id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-56427910
https://www.bbc.com/amharic/news-56427910
አሜሪካ፡ በአትላንታ በተፈፀመ ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገደሉ
በአሜሪካ ጆርጂያ ግዛት ባሉ ስፓዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ስምንት ሰዎች ተገደሉ። አብዛኛዎቹ ሟቾች የእስያ ተወላጅ ሴቶች ናቸው ተብሏል።
ጥቃቱ የደረሰው ከአትላንታ በስተሰሜን በምትገኘው አክዎርዝ ማሳጅ ቤት እና በከተማዋ ውስጥ ባሉ ሁለት ስፓዎች መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡ ደቡብ ኮሪያ ከተጎጂዎች መካከል አራቱ የኮሪያ ዝርያ ያላቸው መሆናቸውን አረጋግጣለች፡፡ ባለስልጣናት የ 21 አመት ወጣት በቁጥጥር ስር መዋሉን እና ከሁሉም ጥቃቶች ጀርባ እንዳለበት ይታመናል ብለዋል፡፡ የግድያው መነሻ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም፡፡ በእስያ-አሜሪካውያን ላይ የጥላቻ ወንጀሎች ከቅርብ ወራት ወዲህ እየጨመሩ ናቸው። ለኮቪድ -19 መስፋፋት ተጠያቂ መደረጋቸው ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ንግግር በእስያ-አሜሪካውያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት፣ እንግልት፣ ክስ እና ውንጀላ ኮንነዋል፡፡ ስለ ተኩስ ምን እናውቃለን? የመጀመሪያው የተኩስ ልውውጥ የተከናወነው በቼሮኪ አውራጃ በአክዎርዝ በሚገኘው በያንግ ኤሲያን ማሳጅ ፓርለር ነበር፡፡ የፖሊስ ቃል አቀባዩ ካፕቴይን ጄይ ቤከር ሁለት ሰዎች በቦታው መሞታቸውንና ሶስት ሰዎች ደግሞ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልፀዋል። ሆስፒታል ውስጥ ሌሎች ሁለት ሰዎች እንደሞቱ ተናግረዋል፡፡ ከተጎጂዎቹ ሁለቱ የእስያ ዝርያ ያለባቸው ወንድ እና ሴት መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ሌላ የሂስፓኒክ ዝርያ ያለበት ግለሰብ መቁሰሉን ተናግረዋል። ከአንድ ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በሰሜን ምስራቅ አትላንታ በሚገኘው ጎልድ ስፓ "ዝርፊያ እየተካሄደ ነው" በሚል ፖሊስ መጠራቱን ገልጿል። ፖሊስ በሪፖርቱ እንደገለጸው "ፖሊሶች በቦታው በደረሱበት ወቅት የሞቱ ሶስት ሴቶች ተገኝተዋል፡፡ ከመንገዱ ባሸገር በሚገኘው የአሮማቴራፒ ስፓ የተጠሩት ፖሊሶች የተገደለች ሌላ ሴት አግኝተዋል፡፡ የአትላንታ ጆርናል-ኮንስቲትዩሽን፣ ፖሊስን ጠቅሶ እንዳስታወቀው አራቱ የአትላንታ ተጠቂዎች የእስያ ዝርያ ያላቸው ሴቶች ናቸው፡፡ መርማሪዎች በአንዱ ስፓ አቅራቢያ የተቀረጸን የተጠርጣሪ ምስል ለቅቀዋል፡፡ በጆርጂያ ጆርጅ ዉድስቶክ ነዋሪ የሆነው ሮበርት አሮን ሎንግ ከአትላንታ በስተደቡብ 240 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ክሪስፕ ካውንቲ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ካፕቴን ቤከር እንዳሉት በሦስቱም ግድያዎች ተጠርጣሪው ተመሳሳይ ግለሰብ እንደሆነ መርማሪዎች በጣም እርግጠኞች ናቸው፡፡ ምላሹ ምን ነበር? ተጎጂዎቹ በዘር ወይም በጎሳ ምክንያት የተለዩ ስለመሆናቸው ለማወቅ ምርመራው ገና መሆኑን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል፡፡ ኤሺያን አሜሪካንስ ኤንድ ፓስፊክ አይስላንደርስ የተባለው ተሟጋች ቡድን በበኩሉ "ሊገለጽ የማይችል አሳዛኝ አደጋ" ብሎታል፡፡ "በአሁኑ ወቅት በእስያ አሜሪካዊያን ማህበረሰብ ውስጥ መፍትሄ ሊበጅለት የሚገባው ከፍተኛ ፍርሃትና ህመም አለ" ሲል በትዊተር ገፁ አስፍሯል፡፡ የአትላንታ ፖሊስ ጥቃት ከተሰነዘረባቸው ጋር ተመሳሳይ በሆኑ የንግድ ተቋማት ዙሪያ የጥበቃ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የጆርጂያው ገዥ ብራያን ኬምፕ ለጉዳዩ ምላሽ የሰጡትን የህግ አስከባሪዎች አመስግነው "ለዚህ ዘግናኝ ድርጊት ሰለባዎች እየጸለይን ነው" ብለዋል፡፡ የኒው ዮርክ ፖሊስ መምሪያ የፀረ-ሽብርተኝነት ክፍል በበኩሉ "በከተማው ባሉ ታላላቅ የእስያ ማህበረሰቦቻችን ዙሪያ ለጥንቃቄ ሲባል ኃይል ያሰማራል" ብሏል፡፡
news-48376621
https://www.bbc.com/amharic/news-48376621
በአሜሪካ ድንበር፡ ያነጋገረው የስድስት ስደተኛ ሕጻናት ሞት
ከኤል ሳልቫዶር የመጣችው የ10 ዓመቷ ታዳጊ በአሜሪካ የስደተኞች ማቆያ ውስጥ ባለፈው ዓመት ነበር ሕይወቷ ያለፈው። ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ በአሜሪካ የድንበር ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ስድስት ሕፃናት ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ታዳጊዋ የልብ ሕመም ያለባት ሲሆን ባለፈው መስከረም ወር ናብራስካ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላት ሕይወቷ አልፏል። ታዳጊዋ በቴክሳስ ሳን አንቶኒዮ ስደተኞች ካምፕ የገባች መሆኗን የጤናና የደህንነት አገልግሎት ክፍል ቃል አቀባይ ማርክ ዌበር በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በክፍሉም የጤና ክትትል ሲደርግላት ነበር። • በገላን አሰሪዋን በዘነዘና የደበደበችው እየታደነች ነው ምንነቱ ያልተገለፀው የቀዶ ሕክምና የተደረገላት ሲሆን ከዚያ በኋላ ለተጨማሪ የጤና ችግር ተዳርጋለች፤ በግንቦት ወር ከሆስፒታል ከወጣች በኋላም ወደ አሪዞና የህፃናት ማቆያ ተዛውራለች። መስከረም ወር ላይ ለቤተሰቦቿ እንድትቀርብ በሚል ምክንያት ከዚያ ወጥታ ወደ ናብራስካ የህፃናት ማቆያ ተልካለች። በከፍተኛ ትኩሳትና የአተነፋፈስ ችግርም ከሦስት ቀናት በኋላ ሕይወቷ እንዳለፈ ዌበር ተናግረዋል። • በሳዑዲ አረቢያ 3ሺህ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች አሉ ተባለ ባላሰልጣናቱ መሞቷን ይፋ ማውጣት ያልፈለጉ ሲሆን ከአውሮፓውያኑ 2010 ወዲህ ሕፃን ስደተኛ በአገሪቱ የስደተኞች ማቆያ ሕይወቱ ሲያልፍ ታዳጊዋ የመጀመሪያዋ ናትም ተብሏል። የታዳጊዋ ስም እና ድንበር ተሻግራ እንዴት ወደ አሜሪካ እንደገባች የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ዲሞክራቶች የሞቷን ምክንያት ለማጣራት ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ባሳለፍነው ሰኞም ከጓቲማላ የመጣው የ16 ዓመቱ ሕፃን በቴክሳስ በሚገኘው ማቆያ ውስጥ ሕይወቱ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን ጉዳዩ ተሸፋፍኖ ቀርቷል። ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካና ሜክሲኮን ድንበር አልፈው ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሕገወጥ ስደተኞች ላይ ቁርጠኛ ውሳኔ ካሳለፉ በኋላ ድንበሩን ለማቋረጥ የሚሞክሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። • የዓለማችን 'ጭንቀታም' እና 'ደስተኛ' ሃገራት ደረጃ ይፋ ሆነ ከባለፈው ጥርና ሚያዚያ ወር ብቻ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ከ300 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ቁጥሩም ከወር ወር እየጨመረ ነው። ባለሥልጣናቱ ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣቱ መሠረታዊ ፍላጎታቸውን እንኳን ማሟላት እንዳልቻሉ ገልፀው ስደተኞቹ በአብዛኛው ከጓቲማላ፣ ሆንዱራስ እና ኤል ሳቫዶር የሚመጡ ናቸው ብለዋል። ብዙዎቹም ስደተኞች በግጭትና በድህነት ምክንያት አገራቸውን ጥለው የወጡ ሲሆን በአሜሪካ ጥገኝነት የሚፈልጉ ናቸው።
news-57251127
https://www.bbc.com/amharic/news-57251127
በፖሊስ ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ ሄሊኮፕተር ተከራይቶ እጁን ሰጠ
በኒው ዚላንድ የገጠር አካባቢ ተደብቆ በፖሊስ ሲታደን የነበረው ግለሰብ ወደ'ሚፈለግበት ፖሊስ ጣቢያ የሚያደርሰው ሄሊኮፕተር ተከራይቶ እጁን ሰጠ።
ብርያንት እጁን ለመስጠት ሄሊኮፕተር ተከራይቶ የሄደባት ከተማ ጀምስ ብሪያንት በሰው ላይ በፈጸመው ጥቃት በተከፈተበት ክስ በኒው ዚላንዷ ትንሽ ከተማ ሰሜን ኦታጎ ውስጥ ከፖሊስ ተሰውሮ ለአምስት ሳምንታት መቆየቱ ተነግሯል። እጁን ከሰጠ በኋላ ለአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደተናገረው ተደብቆ የቆየበትን ጊዜ "ባጣም ጥሩ" እንደነበር ተናግሮ፤ ነገር ግን "ምንም ነገር ከሌለበት ስፍራ" ለመውጣት ዝግጁ ስለነበረ ፈልገው ሊያገኙት ወዳልቻሉት ፖሊሶች በፈቃዱ መምጣቱን ገልጿል። ተፈላጊው ብርያንት በሰላም እጁን እንዲሰጥ ያግባባው የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተለው አርተር ቴይለር እንዳለው፤ ግለሰቡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከመግባቱ በፊት የምግብና የመጠጥ ግብዣ አድርጎለታል። በገዛ ፈቃዱ እጁን የሰጠው ተፈላጊው ብርያንት የቀረቡበት ክሶች በጦር መሳሪያ ጥቃት መፈጸም፣ ሆን ብሎ ጉዳት ማድረስና ጎጂ የዲጂታል መልዕክቶችን ማስተላለፍን ይጨምራል። ፖሊስ ብርያንን ለመያዝ እያፈላለገው በነበረበት ጊዜ ለነዋሪዎች ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ ግለሰቡ አደገኛና ማንም እንዳይቀርበው ብሎ ነበር። ተጠርጣሪው ለአካባቢው ጋዜጣ እንደተናገረው ከፖሊስ ተሰውሮ በቆየበት ጊዜ ጊዜውን ዮጋ በመስራት ያሳልፍ እንደነበር አመልክቶ፤ በመጨረሻም ለኅብረተሰቡ ደኅንነት አደገኛ መባሉ ስላሳሰበው እጁን ለመስጠት መወሰኑን ገልጿል። በዚህም ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሚያደርሰው ሄሊኮፕተር በገዛ ገንዘቡ ተከራይቶ "ለየት ባለ ሁኔታ" ለፖሊስ እጁን በመስጠት ታሪክ እንደሰራ ተነግሯል። ተፈላጊው በተከራየው ሄሊኮፕተር ከተደበቀበት ወጥቶ ያለምንም ግርግር ወደ ፖሊስ ጣቢያ በማምራት እጁን በመስጠት ለሳምንታት ሲፈልጉት የነበሩ ፖሊሶችን አሳርፏቸዋል።
news-52697069
https://www.bbc.com/amharic/news-52697069
በእስራኤል የቻይናው አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ
በእስራኤል የቻይናው አምባሳደር በቴል አቪቭ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
የ58 ዓመቱ አምባሳደር ዱ ዌ አልጋቸው ላይ ሕይወታቸው አልፎ የተገኘ ሲሆን ለሞታቸው ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የተባለ ነገር የለም። በቅርቡ የካቲት ወር ላይ የተሾሙት አምባሳደሩ ከዚህ በፊት ዩክሬን ውስጥ የቻይና ልኡክ ሆነው ሲሰሩ ነበር። •ታይዋን የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ወሳኝ ጉባኤ ላይ እንዳትሳተፍ ለምን ተደረገች? •"ለሃያ ዓመታት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስዘጋጅ ነበር" የንፅህና ሱሰኛው •በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ አምባሳደሩ የአንድ ልጅ አባት ሲሆኑ ባለቤታቸውም ሆነ ልጃቸው በአገር ውስጥ እንዳልነበሩ ተገልጿል። አምባሰደር ዱ በቴልአቪቭ ሄርዚሊያ በምትባል አካባቢ ነዋሪ ነበሩ። የእስራኤል ፖሊስ ቃለ አቀባይ ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ፖሊስ የሞቱበት ስፍራ ደርሶ ሁኔታውን እያየ መሆኑን ነው። የእስራሌል ቴሌቪዥን ጣቢያ ስሙ ካልተጠቀሰ የህክምና ምንጭ አገኘሁት ባለው መረጃ የመጀመሪያ ምርመራ እንደሚጠቁመው አምባሳደሩ በእንቅልፍ ላይ እንዳሉ በተፈጥሯዊ ሞት መሞታቸውን ነው። አምበሳደሩ ገና በእስራኤል በተሾሙበት ወቅት "በአለም ሁለተኛ ኢኮኖሚ ያላት ሃገር ቻይናና ገና ጀማሪዋ እስራኤል" ያላቸውን ግንኙነት ማድነቃቸውን በኤምባሲው ድረገፅ የወጣው ፅሁፍ አትቷል። በዚህ ሳምንት አርብም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ በእስራኤል ጉብኝታቸው ቻይና ወረርሽኙን የተቆጣጠረችበትን መንገድ መተቸታቸውን ተከትሎ ኤምባሲያቸው የሰላ አፀፋዊ ምላሽ ሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ ጀሩሳሌም ፖስት ባወጣው ፅሁፍ ላይ ቻይናና ወረርሽኙን ሸፋፍናለች የሚለውን ውንጀላ ኤምባሲው ማውገዙንም ተጠቅሷል።
50535121
https://www.bbc.com/amharic/50535121
መደመር፡ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መፅሐፍ ኬንያ ገብቷል
የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ "መደመር" መፅሐፍ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ተመርቋል።
ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ነው መፅሐፉን ያስመረቀው። ናይሮቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ኬንያውያን እንዲሁም የሌሎች ሃገራት ዲፕሎማቶች የምረቃ ስነ ስርአቱ ታዳሚዎች ነበሩ። መፅሐፉ እስካሁን ለገበያ የቀረበው በአማርኛና ኦሮምኛ በመሆኑ ከኢትዮጵያውያን ውጭ ሌሎች ዲፕሎማቶች መፅሃፉን ገዝተው ለማንበብ አልቻሉም። ቢሆንም የመፅሐፉን ይዘት በተመለከተ የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ባለሟሎች፤ አማካሪዎችና ሌሎችም የፌደራል መስሪያ ቤቶች የስራ ኃላፊዎች በእንግሊዝ አፍ ማብራሪያ ሰጥተዋል። መፅሐፉ አሁን ያለውን የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ለመቀየር አጋዥ ነው ይላሉ ማብራሪያ ሰጭዎቹ። ከዚህም በተጨማሪ መፅሐፉ ከተለያዩ እሳቤዎች ሃሳብ ያዋጣ በመሆኑ ሚናው በተግባር የሚለካ ለውጥ ለማምጣት ዕድል ይፈጥራል ባይ ናቸው። መፅሐፉ በናይሮቢ እንዲመረቅ ያስተባበሩት አምባሳደር መለስ አለም «ኬንያዊያን ጎረቤቶቻችን ሳይሆኑ ወንድሞቻችን ናቸው፤ ለዚህም ነው መፅሐፉን እዚህ እንዲመረቅ የሻትነው» ሲሉ ተደምጠዋል። «በአሁኑ ወቅት የሚገጥሙን ችግሮች ማንኛውም በለውጥ ሂደት ላይ ያለ አገር የሚገጥመው ችግር ነው» ያሉት አምባሳደሩ ይህንንም በቀላሉ ለማለፍ መደመር መፅሐፍ ድርሻ ይኖረዋል የሚል ሃሳብ አንስተዋል። መፅሃፋ በኢትዮጵያ በ13 ከተሞች ከሳምንታት በፊት መመረቁ ይታወሳል። ከአገር ውጭ ሲመረቅ ደግሞ ከአሜሪካ ቀጥሎ የናይሮቢው ፕሮግራም ሁለተኛው መሆኑ ነው። በናይሮቢው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት 'መደመር' መፅሐፍ ለገበያ የቀረበ ሲሆን 3 ሺህ የኬንያ ሺልንግ ወይም ደግሞ 30 የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለት ነበር። አሁን ባለው የውጭ ምንዛሪ ገበያ ወደ 890 ብር ገደማ ያወጣል። ነገር ግን በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ መፅሐፉን የሚገዙ ሰዎች ቁጥር እምብዛም መሆኑን ታዝቧል። ዋጋው መፅሐፉ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚሸጥበት በ3 እጥፍ የጨመረ መሆኑና መፅሐፉ በሃገር ውስጥ ቋንቋዎች ብቻ ለገበያ መቅረቡ ለሸመታው ማሽቆልቆል ምክንያት ሳይሆን አልቀረም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ አንባቢዎች የፓርቲ ማኒፌስቶ ሽታ አለው ሲሉ ከገመገሙት 'መደመር' ባሻገር፤ 'ዲርአዝ' በተሰኘ የብዕር ስም አራት የታተሙ ሁለት ያልታተሙ መጽሐፎች እንዳሏቸው መናገራቸው ይታወሳል።
news-41311556
https://www.bbc.com/amharic/news-41311556
ከድንበር ውዝግብ በኋላ ቻይናና ህንድ በውሃ ምክንያት ተፋጠዋል።
ቻይናና ሕንድ አሁንም ሊከሰት የሚችል የድንበር ጦርነትን ቢያረግቡም ፍጥጫው ግን ወደ ሌላ አከራካሪ አለመግባባት አምርቷል፤ ውሃ።
በየዓመቱ በዝናብ ወቅት ወንዙ በጣም ይሞላና በሰሜን ምስራቅ ሕንድ እና በባንግላዴሽ ትልቅ ኪሳራ ያስከትላል። በዚህ የዝናብ ወቅት በስምምነታቸው መሠረት ዴልሂ ከቻይና ስለ ብራሕማፑትራ ወንዝ ማግኘት የነበረባትን የሃይድሮሎጂ ማለትም የውሃ ደረጃ እንቅስቃሴና ስርጭትን የተመለከተ የሳይንሳዊ ጥናት መረጃ እንዳልተረከበች ተናግራለች። የእስያ ትልቁ ወንዝ የሆነው ብራሕማፑትራ ከቲቤት ተነስቶ ወደ ሕንድ ፈሶ ከዚያም ወደ ባንግላዴሽ በማምራት ከጋንጂዝ ጋር ተቀላቅሎ በቤንጋል ሠርጥ ያበቃል። ቤይጂንግ የሃይድሮሎጂ ጣቢያዎቹ ማሻሻያ እየተደረገላቸው በመሆኑ ምንም አይነት መረጃ ማቅረብ እንደማይቻል ኣሳውቃለች። ቢቢሲ እንደሚለው ግን ባንግላዴሽ ከብራሕማፑትራ ተፋሰስ የታችኛው ክፍል ላይ ያለች አገር ብትሆንም ከቻይና እስካሁን ድረስ መረጃ እየተቀበለች እንደሆነ ነው። ይህ የወንዝ መረጃ ጠብ በቻይናና በሕንድ መካከል በሂማላያ ድንበር ተነስቶ ለሁለት ወራት የቆየውን ፍጥጫ ተከትሎ የተከሰተ ነው። በቻይናና በሕንድ መካከል የነበረው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው። አለመተማምን የባንግላዴሽ የዉሃ ሀብቶች ሚኒስቴር አኒሱል ኢስላም ሞሃማድ አገራቸው ውሃን የተመለከተ መረጃዎችን ከቻይና እየተቀበለች እንደሆነ ለቢቢሲ ኣሳውቀዋል። ለሕንድ ግን ቻይና መረጃ የማካፈሉን ተግባር ድጋሚ ትቀጥላለች የሚለው ሃሳብ አጠራጣሪ ሆኖባታል። የቻይና ቃልአቀባይ የሆኑት ጌንግ ሽዋንግ "ይህን በተመለከተ ተገቢውን የሃይድሮሎጂ መረጃ መስጠት መቀጠል መቻል ወይም አለመቻላቸው ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የማሻሻያ ሥራ ሂደት ላይ ተወሰነ ነው።" ሕንድና ከቻይና ጋር ስለ ብራሕማፑትራ ወንዝ የፍሰት መረጃዎችን ለመቀበል ስምምነት ውስጥ ላይ የደረሰችው ከብዙ ዓመታት ጥረት በኋላ ነው። በድርቅ ወቅቶች ቻይና የብራሕማፑትራን ውሃ ወደ ደረቅ ክልሎችዋ ታዛውራለች ብለው ስለሚጠረጥሩ ዴልሂ የወንዙን ውሃ ፍሰት መረጃ ዝናብ በሌለበት ወቅትም እንዲሰጣት ጥያቄ አቅርባለች። ወንዙ ወደ ባንግላዴሽ ከመውረዱ በፊት ወደ ሕንድ ይፈሳል። ቤይጂንግ በወንዙ ላይ ብዛት ያላቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ ግድቦችን ገንብታለች። በመቀጠልም ውሃውን እንደማይገድቡ ወይም አቅጣጫ እንደማያስቀይሩና ከወንዙ በታች በኩል ያሉ አገራትን ፍላጎቶች እንደማይጻረሩ ተናግረዋል። በቅርብ ዓመታት በተለይም በሰሜን ምሥራቅ ሕንድ ውስጥ ቻይና በአንድ ጊዜ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ትለቃለች የሚል ፍራቻ አለ። ወንዙ ሰፊ ቦታን ለሚሸፍንባቸው አካባቢዎች አንዱ በኣሳም ሲሆን የዲበሩጋር ነዋሪዎችም የብራሕማፑትራ ውሃ መጠን በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምርና ሲቀንስ እንዳዩ መስክረዋል።
news-47607896
https://www.bbc.com/amharic/news-47607896
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ከኢንዶኔዢያው ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ተነገረ
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ የተገኘው የበረራ መረጃ አደጋው ባለፈው ጥቅምት ወር በኢንዶኔዢያ ባሕር ላይ ከተከሰከሰው አውሮፕላን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው እንደሚያመለክት የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ገለጹ።
አደጋው የገጠማቸው ሁለቱ አውሮፕላኖች ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት የተባሉ ሲሆኑ በደረሰባቸው አሰቃቂ አደጋ በውስጣቸው የነበሩ የሁሉም ተጓዦች ህይወት አልፏል። ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ይዟቸው የነበሩት 157 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። • የተከሰከሰው አውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ወደ ፈረንሳይ ተወሰደ • የካፕቴን ያሬድ ሃይማኖታዊ የሐዘን ሥርዓት ያለ አስከሬን ተፈፀመ የአውሮፕላኑ የበረራ መመዝገቢያ ሳጥኖች ወደፈረንሳይ ባለፈው ሳምንት ተወስደው የነበረ ሲሆን፤ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ የበረራ መረጃው ከአውሮፕላኑ የመረጃ ማስቀመጫ ክፍል ላይ በአግባቡ እንደተሰበሰበ ተናግረዋል። ከአውሮፕላኑ የተገኘውና አደጋው ስለደረሰበት አውሮፕላን ለሚደረገው ምርመራ ጠቃሚ መረጃ ይሆናል የተባለው የበረራ መረጃ ምርመራውን ለሚያከናውነው ቡድን መሰጠቱም ተገልጿል። ከተሰበሰበው መረጃም "በኢትዮጵያ እየር መንገድ አውሮፕላን ላይ የደረሰው አደጋ ከወራት በፊት በኢንዶኔዢያው ተመሳሳይ አውሮፕላን ላይ ከደረሰው አደጋ ጋር ግልፅ መመሳሰል ታይቷል" ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። • ለ60 ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የቦይንግ ግንኙነት • "አደጋውን ስሰማ በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ" የረዳት አብራሪው ጓደኛ የበረራ መመዝገቢያ መረጃ እንደሚያመለክቱት በሁለቱም የአውሮፕላን አደጋዎች ላይ ድንገተኛ የከፍታ መለዋወጥ እንደታየ፤ ይህም አውሮፕላኖቹ ያልተጠበቀ ከፍና ዝቅ የማለት ተመሳሳይ አጋጣሚዎች እንደተስተዋለባቸው ተገልጿል። የኢትዮጵያ የምርመራ ባለሙያዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደሃገራቸው እንደሚመለሱና ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚቻል ጠቁመው፤ "የመጀመሪያ ደረጃ የምርመራው ውጤት በ30 ቀናት ውስጥ ይፋ ይሆናል" ብለዋል ሚኒስትሯ። የቦይንግ ኩባንያ ሊቀመንበርና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዴኒስ ሙሊንበርግ እንደተናገሩት ድርጅታቸው በአውሮፕላን አደጋው ዙሪያ በሚደረጉ ምርመራዎች ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። • "የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ ከድርጅቱ በወጣው መግለጫ ላይ ሥራ አስፈጻሚው እንዳመለከቱት በአውሮፕላኑ ውስጥ ያለውን የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት የሚመራውን ሶፍትዌር ለማሻሻል እየሰራ እንደሆነም ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ምን ገጠመው? የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 302 መጋቢት 01 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ከአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ በመነሳት ናይሮቢ ለመድረስ ነበር ዕቅዱ። አውሮፕላኑ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አብራሪው ችግር እንደገጠመው አመልክቶ ተመልሶ እንዲያርፍ ጠየቀ። በአየር ሁኔታ ምክንያት ዕይታን የሚያስቸግር ነገር አልነበረም የሚለው የአየር ትራንስፖርት እንቅስቃሴን የሚከታተለው ፍላይትራዳር24 "አውሮፕላኑ ከተነሳ በኋላ ወደላይ የሚወጣበት ፍጥነት የተረጋጋ አልነበረም" ብሏል። አደጋው በተከሰተበት ስፍራ ነበርኩ ያለ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ እንደተናገረው አውሮፕላኑ መሬት ላይ ሲወድቅ ከባድ እሳት ተፈጥሮ ነበረ። የፈረንሳይ የአየር ትራንስፖርት ደህንነት መርማሪዎች የአውሮፕላኑን የበረራ መረጃ መመዝገቢያንና የበረራ ክፍል የድምጽ መቅጃን በመመርመር ያገኙትን ምርመራውን ለሚያከናውኑት የኢትዮጵያ ባለሙያዎች አስረክበዋል። በኢንዶኔዢያው አውሮፕላን ላይ ምን ተከሰተ? ጥቅምት 19/2011 ዓ.ም የላየን ኤር በረራ 610 ከኢንዶኔዢያዋ መዲና ጃካርታ ከተነሳ በኋላ በመከስከሱ የ189 ሰዎች ህይወት አልፏል። በኋላ ላይ የአደጋ መርማሪዎች እንደደረሱበት አውሮፕላኑ ሽቅብ በጣም ከፍ ወዳለ አቅጣጫ እንዳይወጣ የሚቆጣጠረው የአውሮፕላኑ ሥርዓት ላይ ችግር እንደነበረበት አመልክተዋል። በዚህም ሳቢያ በዚህ በረራ ወቅት የመቆጣጠሪያ ሥርዓቱ በተደጋጋሚ አውሮፕላኑን ወደታች እንዲያዘቀዝቅ ያደርገው ነበር ተብሏል። የአውሮፕላኑ የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ወደታች እንዲያዘቀዝቁ ከማድረጉ በፊት አብራሪዎቹ ይህንን ችግር የአውሮፕላኑን አፍንጫ ወደላይ ከፍ በማድረግ ለማስተካከል ጥረት አድርገዋል። ይህም በአውሮፕላኑ ላይ ከሃያ ጊዜ በላይ እንደተከሰተ ተገልጿል። የኢንዶኔዢያው አውሮፕላን ከተከሰከሰ ከወራት በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ያሉ አየር መንገዶች ያሏቸውን ቦይንግ ማክስ ኤይት አውሮፕላኖችን ከበረራ ውጪ አድርገዋል።
news-55012343
https://www.bbc.com/amharic/news-55012343
ትግራይ፡ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልል እና በዞን ደረጃ አዲስ አመራሮች እንደሚሾም አስታወቀ
በትግራይ ክልል እንዲቋቋም የተወሰነው ጊዜያዊ አስተዳደር ከተሰጡት ኃላፊነቶች አንዱ በክልሉ ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ማስቻል መሆኑ ተገለጸ።
ዶ/ር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት ሙሉ ነጋ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ በትግራይ ክልል ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ይደረጋል ብለዋል። "ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ኃላፊነቶች አንዱ በምርጫ ቦርድ መርህ መሠረት በክልሉ ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ እንዲከናወን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው። ሕዝቡ በነፃነት መሪዎቹን ይመርጣል" ብለዋል። በተጨማሪም ጊዜያዊ አስተዳደሩ የክልሉን አስተዳደር መልሶ እንደሚያዋቅር ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። "ህወሓት ሕገ ወጥ ምርጫ ነው ያካሄደው። ይህም በፌደሬሽን ምክር ቤት እውቅና አልተሰጠውም። ስለዚህም የክልሉ ምክር ቤት እውቅና የለውም። በክልሉ አመራር ደረጃ ያለውም እውቅና የለውም" ብለው፤ በክልል እና ዞን ደረጃ አዲስ አመራሮች እንደሚሾሙ አስረድተዋል። የመሠረተ ልማት አገልግሎት የሚሰጡ የወረዳ እና ቀበሌ መዋቅሮች ግን ባሉበት ይቀጥላሉ። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለክልሉን እቅድና በጀት ፍቃድ የመስጠት፣ ሕግና ደንብን የማስከበር እንዲሁም የክልሉን ነዋሪዎች መብት የማስጠበቅ ኃላፊነት እንደተሰጠው ተገልጿል። "አስተዳደሩ እነዚህን ኃላፊነቶች እንዴት እንደሚተገብር ረቂቅ እየነደፈ ነው። የአስተዳደር መዋቅሩ ሲለወጥ ምን መርህ መከተል አለበት የሚለው በረቂቁ ይካተታል" ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሙሉ (ዶ/ር)። በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ሲመረጡ እና ሌሎች ሂደቶች ሲከናወኑን ሕዝቡን እንደሚያማክሩ አያይዘው ገልጸዋል። በክልሉ ሰላም፣ መረጋጋትና ጸጥታ ማስፈን ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ሲሉም ተናግረዋል። "ሌላው ኃላፊነት ፍትሕ ማስፈን ነው። የትግራይ ሕዝብ ፍትሕ እና መልካም አስተዳደር በማጣት ተሰቃይቷል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህ እንዲለወጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል" ብለዋል። በሌላ በኩል በግጭቱ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን ለመመለስ ከፌደራል ተቋሞችና የሰብዓዊ እርዳታ ሰጪዎች ጋር እንደሚሠሩ አስረድተዋል። ትምህርትን ጨምሮ ሌሎችም ማኅበራዊ አገልግሎቶች በአግባቡ እንዲሰጡ እንደሚያደርጉና በክልሉ የፖለቲካ ምህዳሩን እንደሚያሰፉም ተናግረዋል። "ጠባብ የፖለቲካ ምህዳርና ዴሞክራሲ ማጣት የክልሉ ችግሮች ነበሩ። የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ሁሉንም የክልሉን ፓለቲካዊ ፓርቲዎች እናሳትፋለን" ሲሉ ገልጸዋል። በትግራይ ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ሰላም ማውረድ እንደሚሹም ጠቁመዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ሌላው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ኃላፊነት "የፖለቲካ እስረኞችን ጉዳይ የሚመረምር ግብረ ኃይል አቋቁመን እንዲለቀቁ ማድረግ ነው" ብለዋል። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በትግራይ ውስጥ በነበረው ሠራዊቱ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ሕግን ማስከበር ባለው ውሳኔ በክልሉ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ መ፥ጀመሩን ተከትሎ በትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉ ይታወሳል። በተጨማሪም የአገሪቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የነበረውን የትግራይ ክልል መስተዳደር ሕገወጥ በማለት ከበተነው በኋላ አዲስ ጊዜያዊ አሰተዳደር እንዲመሰረት መወሰኑ ይታወሳል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ክልልን በሚመለከት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚሰራ ሲሆን፤ በአሁኑ ጊዜ በመንግሥት ሠራዊት በተያዙ አካባቢዎች ያለውን መዋቅር ለማቋቋም ጥረት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
news-54384336
https://www.bbc.com/amharic/news-54384336
የአውሮፓ ሕብረት ቱርክ ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ሲል አስጠነቀቀ
የአውሮፓ ሕብረት ቱርክ በምስራቅ ሜደትራኒያን ከግሪክ ጋር እየፈጠረችው ባለችው “ጠብ አጫሪ እንቅስቃሴ እና ጫና” ምክንያት ማዕቀብ ልጥልባት እችላለሁ ሲል አስጠነቀቀ።
ቱርክ እና ግሪክ በምስራቅ ሜደትራኒያን በባህር ድንበር እና የኃይል ምንጭ ጋር በተያያዘ አለመግባባት ውስጥ ከገቡ ሰነባብተዋል። የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደነት ኡራሱላ ቮን ደር ላየን ቱርክ በምስራቅ ሜደትራኒያን እየወሰደች ካለችው የአንድ ወገን እርምጃ መቆጠብ አለባት ሲሉ አሳስበዋል። ቱርክ በፈረንጆቹ 2020 መጀመሪያ ላይ የነዳጅ ክምችት ለማሰስ የይገባኛል ጭቅጭቅ ወደሚያስተናግደው ምስራቅ ሜደትራኒያን መርከብ መላኳን ተከትሎ በቱርክ እና በግሪክ መካከል ውጥረት ኃይሏል። ግሪክ እና ቱርክ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን- ኔቶ አባላት ቢሆኑም በድንበር እና የውሃ ክፍል ይገባኛል በሚሉ ምክንያቶች በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ይገባሉ። የአውሮፓ ሕብረት የአባል አገር ለሆነችው ግሪክ ድጋፉን ሲግልጽ ቆይቷል። የአውሮፓ ሕብረት ፕሬዝደንቷ በብራሰልስ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ የአውሮፓ ሕብረት ከቱርክ ጋር መልካም እና ገንቢ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረው ይሻል፤ በዚህ ደግሞ ትልቁ ተጠቃሚ የቱርክ መንግሥት ነው ብለዋል። ቱርክ በቀጠናው እየፈጠረች ያለችውን ጫና እና ከጠብ አጫሪ እንቅስቃሴዋ የማትቆጠብ ከሆነ፤ የአውሮፓ ሕብረት ያሉትን ሌሎች አማራጮች ይመለከታልም ብለዋል። የሕብረቱ አባል አገራት መሪዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ቱርክ ከዚህ እንቅስቃሴዋ የማትቆጠብ ከሆነ ማዕቀብ እንዲጣልባት መስማማታቸው ተጠቁሟል። የኦስትሪያው ቻንስለር ሴባስቲያን ኩርዝ በትዊተር ገጻቸው ቱርክ ዓለም አቀፍ ሕጎችን መተላለፍ የምትቀጥል ከሆነ ሕብረቱ ማዕቀብ ይጥላል ብለዋል። ቱርክ እና የአውሮፓ ሕብረት ከዚህ ቀደምም መልካም የሚባል ግነኙነት የላቸውም። ቱርክ የሕብረቱ አባል ለመሆን ለዓመታት ጥረት ስታደርግ የቆየች ቢሆንም ጥረቷ ግን ፍሬ ሳያፈራ ዓመታት አልፈዋል። ሕብረቱ ቱርክ የሰብዓዊ መብት ጥስት ተፈጽማለች ይላል። በተለይ እአአ 2016 የረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን መንግሥትን ለመፈንቀል ሞክረዋል ተብለው በተወነጀሉ ሰዎች ላይ ቱርክ የወሰደችው እርምጃ ከሕብረቱ ጋር ቅራኔ ውስጥ ከትቷታል። ቱርክ ምንም እንኳ ከሕብረቱ ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት ባይኖራትም ለአውሮፓ ሕብረት አገራት ወሳኝ አገር ሆና ቆይታለች። ቱርክ መዳረሻቸውን አውሮፓ ማድረግ የሚሹ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች ይዛ ትገኛለች። ሰደተኞች ወደ ግሪክ እንዳይሻገሩ ይዛ ለመቆየትም ቱርክ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ከስምምነት ደርሳለች።
news-48429702
https://www.bbc.com/amharic/news-48429702
የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር የኮሎኔል መንግሥቱን ልደት ሊያከብር ነው
የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር የደርግ ሊቀመንበር ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ልደትና የምስጋና ፕሮግራም በመጪው ሰኞ ሰኔ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ሊያሰናዱ መሆናቸውን የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጆኒ መርጊያ ለቢቢሲ ገለፀዋል።
"ከዚህ በፊት ልደታቸውን በይፋ አክብረን አናውቅም" የሚሉት አቶ ጆኒ ዘንድሮ ለማክበር የማህበሩን አባላት ያነሳሳውን ጉዳይ ይገልፃሉ። ነገሩ ወዲህ ነው፤ ከወር በፊት አንድ በህፃናት አምባ ያደገና የማህበሩ አባል ኮሎኔሉን ለማግኘት እርሳቸው በስደት ወደ ሚኖሩበት ዚምባብዌ ለማቅናት ይነሳል። ግለሰቡ ስሙ እንዲጠቀስ ባይፈልግም አካሄዱ ግን እርሳቸውን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ነበር። • የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ • የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ ያሰበውም አልቀረ ታዲያ ወደ ዚምባብዌ ተሻገረ። ምንም እንኳን ኮሎኔሉን ለማግኘት ቁጥጥሩና ጥበቃው ጥብቅ ቢሆንም በወንድማቸውና እዚያው ዚምባብዌ በሚኖር አንድ የህፃናት አምባ ልጅ አማካኝነት ፈቃድ ማግኘት እንደቻሉ የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጆኒ ይገልፃሉ። ታዲያ የማህበሩ አባላት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ለእርሳቸው የሰላምታ ደብዳቤ ለመላክና በደብዳቤያቸው ላይም በትክክል የተወለዱበትን ቀን እንዲነግሯቸው ለመጠየቅ አሰበ። አቶ ጆኒ የልደት ቀናቸውን የጠየቁበትን ምክንያታቸውን ሲያስረዱም "የኮሎኔሉ የልደት ቀንና ከአገር የወጡበት ቀን ተመሣሣይ ነው፤ እርሱም ግንቦት 13 ቀን ነው የሚሉ መረጃዎች ይወጡ ስለነበር ትክክለኛ የልደት ቀናቸውን ለማወቅ ነው" ብለዋል። "ልደታቸውን ስናከብር እናስታውሳቸዋለን ብለን እንጂ ለምርምር ፈልገነው አይደለም" ሲሉም ያክላሉ። የማህበሩ ኮሚቴ ለኮሎኔሉ የፃፉት ደብዳቤ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ይዘት የለውም የሚሉት አቶ ጆኒ ደብዳቤው ልጅ ለአባቱ የሚፅፈው ዓይነት እንደሆነ አስረድተዋል። • ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት በመሆኑም ደብዳቤው ስለ ደህንነታቸውና ስለ ልጆቻቸው ሁኔታ የጠየቁበት፣ ቤተሰባዊ ሰላምታ ያቀረቡበትና የልደት ቀናቸውን የጠየቁበት እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ጆኒ እንደገለፁልን ከደብዳቤው ጋር ባህላዊ የአልጋ ልብስ፣ ግድግዳ ላይ የሚሰቀል የመስቀል ቅርፅ ያለበት ጌጥ እና ለባለቤታቸው ውብአንች ቢሻውና ለእርሳቸው የሚሆን ባህላዊ ፎጣ ስጦታም ልከውላቸዋል። እርሳቸውም እንደ አባት ምላሻቸውን እንደላኩላቸው አቶ ጆኒ ነግረውናል። በምላሹ በላኩላቸው ደብዳቤ ላይም በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳሉ፣ የተጋነነ የጤንነት ችግር እንደሌለባቸው፣ በልጆቻቸው እንደተባረኩ፣ አምስት የልጅ ልጆች እንዳዩ፣ ሁል ጊዜ ስለ ሃገራቸው እንደሚያስቡና ሃገራቸውን እንደሚናፍቁ የሚገልፅ አጭር ደብዳቤ ፅፈውላቸዋል። በደብዳቤው መጨረሻ ላይም "የተወለድኩት፡ በአዲስ አበባ ፡ እንደኢትዮጵያ፡ አቆጣጠር፡ በ1933.ዓ.ም፡ ግንቦት አስራዘጠኝ ቀን፡ነው።" ሲሉ በደብዳቤያቸው ላይ እንዳሰፈሩ አቶ ጆኒ ገልፀዋል። ከኮሎኔል መንግሥቱ የተላከላቸው ደብዳቤ ማህበሩ ቢሮ እንዳለውና እንደሌለው በመጠየቅም ቢሯቸው ላይ የሚያስቀምጡት የአፍሪካ ካርታ ያለበት ሰዓት ከደብዳቤያቸው ጋር ልከዋል። ይህ ብቻም ሳይሆን የእርሳቸው ፊርማ ያረፈበት፣ 'ለህፃናት አምባ ልጆች'፤ መልካም ንባብ' የሚል ፅሁፍ ያለበት የመጀመሪያ መፅሃፋቸውን አክለዋል። "በዋነኛነት እንደ ልጆች የሚሰሙን ነገሮች አሉ፤ በእርሳቸው ጊዜ በነበረው ሥርዓት ያልተገቡ ነገሮች ተከናውነዋል፤ ነገር ግን በዘመኑ በጣም ጥሩ ሥራዎችንም ሰርተዋል" የሚሉት አቶ ጆኒ ባለፈው ሥርዓት በአጠቃላይ ደርግ በሚል መንፈስ የእርሳቸው ሥራ መጥፎነት ነው የተሳለው ይላሉ። በመሆኑም የህፃናት አምባ ልጆች ማህበር እርሳቸው በዘመኑ ከሰሯቸው በጎ ሥራዎች መካካል አንዱ የህፃናት አምባን ማቋቋም መሆኑን በመጥቀስንና መሰል ሥራዎችን በማንሳት የልደትና የምስጋና ፕሮግራም ለማዘጋጀት አስቧል። • ከማደጎ ልጅነት ወደ እውቅ ገጣሚና የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ሃላፊነት ግንቦት 18/2011 ዓ.ም የተወሰኑ የህፃናት አምባ ልጆች በግል በነበራቸው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ የኮሎኔሉን ልደት ያካበሩ ቢሆንም ዋናው ማህበር በመጭው ሰኞ ሰኔ 2 ቀን/2011 ዓ.ም ፕሮግራሙን ለማካሄድ እንዳቀደ አቶ ጆኒ መርጊያ ነግረውናል። "በፕሮግራሙ ላይ እንደማንኛውም ልደት ኬክም ዳቦም ይኖራል፤ በዘመኑ የነበሩ ሰዎችንና ሌሎች እንግዶችን ጋብዘን ሞቅ አድርገን ለማክበር ነው ያሰብነው" ብለዋል። ፕሮግራሙ የሚካሄድበትን ሰዓትና ቦታ ጊዜው ሲቃረብ እንደሚገልፁ ተናግረዋል። በአጠቃላይ በህፃናት አምባ ያደጉ ልጆች ቁጥራቸው ከ7 ሺህ በላይ ሲሆኑ አዲስ አበባ የሚገኙና የማህበሩ አባል የሆኑ ልጆች ቁጥር ስድስት መቶ እንደሚሆን የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጆኒ ለቢቢሲ ገልፀዋል። የህፃናት አምባ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ክፍለ ሃገር ሀይቆችና ቡታጂራ አውራጃ፤ አላጌ በሚባል አካባቢ የተቋቋመ ሲሆን ወላጆቻቸውን በጦርነትና በሌሎች ምክንያቶች ያጡ ህጻናትን ተቀብሎ የማሳደግ ዓላማ ነበረው። ህፃናት አምባው 'ሰብለ አብዮት'፣ መስከረም ሁለት፣ ኦጋዴን፣ ዘርዓይ ደረስ እና መንግሥቱ ኃይለማሪያም የተባሉ 5 መንደሮችም ነበሩት።
news-54460664
https://www.bbc.com/amharic/news-54460664
ኮሮናቫይረስ፡ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን በአካላዊ ርቀት ምክንያት ለማፅናናት ያልቻለው ግለሰብ
በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን ለማፅናናት አቅፏት የነበረው እንግሊዛዊ አካላዊ ርቀትህን ጠብቅ መባሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳበሳጨው ገልጿል።
ክሬይግ ቢክኔል ከሟች አባቱ ጋር አለን ራይት ጋር ክሬይግ ቢክኔል ይህ የተነገረው ክራውንሂል በተባለው የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ሰራተኛ ነው። ክሬይግም ሆነ ወንድሙ ወንበራቸውን ራቅ አድርገው እንዲቀመጡ ከመንገር በተጨማሪም የኃዘን ስነ ስርአቱም እንዲቋረጥ ተደርጓል። በኃዘን ልቧ ተሰብራ ከነበረው እናቱ ጎን ተቀምጦም በማፅናናትም ላይ እንደነበረ ተናግሯል። የሚልተን ኬይንስ ምክር ቤት በበኩሉ በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑንና ለወደፊቱም የተሻለ አማራጭ እንጠቀማለንም በማለት ምላሽ ሰጥቷል። የ43 አመቱ ክሬይግ በበኩሉ "እናቴን ማፅናናት እንደምፈልግ ለሁሉም ተናግሬ ነበር። በከፍተኛ ሁኔታ ሃዘኗም ጨምሮ ስብርብር ስትል አቀፍኳት" ብሏል። በአባቱ የኃዘን ስርአት ላይ ወንበሮቹ አካላዊ ርቀትን በሚያስጠብቅ መልኩ ተራርቀው የነበረ ሲሆን የናቱንም የበረታ ኃዘንም ተመልክቶ ወደናቱ የተጠጋ ሲሆን ወንድሙም ተከትሎት እናታቸውን ማፅናናት ጀመሩ። የቀብር አስፈፃሚ ሰራተኞቹም ወንበሮቹን በየቦታቸው እንዲመልሱና ማንቀሳቀስ አትችሉም ተብለዋል። በዚህ ሃዘን ላይ እያሉ እንዲህ መባላቸው ከፍተኛ ንዴትና ሃዘን እንደፈጠረበትም ገልጿል። "በከፍተኛ ሁኔታ የባዶነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል" ያለው ክሬይግ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልና በሰላም እንዲጠናቀቅም ከራሱ ጋር ትግል ማድረግ ነበረበት። "ፈታኝ ነበር። የአባቴ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልም ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረብኝ" ያለው ክሬይግ አክሎም "በጣም ያዘንኩበትና የፈራሁበትም ወቅት ነው፤ እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም" ብሏል። የሚልተን ኬይነስ ምክር ቤት በበኩሉ ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ሁኔታ ተፈፅሞ እንደማያውቅና ቤተሰቡንም በማሳዘናቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የኃዘንም ሆነ የቀብር አስፈፃሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ሰብሰብ ብለው ቢቀመጡም ችግር እንደሌለው ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በኃዘንም ሆነ በቀብር ስርአት ላይ መገኘት ያለባቸው 30 ሰዎች መሆናቸው በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ሲሆን እነሱም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆኑንም አስፍሯል።
news-49457667
https://www.bbc.com/amharic/news-49457667
ዋናተኞችን አዞ ሲቀርባቸው የሚጠቁም ድሮን ተሠራ
ዋናተኞች አቅራቢያ አዞ መኖሩን የሚጠቁም ድሮን መፈጠሩ ተሰምቷል።
'ሊትል ባይ ሊትል ሪፐር ግሩፕ' የተበለ የአውስትራሊያ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፤ አዞን ጨምሮ 16 የባህር ውስጥ እንስሳትን ለዋናተኞች የሚጠቁም ድሮን (አነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላን) አስተዋውቋል። 93 በመቶ አስተማማኝ ነው የተባልው ድሮኑ፤ በዋናተኞች ቅርብ ርቀት የባህር እንስሳት እንደሚገኙ በድምፅ ይጠቁማል፤ የአደጋ ጊዜ መንሳፈፊያም ያቀብላል። • የኢትዮጵያ አዞ ቆዳና ሥጋ ገበያ አጥቷል • ከአዞዎች ጋር ለ30 ዓመታት የኖሩት ኢትዮጵያዊ • ከአዞዎች ጋር ለ30 ዓመታት የኖሩት ኢትዮጵያዊ ሊቨርፑል ጆን ሞረስ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩት ዶ/ር ሰርጌ ዊች ድሮኑን "ድንቅ ሀሳብ" ሲሉ አሞካሽተውታል። መምህሩ፤ ድሮን ለመልካም ነገር በመዋሉ የተሰማቸውን ደስታ ሳይገልጹም አላለፉም። "ድሮን የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ መዋሉ በጎ ነገር ነው" ብለዋል። የድሮኑን አምራች ድርጅት ከመሰረቱት አንዱ የሆነው ፖል ስከሊ-ፓወር እንዳለው፤ አዞዎች በደፈረሰ ውሃ ውስጥ በመሽሎክሎክ ከዕይታ ለመሰወር ቢሞክሩም ድሮኑ በቀላሉ ይይዛቸዋል።
news-56040685
https://www.bbc.com/amharic/news-56040685
የአየር ብክለት፡ ስድስት ሚሊየን እንግሊዛውያን ከባድ የሳምባ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል ተባለ
እድሜያቸው ከ65 በላይ የሆኑ ወደ ስድስት ሚሊየን የሚጠጉ እንግሊዛውያን ከባድ ለሆነ ሳምባ ጉዳትና አስም ሊጋለጡ እንደሚችሉ አንድ አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ምክንያቱ ደግሞ የተበከለ አየር ነው ተብሏል።
በጥናቱ መሰረት እድሜያቸው የገፉ ሰዎችና ከዚህ ቀደም የመተንፈሻ አካላት በተለይ የሳምባ ችግር ያለባቸው ሰዎች በአየር ብክለት ጉዳት የሚደርስባቸው ሲሆን በተጨማሪ ደግሞ ከሌሎች በተለየ ተጋላጭም ናቸው ተብሏል። ጥናቱን የሰሩት የእንግሊዝ ሳምባ ፋውንዴሽን እና 'አዝመ ዩኬ' ናቸው ተብሏል። በርካታ የህዝብ እንደራሴዎች መንግስት የአየር ብክለትን በተመለከተ ጠበቅ ያሉ እርምጃዎችን እንዲወስድ እየወተወቱ ይገኛሉ። ''በዩኬ ከወረርሽኙ በኋላ በሚደረጉ የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ውስጥ የምንተነፍሰውን አየር ጥራት ማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል'' ብለዋል በአየር ንብረት ላይ የሚያተኩረው ኮሚቴ አባል የሆኑ አንድ የሕዝብ ተወካይ። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ሁለቱ ተቋማት የሰሩት ጥናት እንደሚለው ከሆነ በተበከለአየር ውስጥ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች ወደ ሳምባችን ከገቡ በኋላ ወደ ደም ስራችንም ይሰራጫሉ። ይህ ደግሞ ከሳምባ በተጨማሪ የደም ቧምቧዎቻችንም ሊጎዱ እንደሚችሉ ማሳያ ነው ተብሏል። እነዚህ ጎጂ ንጥረ ነገሮች ሁሉንም ሰው የሚያጠቁ ሲሆን ጉዳታቸው ግን እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ይረታል። ሳምባቸውን በማዳከም ወደ ከፍተኛ የመተንፈስ ችግር ውስጥ እከታቸዋል። የአየር ብክለት በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በጣም የተንሰራፋ ነገር ነው ይላሉ በጥናቱ ላይ የተሳተፉት ዶክተር ኒክ ሆፕኪንስ። ዶክተሩ እንደሚሉት በየዓመቱ ከ30 ሺ እስከ 40 ሺ የሚደርሱ መከላከል የሚቻሉ ሞቶች ምክንያታቸው ለተበከለ አየር መጋለጥ ሊሆን እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ። የአየር ብክለት ከዚህ በተጨማሪም የአንድን ሰው በሳምባ ካንሰር የመያዝ እድል ከፍ የሚያደርግ ሲሆን ለተለያዩ የልብ ህመሞችም ቢሆን የማጋጥ ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ''ሁላችንም እንደምነዋቀው እድሜያቸው የገፉ ሰዎች ለተበለከ አየር የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነው፤ ደሀው የማህበረሰብ ክፍል የሚኖርባቸው አካባቢዎች ደግሞ ያላቸው የንጹህ አየር መጠን ዝቅተኛ ነው። ስለዚህ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው አረጋውያን በቀላሉ በአየር ብክለት ይጎዳሉ'' ይላሉ ዶክተር ኒክ ሆፕኪንስ። ጥናቱን ያካሄዱት ሁለቱ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋማት መንግስት ዜጎች የሚተነፍሱትን አየር ጥራት የሚቆጣጠር ሚኒስትር መስሪያ ቤት እንዲያቋቁምና ብሄራዊ የጤና ስርአቱን ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ እንዲሰራ ጥሪያቸው አቅርበዋል። ኪምበርሊ ኮል ከባድ የሳምባ ችግር ያለባት ሲሆን የተበከ አየር ስትተንፍስ ደግሞ ህመሟ እንደሚጠናባት ትናገራለች። ሳምባዋ በጣም ጉዳት ስለደረሰበት ልክ የተበከለ አየር ስትተነፍስ ወዲያው ህመሙ ይጀምራታል። በቀላሉ ንጹህና የተበከለ አየር መለየት እንደምትችልም ትገልጻለች። ''አንዳንድ ጊዜ በእጅጉ የተበከለ አየር ስተንፍስ ሳምባዬ ይደማል። አንዳንድ ጊዜ በጣም ያስለኝና ለቀናት እታመማለው።'' የተሰራውን ጥናት ተከትሎ የአካበቢ ጥበቃ ሚኒስትሯ ሬቤካ ፖው ''ከ2010 በኋላ የአየር ብክለት በእጅጉ ቀንሷል፤ የበካይ ንጥረነገሮች ልቀትም ቢሆን 9 በመቶ መቀነስ ተችሏል። ነገር ግን አሁንም ብዙ መሰራት ያለባቸው በገሮች እንዳሉ እናምናለን'' ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
news-55258557
https://www.bbc.com/amharic/news-55258557
ትግራይ፡ መንግሥት በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታን የሚያስተጓጉል ችግር የለም አለ
በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማቀረብ የሚደረገው ጥረት በውጊያ ምክንያት እንደተስተጓጎለ የሚነገር እውነት እንዳልሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው በክልሉ በሚገኙ "በርካታ ከተሞችና በዙሪያቸው ባሉ አካባቢዎች በሚካሄድ ውጊያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራው እንቅፋት እንደገጠመው ተደርጎ የሚነገረው ሐሰት" እንደሆነ ገልጾ ይህም በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ክልሉን ለማረጋጋት የተከናወኑ ወሳኝ ተግባራትን የሚቃረን ነው ብሏል። ጨምሮም በትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት እየሸሹ ያሉ የወንጀለኛው ቡድን አባላትን ለመያዝ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አልፎ አልፎ ከታጣቂዎች ጋር የሚደረግን የተኩስ ልውውጥን እንደ ውጊያ አድርጎ ማቅረብ ተገቢ እንዳልሆነ አመልክቷል። የተባበሩት መንግሥታት በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ መንግሥታ ጋር ስምምነት ከተፈራረመ በኋላ ትግራይ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች በሚካሄድ ውጊያ ምክንያት እርዳታ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት እንደተስተጓጎለበት ባለፈው ሳምንት ለፈረንሳይ ዜና ወኪል መግለጹ ይታወሳል። ጨምሮም ለሳምንታት በዘለቀው ግጭት ሳቢያ በርካታ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው መሠረታዊ አቅርቦት መሟጠጡን በመግለጽ እርዳታውን ለሚፈልጉ ዜጎች ለማድረስ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ ቢደረስም ወደ አካባቢዎቹ መድረስ እንዳልቻሉ ገልጾ ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ዛሬ [አርብ] ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የፌደራል መንግሥቱ በክልሉ ለሚደረጉ የሰብዓዊ እርዳታዎች አቅርቦት አስተማማኛና ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት ጠቅሶ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት የአቅርቦት መስመሮች እንደሚመቻቹ አመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለት ዓለም አቀፍ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸው በትግራይ እንደተገደሉባቸው አስታውቀዋል። ዳኒሽ ሪፊውጂ ካውንስል እና ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ (አይአርሲ) ዛሬ እና ትናንት ባወጡት መግለጫ በትግራይ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ባልደረቦቻችን ተገድለዋል ብለዋል። ዳኒሽ ሪፊውጂ ካውንስል ባሳለፍነው ወር ሦስት የሰብዓዊ እርዳታ ሠራተኞቹ መገደላቸውን ሲያስታውቅ ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ (አይአርሲ) በበኩሉ በሽሬ ከተማ ህጻጽ የሰደተኞች መጠለያ ካምፕ ይሰራ የነበረ ባልደረባው መገደሉን አስታውቋል። የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት መንግሥት የዜጎቹን ደኅንት በሁሉም በኩል ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጾ በትግራይ ክልል ያሉና ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች አስፈላጊው የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ እንደሚሰራ፤ ነገር ግን ከዚህ ተቃራኒ የሚወጡ ሪፖርቶች የፌደራል መንግሥቱን ጥረት ለማሳነስ በሚካሄድ የተሳሳተ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ምክንያት ነው ብሏል። የእርዳታ አቅርቦቱ በተገቢው ሁኔታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እንዲደርስ ከተመድ ጋር በተደረሰው ስምምነት በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት አላማ፣ መርህ፣ የአቅርቦት ቅንጅት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ላይ ከስምምነት ተደርሶ በዚሁ መሠረት ሥራዎች እንደሚከናወኑ አመለክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት እንዳለው ከሳምንታት በፊት ጀምሮ ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የመሠረታዊ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች በመንግሥት አማካይነት ሲቀርብ መቆየቱን አመለክቶ አሁንም የክልሉን ዋና ከተማን ጨምሮ ወደ ተለያዩ ስፍራዎች የምግብና የመድኃኒት ድጋፎች እየቀረቡ መሆኑን አመለክቷል። ከሳምንታት በፊት በአንዳንድ አካባቢዎች የእርዳታ አቅርቦት መዘግየት አጋጥሞ እንደነበረ አመለክቶ መቀለ ከተያዘች በኋላ ግን ወታደራዊው ዘመቻ አብቅቶ ተፈላጊ "የወንለኛ ቡድኑ አባላትን" የመያዝ ሥራ እየተከናወነ በመሆኑ የእርዳታ አቅርቦቶች እየተከፋፈሉ መኖናቸውን ገልጿል። በዚሁም መሠረት በመጀመሪያው ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ ወደ ዳንሻ፣ ወልቃይት፣ ቃፍታ፣ ሁመራና ደባርቅ አካባቢዎች መላካቸውን እንዲሁም ባለፈው ሳምንት 18 ሺህ 200 ኩንታል የምግብ ድጋፍ የያዙ 44 ካባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ለማከፋፈል ወደ ሽረ መላካቸው ተነግሯል። በተጨማሪም 5500 ኩንታል የምግብ ድጋፍ ወደ አላማጣ፣ 7 ሺህ ኩንታል ዱቄት እና 12ሺህ 500 ኩንታል የምግብ ድጋፍ ወደ መቀለ እንደተላከ እንዲሁም የህክምና ግብዓቶች ወደ መቀለ፣ ሽረና አዲግራት ከተሞችም መላካቸው ተገልጿል። በትግራይ ክልል በሚገኘው የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ በክልሉ እለታዊ የመሠረታዊ ፍላጎት አቀርቦት መስተጓጎሉ ይታወቃል። በዚህም ሳቢያ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የሚገኙና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች የሚያስፈልጋቸውን የምግብና የመድኃኒት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጥረት ቢያደርጉም እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ሲገልጹ እንደነበር ይታወሳል። ለሳምንታት በዘለቀው ወታደራዊ ግጭትን ተከትሎ በርካቶች የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የተገለጸ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉት ደግሞ ግጭቱን በመሸሽ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን መግባታቸውን የእርዳታ ድርጅቶች አመልክተዋል።
56115854
https://www.bbc.com/amharic/56115854
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ጀዋር የህክምና ቦታ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጠ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የሕክምና ቦታ ክርክር ላይ ብይን ለመስጠት በዛሬው ዕለት፣ የካቲት 12/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እነ አቶ ጀዋር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላንድማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ክርክር ተካሂዷል። ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቶ ጀዋርን ጨምሮ አምስት ሰዎች በመረጡት የላንድ ማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ ማዘዙን በመቃወም ማክሰኞ የካቲት 9/ 2013 ዓ.ም ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ በመደረጉ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወስዶታል። በዛሬው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሃ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ እንዲገኙ ቢያዝም ማረሚያ ቤቱ ሳያቀርባቸው መቅረቱን ከተከሳሾቹ ጠበቆች መካከል አንዱ አቶ ሚልኪያስ ቡልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የማረሚያ ቤቱ ተወካዮችም እንዲሁ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሲሆን ተከሳሾችን እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ቢደርሳቸውም፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾቹ በአካል በማቅረብ ፈንታ በማረሚያ ቤቱ እንዳሉ በቪዲዮ እንዲሳተፉ እንዲያደርጉ መታዘዛቸውን ጠበቃቸው ጨምረው አስረድተዋል። በመቀጠልም እነ አቶ ጀዋር በሌሉበት ጉዳዩ መታየት የለበትም በሚለው ላይ በጠበቆችና በዓቃቤ ሕግ መካከል ክርክር መካሄዱንም አቶ ሚልኪያስ ተናግረዋል። የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የግራ እና ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ እነ አቶ ጀዋር በሌሉበት ጉዳዩ እንዲታይ ማዘዙን ተናግረዋል። የሕክምና ጉዳይ ክርክር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የእነ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሐምዛ አዳነ፣ አቶ ሸምሰዲን ጠሃ እና አቶ ደጀኔ ጣፋ በላንድ ማርክ የግል ሆስፒታል እንዲታከሙ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት መወሰኑ ትክክል እንዳልሆነ በመጥቀስ አቤቱታ አቅርቧል። "የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የሕግ ክርክርን ያልተከተለ፣ የእኩልነትን መብትና ሕገ መንግሥቱን የተቃረነ፣ የፌደራል ማረሚያ ቤት የተመሰረተበትን አዋጅ የሚፃረር ነው" በማለት አቃቤ ሕጉ መከራከሪያ ማቅረባቸውን አቶ ሚልኪያስ ይናገራሉ። ጠበቆች በበኩላቸው "የታችኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ትክክል ነው። ጊዜው ያለፈበት ስለሆነም ዓቃቤ ሕግ አቤቱታ ማቅረብ አይችልም። ደንበኞቻችንም በግል ሀኪማቸው እና ራሳቸው በመረጡት የሕክምና ተቋም እንዲታከሙ ትዕዛዝ የተሰጠው በመስከረም 2013 ዓ.ም ነው ብለዋል። ስለዚህ ዓቃቤ ሕጉ በጊዜው አቤቱታ አላቀረበም በማለት የአቃቤ ሕጉ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ መከራከራቸውን ይናገራሉ። ጀዋርን ጨምሮ የሌሎች 24 ተከሳሾች ጠበቆች ከሆኑት መካከል አንዱ አቶ ሚልኪያስ ቡልቻ፤ ዓቃቤ ሕግም ሆነ ግለሰብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ አቤቱታ ካላቸው በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንዲችሉ ወይንም ደግሞ አቤቱታ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቅ እንዳለባቸው ሕግ እንደሚያዝ ይናገራሉ። ከዚህም ውጪ ደንበኞቻቸው በተለያየ የግል ሕክምና ተቋም ሲታከሙ እንደቆዩ የተናገሩት አቶ ሚልኪያስ፤ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 21 ቁጥር 2 በሕግ ጥላ ስር የዋሉ ሰዎች በግል ሐኪም የመታከም መብት እንዳላቸው እንደሚገልጽ በመጥቀስ መከራከራቸውን ይናገራሉ። የሁለቱንም ወገን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመስጠት ለየካቲት 16፣ 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል። ከዚህ ቀደም ፍርድ ቤቱ በግል ሃኪም ቤት እንዲታከሙ የወሰነላቸው ሲሆን፤ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ የፀጥታና ደህንንነት በተመለከተ ያለውን ሁኔታ አቅርቦ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም የካቲት 2፣ 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲወሰዱ ወስኖ ነበር። በወቅቱ ማረሚያ ቤቱ ታሳሪዎቹ የረሃብ አድማ ላይ በመሆናቸው "ታመው ከወደቁ ዝም ብለን ማየት ስለማንችል፣ ቀደም ብለው ስለማይነግሩንና በዛ አጭር ሰዓት ውስጥ እነሱ የፈለጉት ሆስፒታል ላይ ሃይል አሰባስበን ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስለምንቸገር ድንገት ከወደቁ ግን ጦር ሃይሎች ሆስፒታል እንድናሳክም ይፈቀድልን" ብለው በማመልከታቸው ለጊዜው ፍርድ ቤቱ ይኼንን ፈቅዶላቸው እንደነበር ከጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሃመድ ጅማ ያስረዳሉ። ጠበቆቻቸው በበኩላቸው ሆስፒታሉን ከስምንት ሰዓት በፊት እንደጠየቁና ደንበኞቻቸው በመረጡት ሆስፒታል እንዲታከሙ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲያስተላልፍና ከዚህ ቀደም የነበረውን ውሳኔ እንዲያፀና ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱም ሰኞ እለት የካቲት 8፣ 2013 ዓ.ም እነ አቶ በቀለ ገርባን የግል የጤና ተቋም በሆነውና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዲታከሙ ውሳኔ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ አቶ በቀለ ገርባ በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ መንግሥታዊው የጤና ማዕከል ጦር ሃይሎች ሆስፒታል መወሰዳቸውን ሃኪማቸውና ጠበቃቸው ተናግረዋል። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመተላለፍ አቶ በቀለ ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል በኃይል መወሰዳቸው "ከህግ አግባብ ውጭ ነው" ሲሉ ከአቶ በቀለ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሃመድ ጅማ ለቢቢሲ አስረድተዋል። እነ አቶ በቀለ የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነ ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። ከጥር 19፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ውሃ ምንም የማይቀምሱትና የረሃብ አድማ ላይ ናቸው የተባሉት እነ አቶ በቀለ ገርባ የጤና ሁኔታም አሳሳቢ ነው ተብሏል። እነ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል።
news-56277301
https://www.bbc.com/amharic/news-56277301
ህዳሴ ግድብ፡ ሱዳንና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች እንዲሳተፉ ጠየቁ
ግብጽና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያደርጉት ድርድር ላይ ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች እንዲሳተፉ በድጋሚ ጥሪ አቀረቡ።
የግብጽ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ እና የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄነራል አል ቡርሐን በተለይ በሱዳን በኩል ሲቀርብ የነበረው ይህን ጥያቄ፣ ቅዳሜ ዕለት ካርቱምን የጎበኙት የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ከሱዳን ሲቪልና ወታደራዊ መሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ በድርድሩ ተጨማሪ አሸማጋዮች እንዲሳተፉ በጋራ ጠይቀዋል። ሁለቱ አገራት ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ግዙፍ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ዙሪያ አዲስ ዙር ድርድር ላይ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ ሕብረትና ከተባበሩት መንግሥታት የተውጣጡ አሸማጋዮች የሚሳተፉበት እንዲሆን ጠይቀዋል። ከዚህ ቀደም ለወራት በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት በሦስቱ አገራት መካከል ሲካሄድ የቆየው እና መቋጫ ባላገኘው ድርድር ላይ ሌሎች አገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሳተፉ የቀረበውን ጥያቄ ኢትዮጵያ አለመቀበሏ ይታወሳል። ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት አሸማጋይነት እየተከናወነ ባለበት ወቅት ሌሎች አደራዳሪዎች ይግቡ ማለት "የድርጅቱን አስተዋፅኦ የሚያኮስስ ነው" ብለዋል። የቀድሞው አምባገነን መሪ ኦማር አልበሽር በሕዝባዊ አመጽ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ሱዳንን ለመጀመሪያ ጊዜ እየጎበኙ ያሉት የግብጹ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ "በአስቸኳይ ፍትሃዊ፣ ሚዛናዊና አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት" ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከግዛቷ 85 በመቶ ያህል ውሃ ከምታበረክተበት ከአባይ ወንዝ ውሃ ለመጠቀም ያላትን መብት ለድርድር የማታቀርብ መሆኑን መግለጿ ይታወሳል። ይህ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበው ግዙፍ ግድብ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌቱ ተካሄዷል። ሱዳንና ግብጽ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ለማካሄድ ያቀደችው ሁለተኛው ዙር የግድቡን ውሃ ሙሌት ከመጀመሯ በፊት ስምምነት መደረስ አለበት እያሉ ነው። ግብጽና ሱዳን ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የህዳሴ ግድብ ከአባይ ወንዝ በሚያገኙት የውሃ መጠን ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል በሚል ስጋታቸውን ከመግለጻቸው ባሻገር ለዓመታት ሲካሄድ የቆየው ድርድር መቋጫ እንዳያገኝ አድርጎታል። በሦስቱ አገራት መካከል ያለውን አለመግባባት በውይይት ለመፍታት ለዓመታት የዘለቀ ውይይት ቢካሄድም፣ ሁሉንም በሚያስማማ ሁኔታ ሳይቋጭ አስካሁን የቆየ ሲሆን በአፍሪካ ሕብረት አሸማጋይነት ሲካሄድ በቆየው ድርድር ግብጽና ሱዳን በአንድ ላይ በመቆም ጥቅማቸውን ለማስከበር እየጣሩ ነው። የግብጹ ፕሬዝዳንት የሱዳን ጉብኝት ባለፉት ሳምንታት የሁለቱ አገራት ሲቪልና ወታደራዊ ከፍተኛ ባለስልጣናት በካርቱምና በካይሮ ጉብኝትና ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። ከዚህ ውስጥም ባለፈው ማክሰኞ የሁለቱ አገራት በከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በተከታታይ ሲያካሂዱ የነበረውን ውይይት አጠናቅቀው የጋራ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። ቀደም ሲልም ሱዳንና ግብጽ ከዚህ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ያደረጉ ሲሆን ተመሳሳይ ልምምዶች በቀጣይነት እንደሚኖሩ ተነግሯል። ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የድንበር ውዝግብ ውስጥ ከገባች ወራት ተቆጥረዋል። ይህም ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ ሱዳን ወታደሮቿን በማሰማራት በሰሜን ምዕራብ የአገሪቱ ክፍል፣ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ሰፍረውበት የነበሩትንና የግዛቴ አካል ናቸው የምታላቸው ቦታዎች በቁጥጥሯ ስር ማስገባቷ ይታወሳል። ኢትዮጵያም በሱዳን ሠራዊት ወረራ እንደተፈጸመባት በመግለጽ ወታደሮቿ ከግዛቷ እንዲወጡና የድንበሩ ጉዳይ ቀደም ሲል በተጀመረው ውይይት እንዲፈታ እየጠየቀች ትገኛለች።
news-55681377
https://www.bbc.com/amharic/news-55681377
ስፖርት፡ በቻን የወንዶች እግር ኳስ ውድድር ላይ በዋና ዳኝነት የምትሳተፈው ሊዲያ ታፈሰ
ዛሬ ቅዳሜ ጥር 08/2013 ዓ.ም ካሜሩን ውስጥ የሚጀመረው 'ቻን' በመባል የሚታወቀው የአፍሪካ አገራት የእግር ኳስ ሻምፒዮና ውድድር ጨዋታዎችን እንዲዳኙ በአህጉሪቱ የእግር ኳስ የበላይ አካል ካፍ ከ31 አገራት 47 ዋና ዳኞችና ረዳት ዳኞችን ሰይሟል።
በካሜሮን በሚካሄደው ቻን የወንዶች እግር ኳስን ከሚዳኙ 19 ዋና ዳኞች መካከል ብቸኛዋ የመሃል ዳኛ የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ ይህን የወንዶች የእግር ኳስ ውድድር ከሚዳኙት ዳኞች መካከል አራት ሴቶች ከወንዶች አቻዎቻቸው ጋር በአካላዊና ስፖርታዊ እንዲሁም የእግር ኳስ ጨዋታን በመረዳት ባላቸው ብቃት ተመዝነው እንደተመረጡ ተገልጿል። ለውድድሩ ዳኝነት ከተመረጡት 47 ዳኞች መካከል፣ 19ኙ በዋና ዳኝነት ጨዋታዎችን የሚመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ በመስመር ዳኝነትና በቪዲዮ ዳኝነት የመሃል ዳኞችን የሚያግዙ ናቸው። ታዲያ ከ19ኙ ዋና ዳኞች መካከል ብቸኛዋ የመሃል ዳኛ ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ ናት። ሊዲያ በአገር ውስጥና በተለያዩ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድሮችን በመዳኘት ብቃቷን ያስመሰከረች ስትሆን የአፍሪካ የእግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ውስጥ አንዱ በሆነው 'የቻን' የወንዶች የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ በዋና ዳኝነት ጨዋታ የምትመራ ቀዳሚዋ ሴት ሆናለች። ካፍ የሚያዘጋጃቸው የወንዶች የእግር ኳስ ውድድሮችን በመዳኘት በኩል ሴቶች እንዲሳተፉ ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ፣ በውድድሮቹ ሂደት ውስጥ ሴቶች የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመያዝ እንዲሳተፉ እያደረገ ነው። በዚህም መሠረት ከሊዲያ ታፈሰ በተጨማሪ በቻን ውድድር ላይ በረዳት ዳኝነት ከማላዊ፣ ከናይጄሪያና ከካሜሩን የተመረጡ ሴቶች ይሳተፋሉ። የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሊዲያ ታፈሰ ወደ ስፖርት የገባቸው ጅማ ውስጥ ባዳበረችው የቅርጫት ኳስ ጨዋታ ፍቅር ምክንያት ነው። ሊዲያ በታዳጊነቷ እግር ኳስ ትጫወት የነበረ ሲሆን ዋነኛው ስፖርቷ ግን ቅርጫት ነበር። አሁን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የወንዶች እግር ኳስ ሊግ ውስጥ በብቃታቸው ከሚጠቀሱ ዳኞች መካከል አንዷ የሆነችው ሊዲያ፣ መጀመሪያ ላይ ባገኘችው ስልጠና ተስባ ነበር ወደ ዳኝነቱ የገባችው። በዳኝነቱ ዘርፍ ከሴቶች አንጻር ከቀዳሚዎቹ ውስጥ የምትጠቀሰው ሊዲያ፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን መዳኘት በጀመረች ጊዜ፣ ጥያቄና ፈተናዎች ገጥመዋት እንደነበር ካፍ ድረ ገጽ ላይ በወጣው ታሪኳ ላይ ሰፍሯል። "በጣም አስቸጋሪ ነበር። አንዳንዶች ሌላ ሴት በሌለችበት ዘርፍ ላይ በእግር ኳስ ዳኝነት ለመሰማራት ለምን እንደወሰንኩ ሁሉ የሚጠይቁኝ ሰዎች ነበሩ" ትላለች። ሴት ዳኞችን ለማፍራት በታቀደ ፕሮጀክት ውስጥ ስልጠና አግኝታ፣ ከ15 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ልጆች የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በዳኝነት በመምራት የጀመረችው ሊዲያ፤ በአገሪቱ ፐሪሚየር ሊግ ውስጥ ጨዋታዎችን በዳኝነት መምራት ችላለች። በዳኝነቱ ላይ ያሳደረችው ፍቅር ቢጠነክርም፣ ሴት ሆና የወንዶችን ጨዋታዎች ስትዳኝ እንደ እንግዳ ነገር የሚመለከቷት ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን ከወንዶች ጋር እግር ኳስ በምትጫወትበት ጊዜ ያዳበረችው በራስ መተማመን የወንዶችን ውድድሮች ያለችግር እንደትመራ እንደረዳት የምትናገረው ሊዲያ፤ የቤተሰቧ ድጋፍ ደግሞ ወሳኙ እንደነበር ታነሳለች። በአገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ባሳየችው የዳኝነት ብቃት ለዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎች የታጨችው ሊዲያ፤ በመጀመሪያ ከ15 ዓመት በፊት ናይጄሪያና ላይቤሪያ አቡጃ ውስጥ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ውድድር ለዋንጫ ለማለፍ ያደረጉትን ግጥሚያ ዳኝታለች። "ያንን ጨዋታ አልረሳውም ምክንያቱም በጣም አስቸጋሪ ነበረ። ስታዲየሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምናውቀው በጣም ይተልቃል፣ ተመልካቹም የተለየ ነበር" ትላለች። በመቀጠልም የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ግጥሚያዎችን ያጫወተች ሲሆን በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደውን የአፍሪካ የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን በተከታታይ ለአራት ጊዜ በመዳኘት ለቀጣዩ እየተዘጋጀች ነው። ከዚህ በተጨማሪም ከአራት ዓመት በፊትና ከአንድ ዓመት በፊት የተካሄዱትን የፊፋ የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫን፣ እንዲሁም የፊፋ ከ17 ዓመት በታች የታዳጊዎች የዓለም ዋንጫንና ከ20 ዓመት በታች ውድድሮች ላይ በዳኝነት ተሳትፋለች። ሊዲያ ልጇን በጸነሰችበትና ከወለደች በኋላም ወደምትወደው የዳኝነት ሙያዎ ለመመለስ ፈተናዎች ገጥመዋት ነበር። "ከእርግዝና በኋላ አካላዊ ለውጥ ያጋጥማል። ክብደቴ በጣም ጨምሮ ስለነበር ወደ ቀድሞ አቋሜ ለመመለስ በጣም መስራት ነበረብኝ። በርትቼ በመስራት መጨረሻ ላይ ተሳክቶልኝ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ እድሉን አገኘሁ" ብላለች። ለዚያ ውድድር በምትዘጋጅበት ጊዜ ጉዳት አጋጥሟት እንደነበር የምትናገረው ሊዲያ፣ ወደ አገሯ እንደምትመለስና በዚህ ምክንያት ከስፖርቱ ልትወጣ እንደሆነ ስጋት ፈጥሮባት ነበር። ነገር ግን በኋላ ላይ አገግማ ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከጉዳቷ በኋላ ወደ ተጨማሪ ሰዓት የተሸጋገረውን የካሜሩንና የኮትዲቯርን የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መርታ ነበር። "ጨዋታው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ሲሸጋገር ሜዳ ውስጥ ከእግር ኳስ ተጫዋቾቹ በላይ ጠንካራ ነበርኩ። በጣም ደስ ብሎኝ ነበረ" ስትል ሊዲያ ታስታውሳለች። ሊዲያ በበርካታ ታላላቅ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ወሳኝ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ በዳኝነት ተሳትፋለች። ወደፊትም በታላቁ የአፍሪካ የወንዶች ዋንጫ ላይ በዳኝነት እንደምትሳተፍ ተስፋ አላት። ሊዲያ ከዳኝነቱ በተጨማሪ የፋርማሲ ባለሙያ ስትሆን፣ በዚህ የኮሮናቫይረስ ዘመን የእግር ኳስ ውድድሮች ለወራት ተቋርጠው በነበረበት ጊዜ በሙያዋ ወገኖቿን ለማገልግል ሰርታለች። በዚህም ሰዎች ራሳቸውንና ሌሎችን ከወረርሽኙ እንዲከላከሉ የህክምና መረጃዎችን በተለያዩ መንዶች ስትሰጥ ቆይታለች። በየትኛውም ጊዜ ከልምምድ ርቃ የማታውቀው ሊዲያ፣ እንደ ሴት በቤተሰቧና በእግር ኳስ ዳኝነት ሙያዋ መካከል ያለውን ሚዛን በመጠበቅ እንደተሳካላት ትናገራለች። ለዚህ ደግሞ ከባሏና ከልጇ የምታገኘው ድጋፍና ማበረታታት በሙያዋ በስኬት እንደትቀጥል እንዳደረጋት ገልጻለች። በአፍሪካ አህጉር አሉ ከሚባሉ ኮከብ ሴት የእግር ኳስ ዳኞች መካከል ከፊት የምትጠቀሰው ሊዲያ ታፈሰ፣ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ውስጥ ወደፊት ለሚመጡ ሴት ዳኞች መልካም አርአያ እንደምትሆን ታምናለች። ወደፊትም ከሙሉ ጊዜ የእግር ኳስ ዳኝነት አረፍ ስትል በፋርማሲ ሙያዋ ከመቀጠል በተጨማሪ፣ በዳኝነቱ የእሷን እግር ተከትለው መሥራት የሚፈልጉትን የማሰልጠን ፍላጎት አላት።
45649219
https://www.bbc.com/amharic/45649219
አሜሪካዊው ኮሜድያን ቢል ኮዝቢ በፆታዊ ትንኮሳ ውንጀላ ወደ ዘብጥያ ወረዱ
በፔንሲይልቫኒያ የሚገኝ ዳኛ ታዋቂው አሜሪካዊውን ኮሜዲያን ቢል ኮዝቢን በተወነጀሉባቸው ወሲባዊ ትንኮሳዎች ከ3-10 ዓመት ፈርደውባቸዋል።
የ81 ዓመቱ የእድሜ ባለፀጋ ቢልኮዝቢ ከዚህም በተጨማሪ ወሲባዊ ተንኳሽ በሚል የተመዘገቡ ሲሆን እስከ ህይወታቸው መጨረሻም ድረስ ምክርን በመቀበል አገልግሎት እንዲያልፉም ተወስኖባቸዋል። ተዋናዩ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። •በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች •ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው •አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ በሚያዝያ ወርም በአውሮፓውያኑ 2004 አንድሪያ ኮንስታንድ የተባለች ሴትን ማደንዘዣ በመጠቀም ወሲባዊ ጥቃት በመፈፀም ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ሆነው አግኝተዋቸዋል። ቢል ኮዝቢ የዋስ መብት እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ውድቅ ተደርጎባቸዋል። በአውሮፓውያኖቹ 1980 ከፍተኛ ዝናን ያተረፉት ተዋናዩ ኮዝቢ ሾው በሚለው የቲቪ ፕሮግራም አድናቆት ተችሯቸዋል። በኒውዮርክ ብሩክሊን ኑሯቸውን ስላደረጉ አንድ የቤተሰብ ታሪክ የሚተርከው ይህ ፊልም ቢልኮዝቢም የአባት ገፀ-ባህርይን ወክለውም ይጫወታሉ። በቲቪ ፕሮግራማቸውም ባገኙት ዝና "አሜሪካዊ አባት" የሚል ቅፅል ስምም አግኝተው ነበር። "ይህ ከፍተኛ ወንጀል ነው" ያሉት ዳኛ ስቲቨል ኦኒል ፍርዱንም ካስተላለፉ በኋላም "ሁሉም ነገር ወደ አንተ ተመልሷል። ቀኑም ደረሰ፤ ጊዜውም አሁን ነው" ብለዋል። በባለፈው አመት በቴምፕል ዩኒቨርስቲ አስተዳደር የምትሰራ አንዲት ሴት እንደ ታላቅ ሰው ታየው የነበረው ቢል ኮዝቢ ከጥቂት አመታት በፊት አደንዛዥ እንክብል ሰጥቶ ጥቃት ስለሰጣትም የደረሰባትን ወሲባዊ ትንኮሳን መከላከል አልቻለችም። ለናሽናል ፖስት በሰጠችውም መግለጫ " የወሲባዊው ትንኮሳ ያደረሰብኝን ጉዳት ለማወቅ ምን አይነት ሰው እንደነበርኩ መረዳት ያስፈልጋል" ብላለች። በህይወቷ ከፍተኛ ቦታን እደርሳለሁ ብላ አልማ የነበረ ሲሆን በትምህርቷም ሆነ በአትሌቲክስ ስልጠና ላቅ ወዳለ ደረጃ እደርሳለሁ ብላ አልማ ነበር። ከወሲባዊው ትንኮሳ በኋላ ሁሉ ነገር ብዥ ብሎባት የነበረ ሲሆን እፍረቱ፣ ራሷን መጠራጠር፣ ብቸኝነቱ ውዝግብና ሌሎችም ቀውሶች እንደደረሱባት ትናገራለች። መብላት አቁማ እንደነበር፣ እንዲሁም መተኛትና ከማህበረሰቡም ጋር መቀላቀል አቁማ ነበር። "ቢል ኮዝቢ ውበቴን፣ ጤናየንና የወጣትነቴን መንፈሴን ወስዶ ሰባብሮታል" ብላለች።
news-50876649
https://www.bbc.com/amharic/news-50876649
የሐኪሞች እጅ ጽሑፍ የማይነበበው ለምንድን ነው?
በተለያየ ምክንያት የሕክምና ደጃፍ ይረግጣሉ። ቀላል ለሆነ ራስ ምታትም ሆነ ተኝቶ ለመታከም ፈውስ በእጁ ነው የተባለ ዶክተር ባለበት እርስዎ አይጠፉም።
'አይ እኔ ለበሽታ እጅ አልሰጥም' ቢሉ እንኳ አንድ ቀን እግር ጥሎዎት ሐኪም ፊት መቅረብዎ አይቀርም። ለሐኪሙ 'ሽቅብ ሽቅብ ይለኛል'፤ 'ወገቤን ከፍሎ ያመኛል'፤ 'ጭው እያለ ይዞርብኛል'. . . ካሉት በኋላ ነጭ ወረቀት ላይ እንደ ነገሩ የተሞነጫጨረ ነገር ጽፎ ይሰጥዎታል። ትዕዛዙ ይለያያል፤ ወይ ወደ መድሃኒት ቤት፤ አልያም ላብራቶሪ ወይንም አልትራሳውንድ፣ ራጅ ብቻ እንደ በሽታዎ አይነት ያስፈልጋል ያለውን ይጽፍልዎታል። እርስዎም ፊደል የቆጠሩ ስለሆኑ ምን ተጻፈ ብለው አይንዎን ወረቀቱ ላይ ያንከራትታሉ። ምንም ያህል ቢማሩ ግን የዶክተሩን የእጅ ጽህፈት ምስጢር ሊደርሱበት አይቻልዎትም። • 'ሀሰተኛ' የተባለችው ሀኪም ታሰረች • ያለታካሚዎች ፈቃድ ቀዶ ህክምና ያደረገው የማህጸን ሀኪም ተከሰሰ የጻፈው በምን ቋንቋ ነው? ሊሉም ይችላሉ። ኢትዮጵያ ሁሉም ሀኪሞች በእንግሊዘኛ ነው የሚጽፉት። እርስዎ ግን የእነርሱን እንግሊዘኛ ማንበብም ሆነ መገመት የእንጦጦ ዳገት ነው የሚሆንብዎ። ለምን? የሐኪሞች እጅ ጽሑፍ ለምን አይነበብም? የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መምህርና ሐኪም የሆት ዶ/ር ናሆም ግሩም ''የእኔ እጅ ጽሑፍ ስለሚነበብ እንደ ሐኪም የማያዩኝ ሰዎች አሉ'' አሉን። ቆይ ቆይ ዶክተር በቅድሚያ አንድ ህመምተኛ ወደ ሐኪሙ ዘንድ ከገባበት እና ወንበር ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ አቀርቅራችሁ በሽተኛው የተነፈሰውን ሁሉ የምትጽፉት ለምንድን ነው? አልናቸው። የተለያዩ ሰዎች ሊስማሙበት ባይችሉም እንኳን ከሥራ መስኮች መካከል እንደ ሀኪሞች የሚጽፍ የለም አሉን። "ጋዜጠኞችስ ዶክተር?" የኛ ጥያቄ ነው። በፈገግታ ታጅበው፤ ምክንያቱ ደግሞ አንድ ሐኪም ለህመምተኛው ሕክምና ካደረገ በኋላ የሠራቸውንና የተነጋገራቸውን በሙሉ መዝግቦ በታካሚው መዝገብ ላይ ማስቀመጥ ስላለበት ነው ሲሉ አብራሩ። • የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም • ለ20 ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም ''ለበሽተኛው አገልግሎት ሲሰጥ የዋለ፤ የተነጋገረውን የሕክምና አገልግሎት በአግባቡ መዝግቦ ካላስቀመጠ አገልግሎት እንዳልሰጠ ይቆጠራል'' በቀን ለ50 ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ ሐኪም፤ የ50 ታካሚ ታሪክ ሲጽፍ ይውላል ማለት ነው። ደራሲ ቢሆኑ ስንት መጽሐፍ ይወጣው ይሆን? የኛ ሃሳብ ነው። ዶ/ር ናሆም ሙያዊ ማብራሪያቸውን ይቀጥላሉ፤ ከዚህም በተጨማሪም ''በብዛት በጻፍን ቁጥር በጣቶቻችን ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ነርቮች ስለሚደክሙ እንዳይነበብ ሆኖ ሊጻፍ ይችላል'' ካሉ በኋላ በተመሳሳይም በፍጥነት መጻፋ ራሱ የሐኪሞቹ የእጅ ጽሑፍ በቀላሉ እንዳይነበብ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ይጠቀሳል አሉን። እንደ ኢትዮጵያ ባለ አንድ ዶክተር በርካታ ሕሙማንን በሚያክምበት አገር የእያንዳንዱን ታካሚ ታሪክ መመዝገብ የግድ መሆኑን ይናገራሉ። ደግሞ ወረፋ በበዛበት ወቅት አንዱን ህመምተኛ ካከመ በኋላ ሌላኛውን ለማከም ጥድፊያ ይኖራል። የእጅ ጽሑፍ ደግሞ እንኳንስ ተጣድፈውበት እንዲሁም ሆደ ባሻ ነው። ዶ/ር ናሆምም በዚህ ሀሳብ ይስማማሉ፤ ''ከዚህ የተነሳ ነው የሐኪሞች እጅ ጽሑፍ የማይነበብ ወይንም የማያምር የሚሆነው ይሆናሉ'' በማለት። ለዶ/ር ናሆም ያቀረብነው ሌላ ጥያቄ የሐኪሞች እጅ ጽሑፍ ለምንድን ነው ከዘርፉ ባለሙያዎች ውጪ የማይነበበው? • ከበለስ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የምትመራመረዋ ኢትዮጵያዊት • ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ ያለማቋረጥ የዋኘችው የጡት ካንሰር ታማሚ "የሕክምና ሳይንስ ራሱን የቻለ የሙያ ቋንቋና ቃላት ስላሉት ሰዎች እኛ የምንጽፈውን ጽሑፍ በትክክል ማንበብ የማይችሉ ይመስላቸዋል እንጂ የጤና ባለሙያ ማለትም ነርሶችና ፋርማሲስቶች በቀላሉ ሊያነቡት ይችላሉ።" በተጨማሪም ይላሉ ዶ/ር ናሆም፤ ሀሳባቸውን ሲያብራሩ፤ የሕክምና ሳይንስ በአጭርና በአህጽሮተ ቃላት የሚገለጹ ብዙ አባባሎች ስላሉት ሐኪም የጻፈውን ጽሁፍ ማንበብ ሊያስቸግር ይችላል አሉን። ለዚህ ማስረጃ ፈለግን፤ እርሳቸውም ለምሳሌ ካሉ በኋላ BID የሚለው አጽህሮተ ቃል ይህንን መድሀኒት በቀን ሁለት ጊዜ ይውሰዱ የሚል አገላለጽን ይተካል አሉን፡፡ "ህመምተኛ ስለ በሽታው የማወቅ ሙሉ መብት አለው" ታካሚዎች ስለ በሽታቸው፣ ስለታዘዘላቸው መድሃኒትና፣ የምርመራቸውን ውጤት ለማወቅ የመጀመሪያዎቹና ባለ ሙሉ መብትም ናቸው ይላሉ ዶ/ር ናሆም። ይሁን እንጂ የሕክምና ሙያ ያላቸው ራሳቸው የሐኪሞች የእጅ ጽሑፍ ሳይነበባቸው ቀርቶ የመድሃኒት ማዘዣ ተመልሶ ወደ ዶክተሩ የሄደበት ጊዜ መኖሩን ያስታውሳሉ። አንድ ሌላ ገጠመኛቸውን ጨመሩልን። "ሐኪም መጥቶ እስኪያነብላቸው ድረስ ታካሚው መድሀኒት ሳይወስድ የቆየበት ጊዜ አውቃለሁ" አሉን። የባሰ አለ አገርህን አትልቀቅ ማለት እዚህ ጋር ነው. . . እንደው ለመሆኑ የዶክተሮች እጅ ጽሑፍ ላይ የተሠራ ጥናት ይኖር ይሆን? በሕንድ አገር የሀኪሞች እጅ ጽሁፍ በትክክል መነበብ ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ 60 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን በአገሪቱ የተሠራ ጥናት ያሳያል አሉን። በእኛ አገርስ ቢሠራ ታዲያ ምን ውጤት ይገኝ ይሆን? ሌላ ጥያቄ እናንሳ፤ ከሕክምና ሥነ ምግባር አንጻርስ የእጅ ጽሑፍ እንዴት ይታያል? "የሕክምና ሳይንስ ሥነ ምግባር አንድ ሐኪም የሚጽፋቸው ጽሑፎች ሁሉም ሰዎች በሚያነቡት መልኩ እንዲሆን ያዛል" በማለት መልስ ሰጥተውናል። እኛም እንደ ሐኪም በዚህ እናምናለን ብለው "ሌሎቹንም እንዲሁ እንመክራለን" ብለዋል ዶክተሩ። • በአንድ የጦር አውድማ ላይ ከወላጅ አባቷ ጋር የተፋለመችው ታጋይ • "የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ በምዕራባውያኑ አሰራር አንድ ታካሚ ስለ ጤና እክሉ አንብቦ እንዲረዳ በኮምፒውተር ተጽፎ ይሰጠዋል። በኢትዮጵያ ግን ከህመምተኞች ቁጥርና ካለው መዋቅር የተነሳ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ጽፎ ማዘጋጀት አስቸጋሪ ነው ይላሉ ዶ/ር ናሆም። አንዳንድ ሰዎች በህክምና ትምህርት ዓመት መጨረሻ አካባቢ ሲደርሱ "ሐኪሞች የእጅ ጽሑፍ ኮርስ ይሰጣችኋል?" በማለት ይጠይቃሉ ያሉት ዶ/ር ናሆም፤ በሕክምና ትምህርት ውስጥ ስለእጅ ጽሑፍ የሚሰጥ ትምህርት እንደሌለ ይገልጻሉ።
51830419
https://www.bbc.com/amharic/51830419
የህክምና ባለሙያዎች ሁለተኛውን ሰው ከኤች አይ ቪ ፈወሱ
በለንደን ኗሪ የሆነው አዳም ካስቲሊዮ ከኤች አይ ቪ በተጨማሪ የካንሰር ህመምተኛም ስለነበር ለካንሰሩ የስቲም ሴል ህክምና ሲደረግለት ነበር።
ግለሰቡ የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት መውሰድ ካቆመ አንድ ዓመት ከመንፈቅ የሞላው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ከኤች አይ ቪ ነፃ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል። የላንሴት ኤችአይቪ ጆርናል ላይ የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው አዳም ካስቲሊዮ ዓለም ላይ በህክምና ምርምር ከኤችአይቪ መፈወስ የቻለ ሁለተኛው ሰው ነው። ግለሰቡ የዳነው ግን በፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒት ሳይሆን ለካንሰር ይደረግለት በነበረው የስቲም ሴል ህክምና እንደሆነ ተገልጿል። • ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው • ኤች አይ ቪን የሚከላከለው መድሃኒት ተስፋ ሰጪ ነው ተባለ • ስለኤች አይ ቪ /ኤድስ የሚነገሩ 8 የተሳሳቱ አመለካከቶች ለህክምናው ስቲም ሴል የለገሱት ሰዎች ዘረመል ባልተለመደ መልኩ ኤች አይ ቪን የመከላከል አቅም ያለው ሲሆን በዚህ የዘረመል ባህሪ ምክንያት ኤች አይ ቪ ፖዘቲቭ የነበረው አዳም ካስቲሊዮም ሊፈወስ መቻሉ ተገልጿል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 ቲሞቲ ብራውን የተባለ የጀርመን ኤች አይ ቪ ህመምተኛ በዓለም ላይ ከኤችአይቪ የተፈወሰ የመጀመሪያው ሰው ነበር። ተመሳሳይ የስቲም ሴል ህክምና የተደረገለት ለሶስት ዓመት ተኩል ነበር። የስቲም ሴል ህክምና የበሽተኞችን የበሽታ ተከላካይ ህዋሶች ኤችአይቪን መቋቋም በሚችሉ የለጋሾች በሽታ ተከላካይ ህዋስ በመተካት የቫይረሱን መራባት ይገታል። የድህነት ታሪኩን በአደባባይ መናገር የመረጠው ሁለተኛው ተፈዋሽ አዳም ካስቲሊዮ 40 ዓመቱ ነው። በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት የኤችአይቪ ኢንፌክሽን በደሙ እንደሌለ ዶክተሮቹ አረጋግጠዋል። በዚህ ህክምና ላይ እየተደረገ ያለውን ምርምር የሚመሩት ፕሮፌሰር ኩማር ጉፕታ ለቢቢሲ ይህ ለኤችአይቪ ፈውስ እየተገኘ ለመሆኑ ማረጋገጫ እንደሆነ ገልፀዋል። "ያገኘውነው ነገር እንደሚያሳየው የስቲም ሴል ንቀለ ተከላ ለኤችአይቪ ፈውስ ነው። ይህንን የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በበርሊኑ ታማሚ አረጋግጠናል" በማለት ይህንኑ አሰራር መከተል እንደሚያዋጣ ተናግረዋል።
news-45041508
https://www.bbc.com/amharic/news-45041508
የምርጫ ውጤት መገለጹን ተከትሎ በዚምባብዌ ሶስት ሰዎች ተገድለዋል
ዚምባብዌ ታሪካዊ ነው የተባለለትን ምርጫ ካካሄደች በኋላ የምርጫው ውጤት ሲገለጽ በሃገሪቱ አለመረጋጋት የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ሦስት ሰዎች ተገድለዋል።
መንግሥት አመጹን ለማረጋጋት በሚል እየወሰደ ያለውን እርምጃ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና መንግሥታት እየተቹ ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት እና የሃገሪቱ የቀድሞ ቀኝ ገዢ የነበረችው እንግሊዝ በሃገሪቱ መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን መንግሥት እየወሰደ ካለው እርምጃ እራሱን እንዲቆጠብ ጭምር ጠይቀዋል። ሮበርት ሙጋቤ ተሳታፊ ባልነበሩበት ምርጫ ገዢው ፓርቲ ዛኑ-ፒኤፍ አሸናፊ መሆኑ ተገልጿል። ይሁን እንጂ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ዛኑ-ፒኤፍ ምርጫውን አጭበርብሯል ይላሉ። • ሙጋቤ የማይሳተፉበት የመጀመሪያው የዚምባብዌ ምርጫ • ዚምባብዌ እንዴት ሰነበተች? • 'መፈንቅለ መንግሥት' በዚምባብዌ? የገዢው ፓርቲ ዋነኛው ተቀናቃኝ ኔልሰን ቻሚሳ ፕሬዝደንት ኤምርሰን ምናንጋግዋን እንዳሽነፉ አውጀዋል። የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፖለቲከኞች ከአመጽ እንዲቆጠቡ የጠየቁ ሲሆን እንግሊዝ አመጹ ''እጅጉን እንዳስሰባት'' አሳውቃለች። በዚምባበውዌ የአሜሪካ ኤምባሲም ሁሉም አካላት ከአመጽ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ጠይቋል። የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ቡድን የሆነው አምነስቲ እንተርናሽናል በበኩሉ ተኩስ ከፍተው ህይወት ያጠፉ የመንግሥት ወታደሮች ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቋል። ከምርጫው በኋላ ምን ተፈጠረ? የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ገዢው ፓርቲ ዛኑ-ፒኤፍ የብሄራዊ ምክር ቤቱን መቀመጫ በሁለት ሦስተኛ ማሸነፉን ከገለጸ በኋላ በመዲናዋ ሃራሬ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ። የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህን አይነት የተቃውሞ ሰልፍን መንግሥት ''አይታገሰም'' ሲሉ አስጠነቀቁ። የተቃዋሚ ጥምር ፓርቲ መሪው ቻሚሳ መንግሥት ወታደሮችን በከተማ ውስጥ ማሰማራቱን እና ህይወት መጥፋቱን አጥብቀው ኮነኑ። ''ወታደሮች የሰለጠኑት በጦርነት ላይ ጠላት እንዲገድሉ ነው። እነኚህ ዜጎች የሃገር ጠላት ናቸውን?'' ሲሉም ጠይቀዋል። የምርጫ ኮሚሽኑ እንደሚለው ከሆን ድመጻቸውን ለመስጠት ከተመዘገቡ መርጫች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ድምጻቸውን ሰጥተዋል። የምርጫ ታዛቢዎች ምን ይላሉ? የአውሮፓ ህብረት ምርጫው ዘግይቶ ይፋ መደረጉን ኮንኗል። የመገናኛ ብዙሃን ጣልቃ ገብነት፣ መራጮችን ማዋከብ እና የምርጫ ኮሚሽን ላይ እመነት አለመኖሩን መታዘቡን የአውሮፓ ህብረት ገልጿል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራው የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ ቡድን በበኩሉ ምርጫው የተካሄደው ''እጅግ በጣም ሰላማዊ በነበረ ሁኔታ ውስጥ ነው። እንዲሁም ምርጫው በፉክክር የተሞላ ነበር'' ብሏል። የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ ቡድን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ክስ ማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል።
news-53492807
https://www.bbc.com/amharic/news-53492807
አንድ ሩሲያዊ ታጣቂ 20 ሰዎችን አውቶብስ ላይ አግቶ ከፖሊስ ጋር ተፋጧል
የዩክሬን ፖሊስ 20 ሰዎችን አውቶብስ ላይ አግቶ ከያዘው ሩሲያዊ ጋር ተፋጦ እንደሚገኝ ተነገረ።
ሩሲያዊው አጋች በከፍተኛ ደረጃ የታጠቀ ሳይሆን እንደማይቀር የተገመተ ሲሆን፤ አጋቹ ወደ ፖሊስ ሁለት ጊዜ መተኮሱን እና የእጅ ቦምብ ወርውሮ እንደነበረ ፖሊስ አስታውቋል። አጋቹ የወረወረው የእጅ ቦምብ እንዳልፈነዳ ተነግሯል። "አጋቹ ከአውቶብሱ ውስጥ ሆኖ ቦምብ ወርውሮ ነበር። መልካም አጋጣሚ ሆኖ ቦምቡ ሳይፈነዳ ቀርቷል" ይላል ፖሊስ ያወጣው መግለጫ። አጋቹ የሩሲያ ዜጋ የ44 ዓመት ጎልማሳ ማከሰይም ክራይቮሽ እንደሚባል እና ከዚህ ቀደም በወንጀል ድርጊቶች የተፈረደበትበን አጠናቆ ከእስር የወጣ ስለመሆኑ፤ እንዲሁም የአእምሮ ጤና ችግር አጋጥሞት የህክምና ድጋፍ ሲደረግለት እንደነበረ ተነግሯል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በማጭበርበር እና ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ በመያዝ በሚል የወንጀል ድርጊቶች 10 ዓመታትን በእስር አሳልፏል። በምሥራቅ ዩክሬን በምትገኘው ሉተስክ ከተማ 20 ሰዎችን አግቶ የያዘው ሩሲያዊ፤ ተቀጣጣይ ነገሮችን ታጥቆ እንደሚገኝ በማሳወቅ እውቅ ፖለቲከኞች እራሳቸውን "ሽብርተኛ ነን" ብለው እንዲጠሩ እየጠየቀ ስለመሆኑ ፖሊስ አስታውቋል። የአገሪቱ አቃቤ ሕግ በበኩሉ አጋቹ በከተማዋ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች በርቀት መፈንዳት የሚችሉ ቦምብ አጥምዶ እንደሚገኝ መናገሩን አስታውቋል። የዩክሬን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር አንቶን ሄራቼንኮ፤ ፖሊስ ጉዳዩን በድርድር ለመፍታት ካለው ፍላጎት የመነጨ አጋቹን ለማነጋገር ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል። በአውቶብሱ ላይ ለበርካታ ሰዓታት ታግተው የሚገኙት የታጋቾች ሁኔታ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። ፖሊስ የከተማዋ ነዋሪዎች በያሉበት እንዲቆዩ፤ ከቤት እና ከቢሯቸው እንዳይወጡ ጠይቋል። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎደሜይር ዜሌኒስኪ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆነም ተናግረዋል።
news-53568629
https://www.bbc.com/amharic/news-53568629
ዶናልድ ትራምፕ የወባ መድኃኒት ለኮሮናቫይረስ ፈውስ ነው አሉ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃይድሮክሲሎሮኩዊን ፍቱን መድኃኒት ነው ሲሉ በድጋሚ ተናገሩ።
ይህ የወባ መድኃኒት ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ፈውስ እንደማይሰጥ የዓለም ጤና ድርጅትም ሆነ የእርሳቸው የጤና አማካሪዎች በተደጋጋሚ የመሰከሩ ቢሆንም ትራምፕ ግን ወይ ፍንክች በማለት በአቋማቸው ጸንተዋል። እንዲያውም "ሃይድሮክሲክሎሮኩዊን እያጣጣላችሁት ያላችሁት እኔ ጥሩ ነው ስላልኩ ነው" ብለዋል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ። ትዊተር የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ይዘት ያለው አሳሳች ተንቀሳቃሽ ምስልን አጋርቷል በሚል ሰሌዳውን አጥፍቶበት ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ይህን አወዛጋቢ አስተያየት የሰጡት የልጃቸው የትዊተር ሰሌዳ ለጊዜው እንዲዘጋ መደረጉን ተከትሎ ነው። በጤና ባለሞያዎች ዘንድ ሀይድሮክሲክሎሪን ኮቪድ-19ን ይዋጋል የሚል አስተማማኝ ማስረጃ እስካሁን አልተገኘም። ከዚያ ይልቅ እንዲያውም መድኃኒቱ ለልብ ህመም ስለሚዳርግ ጥንቃቄ አድርጉ የሚሉ መረጃዎች ናቸው ተጠናክረው እየወጡ ያሉት። ለምሳሌ ባለፉት ወራት የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ባወጣው ማስጠንቀቂያ ይህ የወባ መድኃኒት ለአደገኛ የልብ ህመም ስለሚዳርግ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ዶናልድ ትራምፕ ይህን መግለጫ በሚሰጡበት ሰዓት በበሽታው የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር አሻቅቦ ታይቷል። በ24 ሰዓት ብቻ 1ሺህ 600 ሰዎች በመላው አሜሪካ መሞታቸው በወራት ውስጥ ያልተሰማ ክፉ ዜና ነው። ይህን ተከትሎ መድኃኒት ከተገኘ በሚል ካሜራ በመፈብረክ የሚታወቀው ኮዳክ ኩባንያ ወደ መድኃኒት ምርት የገባ ሲሆን ከመንግሥት 765 ሚሊዮን ዶላር ብድር አግኝቷል። ይህ በካሜራ ማምረት ሥራ ለዘመናት የቆየው ኮዳክ ኩባንያ ለቫይረሱ አዲስ መድኃኒት ሲገኝ ያንን ቶሎ አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ ነው ዝግጅት እያደረገ ያለው። ሀይድሮክሲክሎሮኩዊንን ለመጀመርያ ጊዜ በዓለም ላይ ዝናና እውቅና እንዲያገኝ ያደረጉት የ74 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲሆኑ ይህም በመጋቢት ወር ነበር የሆነው። ያን ከተናገሩ ከሁለት ወራት በኋላ ደግሞ ትራምፕ መድኃኒቱን ራሳቸው እየወሰዱት እንደሆነ በመናገር የጋዜጠኞችን አፍ አስከፍተዋል። አሁን ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ በዚህ መድኃኒት ዙርያ እጅግ ጥልቅ ንባብ ስለማድረጋቸውና መድኃኒቱ በሽታውን እንደሚፈውስ እንደደረሱበት ያለ ምንም ሀፍረት አብራርተዋል። "ይህን መድኃኒት ብትወስዱት ምንም አትጎዱም። እኔ አንድ ነገር ጥሩ ነው ስል ሁላችሁም በተቃራኒው ስለምትቆሙ ነው እንጂ መድኃኒቱ ፍቱን ነው" ብለዋል። ትራምፕ ሰኞ ማታ 'አሜሪካ ፍሮንትላይን ዶክተርስ' የሚባል አንድ የሐኪሞች ቡድን ስለ ሀይድሮክሲክሎሮኩዊን የተናገረውን ቪዲዮ አጋርተው መነጋገሪያ ሆነው ቆይተዋል። ፌስቡክም ሆነ ትዊተር ግን ፕሬዝዳንቱ ያጋሩትን ቪዲዮ ከሰሌዳቸው አንስቶባቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ ሐሰተኛ መረጃ ነው በሚል ነው። ሆኖም ፌስቡክና ትዊተር እርምጃውን ከመውሰዳቸው በፊት ቪዲዮዉን 17 ሚሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል። ትዊተር እንዲያውም ይህንኑ ቪዲዮ የፕሬዝዳንቱ የበኩር ልጅ በማጋራቱ ልጁን ለ12 ሰዓታት ከትዊተር አግዶ አቆይቶታል። በዚህ ቪዲዮ ላይ የምትታየው ዶ/ር ስቴላ ኢማኑኤል የተባለች ሴት በርካታ ስሜት የማይሰጡ ንግግሮችን ከተናገረች በኋላ ሀይድሮክሲክሎሮኩዊንን በመጠቀም 350 ሰዎችን እንደፈወሰች ስትናገር ትታያለች። ዶናልድ ትራምፕ በምሽቱ መግለጫቸው ይህቺን ሴት ዶክተር መድኃኒቱን በማድነቋ እጅግ አድርገው አሞካሽተዋታል። ትራምፕ ሰኞ ዕለት ከከፍተኛ የጤና አማካሪያቸው ከዶ/ር አንተኒ ፋውቺ አቋም የሚጻረሩ በርካታ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን ጋዜጠኞች ይህን ተከትሎ ከዶ/ር ፋውቺ ጋር ቅያሜ ይኖራቸው እንደሁ ፕሬዝዳንቱን ጠይቀዋቸዋል። ትራምፕ በሰጡት ምላሽ ከዶ/ር አንተኒ ፋውቺ ጋር በተደጋጋሚ የሐሳብ ልዩነት እንደሚያሳዩ አልካዱም። ሆኖም ግን ይህ ተፈጥሯዊ ነው ብለዋል። "ቫይረሱ የተቀሰቀሰ ሰሞን እኔ ድንበራችንን ለቻይና እንዝጋ ስል ዶ/ር ፋውቺ ተቃውሞኝ ነበር። አሁን ያን ውሳኔ በመወሰኔ ዶ/ር ፋውቺ ያደንቀኛል። . . . እርሱ በአሜሪካዊያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው፤ ያ ለእኔና እኔ ለምመራው አስተዳደር መጥፎ ነገር አይደለም" ብለዋል ትራምፕ። ዝነኛው የጸረ ተላላፊ በሽታዎች ጠቢብ ዶ/ር ፋውቺ ዶናልድ ትራምፕ ስለሚያሞካሹት ሀይድሮክሲክሎሮኩዊን መድኃኒት ከዚህ ቀደም በኤቢሲ ቴሌቪዥን ተጠይቀው መድኃኒቱ ለኮሮናቫይረስ ምንም እርባና እንደሌለው በማያሻማ ሁኔታ ተናግረዋል። ትራምፕ ስለምን ዶ/ር ፋውቺና ሌሎች አማካሪዎቻቸው በአሜሪካዊያን ዘንድ ከርሳቸው ይልቅ ተቀባይነት እንዳላቸው ተጠይቀው ነበር። ትራምፕ ሲመልሱ "ባህሪዬ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። አሜሪካ በአሁኑ ሰዓት 4.3 ሚሊዮን ሰዎች በቫይረሱ ተይዘውባል። የሟቾች ቁጥርም መቶ ሺህ ተኩል አልፏል።
news-56156451
https://www.bbc.com/amharic/news-56156451
ኮሮናቫይረስ፡ ኦማን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ10 አገራት የሚመጡ መንገደኞችን አልቀበልም አለች
ኦማን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአስር አገራት የሚመጡ መንገደኞችን ለቀጣዮቹ 15 ቀናት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት የተነሳ እንደማትቀበል አስታወቀች።
ኦማን እገዳ ከጣለችባቸው አስር አገራት መካከል ስምነቱ የአፍሪካ አገራት ሲሆኑ እነሱም ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ጋና፣ ጊኒ እና ሴራሊዮን ይገኙባታል። ቀሪዎቹ ሁለት አገራት ደግሞ የመካከለኛ ምሥራቅ አገሯ ሌባኖስና የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል ናቸው። እንደ ኦማን የጤና ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ከሆነ የአገሪቱ ዜጎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ቤተሰቦቻቸው ብቻ ከእነዚህ አገራት የሚመጡ ከሆነ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል። ኦማን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከምሥራቅ አፍሪካ ወደ አገሯ ከገቡ መንገደኞች መካከል 18 በመቶ ያህሉ በኮሮናቫይረስ ተይዘው በመገኘታቸው ነው። ከኦማን ጋር የታሪክ እና የባህል ትስስር ላላቸው አገራት ይህ ውሳኔ አስደንጋጭ ነው ተብሏል። ዕገዳው ከተጣለባቸው መካከል የምትገኘው ታንዛኒያ ካለፈው ዓመት ግንቦት ወር ጀምሮ አንድም በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው በአገሯ ስለመኖሩ አላሳወቀችም። ለበርካታ ወራት ከኮቪድ ወረርሽኝ ነጻ መሆኗን ስትናገር የቆየችው ታንዛኒያ በድንገት ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ሕዝባቸው ከኮቪድ-19 እንዲጠነቀቅ ምክራቸውን ለግሰዋል። እንደ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ ያሉ አገራት ደግሞ በየዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በቫይረሱ የተያዘ ሰው እየመዘገቡ ነው። እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ከሆነ ኦማን 140,000 በኮሮና ተሕዋሲ የተያዙ ሰዎች በአገሯ መኖራቸውን በምርመራ ስታረጋግጥ ከእነዚህ መካከል 1,500 ያህሉ ሞተዋል። በኦማን ከባለፈው ወር ጀምሮ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቀስ በቀስ መጨመር እያሳየ ነው።
news-49342543
https://www.bbc.com/amharic/news-49342543
የቀድሞው የአንጎላ መሪ ልጅ የ15 ሚሊዮን ዶላር ቤቷን አፍርሳ ልትገነባ ነው
ለበርካታ አስርት ዓመታት አንጎላን የመሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ልጅ ለንደን ውስጥ ያላትን ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ቅንጡ መኖሪያ ቤቷን አፍርሳ ልትገነባ መሆኑ ተነገረ።
ኢዛቤላ ዶስ ሳንቶስ ከዓለማችን ውድ ከተሞች መካከል በምትጠቀሰው ለንደን ውስጥ ያላትን ግዙፍ ቅንጡ መኖሪያ ቤቷን አፍርሳ እንደገና ልታስገነባው መሆኑን የእንግሊዙ ታይምስ ጋዜጣ ዘገበ። የናጠጡ ሃብታም ከሚባሉት አፍሪካዊያን ሴት መካከል እንደሆነች የሚነገርላት ቢለየነሯ የቀድሞው የአንጎላ ፕሬዝዳንት ልጅ ኢዛቤላ የቤቱ ባለቤት መሆኗ የታወቀው ፈርሶ በሚገነባው ውድ ቤት ዕቅድ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ እንደሆነ ተዘግቧል። • "ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል" ደበበ እሸቱ • የውሃ እጥረት ዋነኛው የዓለማችን ስጋት • ካለሁበት 30፡ መስቀል እና አረፋን ሳስታውስ ውስጤ ይረበሻል የተትረፈረፋቸው ባለጸጎች ይኖሩበታል ተብሎ በሚነገርለት ኬንሲንግተን በተባለው የለንደን ክፍል ውስጥ የሚገኘው ፈርሶ የሚገነባው የኢዛቤላ ዶስ ሳንቶስ መኖሪያ ቤት ዕቅድ በጎረቤቶቿ ዘንድ ቁጣን እንደቀሰቀሰ ተገልጿል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ ግን ኢዛቤላ መልሳ ልትገነባው ያሰበችውና ድንቅ የሥነ ህንጻ ምኞቷን እውን ለማድረግ ያሰበችውን የቤቷን ግንባታ ዕቅድ በዙሪያዋ ባሉ ነዋሪዎች ተቃውሞ ቢቀርብበትም ግንባታውን ለማከናወን ከሚመለከተው አካል ፈቃድ አግኝታለች። በእንግሊዝ ጋዜጦች ላይ የወጡ ዘገባዎች የግዙፉን ቤት ፎቶ ግራፎች ይዘው የወጡ ሲሆን ኤዛቤላ ዶስ ሳንቶስ ቤቱን ከ12 ዓመት በፊት መግዛቷን ጠቅሰዋል።
news-46232017
https://www.bbc.com/amharic/news-46232017
ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣኑን ባቡር በይፋ አስመረቀች
ሞሮኮ በአፍሪካ ፈጣን የሆነውን ባቡር አስመረቀች ፤ ባቡሩ የንግድ ከተማ ከሆነችው ካዛብላንካ ወደ ኢንዱስትሪ ማዕከሏ ታንጌር ለመሄድ የሚወስደውን ጊዜ በግማሽ ይቀንሳል።
በምረቃ ሥነ ስርዓቱም ላይ የሞሮኮው ንጉስ መሃመድ ስድስተኛና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባቡሩን ለመመረቅ ከታንጊያር ከተማ ወደ መዲናዋ ራባት ጉዞ አድርገዋል። • ስሜታዊ ድራማ በሙምባይ ባቡር ጣቢያዎች ውስጥ • የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ መቱ • ሜጀር ጄኔራል ክንፈ: ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም፤ ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’ ባቡሩ በሰዓት 320 ኪሎሜትር ወይም 198 ማይል ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ከዚህ ቀደም ከካዛብላንካ ወደ ታንጊር ለመሄድ በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር ወይም 124 ማይል ይወስድ የነበረውን በግማሽ ቀንሶታል። የሞሮኮው አዲሱ ባቡር በደቡብ አፍሪካ መዲና ጆሐንስበርግ ከሚገኘው ኦሊቨር ታምቦ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማዋ የንግድ መናሀሪያ ሳንተን የሚያጓጉዘውን ፈጣን ባቡር በእጥፍ ይበልጠዋል። ባቡሩ 2.4 ቢሊየን ዶላር (22.9 ቢሊዮን ድርሃም) እንደፈጀና በ7 ዓመታት እንደጠናቀቀ የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።
news-52975241
https://www.bbc.com/amharic/news-52975241
ኮሮናቫይረስ ያቀጣጠለው የቻይናና የአሜሪካ ፉክክር በአፍሪካ
ዘግየት ብሎ የኮሮናቫይረስ በተከሰተባት አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አሜሪካና ቻይናም ለአህጉሪቱ ከፍተኛ ድጋፍ በመስጠት እኔ እበልጣለሁ በሚል እሰጣገባና እሽቅድምድሞሽ ተጠምደዋል።
ሁለቱ አገራት እያደረጉት ያለው ፉክክር በአፍሪካ የቫይረሱን ስርጭት ከመቆጣጠር በዘለለ ኃያልነታቸውን የማስፈን ተግባር እንደሆነ የቢቢሲ አፍሪካ ዘጋቢው አንድሪው ሃርዲንግ ያትታል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ ከሰሞኑ "በአፍሪካ ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ትግል የሚደግፍ ከአሜሪካ በላይ አገር ከየትም አይመጣም" ያሉ ሲሆን አክለውም "ለዓለም አቀፉ የጤና ሥርዓት አሜሪካ እንደምታደርገው ድጋፍ የትኛውም አገር አድርጎ አያውቅም፤ መቼም አይደረግም" ብለዋል። ማይክ ፖምፔዮ ይሄንን ያሉት በአፍሪካ ውስጥ ካሉ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው። የቢቢሲው አንድሪው ሃርዲንግም 'አንዱ እኔ ነበርኩ" ይላል። ባለፈው ወርም እንዲሁ በትራምፕ አስተዳደደር የተለመደውን "ማንኛውም አገር ከእኛ በበለጠ አይሰራም" የሚለውን ንግግር ከአሜሪካ ባለስልጣናት የተሰማ ሲሆን፤ እንዲህ አይነት ተደጋጋሚ ንግግርም የሚሰማው አገሪቱ ለዓለም ጤና ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ ከማቋረጧ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ትችቶችን ፀጥ ለማሰኘት ነው። በተለይም አሜሪካ ለድርጅቱ ታደርገው የነበረውን ድጋፍ ይህ ዓለም አቀፍ ቀውስ ጣራ በነካበት ወቅት ከማቋረጧ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ወቀሳቸውን አሰምተዋል። አሜሪካም ከዚህ ለማምለጥ ጥረት እያደረገች ነው። በጋና የሚገኙ ህፃናት ለሜላኒያ ትራምፕ አቀባበል ሲያደርጉ ማይክ ፖምፔዮ አሜሪካ ለአፍሪካ አድርጋዋለች ብለው ከሚኮሩበት የገንዘብ እርዳታ መጠን በቅርቡ የተለገሰው 170 ሚሊዮን ዶላር ነው። ነገር ግን ይህ የገንዘብ መጠን ከቻይና እንደ አገር ከተሰጠው ቀርቶ ቻይናዊው ቢሊየነር ጃክማ ከሰጠው ጋር ሲወዳደር ያንሳል። ከሰሞኑ የአሜሪካና የቻይና ባለስልጣናት አህጉሪቷ ጋር በተያያዘ የሚያደርጓቸውን ንግግሮችን ለታዘበ አፍሪካ ለሁለቱ ኃያላት አገራት አዲሱ የቀዝቃዛ ጦርነት ሜዳ መሆኗን ለመረዳት አይቸገግርም። ከዚህ ቀደምም ሁለቱ አገራት የነበራቸው የቃላት ጦርነት በኮቪድ-19 ቀውስ የተባባሰ ሲሆን አህጉሪቷንም ማዕከል በማድረግ ወደ ውክልና ጦርነት እያመሩ ይመስላሉ። "የከሸፈው መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ" በቅርቡ በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ስር ያለው ግሎባል ታይምስ ይዞት በወጣው ፅሁፍ አገሪቱ እያራመደች ያለችው የፖለቲካ ሥርዓት የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመግታት እንዴት እንደጠቀማት ያትታል። በመቀጠልም የከሸፈው የምዕራባውያን መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ በአፍሪካ አገራት ላይ ኢ-ፍትሃዊነት፣ ተበላላጭነት፣ የብሔርና የሐይማኖት መከፋፈል፣ ግጭት እንዲሁም የህይወት መጥፋትና የንብረት መውድም ማስከተሉን አስፍሯል። እናም አፍሪካውያን ከዚህ ከከሸፈ ሙከራ ራሳቸውን ገሸሽ በማድረግ የቻይናን የአንድ ፓርቲ መንገድ ሊከተሉ እንደሚገባም ምክር ለግሷል። በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ስር ያለ ዕለታዊ የቻይና ጋዜጣም እንዲሁ ቻይና በአህጉሪቷ መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ እያፈሰሰችው ያለችውን መዋዕለ ንዋይና ኢንቨስትመንት አፍሪካን ከታሪካዊ ጭቆና እንዲሁም አሁን ካለችበት መበዝበዝ ያድናታል ብሏል። "አፍሪካ ለምዕተ ዓመታት በባርነት ቀንበር፣ ቅኝ ግዛት፣ እጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ አሁን ደግሞ በኮሮናቫይረስ ቀውስ ውስጥ ገብታለች። የቻይና የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አላማም አህጉሪቱ ከዚህ አዙሪት እንድትወጣና እንድታገግም ነው" በሚልም አስፍሯል። የቻይና መንግሥት ለአፍሪካ እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት ማንቆለጳጰስ ለማይክ ፖምፔዮ አልተዋጠላቸውም። የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ በአፍሪካውያን ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍና ለረዥም ዘመናት የሚቆይ የእዳ ጫና እየከመረባቸው ነው ሲሉ ወርፈዋል። በቅርብ ቀናትም የቻይናና አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ አንድ ውይይትም ተደርጎ ነበር። የውይይቱ አስተናባሪ ሁለቱ አገራት በአህጉሪቱ ላይ የሚያደርጉትን እሽቅድምድም "መርዛማ" ብለውታል። በወቅቱም አንድ የቻይና ፐሮፌሰር ኮሮናቫይረስ ለአፍሪካውያን ጋዜጠኞች የቻይናን የሚዲያ እሴቶችና ጥሩ ተሞክሮ እንዲያደንቁ አድርጓቸዋል ብለዋል። "የምዕራባውያን ሚዲያ በጨለምተኛ ዜና የተሞላ ነው፤ ሁሌም አሉታዊ ነው" ያሉት ፕሮፌሰር ዛንግ ያንኪዩ በእንደዚህ አይነት ቀውስ ወቅት ግን ተስፋን የሚፈነጥቁ ታሪኮችን ሰዎች ማንበብ ይፈልጋሉ ብለዋል። በሌላ መንገድ አፍሪካውያን የቻይና የሚዲያ ሞዴል የሆነውን 'ገንቢ ጋዜጠኝነት'ን (constructive journalism) ይፈልጋሉ ብለዋል። በቅርቡም ፕሮፌሰሯ በኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ዘንድ ለገንቢ ጋዜጠኝነት ያላቸውን ጉጉትና ፍላጎት መታዘባቸውን አስረድተዋል። ነገር ግን ጥያቄው የአፍሪካ ጋዜጠኝነት እንዲህ በቀላሉ ተፅእኖ ውስጥ የሚወድቅ ነው? በንግግራቸው አወዛጋቢ የሚባሉት ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ፀረ-ተህዋሲ (ዲስኢንፌክታንት መጠቀም) እንዲሁም የፀሐይ ጨረር ፈውስ ነው ማለታቸው በአፍሪካውያን ዘንድ ያላቸውን ስም የበለጠ አላጠለሸውም ወይ ተብለው የተጠየቁት ማይክ ፖምፔዮ በቀጥታ አልመለሱም። ነገር ግን ትራምፕ የሚያደርጓቸው ንግግሮችን ብዙ ሰው እንደማይረዳው እንዲሁም በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ ሚዲያዎች ሆን ተብሎ ሌላ ትርጉም ይሰጣቸዋል ብለዋል። ከማይክ ፖምፔዮ ጋር የነበረው ቆይታ ለበርካታ ጋዜጠኞች እንግዳ የሆነ ክስተት የተስተናገደበት ነበር። ለአስርት ዓመታት አሜሪካ በአፍሪካ የምትከተለው ዲፕሎማሲ በተወሰነ ደረጃ አምባገነን መንግሥታትን የሚቃወም፣ ከሳንሱር ነፃና ገለልተኛ ጋዜጠኝነትን መሰረት ያደረገ ነበር። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሚተቿቸውን የአገራቸውን ጋዜጠኞች "ሐሰተኛ" "የሕዝብ ጠላት" በማለት መወንጀልና ማዋረድ የየዕለት ሥራቸው ሆኗል። ምናልባትም የአሜሪካና የቻይና ገንቢ የጋዜጠኝነት ሃሳብ መንግሥትን አለመተቸት ከሆነ እሳቤያቸው ተቀራርቧል ማለት ይቻላል። በቀድሞው የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ወቅት አሜሪካ ፔፕፋር በተባለው ፕሮግራም ለኤድስ የሚውል እርዳታን ለአፍሪካ የጤና ሥርዓት ተለግሷል። አሜሪካ ካላት የውስጥ ትግልና መከፋፈል ጋር ተያይዞ በአሁኑ ሰዓት ቻይና የኮሮናቫይረስን ሽፋን በማድረግ በአፍሪካ ላይ ፖለቲካዊ አጀንዳዋን ለማስረፅና አሻራም ለማሳረፍ ጥረት እያደረገች ትገኛለች። የአፍሪካ አገራትም ሆነ ጋዜጠኞች ባለው የልዕለ ኃያላን ጉልበት ተጽእኖ ተንበርክከው የሚያሸረግዱ ላይሆኑ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን በርካታ አገራትም ባለባቸው ከፍተኛ የቻይና የብድር ጫና እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ባስከተለው የኢኮኖሚ ድቀት የተነሳ "የከሸፈ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓትን" ገሸሽ በማድረግ የቻይናን የፖለቲካ ሥርአት ይቀበሉ ይሆን? የምናየው ይሆናል።
news-50626172
https://www.bbc.com/amharic/news-50626172
በህንድ በቡድን ተደፍራ የተገደለችው የ27 ዓመቷ ዶክተር ጉዳይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ
በህንድ ሃይደራባድ በምትባል ግዛት አንዲት የ27 ዓመት የእንስሳት ዶክተር ተደፍራ መገደሏ ከተሰማ በኋላ ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሷል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም በከተማዋ የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሰልፍ በመውጣት ግለሰቦቹ የሞት ቅጣት ይገባቸዋል በሚል ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። የሟች ቤተሰቦች ልጃቸው ጠፍታ በነበረበት ወቅት ፖሊስ ኃላፊነቱን በሚገባ አልተወጣም በማለታቸውም እስካሁን ሶስት የፖሊስ አባላት ከስራ ታግደዋል። • የተነጠቀ ልጅነት • የታዳጊዋ ሬስቶራንት ውስጥ መደፈር ደቡብ አፍሪቃውያንን አስቆጥቷል የሟች ቤተሰቦችም ሊጎበኟቸው የሚመጡ ፖለቲከኞችንም ሆነ የፖሊስ ኃላፊዎች ገዳዮችዋን ለፍርድ እስካላቀረቡ ድረስ ወደ ቤታቸው ዝር ማለት እንደማይችሉ አሳውቀዋል። የግለሰቧ የተቃጠለና የጠቆረ አስከሬን የተገኘው ባለፈው ሃሙስ ዕለት ነው። ከመሞቷም በፊት በቡድን እንደተደፈረችም ፖሊስ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከግድያዋ ጋር ተያይዞ አራት ወንዶች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የሁለቱ ወንዶች እናቶችም ጥፋተኛ ከሆኑ እንዲቀጡ መንግሥትን በመማፀን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። •የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት •"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" "ማንኛውንም ቅጣት ይቀጡ፤ እኔም ሴት ልጅ አለችኝ" በማለት አንደኛዋ እናት 'ለትረስት ኦፍ ኢንዲያ ሚዲያ' ተናግረዋል። የግለሰቧ ሞት ብሔራዊ ቁጣንም ቀስቅሷል፤ ብዙዎችም ጥቃት አድራሾቹ በሞት እንዲቀጡ እየጠየቁ ነው። በአብዛኛው የሃገሪገቷ ክፍል ከተቃውሞ ሰልፍ በተጨማሪ የሻማ ማብራት ስነስርዓትም ተካሂዷል። በሃይደራባድ ግዛትም በሟቿ መኖሪያ ቤት በር ላይ ማህበረሰቡ "ፖሊስ፣ ሚዲያ፣ የውጭ ሰውም አንፈልግም፤ ሃዘን አያስፈልገንም፤ ፍትህ ብቻ ነው የምንሻው" የሚሉ መፈክሮችንም ይዘው ታይተዋል። ታዋቂ ፖለቲከኞችም ሴቶች በየቀኑ የሚያልፉበትን ጥቃት ልንቀበለው አይገባም በሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እስካሁን ዝምታን መርጠዋል። ሟቿ ረቡዕ ዕለት የዶክተር ቀጠሮ ስለነበራት ከቤቷ የወጣችው አስራ ሁለት ሰዓት ላይ ነበር። ትንሽ ቆይታም ለቤተሰቦቿ ደውላ የሞተር ሳይክሏ ጎማ መተንፈሱንና አንድ ጭነት መኪና ሊረዳት መሆኑን ነግራቸው ነበር። • "በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል" • መአዛን በስለት ወግቶ ከፖሊስ ያመለጠው አሁንም አልተያዘም ያም የስልክ ልውውጥ የመጨረሻ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ድምጿም አልተሰማም። አስከሬኗም በድልድይ ውስጥ ተጥሎ አንድ ወተት በሚሸጥ ሰው አማካኝነት ሐሙስ ጥዋት ተገኘ። ምንም እንኳን በህንድ ህግ መሰረት በመደፈር ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ማንነት እንዳይገለፅ የሚያዝ ቢሆንም አርብ እለት የግለሰቧን ስም በትዊተር ሰዎች ሲቀባበሉት ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ፍትህን በመሻት ቁጣቸውን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በመዲናዋ ደልሂ ከሰባት አመታት በፊት በአውቶብስ ውስጥ በቡድን ተደፍራ የተገደለችው አንዲት ተማሪን ተከትሎ መንግሥት ትኩረት ቢያደርግም አሁንም ቢሆን መደፈርና ግድያ በከፍተኛ ቁጥር እያሻቀበ እንደሆነ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ከሁለት አመታት በፊት ፖሊስ ባወጣው መረጃ 33 ሺ 658 የመደፈር ኬዞች የተመዘገቡ ሲሆን፤ ይህም በየቀኑ የምትደፈረውን ሴት ቁጥር ወደ 92 ያደርሰዋል።
news-54223312
https://www.bbc.com/amharic/news-54223312
'ዘ ሻዶው ኪንግ'ን ለመፃፍ አስር ፈታኝ አመታት እንደወሰደባት ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ ትናገራለች
ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ሴት የነፃነት ታጋዮችን በሚዘክረው 'ዘ ሻዶው ኪንግ' መፅሃፏ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ ለቡከር ሽልማት እጩዎች መካከል አንዷ ሆናለች።
ለነፃነት በተደረገው ትግል ላይ የጥቂት ወንዶች ሚና በጎላበት ሁኔታ ሴት ነፃነት ታጋዮች ከታሪክ መዝገብ መፋቃቸውንና ግዙፍ አስተዋፅኦቸው ምን ይመስል ነበር በማለት አስርት አመታትን ወደ ኋላ ተጉዛም መዓዛ በ'ዘ ሻዶው ኪንግ' ታስቃኛለች። የፅሁፍ ስራው ግን ቀላል አልነበረም፤ መዓዛ እንደምትለው ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች የተደራረቡበት ሁኔታም ነበር። ጣልያንኛ መማር ነበረባት እንዲሁም የመጀመሪያ ረቂቅ ፅሁፉን ለማጠናቀቀም አሰልቺና አድካሚ የሚባሉ አምስት አመታት ፈጅተውባታል። በመሰላቸት ፅሁፉን ጥላው እንደነበርም ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ሬድዮ ፕሮግራም ተናግራለች። "በጣም ፈታኝና ከፃፍኩዋቸው ሁሉ መጥፎ የምለው ነው። እስርስር አድርጎኝ ነበር፤ የሞራል ውድቅትም ደርሶብኝ ነበር። የመጀመሪያ ረቂቄንም ጥዬ እንደገና ከዜሮ ጀምሬያለሁ" ብላለች። መፅሃፏንም ፅፋ ለማጠናቀቅ አስር አመት ወስዶባታል። ስለ ፅሁፍ ስታወራም " የፅሁፍ ስራ በደንብ ውስጥን መመልከትና መነሳሳትን ይጠይቃል። አንዳንዴ ወንበሬ ላይ ተቀምጬ መፃፍም ከፍተኛ ትግል ነበረው። ከመፅሃፌም ጋር አብሬ አድጌያለሁ። ለዚህ ሽልማትም ዕጩ በመሆኔ የተሰማኝ ፍፁም ደስታ ነው" ትላለች። መጽሐፉ መቼቱን ያደረገው የሁለተኛው አለም ጦርነት ጅማሮ የሚባለውና ፋሽስት ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ነው። "ስለ ጣልያኖች በተለምዶ የሚባሉ ነገሮችን ማካተት አልፈለፈግኩም፤ ስለዚህ ጣልያንኛ ተማርኩ። ጣልያኖችን አዋርቻለሁ። የወታደሮቹን ልጅና ልጅ ልጆችም እንዲሁ። በጦርነቱ ወቅት የመዘገቧቸውን ሁኔታዎች፣ ደብዳቤዎችና የግል መረጃዎችም በራሴ ፈትሻለሁ" ትላለች መዓዛ "የቋንቋ ችሎታዬም ሲዳብር፣ ገፀ ባህርያቶቼም እየተወሳሰቡ መጡ" በማለትም ታስረዳለች። በዩናይትድ ኪንግደም የፅሁፍ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው የቡከር ሽልማት በእንግሊዝኛ ለተፃፉ ድርሰቶች ሽልማትን ይሰጣል። በዩናይትድ ኪንግደም፣ አየርላንድ ለታተሙ ወይም ዬየትኛውም አገር ዜጎች ፅሁፋቸው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሆኑ ነው። ከመዓዛ መንግሥቴ በተጨማሪ የዚምባብዌዋ ፂፂ ዳንጋሬምባም 'ሞርነብል ቦዲ' በሚለው ድርሰቷ እጩ ሆናለች። አሸናፊዎቹም ህዳር መጀመሪያው ሳምንት ላይ ለህዝብ ይፋ ይሆናሉ።
news-53900409
https://www.bbc.com/amharic/news-53900409
የኢትዮጵያ መንግሥት ኤምባሲውን በተመለከተ ቅሬታውን አሰማ
የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባጋጠመው ክስተት አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ የብሪታኒያ ኤምባሲ ከፍተኛ ባለስልጣን በይፋ ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ተገለጸ።
ይህ የሆነው በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጅ ላይ ከሰሞኑ ለተቃውሞ በተሰበሰቡ ኢትዮጵያዊያን ሰልፈኞች የአገሪቱ ባንዲራ እንዲወርድ በመደረጉና በኤምባሲው ሠራተኛ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ነው። በዚህም ሳቢያ አምባሳደር ሬድዋን ኤምባሲው ላይ ስለተከሰተው ነገር በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታኒያና የዩናይትድ ኪንግደም ቻርጅ ዲ አፌር ለሆኑት አሌክስ ካሜሩን የመንግሥታቸውን ቅሬታ አቅርበዋል። በዚህም ለንደን በሚገኘው ኤምባሲ ዙሪያ እየተከሰቱ ባሉ ጉዳዮችና የጽህፈት ቤቱን ደኅንነት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት የተሰማውን ቅሬታ ለኤምባሲው ባለስልጣን አሳውቀዋል። ጨምረውም ዩናይትድ ኪንግደም በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት የአገሪቱን ኤምባሲና ሠራተኞች ከየትኛውም አይነት ጣልቃ ገብነት መጠበቅ እንዳለባት አሳስበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይም የዩናይትድ ኪንግደም ቻርጅ ዲ አፌር አሌክስ ካሜሩን በኤምባሲው ላይ ስላጋጠመው ክስተት ይቅርታ መጠየቃቸውን ጠቅሶ፤ አገራቸው የኤምባሲውን ደኅንነት ለማስጠበቅ ተገቢውን እርምጃ ትወስዳለች ማለታቸውን ገልጿል። በኤምባሰው ደጅ ተሰባስበው ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩትን ከስፍራው እንዲሄዱ በፖሊስ በተደረገው ጥረት መካከል ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉ በስፍራው የነበረ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ተናግሯል። በኤምባሲው ደጅ ተሰብስበው ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩት ሰዎች በፖሊሶች ከቦታው ገለል እንዲሉ በተደረገው ጥረት ከተፈጠረ ግብግብ በኋላ በወቅቱ በፖሊስ የተያዙ መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሏል። ተቃዋሚዎቹ በኤምባሲው ደጅ ላይ በመሰባሰብ መንግሥትን የሚቃወም መፈክሮችን ሲያሰሙ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይም በኤምብሲው ህንጻ ላይ በመውጣት የአገሪቱን ባንዲራ አውርደው በሌላ ተክተዋል። ለንደን የሚኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በይፋዊ የትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት ሰኞ ዕለት "ተቃውሞ ለማሰማት የመጡ ጥቂት ሰልፈኞች በአንድ የኤምባሲው ሠራተኛ ላይ ድብደባ መፈጸማቸውንና የኤምባሲው አገልግሎት እንዲስተጓጎል መደረጉን" ገልጿል፡፡ ኤምባሲው አክሎም በአሁን ሰዓት ጥቃት የደረሰበት የኤምባሲው ሠራተኛ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝና ጥቃቱን የፈጸሙት ዜጎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አስታውቋል፡፡ ቢቢሲ ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የኤምባሲው ሰራተኛ በኤምባሲው ደጃፍ በተከሰተው ተቃውሞ ራሳቸውን ጨምሮ ሌሎች የኤምባሲው ሠራተኞች ለደኅንነታቸው በመስጋት በቤታቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። ከዚህ ቀደምም ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ተቃዋሚዎች ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸማቸው የሚታወስ ሲሆን አንድ ግለሰብ ላይም ጥቃት ተፈጽሞ ነበር።
43565707
https://www.bbc.com/amharic/43565707
ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰዎች ምን ይጠብቃሉ?
የኢህአዴግ ምክር ቤት ለሳምንት ካደረገው ስብሰባ በኋላ ዶ/ር አቢይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀ-መንበር አድርጎ መምረጡን ይፋ አድርጓል። በዚህም ዶ/ር አቢይ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ካቀረቡበት ዕለት አንስቶ ማን ሊተካ ይችላል የሚለው ጥያቄ በሃገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ዋነኛ ጉዳይ ሆኖ ከአንድ ወር በላይ ቆይቷል። ዶ/ር አብይ አህመድ የገዢው ፓርቲ ሊቀ-መንበር ሆነው በመመረጣቸው የተለያዩ ሰዎችን አስተያየትና ምን እንደሚጠብቁ ጠይቀናል። አቶ የሽዋስ አሰፋ፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር የሚመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን መሆን ያለበት የህዝቡን ጥያቄ የተረዳና አስፈላጊውን ለውጥ ሊያግዝ የሚችል መሆን አለበት። ዶ/ር አብይ አህመድም በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የለውጥ ፍላጎትና እንቅስቃሴ በደንብ ይረዱታል። መጀመሪያ የቀሩተን የፖለቲከኞችና የህሊና እስረኞችን ሙሉ በሙሉ መፍታት፤ ሁለተኛው ደግሞ እነርሱን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ ውይይት ማድረግ ከዚያም መስተካከል ያለባቸውን ተቋማት አስተካክሎ ህዝቡ በመረጠው እንዲተዳደር ማድረግ ናቸው። በኦህዴድ አካባቢ ለህዝቡ ጥያቄ የተሻለ ግንዛቤ ነበር። ዶ/ር አቢይም ከዚህ በፊት ባደረጉት ንግግር ለህዝቡ ጥያቄ ቀና ምላሽ እንዳላቸው ገልጠዋል። እንግዲህ አሁን ይህንን ጥያቄ የሚመልሱበት ታሪካዊ አጋጣሚ ላይ ይገኛሉ ሲሉ መልካም እኞታቸውን ያክላሉ። አቶ በቀለ ገርባ፡ የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር ዋናው ማን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ሳይሆን በምን ፖሊሲዎችና በምን ርዕዮተ-ዓለም ዙሪያ ነው ሀገሪቱ የምትመራው የሚለውን መመልከት ነው። ያንን የምናይ ከሆነ ከበፊቱ ምንም የተለየ ለውጥ ይመጣል ብለን አናስብም። ነገር ግን ግለሰቦችም የራሳቸው ሚና እንደሚኖራቸው ይታወቃል ። ስለዚህ አሁን የኢህአዴግ ሊቀ-መንበር የሆኑት እና ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት ግለሰብ ጦር ሠራዊቱንና ደህንነቱን ምን ያህል ይቆጣጠሩታል? የሚለውን እና እነዚህ ተቋማት ሕገ-መንግሥቱ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው ከፖለቲካ ነፃ ሆነው አመራር እንደሚቀበሉ፣ ምን ያህል ለሕገ-መንግሥቱ ታማኝ እንደሚሆኑ፣ በዚያው ልክም ደግሞ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ያላቸው ታዛዥነት እንዴት እንደሚሆን፤ የሀገሪቱን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስን ይመስለኛል ይላሉ። የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊ ነው ብለን አናምንም ይልቁኑም ከታወጀ በኋላ መፍትሔ ሳይሆን የተለያየ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲገጥመው እና ሁከት ሲፈጠር ነበር። ስለዚህ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾም በኋላ ይህንን አዋጅ ማንሳት የሚችሉ ከሆነ እንደ አንድ ትልቅ መነሻ ይሆናል ብለን ነው የምንገምተው። አቶ ጃዋር ሞሃመድ፡ አክቲቪስትና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትውርክ ዳይሬክተር በኦሮሚያ ደረጃ የታዩ ለውጦች ወደ ፌደራል ይሸጋጋራሉ የሚል ተስፋ አለኝ። በተጨባጭ ግን ምን ለውጥ ይመጣል የሚለውን በጊዜ ሂደት የሚታይ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢህአዴግ ባህልና መመሪያዎች ሳይያዝ ሕገ-መንግሥቱ የሚሰጠውን ስልጣን ሳይጨምርና ሳይቀንስ ከተጠቀመበት ለውጥ ለማምጣት አይቸግረውም። ስለዚህ በሕገ-መንግሥቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ስልጣንን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለሚገድበው ተመራጩ ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በቀዳሚነት ማንሳት አለበት። በተጨማሪም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ወደ ዲሞክራሲ ስለሚደረገው ሽግግር መደራደርና የቀሩ እንዲሁም አሁንም የታሰሩ እስረኞችን መፍታት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው። የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሃገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንፃር የዶክተር አብይ መመረጥ ጥሩ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ። በሃገሪቱ ውስጥ የተከሰቱትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያነሱ፣ የተቋረጠው ኢንተርኔት ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥና በህዝቡ መካከል የአንድነት መንፈስ እንዲጠናከር እንዲያደርጉ እፈልጋለሁ። አቶ መሃመድ አሊ፡ የወልዲያ ከተማ ነዋሪ በአማራ እና ኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በነበሩ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብተን ነበር። በአፋር እና እዚህ ወልዲያ የሚገኙ ጓደኞቼም ሆኑ እራሴ ቀድመውንም ቢሆን የዶ/ር አቢይን መመረጥ በጉጉት እንጠብቀው ነበር ። በቅድሚያ የሀገሪቱ ሰላም ወደ ነበረበት እንዲመለስ ሌላው ደግሞ ኢትዮጵያዊ አንድነትን አንግበው ሀገሪቱን ወደፊት ያራምዷታል የሚል ተስፋ አለኝ። አቶ መብራቱ ዱባለ፡ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የዶ/ር አቢይ አህመድ መመረጥ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የመልካም አስተዳደር ሥራ የዲሞክራሲ እና የልማት ጥያቄዎችን በየደረጃው ይፈታል የሚል እምነት አለኝ። በተለይ ደግሞ ወጣት ከመሆናቸው አንፃር ወጣቱን ትውልድ የመረዳት አቅም ይኖራቸዋል ብዬ አምናለሁ። እንዲሁም በየመድረኩ ይነሱ የነበሩ የህዝብ ጥያቄዎችን ይመልሳሉም የሚል ፅኑ እምነት አለኝ።
44625191
https://www.bbc.com/amharic/44625191
ኢትዮጵያና ኤርትራ፦ ከእራት በኋላ ምን ተወራ?
በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልሕና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ በሆኑት የማነ ገብረአብ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የእራት ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን ከእራት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት አማካሪ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ የማነ ገብረአብ አጠር ያለ ንግግር አድርገዋል። የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ጦስ በሶማሊያ? የኤርትራው ፕሬዝዳንት አማካሪ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ የማነ ገብረአብ ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፣ "ዛሬ ስንገናኝ ከ20 ዓመት በኋላ ነው፤ ነገር ግን 20 ዓመት ተለያይቶ እንደተገናኘ አልነበረም" በማለት የተደረገላቸውን አቀባበል አድንቀዋል። "በመካከላችን ምንም የአስተሳሰብ ልዩነት የለም። አንድ የሚያሳዝን የታሪክ ምዕራፍ ዘግተን ወደ አዲስ ምዕራፍ ገብተናል የሚል እምነት አለን" ብለዋል። አቶ የማነ ገብረዓብ አክለውም በሁለቱ አገራት መካከል ትንንሽ ችግሮች ቢኖሩም እንኳ "በመነጋገር በመግባባት እንደምናሸንፋቸው እናምናለን" ብለዋል። ይህንን እምነታቸውን የሚያፀናው ምን እንደሆነ ሲያስረዱም፣ "የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ቁርጥ ፍላጎትና ውሳኔ በመሆኑ ነው" ብለዋል። ንግግራቸውን ሲያጠናቅቁም "ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ፍቅርን ልዋስና በማለት ላሳያችሁን ፍቅር እናመሰግናለን" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በበኩላቸው አርቲስቶች መጪው መስከረም የምናከብረው አዲስ አበባና አስመራ ስለሆነ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ በማለት በእራት ግብዣው ላይ ለተገኙ የጥበብ ባለሙያዎች ጥሪ አቅርበዋል። ምፅዋ ላይ መንሸራሸር ለናፈቃችሁ ኢትዮጵያውያን በማለትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ እንደሚጀምር ተናግረዋል። "ከኤርትራውያን ወንድሞቻችን ጋር የሚያዋጣን ፍቅር ብቻ ነው" ካሉ በኋላ፣ "ፀቡን ሞክረነዋል በሁለቱም ወገን አክሳሪ ነው" ብለዋል። ጦርነት "ሰው ይበላል፤ ጊዜ ይበላል፤ ሐብት ይበላል፤ ጠቃሚ ሐሳብ ማመንጨት የሚያስችል ጭንቅላትም ይበላል" በማለት ተናግረዋል። ለእርቅ የሚከፈል ማንኛውንም ዋጋ ተከፍሎ ከኤርትራውያን ወንድሞቻችን ጋር ተደምሮ ለማደግ ከፍተኛ ፍላጎት ያለ መሆኑንንም ተናግረዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ለሚኖረው ሰላምና ፍቅር ተባባሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ያመሰገኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኤርትራውያን ወንድምና እህቶቻችን በማለት ክረምቱ ሳያልፍ መጥተው እንዲጎበኙ አዲስ ዓመትንም አብረው እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል። በመጨረሻም ሰላምና ብልፅግና ለሁለቱም ሀገራት ተመኝተዋል።
news-54238570
https://www.bbc.com/amharic/news-54238570
ኮሮናቫይረስ፡ ዓለምን ለሁለት የከፈለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ
በቅርቡ በተሰራ አንድ ዓለማቀፍ ጥናት መሰረት የዓለማችን ዜጎች የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተና መወሰድ አለበት ብለው በሚያምኑት እርምጃ ዙሪያ ከባድ ስጋት እንዳለባቸው በመጠቆም በዚሁ ረገድ ግን በሁለት የተከፈለ ሀሳብ እንዳለ ይፋ አድርጓል።
በርካታ ቁጥር ያላቸው በድሀ አገራት የሚኖሩ ዜጎች የአየር ጸባይ ለውጥ ጉዳይ ልክ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተሰጠውን አይነት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ከፍተኛ እምነት አላቸው ተብሏል። ነገር ግን በሀብታም አገራት የሚኖሩ ዜጎች የአየር ጸባይ ለውጥ ላይ ለዘብ ያለ አመለካከት እንዳላቸው ተጠቁሟል። በሌላ በኩል ደግሞ የዌልሱ ልዑል የአየር ጸባይ ለውጥ ጉዳይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ጉዳት እንደውም ያሳንሰዋል ሲሉ ተደምጠዋል። ግሎብስካን የሚባል ተቋም በሰራው በዚሁ ጥናት መሰረት የዓለማችን ሕዝቦች የአየር ጸባይ ለውጥ ጉዳይ እጅጉን እያሳሰባቸው እንደሆነና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ነገሮችን ይበልጥ ከባድ እንዳደረገባቸው አስታውቋል። በዓለማችን ከሚገኙ 27 አገራት በተሰበሰበው መረጃ መሰረት 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች የአየር ጸባይ ለውጥ ጉዳይ እጅግ በጣም አሳሳቢ ወይም አሳሳቢ በሚባል ደረጃ እንደሚገኝ ያምናሉ። ሰዎችም ሆኑ ፖለቲከኞና ባለሀብቶች ጉዳዩን በተመለከተ አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ አለባቸው ብለው ከሞገቱት መካከል የካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ሕንድ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ እና የአሜሪካ ዜጎች ይገኙበታል። ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለጉዳዩ እምብዛም ትኩረት ባይሰጡም አሜሪካ ውስጥ የአየር ጸባይ ለውጥ እንደ ትልቅ የዓለማችን ችግር መታየት አለበት ብለው የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር በአውሮፓውያኑ ከነበረበት 60 በመቶ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ሰኔ ካይ ወደ 81 በመቶ ከፍ እንዳለ ጥናቱ ጠቁሟል። ሕንድ ውስጥ ደግሞ በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት ጉዳዩ በእጅጉ ያሳስበናል የሚሉ ሰዎች ቁጥር ከ70 በመቶ ወደ 93 በመቶ ከፍ ብሏል። ነገር ግን ዜጎች ልክ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ላይ የታየው አይነት መነሳሳትና ቁርጠኝነት መንግሥታቸው የአየር ጸባይ ለውጥን በተመለከተ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ አለበት ወይ በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ለሁለት ተከፍለዋል። ልዩነቱ ደግሞ ያለው በደሃና ሀብታም በሚባሉት አገራት መካከል ነው። በጃፓን፣ ስዊድን፣ አውስትራሊያ፣ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች መካከል መንግሥታቸው የአየር ጸባይ ለውጥን በተመለከተ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት ብለው የሚያምኑት 45 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ናቸው። ነገር ግን በኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ሜክሲኮ፣ ቱርክና አርጀንቲና የሚገኙ ዜጎች መንግሥታት ፈጣንና ውጤታማ እርምጃ መውሰድ አለባቸው ብለው የሚያምኑት ከ70 በመቶ በላይ መሆናቸውን ይሄው ጥናት ጠቁሟል። በተመሳሳይ በአየር ጸባይ ለውጥ ምክንያት ማነው ዋነኛ ተጎጂ ተብለው የተጠየቁት የነዚሁ አገራት ዜጎች 60 በመቶ የሚሆኑት ድሀ የዓለማችን ዜጎች የቀጥታ ተጎጂ እንደሆኑ ያምናሉ። ነገር ግን በጃፓን፣ አውስትራሊያ፣ አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ ሰዎች መካከል ከ40 በመቶ በታች የሚሆኑት ብቻ ናቸው ዋነኛ ተጎጂዎች በድሀ አገራት የሚኖሩ ሰዎች እንደሆኑ የሚያስቡት። በዩናይትድ ኪንግደም በዳሰሳ ጥናቱ ከተካተቱ ሰዎች መካከል 13 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው የዓለማችን ሙቀት መጨመር በግል ሕይወታቸው ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ የገለጹት። ነገር ግን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምን ያክል ተጽዕኖ አሳደረባችሁ ተብለው ከተጠየቁት እነዚሁ ሰዎች መካከል 34 በመቶ የሚሆኑት አዎ ቀጥተኛ ተጽህኖ አሳድሮብናል ብለዋል። ይሄው አይነት ተመሳሳይ አስተሳሰብ እንደ አሜሪካ፣ ስዊድን እና ጃፓን ባሉ አገራትም ተስተውሏል። ነገር ግን በሜክሲኮ፣ ቱርክ፣ ቪዬትናም እና ኬንያ በመሳሰሉት አገራት ከሚገኙ ሰዎች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት የአየር ጸባይ ለውጥ በሕይወታቸው ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንዳሳረፈባቸው ገልጸዋል። ይህ ጥናት የተሰራው ከእያንዳንዱ 27 አገራት የተመረጡ 1ሺ አዋቂዎችን በማሳተፍ ነው። ጥናቱም ይፋ የተደረገው በኒውዮርክ እየተካሄደ ለሚገኘው ዓለም የአየር ጸባይ ሳምንት 2020 መክፈቻ ላይ ሲሆን በዚህ ዓመት ከሚካሄዱ የአየር ጸባይ ለውጥን ከሚመለከቱ ትልልቅ ስብሰባዎች መካከል አንዱ ነው።
54183500
https://www.bbc.com/amharic/54183500
ምጣኔ ኃብት፡ ከመቶ ሺህ ብር በላይ ያላቸው በአንድ ወር መቀየር እንዳለባቸው ተገለፀ
አዲሱ የብር ኖት ቅየራ በዛሬው ዕለት፣ መስከረም 6/2012 ዓ.ም ከሰዓት መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ አልሰን አሰፋ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በዝግጅቱ ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ የተገኙ ሲሆን፤ ዛሬ ከቀኑ 9፡30 ጀምሮም በአዲስ አበባ አካባቢ ባሉ ባንኮች ብር መቀየር ተጀምሯል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ። በመሆኑም የብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት፤ 100 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ገንዘብ በእጃቸው ላይ ያለ ግለሰቦችና አካላት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ወደ ባንክ በመሄድ ገንዘቡን መቀየር እንደሚችሉም አቶ አልሰን ገልፀዋል። አገልግሎቱ በማንኛውም የባንክ ቅርንጫፍ እንደሚሰጥ የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፤ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች እጃቸው ላይ ያለውን ብር ወደ አዲሱ መቀየር አሊያም ከሒሳብ ቁጥራቸው አዲሱን የብር ኖት ማውጣት እንደሚችሉ ተናግረዋል። እጃቸው ላይ ከ100 ሺህ ብር በታች ያላቸው ግለሰቦችም እስከ 2 ወር ከግማሽ ድረስ ገንዘባቸው እንዲቀይሩ ቀነ ገደብ ተቀምጧል ብለዋል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ያላቸው ግን በዚህ አንድ ወር ብቻ ቅየራውን ማጠናቀቅ ያለባቸው ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ የሚመጣ በየትኛውም ባንክ እንደማይስተናገድ ሥራ አስኪያጁ አስጠንቅቀዋል። በመሆኑም በዚህ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን ከኮሮና በመጠበቅ እጃቸው ላይ ገንዘባቸው በአዲሱ የብር ኖት እንዲለውጡ አሳስበዋል። ከዚያ በታች የገንዘብ መጠን ያላቸው ሰዎች የተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እስከ ሁለት ወር ከግማሽ ቢሆንም በዚህ ወር ውስጥም ግን መቀየር እንደሚችሉ አቶ አልሰን ጠቁመዋል። 10 ሺህ እና ከዚያ በላይ እጃቸው ላይ ያለ ሰዎች ደግሞ ገንዘባቸው አካውንታቸው ላይ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን የሒሳብ ቁጥር ከሌላቸውም መታወቂያ እና ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ የሒሳብ ቁጥር ከፍተው ገንዘባቸው እዚያ ማስቀመጥ ይችላሉም ተብሏል። በተቀመጠው ጊዜም ከባንክ ውጪ የሚገኙ ገንዘቦች የሚሰበሰቡበት ሁኔታዎች መመቻቸታቸውንም ሥራ አስኪያጁ አክለዋል። አቶ አልሰን እንዳሉት ገንዘቡን ለመሰብሰብ የተሰጠው አጠቃላይ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት ውስጥ ነው። በዚህ ጊዜም ከባንክ ውጭ አለ ተብሎ የሚገመተው ወደ 113 ቢሊየን ብር ወደ ባንክ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኃላፊው ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50 እና የ100 የገንዘብ ኖቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶችን ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል። ከአዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች ውስጥም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባለ ሁለት መቶ ብር ኖትም አሳትማለች። አገሪቷ ነባሮቹን የብር ኖቶች ለመቀየር ሌላ ወጪን ሳይጨምር ለህትመት ብቻ 3.7 ቢሊየን ብር ማውጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታውቀዋል።
news-56539797
https://www.bbc.com/amharic/news-56539797
ኮሮናቫይረስ፡ ኬንያ በናይሮቢና በሌሎች ግዛቶቿ ጥብቅ የኮቪድ-19 ክልከላዎችን ጣለች
ኬንያ እንደ አዲስ የተቀሰቀሰውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር መዲናዋ ናይሮቢን ጨምሮ በአምስት ግዛቶች ጥብቅ የኮቪድ-19 መቆጣተሪያ ክልከላዎችን ጣለች።
ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያት በአገሪቱ በተለይም የኮቪድ-19 ክልከላዎች በተጣለባቸው ግዛቶች የኮሮናቫይረስ ስርጭት በፍጥነት እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዘደንቱ እንዳሉት ባለፉት ሦስት ወራት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2 በመቶ ወደ 22 በመቶ ከፍ ብሏል ያሉ ሲሆን፤ በየቀኑ 7 ሰዎች ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው እንደሚያልፍ አመልክተዋል። ፕሬዝደንቱ በናይሮቢ፣ በካጂያዶ፣ በኪያምቡ፣ በማቻኮስ እና በናኩሩ ግዛቶች እና ከግዛቶቹ ውጪ የሚደረጉ ማናቸውም አይነት ጉዞዎችን አግደዋል። ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉም ወስነዋል። በምግብ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦ መመገብ ተከልክሏል። መጠጥ ቤቶችም አልኮል መሸጥ አይችሉም ብለዋል ፕሬዝደንቱ። ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዝደንቱ ከዚህ ቀደም ከምሽቱ አራት ሰዓት ይጀምር የነበረው ሰዓት እላፊን በማሻሻል ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋት 10 ሰዓት የሚዘልቅ እንዲሆን አውጀዋል። የአገሪቱን ፓርላማም ላልተወሰነ ጊዜ በእረፍት ላይ እንዲቆይ ጠይቀዋል። በሐይማኖት ተቋማትም ሰዎች በጋራ ተሰብሰበው መጸለይ ወይም ማምለክ አይችሉም ሲሉ አውጀዋል። የግል እና የመንግሥት ተቋማት ሠራተኞችም ከቤት ሆነው እንዲሰሩ ፕሬዝደንቱ የጠየቁ ሲሆን፤ በቀብር ሥነ-ሥርዓት ላይም ከ50 ያልበለጡ፤ በሠርግ እና መሰል ሥነ-ሥርዓቶች ላይ ደግሞ ከ30 ያልበለጡ ሰዎች ብቻ እንዲገኙ አዘዋል። ኬንያ አስትራዜኔካ ሰራሹን የኮቪድ-19 ክትባት ለዜጎቿ መስጠት የጀመረች ሲሆን፤ ክትባቱ እድሜያቸው ከ58 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል። ፕሬዝዳንቱም በዛሬው ዕለት የወረርሽኙን መከላከያ ክትባት በቀጥታ በቴሌቪዥን እየታዩ ወስደዋል።
54343331
https://www.bbc.com/amharic/54343331
በአርሜኒያና በአዘርባጃን መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ 100 ሰዎች ሞቱ
በቀድሞው የሶቪየት ሪፐብሊክ አካል በነበሩት አርሜኒያና አዘርባጃን መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ ቢያንስ 100 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በሁለቱ አገራት መካከል ግጭቱ የተቀሰቀሰው በናጎርኖ- ካራባክህ ግዛት ይገባኛል ጥያቄ ጋር ተያይዞ ነው። ተራራማው በናጎርኖ ካራባክህ ግዛት የአዘርባጃን አካል እንደሆነ ቢታወቅም፤ ከጎርጎሮሳዊያኑ 1994 ጦርነት ማብቂያ ወዲህ ግን የሚተዳደረው በአርሜኒያዊያን ነው። ራስ ገዝ አስተዳደሯ ከእሁድ እለት ጀምሮ 84 ወታደሮች እንደሞቱባት ያስታወቀች ሲሆን ንፁሃን ዜጎችም ከተጎጂዎቹ መካከል ይገኙበታል ተብሏል። አዘርባጃን ግን ምን ያህል ወታደሮች እንደሞቱባት ባትገልፅም፤ ሰባት ንፁሃን ሰዎች መሞታቸውን ግን ገልፃለች። ማክሰኞ ዕለት የአርሜኒያ መከላከያ ሚኒስተር በአርሜኒያ ምስራቃዊት ከተማ ቫርዴኒስ አንድ የመንገደኞች አውቶብስ በአዘርባጃን ሰው አልባ አውሮፕላን መመታቱን ተናግረዋል። ነገር ግን በሰው ላይ ስለደረሰው ጉዳት የተባለ ነገር የለም። ከአንድ ቀን በፊት ከአንድ ቤተሰብ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎም፤ አዘርባጃን ሁለት ሰላማዊ ሰዎች በአርሜኒያ መገደላቸውን አስታውቃለች። ግጭቱ ከአራት ዓመታት ወዲህ የታየ ከባድ ግጭት ነው ተብሏል። ይህንን ተከትሎም ማክሰኞ ዕለት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ውይይት ሊያካሂድ መሆኑ ተገልጿል። አርሜኒያ እና አዘርባጃን በርካታ ወታደሮችን በማንቀሳቀስ በተወሰኑ አካባቢዎች ወታደራዊ ሕግ በማወጅ ግጭቱ ለመጀመሩ አንዳቸው በአንዳቸው ሲያሳብቡ ነበር። በግጭቱ ሌሎች አገራት በቀጥታ ሊሳተፉ ይችላሉ የሚል ስጋቶችም ተፈጥረዋል። ቱርክ አዘርባጃንን በግልፅ መደገፍ የጀመረች ሲሆን በአርሜኒያ ወታደራዊ ካምፕ ያላት ሩሲያ ደግሞ ሁለቱ አገራት በአስቸኳይ ተኩስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርባለች። ስለ ናጎርኖ- ካራባክህ
57319820
https://www.bbc.com/amharic/57319820
የግብፅ እና ሱዳን መገናኛ ብዙሃንን ያነጋገረው የጠ/ሚ ዐቢይ ንግግር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሚቀጥለው ዓመት ኢትዮጵያ ቢያንስ 100 መካከለኛና አነስተኛ ግድቦችን መገንባት ትጀምራለች ማለታቸውን ተከትሎ የግብፅ እና የሱዳን መገናኛ ብዙሃን በጉዳዩ ሰፊ ዘገባ ሠርተዋል።
ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሚቀጥለው ዓመት ኢትዮጵያ ቢያንስ 100 መካከለኛና አነስተኛ ግድቦችን የመገንባት እቅድ እንዳላት የተናገሩት በኢትዮ-ጂቡቲ የምዕራፍ አንድ አዳማ-አዋሽ የመንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው። "ቢያንስ ከ100 በላይ ግድቦችን የመስራት እቅድ አለን። ውሃ ላይ አበክረን ካልሠራን፣ ውሃን እንደ ትልቅ ሀብትና እንደ ልማት መግቢያ በር አድርገን ካልወሰድን አጠቃላይ የምናስበውን ብልጽግና ማረጋገጥ ስለሚያስቸግር የመንግሥት ትኩረት ትናንሽና መካከለኛ ግድቦች በመሥራት ውሃን ማቆየት ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። የግድቦች ግንባታ ዓላማ በዓመት ሦስት ጊዜ ማምረት እንዲቻል መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ አስረድተዋል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በትክክል በየትኞቹ አካባቢዎችና የውሃ አካላት ላይ ግድቦቹ እንደሚገነቡ ያሉት ነገር የለም። ይህን ተከትሎ በርካታ የግብፅ እና የመካከለኛው ምሥራቅ መገናኛ ብዙሃን በጉዳዩ ላይ ዘገባ ሰርተዋል። መገናኛ ብዙሃኑ ምን አሉ? 'አህራም ኦንላይን' ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ኢትዮጵያ ከ100 በላይ ግድቦችን የመገንባት እቅድ አላት ማለታቸውን ግብፅ 'ለዓለም አቀፍ ሕግጋትን ቁብ አለመስጠት ነው' ብላለች ሲል ዘግቧል። ቃል አቀባዩ፤ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ንግግር ድንበር ተሻጋሪ የውሃ አካላት ሕጎችን የተላለፈ እና የታችኛው ተፋሰስ አገራት መብትን ያላከበረ ነው ስለማለታቸው አሃራም ኦላይን አስነብቧል። በተመሳሳይ 'አረብ ኒውስ' የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አህመድ ሃፌዝ የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ምክንያታዊ ፍላጎት እንደሌላት የሚያሳይ ነው በማለት አጣጥለዋል። 'ኢጂፕት ኢንዲፐንደንት' መረጃውን ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳገኘው በመጥቀስ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገራቸው ላይ ለሚደርሱ ማንኛውም አይነት ጫናዎች መልስ የምትሰጠውና ጫናዎቹን መቋቋም የምትችለው ግድቦችን በመገንባት ነው ስለማለታቸው ዘግቧል። 'ኢጂፕት ኢንዲፐንደንት'፤ ኢትዮጵያ እየገነባች ያላችው የሕዳሴ ግድብ የውሃ ድርሻዬን ያሳንስብኛል በማለት ግብፅ እንደምትሰጋ አስታውሷል። 'ሱዳን ትሪቢዩን' በበኩሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ በቀጣይ በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከ100 በላይ ግድቦችን የመገንባት እቅድ አላት ማለታቸውን ከዘገበ በኋላ፤ በትግራዩ ግጭት ኢትዮጵያ ከምዕራባውያኑ አገራት ከፍተኛ ጫና እየደረሰባት ይገኛል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር "መንግሥት ባለፉት ዓመታት በጤና፣ በትምህርት፣ በመንገድ ግንባታ ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን እንዳሠራ ሁሉ የሚቀጥለው ዓመት ዋናው እቅዳችን ትናንሽና መካከለኛ ግድቦች በየክልሉ ማስፋፋት ነው" ብለዋል። የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር ግንባታ ምስል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር አካል የሆነውን የአዳማ-አዋሽ ምዕራፍ አንድ 60 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ በይፋ ሲያስጀምሩ፤ ኢትዮጵያን በአራቱም አቅጣጫ ከሚገኙ ጎረቤት አገራት መንገድን ጨምሮ በሁሉም መስክ ለማስተሳሰር በትኩረት እየተሠራ ስለመሆኑ ፕሮጀክቱ ጉልህ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ "ቀን ከሌት እየሠራ የአባቱን ሀብት የሚያበዛ ወጣት ትፈልጋለች" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ወቅቱ "የልማት ስኬትን በማረጋገጥ ወደ ለውጥ የምንሸጋገርበት በመሆኑ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለሥራ እንነሳ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የመንገዱ የግንባታ ወጪ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በብድር በተገኘ 6.6 ቢሊዮን ብር የተጀመረ ሲሆን ሁለተኛው ምዕራፍ (70 ኪሎ ሜትር) ጨረታ ወጥቶ በሂደት ላይ መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በፊት የታላቁ ሕዳሴ ግድብን መገንባት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ደግሞ ከግብፅ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች መግባባት ላይ መድረስ ሳትችል ቀርታለች። ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አንዳንድ እውነታዎች ግብፅ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሐሳብ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ሕልውናዋ ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር መሆኑን በመግለጽ የግንባታው እና ውሃ ሙሌቱ የግብፅ ይሁንታ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት ስትል ቆይታለች። ኢትዮጵያ ደግሞ ከአባይ ወንዝ 80 በመቶ ድርሻ እንዳላት በመግለጽ በሚሊዮኖች ለሚቆጠረው ሕዝቧ የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ ዓላማዬ ነው ትላለች። ባለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ደረጃ የዉሃ ሙሌት መጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ገልጸው ነበር። በያዝነው ዓመትም የክረምቱን ወር ተከትሎ የሙሌት ሥራው እንደሚቀጥል ይጠበቃል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የሕዳሴ ግድቡ ግንባታ 80 በመቶ መድርሱን ስትገልጽ ግብፅ በበኩሏ የግድቡ የቀጣዩ ክረምት ሙሊት የጎላ ተጽዕኖ አያደርስብኝም ብላ ነበር። የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ለብሔራዊ ጣቢያው በሰጡት አስተያየት፤ የግድቡ የሲቪል ግንባታ 91.8፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታው 54.5 በመቶ እንዲሁም የሃይድሮሊክ ስትራክቸር ሥራው ደግሞ 55.2 በመቶ መድረሱን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የሕዳሴ ግድቡን የውሃ ሙሌት እጀምራለሁ ባለው ጊዜ መሠረት ባለፈው ዓመት ሙሌቱን ማከናወን ጀምሯል። በዚህም መሠረት ግድቡ 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ድረስ ውሃ እንደያዘ ይገመታል። ግንባታው ሲጠናቀቅ 1,800 ሜትር ርዝመት እና ከ145 እስከ 170 ሜትር የመጨረሻ ከፍታ የሚኖረው ሲሆን አጠቃላይ የሚይዘው የውሃ መጠንም 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር እንደሆነ ተገልጿል። የሕዳሴ ግድቡ በመጪው ክረምት ውሃ ከመያዝ በተጨማሪ በተየዘው ዓመት መገበደጃ ላይ ቅድመ ኃይል እንደሚያመነጭም የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል የሆኑት በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
news-47391380
https://www.bbc.com/amharic/news-47391380
የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል?
ብዙ ጊዜ ከምግብ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ነገር የቤተሰብ አባላት ስለ ምግብ ያላቸው አስተሳሰብ ነው። በዚሁ ዙሪያ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት አብዛኞቹ አሜሪካዊያን ቤተሰቦች ስለሚመገቡት ምግብ ጤናማነት አብዝተው ይጨነቃሉ።
በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ ቤተሰቦች ደግሞ ምግቡ ምንም ይሁን ምን ዋናው ነገር መጣፈጡ ነው ብለው ያስባሉ። እርስዎ ጥሩ ምሳ በላሁ የሚሉት ምን ሲመገቡ ነው? ምናልባት አንዳንዶች አትክልት የበዛበት ነገር ሊመርጡ ይችላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሥጋ ነክ የሆኑ ምግቦችን ሊያስቀድሙ ይችላሉ፤ በርገር አልያም ፒዛ የሚሉም አይጠፉም። • እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል? የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት የምግቡ አይነት ብቻ ሳይሆን ስለምግቡ የምናወራበት መንገድና ባህላችን ጥሩ ወይም መጥፎ ብለን ለመለየት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ባለሙያዎቹ እንዲያውም ምግብና ስለምግብ የሚደረጉ ውይይቶች የአንድን ማህበረሰብ ባህል፣ ማንነትና ፖለቲካዊ አቋም እስከመግለጽ ይደርሳሉ ይላሉ። ተመራማሪዋ ማርታ ሲፍ ካረባይክ፣ ዴንማርክ ውስጥ ስላጋጠማት ነገር ስታወራ ተማሪዎች 'ሪይ' የተባለውን የዳቦ አይነት ለምሳ ይዘው እንዲመጡ ይመከራሉ ትላለች። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ግን ምግባቸው ጤናማ እንዳልሆነ በአስተማሪዎቻቸው ተነግሯቸው ለቤተሰቦቻቸው ማስጠነቀቂያ ይላካል ስትል ባህል በምግብ ላይ ያለውን ተጽእኖ ታስረዳለች። ''ይህ የሆነው 'ሪይ' የተባለው የዳቦ አይነት የተለየ ጤናማ ንጥረ ነገር በውስጡ ስለያዘ ሳይሆን ባህልና ማንነትን ለመግለጽ ስለሚጠቀሙበት ነው።'' ሌላዋ ተመራማሪ ካትሊን ራይሊ ደግሞ በፈረንሳይ በነበራት ቆይታ አስገራሚ ነገር እንደታዘበች ትናገራለች። የአንድ ማህበረሰብ አባላት ምግባቸው የማይጣፍጥ አልያም መጥፎ እንደሆነ ከተነገራቸው፣ ሰዎቹ ራሳቸው መጥፎ እንደተባሉና ባህላቸውም እንደተሰደበ ይቆጥሩታል። እነዚህ ሰዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ከፍ ያለ ቦታ ከሌሎች ለመለየትና አስጠብቆ ለማስቀጠል ከሚጠቀሟቸው መንገዶች መካከል የሚበሉት የምግብ አይነት በዋነኛነት ይጠቀሳል። ምግቦቻችን ለዓለም ያለንን አመለካከት የሚቀርጹት እንዴት ነው? ማርታ ሲፍ ካረባይክ እንደምትለው ባለፉት አስር ዓመታት አሳማና የአሳማ ተዋጽኦዎችን አብዝቶ መጠቀም የዴንማርኮች መገለጫ እየሆነ መጥቷል። • አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች ዴንማርክ ውስጥ በአንድ ወቅት ትምህርት ቤቶች የአሳማ ስጋን ከምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ አስወጥተው ነበር። ይህ ደግሞ ከዓለም አቀፋዊነትና ስልጣኔ ጋር ተያይዞ እንደመጣ ይታሰባል። ጉዳዩ ያሳሰበው የአንድ ግዛት ምክር ቤት ትምህርት ቤቶች የአሳማ ስጋን በምግብ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዲያካትቱ የሚያስገድድ ሕግ አውጥቶም ነበር። በሕጉ መሰረት ማንኛውም ተማሪ የየትኛውም ሃይማኖት ተከታይ ቢሆን የዴንማርክ መገለጫ የሆኑ ምግቦች የመመገብ ግዴታ አለበት። የአሳማ ስጋ ደግሞ ዋነኛው ምግባቸው ነው። ስለዚህ ዴንማርካዊያን 'ሪይ' የተባለውን ዳቦ ሲመገቡ ስለጤናቸው በማሰብ ሲሆን የአሳማ ስጋን ሲበሉ ደግሞ ባህላቸውንና ማህበረሰባዊ እሴቶቻቸውን ከማስቀጠል አንጻር ነው። • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች ካትሊን ራይሊ እንደምትለው ድሮ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ምግብ ሳይሆን የተሻለ ሥራ ነበር። ዛሬ ዛሬ ግን ሰዎች የሚበሉትን ምግብ በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ቦታ እንደማሳያ ይጠቀሙታል።
news-49111947
https://www.bbc.com/amharic/news-49111947
ደኢሕዴን የሐዋሳና የሲዳማ ዞን አመራሮችን አገደ
የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ገዢ ፓርቲ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) የሲዳማ ዞን አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ከሃላፊነታቸው አገደ።
ከክልሉ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ቢቢሲ ማረጋገጥ እንደቻለው የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ የሲዳማ ዞንና የሐድያ ዞን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከነበሩበት የኃላፊነት ቦታ ታግደዋል። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? ድርጅቱ ለከፍተኛ አመራሮቹ መታገድ እንደ ምክንያት የጠቀሰው በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ በሐዋሳ ከተማና በሌሎች የሲዳማ አካባቢዎች ሰሞኑን ያጋጠሙትን ቀውሶች ሲሆን፤ የሐድያ ዞን ከፍተኛ አመራሮችም በዞኑ ውስጥ ታይተዋል በተባሉ የጸጥታ ችግሮች ውስጥ ሚና አላቸው ተብለው በመጠርጠራቸው ነው ተብሏል። ከሐምሌ 11 2011 ጀምሮ በሐዋሳ፣ በአላታ ወንዶ፣ በሀገረ ሰላም፣ በወንዶ ገነትና ሌሎች የሲዳማ ዞን ወረዳዎች በተፈጠረ ግጭት እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ሲሞቱ በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች፣ በንግድ ተቋማትና በአብያተ ክርስትያናት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ውድመት አጋጥሟል። • 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች • ከሐዋሳ ተነስቶ በሌሎች አካባቢዎች ጉዳት ያደረሰው ሁከት ደኢሕዴን ከተጠቀሱት አካባቢ ከፍተኛ ባለስልጣናት በተጨማሪ በተመሳሳይ ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፈው ተገኝተዋል የተባሉ በክልሉ ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ባለስልጣናት ላይም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። በተያያዘ ዜና በሐዋሳ ከተማና በዙሪያዋ አጋጥሞ ከነበረው ሁከት ጋር በተያያዘ ለጸጥታ ሲባል በከተማዋ ውስጥ ሞተር ሳይክሎች እንዳይቀሳቀሱ እገዳ መጣሉን ቢቢሲ ያናገራቸው የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። እርማጃው የተወሰደው ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው ብለው የሚያምኑት የከተማዋ ነዋሪዎች እገዳ መጣሉ በክልሉ መገናኛ ብዙሃን በኩል እንደተገለጸ ጠቅሰዋል። አሽከርካሪዎች ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በወንዶ ገነት ከተማ በነበረ ተቃውሞ 3 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ በዚህም ምክንያት በሐዋሳ ከተማ በብዛት ይተዩ የነበሩት ሞተር ሳይክሎች ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ እንደሌሉ የገለጹት አንድ ነዋሪ ትራፊክ ፖሊሶችም መንገድ ላይ ያገኟቸውን ሲያስቆሙ መመልከታቸውንና መኪኖችና ባጃጆች ግን በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ እንደሚታዩ ገልፀዋል። የሲዳማ ዞን ክልል እንዲሆን ጠይቆ የምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ የአምስት ወራት ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
news-56073529
https://www.bbc.com/amharic/news-56073529
መቃብሮችን የምታፀዳው የ12 ዓመቷ አውስትራሊያዊት
አውስትራሊያዊቷ ቲጄ ክሌማን አራት አመት ሲሆናት ነበር የመቃብር ሥፍራዎቹ አቅራቢያ ወደሚገኘው የመኖሪያ ቤታቸው ከቤተሰቦቿ ጋር የመጣችው።
የመቃብር ስፍራዎቹ ከቤታቸው ጀርባ እንደመገኘታቸው የተለያዩ ፍርሃቶች የልጅነት አእምሮዋን ያስጨንቁት ነበር። ከፍርሃቶቹ ሁሉ አእምሮዋን በብርቱ የተቆጣጠረው ግን የሙታን መናፍስት ቢመጡስ የሚለው ነው። የልጃቸውን ፍርሃት የተመለከቱት እናቷ ወደ መቃብር ሥፍራዎቹ በመውሰድ እንድትጎበኝ አደረጓት። የልጃቸውን ፍርሃት ለማስወገድ በተጨማሪ ሌላ መላም ዘየዱ። 'መቃብሮቹን ለምን አናፀዳቸውም' አሏት። እርሷም መቃብሮቹን በማጽዳት ስትጠመድ የሙታን መናፍስት ሃሳብ ከአእምሮዋ እየጠፋ መጣ። ገና በአራት ዓመቷ የጀመረችውን መቃብሮችን የማጽዳት ተግባሯን ዛሬ ድረስ ቀጥላበታለች። ከስምንት ዓመት በኋላም ለዚሁ ተግባሯ በአካባቢዋ ላበረከተችው የማህበረሰብ አገልግሎት ከአውስትራሊያ መንግሥት ሽልማትን አግኝታለች። ሽልማቱ የተለየ ስሜት እንደፈጠረባት የምትናገረው ቲጄ,፣ በወቅቱ እናቷም ማልቀሳቸውን ታስታውሳለች። "ሽልማቱን ስላገኘው የደስታ ስሜት ተሰምቶኛል፤ ምክንያቱም ለሌሎች እናንተም ይህንን ማድረግ ትችላላችሁ ብዬ መናገር አስችሎኛል" የምትለው ቲጄ፣ እርሷ በ12 ዓመቷ ይህንን ለማህበረሰቡ ማድረግ ከቻለች፤ ሌሎች በሳምንት የአንድ ወይንም ሁለት ሰዓት ብቻ በመውሰድ ለማህበረሰቡ በርካታ አስተዋጽኦ እንዲሁም የደስተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ እንደሚችሉ ትገልጻለች። ቲጄ ወደ መቃብር ስፍራዎቹ በሳምንት አንዴ ወይንም ሁለቴ በመሄድ የጽዳት ስራዋን ታከናውናለች። በሥፍራው በመቶዎች የሚቆጠሩ መቃብሮች የእርሷን እጅ ይጠብቃሉ። ሁሉንም ለማጽዳት ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል የምትናገረው ታዳጊዋ፣ ከዓመት በኋላ ዳግመኛ ሁለተኛ ዙር ማጽዳት እንደምትጀምር ትገልጻለች። ለራሷም "አጃሂብ፤ እኔ ነኝ ይህንን ሁሉ ያፀዳሁት" እንደምትልም ታክላለች። ቲጄ በቅርቡ በእጇ ላይ የቀዶ ጥገና ብታካሂድም፣ ከዚህ ተግባሯ ግን ምንም የሚያግዳት ነገር እንደሌለ ገልጻለች። ሰዎች ሲመለከቱኝ ደስ እንዲላቸው ካደረግሁ፣ እርሱ ያኮራኛል ስትልም ትናገራለች። የአካባቢው ነዋሪዎች የሚወዷቸው ሰዎች አስከሬን ያረፈበት ስፍራ ፀድቶ ሲመለከቱት እርሷን ስለመልካም ድርጊቷ እነደሚያመሰግኗትም ታክላለች። ያ ደግሞ የሚፈጥረውን ስሜት በቃላት ለመግለጽ እንደሚከብዳት አልሸሸገችም። ቲጄ አሁን የቀድሞ ፍርሃቷን አታስታውሰውም። በዚያ የመቃብር ስፍራ ነጻ መሆን ይሰማኛል የምትለው ቲጄ፣ "ልክ ቤት እንዳለሁ ያህል ይሰማኛል፤ ደግሞም እወደዋለሁ" ብላለች። ቲጄ በየወሩ የንጽህና ቀን ለማዘጋጀትና በርካቶች ለሚኖሩበት ማህበረሰብ የበጎ ፈቃደኝነት የማህበረሰብ ግልጋሎት እንዲሰጡ ለማነሳሳት እቅዱ አላት። እስካሁን ድረስ ይህንን በማድረጌ ደስተኛ ነኝ፤ በቀሪው የሕይወት ዘመኔ ሁሉ ይህንን ተግባር መቀጠል እፈልጋለሁ ስትልም ገልፃለች።
news-55246627
https://www.bbc.com/amharic/news-55246627
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በፎርብስ የዓመቱ ኃያል/ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ።
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፎርብስ ባወጣው 100 የዓመቱ (2020) ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ፕሬዘዳንቷ በ96ኛ ደረጃ ተቀምጠዋል። የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሳህለወርቅ፤ በዝርዝሩ የተካተቱ ብቸኛዋ አፍሪካዊ ናቸው። ፎርብስ በድረ ገጹ "ለምክር ቤት ባደረጉት የመጀሪያ ንግግር ለሴቶች ድምጽ ለመሆን ቃል ገብተዋል" ሲል ገልጿቸዋል። የፕሬዝዳንቷ መመረጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጠኑም ቢሆን የሴቶች ውክልና እየጨመረ መምጣቱን እንደሚያሳይም ፎርብስ አስነብቧል። በዝርዝሩ እነማን ተካተቱ? በዝርዝሩ አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት የጀርመኗ መራሔተ መንግሥት አንግላ መርከል ናቸው። መርከል በዝርዝሩ ለአስር ተከታታይ አመታት መሪነቱን ይዘዋል። በዝርዝሩ ሲካተቱ ደግሞ ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ ነው። በሦስተኛ ደረጃ ላይ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት ከማላ ሃሪስ ይገኛሉ። የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን ደግሞ 32ኛ ናቸው። ይህ ዓመታዊ ዝርዝር ሲወጣ ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ መሆኑን የፎርብስ ድረ ገጽ ይጠቁማል። በዘንድሮው ዝርዝር ከ30 አገራት የተውጣጡ ሴቶች ተካተዋል። ከእነዚህ መካከል አስሩ የአገር መሪዎች ሲሆኑ፣ 38ቱ ሥራ አስኪያጆች፣ አምስቱ ደግሞ በመዝናኛው ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ናቸው። በዝርዝሩ ከተካተቱት ሴት መሪዎች መካከል የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መገደብ የቻሉ እንደሚገኙበት ተገልጿል። ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው የተመረጡት ጀሲንዳ አርደን፤ በኒው ዚላንድ የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን ዙር ወረርሽን በብቃት መወጣት ችለዋል። በ37ኛ ደረጃ የተቀመጡት የታይዋኗ ፕሬዘዳንት ሳይ ኢንግ ዌን፤ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለማግኘት ውጤታማ አሠራር ዘርግተዋል። 23 ሚሊዮን ሰዎች በሚኖሩባት ታይዋን በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡት ሰባት ሰዎች ብቻ ናቸው። የኖርዌይ ጠቅላይ ሚንስትር ኤርና ሶልበርግ (52ኛ) "ዴሞክራሲ ሰፍኖ ሰብአዊ መብት የተከበረባቸውና ሴቶች በማኅበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ የደርሱባቸው አገራት ኮቪድ-19ን መዋጋት ችለዋል" ብለው ነበር። በዝርርዝሩ ከተካተቱ መካከል በአምስተኛ ደረጃ ሜሊንዳ ጌትስ እና በሰባተኛ ደረጃ ናንሲ ፔሎሲ ይጠቀሳሉ። ኦፕራ ዊንፍሪ በ20ኛ ደረጃ ተቀምጣለች። ከመዝናኛው ዘርፍ ድምጻውያኑ ሪሀና (69) እና ቢዮንሴ (72) ይጠቀሳሉ። ጥቂት ስለ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናቸው። ለዓመታት በዲፕሎማሲው ዘርፍ ሠርተዋል። በወርሃ የካቲት 1942 የተወለዱ ሲሆን ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛና አማርኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከፈረንሳዩ ሞንተፔለ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ምሩቅ ሲሆኑ፤ እአአ ከ1989-1993 ተቀማጭነታቸውን ሴነጋል በማድረግ የማሊ፣ የኬፕ ቨርዴ፣ የጊኒ ቢሳዎ፣ የጋምቢያና የጊኒ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። እአአ ከ1993-2002 ደግሞ በጅቡቲ አምባሳደር ሆነው የሠሩ ሲሆን፤ በወቅቱ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይም ነበሩ። ከዚያም በመቀጠል ከ2002-2006 በፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ተወካይ ሆነው ሠርተዋል። በኋላም በተባበሩት መንግሥታት ልዩ መልዕክተኛ ውስጥ የተቀናጀው የሰላም አስከባሪ ኃይል ተወካይ በመሆን በሴንትራል አፍሪካ (BINUCA) ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። በአፍሪካ ሕብረት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥም የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው አገልግለዋል። በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥም የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ሰርተዋል። እአአ በ2011 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ የነበሩት ባን ኪሙን፤ በኬንያ የተባበሩት መንግሥታት ዳይሬክተር ጄነራል አድርገው ሾመዋቸው አገልግለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተወካይ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል። ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው እያገለገሉ ነው።
news-51424994
https://www.bbc.com/amharic/news-51424994
"በረራ ማቋረጥ በሞራልም በሥነ ምግባርም ተቀባይነት የለውም" አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች ቻይና ጊዜያዊ ችግር ባጋጠማት በዚህ ወቅት ማቋረጥ ተቀባይነት የለውም ሲሉ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናገሩ።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም እንዳሉት "አየር መንገዱ ከ1973 ጀምሮ ወደቻይና በረራ ሲያደርግ ቆይቷል። አሁን ጊዜያዊ ችግር ስላጋጠማቸው ማቋረጥ በሞራልም በሥነ ምግባርም ተቀባይነት የለውም" በማለት ከቻይናዊያን ጎን መቆም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። አክለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች ቢያቆም የቻይናና የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ሙሉ ለሙሉ ይቋረጣል፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ያለ ማንም ሰው ይህ እንዲሆን እንደማይፈልግ ተናግረዋል። በዚህም ቻይና ከአፍሪካ ጋር ካላት ግኙነት አንጻር "ከአፍሪካዊያን እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ጎን መቆም አለብን" ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው። የተከሰተውን የበሽታ ወረርሽኝ በመፍራት በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጓቸውን በረራዎች በማቋረጣቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት እየተደረገበት ባለበት ጊዜ ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህንን ያሉት። በአሁኑ ወቅት የተከሰተውን ችግር ለመከላከልም "ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፤ በረራዎችን ማቋረጥ ግን ካሉ አማራጮች ውስጥ አይደለም" ሲሉም ተናግረዋል። አቶ ተወልደ እንዳሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች ቢያቆም መንገደኞች በሲንጋፖር፣ በማሌዢያና በአውሮፓ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን እንደማያቆሙ አመልክተዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራዎች ከበሽታው መከሰት ጋር በተያያዘ ያቋረጡ አየር መንገዶች የእራሳቸው ምክንያት እንዳላቸው ጠቅሰው፤ እንደ ምሳሌም "የብሪቲሽ አየር መንገድ በረራውን እንዲቆም ያደረገው በእራሱ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ነው" በማለት ጠቅሰውታል። ነገር ግን የቻይና አየር መንገዶች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በረራዎቻቸውን እያከናወኑ መሆናቸውን አቶ ተወልደ ተናግረዋል። ምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ኢቦላ ከ8 ሺህ በላይ ሰዎችን መግደሉ አይዘነጋም። ነገር ግን በሽታው ዴሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ እያለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደዚያው እየበረረ መሆኑን ጠቅሰዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህንን የተናገሩት አየር መንገዱን ለረጅም ጊዜ ላገለገሉ ሠራተኞች በተዘጋጀ የእውቅና ዝግጅት መዝጊያ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አምስት የቻይና ከተሞች በሳምንት 35 በረራዎችን በማድረግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መንገደኞችን ወደ አፍሪካ ያጓጉዛል። በዚህም ከአፍሪካ ወደ ቻይና በሚደረጉ በረራዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሚፎካከር አህጉራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ የአየር ትራንስፖርት ሰጪ ተቋማት የለም።
news-48442249
https://www.bbc.com/amharic/news-48442249
ህንድ፡ ክፍያ ባልከፈለ ተማሪ እጅ ላይ ማህተም የመታው ትምህርት ቤት ተወገዘ
ምን ዓይነት ትምህርት ቤት ነው የተማሩት? ከፍተኛ ክፍያ የሚፈፀምባቸው፣ መጠነኛ ክፍያ የሚፈፀምባቸው የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ወይስ ምንም የማይከፈልባቸው የመንግሥት ትምህርት ቤቶች?
ትምህርት ቤቱ ተማሪው ማስታወሻ ደብተሩን ረስቶ በመምጣቱ በእጁ ላይ ማህተም ለማድረግ መገደዳቸውን ገልፀዋል። ክፍያ በሚከፈልባቸው ትምህርት ቤቶች የተማራችሁት የትምህርት ክፍያ ስታሳልፉ መምህራኑ አሊያም ትምህርት ቤቱ የወሰደባችሁ እርምጃ ምንድን ነው? ስንገምት ወላጅ እንድታመጡ ልትጠየቁ ትችላላችሁ፤ አሊያም ደግሞ በስልክ ቤተሰቦቻችሁ ጋር ሊነጋገሩ ይችላሉ። ግፋ ካለም ከትምህርት ቤቱ ማሰናበት ሊሆን ይችላል። • የህንድ ፊልም አፍቃሪዎች ወተት እየሰረቁ ነው • የ'ሰከረ' አዋላጅ ሐኪም እናትና ልጅን ገደለ በህንድ ፑንጃብ የሚገኘው ትምህርት ቤት የተፈፀመው ግን ባልተለመደ መልኩ ከዚህ ለየት የሚል ተግባር ነው። ትምህርት ቤቱ የትምህርት ክፍያ ባልከፈለ ተማሪ እጅ ላይ ማህተም በመምታት ወደ ቤቱ ልኮታል። ይህንኑ ተከትሎ በሰሜን ህንድ ግዛት ፑንጃብ የትምህርት ባለሥልጣናት የትምህርት ክፍያ ባለመከፈሉ በተማሪው እጅ ላይ ማህተም የመታው ትምህርት ቤት ላይ ምርመራ እያካሄዱ መሆናቸውን ገልፀዋል። የ13 ዓመቱ ታዳጊ ቤተሰቦች በበኩላቸው ተማሪው ላይ አሳፋሪ ነው ያሉት ድርጊት ከተፈፀመ በኋላ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ እንደማይፈልግ መናገሩን ገልፀዋል። የዚሁ የግል ትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ድርጊቱን መፈፀማቸውን አምነው በተማሪው እጅ ላይ ማህተም የመቱት ማስታወሻ ደብተሩን ረስቶት በመምጣቱ እንደሆነ ተናግረዋል። • ለሴቶች የተከለከለ ተራራን የወጣችው የመጀመሪያ ሴት ምንም እንኳን የማህተሙ ቀለም በቀላሉ በውሃ የሚለቅ ቢሆንም የመምህሩ ድርጊት ግን ያልተገባ ነው ሲሉ ርዕሰ መምህሩ ድርጊቱን አውግዘውታል። የተማሪው ወላጆች ለተከታታይ ሁለት ወራት ክፍያ ያልፈፀሙ ሲሆን እንዲከፍሉም ማሳሰቢያ ቢላክላቸውም ችላ ማለታቸውን ትምህርት ቤቱ ገልጿል። ትምህርት ቤቱ ምክንያቶችን ቢደረድርም የተማሪው ወላጆች ግን ድርጊቱን ያልተገባ ነው ሲሉ ኮንነውታል። በባጃጅ ሹፌርነት ሕይወታቸውን እንደሚመሩ የሚናገሩት የተማሪው ወላጅ አባት " ግለሰቡ ክፍያ የጠየቀው ባልተገባ መንገድ ነው" ብለዋል። ክፍያውን ለመፈፀም የተወሰነ ጊዜ እንዲሰጣቸው ትምህርት ቤቱን እንደጠቁ የሚናገሩት የተማሪው አባት በልጃቸው ላይ የተፈፀመው ድርጊት መላ ቤተሰቡን እንዳሳፈረ ተናግረዋል። የአካባቢው የትምህርት ባለሙያ ስዋርንጀት ካውር " በጣም ስህተት ነው" በማለት ድርጊቱን የፈፀሙት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀዋል።
news-46678525
https://www.bbc.com/amharic/news-46678525
እንግሊዝ-የገና እለት ወደ ሀገሩ እንዲመለስ የተገደደው ስደተኛ
ኦቲስ ቦላሙ ይባላል። የተወለደው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቢሆንም ከሀገሩ ተሰዶ እንግሊዝ ውስጥ ጥገኝነት ለመጠየቅ ተገዷል።
የኦቲስ ጓደኞች ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ለተቃዋሚዎች በመሰለል ስለተጠረጠረ ከባድ አደጋ እንደተጋረጠበት ሲነግሩት ነበር ወደ እንግሊዝ፣ ስዋንሲያ የተሰደደው። • በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ባለሙያዎች ጥቃት ደረሰባቸው • በኮንጎ ህፃናትን በክርስትና ስም የደፈሩት ታሰሩ • ከሶሪያ የሚያይል ቀውስ በኮንጎ ኦቲስ እንግሊዝ ውስጥ ጥገኝነት ቢጠይቅም፤ የገና በአል በሚከበርበት የዛሬው እለት ወደ ትውልድ ሀገሩ እንዲመለስ ይደረጋል የሚል ዜና መሰማቱን ተከትሎ መነጋገሪያ ሆኗል። የኦቲስ የጥገኝነት ጥያቄ በስደተኞች ጉዳይ መርማሪዎች ሳይታይ በአውደ አመት ወደ ኮንጎ ለመመለስ መገደዱን በመቃወምም 3,000 ሰዎች ፊርማቸውን አኑረዋል። በሀገሪቱ የስደተኞችን ጥያቄ የሚመረምረው አካል፤ ጉዳዩን ከተለያየ አቅጣጫ ተመልክቶ እየፈተሸ መሆኑን ተናግሯል። ሆኖም የተለያዩ ተቋሞች የስደተኛውን መመለስ እየተቃወሙ ነው። 'ሄይ ብሬኮን ኤንድ ታልጋርት ሳንክችወሪ ፎር ሬፍዩጂስ' የተባለ የስደተኞች ተቋም እንደሚለው፤ ኦቲስ እንደ አውሮፓውያኑ ታህሳስ 19 እለት ታግቶ የስደተኞችን ጉዳይ በሚመረምረው አካል ተጠርቷል። በሌላ በኩል ቃል አቀባይ ማሪያ ዱጋን የኦቲስን ጉዳይ የሚከታተለው ግለሰብ የገና በአል እረፍት ላይ እንደሆነ ተናግረው፤ "ጉዳዩ የት እንደደረሰና ለምን ጥገኝነት አንደተከለከለ አላውቅም" ብለዋል። የ'ሄይ ፌስቲቫል' ዳይሬክተር ፒተር ፍሎራንስ፤ የጥገኛነት ጥያቄው ሳይመረመር ወደ ትውልድ ሀገሩ የሚመለስበት አካሄድ ግልጽ አይደለም ብለዋል። በተለይም በበአል ወቅት ኦቲስ እንዲመለስ መደረጉ አሳዝኗቸዋል። 'ስታንድ አፕ ቱ ሬሲዝም ዌልስ' በተባለው ተቋም የሚሠሩት አሊስ ጋርድነር፤ ኦቲስ ወደ ሀገሩ ከተመለሰ ለአደጋ መጋለጡ አስግቷቸዋል። "የገና እለት ያለ ፈቃዱ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ይደገራል ተብሏል። ምግብ እየበላ አይደለም። አይተኛም። ድብርት ተጭኖታል።" ሲሉ ያለበትን ሁኔታ ገልጸዋል። የስደተኞችን ጉዳይ የሚመለከተው ቢሮ ቃል አቀባይ፤ እንግሊዝ ጥበቃዋን ለሚሹ ስደተኞች መጠጊያ መሆኗን ተናግረዋል። በዚህ ተግባርም "የምንኮራበት ታሪክ አለን" ብለዋል። ኦቲስ ወደ ሀገሩ እንዳይመለስ የፊርማ ማሰባሰብ የተጀመረው ባለፈው አርብ ነበር።
57326568
https://www.bbc.com/amharic/57326568
የዓለም ጤና ድርጅት የቻይናው ሲኖቫክ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደ
የዓለም ጤና ድርጅት የቻይናውን ሲኖቫክ የተባለው የኮቪድ-19 ክትባት ለአስቸኳይ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ሰጠ።
የኮሮናቫይረስ የመጀመሪያ መነሻ እንደሆነች የሚነገርላት ቻይና ያመረተችው ሲኖቫክ የተሰኘው ክትባት የአስቸኳይ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ፈቃድ ከአለም የጤና ድርጅት አገኘ። የዓለም የጤና ድርጅት እንዳለው ክትባቱን ከወሰዱ ሰዎች ውስጥ 51 በመቶው የኮሮናቫይረስ የሚያስከትላቸው የህመም ምልከቶች አልታዩባቸውም። እንዲሁም ናሙና ከተወሰደባቸው ሰዎች ውስጥ 100 በመቶ ከባድ ምልክቶችን እና ወደ ሆስፒታ ገብቶ መተኛትን መቀነስ አስችሏልም ተብሏል። የዓለም የጤና ድርጅት ባለሙያዎች አሁንም አንዳንድ ማስረጃዎች እና የመረጃ ክፍተቶች ያለመሟላታቸውን ግን አልሸሸጉም። ይህ ክትባት ከሲኖፋርም ቀጥሎ አረንጓዴ መብራቱን ከአለም የጤና ድርጅት የሚቀበል ሁለተኛው የቻይና ክትባት ሆኗል። ክትባቱን ፍትሃዊ በሆነ የኮሮናቫይረስ ክትባት ማስገኛ ማዕቀፍ በሆነው የኮቫክስ ፕሮግራም ውስጥ እንዲካተት ይህ የዓለም የጤና ድርጅት ፈቃድ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። በበርካታ ሀገራት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ሲኖቫክ ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ አዋቂዎች የሚመከር ሲሆን ከሁለት እስከ አራት ሳምንት ባለው ግዜ ውስጥ ሁለተኛው ክትባት ይሰጣል። የአስቸኳይ ጊዜ ፈቃድ ማግኘት ማለት ክትባቱ "የደህንነት፣ የውጤታማነት እና የምርት መለኪያዎች የሆኑ ዓለም አቀፍ ግዴታዎችን ያሟላል" ማለት ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል። በብራዚል በምትገኝ አንድ ከተማ ውስጥ በተደረገ ጥናት የሲኖቫክ ክትባት ከወሰዱ አዋቂዎች ውስጥ በኮቪድ የሚከሰት ሞት 95 በመቶ መቀነስ ችሏል። በደቡብ ምስራቅ ብራዚላዊቷ ሳኦ ፓውሎ የምትገኘው ሴራና ከተማ 45,000 ነዋሪዎችን ይዛለች። ከእነዚህ ውስጥ 75 በመቶ የሚሆኑት የሲኖቫክ ክትባትን ከወሰዱ በኋላ የህመምተኞች ቁጥር እና ሆስፒታል የመተኛት ምጣኔ እንደቀነሰ ጥናቱ አመልክቷል ። የዓለም የጤና ድርጅት ረዳት ዋና ዳይሬክተር ማሪያንጌላ ሲማኦ "በመላው ዓለም ያጋጠመውን ፍትሃዊ የክትባት እጦትን ለመቅረፍ በርካታ የኮቪድ ክትባቶችን ማካታት ያስፈልጋል" ብለዋል። አምራቾች በኮቫክስ ተቋም ውስጥ እንዲሳተፉ፣ ዕውቀታቸውን እና መረጃዎቻቸውን እንዲያካፍሉ እና ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ለማዋል አስተዋፅዖ እናደርጋለን ብለዋል። ከሲኖቫክ ዋነኞቹ ጠቀሜታዎች አንዱ በመደበኛ ማቀዝቀዣ ውስጥ ከሁለት እስከ ስምንት ዲግሪ ሴልሺየስ ውስጥ መቀመጥ መቻሉ ነው። ይህም በከፍተኛ ወጪ በርካታ ክትባቶችን ለማከማቸት አቅም ለሚያጥራቸው ታዳጊ አገራት ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
news-50237471
https://www.bbc.com/amharic/news-50237471
በፌስቡክ የሐሰት ዜና ለማሰራጨት ሲል ፖለቲከኛ ለመሆን ያሰበው ግለሰብ
በማህበራዊ ሚዲያዎች የሀሰት ዜና ማሰራጨት ትፈልጋላችሁ? እንግዲያውስ ፖለቲካኛ ብትሆኑ ያዋጣችኋል፤ ይላል አሜሪካዊው አክቲቪስት አድሪዬል ሃምፕተን። ፖለቲካዊ ማስታወቂያዎች ላይ ፌስቡክ ያለውን አቋም መፈተሽ እፈልጋለው ብሏል አድሪዬል።
ሳንፍራንሲስኮ የሚገኘው አድሪዬል ሃምፕተን ፌስቡክ ፖለቲካዊ ቅስቀሳዎችን ምንም ማጣራት ሳያደርግ እንዲተላላፉ ይፈቅዳል፤ የሌሎች ሰዎችን መልዕክት ግን አብጠርጥሮ ይመለከታል ሲል ይከሳል። • ፌስቡክ ሐሰተኛ ዜናዎችን መለየት ሊጀምር ነው • የፌስቡክ ዲጅታል ገንዘብ 'ሊብራ' ጥያቄን አስነሳ ለሃሳቡ ማጠናከሪያ እንዲሆነው ደግሞ በ2022 ለሚካሄደው ምርጫ በካሊፎርኒያ ተፎካካሪ ለመሆን አስቧል። በዚያውም ሐሰተኛ ፖቲካዊ መልዕክቶቹን በፌስቡክ ያስተላልፋል። ''የዚህ ሃሳብ ዋነኛው ግብ ፌስቡክ በፖለቲካዊ መልዕክቶች ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር መመርመርና እንደ ዶናልድ ትራም ያሉ ፖለቲከኞች ሐሰተኛ መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ ዝም እየተባሉ ሌሎች ላይ እንዴት ቁጥጥር እንደሚደረግ ማሳየት ነው'' ብሏል አድሪዬል። ፌስቡክ በበኩሉ ይህ ሰው ይህንን በማለቱ በራሱ ሐሰተኛ ዜና እያስተላለፈ ነው ጉዳዩንም በቀላሉ አልተወውም ብሏል። ማህበራዊ ሚዲያን ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከል 99 በመቶ የሚሆኑትን እንወክላለን የሚለው የበይነ መረብ ሊግ አባል የሆነው አድሪዬል፤ ግባችን አጥባቂ ፖለቲከኞች በማህበራዊ ሚዲያዎች እንዴት ጡንቻቸውን እንደሚጠቀሙ ማሳየትን መከላከል ነው ይላል። ''ከሩሲያ የኢንተርኔት ምርምር ኤጀንሲ እስከ ትራምፕ 'ዲጂታል ብሬይን ትረስት' ድረስ ፖለቲከኞች በማህበራዊ ሚዲያ ቀውስ በመፍጠር ነው የሚታወቁት። እኛ ደግሞ እነሱን እየተዋጋን ነው'' ይላል አድሪዬል። አክሎም ''ማህበራዊ ሚዲያ በጣም ትልቅ አቅም አለው። ፌስቡክ በራሱ የምርጫ ሂደቶችን ማስቀየር ይችላል'' ብሏል። • የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃል ደህንነት አስተማማኝ አይደለም ተባለ የአድሪዬል ውሳኔ የፌስቡክ 200 ሰራተኞች ለዋና ሥራ አስኪያጁ ማርክ ዙከርበርግ ድርጅቱ ፖለቲካዊ መልዕክት ያላቸው ማስታወቂያዎችን በተመለከተ ስላለው ፖሊሲ ይፋዊ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ የመጣ ነው። ''ነጻ ንግግርና የተከፈለባቸው ንግግሮች እኩል አይደሉም'' ይላል ሰራተኞቹ የጻፉት ደብዳቤ። ''በፖለቲካዊ ሃላፊነቶች ላይ ያሉ ሰዎችና ለስልጣን የሚወዳደሩ ፖለቲከኞች ስለሚያስተላልፉት መልዕክት ቁጥጥር አለመደረጉ ከፌስቡክ ዓላማ ጋር ይጣረሳል'' ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አድሪዬል ሃምፕተን ለፖለቲካዊ ስልጣን እወዳደራለሁ ማለቱን ተከትሎ ፌስቡክ የመረጃ ማጣራት ካደረግኩ በኋላ ፖለቲካዊ መልዕክቶቹን አጠፋቸዋለው ብሏል። ጉዳዩ ደግሞ ወደ ፍርድ ቤት ሊያመራ እንደሚችል እየተዘገበ ነው። • ሶሻል ሚድያ በተጠቃሚዎች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ? የፌስቡክ ቃል አቀባይ ለሲኤንኤን በሰጡት መግለጫ ''ይህ ሰው በእኛ ፖሊሲዎች ላይ እንከን ለማግኘት ሲል እንደ አንድ የፖለቲካ ተፎካካሪ ተመዝግቧል፤ ይህ ደግሞ መልዕክቶቹን በፌስቡክ ማስታወቂያ በኩል ሊያስተላልፍ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ሌላ ሦስተኛ ወገን እንዲያጣራው እናደርጋለን'' ብለዋል። አድሪዬል ሃምፕተን ደግሞ የእኔ ጉዳይ ተለይቶ በሦስተኛ ወገን እንዲጣራ የሚያደርጉ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍር ቤት ለመውሰድ እያሰበ እንደሆነ አስታውቋል።
42408169
https://www.bbc.com/amharic/42408169
ሸማቹ በውጭ ምንዛሪ ለውጡ ማግስት
የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ከተደረገ ሁለት ወራት አልፈዋል። ይህም በብዙዎች የዕለት ተዕለት ህይወት ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ አሳደረ? መንግሥትስ በወሰደው እርምጃ ያሰበውን ውጤት ማስመዝገብ የሚችልበት አቅጣጫ ላይ ነው ወይ? የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዲነሱ ግድ ይላል።
ከተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ቢቢሲ ያነጋገራቸው አዲስ አበቤዎች ባለው የኑሮ ውድነት ላይ የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ መደረጉ የዕለት ከዕለት ኑሯቸውን በእጅጉ እንዳከበደው ገልፀዋል። ወ/ሮ አስቴር ገብሩ እንደሚሉት ከዶላር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው እቃዎችን ጨምሮ መሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ሳይቀር ጭማሪ ታይቷል። የሚጠቀሙት ባለ አንድ ሊትር ዘይትን በ52 ብር ነበር የሚገዙት። የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ በተደረገ በጥቂት ቀናት ውስጥ ግን ዘይቱ የስምንት ብር ጭማሪ አሳይቷል። በተመሳሳይ የሳሙና ዋጋ እጅጉን መጨመሩን በምሬት ይገልፃሉ። ድንገት በሚገዟቸው ሸቀጦች ላይ በተደረገው ጭማሪ ምክንያት ወ/ሮ አስቴር ከባለሱቅ ደንበኞቻቸው ጋር በተደጋጋሚ እሰጥ አገባ ውስጥ መግባታቸውን ይናገራሉ። እሳቸው እንደሚሉት ቸርቻሪ ደንበኞቻቸው ለዋጋ ጭማሪው የሚሰጡት ምክንያት የተደረገው የዶላር ምንዛሬ መጨመርን ተከትሎ ጅምላ አከፋፋዮች ዋጋ መጨመራቸውን ነው። ጅምላ ሻጮች በበኩላቸው ደግሞ አስመጪዎች ዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው የሚያከፋፈሉበት ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ መገደዳቸውን ይናገራሉ። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ጅምላ አከፋፋዮች አንዱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ጅምላ አከፋፋዮች በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርገው እያከፋፈሉ መሆናቸውን አምነው ለዚህም ምክንያቱ አስመጪዎች ያደረጉት የዋጋ ጭማሪ መሆኑን እንደምክንያት ይተቅሳሉ። እንደማስረጃም ከአንድ አስመጪ ጋር ከሁለት ወራት በፊት የነበራቸውን ውል አሳይተውናል። ይህ አስመጪ ኩባንያ ከጅምላ አከፋፋይ ድርጅታቸው ጋር አንድ ፍሬ የጠረጴዛ ናብኪን በ12 ብር ሊያቀርብላቸው ተስማምቶ ነበር። ከ10 ቀናት በኋላ ግን የዶላር መጨመርንና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን እንደ ምክንያት ጠቅሶ በጻፈው ደብዳቤ ዋጋውን 14.50 ብር አድርሶታል። ያለቀላቸውን ምርቶች ከውጭ ከሚያስገቡ ኩባንያዎች አንዱ የሌግዠሪ እና ፖፑላር ትሬዲንግ ነው። የኩባንያው ማርኬቲንግ ሃላፊ አቶ አቤል አለባቸው ለዋጋ ጭማሪው ዋናው ምክንያት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ነው ይላሉ። አቶ አቤል እንደሚሉት የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት በጣም ከባድ ስለሆነ ወደ ሀገር ውስጥ ምርቶችን በፍጥነት ማስገባት አዳጋች እንደሆነ ያስረዳሉ። ''ለምሳሌ ሳሙና እናስመጣለን፤ ምርቱ በገበያ ላይ ምንም ያህል ተፈላጊ ቢሆንም በመጋዝን ውስጥ ያለንን በሙሉ በአንድ ግዜ አውጥተን አንሸጥም። ምክንያቱም በአጭር ግዜ ውስጥ ዶላር አግኝቶ ምርቱን እንደገና ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ስለማንችል ከማርኬቲንግ ስትራቴጂ አንጻር ምርታችን ከገብያ ጠፍቶ እንዳይረሳ በአንስተኛ መጠን ወደ ገብያ እናወጣዋለን'' ሲሉ ያስረዳሉ። ይህ አይነት አካሄድ ደግሞ በገበያ ላይ የምርት እጥረት በመፍጠር የሸቀጦች ዋጋ ከፍ እንዲል እንደሚያደርግ የሚናገሩት የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ሳሙኤል ሳህሌ ናቸው። አቶ ሳሙኤል መንግስት የብር የመግዛት አቅምን የቀነሰው የወጪ ንግድን ለማቀላጠፍ በማሰብ እንደሆነና የዚህ ውሳኔ የመጨረሻ ግብም ወደ ውጪ የሚላከው ምርት ወደ ሀገር ውስጥ ከምናስገባው ምርት ጋር መጣጣም እንዲችል ማድረግ መሆኑን ይገልፃሉ። መንግሥት በወሰደው እርምጃ አዎንታዊ ለውጦችን መመልከት ተችሏል? የሚለው ደግሞ ሌላው ጥያቄ ነው። አቶ ሳሙኤል ''ሀገሪቱ ከምትገኝበት ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አንጻር መንግሥት የወሰደው እርምጃ ትክክለኛ ነው ብዬ አላምንም'' ይላሉ። ሆኖም ግን የመንግሥት ውሳኔ ውጤታማ ነው ወይም አይደለም ለማለት ጊዜው ገና መሆኑንና ቢያንስ ሦስት ወራት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ያስረዳሉ። በንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የገበያ መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኢቲሳ ደሜ በበኩላቸው አስመጪዎች እና አከፋፋዮች ወደፊት ምን ሊፈጠር ይችላል በሚል ስጋት ብቻ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖራቸው የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዳቸውን፤ በዚህም የዋጋ ጭማሪዎች መታየቱን ይናገራሉ። እስከ 120 በመቶ አግባብ ያልሆነ ጨማሪ ያደረጉ ስምንት አስመጪዎች እና አከፋፋዮች መከሰሳቸውንም ጠቁመዋል። እንዲሁም ሌሎች በርካታ ድርጅቶችንም ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው ወደ ህግ ለማቅረብ አስፈላጊ መረጃዎችን እያሰባሰቡ መሆኑን አቶ ኢቲሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አላግባብ ጭማሪ ያደረጉ ነጋዴዎችን ተጠያቂ የማድረጉ እርምጃ እንዳለ ሆኖ፤ የሸማቹን የዕለት ከዕለት ኑሮ ያከበደና ትከሻውን ያጎበጠውን ገበያ ለማረጋጋትስ የመንግሥት እጅ ከምን? የሚለው ጥያቄም ከምንም በላይ ምላሽ የሚሻ መሆኑን ያነጋገርናቸው ሸማቾች ተናግረዋል።
news-45318973
https://www.bbc.com/amharic/news-45318973
ሃሰተኛ የመዋቢያ ምርቶች መርዛማ ንጥረ-ነገሮችን ይዘው ተገኙ
ሜርኩሪን የመሳሰሉ መርዛማ ንጥረ-ነገሮች በሃሰተኛ የመዋቢያ ምርቶች ውስጥ ተገኙ።
የእንግሊዝ የአካባቢ ባለስልጣናት ማህበር ከሆነ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ፓዎንድ ሊያወጡ የሚችሉ ሃሰተኛ የመዋቢያ ምርቶች ገበያ ላይ መኖራቸውን ደርሼበታለው ብሏል። ማህበሩ ጨምሮ እንዳለው ምርቶቹ ''ከፍተኛ የሆነ የጤና መታወክ ያስከትላሉ'' እንዲሁም የአምራቾች ንግድ ይጎዳሉ፤ ተጠቃሚዎችንም ያሳስታሉ። ሃሰተኝ ምርቶቹ ታዋቂ የሆኑ እንደ ማክ፣ ሽኔል እና ቤኔፊት የተሰኙ ምርቶችን ስም እና መልክ ይዘው ይወጣሉ። • እውነተኛ ውበትን ፍለጋ ማህበሩ ሃሰተኛ ምርቶቹ የያዟቸው አደገኛ ምርቶች በቆዳ ላይ ጉዳት ያደርሳሉ ብሏል። ቆዳ ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት በተጨማሪ፤ ''በስርዓተ-ልመት፣ በሳምባ፣ በኩላሊት፣ በዓይን እና በበሽታ የመከላከል ስርዓት አቅማችን ላይ ጉዳት ያስከትላሉ።" በቅርቡ የተያዙ ሃሰተኛ ምርቶች በውስጣቸው ሜርኩሪ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ቆዳን ለማንጣት ጥቅም ላይ የሚውል ሃይድሮኩኢኖን የተሰኙ ንጥረ-ነገሮች ተገኝተዋል። • ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለገበያ ያቀረቡ ተፈረደባቸው የማህበሩ ሰብሳቢ ሳይመን ብላክበርን ''ከምንም በላይ የመዋቢያ ምርቶችን ከመግዛታችን በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ምርቶቹን ለገብያ ያቀረበው ሻጭ ማን እንደሆነ ለማጣራት እንሞክር። ዘወትር ማስታወስ ያለብን አንድ የመዋቢያ ምርት ዋጋው ከተለመደው ዝቅተኛ ከሆነ ሃሰተኛ ሊሆን ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል'' ብለዋል።
news-53747880
https://www.bbc.com/amharic/news-53747880
ትግራይ፡ በመቀለ 'ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ነበር' የተባሉ 9 ወጣቶች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው
በመቀለ 'ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ሲሉ ተይዘዋል' የተባሉ ዘጠኝ ወጣቶች ላይ ከሰባት ቀን በኋላ ክስ ሊመሰረት ነው።
ወጣቶቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጀምሮ የትግራይ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መቆየቱን ትናንት [ሐሙስ] ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ ምርመራውን በመጨረሱ ፋይላቸውን ክስ እንዲመሰረት ወደ ዐቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው እየታየ የሚገኝበት የመቀለ ከተማ ቀዳማይ ወያነ ፍርድ ቤትም ዘጠኙን ወጣቶች እስር ቤት እንዲቆዩ አዟል። በትግራይ "የክልሉን መንግሥት ለመጣል የሚያነሳሳ መፈክር ይዛችሁ ተገኝታችኋል" በሚል በቁጥጥር ስር የዋሉት እነዚህ ዘጠኝ ወጣቶች ትናንት ለሦስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል። ወጣቶቹ ከ46 ቀናት በፊት፣ ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ በመቀለ የሮማነት አደባባይ ላይ መንግሥትን በኃይል ለመጣል የሚያነሳሳ መፈክር ይዘው መገኘታቸውን እንዲሁም ያልተፈቀደ ሠልፍ ለማካሄድ ሲወጡ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ገልጾ ነበር። በወቅቱ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም ፖሊስ በተደጋጋሚ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በመጠየቅ ከ46 ቀናት በላይ በእስር ላይ ቆይተዋል። ወጣቶቹ ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ወቅት ችሎቱን ማንም እንዲታደም ያልተፈቀደ ሲሆን ቢቢሲ ከችሎቱ በኋላ የሚመለከታቸውን በማናገር መረዳት እንደቻለው ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ በመጨረስ ጉዳያቸውን ለዐቃቤ ሕግ አስረክቧል። በዚህም ከሰባት ቀናት በኋላ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ታውቋል። ወጣቶቹ 'ፈንቅል' ከተባለው እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት እንደሌላለቸው መናገራቸውንና ቡድኑም ይህንኑ ማረጋገጡን ቢቢሲ መረዳት ችሏል። ዘጠኙ ወጣቶች በሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ ላይ የክልሉን መንግሥት በመቃወም ሕገወጥ የተቃወሞ ሰልፍ ሊያካሂዱ ነበር በሚል በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ቆይተዋል።
news-46402439
https://www.bbc.com/amharic/news-46402439
በአፍጋኒስታን የአየር ጥቃት 23 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ
በአፍጋኒስታን ደቡባዊ ግዛት ሄልማንድ አሜሪካ በፈፀመችው የአየር ድብዳባ ቢያንስ 23 ንፁሃን ዜጎች ተገደሉ። የተባበሩት መንግስታት እንዳስታወቀው አብዛኞቹ ተጎጂዎች ሴቶችና ህፃናት ናቸው።
10 የሚሆኑ ህፃናት ሲገደሉ 3 ቱ ለጉዳት ተዳርገዋል የአየር ድብደባው የደረሰው የአፍጋን ወታደሮችና የአሜሪካ ኃይሎች ባካሄዱት ውጊያ ወቅት ነው። • በአዲስ አበባ አፍላ ወጣቶች በከፍተኛ መጠን በኤች አይቪ እየተያዙ ነው • በዌስት ባንክ ዘጠኝ ሺህ ዓመት ያስቆጠረ ጭምብል ተገኘ ቢያንስ 10 ህፃናት እና 8 ሴቶች በጥቃቱ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ገልፀዋል። የአሜሪካ ኃይሎች ግን የተጎጂዎችን ቁጥር በማጣራት ላይ እንደሚገኙ መርማሪዎች አስታውቀዋል። አሜሪካ ባለፈው ዓመት በአፍጋን ላይ ጥቃት ለማድረስ አዲስ ስልት ካወጀች ወዲህ በንፁሃን የሚደርሰው ጉዳት እየተባባሰ መጥቷል። ስልቱ ፈንጂዎችንና በርካታ ቦምቦችን መጠቀምን የሚፈቅድ ነው። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የታሊባንና እስላማዊ ታጣቂ ቡድኖችን ለማጥቃት የወታደሮችን ቁጥር ለማሳዳግ ባለፈው ዓመት ነበር ውሳኔውን ያሳለፉት። በአፍጋኒስታን በአሜሪካ የሚመራው የኔቶ ጦር እንዳስታወቀው በጋርምሰር አካባቢ የሄሊኮፍተር ድብደባው የተፈፀመው በአሜሪካ የሚደገፈው የአፍጋን ልዩ ኃይልና ታሊባን ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ ወቅት ነው። ኔቶ በበኩሉ ታሊባኖች በርካታ ንፁሃን ዜጎች የሚጠለሉበትን ህንፃ እንደ ምሽግ መጠቀሙ ለበርካታ ንፁሃን ዜጎች ሞት ምክንያት ሆኗል ብሏል። ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው የአካባቢው ነዋሪ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የአየር ድብደባው ሲፈፀም የታሊባን ተዋጊዎች በህንፃው አቅራቢያ ነበሩ። እማኙ ጨምረው እንደተናገሩት በጥቃቱ ከተጎዱት በዕድሜ ትንሹ የ 6 ዓመት ህፃን እንደሆነ ተናግረዋል። • የሰከረው ጃፓናዊ አብራሪ የ10 ወራት እስር ተበየነበት በአፍጋኒስታን የተባበሩት መንግስታት እንዳስተወቀው ባለፉት 9 ወራት ብቻ በተፈፀመ የአየር ድብዳባ 649 ንፁሃን ዜጎች ለሞትና ለጉዳት ተዳርገዋል። ከአውሮፓውያኑ 2009 ጀምሮ የተጎጂዎች ቁጥርም እየጨመረ እንደመጣ ተናግረዋል። ባለፈው ሚያዚያ ወር ብቻ በሰሜን ምስራቋ ኩንዱዙ ግዛት በአንድ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ በአሜሪካ የሚመራው የአፍጋን የአየር ጥቃት 30 ህፃናት መገደላቸውን አስታውሰዋል። የአሜሪካ አየር ኃይል በዚህ ዓመት ብቻ ባለፉት 10 ወራት ቀደም ካሉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቁጥር ያለው 6 ሺህ የሚጠጉ የጦር መሳሪያዎችን አስገብቷል። በአፍጋኒስታን የሚደርሰው እልቂት በይበልጥ የመንግስት ተቀናቃኝ በሆኑት የታሊባን ታጣቂዎችና በእስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች የሚፈፀም ነው።
news-55285171
https://www.bbc.com/amharic/news-55285171
አሜሪካ ፡ የትራምፕ ሥልጣን ሊያበቃ በተቃረበበት ጊዜ ሁለተኛው የሞት ቅጣት ተግባራዊ ሆነ
ከ20 ዓመታት በፊት አሜሪካ ውስጥ ታዳጊ ልጁን በመግደል ወንጀል ሞት የተፈረደበት አልፈርድ ቦርጊዎስ ቅጣቱ ተግባራዊ ሆኖበታል።
በዚህም በአገሪቱ ውስጥ ከሌላው ጊዜ በተለየ ባለፉት ሁለት ቀናት የሞት ቅጣት የተግባራዊ የሆነበት ሁለተኛው ሰው ሆኗል። ከአልፈርድ በፊት ባለፈው ሐሙስ ብራንደን በርናንድ በሞት ተቀጥቷል። የዶናልድ ትራምፕ የሥልጣን ዘመን ጥር 20 ከመገባደዱ በፊት ሦስት ተጨማሪ ሰዎች የሞት ቅጣት እንደሚፈጸምባቸው ተገልጿል። የሞት ቅጣት ላለፉት 17 ዓመታት ተቋርጦ ነበር። በዚህ ዓመት መባቻ ላይ ግን ቅጣቱ በድጋሚ እንዲጀመር ትራምፕ አዘዋል። የሞት ቅጣት በተወሰነባቸው ሰዎች ላይ በአጠቃላይ ከተተገበረ፤ ከሌሎቹ በተለየ ትራምፕ ፕሬዘዳንት ብዙ ሰው በሞት የቀጡ መሪ ይሆናሉ። ላለፉት 130 ዓመታት የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ሥልጣን ሊለቁ ሲሉ የሞት ቅጣትን ይገታሉ። ቀጣዩ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ጥር 20 በዓለ ሲመታቸው ይከናወናል። ባይደን የዳልዌር ሴናተሩ ሳሉ ጀምሮም ለአስርት ዓመታት የሞት ቅጣትን እንደሚቃወሙ ሲገልጹ ነበር። ሥልጣን ከያዙ የሞት ቅጣትን እንደሚያስወግዱም አስታውቀዋል። ፍርድ ቤት እንዳለው የሞት ቅጣት የተፈጸመበት አልፈርድ የሁለት ዓመት ሴት ልጁ ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንዳደረሰ ተነሯል። የጭነት መኪና አሽከርካሪ ሳለ በቴክሳስ በኩል ሲያልፍ ልጁን እንደገደላትም ፍርድ ቤቱ ገልጿል። ዐቃቤ ሕግ እንዳለው፤ መኪናውን እያቆመ ሳለ ልጁ መኪናው ውስጥ ፈሳሽ ሲደፋባት ከመኪናው መስታወትና ከውስጠኛው ክፍል ጠርዝ ጋር አጋጭቶ ነበር የገደላት። የአልፈርድ ጠበቆች እንዳሉት፤ አልፈርድ የአእምሮ ውስንነት (ኢንተለክችዋል ዲስኤቢሊቲ) ስላለበት በሞት ሊቀጣ አይገባም ነበር። ሌሎች የሞት ቅጣት የተላለፈባቸው ታራሚዎች ሊሳ ሞንተግመሪ፡ እአአ 2004 ላይ ሚዙሪ ውስጥ ነፍሰ ጡር ሴትን አንቃ ልጇን ከማህጸኗ ወስዳ አፍናለች። ጥር 12 የሞት ቅጣት ይፈጸምባታል ተብሏል። ጠበቃዋ እንደሚሉት ሊሳ ልጅ ሳለች በደረሰባት ድብደባ ምክንያት ከፍተኛ የአእምሮ ህመም አለባት። ከ1953 ወዲህ በሞት የተቀጣት የመጀመሪያዋ ሴት ትሆናለች። ኮሪ ጆንሰን፡ ሪችመንድ፣ ቨርጂንያ ውስጥ ከነበረ አደንዛዥ እጽ ዝውውር ጋር በተያያዘ በሰባት ሰዎች ግድያ ነው የተከሰሰው። ልጅ ሳለ በደረሰበት አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት ሳቢያ የአእምሮ ውስንነት እንዳለበት ጠበቆቹ ተናግረዋል። ደስቲን ጆን ሂግስ፡ እአአ 1996 ላይ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ሦስት ወጣት ሴቶችን አፍኖ በመግደል ነው የተከሰሰው። ግለሰቡ ሴቶቹ እንዲገደሉ ዊሊስ ሀይንስ የተባለ ግብረ አበሩን አዟል እንጂ ግድያውን አልፈጸመም። ጥር 15 የሞት ቅጣት ይፈጸምበታል ተብሏል።
news-46453324
https://www.bbc.com/amharic/news-46453324
ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች
እርግጥ ነው የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ነዳያን አያጣቸውም። ሶሪያውያንን ማየት ግን እንግዳ ነው።
በተረጂነት እምብዛም የማይታወቁ አረቦች በየጥጋጥጉ ምጽዋት ሲጠይቁ ማየት ለበርካታ አዲስ አበቤ ጥያቄ ቢያጭርበት አይደንቅም። የሶሪያውያን ነገር መነጋገሪያ የኾነውም ለዚሁ ይመስላል። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? በዚህ ዘመን ከዕልቂቶች ሁሉ የከፋው እልቂት የደረሰው በሶሪያ ምድር ነው። ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧ በእርስ በርስ ጦርነት አልቋል። ከጠቅላላው የሶሪያ ሕዝብ ገሚሱ ተፈናቅሏል። በየዓለማቱ እየተንከራተቱ ካሉት ሶሪያውያን ጥቂቶቹ ከቅርብ ወራት ወዲህ የኢትዮጵያን ምድር መርገጥ ጀምረዋል። እንዴት ኢትዮጵያን መረጡ? ኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይ አገር ናት ሲባል በመንግሥት ደረጃም የሚገለጽ፣ በአሐዝም የሚደገፍ ሐቅ ነው። ምንም እንኳ በድህነት ተርታ ያለች ቢሆንም ኢትዮጵያ በዓለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን በማስጠለል ከቀዳሚ አገራት ተርታ ትመደባለች። አያሌ ሶማሊያውያን፣ ኤርትራውያንና ደቡብ ሱዳናውያን በመጠለያ ጣቢያዎችና በዋና ዋና ከተሞች ጭምር ይገኛሉ። ሶሪያዊያኑ ግን የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ናቸው። • በዩቲዩብ 22 ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው የሰባት ዓመቱ ህፃን ስምንት ዓመታትን ካስቆጠረው የሶሪያ ጦርነት የሸሹ ስምንት ሚሊዮን ዜጎች በጎረቤት አገራትና በአውሮፓ ተጠልለዋል። ጥቂቶች ወደ አፍሪካ አቅንተዋል። ግብጽ ከአፍሪካ አገራት በርካታ የሶሪያ ስደተኞች የሚገኙባት ናት። ከግብጽ ሌላ ሊቢያ፣ አልጄሪያና ሱዳን ወደ 33ሺህ የሚጠጉ ስደተኞችን ያስተናግዳሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰሜን አፍሪካ የሚገኙት የሶሪያ ስደተኞች በአየርም በምድርም አቆራርጠው ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ማማተር ጀምረዋል። ከእነዚህ መሐልም የተወሰኑት ኢትዮጵያን መርጠዋል። "የምንማጸነው እንደትረዱን ነው" አናስ መሐማት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ከአንድ ወር በፊት ነው። ቤተሰቡን ይዞ ከንጋት እስከ ምሽት ለምጽዋት እጁን ይዘረጋል፤ በአዲስ አበባ ጎዳና። ከአረብኛ ሌላ አይናገርም። በአንድ እጁ ሮጦ ያልጠገበ ልጅ ይዞ በሌላ እጁ በነጭ ወረቀት ላይ በአማርኛ የተጻፈለትን የድረሱልኝ ጥሪ ከፍ አድርጎ ለወጪ ወራጁ ያሳያል። አትላስ አካባቢ። • ለየት ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ደብዳቤ ለየመኖች ያነገበው ጽሑፍ፣ "እኛ ወንድሞቻችሁ ከሶሪያ ተሰደን የመጣን ሲሆን አሁን በችግር ላይ ስለሆንንን ያላችሁን እንድትረዱን በፈጣሪ ስም እንለምናችኋለን። አላህ ይስጥልን" የሚል ነው። አናስ አትላስ አካባቢ በልመና ላይ ሳለ የቢቢሲ የአዲስ አበባ ወኪል አግኝቶት ነበር። "...በሕይወት ለመቆየት እየታገልን ነው። መንገድ ላይ፣ ትራፊክ መብራት አካባቢ እና በየመስጊዶች እንለምናለን። ባንለምን ደስ ይለን ነበር። ኾኖም በሕይወት ለመቆየት ሌላ አማራጭ የለንም። ፈጣሪ ይርዳን...." ብሎታል። "ሕሊናዬ ሊያርፍ አልቻለም" ያለፉት ጥቂት ወራት በርከት ያሉ ሶሪያዊያን በኢትዮጵያ ጥገኝነት እየጠየቁ ነው። ስደተኞቹ የነበራቸውን ጥሪት ኢትዮጵያ ለመድረስ በጉዞ ወጪዎች አሟጠውታል። በቁጥር ምን ያህል ሶሪያዊያን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል የሚለው በይፋ ባይታወቅም መንግሥት ግን የስደተኞች ምዝገባ እያካሄደ እንደሆነ ይገልጻል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ በየጎዳናው ጥጋጥግ የሚተኙ በርካታ ሶሪያዊያን እየተታዩ ነው። በጎ ፈቃደኞች አይተው ማለፍ አልቻሉም፤ አይሻ መሐመድ ከነዚህ አንዷ ናት። "የሚያሳዝኑ ሕዝቦች ናቸው። እዚህ ከደረሱ ጀምሮ እያገዝናቸው ነው። የምንችለውን ሁሉ እየለገስን ነው። ብርድልብስ፣ ምግብ፣ አልባሳት። ሰዎችም በተቻላቸው መጠን እንዲረዷቸው እየጠየቅን ነው። ትንንሽ ልጆችን ይዘዋል። በዚያ ላይ ቋንቋ አይችሉም።" • ሴቶችና ወጣቶች የራቁት የተቃውሞ ፖለቲካ የአዲስ አበባ ነዋሪ የኾነው ቢኒያም ታምሩ በበኩሉ ከሁሉም በላይ ሕጻናትን ይዘው የሚንከራተቱ ሶሪያዊ እናቶች ስሜቱን የሚረብሹት ይመስላል። "ሴቶችና ሕጻናት በዚህ መልኩ ሲንገላቱ ሕሊናዬ እያየ ዝም ሊል አልቻለም። ያለኝን ሁሉ ለማካፈል አልሳሳም። ምንም ትንሽ ቢሆን። 20 ብር ካለኝ 10 ብሩን እሰጣቸዋለሁ።" ሩሲያና የአሳድ መንግሥት ግጭቶች ስለረገቡ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየጠየቁ ነው። ነገር ግን ከ5 ሚሊዮን የሚልቁት ስደተኞች ለመመለስ እያመነቱ ነው። በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም ሳይሰፍን መመለሱ ስጋት ጥሎባቸው በሰው አገር ይንከራተታሉ። "መቼስ ምን ይደረጋል። እንደዚህ አልነበርንም። አሁን ያለንበት እውነታ ግን ይኸው ነው። ኢትዮጵያዊያን የሚቻላቸውን እንዲያደርጉልን ነው የምንማጸነው" ይላል አናስ። ለአናስና ቤተሰቡም ሶሪያ የምትባለው እናት አገራቸው የሩቅ ትዝታ ሆናባቸዋለች። ሶሪያዊያን ስደተኞች በአዲስ አበባ
news-54122225
https://www.bbc.com/amharic/news-54122225
እስራኤልና ባህሬን ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ስምምነት ላይ ደረሱ
እስራኤልና ባህሬን ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ ለማሻሻል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
"ሁለተኛዋ የአረብ አገር በ30 ቀናት ውስጥ ከእስራኤል አገር የሰላም ስምምነት ላይ ትደርሳለች።" ሲሉ ትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አስፍረዋል። ለበርካታ አስርታት በርካታ የአረብ አገራት እስራኤልን የፍልስጥኤም ጉዳይ ከተፈታ በኋላ ግንኙነታቸውን እንደሚቀጥሉ በመግለጽ አግልለው ነበር። ነገር ግን ባለፈው ወር የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ስምንት ላይ ደርሳለች። ከዚያ ጊዜ ወዲህ ባህሬን ትከተላለች የሚል ግምት ነበር። በእስራኤል እና በአረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው ግንኙነት የተለሳለሰው በአሜሪካ አሸማግይነት ሲሆን፤ ነሐሴ 13 ነበር ወዳጅነታቸውን ይፋ ያደረጉት። በአብዛኛው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ይህ ዜና በመልካም ቢወሰድም፤ ፍልስጥኤም ግን ተቃውሞዋን ገልጻለች። በተለይም የአረብ ኤምሬትስ ለፍልስጥኤም እውቅና ካልሰጠችው እስራኤል ጋር ግንኙነት መፍጠራቸው፤ ፍልስጥኤምን መክዳት ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ከአረብ ኤምሬትስ ጋር ዳግመኛ መወዳጀታቸውን አስታከው በወረራ የተያዘውን ዌስት ባንክ በግዳጅ የእስራኤል ይዞታ የማድረግ እቅዳቸውን ለማዘግየት ተስማምተዋል።
news-55086096
https://www.bbc.com/amharic/news-55086096
ትግራይ፡ የማይካድራ ሰቆቃ በመርማሪ ቡድኑ አባል አንደበት
በጥቅምት ወር የመጨረሻ ቀን በምዕራብ ትግራይ ማይካድራ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት በትንሹ ስድስት መቶ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከቀናት በፊት ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ የምርመራ ሪፖርት አመልክቷል።
በማይካድራ የተገደሉ ሰዎች አስክሬን በዚህ መሰል አልጋዎች ሲሰበሰቡ ነበር በኢሰመኮ የምርመራ ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰው በነዋሪዎች ላይ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሟል። መርመራውን ያካሄደው ቡድን አባል ለቢቢሲ እንደገለጸችው ማይካድራ ከተማ ሲደርሱ በከተማ የሚረብሽ የአስክሬን ጠረን እንደነበር ተናገራች። "በዚህ መሰል የምርመራ ሥራ ላይ ተሳትፎ ሲደረግ በተቻለ መጠን ግላዊ ስሜትን ወደ ጎን በማድረግ ሙያዊ ሥራ ላይ ማተኮር ይጠበቃል" የምትለው ሐይማኖት አሸናፊ፤ በማይካድራ በነበራት ቆይታ ግን "የተፈጸሙት ኢ-ሰብዓዊ ደርጊቶች እንደ አንድ ሰው ስሜትን የሚጎዱ ነገሮች አጋጥመውኛል" ብላለች። በማይካድራ ነዋሪዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የሆነውን ለማጣራት የሄደው የምርመራ ቡድኑ አባል በመሆን ወደ ስፍራው ያቀናችው ሐይማኖት፤ ወደ ከተማዋ የደረሱት ጥቃቱ ከተፈጸመ ከቀናት በኋላ እንደነበረ ታስረዳለች። ከተማዋ እንደደረሱ በጥቃቱ ወቅት "ንብረት የመዝረፍ እና ማቃጠል በማጋጠሙ አስፓልቱ በሙሉ በቆሻሻ የተሞላ ነበር። የተቃጠሉ እቃዎች በየመንገዱ ተጥለው ይታያሉ። የወዳደቁ ጫማዎች እና አስክሬን የተሰበሰቡባቸው ቃሬዛዎች እዚያም እዚህም ይታያሉ" በማለት ወደ ከተማዋ ለቀናት ተመላልሰው ሪፖርቱን ባጠናቀሩበት ወቅት የተመለከተችውን ታስረዳለች። የመርማሪ ቡድኑ አባላት ወደ ማይካድራ ሲደርሱ ምንም እንኳ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቀብር የተፈጸመ ቢሆን፤ በከተማዋ ውስጥ ግን "የሚረብሽ የአስክሬን ጠረን ነበር" ትላለች። ተዘዋውረው እንደተመለከቱትም በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎችን ቀብር ያስፈጸሙ ሰዎች በከተማዋ በሚገኘው የአቡነ አረጋዊ ቤተ-ክርስቲያን በርካታ ሰዎችን የቀበሩባቸውን የጅምላ መቃብር እንዳሳይዋቸው ትናገራለች። "በቀብሮቹ ላይ የተሳተፉ ሰዎች እንደነገሩን የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ስለነበረ፤ ሟቾችን ለመቅበር ቀናት እንደፈጀባቸው ነግረውናል" ትላለች። አምነስቲ ትክክለኛነታቸውን አረጋግጫለሁ ያላቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች በቃሬዛ ወደ ቀብር ስፍራ የሚወሰዱ በርካታ አስከሬኖችን የሚያሳዩ ናቸው። በርካታ ሰዎች በተገደሉባት ከተማ ውስጥ "ከጥቃቱ ያመለጡ ሰዎች እና የዓይን እማኞችን ታሪክን መስማት ከባድ ስሜት ይፈጥራል" የምትለው ሐይማኖት፤ ክስተቱ በነዋሪው ላይ ያስከተለው የሐዘን ድባብ ከባድ ነው በማለት ሁኔታውን ታስረዳለች። ከሁመራ ከተማ በስተደቡብ በ30 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው የማይካድራ ከተማ የትግራይና የአማራ ተወላጆችን ጨምሮ የሌሎችም ብሔር አባላት የሚኖሩባት ሲሆን የነዋሪዎቿ ቁጥርም እስከ 50 ሺህ የሚገመት ነው። ከጥቃቱ በኋላ የደረሰውን ጉዳት ለመመርመር ወደ ስፍራው የተጓዙት ባለሙያዎች በከተማዋ የነበረው የሰዎች እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቃዛ እንደነበር ሐይማኖት ትናገራለች። በማይካድራ ከተማ ውስጥ "ብዙ ሰዎች አልነበሩም። አብዛኞቹ ሰዎች ከተማውን ጥለው ወጥተው ነበር። ስንደርስ ከጥቃቱ የተረፉና ከከተማዋ ሸሽተው ቆይተው የተመለሱ ሰዎችን ነበር ያገኘነው" ትላለች። ማይካድራ ከተማ አቅራቢያ ሰፋፊ የንግድ እርሻዎች መኖራቸውን የምትገልጸው ሐይማኖት፤ የእርሻ ሥራው ብዙ የሰው ኃይል ስለሚያስፈልግ ብዙ ወጣት የሆኑ ወንዶች ከተለያዩ ስፍራዎች ወደ ከተማዋ ለሥራ እንደሚጓዙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚስን ሪፖርት ይጠቅሳል። በተለይ ለወቅታዊው የእርሻ ሥራ ወደ አካባቢው የሚሄዱ ወጣቶች ከአንድ ስፍራ የሚመጡት በአንድ ቦታ የመስፈር ዝንባሌ እንዳላቸውና ነዋሪዎቹም በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ይገኛሉ። በዚህም "የ'ሳምሪ ሰፈር' የሚባል ቦታ አለ። 'ግንብ ሰፈር' ተብሎ በሚጠራ ቦታ ደግሞ የአማራ ተወላጆች የሚኖሩበት አካባቢ ነው" እንደሆነ ሐይማኖት ትገልፋለች። ሳምሪ እነማን ናቸው? የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ወገን ለይተው በማይካድራ ከተማ ጥቃቱን ያደረሱት 'ሳምሪ' ተብሎ የሚጠራ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን በከተማዋ ከነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ መዋቅር ጋር በመጣመር ነው ብሏል። ሐይማኖት የነበረችበት የምርመራ ቡድን ከአከባቢው ባገኘው መረጃ "ሳምሪ የሚባለው ቡድን ኢ-መደበኛ የሆነው የወጣቶች ስብሰብ ሲሆን ከሌላ የትግራይ አካባቢ የመጡ ወጣቶችን ያቀፈ ሳይሆኑ እንደማይቀር ይገመታል" ትላለች። "'ሳምሪ' የተባለው የወጣቶች ቡድን አሰቃቂ ወንጀል ቢፈጽምም፤ በአንጻሩ የትግራይ ተወላጅ ከሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያንና በእርሻ ቦታዎች ሸሽገው በመደበቅ የብዙ ሰዎች ሕይወትን እንዳተረፉ" ኢሰመኮ በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል። በምሳሌነትም አንዲት የትግራይ ተወላጅ 13 ሰዎችን በቤቷና በእርሻ ቦታ ደብቃ እንዳተረፈች፤ እንዲሁም ሌላ ሴት "አጥቂዎቹ በእሳት ሲያቃጥሉት የነበረን የአንድ ተጎጂን ሕይወት ለማትረፍ ስትሞክር በጥቃት አድራሾቹ እጇን በገጀራ ተመትታ ቆስላለች" ሲል ሪፖርቱ እራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው ሌሎችን ለማዳን የጣሩ ሰዎችን ጠቅሷል። ከቀናት በፊት ስለክስተቱ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ አምነስቲ ኢንትርናሽናል በማይካድራ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ የወጡ ምስሎች ሐቀኝነት በማራትና የዓይን እማኞችን በመጥቀስ በከተማዋ ውስጥ ማንነትን መሰረት ያደረገ አሰቃቂ ጥቃት መፈጸሙን ባወጣው ሪፖርት ላይ ድርጊቱ ማንነት ለይቶ የተፈጸመ መሆኑን ገልጾ ነበር። ኮሚሽኑ በዚህ ድርጊት ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ ጥፋተኞችን በሕግ ፊት በማቅረብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏልል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ሚሼል ባችሌትም በማይካድራ ከተማ የተፈጸሙት "ግድያዎች መረጋገጥ ከቻሉ እንደ ጦር ወንጀል ይቆጠራል" በማለት ተናግረዋል። በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና የትግራይ ክልል ኃይሎች ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከገቡ ከሳምንት በኋላ በምዕራብ ትግራይ የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ነበር በማይካድራ ከተማ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሚያመልክቱ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ፎቶግራፎች መታየት የጀመሩት። ይህ ድርጊት በማይካድራ የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ መዋቅር የፌዴራሉ ሠራዊትን እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቆ ከመውጣቱ በፊት "ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በመተባበር በተለይ "አማሮችና ወልቃይቴዎች" ያሏቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት" መፈጸማቸውን አመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ የመንግሥት ባለስልጣናት ጥቃቱን የፈፀሙት የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው ማለታቸው ይታወሳል። የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው በማይካድራው ድርጊት ውስጥ እጃቸው እንደሌለበት የገለጹ ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ውንጀላውን "መሠረት ቢስ" በማለት፤ ጥቃቱ በገለልተኛ ወገን ይጣራ ሲሉ ጠይቀው ነበር።
45142161
https://www.bbc.com/amharic/45142161
አፍሪካዊው ተማሪ የምግብ ብክነትን ለመፍታት ጥረት ላይ ነው
የ23 ዓመት የምህንድስና ተማሪ የምግብ ብክነት ችግርን ሊፈታ የሚችል የፈጠራ ውጤት እውን ሊያደርግ ይችላል?
ላውረንስ ብዙ ጊዜ በኡጋንዳ ገበያዎች በመሄድ ስለ ፈጠራ ሥራው ለነጋዴዎች ያብራራል ላውረንስ ኦኬታዮት ዩጋንዳን በመኪና እየዞረ ነው። ለአፍሪካ የምግብ ብክነት ቀውስ መፍትሄ ሊሆን ይችላል ብሎ የፈጠረውን መሳሪያ በተመለከተ ወሬውን እያደረሰ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው በአህጉሪቱ በየዓመቱ የሚጣለው ምግብ እስከ 300 ሚሊዮን ሰዎችን ሊመግብ ይችላል። በኡጋንዳ ብቻ እስከ 40 በመቶው አትክልትና ፍራፍሬ መጨረሻው መደፋት ነው። ነገር ግን የ23 ዓመቱ የምህንድስና ተማሪ ላውረንስ የእርሱ የፈጠራ ውጤት የሆነው 'ስፓርኪ ድራየር' የተባለው ማሽን ሁሉንም ነገር እንደሚቀይር ተስፋ ሰንቋል። • የዕለት ከዕለት ኑሮን የሚለውጡ ፈጠራዎች • አንበሶችን ያባረረው ወጣት ምን አጋጠመው? • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ መሳሪያው ከአትክልት ቦታ በሚወጣ ቆሻሻ የሚሰራ ማድረቂያ ሲሆን አትክልትና ፍራፍሬዎችን በፍጥነት ያደርቃል። ምንም የካርቦን ልቀት እንዳይኖር በማድረግ ከቀናት አልፎ ለወራት እንዲቆዩ ያስችላል። ትንሽ ማቀዝቀዣ የሚመስልና ኡጋንዳን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሃገራት ውሱን ሰዎች ብቻ በሚያገኙት የኤሌክትሪክ ኃይል ሳይሆን ከቆሻሻ በሚገኝ የኃይል አቅርቦትን የሚጠቀም ነው። ስፓርኪ ድራየር ኤሌክትሪክ ኃይል ሳያስፈልገው ከአትክልት ተረፈ ምርት በሚመነጭ ኃይል ይሰራል የበሰበሰ ምግብ "በገበያዎች ውስጥ የሚሸጡት አብዛኛዎቹ ምግቦች ከጥቅም ውጪ የሚሆኑት አርሶ አደሮቹ በተገቢው ሁኔታ ማከማችት ስለማይችሉ ነው። እናም በሚቀጥለው ቀን ለመሸጥ ወደ ቤታቸው ተመልሰው ትኩስ ፍራፍሬ እና አትክልት መውሰድ አለባቸው።" "በበጋ ወቅት እዚህ የሚበቅለው ጥቂት ስለሆነ ሰዎች ይራባሉ" ይላል ላውረንስ በኪትጉም የሰሜናዊ ክፍል ዋና ከተማ በሚገኝ እና በሞቀ ገበያ መሃል እየተጓዘ ትናንሽ ሱቆችንና የበሰበሰ ምግብ ቁልልን እያለፈ። የእያንዳንዱ ስፓርኪ ድራየር የመነሻ ዋጋው 80 ዶላር ወይም 2200 ብር ገደማ ነው። እያንዳንዱ ማሽን 10 ኪሎ ግራም ማንጎን በሁለት ሰዓታት ውስጥ ያደርቃል። ማሽኑ በጋዝ የሚነድ እሳት የሚገጠምበት ትንሽ ክፍል ያለው ሲሆን ቁርጥራጮች የተከማቹበትንና ከላይ ያለውን የማድረቂያ ክፍል ያሞቃል፡፡ በተጨማሪም በማድረቁ ሂደት ወቅት ጎጂ አየር እንዳይወጣ የሚከላከል አቀጣጣይ መቀየርያ አለው፡፡ ላውረንስ በመኖርያ ቤቱ ለናሙና ከሰራው ስፓርኪ ድራየር አጠገብ የስፓርኪ ድራየር አማራጮች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ማድረቂያዎች ናቸው። ነገር ግን በጣም ውድ ናቸው። በፀሐይ ኃይል ወይም በፀሐይ ሙቀት በመጠቀም የሚያደርቁ ባህላዊ የማድረቂያ ዘዴዎች ደግሞ በዝናብ ወቅት ካለመስራታቸውም ባሻገር በጣም ዘገምተኛ ናቸው። ይሄን ያህል አቅም ቢኖረውም ላውረንስ እስካሁን የሸጠው ማስን ብዛት በጣም ጥቂት ነው፤ ሰባት ብቻ። ታዲያ የእርሱ የፈጠራ ውጤት በእርግጥ ይሰራል? ከኪቱጉም የሦስት ሰዓት መንገድ ርቆ የሚኖረው የላውረንስ አጎት ጆይ ኦኬታዮት ማድረቂያውን ከሚጠቀሙት የመጀመሪያዎቹ አርሶ አደሮች አንዱ ነው። ላውረንስ ሀሳቡን ለማመንጨት የተነሳሳው አጎቱ የግብርና ሥራን ለመተው እንዳሰበ ከነገረው በኋላ ነው። "ከምናመርተው አብዛኘውን እንጥለው ነበር፤ አሁን ዝናብ ሲጥል እንኳን ማንጎ እና ሌሎች ፍራፍሬዎችን ማድረቅ እንችላለን። ስለዚህ ከአሁን በኋላ ምንም የምናባክነው ነገር አይኖርም" "በበጋ ወቅት የደረቁ ምግቦችን በተመረቱበት ወቅት ከሚሸጡበት ዋጋ በአራት እጥፍ እንሸጣለን" ይላል ጆይ ለተጨማሪ ገቢው ምስጋና ይግባው እና በእርሻው መሃል የገነባውን ህንጻ እየጠቆመ። ባለስልጣናት ምግብ ብክነት ችግር እንዳለ ቢያምኑም መፍትሄ ማፈላለግ ግን ተስኗቸዋል። "በኡጋንዳ ያሉን ሁለት የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ብቻ ናቸው" ይላል የግብርና ሚኒስቴር ሠራተኛው ጀምስ ቱምዋይን። "መንግሥት በዚህ የንግድ ዘርፍ ላይ አይሰማራም፤ የግል ድርጅቶች ደግሞ እዚህ ያለውን እምቅ የገበያ አቅም አልተረዱትም።" በተለያዩ አካባቢዎች ለተለዩ ምርቶች የምግብ ማቀነባበሪያ ማዕከላት ለመገንባት እቅድ አላቸው። ነገር ግን ሂደቱ በጣም አዝጋሚ ነው። ወደ ኪትጉም ስንመለስ ላውረንስ ነገን ተስፋ አድርጓል። የፈጠራ ሥራውን በማስፋፋት ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች ማዳረስ ይፈልጋል። ኬንያ ውስጥ የእግር ኳስ ውድድር በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሴቶችን ያለእድሜ ጋብቻ፣ ያለእድሜ እርግዝናና ከግርዛት እየታደጋቸው ነው።
news-53935476
https://www.bbc.com/amharic/news-53935476
ትግራይ ክልል ፡ የልዩ ኃይል አባላቱ ወደ አማራ ክልል ኮብልለዋል መባሉን አስተባበለ
ስድሳ የሚሆኑ የታጠቁ የትግራይ የልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን የአማራ ክልል ሲያስታውቅ የትግራይ ክልል በበኩሉ ጉዳዩን "ተረት ተረት ነው" በማለት አጣጥሎታል።
አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ከትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል እየመጡ መሆኑን ጠቅሰው 60 የሚሆኑ የታጠቁ የልዩ ኃይል አባላት ወደ ክልሉ ከነትጥቃቸው መግባታቸውን አስታውቀዋል። እነዚህ ኃይሎች ከወልቃይትም ከራያ አካባቢ፣ አማራ የሆኑና እና አብዛኛዎቹ ደግሞ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን ጠቅሰው አባላቱን ተቀብለው ትጥቅ በማስፈታት በአንድ ካምፕ ማስቀመጣቸውንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። ወደ አማራ ክልል የኮበለሉ የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል አባላት አሉ ስለመባሉ በቢቢሲ የተጠየቁት የትግራይ የክልል የሕዝብና መንግሥት ግንኙነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሐዱሽ ካህሱ፤ "ይህ የበሬ ወለደ ንግግር ካልሆነ በስተቀር እውነት አይደለም" ብለዋል። "ምናልባት ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ ነው እየሄደ ያለው የሚለውን እነርሱ ይመልሱ እንጂ፤ ከትግራይ ወደ አማራ ክልል የሚሄድ የለም" ብለዋል። በሌላ በኩል አቶ ግዛቸው "የማንነት እና ወሰን ጥያቄን የአማራ ክልላዊ መንግሥት ትቶታል የሚለው ትክክል አይደለም" ያሉት አቶ ግዛቸው፤ የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄዎች እያነሳ መሆኑን ጠቁመው የማንነት እና ወሰን፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ የሕገ መንግሥት መሻሻል፣ ሃቀኛ ፌደራሊዝም ትግበራ እና ሌሎችም አቋም የተያዘባቸው መሆናቸውን አስረድተዋል። ጥያቄዎቹ ውስብስብ መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ጥያቄዎቹ በፌደራል ደረጃ የሚመለሱ መሆኑን ጠቁመው ኢኮኖሚ ሪፎርም እና መሠረተ ልማት ላይ የተወሰኑ ጥያቄዎች እየተመለሱ ነው ሲሉ አስረድተዋል። "በወልቃይ እና ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ያነሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች አፈና፣ እስራት እና እንግልት እየደረሰባቸው ነው" ብለዋል። ይህንን ለማስመለሰም በዴሞክራሲያዊ መንገድ ክልሉ ይንቀሳቀሳል ብለዋል። "ህወሓት ምርጫ አካሂዳለሁ" ብሎ ሕዝቡን "መከራ እያበላ" ነው ያሉት አቶ ግዛቸው፤ ችግሩ ከዚህ በላይ እየከረረና አደብ የማይገዛ ከሆነ ፌደራል መንግሥት ሕግና ሥርዓት ማስከበር የሚያስችል አቅምና ሥልጣን ስላለው፤ በዚህ መሠረትም ህወሓትና የትግራይ ሕዝብን በመለየት ሕግ ማስከበር እንዳለበት አቶ ግዛቸው ተናግረዋል። "አሁንም የወሰን ጥያቄ መኖሩንና የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ እያሉ ነው፤ ነገር ግን ይህን የሚሰማቸው የለም" ብለዋል። በመሆኑም "ከአማራ ክልል በኩል የሚሰማው ወሬ ከተረት ተረት ያለፈ ሐቅ የለውም" ሲሉ አቶ ሐዱሽ ለቢቢሲ ገልፀዋል። "የአማራ ክልል መንግሥት ለትከንኮሳ አይነሳም" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ግዛቸው፤ ክልሉ ዴሞክራሲያዊ መፍትሔ ብቻ ነው የሚያስፈልገው የሚል እምነት አለው ብለዋል። ከወልቃይት እና ጠገዴ ውጭ ያሉ የማንነት እና ወሰን ጥያቄዎችም ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለመንግሥት ቀርበው በሕግ እንደሚፈቱ መታወቅ አለበት ሲሉ ዳይሬክተሩ አክለዋል። መግለጫውን የሰጡት የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ዳሬክተር ክልሉ ወደ ሠላም ወደ አንድነት የመጣበት ወደ ልማት ፊቱን ያዞረበትና ከሌሎች ክልሎች በተነጻጻሪነት የተሻለ ሠላም ያለበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
57278701
https://www.bbc.com/amharic/57278701
ፈረንሳይ ከዘር ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ ለነበራት ሚና ሩዋንዳን ይቅርታ ጠየቀች
ፈረንሳይ በሩዋንዳ ከ27 ዓመታት በፊት በተፈጸመው የዘር ፍጅት ለነበራት ሚና አገሪቱን ይቅርታ ተማጸነች፡፡
ፈረንሳይ ይቅርታ የጠየቀችው በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አማካኝነት ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሩዋንዳ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ እንደ አውሮጳዊያኑ በ1994 በሩዋንዳ በተፈጸመ እጅግ አሰቃቂ የዘር ፍጅት በመቶ ቀናት ብቻ 800ሺህ ሩዋንዳዊያን ተገድለዋል፡፡ ይህን አሐዝ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚያስጠጉትም አሉ፡፡ በዚያ የዘር ፍጅት በዋናነት የተጨፈጨፉት ቱትሲዎች ቢሆኑም ለዘብተኛ ሁቱዎችም ከሞት አላመለጡም፡፡ ኪጋሊ ላይ ለዚህ የዘር ፍጅት መታሰቢያ እንዲሆን በተገነባው ዝክረ-ማዕከል ቆመው ኢማኑኤል ማክሮን ባደረጉት ንግግር ፈረንሳይ እልቂቱ እንደሚመጣ ቀድማ ማስገንዘብ ባለመቻሏ እንዲሁም እውነታው እንዲወጣ ምርመራ ማድረግ ሲገባት ለረዥም ጊዜ ዝምታን በመምረጧ ትጸጸታለች ብለዋል፡፡ ነገር ግን ፈረንሳይ በዘር ማጥፋቱ ተሳትፎ እጇ እንዳልነበረበት ማክሮን አበክረው አስገንዝበዋል፡፡ የሩዋንዳው አቻቸው ፖል ካጋሜ የማክሮንን ንግግር አወድሰው ይቅርታ መጠየቃቸው ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመጋቢት የተሰየመው የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽን ፈረንሳይ በወቅቱ የሩዋንዳው የዘር ፍጅትና እልቂቱን ማስቆም እየቻለች ቸልታን መርጣ ነበር፤ ሆኖም ግን በፍጅቱ እጇ የለበትም ሲል ብያኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ ይህ ብያኔ በዋናነት ፈረንሳይ በዚያ እልቂት ያ ሁሉ ሲሆን ዓይኔን ግንባር ያድርገው ብላ እንደነበር አጋልጧል፡፡ ማክሮን በይቅርታ ተማጽኗቸው ‹ያን ምሽት በዚያ ሰቆቃ ያለፉት ብቻ ናቸው ይቅርታቸውን የምንማጸናቸው› › ሲሉ በመታሰቢያው ባደረጉት ንግግር ጸጸታቸውን አስተጋብተዋል፡፡ ኢማኑኤል ማክሮን ተገኝተው ንግግር ያደረጉበት የዘር ፍጅት ዝክረ ማዕከሉ ሩብ ሚሊዮን ሩዋንዳዊያን የተቀበሩበት ቦታ ነው፡፡ ‹‹ እዚህ ለናንተ ክብር ዝቅ ብዬ ከጎናችሁ ቆሜያለሁ፤ ኃላፊነታችንን ለመወጣት ምን ያህል እንዝህላል እንደነበርን ለመረዳት በቅቻለሁ›› ብለዋል ማክሮን፣ በይቅርታ ተማጽኗቸው፡፡ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ዋዜማ በአገሪቱ አመራር ሥልጣን ላይ የነበሩት የሁቱ ዘር ያላቸው ልሂቃን ነበሩ፡፡ እንደ አውሮጳዊያኑ በ1994 ከመጋቢት እስከ ሰኔ በተደረገው ጦርነት ቱትሲዎች የሚመሩት አማጺ ቡድን ኪጋሊን መቆጣጠር ቻለ፡፡ የዚህ የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር(አር ፒ ኤፍ) አማጺ የያኔው የጦር አበጋዝ ፖል ካጋሜ በሁቱ የሚመራውን መንግሥት ድል ካደረጉ በኋላ ዛሬም ድረስ ሩዋንዳን እየመሩ ይገኛሉ፡፡ በዚያን ዘመን ፈረንሳይን ይመሩ የነበሩት ፍንኮስ ሚተራንድ ለሁቱ የያኔው ፕሬዝዳንት ለጁቬናል ሐቢየሪማና ቅርብ ወዳጅ ነበሩ፡፡ የሩዋንዳ የዘር ፍጅት የተጀመረው በመጋቢት 6፣ 1994 የሁቱ ዘር የነበራቸው እኚሁ ፕሬዝዳንት ጁቬኔል ሐቢያሪማና እና የቡሩንዲው አቻቸውና የሁቱ ዘር ያላቸው ሳይፕሪን ንታሪያሚራ የተሳፈሩበት አውሮፕላን አየር ላይ ሳለ ተመቶ በመጋየቱ ሁለቱም መሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሁለቱ መሪዎች የተሳፈሩበት አውሮፕላን ማን አጋየው የሚለው እስከዛሬም ምላሽ አላገኘም፡፡ ፈረንሳይ በሩዋንዳ ጭፍጨፋ እጇ ይኑርበት አይኑርበት ለመበየን በወቅቱ የነበሩ መዛግብቶች ብሔራዊ ምስጢር ሆነው በመደበቃቸው ውሉ ሳይለይለት ቆይቶ ነበር፡፡ በመጨረሻም ፕሬዝዳንት ማክሮን ሰነዶቹ ለምርመራ እንዲወጡ በመፍቀዳቸው ነው እውነት አፈላላጊ ኮሚሽኑ ሪፖርት ማውጣት የቻለው፡፡
news-56304723
https://www.bbc.com/amharic/news-56304723
ዩኬ ለየመን የምትሰጠውን እርዳታ መቀነሷን የረድኤት ድርጅቶች አወገዙ
የረድዔት ድርጅቶች የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በየመን ላይ ያደረገውን የእርዳታ ቅነሳ አወገዙ።
በመቶ የሚቆጠሩ የረድዔት ድርጅቶች ተቀባይነት የለውም በሚልም ነው ያወገዙት። በዘንድሮው ዓመት ለመካከለኛ ምስራቋ አገር፣ የመን 87 ሚሊዮን ፓውንድ እርዳታ እንደሚሰጥ እንግሊዝ ቃል ገብታለች። ከአመት በፊት የነበረው ዕጥፍ ፣ 164 ሚሊዮን ፓውንድ ነበር። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ በበኩላቸው መንግሥታቸው የየመንን ህዝብ ለመርዳት የገባውን ቃል አያጥፍም ብለዋል። ነገር ግን የመን ከመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ አገራት መካከል የዩኬ እርዳታ ሊያሽቆለቁልባት ይችላል ከተባሉት ዋነኛዋ እንደሆነች ሾልኮ የወጣ ኢ-ሜይል አስታውቋል። በመጀመሪያ ጉዳዩን ሪፖርት ያደረገው ኦፕን ዲሞክራሲ እንዳስታወቀው በባለፈው ወር ከመንግሥት ባለስልጣናት ሾልኮ የወጣ መረጃን መሰረት አድርጌያለሁ በማለት በሶሪያ 67 በመቶና በሊባኖስ 88 በመቶ እርዳታ ይቀንሳል ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በናይጄሪያ 58 በመቶ፣ በሶማሊያ 60 በመቶ፣ በደቡብ ሱዳን 59 በመቶና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 60 በመቶ እርዳታ እንደሚቀንስ አስነብቧል። እነዚህ የረድዔት ድርጅቶች ለመሪው ቦሪስ ጆንሰን በፃፉት ደብዳቤ ህዝቡ በድህነት፣ በበሽታና በጦርነት የተጠቁ አገራትን ፊቱን ገሸሽ ያደርጋል ብሎ መንግሥት ማሰቡ ስህተት ነው ብለዋል። "የዩኬ መንግሥት በዚህ ወቅት የየመንን ህዝብ ችላ ብሎ የማይረዳ ከሆነ ታሪክ በጥሩ መልኩ አይዳኘውም። ከዚህ በተጨማሪ ለተቸገሩ አገራት አለሁ በማለት የምትረዳውን የዩናይትድ ኪንግደም አለም አቀፍ ስም የሚያጠለሽ ነው" ይላል ደብዳቤው ኦክስፋም፣ ክርስቲያን ኤይድ፣ ሴቭ ዘ ችልድረን፣ ኬር ኢንተርናሽናልን ጨምሮ 101 ድርጅቶች ናቸው ተቃውሟቸውን ያስገቡት። የእንግሊዙ ኦክስፋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዳኒ ስሪስካንዳራጅ እንዳሉት "ምጣኔ ኃብታችን ተጎድቷል በሚል የሚደረግና የበርካታ ሚሊዮናውያንን የመኖችን ህይወት የሚነጥቅ የእርዳታ ቅነሳ ሃሰተኛ ኢኮኖሚ ነው። በርካቶች ቤተሰቦቻቸውን መመገብ አልቻሉም፤ ቤታቸውን አጥተዋል፤ በኮሮናቫይረስና በግጭት ምክንያትም ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ እንዲህ በጦርነት በምትበጠበጥ አገር ላይ የጦር መሳሪያ በመሸጥ "'ኢ-ሞራላዊ' ተግባር እንዲታቀብ አስጠንቅቀዋል።
news-49671958
https://www.bbc.com/amharic/news-49671958
በጠርሙስ በላኩት መልዕክት ሕይወታቸው የተረፈው ቤተሰብ
አሜሪካ ውስጥ ባላሰቡት ሁኔታ የውሃ ፏፏቴ ውስጥ ገብተው አደጋ ላይ የነበሩ ሦስት የቤተሰብ አባላት ለማንኛውም ብለው የድረሱልን መልዕክታቸውን በጠርሙስ ላይ ጽፈው ወደ ወንዝ ከተው ነበር።
በሕይወት የተረፈው ቤተሰብ በሚያስገርም ሁኔታ በጠርሙሱ ላይ የነበረውን መልዕክት ሰዎች አግኝተው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሕይወታቸውን መታደግ ችለዋል። • 'የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም'፡ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች • ሰዓትን በትክክል የመቁጠር ጠቀሜታ ከርቲስ ዊትሰን፣ የፍቅር ጓደኛውና የ13 ዓመት ልጃቸው ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ነበር ወደ ማዕከላዊ ካሊፎርኒያ ግዛት በመሄድ የቤተሰብ ጉዟቸውን የጀመሩት። እቅዳቸው ደግሞ አሮዮ ሴኮ የተባለውን ወንዝ በመከተል መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ፏፏቴ መመልከት ነበር። ልክ ፏፏቴው ጋር ሲደርሱም በገመድ ታግዘው በመውረድ እዛው አካባቢ ጊዜያዊ መጠለያቸውን ሠርተው ለመቆት ነበር ያሰቡት። በሦስተኛው ቀን ግን ከትልልቅ ቋጥኞች ሥር መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ እራሳቸውን አግኝተዋል። ቋጥኞቹ በሁለቱም በኩል 15 ሜትር ወደላይ ከፍታ ያላቸው ሲሆን፤ ይዘውት የነበረውም ገመድ ወደታች ለመውረድ እንጂ ወደላይ ለመውጣት የሚያገለግል አልነበረም። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፤ እነሱ የነበሩበትና በቋጥኞቹ መካከል ያለው ቦታ ከወንዙ በሚመጣ ውሃ መሞላት ጀመረ። ''ውሃው ከፍ እያለ ሲመጣና ምን አይነት አደጋ ውስጥ እንደገባን ስረዳ ልቤ ቀጥ ብላ ነበር'' ብሏል ከርቲስ ከሲኤንኤን ጋር ባደረገው ቆይታ። • የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች? ምንም አይነት የስልክ ኔትዎርክ በቦታው ስላልነበር የድረሱልን መልዕክት ማስተላለፍ እንኳን አቅቶት የቆየው ቤተሰብ በመጨረሻ ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ወሰነ። በእጃቸው ላይ የነበረውን ጠርሙስ በመፈቅፈቅ ''በፏፏቴው በኩል መውጣት አቅቶን ተይዘናል፤ እባካችሁ ድረሱልን'' የሚል መልእክት ጽፈው ወደ ወንዙ ወረወሩት። መልዕክቱ የተጻፈበት ጠርሙስ ጠርሙሱ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል በወንዙ ላይ እየተንሳፈፈ ከተጓዘ በኋላ በአካባቢው ጉዞ እያደረጉ የነበሩ ሁለት ሰዎች ያገኙታል። ወዲያውም ጉዳዩን ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ያሳውቃሉ። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም ወዲያው ፍለጋቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ እኩለ ሌሊት አካባቢ ሦስቱንም የቤተሰብ አባለት ከባድ የሚባል ጉዳት ሳይደርስባቸው አግኝተዋቸዋል። ከርቲስ ዊትሰን እና ቤተሰቡ "ሕይወታችን በመትረፉ እጅግ ደስተኞች ነን። ሕይወታችንን ያተረፉት እነዛ ሁለት ተጓዦችን አግኝተን ማመስገን እንፈለጋለን" ብለዋል።
43665518
https://www.bbc.com/amharic/43665518
የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት መመለሳቸውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ምላሽ ምንድን ነው?
የእንግሊዙ ቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየም ከ150 ዓመታት በፊት በነበረው የመቅደላ ውጊያ በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፈው የተወሰዱ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ዘውድ፣ የሰርግ ቀሚስና የወርቅ ዋንጫዎችን ለአውደ ርዕይ አቅርቧል።
የንግስት ጥሩነሽ የአንገት ጌጥና ሙሉ በሙሉ ከወርቅ የተሰራ ዋንጫም ለእይታ ይቀርባሉ። ሙዚየሙን እነዚህን ቅርሶችም ኢትዮጵያ ፍላጎቱ ካላት በውሰት መልክ ሊሰጥ ፈቃደኛ መሆኑን ገልጿል። ከእነዚህ ቅርሶች መካከል የተወሰኑት እንደ አውሮፓውያኑ በ1868 የተካሄደው የመቅደላ ጦርነት የተዘረፉ ናቸው። በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን መስሪያ ቤት የቅርስ ምዝገባና ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ደሳለኝ አበባው እንዳሉት እርሳቸውም ሆኑ ድርጅታቸው ስለጉዳዩ ምንም መረጃ የላቸውም። በቅርሶቹ ለእይታ መብቃት ላይ ግን ያላቸው አቋም መልካም እንደሆነ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከኢትዮጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በውሰት መመለስ ለብዙዎች ብዥታንና መነጋገሪያን ፈጥሯል። ለዓመታትም ከኢትዮጵያ የተዘረፉ ቅርሶች እንዲመለሱ የተለያዩ ምሁራንም ሆነ ግለሰቦች ሲጥሩ ነበር። ከነዚህም ውስጥ ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ከሪቻርድ ፓንክረስት እና ሌሎች ግለሰቦች ጋር በመሆን ብዙ ሙከራዎችን አድርገዋል። ሙዚየሙ ዛሬ በጀመረው አውደ ርዕይ ላይ የፕሮፌሰር አንድርያስ ምላሽ ኦዎንታዊ ነው። "ሙዚየሙ በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተዘረፉና በእንግሊዝ የሚገኙ ቅርሶቻችን ለህዝብ እይታ የሚበቁበት አጋጣሚ በጣም አናሳ ነው። ስለዚህ ለህዝብ እይታ መቅረባቸው ኢትዮጵያውያንንም ሆነ የኢትዮጵያን ወዳጆች ደስ ያሰኛል ብዬ እገምታለሁ።" ብለዋል ጨምረውም "እነዚህ ቅርሶች እንዲመለሱ ለመሞገትም ቢሆን ለረጅም ጊዜ በብድር ወደ ኢትዮጵያ ቢመጡ በጣም መልካም ነው። ሀይማኖታዊ፣ ታሪካዊ ወይም ደግሞ ለቅርስጥበቃ የተለየ መነሳሳት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ደስተኛ ይሆናሉ ብዬ አምናለሁ።" ይላሉ ከዚህ በተጨማሪም በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኃይለሚካኤል አፈወርቅ በበኩላቸው ቅርሶቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ የሚደረገውን ጥረት አካል እንደሆነና ደረጃ በደረጃ ወደዛ የሚወስድ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። መቅደላ ውጊያ ላይ የተመዘበሩት ቅርሶችና ንብረት ብቻ አልነበረም ከዚህም በላይ የሰባት ዓመት እድሜ ያለውን የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁ ተጠልፎ ተወስዷል። ልዑሉ በብቸኝነት ሲሰቃይ ቆይቶም በ18 ዓመቱ እንደሞተ የታሪክ መዛግብቶች ያወሳሉ። የመጨረሻ ጊዜውን አስመልክቶ ከልዑል አለማየሁ አንደበት የተወሰደውን አሉላ ፓንክረስት በፅሁፉ አስቀምጦታል ይህም " ተመርዣለሁ" የሚል ነው። ተጠልፎ ተወስዶ ህይወቱ ያለፈው የልጅ ልዑል አለማየሁ ህይወት አሳዛኝ እንደሆነ ህይወቱ ላይ የወጡ ፅሁፎች ያሳያሉ። ከሞተ በኋላ እንኳን አፅሙ ኃገሩ ይረፍ ተብሎም ለእንግሊዝ መንግሥት በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም እስካሁን ምላሽ የለም። ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ እንደሚሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ እንግሊዝ በሄዱበት ወቅት ያረፈበትን ቦታ መጎብኘታቸውን ይጠቅሳሉ። "ይህ ሀሳብ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ውስጥ ይነሳ እንደነበር አውቃለሁ። ከልዑል አለማየሁም ጋር ቁርኝት አለን። አስክሬኑ ቢመጣም ጥሩ ነው። ያ ደግሞ ልዑል አለማየሁ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጋር ያለውን ቁርኝት የሚያሳይ ነው። " ብለዋል።
50998591
https://www.bbc.com/amharic/50998591
ቤተሰብ፡ የአማት እጅ የሚረዝምበት ትዳር የተባረከ ወይስ የተረገመ?
አማት በትዳር ውስጥ በጎ ስም የላትም። በተለይ የባል እናት ስሟ በክፉ ሲብጠለጠል ይሰማል፤ በሚስትና በዘመዶቿ። ለደራሲያንም ቢሆን የሴራ መጎንጎኛ የጡዘቱ ማክረሪያ አጀንዳ ሆኖ አገልግሏል። በአማርኛ ተረትና ምሳሌዎች ውስጥም ፈለግ ፈለግ ቢደረግ አይጠፋም።
አብዛኛውን ጊዜ በሕንድ አማቶች ፈላጭ ቆራጭ ናቸው አማትና ምራት ሳይስማሙ መሬት፣ ለቅልብልብ አማት ሲሶ በትር አላት... ወዘተርፈ • የወንዶች ያለዕድሜ ጋብቻ • ሁለት እምነቶችን በአንድ ጣራ ለአስርታት ያሳደሩ ጥንዶች ሕንዶች ከልብ ወለዶቻቸውም ወጣ አድርገው ከተረትና ምሳሌዎቻቸውም አፈንግጠው 'የአማትን ነገር ማየት በብልሀት' በሚል ጥናትና ምርምር አድርገዋል። እ.አ.አ. በ2018 ከቦስተንና ከዴልሂ የተውጣጡ ተመራማሪዎች 671 ያገቡ ሴቶችን አነጋግረዋል። እነዚህ ባለትዳር ሴቶች ከ28 መንደሮች የተመረጡ ሲሆኑ መኖሪያቸውን ያደረጉትም በጃንፑር አውራጃ ኡታር ፓርዴሽ ነው። በዚህ አውራጃ የሚኖሩ ባለትዳር ሴቶች የተመረጡበት ምክንያት ማህበረሰቡ እጅጉን ወግ አጥባቂ በመሆኑ ነው ተብሏል። በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት ሴቶች ዕድሜያቸውም ከ18 እስከ 30 እንደሆነ ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ። እነዚህ ሴቶች የሂንዱ ሀይማኖት ተከታይ ሲሆኑ ከዝቅተኛው ማህበረሰብ የተገኙ መሆናቸውም በጥናቱ ላይ ተጠቅሷል። አብዛኞቹ ኑሯቸውን በግብርና የሚገፉ ሲሆን ሁሉም ማለት በሚያስደፍር መልኩ የሚኖሩት ከአማቶቻቸው ጋር ነው። ተመራማሪዎቹ እነዚህን ባለትዳር ሴቶች ከቤት ውጪ ከዘመዶቻችሁና ከጓደኞቻችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ይመስላል ሲል ጠይቀዋል። አማቶቻቸው ይህ ግንኙነት ላይ ያላቸው ተጽዕኖ ምን ያህል ነው ብለው በነፃነታቸው ላይ ያለውን ተጽዕኖ፣ የጤና አገልግሎት መፈለግ ላይ ያለውን አሉታዊና አዎንታዊ ጎን ፈትሸዋል። በመጨረሻም አማቶች ያሉበት ቤት የምትኖር ሴት የመንቀሳቀስ ነጻነቷ የተገደበ መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል ተመራማሪዎቹ። በጥናቱ ውስጥ የተካተቱ ሴቶች ከቤቷ ውጪ ያላት ማህበራዊ ግንኙነት በአማት ጠንካራ ገመድ የተቀፈደደ ነው፤ በተለይ ደግሞ የቤት እመቤቶች በተንቀሳቀሱ ቁጥር አዳዲስ መረጃ የማግኘት፣ ከአቻዎቻቸው ጋር በሚፈጥሩት ወዳጅነት፣ በራስ መተማመናቸውን የመጨመር እንዲሁም ለሕይወት ያላቸውን በጎ ገፅታና መሻሻል የማበልፀግ እድል ቢኖራቸውም አማት ግን በአጭር ገመድ ይዛ አላላውስ በማለት ከዚህ ሁሉ እድል ገድባቸዋለች ይላል የጥናቱ ውጤት። • ሥራ እና ፍቅር፡ ከሥራ አጋርዎ ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመር ሊያስባርር ይገባል? • አጭር ወንዶች የፍቅር ጓደኛ ለማግኘት ይቸገራሉ? እንዲሁም ይላል ጥናቱ፤ የጤና፣ የወሊድ፥ እና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ላይ የምትወስነው ውሳኔን፣ በሚኖራት ማህበራዊ ግንኙነትና ትስስር ጭምር የሚወሰን ሆኖ ሳለ ከዚህ ሁሉ እድል ተገልላ ትኖራለች ሲል ያስቀምጣል። በጥናቱ ከተካተቱ ሴቶች መካከል 36 በመቶዎቹ የቅርብ ጓደኛም ሆነ ዘመድ በሚኖሩበት አውራጃ የላቸውም። 22 በመቶዎቹ ደግሞ ጭራሹኑ የልብ ወዳጅም ሆነ የቅርብ ዘመድ የላቸውም። 14 በመቶዎቹ ብቻ ለብቻቸው ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ፣ 12 በመቶዎቹ ደግሞ በመንደራቸው የሚገኙ ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸውን ሄደው እንዲጠይቁ ይፈቀድላቸዋል። በጃንፑር ለጥናቱ ተሳታፊ ከሆኑ ሴቶች መካከል ከባለቤታቸውና ከአማታቸው ውጪ በተለያየ ጉዳይ የተወያዩ ሴቶች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ተመራማሪዎቹ ከአማታቸው ጋር የሚኖሩና ከአማቶቻቸው ጋር የማይኖሩ ሴቶችንም በመለየት አጥንተዋል። ከዚህም ጥናታቸው ያገኙት ከአማቶቻቸው ጋር የሚኖሩ ሴቶች በጣም ትንሽ የቅርብ ጓደኞች ያላቸው ሲሆን ይህም የሚያሳየው አማቶች ምራቶቻቸው ብቻቸውን እንዳይንቀሳቀሱ፣ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ከሌላ ሰው ጋር እንዳያጠናክሩ በማድረግ የቤተሰብ ምጣኔ ምርጫቸውን እንዲሁም የቤተሰብ ቁጥራቸውን እንደሚወስኑ ተጽዕኖ እንደሚያደርጉ ነው ተብሏል። አንዳንዴ አማቶች በርካታ የልጅ ልጆች እንዲኖሯቸው ይፈልጋሉ። በተለይ በርካታ ወንዶች። በጥናቱ ከተካተቱት ግማሸ ያህሉ እንደተናገሩት አማቶቻቸው የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን አይደግፉም። በተለይ ባላቸው ከቤት ውጪ ራቅ ያለ ስፍራ በመሄድ የሚሰራ ከሆነ የአማቶች ቁጥጥር ጠበቅ ያለ ይሆናል። ይህም በመንቀሳቀስ ነጻነታቸው፣ በውሳኔዎቻቸው ላይ ነጻነት እንዳይኖራቸው በማድረግ የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳርፋል። በጥናቱ የተገኘው ሌላው ነጥብ አማቶች ሁሌም ቢሆኑ መጥፎ አለመሆናቸው ነው። አማቶች ምራቶቻቸው ባረገዙ ወቅት ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ በማድረግና ክትትላቸው እንዳይስተጓጎል በጎ አስተዋጽኦ በመጫወት ስማቸው በደግ ተነስቷል።
news-50259099
https://www.bbc.com/amharic/news-50259099
በሽብር ጠርጥሮ በመታወቂያ ዋስ መልቀቅና የፍትህ ሥርዓቱ ማሻሻያ
በለውጡ ዋዜማ ስለ አፋኝነቱ ብዙ ብዙ የተባለለት የፀረ ሽብር አዋጁን በሚመለከት "...አሸባሪው መንግሥት ነው" የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የፓርላማ ንግግር ለብዙዎች አይረሴ ነው።
የፀረ ሽብር አዋጁ መንግሥታቸው ትኩረት ሰጥቶ ከሚያሻሽላቸው ህጎች ቀዳሚው እንደሚሆን በተናገሩት መሰረት ህጉን የማሻሻል ሥራው ተጠናቆ ረቂቁ ለመፅደቅ የፓርላማ ተራ እየጠበቀ ይገኛል። በዚህ መሃል ይህ ህግ ተጠቅሶ ሰዎች በሽብር መጠርጠራቸው ሲያነጋገር፤ መንግሥት በእርግጥም የፍትህ ሥርዓቱን የማሻሻል መልካም ፍቃድ አለው ወይ? የሚል ከባድ ጥያቄንም ማስነሳቱ ይታወቃል። • "ሽብር ምንድን ነው ፣ አሸባሪ ማን ነው?" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሰኔ 15ቱ "የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ" ጋር በተያያዘ በሽብር የተጠረጠሩ ሰዎች ከአራት ወራት እስር በኋላ በመታወቂያ ዋስ ከቀናት በፊት መፈታታቸውም እንደገና የፍትህ ስርዓቱን መነጋገሪያ አድርጎታል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ህብረት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሱድ ገበየሁ "መንግሥት አሸባሪው እኔው ራሴ ነኝ ባለ ማግስት ይህን ህግ የተጠቀመው ሆን ብሎ የሰዎችን ሰብአዊ መብት ለመጣስ ነው" ይላሉ። "ለቀጣይ ዓመት ይሻሻላል ተብሎ ሼልፍ ላይ ያደረን ህግ ተጠቅሞ መጠርጠር በራሱ ጤነኛ አደለም" የሚሉት አቶ መሱድ ሰዎችን በመፈንቅለ መንግሥት መጠርጠር ካስፈለገ በፀረ ሽብር ህጉ ሳይሆን በመደበኛ የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና በወንጀል ህግ መሰረት መጠርጠር እንደነበር ትክክለኛው አካሄድ ያስረዳሉ። ሰዎችን በፀረ ሽብር ህጉ መጠርጠር ሙሉ በሙሉ ፖለቲካዊ እርምጃ እንደሆነ ይደመድማሉ። በሽብር በተጠረጠሩ ሰዎች ከሃያ በላይ መዝገቦች ላይ ጠበቃ እንደነበሩ የሚናገሩት አቶ መሱድ ተጠርጣሪዎቹ ላይ በተለይም በመጀመሪያዎቹ 26 ቀናት መሰረታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው ነበር ይላሉ። • “በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ የፍትህ ወር በሚል ከፍተኛ የፍትህ ተቋማት ባለስልጣናትና የህግ ባለሙያዎች ለውይይት በተሰባሰቡበት መድረክ "ለምድን ነው እስካሁን በፀረ ሽብር ህጉ የምትከሱት?" የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር። እስካሁንም የፀረ ሽብር ህጉ በህግ ስላልተሻረ ይህን ህግ ጥቅም ላይ ማዋል ምንም አይነት ህጋዊ ችግር እንደሌለበት "ከህግ አንፃር ይችላሉ፤ ከፖለቲካ አንጻር ግን አጥፊ ነው" በማለት ነገሩ ፖለቲካዊ እንደሆነ ያስረዳሉ። "በአንድ ቀጠሮ 28 ቀን አስሮ ማቆየት እድል ይሰጣል። የወንጀል ህጉ የሚፈቅደው 14 ቀን ነው። ስለዚህ ዳኞች የተጠቀሰውን ህግ ብቻ በማየት ፖሊስ ወይም አቃቤ ህግ የጠየቀውን ያልተገባ ቀን ይፈቅዳሉ" የሚሉት አቶ ሙሉጌታ በዚሁ መሰረት መንግሥትም አስሮ ማቆየት የሚፈልጋቸውን ሰዎች ለማሰር የሽብር ህጉን እንደመረጠው ያምናሉ። እሳቸው እንደሚሉት የፀረ ሽብር ህጉ ከአራት ወር በላይ ሳይከሱ ማሰርን ስለማይፈቅድ ተጠርጣሪዎቹ በመጨረሻ ከእስር ተለቀዋል። ህጎችን በማሻሻል ሂደት ላይም ተሳታፊ በመሆናቸው አዲሱ ረቂቅ ህግ በቅርቡ ፀድቆ አሁን እየተጠቀሰ ያለው የፀረ ሽብር ህጉ የሚሻር ይመስልዎታል ወይ? የሚል ጥያቄ ለአቶ ሙሉጌታ አንስተን ነበር። ተሻሽሎ የፀደቀውን የማህበራትና የሲቪል ሶሳይቲ ህግን፤ አሁንም እየተሻሻሉ ያሉ ህጎችን በመጥቀስ ይህ ህጎችን የማሻሻል ሥራ በጣም አዎንታዊ እንደሆነ ያስረዳሉ። • “ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ "ቢሆንም ግን በፖለቲካው መንግሥት ችግር እየገጠመው ነው፤ የፖለቲካ ማሻሻያውና የህግ ሥርዓቱን ማሻሻል ጎን ለጎን እየሄዱ አይደለም። የፖለቲካ ማሻሻያው ወደ ኋላ ቀርቷል" ይላሉ አቶ ሙልጌታ። በመጨረሻም ጉዳዩ የፖለቲካና የፖሊሲ ጉዳይ እንጂ የህግ እንዳልሆነ፤ ስለዚህም ፖለቲካዊ መልካም ፍቃድ ከሌለ ህግ ቢወጣም ህጉን ያወጣው መንግሥት ራሱ ህጉ እንዳይፈፀም እንደሚያደርግ የሚያስረዱት አቶ ሙሉጌታ አሁን በአገሪቱ የፖለቲካና የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያዎች ላይ እየሆነ ያለውም ይኸው እንደሆነ ይደመድማሉ። "የተጣለ ህግ አንስቶ ህይወት ሲዘራበት ይታያል። የፀረ ሽብር ህጉ ለእኔ ሆስፒታል የተኛ ህግ ነው፤ ይህ ህግ እንዴት ፍርድ ቤት ይጠቀሳል?" ሲሉ አጥብቀው ይጠይቃሉ።
51940729
https://www.bbc.com/amharic/51940729
ሕንድ በስልክ ጥሪ ስለኮሮናቫይረስ መረጃ እየሰጠች ነው
በሕንድ የሚገኙ በርካታ የሞባይል ኔትወርክ አቅራቢዎች ደንበኞቻቸው ማንኛውንም ጥሪ ከማድረጋቸው በፊት ለ30 ሰከንድ የኮሮናቫይረስ መረጃ እንዲያገኙ እያደረጉ ነው።
በሕንድ እስካሁን ድረስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከሌላ አገራት አንፃር ሲታይ አነስተኛ ነው ጂሎ፣ ቢኤስኤንኤል እና ቮዳፎን የተባሉት ኩባንያዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው ተግባራዊ ካደረጉት መካከል ይገኙበታል። መልዕክቱ በእንግሊዘኛ የሚሰራጭ ሲሆን ማንኛውም ሰው ሲደውል ከጥሪው በፊት የሚያስል ሰውና የጤና መልዕክቱን ይሰማሉ። ነገርግን አንዳንድ ደንበኞች በመልዕክቱ መበሳጨታቸውን ደጋግመው በመግለጻቸው የተነሳ በርካታ ድረ-ገጾች መልዕክቱን እንዴት ማስቆም እንደሚቻል የሚገልፅ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ። ስለቫይረሱና ስለምልክቶቹ መረጃ የያዘው ይህ መልዕክት ደዋዩ ብቻ የሚሰማው ሲሆን የመደበኛው ጥሪው አካል አይደለም ተብሏል። የቢቢሲ ደልሂ ቢሮ ባልደረቦች ይህንን መልዕክት መስማት ከጀመሩ ሳምንት እንደሆናቸው ገልፀዋል። አክለውም ሰዎች ስለበሽታው ምልክቶች እና ቫይረሱ ከተገኘባቸው ምን ማድረግ እንደሚኖርባቸው መረጃ ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ ቀድሞም ስለቫይረሱ የበለጠ ፍርሃት በነበረባቸው ሰዎች ዘንድ "መረበሽ" መፍጠሩ እንዳልቀረ ገልፀዋል። አገልግሎቱ የተጀመረ ዕለት በርካታ መገናኛ ብዙኀን ትኩረት ሳይሰጡ የቀሩ ቢሆንም በማግስቱ ግን አገልግሎቱን ለማቋረጥ የሚረዱ መረጃዎች ሲሰጡ ቆይተዋል። በሕንድ እስካሁን ድረስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከሌላ አገራት አንፃር ሲታይ አነስተኛ ነው።
news-55359739
https://www.bbc.com/amharic/news-55359739
ናይጄሪያ፡ በቦኮሀራም ታግተው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተለቀቁ
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ካትሲና ግዛት ባሳለፍነው ሳምንት ከወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ታፍነው የተወሰዱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናት መለቀቃቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ገልጹ።
የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ቃል አቀባዩ ለቢቢሲ እንደገለጹት 344 ወንድ ህጻናት ተማሪዎች ተለቀው እንደሚገኙና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ገልጸዋል። ነገር ግን ከሌሎች ምንጮች እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት እስካሁንም ድረስ ጥቂት ተማሪዎች በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ለጠፉትና ለታገቱት በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንድ ተማሪዎች ኃላፊነቱን ፅንፈኛው ቦኮ ሃራም የወሰደ ሲሆን ከሰአታት በፊት አንዳንድ ህጻናትን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቅቆ ነበር። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ቃል አቀባይ አብዱል ላብራን እንዳሉት ተማሪዎቹ ወደ ግዛቲቱ ዋና ከተማ ካትሲና ሲቲ እንደተወሰዱ ገልጸዋል። አክለውም ተማሪዎቹ የሚታዩበት ቦኮ ሀራም የለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ትክክለኛ መሆኑን ገልጸው በቡድኑ መሪ ተላልፏል የተባለው መልዕክት ግን መሪውን መስሎ በቀረበ ሰው የተሰራ እንደሆነ አስታውቀዋል። ማክሰኞ ዕለት ባለስልጣናት ታግተዋል ስለተባሉት ህጻናት ቁጥር አነስተኛ ግምታዊ ቁጥር አስቀምጠው የነበረ ሲሆን እስካሁንም ድረስ ግን በትክክል የታገቱት ወንድ ተማሪዎች ምን ያክል እንደሆኑ አይታወቅም ተብሏል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ አሚኑ ቤሎ ማሳሪ ከሮይተርስ የዜና ወኪል ጋር በነበራቸው ቆይታ ''አብዛኛዎቹን ተማሪዎች አስመልሰናል። ግን ሁሉንም አይደለም'' ማለታቸው ተገልጿል። ኤኤፍፒ ያነጋገራቸው አንዳንድ ሰዎች ደግሞ አሁንም ድረስ ጥቂት ህጻናት በአጋቾቹ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። የአስተዳዳሪው ቃል አቀባይ አብዱል ላብራን በበኩላቸው ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዳቸውም ህይወታቸው አላላፈም ብለዋል። ነገር ግን በአንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ አንድ ህጻን የናይጄሪያ ተዋጊ ጄቶች በተኮሱት ጥይት አንዳንድ ተማሪዎች ተገድለዋል ሲል ይታያል። ምንም እንኳን ተማሪዎቹ እንዴት ባለ ሁኔታ ሊለቀቁ እንደቻሉ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ተማሪዎቹ በእርግጥም ስለመለቀቃቸው ግን ከግዛቲቱም ሆነ ከሌላ የመንግስት ኃላፊ ቢቢሲ መረጃ አግኝቷል። ጥቃቱ እንዴት ተፈጸመ ታጣቂዎች በሞተርሳይክል ተጭነው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ከደረሱ በኋላ ወደ ሰማይ መተኮስ እንደጀመሩና በርካቶችም በፍራቻ ተበታትነው ከአካባቢው እንደጠፉ አንድ የአይን እማኝ ተናግሯል። ካትሲና ግዛት የሚገኘው የመንግሥት አዳሪ ትምህርት ቤት 800 ተማሪዎች ያሉበት ሲሆን ከበባውም የደረሰው ባሳለፍነው ሳምንት አርብ አመሻሹ ላይ ነው። እሁድ ዕለት ደግሞ የናይጄሪያ ጦር ታጣቂዎቹ የተደበቁበትን ስፍራ እንዳገኘውና ከሰራዊቱ አባላትም ጋር የተኩስ ልውውጥ እንደነበርም ተገልጿል። በዚህ የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ተኩስ ከምሽቱ አምስት ሰዓት አካባቢ እንደሰሙና ለአንድ ሰዓትም የዘለቀ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል። በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች ፖሊስ በቦታው ከመድረሱ በፊት ታጣቂዎቹን መግታት እንደቻሉ ባለስልጣናት አስረድተዋል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የትውልድ ቦታ በሆነችው ካትሲና የደረሰው ጥቃት መንግሥት በደህንነት ቁጥጥር ላይ ያለውን ቸልተኝነት ያሳየ ነው በሚል ከፍተኛ ትችት እየደረሰበት ነው። በሃምሌ ወር ቡድኑ ባወጣው ቪዲዮ ግዛቱን እያስፋፋ መሆኑንና በአገሪቷ ሰሜን ምዕራብ ክፍልም መግባቱን አስታውቋል። በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መንግሥት "ሽፍቶች" አደረሱት ባሉት ጥቃቶች ተገድለዋል። እነዚህ "ሽፍቶች የተባሉት የወንጀለኞች ቡድን ከቦኮ ሃራም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳላቸው ግልፅ አይደለም። ሆኖም ከአልቃይዳ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው የሚባለው አንሳሩ የተባለ ሌላ ቡድን በግዛቲቱ በከፍተኛ ሁኔታ ይንቀሳቀሳል። ቦኮ ሃራም ከ2009 ጀምሮ አስከፊ የሆነ የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ ሲሆን በተለይም በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ በኩል አትኩሮቱን አድርጓል ። በዚህም ግጭት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል እንዲሁም ከሁለት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን ትተው ተፈናቅለዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ ከ1 ሺ 100 በላይ ሰዎች በሰሜናዊ ናይጄሪያ በሽፍታዎች የተገደሉ ሲሆን መንግሥት እስካሁን ተጠያቂዎችን ለሕግ ማቅረብ አልቻለም።
49590211
https://www.bbc.com/amharic/49590211
ዩቲዩብ የህጻናትን መብት በመጋፋቱ 170 ሚሊየን ዶላር ተቀጣ
ዩቲዩብ ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን የግል መረጃ ያለቤተሰቦቻቸው ፍቃድ በመሰብሰቡ በአሜሪካ የንግድ ተቆጣጣሪ ተቋም 170 ሚሊዮን ዶላር ተቀጣ።
ዩቲዩብ የህጻናትን የግል መረጃ በመሰብሰብ ልጆች ላይ ያነጣጠሩ ማስታወቂያዎችን ለማሠራት አውሏል ተብሎ ነው የተከሰሰው። የአሜሪካው የፌደራል ንግድ ተቆጣጣሪ ተቋም (ፌደራል ትሬድ ኮሚሽን) ፤ ዩቲዩብ የህጻናትን የግል መረጃ መብት ጥሷል ብሏል። • ዩቲውብ 'ፕራንክ' ሊያግድ ነው • ፌስቡክ ሦስት ቢሊዮን አካውንቶችን አገደ • ሥራ የማዘግየት ልማድን ለመቅረፍ የሚረዱ 8 ነጥቦች የዩቲዩብ ባለቤት የሆነው ጉግል፤ ዩቲውብ ያሰራቸው ማስታወቂያዎች ህጻናት ላይ ያነጣጠሩ አይደለም ቢልም፤ "ዩቲዩብ ከስድስት እስከ አሥራ አንድ ዓመት ባሉ ታዳጊዎች ዘንድ ተደራሽ ነው" የሚል ማስታወቂያ አሠርቷል። ስለዚህም 136 ሚሊዮን ዶላር ለ'ፌደራል ትሬድ ኮሚሽን' እንዲሁም 34 ሚሊዮን ዶላር ለኒው ዮርክ ከተማ እንዲከፍል ተወስኗል። ከንግድ ተቆጣጣሪ ተቋሙ ኃላፊዎች አንዱ የሆኑት ሮሂት ቾፕራ፤ ዩቲዩብ ከዚህም በላይ መቀጣት ነበረበት ብለዋል። ዩቲዩብ የህጻናት ሙዚቃና ፊልም በመጠቀም ልጆችን "ያለአግባብ አማሏል" ብለዋል። ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ፤ ዩቲዩብ ልጆች ላይ ትኩረት ያደረገ መርሀ ግብር በግልጽ እንዲያስቀምጥም ተወስኗል። የዩቲዩብ ዋባ ኃላፊ የሆኑት ሱዛን ዎጂኪኪ እንዳሉት፤ ዩቲዩብ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም ለህጻናት የተዘጋጁ መርሀ ግብሮችን ለይቶ ያስቀምጣል። ኩባንያው የህጻናት ቪድዮ የተመለከቱ ተጠቃሚዎችን መረጃ ሰብስቦ ለማስታወቂያ ግብዓት ማዋሉን እንደሚያቆምም ገልጸዋል። ጉግል የሰዎችን ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ካሜራ ተጠቅሞ፣ በሚስጥር መረጃ ሰብስቦ፣ መረጃውን ማስታወቂያ ለሚያስነግር ሦስተኛ ወገን ያስተላልፋል በሚል አውሮፓ ውስጥ ክስ ቀርቦበታል። የጉግል ቃል አቀባይ በበኩላቸው "ያለተጠቃሚዎች ፍቃድ ማስታወቂያ አናሰራጭም" ብለዋል።
news-50555337
https://www.bbc.com/amharic/news-50555337
የተትረፈረፈ ቢመስልም የአሸዋ እጥረት ዓለም ላይ ተፈጥሯል
በተለይም በበረሃና በባህር ዳርቻዎች የሚገኘው አሸዋ የትም የሚገኝ ቢመስልም በዓለም ላይ ሰዎች እጅጉን እየተጠቀሟቸው ካሉ ነገሮች ሁለተኛው ነው።
ባለፈው መስከረም ወር ብቻ ደቡብ አፍሪካዊ ሥራ ፈጣሪ፣ ሁለት ህንዳዊያን እንዲሁም ሜክሲኳዊ የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋች ብዙ ዋጋ ባልተሰጠው ነገር ግን በጣም አስፈላጊ በሆነው አሸዋ ምክንያት ተገድለዋል። • እየጨመረ የመጣው የአሸዋ ፍላጎት ወንዞችን እያጠፋ ነው • አሸዋ የሰረቁ ፈረንሳያውያን ጥንዶች ለእስር ተዳረጉ ብዙም ባይመስልም አሸዋ እጅጉን አስፈላጊ ነገር ነው። በጥቅሉ ለከተሞች ግንባታ ወሳኝ ግብአት ነው- አሸዋ። የገበያ ማዕከሎች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የአስፓልት መንገዶች ግንባታ ያለ አሸዋ የሚታሰብ አደለም። በየቦታው የሚታዩት የመስታወት መስኮቶች፤ የስማርት ስልኮች ስክሪን ጭምር ከቀለጠ አሸዋ የሚሰሩ ናቸው። በስልኮቻችን እንዲሁም በኮምፒውተሮቻችን ውስጥ ያሉ ሲልከን ቺፖችም ከቀለጠ አሸዋ የተሰሩ ናቸው። ይህም ብቻ አይደለም በመኖሪያ ቤቶቻችን ለሚገኙ የኤሌክትሪክ መገልገያ እቃዎች ስሪትም አሸዋ ግብአት ነው። ምንም እኳ ከሰሃራ እስከ አሪዞና ባሉ ሰፋፊ በርሃዎችና በባህር ዳርቻዎች ቢገኝም፤ በአቅራቢያ ከሚገኝ መደብር በቀላሉ ልንገዛው የምንችለው ነገር ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ የአሸዋ እጥረት አጋጥሟል። • ሳናውቀው እያለቁብን ያሉ ስድስት ነገሮች ለመሆኑ በዓለም ላይ የትም ቦታ የሚገኝ ነገር እንዴት እጥረት ሊፈጠርበት ይችላል? በዓመት 50 ቢሊዮን ቶን አሸዋ በሰዎች ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ የአሸዋ መጠን መላዋን እንግሊዝ ሊያለብስ የሚችል ነው። አጥኚዎቹ እንደሚሉት ችግሩ ያለው ጥቅም ላይ እየዋለ ባለው አሸዋ አይነት ምክንያት እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ከላይ ለተጠቀሱት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ለስላሳውና በቀላሉ በንፋስ የሚበነው የበረሃ አሸዋ አይደለም። ይህ በጣም ደቃቅ የበረሃ አሸዋ ለኮንክሪት የሚሆን አይደለም። ይልቁንም ለሰዎች አስፈላጊ የሆነው ባለ ማእዘኑ እና በወንዞች እና በሃይቆች የሚገኘው ነው። ስለዚህም ይህኛውን አሸዋ ለማግኘት በወንዞች መድረሻ፣ በእርሻ ማሳዎ እንዲሁም በጫካዎች ውስጥ ሕገ ወጥ ፍለጋ ይካሄዳል። ጥቂት በማይባሉ አገራትም የወንጀለኛ ቡድኖች በዚህ የአሸዋ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል፤ በዚህ ሳቢያ ደግሞ የአሸዋ ጥቁር ገበያም ተስፋፍቷል። • ኢትዮጵያ አርባ በመቶ ዕፀዋቶቿን ልታጣ እንደምትችል ተነገረ "የአሸዋ እጥረት ጉዳይ ብዙዎች እያስገረመ ነው ግን ሊያስገርም አይገባም። ያለ ምንም አካባቢያዊ ተፅዕኖ የአንድን ተፈጥሯዊ ሃብት 50 ቢሊዮን ቶን የሚያክል ነገር ማውጣት የሚቻል ነገር አይደለም" ይላሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ተመራማሪው ፓስካል ፔዱዚ።
news-52410520
https://www.bbc.com/amharic/news-52410520
ኮሮና ቫይረስ፡ በኒውዮርክ የመድኃኒት መደብሮች የኮሮና ምርመራ ሊጀመር ነው
በኮሮና ክፉኛ እየተጠቃች ባለችው የአሜሪካዋ ግዛት ኒውዮርክ የኮሮናቫይረስ ምርመራ በመድኃኒት መደብሮች (ፋርማሲዎች) ሊጀመር መሆኑን የኒውዮርክ አስተዳዳሪ አሳውቀዋል።
የኒውዮርክ አስተዳዳሪ አንድሪው ኩሞ እንዳሉት አምስት ሺህ ያህል የመድኃኒት መደብሮች ምርመራውን ለማድረግ የተመረጡ ሲሆን፤ በከተማው ያለውን የምርመራ ቁጥርም ወደ 40 ሺህ ያህል ለማድረስም ያለመ ነው። •በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበር መስራች አቶ መንግሥቴ አስረሴ በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው አለፈ •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት በከተማዋ በሚገኙ ሆስፒታሎች የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን የተናገሩት አስተዳዳሪው፤ የቀውሱ ማብቂያ ሊሆን ይችላልም ብለዋል። ሆኖም ሰዎች እንዳይዘናጉና ጥንቃቄያቸውን እንዲቀጥሉበት አሳስበዋል። በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 938 ሺ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ከ53 ሺህ 751 አንድ ሶስተኛው ሞት የተመዘገበው በኒውዮርክ ነው። በተያያዘ ዜና በየቀኑ በሚሰጧቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች እያወዛገቡ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናው እለት መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል። በትናንትናው እለት በትዊተር ገፃቸው ላይ ሚዲያውን የወነጀሉ ሲሆን ጋዜጠኞች የሚጠይቁት ጥያቄ "ግጭት የተሞላባቸው" ናቸው ብለዋል። ከሰሞኑ ለኮሮናቫይረስ በሽታው ፈውስ የረቂቅ ተህዋስያን ማጥፊያ (ዲስ ኢንፌክታንት) ኬሚካል በመርፌ የሚሰጥበት ምርምር እንዲደረግ ሃሳብ ማቅረባቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ውግዘትንና ትችትን እያስተናገዱ ነው። •በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? •ከሚስታቸውና ከልጃቸው ጋር ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የአዳማ ነዋሪ ወደ ቤታቸው ተመለሱ በህክምናው ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች የረቂቅ ተህዋስያን ማጥፊያ ለሰውነት መርዛማ የሆነና ህይወትንም በከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ እንዲህ አይነት ሃሳብ እንዴት ይቀርባል ሲል ቁጣቸውን ገልፀዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህንን ሃሳባቸውን መናገራቸውንም ተከትሎ በርካቶች የረቂቅ ተህዋስያን ማጥፊያን መውሰዳቸውን በኒውዮርክ ድንገተኛ ጥሪዎችን የሚያስተናግዱ አሳውቀዋል፤ ሰላሳ ሰዎችንም አስተናግደዋል ተብሏል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የኮሮና ቫይረስ ግብረ ኃይል በጥምረት የሚያደርጓቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች ከሁለት ሰአታት በላይ የሚቆዩ ቢሆኑም በዚህ ሳምንት ሃሙስ ላይ ፕሬዚዳንቱ የሰጡት አስተያያት ተቃዋሚዎቻቸውን ብቻ ሳይሆን ደጋፊዎቻቸውንን ያሳፈረና ያሸማቀቀ እንደሆነ የቢቢሲ የአሜሪካ ዘጋቢ ፒተር ቦውስ ገልጿል። በነገታውም የፕሬዚዳንቱ መግለጫ ከተለመደው ውጭ አጭር የነበረ ሲሆን፤ ለሃያ ደቂቃ ብቻ ነበር የቆየው፤ በጋዜጠኞችም ለመጠየቅ ፈቃደኛ አልነበሩም። ምንም እንኳን የጤና ባለሙያዎችም ቤት መቀመጡ መቀጠል እንዳለበትና፣ ወረርሽኙም እንደሚዛመት ቢያስጠነቅቁም በአሜሪካ የሚገኙት ጆርጂያ፣ ኦክላሆማና አላስካ የተወሰኑ የንግድ ቦታዎች እንዲከፈቱ ተወስኗል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጀምሮ ከሃያ ስድስት ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ስራ ያጡ ሲሆን ይህም የአገሪቷ 15 በመቶ ሰራተኛ ኃይል ነው ተብሏል። የተለያዩ ግዛቶችም ኮሮና ያስከተለውን ጫና መቋቋም አቅቷቸዋል። ለስራ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በፍሎሪዳና ካሊፎርንያ ግዛቶች ለመዝናናት ወደ ባህር ዳርቻዎች እንዳቀኑም ሮይተርስ ዘግቧል።
news-57146301
https://www.bbc.com/amharic/news-57146301
ምርጫ 2013፡ የምርጫው መራዘም የቆሰቆሳቸው ስጋቶች
በኢትዮጵያ 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ በተወሰኑ ሳምንታት መገፋት አገሪቱ ውስጥ ሌላ የፖለቲካ ትኩሳት ይፈጥር ይሆን የሚል ስጋት ቆስቁሷል።
36 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከበርካታ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ተሰብስበው ነበር። ምርጫ በማስፈጸሙ ሂደት፣ በተለይም ከመራጮች ምዝገባ ጋር ተያይዞ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን በማሰልጠንና ድምጽ መስጫ ካርዶችን በወቅቱ በማዘጋጀት በኩል ወዘተ ፈተናዎች እንደሚኖሩ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። ብርቱካን ሚደቅሳ ምርጫው ምናልባት በተያዘለት ዕለት ግንቦት 28 እንደማይካሄድ ጠቁመው፤ ምናልባት በሁለትና በሦስት ሳምንታት ሊገፋ እንደሚችል አብራርተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም ምክረ ሐሳባቸውን እንዲያስገቡ ጋብዘዋል። ይህ ምርጫ በመጀመርያ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ ነበር። በአንድ ዓመት እንዲገፋ ያደረገው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት እንደነበር ይታወሳል። ምርጫው በድጋሚ ሊራዘም ይችል ይሆን? በምርጫ ቦርድ በተጠራው ስብሰባ ላይ ቦርዱድ የገጠመውን የሎጂስቲክ ፈተና ለፓርቲ ተወካዮች አስረድቷል። በተለይም የመራጮች ምዝገባ እና የምርጫ ቁሳቁሶችን የማዳረስ ተግዳሮቶች ተጠቅሰዋል። አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በበኩላቸው የፌዴራል መንግሥት በአገሪቱ እዚህም እዚያም በሚፈጠሩ የጸጥታ ስጋቶች መወጠሩን አንስተው፤ በምርጫው ወቅት የጸጥታ ኃይሎች በመላው አገሪቱ ደኅንነት ለማስጠበቅ ብዙ ቦታ መሸፈን ፈተና ሊሆንባቸው እንደሚችል ጠቁመዋል። በተለያዩ አካባቢዎች የተቆሰቆሱ ብሔር ተኮር ግጭቶች የምርጫ ቁሳቁሶችን እንደልብ ወደ በርካታ ቦታዎች ለማድረስ ፈታኝ አድርጎታል። በሰኔ ወር የሚጀምረው የዝናብ ወቅት በሐምሌና በነሐሴ መጠኑን ጨምሮ እየተስፋፋ ይሄዳል። በዚህ ወቅት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ምርጫ ማካሄድ እንዴት አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ያነሱ የፓርቲ ተወካዮችም ነበሩ። ሌሎች ደግሞ ምርጫው በአዲሱ ዓመት ወደ መስከረም ቢሻገር የተሻለ እንደሚሆን ያስገነዘቡም ነበሩ። ነገር ግን ያ ሌላ የፖለቲካ ምስቅልቅል የሚፈጠር ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም አዲስ መንግሥት ተመሥርቶ ሥራ የሚጀምርበት ወር ስለሚሆን። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲ ብልጽግና ቅስቀሳ ሲያካሂድ በምርጫው መራዘም ማን ምን አለ? የምርጫው መራዘም ሐሳብ እምብዛምም በአገሪቱ የተለየ ስሜት የፈጠረ አይመስልም። አንዳንዶች ምርጫው በሁለትና ሦስት ሳምንታት መገፋቱ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ለማስፈጸም እንዴት የተሻለ ሁኔታ ሊፈጥርለት እንደሚችል አልታይ ብሏቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ ነጻ ሆኖ እየሰራ እንደሆነ ካሰመሩበት በኋላ ምርጫውን በማራዘሙ ሐሳብ እንደተስማሙ በትዊተር ሰሌዳቸው ጽፈዋል። "ለኢትዮጵያ ሕዝብ ላረጋግጥ የምፈልገው በምንችለው ሁሉ ካለፉት ምርጫዎች የተሻለ፣ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ እየሰራን እንደሆነ ነው" ብለዋል። ጨምረውም ምርጫው በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንደሚካሄድና ከብዙዎች ግምት በተለየ መልኩም የመራጮች ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን ተናግረዋል። ነገር ግን አንዳንድ ቡድኖች መንግሥት ከብሔራዊ ምርጫው በፊት ብሔራዊ ንግግርና መግባባትን እንዲያስቀድም ይጠይቃሉ። በትግራይ ያለው ቀውስና በሌሎች አካባቢዎችም እየጋመ ያለው የብሔር ግጭት ብሔራዊ ምርጫ ሳይሆን ብሔራዊ ምክክር እንደሚያስፈልግ ማሳያ ናቸው ይላሉ እነዚህ ወገኖች። እነዚህ ወገኖች መንግሥት የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት ለብሔራዊ እርቅ ራሱን ማዘጋጀት አለበትም ይላሉ። ምርጫው ከትግራይ ግጭት ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው? ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ ሊካሄድ የነበረው ምርጫ መራዘም ማዕከላዊው መንግሥት በወቅቱ በትግራይ ከነበሩት አመራሮች ጋር ፍጥጫ ውስጥ እንደከተተው አይዘነጋም። የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን መልቀቅን ተከትሎ ወደ ሥልጣን የመጡት ዐቢይ አህመድ ምርጫው በወረርሽኙ ምክንያት መራዘሙ የግድ እንደሆነ አስምረውበት ነበር። ይህ ውሳኔ ታዲያ በወቅቱ የህወሓት ሰዎችን አበሳጭቶ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩንም የሥልጣን ጊዜያቸውን በሕገወጥ መንገድ ለማራዘም እየሞከሩ ነው ሲሉ ከሰዋቸውም ነበር። በመጨረሻም ዐቢይ አህመድ ከመስከረም 30 በኋላ ሕገወጥ መሪ ናቸው እስከማለት ደርሰው እንደነበር ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ህወሓት በትግራይ የራሱን የተናጥል ምርጫ ለማድረግ ደፋ ቀና ማለት ጀመረ። ምርጫውም ተካሄዶ ህወሓት በከፍተኛ ድምጽ መመረጡን ገለጸ። ይህ በትግራይ የተደረገው ምርጫ ህወሓትን ከማዕከላዊው መንግሥት ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ ከተተው። ሁለት ወራትን ቆይቶ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፈቱ። ይህም የማዕከላዊው መንግሥት ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስድ አስገደደው። በዚህ መልኩ የተቆሰቆሰው ጦርነት አሁን ሰባተኛ ወሩን ይዟል። ሺዎችን ለሞትና ለመፈናቀል ዳርጓል። የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች በዚህ ጦርነት የተፈጸሙ በርካታ አሰቃቂ ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ሪፖርት አድርገዋል። ይህም ግድያን፣ አስገድዶ መድፈርንና ሌሎች ኢሰብአዊ ድርጊቶችን የሚጨምር ነው። አንዳንዶቹ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ማዕከላዊውን መንግሥት ለማገዝ ወደ ጦርነት በገባው የኤርትራ ሠራዊት የተፈጸሙ ናቸው። የሰብአዊ ድግፍ ሰጪዎች የምግብና መድኃኒት እርዳታዎች ወደ ተጎጂዎች እንዳይደርሱ ሆነዋል ሲሉ ተደጋጋሚ ክስ ያቀርባሉ። ለምርጫው ምን ያህል ሰዎች ተመዘገቡ? 110 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት በተጠናቀቀው የምርጫ ምዝገባ በትንሹ 36 ሚሊዮን ዜጎች ተመዝግበዋል። ይህ አሃዝ ይጠበቅ ከነበረውና ይመዘገባል ተብሎ ተተንብዮ ከነበረው ሕዝብ ቢያንስ በ10 ሚሊዮን ያነሰ ነው። ነገር ግን ቁጥሩ በፈረንጆች 2015 ከተደረገው ምርጫ ጋር ተቀራራቢ ነው። በኦሮሚያ 15 ሚሊዮን ሕዝብ ለመራጭነት መመዝገቡ ያልተዋጠላቸው ሰዎች አሉ። ምክንያቱም በዚህ ክልል ዋንኛ የሚባሉ ተቃዋሚዎች በማይሳተፉበት ሁኔታና ዋንኛው የፖለቲካ ተቀናቃኝ አቶ ጃዋር መሐመድ እስር ቤት ባሉበት ሁኔታ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ሕዝብ በክልሉ ለምርጫ ሊመዘገብ አይችልም ብለው የሚከራከሩ አሉ። ቀደም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር በምርጫው ዙሪያ የሚደረጉ ዝግጅቶችን በተመለከተ ሲሰነዘሩ የነበሩ ትችቶችን ገሸሽ ማድረጉ ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት ተወካዮቹን እንደማይልክ ከገለጸ በኋላ መንግሥት ውሳኔያቸውን እምብዛም ተጽእኖ የሌለው እንደሆነ በመግለጽ ነበር ያጣጣለው።
news-53536621
https://www.bbc.com/amharic/news-53536621
የባርያ ንግድ በዘረ መል ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ የሚያሳይ ጥናት ይፋ ተደረገ
ከ50 ሺህ በላይ ሰዎችን ያሳተፈ አንድ ትልቅ የዘረ መል ምርምር ተካሂዷል። ጥናቱ፤ ከ16ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን በባርያ ንግድ ከአፍሪካ ለአሜሪካ የተሸጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በተመለከ አዲስ መረጃ አስገኝቷል።
የባርያ ንግድ አሁን ባለው የአሜሪካውያን የዘረ መል መዋቅር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ጥናቱ ያመለክታል። ጥናቱ የመደፈር፣ የመሰቃየት፣ የበሽታ እና የዘረኝነትን ጫና ያሳያል። ከ1515 እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ከ12.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አፍሪካውያን ተሸጠዋል። ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሴቶች፣ ወንዶችና ሕፃናት ወደ አሜሪካ እየተወሰዱ ሳለ ሕይወታቸው አልፏል። የዘረ መል ምርምሩ የተካሄደው ‘23ኤንድሚ’ በተባለ ድርጅት ነው። በ ‘አሜሪካን ጆርናል ኦፍ ሂውማን ጄነቲክስ’ መጽሔት የታተመው ጥናት፤ ከሁለቱም የአትላንቲክ ክፍሎች አፍሪካዊ የዘር ሀረግ ያላቸውን 30 ሺህ ሰዎች አካቷል። የማሕበረሰብ ዘረ መል ተመራማሪው ስቲቨን ሚሼሌቲ ለኤኤፍፒ እንዳሉት፤ የሚያገኙትን የዘረ መል ውጤት ከባርያ ንግድ መርከቦች ጋር ለማነጻጸር አቅደው ነበር ጥናቱን የጀመሩት። አብዛኛው ግኝታቸው ከታሪካዊው ሰነዶች ጋር ይጣጣማል። ሰዎች ከየትኛው የአፍሪካ አካባቢ እንደተወሰዱ እና አሜሪካ ውስጥ የት ለባርነት እንደተዳረጉ ከሚያሳዩ ሰነዶች ጋር አብዛኛው ውጤታቸው ተመሳሳይ ነው። ሆኖም ግን አንዳንዶቹ ግኝቶቻቸው ከታሪካዊው ትርክት ጋር ሰፊ ግንኙነት እንዳላቸው ተመራማሪው ይናገራሉ። ብዙሃኑ የአፍሪካ የዘር ግንድ ያላቸው አሜሪካውያን መነሻቸው የዛሬዎቹ አንጎላ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል። ይህም ዋነኛው የባርያ ንግድ መስመር ነው። ከሰዎች ብዛት አንጻር፤ የዘር ሀረጋቸው ከናይጄሪያ የሆኑ ሰዎችን በተመለከተ በአሜሪካ እና በላቲን አሜሪካ የተጋነነ ትርክት እንዳለ ጥናቱ ጠቁሟል። ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ የዚህ መረጃ መነሻው በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ1619 እስከ 1807 የነበረው የባርያ ንግድ ነው። ናይጄርያውያን ከካረቢያን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ይሸጡ ነበር። “ምናልባትም የአትላንቲክ የባርያ ንግድን የተመረኮዘውን ምጣኔ ሀብት ማስቀጠል ስለተከለከለ ሊሆን ይችላል” ይላሉ ተመራማሪው። በሌላ በኩል የሴኔጋል እና የጋምቢያ ተወላጆች ቁጥር በርካታ መሆኑ በታሪክ አለመታየቱ ተመራማሪዎቹን አስገርሟል። እነዚህ አገሮች የባርያ ንግድ ከተጀመረባቸው መካከል ናቸው። ተመራማሪዎቹ ይህንን በተመለከተ ሁለት እውነታዎች ላይ ደርሰዋል። አንደኛው አብዛኞቹ ሰዎች በሩዝ እርሻ እንዲሠሩ መደረጋቸው ነው። ቦታው ወባ የተስፋፋበትና አደገኛም ነበር። በቀጣይ ዓመታት ወደዚህ አካባቢ የተላኩት በርካታ ሕፃናት በሕይወት መትረፍ አልቻሉም። ጥናቱ እንደሚያሳው፤ በባርነት የተሸጡ ሴቶች በአሜሪካ ይደርስባቸው የነበረው ስቃይ አሁን ባለው የዘረ መል መዋቅር ላይ ጫና አሳድሯል። አብዛኞቹ በባርነት የተሸጡት ወንዶች ነበሩ። ሴት አፍሪካውያን ይደረስባቸው የነበረው መድልዎ ዛሬ ያለው የዘረ መል መዋቅር ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል። ተመራማሪዎቹ ለዚህ ምክንያቱ በባርነት የተሸጡ ሴቶች መደፈራቸው፣ ለበርካታ ወሲባዊ ጥቃት መጋለጣቸውም ነው ይላሉ። በላቲን አሜሪካ 17 አፍሪካውያን ሴቶች ከአንድ አፍሪካዊ ጋር መጣመራቸው ለዘረ መል መዋቅሩ መለወጥ ምክንያት መሆኑን አጥኚዎቹ ይናገራሉ። ለዚህ ምክንያቱ ‘ብራንክውሜንቶ’ የተሰኘው ጥቁሮችን ነጣ ወዳለ የቆዳ ቀለም የመለወጥ ፖሊሲ ነው። “በርካታ አውሮፓውያን በግብረ ሥጋ ግንኙነት አፍሪካዊ የዘር ግንድ ያላቸው ሰዎችን የቆዳ ቀለም እንዲለውጡ ተደርጓል” ይላሉ ተመራማሪው። በብሪትሽ ቅኝ ግዛት ሥር በነበረችው አሜሪካ ሁለት አፍሪካውያን ሴቶች ከአንድ አፍሪካዊ ጋር ያጣመራሉ የሚለው ትርክትም ሴቶችን የሚበዘብዝ ነበር። የአትላንቲክ የባርያ ንግድ ሊቆም ሲል፤ በባርነት የተሸጡ ሰዎች ልጅ እንዲወልዱ በማስገደድ፤ ባርያ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት እንደነበረ ጥናቱ ያሳያል። አሜሪካ ውስጥ ሴቶች ከወለዱ ነፃ እንደሚወጡ ቃል ይገባላቸው ነበር። ዘረኛው ፖሊሲ አንድ ዘር ከሌላው ጋር እንዲቀላቀል አይፈቅድም ነበር። ለጥቁሮች መብት የሚታገለው ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ ንቅናቄ የባርያ ንግድ እና ቅኝ ግዛት በጥቁር አሜሪካውያን እንዲሁም በመላው ዓለም ባሉ ጥቁሮች ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ አጉልቶ ያሳያል። በቅኝ ግዛት ዘመን በባርያ ንግድ የተሳተፉ ሰዎች ሀውልቶች እንዲነሱ የሚጠየቀውም ለዚሁ ነው። የባርያ ንግድ ምልክት የሆኑ ሰዎችን ማሞገስ ያክትም የሚለው እንቅስቃሴም ቀጥሏል።
news-50163987
https://www.bbc.com/amharic/news-50163987
የድብ መራቢያ አካል የበላው ህንዳዊ ነብር አዳኝ በቁጥጥር ሥር ዋለ
የህንድ ፖሊስ ክትትል ሲያደርግበት የነበረውንና የድብ መራቢያ አካል ሲበላ ነበር ያለውን የእንስሳት አዳኝ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። ግለሰቡ አርለን በመባል የሚታወቅ ሲሆን ለዓመታት ተሰውሮ ነበር።
የድብ ሀሞት በዓለም ጥቁር ገበያ ከፍተኛ ገንዘብ ያስገኛል በህንድ የፓርዲሂ ብህሊያ ጎሳዎች በጫካ ውስጥ ይኖራሉ። ኑሯቸውም የተመሠረተው በአደን ላይ ነው። የማድህራ ፕራደሽ የደን ክፍል ኃላፊ እንዳሉት ይህ ግለሰብ አባል የሆነበት ፓርደሂ ቤሄሊያ ጎሳ አድኖ አደር ሲሆን፣ የእንስሳትን መራቢያ አካልን መብላት የወሲብ ፍላጎትን ይጨምራል የሚል እምነት አላቸው። ግለሰቡም የተያዘው በዚያው አካባቢ ደቡባዊ ክፍል ሲሆን በአንድ ብሔራዊ ፓርክ መራቢያ አካሉ የተቆረጠ ድብ በማየታቸው የመጀመሪያ ፍንጭ እንዳገኙ ባለሥልጣናት ገልጸዋል። • በኢትዮጵያ የኤሊ አደን ለምን አየተበራከተ መጣ? • ጣልያናዊው በአደን ወቅት በስህተት አባቱን ተኩሶ ገደለ ከአምስት ቀናት በፊት በጉጃራት ግዛት በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ በማዕከላዊ ህንድ በነብር አደንና በሕገ ወጥ ንግድም ይታወቃል። ግለሰቡ በማዕከላዊና ምዕራብ ህንድ ነብርን ጨምሮ የዱር እንስሳት አደንና ንግድን የተመለከቱ በርካታ ወንጀሎች ተጠርጣሪ ነው። ትናንት ፍርድ ቤት የቀረበው ያርለንም ሆነ ጠበቃው ክሱን በተመለከ ያሉት ነገር የለም። "እሱን ለመከታታል እና በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለየ ዘዴ ተጠቅመናል፤ ለስድስት ዓመታት ያህል ረጅም ክትትል ያደረግንበት ጉዳይ ነው" ሲሉ የደን ክፍል ኃላፊ ሲሮሺያ ክትትሉ ምን ያህል ፈታኝ እንደነበር አስረድተዋል። ፖሊስ በካንሃ ብሔራዊ ፓርክ ሁለት የተሰለቡ ድቦችን በማግኘቱ ያርለን ለመጀመሪያ ጊዜ እኤአ በ2013 በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር። ከዚያም ለአንድ ዓመት ያህል በእስር ቆይቶ በዋስ ተለቋል። ከዚያ በኋላ ግን የተለያዩ ማንነቶችን በመጠቀም ራሱን ሰውሮ ነበር የቆየው። ሲሮሽያ እንዳሉት በግለሰቡ ላይ ስድስት የሚሆኑ ክሶች የተመሠረቱበት ሲሆን ሦስቱ ነብሮችን ማደንን የተመለከቱ ናቸው። የድብ ሐሞት ለመቶ ዓመታት ያህል ቻይናዊያን ለባህላዊ መድሃኒትነት ይጠቀሙበት ነበር። በዚህም ምክንያት የድብ ሐሞት በዓለም ጥቁር ገበያ ሲቀርብ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ያስገኛል። ምንም እንኳን በህንድ አደን በሕግ የተከለከለ ቢሆንም እነዚህን ጎሳዎች ጨምሮ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም ድርጊቱ እንደቀጠለ ነው። በአደን ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ሕይወታቸውን የሚመሩበት አማራጭ መንገድ ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን የህንድ መንግሥት አስታውቋል።
news-54531791
https://www.bbc.com/amharic/news-54531791
ተመድ፡ “የከፋ የአየር ንብረት ለውጥ ከመከሰቱ በፊት ማስጠንቀቂያ ያስፈልጋል”
ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያስከትል የአየር ሁኔታ ከመከሰቱ በፊት ማስጠንቀቂያ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አስታውቋል።
ድርጅቱ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ የከፋ የአየር ሁኔታ ከመከሰቱ በፊት ማስጠንቀቂያ የሚሰጥበት መንገድ እንዲኖር አገራት ገንዘብ ፈሰስ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ባለፉት 50 ዓመታት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተፈጥሮ አደጋዎች እየተበራከቱ ነው። ዓለም ላይ ከሦስት ሰዎች አንዱ/አንዷ የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ እንደማይደርሳቸው ጥናት ያሳያል። በቀጣይ አሥር ዓመታት በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ይገመታል። በጥናቱ ከ16 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ከዓለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ትንበያ ተቋም የተወጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። ባለፉት 50 ዓመታት ከአየር ሁኔታ፣ ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከውሃ አካል ጋር የተያያዙ 11 ሺህ አደጋዎች ተከስተው፤ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። ምጣኔ ሀብትም የ3.5 ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ ገጥሞታል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2018፤ 108 ሚሊዮን ሰዎች ተፈጥሯዊ አደጋ ከፈጠረባቸው ጫና ለመላቀቅ የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ድጋፍ ጠይቀዋል። የተመድን ሪፖርት የጻፉት ባለሙያዎች፤ በ2030 እርዳታ የሚሹ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ አድጎ፤ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚያሳድረው ጫና በዓመት 20 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ያስረዳሉ። “የከፋ የአየር ሁኔታ ከመምጣቱ በፊት ማስጠንቀቂያ ያስፈልጋል” ተመድ እንደሚለው፤ የከፋ የአየር ሁኔታ ከመከሰቱ በፊት በተገቢው መንገድ ማስጠንቀቂያ መሰጠት አለበት። ይህም የአየር ሁኔታ ምን እንደሚመስል ከመተንበይ ባለፈ፤ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ያካተተም መሆን ይገባዋል። ማስጠንቀቂያዎች በታዳጊ አገራት እንዲሁም በደሴቶች የበለጠ አስፈላጊ ናቸው። እነዚህ አገራት ባለፉት አምስት አሠርታት ከአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አጥተዋል። ከተፈጥሮ አደጋ ጋር በተያያዘ ከተከሰቱ ህልፈቶች 70% የተከሰቱት በድሃ አገራት ነው። የዓለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ትንበያ ተቋም እንደሚለው፤ አፍሪካ ውስጥ ካሉ የአየር ሁኔታ ትንበያ ተቋሞች ደረጃቸውን የጠበቁት 26% ብቻ ናቸው። ኮሮናቫይረስ የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ ላይ ጫና ማሳደሩን የድርጅቱ ሪፖርት ይጠቁማል። ሆኖም ግን የአየር ንብረት ለውጥ ተፈጥሯዊ አደጋ እያስከተለባቸው ያሉ ድሃ አገራት መረሳት እንደሌለባቸውም ተገልጿል። የዓለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ትንበያ ተቋም ዋና ጸሐፊ ፕ/ር ፔትሪ ታላስ “ዝግጁ ሆኖ በተገቢው ጊዜ፣ በተገቢው ቦታ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። የሰዎችን ሕይወትና ቤት ንበረታቸውን ለመታደግ ያስችላል” ሲሉ ገልጸዋል። አያይዘውም፤ “ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ የጤና ሥርዓትና ምጣኔ ሀብትንም አቃውሷል። ከዚህ ለማገገም ዓመታት ይወስዳል። የአየር ንብረት ለውጥ ለዘመናት በሰው ልጆች፣ በሥነ ምህዳር፣ በምጣኔ ሀብት ላይ ዘላቂ ተጽዕኖ እንዳለው መረሳት የለበትም” ብለዋል። በተመድ የአደጋ ቅነሳ ክፍል ልዩ ተወካይ ማሚ ሚዙቶሪ እንዳሉት፤ ኮቪድ-19 ያመጣው የአደጋ ጊዜ ርብርብ ዓለምን ከአየር ንብረት ለውጥ ለመታደግም መተግበር አለበት። ምን ይደረግ? በተመድ ሪፖርት መሠረት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ስድስት ነጥቦች ቀጣዮቹ ናቸው፦
news-54209688
https://www.bbc.com/amharic/news-54209688
ለጡረታ እየተዘጋጁ ያሉት አለቃ ሰራተኞቻቸውን ለማመስገን 13 ሚሊዮን ዶላር ሊሰጡ ነው
በዩናይትድ ኪንግደም ጡረታ ለመውጣት በዝግጅት ያሉ አለቃ ሰራተኞቻቸውን ለማመስገን 13 ሚሊዮን ዶላር፣ 480 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሊሰጡ ነው።
አድማይራል የተባለው አለም አቀፍ ኩባንያ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዴቪድ ስቲቨንስና ባለቤታቸው ሄዘር ለሰራተኞቻቸው በስጦታ መልክ የሚሰጡት ብር በሳውዝ ዌልስ ለሚገኙት 7 ሺህ 500 ሰራተኞችና በተለያዩ አገራት ደግሞ ላሉ 3 ሺህ ሰራተኞች ይከፋፈላል ተብሏል። ለቋሚ ሰራተኞች 1 ሺህ 300 ዶላር (48 ሺህ ብር) እንዲሁም ለጊዜያዊ ሰራተኞች ግማሹን 24 ሺህ ብር ስጦታ ይሰጣቸዋል። ዴቪድ ስቲቨንስ አድማይራል የተሰኘውን አለም አቀፍ የመኪናና የሞተር ኢንሹራንስ ኩባንያን የመሰረቱትና ያቋቋሙት ከባለቤታቸው ጋር በጎሮጎሳውያኑ 1991 ነበር። "ከእንደነዚህ አይነት ምርጥ ሰራተኞች ጋር አብሬ በመስራቴ እድለኛ ነኝ፤ እኮራባቸዋለሁ" ያሉት ኃላፊው "ሰራተኞቼን በዚህ መንገድ ማመስገንም ትክክለኛ ጉዳይ ነው ብዬ አምናለሁ" ብለዋል። "በነሱ የስራ ትጉህነትና ጠንካራ ሰራተኝነት አድማይራል ከትንሽ ነገር ተነስቶ በአለም አቀፍ ደረጃ 11 ሺህ ሰራተኞች ያሉት ትልቅ ኩባንያ ሊሆን የበቃው" በማለት ስለ ሰራተኞቻቸው መስክረዋል። ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ምርጥ የሚባሉት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ጠቅሰው በሳቸውና በባለቤታቸውም ስም ሰራተኞቻቸውን በሙሉ አመስግነዋል። ከዚህ ቀደምም ሄንሪ ኤንግልሃርድት የተባሉትና ከዴቪድ ስቲቨንስ ጋር አድማይራልን የመሰረቱት የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚም ከአራት አመት በፊት ጡረታ ሲወጡ 48 ሺህ ብር ለእያንዳንዱ ሰራተኛ ሰጥተው ነበር። በወቅቱም ለአጠቃላይ ሰራተኞቻቸውም የገንዘብ ስጦታውን ለመስጠት ከ 9 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርገዋል። ዴቪድ ስቲቨንስም በሚሌና ሞንዲኒ ይተካ ተብሏል። አድማይራል የተባለው ኩባንያ በካርዲግ ግዛት የመኪና ኢንሹራንስን በመሸጥ ሲጀመር 57 ሰራተኞች ብቻ ነበሩት። ከዩናይትንድ ኪንግደም ቢሮዎቹ በተጨማሪ በስፔን፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ፣ አሜሪካና ህንድ ቅርንጫፎች አሉት።
news-53892835
https://www.bbc.com/amharic/news-53892835
አሜሪካ፡ ፖሊሶች ጥቁር አሜሪካዊው ላይ መተኮሳቸውን ተከትሎ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
በአሜሪካዋ ዊስኮንሰን ግዛት ፖሊሶች ጥቁር አሜሪካዊው ጃኮብ ብሌክ ላይ በተደጋጋሚ መተኮሳቸውን ተከትሎ ተቃውሞ ተቀስቅሷል።
ጃኮብ ሆስፒታል ውስጥ በአስጊ ሁኔታ ይገኛል። ኮኖሻ በተባለች ከተማ ጃኮብ ወደ መኪናው እየገባ ሳለ ፖሊሶች ከጀርባው ሲተኩሱ የሚያሳይ ተንቀሰቃሽ ምስል በማኅበራዊ ድረ ገጽ ተሰራጭቷል። በከተማዋ ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን፤ አስቸኳይ የሰዓት እላፊ ታውጇል። ትናንት ምሽት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፖሊስ ዋና ጽሕፈት ቤት ተቃውሞ አሰምተዋል። መኪኖች ተቃጥለዋል። ተቃዋሚዎችም “ወደኋላ አንልም” ሲሉ ተደምጠዋል። ፖሊስ ዘረፋ ይካሄዳል፣ ተኩስም ይኖራል የሚል መረጃ ደርሶኛል ብሎ፤ 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋሞች እንዲዘጉ አሳስቧል። ፖሊሶች ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመዋል። ተቃዋሚዎቹ ሰልፍ የወጡት በአገሪቱ የተጣለውን የሰዓት እላፊ ገደብ ተላልፈው ነው። የዊስኮንሰን አገረ ገዢ ቶኒ ኤቨርስ ምንም መሣሪያ ያልታጠቀው ጃኮብ ላይ ፖሊስ መተኮሱን ኮንነዋል። “ሙሉ መረጃው ገና ባይኖረንም በአገራችን ወይም በግዛታችን በፖሊስ የተተኮሰበት፣ አካላዊ ጉዳት የደረሰበት ወይም ያለ ርህራሄ የተገደለ የመጀመሪያው ጥቁር ሰው አለመሆኑን እናውቃለን” ብለዋል። አያይዘውም “ሀዘናችንን ከመግለጽ ባሻገር እርምጃም መውሰድ አለብን። በግዛታችን ለተንሰራፋው ዘረኛነት እውቅና ያልሰጡ ባለሥልጣኖች እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን” ብለወላል። የጃኮብ ስም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተነሳ ሲሆን፤ በተኩሱ እጃቸው ያለበት ፖሊሶች ለፍርድ እንዲቀርቡ ፊርማ እየተሰበሰበም ነው። በቅርቡ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ ለበርካታ ሳምንታት የዘለቀ አገር አቀፍ ተቃውሞ መካሄዱ አይዘነጋም። የተፈጠረው ምንድን ነው? የኪኖሻ ፖሊስ እንዳለው ጃኮብ ላይ ፖሊሶች የተኮሱት ትናንት ከሰዓት ነው። ፖሊሶች ጃኮብ ላይ ከተተኮሰ በኋላ “በፍጥነት እርዳታ አድርገዋል” ብሏል የፖሊስ ክፍሉ። ፖሊሶች ከቤት ውስጥ ጥቃት ጋር በተያያዘ ምላሽ ለመስጠት በቦታው እንደተገኙ ቢገለጽም፤ ተኩስ ስለተከፈተበት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። የዊስኮንሰን የፍትሕ ተቋም ክስተቱን እየመረመረ ይገኛል። ከተኩሱ ጋር በተያያዘ ሁለት ፖሊሶች ሥራ እንዲያቋርጡ መወሰኑም ተገልጿል። በማኅበራዊ መዲያ የተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ሦስት ፖሊሶች ጃኮብ ወደ መኪናው ሲያመራ መሣሪያ ደግነውበት ይታያል። የመኪናውን በር ከፍቶ ሊገባ ሲል አንድ ፖሊስ ካናቴራውን ጎትቶ ሲተኩስበት ይታያል። ሰባት ጊዜ ሲተኮስና የአይን እማኞች ሲጮሁም ይሰማል። በተኩሱ እጃቸው ያለበት ፖሊሶች ማንነት እስካሁን ይፋ አልተደረገም። ታዋቂው ጠበቃ ቤን ክራምፕ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት፤ የጃኮብ ቤተሰቦች ደውለውላቸው እርዳታቸውን ጠይቀዋል። ጃኮብ ሲተኮስበት መኪና ውስጥ ሦስት ልጆቹ እንደነበሩም ጠበቃው በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። “ፖሊስ አባታቸው ላይ ሲተኩስ ተመልክተዋል። እስከ ወዲያኛው ጠባሳ ጥሎባቸዋል። እኛን መጠበቅ የሚገባቸው ፖሊሶች መብታችንን እንዲገፉ ልንፈቅድላቸው አይገባም” ሲሉም ተናግረዋል። ጠበቃው እንዳሉት ከተኩሱ በፊት ጃኮብ የሚደባደቡ ሰዎችን ለመገላገል ሲሞክር ነበር። የአይን እማኞች እንደሚሉት፤ ጃኮብ በሁለት ሴቶች መካከል የተፈጠረ ድብድብን ለመገላገል ሲሞክር ፖሊሶች የኤሌክትሪክ ኃይል ያለው መሣሪያ (ቴዘር) ተጠቅመዋል። የብላክ ላይቭስ ማተር የአካባቢው ቃል አቀባይ ክላይድ ማክለሞር፤ “የሚከሰተው ነገር እጅግ የሚያስቆጣ ነው። በጣም መሮናል፣ ታክቶናል” ብለዋል።
news-47621603
https://www.bbc.com/amharic/news-47621603
ወንዶች ከሴቶች በበለጠ ለምን እራሳቸውን ያጠፋሉ?
በዓለማችን ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ለጭንቀትና እራስን ለማጥፋት ተጋላጭ ናቸው። ይህ ሆኖ ሳለ ታዲያ ለምን እራሳቸውን በማጥፋት ወንዶች ከሴቶች በብዙ ዕጥፍ ይበልጣሉ?
እራስን ማጥፋት አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት በጣም ጥቂት አይደለም። የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ 2016 (እ.አ.አ) 793 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እራሳቸውን አጥፍተዋል። ብዙዎቹ ደግሞ ወንዶች ነበሩ። እራስን ማጥፋት በጣም የተወሳሰበ ምክንያት ያለው ሲሆን በባህሪው ደግሞ በእርግጠኝነት የሞቱን ምክንያት እንዲህ ነው ብሎ ለመናገር የያስቸግራል። ስለ አዕምሮ ጤንነት የሰዎች እውቀት እያደገ ባለበት ሁኔታ ብዙዎች እራሳቸውን ለማጥፋት የሚየበቁ የተለያዩ ምክንያቶችን ይጠቅሳሉ። እስካሁን ግን መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ አሃዙ ከሁለቱ ፆታዎች አንጻር ያለው ሰፊ ልዩነት ነው። • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና • ኢትዮጵያ የተካተተችበት ከባድ የአእምሮ ህመሞች ላይ ጥናት እየተደረገ ነው • ኢትዮጵያዊቷ ሰው አልባ አውሮፕላን ልዩነቱን ይበልጥ የሚያሰፋው ደግሞ ሴቶች ለጭንቀት ከወንዶች በላይ ተጋላጭ መሆናቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪም ሴቶች ከወንዶች በላይ እራሳቸውን ለማጥፋት ይሞክራሉ። ነገር ግን የወንዶች እራሳቸውን የሚያጠፉበት መንገድ ጭካኔ የተሞላበት ስለሆነ ሰዎች እርዳታ ከመድረሱ በፊት ህይወታቸው ያልፋል። ወንዶች እራስን በማጥፋት ለምን ይሰቃያሉ? መፍትሄውስ ምንድን ነው? ለወንዶች እራስን ማጥፋት ምክንያቶች ዋናው ቁልፍ ምክንያት የወንዶች የውስጣቸውን ስሜት ለመግለፅ መቸገራቸው ነው። ሴቶች ችግራቸውን በቀላሉ የማካፈልና የመናገር ባህሪ ሲኖራቸው ወንዶች ግን ለብቻቸው በውስጣቸው መያዝን ይመርጣሉ። ለዓመታት የብዙ ማህበረሰቦች አመለካከት ወንዶች 'ጠንካራ' እንዲሆኑና የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች አምነው እንዳይቀበሉና እርዳታ እንዳይሹ አድጓቸዋል። ይህ የወንዶች ባህሪ ከልጅነት ጊዜ ይጀምራል። "ወንድ ልጆችን 'ወንድ ልጅ አያለቅስም' እያልን ገና በለጋ እድሜያቸው ስሜታቸውን እንዳያካፍሉ እናደርጋቸዋልን። ምክንያቱ ደግሞ ስሜትን ማጋራት 'ልፍስፍስ' መሆን መገለጫ አድርገን መውሰዳችን ነው" በማለት የማህበረሰቡን ተፅዕኖ ኮልማን ኦ ድሪሰኮል የላይፍላይን ሃላፊ ትናገራለች። "ወንዶች ስለ አዕምሮ ጤናቸው የህክምና ባለሙያን የማማከር ልምዳቸው አነስተኛ ነው። ይህ ግን ወንዶች እንደሴቶች ተመሳሳይ ችግር ስለሌላቸው አይደለም። ይልቁንም ወንዶች እራሳቸውን እስከ ማጥፋት ሊያበቋቸው የሚችሉትን እያስጨነቋቸው ያሉ ነገሮችን ለይተው ለማወቅ መቸገራቸው ነው" በማለት ሃርካቪ ፍሬደማን በአሜሪካ እራስን ማጥፋት የሚከላከል ድርጅት ምክትል ፕሬዝዳንት ይናገራሉ። አንዳንድ ወንዶች የህክምና አገልግሎት ከመሻት ይልቅ አደገኛ በሆነ መልኩ እራሳቸውን ለማከም ይሞክራሉ። "ዕፆችን የመጠቀምና አልኮልን የማዘውተር ባህሪ በወንዶች ዘንድ ከፍተኛ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ያሉበትን የጭንቀት ስሜት ያንፀባርቃል። እራስን ለማጥፋት ያለውን እድልም ያመለክታል" ሲሉ ሃርካቪ ፍሬድማን የጨምራሉ። በእራሳችን ውሳኔ የምንወስዳቸው መድሃኒቶች አደጋን ያስከትላሉ ሌሎች እራስን ለማጥፋት ሊያጋልጡ የሚችሉ መንስኤዎች ደግሞ ከቤተሰብና ከሥራ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ናቸው። ከኢኮኖሚ መውደቅ እና ከሥራ አጥነት ጋር በተያያዘ እራስን የማጥፋት አጋጣሚም ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ ከኢኮኖሚ መሽቆልቆሉ በኋላ ባሉት 18 እስከ 24 ወራት ውስጥ ጎልቶ ይታያል። እ.አ.አ 2015 ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው በእያንዳንዱ ሥራ አጥነት ላይ ለሚታይ የ1 በመቶ ጭማሪ፤ እራስን ማጥፋት በ0.79 በመቶ በሚሆን መጠን ከፍ ይላል። ስለ ገቢ መጨነቅና ሥራ ለማግኘት የሚደረግ ፍለጋ የማንኛውንም ሰው የአዕምሮ ጤንነትን ይጎዳል። ነገር ግን ከዚህ በተጨማሪ የማህበረሰብ ተፅዕኖና የማንነት ቀውስ ምክንያቶች ናቸው። "የምናድገው እራሳችንን ከሌሎች ሰዎች ጋር እያነፃፀርን በገቢ ደግሞ ስኬታማ እንድንሆን ነው። በዚህ ምክንያት ከገቢ አንፃር የማንቆጣጠራቸው ችግሮች ሲያጋጥሙን በጣም ይከብደናል" ይላሉ ሲሞን ገኒንግ። ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ብቸኝነት ነው። • የሙዚቃ ሕክምና በኢትዮጵያ ከራስ ውጭ የሆኑ ክስተቶች እራስን ወደማጥፋት እየተቃረበ ያለን ሰው ሁኔታን ሊያባብሱ ቢችሉም መቼም ቢሆን ግን ብቸኛው ምክንያት ሊሆኑ አይችሉም። "በጣም ብዙ ሰዎች ሥራቸውን ያጣሉ፣ ሁላችንም በተለያዩ አጋጣሚዎች ከምንወዳቸው ጋር ያለንን ግንኙነት አጥተናል፤ ነገር ግን እራሳችንን አናጠፋም" ሲሉ ሃርካቪ ፈሬድማን ይናገራሉ። መፍትሄዎች እራስን ማጥፋትን ለመሰለ የተወሳሰበ ሁኔታ ቀጥተኛ መልስ ማግኘት አይቻልም። ነገር ግን የተለያዩ መድረኮች፣ ፖሊሲዎች እና አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለመፍትሄዎች በር እየከፈቱ ነው። ባጠቃላይ ትኩረት እየተደረገበት ያለው "ለወንዶች ስሜታቸውን ማካፈል ምንም ማለት እንዳልሆነና ሲያካፍሉም እንደ ጥንካሬ እንዲወሰድ ማድረግ ላይ ነው" ይላሉ ኦ ድሪስኮል። ጎን ለጎን ቴክኖሎጂ ሌሎች አማራጮችንም እያቀረበ ነው። ሁሉም ሰው የውስጡን ለሌላ ሰው ለመናገር ላይፈልግ ይችላል። ለዚህም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እርዳታ የሚሻ ሰውን በማነጋገር የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንዲያገኙ ሊረዷቸው ይችላሉ። ሌላኛው መፍትሄ ደግሞ እራስን ማጥፋት በቤተሰብ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ሰዎች እንዲገነዘቡ ማድረግ ነው። ይህ በአንዳንድ ወንዶች "እራሱን ማጥፋቱ ትክክለኛ ውሳኔ ነው" የሚለውን ሃሳብ ለመግታት ይረዳል ይላሉ ገኒንግ።
news-56080426
https://www.bbc.com/amharic/news-56080426
“ጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤትን በመናቅ ክስ ዘብጥያ ሊወርዱ ይገባል” የደቡብ አፍሪካ ዳኛ
አንድ የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽን ልዩ ፍርድ ቤት ዳኛ የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማን ፍርድ ቤት ተዳፍረዋል ሲሉ ከሰሱ። በዚህም የእስር ቅጣት ሊጣልባቸው ይገባል ብለዋል።
የ79 ዓመቱ ጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤት ተዳፍረዋል የተባሉት እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን ፍርድ ቤት መገኘት ሲኖርባቸው በዚህ የኮሚሽኑ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ፍቃደኛነት ባለማሳየታቸው ነው። ፍርድ ቤቱ እውነትን አፈላላጊ ኮሚሽን አቋቁሞ የዙማን ጉዳይ እየተመለከተ የነበረ ሲሆን ጃኮብ ዙማ ግን ዳኛ ሬይ ዞንዶ በሚመሩት የዚህን እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን የፍርድ ሂደት ላይ ሊገኙ አሻፈረኝ ብለዋል። ዳኛው እንዳሉት የጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤቱን የመናቅና የመድፈር ተግባር ሕግ አልባነትን የሚያበረታታ ነው። ዜጎችም በሕግ ሂደት እንዳያምኑ ጥርጣሬ ውስጥ የሚከት ነው።በመሆኑም የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዙማን ፍርድ ቤትን በመዳፈር ክስ የእስር ቅጣት እንዲበይንባቸው እጠይቃለሁ ብለዋል። ጃኮብ ዙማ በበኩላቸው የኮሚሽኑ ዳኛ ሬይ ዞነዶ ገለልተኛ አይደሉም እርሳቸው በሚያስችሉት ፍርድ ቤትም አልገኝም ብለዋል። ከዚህ ቀደምም እኚህ የኮሚሽኑ ዳኛ ከቦታቸው እንዲለቁ ጃኮብ ዙማ መጠየቃቸው ይታወሳል። ዳኛ ዞንዶ ግን የዙማን ክስ ቸል ብለዋል። ሥራዬን ገለልተኛ ሆኜ የምሠራ ሰው ነኝ ሲሉም ተናግረዋል። እስከ አሁን 40 የሚሆኑ ምስክሮች ዙማ ሙስኛ እንደነበሩ መስክረዋል። ዙማ ከቀረበቡባቸው ክሶች መካከል ብልጹግ የሚባሉትን ቢሊየነሮቹን የጉብታ ቤተሰብ አባላት የደቡብ አፍሪካን ሀብት እንዲቀራመቱ አድርገዋል የሚሉ ይገኙበታል። የጉብታ ቤተሰብ በደቡብ አፍሪካ ፖሊሲ እንዲቀየር፣ የካቢኔ አባላት ሹም ሽር እስከማድረግ ተጽእኖ ነበራቸው፤ ይህም የሆነው በዙማ ምክንያት ነው ተብሏል። ጃኮብ ዙማም ሆኑ የጉብታ ቤተሰብ ክሱን ያስተባብላሉ። የደቡብ አፍሪካ የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት ባለፈው ወር ጃኮብ ዙማ በዚህ የኮሚሽን ችሎት እንዲገኙ አዝዞ ነበር። ሆኖም ትናንት ሰኞ ጃኮብ ዙማ በችሎት አለመገኘታቸውን ተከትሎ ዳኛ ሬይ ዞንዶ “ሁሉም ሰው በሕግ ፊት እኩል ነው፣ ዙማ ግን ከዚህ አስተሳሰብ የሉበትም፤ ይህ ደግሞ ሕዝብ በሕግ የበላይነት እንዳያምን የሚያደርግ ነው ብለዋል። በመሆኑም ጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤቱን በመናቅና በመዳፈራቸው ከፍተኛው ፍርድ ቤት የእስር ቅጣት እንዲበይንባቸው ጠይቀዋል። ዙማ ዳኛ ዞንዶ ይህን አስተያየት ከሰጡ በኋላ ያሉት ነገር የለም። ሆኖም የዙማ ደጋፊዎች የወታደር የደንብ ልብስ ለብሰው የዙማ የትውልድ ስፍራ በመሄድ ባሳዩት ትእይንት የሚወዷቸውን ጃኮብ ዙማን እስከመጨረሻው እንደሚከላከሉ ቃል ገብተዋል። ጃኮብ ዙማ ከሥልጣን በሕዝብ ግፊት እንዲለቁ የሆኑት በ2018 ሲሆን ይህም የቀረበባቸውን የሙስና ክስ ተከትሎ ነው። ጃኮብ ዙማ 9 ዓመት ያህል በደቡብ አፍሪካ በሥልጣን ቆይተዋል። ተተኪያቸው ሲሪል ራማፎሳ ወደ ሥልጣን የመጡት የሙስና መረቡን እበጣጥሳለሁ በሚል ቃል ገብተው ነበር።
53393150
https://www.bbc.com/amharic/53393150
የኔልሰን ማንዴላ ሴት ልጅ ዚንዲዚ ማንዴላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደንት ኔልሰን ማንዴላ እና የፀረ አፓርታይድ ተሟጋቿ ዊኒ ማዲኪዜላ ማንዴላ ሴት ልጅ የሆኑት ዚንዲዚ ማንዴላ በ59 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ዚንዲዚ ሰኞ ጠዋት በጆሃንስበርግ ሆስፒታል ሕይወታቸው እንዳለፈ የአገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል። ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስም በዴንማርክ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ዚንዲዚ በዴንማርክ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ከአምስት ዓመታት በፊት ሲሆን በላይቤሪያ ሞንሮቪያ ደግሞ ዲፕሎማት ሆነው አገልግለዋል። በምን ምክንያት እንደሞቱ ግን የተገለፀ ነገር የለም። ዚንዲዚ የኔልሰን ማንዴላ ስድስተኛ ልጅ ሲሆኑ፤ ከሁለተኛ ባለቤታቸው ከዊኒ ማዲኪዜላ የወለዷት ሁለተኛ ልጃቸው ነበሩ። ዚንዲዚ ዓለም አቀፍ እውቅናን ያገኙት በአውሮፓውያኑ 1985 ሲሆን የወቅቱ ነጭ መንግሥታት ኔልሰን ማንዴላ የሚደረጉ የትግል እንቅስቃሴዎችን ካወገዙ ከእስር እንደሚለቀቁ የሰጧቸውን እድል ውድቅ ያደረጉበትን ደብዳቤ በአደባባይ ካነበቡ በኋላ ነበር። ዚንዲዚ በደቡብ አፍሪካ የመሬት ተጠቃሚነት ማሻሻያ ላይ ድምፃቸውን በማሰማትም ይታወቁ ነበር። ሕልፈታቸውን አስመልክቶ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ በሰጡት መግለጫ ላይ ዚንዲዚ "በትግላችን ወቅት ኢ- ሰብዓዊ የሆነው የአፓርታይድ አገዛዝ ሥርዓት በመታገልና ለነፃነት ትግላችን የማይናወጥ መፍትሔ ያመጡ ሴት ናቸው" ሲሉ ገልፀዋቸዋል። የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስተር ናሌዲ ፓንዶር በበኩላቸው፤ "ዚንዲዚ የሚታወሱት የነፃነት ታጋያችን ልጅ በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን ለመብታቸው የቆሙ ጀግና ሴት በመሆናቸውም ጭምር ነው" ብለዋል። ዚንዲዚ ያደጉት በፀረ አፓርታይድ ትግል ወቅት ሲሆን በወቅቱ አባታቸው በሮበን ደሴት በእስር ላይ ነበሩ። በወቅቱም ቤተሰቡ በአፓርታይድ አገዛዝ ሥርዓት ከፍተኛ በደል ይደርስባቸው እንደነበር ይነገራል። ከኔልሰን ማንዴላ ስድስት ልጆች በሕይወት ያሉት ሁለት ብቻ ናቸው።
news-54098816
https://www.bbc.com/amharic/news-54098816
አሜሪካ የ1ሺህ ቻይናዊያን ተማሪዎችን ቪዛ ሰረዘች
አሜሪካ ለደኅንነቴ ያሰጉኛል በሚል የ1ሺህ ቻይናዊያን እና ተመራማሪዎችን ቪዛ መሰረዟን አስታወቀች፡፡
ይህ እርምጃ ባለፈው ግንቦት ዶናልድ ትራምፕ ‹‹ቻይናዊያን ተማሪዎች መረጃ ይሰርቃሉ፤ ፈጠራ መብትን ይመነትፋሉ›› ብለው ቅሬታ ካቀረቡ በኋላ የተወሰደ የመጀመርያ ውሳኔ ነው፡፡ ቻይና በጉዳዩ ላይ ለጊዜው ምንም ያለችው ነገር የለም፡፡ በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በ2018 እና 19 ብቻ 370ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በበኩሏ ‹‹ቪዛ የከለከልናቸው 2ኛ ዲግሪና የምርምር ሥራ ላይ ሊሰማሩ የነበሩትንና ስጋት የሆኑት ብቻ ነው››ብላለች፡፡ ይህ ቁጥር ከጠቅላላ የቻይና ተማሪዎች ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ብለዋል፡፡ ‹‹ቻይናዊያን ተማሪዎች አገራችን ገብተው እንዲማሩ አንከለክልም፡፡ ዓለማቸው ለኮሚኒስቱ ፓርቲ መረጃ ማቀበል እስካልሆነ ድረስ›› ብላለች ቃል አቀባይዋ፡፡ በግንቦት ወር በአሜሪካ የወጣው መመሪያ የቻይና መንግሥት ቻይናዊ ተማሪዎችን በመጠቀም ለብሔራዊ ደኅንነት አደገኛ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ከአሜሪካ ይጠልፋል፣ የፈጠራ መብቶችን ይመነትፋል፣ ወሬም ያቀብላል ሲል ያውጃል፡፡ አንዳንድ በአሜሪካ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ያሉ ቻይናዊያን በበኩላቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በካምፓሶች ውስጥ በጥርጣሬ እንደሚታዩና የጥላቻ ንግግሮችን እንደሚያስተናግዱ በመግለጽ ሁኔታዎች እንዲለወጡ ጠይቀዋል፡፡
news-53762522
https://www.bbc.com/amharic/news-53762522
ወላይታ ፡ "ልጄ ታናሽ ወንድሙን ለመፈለግ በወጣበት ነው የተገደለው" የሶዶው አባት
በወላይታው አለመረጋጋት የመጀመሪያ ልጃቸውን ተስፋዬን የተነጠቁት አባት አቶ ተፈሪ ሰይፉ ልጃቸው ታናሽ ወንድሙን ሊፈልግ እንደወጣ መቅረቱን በሐዘን ተሰብረው ተናግረዋል።
ቢቢሲ በትናንትናው ዕለት ባናገራቸው ወቅት አቶ ተፈሪ በበኩር ልጃቸው ሐዘን ላይ የነበሩ ሲሆን የሚኮሩበትን ልጃቸው ማጣታቸው ልባቸውን እንደሰበረው በምሬት ተናግረዋል። ስለ 28 ዓመቱ ልጃቸው ተስፋዬም ሲያወሱ፤ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቆም ኢንተርፕራይዝ ልማት በሚባል ድርጅትም ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር ገልጸዋል። ለእረፍት ቤተሰቦቹን ሊጠይቅ መጥቶ ባለበት ወቅት እሁድ ምሽት ከተማው ውስጥ የጥይት ተኩስ በተከፈተበት ጊዜ ታናሽ ወንድሙ ቤት ስላልነበረ እሱን ፍለጋም ወጣ። አቶ ተፈሪ እንደሚሉት ወንድሙን ወደቤት ለመመለስ የወጣው ተስፋዬ ላይመለስ በጥይት ተመትቶ ተገደለ። እንደወጣ በቀረው ልጃቸው ሐዘን ክፉኛ የተሰበሩት ሳግ በሚቆራርጠው ድምጽ "ልጄ ለሞት ተዳርጓል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ሲቪል ነው፣ መሳሪያ አልታጠቀም፣ ምንም አያውቅም፣ ልጄ ባዶ እጁን ታናሽ ወንድሙን ለመፈለግ እንደወጣ ቀረ" ብለዋል። የወላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄን ካነሰ ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ እንደሆነው የሚናገሩት አባት ያ ምላሽ ባለገኘበት ወቅት በተጨማሪ አመራሮቹ መታሰራቸው ቁጣን ቀስቅሷል። በዚህም ሳቢያ ወጣቶች የታሰሩት ሰዎች ይፈቱ በሚልም እሁድ ዕለት ከተሞቹ ላይ ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸውን ጠቅሰው ልጃቸው ተስፋዬም ወንድሙን ከሰልፈኞቹ መካከል ፍለጋ ለመፈለግ ሲሞክር ነው የተገደለው። "ልጁ አንድ ነገር እንዳይደርስበት፣ ጥይትም እንዳያገኘው በሚል ይዤው ልምጣ ብሎ ነው የወጣው። አካሄዱ ለተቃውሞ ሰልፍ አልነበረም፤ ትንሽ ወንድሙ በጥይት እንዳይመታ ለማምጣት ነበር" ይላሉ አባት አቶ ተፈሪ። አለመረጋጋቱ ከተከሰተ በኋላ ተስፋዬ ወንድሙን ሊፈልግ ሲወጣም የተጨነቁት አባት "ተው አትሂድ ብዬው ነበር" ይላሉ። በጥይት የመመታቱንም መርዶ የሰሙት ከጓደኛቸው በስልክ ነው ነው "ልጅህ በጥይት ተመትቷል፤ ሆስፒታል ተወስዷል ይባላል ተከታተለው። እኔ መውጣት አልቻልኩም ተብሎ ተደወለልኝ።" እሳቸውም በዜናው ደንግጠው ወደ ሶዶ ሆስፒታል በፍጥነት አቀኑ። እዚያም በደረሱበት ወቅት የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ስላሉ አናስገባም አሏቸው። "እዚያ ሰው መግባትም ሆነ መውጣት አይችልም አሉኝ" ክርስቲያን ሆስፒታልም እንዲሞክሩ ነገሯቸው። አቶ ተፈሪ የተባሉትን ሰምተው ወደ ክርስቲያን ሆስፒታል ሄዱ። ክርስቲያን ሆስፒታል ውስጥ ፅኑ ህሙማን ክትትል ወደሚያገኙበት ክፍል እንደገባና በአምስት ጥይት እንደተመታም ተረዱ። ሆዱ ውስጥ ያለውንም ጥይት ለማውጣት ቀዶ ጥገናም እየተካሄደ ነበር። ቀዶ ጥገናውም ሳይጠናቀቅ ህይወቱ አለፈ "ፅኑ ህምሙማን ክፍል ውስጥ እያለ አይኑን ሳላየው ልጄ ደክሞ ሞተ" የሚሉት አባት ከመሞቱ በፊትም ልጄ ከምን ደረሰ? እያሉ የሆስፒታሉን ሠራተኞችም እየወተወቱ እንደነበር ያስታውሳሉ። ዶክተሮቹም አባቱን እንዴት እንደሚያረዷቸው ለመንገር ዘገዩ፤ ቆይተው ከሁለት ሰዓት በኋላም ራሳቸው በቀጥታ ሳይሆን "በሌላ ሰው በኩል ልጄ እንደሞተ ነገሩኝ" ይላሉ። የሚረዷቸውን ሰዎችም ጠርተው መኪናም ለምነው አስከሬኑን አመሻሹ ላይ ወደቤታቸው ወሰዱ። ሌላኛው ልጃቸው ግን ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ወደቤት መመለሱንም የአምስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ተፈሪ ይናገራሉ። "ከታላቅ ልጄ በላይ፣ ምንም ካላዬው ልጄ፣ ካላገባ፣ ልጅ ካልወለደ፤ እንዲሁ ያለ ስም የሚሞት ልጅ ያሳዝናል" የሚሉት አቶ ተፈሪ፤ ልጃቸው ዩኒቨርስቲ ጨርሶ ለፍቶ፣ ሥራ ይዞ ትዳር ሳይዝ ወግ ማዕረጉን ሳያዩ እንደወጣ መቅረቱ የእግር እሳት ሆኖባቸው ሐዘናቸውን አበርትቶባቸዋል። "እንዲህ አይነት ሁኔታ በጥይት ተቃጥሎ ሲሞት፣ አምስት ጥይት ተተኩሶበት ሲገደል እጅግ የሚያስመርር ነው" የሚሉት አባት "አዝናለሁ፣ እጅግ አዝናለሁ፤ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝነናል" ሲሉ ሐዘናቸው የእሳቸው ብቻ እንዳልሆነ ተናግረዋል። እንዴት ሞተ ብሎ የሚጠይቅ የመንግሥት አካል አለመኖሩም ቁጭት እንደፈጠረባቸው ለቢቢሲ አዋይተዋል። ከሰሞኑ በወላይታ በነበረው አለመረጋጋት 16 ያህል ሰዎች መሞታቸውን ቢቢሲ ያናገራቸው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሐኪም የሆኑት ዶ/ር መብራቱ ጪሻ ከተለያዩ ሆስፒታሎችና ከአካባቢው የተጠናቀሩ መረጃዎች እንደሚያሳዩ የተናገሩ ሲሆን ልጃቸውን በዚህ አለመረጋጋት የተነጠቁት አባት አቶ ተፈሪ ሌሎች አምስት ሰዎችም መገደላቸውን ሰምተዋል። ዶ/ር መብራቱ ጪሻ ጨምረውም በአካባቢው በነበረው አለመረጋጋት ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሕክምና ተቋማት የመጡት 49 ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰው በጥይት ተመትተው መሆኑን አመልክተዋል። ዞኑን በክልልነት ለማደራጀት ከተቋቋመው ሴክሬታሪያት ስብሰባ ተሳታፊ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሕግ ባለሙያዎችና የአገር ሽማግሌዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነው ወላይታ ውስጥ ችግሩ የተከሰተው። የወላይታ ዞን ምክር ቤት ሰኔ 15/2012 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንዲቋቋም ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። የክልሉን መንግሥት ለማደራጀት የሚያስችል ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤትም እንዲቋቋምና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንዲከናወኑም በዚሁ ወቅት ወስኖ ነበር። የወላይታ ዞን ከደቡብ ክልል በመውጣት እራሱን ቻለ ክልል ለመሆን ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ በተከሰተ አለመረጋጋት ነው ተስፋዬ ተፈሪን ጨምሮ ከ15 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወት ያለፈው።
43985854
https://www.bbc.com/amharic/43985854
"በምንም ዓይነት መልኩ ሕዝቡን የሚጎዳ ከሆነ ተቀባይነት የለውም"
ምንም እንኳ የአካባቢው ሰዎች ጉዳት እያደረሰብን ነው ብለው ቅሬታ ቢያሰሙም የሚድሮክ ለገደምቢ የወርቅ ማምረቻ የንግድ ፍቃድ እንደተደረገለት ተሰምቷል።
ይህንን ተከትሎ ነው ከሰሞኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የሰሚ ያለህ ሲሉ ጩኸታቸውን ያሰሙ የቀጠሉት። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አቋም የትኛውም ኢንቨስትመንት ሕዝቡን የሚጠቅም መሆን አለበት የሚል ነው የሚሉት የክልሉ ኮሚዩኑኬሽን ኃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ናቸው። "በምንም አይነት መልኩ ሕዝቡን የሚጎዳ ከሆነ ተቀባይነት የለውም" ሲሉም ያስረግጣሉ። ቢቢሲ የለገደንቢ ሚድሮክ የወርቅ ማምረቻ በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦች የጤና ጠንቅ እንደሆነባቸው የሚያትት ዘበጋ ከዚህ ቀደም ሰርቶ እንደነበር የሚታወስ ነው። ይህንን ጉዳይ ሕዝቡና አመራሩ በተለያየ ወቅት ያነሱ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ነገሪ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሕፃናት መወለዳቸውን እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ነፍሰጡር እናቶች ውርጃ እያጋጠማቸው እንደሆነ በምሳሌ በመጥቀስ የነገሩን ክብድት ያስረዳሉ። ከዚህ ቀደም ይህንንም ችግር ለመፍታት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና ከድርጅቱ አመራሮች ጋር ውይይት መደረጉንና የመፍትሔ አቅጣጫ ይሆናል ያሏቸውን ነጥቦች ማስቀመጣቸውንም ያስታውሳሉ። "በተደረገው ውይይት ደረሰ ለተባለው የአካል ጉዳት እና ውርጃ ያሉ ማስረጃዎች ተወስደው ሳይንሳዊ ጥናት ተደርጎ እንዲለይ ተስማምተን ነበር" የሚሉት ዶ/ር ነገሪ ይህንን ተንተርሶም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥናት መጀመሩን አሁን በአካባቢው ያለመረጋጋት ከተፈጠረ በኋላ ባደረጉት ውይይት እንደተረዱ ተናግረዋል። "ሕዝቡ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ እያነሳ ሳለ የተደረገ ጥናት ውጤትም ውይይት ሳይደረግበት የውል እድሳት መደረጉ ትክክል አይደለም" ባይ ናቸው ኃላፊው። "ድርጅቱ ከዚህ በፊት የተለያዩ የሰው ኃይል ፍላጎቱን ለማሟላት በሌላ ስፍራ ማስታወቂያ አውጥቶ ይቀጥር እንደነበረ ያስታወሱት ዶ/ ር ነገሪ አሁን ግን መስራት ለሚችሉ አቅሙ እና ብቃቱ ላላቸው ለአካባቢው ወጣቶች እድል ለመስጠት ማስታወቂያ በስፍራው እንዲወጣና እንዲወዳደሩ ስምምነት የተደረሰ ቢሆንም ይህ ጉዳይ ምን ያህል እንደተስተካከለ ግልፅ አይደለም።'' በተወሰነ ደረጃ በድርጅቱ በኩል እዚያ አካባቢ ማስታወቂያው እንዲለጠፍ ቃል የተገባ ቢሆንም ይህንን ከህዝቡ ጋር በዚህ መልኩ ተስተካክሏል በሚል ውይይት ሳይደረግበት ነው ወደ ውል እድሳት የተገባው ይላሉ። "አካባቢው ለማዕድን ልማት በሚደረገው ቁፋሮ የተጎዳ ስለሆነ የተፈጥሮ ሃብቱን ወደነበረበት ለመመለስ የሚያስችል የመልሶ ማልማት ስራ መሰራት እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጦ ነበር" የሚሉት ዶ/ር ነገሪ ይህም በሚፈለገው ደረጃ እንዳልተሰራ አስታውሰዋል። "የትኛውም ድርጅት ንብረቱን የሚጠብቅለት የፀጥታ አካል ሳይሆን ማሕበረሰቡ ነው" የሚሉት ዶ/ር ነገሪ ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች መሰራት እንደሚኖርባቸው አስመረዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ድርጅቱ ገንዘብ መድቦ የተወሰኑ ስራዎች እየሰራ ነው የሚሉ ነገሮች ቢኖሩም ሕዝቡ ግን በሚፈልገው መጠን ተጠቃሚ አለመሆኑን እያነሳ ባለበት ወቅት ነው ይህ የውል እድሳት ወሬ ይፋ ባልሆነ መልኩ በአንዳንድ የግል ብዙሃን መገናኛዎች በኩል የተሰማው ይላሉ ዶ/ር ነገሪ። "ሕዝቡን ለማረጋጋት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። የክልሉ መንግስትም ሕዝቡን የሚጎዳ ኢንቨስትመንትን እንደማይቀበለው ልናረጋግጥ እንወዳለን፤ ይህንን ለማስተካከል ከሚመለከታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ጋር ጥብቅ ውይይት ላይ ነን። የተሰራው ስህተት ላይ ግን መግባባት ላይ ደርሰናል" ሲሉ ይገልፃሉ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ስለተፈጠረው ስህተት ሕዝቡን ይቅርታ ለመጠየቅ ወደ ስራ እንደሚገቡ የተናገሩ ሲሆን የተጠናው ጥናት ላይም ውይይት ከህዝቡ ጋር እንደሚያደርጉ ስለገለፁ የተፈጠረው ችግር በቅርቡ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። የማዕድን፣ ፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ባጫ ሩጂ የሜድሮክ ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ውል ከአንድ ወር በፊት መራዘሙን አስረግጠውልናል። አቶ ባጫ የወርቅ ማምረቻው ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ውጤቱ ህብረተሰቡን የሚጎዳ ሆኖ ከተገኘ ውሉ እንደሚቋረጥ አስታውቀዋል።
news-47986562
https://www.bbc.com/amharic/news-47986562
ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ጠቅላለ ባለስልጣናት ስልጣን ለቀቁ
ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ሁሉም የመንግሥት ኃላፊዎች በማሊ እየጨመረ የመጣውን ሥርዓት አልበኝነትን ተከትሎ እራሳቸውን ከኃላፊነት አገለሉ።
የመዲናዋ ከተማ ነዋሪዎች መንግሥት ሰላም እና መረጋጋት ለሃገሪቱ ማምጣት ተስኖታል በሚል አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን ገልጸዋል። ከሁለት ቀናት በፊት የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት ጠቅላይ ሚንስትር ሶሜይሉ ቡብሄ ማኢጋ በሃገሪቱ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን ሥርዓት አልበኝነት መቆጣጠር አልቻሉም በማለት የመተማመኛ ድምጽ ነፍገዋቸዋል። ባለፈው ወር በርካታ አርብቶ አደሮች በተደራጁ የተቀናቃኝ ጎሳ አባላት ተገድለዋል። • በማሊ 37 ሰዎች ገደማ በታጣቂ ተገደሉ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ቦባካር ኬይታ በሰጡት መግለጫ የጠቅላይ ሚንስትሩን ከኃላፊነቴ ልነሳ ጥያቄ ተቀብለዋል። የፕሬዝዳንቱ መግለጫ ''በሃገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር ከተደረገ በኋላ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር እና መንግሥት ይሰየማል'' ይላል። የማሊ መንግሥት እአአ በ2012 ላይ ከአልቃይዳ ጋር ግነኙነት እንዳላቸው የሚታመን ጸንፈኛ ቡድኖች የሃገሪቱን ሰሜናዊ በረሃማ ከፍል መቆጣጠራቸውን ተከትሎ አካባቢውን ከጸንፈኛ ቡድኖቹ ማጽዳት ተስኖታል። 160 አርብቶ አደሮች በግፍ መጨፍጨፋቸውን ተከትሎ የማሊ መንግሥት በሃገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት ማስፈን ተስኖታል በሚል ከፍተኛ ጫና ሥር ወድቋል። • ባባኒ ሲሶኮ፦ 'ዓለም አቀፉ ምትሃተኛ' በአርብቶ አደሮቹ ግድያ ማሊያዊያን ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገቡ ሲሆን፤ ይህን በመቃወም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመዲናዋ ባማኮ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። የተቃውሞ ሰልፉን ተከትሎም ፕሬዝደንቱ በቴሌቪዥን ለህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት ''ንዴቱን ስምቻለሁ'' ሲሉ ተደምጠዋል።
news-50732720
https://www.bbc.com/amharic/news-50732720
በኬንያ ግለሰቡን በልቶ የተሰወረው አንበሳ እየታደነ ነው
የኬንያ የዱር እንስሳት አገልግሎት በዋና መዲናዋ ናይሮቢ ዳርቻ በሚገኝ የመኖሪያ መንደር አካባቢ አንድን ግለሰብ የበላውን አንበሳ እያደነ መሆኑን አስታወቀ።
አሁንም አንበሳውን የመፈለግ ሥራው በመቀጠሉ ነዋሪዎች ቤት ውስጥ እንዲያሳልፉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። • ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። • ከሺዎች እስከ ኳትሪሊየን እንስሳት በአንድ ቀን የሚወለዱባት ምድር በሮንጋይ አካባቢ በአንበሳ የተባለው ግለሰብ አስክሬን ቀሪ ክፍል ትናንት ሰኞ መገኘቱን ተከትሎ አሁንም ጭንቀት እንደነገሰ ነው። ግለሰቡ ከናይሮቢ ብሔራዊ ፓርክ አካባቢ አምልጦ እንደወጣ በተነገረው አንበሳ ግማሹ የአካል ክፍሉ ተበልቷል። የኬንያ የዱር እንስሳት አገልግሎት በመግለጫው፤ በግለሰቡ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ፤ ግለሰቡን የበላውን አንበሳ አድኖ ለመያዝ የፓርክ ጠባቂዎች እና የእንስሳት ሐኪም ቡድን መላኩን አስታውቋል። አንበሳው በቁጥጥር ሥር እስከሚውልም ድረስ የአካባቢው ማሕበረሰብ በምሽት ቤታቸው ውስጥ እንዲያሳልፉ አሳስበዋል። ከናይሮቢ ብሔራዊ ፓርክም ሆነ ከሌሎች የዱር አንስሳት ፓርኮች በተለይ አንበሳ አምልጦ መውጣት ያልተለመደ ቢሆንም፤ ፓርኮቹ ለከተማዋ ቅርብ በመሆናቸው ለእንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ክስተቶች ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንስሳት ፈጣን መንገድን ዘግተው እንደነበር በድርጊቱ የተደነቁ ተጓዦች ምስላቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ ማጋራታቸው ይታወሳል።
news-56206463
https://www.bbc.com/amharic/news-56206463
ለሳዑዲው ንጉሥ ስልክ የመቱት ባይደን ስለ ሰብዓዊ መብት አነሱ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ከሳዑዲ አራቢያው ንጉሥ ሳልማን ጋር ስለሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ተነጋገሩ።
ባይደን እና ንጉስ ሰልማን ባይደን የአሜሪካ 'ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅ' ከሆነችው ሳዑዲ ጋር በአዲስ መልክ ግንኙነት መጀመር ፈልገዋል። ባይደን አሜሪካ "በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶችና የሕግ መከበር" ዙሪያ ያላትን አቋም "አስረግጠው ተናግረዋል" ብሏል ዋይት ኃውስ። ባይደን ወደ ሳዑዲ ስልክ የደወሉት የጃማል ካሾግጂን ግድያ የተመለከተ አንድ ምስጢራዊ መረጃ ካነበቡ በኋላ ነው። በቅርቡ ይለቀቃል የተባለው መረጃ በጃማል ኻሾግጂ ግድያ ዙሪያ የሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ እጅ አለበት ወይ የሚለውን የሚዳስስ ነው ተብሏል። ከባይደን በፊት አሜሪካን የመሩት ዶናልድ ትራምፕ ከሳዑዲ ጋር የቀረበ ግንኙነት ነበራቸው። መረጃው በ2018 ወጥቶ የነበረና በሲአይኤ የተገኘ ሲሆን ነገር ግን የወቅቱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተባብለውት ነበር። ባይደን ከሳዑዲ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት በአንዳንድ ጉዳዮች ዙሪያ ጠንከር ያለ አቋም ያንፀባርቃሉ ተብሏል። ጋዜጠኛው ጃማል ኻሾግጆ ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ውስጥ ሰውነቱ ተቆራርጦ መገደሉ ቢዘገብም የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ እጄ የለበትም ሲሉ በተደጋጋሚ አስተባብለዋል። የሳዑዲ ባለሥልጣናት ኻሾግጂን በሕይወት ይዘው እንዲመለሱ የተላኩ ሰዎች ናቸው በጭካኔ የገደሉት በማለት የሚቀርብባቸውን ክስ ያስተባብላሉ። የሳዑዲ መንግሥት በግድያው ተሳትፈዋል ያላቸውን አምስት ሰዎች በሞት እንዲቀጡ ከወሰነ በኋላ ወደ 20 ዓመት እሥር እንዲቀልላቸው አድርጓል። ባይደን ምን አሉ? ዋይት ኃውስ እንዳለው የኻሾግጂ ስም በስልክ ልውውጡ ላይ ባይነሳም "ፕሬዝደንቱ በቅርቡ ሳዑዲ የመብት ተሟጋቾችን ከእሥር በመልቀቋ አመስግነው፤ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት ላይ ያለትን አቋም አንፀባርቀዋል።" የሳዑዲ ሴቶች መብት አቀንቃኝ የሆነችው ሉጄይን ሃትሉል ከሶስት ዓመት እሥር በኋላ የተለቀቀችው በቅርቡ ነው። ነገር ግን ወደ ውጭ ሃገር መጓዝም ሆነ ለመገናኝ ብዙሃን ድምጿን መስጠት አትችልም። ሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን እንዴት ማጠንከር እንደሚቻል እንዲሁም በኢራን የሚደገፉ የሳዑዲ ጠላቶችን እንዴት መመከት እንደሚቻል መክረዋል። ምንም እንኳ ዋይት ኃውስ የስልክ ልውውጡን ሙሉ ፅሑፍ ይፋ ባያደርግም የሁለቱ መሪዎች የስልክ ንግግር ከዚህ በፊቱ ለየት ያል ሊሆን እንደሚችል ተንታኞች ይገምታሉ። ባይደን የኻሾግጂን ግድያ የተመለከተ ምስጢራዊ መረጃ ከደረሳቸው በኋላ ለሳዑዲው ንጉሥ ስልክ መምታቸው ግጥጥሞሽ አይደለም የሚሉ በርካቶች ናቸው። የሲአይኤው መረጃ ኤምቢኤስ በተሰኘ ቅፅል ስማቸው የሚታወቁት የሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን፤ በኻሾግጂ ግድያ እጃቸው እንዳለበት ያመለክታል ሲሉ በርካቶች ዘግበዋል። የኻሾግጂን ስም በግላጭ ማንሳት የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የበለጠ ሊያሻክረው ይችላል ተብሏል። ባይደን የሳዑዲው አልጋ ወራሽና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ ጫና ይደርስባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ልዑል አልጋ ወራሽ አንድ ቀን ምናልባትም በቅርቡ የሳዑዲ ንጉሥ ሆነው ሊሾሙ ይችላሉ። ጃማል ኻሾግጂ እንዴት ነበር የተገደለው? የ59 ዓመቱ ጋዜጠኛ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው ቱርክ፤ ኢስታንቡል ወደሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ቅጥር ግቢ ሲገባ ነበር። ኻሾግጂ ወደ ቆንስላ በፈረንጆቹ ጥቅምት 2/2018 ያመራው ቱርካዊቷን ዕጮኛውን ለማግባት የሚያስችሉ ወረቀቶች ለመቀበል ነበር። እንደ ሳዑዲ አቃቤ ሕግ 'ከሆነ ካሾግጂ በግዳጅ ከግቢው እንዳይወጣ ተደርጓል፤ መጠኑ ከፍ ያለ መድኃኒትም ተሰጥቶታል። ለሞቱ ምክንያት የሆነውም ይህ ነው። ከዚያም ሬሳው ተቆራርጦ ከቆንስላው ውጭ ላለ 'ተባባሪ' ተሰጥቶ ነበር። ቅሪቱ እስከዛሬ አልተገኘም።' ኻሾግጂ በአንድ ወቅት የሳዑዲ መንግሥት አማካሪና የንጉሣዊው ቤተሰብ ቅርብ ሰው ነበር። ነገር ግን ከሳዑዲ አገዛዝ ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት በፈረንጆቹ 2017 ሃገሩን ጥሎ ወደ አሜሪካ ተሰደደ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ የሚወጣ የሳዑዲው ልዑል ሞሐመድን ፖሊሲዎች የሚተች ወርሃዊ ዓምድ ያሳትም ነበር። ኻሾግጂ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጣው ላይ ባሳተመው ፅሑፍ የሳዑዲ መንግሥት ሊያስረኝ ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳለው ፅፎ ነበር። በመጨረሻው ፅሑፉ ደግሞ የሳዑዲን መንግሥት በየመን ግጭት ጣልቃ በመግባቱን ተችቶት ነበር።
news-49658875
https://www.bbc.com/amharic/news-49658875
መምህራንን ተክቶ ያስተማረው ወታደር እየተወደሰ ነው
ኬንያ ውስጥ በአንድ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህራን በስራ ገበታቸው ባለመገኘታቸው በአካባቢው የነበረ አንድ ፖሊስ ወደ ክፍል ውስጥ በመግባት ሲያስተምር የሚያሳየው ምስል የሃገሬውን ሰዎች በእጅጉ አስገርሟል።
ጃይረስ ሙሊማ ሒሳብ ሲያስተምር ኬንያውያንም ጀግናችን ነህ እያሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች እያሞካሹት ነው። ምስሉን በፌስቡክ ለህዝብ ይፋ ያደረገው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደገለጸው ጃይረስ ሙሊማ የተባለው የፖሊስ ሃይል አባል በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ላይ በሚገኝ ፎሮሌ በተባለ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ሂሳብ ሲያስተምር ነበር። • "እናቴ ኤች አይ ቪ እንዳለብኝ ሳትነግረኝ ሞተች" • ላጤ እናት መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የድርጅቱ ሃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ አካባቢው የደህንነት ስጋት አለበት በማለት መምህራኑ በስራ ገበታቸው ላይ እየተገኙ አይደለም። በዚህም ምክንያት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ያለምንም ትምህርት ተቀምጠው እንዲውሉ ተገደዋል። ''ከትምህርት ቤቱ ሃላፊ ፍቃድ ካገኘ በኋላ ጃይረስ ሙሊማ አምስተኛ ክፍል በመግባት የሂሳብ ትምህርት ሲያስተምር ነበር'' ብለዋል ሃላፊው። ትምህርት ቤቱ በሚገኝበት አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት ሽፍታዎች ድንገተኛ ጥቃት የሚያደርሱ ሲሆን ጥቂት ለማይባሉ ሰዎችም ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል። በርካታ ኬንያውያን ጃይረስ ሙሊማ የሰራው ስራ እጅግ የሚያኮራና ለሁላችንም ምሳሌ መሆን ያለበት ነገር ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ነው። • ፀረ-መውለድ ፍልስፍናን ያውቁታል? አንድ ኬንያዊ ያልተዘመረለት ጀግና ሲል አሞካሽቶታል። ጃይረስ ሙሊማ በድንበር አካባቢ የተከሰተውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ከተመደቡ የጸጥታ ሃይሎች አንዱ ሲሆን በትምህርት ቤቱ አካባቢ ጥበቃ ሲያደርግም ነበር ተብሏል። ጃይረስ የሂሳብ ትምህርት ሲያስተምር በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ወደ ትምህርት ቤት ለመምጣት ድፍረት የነበራቸው ጥቂት ሴት ተማሪዎች ብቻ ነበሩ ተብሏል።
news-49322808
https://www.bbc.com/amharic/news-49322808
ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል?
የአማራ ክልልን በማቋረጥ ትግራይን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው መስመር ዝግ ነው፤ አልተዘጋም የሚለው መከራከሪያ ከሰሞኑ የመወያያ ርዕስ ሆኗል።
የአማራ ክልል የመንገድና የትራንስፖርት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዳጆን ጨምሮ የሚመለከታቸው የዞን ባለስልጣናት መንገዱ አልተዘጋም ሲሉ፤ የትግራይ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ በበኩሉ በደህንነት ስጋት ምክንያት ህዝቡ አቅጣጫ ለመቀየር ተገዷል ይላል። •በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው •በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ የሰሜን ወሎ ዞን የመንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጸሃይነው ሲሳይ በአሁኑ ሰዓት ወደ መቀሌም ይሁን ወደ አዲስ አበባ ምንም አይነት የትራፊክ መስተጓጎል እንደሌለና ኃገር አቋራጭ አውቶብሶችም እንደተለመደው እያለፉ መሆኑንም አበክረው ይናገራሉ። መነሻቸውን ከወልዲያ አድርገው በኮረም በኩል ሰቆጣ የሚሄዱትም መደበኛ ስምሪታቸውን ይዘው እየሰሩ ነው የሚሉት አቶ ጸሃይነው፤ በሰሜን ወሎ ዞን በመንገድ መዘጋት ምክንያት የተቋረጠ የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖሩን ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም በጥቅምት ወር ላይ በአላማጣ ከተማ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ በጠየቁ የቆቦ ከተማ ወጣቶች የአላማጣ ቆቦ መስመር ለቀናት መዘጋት፣ እንዲሁም በወልዲያ በኩል ወደ ትግራይ ለበዓል ሲጓጓዙ የነበሩ በጎች በወጣቶች መዘረፍ፣ እንዲሁም ወደ ትግራይ ክልል ይጓዝ የነበረ ተሳቢ አማራ ክልል ውስጥ በወጣቶች እንዲቆም ተደርጎ ጭነቱ የመዘረፍ ሁኔታ ተከስቶ ነበር። በዚህም ምክንያት የፀጥታ ስጋት በመፈጠሩ ወደ ትግራይ ክልል ለመጓዝ በአፋር በኩል ተለዋጭ መንገዶችን መጠቀም ጀምረዋል የሚሉ ጉዳዮች በማህበራዊ ሚዲያ እየተነገረ ቢሆንም አቶ ጸሃይነው ይህ ከእውነት የራቀ ነው ይላሉ። አሽከርካሪዎች በአፋር በኩል ያለውን ተለዋጭ አማራጭ መንገድ መጠቀማቸውን አምነው ይህ ግን እንደሚባለው ሳይሆን ደሴ እና ደብረ ብርሃንን አቆራርጦ ከወልዲያ-አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ላይ ብዛት ያለው የፍጥነት መቀነሻ ግንባታ በመኖሩ ይህን ሽሽት የአፋሩን ተለዋጭ መስመር እንደማራጭ እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል ይላሉ "ከፍጥነት መቀነሻዎቹ ብዛት የተነሳ 'በአሽከርካሪዎች፣ በተሽከርካሪዎች እና በተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው። በሰዓታችን እየደረስን አይደለም' በማለት የታችኛውን [አፋር] ተለዋጭ መንገድ ሲጠቀሙ ነበር። እኛም ከፌደራል መንገዶች ባከስልጣን ጋር በመነጋገር የፍጥነት መቀነሻዎቹ እንዲነሱ ተደርጎ መንገዱ ክፍት ተደርጓል።" ይላሉ አቶ ጸሃይነው። የደቡብ ወሎ ዞን የሰላም እና ደህንነት መምሪያ ተወካይ ኃላፊ አቶ እጅጉ መላኬም በአቶ ጸሃይነው ሐሳብ ይስማማሉ ከትግራይም ወደ አማራ ክልል እንዲሁም ከአማራ ወደ ትግራይ ያሉ የተሽካርካሪዎች እንቅስቃሴ በተለመደው ቀጥለዋል ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ የአማራ ክልልን በማቋረጥ ትግራይን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘውን መስመር ዝግ አለመሆኑንና ምንም አይነት የፀጥታ ስጋት እንደሌለም አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። ከዚህ ቀደም በአንድ ወቅት ለጥቂት ሰዓታት መንገዶች የተዘጉበትን አጋጣሚ አንስተው እሱም ችግሩ ተቀርፎ ወዲያው ተከፍቷል ይላሉ። "በአንድ ወቅት ብቻ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን የፍጥነት መቆጣጠሪያ መቀነሻዎችን ሲያፈርስ የተቀየሙ ወጣቶች መንገዱ ለጥቂት ሰዓታት ዘግተውት ነበር። ከዚህ ውጪ እኛ የምናውቀው ችግር የለም" ብለዋል። •“በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር ከዚህ ቀደም ጤፍ እና በጎች ከመኪና ላይ ተወሰዱ የሚባለው ባለፈው ዓመት መጀመሪያ ላይ የተፈጠረና በጣም የቆየ መረጃና የአንድ ጊዜ ክስተት መሆኑንም ገልፀዋል። ባለፈው አመት ወጣቶች የፍጆታ እቃዎችን የጫኑ መኪኖችን አያልፉም ብለው መንገድ ዘግተው የነበረ ሲሆን በወቅቱም የፀጥታ ኃይሉን በማሰማራት እንዲሁም ከወላጆች፣ ከወጣቱና ከማህበረሰቡ ጋር በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች ችግሮቹን እንደፈቷቸው ያስረዳሉ። •ሁለት መልክ ያለው የጅግጅጋ የአንድ ዓመት ክራሞት ከዚህም በተጨማሪ ተዘረፍን ብለው አቤቱታ ላሰሙት ገንዘብ እንዲከፈላቸውና ከዚህም በተጨማሪ ጥፋቱን አጠፉ የተባሉ ወጣቶች ህግ ፊት እንዲቀርቡ መደረጉንና አሁንም በህግ የተያዘ ጉዳይ መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል። "ተከታትለን ያረምነው የአንድ ጊዜ ስህተት ነው። ይሄንን የሚያውክ ምንም አይነት ኃይል የለም። ይሄ ሁኔታ እንዲቀጥል እኛም አንፈቅድም፤ በኛ በኩል ምንም አይነት ስጋት የለም። ነገር ግን የተለየ ስጋት አለን የሚሉና ያላቸው እኛን ሊያናግሩን ይችላሉ" ብለዋል። የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽን፣ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አልማዝ ገብረጻዲቅ ከአቶ እጅጉ የተለየ ሃሳብ ነው ያላቸው። እሳቸው እንደሚሉት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የደህንነት ስጋቶች በመከሰታቸው ህዝቡ ሳይፈልግ የሚጓዝበትን መስመር ለመቀየር መገደዱን ይናገራሉ። "ከ2010 መጨረሻ ጀምሮ አንዳንድ የጸጥታ ችግሮች ስለነበሩ እና ኃላፊነት የሚወስድ አካል ስለሌለ ህብረተሰቡ የሚጠቀምበትን መስመር ለመቀየር ተገዷል" ሲሉ ወ/ሮ አልማዝ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአፋር ክልል የሚደረገው ጉዞ በሎጊያ፣ በሰመራ እና በአዋሽ በኩል ተደርጎ አዲስ አበባ እንደሚደርስ የሚናገሩት ወ/ሮ አልማዝ፤ ምንም እንኳ ይህ መስመር ርዝመቱ ቢጨምርም ህብረተሰቡ ይህን አማራጭ ለመውሰድ እንደተገደደ ያስረዳሉ። ለደህንነታቸው የሰጉና አቅም ያላቸው የህብረተሰቡ ክፍልም የአየር ትራንሰፖርት አማራጭን እየተጠቀሙ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ችግሩን ለመፍታት ከፌደራል መንግሥቱ እና ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር ውይይት መደረጉን ገልፀው ምንም የተቀየረ ነገር የለም ብለዋል። "ከነዚህ አካላት ጋር በነበረን ግምገማ መንግሥት ለምን ኃላፊነቱን እንዳልወሰደ አንስተን ነበር። እስካሁን ግን እንደ መንግሥት ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።" ሲሉ ተናግረዋል። የህዳሴ አውቶብስ ኃላፊዎች ማህበር አቶ ተዓምራት ዮሴፍ ማህበሩ ወደተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚያሰማራቸው ከ50 በላይ የሚሆኑ አውቶቡሶች እንዳሉት ገልፀው ከዚህ ቀደም መኪኖቻቸቸው መደበኛ መስመር በነበረው በደሴ በኩል ይጓዙ የነበረ ሲሆን ይህ ግን ከሶስት አመታት ወዲህ ተቀይሯል ይላሉ። "ባለፉት ሶስት ዓመታት በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ግን ከአዲስ አበባ፣ መተሃራ፣ አዋሽ፣ ከዛም በአፋር አድርገን ነው ወደ መቀለ የምንመጣው። ከአዲስ አበባ ወደ ሽሬ፣ ራማ፣ አድዋ እና አክሱም የሚጓዙ ተሽከርካሪዎችም የአፋርን መስመር ነው የሚጠቀሙት።" በማለት ይናገራሉ። •የሆንግ ኮንግ ፖሊስ፡ «ሰልፈኛ አስመስለን ፖሊስ አሰማርተናል» በአማራ ክልል በኩል አቆራርጦ የሚያልፈው እና ትግራይን ከመሃል ሃገር ከሚያገናኘው መንገድ የአፋርን መንገድ እንደአማራጭ ከመጠቀም በተጨማሪ ከመቀሌ ወደ ደሴ ይደረግ የነበረው ጉዞ እንዲቋረጥ ከተደረገ አንድ ዓመት ያህል እንደሆነውም ገልጸዋል። ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚያነሱት ጥቃት መድረሱን ነው። "ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች የትግራይ መሆናቸው ስለሚታወቅ እንዲቃጠሉ ይደረጋል አልያም የመኪናው መስታወት ይስበራል።" ይላሉ ይህም ለኪሳራ እንደዳረጋቸው ገልፀው "የፊተኛው የመኪና መስታወት ዋጋው ከ100 ሺ ብር በላይ ነው። 20 ሺ ብር ለማግኘት 100 ሺ እንከስራለን። የመንገደኞች ድህንነትም አደጋ ውስጥ ነበር። ተጓዦች እንዲወርዱ ይደርጉና መታወቂያቸው እየታዬ የሚዘረፉበት አጋጣሚ ነበር።" በማለት የጉዞ አቅጣጫ ለውጥ ወይም የአንዳንድ መስመሮች አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ የተደረገበትን ምክንያት ያስረዳሉ።
news-46388991
https://www.bbc.com/amharic/news-46388991
100 ሴቶች፡ የነጻነት ቅርጫት ፕሮጀክት
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሴቶች ውጥኖቻቸውን እንዳያሳኩ እክል የሚሆኑባቸው ቁሶች ምንድን ናቸው?
ቁሶቹን ስበው የቆሻሻ መጠያው ውስጥ ይጣሉ። ከዚያም ስለዚያ ቁስ ለመረዳት 'ይጎብኙ' የሚለውን ይጫኑ። ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ። መዋቢያ ቁሳቁስ "ወንዶች ፊታቸውን ሳያስውቡ ቢወጡ ምንም ነገር አይባሉም" ምቾች የሌለው ፋሽን "ሰዎች ለምን እንደሚያደርጓቸው አይገባኝም። ያማሉ፣ አይመቹም ደግሞም ቋሚ የሰውነት በሽታ ያስከትላሉ" ቤት ውስጥ የተዘጋጀ ምግብ "ሴት ልጅ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ብቻ ነው መሆን ያለባት የሚለው ሃሳብ ሰልችቶኛል" - ኤማ የቤት ውስጥ ሥራዎች "እኩልነት ከቤት ስለሚጀምር ወንዶች ተነስታችሁ ቤት አፅዱ።" ጡት መያዣ "መዋብ ግዴታዬ አይደለም። ያለእሱ ቆንጆም አዋቂም ነኝ̃።" - ሊዛ ዝነኛ ሰዎችን የማድነቅ ባህል "ሁሉም የቁንጅና ሞዴሎች ሰውነት አንድ ዓይነት ነው፤ ደግሞም ደስተኛ አይመስሉም። ይሰለቻል።"- ዌንዲ ጋብቻ "እንደኔ እንደኔ የቃልኪዳን ቀለበቶች በሴት መብት ተሟጋቾች ዘንድ የስድብ ያህል ናቸው። ምክንያቱም ቀለበት ያደረገች ሴት የሌላ ሰው ንብረት መሆኗን ስለሚያመለክት።" ማቲልድ ማህበራዊ ድረ ገፆች "ለታዳጊ ወጣቶች አዕምሮ ሰላም በጣም አደገኛ ነው። በተለይ ለሴቶች። ምክንያቱም ከእውነታ የራቁና አደገኛ በሆኑ አመለካከቶች ተከበዋል።" - ሮሻን በፆታ የተለዩ መጫወቻዎች "በፆታ የተከፋፈሉ መጫወቻዎች በሙሉ ወንዶችንም ሴቶችንም ልጆች የተወሰኑላቸውን ነገሮችን ብቻ እንዲወዱ ያደርጋሉ።" - አና ተጨማሪ ዕቃ የጭቆና መሣሪያዎች ምንድን ናቸው? 'የፀረ-ነፃነት ቆሻሻ መጣያ' የተሰኘውን አመላከከት ምን እነዳስጀመረው ለማየት የራስዎን መሣሪያ ያጋሩን። በመላው ዓለም የሚገኙ ሴቶች ህይወታቸውን ባሻቸው መንገድ እንዳይመሩ እክል የሚሆኑባቸው ቁሶች ምን እንደሆኑ እየጠየቅን ነው።
news-56036402
https://www.bbc.com/amharic/news-56036402
የትዊተር መሥራች እና ጄይ ዚ በአፍሪካ ቢትኮይን እንዲስፋፋ ገንዘባቸውን ፈሰስ አደረጉ
የትዊተር መሥራቾች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነው ጃክ ዶርሲ እና ራፐር ጄይ ዚ በአፍሪካ እና በሕንድ ቢትኮይን እንዲስፋፋ ከፍተኛ ገንዘባቸውን ፈሰስ ማድረጋቸውን ገለፀ።
ዶርሲ እንዳለው 23.6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ 500 ቢትኮይኖችን ቢትረስት (₿trust) ለተባለ ፈንድ መመስረቻነት ሰጥተዋል። ኳርትዝ የተሰኘው ድረ ገጽ እንደዘገበው ከሆነ ባለፉቱ አምስት ዓመታት በቢትኮይን ገበያ ከአሜሪካ በመቀጠል ስሟ የሚነሳው አገር ናይጄሪያ ናት። የአፍሪካ ትልልቅ ከተሞች ከሆኑት መካከል ጆሃንስበረግ፣ ሌጎስና ናይሮቢ የሚኖሩ ሰዎች ገንዘባቸውን ከአንድ አገር ወደ ሌላው ለማዘዋወር ቢትኮይንን እንደ ቀላል አማራጭ እንደሚወስዱት ቢቢሲ የሰራው ዘገባ ያሳያል። ይኹን እንጂ የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ ጉዳዩ ስላሳሰበው ባለፈው ሳምንት በክሪፕቶከረንሲ ከሚገበያዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካውንቶች በሙሉ እንዲዘጉ ወስኗል። ባለፈው ሳምንት የኤለን መስክ የመኪና ኩባንያ ተስላ 1.5 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ ቢትኮይን በታህሳስ ወር መግዛቱን አስታወቆ ነበር። ኩባንያው ገንዘቡን ወደፊት መቀበል እንደሚጀምርም ጨምሮ ይፋ አድርጓል። ይህ ዜና እንደተሰማ የቢትኮይን ዋጋ በ 17 በመቶ ወደ 44 ሺህ 220 አሻቅቧል ተብሏል። ቢትኮይን ምንድነው? ቢትኮይን ማለት በቀላል ቋንቋ፤ ዲጂታል ገንዘብ+መገበያያ በማለት ማጠቃለል ይቻላል። ይህ መገበያያ በኪሳችን ተሸክመን እንደምንዞረው የብር ኖት ወይም ሳንቲም ሳይሆን 'ኦንላይን' የሚቀመጥ ዲጂታል ገንዘብ ነው። • በአሁኑ ወቅት በጣም ተፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘርፍ ሥራዎች የትኞቹ ናቸው? ሌላው የቢትኮይንና የተቀሩት የክሪይፕቶከረንሲዎች ልዩ ባህሪ በመንግሥታት እና በባንኮች አለመታተማቸው እንዲሁም ቁጥጥር አለመደረጉ ነው። ቢትኮይን የሚፈጠረው 'ማይኒንግ' በሚባል ሂደት ነው። በመላው ዓለም በኔትወርክ በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች ቁጥጥር ይደረግበታል። ቢትኮይንን የፈጠረው ግለሰብ/ቡድን በዓለም ላይ 21 ሚሊዮን ቢትኮይኖች ብቻ እንዲፈጠሩ ገደብ እንዳስቀመጡ ይታመናል። የብሎክቼይን መረጃዎች እንደሚያሳዩት እስካሁን 17 ሚሊዮን ያህል ቢትኮይኖች ማይን ተደርገዋል። ማይክሮሶፍት፣ የፈጣን ምግብ አቅራቢዎቹ ኬኤፍሲ እና ሰብዌይ፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ። በቢትኮይን አማካኝነት ክፍያ ሲፈጸም የገዢውን ማንነት ይፋ አለማድረግ ያስችላል። ይህም በርካቶች በኢንተርኔት አማካኝነት ማንነታቸውን ሳይገልጡ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ስለሚያስችላቸው በቢትኮይን አማካኝነት የሚደረጉ የንግድ ልውውጦች ቁጥር እጅጉን ጨምሯል። ቢትኮይን እንደ ስጋት? አሸረትስ በተባለ የፋይናንስ ተቆጣጣሪ ኩባንያ ውስጥ ባለሙያ የሆኑት ብራደሊይ ራይስ በቢትኮይን ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር እንደማይደረግበት ያስታውሳሉ። ቢትኮይንን በመጠቀም የገዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ በየትኛውም ሰዓት እና በየትኛውም ስፍራ የቢትኮይን ዝውውር ማድረግ ይቻላል። የገዢው ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት መፈጸም ይቻላል። በዚህም ሕገ ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያዎች እና እጾችን ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ፣ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና አሸባሪዎችን ለመደገፍ ያስችላል በማለት ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪይፕቶከረንሲዎች ላይ ያላቸውን ስጋት የሚያነሱ በርካቶች ናቸው። በሌላ በኩል በርካታ የፋይናንስ ባለሙያዎች ቢትኮይን ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር አለመደረጉ ተፈላጊነቱን እንደጨመረው ያወሳሉ።
news-55156379
https://www.bbc.com/amharic/news-55156379
ትግራይ ፡ እጃቸውን ለመንግሥት የሰጡት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ማን ናቸው?
የኢትዮጵያ ፌደራል ሠራዊት የትግራይ ክልል ዋና ከተማን ባለፈው ቅዳሜ ከተቆጣጠረ በኋላ እየተፈለጉ ካሉት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግሥት እጃቸውን መስጠታቸው ተገልጿል።
የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነው የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለዓመታት በክልልና በፌደራል በመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ሲሆን በመጨረሻም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው አገልግለዋል። ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ባለፈው ዓመት ሊደረግ የነበረው ምርጫ ወደ ሌላ ጊዜ በመሸጋገሩ ሳቢያ፤ በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ በነበረው በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል ተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎ ወደ ትግራይ በመመለስ ባለፈው ዓመት ሠኔ ወር መጀመሪያ ላይ ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል። በወቅቱ ምርጫ ማካሄድ አለመቻሉና የተፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ያስችላሉ የተባሉ አማራጮችን ለመፈለግ የተደረገውን እንቅስቃሴ የተቃወሙት ወይዘሮ ኬሪያ በትግራይ ክልል ቴሌቪዥን ላይ ወጥተው ተቃውሟቸውን አሰምተው ነበር ስልጣን የለቀቁት። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሒም በወቅቱ "ሕገ መንግሥት ከሚፈቅደው ውጪ አምባገነናዊ መንግሥት ሲመሰረት ተባባሪ ላለመሆን እና ሕገ መንግሥት በየቀኑ ከሚጥስና አምባገነንነትን ከሚያራምድ ቡድን ጋር ለመስራት ፈቃደኛ ስላልሆንኩ ነው" በሚል በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀው ነበር። ወይዘሮ ኬሪያ የፌደራል መንግሥት ኃላፊነታቸውን ለቀው ወደ ትግራይ ከተመለሱ በኋላ የፌዴሬሽን ምክር ቤት "ሕገወጥና ተፈጻሚነት የሌለው" ባለው በትግራይ ክልል በተናጠል በተካሄደው ክልላዊ ምርጫ ላይ ተሳትፈው ለክልሉ ምክር ቤት አባልነት መመረጣቸው ተነግሯል። ወይዘሮ ኬሪያ ከሳምንታት በፊት መንግሥት ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀምና በአገር ክህደት ወንጀል የመያዣ ትዕዛዝ ካወጣባቸው 96 ግለሰቦች መካከል አንዷ ናቸው። ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ማን ናቸው? በኤርትራዋ መዲና በአሥመራ ከተማ የተወለዱት ወይዘሮ ኬሪያ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በኢኮኖሚክስ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኢንቫይሮታል አንትሮፖሎጂ ማግኘታቸው ይነገራል። ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በትግራይና በፌደራል መንግሥቱ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ በነበረው የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ መግባት ከቻሉ ጥቂት ሴቶች አንዷ ናቸው። ወይዘሮ ኬሪያ የአገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን አካላት ከሁኑት ሁለት ምክር ቤቶች የላይኛው ምክር ቤት የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ከሁለት ዓመታት በላይ የሰሩ ሲሆን፤ በዚህ የኃላፊነት ደረጃም ሁለተኛዋ ሴት ነበሩ። ወይዘሮ ኬሪያ ወደ ከፍተኛው የፌደራል መንግሥቱ የስልጣን ቦታ ከመምጣታቸው በፊት ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ክልል ከወረዳ አንስቶ ባሉ የአስተዳደር መዋቅሮች ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ ሰርተዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትን አፈጉባኤ ከመሆናቸው በፊት በዋናነት በትግራይ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም በትግራይ የደቡብ ምሥራቅ ዞና የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። መነሻ በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው አለመግባባት ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ መካረሩ ይታወሳል። ተከትሎም የፌደራል መንግሥቱን ውሳኔ ባለመቀበል ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተካሄደው የተናጠል ምርጫ የፌደራል መንግሥቱን ተቀባይነት ካለማግኘቱ በተጨማሪ በአገሪቱ ምክር ቤቶች ሕገ ወጥ ተብሎ ውድቅ ተደርጓል። የክልሉ ባለስልጣናትም በበኩላቸው ፌደራል መንግሥቱ በኮቪድ ሰበብ ምርጫን ማራዘሙ "ሕገመንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ነው ስልጣኑን አራዝሟል" በማለት የፌደራሉን መንግሥት "ሕገወጥ" ብለው እውቅና መንፈጋቸው አይዘነጋም። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የክልሉን አስተዳዳሪዎች ሕገ መንግሥቱን በመጣስና ከሕግ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በማለት የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ክልል ክልል አስተዳደር ጋር የነበረውን የቀጥታ ግንኙነት አቋርጦ የበጀት ዕቀባ ጥሎ ነበር። አለመግባባቱና መካሰሱ ያለማቋረጥ በቀጠለበት ሁኔታ ጥቅም 24/2013 ዓ.ም ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ክልል በነበረው የፌደራሉ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት በትግራይ ክልል ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ይታወሳል። መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ባለውና ከሦሰት ሳምንታት በላይ በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል። ባለፈው ቅዳሜ የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ሰር ከዋለች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳውቀዋል።
news-49328060
https://www.bbc.com/amharic/news-49328060
የሆንግ ኮንግ ፖሊስ ሰልፈኛ አስመስሎ ፖሊስ ማሰማራቱን አምኗል
የሆንግ ኮንግ ፖሊስ እሁድ ዕለት በከተማዋ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ በማስመሰል የፖሊስ መኮንኖችን ማሰማራቱን አምኗል።
የፖሊስ አፈ-ቀላጤ የሆኑት ኃላፊ 'አዎ አሰማርተናል' ሲሉ አምነው 'ይህንን ያደረግነው አመፀኞችን ለመበታተን ነው' የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሆንግ ኮንጉን ተቃውሞ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከፖሊሶች ጋር በመተባበር ሰልፈኞችን ሲያስሩ ከታዬ በኋላ ነው ነገሩ የከረረው። ተቃዋሚዎቹ ጉዳዩን ይጣራልን ሲሉ አቤት ብለዋል። • ተቃውሞ በቻይና፡ መንግሥት 'የውጭ ኃይሎችን' እየወቀሰ ነው ቻይና ወንጀል ፈፅመው ወደ ሆንግ ኮንግ የሚያመሩ ሰዎችን የሆንግ ኮንግ አስተዳደር አሳልፎ እንዲሰጣት የሚያዝ ሕግ ለማውጣት ማቀዷን ተከትሎ ነው የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች አደባባይ የከተሙት። ይኸው ከሁለት ወራት በኋላም ሆንግ ኮንግ በሕዝባዊ ተቃውሞ እና እሥር በመናጥ ላይ ትገኛለች። ሰኞ ዕለት ሰልፈኞች የሆንግ ኮንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን በቁጥጥር ሥር በማዋላቸው ምክንያት በረራዎች እንዲሠረዙ ሆነዋል። ምንም እንኳ የሃገሪቱ ባለሥልጣናት አውሮፕላን ማረፊያው ሥራ ጀምሯል ቢሉም በርካታ አየር መንገዶች አሁን በረራቸውን እንደሠረዙ ናቸው። • የሆንግ ኮንግ የሕዝብ እንደራሴዎች ተቧቀሱ የፖሊስ አፈ-ቀላጤ እና ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ታንግ ፒንግ-ኩዌንግ 'ባንዳ ፖሊሶች' ማሰማራታቸውን ደግፈው ተከራክረዋል። «እኛ ፖሊሶቻችን ሰልፍ ውስጥ ገብተው አመፅ እንዲቀሰቅሱ አይደለም ያሰማራናቸው፤ እጅግ አመፀኛ የሆኑ ሰልፈኞችን ለቅመው እንዲያመጡልን እንጂ።» አንዲት ሴት ዓይኗ ግድም ተመታ ደም ሲፈሳት የሚያሳይ ፎቶ በማሕበራዊ ድር-አማባዎች መሰራጨቱን ተከትሎ ፖሊስ ወቀሳ እየዘነበበት ይገኛል። ፖሊስ 'ከደሙ ንፁህ ነኝ' ቢልም። መቆሚያ ባላገኘው የሆንግ ኮንግ ሕዝባዊ ተቃውሞ የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ ሰልፈኞች መጎዳታቸው እየተዘገበ ነው። የቻይና ሕግ የሆንግ ኮንግን ነፃነት የሚገዳደር ነው፤ አልፎም ቻይና የፖለቲካ ሰዎችን ማሠር ሲያሻት ልትጠቅመበት ያሰበችበት ሕግ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ይተቻሉ። • ባህር አቋራጩ የቻይና ድልድይ ተከፈተ
news-41884082
https://www.bbc.com/amharic/news-41884082
ካለሁበት 8፡ በኦሎምፒክ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ የበረዶ ሸርተቴ ተወዳዳሪው ሮቤል
ሮቤል ተክለማርያም እባላለሁ የምኖረው ከጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ የአራት ስዓት መንገድ ርቀት ላይ በምትገኘው ናጋኖ በምትባል ከትማ ውስጥ ነው።
ሮቤል ተክለማርያም እዚህ የበረዶ ሸርተቴ (አልፓይን ስኪንግ) አስተምራለሁ ትምህርት ቤቱንም በበላይነት የምቆጣጠረው እኔ ነኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚህ ሃገር የመጣሁት ከአስር ዓመታት በፊት ሲሆን ጠቅልዬ ከመጣሁ ደግሞ ሶስት ዓመታትን አስቆጠርኩ። አሜሪካ በነበርኩበት ወቅት ሜይድ ክለብ የሚባል የፈረንሳይ ድርጅት ውስጥ የበረዶ ሸርተቴ አስተምር ነበር። በተጨማሪም ስፖንሰሮቼም ነበሩ። ለድርጅቱም በኢንዶኔዥያ፣ አውስትራሊያ፣ ቱርክ፣ ቱኒዝያ፣ ታይላንድ እና ቻይና ውስጥ ሰርቻለሁ። ከኦሎምፒክ ውድድሬ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ጃፓን ለሚደረግ ዓለም አቀፍ የሻምፒዮና ውድድር ዝግጅት እያድረግኩ ባለበት ወቅት ይሔው ድርጅት አሜሪካ መጥቼ እንዳስተምር ጠየቁኝ። ውድድሩ ላይ ብቻ ማተኮር እንድምፈልግ ስነግራቸው ጃፓንም የበረዶ ሸርተቴ ማስተማሪያ እንዳላቸው ሳውቅ በክረምት ለማስተማር መጣሁ። ከበረዷማው ኮሎራዶ ብመጣም የጃፓን የበረዶው ጥራትም ሆነ ብዛት በጣም ነው ያስደነቀኝ። በዓለም ምርጥ በረዶ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው። የተወለድኩት አዲስ አበባ ሲሆን እስከ ሶስተኛ ክፍልም የተማርኩት ቅዱስ ዮሴፍ የወንዶች ትምህርት ቤት ነው ። በጊዜው ከደርግ መንግሥስት ጋር ተያይዞ በነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እናቴ ኒው ዮርክ ወዳለው የተባበሩት መንግስታት ቢሮ ተዛወረች። በኒው ዮርክ የባህል ግጭት ነው የደረሰብኝ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ህፃን ልጅ ውጭ ተጫውቶ፤ ተንቦጫርቆ ነው የሚያድገው። የኒው ዮርክ ኑሮ አንድ አፓርትመንት ውስጥ ተቆልፎ መዋል ነው። ከዚያ በላይ እንግሊዝኛ ቋንቋ አለመቻሌ ሁኔታውን አከበደብኝ። የመጀመሪያ ትምህርት ቤት የሄድኩባት ቀን በህይወቴ መጥፎ ከምላቸው ቀናቶች አንዷ ናት። አስታውሳለሁ የጥዋቱን ክፍለጊዜ ከተማርን በኋላ ለምሳ ወጣን። ልጆቹ ሲያዋሩኝ የምመልሰው በአማርኛ ነበር። ሰምተውት የማያውቁት ቋንቋ በመሆኑ ሁሉም መሳቅ ጀመሩ።ተሳቅቄም እያለቀስኩ ከትምህርት ቤት ወጥቼ መንገዱን ባላውቅዉም እግሬ ወዳመራኝ ሄድኩ። በህይወቴ የማልረሳት ሴትም ያጋጠመችኝ በዚሁ አጋጣሚ ነበር። ሁኔታዬ ግራ ቢያጋባት ልትረዳኝ መኪና ውስጥ አስገባችኝ። እዬሄድንም እያለ እንደ እድል ሆኖ የምኖርበትን ህንፃ ሳየው ጠቆምኩዋት። የህንፃው አከራይ እንዳየኝ አወቀኝ። ከዚያ ደግሞ ሌላ ጭንቀት፤ ለምን ትምህርት ጠፍቼ እንደመጣሁ በውቅቱ ቤት ለነበረችው አክስቴ ምን ብዬ ልመልስ። እናም የዶሮ አጥንት አንቆኝ ነው አልኩ፤ እምቡላንስ ተጠራ፤ እናቴም ተጠራች። ባጭሩ እዛ ትምህርት ቤት ተመልሼ አልሄድኩም። በአማራጩ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዳሻሽል በግል ቋንቋ የሚያስተምሩ እስተማሪ ጋር ተላኩ። ከዚያም ሌክ ፕላሲድ የሚባል አዳሪ ትምህርት ቤት ገባሁ። እንግዲህ በዚሁ አጋጣሚ ነው የበረዶ ሸርተቴ ስፖርትም ጋር የተዋወቅኩት። ገና እንዳየሁት ነው በፍቅር የተለከፍኩት። የበረዶ ሸርተቴ ውድድርንም ጀመርኩ። በሀገር አቀፍ የተለያዪ ውድድሮችም ላይ መሳተፍ ጀመርኩ። ዪኒቨርስቲም በዛው ቀጠልኩብት፤ የአትሌቲክስ የትምህርት እድል በማግኘቴ በበረዶ ሸርተቴ አሉ ከሚባሉት ከአስሩ ዪኒቨርስቲዎች በአንዱ ነው ። ለኢትዮጵያ መወዳደር ያሰብኩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበርኩበት ወቅት ነው። በምወዳደርበት ወቅት ከየት ነው የመጣው የሚሉ ጥያቄዎች ለአሰልጣኜ ይሰነዘርለት ጀመር። ከኢትዮጵያ ነው ሲላቸው አንደኛው በቀልድ መልኩ ለኢትዮጵያ ቢወዳደር የሚል አስተያየት ሰጠ። ለኔ ግን ቀልድ አልነበረም። በዛን ወቅት ስለ አበበ ቢቂላ እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ እየተማርኩ የነበረበት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያዊ ዜግነቴን ባልቀይርም፤ እንዴት ኢትዮጵያን መወከል እንደምችል ባጠያይቅም መልስ የሚሰጠኝ አጣሁ። ከዩኒቨርስቲ በኃላ የኬንያ የበረዶ ሸርተቴ ተወዳዳሪዎችን ሳይ እንደገና ለኢትዮጵያ መወዳደር እንዳለብኝ ወሰንኩ። በውቅቱም በስፖርቱ ከፍትኛ ደረጃ የደረስኩብት ጊዜ ነበር። ሳጠያይቅም ከዓለም ዓቀፍ የበረዶ ሸርተቴ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ እውቅና ያለው የበረዶ ሸርተቴ ማህበር መመስረት እንደሚያስፈልገኝ ነገሩኝ። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን እንዲሁም የወጣቶች ስፖርትና ሚኒስትርን መወዳደር እንደምፈልግ ነገርኩዋችው። ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጀምሮ የነበረው ምላሽ ቀና ቢሆንም የበረዶ ሸርተቴ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለመኖሩ እንደ አዲስ ፌዴሬሽን ማቋቋሙ ብዙ አመታትን ፈጀ። የኦሎምፒክ ውጤቴ ጥሩ እልነበረም ለኔ ግን ዋናው ነገር ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የማትታወቅበት ስፖርት መወከሉ ነበር። ይህ እጋጣሚም ከ 22 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሬ የመመለስን አጋጣሚን ፈጥሮልኛል። ብዙ ዓመት ርቄ ስለቆየሁ ከህዝቡ ጋር ለመግባባት ይከብደኛል የሚል ፍራቻ ነበረኝ። በተቃራኒው ከአሜሪካ በበለጠ የሃገር ስሜት የተሰማኝ ኢትዮጵያ ነው። ወደ ኢትዮጵያ ብመላለስም አሁን ቋሚ መኖሪያዬ ጃፓን ናት። ጃፓንና ኢትዮጵያ በባህል በጣም የሚመሳሰሉ ህዝቦች ናችው። ለሰዎች ያላቸው ከበሬታ፣ ስላምታ ሲያቀርቡ ጎንበስ የሚሉበት መንገድ እንዲሁም የሻይ አፈላል ስርዓታችው ከኛ ቡና ጋር ተመሳሳይ ነው። ጃፓን የምትመች ሃገር ናት። የምኖርበት ከተማ በተራራና በህይቅ የተከበበች ናት። በተለያዩ ወቅቶችም መልክአምድሩ መለያየቱ ስፍራው የልብ እርካታን ይሰጣል። ይህ ቦታም ልጄን ልያን ያፈራሁብት ስለሆነ ልዩ ትርጉም አለው። ከልያ በተጨማሪ የእንጀራ ልጄም ሌላ ስጦታዬ ናት። ምግባቸውንም በጣም ነው የምወደው፤ በተለይም ከሩዝና ጥሬ አሳ የሚሰራው ሱሺ ፤ እንዲሁም ከአትክልትና ስጋ የሚሰራው ያኪኒኩ የኔ ምርጫ ናቸው። ጃፓን በስርዓት የትሞላች፤ ሁሉ ነገር የደራጀች ሀገር ናት። ከኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከዓለም የሚለያት የሚገርም የስራ ባህላቸው ነው። ከ30 ሃገራት በላይ ሃገራትን አይቻለሁ ይሁን እንጂ እንደዚህ አይነት የስራ ባህል አስተውዬ አላውቅም። ከዚህ በተጨማሪ ለጊዜ የሚሰጡት ትኩረት ያስደንቃል። ስከንዶች ትርጉም አላችው። ለምሳሌ አውቶብሱ ይመጣል ከተባለበት ሰከንድ አታልፍም። ሮቤል ተክለማርያም ለቢቢሲ ጋዜጠኛ ጥበበሥላሴ ጥጋቡ እንደነገራት። ለጥበበስላሴ ጥጋቡ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 9፡ በኑሮዬ ደስተኛ ብሆንም ለቁርስ ቋንጣ ፍርፍር ባገኝ እወዳለሁ ካለሁበት 10፡ የምመኘው በአንድነታችን ተዋደንና ተከባብረን በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኖር ነው
48918365
https://www.bbc.com/amharic/48918365
ታዳጊዎቹ በገጣጠሟት አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ተነስተው ካይሮ ገቡ
ደቡብ አፍሪካውያን ታዳጊዎች ራሳቸው በገጣጠሟት ስሊንግ 4 አውሮፕላን ከኬፕታወን ደቡብ አፍሪካ ተነስተው ስድስት ቀን ያህል ከበረሩ በኋላ ካይሮ ግብጽ ገብተዋል።
አራት ሰዎችን የመሸከም አቅም ያላትን ይህች አውሮፕላን 20 ከተለያየ ዘርና ቀለም የመጡ ተማሪዎች ናቸው የገጣጠሟት። የአብራሪ ቡድን አባላቱ በእስካሁን በረራቸው ከ12ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሸፈኑ ሲሆን ናሚቢያ፣ ማላዊ፣ ኢትዮጵያ፣ ዛንዚባር፣ታንዛኒያ እና ኡጋንዳን ረግጠዋል። የ17 ዓመቷ ፓይለት ሜጋን ዌርነር የዩ ድሪም ግሎባል ፕሮጀክት መስራች ስትሆን በእስካሁን ስኬታቸው መደነቋን ትናግራለች። "በቆምንበት ሀገር ሁሉ ልዩነት በመፍጠራችን ክብር ይሰማኛል።" አክላም "የዚህ ፕሮጀክት ዓላማ አፍሪካውያን ምንም ነገር ለመስራት አእምሯችንን ካዘጋጀነው እንደምንችል ለማሳየት ነው" ብላለች። • የኤሌክትሪክ ኃይል በፈረቃ መከፋፈሉ መቅረቱ ተገለፀ • ከኮርማዎች ጋር በተደረገው ሩጫ ሦስት ሰዎች ተጎዱ እነዚህ ታዳጊዎች ከሚያበሯት አውሮፕላን ጎን ለጎን ሌላ ስሊንግ 4 አውሮፕላን በባለሙያ አብራሪዎች የበረረ ሲሆን በመንገዳቸው ላይ የተለያዩ የማነቃቂያ ንግግሮችን እያደረጉ ድካምና መሰላቸት እንዳይሰማቸው ሲያደርጉ ነበር። ተማሪዎቹ አውሮፕላኑን የገነቡት ደቡብ አፍሪካ በሚገኝ አውሮፕላን ማምረቻ ከተሰራ ቁሳቁስ ሲሆን ለመገጣጠምም ሶስት ሳምንት ፈጅቶባቸዋል። ግንባታው በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን የአውሮፕላን ክፍሎች መገጣጠም ያካትት ነበር። የሜገን አባት ዴስ ዌርነር፣ የንግድ አውሮጵላን አብራሪ ሲሆኑ ይህንን አውሮፕላን አንድ ሰው ሊገጣጥም ቢፈልግ 3000 ሰዓት ይፈጅበታል ሲሉ ተናግረዋል። ሜጋን የዚህ ጉዞ አስገራሚ ነገሮች ተግዳሮቶቹ ናቸው ትላለች። ኢትዮጵያ በሄዱበት ወቅት አዲስ አበባ ነዳጅ ማግኘት አልቻሉም ነበር። "እዚያ ስንደርስ አብሮን የሚበረው ድጋፍ ሰጪ አውሮፕላን ነዳጅ ማፍሰስ ጀመረ። ስለዚህ እኔና ድሪያን ቫን ዴን ሂቨር ብቻ ጉዞውን ቀጠልን ብላለች" ሜጋን። በሱዳን ሰማይ ላይም ስንበር በሀገሪቱ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት የተነሳ ስጋት ገብቶን ነበር ስትል ትናገራለች። ሜጋን የማብረር ፈቃድ ካገኙት ስድስት የቡድኑ አባላት መካከል አንዷ ስትሆን ስድስቱም እየተፈራረቁ ክንፎቿን በአፍሪካ ካርታ ያስጌጠችውን አውሮፕላን አብርረዋል። • ''ምን እንደተፈጠረ አልገባኝም" አትሌት ሃጎስ ገ/ሕይወት አብራሪዎቹ ፍቃድ ሲሰጣቸው ከመሬት የሚኖራቸውን ርቀት የሚወስን የነበረ ሲሆን ከፍ ብሎ በደመና ውስጥ መብረር አልተፈቀደላቸውም ነበር። የመጨረሻው የፓይለቶቹ በረራ ከአዲስ አበባ ግብፅ በአስዋን በኩል የነበረ ሲሆን ይህም አብራሪዎቹን የፈተነ እንደነበር ተጠቅሷል። "ያለ ድጋፍ ሰጪ አውሮፕላን፣ ሁለት አዳጊዎች፣ እኔና ድሪያን ቫን ዴን ሂቨር ለአስር ሰዓታት ያህል በረናል" ብላለች ሜጋን። ሁለቱ አብራሪዎች ግብፅ የአየር ክልል ውስጥ ከገቡ በኋላ ስለመንገዳቸው የአየር ንብረት መረጃውን የሚሰጣቸው ስርዓት ችግር አጋጥሞት ነበር። ስለዚህም በካይሮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደ እቅዳቸው ከማረፍ በካይሮ ቅርብ ርቀት የሚገኝ የአየር ማረፊያ ማረፍ የተሻለ መሆኑን በመወሰን እዚያ አርፈዋል። ይህ ትንሽ መረባበሽ ፈጥሮ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን የተፈጠረውን ነገር ተቆጣጥረው በሰላም ማረፍ ችለዋል። አውሮፕላናቸው ካረፈች በኋላ የተፈጠረውን ሲመረምሩ በአግባቡ ያልተያያዘ መስመር በመኖሩ ችግሩ መፈጠሩን ተረድተዋል። ካይሮ እንደደረሱ የግብፅ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው የሞከሩ ሲሆን ፓስፖርታቸውንና አብራሪ ፈቃዳቸውን ተነጥቀው ከአራት ሰዓት በኋላ የተፈጠረው አለመግባባት ተፈትቶ ነዳጅ ሞልተው በአስዋን በኩል ወደካይሮ በመብረር የካይሮ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አርፈዋል።
news-53577109
https://www.bbc.com/amharic/news-53577109
ማልታ ከባሕር ላይ የታደገቻቸው 65 ስደተኞች ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
የማልታ የጠረፍ ጠባቂዎች ከሜዲትራንያን ባሕር ላይ ከታደጓቸው 94 ስደተኞች መካከል ሁለት ሦስተኛዎቹ በኮቪድ-19 የተያዙ መሆናቸው ተገለፀ።
ለስደተኞቹ ምርመራ የተደረገው እንደደረሱ ሲሆን 65 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ከስደተኞቹ መካከል ሃያዎቹ ነፃ መሆናቸው ሲረጋገጥ ዘጠኙ ደግሞ ውጤታቸውን ገና አልተቀበሉም ተብሏል። ስደተኞቹ ከኤርትራ፣ ሞሮኮ እና ሱዳን የሄዱ መሆናቸው ሲገለፅ፣ በማልታ የድንበር ጠባቂዎች እይታ ውስጥ እስኪገቡ ድረስ ባሕር ላይ ለ30 ሰዓታት መቆታቸው ተገልጿል። ስደተኞቹ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ እንደሚቆዩም ታውቋል። "በጀልባ ማልታ የደረሱት ስደተኞች ወዲያውኑ ለ14 ቀን ያህል ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ አድርገናል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ተለይተው እንዲቀመጡ ሲደረግ ቀሪዎቹ ደግሞ ክትትል ይደረግላቸዋል" ያሉት የማልታ ጤና ሚኒስትር ናቸው። 94 የስደተኞች ቡድን ከሊቢያ በአነስተኛ ጀልባ መነሳቱ ተገልጿል። ስደተኞቹ በድንበር ጠባቂዎቹ የተገኙት የመዛልና የተሰፋ መቁረጥ ምልክት ካሳዩ በኋላ መሆኑንም አክለው ተናግረዋል። "ቡድኑ ማልታ የደረሰው በጋራ ሲሆን ከመመርመራቸው በፊት ከጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ ግንኙነት ነበራቸው" ያሉት ሚኒስትሩ የአካባቢው ሰዎች በዚህ የተነሳ በኮቪድ-19 ሊጋለጡ ይችላሉ የሚለውን ስጋት ውድቅ አድርገዋል። እንደ ፈረንሳይ የዜና ወኪል ከሆነ እነዚህ ስደተኞችን ጨምሮ በማልታ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች 99 ብቻ ናቸው። በዚህች አነስተኛ ደሴት ኮቪድ-19 የተያዘ የመጀመሪያው ሰው የተገኘው በመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሲሆን እንዲህ ቁጥሩ በዛ ያለ ሰው በአንድ ጊዜ በቫይረሱ መያዙ ሲታወቅ የመጀመሪያው ነው ተብሏል። በማልታ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ ብቻ ነው። ቫይረሱ በአውሮፓ ሲሰራጭ 450 000 ነዋሪ ያላት ይህች ደሴት ድንበሮቿን ሙሉ በሙሉ ዘግታ ስደተኞች የመታደግ ሥራዋንም ሙሉ በሙሉ አቋርጣ ቆይታ ነበር።
news-52831184
https://www.bbc.com/amharic/news-52831184
በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች ሥራ ሊያጡ እና የአገር ውስጥ ምርት እድገት 11.2 በመቶ ሊቀንስ ይችላል
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ከበድ ያለ ነው። ግዙፍ የምጣኔ ሃብት አላቸው የሚባሉት እንደ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንገድደም እና ሕንድ ባሉ አገራት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው ቫይረሱ ባመጣው ሰበብ ሥራ ፈላጊ ሆነዋል።
የብር የመግዛት አቅም እየቀነሰ ነው ወረርሽኙ በአገራችንም ምጣኔ ሃብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ግልጽ ነው። ወረርሽኙ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ክፍል መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥናት ሠርተዋል። • "ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ የገደለው ፖሊስ 'አስቦና አቅዶ' ነው" የፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጥናት እንዳሳየው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የአገሪቱን ምጣኔ ሃብት 5.6 በመቶ ሊጎዳው እንደሚችል ይጠቁማል። የአገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) በአማካይ 11.2 በመቶ ሊላሽቅ ይችላል "ልክ አውሮፓ እና አሜሪካ እንደተስፋፋው፤ ቫይረሱን እኛም አገር ቢሰራጭ ኢኮኖሚያችን እሱን የሚሸከምበት አቅም የለውም። ከሚጠበቀው በላይ ነው የሚጎዳን። ምክንያቱም እነሱ [ምዕራባውያን አገራት] የተሻለ ኢኮኖሚ፣ የሰው ኃይል እና ቁጠባ አላቸው። እኔ ባሰላሁት መሠረት ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ እጅግ ትልቅ ነው" ይላሉ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰሩ አለማየሁ ገዳ። የፕሮፌሰሩ ጥናት እንደጠቆመው ኢትዮጵያ በ2020 (በአውሮፓውያን አቆጣጠር) የበጀት ዓመት የአገር ውስጥ ምርት እድገት (ጂዲፒ) በአማካይ 11.2 በመቶ ሊላሽቅ ይችላል። ፕሮፌሰር አለማየሁ እንደሚሉት ከሆነ፤ ከሐምሌ 2012 እስከ ሰኔ 2013 በሚዘልቀው የበጀት ዓመት ላይ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሚገታ ከሆነ፤ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ ሊቀንስ የሚችለው በ5.6 በመቶ ነው። ቫይረሱ የሚስከትለው ጉዳት ግን እስከ ሶስተኛው ሩብ ዓመት የሚዘልቅ ከሆነ የአገር ውስጥ ምርት እድገቱ የሚቀንሰው በ16.7 በመቶ ይሆናል። • “ሚድያውን ደፍረን ማስተካከል ካልቻልን፤ ይህቺን አገር ነገ ላናገኛት እንችላለን” ዘነበ በየነ (ዶ/ር) ፕሮፌሰሩ የቫይረሱ ስርጭት የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ድቀት ለመቀነስ "ያለ ኃይልን በማሰባሰብ ቫይረሱ ወደ ህብረተሰቡ ከመሰራጨቱ በፊት በቁጥጥር ሥር ማድረግ ነው" ሲሉ ይመክራሉ። ከውጪ የሚላክ ገንዘብ መቀነስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ዘመዶቻችን ከውጪ በባንክ በኩል የሚልኩት ገንዘብ አገሪቱ ምርት ወደ ውጪ ልካ ከምታገኘው ዶላር በላይ መሆኑን ይናገራሉ። "የመንግሥት አሃዞችን ብንመለከት እንኳ፣ አገሪቱ ወደ ውጪ አገራት ምርት ልካ የምታገኘው ገቢ 2.8 እስከ 3 ቢሊዮን ነው። እንደውም ወደ ውጪ የሚላከው ምርት እየቀነሰ ነው። ከውጪ የሚላከው ገንዘብ ግን ከ4.5 እስከ 6 ቢሊዮን ዶላር ነው" ይላሉ። "መንግሥት ወደ ውጪ እንደሚላኩ ምርቶች ሁሉ ከውጪ ወደ አገር በሚላክ ገንዘብ ላይ በቂ አትኩሮት አይሰጥም የሚሉት ፕሮፌሰሩ፣ "ምርት ወደ ውጪ ልከን የምንሸጠው 3 ቢሊዮን ነው። የምናስገባው ደግሞ 17-18 ቢሊዮን ዶላር ነው" በማለት ይሄን የንግድ ክፍተት ለመሸፈን 'ሬሚታንሱ' ከፍተኛውን ሚና እንደሚጫወት ይናገራሉ። • የደረሱበት ያልታወቀው ተማሪዎች ስድስት ወር ሆናቸው በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ይልኩ የነበሩ ሰዎች እንደ ከዚህ ቀደም መላክ ባለመቻላቸው አገሪቱ ከ'ሬሚታንስ' ወይም ከውጪ ይላክ ከነበረ ዶላር ታገኝ ነበረውን ገንዘብ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አድርጓል ይላሉ። ዓለም አቀፍ ትንበያዎች ከሃብታም አገራት ወደ ትውልድ አገራት የሚላክ ገንዘብ መጠን በ26 በመቶ እንደሚቀንስ ማሳየታቸውን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ይናገራሉ። ሥራ አጥነት ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአሜሪካ እና አውሮፓ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ሥራ አጥ አድርጎ የመንግሥት ድጎማን እንዲጠብቁ አስገድዷል። ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳም፤ በአገራችንም ኮቪድ-19 ቢያንስ እስከ 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ሥራ አጥ ሊያደርግ እንደሚችል በጥናታቸው አመላክተዋል። "1.8 ሚሊዮን ሰው የመንግሥት ሰራተኛ ነው። የመንግሥት ሰራተኛው በወረርሽኙ ሳብያ ከሥራው ይፈናቀላል ብለን አንጠብቅም" የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ "የግል ሴክተሩ ደግሞ 1.5 ሚሊዮን ሰዎችን ቀጥሯል። ከእነዚህም መካከል ግማሽ ያክሉ ሥራ አጥ ሊሆኑ ይችላሉ" ይላሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ "ራሱን ቀጥሮ የሚያሳድር ደግሞ 3.1 ሚሊዮን አለ። እነዚህም ተጋላጭ ናቸው። ሥራቸውን በቀላሉ ሊያጡ ይችላሉ" ይላሉ። በምግብ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ መጨመር መፍትሄ "የእርሻው ክፍለ ኢኮኖሚ ብዙ አይጎዳም። ብዙ የሚጎዱት የአገልግሎት እና ኢንደስትሪ ዘረፎች ናቸው። ስለዚህ ያለ የሌለ አቅማችንን በእርሻው ላይ ማድረግ አለብን። ግብርናው የሚወድቀውን ኢኮኖሚያችንን ሊታደግልን ይችላል" በማለት እንደመፍትሄ ካስቀመጧቸው የመጀመሪያውን ነጥብ ያነሳሉ። ለዚህም በሽታው ወደ ገጠር እንዳይገባ ጥንቃቄ መድረግ እንዳለበት ፕሮፌሰር አለማየሁ ያሳስባሉ። መንግሥት ከግል ሴክተሩ ጋር በመነጋገር ሊታገዙ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ እቅድ ማውጣት ያስፈልጋል ሲሉም ያክላሉ። • በምዕራብ ወለጋ የአራት ልጆች እናት የሆኑትን ግለሰብ ማን ገደላቸው? ፕሮፌሰር አለማየሁ እንደሚሉት በቫይረሱ ስርጭት እጅጉን ከሚጎዱት መካከል ራሳቸውን ቀጥረው የሚገኙት 3.1 ሚሊዮን ዜጎች እና ቤተሰቦቻቸው ናቸው በማለት "ሥራ በሌለበት የሥራ ቦታ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ እየከፈሉ ነው። መንግሥት እያለ ያለው 'እባካችሁ ቤት ኪራይ ቀንሱላቸው' ነው። እንደዛ ብቻ መሆን የለበትም። መንግሥት የቤት ኪራይ የማይከፍሉበትን መንገድ ቢፈልግ እና ለአከራዮች ደግሞ እንደ ቼክ ወይም ቦንድ ባሉ ሰነዶች ማረጋገጫ ቢሰጥ ይረዳል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል። የግል ዘርፉም ከመንግሥት ድጋፍ ማግኘት እንዳለበትም ሃሳባቸውን ኣቀርባሉ።
48237004
https://www.bbc.com/amharic/48237004
በቤተ ሙከራ ስሚሠራው ስጋ ምን ያህል ያውቃሉ?
ስጋ አፍቃሪ ቢሆኑም በተለያየ ምክንያት ስጋ ላይመገቡ ይችላሉ። ነገር ግን እንደ ስጋ ያለ ሲጎርሱት አፍ የሚሞላ፣ ሆድ ላይ ቁጭ ሲልም አንጀት የሚያርስ ደግሞም አምሮት የሚቆርጥ ነገር ቢፈልጉ ምን ይመገባሉ?
ሀሳብ አይግባዎ። ተፈጥሯዊውን ስጋ የሚመስል ነገር ግን ከስጋ ነፃ የሆነ ምርት መጥቷል። ምርቱ የስጋ በርገር ወይም ደግሞ የቋሊማ ተመጋቢዎችን ፍላጎት ያረካል ተብሎ ይታሰባል። • የምግብ ምርጫዎ ስለማንነትዎ ይናገራል? አትክልት ተመጋቢዎች ስጋ በጤና ላይ ከሚያስከትለውን ጉዳት ለመዳንና ለአካባቢ ጥበቃ ሲሉ ከስጋ ጋር ተለያይተዋል። የአትክልት ተመጋቢዎች ምርጫ በምግብ ምርት ዘርፍ ውስጥ ስማቸውን ለተከሉ ድርጅቶች ጥሩ የገበያ እድል ፈጥሯል። ስጋን ተክቶ የመጣው ስጋ መሰል ምርት የትክክለኛው ስጋ መአዛ፣ መልክና ይዘት አለው። • የአየር ንብረት ለውጥ፤ የት ደረስን? ተፈጥሯዊውን ስጋ ይተካል የተባለው ሰው ሰራሽ ስጋ የተሠራው ከአትክልት ምርቶች ነው። በአትክልት ውስጥ ያሉ ፕሮቲኖች ያሉት ሲሆን፤ ቀይ ስር ተጨምቆ የሚወጣው ፈሳሽ እንደ ደም ሆኖ ጥቅም ላይ ይውላል። ቤተ ሙከራ ውስጥ ሰው ሰራሽ ስጋ ከእንስሳት ህዋስ የሚሠሩ ድርጅቶችም አሉ። ሰው ሰራሽ ስጋው በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል ተብሎም ይጠበቃል። 'ጀስት' የተባለ የአሜሪካ ድርጅት በቤተ ሙከራ የተዘጋጀ የዶሮ ስጋ ምርቱን በዚህ ዓመት መጨረሻ ለሽያጭ ያቀርባል ተብሎ ያጠበቃል። • በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች እነዚህ ምርቶች ታሳቢ ያደረጉት አትክልት ተመጋቢዎችን ብቻ ሳይሆን ስጋ የሚበሉ ሰዎችን ጭምርም ነው። መሰል ምርቶች ገበያ ላይ ከመዋላቸው በፊት ጤናማ ስለመሆናቸው ምርመራ ይደረግባቸዋል። አውሮፓ ውሰጥ የምርምር ሂደቱ እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ ይችላል። ሰው ሰራሽ ስጋ አምራቾች ተመጋቢዎችን ያሳምኑ ይሆን? ብዙዎች ቤተ ሙከራ ውስጥ የሚሠራ ስጋ ለመመገብ ፍቃደኛ አይደሉም። በተቃራኒው የስጋው አሠራር ሂደት በግልጽ ከተነገራቸው ሰው ሰራሽ ስጋ መመገብ የሚሹ ሰዎች አሉ። ሰው ሰራሽ ስጋ ከተፈጥሯዊ ስጋ ጋር ተመሳሳይ ስም ሊኖረው ይገባል ወይ? ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። 'ካትል አሶሴሽን' የተባለ የአሜሪካ ድርጅት ስጋ የሚለው ቃል የተፈጥሯዊ ስጋ ብቻ መጠሪያ መሆን አለበት ሲል ይከራከራል። • መጠቀም ያቆምናቸው ስድስት የአካል ክፍሎች አውሮፓ ውስጥ ሰው ሰራሽ ስጋ ተጠቅመው በሚዘጋጁ ምግቦች በሰው ሰራሹ መካከል የመጠሪያ ልዩነት እንዲኖር የማድርግ እቅድ አለ። ፈረንሳይ ተጠቃሚዎችን ግራ ያጋባሉ ያለቻቸውን የሰው ሰራሽ ስጋ ስያሜዎች ለማገድ ወስናለች። ሰው ሰራሽ ስጋ አምራቾች ምርታቸው የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ላለው ተጽዕኖ መፍትሄ እንደሚሰጥ ያምናሉ። ተመራማሪዎች እንደሚሉት ተፈጥሯዊው ስጋ ለ 'ግሪን ሀውስ' ጋዝ ልቀት ምክንያት ነው። ተመራማሪዎቹ ተፈጥሯዊ ስጋ መመገብ ከሚያስከትለው ተጽእኖ ለመዳን ሰው ሰራሽ ስጋ መመገብን ቢደግፉም፤ ሰው ሰራሽ ስጋ በቤተ ሙከራ ውስጥ ለመሥራት የሚያስፈልገው ሀይል ጥያቄ ያስነሳል። ሰው ሰራሽ ስጋ የአርብቶ አደሮች ሕይወት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተጽእኖ ሌላው ጥያቄ ነው።
news-53963768
https://www.bbc.com/amharic/news-53963768
ኮሮናቫይረስ ፡ በኢትዮጵያ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ለማስጀመር መመሪያ ተዘጋጀ
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን መልሶ ለማስጀመር የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ እንዳለው የወረርሽኙ ስጋት ባለበት ሁኔታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መልሰው እንዲጀመሩ ለማድረግ በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል። የአገሪቱ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንደተናገሩት በበሽታው ምክንያት የተቋረጡትን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ከዚህ በላይ እንዲዘገዩ ማድረግ በስፖርት ቤተሰቡ ላይ የሚፈጠረው ጫና ከፍተኛ ነው ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር ሲባል በአገሪቱ ስፖርታዊ ስልጠናዎች፣ ውድድሮች በአጠቃላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲቆሙ ተደርጎ ቆይቷል። በዚህም ሳቢያ የስፖርት ዘርፍ ክፉኛ መጎዳቱን ያመለከተው ኮሚሽኑ፤ ክለቦች የመፍረስ አዳጋ እንደተጋረጠባቸውና የስፖርት ቤተሰቡም የሥነ ልቦና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባታቸውን ገልጿል። በመሆኑም አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችንና የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት በማድረግ ረቂቅ መመሪያው ተዘጋጅቶ ውይይት ተካሂዷል። መመሪያው አጠቃላይ የስፖርት እንቅስቃሴዎች በምን ሁኔታ መከናወን እንዳለባቸው የሚያሳይ ሲሆን የስፖርት ተቋማትና ማኅበራት ከሚያካሂዷቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ባህሪ አንጻር አስፈላጊ የጥንቃቄና የአሠራር ሥርዓት ሊያዘጋጁ እንደሚችሉ እንደሚያመለክት ኮሚሽኑ ገልጿል። በዚህም መሰረት የስልጠናና የውድድር ስፍራዎች ለበሽታው ያላቸውን ተጋላጭነት ባገናዘበ ሁኔታ ደረጃ በደረጃ በግልና በቡድን አነስተኛ ተሳታፊ ቁጥርን ታሳቢ ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ ተቀምጧል። እንዲሁም ወደ ስልጠናና ወድድር የሚገቡ አካላት ምርመራ ማድረግ፣ የንጽህና መጠበቂያዎችን መጠቀምና ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያገለግሉ ቦታዎች፣ ቁሳቁሶችና መሳሪያዎች ንጽህናቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ መመሪያው ጠቅሷል። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ውድድርን መልሶ ለማስጀመር እየታሰበ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ውድድሩ ሲጀመር የተመልካቹንና የስፖርተኞቹን ጤና ደኅንነት ያስጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑና በርካታ ሰው የሚታደምባቸው ስፖርታዊ ውድድሮችን የመሰሉ እንቅስቃሴዎች እንዳይካሄዱ መደረጉ ይታወሳል።
news-49869728
https://www.bbc.com/amharic/news-49869728
የሳኡዲ አረቢያው ንጉሥ ጠባቂ በጥይት ተገደለ
የሳኡዲው ንጉሥ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ የግል ጠባቂ የነበረው ግለሰብ ከጓደኞቹ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ተተኩሶበት መገደሉን ባለስልጣናት አስታወቁ።
ጀነራል አብደል አዚዝ አል ፋጋም ቅዳሜ ምሽት ላይ ነበር ጓደኛውን ለመጠየቅ በሄደበት ከሞሃመድ ቢን ሚሻል ሰል አሊ ጋር ግጭት ተፈጥሮ ለሞት የበቃው። የፖሊስ መግለጫ እንደሚያመለክተው ሁለቱ ግለሰቦች ከተጋጩ በኋላ አሊ የተባለው ተጠርጣሪ ጅዳ ሁለቱ ከነበሩበት ቦታ ወጥቶ በመሄድ ሽጉጥ ይዞ በመመለስ ተኩስ ከፍቷል። • ኢራን የአውሮፓ አገራትን ውንጀላ አጣጣለች • በሳዑዲ የደረሰው ጥቃት እጅጉን እንዳሳሰባቸው የኔቶ ኃላፊ ገለፁ • የጀማል ኻሾግጂ አገዳደል በዝርዝር ይፋ ሆነ ተኳሹም ለፖሊስ እጁን እንዲሰጥ ቢጠየቅም እምቢ በማለት ተተኩሶበት መሞቱ ተገልጿል። ጀነራል ፋጋም በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምከንያት ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ አልፋለች። በተጨማሪም ሌሎች ሰባት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱም ታውቋል። ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ሁለቱ የሟች ጀነራል ፋጋም ጓደኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን የደህንነት አባላት ናቸው ተብሏል። ጀነራል ፋጋም በብዙ የሳኡዲ ዜጎች ዘንድ የሚታወቅ ሲሆን ከንጉሥ ሳልማን ጋርም የቅርብ ግንኙነት ነበረው። ለብዙ ዓመታትም የንጉሡ ግል ጠባቂ ሆኖ አገልግሏል። ብዙዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች 'ጀግና' ነበር እያሉ አሞካሽተውታል።
news-49829975
https://www.bbc.com/amharic/news-49829975
ሴቶችን እያነቀ የሚገድለው ናይጄሪያዊ በቁጥጥር ሥር ዋለ
በናይጄሪያ በየሆቴሉ እየገባ ሴቶችን እያነቀ የመግደል ሱስ ያለበት ሞገደኛ ወንጀለኛ ድርጊቱን አመነ። ለጊዜው "ሲጥ ያደረኳቸው" ሴቶች ብዛት 15 ብቻ ነው ብሏል፤ ለፖሊስ።
ባለፈው ሳምንት ወንጀለኛው እንዲታደን ለመጠየቅ በርካታ ሴቶች አደባባይ ወጥተው ነበር መርማሪ ፖሊስ ሙስጠፋ ዳንዳርዋ እንደተናገሩት "ተጠርጣሪው መጀመርያ ላይ 5 ሴቶችን ብቻ ነው ያነቅኩት ብሎን የነበረ ቢሆንም አሁን ከብዙ ምርመራ በኋላ ቁጥሩን 15 አድርሶታል" ብለዋል ለቢቢሲ። ተጠርጣሪው የተያዘው በርካታ ሴቶች በተመሳሳይ መንገድ እየታነቁ ተገድለው ከተገኙ በኋላ በተደረገ ጥብቅ ክትትል ነው። ሁሉም ሟቾች የተገኙት በሆቴል አልጋቸው ላይ ሳሉ ነው። ብዙዎቹ ደግሞ የናይጄሪያ የነዳጅ ከተማ በሆነችው ፖርት ሃርኮርት ባሉ ሆቴሎች ነው ታንቀው የተገኙት። የፖሊስ አለቃና መርማሪ አቶ ሙስጠፋ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው በዚያች ከተማ በየሆቴሉ እየወሰደ 9ኙን እንዴት እንደገደላቸው መርቶ አሳይቶናል ብለዋል። • ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች የሚያስታውሰው ካርታ • ባለፈው አንድ ዓመት ከ1200 ሰዎች በላይ መገደላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ ከዚህች ከተማ ሌላም ብዙ ቦታ ሴቶችን ገድሏል ያሉት እኚሁ የፖሊስ አለቃ በሌጎስ አንድ፣ በኦዌሪ አንድ፣ በሳፔሌ አንድ በአባ አንድ በቤኒንና በኢባዳንም እንዲሁ አንድ አንድ ሴቶችን መግደሉን አምኗል። ተጠርጣሪው ሴቶቹን ከመግደሉ በፊት እግርና እጃቸውን በተመሳሳይ መንገድ ጥፍር አድርጎ ያስራል። ይህም የድርጊት መመሳሰል ለፖሊስ ምርመራ እገዛ አድርጓል። ባለፈው ረቡዕ ወንጀለኛው ታድኖ እንዲያዝ ነዋሪዎች አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ ነው ፖሊስ ምርመራውን ያፋፋመው። የዚህን ሞገደኛ ወንጀለኛ ድርጊት ተከትሎ ሁሉም ሆቴሎች ሲሲቲቪ ካሜራ እንዲገጥሙ እና የተስተናጋጆችን ማንነት መዝግበው እንዲይዙ አዲስ መመሪያ ተላልፎላቸዋል።
news-46015069
https://www.bbc.com/amharic/news-46015069
188 ሰዎችን አሳፍሮ የተነሳው የኢንዶኔዢያ ላየን ኤይር ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተከሰከሰ
188 ሰዎችን የተነሳው ላየን ኤይር ቦይንግ 737 የተሰኘ የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከዋና ከተማዋ ጃካርታ መብረር ከመጀመሩ ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መከስሰከሱ ተሰምቷል።
ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ የተሰማው ጄቲ-610 በሚል መጠሪያ የሚታወቀው አውሮፕላን ባንግካ ቤሊቱንግ ወደተሰኘች ደሴት በመብረር ላይ ነበር። ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ስለመኖራቸው እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም። እሁድ ሌሊት 7፡30 ገደማ መጓዝ የጀመረው ጄቲ-610 ዘመናዊ አውሮፕላን ከአንድ ሰዓት በረራ በኋላ መዳረሻው ይደርስ ነበር። • ሰባኪው አውሮፕላን ግዙልኝ አለ ከአደጋው በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ባልሠልጣናት፤ 178 ጎልማሶች፣ 1 ጨቅላ፣ ሁለት ህፃናት እና አብራሪዎችን ጨምሮ 7 የአየር መንገዱ ሰራቶኞች የአደጋው ሰለባ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ጠቁመዋል። የሃገሪቱ አደጋ መቆጣጠር ባለሥልጣን ሱቶፖ ፑርዎ የአደጋውን ክብደት የሚያሳዩ ምስሎች በትዊተር ገፃቸው አጋርተዋል። አውሮፕላኑ ባህር ላይ መውደቁ ደግሞ የተረፉ ሰዎች ሊኖሩ አይችሉም የሚለውን መላምት የጎላ አድርጎታል። ከፈረንጆቹ 2016 ጅምሮ ጥቅም ላይ መዋል የጀመረው ቦይንግ 737 ሞዴል ወደገበያው ከገባ ጀምሮ እክሎች ያጋጥሙት እንደነበርም ተዘግቧል። • ኢትዮጵያዊቷ ሰው አልባ አውሮፕላን የኢንዶኔዢያው ላየን አየር መንገድ ወርሃ ነሃሴ ላይ ነበር ይህንን አውሮፕላን ገዝቶ የግሉ ያደረገው። የደሴቶች ስብስብ የሆነችው ኢንዶኔዢያ በውሃ ከመከበቧ አንፃር የበረራ ትራንስፖርት ላይ ጥገኛ የሆነች ሃገር ናት፤ ቢሆንም አየር መንገዷ አደጋ አያጣውም። 2013 ላይ ደግሞ አንድ አውሮፕላኗ በእክል ምክንያት ውሃ ላይ ለማረፍ ቢገደድም 108 ተሳፋሪዎቹ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ ሳይደርስ መትረፍ ችለዋል። በ2004 ዓ.ም በአውሮፕላን አደጋ ምክንያት 25 ሰዎች መሞታቸው የሚዘነጋ አይደለም። እንኳን ወደ አውሮፕላን ካፌ በደህና መጡ
news-52081141
https://www.bbc.com/amharic/news-52081141
ኮሮናቫይረስ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለሕዝባቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጻፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ቀውስ ከመሻሻሉ በፊት የከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ብሪታኒያ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች በላኩት ደብዳቤ ላይ አስጠነቀቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅዳሜ በቪዲዮ አማካይነት ስለበሽታው የተደረገ ስብሰባን ሲመሩ በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ እራሳቸውን ለይተው የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አስፈላጊ ከሆነ ጥብቅ የሆኑ ክልከላዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም ገልጸዋል። የአገሪቱ ዜጎች ከቤታቸው ውጪ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦችና የጤና መረጃዎችን ያየዙ በራሪ ወረቀቶች እንዲሰጧቸው ተነግሯል። ይህም የሚደረገው መንግሥት ዜጎች ማድረግ ስለሚገቧቸው ነገሮች ግልጽ የሆነ መምሪያ አልሰጠም በሚል ከተተቸ በኋላ ነው። ለ30 ሚሊዮን ቤተሰቦች እየተሰራጨ ያለውና 5.8 ሚሊዮን ፓዉንድ ወጪ ወጥቶበታል በተባለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ላይ "ከመጀመሪያው ትክክለኛውን እርምጃ በትክክለኛው ሰዓት ለመውሰድ ሞክረናል። "ከሳይንስና ከህክምናው ዘርፍ የሚሰጡ ምክሮች ከዚህም በላይ የምንወሰድው እርምጃ እንዳለ ካመለከቱ ከማድረግ ወደ ኋላ አንልም" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን በደብዳቤያቸው ላይ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም "ግልጽ ላደርግላችሁ የምፈልገው ነገር፤ ከበሽታው ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ ከመሻሻሉ በፊት የከፉ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ እናውቃለን" ብለዋል በደብዳቤያቸው። "ነገር ግን ዝግጅቶችን እያደረግን ሲሆን፤ ሁላችንም የተሰጠንን መመሪያ መከተል ከቻልን በበሽታው የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ጥቂት ይሆናል። በቅርቡም ህይወት ወደ መደበኛ መስመሯ ትመለሳለች።" ባለሙያዎች እንደሚሰጉት ከሆነ አሁን እየተወሰዱ ያሉት የእንቅስቃሴ እገዳ እርምጃዎችና አካላዊ እርቀትን የመጠበቅ ምክሮች ተግባራዊ ሆነው ውጤታቸው እስኪታይ ድረስ በሚኖሩት ሁለትና ሦስት ሳምንታት ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር መጨመሩ አይቀርም። በታላቋ ብሪታኒያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1,019 የደረሰ ሲሆን ትናንት ብቻ 260 ሰዎች ሞተዋል። በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ 17,089 በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ይገኛሉ።
news-51848153
https://www.bbc.com/amharic/news-51848153
ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ከወንዶች ያነሰ ክፍያ ይገባቸዋል-አሜሪካ
የአሜሪካ እግር ኳስ ተቋም የአገሪቱ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ከወንዶቹ ጋር ሲነፃፀር ብቃቱ ያነሰ፤ የሚጣልበት ሃላፊነትም ትንሽ እንደሆነ አስታውቋል።
28 ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ተቋሙ ላይ ከወንዶች እኩል ይከፈለን የሚል ክስ መስርተው የነበረ ሲሆን የተቋሙ ጠበቆች ከላይ የተጠቀሰውን ነጥብ በማስረጃነት ለፍርድ ቤት አቅርበዋል። የጽሑፉ መከራከሪያ የብሄራዊ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አባል መሆን "ፍጥነትና ጥንካሬ ላይ የመሰረተ ትልቅ የኳስ ችሎታ የሚጠይቅ ነው" ይላል። • ትኩረት እየሳበ የመጣው የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫ ክሱ ግንቦት ወር ላይ መሰማት ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። የሴቶች ቡድን ኮኮብ ተጫዋች የሆነችው ሜጋን ራፒኖይ 'ግልፅ የዖታ አድልኦ' የአሜሪካ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን አንድም ዓለም አቀፍ ውድድር ሳያሸንፍ የሴቶቹ ቡድን ግን አራት ጊዜ አሸናፊ ሆኗል። አምስት ጊዜ ደግሞ የኦሊምፒክ ሜዳሊያ አግኝቷል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደ ቡድን ገቢ በማስገኘትም የሴቶቹ ቡድን የወንዶቹን ጥሎት ሄዷል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 እና በ2018 የሴቶቹ ቡድን በትኬት ሽያጭ ከፍተኛ ገቢ አግኝቷል። ይህ ቢሆንም ግን ሴት ተጫዋቾች ከወንዶቹ ያነሰ እየተከፈላቸው እንደሆነ የሴቶች ቡድኑ ጠበቆች ገልፀዋል። ስለዚህም ሴቶቹ ተጫዋቾች በብሄራዊ ቡድን ደረጃ በሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ የሚያገኙት ጉርሻ 4950 ዶላር ሲሆን የወንዶቹ ቡድን በተመሳሳይ ጨዋታ 13000 ዶላር ከማግኘቱ ጋር ሲነፃፀር ክፍያው ኢፍትሃዊ ነው የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ የግድ ብሏል። • ሴት እግር ኳሰኞች እና ቡድኖች ስንት ይከፈላቸው ይሆን? • የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው የሴቶች ቡድኑ ቃል አቀባይ ሞሊ ሊቪንሰን " 'ወንድ ተጫዋቾች ከፍተኛ ሃላፊነት አለባቸው' የሚለው መከራከሪያ ግልፅ የፆታ አድልኦ እንደሆነ የትም ዓለም ላይ ያለ ሰው በግልፅ ይረዳዋል" ብለዋል። ክሱን ለመመስረት የገፋቸውም ይህ የፆታ አድልኦ እንደሆነ ገልፀዋል። የሴቶች እግር ኳስ ቡድኑ የዛሬ ዓመት ክስ የመሰረተው ሴት ተጫዋቾች ከወንድ ተጫዋቾች እኩል ይከፈላቸው፤ 66 ሚሊዮን ዶላርም ለእስከዛሬው ጥፋት ካሳ ይከፈለን የሚል ነበር። ከዚህም ባሻገር የአሜሪካው እግር ኳስ ተቋምን የተቀናጀ ፆታዊ አድልኦን በአሰራሩ የሚከተል ነው ሲሉም ወንጅለውታል። የሴቶች ቡድኑ ኮኮብ ተጫዋች የሆነችው ሜጋን ራፒኖይ "ከእኩል ክፍያ ያነሰ የምንቀበለው ምንም ነገር አይኖርም" ብላለች ከኤቢሲ ቴሌቪዥን ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ። "ሁሌም ለጨዋታ እንዘጋጃለን፣ ብናሸንፍም፣ ብንሸነፍም እኩል እንዲከፈለን እንፈልጋለን በቃ ይኸው ነው።" ካርሎስ ኮርዴሮ ተቋማቸው በራሱ ቁጥጥር ስር ባሉ ውድድሮች ላይ ብቻ እኩል ክፍያ ለመስጠት መስማማቱን ገልፀው ነበር የእኩል ይከፈለን ጥያቄ የሴት ተጫዋቾቹ እኩል ይከፈለን ጥያቄ በአጠቃላይ ህዝቡ በወንድ ተጫዋቾችም ድጋፍ ያገኘ ነው። ባለፈው ወር የወንዶቹ ብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ተቋሙን ነቅፎ መግለጫ አውጥቶ ነበር። "እውነት ነው ከክፍያና ከስራ ሁኔታ አንፃር ፌደሬሽኑ ሴቶች ላይ አድሎ ያደርጋል" ይላል ቡድኑ በጽሑፍ የሰጠው መግለጫ። • የአውስትራሊያ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች በወር 2 ሚሊዮን ብር ሊከፈላቸው ነው አሜሪካዊቷ የስፖርት ጋዜጠኛ ክርስቲን ሼልዊትዝ ህዝቡ ለሴቶቹ ቡድን ጥሩ አመለካከት እንዳለውና ጥያቄያቸውንም እንደሚደግፍ ትናገራለች። የአሜሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት ካርሎስ ኮርዴሮ የሴቶች ቡድኑ ጥያቄዎችን ለመመለስ ተቋሙ በርካታ ጥረቶችን ሲያደርግ እንደነበር በደብዳቤ አስታውቀዋል። የሽልማት ገንዘብ ልዩነት ተቋማቸው የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ እንዳለ የሚናገሩት የፌደሬሽን መሪው ካርሎስ ኮርዴሮ ተቋማቸው በራሱ ቁጥጥር ስር ባሉ ውድድሮች ላይ ብቻ እኩል ክፍያ ለመስጠት መስማማቱን ገልፀው ነበር። ነገር ግን ፌደሬሽኑ ሴቶች እግር ኳስ ቡድኑ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ከወንዶቹ እኩል የሽልማት ገንዘብ ላለማግኘቱ ካሳ የመክፈል ፍላጎት የለውም።
news-53568627
https://www.bbc.com/amharic/news-53568627
የጀርመን ባለስልጣናት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መባባስ "በጣም አሳስቧቸዋል"
የጀርመን ማኅበረሰብ ጤና ተቋም ኃላፊ በአገሪቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እየተባባሰ መምጣት "በጣም እንዳሳሰባቸው" ገለፁ።
የሮበርት ኮች ተቋም ኃላፊ ሎተር ዌይለር "ያለነው በፍጥነት እያተስፋፋ በሚሄድ ወረርሽኝ መካከል ነው" በማለት ለሮይተርስ ተናግረዋል። ዌይለር አክለው ጀርመናውያን "ቸልተኛ" እየሆኑ መምጣታቸውን በመግለጽ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያደርጉ እና ማኅበራዊ ርቀታቸውን እንዲሁም ንጽህናቸውን እንዲጠብቁ አሳስበዋል። ባለፉት ሳምንታት በጀርመን 3,611 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰማው በአውሮፓ ባሉ አገራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዳግም እየተስፋፋ በመጣበት ወቅት እና በፈረንጆች የበጋ ወር የተነሳ ጎብኚዎች ከአገር አገር መንቀሳቀስ በጀመሩበት ጊዜ ነው። ማክሰኞ ዕለት ጀርመን ከስፔን ሦስት አካባቢዎች የሚመጡ መንገደኞችን በሚመለከት ማስጠንቀቂያ አውጥታለች። በቅርብ ጊዜያት በስፔን ሦስት ዛቶች፣ በአራጎን፣ ካታሎኒያ እና ናቫራ ቫይረሱ በስፋት እየተሰራጨ መሆኑ ተገልጾ ነበር። ዩናይትድ ኪንግደምም ከስፔን ለሚመጡ መንገደኞች ለ14 ቀን ያህል ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ የወሰነች ሲሆን የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር እርምጃውን "ኢፍትሃዊ" ብለውታል። ጀርመን ሰኞ የቫይረሱ ስርጭት ከተስፋፋባቸው አገራት የሚመጡ መንገደኞች በነጻ አስገዳጅ የኮሮናቫይረስ ምርመራ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፋለች። እነዚህ አገራት ብራዚል፣ ቱርክ እና አሜሪካ ሲሆን ባለስልጣናት በየእለቱ መረጃው ሊሻሻል ይችላል ብለዋል። ማክሰኞ እለት ዌለር ዜጎች ከቤታቸው ውጪ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት 1.5 ሜትር አካላዊ ርቀት መጠበቅ የማይችሉ ከሆነ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው መመሪያ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች፣ ቤት ውስጥም እንዲደረግ የሚያዝ ነበር። ኃላፊው አክለውም ጀርመኖች "በፍጥነትና ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መልኩ" ቫይረሱ ዳግም እንዳይስፋፋ አካላዊ ርቀታቸውንና ንጽህናቸውን በመጠበቅ ሊያስቆሙት ይገባል ብለዋል። "ይህ የሁለተኛው ዙር ወረርሽኝ መሆንና አለመሆኑን የምናውቀው ነገር የለም ነገር ግን ሊሆን ይችላል" ያሉት ዌለር "ነገር ግን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል መመሪያዎችን ከተከተልን መከላከልና ማስቆም እንደምንችል ተስፋ አለኝ" ብለዋል። በጀርመን እስካሁን ድረስ ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 206,242 ሲሆን 9,122 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በጀርመን የተከሰተው ሞት ከሌሎች የአውሮፓ አገራት አንጻር ሲታይ በጣም አነስተኛ ሲሆን፣ በዚህም በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ወርሽኙን በፍጥነት በቁጥጥር ስር በማዋሏና ሰፊ ምርመራ በማካሄዷ አድናቆት ተቸሯት ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በቫይረሱ መያዙ ታውቋል።