ትኩረት ናቸው። በንግሥቲ የሚሠሩት ቦርሳዎችን ስም ያወጣላቸዋል። ስሞቹ ለእራስ ቅርብ የማድረግ ኃይል እንዳላቸው ያምናል። ለምሳሌ 'አክሱም' ብሎ የሰየመው ቦርሳ የአክሱም ሐውልትን መነሻ አድርጎ የሠራው ነው። "ንጉሱ" ብሎ የሰየመው ሥራው በሴቶች መካከል የተገኘ ብቸኛው ወንድ ነበር። ስራውን በዚያ ሰየመው። ኮቼላ የተሰኘው ሥራው ደግሞ በአምስት መልኩ መያዝ ይቻላል። ሲቀመጥ ደግሞ እግር ኖሮት ሸረሪት ይመስላል ይላል። ኮቼላ በአሜሪካ የሚዘጋጅ ትልቅ የሙዚቃ ድግስ ነው የሚለው አሮን፣ ቦርሳው እንዲህ ዓይነት ድግስ ላይ የሚገኝ ሰው የሚይዘው ነው ይላል። በከረዩዎችና በኃይለ ሥላሴ መነሻነት የተሠሩ ቦርሳዎችም የእጅ ሥራው ውጤቶች ናቸው። በጥንቸል መነሻነት የተሠራው ሌላው ሥራ 'ምናለበት' የተሰኘው ነው። ሥራዎቹን ለማስተዋወቅ የሚጠቀመው ኢንስታግራምን ሲሆን ከሄሎ ካሽ ጋር በመሆን የእራሱን ድረ-ገፅ እየሠራ እንደሆነ ይናገራል። ከድምፃዊ ቤቲ ጂ ጋር የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች በቀጣዮቹ 5 ዓመታት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ መገኘት ይፈልጋል። "ከልጅነቴ ጀምሮ የፍሬንች ሃውስን ዲዛይን ባደርግ ደስ ይለኛል እል ነበር" ያለው አሮን ዛሬም ያ የልጅነት ህልሙ ቢሳካ ደስ ይለዋል። ደንበኞች "ኢትዮጵያዊያን በሁሉም አቅጣጫ በፋሽን በደንብ አልተገለፁም" ብሎ የሚያምነው አሮን ሽሮሜዳና መርካቶ የሚሸጡ የባህል አልባሳት የፋሽን አስተሳሰባችንን ቀፍድደው ሳይዙት አልቀሩም ይላል፤ "የፋሽኑ ዓለምም በሚፈለገው መጠን ሲበረታታ አይታይም። የሚታዩ የዲዛይነር ሥራዎችም ጥበብን ማዕከል ያላደረጉ ይበዛሉ" ይላል። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት አሮን የቀደምት አባቶችና እናቶቻችን የፈጠራ እና የጥበብ ውጤት የሆኑትን ሥራዎች በመመልከት በእነርሱ ደረጃ የውሃ ልክነት የእራሱን ሥራዎች መሥራት ይፈልጋል። ላሊበላን በማነፅ ድንቅ የሥነ-ሕንፃ ባለሙያነትን ያስመሰከሩ፣ አክሱምን አልያም ፋሲለደስን በማቆም የፈጠራ ልህቀታቸውን መስመር ያሰመሩ ኢትዮጵያዊያን፤ ለፈጠራ እና ለዲዛይን ሥራዬ የመስፈርቴ ጣሪያ ናቸው ይላል። አሮን ኢትዮጵያዊያን በፋሽኑ ዓለም ከምዕራባዊያንም ሆነ ከአፍሪካውያን እንደሚለዩ ተረድቷል። ስለዚህ የፋሽን ሥራዎቹ ሴትነትን የበለጠ እንዲያጎሉ፣ በሚደምቁበት አደባባይም የተሰማሩበትን ተግባር እያከናወኑ፣ የሚከተሉት ፋሽን ደጀን እንዲሆናቸው ይፈልጋል። ሥራዎቹንም ኢትዮጵያዊ አሻራን ከዘመናዊነት ጋር ያጣመሩ እንዲሆኑ ይጥራል። • ውክልናን በቪድዮ • ስለ ጠልሰም ወይም በተለምዶ የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ? • ጥበብን በወር-አበባና በአጽም ባህሉን ሳያፈርስ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሳይጥስ ከደንበኞቹ ማንነት፣ ከሴትነታቸው ጋር ፋሽኑን ማጋመድ የእርሱ ሃሳብ ነው። አሮን፤ ፋሽን የንግድ ሃሳብም መሆኑን አላጣውም። ዘርፉ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ በፈረንሳይ ለ1 ሚሊዮን ሰዎች የሥራ ዕድል በመፈጠር የ150 ቢሊዮን ዩሮ ባለ ካፒታል ባለቤት ነው ይላል። ንግሥቲ ለደንበኞቿ የምታቀርባቸው ውጤቶች ይህንን ትልቅ ምስል ያየ የሃገር ውስጥና የውጪውን ዓለም የገበያ አድማስ የዳሰሰ እንደሚሆን ይናገራል። በሃገር ውስጥ በሕይወት መንገድ ላይ ጥቂት ገንዘብ አጠራቅመው መግዛት የቻሉ፣ እንዲሁም ገንዘብ ያላቸው ሁሉ ደንበኞቹ ናቸው።
news-44165233
https://www.bbc.com/amharic/news-44165233
በኮንጎ የኢቦላ ቫይረስ እየተዛመተ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
የዓለም ጤና ድርጅት ኢቦላ በፍጥነት የመዛመት ጉዳይ አሳስቦት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ።
በድሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ የተጠረጠሩ ሰዎች ተለይቶ በተዘጋጀላቸው ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው ነው። ውይይቱ በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል አለም አቀፋዊ ትኩረት ለማግኘትና የአስቸኳይ ጥሪ ለማስተላለፍ ወሳኝ ነው ተብሏል። ኢቦላ አሁንም ቀድሞ ካገረሸበት አካባቢ ምባንዳካ ወደ ተባለ ትንሽ የገጠር አካባቢም እንደተዛመተ ታውቋል። አንድ ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች የሚኖሩባት ከተማዋ ኮንጎ ወንዝን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለመጓጓዝ በመጠቀማቸው ቫይረሱ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ሊዛመት እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል። ዋና ከተማዋን ኪንሻሳን እና በዙሪያዋ ያሉ ሌሎች ከተሞችንም አስግቷል። በቅርቡ እንደገና ባገረሸው ኢቦላ በትንሹ 44 የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ 23 የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ እንደሞቱ ተረጋግጧል። ኢቦላ የሰውነት መድማትን የሚያስከትል ኢንፌክሽን ሲሆን ከሰውነት በሚወጡ አነስተኛ መጠን ባለቸው ፈሳሸ ሳይቀር በንክኪ ምክንያት በመተላለፉ እንዲሁም ያልተለመዱ ምልክቶች ስላሉት በፍጥነት እንዲዛመት ምክንያት ሆኗል። ኢቦላ ለምን አገረሸ? የአለም ጤና ድርጅት ባላስልጣን ፒተር ሳላማ በሽታው በአጭር ጊዜ ወደ ምባንዳካ መዛመቱ ወደሌሎች አገራትም የመዛመት ዕድሉን ያሰፋዋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የዓለም ጤና ድርጅት አጠቃላይ የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ምክትል ዳይሬክተር እንዳሉት ኢቦላው በኮንጎ ወንዝ አቅራቢያ ከምትገኘው ምባንዳካስ ወደ ኮንጎ ብራዛቪል እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሊዛመት ይችላል ብለዋል። በተለያየ አቅጣጫ መመልከታችን በምባንዳካ የታየውን የመሰራጨት እድል ለማቆም አስቸኳይ እርምጃ ለመውስድ ያስችላል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። እአአ ከ2014-2016 ምዕራብ አፍሪካ የተከሰተው ኢቦላ ወደ ጊኒ፣ ሴራሊዮንና እና ላይቤሪያ በመዛመቱ ለብዙ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። ኢቦላን ለመቆጣጠር ምን ተሰራ? የዓለም ጤና ድርጅት 44 የኢቦላ ኬዞችን እንዳገኙና ከእነዚያ መካከል 20 የሚሆኑት በቫይረሱ ሳይያዙ እንዳልቀሩና ቀሪዎቹ 21 የሚሆኑት ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ጥርጣሬ እንዳላቸው አስታውቋል። ኬዞቹም በምባንዳካ የኮንጎ ኢኳተር ክፍል እንደተመዘገቡ ተነግሯል። ምክትል ዳሬክተሩ እንደተናገሩት በከተማዋ የተለየ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ሁኔታዎች እንደተመቻቹ ገልፀው በሽታው በቢኮሮ ከተማ በኢቦላ የሞቱ ሰዎች የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ወደ ከተማዋ በሄዱ ሰዎች አማካኝነት ሳይዛመት እንዳልቀረ ተናግረዋል። ባሳለፍነው ረቡዕ 4000 የሚሆን የሙከራ ክትባት ኪንሻሳ የደረሰ ሲሆን ተጨማሪ ክትባት በቅርቡ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። ክትባቱ በምባንዳካ ከተማ ለሚኖሩና ቫይረስ ካለባቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት ላላቸው ሰዎች ቅድሚያ ይሰጣል ሲሉ ምክትል ዳሬክተሩ ተናግረዋል። ፈቃድ ባያገኝም ከዚህ ቀደም በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ ተከስቶ በነበረ ጊዜ በተወሰነ መልኩ ሙከራ ተደርጎ አዋጭ እንደነበር የተናገሩት ዳሬክተሩ ክትባቱ -60እና -80 ሴልሽየስ የሙቀት መጠን መቀመጥ የሚኖርበት ቢሆንም በኮንጎ ያለው የኤሌክትሪክ አቅርቦት አስተማመኝ ባለመሆኑ የክትባቶቹን ቁጥር ለመጨመር አዳጋች አድርጎታል ይላሉ። ስርጭቱን በአፋጣኝ ለመቆጣጠር የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች ከቫይረሱ ጋር ንክክኪ አላቸው የተባሉ 430 ሰዎችን የለዩ ሲሆን ሌሎች ከኢቦላ ታማሚዎች ጋር ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ 4000 ሰዎችን የመለየት ስራ እየሰሩ ነው። አብዛኞቹ ሰዎች በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ናቸው። ኢቦላ ደግሞ ደጋግሞ ለምን አገረሸ ከ2014-2016 በድሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወረርሽኑ ለሶስተኛ ጊዜ አገርሽቷል። ኢቦላ ፍራፍሬ በሚመገቡ የሌሊት ወፎችና ከዱር እንስሳቶች ጋር ግንኑነት ባላቸው ሰዎች አማካኝነት በመተላለፉ ድንበር ሳይከልልው ይዛመታል። በሽታው ከያዛቸው እንስሳት በደም እና በአካል ንክኪ እንዲሁም በሌላ የሰውነት ፈሳሾች ይተላለፋል። ዝንጀሮዎች፣ ቺምፓንዚዎች፣ አጋዘኖች እና ጎሪላዎች በሽታውን ከሚያስተላልፉ እንስሳት ይጠቀሳሉ። በሽታውን የሚያዛምቱ ሁሉንም እንስሳትን ማጥፋት ስለማይቻልና ሰዎች ከእንስሳቶቹ ጋር ግንኙነት እስካላቸው ድረስ ኢቦላ መልሶ መላልሶ ሊያገረሽ ይችላል።
56036403
https://www.bbc.com/amharic/56036403
ውሻዋ የአሳዳጊዋን ሀብት ወርሳ ሚልየነር ሆነች
ይህች ውሻ ሚሊየነር ናት። ገንዘቡን ያገኘችው ቀን ተሌት ሰርታ ለፍታ አይደለም፣ ያለ ስስት ብዙ ፍቅር ለባለቤቷ በመስጠቷ ገንዘቡን ወርሳ ነው።
አሳዳጊዋ 5 ሚሊዮን ዶላር በውርስ ትቶላት ወደ ማይቀረው ዓለም ሄዷል፤ ሞቷል። የውሻዋ ስም ሉሉ ይባላል። አሳዳሪዋ የነበረው ግለሰብ ደግሞ የናጠጠ ሃብታም የነበረው ቢል ዶሪስ ነው። በናሽቪል ቴኔሲ የምትኖረው ሉሉ ስምንት ዓመቷ ሲሆን ባለፈው ዓመት ቢል ዶሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ተናዝዞላታል። ማርታ በርተን የዶሪስ ጓደኛ የነበረች ስትሆን አሁን ደግሞ የሉሉ ቋሚ ተንከባካቢ ነች። ስለ ሁኔታው ስትጠየቅም "እውነቱን ለመናገር ምን እንደሚሰማኝ ለማወቅ አልችልም" ብላለች። በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ናት፤ ቢል ከመሞቱ በፊት ለውሻው ሉሉ ብርቱ ፍቅር ነበረው። እጅግ የበረታ፤ ከብረት የጠነከረ ማለት ይቻላል። ቢል ባስቀመጠው ኑዛዜ ላይ በየወሩ በርተን ሉሉን ለመንከባከብ ያወጣችው "ምክንያታዊ ወጪ" እየተሰላ እንዲከፈላት ይላል። እንዲህ ሚሊየኖች በኑዛዜ የተተወላት ሉሉ ምን ዓይነት ውሻ ብትሆን ነው? "መልካም ጠባይ ነው ያላት" ትላለች በርተን። በርተን 5 ሚሊዮን ዶላሩንም ሉሉን ለመንከባከብ መንዝራና ዘርዝራ የምትጨርሰው ይመስላት ይሆን? "እንግዲህ መቼስ ምን ይደረጋል፤ እሞክራለኋ" ሳቅ የታጀበ የእርሷ መልስ ነበር። ሉሉ እንደ ባለቤቷ ዶሪስ ወደማይቀርበት ዓለም ብትሄድ፣ ከወጪ ቀሪ የሚተርፋት ገንዘብ ምን እንደሚሆን የታወቀ ነገር የለም። እኤአ በ1992 እንዲህ እንደ ሉሉ እድለኛ የነበረ ውሻ 80 ሚሊዮን ዶላር መውረሱ የተዘገበ ሲሆን፤ በ2002 ደግሞ ማይለስ ብላክዌል የተባለ ደራሲ ጊጉ ለተሰኘች ዶሮው 15 ሚሊዮን ዶላር እስካለሽ ድረስ ተምነሽነሺበት በሚል ተናዝዞላታል። ባልበላውም ልበትነው ብላ ካላባከነችው በቀር እርሷስ ያን ያህልም አትፈጅ!
news-44234737
https://www.bbc.com/amharic/news-44234737
የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር አልተሳካም
በቅርቡ የተካሄደው የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ስምምነት ላይ ሳይደረስ ተጠናቀቀ።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በሶስት አዳዲስ ሃላፊነቶች የስልጣን ክፍፍል ዕቅድ አቅርቦ ነበር። ከእነዚህ ሃላፊነቶች አንዱ የአማፂያኑ መሪ ለሆኑት ሪያክ ማቻር እንዲተላለፍ የሚጠይቅ ነበር ። ተቃዋሚ የሆነው የኤስፒኤልኤአይኦ አባል የሆኑት ማቢኦር ጋራንግ እንደተናገሩት "የቀረበው የስልጣን ክፍፍል ዕቅድ ፍትሃዊ አይደለም፤ ያለውን ችግር የሚያባብስና ስልጣን በገዥው መንግስት እጅ እንዲሆን የሚያጠናክር ነው" ብለዋል። በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪያክ ማቻር ከአምስት ዓመታት በፊት በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት አገሪቷ እርስ በርስ ግጭት እየታመሰች ነው። በዚህም ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱ ሲሆን አራት ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ተፈናቅለዋል።
news-55500053
https://www.bbc.com/amharic/news-55500053
ዓይነ ስውሩ የሕግ ተመራቂ ስለምን ራሱን በእሳት አቃጠለ?
የዛሬ ሳምንት አርብ ታኅሳስ 16/2013 ዓ.ም አንድ ዓይነ ሥውር የሕግ ተማሪ ራሱን በእሳት አቃጥሎ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ህክምና ላይ ሳለ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
አብርሃም ዱሬሳ አብርሃም ዱሬሳ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዲግሪውን እንዳገኘ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና በመውሰድ ላይ እንደነበር ጓደኛው ጣሰው ሃብታሙ ለቢቢሲ ተናግሯል። ፈተናው ባለፈው ዓመት በ2012 ዓ.ም ይሰጥ የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት በመራዘሙ ለረጅም ጊዜ ለፈተናው ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ያስታውሳል። ከአብርሃም ጋር በአንድ ግቢ ውስጥ ተከራይተው መኖር ከጀመሩ አምስት ዓመት እንደሆናቸው የሚያስታውሰው ጣሰው፣ ሲዘጋጅበት የነበረውን የመውጫ ፈተና ማክሰኞ ዕለት መውሰድ መጀመሩን ይናገራል። የመውጫ ፈተናውን ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ፣ ረቡዕ እና ሐሙስ በሰላም ተፈትኖ እንደነበር የሚናገረው ጣሰው ደስተኛም እንደነበር ለቢቢሲ ያስረዳል። የመጨረሻው የፈተና ዕለት፣ ማለትም አርብ፣ ረፍዶበት ስለነበር የመፈተኛ ኮዱን [የመለያ ቁጥሩን] ረስቶ በችኮላ ፈተናው ወደ ሚሰጥበት ወደ ስድስት ኪሎ ግቢ መሄዱን ያስታውሳል። ፈተናው የሚሰጠው ስድስት ኪሎ ኤፍ ቢ ተብሎ በሚታወቀው ካምፓስ ስለነበር ወደ ውስጥ ዘልቆ መፈተኛ ኮዱን መርሳቱን እና ይፈትኑት እንደሆነ ቢጠይቅም፣ "ያለእርሱ አይሆንም፣ ሄደህ አምጣ" በመባሉ ወደ ቤቱ መመለሱን ጓደኛው ጣሰው ያስረዳል። ካለመፈተኛ ኮዱ መግባት ስለማይችል ወደ ቤቱ ሽሮ ሜዳ ተመልሶ፣ ከትራንስፖርት ከወረደ በኋላ ወደ ቤቱ የሚያቀናውን የእግር መንገድን አቋርጦ፣ የመፈተኛ ኮዱን በመያዝ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ሲደርስ ፈተናው መሰጠት ከጀመረ የተወሰኑ ደቂቃዎች ማለፉን ጣሰው ለቢቢሲ ተናግሯል። "ፈተናው አላለቀም ተማሪዎች አልወጡም ቢያንስ ከ20 ደቂቃ በላይ ይቀር ነበር" ብሎኛል ሲል የሟች አብርሃም የቅርብ ወዳጅ ጣሰው ለቢቢሲ የነበረውን ሁኔቴ አስረድቷል። የፈተና ተቆጣጣሪዎችን ለማሳመን እና ልባቸውን ለማራራት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም የሚለው ጣሰው፤ ነገር ግን ምንም ፍሬ እንዳላፈራለት ይናገራል። "መግባት እንደማይችል ሲነግረው ስላረፈደበት ምክንያት ሊያስረዳ ቢሞክርም፤ "በቀረችው 20 ደቂቃ አብቃቅቼ እሰራለሁ" እያለ ዓይነ ስውር መሆኑን ታሳቢ አድርገው እንዲተባበሩት ቢለምንም፣ ቢያለቅስም፣ ፈተናውን እንዲወስድ ግን አልተፈቀደለትም።" የሟች አብርሃም ጓደኛ ጣሰው፣ ፈተናውን መፈተን ባለመቻሉ ሲያለቅስ፣ ሲበሳጭ መዋሉን ያስታውሳል። ጓደኞቹ ሊያጽናኑት ቢሞክርም "በቃ የእድሌ መጨረሻ ነው፣ ዓይነ ስውር ካልተማረ ውጤታማ አይሆንም" እያለ ያለቅስ እነደነበር ይናገራል። ምሽት ላይ ወደ ቤቱ ሲገባ ወዳጆቹ የመሰላቸው እረፍት ሊያደርግ ቢሆንም፣ እርሱ ግን ቤቱን ዘግቶ፣ በራሱ ላይ ጋዝ አርከፍክፎ፣ በዙሪያዎቹ ተቀጣጣይ ነገር በማኖር ራሱ ላይ እሳት መለኮሱን ጣሰው ገልጿል። ግቢ ውስጥ ያሉ ሰዎች ተረባርበው የቤቱን በር በመገንጠል እሳቱን አጥፍተው፣ ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተወስዶ ሕክምና ቢያገኝም ቃጠሎው ከፍተኛ ስለነበር ቅዳሜ ማለዳ 3፡00 ላይ ህይወቱ አልፋለች። የአብርሃም ቤተሰብ አብርሃም ዱሬሳ ባለትዳር ሲሆን ባለቤቱ ነፍሰጡር በመሆኗ መስከረም ወር ላይ ለመውለድ ትግራይ ወደ ሚገኙት ቤተሰቦቿ መሄዷን ጓደኛው ጣሰው ለቢቢሲ ተናግሯል። አብርሃም ብቻውን ለመኖር የተገደደው በተፈጠረው ችግር ምክንያት በረራ ተቋርጦ ስለነበር ባለቤቱ ልጃቸውን ክርስትና አስነስታ መምጣት ስላልቻለች በመዘግየቷ ነበር። "ለብቻው የሆነው ለዚህ ነው እንጂ ከሚስቱ ጋር ነበር የሚኖረው" የሚለው ጣሰው በጓደኛው ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል። በየካቲት 12 ሆስፒታል አብረውት የነበሩት አቶ አሸብር ገብረ ሕይወትም ቅዳሜ ዕለት ሆስፒታል ሲደርሱ አብርሃም ነፍሱ እንደነበረችና ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥሎ ማየታቸውን ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኅበር ፕሬዚደንት አቶ ወሰን አለሙ፣ በማኅበሩ ሦስት ዓመታትን አንዳገለገሉ ገልፀው፤ ከዚህ ቀደም በድሬደዋ ከተማ ከኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎች የተሳሳተ ግንዛቤ ጋር በተያያዘ አንድ ዓይነ ስውር በተመሳሳይ ሁኔታ ራሱን አቃጥሎ መሞቱን ያስታውሳሉ። አቶ ወሰን፣ "በአብርሃም ዱሬሳ አርፍዶ በመምጣቱ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አትችልም መባሉ ሕግን ካለማወቅ የመጣ ነው" ይላሉ። "የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ኮንቬንሽን ተመጣጣኝ ሁኔታን ማመቻቸት ይላል" በማለትም ይህ ማለት የሰዓት፣ የቦታ ማስተካከያ ማድረግ ሊሆን እንደሚችል ያብራራሉ። አብርሃም ቀደም ባሉት ሦስት የፈተና ቀናት በሰዓቱ ተገኝቶ መፈተኑን ከግንዛቤ በማስገባት፣ ያለ ኮድ ማስተናገድንም ሊያካትት እንደሚችል ያስረዳሉ። "ይህ በግልጽ ስህተት ነው" የሚሉት ፕሬዝዳንቱ "ፈተናውን የሚያከናውነው አካል እንዲህ አይነት ሥርዓቶችን መዘርጋት ነበረበት" ብለዋል። የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ፌደሬሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ በተማሪ አብርሃም ዱሬሳ ላይ የተፈጸመዉ ክልከላ "ሰብአዊነት የጎደለዉ በመሆኑ መንግሥት ክትትል አድርጎ እርምጃ እንዲወስድ" ሲል ጠይቋል። ቢቢሲ ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል ቢደውልም ጉዳዩ እነርሱን እንደማይመለከት ገልፀዋል። በተጨማሪም ይመለከተዋል የተባለው የፈተናዎች ኤጀንሲም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።
news-53578736
https://www.bbc.com/amharic/news-53578736
አሜሪካ ባለሥልጣኗ ‘ወንበዴ’ ስለመባላቸው ከዚምባብዌ አምባሳደር ማብራሪያ ጠየቀች
አሜሪካ በዚምባብዌ ባለሥልጣን ስለተሰጠው አስተያየት የአገሪቱ አምባሳደር ማብራሪያ እንዲያቅርቡ ጠይቃለች።
አሜሪካ ዚምባብዌ ውስጥ የምታካሂደውን ምርመራ በተመለከተ ትችት አዘል አስተያየት ተሰንዝሮ ነበር። የዚምባብዌ ገዢ ፓርቲ ዛኑ-ፒኤፍ ቃል አቀባይ፤ “አሜሪካ ጸረ መንግሥት ንቅናቄ ትደግፋለች” ብለው ሰኞ እለት ከሰው ነበር። የአሜሪካው አምባሳደር ብራየን ኒኮላስን ‘ወንበዴ’ ብለው ዘልፈውም ነበር። • በሙምባይ በድሃ ሰፈሮች የሚኖሩ ከግማሽ በላይ ነዋሪዎች በኮቪድ ተይዘዋል • የጀርመን ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መባባስ "በጣም አሳስቧቸዋል" • ኮሮናቫይረስ፡ የህሙማን ቁጥር ከሆስፒታሎች አቅም እንዳያልፍ የሰጋችው ከተማ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ተባባሪ ጸሐፊ ቲቦር ናጊ፤ የተባለው ነገር “በጣም አስጸያፊ ነው” ብለዋል። የአሜሪካ ምክር ቤት የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ ኃላፊ ጂም ሪች፤ ዚምባብዌ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት እና ባለሥልጣኖችን በመዝለፍ የምጣኔ ሀብት እና የፖለቲካ ቀውሷን ለመሸፈን እየሞከረች ነው ብለዋል። የአሜሪካው አምባሳደር ብራየን ኒኮላስ ከዚምባብዌ መንግሥት ጋር ሲጋጩ የመጀመሪያቸው አይደለም። የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አምና አምባሳደሩን ለማባበበር ሲዝት እንደነበር ይታወሳል። አምባሳደሩን “እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ አባል እየሆኑ ነው” በሚልም ወንጅሏቸዋል። ዚምባብዌ በአሜሪካ የተጣሉባትን ማዕቀቦች በጥብቅ ትቃወማለች። ባለፈው ሳምንት ዛኑ ፒኤፍ በአገሪቱ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ድጋፍ በማድረግ የአሜሪካ ኤምባሲን መወንጀሉ አይዘነጋም። አምባሳደሩን ከአገር አባርራለሁ በማለትም አስፈራርቷል። ተቃውሞ በአገሪቱ የተስፋፋው ሙስናን ለመቃውም ነው ቢባልም፤ የፓርቲው ቃለ አቀባይ ፓትሪክ ቺናማሳ መንግሥትን ለመገልበጥ የተደረገ ሙከራ ነው ብለዋል። ተቃዋሚዎቹ በዚህ ተግባራቸው የሚቀጥሉ ከሆነም ተመጣጣኝ ኃይል መንግሥት እንደሚጠቀምም አስጠንቅዋዋል።
52873324
https://www.bbc.com/amharic/52873324
በብራዚል በአንድ ቀን ብቻ 33 ሺህ ሰዎች በኮሮና ተያዙ
የብራዚሉ ቀኝ አክራሪ ፕሬዝዳንት ጄር ቦልሶናሮ ዛሬም ድረስ ‹‹ለጉንፋን እጅ አትስጡ›› እያሉ ነው፡፡ የአገራቸው ሕዝብ ግን በኮቪድ- 19 እየረገፈ ነው፡፡
ቅዳሜ ዕለት ብቻ የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ይፋ እንዳደረገው 33 ሺህ ዜጎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ትናንትና ደግሞ 1000 ሰዎች ሞተዋል፡፡ አሁን ብራዚል በዓለም ላይ በሟቾች ቁጥር ፈረንሳይን በልጣ ከአሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ጣሊያንን ተከትላ 4ኛ ሆናለች፡፡ በጠቅላላ የሞቱባት ዜጎችም 28 ሺህ 834 ደርሰዋል፡፡ ብራዚል አሁን በሟቾች ቁጥር ከዓለም 4ኛ ትሁን እንጂ በቀጣይ ቀናት አሜሪካንን ተከትላ 2ኛ እንደምትሆን ባለሞያዎች ቅንጣት ጥርጣሬ የላቸውም፡፡ ይህን እንዲተነብዩ ያስቻላቸው ደግሞ ቫይረሱ በዚያች አገር የሚዛመትበት ፍጥነት አስደንጋጭ በመሆኑ ነው፡፡ • የጆርጅ ፍሎይድ የመጨረሻዎቹ 30 ደቂቃዎች • በአሜሪካ ግዛቶች የሰዓት እላፊ ቢታወጅም ተቃውሞዎች እንደቀጠሉ ነው • ሐኪሞችን ግራ ያጋባው የኮሮናቫይረስ ወረርሽንና የሚያስከትለው ጉዳት አወዛጋቢው የቀኝ አክራሪ መሪ ጄር ቦልሴኔሮ አሁንም ሕዝባቸውን ለኮቪድ እጅ መስጠቱን ትቶ ወጥቶ ሥራ እንዲሰራ እየመከሩት ነው፡፡ ለዚህ አመለካከታቸው በርካታ ደጋፊም አላቸው፡፡ ብራዚል በቫይረሱ የተያዙትባት ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን ደርሷል፡፡ ይህም ከአሜሪካ ቀጥላ ዓለምን በ2ኛነት ተጎጂ አገር ያደርጋታል፡፡ በአሜሪካ አሁን የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ከፍ ብሏል፡፡ ፕሬዝዳንት ቦልሴኔሮ ከሪዮ ዴጄኔሮ ገዢና ከሌሎችም አስተዳዳሪዎች ጋር ሽኩቻ ውስጥ ናቸው፡፡ እርሳቸው ሰው እየሞተ ነው ብሎ ቤት መቀመጥ አገሪቱን በምጣኔ ሀብት መቀመቅ ውስጥ መክተት ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ሌሎች የግዛት ገዢዎች ግን ‹‹እርስዎ ሰውዬ ጤና የለዎትም ወይ›› እያሏቸው ነው፡፡ ‹‹ቦልሴኔሮ በቫይረሱ የሚመጣውም ሞት ነው፤ ቤት ብንቀመጥም ኢኮኖሚው ተንኮታኩቶ በረሀብ እንሞታለን›› ሲሉ በር ዘግቶ መቀመጥን ክፉኛ ሲቃወሙ ቆይተዋል፡፡ በአንድ ወቅት ይህንኑ ጉዳይ በምሳሌ ሲያሰረዱ የመኪና አደጋ አለ ብለን ቤት እንደማንቀመጠው ቫይረስ አለ ብለን በር ዘግተን አንቀመጥብ ብለው ነበር፡፡ በዚህ ወጣ ያለ አመለካከታቸው ተቃዋሚዎች እንዳሏቸው ሁሉ ከፍተኛ ድጋፍ የሚሰጧቸውም አሉ፡፡ ፕሬዝዳንት የአፍ-አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሳያደርጉ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ፎቶ ሲነሱና ሲተቃቀፉም ለበርካታ ጊዜ በአደባባይ ታይተዋል፡፡
news-50969838
https://www.bbc.com/amharic/news-50969838
2019፡ የአውሮፕላን አደጋ ተጎጂዎች ቁጥር የቀነሰበት ዓመት ነው ተባለ
የፈረንጆቹ 2019 በአውሮፕላን አደጋ የሚጎዱ ሰዎች ቁጥር በ50 በመቶ የቀነሰበት ዓመት ነው ተባለ።
ቱ70 የተባለ የበረራ ኢንዱስትሪ ጥናት አካሂያጅ ድርጅት፤ ባለፈው ዓመት በአውሮፕላን አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር 257 ሲሆን ከዚያ በፊት በነበረው ዓመት [2018] ግን 534 እንደነበር ዘግቧል። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከባድ የሚባል አደጋ ቢደርስበት በጠቅላላው በዓመቱ የተመዘገበው አደጋ ብዛት በተነፃፃሪ ዝቅ ያለ ነው። እንደ ጥናቱ ከሆነ በአውሮፕላን አደጋ የሚመዘገቡ አደጋዎች ቁጥር ከዓመት ዓመት መቀነስ እያሳየ ሲሆን የአውሮፕላን በረራዎች ደግሞ እጅግ እየጨመሩ መጥተዋል። ድርጀቱ ባደረገው ጥናት መሠረት ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 86 አደጋዎች ትላልቅ በሚባሉ የንግድ አውሮፕላኖች ላይ የደረሰ ሲሆን፤ 8 ከባድ አደጋዎች ተከስተው 257 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ከጠቅላላው የዓመቱ 257 ተጎጂዎች መካከል 157 ሰዎች ያለቁት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ መከስከስ ምክንያት ነው። በዓለማችን ከሚከወኑ 5.58 ሚሊዮን የትላልቅ ንግድ አውሮፕላን በረራዎች መካከል አንድ ከበድ ያለ አደጋ ደርሷል። አቪዬሽን ሴፍቲ ኔትዎርክ የተሰኘ ተቋም ያለፈው ዓመት በንግድ አውሮፕላን በረራ ኢንዱስትሪው የተሻለ የሚባለው ነው ሲል ተደምጧል። ቢሆንም 2017 በበረራ ታሪክ 13 ጉዳቶች ብቻ የተመዘገቡበት ሆኖ አልፏል። ጥናቱ ትላልቅ የንግድ አውሮፕላኖችን ብቻ አካቶ የተሠራ ሲሆን አነስተኛ አውሮፕላኖች አልተካተቱበትም። አልፎም ወታደራዊ፣ የልምምድ እና የግል አውሮፕላኖች በጥናቱ ውስጥ አልተካተቱም። በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢንዶኔዥያው ላየን አየር መንገድ ላይ የደረሱት ሁለት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋዎች በበረራ ኢንዱስትሪው ላይ በጎ የማይባል አሻራ ጥለው አልፈዋል።
news-55407744
https://www.bbc.com/amharic/news-55407744
የኮሮናቫይረስ ፡ ነፍሰጡር እናቶች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ይችላሉ?
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የኮሮናቫይረስ ክትባት በተለያዩ አገሮች እየተሰጠ ነው። ነፍሰጡሮች ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ? የሚለው ጥያቄም እየተነሳ ነው።
የፋይዘርና ባዮንቴክ ክትባቶች ሙከራ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶችን አላካተተም። ክትባቱ በእነሱ ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ በቂ መረጃ ስለሌለ፤ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች ክትባቱን እንዳይወስዱ ተመክሯል። በሌላ በኩል አሜሪካ፤ ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች ክትባቱን መውሰድ ወይም አለመውሰድን በተመለከተ የግል ምርጫቸው ነው ብላለች። እስካሁን የተገኙት መረጃዎች ምን ያሳያሉ? በነፍሰጡር ሴቶች ጤና ዙርያ በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የሚሰሩት ዶ/ር ሩት ፋደን፤ "እስካሁን ይህ ነው የሚባል መረጃ አልተገኘም" ሲሉ ይናገራሉ። ክትባቱ ለነፍሰጡር ወይም ለሚያጠቡ ሴቶች አስጊ መሆኑን የሚጠቁም በቂ መረጃ የለም። የመድኃኒት አምራቹ ፋይዘር የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ተቋም ባወጣው መመሪያ መሠረት ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶችን በሙከራው እንዳላካተተ ተናግሯል። ዳርት ወይም ዴቨሎፕመንታል ኤንድ ሪፕሮዳክቲቭ ቶክሲሲቲ የተባለው በእድገትና በሥነ ተዋልዶ ሂደት ላይ ሊኖር የሚችል ውጤትን የሚያሳይ ምርምር በእንስሳት ላይ ተካሂዶ እስኪጠናቀቅ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ ሴቶች በሙከራው እንደማይካተቱ ፋይዘር አስረድቷል። ዶ/ር ሩት እንደሚሉት፤ ከወረርሽኝ ውጪ ያሉ በሽታዎች ሲከሰቱና ክትባት ሲሰራላቸው በመጀመሪያው የምርምር ደረጃ ነፍሰጡር ሴቶች አይካተቱም። ከእናት በተጨማሪ ልጅም ከግምት ስለሚገባ፤ በዘርፉ ነፍሰጡር ሴቶች በተለየ ሁኔታ ትኩረት ይሰጣቸዋል። ወረርሽኞች ሲከሰቱ ግን ነፍሰጡሮችን በምርምር አለማካተት ፈታኝ ይሆናል። "በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነን። በምርምሩ ነፍሰጡር ሴቶችን ማካተት ጥቅምም ጉዳትም አለው" የሚሉት ዶ/ር ኤምሊ ስቲኔት ናቸው። በሌላ በኩል ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶችን በክሊኒካል ውሳኔዎች ለማሳተፍ እስካሁን በቂ መረጃ አልተኘም። በየአገሩ ያሉ የተለያዩ መርሆች አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደምን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ሁለቱም አገሮች በጉዳዩ ላይ በቂ መረጃ የላቸውም። ሆኖም ግን የተለያየ የፖሊሲ አቅጣጫ ይከተላሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ያለውን የመረጃ ክፍተት ከግምት በማስገባት፤ ተጨማሪ መረጃ እስከሚገኝ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች ክትባቱን እንዳይወስዱ ብላለች። የሮያል ኮሌጁ ዶ/ር ኤድዋርድ ሞሪስ እንደሚሉት፤ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ ሴቶች በክትባት ምርምር ወቅት ስላልተካተቱ ክትባቱን መስጠት አስተማማኝ አይሆንም። የአሜሪካ ባለሙያዎች ግን ከዚህ የተለየ አቅጣጫ ተከትለዋል። ክትባት የመውሰድ ውሳኔውን ለነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች ትተዋል። ዶ/ር ሩት እንደሚሉት፤ እነዚህ ባለሙያዎች ክትባቱ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ውስን እንደሚሆን ተስማምተዋል። አስፈላጊውን የምርመራ ሂደት ያለፉት ክትባቶቹ ደኅንነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው በዩናይትድ ኪንግድም እና በአሜሪካ ፍቃድ የተሰጣቸው። በሁለቱም አገሮች ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች ክትባቱን የሚመለከት ምክር ከማግኘታቸው በፊት ተጨማሪ መረጃ ሊኖር ይገባል። ፋይዘር በዚህ ዙርያ የሚያደርገው ምርምር በዚህ ዓመት መጨረሻ ይገባደዳል ተብሎ ይጠበቃል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ ያረገዙ ሴቶች በቅርብ ክትትል ይደረግላቸዋል። ክትባቱን ከወሰዱ ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊው መረጃም ይሰበሰባል። አሜሪካ ውስጥ ክትባቱን ለመውሰድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ከተባሉ የጤና ባለሙያዎች 330 ሺህ ያህሉ ነፍሰጡር ወይም የሚያጠቡ እናቶች ናቸው። አሜሪካ፣ ኦሀዮ ውስጥ የምትኖረው የ35 ዓመቷ ነፍሰጡር ከመውለዷ በፊት ክትባት የመውሰድ እቅድ የላትም። ክትባቱ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ስለማታውቅና የመጀመሪያ እርግዝናዋ ስለሆነ ክትባቱን ነፍሰጡር ሳለች ለመውሰድ እንዳላሰበች ተናግራለች። የ34 ዓመቷ የእንግሊዝ ነዋሪ ኤሚ ኮልድነር በበኩሏ የሁለት ዓመት ልጇን እያጠባች ቢሆንም ክትባቱን ለመውሰድ ወስናለች። ገና ነፍሰጡር ብትሆን ኖሮ ተጨማሪ መረጃ እስክታገኝ ክትባት እንደማትወስድ አያይዛ ተናግራለች። ነፍሰጡሮች ልጃቸውን ለአደጋ ላለማጋለጥ ሲሉ በክትባት ሙከራው ላይሳተፉ እንደሚችሉ ኤሚ ትገምታለች። ዶ/ር ሩት እንደሚናገሩት ከሆነ ግን ነፍሰጡርና የሚያጠቡ ሴቶች በሙከራ ሂደቱ ሲሳተፉ የክትባቱን አስተማማኝነት ማረጋገጥ ይቻላል።
news-50709908
https://www.bbc.com/amharic/news-50709908
ደቡብ አፍሪካዊቷ የዘንድሮው 'ሚስ ዩኒቨርስ' ቁንጅና ውድድር አሸነፈች
ደቡብ አፍሪካዊቷ ዞዚቢኒ ቱንዚ የዘንድሮውን 'ሚስ ዩኒቨርስ' ቁንጅና ውድድር አሸናፊ ሆናለች።
ዞዚቢኒ አሸናፊ የሆነችው በተለያዩ ዙሮች ላይ ባደረገቻቸው አልባሳት፤ እንዲሁም ለቀረቡላት ጥያቄዎች መልሶች ዳኞችንና አድናቂዎቿን ማስደመም በመቻሏ ነው። የፖርተሪኳዋ ማዲሰን አንደርሰንና የሜክሲኮዋ ሶፊያ አራጎን ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል። •አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ •ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . ዞዚቢኒ በጥያቄና መልስ ወቅት በዋናነት ለሴት ልጅ ጠቃሚው ነገር መሪነት ነው ብላለች። "ለዘመናት በታዳጊ ሴቶችም ሆነ በአጠቃላይ ሴቶች የታጣው መሪነት ነው፤ ስለማንፈልግ ሳይሆን ማህበረሰቡ ሴቶች አይገባቸውም በሚል ስላስቀመጠው ነው" ብላለች። •የጌዲዮ ዞን የክልል እንሁን ጥያቄ ምን ደረሰ? ዞዚቢኒ በኢንተርኔትም ላይ አንድ ዘመቻ ጀምራ ነበር፤ ደቡብ አፍሪካውያን ወንዶች ለሴቶች የፍቅር ደብዳቤ እንዲፅፉላቸው። እነዚህንም የፍቅር ደብዳቤዎች አሰባስባ በሃገሯ ሰንደቅ አላማ በታጀበ ባህላዊ ልብሷ ላይ አካታው ነበር።
news-53717564
https://www.bbc.com/amharic/news-53717564
ለማ መገርሳ፡ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት አመራሮችን በጊዜያዊነት አገደ
የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከፍተኛ አመራሮቹ ላይ ጊዜያዊ እገዳ ማስተላለፉን አሳወቀ።
የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ በኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን (ኦቢኤን) ላይ ቀርበው በፓርቲው ስለተላለፈው የእገዳ ውሳኔ ዕሁድ ምሽት ላይ እንደተናገሩት የመከላከያ ሚኒስትሩና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ በጊዜያዊነት ታግደዋል። በተጨማሪም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ የሆኑት ወይዘሮ ጠይባ ሐሰን እንዲሁም ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የነበሩትና በኋላም የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ አማካሪ እንደሆኑ የተነገረላቸው ሚልኬሳ ሚደጋ (ዶ/ር) ከታገዱት ውስጥ ናቸው። ይህ ውሳኔ የተላለፈው የኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ለሁለት ቀናት በክልሉ ውስጥ ስላለው ሁኔታና በፓርቲው ጉዳዮች ላይ ያደረገውን ውይይትና ግምገማ ሲያጠናቅቅ መሆኑ ተነግሯል። አቶ ፈቃዱ እንዳሉት አቶ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ጠይባ ሐሰንና ሚልኬሳ ሚደጋ (ዶ/ር) ከፓርቲው የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት አልቻሉም በሚል ነው። ጨምረውም እግዱ የተጣለባቸው የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛውም ጊዜ መመለስ አንደሚችሉ ተናግረዋል። ይህም በሦስቱ የቀድሞው የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ላይ የተላለፈው እገዳው ጊዜያዊ በመሆኑ ወደ ፓርቲው የመመለስ እድል እንዳላቸው ያመልክታል። ከዚህ ባሻገርም ፓርቲው "ከ800 በላይ የወረዳ ባለስልጣናት፣ በከተማ እና በዞን ደግሞ 117 አመራሮች ላይ የማጽዳት ሥራ ለመስራት ተሞክሯል" በማለት በተለያዩ ደረጃዎች የተወሰዱ እርምጃዎች እንዳሉ ተናግረዋል። የአዲሱ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቀጥለው ጎልተው ይታዩ የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደርነት ተነስተው የመከላከያ ሚኒስትርነት ኃላፊነትን ከያዙ በኋላ ከዕይታ ርቀው ቆይተዋል። አቶ ለማ ከቀድሞው ኢህአዴግ መክሰም በኋላ የገዢ ፓርቲነቱን ቦታ በተረከበው የብልጽግና ፓርቲ ምስረታ ሂደት ላይ ጥያቄ እንዳላቸው በይፋ ወጥተው የተናገሩ ሲሆን፤ በካቢኔ ስብሰባዎች ላይ ከመገኘት ባሻገር በፓርቲውም ሆነ በመንግሥት እንቅስቃሴዎች ውስጥ የነቃ ተሳትፎ ሲያደርጉ ብዙም ሳይታዩ ቆይተዋል። ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ከኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርነት ከተነሱ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ውስጥ በከፍተኛ የአማካሪነት ቦታ ላይ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከወራት በፊት ከወለዱ በኋላ በሥራ ቦታቸው ላይ እንዳልታዩ የቅርብ ሰዎች ተናግረዋል። የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ከፓርቲው ስብሰባ መጠናቀቅ በኋላ ለኦቢኤን እንደተናገሩት ፓርቲው በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ መስጠቱን ገልጸዋል። በስብሰባው የፓርቲው አመራር ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት በኩል ክፍተት እንዳለና በዚህም ላይ ግምገማ ተደርጎ የማስተካከያ አቅጣጫ መቀመጡን አመልክተዋል። ፓርቲው በተለይ የእገዳ ውሳኔ ያስተላለፈባቸው ከፍተኛ አመራሮቹ አቶ ለማ መገርሳ፣ ወይዘሮ ጠይባ ሐሰን እና ሚልኬሳ ሚደጋ (ዶ/ር) ከያዙት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መታገዳቸው ተገልጿል። እገዳው በፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚጸድቅ ሲሆን እግዱ የተጣለባቸው አባላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ በሚሆኑ ጊዜ ግን ሊመለሱ እንደሚችሉ አመልክተዋል። የኦሮሚያ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ጨምረውም ከፍተኛ አመራሩና አባላቱ "የፓርቲውን አቋም ይዞ በመታገል ላይ ክፍተት እንዳለ እንዲሁም ሌብነትም እንደ ተግዳሮት" ተጠቅሶ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም በጋራ ለመስራት ውሳኔ ላይ መደረሱን ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ባጋጠመው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነሐሴ 2 እና 3/ 2012 ዓ.ም በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን፤ በዚህም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድን ጨምሮ የክልሉና የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል።
news-51723206
https://www.bbc.com/amharic/news-51723206
በአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ዳኞች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው
በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በዳኞች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እየተበራከተ መምጣቱ ተገለጸ።
ይህ ጥቃት በተለያዩ የክልሉ የፍትሕ መዋቅር ውስጥ በመሆን ሕግን እንዲተረጉሙ በተመደቡ ዳኞች ላይ እየተፈጸመ መሆኑን ዳኞችና የክልሉ ፍትህ ቢሮ አመልክቷል። የክልሉ መንግሥትም ይህንን ድርጊት በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርማጃ ለመውሰድ ምርመራ እኣካሄደ መሆኑንም አመልክቷል። በቅርቡም የወረዳ ፍርድ ቤት የፍትሐ ብሔር ዳኛ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ኪዳኔና ባልደረቦቻቸው ተመሳሳይ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። አቶ ኤፍሬም ከሁለት የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር አረፍ ብለው ስለ ውሏቸው እና ሥራቸው እየተጫወቱ ነው። "የካቲት 18 ከሥራ በኋላ ቤተክርስቲያን ጸሎት አድርገን አረፍ ብለን ነበር" ሲሉ ዕለቱን ያስታውሳሉ። ባላሰቡት እና ባልጠበቁት ሁኔታ ነበር መምጣታቸውን ያላስተዋሏቸው ግለሰቦች ከኋላ ደርሰው ጥቃት ያደርሱባቸው የጀመሩት። ጥቃት አድራሾቹ ሁለት መሆናቸውን ይገልጻሉ። "ከፍተኛ ጉዳት ነው" ይላሉ አቶ ኤፍሬም "በተለይ አንደኛው ዳኛ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ነው የደረሰበት። የዱላ ድብደባ ነው። እኔን ማጅራቴ አካባቢ ነው የመቱኝ። ሌላውን ጓደኛዬን ራሱን ነው የመቱት። ሦስተኛው ጥርሱ ረግፏል፤ ዓይኑ አካባቢ ጉዳት ደርሶበታል፤ አፍንጫውም ተሰብሯል። በጣም ዘግናኝ ጉዳት ነው የደረሰበት" ሲሉ የጉዳቱን መጠን ያስረዳሉ። አቶ ኤፍሬም ጥቃት አድራሾችንም ሆነ ምክንያታቸውን እንደማያውቁ ነው ለቢቢሲ የገለጹት። ባሉበት ድንገተኛ የሆነ ጥቃት እንደደረሰባቸው እንጂ ከጥቃቱ ጀርባ ስላለው ሁኔታ መናገር እንደማይችሉ ገልጸዋል። ጥቃቱ የደረሰባቸው ከሥራቸው ጋር ተያያዥ በሆነ ምክንያት እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "ከሥራ ውጭ ምን ሊሆን ይችላል? ጸብ የለንም። ከሥራችን ውጭ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም ከማንም ጋር ግላዊ ጸብ የለንም። ለዚህ ሊያደረስ የሚችል ነገር የለንም። መቶ በመቶ ባይባልም በሥራችን ምክንያት ነው ሊባል ነው የሚችለው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ጥቃቱን "አስነዋሪ፣ አሳዛኝ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው" ያሉት ደግሞ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ታዘባቸው ጣሴ ናቸው። "በዱላ እና በድንጋይ ነው ጠጥቃቱ የተፈጸመው። ተዘናግተው በተቀመጡበት ከኋላ መጥተው ነው ያጠቋቸው። ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት ሁኔታም አልነበረም" ሲሉ ያስረዳሉ። "ዳኞች የድርብ ችግር ሰለባ ሆነዋል" የሚሉት አቶ ታዘባቸው፤ "ውስብስብ መዝገቦችን በአግባቡ ለመወሰን ቀን ከሌት ከመሥራታቸውም ሌላ ሕገ ወጦች ጥቃት እያደረሱባቸው ነው" ይላሉ። "በርካታ ዳኞች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው። ስለሆነም በቀላሉ መታየት የለበትም። እልባት ማግኘት አለበት። ጥቃቱም መታየት እና መፈተሽ አለበት።" ይህ ጥቃትም የመጀመሪያ አለመሆኑን ጠቁመው ሁኔታውም ዳኞችን ተስፋ እስከማስቆረጥ እንደደረሰ ገልጸዋል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ይህን ምክንያት አድርጎ መግለጫ አውጥቶ ነበር። የክልሉ ዳኞች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ስጋት ላይ ወድቆ በነበረበት ጊዜ ሳይቀር ያለማንም ተጽዕኖ በሕግ ብቻ ውሳኔ በመስጠት የዳኝነት አገልግሎቱ ላቅ እንዲል እየሠሩ መሆኑን በመግለጫው ተመልክቷል። በተለያዩ ወቅቶች በማዕከላዊ ጎንደር፣ በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ጎንደር፣ በአዊ ብሔረሰብ፣ በሰሜን ወሎ እና ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በሚገኙ ዳኞች ላይ የተለያዩ ጥቃቶች እና ተፅዕኖዎች መድረሳቸውን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል። "ጥቃቱ በተመታው ዳኛ ላይ ብቻ ሳይሆን በፍትህ ሥርዓቱና በሕዝቡ ላይ እንደደረሰ ታስቦ መንግሥት እና ኅብረተሰቡ ርብርብ በማድረግ ጥበቃ ሊያደረግላቸው ይገባል" የሚሉት አቶ ታዘባቸው፤ "በዚህ መልኩ ከተሄደ [የፍትህ] ሥርዓቱ ችግር ውስጥ ይወድቃል" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ችግሩ በተደጋጋሚ የተከሰተው ሙሉ በሙሉ በቸልታ ስለታለፈ አይደለም ብለዋል። "የደህንነት ጥበቃ የላቸውም። በየቀኑ ፍርድ ይሰጣሉ። የተፈረደበት ወገን ላይደሰት የሚችልበት ሁኔታ አለ። በየደረጃው ያሉ ዳኞች ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል። ራሳቸውን የሚከላከሉበት መሣሪያ የላቸውም። "ጠባቂያችን ሕዝብ፣ ህሊናችንና ሥራችን ነው ባሉበት ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። መንግሥት የደህንነት ጥበቃ ማድረግ አለበት። መሣሪያ ሰጥቶ ራሳቸውን እንዲከላከሉ በማድረግ ኃፊነቱን መወጣት አለበት" ሲሉ መፍትሔ ያሉትን አስቀምጠዋል። በዚህ ሃሳብ ዳኛ ኤፍሬምም ይስማማሉ። "ለዳኞች ጥበቃ ሊደረግ ይገባል ምክንያቱም በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ነው ውሳኔ የሚሰጠው። መንግሥት በተለየ መንገድ ለዳኞች ጥበቃ ማድረግ አለበት። ትኩረት መሰጠት አለበት። ጉዳት አድራሾቹም ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለባቸው። በመንግሥት በኩል የዳኞች ጉዳይ ያን ያህል ትኩረት የሚሰጠው አይደለም።" "ጥቃቱ በፍትህ ሥርዓቱም ሆነ በዳኞች ላይ ትልቅ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል። ዳኞች ነጻ ሆነው ሕግን መሠረት አድርገው ውሳኔ እንዳይሰጡ ነው የሚያደርገው። መጀመሪያ የዳኞች ደህንነትና ህልውና ካልተረጋገጠ እንዴት ተብሎ ትክክለኛ የሆነ ፍትህ ሊሰጥ ይችላል?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ፍርድ ቤቶች መቶ በመቶ እንከን አልባ አለመሆናቸውን የሚገልጹት አቶ ታዘባቸው፤ "ተበድለናል ወይም ፍርዱ ትክክል አይደለም ካሉ በይግባኝ መጠየቅ ይቻላል። የሥነ ምግባር ችግር ያለባቸው ዳኞች ይኖራሉ። ዳኞች ላይ እርምጃ ይወሰዳል። እርምጃ የተወሰደባቸውም አሉ። የተባረሩ፣ የታሰሩም አሉ።" አክለውም "ካልሆነ ግን የፍትህ ሥርዓቱን መጋፋት ነው። የሕግ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ እየወደቀ ስለሆነ በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና የጸጥታ አካላትም ልዩ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል። ከአመራር እና የጸጥታ አካላት ጋር እንሠራለን። መንግሥት ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። ዱር ቤቴ ከተማ ጉዳት ከደረሰባቸው ሦስት ዳኞች መካከል ሁለቱ ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። ሦስተኛው ግን ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ በህክምና ባለሙያዎች ርብርብ በማገገም ላይ ይገኛል። ጉዳዩን ለማጣራት የምርመራ ቡድን ተቋቁሟል። "ቡድኑ እየሠራ ነው። የምርመራ ቡድኑ በራሱ መንገድ በነጻነት እየተንቀሳቀሰ ነው። በቅርቡ ወንጀለኞችን ለፍርድ ያቀርባሉ ብለን እናስባለን" ሲሉ አቶ ታዘባቸው ገልጸዋል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሕግ እና ሥርዓት የማፍረስ ተግባርን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ፤ ጥፋተኞች ለሕግ እንዲቀርቡ እና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
48197254
https://www.bbc.com/amharic/48197254
ማይክሮሶፍት ጽሁፍን የሚያቀል አሠራር ፈጠረ
የማይክሮሶፍት ተቋም የጸሀፊዎች ሥራ የሚያቀል አዲስ አሰራር ይፋ አድርጓል።
ማይክሮሶፍት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጽሁፍን ለማሻሻል ወጥኗል በ 'ማይክሮሶፍት ወርድ' የሚጽፉ ሰዎች ከእንግዲህ ስለ ቃላት ድግምግሞሽና ስለ ሰዋሰው አወቃቀር መጨነቅ የለባቸውም ብሏል። 'ማይክሮሶፍት ወርድ' ከዚህ ቀደምም የእንግሊዘኛ ቃላትና ሰዋሰው ግድፈት ያርም ነበር። አሁን ግን አሰራሩን ወደላቀ ደረጃ ወስጄዋለሁ ብሏል። • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ • የታኘከ ማስቲካ ዳግም ነብስ ሲዘራ ማይክሮሶፍት እንዳለው፤ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) በመጠቀም የተጣመመ አረፍተ ነገር እንዲቃና፣ ሴት ወይም ወንድን ብቻ የሚገልጽ ቃል ሁለቱንም ያማከለ እንዲሆን የሚያስችል አሰራር ፈጥሯል። በጽሁፍ ውስጥ ሰነድ ወይም ሰንጠረዥ ካለ በተገቢው ሁኔታ እንዲቀመጥ ይጠቁማል። ጽሁፍን አጭርና ግልጽ ለማድረግ ለቃላትና ሀረጎች አቻ ትርጉም ይሰጣል። አሰራሩ የቀረበው 'ማይክሮሶፍት ወርድ' ን በኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ተገልጋዮች ሲሆን ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ተግባር ላይ ይውላል። ተቋሙ እንዳለው፤ ጽሁፍ ልዩ የሰው ልጅ የፈጠራ ችሎታ የሚጠይቅ በመሆኑ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መተካት አይቻልም። ሆኖም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሰውን እንዲያግዝ ማድረግ ይቻላል። ጸሀፊና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኤክስፐርት ካሉም ቼስ፣ አዲሱ አሠራር ውጤታማ እንደሚሆን ይናገራሉ። • በእውቀቱ ስዩም፣ አለማየሁ ገላጋይና ዳንኤል ወርቁ ተሸለሙ • «በስልክዎ ታካሚና አካሚ እናገናኛለን» ሥራ ፈጣሪው ወጣት "አሰራሩ ቃላት ከማስተካከል ጀምሮ አረፍተ ነገርና አንቀጽ ወደማስተካከል ያድጋል" ይላሉ። አሰራሩ ለጋዜጠኞች፣ ለጸሀፊዎችም ጠቃሚ መሆኑ ባያጠያይቅም የሰው ልጅን እውቀት የሚተካም እንደሌለ አስረግጧል።
news-53422737
https://www.bbc.com/amharic/news-53422737
የሩሲያ የመረጃ መረብ ሰርሳሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ምርምርን ኢላማ ማድረጋቸው ተነገረ
ሩሲያዊያን የመረጃ መረብ ሰርሳሪዎች [ሃከርስ] የኮሮናቫይረስ ክትባት ለመስራት እየጣሩ ያሉ ተቋማትን ኢላማ ማድረጋቸውን የብሔራዊ ደኅንነት አገልግሎት ቡድን አስጠነቀቀ።
የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የመረጃ መረብ ደኅንነት ማዕከል፤ መረጃ መንታፊዎቹ ከሞላ ጎደል "የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አካል" እንደሆኑ በመምሰል እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ጠቁሟል። ቡድኑ ከኮቪድ -19 ክትባት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለመስረቅ በኮምፒዩተሮች፣ በመረጃ ቋት አሊያም የኮምፒዩተር መረቦች ላይ ጉዳት ለማድረስ ሆነ ተብሎ የተሰራ ሶፍትዌር መጠቀሙን ተቋሙ አስታውቋል። በተቋሙ የኦፕሬሽኑ ዳሬክተር ፖል ቺቸስተር ድርጊቱን "አስቀያሚ" ብለውታል። ይህ የደኅንነት ተቋሙ ማስጠንቀቂያ የወጣው በዩናይትድ ኪንግደም፣ በካናዳና በአሜሪካ የመረጃ መረብ ደኅንት ተቋማት አማካይነት ነው። መረጃ መንታፊዎቹ 'ኤፕቲ29' የተባለ ቡድን አካል መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን 'ዘ ዳክስ' ወይም 'ኮዚ ቤር' በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ ቡድኖች ተጋላጭ የሆኑ የኮምፒዩተር ሥርዓቶች ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመጠቀም፤ ከተጠቁ ማሽኖች መረጃዎችን ለመጫንና ለማውረድ የሚያስችሉ 'ዌልሜስ' እና 'ዌልሜል' የተባሉ ማልዌር ሶፍትዌሮችን ተጠቅመዋል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ግለሰቦች በማታለል ወደ ኮምፒውተር ሥርዓቶች የመግቢያ የይለፍ አድራሻዎችን እንዲሰጧቸው በማድረግ በተለያዩ መንገዶች ጥቃቱን እንደሚፈጽሙ ተገልጿል። እንዱሁም ለግለሰቦች ከታወቀ ሰው የተላከ በማስመሰል የኢሜል መልዕክቶችን በመላክ እንዲሁም ለተለያዩ ወገኖች በተለይ የተዘጋጁ ማታለያዎችንም በመጠቀም ለሚፈጽሙት የመረጃ መረብ ጥቃት አመቺ የሆኑ ዘዴዎችን እንደሚጠቀሙ ተጠቁመወል። "በዚህ ዓመት ኤፒቲ29 የተባለው ይህ ቡድን በካናዳ፣ በአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም በኮቪድ -19 ክትባት ላይ የሚሰሩ በርካታ ድርጅቶችን ኢላማ ያደረገ ሲሆን፤ ከምርምሩ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን የአዕምሯዊ ንብረቶችን ለመስረቅ የታሰበ ሊሆን ይችላል" ብሏል ይህንኑ በተመለከተ ከመረጃ ደኅንነት ቡድኑ የወጣው ሪፖርት። ነገር ግን ሪፖርቱ የተሰረቁ መረጃዎች ስለመኖር አለመኖራቸው በግልጽ የጠቀሰው ነገር የለም።
news-49724623
https://www.bbc.com/amharic/news-49724623
በምዕራብ ኦሮሚያ የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ ግድያ የነዋሪውን ስጋት አባብሷል
በምዕራብ ወለጋ የምትገኘው የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ተካልኝ በመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ በታጣቂዎች ተገደሉ።
የጉሊሶ ከተማ ከተማዋን ላለፉት ጥቂት ወራት ያስተዳደሩት የከንቲባው ሥርዓተ ቀብር ትናንት መፈጸሙም ተነግሯል። አቶ አበበ ዕሁድ ምሽት ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ በታጣቂዎች መገደላቸውን የጉሊሶ ወረዳ የአስተዳደር እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋ ሊካሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። "ደጃፋቸው ላይ በሁለት ጥይት ግንባራቸውን ተመትተው ነው የተገደሉት" ሲሉ የጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊው ተናግረዋል። • የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ስጋትና ሰቆቃ ታጣቂዎቹ ከንቲባውን ደጃፋቸው ላይ ከገደሉ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ዘልቀው በመግባት "ለስብሰባ የተዘጋጀ ጽሑፍ እና የአካባቢውን ባለስልጣናት ስም ዝርዝርን የያዘ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ይዘው ሄዱ'' ሲሉ አቶ ተስፋ ጨምረው ተናግረዋል። ከንቲባውን ገድለው ላፕቶፕ ዘርፈው ሄዱ የተባሉት ታጣቂዎች በቁጥር ወደ ስድስት እንደሚጠጉ የሟች የቤተሰብ አባላት ለመንግሥት የጸጥታ አካል መናገራቸውም ተገልጿል። ግድያው እንዴት ተፈጸመ?ጥቃቱ በተፈጸመበት ምሽት የሁለት ልጆች አባት የነበሩት ከንቲባ አበበ ተካልኝ እሁድ ምሽት ላይ ከልጆቻቸው ጋር ቴሌቪዥን እየተመለከቱ ላፕቶፓቸው ላይ እየጻፉ ነበር። • በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም፡ ግብጽ አራት ሰዓት ገደማ ላይ ከንቲባውን የሚፈልግ ሰው ከውጪ እንደተጣራና 10 ዓመት የማይሞለው ልጃቸው ወደ ውጪ ሊወጣ ሲል አባት ልጅን ከልክለው እንደወጡ ደጃፋቸው ላይ በሁለት ጥይት ግንባራቸውን ተመትተው መገደላቸውን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ከዚህ ቀደምም በምዕራብ ኦሮሚያ በነዋሪች ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች በተጨማሪ፤ የአካባቢው ባለስልጣናት የታጣቂዎች ኢላማ ሆነው ቆይተዋል። ከጥቂት ወራት የቄለም ወለጋ ዞን የደህንንት እና የኦዲፒ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ግለሰብ ተገድለዋል። በተመሳሳይ የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕረዝዳንት በታጣቂዎች ታግተው የነበረ ሲሆን የዚያው የደንቢ ዶሎ ከተማ ከንቲባም ቀደም ሲል በጥይት ተመተው በህይወት መትረፍ ችለዋል። የተያዘ አለ? ይህ ግድያ ከተፈጸመው በኋላ እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋለ ተጠርጣሪ እንደሌለ የሚናገሩት አቶ ተስፋ ፖሊስ የጥቃቱን ፈጻሚዎች ለመያዝ የክትትልና የማጣራት ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ተናግረዋል። በታጣቂዎች የተገደሉት ከንቲባ ሚስት ከክስተቱ በኋላ ለጸጥታ አካላት ተናገረዋል ብለው አቶ ተስፋ ሊካስ እንደጠቀሱት፤ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች የሲቪል ልብስ ለብሰው እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም የገጠሩም ሆነ የከተማ ነዋሪ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ ስለገባ፤ ''ነጋዴው ወደ ሌላ ከተማ እየሸሸ ነው። አርሶ አደሩም ከገጠር ወደ ከተማ እየሸሸ ነው'' በማለት ነዋሪዎች የገቡበትን የደህንነት ስጋት ቀደም ሲል ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ከግድያው በኋላ የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይ ደግሞ የመንግሥት ሰራተኞች እጅጉን ተደናግጠዋል ሲሉ የጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊው በአካባቢው የተፈጠረውን ስጋት ተናግረዋል። • ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ "ከግድያው በኋላ የመንግሥት ሰራተኞች ተደጋግጠዋል። ግድያው በእኛ ላይ ሊፈጸም ይችላል የሚል ስጋት ስላደረባቸው ትናንት (ሰኞ) ወደ ሥራ አልገቡም።''የዚያው አካባቢ ተወላጅ የነበሩት ከንቲባው አቶ አበበ ተካልኝ በታጣቂዎቹ የተገደሉበት ምንክንያት እስካሁን ግልጽ አይደለም። የአስተዳደር እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊው ይህን ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉት ግለሰቦች ወደ ጫካ መሸሻቸውን ይናገራሉ። ኃላፊው "በአካባቢው የሚንቀሳቀሱና እራሳቸውን የኦነግ ሠራዊት እየሉ የሚጠሩት ታጣቂዎች ይህን ግድያ የፈጸሙት ናቸው ብለን እናምናለን" ብለዋል። አቶ ተካልኝ ከመገደላቸው ከሁለት ቀናት በፊት (ቅዳሜ) ከምሽት በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል። "ቅዳሜ ምሽት ተኩስ ነበር። በዚያ ተኩስ ሳቢያ ነው ሁለቱ ነዋሪዎች የተገደሉት። እነሱን የገደለው አካል የቱ እንደሆነ ደግሞ መለየት አልቻልንም" በማለት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅስ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ነግረውን ነበር። በምዕራብ ኦሮሚያ ይህን መሰሉ በነዋሪዎችና በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና ግድያ ሲፈጸም ወራት የተቆጠሩ ሲሆን ለጥቃቱ በይፋ ኃላፊነት የሚወስድም ሆነ ተጠያቂ የሆነ አካል አልተገኘም። ከአንድ ዓመት በፊትም በዚሁ ጉሊሶ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ እና አዋሽ ባንክ በታጣቂዎች መዘረፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ መንግሥት የኦነግ ሠራዊት አባላት ዘረፊያውን መፈጸማቸውን አሳውቆ ነበር።
news-55098001
https://www.bbc.com/amharic/news-55098001
ትግራይ፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከአፍሪካ ኅብረት ልዑካን ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ በአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበርና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ከተላኩት ልዩ ልዑካን ጋር መወያየታቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ጋር ከሦስት ሳምንታት በላይ በሆነውና በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያጋጠመውን ወታደራዊ ግጭት በተመለከተ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የተሰየሙት ሦስቱ የቀድሞ የአፍሪካ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ መግባታቸው የተነገረው ትናንት ነበረ። ጠቅላይ ሚንሰትሩ በውይይቱ ቡድኑ ለኢትዮጵያ ጉዳይ ትኩረት መስጠቱን አንስተው ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን "በትግራይ እየተከናወነ ስላለው የሕግ ማስከበር እርምጃ" ማብራሪያ እንደሰጡና ባለፉት ሁለት ዓመታት የህወሓት ኃይል በአገሪቱ የዲሞክራሲ ግንባታ ላይ ሲፈጥር ነበር ያሉትን እንቅፋት በዝርዝር አስረድተዋል ብሏል ጽ/ቤታቸው። ማዕከላዊው መንግሥት የትግራይ ክልልን ከሚያስተዳድረው ህወሓት ጋር የነበረው አለመግባባት ተካሮ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወደ ወታደራዊ ግጭት የተገባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የትግራይ ኃይሎች በሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ከገለጹ በኋላ ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድን አግኝተው ተወያዩት የቀድሞው የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ዮአኪም ቺሳኖ፣ የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ሰርሊፍ ጆንሰንና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዝደንት የነበሩትን ጋሌማ ሞትላንቴ ናቸው። ልዑኩ ትናንት አዲስ አበባ የገባው በኢትዮጵያ መንግሥትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት ሦስት ሳምንት ካስቆጠረ እና የመጨረሻ የተባለው ዘመቻ እንዲካሄድ ጠቅላይ ሚንሰትሩ ካዘዙ በኋላ ነው። ግጭቱ ያሳሰባቸው የአፍሪካ ኅብረትና የተለያዩ አካላት ውይይት እንዲደረግ ሲወተውቱ የቆዩ ሲሆን የወቅቱ የኅብረቱ ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳም መፍትሔ የሚያፈላልጉትን ልዑካን የሰሙት ባለፈው ቅዳሜ ነበር። ልዑካኑ በቀዳሚነት ግጭቱን ለማስቆም ከሁሉም ወገኖች ጋር በመነጋገር ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣትና "ግጭቱን ባስከተሉት ጉዳዮች ላይ መፍትሔ ለማስገኘት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራሉ" ተብሎ ነበር። ጠቅላይ ሚንሰትሩ ከልዑካኑ ጋር በተወያዩበት ወቅት የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል እና በመላው አገሪቱ ሕግ የማስከበር ግዴታ እንዳለበት መጥቀሳቸውንና ይህን ማድረግ የሚሳነው ከሆነ ብዙ ኪሳራ ሊያደርስ እንደሚችል ማስረዳታቸውን የወጣው መግለጫ አመልክቷል። በተጨማሪም መንግሥት በትግራይ ክልል ውስጥ እየወሰደ ባለው እርምጃ ለሰላማዊ ዜጎች ጥንቃቄ እንደሚደረግ፣ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ መንግሥት የደርሻውን እንደሚወጣ እና ግጭቱን በመሸሽ ቀያቸውን ጥለው የተሰደዱ ዜጎችን በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለማስፈር እና ወደፊት ወደ ቀያቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ገልፈዋል። ቀደም ሲል ልዑኩ ጉዳት እያደረሰ ያለው ግጭት ቆሞ ውይይት የሚጀመርበትን መንገድ ይፈልጋል ተብሎ የተነገረ ቢሆንም ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም። የትግራይ ክልልና የህወሓት አመራሮች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት እንዲሁም አገራት ግጭቱ እንዲቆምና ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን፤ መንግሥትም ይህንኑ እንዲቀበል ከተለያዩ ወገኖች ግፊት ሲደረግበት መቆየቱ ይታወሳል። ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሕግን ማስከበበር ስለሆነ ከህወሓት አመራሮች ጋር ምንም አይነት ድርድር ለማድረግ ፍላጎት እንደሌለ ገልጸዋል። ልዑካኑ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ እንደተገለጸ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመንግሥት ስለጉዳዩ በተሰጠ መግለጫ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ የሚልኳቸውን ልዩ መልዕክተኞች በግል ተቀብለው ከማነጋገር ውጪ ድርድር እንደማይኖር አመልክቶ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከልዑካኑ ጋር ባደረጉት ውይይት የትግራይ ክልል ሕዝብ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኝ ሕገ-መንግሥታዊ የሆነ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮችን ለማቋቋም ጥረቶች እየተካሄዱ መሆኑንና በወንጀል የሚፈለጉ የህወሓት ኃይሎችን ለሕግ ለማቅብ አስተዳደራቸው ቁርጠኛ መሆኑን ከጽህፈት ቤታቸው የወጣው መግለጫ አመልክቷል። በመንግሥት ላይ የሚደረገውን ግፊት በተመለከተ በዚህ ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሰጡት ምላሽ መንግሥታቸው እየወሰደ ያለው እርምጃ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ ማሳሰባቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት መንግሥት ተፈጸሙ ላላቸው ወንጀሎች ተጠያቂ የሆኑ የህወሓት አመራሮችን ለፍርድ ለማቅረብ ጥረት እያደረገ በመሆኑ ለድርድር እንደማይቀመጥ አሳውቋል። በትግራይ በኩል ያሉ ባለስልጣናት ግን እራስን በራስ የማስተዳደር መብታችንን ተጠቅመን ምርጫ በማካሄዳችንና መብታችንን በማስከበራችን የፌደራል መንግሥቱ ዘመቻ ከፍቶብናል ሲሉ ይከሳሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ክልል አመራር ከአፍሪካ ኅብረትና ከሌሎች ዓለም አቀፍ አካላት ጋር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚደረገው ግጭት በአስቸኳይ በሚቆምበት ሁኔታ ላይ የሚወያይ ተወካይ መሰየሙን ገለጸ። በወጣው መግለጫ ላይ ያልተቋረጠ ሰብአዊ እርዳታ የሚቀርብበት መንገድ እንዲመቻችና ተፈጸሙ የተባሉ የትኞችም የጦር ወንጀሎች በገለልተኛ ወገን ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠይቋል። በትግራይ ክልል የተከሰተው ቀውስ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት የህወሓት ባለስልጣንት የአፍሪካ ሕብረትና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጣልቃ ገብተው እንዲያሸማግሏቸው ሲጠይቁ እንደነበር ይታወሳል። በትግራይ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ግጭት ተጠናክሮ መቀጠሉ የተነገረ ሲሆን፤ በመንግሥት በኩል የመጨረሻ የተባለውና ትናንት የተጀመረው ዘመቻ በክልሉ ዋና ከተማ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚካሄድ ተገልጿል። በትግራይ ክልል ከሦስት ሳምንታት በላይ ተቋርጦ ባለው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ምክንያት በአካባቢው እተካሄደ ስላለው ግጭት አስተማማኝ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል።
news-43619934
https://www.bbc.com/amharic/news-43619934
እስራኤል ስደተኞች የማስወጣት ዕቅዷን ሰረዘች
እስራኤል ስደተኞችን ከሃገሯ የማስወጣቱን መርሃ ግብር እንዳቋረጠች የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ቢሮ አስታወቀ።
ውሳኔው የተላለፈው ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በተደረገ ስምምነት መሆኑም ይፋ ሆኗል። 16 ሺህ ያህል ስደተኞች በጀርመን፣ጣልያንና ካናዳ እንደሚጠለሉ እንዲሁም 18 ሺህ ያህል ደግሞ በእስራኤል ቋሚ የነዋሪነት መታወቂያ እንደሚሰጣቸው ተነግሯል። የእስራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እሁድ ዕለት ሊፈፀም እቅድ ተይዞለት የነበረው አፍሪካውያን ስደተኞችን የማበራር መርሃ ግብር ለተወሰኑ ቀናት እንዲገታ ማድረጉ የሚታወስ ነው። ስደተኞቹን ይቀበላሉ ተብለው የታሰቡት ሃገራት ኡጋንዳና ሩዋንዳ ሲሆኑ ይህንን ሃሳብ የተቃውሙ በእስራኤል ያሉ የመብት ተሟጋቾች አለመስማማታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ሲገልፁ ቆይተዋል። አዲሱ ዕቅድ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ሥራ ላይ ይውላል። የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ መሥሪያ ቤት ይህን ስምምነት 'ታይቶ የማይታወቅ' በማለት ገልፆታል። በእስራኤል ከሚገኙ በርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች መካከል አብዛኛዎቹ የዜጎችን መብት በመጣስ በተባበሩት መንግሥታት የምትወቀሰው የኤርትራና በጦርነት ከተናወጠችው ሱዳን ዜጎች ናቸው። ስደተኞቹ በሃገራቸው ከነበረው አደጋ ህይወታቸውን ለማትረፍ እንደተሰደዱ ሲናገሩ የእስራኤል መንግሥት ግን አብዛኞቹ ጥገኝነት የጠየቁበት ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ነው በማለት ይከራከራል።
news-57068238
https://www.bbc.com/amharic/news-57068238
ኮሮናቫይረስ፡ በዩኬ እስከ 10ሺህ ተመልካቾች ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ሊፈቀድ ነው
እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ደጋፊዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በእግር ኳስና ሌሎች ሜዳዎች ተገኝተው የሚደግፉትን ቡድን ማበረታታት እንደሚችሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አስታወቁ።
በዚህም መሰረት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ቡድኖች የሚያድርጓቸው የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ላይ ደጋፊዎች ገብተው መመልከት ይችላሉ ማለት ነው። ''ወደ ስታዲየም የሚገቡትን ሰዎች ቁጥር ቀነስ አድርገን የስታዲየሞቻችንን በሮች መክፈት እንጀምራለን'' ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ምሽት ባስተላለፉት መልዕክት። ''ደጋፊዎቸ በስታዲየሞቻችን በጣም ተናፍቀው ነበር፤ ፕሪምየር ሊጉም ቢሆን ያለእነሱ ቀዝቀዝ ብሏል። የደጋፊዎች መመለስ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት መጨረሻ ያሳምረዋል'' ብለዋል። ካሳለፍነው ታህሳስ ወር ጀምሮ በአንዳንድ ስታዲየሞች እስከ 2 ሺህ የሚደርሱ ደጋፊዎች ገብተው እንዲመለከቱ ተፈቅዶ የነበረ ሲሆን በአገሪቱ የተቀሰቀሰውን አዲስ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ ተመልሶ ተቋርጧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ 10 ሺህ ተመልካቾች ተገኝተው ጨዋታዎችን መመልከት ይችላሉ ከማለታቸው በፊት በካራባዎ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ እና ቶተንሃም ያደረጉት ጨዋታ ላይ ለሙከራ ተብሎ 2 ሺህ ተመልካቾች ገብተው እንዲመለከቱ ተደርጎ ነበር። በአዲሱ መመሪያ መሰረት በትልልቅ ስታዲየሞች እስከ 10 ሺህ ተመልካቾች አልያም ስታዲየሙ መያዝ ከሚችለው 25 በመቶ የተፈቀደ ሲሆን በአነስተኛ ስታዲየሞች ደግሞ 50 በመቶ ወይም እስከ 4 ሺህ የሚደርሱ ተመልካቾች ገብተው እንዲታደሙ ተብሏል። የቤት ውስጥ ሜዳዎች ደግሞ እስከ 1 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን ወይም መያዝ ከሚችሉት 50 በመቶውን ብቻ አገልግሎት ላይ እንዲያውሉ ተወስኗል። ባለፈው ዓመት የኮሮናቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ከመጋቢት ወር ጀምሮ እንግሊዝ ውስጥ የሚካሄዱ አብዛኞቹ የእግር ኳስ ውድድሮች በዝግ ስታዲየሞች ሲካሄዱ ቆይተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከሰኔ ወር አጋማሽ ጀምሮ በስታዲየሞች ገብተው የሚመለከቱ ደጋፊዎችን ቁጥር እስከ 21 ሺህ ድረስ ከፍ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን በዛውም አብዛኛዎቹ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንደሚነሱ ይጠበቃል። በያዝነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ደግሞ የሙከራ ስራዎቹ ቀጥለው በኤፍኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ቼልሲ እና ሌስተር ሲቲተ ሲገናኙ እስከ 21 ሺ የሚደርሱ ደጋፊዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል።
news-50501071
https://www.bbc.com/amharic/news-50501071
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦሮሚያ የመንግሥት ኃላፊ በታጣቂዎች ተገደሉ
በምዕራብ ወለጋ ዞን አንድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣን መንገድ ላይ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ተገደሉ።
አቶ ቶላ ገዳ ጥቃቱ በተፈጸመበት ስፍራ ሕይወታቸው ማለፉ ተነግሯል ትናንት [ረቡዕ] በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ውስጥ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ቶላ ገዳ ለሥራ ጉዳይ ወደ ምዕራብ ወለጋ ቄለም ወለጋ ዞን እየሄዱ ባሉበት ወቅት፣ ላሎ አሳቢ ተብሎ በሚታወቀው ወረዳ ውስጥ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን ቢቢሲ አረጋግጧል። የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኤሊያስ ኡመታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ይህ ግድያ የተፈጸመው ላሎ አሳቢ ወረዳ ውስጥ ጋራ ቶሬ በሚባል ቦታ ላይ ረቡዕ ዕለት ጠዋት አምስት ሰዓት አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል። • የደምቢ ዶሎ ከንቲባ በጥይት ተመትተው ቆሰሉ • ኢትዮጵያዊያን፣ ጃፓናዊትና ህንዳዊ በታጣቂዎች ተገደሉ አስተዳዳሪው ጨምረው እንደተናገሩት አቶ ቶላን የገደሉት ታጣቂዎች እየተጓዙበት በነበረው መኪና ላይ ከግራና ከቀኝ ሆነው በከፈቱት ተኩስ በመኪናው ውስጥ እየተጓዙ የነበሩ መንገደኞችን ኢላማ አድርገው እንደሆነ አመልክተዋል። በታጣቂዎቹ ጥቃት የተገደሉት አቶ ቶላ ገዳ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር የመንገዶች ባለስልጣን ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ እንደሆኑ አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልጸዋል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ከአቶ ቶላ ጋር ለሥራ ጉዳይ ሌሎች ሰዎች በመኪናው ውስጥ የነበሩ ሲሆን ከእነርሱም መካከል፤ በመኪናው ውስጥ የቄለም ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ከጸጥታና አስተዳደር ጽህፈት ቤትም ሌሎች ሰዎች አብረዋቸው ነበሩ። በተጨማሪም የጸጥታ አካላትም በመኪናው ውስጥ ከተጓዦቹ ጋር የነበሩ ሲሆን ጥቃቱ በተፈጸመበት ቅጽበት ፈጻሚዎቹን ለመያዝ ለመከተል ሙከራ ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው እንደቀረም ተነግሯል። • በምሥራቅ ወለጋ ሁለት ሰዎች ተገደሉ • ከተገደሉት አንዱ የማዕድን ኩባንያው ባለቤት ነበር ጥቃቱ በተፈጸመበት ጊዜ የአቶ ቶላን ሕይወት ለህልፈት የዳረገው ጥይት በመኪናው የፊት መስታወት በኩል የተተኮሰ ሲሆን፤ አቶ ቶላ በጥይት እንደተመቱ ጥቃቱ በተፈጸመበት ስፍራ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉን አስተዳዳሪው ገጸዋል። በተሽከርካሪው ላይ በታጣቂዎች በተከፈተው ተኩስ ከአቶ ቶላ ውጪ አብረዋቸው ይጓዙ በነበሩት ሰዎች ላይ ግን ምንም ጉዳት ሳይርስባቸው ሊተርፉ ችለዋል ተብሏል። አቶ ቶላ ገዳ በጥቃቱ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ አስከሬናቸውም በአቅራቢያው ወደሚገኘው የአይራ ሆስፒታል እንደተላከና በኋላም ወደ ቤተሰቦቻቸው መሸኘቱን አስተዳዳሪው አቶ ኤሊያስ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ይህ ጥቃት በማን እንደተፈጸመ በአሁኑ ወቅት የታወቀ ነገር እንደሌለ የተነገረ ሲሆን ሲሆን በአካባቢው ያሉ የጸጥታ አካላት በክስተቱ ፈጻሚዎች ዙሪያ ክትትልና ምርመራ እያደረጉ ስለሆነ ከምርመራው የሚገኘው ውጤት በወቅቱ ይፋ እንደሚደረግም ተናግረዋል። • በምዕራብ ኦሮሚያ የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ ግድያ የነዋሪውን ስጋት አባብሷል • በምዕራብ ወለጋ መንዲ በመከላከያ ካምፕ ላይ የተወረወረ ቦምብ አንድ ሰው ገደለ በአቶ ቶላና በባልደረቦቻቸው መኪና ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ስፍራ ላይ የሰዎች ሕይወት አይጥፋ እንጂ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ድርጊት የተፈጸመበት መሆኑንም አቶ ኤሊያስ ጠቅሰዋል። በቅርብ ጊዜያት ውስጥ በምዕራብ ወለጋና በቄለም ወለጋ ዞኖች ውስጥ የመንግሥት ባለስልጣናትን ኢላማ ያደረጉ ግድያና ጥቃቶች በተደጋጋሚ ሲፈጸም የቆየ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሰራተኞችና በተለያዩ የግል ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከተለያዩ አካላት የተዋቀረ ኮማንድ ፖስት የአካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበቅ ጥረት እያደረገ ሲሆን ነዋሪዎችም በተደጋጋሚ ስላለው የጸጥታ ስጋትና ችግር ቅሬታ ሲያርቡ ቆይተዋል። አንዳንድ ወገኖች በአካባቢው ለሚፈጸመው ጥቃት ከኦነግ ተለይቶ የወጣውና ኦነግ ሸኔ ተብሎ የሚጠራውን ቡድን ተጠያቂ ያደርጋሉ።
news-44716234
https://www.bbc.com/amharic/news-44716234
ለተመራቂ ተማሪዎች አምስት ጠቃሚ ነጥቦች
ተመራቂዎች እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ የሚለው ህብረ ዝማሬ ሲሰማ በትምህርት አለም ለቆየ የሚፈጥረው ስሜት አለ።
የጅማ ዩኒቨርስቲ የ2010 ተመራቂዎች ለአንዳንዱ ስሜቱ ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ፀጉር ድረስ የሚነዝር ነው። ለአንዳንዱ ወደ ኋላ የሚመልስ። ለበርካቶች ደግሞ የተማሪነት ህይወት የሚያበቃበት ደወል ነው። እንዲህም ተባለ እንዲያ የምርቃት ቀን ልዩ ናት። የበርካታ ዓመታት ጥረት ዕውቅና የሚሰጥበት ዕለት! ከዚህም በላይ ደግሞ ተመራቂ ተማሪዎች ወደሌላኛው የህይወት ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት ቀን ነው። ማንም የማይክደው ሀቅ ደግሞ ለስራ ዝግጁ የመሆን የመጀመሪያው ደወል ነው። በያዝነው እና በቀጣዩ ወር በሺዎች የሚቆጠሩት ተማሪዎች ይመረቃሉ። በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በርካቶች ተመርቀው ስራ ማግኘት ቀላል አልሆነላቸውም። ለሊሴ ብርሃኑ ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ትመረቃለች። "ወደ ሥራው ዓለም ለመቀላቀል በዩኒቨርሲቲ ቆይታችን ወቅት ያስመዘገብነው ውጤት በሥራው ዓለም ስኬታም እንድንሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል''ትላለች። በህንድ አገር የፑጃብ የኒቨርሲቲ የዶክትሬት ተማሪ እና በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የማሕበራዊ ስነ-አዕምሮ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ዋቅቶላ ደምሰው አዲስ ተመራቂ ተማሪዎች የሚገጥማቸውን ፈተና እንዴት መወጣት እንዳለባቸው ያስረዳሉ። አቶ ዋቅቶላ እንደሚሉት ከሆነ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች በሚኖሩባት አገር ለአዲስ ተመራቂዎች ስራ በቀላሉ ያገኛሉ ማለት ይከብዳል። ነገር ግን ቀጣዩቹ 5 ነጥቦች ወሳኝ ናቸው። የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ ማደራጀት የአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች የመጀመሪያው የቤት ሥራ የሚሆነው የትምህርት እና ክህሎት እንዲሁም የሥራ ልምድ ካላቸው በተሟላ መልኩ በሲቪያቸው ላይ መጥቀስ ነው። ለሥራ ቅጥር ለጽሑፍም ይሁን ለቃለ መጠይቅ ፈተና ከመቅረባቸው በፊት የትምህርት እና የሥራ ማስረጃቸው አይቀሬ ነው። ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት መንግሥት ተመራቂዎችን በሙሉ ሊቀጥር የሚችል አቅም የለውም። ወይም የተመኘነውን የሥራ ዓይነት ማግኘት ቀላል አይሆንም። ስለዚህም ያለውን ውስን እድል ለመጠቀም ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል። አቶ ዋቅቶላ ሲያስረዱ የቅጥር ማመልከቻ ከማቅረባችን በፊት ሥራው ምን አይነት ክህሎቶችን ይፈልጋል ብለን መጠየቅ አለብን። መረጃ የሥራ ቅጥር መረጃዎችን፣ ስለ ቀጣሪው ማንነት እና የምታመለክቱበት ስራው ስለሚፈልገው እውቀት እና ክህሎት በቂ መረጃ ይኑራችሁ። ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ተለይቶ መገኘት ከትምህርት ማስረጃችን በተጨማሪ ያመለከትንበት የሥራ ዘርፍ፣ ቀጣሪው ድርጅት የሚፈልገውን ክህሎት ማወቅ እና ይህንንም ለቀጣሪው ድርጅት በማሳየት የቅጥር እድላችንን ማስፋት እንችላለን። የአዕምሮ ዝግጅት ማድረግ በተማሪነት ዘመናችን ያሰብናቸውን እና ያለምነውን ማሳካት ላይሆንልን ይችላል። ለዚህም የአዕምሮ ዝግጅት ማድረግ ጠቃሚ ነው።
news-56973471
https://www.bbc.com/amharic/news-56973471
አምነስቲ፡ "የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የተቀዛቀዘ ምላሽ ለትግራይ ግጭት አስተዋፅዖ አድርጓል"
የአፍሪካና የተቀረው ዓለም መሪዎች በትግራይ ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድምፃቸውን የበለጠ እንዲያሰሙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ድርጅት ጥሪ አቀረበ።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተሟጋች ቡድን ባወጣው መግለጫ ለስድስት ወራት በዘለቀው የትግራይ ጦርነት በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተካሂደዋል ብሏል። ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፤ መቶ ሺዎች ክልል ውስጥ ተፈናቅለዋል፤ እንዲሁም 63 ሺህ ሰዎች ወደ ሱዳን ተሰድደዋል ብሏል ድርጅቱ። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎች ተቋማት እስከ የጦር እና ሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀልን ጨምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅመዋል ይላል የድርጅቱ መግለጫ። መግለጫው አክሎም የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች በጋራ መድፈርን ጨምሮ ታዳጊና አዋቂ ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደፈፀሙ ማስረጃዎች አሉ ይላል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በትግራዩ ግጭት ተፈጽመዋል የተባሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተመርምረው ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ የሠራዊቱ አባላት ለሕግ ይቀርባሉ ብለው ነበር። ከዚህ በተጨማሪም፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከአፍሪካ ሕብረት ሰብዓዊ አጥኒ ኮሚሽን ጋር የተፈጸሙ የመብት ጥሰተኞችን በጋራ እንደሚመረምሩ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። በሌላ በኩል ከመብት ጥሰቶቹ ጋር ተያይዞ ሰሙ በተደጋጋሚ ለሚነሳው የኤርትራ ጦር በተመለከተ አገሪቱ መንግሥት ከሶቹ መሠረተ ቢስ ናቸው ሲል አጣጥሎ ነበር። "ስድስት ወራት ባስቆጠረው የትግራይ ግጭት የሰብዓዊ መብትና የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ሕግጋት ጥሰቶች እንዳሉ የሚያሳዩ ማስረጃዎች እጥረት ባይኖርም ከአፍሪካ ሕብረትና ከተባበሩት መንግሥታት በቂ ምላሽ አልተሰጠም" ይላሉ የአምነስቲ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ኃላፊ ዴፕሮስ ሙቼና። "የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ከወራት በኋላ በትግራይ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰበው ገልጿል። የአፍሪካ ሕብረትና የቀጣናው ሃገራት ግን በተነፃፃሪ ዝምታን መርጠዋል" ይላሉ ኃላፊው። በሁሉም ወገን የተፈፀመ ጥሰት የኢትዮጵያ መንግሥት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወደ ትግራይ ለመግባት የጠየቀውን ፈቃድ ችላ በማለቱ አሁን ባለው አስቸጋሪ የግንኙነት መስመር ተፈፀሙ የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ማጣራት ከባድ ነው ይላል የድርጅቱ መግለጫ። ነገር ግን አምነስቲ፤ 'ኦፕን ሶርስ' የተሰኘ የምርመራ መንገድ እንዲሁም የሳተላይት ምስሎች ትንተና እና የቪድዮ ምስሎች ማስረጃዎችን በመጠቀም የተለያዩ ጥሰቶችን እንደመዘገበ በመግለጫው አሳውቋል። አልፎም ድርጅቱ ከጥቃት የተረፉ ሰዎችን እንዲሁም በምስራቅ ሱዳን ያሉ ስደተኞችን በቴሌፎንና በአካል በማናገር መረጃ እንደሰበሰበ በመግለጫው አትቷል። አምነስቲ መዝቤያቸዋለሁ ካላቸው ጥሰቶች መካከል በማይ ካድራ ከሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው በተባሉ ኃይሎች የተፈፀመው ጅምላ ግድያ እንደሚገኝበት አሳውቋል። ይህን ተከትሎ የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የማይ ካድራ ነዋሪዎች ላይ የአፀፋ ጥቃት፣ ሕግን ከለላ ያደረገ ግድያ፣ ዘረፋና ጅምላ እሥር እንደተፈፀመ መመዝገቡን ይገልፃል። አምነስቲ አክሎ በአክሱም ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውንና ይህም ሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ተደርጎ ሊቆጠር እንደሚችል እንዲሁም በአድዋ ከተማ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን በመግለጫው አትቷል። አምነስቲ ከሲኤንኤን ጋር ተባብሬ አረጋገጥኩት ባለው ወንጀል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በማሕበረ ደጎ ከተማ ሕግን ከለላ አድርገው በፈረንጆቹ ጥር 15/2021 ግድያ ፈፅመዋል ብሏል በመግለጫው። ወደ ትግራይ እንዲገቡ በየካቲት ወር ፈቃድ የተሰጣቸው መገናኛ ብዙሃን በአምነስቲና ሌሎች ድርጅቶች ተፈፅመዋል ተብለው የተጠቀሱትን ጥሰቶች እንዳረጋገጡና አስከፊ ጥሰቶችን እንዳጋለጡ ድርጅቱ ይገልፃል። በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት ወኪሎችና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በለቀቁት መግለጫ "እየጨመረ የመጣው በሕፃናትና አዋቂ ሴቶች ላይ የሚፈፀም ወሲባዊ ጥቃት" እንዳሳሰባቸው "ለዚህ ጥቃት የተሰጠው ምላሽ በቂ እንዳልሆነ" ገልፀዋል ይላል አምነስቲ። በሌላ በኩል የሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሆስፒታሎችና ሌሎች የጤና ተቋማት ጥቃት እንደደረሰባቸውና እንደተዘረፉ ዘግበዋል ይላል የመብት ተሟጋቹ አምነስቲ። "ዓለም እየተመለከተ በትግራይ ያሉ አዋቂና ታዳጊ ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት እየተጋረጠባቸው መሆኑ ትክክል አይደለም። ሰብዓዊ እርዳታ ሰጪዎችና ሆስፒታሎች አቅርቦታቸው በግጭቱ ምክንያት በመጎዳቱ የእርዳታ አቅም የላቸውም" ይላሉ ዴፕሮስ ሙቼና። የሰብዓዊ እርዳታ ክልከላና የረሃብ ስጋት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በተደጋጋሚ በትግራይ ግጭት ተሳታፊ የሆኑ አካላት ለእርዳታ ሰጪዎች መንገድ እንዲሰጡ መጠየቁን በመግለጫው ያትታል። በፈረንጆቹ ከሚያዚያ 27/2021 ጀምሮ የተባበሩት መንግሥታት መሻሻል እንዳለ ቢገልፅም "በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ አሁንም የተረጋጋ አለመሆኑና እርዳታ በጊዜው እንዲደርስ እንዳላስቻለ" ገልጿል ይላል አምነስቲ። በወርሃ መጋቢት ብቻ ድንበር አልባው የዶክተሮች ቡድን [ኤምኤስኤፍ] በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ የነበራቸው ተልዕኮ ሁለት ጊዜ መቋረጡን አምነስቲ ይናገራል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የሰብዓዊ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን እና ለበርካቶች ተደራሽ ለመሆኑን ከተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑን አስታውቆ ነበር። በመጀመሪያው አጋጣሚ ድንበር አልባው የዶክተሮች ቡድን ወታደሮች ሕግን ከለላ ያደረገ ግድያ ሲፈፀም ማየቱን፣ እንዲሁም ወታደሮች የቡድኑን መኪና አስቁመው ኢትዮጵያዊውን አሽከርካሪ እንደደበደቡና የግድያ ዛቻ እንዳደረሰቡት የአምነስቲ መግለጫ ያወሳል። በትግራይ በግብርና ምርት የሚተዳደሩ ቦታዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው እንዲሁም ሰብል ሆን ተብሎ እንዲወድም በመደረጉ የተባበሩት መንግሥታትና ሌሎች ድርጅቶች አስከፊ የምግብ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል ከማስጠንቀቁም በላይ ጉዳዩ ወደ ረሃብ የማምራት ስጋት እንዳለው አምነስቲ ፅፏል። አምነስቲ መግለጫውን ሲያገባድ እንደ አማራ፣ ቤኒንሻንጉል እንደ ኦሮሚያ ክልል ባሉ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ ነው ብሏል። በጭልጋ ወረዳ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በአማራ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ በቤኒንሻንጉል ክልል በመተከል ዞን ንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈፀሙ እንደተዘገበ፤ እንዲሁም በምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች የታጠቁ ሰዎች የአማራ ተወላጆችን እንደገደሉ እንዳፈናቀሉ አምነስቲ ጠቅሷል። "ዓለም አቀፍና ገለልተኛ መርማሪዎች በሁሉም ወገኖች ተፈፅመዋል የተባሉትን ጥሰቶች ማጣራት አለባቸው። ጥፋቱን ፈፅመው የተገኙ ሊጠየቁ ይገባል። ከፍርድ የሚድን እንደሌለ መልዕክት መላክ ያሻል" ይላሉ ሙቼና። "ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በትግራይ ክልል ስላለው ግጭት ያለው ምላሽ የተቀዛቀዘ ከሆነ አሁን ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል።" የአምነስቲን ሪፖርት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተያየት በዚህ ዘገባ ላይ ለማካተት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።