id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
50272641
https://www.bbc.com/amharic/50272641
'ሀሰተኛዋ' ጀርመናዊት ሀኪም ታሰረች
ጀርመን ውስጥ ለአራት ህመምተኞች ሞት ተጠያቂ ናት የተባለችው ሀሰተኛ የህክምና ባለሙያ በቁጥጥር ሥር ዋለች።
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ 2015 እስከ 2017 በማዕከላዊ ጀርመን ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ትሠራ የነበረው በሀሰተኛ ማስረጃ እንደሆነም ተገልጿል። የ48 ዓመቷ ሴት፤ የሰው ሕይወት በማጥፋት፣ ሰነድ በማጭበርበርና የኃላፊነት ቦታን ያላግባብ በመጠቀም ምርመራ እየተደረገባት እንደሆነ ታውቋል። • ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት የአይጥ እርዳታ ያስፈልገን ይሆን? • የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም • በሀሰተኛ መድሃኒት ሰዎች እየሞቱ ነው ትሠራበት በነበረው ሆስፒታል ውስጥ ከማደንዘዣ ጋር በተያያዘ ስሀትት ሳቢያ፤ አራት ሰዎች ሲሞቱ ስምንት ሰዎች ደግሞ የጤና እክል ገጥሟቸዋል። ማደንዘዣ እንዴት መጠቀም እንዳለባት ተገቢውን ትምህርት ሳትወስድ በሥራው በመሰማራቷ ጉዳቶቹ እንደደረሱም ተመልክቷል። በሆስፒታሉ ውስጥ ለነበሩ ታካሚዎች የተሳሳተ መድሀኒት በመስጠትም ተጠርጥራለች። ከወራት በፊት የጀርመን መገናኛ ብዙህን በዘገባቸው እንደገለጹት፤ አቃቤ ሕግ ሆስፒታሉ ውስጥ ሰዎች ስለመጎዳታቸው ማስረጃ የለም ብሎ ነበር። የኋላ ኋላ ግን ፖሊሶች ሆስፒታሉን ፈትሸው ሰነዶች ሰብስበዋል። ሆስፒታሉም ለምርመራው ሙሉ ትብብር እንደሚያደርግ አሳውቋል።
news-48861251
https://www.bbc.com/amharic/news-48861251
ከአሜሪካ የጥላቻ ንግግርን የሚያሠራጩ ኢትዮጵያዊያን እንዴት በህግ ይጠየቃሉ?
በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ ኢትዮጵያዊያንን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የዜጎች ምክር ቤት አስታውቋል።
ያነጋገርናቸው የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት አቶ አምሳሉ ፀጋዬ፤ ወንድም ወንድሙን በማጣላት፤ ብሔር ከብሔር በማጋጨት እንደ ሃገር ለመቀጠል ፈታኝ ሆኗል፤ ይህንን የሚያደርጉ ግለሰቦችን ለማስተማር ብዙ እየተሞከረ ቢሆንም ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለመጣ ምክር ቤቱ ግለሰቦቹን ወደ ህግ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ይናገራሉ። • ፌስቡክ የአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው? • "ሽብር ምንድን ነው ፣ አሸባሪ ማን ነው?" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እርሳቸው እንደሚሉት በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር በሌላ ማህበረሰብ በማሰራጨት፤ ሞትና መፈናቀልን ማስከተል በሕግ እንደሚያስቀጣ ይገልፃሉ።በዚህ ረገድ የሚጠቅሱት ፈርስት አመንድመንት የተሰኘው የአሜሪካ ህግን ነው። እሳቸው እንደሚሉት ምንም እንኳን በፈርስት አመንድመንት የመናገር ነፃነት የተጠበቀ ቢሆንም በዚሁ ህግ ላይ በመናገር ነፃነት የማይካተቱ ድርጊቶችም ተዘርዝረው ይገኛሉ። "ግድያ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ብሔርን ከብሔር (ማኅበረሰብን ከማኅበረሰብ) የሚያጋጭ ከሆነ፤ የጥላቻ ንግግሩ ያስከተለው የጉዳት መጠን ተለይቶ ግለሰቦቹን ተጠያቂ ለማድረግ ይቻላል" ይላሉ አቶ አምሳሉ። የሕግ ሂደቱን የሚከታተል የጠበቆች ቡድን ያለ ሲሆን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማስረጃዎችን በማቅረብ የጥላቻ ንግግርን የሚያሰራጩ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ እንደሚያደርጉም ያክላሉ። "አብዛኞቹ እዚህ የሚኖሩ ለአገር የሚያስቡ ናቸው፤ ነገርግን የመጡበትን ማህበረሰብ በመርሳት ያ - ማህበረሰብ ቢፈርስ ደንታ የሌላቸው ጥቂቶች አሉ " የሚሉት አቶ አምሳሉ በህጉ መሰረት ቅጣቱ ከእስር ወደ አገር ተጠርንፎ እስከመመለስ የሚደርስ እንደሆነ ይናገራሉ። በሕጉ መሠረት ጥላቻን መንዛት ፤ የግድያ ዛቻና ቅስቀሳ፣ የወሲብ ፊልም፤ ወንጀል ለመፍጠር መደራጀትን መሠረት ያደረገ ቅስቀሳን የሚያደርግ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ያስረግጣሉ። እርሳቸው እንደሚሉት እንቅስቃሴው አሜሪካን አገር ብቻ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ በሌሎች አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እየተነጋገሩ መሆናቸውንም ገልፀውልናል። ጉዳዩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ንግግር አድርገው ከሆነ ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ አምሳሉ" ምንም ምክክርም ሆነ ንግግር አላደረግንም" በማለት የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ብቻ እንቅስቃሴውን እንደጀመሩ ነግረውናል። ከምክር ቤቱ ጋር ግንኙነት ባይኖራቸውም በሚኖሩበት ሜኒሶታ ግዛት ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደ ጀመሩ የነገሩን ደግሞ የአንድ ጥብቅና ቢሮ ባልደረባ የሆኑት አቶ ነጋሳ ኦዱዱቤ ናቸው። እርሳቸውም ከአቶ አምሳሉ ጋር ተመሳሳይ ኃሳብ ነው ያላቸው፤ 'ፈርስት አመንድመትን' ጠቅሰው የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩን ከሕግ ፊት ማቅረብ እንደሚቻል ያረጋግጣሉ። • በሃሰተኛ ዜናዎች "የሞቱ" የኪነጥበብ ሰዎች • "ሽብር ምንድን ነው ፣ አሸባሪ ማን ነው?" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ "በአሜሪካ የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ለብዙ ዘመናት የተከበረ ነው፤ ይሁን እንጂ 'ፈርስት አሜንድመንት' ላይ የተወሰኑ ገደቦች አሉበት" ይላሉ። ከእነዚህም መካከል የሀሰት ንግግር፣ ስም ማጥፋት፣ ለወንጀል የሚያነሳሱ ንግግሮች፣ ወደ ኃይል ተግባር የሚያነሳሱና የሌላውን መብት የሚጥሱ ንግግሮች በሕጉ ተገድበው ይገኛሉ። ተፅዕኖው ኢትዯጵያ ውስጥ በሚታይ ድርጊት ግለሰቦችን አሜሪካ ላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚያዋጣ ክርክር ነው ወይ? ስንል የጠየቅናቸው አቶ ነጋሳ " የጁሪዝዲክሽን (የፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን) ጉዳይ አከራካሪ ነው። ነገር ግን ከሶ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ መከራከር ይቻላል፤ ውጤቱ ኢትዮጵያ ነው ብሎ መከላከል ይቻላል" ሲሉ ይህ በፍርድ ሂደት እንደሚታይ ይናገራሉ። ከዚህም ባሻገር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚኖረው ጥገኝነት ጠይቆ በመሆኑ ይህንን ከሚቆጣጠረው 'አሜሪካ ኢምግሬሽን ሰርቪስ' (ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ) በክስ ሂደቱ ሊካተት እንደሚችል ይናገራሉ። "እንደ ኢትዮጵያዊያን አገሪቷ ወደ ፍቅርና ሰላም እንድታመራ የሞራል ግዴታ አለብን" የሚሉት አቶ ነጋሳ ነገሩን ወደ ህግ ከመውሰድ ይልቅ የሚያዋጣው የኢትዮጵያ ደህንነት ግድ እንደሚለው ዜጋ መመካከር ነው ይላሉ።
news-49631348
https://www.bbc.com/amharic/news-49631348
''ከአባቴ ጋር በተቃራኒ ጎራ ተዋግቻለሁ'' ታጋይ ዓለምጸሃይ
ጊዜው ኢትዮጵያ ከዘውዳዊው ሥርዓት ወደ ወታደራዊው የደርግ መንግስት የተሸጋገርችበት ወቅት ነው።
ዓለምጸሃይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ትክክል ነው ባሉት የፖለቲካ መስመር የከተማ እና የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱበት ጊዜ። የአንድ ቤተሰብ አባላት በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ተሰልፈው እርስ በእርሳቸው የሚገዳደሉበት የታሪክ ምዕራፍም ነበር። • ሊገዳደሉ ከአንድ ጦር አውድማ የተገኙ ወንድማማቾች • ለ20 ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም አለምጸሃይ ካሳ ሃይሉ ትባላለች። በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ዕዳጋ ዓርቢ ተወልዳ እስከ ስምንተኛ ክፍል ተምራለች። ወደ ትግል ስትገባ የ14 ዓመት ልጅ እንደነበረች የምትናገረው አለምጸሃይ፤ በደርግ ስርዓት ይፈጸሙ የነበሩ ኢ-ፍትሀዊ ተግባራትና የህወሓት ታጋዮች ሰብዓዊ ባህሪ ገና በጨቅላ ዕድሜዬ ወደ ትግል እንድቀላቀል ምክንያት ሆኖኛል ትላለች። ወደ ትግል ከመግባትዋ በፊትም የህወሓት ህቡዕ የከተማ አደረጃጀት አባል ሆና ትሰራ እንደነበር የምታስታውሰው አለምጸሃይ "ደርግ በአድዋ አካባቢ ሰዎች መግደል በመጀመሩ ፈጥኜ ወደ ትግሉ እንድቀላቀል አድርጎኛል" ትላለች። ማይ ደጉዓለ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ወታደራዊ ስልጠና ወስዳ ወደ ሰራዊቱ ስትቀላቀል የ14 ዓመት ልጅ ብትሆንም "አካሌ ግዙፍ ስለነበር ጠመንጃ ታጥቄ ለመታገል ቀላል ነበር" በማለት ትውስታዋን አካፍላናለች። ለሁለት የተከፈለው ቤተሰብ የአለምጸሀይ ወላጅ አባትዋ አቶ ካሳ ሀይሉ ከአጼ ኃይለስላሴ ስርዓት ጀምሮ የወረዳ ጸሃፊ በመሆን ያገልግሉ ነበር። በትምህርቷም ጎበዝ እንድትሆን የላቀ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ታስታውሳለች። የአጼው ስርአት ወድቆ ወታደራዊው መንግስት ስልጣን ከተቆናተጠጠ በኋላ አቶ ካሳ የደርግ አባል ሆነው ከህወሓት ጋር በሚደረገው ፍልሚያ ይሳተፉ ነበር። በተቃራኒው የእሳቸው ባሌቤት "በህወሓት አይምጡብኝ'' ብለው የመጀመሪያ ልጃቸው አለምጸሃይ ከተሰለፈችበት ዓላማ ጎን በመቆም ደርግን ለመፋለም መርጠው ነበር። ከአለምጸሃይ በተጨማሪ የአቶ ካሳ አራት ልጆች የታላቅ እህታቸውን ፈለግ በመከተል የህወሓት ትግልን ተቀላቅለው አባታቸው የሚደግፉትን የደርግ ስርዓት ለመዋጋት ወስነው ነበር። በዚህ ምክንያት ቤተሰቡ ለሁለት ተከፍሎ እርስ በእራሱ እንዲዋጋ ግድ ሆነ። እናት፤ ልጆቿ በአንድ በኩል፣ ባለቤቷ ደግሞ በሌላ በኩል ሆነው በጦር አውድማዎች ላይ የመገናኘታቸው ነገር ህሊናቸውን እርፍት ይነሳው ነበር። ምናልባት ባለቤታቸው ሃሳባቸውን የሚቀይሩ ከሆነ ብለው ወይዘሮ ግደይ ተላ ወደ አቶ ካሳ የተማጽኖ ደብዳቤ ጻፉ። እንዲህ ይላል፤ "ምናልባት 'የመንግሥት ስራ ጥዬ ከወጣሁኝ የገቢ ምንጭ ላይኖረኝ ይችላል' ብለህ ተጨንቀህ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የምትታገልለት ዓላማ ጨቋኝ ከመሆኑ ባሻገር ከመጀመሪያ ልጃችን ጋር በጦር ሜዳ እንድትገናኙ ስለማልፈልግ እባክህን ሰራዊቱን ጥለህ አገርህ ግባ። ሌላው ቢቀር እኔ ሰርቼ አኖርሃለሁ።" የወ/ሮ ግዳይ ተማጽእኖ ሳይሳካ ቀረ። ወላጅ አባቷ ለደርግ ስርዓት ታማኝ ስለነበሩ በሃሳባቸው ሳይስማሙ መቅረታቸውን ዓለምጸሃይ ታስታውሳለች። ተስፋ ያልቆረጡት እናት በድጋሚ በልጃቸው አማካኝነት ሌላ ደብዳቤ እንዲጻፍለት ሃሳብ አቀረቡ። አለምጸሃይ [ከግራ ወደ ቀኝ ሁለተኛ] ከእያሱ በርሄ [ከግራ ወደ ቀኝ ሶስተኛ] ጋር በትጥቅ ትግል ወቅት። • ኢትዮጵያ እና ኤርትራ - ከሰኔ እስከ ሰኔ "በአባልነት የምታገለግለው ስርዓት የልጆችህን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኝ እና የጸረ-ዲሞክራሲ አራማጆች ስብስብ ነው። የእኔ ወላጅ አባት ሆነህ የዚህ ጨቋኝ ስርዓት ታሪክ ተጋሪ መሆን የለብህም። ልጄ ተሳስታለች ብለህ ብታስብ እንኳ አባት በልጁ አይጨክንምና ከእኔ በተቃራኒ ሆነህ መዋጋት የለብህም" የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ እንደላከችለት ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ አለምጸሃይ አጭውታናለች። ይሁን እና አቶ ካሳ ሀይሉ ደብዳቤው ቢደርሳቸውም የልጃቸውን ተማጽኖ እንደማይቀበሉ በጻፉት ደብዳቤ በመግለጽ ባለቤታቸውን ደግሞ 'ለምንድነው ልጅትዋን ወደ 'ወንበዴዎቹ' የላክሻት? አሁንም ሳይረፍድ መልሻት' የሚል መልዕክት እንዳስተላለፉ አለምጸሃይ ታስታውሳለች። አቶ ካሳ ሀይሉ ከልጆቻቸው ጋር በተለያዩ ጎራዎች እየተፋለሙ 1974 ዓ/ም ደረሰ። ልጆቻቸው አለምጸሀይ ካሳ፣ ተስፋይ ካሳ፣ ኃይለኪሮስ ካሳ፣ ጸጋይ ካሳ እና ጽገወይኒ ካሳ በወቅቱ የለየላቸው የህወሓት ታጋዮች ሆነው ነበር። • 360 ብር ለአንድ ሕጻን ምንም እንኳ አባት ከመጀመሪያ ልጃቸው አለምጸሃይ ጋር ብቻ በአንድ የጦር አውድማ ላይ ቢፋጠጡም፤ ከሁሉም ልጆቻቸው ጋር ግን በዓላማ ልዩነት ታግለዋል። አለምጸሃይ በተሳተፈችበት እና ዓዲ እምሩ በተባለው አከባቢ በተካሄደው ውጊያ አቶ ካሳ ጦርነቱ ካበቃ በኋላ የቆሰሉ የደርግ የሰራዊት አባላትን ይዘው ወደ ሽረ እንዳስላሰ እንዳፈገፈጉ አለምጻሃይ ትናገራለች። በ1974 ዓ.ም. ግን የደርግ ሰራዊት እና የህወሓት ታጋዮች በፈረስ ማይ አውድማ ሲዋጉ ውለው በስተመጨረሻ የአለምጸሀይ አባት፣ አቶ ካሳ ሀይሉ በጓዶችዋ አማካኝነት ተማረኩ። የህወሓት ታጋዮች በውግያው የታጋይ ልጆች አባት መሆናቸውን ተገንዝበው በስነ ስርአት እጅ እንዲሰጡ ቢማጸኗቸውም በሃሳቡ ስላልተስማሙ ከጉልበታቸው በታች መትተው እንደማረኳቸው አለምጸሃይ ታወሳለች። በመጨረሻ ግን በምርኮኝነት ከቆዩ በኋላ ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ህይወታቸው አልፏል። አቶ ካሳ ሀይሉ ወላጅ አባትሽ ተማርኮ ህይወቱ ማለፉን ስትሰሚ ምን ተሰማሽ? ለአለምጸሃይ ያቀረብንላት ጥያቄ ነበር። "በታሪክ ተጠያቂ ከሆነ ስርአት ጋር ወግኖ፤ እስከ መጨረሻ በተደረጉ ውግያዎች ተዋግቶ ህይወቱ ማለፉን ስሰማ ከልቤ ነው ያዘንኩት" የምትለው አለምጸሀይ "እኛ ቤተሰቦቹ እና ድርጅቴ ህወሓት ለማድረግ ያሰብነው ነገር ሳይሳካልን ቀርቶ መጨረሻው እንዲህ መሆኑ አሳዝኖኛል" በማለት በሁኔታው እጅግ ሀዘን እንደተሰማት ገልጻለች። ወላጅ አባትዋ በትምህርትዋ ጎበዝ እንድትሆን የነበራቸው አስተዋጽኦ በማስታወስ [እምባ እየተናነቃት] "በምንም መተከያ የሌለው ውድ አባቴን እኮ በጣም እወደዋለሁ፤ እሱ በህይወት ቢኖር ትግላችን ፍሬ አፍርቶ አዲስ ስርዓት አብረን እንድንገነባ ነበር ምኞቴ።" • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" • የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ ሁለቱ የአቶ ካሳ ልጆች ተስፋይ ካሳ እና ጽገወይኒ ካሳ በትጥቅ ትግሉ ወቅት በተለያዩ ጊዜዎች በተደረጉ ውግያዎች ህይታቸው አልፏል። የትግል ጓዶቿ እና የቅርብ አመራሮች ብዙ ግዜ "የነጭ ለባሽ ልጅ፣ ነጭ ለባሹ አባትሽን በእጅሽ ነው መማረክ ያለብሽ" ብለው ይቀልዱባት እንደነበር የምታስታውሰው አለምጸሀይ አባት በልጃቸው ተማርከው በትግሉ ግዜ ታሪክ ይሰራል ብለው ያስቡም እንደነበር ነግራናለች። "ይሁን እንጂ በእጄ ልማርከው ባይሳካልኝም ሁለታችንም ላመንበት ዓላማ ታግለን እኔ የታገልኩበት አላማ በማሸነፉ ሁሌም የምደሰትበት የህይወቴ ምዕራፍ ነው።" ታጋይ አለምጸሀይ ካሳ በአሁኑ ሰአት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ረዳት ኮምሽነር በመሆን እያገለገለች ሲሆን የሁለት ሴት ልጆች እናት ነች።
news-57326569
https://www.bbc.com/amharic/news-57326569
የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እና ኬንያ ጉዞ ጀመሩ
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፈሪ ፌልትማን በአራት አገራት የሚያደጉትን ጉብኝት መጀመራቸውን የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።
ፌልትማን ካለፈው ሰኞ ግንቦት 23 ጀምሮ እስከ መጪው ቅዳሜ ግንቦት 29 ድረስ በሚያደርጉት ጉዞ ኳታርን፣ ሳዑዲ አረቢያን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችን እና ኬንያን ይጎበኛሉ። የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ፌልትማን በዚህ ጉዟቸው በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስላሉ ጉዳዮችና እና በአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ይወያያሉ ተብሏል። የልዩ መልዕክተኛውን ጉዞ በተመለከተ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ላይ ፌልትማን ከየአገራቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ይገናኛሉ። የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በመግለጫው፤ ልዩ መልዕክተኛ ፌልትማን "ከአራቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው የአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋ እና የበለጸገ እንዲሆን መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ" ብሏል። ጨምሮም "በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በሁሉም አካላት ዘንድ ተቀባይነት ያለው ስምምነት እንዲደረስ" እንደሚመክሩ መግለጫው አትቷል። ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው መግለጫ ያወጡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ ልዩ መልዕክተኛቸው በዚህ ሳምንት ወደ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ተመልሰው እንደሚያቀኑ የገለጹ ቢሆንም፤ በዚህ ዙር ጉዟቸው ግን ዋነኛ ትኩረታቸው የመካከለኛውና የባሕረ ሰላጤው አገራት እንደሆነ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። ልዩ መልዕከተኛው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እና ኬንያ ለምን? የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ የሚጎበኟቸው አገራት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ጉዳዮች ውስጥ እየጎላ የመጣ ሚና ያላቸው ሲሆን አሜሪካ ጥረቷን እንዲያግዙ ከጎኖ እንዲሰለፉ ለማድረግ እንደሆነ ይገመታል። ኬንያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የምሥራቅ አፍሪካ ያላት ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነት እየጎላ መጥቷል። የጆ ባይደን አስተዳደር የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በቅርቡ ከኬንያ ጋር የጦር ልምምድ ለማድረግ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ጦር ወደ ኬንያ እንደሚልክ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። በባሕረ ሠላጤው ብሎም ከዚያ ባሻገር ተጽእኖዋ እየጎላ የመጣው ኳታር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያላት የደኅንነትና የዲፕሎማሲ ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። ቀደም ሲል ከሱዳንና ከኤርትራ ጋር የቀረበ ግንኙነትን ያዳበረችው ኳታር ከቀርብ ዓመታት ወዲህ ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ጋርም ግንኙነቷን አጠናክራላች። በዚህም በሱዳንንና በኤርትራ እንዲሁም በኤርትራና በጂቡቲ መካከል የነበሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ጥረት ማድረጓ ይታወሳል። ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በመካከለኛው ምሥራቅና በባሕረ ሰላጤው አካባቢ ሰፊ ተጽእኖ ያላቸው አገራት ሲሆኑ በአፍሪካ ቀንድም የማይናቅ ሚና እየተጫወቱ ነው። ሁለቱ አገራት ከኤርትራና ከኢትዮጵያ ጋር ወዳጅ ሲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ኤርትራና ኢትዮጵያ ለአስርት ዓመታት የዘለቀውን ጠላትነታቸውን እንዲያበቁ በማድረግ በኩል የጎላ ሚና እንዳላቸው ይታመናል። በተጨማሪም በኢኮኖሚና በደኅንነት በኩል ያላቸው ግንኙነት ቀላል የሚባል አይደለም። የፌልትማን የከዚህ ቀደሙ ጉብኝት ከጥቂት ወራት በፊት በፕሬዝደንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ፌልትማን ከሳምንታት በፊት ግብጽን ጨምሮ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ አገራት ጉዞ ማድረጋቸው ይታወሳል። ፌልትማን በመጀመሪያው ጉዟቸው ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 5 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ወደ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ተጉዘው ነበር። በዚህም በትግራይ ያለው ግጭት እንዲሁም በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ለዓመታት በዘለቀው አለመግባባት ዙሪያ ግፊት ለማድረግ የፈለጉት በአገራቱ ወዳጆች በኩል እንደሆነ የጉዟቸው አቅጣጫ ያመለክታል። ጉዟቸውን በግብጽ ጀመረው የነበሩት ፌልትማን፤ በካይሮ ቆይታቸው ከግብጽ ፕሬዝደንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር ተገናኝተው ነበር። በውይይታቸው ወቅት አል-ሲሲ ግብጽ ከአባይ ውሃ የምታገኘው ድርሻ መቀነስን አትታገስም በማለት ስለመናገራቸው ዋሽግተን ፖስት ዘግቦ ነበር። አምባሳደር ፌልትማን በበኩላቸው የጆ ባይደን አስተዳደር በቀጠናው ላሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት ትኩረት ያደርጋል ሰለማለታቸው ዋሽንግተን ፖስት ምንጮቹን ጠቅሶ ጨምሮ ዘግቧል። ፌልትማን ወደ አሥመራ በተጓዙ ወቅትም ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ረዘም ላለ ሰዓት መወያየታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀው ነበር። አራት ሰዓት በቆየው ውይይት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ኤርትራ ከአሜሪካ ጋር አብራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል ሲሉ የማስታወቂያ ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ፌልትማን ማን ናቸው? ጄፍሪ ፌልትማን በሹመታቸው ወቅት በተለይ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ስላሉ ሁኔታዎች የተለየ ትኩረት እንደሚሰጡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አስታውቆ ነበር። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ዋና ጸሐፊዎች ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅትም በልዩ መልዕክተኝነት አገልግለዋል፤ በተጨማሪም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ፌልትማን በሊባኖስ፣ በኢራቅ፣ በእስራኤል፣ በቱኒዚያ፣ በሃንጋሪና በሄይቲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል።
50443850
https://www.bbc.com/amharic/50443850
የ31 ዓመቱ ኢሕአዴግ ማን ነው?
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እንደ ጥምር ግንባር የተመሰረተው ከ31 ዓመታት በፊት ግንቦት 1981 ዓ. ም. በትግራይ ክልል በተምቤን ዓዲ ገዛእቲ በሚባል አካባቢ ነበር።
ወደ ስድስት ሚለየን ገደማ አባላት እንዳሉት የሚነገርለት ገዢው ፓርቲ፤ ከግራ ዘመም ፓለቲካዊ መርህ በሚመነጨው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሲመራ ቆይቷል። ዋና መስራቹ ፓርቲ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የደርግ ሥርዓትን በመቃወም የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ. ም. ወደ ትጥቅ ትግል ከገባ ዘንድሮ 44ኛ ዓመቱን ይዟል። የቀድሞው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የአሁኑ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ)፣ የቀድሞው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የአሁኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የደቡብ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደሕዴን) ብሄራዊ ድርጅቶች ግንባሩን ተቀላቅለዋል። ደርግ ከሥልጣን ከተወገደበት ጊዜ አንስቶ የፓርቲው የረዥም ጊዜ ሊቀ መንበር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ከሰባት ዓመት በፊት ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ አገሪቷንም በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋል። ከሰባት ዓመት በፊት አቶ መለስ ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ ምክትላቸው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ነበር ሥልጣኑን የተረከቡት። በዋነኛነት በኦሮሚያ ተነስቶ በመላው አገሪቱ የተቀጣጠለውን ተቃውሞ ተከትሎ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በፍቃዳቸው ሥልጣናቸውን በመልቀቃቸው መንበሩን ዐብይ አሕመድ ተረክበዋል። ሥልጣን ለዓመታት አውራ ፓርቲ ከነበረው ሕወሓት ወደ ኦዴፓ መሸጋገሩ በወቅቱ ተገልጾ እንደነበር ይታወሳል። • ኢህአዴግ እዋሃዳለሁ ሲል የምሩን ነው? • "ለውጡን ለማደናቀፍ ከተቻለም ለመቀልበስ የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ" የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው ኢሕአዴግ፤ በየሁለት ዓመቱ ከእያንዳንዱ አባል ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴው መካከል በሚመረጡ 36 የሥራ አስፈጻሚ አባላት ይመራል። ሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ)፣ የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (አብዴፓ)፣ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን)፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶህዴፓ) የአሁኑ ሶማሊ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ሶዴፓ) እና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉሕዴፓ) አምስቱ የኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎች ናቸው። ኢሕአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኃላ ከግንቦት 24-28 ቀን 1983 ዓ. ም. በተካሄደው የልዩ ልዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጉባኤ የሸግግር መንግሥት ተመስርቶ፤ በሽግግር ወቅቱ እንደ ሕገ መንግሥት የሚያገለግል ቻርተር ጸድቋል። በቻርተሩ መሠረት 86 አባላት ያሉት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የተሳተፉበት የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት ተመስርቷል። የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 11/1984 ዓ. ም. በሽግግር ወቅቱ ምክር ቤት ተዘጋጅቶ በየካቲት ወር 1984 ዓ. ም. የአከባቢና ክልላዊ ጊዜያዊ አስተዳደር አካላት ምርጫ ተደርጓል። የመጀመሪያው አገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 1987 ዓ. ም. የተካሄደ ሲሆን፤ ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በያዝነው ዓመት ግንቦት ወር ላይ እንደሚካሄድም ተገልጿል። በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ በጉልህ ከሚታወሱት ዋነኛው የ1997 ዓ. ም. ምርጫ ነው። ከ90 በመቶ በላይ ድምፅ እንዳገኘ በመግለጽ ከአንዱ የሥልጣን ዘመን ወደ ሌላው የሚሸጋገረው ኢሕአዴግ፤ በተለይ ከቅንጅት ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ ፉክክር የገጠመው በዚሁ ምርጫ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን ኢሕአዴግ ከ90 በላይ ድምፅ ማግኘቱን ዳግመኛ በመግለጽ በመንበሩ ቆይቷል። ቀደም ሲል የመወሀድ አጀንዳ ተደጋግሞ በግንባሩ ጉባኤዎች ሲነሳ ቆይቷል። • ዶ/ር ዐብይ በግላቸው ለውጥ ያመጣሉ? • ኢህአዴግን ያጣበቀው ሙጫ እየለቀቀ ይሆን? ይሁን እንጂ ከዐብይ አሕመድ ወደ ሊቀ መንበርነት መምጣት ጋር ተያይዞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአባል ድርጅቶች መካከል ቅራኔና መከፋፈል ሲፈጠር ይሰተዋላል። ፓርቲው ከተመሰረተ ግዜ ጀምሮ ሲመራበት የቆየውና የአገሪቱ የልማታዊ መንግሥት ፖሊሲ ምንጭ እንደሆነ የሚነገርለት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ሊቀ መንበሩ ይህ ርዕዮተ ዓለም በ 'መደመር' ሃሳብ እንደሚቀየር አሳውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢሕአዴግ ተዋህዶ 'የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ'ን የመመስረት እቅድ እንዳለው መነገሩን ተከትሎ፤ ሕወሓት ከሕግም፣ ከተቀባይነትም አንጻር ሕገ ወጥ አካሄድ ሲል መንቀፉን ይታወሳል። በየዕለቱም በፓርቲውና በግንባሩ መካከል የታየው ልዩነት እየሰፋ መሄዱ ይስተዋላል። ሆኖም ከህወሓት ውጪ ያሉት ሦስቱ እህት ፓርቲዎች የውህደቱ አካል እንደሚሆኑ እየተነገረ ነው። የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ ምዕራፍ ስድስት፣ አንቀጽ 91 ላይ እንደተቀመጠው የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደት ለመፍጠር በፓርቲዎቹ የመተዳደርያ ደንብ መሰረት ውህደቱ በእያንዳንዱ የፓርቲው ጉባኤ መረጋገጥ እንዳለበት ይደነግጋል። • "ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች ኢሕአዴግ ከግንባርነት ወደ ውህድ ፓርቲነት የሚያደርገው ጉዞ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ቢነሳም እውን ሆኖ አልታየም። የብሔር ድርጅቶች ግንባር የሆነው ኢሕአዴግ እውን ይዋሀዳል? የሚል ጥያቄ እየተነሳ ሲሆን፤ በቅርቡ ግንባሩ ከሕወሓት ውጪ ሊዋሀድ ይችል ይሆናል የሚል ጭምጭምታ አስነስቷል። በተለይ በ1993 ዓ. ም በሕወሓት ውስጥ የተፈጠረው መከፋፈል ግንባሩም ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሮበት ነበር። አሁንም በግንባሩ ውስጥ የሚታየው መከፈፋልና አለመግባበት ወዴት ሊያመራው ይችላል? የሚል ጥያቄ እየፈጠረ ይገኛል።
news-51102379
https://www.bbc.com/amharic/news-51102379
ሁለት የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በአሶሳ መታሰራቸው ተገለፀ
ሁለት የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ጋዜጠኞች ለሥራ ባቀኑበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ለእስር መዳረጋቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ለእስር የተዳረጉት የአማርኛ ክፍል ባልደረቦች ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ እና የካሜራ ባለሙያው በኃይሉ ውቤ መሆናቸውን ኤጀንሲው ገልጿል። • የግዙፉ ግድብ ግንባታ፡ የኢትዮጵያና ግብፅ ቅራኔ • በቀጥታ ሥርጭት ደስታዋን መቆጣጠር ያልቻለችው ጋዜጠኛ ይቅርታ ጠየቀች ኤጀንሲው በአሶሳ ከተማ በሚካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት መድረክ ላይ ሽፋን እንዲሰጥ በቀረበለት ጥሪ መሠረት ሁለቱ ጋዜጠኞች ወደ ሥፍራው መላካቸውን የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሻለ በቀለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ጋዜጠኞቹ ቅዳሜ ዕለት ነው የሄዱት፤ እሁድና ትናንት ሲዘግቡ ውለው፤ ትናንት ጥር 4/2012 ዓ.ም ምሽት 3፡00 አካባቢ ካረፉበት ሆቴል ፖሊሶች መጥተው ወሰዷቸው" ሲሉ የተያዙበትን ሁኔታ አስረድተዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ባየታ በአሶሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በኩል የተያዙ ጋዜጠኞች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ የተያዙበትን ዝርዝር ምክንያት ግን እንደማያውቁ ገልጸዋል። የአሶሳ ከተማ አስተዳዳር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር እስማኤል አስፒክ በበኩላቸው "ጋዜጠኞቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ደብዳቤ ይዘው ስላልተገኙ ነው" ብለዋል። ዋና ኢንስፔክተር እስማኤል፤ ሁለቱ ጋዜጠኞች የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትን ለመዘገብ ከኤጀንሲው አዲስ አበባ ቅርንጫፍ መላካቸውን እንደነገሯቸው ጠቅሰው፤ ጋዜጠኞቹ ወደ አሶሳ ሲመጡ ደብዳቤ ባለመያዛቸው እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስለ ሁለቱ ጋዜጠኞች ወደ ክልሉ መምጣት የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ መታሰራቸውን ይናገራሉ። • የአውስትራሊያን ጭስ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እናየው ይሆን? ጋዜጠኞቹ መጡበት ወደተባለው የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ቢደውሉም ገና ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልፀዋል። በሌላ በኩል የኤጀንሲው ሥራ አስኪያጅ ስለ ጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ወደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንና ወደ ከተማው ፖሊስ በተደጋጋሚ ቢደውሉም ማብራሪያ ሊሰጣቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል። ጉዳዩንም ለክልሉ መንግሥት እንዳሳወቁና የክልሉ መንግሥት እየተከታተለው መሆኑን አክለዋል። ጋዜጠኞች በመሆናቸው ያለ ደብዳቤ በመታወቂያ መሥራትና በነፃነት መንቀሳቀስ አይችሉም ወይ? ያልናቸው ኢንስፔክተሩ፤ "አሠራሩ እንደዚያ ነው፤ አንድ የመንግሥት ሰራተኛ ወይም ለአንድ ሥራ ወደ አንድ ቦታ የተንቀሳቀሰ ሰው 'ለሥራ ጉዳይ ነው የመጣው' የሚል ደብዳቤ መያዝ አለበት ነው የሚለው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በጉዳዩ ላይ ከመገናኛ ብዙኃኑ ጋር ያደረጉት የመረጃ ልውውጥ ስለመኖሩ የተጠየቁት ዋና ኢንስቴክተሩ፤ ፖሊስ ኮሚሽን ከትግራይ ክልል መገናኛ ብዙሃን አዲስ አበባ ካለው ቅርንጫፍ ጋር በጉዳዩ ላይ በስልክ እየተነጋገረ መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-49943841
https://www.bbc.com/amharic/news-49943841
ተማሪዎች መገረፍ አለባቸው የሚሉት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት
የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የማደሪያ ክፍላቸውን በእሳት የለኮሱ ተማሪዎችን በልምጭ የገረፉ ከፍተኛ ባለስልጣንን አንቆለጳጰሱ።
አልበርት ቻላሚላ የተባሉት እኚህ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን፤ በሃገሪቱ ውስጥ ያለ የአንድ ግዛት ባለስልጣን ናቸው። ባለስልጣኑ ቆመው፣ ተማሪዎቹ በደረታቸው ተኝተው በልምጭ ጀርባቸው እስኪላጥ ሲገረፉ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ በስፋት ተሰራጭቷል። ከዚህ ቀደም ቻላሚላን ሌላ የታንዛኒያ ሚኒስትር ቅጣቶችን የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ብቻ እንዲፈፅሙ ያደርጋሉ ሲሉ ተችተዋቸው ነበር። • 10 ሚሊዮን ሕዝብ ይታደምበታል የተባለው ኢሬቻ በአዲስ አበባ • በኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የደረሱት ሥምምነት ምንድን ነው? • ኔታኒያሁ ከጠ/ሚ ዐብይ ጋር ስለኤርትራዊያን ስደተኞች መወያየታቸውን ተናገሩ ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ተማሪዎች መቆንጠጥ ሲከፋም መገረፍ አለባቸው በሚለው አቋማቸው የሚታወቁ ሲሆን ባስ ሲልም በዚህ ረገድ ያለው ሕግ ተለውጦ እያንዳንዱ መምህር የሚያጠፋ ተማሪን 'ልቡ እስኪጠፋ' እንዲገርፈው እንዲፈቀድ ሀሳብ አቅርበዋል። ፕሬዝዳንቱ አንድ ተማሪ መቼ መቀጣት አለበት የሚለው መመሪያ ለቀቅ ያለ እንዲሆን ይፈልጋሉ። በአሁኑ ወቅት የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እንኳ ቢሆኑ ተማሪዎችን መቅጣት አይፈቀድላቸውም። ተማሪዎችን የሚቀጡ እንኳ ከሆነ ጠንካራ ምክንያት ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን አራት ጊዜ ብቻ 'ሾጥ ሾጥ' ማድረግ ነው የተፈቀደው። ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ተማሪ መቅጣት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው ያሉትን ከሥራ ገበታቸው አባርረዋል። "ኮሚሽነር ቻላሚላን አነጋግሬዋለሁ፤ እናም ደግ አደረግህ በማለት ላደረገው ነገር ያለኝን አድናቆት ገልጨለታለሁ" ብለዋል። "እንደውም ልባቸው እስኪጠፋ ቢገርፋቸው ጥሩ ነበር። ይህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው የሚሉ ለተቃጠለው የተማሪዎች ማደሪያ መክፈል አለባቸው። እነዚህ ሕንፃዎች የተገነቡት በደሃ ወላጆች መዋጮ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
news-48673766
https://www.bbc.com/amharic/news-48673766
ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ?
ምንም እንኳ ባለፉት ዘመናት ክትባቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ቢታደጉም፤ በበርካታ ሃገራት ውስጥ ለክትባቶች ያለው አሉታዊ አመለካከት እየጨመረ መምጣቱን ባለሙያዎች ይናገራሉ። .
የዓለም ጤና ድርጅት ባለንበት የፈረንጆች ዓመት ውስጥ በምድራችን ለጤና ስጋት ናቸው ብሎ ከዘረዘራቸው 10 ነገሮች መካከል ለክትባት እየታየ ያለው ቸልተኝነት አንዱ ነው። ክትባት እንዴት ተገኘ? ክትባቶች ከመገኘታቸው በፊት ዓለም ለሰው ልጆች አደገኛ ቦታ ነበረች። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በየዓመቱ አሁን በክትባት በምንከላከላቸው በሽታዎች ሳቢያ ይረግፉ ነበር። በ10ኛው ክፍለ ዘመን ቻይናዊያን የመጀመሪያውን የክትባት አይነት አግኝተዋል። በዚህም ጤናማ ሰዎችን በሽታ አምጪ ለሆኑ ተዋህሲያን በማጋለጥ በሽታን የመከላከል አቅማቸው እንዲገነባ ያደርጉ ነበር። • ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ • የደምቢ ዶሎ ከንቲባ በጥይት ተመትተው ቆሰሉ ከስምንት ክፍለ ዘመኖች በኋላ ብሪታኒያዊው ዶክትር ኤድዋርድ ጀነር ወተት አላቢዎች ቀለል ባለው የላሞች ፈንጣጣ ቢያዙም በአደገኛው የላሞች ፈንጣጣ ፈጽሞ እንደማይያዙ ተገነዘበ። በወቅቱ ፈንጣጣ በከፍተኛ ደረጃ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ገዳይ በሽታ ሲሆን ከተያዙት ሰዎች መካከል 30 በመቶውን ለሞት ይዳርግ ነበር። በህይወት የተረፉት ላይም መታወር ወይም የማይሽር ጠባሳን ይጥላል። እ.ኤ.አ በ1796 ጀነር፣ በስምንት ዓመቱ ታዳጊ ጄምስ ፊሊፕስ ላይ አንድ ሙከራ አደረገ። ሃኪሙ በላሞች ኩፍኝ ከተጠቃ ሰው ቁስል ላይ መግል በመውሰድ በልጁ ላይ አደረገ፤ ከዚያም ታዳጊው የበሽታውን ምልክቶች ማሳየት ጀመረ። ታዳጊው ከበሽታው ከዳነ በኋላ የፈንጣጣ ተዋህሲያን ወደ ሰውነቱ እንዲገባ ቢደረግም በበሽታው ሳይያዝ ጤናማ ሆኖ ቆየ። ምክንያቱም የላሞቹ ፈንጣጣ የመከላከል አቅሙን እንዲያዳብር ስላደረገው ነው። በ1998 (እአአ) ዶክተሩ ያገኘው ውጤት ይፋ ሲደረግ 'ቫክሲን' የሚለው የእንግሊዝኛው የክትባት አቻ ቃል ከላቲኑ ላም ከሚለው 'ቫካ' ተወስዶ ይፋ ሆነ። ስኬቶቹ ምን ነበሩ? ክትባት ባለፉት ዘመናት የሰው ልጅን ሲያረግፉ የነበሩ በርካታ በሽታዎችን በመከላከል በኩል ከፍ ያለ አስተዋጽኦን አበርክቷል። በ1960ዎቹ የመጀመሪያው የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ከመተዋወቁ በፊት 2.6 ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው ምክንያት በየዓመቱ ይሞቱ ነበር። በአውሮፓውያኑ 2000 እና 2017 መካከል በነበሩት ዓመታት በዓለም ዙሪያ በኩፍኝ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ80 በመቶ ቀንሷል። ከጥቂት አስርታት በፊት በነበረው ጊዜ በፖሊዮ ምክንያት መራመድ አለመቻልና ሞት የሚሊዮኖች ተጨባጭ ስጋት የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን ፖሊዮ ከሞላ ጎደል ከዓለም ጠፍቷል። አንዳንዶች ለምን ክትባትን ይቃወማሉ? ዘመናዊ ክትባቶች ከተዋወቁበት ጊዜ አንስቶ ሰዎች በክትባቶች ላይ ጥርጣሬ ነበራቸው። ቀደም ሲል በርካቶች ክትባትን የማይፈልጉት ከሃይማኖታዊ አስተሳሰብ በመነሳት ነው፤ ምክንያታቸውም ክትባቶቹ ንጹህ አይደሉም ወይም ደግሞ የመምረጥ ነጻነታቸውን ስለሚጻረር እንደሆነ ይናገሩ ነበር። በ1800ዎቹ ታማሚዎችን ለብቻቻው ለይቶ ማስቀመጥን የመሰሉ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም አለብን የሚሉ ጸረ ክትባት ቡድኖች ብሪታኒያ እና አሜሪካ ውስጥ ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። በ1998 መቀመጫውን ለንደን ያደረገ አንድ ዶክተር ኩፍኝን፣ ጆሮ ደግፍንና ሩቢላን የሚከላከለውን አንድን ክትባት ከኦቲዝምና ከሌላ ህመም ጋር በሃሰት በማያያዝ አንድ ዘገባ ይፋ አድርጎ ነበር። በዚህም ሳቢያ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የሚከተቡ ህጻናት ቁጥር ቀነሰ። በ2004 (እአአ) ብቻ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ይህንን ክትባቱን የወሰዱ ህጻናት ቁጥር 100 ሺህ ብቻ ነበር። ይህም በሃገሪቱ የሚከሰተውን የኩፍኝ በሽታ ተከታታይ በነበሩት ዓመታት እንዲጨምር አድርጓል። የክትባት ጉዳይ ፖለቲካዊ ገጽታንም ይዞ ነበር። የጣሊያን የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ማቲዮ ሳልቪኒ ከጸረ ክትባት ቡደኖች ጋር ሕብረት ፈጥረው ነበር። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካለምንም ማስረጃ ኦቲዝምን ከክትባት ጋር አያይዘውት የነበረ ቢሆንም፤ በኋላ ላይ ግን ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር። ባንከተብ ምን ይከሰታል? ከአንድ ሃገር ህዝብ ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው ነዋሪ ክትባትን ካገኘ በሽታዎችን በመከላከል ለበሽታ ተጋላጭ የሆኑትንና ሊከተቡ የማይችሉትን ሰዎች ጭምር ከገዳይ በሽታዎች መከላከል ይቻላል። • ኢሳያስን ለመጣል ያለመው'#ይበቃል' የተሰኘው የኤርትራውያን እንቅስቃሴ • በሠርግ ዕለት ማታ በጉጉት የሚጠበቀው 'የደም ሸማ' በዚህ ዘዴ በሽታን ለመከላከል መከተብ ያለበት የሕዝብ ቁጥር እንደየበሽታዎቹ ይለያያል። ኩፍኝ ለመከላከል ከአጠቃላዩ ሕዝብ ከ90 በመቶው በላይ መከተብ ሲኖርበት ለፖሊዮ ደግሞ ከ80 በመቶው በላይ ክትባቱን ማግኘት አለበት። ባለፈው ዓመት አሜሪካ ብሩክሊን ውስጥ የሚገኙ አይሁዳዊያን ክትባት ከኦቲዝም ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚገልጽ ጽሑፍ አሰራጭተው ነበር። በዚህም ሳቢያ ይህ የማኅበረሰብ በአሜሪካ በአስርታት ውስጥ ካጋጠሙት የኩፍኝ ወረርሽኞች መካከል አንዱን አስተናግደዋል። የእንግሊዝ አንድ ታዋቂ ሃኪም እንዳስጠነቀቁት በርካታ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለክትባቶች በሚወጡ የተሳሳቱ መረጃዎች እየተታለሉ ነው ብለዋል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በዓለም ዙሪያ ህጻናት መውሰድ ያለባቸውን ክትባቶች የወሰዱ ቁጥር ብዙም ለውጥ ሳያሳይ 85 በመቶ ላይ ይገኛል። ድርጅቱ እንደሚለው ክትባቶች በየዓመቱ ከሁለት እስከ ሦስት ሚሊዮን የሚደርሱ ሞቶችን ያስቀራል። ባለንበት ዘመን የሚከተቡ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ ዋነኛ ምክንያት የሆኑት ግጭቶችና ዝቅተኛ የጤና አገልግሎት አቅርቦቶች ሲሆኑ፤ ከዚህ አንጻርም አፍጋኒስታን፣ አንጎላና ዲሞክራቲክ ኮንጎ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በአደጉት ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በሽታዎች የሚያስከትሉትን ከባድ ጉዳት ስለዘነጉ ለክትባት ቸልተኝነት እየታየ ነው።
news-51675463
https://www.bbc.com/amharic/news-51675463
ዓድዋ፡ የቅኝ ግዛት ዘመን ትርክትን የቀየረ ገድል
በካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በአጼ ምኒልክ በተመራው የኢትዮጵያ ሠራዊትና ባህር አቋርጦ ከአውሮፓ ከመጣው የጣሊያን ሠራዊት ጋር የተካሄደው የዓድዋው ጦርነት በታሪክ ውስጥ ከሚጠቀሱ ጉልህ ክስተቶች መካከል አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ አርበኞች የዓድዋ ድል ጣሊያን አፍረካ ውስጥ በተለይ ደግሞ በምሥራቁ የአህጉሪቱ አካባቢ ለማስፋፋት አቅዳ የተነሳችለትን የቅኝ ግዛት ዕቅድን ያጨናገፈ ከመሆኑ ባሻገር፤ በዘመኑ የአውሮፓዊያን ሠራዊት በአፍሪካዊያን ካበድ ሽንፈት ሲገጥመው የመጀመሪያ በመሆኑ ድንጋጤንም ፈጥሮ ነበር። ለዓደዋው ጦርነት ዋነኛ ምክንያት የሆነው በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግሥታት መካከል የተፈረመው የውጫሌ ውል ነበር። በዚህ ውል አንቀጽ 17 ላይ በጣሊያንኛ የሰፈረው ጽሑፍ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን ግንኙነት በጣሊያ በኩል መሆን እንዳለበት ሲያመለክት የአማርኛው ግን ግንኙነቱን በኢጣሊያ በኩል ማድረግ ትችላለች ይላል። ይህ የትርጉም ልዩነት እንደታወቀ መጀመሪያ ላይ አጼ ምኒልክ የውሉን አንቀጽ አስራ ሰባት እንደማይቀበሉ ካሳወቁ በኋላ ቀጥሎም የውጫሌውን ውል ሙሉውን ውድቅ አደረጉት። ይህም ጣሊያን ጦሯን በማዝመት ወረራ እንድትፈጽም ሊያደርጋት እንደሚችል የተረዱት ንጉሡ ዝግጅት ማድረግ ጀምረው ነበር። የተፈራው አልቀረም የጣሊያን ሠራዊት ለወረራ እንቅስቃሴ ጀመረ። ከኢትዮጵያ በኩል የንጉሡን ጥሪ ተከትሎ ከመላዋ አገሪቱ የተሰባሰበው ሠራዊት አገሩን ከጣሊየን ወረራ ለመከላከል ያለውን መሳሪያ ይዞ ወደ ሰሜን አቀና። በአጼ ምኒልክ የተመራው ሠራዊት እስከ ሃያ ሺህ የሚደርሱ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከአንድ መቶ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አርበኛ ወደ አድዋ ሲተም መነሻው ከአዲስ አበባ ነበር። ሠራዊቱ ዓድዋ ለመድረስ አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር አካባቢ በእግሩና በጋማ ከብት መጓዝ ነበረበት። ሠራዊቱ ዓድዋ ከደረሰ በኋላ ለፍልሚያ አመቺ ጊዜን ሲጠብቅ ቆይቶ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ከ17 ሺህ በላይ ወታደሮችን ካሰለፈው አውሮፓዊ ኃይል ጋር ጦርነት ገጠመ። ጦርነቱ በተጀመረ በግማሽ ቀን ውስጥ የኢትዮጵያ አርበኞች በሁሉም አቅጣጫ በጣሊያን ሠራዊት ላይ በሰነዘሩት ጥቃት ከባድ ጉዳት ስላደረሱበት በአንድ ላይ ተሰልፎ ኢትዮጵያዊያኑን ለመቋቋም ሳይችል ቀረ። በሺዎች የሚቆጠሩ የጣሊያን ሠራዊት አባላት ሲገደሉ ሌሎች ሺህዎች ደግሞ ተማርከዋል። በዚህም መድፎችን ጨምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያም ተማርኳል። በተጨማሪም የጣሊያንን ሠራዊት ከመሩት መኮንኖች መካከል ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ሸሽቶ አመለጠ። የጦርነቱ ውጤት የዓድዋ ጦርነት ድል ለጣሊያኖች ሽንፈት አስከትሎ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከማጽናት ባሻገር ከአድማስ ተሻግሮ አህጉራትን አቋርጦ የተሰማ ጉልህ ተጽዕኖን በዓለም ዙሪያ አስከትሏል። በዘመናዊው ዓለም የጸረ ቅኝ ግዛት ትግል ውስጥ የኢትዮጵያ ስም ተደጋግሞ ከሚነሳባቸው ክስተቶች መካከል አንዱ ለመሆን ከመብቃቱ ባሻገር በተለይ ደግሞ በጥቁሮች ዘንድ የዓድዋ ድል ለነጻነት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ መነቃቃትንና ተስፋን የሰጠ ክስተት ሆኗል። የዓድዋ ድልን ተከትሎ የታዩ ክስተቶችን በመመልከት የተለያዩ የታሪክ አጥኚዎች የኢትዮጵያዊያን ድል ያስከተለው ውጤት በሚል የሚከተሉትን ነጥቦች አስፍረዋል።
news-48715703
https://www.bbc.com/amharic/news-48715703
ተጠቃሚዎች የማይከፍሉበት ቁርስ ቤት
በሰሜን ምስራቅ ለንደን በሚገኘው ካፌ ተጠቃሚዎች በልተውና ጠጥተው ሳይከፍሉ ውልቅ የሚሉበት ነው።
ቲሊያ አዲና ልጇ ኤታን በሳምንት ሶስት ቀን ቁርስ ቤቱን ይጎበኛሉ ካፌው በበጎ አድራጎት ድርጅቶች 'ደስ ያላችሁን፣ የምትችሉትን ክፈሉ ባትከፍሉም ችግር የለም' በሚል ብሂል በመላ እንግሊዝ ከተከፈቱ ካፌዎች አንዱ ነው። በዚህ ካፌ እንቁላል፣ ዳቦ፣ ፖሬጅ ከሻይ ከቡና ጋር ለተጠቃሚዎች ይቀርባል። የብርቱካን ጭማቂም አይጠፋም። ወዲያ ወዲህ ብለው አረፍ ለማለትም ይሁን ጓደኞችን ቀጥሮ ሻይ ቡና ለማለት የነፃው ካፌ ምርጥ ቦታ እንደሆነ ተጠቃሚዎቹ ይናገራሉ። የነፃው ቁርስ ቤት ድባብ ደስ የሚልና አውዳመት አውዳመት የሚል ነው ያሉም አልጠፉም። የኢንሹራንስ ባለሙያ የሆነው ጋይ ካፌው በሁሉም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን እኩል የሚያደርግ ነው ይላል። ምክንያቱም ገንዘብ ጥያቄ ውስጥ ሳይገባ ማንም ወደ ካፌው ሄዶ ሻይ ቡና እያለ መጫወት ይችላልና። • ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ • የደም ሻጮችና ለጋሾች ሠልፍ የካፌው ደንበኛ የሆኑት ሺላና የስድስት ዓመት ህፃን ልጇ በሳምንት ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ ጎራ ይላሉ። "አንዳንዴ የምንመጣው ቀለል ያለ ቁርስ ለመብላት ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ገንዘብ ሲያጥረን ነው። ደግሞ እኔም ልጄም እዚህ ጓደኞች አፍርተናል" ትላለች ሺላ። ካፌውን ለየት የሚያደርገው ተጠቃሚዎች በልተው ጠጥተው ሳይከፍሉ መውጣት የሚችሉበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ተጠቃሚ ራሱን የሚያስተናግድበት መሆኑም ነው። የካፌው ተጠቃሚዎች ወላጆች ፣ ህፃናት፣ አዛውንት፣ ባለሙያዎች፣ ጎልማሶችና አካል ጉዳተኞችና መሰሎች ናቸው። የካፍቴሪያውን የጋራ ትልልቅ ጠረጴዛዎች ተጋርተው ሰዎች ስለ ተለያዩ ነገሮች እንዲያወሩ የሚጋብዝ ነው የካፌው ሁኔታ። የዚህ አይነት ካፌዎች የሚከፈቱት የዕለት ምግባቸውን ማግኘት የሚቸግራቸው ሰዎች ማእድ እንዲቋደሱ ነው። ብዙዎቹ ካፌዎች የሚጠቀሙት ሱፐር ማርኬቶች፣ ሬስቶራንቶችና ሌሎች የለገሷቸውን ምግቦች ነው።
news-53523369
https://www.bbc.com/amharic/news-53523369
አወዛጋቢው አያ ሶፊያ ቅርስ ዛሬ ለጁምአ ጸሎት ክፍት ይሆናል
1ሺ 500 ዓመት ዕድሜ ያለው ዝነኛው የአያ ሶፊያ ቅርስ መስጊድ እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።
ድሮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የነበረው አያ ሶፊያ አሁን መስጊድ ሆኗል፡፡ ቱርክም ሆነች መላው ዓለም የሚደመምበት የአያ ሶፊያ ሕንጻ በከፊል መስጊድ ሆኖ እንዲያገለግል የወሰነው ፍርድ ቤት ነው፡፡ በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው አያ ሶፊያ ከዓለም ቅርሶች ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ ሙስሊሞች በዜናው ተደስተዋል፤ ጁምዓ ሁሉም ሰው እዚያ ለመገኘት ይፈልጋል ብለዋል የኢስታንቡል ከንቲባ የርሊካያ አሊ፡፡ አንድ ሺ አምስት መቶ ዓመት ያስቆጠረው ይህ በዩኔስኮ ልዩ ቦታ የሚሰጠው ታሪካዊ ሕንጻ ወደ ሙዚየምነት የተቀየረው በፈረንጆቹ በ1934 ነበር፡፡ ከዚያ ቀደም ባሉ ረዥም ዓመታት ግን መስጊድ ነበር፡፡ ይህንን ቅርስ ወደ መስጊድነት እንዲመለስ መወሰኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል፡፡ ይህም የሆነው ቅርሱ በቢዛንታይን ጊዜ ሲገነባ የዓለም ትልቁ ቤተ ክርስቲያን የነበረ በመሆኑ ነው፡፡ ከዛሬ አርብ ጀምሮ በአንድ ጊዜ አንድ ሺ ሰዎች በአያ ሶፊያ ተገኝተው ሊሰግዱበት ይችላሉ ተብሏል፡፡ የቱርኩ መሪ ጣይብ ኤርዶጋን ዛሬ ለጁምአ ከሚገኙት ምዕመናን መካከል አንዱ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ ይህ ቅርስ መስጊድ ይሁን ወይስ ቅርስ ሆኖ ይቀጥል የሚለው ጉዳይ ላይ ለዓመታት የቱርክ ማኅበረሰብን ሲያነታረክ ነበር፡፡ ኤርዶጋን ይህ ቅርስ መስጊድ እንዲሆን መወሰኑን ሲያሳውቁ በርካቶች የተደሰቱትን ያህል ከፍተኛ ቅሬታዎችም ተስተናግደዋል፡፡ ለምሳሌ የካቶሊኩ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ‹‹ለኢስታንቡል እጸልያለሁ፤ ሳንታ ሶፊያን ባሰብኩ ቁጥር ሐዘኔ ይበረታል›› ብለዋል ውሳኔውን ተከትሎ፡፡ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትም በውሳኔው ሐዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ፓትሪያርክ ባርቶሎሜ እንደተናገሩት ይህ ቅርስ መስጊድ መሆኑ የብዙ ኦርቶዶክሶችን ልብ የሚሰብር ነው፡፡ 350 ቤተክስትያኖችን ያቀፈው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በበኩሉ ውሳኔው እንዲቀለበስ ጠይቋል፡፡ ይህ ውሳኔ አንድነትን ሳይሆን ክፍፍልን የሚፈጥር ነው ሲሉ አስጠንቅቋል፡፡ ‹‹ኤርዶጋን ግን ሉአላዊ አገር ነን፡፡ ውሳኔያችንም ሉአላዊነታችንን የሚያረጋግጥ ነው›› ብለዋል፡፡ በሕንጻው ውስጥ የሚገኙ የቅድስት ማርያምና ሌሎች ክርስቲያናዊ ምሥሎችና ምልክቶችም ተጠብቀው እንደሚቆዩ አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹አያ ሶፊያ ከ86 ዓመታት በኋላ ወደ መስጊድነት ተቀይሯል፡፡ የኢስታንቡል ወራሪ የነበረው የሕንጻው ባለቤት በኑዛዜው ቤቴ መስጊድ እንዲሆን ባለው መሰረት ኑዛዜው እነሆ ተከብሮለታል›› ብለዋል ኤርዶጋን፡፡ ሆኖም ኤርዶጋን ሕንጻው ለክርስቲያኖችም ክፍት መሆኑን አስምረውበታል፡፡ ከክርስቲያች በተጨማሪም ለጎብኚዎች ዓመቱን ሙሉ ክፍት ይደረጋል፡፡ አያ ሶፊያ የማን ነው? አያ ሶፊያ በ537 በቢዛንታይን ኢምፐረር ጀስቲኒያን የተገነባ ልዩና ብርቅዬ ቤተክርስቲያን ነበር፡፡ ንጉሡ ይህ ስፍራ ትልቁ የዓለም ቤተ ክርስቲያን እንዲሆን አስቦ እንዳስገነባው ይነገራል፡፡ ሆኖም እንደ አውሮጳዊያኑ በ1453 ኦቶማን ሱልጣን አሕመድ ዳግማዊ ቀድሞ ኮንስታንቲኖፕል ትባል የነበረችውን ኢስታንቡልን በመውረር ተቆጣጠረ፡፡ ወረራውን ተከትሎም የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ካቴድራል የነበረችው አያ ሶፊያ ወደ መስጊድነት ተቀየረች፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ መስጊድነት በመቀየሩ ረገድ በዚያ ዘመን አራት ሚናሬቶችም እላዩ ላይ እንዲገነቡ ተደርጓል፡፡ አያ ሶፊያ ለብዙ መቶ ዓመታት መስጊድ ሆኖ ካገለገለ በኋላ ይህ ስፍራ በከማል አታቱርክ ግፊት ወደ ሙዝየምነት ተቀየረ፡። አያ ሶፊያን በዓመት ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ቱሪስቶች ይጎበኙታል፡፡
news-54422255
https://www.bbc.com/amharic/news-54422255
ትግራይ፡ የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ "ቅቡልነት የለውም"- የትግራይ ክልል
የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ የትናንቱ የፌዴሽን ምክር ቤት ውሳኔ ቅቡልነት የሌለው ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ።
አፈ ጉባኤው፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት ከመስከረም 25፣ 2013 ዓ. ም. ጀምሮ የሥልጣን ዘመኑ ማብቃቱን በማጣቀስ፤ ያስተላለፈው ውሳኔ "ሕጋዊ መሠረት የለውም፤ ተቀባይነት የለውም፤ ተግባራዊም ሊሆንም አይችልም" ብለዋል። ከክልል መንግሥት በታች ያሉ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ መዋቅሮችን የማደራጀት ሥልጣን የክልሉ መሆኑን የሚናገሩት አፈ ጉባዔው፤የፌደራል መንግሥት በቀጥታ ወደ ታች ወርዶ ሊሠራ የሚችልበት ሕጋዊ ሥልጣን የለውም በማለት ውሳኔውን "የአሃዳዊነት አስተሳሰብና ተግባር" ሲሉ ኮንነዋል። አፈ ጉባዔ ሩፋኤል፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ መሠረት የብሔር ብሔረሰቦች ወኪል ነው ካሉ በኋላ፤ በዋናነት ከየክልሎች የሚወከሉ አባላት ያሉበት ምክር ቤት መሆኑን ይገልጻሉ። ምክር ቤቱ ሥልጣኑን ከሕገ መንግሥቱ ውጪ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም በመስጠት ያራዘመ ስለሆነ፤ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የለውም ብለዋል። "ምክንያቱም የክልል ምክር ቤቶችም ሆኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየአምስት ዓመቱ ምርጫ ማካሄድ አለባቸው" በማለት በቂ ያልሆነ ምክንያት በማቅረብ ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ሰጥቶ ሥልጣኑን ያራዘመ ስለሆነ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የለውም ብለዋል። ከዚህ በፊትም የትግራይ ክልል ምክር ቤት ተወካዮቹ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደማይሳተፉ አስታውቋል። ለዚህም ምክንያቱ የምክር ቤቱ የሥልጣን ዘመን ስላበቃ፤ አዲስ ምርጫ ተደርጎ ክልሎች ወኪሎቻቸውን ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት መላክ ስላለባቸው መሆኑን አንስተዋል። አፈ ጉባዔው፤ የምክር ቤቱን ውሳኔ ተፈጻሚነት የሌለው በማለት "ለሕጋዊ አካልና ለትግራይ ሕዝብ ያለውን ንቀት ለማሳየት ካልሆነ በስተቀር" በማለት ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሰው ምርጫ ላይ ተሳትፎ ተወካዮቹን መምረጡን አስታውሰዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ምን ይላል? የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የፌደራል መንግሥቱ ከሕግ ውጪ እየተንቀሳቀሰ ነው ካለው የትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ያውን ግንኙነት እንዲያቋረጥ ወሰነ። ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የወጣውን መረጃ በመጥቀስ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ምክር ቤቱ ባካሄደው ስብሰባ የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ ማሳለፉ ተነግሯል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከዚህ ቀደም የትግራይ ክልል ምርጫ ለማካሄድ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ድርጊቱ ሕግን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መጻፉ ይታወሳል። ከዚያም በኋላ ክልሉ ምርጫውን ለማካሄድ በተዘጋጀበት ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ክልላዊው ምርጫ ሕገ ወጥና ተፈጻሚነት የሌለው እንደሆነ በመግለጽ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ነገር ግን የምክር ቤቱ ውሳኔ በክልሉ መንግሥት በኩል ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀርቶ ምርጫ ተካሂዶ አዲስ ምክር ቤት መቋቋሙ መገለጹ ይታወሳል። ከትግራይ ክልል ምርጫ አንጻር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን በተመለከተ የሕገ መንግሥት ጉዳዮችና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ፤ ክልሉ የምክር ቤቱን ውሳኔ አክብሮ ተግባራዊ ባለማድረጉ የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ወስኗል። በዚህም መሰረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳላፈውን ውሳኔ አላከበረም ያለው ትግራይ ክልል መንግሥትን በሚመለከት የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል። በቀዳሚነት የትግራይ ክልል ያካሄደውን ከሕገ መንግሥቱ ተጻራሪ ነው ያለውን ምርጫ ተከትሎ ከተመሰረቱ የክልሉ ምክር ቤትና ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካል ጋር የፌዴራል መንግሥት ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አሳልፏል። በተጨማሪም የፌደራል መንግሥት የክልሉን ሕዝብ የልማትና መሠረታዊ አገልግሎቶችን ፍላጎት ላይ በማተኮር የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ሕጋዊ ተቋማት ጋር ብቻ ግንኙነት እንዲያደረግ ወስኗል። የእነዚህ ውሳኔዎችም ተግባራዊነትና አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እንዲሁም በሚመለከታቸው የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች አማካይነት ክትትል እንደሚደረግ አመልክተዋል። በትግራይ ክልል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለመግባባት እየተካረረ ሄዶ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከመስከረም 25 በኋላ ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚያበቃ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል። ሰኞ ዕለት ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና በተለያዩ የፌደራል መንግሥት የፖለቲካ ሹመት ቦታ ላይ ያሉ አባላቱ ኃላፊነታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዙን አቶ ጌታቸው ረዳ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። በወቅቱ አቶ ጌታቸው ረዳ "በአሁኑ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ካቢኔያቸው፣ እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ምንም አይነት ሕጋዊ ስልጣን የላቸውም፤ ከእነዚህ አካላት ጋር ምንም አይነት ሕጋዊ ግንኙነት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም" ብለዋል። "መንግሥት በትክክለኛው መንገድ ለመመስረት የሚያስችል እድል እስኪገኝ ድረስ ግንኙነታችን ከእነዚህ ጋር ብቻ ይሆናል" በማለት "ፈርሰዋል" ካሏቸው ጋር ያላቸው ግንኙት መቋረጡን አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል መንግሥት ሕገ መንግሥቱን በሚጻረር ተግባራት ላይ ተሰማርቷል በማለት ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የቆው የፌዴሬሽን ምክር ቤት እርምጃዎችን እንደሚወስድ ሲገልጽ ቆይቷል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ ከቀናት በፊት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይህንኑ በተመለከተ እንደተናገሩት "በእስካሁኑ እንቅስቃሴ ክልሉ ሕገ-መንግሥቱን አደጋ ላይ ጥሏል" ለዚህም እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ መሰረት መኖሩን አመልክተዋል። ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል የክልሉን ሕግ አውጪና ሕግ አስፈጻሚውን ማገድ የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ አካሄድ አንዱ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋምና የፌደራል የፀጥታ አካላት በማሰማራት ሕገ መንግሥቱን አደጋ ላይ የጣለውን ድርጊት መቆጣጠር ሌላኛው መሆኑን አፈጉባኤው ገልጸዋል።
46218898
https://www.bbc.com/amharic/46218898
በሃሰተኛ ዜናዎች "የሞቱ" የኪነጥበብ ሰዎች-ገነት ንጋቱ፣ ጋሽ አበራ ሞላ እና አምለሰት ሙጩ
በግለሰብም ሆነ በሀሰተኛ የድርጅት ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የሚሰራጩ ሀሰተኛ ዜናዎች የበርካቶችን ቤት አንኳክተዋል። በተለይ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ታዋቂ ፖለቲከኞች በሀሰተኛ ገፆች ሰበር ዜና ስር ሕይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።
ከግራ ወደቀኝ ስለሽ ደምሴ፣ ጌታቸው ማንጉዳይ እና ገነት ንጋቱ እንደነዚህ ያሉ ዜናዎች ብዙዎችን አስደንግጠዋል። ህልፈታቸው በሃሰተኛ ዜናዎች ከታወጀ መካከል አርቲስት ስለሺ ደምሴን (ጋሽ አበራ ሞላ)ና አርቲስት ገነት ንጋቱን ማንሳት ይቻላል። •የ7 ዓመቷ ህጻን ግድያ፡ ''ከልክ ያለፈ ቅጣት የልጄን ህይወት አሳጣኝ'' •በሞያሌ በተከሰተ ግጭት የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ •የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር በጋዛ ተኩስ አቁም ውሳኔ ምክንያት ለቀቁ አርቲስት ስለሹ ደምሴ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ባይሆንም በተለያዩ ግለሰቦች ላይ ያልሆነው ሆነ፣ ያልተፈጠረው ተፈጠረ፣ ያላጋጠመው አጋጠመ፣ ያልተደረገው ተደረገ እየተባሉ የሚሰራጩ ሃሰተኛ ወሬዎችን ከሰው ከሰው እንደሚሰማ ይናገራል። ከዓመታት በፊት ስለሺ ደምሴ ሞቷል የሚል ሃሰተኛ ዜና ተሰራጨ፤ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ተቀባበሉት። እርሱ ግን የሚዲያው ተጠቃሚ ባለመሆኑ ቶሎ ጆሮው አልደረሰም ነበር፤ እንደ አጋጣሚ አንድ ቦታ ቁጭ ብሎ ሳለ አንድ ወዳጁ ይመጣና " ሞተሃል ተብሎ አልነበረም እንዴ?" ሲል እየሳቀ ይጠይቀዋል። ለማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት ሰጥቶ እንደማያውቅ የሚናገረው ስለሺ ደምሴ "ታዲያ መሞትማ አይቀርም፤ እኔ አንደውም ብዙ ጊዜ ነው የሞትኩት፤ በየቀኑ አይደል እንዴ የምሞተው?" ብሎ በቀልድ የታጀበ ምላሽ እንደሰጠው ያስታውሳል። ይህንን ዜና ተከትሎ በቤተሰቡ ላይ የደረሰው ተፅዕኖ ምን ነበር ስንል የጠየቅነው አርቲስቱ "እንኳንስ እንዲህ አይነት አሉባልታዎችን ይቅርና ትክክለኛ ዜናዎችን ቁጭ ብሎ የሚሰሙ ሰዎች ቁጥራቸው ብዙ አይደለም" ሲል ይመልሳል። በርካታ ሰዎችም ሳይሞቱ ሞቱ እየተባለ ይናፈሳል ይህም የተለመደ በመሆኑ ትኩረት አይሰጠውም። በአብዛኛው በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎች እንደ እውነት አይወሰዱም የሚለው አርቲስት ስለሺ አጋጣሚ ሆኖ በተነዛው ሀሰተኛ ወሬ ሳቢያ ቤተሰቦቹም ድንጋጤ እንዳልተፈጠረባቸው ይናገራል። እንዲህ ዓይነት መረጃዎችን የሚያስተላልፉትም ሰሚ አናጣም፣ ተከታይ አለን፤ ወሬ የሚፈልግ አለ በሚል እንደሆነ ያምናል። " ችግሩ ያለው ከፀሐፊዎቹ ሳይሆን ወሬያቸውን ሳያጣራ እህ ብሎ ከሚሰማው ነው" የሚለው አርቲስቱ ደግሞ ይባስ ብሎ ያላጣሩትን ወሬ ለሌላ ሰው ማቀበላቸው አግራሞት ይጭርበታል። ተከታዮችና ሰሚዎች እንዲህ ዓይነት የሚነዙ አሉቧልታዎችን ባይሰሙ፣ ባይከተሉና ባያሰራጩ ፀሐፊዎቹም ይመክናሉ ሲል ምክንያቱን ያስቀምጣል። ይሁን እንጂ ቀስ በቀስ ሰው እየተገነዘበው ሲመጣ ይህ እንደሚለወጥ ተስፋ ያደርጋል። እንዲህ አይነት ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ሆነ ብሎ ትኩረት ሰጥቶ መከታተሉና ማራገቡ ስራ ማጣት፤ በጊዜና በገንዘብ ላይ መቀለድ በመሆኑ እውነተኛና ሃሰተኛ መረጃን ለመለየት ማጣራት እንደሚያስፈልግም ያስረዳል። አርቲስት ገነት ንጋቱም የዚሁ ሐሰተኛ መረጃ ተጎጂ ናት፤ በአንድ ወቅት በህመም ላይ በነበረችበት ጊዜ አርፋለች ተብሎ ሀሰተኛ መረጃ ተሰራጭቶ ነበር። "ህመም ላይ እያለሽ መዳን በምትፈልጊበት ጊዜ እንዲህ ዓይነት ዜና መስማቱ ያማል" ትላለች። ሀሰተኛ ዜናውን የሰማችው መረጃው የደረሳቸው ዘመድ አዝማዶች መርዶውን ሰምተው እያለቀሱ ወደ ቤት ሲገቡ ነው፤ ከዚያም በኋላ ስልክ እየደወሉ ድምጿን ሲሰሙ ይረጋጉ አንደነበር ታስታውሳለች። በተለይ እናቷ በተሰራጨው የሀሰት ዜና ተንሰቅስቀው እንዳለቀሱ የምትረሳው አይደለም። "እንደው ምን ብታደርጊያቸው ነው?" ሲሉ እንደጠየቋትም አትዘነጋውም። አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ተመሳሳይ መረጃዎች ይናፈሱ ነበር የምትለው ገነት፤ ለህክምና ወደ ህንድ አገር ስትሄድም "አውሮፕላን ላይ አረፈች ተብሎ" መወራቱን ትናገራለች። ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነት ሃሰተኛ ዜናን የሚፈጥሩ ሰዎች ምን አይነት አስተሳሰብና አመለካከት እንዳላቸው የዘወትር ጥያቄዋ ነው። ስለ ቴዎድሮስ ካሰሁንና ባለቤቱ አምለሰት ሙጨ ምን ተባለ? የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ሥራ አስኪያጅ ጌታቸው ማንጉዳይም "ሰው ለምን ሰውን በሀሰት ይገላል? ምን ጥቅም ያገኛል" በማለት ከገነት ጋር ተመሳሳይ ጥያቄ ይሰነዝራል። ሀሰተኛ መረጃ ሲሰራጭ ብዙዎችን ቢያደናግጥም፤ መረጃውን የሚያስተባብል ምላሽ አይሰጥም። ሀሰተኛ ዜና የሚያሰራጩ ሰዎች፤ ትኩረት ማግኘት ቀዳሚ ግባቸው በመሆኑ፤ መረባቸው ውስጥ ላለመውደቅ ጆሮ አለመስጠትን ይመርጣል። "የተቆፈረ ጉድጓድ አለ፤ ወጥመድ ይዘጋጅልሀል። ለምን ወደጉድጓድ ትገባለህ" ሲል መልስ መስጠት እንደማያሻ ያስረዳል። የምዕራቡ ዓለም የኪነጥበብ ሰዎች እያንዳንዱን እንቅስቃሴያቸውን ማኀበራዊ ሚዲያ ላይ ያጋራሉ። የኢትዮጵያ እውነታ ከዚህ ይለያል። ጌታቸው እንደሚለው ሁኔታው እንደየሰው ባህሪ ይለያያል። "በኛ ባህል እዚህ ገባሁ እዚህ ወጣሁ ማለት አይደለም። ይህ የምእራባውያን ባህል ነው" ይላል። ፈጠራ ሥራ ላይ ያለ ሰው አእምሮው መረጋጋት አለበት የሚለው ጌታቸው፤ "ለሀሰተኛ ዜና ጆሮ ክፍት ካደረጉ ፈጣሪ መሆን አይቻልም" ሲል ያክላል። በቅርቡ የኢትዮጵያና ኤርትራ የወዳጅነት ሩጫ በባህርዳር እንደተካሄደና በስፍራው ላይ ቦንብ ፈንድቶ በርካቶች እንደሞቱ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ስም በተከፈተ ሐሰተኛ የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ተዘግቦ ነበር። በዚህ ገፅ ላይም በፍንዳታው ቴዲ አፍሮ መጎዳቱንና ባለቤቱ አምለሰት ሙጬም እንደሞተች ተወርቷል። ጌታቸው "ብዙ ነገር ይወራል። እኛ አንሰማም። በራችን ዝግ ነው። ቴዲ አፍሮ ጥሩ ሥራ የሚያቀርበው ለዚህ ነው" ይላል። "ለሀሰተኛ ዜና ትኩረት ከተሰጠ አንድ እርምጃም መሄድ አይቻልም" የሚለው ጌታቸው ሀሰተኛ ዜና ቢያስደነግጥም፤ ማኀበረሰቡ እውነተኛ መረጃን ከሀሰተኛ መለየት እንደሚችል ይተማመናል።
50555266
https://www.bbc.com/amharic/50555266
የዘጠኝ ዓመቱ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ
ላውረንት ሳይመን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገባ አራት ዓመቱ ነበር። ሆኖም የእድሜ እኩዮቹ ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳይሆኑ እሱ በዘጠኝ ዓመቱ ዲግሪ ሊጭን ነው።
በቀጣይ ወር በእድሜ ትንሹ ተመራቂ የሚሆነው ታዳጊ ላውረንት ሳይመን ላውረንት እንደ ማንኛውም ልጅ የአንደኛ ክፍል ትምህርቱን ያጠናቀቀው በአንድ ዓመት ውስጥ ነበር። ወደ ሁለተኛ ክፍል ከተሸጋገረ በኋላ ግን ነገሮች ተለወጡ። በአንድ ዓመት ውስጥ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለውን ትምህርት ጨረሰ። በስድስት ዓመቱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የተቀላቀለው ላውረንት፤ ስድስት ዓመት ይወስድ የነበረውን ትምህርት በ18 ወር ውስጥ አገባደደ። ከዛም የስምንት ዓመቱ ታዳጊ ለስድስት ወር አረፍ ብሎ ዩኒቨርስቲ ገባ። ከስምንት ወር በፊት ዩኒቨርስቲ የገባው ላውረንት፤ በዘጠኝ ወር የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቱን አጠናቆ በቀጣዩ ወር በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ይመረቃል። ታዳጊው፤ በምን ተአምር በዘጠኝ ዓመቱ የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ ለመሆን አንደበቃ አያውቅም። ከቢቢሲ ጋር በነረው ቆይታም "እንዴት እንዳሳካሁት አላውቅም" ሲል ተናግሯል። • የዘንድሮ ተመራቂዎች እንዴት ሥራ ያገኛሉ? • ከበለስ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የምትመራመረዋ ኢትዮጵያዊት ኢንጂነሪንግ፣ ህክምና ወይስ ሁለቱንም? ላውረንት በቴክኖሎጂ ታግዞ እንዴት የሰው ልጆችን መርዳት እንደሚቻል መመራመር ያስደስተዋል። ለመመረቂያው የሠራውም የሰው ልጆችን የአዕምሮ እንቅስቃሴ የሚለካ መሣሪያ ነው። ላውረንት በቴክኖሎጂ ታግዞ እንዴት የሰው ልጆችን መርዳት እንደሚቻል መመራመር ያስደስተዋል ከሀኪም ቤተሶች የተወለደው ላውረንት፤ ለሦስተኛ ዲግሪው ህክምና የማጥናት እቅድ አለው። "ህልሜ ሰው ሰራሽ የሰውነት ክፍሎችን መሥራት ነው" የሚለው ታዳጊው፤ የሰው ልጆች ልብ፣ ኩላሊት ሲያስፈልጋቸው በመተካት የተሻለ ሕይወት መስጠትና እድሜያቸውን ማራዘምም ይሻል። "ቅድመ አያቶቼን ጨምሮ የሌሎችን ሰዎችም እድሜ ማርዘም እፈልጋለሁ" ይላል። ላውረንትን ያሳደጉት አያቶቹ ናቸው። ገና ህጻን ሳለ ጀምሮ ልዩ ተሰጥኦ እንዳለው ተረድተውም እንደነበር አባቱ አሌክሳንደር ሳይመን ይናገራሉ። ላውረንት ከቅድመ አያቶቹ ጋር ላውረንት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሲጀምር፤ ልዩ ተማሪ መሆኑን አስተማሪዎቹ ለቤተሰቦቹ ገለጹ። ቤተሰቦቹ ለምን ፈጣን እንደሆነ ለማወቅ ጥረት ያደርጉ ነበር። ችሎታው እነሱን ብቻ ሳይሆን ባለሙያዎችንም ያስደመመ ነበር። • ከአንደኛ ክፍል ዲግሪ እስኪጭኑ ከልጃቸው ጋር የተማሩት አባት • "እቴጌ" ካንሰርን ለመታገል የተሰራ የስልክ መተግበሪያ ታዳጊው ከፍተኛ የማስታወስ ችሎታ (ፎቶግራፊክ ሜሞሪ) ያለው ሲሆን፤ አይኪው ሲለካ 145 ነው። ሂሳብና ሳይንስ የሚወደው ታዳጊው፤ ለቋንቋ ግን የተለየ ፍላጎት አያሳይም። አባቱ እንደሚናገሩት፤ አንዳንድ ቀን ትምህርት ቤት ቀርቶ ባህር ዳርቻ ሄዶ መዝናናት ይፈልግ ነበር። ዩኒቨርስቲ ሲገባ ግን የተለየ መርሀ ግብር መከተል ጀመረ። "ሰኞ የትምህርቱን መግቢያ ይወስድና ማክሰኞ ቤተ ሙከራ ይገባል። እሮብ ቤት ሆኖ ለስምንት ሰዓት ያጠናል። ሀሙስ ለትምህርት ክፍሉ ጥያቄ ያቀርብና አርብ ይፈተናል" ሲሉ አባቱ ያስረዳሉ። ሌሎች ተማሪዎች ይህንን ሂደት ለማጠናቀቅ ከዘጠኝ እስከ 12 ሳምንት ይወስድባቸዋል። የክፍል ጓደኞቹ ባጠቃላይ በእጥፍ እድሜ የሚበልጡት ላውረንት፤ ትምህርቱን የሚከታተለው ከሌሎች ተማሪዎች በተለየ ክፍል ውስጥ ነው። ላውረንት በውሀ ዳርቻ ሲዝናና አባቱ እንደሚሉት፤ እንደ ሌሎች ልጆች የሚጫወትበት ጊዜም አለ። ቤተሰቦቹም ጫና አያሳድሩበትም። ታዳጊው ኢንስታግራም ላይ 35ሺህ ተከታዮች አሉት። ሲዝናና የሚያሳዩ ፎቶዎችን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹም ይለቃል። ለጓደኞቹ፤ በቴሌቭዥን ቃለ መጠይቅ እንደተደረገለት በኩራት እንደሚያወራም አባቱ ይናገራሉ። ሞዛርት በአምስት ዓመቱ ሙዚቃ ያቀናብር ነበር። ፒካሶም የመጀመሪያ ሥዕሉን የሠራው በዘጠኝ ዓመቱ ነው። ቢሆንም ሌሎች በልጅነታቸው እውቅና ያተረፉ ሰዎች በእድሜ ከፍ ሲሉ ይጠፋሉ። ምናልባት ላውረንት በእድሜ ከገፋ በኋላም ስኬታማ ሆኖ እናየው ይሆን? አባቱ እንደሚሉት፤ ላውረንት አደርጋለሁ ያለውን ነገር ሳያሳካ ቀርቶ አያውቅም።
51131140
https://www.bbc.com/amharic/51131140
ናይጄሪያ፡ በርካቶች መርሳት ያልቻሉት ጦርነት ሲታወስ
ከአንድ ሚሊዮን በላይ ናይጄሪያውያንን ቀጥፏል። የዛሬ 50 ዓመት ያበቃው የናይጄሪያው የእርስ በርስ ጦርነት። ጦርነቱ ናይጄሪያ ላይ ጥሎ ያለፈው ጠባሳ ግን አሁንም አለ።
ባያፍራ በተሰኘችው ግዛት ምክንያት የተነሳው ጦርነት ናይጄሪያውን ሊረሱት የሚፈልጉት ቢሆንም ለኢግቦ ሰዎች ግን የሕይወት ጉዳይ ነው። በግሪጎሪ አቆጣጠር 1967 ላይ ናይጄሪያ ውስጥ ሁለት ጊዜ የመፈንቅለ መንግሥት ሙክራ ተደረገ፤ ይህንን ተከትሎ አንድ ሚሊዮን ገደማ የኢግቦ ሰዎች ወደ ደቡብ ምስራቅ ናይጄሪያ ተመሙ፤ ነፃነታቸውንም አወጁ። ይህ ያልተዋጠለት የወቅቱ የናይጄሪያ መንግሥት ጦርነት አወጀ። ከ30 ወራት ጦርነት በኋላ ባያፍራ እጅ ሰጠች። ጥር 7/1970 ጦርነቱ በይፋ ማብቃቱ ተነገረ። መንግሥት በጦርነቱ ማንም አላሸነፈም፤ ማንም አልተሸነፈም ቢልም የኢግቦ ልጆች ግን ስለ ጦርነቱ እየተነገራቸው ነው ያደጉት። ከጦርነቱ ከተረፉት መካከል ክርስቶፈር ኤጂኮ አንዱ ናቸው። ጦርነቱ ሲጀመር በናይጄሪያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበር። የማውቃቸው ተማሪዎች ሁላ በጦርነቱ ተሳትፈዋል ይላል። የባያፍራን ጦር ተቀላቅሎ የናይጄሪያ ጦር እንዲሰልል ተሾመ። የ76 ዓመቱ ክሪስ ራሳችንን እንደ አስማት ሰሪ ነበር የምንቆጥረው ይላሉ። «የምንዋጋው ከሰለጠኑ ወታደሮች ጋር ነበር። እኛ ግን የሁለት ቀናት ሥልጠና ነበር ተሰጥቶን ወደ ጦርነት የገባነው፤ ረሃቡም አለ። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ጦርነት መግጠም በጣም ከባድ ነው።» ነገር ግን የኢግቦ ጦር ታዋቂውን የጦር ጄኔራል አሕማዱ ቤሎን ገደለ። ይህ ደግሞ ለአፀፋ ምላሽ ዳረገ። የመንግሥት ጦር የኢግቦ ሰዎችን በጅምላ መግደል ያዘ። በዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አለቁ፤ የቀሩቱ ደግሞ ምስራቃዊ ክፍለ ሃገር ወደ ሚባለው ክፍል ተሰደዱ። የወቅቱ የምስራቃዊ ክፍለ ሃገር መሪ ኤሜካ ኦጆኩ ነበር። ይህ ያስመረረው ኦጆኩ ምስራቃዊውን ክፍል ለመገንጠል እንቅስቃሴ ጀመረ። ኦጆኩ ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ እየሄደ ተማሪዎችን በመመልመል ለነፃ እንውጣ ጦርነት ያዘጋጅ ነበር። ተማሪዎቹን ለማጋዝ ሄሊኮፕተር ይመጣ እንደነበር የሚያወሱት ክሪስ ተማሪዎች እንዴት እየሮጡ ወደ ሄሊኮፕተሯ ይገቡ እንደነበር አይዘነጉም። የመጀመሪያው የጦርነት ዓመት የመንግሥት ጦር የውቅያኖስ ዳር ከተማ የሆነችው ፖርት ሃርኮርትን ተቆጣጠረ። ወደ ባያፍራ ምግባን መሰል ምርቶች እንዳይገቡ ከለከለ። ረሃቡ በጣም ከመፅናቱ የተነሳ ሰዎች ዓይጥ እያየዙ ይበሉ እንደነበር ክሪስ ያስታውሳሉ። ነገር ግን መሃል የባያፍራ ጦር ወሳኝ የሆነ ድል የመንግሥት ጦር ላይ ተቀናጀ። «ያኔ ትንሽ ተስፋ ተሰምቶን ነበር። ከውጭ ኃይል እርዳታ እስክናገኝ ድረስ መጠበቅ ያዝን።» በ1969 መጨረሻ ግን ለኢግቦዎች ሁሉም እንዳልሆነ ሆነ። ጦርነቱ ሲያበቃ የዛኔው ወጣቱ ክሪስ ለሁለት ዓመታት ያላቸውን ቤተሰቦቹን ፍለጋ መኳተን ያዘ። በወቅቱ የተሰጠውን የእርዳታ ሩዝ ሰብስቡ ቤተሰቦቹ ይገኙበት ይሆናል ወዳለው አካባቢ ጉዞ ጀመረ። ረሃብ ቢያዳክመውም ሩዙን በጀርባው እንደተሸከመ ቤተሰቦቹን ፍለጋ ቀጠለ። ጓደኞቹና የትምህርት ቤት አጋሮቹ በጦርነቱ ምክንያት አልቀዋል። እሱማ ሞቷል ብለው ተስፋ የቆረጡ ቤተሰቦቹን ግን አገኛቸው። ከጀርባው ያዘለው ሩዝ ደግሞ ደስታውን እጥፍ አደረገው። በወቅቱ በረሃብ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በጥይት ከሞቱት እንደሚበልጥ ይነገራል። ይማርበት የነበረው ዩኒቨርሲቲ እንደ አዲስ ሲከፈት ክሪስ አጎ ከጥቂት ወራት በኋላ ተቀላቅሎ በዕፅዋትና አፈር ሳይንስ ድግሪውን ጫነ። ክሪስ ኦጎና ጓደኞቹ በጦር አለቃቸው ተመርተው ባይዋጉ ኖሮ ጦርነቱ 30 ሰዓታትም አይፈጀም ነበር ይላሉ ሌላኛው የጦርነቱ ተሳታፊ ፌሊክስ። በወቅቱ ባያፍራ የራሷ መገበያያ ገንዘብ ነበራት። ነገር ግን በጦርነቱ ምክንያት ብዙዎች ያከማቹት ቤሳ ከጥቅም ውጭ ሆነ። በወቅቱ የመገንጠል እነቅስቃሴውን ሲያራምድ የነበረው የጦር መሪው ኤሜካ ኦጆኩ በግሉ አውሮፕላኑ ወደ አይቮሪ ኮስት ማምለጥ ችሏል። 13 ዓመታት ያክልም በስደት ሊኖር ግድ ሆነ፤ በስተመጨረሻ ግን የናይጄሪያ መንግሥት ምሕረት አድረጎለት ወደ ሃገር ቤት ተመለሰ። 2011 ላይ ሕይወቱ ያለፈችው ኦጁኩ በወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት ነው እንዲቀበር የተደረገው። የወቅቱ የናይጄሪያ ፕዝደንት ጉላክ ጆናታንን ጨምሮ ሌሎች ባለሥልጣናት በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል። የባያፍራ ጦርነት 50 ዓመታት ደፈነ። ናይጄሪያ አሁንም አንድነቷን ለማስጠበቅ እየታገለች ነው። የኢግቦ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ማሕበረሰቦች ናይጄሪያ እንደ አዲስ መዋቀር አለባት የሚል ድምፅ ያሰማሉ። ማንም ግን ስለ ጦርነቱ ማውራት አይፈልግም። መንግሥትም ቢሆን የመገንጠል ሙከራ ተደርጎ የሆነውን አይታችኋል ማለት አልተጠበቀበትም። ሁሉም የገፈቱ ቀማሽ ናቸው እና።
news-51058879
https://www.bbc.com/amharic/news-51058879
ካናዳ፣ አሜሪካ እና ዩኬ አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ እምነት አለን አሉ
ምዕራባውያን መሪዎች የዩክሬኑ አውሮፕላን ቴህራን አቅራቢያ የመከስከሱ ምክንያት ኢራን በስህተት በሚሳኤል መትታ ስለጣለችው ነው አሉ።
የአሜሪካ፣ ካናዳ እና ዩናይትድ ኪንግደም መሪዎች አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ ማስረጃ መኖሩን ጠቁመዋል። ከምዕራባውያን ሃገራት በተጨማሪ የኢራቅ እና የዩክሬን መንግሥታትም አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ እምነት አድሮባቸዋል። ለ176 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የአውሮፕላን መከስከስ ዙሪያ ዝርዝር ምርመራዎች እንዲደረጉ የዩናይድ ኪንግደም እና ካናዳ መንግሥታት ጠይቀዋል። ትናንት አመሻሽ ላይ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ኃላፊ ለሲቢኤስ የዜና ወኪል ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን በኢራን ሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ ጥቆማ ከሰጡ በኋላ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ዩክሬን ቀደም ብላ አውሮፕላኑን እንዲከሰከስ ያደረገው ከኢራን የተተኮሰ ሚሳኤል ሊሆን እንደሚችል ግምት አስቀምጣ የነበረ ሲሆን፤ ኢራን ግን የዩክሬንን ምልከታ አጣጥላው ነበር። ኢራን ሩሲያ ሰራሽ ቶር የመከላከያ ሚሳኤል ሥርዓት ባለቤት መሆኗ ይታወቃል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ኢራን አውሮፕላኑን መትታ የጣለችው የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ጋር አሳስታ ስለመሆኑ በስፋት እየዘገቡ ነው። አንድ አውሮፕላን በሚሳኤል ተመትቶ ከወደቀ ለጥቃቱ ጥቅም ላይ የዋለው ሚሳኤል በራዳር፣ ኢንፍራሬድ ወይም ሳተላይት ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት ሲግናሉን ማግኘት እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሲቢኤስ የዜና ወኪል አንድ የአሜሪካ የደህንነት ባለሙያን ጠቅሶ እንደዘገበው ሁለት ሚሳኤሎች ሲወነጨፉ እና ሚሳኤሎች ያስከተሉት ፍንዳታ በሳተላይት ተመዝግቦ ተገኘቷል። በሌላ በኩል ኒውስዊክ የተሰኘው ሌላው የአሜሪካ የዜና ተቋም የፔንታጎን፣ የአሜሪካ እና የኢራቅ መንግሥታት የደህንነት ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው፤ አውሮፕላኑ ተመትቶ የወደቀው በሩሲያ ሰራሽ ቶር ሚሳኤል ነው። የዩክሬን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ አውሮፕላን ቴህራን ከሚገኘው ኢማም ኮሜይኒ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው የተከሰከሰው። አውሮፕላኑ ጉዞውን ወደ ዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ አድርጎ ነበር የተነሳው። ኢራን የአውሮፕላኑን የበረራ መረጃ መመዝገቢያ ጥቁር ሳጥን (ብላክ ቦክስ) ለአሜሪካም ሆነ ለቦይንግ አልሰጥም ማለቷ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ኢራን የዩክሬን እና ቦይንግ መርማሪዎች በምርመራው ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢራን እንዲገቡ ፍቃድ ሰጥታለች። እንደ ዓለም አቀፍ አቪዬሽን ሕግ ከሆነ ኢራን ምርመራውን የመምራት መብት ያላት ሲሆን፤ በተለምዶ ግን የአውሮፕላኑ አምራቾች በምርመራው ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ይኖራቸዋል። ምዕራባውያን መሪዎች ምን አሉ? የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ፤ አውሮፕላኑ ከምድር ወደ ሰማይ ተወንጫፊ በሆነ ሚሳኤል ተመትቶ ስለመጣሉ ብዙ የደህንነት መረጃዎች ደርሰውኛል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ትሩዶ፤ ባገኙት መረጃ መሠረት ኢራን አውሮፕላኑን ሆነ ብላ አልመታችም። "ካናዳውያን ጥያቄዎች አሏቸው። ለጥያቄዎቻቸውም ምላሽ ማግኘት ይገባቸዋል" በማለት በአደጋው ዙሪያ ዝርዝር ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ለአደጋው የትኛውንም አካል ተጠያቂ ለማድረግም ሆነ ሙሉ በሙሉ ከውሳኔ ላይ ለመድረስ ጊዜው ገና መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍረው ከነበሩት 178 ሰዎች መካከል 63 ካናዳውያን ሲሆን፤ ከዩክሬኗ ኪዬቨ ወደ ቶሮንቶ ካናዳ የሚያቀኑ ነበሩ። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ትናንት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ''ከዚህ አውሮፕላን ጋር በተገናኘ ጥርጣሬ አለኝ። የሆነ አካል ስህተት ሳይሰራ አይቀርም'' ከማለት ውጪ ዝርዝር ነገር መናገርን አልፈቀዱም። የዩናይት ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰንም፤ ሃገራቸው ከካናዳ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አገራት ጋር በትብብር እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል። ቀደም ሲል የዩክሬን የደህንነት ኃላፊ ለአውሮፕላኑ መከስከስ ሦስት ምክንያቶችን አስቀምጠው ነበር። እነዚህም፦ ኢራን ምን እያለች ነው? የኢራን ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኃላፊ አሊ አቤደዛዱህ "አውሮፕላኑ በምዕራብ አቅጣጫ ከአየር ማረፊያ ተነስቶ መብረር ከጀመረ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ወደ ቀኝ ዞሮ ተመልሶ ለማረፍ እየመጣ ሳለ ነው የተከሰከሰው" ብለዋል። ኃላፊው ጨምረውም የዓይን እማኞች አውሮፕላኑ አየር ላይ ሳለ በእሳት ተያይዞ ማየታቸውን ገልጸዋል። "በሳይንሳዊ መንገድ ከተመለከትነው፤ ይህ አውሮፕላን በሚሳኤል ተመትቶ ነው የወደቀው የሚለው የሚያስኬድ አይደለም" ብለዋል። የአሜሪካ እና ኢራን ፍጥጫ ለበርካታ ንጹሃን ዜጎች ሞት ምክንያት የሆነው ይህ ሁሉ እሰጣ ገባ የጀመረው አሜሪካ በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒን ከገደለች በኋላ ነው። ዶናልድ ትራምፕ፤ ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒን 'አሸባሪ' ይበሉት እንጂ በኢራናውያን ዘንድ እንደ 'ጀግና' ነበር የሚቆጠረው። የጦር ጀነራሉ፤ ከፕሬዝደንቱ በላይ እና ከኃይማኖት መሪው በታች የሚገኙ ሁለተኛው የኢራን ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ ነበሩ። ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ፤ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኩድስ ኃይል አዛዥ ነበሩ። ኢራን ለጀነራሉ ግድያ በአሜሪካ ላይ የአጸፋ ምላሽ ለመውሰድ ብዙ ከዛተች በኋላ፤ በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር መንደሮች ላይ የሚሳኤል ድብደባ አድርጋ ነበር።
news-54145142
https://www.bbc.com/amharic/news-54145142
ትግራይ ፡ በመቀለ ከተማ ሦስት ወጣቶች ሞተው ተገኙ
በመቀለ ከተማ በአይደር ክፍለ ከተማ አዲሓ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር አንዲት ሴትና ሁለት ወንድ ጓደኛሞች በአንድ ቤት ውስጥ ሞተው ተገኙ።
ግርማይ ኃይለሚካኤል እና ርእሶም ገብረእግዚአብሔር ወጣቶቹ ሞተው የተገኙት በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ መሆኑን በከተማዋ የሚገኘው የአይደር ክፍለ ከተማ ፖሊስ ለቢቢሲ ገልጿል። ህይወታቸው አልፎ የተገኙት ሦስቱ ወጣቶች ርዕሶም ገብረእግዚአብሔር፣ ግርማይ ኃብተሚካኤል እና መርሃዊት ሐድጉ የተባሉት ጓደኛሞች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን እድሜያቸው ደግሞ በ20ዎች ውስጥ እንደሆነ ተነግሯል። ሦስቱም ወጣቶች ባለፈው ቅዳሜ መስከረም ሁለት ቀን በጋራ ሲጫወቱ አምሽተው ወደ ቤታቸው እንደገቡ የተገለጸ ሲሆን፤ በማግስቱ እሁድ ከሰዓት ግን በአንደኛው ሟች ቤት ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ታውቋል። በአይደር ክፍለ ከተማ የወንጀል ምርመራ ክፍል ባልደረባ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ገብረማርያም የማነ እንዳሉት የወጣቶቹ ሞት መንስዔ ለማወቅ ፖሊስ መርመራ እያካሄደ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ጨምረውም እስካሁን ባገኘው መረጃ ፖሊስ ለወጣቶቹ ሞት መንስዔ ተብሎ የሚጠረጠር ፍንጭ ያገኘ ቢሆንም፤ በአይደር ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ተደርጎ ውጤት እስኪመጣለት ድረስ እየጠበቀ መሆኑንም መርማሪው ጨምረው ተናግረዋል። የሟች ርዕሶም ገብረእግዚአብሔር ወንድም የሆነው ገብረ መድኅን ገብረእግዚአብሔር ለቢቢሲ እንደተናገረው ወጣቶቹ ተኝተውበት በነበረው ክፍል ውስጥ የነበረው ጄነሬተር ለሞታቸው መንስኤ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል። ገብረመድኅን እንደሚለው ከሆነ ቅዳሜ ዕለት ወጣቶቹ በሚኖሩበት አካባቢ መብራት ጠፍቶ ስለነበር ጄኔሬተሩ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ቢሆንም ማታ ግን ተለኩሶ ስለመቆየቱ መረጃ እንደሌለው ተናግሯል። ህይወታቸው አልፎ የተገኙት ሦስቱ ወጣቶች አስከሬን ወደ አይደር ሆስፒታል ሲወሰዱ ከህልፈታቸው በፊት ከአፋቸው አረፋ ይደፍቁ እንደነበርም ጨምሮ ተናግሯል። የጆስቱ ወጣቶች ድንገተኛ ሞት ዜና በርካታ የመቀለ ከተማ ነዋሪዎችን ያስደነገጠ ሲሆን፤ ለሞታቸው ሰበብ የሆነውን ምክንያት ለማወቅ የህክምናና የፖሊስ የመርመራ ውጤት እየተጠበቀ ነው።
news-50798738
https://www.bbc.com/amharic/news-50798738
ኬንያዊው አትሌት ኪፕቾጌ የዓመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመረጠ
የማራቶኑ ጀግና ኤሉድ ኪፕቾጌ ቢቢሲ በሚያደርገው ምርጫ የአመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በማጠናቀቅ ታሪክ የሰራ የመጀመሪያው ሯጭ መሆን ችሏል። የ35 አመቱ ኬንያዊ በኦስትሪያዋ መዲና ቪየና በተደረገው የማራቶን ወይም የ42.2 ኪሎሜትር ርቀትን በ1 ሰዓት ከ 59 ደቂቃ ከ 40 ሰኮንዶች በመግባት አለምን አስደምሟል። • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች አጠናቀቀ • ኬኒያዊው አትሌት የዓለምን የማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለመሮጥ ዝግጅቱን አጠናቀቀ ይህንንም ውድድር ከማሸነፉ ከስድስት ወራት በፊት የለንደንን ማራቶን ለአራተኛ ጊዜ አሸንፏል። ከሶስት ዓመት በፊት ሪዮ በተደረገው የኦሎምፒክ ውድድር አሸንፎ የነበረው ኪፕቾጌ፤ ለንደን ላይ ባደረገው ውድድርም በሃያ ስምንት ሰኮንዶች የሪዮ ሰአቱን አሻሽሎታል። ለህዝብ ክፍት በነበረው በዚህ የኮከብነት ምርጫም አሜሪካዊቷን የጂምናዝየም ስፖርተኛ ሲሞን ቢሌስ፣ የደቡብ አፍሪካ የራግቢ ተጫዋቹን ሲያ ኮሊሲ፣ የክሪኬት ተጫዋቹን ስቲቭ ስሚዝ፣ አሜሪካዊው ጎልፍ ተጫዋች ታይገር ውድስና አሜሪካዊቷ እግር ኳሰኛ ሜጋን ራፒኖን በመርታት ኪፕቾጌ አሸንፏል። በባለፈው አመት ጣልያናዊው የጎልፍ ተጫዋች ፍራንቸስኮ ሞሊናሪ ማሸነፉ ይታወሳል።
news-49590130
https://www.bbc.com/amharic/news-49590130
ታዋቂ አፍሪካውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ አንሄድም አሉ
ጥቂት የማይባሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ አፍሪያውያን ከዚህ በኋላ እግራቸው ደቡብ አፍሪካን እንደማይረግጥ እየገለጹ ነው። ምከንያታቸው ደግሞ በሰሞኑ ከሌላ አገራት የመጡ አፍሪካውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግድያና ዝርፊያ በመቃወም ነው።
ናይጄሪያውያን ሙዚቀኞች እና የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ውሳኔያቸውን ይፋ ለማድረግ ግንባር ቀደሞች ሆነዋል። • የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት የተፈጸሙትን ጥቃቶች አወገዙ • ደቡብ አፍሪቃዊቷን የቦክስ ቻምፒዮን የገደለው ተያዘ ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ከሆኑ አገራት አንዷ ስትሆን፤ በርካታ አፍሪካውያን ሠርተን እንቀየራለን በማለት ወደ አገሪቷ ያቀናሉ። ይህ ደግሞ ሥራ አጥ ለሆኑ በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን እንደ ትልቅ ስጋት ነው የሚታየው ብለዋል የአገሪቱ የማህበረሰብ ልማት ሚኒስትር። ናይጄሪያዊው ታዋቂ የአፍሮቢት ስልት አቀንቃኝ 'በርና ቦይ' የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ከእንቅልፉ እስከሚነቃ ድረስ ወደ ደቡብ አፍሪካ ድርሽ አልልም ሲል መልእክቱን በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል። ''ከዚህ በፊት እ.አ.አ. በ2017 ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የጥላቻ መልዕክቶችና ጥቃቶችም ደርሰውብኝ ነበር'' ብሏል። ሌላዋ ናይጄሪያዊ ዘፋኝ 'ቲዋ ሳቬጅ' በበኩሏ፤ በያዝነው ወር በደቡብ አፍሪካ ልታዘጋጀው የነበረውን የሙዚቃ ኮንሰርት መሰረዟን በትዊተር ገጿ አስታውቃለች። ''ደቡብ አፍሪካውያን በሕዝቦቼ ላይ እየፈጸሙት ያለው ኢ-ሰብአዊና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊትን እቃወማለሁ'' ብላለች። የናይጄሪያ መንግሥት ደግሞ በደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል። ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዬሚ ኦሲባንጆ ስብሰባውን እንደሚታደሙ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ኬፕ ታውን እንደማይሄዱ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ሞሃመዱ ቡሃሪ ናይጄሪያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳይሄዱ በትዊተር ገጻቸው አስጠንቅቀዋል። በሌላ በኩል የዛምቢያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የፊታችን እሁድ ከደቡብ አፍሪካ ጋር በዋና ከተማዋ ሉሳካ ሊያደርገው አስቦት የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ መሰረዙን አስታውቋል። ''ይህንን የወሰንነው ከደህንነት ስጋት አንጻር ነው። ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማንም ሊያውቅ አይችልም። የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድንን ደህንነት ማረጋገጥ እንፈልጋለን'' ብለዋል የፌደሬሽኑ ዋና ጸሃፊ አድሪያን ካሻላ። • ትሬቨር ኖዋ የዓለማችን አራተኛው ቱጃር ቀልደኛ ሆነ • እራስን ለማጥፋት ከማሰብ ወደ ሚሊየነርነት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ፤ አገራችን የሁሉም አፍሪካውያን ቤት ናት የሚል መልዕክት ቢያስተላልፉም፤ የአገሬው ሰው ሊሰማቸው ፍቃደኛ የሆነ አይመስልም። ብዙዎች አሁንም በንግድ ሥራ የተሰማሩ የሌሎች አገራት ዜጎች ከደቡብ አፍሪካ ይውጡልን እያሉ ነው። በናይጄሪያ ደግሞ የደቡብ አፍሪካውያን የሆኑ ድርጅቶች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። 'ሾፕራይት' የተባለው ታዋቂ ደቡብ አፍሪካ መደብር ናይጄሪያ ውስጥ ጥቃት ተፈጽሞበታል። የአገሪቱ ፖሊስም ሁኔታውን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ ለመጠቀም ተገዷል። 'ኤምቲኤን' የተባለው የደቡብ አፍሪካ የቴሌኮም ድርጅትም በናይጄሪያ የሚገኙ ሁሉንም ሱቆቹን እየዘጋ እንደሆነ አስታውቋል። በደቡብ አፍሪካ ቢያንስ አምስት ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ የገለጸ ሲሆን፤ ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ ደቡብ አፍሪካውያን መሆናቸውን አረጋግጫለው ብሏል። የቀሪዎቹ ዜግነት ግን እስካሁን አልታወቀም ተብሏል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ እስካሁን 189 ሰዎች በቁጥጥር ውለዋል።
news-54136782
https://www.bbc.com/amharic/news-54136782
ኮሮናቫይረስ፡ ቱርካዊቷ መምህርት ኢንተርኔት ለሌላቸው ተማሪዎች በየቤታቸው እየሄደች ማስተማር ጀመረች
የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አገራት በርካታ መመሪያዎችን አውጥተዋል።
Gamze Arslan teaches villages beyond the internet's reach ከነዚህም መካከል እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ መገደብና ትምህርት ቤቶችን መዝጋት ይገኙበታል። በበርካታ ከተሞች በተለይ አቅማቸው የተጠናከሩ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ትምህርት እንዳያመልጣቸው በማለት በበይነ መረብ የሚሰጠውን ትምህርት እንዲከታተሉ አድርገዋል። አቅሙ ወይም አቅርቦቱ የሌላቸውስ? በምስራቃዊ ቱርክ በምትገኘው ቫን ግዛት የምትገኝ ጋምዜ አርስላን የተባለች መምህርት በበይነ መረብ ትምህርታቸውን መከታተል ለማይችሉ ተማሪዎች ቤት ለቤት እየዞረች ትምህርት ትሰጣለች። "በትምህርት ቤታችን ውስጥ ኢንተርኔት አለ ነገር ግን በዚያ ማስተማር እልቻልንም። ምክንያቱም በርካታ ወላጆች በቤት ውስጥ ኢንተርኔት የላቸውም" በማለት ሃበርቱርክ ለተባለው የዜና ወኪል ተናግራለች። "ነጭ ሰሌዳዬን ይዤ ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት እየሄድኩ አስተምራለሁ" በማለት የምትናገረው ጋምዜ በቫን ቱስባ ግዛት ውስጥ ያሉ መንደሮችንም ማካለል አለባት። በየቀኑም ማስተማር፣ የቤት ስራቸውን በአግባቡ ሰርተው እንደሆነ መቆጣጠርና መከታተል ከዚያም በተጨማሪ አካላዊ ርቀታቸውንና ንፅህናቸውን በጠበቀ መልኩ የመማር የማስተማር ሂደቱ እንዲከናወንም ዋናው ኃላፊነት የሷ ነው። የጋምዜ መልካም ተግባር ከተሰማ በኋላ በርካቶች እያሞገሷትና እያወደሷት ይገኛሉ። የተለያዩ ሚዲያ ቀልብንም መሳብ ችላለች። "ኢንተርኔት ላይኖር ይችላል ግን መምህርት ጋምዜ አለች" በሚልም በአንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ፕሮግራም ተሰርቶላት ነበር። የአካባቢው ባለስልጣናት ቢሆን ምስጋና ችረዋታል። "ግዛታችን እንዲህ ባለ ፈታኝ ወቅትና አቅመ ቢስነት በተሰማን ወቅት እንዲህ አይነት አማራጭ በመኖሩ ደስተኛ ነን " በማለት የቱስባ የትምህርት ዳይሬክተር መህመት ባኪር ቤድቪዮግሩ ለሃበርተርክ ተናግረዋል። "ይህ ተግባሯ እንደ መስዋዕትነት በተምሳሌትነት የምናየው ነው። እንዲህ አይነት ሳይሰስቱ መስጠትን ልምድ እንድናዳብር ምሳሌ ይሆነናል" ብለዋል። በርካታ የአውሮፓ አገራት ትምህርት ቤቶችን ቢከፍቱም ቱርክ ግን በተወሰነ መልኩ ለመክፈት ከአንድ ወር በኋላ አቅዳለች። ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሚዲያዎች ለወራት ያህል ተማሪዎች የኢንተርኔት አቅርቦት ስለሌላቸው ችግር እያጋጠማቸው ነው በማለትም ሲተቹ ነበር።
news-56398434
https://www.bbc.com/amharic/news-56398434
ፊልም፡ አቫተር ከ12 ዓመት በኋላ ከፊልሞች ሁሉ የላቀ ገቢ አገኘ
ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ገቢን ያስገኘው አቫተር ፣ ቻይና ውስጥ በድጋሚ እንዲታይ በመደረጉ ከየትኛውም ፊልም በላይ ከፍተኛ ገቢ ያስገኘ ፊልም በመሆን መሪነቱን ያዘ።
ተዋናይት ሱዛን ዊቨር እና የአቫተር ዳይክተር ጄምስ ካሜሩን የሳንይንስ ልቦለድ ፊልም የሆነው አቫተር ከ10 ዓመት በፊት ለዕይታ የበቃ ሲሆን፣ ከሁለት ዓመት በፊት 'አቬንጀርስ፡ ኢንድጌም' የተባለው ሲኒማ ቦታውን እስኪረከበው ድረስ በዓለም አቀፉ የቦክስ ኦፊስ ሰንጠረዥ ላይ የመሪነቱን ቦታ ይዞ ለዓመታት ቆይቷል። አቫተር የዓለማችን ከፍተኛ የሲኒማ ተመልካች ገበያ ባለባት ቻይና ውስጥ በድጋሚ እንዲታይ ከተደረገ በኋላ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ ሽያጩ ከ2.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ከተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ጋር ተያይዞ ቻይና በፊልሙ ዘርፍ ከፍተኛ ገበያ ያለባት አገር ሆናለች። "እዚህ ደረጃ ላይ በመድረሳችን ኩራት ይሰማናል። ነገር ግን እኔና ጄምስ ካሜሩን የበለጠ የተደሰትነው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አቫተር በድጋሚ በሲኒማ ቤቶች ለዕይታ በመብቃቱ ነው። ለዚህም ቻይናውያን አድናቂዎቻቸንን ማመስገን እንፈልጋለን" ሲል የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ጆን ላንዱ ተናግሯል። በቻይና በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ ከተነሳ በኋላ ሲኒማ ቤቶች ተከፍተው ሥራ ከጀመሩ ወራት ተቆጥረዋል። በዚህ ጊዜ የአገር ውስጥ ፊልሞችም ከፍተኛ ሽያጭን ማስመዝገብ ችለዋል። 'አቫተር' ቻይና ውስጥ በድጋሚ እንዲታይ ከመደረጉ በፊት አሜሪካ ውስጥ 760 ሚሊዮን ዶላር ሲያስገኝ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ አስገኝቶ ነበር። ዋልት ዲዝኒ ባወጣው መረጃ መሰረት በጄምስ ካሜሩን ዳይሬክት የተደረገው አቫተር ባለፈው ቅዳሜ ብቻ 4 ሚሊዮን ዶላሮችን በማስገባት 'ኢንድጌም' ከተሰኘው ፊልም ቀዳሚ ለመሆን ችሏል። የአቫተርና ኢንድጌም ፊልሞች ባለቤት የሆነው ዲዝኒ ከፍተኛ ገቢን በማስገኘት በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የታይታኒክ ፊልም ባለቤት ነው። ጄምስ ካሜሩን በአሁኑ ጊዜ የአቫተር ተከታይ የሆነውን ፊልም በመስራት ላይ ሲሆን፤ በተከታታይ የሚወጣበት ጊዜ እንዲዘገይ ሲደረግ የነበረው ቀጣይ ፊልሙ ከዓመት በኋላ ወደ ሕዝብ ይደርሳል ተብሏል።
54807197
https://www.bbc.com/amharic/54807197
በትግራይና በፌደራል መንግሥት መካከል ስላለው ግጭት እስካሁን የምናውቀው
በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግሥት መካከል የነበረው መካረር ትላንት ምሽት ወደ ግጭት አምርቷል።
ትናንት ሌሊት (ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ. ም) ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ በመቀሌና አስራ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኩዊሃ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር የቢቢሲ ዘጋቢ ከስፍራው አድርሷል። ቀጣዮቹ እስካሁን የምናውቃቸው ነጥቦች ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የሰጡት መግለጫ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ዛሬ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው የአገር መከላከያ ሠራዊት በሕወሓት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ መሰጠቱን ተናግረዋል። "ሕወሓት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል" ብለዋል። "ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ አገር ሠራዊት ቆጥሮ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል" ብለዋል። አክለውም "የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ አገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል" በማለት ገልፀዋል። የስልክ፣ ኢንተርኔት እና በረራ መቋረጥ በትግራይ ክልል ከትናንት ሌሊት ጀምሮ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት መቋረጡ ተገልጿል። በኢንተርኔት ነፃነት ላይ የሚሰራው ኔት ብሎክስ የተሰኘው ድርጅትም፤ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት መቋረጡን አስታውቋል። ወደ መቀለ እና ጎንደር የሚደረጉ በረራዎች መቋረጣቸውም ታውቋል። ቢቢሲ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ ገጽ ላይ ወደ ሁለቱ ከተሞች የሚካሄድ በረራ እንደሌለ ተመልክቷል። የትግራይ ክልል በሰጠው መግለጫም ወደ ክልሉ ማንኛውም በረራ እንደማይካሄድ አስታውቋል። የአማራ ክልል ምን አለ? የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ትናንት ምሽት 4፡30 ጀምሮ በአጠቃላይ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሠራዊት ካምፖች፣ ዴፖዎች፣ እና የተለያዩ መሰረተ ልማት ባሉባቸው አካባቢዎች ላይ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ፣ የተቀናጀ ጥቃት ማድረስ መጀመሩን በዛሬው ዕለት ለአማራ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል በክልሉ የሚገኘው የመከላከያ ኃይል አዛዦች እንዳይንቀሳቀስ ከማድረግ ጀምሮ አሁን ደግሞ ወደጥቃት መሸጋገሩን ተናግረዋል። ሠራዊቱ ያለውን ትጥቅ ወደ መቀማት ሄዶ እንደነበርም አቶ ተመስገን አስታውቀዋል። አቶ ተመስገን አክለውም በአማራ ክልልም ሶሮቃ እና ቅራቅር በሚባሉ አካባቢዎች የጥቃት ሙከራ ማድረጉንና በክልሉ ልዩ ኃይል መመከቱን ተናግረዋል። የትግራይ ክልል የሰጠው መግለጫ የትግራይ ክልል ዛሬ ባወጣው መግለጫ በክልሉ የሚገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሰራዊት አባላትና አዛዦች ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን ለመሰለፍ መወሰናቸውን አሳውቋል። የትግራይ ክልል መንግሥት የተፈጠሩት የፖለቲካ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም የተሰጠው "እንደ ሕዝብ ቅጣት ነው" በማለትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰሜን ዕዝ ሰራዊትና አባላት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጎን በመቆም አብረው መታገል መጀመራቸውን ገልጿል። መግለጫው ከዛሬዋ እለት ጀምሮ ጥቅትም 25/ 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ውስጥና ድንበር አካባቢ ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ የተከለከለ እንደሆነ ያትታል። በተጨማሪም ወደ ትግራይ ክልል የሚደረግ ማንኛውም በረራ እንዳማይኖር የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል። ይህንን ውሳኔ በመጣስ በሕዝብ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚወሰድ እርምጃ ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።። ለሌሎች የሰራዊት አባላት እና አዛዦችም ከሰሜን እዝ ሰራዊትና አዛዦች ጎን በመቆም ታሪካዊ ኃላፊነታቸውነ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል። በትግራይ ውስጥ ማንኛውም የትራንስፖርት አገልግሎትም እንደማይኖር በተጨማሪ ተገልጿል። የፌደራል ፖሊስ የሰጠው ጥቆማ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ አስር ክፍለ ከተሞች የጸጥታ ችግርም ሆነ ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ በተመለከተ መረጃ መስጠት የሚቻልባቸው ስልክ ቁጥሮች አስታውቋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ለስድስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። ምክር ቤቱ ዛሬ፣ ጥቅምት 25/2013 ባደረገው አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ መንግሥት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93/1/ሀ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን አስታውቋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት መግለጫ አክሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት ተፈጻሚ እንደሚሆን አስታውቆ ይህንን አዋጅ የሚያስፈፅም በኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሰብሳቢነት የሚመራና አግባብነት ካላቸው አካላት የተወጣጡ አባላት ያሉት ግብረኃይል መቋቋሙን ገልጿል። ግብረኃ ይሉ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረሀይል" ተብሎ ይጠራልም ተብሏል። ዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ ማራዘማቸው በአገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የተማሪዎችን ቅበላን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመዋል። ተማሪዎችን ላልተወሰነ ጊዜ እንደማይቀበሉ ካስታወቁት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አምቦ፣ ባህር ዳር ፣ ደብረ ማርቆስና ወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች ተጠቃሽ ናቸው።
news-55105407
https://www.bbc.com/amharic/news-55105407
ከማራዶና አስከሬን ጋር ፎቶ የተነሱ የቀብር ሠራተኞች ጉዳይ ቁጣን ቀሰቀሰ
ከሰሞኑ ህይወቱ ያለፈውን ድንቁን እግርኳስ ተጫዋች ዲያጎ ማራዶና የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ሊያስፈፅሙ የተቀጠሩ ሠራተኞች ከአስከሬኑ ጋር ፎቶ በመነሳታቸው ውግዘት እያስተናገዱ ነው።
ረቡዕ ኅዳር 16/ 2013 ዓ.ም ህይወቱ ያለፈው የማራዶናን የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማስፈፀም ኃላፊነቱን በዋነኝነት የወሰደው ድርጅት ለሥራው የቀጠራቸው ሦስት ግለሰቦች ናቸው ፎቶ ሲነሱ የሚታዩት። ለሕዝብ ይፋ በሆኑት ሁለት ፎቶዎች ላይ ግለሰቦቹ የሬሳ ሳጥኑ ክፍት ሆኖ እየሳቁና፣ እጃቸውንም ከፍ አድርገው የአውራ ጣታቸውን ምልክት ያሳዩበታልም ተብሏል። ፎቶዎቹም ከፍተኛ ውግዘትና ቁጣን ቀስቅሷል። የማራዶና ተወካይና ጠበቃ ማቲያስ ሞርላ በበኩላቸው አፀያፊ ነገር እንደተከናወነ ጠቅሰው፤ ፎቶውን ያወጡት አካላት በሕግ አግባብ እጠይቃለሁ ብለዋል። "ለጓደኛዬ ትዝታ ስል ይህንን የጭካኔ ተግባር የፈፀመውን ሳልፋረዳው አልተኛም" በማለት ሞርላ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። በቦነስ አይረስ ሴፒሎስ ፒኒየር የቀብር አስፈፃሚ ሥራ አስኪያጅ ማቲያስ ፒኮን ለአገሪቱ ሚዲያ እንደተናገሩት በፎቶው ላይ የሚታዩት ሦስት ሰዎች የሬሳ ሳጥኑን ለማንቀሳቀስ ረዳት አድርገው የተቀጠሩ ናቸው ብለዋል። "በተፈጠረው ነገር በጣም ነው ያዘንነው" በማለት ማቲያስ ፒኮን ለኒውስ ቻናል ተናግረዋል። "ቤተሰቡ እኛን አምኖ ነበር፤ ከቤተሰቡም ጋር ለረዥም ጊዜ አብረን ሰርተናል" ብለዋል። ማቲያስ ፒኮን እንዳሉት ኩባንያቸው ከዚህ ቀደምም ለማራዶና ቤተሰቦች የቀብር ሥነ ሥርዓት እንዳዘጋጁም ገልፀዋል። "ቤተሰቦቹ በእኛ ሥራ ይተማመናሉ፤ ለዚያም ነው ይህ ተግባር ልባችንን የሰበረው" በማለት ተናግረዋል። አክለውም "የ75 ዓመቱ አባቴ እያለቀሰ ነው፣ እኔም እያለቀስኩ ነው ወንድሜም እንዲሁ። በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶናል" በማለት ተናግረዋል። የማራዶና የቀድሞ ባለቤት ክላውዲያ ቪላፋኔን ስለፎቶዎቹ ሲነገራት በጣም ተበሳጭታ እንደነበረም ማቲያስ ገልፀዋል። የማራዶና ቤተሰቦች ሕጋዊ እርምጃ ይውሰዱ ማቲያስ ባያውቁም፤ ሆኖም እስካሁን ድረስ ከፎቶዎቹ ጋር ተያይዞ ወንጀል ሪፖርት እንዳልተደረገ ቴላም የተባለ የዜና ወኪል የፍትህ አካላትን ምንጭ አድርጎ ዘግቧል። ማራዶና በትናትንናው ዕለት የተቀበረ ሲሆን ህልፈተ ህይወቱንም ተከትሎ የሦስት ቀን ሐዘን በአገሪቱ ታውጇል። የሬሳ ሳጥኑ በአርጀንቲና ሰንደቅ አላማ እንዲሁም እግር ኳስ ሲጫወት መለያው በነበረው አስር ቁጥር ማልያ ተሸፍኖ በቦነስ አይረስ የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ሕዝቡ እንዲሰናበተው ተደርጓል። በሺህዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹም የእግር ኳስ ጀግናቸውን ለመሰናበት መጥተው ነበር፤ ሆኖም ፖሊስና በሰልፍ ላይ የነበሩ ለቀስተኞች መጋጨታቸውን ተከትሎ የስንብት ፕሮግራሙ በአጭር ተቋጭቷል። በበርካቶች ዘንድ የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ የሚወደሰው ማራዶና በልብ ህመም ቦነስ አይረስ አቅራቢያ በምትገኘው ትግሬ ከተማ በቤቱ ውስጥ ነው ህይወቱ ያለፈው።
news-50668951
https://www.bbc.com/amharic/news-50668951
ገንዘብ ያለው ሊገዛው የሚችለው 'ወርቃማው' ፓስፖርት ለምን ተፈላጊ ሆነ?
የአውሮፓ ሕብረት ተልዕኮ አባላት በማልታ ያለውን የሕግ የበላይነት ለመመርመር ጉብኝት እያደረገ ሲሆን የታዋቂዋ የምርመራ ጋዜጠኛ መገደልም አገሪቱን ጫና ውስጥ ከቷታል።
በፈረንጆቹ 2017 የተፈጸመው የጋዜጠኛ ዳፊን ካሩዋና ጋሊዚያ ግድያ የማልታን ፖለቲካዊ መዋቅር ያፍረከረከና በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው የሚሉም አልጠፉም። ከዚህ በተጨማሪ 'ወርቃማ ፓስፖርት' ሥርዓት የሚባለው የሌላ አገር ዜጎች ከፍተኛ ገንዘብ በማፍሰስ የማልታን ዜግነት ሲገዙ ተስተውሏል። ይህም ለግለሰቦቹ ከግብር ማምለጫና ፖለቲካዊ ሽሽት ለሚያደርጉ ሰዎች ጥሩ መሸሸጊያ እንዲሆን በሩን ከፍቷል። ለመሆኑ የማልታን ዜግነት ለመግዛት ምን ያክል ገንዘብ ያስከፍላል? ይህንን አሰራር የማልታ መንግሥት ያስተዋወቀው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 ሲሆን ባለሃብቶችንና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ነው ያዘጋጀሁት ይላል። በዚህ አንድ ግለሰብ የማልታን ፓስፖርት ለማግኘት የሚከተሉትን ማድረግ አለበት፡ እነዚህ ሁሉ ወጪዎች ሲደመሩ ከ 1.1 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ወጪን ይጠይቃል ማለት ነው። በተጨማሪም አመልካቾች በማልታ ቢያንስ የ12 ወራት የኑሮ ፈቃድ ማግኘት ያለባቸው ሲሆን ነገር ግን በሀገሪቱ መኖር አይጠበቅባቸውም። የማልታ መንግሥት ይህንን አሰራር ካስታወቀ በኋላ 833 ባለሀብቶችና 2109 የቤተሰብ አባላት የማልታ ዜግነትን ማግኘት ችለዋል። ማንኛውም የማልታ ፓስፖርት የያዘ ሰው ደግሞ በመላው አውሮፓ እንደልቡ መንቀሳቀስ ይችላል። በአውሮፓዊያኑ 2017 እና 2018 ግማሽ ድረስ ማልታ ለውጭ አገራት ዜጎች ከሸጠችው ፓስፖርት ከ162 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ማግኘት የቻለች ሲሆን ይህም ከአገሪቱ ዓመታዊ አጠቃላይ ምርት 1.38 የሚሆነውን ሸፍኗል። ምንም እንኳን የማልታ መንግሥት ከየትኞቹ አገራት የሚመጡ ሰዎች ፓስፖርቶችን እንደሚገዙ ግልጽ ባያደርግም አገራቱ የሚገኙባቸውን አካባቢዎች ግን አስቀምጧል። በዚህም መሰረት አብዛኛዎቹ ፓስፖርት የገዙት ሰዎች የመጡት በቀዳሚነት ከአውሮፓ ሲሆን በመቀጠል ከመካከለኛው ምሥራቅና እሲያ ተቀምጠዋል። ነገር ግን የአውሮፓ ሕብረት በየዓመቱ የሚደረጉ የዜግነት ጥያቄዎችን ለህዝብ ይፋ የማድረግ ግዴታ አለበት። ማልታ ይህንን ሥርዓት ይፋ ካደረገች ወዲህ በርካታ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከሩሲያ እና ከቻይና የመጡ ግለሰቦች ዜግነት ገዝተዋል። ለምሳሌ ሳዑዲ አረቢያ በአውሮፓዊያኑ እስከ 2015 ድረስ የትኛውም ዜጋዋ የማልታ ፓስፖርት ገዝቶ አያውቅም ነበር። ከ2015 በኋላ ግን 400 ሳዑዲዎች ወርቃማውን የማልታ ፓስፖርት ገንዘባቸውን ፈሰስ አድርገው ገዝተዋል። ይህንን ሥርዓት በመጠቀም በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸው የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ በማሰብና ባሉበት አገር ችግር ሲያጋጥማቸው በማንኛውም ሰዓት ወደ ሁለተኛ አገራችው እንዲሄዱ በማሰብ ጥሪታቸውን እያሟጠጡ ወርቃማውን የማልታ ፓስፖርት እየገዙ ነው። በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ቆጵሮስ እና ቡልጋሪያ ተመሳሳይ ሥርዓት አላቸው። በአውሮፓዊያኑ ከ2008 እስከ 2018 ድረስ ቆጵሮስ ለ1685 ኢንቨስተሮችና ለ1651 የቤተሰብ አባላት ዜግነት እንደሰጠች ታውቋል።
news-45469059
https://www.bbc.com/amharic/news-45469059
በደቡብ ሱዳን አውሮፕላን ተከስክሶ '19 ሰዎች ሞቱ'
በደቡብ ሱዳን አንድ አነስተኛ አውሮፕላን በደመናማ የአየር ሁኔታው ውስጥ ለማረፍ ስትሞክር ሃይቅ ላይ ተከስክሳ 19 ሰዎች ሞቱ።
ከአደጋው አራት ሰዎች ብቻ የተረፉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሁለቱ ህጻናት መሆናቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ከሟቾቹ መካከል ዋና እና ምክትል አብራሪ እንዲሁም የቀይ መስቀል ባልደረባ እንደሚገኙበት የአካባቢው ባለስልጣናት ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። • 40 ታጣቂዎች በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተያዙ 23 ሰዎችን አሳፍራ የነበረችው አውሮፕላን እሁድ ዕለት ከደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ ዪሮል ወደሚባል ሥፍራ እያመራች ነበር። ''ዪሮል ስትደርስ የአየር ጸባዩ ደመናማ ነበር። ለማረፍ ስትሞክር ዪሮል ሃይቅ ላይ ተከሰከሰች'' ሲሉ የቀጠናው የመንግሥት ባለስልጣን አቤል አጉኤክ ተናግረዋል። • ከነመንገደኞቹ የጠፋው አውሮፕላን ሳይገኝ ቀረ ''ሙሉ የከተማው ህዝብ ተደናግጧል፤ ሱቆች በሙሉ ዝግ ናቸው። ወዳጅ ዘመዶች የተጎጂዎችን አስክሬን ተረክበዋል። የተከሰከሰው የንግድ አውሮፕላን ነው'' በማለት አቤል አክለዋል። አውሮፕላኗ ስትከሰከስ በአካባቢው የነበሩ አሳ አስጋሪዎች በታንኳ በመታገዝ ከአደጋው ህይወታቸው የተረፉትን ለማደን ሲጥሩ ታይተዋል። • ሰባኪው አውሮፕላን ግዙልኝ አለ
news-54387277
https://www.bbc.com/amharic/news-54387277
ኮሮናቫይረስ፡ ወረርሽኝ የወለደው የአውሮፓ የብስክሌት አብዮት
ከቡካሬስት እስከ ብራሰልስ፣ ከለንደን እስከ ሊዝበን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በመላው አውሮፓ በብስክሌቶች ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ብስክሌትን የመጠቀምን ባህልን በእጅጉ ከፍ አድርጎታል።
ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ ብቻ በአውሮፓ ብስክሌቶች እና የብስክሌት መሰረተ ልማት ላይ አንድ ቢሊየን ዩሮ ወጪ የተደረገ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበረው በተጨማሪ 2300 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድም ተገንብቷል። ''በዚህ የወረርሽኝ ወቅት ከቦታ ለቦታ ለመንቀሳቀስ ብስክሌት መጋለብ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ብቅ ብሏል'' ይላሉ መቀመጫውን ብራሰልስ ካደረገው የአውሮፓ የሳይክል ፌደሬሽን የመጡት ጂል ዋረን። ''ይህ ወረርሽኝ የብስክሌት ዘርፍ ምን ያክል ሊጓዝ እንደሚችልና ሕይወታችንን እንዴት መቃኘት እንዳለብን አሳይቶናል'' ይላሉ። ለመሆኑ ለብስክሌት እና የብስክሌት መሰረተ ልማት ምን ያክል ወጪ ሆነ? ''ከዚህ በፊት ተጨማሪ የብስክሌት መንገዶችን ለመገንባት ሞክረን ነበር፤ ነገር ግን መኪና አሽከርካሪዎች ሃሳቡን በመቃወማቸው ተውነው'' ይላሉ የጣልያኗ ሚላን ከተማ ምክትል ከንቲባ ፒዬርፍራንሴስኮ ማራን። በሰሜናዊ ጣልያን የምትገኘው የፋሽን ኢንዱስትሪ ማዕከሏ ሚላን ሰዎች በቀላሉ እንዲንቀሳቀሱ ለማገዝ ብስክሌት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ከጀመሩ የአውሮፓ ከተሞች መካከል የመጀመሪያዎቹ ውስጥ ትጠቀሳለች። አዲስ 35 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ ብትገነባም አብዛኛዎቹ መንገዶች ግን ጊዜያዊ ናቸው። ''በአሁኑ ሰአት ብስክሌት የሚጠቀሙ ሰዎች ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሕዝብ ትራንስፖርት ነበር የሚጠቀሙት። ነገር ግን አሁን ላይ ሌላ አማራጭ አስፈልጓቸዋል። ከኮቪድ-19 በፊት በከተማችን ዋና የግብይት ጎዳናዎች ላይ 1 ሺግ ገደማ ሳይክል የሚጋልቡ ሰዎች የነበሩ ሲሆን አሁን ግን ቁጥሩ ወደ 7 ሺህ ከፍ ብሏል"። በዚህ የጣልያን ክፍል ውስጥ መንግሥት የብስክሌት ዘርፉን ለማበረታታት በማሰብ 115 ሚሊየን ዩሮ ፈሰስ ያደረገ ሲሆን ሳይክል መግዛት ለሚፈልጉ ዜጎች ደግሞ እስከ 500 ዩሮ ድረስ የዋጋ ቅናሽ እንደሚያደርግ አስታውቋል። በፈረንሳ መዲና ፓሪስ ደግሞ ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ከብስክሌት ጋር ለተያያዙ መሰረተ ልማቶች እስከ 20 ሚሊየን ዩሮ ድረስ ወጪ ተደርጓል። በፈረንሳይ ከዚህ በተጨማሪ የብስክሌት ተጠቃሚዎች ቁጥር በ27 መቶ ከፍ ብሏል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ምክንያቱ የፈረንሳይ መንግሥት ዜጎች ብስክሌታቸውን ለማሳደስ ሲፈልጉ የ50 ዩሮ ድጎማ ማድረግ በመጀመሩ ነው ተብሏል። በአምስተርዳም ደግሞ ከወረርሽኙ በፊት ለብስክሌት የሚሆን መሰረተ ልማት በአግባቡ ተዘርግቶ ነበር። የኔዘርላንዷ ዋና ከተማ በብስክሌተኞች የምትታወቅ ሲሆን 767 ኪሎ ሜትር እርዝማኔ ያለው የብስክሌት መንገድም አላት። በኔዘርላንድ በአሁኑ ወቅት በጣም እየተቸበቸበ የሚገኘው የብስክሌት አይነት በኤሌክትሪክ የሚሰራው ነው። በተጨማሪም በብስክሌት እቃዎችና ምግቦችን ወደ ሰዎች ቤት የማድረስ ስራ 53 በመቶ ጨምሯል በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ዘመን። በአሁኑ ሰአት በርካታ ከተሞች ወደፊት ምን ሊፈጠር እንመዲችል ባለማወቃቸው ከዚህ በኋላ ስለሚኖሩ የእንቅስቃሴ አይነቶች ቆም ብለው እያሰቡ ነው። ወረርሽኙም ሕይወት ምን ሊመስል እንደሚችል በትንሹም ቢሆን አሳይቷል። አሁን ባለው አካሄድ ደግሞ ብስክሌትን እንደ አማራጭ የትራንስፖርት ዘዴ መጠቀም ስኬታማነቱ ታይቷል። ነገር ግን በበርካታ የአውሮፓ ከተሞች ዋናው ጥያቄ ብስክሌትን በቋሚነት መጠቀም አለብን ወይስ የለብንም የሚለው ሆኗል።
news-55690052
https://www.bbc.com/amharic/news-55690052
ትግራይ ፡ የነዋሪዎችና የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ ወደ ሰብአዊ ቀውስ ሊያመራ ይችላል፡ ኢሰመኮ
ጦርነት በተካሄደባቸው የትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ደኅንነትና ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰብአዊ ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ።
ኮሚሽኑ ይህንን ያለው ወደ ትግራይ ክልልና አንዳንድ የአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በመጓዝ የችግሩ ተጠቂዎች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር አገኘሁት ባለው መረጃ በመመስረት ባወጠው ሪፖርት ላይ ነው። ኢሰመኮ በተመለከታቸው በዳንሻ፣ በሁመራ፣ በቢሶበርና በኡላጋ የተካሄደው ጦርነት የሠላማዊ ሰዎች ሞትና አካላዊ ጉዳት፣ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎች ዝርፊያና የተለያዩ ጉዳቶች አስከትሏል። በዚህም በቢሶበርና በኡላጋ 31 ሠላማዊ ሰዎች ሲሞቱ፤ 104 መኖሪያ ቤቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሲቃጠሉ የአካባቢው ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። በተጨማሪም በመሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት የደረሰ ሲሆን የኤሌክትሪክ፣ የውሃና የመሳሰሉ አገልግሎቶች መልሰው ሥራ አለመጀመራቸው በነዋሪዎችና በተፈናቃናዮች ላይ የበለጠ ሰብአዊ ቀውስ እንዳያስከትል የሚያሰጋ ነው። በተመሳሳይ መልኩ በሁመራና በዳንሻ የሠላማዊ ነዋሪዎች ንብረት የሆኑ የመኖሪያና ንግድ ቤቶችን ጨምሮ የአካባቢው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ውድመትና ዝርፊያ መፈጸሙን ኮሚሽኑ ገልጿል። "ሠላማዊ ነዋሪዎች በብሔራቸው ምክንያት ወይም በአካባቢዎቹ የፀጥታ መጓደል ምክንያት ለደኅንነታቸው እንደሚሰጉ" ለኮሚሽኑ ገልጸዋል። "በአጠቃላይ በእነዚህ አራት ከተሞች ያለው የፀጥታ ስጋትና የፍትሕ አካላት ወደ መደበኛ ሥራቸው አለመመለስ፣ የሰዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅና የሰብአዊ መብቶቻቸውን ጥበቃ ለማረጋገጥ አዳጋች አድርጎታል" ብሏል ኢሰመኮ። "በአካባቢዎቹ ያለው የፀጥታ ሁኔታ፣ የነዋሪዎቹንም ሆነ ከትግራይ ክልል ወደ አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎችን የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት እንዲጨምርና የመቋቋም አቅማቸውን በአስከፊ ሁኔታ እንዲፈተን አድርጓል" ሲሉ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ኮሚሽነሩ ጨምረውም የችግሩ ተጎጂዎች በቂ ያልሆነ ወይም ምንም እርዳታ እንዳላገኙ ገልጸው "በአካባቢዎቹና በሠላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ጉዳት ከሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛና አፋጣኝ ርብርብ የሚጠይቅ ነው" በማለት ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሁን በተወሰኑ አካባቢዎች ካደረጋቸው ምልከታዎች በተጨማሪ ለመስክ ምልከታ ወደ መቀለ ከተማና ወደ ሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች በመንቀሳቀስ፣ በግጭቱ ምክንያት የተፈጠረውን የሰብአዊ ቀውስና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች በመመርመር ላይ እንደሚገኝና ሥራው ሲጠናቀቅ ተጨማሪ ሪፖርት እንደሚያወጣ ገልጿል። በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በርካታ ሰዎች ለአካል ጉዳትና ለመፈናቀል የተዳረጉ መሆናቸው ቢገለጽም ትክክለኛው አሃዝን በተመለከተ የሚታወቅ ነገር የለም። በግጭቱ የመጀመሪያ ሰሞን ከ50 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን መሰደዳቸው የተነገረ ሲሆን፤ በአገር ውስጥ ተፈናቅለው የሚገኙ ሰዎች ደግሞ ከዚህ በብዙ ሺህ እንደሚበልጥ የተራድኦ ድርጅቶች ይገምታሉ። በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ባለው ጊዜ ውስጥ የሰብአዊ እርዳታ በአስፈላጊው መጠን መቅረብ ካልቻለ የረሃብ አደጋና የከፋ ችግር ሊከሰት እንደሚችል እየተነገረ ሲሆን፤ መንግሥትና እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በአፋጣኝ የሰብአዊ እርዳታ እንዲያቀርቡ ጥሪ እየቀረበላቸው ነው። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም በሪፖርቱ በዳሰሳቸው አካባቢዎች ያለው የነዋሪዎች ሁኔታ ወደ ሰብአዊ ቀውስ ሊያመራ ስለሚችል የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቋል። በተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውና የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሚለው በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል።
news-52411348
https://www.bbc.com/amharic/news-52411348
ኮሮናቫይረስ፡ በርካታ ሰዎች ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እየተሻገሩ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል
በርካታ ሰዎች በኮረናቫይረስ ከተያዙባት ጎረቤት አገር ጂቡቲ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ፤ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የአፋርና አማራ ክልሎች ጥረት እያደረጉ መሆኑን አመለከቱ።
ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የጭነት መኪናዎች ጸረ ተዋህሲያን ይረጫሉ የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ያሲን ሙስጠፋ ለቢቢሲ፤ "ከጅቡቲ ከበሽታው የሚሸሹ እንዲሁም ጾም ስለሆነ ሙቀቱን ለማሳለፍ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ በርካታ ሰዎች አሉ" ብለዋል። መንግሥት የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመቆጣጠር በድንበሮች በኩል የሰዎች እንቅስቃሴን ቢያግድም ከጂቡቲ "የሚገቡት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ይላሉ ኃላፊው። አንድ ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ያላት ጂቡቲ አንድ ሺህ የሚጠጉ በበሽታው የተያዙ ሰዎችን በግዛቷ ውስጥ ማግኘቷን ተከትሎ ድንበር እየተሻገሩ በሚገቡ ሰዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ መጀመሩ ተገልጿል። ከጅቡቲ በአፋር ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡ አስራ አምስት የመግቢያ በሮች ሲኖሩ ሦስቱ ዋና የሚባሉ መሆናቸውን ያመለከቱት ኃላፊው በሁሉም ላይ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከአፋር ክልል ጋር ወደሚዋሰነው የአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከጅቡቲ በኩል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የዞኑ የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሊድ ሙስጠፋም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት ሰዎቹ በእግር ድንበር ተሻግረው የሚገቡባቸው የተለያዩ ቦታዎች መኖራቸውን አመልክተው "አንዱ ባቲ ወረዳ ነው። ባቲ ላይ አቢላል የሚባል ቦታ በተለይ በእግርና በመኪና ሰዎች ስለሚገቡ የሙቀት ልኬት ጀምረናል" ሲሉ የበሽታው ምልክቶችን ለመለየት እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ ካሉት ሰባት ወረዳዎች አምስቱ ከአፋር ክልል ጋር ስለሚዋሰኑ "ከጅቡቲ በአፋር በኩል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በርካታ በመሆኑ አራቱ ወረዳዎች ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ የስጋት ቀጠና ናቸው በሚል ተለይተዋል" ሲሉ የዞኑ ጤና ኃላፊ አቶ ካሊድ አመልክተዋል። በአፋር ክልል "18 የለይቶ ማቆያ ስፍራዎች ተዘጋጅተዋል" ያሉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ በተለይም ደግሞ በሦስቱ ዋና ዋና መግቢያዎች በኩል ብዛት ያላቸው ሰዎች በመኪናና በእግር ስለሚገቡ ትኩረት መደረጉን ለቢቢሲ አስረድተዋል። እስካሁንም የአፋር ክልል መንግሥት ከጅቡቲ የሚመጡ ሰዎችን ለመቆጣጠር እያከናወነ ባለው ሥራ ወደ ለይ 380 የሚሆኑ ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ መደረጉንና ከለይቶ ማቆያ ለመውጣት የሚሞክሩ በመኖራቸው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ጨምረው ገልፀዋል። በጅቡቲ በሽታው ከፈጠረው ስጋትና በአሁኑ ወቅት ካለው ሞቃት የአየር ሁኔታ ለመሸሽ ድንብር አልፈው የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ ለዚሁ ተብሎ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ወደተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ እንዲዛወሩ እንደሚደረግ አቶ ያሲን ለቢቢሲ ጨምረው አስረድተዋል። በአፋር ክልል እስካሁን አንድ ሰው በኮሮናቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፤ በክልሉ የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ቤተ ሙከራ በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተው አሁን ግን ናሙናዎች ወደ አዲስ አበባ ተልከው እንደሚመረመሩ ኃላፊው ገልፀዋል። በአገሪቱ በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት የድንበር መግቢያዎች ዝግ ቢሆኑም ከጂቡቲ የሚመጡ ኢትዮጵያዊያንን መመለስ እንደማይቻል ያመለከቱት ኃላፊው ነገር ግን "ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው ከተመረመሩ በኋላ ነጻ መሆናቸው ሲረጋገጥ ይወጣሉ" ብለዋል። በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 117 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከጂቡቲ መጥተው በድሬዳዋ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሰዎች እንደሚገኙበት የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል። ጂቡቲ ከ980 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሁለቱ ሞተዋል። በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ የጨመረው በአንድ ሳምንት ውስጥ ነው። ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካ መከላከያ ኃይል በጅቡቲ ባሉት ወታደራዊ የጦር ሰፈሮች በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አውጇል። ድንብር ተሻጋሪ የሰዎች እንቅስቃሴን ለመቆጠጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ 'ዳጉ' የተባለውን የአፋር ማኅበረሰብ ባህላዊ የመረጃ መለዋወጫ መንገድን እየተጠቀሙ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክልት ኃላፊ አቶ ያሲን አመልክተዋል። የማኅበረሰቡ አባላት ጂቡቲ ውስጥ እየተስፋፋ ስላለው ወረርሽኝ ትኩረት አድርገው መረጃ እንደሚለዋወጡ "በየጊዜው ለእኛም ሪፖርት ያደርጋሉ። መረጃውን እየተለዋወጡ ስለሆነ እኛን በጣም እየጠቀመን ነው" በማለት ተናግረዋል። በእግር ድርበር አቋርጠው የሚገቡትንም ከፀጥታ ኃይሉ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ እየተከታተለ እንደሚጠቁም ገልጸው "ሕዝቡ ከጂቡቲ የሚመጡ ንክኪ ይኖራቸዋል በሚል ዘመዶቻቸውን ጭምር ወደ እኛ ያመጧቸዋል፤ ይሄም ለሥራችን አጋዥ ሆኗል" ብለዋል። ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መኪኖችም ጋላፊ ላይ ጸረ ተዋህሲያን እንደሚረጩና የከባድ መኪኖች አሽከርካሪዎችም ሲገቡና ሲወጡ አስፈላጊውን በሽታውን የመከላከያ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይደረጋል ብለዋል ኃላፊው።
48089610
https://www.bbc.com/amharic/48089610
በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተሞሸሩት ጥንዶች
እሁድ ሚያዝያ 20፣ 2011 ዓ. ም. መሀመድ ጣሂርና አሲያ አብዱጀሊል ባልተለመደ መልኩ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተሞሽረዋል። ጥንዶቹ ኤምባሲው ውስጥ የሰርግ ፎቶ ተነስተዋል። ኬክም ቆርሰዋል።
ሙሽራው መሀመድ ጣሂር በስደት ወደ ኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ከመጣ 12 ዓመታት ተቆጥረዋል። በኬንያ በቆየባቸው ዓመታት እንደዚህ አይነት ነገር አጋጥሞት እንደማያውቅና እድለኛ ነኝ ብሎ እንደሚያምን ይናገራል። ከሳምንታት በፊት የሰርግ ሥነ ስርአቱን በአንድ ኬንያ ውስጥ በሚገኝ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ውስጥ ለማድረግ በማሰብ ወደ ሬስቶራንቱ የሄደው መሀመድ፤ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን አቶ መለስ አለምን እዛው እንዳገኛቸው ይናገራል። • አባቶች ከትዳር ውጪ ለሚወለዱ ልጆች የወሊድ ፈቃድ ሊያገኙ አይገባም • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች ''በቅርቡ ላገባ እንደሆነና የምሳ ግብዣውን በሬስቶራንቱ ላደርግ እንደሆነ ለአምባሳደሩ ስነግራቸው፤ ለምን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰርጋችሁን አትፈጽሙም አሉኝ። ሙሉ ወጪውን ኤምባሲው እንደሚሸፍንም ነግረውኝ ነበር'' ይላል። ''ለምሳ ግብዣው አስቀድመን ስለከፈልን የፎቶና ኬክ የመቁረስ ሥነ ስርአቱን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ማከናወን እንደምንችል አምባሳደሩ ነገሩኝ።'' በመላው ዓለም ወደ ስልሳ የሚደርሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እንዳሉ የሚናገሩት በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ መለስ ዓለም፤ እስካሁን ድረስ በየትኛው ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደዚህ አይነት ድግስ ተዘጋጅቶ እንዳልተመለከቱ ገልጸዋል። በኤምባሲው የቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ ይህ አጋጣሚ የመጀመሪያው ነው ሊባል እንደሚችልም አምባሳደሩ ያስረዳሉ። ''በዜጎችና በኤምባሲዎች መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት ታሪክ ሆኖ የኤምባሲው ግቢ ውስጥ እንዲደግሱ በምንችለው መጠን ለማስተናገድ ሞክረናል።'' በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ ዜጎች ሰርግ ወይም መሰል መሰናዶ ሲኖራቸው 'የአዳራሹን ነገር በኛ ጣሉት' የሚል መልእክት ከሳምንታት በፊት አስተላልፎ እንደነበር የሚያስታውሱት አምባሳደሩ፤ የጥንዶቹ የሰርግ ሥነ ስርአት ለሌሎችም በር ከፋች ሊሆን እንደሚችል ያምናሉ። ''በኛ እምነት ዜጎች የማይገቡበትና የማይወጡበት ኤምባሲ ኦና ነው። ንብ የሌለው ቀፎ እንደማለት ነው። ዜጎች ሲደሰቱና ሲከፉም የሚመጡበት ኤምባሲ ማድረግ ያስፈልጋል። እኛ ደግሞ ለዚህ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገናል።'' • 360 ብር ለአንድ ሕጻን • የጂግጂጋ ነዋሪ ጥንዶች ስጋት ላይ ነን እያሉ ነው መሀመድ ጣሂርና አሲያ አብዱጀሊል የምሳ ዝግጅታቸውን ጨርሰው ወደ ኤምባሲው ሲሄዱ ኬክና የሚጠጣ ነገርም ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው። ''እኛ የጠራናቸው 60 ሰዎች ቢሆኑም በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ስንደርስ የኤምባሲው ሠራተኞችና ሌሎች ሰዎችም ተጨምረው ወደ 100 የሚደርሱ ሰዎች ተሰብስበው ነበር። እጅግ የደመቀ ሥነ ስርአት ነበር የተካሄደው። በጣም ደስ ብሎኛል።'' አምባሳደሩ ''ኢትዮጵያውያን መጥተው ሰርግ ደግሰው፤ ደስታቸውን ማየት፤ ህጻናት በኤምባሲው ግቢ ውስጥ ሲቦርቁ መመልከት በጣም ደስ ይላል'' ብለዋል። ''ይሄ የኢትዮጵያውያን ቤት ነው። ኢትዮጵያውያን ግብር ከፋዮች የሠሩት ቤት ነው። የኛ አባቶችና አያቶች ባወጡት ገንዘብ የተሠራ ግቢ ነው። ስለዚህ ኤምባሲው ጥቅም ላይ ውሏል ብለን እናስባለን" ይላሉ።
news-52740283
https://www.bbc.com/amharic/news-52740283
ወጣቶቹ ሴቶች ከመኪና መለዋወጫ ለኮቪድ-19 ህሙማን መተንፈሻ ሰሩ
አፍጋኒስታን ውስጥ ያለ አንድ ወጣት ሴቶች ብቻ ያሉበት ቡድን የመኪና መለዋወጫዎችን በመጠቀም በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ለመርዳት የሚያገለግለውን የመተንፈሻ መሳሪያ [ቬንትሌተር] እየሰሩ ነው።
አሳሳቢ እየሆነ የመጣው ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማከም ጥቅም ላይ የሚውለውን የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ሰርተው የሚጨርሱ ሲሆን ዋጋም በጣም ዝቅተኛ ነው። ለዓመታት በጦርነት ስር የነበረችውና አርባ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት አፍጋኒስታን 400 ቬንትሌተር ብቻ ነው ያላት። እስካሁንም በአገሪቱ ከ7,650 በላይ የኮሮናቫይረስ ህሙማን የተመዘገቡ ሲሆን 178 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሞተዋል። የአገሪቱ ባላስልጣንት ወረርሽኙ ሊከፋና ደካማውን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት ሊያሸዕመደምደው ይችላል ብለው ሰግተዋል። "በምንሰራው የመተንፈሻ መሳሪያ አንድ ሰው እንኳን ማዳን ከቻልን ትልቅ ነገር ነው" ስትል የቡድኑ አንድ አባል የሆነችው የ17 ዓመቷ ናሂድ ራሂሚ ለቢቢሲ ተናግራለች። "የአፍጋኒስታን ባለህልሞች" በሚል ስም የሚጠሩት ወጣት ሴቶቹ የሚገኙት በአገሪቱ ውስጥ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ በሽተኛ በተገኘባት የሄራት ክፍለ ሃገር ውስጥ ነው። ክፍለ ሃገሯ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተመታችው ኢራን ጋር የምትዋሰን በመሆኗ በአፍጋኒስታትን ከፍተኛ የወረርሽኙ ስጋት ያለባት ናት። ወጣት ሴቶቹ እድሜያቸው በ14 እና 17 ውስጥ ሲሆን የመጀመሪያውን የሙከራ ምርታቸውን የሰሩት የቶዮታ ኮሮላ ሞተርንና ሌላ ክፍል ደግሞ ከሆንዳ ሞተርሳይክል ላይ በመውሰድ ነው። ወጣቶቹ እንደሚሉት የሚሰሩት ቬንትሌተር መደበኛው የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ በማይገኝባቸው ሆስፒታሎች ውስጥ ለሚገኙ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ጊዚያዊ መፍትሔ ይሰጣል ብለው ያምናሉ። በወረርሽኙ ሳቢያ በዓለም ላይ በተፈጠረው ከፍተኛ የቬንትሌተር ፍላጎት ምክንያት የመሳሪያው እጥረት አጋጥሟል። በዚህ የተነሳም 30 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያወጣ የነበረው መሳሪያ አሁን ወደ 50 ሺህ ዶላር ከፍ በማለቱ ከአብዛኞቹ ድሃ አገራት አቅም በላይ ሆነወል። ነገር ግን ህሙማንን ለመርዳት ቀን ከሌት የሚጥሩትን የህክምና ባለሙያዎችን ለማገዝ እየጣሩ እንደሆነ የሚናገሩት ወጣቶቹ፤ የሚሰሩት ቬንትሌተር ዋጋው 600 መቶ ዶላር በታች ነው። ታዳጊ ሴቶቹ እንደሚሉት በበሽታው ምክንያት መደብሮች ዝግ በመሆናቸው ለሚሰሯቸው ቬንትሌተሮች የሚያስፈልጉ እቃዎችን ለማግኘት ችግር ገጥሟቸዋል። የቡድኑ መስራችና ከዚህ ቀደም በታይም መ፥ጽሔት ተጽዕኖ ፈጣሪ ተብለው ከተመረጡ አንድ መቶ ሥራ ፈጣሪዎች መካከል አንዷ የሆነችው ሮያ ማህቡብ እንደመትለው የሰሯቸውን ቬንትሌተሮች በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ለአገልግሎት ያቀርባሉ። "የቬንትሌተሮቹ የመጀመሪያ ደረጃ ምርት ከቀናት በፊት ሆስፒታል ውስጥ ተሞክሯል። ቡድኑ በሁለተኛው የምርት ደረጃ ላይ እየሰራ ነው። ይህ ካለቀ በኋላ ምርቶቹ ለገበያ ይቀርባሉ" ብላለች። ከሰላሳ ከመቶ በታች ሴቶች የትምህርት ዕድል ያገኙ ሴቶች ብቻ ባሉባት በአፍጋኒስታን ውስጥ የወጣቶቹ ሥራ ሴቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ በማሳየት ሌሎችን የማነቃቃት ዓላመ አለው። የወጣቶቹ ሥራ በአፍጋኒስታን መንግሥት ተቀባይነትን በማግኘት ድጋፍ ያገኘ ሲሆን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒም ባለስልጣናት ሥራውን እንዲከታተሉና አስፈላጊው ድጋፍ እንዲሰጣቸው በማዘዛቸው ለቡድኑ አባለት ትልቅ መነቃቃትን ስጥተወል። የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴርም ለወጣት ሴቶቹ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑም ተነግሯል። የሚሚስቴር መስራያ ቤቱ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ወጣቶቹ የሚያመርቱት የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ አስፈላጊውን ሳይንሳዊ የመርት ሂደትና ፍተሻ እንዲያልፍ ተደርጎ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል ብለዋል።
news-41441951
https://www.bbc.com/amharic/news-41441951
የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ለሮሂንጂያ ሙስሊሞች አልደረሰላቸውም ተባለ
በሚያንማር የሚገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አመራሮች የሮሂንጂያን ጉዳይ መንግሥት እንዳይመለከተው ማድረጉን የቢቢሲ ምርመራ ይፋ አደረገ።
ከ500 ሺ በላይ ሮሂንጂያዎች ከማይናማር ሸሽተዋል የድርጅቱ የቀድሞ አመራር እንዳሉት በሚያንማር የሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊ የሰብዓዊ መብት ተማጓቾች ውጥረት ወዳለበት የሮሂንጂያ አካባቢ እንዳይጎበኙ አድርገዋል። 500 ሺህ የሚሆኑ ሮሂንጂያዎች በመከላከያ ሠራዊት የሚደርሰውን ጥቃት በመፍራት ሸሽተው አብዛኛዎቹ ባንግላዲሽ ደርሰዋል። በሚያንማር የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ግን የቢቢሲን ዘገባ አስተባብሏል። በሰሜናዊ ራክሂን የሚገኙ ጥቂት የሮሂንጂያ መንደሮች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል። ሮሂንጂያዎች ወደ ባንግላዲሽ መሰደዳቸውን ተከትሎ ድርጅቱ ድጋፍ በማድረግ ቀዳሚ ነው። ከድጋፉ በተጨማሪም የበርማ ባለስልጣናትንም ሲኮንን ተስተውሏል። ይሁን እንጂ የአሁኑ ችግር ከመከሰቱ ከአራት ዓመት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሃገሪቱ ቡድን መሪ ካናዳዊቷ ሬናታ ሎክ-ድሳሊየን፡ ሮሂንጂያዎች ወደ ባንግላዴሽ ይሸሻሉ። ውስብስብና ግጭት እ.አ.አ በ 2012 በሮሂንጂያ ሙስሊሞችና በራክሂን ቡዲስቶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከ 100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሲሞቱ፤ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የሮሂንጂያ ሙስሊሞች ደግሞ መጨረሻቸው በመጠለያ ጣቢያዎች ሆኖዋል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ግጭቶች በየጊዜው የተከሰቱ ሲሆን የሮሂንጂያ ወታደራዊ ቡድንም ተቋቁሟል። ለተጎጂዎች ድጋፍ እንዳይደርስ ደግሞ በራክሂን ቡዲስቶች የተለያዩ ሥራዎች ተሠርተዋል። ይህም የሮሂንጂያዎች መሠረታዊ እርዳታ እንዳየገኙ እንቅፋት ሆኗል። የባንግላዲሽ ወታደሮች ለሮሂንጂያ ህፃናት ምግብ ሲያከፋፍሉ የሮሂንጂያን ችግር ወይም ዘር ጭፍጨፋ እንደሚመጣ በዋና ዋና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባዎች ላይ መናገር የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደረሰ ሲሉ አንድ ድርጅቱ የቀድሞ አመራር ተናግረዋል። በ2015 ድርጅቱ የአካባቢውን ችግር ለመፍታት ያቀደበት መንገድ ለቢቢሲ እነዳጤነው የችግር አፈታቱ መንገድ ብዙ ክፍተት ያለበት ነው። "የሰብዓዊ መብት ችግሩን የሚቀረፈው ኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት ነው በሚል ታልፏል።" ይህንን አስመልክቶ ድሳሊየን ከቢቢሲ ለቀረቡላቸው ጥኣቄዎች ምላሽ ለመስተት ፈቃደኛ አልሆኑም።
42914332
https://www.bbc.com/amharic/42914332
ደቡብ አፍሪካ፡መውጫ አጥተው የነበሩ 955 የማእድን ቁፋሮ ሰራተኞች ወጡ
ወደ 955 የሚሆኑ ሰራተኞች በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ማምረቻ ሰፍራ በአውሎ ንፋስ አማካኝነት መብራት በመጥፋቱ ከእሮብ ምሸት ጀምሮ መውጣት እንዳልቻሉ ተዘግቧል።
መብራት ከመቋረጡም ጋር ተያይዞ አሳንሰሮቹ ባለመስራታቸው በማታ ፈረቃ የሚሰሩትን ሰራተኞች ከመሬት ስር ማውጣት አልቻሉም። የአሰሪው ኩባንያ ቃል አቀባይ በበኩሉ ሁሉም ደህና ናቸው ብሏል። በተቃራኒው የሰራተኛ ማህበሩ ኃላፊዎች ከሮብ ምሽት ጀምሮ ከመሬት ስር ተቀርቅረው መቆየታቸው ለህይወታቸው ፈርተው እንደነበር ገልፀዋል። ደቡብ አፍሪካ በአለም ላይ ካሉ ከፍተኛ ወርቅ አምራች አንዷ ስትሆን ነገር ግን ኢንዱስትሪው ሰራተኞችን ዝቅተኛ ደመወዝ በመክፈልና ሁኔታቸውም መጥፎ እንደሆነም ይነገራል። ከጆሀንስበርግ በ290 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ቢትሪክስ የማእድን ቁፋሮ ስፍራ ባለቤትነቱም ሲባንየ ስቲል ዋተር የሚባል ኩባንያም ነው። ወደ ላይ 23 ደረጃዎች ያሉት ሲሆን ከመሬት በታችም አንድ ሺ ሜትር ወደታች ጥልቀት አለው "ሁሉም ሰራተኞች በደህና ሁኔታ ላይ ነው ያሉት። ውሃና ምግብም እያቀረብንላቸው ነው" በማለት የኩባንያው ቃል አቀባይ ጄምስ ዌልስቴድ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል። ኢንጅነሮቹም ጄነሬተሩን ማስነሳት ባለመቻላቻውም አሳንሰሮቹን ማስነሳት እንዳልቻሉ በተጨማሪ ተናግረዋል። "ይህንን ችግር ለመቅረፍም ተግተን እየሰራን ነው" በማለት ጄምስ ዌልስቴድ ተናግረዋል። አገር አቀፉ የማዕድን ሰራተኞች ማህበር በበኩሉ የአድን ስራ የተንቀራፈፈ ነው ሲሉ ተችተውታል። "ዋናው ችግራቸው የተቀናጀ ባለመሆኑ በአንድ ጊዜ ማዳን የሚችሉት አንድ ሰራተኛ ነው። በጣም አስጨንቆናልም" በማለት የማህበሩ ቃል አቀባይ ሊቩህዋኒ ማምቡሩ ተናግረዋል። የሰራተኞቹ ቁጥር ከፍተኛ ከመሆን ጋርም ተያይዞ የውሃ እጥረት እንዲሁም የምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው እንደሚችልም ማህበሩ ፍራቻ ነበረው። "የማዕድን ቁፋሮ አደገኛ ስራ ነው። የእለት ምግባቸውን ለማግኘትና ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር ሲሉም የማዕድን ቆፋሪዎችም ህይወታቸውን አደጋ ላይ ይጥላሉ" በማለት የማህበሩ መሪ ጆሴፍ ማቱንጃዋ ተናግረዋል። ደቡብ አፍሪካ አደገኛና ጥልቅ የሚባሉ የማዕድን ቁፋሮዎች የሚገኙባት ናት። በባለፈው አውሮፓውያኑ አመት በአገሪቷ ውስጥ ከማእድን ቁፈሮም ጋር በተያያዘ ከ80 በላይ ሞቶችም ተመዝግበዋል
47275534
https://www.bbc.com/amharic/47275534
ዶናልድ ትራምፕን ከሥልጣን ለማባረር ተስፋ የተጣለበት ሕግ
አሜሪካ በመሪዋ እንዲህ ተወዛግባ አታውቅም። ሕዝቧ ሁለት ጫፍ ረግጧል፤ ፕሬዝዳንቱን አምርረው በሚጠሉና ራሳቸውን እስኪስቱ በሚደግፏቸው ዜጎች መሀል።
ብዙዎች የትራምፕን የመጀመርያ ሳምንታት አያያዝ በማየት ሰውየው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከነጩ ቤተ መንግሥት በቅሌት እንደሚባረሩ ተስፋ አድርገው ነበር። እነሆ ሁለት ዓመት ደፈኑ። አሁን "25ኛው ማሻሻያ" ተብሎ የሚጠራው ሕግ የአሜሪካንን ፕሬዝዳንት ከሥልጣን ለማውረድ ለጊዜው ብቸኛውና ተስፋ ሰጪው መንገድ ኾኗል። ነገሩ ከወዲህ በአሜሪካ ሚዲያ መነጋገሪያ መሆኑ 'ይህ ነገር የትራምፕን መጨረሻ ይሆን እንዴ?' የሚል ጥያቄን አጭሯል። • አሜሪካ የቬንዙዌላ መንግሥትን አሰጠነቀቀች • አሜሪካ ሩሲያዊቷን በሰላይነት ከሰሰች ይህ ጉዳይ መነጋገሪያ የሆነው የቀድመው የኤፍ ቢ አይ ተጠባባቂ ኃላፊ አንድሩ ማካቤ ትናንት '60 ሚኒት' በተሰኘው የቲቪ መርሐግብር ላይ ተገኝተው ፕሬዝዳንቱን ለማንሳት ውጥኖች እንደነበሩ የሚጠቁም አስተያየት ከሰጡ ወዲህ ነው። ሕጉ ተፈጻሚ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? ይህ ሕግ ለአሜሪካ ሴኔት ርዕሰብሔሩን ለማሰናበት ዕድል ይሰጣል። የፕሬዝዳንቱ ካቢኔ ከደገፈው ደግሞ ነገሩ ያለቀለት ጉዳይ ይሆናል። ሆኖም በምክትል ፕሬዝዳንቱ ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል። ሕጉ ተፈጻሚ የሚሆንበት አግባብ በጥቅሉ ርዕሰብሔሩ ታላቋን አገር አሜሪካንን ለመምራት በአንዳች ምክንያት ብቁ አይደለም ተብሎ ሲታመን ነው። ይህ የጤና መታወክንም ያጠቃልላል። በተለይ የአእምሮ ጤናን። 'ሰውየው በእርግጥ ጤነኛ ናቸው?' ብለው የሚጠይቁ አልጠፉም። ትራምፕ አሜሪካንን ለመምራት የሚያስፈልገው የጤነኝነት ደረጃን አያሟሉም ብለው የሚያምኑ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። አንድሩ ማካቤ የቀድመው የኤፍቢአይ ተጠባባቂ ኃላፊ ነበሩ። ይህንን ሕግ ለመጠቀም የትራምፕ የገዛ ካቢኔያቸውና ምክትል ፕሬዝዳንቱ አንድ እጅግ ወሳኝ ደብዳቤ ላይ መፈረም ይኖርባቸዋል። ደብዳቤው "...ርዕሰብሔሩ ሥልጣናቸውንና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ባለመቻላቸው..." የሚል ሐረግን ይይዛል። ይህ ማለት ተቀማጩ ርዕሰ ብሔር ያቺን አገር ለመምራት አካላዊም ሆነ ሥነልቦናዊ ዝግጁነት ይጎድለዋል ተብሎ ታምኗል ማለት ነው። ስለዚህ ነገሩ በአመዛኙ አገር የማዳን ተግባር ኾኖ ይታያል። እዚህ ዳብዳቤ ላይ የሚፈለገው ቁጥር ያላቸው ሴናተሮችና የካቢኔ አባላት ፈረሙ ማለት ትራምፕ በነገታው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ነጩን ቤተ መንግሥት መልቀቅ ይኖርባቸዋል። ምርጫ እስኪደርስም ምክትል ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ይቀጥላሉ። ትራምፕ ከመሰናበታቸው በፊት ግን ውሳኔውን በመቃወም አንድ ደብዳቤ መጻፍ እንዲችሉ ሕጉ ይፈቅዳል፤ 25ኛው ማሻሻያ። • በጦር መሣሪያ ፍቅር የወደቀችው አሜሪካ • አሜሪካ ከጥገኝነት ጋር በተያያዘ ውሳኔ አሳለፈች የታችኛውና የላይኛው ምክር ቤት 2/3ኛው ታዲያ ይህንን ሕግ ደግፎ ድምጽ መስጠት ይኖርበታል። ይህ ብቻም ሳይሆን ምክትላቸው ማይክ ፔንስም መፈረም ይኖርባቸዋል። እርሳቸው ካልፈረሙበት ተፈጻሚ አይሆንም። በአሁኑ እውነታ ይህ የመሆን ዕድሉ ጠባብ የሚሆነው ታዲያ ሰውየው ለርሳቸው በሚያደገድጉ ካቢኔ አባላት መከበባቸው ነው። ሁለተኛው ፈተና የላይኛው ምክር ቤት የተሞላው በሪፐብሊካን መሆኑ ነው። በአሜሪካ ታሪክ አንድም ጊዜ ይህ '25ኛው ማሻሻያ' የሚባለው ሕግ ተግባራዊ ሆኖ አያውቅም።
news-54114419
https://www.bbc.com/amharic/news-54114419
ኮሮናቫይረስ ፡ ተስፋ የተጣለበት የኦክስፎርዱ የኮቪድ-19 ክትባት ለምን እንዲቆም ተደረገ?
አስትራዜኔካና ኦክስፎርድ ተባብረው ከፊት ቀድመው እየሰሩ ነበር። ከክትባት ሙከራዎች ሁሉ ተስፋ ሰጪዎቹ ሆነው ነበር። ዓለም ትንፋሹን ሰብስቦ እየጠበቃቸው ነበር።
አስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ በጋራ የኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት እየሰሩ ነው ድንገት እክል ገጠማቸው። አንድ ሰው ታመመባቸው። ከዚያም ሁሉም ነገር ቆመ። ለጊዜው ነው ታዲያ። ቢሆንም ዜናው ብዙ መንግሥታትን አስደንግጧል። ምክንያቱም በወረርሽኝ የተፍረከረከችውን ዓለማችንን ይታደጋል ተብሎ ነበር የሚጠበቀው፤ክትባቱ። የነኦክስፎርድ ክትባት ምንም እክል እንዲገጥመው አይፈለግም ነበር። በተለይ ዶናልድ ትራምፕ ከኅዳር በፊት ይደርስልኛል ብለው በተስፋ እየጠበቁ ነበር። አውስትራሊያና እንግሊዝ ከወዲሁ ክፍያ ፈጽመው ነበር። አሜሪካም እንዲሁ። በርካታ መድኃኒት ፋብሪካዎች የነኦክስፎርድ ክትባት ይሳካል በሚል ማምረቻ ማሽናቸውን መወልወል ጀምረውም ነበር። ለዚህም ነው ይህ ሙከራ እንዲቆም መደረጉ ድንጋጤ የፈጠረው። ደግሞ ከብዙ ክትባቶች በተሻለ ይህኛው ክትባት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነበር። በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአሜሪካ፣ በብራዚልና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ በጎ ፍቃደኞች ክትባቱን ወስደውታል። እነዚህ ሰዎች በድምሩ 30 ሺህ ይሆናሉ። ከእነዚህ መካከል አንድ ሰው መታመሙ ነው አሁን ያ ሁሉ የተደከመበት ክትባት እንዲቆም ያደረገው፤ ለጊዜውም ቢሆን። አስትራዜኔካ ግን "እረ ምንም መደናገጥ አያስፈልግም፤ በመድኃኒት ሙከራ ጥርሳችንን ነቅለንበታል። ይህ ሁልጊዜም የሚያጋጥም ነገር ነው እኮ" ብሏል። ጨምሮም "ምርምሩ የቆመውም ለጊዜው ነው። ደግሞ ታማሚው በምን ምክንያት እንደታመመ አልታወቀም። ምናልባትም ከክትባቱ ጋር ተያይዞም ላይሆን ይችላል" ብለዋል። ለመሆኑ ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ በመድኃኒት ፍብረካ ሂደት ምን ያህል የተለመደ ነው? የነኦክስፎርድ ሙከራ ከወዲሁ ከሽፎ ይሆን? የክትባቱ ሙከራ በብራዚል፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በአሜሪካና በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 30 ሺህ ሰዎችን አሳትፏል። ምንም ማለት ላይሆን ይችላል፤ ሊሆንም ይችላል አስትራዜኔካ ግዙፍ መድኃኒት አምራች ነው፡፡ ከኦክስፎርድ ጋር በጥምረት እየሰሩ መሆኑ ከተነገረ ጀምሮ ጥሩ እምርታ እያሳዩ ነው የመጡት። ዓለም ተስፋ ያደረገውም በሁለቱ ላይ ነው። ምንም እንኳ እነሱ ሲደናቀፉ ዓለም ክው ብሎ መቅረቱ የሚያስገርም ባይሆንም አሁን በሙከራ ለይ ካሉ 24 የሚሆኑ ክትባቶች ውስጥ እንደ ኦክስፎርድና አስትራዜኔካ መስመሩን ተከትሎ፣ ሳይንሱን ሳያዛንፍ እየሄደ ያለ የለም። ለምሳሌ ሩሲያ ጣጣዬን ጨርሻለሁ ብትልም ያመናት የለም። የሩሲያን መድኃኒት ፈብርኪያለው ፉከራ ዓለም ቁብም አልሰጠውም። ወይም አላመነበትም። ሩሲያዊያን ግን እኛ እንዲያውም ለሕዝባችን ማደል ልንጀምር ነው እያሉ ነው። ፑቲን ያልታመኑት እንዲሁ ምዕራቡ ስለማይወዳቸው ብቻ አይደለም። አንድን መድኃኒት ለመፈብረክ በአቋራጭ የማይኬድባቸው የጊዜ ሰሌዳዎች አሉ። ፑቲን ወታደራዊ የቆረጣ ስልታቸውን ወደ መድኃኒት ሳያመጡት አልቀሩም። የዚህ የኦክስፎርድና አስትራዜኔካ ጥምረት እክል እንደገጠመው ለመጀመሪያ ጊዜ የዘገበው ስታትኒውስ ነው። በዚህ ዘገባው እንዳብራራው እክሉ የተፈጠረው ከ30 ሺህ ክትባት ወሳጆች መካከል አንድ በዚያው በዩናይትድ ኪንግደም የምትገኝ ተሳታፊ መታመሟን ተከትሎ ነው። ሕመሟ ደግሞ ከክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት ጋር ተያይዞ ሊሆን ይቸላል የሚል ስጋት አለ። ከዚህ ከፍ ያለ ዝርዝር መረጃ የለም። ሆኖም ስታትኒውስ የአስትራዜኔካ ምንጮቼ ነገሩኝ እንዳለው ታማሚዋ አሁን እያገገመች ነው። አስትራዜኔካ ባወጣው መግለጫ "ምርምሩ እንዲቆም የሆነው አሰራሩ እንዲያ እንዲሆን ስለሚያዝ ነው ብሏል። እንዲህ ዓይነት ነገሮች ሲከሰቱ የጥንቃቄ ሂደቶች በድጋሚ ይፈተሸሉ። የተለመደ አሰራር ነው" ብሏል። ይህ ሂደትም ቀናትን ሊወስድ ይችላል። በአንድ ሰው ላይ ያልተጠበቀ ውጤት ከታየ የክትባት ሙከራው እንዲቆም ተደርጎ መርምራ ይደረጋል ይህ በክትባት ፈጠራ ሂደት ምን ያህል የተለመደ ነገር ነው? ክስተቱ ተሰምቶ የማያውቅ ነገር አይደለም። "አንድ መድኃኒት ሦስተኛ ምዕራፍ ሙከራ ላይ ካለና ከሚሞከርባቸው ሰዎች አንድ እንኳ ሰው ሆስፒታል ቢገባ ወዲያውኑ ሙከራ እንዲቆም ይደረጋል" ተብሏል። ገለልተኛ ወገን ምርምሩና ሙከራው የሄደበትን መንገድ ይፈትሻል እንጂ። ሙከራው ይቆማል ማለት ግን አይደለም። የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ "በትልልቅ የሕክምና ሙከራዎች ሂደት ሰዎች መታመማቸው የለመደ ነው። ይህ ሲሆን ሁልጊዜም ቢሆን ገለልተኛ አካል የሙከራ ሂደቱን ይፈትሻል። እየሆነ ያለውም ይኸው ነው" ብለዋል። ለበኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት በሚደረግ ሂደት ውስጥ ሰው ታሞ ሙከራ እንዲቆም ሲደረግም ይህ የመጀመርያው አይደለም። በሚያዝያ ወር በተመሳሳይ አንድ ሰው እንዲሁ ታሞ የክትባት ሙከራው እንዲቆም ተደርጎ ነበር። ሰው እንዲህ እየታመመ ክትባቱን መውሰድ ችግር አይኖረውም? ይህ ዜና ገና ከመውጣቱ ጸረ-ክትባት አቀንቃኞች "ምን ብለናችሁ ነበር" ማለት ጀመሩ። ክትባቱ ይቅርብን፣ የዓለምን ሕዝብ ሊጨርሱ ነው ሐሳባቸው" ብለው አስወሩ። ኦክስፎርድና አስትራዜኔካ በጋራ በሰጡት መግለጫ ግን ይህ የሚደረገው አስተማማኝ ክትባት ለመፈብረክ ሲባል ነው። ምርምሩ እንዲቆም መደረጉ ምን ያህል ለሰዎች ጤና ቅድሚያ እንደሚሰጥም ማሳያ ነው ብለዋል። እንዲያውም ባለፈው ማክሰኞ ለኮሮናቫይረስ ክትባት እያመረቱ የሚገኙ የዓለም መድኃኒት አምራቾች፤ ዝነኛው አስትራዜኔካን ጨምሮ ማለት ነው፤ የሰዎችን ጤና ደኅንነት ለማስቀደም የስምምነት ሰነድ ፈርመዋል። ይህም ታሪካዊ ነው። ይህንን ፊርማ ካኖሩት መካከል ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን፣ ባዮኤንቴክ፣ ግላክሶስሚዝክላይን፣ መርክ ሞደርና፣ ሳኖፊ እና ኖቫቫክስ ይገኙበታል። የስምምነት ሰነዱ ቅድሚያ ለገበያ ሳይሆን ለሳይንስ እንዲሰጡ የሚያስገደድ ነው። እኛ ፈራሚዎች ለሥነ ሣይንሳዊ ዘዴ ታማኝ ሆነን፣ ሥነ ምግባር ኖሮን እንሰራለን ብለው ነው የተስማሙት። ከዚህም በተጨማሪ ክትባቱ ሲገኝ ለዓለም ሕዝቦች በበቂ እንዲዳረስ እንደሚያግዙም ቃል ገብተዋል። ሩሲያ የኮሮናቫይረስ ለማግኘት እየተቃረበች መሆኗን አሳውቃለች መድኃኒቱን ለማግኘት ምን ያህል ተቃርበናል የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው አሁን በመላው ዓለም 180 ክትባቶች እየተሞከሩ ነው። ነገር ግን አንዳቸውም የክሊኒካል ሂደትን አላጠናቀቁም። ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት ድርጅት እንደሚለው ሳይንሳዊውን የመድኃኒት ፍብረካ ተከትለው በዚህ ዓመት ሊደርሱ የሚችሉ ክትባቶች አይኖሩም። ድርጅቱ እዚህ ይህን ከወዲሁ እንዲደመድም ያስቻለው ታዲያ አንድን መድኃኒት ለማምረት የሚወስደውን መደበኛ ጊዜ ከግምት በማስገባት ነው። የአስትራዜኔካና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ጥምረት የመጀመርያው ፈብራኪ ለመሆን ሰፊ ዕድል አለው የተባለው እስከአሁን ያሉ ሂደቶችን (ምዕራፍ አንድ እና ሁለትን) በአጥጋቢ ሁኔታ ማለፍ በመቻሉ ነው። ወደ ሦስተኛ ምዕራፍ ከገባም ቆይቷል፤ መውጣት ነው አሁን ያቃተው። 30 ሺህ ሰዎች ላይ ክትባቱ ተሞክሮባቸው የሚያሳዩት ውጤት እየተጠበቀ ሳለ ነው አንድ ሰው መታመሙ ነገሩን ያሰናከለው። በተለመደው ጥብቅ የመድኃኒት ግኝት ሳይሳዊ አካሄድ ምዕራፍ ሦስት የሙከራ ሂደት ብዙ ሺህ ፍቃደኞች ላይ መድኃኒቱ የሚሞከርበት ሂደት ሲሆን ይህ ምዕራፍ እስኪጠናቀቅ ዓመታትን ሊወስድ ይችላል።
news-49068334
https://www.bbc.com/amharic/news-49068334
"አዲስ አበባ የምንወዛገብባት ሳትሆን በጋራ የምንኖርባት ከተማ ናት" ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ
አዲስ አበባ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የምትሆን ከተማ በመሆኗ ለውዝግብና አለመግባባት ምክንያት መሆን እንደሌለባትና የተለያዩ ሃሳቦችን በማቅረብ ልናሳድጋት እንደሚገባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለቢቢሲ ተናገሩ።
አዲስ አበባ የሃገሪቱ እምብርት መሆኗን የሚጠቅሱት ምክትል ከንቲባው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መቀመጫም መሆኗን ጠቅሰው "አዲስ አበባ ሁሉንም የምታቅፍ የሁሉም ከተማ ናት። ከተማዋ የመወዛገቢያ ርዕስ ሳትሆን ኢትዮጵያዊያን በጋራ የምንኖርባትና የምናሳድጋት ልትሆን ይገባል" ብለዋል። • የአዲስ አበባ መስተዳደርና የባላደራው ምክር ቤት አስተዳደራቸው የከተማዋን ነዋሪ ችግሮች ለመቅረፍ የተለያዩ እቅዶች እንዳሉት የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፤ በአዲስ አበባ ውሰጥ ያለው የቤት ችግር በከተማዋ ካሉ ዋነኛ ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑን ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለችግረኞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማዋ ነዋሪዎችን ችግር ለመቅረፍ በቤቶች ልማት በኩል ትልቅ የሚባል ተግባር አከናውኗል የሚሉት ምክትል ከንቲባው፤ የቤቶች ልማት ፕሮጀክትን በተመለከተ እስካሁን የነበረውን አሰራር በመለወጥ፣ በመንግሥት ሲከናወን የነበረውን የቤቶች ግንባታ የሪል እስቴት አልሚዎች እንዲገቡበት ይደረጋል ብለዋል። ለዚህም "የከተማዋ አስተዳደር ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማዘጋጀት የተለያዩ የገንዘብ ተቋማት እንዲሳተፉና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሥርዓት ተግባራዊ ያደርጋል" ብለዋል። • በአዲስ አበባ ቢያንስ 3.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ትራንስፎርመሮች ተሰረቁ በመጪው አዲስ ዓመትም በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለመንግሥት ሰራተኞች በርካታ ቁጥር ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል ያሉት ከንቲባው፤ ግንባታው የሚካሄደው እንደከዚህ ቀደሙ በመንግሥት ሳይሆን በግል ተቋማት ይሆንና መንግሥት የመቆጣጠርና የማስተባበር ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተናግረዋል። በከተማዋ ውስጥ የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ አሳሳቢ ከሆኑት ነገሮች መካከል የሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀል መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ከንቲባው "ስጋቱ ትክክለኛ ነው። ነገር ግን በግልጽ መናገርና ማረጋገጥ የምፈልገው በየትኛውም የኢንቨስትመት ሥራ ምክንያት ሰዎች አይፈናቀሉም" ብለዋል። ለዚህም ባለፈው ዓመት የምክትል ከንቲባነት መንበሩን ሲረከቡ ቃል መግባታቸውን የሚያስታውሱት ከንቲባው "በመልሶ ማልማትና ከተማዋን ለማሳደግ ነዋሪውን እንደማናፈናቅል ለሕዝቡ ቃል ገብተናል። ከዚያ ይልቅ ነዋሪውን ማልማትና ልማቱንም እዚያው እናካሂዳለን" በማለት ነዋሪዎችን ከመሃል ከተማ በማንሳት ራቅ ያሉ አካባቢዎች ማስፈር እንደማይኖር ገልጸዋል። • ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኦሮሚያ ተቃውሞን ቀሰቀሱ ለገሃር አካባቢ የሚካሄደው ግንባታንም በተመለከተ ሲናገሩ በስፍራው ከሚከናወኑት ግዙፍ ግንባታዎች ጎን ለነዋሪው የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች እንደሚገነቡ ጠቅሰው፤ በዚህም ሳቢያ የግለሰቦች መፈናቀል እንደማይኖር ሲያስረዱ "ማረጋገጥ የምፈልገው በልማት ስም የትኛውም የአዲስ አበባ ነዋሪ አይፈናቀልም። ይህ ታሪክ በእርግጠኝነት ያለፈ ክስተት ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በተጨማሪም የአዲስ አበባን ሰላም የተጠበቀና አስተማማኝ ለማድረግ የጸጥታና የደህንነት ጉዳይን ትኩረት ሰጥተው እየሰሩበት እንደሆነ ጠቅሰው የከተማዋ የጸጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማዋ ውስጥ ሞተር ሳይክሎች እንዳይንቀሳቀሱ የተጣለውን እገዳን በተመለከተም የተጠየቁት ም/ከንቲባው እዚህ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት በየአንዳንዱ ቀን አዲስ አበባ ውስጥ በሞተር ሳይክሎች አማካይነት ዝርፊያ ይፈጸም ነበር ብለው፤ በዚህ ምክንያትም ሞተር ሳይክሎች ላይ በተጠና መልኩ ክልከላ መጣሉን ይናገራሉ። • "ታከለ ኡማ አዲስ አበባን መምራት የለባቸውም" እስክንድር ነጋ እስካሁን የነበረው ሁኔታ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡትን ሞተር ሳይክሎች ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ነገሮች እንዳልነበሩና በዚህም ምክንያት ዝርፊያና የደህንነት ስጋት እንደተፈጠረ በመግለጽ "በቀጣይ ሞተር ሳይክሎቹ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችል ሕግና ደንብ ይዘጋጃል" ብለዋል። የከተማው አስተዳደር ሞተር ሳይክሎች ላይ እገዳውን ከጣለበት ዕለት ጀምሮ "በሚያስደንቅ ሁኔታ በከተማዋ ውስጥ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ያጋጥሙ የነበሩ የጸጥታ ችግሮች ከግማሽ በላይ በሆነ ሁኔታ ለመቀነስ አስችሏል" ሲሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል። ስለሞተር ሳይክሎቹ ዝርዝር መረጃ እንኳን እንደሌለ እገዳውም ያሉት ችግሮች እስኪፈቱ ድረስ እንደሚቆይ የሚናገሩት ምክትል ከንቲባው አስፈላጊው ህጋዊ የቁጥጥር ሥርዓት ከተዘረጋ በኋላ ግን ወደ ሥራቸው እንደሚመለሱ ገልጸዋል። ም/ከንቲባው አክለውም ሞተር ሳይክሎቹን የመቆጣጠሪያ ዘመናዊ የጂፒኤስ ሥርዓት እንደሚዘረጋ አመልክተው፤ ከሚዘረጋው ሥርዓትና ደንብ ውጪ ማንም በከተማዋ ውስጥ እንዲሰራ አይፈቀድለትም ብለዋል።
news-56855669
https://www.bbc.com/amharic/news-56855669
በነጆ የወርቅ ማዕድን ማውጫ በተፈጠረ አለመግባባት የሰዎች ህይወት ጠፋ
በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ በተፈጠረ አለመግባባት የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያለፍ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በነጆ ወራዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በባህላዊ መንገድ ወርቅ ያወጣሉ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተረፈ እንደተናገሩት ይህ ክስተት ያጋተመው በነጆ ወረዳ ጉቴ ዲላ ተብላ በምትጠራ ቀበሌ ውስጥ ሲሆን ምክንያቱም በአካባቢው በባህላዊ መንገድ ከሚወጣ የወርቅ ማዕድን ጋር የተያያዘ ነው። አስተዳዳሪው በአካባቢው ካሉ ከተለያዩ ወረዳዎች የመጡ "ከ7000 በላይ በሕገወጥ መንገድ ወርቅ የሚያወጡ ሰዎች" መኖራቸውን ይናገራሉ። እነዚህ በሕገወጥ መንገድ ወርቅ የሚያወጡ የሚሏቸው ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ከአምስት ጊዜ ያላነሰ ተደጋጋሚ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን እነዚህ በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚያወጡ ሰዎች "ፍቃደኛ ሆነው ቦታውን ለቀው ለመውጣት ፍቃደኛ አልሆኑም" የሚሉት አቶ ተሊላ ችግሩ የተፈጠረው በድጋሚ ለመወያየት በሄዱበት ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል። "ለመጨረሻ ጊዜ ልናወያያቸው ወደ ስፍራው ስንሄድ ወደ 5ሺህ የሚገመቱ ሰዎች በአንድ ቦታ ላይ ተሰብስበው ነበር። በዚህ መካከልም ረብሻ ተነሳ" ይላሉ። አለመግባባቱ በተፈጠረበት ጊዜ ሁኔታውን ለማረጋጋት የመንግሥት ጸጥታ ኃይል በቦታው እንደነበር ገልጸው፤ "የኦነግ- ሸኔ ታጣቂዎችም በስፍራው ይንቀሳቀሳሉ። በዚህ መካከል ተኩስ ተከፍቶ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ ሦስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል" በማለት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል። አስተዳዳሪው ለሦስቱ ሰዎች ሞትና ለሌሎች መቁሰል ምክንያት የሆነ ተኩስ ከየትኛው ወገን እንደተተኮሰ ተጠይቀው በሰጡት መልስ "አሁን የምናውቀው ነገር የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ነው። ከየት እንደተተኮስ አላውቅንም" ብለዋል። በምዕራብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በምዕራብ ወለጋ የምትገኘው የነጆ ወረዳ በወርቅ ማዕድን የምትታወቅ ስትሆን በወረዳው በርካታ ሰዎች ወርቅ በማውጣት ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። በዚህ ዓመትም ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ መውጣቱን የወረዳው አስተዳዳሪ ይናገራሉ። "ግለሰቦች እንዳሻቸው የግል መሬታቸውን ይሸጣሉ። ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎችም ከሌሎች ስፍራዎች በመኪና ተጭነው ወደ ወርቅ ማውጫ አካባቢው ይመጣሉ" ይላሉ። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ እንደሚሉት የማዕድን ማውጫ ስፍራዎቹ "የተለያዩ ወንጀሎችን የፈጸሙ ሰዎች መሰባሰቢያ እየሆነና የሚወጣው ወርቅም ለግል ጥቅም በሕገወጥ መንገድ ለገበያ ይውላል" በማለት ያስረዳሉ። በዚህ ስፍራ ማዕድን አውጪዎች በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚያወጡ በመሆናቸው የተለያዩ አደጋዎች ሲከሰቱ ይስተዋላል። ከዚህ ቀደም በነጆ ወረዳ ወርቅ ሲያወጡ በነበሩ ሰዎች ላይ የመሬት መናድ አጋጥሞ ማዕድኑን በማውጣት ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል። መንግሥት የአካባቢው ነዋሪዎች በማኅበር ተደራጅትው ሕጋዊ በሆነ እና ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወርቅ የማውጣት ሥራ እንዲያከናውኑ ለማድረግ ሲያደርገው የነበረው ጥረት የተፈለገውን ውጤት እስካሁን ማምጣት አለመቻሉን የወረዳው አስተዳዳሪ ተናግረዋል።
news-54950896
https://www.bbc.com/amharic/news-54950896
ቤንሻንጉል ጉሙዝ፡ በአውቶብስ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ተገደሉ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በርካታ ሰዎችን ይዞ በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
ኮሚሽኑ እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው በክልሉ ቅዳሜ በደባጤ ወረዳ ከወንበራ ወደ ቻግኒ በመጓዝ ላይ በነበረ አውቶብስ ላይ "ዘግናኝ" ያለው ጥቃት ተፈጽሞ ቢያንስ 34 ሰዎች መገደላቸውን ገልጾ የሰለባዎቹ ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል። በመግለጫው በተፈጸመው ጥቃት የተሰማውን ሐዘን የገለጹት ኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ "ይህ ጥቃት ሁላችንም በጋራ የተሸከምነውን የሰው ሕይወት ክፍያ ዛሬም በአሳዛኝ ሁኔታ የሚያሻቅብ ነው። የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በፍጥነት ጥቃቱ የበለጠ እንዳይባባስ እርምጃ መውሰዳቸው አበረታች ነው" ብለዋል። ከዚህ ጥቃት ቀደም ብሎም በክልሉ መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ "ያምፕ ቀበሌ" የታጠቁ ኃይሎች በነዋሪዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ አንድ ነዋሪ ሲገደል ሁለት የክልሉ የፖሊስ አባላት እንዲሁም የወረዳው አስተዳዳሪ መቁሰላቸውን የክልሉ ኮሙኑኬሸን ኃላፊ አቶ መለሰ ቅዳሜ ዕለት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። "አካባቢው ከዚህ ቀደም የተረጋጋ ነበር" የሚሉት ኃላፊው፣ በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ታጣቂዎች ገብተው ጥቃት ማድረሳቸውንና በነዋሪው ላይ ስጋት መፍጠራቸውን አመልክተዋል። የክልሉ ፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ከመከላከያ ኃይል ጋር ተባብረው በአካባቢው የተፈጠረውን ለማረጋጋት በሚሞክሩበት ወቅት ነበር ታጣቂዎቹ ከወንበራ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ቡለንና ዲባጤን በማቋረጥ ወደ ግልገል በለስ የሚሄድ አውቶብስ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት ብለዋል። ታጣቂዎቹ በርካታ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረን አውቶብስ አስቁመው በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና የተረፉም እንዳሉ ኃላፊው ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ የመከላከያ ሠራዊት በታጣቂዎቹ ላይ ተከታታይ እርምጃ መውሰዱን የገለጹት አቶ መለሰ በጥቃቱ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳትና በታጣቂዎቹ ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ውጤት ሙሉ ማጣራት ከተደረገ በኋላ እንደሚገለጽ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዕሁድ ዕለት እንደገለጹት፤ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በወሰዱት እርምጃ ጥቃቱን ፈጽመዋል የተባሉ 16 ታጣቂዎች "ተደምስሰዋል" ብለዋል። በተጨማሪም ከጥቃት ፈጻሚዎቹ መካከል ሁለቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና የቀረቱም ላይ እርምጃ ለመውሰድ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። ኢሰመኮ ጥቃቱን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት መቀጠሉን አመልክቶ በፌዴራልና በክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ተመሳሳይ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችል "የተሻለ ቅንጅት" እንደሚያስፈልግ ገልጿል። ኮሚሽነሩ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ጨምረውም "የፌዴራልና የክልሉ የፀጥታና የፍትሕ አካላት ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመሆን እነዚህን ጥቃቶች ሊያስቆም የሚችል አዲስ ክልላዊ የፀጥታ ስትራቴጂ ሊነድፉ ይገባል" በማለትም አሳስበዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ስፍራዎች ከባለፈው ዓመት ማብቂያ ወዲህ በተለያዩ ጊዜያት በታጣቂዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ ግድያና ጥቃት ሲፈጸም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ይንንም ተከትሎ የየክልሉና የፌደራል መንግሥቱ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በርካታ ጥቃት ፈጻሚዎችን እንደገደሉና እንደያዙ ሲናገሩ ቆይተዋል። በክልሉ ባለስልጣንት "ጸረ-ሠላም" ኃይሎች ተብለው በሚጠሩትና ማንነታቸው በውል ባልተለየው ታጣቂዎች በሚፈጸመው ጥቃት በነዋሪዎች ዘንድ ስጋት ያለ ሲሆን በዚህም ሳቢያ ከወራት በፊት ጀምሮ አንዳንድ የክልሉ ወረዳዎች በጸጥታ አካላት በሚመራ ኮማንድ ፖስት ሰር እንዲተዳደሩ መወሰኑ ይታወሳል።
news-51276517
https://www.bbc.com/amharic/news-51276517
አምነስቲ በኢትዮጵያ የጅምላ እስር እየበረታ መሆኑ ያሳስበኛል አለ
የዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ባወጣው መግለጫ በተለይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ደጋፊ የሆኑ 75 ሰዎች በሳምንቱ መጨረሻ በጅምላ ተስረዋል፤ በአስቸኳይ ይፈቱ ሲል አሳስቧል።
ደጋፊዎቹ የታሰሩት በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ነው ያለው መግለጫው በተለይም በምዕራብ ጉጂ ዞን ፊንጫ ከተማ እንዲሁም በሻምቡ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ተጠቅሰዋል። ጋብ ብሎ የነበረው የመብት ተቆርቋሪዎች፣ የተቃዋሚዎችና የፓርቲ ደጋፊዎች የጅምላ እስር እየተመለሰ እንደሆነ ምልክቶችን እያየን ነው፤ ይህ ደግሞ ያሳስበናል ብሏል በመግለጫው። • ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ • መንግሥት ልዩ ፖሊስን እንዲበትን አምነስቲ ጠየቀ "ይህ ድንገቴ የጀምላ እስር የዲሞክራሲ መብቶችን ሚሸረሽር ነው፤ በተለይም ነጻና ገለልተኛ እንዲሆን በሚጠበቀው የመጪው ምርጫ ላይ ጥላውን ያጠላል" ብለዋል የአምነስቲ ኢንርናሽናል የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ዲፕሮሴ ሙቼና። ከታሳሪዎቹ መካከል ጫልቱ ታከለ ትገኝበታለች። ፖሊስ የጫልቱ ቤተሰቦች ይኖሩበታል ተብሎ በሚገመተውና ሻምቡ በሚገኘው መኖርያ ቤት እሁድ ጥር 17 ሌሊት 11፤00 ሰብሮ በመግባት በቁጥጥር ሥር አውሏታል ብሏል መግለጫው። አሁን በሻምቡ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኝም ገልጿል። ጫልቱ በፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ 'የአሸባሪው' የኦነግ አባል ናት በሚል ለስምንት ዓመታት በእስር ማሳለፏን የጠቀሰው መግለጫው፤ ኦነግ ከአሸባሪ ድርጅትነት በመሰረዙ ለውጦች ታይተው ነበር ብሏል። ሆኖም ጫልቱ በድጋሚ 2017 ለአጭር ጊዜ መታሰሯን በኋላም በ2019 እርጉዝ ሳለች በድጋሚ መታሰሯን ያወሳል። • የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን፤ የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጩኸት ባለፉት የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የተካሄዱት የጅምላ እስሮች ያሳሰቡት አምነስቲ ፖሊስና መከላከያ የመልሶ ማቋቋሚያ ስልጠና በሚል ከባለፈው ዓመት የካቲት ወር ጀምሮ እስር ሲያካሄድ ነበር ሲል ይከሳል። ሆኖም ብዙዎች በተለያዩ የመከላከያና የፖሊስ ማጎሪያዎች ጊዜያቸውን ካሳለፉ በኋላ በመስከረምና ጥቅምት ወር ላይ መፈታታቸውን ያስታውሳል፤ መግለጫው።
news-45168231
https://www.bbc.com/amharic/news-45168231
በቡሩንዲ ርዕሰ-መምህሩ ለተማሪ ሲፈተኑ በፖሊስ ተያዙ
በቡሩንዲ የሚገኝ የአንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ-መምህር ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ተማሪዎች መውሰድ ያለባቸው ፈተና ላይ በአንድ ተማሪ ስም ወደ ፈተና ክፍል ገብተው ሲፈተኑ ተይዘዋል።
ርዕሰ-መምህር ቤንጃሚን ማኒራምቦና በፖሊስ ተይዘው በዋና ከተማዋ ቡጁምቡራ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኘው ቡቴሬሬ የቴክኒክ ኮሌጅ ርዕሰ-መምህር የሆኑት ቤንጃሚን ማኒራምቦና የመጨረሻውን የፈተና ወረቀት እየሰሩ ሳለ ነበር ፖሊስና የሃገሪቱን የትምህርት ሚኒስትርን ጨምሮ ባለስልጣናት ወደፈተናው አዳራሽ በመግባት ያፋጠዋቸዋል። እጅ ከፍንጅ ተይዘው ማምለጫ ያላገኙት ርዕሰ-መምህሩ ቤንጃሚን ማኒራምቦና የፈፀሙትን ወንጀል እዚያው ፈተና አዳራሽ ውስጥ አምነው ተናዘዋል። • ትምህርት ዕድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ • 'ዕውቀት ሳያገኙ ትምህርት ቤት መመላለስ' • በኬንያ በርካታ ትምህርት ቤቶች በተማሪዎች ተቃጠሉ ድርጊቱን ለምንና ለማን እንደፈፀሙ ሲጠየቁም፤ ሠላም ለማስከበር ወደ ሶማሊያ ለተሰማራ የቡሩንዲ ወታደር እየተፈተኑ እንደነበርና እሱም ከግዳጅ ሲመለስ ለውለታቸው ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ቃል እንደገባላቸው ተናግረዋል። "የምትለው በሙሉ ውሸት ነው፤ ወደ እስር ቤት ትወሰዳለህ" ሲሉ ከፖሊሶች ጋር በስፍራው የነበሩት የቡሩንዲ ትምህርት ሚኒስትር ጃንቪየር ንዲራሂሻ ተናግረዉታል። ፖሊስ ስለድርጊቱ ጥቆማ ካገኘ በኋላ ርዕሰ-መምህሩን ሲያጭበረብሩ ከተገኙ ሌሎች ተማሪዎች ጋር እንደያዛቸው ተገልጿል። ጨምረውም "ምርመራ እናካሂዳለን ምክንያቱም ይህንን ስታደርግ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳልሆነ ሰምተናል" ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ከፖሊስ በተጨማሪ ሚኒስትሯን ተከትለው ዜናውን ለመዘገብ በርካታ ሪፖርተሮች በፈተናው ስፍራ ተገኝተው ነበር። ርዕሰ-መምህሩ ፈተና በማጭበርበር ከተጠረጠሩ አራት ተማሪዎች ጋር የተያዙ ሲሆን፤ አንደኛው ተማሪ ርዕሰ-መምህሩን ከተባለው ወታደር ጋር አገናኝቷል በሚል ተከሷል። ርዕሰ-መምህሩ ቤንጃሚን ማኒራምቦና በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ቡሩንዲ ውስጥ ወሳኝ ብሔራዊ ፈተናዎችን የሚወስዱ ተማሪዎች ከትምህርት ቤታቸው ውጪ በሌላ ትምህርት ቤት ውስጥ ስለሆነ ቤንጃሚን ማኒራምቦናም ፈተና በወሰዱበት ስፍራ ሊታወቁ አልቻሉም ነበር።
news-52629957
https://www.bbc.com/amharic/news-52629957
ኮሮናቫይረስ፡ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ ይችላሉ
የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሊጉ በቅርቡ ጀምሮ በዝግ ስታዲየም ቢጫወቱም እንኳን ለአገር ውስጥና ለዓለማቀፍ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እስከ 419 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍሉ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል።
ቢቢሲ ስፖርት ባገኘው መረጃ መሰረት ሊጉ ከነጭራሹ የሚቋረጥ ከሆነ አልያም ከሊጉ የሚወርዱ ቡድኖች የሚኖሩ ካልሆነ ክለቦቹ ከተገለጸው ገንዘብ ተጨማሪ ሊከፍሉም ይችላሉ። • የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በገለልተኛ ሜዳ ሊጠናቀቅ ይሆን? • ኮሮናቫይረስን ለማሸነፍ ከኢቦላ በሽታ ምን ልምድ መውሰድ ይቻላል? የፕሪምረየር ሊግ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ማስቀጠል በሚቻለበት ሁኔታ ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ትናንት አስቀጥለዋል። የ2019/20 ወድድር ዘመን 92 ጨዋታዎች ይቀሩታል። እነዚህን ጨዋታዎች እንዴት እናጠናቅ በሚለው ዙሪያ የሊጉ ክለቦች ላለፉት ሳምንታት የቪድዮ ስብሰባ ሲያደርጉ ነበር። የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ደግሞ ሊጉን ለማጠናቀቅ ቆርጠው ተነስተዋል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ቢያንስ 10 ገለልተኛ ሜዳዎች ያስፈለጋሉ ነው የሚሉት። ገለልተኛ ሜዳዎችን መጠቀም ያስፈለገው ደጋፊዎች ከሜዳ ውጪም ቢሆን እንዳይሰበሰቡ በማሰብ ነው ተብሏል። አልፎም የሚመረጡት ሜዳዎች ከፖሊስና የስፖርት ሜዳዎችን ደህንነት ከሚመረምር አካል ይሁንታ ያገኙ መሆን አለባቸው ተብሏል። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መጋቢት ወር መግቢያ ላይ ነበር በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው። ሁሉም የሊጉ ክለቦች የቀሩትን 92 ጨዋታዎች ለመጫወት ተስማምተዋል። የዚህ ዓመት ወድድር ይቋረጥ የሚል ሐሳብ ከየትኛውም ክለብ አልመጣም ተብሏል። የገንዘብ ክፍያው የተጠየቀው የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች በታሰበላቸው ጊዜ ባለመካሄዳቸው ነው። በተጨማሪም ሊጉ የሚቀጥል ቢሆን እንኳን ጨዋታዎቹ ያለ ተመልካች መካሄዳቸውና ከቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር ስምምነት ከተደረሰበት ጊዜ ውጪ ስለሚካሄዱ ነው። • በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች • በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች የፕሪምየር ሊግ ዋና ስራ አስፈጻሚው ሪቻርድ ማስተርስ በቅርቡ እንደገለጹት ደግሞ የዘንድሮው ሊግ የሚቋረት ከሆነ ክለቦች በአጠቃላይ እስከ 1 ቢሊየን ፓውንድ ኪሳራ ሊያጋጥማቸው ይችላል። ገለልተኛ ሜዳዎች ላይ ጨዋታዎቹን መቀጠል በሚለው ሀሳብ አንዳንድ ክለቦች አልተስማሙም። የሊጉ ኃላፊዎችም ቡድኖቹን ለማሳመንና በተቻለ መጠን ጨዋታዎቹን በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ለማስጀመር እየሞከሩ ነው። እስካሁን ዋትፎርድ፣ አስቶን ቪላ እና ብራይተን ጨዋታዎቹን በገለልተኛ ሜዳ ማካሄድ የሚለውን ሀሳብ በይፋ የተቃወሙ ሲሆን በሜዳቸው ደህንነቱ የተጨበቀ ጨዋታ ማካሄድ እንደሚችሉ መንግስትን ማሳመን ይጠበቅባቸዋል። የሊቨርፑል ከተማ ከንቲባ ደግሞ ጨዋታዎቹ በገለልተኛ ሜዳ ተካሂደውም ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የሚያነሳ ከሆነ ደጋፊዎች በአንፊል ስታዲየም ዙሪያ ተሰባስበው ደስታቸውን ሊገልጹ እንደሚችሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
news-53497175
https://www.bbc.com/amharic/news-53497175
ሕንድ፡ “ጠቅላይ ሚንስትራችን እባክዎን ወንዶች ቤት ውስጥ ሥራ እንዲያግዙን ንገሩልን”
በሕንድ የቤት ውስጥ ሥራ አታካች ነው። ጽዳት፣ ልብስ ማጠብ፣ ማብሰል ወዘተ. . .
ፊርማ የማሰባሰብ ሂደቱን የምትመራው ሱምባራ ጎሽ አብዛኞቹ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች የቤት ሠራተኛ ይቀጥራሉ። አሁን ግን በአገሪቱ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት የእንቅስቃሴ ገደብ ስለተጣለ ሠራተኞች ከቤታቸው ስለማይወጡ፤ ሴት የቤተሰብ አባላት የቤት ውስጥ ሥራ ጫናን ብቻቸውን ለመሸከም ተገደዋል። ይህን በመቃወም ሴቶች ፊርማ እያሰባሰቡ ነው። የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡም ተጠይቋል። ንቅናቄው እየተካሄደ ያለው ቼንጅ [ለውጥ] በተባለ ድረ ገጽ ነው። መጥረጊያ ላይ ‘ሴቶች ብቻ የሚገለገሉበት ነው እንዴ?’ የሚል ጥያቄ ተጽፎ በድረ ገጹ ይታያል። ወንዶች ለምን ልብስ አያጥቡም? ለምን አያበስሉም? ለምን ኃላፊነታቸውን አይወጡም? የሴቶቹ ጥያቄ ነው። ፊርማ የማሰባሰብ ሂደቱን የምትመራው ሱምባራ ጎሽ ትባላለች። ቤት ሆና የቢሮ ሥራ ከመሥራቷ ጎን ለጎን ታበስላለች፣ ታጸዳለች፣ ልበስ ታጥባለች። “ጠቅላይ ሚንስትሩ ሁሉም ሕንዳዊያን ወንዶች በቤት ውስጥ ሥራ የድርሻቸውን እንዲወጡ እንዲያሳስቡልን እንፈልጋለን” ትላለች። እስካሁን 70,000 ሰዎች ፊርማቸውን አኑረዋል። "ስለጫናው ስናገር ሰዎች የቤት ውስጥ ሥራውን ተይው አሉኝ” ከሁለት ዓመት በፊት የወጣ አንድ ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ በሕንድ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች ሴቶች በቀን 312 ደቂቃ ሳይከፈላቸው ሲሰሩ፤ ወንዶች ግን ለ32 ደቂቃ ብቻ ይሠራሉ። ሙምባይ የምትኖረው ሱምባራ፤ ፊርማ ማሰባሰብ የጀመረችው የራሷን እንዲሁም በአካባቢዋ ያሉ ሴቶች የሚደርስባቸውን ጫና መነሻ አድርጋ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግራለች። “የቤት ሥራ የሴት ኃላፊነት ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል። አበስላለሁ፣ አጸዳለሁ፣ አልጋ አነጥፋለሁ፣ ልብስ አጥፋለሁ፣ በቃ ሁሉንም ነገር እሠራለሁ” ትላለች። የባንክ ሠራተኛው ባለቤቷ አንዳችም እገዛ አያደርግላትም። ሁለት ልጆቿ አልፎ አልፎ ይረዷታል። ሱምባራ በሥነ ተዋልዶ ጤና ላይ ነው የምትሠራው። እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ከተጣለ ወዲህ ከቤት የቢሮ ሥራዋን ብትቀጥልም፤ በቤት ውስጥ ሥራ ስለምትጠመድ እንደቀድሞው በቢሮ ሥራዋ ውጤታማ መሆን አልቻለችም። “በጣም ስለሚደክመኝ የቢሮ ሥራዬን በአግባቡ መሥራት አልቻልኩም። ስለጫናው ስናገር ሰዎች የቤት ውስጥ ሥራውን ተይው አሉኝ።” ከዚያም ለሦስት ቀን ቤት ውስጥ ምንም ሳትሠራ ዋለች። ቤቱ ባልታጠበ እቃ እና በቆሸሸ ልብስ ተሞላ። ባለቤቷና ልጆቿ መቆጣቷ ገብቷቸው እቃና ልብስ አጠቡ፣ ቤትም አጸዱ። “ባለቤቴ አሁን አሁን ያግዘኝ ጀምሯል። የቤት ውስጥ ሥራ ምን ያህል ጫና እንደሚያሳድር ተረድቷል። ሆኖም ግን በርካታ ወንዶች የቤት ውስጥ ሥራ እየሠሩ አላደጉም።” ሕንድን ጨምሮ በሌሎችም አባታዊ ሥርዓት በሰፈነባቸው ማኅበረሰቦች ሴቶች ከልጅነታቸው ጀምሮ የቤት ውስጥ ሥራ እንዲያከናውኑ ይጠበቃል። የቤት ውስጥ ሥራ የሴቶች ብቻ ግዴታ እንደሆነ ይታመናል። ሴቶች መደበኛ ሥራ ሲይዙ የቤት እና የቢሮ ሥራን ደርበው እንዲሠሩም ይገደዳሉ። “ልጅ ሳለሁ ቤት ውስጥ እኔ ብቻ ነበርኩ የምሠራው። ወንድሜ ለራሱ እንኳን ምሳ አያቀረብም ነበር” ስትል ፓሊቪ ሳረን የተባለች ሴት ጽፋለች። አፓሳና ባሀት የተባለች ሴት ደግሞ “የቤት ውስጥ ሥራ የሴት ኃላፊነት ተደርጎ ይወሰዳል። ወንዶች እናግዝ የሚሉትም ወላጆቻቸው በአቅራቢያቸው ከሌሉ ነው” ብላለች። ኦክስፋም እንደሚለው፤ ሕንድ ሴቶች በየቀኑ ከሦስት ቢሊዮን ሰዓታት በላይ ያለ ክፍያ ይሠራሉ። ይህ ወደ ገንዘብ ሲቀየር በትሪሊዮን ሩፒ የሚቆጠር የአገር ውስጥ ምርት ይሆናል። ኦክስፋም እንደሚለው፤ ሕንድ ሴቶች በየቀኑ ከሦስት ቢሊዮን ሰዓታት በላይ ያለ ክፍያ ይሠራሉ። "ለምን ስለ ጾታ እኩልነት አይናገሩም?” ሱምባራ ታዳጊ ሳለች እናቷ እና አክስቶቿ በቤት ውስጥ ሥራ ደፋ ቀና ሲሉ ስታይ፤ “እኔ ሳድግ እንደነሱ አልሆንም” ትል ነበር። ስታገባ በቤቷ እኩልነት የሰፈነ ቢመስልም፤ እውነታው ግን የሥራ ጫና ሙሉ በሙሉ እሷ ላይ መውደቁ ነው። “እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ሲጣል፤ እኔ ላይ የተጣለው የቤት ኃላፊነት በግልጽ መታየት ጀመረ” ትላለች። በምትኖርበት አካባቢ ያሉ ሴቶችም ተመሳሳይ እሮሮ ያሰማሉ። ለጠቅላይ ሚንስትሩ አቤቱታ ለማሰማት የወሰኑትም ለዚሁ ነው። አንዳንድ ሴቶች አጋራቸው መሥራት እንደሚጠበቅበት ላያስቡም ይችላሉ። “የማበስለውን ምግብ ቅሬታ ሳያሰማ ነው የሚበላው፤ እንዴት ያለ መልካም ወንድ ነው” የሚሉም አሉ። ሱምባራ እንደምትለው ችግሩን በቀላሉ መቅረፍ ያልተቻለው እነዚህ ወንዶች የቅርብ ሰው ስለሆኑ ነው። “የገዛ አባትሽን፣ ወንድምሽን፣ ባልሽን እንዴት ትወቅሻለሽ? ከባድ ይመስላል። ግን ጉዳዩ የኔም ጭምር ስለሆነ ከመናገር ወደኋላ አልልም” ትላለች። ባለቤቷ ፊርማ እያሰባሰበች መሆኑን ሲሰማ ደግፏታል። ጓደኞቹ ግን እንደተሳለቁበት ትናገራለች። “ቤት ውስጥ ባለቤትህን ብታግዝ ኖሮ ለሞዲ ደብዳቤ አትጽፍም ነበር” ብለውታል። ባለቤቷ “አብዛኞቹ ወንዶች ከባለቤታቸው ይልቅ ሞዲን ይሰማሉ” ሲል ለጓደኞቹ ምላሽ ሰጥቷል። ሱምባራ ፊርማ በማሰባሰቧ የወቀሷትም አልታጡም። ጠቅላይ ሚንስትሩን “በተራ ጉዳይ” እያስቸረች ነው ያሏትም አሉ። “አንዳንድ ሰዎች የሕንድ ሴቶች መሥራት አለባቸው ብለው ጽፈውልኛል። አዎ መሥራት አለብን። ግን ወንዶችስ?” ስትል ትጠይቃለች። ለመሆኑ ሞዲ በቀጣይ ንግግር ሲያደርጉ ስለ ቤት ውስጥ ሥራ ክፍፍል ያወራሉ ብለሽ ትጠብቂያለሽ? የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ ለሱምባራ ቀርቦላት ነበር። እንዲህ ስትል መልሳለች፦ “ሞዲ በርካታ ሴት ደጋፊዎች አሏቸው። ስለዚህ ለሴቶች ስለሚጠቅም ጉዳይ መናገር አለባቸው። ክረምቱ ሲገባ ስለ ብርድና ስለ ሳል አውርተዋል። ታዲያ ለምን ስለ ጾታ እኩልነት አይናገሩም?”
48406744
https://www.bbc.com/amharic/48406744
ሞና ሊሳ ዲፕ ፌክ በተሰኘ ቴክኖሎጂ "ነፍስ ዘራች"
የሊዮናርዶ ዳ ቬንቺ ዝነኛ የጥበብ ሥራ የሆነችው 'ሞና ሊሳ' በግጥም፣ በዘፈን፣ በልብ-ወለድ ወይንም በአጭር ወግ ውስጥ ነፍስ ዘርታ አብረናት የልቦለዱን ዓለም ብንገማሸርበት አይደንቅም።
የ 'አርተፊሻል ኢንተለጀንስ' የጥናት ባለሙያዎች የወደድነው አይኗን፣ ያደነቅነው አንገቷንና አፏን በተንቀሳቃሽ ምስል ማሳየት ችለዋል። እንዴት? ካሉ፤ አንዲት ነጠላ ምስሏን ወስደው በቤተ ሙከራ ውስጥ ነው ማንቀሳቀስ ቻሉ መልሳችን። • "ሀኪሙ ትግሉን አቀጣጠለው እንጂ የሚታገለው ለታካሚው ነው" • ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ለምንስ ግድ ይሰጠናል? ቴክኖሎጂው 'ዲፕ ፌክ' ይሰኛል። ይህ ቴክኖሎጂ የአንድ ነገር ድግምግሞሽን ተጠቅሞ ነው ሥራውን የሚከውነው። የግኝቱ ባለቤት ሞስኮ የሚገኘው የሳምሰንግ ቤተ ሙከራ ነው ። ነገሩ ብዙዎችን አላስፈነጠዘም። ፊታቸውን ቅጭም አድርገው፤ "ይህ 'ዲፕ ፌክ' ያላችሁት ቴክኖሎጂ ላልተገባ ተግባር የመዋል እድሉ የትየለሌ ነው" ሲሉ የተቃወሙ አሉ። ይህንን የምርምር ሥራ ይበል የሚያሰኝ ብለው ያጨበጨቡ፣ የወደፊቱ የቴክኖሎጂ እመርታ ቀድሞ ያሳየ ብለው ያደነቁም አልጠፉም። ይህ የሳምሰንግ ቴክኖሎጂ ግን የ7ሺህ ስመ ጥር ሰዎችን ምስሎች ከዩቲዩብ ሰብስቧል። ከዚያም ከምስሉ ላይ የፊት ቅርፅንና እንቅስቃሴን ወስዶ 'እፍ' በማለት ሕይወት ይዘራባቸዋል። እንደውም ይግረማችሁ በማለት የሳልቫዶር ዳሊን፣ የአልበርት አንስታይንን፣ የፌይዶር ዶስቶቭስኪ እና የማርሊን ሞንሮ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለቅቋል። እ.ኤ.አ በ2017 በቴልአቪቭ ዩኒቨርስቲ ተመሳሳይ የምርምር ሥራ ይፋ ተደርጎ ነበር። • ታዋቂው ኬንያዊ ደራሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ያኔ ምስላቸው ተወስዶ በሌሉበት፣ ባልዋሉበት እንደዋሉ ተደርገው የቀረቡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ነበሩ። የዚህ ፈጠራ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሱፓሶርን ሱዋይናኮርን በወቅቱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ቴክኖሎጂው ላልተገባ ድርጊት ሊውል ይችላል ነገር ግን በጎ ጎንም አለው። የምንወደውን ሰው በሞት ስንነጠቅ፣ ፊታችንን ነጭተን፣ ከል ለብሰን ከል መስለን ከምንቀመጥ፣ ምስላቸውን ሕያው እንዲሆን በማድረግ መፅናናት እንችላለን ይላሉ። ባለሙያዎች ግን የፖለቲከኞች ምስል በዚህ ቴክኖሎጂ ተቀነባብሮ፤ ሀሰተኛ መረጃ ለማሰራጨት ወይም የአንድን አገር ሕዝብ ግራ ለማጋባት ሊውል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ይገልፃሉ። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት ይህ 'ዲፕ ፌክ' ቴክኖሎጂ ዝነኛ ሰዎችን ባልዋሉበት አስውሎ የወሲብ ፊልሞች ላይ ሊያሳትፋቸው ይችላል ያሉም አልታጡም። የ 'አርተፊሻል ኢንተለጀንስ' ቴክኖሎጂ አማካሪ የሆኑት ዴቭ ኮፕሊን፤ በዚህ 'ዲፕ ፌክ' ቴክኖሎጂ ላይ እንኳንም በጊዜ መወያየት ጀመርን ይላሉ። "በጊዜ ውይይት መጀመራችን መልካም ነው፤ እውነት የሚመስሉ ሀሰተኛ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በቀላሉ መሥራት እንደሚቻል ማህበረሰቡ ማወቅ አለበት" ብለዋል።
news-54179473
https://www.bbc.com/amharic/news-54179473
እባብ ፡ በሕይወት ያለ እባብን እንደ ጭምብል ለብሶ አውቶቡስ የተሳፈረው ግለሰብ
ሕይወት ያለው እባብን እንደ ጭምብል አፉን አስኪሸፍን ድረስ በአንገደቱ ዙሪያ ጠምጥሞ አውቶቡስ የተሳፈረው ግለሰብ አግራሞት ፈጠረ።
ግለሰቡ እባቡን አንገቱ ላይ ጠምትሞ አውቶብስ ውስጥ ተቀምጦ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከስዊንተን ወደ ማንችስተር ከተማ በሚሄደው አውቶብስ ላይ የተሳፈረው ግለሰብ አንገቱ ላይ የጠመጠመው እባብ ነው ብለው አላሰቡም ነበር። ሰውየው የአንገት ሹራብ ያደረገ ነበር የመሰላቸው ብዙዎቹ ተሳፋሪዎች። አንድ ተሳፋሪ ለቢቢሲ እንደገለጸችው እንዲሁ ስካርፍ ነበር የመሰለኝ ሲንቀሳቀስ ነው የደነገጥኩት ብላለች። በማንችስተር የትራንስፖርት ስምሪት ተቆጣጣሪዎች እውነተኛ እባብ በዚህ በኮቪድ-19 ዘመን እንደ አፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አይቆጠርም ሲሉ ድርጊቱ ተቀባይነት እንደሌለው አረጋግጠዋል። አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገች የዓይን እማኝ ነገሩ በጣም እንደገረማትና በጣም እንዳሳቃት ተናግራለች። ጨምራም ግለሰቡ አንገቱ ላይ የጠመጠመው እባብ አብረውት ይጓዙ የነበሩት መንገደኞችን ይህን ያህል ያሰበረ አልነበረም ስትል መስክራለች። በዩናይትድ ኪንግደም በሕዝብ መጓጓዣዎች የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ ከ11 ዓመት በታች ላሉ ሕጻናት ካልሆነ በስተቀር ግዴታ ነው። ነገር ግን በጤና ችግር ላይ ያሉ ሰዎች ወይም የተለየ ምክንያት ያላቸው ሰዎች ጭምብል እንዲያጠልቁ አይገደዱም። የግሬተር ማንችስት ቃል አቀባይ በጉዳዩ ዙርያ ተጠይቆ "ጭምብል ለሰርጀሪ አይደለም የተፈለገው፤ ከምንም ይሰራ ምንም ይሁን አፍና አፍንጫን እስከሸፈነ ድረስ ስካርፍም ይሁን እባብ ምን ለውጥ ላይኖረው ይችላል" ብሏል። ጨምሮም "…ነገር ግን አፍና አፍንጫን መሸፈን በምን በሚለው ዙርያ ሁሉንም የሚያስማማ ነገር ባይኖርም ነፍስ ባለው እባብ አፍና አፍንጫን መሸፈን ግን የሚጠበቅ አልነበረም" ሲል የግለሰቡ ድርጊት ያልተጠበቀ መሆኑን ተናግሯል።
53470938
https://www.bbc.com/amharic/53470938
በርካታ ኬንያውያን ለምን ኮሮናቫይረስ የለም ብለው ያምናሉ?
ሳይንስን የተመረኮዘው ዓለም አቀፍ መረጃ እንደሚያሳየው ወደ 600,000 ሰዎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ሆኖም ግን ኬንያ ውስጥ አንድ ሰው “ኮሮናቫይረስ ይዞኛል” ቢል ውሸታም ወይም የመንግሥት ቅጥረኛ ሊባል ይችላል። ለመጀመሪያ ጊዜ ከበሽታው አገግማ ከሆስፒታል የወጣችው አይቪ ብሬንዳ ሮቲችን ብዙዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ሲያብጠለጥሏት ነበር። መንግሥት፤ ሕዝቡን ስለ ኮሮናቫይረስ መኖር ለማሳመንና ድጎማ ለማግኘት ሲል አይቪን እንደመለመለ ብዙዎች ያምናሉ። በሽታው መሰራጨት በጀመረበት ወቅት፤ ኮቪድ-19 አፍሪካውያንን አይዝም የሚል የተሳሳተ እሳቤ ነበር። • በኮሮናቫይረስ ሰበብ ትኩረት የተነፈጉት የዓለማችን ገዳይ ችግሮች • ሩሲያ የኮሮናቫይረስ ክትባት መረጃዎችን ለመመንተፍ ሞክራለች መባሏን ውድቅ አደረገች • የሩሲያ የመረጃ መረብ ሰርሳሪዎች የኮቪድ-19 ክትባት ምርምርን ኢላማ ማድረጋቸው ተነገረ አሁን ላይ ኬንያ ውስጥ 11,000 ሰዎች በበሽታው እንደተያዙና 200 ሰዎች እንደሞቱ ሪፖርት ቢደረግም፤ ኮሮናቫይረስ የሚባል ወረርሽኝ የለም ብለው የሚያምኑ ጥቂት አይደሉም። አንድ መኪና አጣቢ “ኮሮናቫይረስ የዘመናችን ትልቁ ውሸት ነው” ሲል፤ አንዳንድ ጋዜጠኞች ደግሞ “ዘለግ ያለ ጊዜ የወሰደ ጉንፋን ነው” ይላሉ። ፓስተር ሮበርት ቡራሌ የተባሉ ታዋቂ ተናጋሪ፤ በበሽታው ተይዘው ናይኖቢ ሆስፒታል ቢገቡም፤ የምርመራ ውጤታቸው የሐሰት ነው የሚል ወሬ ተናፍሷል። ቤንሰን ሙሱንጉ የተባሉ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ፤ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ለ15 ቀናት ህክምና ተደርጎልኛል ብለው እንዲዋሹ መንግሥት ገንዘብ ከፍሏቸዋል የሚል የተሳሳተ መረጃ መሰራጨቱም አይዘነጋም። መሰል ወሬዎች በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች እውነታውን እንዳይናገሩ ጫና እያሳደሩ ነው። “የሕዝብ እንደራሴዎች ጥርጣሬ እያጫሩ ነው” ፖለቲከኞችና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በቫይረሱ ቢያዙም፤ ማኅበረሰቡ ያገለናል ብለው ስለሚፈሩ የምርመራ ውጤታቸውን ለሕዝብ አያሳውቁም። ስለበሽታው በግልጽ የሚናገሩ ጥቂቶች ናቸው። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ “እርስዎ ወይም የሚወዱት ሰው በኮቪድ-19 ተይዟል? ተብሎ ሲጠየቅ” የበርካቶች መልስ “በፍጹም” ነው። የእነዚህን ሰዎች ጥርጣሬ ያጎላው የሕዝብ እንደራሴ ጁድ ንጆሞ ሐምሌ ላይ ለፓርላማ አባላት ያደረጉት ንግግር ነው። እናታቸው ከሞቱ በኋላ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ስለተረጋገጠ በሌሊት፣ በአስቸኳይ ለመቅበር መገደዳቸውን ለፓርላማው የጤና ዘርፍ ኮሚቴ አስረድተዋል። “ጊዜ እንዲሰጠን ለምኜ ነበር፤ ነገር ግን በአስገዳጅ ሕጉ ምክንያት ዘጠኝ ሰዓት ላይ መረጃው ደርሶን፣ ማታ ሁለት ሰዓት እንድንቀብር ተደረገ፤ ለ82 ዓመታት ሕይወቷ የሚመጥን ሽኝት አላደረግንም” ብለዋል። የሕዝብ እንደራሴው እናታቸውን ከቀበሩ በኋላ ስለ ኢንፍሉዌንዛ ለሚያጠና ማዕከል እና ለናይሮቢ ሆስፒታል ናሙና ሰጥተው፤ ሟቿ ኮሮናቫይረስ እንዳልያዛቸው ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል። የኬንያ የህክምና ምርምር ተቋም የምርመራ ውጤት፤ ቫይረሱ መኖሩንም አለመኖሩንም ሊያሳይ የሚችልበት እድል እንዳለ ለማስረዳት ሞክሮ ነበር። ሆኖም የሕዘብ እንደራሴው ንግግር በሽታው የለም የሚለውን ጥርጣሬ አጉልቷል። አሁንም ድረስ በሽታው እንዳለና አስጊ እንደሆነም ያልተረዱ ኬንያውያን አሉ። በሴራ ትንተና የሚያምኑ መብዛታቸው በመንግሥት እና በሕዝቡ መካከል ያለውን መተማመን ቀንሷል። በሌላ በኩል አገሪቱ ጥላቸው ከነበሩ እገዳዎች አንዳንዶቹን እያነሳች ነው። ለሕዝቡ ግልጽ መረጃ መስጠት ያሻል በናይሮቢ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ኦሙ አንዛላ እንደሚሉት፤ አፍሪካ ውስጥ በሽታን በተመለከተ ለሕዝብ ግልጽ መረጃ ያለመስጠት ልማድ አለ። የአገር መሪዎች ሲታመሙ እንኳን በሚስጥር ለህክምና ወደ ውጪ አገራት ይሄዳሉ እንጂ በአደባባይ ስለህመማቸው አይናገሩም። በጤናው ዘርፍ የሚሠሩ ሙያተኞች ለሕዝቡ በቂ መረጃ አልሰጡም ሲሉ ፕሮፌሰሩ ይወቅሳሉ። የማኅበረሰቡን ጥያቄ በማድመጥ፤ ሰው ሊረዳው በሚችለው አገላለጽ ስለበሽታው ማስረዳት እንደሚገባቸውም ይመክራሉ። ለሕዝቡ መግለጫ ሲሰጥ የጤና ባለሙያዎች ብቻ በሚረዱት ቋንቋ መሆን የለበትም። በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ያለ ሰው በሚረዳው መንገድ መረጃ መስጠት ያስፈልጋል። መግለጫው ይህን አታድርጉ፣ ያን አድርጉ ከሚል ትዕዛዝ ባለፈ ዝርዝር መረጃ የያዘ መሆንም ይጠበቅበታል። ሕዝቡ ጥያቄው ከተመለሰለት እንዲሁም እውነታውን ከተረዳ፤ የበርካቶችን ሕይወት መታደግ ይቻላል። [ይህ ጽሑፍ በዋይሂጋ ሙዋራ ተዘጋጅቶ ከአፍሪካውያን ጋዜጠኞች የተላኩ ደብዳቤዎች በሚስተናገዱበት አምድ የተነበበ ነው።]
56954701
https://www.bbc.com/amharic/56954701
አምስት ሴናተሮች ቀጣዩ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ 'ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም' አሉ
አምስት የአሜሪካ ሴናተሮች ኢትዮጵያ ከአምስት ሳምንታት በኋላ የምታካሂደው ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም አሉ።
ቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም ያሉት ሴናተሮች ሴናተሮቹ ይህን ያሉት በቅርቡ የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ለተሾሙት አምባሳደር ጆፍሪ ፌልትማን በጻፉት ደብዳቤ ነው። ሴናተሮቹ ቤንጃሚን ኤል ካርዲን፣ ቲም ኬይን፣ ጃኪ ሮስን፣ ኮርይ ኤ ቡከር እና ኤድዋርድ ጄ ማርኬይ ስለመጪው አገራዊ ምርጫ፣ ስለትግራይ እና በሌሎች የአገሪቱ ስፍራዎች ስላሉ ግጭቶች ለተሿሚው ልዩ መልዕክተኛ መልዕከታቸውን አጋርተዋል። "ምርጫው ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም" ሴናተሮቹ ከሳምንታት በኋላ የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ነጻ፣ ሚዛናዊ እና ግልጽ ሆኖ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አያሟላም ብለዋል። በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው ተዓማኒነት ባለው መልኩ ሊካሄድ አይችልም በሚል ምክንያት ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ሴናተሮቹ በደብዳቤያቸው አስታውሰዋል። በሺህዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊዎች እና አመራሮች መታሰር በምርጫው እምነት ለማጣታቸው አንዱ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል። ሴናተሮቹ ምርጫውን በተመለከተ ይህን ማለታቸውን ተከትሎ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስተያየትን ለማካተት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲዎች አባላቶቻችን እና አመራሮችን ለእስር እየተዳረጉ ነው፣ ቢሮዎቻችን እየተዘጉ ስለሆነ በምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችል ሁኔታ የለምበሚል ምክንያት በምርጫው እንደማይሳተፉ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ይሁን መንግሥት ቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ እና ተዓማኒነት ያለው ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጸዋል። ሴናተሮቹ፤ "የኢትዮጵያን ሕዝብ እምነት ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑ ማሻሽያዎች ሳይደረጉ ምርጫው የሚካሄድ ከሆነ ዘርን እና ፖለቲካን መሠረት ያደረገው ውጥረት በመላው አገሪቱ ነግሶ ወደ ከፋ ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት አለን" ብለዋል። የትግራይ ቀውስ ሴናተሮቹ በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልገው፣ 1.7 ሚሊዮን ሕዝብ በክልሉ ውስጥ ተፈናቅሎ እንደሚገኝ እና ወደ 62ሺህ የሚጠጉ ሰዎች አገር ጥለው መሰደዳቸውን በደብዳቤያቸው አትተዋል። ሴናተሮቹ ለልዩ መልዕክተኛው በጻፉት ደብዳቤ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲረጋገጥ፣ የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንዲወጣ፣ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ እና ጥፋተኞች ለሕግ እንዲያቀርቡ ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን እንዲጠቀሙ እናበረታታዎታለን ብለዋል። የኤርትራ ሠራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ያለፉት የደህንነት ስጋት ስላለባቸው መሆኑን በመግለጽ ከኢትዮጵያ እንደሚወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መናገራቸው ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኤርትራ መንግሥትም ጦሩን ከኢትዮጵያ እንደሚያስወጣ ገልጿል። ብሔር ተኮር ግጭቶች አራቱ ሴናተሮች በኢትዮጵያ ያለው ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት ያሳስበናል ብለዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የደረሱ ጥቃቶችን አስታውሰው፤ ልዩ መልዕክተኛው በኢትዮጵያ ሰላም፣ እርቅ እና መቻቻልን እንዲኖር እንዲሰሩ አሳስበዋል። ጄፍሪ ፌልትማን ፌልትማን ማን ናቸው? አሜሪካ በኢትዮጵያና በአካባቢዋ ባሉ አገራት ውስጥ ስላሉ ጉዳዮች በቅርበት እንዲከታተሉላት አምባሳደር ጆፈሪ ፌልትማንን መሾሟን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ዋና ጸሐፊዎች ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው ወቅትም በልዩ መልዕክተኝነት አገልግለዋል፤ በተጨማሪም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ፌልትማን በሊባኖስ፣ በኢራቅ፣ በእስራኤል፣ በቱኒዚያ፣ በሃንጋሪና በሄይቲ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል።
news-51134346
https://www.bbc.com/amharic/news-51134346
የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ጥር ላይ እንዲካሄድ ተወሰነ
ቀጣዩ የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ አዘጋጅ ሃገር ካሜሮን አስታወቀች።
የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ይዘጋጅ የነበረው በወርሃ ሰኔ እና ሐምሌ ላይ የነበረ ሲሆን፤ ግን እነዚህ ወራት በካሜሩን ዝናባማ ስለሚሆኑ ወደ ጥር እንዲዘዋወር ተደርጓል ተብሏል። ይህ ማለት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወቱ እና ለአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፉ ሃገራት ተጫዋቾች እስከ ስድስት የክለብ ጨዋታ ያመልጣቸዋል። ትናንት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን-ካፍ እና የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያካሄዱትን ስብሰባ ተከትሎ የካፍ ፕሬዝደንት በትዊተር ገጻቸው ላይ "የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ከጥር 1 እስከ ጥር 29 ድረስ ይካሄዳል። የጊዜ ለውጡ በአየር ጠባይ ምክንያት በካሜሮን ጥያቄ መሠረት ተቀይሯል" ሲሉ አስፍረዋል። የካፍ ምክትል ፕሬዚደንት ቶንይ ባፉኤ በበኩላቸው፤ በቀን ለውጡ ላይ ከካሜሮን ሜትዮሮሎጂ ባለሥልጣናት፣ አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች ጋር እንዲሁም የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋር በጥልቅ መወያየታቸውን አስረድተዋል። ካሜሮን የ2019 ዋንጫን እንድታዘጋጅ ተመርጣ እንደነበረ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ከስታዲየም ግንባታ እና ከአጠቃላይ ዝግጅት ጋር ተያይዞ የነበራት ዝግጁነት ዘገምተኛ ነው ከተባለ በኋላ ነበር ግብጽ እንድታዘጋጅ እድሉ የተሰጣት። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ
news-53386930
https://www.bbc.com/amharic/news-53386930
ለዛሃ ዘረኛ መልዕክት የላከው የ12 ዓመት ልጅ በቁጥጥር ሥር ዋለ
የአይቮሪ ኮስት ብሔራዊ ቡድንና በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የክርስታል ፓላስ ተጫዋች ለዊልፍሬድ ዛሃ የዘረኝነት መልዕክት የላከው የ12 ዓመት ልጅ በፖሊስ መያዙ ተነገረ።
ዊልፍሬድ ዛሃ (ከፊት ለፊት) ዛሃ ከዚህ በተጨማሪም በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት መሰል መልዕክቶች እንደሚደርሱት አስታውቋል። የክርስታል ፓላስ አሰልጣን ሮይ ሆድሰን የዘረኝነት ምልዕክቶቹን "የፈሪ ድርጊትና አሳፋሪ" ተግባር ሲሉ ገልጸውታል። ፕሪሚየር ሊጉም በ27 ዓመቱ አጥቂ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት "በምንም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው" ሲል አውግዞታል። ፖሊስ የዛሃ የቆዳ ቀለም ላይ ያነጣጠሩ ዘረኛ መልዕክቶችን እየመረመርኩ ነው ካለ ከሰዓታት በኋላ አንድ የ12 ዓመት ታዳጊን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። የዌስት ሚድላንድስ ፖሊስ ትናንት በትዊተር ገጹ ላይ "ለእግር ኳስ ተጫዋቹ በርካታ ዘረኝነት የተሞላባቸው መልዕክቶች እንደደረሱት ሪፖርት ደርሶናል። ባደረግነው ማጣራትም ከሶሊሁል ከተማ የ12 ዓመት ልጅ በቁጥጥር ሥር ውሏል። ዘረኝነትን አንታገስም" ብሏል። ዛሃ በትዊተር ገጹ ላይ የደረሱትን ዘረኛ መልዕክቶች አስፈሯል። "በግጥሚያ ቀን እንዲህ አይነት መልዕክት ሲደርስ በጣም ያሳዝናል። መልካም ነገሩ ዛሃ የደረሰውን መልዕክት ሰዎች እንዲያውቁት አድርጓል። በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም ሰው ዝምታን መምረጥ የለበትም" ብለዋል የክሪስታል ፓላስ አሰልጣኑ ሮይ ሆድሰን። ፕሪሚየር ሊጉ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ ከተመለሰ በኋላ ተጨዋቾች ዘረኝነትን በመቃወምና በጥቁሮች ላይ የሚፈጸሙ በደሎችን ለመቃወም ጨዋታዎች ከመጀመራቸው በፊት የ'ብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴን በመደገፍ ተንበርክከው አጋርነታቸው ይገልጻሉ።
news-51253933
https://www.bbc.com/amharic/news-51253933
የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር ቦይንግ አውሮፕላን የሙከራ በረራውን አደረገ
ቦይንግ 777ኤክስ የተሰኘው የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር አውሮፕላን የሙከራ በራራውን በድል አጠናቋል።
ቦይንግ የተሰኘው አውሮፕላን ፈብራኪ ድርጅት 737 ማክስ በተሰኙ አውሮፕላኖቹ ላይ በደረሰ እክል ምክንያት የሰው ሕይወት ከጠፋ በኋላ ገበያ ለማግኘት ሲዳክር ከርሟል። የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢንዶኔዢያ አቻው ንብረት የሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች በወራት ልዩነት ተከስክሰው በድምሩ 346 ሰዎች ሞተዋል። ከአደጋዎቹ በኋላ የተቀሩትን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ ያገደው ቦይንግ እነሆ ግዙፍ አውሮፕላን ይዞ ብቅ ብሏል። ለአራት ሰዓትታ የዘለቀው የሙከራ በረራ ሲያትል የተሰኘችው የአሜሪካ ከተማ አቅራቢያ ነው የተከወነው። የተሳካው በረራ ከመካሄዱ በፊት ሁለት ጊዜ በአየር ፀባይ ምክንያት በረራዎች እንዲቋረጡ ተደርገዋል። 252 ጫማ [76 ሜትር] የሚረዝመው አውሮፕላን የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር የንግድ አውሮፕላን ነው ተብሎለታል። ቦይንግ እስካሁን 309 777ኤክስ አውሮፕላኖች ሸጫለሁ የአንዱ ዋጋ ደግሞ 442 ሚሊዮን ዶላር ነው ብሏል። የድርጅቱ ግብይት ባለሙያ ዌንዲ ሶወርስ "ድርጅታችን ትልቅ ነገር ማድረግ እንደሚችል ያሳየ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። አውሮፕላኑ 360 ሰዎች የመጫን አቅም ካለው ኤርባስ ኤ350-1000 ጋር ተመሳሳይ ባሕሪ አለው ተብሏል። ቦይንግ አደጋ የጠናባቸውን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ሲያመርት ለደህንነት የሰጠው ዋጋ ዝቅ ያለ ነው ተብሎ ብዙ ወቀሳ ደርሶባታል። እንዳይበሩ የታገዱት አውሮፕላኖች እንደገና ተፈትሸው ወደ ሰማይ ይወጣሉ ሲል ድርጅቱ ማሳወቁ አይዘነጋም። ማክስ 737 የቦይንግ እጅግ በብዛት የተሸጡ አውሮፕላኖች ሲሆን አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ በመተጋዳቸው ምክንያት ቦይንግ 9 ቢሊዮን ዶላር እንደከሰረ ይገመታል።
news-55467434
https://www.bbc.com/amharic/news-55467434
ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ ሆስፒታሎች እየተጨናነቁ ነው
በደቡባዊ እንግሊዝ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሆስፒታሎች እየተጨነናነቁ መሆኑ ተገልጿል።
ያሳለፍነው ቅዳሜ ደግሞ በለንደን የአምቡላንስ አገልግሎት ታሪክ ውስጥ እጅግ ስራ የበዛበት ቀን ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ አዲሱ የኮሮናቫይረስ አይነት እንደሆነ ተገልጿል። የአምቡላንስ አገልግሎት ሰጪውና ሌሎች ተጨማሪ ሁለት የድንገተኛ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፤ ሰዎች በጣም አሳሳቢ የጤና እክል ካልገጠማቸው የአደጋ ጊዜ ቁጥር ወደሆነው 999 እንዳይደውሉ ጭምር እስከማሳሰብ አድርሷቸዋል። የድንገተኛ ህክምና ኮሌጅ ፕሬዝደንት የሆኑት ዶክተር ካትሪን ሄንደርሰን አንድ ለንደን ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ሁሉም ታማሚዎች የኮሮናቫይረስ ህሙማን መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቷ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ''በአሁኑ ሰአት ነገሮች በጣም አስቸጋሪ ናቸው። በገና በአል ሳምንት ይህን ያክል ቁጥር ያለው ታማሚ ማስተናገድ አዳጋች ነው'' ብለዋል። አክለውም ''በአሁኑ ሰአት በርካታ ታማሚዎች እያስተናገድን ነው፤ ነገር ግን ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን የተሟላ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ላይ የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ነው'' ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የስኮትላንድ የጤና ስርአት ከአቅሙ በላይ ታካሚዎችን እያስተናገደ እንደሆነ ዶክተሮች የገለጹ ሲሆን፤ አንዳንድ ሆስፒታሎች የኮቪድ-19 ታካሚዎችን ለመርዳት የሚያስችል ድጋፍ ጠይቀዋል። የግላስኮው ሕክምና ባለሙያዎች ኮሌጅ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ጃኪ ታይለር በበኩላቸው በአሁኑ ሰአት በደቡባዊ እንግሊዝ እየታየ ያለው ሁኔታ ስኮትላንድ ውስጥ ባሳለፍነው ሕዳር ወር ላይ ከተከተሰተው ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ገልጸዋል። ''እስካሁኑ ሰአት ድረስ እንኳን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኮቪድ-19 ታማሚዎች ወደ ሆስፒታሎች እየመጡ ሲሆን አብዛኛዎቻቸው የመተንፈሻ አካላት እክል ያጋጥማቸዋል'' ብለዋል። እሁድ ዕለት በዩናይትድ ኪንግደም 30 ሺህ 501 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን፤ 316 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ቫይረስ የተነሳ ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። ነገር ግን ስኮትላንድ ባለፉት አራት ቀናት በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ቁጥር አለመግለጿ እና ኖርዘርን አየርላንድ የሚያዙትንም ሆነ የሚሞቱን ሰዎች ቁጥር አለመግለጿ አጠቃላይ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል አስገምቷል። ከሳምንት በፊት በመላው ዩናይትድ ኪንግደም 21 ሺህ 286 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል መግባታቸውም ተገልጿል። እሁድ ዕለት ቢቢሲ የተመለከተው ሰነድ ላይ የድንገተኛ ክፍል ሰራተኞችና የአምቡላንስ አገልግሎት ሰጪዎች የኮሮናቫይረስ ታማሚዎችን ለሆስፒታል ሰራተኞች ለማስረከብ እስከ ስድስት ሰአት ድረስ ፈጅቶባቸው ነበር። አንድ የድንገተኛ ክፍል ሰራተኛ ለቢቢሲ ሲናገር ''አንዳንድ ታማሚዎች አምቡላንስ ውስጥ ጭምር ህክምና ተደርጎላቸዋል። ምክንያቱም ሆስፒታሎች ውስጥ የሚገኙት አልጋዎች ሞልተው ነበር'' ብሏል።
news-49404011
https://www.bbc.com/amharic/news-49404011
ዕውቁ አሜሪካዊው ተዋናይ ዘ ሮክ በሚስጢር ተሞሸረ
እውቁ አሜሪካዊ ተዋናይና ፕሮድዩሰር ድዋይን ዳግላስ ጆንሰን፤ በቅፅል ስሙ 'ዘ ሮክ' በህዋይ በተካሄደ ሚስጢራዊ የሠርግ ሥነ-ሥርዓት ለረዥም ዓመታት ፍቅረኛው ከነበረችው ሎረን ሃሺያን ጋር በጋብቻ መተሳሰሩ ተነገረ።
• ፍቅርና ጋብቻ በቀይ ሽብር ዘመን • ከስም ፊት የሚቀመጡ መለያዎና አንድምታቸው የ47 ዓመቱ ጎልማሳ ዘ ሮክ ይህንን ዜና ይፋ ያደረገው 154 ሚሊየን ተከታዮች ባሉት የኢንስታግራም ገፁ ላይ ነው። ጥንዶቹ ላለፉት 13 ዓመታት የዘለቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ግንኙነቱን የጀመሩት 'ዘ ጌም ፕላን' የተሰኘውን ፊልሙን በመቅረፅ ላይ ሳለ ነበር፤ ከዚያም የሁለት ልጆች ወላጆች ለመሆን በቅተዋል። ታዲያ ይህንን ሚስጥራዊ የሠርግ ሥነ ሥርዓታቸውን የሚያሳየው ፎቶግራፍ በኢንስታግራም ከተለቀቀ በኋላ በሦስት ሰዓታት ውስጥ ከሰባት ሚሊየን በላይ ሰዎች ወደውታል። የዓለማችን ዝነኛ የፊልም ኮከብ ዘ ሮክ [በመዝገብ ስሙ ድዋይን ጆንሰን] ከሆሊውድ እውቅ ተዋናዮች የእንኳን ደስ አለህ መልዕክቶችም ጎርፈውለታል። በፎቶግራፉ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት የሆሊውድ ኮከቦች መካከል ራያን ሬይኖልድስ፣ ካረን ጊላን፣ ፒ ዲዲ፣ ጀሲካ ቸስቴይን፣ እና ናኦሚ ካምፕቤል ይገኙበታል። • ፍቅር እና ግንኙነት ከቲንደር አብዮት በኋላ ባለቤቱ ሎረን በ1980ዎቹ በነበሩት ሙዚቃዎች በቦስተን ባንድ በተሰራው 'ሞር ዛን ኤ ፊሊንግ' ሙዚቃ አባቷ ድራም ተጨዋች ነበሩ። እሷም ሙዚቀኛ ስትሆን በኦንላይን በምትለቃቸው የሙዚቃ ሥራዎች ትታወቃለች። ይህ ለ ዘ ሮክ ሁለተኛ ጋብቻው ነው ። ከመጀመሪያው ሚስቱ ዳኒይ ጋርሺያ ጋር በአውሮፓዊያኑ 1997 ትዳር መስርተው 18 ዓመት ወጣት ልጅ አድርሰዋል።
news-55205427
https://www.bbc.com/amharic/news-55205427
ፋሮ ደሴቶች፡ በባህር ውስጥ የተገነባው አስደናቂው አደባባይ
በዴንማርክ ውስጥ የምትገኘው ራስ ገዟ የፋሮ ደሴቶች በባህር ውስጥ ስትሰራ የነበረውን የመኪኖች መተላፊያ ዋሻዎችና የ አደባባይ ግንባታ አጠናቃለች ። የግንባታ ስራውም ሶስት አመታትን ወስዷል።
የባህር ውስጡ የመኪኖች መተላለፊያ ዋሻዎች ስትሪይሞይና ኤይስቱሮይ የተባሉ ደሴቶችን የሚያገናኙ ሲሆን አስራ አንድ ኪሎ ሜትር እርዝማኔ አላቸው ተብሏል። ይህ መንገድም ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለመኪኖች ክፍት ይሆናል። በዋነኝነት እነዚህን መተላለፊያ ዋሻዎች መገንባትም ያስፈለገበት ምክንያት ነዋሪዎች በቀላሉ ከአንዱ ከተማ ወደ አንዱ ከተማ በአጭር ሰዓት እንዲጓዙ ነው። ከዚህ ቀደም ከመዲናዋ ቶርሻቫን ወደ ሌላኛዋ ከተማ ሩናቪክ ለመድረስ አንድ ሰዓት ከሩብ ይወስድ የነበረው መንገድ በአዲሱ የባህር ላይ ዋሻ 16 ደቂቃዎችን ብቻ ይፈጃል። ዝቅተኛው የዋሻዎቹ መተላለፊያ ከባህር ወለል በታች 187 ሜትር ነው የመተላለፊያ ዋሻዎቹም ደህንነትም በደንብ ተጠንቶበት እንደተሰራ ግንባታውን የተቋረጠው ኩባንያ አስታውቋል። ዋሻዎቹም ሆነ አደባባዩ አገልግሎት ከመስጠታቸው በፊት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ያካተተ ቡድን ሙከራውን ቀድሞ እንደሚያከናውን የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋልል። በዋሾቹ መሃል የተገነባው አደባባይም የደሴቲቷን አርቲስት ትሮንዱር ፓቱርሰን የጥበብ ስራዎች ይንቆጠቆጣል። የሃውልት ሰራዎችን ጨምሮ ውብ የሆኑ መብራቶችም ይኖሩታል። በዋሻው መተላለፍ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ገንዘብ መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህም አንዴ ለሚያልፉበት 9 ፓውንድም እንደሆነ የአገሪቱ ድረገፅ አስፍሯል። ክፍያቸውን ተመዝግበው ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ ወይም አመታዊ የሚያደርጉት ከሆነ ረከስ ይልላቸዋል። የግንባታው ተቋራጭ ኤንሲሲ እንደሚለው ከሆነ እነዚህ መተላለፊያ ዋሻዎች ደሴቲቷ እስካሁን ድረስ ለመሰረተ ልማት ብላ ካወጣችው ገንዘብ ከፍተኛ እንደሆነ ነው። በአሁኑ ወቅትም ሳንዶይና ስትሪይሞይ የተባሉ ደሴቶችን ለማገናኘትም ሌሎች መተላለፊያ ዋሻዎች እየተገነቡ ነው። የፋሮ ደሴቶች፣ በሰሜን አትላንቲክ አገራት በአይስላንድና በኖርዌይ መካከል የምትገኝና 18 ደሴቶችን የያዘች ሲሆን፤ በዴንማርክም ውስጥ የምትገኝ ራሰ ገዝ አስተዳደር ናት።
news-47208152
https://www.bbc.com/amharic/news-47208152
የዩክሬን ባለሥልጣናት በአሲድ ጥቃት ግድያ ክስ ተመሠረተባቸው
የዩክሬን አቃቤ ሕግ ታዋቂ የፀረ-ሙስና ተሟጋችን በኢሰድ ጥቃት ለሞት ዳርገዋል ያላቸው ባለስልጣናት ላይ ክስ መሠረተ።
የ33 ዓመቷ ካትሪያና ሃንድዝዩክ ሕልፈት ዩክሬናውያንን እጅጉን ያስደነገጠ ነበር። የአሲድ ጥቃቱ ካደረሰባት ቃጠሎ በኋላ በሕክምና ስትረዳ ብትቆይም ከሦስት ወራት በፊት ሕይወቷ አልፏል። የፀረ-ሙሰና ተሟጋቿን ሕይወት ለማትረፍ ከ10 በላይ የቀዶ ሕክምና ተደርጎላት ነበር። • "ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ ክስ ከተመሠረተባቸው ባለሥልጣናት መካከል የአንድ ግዛት ምክር ቤት ኃላፊ ግድያውን በማቀነባበር ተጠያቂ ሆነዋል። ከእኚህ ግለሰብ በተጨማሪ ሌሎች 5 ሰዎች ከግድያው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ይገኛሉ። በፀረ-ሙስና አቀንቃኟ ላይ የደረሰው ጥቃት በርካቶችን ያስቆጣ ሆኗል። የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ ወደ 50 በሚጠጉ የፀረ-ሙስና አቀንቃኞች ላይ የተለያየ መልክ ያላቸው ጥቃቶች ተሰንዝረዋል። • አሲድን እንደ መሳሪያ • የሶስት ዓመት ጨቅላን በአሲድ ያጠቁ ታሰሩ ግድያውን በማቀነባበር የተከሰሱት ግለሰብ ቤት በፖሊስ የተበረበረ ሲሆን የተከሳሹ ጠበቃ ግን በደንበኛዬ ላይ የተገኘ ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም ይላሉ። ክስ የተመሠረተባቸው የምክር ቤት ኃላፊም ሟቿን እንደማያውቋት እና ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌላቸው በመናገር ለምርመራው ተባባሪ መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።
news-52306308
https://www.bbc.com/amharic/news-52306308
ምዕመናን ለምን በኮሮናቫይረስ ዘመን በቤተክርስቲያንና መስጊድ ውስጥ ካልተሰባሰብን ይላሉ?
በበርካታ አገራት አማኞች በኮሮናቫይረስ ምክንያት በቤተ ዕምነቶች ተሰብስበው ጸሎትና ሐይማኖታዊ ሥርዓቶችን እንዳይፈጽሙ ተከልክለዋል። ነግር ግን ይህ ሁሉም ቦታ እየተከበረ ያለ አይደለም።
አሜሪካ ውስጥ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት በፋሲካ ወቅት ክፍት ክፍት ነበሩ በተባበሩ መንግሥታት ድርጅት የእምነት ነጻነት ተሟጋች ዶክትር አህመድ ሻሂድ መንግሥታት አንዳንድ የእምነት መለገጫዎችን ለምዕመኑ ጤና ሲሉ ሊሽሯቸው ግድ ይላል፤ ይህም የዓለም አቀፍ ሕግ ድጋፍ አለው ይላሉ። ዶ/ር አሕመድ በተለይ ለቢቢሲ በሰጡት ቃለ ምልልስ የእምነት አባቶች ምዕመኖቻቸው ርቀታቸውን እንዲጠብቁ የማበረታታትና የማሳመን ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። ጨምረው እንደሚሉትም የዕምነት ተቋማት ምዕመናን የማኅበረሰቡን ጤና ከሚያቃውሱ ተግባራት እንዲጠበቁ የማሳመን የሕግ ባይሆንም የሞራል ግዴታ አለባቸው። አምላክን እንጂ ኮረናቫይረስን አንፈራም ምንም እንኳ በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን የፈረንጆቹን ፋሲካ በቤተ ክርስቲያን ሳይሰባሰብ ቢያከብርም በአሜሪካ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ግን ይህ አልሆነም። የሉዊዚያና ፓስተር ቶኒ ስፔል እንደሚለው እርሱ በሚመራው የተበርናክል ቤተክርስቲያን በሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናን ተገኝተዋል። በሉዊዚያና ከ50 ሰዎች በላይ በአንድ ቦታ እንዳይሰባሰቡ ተከልኳል። ይህን ክልከላ ጥሰው ነው ምዕመናኑ የተገኙት። ወደ ፓኪስታን ስናመራ በዚያ ከ5 ሰው በላይ ለጸሎት እንዳይሰባሰብ ቢባልም አብዛኛዎቹ የሙስሊም ሼኾች ይህንን መመሪያ ሲጥሱ ተስተውለዋል። ፓኪስታን አሁን አንዳንድ መመሪያዎችን ማላላት ጀምራለች። ይህን ተከትሎ አንዳንድ የሐይማኖት አባቶች መጪውን የረመዳን ጾምን በማስመልከት ተሰባስቦ መጸለይ ይፈቀድ እያሉ ነው። ፓኪስታን ውስጥ አንዳንዶች ለጸሎት ወደ መስጊዶች ሄደው ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን ነገሩን ከአገሪቱ የሐይማኖት አባቶች ጋር እመክርበታለሁ ታገሱኝ ብለዋል። በፓኪስታን በኮቪድ-19 ከተያዙ ሰዎች መካከል ቀላል ቁጥር የማይባሉት ከመካ መዲና ጉብኝት ተመላሾች ናቸው። ሌሎች ደግሞ ተብሊግ አልጃምአት የሚባሉ የሰበካ (ዳእዋ) ጉባኤ አባላት ናቸው። እነዚህ የተብሊግ አልጃምአት ጉባኤ አባላት በፓኪስታን ብቻ ሳይሆን በህንድ፣ በኢንዶኒዢያ እና በማሌዢያም ተህዋሲው እንዲስፋፋ ምክንያት ሆነዋል። በደቡብ ኮሪያ በሺህ የሚቆጠሩ የተህዋሲው ተጠቂዎች ከሺንሾንጂ ቤተክርስቲያን የተያያዙ ናቸው። ይህ ምስጢራዊ መንፈሳዊ የክርስቲያ ቡድን ለኮቪድ-19 መስፋፋት ዋናውን ቦታ ይይዛል። ምክንያቱ ደግሞ አንዳንድ የዚህ ቤተክርስቲያን አባላት ለመመርመር ፍቃደኛ አለመሆናቸው ነው። አባላቱም በይፋ እንዲታወቁ አይሹም። በዚህ ምስጢራዊነቱ ክንያትም አማኞቹ ቫይረሱን እንዳስፋፉት ይነገራል። የዚህ ለየት ያለ የክርስቲያን ቡድን አባላት አመራሮች ለሆነው ነገር መንግሥትንና የደቡብ ኮሪያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል። ሳይንቲስቶችና የሕክምና ባለሞያዎች በቂ ርቀት ሳይጠብቁ መቆየትና በአንድ አካባቢ መሰባሰብ ለበሽታው የመጋለጥ እድልን ሰፊ እንደሚያደርገው ደጋግመው ቢናገሩም በርካታ አማኞች ግን መስማት አልቻሉም። ለምን? ጸሎት እንደ አየርና ምግብ ማቴው ሽሚዝ የካቶሊክ ክርስቲያን ነው። በአሜሪካ ፔኒሲልቪኒያ ይኖራል። በዚያ አብሮ ማምለክ ተከልክሏል። ሽሚዝ እንደሚለው ጸሎት እጅግ መሠረታዊ ነገር ነው፤ ለምን በግሮሰሪ ርቀት ጠብቆ መስተናገድ እንደሚቻለው ቤተክርስቲያንም ውስጥ ይሄ ሊሆን እንዳልቻለ አይገባውም። "መንግሥት በግሮሰሪ ርቀታችሁን ጠብቃችሁ ተስተናገዱ፤ ቤተክርስቲያን ግን ርቀታችሁን ጠብቃችሁም ቢሆን አታምልኩ ማለቱ ምን ያህል ከእምነት ይልቅ ለንግድ ከፍ ያለ ቦታ እንደሚሰጥ ማሳያ ነው" ይላል። ከአምላክ ጋር በየትም ቦታ ሆኖ መገናኘት አይቻልም ወይ? የግድ በርከት ብሎ በቤተ ክርስቲያን መሰባሰብ ለምን? ለሚለው ጥያቄ ሽሚዝ ሲመልስ፡- "ባል ወይም ሚስት አብረው በአካል እንዲገናኙ ሲሹ በተናጥል ራሳቸውን ችለው መቆም አይችሉም ማለት አይደለም፤ ወይም ደካማነታቸውን አይደለም የሚያሳየው፤ ፍቅራቸውን እንጂ፤ አምላክም ጋር መቅረብ እንደዚያው ነው።" መንግሥትን እንደ ፀረ ሐይማኖት የማየት አባዜ ባስቲያን ሩጀንስ የደች የአእምሮ ጤና ባለሞያ ነው፤ ከፍተኛ ትምህርቱን የተከታተለው ሃይማኖትና አአምሮን በተመለከተ ነው። እሱ እንደሚለው ሰዎች መንግሥታቸውን የሚያዩበት መንገድ ትዕዛዙን ለመቀበል ያላቸውን ዝግጁነት ይወስናል። ለምሳሌ በአሜሪካ ሕዝቡ መንግሥትን በጥርጣሬ ነው የሚመለከተው፤ መንግሥት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች ለመከተል ችግር የሚሆንባቸው መጀመሪያውኑም መንግሥትን በጥርጣሬ ስለሚመለከቱት ነው ይላል። ይህም ማለት ይላል ሩትጀንስ . . . የሕክምና ባለሞያዎች ሳይቀሩ መሰባሰብ አደጋ አለው ሲሉ ቢመክሩም የመንግሥት ሰዎች ናቸው ተብሎ ስለሚታመን ሕዝቡ እነሱን በቀላሉ ለማመን ይቸገራል። እንዲህ ዓይነት በሕዝብና በመንግሥት መካከል ያለ አለመተማመን ግን እዚህ በኔዘርላንድስ አታይም፤ ስለዚህ ሕዝቡ በቤተ እምነት አትሰባሰብ ሲባል ቶሎ ይቀበላል። የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ሰዎች ተሰብስበው ከማምለክ መከልከል የለባቸውም ይላሉ የእመነት አባቶችን ለምን አንሰማቸውም? አንዳንድ አገራት ከሕዝቡ ይልቅ መሪዎቹ ችግር ፈጣሪዎች ናቸው። ለምሳሌ በታንዛኒያ ፕሬዝዳንቱ ጆን ማጉፉሊ ሕዝቡ ወደ መስጊድና ቤተክርስቲያን ያለ ምንም ስጋት እንዲሄድ መክረዋል። ማጉፉሊ በኬሚስትሪ የዶክትሬት ዲግሪ አላቸው። በአንድ የቤተክርስቲያን ጉባኤ ላይ ጆን ማጉፉሊ ሲናገሩ "ኮሮናቫይረስ ሰይጣን ነው፤ በእየሱስ ክርስቶስ በሚያምን ልብና ሰውነት ውስጥ ሊኖር አይቻለውም፤ ወዲያውኑ ይቃጠላል። ስለዚህ እምነታችንን እናጠንክር" ሲሉ ለምዕመናን ንግግር አድርገዋል። አሁን ታንዛኒያ ውስጥ እንቅስቃሴዎች ዝግ ባይሆኑም ትምህርት ቤቶችና የሰዎች ስብስብ ግን ክልክል ነው። በታንዛኒያ ውስጥ ሰሞኑን በአንድ ቀን ብቻ 28 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሼክ ሐሰን ሳይድ ሺዘንጋ የታንዛኒያ ተቀዳሚ ሙፍቲህ ናቸው። እርሳቸውም ከፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ሀሳብ ጋር ይስማማሉ። "አንድ ሰው ቤቱ የሚሰግደው ሶላት በመስጂድ በደቦ ሲፈጽመው 27 እጥፍ ምንዳ ያገኝበታል" ይላሉ። ስለዚህ አሉ ሙፍቲሁ ሼኽ ሐሰን፤ በዚህ በቫይረሱ ወቅትም ቢሆን ፈጣሪ በሽታውን እንዲይዝልን በመስጊድ እየተሰባሰብን ልንለማመነው ግድ ይላል። ሙፍቲሁ በታንዛኒያ መስጊዶች ይዘጉ የሚል ውሳኔ ከተላለፈ እርሳቸው የሚመሩት የታንዛኒያ ብሔራዊ ሙስሊም ምክር ቤት ቅሬታውን ለሚመለከተው ከመግለጽ እንማይቆጠብ አረጋግጠዋል። ይህ ሲባል ጥንቃቄ እርቋቸዋል ማለት አይደለም። ሼክ ሐሰን እንደሚሉት ወደ መስጊድ የሚመጡ ምዕመናን የራሳቸውን መስገጃ ይዘው እንዲመጡ አድርገናል፤ የጸሎት ሰዓቱም እንዲያጥር፣ አማኞች ቶሎ ቶሎ እጃቸውን እንዲታጠቡም ያደረግነው በሽታውን ለመከላከል ነው ይላሉ። ይህ እርምጃ ግን ለኅብረተሰብ ጤና ባለሞያዎች በቂ አይደለም። ሰዎች ተሰባሰቡ ማለት በሽታውን የመለዋወጥ እድላቸው ከፍ አለ ማለት ነው። ታንዛኒያ ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ የሐይማኖት ነጻነት በኮሮናቫይረስ ምክንያት እየተጣሰ ይሆን? አንዳንዶች ምዕመናን እምነታቸውን እንዳይፈጽሙ ሊከለከሉ አይገባም፤ በዚህ ወቅትም ቢሆን ሲሉ ይከራከራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእምነት ነጻነት ተሟጋች አህመድ ሻሂድ ግን በዚህ አይስማሙም። አንድ ሰው የማምለክ መብቱ ሌሎችን ከመጉዳት መለስ ባለው ክልል የሚወሰን ነው፤ ስለዚህ ሐይማኖታዊ መብቴ ነው ማለት ይህንን ገደብ ካለመረዳት የሚመጣ ነው ይላል። አንድ ሰው ሐይማኖቴ ያዘኛል ብሎ ሌሎች ላይ ጉዳት ማድረስ አይችልም፤ በዚህ ወቅት ተሰባስቤ ላምልክ ማለት በኅብረተሰብ ጤና ላይ ጉዳት ማድረስ ነው። ይህ መብት አይደለም።
news-50080786
https://www.bbc.com/amharic/news-50080786
በመቀሌ ከተማ ፆታዊ ጥቃትን በመቃወም ሊደረግ የነበረው ሰልፍ ተከለከለ
ባለፈው ሳምንት በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን፤ ሕዝብና የመንግሥት አመራሮች ግምገማ ካደረጉ በኋላ ሦስት ሴቶች በአንድ የፖሊስ አባል ጥቃት ተፈፅሞብናል ሲሉ ተናግረው ነበር።
በፖሊስ አባሉ ተፈፅሟል የተባለውን ጥቃት በመቃወም በዓዲ ዳዕሮ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዶ ነበር የአዲ ዳዕሮ ከተማ ፖሊስ አባል የሆነው ተጠርጣሪ አንዲት ሴት በመድፈር ክስ የቀረበበት ሲሆን ሌሎች ሴቶችም በዚሁ የፖሊስ አባል ላይ ተመሳሳይ ጥቃት እንደደረሰባቸው ገልፀው ነበር። ተከሳሹ ጉዳዩ እስከሚጣራ በስድስት ሺህ ብር ዋስ መለቀቁ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር። • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? ይህንን ተከትሎ ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል አልታሰረም በሚል መስከረም 28 2012 ዓ.ም የከተማው ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ቁጣውን መግለፁ የሚታወስ ነው። በጊዜው በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠን የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ውሎ የነበረ መሆኑን በመግለፅ "ክስ ያቀረበችበት አንዲት ሴት ናት፤ የቀረበበት ክስም በሕጉ ዋስትና የሚያስከለክለው አይደለም" ብሏል። በመሆኑም ግለሰቡ በዋስ ተለቆ ጉዳዩ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ አስታውቆ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ በመጭው እሁድ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመቃወም በመቀሌ ከተማ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ መከልከሉ ተሰምቷል። የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆነችው ዶ/ር ሄለን ቴዎድሮስ ስለ ክልከላው "ማድረግ ያለብንን ሂደት ነው የተከተልነው፤ እኛ ያገባናል ብለን የተሰበሰብን ልጆች ፊርማችን ያለበት እና ለሰልፉ ኃላፊነት እንደምንወስድ ደብዳቤ ፅፈን ወደሚመለከተው አካል፤ መቀሌ ከተማ አስተዳደር ነው የሄድነው።" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ዶ/ር ሄለን እንደምትለው ሄደው ባነጋገሯቸው ወቅት የመንግሥት አካል ካልሆነ በስተቀር በግለሰቦች ደረጃ ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ እንደማይችል በመግለፅ እንደተከለከለ ነገረዋቸዋል። "ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ ነው የሚሄደው፤ አዲ ዳዕሮ የተፈጠረውን ነገር ማንሳት ይቻላል" የምትለው ዶ/ር ሄለን ምንም እንኳን ግለሰቡን የተመለከተ የተለያዩ ወሬዎች ቢወሩም፤ አንዲትም ሴት ትሁን 50 ሴቶች መደፈራቸውን ሄደው መናገራቸውን ታስታውሳለች። "ተጠርጣሪው ግለሰብ በ6 ሺህ ብር ዋስ ተለቋል፤ ለዚያውም የሕግ አስከባሪ የሆነ ፖሊስ። ይህም ትልቅ ነገር ነው የሚያሳየን። የብዙ ሴቶችን ታሪክ እናውቃለን፤ ተጠርጣሪዎቹ በትንሽ ብር ዋስ ነው የሚለቀቁት፤ ስለዚህ መንግሥት አስፈላጊውን ትኩረት እየሰጠው አይደለም" ስትል ትወቅሳለች። • የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት በዚህም ምክንያት ነበር ጉዳዩ ያገባናል የሚሉና ከተለያየ ሙያ የተውጣጡ ግለሰቦች ተሰባስበው ድርጊቱን በመቃወም ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተነሱት። ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የመቀሌ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማይ ተስፋይ፤ "ሰልፍ ለማካሄድ ጥያቄ ላቀረበ ሁሉ ማስተናገድ አይቻልም። ዓላማው መታወቅ አለበት" ብለዋል። አቶ ግርማይ ሠላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጥያቄ ላቀረቡት ግለሰቦች የሕጋዊ ድርጅት ማህተም ያለው የድጋፍ ደብዳቤ እንዲያመጡ ከመጠየቅ በዘለለ ሰልፍ ማካሄድ አልከለከልንም ሲሉ ግለሰቦቹ ያቀረቡት ደብዳቤ ማህተም እንደሌለው ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም ሰልፉን ለማካሄድ የሲቪክ ማህበረሰብም ይሁን የመንግሥት ድጋፍ ያለው ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው ብለዋል።
news-55761772
https://www.bbc.com/amharic/news-55761772
በትግራይ ግጭት፣ የአየር ንብረት ለውጥና የኮሮናቫይረስ ሚሊዮኖችን ለከፋ አደጋ ጥሏል- ኦክስፋም
በትግራይ ክልል በቅርቡ የተከሰተው ወታደራዊ ግጭት፣የአየር ንብረት ካስከተለው ከአንበጣ ወረራና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተደራርቦ ሚሊዮኖችን ለከፋ አደጋ እንደጣላቸው ኦክስፋም አስታውቋል።
የክልሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ቢያስፈልጋቸውም ከአቅርቦት ጋር በተያያዘ ያለው ገደብ የቀጠለ መሆኑንም አሳሳቢነቱን በመጥቀስ ድርጅቱ በዛሬው ዕለት፣ ጥር 14/ 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በቅርቡ በምዕራባዊና ደቡባዊ ትግራይ እንዲሁም በክልሉ አጎራባች ባሉ የሰሜን አማራ አካባቢዎች ላይ ግምገማዎችን አካሂጃለሁ ያለው ድርጅቱ ወታደራዊው ግጭት ከመፈጠሩ፣ ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም በፊት ቢሆንም ማህበረሰቡ በምግብ እጦት ሲሰቃዩ እንደነበረና በግጭቱ ሁኔታም ተባብሷል ብሏል። መግለጫው የኦከስፋም የኢትዮጵያ ተወካይ ገዛኸኝ ከበደ ገብረሃናን ጠቅሶ እንዳሰፈረው "ሶስቱ ገዳይ የምንላቸው፤ ግጭት፣ የአየር ንብረት ለውጥና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ነዋሪዎችን የከፋ አደጋ ላይ ጥሏቸዋል። ከግጭቱ በፊትም ቢሆን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በተነሳው የአንበጣ መንጋ በርካቶች ግማሽ የሚሆነው ምርታቸው ወድሞ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው የጤናና ምጣኔ ኃብታዊ ቀውስ ማህበረሰቡ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነበር" ብለዋል። ግጭቱ የተነሳበት ወቅት የምርት መሰብሰቢያ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ በርካቶች ምርታቸውን እንዳይሰበስቡ እንቅፋት ሆኖባቸዋል። በክልሉ ውስጥ ያለው ሁኔታ አስከፊ እንደሆነና "በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ" አንድ የመንግሥት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ የሰፈረ ጽሁፍ ማመልከቱ የሚታወስ ነው። በደቡብ ትግራይ የሚገኙ ቤተሰቦችም ለኦክስፋም እንደተናገሩት ግጭቱን ፈርተው አካባቢያቸው ወደሚገኙ መንደሮችና ጫካዎች ያገኟትን ውሃና ምግብ እየተቋደሱ ህይወታቸው ማትረፍ እንደቻሉ ነው። ነገር ግን ወደቀያቸው በተመለሱበት ወቅት ቤታቸውና ንብረታቸው ወድሞ ወይም ተዘርፎ ነው ያገኙት። በትግራይ የሚገኙ ተስፋይ ጌታቸው የሚባሉ አርሶ አደር "እህላችን፣ ምርታችን ተቃጥሏል የኔንም ጭምር ወድሟል። በአጠቃላይ ያጣሁት 1.5 ቶን (13.6 ኩንታል) ይገመታል። ይህ ሰባት ቤተሰቤን ለአስር ወራት ይመግብ ነበር" በማለት ለኦክስፋም ተናግረዋል። አርሶ አደሩ በግጭቱ ከደረሰባቸው የእህል ውድመት በተጨማሪ በርካታ አርሶ አደሮች ከዚህ ቀደም በአንበጣ መንጋው ከፍተኛ ምርታቸውን እንዳጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ጠንክሮ የተስተዋለው የአንበጣ መንጋ ብርቱ ጉዳት ካደረሰባቸው ክልሎችም አንዷ ናት ትግራይ። በተለይም በትግራይ ክልል ማዕከላዊና፣ ሰሜን ምዕራብ በሚገኙ አካቢዎች መንጋው የከፋ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል። ከነበረው የአንበጣ መንጋና የሰብል ጉዳትም ጋር ተያይዞ ከ600 ሺህ የሚበልጡ የክልሉ ነዋሪዎች ለእርዳታ ጥገኛ ሆነው ነበር ይላል ኦክስፋም በመግለጫው። በአሁኑ ወቅት ጦርነት ጦርነት በተካሄደባቸው የትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ደኅንነትና ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰብአዊ ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መግለፁ የሚታወስ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት በቅርቡ ባወጣውና የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሚለው በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ነው። ግጭቱ ያስከተለውን መሰረታዊ ነገሮች የዳሰሰው መግለጫው መሰረታዊ የሚባሉ የውሃ፣ጤና አገልግሎቶች፣ ትምህርት እንደተቋረጡም ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የመንግሥት ተቋማት ሰራተኞች ለሶስት ወራት ያህል ባለመከፈላቸውም ኑሯቸውን አዳጋች እንዳደረገው፣ የገንዘብ እጥረቱና ካለው የፀጥታ ችግር ጋርም ተደራረርቦ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦችን መሸመት አዳጋች እንዳደረገው የጠቆመው መግለጫው የምርቶች ዋጋ ንሯል ብሏል። የተባበሩት መንግሥታትም እንዲሁ በሪፖርቱ "ምግብ አለመኖር ወይም በገበያዎች ላይ ያለው አቅርቦት ውስን መሆን እየባሰ የሚሄድ የምግብ እጥረት አደጋን እየፈጠረ መሆኑን ሪፖርቶች እያመለከቱ ነው" ብሏል። ነዋሪዎች ከጤና አገልግሎት እጥረት ጋር በተያያዘ እየሞቱ እንደሆነና በምግብና ውሃ እጥረትም በከፍተኛ ሁኔታም መጎዳታቸውን ሮይተርስ በአዲግራትና አክሱም እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የገጠር አካባቢዎችን የጎበኘው ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን(MSF) ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በጎበኙባቸውም አካባቢዎች የምግብ እጥረት፣ ውሃ፣ የጤና አገልግሎት ችግርና በፍራቻ የተዋጡ ሰዎችን ያገኙ ሲሆን "ሁሉም ምግብ ነው" የሚጠይቁት በማለት የቡድኑ ድንገተኛ ፕሮግራም ኃላፊ ማሪ ካርመን ቪኖሌስን ጠቅሶ ሮይተርስ አስነብቧል። የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በዚህ ሳምንት ሰኞ እለት ባወጣው መግለጫ በሽረ ባሉ ክሊኒኮች በርካቶችን እየገደለ ያለው የምግብ እጥረት እንዳለ ያሳወቀ ሲሆን ሁኔታውንም የከፋ ነው ብሎታል። ኦክስፋም በክልሉ ባለው አስቸኳይ የምግብ፣ መጠለያና ነዋሪዎች ኑሯቸውን እንዲያቋቁሙ ለማስቻል ካለው የሰብዓዊ ድርጅቶች ጥረት ጋር ተያይዞ በክልሉ ባለው ግጭትና የደህንነት ስጋት፤ የቢሮክራሲ ሁኔታና የኮሚዩኒኬሽን መቋረጥ ፈታኝ እንዳዳረገው ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ እርዳታ እያደረሰ እንደሆነ ይናገራል፤ ከሰሞኑ እንዲሁ በክልሉ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችና የሕክም አቅርቦቶች የሰብዓዊ ድጋፍ ለ1.8 ሚሊዮን ሰዎች መድረሱን የሠላም ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች እየቀረበ ያለውን እርዳታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ ከተጠቀሱት ሰዎች በተጨማሪ በክልሉ 2.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን አመልክቷል። ሮይተርስ በተጨማሪ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙሉ ነጋን (ዶ/ር) ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ባለስልጣኑ ተራራማ የሆኑ የክልሉ ገጠራማ ቦታዎች እርዳታ ለማድረስ የመጓጓዣ እጥረት የነበረ ቢሆንም፣ እርዳታ ማድረስ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። በትግራይ ክልል ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በወቅቱ ክልሉን ያስተዳድር የነበረው ሕወሓት የሰሜን ዕዝን ማጥቃቱ ከተገለፀ በኋላ ነበር። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል። ነገር ግን አልፎ አልፎ ውጊያ እንደሚካሄድ የተነገረ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ "የከፋ" ሲል ገልጾታል። ኦክስፋም እንዲሁ ግጭቱ እንዳልቆመ በገለፀበት መግለጫው ሁለቱም ወገኖች ከግጭቱ እንዲታቀቡና ቀውሱንም ለመፍታት ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጥሪ አድርጓል። ከዚህም በተጨማሪ ለአለም አቀፉ የበጎ አድራጎትና የሰብዓዊ መብቶች እንዲገዙና እርዳታ ድርጅቶችም በአስቸኳይ እርዳታ እንዲያደርሱ ደህንነቱ የተጠበቀ ሁኔታ እንዲያመቻቹ ለሁለቱም ወገኖች ጥሪ አቅርቧል።
news-56714417
https://www.bbc.com/amharic/news-56714417
ጥቁር አሜሪካዊ ሻምበል ላይ ጥቃት የፈጸመው ፖሊስ ከሥራው ተባረረ
ቨርጂኒያ ውስጥ የትራፊክ መብራት ባስቆመው የአሜሪካ ሠራዊት አባል ላይ ሽጉጥ ደግኖ ዓይንን የሚያቃጥል ፈሳሽ የረጨበት የፖሊስ አባል ከሥራው ተባረረ።
ካሮን ናዛሪዮ የተባለው ወታደር ደረቱ ላይ በተገጠመው ካሜራ ፖሊሶቹ ያደረሱበትን እንግልት ቀርጾ ነበር። ፖሊሶቹ ወታደሩን ያስቆሙት የሰሌዳ ቁጥሩ አይታይም በሚል ሲሆን ነገር ግን ቪዲዮው ላይ ጊዜያዊ የሰሌዳ ቁጥር ይታይ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ሻምበል ናዛሪዮ ጆ ጉቴሬዝ እና ዳንኤል ክሮከር በተባሉት የፖሊስ መኮንኖች ላይ ባለፈው ሳምንት ክስ መስርቶ ነበር። ዊንድሰር የምትባለውና ቨርጂኒያ ውስጥ የምትገኝ ከተማ ባለስልጣንት ክስተቱ "የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግና ለፖሊስ አባላቱ ተጨማሪ ስልልጠና እንዲሰጥ ምክንያት ሆኗል" ብሏል። ጨምሮም "ድርጊቱን የፈጸመው የፖሊስ መኮንን ጆ ጉቴሬዝ ከሥራው እንዲባረር ተደርጓል" ሲል ገልጿል። እሁድ እለት ጉዳዩን በተመለከተ የተናገሩት የቨርጂኒያ ገዢ ራልፍ ኖርዛም ክስተቱ "እንደረበሻቸውና እንዳስቆጣቸው" ገልጸዋል። ምን ነበር የሆነው? የአሜሪካ የጦር ሠራዊት አባል የሆነው ሻምበል ሁለት የትራፊክ ፖሊሶች ሽጉጥ በመደቀን ብሎም ዓይንን የሚያቀጥል ፈሳሽ በመርጨት (ፔፐር ስፕሬይ) ጥቃት ፈጽመውብኛል ሲል ነበር ክስ የመሰረተው። ካሮን ናዛሪዮ የተባለው ይህ ምክትል ሻምበል የአሜሪካ ሠራዊትን የደንብ ልብስ እንደለበሰ ፖሊሶቹ ተግባሩን መፈፀማቸውን በፖሊሶች ደረት ላይ ከሚቀመጠው ካሜራ ላይ የተገኘው ተንቀሳቃሽ ምስል አመላክቷል። ቪዲዮው እንደሚያሳየው "እውነት ለመናገር ከመኪናው ለመውረድ ፈርቻለሁ" ሲል ሁለቱን ፖሊሶች ተማፅኗል። "አዎ መፍራት አለብህ" ሲል አንደኛው ፖሊስ ሲመልስለትም ይደመጣል። ወታደሩን ለምን እንዳስቆሙት እንዲያብራራ የተጠየቀው ፖሊስ በወቅቱ ያለ ሰሌዳ እያሽከረከረ ነበር ቢልም በቪዲዮው ላይ ግን ግዜያዊ ሰሌዳ መለጠፉ ይታያል። ፖሊሶቹ የወታደሩን መኪና በመፈተሸ ላይ ሳሉ ሁለት እጁን በካቴና ወደ ኋላ አስረውት እንደነበር በምስሉ ላይ ይታያል። ለምን ኃይል እንደሚጠቀሙ የሚጠይቀው ሻምበል "እየተባበርከን ስላልሆነ ነው" የሚል መልስ ከአንደኛው ፖሊስ ተሰጥቶታል። ቆይቶም ያለምንም ክስ ተለቋል። ሻምበሉም ሕገ መንግሥታዊ መብቶቼ ተጥሰዋል ሲል በቨርጂኒያ ሁለቱን ፖሊሶች ከስሷል። በተጨማሪም ጥቃት ተፈፅሞብኛል፣ ሕገ ወጥ ፍተሻ ብሎም እስርም ተፈፅሞብኛል ሲል ፖሊሶቹን ፍርድ ቤት ገትሯቸዋል። ከቨርጂኒያ ዊንድሶር የፖሊስ ክፍል እስከ አሁን ድረስ ምላሽ አልተገኘም። ይህንኑ ድርጊት የሚያሳየው የቪዲዮ ማስረጃ በመገናኛ ብዙሃን በሰፊው የተሰራጨ ሲሆን የሚሊዮኖች መነጋገሪያ ሆኗል። በተጨማሪም የጆርጅ ፍሎይድን ህልፈት ተክትሎ እየተሰማ ያለው ይፋዊ የችሎት ሂደት በመላው ዓለም በመተላለፍ ላይ ባለበት ወቅት የተፈጠረ ድርጊት መሆኑም አነጋጋሪ አድርጎታል።
news-53976390
https://www.bbc.com/amharic/news-53976390
ጋምቤላ ፡ ባለስልጣናት ላይ ጥቃት የማድረስ ሙከራ መክሸፉን ፖሊስ አስታወቀ
ከሰሞኑ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ላይ የግድያ ሙከራ የፈጸሙ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር፣ አፈጉባኤ፣ ምክትል አፈጉባኤ፣ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናትን ሊገድሉ ሙከራ አድርገዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል። ነሐሴ 22/2012 ነበር በበክልሉ አኙዋ ዞን ጆር ወረዳ ከፍተኛ አመራሮቹ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመወያየት ወደ ስፍራው ያቀኑት። የጋምቤላ ክልል ምክትል የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቱት ኮር ለቢቢሲ እንደገለጹት በርዕሰ መስተዳድሩ የሚመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በጎንግ ወረዳ ያደረገውን ጉብኝት በማጠናቀቅ ነበር ወደ ጆር ወረዳ ያቀናው። የጉብኝቱ ዓላማም አካባቢውን ለመጎብኝት እና ያለውን የጎርፍ ሁኔታ በማየት ከአካባቢው ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ጋር ለመወያየት እንደነበረ ተናግረዋል። በጆር ወረዳ በሚገኘው ምክር ቤት ውስጥ በተደረገው ውይይት ላይ የተደራጁ ወጣቶች በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል። ምክትል የፖሊስ ኮሚሽነሩ እንዳሉት ይህ ጥቃት ቀደም ሲል ጀምሮ ዝግጅት የተደረገበት እንደነበር አመልክተው፤ የግድያ ሙከራው በከፍተኛ አመራሮቹ ጠባቂዎች አማካእነት መክሸፉን ተናግረዋል። ከጥቃቱ ሙከራ ጋር በተያያዘም 19 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ወዲያውኑ በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ለቢቢሲ ተናግዋል። ጥቃቱን ለመፈጸም መሞከራቸው የተነገረውና በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች መነሻቸው ከጋምቤላ ከተማ ነበር ያሉት አቶ ቱት ከእነርሱ ጋር አንድ የአሜሪካ ዜግንት ያለው ዶክተርም በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቅሰዋል። አሜሪካዊው ወጣቶቹን ከማደራጀት ባለፈ በስሙ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ማምጣቱን እና ወጣቶቹ እጅ ላይ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ መያዙንም ጠቁመዋል። ተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ ድምጽ አልባ መሣሪያን ጨምሮ አንድ ሕገ ወጥ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክተው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ ነው። ተጠርጣሪዎቹ ጥቃቱን ለማድረስ በታሰበበት አዳራሽ ውስጥ ድንገተኛ ግጭት በመፍጠር አቅጣጫ ለማስቀየር ሙከራ ማድረጋቸውን የተናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ በወቅቱ የከፍተኛ አመራሮቹ ጠባቂዎች ክስተቱን ለመቆጣጠር ወደ ሰማይ ጥይት መተኮሳቸውን ተናግዋል። ስለጉዳዩ ቀደም ሲል መረጃ እንደነበራቸውና አስፈላጊው ክትትል ሲደረግ እንደነበር የገለጹት አቶ ቱት ተጠርጣሪዎቹ ርዕሰ መስተዳድሩ ከጋምቤላ ከተማ ሳይወጡ ጥቃቱን የመፈጸም ዓላማ ነበራቸው ብለዋል። "ከጋምቤላ ብዙ ብዙ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ነበር። እነሱን መነሻ አድርገን ብዙ መረጃዎች ነበሩን። የይህን መሠረት አድርጎ ነው የማክሸፍ ሥራው የተሰራው" ብለዋል። የተጠርጣሪዎቹ ዓላማ "ርዕሰ መስተዳድሩ ላይ እርምጃ መውሰድ እና በኃይል ከስልጣን ለማሰወገድ ነበር" ብለዋል። እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች ቁጥር 25 መድረሱን ጠቁመው እየተፈለጉ ያሉ ሌሎች ሰዎች እንዳሉም ጨምረዋል ምክትል ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።። በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ ቅዳሜ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ምርመራው ዛሬ መጀመሩን እና ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል። አካባቢው አሁን ሠላማዊ መሆኑን ጠቁመው ምንም የተለየ ነገር አለመኖሩን እና ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
news-55314974
https://www.bbc.com/amharic/news-55314974
ትግራይ፡ የአውሮፓ ሕብረት እርምጃውን የወሰደው በተሳሳተ ግምገማ ላይ ተመስርቶ ነው- ኢትዮጵያ
የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ ከመደበው የበጀት ድጋፍ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዮሮ (110 ሚሊዮን ዶላር) እንዲዘገይ ያሳለፈው ውሳኔ በተሳሳተ ግምገማ ላይ የተመሰረተ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታውን ገለጸ።
የአውሮፓ ሕብርት የበጀት ድጎማውን ያዘገየው በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ነው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሕብረቱ የደረሰበት ውሳኔ "ሁኔታውን በተገቢው ሁኔታ ካለመገንዘብ" የተወሰደ ነው ሲሉ ገልፀውታል። ሕብረቱ ለቢቢሲ እንዳስታወቀው የያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ከመገባደዱ በፊት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ ይችል ከነበረው 90 ሚሊዮን ዩሮ የበጀት ድጎማ ገንዘብ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘገይ ተወስኗል። ሕብረቱ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ለኢትዮጵያ ሊያደርግ የነበረው የ90 ሚሊዮን ዮሮ የክፍያ ውሳኔ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ የተደረገው በሰሜን ኢትዮጵያ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ነው። "አሁን ባለው ሁኔታ የአውሮፓ ሕብረት የበጀት ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታ ላይ አይደለም" ብለዋል የአውሮፓ ሕብረት ቃል አቀባይ ፒሶኔሮ ሄርናንዴዝ ለቢቢሲ በላኩት የኢሜይል መልዕክት። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሙፍቲ በበኩላቸው የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በተገቢው መንገድ አለመረዳቱን ገልፀዋል። ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ስትራቴጂካዊ የሆነ ግንኙነት የመፍጠር ፍላጎት እንዳላት ያመለከቱት አምባሳደሩ፣ በአገር ውስጥ እየተወሰደ ያለውን "ሕግ ማስከበር እርምጃ ካለመረዳት፣ ይህንንም በማይሆን መንገድ የመተርጎም አዝማሚያ ነው ያለው" ብለዋል። ይህ ኢትዮጵያ እየወሰደችው ያለው እርምጃ በእያንዳንዱ የአውሮፓ አባል አገራት ዘንድ ሳይሆን፣ በሕብረቱ ደረጃ "የታየ ግርታ" መሆኑን የገለፁት አምባሳደሩ፣ "ግርታውን ለማጥራት ጥረት እናደርጋለን" ብለዋል። እርምጃው በተሳሳተ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የተወሰደ ነው ያሉት አምባሳደሩ ይህም "አሳዛኝ፣ መሆን ያልነበረበት እና ተገቢ ያልሆነ" በማለት ገልፀውታል። ሕብረቱ ውሳኔውን በተመለከተ የበጀት ድጋፍ የሚያደርገው ቀድሞ ስምምነት የተደረሱባቸው ጉዳዮች መሟላታቸው ሲረጋገጥ እና እንደአስፈላጊነቱ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ከግምት እየገቡ ነው ብሏል። በዚህም መሠረት የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የበጀት ድጎማ ማድረጉን የሚቀጥለው የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ ሲገኝ እንደሆነ አመልክቷል። ይሁን እንጂ ሕብረቱ በኢትዮጵያ እያከናወናቸው ያሉት ሌሎች የሰብዓዊ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ልማታዊ ፕሮግራሞች በዚህ የድጋፍ መዘግየት ውስጥ እንደማይካተቱ ተገልጿል። ሮይተርስ በአውሮፓ ሕብረት ውሳኔ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ ምን እንደሆነ ለማወቅ ባደረገው ሙከራ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ የገንዘብ ሚኒስቴርን እንዲያናግር በመሩት መሰረት ለጥያቄው ምላሽ አለማግኘቱን ጠቅሷል። የአውሮፓ ሕብረት በዓመት በአማካይ 214 ሚሊዮን ዩሮ የልማት ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጥ የሕብረቱ ድረ ገጽ ያመለክታል። በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው እና ከስድስት ሳምንታት ባላይ ባስቆጠረው ግጭት ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች ሲሞቱ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሸሽተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግጭቱን በመሸሽ ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ወደ 50 ሺህ እንደሚጠጋ አስታውቋል። በትግራይም ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው ሲል ተመድ መግለጫዎችን አውጥቶ የነበር ሲሆን፤ በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን እና የመድኃኒት እና ምግብ እጥረት እንደተከሰተም አስታውቆ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግሥት የትግራይን መዲና መቀለን ከህወሓት ኃይሎች መቆጣጠሩን ይፋ ካደረገ በኋላ ክልሉን መልሶ የመገንባታ እና የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እርዳታ የማቅረብ ሥራ እንደሚከናወን አስታውቆ ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ንግግርም ኢትዮጵያ ስደተኞችን መልሶ ማቋቋም ላይ ያላትን ልምድ በማውሳት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ስደተኞችን መልሶ ማቋቋሙ ለአስተዳደራቸው ከባድ የቤት ሥራ እንደማይሆን ተናግረዋል። ከቀናት በፊትም የሰብዓዊ እርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎችም ወደ ትግራይ ከተሞች ሲገቡ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ባለፉት ጥቂት ቀናት መቀለን ጨምሮ በትግራይ አንዳንድ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል እና የቴሌኮም አግልግሎቶች ዳግም ወደ ሥራ እየገቡ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአራት ብሔራዊ ፓርቲዎች ጥምረት የነበረውን ኢህአዴግ በማክሰም ብልጽግና ፓርቲን እንዲመሰረት ማድረጋቸውን ተከትሎ ማዕከላዊው መንግሥት ከህወሓት ጋር የነበረው ግንኙነት መበላሸቱ ይታወሳል። በተለይ ባለፈው ዓመት መካሄድ የነበረበትና በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈው ምርጫ ነገሮችን በከፍተኛ ደረጃ እንዲካረሩ አድርጓል። በበሽታው ምክንያት የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች የስልጣን ዘመን ምርጫው አስኪደረግ ድረስ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ሲወሰን ህወሓት ግን "ሕገወጥ እርምጃ ነው" በማለት ተቃውሞውን አሰምቶ በትግራይ ክልል የተናጠል ምርጫ አካሂዷል። ይህ ህወሓት ያካሄደው ክልላዊ ምርጫ፤ ከምርጫ ቦርድ፣ ከፌደራል መንግሥቱና ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ተቀባይነትን አላገኝም ነበር። መጀመሪያም ምርጫው ተቀባይነት የለውም በማለት ሲያስጠነቅቅ የነበረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግሥቱ ከክልሉ መስተዳደር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳያደርግ በማዘዘዝ በጀት የማቀብ እርምጃ ወሰደ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነበር ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የህወሓት ኃይሎች በትግራይ ክልል የሚገኘውን ከአገሪቱ ሠራዊት ትልቁ ክፍል የሚባለውን የሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው የተነገረው። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በህወሓት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ በምድርና በአየር ለሦስት ሳምንታት ያህል የዘለቀ ዘመቻ ተካሂዶ የክልሉ ዋና ከተማ በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት እጅ ስትገባ መንግሥት ሕግ የማስከበር ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ማብቃቱን ማሳወቁ ይታወሳል።
54635973
https://www.bbc.com/amharic/54635973
ኮሮናቫይረስ፡ የፊት መከለያ መሳሪያ ያመረቱት የሥነ ሕንጻ ባለሙያ
አቶ አሸናፊ ዘመቻ በሙያቸው የሥነ ሕንጻ ባለሙያ ናቸው። ለሥራቸው የሚያግዟቸውን የተለያዩ ነገሮችም ዲዛይን በማድረግ ይሰራሉ።
ለዚሁ ስራቸውም እንዲረዳቸው በሚል የ3ዲ ፕሪንተር ያላቸው ሲሆን በዚያም የተለያዩ ባሕላዊ የሆኑ እቃዎችን፣ መብራቶችን ለማተም ይገለገሉበታል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ በቅርበት ጉዳዩን ሲከታተሉ እንደነበር የሚገልፁት አቶ አሸናፊ፣ በወቅቱ ወረርሽኙ ስጋት ውስጥ ከትቷቸው እነደነበር ያስታውሳሉ። በወቅቱ ከመደናገጥ ይልቅ ምን ዓይነት አስተዋፅኦ ላበርክት የሚል ሃሳብ ይዘው ዙሪያቸውን ሲቃኙ ባላቸው 3ዲ ፕሪንተር የተወሰነ አገለግሎት መስጠት እንደሚችሉ አሰቡ። ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከቻይና አልፎ አውሮፓ፣ አሜሪካ እንዲሁም አፍሪካን ሲያዳርስ ግለሰቦችንም ሆነ የሕክምና ባለሙያዎችን ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ለማድረግ በሙያቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲያስቡም ባላቸው ሕትመት መሳሪያ የፊት መሸፈኛ መስራት እንደሚችሉም ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ቻይና ላይ ቫይረሱ መከሰቱ በተሰማበት ወቅት ጀምሮ ጉዳዩ ያሳስባቸው እንደነበር ለቢቢሲ የሚናገሩት አቶ አሸናፊ፣ በወቅቱበአገር ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ዋጋ በፍጥነት መናሩ እንዲሁም የአቅርቦት ችግር መኖሩ ማስተዋላቸው ምን ማድረግ አለብኝ ወደሚል ጥያቄ እንደመራቸው ይገልጻሉ። 3ዲ ፕሪንተር ካላቸው እና በእንግሊዝ አገር ከሚገኙ ሌሎች ባለሙያዎች ጋር በኢንተርኔት ላይ በነጻ የሚገኙ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ለአገራቸው የሚጠቅም ነገር ለማበርከትም አቀዱ። በዚህ የፊት መሸፈኛ የሕክምና ባለሙያዎችም ሆኑ ሌሎች ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ፊታቸውን የሚከልሉበትን መሳሪያ ከበይነ መረብ ላይ በመመልከት ሰሩ። እርሳቸው በ3ዲ ፕሪንተር ተጠቅመው ያመረቷቸውን የፊት መከለያዎች፣ ለሆስፒታሎችና ለሕክምና ባለሙያዎች በነጻ ሲሰጡ የፊት መከለያ መጠቀም በስፋት በባለሙያዎች ዘንድ አለመለመዱን ያስታውሳሉ። መጀመሪያ ላይ ያመረቷቸውን የፊት መከለያዎች በነጻ ለተወሰኑ ሆስፒታሎችና የሕክምና ባለሙያዎች ለግሰዋል። በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታሎች፣ እንዲሁም በግል ለሚያውቋቸው ሕክምና ባለሙያዎች በነጻም በሽያጭም መስጠት የጀመሩት አቶ አሸናፊ፣ ይህ የሕክምና ባለሙያዎች ፊታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚከልሉበትን (ፌስ ሺልድ) መሳሪያ በበርካታ ባለሙያዎች ዘንድ ፍላጎትን በመፍጠሩ በክፍያ ለማቅረብ ተነጋገሩ። ይህንን የፊት መከለያ ማንም የ3ዲ ፕሪንተር ያለው ግለሰብ በቀላሉ በሚጫኑ ሶፍት ዌሮችን በመጠቀም ማተም የሚችል ቢሆንም ህትመቱ ግን ዘገምተኛ በመሆኑ በብዛት ለማዳረስ አስቸጋሪ እንዳደረገው ይገልጻሉ። በአገር ውስጥ 3ዲ ፕሪንተር ያለው ግለሰብ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የገለፄት አቶ አሸናፊ ዘመቻ፣ ለህትመት የሚያገለግለው ቁስ በቀላሉ አለመገኘቱ ደግሞ ሌላ ፈታኝ ነገር ነበር። ፊትን የሚሸፍነው ማይካ በቀላሉ ገበያ ላይ የሚገኝ ቢሆንም እርሱን አቅፎ የሚይዘው ፍሬም ግን በ3ዲ ፕሪንተር መታተም እንዳለበት ጨምረው ያብራራሉ። ይህ መሸፈኛውን የሚያቅፈው ፍሬም ፀጉር ላይ እንደሚቀመጥ ቲያራ ዓይነት ሲሆን፣ ተበስቶ የፊት መሸፈኛውን እንዲታሰርበት ይደረጋል። በ3 ዲ ፕሪንተር ላይ ለማተም ይጠቀሙበት የነበረው ቁስ አንዴ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ እንደማያገለግል የሚናገሩት አቶ አሸናፊ፣ ልጠቀምበት ቢባል እንኳ በቀላሉ ባክቴሪያ እንደሚስብ በተጨማሪም የአቅርቦት እጥረት መኖር ፈታኝ ማድረጉን ያስረዳሉ። ይህ የፊት መከለያ ማይካ ከቻይና እንደሚገባ የሚገልፁት ባለሙያው፣ ነገር ግን ግንባር ላይ የሚያርፈው የፊት መሸፈኛ አካሉ ስፖንጅ መሆኑን ይገልጻሉ። ይህ ደግሞ በቀላሉ ባክቴሪያን ስለሚይዝ በየጊዜው በፀረ ተህዋሲያን ኬሚካል ለማጽዳት አስቸጋሪ መሆኑን አብራርተዋል። ነገር ግን ይህንን ከ3ዲ ፕሪንተር ውጪ መስራት አስፈላጊመሆኑን እንዲሁም በአገር ውስጥ በቀላሉ በሚገኝ ቁስ ቢሰራ መልካም መሆኑን ማስተዋላቸው የራሳቸውን የፊት መሸፈኛ ዲዛይን አድርገዋል። በዚህም ወቅት መሳሪያው ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጎ ቢሰራ መልካም መሆኑን ማስተዋላቸውንም ይገልጻሉ። በዚህም የተነሳ የሰሩት የፊት መሸፈኛ ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፣ ፊትን የሚከላከለው ማይካ ደግሞ በትንፋሽ አማካኝነት በቀላሉ ጭጋግ አይለብስም ሲሉ ያብራራሉ። እርሳቸው የሰሩት የፊት መከለያ ወጥ የሆነ ከፕላስቲክ የተሰራ ሲሆን ተቆርጦ በሌዘር ውስጥ እንደሚገባ ገልፀዋል። ለማጽዳት በሚፈለግበትም ወቅት ተፈትቶ በኬሚካል በቀላሉ ለማጽዳት እንዲቻል ተደርጎ መሰራቱን ያስረዳሉ። እነዚህ መሳሪያዎች ለየት የሚያደርጋቸው በቀላሉ ተፈታትተው መገጣጠማቸው ብቻ ሳይሆን፣ አገር ውስጥ በቀላሉ ከሚገኙ ቁሶች መሰራታቸውም ሌላው ለየት የሚያደርጋቸው ነገር መሆኑን ይገልጻሉ። አቶ አሸናፊ የሰሩት የፊት መሸፈኛ ቅርፁን ጠብቆ እንዲቆይ እና በቀላሉ እንዳይሰብ ተደርጎ መሰራቱን ጨምረው ተናግረዋል።
news-53089294
https://www.bbc.com/amharic/news-53089294
ጠቅላይ ፍርድ ቤት በስደተኞች ጉዳይ የዶናልድ ትራምፕን ሐሳብ ውድቅ አደረገ
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወጣት ስደተኞችን ከአገር ለማባረር ያቀደውን የዶናልድ ትራምፕ ሐሳብ የሚቃረን ውሳኔን አስተላልፏል።
በምህጻር ቃሉ "ዳካ" የሚባለው ፕሮግራም የተነደፈው በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሲሆን በልጅነታቸው ከሌላ አገር ወደ አሜሪካ የመጡ ልጆች፣ አዳጊዎችና ወጣቶችን ከአሜሪካ እንዳይባረሩ ከለላ የሚሰጥ ልዩ ፕሬዝዳንታዊ ውሳኔ ነበር። ይህን በኦባማ የተፈረመውን ልዩ ውሳኔ ሕገ ወጥ ነው በሚል እንዲሻር ዶናልድ ትራምፕ ትግል ሲያደርጉ ከርመዋል። የታችኛው ፍርድ ቤት የዶናልድ ትራምፕን እቅድ ውድቅ በማድረጉ ጉዳዩን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲመለከተው ቆይቷል። በትናንቱ ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለረዥም ጊዜ ካጤነው በኋላ 5 ለ 4 በሆነ ድምጽ የዶናልድ ትራምፕን ሐሳብ ሳይቀበለው ቀርቷል። ይህ ውሳኔ በልጅነታቸው ወደ አሜሪካ የመጡ በሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞችን አስፈንድቋል። 'ዳካ' ምንድነው? 'ዳካ' ምህጻረ ቃል ሲሆን 'ዲፈርድ አክሽን ፎር ቻይልድሁድ አራይቫል' የሚል የፕሬዝዳንቱን መመሪያን የያዘ ሰነድ ነው። ይህ መመሪያ በአሜሪካ ሕግ የፕሬዝዳንቱ ልዩ መመሪያ ሆኖ እስከ ታች ባሉ በሁሉም የሕግ አስፈጻሚው አካላት እንዲፈጸም የሚጠበቅ ነው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በተለምዶ "ሕልመኞች" የሚባሉና በልጅነታቸው ያለ ምንም ሕጋዊ ሰነድ የአሜሪካ ምድርን የረገጡ ስደተኞችን ፖሊስ ከአገር እንዳያባርራቸው የሚከለክል ልዩ መመሪያን አጽድቀውላቸዋል። ይህ ልዩ መመሪያ ነው 'ዳካ' በመባል የሚጠራው። በዚህ ፕሮግራም የሚካተቱት አብዛኞቹ ወጣት ስደተኞች ከሜክሲኮና ከላቲን አሜሪካ አገራት ያለ ምንም ሰነድ ወደ አሜሪካ ምድር የገቡ ናቸው። በ2012 ኦባማ እነዚህ ሕልመኛ ወጣቶች ከአገር እንዳይባረሩ ማድረግ ብቻም ሳይሆን እንዲማሩና እንዲሰሩም ፈቅደውላቸዋል። ኦባማ በዚህ ጉዳይ ላይ ልዩ ፕሬዝዳንታዊ መመሪያ ለመፈረም የተገደዱት የስደተኞቹን ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊመልስ የሚችል ማሻሻያ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ሊጸድቅላቸው ባለመቻሉ ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ወደ ሥልጣን መምጣቸውን ተከትሎ ይህን በኦባማ የተፈረመውን ልዩ መመሪያ ለመሻርና ሕገ ወጥ ለማሰኘት ብሎም ስደተኞችን በሙሉ ጠራርጎ ከአገር ለማስወጣት በመፈለጋቸው ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሊሄድ ችሏል። ዶናልድ ትራምፕ ይህን መመሪያ ሕገ ወጥ መሆኑን በፍርድ ቤት ቢያስወስኑ ኖሮ 650 ሺህ በአሜሪካ እየኖሩ ያሉ ልጆች፣ አዳጊዎችና ወጣቶች በፍጥነት ከአገር እንዲወጡ ይደረግ ነበር። ዶናልድ ትራምፕ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተበሳጩ ሲሆን ደጋፊዎቻቸውን በድጋሚ ከመረጣችሁኝ ወግ አጥባቂ ዳኞችን እሾማለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል። "ይህ የማይረባና በፖለቲካ የተለወሰው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ራሳቸውን በኩራት ሪፐብሊካን በሚሉ አሜሪካዊያን ግንባር ላይ የተተኮሰ ጥይት ነው" ብለዋል በትዊተር ሰሌዳቸው። በመጪው ኅዳር በድጋሚ ከመረጣችሁኝ የእኛን ዓላማ የሚያስፈጽሙ ወግ አጥባቂ ዳኞችን በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ እሾማለሁ ብለዋል። "የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች እንደማይወዱኝ አያችሁልኝ አይደል?" ሲሉም ጽፈዋል ትራምፕ። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በበኩላቸው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ "ይበል የሚያሰኝ" ሲሉ አሞካሽተዋል። ለደጋፊዎቻቸውም ዶናልድ ትራምፕን በመጪው ኅዳር ከዋይት ሐውስ አባረው አሜሪካንን የሚመጥናት የዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ እንዲመርጡ ጥሪ አድርገዋል። የትራምፕ ተፎካካሪ ጆ ባይደን በበኩላቸው ከተመረጡ 'ዳካ' ፕሮግራምን ቋሚ እንደሚያደርጉት ቃል ገብተዋል።
news-57306935
https://www.bbc.com/amharic/news-57306935
ምርጫ ቦርድ በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ እስክንድር ነጋን በዕጩነት ሊመዘግብ ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮችን በምርጫ ላይ እንዲሳተፉ ሊመዘግብ መሆኑን ፓርቲው ገልጸ።
በምርጫው በዕጩነት እንዲቀርቡ ተወሰነላቸው የተባሉት ግለሰቦች ክስ ተመስርቶባቸው አንድ ዓመት ለሚሆን ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ አመራሮች አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ናቸው። በዚህም መሠረት ዛሬ በጠቅላይ ፍርድ ቤት በነበረው ችሎት ላይ የተገኙት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ችሎቱ በእስር ላይ ያሉ የፓርቲው አመራሮች በዕጩነት እንዲመዘገቡ የሰጠውን ውሳኔ በመፈፀም ላይ እንደሆኑ መግለጻቸው ተነግሯል። ዛሬ ግንቦት 26/2013 ዓ.ም ጉዳዩን በተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ላይ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ የባልደራስ ፓርቲ ለምርጫ እንዲቀርቡለት የሚፈልጋቸውን ዕጩዎች እንዲያሳውቅ ቦርዱ መጠየቁን አስፈላጊው ነገር እተከናወነ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ሰበር ሰሚ ችሎት እነ አቶ እስክንድር ነጋ በዕጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ያሳለፈውን ውሳኔ ለማስፈፀም እንደሚቸገር አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል። ሰብሳቢዋ ጨምረውም ቦርዱ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መስራች እና ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት የፓርቲው አባላትን በምርጫው እንዲሳተፉ ለማድረግ ቦርዱ 1.3 ሚሊዮን ወረቀት ማስወገዱንና በአምስት ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ዕጩዎቹን ለማካተት እየሰራ መሆኑን መናገራቸውን ባልደራስ ገልጿል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ የባልደራስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ገለታው ዘለቀ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የታሰሩ አባላቱን ከግምት ውስጥ አስገብተው ቅስቀሳ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ ከዚህ ውሳኔ በኋላም ቅስቀሳውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። "ለእነ እስክንድር ስለተፈረደ ሳይሆን ለፍትህ ሲባል ወደ ታች ያሉ ዳኞችም እንደዚህ ቆራጥ ውሳኔ መስጠት አለባቸው፤ በውሳኔው እና ሂደቱ በዚህ በመዘጋቱ ደስተኞች ነን" ሲሉ አቶ ገለታው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባልደራስ ሊቀ መንበሩን አቶ አስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች አመራሮቹ በምርጫ ቦርድ በዕጩነት እንዲመዘገቡ መጠየቁ የሚታወስ ሲሆን፤ ቦርዱም አመራሮቹ በሕግ ቁጥጥር ስር የሚገኙ በመሆናቸው በምርጫው በዕጩነት መመዝገብ እንደማይችሉ በመግለጽ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎት ነበር። ይህንን ውሳኔ ያልተቀበለው ፓርቲው ጥያቄውን በተመለከተ በምርጫ ቦርድ ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ የነበረ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ የምርጫ ቦርድን ውሳኔን አጽንቶ ነበር። ነገር ግን ባልደራስ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ሰበር ሰሚ ችሎት በመውሰድ ባቀረበው አቤቱታ ፍርድ ቤቱ የቀረቡ መከራከሪያዎችን ከመረመረ በኋላ በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች በዕጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል። አቶ አስክንድር ነጋና ሌሎች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከተፈጸመ በኋላ ከተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ።
news-45584930
https://www.bbc.com/amharic/news-45584930
ኢትዮ-ኤርትራ፡ "አሁን ያገኘነው ሰላም፡ ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው" - ዘማሪ ሳሙኤል ተስፋሚካኤል
"የኢትዮ ኤርትራ የሠላሙን ወሬ እንደሰማሁ፤ እነዚያን ከ 21 ዓመታት በፊት የተለየኋቸውን ቤተሰቦቼን ለማየት ነበር የጓጓሁት" ይላል በመንፈሳዊ መዝሙሮቹ የሚታወቀው ሳሙኤል ተስፋሚካኤል።
ሳሙኤል በአስመራ ካቴድራል ይሄ እውን ሆኖ ወደተወለድኩባት ምድር መመለሴን ሳስበው ደግሞ ተመስገን ነው የምለው። ሳሙኤል መጀመርያ ወደ አስመራ ከበረሩት አውሮፕላኖች ጋር ነበር ከአትላንታ ወደ አዲስ አባባ፡ ከአዲስ አበባ ደግሞ ወደ አስመራ ያመራው። "1989፡ የ 12 ዓመት ልጅ ሳለሁ ነው ከአስመራ የወጣሁት። ትንሽ ቆይቶ ጦርነቱ ተከተለ። ከአባቴ ጋር አዲስ አበባ ቆይቼ፤ ወደ አትላንታ ጆርጂያ አመራሁ" ይላል ኢትዮጵያዊ-ኤርትራዊው ሳሙኤል። • የትናንትናዋ እለት- በኢትዮ ኤርትራ ግጭት ቤተሰባቸው ለተለያየ? • የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ? • ኢትዮጵያና ኤርትራ የመጨረሻውን የሠላም ስምምነት ፈረሙ ጦርነቱ፤ ቤተሰቦቹ ላይ ጥቁር ጥላውን አጥልቷል። "ሶስቱንም እህት ወንድሞቼን ካየኋቸው ዓመታት አለፉ። የስድስት ዓመት ልጅ ሆኖ የማውቀው ታናሽ ወንድሜ የ 27 ዓመት አዋቂ ሆኖ አገኘሁት፤ የአራት ዓመት የነበረችው እህቴም አግብታ፣ ልጅ ወልዳ ጠበቀችኝ። ከዚያ በኋላ የተወለደችው የቤታችን ታናሽ ደግሞ፤ ኮሌጅ ጨርሳ፣ ሥራ ይዛ ነው ያገኘሁዋት። በዘመኔ ይሄ ስቃይ አብቅቶ ስላሳየኝ አምላኬን አመሰግነዋለሁ'' ይላል። ሳሚ ተስፋሚካኤል የኢትዮጵያና የኤርትራ ዜግነት ካላቸው ቤተሰቦች የተገኘ ነው። ሳሚ ከእናቱ ጋር አባቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ እስኪሄድ ድረስ መሐል አስመራ፡ ዕዳጋ ሓሙስ በሚባለው አካባቢ ነው ያደገው። ወወክማ የሚባለውን የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ሁሌም ይናፍቀዋል። የሚወደውን አክሮባት እዚያው አስመራ ጥሎት እንደወጣ ያስታውሳል። ለረጅም ግዜ የተዋትን አስመራ፤ ዳግም ሲያያት ምን እንደተሰማው ሲገልፅ "የኤርትራ የአየር ክልል ላይ እስክደርስና መሬቷን እስክረግጥ ድረስ አላመንኩም ነበር" ካለ በኋላ በጨቅላነቱ ያየውን የምፅዋ አሰቃቂ ትውስታ ይተርክ ገባ። አልሞት ባይ ተጋዳይነትና ሳሚ "አክስቴና አያቴ ምፅዋ ይኖሩ ስለነበር በዕረፍት ግዜዬ እነሱጋ እሄድ ነበር።" ድንገት እነርሱ ጋር ሳለሁ ጦርነት ተጀመረ። ጦርነቱ፤ ምፅዋን ለመቆጣጠር የኤርትራ ታጋዮች የከፈቱት ነበር። የተኩስ ልውውጡ መጀመርያ ላይ ቀልድ ነበር የሚመስለው፤ እየቆየ ግን እየበረታ ሄደ። የአውሮፕላን ድብደባውና የከባድ መሣርያዎች ተኩስ ተጨምሮበት ነፍሴ ተጨነቀች። ገና የስምንት ዓመት ልጅ ነበርኩ። • ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ? • የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት 20ኛ ዓመት - መቋጫ ያላገኘ ፍጥጫ • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች "አክስቴና ባለቤቷ፡ ካጠላብን ሞት እንወጣ ዘንድ፤ ከነበርንበት የገበያ አካባቢ ወደ መሃል ምፅዋ ይዘውን ሄዱ።" "ከፊታችን ብዙ ሰዎች አስፓልት ላይ ሞተው፤ እያለፍናቸው ነበር የምንሸሸው።" "ከሁሉም የማልረሳው ግን፤ በደንብ የማቃቸው የአክስቴ ጎረቤት የሆኑ ሁለት እህትማማቾች ሲሞቱ በዓይኔ በበረቱ አየሁ።" ሌላ ግዜ ደግሞ፤ አንድ ሰው በአውሮፕላን ድብደባ የሞተች ሚስቱን በድንጋጤ አዝሏት እየሄደ ሳለ፤ መሞቷን ያዩ ቄስ 'አውርዳት' ብለው፤ ዓይኗ ላይ ትንሽ አፈር አልብሰውባት ትተናት ሄደናል።" ሳሙኤል፤ በወቅቱ 'የአልሞት ባይ ተጋዳይነት' ሲባል የተገለፀውን ጦርነት፤ ይህን በመሰሉ መጥፎ ትዝታዎች ነው የሚያስታውሰው። "እስካሁን በህይወት ያለሁት፤ ያኔ ስላልሞትኩ ነው" ይላል። ከብዙ ትግል በኋላ፤ ከሞት አምልጠን መስከረም በምትባለው መርከብ ከምፅዋ ወደ አሰብ ስንሄድ፤ እናቴ ደግሞ አሰብ ነበረችና፤ ከልጄ ጋር እሞታለሁ ብላ እኔ ጋር ለመምጣት ወደ ምፅዋ በመርከብ ስትጓዝ የኤርትራ ሽምቅ ተዋጊዎች መርከቧን አቃጠሏት። መርከቢቷ የኢትዮጵያ ወታደሮችን የጫነች ስለመሰላቸው ነው ነበር ያጠቋት። እናቴና ሌሎች ተሳፋሪዎች ነፍሳቸውን ለማዳን ወደ ባህሩ ዘለው ሲገቡ፤ ሲቪል መሆናቸውን ያዩ ታጋዮች ታደጓቸው። አያቴ በነጋታው፤ እናቴ የነበረችባት መርከብ መቃጠሏን በሰማች ግዜ፤ እንዲህ ታለቅስ ጀመር። ውሃው ነው ወይ የበላሽ? እሳቱ ነው ወይ የበላሽ? አሳው ነው ወይ የበላሽ? "ትንሽ ቆይቶ፤ እናቴ ስልክ ደውላ በህይወት እንዳለች ነገረችን።" ሳሙኤል ዳግም እናቱን ያገኘው ግን፤ ከነፃነት በኋላ እርሷ ታጋይ ሆና ነው። "ይህ ሰላም የፀሎታችን መልስ ነው። መጪው ዘመናችን፤ ስደት፣ ረሃብ እና ጦርነት የሌለበት፤ ሰላም የሰፈነበት ይሆን ዘንድ ነው'' የሚለው ሳሙኤል፤ ምንም እንኳ ሁለት ባንዲራ ቢኖረንም፤ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች ይበዛሉ ባይ ነው። "አሁን ያገኘነው ሰላም፡ ከሰው ሳይሆን ከአምላክ ነው።"
50569418
https://www.bbc.com/amharic/50569418
የሩስያ ላሞች ከጭንቀት እንዲገላገሉ 'ቪአር' ተገጥሞላቸዋል
አንድ የሩስያ ግብርና ድርጅት ወተት አምራች ላሞቹ ከጭንቀት እንዲገላገሉ 'ቨርችዋል ሪያሊቲ' የተሰኘ ቴክኖሎጂ ግንባራቸው ላይ ገጥሞላቸዋል።
አርብቶ አደሩ ድርጅት ለላሞች ተብለው የተዘጋጁ 'ቪአሮችን' ነው ላሞቹ ግንባር ላይ የገጠመው። 'ቪአር' የተሰኘው ዓይን ላይ የሚደገን መሣሪያ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በ360 ድግሪ በማሳየት እውነተኛ እስኪመስሉ ድረስ ያደናግራል። ላሞቹ የተገጠመላቸው ቪድዮ የክረምት ሽታ ያለው ያማረ መስክ ነው ተብሏል። የሩስያ ግብርናና ምግብ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት፤ አንድ ያስጠናሁት ጥናት ላሞች የሚሰጡት ወተት መጠንና ያሉበት ስሜት (ሙድ) ተያያዥነት እንዳለው ያሳያል ይላል። የቪአር ቴክኖሎጂ ግንባራቸው ላይ የተሰካላቸው የመጀመሪያዎቹ ላሞች 'ደስተኛ ቀን አሳልፈዋል፤ ጥሩ የወተት ምርትም ሰጥተዋል' ተብሏል። ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ የለቀቀው መግለጫ እንዳመላከተው፤ የሙከራ ትግበራውን ያከናወነው ሞስኮ ጥግ ላይ ያለ አንድ የእንስሳት ተዋፅዖ አምራች ድርጅት ነው። "በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያደረግነው ሙከራ እንደሚያሳየው ላሞች በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ፤ የሚሰጡት ወተት መጠንና ጥራት ይጨምራል" ይላል መግለጫው። የሙከራ ትግበራውን ተከትሎ አጥኚዎች የቴክኖሎጂውን የረዥም ጊዜ ጥቅምና እና ጉዳት ይመረምራሉ። ውጤቱ አመርቂ ከሆነ የሩስያ ላሞች ግንባራቸው ላይ ቴሌቪዥን ሰቅለው ሊውሉ መሆኑ ነው።
news-42700061
https://www.bbc.com/amharic/news-42700061
በካሊፎርኒያ 13 ልጆች በቤታቸው ውስጥ በሰንሰለት ታስረው ተገኙ
ሁለት ወላጆችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ 13 ልጆቻቸውን በሰንሰለት አስረው በማቆየታቸው በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው የካሊፎርኒያ ፖሊስ አስታወቀ።
ሁለቱ ወላጆች፤ ልጆችን በማሰቀየት እና አደጋ ላይ መጣል የሚሉ ክሶች ተመስርቶባቸዋል። የ57 ዓመቱ ዴቪድ ተርፒን እና የ49 ዓመቷ ባለቤቱ ሉዊዝ አን ልጆችን በማሰቀየት እና አደጋ ላይ መጣል የሚሉ ክሶች ተመስርቶባቸዋል። ካሊፎርኒያ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በሰንሰለት ታስረውና ተቆልፎባቸው የተገኙት ልጆች እድሜያቸው ከ 2-29 እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ጨምሮ እንዳስታወቅም ታስረው የተገኙት 13ቱ ሰዎች ወንድምና እህት ናቸው። የፖሊስ አዛዡ በሰጡት መግለጫ፤ ፖሊስ ከቦታው መድረስ የቻለው ከታሳሪዎቹ መካከል የ10 ዓመት እድሜ ያላት ህጻን አምልጣ ቤቱ ውስጥ ባገኘችው ተንቀሳቃሽ ስልክ ወደ ፖሊስ ከደወለች በኋላ ነው ብለዋል። የ10 ዓመቷ ህጻን ወደ ፖሊስ ደውላ ሌሎች 12 ወንድም እና እህቶቿ በወላጆቻቸው ታስረው እንደሚገኙ ተናግራለች። ፖሊስ በቦታው ሲደርስ በምግብ እጥረት የተጎሳቆሉ እና ንጸህና በጎደለው ጨለማ ክፍል ውስጥ የታሰሩ 12 ሰዎችን ማግኘቱን ተናግሯል። ወላጆቹ ልጆቻቸውን ለምን በዚህ አይነት ሁኔታ እንዳቆዩ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ መስጠት አልቻሉም። ፖሊስ ከታሳሪዎቹ መካከል 7ቱ እድሜያቸው ከ18-29 የሚገመቱ አዋቂ መሆናቸው ድንጋጤን ፈጥሮብኛል ብሏል። 13ቱም ልጆች አሁን በአካባቢው በሚገኙ ሆስፒታሎች እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።
54356741
https://www.bbc.com/amharic/54356741
የአንበጣ መንጋ፡ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ኬሚካል በመርጨት ላይ የነበረ ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ
በአማራ ክልል ወረባቦ ወረዳ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል በመርጨት ላይ የነበረ ሄሊኮፕተር ዛሬ መስከረም 22/2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ላይ በወረዳው 014 ቀበሌ ልዩ ስሙ ፍራንጉል በሚባል ቦታ መከስከሱ ተገለጸ።
የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአደጋው በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንና የሄሊኮፕተሩ አብራሪ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞት በሰመራ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል። ኃላፊው የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑንም ገልፀዋል። የአንበጣ መንጋው ከዚህ በፊት ከተከሰተው በበለጠ በወረዳው 6 ቀበሌዎች መከሰቱን የገለፁት አቶ ሳዳም፤ አንበጣው በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም ተናግረዋል። ኃላፊው እንዳሉት አንበጣውን ለመከላከል የአካባቢው ነዋሪዎች ባህላዊ መንገዶችን ሲጠቀሙ የቆዩ ሲሆን፤ በሄሊኮፕተር የኬሚካል ርጭት የተጀመረው ባለፈው ቅዳሜ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከሰመራ የሚነሳው ሄሊኮፕተርም በየሁለት ቀኑ ገደማ የኬሚካል ርጭት ሲያደርግ እንደነበር ተናግረዋል። የአንበጣ መንጋው በወረዳው ከ5 ሺህ ሔክታር በላይ ሰብል ያወደመ ሲሆን፤ እስከ ትናንት ድረስ ከ14 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የኬሚካል ርጭት መደረጉንም ኃላፊው ገልፀዋል። የአንበጣ ወረራው አስጊ እንደሆነም ኃላፊው አክለዋል። ሚያዚያ ወር ላይ ከሶማሌላንድና የመን እንደተነሳ የተነገረው የአንበጣ መንጋ በምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ተከስቶ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉ ይታወሳል። አሁንም በድጋሚ የተከሰተው የአንበጣ መንጋው በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው። የአንበጣ መንጋን በባህላዊ መንገድ እንዴት መከላከል ይቻላል ? ማኅበረሰቡ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ድምፅ የሚፈጥሩ ነገሮችን በማቃጨል፣ በጅራፍ፣ በጥይት፣ በጩኸት፣ በርችት፣ በዘፈን፣ በፉጨት፣ ጨርቅ በማውለብለብ ለመከላከል ሲሞክሩ ተስተውለዋል። ይህንን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በግብርና ሚኒስቴር የዕፅዋት ጥበቃ ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ዘብዲዎስ ሰላቶን ለቢቢሲ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። አቶ ዘብዲዮስ አንበጣ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አዲስ አይደለም በማለት አንበጣን በባህላዊ መንገድ መከላከል በሳይንስም የሚደገፍ ነው ይላሉ። ከዚህ ቀደም ወደ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር አካባቢና ከዚያ ባሻገር ካሉ የአረብ አገራት የአንበጣ መንጋ ይመጣ ስለነበር አንበጣን በባህላዊ መንገድ የመከላከል ልማድ እንደነበር ይናገራሉ። አንበጣው ሰብል ላይ እንዳያርፍ የማባረር ሥራም ይሠራ ነበር። ነገር ግን ከቦታ ቦታ የመረጃ ልውውጥ መኖሩ እጅግ አስፈላጊ ነው። ወደ ሄደበት አካባቢ ሪፖርት ማድረግ መዘንጋትም የለበትም ይላሉ። ይሁን እንጅ አሁን በተለያዩ አካባቢዎች አንበጣን በጥይት ለማባረር የሚደረገው ሙከራ ትክክል አይደለም ሲሉ ነቅፈዋል- በጥይት የማባረር ተግባር ከአራት ዓመታት በፊት ጉዳት እንዳስከተለም ያስታውሳሉ። እንደ ዳይሬክተሩ ከሆነ በወቅቱ ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ከምሥራቅ ኢትዮጵያ መከላከል አምልጦ ወደ አዲስ አበባ የገባው በጥይት ምክንያት ነው። ከዚያም ወደ ሰሜን የአገሪቷ ክፍሎች አምርቶ በርካታ ቀበሌዎችን ማዳረሱ የቅርብ ጊዜ ትውስታቸው ነው። በመሆኑም "ብዙ ጭስ ማጨስ ሳያስፈልግ፤ በጭስ፣ በቆርቆሮ ድምፅ፣ በልጆች ጩኸት ድምፅ፣ በተለይ በጅራፍ ከሰብል ላይ መንጋውን ማባረር በቂ ነው" ሲሉ ይመክራሉ። ነገር ግን ከሰብል አቅራቢያ ያለ የግጦሽ መሬት ላይ፣ ደን አካባቢ እና ሌሎች አካባቢዎች ሄዶ ካረፈ ማደሪያውን ብቻ መከታተል እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። በርካታ ሕዝብ የማይኖርበትና ለመጠጥና ለምግብነት የሚውሉ ሰብሎች ባሉበት ቦታ ካልሆነ በስተቀር ፀረ ተባይ ኬሚካል መርጨት እንደሚቻል አቶ ዘብዲዎስ አስገንዝበዋል።
news-49310398
https://www.bbc.com/amharic/news-49310398
ማንቸስተር ሲቲ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አደጋ?
እጅግ ድንቅ ፉክክር የታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያለፈው ወድድር ዘመን እነሆ በአዲሱ ተተክቷል።
አውሮፓ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የዓለማችን ልጥጥ ክለቦች የሚገኙበት ቢሆንም አደጋ የተጋረጠበት ይመስላል። አደጋው ደግሞ የባለፈው ውድድር ዘመን ቻምፒዮና - ማንቸስተር ሲቲ፤ ይላል የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ቤን ሱዘርላንድ። •ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» •"የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተወዳጅ እንዲሆን ካደረጉት ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ልብ-አንጠልጣይ ፉክክር የሚታይበት መሆኑ ነው። ፈጣን፣ ፈታኝ እና የማይጠበቁ ውጤቶች የሚመዘገቡበት ሊግ ነው። ቢሆንም ይህ ምስል አደጋ ላይ ይመስላል። በዓመታት ሂደት ሊጉ ስድስት ኃያላን ክለቦች ተብለው የሚታወቁትን አምርቷል። ዩናይትድና ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ አርሴናል እና የከተማ ተቀናቃኙ ቶተንሃም እንዲሁም የምዕራብ ለንደኖቹ ቼልሲ። አደጋው እዚህ ጋ ነው። በሂደት ስድስቱ ኃያላን ቀርቶ አንድ ኃያል እንዳይሆን የሚል ስጋት። 'እግር ኳስ ከስማለች' ያለፈው ውድድር ዘመን እጅግ ተወዳጅ ያደረገው ሊቨርፑል የሲቲን እግር እየተከተለ ዋንጫ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ነበር። ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች የቋመጡለትን ዋንጫ ተቀያይረው አግኝተዋል። ፕሪሚዬር ሊግን የቋመጠው ሊቨርፑል ቻምፒዮንስ ሊግ ሲያነሳ፤ ቻምፒዮንስ ሊግን ለማንሳት የሻተው ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ወስዷል። •ታዳጊዎችን በወሲብ ንግድ በማሰማራት ተከሶ የነበረው ቱጃር አሟሟት ጥያቄን ፈጥሯል ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ካነሳ ሶስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል፤ በአቡ ዳቢ ቱጃሮች የተያዘው ሲቲ ደግሞ ቻምፒዮንስ ሊግ አንስቶ አያውቅም። ሲቲ ዘንድሮ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ከቻለ ሌላ ታሪክ ይፅፋል። በአንድ ውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች በማስቆጠር እና በርካታ ነጥቦች በማምጣት ሲቲ ሪከርዱን ይዟል። በኤፍ ኤ ዋንጫ ዋትፈርድን 6-0 በመርታት ተመልካችን አጀብ አሰኝተዋል። ይህን ያዩ የኳስ ተንታኞች 'እግር ኳስ ከስማለች' እስከማለት ደርሰዋል። የፈርናንዲሆ ምትክ ያስፈልጋቸዋል እየተባሉ ሲታሙ የነበሩት ሲቲዎች ባለተሰጥዖው ሮድሪን አስፈርመዋል። በዘመናዊ እግር ኳስ ምርጡ አሰልጣኝ የሚል ስያሜ የተሰጠው ፔፕ ጉዋርዲዮላን የያዙት ሲቲዎች ወደፊትም ተፅዕኖዋቸው እንደሚቀጥል ይገመታል። የተሻለ የእረፍት ጊዜ ያሳለፉት ሲቲዎች በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ሊቨርፑልን መርታት ችለዋል። በአቋምም ሆነ በስነልቡና ጥንካሬ ከሊቨርፑል የተሻሉ ሆነው ነበር የታዩት። በሌላ በኩል ሌሎች ኃያላን ሲቲን ተቋቁመው የሊጉን ዋንጫ ያነሳሉ ማለት ከባድ ነው። አርሴናሎች ፔፔን ቢያስፈርሙም፤ ተከላካይ መስመሩ አሁንም ጥገና የሚያሻው ይመስላል። ኪዬራን ቲየርኒን ከሴልቲክ፣ ዴቪድ ልዊዝን ደግሞ ከቼልሲ ማስፈረማቸው ሳይዘነጋ። አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት ቼልሲዎች ኤደን ሃዛርድን ለቼልሲ ቢሸጡም በተጣለባቸው ቅጣት ምክንያት ተጫዋች መግዛት አልቻሉም። ይህ ደግሞ ለአዲሱ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ሁኔታዎችን የሚያከብድበት ይመስላል። የዩናይትዱ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ቡድኑን የተቀበለ ሰሞን ድንቅ አቋም ቢያሳይም ወደ መጨረሻ ከበድ ያለ ጊዜ አይቷል። ዩናይትዶች ሊጉን ያሸንፋሉ ተብሎ የተሰጣቸው ግምት ከእስከዛሬው እጅግ ዝቅ ያለ ነው። •ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ ታድያ የእነዚህ ኃያላን ቡድኖች እንደ ሲቲ ዝግጁ አለመሆን ለሊጉ አደጋ መሆኑ አይቀርም። እንደ ጣልያን [ጁቬንቱስ ለ8 ተከታታይ ዓመታት ዋንጫ ያነሳበት]፤ እንዲሁም ጀርመን [ባየርንሚዩኒክ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት] ሊጎች አጓጊነቱ የወረደ እንዳይሆን ነው ዋነኛው ስጋት። በየወሩ ክፍያ እየከፈሉ የሚመለከቱ ተመልካቾች ክፍያቸውን ሊያቋርጡ ይችላሉ፤ በተለይ ደግሞ እንግሊዝ የሚገኙቱ የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ማሽቆልቆል ከማሳየቱ ጋር በተያያዘ። በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን ፉክክር የማይታይበት ሊግን ለማዬት ተመልካቾች ብዙም ጉጉት ላያሳዩ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ጣልያን እና ጀርመን የአፍሪቃ እና እስያ ተመልካቾችን ለመመለስ ብዙ ትግል እያደረጉ እንዳለ ልብ ይሏል። የአውሮፓ ሱፐር ሊግ አውሮፓ ሱፐር ሊግ እውን ከሆነ አደጋው ለፕሪሚዬር ሊግም ጭምር ነው። ሲቲ በገንዘቡ ነው ዋንጫ እየገዛ ያለው የሚለው ትላልቅ የሊጉ ክለቦች ጭምር ሊቀላቀሉ ይችላሉ። 500 ሚሊዮን ዩሮ ደግሞ የሱፐር ሊግ ዓመታዊ ገቢ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ምንም እንኳ የሱፐር ሊግ ሃሳብ ከ98 የአውሮፓ ክለቦች በ94ቱ ተቃውሞ ቢገጥመውም። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ግን ዕቅዱ እንዳለ ነው። ማን ያውቃል ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊዎች ቁጥር እየጨመረ ሊመጣ ይችል ይሆናል። ቶተንሃም፣ ቼልሲ እና አርሴናል ባለፈው ዓመት አንድ ወቅት ላይ ለሊጉ ለዋንጫ ያሰፈሰፉ ቡድኖች ነበሩ። ቢሆንም ከተስፋ ውጭ ምንም የተጨበጠ አልነበረም። ይህ ደግሞ ደጋፊዎቻቸው በጊዜ ሂደት እየሸሹ እንዲመጡ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። ደጋፊዎች ሁሉንም የቀጥታ ሥርጭት ጨዋታዎች ከፍለው መመልከት አይችሉም። አውሮፕ ሊግ ጨዋታዎች ግን ክፍያቸው እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያነሰ ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ አደጋ ነው። ማንቸስተር ሲቲ መቆም ካልቻለ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዕጣ ፈንታ ከሴሪ ኤ፣ ቡንደስሊጋ እና የስኮቲሽ ፕሪሚዬርሺፕ የተለየ የሚሆን አይመስልም፤ የአንድ ቡድን ፍፁም ተፅዕኖ የሚታይበት ሊግ። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አሁን ላይ አጓጊና እና ኃያል ይመስላል፤ በዚህ ከቀጠለ ግን አወዳደቁ የሚያምር አይሆንም።
news-46107373
https://www.bbc.com/amharic/news-46107373
ቢቢሲ ለንደን ከሚገኘው ቢሮ ቀጥሎ ግዙፉን ቢሮውን በናይሮቢ አስመረቀ
ቢቢሲ እንግሊዝ ውስጥ ካለው ቢሮው ቀጥሎ እጅግ ግዙፍ የሆነውን ቅርንጫፉን ትላንት በይፋ አስመርቋል።
ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ከእንግሊዘኛ ውጪ በ12 ቋንቋዎች ይሰራጫል በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚገኘው ዘመነኛ ቢሮው ውስጥ ወደ 300 የሚጠጉ ባለሙያዎች ይሰራሉ። ቢቢሲ በመላው አፍሪካ ወደ 600 ያህል ጋዜጠኞች አሉት። የናይሮቢው የቢቢሲ የምስራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ አማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮኦምኛን ጨምሮ ሌሎችም ቋንቋዎች የሚሰራጩበት ነው። የቢቢሲ ኒውስ ዳይሬክተር ፍራንቼስካ አንስወርዝ "ትልቁ ኢንቨስትመንታችን በሙያ የላቁ አፍሪካዊ ጋዜጠኞችን ማፍራት ነው" ብለዋል። በእንግሊዝ መንግሥት የሚደገፈው የቢቢሲ የማስፋፋፊያ ፕሮጀክት 376 ሚሊየን ዶላር ወጥቶበታል። • የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? አዲስ የተመረቀው ቢሮ፤ የቴሌቭዥን ስቱዲዮ፣ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፊያ፣ ሁለት የራድዮ ስቱድዮ እንዲሁም አምስት የቴሌቭዥን አርትኦት ክፍሎች አሉት። በያዝነው ዓመት መባቻ ላይ በናይጄሪያ የቢዝነስ መዲና ሌጎስ ውስጥ ሌላ የቢቢሲ ቢሮ ተከፍቶ ነበር። ከሌጎስ በኢግቦ፣ በዮሩባና በፒጅን ቋንቋዎች መሰናዶዎች ይሰራጫሉ። የፈረናሳይኛ ቋንቋ ስርጭት የሚተላለፈው ደግሞ በሴኔጋል መዲና ዳካር ከተከፈተው ቅርንጫፍ ነው። ቢቢሲ የናይይሮቢውን ቢሮ የከፈተው እንደ አውሮፓውያኑ በ1998 ነበር። አሁን እንግሊዘኛን ጨምሮ በ40 ቋንቋዎች መርሀ ግብሮቹን ያስተላልፋል። የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ የምስራቅ አፍሪካ ኃላፊ ሬቸል አኪዲ ቢሮው ትላንት ሲመረቅ "አፍሪካውያን ጋዜጠኞችን እያከበርን ነው። የቢቢሲን የሙያ ስነ ምግባር፣ መድልዎ የሌለበትን ዘገባ እንደያዝን እንቀጥላለን" ብለዋል። • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? የአዲሱ ቢሮ መመረቅ "መኒ ዴይሊ"ከተሰኘው አዲስ መሰናዶ መጀመር ጋርም ገጥሟል። የቢዝነስ መርሀ ግብሩ የሚሰራው ናይሮቢ ውስጥ ነው። "መኒ ደይሊ" ሲሰናዳ "አፍሪካ አይ" የተባለው የምርመራ ዘገባ መሰናዶ በተጀመሩ በአጭር ጊዜ ከተወደዱ ቅንብሮች አንዱ ነው። በአውሮፓውያኑ 2018 የዓለም ዋንጫ ስለ አንድ ዳኛ ጉቦ መብላት የተሰራው ዘገባ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን (ካፍ) በይፋ ምርመራ እንዲጀምር ያነሳሳ ነበር። በወርሀ መስከረም ሁለት ሴቶችና ሁለት ህጻናትን የገደሉ የካሜሩን ወታደሮችን ከጥልቅ ምርመራ በኋላ ይፋ ማውጣቱም ይታወሳል። • ከኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እስከ ሣህለወርቅ ዘውዴ
53840732
https://www.bbc.com/amharic/53840732
ማሊ ከአፍሪካ ህብረት አባልነት ታገደች
የአፍሪካ ህብረት የፀጥታና ሰላም ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት በመፈንቅለ መንግሥት ፕሬዚዳንቷን ከስልጣን ያስወገደችውን ማሊን ከአፍሪካ ህብረት አባልነት አግዷታል።
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አገሪቷ ህገ መንግሥታዊ ስርአት እስክታሰፍን ድረስና በቁጥጥር ስር ያሉትን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች ባለስልጣኖች እስኪለቀቁ ድረስም እግዱ ይቆያል ብሏል። የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሲሪል ራማፎሳም በወታደራዊ ኃይሉ በቁጥጥር ስር ያሉትን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር ኬታም እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። ሊቀ መንበሩ ሲሪል ራማፎሳ አገሪቷ በአስቸኳይ ወደ ሲቪል አስተዳዳር እንድትመለስም አሳስበዋል። የአውሮፓ ህብረትም ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ባውባካር እንዲለቀቁ መጠየቁን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል። በትናንትናው ዕለት ወታደሮች የፕሬዚዳንቱን ቢሮ ሰብረው በመግባት ፕሬዚዳንቱንና አብረዋቸው የነበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር በቁጥጥር ስር አውለዋል። ከነሱም በተጨማሪ የብሔራዊ ጉባኤ ቃለ አቀባይ የሆነው የፕሬዚዳንቱ ልጅ፣ የውጭ ጉዳይና የገንዘብ ሚኒስትሮችም በቁጥጥር ስር መሆናቸውም ተገልጿል። ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ከስልጣን መልቀቃቸውንም ትናንት አጠር ባለው የቴሌቪዥን መግለጫቸው አስታውቀዋል።
54617480
https://www.bbc.com/amharic/54617480
የፖለቲካ ተንታኙ ቪዲዮ ኮንፈረንስ ላይ ብልቱን ሲነካካ በመታየቱ ይቅርታ ጠየቀ
በአሜሪካ ፖለቲካ አሉ ከሚባሉ የሕግ ተንታኞች አንዱ ነው። ለዝነኛው የኒውዮርከር መጽሔት ይሰራል።
የፖለቲካ ተንታኙ ጄፍሪ ቱቢን በሲኤንኤን ቴሌቪዥን በመቅረብም ጥልቅ የሕግና ፖለቲካ ትንታኔዎችን በመስጠት ይታወቃል። ጄፍሪ ቱቢን 60 ዓመቱ ሲሆን መቼ ለታ ዙም በተሰኘ የኢንተርኔት ቪዲዮ ጥሪ ላይ እያለ ነው ስህተት የፈጸመው። ድርጊቱ ያበሳጨው ኒውዮርከር መጽሔት ከሥራ አግዶታል። የአሜሪካ ምርጫ 15 ቀናት በቀረበት በአሁኑ ወቅት ጄፍሪ በሚዲያዎች ላይ እጅግ ተፈላጊው ተንታኝ ነበር። ጄፍሪ ካሜራ የጠፋ መስሎት ነው ድርጊቱን የፈጸመው። ድርጊቱን በቅድምያ ላጋለጠው ቫይስ ኒውስ ጄፍሪ እንደተናዘዘው ‹‹ድርጊቱን ያደረኩት ካሜራ የጠፋ መስሎኝ ነው፤ ቀሽም ሥራ ነው የሰራሁት፤ አፍሪያለሁ›› ብሏል። ጄፍሪ ለቤተሰቡ ለጓደኞቹና ለባልደረቦቹ ከፍ ያለ ይቅርታን ጠይቋል። የዙም ቪዲዮ ማብሪያና ማጥፊያውን እንደተዘጋ የገመተው ጄፍሪ በዚህ የሥርጭት ልምምድ ወቅት ብልቱን ሲነካካ ነበር። ቫይስ ኒውስ ጄፍሪ ድርጊቱን ሲፈጽሙ ያዩትን እማኞቹን ጠቅሶ ነው ዜናው ለአደባባይ ያበቃው። ነገሩን እስክንመረምር ድረስ ጄፍሪን ከሥራ አግደናዋል ብሏል ኒውዮርከር። ጄፍሪ ለታዋቂው ሲኤንኤን ጣቢያም ዋና የሕግ ተንታኝ ነው። ሲኤንኤን በበኩሉ ጄፍሪ ትንሽ ለራሴ ጊዜ እፈልጋለሁ ብሎናል፤ በሥርጭቶቻችን ላይ ተመልሶ ለመቅረብ ጊዜ ይፈልጋል። ይህንንም ፈቅደንለታል ሲል መግለጫ አውጥቷል። ጄፍሪ በሕግና ፖለቲካ ዙርያ በተለይም ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በተያያዘ በርካታ መጻሕፍትን ለኅትመት አብቅቷል።
news-57340390
https://www.bbc.com/amharic/news-57340390
በዓለም በጥልቀቱ ቀዳሚ የሆነ የውሃ ገንዳ በእንግሊዝ ሊገነባ ነው
ለባህር እና ለጠፈር ምርምር የሚያገለግል በዓለም በጥልቀቱ ቀዳሚ የሆነ የውሃ ገንዳ በእንግሊዝ፣ ኮርንዎል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በ 150 ሚሊዮን ዩሮ የሚገነባው ፕሮጀክት በኮርንዌል አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው ኤሮሃብ ኢንተርፕራይዝ ዞን የሚያርፍ ሲሆን 50 ሜትር ጥልቀት ያለው ገንዳ የሚይዝ የውሃ ማዕከል ይሆናል ፡፡ የውሃ ገንዳው የውሃ ውስጥ ሮቦቶችን ጥናት ለማካሄድ እና ጠፈርተኞችን ለማሰልጠን ሊያገለግል ይችላል የሚል እምነት ተፈጥሯል፡፡ እቅዶቹን የሚደግፉት የጠፈር ተመራማሪው ቲም ፒክ "ፕሮጀክቱ እንደጎዮሂሊ ኤርዝ ስቴሽን እና ስፔስፓርት ኮርንዌልን ያሉ ከፍተኛ ብሔራዊ ሃብቶች ይቀላቀላል። የሰው ልጆችን እና የፕላኔቶችን በሚጠቅም መልኩ እጅግ ከባድ በሆኑ አካባቢዎች ሰዎች እና ቴክኖሎጂዎች እንዴት እንደሚሠሩ ያለንን ዕውቀት ለማስፋት ይረዳል" ብለዋል፡፡ ለዕቅዱ ማስፈፀሚያ ፈቃድ ለማግኘት ማመልክቻ ያስገባው ብሉ አቢይስ የተባለው ኩባን ያለፕሮጀክቱ 10 ሄክታር ቦታ ይኖረዋል፡፡ ገንዳው 40 ሜትር በ 50 ሜትር ነው። 17 የኦሎምፒክ መጠን ያላቸውን የመዋኛ ገንዳዎች ለመሙላት የሚበቃ ውሃ ይይዛል። ተንሸራታች ጣሪያ የሚገጠምለት ሲሆን ትልልቅ ዕቃዎችን ወደ ገንዳው ለማስገባት የሚያስችል መጫኛና ማውረጃም ይኖረዋል። የዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የሚመስሉ ክፍሎችን፣ የውሃ ውስጥ ፊልም ስብስቦችን እና በርቀት መቆጣጠሪያ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ለመፈተሽ እና ጥልቅ ዋናተኞችን ለማሰልጠን የሚያግዝ ዋሻ ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ የብሉ አቢይስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የቀድሞው የጠላቂ ዋና አስተማሪው ጆን ቪከርስ ፈጠራ ነው፡፡ ገንዳው "በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ" እንደሚሆን እና "ሰፊ" ጥቅሞች እንደሚኖሩት ተናግረዋል፡፡ "ብሉ አቢይስ ለኤሮስፔስ፣ ለባህር ኃይል፣ ለዉሃ ሮቦት፣ ለሰው ልጅ ፊዚዮሎጂ፣ ለመከላከያ፣ ለመዝናናት እና ለባህር ኢንዱስትሪዎች ትልቅ የምርምር እንዲሁም ለህፃናት እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድንቅ የትምህርት ማዕከል ይሆናል" ብለዋል፡፡ ቫይከር ለቅድመ-ግንባታ ወጪ የሚያስልገውን 5 ሚሊዮን ፓውንድ ያገኙ ሲሆን በ 18 ወራት ለሚጠናቀቀው ፕሮጀክት ግንባታ የተለያዩ የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎች ተዘርግተዋል፡ ኩባንያው ለ 160 ሰዎች የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር እና ለአከባቢው ኢኮኖሚ በዓመት 8 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚያስገኝ ገምቷል፡፡ የፓርላማ አባል የሆኑት ስቲቭ ደብል ፕሮጀክቱ ኒውኳይን በመምረጡ "እጅግ ደስ ብሎኛል" ብለዋል፡፡ "በርካታ አዳዲስ የኮርንዎል ታዳጊ ኢንዱስትሪዎች እንዲበለፅጉ የሚያደርግ፣ በሙያው የተካኑ ባለሙያዎችን የሚፈጥር እና በኢንዱስትሪዎች፣ በጥናትና ትምሀርት ዘርፎች ትብብር የሚፈጥር" ነው ብለዋል፡፡
news-54316118
https://www.bbc.com/amharic/news-54316118
በናይጄሪያ በስርቆት የተጠረጠሩ የሆቴል ሰራተኞች እርቃን መጋለጥ ቁጣን ፈጠረ
በደቡባዊቷ ናይጄሪያ ዋሪ ግዛት የሚገኙ የሆቴል ሰራተኞች ሰርቃችኋል በሚል ልብሳቸውን ያስወለቋቸው አሰሪዎች ጉዳይ ቁጣን ቀስቅቀሷል።
የግዛቷ የሰብዓዊ መብት ጠበቆችም እንዲህ አዋርደው እርቃናቸውን ስላጋለጧቸው ካሳ ሊከፍሏቸው ይገባልም በሚል እየተሟገቲ ነው። ምንም እንኳን ሰራተኞቹ ገንዘብ ሰርቀዋል በሚል ጠርጥረናቸው ነው ቢሉም የአገሪቱ ሚዲያ ግን ከእንግዶች የተሰጣቸው ጉርሻ (ቲፕ) ነው በማለት ዘግቧል። በስርቆት ተጠረጠሩ የተባሉት አራት ሰራተኞች ሲሆኑ ከነዚህም መካከል ሶስቱ ሴቶች ናቸው። ልብሳቸውን እንዲያወልቁና ፓንት ብቻ እንዲያስቀሩ የተነገራቸው ሲሆን ፖሊስም በቦታው ላይ እንደነበረ ተገልጿል። እርቃናቸውን የተጋለጡት የሆቴሉ ሰራተኞች ፎቶና ተንቀሳቃሽ ምስልም በማህበራዊ ሚዲያ በከፍተኛ ሁኔታ መጋራቱን ተከትሎም ነው በርካቶች የተቹት። የሆቴሉ ባለቤት የአገሪቷ የቀድሞ ሚኒስትር እንደሆኑም ተገልጿል። ጠበቆቹ ለሆቴሉ ባለቤት በላኩት ደብዳቤም የሰራተኞቹን ሰብዓዊ መብት በማዋረድና መሰረታዊ መብታቸውን በመጣስም ፍርድ ቤት እንደሚገትሯቸውም አሳውቀዋቸዋል። ካሳና ይፋዊ የሆነ ይቅርታ እንዲጠይቁም በተጨማሪ ጠበቆቹ አሳስበዋል። የጥቃቱ ሰለባዎች በበኩላቸው ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በኢንተርኔት መለቀቃቸው ሆን ብሎ እነሱን ለማዋረድ የታቀደ ደባ ነው ብለዋል።
news-55785214
https://www.bbc.com/amharic/news-55785214
"የባይደን ሹመት ለአሜሪካ ወደፊት መራመድ ነው"-ቦሪስ ጆንሰን
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአቻቸው አሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደወሉ።
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ሐሙስ ቃለ መሐላ ከፈጸሙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልክ ደውለው ሁለቱ አገራት በጋራ ሊያከናውኗቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች እና ስለሚኖራቸው ትብብር አውርተዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት፣ በእንግሊዝ እና አሜሪካ መካከል ያለውን ጠንካራ ወዳጅነት ለማስቀጠል በተስፋ እየጠበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ሐሙስ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ ካማላ ሐሪስ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የባይደን ሹመት ለአሜሪካ "ወደፊት መራመድ" ነው ብለውታል። በዶናልድ ትራምፕ ዘመን አሜሪካ ራሷን አግልላባቸው የነበሩ የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ እና የዓለም ጤና ድርጅት የመሳሰሉትን አሜሪካ ዳግም እንድትቀላቀል ፕሬዝዳንት ባይደን መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ በአድናቆት ተቀብለዋል። የዳውኒንግ ስትሪት ቃል አቀባይ እንደገለጹት ፕሬዝዳንት ባይደን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ቀድመው የወሰዱት ርምጃ እና በ2050 (እአአ) የአየር ልቀትን ዜሮ ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ያደረጉትን ጥረት ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ማድነቃቸውን ገልጿል። ቃል አቀባዩ አክለውም "መሪዎቹ የሁለቱ አገራትን የቆየ የጸጥታ እና የመከላከያ ትብብር ለማሳደግና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ላይ ያላቸውን አጋርነት ለማሳደግ ተስማምተዋል" ያሉ ሲሆን የሁለቱ አገራት የጋራ እሴት የሆኑት ሰብዓዊ መብትን መጠበቅ እና ዲሞክራሲን ማጎልበት ላይ በጋራ እንደሚሰሩ መሪዎቹ መነጋገራቸውንም ቃል አቀባዩ ጨምሮ ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ መሪዎች በነጻ ንግድ ስምምነት ዙሪያ ያለውን አዋጭነትም አንስተዋል ተብሏል።
news-54094323
https://www.bbc.com/amharic/news-54094323
በአማራና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ የተከሰተው ምንድን ነው?
ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በወልቃይት ጠገዴ በተለይም በአማራ እና ትግራይ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እንደነበር የአካባቢው የፀጥታ አካላት ለቢቢሲ ተናገሩ።
ቢቢሲ የሁለቱንም ክልል የፀጥታ ኃላፊዎች ያነጋገረ ሲሆን አንዳቸው በሌላኛቸው ክልል ወገን ግጭት መቀስቀሱን ገልፀዋል። ቢቢሲ በአማራ ክልል ሥር የሚገኘው የጠገዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ሙሉጌታ ስለ ጉዳዩ ጠይቆ፣ እርሳቸው በሚያስተዳድሩት ወረዳ ምንም ግጭት አለመኖሩን ገልጸው በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የጸገዴ ወረዳ ግን ከምርጫው ጋር ተያይዙ ግጭት መኖሩን እንደሰሙ ለቢቢሲ ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የትግራይ ክልል ፀጥታ ከፍተኛ ኃላፊም በምዕራብ ትግራይ ጸገዴ አካባቢ በትግራይ መሬት ገብቶ የተኮሰ አካል እንደሌለ በመግለጽ "በአማራ ክልል ውስጥ ግን ተኩስ እንደነበረ ሰምተናል" ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ሙከራ "ህዝብን ለማደናገጥ የታሰበ" ቢሆንም ህዝቡ ግን በነቂስ ወጥቶ ድምጹን ሰጥቷል ብለውናል ያነጋገርናቸው የጸጥታ ሃላፊዎች። የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ከቢቢሲ ኒውስ ደይ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ በነበራቸው አጭር ቆይታ በትግራይ ደቡብ አካባቢ ምርጫውን የማደናቀፍ ሙከራዎች እንዳሉ ገልጸዋል። "አሁን ካንተ ጋር በምነጋገርበት ሰዓት በትግራይ ደቡብ አካባቢ ድንበር ላይ ግጭት ለማንሳት የሚሞክሩ ሰዎች አሉ። እኛም እነዚህ ትንኮሳዎችን ስንመክት ቆይተናል" ሲሉም ለጋዜጠኛው አስረድተዋል። የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ "የትምክህት ሃይሎች" ሲል በገለጻቸው አካላት ከምርጫ ጣቢያ ራቅ ባለ አካባቢ ትንኮሳ እንደነበር በፌስቡኩ አሳውቋል። "በቂ ሃይል ስላለ ትንኮሳው አልተሳካም። ሙከራው ለደቂቃዎች ብቻ እንደነበረም ለማወቅ ችለናል" ብሏል ኮሚሽኑ። በሌላ በኩል የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክብረዓብ ቸርነት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው የጸገዴ ወረዳ ውስጥ ልዩ ስሙ ጨቋር ኩዶቢን በሚባል ቦታ ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ የትግራይ ልዩ ኃይል ነዋሪው ወጥቶ እንዲመርጥ እና ሚሊሻው ደግሞ "አማራ ሊወርህ እየመጣ ስለሆነ መንገድ ዝጋ" የሚል ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ይገልጻሉ። ነገር ግን ሕዝቡ የመምረጥም ሆነ መንገድ የመዝጋት ፍላጎት አልነበረውም የሚሉት አቶ ክብረዓብ ሕዝቡ ምላሽ ባለመስጠቱ "ከትግራይ ልዩ ኃይል በኩል ተኩስ ተከፈተበት" ብለዋል። ይህንን ተከትሎም ሕዝቡ ራሱን በመከላከሉ ግጭት ተነስቶ እንደነበር ገልጸዋል። ሆኖም በነበረው የተኩስ ልውውጥ ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጸዋል። አሁን አካባቢው የተረጋጋ ቢሆንም ምርጫውን ተከትሎ ግን የተለየ ነገር ሊኖር እንደሚችልም ገልጸዋል። ባለፉት ወራት በአካባቢው ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱ እንደነበር የሚገልፁት አቶ ክብረአብ ይህንንም ለሚመለከታቸው አካላት ቢያመለክቱም እስካሁን መልስ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በፊትም የምርጫ ካርድ ለምን አላወጣችሁም በሚል ሳቢያ ከ500 በላይ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ወጣቶች በትግራይ ክልል መንግሥት መታሰራቸውን የማንነት ኮሚቴው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ገልጸዋል።
news-41485955
https://www.bbc.com/amharic/news-41485955
ኤም ኤች 370 ጠፍቶ መቅረቱ ማይታሰብ ነው ሲል አንድ ሪፖርት ገለጸ
ንብረትነቱ የማሌዥያ አየር መንገድ የሆነው ኤም ኤች 370 አውሮፕላን ጠፍቶ መቅረቱን "የማይታሰብ" ሲሉ የአውስትራሊያ መርማሪዎች የመጨረሻ ነው ባሉት ሪፖርታቸው ይፋ አደረጉ።
ኤም ኤች 370 እ.አ.አ በ2014 ነበር 239 ሠዎችን ጭኖ ነበር የጠፋው ኤም ኤች 370 እ.አ.አ በ2014 ነበር፤ 239 ሠዎችን አሳፍሮ ከቤጂንግ ወደ ኳላላምፑር ሲያቀና የጠፋው። ማሌዥያና ቻይናን ጨምሮ በትብብር ሲካሄድ የቆው ፍለጋም ከ1046 ቀናት በኋላ በይፋ ቆሟል። የአውስትራሊያ መርማሪዎች አውሮፕላኑ ባለመገኘቱ "ክፉኛ ማዘናቸውን" አስታውቀዋል። "በቀን 10 ሚሊዮን ሠዎች በአውሮፕላን በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ትልቅ የንግድ አውሮፕላን ከነመንገደኞቹ ጠፍቶ መቅረቱ የማይታሰብ እና በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ነው" ሲል የአውስትራሊያ የትራንስፖርት ደኅንነት ቢሮ አስታውቋል። "በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳትፎ የተደረገው ትልቅ የማፈላለግ ሥራም ውጤት አላመጣም" ብሏል። ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ሰዎች ፍለጋው እንዲጀመር እየጠየቁ ነው የመጨረሻ ነው የተባለለት ሪፖርት እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ ቀድሞ ከተገመተበት ቦታ በሰሜን አቅጣጫ ነው የጠፋው። ቦይንግ 777 የሆነውን ይህን አውሮፕላን ለመፈለግ የተደረገው እንቅስቃሴ በአየር ትራንስፖርት ታሪክ ውስጥ ትልቁ ነው ተብሎለታል። ለ52 ቀናት በምድር ላይ ከተደረገ ፍለጋ በኋላ 120 ሺህ ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን የውሃ አካል ላይም ፍለጋው ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር። በ2015 እና 2016 የኤም ኤች 370 ስብርባሪ ነው የተባለላቸው የአውሮፕላን አካላት በተለያዩ ቦታዎች ተገኝተው ነበር። የአውስትራሊያ መንግሥት ፍለጋው በድጋሚ የሚጀመረው አውሮፕላኑ የጠፋበት ቦታ በአስተማማኝ መረጃ ሲታወቅ ነው ብሏል። የማሌዥያ መንግሥት በአውሮፕላኑ መጥፋት ዙሪያ የሚያደርገውን ምርመራ አሁንም ቀጥሎበታል።
news-53355294
https://www.bbc.com/amharic/news-53355294
"ከመረጃ ፍሰት ይልቅ የሕዝባችንን ህይወት ማዳንን ቅድሚያ ሰጥተናል" ዛዲግ አብርሃ
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስቴር ማዕረግ የዲሞክራሲ ግንባታ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከቢበሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ መንግሥት ከእርሱ ሃሳብ ጋር የማይስማሙትን እያሰረ እንዳልሆነ ተናገሩ።
ቢቢሲ በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ በተፈጠረ አለመረጋጋት በቁጥጥር ስር የዋሉ ፖለቲከኞችን፣ ጋዜጠኞችንና ወጣቶችን በመጥቀስ መንግሥት ከፖሊሲው ጋር የማይስማሙትን ማሰሩን ተጠይቀው መልስ ሰጥተዋል። አቶ ዛዲግ በኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ያለውን ለውጥ በመጥቀስ በመንግሥትና በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመቀየር መሰራቱን ያስታውሳሉ። በአገሪቱ ባለፈው ሳምንት የተከሰተውን ሁከት በተመለከተም አሁን እየተደረገ ያለው ከፍተኛ የሆነ የሕግ ጥሰት ነው ያሉት አቶ ዛዲግ፣ በዚህም የተነሳ በርካታ ህይወት መጥፋቱን ጠቅሰዋል። "መንግሥት ነገሮችን መቆጣጠር ይኖርበታል" በማለትም መንግሥት ሕግ እንዲያስከብር ከሕዝቡ ከፍተኛ ፍላጎት ነበር እኛም የሕግ ጥሰት የፈፀሙትን ላይ ነው እርምጃ የወሰድነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህ ደግሞ የመንግሥት መሰረታዊ ዓላማ ነው በማለት መንግሥት እየወሰደ ያለው እርምጃ አግባብ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ዛዲግ አክለውም፣ መንግሥት እያለ ሕግ ካልተከበረ አስፈላጊነቱ ምን ላይ ነው ሲሉም ጠይቀዋል። ከድምጻዊ ሃጫሉ መገደልን ተከትሎ በተነሳው አለመረጋጋት ከ200 በላይ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል። የእነዚህ ሰዎች ህይወት የጠፋው በጸጥታ አካል እርምጃ ነው ተብለው የተጠየቁት አቶ ዛዲግ የፀጥታ ኃይሉ ግጭት ወዳለበት ስፍራ ሲሰማራ እርምጃ ከመውሰድ ታቅቦ ነበር በማለት በዚህም የጸጥታ አባላት ጭምር ህይወት መጥፋቱን ተናግረዋል። አለመረጋጋቱ በተከሰተበት ስፍራ የእርስ በእርስ ግጭት እንደነበር በማስታወስ የሰዎች ሞት ከዚህ ጋር የተያያዘ እንጂ በጸጥታ ኃይሉ አለመገደላቸው ተናግረዋል። መንግሥት ለሁለት ቀን የነበረው ሁኔታ ተቆጣጥሮታል በማለትም፤ በድምጻዊው መገደል ስሜታቸውን የገለፁ ወጣቶች እንደነበሩ ገልፀው ከዚህ በተቃራኒው በብሔሮችና በሀይማኖቶች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የሞከሩ መገናኛ ብዙሃን ስለነበሩ እርመጃ መወሰዱን ተናግረዋል። መንግሥት የመገናኛ ቡዙሃንን መዝጋቱ የመናገር ነፃነትንን ማፈን እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ዛዲግ አሁንም የአገሪቱን ሕግ አክብረው እየሰሩ ያሉ መገናኛ ብዙሃን በሥራ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። አክለውም መንግሥት ከዚህ ቀደም ታስረው የነበሩ እስረኞችን መፍታቱን በመጥቀስ የመናገር ነጻነትን የማፈን ፍላጎት እንደሌለው አብራርተዋል። "የመናገር ነጻነት ፍፁም መብት አይደለም" በማለትም እነዚህ መገናኛ ብዙሃን በብሔሮች መካከል ግጭቶች ለመቀስቀስ መሞከራቸውን ተናግረዋል። "ያ ደግሞ እንዲሆን አንፈቅድም" በማለት "ለሰው ልጆች ሕይወት ቅድሚያ መስጠት አለብን" ብለዋል። በእነዚህ መገናኛ ብዙሃን ቅስቃሳ ህይወቶች መጥፋታቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ይህም የሚያያዘው መገናኛ ብዙሃንን ከመዝጋት ጋር ሳይሆን የአገሪቱ ሕግ ከመከበሩ ጋር ነው ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ዛዲግ አሁንም ከመንግሥት ሃሳብ በተቃራነው የቆሙ መገናኛ ብዙሃን አሉ ካሉ በኋላ እነርሱ ግን የአገሪቱን ሕግ አክብረው እየሰሩ በመሆናቸው አልተዘጉም በማለት ስርጭታቸው የተቋረጠው አንድ እና ሁለት ብቻ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል። ኢንተርኔትን ስመዘጋቱ የተጠየቁት አቶ ዛዲግ፣ ይህ ደግሞ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸውን ማፈን መሆኑን በማስመልከት ሲጠየቁ ኢንተርኔት ለጥላቻ ንግግር ማሰራጫ መሳሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢንተርኔት በብሔሮችና በሐይማኖቶች መካከል ግጭቶች እንዲቀሰቀስ መሳሪያ በመሆን ማገልገሉን የሚናገሩት የዲሞክራሲ ግንባታ ሚኒስትሩ፤ መምረጥ የነበረብን ከመረጃ ነጻ ፍሰትንና የሕዝባችን ህይወት መካከል ነበር ያሉት አቶ ዛዲግ ለሰው ልጅ ሕይወት ቅድሚያ ሰጥተናል ብለዋል። የሕዝቦች አብሮ የመኖር ባህልን አደጋ ላይ ጥሏል ያሉት በኢንተርኔት የሚሰራጭ የጥላቻ ንግግር "ሁሉንም ነገር ስንቆጣጣር ይመለሳል" ሲሉም አስታውቀዋል። በአገሪቱ ውስጥ በተከሰተው አለመረጋጋት ውስጥ የውጪ ኃይሎች መሳተፋቸውን በተመለከተ መንግሥት እርግጠኛ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዛዲግ ማን ነው የሚለው ላይ ግን አሁን ለመናገር ጊዜው ገና ነው በማለት ምርመራው እስኪጠናቀቅ መጠበቅ አለብን ብለዋል።
news-55802355
https://www.bbc.com/amharic/news-55802355
በትግራይ ክልል ዳግም የስልክ ግንኙነት ለምን ተቋረጠ?
በመቀሌ እና አዲሽሁ ከተማ መካከል የሚገኝ ፋይበር በመቆረጡ ምክንያት ከትናንት ተሲያት ጀምሮ በትግራይ ክልል የስልክ አገልግሎት መቋረጡን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጸዓሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ለቢቢሲ አረጋገጡ።
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የስልክ አገልግሎት የተቋረጠው ከትናንትና ማምሻ ጀምሮ መሆኑን ገልፀው ወደ ሥፍራው ባለሙያዎችን መላካቸውንና የጥገና ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል። የፋይበር መቋረጡ ያጋጠመው በመቀሌ እና አዲሽሁ ከተማ መካከል የሚገኝ መሆኑን ገለልፀው፣ በአሁኑ ሰዓት በመቀሌ እንዲሁም ሌሎች አቅራብያ አካባቢዎች ያሉ ቡድኖች ገብተው ጥገና እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል። "በአሁኑ ሰዓት ሶስት ቡድን በጥገናው ላይ ተሰማርቷል" ያሉት ኃላፊዋ በትግራይ ክልል በደረሰው ውድመት የተጎዱ የስልክ መስመሮች ላይ በሚካሄደው ጥገና "ፕሮቴክሽን እና ሪስቶሬሸን ሲስተም ላይ ያሉት በሙሉ ተጠግነው ባለማለቃቸው" አሁን ይህ ጉዳት ሲደርስ በፍጥነት ማገናኘት አለመቻሉን አስታውቀዋል። ፋይበሩ የተቆረጠው በተፈጥሮ ምክንያት አልያም ሆን ተብሎ በሰው መሆኑን ገና አለማወቃቸውን የገለፁት ኃላፊዋ በቦታው የሚገኘው የባለሙያዎች ቡድን ጥገና እያካሄደ መሆኑን ጨምረው አክለዋል። በመቀሌ ከተማ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ የስልክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን የድርጅቱ ኃላፊ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ዛሬ ረቡዕ በሰዓታት ውስጥ ጥገና ተደርጎ ይመለሳል ብለዋል። በትግራይ ክልል የሕወሓት ኃይሎች በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መክፈታቸው ከተገለፀ በኋላ መንግሥት "የሕግ የማስከበር" እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል። ከሁለት ወራት በፊት በክልሉ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ተቋርጠው የነበሩት የመብራት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች በከፊል የተመለሱባቸው አካባቢዎች ቢኖሩም፤ በበርካታ ከተሞች ውስጥ እስካሁን ስልክም ሆነ ኢንተርኔት አለመመለሳቸውን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በአንድ ወቅት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። አገልግሎቶቹን መልሶ በቶሎ ለማስጀመር ያልተቻለው በመሠረተ ልማቶቹ ላይ "የደረሰው ውድመት በጣም ከፍተኛ" የሚባል በመሆኑ እንደሆነ በወቅቱ አስረድተዋል። በመቀሌ የብሮድባንድና የድምፅ አገልግሎት መጀመሩን፣ ከጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ውቅሮ፣ እደጋ ሐሙስ፣ አዲግራትና ነጃሺ አካባቢ የድምፅ አገልግሎት በተወሰነ ደረጃ ማግኘት መጀመራቸው ድርጅቱ ገልጾ እንደነበር ይታወሳል። ነገር ግን በስልክ መስመሮች ላይ የደረሰውን ውድመት ምትክ መሣሪያዎችን አግኝቶና በየከተሞቹ በነፃነት ተንቀሳቅሶ ጥገናዎችን ማድረግ እንደተለመደው ቀላል አለመሆኑን በወቅቱ ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። በትግራይ ክልል የተፈጠረው የአገልግሎት መቋረጥ በድርጅቱ ችግር አለመሆኑን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት የገለፁት ኃላፊዋ፣ በክልሉ ውድመቱ በማን፣ መቼና እንዴት እንደ ደረሰ በጉዳዩ ላይ ምርመራ ያደረገው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቡድን በቅርቡ ውጤቱን ለሕዝብ ይፋ ያደርጓል ብለው ነበር። ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በትግራይ ክልል የደረሰው የቴሌኮም ውድመት ጥገና በአጭር ጊዜ እንደማይጠናቀቅ በድጋሚ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
sport-44920774
https://www.bbc.com/amharic/sport-44920774
በደቡብ አፍሪቃ የታክሲ ሾፌሮች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሕይወት አለፈ
ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የሚኒባስ ታክሲ አሽከርካሪዎችን ዒላማ ያደረገው ጥቃት ለ11 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል።
ከደቡብ አፍሪቃዋ ጉዋቴንግ ግዛት ወደ ጆሃንስበርግ እያሽከረከሩ የነበሩት ባለታክሲዎች ቅዳሜ ዕለት ማታ ነው ያልታሰበ አደጋ የደረሰባቸው። ከሞቱት 11 ግለሰቦች በተጨማሪ አራት ክፉኛ የቆሰሉቱ የሥራ አጋራቸውን ቀብረው እየተመለሱ የነበሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች ናቸው። ዊኒ ማንዴላ -አልበገር ባይ እናት ፖሊስ ግድያው በምን እንደተነሳ "እስካሁን ያጣራሁት ነገር የለም" ያለ ሲሆን መሰል ጥቃቶች ግን አዲስ እንዳልሆኑ አልሸሸገም። በተለምዶ 'ሚኒባስ' ታክሲ በመባል የሚታወቁት ተሽከርካሪዎች 55 ሚሊዮን ገደማ ለሚሆነው የደቡብ አፍሪቃ ሕዝብ ዋነኛ የትራንስፖርት አማራጭ ናቸው። «ከእወደድ ባይ ፖለቲከኞች ተጠንቀቁ» ባራክ ኦባማ የፖሊስ አፈ ቀላጤ የሆኑት ብርጋድዬር ጄይ ናይከር ሁኔታውን ሲያስረዱ «ጥቃቱ እንደደረሰ መኪናው ውስጥ ከነበሩት ግለሰቦች 11 ሕይወታቸው ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን አራት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው አሁን ሆስፒታል ይገኛሉ» ብለዋል። «አካባቢው መሰል የታክሲ አሽከርካሪዎችን ማዕከል ያደረግ ጥቃት ሲከስትበት የመጀመሪያው አይደለም፤ ቢሆንም ሁኔታውን አጣርተን ጥቃት አድራሾቹን ለመያዝ እየተረባረብን ነው» ሲሉም አክለዋል። ''የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር'' አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ የቅዳሜው ጥቃት የደረሰው ጆሃንስበርግ ውስጥ ተፈፀመ ከተባለው አሰቃቂ ግድያ ማግስት መሆኑ ነገሩን አሳሳቢ አድርጎታል። ኬፕ ታውን በተሰኘችው የደቡብ አፍሪቃ ከተማም ወርሃ ግንቦት ላይ በደረሰ ጥቃት 10 የሚኒባስ ታክሲ ሾፌሮች መገደላቸው ይታወሳል።
news-53312108
https://www.bbc.com/amharic/news-53312108
ሰዎች ቤት ተቀምጠው ሳለ ሲሰራ የከረመው ሮቦት
በሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲ ያሉ ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቤቱ ተቀምጦ ሳለ ሥራ ሲሰራ የነበረ ሮቦትን ለሕዝብ ይፋ አድርገዋል።
100 ሺህ ፓውንድ የሚያወጣው ይህ ሮቦት በተጫነለት ፕሮግራም የሚሰራ ነው ተብሎለታል። "በፕሮግራም የሚሰራ ስለሆነ ቤት ቁጭ ብዬ ሥራ ላዘው እችላለሁ" ይላሉ ከተመራማሪዎቹ አንዱ የሆኑት ቤንጃሚን በርገር። ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት ሮቦቱ የሰው ልጅ የሚሰራውን አንድ ሥራ በአንድ ሺህ እጥፍ ፍጥነት ማገባደድ ይችላል። ሮያል ሶሳይቲ ኦፎ ኬሚስትሪ የተሰኘው ተቋም ያወጣው አንድ ዘገባ እንደሚጠቁመው ሮቦት ተጠቅሞ ድህረ-ኮሮናቫይረስ ጥናት ለማካሄድ እየተሞከረ ነው። ጥናቱ ሰው ሰራሽ ልህቀትና [አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ] የላቁ ኮምፒውተሮችን በመጠቀም ሳይንቲስቶች ቤታቸው ሆነው ሥራቸውን እንዲተገብሩ ከማስቻሉም በላይ ሌሎች ዓለም አቀፍ ችግሮችንም ሊፈታ ይችላል እየተባለ ነው። የሮቦት ሳይንቲስቶች በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ ላይ ናቸው። ከእነዚህም አንዱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መግታት ነው። ፕሮፌሰር አንዲ ኩፐር ሮቦቶችን ወደ ቤተ ሙከራቸው አስገብተው የተለያዩ ምርምሮች እያደረጉ ነው። "ኮቪድ-19፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ትብብር የሚሹ የተለያዩ ችግሮች አሉ። የእኛ ዓላማ በማዕከላዊ አእምሮ የተገናኙ ሮቦቶች በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች አሰራጭቶ ምርምር ማድረግ ነው። እርግጥ ነው እስካሁን ያንን አላደረግንም፤ ነገር ግን ማድረጋችን አይቀርም።" ሳይንቲስቶቹ ከቤተ-ሙከራቸው ራቅ ብለው ምርመራ ለማድረግ በተገደዱበት በዚህ ወቅት ሮቦቶች ምርጥ መላ ሆነዋል። "ሮቦት አይደክመው፣ አይሰለቸው። ከንጋት እስከ ንጋት ይሰራል፤ በዚያ ላይ ለበዓል እረፍት ልውጣ አይል" ሲሉ ዶ/ር በርገር ቀልድ ቢጤ ጣል አድርገዋል። ቀልዱን ለጊዜው ረስተነው ይላሉ ሳይኒስቱ ሮቦቱ ለሰው ልጅ በርካታ ጊዜ የሚወስድበትን ሥራ በፍጥነት እያጠናቀቀ ነው። "ይህ ደግሞ እኔ ወደ ፈጠራ ሥራዬ ትኩረቴን እንዳደርግ ረድቶኛል" ይላሉ። ሕዋ ላይ ምርምር እንዲያደርጉ እንደተፈጠሩ ሮቦቶች ሁሉ ይህኛው ሮቦት ፈተናን ተቋቁሞ ሥራውን እንዲከውን እየሠለጠነ ነው። የሮያል ሶሳይቲ ኦፍ ኬሚስትሪ ኃላፊ የሆኑት ዳዬርድሬ ብላክ የዩናይትድ ኪንግደም የሳይንስ ዘርፍ ሮቦቶች ላይ መዋዕለ ነዋይ ሊያፈስ ይገባል ብለው ያምናሉ። ነገር ግን አንድ አንገብጋቢ ጥያቄ አሁንም ምላሽ አላገኘም። እንዲህ ከሆነ ሮቦቶች የሰውን ልጅ ሥራ እየወሰደ ነው ማለት? ዶክተር ብላክ "ኧረ በጭራሽ" ይላሉ። "ሳይንስ ምንም ጊዜ ቢሆን የሰው ልጅን እርዳታ ይሻል" በማለት የሚያሰጋ ነገር እንደሌለ ያሰምሩበታል። ሮቦት ገበሬዎች የሰዎችን ስራ ሊነጥቁ ነው።
news-54875295
https://www.bbc.com/amharic/news-54875295
ትግራይ፡ ለአንድ ሳምንት በዘለቀው ጦርነት የደረሰው ጉዳት በጨረፍታ
በትግራይ ክልል ከተቀሰቀሰ ከአንድ ሳምንት በላይ በሆነው ጦርነት ተሳታፊ የሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች መሞታቸውን እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመለከቱ።
በሰሜን ዕዝ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት ተከትሎ ለወራት በውዝግብ ውስጥ የቆዩት የፌደራል እና የትግራይ ክልል መንግሥት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወደ ግልጽ ጦርነት ውስጥ በመግባታቸው በርካታ ተዋጊዎች መሞታቸውን ከአካባቢው በተለያዩ ምንጮች አማካኝነት የሚወጡ መረጃዎች እያመለከቱ ነው። በተለይ ባለፉት ቀናት በምዕራብ ትግራይ በተካሄደው ውጊያ 550 ያህል ታጥቂዎች መገደላቸውንና 29 የልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል በላይ ስዩም መናገራቸውን ፋና ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪ ሮይተርስ ያናገራቸው አንድ የፌደራል መንግሥቱ ወታደራዊ ባለስልጣን እንዳሉት ከቀናት በፊት ቅራቅር ውስጥ በነበረ ውጊያ ከትግራይ በኩል ወደ 500 የሚጠጉ ተዋጊዎች መገደላቸውን አመልክተዋል። እንዲሁም ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚሰሩ በአማራ ክልል የሚገኙ ሦስት የደኅንነት ምንጮች የፌደራሉ ሠራዊት በመጀመሪያ ዳንሻ ላይ በነበረው ውጊያ በመቶዎች የሚቆጠሩትን እንዳጣ እንደነገሩት ሮይተርስ ዘግቧል። በጦርነቱ ከሞቱት በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተዋጊዎች መቁሰላቸውንና ይህም አሃዝ እየጨመረ መሆኑን ኤኤፍፒ ዜና ወኪል ያመለከተ ሲሆን፤ ከህክምና ተቋማትና ከእርዳታ ሠራተኞች አገኘሁት ባለው መረጃም ከ200 በላይ ወታደሮች መቁሰላቸውንና 8 እንደሞቱ ሰኞ ዕለት ዘግቧል። ጦርነት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው በጦርነቶቹ የደረሰ የጉዳት መጠንን በትክክል ለማወቅ አዳጋች ነው ተብሏል። ነገር ግን ሮይተርስ ያናገራቸው አንድ ዲፕሎማት በሰጡት በሰጡት ግምት በተካሄዱት ውጊያዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች መሞታቸው እንደሚታመን አመልክተዋል። ጦርነቱ በተዋጊዎች ላይ አስከተለ ከተባለው ጉዳት ባሻገር በሽሽትና በመፈናቀል ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን የገቡ ሰዎች እንዳሉ የዜና ምንጮች እየዘገቡ ነው። በዚህም መሰረት ኤኤፍፒ የዜና ወኪል "በሺህዎች የሚቆጠሩ ግጭቱን የሚሸሹ ወደ ሱዳን መሻገራቸውን" የሱዳን ስደተኞች ድርጅት ኃላፊ የሆኑትን አልሲር ኻሊድን ጠቅሶ ዘግቧል። ሮይተርስ በበኩሉ የሱዳን መንግሥት መገናኛ ብዙሃንንና ነዋሪዎችን ጠቅሶ እንዳለው ወታደሮችን ጨምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ እየተባባሰ ያለውን ግጭት በመሸሽ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ገብተዋል ብሏል። ባለፈው ሳምንት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ከባድ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ብለው የሰጉ አህጉራዊና ዓለማቀፋዊ ተቋማት ሰላም እንዲወርድ ተደጋጋሚ ጥሪ አድርገዋል። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት "የተለያዩ ወገኖች ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋታቸው የማይሆንና የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የሚመነጭ ነው" ብለዋል። ጨምረውም በአገሪቱ ሠራዊት እየተከናወነ ያለው ዘመቻ ሕግ የማስከበር ሥራ መሆኑን አመልክተው "ሰላምንና መረጋጋትን በማስፈን ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ያለመ ነው" በማለት፤ ይህም ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ አመልክተዋል። አሁን ወደ ጦርነት የተሸጋገረው በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መስተዳደር በኩል የነበረው ቅራኔ እየተባባሰ የመጣው ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደማይካሄድ ከታወቀ በኋላ በትግራይ የተናጠል ምርጫ በመደረጉ ሳቢያ ነው። ይህንንም ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምርጫውን ሕገወጥና ተፈጻሚነት የሌለው እንደሆነ መወሰኑን ተከትሎ ማዕከላዊው መንግሥት ከክልሉ መስተዳደር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያካሂድና የበጀት ድጋፍ እንዳይሰጥ ከወሰነ በኋላ ነገሮች እየተካረሩ መሄዳቸው ይታወሳል። ይህ ጦርነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው እስካሁን የደረሰው የጉዳት መጠን በይፋ ያልተነገረለት ጥቃት በትግራይ ልዩ ኃይል በሰሜን ዕዝ ላይ መፈጸሙን ከገለጹ በኋላ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ነው። ይህንንም ተከትሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገ ሲሆን የተወካዮች ምክር ቤትም ውሳኔውን ተቀብሎ ማጽደቁ ይታወሳል። በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የተከሰተውን ሁኔታ ተከትሎ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ውስጥ ጣልቃ እንዲገባና ክልሉን የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ወስኗል።
news-55464178
https://www.bbc.com/amharic/news-55464178
ሮይተርስ የካሜራ ባለሙያው አዲስ አበባ ውስጥ መታሰሩን ተቃወመ
የሮይተርስ ዜና ወኪል የካሜራ ባለሙያ፣ ኩመራ ገመቹ፣ አዲስ አበባ ከሚገኘው የመኖሪያ ቤቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሉን ባለቤቱ ሃዊ ደሳለኝ ለቢቢሲ ገለፀች።
ባለቤቱ ለቢቢሲ እንዳለችው ኩመራ በቁጥጥር ሥር የዋለው ባለፈው ሐሙስ፣ ታኅሣስ 15/2013 ዓ.ም ሲሆን በምን ምክንያት በፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ ምታውቀው ነገር እንደሌለ ገልጻለች። ኩመራ የሚሰራበት ዓለም አቀፉ የዜና ወኪል ሮይርስም የእስሩን ምክንኣት ለማወቅ ለፖሊስ ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል። ሮይተርስ ቤተሰቦቹን ጠቅሶ እንደዘገበው እስካሁን ድረስ ኩመራ ላይ ክስ አልተመሰረተበትም። ቢቢሲ ጠቅላይ አቃቤ ሕግን ስለ ኩመራ መታሰር መረጃ ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም ጉዳዩን እያጣሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኩመራ ገመቹ ለሮይተርስ የዜና ወኪል በካሜራ ባለሙያነት ለረዥም ዓመታት እያገለገለ ይገኛል። ኩመራ አርብ ታህሣስ 16/2013 ዓ.ም ያለ ጠበቃ ፍርድ ቤት መቅረቡ የተገለፀ ሲሆን ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀን በመጠየቁ ችሎቱ እንደፈቀደለት ባለቤቱ ለቢቢሲ አረጋግጣለች። ሰኞ ታህሣስ 19/2013 ዓ.ም ሮይተርስ ባወጣው መግለጫ የኩመራን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋል አውግዟል። የካሜራ ባለሙያው በቁጥጥር ሥር የዋለውም ታህሣስ 7/2013 ዓ.ም የድርጅቱን የፎቶግራፍ ባለሙያ ሁለት ፖሊሶች ከደበደቡ በኋላ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል። "ኩመራ በኢትዮጵያ ፍትሃዊ፣ ገለልተኛ እና ነጻ የሆነ ዘገባ የሚሰራው የሮይተርስ ዜና ወኪል ቡድን አባል ነው። የኩመራ ሥራ ገለልተኛ መሆኑን እና ሙያውን የጠበቀ መሆኑን ማሳያ ነው። እንዲሁም ለመታሰሩ ምንም መሰረት እንደሌለ ተረድተናል" ሲል የሮይተርስ ዜና ወኪል ከፍተኛ አርታኢ ስቴፈን ጄ አድለር በመግለጫው ላይ አመልክቷል። "ጋዜጠኞች ያለ አንዳች ፍርሃት ወይንም ጉዳት በየትኛውም ሥፍራ ሆነው መዘገብ አለባቸው፤ ኩመራ ነጻ እስኪሆን ድረስ አናርፍም" ብለዋል አድለር በመግለጫቸው ላይ። ሐሙስ ዕለት ማታ በቁጥር አስር የሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት አዲስ አበባ በሚገኘው የኩመራ ቤት በመገኘት በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉት ባለቤቱ ለቢቢሲ ተናግራለች። የሦስት ልጆች አባት የሆነው ኩመራ በቁጥጥር ሥር ሲውል በልጆቹ ፊት መሆኑን የምትናገረው ባለቤቱ፣ ፖሊሶች እጁን ወደ ኋላ በካቴና አስረው ወስደውታል ስትል ለቢቢሲ የነበረውን ሁኔታ አስረድታለች። ከዚያ ዕለት ጀምሮ ልጆቹ ፍርሃት ውስጥ መሆናቸውንና መተኛት እንደተቸገሩም አክላ ገልጻለች። እንደ ቤተሰቡ ገለፃ ከሆነ ፖሊስ የኩመራን ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ፍላሽ ድራይቭ እንዲሁም ወረቀቶችን ወስዷል። ቢቢሲ ኩመራ በአሁኑ ሰዓት ታስሮ የሚገኘው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ እስር ቤት ውስጥ በአንድ ቀዝቃዛ ክፍል ብቻውን መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዲቀላቀል ቢጠይቅም መከልከሉን ለማወቅ ችሏል። መንግሥት በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ፣ በውጭ አገር መገናኛ ብዙሃን ላይ የተለያዩ ጫናዎችን ሲያሳድር እንደነበር የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል። ሮይተርስ ኩመራ የትግራይ ግጭትን መዘገቡን ገልጾ፣ ለኢትዮጵያ የመንግሥት ባለሥልጣናት የታሰረው በዚህ ምክንያት መሆን አለመሆኑን ቢጠይቅም ምላሽ አለማግኘቱን ተናግሯል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ሮይተርስንና ሌሎች የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን በኅዳር 14/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ላይ "ሐሰተኛ" እና "ሚዛናዊ የሆነ ዘገባ ባለማቅረብ" ከስሶ ነበር። ሮይተርስ በወቅቱ በትግራይ እና በፌደራል መንግሥቱ ግጭት ላይ በሰራው ዘገባ ላይ የቀረበውን ክስ ተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል። መቀመጫውን ኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ በበኩሉ የኩመራ እስር በአገሪቱ እየታየ ያለው የፕሬስ ነጻነት ጥሰት ማሳያ መሆኑን ገልጿል። ሲፒጄ ኅዳር 22/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ሰባት ጋዜጠኞች በሰሯቸው ዘገባዎች ምክንያት እስር ቤት መግባታቸውን ገልጾ ነበር። ከእነዚህ መካከል አምስቱ የታሰሩት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በፌደራል መንግሥቱና በህወሓት ኃይሎች መካከል ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው።
news-41806711
https://www.bbc.com/amharic/news-41806711
የቀይ ሽብር ተከሳሹ ሄግ ፍርድ ቤት ቀረበ
የቀድሞው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መሪ ረዳት ነበር የተባለው ግለሰብ የጦር ወንጀል የፍርድ ሂደት በኔዘርላንድስ ሄግ መታየት ጀመረ።
የ63 ዓመት ዕድሜ ያለው አቶ እሸቱ አለሙ የተባለው ግለሰብ ወታደራዊው መንግሥት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ተቀናቃኞቹን ለመምታት ባካሄደው 'የቀይ ሽብር' ዘመቻ ወቅት 75 ሰዎች እነዲገደሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል ተብሎ ነው የተከሰሰው። የቀድሞው ኮሚኒስት መሪ መንግሥቱ ኃይለማሪያም ረዳት ነበር የተባለው ይህ ግለሰብ በሰዎች ላይ ሰቆቃን በመፈፀምና በከፋ አያያዝ ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ ጭምር ተከሷል። ነገር ግን የቀረቡበትን ክሶች በሙሉ እንዳልፈፀመ ተናግሯል። በቀረቡበት አራት የጦር ወንጀሎች ከ300 የሚበልጡ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ስም ዝርዝርም ቀርቧል። ኢትዮጵያ ውስጥም በሌለበት በቀረበበት ክስ ሞት ተፈርዶበታል። አቃቤ ሕግ እንደሚለው ኢትዮጵያዊና የደች ጥምር ዜግነት ያለው አቶ አለሙ ጎጃም ክፍለ ሃገር ውስጥ የመንግሥቱ ኃይለማሪያም ቀንደኛ ደጋፊ በመሆን አገልግሏል። በኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደቱ ሲከፈት አቶ እሸቱ አለሙ ''አቃቤ ሕግ የተሳሳተ ሰው ላይ ነው ክስ የመሰረተው'' ሲል ተናግሯል። ''አቃቤ ሕግ አደረግከው ብሎ ያቀረበውን ክስ ስሰማ በጣም ነበር የደነገጥኩት፤ የቀረቡብኝን ክሶች በሙሉ አልፈፀምኩም'' በማለት ነበር ጉዳዩን ለሚመለከቱት አራት ዳኞ የተናገረው። አቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ እንዳለው አቶ አለሙ ''በአንድ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ 75 የሚሆኑ እስረኞች እንዲገደሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል።'' የሟቾቹም አስከሬን በአንድ የጅምላ መቃብር ውስጥ እንዲቀበር አድርጓል ይላል ። በተጨማሪም አቶ አለሙ ''ሰላማዊ ሰዎችን እና ትጥቅ የፈቱ ተዋጊዎችን ያለፍርድ እንዲታሰሩና በጭካኔ አያያዝ ስር እንዲቆዩ አድርጓል'' የሚል ክስ ቀርቦበታል። በክሱ እስረኞች እጅና እግራቸው ታስሮ እንዲንጠለጠሉ በማድረግ የውስጥ እግራቸው በዱላ እንዲገረፉ አድረጓልም ተብሏል። በዚህ የፍርድ ሂደትም የሰቆቃው ሰለባዎች ናቸው የተባሉ ሰዎች በምስክርነት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
news-49108157
https://www.bbc.com/amharic/news-49108157
ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ለሳዑዲ የጦር መሳሪያ ሊሸጡ ነው
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ለሳዑዲ አረቢያ እና ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 8.1 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ ሽያጭን አጸደቁ።
ማርች 2018 ላይ ትራምፕ ለሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን አሜሪካ ለሳዑዲ አረቢያ ለሽያጭ ያቀረበቻቸውን የጦር መሳሪያ አይነቶች በሰንጠረዥ ሲያሳዩ ሴኔቱ እና የተወካዮች ምክር ቤት የጦር መሣሪያዎቹ እንዳይሸጡ እገዳ ጥሎ ነበር። ፕሬዝደንት ትራምፕ የሴኔቱ እና የምክር ቤቱ ውሳኔ "አሜሪካ በዓለም ላይ ያላትን ተፎካካሪነት ይቀንሳል፤ ከወዳጅ አገራት ጋር ያላትን ግነኙነትም ያሻክራል" ብለዋል። አንዳንድ የኮንግረስ አባላት የጦር መሣሪያዎቹ በየመን ንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ያስከትላሉ ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አባላቱ ሳዑዲ አረቢያ በየመን በሚደረገው ጦርነት ባላት ተሳትፎና በጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ግድያ አጥብቀው ኮንነዋል። • ስለ ጀማል ኻሾግጂ አሟሟት እስካሁን የምናውቃቸው እውነታዎች • ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ? የሪፐብሊካኑ መሪ ሚች ማኮኔል ትናንት አመሻሽ ላይ ሴኔቱ፤ ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ውድቅ ያደረጉትን ውሳኔ መልሶ ለመሻር በቀጣይ ቀናት ድምጽ ሊሰጥ ይችላል ብለዋል። ሚች ማኮኔል ይህን ይበሉ እንጂ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፤ ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ውድቅ ያደረጉትን ውሳኔ መልሶ ለመሻር በሴኔቱ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ መኖር አለበት። ተንታኞች የትራምፕን ውሳኔ ውድቅ ለማድረግ ይህን አብላጫ ድምጽ በሴኔቱ ማግኘት የማይታሰብ ነው እያሉ ነው። ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ሲጠቀሙ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።
news-51368389
https://www.bbc.com/amharic/news-51368389
በሽታውን ለመደበቅ ባለስልጣናት ዶክተሮችን ያስፈራሩ ነበር
በጥር ወር መጀመሪያ ላይ የኮሮናቫይረስ በዋናነት የተቀሰቀሰባት የዉሃን ከተማ ባለስልጣናት ስለበሽታው መከሰት የሚያመለክቱ መረጃዎችን ለመሸፋፈን ጥረት ሲያደርጉ ነበር።
ዶክተር ሊ ዌንሊያንግ የበሽታውን መከሰት በተመለከተ ለሰዎች በመንገር እንዲጠነቀቁ ሲመክር የነበረ አንድ ዶክትርን ፖሊሶች ቤቱ ድረስ መጥተው ከድርጊቱ እንዲቆጠብ አስጠንቅቀውት ነበር። ነገር ግን ከአንድ ወር በኋላ በሽታው በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ዓለምን ማስጨነቅ ሲጀምርና ሐኪሙ ምን ተብሎ እንደነበረ ሃኪም ቤት ተኝቶ ታሪኩን ይፋ ሲያደርግ ጀግና ተብሎ እየተወደሰ ነው። • ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች • የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች ኮሮና ቫይረስን 'ሊያመርቱ' ነው "ጤና ይስጥልኝ፤ ሊ ዌንሊያንግ እባላለሁ፣ በዉሃን ማዕከላዊ ሆስፒታል የዓይን ሃኪም ነኝ" በማላት ይጀምራል የዶክተሩ መልዕክት። ዶክተሩ ይፋ ያደረገው መልዕክት የኮሮናቫይረስ በተከሰተባቸው የመጀመሪያ ሳምንታት ዉሃን ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት በሽታውን ለመሸፋፈን ያደረጉትን ጥረት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው ተብሏል። ታህሳስ ወር ላይ ወረርሽኙ በተከሰተበት ማዕከል ውስጥ ይሰራ የነበረው ዶክተር ሊ በአንድ እንግዳ ቫይረስ ተጠቅተው የመጡ ሰባት ሰዎችን አግኝቶ ነበር፤ እሱም በሽታው ከ15 ዓመታት በፊት ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ሆኖ የነበረው 'ሳርስ' ነው ብሎ ገምቶ ነር። እነዚህ የበሽታው ክስተቶች ሁናን ተብሎ ከሚጠራው የባሕር ውስጥ ምግቦች መሸጫ ገበያ የተከሰተ እንደሆነ ስለታሰበ ህሙማኑ ከሌሎች ተለይተው በሆስፒታሉ ክትትልና ህክምና እንዲያገኙ ውስጥ ተደረገ። • ኮሮናቫይረስ በመላዋ ቻይና መዛመቱ ተነገረ፤ የሟቾችም ቁጥር እየጨመረ ነው • ቻይና አሜሪካን ኮሮናቫይረስን አስመልክቶ ፍራቻ እየነዛች ነው ስትል ወነጀለች እንደ አውሮፓዊያኑ ታህሳስ 30 ላይ ዶክተሩ በአንድ የቡድን መልዕክት መለዋወጫ መድረክ ላይ ለሙያ አጋሮቹ ዶክተሮች ስለወረርሽኙ መከሰትና እራሳቸውን ለመጠበቅ የመከላከያ አልባሳትን እንዲጠቀሙ የሚመክር መልዕክት አስተላልፎ ነበር። በዚያ ወቅት ዶክትር ሊ ያላወቀው ነገር ቢኖር የወረርሽኙ ምክንያት የሆነው ተህዋስ በኋላ ላይ እንደተደረሰበት ፍጹም አዲስ አይነት የኮሮናቫይረስ እንደሆነ ነበር። ከአራት ቀናት በኋላ ከሕዝብ ደህንንት ቢሮ ባለስልጣናት መጥተው አንድ ደብዳቤ ላይ እንዲፈርም ነገሩት። ወረቀቱም ዶክተሩን "ሐሰተኛ አስተያየቶችን በመስጠት" ይህም "በከፍተኛ ሁኔታ ማኅበራዊ ሥርዓትን የሚያናጋ" መሆኑን በመግለጽ ጥፋተኛ አድርጎ የሚከስ ነበር። ለዶክተሩ የተጻፈው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ "በጥብቅ የምናሳስብህ ነገር ቢኖር፡ በዚህ ድርጊትህ በግትርነት የምትገፋ ከሆነና ሕግን ባለማክበር በሕገወጥ ተግባርህ የምትቀጥል ከሆነ ለፍርድ ትቀርባለህ። ገብቶሃል?" ይላል የቀረበለት ወረቀት። ከስርም ዶክተር ሊ በእጅ ጽሑፉ "አዎ፤ ተረድቻለሁ" የሚል ጽሑፍ ሰፍሯል። "ሐሰተኛ አሉቧልታዎችን በማሰራጨት" በሚል ተጠርጥረው ምርመራ ከተደረገባቸው ስምንት ሰዎች ዶክተሩ አንዱ ነው። በጥር ወር ማብቂያ ላይም ዶክተር ሊ ከባለስልጣናት የተሰጠውን የዚህን ደብዳቤ ቅጂ 'ዌቦ' በተባለው የቻይናዊያን ማህበራዊ የትስስር መድረክ ላይ በማውጣት ምን አጋጥሞት እንደነበረ ይፋ አደረገ። ይህንን ተከትሎም የአካባቢው ባለስልጣናት የበሽታው ወረርሽኝ ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ በኋላ ዶክተሩን ይቅርታ ቢጠይቁትም፤ ይቀርታው የዘገየ ነበር። በጥር ወር መጀመሪያ ሳምንታት ላይ ዉሃን ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት በቫይረሱ የሚያዙት ሰዎች በሽታው ካለባቸው እንስሳት ጋር የቀረበ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ብቻ እንደሆኑ በመግለጻቸው፤ ሐኪሞችን ለመከላከል ምንም መመሪያ አልተሰጠም ነበር። • ቻይና ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን በስምንት ቀናት ሆስፒታል ገነባች • ቻይና በ 6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ ነው ፖሊሶች ዶክትር ሊን ካናገሩት ከሳምንት በኋላ አንዲት የግላኮማ ችግር ያለባትን ሴት እያከመ ነበር። ታካሚዋም አዲሱ የኮሮናቫይረስ እንዳለባት አላወቀም። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈረው ጽሑፉ ዶክትር ሊ በጥር ወር ሁለተኛ ሳምንት ላይ ሳል እንደጀመረው፣ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ትኩሳት እንዳጋጠመውና ከሁለት ቀናት በኋላም ብሶበት ሆስፒታል እንደገባ ገልጿል። ቤተሰቦቹም መታመማቸውንና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንም አመልክቷል። ዶክትር ሊ ላይ የመጀመሪያው የበሽታው ምልክት ከታየ ከ10 ቀናት በኋላ ቻይና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን አወጀች። ዶክትር ሊ እንዳለው የኮሮናቫይረስ ምርመራ በተደጋጋሚ ቢደረግለትም የተገኘው ውጤት ግን ነጻ እንደሆነ ነበር። ነገር ግን በጥር ወር መጨረሻ ላይ የተደረገለት ምርመራ በበሽታው መያዙን አመለከተ። ይህንንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይፋ በማድረጉ አድናቆትና ድጋፍን ከበርካታ ሰዎች አግኝቷል። "ዶክተር ሊ ጀግና ነው" ያለው አንድ ግለሰብ አገሩ ስላለችበት አሳሳቢ ሁኔታ ጠቅሶ "በዚህ ሁኔታ ወደፊት የወረርሽኝ ምልክቶችን ያዩ ሐኪሞች ቀድመው ለማሳወቅ ፍርሃት ሊያድርባቸው እንደሚችል" አስተያየቱን ሰጥቷል። አክሎም "ለሕዝብ ጤና ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን ለመፍጠርም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሊ አይነት ሐኪሞች ያስፈልጋሉ" ሲል የዶክተሩን ድርጊት አወድሷል።
news-56249155
https://www.bbc.com/amharic/news-56249155
ጆን ኤፍ ኬኔዲ፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከአፍሪካ የነፃነት አባቶች ጋር እንዴት ተገናኙ?
ከአፍሪካ ጋዜጠኞች በተከታታይ ከተጻፉት ደብዳቤዎች አንዱ በሆነው የሴራ ሊዮን-ጋምቢያዊው ጸሐፊ አዴ ዳራሚ አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ስላላት ግንኙነት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን የሚያሳዩ ፎቶዎችን ሰንዶ አዘጋጅቷል።
ኬኔዲ በጎርጎሮሳዊያኑ 1961 ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት አገራቸው አሜሪካ በአፍሪካ እየተካሄደ የነበረውን ፈጣን ለውጦች ለመረዳት ብዙም ሙከራ አላደረገችም ነበር። 1963 ላይ በተገደሉ ወቅት ግን ይህ ምስል በከፍተኛ ደረጃ ተለውጧል። ኬኔዲ በሥልጣን በቆዩበት አጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸው ከሁለት ደርዘን በላይ ነፃ የአፍሪካ ሀገር መሪዎችን ወይም አምባሳደሮቻቸውን በኋይት ሃውስ ተቀብለው አነጋግረዋል። ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው ከአንድ ዓመት በፊት 17 የአፍሪካ አገራት ከቅኝ ገዥዎቻቸው ነፃነታቸውን አግኝተዋል። ይህን ተከትሎም ዓለም እየተለወጠ መሆኑን የተገነዘቡት ኬኔዲ አዲስ ግንኙነት መመስረት እንደሚያስፈልግ አውቀዋል። ግንኙነቱ የተመሠረተውም አዲሶቹን የአፍሪካ አገራት በመደገፍ ነበር። ፕሬዝዳንት ኬኔዲ ከጋናው ፕሬዝዳንት ኩዋሜ ንክሩማህ ጋር እአአ መጋቢት 1961 በዋይት ሐውስ በተገናኙበት ወቅት በ 1960 በተካሄደው የምርጫ ዘመቻ ኬኔዲ የአይዘንሃወርን አስተዳደር "የአፍሪካን ህዝብ ፍላጎት እና ምኞት ቸል ብሏል" በማለት ደጋግመው በመተቸት አሜሪካ ከቅኝ ገዥዎች ጎን ሳይሆን ከፀረ-ቅኝ አገዛዝ እና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ጎን መሆን እንዳለባት ሲናገሩ ነበር። ኬኔዲ ስልጣን ከያዙ በኋላ ቀዩን ምንጣፍ ዘርግተው የአፍሪካ መሪዎችን ለጉብኝት ጋብዘዋል። በቀዳማዊት እመቤት ጃኪ ኬኔዲ ታጅበው የኢትዮጵያውን ንጉሠ ነገሥት ኃይለ ሥላሴን እና የሞሮኮውን ንጉሥ ሐሰን አራተኛን ጭምሮ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች አሜሪካ ሲገቡ አቀባበል አድርገዋል። እንዲሁም የክብር ዘበኞች፣ የተትረፈረፈ እራት እና የባሌ ዳንስ፣ ቲያትር እና ታሪካዊ ጉብኝት ተካተዋል። ሁሉም ጉብኝቶቹ በመገናኛ ብዙሃን ጎልተው የታዩ ሲሆን ህዝቡም በደስታ እንዲወጣ ተበረታቷል። ኬኔዲ እና እንግዶቻቸው በእንኳን ደህና መጣህ ጽሑፎች እና በደስታ በተሞላ ህዝብ በተጌጡ ጎዳናዎች እንዲሁም የአየር ሁኔታው ከፈቀደም ክፍት በሆነ መኪና ይጓዛሉ። በእርግጥ በዚህ ሁሉ ውስጥ የፖለቲካ ፍላጎት ነበር። ሶቪዬት ህብረት ከቀድሞ የቅኝ ገዥዎች ራሳቸውን ለማራቅ ከሚፈልጉ የአፍሪካ መንግስታት ጋር ተመሳሳይ ሽርሽር እያደረገች ነበር። ኬኔዲ ስልጣኑን እንደተረከቡ ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር ወዳጅነት ለመመሥረት በፍጥነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ያውቁ ነበር። "አምናለሁ ... የራሳችንን አብዮት የምንመጥን ከሆንን በቀጣዮቹ አስርት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካ አብዮት አካሄድ ወደ ዴሞክራሲ እና ነፃነት ይሆናል። ወደ ኮሚኒዝም በጣም የከፋ የቅኝ ግዛት ዓይነት ወደ ሆነው ኮሙኒዝም አይሆንም" ሲሉም ተናግረዋል። ከበዓለ ሲመታቸው ከአንድ ወር በኋላም የፈረንሳይኛ ተናጋሪ ሃገሮችን ከጎናቸው ለማሰለፍ እንደ ቁልፍ አጋር ያዩቸውን ፕሬዝዳንት ሊዮፖል ሴዳር ሴንጎርን እንዲያገኙ ምክትል ፕሬዝዳንቱን ሊንደን ጆንሰንን ወደ ሴኔጋል ልከዋል። ከአንድ ወር በኋላ ኬኔዲ ወጣት አሜሪካውያንን በዓለም ዙሪያ የላከውን የሰላም ጓድ አስጀመሩ። በጎርጎሮሳዊያኑ ነሐሴ 1961 ወደ ጋና እና ታንጋኒካ ለመሄድ የተዘጋጀውን የመጀመሪያውን በጎ ፈቃደኞች ቡድን ወደ ኋይት ሃውስ ጋብዘው ነበር። ኬኔዲ ስልጣን ከመያዛቸው ከሦስት ቀናት በፊት የኮንጎ የነፃነት ጀግና ፓትሪስ ሉሙምባ የሲአይኤ እጅ አለበት ተብሎ በሚጠረጠርበት ሂደት መገደሉ ከሶቪዬት ህብረት ጋር ቀዝቃዛውን ጦርነት በአህጉሪቱ እየተጫወቱ እንደነበር ያመላክታል። ኬኔዲ ለአህጉሪቱ ልማትና ዕድገት ከልብ የመነጨ ፍላጎት ነበረው ብዬ እከራከራለሁ። ተተኪያቸው የነበሩት ጆንሰን ግንኙነቶችን ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ባለመጋራታቸው ያለጊዜ መሞታቸው ወላፈኑ አፍሪካ ውስጥ እንዲሰማ ምክንያት ሆኗል። ከ 60 ዓመታት በኋላም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለአፍሪካ ያላቸውን ፖሊሲ መቅረፅ ጀምረዋል።
news-50157444
https://www.bbc.com/amharic/news-50157444
"የተፈጸመው መሆን ያልነበረበት ትልቅ ስህተት ነው"
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአክቲቪሲት ጀዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ትናንት ዕኩለ ለሊት ላይ የተፈጸመው ክስተት "መሆን ያልነበረበት ትልቅ ስህተት ነው" አሉ።
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ለክልሉ ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከውጪ ወደ ሃገር ውስጥ ለገቡ ሰዎች የደህንነት ጥበቃ ሲደረግላቸው እንደነበረ ገልጸው "የክልሉ መንግሥትም ሆነ የፌደራል መንግሥት ደህንነቱን እንደሚያስጠብቁ በዚሁ አጋጣሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ" ብለዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው ቀን ለመገናኛ ብዙኀን ጃዋር መሀመድ ለተከታዮቻቸውና ለደጋፊዎቻቸው ልታሰር ነው፣ ጥቃት ሊደርስብኝ ነው በማለት ያስተላለፉት መልዕክት ስህተት ነው ብለው ነበር። በተጨማሪም ኮሚሽነሩ ጀዋር "በፖሊስ ተወሰደብኝ ያሉት እርምጃ ስህተት ነው። ... በመንግሥትም በፖሊስም በኩል ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደባቸውም" ሲሉ ተናግረው ነበር። • "ክስተቱ 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ ነው የምረዳው" ጀዋር መሐመድ • "በመንግሥትም በፖሊስም በኩል ምንም ዓይነት እርምጃ አልተወሰደም" ፌደራል ፖሊስ • በኦሮሚያ ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች 6 ሰዎች ተገደሉ ምክትል ፕሬዝደንቱ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ስህተት ሲሉ የገለጹት ክስተት በማን እንደፈጸመ እና ለምን እኩለ ለሊት ላይ ማድረግ እንደታሰበ የምናጣረው ጉዳይ ይሆናል ብለዋል። ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ለማሰማት አደባባይ ወጥተው ህይታቸው ያለፉ ሰዎችን በተመለከተም በክልላቸው ስም የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። ዛሬ በተደረገው ሰልፍ ላይ ኦሮሚያን የግጭት አውድማ ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ሰልፉ ላይ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋልም ብለዋል፡፡እነዚህ ኃይሎች ጉዳዩ የሃይማኖትና የብሔር መልክ እንዲይዝ ጥረት እያደረጉ ነው ሲሉም አክለዋል።
news-56336640
https://www.bbc.com/amharic/news-56336640
ራሷን፣ እህቶቿንና የአካባቢዋን ልጆች ከግርዛት ያተረፈችው ተማሪ
የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሆና ፖሊሶች የማኅበረሰብ ትምህርት ለመስጠት መምጣታቸውን ታስታውሳለች። ፖሊሶቹ በሰንደቅ ዓላማ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው "ስለ ሴት ልጅ ግርዛት ጉዳት ታቃላችሁ?" ብለው ሲጠይቁ ተማሪው በአንድነት "አናውቅም" ሲል መመለሰ።
ከዚያ በኋላ የእርሷን እንዲሁም የሌሎች ህይወትን መስመር የሚቀይር ትምህርት ሰማች። መስከረም ሙለታ ትባላለች። ሴት ልጅን መግረዝ ጉዳት እንዳለው ያወቀችው ያኔ የአካባቢያቸው ፖሊስ አባላት ትምህርት ቤታቸው መጥተው ባስተማሩበት ወቅት ነው። ትምህርቱን የሰጠው ፖሊስ "ሴት ልጅን መግረዝ ጣታችሁን ከእጃችሁ ላይ ቆርጦ እንደመጣል ነው" ሲል ማስተማሩንም ታስታውሳለች። የተወለደችው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ማረቆ አካባቢ፣ ሐሙስ ገበያ በምትባል መንደር ውስጥ ነው። አሁን እድሜዋ 17 የሆነው መስከረም በማረቆ በሚገኘው ቆሼ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነች። ከሁለት ዓመት በፊት ስለ ሴት ልጅ ግርዛት አስከፊነት የሰማችው ትምህርት ሥራ ላይ የሚውልበት ቀን ሩቅ አልነበረም። እናቷ አንድ ቀን ልታስገርዛት እየተዘጋጀች እንደሆነ አወቀች። "የሰፈሩ ልጆች ሁሉ ተገርዘው አንቺ ከቀረሽ ቀልቃላ ትሆኛለሽ፤ እቃ ትፈጂያለሽ" ማለታቸውን ታስታውሳለች። ስለዚህም እናቷ የሚገርዘውን ሰው ለማምጣት ማሰባቸውን ሲናገሩ ሰማች። በዚህ ጊዜም ትምህርት ቤት ሴት ልጆች ከተገረዙ በወሊድ ጊዜ ብዙ ደም እንደሚፈስሳቸው። ከፍም ሲል በርካታ ደም ከመፍሰስ ጋር ተያይዞ ሊሞቱ እንደሚችሉ መማሯን ለእናቷ ተናገረች። አክላም ድርጊቱ ኋላ ቀር ልማዳዊ ድርጊት ነው በማለት ለእናቷ አስረዳች። እናቷ ግን በአቋማቸው ፀንተው ባለሙያውን ለማምጣት እንደወሰኑ ስታውቅ "እምቢ ብለሽ ካመጣሽው እከስሻለሁ" ስትል ማስፈራራቷን ታስታውሳለች። ይሁን እንጂ የተፈራው አልቀረም። አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስትመለስ 'ባለሙያ' የተባለው ግለሰብ ካፖርቱን ደርቦ፣ ባርኔጣ ደፍቶ፣ ምላጭ ይዞ ከቤት ጠበቃት። መስከረም፣ እናቷና ግለሰቡ ሲጨዋወቱ ትንሿን እህቷን ይዛ ከአካባቢው ጠፋች። ከዚያም እርሱ ከሄደ በኋላ ወደ ቤት መመለሳቸውን ታስታውሳለች። እናትየው በመስከረም እምቢተኝነት ተስፋ ቢቆርጡም ታናናሾቿ ግን ገና በጨቅላነታቸው መገረዝ እንዳለባቸው ወሰኑ። የመስከረም ታናናሽ እህቶች የስምንት እና የስድስት ዓመት ልጆች ናቸው። "እንዳንቺ ሳያድጉ መገረዝ አለባቸው፤ ቁስሉም ቶሎ ይደርቅላቸዋል" እናቷ በማለት መጀመራቸውን ትናገራለች። ከዚያ በመስቀል በዓል ላይ ድግስ ተደግሶ፣ ለልጆቹ ስጦታ እየመጣላቸው የግርዛት ሥነ ሥርዓቱ ሊፈፀም መሰናዶው መጀመሩን አስተዋለች። ግርዛቱን የሚያከናውነው ግለሰብም ቤት መምጣቱን የምትናገረው መስከረም፤ የስድስት እና የስምንት ዓመት የነበሩት እህቶቿን በመውሰድ ሰው ቤት መደበቋን ትናገራለች። ከዚያም ወደ ቤት በመመለስ ለግለሰቡ ድርጊቱ ትክክል እንዳልሆነ ስትናገር "የዚህ ዘመን ልጆች ለሰው ክብር የላቸውም" በማለት መቆጣቱን ታስታውሳለች። ግለሰቡ የምትለውን አልሰማ ሲልም የአገር ሽማግሌዎች እና የማኅበረሰብ መሪዎች ኋላ ቀር ድርጊትን ሊፈጽም እንደሆነ በመግለጽ ተቃውሞዋን ገለፀች። በኋላም የመስከረም ጩኸት ሰሚ አግኝቶ፣ ሽማግሌዎቹ ከድርጊቱ የማይቆጠብ ከሆነ እንደሚከሰስ በመናገራቸው ትቶ ሄደ። መስከረም ወደ ሰባተኛ ክፍል ስትዘዋወር ግን ሌላ ተግዳሮት ገጠማት። ሰባተኛ ክፍል የምትማርበት ትምህርት ቤት ከመኖሪያ አካባቢዋ ርቆ ስለሚገኝ እንደ ሁልጊዜው መንደሯ ውስጥ የሚከናወነውን ሁሉ በንቃት መከታተል አላስቻላትም። የአካባቢዋ ሰዎችም ሴት ልጆቻቸውን ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች እወሰዱ ማስገረዝን እንደ ብልሃት መጠቀም ጀመሩ። ይህንን ያወቀችው መስከረም ከምትማርበት አካባቢ ወደ መንደሯ ስትመለስ ታዳጊዎቹን በመሰብሰብ መገረዝ እንደሌለባቸው ትመክራቸው ነበር። አብረዋት በአንድ ክፍል ውስጥ ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል ሊገረዙ መሆኑን በመጥቀስ ምክር ሲጠይቋት፣ አልገረዝም እንዲሉና ካልሆነ ግን ለፖሊስ እንዲያሳውቁ ትመክራቸው እንደነበር ትናገራለች። የሴት ልጅ ግርዛት የሚፈጸምባቸው ሃገራት 'እኔ አልተገረዝኩም፤ እያልኩን ኅብረተሰቡን አስተምራለሁ' በምትማርበት ትምህርት ቤት እንደ እርሷ ካልተገረዙ ልጆች ጋር በመሆን በየ15 ቀኑ በመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየሄዱ ስለ ሴት ልጅ ግርዛት ጉዳት ማስተማር ጀመሩ። የአካባቢው የሴቶች ጉዳይ ቢሮም ስልጠናዎችን በመስጠት እና መድረኮችን በማዘጋጀት ያግዛቸው ጀመር። ማኅበረሰብን ማስተማር ከራስ ይጀምራል የምትለው መስከረም፣ እኔ አልተገረዝኩም፤ በማለት እስከ ገጠር ትምህርት ቤቶች ድረስ በመሄድ እንደምታስተምር ትናገራለች። የተገረዙት ሴት ልጆችም እንዳያፍሩና እነርሱ ላይ የደረሰው ሌሎች ላይ እንዳይደገም ከእርሷ ጋር በመሆን እንዲያስተምሩ ታደርጋለች። ይህች ታዳጊ በአካባቢውና በትምህርት ቤቶች የምትሰጠው ትምህርት ተቀባይነት እያገኘ ሲሄድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያበረታቷት ጀመር። በዚህም ደስተኛ መሆኗን የምትናገረው መስከረም፤ ዘመዶቿም በጥንካሬዋና በጽናቷ እንደኮሩባት ገልጻለች። የተባበሩት መንግሥታት በዓለማችን ላይ ካሉ ሴቶችና ህጻናት መካከል ወደ 200 ሚሊዮን የሚጠጉት የተለያየ ደረጃ የግርዛት ተግባራት ተፈጽሞባቸዋል ይላል። የሴት ልጅ ግርዛት በስፋት እየተፈጸመ ያለው ወደ 30 በሚጠጉ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ውስጥ ሲሆን፤ በእስያ እና ደቡብ አሜሪካ በሚገኙ አገራትም የሴት ልጅ ግርዛት ይፈጸማል። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው ከሆነ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ አበውስትራሊያ እና በኒው ዚላንድ የሚኖሩ ስደተኞች ሕግን በመተላለፍ ሴት ልጆቻቸውን ያስገርዛሉ። የሴት ልጅ ግርዛት ሆነ ተብሎ የሴት ልጅን የመራቢያ አካልን ክፍልን መቁረጥ ማለት ነው። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው ምንም እንኳ የሴት ልጅ ግርዛት በ29 የአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ውስጥ በሕግ የተከለከለ ቢሆንም በ24 አገራት ውስጥ በስፋት እንደሚፈፀም ይጠቁማል። የግርዛት አይነቶች አራት አይነት የግርዛት አይነቶች አሉ።
news-53257880
https://www.bbc.com/amharic/news-53257880
እስክንድር ነጋ 'ሁከትና ግጭት ለመቀስቀስ በመሞከር' ተጠርጥሮ መያዙ ተገለጸ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ውስጥ ሁከት ለመቀስቀስ በመሞከር ተጠርጥሮ እንደታሰረ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገለጸ።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምሽት ላይ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ጸጋ እንዳሉት በአዲስ አበባ ሁከትና ግጭት እንዲፈጠር በመቀስቀስ ተጠርጥሮ በሕግ ቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ኃላፊው እንዳሉት አቶ እስክንድር በአዲስ አበባ ውስጥ ቡድን በማደራጀት ወጣቶችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመመደብ ሁከትን የሚያነሳሱ ቅስቀሳዎች ሲደረግ እንደነበር ጠቅሰዋል። በዚህም በሕዝቡ መካከል ግጭትን ለመፍጠር በሚችሉ ድርጊቶች ተጠርጥሮ በሕግ ቁጥጥር ሰር መዋሉን አቶ ፈቃዱ ጸጋ ተናግረዋል። የባልደራስ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ዛሬ [ረቡዕ] ከሰዓት በኋላ አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ተይዞ የተወሰደው ከቢሮው ነው ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። አቶ እስክንድር አሁን የት እንዳለ እንደማያውቁ አቶ ናትናኤል ገልጸው፤ ምሽት ላይ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባቀረበው ዜና ላይ ግን እስክንድር በቁጥጥር ስር የዋለው በአዲስ አበባ ውስጥ ሁከትና ግጭት ለመፍጠር በመሞከር ተጠርጥሮ እንደሆነ ተገልጿል። ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሰኞ ምሽት መገደሉ ከተሰማ በኋላ በተለያዩ ስፍራዎች አለመረጋጋት መከሰቱ ይታወቃል። ፡ ትናንት የድምጻዊውን አስክሬን ወደ ትውልድ ቦታው አምቦ ከተማ በማምራት ላይ እያለም የተፈጠረ ግርግርን ተከትሎ አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ 35 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሸን በጋራ በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
news-53125994
https://www.bbc.com/amharic/news-53125994
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎችን እንዲቀንሱ ለባለስልጣናቱ መልዕክት አስተላለፉ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የወጣውን የቤት መቀመጥ መመሪያ ከተጣለ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የምረጡኝ ቅስቀሳ ያደረጉት ስብሰባ ላይ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጠበቁት በታች ሕዝብ መገኘቱ ተነገረ።
በቱልሳ፣ ኦክላሃማ በተካሄደው የዳግም ምረጡኝ ቅስቀሳ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ምርመራን አስመልክቶ አወዛጋቢ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ ባለስልጣናት ምርመራዎችን ከማካሄድ ገታ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ብዙ ምርመራ በተደረገ ቁጥር በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ "ምርመራ ማለት በሁለት በኩል ስለት ያለው ቢላ ማለት ነው። መጥፎው ነገር ይህ ነው። ብዙ ሰዎች ሲመረመሩ በቫይረሱ የተያዙ ብዙዎችን ታገኛላችሁ። ምርመራውን ገታ አድርጉ በተደጋጋሚ ብልም አሁንም በፍጥነት በመመርመር ላይ ናቸው" ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ አንድ የዋይት ሐውስ ባለስልጣን ፕሬዚዳንቱ እየቀለዱ ነው በማለት ለማስተባበል ሞክረዋል። ፕሬዚዳንቱ በተጨማሪ በነጭ ፖሊስ በግፍ በተገደለው ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ማግሥት በተከሰተው ተቃውሞ የሚገረሰሱ ሐውልቶችን በተመለከተም "ታሪካችንን ሊያበላሹ የቋመጡ" ናቸው በማለት በተሰበሰበው ሕዝብ መካከል ድርጊቱን አውግዘዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለሁለት ሰዓታት ያህል በተለያዩ ርዕሶች ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በቦታው የተገኘውንም ሕዝብ "ታጋዮች" በማለት አሞካሽተው ደጋፊዎቻቸውን እንዳይገኙ ያደረጉት ሚዲያዎችንም ወንጅለዋል። ከስብሰባው ስፍራ ውጪ አንዳንድ ረብሻዎች እንደተከሰቱ ሪፖርት ቢደረግም ይህን ያህል የከፋ አልነበረም ተብሏል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኦክላሃማ ቱልሳ ለሚደረገው ዝግጅትም ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ቲኬት ጠይቀዋልም ብለው ሲኩራሩ ፕሬዚዳንቱ ተሰምተዋል። ነገር ግን አስራ ዘጠኝ ሺህ መቀመጫ ያለውን ማዕከልንም መሙላት አልተቻለም። የተሳታፊው ሕዝብ ቁጥር ከተጠበቀው በታች ለምን እንደቀነሰ ግን የተሰጠ ምክንያት የለም። በወረርሽኙ ወቅት እንዲህ አይነት የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ማካሄድ ስጋት አለውም ተብሎ ነበር። በቅስቀሳው ላይ የተሳተፉ የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎችም ለሽታው ቢጋለጡ የቅስቀሳው አዘጋጆችን ተጠያቂ ላለማድረግ ፈርመው ነው የተሳተፉት ተብሏል። ቅስቀሳው ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት የምረጡኝ ዘመቻውን ከሚያስተባብሩት መካከል ስድስቱ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡ ተገልጿል። የትራምፕ ዳግም ምረጡኝ ቅስቀሳ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ በአገሪቱ ብዙ ሕዝብ በአንድ ቦታ የተሰባሰበት ትልቁ ዝግጅት ነው ተብሏል። ዝግጅቱ በተካሄደበት ኦክላሃማ ግዛትም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል። በአሜሪካ 2.2 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 119 ሺህ ሰዎችም በወረርሽኙ ሰበብ እንደሞቱ ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
news-51655544
https://www.bbc.com/amharic/news-51655544
ሳዑዲ አረቢያ ወደ አገሯ የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ጉዞዎችን አገደች
ሳዑዲ አረቢያ ለሐይማኖታዊ ጉብኝት የሚደረጉ ጉዞዎችን አግዳለች። አንድ ጃፓናዊት ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮና መያዟ ተረጋግጧል። ሐምሌ ወር ላይ ሊካሄድ የታሰበለት ኦሎምፒክ 'ሊሰረዝ ይችላል' ተብሏል።
ሳዑዲ አረቢያ የሳዑዲ መንግሥት የውጪ አገር ዜጎች ለሐይማኖታዊ ጉብኝት ወደ አገሩ እንዳይገቡ አገደ። ይህ እገዳ ወደ መካ እና መዲና የሚደረጉ ሐይማኖታዊ ጉብኝቶችንም ያካትታል። ሐምሌ ወር ላይ የሚደረገው የሃጂ ጉዞ በዚህ እገዳ ምክንያት ሊሰረዝ እንደሚችል ግን አልታወቀም። ከዚህ በተጨማሪ ሳዑዲ አረቢያ ኮሮናቫይረስ ከተከሰተባቸው አገራት የሚመጡ ሰዎች ወደ ድንበሬ ድርሽ እንዳይሉ አደርጋለሁ ብለዋል። ሳዑዲ እስካሁን በቫይረሱ የተያዘ ሰው አልተገኘም። ጃፓን በቫይረሱ ተይዛ የዳነችው ጃፓናዊት ሴት እንደገና በቫይረሱ ተያዘች። የ40 ዓመት ሴት የሆነችው ጃፓናዊት ከሁለት ወር በፊት ነበር በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጦ ወደ ሆስፒታል የገባቸው። ለአንድ ወር ያክል በህክምና ላይ ቆይታ ከቫይረሱ መዳኗ ሲረጋገጥ ከሆስፒታል ትወጣለች። ይሁን እንጂ የመትንፈሻ አካል ህመም አጋጥሟት ወደ ሆስፒታል ስትሄድ ቫይረሱ በድጋሚ ተገኝቶባታል። 'ኦሊምፒክ ሊሰረዝ ይችላል' ተባለ የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዲክ ፓዎንድ ለሬውተርስ ኦሊምፒክ ሊሰረዝ የማይችልበት ምክንያት የለም ሲሉ ተናገሩ። የኮሚቴው አባል እንዳሉት የቫይረሱ ስርጭት 'ወረርሽኝ' ተብሎ የሚታወጅ ከሆነ እና ግልጽ የሆነ የጤና ስጋት የሚያስከትል ከሆነ ሊሰረዝ ይችላል ብለዋል። የ2020 ኦሊምፒክን በጃፓን ቶኪዮ በወረሃ ሐምሌ ላይ ለማዘጋጀት እቅድ ተይዟል። ቻናይ በአህዝ የቻይና መንግሥት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ በየዕለቱ አዳዲስ አህዞችን ያወጣል። እስከ ዕረቡ ምሽት ድረስ በቻይና ብቻ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 78497 ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 2744 ደርሷል። የቻይና መንግሥት ቫይረሱን ለመቆጣጠር ለህዝቡ እያስተላለፈ ያለው መልዕክቶች ሦስት ናቸው። ከቤት አትውጡ፣ ሰብሰባዎች አታድርጉ እና ጉዞ አታድርጉ የሚሉ ናቸው። በአሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በአሜሪካና በደቡብ ኮሪያ መካከል ሊደረግ የነበረ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። ደቡብ ኮሪያ በአንድ ምሽት ብቻ 334 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን አስታውቃለች። በትንትናው ዕለት በደቡብ ኮሪያ የሚገኝ አሜሪካዊ ወታደር ቫይረሱ ተገኝቶበታል። ወታደሩ ከአሜሪካ ውጪ በቫይረሱ የተያዘው የመጀመሪያው አሜሪካዊ ወታደር ሲሆን በኮሪያ ወረርሽኙ የተከሰተበት አካባቢ የሚገኝ ወታደራዊ ካምፕን ጎብኝቶ እንደነበር ተገልጿል። በርካታ ደቡብ ኮሪያውያን ወታደሮች ቫይረሱ እንደተገኘባቸውም ማወቅ ተችሏል። አሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕና ምክትላቸው ማይክ ፔንስ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሮናቫይረስ የአሜሪካ ሕዝብ ላይ የሚደቅነው አደጋ ዝቅ ያለ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ ምክትላቸውን ማይክ ፔንስ መንግሥትን ወክለው ኮሮናቫይረስን እንዲከላከሉላቸው ሾመዋቸዋል።
news-51520678
https://www.bbc.com/amharic/news-51520678
"ልጄ በመኪና አደጋ ስለሞተ የትራፊክ አገልግሎት እሰጣለሁ"- ናይጄሪያዊቷ ዳኛ
ናይጄሪያዊቷ ሞኒካ ዶንግባን ሜንሴም በዋናነት ስራዋ ዳኝነት ቢሆንም በትርፍ ጊዜዋ በመዲናዋ አቡጃ የትራፊክ አገልግሎት ትሰጣለች። ለዚህ ምን አነሳሳት ብትሉ ከስምንት አመታት በፊት በመኪና አደጋ የሞተውና ቀን ተሌት ሃዘኑ የሚያብሰከስካት ልጇ ነው።
ሞኒካ ቀን ሰማያዊ የትራፊክ መለዮዋን ለብሳ ከየትኛው አቅጣጫ የሚመጡ መኪኖች መቅደም እንዳለባቸው ትዕዛዝ ታስተላልፋለች። • የደምህት ወታደሮች የመኪና አደጋ ደረሰባቸው • ከአሰቃቂ መኪና አደጋ በተአምር የተረፈችው ሴት በአካባቢው ያለው ታዋቂ በርገር ቤት አደባባዩን በመኪና እንዲጨናነቅ አድርጎታል። ተራቸውን መጠበቅ ያቃታቸው የመኪና አሽከርካሪዎች ክላክስ አሁንም አሁንም ይሰማል። "አብዛኛው ናይጄሪያዊ ትዕግስተኛ አይደለም ይህ ባህርይ ደግሞ ሲነዱ ይታያል" ትላለች ዳኛ ሞኒካ ለልጇ ሞት ማን ተጠያቂ እንደሆነ ባታውቅም፤ በሃገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋውን መጥፎ አነዳድ ለመቀየር የራሷን አስተዋፅኦ እያደረገች ትገኛለች። በተለያዩ የአውቶብስ መናኸሪያዎች ስለ ትራፈክ ደህንነት ለማስረዳት በምትሄድበት ወቅት ክፉኛ ያስደነገጣት ጉዳይ ቢኖር፤ አብዛኛዎቹ አሽከርካሪዎች የመንገድ ደህንነትንም ሆነ የትራፊክ ህጎች ላይ ሁነኛ የሚባል ስልጠና አለመውሰዳቸው ነው። • ''እግሬን ባጣም ትልቁን ነገር አትርፌ ለትንሹ አልጨነቅም'' • በትራፊክ አደጋ የበርካታ ወጣቶች ሕይወት እየተቀጠፈ ነው እንዲህ አይነት ንህዝላልነት የልጇን ህይወት እንዳሳጣት ሳይታለም የተፈታ ከመሆኑ አንፃር ለመቀየር ቆርጣ ተነሳች። የ62 አመቷ ዳኛ በልጇ ክዋፕዳ ስም አንድ የእርዳታ ድርጅት ያቋቋመች ሲሆን ለሞተረኞች ስለ ትራፊክ ደህንነት ስልጠና ይሰጣል። ከዚህም በተጨማሪ መማር ለሚፈልጉ የመኪና አሽከርካሪዎች አጠቃላይ የመኪና አነዳድንም ሆነ የመንገድ ደህንነትን በተመለከተ በነፃ የማስተማርን እቅዷ ውስጥ አስገብታዋለች። አጠቃላይ አገሪቷ ውስጥ ባለው የትራፊክ ፍሰት ያልረካችው ዳኛ ሞኒካ በሳምንታት ስልጠና ነው የትራፊክነት ስራውን ያገኘችው። ምንም እንኳን በብዙ የሃገሪቱ ክፍል ብትንቀሳቀስም ልጇ የሞተበትን ቦታ ለመጎብኘት የእናትነት አንጀት አላስቻላትም፤አቅም አጠራት። ከሞተ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው ልጇን የነጠቃት ጆስ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ የሄደችው። "ቦታው ስሄድ ዋና እቅዴ የነበረው የልጄን አሟሟት የሚነግረኝ አንድ ሰው ማግኘት ነበር" ትላለች። ነገር ግን በቦታው ስትደርስ የቦታው ግርግር ካሰበችው በላይ ስለነበር ግራ መጋባትና ድንጋጤ ነበር የተሰማት። መንገዱ የታቀደበት መንገድ ትክክል አለመሆኑ፣ የአሰራሩ ጥራት መጓደል እንዲሁም ጥገና ከማጣት ብዛት መፈራረስ ይታይበታል። የትራፊክ መብራቶችም በአካባቢው የለም። • የቀድሞው ሰላይ ሞቶ ተገኘ "የልጄ አስከሬን ጎዳና ላይ ነበር" መንገዱ የ32 አመቱ ልጇ ክዋፕዳ ዶንግባንን ጨምሮ በርካታ አደጋዎች የተከሰቱበት ነው። "የመንገዱ አሰራር እግረኞችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ከመሆኑ አንፃር አደገኛ ነው። የበርካቶችም ህይወት ተቀጥፏል። የትኛውም የመንግሥት አካል ችግሩን ለመቅረፍ ተነሳሽነት ሲያሳይ አላየሁም" ትላለች። በጆስ የሚገኙ ባለስልጣናት የተበላሹ መንገዶችን ለመጠገን እቅድ ላይ ቢሆኑም የመንገዱን ሁኔታ በተመለከተ ሞተረኞች እንዲሁም እግረኞች የራሳቸውን ጥንቃቄ ሊወስዱ ይገባል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ለሞቱትም ከማዘን ውጭ ያሉት ነገር የለም። በአካባቢው የሚገኙ ሰዎች ለዳኛዋ እንደነገሯት ልጇ ጎዳና ላይ ወድቆ ቢያዩትም ምንም አይነት እርዳታ ሊሰጡት እንዳልቻሉ ነው። የሞኒካ ልጅ ክዋፕዳ "ሁለቱ እግሮቹ ተጎድተው በህመም እያቃሰተ ነበር። በደም ተለውሶ ቢያዩትም አላፊ አግዳሚው ለመርዳት ፈቃደኛ አልነበረም" በማለት ዳኛ ሞኒካ በንዴት ትናገራለች። "በራሱ ደም እንደተዋጠ ልጄ ማንም ሳይረዳው ህይወቱ አለፈ፤ ሆስፒታል ቢሄድ ህይወቱ ይተርፍ ነበር" ትላለች። ልጇ ከጆስ ዩኒቨርስቲ ዲግሪውን በህግ ያገኘ ሲሆን ወደ ከተማውም የተመለሰው የትምህርት ማስረጃውን ለመውሰድ ነበር፤ ነገር ግን ያልታሰበው ሆነና ላይመለስ ቀረ። "ልጄ አቃቤ ህግ የመሆን ህልም ነበረው፤ ነገር ግን እንደ ዶሮ መንገድ ላይ ተደፍቶ ቀረ" ትላለች መረር ባለ ሃዘን። የናይጄሪያ የመንገድ ደህንነት መረጃ እንደሚያስረዳው በዓመት ውስጥ ከ5000-6000 የሚገመቱ ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ያጣሉ፤ በየቀኑ 13 ሰዎች ማለት ነው። አብዛኛዎቹ አደጋዎች ከአሽከርካሪዎች ስህተት ጋር የተያያዙ ሲሆን፤ መንጃ ፈቃድ የሌላቸው በርካታ ናቸው ተብሏል። በባለፈው ዓመት 60 ሺ የሚሆኑ አሽከርካሪዎች በሌጎስ ያለ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከረክሩ እንደነበርም ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን መመዝገብ ላይ ያለ ክፍተትና በየመንገዱ ካሜራዎች አለመኖር ገጭተው የሚያመልጡ አሽከርካሪዎችን ማንነት ለመለየትም አዳግቷል። በዚህም ምክንያት ነው የዳኛ ሞኒካን ልጅ ገድሎ ያመለጠውን አሽከርካሪ መያዝ ያልተቻለው። ገጭተው ያመለጡ ሰዎች ከተያዙ 14 ዓመት እስር ይጠብቃቸዋል። ዳኛ ሞኒካ ይሄ በቂ ነው ብላ አታስብም፤ ከበድ ያለ ቅጣት ያስፈልጋቸዋል። ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ አሽከርካሪዎች የእድሜ ልክ እስራት እንዲፈረድባቸው እንዲሁም ለቤተሰቦች የገንዘብ ካሳ እንዲከፈላቸው መደረግ አለበት ትላለች። ይህም ቢሆን ያጡትን ቤተሰብ ህመም በምንም መንገድ አይቀንሰውም። "ልጄ ይመለሳል፤ ሲመጣም ያቅፈኛል እያልኩ በር በሩን እያየሁ እጠብቃለሁ። እንቅልፍ የለኝም፤ ሲመጣ ሊርበው ይችላል ብዬ ምግብ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣለሁ"ትላለች። የትኛዋም እናት እሷ ባለፈችበት መንገድ እንድታልፍ አትፈልግም ለዛም ነው የመንገዱን ደህንነት ለማስጠበቅ ቆርጣ የተነሳችው። "ናይጄሪያውያን በመኪና አደጋ መሞት ሲያቆሙ የዛን ጊዜ ነው የእኔ እርካታ" ትላለች።
news-48659574
https://www.bbc.com/amharic/news-48659574
"ለአውሮፕላኑ መከስከስ ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም" አቶ ተወልደ ገብረማርያም
ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ነበር 157 ሰዎችን ያሳፈረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 መብረረር በጀመረ 6 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ የተከሰከሰው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም ለዚህ አደጋ በምንም ዓይነት ፓይለቶች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም ይላሉ። ለአደጋው መከሰት ፓይለቶችን የሚወቅሱ እጅጉን የተሳሳቱና መረጃው የሌላቸው ናቸው ይላሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚው። አንድ የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ለተፈጠሩት አደጋዎች ፓይለቶች ናቸው ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉት ማለታቸውን ተከትሎ ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው ምላሽ የሰጡት። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ • ኢቲ 302 የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል የቦይንግ ምርት የሆነው 737 ማክስ የተሰኘው አውሮፕላን በአምስት ወር ጊዜ ሁለት ጊዜ ነው የተከሰከሰው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢንዶኔዥያው ላየን ኤይር። የሁለቱም አደጋዎች የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ከበረራ ቁጥጥር 'ሲስተም' ጋር የተያያዘ እክል ለአደጋው ምክንያት እንደሆነ ያስረዳል። የኮንግረስ አባል የሆኑት ሳም ግሬቭስ ግን 'የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቶች ላይ የሠፈረው የአደጋ ምክንያት የፓይለቶች ስህተት ነው፤ ሲሉ ተደምጠዋል። •"አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ አክለውም 'አሜሪካ ውስጥ የሠለጠኑ ፓይለቶች ነበሩ እኒህን አውሮፕላኖች በደንቡ ሊቆጣጠሩ የሚችሉት' የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል። አቶ ተወልደ፤ ሳም ግሬቭስ 'ትክክለኛው መረጃ እጃቸው ላይ የለም፤ ሪፖርቱ ደግሞ የሚጠቁመው ፓይለቶቹ የሚፈለገውን ሁሉ እርምጃ እንደወሰዱ ነው' ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። 'ኤምካስ በመባል የሚታወቀው 'ሲስተም' በከባድ ጊዜ እንኳ አውሮፕላኑ ለፓይለቱ እንዲታዘዝ ተደርጎ የተገጠመ ነው። ነገር ግን በሁለቱም አደጋዎች ወቅት ይህ ሲስተም አውሮፕላኖቹ አፍንጫቸውን ወደፊት እንዲደፉ አስገድዷል፤ ፓይለቶቹ አውሮፕላኑን ሊያዙት ቢሞክሩም ሊታዘዝ አልቻለም' ሲል የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ይጠቁማል። ከኢንዶኔዥያው አደጋ በኋላ ቦይንግ ኤምካስ ስለተሰኘው ሲስተም ለአየር መንገዶች ማብራሪያ ልኳል። የኮንግረስ አባሉ ግን የኢቲ302 አብራሪዎች ይህንን ማብራሪያ በደንቡ አልተከታተሉትም ሲሉ ይወቅሳሉ። • የቦይንግ ኃላፊ የሟቾችን ቤተሰቦች በይፋ ይቅርታ ጠየቁ ግሬቭስ ወቀሳውን ሲያቀርቡ በሥፍራው የነበሩት የአሜሪካ ፌዴራል አቪየሽን ጊዜያዊ አለቃ በኮንግረስ አባሉ ሃሳብ የተስማሙ ሲሆን የአብራሪዎቹን ድርጊት 'ዕድለ-ቢስ' ብለውታል። አቶ ተወልደ ወቀሳውን ሊቀበል የሚገባው ማን እንደሆነ በጣም ግልፅ እኮ ነው ይላሉ፤ «አውሮፕላኑ ችግር እንዳለበት እኮ ዓለም ያወቀው ነው። ለዚያ መስሎኝ አውሮፕላኖቹ ከሥራ ውጭ ሆነው ማስተካከያ እየተደረገባቸው ያለው።» አብራሪዎችን የሚወቅሱ ሰዎች አንድ ጥያቄ ራሣቸውን እንዲጠይቁ እፈልጋለሁ። 'ችግሩ የአብራሪዎች ከሆነ በዓለም ዙሪያ ያሉ 380 ቦይንግ አውሮፕላኖችን ከሥራ ውጭ ማድረግ ለምን አስፈለገ?» ምናልባት አሜሪካ ወቀሳውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲወስደው ፈልጋ ይሆን ወይ የሚል ጥያቄ ከቢቢሲ የተሰነዘረላቸው አቶ ተወልደ አይደለም የሚል ድምፅ ያለው ምላሽ ሰጥተዋል። የቦይንግ አለቃ ዴኒስ ሚዩልበርግ 'ቦይንግ ለአየር መንገዶች ጋር በሥርዓት የመረጃ ልውውጥ አላደረገም፤ ቦይንግ ስህተት ሰርቷል' ሲሉ አምነዋል። ጨምረውም ቦይንግ 737 ማክስ በያዝነው ዓመት ወደሥራ ይመለሳል ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል። • ኬንያውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድንና ቦይንግን ሊከሱ ነው
news-48455873
https://www.bbc.com/amharic/news-48455873
ካስተር ሰሜኒያ፡ የ800 ሜትር የኦሎምፒክ ሻምፒዮናዋ ለስዊዝ ፍርድ ቤት ይግባኝ አለች
የ800 ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮና ካስተር ሰሜንያ ከፍተኛ 'ቴስቶስትሮን' የተሰኘው ሆርሞን ያላቸው ሴት ሯጮችን በተመለከተ የወጣውን ሕግ ተከትሎ ለዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም ቅሬታ አቅርባ ነበር።
ሰሜንያ የኦሎምፒክ 800 ሜትር ሁለት ጊዜ አሸናፊ ነች • ኤኤንሲ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ 'ዘረኛ' ነው አለ • "ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ ሰሜኒያ በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን የተጣለውን አዲስ ሕግ በመቃወም ያቀረበችውን አቤቱታ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም (ካስ) ውድቅ ካደረገባት በኋላ ወደ ስዊዘርላንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የጠየቀችው። "እኔ ሴት እና ዓለም አቀፍ ሯጭ ነኝ" የምትለው የ28 ዓመቷ ካስተር ሰሜንያ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ማንነቴን ሊያስለውጠኝ አሊያም ሊያስቆመኝ አይችልም ብላለች። ትናንት በተሰጠው መግለጫ ላይም ሰሜኒያ ዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ያሳለፈውን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው የስዊዝ ፍርድ ቤት ገለልተኛ በሆነ መንገድ እንዲመለከተው እንደምትጠይቅ ተናግራለች። ዋነኛው ጥያቄዋም መሠረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች እንደሆኑ አስታውቃለች። የሰሜኒያን ጉዳይ የሚከታተሉት ዶሮቴ ችራም "ዓለም አቀፉ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም መሠረታዊ የሆኑትን የስዊዝ ፖሊሲ ጥሷል" ብለዋል። ሰሜኒያና ሌሎች ሯጮች በ400 ሜትር ሩጫ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ የሆርሞን ለውጥ ላይ ሕከምና ሊደረግላቸው አሊያም ደግሞ ሌላ የሩጫ ርቀት ሊሰጣቸው ይገባል የሚል አቋምም አላቸው- ዶሮቴ። • በዋግ ኸምራ አስተዳደር 7 የዳስ ት/ቤቶች አሉ • "የግንቦት 20 ታሪካዊነት አጠያያቂ አይደለም" ባለፈው የስፖርት የግልግል ዳኝነት ተቋም አቤቱታዋን ውድቅ የተደረገባት ሰሜኒያም "ላለፉት አስርተ ዓመታት ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከዓላማየ ሊያደናቅፈኝ ሞክሯል፤ ይሁን እንጂ ይህ ጠንካራ እንድሆን አድርጎኛል፤ ተቋሙ ያስተላለፈው ውሳኔም ከዓላማዬ ሊያቆመኝ አይችልም" ብላለች ። ድርጊቱ እንዲያውም ከፍ እያደረጋትና በደቡብ አፍሪካና በሌሎች ዓለማት የሚገኙ ወጣት ሴቶችንና ሯጮችን እንድታበረታታ ምክንያት እንደሆናት ተናግራለች። ዓለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ዳኝነት የወንድ ሆርሞን ከፍ ባለ መጠን ያላቸው ሴት ሯጮችን በተመለከተ ያወጣው ሕግ አግላይ ነው የምትለው ሰሜኒያ የሴት ሯጮችን ስሜትና ፅናት ለመጠበቅ ቢያንስ ሕጉ ምክንያታዊና የተመጣጠነ መሆን ነበረበት ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።
news-55516804
https://www.bbc.com/amharic/news-55516804
ሕዳሴ ግድብ፡ ግብጽ በባለሙያዎች የቀረበውን ሰነድ አልቀበልም ማለቷ ተነገረ
ተቋርጦ የቆየው በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ስብሰባ እሁድ ዕለት ሲካሄድ ግብጽ በአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የተሰየሙ ባለሙያዎች ያቀረቡትን ረቂቅ ሰነድ እንደማትቀበለው ማስታወቋን የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በአፍሪካ ሕብረት አማካይነት ሲያካሂዱት የቆየው የበይነ መረብ ውይይት ለአንድ ወር ያህል ተቋርጦ ቆይቶ ሲጀመር በባለሙያዎች የቀረበውን ረቂቅ ሰነድ ኢትዮጵያና ሱዳን በአዎንታዊ መልኩ እንደሚቀበሉት አሳውቀዋል ብሏል ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ። በሦስቱ አገራት መካከል መልሶ የተጀመረውን ስብሰባ በደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና በአፍሪካ ሕብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢነት ተካሂዷል። እሁድ ዕለት በተካሄደው ውይይት ላይ የሦስቱ አገራት የውጭ ጉዳይና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ የሕዳሴው ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጋቸው እና የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ባቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ላይ መወያየታቸው ተገልጿል። ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ የቀረበውን ሰነድ እንደምትቀበለውና "በቀጣይ በሚካሄደው ድርድር ሰነዱን እንደግብዓት ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆኗን" እንዳሳወቀች ጠቅሶ፤ ሱዳንም "ሰነዱን ለሂደቱ ጠቃሚ አድርጋ እንደምትመለከተው" በመግለጽ ድርድሩን መቀጠል ፍላጎት እንዳላት ስታሳውቅ "የግብጽ ወገን ሰነዱን ጨርሶ እንደማይቀበለው ገልጧል" ብሏል። ሚኒስቴሩ በመግለጫው ላይ እንዳሳወቀው የሕዳሴው ግድብ ሙሌትና ዓመታዊ አስተዳደርን የሚመለከተው ሰነድ ላይ የሚደረገው ድርድር በአመዛኙ መግባባት የተደረሰበት መሆኑን አመልክቶ፤ "ወደፊት በአባይ ተፋሰስ ላይ ከሚገነቡ የውሃ ልማት ሥራዎች ጋር የሚኖረው ቁርኝት ዋነኛ የልዩነት ሃሳብ ነው" ሲል ገልጿል። የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ውይይቱ ከመጀመሩ በፊት በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ሦስቱ አገራት በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ደረጃ የውሃ ሙሌትና በዓመታዊ የሥራ ሂደቱን በሚመለከቱ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸው ነበር። ሚኒስትሩ ጨምረውም በአሁኑ ውይይት ላይ የሚደረገው የውሃ ሙሌት ወይይት ግድቡን ሙሉ ለሙሉ በውሃ መሙላት የሚመለከት መሆኑን አብራርተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍጆታ የሌለው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በመሆኑ የሚደረሰው ስምምነት ይህንን ከግምት ያስገባና የተሟላ የውሃ ስምምነትና ፍትሃዊ አጠቃቀም እንዲኖር ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፤ ስምምነቱ "የኢትዮጵያን የመጠቀም መብት የሚያቅብ እንዲሆን አትፈቅድም" ብሏል። የሦስትዮሽ ውይይቱ የአገራቱ ባለሙያዎች በሚያደርጉት ውይይት ስምምነት የተደረሰባቸውንና የልዩነት ሃሳቦችን በቀጣይ ሳምንት በሚካሄደው የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እንደሚያቀርቡና ውይይቱ እንደሚቀጥል ተገልጿል። በድርድሩ ላይ በታዛቢነት የሚሳተፈው የአውሮፓ ሕብረት የሦስቱ አገራት ውይይት መልሶ መጀመሩን በተመለከተ በቃል አቀባዩ በኩል ባወጣው መግለጫ ላይ ውይይቱ "ግድቡን ስለመሙላትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ወደ ስምምነት ለመድረስ እድልን ይፈጥራል" ብሏል። አምስት ቢሊዮን ዶላር በሚጠጋ ገንዘብ ላለፉት አስር ዓመታት በግንባታ ላይ የሚገኘው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ 78 በመቶ ግንባታው ተጠናቋል። የግብጽ ቅሬታ እሁድ ዕለት መልሶ ከተጀመረው ድርድር ቀደም ብሎ የግብጽ መንግሥት ካይሮ የሚገኙ የኢትዮጵያን ዲፕሎማትን ጠርቶ ባለፈው ማክሰኞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት አስተያየት ላይ ማብራሪያ መጠየቁ ይታወሳል። የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያን ቻርጅ ዲ አፌርን ረቡዕ ዕለት በመጥራት ቃል አቀባዩ ተናግረውታል ባለው ጉዳይ ላይ ማብራሪያ መጠየቁን ቢገልጽም፤ ዝርዝር ነገር አልጠቀሰም ነበር። አህራም የተባለው የግብጽ ጋዜጣ ስለጉዳዩ እንዳለው ዲፕሎማቱ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠሩት በቃል አቀባዩ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት በግብጽ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል በሚል እንደሆነ አመልክቶ፤ የተባለው አስተያየት ምን እንደሆነ ሳይገለጽ ማለፉን ዘግቧል። ይህ ከአገሪቱ በኩል የተሰማው ቅሬታ ምናልባትም ግንባታው ወደ መጠናቀቁ የቀረበውና ግብጽ ከፍተኛ ተቃውሞና ስጋት እያሰማችበት ካለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ቃል አቀባዩ በሰጡት አስተያየት ላይ ሊሆን እንደሚችል ተገምቶ ነበር። እስካሁን መቋጫ ያላገኘውና በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ለወራት ሲካሄድ የቆው ግድቡን የተመለከተው ድርድር ተቋርጦ ቆይቶ በቅርቡ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ለዓመታት በግንባታ ላይ የሚገኘውና በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት ከስምምነት መደረስ አለበት በሚል ሁለቱ አገራት ግፊት ቢያደርጉም ኢትዮጵያ ባለፈው የክረምት ወር መጀመሪያ ደረጃ የውሃ ሙሌትን ማከናወኗ ይታወሳል። አብዛኛው የግንባታ ሥራው እየተጠናቀቀ የሚገኘው ግድቡ በከፊል ኃይል የማመንጨት ሥራውን ከወራት በኋላ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ግብጽ ከአባይ ወንዝ ላይ በማገኘው የውሃ መጠን ላይ መቀነስን ያስከትላል በሚል ጥያቄ በምታስነሳበት ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ፣ ካርቱም፣ ካይሮና ዋሽንግተን ውስጥ ተከታታይ ድርድሮች ቢካሄዱም አስካሁን መቋጫ የሚሆን ስምምነት ላይ አልተደረሰም። በተለይ በአሜሪካ አሸማጋይነት ዋሽንግተን ላይ ሲካሄድ የነበረው ድርድር አንዳች ድምዳሜ ላይ ይደርሳል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም በመጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ ጥቅሜን የሚያስጠብቅ አይደለም በማለት ራሷን ከስምምነቱ ውጪ ማድረጓ ይታወሳል።
51657532
https://www.bbc.com/amharic/51657532
ከፋ ዞን፡ በቦንጋ ሠርግ አስደግሶ "የሙሽራዬ ቤት ጠፋኝ" ያለው ግለሰብ የእስር ጊዜውን አጠናቀቀ
በደቡብ ክልል፤ ከፋ ዞን፤ ቦንጋ ከተማ ሠርግ አስደግሶ "የሙሽራዬ ቤት ጠፋኝ" ያለው ግለሰብ ከእስር መለቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክፍሌ ተካ ለቢቢሲ ገለፁ። ነገሩ እንዲህ ነው. . .
ግለሰቡ በቦንጋ ከተማ ቤት ተከራይቶ ይኖር ነበር። ዕድሜው አሁን ወደ 30 ይጠጋል። የኑሮ ሁኔታውም ዝቅተኛ ደረጃ የሚባል ዓይነት ነው ይላሉ የሚያውቁት። ታዲያ አንድ ቀን ለሠፈሩ ሰዎች "ላገባ ነው" ሲል ያበስራቸዋል። መቼም አንድ ሰው በሕይወቱ ወደ መልካም ምዕራፍ ሲሸጋገር ደስ ያሰኛልና እነርሱም ደስታቸውን ይገልፃሉ። "አበጀህ የእኛ ልጅ" ይሉታል። • 'ወንድ ያገቡት' ኡጋንዳዊ ኢማም ከኃላፊነታቸው ታገዱ • የቴክሳስ ፖሊስ ልማደኛዋን ድንኳን ሰባሪ እየፈለገ ነው ሁሉም ባቅሙ እያዋጣ እርሱም ካመጣው ጋር እየተጨማመረ ድግሱ በትብብር ተዘጋጀ። የሠርጉ ቀን ሲደርስም ሸራ ተወጥሮ፣ ወንበር ተሰባስቦ ለእንግዶች ተሰናዳ። ዳሱም በአበባ እና በዘንባባ ተጌጠ። ጎረቤቱም እንደ ባህሉ ተሰባስቦ በአቅማቸው ድግሱን ሲያስተናብሩ ዋሉ። ሁሉም ተሰናድቶ ካለቀ በኋላ ሙሽራው ከአጃቢዎቹ ጋር [6 ወንድ እና ሁለት ሴት] እየጨፈሩ፣ እየዘፈኑ ሙሽሪትን ለማምጣት ዴቻ ወረዳ፤ ሻፓ ወደ የሚባል ቀበሌ አመሩ። ሻፓ በእግር ቢያንስ 1 ሰዓት ይወስዳል። ሚዜዎቹና አጃቢዎቹ "ደስታህ ደስታችን ነው" ብለው ይህንን ሁሉ ርቀት ተጉዘው ሥፍራው ደረሱ። ይሁን እንጂ ሙሽራው አንዳች ነገር እንደጠፋው ሁሉ መንደሩን መዟዟር ጀመረ። በድካም የዛሉት ሚዜዎቹ "ቤቱ አንደርስም ወይ? ሙሽራዋ የታለች?" ብለው መጠየቃቸው አልቀረም። ግን መዳረሻው አልታወቅ አለ። በአካባቢው የሚታይም ሆነ የሚሰማ የሠርግ ሁናቴ የለም። ግራ የተጋቡት አጃቢዎች "የታለች?" ሲሉ ሙሽራውን ወጥረው ይይዙታል። "ልጅቷ ያለችበት ቤት ጠፋብኝ " ይላቸዋል። 'ሙሽራዋ ጠፋች'። በነገሩ ግራ የተጋቡት አጃቢዎቹ የሚያደርጉት መላ ቅጡ ጠፋቸው። ዳስ ውስጥ ሆነው እየዘፈኑ ሙሽራዋን የሚጠባበቁት ሠርገኞች ፊት እንዴት ባዶ እጃቸውን እንደሚገቡ ጭንቅ ያዛቸው። በዚህ መሃል አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላቸው። ከአጃቢዎቹ አንዱን ጫማው እንዲያወልቅ አድርገው በነጠላ በመሸፋፈን ሙሽራ አስመስለው እየዘፈኑ፣ እየጨፈሩ ይዘው መግባት። በሃሳቡ ተስማሙ፤ እንዳሰቡት አደረጉ። ቤቱ እንደደረሱም "በእግሯ ረዥም ሰዓት ስለተጓዘች በጣም ደክሟታል።" ብለው ወደ ጫጉላው ቤት አዝለው ያስገቧታል። የሆነውን ማንም የገመተ የለም። ትንሽ ቆይቶ "ሙሽራዋ ትውጣና ራት ይበላ" ሲሉ ደጋሽ ጎረቤቶች ይጠይቃሉ። ምላሹ አሁንም "ደክሟታል" የሚል ነበር። አቶ ሙሉጌታ ገ/ሚካኤል ሠርግ ተጠርተው ከተገኙት ጎረቤቶች መካከል አንዱ ነበሩ። "ከሌላ ቦታ መጥቶ እኛ ሠፈር ቤት ተከራይቶ ይኖር ነበር። 'ላገባ ነው' ብሎ የተወሰኑ ጎረቤቶቹን ሠርግ ጠራ። እኔም ተጠርቼ ስለነበር ሠርጉ ላይ ተገኘሁ። ሙሽራዋን እንቀባለለን ብለን ሽር ጉድ ስንል ዋልን። በ'ጂ ፓስ' የሠርግ ሙዚቃ ተከፍቶ እየተጠባበቅን ነበር። በኋላ ላይ አምሽተው መጡ። ነገር ግን ብንጠብቅ ብንጠብቅ ሙሽራዋ አትመጣም። ወሬ አይቀርምና ሴት አስመስለው ይዘው የገቡት ወንድ ነው ተባለ። እንግዶችም ድግሱን ሳይቀምሱ ወዲያው ነበር በብስጭትና በእፍረት የተበታተኑት" ሲሉ አጋጣሚውን ያስታውሱታል። ሚስጢሩ ከጫጉላ ቤቱ ወጥቶ ወደ ዳሱ ሲዛመት ግን አፍታም አልቆየ። "ሴት አይደለም ወንድ ነው" የሚል። 'ጉድ' ተባለ። የሆነውን ባለማመን እያጉመተመቱ ወደየመጡበት የሄዱ እንዳሉ ሁሉ ጉዳዩን ለሕግ አካል ለማሳወቅም ያሰቡ አልጠፉም። ለፖሊስ ጥቆማ ተሰጠ። ፖሊስም በሥፍራው ተገኝቶ 'ሙሽራውን' በቁጥጥር ሥር አዋለ። " እኔ እንዲህ ዓይነት ነገር ሰምቼም አላውቅም።" የሚሉት አቶ ሙሉጌታ፤ በአካባቢው ባህል መሠረት በሠርግ ወቅት ገንዘብ ስለሚሰጥ ግለሰቡ ይህን ያደረገው ገንዘብ ለማግኘት መሆኑን የተረዳነው በኋላ ነው ይላሉ። ቆይተው እንደሰሙትም ሠርጉን ለመደገስ ያልተበደራቸው የጉልት ነጋዴዎች አልነበሩም። ድርጊቱ የአገሬውን ሰው ጉድ ያሰኘ ነበር። ድርጊቱንም እጅግ ኮነኑት፤ "ለዚህ ነው ወይ ደፋ ቀና ያልነው" ሲሉ ተፀፀቱ። የግለሰቡን ፍርድም በጉጉት መጠባበቅ ያዙ። • የቴክሳስ ፖሊስ ልማደኛዋን ድንኳን ሰባሪ እየፈለገ ነው • ሙሽሪት እጮኛዋ መቃብር ላይ ድል ባለ ሠርግ ተሞሸረች በወቅቱ ወንጀሉን ሲከታተሉ የነበሩት የቦንጋ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክፍሌ ተካ እንደነገሩን ግለሰቡ ሠርጉን የሠረገው ጥቃቅን ወጪዎች ሳይቀሩ ተበድሮ ነው። ሽንኩርቱም፣ እንጀራውም፣ ጠላውም ሁሉም ለድግስ የሚያስፈልጉ ነገሮች። የተበደረውም ከተለያዩ ቦታዎችና ሰዎች ስለነበር ማንም የጠረጠረ አልነበረም። "'ከእጮኛዬ ጋር ለመጋባት ባለሁበት ቀበሌ ጨርሼ መጣሁ' ብሎ ጓደኞቹን ሰብስቦ ሲናገር በየዋህነት አመኑት፤ ደስም አላቸው። እንደዚህ አንሸዋዳለን ብሎ ግን ያሰበ አልነበረም" ይላሉ ኮማንደር ክፍሌ። ኮማንደር ክፍሌ፤ ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ውሎ በምርመራው ሂደት ሲጠየቅ "አጭቻት ነበር፤ ከተስማማች በኋላ ቤቷ ጠፋኝ" የሚል መልስ እንደሰጠ ይናገራሉ። "ለትዳር ያጫሃትን ሴት ቤት እንዴት ነው አጣሁት የምትለው?" ሲሉ ጥያቄያቸውን ማስከተላቸው ግን አልቀረም። እሱም "ወደ ቦታው ሄድን፤ ጨለማ ነው፤ ቤቱ ጠፋብኝ። ተመልሼ ባዶ እጄን ወደ ቤት ለመግባት ስለተቸገርኩ እና ድግስ የጠራኋቸው ሰዎች አታለለን እንዳይሉ ብየ፤ ወንዱን ሴት አስመስዬ በጨለማ አስገባሁ" ሲል ምላሽ መስጠቱን ኮማንደር ክፍሌ ያስረዳሉ። ይሁን እንጂ ሴት ሙሽራ መስሎ የተወነውን ሠርገኛ ስምም "አላውቅም' ሲል መልስ ሰጥቷል። እንደዚህ ዓይነት አጋጣሚ ሰምተውም ሆነ አጋጥሟቸው እንደማያውቅ የሚናገሩት ኮማንደር ክፍሌ፤ በሁኔታው እጅግ ተደንቀን ነበር ይላሉ። "ሠርግ ማለት ትልቅ፣ ባህልም ወግም ነው፤ ስለዚህ የኅብረተሰቡን ባህልና ወግ ሊያበላሽ የሚችል እንደሆነ በማሰብ ነው ትኩረት ሰጥተን የተከታተልነው" ይላሉ። በዚህም መሠረት በማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመስርቶበት የቦንጋ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም 6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት አስተላለፈበት። ሴት ሙሽራ መስሎ የገባው ግለሰብን ግን በተባባሪነት ለመክሰስ ጥረት ቢደረግም የግለሰቡን ማንነት ማኅበረሰቡ ሊያጋልጥ ባለመቻሉ እንዲሁም ዋናው ተከሳሽም አላውቀውም በማለቱ ማንነቱ ሳይታወቅ ቀርቷል። ግለሰቡ የተረጋጋ ሕይወት እንዳልነበረው ኮማንደር ክፍሌ አክለዋል። ይህ የሆነው በደቡብ ክልል፤ ከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ነው ሲሆን 'የሠርግ ሥነ ሥርዓቱ'ም ታህሳስ 9 ቀን 2008 ዓ.ም ነበር የተካሄደው።
41930669
https://www.bbc.com/amharic/41930669
ካለሁበት 9፡ በኑሮዬ ደስተኛ ብሆንም ለቁርስ ቋንጣ ፍርፍር ባገኝ እወዳለሁ
ሳሙኤል አርዓያ እባላለሁ። በደቡብ ምስራቅ እስያ በምትገኘው ሲንጋፖር ነው የምኖረው።
ከኢትዮጵያ ከወጣሁ ብዙ ዓመታት አስቆጥሬያለሁ። ወደዚህ ሀገር ከመምጣቴ በፊት ፈረንሳይ ለአሥር ዓመታት ያህል በትምህርት እና በሥራ አሳልፌያለሁ። ወደ ሲንጋፖር የመጣሁት ሳይፔም ተብሎ በሚጠራ ኩባንያ ባገኝሁት የሥራ ዕድል ነው። በዚህ ድርጅት ኤፍ ፒ ኤስ ኦ ካዎምቦ "FPSO KAOMBO'' ለተባለው ፕሮጄክት የጥገና መሃንዲስ ሆኜ ነው የምሥራው። ከባህር ነዳጅ አውጥቶ ለማመላለስ በተዘጋጁ መርከቦች ላይ ያሉትን መሣሪያዎች በመቀየር እና የሚያስፈልጓቸውን ተጨማሪ መሣሪያዎች በመጨመር የመቆጣጠሩን ሥራ አከናውናለሁ። ሲንጋፖር በጣም ውድ ከተማ ሆና አግኝቻታለሁ። ከመጣሁ አንስቶ በጣም የሚያስገርመኝ ያለው ሥርዓት፣ የሰዉ ሕግ አክባሪነትና ሲንጋፖር በጣም ንፁሕ ሀገር መሆኗ ነው። ሁሉም ነገር ሥርዓቱን የጠበቀና ለሁሉም ሰው ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጁ የተሟሉ የሕዝብ መገልገያዎች መኖራቸውም እንድደመም አድርጎኛል። ዲም ሱም የተባለው ምግብ በእንፋሎት የሚበስል ሳምቡሳ የሚመስል ነው። እስካሁን የኢትዮጵያ ምግብ ፈልጌ ማግኘት አልቻልኩም። አምሮቴን ለመወጣት ልመገብ ብል እንኳን ቅርብ የሚባለው የኢትዮጵያ ምግብ ቤት ወደ 2000 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ታይላንድ ርዕሰ መዲና ባንኮክ ነው የሚገኘው። ስለዚህ "ዲም ሱም" እበላለሁ። ዲም ሱም የተባለው ምግብ በእንፋሎት የሚበስል ሲሆን ሀገር ቤት የሚሸጠውን ሳምቡሳ ይመስላል፤ ተመራጭ ምግቤም ሆኗል። ለአሥር ዓመታት ከኢትዮጵያ ውጪ ስለኖርኩኝ ከሀገር ቤት ምን እንደሚናፍቀኝ ለማወቅ ራሴን እጠይቃለሁ። ምላሽ ለማግኘት ግን ይከብደኛል ምክንያቱም የሚናፍቀኝን ብናገር ቤተሰብህን ረሳህ ተብዬ ልወቀስ ነው። ሆኖም ግን ሁሌም ስለኢትዮጵያ ሳስብ ዓመት በዓል ነው በሃሳቤ የሚመጣው። ጠዋት ተነስቶ ቤተ-ክርስትያን ደርሶ፣ ጎረቤት ሄዶ ቁርስ መብላቱ፤ ችቦ ማብራቱ ... ደግሞም ሽታው፤ ጫጫታው... በአጠቃላይ ወከባው ይናፍቀኛል። ኢትዮጵያ ለጉብኝት እንኳን ከተመለስኩኝ ቆየት ብያለሁ። ቢሆንም የማስታውሳቸውና በአዕምሮዬ የሚመላለሱ ብዙ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ብሔራዊ ትያትር ጋር ያለው አንበሳ፣ ቸርችል ጎዳናና ለገሃር አካባቢ ያለው ሁሉ ትዝ ይለኛል። እንደዚያም ሆኖ ግን የቅርብ ትውስታዬ የፈረንሳይ ሀገር ቆይታዬ ነው። በፈረንሳይና በሲንጋፖር መካከል ብዙ ልዩነቶች አላየሁም። በሳሎኔ በረንዳ በኩል በመስኮቴ ስመለከት ደስ የሚል ስሜት ይፈጥርብኛል ያም ሆኖ እንደ ሲንጋፖር ከተማ በሕንፃ የተሞላች ከተማ ያለች አይመስለኝም። እኔ የምኖርበት ሕንፃ ዙርያውን በሌሎች ሕንፃ የተከበበ ቢሆንም ደስ ሚል ስሜት አለው። በሳሎኔ በረንዳ በኩል ስመለከት ደስ የሚል ስሜት ይፈጥርብኛል። ሲንጋፖር የምታስጨንቅም ሆነ የምትጨቁን ከተማ አይደለችም። ሥርዓቱ እስከተጠበቀ ድረስ በጣም ግልጽና ነፃነትን የምታበረታታ ከተማ ሆና ነው ያገኘኋት። በተለያዩ ምክንያቶች የመጡ ብዙ የውጪ ዜጎችን የምታስተናግድ መሆኗም ሊሆን ይችላል እንደዚህ እንድትሆን ያደረጋት። ያለማቋረጥ የሚያስደንቀኝ ግን ሥርዓቱ ነው። በሲንጋፖር መሬት ላይ ምንም አይነት ቆሻሻ መጣል አይቻልም። በሕዝብ ማመላለሻ ላይ ምግብም ሆነ መጠጥ መጠቀም ክልክል ነው። በይበልጥ ደግሞ የሚያስደንቀው ማስቲካ በመንገድ ላይ ማኘክ መከልከሉ ነው። እጅግ በጣም ንፁህ ሀገር መሆኗ ሁሌም ያስገርመኛል። የሲንጋፖር ነዋሪዎች በጣም ሕግ አክባሪ፣ ደግና ጨዋዎች ናቸው። በዚያ ላይ ሁሉም ስለራሱ እንጂ ስለሌላ ሰው ሕይወት ብዙ ትኩረት ሲሰጡ አላየሁም። ሳሙኤል በበረንዳው ላይ 'ሰልፊ' ተነስቶ በኑሮዬ ደስተኛ ብሆንም ለቁርስ ቋንጣ ፍርፍር እንደጎደለብኝ ይሰማኛል። ለማንኛውም ሰው ከተወለደበት ሀገር ወደ ሌላ ቦታ ሲጓዝ ብዙ ነገሮች ሊከብዱት ይችላሉ። እኔ ግን ዕድለኛ ነኝ ምክንያቱም ፈረንሳይም ሆነ ሲንጋፖር ብቻዬን ሆኜ አላውቅም። ምንም ቢሆን ግን የማይታወቅ ሀገር ሲኬድ ፍራቻና ስጋት ይኖራል። የዛሬ አሥር ዓመት ከኢትዮጵያ ስወጣ ልጅነትም ስለነበር ብዙም አልተጨነኩም ነበር። አሁን ደግሞ ተማሪም ስላልሆንኩ ውሳኔዎቼ በሙሉ ሊያስከትሉ የሚችሏቸውን ነገሮች በማስብ ትንሽም ቢሆን ጭንቀት ያድርብኛል። በአጋጣሚ ሆኖ ሲንጋፖር ለመጀመሪያ ጊዜ ስመጣ የማውቀው ሰው ስለነበር ምንም አልተቸገርኩም ነበር። የሥራ ባልደረቦቼም አብረውኝ ስለነበሩ ያን ያህል አዲስ ሀገር እንደሚሄድ ሰው አላስፈራኝም ነበር። ሲንጋፖር አድገዋል ከሚባሉት ሀገሮች መካከል አንዷ ስለሆነች ለአዲስም ሰው ቢሆን ሁሉም ነገር የተመቻቸ ስለሆነ ጫካ እንደመግባት አይደለም። ይህን ስል ደግሞ በትምህርቴም ሆነ በሥራዬ ጥሩ ደረጃና ደህና ኑሮ የምኖር ሰው ነኝ ብዬ ስለማስብ ተቸግሬያለሁ ለማለት አልችልም። ምክንያቱም ሀገር በሚቀየርበት ጊዜ አመጣጥ ይወስነዋል። ገንዘብ ካለ ሲንጋፖር ውስጥ ብዙ ዕድሎች ክፍት ናቸው። ሳሙኤል በኤርታ አሌ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ብሆን ብዬ ሳስብ ኤርታ አሌ ከጓደኞቼ ጋር የፈረንጆችን አዲስ ዓመት ያከበርነው ይታወሰኛል። አሁን ደግሞ እራሴን እዚያ ባገኘው ደስታውን አልችለውም። እንደ ኤርታ አሌ ያለ ቦታ አይቼ አላውቅም። መቼም ደግሞ እንደዚህ አይነት ቦታ የማይ አይመስለኝም። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 10፡ የምመኘው በአንድነታችን ተዋደንና ተከባብረን በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኖር ነው ካለሁበት 11፡ በእንግሊዝ ሃገር ትልቁ ችግር ብቸኝነት ነው
news-53211837
https://www.bbc.com/amharic/news-53211837
ኩባንያዎች ፌስቡክ ላይ አናስተዋውቅም ብለው አድመዋል፤ ሁኔታው ሚዲያውን ይገለው ይሆን?
ለተቃውሞ ማዕቀብን እንደ አንድ መሳሪያ መጠቀም ወይም ማደም አዋጭ መሆኑን ፌስቡክ የተረዳ ይመስላል።
በጎርጎሳውያኑ 18ኛው ክፍለ ዘመን ባርያ ፈንጋይ ስርዓትን ማስወገድ የሚፈልጉ እንቅስቃሴዎች በባርያ ጉልበት የሚመረቱ ምርቶችን እንግሊዛውያን እንዳይገዙ መቀስቀስ ጀመሩ። ውጤታማም ነበር። ከዚህም ጋር ተያይዞ 300 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ስኳር መግዛትን አቆሙ፤ ይህም ሁኔታ ባርነትን እንዲያስወግድ ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረ የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ። በቅርብም "ስቶፕ ሄት ፎር ፕሮፊት' (ጥላቻን ለትርፍ አንጠቀምበት) የተባለው ዘመቻም በቅርቡም ማዕቀብን እንደ ፖለቲካ መሳሪያነት ያለመ እንቅስቃሴ ነው። ዘመቻውም ፌስቡክ ዘረኛና ጥላቻ የተሞሉ መልዕክቶችን ወይም ይዘት ያላቸውን ፅሁፎችን በማጥፋት ኃላፊነቱን አልተወጣም በሚልም ወንጅሎታል። ዘመቻውም ትልልቅ ኩባንያዎችን ማስታወቂያቸውን ከፌስቡክ እንዲሁም ከአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲያቋርጡ አድርጓቸዋል። ከነዚህም ኩባንያዎች መካከል ፎርድ፣ አዲዳስና ኤች ፒ የሚጠቀሱ ሲሆን ከነዚህ ኩባንያዎችም ቀድመው ኮካኮላ፣ ዩኒሊቨርና ስታርባክስም ማስታወቂያቸውን በፌስቡክ ማሰራጨታቸውን አቁመዋል። አክሲዎስ የተባለው ሚዲያ እንደዘገበው ማይክሮሶፍት በፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ የሚያሰራጨውን ማስታወቂያ ባለፈው ወር "ያልተገባ ይዘት" በሚል ስጋት ማቋረጡን ቢቢሲ አረጋግጧል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሬዲት፣ ትዊችና ሌሎች ሚዲያዎች እንዲሁ የጥላቻ ንግግርን እንዲቆጣጠሩ ጫና ላይ ናቸው ተብሏል። ማዕቀቡ ምን ያህል ይጎዳዋል? ማዕቀቡ ፌስቡክን ይጎዳዋል? በአጭሩ መልሱ ይጎዳዋል ነው። ምክንያቱም ፌስቡክ ዋነኛ ገቢውን የሚያገኘው ከማስታወቂያዎች በመሆኑ ነው። የአቪቫ ኢንቨስተርስ ሰራተኛ የሆኑት ዴቪድ ከሚንግ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በፌስቡክ ላይ እምነት ማጣት እንዲሁም ሞራላዊ እሴቶች የሉትም ብሎ ማመን "የፌስቡክን ቢዝነስ ሊያወድመው" ይችላል። ባለፈው አርብ የፌስቡክ ድርሻ ስምንት በመቶ የቀነሰ ሲሆን ይህም ማለት ዋና ስራ አስፈፃሚው ማርክ ዙከርበርግን በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ 6 ቢሊዮን እንዲያጣ አድርጎታል። ነገር ግን ይህ ሁኔታ ከዚህ በላይ ፌስቡክን ሙሉ በሙሉ ይጎዳዋል ወይም ማህበራዊ ሚዲያውን ይገለዋል ለሚለው ጉዳይ ብዙ የታወቀ ነገር የለም። ምክንያቱም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአድማ ዘመቻ ሲመታ የመጀመሪያው አይደለም። በጎርጎሳውያኑ 2017 ታላላቅ የሚባሉ ኩባንያዎች በዩቲዩብ ላይ ማስታወቂያ ማሰራጨት እንደሚያቆሙ አስታውቀው ነበር። ይህም የሆነው ማስታወቂያዎች ዘረኛና ጥላቻ የተሞላባቸው ቪዲዮዎች በዩቲዩብ መለቀቃቸውን ተከትሎ ነው። ያ የነበረው ማዕቀብም ሆነ አድማ አሁን ተረስቷል። ዩቲዩብ የማስታወቂያ ፖሊሲውን በተወሰነ መልኩ የቀየረ ሲሆን ከሶስት አመታትም በኋላ ሲታይ ምንም አይነት ተፅእኖ እንዳልደረሰበት ነው። ምናልባም እንደሚታሰበው ማዕቀቡም ሆነ አድማው ፌስቡክን ላይጎዳው የሚችልበትም ምክንያቶች አሉ። በመጀመሪያ ደረጃ በርካታዎቹ ኩባንያዎች አድማ የሚመቱት የሚቀጥለውን አንድ ወር ብቻ ነው። ከዚህም በተጨማሪ፣ በዋነኝነት ፌስቡክ ገቢውን የሚያገኘው ከትንሽ፣ መካከለኛና ትልልቅ ያሉ በሺዎችና ሺዎች ከሚቆጠሩ ኩባንያዎች ነው። ሲኤንኤን እንደሚለው ባለፈው አመት ፌስቡክ ላይ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ያስተዋወቁ 100 ኩባንያዎች 4.2 ቢሊዮን ዶላር ያፈሰሱ ሲሆን ይህ ግን የኩባንያው ስድስት በመቶ ገቢ ነው። እስካሁንም ድረስ በቁጥር በርካታ የሆኑት መካከለኛ ገቢ ያላቸው ኩባንያዎች ማዕቀቡንም ሆነ አድማውን አልተቀላቀሉም። ዲጂታል ዊስኪ የተባለው የማስታወቂያ ኤጀንሲ የስራ ሂደት ዋና ክፍል ማት ሞሪሰን እንደተናገሩት በርካታ ትንንሽ ኩባንያዎች በፌስቡክ ላይ አናስተዋውቅም ማለት አያዋጣቸውም። ምክንያቱም ለነዚህ ኩባንያዎች በቴሌቪዥን ከማስተዋወቅ ይልቅ በፌስቡክ ላይ ቢያስተዋውቁ ዋጋው ርካሽ እንዲሁም በርካታ ሰዎችንም ከማግኘታቸው አንፃር ፌስቡክን ይመርጡታል ብለዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በፌስቡክ የሚያደርጉትን ማስታወቂያ እንደማያቆሙም አስረግጠው አስረድተዋል። ፌስቡክ እንደ ድርጅት የተዋቀረበት መንገድ ለማርክ ዙከርበርግ ከፍተኛ ስልጣንም አሸክሞታል። ሁኔታዎችን ለመለወጥም ሆነ ያለመቀየር ኃይሉ ያለው በአንድ ሰው እጅ ነው። በፌስቡክ ላይ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ኩባንያዎች ራሱ በማርክ ዙከር በርግ ላይ ተፅእኖ ማሳረፍ አይችሉም። አንድ ነገር ማከናወን ካልፈለገ፤ አልፈለገም፤ በሱ ፈቃድ ይወሰናል። እስካሁን ባለው ማርክ ዙከርበርግ የመለወጥ ፈቃድ እንዳለው አሳይቷል። አርብ እለትም የጥላቻ መልእክት ይዘት ያላቸውን ፅሁፎች፣ የጥላቻ ተብሎ የሚለጠፍባቸው ሲሆን ከዚህም በኋላ ሌሎች እርምጃዎችም እንደሚኖር አረጋግጧል። ነገር ግን እነዚህ ለውጦች ጥላቻን ለትርፍ መጠቀምን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይችልም። አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎችም በራሳቸው አንዳንድ እርምጃዎች የወሰዱ አሉ። በትናንትናው ዕለት ሬዲት ከፀብ አጫሪነትና ተጠቃሚዎች ላይ የቃላት ጥቃት ማድረስ ጋር በተያያዘ በትራምፕ ስም የተፈጠረ የውይይት መድረክ ሚዲያውን እንዳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ እግድ ተፈፅሞባቸዋል። ይሄ የውይይት መድረክ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ይፋዊ የሆነ ቀጥታ ግንኙነት ባይኖረውም ለሳቸው ድጋፍ የሚሰበስቡ መረጃዎችን ያጋራ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ትዊች በበኩሉ በትራምፕ የሚመራውን የምረጡኝ ቅስቀሳ በጊዜያዊነት አግዶታል። በአማዞን ባለቤትነት ስር ያለው ትዊች ሁለት የትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ቪዲዮዎች የጥላቻ ንግግሮችን መመሪያ ጥሷል በሚል ነው። አንደኛው ከመመረጣቸው በፊት በጎርጎሳውያኑ 2015 ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሜክሲኮ ደፋሪዎችን እየላከች ነው በማለታቸው ሲሆን፤ ሌላኛው በዚህኛው ወር ፕሬዚዳንቱ በአሜሪካዊቷ ቤት ሰብረው የገቡትን ሰዎች በማሞገሳቸው ነው። ለብዙዎች ማህበራዊ ሚዲያ ድርጅቶች አመቱ ከባድ ነው። ፌስቡክ ከዚህ የተለየ እጣፈንታ የለውም። ማዕቀቡና አድማው ከቀጠለና ሌሎች ኩባንያዎችም ከተቀላቀሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች እጣፈንታቸው አጣብቂኝ ውስጥ የሚገባ ይሆናል።
news-54445177
https://www.bbc.com/amharic/news-54445177
ሩስያ፡ አሌክሲ ናቫልኒ፡ “ልሞት ይሆን? ብዬ አስብ ነበር”
ተመርዞ የነበረው ሩስያዊው ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫልኒ ሰውነቱ እንዳሻው እንደማይታዘዘውና ቅዠትም እንደሚያስቸግረው ተናግሯል።
አሌክሲ ከባለቤቱና ከልጁ ጋር ሆኖም ግን እያገገመ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። "በጣም እየተሻለኝ ነው" ያለው አሌክሲ ወደ ሩስያ እንደሚሄድም አስረድቷል። ቢቢሲ አሌክሲን ያነጋገረው በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቅ የበርሊን ሆቴል ውስጥ ነበር። እዛው በርሊን የሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ለ32 ቀናት በጽኑ ህሙማን ማቆያ እንደነበረ አይዘነጋም። ይቀዘቅዘውና ያንቀጠቅጠው የነበረ ቢሆንም ህመም እንዳልተሰማው ያስታውሳል። . የተመረዘው ሩስያዊ አሌክሲ ናቫልኒ ወደ ሩስያ ሊመለስ ነው . የሩሲያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ "ተመርዘዋል" - ቃለ አቀባያቸው "ምንም ህመም አልተሰማኝም። መጀመሪያ ላይ አንዳች ክፉ ነገር እንደገጠመኝ ተረድቻለሁ። ከዛ ግን ልሞት ይሆን? ብዬ ሳስብ ነበር።" ነሐሴ 20 ከሳይቤሪያ ወደ ሩስያ እየበረረ ሳለ ነበር ህሊናውን የሳተው። ሕይወቱ ሊተርፍ የቻለው አውሮፕላኑ አርፎ በአፋጣኝ ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል በመወሰዱ ነው። ከዛም ከሩስያ ባለሥልጣኖች ጋር ድርድር ተደርጎ ወደ በርሊን ተወስዷል። ሰመመን ውስጥ ገብቶም ነበር። በኖቪቾክ መመረዙ ተረጋግጧል? የኬሚካል መሣሪያን የሚቆጣጠረው የመንግሥታቱ ተቋም አሌክሲ በኖቪቾክ መመረዙን አረጋግጧል። ይህ ጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደው መርዝ በአሌክሲ የሽንት እና ደም ናሙና ውስጥ መገኘቱንም ይፋ አድርጓል። በፈረንሳይ እና በስዊዘርላንድ ቤተ ሙከራዎች የተሠራ ምርመራ አሌክሲ በኖቪቾክ መመረዙን እንደሚያረጋግጡ ጀርመን ተናግራለች። ኖቪቾክ የተሠራው በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት በሶቪየት ሳይንቲስቶች ነበር። በጣም መርዛማ ስለሆነ ትንሹ መጠን ይገድላል። አሌክሲ የተመረዘው በሩስያ እንደሆነ ተናግሯል። የሩስያ መንግሥት በቀጣዩ ዓመት የምክር ቤት ምርጫ ተፎካካሪ እንዳይሆን እንደመረዘውም አክሏል። . ፑቲን 'አስመርዘውታል' የተባለው አሌክሴ ለህክምና ወደ ጀርመን ተወሰደ . ጀርመን የፑቲን ተቃዋሚው መመረዙን አረጋገጥኩ አለች የሩስያ መንግሥት ግን እጄ የለበትም ብሏል። አሌክሲን የመረመሩት የሩስያ ሀኪሞች በሰውነቱ ምንም መርዝ አላገኘንም ብለዋል። አሌክሲ ባለፈው ሳምንት ለጀርመን መጽሔት "ከድርጊቱ ጀርባ ያለው ቭላድሚር ፑቲን መሆኑን አምናለሁ። ሌላ አካል ሊሆን አይችልም" ብሎ ነበር። አሌክሲ ከመታመሙ በፊት ሳይቤሪያ ውስጥ የጸረ ሙስና ቅስቀሳ እያደረገ ነበር። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ያሉት ሲሆን፤ ፑቲንን አጥብቆ በመተቸት ይታወቃል። ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ ከሩስያ ውጪ በስደት መኖር አልሻም ብሏል። "ለረዥም ጊዜ ከሩስያ ሊያስወጡኝ ሞክረዋል። ከዚህ በኋላ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም። አላማ አለኝ፤ አገሬ አለችኝ" ሲልም ተናግሯል። ቅዠት አውሮፕላን ውስጥ ሳለ ሲመረዝ ምንም ነገር ላይ ለማተኮር እንዳልቻለ ያስታውሳል። በአካባቢው የነበሩ ሰዎችና ቁሳቁሶች ግን ደብዝዘው አይታዩትም ነበር። ሆስፒታል ከገባ በኋላ በተደጋጋሚ ሲነቃ እንደነበርና ከሁሉም በላይ ይህ ስሜት እንደከበደው ይናገራል። "ዘለግ ላለ ጊዜ ያቃዠኝ ነበር" ያለው አሌክሲ፤ በወቅቱ ባለቤቱ ዩሊያ፣ ሀኪሞች እና የመብት ተሟጋች ጓደኛው ሊዮንድ ቮልኮቭ አደጋ ደርሶበት እግሩን እንዳጣ የነገሩት እንደመሰለው ያስታውሳል። ይህ ቅዠት እውነት እንደሆነ አምኖ ነበር። "አዲስ እግር በቀዶ ህክምና ይሰጠኛል" ብሎ ይቃዥም ነበር። በተለይ ሌሊት ላይ ይህ ቅዠት ያሰቃየው ነበር። "መተኛት አለመቻሌ ትልቁ ችግር ነው። ያለ እንቅልፍ ክኒን መተኛት አልችልም። ድሮ ግን እንዲህ ለመተኛት አልሰቃይም ነበር።" በየጊዜው የሕክምና ክትትል ያደርጋል። "አንዳንዴ ያለሁበትን ቦታ አልገነዘብም። በየቀኑ ሁለቴ በእግሬ እንሸራሸራለሁ። በጣም የሚከብደኝ ከመኪና መውጣት ነው" ይላል አሌክሲ። ህመም ስለማይሰማው ደስተኛ ቢሆንም፤ ኳስ እንደመወርወር ያለ ቀላል እንቅስቃሴ ስለሚከብደው ያዝናል።
43911736
https://www.bbc.com/amharic/43911736
የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች
የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ከየትኛውም ሀገር ወደ ቻይና ካቀኑ ስደተኞች ጋር እግር ኳስ ሲጫወቱ መመልከት እንግዳ ነገር ነው።
ኳስ አብሮ አለመጫወት ብቻ ሳይሆን፣ የዕለት-ተለት እንቅስቃሴያቸውንም ከስደተኞች ራቅ ብለው ማከናወን እንደሚመርጡ ሆንግ ኮንግ ዩኒዝን የተሰኘ የተራድኦ ድርጅት የሰራው ጥናት ያመለክታል። ከሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ሲሶው፣ ከሌላ አገር ከመጡ ሰዎች ጋር መቀላቀል አይሹም። በህዝብ ማመላለሻዎች እንኳ አብረው መቀመጥ ጉርብትናም አይፈልጉም። ልጆቻቸው ከስደተኞች ልጆች ጋር በአንድ ክፍል መማራቸውንም አይፈልጉም። ተወዳጁ ስፖርት እግር ኳስ ይህንን እውነታ ይለውጥ ይሆን? ስደተኞች የሚደርስባቸውን የዘር መድልዎ የመቅረፍ ኃይልስ ይኖረዋል? በሚል መነሻ አንድ የእግር ኳስ ቡድን የተቋቋመው እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ነበር። ''ኦል ብላክ'' የተሰኘው ቡድን አባላት በሙሉ ጥቁሮች ናቸው። አባላቱ በሆን ኮንግ ስለ አፍሪካውያን ያለውን የተዛባ አመለካከት ለማቃናት የድርሻቸውን እየተወጡ ነው። ኳስ ተጫዋቾቹ ከሌሎች ዜጎች ጋር በመቀላቀል የመገለልን ግርግዳ ለማፍረስም እየሞከሩ ነው። የቡድኑ መስራች መዳርድ ፕሪቫት ኮያ፣ በሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ሳለ ኳስ ተጫዋች ነበር። ቡድኑን ሲመሰርት ኳስ የሚጫወቱት አፍሪካውያን ስደተኞች ብቻ ነበሩ። አሁን ግን የተለያየ አገር ጥገኝነት ጠያቂዎችና ቻይናውያንም ቡድኑን እየተቀላቀሉ ነው። "እግር ኳስ ሁላችንንም ያስተሳስረናል። ሀሳብ መለዋወጥ እንዲሁም እርስ በእርስ መደጋገፍ እንችላለን።" ይላል። ከቡድኑ በሆን ኮንግ መስራት ለማይፈቀድላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች ግዜ ማሳለፍያ መሆኑም ሌላው ጠቀሜታው ነው። ሆን ኮንግ ውስጥ መስራት ከማይፈቀድላቸው አንዱ የቡድኑ አምበል ዳሪየስ ከቶጎ ከተሰደደ አምስት አመታት ተቆጥረዋል። ሆን ኮንግ ውስጥ መስራት ባይችልም ኳስ መጫወት ለህይወቱ ትርጉም እንደሚሰጠው ይናገራል። "ለአንድ ወጣት አምስት ዓመታት ያለ ሥራ ማሳለፍ ቀስ በቀስ የመሞት ያህል ነው። ህይወቴ ወዴት እያመራ ነው? የሚል ጥያቄም ያስነሳል። ያለ ምንም ስልጠናና ሥራ ልምድ ማን ይቀጥረኛል?" ሲል ይጠይቃል። ለጥያቄው መልስ የሰጠውና የተስፋ ጭላንጭል ያሳየው የእግር ኳስ ቡድኑን መቀላቀሉ መሆኑንም ያስረዳል። የቡድኑ አምበል ዳሪየስ (መሃል ላይ) እና የቡድኑ መስራች ሜዳራ (በቀኝ) ከሌላ ቡድን ተጫዋቾች ጋር ተቀምጠው "እኔን ከሚመስሉ ሰዎች ጋር ተቀላቅያለሁ። ሰዎች በችሎታችን ያከብሩናል። እኛም ለምናምንበት ነገር በጋራ እንታገላለን።" ይላል። ከቡድኑ አባላት የላቀ ችሎታ ያላቸው፣ ኳስ ተጫዋችነታቸውን የመኖርያ ፍቃድ ማመልከቻ ለማስገባትም ይጠቀሙበታል። "ሰዎች ፎቶ ያነሱናል" መዳርድ የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ቢያበረታታም ቡድኑን ለመቀላቀል የሚያመነቱ አሉ። ጥቁሮች የሚደርስባቸው መገለል ከዚህም በላይ መሆኑን ለቢቢሲ የሚገልፀው ደግሞ የ26 አመቱ ጋምቢያዊ ሰለሞን ኒያሲ ነው። ባጠገባቸው ሲያልፍ አፍንጫቸውን የሚይዙ ፎቶ አብረውት ለመነሳት የሚጠይቁትም ገጥመውታል። ቻይናውያን ከበውት ፎቶ ለማንሳት ሲጠይቁት እንደሚያሳፍረውም ይናገራል። የሰለሞንን ሀሳብ በመጠኑ የምትጋራው ቻይናዊት የሴት ጓደኛው ልዊዝ ቻን ናት። የ 20 ዓመቷ ልዊዝ ከሰለሞን ጋር ያላትን ግንኙነት ቤተሰቦቿ ቢደግፉትም፣ አሉታዊ አስተያየት የሚሰነዝሩባትም አሉ። ልዊዝ አፍሪካውያን ወንዶች ብልህና ንቁ እንደሆኑ ታምናለች። በተቃራኒው "የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ስለ ሌላው ማህበረሰብ እውቀት ያንሳቸዋል። አፍሪካውያንን ጥላሸት የሚቀቡ ፅሁፎች ሲልኩልኝ ያሳፍረኛል። " ትላለች። ዳሪየስ እንደሚለው፣ አፍሪካውያን ላይ ያነጣጠረው የተሳሳተ አመለካከት የእግር ኳስ አጨዋወታቸውንም አስተችቷል። አንዳንድ የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ''አፍሪካውያን ኳስ ሲጫወቱ በኃይል ተሞልተው ነው'' የሚል አመለካከት አላቸው። ዳሪየስ ግን እንደ ቡድን አምበልነቱ ተጫዋቾቹ በተገቢው መንገድ እንዲጫወቱ ያበረታታል። "የቆዳ ቀለም አይታየኝም" በሌላ በኩል የጥቁሮች የእግር ኳስ ቡድንን መቀላቀልን እንደ እንግዳ ነገር የማያው የ 34 ዓመቱ ዶንግ ዚ፣ ክለቡን የተቀላቀለው በ 2017 ነበር። ቡድኑን የተቀላቀለ ሰሞን ከተጫዋቾቹ ጋር ለመግባባት ግዜ እንደወሰደበት ያስታውሳል። ለዚህም ምክንያት ሆኗል የሚለው የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች ለአመታት ጥቁሮችን ማግለላቸው ነው። ከብዙ ጥረት በኋላ የቡድኑን አባላት ጓደኞቹ ከማድረግም አልፎ አብሯቸው ረዘም ያለ ግዜ ማሳለፍ መጀመሩን ይናገራል። "ለኔ የቆዳ ቀለም አይታየኝም። ሁሉም ምርጥ ኳስ ተጫዋቾች ናቸው።" ሲል ያስረዳል። በቅርቡ ለቡድኑ ተሰልፎ የተጫወተው የኮሌጅ እግር ኳስ ተጫዋቹ ኬቨን ፉንግ በበኩሉ፣ አፍሪካውያን ተጫዋቾች ብርቱ በመሆናቸው የሆን ኮንግ ተወላጆችን ያነሳሳሉ ብሎ ያምናል። ቢሆንም አብዛኞቹ የሆን ኮንግ ነዋሪዎች በተለያዩ ስራዎች ተጠምደው ኳስ መጫወት ስለሚዘነጉ፣ ጨዋታው በሁለቱ ህዝቦች መሀከል ህብረት ስለመፍጠሩ ይጠራጠራል። "የሀገር ውስጥ የእግር ኳስ ግጥሚያዎችም ያን ያህል ታዋቂ ስላልሆኑ በኳስ አማካይነት የዘር መድልዎን መቅረፍ ይከብዳል።" ይላል። ይህን ሃሳብ የ "ኦል ብላክ" አባላትም ይጋራሉ። ዘላቂ ለውጥ ለማምጣትም ከእግር ኳስ ውጪ በተለያዩ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ይሳተፋሉ። አረጋውያንን በመጎብኘት ከህብረተሰቡ ለመቀራረብ የሚያደርጉት ጥረት ይጠቀሳል። "በእንቅስቃሴያችን አሁን ላንጠቀም እንችላለን። ሆኖም በቀጣዩ ትውልድ ከተለያዩ ሀገሮች የመጡ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የተሻለ ሁኔታ ይጠብቃቸው ይሆናል።" ሲል ተስፋውን ይገልፃል።
news-55984269
https://www.bbc.com/amharic/news-55984269
ሱዳን፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ አዲስ ካቢኔ አዋቀሩ
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ 25 ሚንስተሮች የተካተቱበት አዲስ ካቢኔ አዋቀሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ይህንን ውሳኔያቸውን በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ በቀጥታ በተላለፈ ስርጭት ላይ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "አዲሱ ካቢኔ የተዋቀረበት ዋና ዓላማ አገሪቱን ከውድቀት ለመታደግ ባለመ የፖለቲካ መግባበት ነው።" ብለዋል በጋዜጣዊ መግለጫቸው ወቅት። አዲሱ መንግሥታቸው 25 ሚኒስትሮች እንደሚኖሩት ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የትምህርት ሚኒስትር ማን ይሁን በሚለው ላይ ገና ስምምነት አለመደረሱን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት እንዳረጋገጡት አዲሱ መንግሥት እኤአ በ ታህሳስ ወር 2019 ለተካሄደው ሕዝባዊ አብዮት መርሆዎች ተገዢ የሚሆን ሲሆን ከዚህ በፊት የነበሩ አመራሮች የጀመሩትን ስኬት ይዞ የሚቀጥል ይሆናል። ከዚህ በፊት የነበረው አመራር ትልቅ ስኬት በማለት የጠቀሱትም ሱዳንን አሸባሪነትን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውሰጥ ማስፋቅ ነው። ከአዲሱ ተሿሚ ሚኒስትሮች መካከል ከዚህ ቀደም ፍትሕና እኩልነት እንቅስቃሴ የተሰኘ አማፂ ቡድን ይመራ የነበረው ጂብሪል ኢብራሂም ይገኝበታል። የሟቹ ኢማም ሳዲቅ አል መሃዲ ልጅ የሆነችው መሪያም አል ሳዲቅ ደግሞ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆና ተሾማለች። በአዲሱ መንግሥት ውስጥ የተካተቱ ሰዎች ሹመት የተሰጣቸው ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር የሽግግር መንግሥቱ እና የሱዳን አብዮታዊ ግንባር (ኤስአርኤፍ) የተሰኘው የአማፂያን ቡድኖች ጥምረት በጁባ በደረሱት የሰላም ስምምነት መሰረት ነው ተብሏል። አዲሱ መንግሥት አገሪቱ ምርጫ እስከምታካሄድበት 2024 ድረስ በሥልጣን ላይ ይቆያል ተብሏል።
43496178
https://www.bbc.com/amharic/43496178
ፌስቡክ የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ መበርበሩን አመነ
የፌስቡኩ ፈብራኪና አለቃ የሆነው ማርክ ዙከርበርግ 'በስህተት' የሰዎች ግላዊ መረጃ ያለፍላጎታቸው መበርበሩንና ለአንድ የፖለቲካ አማካሪ ድርጅት ጥቅም መዋሉን አመነ።
'ካምብሪጅ አናሊቲካ' የተባለ የፖለቲካ አማካሪ ተቋም የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋሉን ተከትሎ ነው የማህበራዊ ትስስር ዘዴው ወቀሳው እውነት መሆኑን ያመነው። ዙከርበርግ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ ሲሰጥ "የግለሰቦች ግላዊ መረጃ ያለአግባብ ተበርብሯል" ብሏል። ዘግየት ብሎም ከሲኤንኤን ጋር ቃለ-ምልልስ ያካሄደው ዙከርበርግ በሁኔታው 'በጣም ማዘኑን' እንዲሁም ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት የፈፀመ ሰዎች ላይ ደግሞ 'እርምጃ' ለመውሰድ ማቀዱን ተናግሯል። የአሜሪካ ኮንግረስ ፊት ቀርቦ ስለሁኔታው ማስረዳት መቻሉ እረፍት እንደሰጠው የተናገረው የፌስቡክ አለቃ ዙከርበርግ የሰዎችን ግላዊ መረጃ የሚበርብሩ መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽን) ይህን ማድረግ እንዳያቻላቸው ለማድረግ የማያደርገው ጥረት እንደሌለም አሳውቋል። "የእርስዎን ግላዊ መረጃ የመጠበቅ ግዴታ አለበን። ይህንን ማድረግ ከተሳነን ግን እርስዎን ለማገልገል ብቁ አይደለንም ማለት ነው" ሲልም በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል። የሰሜን አሜሪካው የቢቢሲ ቴክኖሎጂ ነክ ዘገባዎች ተንታኝ የሆነው ዴቭ ሊ ግን የፌስቡክ ይቅርታ አልተዋጠለትም። "ትልቁ ነገር ጥያቄ ይቅርታ መጠየቁ ሳይሆን ይህ ጉዳይ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ምርመራ መካሄዱ ነው" ሲል ይከራከራል። ፌስቡክ በአውሮፓውያኑ 2014 ላይ የገጠመውን ዓይነት የመረጃ መሹለክ ክስተት ድጋሚ ማጋጠሙ ትልቅ ትንታኔ የሚፈልግ መሆኑንም ዴቭ ያስረዳል። የሰዎች ግላዊ መረጃ ያለፍላጎታቸው ሲበረበር ማስጠንቀቂያ እንኳን አልደረሳቸውም ይህም ምላሽ ይፈልጋል ባይ ነው ተንታኙ። ፌስቡክ ላይ ጫናዎች የበረቱ ሲሆን 'ካምብሪጅ አናሊቲካ' የተሰኘው መቀመጫውን ለንደን ያደረገ ተቋም እንዴት አድርጎ የ50 ሚሊዮን ያህል ተጠቃሚዎችን መረጃ እንደበረበረ አሁንም በግልፅ የታወቀ ነገር የለም። የአሜሪካው ፌዴራላዊ የንግድ ኮሚሽን ፌስቡክ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ማዘዙን አንዳንድ ዘገባዎች እየጠቆሙ ይገኛሉ። የአውሮፓ ሕብረትም መሰል እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል እየተነገረ ነው። የአንግሊዝ መረጃ ኮሚሽን ደግሞ ካምብሪጅ አናሊቲካ የተሰኘው ተቋም ላይ ግልፅ ምርመራ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ ነው። የፖለቲካ አማካሪ ተቋሙ በ2017ቱ የኬንያ ድጋሚ ምርጫም ውስጥ እጁ እንዳለበት ዘገባዎች ከጠቆሙ በኋላ ግልፅ ምርመራ እንዲካሄድ ጫናዎች እየበረቱ ይገኛል።