id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-54252616
https://www.bbc.com/amharic/news-54252616
ኮሮናቫይረስ ፡ ወገናቸውን ለመታደግ በመረጃና በጥናት የሚተጉት ዶክተር በአሜሪካ
አሜሪካ ውስጥ በዋሽንግተን ዲሲ በተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ እየሠሩ የሚገኙት ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ የመጀመሪያ ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በጎንደር የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ነው።
የህክምና ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ጋምቤላና አዲስ አበባ ውስጥ ለጥቂት ዓመታት በሙያቸው አገልግለው ወደ አሜሪካ በማቅናት ተጨማሪ የህክምና ትምህርት በመከታተል የውስጥ ህክምና [ኢንተርናል ሜዲሲን] እና በተላላፊ በሽታዎች ተመርቀዋል። ዶ/ር ገበየሁ በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ውስጥ የሚሠሩበት የጤና ተቋም በዋሽንግተን ዲሲ የተለያዩ የህክምና ማዕከላትን ያቀፈ ሲሆን በአካባቢው የተላላፊ በሽታ ጉዳዮችን በተመለከተ አማካሪ ሆነው እየሠሩ ይገኛሉ። ዶ/ር ገበየሁ ባሉበት የቨርጂኒያ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኢትዮጵያና የኤርትራ ማኅበረሰብ አባላት ከመኖራቸው አንጻር በቅርበት ከመስራታቸው በተጨማሪ በሜሪላንድ፣ በዲሲ እና ቨርጂኒያ ውስጥ ከሚገኙት እነዚህ ማኅበረሰቦች በተጨማሪ ሌሎችንም በሙያቸው እያገለገሉ ይገኛሉ። የዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ ዋነኛ ትኩረት በኤችአይቪ፣ ሄፐታይተስ ቢ፣ ሲ እና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች ላይ ሲሆን፤ የሥራ ኃላፊነታቸውም ከእነዚሁ በሽታዎች ጋር ከመያያዙ በተጨማሪ በአካባቢው ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተላላፊ በሽታዎች ላይ በሚደረጉ ጥናቶች ዙሪያ የድርጅቱ ተወካይ በመሆን ይሠራሉ። ሙያን ለማኅበረሰብ ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ቦታና የተለየ ትኩረት ከሚሰጧቸው በሽታዎች አንጻር ይህ አጋጣሚ "ለማኅበረሰቡ በሙያዬ ብዙ ነገር ማብርከት እንድችል አድርጎኛል" ይላሉ ዶ/ር ገበየሁ። በዚህም ከሰባት ዓመታት በፊት ማኅበረሰቡን ለማገልገል በማሰብ የእራሳቸውን ድረ ገጽ ጀመሩ። በድረ ገጻቸውም ዶ/ር ገበየሁ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን ሊጠቅሙ ይችላሉ የሚሏቸውን የጤና መመሪያዎችን፣ ማብራሪያዎችንና የተለያዩ መረጃዎችን ወደ አማርኛ በመተርጎም ይጋራሉ። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ደግሞ የተለመደውን የህክምና አገልግሎት መረጃዎችን ገታ አድርገው ስለ አዲሱ በሽታ ይጠቅማሉ ብለው ያሰቧቸውን መረጃዎችን በየቀኑ እያጋሩ ይገኛሉ። ዶ/ር ገበየሁ "በተቻለኝ አቅም ሕዝቡን ለማገልገል የወሰድኩትን መሃላ ለማሳካት እጥራለሁ። ከድረ ገጹ በተጨማሪ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ላይ በመቅረብ ጠቃሚና ነፍስ አዳን ይሆናሉ ብዬ የማስባቸውን መረጃዎች አካፍላለሁ" ይላሉ። አክለውም ማኅበረሰቡ በሚረዳው በቋንቋ የሚቀርቡ መረጃዎች እጥረት ይኖራል ብለው ስላመኑ፤ እንዲሁም በተለይ በኮቪድ-19 ዙሪያ የተለያዩ የሚያሳስቱ መረጃዎች በማኅበራዊ ድረ ገጾች እየተስፋፉ በመሆናቸው ይህንን "እንደግል ግዴታዬ በመውሰድ የድርሻዬን ላበርክት ብዬ ነው የጀመርኩት" በማለት ስለሥራው አስፈላጊነት ይናገራሉ። "ኅብረተሰቡ ለእንደዚህ ዓይነቱ መረጃ አዲስ ነው" የሚሉት ዶ/ር ገበየሁ "በሚዲያ ይወራ እንጂ፣ ስል ተላላፊ በሽታዎች ሥርጭትና ጉዳት፣ ስለቫይረስ መሰረታዊ እውቀት የሌለው ሰው በሚረዳው ቋንቋ መረጃ መቅረብ አለበት ብዬ ነው እያስተማርኩ ያለሁት" ይላሉ። ትክክለኛ የጤና መረጃ በዚህ ዘመን የምድራችን አሳሳቢው የጤና ጠንቅ የሆነውና አሜሪካንን ክፉኛ ያጠቃት የኮሮናቫይረስ ልክ እንደ አፍሪካ አሜሪካዊያን እና ሂስፓኒክ ዝርያ እንዳላቸው ማኅረሰቦች በዚያ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰቦችም ተጋላጭ ናቸው ይላሉ ዶ/ር ገበየሁ። እነዚህ ማኅበረሰቦች አብዛኛዎቹ የተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ፣ የሚኖሩባቸው አካባቢዎች፣ የአኗኗር ዘይቤያቸው እንዲሁም ባህላቸው ከሰዎች ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ ለበሽታው ያላቸውን ተጋላጭነት ከፍ እንደሚያደርገው ያስረዳሉ። "ከዚያም በተጨማሪ ወረርሽኙ ያልታሰበ በመሆኑ ከማኅበረሰባችን አንዳንዶች ነቃ ብለው የሚያስፈልገውን እርምጃ ቢወስዱ እንኳን ብዙዎች ግን ከመረጃ ማጣትና ከመዘናጋት የተነሳ ተጠቂ የሆኑ ነው" በማለት አመልክተው ይህንን የመረጃ ክፈተት ለመሙላት በሙያቸው እየጣሩ እንደሆነ ዶ/ር ገበየሁ ይናገራሉ። ማኅበረሰቦቹ በተለይ ለወረርሽኙ ተጋላጭ የሚሆኑት ከባህላቸውና ከአኗኗራቸው የተነሳ "በስፋት መገናኘታቸው፣ በመደበኛነት መጠያየቃቸው እና በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ለቫይረሱ በመጋለጣቸው በቫይረሱ የመዛመትና የመሠራጨት ጉልበት የተነሳ ብዙዎችን ጉዳት ላይ ጥላሏል" በማለት ትኩረት የሚሻውን የበሽታው መተላለፊያ መንገድን ትኩረት ይሰጡታል። ዶክተር ገበየሁ በተለይ በበሽታው ተጠቂ የሆኑት የማኅበረሰቡ ክፍሎት ሰፋ ያለ የቤተሰብ አባላት ያላቸው እንደነበሩ አመልከተዋል። በሽታውበዓለም ዙሪያ በርካቶችን እየያዘ በሺህዎች የሚቆጠሩትን ለሞት እየዳረገ ሲሄድ በአሜሪካ ሚሊዮኖች በቫይረሱ መያዘቸው እንዲሁም ከ200 ሺህ በላይ የሚሆኑት በበሽታው ሰበብ ሞተዋል። በሽታውን ለማወቅና እራስን ለመጠበቅ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ጠቃሚ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ገበየሁ እንደሚሉት የተለያዩ ወገኖች እርስበርስ የሚጣረሱና አሳሳች መረጃዎችን በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል በቀላሉ ስለሚያሰራጩ የሚታመኑ የመረጃ ምንጮችን መጠቀምን ይመክራሉ። ለዚህም መፍትሄው "እንደ ዓለም ጤና ድርጅትና በየአገሩ ያሉ ተመሳሳይ ተቋማትን ምክር መከተሉ ተመራጭ ነው" የሚሉት ዶ/ር ገበየሁ፤ የሚወጡ መረጃዎችን በተመለከተም በመረዳትና ተግባራዊ በማድረጉ በኩል ልዩነቶች እንዳሉ ይናገራሉ። ከመረጃዎች አንጻር "በህክምናው ዘርፍ በተሰማሩ ሰዎች መካከል ልዩነት አለ። ሥራችን በተላላፊ በሽታዎች ላይ ያተኮርንና በሌላ ዘርፍ የተሰማሩ ሐኪሞች እንኳን ነገሮችን የመረዳት ሁኔታው የተለያ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ነው ማኅበረሰቡ የሚያገኘው መረጃ በሚገባው ቋንቋና ከመሆኑ በተጨማሪ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል" ይላሉ። ስለዚህም ዶ/ር ገበየሁ እንደሚሉት ዋና ነገር መሆን ያለበት "ለማኅበረሰቡ የሚደርሰው መረጃ በሙያው ላይ በተሰማሩ ሐኪሞች መሆን አለበት" ባይ ናቸው። "በተላላፊ በሽታ የተጠቁ ህሙማን የሚከታተሏቸውን ወይም የሚያክሟቸውን ባለሙያዎች ምክርን መከተል በሽታውን ለመካላከልና ከበሽታው ለመዳን ትልቅ አስተዋጽዖ አለው" ይላሉ። ዶ/ር ገበየሁ ለአሜሪካ ባለስልጣናት ገለጻ ሲያደርጉ የወርሽኞች ስጋት "ኮቪድ-19 ስም እና በሽታው አዲስ ይምሰል እንጂ በየተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር ዘርፍ የቆየ ቫይረስ ነው" የሚሉት ዶ/ር ገበየሁ፤ ከኤችአይቪ አንስቶ የተለያዩ በሽታዎችን እያጠኑ ላሉ እሳቸውን ለመሰሉ ባለሙያዎች አዲስ አይደለም። ተላላፊ በሽታዎች ላይ የተለየ ትኩረት አድረገው የሚሰሩት ዶ/ር ገበየሁ በሽታ አምጪ የሆኑ ቫይረሶች ባህሪያቸው አንዱ ከአንዱ ሊለያይ እንደሚችል ይናገራሉ። በዚህ ዘርፍም የተላላፊ በሽታዎችን ባህሪያትን ለማወቅ እና ለማዳን የሚረዱት ጥናቶች በሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ባሉ እንስሳት ላይ ጭምር እንደሆነ ይናገራሉ። "ኮሮናቫይረሶች ከሰው ጋር አብረው የኖሩ ናቸው። በአጠቃላይ ወደ አራት የሚደርሱ አሉ። ከጥንት ጀምሮ ሰው ላይ ተራ ጉንፋንና የመሳሰሉ የጤና ዕክሎችን የሚያስከትሉ ናቸው። እነርሱም ገዳይ አይደሉም" ይላሉ። ይሁንና ኮሮናቫይረስም [ኮቪድ-19] ምንም እንኳን በርካቶችን ለሞት ቢዳርግም ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው የሚናገሩት ዶ/ር ገበየሁ "በጣም ገዳይ የሆነ ቫይረስ ሰዎችን ገድሎ አብሮ ይከስማል" በማለት ሞትን በሚያስከትሉ ቫእረሶች መካከል ያለውን ልዩነት ያስረዳሉ። ጨምረውም አደገኛ ወይም ገዳይ የሚባል ቫይረስ አብዛኛውን ጊዜ የሚይዘውንና የሚገድለውን ገድሎ አብሮ የሚሞት መሆኑን አመልክተው፤ ለእንዲህ አይነት ቫይረሶች ክትባትና መድኃኒት ለማግኘት ፈታኝ ነው ይላሉ። እንደምሳሌም ሳርስ ቁጥር አንድ የተሰኘው ቫይረስ የሚጠቅሱት ዶ/ር ገበየሁ፤ ይህ በሽታ ተከስቶ ጉዳት አድርሶ በመክሰሙ ክትባት ቢዘጋጅም በሽታው እንደጠፋ የቀረ። የተላላፊ በሽታዎችን በሚያጠኑና በሚያክሙ ባለሙያዎች ዘንድ አሳሳቢውና አስፈሪው ነገር "እየደጋጋሙ የሚመላለሱ ወረርሽኞች ናቸው" ይላሉ፤ ምክንያቱንም ሲያስቀምጡ እንዲህ አይነት ወረርሽኞች ባህሪያቸው የሚጨበጥ አለመሆኑን ይናገራሉ። በተለያዩ ቫይረሶች መካከል የሚፈጠር መዛመድም አደገኛ ውጤትን ሊያስከትል እንደሚችል የሚናገሩት ዶ/ር ገበየሁ "በሙያችን 'ቫይረስ ሴክስ' የሚባል ነገር አለ። ሁለት ቫይረሶች እርስ በእርስ 'ጄኔቲክ ኮድ' [የዘረመል አወቃቀር ይዘት] በመቀያየር አዲስ ቫይረስ ይፈጥራሉ ወይም ልጅ ይወልዳሉ እንላለን።" ለምሳሌ ይህ ኮቪድ-19 ከሜርስ ጋር ቢገናኝና ዘረመል ቢለዋወጡ አደገኛ ውጤትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፤ ምክንያቱም ሜርስ ገዳይ ነው የጎደለው ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ ብቻ ነው። ኮቪድ-19 ደግሞ ነባርና አደገኛ የጤና እክል ያለው ሰው ካልሆነ በስተቀር የመግደል አቅሙ ደካማ ነው። ሆኖም ግን ከሰው ሰው የመተላለፍ አቅሙ በጣም ፈጣን ነው። "ለዚህም ነው ሁለቱ ቢገናኙና የባህሪይ መወራረስ ቢፈጠር በጣም አደገኛ ቫይረስ ሊወልዱ/ሊፈጥሩ ይችላሉ" ብለው ዶ/ር ገበየሁ በቫይረሶች መካከል የሚኖር መዛመድ አንደኛው ከሌላኛው አደገኛ ባህሪዎችን በመውሰድ አደገኛ ውጤትን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ያስረዳሉ። ዶክተር ገበየሁ እንደሚሉት ለሰው ልጆች ጤና ጠንቅ የሆኑ ቫይረሶች በአንድ ስያሜ የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ። "ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ኤችአይቪ ነው" የሚሉት ዶክተሩ፤ "ብዙ ሰው አንድ ዓይነት ኤችአይቪ ያለ ይመስለዋል" ይላሉ። ነገር ግን "ሁለት አይነት የኤችአይቪ ዓይነቶች ያሉ ሲሆን፤ አንደኛው በአራት የሚከፈል ሲሆን ከእነርሱ መካከል ደግሞ አንደኛው 14 ዝርያዎች ያሉት የቫይርስ ዓይነት ነው" በማለት ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ እንኳን መድኃኒት ማግኘት አስቸጋሪ የሆነው በዚህ የቫይረሶቹ አይነት መብዛት እንሆነ ያመለክታሉ። ሲያጠቃልሉም በዚህ ዘመን የተከሰተውን ወረርሽኝን በተመለከተ በሽታው እየቀነሰ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን እየተስፋፋ መሆኑ ብዙ ሰዎች ላይ ፍርሃትን እንደሚፈጥር የሚጠቅሱት ዶ/ር ገበየሁ፤ በዚህም ሳቢያ በሰዎች ዘንድ የተፈጠረውን ፍርሃት በመጠቀም ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች ሊስፋፉ ስለሚችሉ የመጠንቀቅን አስፈላጊነት ያሰምሩበታል።
42025206
https://www.bbc.com/amharic/42025206
ስለ ዚምባብዌ ፖለቲካዊ ቀውስ ሊያውቋችው የሚገቡ ነጥቦች
የሰሞኑ የዚምባብዌ ፖለቲካዊ ቀውስ የጀመረው ሮበርት ሙጋቤ በባለቤታቸው ግፊት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩትን ኤመርሰን ምናንጋግዋ 'ታማኝ አይደሉም' ብለው ከሥስልጣን ካባረሯቸው በኋላ ነበር።
የኤመርሰን ምናንጋግዋን መባረር ይፋ ያደረጉት የኢንፎርሜንሽን ሚኒስትሩ ሳይመን ካሃያ ሞዮ ምናንጋግዋ ''ታማኝ'' አይደሉም ሲሉም ተደምጠዋል። ባላቸው ብልህ አስተሳሰብ "አዞው" በሚል ስም የሚታወቁት ምናንጋግዋ ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ "ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ አንተና ሚስትህ እንደፈለጋችሁ የምታደርጉት የግል ንብረታችሁ አይደለም" ሲሉ ሙጋቤን ተችተውም ነበር። የቀድሞው የደህንነት ሹም የነበሩት ምናንጋግዋ ፕሬዝዳንት ሙጋቤን የመተካት ተስፋ የተጣለባቸው መሪ ነበሩ። ምናንጋግዋ ከሥልጣን በመነሳታቸው የሮበርት ሙጋቤ ባለቤት የሆኑት ግሬስ ሙጋቤ ባለቤታቸውን በመተካት ቀጣይ የዚምባብዌ መሪ እንደሚሆኑ በበርካቶች ዘንድ ተገምቶም ነበር። ከዚህ በፊት ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤ ምክትል ፕሬዝዳንቱን ከስልጣናቸው እንዲያነሱ ሮበርት ሙጋቤን በተደጋጋሚ ይወተውቱ እንደነበርም ይነገራል። • ሙጋቤ ታማኝ አይደሉም ያሏቸውን ምክትላቸውን ከስልጣን አነሱ ግሬስ ሙጋቤ (ግራ) እና ኤመርሰን ምናንጋግዋ (ቀኝ) ከቀናት በፊት ግሬስ ሙጋቤ በሃራሬ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ''እባቡ በሃይል ጭንቅላቱን መመታት አለበት። በፓርቲው ውስጥ መከፋፈል እና አለመግባባትን የሚፈጥሩትን ማስወገድ አለብን። ወደ ቀጣዩ የፓርቲያችን ስብሰባ በአንድ መንፈስ ነው መሄድ ያለበን'' ሲሉ በምናንጋግዋ ላይ ሲዝቱ ተሰሙ። ግሬስ ሙጋቤ ይህን ባሉ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኤመርሰን ምናንጋግዋ ለህይወቴ ሰግቻለው ብለው ሃገር ጥለው ሸሹ። የጦሩ ማስጠንቀቂያ ሙጋቤ ምክትላቸውን ካባረሩ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነበር የሀገሪቱ ጦር በፓርቲው ውስጥ እየተደረገ ባለው ጉዳይ ጣልቃ ልገባ እችላለሁ ሲል ማስጠንቀቂያ የሰጠው። ከ90 የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ነበር የዚምባብዌ ጦር ኃይል ጄነራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ገዢውን ፓርቲ ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከድርጊታቸው ካልተቆጠቡ ጦሩ ጣልቃ እንደሚገባ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ያስጠነቀቁት። • የዚምባብዌ ጦር "ጣልቃ እንደሚገባ" አስጠነቀቀ የዚምባብዌ ጦር ኃላፊ ጄነራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ያልተጠበቀው መግለጫ ምናልባትም ዕለተ ዕረቡ ለዚምባብዌያዊያን ታሪካዊ ቀን ነበረች ማለት ይቻላል። የሃገሪቱ ዜጎች ዕረቡ ጠዋት ከእንቅልፋቸው ሲነቁ የተደበላለቀ ስሜት የፈጠረባቸውን ያልተጠበቀ የቴሌዢን መግለጫ የተመለከቱት። ግመሹ በተፈጠረው ነገር ድንጋጤ ውስጥ ሲገቡ በደስታ የቦረቁም አልጠፉም ነበር። • ጦሩ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያውን ከተቆጣጠረ በኋላ ''መፈንቅለ መንግሥት አይደለም'' ሲል አስታውቋል የዚምባብዌ ጦር ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሆነውን ዜድ ቢ ሲን ተቆጠጠረ። ጦሩ በሰጠው መግለጫ "ይህ መፈንቅለ-መንግሥት አይደለም፤ በፕሬዝዳንት ሙጋቤ ዙሪያ የሚገኙ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ የመውሰድ ተልዕኮ እንጂ። ጦሩ የመንግሥትን ስልጣን ለመቆጣጠር አልተንቀሳቀሰም" ሲል በመግለጫው ጠቅሶ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ እና ቤተሰቦቻቸው ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን አረጋገጠ። እስካሁን የጦሩን እንቅስቃሴ ማን እየመራው እንደሆነ የታወቀ ነገር ባይኖርም ጦሩ በሚሰጠው ተደጋጋሚ መግለጫ እያደረገ ያለው 'መፈንቅለ-መንግሥት' እንዳልሆነና ተልዕኮውን ሲያጠናቅቅ ነገሮች ወደቀድሞው እንደሚመለሱ ማሳወቁን አላቋረጠም። የዚምባብዌ ጦር አባላት በሃራሬ ጎዳና ላይ ''መፈንቅለ-መንግሥት አይደለም'' ጄኔራል ሲቡሲሶ ሞዮ ጦሩን ወክለው በሰጡት መግለጫ "ማሳወቅ የምንፈልገው ጦሩ መንግሥት ገልብጦ ስልጣን አልያዘም" በማለት እየተካሄደ የለው መፈንቅለ-መንግሥት አለመሆኑን በተደጋጋሚ ሲናገሩም ተሰምተዋል። ሰራዊቱ መፈንቅለ-መንግሥት የሚለውን ቃል ለምን ፈራው? ጄኔራሉ መፈንቅለ-መንግሥት አይደለም ማለትንም ይመረጡ እንጂ የጦሩ እንቅስቃሴ መፈንቅለ-መንግሥት ይመስላል ስትል የቢቢሲዋ ሪፖርተር ከሃራሬ መዘገቧ አይዘነጋም። ከዚህ በተጨማሪም የአፍሪካ ሕብረት የጦሩ እንቅስቃሴ መፈንቅለ-መንግሥት ይመስላል ሲል ተደምጧል። የፖለቲካ ተንታኞች ጦሩ መፈንቅለ-መንግሥት የሚለውን ቀል መጠቀም ያልፈለገበት ምክንያት የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማሕበረሰብ (ሳድክ) መፈንቅለ-መንግሥት አካሂደው ስልጣን ለያዙ አካላት ዕውቅና ስለማይሰጡ ነው በማለት ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። ከግራ ወደ ቀኝ ሮበርት ሙጋቤ፣ ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ፣ ከምክትል ፕሬዝዳንትነታቸው የተባረሩት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እና ጄነራል ኮንስታንቲኖ ቺዌጋ አራቱ ቁልፍ ግለሰቦች በዚምባብዌ ፖለቲካዊ ቀውስ መስተዋል የጀመረው ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው የነበሩትን ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከስልጣን በማንሳት በምትካቸው ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤን ሊተኩ ካቀዱ በኋላ ነው። የሃገሪቱ የጦር አዛዥ ጀነራል ኮስታንቲኖ ቺዌንጋ ባሳለፍነው ሰኞ በዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ውስጥ መከፋፈል ካልቆመ ጦሩ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል አስጠንቅቀውም ነበር። በዚህ ሁላ ውጣ ውረድ ውስጥ የአራት ሰዎች ስም ተደጋግሞ ሲደመጥ ይሰማል። የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ መሪ ተውንያውያን እንደሆኑም ይነገራል እኚህ አራት ሰዎች። 1. ሮበርት ሙጋቤ ዚምባብዌ በአውሮፓውያኑ 1980 ነጻነቷን ከቅኝ ገዢዋ እንግሊዝ ከተቀዳጀች በኋላ በተደረገ ምርጫ ነበር አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡት። ሙጋቤ በስልጣን ዘመናቸው ከከወኗቸው ተግባራት በ1990ዎቹ መባቻ ላይ ያከናወኑት ሁሌም ይወሳል። በወቅቱ ሙጋቤ በጥቂት ነጮች ተይዞ የነበረውን ሰፊ መሬት በመንጠቅ ለጥቁር ዚምባብዌውያን አከፋፈሉ። ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በሥልጣን የቆዩት የ93 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ ሙጋቤ ስልጣን ለመልቀቅ ምንም አይነት ፍላጎት ባያሳዩም ጤናቸው ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ መምጣቱን ተከትሎ የሚተካቸው ማነው የሚለው ጥያቄ በበርካቶች ዘንድ ነበር። በተለይም ደግሞ በቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤና በቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት በኤመርሰን ምናንጋግዋ መካከል ለፕሬዝደንትነት በሚደረገው ፍጥጫ ውጥረት ተፈጥሮ ቆይቷል። 2. ግሬስ ሙጋቤ የሮበርት ሙጋቤ ሁለተኛ ሚስት የሆኑትና ከሙጋቤ በ40 ዓመት የሚያንሱት ግሬስ ሙጋቤ ከፕሬዝዳንቱ የቢሮ ፀሐፊነት በመነሳት በሃገራቸው ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴት ለመሆን በቅተዋል። ወዳጅና ደጋፊዎቻቸው "የድሆች እናት" እያሉ የሚጠሯቸው ግሬስ በነቃፊዎቻቸው ዘንድ ደግሞ ለሥልጣንና ሃብት እንደሚስገበገቡ ተደርገው ሲሳሉ ይስተዋላል። ግሬስ ሙጋቤ ከሥልጣን የተባረሩትን ምናንናግዋ "እባብ ስለሆነ ጭንቅላቱ በኃይል መመታት አለበት" ሲሉ መናገራቸውም አይዘነጋም። 3. ኤመርሰን ምናንናግዋ ግሬስ ሙጋቤ ብቅ ብቅ ከማለታቸው በፊት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የሙጋቤ 'ትክክለኛ' ምትክ ተደርገው ነበር የሚቆጠሩት። ከምክትል ፕሬዝደንትነታቸው ከተባረሩ በኋላ ለሕይወቴ ያሰጋኛል በማለት ሃገር ጥለው ሸሽተውም ነበር። ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግን ጦሩ ሃገሪቱ ከተቆጣጠረ በኋላ ኤመርሰን ምናንጋግዋ ወደ ዚምባብዌ ተመልሰዋል። በዚምባቡዌያን ዘንድ 'አዞ' እየተባሉ የሚጠሩት ኤመርሰን የደህንነት ሚኒስቴር ሆነው ከመሥራታቸው አንፃር የሃገሪቱን ጦር ኃይልና የደህንነት ኤጀንሲውን በደንብ እንደሚያውቁት ይነገራል። 4. ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ የምናንጋግዋ ቅርብ ወዳጅ ናቸው የሚባሉት የ61 ዓመቱ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ የዚምባብዌን ጦር ኃይል ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ መርተዋል። የዚምባብዌ ጦር ኃይል በፖለቲካ ኡደቱ ውስጥ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ በሰጡ በማግስቱ ነበር የዚምባብዌ ጦር ሃገሪቱን የተቆጣጠረው። ከቁም እስር በኋላ ሙጋቤ በተማሪዎች የምረቃት ፕሮግራም ላይ የሃገሪቱ ጦር ከሶስት ቀናት በፊት ስልጣን ተቆጣጥሮ ሙጋቤን በቁም እስር ካቆየ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓርብ ከሰዓት ሙጋቤ በአደባባይ ታይተዋል። በዚምባብዌ መዲና በሆነችው ሃራሬ በተማሪዎች የምረቃት ፕሮግራም ላይ ነበር ለህዝብ የታዩት። ሬውተርስ የዓይን እማኝን ጠቅሶ እንደዘገበው ሙጋቤ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከተመራቂዎች ሞቅ ያለ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። ሙጋቤ በአደባባይ ታዩ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ሙጋቤ በቀይ ምንጣፍ ላይ በዝግታ እየተራመዱ ወደ መድረኩ ሲወጡ ሞቅ ያለ ድጋፍ እና ጭብጨባ ሲደረግላቸው ነበር ሲል የቢቢሲው ሪፖርተር አንድሪው ሃርዲንግ ከሃራሬ ዘግቧል። የሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤም ሆኑ የትምህርት ሚንስትሩ በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ አልተገኙም። ሙጋቤ በየዓመቱ በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ መገኘትን ልምድ ያደረጉ ቢሆንም በቁም እስር ላይ እንደመቆየታቸው በፕሮግራሙ ላይ ይገኛሉ ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። ስለ ዚምባብዌ እና ሙጋቤ ምን ተባለ? የአፍሪካ ሕብረት ''ሕገ-መንግሥታዊ ላልሆኑ የመንግሥት ለውጦች የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የደቡብ አፍሪካ የልማት ማሕበረሰብ (ሳድክ) እውቅና አይሰጥም ሲሉ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ቃል አቀባይ የተናገሩት ጦሩ ሃገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ነበር። የቀድሞው የዚምባብዌ የተቃዋሚ ፓርቲ አማካሪና ጠበቃ የሆኑት አሌክስ ማጋኢሳ ደግሞ ''ሙጋቤ እራሳቸው በፈጠሩት አውሬ ተበሉ'' ሲሉ ተደምጠዋል። የደቡብ አፍሪካ መሪ ጃኮብ ዙማና የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ ''ሰላም፣ መረጋጋት እና መከባበር'' በዚምባብዌ እንዲሰፍን ጥሪ አቅርበዋል። ቻይና በበኩሏ''ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልኩ ነው'' ስትል ሃሳቧን አሰምታለች። የሙጋቤ ቀጣይ እጣ ፈንታ ዓርብ ጠዋት ዘሄራልድ የተሰኘው መንግሥታዊ ጋዜጣ ሙጋቤ ለቁም እስር ከዳረጓቸው የሀገሪቱ የጦር ኃላፊ ጋር ሲጨባበጡና ሲወያዩ የሚያሳይ ፎቶ ይዞ ወጥቷል። የዚምባብዌ የረጅም ጊዜ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ዛሬም ከሥልጣናቸውን በፍጥነት እንዲለቁ የቀረበላቸውን ጥያቄ አልቀበልም ስለማለታቸው በሰፊው እየተዘገበ ቢሆንም ጦሩ በሰጠው መግለጫ ከሙጋቤ ጋር እያካሄደ ያለው ውይይት ውጤታማ እየሆነ አንደሆነ ገልጿል። • ሙጋቤ ከሥልጣን አልወርድም እያሉ ነው የረዥም ጊዜ የሙጋቤ ተቃዋሚ የሆኑት ሞርጋን ሻንጋራይ ሙጋቤ የህዝባቸውን ፍላጎት ለማሟላት አሁኑኑ ከሥልጣናቸው መውረድ አለባቸው ይላሉ። የቢቢሲው ዘጋቢ አንድሪው ሃርዲንግ ከሙጋቤ ጋር ተደራድሮ የሽግግር መንግሥት ማካሄዱ ጊዜ መውሰዱ አይቀርም ይላል። በሌላ በኩል የዛኑ-ፒ ኤፍ ፓርቲ መሪዎች ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ እስከሚካሄድ ድረስ ሙጋቤ የመሪነት ስማቸውን ይዘው መቆየት እንደሚችሉና ያኔ ግን ምናንጋግዋ በይፋ የፓርቲውና የሀገሪቱ መሪ እንደሚሆኑ ገልጾ ነበር።
44027223
https://www.bbc.com/amharic/44027223
የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ፡ ያልተቋጨው የአፍሪካ ግጭት
በአፍሪካ ከተከሰቱ የድነበር ጦርነቶች ሁሉ ደም አፋሳሹ በኢትየጵያና በኤርትራ ከተጀመረ እነሆ ሁለት አስርታት ተቆጠሩ።
ጦርነቱ በተካሄደባቸው ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሁለቱም ወገን ለሞት እና ለመቁሰል ታደርገዋል። ምንም እንኳን በታህሳስ 2002 ዓ.ም የሁለቱ ሃገራት መሪዎች አልጀርስ ላይ የሰላም ስምምነት ላይ ቢደርሱም ሠራዊታቸው ድንበር ላይ ለጦርነት እንደተፋጠጠ ይገኛሉ። እስካሁን ፍፃሜ ያላገኘውን የሁለቱ ሃገራት ጦርነትን ከሃያ ዓመታት በፊት ምን ቀሰቀሰው? ይህንን ፍጥጫን ለማብቃት የሚያስችል ምንስ ተስፋ አለ? 'የመላጦች ፍልሚያ ለማበጠሪያ' ጦርነቱ ይህ ነው የሚባል የጎላ ጠቀሜታ በሌላት በትንሿ የድንበር ከተማ ባድመ ምክንያት ግንቦት 28 ቀን 1990 ዓ.ም ነበር የተቀሰቀሰው። የድንበር ከተማዋ የወርቅም ሆነ የነዳጅ ዘይት ሃብት ባይኖራትም ሁለቱም ሃገራት በራሳቸው ግዛት ስር እንድትሆን ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው። በወቅቱም ጦርነቱ "ሁለት መላጦች ለማበጠሪያ የሚደርጉት ፍልሚያ" በሚል ይገለፅ ነበር። ጦርነቱ እየተስፋፋ ሲመጣ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብን ለመፈናቀል ዳርጓል። "ይህ ጦርነት በሁለቱም ሃገራት ያሉ ቤተሰቦችን አፍርሷል" ሲል ለድንበሩ ቅርብ በሆነችው የአዲግራት ከተማ ነዋሪው ካሳሁን ወልደጊዮርጊስ ያስታውሳል። "ድንበር ተሻግረን በጋብቻ የተሳሰርን ነን፤ አንዳችን በአንዳችን ሠርግም ሆነ ቀብር ላይ ለመገኘት አንችልም" የሚለው ደግሞ ለሁለት በተከፈለችው የዛላምበሳ ከተማ ነዋሪ የሆነው አስገዶም ተወልደ ነው። "በኤርትራ በኩል ባለችው ሰርሃ መንደር ውስጥ የሚኖር ቤተሰብ ነበረ፤ ሴት ልጃቸው ኢትዮጵያዊ አግብታ ኢትዮጵያ ውስጥ ትኖር ነበር። ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ስትሞት ቤተሰቦቿ ቀብሯ ላይ መገኘት ስላልቻሉ፤ ከድንበር ባሻገር ኮረብታ ላይ ሆነው የቀብር ሥነ-ሥርዓቷን ለመመልከት ተገደዋል።" ጦርነቱ ተፅእኖውን ያሳረፈው በቤተሰብ ግንኙነት ላይ ብቻ ሳይሆን፤ በድንበር አቅራቢያ በንግድ የሚተዳደሩ ሰዎች ላይም ጭምር ነው። "ከጦርነቱ በፊት ሞቅ ብሎ የነበረው የንግድ እንቅስቃሴ አሁን የለም" ይላል በኤርትራ በኩል ባለች መንደር ውስጥ ነዋሪ የሆነው ክፍሎም ገብረመድህን። የአልጀርስ ስምምነት ሲፈረም ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልአዚዝ ቡቴፍሊካና ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ ጦርነቱ ያበቃው በሰኔ ወር 1992 ዓ.ም ይሁን እንጂ የኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር ኮሚሽንን የመሰረተው የሰላም ስምምነት እሰኪፈረም ድረስ ሌላ ስድስት ወራት አስፈልጎ ነበር። በስምምነቱ በባድመ ምክንያት የተከሰተውን ግጭት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ነበር የታሰበው። ነገር ግን ከ18 ወራት በኋላ በኮሚሽኑ የተሰጠው "የመጨረሻና አሳሪ" ውሳኔ አወዛጋቢዋን ባድመ ለኤርትራ በመስጠቱ በኢትዮጵያ በኩል ተጨማሪ ድርድር ማድረግን በቅድመ ሁኔታነት በመቅረቡ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ። ኤርትራም በበኩሏ ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ ፊት ከቀድሞ ወዳጇ ጋር ውይይት ለማድረግ ሳትፈቅድ ቀረች። ሁለቱም ሃገራት ከያዙት አቋም ፈቀቅ ለማለት ባለመፍቀዳቸው ሰላም የማስፈኑ ተስፋ የማይጨበጥ ሆኖ እስካሁን ዘልቋል። በቀጥታም ሆነ ሃገራቱ በሚደግፏቸው አማፂ ቡድኖች አማካይነት የድንበር ላይ ግጭቶች ቀጥለዋል። በዚህ ሁሉ ውስጥ አወዛጋቢዋ ባድመ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ስር ትገኛለች። በተጨማሪም ይህ ሁኔታ በሁለቱ ሃገራት እንዲሁም በቀሪው ዓለም ላይ ትልቅ ተፅእኖን አስከትሏል። አደገኛ የባሕር ጉዞ "በኢትዮጵያ በወረራ ተይዘው ባሉ ግዛቶች" ምክንያት ቀጣይነት ያለው ግዙፍ ሠራዊት እንደሚያስፈልጋት ኤርትራ ትገልፃለች። በዚህም ሠራዊቷን በዘላቂነት ለማጠናከር የግዴታ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎትን ታካሂዳለች። ቢሆንም ግን ይህን ከመነሻው ለ18 ወራት የታሰበው የግዴታ የውትድርና አገልግሎት በግልፅ ላልታወቀ ጊዜ ሊቆይ ይችላል። በዚህ የውትድርና አገልግሎት ላይ ላለመሳተፍ ለሚፈልጉ በርካታ ወጣቶች ብቸኛው አማራጭ ሃገራቸውን ጥለው መሰደድ ብቻ ነው። በዚህ መልኩ ከኤርትራ የሸሱ ወጣቶች በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ሱዳን ውስጥ የሚገኙ ትላልቅ የስደተኞች መጠለያዎችን አጨናንቀዋል። ወይም ደግሞ ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው የሰሃራ በረሃንና የሜዲትራኒያን ባሕርን በማቋረጥ አውሮፓ ለመግባት ጥረት ያደርጋሉ። ምንም እንኳን በርካቶች አደገኛው ባሕር ውስጥ ሰምጠው ቢሞቱም ወይም የጉዞ መስመሩን የሚቆጣጠሩት ታጣቂዎችና የሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ግፍ ሰለባ ቢሆኑም፤ ኤርትራዊያን ወደ አውሮፓ ለመሻገር ከሚሞክሩት ሁሉ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችበትን ፍጥጫ ሕገ-መንግሥት ሥራ ላይ እንዳይውል ለማድረግ፣ ነፃ ጋዜጦችን ለማገድ እንዲሁም ተቃዋሚዎችን ለመጨቆን እንደምክንያት ተጠቅማበታለች። በ1993 ዓ.ም የኤርትራ መንግሥት በወሰደው እርምጃ ብቅ ብቅ እያሉ የነበሩ የግል ጋዜጦች በርካታ አርታኢያንና ዘጋቢዎች ለእስር ተዳርገዋል። በተመሳሳይ ጊዜም ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጦርነቱን የመሩበት መንገድና ተጠያቂ ለመሆን አለመፍቀዳቸውን የተቹ የገዢው ፓርቲ የሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትህ (ሕግዴፍ) ታዋቂ መሪዎች ታስረዋል። እስካሁንም ድረስ ታሳሪዎቹ ያሉበት ቦታ አይታወቅም። በኤርትራ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ፈፅሞ ፍርድ ቤት ቀርበው የማያውቁ ሲሆን ማንም እንዲጠይቃቸውም አይፈቀድም። የመንግሥት ባለስልጣናት ታሳሪዎቹን የሃገሪቱን "ብሔራዊ ደህንነት" አደጋ ላይ በመጣል ይከሷቸዋል። በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኤርትራን በሰብአዊነት ላይ ሳይፈፀሙ አልቀሩም የሚላቸውን ወንጀሎችን ጨምሮ በከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይከሳታል። ኢትዮጵያም በሰብአዊ መብት ጥሰቶች የምትከሰሰው ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ከድንበር ከተማዋ ባድመ ይልቅ የሚያሳስባት በሃገር ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ነው። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የተቀሰቀሱ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠርም በቅርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አውጃለች። ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚወስደው መንገድ ስለሠላም ማሰብ በባድመ ምክንያት ለዓመታት የዘለቀው ፍጥጫ መቋጫ ያገኝ ይሆን? አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፍጥጫው ሠላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ ቢያቀርቡም ከኤርትራ በኩል የተሰጠው ምላሽ ጥሪዉ ቀደም ያሉት የኢትዮጵያ መሪዎች ካቀረቡት የተለየ አለመሆኑን በመጥቀስ ውድቅ አድርገውታል። "በእርግጥም ሠላም ለሁለቱም ሕዝቦች ጠቃሚ ነው፤ ነገር ግን ይህ መሰረት ማድረግ ያለበት ኢትዮጵያ እስካሁን ሳታከብረው የቆየችውን ዓለም አቀፍ ሕግ በማክበር ነው" ሲሉ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ተናግረዋል። ቢሆንም ግን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅርቡ ወደ ኤርትራ የተጓዙት የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን የዶናልድ ያማሞቶ ጉብኝት አዲስ ተስፋን ፈጥሯል። ባለስልጣኑ በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያም ተጉዘው ነበር። "በሁለቱም ወገን ያለው ሕዝብ ሠላምን ይፈልጋል፤ በአሁኑ ወቅት መሪዎች ስለሠላም ሲናገሩ መስማት መልካም ነው" ይላል ኤርትራዊው ክፍሎም ገብረመድህን። "ሕዝቡ በመንግሥታቱ ላይ ግፊት በማድረግ ሠላም እንዲመጣና የነበረው ግንኙነት እንዲቀጥል እንደሚያደርግ እርግጠኛ ነኝ" ድንበር ተሻግሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ካሳሁን ወልደጊዮርጊስም ይህንኑ ተስፋ ያደርጋል። "ይህ ወደ አስመራ የሚወስደው መንገድ እሰከመጨረሻው ተዘግቶ እንደማይቀር እናምናለን" ይላል።
news-53424332
https://www.bbc.com/amharic/news-53424332
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ተፈጥሯዊ የውሃ ሙሌት ሂደትን ማስቆም ይቻላል?
ከሰሞኑ የወጡ የሳተላይት ምስሎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውስጥ ያለው የውሃ መጠን መጨመሩን ማመልከታቸውን ተከትሎ የግድቡ የመጀመሪያ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት ተጀምሯል የሚሉ መረጃዎች መውጣት ጀምረዋል።
የተለያዩ የማጻጸሪያ የሳተላይት ፎቶዎች የግድቡ ሙሌት በይፋ አለመጀመሩን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ የገለፁ ቢሆንም እየጣለ ባለው ከፍተኛ ዝናብ ግድቡ ውሃ መያዝ መጀመሩን አስረድተዋል። የሳተላይት ምስሎቹ ወደ ግድቡ የሚገባው ውሃ መጨመሩን የሚያሳዩ መሆናቸውን ገልፀው፤ ባለፈው ዓመት ውሃው ያልፍ የነበረው በ520 ሜትር ከፍታ ላይ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት 560 ከፍታ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። ከ560 ሜትር ከፍታ በታች ያለው ውሃ ግድቡ ውስጥ የሚቀር እንደሆነም አስረድተዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በግድቡ ዲዛይንና ባለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የውሃ ሙሌቱ በይፋ መንግሥት ጀምሬዋለሁ ባይልም ግድቡ ውሃ መያዙንም ሚኒስትሩ አሳውቀዋል። ሚኒስትሩም ለፋይናንሻል ታይምስ በሰጡት ቃለ መጠይቅም "የዝናብ ወቅት እንደመሆኑ መጠን ግድቡ ውሃ ይዟል። ይሄ በሁሉም አካላት ዘንድ የሚታወቅ ነው፤ ግብጾችም ያውቁታል። ለሕዝባቸው መንገር አለባቸው" ብለዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ ያዘ ሲባል ምን ማለት ነው? የውሃ ሙሌት በይፋ ተጀረ ሲባል እንዴት ይገለፃል? የሚለውን ለማብራራት ቢቢሲ በውሃ ምህንድስናና በግድብ ግንባታ ዘርፍ የበርካታ ዓመታት ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች አነጋግሯል። የህዳሴው ግድብ ግንባታ ባህሪይ የግንባታውን ሂደት ከመነሻው አንስቶ በቅርበት የሚያውቁና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ኢትዮጵያዊ የዘርፉ ባለሙያ ሲያስረዱ ግድቡ ውሃ ያዘ ወይም ሙሌት ተጀመረ የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ ለመረዳት የህዳሴው ግድብ አገነባብን መረዳት እንደሚያስፈልግ ይገልጻሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ግድቡ የተሰራው ሸለቆ ውስጥ በመሆኑ ኢትዮጵያ ግድቡን ለመሙላት የምትዘጋውም ሆነ የምትከፍተው ነገር እንደሌለ በቀዳሚነት በማስረዳት የተፈጥሮ አካበቢው ለዚሁ ተብሎ የተመረጠ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይም ሆኑ ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በተደጋጋሚ ሲናገሩት እንደነበረው በዚህ ዓመት ግድቡ 25 ሜትር የነበረው ከፍታው ወደ 60 አድጓል። በዚህም የተነሳ ከዚህ ቀደም በግድቡ አናት ላይ ይፈስ የነበረውን የክረምት ውሃ ማጠራቀም ጀምሯል ሲሉ ተደምጠዋል። እንደ እኚህ ባለሙያ ማብራሪያ ከሆነም በክረምት ዝናብ ምክንያት ወደ ውሃ ማጠራቀሚያው የገባው ውሃ የሚወጣበት እድልም የለውም። ለዚህ የግድቡ ማዕከላዊ ክፍል ከላይ የክረምት ውሃ ማሳለፍ እንዲችል በበጋ ደግሞ በዚሁ ማዕከላዊ ክፍል ያለምንም ችግር ማሳለፍ እንዲችል ተደርገው የተሰሩ መዋቅሮች ( ስትራክቸሮች) እንዳለውም ይጠቅሳሉ። ይህ በበጋ ውሃውን ለማሳለፍ የሚያስችለው ክፍል በህዳሴው ግድብ ላይ አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት መሆኑንም ከተመለከቷቸው የግድቡ ዲዛይንና ምስሎች እንደሚረዱ ባለሙያው ያብራራሉ። በክረምት ወቅት ወደ ግድቡ የሚገባው ውሃ እና የሚወጣው ስለማይመጣጠን በክረምት እንዲጠራቀምም ተደርጎ ዲዛይን መደረጉንም በማመልከት ውሃው ግድቡ ላይ እንዳይፈስ ማዕከላዊው የግድቡ ክፍል ዝቅ ተደርጎ ነው የተሰራው። ክረምት ሲመጣ ከስር ለማሳለፍ ተብለው በተሰሩት መዋቅሮች እየፈሰሰ ይሄድና ከማስተንፈሻው አቅም በላይ ሲሆን ደግሞ በዚህ በ25 ሜትር ከፍታ ላይ ይፈሳል። ኢትዮጵያ በዚህኛው የበጋ ወራት ይኸኛውን 25 ሜትር የነበረውን ከፍታ ወደ 60 ሜትር ከፍ እንዳደረገችው ያስረዳሉ። [በምስሉ ላይ ያለውን ቀስት ወደ ግራና ወደ ቀኝ በማንቀሳቀስ በግድቡ አካባቢ በተለያዩ ቀናት የታውን የውሃ ልዩነት ይመልከቱ] Interactive A large reservoir is beginning to form behind the dam 12 July 2020 26 June 2020 በቀላል አገላለጽ በበጋው ወቅት በማስተንፈሻው በኩል ያልፍ የነበረው ውሃ በክረምት ወቅት መጠኑ ከፍተኛ ስለሚሆን ማለፍ አይችልም። ስለዚህ ተወደደም ተጠላ ውሃ እየተጠራቀመ 60 ሜትር ከፍታ ላይ ሲደርስ በግድቡ ላይ ይፈሳል። እስከዚያ ድረስ ግን የትም መሄጃ ስለሌለው ውሃው ይጠራቀማል። የግድቡን ግንባታ ካላቸው ሙያና ከተለያዩ ምንጮች በቅርበት የሚከታተሉት የውሃ ምህንድስና ባለሙያው እንደሚሉት አሁን ባለው ሁኔታ የሚከፈት ወይም የሚዘጋ ነገር አለመኖሩን ደግመው ያረጋግጣሉ። በአተጠቃላይ የታላቁ የህዳሴ ግድብ አገነባብ ውሃው እንዲጠራቀምም እንደሚያስገድደው በመሆኑ አሁን እታየ ያለው የውሃ ክምችት ከፍተኛ ዝናብ እጣለ በመሆኑ በዚህ ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ይናገራሉ። ባለሙያው ሲያጠቃልሉ "ይህ ማንም የሚቆጣጠረው አይደለም፤ ስለዚህ በጋ ሲሆንና የውሃው መጠን ሲቀንስ የግድቡ ማዕከላዊ ክፍል በግንባታ ምክንያት ውሃ እንደ ቀድሞው በማስተንፈሻው በኩል ያልፋል ማለት ነው" ብለዋል። ተፈጥሯዊ የውሃ ሙሌት በግድቡ በስተጀርባ ባለው የውሃ ማጠራቀሚያ ሰፊ ስፍራ ላይ ከሰኔ ጀምሮ እስከ መስከረም ድረስ በሚቆየው የዝናብ ወቅት ላይ በተፈጥሯዊ ሁኔታ ውሃ መጠራቀም ይጀምራል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ በኋላ አንስቶ በቅርብ ሲከታተሉ የቆዩት ዶክትር ኬቭን ዊለር እንደሚሉት አሁን ግድቡ ከደረሰበት የግንባታ ደረጃ አንጻር "የግድቡን ዝቅተኛ የውሃ መያዣ ክፍልን ውሃ እንዳይዝ የሚያደርግ አንዳችም ነገር የለም" ሲሉ የግንባታው ሂደት ውሃ ለማቀብ መድረሱን ይገልጻሉ። የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ከዘጠኝ ዓመት በፊት አንስቶ ግዙፍ የግንባታ ሥራ እየተከናወኑ የአባይ ወንዝ ውሃ ያለችግር ሲከናወን የቆየ ሲሆን፤ በበጋ ወቅት ደግሞ የውሃው መስመር በሌላ በኩል እንዲያልፍ ተደርጎ ቀሪው ክፍል እንዲገነባ ተደርጓል። በአሁኑ ጊዜ የግድቡ ማዕከላዊ ክፍል የታችኛው አካል ተገንብቶ በማለቁ ውሃው በግድቡ ግድግዳ ላይ ባሉ የውሃ ማስተላለፊያዎች በኩል እንዲፈስ እየተደረገ ነው። ከፍተኛ ዝናብ የሚጥልበት በአሁኑ የክረምት ወቅት ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ወደ ግድቡ ስለሚገባ ውሃው በግዙፎቹ የግድቡ የማስተላለፊያ ቦዮች በኩል መፍሰስ ከሚችለው አቅም በላይ ይሆናል። ይህም ማለት በግድቡ በኩል አልፎ ከሚፈሰው ውሃ በተጨማሪ ከፍተኛ መጠን ያከለው ከግድቡ ጀርባ ባለው ውሃ እንዲያርፍበት በተዘጋጀው ሰፊ ቦታ ላይ በመጠራቀም ሐይቅ መፍጠር ይጀምራል ሰሉ ዶክተር ዊለር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጨምረውም ኢትዮጵያ በውሃ ማጠራቀሚው ቦታ ላይ የሚያርፈውን የውሃ መጠን መጨመር ከፈለገች በግድቡ ላይ ያሉትን የውሃ ማፍሰሻ መተላለፊያዎችን መዝጋት ትችላልች። ነገር ግን ይህ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። የህዳሴ ግድብ ቀጣይ ደረጃ የአባይ ወንዝ ዓመታዊ አማካይ የውሃ ፍሰት 49 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን ከዚህ ውስጥ በመጀመሪያው ዓመት የውሃ ሙሌት ታላቁ የህዳሴ ግድብ 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በመያዝ የግድቡ ዝቅተኛው ውሃ መያዝ ደረጃ ድረስ ውሃ ለማቀብ ይችላል። ይህም ኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖችን እንድትሞከር ያስችላታል። በቀጣዩ የበጋ ወቅት ከግድቡ ጀርባ የተጠራቀመው ውሃ ስለሚቀንስ የግድቡን ቁመት መጠን ለመጨመር የሚደረገው ግንባታ እንዲቀጥል ዕድል ስለሚሰጥ ሥራውን በማከናወን በሁለተኛው ዓመት ደግሞ 13 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንዲይዝ ይደረጋል ይላሉ ባለሙያው። በዚህ ጊዜም በግድቡ አማካይነት የሚታቀበው የውሃ መጠን በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተገነቡትን የኤሌክትሪክ ማመንጫ ተርባይኖች ጋር ይደርሳል። ይህ ደግሞ የውሃውን ፍሰት በበለጠ ለመቆጠጠር ያስችላል። ኢትዮጵያ እንዳለችው የግድቡ ከፍተኛ አቅም የሆነውንና አስፈላጊውን የ74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በግድቡ ውስጥ ለመያዝ ከአምስት እስከ ሰባት ዓመታት ያስፈልጋል። ግድቡ በሚጠበቀው መጠን በውሃ ተሞልቶ ሲያበቃ በተጠራቀመው ውሃ የሚፈጠረው ሐይቅ 250 ኪሎ ሜትሮችን የሚያካልል ቦታን በውሃ ይሸፍናል። ግድቡ ተጠናቆ ሥራ ሲጀመር በአፍሪካ ትልቁ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ግድብ ሲሆን በዓለም ካሉ 10 ግዙፍ ተመሳሳይ ግድቦች መካከልም ይመደባል። ያልተቋጨው ውዝግብ ለአስር ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎበት እተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታው ከሦስት አራተኛው በላይ ጠተናቋል። ቢሆንም ግን በግድቡ ዙሪያ በተነሱ ሕጋዊና ቴክኒካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብጽ ጋር ለዓመታት ስታካሂዳቸው የነበሩት ድርድሮች እስካሁን መቋጫ አላኙም። ኢትዮጵያ ከአገራቱ ጋር ከስምምነት ለመድረስ ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ የገለጸች ሲሆን፤ ቢሆንም ግን በድርድሮቹ የሚገኘው ውጤት ግድቡን ውሃ ከመያዝና ሥራውን ከማስጀመር እንደማያግዳት በተደጋጋሚ አሳውቃለች። ሱዳንና ግብጽ በበኩላቸው ግድቡ ከሚያገኙት ዓመታዊ የውሃ መጠን ላይ መቀነስን ስለሚያስከትል ከስምምነት ከመደረሱ በፊት የውሃ ሙሌቱ እንዳይጀመር ሲወተወቱ ቆይተዋል። ኢትዯጵያ የግድሙን ሙሌት ገና እንዳልጀመረች ያሳወቀች ሲሆን ከሰኔ ወር ጀምሮ በአገሪቱ እጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የግድቡ የውሃ ማተራቀሚያ ክፍል ላይ መጠኑ እጨመረ የሚሄድ የውሃ መጠን መታቱ ሱዳንና ግብጽን ሳያሳስባቸው አልቀረም። ይህንን በተመለከተም ግብጽ ኢትዮጵያ መንግሥት በግድቡ የውሃ አያያዝ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጣት ጠይቃለች።
news-53967066
https://www.bbc.com/amharic/news-53967066
አዲስ አበባ ፡ ሕገወጥ የመሬት ወረራ ላይ የወጣው ሪፖርትና የቀድሞው ምክትል ከንቲባ ምላሽ
ትናንት፣ ሰኞ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተባባሰ የመጣ፣ የመንግሥታዊ መዋቅሮች ድጋፍ ያለው ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ እንዳለ ባካሄድኩት ጥናት ደርሼበታለሁ ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።
የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የአሁኑ የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በበኩላቸው በቀጥታ የኢዜማን ጥናት ባይጠቅሱም ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ታከለ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት "የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው።" ብለዋል። አቶ ታከለ አክለውም ለ20ሺህ አርሶ አደሮች የተሰጡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በተመለከተም ከአንድ አመት ተኩል በፊት በካቢኔ የተወሰነና የተተገበረ መሆኑን በዚሁ መልዕክታቸው ላይ አስፍረዋል። ተግባሩ በይፋ የተከናወነ መሆኑን በማንሳትም ከመሬታቸው ላይ ተፈናቅለው በዝቅተኛ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ 67 ሺህ አባወራዎች እንደነበሩ በመጥቀስ ከእነርሱ መካከል "የከፋ ችግር ላይ ለወደቁት 20 ሺህ ኮንዶሚንየም" መሰጠቱን አንስተው ተግባሩንም " ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም።" ብለዋል። በተጨማሪም በዚህ ተግባራቸው እንደሚኮሩ ገልፀው "በግፍ የተገፋን፣ በግፍ ከመሬቱ የተፈናቀለን አርሶ አደር መካስ ያኮራናል!" ብለዋል። አቶ ታከለ በፌስቡክ መልዕክታቸው ኢዜማን ባያነሱም " አንድም ቀን በግፍ ለተፈናቀሉ አርሶአደሮች የመቆርቆር ስሜት አሳይቶ የማያውቅ ቡድን ዛሬ የአርሶአደሮችን ጉዳት ለተቀባይነት ማግኛ መጠቀሚያ ሲያደርገው ማየት " ብለዋል። በተጨማሪም "በሀሰተኛ መረጃ ድካማችንና ስራችንን ለማጠልሸት ቢሞከርም ስራችን ይናገራልና ፍርድ የህዝብ ነው!" ሲሉ መልዕክታቸውን አጠቃልለዋል። የኢዜማ የጥናት ሪፖርት ምን ነበር? የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እየተባባሰ የመጣ፣ የመንግሥታዊ መዋቅሮች ድጋፍ ያለው ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ እንዳለ ባካሄድኩት ጥናት ደርሼበታለሁ ብሏል። ፓርቲው እዚህ ውጤት ላይ ለመድረስ ያስቻለውን ጥናት ያደረገው ከኅብረተሰቡ የመሬት ወረራን እና ሕገ ወጥ የቤት እደላን አስመልክቶ የተሰጡ ጥቆማዎችና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የቀረቡ ዘገባዎች መሰረት በማድረግ ኮሚቴ አዋቅሮ ባደረገው ምርመራ መሆኑን ጠቅሷል። በተለያዩ መንገዶች በተደረጉ የመረጃ ማሰባሰቢያ ዜዴዎች አማካይነት ኢዜማ በተጨባጭ አረጋግጨዋለሁ እንዳለው "ታይቶ በማይታወቅ መጠንና ስፋት ግልፅ የሆነ የመሬት ወረራ እና ሕገ-ወጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕደላ ተድርጓል" ብሏል። በዚህ መልኩ የተያዙ ቦታዎችም ሕጋዊ ይዘት እንዲኖራቸው የሚያስፈልጋቸው ሰነዶች እንደተዘጋጁላቸው እንደደረሰበት የሚገልጸው የፓርቲው የጥናት ውጤት የከተማው አስተዳደር አካላትም ይህን ሂደት እንደሚያወቁ ጠቅሷል። ቢቢሲ በኢዜማ የቀረበውን ይህንን የጥናት ውጤት መሰረት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰጠው ምላሽን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ኢዜማ በጥናቱ ላይ "የከተማው አስተዳደር እያየና እየሰማ በሕገ-ወጥና በተደራጀ መልኩ በወረራ የተያዙ ቦታዎች በፍጥነት ካርታና ፕላን ተሰርቶላቸው ለሦስተኛ ወገን በሽያጭ ተላልፈዋል በማኅበርና በግል ለማምረቻና ለንግድ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርገዋል" ብሏል። የጋራ ቤቶችን በተመለከተም የከተማው አስተዳደር ባወጣው ደንብ መሰረት "በምንም መስፈርት የቤት ተጠቃሚ ሊሆኑ የማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤትና የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል" ሲል በጋራ የመኖሪያ ቤቶች በኩል አሉ ያላቸውን የአሰራር ችግሮች ጠቅሷል። ጥናቱ እንዳለው በከተማዋ የተለያየ አይነት ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ ተግባራት እንደተከናወኑ አመልክቶ፣ እነዚህም በጅምር ቤት ስም ከባለ ይዞታዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በመግዛት ግንባታ የማካሔድ፣ ባዶ መሬቶችን በቡድንና በግለሰብ ደረጃ በማጠር የመያዝ እንዲሁም ለሌላ ወገን የማስተላለፍ በተጨማሪም "በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በተዘረጋው ሰንሰለት በጥቅም ተጋሪነትና በዝምድና" ሠፋፊና ቁልፍ ቦታዎችን መያዝ በከተማዋ ውስጥ መታየቱን ገልጿል። ፓርቲው በጥናት አገኘሁት እንዳለው በመሬት ወረራው ላይ ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበሩት ሰዎች፣ 'ቦታዎቹ ከዚህ ቀደም የቤተሰቦቻችን ናቸው፤ በቂ ካሳ ሳይከፈለን ከቦታችን ተነስተናል' የሚሉ ግለሰቦችና ወረራ የተፈፀመባቸው አካባቢ ላይ የሚገኙ "የክፍለ ከተማና የወረዳ ኃላፊዎችና ፈፃሚዎች ናቸው" ብሏል። ጨምሮም በተደራጀ መልኩ የተፈፀመው የመሬት ወረራ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ያሉ አመራሮች የተሳተፉበት እንደሆነና "ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና አደረጃጀቶች መሬቱን ወርረው እንዲይዙ አመቻችተዋል፤ የመንግሥትን ሥልጣንንም ለሕገ ወጥ ተግባር ከለላ እና ሽፋን እንዲሆን አድርገዋል" በማለት ጠቅሷል። ከዚህ ባሻገርም ፓርቲው ያደረገው ጥናት የጠቀሳቸው የመንግሥት አካላት ሕገ-ወጥ የሆኑ የግንባታ ፈቃዶች፣ ካርታ እና ልዩ ልዩ ሰነዶችን ለማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች በማዘጋጀት ሕገ ወጥ ድርጊቶቹ ሕጋዊ መስለው እንዲቀርቡ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል በማለት ከስሷል። ይህ ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ ተግባር በከተማዋ አዲስ አለመሆኑን ያመለከተው የኢዜማ ጥናት፣ አሁን በአዲስ አበባ ከተማ ከተስተዋለው ጋር ሲነጻጸር በዚህ ደረጃና ፍጥነት የተስፋፋበት ጊዜ አልነበረም። በአሁኑ ጊዜ የተከሰተው የመሬት ወረራ የተከናወነባቸው ስፍራዎች ስፋት ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ፣ ወረራው የከተሞችን አረንጓዴ ቦታዎች፣ የወንዝ ዳርቻዎች እንዲሁም ለመሰረተ ልማት አውታር ዝርጋታ በፕላን የተከለሉ ቦታዎችን ያካተተ በመሆኑ የጉዳቱ መጠን ከፍተኛ ነው ብሏል። ኢዜማ ባደረገው ጥናት ላይ እንዳመለከተው፣ እንዲህ አይነቱ የመሬት ወረራ በስፋት የተከሰተው በከተማዋ ዳርቻ ላይ ባሉ ቦታዎች ላይ ሲሆኑ በአምስት ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የተወስኑ ቦታዎችን በመዳሰስ የተለያዩ ማሳያዎችን አስቀምጧል። እነዚህም ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ የካ፣ ቦሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ናቸው። ጥናቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አሰጣጥ በተመለከተ "የመንግሥት ሕገ ወጥ ተግባር በግልጽ ታይቷል" ብሏል። ለዚህም ኢፍትሐዊ ሕጎችንና መመሪያዎችን በማውጣት፣ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ሕጎችንና ደንቦችን በማሻሻል ለካቢኔውና ለከንቲባው በተሰጠ ልዩ ሥልጣን "ከንቲባውም ሆነ ካቢኔያቸው ቤቶችን እንደፈለጉ እንዲያድሉ ምክንያት ሆኗል" ሲል ጠቅሷል። "በዚህም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢፍትሐዊ በሆነ መልኩ ፈጽሞ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለማይገባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ቤት የማስተላለፍ ተግባር እንደፈፀመና እየፈጸመ መሆኑን አረጋግጠናል" ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ከአሁን ቀደም ቦታና ኮንዶሚኒየም የተሰጣቸው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ደግሞ ድጋሚ በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየታደላቸው መሆኑን እንዳረጋገጡ ጠቅሰዋል። "በዚህ መሠረትም ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቢሮዎች ሳር ቤት አካባቢ ከሚገኘው ጽሕፈት ቤት ሁሉም የተመዘገቡ ሠራተኞች በሰኔ ወር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የድልደላ እጣ የወጣላቸው ሲሆን፣ ሁሉም ሠራተኞች የኮንዶሚኒየም ብሎክ ቁጥርና የቤቱን ቁጥር በስማቸው ተረጋግጦ የተሰጣቸው ሲሆን የነዋሪነት መታወቂያ የተዘጋጀላቸው" መሆኑን ገልጿል። ጥናቱ ጨምሮም "የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንጻዎች ውስጥ የተሠሩ የንግድ ቤቶች በተመለከተ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች፣ ልጅና የልጅ ልጅ ተብለው በገፍ ስለመታደላቸው፤ በእግር ኳስ ደጋፊነት ስም ለተሰባሰቡ ማኅበራት መከፋፈላቸው ተጨባጭ ማስረጃዎች ተገኝተዋል" ሲል በሪፖርቱ ላይ ገልጿል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተከስቷል ስላለው ሕገወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን በተመለከተ ጥናት አድርጎ ያገኘውን ውጤት ይፋ ባደረገበት ዘገባው ላይ መደረግ ስላለባቸው የማስተካከያ እርምጃዎች የመፍትሔ ሃሳብ አቅርቧል። ፓርቲው በጥናት አገኘሁት ያለውን ይህንን ውጤት ይፋ ለማድረግ ባለፈው አርብ እንዲሁም ሰኞ የጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ፓርቲው ማሟላት የነበረበትን ቅድመ ሁኔታ አላሟላም በሚል በፖሊስ እንዳይካሄድ መደረጉ ይታወሳል።
news-53915683
https://www.bbc.com/amharic/news-53915683
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን፡ "የመንግሥት ባለሥልጣናት ኃላፊነታቸውን በወቅቱ እና በብቃት አልተወጡም"
ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ተከትሎ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በአንዳንድ ቦታዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ የቤተክርስቲያኒቱ ምእመናን መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባደረገችው ማጣራት እንደተረዳች አስታወቀች።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህንን በማስመለክት ባወጣችው መግለጫ ላይ እንዳመለከተችው ድርጊቱን በማስቆምና ከተፈጸመም በኋላ ተጎጂዎችን በመካስና ፍትሕ እንዲያገኙ በማድረግ በኩል የመንግሥት ኃላፊዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ስትል ወቅሳለች። ይህንን በተመለከተ የኦሮሚያ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያቀረበችው ቅሬታ የክልሉ ያለበትን ተጨባጭ እውነታ ያላገናዘበና እየተደረገ ያለውን ጥረት ከግምት ያላስገባ ነው ሲሉ ለቀረበው ወቀሳ ለቢቢሲ መልስ ሰጥተዋል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ያወጣችው መግለጫ 'በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ ዞኖች ተቀነባብረው በተፈጸሙ ጥቃቶች የተጎዱ የቤተክርስቲያኗ ምዕመናንን መርዳትና መልሶ ማቋቋምን አስመልክቶ' የወጣ እንደሆነ ያመለከተ ሲሆን፤ በሃጫሉ ሁንዴሳ ድንገተኛ ሞት ሐዘን እንደተሰማትም ገልጿል። "ሆኖም በግድያው የተሰማትን ሐዘን ለመወጣት ጊዜ ሳይሰጣት፣ ሐዘንተኛነቷ ተረስቶ እና እንደ ጠላት ተቆጥራ፣ በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች በክርስቲያን ልጆቿ ላይ ዘግናኝ ፍጅት እና መከራ ተፈፅሞባቸዋል" ሲል መግጫው በመዕእመናን ላይ ደርሷል ያለውን ጉዳት አመልክቷል። የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በእምነታቸው ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ፣ እንደተደፈሩና ቤት ንብረታቸው እንደወደመ ቤተ ክርስትያኗ በመግለጫዋ አትታለች። "ብዙዎች ከሞቀ ቀዬአቸው ተፈናቅለው የክረምቱን ጨለማ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን በሚገኙ መቃብር ቤቶች እና አዳራሾች፣ በልዩ ልዩ መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም በግሰለቦች ቤት ተጠልለው ለማሳለፍ ተገደዱ፤ ለአስከፊ ማኅበራዊ እና ሥነ ልቡናዊ ቀውሶች ተዳረጉ" ሲል መግለጫው ያስቀምጣል። ቤተ ክርስትያኗ፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት ፍትህን በማስከበር ረገድ ተገቢውን እርምጃ አልወሰዱም ስትልም ትወቅሳለች። "ቤተ ክርስቲያናችን፣ ይህንኑ የተቀነባበረ ጥቃት እንደሰማች፣ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም በቋሚ ሲኖዶስ በኩል የሐዘን መግለጫ አውጥታለች፤ በአገር ውስጥ እና በውጭ በሐዘንና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ስታመለክት ከርማለች" በማለት ከመጀመሪያው አንስቶ የተደረገውን ተግባር ጠቅሷል። መግለጫው አክሎም "የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም "አጥፊዎችን አንታገሥም፤ ተገቢውን ፍትሕ እንሰጣለን፤ የተጎዱትን እንክሳለን፤" ብለው ቃል የገቡትን ይፈጽሙ እንደ ኾነ በማለት በትዕግሥት ጠብቃ ነበር። "ሆኖም ዜጎችን ከጥቃት አስቀድሞ የመከላከል እና የመጠበቅ፣ ፍትሕን የማስፈንና ተጎጂዎችን በአግባቡ የመካስ ሐላፊነታቸውን በወቅቱ እና በብቃት ሲወጡ አላየችም" በማለት ወቅሷል።መግለጫው እንደተመለከተው ሲኖዶሱ በምዕመናን ላይ የደረሰውን ጉዳይ የሚያጠና ዐቢይ ኮሚቴ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እንዲቋቋም መመሪያ ሰጥቷል። ኮሚቴው ተጎጂዎችን፤ በጊዜያዊነት ለመርዳት እና በዘላቂነት ለማቋቋም የሚሠራ ይሆናል። ኮሚቴው በመጀመሪያ ዙር ሥራው ጥቃቱ የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች በዝርዝር በመለየት፣ ተጎጂዎችን የማጽናናት እና መረጃ የማሰባሰብ ጉዞ ማካሄዱ ተሰምቷል። "የዐቢይ ኮሚቴው ልኡካን፣ ተጎጂዎችንና በማነጋገር እና ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች በመጎብኘት ባቀረቡት ሪፖርት መሠረት፣ የልጃችን የኃይለ ገብርኤልን [ሃጫሉ ሁንዴሳ] ግድያ ተከትሎ፣ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፣ የመንግሥትን መዋቅር ተገን ያደረጉ የእምነት እና የብሔር ጽንፈኞች አስቀድመው ከተደራጁ ኃይሎች ጋራ በመቀናጀት የፈጸሙት ስልታዊ እና አረመኔያዊ ጥቃት ዋና ዒላማ፣ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን እንደነበሩ ተረጋግጧል» ይላል የሲኖዶሱ መግለጫ። መግለጫው አክሎ ጉዳት ደረሰባቸው ያላቸውን ሰዎች ቁጥር ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት ከሰኔ 22 ቀን ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በተፈጸመው በዚያ ጥቃት ከ67 በላይ ምእመናን በግፍ እና በአሠቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን፤ 38 ምእመናን ከባድ፣ 29 ምእመናን ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው መግለጫው አመልክቷል። ከሰባት ሺህ በላይ ምእመናን ከመኖሪያቸው ከመፈናቀላቸው ባሻገር፣ በተለያየ ደረጃ ለሚገለጽ ሥነ ልቡናዊ እና ሥነ አእምሯዊ ቀውስ ተዳርገዋል፤ ከአምስት ቢልዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረታቸውንም በዘረፋ እና በቃጠሎ ማጣታቸውን፣ ከዐቢይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል» ብሏል። ዐቢይ ኮሚቴው መንግሥት ችግር ያሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን መልሶ ለሟቋቋም ሊያደርጋቸው ይገባል ያላቸውን ተግባራት በዝርዝር አስቀምጧል። «የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና የፌዴራል መንግሥት፣ የኦርቶዶክሳውያን ኢትዮጵያውያንን በሕይወት የመኖር እና ሀብት የማፍራት ሰብአዊ እና ዜግነታዊ መብቶችን በማስከበር፣ የደኅንነት እና የኑሮ ዋስትና በአፋጣኝ እንዲያረጋግጥላቸው ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ታሳስባለች።» መንግሥት፤ 'ጥቃቱን ያቀዱትን፣ የፈጸሙትንና ያስተባበሩትን ኀይሎች እንዲሁም፣ የተጣለባቸውን ሓላፊነት ወደ ጎን በማለት ጥቃቱን በዝምታ የተመለከቱትን በመዋቅሩ ውስጥ ያሉትን ሹማምንት እና የጸጥታ አካላት የኾኑ አጥፊዎችን፣ በቁጥጥር ሥር እንዲያውል' መግለጫው ጠይቋል። በጥቃቱ እጃቸው የሌለ ምእመናን ከእሥር እንዲለቀቁም ቤተ ክርስትያኗ በመግለጫዋ አትታተለች። «በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሱ ያሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶች፣ አብዝቶ እንደሚነገረው፣ "በሽግግር ወቅት የሚያጋጥሙ" ተብለው ብቻ የሚታለፉ አይደሉም» ትላለች ቤተ ክርስትያኗ። ቤተ ክርስትያኗ አገር ቤትና ውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮያውን ተጎጂዎችን ለመርዳት ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና አቅርባለች። ቤተክርስቲያኗ ያወጣችውን መግለጫ በተመለከተ ለቢቢሲ ምላሽ የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ኮምኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የቀረበው ቅሬታ የክልሉን መንግሥት አይመለከትም በማለት "ተጎጂዎችን ወደ ማቋቋም የምንገባው በብሔር ወይንም በሐይማኖታቸው ሳይሆን ሰው በመሆናቸው ወይንም የክልላችን ነዋሪ በመሆናቸው" ነው ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያወጣችው መግለጫ የክልሉን እውነታ ያላረጋገጠ እና ክልሉ እየሰራ ያለውን እንዲሁም አሁንም ያለበትን ሁኔታ ያላገናዘበ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ አቶ ጌታቸው ገለፃ ከሆነ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ በቤተክርስቲያኒቱም ሆነ ከቤተክርስትያኒቱ ውጪ የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ውይይቶች በተለያየ ጊዜያት መደረጋቸውን ጠቅሰዋል። በኦሮሚያ የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ተከትሎ ግጭቱን የሐይማኖትና የብሔር መልክ ለማስያዝ የተሞከረበት ሁኔታ እንደነበር አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህንን ክስተት የክልሉ መንግሥት በቁጥጥር ስር እንዳዋለውና የፀጥታ አካላትም በትኩረት መስራታቸውን ያመለከቱት አቶ ጌታቸው አጥፊዎችን ወደ ሕግ እያቀረቡ መሆናቸውንም ጨምረው አስረድተዋል። የሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ከ150 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት እንደጠፋ ተዘግቧል። በተጨማሪም ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ንብረታቸው ወድሞ ለችግር መጋለጣቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከሳምንታት በፊት ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ 523 መኖሪያ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን 499 መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸው፤ በተጨማሪም 195 ሆቴሎች መቃጠላቸውን ሌሎች 32 ሆቴሎች ደግሞ በንብረታቸው ላይ የመሰባበር ጉዳት መድረሱን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል። ከሁከቱ ጋር ተያይዞም በሺህዎች የሚቆተሩ ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው መነገሩ ይታወሳል።
news-44286514
https://www.bbc.com/amharic/news-44286514
አንድ ሚሊዮን ፈረንሳዊያን ማጨስ አቆሙ
በፈረንሳይ የአጫሾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።
በፈረንጆች 1970ዎቹ ትምባሆ ማጤስ እንደ ዝመና የሚታይበት ዘመን ነበር። የዚያ ዘመን እውቁ ሙዚቀኛ ሰይሽ ገኒሽቡህ (Serge Gainsbourg) ከአፉ ትምባሆ ተለይቶት አያውቅም ነበር። ባለፉት ዐሥርታት ከሕዝበ ፈረንሳዊያን በእንዲህ ያለ ቁጥር የትምባሆ አጫሾች "በቃን" ሲሉ ታይቶም፣ ተሰምቶም አይታወቅም። የፈረንሳይ ጤና ቢሮ ባካሄደው በዚህ ጥናት እንዳመለከተው አፍላ ወጣቶች፣ ጎረምሶች፣ እንዲሁም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎች በአያሌው ማጤስ ማቆማቸውን ጠቁሟል። ጥናቱ ይህ ውጤት እንዴት ሊመዘገብ እንደቻለ መላምቱን ጨምሮ ያስቀመጠ ሲሆን ፈረንሳይ ባለፉት ዓመታት በትምባሆ አሉታዊ ውጤቶች ላይ ያተኮሩ ተከታታይ ዘመቻዎችና እርምጃዎች መውሰዷን ጠቅሷል። ፈረንሳይ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ትምባሆ ማጤስን የሚያቆሙ ዜጎቿን የሚያበረታቱ በርካታ እርምጃዎችን መውሰዷን ያስታወሰው ጥናቱ ከነዚህ መሐል የሲጃራ ዋጋን መቆለልና ከሲጃራ ነጻ የሆነ ወር በአገር አቀፍ ደረጃ ማወጅን ይጨምራል። ይህ የናሙና ጥናት እንዳመላከተው በ2017 ብቻ ዕድሜያቸው ከ18-75 የሆኑ 26.9% በየዕለቱ አጫሽ የነበሩ ሲሆን ከዚያ ቀደም ባለው ዓመት ግን 29.4% አጫሽ ነበሩ። በዚህም መሠረት 13.2 ሚሊዮን አጫሾች የነበሩባት ፈረንሳይ ቁጥራቸው በአንድ ሚሊዮን ቀንሶ 12.2 ሚሊዮን የትምባሆ ወዳጆች ብቻ ቀርተዋል። በዓለም ደረጃ ከአስር ሰዎች ሞት የአንዱ ትምባሆን ከመማግ ጋር የተያያዘ ነው። ከነዚህ ሟቾች ግማሾቹ የሚገኙት ደግሞ በቻይና፣ በሕንድ፥ በአሜሪካና በራሺያ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ገልጧል።
news-47773242
https://www.bbc.com/amharic/news-47773242
340 ሔክታር የሚሸፍነው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በእሳቱ ጉዳት ደርሶበታል
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ሳንቃ በር፣ እሜት ይጎጎ እና ግጭ የተባሉት የፓርኩ ክፍሎች ከመጋቢት 19/2011 ዓ.ም አመሻሽ ጀምሮ እየተቃጠለ ይገኛል። ዛሬም እሳቱ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር አለመዋሉንና አሁንም ጭስ እንደሚታይ የብሔራዊ ፓርኩ ዋና ኃላፊ አቶ አበባው አዛናው ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ኃላፊው በተለያዩ መገናኛ ብዙህንና በማህበራዊ ሚዲያዎች በአካባቢው በረዶ በመዝነቡ እሳቱ ሙሉ ለሙሉ መጥፋቱን በተመለከተ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ኃላፊው አክለውም እሳቱ ከተነሳበት የፓርኩ ክፍል በተቃራኒ ባለ ቦታ ትንሽ ካፊያና ደመና በመታየቱ እርሱ ወደ ቃጠሎው ቦታ ይመጣ ይሆናል በሚል ተስፋ የተሰራጨ መረጃ ሳይሆን እንደማይቀር ገልፀዋል። • አደጋ የተጋረጠበት የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት "እሳቱ እንደ አየር ፀባዩ እየተለዋወጠ ደመና ሲሆን የመቀዝቀዝ ፀሐይ ሲሆን ደግሞ ታፍኖ የቆየው እንደገና የመነሳት ሁኔታዎች ይታያሉ" ብለዋል አቶ አበባው። በዚህም ምክንያት ስጋት መኖሩን ገልፀው ሰዎች የማይደርሱባቸው ቦታዎች አሁንም እሳት እንደሚታይ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከተለያዩ አካባቢዎች ግለሰቦችና የፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢው በማምራት እሳቱን በውሃና በቅጠል እንዲሁም በአፈር ለማጥፋት ቢሞክሩም በፓርኩ የመልከዓ ምድር አቀማማጥ የተነሳ መድረስ የማይቻልባቸው ቦታዎች ላይ ደርሰው ለማጥፋት አለመቻሉን አስረድተዋል። እሳቱን ለማጥፋት ራቅ ካሉ ቦታዎች የሚመጡ ሰዎችም ቦታው ተራራማ በመሆኑ በድካምና በውሃ ጥም ተንገላተው ስለሚደርሱ በሚፈለገው መጠን የማጥፋት ሥራውን ለማከናወን አስቸጋሪ ሆኗል። • ጣና ሐይቅ የተጋረጡበት ፈተናዎች በየዓመቱ እንዲህ ዓይነት የእሳት አደጋዎች እንደሚያጋጥም የሚናገሩት ኃላፊው የዘንድሮው ግን ከፍተኛ ውድመትን ያስከተለና ሰፊ እንደሆነ ተናግረዋል። እስካሁን 340 ሔክታር የሚሸፍነው የፓርኩ ክፍል ውድመት እንደደረሰበት ለማወቅም ተችሏል። ኃላፊው እንደገለፁት ቃጠሎው የደረሰባቸው ቦታዎች የምኒልክ ድኩላና ሌሎች ድኩላዎች እንዲሁም የቀይ ቀበሮና የተለያዩ የዱር እንስሳቶች የሚኖሩበት አካባቢ ነው። ይሁን እንጂ ተሳቢ እንስሳት ካልሆኑ በስተቀር በእሳቱ ምክንያት በዱር እንስሳት ላይ ያጋጠመ ጉዳት እንደሌለ ገልፀውልናል። በብሔራዊ ፓርኩ የሊማሊሞ ሎጂ ሥራ አስኪያጅና አስጎብኝ ሽፈራው አስራት በበኩሉ በአካባቢው ዝናብ አለመዝነቡን ጠቅሶ እዚያ አካባቢ ያለው ማሕበረሰብ በንቃት እየተከታተለና እየጠበቀ እንደሆነ ይናገራል። "ዛሬ ያለው ሁኔታ የሚያሰጋ ቢሆንም እሳቱ ጠፋ ሲሉት እየተነሳ ስለሆነ፤ ለዕይታ ግልፅ ያልሆኑ ቦታዎች በመኖራቸው ጠፍቷል ብሎ መደምደም አይቻልም" የሚለው አቶ ሽፈራው ከ15 ቀናት በፊት የእርሱ መዝናኛ ቦታ የሚገኝበት የፓርኩ ክፍል ላይ እሳት ተነስቶ እንደነበር ያስታውሳል። መዝናኛ ቦታው አሁን ቃጠሎ ካጋጠመው የፓርኩ ክፍል በ200 ሜትር ርቀት ላይ በመገኘቱ "በፓርኩ የሚገኙ እንስሳቶች ሲራወጡ ማየት በራሱ ያማል" ይላል። • የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ሊመለስ ነው ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ የዓለም ቅርስ እንጂ የአንድ አካባቢ ብቻ ሐብት አይደለም የሚለው ሽፈራው "አባቴ የፓርክ ሰራተኛ በመሆኑ ፓርኩን ከ25 ዓመታት በላይ አውቀዋለሁ፤ ፓርኩ ከተፅዕኖ ነፃ ሆኖ አያውቅም" ሲል ያክላል። ለዚህም የህዝብ ብዛት መጨመር፣ የኤሌክትሪክ ዝርጋት፣ የመንገድ ግንባታና ሌሎች ምክንያቶችን ይጠቅሳል። እርሱ እንደሚለው ከዚህ ቀደም በዓለም የቅርስ መዝገብ ለአደጋ ከተጋለጡ ቦታዎች አንዱ ሆኗል ተብሎ ተመዝግቦ ነበር። ከዚያም በተደረገ ጥረት ከዝርዝር ሊወጣ እንደቻለ ያስታውሳል። እንዲህ ዓይነት የእሳት አደጋዎችን የመቆጣጠር ኃላፊነት የማን ነው? በቅርቡ በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፤ አሁን በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰቱ የእሳት አደጋዎችን የማጥፋቱ ኃላፊነት ለሕዝብና ለፀጥታ ኃይሎች የተተወ ነው ያስብላል። ታዲያ በፌደራል ደረጃ እንዲህ አይነት አደጋዎችን የሚቆጣጠረው ማነው? "በአንዳንድ የክልል ከተሞች የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ያለ ቢሆንም አቅማቸው ያን ያህል ጠንካራ አይደለም" ያሉን የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ናቸው። አቶ ንጋቱ ጊዜው ትንሽ የራቀ ቢሆንም ከ15 ዓመታት በፊት በሻኪሶ ጥብቅ ደን እንዲሁም ፉኝዶ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን የእሳት አደጋ ያስታውሳሉ። • ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን? "በወቅቱ የተፈጠረው የእሳት አደጋ ለ15 ቀናት የዘለቀ ነበር፤ በመሆኑም በአገር ውስጥ ባለው አቅም መቆጣጠር ስላልተቻለ ከደቡብ አፍሪካ እርዳታ ተጠይቆ በሔሊኮፕተር የታገዛ የማጥፋት ሥራ ተከናውኗል" ይላሉ። አሁንም ግን በአገር ውስጥ እንዲህ ዓይነት የቱሪዝም ፓርኮችን እንዲሁም የኢንዱስትሪ ፓርኮችንና ሌሎች ግዙፍ ህንፃዎችን ሊያጋጥማቸው ከሚችል የእሳት አደጋ ለመታደግ የሚያስችል አቅም እንደሌለ አበክረው ይናገራሉ -አቶ ንጋቱ። "በቅርቡ የተገነባውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ 54 ፎቅ ህንፃ ነው፤ ነገርግን ባለስልጣኑ 72 ሜትር የሚደርስ የህንፃ ቃጠሎ መቆጣጠር የሚችል መሳሪያ ነው ያለው። ይህም መሳሪያ ሊደርስ ሚችለው እስከ 23ኛው ፎቅ ድረስ ብቻ ነው" ሲሉ ስጋታቸውን ይገልፃሉ። ምንም እንኳን መስሪያ ቤታቸው ለአዲስ አበባ የተቋቋመ ቢሆንም ባሉት ችግሮች ሳቢያ ሌሎች አካባቢዎችም እየሄዱ አገልግሎት ለመስጠት መገደዳቸውን ይናገራሉ። "ብቸኛው የስልጠና ማዕከልና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርገው የእኛ ባለስልጣን ነው" ይላሉ። የአዲስ አበባ ያህል ያደጉ የክልል ከተሞች ቢኖሩም የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ለመቆጣጠር አቅም እንደሌላቸውም ጨምረው ተናግረዋል። ጨምረውም የመከላከል ሥራው ትኩረት የሚሰጠውና ቀዳሚ ቢሆንም በክልል ከተሞች ያለውን አቅም ማጠናከርና አገር አቀፍ አንድ ጠንካራ መስሪያ ቤት መቋቋም እንደሚያስፈልግ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
52455293
https://www.bbc.com/amharic/52455293
ኮሮናቫይረስ ሁለቴ ሊይዘን ይችላል?
ስለ ኮሮናቫይረስ በርካታ ጥያቄዎች እየተሰነዘሩ ነው። ቫይረሱ አንዴ ከያዘን በኋላ በድጋሚ ሊይዘን ይችላል? በበሽታው አንዳንዶች ለምን ከሌሎች በባሰ ይጠቃሉ? ወረርሽኙ ሁሌም ክረምት ላይ ይከሰት ይሆን? ክትባት ቫይረሱን ለመከላከል ውጤታማ ይሆናል? በሽታውን እንዴት በቁጥጥር ስር አውለን ወደፊት እንቀጥላለን? በሽታውን የመከላከል አቅም አዳብረዋል የሚል ማረጋገጫ ያገኙ ሰዎች ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ ይችሉ ይሆን? ወዘተ. . .
ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል በሽታውን የመከላከል አቅም የማዳበር (ኢሚዩኒቲ) ጉዳይ ዋነኛው ቢሆንም አጥጋቢ ምላሽ የለውም። ሰውነታችን ኮሮናቫይረስን የመከላከል አቅም እንዴት ያዳብራል? በሽታን የመከላከል አቅም ሁለት ደረጃ አለው። የመጀመሪያው ሰውነት ወራሪ ነገር ሲገጥመው በመዋጋት የሚሰጠው ምላሽ ሲሆን፤ ‘ኢኔት ኢሚዩን ሪስፖንስ’ ይባላል። በዚህ ወቅት ሰውነት ኬሚካል ያመነጫል። ነጭ የደም ሕዋሳትም ጉዳት የደረሰበትን ሕዋስ ያጠፋሉ። ይህ ለኮሮናቫይረስ ብቻ ሳይሆን ለማንኛውን በሽታ ሰውነት የሚሰጠው ምላሽ ነው። ኮሮናቫይረስ እንዳይዘን የማድረግ አቅምም የለውም። • በአዲስ አበባ ሁለት ወጣቶች በጥይት የተመቱበት ክስተት ምንድን ነው? ሰውነታችን እንደ ኮሮናቫይረስ አይነት በሽታ ሲገጥመው የሚሰጠው የመከላከያ ምላሽ ‘አዳፕቲቭ ኢምዩን ሪስፖንስ’ ይባላል። ቫይረሱ ላይ ያነጣጠሩ ፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲስ) የሚፈጠሩበት ሂደት ሲሆን፤ በቫይረሱ የተጠቁ ሕዋሳትን ለይቶ የሚያጠቃ ‘ቲ ሴል’ ያመነጫል። ሰውነት ኮሮናቫይረስ ላይ ያነጣጠሩ ፀረ እንግዳ አካላት ለማመንጨት እስከ አስር ቀን እንደሚወስድበት ጥናቶች ያሳያሉ። በሽታው ክፉኛ ያጠቃቸው ሰዎች ጠንካራ የመከላከል አቅም ያዳብራሉ። ይሄኛው በሽታን የመከላከል ምላሽ (አዳፕቲቭ ኢምዩን ሪስፖንስ) በጣም ጠንካራ ከሆነ በቀጣይ በበሽታው ላለመያዝ ይረዳል። የኮቪድ-19 መጠነኛ ምልክት የታየባቸው ወይም ከነጭራሹ ምልክት ያላሳዩ ሰዎች፤ በሽታውን በበቂ ሁኔታ መከላከል የሚያስችል አቅም ስለማዳበራቸው የታወቀ ነገር የለም። በሽታን የመከላከል አቅም ምን ያህል ጊዜ ይቆያል? ሰውነታችን አንዳንድ በሽታዎችን ያስታውሳል አንዳንዶቹን ደግሞ ይረሳል። ለምሳሴ ሰውነታችን ኩፍኝን ፈጽሞ አይረሳም፤ ስለዚህ በሕይወት ዘመናችን ከአንድ ጊዜ በላይ ኩፍኝ አይዘንም። አንዳንድ በሽታዎችን ግን ሰውነታችን ይዘነጋቸዋል። እንደ ምሳሌ የሕጻናት መተንፈሻ አካል በሽታዎችን ማየት እንችላለን። ልጆች በተደጋጋሚ በእነዚህ በሽታዎች ይያዛሉ። አዲሱ ኮሮናቫይረስ (Sars-CoV-2) መሰራጨት የጀመረው በቅርቡ ስለሆነ የሰው ልጅ ለምን ያህል ጊዜ በሽታውን የመከላክለ አቅም እንደሚያዳብር ገና አልታወቀም። ግን የሌሎች ስድስት አይነት ኮሮናቫይረሶችን ባህሪ በማየት መገመት ይቻላል። • በዩናይትድ ኪንግደም ኮሮናቫይረስ በተያዙ ህፃናት ላይ ያልተለመደ ምልክት መታየቱ ተገለፀ ከቫይረሱ አይነቶች አራቱ፤ እንደ ጉንፋን አይነት ምልክት ያላቸው ሲሆን፤ በሽታን የመከላከል አቅም የሚገኘውም ለአጭር ጊዜ ነው። ስለዚህም አንዳንዶች በዓመት ሁለቴ ሊያዙ ይችላሉ። ከኮሮናቫይረስ አይነቶች ሁለቱ እጅግ አደገኛ ናቸው። ሳርስ ወይም ‘አክዩት ሪስፓይራቶሪ ሲንድረም’ እና መርስ ወይም ‘ሚድል ኢስት ሪስፓይራቶሪ ሲንድረም’ የሚያስከትሉት እኒህ ናቸው። ለነዚህ በሽታዎች የሰው ልጆች ፀረ እንግዳ አካላት (አንቲቦዲስ) የሚያመርቱትም ከጥቂት ዓመታት በኋላ ነው። የህክምና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ፖል ሀንተር እንደሚሉት፤ ጥያቄው መሆን ያለበት በሽታውን የመከላከል አቅም እናዳብራለን? የሚለው ሳይሆን በሽታውን የመከላከል አቅም ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? የሚለው ነው ይላሉ። “ለእድሜ ልክ የሚሆን በሽታ የመከላከል አቅም እንደማናዳብር እርግጥ ነው። የሳርስ ፀረ እንግዳ አካላት ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው እስከ ሁለት ዓመት የሚቆይ በሽታ የመከላከል አቅም ሊገነባ ይችላል።” አንድ ሰው በበሽታው በድጋሚ ቢያዝም እንደ መጀመሪያው ጊዜ አይጠናበትም። በሽታው ሁለቴ ይዞን ይሆን? በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለቴ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ተዘግቧል። አንዳንዶቹ ዳግመኛ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆኑ፤ የተቀሩት ቫይረሱ በሰውነታቸው ውስጥ ተደብቆ ከጊዜ በኋላ ዳግመኛ በሽታው የተገኘባቸው ናቸው። ከበሽታው እንዳገገሙ ከተነገራቸው ሰዎች መካከል ትክክለኛ ምርመራ ሳይደረግ ‘አገግማችኋል’ የተባሉ እንዳሉም ተመራማሪዎች ይስማማሉ። የሰው ልጆች በሽታውን የመከላከል አቅም አዳብረው እንደሆነ ለማወቅ ሆነ ተብሎ በቫይረሱ ሁለቴ እንዲያዙ ባይደረግም፤ ዝንጀሮዎችን በሽታውን በማስያዝ ጥናት እየተካሄደ ነው። ዝንጀሮዎቹ በሦስት ሳምንት ልዩነት ሁለቴ በበሽታው እንዲያዙ ተደርጎ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ የበሽታው ምልክት አልታየባቸውም። ‘አንቲቦዲስ’ ካለን በሽታውን መከላከል እንችላለን? ስለዚህ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። አንዳንድ አገሮች በሽታውን የመከላከል አቅም አዳብረዋል ላሏቸው ሰዎች ማረጋገጫ ‘ፓስፖርት’ መስጠታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የማይደግፈውም ለዚህ ነው። ፀረ እንግዳ አካላት እንዳላቸው የተረጋገጠ ሰዎች ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ያደረጉ አገሮች አሉ። በተለይም ለአረጋውያን እንክብካቤ ለሚሰጡና ለህክምና ባለሙያዎች ይህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን በሁሉም ህሙማን ላይ ፀረ እንግዳ አካላት ቢገኝም ሁሉም አኩል አይደሉም። ኮሮናቫይረስን መግታት የሚችሉት ‘ኒውትራላይዚንግ አንቲቦዲስ’ የሚባሉት ናቸው። ቻይና ውስጥ ከቫይረሱ ባገገሙ 175 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ የ30 በመቶው ‘ኒውትራላይዚንግ አንቲቦዲስ’ ዝቅተኛ መሆኑን አሳይቷል። በተጨማሪም በ ‘አንቲቦዲስ’ ሰውነታችን ቢጠበቅም እንኳን፤ ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው ልናስተላልፍ እንችላለን። በሽታን የመከላከል አቅም ጠቃሚ ነው? በሽታን የመከላከል አቅም ጉዳይ በኮቪድ-19 በተደጋጋሚ እንያዛለን? ከተያዝንስ በምን ያህል ጊዜ ልዩነት ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። ሰዎች በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም በሽታውን የመከላከል አቅም ካዳበሩ የበሽታውን አደገኛነት ይቀንሰዋል። ስለ ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅም ግንዛቤ ካዳበርን ማን ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆነ፣ በሽታውን ሊያስተላልፍ የሚችለው ማን እንደሚሆን ለማወቅ ይረዳል። እንቅስቃሴ ላይ የተጣለውን ገደብ ለማላላትም ያግዛል። በእርግጥ ለረዥም ጊዜ የሚዘልቅ በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ከባድ ነው። ይህም ክትባት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ሊያከብደው ወይም ክትባቱ በምን ያህል ጊዜ ልዩነት መወሰድ አለበት የሚለውን ሊለውጠው ይችላል። • ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አገሮችን እየረዳ ያለው ቢሊየነር ጃክ ማ ማነው? አንድ ሰው በበሽው ተይዞ አልያም ክትባት ካገኘ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ የሚቆይ በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ይችላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲገኝ የቫይረሱን ስርጭት መግታት የሚቻልበትንም መንገድ ያመላክታል። ከላይ የተነሱት ጥያቄዎች ገና መልስ ያልተገኘላቸው ናቸው።
news-56224264
https://www.bbc.com/amharic/news-56224264
ምርጫ 2013 ፡ የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ተስፋ እና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው?
ኢትዮጵያ ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ ለግንቦት 28 እና ሰኔ 5 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ይዛለች። ለዚህም ፓርቲያቸውን ወክለው የሚወዳደሩ የተለያዩ ዕጩዎች ምዝገባም በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሃረሪ፣ በጋምቤላ እና ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች ከየካቲት 08 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።
በእነዚህ አካባቢዎች የእጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቀው የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑንም በምርጫ ቦርድ ተገልጿል። በአፋር፣ አማራ፣ ሲዳማ ፣ ደቡብ ሕዝቦች እና ሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ደግሞ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ እንደሚሆን ቦርዱ አሳውቋል። በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው ከዛሬ ሰኞ የካቲት 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይሆናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራሮች አባላቶቻቸውና መሪዎቻቸው መታሰራቸውን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ቢሮዎቻቸው መዘጋታቸውን በመግለጽ ይህም በምርጫ ተሳትፏቸው ላይ ጥላ ማጥላቱን ገልፀዋል። አባላቶቻቸው ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸውን አክብሮላቸው እንኳ አለመፈታታቸውን በመግለጽም ተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካላት አቅርበዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ምርጫ መግባት ያሳስበናል ሲሉ ተናግረዋል። ከቀደሙት ምርጫዎች የተለየ ምርጫ ሊሆን ይችላል? በማክስ ፕላንክ ተቋም የፖስት ዶክቶራል ፌሎ የሆኑት ዶ/ር በሪሁን አዱኛ በሕገመንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጥናቶችን ሰርተዋል። ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ ኢትዮጵያ ካካሄደቻቸው ካለፉት አምስት ምርጫዎች ልዩ የሚያደርገው አገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ መሆኑን በመግለጽ ይጀምራሉ። በርካቶች ይህንን ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሙ የዲሞክራሲ፣ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱ ያለችበትን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቅራኔዎች ይፈታል ብለው መጠበቃቸው፤ አገራዊ መሠረታዊ ለውጥ ያስፈልጋል የሚለው ላይ የጋራ መግባባት መኖሩም ለየት እንደሚያደርገው ይናገራሉ። ዶ/ር በሪሁን ይህ ምርጫ መሠረታዊ ምርጫ መሆኑን መንግሥት ማሰብ ይኖርበታል ሲሉም ይመክራሉ። ይህ ምርጫ እንደከዚህ ቀደሞቹ ዓይነት ምርጫ ካልሆነ እና መሠረታዊ ምርጫ ከሆነ ደግሞ "ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መሥራት አለበት፤ ብቻውን ሊያደርገው የሚችለው ነገር አይደለም" ሲሉ አክለዋል። የባለፉት አምስት ምርጫዎች ኢህአዴግ በሚባል ፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ የተደረገ ነው በማለት ይሄኛው ስድስተኛ አገራዊ ምርጫ ግን በአዲስ ብልጽግና በሚባል ፓርቲ መዋቅር ስር የሚደረግ መሆኑን በራሱ ልዩ እንደሚያደርገው ያስረዳሉ። ሌላው ለዶ/ር በሪሁን ይህ ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ምርጫዎች በመላው አገሪቱ የሚካሄድ አለመሆኑም ለየት ያደርገዋል። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ መደፍረስ ይህንን ምርጫ ስጋትና ተስፋ ይዞ እንዲካሄድ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ መሆኑንም ይናገራሉ። የፖለቲካ ለውጥ እና የፖለቲካ ሽግግር ወሬ በሚሰማበት ወቅት የሚደረግ ምርጫ መሆኑ ደግሞ ይህንን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ይስታውሳሉ። ሆኖም ግን ይላሉ ዶ/ር በሪሁን ይህንን ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት ምርጫዎች የተለየ ነው ወይንም አይደለም የሚለውን የሚወስነው የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያቀርቡት ሃሳብ ነው ይላሉ። ከዘንድሮው ምርጫ ምን ይጠበቃል? እንደከዚህ ቀደሙ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ብቻ ይዞ እነርሱን ለመፍታት የሚደረግ የምርጫ ውድድር ከሆነ ካለፉት በብዙ ላይለይ ይችላል ሲሉ ይገልጻሉ። ነገር ግን አሁን አገሪቱ ላይ ያሉትን የማኅበራዊ እና የፖለቲካዊ ችግሮችን በመሰረታዊ መልኩ ለመፍታት የሚደረግ እና በዚያ እሳቤ ለመፍታት የሚካሄድ ምርጫ ከሆነ ደግሞ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ሊሆን ይችላል ብለዋል። በተደጋጋሚ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የመንግሥትን እርምጃዎች በመተቸት የሚታወቁት አቶ እያስፔድ ተስፋዬ በበኩላቸው ይህ አገራዊ ምርጫ ከዚህ በፊት ሲካሄዱ ከነበሩ አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የተለየ ይሆናል ብለው አያስቡም። ይህንን ሃሳቡን ሲያብራሩም ኢህአዴግ ከዚህ በፊት በአውራ ፓርቲነት ከመራቸውና ከተሳተፈባቸው አምስት ተከታታይ ምርጫዎች የተለየ የፖለቲካ ባህል በዚህኛው ምርጫ አለማስተዋላቸውን ይጠቅሳሉ። ከዚህ ቀደም የተካሄዱት ምርጫዎች ከምርጫ በፊት፣ በኋላ እና በምርጫ ወቅት የተለያዩ ጉድለቶች እንደሚስተዋልባቸው የሚጠቅሱት አቶ እያስፔድ፤ ለዚህም ማሳያዎች ፓርቲዎች እንዳይንቀሰቅሱ ማድረግ፣ አባላቶቻቸውን ማሰር፣ ቢሯቸውን መዝጋት መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት ቀጣዩ ምርጫ ከዚህ በፊት ከተደረጉት አምስት ምርጫዎች ሁሉ የተለየ ይሆናል የሚል ተስፋ እንደነበራቸው የገለፁት አቶ እያስፔድ፤ ይህ ግን በሂደት መጥፋቱን ይናገራል። በወቅቱ ተስፋ አድርገው የነበሩበትንም ምክንያት ሲያስረዱ፣ የፖለቲካ ምሕዳሩ ከዚህ በፊት ከነበረው ጊዜ ሁሉ የተሻለ መስፋቱን እና በእስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች መፈታታቸው መሆኑን ያስታውሳሉ። ከዚህ በተጨማሪም ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን እንደ ልባቸው ተንቀሳቅሰው ያሻቸውን ያለ ተጽዕኖ የሚሰሩበት እድል ተመቻችቶ እንደነበርም አልዘነጉም። ከምርጫ እና ዲሞክራሲ ጋር ተያይዞ ያሉ ተቋማትን የሚመሩ ሰዎችንም በሚመለከት በሕዝቡም ሆነ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ ከሞላ ጎደል እምነት የሚጣልባቸውን ግለሰቦች ወደ አመራርነት ማምጣት መቻሉን በማንሳት ቀጣዩ ምርጫ ተስፋ አለው ብለው እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል። "ግን እነዚህ ነገሮች እንዳለ ተቀልብሰው ወደ ነበርንበት ተመልሰናል" የሚሉት አቶ እያስፔድ የፖለቲካ ምሕዳሩ መጥበብ ብቻ ሳይሆን በርካቶች እስር ቤት እንደሚገኙም ይጠቅሳሉ። ዛሬም ፍርድ ቤት ንፁህ መሆናቸውን ገልጾ የታሰሩ መኖራቸውን በተለያዩ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርቶች ላይ መገለፁን የሚያነሱት አቶ እያስፔድ፤ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸውን አክብሮላቸው ነገር ግን ፖሊስ ከመልቀቅ ይልቅ አሁንም ከተማ እና ፍርድ ቤት እየቀያየረ የተለያየ ክስ የሚመሰርትባቸው መኖራቸውን ይገልጻሉ። የባልደራስ አባላት እንዲሁም የተለያዩ የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መታሰር ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የምርጫ ቦርድ ግቢ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ መታገታቸውን ራሱ የምርጫ ቦርድ የገለፀው መሆኑን በማንሳት በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የፖለቲካ ምሕዳሩ ጠብቦ "ፍትሃዊና የተለየ ምርጫ ይደረጋል ብሎ ማሰብ የማይታሰብ ነው" ይላሉ። ጋዜጠኞችን በሚመለከትም ሲናገሩ ሲፒጄ ዶ/ር አብይ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት አንድም ጋዜጠኛ ያልታሰረባት አገር ያላት ኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ከቤላሩስ በመቀጠል በፍጥነት ጋዜጠኞችን በማሰር ሁለተኛዋ አገር በሚል እንደፈረጃት ይጠቅሳሉ። ዶ/ር በሪሁን በበኩላቸው ፖለቲከኞች እስር ቤት ውስጥ ሆነው የሚካሄድ ምርጫ የቅርብ እና የሩቅ ጊዜ ተጽዕኖ እንዳለው ይናገራሉ። በቅርብ ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ ለማካሄድ አለመቻል ሲሆን፣ አርቆ ሲመለከቱት ደግሞ ከምርጫ በኋላ ለሚመጣው የፖለቲካ ሥርዓት አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ፓርቲዎች ይደርስብናል ያሏቸው ችግሮች ከአሁኑ መፍታት አለመቻል በኋላ ላይ ምርጫውን ለማከናወን የሰላም እና የደኅንነት ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉም አክለዋል። ምርጫውም ካለፈ በኋላ ምርጫውን ያሸነፈው ፓርቲ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ሕጎችን ቢያወጣ፣ የሕገመንግሥት ማሻሻያ ማድረግ ቢፈልግ የሚወሰነው ፓርላማ ባሉ ፓርቲዎች እና ሰዎች በመሆኑ፣ ከዚህ ውጪ የሆኑ የአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎችን በአጠቃላይ ትርጉም ባለው መልኩ የማያሳትፍ ይሆናል ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። የምርጫው ነጻና ፍትሃዊነት ዶ/ር በሪሁን በምርጫ ቦርድ አካባቢ የማይካዱ የአስተዳደር እና የሕግ ለውጦች መካሄዳቸውን ይገልጻሉ። የምርጫ ቦርድ አመራሮች ቀጣዩን ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ ቁርጠኝነቱ እንዳላቸው "እንደ ግለሰብ ግምት አለኝ" የሚሉት ዶ/ር በሪሁን አጠቃላይ ሁኔታው ሲታይ ግን ያለው ችግር ከእነርሱ በላይ ነው ይላሉ። ምርጫ ቦርድ በራሱ ብቻ ማስፈፀም የሚችለው ነገር የለም በማለትም መንግሥት፣ ፍርድ ቤቶች፣ የፀጥታና ደኅንነት አካላት ሁሉም የየራሳቸው ድርሻ አላቸው ብለዋል። አሁን ያለው ጉዳዩ ከምርጫ ቦርድ በላይ ነው የሚሉት ዶ/ር በሪሁን፣ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ "ዝም ብሎ በምርጫ ቦርድ ላይ ብቻ የምንንጠለጠል አይሆንም" ይላሉ። መንግሥት፣ ተቃዋሚዎች፣ ሕዝቡ፣ የፍትህ አካላት ሁሉም በትብብር ካልሰሩ አንዱ ተቋም ብቻ ይህንን ምርጫ በሥነ ሥርዓት ማድረግ ይችላል ማለት ከባድ ነው ሲሉ ያክላሉ። ዶ/ር በሪሁን ይህንን ሁሉ ከግንዛቤ አስገብተው ምርጫ ቦርድ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ ይችላል ለሚለው ጥያቄ "መልሴ አይችሉም ነው" ይላሉ። አቶ እያስፔድ የምርጫ ቦርድ ፍትሃዊነት ላይ ያላቸው እምነት እየተሸረሸረ መምጣቱን ገልፀው የኦነግ እና ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ቢሮዎች በተለያዩ አካባቢዎች ተዘግተው፣ ፓርቲዎቹ ምርጫ ላይ እንዴት መሳተፍ ይችላሉ በማለት፣ ምርጫ ቦርድ ይህንን የፓርቲዎቹን ችግር እንኳ ለመፍታት ቁርጠኝነት እንዳልታየበት ያስረዳሉ። እርሳቸው እና ሌሎች ግለሰቦች በጋራ በመሆን ባካሄዱት የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻ የኦነግና ኦፌኮ ቢሮዎች የት የት ቦታ እንደተዘጉ አቅማቸው በፈቀደ በአካል በመሄድ፣ ሌሎቹን ደግሞ ከፓርቲው መረጃ በመሰብሰብ በፌስቡክና ትዊተር ላይ ማስፈራቸውን ያስታውሳሉ። ፓርቲዎቹም ቢሆኑ ይህንኑ ጉዳይ ለቦርዱ በደብዳቤ በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን አቶ እያስፔድ አክለዋል። ምርጫ ቦርድ ግን "ኦነግም ሆነ ኦፌኮ ቢሮዎቻቸው የት የት ቦታ እንደተዘጉባቸው በትክክል ስላላቀረቡላቸው መቸገራቸውን" ሲናገር መስማታቸውን ይጠቅሳሉ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ከፓርቲዎች የሚቀርቡለትን ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን በመቀበል ምላሽና መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እንደሚያደርግ በተለያዩ ጊዜያት መግለጹ ይታወሳል። ምርጫውን የሚያሸንፍ ፓርቲ መሠረታዊ የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት የሚፈልግ ከሆነ አሁን ከምርጫ በፊት ቁጭ ብሎ "በተለይ ኦሮሚያ ውስጥ ካሉ እና ሌሎችም ፓርቲዎች ጋር መነጋገር፤ በተለይ መንግሥትን ለሚያስተዳድረው፣ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በይበልጥ ፓርቲ ለብልጽግና ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ" ይላሉ። ስጋቶች እና ተስፋዎች ኢትዮጵያ ይህንን ምርጫ የምታካሄደው በተለያዩ የደኅንነት እና የፀጥታ ስጋቶች ውስጥ ሆና ነው። የሕዳሴ ግድብ ድርድር ጉዳይ፣ ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ይገባኛል ውዝግብ፣ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የፀጥታ ችግሮች ቢኖሩም አገሪቱ ያለችባቸውን የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት "ቢዘገይም ምርጫ ማካሄድ አማራጭ የሌለው ነገር ነው" ዶ/ር በሪሁን ይላሉ። መንግሥት የሕዝቡን ይሁንታ ማግኘት እንዲችል የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች እና ሕጎች ተቀባይነትና ተፈጻሚነት እንዲያገኙ ምርጫ ማድረጉ አማራጭ የለውም ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ከዶ/ር በሪሁን ጋር ተመሳሳይ አስተያየት ያላቸው አቶ እያስፔድ ይህንን ቀጣይ አገራዊ ምርጫ እስር ቤት ካሉ የፖለቲካ አመራሮች ጋር እውነተኛ የሆነ ድርድር ሳያካሄዱ ማከናወን ከዚህ ቀደም "አገሪቱ የሄደችበትን መንገድ መድገም" ይሆናል ሲሉ ይናገራሉ። አምስተኛው አገራዊ ምርጫ ኢህአዴግ መቶ በመቶ ማሸነፉን ያስታወሱት አቶ እያስፔድ፣ አሁን የተወሰኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ ሁኔታ እንዳይንቀሳቀሱ እድሎችን መዝጋት ወደሌላ አማራጭ ሊያመራ እንደሚችል ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ውይይትና ድርድር እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት አቶ እያስፔድ የመራጮች ምዝገባ እየተጠናቀቀ መሆኑ ግን ይህንን ተስፋቸውን እያመነመነው መሆኑን ተናግረዋል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል የሚሉት አቶ እያስፔድ፣ ሕዝቦች በተለያየ ምክንያት ተወካዮቻቸው ባልተሳተፉበት እና በሌሉበት ምክር ቤት ለሚወጡ ሕጎች ተገዢ ይሆናሉ ብሎ ማሰብ ከባድ መሆኑን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ተቃውሞዎችን በማስረጃነት በመጥቀስ ይናገራሉ። ዶ/ር በሪሁን ምርጫ ማለት አገሪቱን ለቀጣይ አምስት ዓመት ማን ያስተዳድራት በሚል የሚከናወን መሆኑን በማንሳት አሁን ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ፣ የሕግ እና ሌሎች በርካታ ልዩነቶች ያሉበት መሆኑን ጠቅሰው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ለየት እንደሚል ተናግረዋል። አሁን ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲም ሆነ የሚመረጠው ፓርቲ አገሪቱ ያለችበትን ችግሮች ሁሉ ብቻውን የሚፈታቸው አይደሉም የሚሉት ዶ/ር በሪሁን፣ ከምርጫውም በፊት ሆነ በኋላ መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ያሰምሩበታል። ስለምርጫውና ከምርጫው በኋላ ምን ማድረግ እንችላለን፣ የቆዩ መሠረታዊ ጥያቄዎችንና ልዩነቶችን እንዴት መፍታት እንደሚቻል ማሰብ፣ አገሪቱ የምትፈልገውን መሠረታዊ ለውጥ ታሳቢ ያደረገ ውይይት ያስፈልጋል ሲሉም ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ። ዶ/ር በሪሁን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የእንነጋገር ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር ገልፀው አሁንም ግን ጊዜ መኖሩን ይናገራሉ። ለዚህም ረዥም ርቀት መሄድ ያለበት መንግሥት መሆኑን ይናገራሉ። ምርጫው በተለያዩ ልዩነት መንፈሶች ውስጥ የሚካሄድ መሆኑንም በማንሳት፣ ውይይቶች እና ንግግሮች ከምርጫው በፊትም ሆነ በኋላ መደረግ እንዳለባቸው ያሰረዳሉ። አለበለዚያ ግን ከሰኔው ምርጫ በኋላ መንግሥት ችግሮችን ካልፈታ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከምርጫ በኋላ ቀውስ ላለመከተሉ ማረጋገጫ የለም ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።
48389420
https://www.bbc.com/amharic/48389420
የኤርትራ 28ኛ ዓመት ነፃነት ከየት ወደየት?
ኤርትራ ከጣልያንና ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች በኋላ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ መሰረት በ1946 ዓ. ም. ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን እንድትዋሃድ ተደረገች። በወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት አፄ ኃይለሥላሴ ፌዴሬሽኑን አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን እንዲፈርስ አደረጉት።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትንም ሳያማክሩ እንዲሁም የኤርትራ ፓርላማ ይሁንታ ሳይገኝበት ፌዴሬሽኑ መፍረሱ በኤርትራውያን ዘንድ ቅሬታን እንዲሁም ለትጥቅ ትግሉ መነሻ ሆነ። መስከረም 1953 ዓ. ም. የትጥቅ ትግሉ ሀ ተብሎ ተጀመረ። • የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? የትጥቅ ትግሉ ውጤት በትጥቅ ትግሉ የመጀመሪያ አስር ዓመታት የነበሩት ጥቂት ታጋዮች ሲሆኑ፤ ቀስበቀስ እያደገ ሲመጣ በተፈጠረ መከፋፈል በኢሳያስ አፈወርቂ የሚመሩ ጥቂት ታጋዮች ከተሐኤ (ጀብሃ) ተገንጥለው ሕዝባዊ ሓይሊታት' (ሻዕቢያ) የተሰኘ ቡድን አቋቋሙ። በወቅቱ ሁለቱም ቡድኖች በሰው ኃይልና ልምድ በመጠናከራቸው፤ የታጋይነት መንፈስና የአመራር ብስለት ተጣምረው አብዛኞቹን የኤርትራ ከተሞች ነጻ ማውጣት ችለው ነበር። ነገር ግን በ1974 ዓ. ም. የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለገብ ዘመቻ ያካሂዳል። የታሪክ ተንታኞች እንደሚሉት ደርግ እንደ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ከፍተኛ ኃይል አሰልፎ አያውቅም። በዚህም የአየር፣ የምድርና የባህር ኃይሉን ነበር በጋራ ያሰለፈው። ይህንንም ተከትሎ ሁለቱም ቡድኖች ከተቆጣጠርዋቸው የኤርትራ ከተሞች ወደ ሳህልና ባርካ በረሃዎች ተገፉ። የደርግ መንግሥት በከፍተኛ ዘመቻ ሻዕቢያም ሆነ ጀብሃ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ቢያደርስም ሁለቱን ቡድኖች ለማጥፋት አልቻለም። • ታዋቂዎቹ ኤርትራዊያን በሙዚቃቸው ምክንያት ይቅርታ ጠየቁ ሻዕቢያ ለኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ ለዓለም ማህበረሰብ የኤርትራ ሕዝብ በሕጋዊ መንገድ የራሱን ዕድል በራስ እንዲወስን ጥሪ ቢያቀርብም ከደርግ በኋላ ተቀባይነት አላገኘም። ኤርትራ በነፃነት ማግስት ትግሉ ቀጥሎም በ1983 ዓ. ም. የደርግ ሠራዊት የተደመሰሰ ሲሆን፤ ሻዕቢያ አስመራን እንዲሁም አጋሩ ህወሐት አዲስ አበባን መቆጣጠር ቻሉ። በወቅቱም አዲስ አበባ ላይ የሽግግር መንግሥት ሲቋቋም ኢሳይያስ አፈወርቂ በታዛቢነት ተገኝተው ነበር። • ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በአዲስ አበባና ሃዋሳ ጉብኝት ያደርጋሉ የኤርትራ መንግሥትም ሕዝበ ውሳኔ በማካሄድ በ98.9 በመቶ ኤርትራ በነፃ አገርነት ከዓለም አገሮች ተርታ ተመደበች። ለሦስት አስርት ዓመታት መራራ ትግል ሲያካሂድ የቆየው የኤርትራ ሕዝብ በልጆቹ ድል ተደስቶ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት ተቋቁሞ በሰላምም ለአገሩ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተስፋን ሰነቀ። በየውጭ አገራቱ ይኖሩ የነበሩ ኤርትራውያንም በአዲስ ተስፋና መንፈስ ያላቸውን ሃብት ሰብስበው ወደአገራቸው መትመም ጀመሩ። ነገር ግን ያልታሰበው ሆኖ ጊዜያዊው መንግሥት ከዘረጋቸው የሕግ ማእቀፎች እና ፖሊሲዎች ጋር መስማማት ስላልቻሉ ወደየመጡበት መመለስ ጀመሩ። ብዙዎቹ ያልጠበቁት ነገር ሆኖ ተስፋ ቢቆርጡም በሽግግር ወቅት እንደዚህ አይነት እንቅፋቶች የተለመዱ ናቸውና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓት እስኪቋቋም በትግስት እንጠብቅ ያሉና በተስፋ መኖርን የመረጡትም ብዙ ናቸው። ከነፃነት በኋላ የኤርትራ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የነበራቸው ግንኙነት ጠንካራ ስለነበረ የሁለቱ አገራት ንግድ መሳለጥም ለኤርትራ ሕዝብ አንድ ተስፋ ነበር። ብዙ ሳይቆይ በዚህ ተስፋቸው ላይ ውሃ ተቸለሰ፤ በቀጣይም ከጂቡቲ፣ ከየመን እንዲሁም ከሱዳን ጋር ጦርነት ውስጥ መግባቷ የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንደከተታቸው ተሰማቸው። እንዲሁም በጦርነት የወደመች አገራቸውን እንገነባነለን ብለው 18 ወራት የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ሲያገለግሉ የነበሩ ወጣቶች መሞትና በከንቱ መባከን የኤርትራን ሕዝብ እጅግ ያስደነገጠ ክስተት ነበር። በ1994 3ኛውን ድርጅታዊ ጉባኤ ያካሄደው ሻዕቢያ አገራዊ ሸንጎ አቋቁሞ የአገሪቷን ሕገ መንግስት የሚነድፍ ኮሚሽን ማቋቋሙ ጋር ተያይዞ፤ ሕዝቡ ሕገ መንግሥት ተረቆ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወዳድረው ፖለቲካዊ ስልጣን የሚጨብጡበት ስርዓት ይገነባል የሚል ተስፋን አንግበው ነበር። • በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል በ1991 ዓ. ም. ኢትዮጵያና ኤርትራ በድምበር ምክንያት ወደጦርነት ገብተው ከመቶ ሺዎች በላይ ሕይወታቸውን ማጣታቸው የብዙ ኤርትራውያንን ተስፋ ያጨለመ ነው። ምንም እንኳን ጦርነቱ ተቋጭቶ አልጀርስ ላይ ስምምነት ቢፈረምም ሁለቱ አገራት ወደሰላም መምጣት አልቻሉም። ከጦርነቱ በኋላም ፕሮፌሰር በረከት ኃብተሥላሴን ጨምሮ የኤርትራ ልኂቃን 'ጂ-13' የሚባለው ቡድን በርሊን ላይ በመሰባሰብ የኤርትራን መጪ ዕጣ ፈንታ በተመለከተ ሀሳቦቻቸውን በደብዳቤ ወደፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቢልኩም ፍሬ አላፈራም። ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትን ጨምሮ ወታደራዊ አመራሮች፣ ጀኔራሎችንና ነባር ታጋዮች የወከለው 'ጂ-15 የተሰኘው ቡድን በኢትዮጵያና በኤርትራ የተደረገውን ጦርነት ጨምሮ በተለያየ ጉዳዮች ለመመካከር ከፕሬዚዳንቱ ጋር ስብሰባ እንዲደረግ ጠየቁ። ፕሬዚዳንቱ ምንም ምላሽ ሳይሰጧቸው በኤርትራ ቴሌቪዥን በኩል የቡድኑን ስም የሚያጠለሹ ፕሮፓጋንዳዎች መነዛት ተጀመሩ። በሌላ በኩል ደግሞ የግል ጋዜጦች የነሱን ሃሳብ ደግፈው መፃፍ ጀመሩ። በመጨረሻም በአገር ክህደት ተወንጅለው ቡድኑ ብቻ ሳይሆን የነሱን ሀሳብ የደገፉ ጋዜጠኞች ታሰሩ፤ ጋዜጦቹም ተዘጉ። እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤትም አልቀረቡም፤ ያሉበትም አይታወቅም። በተለያዩ ጊዜያት ጠባቂዎቻቸው የነበሩና ከኤርትራ የወጡ ሰዎች አብዛኞቹ እስረኞች በበሽታና በንፁህ አየር እጦት ምክንያት እንደሞቱ ቢናገሩም፤ የኤርትራ መንግሥት ግን እስከቅርብ ጊዜ ምላሽ ሳይሰጥ ቆይቷል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ግን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ ከአንድ የፈረንሳይ ሚድያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ''ሁሉም በሕይወት አሉ። ጤንነታቸው በጥሩ ሁኔታ ይገኛል'' የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የግለሰቦቹ መታሰር በኤርትራ ሕዝብ ዘንድ ጥቁር ጥላ የጣለ ሲሆን፤ ከዚህም በላይ በአልጀርስ ስምምነት ትግበራ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት እምቢተኝነት ተከትሎ የኤርትራ መንግሥት ሕዝቡን ለመጨቆን እንደመሣሪያነት በመጠቀሙ የኤርትራውያን ሕይወት መራር አድርጎታል ብለው የሚተቹ ብዙዎች ናቸው። የኤርትራ ሉዓላዊነትን ለማስከበር ሲባል ብሔራዊ ወታደራዊ አገልግሎት መሳተፍ አለባችሁ ተብለው በግድ የተጋዙ፤ በሰላም ሠርተው መኖር ያልቻሉ ወጣት ኤርትራውያን እግራቸው እንዳመራቸው ስደትን መርጠው ሳይሆን ተገደው መንጎድ ጀመሩ። • ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ? ስደቱ እግር በግር ሳይሆን በውሃ ጥም፣ በሰሃራና በሲናይ ሽፍቶች የገደሏቸው፤ ባህር ውጦ ያስቀራቸው ኤርትራውያንን ቤቱ ይቁጠራቸው። ጭቆናውና የመብት ጥሰቱ በመብዛቱ ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት ኤርትራ ውስጥ ተፈጸመ የተባለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚመረምር ልዩ ቡድን አቋቋመ። ነገር ግን ቡድኑ ኤርትራ ውስጥ ገብቶ የማጣራቱን ሥራ እንዲሠራ የኤርትራ መንግስት ባለመፍቀዱ፤ ሦስት አባላት ያሉት መርማሪ ኮሚሽን አቋቋመ። ኮሚሽኑ ከሁለት ዓመታት ምርመራ በኋላ የደረሰበት እንደሚያሳየው፤ በኤርትራ ውስጥ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙንና፤ ጥሰቱን የፈጸሙ የኤርትራ ባለስልጣናት ወደፍርድ ቀርበው እንዲጠየቁ ውሳኔ አቀረበ። የኤርትራ መንግሥት ግን ከእውነት የራቀና ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው እና የኤርትራ መንግሥትን ለማዳከም የተጎነጎነ ሴራ ነው ሲል ውሳኔውን ውድቅ አድርጎታል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰላም ለኤርትራውያን ምን አመጣ? በዚሁ ሁኔታ ላይ እንዳለ ባለፈው ዓመት ኢህአዴግ የአልጀርስ ስምምነቱን ያለቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበሉት በመግለጽ ከኤርትራ ጋር እርቅ ማውረድ እንደሚፈልጉ ውሳኔ ላይ ደረሱ። ፕሬዚዳንት ኢሳያስም በምላሹ ኢትዮጵያ ውስጥ የመጣውን ለውጥ የሚገመግም ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ ገለጹ። በቀጣይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በደማቅ አቀባበል አስመራ ገቡ፤ በዚህም የጥላቻ ግንቦች በፍቅር ፈረሱ። ተነፋፍቀው የነበሩ ቤተሰቦችና ሕዝቦች ተገናኙ፤ ሰላምም ተበሰረ፤ ብዙዎችም ደስታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው በእንባ ሲታጠቡ ነበር። የሁለቱ አገራት መሪዎች የንግድ ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ስምምነቶችን እንደተፈራረሙ መግለጫ መሰጠት ተጀመረ። ለአስርት ዓመታት ተዘግተው የነበሩት የሁለቱ አገራት ድንበሮችም ተከፈቱ። ነገር ግን ከጥቂት ወራት በኋላም እነዚሁ ድንበሮች ተዘጉ። ከእርቀ ሰላም በኋላ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳደረጉት፤ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ በፖለቲካዊ እይታ ምክንያት ከተራራቁዋቸው ኤርትራውያን ጋር አብረው እንዲሠሩ፣ የረቀቀው ሕገ መንግሥት እንዲተገበር፣ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ አሠራር እንዲተገበር ቢጠበቅም አንዳች ተስፋ የሚሰጥ ነገር አልታየም። ከዚህም በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ጋር ስለተደረገው ስምምነት ከኤርትራ በኩል ዝርዝር እንዲነገር ቢጠበቅም ጠብ የሚል ነገር የለም። ብዙዎች ያገራችንን ጉዳይ ለምን ከኢትዮጵያ መሪዎች አፍ እንሰማዋለን የሚል ቅሬታን በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ገልፀዋል። • ''ኤርትራ የእምነት ነፃነት የምታከብር ሃገር ነች'' አቶ የማነ ገብረ-መስቀል ካለፈው ወር ጀምሮ ደግሞ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኤርትራውያን 'ይኣክል' (ይበቃል) በሚል ሕዝባዊ ጥሪ በኤርትራ ውስጥ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት እንዲኖርና የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ። የዘንድሮውም 28ኛ የነፃነት በአል በኤርትራውያን ዘንድ ዝብርቅርቅ ባለ ስሜት ውስጥ ሆኖ ነው የሚከበረው።
news-54672466
https://www.bbc.com/amharic/news-54672466
አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ሲታወስ
በዛሬው ዕለት ጥቅምት 25 ታዋቂው የማራቶን ሯጭ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ 41 ዓመታትን አስቆጥሯል። አትሌቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካውያን በአትሌቱ ዘርፍ በር ከፋች ነበር። የዚህ ታላቅ ሰው መካነ መቃብር አዲስ አበባ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስትያን ይገኛል። ድሉ ደግሞ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ታትሟል።
የአበበን ታሪክ የታሪክ ሰነዶች፣ የስፖርት መዛግብት፣ የዓለም መገናኛ ብዙኀንና ኢትዮጵያውያን በጉልህ ያስታውሱታል። ከድሎቹ ሁሉ ደምቆ የሚታወሰው ደግሞ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ለአገሩ ኢትዮጵያ እና ለጥቁር ህዝቦች ያስመዘገበው ድል ነው። 17ኛው የዓለም ኦሎምፒክ ውድድር እኤአ በ1960 በጣልያን መዲና ሮማ ነበር የተካሄደው። በዚህ ውድድር ከ83 ሀገራት የተወጣጡ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች መሳተፋቸው ይነገራል። በሮም ኦሎምፒክ ከተሳተፉ ጥቁሮች መካከል ግን ሌላ ባለድልም አለ። መሐመድ ዓሊ በቀላል ሚዛን የወርቅ ሜዳልያ ተጎናፅፎ ነበር። ቢሆንም ኦሎምፒኩ በመሐመድ ዓሊ ወርቅ ሜዳልያ እምብዛም የደመቀ አልነበረም። በወቅቱ ታሪክ የሚያስታውሰው ሌላ ክስተትም ነበር። ጊዜው ደቡብ አፍሪካ በአህጉራዊ ውድድሮች ለመጨረሻ ግዜ ተሳትፋ የታገደችበት ነበር። የእገዳዋ ምክንያት ደግሞ ትከተለው በነበረ የአፓርታይድ ስርአት መሆኑ ነው። ቢሆንም የያኔ የሮሙ ኦሎምፒክ በመሐመድ ዓሊ የወርቅ ሜዳልያም ብሎም በደቡብ አፍሪቃ መታገድ አይደለም የሚታወሰው። ታድያ በምን ይታወሳል ያሉ እንደሆነ በውድድር ዘመኑ የማራቶን ሩጫ ያለ ጫማ ሮጦ የርቀቱ አዲስ ክብረወሰን ባስመዘገበው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ ነው። በወቅቱ በርካታ ሊጠቀሱ የሚችሉ ነገሮች ቢከናወኑም አበበ ግን ታሪኮችን ሁሉ ልቆ የሚታወስ ድንቅ ታሪክ አስመዘገበ። ያኔ፣ አይደለም አበበ በቂላ የሚባል አትሌት፣ ኢትዮጵያ ተብላ ስለምትጠራ ሀገርም የሚያውቅ የውጭ ዜጋ ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። ይሁን እንጂ ውድድሩ በጣልያን መካሄዱ እና የጣልያን ወረራ በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ተጠናቅቆ ነጻነቷን የማግኘቷ ወሬ ገና ከዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የወሬ አጀንዳነት ባለመረሳቱ፣ የአበበ ቢቂላ ድል ገነነ። የዓለም አቀፍ ሚድያዎች ሳይቀር ባልተጠበቀው የአትሌት አበበ በቂላ ድል ተደምመው ደጋግመው፣ በባዶ እግር ሮጦ የወርቅ ሜዳልያ ስላገኘው ኢትዮጵያዊው አትሌት ተናገሩ። "ሙሶሎኒ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች አሰልፎ እና መድፍ እና መርዛማ ጋዝ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ሲወር፣ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ግን ጣልያንን ብቻ ሳይሆን መላውን አለም አሸነፈ" የሚል ዘገባዎች ተሰራጩ። ያቺ አጋጣሚ… የኦሎምፒክ ውድድር እየተካሄደ በነበረበት ግዜ ጥቂት ኢትዮጵያውያን በጣልያን ሮም ይኖሩ ነበር። እነዚህ ኢትዮጵያውያን በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አማካኝነት የሥነ መለኮት ትምህርት እንዲማሩ ተብለው ከኢትዮጵያ የተላኩ ናቸው። እኤአ በ1960 አንዲት እናት በስራ ምክንያት ከአስመራ ወደ ሮም ተጉዘው ነበር። እኚህ ወ/ሮ ሳራ ሰለባ፣ የተሰኙ እናት "የጥቁሮች ፊት ሳላይ እኖራለሁ፣ ያቺ ተወልጄ ያደግኩባት አስመራም በምናቤ ትመላለስ ነበር። አልፎ አልፎ እነዛ የተባረኩ የሥነ መለኮት ተማሪዎች ብቸኝነቴ ተረድተው እየመጡ ይጠይቁኝ ነበሩ" ብለው ያጫውቱት እንደነበር ልጃቸው ያስታውሳል። ወ/ሮ ሳራ፣ አበበ በቂላ ሮጦ ድል ያደረገበ ዕለት ውደድሩ በቴሌቭዥን መስኮት ተከታትለዋል። አብረዋቸው የነበሩ ነጮች ተሰብስበው "የሀገርሽ ልጅ አሸንፏል" እያሉ ይጮሁ እንደነበር ያስታውሳሉ። ታድያ ወ/ሮ ሳራ አብረዋቸው ከመደሰት ይልቅ ማልቀስን መረጡ። ለወ/ሮ ሳራ የለቅሶ ምክንያት የነበረው ደግሞ የአበበ ባዶ እግር መሮጥ ነበር። ሻምበል አበበ እና አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን አበበ ቢቂላ ነሐሴ 30 ቀን 1925 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን አውራጃ፣ ደነባ ልዩ ስሟ ጃቶ በምትባል ሥፍራ ከአባቱ አቶ ቢቂላ ደምሴና ከእናቱ ከወይዘሮ ውድነሽ መንበሩ ተወለደ። ወጣቱ አበበ እንደአካባቢው ልምድ በእረኝነት ቤተሰቡን አገልግሏል። በአሥራ ሁለት ዓመቱም የቄስ ትምህርቱን አጠናቋል። በዚህ በጨቅላ ዕድሜው ስመ ጥር የገና ተጫዋች እንደነበር ይነገርለታል። በ1944 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በክብር ዘበኛ ሰራዊት በወታደርነት ተቀጥሮ በገና ጨዋታ እና በስፖርት እየዳበረ ቆየ። ስዊድናዊው ኦኒ ኒስካነን [1910-1984] የክብር ዘበኛ ስፖርት ክፍል አስልጣኝ ነበር። በወቅቱ የስፖርት ክፍሉ ባልደረቦች ከነበሩት መካከል የሁለቱ አበበዎች የሩጫ ልምድ ትኩረቱን ስቦት እንደነበር ትቶት የሄደው ማስታወሻ ያሳያል። አበበ በቂላ ወደ አትሌቱ መንደር የተቀላቀለው በ24 አመቱ ነበር። ኦኒ ኒስካነን አበበን ወደ ሩጫ እንዲገባ ባያደፋፍረው አትሌትም ላይሆን ይችል እንደነበር ይነገራል። እርግጥ ነው አበበ እግር ኳስ እና ቅርጫት መጫወት ይወድ ነበር። አስለጣኝ ኦኒ ኒስካነን አበበ የሩጫ ውድድር እንዲሞካክር ይገፋፋው ነበር። በአራራጡ እና በራስ መተማመኑ ይወድለት ስለነበር በክቡር ዘበኛ ውድድሮች ሲያሳትፈው ጥሩ ውጤት ያመጣ ጀመር። ኒስካነን የአበበ በቂላ እና አበበ ዋቅጅራ የሩጫ ልምድ አይቶ ሮም ላይ በተካሄደው የዓለም ኦሎሚፒክ ውድድር እንዲሳተፉ አዘጋጃቸው። አበበ ዋቅጅራ ከአበበ ቢቂላ በ10 ዓመት ያህል የሚበልጥ ሲሆን በሮም ኦሎምፒክ ላይ እንደ አበበ ሁሉ በባዶ እግሩ ሮጦ ሰባተኛ መውጣቱን ድርሳናት ያሳያሉ። ሁለቱ አበበዎች ለምን በባዶ እግር ሮጡ በሮም ኦሊምፒክ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ የሮጠበት ምክንያት በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ሲንፀባረቁ ተሰምተዋል። በርካታ መዛግብት ለአበበ የሚስማማ ጫማ መጥፋቱን፣ የሞከረውም ጫማ ስለጠበበው ያለጫማ መሮጥን መምረጡን ጽፈዋል። እነዚህ መዛግብት አበበ ዋቅጅራም በባዶ እግሩ ስለመሮጡ ያነሱት አንዳች ነገር የለም። ይሁን እንጂ እውነታውን በተመለከተ የአበበ ቢቂላ ልጆች እንዲሁም አሰልጣኙ ትተዋቸው ያለፉ ድርሳናትና የይድነቃቸው ተሰማ እሸቴ ማስታወሻዎች ይህንን ይናገራሉ። ኦኒ ኒስካነን እነ አበበን ይዞ ወደ ሮም ከተጓዘ በኋላ እዚያው ሮም የሩጫ ልምምድ ያደርጉ ነበር። ልምምዱ የሚካሄደውም ጫም ተጫምተው እና በባዶ እግር ነበር። ኦኒ ኒስካነን በልምምዱ ሂደት ታድያ አንድ ነገር አስተዋለ። ሁለቱም አትሌቶች በባዶ እግር ሲሮጡ የተሻለ ፍጥነት ማስመዝገብ ችለው ነበር። ውድድሩን በድል ያጠናቅቁ እንጂ እንደ ፍላጎታቸው መሮጥ እንዲችሉ ፈቀደላቸው። አበበ ቢቂላ ጫማ ተጫምቶ ሲሮጥ በአንዲት ደቂቃ ከ5-6 ስንዝር ይዘገይ እንደነበርም አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን መስክሯል። ከውድድሩ በኋላ ስለ ሁኔታው የተጻፉት እውነታነት እንዳልነበራቸውም ኒስካነን ተናግሮ ነበር። 'ጫማ ስላልተገዛላቸው ነው' እና 'የተገዛላቸው ጫማ ስለጠበባቸው ነው' የሚሉ ሀሳቦች ሀቅ አይደሉም ብሏል ኒስካነን። ኦኒ ኒስካነን እንደሚተርከው ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ወደ ሮም ከመሄዳቸው በፊት ስለ ውድድሩ በቂ መረጃ ተሰጥቷቸው ነበር። በውድድሩ የተሻለ ፍጥነት ያላቸው ተወዳዳሪዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ ከሚለው ጀምሮ እስከ የመወዳደርያ ማልያ ቁጥራቸው በሚገባ ተነግሯቸዋል። እነ አበበ ቢቂላን ከሚፎካከሩት መካከል ደግሞ ሞሮኳዊው ሯጭ ራዲ ቢን አብደልሰላም ይገኝበታል። ስለራዲ እነ አበበ መረጃ ቢኖራቸውም የመወዳደሪያ ቁጥሩ መቀየሩን ግን አያውቁም ነበር። ራዲ ቀድሞ የተሰጠው የመወዳደርያ ቁጥር ስላልተገኘ ነበር ሌላ አዲስ ቁጥር የተሰጠው። እነ አበበ ግን ራዲ አዲስ ቁጥር እንደተሰጠው መረጃው የላቸውም። አበበ ከቀሪዎቹ ተወዳዳሪዎች በሰፊ ርቀት ፈንጠር ብሎ በሚሮጥበት ግዜ ሞሮኳዊው ራዲ ግን በቅርብ ርቀት ይከተለው ነበር። በወቅቱ ሞሮኮ በውድድሩ ሶስት ተወዳዳሪዎች አሰልፋ ስለነበር፣ አበበ ከሶስቱ አንዳቸው ይሆናሉ በሚል ሮም የሚገኘው የአክሱም ሀውልት እስኪደርሱ ድረስ ብዙም ግምት አልሰጠውም ነበር። አበበ በውድድሩ በአስልጠኙ እንዲያደርጋቸው ከተነገሩት ነገሮች መካከል አንዱ የአክሱም ሀውልት ሲደርስ ፍጥነቱ እንዲጨምር ነበር። አበበም በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ውድድሩ ሊያልቅ 2 ኪሎ ሜትር ሲቀረው ሮም ፒያሳ በተተከለው አክሱም ሀውልት ሲደርስ በፍጥነት ተፈተለከ። አበበ ያኔ ለጥቂትም ቢሆን ቢዘናጋ ኖሮ ራዲ የማሸነፍ እድል እንደነበረው ይነገራል። እንደ አስልጣኙ ኦኒ ገለጻ ከሆነ አበበ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ አብሮት የተጓዘው ራዲ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ቀድሞት ሊሮጥ ምናልባትም ያስመዘገበው ክብወሰን በተሻለ ያሻሽለው ነበር ይላል። ሻምበል አበበ በቂላ በ1964 በቶክዮ ጃፓን በተካሄደው ውድድርም የራሱን ክብረወሰን በማሻሻል አሸናፊ ሆነ። ከውድድሩ አንድ ወር በፊት ግን ቀዶ ጥገና ተደርጎለት የነበረ ቢሆንም ውድድሩ በአስደናቂ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ችሏል። በ1968 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ36 ዓመቱ በኦሎሚፒክ ውድድር ለ3ኛ ግዜ የተሳተፈ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት ሳይጨርስ የቀረ ሲሆን፣ ውድድሩ በሌኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ማሞ ወልዴ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። አለምን በባዶ እግር ሮጦ በማሸነፍ አንቱታ ያተረፈውን ሻምበል አበበ በቂላ በገጠመው የመኪና አደጋ ምክንያት በ41 ዓመቱ ከዚህ አለም ተለየ።
news-45799644
https://www.bbc.com/amharic/news-45799644
የደምህት ወታደሮች የመኪና አደጋ ደረሰባቸው
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደምህት) ወታደሮች ዛሬ ጠዋት ከኤርትራ ወደ ዛላምበሳ በሚመጡበት ወቅት ነበር ሰገነይቲ በሚባለው የኤርትራ ድንበር ውስጥ የመኪና አደጋ ያጋጠማቸው።
በአደጋው ብዙ የደምህት ወታደሮች እንደተጎዱ ከአካባቢው ወደ ዛላምበሳ የመጣ የድርጅቱ አመራር አባል ለቢቢሲ ተናግሯል። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የወታደሮች ቁጥር በውል ባይገልጽም፤ ሰራዊቶቹን የያዘች መኪና እንደተገለበጠች ግን አረጋግጧል። • ኢትዮጵያና ኤርትራ የመጨረሻውን የሠላም ስምምነት ፈረሙ • ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ? • ኤርትራ ውስጥ በአጋጠመ የመኪና አደጋ 33 ሰዎች ሞቱ መንግሥት ባቀረበው የሰላም ጥሪ መሰረት ከ2000 በላይ የደምህት ወታደሮች ዛሬ ማለዳ ዛላምበሳ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሠራዊቱን አባላት የሚቀበሉ የህዝብ አውቶብሶችም በዛላምበሳ ከተማ ተዘጋጅተዋል።
news-45819930
https://www.bbc.com/amharic/news-45819930
እንግሊዝ "ራስን የማጥፋት" ተከላካይ ሚኒስትር ሾመች
እንግሊዝ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን ነፍስን በገዛ እጅ የማጥፋት ጉዳይ ለመቀነስ በሚኒስትር ደረጃ ራስን የማጥፋት ተከላካይ ሚኒስትር (suicide prevention Minister) መሾሟ ተሰምቷል። ይህ ሹመት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ለነበሩት ጃኪ ፕራይስ ነው የተሰጠው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ይህን ሹመት የሰጡት የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በተከበረበት በትናንትናው ዕለት ነው። የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ትናንት በለንደን ከ50 አገራት የመጡ የጤና ሚኒስትሮች በተገኙበት ተከብሮ ውሏል። • የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ- ትህዴን ማን ነው? • “ትጥቅ መፍታት ለድርድር አይቀርብም”፡ መንግሥት • ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች የእኚህ ሚኒስትር ተደራቢ ሥራ የሚሆነው በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን ነፍስን በገዛ እጅ የሚያጠፉ ዜጎችን ቁጥር የሚቀንስበትን መንገድ መሻት ይሆናል። እንግሊዝ ውስጥ በተደረገ አንድ ጥናት የአእምሮ ጤና ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች በዘርፉ የሰለጠነን ሐኪም ለመጎብኘት እስከ ሦስት ወራት ለመጠበቅ ይገደዳሉ። ከነዚህም ውስጥ በአልኮል ሶስ የተጠመዱና በሐሴት-ሐዘን የስሜት መዋዠቅ (ባይፖላር ዲስኦርደር) ደዌ የተጠቁ ይገኙበታል። በርካታ ዜጎችም ራስን ለማጥፋት እንደ አንድ ምልክት በሚታዩት የድብርትና ጭንቀት በሽታዎች ይሰቃያሉ። አሁን አሁን መጠነኛ መቀነስ ታይቷል ቢባልም በእንግሊዝ በዓመት በአማካይ 4500 ዜጎች ነፍሳቸውን በገዛ እጃቸው ያጠፋሉ።
news-52488485
https://www.bbc.com/amharic/news-52488485
ኮሮናቫይረስ፡ ዓለም ‘ከኅዳር በሽታ’ በኋላ ምን መሰለች? ከወረርሽኙስ ምን እንማራለን?
በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ‘ስፓኒሽ ፍሉ’ የተሰኘ ወረርሽኝ ተከስቶ ነበር። በኢትዮጵያውያን ዘንድ ‘የኅዳር በሽታ’ በሚል የሚታወቀው ወረርሽኝ ለ‘ኅዳር ሲታጠን’ ልማድ መነሻ ምክንያትም ነበር።
‘የወረርሽኞች ሁሉ እናት’ በሚል የሚጠራው ይህ ወረርሽኝ በሁለት ዓመት ብቻ ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ሕይወት ቀጥፏል። ያኔ የዓለም ሕዝብ 1.8 ቢሊዮን ነበር። ከሕዝቡ አንድ ሦስተኛው በወረርሽኙ ተይዞ እንደነበር ተመራማሪዎችና የታሪክ አጥኚዎች ይናገራሉ። • በአማራ ክልል የትምህርት ቤቶች መዘጋትን ተከትሎ ያለዕድሜ ጋብቻዎች መጨመራቸው ተገለፀ ወረርሽኙ ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት በላይ ሰዎችን ገድሏል። ዓለም በኮቪድ-19 ጭንቅ ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት፤ ወደ ኋላ መለስ ብለን ከ‘ስፓኒሽ ፍሉ’ በኋላ ምድር ምን ትመስል እንደነበር ቃኝተናል። ወረርሽኝ ሳይንስ ባልተራቀቀበት ዘመን ያኔ ሳይንስ እንደዛሬው አልተራቀቀም ነበር። በሽታ መከላከልም ቀላል አልነበረም። ሐኪሞች ‘የኅዳር በሽታ’ ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ቢያውቁም፤ የበሽታው መንስኤ ባክቴሪያ እንጂ ቫይረስ መሆኑን አልተገነዘቡም ነበር። በወቅቱ የሕክምና አገልግሎትም ውስን ነበር። ፀረ እንግዳ አካላት (አንቲባዮቲክ) የተገኘው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1928 ነበር። ለጉንፋን ክትባት የተገኘው ደግሞ በ1940ዎቹ ነው። ያኔ ዓለም አቀፍ የጤና ሥርዓት ማዕቀፍ አልነበረም። ሀብታም በሚባሉ አገራት ሳይቀር የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ እንደ ቅንጦት ይቆጠር ነበር። ‘ስፓኒሽ ፍሉ ዓለምን እንዴት ለወጠ’ በሚል መጽሐፍ ያሳተሙት ፔል ራይደር፤ ያኔ ኢንዱስትሪ በተስፋፋባቸው አገራት ሐኪሞች የእራሳቸው ቅጥረኛ ነበሩ ይላሉ። ሐኪሞች በተራድኦ ድርጅቶች ወይም በሐይማኖት ተቋሞችም ይደገፉ ነበር። በዘመኑ አብዛኛው ማኅበረሰብ ሐኪም አያገኝም። ወረርሽኙ ከፍተኛ ቁጥር ያለቸውን ወጣቶች በመግደሉ የተለየ ነበር ‘የኅዳር በሽታ’ ከዚያ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ነበር ጉዳት ያስከተለው። በብዛት የሞቱት ከ20 ዓመት እስከ 40 ያሉ ናቸው። ከመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የተመለሱ ወታደሮች ይኖሩበት በነበረ ማቆያ ውስጥ እንደተቀሰቀሰ የሚታመነው ይህ ወረርሽኝ፤ በዋነኛነት ያጠቃው ወንዶችን ነበር። ድሃ አገሮችም በግንባር ቀደምነት ተጎድተዋል። ዘንድሮ በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ የተሠራ ጥናት፤ በስፓኒሽ ፍሉ 550 ሺህ አሜሪካውያን (ከአጠቃላይ ሕዝቡ 0.5 በመቶው) እንዲሁም 17 ሚሊዮን የህንድ ዜጎች (ከአጠቃላይ ሕዝቡ 5.2 በመቶው) መሞታቸውን ያሳያል። • የኮሮናቫይረስ ተመራማሪው ዶ/ር ቢንግ ሊው ለምን ተገደሉ? የጥናቱ መሪ ሮበርት ባሮ፤ በሽታው ምጣኔ ሀብትን አሽመድምዶት ነበር ይላሉ። አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ስድስት በመቶ ያሽቆለቀለበት ዘመን መሆኑንም ይጠቅሳሉ። “የመጀመሪያው የዓለም ጦርነትና ወረርሽኙ ተደማምረው የዓለምን ምጣኔ ሀብት እንዳልነበረ አድርገውታል” ሲሉም ያስረዳሉ። የቤተሰቦቻቸውን ንግድ የሚረከቡ፣ የሚያርሱ፣ ባቡር የሚነዱ፣ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ወጣት ወንዶች በብዙ አገራት አልቀዋል። “በወቅቱ የወንዶች ቁጥር መቀነሱ ሴቶች የትዳር አጋር እንዳያገኙ አድርጓል” ይላሉ ሮበርት። በርካታ ወንዶች በመጀመሪያው የዓለም ጦርነትና በወረርሽኙ በመሞታቸው ሴቶች በተለያዩ መስኮች እንዲሰማሩ በር ተከፈተ “በአገሬ የሴቶች መብት ትግል ወረርሽኙ ሚና እንደነበረው ማስረጃ አለ” ወረርሽኙ በወንዶችና በሴቶች መካከል የነበረውን የጾታ ሚዛን ለውጧል። የቴክሳስ ዩኒቨርስረቲ አጥኚ ክርስቲን ብላክበር እንደሚሉት፤ አሜሪካ ውስጥ ወንድ ሠራተኞች በወረርሽኙ በመሞታቸው ምክንያት ሴቶች በተለያዩ መስኮች መሰማራት ጀምረዋል። በ1920 ሴቶች ከአገሪቱ ሠራተኞች 21 በመቶውን ይሸፍኑ ነበር። ያ ዓመት ሴቶች እንዲመርጡ የሚፈቅድ ሕግ የፀደቀበትም ነው። በቂ የሠራተኛ ኃይል አለመኖሩ የሴቶች ደሞዝ (ከ21 ሳንቲም ወደ 56 ሳንቲም) ከፍ እንዲልም አድርጓል። • "ስለምንወዳችሁ ሠርጋችን ላይ አትምጡ" የአዲስ አበባዎቹ ሙሽሮች “በአገሬ የሴቶች መብት ትግል ወረርሽኙ ሚና እንደነበረው ማስረጃ አለ” ይላሉ ተመራማሪዋ። በወቅቱ የተወለዱ ሕፃናት ከወርሽኙ በፊት ከተወለዱት በበለጠ በልብ ህመም ይያዙ እንደነበር ተመራማሪዎች ደርሰውበታል። ወረርሽኙ የፈጠረው ጭንቀት የእናቶች ጤና ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ መላ ምቶች አሉ። በዘመኑ የተወለዱ ወንዶች ከሌሎች በአንድ ሚሊ ሜትር ያጥሩ እንደነበረ አሜሪካ ውስጥ የተሠራ ጥናት ይጠቁማል። ከወረርሽኙ በኋላ ጋንዲና ሌሎች የነጻነት ታጋዮች ድምጽ ጎልቶ መሰማት ጀመረ ፀረ ቅኝ ግዛት ንቅናቄ በ1918 ህንድ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ከወደቀች አስር ዓመት አልፎ ነበር። ወረርሽኙ ህንድ ውስጥ ከእንግሊዞች በላቀ ህንዳውያንን ጎድቶ ነበር። የሚገለሉ የሂንዱ ማኅበረሰቦች የሞት መጠን በአንድ ሺህ ሰው 61.6 እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። እንግሊዞች በሽታውን ለመቆጣጠር ተገቢውን እርምጃ እንዳልወሰዱ የህንድ ብሔርተኞች ይናገራሉ። በ1919 በታተመው መጽሐፋቸው ማኅተመ ጋንዲ የእንግሊዝን አስተዳደር ኮንነዋል። • ከኮሮናቫይረስ ለማገገም ምን ያክል ጊዜ ይወስዳል? በሌላ በኩል በሽታው በመላው ህንዳውያን ዘንድ ብሔራዊ ትብብርን ፈጥሯል። ያኔ የዓለም ጤና ድርጅት የተቋቋመው ከተባበሩት መንግሥታት በፊት በነበረው ሕብረት አማካይነት ሲሆን፤ በሐኪሞች በመመራት ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መቆጣጠሪያ መንገዶችን ይቀይስ ነበር። አሁን ያለው የዓለም ጤና ድርጅት የተመሰረተው በ1948 ነው። በርካታ አገራት ከወረርሽኙ በኋላ የጤና ሚኒስቴራቸውን አጠናከሩ የኅብረተሰብ ጤና ምርምር መሻሻል ወረርሽኙ በኅብረተሰብ ጤና ዘርፍ ለሚሠሩ ምርምሮች መነሻ ሆኗል። በ1920 ሩስያ ኅብረተሰቡን ያማከለ የጤና ሥርዓት በመመስረት ግንባር ቀደም ሆናለች። ሌሎች አገራትም ተከትለዋት የጤና ሚንስቴር ማቋቋም ጀምረዋል። አንትሮፖሎጂስቷ ጄኔፈር ኮል እንደሚናገሩት፤ ወረርሽኙ እና የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ለአቅመ ደካሞች ከለላ የሚሰጡ ተቋሞች እንዲመሰረቱም አስችለዋል። “ብዙ ወላጆቻቸውን ያጡ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ የትዳር አጋራቸውን በሞት የተነጠቁም ነበሩ” ይላሉ። በዚያን ዘመን የተነሳውን ‘የኅዳር በሽታ’ ለመቆጣጠር አካላዊ ርቀት መጠበቅን የተገበሩም ነበሩ። • በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ የአሜሪካዋ ፊላዴልፊያ ግዛት አንድ የአደባባይ መሰናዶ ስታካሂድ ሴንት ልዊስ ግዛት ግን ለመሰረዝ ወስና ነበር። ይህ በሆነ በወሩ በፊላዴልፊያ 10 ሺህ ሰዎች ሲሞቱ፤ ሴንት ልዊስ ግን ያጣችው 700 ሰዎችን ብቻ ነበር። አጋጣሚው በሽታው ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ መራራቅ አስፈላጊ መሆኑን አስተምሮ አልፏል። ቴአትር ቤት፣ ትምህርት ቤት፣ ቤተ ክርስቲያንና ሌሎችም ሕዝብ የሚበዛባቸውን ቦታዎች የዘጉ ግዛቶች በአንጻራዊነት ጥቂት ሰው የሞተባቸው ሆነዋል። በ1918 ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ የጣሉ ግዛቶች በቶሎ ምጣኔ ሀብታቸው እንዳገገመ የፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ደርሰውበታል። ወረርሽኙ 700 ሺህ አሜሪካውያንን የገደለው የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳት ከነበረበት ጊዜ ቀድሞ በመነሳቱ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ሮበርት ባሮ እንደሚሉት፤ ለ12 ሳምንታት የቆየ የእንቅስቃሴ ገደብ ቢጣል ኖሮ የሟቾችን ቁጥር መቀነስ ይቻል ነበር። ሆኖም በነዋሪዎች ግፊት ምክንያት ገደቡ ያለ ጊዜው ተነስቷል። በኮቪድ-19 ወቅትም ተመሳሳይ ነገር እየተስተዋለ መሆኑን ባለሙያው ያስረዳሉ። ከመቶ ዓመት በፊትም ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ ይመከር ነበረ የተረሳው ወረርሽኝ? ‘የኅዳር በሽታ’ ብዙ ነገር አስተምሮ ቢያልፍም ከሞላ ጎደል ተዘንግቷል። በዚያን ዘመን የአሜሪካ እና የእንግሊዝ መሪዎች በበሽታው ተይዘው ነበር። የብራዚል ፕሬዘዳንትም የሞቱት በወረርሽኙ ሳቢያ ነበር። ሆኖም ግን የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወረርሽኙን ሸፍኖታል። የዓለም መንግሥታት መገናኛ ብዙሃን ስለ በሽታው እንዳይዘግቡ ማዕቀብ መጣላቸው ደግሞ በቂ ሽፋን ላለማግኘቱ ምክንያት ነው። ስለወረርሽኙ በተለያዩ ባህሎች በስፋት ሲወራ በታሪክ መጻሕፍት ሲጠቀስም አይስተዋልም። የህክምና ታሪክ አጥኚው ማርክ ሆንግስቡም እንደሚናገሩት፤ በወረርሽኙ ሕይወታቸውን ላጡ መታሰቢያ አይደረግም፤ መስዋዕትነት የከፈሉ ሐኪሞችና ነርሶች የሚታወሱትም በጥቂት መቃብር ስፍራዎች ነው። “ስለ 1918ቱ ወረርሽኝ ብዙ ልብ ወለዶች፣ ዘፈኖች እና ሥዕሎችም የሉም” ይላሉ። በ1924ቱ ‘ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ’ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተከሰቱ የማይረሱ ሁነቶች ዝርዝር ውስጥ ወረርሽኙን አልተካተተም። ‘ስፓኒሽ ፍሉ’ ወይም ‘የኅዳር በሽታ’ ለመጀመሪያ ጊዜ የተወሳበት የታሪክ መጽሐፍ የወጣው በ1968 ሲሆን፤ የኮቪድ-19 ስርጭት ደግሞ የያኔው በሽታ አሁን እንዲታወስ ምክንያት ሆኗል።
news-55285692
https://www.bbc.com/amharic/news-55285692
ቴሌሜዲሲን ምንድነው? የርቀት ሕክምና በኢትዮጵያ ይሠራል?
አንድ ታካሚና አንድ ሐኪም በአካል ሳይገናኙ ሕክምና ሊካሄድ ይችላል? ለዚያውም "ወሬ በዓይን ይገባል" በሚል ማኅበረሰብ ውስጥ፤ ለዚያውም በሚቆራረጠው ቀጭኑ ሽቦ?
አቶ አብዲ ድንገታ ይህ ቴሌሜዲስን ተብሎ ይጠራል። ለመሆኑ በእኛ አገር ይህ የአማካሪዎች ሕክምና እንዴት ውጤታማ ሊሆን ይችላል? የሰመመን ሕክምና ባለሙያና የዮኮ ቴሌሚዲስን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዲ ድንገታ፣ "እውነት ነው የማኅበረሰባችን አስተሳሰብ በዚህ ረገድ መቀየር አለበት" ይላሉ። የማኅበረሰቡን ለሕክምና ሂደቶች የሚሰጠውን አረዳድ ሲተቹም፣ "…መርፌ ሳያዝልኝ ነው በኪኒን የላከኝ፤ ዛሬ ደግሞ ራጅ እንኳ ያላዘዘ ሐኪም ነው የገጠመኝ" ብሎ በሐኪሙ ቅር የሚሰኝ ብዙ ሰው መኖሩን አያይዘው ያነሳሉ። "ይህ አስተሳሰብ እኛንም ፈተና ውስጥ ከቶን ነበር። አሁን ግን ኅብረተሰቡ እየለመደን ነው፤ እኛም የጤና መረጃን በጥራት በማቅረብ እምነቱን ለማግኘት እየሰራን ነው" ይላሉ። ዮኮ የማማከር የሕክምና አገልግሎት (ቴሌሜዲሲን) የተጀመረው የኮቪድ-19 ወረርሽን ከመከሰቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ነው። ይሁን እንጂ በጤና ዘርፍ በተለያየ ስፍራ ይሰሩ የነበሩት መስራቾቹ የኮቪድ-19 ወረርሽኙ ከገባ ወዲህ ምሥረታውን ማፋጠን እንዳለባቸው ተሰማቸው። ምክንያቱ ደግሞ ወረርሽኙን ተከትሎ ሆስፒታሎች እየተራቆቱ በመምጣታቸው ነው። ሰዎች ሆስፒታል መሄድ ከፈሩ በጤና ለመቆየት ሐኪማቸውን በስልክ ማግኘት አለባቸው። ይህ ሁኔታ ቀደም ብሎ ተጸንሶ የነበረውን ዮኮ ቴሌሜዴስንን አዋለደ። "በወረርሽኙ ምክንያት ሰዎች የሆስፒታል ደጆችን መርገጥ ፈሩ። ከበድ [ክሮኒክ] በሽታ ያለባቸው ሰዎችም ሆስፒታል አይሄዱም ነበር። በዚህ የተነሳ የቴሌሜዲሲን አስፈላጊነት ከምንጊዜውም በላይ ጎልቶ ታየን" ይላሉ አቶ አብዲ። ቴሌሜዲሲን በአገራቸው አዲስ ዘርፍ ይመስላል። ሐሳቡ ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ታማሚውና ሐኪሙ በአካል ሳይገናኙ በስልክ ብቻ በመገናኘት ማቀበል ነው። አቶ አብዲ ድርጅታቸው የሚሠራቸው ተግባራትን በአራት አምዶች ይቦድኗቸዋል። የመጀመርያው በሽታን ማወቅና መለየት እንዲሁም ስለ ሕክምናው መወያየት ነው። ሁለተኛው ተራ የሚመስሉ ግን ጠቃሚ መረጃዎችን ከታማሚው ጋር መወያየት ነው። "እርግጥ ነው በጤና ዘርፍ ተራ የሚባል መረጃ የለም" የሚሉት አቶ አብዲ ትንሽ የጤና ምክር ስህተት ለትልቅ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል ያወሳሉ። ተራ የሚባል ከታማሚው የሚሰጥ መረጃም በአንጻሩ ለሐኪሙና ለሕክምናው መሳካት ትልቅ ግብአት እንደሚሆን በመግለጸወ፣ የጥቃቅን መረጃን አስፈላጊነት ያስረዳሉ። "አንድ ሰው ከሐኪሙ ጋር ውሎ መድኃኒት ገዝቶ ቤቱ ገብቶ ስለ መድኃኒቱ አወሳሰድ ግራ ቢገባው ደውሎ ከሐኪሞቻችን ጋር ሊወያይበት ይችላል" ይላሉ። ወይም ደግሞ አንድን የሕክምና ሂደት [ፐሮሲጀር] ለማድረግ ያሰበ ታማሚ የሕክምና ሂደቱን በተመለከተ ሊያውቃቸው የሚገቡ ቅድመ ጥንቃቄና ድኅረ ጥንቃቄዎችን ከሐኪሞቹ በተጨማሪ በስልክ ከዮኮ ሐኪሞች ሊመከር ይችላል። ሌላው የቴሌሜዲሰን አገልግሎት አንድ ታማሚ በአካል ሆስፒታል ሄዶ ታክሞ ከሐኪሙ ጋር የነበረው ቆይታ ግን አደናጋሪ ቢሆንበትና ተጨማሪ መረጃን ቢሻ፤ ስልክ ደውሎ ይህንኑ አገልግሎት ማግኘት ይችላል። በጤና ረገድ ተጨማሪ ሐሳብ መስማት የብዙ ተማሚዎች ፍላጎት እንደሆነ ሳይዘነጋ። ሦስተኛው የቴሌሜዲስን አገልግሎት የድንገተኛ የስልክ ሕክምና አገልግሎት ነው። አይበለውና አንድ ሰው ቤት ውስጥ ወይም መንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበትና በቅርብ ያለው ሰው የመጀመርያ እርዳታ ለመስጠት ፈልጎ ነገር ግን ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ቢገባው፤ የስልክ ጥሪ በማድረግ በዚሁ ከሰለጠኑ ሐኪሞች ዘንድ አስፈላጊውን እርዳታን ማግኘት ይችላል። እነዚህ በአራት አምድ የቆሙ ግልጋሎቶች ከጠቅላላ ምክር አገልግሎት ጋር ማቅረብ ነው የቴሌሜዲስን ግብ። ከአራቱ አገልግሎቶች በተጨማሪ ዮኮ ጥቅል የጤና ምክርን ለሚሹ እገዛ ይሰጣል። አንድ ሰው ለምሳሌ የጤና እክል ገጥሞት ነገር ግን የት ሆስፒታል መሄድ እንዳለበት፣ በየትኛው ሐኪምና ስፔሻሊስት ቢታይ እንደሚሻለው አማራጮችን ማወቅ ቢፈልግ፣ የትኞቹ በሽተኞች፣ ለየትኞቹ በሽታዎቻቸው የት መታከም እንዳለባቸው፣ በዘርፉ ያሉ ሐኪሞች መቼና የት እንደሚገኙ፣ ቀጠሮ ከማስያዝ ጀምሮ የተሟላ አገልግሎት መስጠት ተጫማሪ ተግባሩ ነው። ዮኮ ቴሌሜዲስን በሁለት ስፔሻሊስቶችና በስድስት ጠቅላላ ሐኪሞች በመታገዝ ነው የ24 ሰዓት የስልክ የሕክምና ምክር አገልግሎት የሚሰጠው። አንዳንድ በዘርፉ የተጠኑ የምርምር ወረቀቶ በጤናው ዘርፍ የቴሌሜዲስን ትሩፋቶች አያሌ እንደሆኑ ያወሳሉ። ለምሳሌ የሆስፒታል መጨናነቅን ያስወግዳል፤ ታማሚዎች በሆነ ባልሆነው ክሊኖኮችን ማጨናነቃቸውን ማስቀረት ያስችላል፤ ለአቅመ ደካሞች እንግልትን ያስቀራል። በታካሚና በአካሚ መካከል መግባባትን ያሳልጣል፤ ገንዘብና ጊዜን ይቆጥባል። ነገር ግን አተገባበሩ ጥንቃቄን የሚሻ ነው። በዚህ ረገድ ያጋጠሙ ችግሮችን ቆየት ብለን እንመለስባቸዋለን። አቶ አብዲ ሲናገሩ፣ "ብዙ በሽታዎች በቀላል የሐኪም ምክር ብቻ ቤት ውስጥ የሚጠናቀቁ ናቸው። ሁሉም የሕመም ምልክት ሆስፒታል የሚያስኬድ ላይሆን ይችላል፤ ጊዜንም ገንዘብንም ማባከን ነው የሚሆነው፤ ዋናው ነገር ከትክክለኛ ሐኪም ትክክለኛ ምክር ከማግኘቱ ላይ ነው" ይላሉ። ለመሆኑ ወደ ዮኮ ቴሌሜዲስን የሚመቱ የስልክ ጥሪዎች በይበልጥ ለየትኞቹ የጤና እክሎች የምክር መሻቶች የተደረጉ ናቸው? ሥራ አስኪያጁ አቶ አብዲ የተጠና ነገር ባይኖርም ከሐኪሞቻቸው በየቀኑ ከሚሰበስቧቸው ሪፖርቶች በመነሳት ብዙዎቹ የስልክ ጥሪዎች ከባድ [ክሮኒክ] የሚባሉ በሽታዎች ካሉባቸው ሰዎች የሚደወሉ ናቸው ይላሉ። "ባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ5ሺህ በላይ የስልክ ጥሪዎችን ተቀብለናል። በአንደኛ ደረጃ ሊቀመጥ የሚችለው ክሮኒክ የሆኑ ሰው ላይ ለብዙ ጊዜ አብረው የሚቆዩ በሽታዎችና በእነዚህ በሽታዎች የታመሙ ሰዎች የሚደረጉ ናቸው።" ይሄ በሽታ ምን ያመጣብኝ ይሆን? ይሄን መድኃኒት ብወስድስ/ባልወስድስ? የሚሉ አይነት ጥያቄዎች በብዛት እንደሚቀርቡላቸው ለቢቢሲ አብራርተዋል። የስኳር በሽታ ያለበት ሰው ለምሳሌ ምን ብመገብ ትክክል ነው፣ ይህንና ያንን መድኃኒት ብወስድ ምን ተጓዳኝ ችግር ያስከትልብኛል፤ በሚሉና ከመድኃኒት አወሳሰድ ጋር በተያያዘም ብዙ ሰዎች ስልክ ይደውላሉ። ሁለተኛው ወላጆች ከልጆቸው ጋር በተያያዘ የሚያስጨንቋቸው ጥያቄዎች ናቸው ስልክ የሚያስደውላቸው። "ልጄ ትኩሳት አለው፣ ምግብ አልበላ አለ" የሚሉና ሌሎች የጤና መረጃዎች የብዙ ወላጆች ጥያቄዎች ሆነዋል። በሦስተኛ ደረጃ በብዛት የሚደወሉ ስልኮች ከጾታ ግንኙነት ጋር ተያይዞ መረጃን የሚሹ ናቸው። "ከስንፈተ ወሲብ ጋር የተገናኙ፣ ባልና ሚስት በወሲብ ካለመረካት ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሚያነሱ ብዙ ናቸው" ይላሉ አቶ አብዲ። "የጾታ ግንኙነት ትምህርት በአገራችን በግልጽ ስለማይሰጥ ብዙ ሰዎች በርካታ ጥያቄዎች አሏቸው" የሚሉት አቶ አብዲ፤ "ምናልባት ሐኪም ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው እነዚህን ከወሲባ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን የመጠየቅ ድፍረቱ ስለሌላቸው ይሆናል በርካታ ሰዎች በስልክ ምክር የማግኘት ምርጫ ያላቸው" ሲሉ ይገምታሉ። የዮካ ቴሌሜድስን ከቴሌ ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ የሚገልጹት አቶ አብዲ ደንበኞች የጤና መረጃዎችን ለማግኘት በደቂቃ 4 ብር እንደሚስከፍሉ ገልጸዋል። ለመሆኑ አንዲት በመረጃ መዛባት የምትፈጠር የሕክምና ስህተት የሕይወት ዋጋ ልታስከፍል እንደምትችል ከመረዳት አንጻር እንዴት ይሆን የቴሌሜዲስን ድርጅቶች የስልክ ምክሮች ላይ ጥንቃቄ የሚያደርጉት? የጤና ጥበቃስ ቁጥጥሩን የሚያደርገው በምን መልኩ ነው? ታማሚው በሕክምናው ላይ እምነት እንዲኖረው ምንያደርጋሉ? "የእኛ አገልግሎት ማማከር ነው፤ ከደዋዮች ያልገባን ነገር ካለ አጥርተን እንጠይቃለን፤ የስልክ ሕክምናው ጠቃሚ መረጃን በመስጠት ላይ የተመሠረተ ነው እንጂ እኛው ራሳችን ሕክምናውን ጀምረን የማጠናቀቅ ጉዳይ አይደለም" ይላሉ አቶ አብዲ። "ወደ ማከም ሳይሆን ወደ ምክር እናዘነብላለን። ያልገቡን ነገሮች ላይም አንዳፈርም፤ ሐኪም እንደመሆናችን ከታማሚው የተሻለ ስለ በሽታው ስለሚገባን እገዛ ነው የምንሰጠው እንጂ ከዚያ ያለፈ ነገር አንሰራም" ይላሉ። ለጥንቃቄ ሲባልም ታካሚ የስልክ ጥሪ ሲያደርግ እያንዳንዷ የድምጽ ልውውጥ ተቀድታ ትቀመጣለች፤ ይህም ተጣያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ነው ሲሉ በጤና ጉዳይ የጥንቃቄና የተጠያቂነት ርቀቱን ያስረዳሉ። "መታወቅ ያለበት በሽተኛውን ከመረመረው ሐኪም በላይ እኛ እናውቅልሀለን አንልም። ትክክል መስሎ ካልተሰማን ግን ከደዋዩ ጋር በመነጋገር የግል ሐኪሞቻቸው ጋር በመደወል ተጨማሪ መረጃ እንሰበስባለን። ወይም ደግሞ ታማሚው ወደመረመረው ሐኪም በድጋሚ እንዲሄድ እንመክረዋለን። አለበለዚያ ታማሚን የበለጠ ማወዛገብ ነው የሚሆነው።" ከቴሌሜዲስን ወደ ቪዲዮ ሜዲስን የቴሌሜዲሲን ሐሳብ ባደገው ዓለም ከፍ ያለ ደረጃ ደርሶ ቪዲዮሜዲስን ላይ ደርሷል። ከዚያም በላይ የአርቴፊሻል ኢንተለጄንስ [ሰው ሰራሽ ልህቀት] በሕክምና ውስጥ ገብቶ ብዙ ለውጦችን ማየት ተችሏል። በአንዳንድ ብልጹግ አገሮች የሐኪምና ታማሚ በአካል መገናኘት የግድ ወዳለመሆን ደረጃ እየደረሰ ነው። ለመሆኑ የዮኮ ቴሌሜዲስን ምን አስበዋል? ሐኪምና በሽተኛ ሌላና ሌላ ቦታ ሆነውም ሕክምናን ማሳካት ይቻላል ብለው የሚያምኑት አቶ አብዲ፣ በቴሌኮም አለመስፋፋት ምክንያት ይህ በእኛ አገር በቅርብ ጊዜ የሚተገበር እንዳልሆነ ያብራራሉ። ሆኖም ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ሲሄዱ አገልግሎቱን ወደ ገጠር የማስፋፋት ሐሳብ አላቸው። "የቴሌኮም ኢንተርኔት አገልግሎት ወደ ገጠር እየተስፋፋ ሲሄድ ጤና ተቋማት እንደልብ በማይዳረስባቸው የአገራችን ክፍሎች ይህን የቴሌሜዲስን አገልግሎት ማስተዋወቅ እናስባለን። ቨርቹዋሊ ሰዎችን ማከም፣ ሐኪም ቤቶቻችንን የሚጨናነቁበትን ሁኔታ መቀነስ የረዥም ጊዜ እቅዳችን ነው" ይላሉ።
news-54567463
https://www.bbc.com/amharic/news-54567463
አካል ጉዳተኛ መሆኗ ሌሎችን ከመርዳት ያላገዳት ሜሮን ተስፋይ
ሜሮን ተስፋይ ከልጅነቷ ጀምሮ የነርቭ ችግር ገጥሟት ሙሉ የሰውነት ክፍሏን ማዘዝ አትችልም።
በዚህ ሁኔታ ሆና እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ድረስ ትምህርቷን ተከታትላላች። ሌሎችን ማገዝ ዓላማዋ ያደረገችው ሜሮን፣ አይነ ስውራን ሆቴል ቤት ሂደው ለመስተናገድ እንዳይቸገሩ የሚያግዝ የብሬል የምግብ ዝርዝር ማውጫ (ሜኑ) አዘጋጅታለች። የኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ የሚገጠም ብሬልም ሰርታ አይነ ስውራንን እንዲያግዝ አድርጋለች።
news-44765100
https://www.bbc.com/amharic/news-44765100
ልዩ መሰናዶ ካለሁበት 39፡ ሎስ አንጀለስ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ 100 ቀናት ውስጥና በፊት
ብርሃኑ አስፋው እባላለሁ ኑሮዬን በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሎስ አንጀለስ ከተማ ካደረኩኝ ዘመናት ተቆጠሩ።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን እንዳጠናቀኩኝ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን እንድቀጥል ስፖንሰር ወይም የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግልኝ አግኝቼ ነበር ወደአሜሪካ የመጣሁት። በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች እየተዘዋወርኩ የማየትና የመኖር እድል ቢኖረኝም እንደ ሎስ አንጀለስ የሚሆንልኝ ግን አላገኘሁም። ስለዚህ ሥራ ፈልጌ ከተረጋጋሁ በኋላ ቤተሰቤን አምጥቼ ኑሮዬን ሎስ አንጀለስ አደረኩ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት ካሊፎርኒያ ውስጥ ወደ 200 ከተማዎች አሉ፤ ከእነርሱም መካከል ብዙዎቹ አንዳንድ የኢትዮጵያን ገጽታዎች ያስታውሱኛል። ከአየሩ ፀባይ እስከ መልከዓ ምድሩ፤ የካሊፎርኒያ ተራራማነትና ሌሎችም ነገሮች ወደ ኢትዮጵያ ይመልሱኛል። የሳን በርናርዲኖ ካውንቲ አንዳንድ ቦታዎች የድሬዳዋ ከተማን በጣም ያስተውሰኛል። ክረምት ላይም እንደ ሃገር ቤት ዝናባማ አይሁን እንጂ ብዙ ነገሮች ይመሳሰሉብኛል። እንደዚያም ሆኖ ግን በተለይ ድሮ ወደ ሎስ አንጀለስ አየር ማረፊያ አካባቢ በማቀናበት ጊዜ ኢትዮጵያ ሳለሁ በመርካቶ ዙሪያ እመላለስ ስለነበር እዚያው የተመለስኩ ያህል ይሰማኝ ነበር። ከሁሉም በላይ ግን 'ሊትል ኢትዮጵያ' ማለትም 'ትንሿ ኢትዮጵያ' የተሰኘው መንገድ ምን ጊዜም በቅፅበት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ የመጣሁ ያህል እንዲሰማኝ ያደርጋል። መሶብ የተሰኘው የብርሃኑ ምግብ ቤት፣ በ'ሊትል ኢትዮጵያ' ኢትዮጵያን በትንሹ በሎስ አንጀለስ የታክሲ ሹፌሩ፣ ዶክተሩ፣ ኢንጂነሩ እንዲሁም የምግብ ቤት ባለቤቱና አስተናጋጁ ሁሉ በሎስ አንጀለስ እቅፍ ውስጥ ይገኛል። በሎስ አንጀለስ 'ሊትል ኢትዮጵያ' የተሰኘው መንገድ የተሰየመው እ.አ.አ በ2000 ዓ.ም ነው። እዚህ ሎስ አንጀለስ ኢትዮጵያውያን መልከ ብዙ መሆናችን ብቻ ሳይሆን ተራርቀን ስለምንኖር ማህበራዊ ኑሮዋችን ዋሺንግተንና ኒው ዮርክ እንዳሉት አይደለም። ድምፃችን በሃገራችን የፖለቲካ ጥያቄዎች ላይ እምብዛም አይሰማምም ነበር። በአንድ ወቅት ለአንድ ግለሰብ እርዳታ ለማበርከት አራት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተሰባስበው አብሬያቸው እንድሳተፍ ጠየቁኝ። ከዚያ በኋላ የተሳትፏችን መልክ ተቀየረ። በጊዜው ዛሬ 'ሊትል ኢትዮጵያ' በተባለችው ሰፈር ውስጥ ነባር ባህላዊ ምግብ ቤቶችም ይገኙበት ስለነበር፤ መንገዱን በስማችን ለማስጠራት ቅስቀሳ አድርገን ፈቃድ ልናገኝ ችለናል። ይህን ካቋቋምን በኋላ በዚያው ዓመት እኔም መንገዱ አቅራቢያ የነበረች አንድ ምግብ ቤት ከወንድሜ ጋር ከገዛን በኋላ ሥራ ጀመርን፤ ይኸው አሁን 18 ዓመት ሆኖናል። በተጨማሪም የ'ሊትል ኢትዮጵያ የንግድ ማህበር' ፕሬዝዳንት ሆኜ ለ15 ዓመታትም አገልግያለሁ። የመንገዱ ስያሜ ከተፈቀደልን ወዲህ የባህላዊ ሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮች፣ ባህላዊ ምግብ ቤቶችና የልብስ መደብሮች ተከፍተውበታል። በመንገዱ ጫፍና ጫፍም ላይ በሰማያዊ ታፔላ 'ሊትል ኢትዮጵያ' የሚልና የሐረር ጀጎል፣ የቡና፣ የጎንደር ቤተ መንግሥትና አክሱምን የሚያንፀባርቁም ባነሮች ተሰቅለውልናል። በአሜሪካ ከኢትዮጵያ ውጭ መንገድ የተሰየመለት ሌላ አፍሪካዊ ሃገር ስለሌለና እኛ ብቸኛዎቹ በመሆናችን እኮራለሁ። ከዚያም በላይ በጣም እንድኮራ የሚያደርገኝ ግን በምግብ ቤቴ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የተለያየ ሃገር ዜጎችን ማስተናገድ መቻሌ ነው። ኤርትራውያን በተለይ በጣም ደንበኞቼ ናቸው። ለጥምቀት፣ ለምርቃት፣ ለመልስና ለመሳሰሉት ማህበራዊ ስብሰባዎች የምግብ ቤቴን አዳራሽ በተደጋጋሚ ይከራያሉ። በምግብም ሆነ በባህላችን በጣም ስለምንቀራረብ 'መሶብ' ለእነርሱም ቤታቸው ነው። ይህንን መንገድ በይበልጥ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ማንኛውም ከአፍሪካ ጋር የተገናኘ ነገር ሲከሰት ዋና ቦታ መሆኑ ነው። ለምሳሌ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሆኑት ትራምፕ በተመረጡበት ጊዜ የተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የአፍሪካውያንን አስተያየት ለመቀበል ካሜራዎቻቸውን በ'ሊትል ኢትዮጵያ' ነበር ይዘው የመጡት። ይህም ብቻ አይደለም፤ ከኢትዮጵያ ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ ሰልፍ መውጣት ቢፈለግ እንኳን በዚሁ መንገድ ላይ ነው ሰው የሚሰባሰበው። ለዚህም ነው ለኢትዮጵያውን በተለይ ይህች መንገድ በጣም ትልቅ ቦታ ያላት። መንገዱንም ለአዲስ ዓመት መዝጋት ተፈቅዶልን ድንኳን ጥለን ተሰብስበን ስንደገስ አሁን 16 ዓመታት አስቆጥረናል። ኢትዮጵያውያን በ'ሊትል ኢትዮጵያ' አውራ ጎዳና ተሰብስበው ከክፍፍል ወደ ጥምረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሥልጣን ከተረከቡ ወዲህ በጣም እየገረመኝ የመጣው በሎስ አንጀለስ ያሉ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደም ጎራ እየለዩ ይመገቡባቸው የነበሩ ምግብ ቤቶች የነበረ ሲሆን አሁን ግን መንፈሳቸውና ስሜታቸው የታደሰ ይመስል መከፋፈሉን እንደተዉ ማየቴ ነው። ለምሳሌ አልፎ አለፎ የኤምባሲ ሰዎች በሚጠቀሙበት ምግብ ቤት ውስጥ ለመመገብ ፈቃደኛ ያልሆኑና አቋማቸው ከረር ያለ ሰዎች አይጠፉም ነበር፤ አሁን ግን በዚህች አጭር ጊዜ ውስጥ እንኳን መሻሻል ይታያል። ኢትዮጵያዊያን የጎሪጥ መተያየት ትተን መቀራረብና መፋቀራችንን ሳይ ልቤ በደስታ ይሞላል። ከዚህ ቀደም ገንዘብ ወደ ሃገር ቤት መላክ የለበትም ብለው የሚከራከሩ ሰዎች አሁን በሙሉ ደስታ ወደ ሃገር የመመለስ ሃሳብ ሁሉ እያውጠነጠኑ ሳይ ልቤን ይሞቀዋል። የአንድነት ስሜቱ በይበልጥ የሚጎላው በኢትዮጵያም በካሊፎርኒያም ያለው ስሜት ተመሳሳይ መሆኑ ነው። በዚህ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ጥሩ ጥሩና የሚያስደስቱ ለውጦች እያሳዩን በመሆናቸው በሎስ አንጀለስ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሙሉ በሙሉ የዶ/ር ዐብይ ደጋፊዎች ይሆናሉ ብዬ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ። ከግራ ወደ ቀኝ ፡ ብርሃኑና ወንድሙ ሽልማት ሲረከቡ፣ ብርሃኑና ወንድሙ ሽልማቱን በምግብ ቤታቸው ከመስቀላቸው በፊት፣ ሽልማቱ አዲስና ሎስ አንጀለስ ምንና ምን ናቸው? ከሰብዓዊ መብት ጥበቃ አንፃር ወንጀል እስካልተሠራ ድረስ የማንኛውም ሰው መብት የተጠበቀ በመሆኑ ከሃገር ቤት ለየት ያደርገዋል። በዚያ ላይ ደግሞ አንድ ሰው ሊያገኝ ይገባዋል ተብሎ የሚታሰበውን ነገር በሙሉ ያለምንም ችግር ለሁሉም እኩል ይቀርባሉ፤ በዚህ በዚህ ሎስ አንጀለስ ከኢትዮጵያ ትለያለች። ዛሬ ከአካባቢያችን አልፎ፣ ማህበረሰባችንን ማቆራኘት ከዚያም አልፎ በከተማው እውቅና እስከማግኘት በመድረሴ ይህች ሃገር ለሠራተኛና ለትጉህ ሰው በጎ መሆኗን በሙሉ አፌ መመስከር እችላለሁ። ከእንጀራ ውጪ የሉዊዚያና ጋምቦ የተሰኘውን ከአሜሪካ ደቡብ ግዛቶች አካባቢ የተለመደውን ምግብ በጣም እወደዋለሁ። እንዲሁ ሳስበው የወደድኩት ስለሚያቃጥልና እንደ ወጥ ያለ ስለሆነ ይመስለኛል። ምንም ቢሆን ግን እንደ እንጀራ የሚሆንልኝ ምግብ የለም። የሉዊዚያና ጋምቦ የወደፊት ምኞቴ በጣም ሰፊ ባይሆንም እንኳን ለሃገሬ ሰላምና ተስፋን እመኛለሁ። አሁን ደግሞ ሃገሪቱ የተያያዘችው መንገድ በጣም አስደሳች ነው። ሁሌም እመኘው የነበረው የኢትዮጵያዊው ማህበረሰብ ተጠናክሮና ባህሉንም ሆነ አንድነቱን ይዞ እንዲቀጥል ነው። በተለይ ወጣቱ ከወላጅና ከዘመዱ ጫና ውጪ በእራሱ ተነሳሽነት ወደ ባህሉ ሲመለስ ማየት ሕልሜ ነው። ኢትዮጵያ በየተወሰነ ጊዜ እመላለሳለሁ፤ መሬት ገዝቼም ሥራ ለመጀመር አስቤ ነበር ግን ሳይሳካ ቀርቶ ትቼው የነበረ ቢሆንም አሁን በተለይ ቢቻለኝ ሐዋሳ ላይ ሥራ ብጀምር ደስታዬ ነው። ብዙ ከተማዎችን አይቼ ሳይሆን እስካሁን ካየኋቸው ከተሞች መካከል ሐዋሳ በጣም ስባኝ ነበር። በተለይ የሰዉ ባህሪ፣ ሰው ወዳጅነታቸውና ከተለያየ ብሔርና ማህበረሰብ የመጡ ቢሆኑም በአንድ ላይ መኖራቸውን በጣም ወድጄላቸዋለሁ። ስለዚህ እራሴን በቅፅበት ከሎስ አንጀለስ ኢትዮጵያ ብወስደው ሐዋሳ ሐይቅ ዳር ብገኝ እመኛለሁ። ለክሪስቲን ዮሐንስ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 40: "ካለ ቪዛ ወደ 127 አገራት መጓዝ እችላለሁ" ካለሁበት 41: ከባሌ እስከ ቻድ የተደረገ የነጻነት ተጋድሎ
news-46176377
https://www.bbc.com/amharic/news-46176377
የዓመቱ ሐሰተኛ ዜናዎች በአፍሪካ፡ በኢትዮጵያ ሶማሌዎች ጥልቀት ወዳለው መቃብር እየተወረወሩ ነው መባሉ
በአፍሪካ ውስጥ የሐሰት ዜና መሰራጨት የብሔር ግጭቶችን ማባባስ፣ በመራጮች ዘንድ ግራ መጋባትን በማምጣትና የገንዘብ መዋዠቅን እንዳስከተለ እየተወነጀለ ነው።
ቢቢሲ የሐሰት ዜና በአፍሪካ ምን አይነት ገፅታ አለው በሚለው ጉዳይ ላይ ጥናት ያደረገ ሲሆን በባለፉት 12 ወራት ውስጥም ከፍተኛ ተፅእኖ ማምጣት የቻሉ አምስት ሐሰተኛ ዜናዎችን ተመልክቷል። •አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ •'ሃሰተኛ ዜና '፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት? 1. ናይጀሪዊው የፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ድጋፍ ማግኘቱ ዜናው ምን ነበር? በአውሮፓውያኑ 2019 ዓ.ም ለሚካሄደው የናይጀሪያ ምርጫ ተወዳዳሪ በሆኑት አቲኩ አቡባከር ስም የተከፈተ ሐሰተኛ የትዊተር ገፅ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ማህበር የሆነውን "አሶሼስን ኦፍ ናይጀሪያን ጌይ ሜን" ለድጋፋቸው ምስጋናን ለግሷል። በትዊተር ገፁ የሰፈረው ፅሁፍ እንደሚያመለክተው "አቲኩ አቡባከር" ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡ ቀዳሚ ተግባራቸው በአገሪቱ ውስጥ አከራካሪ የሚባለውን የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ህግን መቀየር ሲሆን፤ ይህ ህግ ሆኖ የፀደቀው በፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን በአውሮፓውያኑ 2014 ዓ.ም ነው። የተመሳሳይ ፆታ ፍቅርን መመስረት በናይጀሪያ 14 ዓመት ያህል እስር የሚያስቀጣ ሲሆን፤ ጋብቻም የተከለከለ ነው። ዜናው ምንን አስከተለ? የሐሰተኛ ዜና የወጣበት የጦማርያን ገፅ በመጀመሪያ ይህ ፅሁፍ የሰፈረው በጥቅምት ወር ላይ ሲሆን፤ ቀጥሎም ሁለት ጦማሪያውያን ይህንኑ ዜና አወጡት። በዚያው አላበቃም ከ12 ቀናት በኋላ በናይጀሪያ ውስት ታዋቂ የሚባሉት ዘ ኔሽንና ቫንጋርድ የተባሉት ጋዜጦችም ዜናውን ባለበት ይዘውት ወጡ። ከዚህም በተጨማሪ "ዳይቨርስ" የተባለ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ድርጅት አቡበከር "ነፃ የሆነ አስተሳሰብ" ያላቸው ተወዳዳሪ ናቸው በማለትም ድጋፋቸውን እንደሚለግሱ ገለፁ። ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ግለሰብ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅርን መብት መደገፋቸው ሐሰተኛ ዜና ጠንቅ ሊፈጥር የሚችል ጉዳይ ነው። በናይጀሪያ ውስጥ የተመሳሳይ ፆታ ፍቅርን በመቃወም የሚታወቁት የእስልምናና የክርስትና እምነት መሪዎች ተከታዮቻቸውን እንዳይመርጡ መልዕክት ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ሐሰተኛ ዜና መሆኑ እንዴት ታወቀ? የትዊተር ገፁ የፖለቲከኛው አቲኩ አቡባከር ሳይሆን፤ የፖለቲከኛው ትክክለኛ የትዊተር አካውንታቸው (ገፅ) በትዊተር የተረጋጋጠ ሰማያዊ ምልክት እንዳለው ተረጋገጠ። ከዚሀም በተጨማሪ በትዊተር ገፁ፣ በጦማሪዎቹ ፅሁፍም ሆነ በጋዜጦቹ ዜና ላይ የተጠቀሰው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪው ድርጅትም ስለመኖሩ ምንም አይነት ማረጋገጫ የለም። ድርጅቱ በናይጀሪያ ህግ መሰረት ህጋዊ ሆኖ መመዝገብ አይችልም። ድርጅቱም ሆነ የድርጅቱ ቃል አቀባይ ተብሎ የሰፈረው ስፒንኪ ቪክተር ሊ የመጀመሪያ ፀሁፋቸውን በትዊተር ካሰፈሩበት ከጥቅምት ወር በፊት በኢንተርኔት ላይ ስማቸው ተጠቅሶ እንደማያውቅም የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ሲያጣራ ደርሶበታል። 2. የታዋቂዋ ኬንያዊ ጋዜጠኛ የውሸት ምስጋና ዜናው ምን ነበር? የሲኤንኤን የቢዝነስ ፕሮግራም አቅራቢ ሪቻርድ ኩዌስት በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ጥቅምት ወር ላይ ለቲቪ ፕሮግራም ቀረፃ ላይ ነበር። ይህንን ተከትሎም የቀድሞ ዜና አንባቢና ጋዜጠኛ ጁሊ ጊቹሩ በትዊተር ገጿ ሪቻርድ ኩዌስት የኬንያ ቆይታው እንዳስደሰተው ገልፃ ፃፈች። " የኬንያን አቀባባል የሚወዳደረው የለም። ይሄው በቀጭኔዎች ተከብቤ ቁርስ እየበላሁ ነው። በአለም ባንክ በአፍሪካ ምርጥ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከተባለች ኃገር ይሄንን አይነት አቀባበል ማግኘቴ የሚገርም አይደለም። በእውነቱ ኬንያ ተአምራዊ ናት" የሚል ፅሁፍም እሱን ጠቅሳ በተጨማሪ አሰፈረች። ሐሰተኛው ጥቅስ ዜናው ምን አስከተለ? ጁሊ በትዊተር ከሚሊዮን በላይ እንዲሁም በኢንስታግራም ከ600 ሺ በላይ ተከታዮች ያሏት ሲሆን፤ ዜናው በወጣ በደቂቃዎች ውስጥ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ግለሰቦች ዜናውን አጋሩት። በሚዲያ ኢንዱስትሪው ታዋቂ ከመሆኗ አንፃር እንዲህ አይነት ሐሰተኛ ዜና ማውጣቷ ብዙዎች አፊዘውባታል። ሐሰተኛ መሆኑ እንዴት ታወቀ? የሲኤንኤኑ ጋዜጠኛ ትዊቷን ተመልክቶ እንዲህ አይነት መግለጫ እንዳልሰጠ አስታወቀ። በፃፈችውም ፅሁፍ ላይ ተመርኩዞ ትክክል እንዳልሆነ ምላሽ ሰጥቷታል። በምላሹም ጁሊ ጊቹሩ ይቅርታ የጠየቀች ሲሆን የመጨረሻ ፅሁፏንም አጥፍታዋለች። 3. በኢትዮጵያ ሶማሌዎች ጥልቀት ወዳለው መቃብር እየተወረወሩ ነው ዜናው ምን ነበር? በሐምሌ ወር በአሜሪካ ተቀማጭነቱን ያደረገው ኢሳት ብሄራቸው ኦሮሞ የሆኑ ግለሰቦች ሶማሌዎችን ጥልቀት ወዳለው መቃብር እየወረወሩ እንደሆነ የሚዘግብ ቪዲዮ ይዞ ወጣ። ቪዲዮው ባለፈው አመት በሁለቱ ህዝቦች አስከፊ ግጭት ባጋተመበት የኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የተቀረፀ መሆኑን ተገልጾ ነበር። ቪዲዮው ሰዎች ወደ ጥልቅ ጉድጓሱ ሲወረወሩ ያሳያል ዜናው ምን አስከተለ? የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ክፍል እንደዘገበው ይህ ቪዲዮ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨቱ በጂቡቲና በሶማሊያ የሚኖሩ ኦሮሞዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል። በጂቡቲ ነዋሪ የሆኑ ኦሮሞዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቪዲዮ ምክንያት ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን፤ የንግድ ቦታቸውም ተዘርፏል። ሐሰተኛ መሆኑ እንዴት ታወቀ? ይህ ቪዲዮ በሰኔ ወርም በካሜሮን ፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ ተገንጣዮችም መካከል የተከሰተ ግጭት እንደሆነም ተደርጎ ብዙዎች አጋርተውታል። በኢሳት የቀረበው ቪዲዮ የኦሮሞ ወጣቶችን ድምፅ ከነበረው ትክክለኛ ድምፅ በላይ በማስገባት የቀረበ ነው። ኢሳት ቪዲዮው ትክክለኛ አለመሆኑን ሲያውቅ ወዲያውኑ ቪዲዮውን ከገጹ ላይ በማንሳት በዩቲዩብ ገጹ በኩል በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። ነገር ግን ኢሳት ቴሌቪዥን ቪዲዮውን ስለማቀናበሩና ቪዲዮው ሃሰተኛ መሆኑን እያወቀ ስለማሰራጨቱ የሚያመለክት ነገር የለም። ማስተካከያ ዲሴምበር 23፡ ይህ ጽሁፍ የኢሳት ቴሌቪዥን ቪዲዮውን አለማቀናበሩን ወይም ቪዲዮው ሃሰተኛ መሆኑን እያወቀ እንዳላሰራጨ ግልጽ ለማድረግ መስተካከያ ተደርጎበታል። 4. የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ መልቀቅ ዜናው ምን ነበር? በየካቲት ወር የደቡብ አፍሪካው ኤስኤቢሲ ጋዜጠኛ በወቅቱ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጃኮብ ዙማ ስልጣን ለመልቀቅ መስማማታቸውን ዘገበ። ባለስልጣናትን እንደምንጭ በመጠቀም ሼቦ ኢካኔንግ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ሰበር ዜና በሚል አስተላለፈው። በወቅቱም የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አባላት በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ እጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን ስብሰባ ላይ ነበሩ። ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጠኛም ይህንኑ ዜና በትዊተር ገፁ አጋራው። ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በተለያዩ የሙስና ቅሌቶች ከፍተኛ ግፊት እየተደረገባቸው የነበረ ሲሆን፤ ከፓርቲያቸውም በተደጋጋሚ እንዲወርዱ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ሃገሪቷም ፕሬዚዳንቱ ሊለቁ ይችላል የሚለውን ዜና በጉጉት እየጠበቁት ነበር። ዜናው ምን አስከተለ? ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ለቀቁ የሚለውን ዜና ተከትሎ በአንድ ፐርሰንት ጨምሮ የነበረው የደቡብ አፍሪካ ራንድ፤ ቃል አቀባዩ የኤስኤቢሲ ሪፖርትን ውሸት ነው ብለው ማጣጣላቸውን ተከትሎ ወደነበረበት ተመልሷል። ዜናው ሐሰት ነበር? የፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ቃል አቀባይ "ሐሰተኛ ዜና ነው" በሚል ሪፖርቱን አጣጣለው። ነገር ግን ከሶስት ቀናት በኋላ ጃኮብ ዙማ ከስልጣን ለቀቁ። 5. የታንዛንያው መሪ ሴተኛ አዳሪነትን ለማስቀረት ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን መደገፋቸው ዜናው ምን ነበር? የታንዛንያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሴተኛ አዳሪነትን ለማስቀረት ወንዶች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንዳለባቸው ተናግረዋል የሚል ዜና በከፍተኛ መንገድ ተሰራጨ። በፅሁፉ እንደተጠቀሰው 14000 ወንዶች በተገኙበት ኮንፍረንስ ፕሬዚዳንቱ ከ70 ሚሊዮን ታንዛንያውያን መካከል 40 ሚሊዮኖቹ ሴቶች እንደሆኑና 30 ሚሊዮኖች ወንዶች እንደሆኑ ገልፀዋል የተባለ ሲሆን ፤ በወንዶች እጥረት ምክንያት ሴተኛ አዳሪነትና ዝሙት እየጨመረ መምጣቱን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል ብሎ ፅሁፉ ጠቅሷል። ዜናው ምን አስከተለ? በእንግሊዝኛ ቋንቋ በመጀመሪያ በዛምቢያ ኦብዘርቨር በየካቲት ወር የታተመው ዜና ምንም አልፈጠረም ነበር። ነገር ግን በታንዛንያ ብሄራዊ ቋንቋ ስዋሂሊ በኒፓሽኦንላይን ድረገፅ የታተመው ፅሁፍ ከፍተኛ ተነባቢነትን አገኘ። ድረ ገፁንም ተከትሎ በታዋቂው ጃማይ ፎረምስ ድረገፅ መታተሙን ተከትሎ በኬንያ፣ ዛምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካና ጋና ድረ ገፆች ለመታተም በቃ። ሐሰተኛ መሆኑ እንዴት ታወቀ? የታንዛንያ የመንግሥት ቃል አቀባይ በስዋሂሊ ቋንቋ ፕሬዚዳንቱ እንዲህ አይነት አስተያየት እንደማይሰጡና ሰዎችም ቸላ ሊሉት እንደሚገባ በማውገዝ በትዊተር ገፁ አስቀመጠ። የቢቢሲ ስዋሂሊም እውነተኛነቱን ለማረጋገጥ ባደረገው ምርምር ትክክለኛ አለመሆኑን አረጋግጧል። በሐሰተኛው ዜና ፕሬዚዳንቱ የታንዛንያን የሕዝብ ቁጥር 70 ሚሊዮን እንደሆነና የሴቶች ቁጥር ከወንዶች በአስር ሚሊዮን እንደሚደርስ አስቀምጧል። ነገር ግን በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው የህዝብ ቁጥር ግምት መሰረት የታንዛንያ ህዝብ ቁጥር ከ60 ሚሊዮን በታች እንደሆነና በፆታዎቹም መካከል ይህ ነው የሚባል ልዩነትም እንደሌለ አስቀምጧል። ይህ ሐሰተኛ ዜና የወጣበት ድረ ገፅም ለብዙ ታንዛንያውያን ከታዋቂው የታንዛንያ ጋዜጣ ኒፓሼ ጋር እንደሚመሳሰልም የቢቢሲ ስዋሂሊ ዘገባ ያሳያል። ነገር ግን ሐሰተኛ ዜና የወጣበት ድረ ገፅና ጋዜጣው ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ታውቋል።
news-56966869
https://www.bbc.com/amharic/news-56966869
ነጻ ፕሬስ፡ ለሴት ጋዜጠኞች ተራራ ሆኖ የቀጠለው የኢትዮጵያ ሚዲያ
የኢትዮጵያን ሚዲያ የተቀላቀለችው ከሰባት አመት በፊት ነው። መአዛ ሃደራ ትባላለች። አራት አመታትን ካሳለፈችበት የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር የተለያየችበት አጋጣሚ በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ለሴቶች ያለውን ውጣ ውረድ ያስረዳል።
የስራ መልቀቂያዋን ከማስገባቷ ከወራት በፊት ባላወቀችው ምክንያት የሴቶችን ጉዳይ የሚመለከቱ ዘገባ እንዳትሰራ መደረግ መጀመሩን ታስታውሳለች። አዲስ የተመደበው አለቃዋ በተደጋጋሚ ሴቶችን የሚመለከት ጉዳይ ሲሆን "ስሜ ከተላከ ወዲያ በሌሎች ወንድ ዘጋቢዎች ይተካኛል" ትላለች። በዚሁ ምክንያት አለቃዋን «ለምን» ያለችው መአዛ "ፌሚኒስት ሆነሽ ጋዜጠኛ መሆን አትችይም" የሚል ምክንያት ነበር የተሰጣት። ነገሮችን በፆታ እኩልነት አይን ማየቷ እና ሁሌም ይህንን ለመጠየቅ ወደ ኋላ አለማለቷ ለአዲሱ አለቃዋ ምቾት እንዳልሰጠው ተረድታለች። ይህ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም የምትለው መአዛ በወቅቱ የዘጠኝ ወር ልጅ እናትም ነበረች። ልጇን ለማስከተብ በሆስፒታል ውስጥ እያለች፣ ለአለቃዋ ልጇን አስከትባ ወደ ስራ እንደምትመለስ ብትነግረውም መልሱ "መቅረት አትችይም" የሚል ሆኖባታል። "የሶስት አመት ፈቃድ አልወሰድኩም ነበር። በዛ ላይ በቤቱ ሕግ ልጅን ለማስከተብ ፈቃድ መጠየቅ ይቻላል" ስትል መአዛ ታስረዳለች። ስራዋን ለመተው የመጨረሻ ምክንያት የሆነው ልጇ በመታመሟ የሁለት ቀን እረፍት መጠየቋ እና በአመታት ከምትበልጣት ባልደረባዋ እጅግ ያነሰ የደመወዝ ጭማሪ ማግኘቷ ነበር። ይህም ከብቃት ጋር የተያያዘ ያለመሆኑ አስቆጥቷታል። መዓዛ ሃድራ "መልኳ ላይ ማተኮር" "ወንድ ባልደረቦቼ እኮ ሶስት ልጅ ወልደው አሁንም ይሰራሉ" ስትል መአዛ በጾታ የሚደረጉ ልዩነቶችን ታስረዳለች። ወደ ስክሪን የሚቀርቡ ሴት ጋዜጠኞች እድሜ ብሎም የሰውነት ሁኔታ እንጂ የሚያቀርቡት ይዘት ላይ ትኩረት አለመደረጉ ያበሳጫት ነበር። "ሴት ጋዜጠኛ የፃፈችውን ዜና የሚያስተካክልላት ሳይሆን ሜካፗ እና ልብሷ ላይ ሰአታት የሚፈጅ ሰው ነው ያለው። ጠዋት ለኤዲቶሪያል ስንሰበሰብ የሴቷ አንባቢ አለባበስ እና አቀራብ ላይ እንጂ የወንዱ ሱፍ ላይ አናተኩረም" ትላለች። መአዛ አክላም ሜካፕ መቀባት የማትፈልግ ጋዜጠኛ በቴሌቪዥን ቀርባ መታየት እንደማትችል በምሳሌነት ራሷን በማንሳት ታብራራለች። ምንም እንኳን ልምድ ቢኖራትም ሜካፕ እንዲሁም ቀሚስ ለማድረግ ባለመፈለጓ ወደ ፊት መውጣት የማይታሰብ ነበር። "አብዛኛዋ ሴት አቅራቢ ቀረፃ አልቆ ሂውማን ሄሯን አውልቃ እስክትጥል እና ሜካፗ እስከምታስለቀቅ ነው የምትቸኩለው። ወንዶቹ ግን ለቀረፃ 10 ደቂቃ ሲቀር ነው የሚመጡት። ትኩረታቸውም የሚያቀርቡት ነገር ላይ ነው" መአዛ ታነፃፅራለች። "የደመወዝ ጭማሪ ሲደረግ እኔ አራት አመት የምበልጣት ልጅ የተጨመረላት ጭማሪ ከኔ የአምስት ሺህ ብር ይበልጥ ነበር" ትላለች። "ለምን ብዬ ስጠይቅ፣ 'እርሷ በቴሌቪዥን ስለምትቀርብ ያልሆነ ቦታ እንድትውል እና የማይሆን ልብስ ለብሳ እንድትታይ አንፈልገም' የሚል ምክንያት ነበር የተሰጠኝ። በስራ ልዩነት ቢሆን ደስ ነበር የሚለኝ። የሰጡኝ ምክንያት ግን በአጠቃላይ ለሁሉም ሴት አግባብ ያልሆነ ነበር" ትላለች መአዛ። ፎዮ-አይ ኤም ኤስ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሀን የሚታየውን የስርአተ-ፆታ ምጣኔ አመላካች በሚል ርዕስ ካስጠናው ጥናት ላይ የተወሰደ ሴት የሚዲያ አመራሮች ፎዮ አይኤም ኤስ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሀን የሚታየውን የስርአተ-ፆታ ምጣኔ አመላካች በሚል ርዕስ አስጠንቶ ባለፈው ወር የታተመው ወረቀት ሰባት የመገናኛ ብዙሃንን መርጦ የሴት አመራሮችን ጉዳይ ፈትሿል። ይህ ጥናት የሴቶችን ተሳትፎ የኤዲቶሪያል ውሳኔ ሰጪ አመራሮች እና መደበኛ አመራሮች ሲል ለሁለት ከፍሎ ተመልክቶታል። በጥናቱ ብዙ ሴት ሰራተኞች አሉት የተባለው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ካሉት 25 አመራሮች አንዷ ብቻ ሴት ናት። የኤዲቶሪያል ውሳኔ ከሚሰጡ ሃለፊዎች ደግሞ 40 በመቶው ሴቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ትልቁ ቀጣሪ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ካሉት 64 አመራሮች 13ቱ ብቻ ሴቶች ናቸው። እንዲሁም የኤዲቶሪያል ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያሉ ሴቶች 16.6 በመቶው ብቻ ናቸው። ይህ ጥናት እንደሚያሳያው በብሮድካስት የመገናኛ ብዙሃን ከህትመት የተሻለ በርካታ ሴት ጋዜጠኞች አሏቸው። ለዚህም የህትመት መገናኛ ብዙሃን ቁጥራቸው እየቀነሰ መምጣቱ እንዳለ ሆኖ ዘርፉ ሴት ጋዜጠኞችን ማቆየት አለመቻሉ ሌላው ነው። አንድ የህትመት ሚዲያን በመምራት ከአራት አመት በላይ ያገለገለች እና በቅርቡ ፆታን መሰረት ባደረገ ጥቃት ምክንያት ስራዋን የለቀቀችው ፋሲካ ታደሰ መገናኛ ብዙሃን ለምን ጥቂት ሴት አመራሮች እንዳሏቸው ታስረዳለች። ስምንት አመታት በጋዜጠኝነት ያሳለፈችው ፋሲካ ስለራሷ አጋጣሚ ከመናገሯ በፊት ሴት የሚዲያ መሪዎች ከወንዶች በተለየ በየዕለቱ የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች ታስረዳች። "አንድም ቀን ሴት አለቃ ትኖረኛልች ብሎ አስቦ ከማያውቅ ሰው ጋር መጋፈጥን ይጠይቃል" ትላለች። "ብዙ ወንዶች ባደጉበት ማህበረሰብ እና ቤተሰብ የወንድ የበለይነት የተለመደ ስለሆነ የሴቶችን መሪነት አምኖ መቀበል ይከብዳቸዋል። ስራቸውን ስትተቺ ወይም ትዕዛዝ ሲሰጣቸው 'ንቃኝ ነው፤ ማን ስለሆነች ነው' ማለቱ ይቀናቸዋል" ስትል ፋሲካ ለቢቢሲ አስረድታለች። ከወራት በፊት ከወንድ የስራ ባልደረባዋ በይፋ የተወረወሩ በቃላት ጥቃቶች ምክንያት ስራዋን ጥላ እንደወጣች ትናገራለች። ከዚህ ቀደም ብሎም ተመሳሳይ ቃላትን ቢወረውርም ስሜታዊ ሆኖ ይሆናል ብላ ማለፏን ትገልፃለች ፋሲካ። " አለቆቼን ጨምሮ ሁሉም ባልደረቦቼ ባሉበት ጾተኝነት የተጫናቸው መልዕክቶች የሆነ መልክት ላከ። ይህንን መልክት ለወንድ ባልደረባው ቢሆን በድፍረት እንደማይልከው አውቃለሁ" ትላለች። በጋዜጣው ከፍተኛ የሃላፊነት ደረጃ ላይ ብትገኝም " ነገሩን ያለልክ አጋነንሽው" ከመባል ባለፈ አዳማጭ ማጣቷን ትናገራች። በዚህ ምክንያት ስራዋን ለመልቀቅ መወሰኗን ብሎም ድርጊቱን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ማሰቧን አስታወቀች። በዚህ ወቅት ነበር ድርጅቱ " የስራ ቦታን የሚመጥን ቋንቋ አልተጠቀመም፤ ከዛ ውጪ ሌላ ችግር አላየንበትም" በሚል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የፃፈው። በቅድሚያ በዚህ ጉዳይ ላይ ምርመራ ተደርጎ መቀጣትም ካለበት መቅጣት ብሎም ይቅርታ መጠየቅ ካለበት መጠየቅ እንጂ ይህ አካሄድ ትክክል አይደለም በሚል ተሟግታለች ፋሲካ። " ብዙ ሰው ይህ በሕግ የሚያስጠይቅ ጥፋት መሆኑን አያውቅም። የአሰሪ ሰራተኛ ሕጉ እኮ ይህንን በግልፅ ደንግጓል። ሃላፊዎች ፆታን፣ ሃይማኖትን እና ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ ምላሽ ካልሰጡ በሕጉ ይጠየቃሉ። ይህንን የሚመጥን እርምጃ ያለመውሰዳቸው ከኔ ባለፈ ለሌላውም ሰው የሚያስተላልፈው መልክት ያሳስበኛል። ይህ ኒውስ ሩም ለኔ ስለማይሆን ጥዬ ወጥቻሁ" ትለላች ፋሲካ። የፕሬስ ነፃነትን ከሴት ጋዜጠኞች መብት እና ደህንነት ጋር ምን አገናኘው? ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ሲፒጄ የሰሃራ በታች ተወካይ ሙቱኪ ሙሞ እንደሚሉት ሴት ሰራተኞች ብሎም ሃላፊዎች የሌሉት ተቋም የሴትን እይታ ማጣቱ ችግሩን የፕሬስ ነፃነት ችግር ያደርገዋል ሲሉ ይሞግታሉ። በተለይም በአፍሪካ ሴት ጋዜጠኞች ከወንድ የስራ ባልደረቦቻው ጋር ተመሳሳይ ፈተናዎችን ይጋራሉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሴት በመሆናቸው ብቻ ተጨማሪ ፈተናዎች ይጋፈጣሉ። ይህ በሞያው ውስጥ ለመቆየት አዳጋች ያደርግባቸዋል ይላሉ። " በዩጋንዳ የተቃዋሚ ፓርቲ የጠራውን መግለጫ ለመዘገብ የተሰበሰቡ ጋዜጠኞች ላይ የደረሰው ጥቃት ትዝ ይለኛል። ፖሊስ ወንድ ጋዜጠኞችን ሲደበድብ ሴቷም እኩል የመደብደብ እና የመታሰር አደጋ ነበር የተጋረጠባት። ነገር ግን ማሕህበረሰቡ ሴቶች ሊሰሩት ይገባል ብሎ ከሚጠብቃቸው ስራዎች ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ችግሮችን ትጋፈጣለች" ሲሉ ሙቱኪ ያስረዳሉ። በዚሁ ክስተት ላይ የነበረች ሴት ጋዜጠኛ ባለቤቷ " ይህንን ስራ ወይም እኔን ምረጪ" እንዳላት ማንበባቸውንም ያክላሉ። ሴት ጋዜጠኞች ከአለቆቻቸው፣ ከማህበረሰቡ፣ ከስራ ባልደረቦቻው የሚያጋጥማቸውን ችግር ሽሽት ስራቸውን ሲተዉ የሚወዱትን ስራ መስራት ባለመቻላቸው በቀዳሚነት የሚጎዱት ጋዜጠኞቹ ራሳቸው ናቸው ይላሉ። ነገር ግን አንድ የመገናኛ ብዙሃን የሴቶችን እይታ ያጣ ስራ መስራቱ ትልቅ ጉዳት ሲሆን ማህበረሰቡም የሚያገኘው የመረጃ እይታ ብዝሃነት የሌለው መሆኑ ችግሩን ከፕሬስ ነፃነት ጋር ያያይዘዋል ይላሉ። በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶችን ዋቢ የሚያደርጉት ተወካይዋ ሴት ጋዜጠኞች ከወንድ ጋዜጠኞች ጋር ሲነፃፀር የበለጠ ለዲጂታል ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸውን ያነሳሉ። "በእነዚህ የስነ ልቦና ጥቃቶች ምክንያት ሴት ጋዜጠኞች ራሳቸውን ሳንሱር ማድረግ ይጀምራሉ። ይህም በቀጥታ የፕሬስ ነፃነት ላይ ጫና እያሳደረ ነው ማለት ነው" በማለት ለቢቢሲ አስረድተዋል። ተቋማቸው ለጋዜጠኞች መብት የሚከራከረው ለማህበረሰቡ መብትም ጭምር እንደሆነ የሚገልፁት ሙቱኪ የመገናኛ ብዙሃን በሴት ጋዜጠኞች መመራት በተዘዋዋሪ ከፕሬስ ነፃነት ጋር ይገናኛል ይላሉ። " አንድ ተቋም ሃብቱን የት ላይ ማፍሰስ እንዳለበት፣ ለየትኛው የምርመራ ፕሮጀክት ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት እና የፊት ገፅ ዜናው ምን ይሁን የሚለውን የሚወስኑት ሃላፊዎቹ ናቸው። ሴት ሃላፊ ከሌለው የሴቶችን እይታ ያጣ ውሳኔ ስለሚወስን ይህ የፕሬስ ነፃነት ላይ የራሱን ጫና ያመጣል" ይላሉ። አክለውም ሴቶች አንድ አይነት አመለካከት ያላቸው ተመሳሳይ ቡድን እንደሆኑ የማሰብ ልምድ አግባብ አይደለም ሲሉም ያስረዳሉ። ይልቁንም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚም ሆኑ ማህበራዊ ዘገባዎች በአጠቃላይ የሴትን እይታን እንዲያካትቱ ማስቻል ቁልፍ ነው። ይህም ተመልካቾች ወንዶች ብቻ ባለመሆናቸው እና የማህበረሰቡንም እይታ አንድ ወጥ እንዳይሆን ያደርገዋል ብለዋል። መፍትሄው ምንድን ነው? ያጋጠማት ፈተና አይኗን እንደከፈተላት የምትናገረው መአዛ አሁን ላይ በራሷ የዩትዩብ ቻናል በተለያዩ ሞያ ያሉ ሴቶችን በመጋበዝ ለወጣት ሴቶች ምክር የሚሰጡበትን ፕሮግራም ታቀርባለች። መፍትሄው የሴት ጋዜጠኞች ማህበር ባይጠናከር እንኳን እርስ በእርስ መረዳዳት መሆኑን አጽንኦት ትሰጠዋለች። ሴቶች በእጃቸው ሚዲያን ይዘው ሲጨቆኑ ዝም ማለት እንደሌለባቸውም ትገልፃለች። ቀድመው ወደ ሞያው የገቡ ሴት ጋዜጠኞች ለአዳዲሶቹ ስራዬ ብለው የማለማመድ ስራ ይስሩ የምትለው መአዛ "ወንዶቹ እኮ ይነጋገራሉ፤ እኛም የእህትማማችነት ስሜት ካላዳበርን ነገም የሚመጡ ልጆች ከዜሮ ይጀምራሉ" ስትል ታሳስባለች። መአዛ "ሴት ጋዜጠኛ ከሰው ከተግባባች፣ ወጥታ ከተዝናናች እና የምትፈልገውን ስታደርግ ከታየት ይቺ ከሁሉም ጋር ናት ትባላለች። ከዚህ ተቃራኒ ከሆነች ደግሞ መነኩሴ ይሏታል" የምትለው መአዛ " የኔ ምኞት ይሄ እንዲቆም ነው፤ ሴት ጋዜጠኛ ሳይሆን ጋዜጠኛ ብቻ የምትባልበት ግዜ ይናፍቀኛል። ልብሷ፣ መልኳ፣ ፀጉሯ ሳይሆን በምትሰራው ስራ የምትገመትበት ኢንዱስትሪ ሆኖ ማየት ህልሜ ነው" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። " የትም ብሄድ መፍትሄ አላገኝም። አርፌ ብቀመጥ ይሻለኛል" በሚል ችግሮቹ መድበስበሳቸው ብዙ ተቋማትም የሴት ሰራተኞቻቸውን ደህንነት በቸልታ እንዲያዩት ምክንያት መሆኑን የምታሰረዳው ደግሞ ፋሲካ ነች። " የደረሰባቸውን ቢናገሩ ስራቸውን ስለሚያጡ በዝምታ የሚያልፉት ብዙዎች ናቸው" ትላለች። ተቋማት የሴት ጋዜጠኞቻቸውን ደህንነት ከቁብ የማይቆጥሩበት ዋነኛው ምክንያት የሞያ ማህበራት የቅስቀሳ (አድቮኬሲ) ስራ መዳከም መሆኑንም ታብራራለች። የሴት ጋዜጠኞች ማህበርን ጨምሮ ሌሎች የሞያ ማህበራት መብት ሲጣስ አደባባይ ወጥቶ መከራከር አለመቻለቸው ለሚዲያ ሃላፊዎች ማን አለብኝነት አስተዋፅኦ አለውም ትላለች። በተጨማሪም የፌሚኒስት ንቅናቄዎች መስራት የሚገባቸው ቦታዎች ላይ መስራት አለመቻለቸው ሌላው ክፍተት ነው። " አዲስ አበባ ውስጥ በርካታ የፌሚኒስት ንቅናቄዎች አሉ፤ አቅማቸውን የሚጨርሱት በሌላ ቦታ ነው። የስራ ላይ ደህንነት ዋነኛው አተኩረው መስራት ያለባቸው አካባቢ ነው ብዬ አምናለሁ" ትላለች። እነዚህ ማህበራት ችግሮቹ ሳይመጡ ስልጠና መስጠት እና ተቋማት የውስጥ አሰራራቸውን እንዲፈትሹ ማድረግ ይገባል። " በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ፆታዊ ጥቃት እንዳለም እኮ እንሰማለን። እነዚህ ጋዜጠኞች ይህንን ብንናገር ነገ ማንም አይቀጥረንም ብለው ዝም ይላሉ" የምትለው ፋሲካ ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ሩቅ ብንሆን እንኳን መቀነስ አለብን ትላለች። ሙቶኪ በኩላቸው መገናኛ ብዙሃን ከውስጥ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ብቻ ሳይሆን ከውጪም የሚገጥሙ ጥቃቶችን በተመለከተ ከዘገባው በፊት የሴት ጋዜጠኞቹን ደህንነት ማስቀደም አለበት ይላሉ። በመላው አለም በዚህ ላይ የሚሰሩ በርካታ ተቋማት እንዳሉ እና ሴት ጋዜጠኞች እነዚህን ተቋማት በማግኘት አገልግሎቶቹን መጠቀም ይኖርባቸዋል ይላሉ።
49354067
https://www.bbc.com/amharic/49354067
ተስፋዬ ገብረአብና ለትግል ማገዶ ያዋጡ ድርሰቶቹ
ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ስቶክሆልም እያለ ነበር ያነጋገርነው። ስቶክሆልም የተገኘው አዲሱ መጽሐፉን [የቲራቮሎ ዋሻ] ለማስተዋወቅ እንደሆነ ነግሮናል። ይህ አዲሱ ሥራው ዘጠነኛ መጽሐፉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጽሐፍቶቹ የተነሳ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ አንባቢያን ስሙን ያነሱታል፤ ይጥሉታል። እርሱም ይህንን ያውቀዋል። ስንት ዓ መት ሆነህ?
እድሜዬ ማለትህ ነው? አዎ ልክ 50፤ አረጀህ? አዎ እያረጀሁ ነው። ለመሞት 50 ዓመት ብቻ ነው የቀረኝ [ሳቅ] ከሀገር ከወጣህ ትንሽ ረዘም ያለ ጊዜ ስለሆነህ ከአዲስ አበባ፣ ከኢትዮጵያ ምንድን ነው የሚናፍቅህ? የሚናፍቀኝ አንድ ነገር ብቻ ነው። ቢሾፍቱ ሐይቅ፤ ሆራ፣ የአድዓ መልከዓ ምድር፣ ባቦ ጋያና ጋራ ቦሩ የተባሉ በልጅነት የሮጥኩባቸው መስኮች፣ ሐይቆች፤ እነ በልበላ ወንዝ፣ እነዚህን ድጋሚ ማየት ይናፍቀኛል። በአንድ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለህ ተብሎ በሰፊው ሲወራ ነበር፤ ቀረህ? አይ አልቀረሁም። አልሟላ እያለኝ ዘገየ እንጂ አልቀረሁም፤ እመጣለሁ። በመንግሥት ደረጃም ተጋብዣለሁ። ስላልሞላልኝ ነው እስካሁን ያልመጣሁት። ስለዚህ ቲኬትም ቀንም አልቆረጥክም ማለት ነው? ቀንም አልቆረጥኩም፤ ቲኬትም አልቆረጥኩም። ባለፈው ግን ወደ ስቶክሆልም ስሄድ በአዲስ አበባ በኩል አልፌያለሁ። የአማርኛ ሥነጽሑፍን የሚያጠኑ ሰዎች በሥራዎችህ የት ስፍራ ላይ እንዲመድቡህ ነው የምትፈልገው? ከነ በዓሉ . . . እንደዚህ አይነት ነገር አስቤ አላውቅም። መጻፍ እወዳለሁ፤ ያመንኩበትን ነገር እጽፋለሁ። ሰዎች ቢወዱትም ባይወዱትም በፍፁም አስጨንቆኝ አያውቅም። ካልወደዱትና ከወረወሩት የሰዎቹ ፈንታ ነው። እኔ ማድረግ ያለብኝ ጥሪዬን መከተል ብቻ ነው ብዬ ነው የማስበው። አንባቢዎች አልወደድነውም ያሉህ ሥራ አለህ? ሥራዎቼን በጣም የሚወዱትና በጣም የሚጠሉት ነው የሚያጋጥሙኝ። መካከል ላይ የሆኑ አይገጥሙኝም። ምክንያቱ አይገባኝም። የሚወዱት ሰዎች ለምን ወደድነው እንዳሉህ ኋላ ላይ እናወራለን። አልወደድነውም ያሉህ ሰዎች ምክንያታቸው ምንድን ነው? እነርሱ የሚሉኝን ምክንያት አይደለም መናገር ያለብኝ፤ እኔ ለምን እንደጠሉኝ ሳስብ ያልተለመዱ ነገሮችን ስለምፅፍ ነው። ለምሳሌ የቡርቃ ዝምታን በጣም የሚወዱት ሰዎች አሉ፤ በጣምም የሚጠሉት ሰዎች አሉ፤ ለምን ይጠሉታል ብዬ ሳስብ በአማርኛ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ያልተለመዱ ገፀባሕሪያት እዚያ ውስጥ አሉ። በአማርኛ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ የተለመደው ጫላ ወይንም ጫልቱ የሚል ስም ለቤት ሠራተኛና ለዘበኛ ሲሰጥ ነው፤ ኦሮሞ ስም ያለው ዋና [ዐቢይ] ገፀባህሪ ሆኖ አያውቅም። ከመነሻው በዚህ የተከፉ ሰዎች አሉ። የደነገጡ ሰዎች አሉ። የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ሥራዎች የሆኑ ልብወለዶችን ሰብስበህ ተመልከታቸው። ከፊያሜታ በስተቀር [የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ ረዥም ልብወለድ ገፀባህሪ] በጠቅላላ አማራ ናቸው። ወይንም የአማርኛ ስም ያላቸው ናቸው። ይህ ነው የተለመደው። ፀሐፊው ከኦሮሞም ይሁን ከትግራይም ይሁን በተለምዶ የአማርኛ ስም ነው ለገፀባህሪያቱ የሚሰጠው። ይህ የእኔ አጀማማር ወጣ ያለ ስለነበር ከመነሻው ሰዎች እንዳልወደዱት አይቻለሁ። አንተም ጠቀስ አድርገሀዋል። የአማርኛ ሥነጽሑፍ ላይ ስማቸው የገነነ ደራሲያን ከሌላ ብሔር የመጡ ናቸው። አሁን አንተ የምትላቸውን ጉዳዮች በሥራዎቻቸው ውስጥ ለማንሳት ለእነርሱ ለምን የከበደ ይመስልሀል? አልከበዳቸውም፤ ፈሩ። ኢትዮጵያ ላይ ከኦርቶዶክስ ውጪ ሊነግሥ አይችልም። አሁን በምናወራው ጉዳይ ደግሞ በዚህ መልኩ ነበር የሚፃፈው። ለአብነት በዓሉ ግርማን እንውሰድ። ከአድማስ ባሻገር በሚለው ሥራው ላይ ሉሊት ታደሰ የምትባል ገፀባህሪ በዋና ገፀባህሪነት ተስላለች። ይህቺን ገፀባህሪ ከአበራ ወርቁ ጋር አድርጎ ነው የሚያስተዋውቀን። ከአበራ ጋር ተኝተው ሳሉ ለሊት ላይ ለአበራ ስሟን መቀየሯን ትነግራዋለች። ጫልቱ ነው ስሟ። ጫልቱ ተብዬ አዲስ አበባ ላይ ልኖር አልችልም። ለዚህ ነው የቀየርኩት ትለዋለች። ስም መቀየር የከተሜነት የዘመናዊነት ጣጣ አይመስልህም? የከተሜነት ጣጣ ብቻ አይደለም። ለምሳሌ ከአንድ የጎንደር የገጠር አካባቢ ወይንም ከዚያው ከደብረሲና የገጠር አካባቢ የመጣች ሴት በተመሳሳይ ከበከጆ ከመጣች ሴት ጋር ተመሳሳይ የገጠሬነት ጭቆና ይደርስባቸዋል። ከበከጆ የመጣችው ላይ ግን ድርብ ይሆናል። ድርብ ስልህ ገጠሬነት አንድ መሳቂያ መሳለቂያ ነው፤ ማንነት ደግሞ ሌላ መሳቂያ መሳለቂያ ያደርጋታል። ያቺ ከገጠር የመጣችው ገጠሬነቷ ብቻ ነው መሳለቂያ የሚያደርጋት፤ እንጂ ማንነቷ መሳለቂያ አያደርጋትም። ስለዚህ ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ከፍተኛ ተፅዕኖና ችግር ይደርስባቸዋል። ሌሎች ገጠሬዎች ግን ድርብ ችግር ያጋጥማቸዋል። መራራ የሚያደርገው ይሄ ነው። ይህ ነው የማንነት ጭቆናን የከፋና መራራ የሚያደርገው። በተለያዩ መንገዶች ስንመለከተው ከተሜነት የራሱ መገለጫ አለው። አንተ እነዚህ ከገጠር መጡ የምትላቸው ሰዎች በስማቸው ብቻ ነው ተገፉ ነው የምትለው ወይንስ በሌሎች ባህሎቻቸውም ተገፍተዋል ትላለህ? የስም ለውጥ የከተሜ ብቻ አይደለም። የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ ሆሮ ጉዱሩ ሀገራቸው ነው። የጥንት የቅድም አያታቸው ሀገር ነው ሆሮ ጉዱሩ። ነገር ግን እዛው ሆሮ ጉዱሩ ላይ ነው ስማቸውን እንዲለውጡ የተገደዱት። ሲወለዱ ስማቸው መገርሳ ነበረ። ተማሪ ቤት መገርሳ የሚባል ስም ይዘህ አትገባም ተባሉና ፍሬው ተባሉ። በኋላ ነው ይህ ዳውድ የሚለው ስማቸው የመጣው። ሩቅ ምናስኬደን አባዱላ ገመዳም እንደዛው ነው። ተገዶ ነው ምናሴ የሚለውን ስም ይዞ የነበረው። እርሱም ሦስተኛ ስሙ ነው አሁን። ኩማ ደመቅሳም እንደዛው። የብዙ ሰዎች ታሪክ የሚያሳየን በዚያው በተወለዱበት አካባቢ ሳይቀር ተፅዕኖ እንደሚደርስባቸው ነው። ወደ ደራሲያኑ እስቲ እንመለስ... ርዕሰ ጉዳያችን ተጠምዝዞ ወደዚህ መጣ እንጂ እነስብሀት ገብረእግዚአብሄርም ሆኑ ሌሎች በወቅቱ የነበሩ ደራሲያን ለምን አላሰቡትም ለሚለው ጊዜው የሚፈቅድ አልነበረም። እኔ ያደረኩትን ለማድረግ ወቅቱ ይፈቅድ ስላልነበር እነበአሉ በገደምዳሜ፣ በጨረፍታ ይነኩት ነበር እንጂ ቀጥታ እንደዚያ ማድረግ አይቻልም። የስብሀት ገፀባህሪያትን፣ ሥራዎች መለስ ብለህ ብትቃኝ ይሁነኝ ተብሎ ላይሆን ይችላል ለገፀባህሪያቱ ያንን ስም የሰጣቸው፤ ነገር ግን ሰርቅ ዳንኤል ከእንደዚህ አይነት ነገር ለመዳን በቆንጆዎቹ ረዥም ልብወለድ ላይ በሙሉ ለገፀባህሪያቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ስም ሰጥቶ እናገኛዋለን። ሰርቅ ዳንኤል ከእንዲህ አይነት እሰጥ አገባ ለመዳን ነው ብሎ ነው ብለን በድፍረት መናገር እንችላለን? ለመዳን ብሎ ነው። በፍፁም ሳያስበው ጠቅላላ የመጽሐፍ ቅዱስ ስም ሊያደርግ አይችልም። እንዲህ ያለ የብሔር ችግር ውስጥ ላለመግባት ነጠላቸው ማለት ነው- ገፀባህሪያቱን። ምክንያቱም ሳሙዔል የሚለው የማንም አይደለም። ክርስቲያን የሆነ በሙሉ ሳሙዔል ይላል። በዚህ መንገድ [ከብሔር ጉዳይ] ሊያመልጥ ሞክሯል። እነሐዲስ አለማየሁ የአካባቢያቸውን ስም ስለሚሰጡ ችግር የለባቸውም። ብርሃኑ ዘሪሁን ችግር አልነበረበትም። የሚፅፋቸው ፅሁፎችም በዚያው አካባቢ ስለነበሩ። ስለዚህ የጠየቅከኝ ጥያቄ ለምንድን ነው አንባቢያን የቡርቃ ዝምታ ላይ ጥላቻ ያደረባቸው ለሚለው ይህ ያልተነካው ያልተደፈረው ነገር ላይ በመግባቴ ትንሽ ይልለመዱት ጉዳይ ስለሆነባቸው ይሆናል እንጂ የቡርቃ ዝምታን ሚዛናዊ ሆነህ ስታነበው ሕዝብና ሕዘብን የሚያጋጭ መጽሐፍ አልነበረም። ሥራህን ወደድነው የሚሉህ አንባቢያን ለመውደዳቸው የሚሰጡት ምክንያትስ ምንድን ነው? ለምሳሌ የስደተኛው ማስታወሻ ላይ ጫልቱ እንደ ሄለን የሚል ፅሑፍ ፅፌያለሁ። ብዙ ሰዎች እንባ እያነቃቸው እንዳነበቡት ይናገራሉ። የጫልቱን ታሪክ ለምን ወደዳችሁት ስላቸው እኔ ያለፍኩት ልክ ጫልቱ ባለፈችበት መንገድ ነው ያሉኝ ይበዛሉ። በርካታ መጻሕፍትን ፅፈሀል። በጣም የሚታወቁት የቡርቃ ዝምታ፣ የቢሾፍቱ ቆሪጦች፣ የደራሲው ማስታወሻ፣ የስደተኛው ማስታወሻ የጋዜጠኛው ማስታወሻ ናቸው። የመጀመሪያሥራህ ግን ያልተመለሰው ባቡር የሚል ነው አይደል? ልክ ነህ። በስም የጠቀስኳቸው መጻህፍት በዋናነት የኦሮሞ ፖለቲካን የታሪካቸው ማጠንጠኛ ያደርጋሉ። ያልተመለሰው ባቡር የሚለው መፅሐፍህም እንደነዚሁሥራዎችህ ያለ ነው ጭብጡ? አይ፤ ያን ጊዜ ፖለቲካሊ ኮንሺየስ [በፖለቲካ የበሰልኩ] አልነበርኩም። ያንን ስጽፍ የ24 ዓመት ልጅ ነኝ። ባላሳትመው ይሻል ነበር። እንደው በመቸኮል ያሳተምኩት መጽሐፍ ነው። ለምንድን ነው ባላሳትመው ያልከው? የሥነ ጽሑፍ ይዘቱ ደካማ ነው። የመጽሐፉ አወቃቀር ጭብጡ ደካማ ነው። ከዚያ በተሻለ መስራት እችል ነበር። ብዙ ያልታሰበበት የልጅነት ሥራ ነው ብዬ ነው የማስበው። ቢሆንም አልጠላውም። የፖለቲካ ንቃተ ሕሊናህ ከፍ ብሎ ይህ የኦሮሞ ጉዳይ እያሳሰበኝ ይመጣ ጀመር የምትልበት የታሪክ አጋጣሚ አለ? አሁን በምትለው ረገድ አስቤ አላውቅም። ግን ከማንበብ ብዛት፣ ወደ ሕብረተሰቡ ጠጋ ብለህ ከማዳመጥ ብዛት፣ የተማርኩባቸው ጊዜያት ከ25 ዓመቴ በኋላ ይመስለኛል። ያ ማለት ከውትድርና በኋላ ማለት ነው? ከ25 ዓመት እድሜ በኋላ ማለት የፕሬስ መምሪያ ኃላፊነት ሥራዬን ትቼ የእፎይታ መጽሔት ዋና አዘጋጅ በነበርኩበት ጊዜ ማለት ነው። በኢህአዴግ ውስጥ ጥሩ ተጠቃሚ ነበርክ። በሥርዓቱ ደስተኛ ስላልነበርክ ነው ማለት ነው እነየቢሾፍቱ ቆሪጦችን እነየቡርቃ ዝምታን ለመጻፍ የተነሳሀው? ተጠቃሚ የሆንኩበት ጊዜ የለም። ጋዜጠኛ ነው የነበርኩት። ባለስልጣን ነበርክ ባለስልጣን ነበርኩ። ሁለት ዓመት የፕሬስ መምሪያ ኃላፊ ነበርኩ። ነገር ግን ባለስልጣን መሆን ተጠቃሚ መሆን ማለት አይመስለኝም። በጣም አስቸጋሪ ሥራ ነው የነበረው። ስለዚህ የፕሬስ መምሪያ ኃላፊ ከማለት ይልቅ ወታደርነት በለው። ወያኔ በጣም የተጠላ ሥርዓት ነበር። በተጠላ ሥርዓት ውስጥ በዚያ ከባድ ቦታ ላይ መመደብ ቅጣት ነው እንጂ ምቾት ወይንም ተጠቃሚነት አይመስለኝም። ወታደር ከነበርክበት ጊዜና የፕሬስ መምሪያ ኃላፊ ከነበርክበት ወቅት ስለማህበረሰቡ የተሻለ እንዳውቅ እድል ሰጥቶኛል የምትለው የትኛውን ነው? ወታደር አልነበርኩም እኔ። አስራ ዘጠኝ ቀን ብቻ ነው በሥራ ላይ የነበርኩት። ስለዚህ ወታደር ነበርኩ ለማለት አይቻልም። ከወያኔ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ደግሞ ጋዜጠኛ ነው የነበርኩት። ስለዚህ ሙሉ ሕይወቴን በጋዜጠኝነት ነው ያሳለፍኩት እያልከኝ ነው? በጦርነት ውስጥ ያሳለፍኩት አስራ ዘጠኝ ቀን ብቻ ነው፤ ሌላውን ጋዜጠኛ ሆኜ ነው ያሳለፍኩት። ሌላው የ'ጋዜጠኛው ማስታወሻ' ላይ የተገለፀ ስለሆነ እዚህ መድገም ብዙ አያስፈልግም። መጽሐፍህ ላይ ያነሳሀቸው ጉዳዮችን አሁን ካለው የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ስታያቸው መልስ እያገኙ ነው ትላለህ? እላለሁኝ። በተለይ የኦሮሞ ጥያቄ ፤ እኔ የቡርቃ ዝምታን ስፅፍ ወያኔን አላስደሰተውም ነበር። ምክንያቱም ኦሮሞ ማንም የበላይ አያስፈልገውም። በኦሮሞነቱ መደራጀትና መኖር ካለበት በትክክል ኦሮሞን የሚወድ ኢትዮጵያን የሚወድ ሊመራው ይገባል። እንጂ አቅም በሌላቸው አሽከሮች ሊዘወር አይገባም የሚል መልዕክት ነው የሚያስተላልፈው የቡርቃ ዝምታ። እና ቁጭቴን ነው የገለፅኩት። ቡርቃ ዝም አለ ስል የኦሮሞ ሕዝብ ዝም አለ ማለቴ ነበረ። የኦሮሞ ወጣቶች በቄሮ ቃሬ አማካኝነት ተነስተው ሀገሩን ሲያጥለቀልቁት የቡርቃ ወንዝ ከተደበቀበት ወጣ ብዬ እንደተሳካለት ሰው ራሴን ቆጥሬያለሁ። የኦሮሞ ወጣቶችም እኔን እንደሰሙኝ መጽሐፌን እንዳነበቡ ማወቄ የበለጠ ሞራል ሰጥቶኛል። ለዚህ ትግል የበኩሌን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ ትላለህ? አይ ትእቢተኛ አይደለሁም። በትዕቢት አይደለም። አስተዋፅኦን በመቁጠር አንፃር ነው ያልኩት። ወደ አስተዋፅኦ ስንመጣ አንዲት ትልቅ የኦሮሞ እናት ዱላ ይዛ፣ ከፖሊሱ ፊት ቆማ ስትጮህ ስታይ የእኔ አስተዋፅኦ ከእርሷ ያነሰ ነው። ለዚህ ትግል አስተዋፅኦ ያደረጉ በርካታ ሰዎች አሉ፤ እኔም ከእነርሱ አንዱ ነኝ። ትንሽ ኮራ ብዬ ለመናገር ግን ብዙ ድፍረት የለኝም። እፎይታ አሳታሚ በነበርክበት ጊዜ በአምስት ቅጾች የታተመው እፍታ መጽሐፍ ሀሳብ እንዴት ሊመጣ ቻለ? ወጣት በነበርኩ ሰዓት የምጽፋቸውን መጻሕፍትን የሚያሳትምልኝ አልነበረም። በተለይ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ትንሽ ያጉላላኝ ነበረ። ደራሲና ጋዜጠኛ ብርሃኑ ዘሪሁን ጥሩ ወዳጄ ነበር። ሀዲስ አለማየሁም እንዲሁ ቤታቸው እየሄድኩ እንጨዋወት ነበር። ያኔ ወጣት ነኝ የ19 ዓመት ልጅ። በኢትዮጵያ ውስጥ ለወጣቶች መጽሐፍ ማሳተም ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያጫውቱኝ ነበር። በተለይ ብርሃኑ ዘሪሁን 'ተስፋ አትቁረጥ መበርታት አለብህ' እያለ ይመክረኝ ነበር። እና በዚያን ጊዜ እኔ ድንገት ወደ ስልጣን መጥቼ እድሉን ሳገኝ እኔ እቸገር ስለነበር የወጣቶች ሥራዎች የመታተም እድል እንዲያገኝ በማሰብ ነው እፍታ ቅፅ 1 ብዬ የጀመርኩት። እስከ ቅፅ አምስት ድረስ ባለው በርካታ ወጣቶች ሥራዎቻቸው ታትመውላቸዋል። እነ ተሾመ ገብረ ሥላሴ፣ እንዳለ ጌታ ከበደን የመሳሰሉ ገና ወጣት ደራሲያን ሥራዎቻቸው እንዲታተሙና እንዲታወቁ ማድረግ በመቻሌ እደሰታለሁ። እኔ ከተውኩት በኋላም እንዳለ ጌታ ከበደ ሊቀጥለው መሞከሩ አስደስቶኛል። እንዳለ ጌታ ማስቀጠሉ ስትል 'ደቦ' የተሰኘውን መጽሐፍ ማንሳትህ ነው? አዎ ደቦን ማንሳቴ ነው። እርግጥ ነው እፍታ ላይ ሥራቸው ከታተመላቸው አንዳንድ ደራሲያን መካከል በዛው ቀጥለው በርካታ መጻህፍትን ለአንባቢያን ያቀረቡ አሉ። ነገርግን አንዳንዶቹ በዚያው ጠፍተዋል። ሀገር ውስጥ ብኖር አሁንም ለበርካታ ደራሲያን ሥራዎች የሕትመት ብርሃን ማግኘት አስተዋጽኦ አደርግ ነበር የሚል ቁጭት ተሰምቶህ ያውቃል? በጣም። ለምሳሌ ተሾመ ገብረ ሥላሴ ደቡብ ክልል ሩቅ ቦታ ሆኖ አንድ ደብዳቤ መጀመሪያ የጻፈው ለእኔ ነው። ያቺን ደብዳቤ ሳያት ይህ ልጅ ደራሲ ነው አልኩኝ። ሰዓዳ መሐመድ ወደ እኔ መጥታ ለመጀመሪያ ጊዜ ያበረታታኋት እኔ ነኝ። የሰዓዳ የብዕር ውበት እስካሁን ድረስ አይረሳኝም። እንዳለ ጌታ ከበደ ወልቂጤ ነበር የሚኖረው። ከወልቂጤ እየተመላለሰ እኔንና ስብሀትን ያገኝ ነበር። በዚያን ጊዜ በጣም የምንወደው ትንሽ ልጅ ነበር። እነቶማስ አርጋው፤ በሕይወት የለም አሁን፣ አሁን ፊንላንድ የምትኖረው ማርታ- የአባቷ ስም ተረሳኝ፣ እንደዚህ አይነት ትንንሽ ልጆች ነገር ግን ጠንካራ ብዕር ያላቸውን ሳገኝ ሻይ እየጠጣን እናወራ ነበር፤ እንዲፅፉ አበረታታቸው ነበር። እንደዛሬው ዘመን የአንድ ወገን ጠላት ተብዬ ከመፈረጄ በፊት [ሳቅ]። ከአማርኛ ደራሲያን የማን ተፅዕኖ አለብኝ ትላለህ? በግድ ጥራ ካልከኝ ስብሀት ገብረ እግዚአብሔር፣ ብርሀኑ ዘሪሁን፣ በዓሉ ግርማን የማነሳ ይመስለኛል። ከኢትዮጵያ ከወጣህ በኋላ ደቡብ አፍሪካ፣ ከዚያም አሜሪካ፣ አውሮፓ አሁን ደግሞ ኤርትራ እንደምትኖር ሰምቻለሁ። ቋሚ መኖሪያህ የት ነው? ቋሚ ያልሆነ ሰው ምን ቋሚ መኖሪያ ያስፈልገዋል ብለህ ነው? እስክትሞት ድረስ ዝም ብለህ መኖር ነው [ሳቅ]። ከ50 ዓመት በኋላ ምን ቋሚ መኖሪያ ያስፈልጋል። አሁን ያለሁበት ስድስት ወር እቆያለሁ [ቃለመጠይቁን ስናደርግ ስቶኮልም ነበር] ከዚህ በኋላ አሜሪካ እሄዳለሁ፤ እንደዚህ ስትል 60 ይገባል፤ በዚያው እድሜዬ አለቀ ማለት ነው። ለእኔ መኖር መጻፍ ብቻ ነው። ስለቋሚ መኖሪያ አስቤ አላውቅም። ኢትዮጵያም ስትመጣ ጠይቆ ለመሄድ ብቻ ነው እንጂ ረዥም ጊዜ ቆይቶ ለመኖር አታስብም ማለት ነው? እንደሁኔታው ነው። እዚያ ረዥም ጊዜ ልቆይበት የምችልበት ሁኔታ ከተፈጠረ እቆያለሁ። ቢሾፍቱ ላይ አምስት ዓመትም መቆየት ከተቻለ ጥሩ ነው። ሥራዎችህ በአማርኛ አንባቢያን ዘንድ ነው በስፋት የሚነበቡት። አንተ ደግሞ ርዕሰ ጉዳይ አድርገህ የምታነሳው የኦሮሞን ጉዳይ ነው። በአማርኛ እየፃፍክ በኦሮሚያ ውስጥ ያለው ሠፊው የኦሮሞ ወጣት ሥራዎቼን አንብቧል ትላለህ? እንኳን ኦሮሚያ ላይ አሥመራ ላይ አማርኛ በደንብ የሚናገሩ አሉ። እድሜያቸው ከአርባ ዓመት በላይ የሆነ ኤርትራዊያን አማርኛ በደንብ ይችላሉ። ለምን የትምህርት ቤት ቋንቋ ነበር። ስለዚህ እድሜው ከአርባ ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በአብዛኛው [አማርኛ] ይችላል። ኤርትራ ውስጥም [አማርኛ] ይችላል። እና አማርኛ ሰፊ አንባቢ ያለው ቋንቋ ነው። ይህ ምንም የሚካድ አይደለም። አማርኛ ከሥራ ውጪ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ አይቻልም፤ ሊሆንም አይችልም። አማርኛ በአፍሪካ ቀንድ በሰፊው ከሚነገሩ ቋንቋዎች መካከል አንዱ ነው። ውብ ቋንቋ ነው አማርኛ። በኦሮሞዎች ዘንድ ፖለቲካው ያመጣው ጊዜያዊ ቁጣ አማርኛን መናገር ያለመፈለግ ዝንባሌ አለ። ግን ፍትህ ከሰፈነ በኋላ ሁሉም እንደገና ይመለሳል። ምክንያቱም ጠብ ያለው ከቋንቋው ጋር አይደለም፤ ከጭቆናው ጋር ነው። ስለዚህ አማርኛን ኦሮሞዎች እርግፍ አድርገው ትተውታል ብዬ አስቤ አላውቅም። ጊዜያዊ የፖለቲካው ትኩሳት ያመጣው ስሜት ይመስለኛል። ከሥራዎችህ መካከል የቡርቃ ዝምታ ወደ ኦሮምኛ መተርጎሙን አውቃለሁ ሌሎች ሥራዎችህ ወደ ሌላ ቋንቋ የተመለሱ አሉ? አዎ የኑረነቢን ማህደር ወደ ጣሊያንኛ፣ ወደ እንግሊዘኛና ወደ ትግረ ቋንቋዎች ተመልሷል። የጀሚላ እናት የሚለውም እንዲሁ ተተርጉሟል። አንዳንዶቹ ገና አልታተሙም። ወደ ኦሮምኛ የተተረጎመው እስካሁን የቡርቃ ዝምታ ብቻ ነው፤ ሌላ የለም። ጫልቱ እንደ ሄለን የምትለዋን ጽሑፍ ብቻ ወደ ኦሮምኛ ተርጉመው በድምፅ ጭምር እንዳለ ግን አውቃለሁ።
43918192
https://www.bbc.com/amharic/43918192
ኤኤንሲ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ 'ዘረኛ' ነው አለ
የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ስፖርት የበላይ አካል የሆነው ፌዴሬሽን (አይኤኤኤፍ) አዲስ ያወጣው ደንብ በደቡብ አፍሪካዊቷ የ800 ሜትር ርቀት የኦሊምፒክ አሸናፊ ካስተር ሴሜኒያ ላይ የተሰነዘረ "ግልፅ ዘረኝነት" ነው ሲል የደቡብ አፍሪካው ገዢ ፓርቲ ኤኤንሲ አወገዘ።
"ይህ አዲስ ደንብ ከሌሎች መካከል ባለፉት ዓመታት ተገቢ ባልሆነ ጫና ስር የቆየችውን ካስተር ሴሜኒያን ኢላማ ያደረገ ነው" ሲል ኤኤንሲ ባወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል። አዲሱ ደንብ በመጪው ህዳር ወር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ተነግሯል። በዚህም ከፍተኛ ተፈጥሯዊ የቴስቴስትሮን መጠን ያላቸው ሴቶች ከወንዶች ጋር እንዲወዳደሩ ወይም መድሃኒት የማይወስዱ ከሆነ የሚወዳደሩበትን የስፖርት አይነት እንዲቀይሩ ያዛል። ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንደሚያምነው የተወሰደው እርምጃ ከፍተኛ የቴስቴስትሮን መጠን ያላቸው ሴቶች በውድድሮች ላይ የሚይዙትን የበላይነት ለማስቀረት እንደሆነ ገልጿል። ይህንን ተከትሎም ኤኤንሲ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ፌዴሬሽኑ ያወጣውን አዲስ ሕግ ተቃውሞ ጣልቃ እንዲገባም ተማፅኗል። "ይህ አዲስ ደንብ በአብዛኛው በምሥራቅ አውሮፓ፣ በእስያና በአፍሪካ አህጉሮች የሚገኙትን አትሌቶች ሰብአዊ መብት የሚፃረር ነው" ሲል ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሶ "በውሳኔው የሚንፀባረቀው ዘረኝነት ግን ሊደበቅ አይችልም" ብሏል። ሴሜኒያ እንደ አውሮፓዊያኑ በ2009 በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ800 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ካሸነፈች በኋላ ፆታዋንና አትሌትክስን በተመለከተ በዓለም ዙሪያ የክርክር ርዕስ ሆናለች። ሴሜኒያ ቀደም ሲል በአትሌቲክስ ስፖርት ባለስልጣናት የፆታ ምርመራ እንድታደርግ ተጠይቃ የነበረ ቢሆንም ውጤቱ ግን እስካሁን ለሕዝብ አልተገለፀም።
news-50185538
https://www.bbc.com/amharic/news-50185538
የዓለማችን ረዥም ሰዓታትን የወሰደው፤ አስደናቂ የአውሮፕላን ጠለፋ
ጊዜው እንደ አውሮፓዊያኑ 1960ዎቹ፤ አሜሪካ ውስጥ ቢያስን በስድስት ቀናት አንዴ አውሮፕላን የሚታገትበት ዘመን። የዛሬ 50 ዓመት ታድያ ራፋዔል ሚኒቺዬሎ የዓለማችን ረዥም ጊዜ የወሰደውን ጠለፋ አካሄደ።
ነሐሴ 1962 ደቡባዊቷ የጣልያን ከተማ ኔፕልስ አንዳች ዱብዳ ወደቀባት፤ ምድር ተንቀጠቀጠች። ነገር ግን የአካባቢው ሰዎች አልተደናገጡም። አካባቢው ምድር መንቀጥቀጥ አያጣውም። ከከተማዋ 20 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የሚኒቺዬሎ ቤተሰብ ጎጆ መሥርተው ይኖራሉ። ራፋዔል በወቅቱ የ12 ዓመት ታዳጊ ነበር። • ልክ የዛሬ 21 ዓመት ይህ ሆኗል የመሬት መንቀጥቀጡ ድጋሚ ተሰማ። አሁን ነዋሪዎች ተሸበሩ። ብሎም ለሦስተኛ ጊዜ ምድር እንደተሰጣ አንሶላ ተርገበገች። የራፋዔል ቤተሰቦች ከአደጋው ቢተርፉም ብቻቸውን ቀሩ። ሊረዳቸው ብቅ ያለ ባለሥልጣንም ሆነ አቅም ያለው አልነበረም። በርካቶች ሥፍራውን ለቀው ወጡ። ግማሾች ቤታቸውን እንደ አዲስ እያነፁ ሲመለሱ የራፋዔል ቤተሰቦች ግን ወደ አሜሪካ መሄድን መረጡ፤ ለተሻለ ሕይወት። ነገር ግን አሜሪካ በጊዜው ከሁሉም አቅጣጫ ጦርነት የሚሸታት ነበረች፤ ጊዜው የከፋ ነበር። ጥቅምት መገባደጃ፤ 1969 በወታደራዊ የደንብ ልብስ ያሸበረቀው ራፋዔል ሚኒቺዬሎ ከሎስ አንጀለስ ወደ ሳን ፍራንሲስኮ ለማቅናት አውሮፕላን ተሳፈረ። 15 ዶላር ከሃምሳ ሳንቲም 'ሆጭ አድርጎ' የከፈለበትን ቲኬት በእጁ እንደጨበጠ። የአውሮፕላኑ ጋቢና [የበረራ ክፍል] ውስጥ ሦስት አብራሪዎች አሉ። የበረራ አስተናጋጆቹ ደግሞ አራት ጉብሎች። ከእነዚህ ውስጥ በበረራ አስተናጋጅነት የተሻለ ልምድ የነበራት የ23 ዓመቷ ቻርሊን ዴልሞኒኮ ነበረች። • በአውሮፕላን ጠለፋ ሲፈለግ የነበረው ከ34 ዓመት በኋላ በቁጥጥር ሥር ዋለ ቲደብሊዩኤ85 [TWA85] አውሮፕላን ከካንሳስ ከተማ ተነስቶ፤ ካሊፎርኒያ አርፎ ነው ወደ ሳን ፍራንሲስኮ የሚያቀናው። ከካንሳስ ከመነሳታቸው በፊት ግን ዋና አብራሪ ዶናልድ ኩክ ለበረራ አስተናጋጆች ከሌላው ጊዜ የተለየ ትዕዛዝ አስተላለፈ። 'ወደ ጋቢና [ኮክ ፒት] መግባት ከፈለጋችሁ ደወሉን ተጫኑ፤ ማንኳኳት አይፈቀድም' የሚል ቀጭን ትዕዛዝ። አውሮፕላኑ ከመሸ በኋላ ሎስ አንጀለስ ደረሰ። የሚወርዱት ወርደው የሚቀጥሉት ቀጠሉ። አዳዲስ ተሳፋሪዎችም ቲኬታቸውን እያሳዩ ወደ ውስጥ ዘለቁ። ከሁሉም አዳዲስ ተሳፋሪዎች የቻርሊን ዓይን ያረፈው ከራፋዔል ላይ ነው፤ እንዲሁም በእጁ ካንጠለጠለው ቦርሳ ላይ። ቲደብሊዩኤ85 [TWA85]፤ ጩኸታሟ ቦይንግ 707 አውሮፕላን በጠለፋው ወቅት ጥቅምት 31፤ 1969 ከሌሊቱ 7፡30 አውሮፕላኑ ሎስ አንጀለስን ለቆ ጉዞ ወደ ሳን ፍራንሲስኮ ጀመረ። 15 ደቂቃ ያክል ከተጓዘ በኋላ የእገታው ድራማ ተጀመረ። አውሮፕላኑ ተደላድሎ መብረር ሲጀምር የበረራ አስተናጋጆች የመብራት መጠኑን ቀነስ አደርጉት። በርካታ መንገደኞች ወደ ሕልም ዓለም እያቀኑ ቢሆንም ራፋዔል ግን ይቁንጠነጣል። የበረራ አስተናጋጆቹ የአውሮፕላኑን ኩችና በማፅዳት ላይ ናቸው። ይሄኔ ራፋዔል ሄዶ ይቀላቀላቸዋል። ከቦርሳው ውስጥ ኤም1 የተሰኘ መሣሪያ አውጥቶ በእጁ ይዞታል። «ጌታዬ አውሮፕላን ውስጥ መሣሪያ ይዞ መግባት አይቻልም» ቻርሊን በዝግታ ተናገረች። ራፋዔል እጁን ወደ ቻርሊን ዘረጋ። መዳፉ ውስጥ ያሉትን 7.62 ሚሊ ሜትር ጥይቶች አሳያት። መሣሪያው በጥይት መሞላቱንም ነገራት። ከዚያም ወደ በረራ ክፍሉ እንድትወስደው ነገራት። ቻርሊን ዴልሞኒኮ [በስተቀኝ በኩል] እና የሙያ አጋሮቿ ከተሳፋሪዎች መካከል የአንድ የሙዚቃ ቡድን አባላት ይገኙበታል። ከአባላቱ አንዱ ዓይኑን እያሻሸ ሲነቃ አንድ ሰው የበረራ አስተናጋጇ ላይ መሣሪያ ደግኖ ይመለከታል። የሚሆነውን ባለማመን አጠገቡ ያሉትን ይቀሰቅሳል። አንድ ተሣፋሪ ይነሳና ራፋዔልን ለመሟገት ይሞክራል። ይሄን ያስተዋለው ራፋዔል ለቻርሊን ቀጭን ትዕዛዝ ያስተላልፋል። «ቁሚ!»፤ ቻርሊን፤ ይህ ሰው የምርም ወታደር ሳይሆን አይቀርም ስትል አሰበች። ከራፋዔል ጋር የተፋጠጠው መንገደኛ ነገሩ መረር ያለ መሆኑን ሲረዳ ወደ መቀመጫው ይመለሳል፤ ራፋዔልም ወደ 'ሥራው'። ቻርሊን ጉልበቷ እየከዳት ነው፤ ብርክ ብርክ ብሏታል። ወደ ደረጃ አንድ [ቢዝነስ ክፍል] ደረሱ። ቻርሊን ከፊቷ ላሉ ሰዎች መልዕክት እያስተላለፈች መንገዷን ቀጠለች። «ገለል በሉ! ከኋላዬ መሣሪያ የታጠቀ ሰው አለ» እያለች። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? 'ሥራውን' በፀጥታ ሲከውን የነበረው ራፋዔል ቁጣ ይቀድመው ጀምሯል። ልክ በረራ ክፍሉ ሲደርሱ ቻርሊን ካፕቴኑ የሰጣት ትዕዛዝ ትዝ አላት። ነገር ግን ራፋዔል ስላልፈቀዳላት የግዴታውን ታንኳኳለች። ምናልባት ትዕዛዝ መጣሷ አብራሪዎቹ የሆነ ነገር ቢኖር ነው ብለው እንዲጠራጠሩ ያግዛል ብላ አሰበች። ነገር ግን በሩ ተከፈተ። ከኋላዋ ተሸክማ የመጣችውን ጉድ ለአብራሪዎቹ ሹክ አለች። ራፋዔል ቻርሊንን ወደ ጎን ገለል አድርጎ አፈሙዙን አብራሪዎቹ ላይ አነጣጠረ። ከዚያም አጠር ያለ ትዕዛዝ ሰጣቸው። «አቅጣጫችሁን ወደ ኒው ዮርክ አድርጉ።» የኤፍ ቢ አይ ልዩ መኮንን ስኮት ዌርነር ከቻርሊን የተቀበለው ቀለህ ታድያ ይሄ ሁሉ ሲሆን እንቅላፋቸውን እየለጠጡ ያሉ ብዙ መንገደኞች ነበሩ። የባንዱ አባላት አንድ ላይ ተሰባስበው በሁኔታው መገረም ያዙ። እንዴት አድርጎ ያን የሚያህል መሣሪያ ይዞ ሊገባ ቻለ? ወደየት ሊወስዳቸው አስቦ ይሆን? ከተሣፋሪዎቹ መከካል ጁዲ ፕሮቫንስ ትገኛለች። የበረራ አስተናጋጅ ናት። ነገር ግን ሥራ ላይ አይደለችም። በአደጋ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለባት ሥልጠና ወስዳለች። ሌላኛው ደግሞ ጂም ፊንድሌይ ነው። ቀደም ሲል ከራፋዔል ጋር አንገት ለአንገት ካልተናነቅሁ ያለው ግለሰብ። ጂም አብራሪ ነው። ተራ ሰው መስሎ እየተጓዘ ቢሆንም። ወደ ጠላፊው ቦርሳ ያመራና መበርበር ይጀምራል። ማንነቱን ለማጣራት፤ አልፎም ሌላ የጦር መሣሪያ አለመኖሩን ለማወቅ። ጥይት የተሞላ ካርታም አገኘ። ካፒቴን ኩክ ድምፁ በማጉያው ተሰማ። «አንድ የደነገጠ የሚመስል ወጣት ሰው እዚህ አለ። ወደ ሚፈልገው ቦታ እንወስደዋለን።» • የቱሉ ፈራ ደጋግ ኢትዮጵያዊ ልቦች ጊዜው ከላይ እንደተጠቀሰው የአውሮፕላን ጠለፋ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ የሚሰማበት ነው። ለዚህም አየር መንገዶች የነበራቸው የላላ ጥበቃ ዋነኛው ምክንያት ነበር። የመንገደኞች ሻንጣ የመፈተኛ መሣሪያ ዘግይቶ ነበር ወደ ሥራ የገባው። ለነገሩ በጊዜው አውሮፕላን የጠለፉ ቢበዛ ኩባ ሄደው ቢቀሩ ነው እንጂ ማፈንዳት የሚባል ነገር አልነበረም። ኋላ ላይ የወጡ ምርመራዎች ራፋዔል መሣሪያውን ከፈታታው በኋላ በቱቦ መሰል ዕቃ ውስጥ አድርጎ ነው ወደ አውሮፕላኗ የገባው። መሣሪያውን የገጣጠመውም የአውሮፕላኑ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ነበር። የቦርሳ ፍተሻ እንደ አሁኑ አለመሆኑ ለራፋዔል መልካም አጋጣሚ ነበር። በ1969 ላይ ብቻ አሜሪካ ውስጥ 54 አውሮፕላኖች ተጠልፈዋል። የትኛውም ጠላፊ ግን አውሮፕላን ጠልፎ ከአህጉረ አሜሪካ ወጥቶ አያውቅም። ጠላፊው ራፋዔል ወደ ኒው ዮርክም ወደ ሮምም መሄድ ፈልጓል። ግራ ተጋብቶ አብራሪዎቹን ግራ አጋብቷቸዋል። ታድያ ሁለቱም የሚቻል አልነበረም። ወደ ኒው ዮርክ እንዳይሄዱ በቂ ነዳጅ የላቸውም፤ ወደ ሮም እንዳይገሰግሱ ሁሉም ከአህጉረ አሜሪካ ውጭ አብርረው አያውቁም፤ ልምዱ የላቸውም። ኋላ ላይ ግን ስምምነት ላይ ደረሱ። ዴንቨር፤ ኮሎራዶ አርፈው ነዳጅ ለመቅዳት። ታድያ ነዳጅ እየቀዱ ሳለ ካፕቴን ኩክ ለበላይ አለቆቹ ችግር እንዳጋጠመው ሹክ ይላል። ራፋዔል ዕቅዱን ቀየረ። 39 ተሣፋሪዎችን ዴንቨር ላይ እንዲወርዱ ማድረግ። ትሬሲ ኮልማን ከአንዷ በስተቀር የበረራ አስተናጋጆችንም እንዲሁ። መንገደኞች መውረድ ሲጅምሩ ፊንድሌይ መውጭው ላይ ሲደርስ ''ዕቃ ረሳሁኝ፤ ተመልሼ ልውሰድ ወይ?'' ሲል ጠላፊውን ይጠይቃል። ጠላፊውም ይፈቅድለታል። ሰዓቱ ሌሊት 10 ሰዓት ገደማ በመሆኑ ይህ ሁሉ ሲካሄድ ገና ጎህ አልቀደደም ነበር። መንገደኞቹ ሲወጡ የጠበቃቸው የወዳጅ ዘመድ ፈገግታ አልነበረም። የኤፍቢአይ መኮንኖችና ብዕራቸው እንጂ። የሙዚቃ ቡድኑ አባላት በዚህ ጠለፋ ምክንያት ታዋቂ መሆን ችለዋል አውሮፕሏኑ ከዴንቨር ከተነሳ ሦስት ሰዓት አለፎታል። አውሮፕሏኗ ውስጥ የቀሩት አምስት ሰዎች ብቻ ናቸው። ዋና አብራሪ ኩክ እና ሁለት ረዳቶቹ፣ የበረራ አስተናጋጇ ትሬሲ እና ጠላፊው ራፋዔል። አውሮፕሏኑ ኒው ዮርክ ጆን ኤፍ ኬኔዲ አውሮ ፕላን ማረፊያ በሰላም አረፈ። ከሌሎች አውሮፕላኖች ራቅ ብሎም እንዲቆም ተደረገ። 100 ግድም የኤፍቢአይ መኮንኖች አለባበሳቸው እንደ መካኒክ እንዲሁም ዕቃ አውራጅ እና ጫኝ መስለው በተጠንቀቅ ቆመዋል። ሃሳባቸውም እንደ እባብ ተሹለኩልከው ወደ አውሮፕላኑ መግባት ነው። አውሮፕላኑ ነዳጅ ሊሞላ ዝግጅት ላይ ሳለ አንድ መኮንን ወደ አውሮፕላኑ ጠጋ አለ። ጠላፊው አነጣጥረው እንዳይነድሉት በማሰብ ወደ መስኮቶች ቀረብ ላለማለት ወስኗል። ካፒቴኑም ለመኮንኖቹ ወደ አውሮፕላኑ እንዳይጠጉ በዓይኑ ምልክት ሰጠ። ድንገት የጥይት ድምፅ ተሰማ። ድንጋጤው በረድ ሲል ታድያ ጠላፊው ጥይት እንደባረቀበት ታወቀ። ነገር ግን በሰውም ላይ ሆነ አውሮፕላኗ ላይ ጉዳት አልደረሰም። ጥይቱም የአውሮፕላኗን ጣራ ዘልቆ መሄድ አልቻለም። ይህ ቢሆን ኖሮ ግን የራፋዔል ዕቅድ በእንጭጩ በቀረ ነበር። አሁን አብራሪዎቹ ድንጋጤ ገባቸው። ነገሩ ቀላል እንዳልሆነ ይገባቸው ጀመር። ሁለት የዓለም አቀፍ በረራ ልምድ ያላቸው አብራሪዎች ወደ አውሮፕላኗ ዘለቁ። ጠላፊው ሁሉም አብራሪዎች እጃቸውን ወደ ላይ ሰቅለው አብራሪ ክፍል ውስጥ አርፈው እንዲቀመጡ አዘዘ። አውሮፕላኑም አኮብኩቦ ተነሳ። የያዘው ነዳጅ ግን ሮም የሚያደርስ አልነበረም። አትላንቲክን ማቋረጥ የሚያስችል ነዳጅ ለመሙላት ሜይን የተሰኘ ከተማ ላይ አረፈ። ከዚያም በማስከተል ጉዞ ወደ ሮም ሆነ። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ከጠለፋው ውጭ ለሌላ ርዕስ ዓይንና ጆሮ የለንም አሉ። አዲሶቹ አብራሪዎች አውሮፕላኑን መዘወር ያዙ። ዋና አብራሪ ኩክ ጠላፊው ጋር ቁጭ ብሎ ወጉን ይጠርቅ ያዘ። • የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች ራፋዔል መሣሪያውን ጭኖቹ ላይ አስደግፏል። ማንም የጠላፊውን መሣሪያ ደፍሮ መቀማት አልሻተም። ነገሮች እንዳልነበር እንደሚሆኑ ሁሉም ገብቷቸዋል። ጠላፊው አብራሪዎቹ አግብተው እንደሆነ ሲጠይቅ ኩክ "አዎ ሁላችንም አግብተናል" ሲል መለሰለት። እንደው ቢራራልን ብሎ እንጂ ከአንዱ በቀር ሁሉም ጎጆ ያልወጡ ናቸው። ከሜይን ወደ ሻነን፤ አየርላንድ፤ የስድስት ሰዓታት በረራ። ሻነን ማረፍ ያስፈለጋቸው ነዳጅ ለመቅዳት ነበር። አውሮፕሏኗ ውስጥ ብስኩታብስኩት እንጂ ደህና ምግብ አልነበረም። ነገር ግን ማንም በሕይወት ስለመቆየት እንጂ ስለ ምግብ አላሰበም። አውሮፕላኑ አየርላንድ ሲደርስ ጥቅምት አልፎ ኅዳር ገባ። አውሮፕላኑ ከተጠለፈ 18 ሰዓታት አልፏል። ኅዳር መባቻ ቲደብሊዩኤ85 [TWA85] አውሮፕላን ሮም ፊዩሚቺኖ አየር ማረፊያ ደረሰ። የ20 ዓመቱ ራፋዔል ሚኒቺዬሎ አውሮፕላኑ ራቅ ብሎ እንዲቆምና ያልታጠቀ ፖሊስ መጥቶ እንዲያናግረው አንድ የመጨረሻ ትዕዛዝ አስተላለፈ። 18 ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በኋላ ጠለፋው ሊጠናቀቅ ሆነ። ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ክስተቱን 'የዓለማችን ረዥም ሰዓት የወሰደ፤ አስደናቂ አውሮፕላን ጠለፋ' ሲል በፊት ገፁ አተመ። በጠላፊው ጥያቄ መሠረት አንድ ያልታጠቀ ሰው ቀረበ። ጠብመንጃውን እንደታጠቀ ሰውዬውን ተከትሎ ወደ አንድ መኪና ሄደ። ታድያ ራፋዔል አውሮፕላኑን ለቆ ሲወጣ ግን አብራሪዎችን ይቅርታ ጠይቆና አመስግኖ ነበር። «ወደ ኔፕልስ ውሰደኝ» ራፋዔል አዲሱን ታጋች አዘዘው። መኪናዋ ጉዞዋን ቀጠለች። ነገር ግን አንድ ቦታ ላይ መፈናፈኛ ስታጣ ጊዜ ራፋዔል ከመኪናዋ በመውጣት ይጠፋል። ከመቶ በላይ ፖሊሶች ፍለጋቸወን በሄሊኮፕተር እና በውሾች ታግዘው ቢያደርጉም ደብዛው ጠፋ። አምስት ሰዓታት አለፉ። ታድያ ራፋዔልን ያገኙት ፖሊሶች ሳይሆኑ አንድ ቄስ ነበሩ። ቤተክርስትያን ተጠልሎ የነበረው ራፋዔል በጣልያን የፖሊስ ኃይል ተከበበ። ይሄኔ ጠላፊው ለአገሩ ሰዎች አንድ ጥያቄ ሰነዘረ። «የሃገሬ ሰዎች ስለምን ልታሰሩኝ ፈለጋችሁ?» ሚኒቺዬሎ ከታሠረ በኋላ ሮም ውስጥ፡ "የምን አውሮፕላን? ምን እንደምታወሩ አላውቅም" ራፋዔልን ጋዜጠኞች ከበው ሲጠይቁት 'እኔ ስለምን ጠለፋ እንደምታወሩ አላውቅም' ሲል ካደ። ኋላ ላይ ግን ለምን አውሮፕላን መጥለፍ እንዳስፈለገው እውነቱን አወጣ። ራፋዔል ሚኒቺዬሎ የቪዬትናም ጦርነት ላይ የአሜሪካን ወታደራዊ የደንብ ለብሶ ተዋግቷል። ራፋዔል ሚኒቺዬሎ የቪዬትናም ጦርነት ላይ የአሜሪካን ወታደራዊ የደንብ ለብሶ ተዋግቷል ራፋዔል አሜሪካ የገባው ግንቦት 1967 (እአአ) ነበር። ማረፊያው ደግሞ ሲያትል። ከአምስት ዓመታት በኋላ ታድያ በውዳጅ ወታደር ሆኖ ለአሜሪካ ለመዋጋት ወደ ቪዬትናም ያቀናው። ቪዬትናም ካቀና በኋላ ታድያ ያሰበው አልጠበቀውም። በጣም አሰቃቂ ጊዜ አሳልፏል። ይህን የሚተርኩት አብረውት የተዋጉት የትግል አጋሩ ተርነር ናቸው። 'ያሳለፍነው አይነገር' ይላሉ ተርነር። የዚያን ጊዜው ወጣት ተርነር፤ ራፋዔል አውሮፕላን ጠለፈ የሚለውን ዜና ሲሰሙም ብዙ አልደነቃቸውም። በእርግጠኝነት በጦርነቱ ምክንያት አዕምሮው ተነክቷል ብለው ነው ያሰቡት። የአሜሪካ የቀድሞ ወታደሮች ማሕበር ቢያንስ 30 በመቶው በቪዬትናም ጦርነት ላይ የተሳተፉ ወታደሮች የአዕምሮ ጤና መቃወስ አጋጥሟቸዋል ሲል ግምቱን ያስቀምጣል። ይህ ደግሞ ወደ 810 ሺህ የሚጠጋ ወታደር ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ራፋዔል 2008 ዓመተ ምሕረት ላይ ነው የአዕምሮ ጤና ሕክምና የተደረገለት። • «ሙሉ ቤተሰቤን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ» በካንሰር በሽታ ምክንያት ወደ ኔፕልስ ተመልሰው ኑሯቸውን በመግፋት ላይ የነበሩት የራፋዔል አባት ሉዊጂ ሚኒቺዬሎ ያኔ እንዲህ ብለው ነበር። «ልጄ ይህን ለምን እንዳደረገ አውቀዋለሁ። ጦርነቱ አዕምሮውን አቃውሶታል። ወደ ቤቱ መመለስ ፈልጎ ነው።» ታድያ ትንሽ ቆይቶ ራፋዔል አውሮፕላኑን ሊጠልፍ የቻለበት ሌላ ምክንያት ብቅ አለ። ጦርነት ላይ ሆኖ ያጠራቀመው 800 ዶላር ወደ ቤቱ ሲመለስ 600 መቶ ሆኖ ጠበቀው። ይህ ደግሞ በካንሰር ምክንያት ሊሞቱ እያጣጣሩ የነበሩትን አባቱን ለማዬት በቂ ገንዘብ አልነበረም። 200 ዶላር ጨምሩልኝ ብሎ ለበላይ አለቆቹ ቢያመለክትም በዚያ ቀውጢ ዘመን የሚሰማው አልነበረም። ወደ አንድ ሱቅ ሄዶ 200 ዶላር ለመስረቅ ሞክሮም አልተሳካለትም። ይልቁንም ተይዞ የካቴና ሲሳይ ሆነ። ክስ ቀርቦበት፤ በቀጠሮ ዳኛ ፊት እንዲቀርብ ተወስኖ ተለቀቀ። የቀጠሮው ቀን ደግሞ ከጠለፋው አንድ ቀን በኋላ ነበር። ይሄኔ ነው ከቪዬትናም ይዞት የመጣውን ጠብመንጃ ይዞ ወደ ሎስ አንጀለስ የሸሸው። ታድያ ራፋዔል ጣልያን ውስጥ እንደ ጀግና ነበር የታየው። የአዕምሮ ጭንቀት እንዳለበት አንድ ወጣት ሳይሆን በምድር ገስግሶ፤ ዳመናውን ጥሶ፤ አገሩን ብሎ የመጣ ወጣት። ቢሆንም ከፍርድ አላመለጠም። ነገር ግን ወደ አሜሪካ መልሰው ሊሰዱት አልፈቀዱም። ራፋዔል በጣልያን የአየር ክልል ውስጥ ብቻ የፈፀመው ወንጀል ታይቶ የሰባት ዓመት ተኩል ቅጣት ተፈረደበት። ወዲያውም ፍርዱ እንዲቀል ተደርጎ ከሁለት ዓመት በኋላ [ግንቦት 1971] ተለቀቀ። ራፋዔል ሚኒቺዬሎ [በስተግራ በኩል] እና ኦቲስ ተርነር [በስተቀኝ] ከሌሎች የጦር አውድማ ጓዶቻቸው ጋር ከዚያም መኖሪያውን ሮም በማድረግ አንድ መጠጥ ቤት ውስጥ ሰራተኛ ሆኖ ኑሮውን ይገፋ ጀመር። የመጠጥ ቤቱን ባለቤት ልጅም አግብቶ ልጅ ወልደ። አንድ ሰሞን ፒዛ ቤት ከፍቶ ነበርም ይባላል። የፒዛ ቤቱን የንግድ ስም 'ሃይጃኪንግ' [መጥለፍ] ብሎ ሰይሞትም ነበር። ከጠለፋው 30 ዓመታት በኋላ በ1999 (እአአ) ራፋዔል ሚሊቺዬኖ ወደ አሜሪካ ተመለሰ። እዚያም ከጠለፋው ጋር በተያያዘ ምንም ዓይነት ክስ አልጠበቀውም። ነገር ግን ከጠለፋው በፊት በፈፀመው አነስተኛ ወንጀል ምክንያት ወታደራዊ ታሪኩ እንዲፋቅ ተደረገ። ታድያ አሜሪካ የመጣው በዓላማ ነበር፤ በጠለፈው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሰዎችን እያገኘ ይቅርታ መጠየቅ። ይህን ማድረግ ያሰበው ደግሞ ከጦር አውድማ ጓደኞቹ ጋር በመሆን ነበር። የበረራ አስተናጋጆች እና የተወሰኑ አብራሪዎችን አግኝቶ ይቅርታ ጠይቆ ይቅርታ መቀልም ቻለ። ቢቢሲ ራፋዔልን ለማናገር ጥረት ቢያደርግም ታሪኩን በፊልም መልክ ለመሰነድ ዕቅድ ከያዘ ድርጅት ጋር በመዋዋሉ ምክንያት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።
news-48144716
https://www.bbc.com/amharic/news-48144716
ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ፡ "ከውጪ የገቡ ሚዲያዎች 'ማገገምያ' መግባት ያለባቸው ይመስለኛል"
በተደጋጋሚ እየተገለፀ እንዳለው በአዲሱ ጠ/ሚ እና በለውጥ ሃይል መምጣት የፖለቲካ ምህዳሩን መስፋት ተከትሎ ሚዲያውም ከፈት ብሏል።
አሸባሪ የተባሉና በውጭ የነበሩ ሚዲያዎች መግባታቸው፣ በመንግስት ተዘግተው የነበሩ ድረ ገፆች ዳግም መከፈታቸው፣ በውጪ ሃገር ስርዓቱን ሲታገሉ የነበሩ ጋዜጠኞች ወደ ሃገር መግባት፣ አገር ውስጥ እስር ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች መለቀቅ ፣ የህትመት ውጤቶችና መገናኛ ብዙሃን በመበርከታቸው የተለያዩ ሃሳቦች እየተንፀባረቁ መሆኑ ትልቅ አዎንታዊ እርምጃ ነው። ይህ የሚዲያ ክፍት መሆንና ነፃነት ለማህበረሰቡ ምን አመጣ? ማህበረሰቡን ወደ ውይይትና መግበባት አምጥቷል ወይ? የሚለው ግን አሁንም ጥያቄ ነው። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጠኝነት ትምህርት ቤት የቀድሞ ዲን የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካው ኒው ሜክሲኮ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩት ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይን ከለውጡ በኋላ የሚዲያውን እንቅስቃሴ በማስመልከት አነጋግረናቸዋል። • አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጋዜጠኞች ተስፋ • የፕሬስ ነፃነት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚዲያው ከፈት ከማለቱ ምን ተገኘ? ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ፡ ሚዲያው መከፈቱ ወሳኝ አዎንታዊ እርምጃ ነው። ነፃነቱም በጣም አስፈላጊ ነው ። ነገር ግን ጥያቄ የሚሆኑ ነገሮችም አሉ። ከውጭ የገቡት ሚዲያዎችን ስንመለከት በጫና ከሃገር የወጡ፤ ሙያው የሚመራቸው ሳይሆን ሥርዓቱን ሲታገሉ የነበሩ ነፃ አውጪዎች ናቸው። ስለዚህ አገር ቤት ቢገቡም ከነፃ አውጪነታቸው በሙያ ወደሚመራ ሚዲያ የሚያደርጉት ሽግግር ቀላል አይሆንም። አሁንም የቀደመ የነፃ አውጪነት መንፈስ የለቀቃቸውም አይመስልም። ጋዜጠኞቹ ራሳቸው ናቸው ፤ አሠራራቸውም ያው እንደቀደመው ነው። ስለዚህ ቢሯቸውን ቀይረው አዲስ አበባ ስለከተሙ ብቻ ሙያውን ተከትለው ይሠራሉ ማለት ይከብዳል። በትጥቅ ትግል ኢህአዴግን ሲታገሉ የነበሩ ወደ አገረ ቤት ሲገቡ ትጥቅ ፈትተውና ተሃድሶ ወስደው ነው ወደ ማኅበረሰቡ የተቀላቀሉት። በተመሳሳይ የነፃነት ትግል ላይ የነበሩ ሚዲያዎችም ማገገሚያ መግባት ያለባቸው ይመስለኛል። መስመራቸውን አስተካክለው፣ ቅኝታቸውን ቀይረው ነው የአገር ውስጥ ሚዲያውን መቀላቀል ያለባቸው። የመንግሥት መሣሪያ በመሆን ይተቹ የነበሩት የሕዝብ መገናኛ ብዙኃንስ? ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ፡ የመንግስት ፕሮፖጋንዳ መሳሪያ በመሆን ይተቹ የነበሩት የመንግስት ሚዲያዎችም ልጓሙ ተነሳላቸው ቢባልም እያንዳንዳቸው የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ይዘው ወደ ወገናቸውና ወደ ጎጣቸው ነው የሄዱት። በተለይም የክልል ቴሌቭዥኞች በፕሮከፖጋንዳ የተጠመዱ ፤ የሚያናግሯችው ምሁራንም ከአንድ ውሃ የተቀዱ ነው የሚመስሉት። ዘገባቸው የማህበረሰቦች መስተጋብር ላይ ነውጥ እያነገሰ እንጂ ለአገርና ለማህበረሰብ ጥቅም እየሰራ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። እነዚህ ሚዲያዎች ምናልባትም ከነበሩበት ሁሉ የባሰ አደገኛ መስመር ላይ ነው ያሉት። ሚዲያዎቹ በዚሁ ቀጥለው ምርጫ የሚኖር ከሆነ ነገሮች ይበልጥ ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ። መንግሥት ሚዲያውን ከፈት ሲያደርግ አብሮ የመረጃ በሮችንም ከፍቷል ብለው ያስባሉ? ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ፡ መረጃ የማግኘት ችግር የባሰበት ነው የሚመስለኝ። በፊት በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ከኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ማግኘት ይቻል ነበር። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ፈርሶ ነገሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬስ ሴክሬታሪ ስር ከተጠቃለለ በኋላ ግን አዲሱ ቢሮ በአግባቡ መረጃ ለጋዜጠኞች እንዲደርስ እያደረገ አይመስልም። የሚፃፉ ነገሮች ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረቱ አለመሆን የሚያሳየውም ይህንኑ ነው። አብዛኛው በስማ በለው እየፃፈ ያለ ነው የሚመስለኝ። ለውጥ ላይ ስላለን ነው ሊባል ይችላል። ነገር ግን ብዙዎች እንደሚሉት እውነት ለውጥ ላይ ነን ወይ? ለውጥም ሽግግርም ላይ ነን ብዬ አላስብም እኔ። ይልቁንም አገሪቷ ባልሰራው አሮጌውና ባልተወለደው አዲሱ ስርዓት መካከል ውዥንብር ውስጥ ነው ያለችው። ሚዲያውም የዚህ ፖለቲካ ነፀብራቅ ነው። በእርግጥ ፖለቲካው ነውጥ ውስጥ እያለ ሚዲያውን ስርዓት አስይዛለሁ ማለትም ከባድ ነው። • 'ለአደጋ የተጋለጠው' የኢትዮጵያ ህትመት ሚድያ የሚዲያ መብዛት ጥሩ ቢሆንም የአገሪቱ የሚዲያ ኢኮኖሚ ቁጥሩን ሊሸከም የሚችል ነው ? ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ፡ የሚዲያ ኢኮኖሚው ይህን ሁሉ ይዞ መቀጠል የሚችል አይደለም። ከዚህ በፊትም ስንጮኸበት የነበረ ጉዳይ ነው። ሚዲያ ዝምብሎ የሚያብብ ነገር አይደለም። ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል፤ ለመንቀሳቀስ ገቢ ማግኘት አለባቸው። በበዙ ቁጥር ኢኮኖሚው ከሚሸከመው በላይ ስለሚሆኑ ገበያ ውስጥ ለመቆየት ሲታገሉ በተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎች እጃቸው የመጠምዘዝ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል ፣ የራሳቸው የሆነ አድማጭ ተመልካች ለመፍጠርና ለመያዝ እውነተኛ ጋዜጠኝነት ሳይሆን ነገር ወደ ማራገብ ፣ አንድ የፖለቲካ አቋም ላይ ቸክሎ የመሄድ ነገር ይመጣል። ይህ ነገር የብሄራዊ ጥቅምን ሁሉ አደጋ ላይ ሊጥል የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው። የማህበረሰቡ የአብሮነት ጉዞ ላይም አደጋ ያመጣል ፤ ሽግግሩንም የማደናቀፍ እድል አለው። አሁንም እያየን ያለነው በዚህ አቅጣጫ የተቃኙ ነገሮች ይመስላሉ። ነፃነቱ ቁጥጥርም ስርዓትም የሌለው ከመሆኑ የተነሳ እንዲያውም ወደ ሚዲያ ስርዓት አልበኝነት እየሄደ ነው። ነፃነቱም መስመር ሊበጅለት ይገባል። የአገሪቱ ፖለቲካ በብሄር ላይ የተመሰረተና ብዙ አይነት ውስብስብ ችግር ያለበት ከመሆኑ አንፃር ሚዲያው በሚዛናዊነትና በጥንቃቄ ካልሰራ አብሮነትን የማፍረስ የብሄር ግጭትንም የመቀስቀስ እድሉ ሰፊ ነው። በክልል ቲቪ እና ሬዲዮዎች የሚተላለፉ ነገሮች ሲታዩ በአንድ አገር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ማእቀፍ ውስጥ ሳይሆን የተለያየ አገር ላይ እንዳሉ ወይም እንደ ራስ ገዝ አስተዳደር እያሰበ ዘገባውን ከክልሉና ከብሄሩ አንፃር የሚሰራ ነው የሚመስለው። ፖለቲከኞችም የኔ ነው በሚሉትና እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ይዘግባል ለሚሉት ሚዲያ ብቻ ነው ሃሳባቸውን እየገለፁ ያሉት። • የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ የሚዲያ ነፃነቱን ተከትሎ እየመጣ ያለ አደጋም አለ? ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ፡ ሚዲያው መከፈቱ መልካም ሆኖ ሳለ ነፃነቱ ስርዓት የተበጀለት አለመሆኑ አደጋ አለው። በተለይም አጠቃላይ የፖለቲካ ስርዓቱ የሽግግር ውዥንብር ውስጥ ባለበት በዚህ ጊዜ ሚዲያው በዚሁ ከቀጠለ አገሪቱን ከባድ ነገር ውስጥ ሊከታት ይችላል። ኢህአዴግ ስልጣን በያዘ ማግስት ሚዲያው እንዳሁኑ ክፍት ተደርጎ ነበር። ሚዲያውን መክፈትና ሰዎች በነፃነት ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ማድረግ ከቀድሞ ስርዓት የተሻልኩ ነኝ ያለበት ነበር። ነገር ግን ሚዲያው ሃላፊነት የጎደለው ስለነበር ፣ ስርዓቱ ችግሮችን ለመታገስ ባለመፈለጉ ነፃነቱ አልቀጠለም። አዲስ ስርዓት ሲመጣ ሁሌም ሚዲያን ክፍት ማድረግ የተለመደ ነው። ነፃነት ከሃላፊነት ጋር የሚመጣ ነገር ካልሆነ በጣም አደገኛ ነው። ነፃነት ከሃላፊነት ውጭ ትርጉም የለውም የሚወስደው ወደ ስርዓት አርበኝነት ነው። በውጭም በአገር ውስጥ ያሉ ፖከቲከኛው፣ አክቲቪስትና ጋዜጠኛው ሁሉ ግባ ተብሎ ሜዳው እንዴት ነው መስመርና ስርዓት መያዝ ያለበት የሚለው ነገር ላይ የተሰራ ነገር የለም። ስለዚህም በዚህ አንገብጋቢ ሰዓት ሁሉም እንደመሰለው በግራም በቀኝም እየሄደ በዚህ አንድ ዓመት የሚዲያ ነፃነቱ ጠብ ያደረገው ነገር የለም። ሚዲያው ቁጥጥር ያስፈልገዋል። ነገር ግን መንግሥት ሳይሆን ሚዲያው ራሱን እንዲቆጣር ነው የሚመከረው።አሁን ሚዲያው ራሱን መቆጣጠር የሚችል ይመስልዎታል? ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ፡ የፖለቲካ ለውጥ ሲመጣ የሚዲያ ነፃነትም ይመጣል። ዋናው ነገር ነፃነቱን ይዞ ለመቀጠል በጣም ሃላፊነት የተሞላበት ጋዜጠኝነትን መገንባት እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ነው። ይህ ካልሆነ ግን ነፃነቱ የአጭር ጊዜ ነው የሚሆነው። ነፃነቱን ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ተጠቀማችሁ ብሎ ጫን የሚል ሃይል እንደሚመጣ ማሰብ አስፈላጊ ነው። ሃላፊነትና ተጠያቂነትን ይዞ ነው ሚዲያው ነፃነቱን ማጣጣም ያለበት። የተቋቋመው ሚዲያ ካውንስልስ ሚዲያው ራሱን እነዲቆጣጠር ሃላፊነቱ መወጣት ይችላል ብለው ያምናሉ? ዶ/ር አብዲሳ ዘርአይ፡ በሚዲያ ካውንስሉ ምስረታ ላይ ብዙ ሚና ስለነበረኝ ከሚዲያ ባለቤቶቹንና ከሌሎቹም ጋር አብሬ ሰርቻለሁ። አንዳቸው ሌላውን ያለመቀበል ነገር ያላቸው ናቸው። ሚዲያ ካውንስሉ ስርዓት ይዞ በአሁኑ ወቅት ወደ ስራ እንዳይገባ ያደረገው አንዱ የሚዲያ ተቋማትና አመራሮች አንዳቸው ሌላውን ያለመቀበልና ያለመተማመንም ችግር ስላለ ነው። ቀደም ሲል ካውንስሉን መስመር ለማስያዝ ተብሎ በዩኔስኮ ተመድቦ የነበረ በጀት በማን የባንክ ሂሳብ ይግባ በሚለው መስማማት ባለመቻላቸው ለሌላ የአፍሪካ አገር ሄዷል። ከዚህ በመነሳት ስለ ሚዲያ ካውንስሉ ውጤታማነት በሙሉ ልብ የምናገረው ነገር የለም። ነገር ግን ለሚዲያውም ጤንነት የተገኘውንም ነፃነት ዘላቂ ለማድረግ ሚዲያው በሚዲያ ካውንሰሉ አማካኝነት ራሱን እንዲቆጣጠር ነው የምፈልገው።
news-53422739
https://www.bbc.com/amharic/news-53422739
አጥፊዎች እንዲጠየቁ፣ የተጎዱ እንዲካሱና እንዲቋቋሙ እንሰራለን፡ ኢሰመኮ
የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በተፈጠረ ሁከትንና በተፈጸሙ ጥቃቶች ከ200 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት መውደሙ ይታወቃል።
ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በዚህም ሳቢያ በድርጊቱ ውስጥ እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ 5 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕረስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ከእነዚህ ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉ ኃላፊዎችና የፀጥታ አካላት ይገኙበታል። ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ ስለደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና አያያዝን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነሩ ዳንኤል (ዶ/ር) ከሁለት ሳምንት በፊት በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተከሰተውን ለሰዎች ሞትና ለንብረት ውድመት የሆነውን ክስትት "በጣም አሳዛኝ ነው" በማለት የገለጹት ሲሆን፤ ይህንንም ተከትሎ ኮሚሽኑ የደረሱ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል። በመሆኑም የተፈፀመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓይነት እና የጉዳት መጠን ለይቶ ለማወቅ እንዲሁም አጥፊዎቹ በሕግ እንዲጠየቁ፣ የተጎዱ ሰዎች ደግሞ እንዲካሱና መልሰው እንዲቋቋሙ ለማስቻል የሚረዳ ጥናት ለማካሄድ አንድ ቡድን መቋቋሙን አመልክተዋል። ከዚህም ባሻገር አሁንም ሙሉ ፀጥታና መረጋጋት ያልሰፈነባቸው አካባቢዎች ላይ ወይም ጉዳቱ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው ሕግ የማስከበር እርምጃ፤ ከተፈጠረው ችግር ጋር ምን ያህል ተመጣጣኝ እንደሆነ ለማረጋገጥና ከሁከቱ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች አያያዝ ሕጋዊነትን ለማወቅ ክትትል እያደረጉ እንደሆነ ኮሚሽነር ዳንኤል (ዶ/ር) ለቢቢሲ አብራርተዋል። ኮሚሽነሩ ከሁከቱ ጋር ተያይዞ መንግሥት የሰጠውን ምላሽ በተመለከተ ጥናት እያደረጉ እንደሆነ እስካሁን ባላቸው ቅድመ ምልከታና መረጃ መሠረት በአብዛኛው የፀጥታ አስከባሪዎች ሚና ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን፤ የፀጥታ አካላት ባይደርሱ ኖሮ ጉዳቱ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። የሚቀርበው አብዛኛው ቅሬታም "የፀጥታ አካላት ሕብረሰተቡን ለመጠበቅ በወቅቱ አልደረሱም" የሚሉ እንጂ በፀጥታ አስከባሪዎቹ ጉዳት ደረሰብን የሚሉ አይደሉም ብለዋል። ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ የፀጥታ ኃይሎች ሕግ በማስከበር ሂደት ከሚጠበቀው መስመር በመውጣት የተወሰዱ እርምጃዎች እንደሚኖሩ ግምት መውሰዳቸውን ኮሚሽነር ዳንኤል ተናግረዋል። የእስረኞች አያያዝ ኮሚሽነር ዳንኤል (ዶ/ር) ታሳሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ከአንዴም ሁለት ጊዜ ሄደው እንደተመለከቱና እንዳነጋገሩ አስታውሰዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ታሳሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ጀምሮ ድብደባ ማሰቃየት ተፈፅሞባቸዋል የሚል የተሳሳተ መረጃ በስፋት ይሰራጭ ነበር ብለዋል። በተለይ ወሬው አቶ እስክንድር፣ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 35 ሰዎች መታሰራቸው ይፋ መሆኑ ከታወቀ በኋላ በነበረው ጊዜ በስፋት ይናፈስ እንደነበር ያስረዳሉ። ሁሉም ታስረው የነበሩት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት ውስጥ እንደነበር የሚገልፁት ኮሚሽነሩ፤ ከአቶ እስክንድር ነጋ እና ኦኤምኤን ድረ ገፅ ላይ እንደሚሰሩ ከገለፁላቸው አቶ አህመድ ጠሃ በስተቀር ሁሉም እንዲህ ዓይነት አቤቱታ እንዳላሰሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል። ታሳሪዎቹን በጎበኟቸው ወቅትም "አቶ ጀዋር መሐመድንና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ አንዳንድ ታሳሪዎች የእስር አያያዛቸው ደህና እንደሆነ አረጋግጠውልናል" ብለዋል። "አቶ እስክንድር ነጋና አቶ አህመድ ጣሃ የተባሉት ታሳሪ ግን በእስር ወቅት ድብደባ እንደደረሰባቸው ገልፀውልናል" የሚሉት ኮሚሽነሩ፤ በጎበኟቸው ጊዜ በመልካም አካላዊ ጤንነት ላይ ነበሩ ብለዋል። አቶ እስክንድር በፖሊስ ድብደባ እንደፈፀመበት መግለፁን ተናገረው፤ ጉዳዩን ከፖሊስም ለማጣራት በሞከሩበት ወቅት በእስር ወቅት 'ፍጥጫ' ተፈጥሮ እንደነበር መስማታቸውን ገልፀዋል። ጉዳዩ እንዲጣራና ተገቢ እርምጃ እንዲወሰድ ምክረ ሃሳብ መስጠታቸውንም ኮሚሽነር ዳንኤል ( ዶ/ር) አክለዋል። ለሁለተኛ ጊዜ ታሳሪዎችን ለመጎብኘት በሄዱበት ወቅትም ከዚያ በኋላ አቶ እስክንድር ምንም አይነት ድብደባ እንዳልደረሰባቸው እንዳረጋገጡላቸው አስረድተዋል። የቀረቡ ሌሎች ቅሬታዎች ምንድን ናቸው? ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት አለማቻል ቀዳሚው ቅሬታ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነር ዳንኤል ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ ከቤተሰብ ጋር መገናኘትና ምግብና ልብስ መቀበል ታግዶ ስለነበር እስረኞቹ ይህንን እንደ ቅሬታ አቅርበዋል ብለዋል። ይህንን በሚመለከትም ከእስር ቤቱ አስተዳደር ጋር መነጋገራቸውንና በተወሰነ መጠን መሻሻሉን እንደሚያውቁ ገልፀዋል። ነገር ግን ይህ ችግሩ በአዲሶቹ እስረኞች ላይ ብቻ ሳይሆን ቀደም ብለው የታሰሩት ላይም ተግባራዊ የተደረገና ከወረርሽኙ መከላከል ጋር ተያይዞ የተወሰደው እርምጃ ያስከተለው ውጤት ነው ብለዋል። ያሉበት የማይታወቁ እስረኞች ስለመኖራቸው በተመለከተም፤ በተለይ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ስር የታሰሩ የኦፌኮ አባላት፣ የኦነግ አመራሮች እና ሌሎች አንዳንድ እስረኞች ከቤተሰባቸው ጋር ቶሎ የሚገናኙበት እድል ባለመፈጠሩ "የታሰሩበትን አናውቅም" የሚል አቤቱታ እንደቀረበላቸው የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ በጉዳዩ ላይ ክትትል እያደረጉ እንደሆነና በአፋጣኝ መስተካከል እንደሚገባው አሳስበዋል። ከዚህ በተጨመሪም "አቃቤ ሕግና ፖሊስ እስረኞችን በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት መልካም ቢሆንም፤ አሁንም በ48 ሰዓታት ያልቀረቡ እስረኞች አሉ" ብለዋል ኮሚሽነር ዳንኤል ። ሁሉንም እስር ቤቶችና እስረኞችን ጎብኝተው ያልጨረሱ ቢሆንም በፌደራልና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሥር ያሉ ታሳሪዎችን ግን ማየታቸውን ገልፀዋል። ጭሮ፣ ቡራዩ እና አርሲ ነገሌ እንዲሁም ዴራ በርካታ እስረኞች ስለመኖራቸው መረጃ እንደደረሳቸው የገለፁት ኮሚሽነር ዳንኤል፤ ክትትል ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸው ለቢቢሲ አስረድተዋል። ኮቪድ-19 እና የእስረኞች ቁጥር መበራከት በሺህ የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ባሉበት ሁኔታ የወቅቱ አሳሳቢ የጤና ችግርን ጉዳይ አብሮ የሚነሳ ነገር ነው። ይህንንም ስጋት በተመለከተ ኮሚሽነሩ "ፖሊስና አቃቤ ሕግ እንዳስታወቀው ምርመራው እየተፋጠነ ሲሄድ የሚለቀቁ ታሳሪዎች ሊኖሩ ይችላሉ" የሚል እምነት እንዳላቸው ይገልፃሉ። ከዚህም ባሻገር በእስር ቤቶች ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑን መመልከታቸውን አክለዋል። ከእነዚህም ጥንቃቄዎች መካከልም፤ አልፎ አልፎ በሚደረግ የናሙና መረጣም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ምርመራ፤ አዲስ ታሳሪዎች ከእስረኞች ጋር ከመቀላቀላቸው በፊት የሙቀት ልኬት፤ ምልክት አለባቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ካሉም ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ እንደሚደረግ መታዘባቸውን ተናግረዋል። "የምግብና የልብስ አለመግባቱ ዓላማም የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት ከተወሰዱ እርምጃዎች አንዱ ነው፤ የአቅም ውስንነት ስላለ በሚፈለገው መልኩ የተሟላ ነው ማለት ግን አይቻልም " ብለዋል። የመገናኛ ብዙሃን መዘጋትና የጋዜጠኞች መታሰር ይህንን በተመለከተ መንግሥት "ሕግ ጥሰዋል" በሚል በእነዚህ አካላት ላይ ክስ ማቅረቡ በማስታወስ፤ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት የምርመራውን ውጤት መጠበቅ ግድ ይላል ብለዋል ኮሚሽነሩ። "በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ቀውስ ሚዲያ ሚና አልነበረውም ማለት አይቻልም፤ ሚዲያ በዚህ ውስጥ ሚና የነበረው መሆኑ አከራካሪ አይመስለኝም" የሚሉት ኮሚሽነር ዳንኤል፤ የትኞቹ ሚዲያዎች ምን ዓይነት ሚና ነበራቸው የሚለው በማስረጃ የሚረጋገጥ መሆኑን ገልፀዋል። ነገር ግን "በምርመራው ሂደት ጣልቃ ባንገባም ሂደቱ ምን ያህል ሕጋዊና ፍትሃዊ መሆኑን ለማረጋጋጥ መታዘባችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
47743552
https://www.bbc.com/amharic/47743552
ዓለም ለሴቶች እንዳልተሰራች የሚያሳዩ ነገሮች
ካሮላይን ክሪያዶ ፔሬዝ ነገሮች ሁሌም ከወንዶች አንፃር ብቻ መቃኘታቸውንና ይህች ዓለም እንዴት ለወንድ ብቻ እንድትሆን ተደርጋ እየተቀረፀች እንዳለ ጥናት መስራት የጀመረችው በአንድ ወቅት የልብ ህመምን በሚመለከት የተሰበሰቡ መረጃዎች ሁሉ በወንዶች የህመሙ ምልክት ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆናቸውን ካስተዋለች በኋላ ነው።
ጡትን ከግንዛቤ ካልከተቱት የፖሊስ ጥይት መከላከያ ልብሶችና ጫማዎች ጀምሮ በርካታ ነገሮች ወንድን ብቻ ታሳቢ በማድረግ የተሰሩ እንደሆኑ ትናገራለች። የህዋ ልብሶች በአንድ ወቅት ናሳ ሴቶች ብቻ ወደ ህዋ የሚያደርጉትን ጉዞ በመሰረዙ በትዊተር ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበት ነበር። ጉዞው የተሰረዘው ጠፈርተኛዋ አኒ ማክሌን ከዚህ በፊት ትለብስ የነበረው የህዋ ጉዞ ልብስ ትልቅ የነበረ ቢሆንም ሙሉ የሴት ቡድን በሚያደርገው ጉዞ ላይ ግን መካከለኛ መጠን ያለው ልብስ የበለጠ ልኳ ስለሆነ እሱን እለብሳለሁ በማለቷ ነበር። • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? የህዋ ልብሶቹ ወንዶችን ብቻ ታሳቢ አድርገው የሚሰሩ በመሆናቸው ትልቅ፣ በጣም ትልቅና ምናልባትም መካከለኛ መጠን ብቻ እንዲኖራቸው ተደርገው ነው የተሰሩት፤ ትንሽ ሚባል ነገር የለም። በወቅቱ በናሳ ሁለት መካከለኛ መጠን ያላቸው የህዋ ልብሶች የነበሩ ቢሆንም ለጉዞ ዝግጁ ተደርጎ የነበረው ግን አንዱ ብቻ ነበር። የጦር መሳሪያዎች እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 አሜሪካ ቀደም ሲል ወንዶችን ብቻ ትመለምልበት ለነበረው የምድርና ባህር ኃይል ክፍል ሴቶችን መመልመል ብትጀምርም በእነዚህ ክፍሎች ያሉ የጦር መሳሪያዎች ሁሉ ግን ለወንድ ብቻ እንዲመቹ ሆነው የተሰሩ ናቸው። የዲሞክራቲክ ፓርቲዋ የኮንግረስ አባል ኒኪ ሶንጋስ ይህ የአገሪቱ ጦር ኃይል ምን ያክል ለሴት አባላቱ ፍላጎቶች ምላሽ እንደማይሰጥ ማሳያ መሆኑን ተናግረው ነበር። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና በዚህ ምክንያት ሴት ወታደሮች መሳሪያ ለመተኮስና የጥይት መከላከያ ልብሶችን መልበስ እንኳ እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። እንደ አውሮፓውያኑ ባለፈው ዓመት የጦር ኃይሉ ለሴቶች ምቹ የሆኑ መሳሪያዎችን እንደሚያቀርብ አስታውቆ ነበር። በሴቶች የወታደራዊ አገልግሎት ላይ ጥናት የሰሩት አሌክስ ኤሊያስ "ሴቶች እስከ 2018 ለወንዶች በተሰሩ መሳሪያዎች በኢራቅና በአፍጋኒስታን ተሰማርተው ነበር" ብለዋል። ስማርት ስልኮች የስማርት ስልክ መተግበሪያዎችና የስልኮቹ መጠን ራሱ ለወንዶች እንዲሆኑ ተደርገው ተሰርተዋል ብለው የሚያስቡ ብዙ ሴቶች ናቸው። በአማካይ የሴቶች እጅ ከወንዶች በአንድ ኢንች የሚያንስ ሲሆን የስማርት ስልክ አምራች ኩባንያዎች ደግሞ የስልኮቹን መጠን እያሳደጉ መምጣታቸው ችግር ነው ይላሉ። 12 ሴ.ሜ በሆነ ወይም በትልቅ አይፎን በአንድ እጅ ስልክን ይዞ መልዕክት መላክ ለበርካታ ሴቶችና ትንሽ እጅ ላላቸው ወንዶች ከባድ ወይም የማይቻል ነው። የስፖርት ልብሶች ታዋቂው የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ስቴፈን ከሪ አዲስ የህፃናት የስፖርት ጫማ ንድፍ ሲያወጣ የሰራው ለወንዶች ብቻ የነበረ ሲሆን፤ አንዲት የዘጠኝ ዓመት ህፃን ለምን የወንዶች ብቻ የሚል ደብዳቤ ፅፋለት ነበር። "የሴቶችን የሩጫ ስፖርት እንደምትደግፍ አውቃለሁ ምክንያቱም ሁለት ሴቶች ልጆች አሉህ" በማለት ስህተቱን እንደሚያርም ተስፋ እንደምታደርግ ገልፃ ነበር። • ሴቶች በሰሜን ኮሪያ ሠራዊት ውስጥ እሱም ህፃኗን ስለደብዳቤዋ አመስግኖ ስለተፈጠረው ነገር ማብራሪያ ሰጥቷል። ሳይንሳዊ መሳሪያዎች በካንሳስ አልያንስ የባይሎጂ ተመራማሪ የሆኑት ጀሲካ ማውንትስ በቤተ ሙከራ የሚጠቀሟቸው የምርምር መሳሪያዎች በሙሉ ለወንድ ተብለው የተሰሩ እንደሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ ይህ መሆኑ ደግሞ የሚረብሽ ብቻ ሳይሆን ለአደጋ ስጋት እንደሚሆንም ይናገራሉ። ሰፋፊ ገዋኖች እንቅስቃሴ ላይ በቁሳቁሶች ሲያዙ ትልልቅ ቡትስ ጫማዎች ደግሞ ለመውደቅ ይዳርጋል። የሥራ ቦታዎች የታሪክና ሌሎችም ምሁራን ወንበሮችና ሌሎችም የቢሮ እቃዎች ለወንዶች ምቹ እንዲሆኑ ተደርገው መሰራታቸውን የሚመለከቱ ጥናቶችን አድርገዋል። ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆኑት የታሪክ ምሁሯ ዋጅዳ ሺርሊ በኩባንያዎች ውስጥ ሁሌም ስለ ቡድን ሥራ ውጤታማነት እንደሚወራ፤ ነገር ግን ይህ ትርጉም እንደማይሰጥ "ምቹ በሆነ አካባቢ ሳይቀመጥ ማን ስለ ቡድን ስራ ሊጨነቅ ይችላል?" በማለት ያስረዳሉ።
news-55127135
https://www.bbc.com/amharic/news-55127135
ኢራን ፡ ጎምቱውን የኒኩሊየር ሳይንቲስት ማን ገደላቸው? ለምን?
ሰውየውን እንኳንስ ሌላው ዓለም፤ ኢራኒያዊያንም በቅጡ አያውቋቸውም። ካለፈው አርብ በፊት ስማቸውን የሚያውቅ ኢራናዊ ብዙ አልነበረም።
ሳይንቲስቱን ሙህሲን ፋኽሪዳዛን በርካታ ኢራናዊያን ባያውቋቸውም ቅሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጠንቅቀው ያውቋቸዋል። ኢራናዊያን ባያውቋቸውም የሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ግን መሐመድ ቢን ሰልማን አሳምረው ያውቋቸዋል። ኢራናዊያን ባያውቋቸውም የአሜሪካ የደኅንነት ሰዎች አሳምረው ያውቋቸዋል። የኢራን ሚዲያ ጉምቱውን ሳይንቲስት ሙህሲን ተገድለውም ስማቸውን ማግነን አልፈለጉም። እንዲያውም ብዙም ቁልፍ ሰው እንዳልነበሩ ነው የሚያወሱት። "ሰውየው አገር በቀል የኮቪድ-19 መድኃኒት ለመፍጠር ተመራማሪ ነበሩ" ሲሉ ነው ስማቸውን የሚያነሷቸው። ማርክ ፊዝፓትሪክ በለንደን የስትራቴጂ ጥናት ተቋም ተመራማሪ ናቸው። የኢራንን የኒክሉየር ፕሮግራም በቅርብ ከሚከታተሉ ምሁራን አንዱ ናቸው። ግድያውን ተከትሎ በጻፉት የትዊተር መልዕክት "የኢራን ኒኩሊየር ፕሮግራም በአንድ ግለሰብ ላይ የሚንጠለጠልበት ዘመን አልፏል" ሲሉ የሰውየው ሞት መሬት ላይ ብዙም የሚቀይረው ነገር እንደሌለ አስገንዝበዋል። ሆኖም ሳይንቲስቱ የዋዛ እንዳልነበሩ የሚያውቁ ያውቃሉ። በተገደሉበት ወቅትም ከፍተኛ አጀብ ውስጥ ነበሩ። ይህም የሳይንቲስቱን ቦታ የሚጠቁም ነው። ይህን ሁሉ ጥበቃ አልፈው የሰውየውን ነፍስ ከነጠቁት ነፍሰ ገዳዮቹ ጀርባ ማን እንዳለ የሚጠቁም ነው። እስከአሁን ለሳይንቲስቱ ሞት ኃላፊነት የወሰደ የለም። ነገር ግን እርምጃው ፖለቲካዊ እንዲመስል ነው የተደረገው፣ ከኒኩሊየር ጋር ላለማያያዝም ተሞክሯል። ይህ የኢራንም ፍላጎት ጭምር ነው። በዚህ ረገድ ሁለት ምክንያቶች ጎልተው ይነሳሉ። አንዱ የጆ ባይደን መምጣት ነው። የትራምፕ በጆ ባይደን የመሸነፍ እውነት ኢራን የሻከረ ግንኙነቷ እንዲለሰልስ የሚያደርግ ዕድል ይዞ ይመጣል የሚል ፍርሃት አለ። ይህ ከኢራን ጠላቶች መርዶ ነው። ሁለተኛው መላምት ኢራንን በጉምቱው ሳይንቲስት ግድያ አስቆጥቶ ስሜት ውስጥ በመክተት የአጸፋ እርምጃ እንድትወስድ ለማድረግ ነው። የአጸፋ እርምጃ ከወሰደች ደግሞ አካባቢው ሌላ ዙር ረብሻ ውስጥ ስለሚገባ የባይደን ወደ ስምምነቱ መመለስን ያዘገይ ይሆናል የሚል ነው። የኢራኑ ፕሬዝዳንት ግድያውን ተከትሎ "ጠላቶቻችን አስጨናቂ ሳምንት ነው እያሳለፉ ያሉት" ያሉትም ይህንኑ ለማመላከት ነው። "ዓለም አቀፉ ሁኔታ እየተቀየረ እንደሆነ ጠላቶቻችን ተገንዝበዋል። ያልተረጋጋ ሁኔታ ለመፍጠር የሞከሩትም ለዚህ ነው" ብለዋል የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሩሐኒ። ሩሐኒ የኢራን ጠላቶች ሲሉ የትራምፕ አስተዳደርን፣ ሳዑዲንና እስራኤልን ማለታቸው ነው። ኢራንና ሳዑዲ የጆ ባይደን መምጣትና በትራምፕ መውጣት ምቾት ሊሰማቸው አልቻለም። ይህ ሁኔታም መካከለኛው ምሥራቅን የፖለቲካ አሰላለፍ በተወሰነ ደረጃ የሚቀይር ውጤት ሊኖረው ይችላል። ሳይንቲስቱን ሆስፒታል ውስጥ ለሞት ያበቃው ጥቃት የተፈጸመበት መኪና ጆ ባይደን በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ግልጽ እንዳደረጉት ወደ ኢራን የኒኩሊየር ስምምነት መመለስን ይሻሉ። ይህ ስምምነት በባራክ ኦባማ ዘመን ጆ ባይደን ምክትል ሳሉ የጸና ነበር፤ ትራምፕ እስኪሰርዙት ድረስ። በዚህ ለውጥ ፖለቲካዊ ድንጋጤ ውስጥ የገቡት ሳዑዲና እስራኤል በድብቅ ተገናኝተው ለመምከርም ተገደዋል። ናታንያሁና ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን በአዲሷ የሳዑዲ ከተማ ኒዮም እሑድ ዕለት በምስጢር መገናኘታቸው የእስራኤል ሚዲያዎች አጋልጠዋል። የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግን የናታንያሁ ወደ ሳዑዲ፣ ኒዮም መምጣት ዜና ሐሰት ነው፤ አልተወያየንም ብለዋል። ናታንያሁ በዚህ ኒዮም በተሰኘችው አዲስ ከተማ ውስጥ በነበረው ዝግ ስብሰባ ልዑል አልጋ ወራሹን መሐመድ ቢን ሰልማንን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እንደ ሳዑዲና ባህሬን እንዲሁም ኢምሬትስ ሁሉ ለማደስ ጥያቄ ቢያቀርቡም አልተሳካላቸውም ተብሏል። በስብሰባው ማግስት ሰኞ ዕለት በኢራን የሚደገፈው የሁቲ ሚሊሻ በየመን ባደረሰው ጥቃት የዓለም ቁጥር አንዱን ሀብታም ኩባንያ አራምኮን ጉዳት አድርሶበታል። በቀይ ባሕር ዳርቻ ጂዳ የሚገኘውን የዚህ ነዳጅ ኩባንያ ንብረቶች በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል። አራምኮ የሳዑዲ አረቢያ ጉሮሮ እንደማለት ነው። የኢራን ወግ አጥባቂ ሚዲያዎች የሁቲዎቹን ጥቃት "የጀግነነት ጥግ" ሲሉ አሞካሽተውታል። "ይህ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም። የሳዑዲና የእስራኤል ግንኙነት መደረጉን ተከትሎ ሆን ተብሎ የተሰነዘረ ጥቃት ነው" ይላል ማህር ዜና አገልግሎት። መልዕክቱም በኢራን ላይ አንዳች ነገር የምታስቡ ከሆነ በደንብ አስቡበት ለማለት ነው። እርግጥ ነው ሳዑዲ በጥቃቱ ተቆጥታለች። አጋሯ አሜሪካም ነገሩ አበሳጭቷታል። እንዲያውም ናታንያሁና ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን በኒዮም ያደረጉት ምስጢራዊ ስብሰባን ያመቻቹት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ናቸው። በዚያው ሰሞን ኳታርና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስን ጎብኝተው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ ከ2 ሳምንታት በፊት ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የደኅንነት አማካሪዎቻቸውን ምክር ጠይቀው ነበር። "የኢራንን የኒክሊየር ማብላያን ልንመታው የምንችልበት ዕድል እንዴት ነው" ሲሉ ከአማካሪዎቻቸው ጋር ተማክረዋል ተብሏል። ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግሥት ከመሰናበታቸው በፊት በኢራን ላይ ከፍ ያለና የማያዳግም ጉዳት አድርሰው መውጣት ይሻሉ ይላሉ የአሜሪካ ሚዲያዎች። በጥር ወር ትራምፕ የኢራኑን ኃያል ኮማንደር ቃሲም ሱለይማኒን በማስወገዳቸው ከፍ ያለ ኩራት እንደተሰማቸው ሲናገሩ ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እርምጃውን ቢያወግዘውም ቅሉ። "ኮማንደሩን አስቁመነዋል፣ ፈጣን እርምጃ ነው የወሰድነበት፣ በእኔ ትዕዛዝ ነው ያስወገድነው" ብለው ነበር ትራምፕ ስለ ሱለይማኒ ግድያ ሲናገሩ። ይህ የሚያመለክተው ትራምፕ ከነጩ ቤተ መንግሥት ከመውጣታቸው በፊት ቁልፍ የኢራን ሰዎችን የማስወገዱን ነገር ሊያበረታቱ እንደሚችሉ ነው። ግድያው በአሜሪካ በኩል በቀጥታ ባይፈጸምም በእጅ አዙር ደግፈው ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ የሰጠ ነው። ሌላዋ ተጠርጣሪ እስራኤል ናት። ይህ ግድያ እስራኤል ሳታውቀው ሊፈጸም አይችልም የሚሉ ሰዎች ናታንያሁ በ2018 የተናገሩትን ንግግር መዘው ያወጣሉ። በቴሌቪዥን በተላለፈ አንድ መግለጫቸው ቤንያሚን ናታንያሁ ሙህሲን የተባሉትን እኚህን ጎምቱ የኒክሊየር ሳንቲስት ስም ጠቅሰው ነበር። ይባስ ብለውም፤ "ይህንን ስም በደንብ ያዙልኝ" ሲሉ የሙህሲን ፋኸሪዛደህ ነገር ጠበቅ አድርገውት ነበር። ይህ የሚያመላክተው እስራኤል በግድያው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ልትኖርበት እንደምትችል ነው። እርግጥ ነው እስራኤል የጆ ባይደን መምጣት ሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን እንዳስጨነቅ ላያስጨንቃት ይችላል። ሆኖም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ሚስተር አንተኒ ብሊንከንና በመካከለኛው ምሥራቅ ያላቸው አቋም እስራኤልን አሳስቧታል። ሚስተር ብሊንከን ቀንደኛ የኒክሊየር ስምምነት ደጋፊ ናቸው። ሚስተር ብሊንከን አሜሪካ ኤምባሲዋን ወደ እየሩሳሌም ማዛወሯን ጭምር በግልጽ የተቹ ሰው ናቸው። የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አሊ ኻመኒ ለግድያው ጠንከር ያለ አጸፋዊ ምላሽ እንደሚኖር ፍንጭ ሰጥተው ነበር። ሆኖም ይህ እውን ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። ሌላኛው የኢራን ባለሥልጣን ሞህሲን ረዚ ጥቃቱ መፈጸሙ የኢራን የደኅንነት መሥሪያ ቤት ድክመት አለበት ሲሉ ያልተለመደ ትችት ሰንዝረዋል። ግድያው ሊኖር እንደሚችል ቀድሞ መረጃ በመጥለፍ ደርሶ ማምከን ነበረበት ብለዋል። የእኚህን ባለሥልጣን ቅሬታ ብዙ ኢራናዊያን ተጋርተውታል። እንዴት በወታደራዊና ደኅንነት ትልቅ ስም ያላት ኢራን አንድዬ ኒክሊየር ሳንቲስቷን ግድያ ማስቆም አቃታት የሚለው ኢራናዊያንን አስቆጥቷል። ሳይንቲስቱ የተገደሉት በጠራራ ፀሐይ ነው። ገዳዮቹም አልተያዙም። ምናልባት ኢራን ገዳዮቹን ለመያዝ በሚል በርካታ የተቃዋሚ ድምጾችን እንደምታፍን ይገመታል። አሁን ለሳዐዲና እስራኤል እጅግ ውድ ወዳጅ የነበሩት ባለውለታቸው ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግሥት የመልቀቂያ ጊዜያቸው እየተቃረበ ነው። ይህ እውነታ የኢራን ጠላቶችን የልብ ምት የሚጨምር ነው። ጭንቀታቸው ደግሞ ትራምፕ ቀዳደው የጣሉትን የኢራን ኒክሊየር ስምምነት ባይደን ከተመለሱበት እየደቀቀች የነበረችው ጠላታቸው ኢራንና ምጣኔ ሀብቷ ዳግም ያንሰራራሉ ከሚል የመነጨ ነው። ማዕቀብ እያከሳት የምትገኘው ኢራን ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን የሚያስረክቡበትን የጥር ወር ከማንኛውም አሜሪካዊ በላይ በጉጉት ትጠብቀዋለች። ጠላቷ ትራምፕ ከነጩ ቤተ መንግሥት መውጣታቸው ለኢራን ትልቅ ተስፋ ነው። አሁን በጉምቱው የኒክሊየር ሳይንቲስቷ መገደል ተነሳስታ በአካባቢው ሌላ ጫጫታ የሚፈጥር የበቀል እርምጃ መውሰድ የማትሻውም ለዚሁ ነው። ዋናው ነጥብ ኢራን በዚህ ሰዓት ብቸኛ ተስፋዋ የሆነውን የጆ ባይደንን አስተዳደር ማስቀየምም አትሻም። የበቀል እርምጃ ከወሰደችም የባይደን አስተዳደር ወደ ስምምነቱ ካልተመለሰ ብቻ ነው የሚሆነው ይላሉ የአካባቢው ተንታኞች። የውድ ሳይንቲስቷ ሞት ቢያንገበግባትም ያላት አማራጭ ሐዘኗን ዋጥ ማድረግ ብቻ ነው።
51266769
https://www.bbc.com/amharic/51266769
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር በኋላ ሚዲያና የሚዲያ ቁጥጥር ምን ይመስላል?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን መለቀቃቸው፣ የግል መገናኛ ብዙሃን ቁጥር መጨመር ከታዩት ለውጦች መካከል አንዱ እንደሆነ ይነገራል።
በሌላ በኩል የሚዲያ አዘጋገቦች ከወገንተኝነት የፀዱ አለመሆናቸው ይህም በማኅበረሰብ መካከል ለሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት እንደሆኑ ተደጋግሞ ይነገራል። ለዚህም ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ በሚዲያዎች ነፃ፣ ከወገንተኝነት የፀዳ፣ ሚዛናዊ እና ሙያዊ አዘጋገብ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ቁጥጥር መላላት እንደሆነ ይጠቀሳል። • የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ • ብሮድካስት ባለሥልጣን ሥልጣኑ የት ድረስ ነው? ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ናቸው። ዶ/ር ጌታቸው ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ለሚዲያ የተሻለች አገር እንድትሆን ብሮድካስት ባለሥልጣን የተለያዩ ማሻሻያዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ይናገራሉ። "በሚዲያ ነፃነትና በሚዲያ ሙያ ጎረቤት አገር ኬንያ የተሻለች አገር ናት" የሚሉት ዶ/ር ጌታቸው ከእነርሱ ልምድ ለመውሰድ የልዑካን ቡድኑን በመምራት እዚህ እኛ የምንገኝበት ኬንያ መጥተው ነበር። በዚህ አጋጣሚም የቢቢሲን ቢሮ ለመጎብኘት ጎራ ባሉበት ወቅት፤ ከለውጡ በኋላ ያለውን የሚዲያ ዘገባ ይዘትና የቁጥጥር ሥራን አስመልክተን ቃለ ምልልስ አድርገንላቸው ነበር። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በአገሪቷ ያለውን የሚዲያ ሁኔታ እንዴት ይገመግሙታል? ከፍተኛ መሻሻል አለ። ከብዝሃነት አንፃር ቁጥራቸው ጨምሯል። መንግሥት በፊት በተለይ ለኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ፈቃድ ለመስጠት ፈራ ተባ ይል ነበር። አሁን ግን ቁጥራቸው ጨምሯል። በተለይ በሳተላይት የሚሠራጩ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ለመጀመር የሚፈልጉ ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ካቀረቡ ፈቃድ ይሰጣል። ጋዜጦች [በቀጥታ እኛን ባይመለከቱም] ብዙ መፅሔቶችና ጋዜጦች ገበያ ላይ ይታያሉ። ተዘግተው የነበሩ ድረ ገፆችም ተከፍተው የተለያዩ መረጃዎች እያስተላለፉ፤ ሕብረተሰቡ መረጃ የሚያገኝባቸው አማራጮች በዝተዋል። ነገር ግን አሁን በአንገብጋቢነት የሚነሳው የጥራት ችግርና ወገንተኝነት ነው። እንዲህ መሆኑም በሕብረተሰቡ ዘንድ አሉታዊ ተፅዕኖ እያደረሰ እንደሆነ ይነገራል። ባለሥልጣኑ እዚህ ላይ ምን ይላል? ታፍኖ የነበረ ሚዲያና የሚዲያ ምህዳር በሚከፈትበት ጊዜ ወደ ሜዳው መጥተው የሚጫወቱት ሁሉ ሙያዊ በሆነ መንገድ ሥራውን ይሠሩታል ተብሎ አይታሰብም። አንዳንዶች ነፃነቱን ተጠቅመው በኃላፊነት ሲሠሩ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለተለያየ ምክንያት ሚዲያውን ይጠቀሙበታል። ለፖለቲካ አላማ ማስፈፀሚያ፣ ለቡድን ዓላማዎች ማስፈፀሚያ እንደሚጠቀሙበት አስበው ይገባሉ። ሲያመለክቱ እንደሱ ቢሉ እኛ ፈቃድ አንሰጣቸውም፤ ሁሉንም ሕብረተሰብ በእኩል እናገለግላለን ብለው ነው ፈቃድ የሚሰጣቸው፤ ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ግን መንሸራተት ያሳያሉ። ወገንተኝነት ከሚዲያ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል ተብሎ ባይታሰብም፤ እኛ አገር እንዳለው ጭልጥ ያለ ወገንተኝነት፤ አንዱን እያሞገሱ፤ አንዱን እያኮሰሱ የሚሠራ ሚዲያ ግን ብዙም የለም። ይህንን የመቆጣጠር ኃላፊነት እኮ የእናንተ ነው። እንዲህ ያደርጋሉ ባለችኋቸው ሚዲያዎች ላይ ምን እርምጃ ወሰዳችሁ? ሁለት ነገሮችን ለማመዛዘን እንሞክራልን። ቸኩለን ወደ እርምጃ አንሄድም። ባንድ በኩል አሁን የተጀመረው የሚዲያ ነፃናትና ተደራሽነት መስፋት፤ የተለያዩ ድምፆች በሚዲያ የመስተናገዳቸው ጉዳይ እንዲቀጥል ስለምንፈልግ፤ አንዴ መስጠት፤ አንዴ መንፈግ እንዳይሆን ቸኩለን ወደ እርምጃ አንገባም። ቢያምም አንዳንድ ነገር መታገስን ይጠይቃል። እስከምን ድረስ ነው መታገስ የሚቻለው? ይገባኛል እመጣበታለሁ። እና ሁለተኛው ደግሞ ሕብረተሰብ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የሚዲያ አዘጋገቦች ሲኖሩ፤ ገና ለገና መማር አለብን እያልን ሕብረተሰቡን የሚጎዳ ቀጥተኛ ነገር ሲፈፀም ዝም አንልም። ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ የቁጥጥር ሥራ እየሰራን መዝግበን እየያዝን በየወሩ መጨረሻ በቁጥር የተደገፈ ሪፖርት ለየሚዲያ ተቋማቱ እንሰጣለን። እንዲታረሙበት ይዘቱንም አስመልክተን በዝርዝር ሪፖርት እንሰጣለን። አንዳንዶቹ ቀና ምላሽ ይሰጡናል። አንዳንዶቹ ሙግት የሚገጥሙ አሉ። ግን በሂደት ሚዲያው በየጊዜው የሚሰራው ልምድ ይታያል። ያኔ የማያሻሽል ከሆነ በአካል እናነጋግራለን፤ ከዚያ በኋላ የማያሻሽሉ ከሆነ የማሳሰቢያ ደብዳቤም፤ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤም ይሰጣል። ከዚያ የማገድ እና ፈቃድ የመሰረዝ የእርምጃ ሂደቶችን እንከተላለን። ስለዚህ አንቸኩልም እንጂ እርምጃ አንወስድም ማለት አይደለም። ከዚህ በፊት በዚህ ሂደት ያለፉና እርምጃ የተወሰደባቸው ሚዲያዎች አሉ? ደረጃው ይለያያል እንጂ ደብዳቤ የፃፍንባቸው ሚዲያዎች አሉ። አንዳንዴ ከግል፣ ከሕብረተሰቡ እንዲሁም ከመንግሥትም ጥቆማዎች ይደርሳሉ። ያኔ መጥተው ማብራሪያ እንዲሰጡ ይደረጋል። የመረጃ ትክክለኝነት በሌለበት ቦታ ላይ ደግሞ ይቅርታ እንዲጠይቁና የተስተካከለ መረጃ እንዲያስተላልፉ ይደረጋል። ይህ የየቀን ሥራችን ነው። ከዚያ ባለፈ ግን ግጭት ቀስቃሽ የሆነ፣ አንድን ብሔር በሌላው ላይ የሚያነሳሳ ዓይነት፣ ሰላማዊ የሆነን የተቃውሞ መንገድ ከማስተዋወቅ ይልቅ ግጭት ቀስቃሽ የሆነ መንገድን ተከተሉ የሚል የሚዲያ ሪፖርትን አግኝተን ከባድ ማስጠንቀቂያ ጽፈንበታል። የትኛው የሚዲያ ተቋም ነው? ሚዲያውን ለጊዜው መጥቀሱ ብዙ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም እኛ ዓላማችን ስም በመጥቀስ ማሳፈር [naming and shaming] ሳይሆን እንዲታረሙ ነው። ሚዲያውም ለእኛ ቀና ምላሽ ሰጥቷል። ተሳስተናል አንደግምም ብለዋል። አሁንም እየተከታተልን ነው፤ እንደሱ አይነት ፈር የለቀቁ ሪፖርቶች አልተደገሙም። በፍርድቤት የተያዙ ጉዳዮች በሪፖርት መልክ፣ በዘጋቢ ፊልም መልክ ይቀርባሉ። ይህን በተመለከተ የፍርድ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፤ ከሕግም አንፃር አግባብ አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ? የፍርድ ቤት ጉዳዮች አዘጋገብ መመሪያ እያዘጋጀን ነው። በባለሥልጣኑ ከዚህ በፊት እንዲህ ዓይነት መመሪያ አልነበረንም። ከእውቀት ማነስም ይመጣል። ሁሉም ነገር ከክፋት ብቻ ላይሆን ይችላል ስህተቱ የሚፈፀመው። የማን የዕውቀት ክፍተት? እንዲህ ዓይነት ነገሮች የሚተላለፉት በመንግሥት በሚመሩ ልምድ ባላቸው ሚዲያዎች ጭምር ነው። እነሱም ሊሆኑ ይችላሉ። የመንግሥት፣ የሕዝብ የሚባሉትም ሚዲያዎች ስህተት ሊሰሩ ይችላሉ። ነገር ግን በፍርድ ቤት የተያዙ ጉዳዮች ላይ፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ወንጀለኝነቱ በፍርድ ቤት ሳይረጋገጥ ቀድሞ ያን ሰው ወንጀለኛ አድርጎ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም። እናንተ ኃላፊነት አለባችሁ። ሙያውን ታውቁታላችሁና ይህንን ባሠራጩት ላይ ምን የወሰዳችሁት እርምጃ አለ? በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ባልተገባ መልኩ ተዘገበ የሚል ለብሮድካስት ባለሥልጣን የቀረበ ቅሬታ የለም። ቅሬታ በሚቀርብበት ጊዜ እሱ ላይ ተመስርተን ተጨማሪ ምርመራ እናደርጋለን። በቅርብ፤ ሦስት ወር ገደማ ቢሆነው ነው የጀመረውና በመደበኛነት በምናደርገው የቁጥጥር ሥራ ናሙና ወስደን ነው የምናከናውነው እንጂ ሁሉንም ሚዲያዎች 24 ሰዓት፤ ሰባቱንም ቀን የቁጥጥር ማድረግ አቅሙ የለንም። አንዳንድ ነገሮችን ልንስት እንችላለን። ለምሳሌ ሜቴክ ላይ ተፈፀመ ከተባለውን የሙስና ቅሌትን ያቀረበ ዘጋቢ ፊልም ከአንድ በላይ ሚዲያዎች ላይ፤ ያውም በተመሳሳይ ሰዓት መዘገቡ ይታወሳል። ይህንን ዐብይ ዘገባ ትስቱታላችሁ ብዬ አላስብም። እሱ በተላለፈበት ጊዜ እኔ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበርኩ። በዚያ ሰዓት ከመምህራን ጓደኞቼ ጋር ስናወራ የዘጋቢ ፊልሙ ተገቢነት ብዙም አልታየንም፤ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል ገብቶናል። እንደ አስተማሪም ተወያይተንበታል። ብሮድካስት ባለሥልጣን ከመጣሁ በኋላ ያወቅኩት በወቅቱ እሱን የተመለከተ ቅሬታ አልነበረም። መቀለ ላይ በነበረን ሕዝባዊ ስብሰባ ይሄው ሃሳብ ተነስቶ ትክክለኛ ነው ብዬ እንደማላምን ነግሬያቸዋለሁ። • "የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ" መሐመድ አደሞ • ጋዜጠኞች ስለ ለውጡ ማግስት ሚዲያ ምን ይላሉ? ባለሥልጣኑ ለምን እርምጃ አይወስድም ብለው ሲሉ። በብሮድካስት ሕግ መሠረት 6 ወር ውስጥ ቅሬታ ካልቀረበበት አንድ ፕሮግራም ሚዲያውም ዶክመንት አድርጎ የመያዝ ግዴታ የለበትም። ባለሥልጣኑም መረጃን ቢበዛ ለስድስት ወር ነው ማስቀመጥ የሚችለው። እንደውም እዚህ አገር አጭር ነው፤ ሦስት ወር ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ቅሬታ ካልቀረበ በስተቀር ከዚያ በኋላ ቅሬታ ሊቀርብበት አይችልም። ታሪኩም ወደ ኋላ እየተጠቀሰ እርምጃ ሊወሰድ አይችልም ሥልጣኑም አይፈቅድለትም። ብሮድካስት ባለሥልጣን የሚቆጣጠረው ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጣቢያዎችን ብቻ ነው። በእነዚህ ጣቢያዎች በዲጂታል [ማህበራዊ ሚዲያና ድረ ገፅ] የሚተላላፉትን ይዘቶች ማን ነው የሚቆጣጠረው? እንኳን የኦንላይን ይቅርና የጋዜጣም ይዘት አንቆጣጠርም። ፈቃድ የምንሰጠውን ብቻ ነው የምንቆጣጠረው። የብሮድካስት አዋጅ 533/99 ላይ እንድንሠራ የተሰጠንን ሥራዎች መሥራት ነው የምንችለው፤ ከዚያ ወጥተን መሥራት አንችልም። ያ ሥልጣን ስለሌለን በኢንተርኔት ላይ የሚተላለፉ ይዘቶችን በተመለከተ ችግሩ ቢገባንም ኢትዮጵያ ግን የሕግ ማዕቀፍ የላትም። ምን አልባት አሁን በፓርላማ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ያለ የሀሰተኛ መረጃ እና ጸረ ጥላቻ ንግግር አዋጅ አለ። አዋጁ ጸድቆ በሚወጣበት ጊዜ እሱን የመቆጣጠር ኃላፊነት የሚሰጣቸው መሥሪያ ቤቶች ይኖራሉ። ምን አልባት ወደ ብሮድካስት ሊመጣ ይችላል፤ አይታወቅም። እንዲሁ እኛ ስለወደድን ተነስተን እንቆጣጠር ብንል በየትኛው ሥልጣናችሁ ነው? የምንባለው። አንዳንድ አገራት እንደ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ ሕግ ካረቀቁ በኋላ ለመቆጣጠር ይሞክራሉ። ሌሎች አገራት ደግሞ ይህ ሰዎች ሃሳባቸውን በነፃነት የሚገልፁበት ስለሆነ ቁጥጥር አያስፈልገውም ይላሉ። ስለዚህ ክርክር ያለበት ዘርፍ ስለሆነ፤ አገር የምትወስደውን አማራጭ ሳትወስን አንድ ሥራ አስፈፃሚ ተቋም ለዚያ ኃላፊ ሊሆን፤ ሊጠየቅም አይችልም። ለቴሌቪዥን ጣቢያዎች ወይም ለሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ሲሰጥ ሊያካትቷቸው የሚገቡ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች ተለይተው ተቀምጠዋል? የለውም። ቴክኖሎጂው እየቀደመን ነው። የእኛ ሕግ የተረቀቀው በ1999 ነው። ሕጎቹ እነዚህን ሊያካትቱ አይችሉም። እኛ ፈቃድ በምንሰጥበት ጊዜ፤ በሬዲዮ የሚሠራጭ፣ በቴሌቪዥን የሚሠራጭ ይዘት ብለን ነው። እውቅና የምንሰጠውም፤ ፈቃድ የምንሰጠውም ለዚያ ነው። ሕጉ ይዘቶቻቸውን በምን ሌሎች ማሠራጫ ያሰራጫሉ ብሎ ገምቶ፤ እሱን ባካተተ መልኩ አልተቀረፀም። ሕጉም በመከለስ ላይ ነው፤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። የብሮድካስት አዋጁና ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ሕግ ከጸደቀ ተጋግዘው ይህንን ዘርፍ መቆጣጠር ይችሉ ይሆናል። ኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ያለዎት ተስፋና ሥጋት ምንድን ነው? ብዙ ተስፋ አለ። በመንግሥት በኩል የታየው ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት መልካም ነው። ነገር ግን ሁሉን ነገር እናውቃቸዋለን፣ ይዘነዋል፣ ለዚያም ዝግጁ ነን ማለት ደግሞ አይቻልም። ስጋቶቹ የሚመጡት የበዛ ወገንተኝነት የሚታይባቸው ሚዲያዎች አሉ። እንደ ትግል ሚዲያና አንድን ወገን ሃሳብ ሊያስፈፅሙ እንደተቋቋሙ ራሳቸውን የሚያዩ አሉ። እኔ 'የትግል ሚዲያ' የሚል ፈቃድ አልሰጠንም እላለሁ። የምንሰጠው ፈቃድ ሦስት ዓይነት ነው። የፐብሊክ፣ የንግድና የማህበረሰብ ሚዲያ ፈቃድ ነው የምንሰጠው። የትግል ፈቃድ እኛ ሰጥተን አናውቅም። እና ራሳችሁን ከዚህ ቆጥቡ የሚል ነገር እናደርጋለን። ራሳቸውን ግን ለአንድ ወገን፣ ለአንድ ፖለቲካ አላማ፣ ለአንድ አስተሳሰብና ርዕዮተ ዓለም ጠበቃ አድርገው ሊያቆሙ የሚወዱ ዓይነት ሚዲያዎችን እያየን ነው። አሁን ሕብረተሰቡም እንደዚህ ዓይነት ሚዲያዎችን እየለያቸው ነው። እየከሰሙ ይመጣሉ የሚል ተስፋ አለን። ይህ መለወጥ መቻል አለበት። ለጊዜው ያለው ትዕግስትም ያበቃል ብዬ አስባለሁ። ሕብረተሰብ እየተቆጣ ይሄዳል። መንግሥትም ደግሞ ሕብረተሰብን የመስማትና ሕግን የማስፈፀም ኃላፊነት አለበት። ኃላፊነቱን በሚወጣበት ጊዜ ነገሮች እንዳይከብዱ ከወዲሁ ሚዲያዎቹ ራሳቸውን እያስተካከሉ ሙያዊ በሆነ፣ በእውነት ላይ የተመሠረተ፣ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ መዘገብን ማዳበር አለብን። የምርጫ አዘጋገብ ዶ/ር ጌታቸው የዘንድሮውን ምርጫ አዘጋገብም በተመለከተ ቅድመ ዝግጅቶች እያደረጉ እንደሆነ ነግረውናል። በምርጫ አዘጋገብ ዙሪያ በተለያዩ ዙሮች ጋዜጠኞች ሥልጠና እየተሰጣቸው ነው። መመሪያዎችም ተዘጋጅተዋል። በምርጫ ቦርድ ይህ መመሪያ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በምርጫ ወቅት የጋዜጠኞችና የሚዲያ ሥነ ምግባር ምን መምሰል አለበት፣ ጋዜጠኞች ማወቅ ስላለባቸው የምርጫ ሂደቶች፣ የሚከለከሉና የሚፈቀዱ ጉዳዮችን የሚመለከት መመሪያ ተዘጋጅቷል። ይህ ሲፀድቅም ይህንን ተከትሎ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። የአገር ውስጥም የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ተቋማትም ሥልጠና እየሰጡ እንደሚገኙም አክለዋል።
54612586
https://www.bbc.com/amharic/54612586
አንበጣ መንጋ፡ በኢትዮጵያ 420 ሺህ ሔክታር ላይ የሰፈረ ሰብል በአንበጣ መንጋ ጥቃት ደርሶበታል
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በኢትዮጵያ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ጥቃት ያደረሰው በ240 ወረዳዎች መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ሰኞ እለት በተካሄደው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ የተከሰተባቸው አካባቢዎች አፋር፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መሆናቸውን ገልፀዋል። በእነዚህ የአንበጣ መንጋ ጥቃት የደረሰባቸው አካባቢዎች በጥቅሉ 240 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ በእነዚህ ወረዳዎች ስር ከሚገኙ ቀበሌዎች መካከል ደግሞ በ705 ቀበሌዎች ላይ ብቻ አንበጣው ጥቃት ማድረሱን ገልፀዋል። በእነዚህ አካባቢዎች በድምሩ 4 ሚሊየን ሄክታር ታርሷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከዚህም መካከል ጥቃት የደረሰበት 420ሺህ ሔክታር ገደማ መሆኑን ተናግረዋል። ከውጪ ኬሚካል የሚረጩ አውሮፕላኖችን እና ድሮኖችን [ሰው አልባ አውሮፕላን] ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሂደቱ ግን አልጋ ባልጋ አለመሆኑን አመልክተዋል። የበረሃ አንበጣ መቼ ተከሰተ? ከ25 ዓመታት ወዲህ የከፋ ነው የተባለለት የበረሃ አንበጣ ለወራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ ያሉ አገራት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ አስካሁን በተከታታይ ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ ምክንያቱ እንደ አውሮፓዊያኑ በ2018 እና 2019 ያጋጠመው ከባድ ነፋስና ዝናብ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንዳመለከተው ከሁለት ዓመት በፊት በደቡባዊ የአረብ ልሳነ ምድር ላይ የነበረው እርጥብና አመቺ የአየር ሁኔታ የአንበጣው ሦስት ትውልድ ሳይታወቅ እንዲራባ እድል ፈጥሮ በአካባቢው አገራት ላይ የሚታየውን የአንበጣ መንጋ ወረራ አስከትሏል። የግብርና ሚኒስቴር የበረሃ አንበጣ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ከሰኔ 2011 ዓ.ም ጀምሮ የመቆጣጠር ስራ ሲሰራ እንደነበር ገልጾ በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም ከየመንና ከሱማሌ ላንድ መነሻውን በማድረግ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ ይፋ ያደረገው መረጃ ያሳያል። የአንበጣ ወረርሽኙ መከላከል ሥራ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር እና የክልል ባለሙያዎችም ሰፊ-ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ይናገራሉ። የግብርና ሚኒስቴር በበኩሉ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን የአሰሳ ሄሊኮፕተሮችን፣ የኬሚካል መርጫ አውሮፕላኖችን፣ ተሸከርካሪ ላይ የሚገጠምና በሰዉ የሚያዝ ሞተራይዝድ መርጫዎችን በማቅረብ እንዲሁም ኬሚካል፣ የኬሚካል መከላከያ አልባሳትንና የመስክ ተሸከርካሪዎችን ማቅረቡን ገልጿል። ሆኖም ግን የአዉሮፕላን እጥረት መኖሩ ክስተቱን በሚመጥን ሁኔታ ለመከላከል ዋና ተግዳሮት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚንስቴሩ ይህን ችግር ለመፍታትና የርጭት ስራውን በውጤታማ ሁኔታ ለማከናወን እንደአገር በተደረገ ጥረት በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ተጨማሪ ኬሚካል የሚረጩ አውሮፕላኖች ከውጭ በማስመጣት የመቆጣጠር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ አሁን ባለው ትንበያ መሰረት የተባዩ ክስተት ለተወሰነ ጊዜ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችልና የአንበጣን መንጋውን ለመከላከል እስከ 10 አውሮፕላኖችና 150 የመስክ ተሽከርካሪ እንደሚያስፈልግ እና ይህንም ለማሟላት ከተለያዩ ተቋማትና ሀገሮች ጋር መንግስት እየተነጋገረ እንደሚገኝ የገለፀው ደግሞ ግብርና ሚኒስትር ነው። ኦሮሚያ በኦሮሚያ ክልል የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በሁለቱ የሐረርጌ ዞኖችና በሰሜንሸዋ ዞን መከሰቱን የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የከልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ወረርሽኙ በሰሜን ሸዋ የተከሰተው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው። ከባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ የአፋር ክልልን በሚያዋስነው የሰሜን ሸዋ ፈንታሌ ወረዳ ውስጥ መታየት ጀምሯል ብለዋል። እንደ ግብርና ቢሮ ኃላፊው ባለፉት ሶስት ወራት በ850ሺህ ሄክታር ላይ በተደረገ ዳሰሳ 288 ሺህ በሚሆን ሄክታር በአንበጣ መጠቃቱን ታውቋል። ይህንኑ ጉዳት ለመቆጣጠር የኬሚካል ርጭት እየተደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት ዳይሬክቶር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኢሳያስ ለማ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተመሳሳዩም አቶ ዳባ በሁለቱ የሐረርጌ ዞኖች በአንበጣው ወረርሽኙ ከተጎዱ ሰብሎች መካከል ማሽላ አንደኛው መሆኑን ተናግረዋል። ወረርሽኙን ለመከላከል ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዳባ ከእነዚህም መካከል በማህበረሰብ ተሳትፎ የሚከናወነው መከላከል አንዱ መሆኑን ገልፀዋል። ከመከላከል እርምጃዎቹም መካከል ማህበረሰቡን ከማሳሰብ በተጨማሪ ጭስ ማጨስና ድምጽ ማሰማት አንዱ መሆን አቶ ዳባ ተናግረዋል። ከዚያ በተጨማሪ የኬሚካል ርጭት እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል። የኬሚካል ርጭቱን ደግሞ በእጅ ማሽን፣ በመኪና እና ላይ በመጫንና በአውሮፕላን በድሮን በመታገዝ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል። የመሳሪያ እንዲሁም የአውሮፕላን አቅርቦት ችግር መኖሩን የሚገልፁት እኚህ ኃላፊ ነገር ግን በመንግሥት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።\ የአውሮፕላን ችግሩ እየተፈታ ነው ያሉት ኃላፊው "ሂሊኮፕተር አለን፣ መድሃኒት ለመርጨት የሚውሉ ትንንሽ አውሮፕላኖችም አሉን እንዲሁም ሰው አልባ አውሮፕላን ለመጠቀም እየሞከርን ነው" ብለዋል። ከግብርና ሚኒስትር፣ ከኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ተውጣጥተው ችግሩ ወደ በሚታይባቸው ስፍራዎች በመውረድ የመከላከል ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ኃላፊው አስታውቀዋል። አማራ በአማራ ክልል ከሰሜን ሸዋ እስከ ሰሜን ወሎ ድረስ የአንበጣ መንጋው ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገደባቸው ወረዳዎች አንዱ የሃብሩ ወረዳ ነው። በወረዳው ሰባት ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በአንበጣ መንጋው ወድመዋል። አርሶ አደር አሊ ሰዒድ ከእነዚህ ቀበሌዎች አንዷ በሆነችው ጥልፌ ቀበሌ ይኖራሉ። ከአራት እርሻዎቻቸው መካከል የ13 ጥማድ [3 ሄክታር በላይ] መሬት ወድሞባቸዋል። አንድ እርሻ ማትረፋቸውን የሚናገሩት አቶ አሊ፣ "የተረፈው እርሻ የአንድ ወር ቀለብ እንኳን የሚሆን አይደለም፣ ዓመት ሙሉ የደከምንበት እንኳን ለእኛ ለከብቶቻችንም የሚሆን እንዳይተርፍ አድርጎ አውድሞብናል" በማለት አንበጣው ያደረሰባቸውን ጉዳት ይገልጻሉ። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ የአንበጣ መንጋው በክልሉ 4 ዞኖች፣ 18 ወረዳዎች በ136 ቀበሌዎች መከሰቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በእነዚህ አካባቢዎች በአጠቃላይ 328 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ መውረሩን የተናገሩት አቶ ተስፋሁን ግማሽ የሚሆነውን መሬት የአውሮፕላን ርጭትን ጨምሮ በተለያዩ የመከላከያ ዘዴዎች የመከላከል ሥራ ተሠርቶበታል ሲሉ ይናገራሉ። የአንበጣ መንጋው 87 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ በሰብልና በእንስሳት መኖ ላይ ጉዳት አድርሷል የሚሉት አቶ ተስፋሁን፣ ከእነዚህም መካከል 30 ሺህ 500 ሄክታር የሚሆነው የሰብል ምርት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። የአንበጣ መንጋው ባደረሰው ከፍተኛ ውድመት የተጎዱ አርሶ አደሮችን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ድጋፍ ለማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል። ትግራይ አርሶ አደር ንጉስ ሲሳይ በትግራይ ክልል የራያ ጨርጨር ወረዳ ኗሪ ናቸው። እኚህ የ50 አመት አርሶ አደር ሰባት የቤተሰቦች አባላትን ያስተዳድራሉ። ሁሉም ልጆቻቸው ወንዶች ስለሆኑ፤ በእድሜ ተለቅ ያሉት ሁለት ወንድ ልጆቻቸው ይዘው ባለፈው አመት የመጋቢት ወር ላይ ማሳቸውን ሲንከባከቡና ለምርት ሲያበጃጁ መክረማቸው ይናገራሉ። ባለቤታቸውም፤ የተዘራው እህል አረም እንዳያጠፋው ከስር ከስር ማገዛቸው የሚገልጹት አርሶ አደር ንጉስ፤ ከመጋቢት እስከ ግንቦት 2012 ባሉት ወራት ውስጥ በ250 ሄክታር መሬት ላይ ጤፍ፣ በቆሎና ሽምብራን ዘርተው እንደነበር ይናገራሉ። "ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ዝናብ ስለነበረ፣ ከአንድ ሄክታር እስከ 80 ኩንታል በቆሎ፣ 40 ኩንታል የሚደርስ ደግሞ ጤፍ አገኛለሁ የሚል ተስፋ ነበረኝ። አሁን ይሄ ሁሉ በአንበጣ መንጋ ተበልቶ ወድሟል" ይላሉ። በዚህ ወቅት፣ በቴክኖሎጂ ታግዘው በመስራታቸው ትልቅ ተስፋ የጣሉበት የምርት ዘመን ድንገት በአንበጣ መንጋ ሲወረር ቢቻል ከውድመት ለማትረፍ ባህላዊ በሆኑ መንገዶች በወጣቶችና ህብረተሰቡ እገዛ መከላከል ቢሞክሩም ውጤታማ እንዳልሆነ አርሶ አደሩ ገልጸዋል። "በቅርቡ ለሦስተኛ ጊዜ የመጣው የአንበጣ መንጋ ከአቅማችን በላይ ስለነበረ መከላከል አልቻልንም። እህሉን ጨርሶ በሰው አይን ላይ ያርፍ ነበር። በዚህ ወቅት ሴቶች እጅግ ተጨንቀዋል። ሚስቶቻችን ደህና የነበረው ሰውነታቸው ከስቶ በተስፋ መቁረጥ ጠቁረዋል፤ ምን እንበላለን? ወዴት እንሄዳለን? እያሉ ነው" ብለዋል።
news-41780127
https://www.bbc.com/amharic/news-41780127
በስዊድን ያሉ የስደተኛ ልጆች ሚስጥራዊ ህመም
ስዊድን ለሃያ ዓመታት ምንነቱ ካልታወቀ በሽታ ጋር እየታገለች ነው። 'ሪዛይኔሽን ሲንድረም' የሚባለው በሽታ ጥገኝነት የጠየቁ ልጆችን ብቻ ነው የሚያጠቃው።
በሽታው ሙሉ ለሙሉ እንዳያወሩ ወይም እንዳይራመዱ ወይንም ዓይናቸውን እንዳይከፍቱ የሚያደርግ ነው። ጥያቄው ግን በሽታው ለምን በስዊዲን ብቻ ተከሰተ? አባትዋ ከተሽከርካሪ ወንበር ላይ ሲያነሳት የዘጠኝ ዓመቷ ሶፊ ህይወት አልባ ነበረች። በተቃራኒው ግን የቆዳዋና የጸጉሯ አንጸባረቂነትና ጠንካራነት ከጤነኛ ህጻናት ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም የሶፊ አይኖች ተከድነዋል። ዕድሜዋ በአስራዎቹ ቢገኝም ከውስጥ ሱሪዋ ውስጥ ደግሞ የጽዳት መጠበቂያ (ዳይፐር) አድርጋለች። ላለፉት 20 ወራት ስትመገብበት የነበረው ቱቦ ደግሞ በአፍንጫዋ በኩል ተተክሎላት ይገኛል። ሶፊና ቤተሰቦቿ ከቀደሞዋ ሶቪየት ህብረት የመጡ ጥገኝነት ጠያቂዎች ናቸው። እ.አ.አ ታህሳስ 2015 የመጡት እነሶፊ በማዕከላዊ ስዊድን በሚገኝ የስደተኞች ማቆያ ውስጥ ይኖራሉ። "የደም ግፊቷ የተስተካካለ ነው" ይላሉ ዶክተርስ ኦፍ ዘ ዎርልድ ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉት ዶ/ር ኤልሳቤት ሃልትክራንትዝ። "የልብ ምቷ ግን ከፍተኛ ነው። ዛሬ ብዙ ሰዎች ሊጠይቋት ስለመጡ ምላሽ እየሰጠች ነው" ብለዋል። ሃልትክራንትዝ ሶፊ ሳታስብበት በተፈጥሮ የምትሰጣቸውን አካላዊ እንቅስቃሴዎችና ምለሾች ያጠናሉ። ሁሉም ነገር ግን በትክክለኛው መንገድ ይሰራል። ሆኖም ልጅቱ መንቀሳቀስ አትችልም። ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት ከአንገት በላይ ሃኪም የነበሩት ዶ/ር ሃልትክራንትዝ፤ ሶፊ አፏን እንኳን መክፈት አለመቻሏ ያሳስባቸዋል። ይህ አደገኛ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም በመመገቢያ ቱቦዋ ላይ ችግር ካለ መተንፈስ ሊያስቸግራት ይችላል። ታዲያ መደነስ የምትወደው ልጅ እንዴት ለመንቀሳቀስ የሚሆን ጉልበት እንኳን አጣች? "ጉዳዩን ለቤተሰቦቿ ሳስረዳ፤ የሶፊ ሰውነት ንቁ ከሆነው የአዕምሮዋ አካል ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጧል በሚል ነው" ብለዋል ሃልትክራንትዝ። እነዚህን ህጻናትን የሚረዱት የህክምና ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ በሽታው የሚፈጥረው ተጽዕኖ ልጆቹ ራሳቸውን ከተቀረው ዓለም እንዲያርቁ ያደርጋቸዋል። ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት ደግሞ ቤተሰቦቻቸው ወይም ቤተሰቦቻቸው እጅግ አስቸጋሪ ከሆነ ችግር የሸሹና ከባድ ግጭትን የተመለከቱ ናቸው። የሶፊ ወላጆች ገንዘብ በህገወጥ መንገድ በማግኘት እና ከማፊያዎች ጋር ባላቸው መጥፎ ግንኙነት አስፈሪ ታሪክ አላቸው። እ.አ.አ መስከረም 2015 ላይ የፖሊስ ዩኒፎርም በለበሱ ሰዎች መኪናቸው እንዲቆም ተደረገ። "ተጎትተን ወጣን። እኔና እናቷ ስንደበደብ ሶፊ መኪና ውስጥ ሆና ሁኔታውን ስትከታተል ነበር" ሲል ሶፊ አባቷ ጉዳዩን ያስታውሳል። ሰዎቹ የሶፊን እናት ሲለቋት ልጇን ይዛ ከአካባቢው ታመልጣለች። የሶፊ አባት ግን ማምለጥ አልቻለም ነበር። "እኔን ይዘውኝ ከሄዱ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ግን አላስታውስም" ይላሉ የሶፊ አባት። የሶፊ እናት ልጇን ወደ ጓደኛዋ ቤት ይዛት ሄደች። ትንሿ ልጅ በጣም ተበሳጭታ ነበር። እያለቀሰች "እባካችሁ ሂዱና አባቴን ፈልጉት" እያለች ግድግዳውን በእግሮቿ እየደበደበች ትጮህ ነበር። ከሶስት ቀናት በኋላ አባት ድምጹን ካለበት ያሰማ ሲሆን፤ ከሶስት ወር በኋላ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስዊድን እስከሚያቀኑ ድረስ በተለያዩ ጓደኞቻቸው ቤት እየተዘዋወሩ ቆይተዋል። ሲደርሱም ለአራት ሰዓታት በስዊድን ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ነበሩ። የሶፊ ጤንነትም ወዲያው ነበር በፍጥነት እያሽቆለቆለ የሄደው። "ከሁለት ቀናት በኋላ ቀደም ሲል ከእህቶቿ ጋር የምትጫወተውን ያህል እየተጫወተች አለመሆኑን ተገነዘብኩ" ትላለች በቅርቡ ሌላ ልጅ የምትጠብቀው የሶፊ እናት። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቤተሰቡ በስዊዲን እንደማይቆይ ተነገረው። የስደተኞች ቦርድ ስለጉዳዩ ሲያወራን ሶፊ ጉዳዩን ሙሉ ለሙሉ የሰማች ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን መናገርም ሆነ መብላት አቆመች። 'ሪዛይኔሽን ሲንድረም' ስውዲን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሪፖርት የተደረገው እ.አ.አ በ1990ዎቹ ነበር። ከ2003 እስከ 2005 ባሉት ሁለት ዓመታት ከ400 በላይ ህሙማን ተገኝተዋል። ብዙ ስዊድናዊያን በስደተኞች ምክንያት ስጋት በገባቸው ወቀት የእነዚህ "ምንም ፍላጎት የሌላቸው ህጸናት" ጉዳይ ትልቅ ፖለቲካዊ ትኩሳት ሆኗል። ልጆቹ አውቀው ነው አልታመሙም የሚሉና ወላጆቻቸው መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ልጆቻቸውን እየመረዙ ነው የሚሉ ሪፖርቶችም ወጥተዋል። ሆኖም እነዚህን ታሪኮች ማረጋገጥ አልተቻለም። የሶፊ እናት፣ እህትና አባት ባለፉት አስር ዓመታት በሪዛይኔሽን ሲንድረም የተጠቁ ህጻናት ቁጥር ቀንሷል። እ.አ.አ በ2015 እና 2016 በበሽታው የተጠቁ ህጻናት ቁጥር 169 መሆኑን የስዊድን ብሄራዊ የጤና ቦርድ አስታውቋል። ከተወሰነ የዓለም ክፍልና ብሄር የመጡ ህጻናት በበሽታው የመያዛቸው ነገር ከፍተኛ ነው። በተለይ ደግሞ ከቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት፣ ባልካን፣ ሮማ እና በቅርቡ ደግሞ የያዚዲ ስደተኛ ልጆች ናቸው በብዛት የሚጠቁት። ከስደተኛ ቤሰተብ ውጭ ያሉ እና ኤስያዊን በበሽታው የመያዛቸው ዕድል አነስተኛ ሲሆን አፍሪካዊያን ግን በችግሩ አልተጠቁም። ከሶፊ በተለየ ሁኔታ ሌሎቹ በችግሩ የተጠቁት ህጻናት ለዓመታት በስዊዲን የኖሩ፤ ቋንቋውን የሚናገሩ እና ከኖርዲክ አኗኗር ጋር ራሳቸውን ያዋሃዱ ናቸው። ከዚህ ቀደም ለምሳሌ በናዚ ማቆያ ጣቢያ ያሉ ሰዎችን ጨምሮ ሪዛይኔሽን ሲንድረንምን የሚመስሉ የተለያዩ ሽታዎች ተከስተዋል። በእንግሊዝም እ.አ.አ በ1990ዎቹ ፕሪቫሲቭ ሬፉሳል ሲንድረም የተባለ ተመሳሳይ በሽታ ተከስቶ ነበር። የተጠቂዎች ቁጥር አነስተኛ ከመሆኑም በላይ አንድም ስደተኛ በችግሩ አልተጠቃም። "እስከምናውቀው ድረስ ከስዊድን ውጭ ችግሩ አልተከሰተም" ሲሉ የህጻናት ሃኪም ሆኑት አስትሪድ ሊንድግረን አስታውቀዋል። ሪዛይኔሽን ሲንድረምን ለመረዳት እንቅፋት የሆነው በጉዳዩ ላይ ጥናት አለመደረጉ ነው ይላሉ። በልጆቹ ላይ ምን እንደተከሰተ ማንም ክትትል አላደረገም። የምናውቀው በህይወት መኖራቸውን ብቻ ነው። ካርልሻመር፡ በሽታው ከስደተኝነት ጋር ሳይሆን ካለፈ ስቃይ ህይወት ጋር የሚያያዝ ነው ለሶፊ ወላጆች ግን ይህ ከባድ ነው። ባለፉት 20 ወራት በልጃቸው ላይ ምንም ለውጥ አላዩም። ሙሉ ለሙሉ ጊዜያቸውን በሶፊ ፕሮግራም የተያዘ ነው። ጡንቻዎቿ ሙሉ ለሙሉ እንዳይዝሉ አነስተኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማሰራት፤ በተሸርካሪ ወንበር ይዘዋት መዞር እና መመገብ ደግሞ የሚጠበቅባቸው የዕለት ተዕለት ተግባር ነው። በደቡብ ስዊድን የምትገኘው ስካራ ከተማ መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ ህጻናቱን ከሪዛይኔሽን ሲንድረም ማዳን ይቻላል። "ከእኛ ዕይታ አንጻር ይህ በሽታ የሚከሰተው ከስደት ጋር በተያያዘ ሳይሆን ቀደም ሲል ካጋጠመ ችግር ወይም አደጋ ጋር የሚገናኝ ነው" ሲሉ የሚገልጹት በሶልሲዳን ህጻናት ማቆያ የግርይኒንግ ሄልዝ ከፍተኛ የማህበረሰብ ሠራተኛ አኒካ ካርልሻምሬ ናቸው። ህጻናት በወላጆቻቸው ላይ ጥቃት ወይም ማስፈራሪያ ሲመለከቱ በህይወታቸው ያለው ወሳኙ ግንኙነት ይቆራረጣል ይላሉ በሶለስደን የሚገኙ የህጻናት ተንከባካቢዎች። "ከዛ በኋላ ህጻናቱ እናቴ ልትንከባከበኝ አትችልም የሚል ግንዛቤ ይይዛሉ። በዚህም በወላጆቻቸው ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጥገኛ የነበሩ በመሆናቸው ተስፋ ይቆርጣሉ። ይህ ሲከሰት ድጋፍ ለማግኘት ወደማን እና ወዴት ሊያዩ ይችላሉ?" ይላሉ ካርልሻመር። ይህ የቤተሰብ ትስስር በድጋሚ ሊገነባ ይገባዋል። ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ግን ልጆቹ እንዲያገግሙ ማድረግ ነው። የሶልሲዳን የመጀመሪያ እርምጃም ልጆቹን ከቤተሰቦቻቸው መለየት ነው። "ያላቸውን ለውጥ ለቤተሰቦቻቸው እንነግራቸዋል። ሆኖም ልጆቹ በሠራተኞቻችን ላይ እንደዲደገፉ ስለምንፈልግ እንዲያወሯቸው አንፈቅድም። ልጆቹን አንዴ ከለየናቸው በኋላ ግን የመጀመሪያውን ምልክት ለማየት ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው የሚያስፈልጉት። ይላሉ። ስለስደተኞች የሚካሄዱ ውይይቶችም በልጆች ፊት አይወሩም። "በራሳቸው መጫወት እስከሚችሉ ድረስ እኛ እንጫወትላቸዋለን፤ እንደንሳለን፤ ሙዚቃ እንሰማለን። ለምሳሌ ጥቂት ኮካ ኮላ አፋቸው ላይ ጠብ እያደረግን የጣፋጭን ጣዕም እንዲቀምሱ እናደርጋቸዋለን። ገና ምግብ በአፍንጫቸው እየወሰዱ ራሱ ማዕድ ቤት ወስደን ምግቡን እንዲያሸቱ እንደርጋለን'' "በህይወት የመቆየት አቅማቸው አብሯቸው እንዳለ እናምናለን። ግን እነርሱ አቅማቸውን ዘንግተውት ሊሆን ይችላል።በእርግጥ ይህን ማድረግ ከፍተኛ ኃይል ይፈልጋል ምክንያቱም ልጆቻቸው በራሳቸው መኖር እስኪጀምሩ እኛ እንኖርላቸዋለን'' አንድ ጨቅላ ለማገገም የሚፈጅበት ረጅሙ ጊዜ ስድስት ወር ነው። (የቤተሰቦቿን ማንንት ለመጠበቅ የሶፊ ስም ተቀይሯል)
news-53019132
https://www.bbc.com/amharic/news-53019132
የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዓመቱ ከማለቁ በፊት ምርጫ እንዲደረግ ወሰነ
የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ምርጫ እንዲደረግ መወሰኑ ተሰማ።
ፎቶ፡ፋይል-የትግራይ ምክር ቤት አባላት ምክር ቤቱ ክልላዊ ምርጫው ይህ ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት አንዲካሄድ ይወስን እንጂ ምርጫው መቼ እንደሚካሄድና በማን እንደሚከናወን አልጠቀሰም። የትግራይ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ታረቀ ምርጫው ከጵጉሜ በፊት እንዲካሄድ መወሰኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የኮሮነቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዘንድሮ ነሐሴ መጨረሻ ላይ ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን አገራዊ ምርጫ ማከናወን አልችልም ማለቱ ይታወሳል። በዚህም ምክንያት የሕገ መንግሥት አጣሪ የመንግሥትን የሥራ ዘመን ባማራዘም ምርጫው የሚራዘምበትን አማራጮች ካቀረበ በኋላ፤ የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ የሚለው አማራጭ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል። ጉዳዩን የመረመረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደግሞ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድስረ ሁሉም የፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች በሥራ ላይ እንዲቆዩ እና ምርጫው የበሽታው ስጋት መወገዱ ከተረጋገጠ በኋላ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው ጊዜ እንዲካሄድ ሲል ከቀናት በፊት መወሰኑ ይታወሳል። ህወሓት ክልላዊ ምርጫ ቢያከናውን "ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም" የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህወሓት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ምርጫው መካሄድ አለበት ሲል አቋሙን ሲያንጸባርቅ ነበር። ህወሓት ከዚህ ቀደም የፌደራል መንግሥቱ የሥራ ዘመኑን በማራዘም ምርጫ ለማካሄድ ያቀረበውን አማራጭ በመቃውም፤ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱኳን ሚደቅሳ ህወሓት ክልላዊ ምርጫ ቢያከናውን "ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም" ብለው ነበር። ወ/ት ብርቱኳን ይህን ያሉት ህወሓት ለቀናት ሲያደርግ የነበረውን ስብሰባ ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው መግለጫ ላይ "መንግሥት የሥራ ዘመኑን በማራዘም ምርጫ ለማካሄድ ያቀረበውን አማራጭ በመቃውም፤ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት አደርጋለሁ" ማለቱ ተከትሎ ነበር። "ክልላዊ ምርጫውን ለማካሄድ አስበው ከሆነ ትክክለኛ አካሄድ አይሆንም። ሕገ-መንግሥታዊም አይሆንም" ያሉት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102 የተቋቋመው እርሳቸው የሚመሩት ምርጫ ቦርድ በፌደራል፣ በክልል እና በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የማስፈጸም ብቸኛ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰው ነበር። ከዚህ ውጪ የክልል መንግሥታትም ሆኑ የፌደራል አስፈጻሚ አካል ተነስተው ምርጫን በተመለከተ ውሳኔ ቢያስተላልፉ ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንምም ብለዋል።
news-56339917
https://www.bbc.com/amharic/news-56339917
ሕጻናት ጤና፡ አሰቃቂ ጥቃቶች ሲፈፀሙ ያዩ ሕፃናት ለምን ዓይነት የአዕምሮ ጤና ችግር ይጋለጣሉ?
ሃዘን ያጠላበት መንደር፤ ስጋት ያንዣበበት አድባር። የተጎሳቆሉ እናቶች፣ ብርታት የከዳቸው አባቶች። ባረሱበት እጃቸው፤ የእርዳታ እህል የሚለምኑ ቤተሰቦች።
እንባ ያቆሩ ዐይኖች ፣ በእንባ የራሱ ተርበትባች ጉንጮች፣ ያደፈ ልብስ ፣ ያረረ ከንፈር፣ መሄጃ የቸገራቸው ትንንሽ እግሮች። ጥቃቶችን ተከትሎ ማሕበራዊ ሚዲያዎችን የሚያጨናንቁ ምስሎች ላይ የሚታዩ ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተፈፀሙ ጥቃቶች ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል። ጉዳት ደርሶባቸዋል። ንብረታቸው ወድሟል። ዘግናኝ ጥቃቶች ቦታና ጊዜን ሳይመርጡ፤ በጨቅላ ሕጻናት ፊት ተፈፅመዋል። ራሳቸው ሕጻናቱ ሳይቀሩ የጥቃቶቹ ሰለባ ሆነዋል። ከእናታቸው አሊያም ከአባታቸው ጉያ ሥር ሳሉ ወላጆቻቸው ተነጥቀው ተገድለውባቸዋል። ድርጊቱ ከልጅነት አዕምሯቸው በላይ የሆነባቸው ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረዋል፤ ያጠፉም እንዳሉ ሰምተናል። በአሃ የሥነ ልቦና አገልግሎት ዳሬክተርና አማካሪ የሆኑት አቶ ሞገስ ገብረ ማሪያም በዓለም አቀፍ ደረጃ በጦርነትና በግጭት ምክንያት የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ይላሉ። በተለይ ደግሞ ካለፉት ሁለት አስርታት ወዲህ ቅርፁን በቀየረ መልኩ የልጆችን አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሁኔታ በሚጎዳ ሁኔታ እጅግ ተባብሶ እንደሚገኝ ይናገራሉ። ሕጻናት በግጭቶችና ጥቃቶች የሚደርስባቸው የሥነ ልቦና ተፅዕኖ እንደ እድሜ ደረጃቸው፤ ማለትም ባላቸው የስሜት፣ የቋንቋና የአስተሳሰብ መዳበር እንደሚለያይ የሚናገሩት አቶ ሞገስ፤ ሕጻናት በዚህ የስሜት ስስነት ላይ ሳሉ ጥቃቶችን ማየታቸው ወይም ማስተናገዳቸው ለከፋ የአዕምሮ ጤና ችግር ይዳርጋቸዋል ይላሉ። እንዲህ ዓይነት አሰቃቂ ጥቃቶችን ሲያዩ፤ የሰው ልጅ ስሜቱን በውጫዊ መንገድ የሚቆጣጠርበትን ሥርዓት [Emotional Regulation] ያፈርሰዋል። ከአስተሳሰብ ጋር ያለውን ሥርዓት ያዛባዋል። ይህ ግን እንደ እድሜ ደረጃቸው ሊለያይ ይችላል። ሥነ ልቦና ማለት አስተሳሰብ፣ ስሜትና ባህርይ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ ስሜትና አስተሳሰብ ሲፈርሱ በባህርይና በአካል ላይ ያለው ተፅዕኖ ጎልቶ እንደሚታይ ይናገራሉ። ሕጻናት እንዲህ ዓይነት ጥቃቶች ሲፈፀሙ ሲያዩ የሚሰማቸው ምን ይሆን? ሕጻናቱ አሰቃቂ ጥቃቶችን ሲያዩ ወዲያው እና እየቆየ ሲሄድ የሚሰማቸው ስሜት አለ። የሚያሳዩት ባህርይም እንዲሁ። ባለሙያው በአጭርና በረዥም ጊዜ የሚታዩ ባህርያት ሲሉ ይለዩታል። . በአጭር ጊዜ በስሜት፡ የመደንገጥ፣ የመረበሽ፣ የፍርሃት ስሜት ይታይባቸዋል። በባህርይ፡ ይህ ለውጥ በእድሜ ደረጃ ቢለያይም ፤ ሕጻናት ከወላጅ ወይም ከተንከባካቢ ጋር ባልተለመደ ሁኔታ የመጣበቅ ወይም መለየት አለመፈለግ ይታይባቸዋል። በተቃራኒው ደግሞ እድሜያቸው ከፍ ባሉት ለብቻቸው መሆን መፈለግ ይስተዋላል። እድሜያቸው እስከ ስድስት ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉት ህፃናት ደግሞ ለብቻ መተኛት ይፈራሉ። መመገብ፣ መጠጣት፣ መተኛት ይቸገራሉ። ቅዠት፣ ሽንትና ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል ዓይነት ከአካል ጋር የተያያዙ ችግሮችም ይታይባቸዋል። በአስተሳሰብ፡ መርሳት ያጋጥማቸዋል፤ ትኩረት ለማድረግ ይቸገራሉ። . በረዥም ጊዜ በረዥም ጊዜ በአብዛኛው የሚታየው የባህርይ ችግር ነው። በባህርይ፡ የሱስ ተገዥ መሆን ፣ የአልኮል ተጠቂ መሆን፣ ወጣት ጥፋተኝነት ከዚህም ሲያልፍ በጎልማሳነት ዘመናቸው ወንጀለኛ የመሆን እድላቸው ከፍተኛ ነው። ያዩትን ወይም የደረሰባቸውን ነገር እነርሱም ሲያደርጉት ሊገኙም ይችላሉ። በአስተሳሰብ፡ የትምህርት ስኬት ላይ አነስተኛ መሆን በስሜት፡ የሃዘን ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ እና ዋጋ የለኝም የሚል ስሜት ይስተዋልባቸዋል። ከዚህ አስከፊ የሆኑ ምልክቶችም ሊታይባቸው ይችላል። እነዚህ ምልክቶች ታዲያ ቶሎ እርምጃ ለመውሰድና መፍትሔ ለመፈለግ እንደሚረዱ አቶ ሞገስ ይናገራሉ። እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱት ሕጻናት ሌላ ሰው ያላየው፣ ያልሰማውና ያልሸተተው ለእነርሱ ሊታያቸው፣ ሊሰማቸውና ሊሸታቸው ይችላል። ጉዳቱ ሲደርስ የሰሙት ድምፅ፣ ሽታ ወይም ያዩት ነገር ተመልሶ ይመጣባቸዋል። ወይም በሌላ ሽታና ዕይታ ቅርፁን ቀይሮ ሊከሰት ይችላል። ይህ ከፍ ባለ የእድሜ ክልልም ሊታይ ይችላል። የሚያጋጥማቸው የጤና ችግር ምንድን ነው? ባለሙያው እንደሚሉት እነዚህ ሕጻናት ከሥነ ልቦና ቁስለት ጋር በተያያዘ ለሚታይ ከፍተኛ የአዕምሮ ጤና ችግር [Post Traumatic Disorder] ይጋለጣሉ። ይህ ችግር ሥር እየሰደደ ሲመጣ ፤ ድባቴ፣ ጭንቀት፣ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የአዕምሮ ህመም -እብደት ደረጃ ሊደርስ ይችላል። በባህርይም፣ በስሜትም፣ በአስተሳሰብም ሆነ በመስተጋብር የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ማከናወን አይችሉም። ከዚህ ችግር እንዴት መውጣት ይችላሉ? አቶ ሞገስ እነዚህ የሥነ ልቦና ችግሮች ልጆች ላይ እንዳይከሰቱ መከላከል ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ይላሉ። ጥቃት ሲፈፀም በማየታቸው ደህንነታቸው ጥያቄ ውስጥ ስለሚገባም ያንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። "በድጋሜ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥበቃ ማድረግ፣ ከፍተኛ የስሜት ጫና ውስጥ ስለሚሆኑ ያንን በማቃለል ጉዳቱን መቀነስ ይቻላል" ይላሉ ባለሙያው። እንዲህ ዓይነት አጋጣሚ እንደሚያጋጥም መንገርና ማረጋገጫ መስጠት እንደሚያስፈልግም ያክላሉ። ይሁን እንጂ ባለሙያው እንዳሉት የስሜት ደህንነታቸው ማረጋገጥ የሚቻለው የደህንነት ሁኔታቸው ሲረጋገጥ ነው። ስሜት በአዎንታዊም በአሉታዊም መልኩ ስለሚጋባ ተንከባካቢዎቻቸው ያለባቸውን የስሜት ጫና የመቋቋም አቅማቸውን ማሳደግም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ባለሙያው ይመክራሉ። የሕጻናቱን ስሜትና ባህርይ መከታተል፣ እንዲያወሩ መፍቀድ፤ ለከፍተኛ የሥነ ልቦና ቀውስ የሚደርሱ ከሆነም ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል። "ብዙ ጊዜ ጥቃቶችና ግጭቶች ሲያጋጥሙ መሰረታዊ ፍላጎቶች ላይ እንጂ ሥነ ልቦናዊ ቁስሉን የሚያይ የለም" የሚሉት አቶ ሞገስ፤ ይህ ችግር የተደበቀና በቀላሉ የሚታይ ስላልሆነ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይናገራሉ። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍላ ወጣቶችን የአዕምሮ ጤና በተመለከተ ባለፈው ዓመት በድረ ገጹ ላይ ያስቀመጣቸው ጥሬ ሀቆች የሚያሳዩት የታዳጊዎች የአዕምሮ ጤና ችግር አሳሳቢ መሆኑን ነው። እነዚህን ችግሮች ለመቀነስ የባለሙያ እገዛ በሌለበት አገር በቀል መፍትሔዎችን ማሰብ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ባለሙያው ይናገራሉ። ለዚህም እንደ እድር፣ ማሕበርና የቡና ዝግጅት ያሉ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ድጋፎችን ማሳደግ ያስፈልጋል። በማውራትና በመነጋገር አንዱ በአንዱ እንዲሽር ለማድረግ እነዚህ ባህላዊ ክንውኖች ያላቸው አስተዋፅኦ የሚናቅ እንዳልሆነ ባለሙያው ያሰምሩበታል። "ሩዋንዳና ደቡብ አፍሪካን በፈታኝ ጊዜዎቻቸው የረዳቸው ይህ ባህላዊ ዘዴ ነው" ሲሉ ምሳሌ ያጣቅሳሉ። "በሥነ ልቦና ቁስል እሽክርክሪት ውስጥ ነው ያለነው" ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፈጣን የሆነ የአዕምሮ እድገት የሚካሄደው በሕፃንነት የእድሜ ክልል ነው። በመሆኑም የወደፊት የአዕምሮ ጤናቸውን የሚወስነውን እውቀት፣ ማሕበራዊና ስሜታዊ ክህሎት የሚቀስሙት በዚህ እድሜ ነው። ልጆች የሚያድጉበት አካባቢም በደህንነታቸውና በእድገታቸው ላይ ወሳኝ ነው። በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት ወይም በሌላ ቦታ የሚያዩት አሉታዊ ድርጊት ለአዕምሮ ህመም የመጋለጥ እድላቸውን እንደሚጨምረው ጥናቶቹ ያመለክታሉ። ይህንን አቶ ሞገስም በሥራ ልምዳቸው ያረጋገጡት ነው። "የዛሬ ፍርሃት፣ ጭንቀትና ግጭት አብዛኛው በልጅነት ያሳለፍነው ቁስል መገለጫ ነው" ይላሉ። ባለሙያው እንደሚሉት ይህ ቁስል በወቅቱ ባለመታከሙ በጉልምስና ወቅት ተንጠባጥቦ ይገኛል። ይህም በትዳር ሕይወት፣ በመሥሪያ ቤት እንዲሁም በአካባቢ ላይ ይገለጻል። "በሥነ ልቦና 'ቁጣ ቁጣን ይወልዳል' ይባላል" የሚሉት አቶ ሞገስ፤ እነዚህ ሕጻናት ያዩት ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ሲደፈር፣ ሲገደል ወይም ራሳቸው ላይ ሲደርስ በመሆኑ አዕምሮ ደግሞ ይህን እንደሚለማመድ ይናገራሉ። የተለመደ ያደርገዋል። በዚህም ምክንያት እነዚህ ሕጻናት የቤተሰብ፣ የመሥሪያ ቤት ወይም የአገር መሪ ሲሆኑ የሚደግሙት ይህንኑ ይሆናል ይላሉ። "ኢትዮጵያ የሥነ ልቦና ቁስል እሽክርክሪት ውስጥ ነው ያለችው" የሚሉት ባለሙያው፤ ይህንን በጊዜ በማስቆምና በማከም አዙሪቱን መቁረጥ እንደሚያስፈልግ መክረዋል።
news-55645230
https://www.bbc.com/amharic/news-55645230
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፡ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዳሊቲ መንደር ስለተፈጸመው ጥቃት የዓይን እማኞች ምስክርነት
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በደባጤ ወረዳ፣ ዳለቲ በሚባል ሰፍራ ማክሰኞ ጥር 4/2013 ዓ.ም ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የገለጸ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የሟቾች ቁጥር ከዚህ በእጅጉ እንደሚጨምር ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አንድ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ድባጤ ወረዳ ጋሊሳ ቀበሌ ተፈናቅለው የሚገኙ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በወረዳው በሚገኝ ቆርቃ ቀበሌ፣ ዳለቲ በተባለች መንደር ላይ ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉ የ82 ንፁሃን ሰዎችን "አስከሬን አንስተናል" ብለዋል። ግለሰቡ ከጥቃቱ በኋላ የተጎዱ ሰዎችን ለመርዳትና የሞቱትንም ለማንሳት ወደ ስፍራው ከደረሱ ሰዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ በጥቃቱ የተገደሉት ሰዎች ቁጥርም ከ100 ሊበልጥ እንደሚችል ጨምረው ተናግረዋል። ቢቢሲ ያናገራቸውና ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቻው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሌላ የዓይን እማኝ ደግሞ በቀበሌዋ ይኖሩ የነበሩ ቤተሰቦቻቸው በሙሉ እንደተገደሉባቸው ገልጸዋል "እኔ ራሴ 105 አስከሬን አንስቼ መኪና ላይ ጭኛለሁ" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ማክሰኞ ዕለት በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 45 ዓመት ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች መሆናቸውን አመልክቷል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለይም በመተከል ዞን ውስጥ ካለፈው ዓመት ማብቂያ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። በተለይ ቡለን በተባለው ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ውስጥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ታኅሣስ 13/2013 ዓ.ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት 207 ንፁሃን ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም ጥቃቱን "ጭፍጨፋ" መሆኑን ገልጸው "በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ" በማለት ሐዘናቸውን በወቅቱ ገልጸው ነበር። በመተከል ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በታጣቂዎች የሚፈፀመውን ግድያ ለማስቀረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የዞኑን የፀጥታና የሕግ ማስከበር ሥራ ተረክቦ እየሰራ ቢገኝም ጥቃቱ አለመቆሙን ከሰፍራው የሚወጡ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ድባጤ ወረዳ እና በጥቃት የሚናጡት ቀበሌዎቿ በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ስር በሚገኙት ስምቦሰሪ፣ ቆርቃ፣ አልባሳ፣ ገፈሬ እና ሙዘን ቀበሌዎች ውስጥ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም እና ኅዳር 5/2013 ዓ.ም ጥቃቶች መፈጸማቸውን እና ሰዎች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አልባሳ፣ ገፈሬና ሙዘን ቀበሌዎች ውስጥ ኅዳር 5 እና 6/2013 ዓ.ም ጥቃት መፈፀሙን የሚናገሩት ነዋሪ፤ በእነሱም ቀበሌ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ለአካባቢው ኃላፊዎች ከሁለት ወራት በላይ እየገለጹ ቆይተው ጥር 4/2013 ዓ.ም ማክሰኞ ዕለት ዳለቲ ቀበሌ ላይ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን አስረድተዋል። በአሁኑ ጊዜ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ቀበሌዎች የተፈናቀሉ ሰዎች በአጠቃላይ ተሰባስበው የሚገኙት በጋሊሳ ቀበሌ መሆኑን ገልጸው፤ ለፈናቃዮቹ ልዩ ኃይልና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጥበቃ እያደረጉላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ጥቃቱ በተፈጸመባቸው ቀበሌዎች ውሰጥ የተለያዩ ብሔሮች ተሰባጥረው እንደሚኖሩ የሚናገሩት ነዋሪዎች ጉሙዝ፣ ሽናሻ፣ አማራ፣ ኦሮሞ እንዲሁም የአገው ማኅበረሰቦች በጋራ የሚኖሩባቸው ቀበሌዎች ላይ ጠቃቱ መድረሱን ተናግረዋል። የተፈፀመው ማንነትን የለየ ጥቃት እንደሆነ በመግለጽም፣ ለዚህም እንደ ማስረጃ ቤታቸው የተቃጠለባቸውና የሞቱ ሰዎች ከአንድ ወገን መሆናቸውን ያስረዳሉ። ግለሰቦቹ ወደ ጋሊሳ ቀበሌ ተፈናቅለው የመጡት ኅዳር 5/2013 ዓ.ም መሆኑን ተናግረው፤ በወረዳው ላለፉት ሁለት ወራት ነዋሪው ያለበትን የደኅንነትና የፀጥታ ስጋት ቢናገርም ሰሚ አለማግኘቱን ይገልጻሉ። ከአራት ወር ሕጻን ጀምሮ ሴቶች እና አዛውንትን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸውን ግለሰቦቹ ያስረዳሉ። ጥቃቱ የተፈፀመ ዕለት የሆነው ምን ነበር? ጥር 4/2013 ዓ.ም ሊነጋጋ ሲል 11፡00 አካባቢ ከቆርቃ ቀበሌ፣ ዳሌቲ በተባለች መንደር የሚኖሩ ግለሰቦች የድረሱልኝ ጥሪ ጋሊሳ ቀበሌ ለሚኖሩ ተፈናቃዮች ማሰማታቸውን ቢቢሲ ያናገራቸው የዓይን እማኝ ያስታውሳሉ። በጋሊሳ ቀበሌ ለሚገኘው የመከላከያ ኃይል ጉዳዩን ማሳወቃቸውንና መኪና ተፈልጎ ወደ ሥፍራው እስኪንቀሳቀሱ ድረስ መርፈዱን በመግለጽ፤ የመከላከያ ሠራዊትና የክልሉ ልዩ ኃይል ባላቸው መኪኖች ተጭነው የተወሰኑት ደግሞ በእግራቸው ወደ መንደሯ ማምራታቸውን ገልፀዋል። መንደሯም ከጋሊሳ ቀበሌ በእግር የ3፡30 ተኩል መንገድ መሆኗን የሚገልጹት ነዋሪዎች ለጸጥታ ለኃይሉ ለመሳወቅና ከቦታው እስኪደርስ ድረስ ሰዓታትን ፈጅቷል። በተጨማሪም ቦታው ለመከላከያ ሠራዊት አዲስ በመሆኑ መንገድ በመምራት ወደ ቀበሌዋ እንደወሰዷቸው ተናግረዋል። ረፋድ ላይ ጥቃቱ ከተፈጸመበት ስፍራ ሲደርሱ በመንደሯ የሚገኙ ቤቶች በእሳት ተኩሰው አየሩ በጭስ ተሸፍኖ ከሦስት የተለያዩ አቅጣጫዎች ታጣቂዎች ከበባ በመፈፀም ተኩስ ይሰማ እንደነበር ያስታውሳሉ። "የመከላከያ ሠራዊቱም ከታጣቂዎች ጋር ተኩስ ገጥሞ የተወሰኑትን መማረኩን እንዲሁም የተወሰኑ ደግሞ መግደሉን" በአካባቢው ነበርኩ ያሉ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የጸጥታ ኃይሉ በቦታው እንደደረሰ በርካታ ንፁሃን ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለው የተወሰኑት ደግሞ ቆስለው የተገኙ ሲሆን፤ የቆሰሉት የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ጤና ተቋም መወሰዳቸውን አክለው ተናግረዋል። የመከላከያ ሠራዊትም በጥቃቱ የተገደሉትን ሰዎች አስከሬን በሁለት አይሱዙ የጭነት መኪኖች መሰብሰቡንና ቢቢሲ ግለሰቡን እስካናገረበት ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ሳይቀበሩ መቆየታቸውን የዓይን እማኙ ገልፀዋል። ሌላ የዓይን እማኝ በደግሞ "ቦታው ላይ በመገኘት ያየሁት እና መኪና ላይ የጫንኳቸው በአጠቃላይ 82 አስከሬኖችን ቆትሬያለሁ" ሲሉ አስከሬኖቹም ወደ ጋሊሳ ቀበሌ መምጣታቸው ተናግረዋል። ሌላኛው የአይን እማኝ በበኩላቸው "እኔ ራሴ 105 አስከሬኖችን" መኪና ላይ ጭኛለሁ ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ከዚያ በኋላ መከላከያ ተጨማሪ አስከሬኖችን ማንሳቱን መስማታቸውና በአጠቃላይ በጥቃቱ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸው ሲነገር መስማታቸውን ለቢቢሲ አስረድተዋል። ግለሰቦቹ አክለውም ነዋሪዎች ጥቃት ሸሽተው ከሙዘን፣ አልባሳ፣ ገፈሬ ቀበሌዎች ሲፈናቀሉ አስከሬኑ አለመነሳቱን ያስታውሳሉ። በአሁኑ ጊዜ "የመተከል ዞን በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ፣ ሰላም መሆኑ እየተነገረ እያለቅን ነው። አስከሬኑን ይዘን ለሰሚ አካል አቤት እንላለን" ያሉ ተፈናቃዮች ንዴትና እሮሯቸውን ለመከላከያ ሠራዊቱ ማሰማታቸውን የዓይን እማኙ ይናገራሉ። በጥቃት ፈጻሚዎቹ ኢላማ ያደረጓቸውን ሰዎች በስለት፣ በጥይትና በቀስት እንደገደሏቸው አስከሬኖቹን የሰበሰቡት የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጋሊሳ ቀበሌ የሚኖሩ ተፈናቃዮች አሁንም ፍርሃት እንዳላቸው ገልፀው፣ መከላከያ ሠራዊት በአካባቢው ከሌለ "ታጣቂዎቹ መጥተው ይገድሉናል" ሲሉ ይሰጋሉ። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈፀመ ባለው ቡድን ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በዞኑ የተቋቋመው ግብረ ኃይል አስታውቆ ነበር። ግብረ ኃይሉ እየወሰድኩት ነው ባለው እርምጃ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የመንግሥት አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢዜአ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ታኅሣስ 13/2013 ዓ.ም በመተከል ዞን ከተፈጸመው የበርካታ ሰዎች ግድያ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አራት የምክር ቤቱ አባላትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወሳል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ካለፈው ዓመት ጳጉሜ ወር አንስቶ በንፁሃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈፀም የቆ ሲሆን በዚህም የተነሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ሲሰደዱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
news-45085694
https://www.bbc.com/amharic/news-45085694
መንግሥት ከኦነግ ጋር ለመደራደር ልዑካን ወደ አሥመራ ላከ
መቀመጫውን ኤርትራ ባደረገው እና በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ ጋር ለመደራደር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የሚመራ ልዑክ ዛሬ ረፋዱ ላይ ወደ ኤርትራ መሄዱን የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኅላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለቢቢሲ ተናገሩ።
በየውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ እና የኦሮሚያ ፕሬዝደንት ለማ መገርሳ የሚመራው የልዑካን ቡድን ኤርትራ ደርሷል ዶ/ር ነገሪ እንዳሉት ውይይቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ይጀመራል። የተቀሩት የልዑካን ቡድኑ አባላት እነማን እንደሆኑ እና ውይይቱ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ ማወቅ ግን አለተቻለም። የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ቀደም ሲል ሦስተኛ ወገን በድርድሩ እንዲኖር መጠየቁ የሚታወስ ነው። • መንግሥት ከኦነግ ጋር ካገር ውጭ ሊወያይ ነው • ኦነግ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን ገለፀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ኤርትራ በሄዱበት ወቅት ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረው ነበር። በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት መንግሥት ከኦነግ ጋር ያለውን ልዩነት ለምን ማጥባብ እንዳልቻለ ተጠይቀው በቅርቡ ልዑክ እንደሚላክ ገልጸው ነበር። የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ይህ ውይይት በስምምነት እንደሚጠናቀቅ እና በምዕራብ ኦሮሚያ ያለውን የደህንነት ስጋትም ይቀርፋል የሚል እምነት አላቸው። • ከምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው? • ''በደኖ የሚባል ቦታን ረግጨው አላውቅም'' አቶ ሌንጮ ለታ
46135126
https://www.bbc.com/amharic/46135126
"የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው" ጄኔራል አሳምነው
ከሰሞኑ በአማራ ክልል ውስጥ በቅማንት ህዝቦች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው፤ ከዚህም በተጨማሪ መተማ ላይ የቅማንትና የትግራይ ተወላጆች ላይ በታጣቂዎች ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ መረጃዎች እየተሰሙ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ የአማራ ክልል የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ቢቢሲ፦ በቅርቡ በቅማንት ተወላጆች ላይ አማራ ክልል ውስጥ ጥቃት እየደረሰ ነው የሚሉ ዘገባዎች ይደመጣሉ። ስለዚህ ያለዎት መረጃ ምንድነው? ጄነራል አሳምነው፦ የቅማንትና የአማራ ሕዝብ ለዘመናት አብሮ የዘለቀ ሕዝብ ነው። በብዙ ነገር የተሳሰረ ሕዝብ ነው፤ ሕብረተሰብ በሚያገናኙ እንደ ባህል እና ቋንቋ ባሉ እሴቶች የተሳሰረ ነው። ሰሞኑን የተፈጠረው ሁኔታ ቀደም ብሎ የተለያዩ ኃይሎች በተለያየ መንገድ የአካቢቢውን ሰላም ለመንሳትና አለመረጋጋቱ እንዲቀጥል ለማድረግ በፈጠሩት ሥራ የተፈጠረ ችግር ነው። እንደ ሕዝብም ሆነ እንደ ተቋም ሲታይ፤ የቅማንት ሕዝብ በተለየ መንገድ ጥቃት የሚደርስበት ተጨባጭ ሁኔታዎች የሉም። ስለዚህ የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኛ ኃይሎች ከሌሎች ጋር በቅንጅት በመሥራት አካባቢው እንዲቃወስ ለማድረግ ሞከረዋል። •"ምንም ከህዝብ የሚደበቅ ነገር አይኖርም" አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ አብዲሳ •አቶ መላኩና ጄነራል አሳምነው ለማዕከላዊ ኮሚቴ ተመረጡ •ከጄኔራሎቹ ሹመት ጀርባ? ለምሣሌ በቅርቡ በተነሳው ግጭት ከአማራም፤ ከቅማንትም ሰዎች ሞተዋል። ቁጥሩ መጣራት ቢኖርበትም በአማራ በኩል የሞተው ያይላል። ይህ ጥቃትን ሳይሆን ግጭትን የሚያመለክት ነው። ነገር ግን ይህንን ለመጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎች ይኖራሉ። በገበሬ ደረጃ ሊያዙ የማይችሉ ትጥቆች ሁሉ ተገኝተዋል። ከጎረቤት ሃገር ሊሆን ይችላል፤ ከጎረቤት አካባቢ ወይም ክልል ሊሆን ይችላል፤ ብቻ የቆየ ጥቅማቸውን ለማሳካት 'ስትራቴጂ' ነድፈው እየተንቀሳቀሱ ያሉ አሉ። ቢቢሲ፦ ብዙ ጊዜ የውጭ ኃይሎች፤ ሰላም የማይፈልጉ እና መሰል አገላለፆች አሉ። ነገር ግን ጣልቃ የሚገባ ኃይል አለ ተብሎ የሚታመን ከሆነ ለምን ስም መጥራት አልተፈለገም? ጄነራል አሳምነው፦ እሱ ይጣራል። ይጣራል ብቻ ሳይሆን አደጋ እስከሆነ ድረስ ደግሞ ትግል ይካሄድበታል። በመረጃ የበለጠ አጠናክረን ይህንን ኃይል ማጋለጥም፤ መታገልም ይቻላል። ብቅ ብቅ የሚሉት መረጃዎች አንድ ላይ 'ሰመራይዝ' (ተጠቃለው) ፤ ከዚህ በኃል እየሆነ ያለው ነገር እናያለን። ለምሳሌ ቅማንት 69 ቀበሌዎች እንዲያደራጅ ተፈቅዶለታል። ኃይሉ ይህ እንዲደራጅ አልፈለገም፤ የብጥብጥ ቀጠና እንዲሆን ነው የፈለገው። እነኚህ ኃይሎች ደግሞ ከጎረቤት ክልል የሚድያ ሽፋን ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ የዛሬ ሁለትና ሶስት ዓመት የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ከሰሞኑ እንደተደረጉ ተደርገው ይቀርባሉ። የሞተው ሌላ ሆኖ እያለ የሞተው ይሄ ነው ይባላል። ላሊበላ ላይ የደረሰ ግጭት እንደቅማንት ሆኖ ይቀርባል። እንዲህ ዓይነት ከእውነታ የራቀ መረጃ ይለቀቃል። ፌስቡክ ያለው ጥሩ ገፅታ እንዳለ ሆኖ መጥፎ የሆኑ መረጃዎች ይሰራጩበታል። ይህንን መረጃ ባትቀበሉት ጥሩ፤ ከተቀበላችሁት ደግሞ ብታጣሩት ደስ ይለኛል። ቢቢሲ፦ ከጎረቤት ክልል ድጋፍ ይደረግላቸዋል የሚል ነገር ነግረውናል፤ የትኛው ክልል ይሆን? ጄነራል አሳምነው፦ እሱን እነግርሃለሁ፤ በሂደት ብዬ ነው። እነርሱም ያውቁታል፤ እኛም እናውቀዋለን። ከእኔ ይበልጥ ሚድያ ላንተ ይቀርባል። ከኔ ልስማው ብለህ ካልሆነ በስተቀር 'ዩ ኖው ኢት ቬሪ ዌል' (በደንብ ታውቀዋለህ)፤ ይሄ በአደባባይ እየተሰራ ያለ ሥራ ስለሆነ። ነገሮች እየጠሩ ሲሄዱ መረጃዎችን አጠናክረን ለእናንተ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሚድያዎችም መረጃ እንሰጣለን። ቢቢሲ፦ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ መተማ ውስጥ ያጋጠመ ችግር አለ። ለምሳሌ የቅማንት እና የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ተፈፅሟል የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው። ስለዚህስ ያለዎት መረጃ አለ? ጄነራል አሳምነው፦ እውነት ነው። ይሄ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቦታዎችም ቤቶች ተቃጥለዋል። የመንግሥት ንብረት ተቃጥሏል፤ የግል ድርጅቶችም ተቃጥለዋል። አሁንም ተልዕኮ ያላቸው ግን ደግሞ ሕብረተቡን የማይወክሉ ሰዎች መተማና ሌሎች አካባቢዎች ችግር ፈጥረዋል። ይሄ እውነት ነው። ሆኖም ግን ሰዉ ከዚህ በፊት አንዳንድ ችግሮች ደርሰውበት ስለነበር እነዚህ ኃይሎች ቢጋጩ የሚደርሰውን በመስጋት እየለቀቀ ካምፕ (ማዕከል) ውስጥ ይገባል፤ ወደውጭም ይሄዳል፤ ሌሎችም አማራጮች ይጠቀማል። ይሄ አጋጣሚውን መጠቀም የፈለጉ ዘራፊዎች የወሰዱት እርምጃ ካልሆነ በቀር ይህ ሕዝብ ውጣልኝ፤ ልቀቅልኝ የሚል ሕዝብም አይደለም። በማንነታቸው ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከለላ እየሰጠ ያለ ሕዝብ ነው። ግጭቱ እውነት ቢሆንም መንስዔውና አካሄዱ ግን አሁን ባልኩት መንገድ ነው። ከሕብረተሰቡ ጋር የመነጋገር ዕድል ገጥሞን ነበር፤ አንድም ሕዝብ እንዲወጣ አይፈልግም። የነሱም ቤተሰቦች ሌላ ቦታ ይገኛሉ። እንዲህ ዓይነት ነገር በሃገራችን እንዲፈጠር አይፈልጉም። ቢቢሲ፦ ያነጋገርናቸው እና ከዚህ አካባቢ ተፈናቅለናል የሚሉ ሰዎች ሕዝቡን ሳይሆን የሚወቅሱት የአማራ ክልል ታጣቂዎችን ነው። ጄነራል አሳምነው፦ 'ኔቨር'። ይሄ ከእውነት የራቀ ነው። የአማራ ታጣቂዎች የሉም። ምናልባት በተለያየ ወንጀል ወደበረሃ ወጥተው፤ ወደ ውጭ ወጥተው መጥፎ ድርጊት የሚፈፅሙ ወገኖች አሉ። 'ባይዘወይ' (በነገራችን ላይ) አካባቢው የግብርና ኢንቨስትመንት በስፋት የሚከወንበት በመሆኑ ሰዎች ከየትኛው የሃገሪቱ ክፍሎች መጥተው ይሰራሉ። ወቅቱ ደግሞ ሰሊጥ የሚታጨድበትና የሚወቃበት ነው። እና እንዲህ ዓይነት ችግር ሲፈጠር አጋጣሚውን ተጠቅመው ለመውረርና ለመዝረፍ ሙከራ ያደርጋሉ። 'ኤክሰፕሽናል' (ያልተለመደ) ሁኔታ አይደለም። እዚያ አካባቢ ያለው ሁኔታ የፈጠረው ነው። እንጂ የአማራ ክልል ታጣቂ የፈጠረው አይደለም። እንዴት ተደርጎ ይታሰባል? እምልህ ጥያቄውም ይከብዳል፤ አይደለም ድርጊቱ። ቢቢሲ፦ መተማ ውስጥ ግጭት ከሆነ የተፈጠረው፤ ማን ከማን ጋር ነው የተጋጨው? ጥቃትም ከሆነ ማን አጥቂ? ማንስ ነው ተጠቂ? ጄነራል አሳምነው፦ አሁን እዚያ አካባቢ ልዩ ኃይል አለ፤ መከላከያ አለ፤ ፖሊስ አለ፤ በአካባቢ ደረጃ የተደራጁ ሚሊሻዎች አሉ። እነሱ የሚችሉትን ያህል እየተከላከሉ ነው። እያገዙት ነው ሕዝቡን። ግን አንድ ቦታ እንትን ስትል እኛ የምንሸፍነው እና እንቅስቃሴው ይለያያል። በእንዲህ ዓይነት አጋጣሚ የሚፈጠር ካልሆነ በስተቀር ማን ከማን ጋር ነው ልትለው አትችልም። ይሄ ከተራ የወሮበላ ድርጊት ያለፈ ሌላ ሁኔታ ይኖረዋል ብዬ አላምንም። እና ስለሰጠኸኝ ዕድል በጣም አመሰግናለሁ። ቢቢሲ፦ አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ጀኔራል. . . ከመተማው ክስተት በኋላ የትግራይ ክልል መንግሥት መግለጫ አውጥቶ ነበር። መግለጫው ላይ 'አንዳንድ የአማራ ክልል ባለሥልጣናትም እጃቸውን አስገብተዋል' ይላል. . . ጄነራል አሳምነው፦ ይሄ. . . በፍፁም ስህተት ነው። እንደተለመደው የሚድያ ሽፋን እውነት ነው፤ ስህተት ነው ለማለት አይደለም። በአካባቢው የተንቀሳቀሰ የመንግሥት አካል የለም። ካለም እኔ ነኝ የተንቀሳቀስኩት። እኔ ደግሞ ለአካባቢውና ለሃላፊነቱ እንግዳ ነኝ። ስለዚህ ከአካባቢው ሰዎች ጋር ለመተዋወቅ፤ ችግሩን አነጋግሮ ለመፍታት ነው የሄድኩት። ይሄን 'ኦፊሻሊ' እነሱም ያውቁታል። የኔና የሕዝብ ግንኙነት ደግሞ ይታወቃል። እና 'አንዳንድ' የሚሉት እንዳው ለማለት ካልሆነ በቀር እውነታው ይህ ነው። ሶሳይቲው (ማሕበረሰቡ) መረጃ አይደርሰውም ተብሎ ስለሚታሰብ እውነት ለማስመሰል፤ እሳቱን እያቃጠሉ ያሉት እነሱ ሆነው እያለ፤ መልሰው ደግሞ ይህን መግለጫ ይሰጣሉ። የክህደት ፕሮፓጋንዳቸው ሁሉ እንደቀጠለ ነው ያለው፤ እነዚህ ሰዎች አልደከሙም። እና እነሱ ያወጡት መረጃ እውነት አይደለም። የሄድኩትም እኔ ነኝ፤ ያነጋገርኩትም እኔ ነኝ። እኔ ደግሞ የዛ ምንጭ ልሆን አልችልም። ምክንያቱም ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎችን ከመርዳት ውጭ ያለፈ ራዕይ የለኝም እኔ። ይሄንን ጥያቄ እንደው እንዲሁ በሌላ መንገድ ብታየው ጥሩ ነው።
news-46691336
https://www.bbc.com/amharic/news-46691336
"በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ
የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር የሆኑትና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋን በጽህፈት ቤታቸው አግኝተናቸው በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገናል። ቢቢሲ አማርኛ፡ አንዳርጋቸው ታፍኖ መወሰዱን ባወቅክባት ቅፅበት ምን ተሰማህ?
ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ፡ አንዳርጋቸው የተያዘ ጊዜ ኒው ዮርክ ነበርኩ። እንደተያዘ እዚያው የመን እያለ ነው የሰማሁት፤ በተያዘ በግማሽ ወይንም በአንድ ሰዓት አብረው ሲበሩ ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ነው የሰማሁት። እዚያ ያሉ እኛን የሚያውቁ ሰዎች እንደዚህ አይነት ነገር አለ ተከታተሉ ብለው የነገሩን ያኔ ነው። በዚያ በኩል እንደሚሄድም አላውቅም ነበር፤ በሌላ በኩል እንደሚሄድ ነበር የማውቀው። ያው መጀመሪያ ላይ ትደነግጣለህ። የመጀመሪያ ሥራህ የሚሆነው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄድ ወይንም ችግር እንዳይደርስበት ማድረግ የሚቻለውን ለማድረግ ለተለያዩ መንግሥታት፣ አቅም ላላቸው ሰዎች፣ መንገርና አንድ ነገር እንዲያደርጉ መሞከር ነበር። ቢቢሲ አማርኛ፡ እርሱ እስር ቤት በነበረበት ወቅት እርሱን በተመለከተ ምን አይነት ስሜቶችን አስተናገድክ? ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ፡ ከአንዳርጋቸው ጋር ለረዥም ጊዜ ነው የምንተዋወቀው። ብዙ አውርተናል። ምን እንደሚፈልግ አውቃለሁ። እኔም ምን እንደምፈልግ ያውቃል። ሲታሰር የተወሰነ የድርጀቱን ሥራ ኃላፊነት እርሱ ስለነበር የወሰደው ኢትዮጵያ መምጣቱን ካወቅሁ ጊዜ ጀምሮ ለእኔ ግልፅ የሆነልኝ በምንም አይነት እንደማይፈቱት፣ እንደማይገድሉትም አውቅ ነበር። ጥያቄው ያለው እንዴት ታግለን ቶሎ ይህንን ነገር እናሳጥራለን የሚል ነው። ከዛ በኋላ ብዙ ጊዜ አልፈጀብኝም ሥራዬን ሁሉ ትቼ እርሱ የጀመራቸውን ሥራዎች ወደ መቀጠል ነው የገባሁት። በእንዲህ አይነት የትግል ወቅት አንዳርጋቸው ሲታሰር ምን ይፈልጋል? ማንም ሰው ቢለኝ፤ የታገለለትን አላማ ከዳር እንድናደርስለት ነው እንጂ የሚፈልገው ሌላ ለግሉ እንዲህ አይነት ነገር ይደርስብኛል የሚል የስሜት ስብራት ውስጥ እንደማይገባ አውቅ ስለነበር፤ ያለኝን ጠቅላለ ጉልበቴን ያዋልኩት እንዴት አድርገን ይህንን ትግል በቶሎ ገፍተን እርሱንና በየቦታው የሚታሰሩትን ጓዶቻችንን ነፃ እናወጣለን ወደ ሚለው ነው። • «አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7 •"ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ተገንጥሎ የሚወጣ አካል የለም"-ኤፍሬም ማዴቦ • አርበኞች ግንቦት 7 ፈርሶ አዲስ ፓርቲ ሊመሰረት ነው ከዚያ ባሻገር ግን የታገልንለትን አላማ፣ ኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ የማድረግ አላማ፣ ከዳር እንዴት እናደርሳለን የሚለው ነው፤ ከዚያ ውጪ ሌላ አልነበረም። ከመጀመሪያው አንድ ቀን ሁለት ቀን ውጪ ጠንካራ የሆነ የስሜት መዋዠቅ ውስጥ መግባት አይገባም ብዬ ነው ለራሴ የነገርኩት። አሁን ሥራው ይህንን ነገር ከዳር ማድረስ ነው። በእንዲህ አይነት ትግል ውስጥ ችግሮች ይፈጠራሉ፤ ግን እያንዳንዱ ችግር ላይ ከፍተኛ የሆነ የስሜት መዋዠቅ ካስቀመጥክ ሥራ አትሰራም። ሁሉን ነገር ዘግቼ ይህንን ነገር እንዴት ከዳር እናደረሳለን የሚለው ላይ ነው ጊዜዬን ያጠፋሁት። ቢቢሲ አማርኛ፡ አሁን ያለውን ለውጥ የሚሾፈረው በኢህአዴግ መሆኑ ምን አይነት ስሜት ነው የሚፈጥረው? ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ- አንዱ ትልቁ ጥያቄ ኢህአዴግን የምናየው የድሮው ኢህአዴግና የአሁኑ ኢህአዴግ አንድ ነው፤ ወይንስ ቢያንስ ያንን ለውጥ ካመጡ ሰዎች በኋላ በመሰረታዊ መልኩ ለውጥ አድርጓል የሚለውን መመለስ አለብህ። የትግል ለውጥ ስትራቴጂ ለውጥ ስናደርግ የወሰንነው ይህንን ለውጥ ለማምጣት የመጡት ሰዎችን፤ በእንዲህ አይነት የተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ ስትሆን አንዱ ሥራህ የመንግሥት ስልጣንን በያዘው ኃይል ውስጥ ያለውን ነገር ማጥናት ነው። ስለዚህ በኢህአዴግ ውስጥ የሚደረጉትን ለውጦች እንከታተል ነበር፤ እና አንዱ ትልቁ ጥያቄ የነበረው እነ ዐቢይ ሲመጡ ኢህአዴግን በአዲስ መልኩ ለማስቀጠል የመጡ ሰዎች ናቸው ወይንስ እውነተኛ ለውጥ ፈልገው የመጡ ናቸው የሚለውን መመለስ ነበር። እነዚህ ሰዎች ዝም ብሎ በፊት የወያኔ ሥርዓት ይከተል የነበረውን ነገር ለማስቀጠል የሚያስቡ ሰዎች እንዳልሆኑ ስንረዳ ብዙ ጊዜ አልወሰደብንም። ምክንያቱም በከፊል የመጡትም በህዝብ ትግል ነው። ሀያ ምናምን ዓመት ያልተቋረጠ ትግል ሲካሄድበት የነበረው ከዛም ሦስት ዓመት ደግሞ ያላቋረጠና የተጋጋለ ሰፊ የህዝብ ትግል ሲካሄድበት የነበረው ነው። ኢህአዴግ በነበረበት ሊቀጥል እንደማይችል ግልፅ የሆነበት ጊዜ ነው። በዚያን ጊዜ የመጡት እነዚህ ሰዎች ኢህአዴግን ሸውደን ሌላ አዲስ መልክ አምጥተን እናስቀጥል ብለው የሚያምኑ ሳይሆኑ በርግጥም የበፊቱ ሥርዓት ተሸንፎ የመጡ ናቸው። ይህንን አንዴ ከወሰንክ በኋላ፣ ተጋግዘህ ያንን ሥርዓት ለማቆም ትሞክራለህ እንጂ በፊት የነበሩት ሰዎች እንዲህ ነበሩና በመሳሪያ ልቀጥል የምትለው ነገር አይደለም። እኛ በምንም አይነት፣ መቼም ቢሆን የመሳሪያ ትግልን እንደጥሩ ነገር አድርገን ገብተንበት አናውቅም። ምርጫ አጥተን የገባንበት ነው። ያን አላስፈላጊ የሚያደርግ ነገር ሲፈጠር ደቂቃም አልፈጀብንም። ተመልሰን ወደ እውተኛ ሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ ወደ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ መንገድ መሄድ የተሻለ ነው ብለን ነው የገባንበት። • "ወትሮም ቢሆንም የትጥቅ ትግል ፍላጎት የለንም" ግንቦት 7 • "ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢህአዴግ ውስጥ ወጥ ነው ማለት ባይቻልም ለውጡን ይዘው የመጡት ኃይሎች በርግጥም ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚፈልጉ መሆናቸውን እናምናለን። ያንን ሥርዓት ለማምጣት ከእነርሱ ጋር አብረን እንሰራለን፤ ከዚያ በኋላ ኢህአዴግ ካሸነፈ፤ እኛ እኮ በፊትም ኢህአዴግ ለምን አሸነፈ አይደለም፤ የሕዝብ ፍላጎት የህዝብ ፈቃድ አግኝቶ ያሸንፍ ነው የምንለው። ማንም የህዝብ ፍቃድ አግኝቶ ያሸንፍ የህዝብ መብት ይከበር፣ ሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ። የህግ ልዕልና ይኑር። እነኚህ ናቸው ጥያቄዎቹ። ማን ስልጣን ያዘ አይደለም። ዋናው ጥያቄ በምን መልክ ስልጣን ይያዛል? የህዝብ ፈቃድ አግኝቶ ነወይ? ህዝብ በፈለገ ጊዜ ሊያወርደው የሚችል ነወይ? ከዛ በተጨማሪ ደግሞ እውነተኛ ነፃ የሆኑ ተቋማት አሉ ወይ? ፍርድ ቤቱ በነፃነት ይሰራል ወይ? ጦር ኃይሉ በርግጥም ህብረተሰቡን የሚጠብቅ ነው ወይስ የአንድ ፓርቲ መሳሪያ? የምርጫ ተቋሞቹ እርግጥም ነፃና የህዝብ ፍላጎት የሚንፀባረቅባቸው ምርጫዎች ለማድረግ ፈቃደኞች ናቸው? እነዚህ ናቸው ጥያቄዎቹ። ያንን ለማድረግ ፍላጎት ያለው አካል እስከመጣ ድረስ እኛ ምንም ችግር የለብንም። ቢቢሲ አማርኛ፦ ሥርዓቱን ሰው ባይጥለው ኢኮኖሚ ይጥለዋል ትል ነበር። አሁን ያለውንስ መንግሥት? ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ፡ ይኼ አዲሱ የለውጥ ኃይል ከነበረው የወጣ ነው ብለህ ብታስብ፣ ፕሮፓጋንዳውን ምናምኑን ትተህ የተረከበው ኢኮኖሚ ደንበኛ የዝርፊያ ሥርዓት የሽፍታ ኢኮኖሚ ሥርዓት ነበር። ዝም ብለህ ያገኘኸውን ዘርፈህ የምትሄድበት። የነበሩትን ፕሮጀክቶች ይካሄዱ የነበሩትን እንዳለ ብታይ ከዝርፊያ ጋር የተያያዙ ናቸው። የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ምናምን ብለህ አንድ ጤነኛ ሰውና ስለከተማ ትራንስፖርት የሚያውቅ ሰው እንዲህ አይነት የከተማ ትራንስፖርት፣ በዚህን ያህል ወጪ አውጥቶ አይተክልም ነበር። በጣም ቀላል የሆኑ፣ በቀላሉ የከተማዋን የትራንስፖርት ችግሮች የሚፈቱ፣ እንደዚህ ከተማዋን ለሁለት ከፍለህ አስቀያሚ ሳታደርገው ልትፈታ የምትችልባቸው መንገዶች ነበሩ። ፕሮጀክቶቹ በአንድ መልኩ ወይም በሌላ ለመስረቂያ ተብለው የተዘረጉ ናቸው። ለዚህ ነው ማለቅ ያልቻሉት። ለዚህ ነው ከአስር ከሃያ እጥፍ በላይ ወጪ የሚያስወጡት። እነኚህ ሁሉ የሆኑት ደግሞ በሕዝብ ስም በሚገኝ ብድር ነው። ይህ ሁሉ ብድር ሀገሪቱ ላይ ተከምሮ ወደ ሰላሳ ቢሊየን ዶላር ብድር ያለባት ሀገር ነች። ይህ የሆነው ያ ሁሉ ብድር ከተሰረዘ በኋላ፣ በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ የመጣ ይህንን የዘረፋ ሥርዓት ለማቆየት የተዘረጋ ሥርዓት ነው። ይኼ ነገር መጥቶ መጥቶ በተወሰነ ደረጃ ኢኮኖሚውን ዝም ብሎ ያራግበዋል። ምክንያቱም ዝም ብሎ ገንዘብ ኢኮኖሚ ውስጥ ስላለ። በኋላ ላይ ግን ተንገራግጮ መቆሙና ችግር ውስጥ መጣሉ የማይቀር ነው። እና በዚህ ምክንያት ይህንን ሥርዓት የተረከቡት ሰዎች በጣም ከባድ የሆነ ችግር ይገጥማቸዋል። አንደኛው እዳውን መክፈሉ፤ ሁለተኛ በአጠቃላይ የንግድ ሥራን በሚመለከት ያለው ባህል ተበላሽቷል። ሁሉም በስርቆት በማጭበርበር በምናምን አገኛለሁ ብሎ የሚያስብ የኢኮኖሚ ክላስ ነው የተፈጠረው። ሀብታም የሚባሉትን፣ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ሚሊየነር ሆኑ የሚባሉትን፣ አይነት ግለሰቦችን ብታይ ቁጭ ብለው አስበው ምን ያዋጣል ለህብረተሰቡ የተሻለ እቃ እንዴት እናቅርብ በማለት አይደለም። ወይ መሬት ዘርፈው፣ ወይ ከባንክ ገንዘብ ተበድረው ያገኙት ነው። በዚያ አይነት መሰረት ላይ የቆመ ኢኮኖሚ ሁል ጊዜ ችግር ይገጥመዋል። ይህንን ሁሉ መቀየር በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ ያሉብህን ችግሮች መፍታት ብቻ ሳይሆን የንግድ አመለካከቱን ባህሉን ራሱ መቀየር በጣም ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ ነገር ነው። • "አንዳርጋቸው ይለቀቅ አለበለዚያ ሥልጣኔን እለቃለሁ" • "ሰው እየሳቀ መሞት እንደሚችል አሳያችኋለሁ ነበር ያልኳቸው'' አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ • «የሠራዊታችን አባላት በክብር ይሸኛሉ» ግንቦት 7 ይህንን ለማስተካከል ግን በመጀመሪያ የፖለቲካው ሥርዓቱ መስተካከል አለበት። ከዚያም ባሻገር ግን ሰላምና መረጋጋቱ ወዲያውኑ መምጣት አለበት። ይህንን የፖለቲካ ነገር ሳታስተካክል የኢኮኖሚውን ነገር ማስተካከል ከባድ ነው። ለዚህ ነው ቅድሚያ የፖለቲካ ማስተካከያዎች መወሰድ ያለባቸው እንጂ፤ ቶሎ ብሎ የእነዚህን የኢኮኖሚ ችግሮች አንድ በአንድ መመልከት ግዴታ ነው። መንግሥትም ይኼን ይገነዘባል ብዬ አስባለሁ። የለውጥ ኃይልም ስለሆነ ከሌሎችም ሀገሮች በተወሰነ መልኩ እዳውን ለመቀነስ ትብብር ያገኛል ብዬ አስባለሁ። ምንም እንኳ ፖለቲካውን የመፍታት እርምጃ መውሰድ ቀዳሚ ቢሆንም የኢኮኖሚውንም ችግር ለመፍታት በአንድ ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት። ቢቢሲ አማርኛ-አንዳንድ የተወረሱብህን ንብረቶች ለማስመለስ ሞክረሃል? ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ እስካሁን አልተመለሱም። ይኼ ለውጥ ስለእኔ አይደለም። 100 ሚሊየን ህዝብ የሚበላው ያጣ ያለበት ሀገር አሁን የእኔን ንብረት መለሱ አትመለሱ በጣም ትልቅ ነገር አይደለም። ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀ-መንበር ቢቢሲ አማርኛ- ከኢኮኖሚ ውጪ የአብይ አስተዳደር ትልቁ ፈተና ከየት ይመጣል? ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ የደህንነት፣ ሰላም የማረጋጋት፣ ባለፈው27 ዓመት የተፈጠረው የክልል አደረጃጀት። የክልል አደረጃጀቱ ደግሞ ዝም ብሎ በዘር ላይ፣ በደም ቆጠራ ላይ መመስረቱ ብቻ አይደለም። በዚያ ላይ የተመሰረተው አከላለል የራሱ ጦር ያለው አገር ነው። አሁን እነዚህ ክልሎች የምትላቸው የራሳቸው ሀያ ሺህ፣ ሰላሳ ሺህ. . . ጦር አላቸው የሚባል ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም። በአንድ ሀገር እንደዚህ አይነት ኃይል ሊኖር የሚገባው የመንግሥት መከላከያ ነው። ለሁሉም እኩል የሆነ፣ ሁሉንም በጋራ የሚያገለግል፣ የሁላችንንም ደህንነት የሚጠብቅ ኃይል። አሁን ግን በሁሉም ክልሎች ያሉ ኃይሎች አሉ። እነዚህን ሁሉ እንዴት አድርጎ በአንድ ሀገራዊ የመከላከያ እዝ ስር ታደርጋቸዋለህ? በየአካባቢው ከብሔር ጋር በተያያዘ የተነሱ ግጭቶችን እንዴት ታስቆማቸዋለህ? እንደ አገር ወይ ከዚህ ችግር ወጥተን እንበለፅጋለን። ወይ እንደሃገር እንፈርሳለን። የተወሰነ ቡድን አልፎለት፣ ሌላው የማያልፍለት አገር ሊኖረን አይችልም። ሁላችንም ተሰባስበን የምንኖርባት፣ የሁላችንም መብት የተከበረባት፣ የሁላችንም ባህል የሚከበርባት፣ የሁሉም ቋንቋ የሚከበርባት የተረጋጋች ሀገር መፍጠር በጣም ከባዱ ከእነ ዶ/ር አብይ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ይሄንን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት ሂደት ላይ የሚገጥመን ችግር ነው። • የእስረኞች መፈታትና የማዕከላዊ መዘጋት ውሳኔ አንድምታዎች ነገር ግን በደንብ መነጋገር ከቻልን በማስፈራራት ሳይሆን ቁጭ ብለው እየተነጋገሩ ህብረተሰቡ ያሉትን አማራጮች እየሰማ የምንነጋገርበት አይነት የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር ከቻልን፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በምን አይነት የፖለቲካ ሂደት ፖለቲካቸውን እንደሚያስተዋውቁ በደንብ ከተስማሙና ሁሉም ለዚያ ታማኝ ከሆኑ የምንወጣው ችግር ነው። የሚያቅተን አይደለም። አሁን ብዙ ችግር ያለ ይመስላል። ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች ማስተካከል ከቻልን ወደዚያ እንሄዳለን። ግን ትልቁ ተግዳሮት አሁን ያለው ግን ይኼ ነው። ፖለቲካውን ማረጋጋት፣ ፖለቲካውን ወደ ሰለጠነ ፖለቲካ መውሰድ ትልቁ ተግዳሮት ነው የሚመስለኝ። ቢቢሲ አማርኛ፦ አሁን ያለው የሀገሪቷ ነባራዊ ሁኔታ አንተ ስትሄድ ከነበረው በበለጠ የብሔርተኝነት ስሜት ናኝቶ በኦሮሚያና በአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ተቃውሞ ሲገጥማችሁ እያየን ነው። እንዲህ ባለው ሁኔታ የድጋፍ መሰረታችን የት ነው የምትሉት? ፕሮፌ. ብርሃኑ፦ ሁለት ነገር ማንሳት እፈልጋለሁ። አንደኛ ለእኛ የሚያሳስበን ነገር ምን ያህል የፖለቲካ ድጋፍ የት እናገኛለን የሚለው አይደለም። ትልቁ የሚያሳስበው ጥያቄ ይህችን አገር እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አገር ማድረግ ላይ ነው። ትልቁ ጉልበታችንን የምናፈስበት ጉዳይ እሱ ነው። ሁለተኛ አንድ ነገር እውነታ ሆኗል ማለት አይቀየርም ማለት አይደለም። ኢትዮጵያ እኮ ደሃ ሀገር ነች። ይሄ እውነታ ሁሌም ደሃ አገር ያደርጋታል ማለት አይደለም። የተለያዩ ፖሊሲዎችንም ያረቀቅነው ይህንን እውነታ ለመቀየር ነው። የኢትዮጵያም የፖለቲካ እውነታ በአብዛኛው ለ27 ዓመት ይሰማው የነበረ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ብሔር ብሔረሰቦች ስሜት ውስጥ ገብተዋል ከሆነ አንደኛ ቁጥሩ ላይ መስማማት አንችልም። ምክንያቱም በተጨባጭ የምናውቀው ነገር የለም። ምን ያህሉ ሰው በዜግነት ፖለቲካ ያምናል? ምን ያህሉስ በብሔር? የሚለው ሁኔታ ላይ በተጨባጭ የተሰራም ሆነ የተሰበሰበ ጥናት የለም። በአብዛኛው ልኂቅ በብሔር ፖለቲካ ውስጥ እንደተዘፈቀ ግልፅ ነው። ህብረተሰቡ ገብቷል ወይ? የሚለው አጠራጣሪ ነው። ሁለተኛ ብዙ ሰው ዘንግቶታል እንጂ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ኢትዮጵያ ማህበረሰቧ የተደባለቀ ነው። ንፁህና ያልተቀላቀለ ማህበረሰብ ለማግኘት አዳጋች ነው። ሦስትና አራት ትውልድ ብንቆጥር ሁላችንም ከተለያየ ብሔር ጋር የተደባለቅን ነን። እሱ ቀርቶ በአንድ ትውልድ እንኳን አባት አንድ ብሔር እናት ሌላ ብሔር ሆና የተወለደው በትክክለኛ መንገድ ቢቆጠር ከማንኛውም ከአንድ ብሔር ነኝ ከሚለው የሚበልጥ ይመስለኛል። ይሄ ሁሉ ከዚህ የብሔር ፖለቲካና ከመጣው ግጭት መውጣት የሚፈልግ የማህበረሰብ አካል ነው። እኛ የምንለው አንደኛ እነዚህ ሃሳቦች በነፃነት የሚገለፁበት፣ ህብረተሰቡ ከስሜት ወጥቶ ለአገራችን፣ ለህዝባችን፣ ለራሳችን የሚጠቅመን የቱ ነው ብሎ በደንብ ማሰብ በሚጀምርበት ጊዜ እነኚህ ነገሮች ይቀየራሉ። የፖለቲካ ስሜት የማይቀየር በድንጋይ ላይ የታተመ ነገር አይደለም። ሁልጊዜም ይቀያየራል። ከአርባ አመት በፊት ሁላችንም ሶሻሊስቶች ነበርን። የሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለም በተግባር ሲታይ ምን እንደሆነ ካየ በኋላ ነው ሰው ሁሉ የሚያዋጣ አለመሆኑን ተረድቶ የተቀለበሰው። ከ27 ዓመት በፊት ይሄ የዘር ፖለቲካ ሲመጣ፤ ብሔር ብሔረሰቦች በሰላም የሚኖሩበት ብልፅግና ያለበት ሁሉም እኩል የሚሆንበት ተብሎ ነበር። አሁን ስናየው ግን ሰላምና እኩልነት የሌለበት፣ ብሔርና ብሔረሰቦች ራሳቸውን ማስተዳደር ያልቻሉበት፣ የውሸት እንደሆነ ማህበረሰቡ ተገንዝቦታል። አሁን እንግዲህ መጪውን ጊዜ ሰው ቁጭ ብሎ ማሰብ የሚጀምርበት ጊዜ ነው። በነፃነት ማሰብ፣ መወያየትና ሃሳቦቹን ለህብረተሰቡ ማቅረብ ከቻልን እኔ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያን በዜግነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ይመርጣሉ ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ አያስፈራኝም! ስለዚህ ትልቁ ነገር እኛ እንደ ፓርቲ ምን ያህል ድምፅ እናገኛለን፣ የቱጋ እናሸንፋለን የሚለው አይደለም፤ ጥሩ የፖለቲካ ምህዳር ተፈጥሮ ሁሉም ሃሳቦች በነፃ የሚንሸራሸሩበት፤ በውሸት ስሜት ህብረተሰብን ማነሳሳት የሚቀርበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንፈልጋለን። ስሜት፣ መገፋፋትና ዘላቂ ጥቅምህን ማወቅ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ቀስ ብለው ሰዎች መወያየት ሲጀምሩም ነው ለእኔ፣ ለቤተሰቤ የሚበጀኝ፤ ዘላቂ ጥቅሜ ምንድን ነው? ብለው ማሰብ የሚችሉት። በዚያ ጉዳይ ላይ የዜግነት ፖለቲካ ከምንም ነገር በላይ ለዚች ሀገር ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና መሰረት እንደሆነ ጥያቄ የለንም። ለዚሀም ነው ዛሬ ባይሆን መቼም ወደፊትም የዜግነት ፖለቲካ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የማናስገባው። ቢቢሲ አማርኛ፡ ኤርትራውስጥ ስትንቀሳቀሱ በነበረበት ወቅት ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር የነበራችሁ ግንኙነት ምንድን ነው? ፕሮፌ. ብርሃኑ፡ ኤርትራ በነበርንበት ጊዜ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር ጋር ተገናኝተን አናውቅም። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላት ጋር [ማለትም] ከተራ አባላት ጋር በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ከተለያዩ ሰዎች ጋር እንገናኛለን። ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የመጡ ብዙ የኦሮሞ ተወላጅ አባሎች ነበሩን፤ አሉን። ከብሔር ውጪ የሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ክፍት የሆነ ድርጅት ስለሆነ ከየትም አማራም፣ ትግሬም፣ ኦሮሞም የሚገባበት ድርጅት ነው። ብዙም ችግር ስላልነበረ ብዙ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጋዮች የነበሩ አባሎች ነበሩን። እኛም ጋር አባል ሳይሆኑ ኤርትራ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ብዙ የኦሮሞ ወገኖቻችን ጋር በጓደኝነት፣ በወዳጅነት ስንሠራ ነበር። ከኦነግ ከወጡት ከእነ ከማል ገልቹ፣ ኮለኔል አበበ ጋር ብዙ ጉዳዮች ላይ አብረን እንወያያለን። ለሀገራችን የሚሻለው ምንድን ነው? የሚሉ ነገሮች ላይ እንወያያለን። እንደ ድርጅት ከዚህ በፊት ጀምሮና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ከሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ጋር አብረን እንሠራ ነበር። ከኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፍሮንት ጋር በጋራ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የሚል ፈጥረን ስንንቀሳቀስ ነበር። ከነከማል ገልቹ ጋርም ተመሳሳይ ነበር። ስለዚህ ለእኛ ኦሮሞ ሆነ፣ ትግሬ ሆነ፣ አማራ ሆነ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። እንደ ድርጅት የሀገሪቱን አንድነትና ለሁሉም ሕዝቦቿ እኩል የሆነች ሀገር እንድትሆን የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጋር አብረን እንሰራለን። አሁንም የኦሮሞ ወገኖቻችን ድርጅታችን ውስጥ አባል ናቸው። አሁን ካለው በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ ጋር ኤርትራ ከገባን ሳይሆን ከሰባት፣ ስምንት ዓመት በፊት እንዴት በጋራ አብሮ እንደሚሠራ ውይይት ነበረን። ከዚያ በኋላ እዛም ውስጥ ችግሮች ነበሩ። እኛ ከበፊትም የነበረን ግልጽ የሆነ አንድ አቋም ነው። ለአገር አንድነት ቅድሚያ መስጠት አለብን። እንደ ሀገር አንድ ካልሆንን በጋራ ፖለቲካ መሥራት አንችልም የሚል አቋም ነው። ከማንኛውም ድርጅት ጋር ስንሠራ የምንለው በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት ታምናለህ? በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ታምናለህ? ነው። ከዚያ በኋላ ሌላውን ውይይት ማድረግ፤ መደራደርም እንችላለን። • ኦነግ ከመንግሥት ጋር ያደረኩት ስምምነት አልተከበረም አለ • ኦዲፒ፡ ኦነግ እንደ አዲስ ጦር መልምሎ እያሰለጠነ ነው • «ኦሮሞ እና አማራን የሚነጣጥሉ አይሳካላቸውም» ለመጨረሻ ጊዜ አቶ ዳውድን ያገኘሁት ወደ ኤርትራ ለአንድ ጉዳይ ስመለስ ኤርፖርት ውስጥ ነው። ሰላም እንባባላለን። እዚህም ተገናኝተናል። በፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች ውይይት ውስጥ ገንቢ የሆነ ውይይት እናደርጋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ይቺ አገር የጋራችን ነች። ለሁላችንም የምትሆን ሀገር መፍጠር ነው። የተሻለ ሀሳብ አለን የሚሉ ሀሳባቸውን ለማኅበረሰቡ አቅርበው በዚያ በሚደረግ ውይይት ሕዝብ የመረጠውን መቀበል ግዴታችን ነው። ሁላችንም መረዳት ያለብን በአንድ ሀገር ውስጥ ሦስት ወይም አራት የታጠቁ ኃይሎች ሊኖሩ አይችሉም። ፖለቲካ እንደዛ ሊሆን አይችልም። በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካችንን እንሠራለን ብለን ካሰብን፤ ሁላችንም መሳሪያ አውርደን እንገባለን ነው ያልነው። ስለዚህ አውርደን በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካው ውስጥ ገብተን ለሀገራችን ይበጃል የምንለውን ለኅብረተሰቡ አቅርበን ሕዝቡ የሚወስነውን መቀበል ነው። ቢቢሲ አማርኛ፡ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘሀቸውስ መቼ ነው? ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ መጨረሻ የተገናኘነው ነሀሴ ላይ ነው። ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት ለመሰነባበት ተገናኝተን በሀገራችን በአካባቢያችን ጉዳዮች ላይ አውርተናል። ቢቢሲ አማርኛ፡ ምን አይነት ግንኙነት ነበራችሁ? ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ እሳቸው ፕሬዘዳንት ናቸው። እኔ አንድ ታጋይ ነኝ። ስለዚህ ምን ግንኙነት ይኖረናል? አንዳንድ ጊዜ እንገናኛለን። በሀገርና በአካባቢ ጉዳይ እናወራለን። ግን ከእሳቸው በታች ያሉ በእኛ ሥራ ዙሪያ አብረናቸው የምንሠራ ሌሎች ሰዎች አሉ። ፕሬዘዳንቱ ፕሬዘዳንት ናቸው፤ በየጊዜው እየሄድኩ እሳቸውን የማገኝበት ሁኔታ የለም። ቢቢሲ አማርኛ፡ለወደፊት ጡረታ ወጥተህ ምናልባት በሲቪል ወይም በቢዝነስ ዘርፍ ስትሳተፍ ራስህን ታያለህ? ፕሮፌ. ብርሀኑ፡ በጣም አያለሁ። የጀመርነው፣ በጣም ብዙ ሰው የሞተበት፣ የተጎዳበት፣ ይቺን ሀገር ዴሞክራሲያዊ የማድረግ ነገር በደንብ መሰረት ከያዘ በኋላ ለረዥም ጊዜ ፖለቲካ ውስጥ የመቆየት ፍላጎት የለኝም። በ94 [በአውሮፓውያኑ] ስመጣም ፖለቲካ ውስጥ ልገባ አልነበረም። አስተምር ነበር። በኢኮኖሚው ዙሪያ እሳተፍ ነበር። ጋዜጦች ላይ እጽፍ ነበር። የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር ውስጥ እሠራ ነበር። ፖለቲካ የሚባል ነገር ውስጥ ተመልሼ እገባለሁ አላልኩም። በልጅነቴ ኢሕአፓ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ተመልሼ [ፖለቲካ ውስጥ] እገባለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። በአንድ መልኩ ወይም በሌላ ፖለቲካ ውስጥ መልሶ ያስገባኝ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለተማሪዎች ስለ አካዳሚክ ነጻነት ንግግር ካደረግን በኋላ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር ስንታሰር ነው። እንዲህ አይነት ሥርዓት ካለ፣ ነጻነት ከሌለ፣ በነጻነት መነጋገር ካልተቻለ ሌሎች የሚሠሩ ሥራዎችም የውሸት ይሆናሉ። አካዳሚሽያን [ትምህርታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ባለሙያ] ነኝ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ አስተምራለሁ ብለህ ነጻነት ከሌለህ፣ የምታስተምረውን ነገር በነጻነት ማስተማር ካልቻልክ፤ የምታስተምረው በተወሰነ ደረጃ የውሸት ነው የሚሆነው። የፖለቲካ ሥርዓቱ ለፖለቲካ ስልጣን ሳይሆን ለዕለት ተዕለት ሥራዎች እንኳ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አይደለም። • «የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ ባለፈው 27 ዓመት ውስጥ ነጋዴ ብትሆን የሚያሳብድ ነው የሚመስለኝ። ንግድ ማለት የውድድር ቦታ ከሆነ፤ የኢኮኖሚው ሥርዓት ሙሉ በሙሉ በአድልዎ ላይ የተመሰረተ ከሆነ ምንም ልትነግድ አትችልም። አንተንም ከፀባይህ አውጥተው እንደነሱ አጭበርባሪ ሆነህ የምትኖርበት ሁኔታ ነው የሚፈጠረው። እንደ አንድ እውነተኛ ዜጋ ለመኖር የፖለቲካ ምህዳሩ ነጻነትህን የሚያከብር፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሀሳብህን በነጻነት መግለጽ መቻልህ፣ በምትሠራው ሥራ ጣልቃ የማይገባ መሆኑ አስፈላጊ ነው። ከብዙ ሰዎች ጋር የምለየው በዚህ ነው። እነሱ ይሄ ፖለቲካ ውስጥ መግባት ነው የሚመስላቸው። እኔ ፖለቲካ ውስጥ መግባት አልለውም። ይሄ መሰረታዊ የሆነ ዜግነትህን ማስከበር ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ካልኩ እንደ ኢትዮጵያዊ ይገባኛል የምለው መሰረታዊ ነጻነት አለ። ያንን ካላገኘሁ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም። ከዚህ ጠፍቼ፤ ከዚህ ሸሽቼ አሜሪካና አውሮፓ የምኖር ጊዜ ያለኝ ነጻነት ሀገሬ ውስጥ ካለው ነጻነት የበለጠ ከሆነ እውነተኛ ዜጋ አይደለሁም። ፖለቲካ ውስጥ ያስገባኝ ይሄ ነው። እስር ቤት ከገባን በኋላ በጣም ብዙ ኦሮሞ ወገኖቻችን ታስረው ሳይ ሀገሪቱ ወደ ምን አይነት አደጋ ውስጥ እየገባች እንደሆነ ነው ያየሁት። አሁንም ለእኔ ፖለቲካ ማለት እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ የዜግነት መብቶች ማስከበር፤ ሁሉም የሀገሩ ባለቤት የሚሆንበት ድባብ መፍጠር ነው። ይሄ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ግዴታችን ነው። ያንን ማድረግ ካልቻልክ፤ የዜግነት መብትህን እየወረወርክ ነው። ይህንን በፍጹም ማንኛውም ዜጋ ማድረግ የለበትም ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ፖለቲካ የሚያያዘው ከዚህ ጋር ነው። ከዚያ በኋላ ያለው ምርጫ ምናምን አድካሚውና በፍጹም የማይረባው የፖለቲካ ክፍል ነው። ዋናው ሥራ ካደረስኩ በኋላ ለጡረታም ደርሻለሁ፤ ትንሽ የማርፍበት ጊዜ ነው።
51986050
https://www.bbc.com/amharic/51986050
ኮሮናቫይረስ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ምን አሉ?
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ትናንት አርብ አመሻሽ ላይ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በተመለከተ በጽህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተወው ነበር። በዚህ መግለጫቸው ላይም የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ፣ የጤና እና የማህበራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ተቋቁሞ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቀዋል።
በዚህም መሠረት አዳዲስ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ተወስኗል በማለት ውሳኔዎቹን ገልፀዋል።. ማንኛውም ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰው ለ14 ቀናት በራሱ ወጪ ወደ ለይቶ ማቆያ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከ 30 በላይ አገራት የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ መወሰኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አየር መንገዱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት አስታውቀዋል። "አየር መንገዱ 190 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ አጋጥሞታል። በዚህም ወደፊት ከፍተኛ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ይጠበቃል" ብለዋል። የአምልኮ ስርዓቱ እና ልምዱ ለበሽታው ተጋላጭ ያደርጋል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም "በእነሱ [ኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች] በኩል መልዕክት እንደሚተላለፍ ይጠበቃል" ያሉ ሲሆን፤ የፕሮቴስታንት መሪዎችም ቴክኖሎጂን በመታገዝ አገልግሎት እንዲሰጡ አማራጭ መቀመጡን ተናግረዋል። በእስልምናም የሚደረጉ ሰላቶች ንክኪ ስለሚኖራቸው፤ የሃይማኖት መሪዎች እርምጃ እንደሚወስዱ እና መግለጫ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አስተላልፏል ብለዋል። በማረሚያ ቤቶች በሽታው ከገባ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ታራሚዎችን ወደ ሌሎች ቦታዎች ወስዶ ዘርዘር ለማድረግ ተጨማሪ ቦታዎች ተዘጋጅቷል ብለዋል። አክለውም አዳዲስ ታራሚዎች ምርመራ ሳይደረግላቸው ወደ ማረሚያ ቤት አይገቡም ብለዋል። እንዲሁም የቤተሰብ ጥየቃ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም መደረጉን ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ እና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እንዲለቀቁ መወሰኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከሰሞኑ የወረርሽኙን ስርጭት ተከትሎ በአዲስ አበባ በውጪ አገር ዜጎች ላይ የደረሰው ጥቃት ''ኢትዮጵያዊ ባህሪ የሌለው ነው'' በማለት ጥቃቱን አውግዘዋል። ከሰሞኑ በርካታ ወጣቶች ሰዎችን እጅ ማስታጠብ ጨምሮ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ሲያከናውኑ ነበር። መንግሥት የበጎ አድራጎት ሥራዎቹን በአክብሮት የሚመለከተው ነው ካሉ በኋላ፤ ነገር ግን አገልግሎቱን የሚሰጡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የእስካሁኑን የሕክምና ባለሙያዎችን ጥረት አድንቀዋል። የቫይረሱ ስርጭት የሚስፋፋ ከሆነም በሽታውን ለማሸነፍ ብዙ ጥረት ይጠበቅባችኋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከጃክ ማ፣ ከቢል ጊቴስ እና ከዓለም ባንክ በተገኙ ድጋፎች የዜጎች ሕይወት እንዳያልፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የመሽት መዝናኛ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ይሆናሉ ብለዋል። በጠባብ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ስለሚያስተናግዱ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ዝግ ይደረጋሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ። "በሽታውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠራችንን እስክናረጋግጥ ድረስ የምሽት መዝናኛዎች እንዲዘጉ ተወስኗል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት በሞከሩ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውሰው አሁንም ሕጋዊ የማስተካከያ እርምጃዎች መውሰድ ይቀጥላል ብለዋል። በክልሎች የሚገኙ ዋና ዋና ሆስፒታሎች ምረመራ የማድረግ አቅማቸውን ለማሳደግ ስራዎች ሲከናወኑ እንደነበረ አስታወሰዋል። ለዚህም የሚረዳ የምረመራ እና የማዳን ሥራ እንዲሰራ ተግባብተናል ብለዋል። ወረርሽኙ ከወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ስለሚኖረው ጫና ሲያስረዱ፤ "ምርጫ ቦርድ የራሱን ግምገማ እያካሄደ ነው፤ ግምገማውን መሰረት በማድረግ የመጨረሻው ውጤት ይፋ ይደረጋል" ብለዋል። የመጠጥ ውሃ እጥረት ባለባቸው ቦታዎች በቦቴ የማቅረብ ሠራዎች እየተካሄዱ እንደሆነ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። በተለይ በከተማ አከባቢ ከፍተኛ የውሃ እጥረት መኖሩን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው መጨረሻ ላይ "የብልጽግና ፓርቲ የገንዘብ መዋጮ ላይ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን እና የፖለቲካ ምሁሮችን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር በርካቶች ማዘናቸውን ሰምቻለሁ" ብለዋል። "ጉዳዩ የማይመለከታችሁ እና በንግግሬ እንድትከፉ የሆናችሁ፣ የተማራችሁ እና በተማራችሁበት ዘርፍ አገራችሁን በቅንነት የምታገለግሉ፣ ውጤትም ያመጣችሁ ሰዎች ጉዳዩ እናንተን የማይመለከት ቢሆንም፤ ጉዳዩ እናንተን የማይመለከት መሆኑን በግልጽ ባለማስቀመጤ እናንተን ይቅርታ እጠይቃለሁ" ብለዋል። ወረርሽኝ ምንድን ነው? ዓለም እስካሁን ያስተናገደቻቸው ወረርሽኞችስ ምን ዓይነት ነበሩ?
news-48552540
https://www.bbc.com/amharic/news-48552540
ሎዛ አበራ፡ «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ ትልቅ እምነት አለኝ»
ሰባት ልጆች ላፈሩት እናት እና አባቷ አምስተኛ ልጅ ናት፤ ተወልዳ ያደገችው የከንባታ ጠምባሮ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ዱራሜ ነው።
ሎዛ አበራ ከደደቢት ጋር ዋንጫ ባነሳችበት 2010 ዓ.ም. ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበረች ሶስት ወንድሞች አሏት፤ ሁለቱ ታላቆቿ አንድ ደግሞ ታናሿ። ገና ልጅ ሳለች ነበር በኳስ ፍቅር የወደቀችው። ባደገችበት ሠፈር ካሉ ወንድ እኩዮቿ ጋር እየተጋፋች ኳስን ከመረብ [እርግጥ የሠፈር ሜዳ መረብ ባይኖረውም] ማገናኘት ያዘች። ጉዞዋ ሠፈራቸው ከሚገኘው ሌሊሶ ሜዳ እስከ ብርቅዬው አዲስ አበባ ስታድዬም እንዲሁም ስዊድን ያደርስታል ብሎ የገመተ ላይኖር ይችላል፤ እርሷ ግን ውስጧ ነግሯታል። ሎዛ አበራ ሴት ልጅ ማዕድ ቤት እንጂ ከወንዶች እኩል ውስጧ የሻተውን ማድረግ በማትችልበት ማሕበረሰብ ውስጥ ብታድግም ሕልሟን ከማሳካት አላገዳትም። እንደው ከወንዶች ጋር መጫወት አይከብድም? «እኔ ምንም አልከበደኝም ነበር። እንደውም ወንዶች እኔ ያለሁበት ቡድን ውስጥ ለመጫወት ይጣሉ ነበር''። የሎዛ ፕሮፌሽናል ኳስ ተጫውነት ጉዞ የተጀመረው የከንባታ ዞንን ወክላ ስትጫወት ባይዋት መልማዮች አማካይነት ነው። ከዚያ ጉዞ ከዞን ወደ ክልል ሆነ። ደቡብ ክልልን ወክላ ለመላው ኢትዮጵያ ውድድር እንድትሳተፍ ሆነ። ጨዋታው ደግሞ የነበረው አዳማ ላይ። • የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች የያኔው የሐዋሳ ሴቶች እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ የሆነው ዮሴፍ ገብረወልድ [ወፍዬ ይሉታል ልጆቹ ሲጠሩት] ነበር ሎዛን የመለመላት። ፈጣኑ የሎዛ ጉዞ ኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ደርሷል። ምንም እንኳ ሎዛ ከሐዋሳ ጋራ ዋንጫ ባታነሳም እዚያ በቆየችባቸው ሁለት ተከታታይ ዓመታት የክለቡ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበረች። ሐዋሳም ቢሆን ሁለቱንም ዓመታት ፕሪሚዬር ሊጉን 3ኛ ደረጃ በመያዝ ነው ያጠናቀቀው። አሁን ደግሞ ጉዞ ከሐዋሳ ወደ ደደቢት። ምንም እንኳ አሁን ደደቢት የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ቢከስምም በጊዜው አጅግ ድንቅ ብቃት ያሳዩ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች ስብስበ ነበር። «በደደቢት አራት ዓመታትን ቆይቻለሁ፤ እስከ አምና ማለት ነው። በእነዚህ ዓመታት በተከታታይ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ነበርኩኝ። እንደገና ሶስት ተከታታይ ዓመት ደግሞ የሴቶች ፕሪሚዬር ሊግ ሻምፒዮና ነበርን። ግን አሁን ደደቢት ፈርሷል፤ እኛም በተፈጠረው ነገር በጣም አዝነናል።» ጉዞ ወደ ስዊድን ሎዛ ደደቢት ከመፍረሱ በፊት ነበር ለሙከራ ወደ ስዊድን ያቀናችው። «ደደቢት ነበርኩኝ። ፕሪሚዬር ሊጉ ሊጠናቀቅ ሁለት ጨዋታ ሲቀሩት እኔ ወደ ስዊድን አቀናሁ» ትላለች። ግን እንዴት ወደ ስዊድን ልታቀና ቻለች? «ስዊድናዊ ነው ሰውዬው። ላርስ ይባላል። ባለቤቱ ኢትዮጵያዊት በመሆኗ ይመጣ ነበር። ስለኔ ሲነግሩት ጊዜ ማዬት አለብኝ ብሎ ስጫወት ተመለከተኝ። ከዚያ እኔና ቱቱ [የብሔራዊ ቡድኑ የቀድሞ አምበል ቱቱ በላይ] ስዊድን ሄደን የሁለት ወር የሙከራ ልምምድ እንድናደርግ አመቻቸልን። ስዊድን የሚገኙ ክለቦች ውስጥ [ሮዘንጋርድ እና ፒቲያ አይ ኤፍ] ለአራት ወራት ያክል ቆየን። ከዚያ በኋላ የስዊድን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፈቃድ ሰጡን። ፊርማ ያኖርንለት ክለብ ግን አልነበረም። ልክ የስዊድን የሴቶች 'ቶርናመንት' ሲጠናቀቅ ተመለስን።» ከዚያስ? «ጥር ስዊድን የሴቶች ውድድር የሚጀምርበት ወር ነበር። እኛ ግን ተመልሰን መሄደ አልቻልንም። ምክንያቱ ደግሞ ፋይናንስ ነው። ከአውሮፓ የምትመጣ ሴት ሲያስፈርሙ ተጨማሪ ወጪ የለባቸውም። ከሌላ አህጉር ለምትመጣ ተጫዋች ግን ቀረጥ [የስራ ፈቃድ ወጭ] መክፈል ግድ ነው። ክለቡ ይህንን ማድረግ አልቻለም። እንጂ የችሎታ ወይም የአቅም ማነስ ጉዳይ አልነበረም።» «ይገርምሃል እነሱ 1ኛ ደቂቃ ላይም 90ኛው ደቂቃ ላይ ያላቸው አቅም ተመሳሳይ ነው። እኛ ችግራችን ኳስ አለመቻል አይደለም፤ ችግራችን ፊትነስ ነው» በስዊድኖች የቀናሁት በዚህ ነው ትላለች ሎዛ። ሎዛ ከስዊድኑ ክለብ በፊት ለአንድ ወር ሙከራ ልምምድ ወደ ቱርኩ አንታልያስፖር ማቅናቷ የሚዘነጋ አይደለም። የቱርኩ ክለብ ያቀረበላት ክፍያ ግን፤ እንደ ሎዛ አገላለፅ 'ከኢትዮጵያም ያነሰ' ነበር። ሉሲ የሎዛ የብሔራዊ ቡድን ጉዞ ከክለብ ቀድሞ የሚመጣ ነው። «ወቅቱ የሴቶቸ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪቃ ዋንጫ ያለፈበት ነበር። 'ሉሲ ተስፋ' ተብሎ 70 ገደማ ታዳጊዎች ለአንድ ወር ያክል ሥልጠና እንድናደርግ ተጠራን። ከመሃከላችን 8 ልጆች ለብሔራዊ ቡድን ተመረጡ። እኔ አንዷ ነበርኩ። ይህ የሆነው ገና ለሐዋሳ መጫወት ከመጀመሬ በፊት በነበረው ክረምት ላይ ነው።» ሎዛ ለብሔራዊ ቡድን እንደተመረጠች ከቡድኑ ተቀንሳ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ገና ልጅ ነሽ በመባሏ ነበር። ከአንድ ዓመት በኋላ ግን በአሠልጣኝ ስዩም ከበድ ቡድን ውስጥ መካተት ቻለች። 23 የብሔራዊ ቡድን ጎሎች በዓለም አቀፍ መድረክ! ሎዛ ይህን በማሳካት የምንጊዜም የሉሲ ከፍተኛ ጎል አግቢነቱን ተቆጣጥራዋለች። ምንም እንኳ ሎዛ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ዋንጫ ባትበላም፤ ሜዳልያ ባታጠልቅም፤ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የነበራትን ቆይታ አትዘነጋውም። ከ20 ዓመት በታች ሉሲ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ሶስቱን ማጣሪያዎች ካለፈች በኋላ ማለፍ ሳትችል ብትቀርም ሎዛ ራሴን የፈተሽኩበት የማልረሳው ውድድር ነው ትላለች። • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' • ካፍ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ድጋሚ እንዲካሄድ አዘዘ እንደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያን ለብሶ ደጋፊ ፊት መጫወት ምን ዓይነት ስሜት ይሰጥ ይሆን? «በጣም ደስ....የሚል ስሜት አለው። ሕልሜም ነበር ይህንን ማሳካት። ስታድዬም ገብቶ ሃገርን ወክሎ መጫት። የመጀመሪያ ጊዜ በጣም ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ። በቃ ይሄ በቃላት የማትገልፀው ዓይነት ስሜት አለ አይደል?. . . ጎል ማስቆጠር ደግሞ ሌላ ደስታ በቃ።» ሎዛ የእሷ ትውልድ ብሔራዊ ቡድን ታሪክ ይሠራል የሚል እምነት አላት። «ሁሌም የማስበው ነገር ነው። ዓላማዬ ሃገሬን ወክዬ የአፍሪካ ዋንጫ መጫወት፤ የሴካፋ ሻምፒዮን መሆን ነው። እንደ ሃገር በምንጫወትባቸው መድረኮች ላይ የኔ ትውልድ ትልቅ ውጤት እንደሚያመጣ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ። ከእግዚአብሔር ጋር ይሳካል የሚል እምነት አለኝ።» ክፍያ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚያበሉ ሥራዎች ውስጥ አንዱ እግር ኳስ ነው አሉ [የወንዶቹ ማለት ነወ]። የሴቶቹስ? የእነ ሎዛ ክፍያ ልከ እንደወንዶቹ አፍን በመዳፍ የሚያስከድን ይሆን? «ኧረ በፍፁም አይገናኝም። ሰማይ እና ምድር ነው። እርግጥ እግዚአብሔር ይመስገን ክፍያችን ከቀድሞው የተሻለ ነው። ከጊዜ ጊዜም እየተሻሻለ መጥቷል። ግን ከወንዶች ጋር ስናነፃፅረው በፍፁም አይገናኝም። በፍፁ....ም ማለት ነው። በፊት የፊርማ ተብሎ ነበር የሚሠጠን፤ አሁን ግን በወር ተከፋፍሎ በደሞዝ መልክ ነው ምናገኘው። ይህ የገንዘቡን መጠን ያነሰ ያደርግብናል። ስለክፍያ ብዙ ጊዜ ተብሏል። እንደውም የሴቶች እግር ኳስ ክፍያ እየወረደ እንዳይሄድ ነው ስጋታችን።» ሎዛ ዘንድሮ ከአዳማ ጋር ዋንጫ ማንሳት ችላለች። ምንም እንኳ ሊጉን ዘግየት ብላ ብትቀላቀልም [ስዊድን በመጓዟ ምክንያት] ኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱን ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች። ከሌሊሶ ሜዳ እስከ ስዊድን ሎዛ በዙሪያዋ የነበሩ ሰዎች አሁን ለደረሰችበት ደረጃ ያላቸው ሚና ትልቅ እንደሆነ ተናግራ የምትጠግብ አትመስልም። ከቤተሰቦቿ እስከ ወፍዬ አሠልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ፤ ከደደቢት አጋሮቿ እስከ ስዩም ከበደ...ብቻ ስማቸውን ዘርዝራ የማትጨርሳቸው ሰዎች ምስጋና ይገባቸዋል ትላለች። ከሠፈሯ 'ሌሊሶ' ሜዳ አሁን ያለችበት ትደርሳለች ብለው ብዙዎች ባይገምቱም እሷ ግን ልጅ እያለሁ እንኳ የሚታየኝ በእግር ኳስ ሃገሬን ወክዬ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ስጫወት ነው ትላለች። «ከምንም ነገር በፊት ፍላጎት ይቀድማል። እግር ኳስ መጫወት ከሆነ ፍላጎታችን፤ ያንን ፍላጎታችንን ለማሳካት ሳይደክሙ መሥራት። ሌላም ከሆነ እንደዚሁ። ተስፋ ሳይቆርጡ እድርሳለሁ ያሉበት ቦታ እንደሚደረስ ሁሌም ለአእምሮ መናገር፤ ራስን ማሳመን፤ ሥራን ማክበር ማለትም አንድ ሙያ የሚጠይቀውን ዲሲፕሊን መከተል ያስፈልጋል» የሎዛ መልዕክት ነው። እኛም የሷ ትውልድ ሉሲ፤ ድል አምጥታ ከመቀመጫችን ተነስተን የምንቦርቅበት ጊዜ በጉጉት ከመጠበቅ እና ከመመኘት ወደኋላ አንልም። • ፌዴሬሽኑ፡ «የቡና እና መቀለ ደጋፊዎች ባሉበት ጨዋታ ሊካሄድ አይችልም»
50054046
https://www.bbc.com/amharic/50054046
የዛሬዋን አዲስ አበባ በፎቶ መሰነድ ለምን አስፈለገ?
አዲስ አበባ በፈጣን ለውጥ ውስጥ ናት። ትላንት የነበረ ቤት ዛሬ ፈርሶ ሊሆን ይችላል። ዛሬ የሚታይ ሰፈር ነገ ገጽታው ሊቀየር የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው።
የአዲስ አበባን ለውጥ ለማስተዋል ዓመታት መጠበቅ አያስፈልግም። በሳምንታት ውስጥ ተገንብተው ያለቁ የሚመስሉ አንጸባራቂ ህንጻዎች የከተማዋን ገጽታ በፍጥነት እየቀየሩት ይገኛሉ። • ስዕልን በኮምፒውተር • ትኩረት የተነፈገው የባህር ዳር መለያ ባህላዊ ጥበብ ቀደምትና የከተማዋ ታሪክ ቋሚ ምስክር የሆኑ አካባቢዎች ለውጥ እየተሰነደ ነው ወይ? የብዙዎች ጥያቄ ከሆነ ሰነባብቷል። እድሜ ጠገብ ሰፈሮች ወይም ታሪካዊ ህንጻዎች መፍረሳቸው በበርካታ ባለሙያዎች ይተቻል። እነዚህ አካባቢዎች ከመፍረሳቸው ባሻገር በአንድ ወቅት ስለመኖራቸው የሚዘክር መረጃ በአግባቡ አለመያዙም ጥያቄ ያጭራል። አዲስ አበባ ምን ትመስል ነበር? የሚለውን በታሪክ መዝገብ ለማስፈር ቆርጠው የተነሱ ፎቶ አንሺዎች የከተማዋን ገጽታ የሚያሳዩ ፎቶዎች በማንሳት ዓውደ ርዕዮች አዘጋጅተዋል። አዲስ አበባን በመሰነድ ዙርያ የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄዎች መጀመራቸው ይታወቃል። "ስትሪትስ ኦፍ አዲስ" በፎቶ አንሺ ግርማ በርታ የተጀመረ የማኅበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ ነው። የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎችን እንዲሁም የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ ፎቶ በማንሳት፤ በዋነኛነት በኢንስታግራም ላይ በማጋራት ይታወቃል። "ቪንቴጅ አዲስ" በከተማዋ በ1970ዎቹ አካባቢ የተነሱ ፎቶግራፎች ስብስብ ላይ ያተኮረ ነው። ከተማዋን ወደኋላ መለስ አድርገው የሚያስቃኙ ፎቶዎችን በመሰነድ የሚታወቅ ሲሆን፤ "የአዲስ አበባ ትዝታ" የተሰኘ የፎቶ መጽሐፍም ታትሟል። "ቪንቴጅ አዲስ" የተመሰረተው በወንጌል አበበ፣ ፊሊፕ ሹትዝ እና ናፍቆት ገበየሁ ነው። "አዲስን እናንሳ" የአዲስ አበባን ነባራዊ ገጽታ መመዝገብን አላማው ያደረገ የፎቶግራፍ ፌስቲቫል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መተዋወቅ ከጀመረ ቆይቷል። ፌስቲቫሉ "ካፕቸር አዲስ" ወይም "አዲስን እናንሳ" ይሰኛል። ፎቶ አንሺዎችን ብቻ ሳይሆን ማንኛውም የከተማዋን ገጽታ ማሳየት የሚፈልግ ሰውን ያሳትፋል። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከተማዋን የሚገልጹ ፎቶዎችን ለፌስቲቫሉ አዘጋጆች እንዲያስገቡ ጥሪ መቅረቡን ተከትሎ፤ ብዙዎች የአዲስ አበባን የእለት ከእለት እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ፎቶዎች በማኅበራዊ ሚዲያ እየተጋሩ ነው። • የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ • ስለ ጠልሰም ወይም በተለምዶ የአስማት ጥበብ ተብሎ ስለሚጠራው ምን ያህል ያውቃሉ? አንበሳ አውቶብስ፣ የተለያዩ ጎዳናዎች እና ሰፈሮች፣ ሀውልቶች፣ በመፍረስ ላይ ያሉ ቤቶች፣ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች እንዲሁም ሌሎችም ከተማዋን የሚገልጹ ፎቶዎች ይገኙበታል። ሌላ ቀለም የተባለ ድርጅት ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፎቶግራፍ ፌስቲቫል ከጥቅምት 15 እስከ 21፣ 2012 ዓ. ም. በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ግቢ ውስጥ ይካሄዳል። ከፌስቲቫሉ አዘጋጆች አንዷ የሆነችው ሀምራዊት ግዛው፤ ፌስቲቫሉ ከተሰናዳበት አላማ አንዱ የአዲስ አበባን ለውጥ በፎቶ በመመዝገብ ለታሪክ ማስቀመጥ እንደሆነ ትገልጻለች። "በየጊዜው ያለውን የአዲስ አበባ የለውጥ ሂደት መመዝገብ፣ ለውጡንም ለታሪክ ማቆየት እንፈልጋለን። ባለፈው ዓመት የነበሩ ህንጻዎች አሁን ምን ይመስላሉ? የሚለውን ለማየትም ይረዳል" ስትል ትገልጻለች። የከተማዋን ፈጣን ለውጥ ሙሉ በሙሉ መመዝገብ ባይቻልም በተቻለው መጠን ሂደቱን ማሳየት አስፈላጊ መሆኑንም ታክላለች። የአዲስ አበባ ለውጥ በተገቢው መንገድ እየተመዘገበ አለመሆኑን የምታስረዳው ሀምራዊት፤ ፌስቲቫሉ ክፍተቱን በመጠኑም ቢሆን እንደሚደፍነው ታምናለች። "ሥነ ቃል እና ሌሎችም እንደሚመዘገቡት የከተማዋ ለውጥ እየተመዘገበ አይደለም። ብዙ ሥራ ይቀረናል። ተሳታፊዎች ፎቶ መነሳት ያለባቸው የፈረሱ ታሪካዊ ቦታዎችን ወይም ቅርሶችን ፎቶ እንዲያነሱም አበረታተናል" ትላለች። ከስልክ እስከ ካሜራ. . . ፌስቲቫሉ ላይ የሚካተቱ ፎቶዎች በቴክኖ ስልክ አልያም በአይፎን ወይም ደግሞ በማንኛውም ዘመናዊ ካሜራ የተነሱም ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ሰው የሚጠቀመው መሣሪያ ሳይሆን ስለከተማዋ ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ትኩረት እንደሚሰጠው ሀምራዊት ትናገራለች። ሀምራዊት ከቢቢሲ ጋር ቆይታ እስካደረገችበት የጥቅምት ወር የመጀመሪያው ሳምንት ድረስ 500 ፎቶዎች ለፌስቲቫሉ አዘጋጆች ተሰጥተዋል። ከነዚህ መካከል ወደ 250 የሚጠጉት በከተማዋ ነዋሪዎች የተነሱ ፎቶግራፎች ናቸው። • አርባ ምንጭ፡ የዶርዜ የሽመና ጥበብ መናኸሪያ • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ ለአዘጋጆቹ ከቀረቡት ፎቶዎች 150ው ተመርጠው ለሰባት ቀናት በዓውደ ርዕይ ይቀርባሉ። ከፎቶግራፎቹ መካከል በሦስት ዘርፍ፣ ሦስት ፎቶዎች ተመርጠውም ፎቶ አንሺዎች ይሸለማሉ። በፌስቲቫሉ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦች የሚወደደሩበት ዘርፍ በሦስት ተከፍሏል። በመጀመሪያው ዘርፍ ፎቶ አንሺነትን እንደ ሙያ የያዙ ሰዎች ይወዳደራሉ። ሁለተኛው ዘርፍ ለዲፕሎማቶች ወይም ዓለም አቀፍ ተጓዦች የተሰጠ ሲሆን፤ በሦስተኛው ዘርፍ ማንኛውም ሰው መሳተፍ ይችላል። "ብዙ ፎቶግራፈር የሚጀምረው በስልክ ፎቶ ከማንሳት ነው" የምትለው ሀምራዊት፤ በተራቀቀ ካሜራም ይሁን በእጅ ስልክ የተነሱ ፎቶዎችን በፌስቲቫሉ እንዳካተቱ ትናገራለች። ተሳታፊዎች ይህንን ቦታ፣ በዚህ አይነት የፎቶ ጥራት ፎቶ ያንሱ የሚል ገደብ ባለመጣል ሁሉንም አካታች አሠራር መዘርጋቱን ታስረዳለች። በተሳታፊዎች ዘንድ የኔ እይታም ዋጋ አለው የሚል ስሜት መፍጠርን ግባቸው አድርገዋል። ብዙዎች በስልክ የተነሳ ፎቶግራፍ በካሜራ የተነሳ ፎቶ ያህል ጥራት ላይኖረው ይችላል ሲሉ ስለ ውድድሩ ቢጠይቁም፤ ውድድሩ ሲካሄድ ፎቶው የተነሳበት መሣሪያ ከግምት ገብቶ ሁሉም ተሳታፊ ባለበት ደረጃ እንደሚመዘን ሀምራዊት ትናገራለች። "ያልታየችው" አዲስ አበባ "ካፕቸር አዲስ" የአዲስ አበባን ገጽታ በመሰነድ ከሚታወቁት "ስትሪትስ ኦፍ አዲስ" እና "ቪንቴጅ ኢትዮጵያ" ጋር በጥምረት ይሠራል። የዩጋንዳ እና የኬንያ ፎቶ አንሺዎችን ወደ አዲስ አበባ በመጋበዝ የከተማዋን የተለያዩ ገጽታዎች በካሜራቸው የሚያስቀሩበት መሰናዶ (ፎቶ ዋክ) ይካሄዳል። በፌስቲቫሉ የአዲስ አበባን ህንጻዎች፣ ቀለበት መንገዶችን ወይም ታዋቂ ሰፈሮችን ከማሳየት ባሻገር የከተማዋን ነዋሪዎች የእለት ከእለት ሕይወት ለማንጸባረቅም ታልሟል። "አዲስ አበባ ትልቅ ናት። በፌስቲቫሉ ሁሉንም ሰው ያካተትነው በፕሮፌሽናል ፎቶግራፈር ያልታዩ ገጽታዎችም እንዲካተቱ ነው። ማንኛውም ሰው አዲስ አበባ ውስጥ እየኖረም፣ እየሠራም የሚያየውን በፎቶ ማሳየት ይችላል" ትላለች ሀምራዊት። ብዙ ጊዜ በፎቶ አንሺዎች እይታ ከሚገቡ አካባቢዎች ጎን ለጎን፤ ያልታዩ ወይም ትኩረት ያልተሰጣቸው ገጽታዎችም ማካተት አስፈላጊ እንደሆነም ታክላለች። ገበያ ላይ ወይም የአደባባይ በዓሎች ሲከበሩ የተነሱ ፎቶዎችን እንደ ምሳሌ ታነሳለች። በቅርቡ በማኅበራዊ ሚዲያዎች በስፋት የተሰራጨውን በመስቀል አደባባይ ደመራ ተደምሮ በሕዝብ መሀል እያቆራረጠ የሚሮጥ በሬ ፎቶንም ትጠቅሳለች። የፌስቲቫሉ አዘጋጆች፤ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ወይም ከተማዋን የሚጎበኙ የውጪ አገራት ዜጎችም ፎቶ እንዲያነሱ፣ ያነሱትን ፎቶ ለተቀረው ማኅበረሰብ አንዲያጋሩ ማነሳሳት እንደሚፈልጉም ሀምራዊት ትገልጻለች። "አዲስ አበባን በአገር አቀፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በጥሩ ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ማሳየት እንፈልጋለን።" ፎቶ ማንሳት የሰው፣ የቁስ ወይም የእንቅስቃሴን ምስል በካሜራ ማስቀረት ብቻ ሳይሆን አንዳች መልዕክት ማስተላለፊያ መንገድ ጭምር እንደሆነም ታስረዳለች። ስለዚህም በፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች መካከል ውድድር ሲካሄድ ታሪክ ነገራ ከግምት ይገባል።
49541374
https://www.bbc.com/amharic/49541374
ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት ፅህፈት ቤት ጥያቄን በ30 ቀናት እንዲመልስ ቀነ ገደብ ተቀመጠ
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት በክልል ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ቅዱስ ሲኖዶሱ በ30 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቃቸው፤ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስዱ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን አስታውቀዋል።
በዛሬው ዕለት ነሐሴ 26፣2011ዓ.ም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሚቴው ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ የክልላዊ ፅህፈት ቤቱን ጥያቄ የሚቀበለው ከሆነ የሰው ኃይል አመዳደቡም ሆነ አፈፃፀሙ ይህ አደራጅ ኮሚቴና ጠቅላይ ቤተ ክህነት በጋራ የሚወስኑት እንደሚሆን ተገልጿል። •ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም ጠየቀ •ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ? በተጠየቀው መሰረት አስቸኳይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ የምዕመኑን ጥያቄ ለመመለስ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚቴው አስጠንቅቋል። እርምጃው ምን እንደሆነ በዚህ ወቅት ግልፅ ባያደርጉም ከዚህ ቀደም እንደተናገሩት በራሳቸው ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት እናቋቁማለን ማለታቸው የሚታወስ ነው። ቀሲስ በላይ በዚህ ወቅት እንደገለፁት የዚህ ጉባኤ እምነቱ አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ አንድ ፓትርያርክና አንዲት ቤተ ክርስቲያን መሆኑን አምነው የቤተ ክርስቲያኗን ሌላ ህግ ማውጣት እንደማያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት የማቋቋም ጥያቄ የቤተ ክርስቲያኗ የዶግማና የቀኖና ትውፊት ለውጥ ሳይኖር አስተዳደራዊ ችግሮችን ለመፍታት መዋቅር የማበጀት ጥያቄ መሆኑንም ገልፀዋል። ጥያቄው አዲስ እንዳልሆነና ታሪካዊ ዳራ ያለው መሆኑን ተናግረው ቤተክርስቲያኗ በአፄ ኃይለ ስላሴ አገዛዝም ወቅት በጠቅላይ ግዛት በአውራጃና በወረዳ ደረጃ የመንግሥት አደረጃጀት ተከትላ ትሰራ እንደነበርና እንዲሁም በደርግ ወቅትም ይህ አሰራር እንደቀጠለ ገልፀዋል። በኢህአዴግ አገዛዝም ወቅት የፌደራል አደረጃጀቱን ተከትሎ ኃገረ ስብከቶች መቋማቸውንና በክልል ደረጃ ፅህፈት ቤት ማጣቷ ላለው ማህበረሰብ ተደራሽነት ሳይኖረው እንደቀረ ተናግረዋል። "በክልል ደረጃ መብቷን የሚያስከብርላት የለም" ብለዋል። ቀሲስ በላይ አክለውም ቤተ ክርስቲያኗ በልዩ ልዩ ቋንቋና ለተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ለመደረስ መዋቅር መዘርጋት ከአንድነቷ ጋር የማይፃረር ነው ብለዋል። ከአስተዳደራዊ ችግሮችም ጋር በተያያዘ የተደራሽነቷ መጠን መቀነሱን ተናግረው የቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን መኮብለላቸውን፣ አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ ቁጥር የቀነሰ ሲሆን ይህም በከፍተኛ የሚስተዋልበት የኦሮሚያ ክልል አንዱ መሆኑን አስረድተዋል። •በፊሊፒንስ ጥቁሩን የኢየሱስ ሀውልት ለማክበር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አደባባይ ወጡ የኦሮምኛ ቋንቋ በክልሉም ሆነ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል ቢነገርም ቤተ ክርስቲያኗ ያሏት ጥቂት ዲያቆናት፣ አገልጋዮችና መምህራን ብቻ በመኖራቸው እነዚህም ለአዲሱ ትውልድን ያማከለ ቋንቋ የሚናገሩ ባለመሆኑ ክልላዊ መዋቅሩ መፍትሄ ሊያበጅለት ይችላል ብለዋል። ይህ ችግር ሁሉንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን የሚመለከት መሆኑንም አስምረዋል። በክልሉ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት እንዲቋቋም በተደጋጋሚ ለቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስና ለቅዱስ ሲኖዶሱ የቀረበ ሲሆን አስፈላጊነቱ ቢታመንም ምላሽ እንዳላገኘ ገልፀዋል። በአቡነ ማትያስ የፓትርያርክነት ዘመንም የክልሉ አባገዳዎችና ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶሱ በ2010 ዓ.ም ጥያቄው ቢቀርብም እሰስካሁን ምላሽ እንዳልተገኘ ተናግረዋል። "አላማው ምድራዊ ፖለቲካ፣ ቁሳዊ ፍላጎትን በቤተ ክርስቲያን ላይ ለመጫን አይደለም። ዋናው አላማ ቤተክርስቲያኗ ሁሉም በእኩልነት የሚገለገልባት እንድትሆን ነው፤ አድሎንም እንጠየፋለን" ብለዋል •በመቀሌ የከተሙት ኤርትራውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቤተ ክህነት በኦሮሚያ ቤተክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ የተጠራውን መግለጫ እንደማያውቀውና እውቅናም እንዳልሰጠው የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ ርዕሰ ደብር መሀሪ ኃይሉ በትናንትናው እለት መግለፃቸው የሚታወስ ነው።
news-44075506
https://www.bbc.com/amharic/news-44075506
በጉጂ እና ጌዲዮ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ዘገባ እንደሚያመለክተው በምዕራብ ጉጂ እና በጌዲዮ ዞኖች አዋሳኝ ድንበር ላይ በተከሰተ ግጭት ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
ትናንት ይፋ የሆነው የኦቻ ዘገባ እንደሚለው የኢትዮጵያ መንግሥት እና ጥቂት አጋሮች አነስተኛ ድጋፍ አድርገዋል፤ ይሁን እንጂ ከተፈናቃዮቹ ቁጥር እና ፍላጎት አንጻር የተደረገው ድጋፍ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ሚያዝያ 5 በሁለቱ ዞኖች አዋሳኝ ድንበር ላይ በተቀሰቀሰው ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ በርካቶች ተፈናቅለዋል፤ እንዲሁም ንብረት ወድሟል። ወደ 200 ሺህ ይጠጋሉ ከተባሉት ተፈናቃዮች መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት ከጌዲዮ ዞን የተፈናቀሉ ሲሆኑ የተቀሩቱ ደግሞ ከምዕራብ ጉጂ ዞን የተፈናቀሉ ናቸው ሲል ዘገባው ያትታል። ቀያቸውን ጥለው ከተሰደዱ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሁለቱ ክልል መሪዎች ተፈናቃዮቹን ወደ ነበሩበት ቦታ ለመመለስ የተስማሙ ሲሆን እስካሁን ወደ 85 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ወደ ቀደመ መኖሪያቸው የተመለሱ ሲሆን በርካቶች ግን ለደህንነታቸው በመስጋት ለመመለስ እስካሁን ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ዘገባው አክሎ ይጠቁማል።
news-44116728
https://www.bbc.com/amharic/news-44116728
ምን ያህል እንደምንኖር የሚያሳዩ ዘጠኝ እውነታዎች
በ195 ሃገራት ሴቶች ከወንዶች በተሻለ ብዙ ዓመታት ይኖራሉ። በሩሲያ ደግሞ ለተጨማሪ 11 ዓመታት ይኖራሉ። ኢትዮጵያውያን በ1990 ከነበራቸው የእድሜ ጣራ በተሻለ 19 ተጨማሪ ዓመታት እየኖሩ ነው። ከፍተኛ የእድሜ ጣራ ያስመዘገቡ ያደጉት ሃገራት ደግሞ ከዝቅተኞቹ ጋር ሲነጻጸር 34 ተጨማሪ ዓመታት ይኖራሉ።
ይህ መረጃ የተገኘው የዓለም አቀፉን የበሽታ ጫና ጥናት ከሚጠቀመው የቢቢሲ የእድሜ ጣራ መለኪያ ነው። እስቲ ሙሉ መረጃውን እናጋራዎ። 1. ብዙ እየኖርን ነው ከ1990 በሁዋላ የዓለም- አቀፉ የእድሜ ጣራ ከ7 ዓመት በላይ ከፍ ብሏል። የዓለም ህዝብ ብዙ ዓመታት እየኖረ ያለበት ምክነያት፤ ባደጉት ሃጋራት በልብ በሽታ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ስለቀነሰ እና በማደግ ላእ ባሉ ሃገራት ደግሞ የህጻናት ሞት በመቀነሱ ነው። የተሻለ የጤና አገልግሎት፣ ንጽህና እና የተራቀቁ የህክምና ግኝቶች ሳይረሱ ማለት ነው። ጤናማ የእድሜ ጣራ- በጥሩ ጤና የምንኖረው እድሜም በ6.3 ዓመታት ጨምሯል። 2. ምሥራቅ አውሮፓውያን ብዙ እየኖሩ ነው ምንም እንኳ ጃፓን እና ሲነጋፑር የተወለዱ ሰዎች 84 ዓመታት እንደሚኖሩ ቢገመትም በአህጉር ደረጃ ግን ከፍተኛ የእድሜ ጣራ ካስመዘገቡት 20 ሃገራት መካከል 14ቱ በምሥራቅ አውሮፓ ይገኛሉ። እንግሊዝ በአማካይ 81 ዓመታት በማስመዝገብ 20 ሃገራትን ተቀላቅላለች። 3. የአፍሪካ ሃገራት ወደ መጨረሻ ናቸው ከሁለት ሃገራት በስተቀር የመጨረሻዎቹ ቦታዎች በአፍሪካ ሃገራት የተያዙ ናቸው። በእርስ በርስ ጦርነት በምትታመሰው በማዕከላዊ አፍሪካ እና በሌሴቶ በ2016 የተወለዱ ህጻናት ከፍተኛው የእድሜ ጣራቸው 50 ዓመታት ብቻ ሲሆን፤ በጃፓን ከሚወለዱት ህጻናት ጋር ሲነጻጸር በ 34 ዓመታት ያነሰ ነው። በሌላ በኩል ጦርነት፣ ድርቅ እና ህግ አልባነት የሚያሰቃያት አፍጋኒስታን በ58 ዓመታት ብቸኛዋ እሲያዊ ሃገር በመሆን የመጨረሻውን ቦታ ይዛለች። 4. ሴቶች ከወንዶች በተሻል ብዙ እየኖሩ ነው ከ198 ሃገራት በ195ቱ ሴቶች ከወንዶች በተሻለ በአማካይ ስድስት ተጨማሪ ዓመታት ይኖራሉ። በአንዳንድ ሃገራት እንዲያውም ልዩነቱ ወደ 11 ይሰፋል። በምሥራቅ አውሮፓ እና ሩሲያ በእድሜ ጣሪያ ዙሪያ ከፍተኛ የጾታ ልዩነት ሲኖር፤ የአልኮል ሱሰኝነት እና አስቸጋሪ የሥራ ሁኔታ ወንዶች ቶሎ እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል ይላል ጥናቱ። ወንዶች ከሴቶች በተሻል ብዙ ዓመታት ሚኖረሩባቸው ሦስት ሃገራት የኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ኩዌት እና ሞሪታንያ ናቸው። 5. ኢትዮጵያ ውስጥ የእድሜ ጣራ በ19 ዓመታት ጨምሯል 96 በመቶ በሚሆኑ ሃገራት ከ1990 በኋላ የእድሜ ጣራ ተሻሽሏል። ከፍተኛ ለውጥ ካስመዘገቡት አስሩ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት ናቸው። በ1990 የኢትዮጵያ የእድሜ ጣራ 47 ብቻ የነበረ ሲሆን፤ ከ2016 በሁዋላ የተወለዱ ህጻናት ግን 19 ተጨማሪ ዓመታት እንደሚኖሩ ታውቋል። ይህ የሆነው በዋነኛነት የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች እና እንደ ኮሌራ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሳቸው ነው። 6. በስምንት ሃገራት ግን የእድሜ ጣራ ቀንሷል ምንም እንኳን ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ የእድሜ ጣራ ቢያስመዘግቡም፤ ከስምንቱ አራቱ ሃገራት የእድሜ ጣራቸው ከ1990 በኋላ አሽቆልቁሏል። ከፍተኛው መቀነስ የታየው በሌሴቶ ሲሆን፤ እንደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግምት ከሆነ በዚች ሃገር ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ በኤች አይቪ ኤድስ የተጠቃ ነው። 7. ድንበር ተሻጋሪ ልዩነቶች የእድሜ ጣራ በሚገርም ሁኔታ በጎረቤት ሃገራት እንኳን የ20 ዓመት ልዩነት ያሳያል። ለምሳሌ በጎረቤታሞቹ ቻይና እና አፍጋኒስታን መካከል የ18 ዓመታት ልዩነት አለ። አፍሪካ ውስጥ ደግሞ በሽብር እና በጦርነት የምትታወቀው ማሊ ከፍተኛው የእድሜ ጣራዋ 62 ሲሆን፤ ጎረቤቷ አልጄሪያ ግን 77 ዓመት አማካይ እድሜ አስመዝግባለች። 8. ጦርነት ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው በ2010 የሶሪያ በአማካይ የእድሜ ጣራ ከዓለም ስድሳ አምስተኛ ላይ ተቀምጣ ነበር። ለዓመታት የቆየው ጦርነት ግን በ2016 ሃገሪቱ ወደ መቶ አርባ ሁለተኛ እንድታሽቆለቁል አድርጓታል። በ1994 በተፈጸመው የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወቅት የተወለዱ ህጻናት ደግሞ አማካይ የእድሜ ጣራቸው 11 ዓመት ብቻ ነበር። 9. ረሃብ እና የተፈጥሮ አደጋዎችም ትልቅ ቦታ ይይዛሉ ሰሜን ኮሪያ በ 1994 እና 1998 ባጋጠማት ከባድ ረሃብ ምክንያት አማካይ የእድሜ ጣራዋ እስከ 2000 ዓ/ም ድረስ አሽቆልቁሎ ነበር። በ2010 በሄይቲ የ200 ሺህ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመሬት መንቀጥቀጥ ሲደርስ የሃገሪቱ የእድሜ ጣራ የቀነሰ ቢሆንም በቀጣዩ ዓመት ግን ወደ ቦታው ተመልሷል። ምን ያህል ዓመት ይኖራሉ?
news-49438537
https://www.bbc.com/amharic/news-49438537
ከሶማሌላንድና የመን የመጣው አንበጣ በአምስት ክልሎች ተከስቷል
ወደ ኢትዮጵያ የተንቀሳቀሰው አንበጣ የመንና ሶማሌላንድ እድገቱን የጨረሰ ነው። ይሁንና ይህ አንበጣ በራሱ ጉዳት የማያደርስ ሲሆን ነገር ግን እንቁላል ጥሎ በእንቁላሉ አማካኝነት ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት በግብርና ሚኒስቴር የዕጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘብዲዎስ ሰላቶ ገልጸዋል።
• የኢትዮጵያን በቆሎ እያጠቃ ያለው ተምች • የአለም የምግብ ቀን: አስገራሚ የአለማችን ምግቦች "እድገቱን የጨረሰ አንበጣ ብዙም አይመገብም" የሚሉት ዳይሬክተሩ እድገቱን ያልጨረሰው ግን አዝዕርትን ያለ ዕረፍት በመመገብ ጉዳት ስለሚያደርስ እንቁላሉ እንዳይፈጠር ርብርብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። አቶ ዘብዲዎስ ይህንን ለመከላከል ቅድም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ ወቅት በሶማሌ፣ በኦሮሚያ ምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ፣ በአፋር፣ ድሬዳዋና ሰሜን ምስራቅ አማራ አንበጣው የደረሰባቸው አካባቢዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። በእነዚህ አንበጣው በተንቀሳቀሰባቸው የተወሰኑት አካባቢዎችም ቅድመ መከላከል ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል። ቦታውን በትክክል መለየትና የሚረጩት ኬሚካሎች ጉዳት ስለሚያደርሱ ነዋሪው ከብቶቹንና ልጆቹን እንዲጠብቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። ርጭቱን ለሚያከናውኑ ሰዎችም በተመሳሳይ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል። አሁን ባለው ሁኔታ አንበጣው እድገቱን የጨረሰ በመሆኑ በሰብል ላይ ጉዳት የማድረስ ዕድል እንደሌለው ገልጸው ነገር ግን አሁንም ከየመንና ሶማሌላንድ ሊመጣ የሚችል የአንበጣ መንጋ ሊኖር እንደሚችል አለም አቀፍ ትንበያ መኖሩን አስረድተዋል። ይህንንም ታሳቢ በማድረግ የመርጫ መሳሪያዎችን ወደ አካባቢዎቹ የማንቀሳቀሱ ሥራ ተጀምሯል ብለዋል ዳይሬክተሩ። ዳእሬክተሩ እንደሚሉት አንበጣው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው እርጥበትና አረንጓዴ ዕጽዋትን ለማግኘት የነፋስን አቅጣጫ በመከተል ነው። የአንበጣ እንቁላል ምቹ የአየር ሁኔታ ከገጠመው እስከ አስር ቀን ይፈለፈላል። • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? እርጥበት ካለ እስከ 17 ቀን የሚቆይ ሲሆን አልፎ አልፎ እስከ 60 ቀን የሚቆይበትም ጊዜ አለ። በመሆኑም እስከ 50 ቀን ድረስ ክንፍ ስለማያወጣ በዚህ ጊዜ ውስጥ መከላከል እንደሚያስፈልግ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ይህ ካልሆነ ግን በርሮ ወደ ሌላ አካባቢ በመዛመት በርካታ አካባቢዎችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ብለዋል። እንደዚህ አይነት ሁኔታዎችን ህብረተሰቡ ሲያይም ከ24 ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለየአካባቢው የግብርና ሞያተኛ ማስረዳት መቻል አለበት ብለዋል።። እስከዛሬ የተደረጉ ጥናቶችን መሰረት በማድረግም ነገ በ17/12/11 አፋር አንድ ቦታ ላይ ለርጭት የበቃ የአንበጣ እንቁላል መኖሩ ስለተረጋገጠ ርጭት እንደሚጀመር አቶ ዘብዴወስ ተናግረዋል። በአምስት ክልሎች አንበጣው የደረሰ ቢሆንም እስካሁን ባለው ሁኔታ ግን ምንም ስጋት የሚያደርስ ነገር አለመኖሩንና ለርጭትም ከተባለው ቦታ ውጭ ልየታ የተደረገለት ቦታ አለመኖሩንም ገልጸዋል። ይሁንና ይህ አንበጣ በራሱ ጉዳት የማያደርስ ሲሆን ነገር ግን እንቁላል ጥሎ በእንቁላሉ አማካኝነት ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት በግብርና ሚኒስቴር የዕጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘብዲዎስ ሰላቶ ገልጸዋል።
news-55019590
https://www.bbc.com/amharic/news-55019590
ከትራምፕ በኋላ ባይደን በኢራን ጉዳይ ላይ ምን ያደርጉ ይሆን?
አዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የዓለም አቀፉ ሥርዓት "እየተሳሰረ፤ እየተጋመደ ነው" ይላሉ።
አሜሪካ ያላትን ስምና ተቀባይነትም ለመመለስ ጠንክረው እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል። "የምናባክነው ጊዜ የለም" በማለትም የውጭ ጉዳይ መፅሄት ላይ ሃሳባቸውን አስፍረዋል። አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በስልጣናቸው ዘመን አከናውናቸዋለሁ ብለው ከዘረዘሯቸው ጉዳዮችም መካከል የ2015ቱን የኢራን የኒውክሊየር ስምምነትን መመለስ አንዱ ነው። ባራክ ኦባማ በስልጣን ዘመናቸው ወቅት አሳክተዋቸዋል ከሚባሉት ጉዳዮች ውስጥ (JCPOA) ተብሎ የሚጠራው የኢራን የኒውክሊየር ፕሮግራም ሲሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2018 ስምምነቱን አፍርሰዋል። ኃያላኑ አገራት የደረሱበትን ስምምነትና የፀጥታው ምክር ቤት ያፀደቀውን ውሳኔ ዕውቅናም አልሰጡም በሚልም ትራምፕ ተተችተው ነበር። ትራምፕ አገራቸውን ከስምምነቱ በማውጣት በሁለቱ ዓመታት ውስጥ ኢራን የኒውክሊየር ፕሮግራሟን እንዳትቀጥል ከፍተኛ ጫና ለማድረግ ቢሞክሩም ፍሬ አላፈራም። በጥር ወር ላይ ስልጣን የሚረከቡት ጆ ባይደንስ ኢራንን ይገቷት ይሆን? በተለይም የአሜሪካ ፖለቲካ እንዲህ በተከፋፈለበት ወቅትና የዓለም ሥርዓትም በተወሰነ መልኩ በተቀየረበት ወቅት፤ ማሳካት ይችሉ ይሆን? "ስትራቴጂያቸው ግልፅና ግልፅ ቢሆንም ቀላል አይሆንም" በማለት በሮያን ዩናይትድ ሰርቪስ ተቋም የኢራን ባለሙያ አኒሼህ ባሳሪ ታብሪዚ ይናገራሉ። ወደኋላ መመለስ የለም የተወሰኑ ፈተናዎች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ግልፅ ነው። አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የተወሳሰበ ማዕቀብ መጠቀም ከፈለጉ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እንደ ማስገደጃ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ፕሬዚዳንቱ እስካሁን ድረስ የተናገሩት ኢራን የተደረሰውን የስምምነት ግዴታዋን እንድትወጣ ብቻ ነው። "ቴህራን ስምምነቱን በጥብቅ ልታከብር ይገባል" በማለት ጆ ባይደን ቢፅፉም ይህ ሁኔታ ግን አስቸጋሪ ሆኗል። ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱን ማፍረሳቸውን ተከትሎ ኢራንም የገባችውን ቃል አልጠበቀችም ተብሏል። የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የሩብ ዓመት ሪፖርት እንደሚያሳየው ኢራን ስምምነቱ ከሚፈቅዳላት በዝቅተኛ ሁኔታ የበለፀገ ዩራኒየም አስራ ሁለት እጥፍ አከማችታለች ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ዩራኒየሟን በከፍተኛ የጥራት ደረጃም ማበልፀግ ጀምራለች የተባለ ሲሆን ስምምነቱ ይፈቅድላት የነበረው 3.67 በመቶ ነው። በዝቅተኛ የጥራት ደረጃ የበለፀገ ዩራኒየም ለተለያዩ አገልግሎቶች ቢውልም በከፍተኛ የጥራት ደረጃ ጥርት ብሎ ከበለፀገ ግን በጦር መሳሪያነት፣ ለኒውክሊየር ቦምብነት ይውላል። ይህም ከፍተኛ ስጋት ነው። ምንም እንኳን እንዲህ አይነት ጉዳዮች ቀላል ቢመስሉም የኢራን ባለስልጣናት በበኩላቸው "አገሪቷ በምርምር ያባከነችውን ጊዜ ዝም ብላ አታቃጥልም፤ ሙሉ በሙሉም አታጠፋም" ይላሉ። "ወደ ኋላ አንመለስም። በአሁኑ ወቅት የደረስንበት ደረጃ አለ፤ እሱ ነው መታየት ያለበት" በማለት በዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የኢራን የቀድሞ አምባሳደር አሊ አስጋር ሶልታኒየህ ይናገራሉ። ፖለቲካዊ ጫና ከትራምፕ ይደረግባት የነበረውን ጫና መቋቋም የቻለችው ኢራን በአሁኑ ወቅት መመለስ ይገባቸዋል የምትላቸው ጥያቄዎች አሉ ትላለች። ባለስልጣናቱ ማዕቀቡ መነሳቱ በቂ አይደለም ይላሉ። በባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል ውስጥ አገሪቷ በማዕቀቡ ምክንያት ላጋጠማት የምጣኔ ሃብት ማሽቆልቆል ካሳ ሊከፈለኝ ይገባልም በማለት ትሞግታለች። ኢራን በመጪው ሰኔ ወር በምታደርገው ምርጫ ለውጥ ፈላጊዎችና የቀድሞው ሥርዓት በሚልም እየተፎካከሩ ይገኛሉ። የአገሪቱ የምጣኔ ሃብት መሽመድመዱን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሩሃኒ ተቀባይነት ዝቅ ብሏል። ጆ ባይደን የኢኮኖሚ እቀባውን በማላላት የፕሬዚዳንቱን ማሸነፍ እድል ከፍ የማድረግ ፍላጎት ይኖራቸው ይሆን? በቴህራን ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ናስር ሃዲን ጄዚ፤ ጆ ባይደን የስልጣን ዘመናቸውን ከመጀመራቸው በፊት በኢራን ላይ ያላቸውን ጉዳይ ግልፅ ሊያደርጉት ይገባል ይላሉ። "ወደ ስምምነቱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በፍጥነት እንመለሳለን ብለው ለሕዝቡ ቢነግሩ በቂ ይመስለኛል" ይላሉ። ፕሬዚዳንቱ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ሁኔታዎች በበለጠ እንደሚበላሹ ያስረዳሉ። የጆ ባይደን ወደ ኒውክሊየር ስምምነቱ መመለስ ጉዳይ በእሳቸው ብቻ አይወሰንም። የኒውክሊየር ስምምነቱ በአሜሪካ ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ ልዩነትን ያመጣ ሲሆን ሪፐብሊካኑ በከፍተኛ ሁኔታ ይቃወሙታል። በጆርጂያ ያለው የምክር ቤቱ ምርጫ ውጤት በጥር ወር ሲጠናቀቅ በዋሽንግተን ያለውን የኃይል ሚዛን የሚወስን ይሆናል። ይህም ሁኔታ አስተዳደሩ በምን አይነት ነፃነትም ተግባሩን ያከናውናልም የሚለውንም ያሳያል። አዲስ ጥምረቶች የኒውክሊየር ስምምነቱ የሁለትዮሽ ጉዳይ ብቻ አይደለም። ኃያላኑ አገራት ሩሲያ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ኪንግደምና ጀርመን እንዲሁም የአውሮፓ ኅብረት በስምምነቱ ላይ ድርሻ አላቸው፤ ዓለም አቀፍም ደጋፊም ተብለው ተካተዋል። በተለይም የአውሮፓውያኑ አሜሪካ ወደ ስምምነቱ ተመልሳ እንዲሳካ ታደርገዋለች የሚለውን በጉጉት የሚጠብቁት ይሆናል። ትራምፕ ስምምነቱን ካፈረሱት በኋላም ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይና ጀርመንም ስምምነቱ እንዲቀጥል የራሳቸውን ሚና እየተጫወቱ ነበር። ሆኖም ሦስቱም የአውሮፓ አገራት ዓለም እንደተቀየረችና ወደቀድሞው ስምምነት መመለስም የማይቻል መሆኑንም ይረዱታል። ፕሮፌሰር አኒሴህ ባሲሪ ታብሪዚ እንደሚሉት ኢራን በቀጣናው የምታደርገው እንቅስቃሴ፣ የባሊስቲክ ሚሳይል ልማትና እንዲሁም የኒውክሊየር ስምምነቱ ጊዜ ማለፉም ጋር ተያይዞ የአውሮፓውያን አገራቱ ስምምነቱ በአዲስ መልክ እነዚህን ጉዳዮች ሊያካትት ይገባልም እያሉ ነው። የኒውክሊየር ስምምነቱን (JCPOA) በመጀመሪያ ሲቃወሙ የነበሩት እስራኤል፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ባህሬንን የመሳሰሉ የቀጣናው አገራት በትራምፕ አማካኝነት ግንኙነታቸውን ለማደስ መወሰናቸው አዲስ ለሚመጣው ስምምነት በራቸው ክፍት ላይሆን ይችላል። "በአካባቢያችን ያለውን የደኅንነት ጉዳይ በተመለከተ ስምምነት መፈረም ካለበት እኛም መኖር አለብን" በማለት በዋሽንግተን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምባሳደር ዩሴፍ አል ኦታቢያ በቴልአቪቭ ዩኒቨርስቲ በነበረ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል። የእስራኤልም አቻቸው አሞስ ያድሊን ይህንኑ አስተያየት የተጋሩት ሲሆን "እስራኤል ከመካከለኛው ምሥራቅ አጋሮቿ ጎን በመሆን ስምምነቶቹ ላይ መገኘት ትፈልጋለች" ብለዋል። የሳዑዲ አረቢያው ንጉሥ ሳልማን በበኩላቸው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢራንን ተቃውሞ እንዲቆም ጥሪ አድርገዋል። በዚህ ሁሉ ፍራቻ፣ መጠራጠርና የተለያየ ፍላጎት መካከል ወደ ኒውክሊየር ስምምነት መመለስ ለጆ ባይደን ቀላል አይሆንም። መረሳት የሌለበት ጉዳይ ደግሞ ትራምፕ ስልጣናቸውን አላስረከቡም። ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት ትራምፕ የኢራን የኒውክሊየር ማበልፀጊያ ጥቃት እንዲደርስበት ከፍተኛ አማካሪዎቻቸውን ጠይቀዋል የሚልም ዜና የአሜሪካ ሚዲያዎች ይዘው ወጥተዋል። በምርጫ የተሸነፉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራንን አልለቀቋትም አዲስ ማዕቀብም እያስተዋወቁ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ እቀባዎችም ይኖራሉ በማለትም እያስፈራሩ ነው። ትራምፕ እስከ ጥር ድረስ የሚያደርጉት ተግባር ግልፅ ይመስላል፤ ከእሳቸው ስልጣናቸውን ለሚረከቡት ጆ ባይደን ሥራቸውን ማክበድና፤ የደረሰውንም ጉዳት እንዳይቀለበስ ማድረግ ነው።
news-55071986
https://www.bbc.com/amharic/news-55071986
ኮሮናቫይረስ፡ የኦክስፎርድ የኮቪድ-19 ክትባትን እንዴት በዚህ ፍጥነት ሊሰራ ቻለ?
አስር ዓመታት ይፈጅ የነበረ ሥራ በአስር ወራት ውስጥ ተጠናቋል። ነገር ግን በዲዛይን ፣ በሙከራ እና በምርት ሂደት ውስጥ የቀሩ ነገሮች የሉም።
እነዚህ ሁለት አረፍተ ነገሮች እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ይመስላሉ። ምክንያቱም የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ክትባት ኮቪድ-19ኝን በመከላከል ረገድ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማ ነው መባሉ አስደሳች ዜና ቢሆንም፤ በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሰራቱ ግን ደኅንነቱ ላይ በርካቶች ጥያቄ እንዲያነሱ አስገድዷል። ስለዚህ ይህ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ክትባት እንዴት በዚህ ፍጥነት እንደተሰራ የሚገልጽ ነው። በአፍሪካ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ምናልባት ለተመራማሪዎች በርካታ ትምህርት የሰጠ ይመስላል። ኢቦላ በቫይረሱ ከተያዘ ግለሰብ ሰውነት ውስጥ በሚወጣ በጣም አነስተኛ መጠን ባለው ፈሳሽ ሳይቀር በመተላለፉና ያልተለመዱ ምልክቶች ስላሉት ችግሩን ከቁጥጥር ውጭ ያደርገዋል። ምክንያቱ ደግሞ ሰዎች የሚገናኙበት፣ የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና እንቅስቃሴዎች የሚዘወተሩበት አካባቢ ለቫይረሱ የሚያጋልጥ አይነት በመሆኑ ቫይረሱ የሚዛመትበትን እድል ስለሚያፋጥነው ነው። እንደ አውሮፓውያኑ ከ2014-2016 በምዕራብ አፍሪካ የተከሰተው ኢቦላ መነሻው ጊኒ ውስጥ በምትገኝ ትንሽ መንደር ውስጥ ሲሆን፤ መጀመሪያ በቫይረሱ የተያዘውም እደሜው ሁለት ዓመት የሚሆነው ህፃን ነበር። በሽታው በጊኒ እንዲሁም በጎረቤቶቿ ሴራሊዮንና ላይቤሪያ በተለይ በከተሞች አካባቢ በፍጥነት ተሰራጭቶ ነበር። ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከእነዚህ አገራት በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ብትገኝም ልታመልጥ ግን አልቻለችም። እስካሁን ኢቦላ ተገኝቶባቸዋል የተባሉ አምስት ቀጠናዎች የተለዩ ሲሆን የሞቱት ዜር በተሰኘው ቀጠና ነው። በእነዚህ ቀጠናዎች ለመጠባበቂያ የተዘጋጀው ክትባት ለድንገተኛ ክስተቶች ይውላል። በእንግሊዝና በኖርዌይ መንግሥታት ድጋፍ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 ክትባቱ ተቀባይነት ያገኘ ቢሆንም ለሰዎች እንዲሰጥ እስካሁን ሙሉ ፈቃድ አልተገኘም። ይሁን እንጂ ጠጥቅም ላይ እንዲውል ለመጠባበቂ 300 ሺህ የሚሆኑ ክትባቶች ተዘጋጅተዋል። ክትባቱ ቫይረሱ ይኖርባቸዋል ተብለው ለተጠረጠሩ ህሙማን፣ ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች መሰጠት እንዳለበት የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ሚኒስቴር ውሳኔ ብቸኛው አማራጭ ነው። ኢቦላ በቀላሉ ሊጠፋ እንደሚችል ተስፋ በማድረግ የሚያጋጥሙትን እያንዳንዱን ጥቃቅን ችግሮች በመፍታት ችግሩ ስር ሳይሰድ አሁን ባለበት ደረጃ ማስቀረት ይቻላል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ከ2014 እስከ 2016 ለነበረው የኢቦላ ወረርሽኝ የተሰጠው ምላሽ በጣም የዘገየ ስለመነበር 11 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። "ዓለም ከዚህ የተሻለ ማድረግ ትችል ነበር'' ይላሉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ክትባት ምርምርን የሚመሩት ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት። ''ከኢቦላ የተገኘውን ተሞክሮ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ሰው ሰውነት ውስጥ በፍጥነት ክትባቱ እንዲሰራ ለማድረግ አቅደን ነበር የጀመርነው። ምንም እንኳን እቅዱን ባንጨርሰውም በጣም አመርቂ ሥራ ነው የሰራነው።" ጥር 1/2020 (እአአ) አብዛኛው የዓለማችን ሕዝብ የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት በማስመለክት በየቦታው ደስታውን ሲገልጽና በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ በዓሉን ሲያከብር ፕሮፌሰር ሳራህ ጊልበርት ግን ከወደ ቻይና አንድ አስደንጋጭ ዜና ሰምተው ነበር። ይኽውም ከዉሃን ከተማ "አንድ ጉንፋን መሰል ቫይረስ እየተሰራጨ ነው" የሚል ነበር። በወቅቱ ተመራማሪዎች ስለቫይረሱ ማወቅ የቻሉት ብዙ ነገር ባይኖርም ከሰዎች ወደ ሰዎች ሊተላለፍ እንደሚችል ግን ገምተው ነበር። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡድን ምንም እንኳን ለአንድ ተላላፊ ቫይረስ የሚሆን ክትባት እንደሚሰራ ቢያውቅም ነገር ግን ይህ ቫይረስ ብዙ ጉዳት ሳያደርስ እንደሚጠፋ ነበር የታሰበው። "ልክ እንደ ማንኛውም አይነት ፕሮጀክት ነበር የያዝነው። ቫይረሱም በራሱ ጊዜ ሊጠፋ እንደሚችልም ገምተን ነበር" ይላሉ ፕሮፌሰሯ። ከዚህ በፊት የነበሩት የኮሮረናቫይረስ ክስተቶች ለዚህ ቡድን ጠለቅ ያለ ቅድመ እውቀት ሰጥቶታል። ለምሳሌ በ2002 ተከስቶ የነበረው የሳርስ ኮሮናቫይረስ እና በ2012 የተከሰተው የመርስ ኮሮናቫይረስ የሚጠቀሱ ናቸው። ይህ ማለት ተመራማሪዎች ቫይረሱ እንዴት እንደሚራባና ከሰው ወደ ሰው፣ ከሰው ወደ እንስሳት አልያም ከእንስሳ ወደ እንስሳ እንደሚተላለፍ አጠቃላይ እውቀት ነበራቸው። ለሙከራ በተሰራው ክትባት ውስጥ ያለው የፕሮቲን ከፍ ማለት ቫይረሱ በሰውነታችን ሴሎች ውስጥ የሚገቡበትን በሮች ለመክፈት የሚጠቀምበት ቁልፍ ነው። ክትባቱ የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል ሥርዓትን ቫይረሱን በከፍተኛ ፍጥነት ለማጥቃት የሚያሰለጥን ከሆነ ቡድኑ እሱን ለመሳካት ዕድለኛ ይሆናል ማለት ነው። "ይህ ሙሉ በሙሉ ያልታወቀ ቫይረስ ቢሆን ኖሮ በጣም በተለየ ሁኔታ ውስጥ እንገባ ነበር" ይላሉ ፕሮፌሰሯ። እንዲሁም ኮሮናቫይረስ የአጭር ጊዜ ኢንፌክሽኖችን ብቻ ማስከተሉ ነገሮች እንዳይወሳሰቡ አድርጎ ነበር። ይህ ማለት ሰውነታችን ቫይረሱን የማሸነፍ አቅም አለው ማለት ነው፤ እናም ክትባቱ ወደዚያው የተፈጥሮ ሂደት ውስጥ መግባት አለበት ማለት ነው። ባለፈው ዓመት ልክ ጥር 11 ላይ የቻይና ሳይንቲስቶች የኮሮናቫይረስ ሙሉውን የዘረመል ኮድ አሳትመው ለዓለም አጋሩ። ቡድኑ አሁን የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ አግኝቷል። ገንዘብ፣ ገንዘብ፣ ገንዘብ ክትባት መስራት በጣም ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል። "የመጀመሪያው ዙር በተለይ በጣም ከባድ ነበር። በአንድ ወቅት እንደውም በባንክ አካውንታችን ውስጥ ምንም አይነት ገንዘብ አልነበረም" ይላሉ ፕሮፌሰሯ። ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ትንሽ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ቢሆንም በተቀረው ዓለም ምርምር ከሚያደርጉ ተመራማሪዎች የተሻለ ብልጫ ግን ነበራቸው። ምክንያቱም ክትባት የማግኘት ሥራውን የጀመሩት ቀደም ብለው ስለሆነ ነው። ኦክስፎርድ ውስጥ በሚገኘው የቸርችል ሆስፒታል ውስጥ የተመራማሪዎች ቡድኑ የራሱ የክትባት ማምረቻ ማዕከል አለው። "እስከ ሚያዝያ ወር ድረስ ለምርምሩ የሚሆን ገንዘብ ማፈላለግ ዋነኛ ሥራችን የነበረ ሲሆን ሰዎች ሥራችንን በገንዘብ እንዲደገፉ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረቶችን ማድረግ ነበረብን።" ነገር ግን የኮሮረናቫይረስ ወረርሽ በበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ያሳረፈውን ተጽዕኖ ተከትሎ በቂ ገንዘብ ማግኘት ለቡድኑ አዳጋች ነበር። በተለይ ደግሞ በበርካታ አገራትና ከተሞች የእንቅስቃሴ ገደቦች ሲጣሉ ይበልጥ ከባድ ሆኖ ነበር። ልክ ቡድኑ የሙከራ ክትባቱን ሲሰራ በብዛት ማምረት እንዲቻል ተብሎ የምርት ሂደቱ በጣልያን እንዲካሄድ በመደረጉ በተገኛው ገንዘብ በአውሮፓ የእንቅስቃሴ ገደቡን ተከትሎ ያጡትን ገንዘብ በመጠኑም ቢሆን እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። ከዚህ በኋላ ተመራማሪዎቹ ወዲያው ክትባቱን በእንስሳት ላይ ወደ መሞከሩ ተሸጋገሩ። በዚህም የክትባቱን ደኅንነት እና በሰዎች ላይ ሊኖረው የሚችለውን የጎንዮሽ ጉዳት ለመፈተሽ እድል አግኝተዋል። ሚያዝያ 23 ላይ ደግሞ ክትባቱን በሰዎች ላይ መሞከር ጀመሩ። አንድ ክትባት ውጤታማነቱ እንዲረጋገጥና የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያስከትል ለማወቅ ወሳኝ የሚባሉ ሦስት ሂደቶችን ማለፍ አለበት። የኦክስፎርድ ክትባት እንዚህን ሁሉ ሂደቶች አልፎ ነው እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የቻለው። በእነዚህ ሙከራዎች ላይ 30 ሺህ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞች በሦስቱም ሂደቶች ላይ ተሳትፈዋል። በዚህ አካሄድ ታዲያ እስከ አስር ዓመት ሊፈጅ ይችል የነበረውን ክትባት የመስራት ሂደት በአስር ወራት ውስጥ ማጠናቀቅ ተችሏል። በአሁኑ ጊዜ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሰዎችን 70 በመቶ ከቫይረሱ መጠበቅ ያስችላል ተብሎለታል። ከዚህ ቀደም ይፋ የተደረጉት የፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶች አስተማማኝነት 95 በመቶ መሆኑ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የኦክስፎርድ ክትባት ከሁለቱ ክትባቶች አንጻር ዋጋው ርካሽ መሆኑ እንዲሁም ኦክስፎርድ ሰራሽ ክትባትን ማጓጓዝ እና ማከማቸት ከሁለቱ ክትባቶች አንጻር እጅግ ቀላል መሆኑ በመልካም ጎኑ ተጠቃሽ ሆኗል። በዚህም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የኦክስፎርድ ክትባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አስቀድሞ 100 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ክትባት ብልቃጦችን ለመግዛት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር ውል አስሯል። ይህ ማለት ለ50 ሚሊዮን ሰዎች የሚበቃ ነው። ሰዎች ክትባቱን በሦስት ሳምንት ልዩነት ሁለት ጊዜ ይወስዱታል ተብሏል። የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ጥበቃ ኃላፊ ማት ሃንኮክ ለቢቢሲ፤ "ይህ ወደ መደበኛው ሕይወት ለመመለስ አንድ እርምጃ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ነዋሪነታቸው በዩናይትድ ኪንግደም እና ብራዚል የሆኑ 20 ሺህ ሰዎች ላይ የኦክስፎርድ ክትባት ሙከራው ተከናውኗል። የዩናትድ ኪንግደም መንግሥት ደግሞ 4 ሚሊዮን ክትባቶች ተረክቧል። 96 ሚሊዮን ብልቃጦችን ደግሞ በቅርቡ ከአምራቹ ይቀበላል ተብሏል። ክትባቱ ግን የመድኃኒት ተቆጣጠሪዎችን ይሁንታ ሳያገኝ ለሰዎች አይሰጥም። መድኃኒት ተቆጣጣሪዎች የክትባቱን አቅም ለመፈተሽ እና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደማያስከትል ለማረጋገጥ ቢያንስ ሳምንታት ያስፈልጋቸዋል። በዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱን በቅድሚያ ከሚያገኙት መካከል እድሜያቸው የገፋ ሰዎች፣ በአረጋውያን መኖሪያ ውስጥ የሚገኙ አዛውንቶች እና የተቋማቱ ሠራተኞች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ የሆናቸው አዛውንቶች ተጠቃሽ ናቸው። የክትባቱ ዘላቂነት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እስካሁን አልታወቀም። ይህን ለማወቅ ተሳታፊዎች ላይ የሚደረገው ክትትል ይቀጥላል። ክትባቱ በዕድሜ ለገፉ ሰዎች የተሻለ መከላከል እንደሚሰጥ ቢጠቆምም ሙሉ መረጃ ግን ያሻል ተብሏል። ሌላው የማይታወቀው ነገር ክትባቱ ሰዎች በጣም እንዳይታመሙ ከማድረግ ያግዳል ወይ የሚለውና ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፉስ ያግዛል ወይ የሚለው ነው። ደኅንነቱስ? ክትባቱ እስካሁን በደኅንነት ጉዳይ ይህ ነው የሚባል ነገር አልተነሳበትም። ነገር ግን የትኛውም መድኃኒት 100 በመቶ እንከን አልባ ሊሆን አይችልም። አንዳንድ ተሳታፊዎች ክትባቱን የወሰዱ ሰሞን መጠነኛ ድካም፣ ራስ ምታትና ሕመም እንደተሰማቸው አስታውቀዋል። የሞዴርና እና የፋይዘር ክትባት ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆናቸው ተነግሯል። ነገር ግን የሁለቱም ድርጅቶች ውጤት የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም። ውጤታማነቱም ሊቀየር ይችላል ተብሏል። ቢሆንም የሞዴርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ ከሌሎቹ ክትባቶች በተለየ ቀላል እንደሆነ ተነግሯል። የሞዴርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ እስከ አንድ ወር መቆየት ሲችል የፋይዘር ግን ለአምስት ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው። ሩስያ ይፋ ያደረገችው ስፑትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትም 92 በመቶ የመከላከል አቅም እንደለው ተነግሯል።
48868370
https://www.bbc.com/amharic/48868370
የጥሩ አባትነት ሚስጥሮች ምንድናቸው?
በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሚኖሩ አካ የተባለ ጎሳ አባላት የሆኑ ወንዶች ትንንሽ ልጆችን የመንከባከብ ሃላፊነት ያለባቸው ሲሆን ሴቶቹ ደግሞ ወደጫካ ሄደው የማደንና ምግብ የመሰብሰብ ተግባር ይፈጽማሉ። አባቶች ቤት ማጽዳት፣ ከልጆች ጋር መጫወት እና ምግብ የመመገብ ሥራ ሲሰሩ ነው የሚውሉት።
በዚህ ተግባራቸውም የዓለም ህዝብ ከእነዚህ ሰዎች ብዙ የምንማረው ነገረ አለ በማለት አድናቆት ሲያጎርፍላቸው ቆይቷል። ጥሩ አባትነት ከብዙ ዓመታት በኋላ ትርጓሜው እየተቀየረ የመጣ ይመስላል። በአሁኑ ሰዓት ስለልጆቻቸው ስሜት የሚጨነቁና በተሻለ መልኩ ከልጆቻቸው ጋር ጊዜ የሚያሳልፉ አባቶች እንደ ጥሩና አስተዋይ አባት ይታያሉ። በአጠቃላይ በሚባል ደረጃ እስከ ጎርጎሳውያኑ 1970ዎቹ ድረስ ከህጻናት ጋር በተያያዘ ስለአባቶች ሃላፊነት ብዙም እውቀት አልነበረም። ዋነኛውና ብዙ ጊዜ ብቸኛው ሃላፊነታቸው ኦኮኖሚያዊ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ነበር። • ላጤ እናት መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች • የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ልጆቻቸው 'ሞባይል' እንዳይጠቀሙ የሚያግዱት ለምን ይሆን? በአምስተርዳም ቭሪጅ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ማሪያን ቤከርማንስ በሰሩት ተከታታይ ጥናት መሰረት ምንም እንኳን አንድ ልጅ ሁለት ቤተሰቦች ቢኖሩትም 99 በመቶ የሚሆነው የልጆች ሃላፊነት የሚሸፈነው በሴቶች (እናቶች) ነው። ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ከአባቶቻቸው ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት ኖሯቸው ልጅነታቸውን ያሳለፉ ህጻናት የተሻለ የአእምሮ እድገትና ጥሩ ባህሪ ይታይባቸዋል። በህይወታቸውም ደስተኛ የመሆናቸው እድል ከፍ ያለ ሲሆን ከሌሎች ህጻናት ጋር ያላቸው ግንኙነትም ጥሩ ነው። በሌላ በኩል ከአባቶቻቸው እምብዛም ፍቅር ማግኘት ያልቻሉት ህጻናት ግን ብዙ የሥነ አእምሮ ችግሮች ይስተዋሉባቸዋል። ቀን ሥራ ውለው ማታ ላይ ወደቤት የሚመለሱ አባቶች ሁሌም ቢሆን ከልጆቻቸው ጋር መጫወት ይፈልጋሉ። በዚህ ሰዓት አባትና ልጅ የማይረሱ የጨዋታ ጊዜዎችን ማሳለፍ ይችላሉ። ድብብቆሽና አባሮሽ እንዲሁም ሌሎች ጨዋታዎችንም ያዘወትራሉ። አብዛኛውን የቀኑን ጊዜ ቤት ውስጥ ከልጆች ጋር የሚያሳልፉት እናቶች ደግሞ ከልጆቻቸው ጋር ረጋ ያለና በመርህ ላይ የተመሰረት ግንኙነት ለመመስረት ይሞክራሉ። በተጨማሪም ምግብ መመገብ እንዲሁም ንጽህናቸውን መጠበቅን ያዘወተውራሉ። ይህ ደግሞ ልጆች ጨዋታና መዝናናትን ከአባቶቻቸው ብቻ እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል። ይህ በማይሆንበት ጊዜ ልጆች ላይ ድብርትና አንዳንዴም የከፋ የአእምሮ ችግር ያስከትልባቸዋል። • "እናቴ ኤች አይ ቪ እንዳለብኝ ሳትነግረኝ ሞተች" ''ምናልባት ጥሩ አባትነት ሲባል ብዙዎች እጅግ ከባድና ብዙ ጊዜ የሚጠይቅ ነገር መስሎ ሊታያቸው ይችላል። ነገር ግን ልጆችን በጉልበታችን ላይ አስቀምጠን አይን አይናቸውን ማየት በራሱ እጅጉን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይችላል። በተለይ ደግሞ አዲስ የተወለዱ ህጻናት ከእናትና አባታቸው ጋር የሚያሳልፏቸው ጊዜያት ወደፊት ማንነታቸውን የመገንባት ትልቅ አቅም አላቸው'' ይላሉ ዶክተር ቤከርማንስ ። በልጅ ማሳደግ ሂደት ውስጥ ትልቁ ነገር ጥሩም ይሁን መጥፎ አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ነው። አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ውስጥ ልጆች ቤተሰቦቻቸውን የመላመድና ስሜታቸውን በቀላሉ መግለጽን ይማራሉ። ቤተሰቦች በተለይ ደግሞ ብዙ ጊዜን ከልጆቻቸው ጋር ማሳለፍ የለመዱ አባቶች ልጆቻቸው ምን እንደሚያስደስታቸውና ምን እንደማያስደስታቸው በቀላሉ መለየት ይጀምራሉ። ከዚህም ባለፈ ጥሩና መጥፎ የሚሏቸውን ነገሮች በጨዋታዎች መሃል ለማሳየት እድሉን ይከፍትላቸዋል። ከልጆች አስተዳደግ ጋር በተያያዘ ባለንበት ዘመናዊ ዓለም ለብዙ አባቶች ችግር እየሆነ ያለው ነገር፤ በሥራ አካባቢና በሌሎች ቦታዎች ስለልጆቻቸው በነጻነት ማውራት አለመቻላቸው ነው። በተቃራኒው እናቶች የፈለጉትን ያክል ስለልጆቻቸው ሁኔታ በሥራ ቦታም ሆነ ከጓደኞቻቸው ጋር ማውራት ይችላሉ። እስቲ ስንቶቹ አባቶች ናቸው ታዳጊ ልጆቻቸውን ወደሥራ ቦታ ይዘው የሚመጡት? ምን ያህሉ አባቶች ናቸው ልጆች ሲታመሙ ወደ ህክምና ቦታ የሚወስዱት? ለእነዚህና ለሌሎች መሰል ጥያቄዎች ያለው ምላሽ "በጣም ጥቂቶቹ" የሚል ነው። ነገር ግን አባቶች ብዙ ጊዜያቸውን ከልጆቻቸው ጋር ማሳለፍና ጨዋታዎችን ማብዛት ሲጀምሩ በየትኛውም ጊዜም ሆነ ቦታ አብረዋቸው ለመሆን ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ ይመጣል ይላል ጥናቱ።
news-51066440
https://www.bbc.com/amharic/news-51066440
የታገቱት 17ቱ ተማሪዎች፡ "ከታገቱት መካከል አንዷ ነበርኩ፤ በሦስተኛ ቀኔ አምልጫለሁ"
17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ በታጣቂዎች ከታገቱ ሳምንታት ተቆጠሩ።
ተማሪዎቹ የታገቱት ከደምቢ ዶሎ ጋምቤላ በሚወስደው መንገድ ላይ ነው በታጣቂዎች ታግተው ከሚገኙት 17ቱ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል 13ቱ ሴት ተማሪዎች መሆናቸውን ከአጋቾቹ ካመለጠች ተማሪ ማወቅ ተችሏል። "ከታገቱት መካከል አንዷ ነበርኩ፤ በሦስተኛ ቀኔ አምልጫለሁ" ተማሪ አስምራ ሹሜ ተማሪ አስምራ ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዷ ነበረች። የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ታስረዳለች። "በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት የኢንጅነሪንግ ተማሪ ነበርኩ። አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው በመዘጋቱ ወደ ትውልድ አካባቢዬ ተመልሼ አዲስ ዘመን ከተማ ነው ያለሁት። ከታገቱት ተማሪዎች መካከል አንዷ ነኝ። መጀመሪያ በአጋቾቹ የተያዝነው 18 ተማሪዎች ነበርን። እኔ ማምለጥ ስለቻልኩ አሁን ታግተው ያሉት ተማሪዎች ቁጥር 17 ነው። ከእነዚህ መካከል 4ቱ ወንዶች ሲሆኑ 13ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው። አሁን ታግተው ያሉት ተመራቂ ተማሪዎች እና የኢንጅነሪንግ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ናቸው። በወቅቱ በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ስለነበር ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተው ነበር። እኛም መውጣት አሰብን ወደ አዲስ አበባ በቀጥታ የሚያስመጣው ዋና መንገድ በመዘጋቱ ከደምቢ ዶሎ በጋምቤላ በኩል አድርገን አዲስ አበባ ለመግባት ወሰንን። ሁላችንም ከአማራ ክልል አካባቢዎች የመጣን ተማሪዎች ነን። ከደምቢ ዶሎ ጋምቤላ የ30 ብር ትራንስፖርት ሲሆን እቅዳችን ጋምቤላ አድረን ወደ አዲስ አበባ ነበር። ነገር ግን ያሰብነው ቦታ ሳንደርስ ደምቢ ዶሎ እና ጋምቤላ መካከል 'ሱድ' የምትባል ቦታ ላይ ስንደርስ መኪናውን አስቁመው፤ ወጠምሻ ወጣቶች መጥተው አፈኑን። የአፋኞቹ ቁጥር ከእኛ ቁጥር በላይ ነበር። አካባቢው ጥቅጥቅ ያለ ጫካ በመሆኑ በእርሱ ውስጥ ይዘውን ገቡ። ይዘውን ሲሄዱ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ከማየት ውጭ ለማስጣል የሞከረ አልነበረም። እየጮህን ነው ይዘውን የሄዱት። የጫካውን ግማሽ እንደተራመድን የተወሰኑት ሴቶች መራመድ አቃታቸውና ወደቁ። ታዲያ እነርሱን 'ተነሱ፤ አትነሱ' እያሉ ለማንሳት ሲሞክሩ ነበር እኔ ከአይናቸው የተሰወርኩት። በጫካው ውስጥ ለሁለት ቀናት ያህል ካደርኩ በኋላ፤ በሦስተኛው ቀን ወደ ዋናው የመኪና መስመር መውጣት ቻልኩ። ግራ ተጋባሁ፤ ስልኬን ስለወሰዱት ስልክ መደወል አልቻልኩም፤ ምንም ማድረግ አልቻልኩም ነበር። እንደምንም ብዬ ወደ መስመር ስወጣ አንድ አማርኛ በትንሹም ቢሆን መናገር የሚችሉ አባት አገኘሁ። እርሳቸው እንዳዩኝ 'የእኔስ ልጆች እንዲህ አይደል የሚሆኑት' ብለው በማዘን ኮታቸውን አለበሱኝ። 'ከታየሁ እኔም እገደላለሁ' ብለው ደብቀው አስቀመጡኝ። 'የት ነው መሄድ የምትፈልጊው' አሉኝ። 'ደምቢ ዶሎ ለፌደራል ፖሊሶች ስጡኝ' አልኳቸው። ከዚያም መኪና ለምነው አሳፍረው ላኩኝ። መረጃውንም ለፌደራል ፖሊሶቹ ተናግሬያለሁ። ፌደራል ፖሊሶቹ 'ቦታው እንኳን ለተማሪ ለወታደርም አስጊ ነው፤ እንከታተላለን' አሉኝ። ከታገቱት መካከል አንዷ ጓደኛዬ መጀመሪያ አካባቢ ስልክ እየሰጧት ትደውልልኝ ነበር። ለማውራት ብዙም ነፃነት ባይኖራትም 'በጣም እያሰቃዩን ነው፤ ምግብም ሲያሻቸው ይሰጡናል፤ ሲፈልጉ ደግሞ ይከልክሉናል' ስትል ነግራኛለች። የምትደውልበትን ስልክ 'የእነርሱ ነው ያዥው' ብላኝ ነበር። ከዛን ቀን በኋላ ግን አይሰራም፤ እነርሱም ደውለው አያውቁም፤ እኛም አግኝተናቸው አናውቅም። ይመለከታቸዋል ለተባሉ አካላት፤ ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ለአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት፣ ለፀጥታ እና ደህንነት መረጃውን ሰጥቻለሁ፤ ጠይቄያለሁ። 'እንከታተላለን' ነው ያሉኝ። ከዚያ መምጣቴን የሚያውቁ የተማሪዎቹ ወላጆችም ያለሁበት ድረስ እየመጡ ያለቅሳሉ፤ እኔ ግን 'መንግሥት ይዟቸዋል፤ አሁን ይመጣሉ' እያልኩ ከማረጋጋት ውጭ የማደርገው ጠፍቶኛል።" የታጋች ተማሪዎች ቤተሰቦች ምን ይላሉ? ቢቢሲ ያነጋገራቸው እና ስማቸውን ለልጆቹ ደህንነት ስንል ያልጠቀስናቸው የታገቱት ተማሪ ቤተሰቦች፤ ተማሪዎቹ ከታገቱ አንድ ወር እንዳለፋቸው ይናገራሉ። "በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ስልክ ይደውሉ ነበር፤ አሁን ግን ድምፃቸውን ከሰማን ሦስት ሳምንታት አልፈዋል" ይላሉ። እህቱ እንደታገተችበት የነገረን አንድ ግለሰብ፤ በዩኒቨርሲቲው ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ሌሎች ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ሲወጡ፤ እርሱም እህቱን ጨምሮ ሌሎች ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ቢነግራቸውም እነርሱ ግን ከአሁን አሁን ይረጋጋል እያሉ መቆየታቸውን ያስረዳል። ይህ ግለሰብ እንደሚለው ስልክ ተደውሎለት እህቱን ጨምሮ ሌሎች ተማሪዎች ስለመታፈናቸው የሰሙት ሕዳር 24፣ 2012 ዓ.ም ነው። ተማሪዎቹ ከታገቱ በኋላ በነበሩት ሁለት ሳምንታት በተማሪዎቹ ስልክ ከዚያ በኋላ 'የአጋቾቹ ነው' ባሏቸው ስልክ ይደውሉላቸው ነበር። ቦታውን ሲጠይቋቸው ግን እንደማያውቁት ነበር ሲነግሯቸው የቆዩት። "የሆነ ሰዓት ላይ ስልክ ተሰጥቷት የፅሁፍ መልዕክት ላከችልኝ፤ ''አሻና አፋን ገደራ' የሚባል ቦታ ነው ያለነው፤ ለመከላከያ ደውሉና እዚህ አካባቢ ይፈልጉን' ብላ ፃፈችልኝ" ይላል። በመጨረሻው የስልክ ልውውጣቸው፤ "አሁንም እዚያው ቦታ ነሽ ወይ?" ብሎ ሲጠይቃት "በፊት ቢሆን ጥሩ ነበር፤ አሁን ቦታ ቀይረናል፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የሁለት የሦስት ሰዓት መንገድ በጫካ እንጓዛለን፤ አታገኙንም፤ አሁንም ልትንቀሳቀሱ ነው ተብለናል፤ እስካሁን ባለው ደህና ነን'' ስትል ስልኩን ከዘጋች ወዲህ እህቱን በስልክ ማግኘት እንዳልቻለ ይናገራል። ከታጋች ተማሪዎች ወላጆች መካከል ሁለት ሰዎች፤ ስለ ልጆቻቸው መረጃ ፍለጋ ወደ ደምቢ ዶሎ ተጉዘው እንደነበረ ይሄው እህቱ የታገተችበት ወንድም ይናገራል። እሱ እንደሚለው ወደ ሥፍራው የሄዱት ሰዎች ከዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከሚመለከታቸው የክልሉ መንግሥት ምላሽ ማግኘት አልቻሉም። ሌላኛዋ የታጋች ተማሪ እህት እንደነገረችን፤ ቀደም ብሎ በዩኒቨርሲቲው አንድ የአማራ ተወላጅ ተማሪ መገደሉን ተከትሎ ወንድሟ ከፍተኛ ስጋት አድሮበት እርሷ ጋር ደውሎ ገንዘብ እንድትልክለት መጠየቁን ታስታውሳለች። "የደወለው ቅዳሜ ቀን ስለነበር እስከ ሰኞ እንዲታገስ ነገርኩት፤ ሰኞ ዕለት ብር ልልክለት ስደውል ስልኩ አይሰራም። በማግስቱ ደውሎ መያዛቸውን ነገረኝ። ከተያዙ ጀምሮ ሁለት ሳምንታት ድረስ ይደውሉ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ድምፃቸው አልተሰማም" ትላለች። እስካሁን የምንችለውን ነገር ሁሉ እያደረግን ነው የምትለው የተማሪው እህት፤ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የምታገኛቸው የታጋች ወላጆች በከፍተኛ ሃዘንና ጭንቀት ላይ እንደሚገኙ ትናገራለች። "አንጀታቸውን በገመድ አስረው መሬት ላይ ተኝተው ይፀልያሉ፤ 'ሞተው ከሆነ አስክሬናቸው ይምጣልን'" እያሉ ነጋ ጠባ እያለቀሱ ነው" ትላለች። ተማሪዎቹ ላይ ወሲባዊ ጥቃት እንደሚፈፀምባቸውና እየተሰቃዩ እንደሚገኙ መስማታቸውንም አክላለች። የአጋቾቹ ፍላጎት ምንድነው? ወንድሟ የታገተባት እህት ከወንድሟ ባገኘችው መረጃ መሠረት አጋቾቹ ገንዘብ አይፈልጉም። ከአጋቾቹ እጅ ያመለጠችው አስምራ እንደምትናገረው፤ አጋቾቹ በተደጋጋሚ "ከእናንተ ጋር ጸብ የለንም። ጸባችን ከመንግሥት ጋር ነው" እንደሚሉ ትናገራለች። አጋቾቹ "የአማራ ሕዝብ ልጆቻችን ታግተዋል ብሎ ሰልፍ ሲወጣ፤ መንግሥት እኛን ያነጋግራል። የዛኔ እኛ ጥያቄያችንን ለመንግሥት እናቀርባለን፤ ጥያቄያችንም ይመለሳል" እንዳሉ አስምራ ገልፃልናለች። የመንግሥት አካላት ምላሽ? ኦሮሚያ የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ "ምንም አይነት መረጃ የለኝም። እኔ የሰማሁት ነገር የለም" ይላሉ። ጉዳዩ እርሳቸው የሚመሩትን ቢሮ በቀጥታ የሚመለከት መሆኑን በመጥቀስ ስለጉዳይ እንዴት መረጃ ሳይኖራቸው እንደቀረ የተጠየቁት ኮሎኔል አበበ ገረሱ፤ "እኔ ምንም አልሰማሁም ነው የምልህ። ለምድን ነው የምትጠይቀኝ?" በማለት መልሰዋል። የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በበኩላቸው ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች የሉም ብለዋል። ኃላፊው "ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም" ከማለት ውጪ ማብራሪያ መስጠት አልፈለጉም። አማራ የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገርም፤ "አሁን ማውራት የማልችልበት ቦታ ነው ያለሁት" በማለት የእጅ ስልካቸውን ዘግተውታል። አቶ አገኘው ተሻገርን መልሰን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከአምስት ቀናት በፊት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ "አራት ተማሪዎች ታግተው እንደሚገኙ መረጃው አለኝ" ማለታቸው ይታወሳል። ታግተው የሚገኙት ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር በስልክ አልፎ አልፎ እንደሚገናኙ ጭምር ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳደሩ ተማሪዎቹ ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ከአባ ገዳዎች፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ እና ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር ውይይት እያደረግን ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡን ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረትም ስልካቸው ዝግ በመሆኑ አልተሳካም። ተማሪዎቹ ከታገቱ በኋላ መንግሥት ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ የወሰደው እርምጃ የለም በማለት በርካቶች የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። ከእነዚህ መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ትናንት ባወጣው መግለጫ የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ እና ጥቃት አድራሾቹ ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ዛሬ በገፁ ላይ ባወጣው መግለጫም፤ የታገቱት ተማሪዎች ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዲለቀቁ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባስቸኳይ እንዲወጣ ጠይቋል። 'የታገቱት ተማሪዎች ይለቀቁ' የሚል ዘመቻም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተካሄዱ ነው፤ መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጥም እየተጠየቀ ነው። የጠቅላይ ሚንስትሩን ካቢኔዎች 50 በመቶው ሴቶች መሆናቸውን በማስታወስ፤ በደህንነት ስጋት የዩኒቨርሲቲ ግቢ ለቀው ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲያመሩ የታገቱ ሴት ተማሪዎች ትኩረት አለማግኘት በመጥቀስ ብስጭት አዘል አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።
48361915
https://www.bbc.com/amharic/48361915
የ 'ምን ልታዘዝ' ድራማ ሰምና ወርቅ
ኢትዮጵያ ውስጥ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ድራማዎች በተለያየ ዘመን ታይተዋል፤ 'ባለጉዳይ'፣ 'ማን ገደላት'፣ 'ገመና'፣ 'ቤቶች' እና ሌሎችም ትችት አዘል የቴሌቪዥን ድራማዎች ይጠቀሳሉ።
የቅርብ ጊዜው 'ምን ልታዘዝ' የነዚህን ድራማዎች ዝርዝር የተቀላቀለ ይመስላል። ከላይ የተጠቀሱት ድራማዎች ማኅበራዊ ህጸጽን አጉልተው ሲያሳዩ 'ምን ልታዘዝ' በአንጻሩ ፖለቲካዊ ሽሙጥን በሚገባ ይጠቀማል። ድራማው በቴሌቪዥን መተላለፍ የጀመረው ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ በገነነበት፣ የፖለቲካው አካሄድ ሚናው ባልለየበት ወቅት ነበር። ድራማው በዚህ ወቅት በድፍረት ፖለቲካውን መሸንቆጡ ተወዳጅ አድርጎታል። የ 'ምን ልታዘዝ' መቼት አንድ ካፌ ነው። የካፌው ባለቤት እትዬ ለምለም ቢሆኑም በበላይነት የሚመሩት አቶ አያልቅበት ናቸው። • በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ? • ኬንያዊው ፀሀፊ ቢንያንቫንጋ ዋይናይና ሲታወስ አቶ አያልቅበት፤ የካፌው አስተናጋጆች፤ ዕድል፣ የንጉሥና ደግሰውን ክልል ከፋፍለው እንዲሠሩ መድበዋቸዋል። በየወቅቱም ስብሰባ ይወዳሉ። ይህንን 'የካፌ ዓለም' ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚያነፃፅሩ ተመልካቾች አሉ። ነፃነት ተስፋዬና ታመነ በአመቻቸው ጊዜ ሁሉ ድራማውን ይከታተላሉ። ድራማው የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ እየተከታተለ የሰላ ትችት እንደሚያቀርብ ይስማማሉ። ረጋ ያለው፣ ጢማሙ ባሬስታ ዳኜ፣ ጋዜጣ አዟሪው ሱዳን፣ የልጥ ፓርቲ ሊቀ መንበር፣ ጨርቦሌ፣ ደራሲው ዶኒስና ሦስቱ የባንክ ሠራተኞች የድራማው ገፀ ባህሪያት ናቸው። ሌሎች ቋሚና አልፎ ሂያጅ የካፌው ደንበኛ ገፀ ባህሪያትም አሉት። ታዲያ ታመነ በገፀ ባህሪያቱ ብሽቅ ይላል። ለምን? ስንለው "ይልፈሰፈሱብኛል" ነው መልሱ። ካፌው ውስጥ በየሳምንቱ የሚነሱ ጉዳዮች ፖለቲካዊ ናቸው። በየወቅቱ አገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ነገሮች በአቃቂር ተለብጠው፣ በሳቅ ተከሽነው ወደተመልካች ይደርሳሉ። ድራማው በፋና ቴሌቪዥን መቅረቡ ለአንዳንዶች ግርምት አጭሯል። ታመነ እንደሚለው፤ ማኅበረቡ ውስጥ ያለውን፣ የሚብላላውን ነገር ከማቅረብ ባለፈ ጠንካራ መልእክት የለውም። ነፃነትም በሀሳቡ ይስማማል። ሆኖም ገፀ ባህሪያቱ የገሀዱ ዓለም ወካይ መሆናቸውን ያምናል። ድራማው የብዙሀን መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ መሆኑ ታመነና ነፃነትን የሚስማማ ሌላው ጉዳይ ነው። የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊና ለዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴአትር ያስተማሩት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፤ የ 'ምን ልታዘዝ' ፖለቲካዊ አቃቂር ለኢትዮጵያ የድራማና ቴአትር ዘርፍ አዲስ አይደለም ይላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው ቴአትር ፖለቲካዊ ይዘት እንደነበረውም ያጣቅሳሉ። በጅሮንድ ተክለኃዋርያት ተክለማርያም የጻፉት ግንባር ቀደሙ ኢትዮጵያዊ ቴአትር የ 'አውሬዎች ኮመዲያ መሳለቂያ' ከአንዴ በላይ ለመታየት እድል አለማግኘቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩት አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ይናገራሉ። ምክንያቱ ደግሞ የወቅቱ ባለስልጣናት በጭብጡ በመቆጣታቸው ነው ይላሉ። ትችትን በቴአትር ማቅረብ ለኢትዮጵያውያን አዲስ እንዳልሆነ ሁለቱም ይስማማሉ። "ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ትችትን በቅኔ ማቅረብ አዲስ አይደለም" የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ሸፈንፈን አድርጎ ማቅረብ ሥነ ጽሁፋዊ ባህላችን ነው ሲሉ ያክላሉ። • በመፈንቅለ መንግሥቱ ዙሪያ ያልተመለሱት አምስቱ ጥያቄዎች • ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ማዕድ የቀረቡት ምን ይላሉ? አቶ ዘሪሁንም 'ምን ልታዘዝ' እውነት አለው፤ ውበትም እንዲሁ በማለት ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ። 'ባለጥርሱ' ምን ልታዘዝ በየሳምንቱ እሁድ ከሰዓት በኋላ የሚቀርበው የቴሌቪዥን ድራማ፤ ወቅታዊ ጉዳዮችን እግር በእግር ተከታትሎ ለመተቸት እድሉን አግኝቷል። በፋና ብሮድካስቲንግ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ዋና አዘጋጅና የተባባሪ ፕሮግራሞች ክፍል ኃላፊ ዘካሪያስ ብርሃኑ፤ የ 'ምን ልታዘዝ' ፕሮፖዛል ወደቢሯቸው ሲሄድ አላማው ፖለቲካዊ ጉዳዮችን መተቸት እንደነበር ያስታውሳሉ። የፋና ብሮድካስቲንግ ባለሙያዎች ከደራሲዎቹ ጋር በመወያየት አሁን ያለውን ቅርፅ እንዲይዝ ማድረጋቸውንም ያስታውሳሉ። አውዳዊነትንና አሁናዊነትን አጣምሮ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ትችቱን ለማቅረብ እድል ያገኘው 'ምን ልታዘዝ'፤ ተወዳጅነት ካተረፈባቸው ምክንያቶች አንዱ ብዙሀኑ በሚመለከቱት ቴሌቪዥን መተላለፉ መሆኑን ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ይናገራሉ። አቶ ዘሪሁን በበኩላቸው፤ 'አይነኬ ናቸው' የምንላቸውን ጉዳዮች የደፈረ ነው ይላሉ። ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት ፖለቲካውን ደፍረው በጥበብ ሥራቸው የነኩ ባለሙያዎች እየተሳደዱ፣ ጫና ውስጥ የመውደቅ እድላቸው ሰፊ ነበር በማለት የበጅሮንድን ተውኔት ይጠቅሳሉ። በአሁን ሰዓት ቴሌቪዥን ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ስለሚታይ 'ምን ልታዘዝ' በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የመታየት እድል አግኝቷል የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ለመወደዱ እንደምክንያት ያቀረቡት ሌላ አስረጅ የደራሲያኑን ችሎታ ነው። የሰላ ትችት የሚቀርብበትን መንገድ በደንብ አውቀውታል የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህንን ገፀ ባህሪቱን በማንሳት ያስረዳሉ። ገፀ ባህሪያቱ ቋሚ ሆነው፣ ባህሪያቸውም ታውቆ ሁሌም አዳዲስ ነገሮችን ያቀርባሉ። አቶ አያልቅበት፣ ጨርቦሌ፣ ባሬስታው ዳኜ፣ ጋዜጣ አዟሪው ሱዳን በባህሪያቸው ይታወቃሉ። በባህሪያቸውና በድርጊታቸውም ያስቁናል። አቶ ዘሪሁን እንደሚናገሩት፤ ተመልካች በገፀ ባህሪያቱ ድርጊትና ንግግር ከመሳቅ ባሻገር፤ ንግግራቸውን ሳይዘነጋ ለቀናትና ለሳምንታትም ፈገግ ይላል። የ 'ምን ልታዘዝ' ጉልበት የሚመነጨው በማሳቁ ወይንም በመተቸቱ ብቻ ሳይሆን፤ በየሳምንቱ የሚታወሱ ቃለ ተውኔቶች እንዲሁም ክስተቶች በማቀበሉ መሆኑን ሁለቱ ባለሙያዎች ይስማማሉ። በገፀ ባህሪያቱ ስም አወጣጥ፤ ልጥ (ልማታዊ ጥምረት) እና ጨርቦሌ (ከጨርቆስ እስከ ቦሌ) ውስጥም እንዲህ አይነት ነገር ይስተዋላል ሲሉም ያክላሉ። • የመጭው ዘመን አምስቱ ምርጥ ምግቦች • የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ? "ጉልበቱ ሳቅ መፍጠር ሳይሆን ትችት መሰንዘር ነው" የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ሰዎች ሲስቁ ነገ ያንን ድርጊት ላለመደገም፣ መሳቂያ መሳለቂያ ላለመሆንም ትምህርት እየወሰዱ መሆኑን ይገልጻሉ። 'ምን ልታዘዝ' መጀመሪያ አካባቢ ፖለቲካውን ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ ጉዳዮችንም ይዳስስ እንደነበር አቶ ዘሪሁን ያስታውሳሉ። የፖለቲካው ሁኔታ ሲለወጥ ግን የድራማው ሂስም ጠንከር ማለቱን ይጠቅሳሉ። ጸሀፊዎቹ ካለው የፖለቲካ እውነታ መውጣት አይችሉም ሲሉም ያስረዳሉ። አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ (ሲትኮም) ማኅበራዊ ጉዳይ የመሄስና ወቅታዊ ጉዳይ እያዋዛ የመተቸት ባህሪ አለው። 'ምን ልታዘዝ' ይህን ማሳካት መቻሉን ይገልጻሉ። የደራሲያኑ አቋም መታየትና መከበር እንዳለበት "መሥራት የምንፈልገው ፖለቲካዊ ሳታየር ነው ካሉ አቋማቸው ሊከበር ይገባል" ሲሉም ያስረዳሉ። የፋና ብሮድካስቲንግ ባልደረባ አቶ ዘካሪያስም፤ የአገሪቱ ፖለቲካ ሲከር ፖለቲካውን አምርረው መተቸታቸው ተጠባቂ ነገር ነው ይላሉ። ጥበብ እንደፈቺው ነው ለአቶ ዘሪሁን፤ በድራማው ውስጥ በአልፎ ሂያጅም ሆነ በዋናነት የተሳሉ ገፀ ባህሪያት፤ እኛን መስለው እኛን አክለው የተሳሉ ሰዎች ናቸው። ለረዳት ፕሮፌሰር ነቢዩ ግን 'ምን ልታዘዝ' ኢትዮጵያዊ ብቻ አይደለም። ለኢትዮጵያውያን የቀረበ ዓለም ቢፈጥሩም፤ የሚቃኙት ግን በአፍሪካና በተቀረው ዓለም ላይ የሚካሄዱ አበይት ክስተቶችን ነው ይላሉ። ገፀ ባህሪያቱ ሁሌም ከገሀዱ ዓለም ጋር በአቻነት የቆሙ ናቸው በሚለው ረዳት ፕሮፌሰሩም ሆነ መምህሩ አይስማሙም። ጋዜጣ አዟሪው ዛሬ እከሌ የሚባለውን ጋዜጠኛ ቢመስል፣ ነገ ደግሞ ሌላ ጋዜጠኛ ይመስላል፣ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ሌላ ሰው ይወክላል። ተቃዋሚ ፓርቲውንም ሆነ አክቲቪስቱን የሚመስሉ ገፀ ባህሪያት ውክልናም ይለዋወጣል። "የተፎካካሪ ፓርቲዎችንና የአክቲቪስቶችን ፅንሰ ሀሳብ ወክለው የተሳሉ እንጂ የአንድ ሰው ቅጂ ናቸው ብዬ አላስብም" ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ። አቶ ዘሪሁን በበኩላቸው፤ ተመልካች የራሱን ትርጉም የመስጠት እድል እንዳለው መዘንጋት እንደሌለበት ያስታውሳሉ። በጎ ምላሽ እንደሚሰጠው ሁሉ ያልተገባ ትርጉም ተሰጥቶት ልንሰማ እንደምንችልም ያነሳሉ። በድራማው ላይ የሚስተናገዱ አካላት የአንድ ክልል ወይም ክፍለ ከተማ ወካይ ናቸው ብሎ አስተያየት መስጠት አይቻልም ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ። የተለያዩ ተመልካቾች ቅሬታቸውንም ሆነ ሙገሳቸውን ወደቢሯቸው መውሰዳቸውን የሚያስታውሱት አቶ ዘካሪያስ፤ "እንደተመልካች እከሌ እከሌን ይመስላል ማለት ከባድ ነው" ይላሉ። ከቀረቡ ጥያቄዎች አንዱ ድራማው ከፋና ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ጋር ይጣረሳል? የሚለው ሲሆን፤ አቶ ዘካርያስ ከፖሊሲያቸው ጋር እንደማይጋጭ ይናገራሉ። በ 'ምን ልታዘዝ' ውስጥ ያሉ ገፀ ባህሪያት አንዳቸው ከሌላቸው የተለዩ ተደርገው ስለተቀረጹ የሚያፈልቋቸው ሀሳቦች የተለያዩ ናቸው። አቶ አያልቅበት ከጨርቦሌ፣ ደግሰው ከዕድል የተለየ ሀሳብ ያላቸው ገፀ ባህሪያት መሆናቸው ጥንካሬ ሰጥቷቸዋል ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰሩ። ይህ ልዩነት ገፀ ባህሪያቱ በቀላሉ በተመልካች አንዲለዩ ብቻ ሳይሆን፤ ግጭት ለመፍጠርና የድራማውን ታሪክ ለማንቀሳቀስ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል። የገፀ ባህሪያቱ ሥነ ልቦና፣ ሞራልና ማኅበራዊ ሁኔታ ቁልጭ ብሎ የሚታይ በመሆኑ በተመልካች ዘንድ ገፀ ባህሪያቱን ከእውኑ ዓለም ሰዎች ጋር በማመሳከር ጨርቦሌ እንትና ነው፣ ልጥ ደግሞ እንትና ነው ይባላል። "ይህ የሆነው ገፀ ባህሪያቱ በደንብ ተደርገው ስለተሳሉ ነው" ይላሉ። በ 'ምን ልታዘዝ' ድራማ የሚስቅ ተመልካች ምን ያተርፋል? ድራማው ለማስተማር የተዘጋጀ አይደለም የሚሉት አቶ ዘካርያስ፤ ከማዝናናት ባሻገር የአገሪቱ ፓለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ የመተው ግብ አለው ይላሉ። ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ በበኩላቸው፤ "ሥነ ጥበብ ሕሊናን በመሸንቆጥ፤ ሰልፍ ላይ ወጥቶ ድንጋይ ከመወርወር፣ መስታወት ከመስበርና ሕይወት ከሚጠፋ፣ ነገሮች እንዲስተካከሉ እድል ይሰጣል" ይላሉ። ሥነ ጥበብ የመማር እድል ይሰጣል የሚሉት ባለሙያዎቹ፤ ገፀ ባህሪያቱ ባደረጉት ነገር ስንስቅ እግረ መንገዳችንን እየተማርን መሄድ አለብን ይላሉ። የ 'ምን ልታዘዝ' የመተቸት ነፃነት ከየት መጣ? 'ምን ልታዘዝ' በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ፖለቲካዊ እርምጃዎች ዜና በሆኑ ማግስት ለሳቅና ለስላቅ ያበቃቸዋል። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ የሆኑትን እንከኖች በጥበብ አሽቶና አዋዝቶ ያቀርባቸዋል። ይህ ነፃነቱን ከሌሎች ድራማዎች በተለየ ከወዴት አገኘው? የሥነ ጥበብ ነፃነት ከመናገር ነፃነት ጋር የተያያዘ ነው የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ ሕገ መንግሥቱ ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ቢፈቀድም "በተለያየ ጊዜ በተለያየ ምክንያት አንዳንዴ ስንጠቀምበት ሌላ ጊዜ ስንተወው ነበር" ይላሉ። "በአሁን ወቅት በነጻነቱ ተናዶ ጡንቻውን የሚያሳይ ስለሌለ በጥሩ ሁኔታ እየኮመኮምን" ይላሉ። አቶ ዘካሪያስ በበኩላቸው፤ ከድራማው ነፃነት የተነሳ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ "ድራማው ሊቋረጥ ነው" እና "ደጋፊ አካላት ውላቸውን አቋረጡ" ተብሎ ሲወራ መስማታቸውን በመግለጽ፤ "ፋና ውስጥ ሁሌም የምንቆምለት ነገር የመናገር ነፃነት ነው። ድራማዎቻችንም የዚህ ማሳያ ናቸው" ይላሉ። በጣቢያቸው ስለሚተላለፉ ድራማዎች ሁልጊዜ እንደሚወያዩ ገልጸው፤ ከሕዝብ የሚላኩ አስተያየቶች ላይ ከ 'ምን ልታዘዝ' ደራሲዎችና ፕሮዲውሰሮች ጋር እንደሚወያዩ ያስረዳሉ። የድራማው ቡድን አባላትም እርስ በእርስ እንደሚወያዩ ያክላሉ። ምን ይሻሻል? ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ 'ምን ልታዘዝ' ማኅበራዊ ሂሱንም፣ ፖለቲካውንም ኢኮኖሚውንም የሚሄስ ነው ይላሉ። "ወደአንድ ኢኮኖሚያዊ ወይም ማኅበራዊ ጎን ያደላ ባለመሆኑ ደራሲያኑም ሆነ አዘጋጆቹም በእውቀት እንደሚሠሩት ያሳያል" በማለት የፈጠራ ችሎታቸውን ያደንቃሉ። የደራሲዎቹን እና የፕሮዲውሰሮቹ ልምድ ለዚህ ድራማ ተወዳጅነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን አቶ ዘካሪያስም ይጠቅሳሉ። በሌላ በኩል ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ፤ የሀሳብ መደጋገም መመልከታቸውን በማንሳት፤ በአገሪቱ የሚታዩ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ሕፀፆችን እንደሚተቹ ሁሉ በግለሰቦች ዙሪያም ቢያተኩሩ መልካም ነው ይላሉ። ገፀ ባህሪያቱ በፍቅር፣ በገንዘብ፣ በሥነ ልቦና፣ በአስተዳደግ ምክንያት ችግር ሊገጥማቸው እንዲሁም እርስ በእርሳቸው በሚኖራቸው ግንኙነት ምክንያት እንቅፋት ሊገጥማቸው ይችላል። እንደዚህ ያሉ በግለሰብ ደረጃ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በማምጣት ለማሳየት ቢሞክሩ ሲሉም አስተያየት ይሰነዝራሉ። አቶ ዘሪሁንም ፖለቲካዊ ጉዳዮች መብዛታቸውን ይጠቅሳሉ። ያላየናቸውን ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማሳየት እና ሀሳብ ማፈራረቅም መልካም ነው ሲሉ ይመክራሉ። ለአቶ ዘካሪያስ ግን ፖለቲካዊ ሂስ የ 'ምን ልታዘዝ' ካስማ ነው። እናም ፖለቲካው እስካለ፣ የደራሲያኑ ብዕር እስካልነጠፈ ድረስ ይቀጥላል ይላሉ።
news-48277803
https://www.bbc.com/amharic/news-48277803
"በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል"
በሲቪል ምህንድስና ዘርፍ አዲስ ተመራቂ የሆነችው ወጣት ወጥታ የምትገባበት ሥራ በማግኘቷ ደስተኛ ነበረች። ኑሮዋን ያደረገችው ሥራ ባገኘችበት አዲስ አበባ ነው።
በአንድ አጋጣሚ ወደጉዳይዋ ለመሄድ በተሳፈረችው ታክሲ ውስጥ አንድ ወጣት ተዋወቀች። ወጣቱ ጨዋታ ጀመረ፤ ጨዋታው ወደስልክ ልውውጥ አደገ። ይህ የስልክ ልውውጥ ወደ ፍቅር ግንኙነት ከፍ ለማለት ወር አልፈጀበትም። ፍቅሩ ፍሬ ሳያፈራ ግን ባለፈው ዓመት መስከረም ወር ላይ ፍቅረኛዬ ያላትን ወጣት ገደላት። ፍቅረኛውን በገደለበት ሌሊት ተከራይታ ትኖርበት ከነበረው ቤት ወደ እሱ መኖሪያ የወሰዳት "ጠዋት ጠበል እንጠመቃለን" በሚል ነበር። ነገሩ ያላማራት አፍቃሪ ግን፤ አብረው ተኝተው እያሉ አለቀሰች፤ እሱ እንደሚለው "ከማልቀስም በተጨማሪ እኩለ ሌሊት ላይ ተናደደች"። ለሰሚም ለነጋሪም በሚከብድና ሰቀጣጭ ሁኔታ የገደላት ወጣት ለፖሊስ በሰጠው ቃል፤ ሊገድላት አቅዶ እንዳላደረገው በማስረዳት ተከራክሯል። ፖሊስ ወጣቱን በቁጥጥር ሥር ሲያውለው ከሌላ ሴት ጋር በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ዓለሙን እየቀጨ ነበር። ይህ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ ቢመስልም፤ እንደአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት ከሆነ ካለፈው ሐምሌ እስከ ዘንድሮ መጋቢት ድረስ ባሉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 13 ሴቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ምንም እንኳን ብዙዎች ጥቃትን አካላዊ ወይም ፆታዊ ብቻ ነው የሚል እሳቤ ቢኖርም እንደ የሥነ ልቦና አማካሪና ማኅበራዊ ሠራተኛዋ ዘሃራ ለገሰ ግን ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት አምስት አይነት ነው። እነዚህም የሥነ የልቦና፣ አካላዊ ፣ የአእምሮ ፣ ፆታዊና የኢኮኖሚ ጥቃት ናቸው። በዝምታ ማንባት ወ/ሮ ዘሃራ እንደሚሉት በሴቶች ላይ የሚደርሰው የመጀመሪያው ጥቃት የሥነ ልቦና ነው። "ራሷን እንዳታምን፣ እንድትጠራጥር፣ እንድትፈራ ያደርጋል። ከተጋቡ ወይንም የፍቅር ጓደኝነት ከጀመሩ በኋላ ቶሎ ብሎ ከጓደኞቿ ወይም ከቤተሰቦቿ ጋር ይነጣጥላታል። ብቸኛ እንድትሆንም ያደርጋል" ሲሉ ጥቃትን የሚያደርሱ ወንዶች ሴቶችን በምን መንገድ ብቸኛ እንዲሆኑ እንደሚያደርጉ ያስረዳሉ። • የተነጠቀ ልጅነት አንዲትን ሴት 'እኔ ነኝ ያለሁልሽ'፣ 'አብሬሽ ነኝ' በማለት ከአካባቢውና ከማኅበረሰቡ እንድትገለል ካደረገ በኋላ እምሮዋና ልቦናዋ ላይ ጥቃት ያደርሳል በማለት ሴቶች ጥቃት ሲደርስባቸው ደፍረው ለመናገር እንደሚቸገሩ ይገልጻሉ። ባለሙያዋ እንደሚሉት፤ ከሥነ ልቦናዊ ጫናው ባሻገር የኢኮኖሚ ጥገኛ ማድረግ አንድ የጥቃት መንገድ እንደሆነ ይገልፃሉ። አክለውም "ልጆች ካሏት ደግሞ ጥቃትን የምትሸከምበት ጫንቃ ይደነድናል" ይላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ሴት ልጅ ምንም አይነት በደል ቢደርስባት ሴት ልጅ 'ባሏን እንዳመሉ ችላ መኖር አለባት' የሚለው የተዛባ አመለካከት ከፍተኛ ተፅእኖ ከማድረሱ በተጨማሪ ይህንን እንኳን ጥሳ 'ከፋኝ'፤ 'ተበደልኩ'፤ ብላ ወደቤተሰቦቿ ዘንድ ብትሔድም 'ተመለሺ' ትባላለች። ። ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ሐይማኖት በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ ምንም አይነት ጥቃት ቢደርስባቸው በተለያዩ እምነቶች ዘንድ ፍች ሃጥያት ነው ስለሚባል እንደ አማራጭም አይታይም። • መአዛን በስለት ወግቶ ከፖሊስ ያመለጠው አሁንም አልተያዘም ከንብረት ክርክር፣ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ፣ የባህልና እምነት ጉዳይ ከጥቃቱ በአንዴ እንዳትወጣ ስለሚያግዷትም ጥቃት የሚደርስባት ባለትዳር ሴት ከግንኙነቱ ለመውጣት 10 ዓመት እንደሚፈጅባት ወ/ሮ ዘሃራ ይናገራሉ። ብዙ ጊዜ በፍርድ ቤት ክርክር ወቅት ባሎች 'ልጅ አልሰጥም' ስለሚሉ፣ በተለያዩ ነገሮች ስለሚያስፈራሩና አብዛኞቹ ሴቶች በራሷቸው የሚያዙበት ገቢ ስለሌላቸውም ለመውጣት እንደሚቸገሩ ይገልጻሉ። "የሚያስፈራ ነገር ውስጥ ካለች ወደጥቃቱ ተመልሳ ልትገባም ትችላለች" ይላሉ። "በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል" አንዲት ሴት ሥራ ቢኖራትም የምታገኘውን ገንዘብ በአጠቃላይ ለቤት ወጪና ለልጆች ማሳደጊያ እንድታውለው ስለሚያደርጋት ከዕለት ጉርስ፣ ከልጆች ትምህርት ቤት ክፍያና ቀለብ የሚተርፍ ገንዘብ አይኖራትም የሚሉት ባለሙያዋ፤ የትዳር አጋሯ ግን የሚያገኘውን ገቢ ለቤትና ለተያያዥ ወጪዎች ስለማያውል ገንዘብ እንደሚያጠራቅም ያስረዳሉ። "እሷ ገንዘብ ስለማይኖራት የጥቃት ሰለባ ሆና አብራው ትኖራለች" ይላሉ። ሌላው በአፍላ ፍቅር ላይ ያሉ ወጣቶች ጉዳይ ነው። "ወጣቶች ፍቅረኛ ሲይዙ የምንመለከተው የመነጠል ባህሪ ሌላው ችግር ነው" ይላሉ ባለሙያዋ። ወጣቶች የጦፈ ፍቅር ውስጥ እንደሆኑ ሲሰማቸው ከፍቅረኛቸው ጋር የሚለዋወጡት ተደጋጋሚ የጽሑፍ መልዕክት ሳይቀር ለጥቃት በር ይከፍትላቸዋል ሲሉ ያስረዳሉ። በተለይም ቁጥጥር በሚመስል ሁኔታ እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋን ማሳወቅ የሚኖርባትን ሁኔታ ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንደሆነ ይናገራሉ፥ "ክፍል ስትገባ 'ገባሁ' ብላ መልእክት እንድትልክ፣ ቤት ስትገባ መግባቷን እንድትናገር፣ ከጓደኞቿ ጋር ስትሆን ከነማን ጋር እንደሆነች እንድትገልፅ የምትገደደው በፍቅር ስም ነው። ይህ በፍቅር ስም የሚደረግ ክትትል እሷን ከማኅበራዊ መስተጋብሯ በመነጠል ከሱ ጋር ብቻ እንድትሆን ያደርጋል። በኋ ላይ ጥቃት ሲደርስባት መሸሺያ እንድታጣም ያደርጋታል" ይላሉ። • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" • አሲድን እንደ መሳሪያ ወጣቶች ስለፍቅረኛቸው ባህሪ ሲጠየቁና ፍቅሩን ስለሚገልፅበት መንገድ ሲናገሩ በቀን ምን ያህል ጊዜ የጽሑፍ መልእክት እንደሚላላኩ እንደማስረጃ ያቀርባሉ። ይህ ግን የፍቅር መግለጫ ሳይሆን መከታተል ነው። አንዲት ሴት ታክሲ ድረስ ለሸኘ አፍቃሪ፣ ቤት ስትደርስ ማሳወቅ እንዳለባት ከተሰማት፣ ካላሳወቀች ዘለፋና ማስፈራሪያ ካደረሰባት ጉዳዩ የጥቃት ምልክት ስለሆነ እድትጠነቀቅ ይመክራሉ። "የመከታተል ጠባይ ያለበት አፍቃሪ በራሱ የማይተማመን፣ እሷንም ቶሎ መቆጣጠር የሚፈልግ ሰው ነው" በማለት ባለሙያዋ ያብራራሉ። ጥቃት የሚያደርሱ ወንዶች በደሉን ከፈፀሙ በኋላ ይቅርታ በመጠየቅ ይታወቃሉ የሚሉት ወ/ሮ ዘሃራ፤ 'እንዲህ ያደረኩት ስለምወድሽ ነው'፣ 'ሥራ በዝቶብኝ ተጨናንቄ ነው'፣ 'ያለሽኝ አንቺ ብቻ ነሽ'፣ 'ያለአንቺ መኖር አልችልም' ሲል ይቅርታ እንደሚደረግለት ገልጸው፤ ይህ ግን የማያልቅ የጥቃት ኡደት ነው" ይላሉ። ጥቃቱ ከአካል ማጉደል ነፍስ እስከማጥፋት እንደሚደርስም ያስረግጣሉ። • 'አስጸያፊ' ከመባል ኦስካር ወደማሸነፍ ጥቃት በከተማና በገጠር፣ በተማሩና ባልተማሩ አንዲት የ26 አመት ወጣት ናት። ትውልዷ አምቦ ሲሆን፤ ያደገችው ቢሾፍቱ ነው። እናቷ የአእምሮ ታማሚ ስለነበረች እሷና ሦስት ወንድሞቿን ጥላ የሄደችው ገና ጨቅላ ሳሉ ነበር። ስለዚህም በየሰዉ ቤት እየተንከራተቱ የእለት ጉርሳቸውን ለማግኘት መሞከር ግድ ሆነባቸው። ወጣቷ ቢሾፍቱ አንድ ገበሬ ቤት በሠራተኝነት ተቀጠረች። የተቀጠረችበት ቤት ጎረቤት ግን ለክፉ ተመኛት። አሳቻ ቦታ ጠብቆ፣ አስፈራርቶ ደፈራት። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ብዙም ሳይቆይ ነፍሰ ጡር መሆኗን አወቀች። ሚስጥሯንና ልጇን በሆዷ ይዛ ወደከተማ ሄደች። ከተማ የቀን ሥራ እየሠራች ሲከፋም ጠላ እየቸረቸረች ልጇን በሰላም ተገላገለች። አንድ ዕለት ልጇን እያሳደገች ጠላ የምትቸረችርበት ሰፈር ዘወትር አተላ እየመጣ ለሚወስድ አንድ ሰው ልጇን አደራ ብላ ውሃ ለመቅዳት ሄደች። ስትመለስ ግን ልጇ በደም ተለውሳ አገኘቻት። ወጣቷ የእሷም የልጇም እጣ መመሳሰሉ አቅሏን አሳታት። ባደጉ አገሮች ከአራት ሴቶች አንዷ ጥቃት እንደሚደርስባት ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ከሁለት ሴቶች አንደኛዋ ጥቃት ይደርስባታል የሚል ጥናት ሲሆን ሌላው ጥናት ደግሞ ከሦስት ሴቶች አንዷ የጥቃት ሰለባ ነች የሚል እንደሆነ ወ/ሮ ዘሃራ ይናገራሉ። "የየትኛውም ሐይማኖት ተከታይ፣ የየትኛውም ጎሳ አባል ብትሆን ጥቃት ያጋጥማታል ማለት ነው።" ይላሉ። የሥነ ልቦና ባለሙያዋ እንደሚሉት፤ በአንጻራዊነት ፊደል የቆጠረች ሴት የሚደርስባትን ጥቃት በይፋ ለመናገርና በደሏን ወደፍትሕ አደባባይ ለማድረስ ድፍረት አላት። "የጥቃት መጀመሪያው ማስፈራራት ነው" የሚሉት ወ/ሮ ዘሃራ፤ 'ይህንን ካደረግሽ እገልሻለሁ?'፣ 'ልጅሽን አልሰጥሽም' ወዘተ. . . የሚሉ ማስፈራሪያዎች አእምሮና ልቦና ላይ የሚሰነዘሩ ከባድ ጥቃቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ። ይህ ለአካላዊና ለጾታዊ ጥቃት መንገድ ይከፍታል የሚሉት ባለሙያዋ፤ ትዳር ውስጥ ያለች ሴት የሚደርስባት የልቦናና የአእምሮ ጥቃት ራሷን ዝቅ አድርጋ እንድትመለከትና ራሷን እንዳታምን እንደሚያደርግ ይገልጻሉ። "አይኗን ሰብራ የምትኖር፣ ድምጿን ዝቅ አድርጋ የምትናገር ትሆናለች፤ ራሷን መጠበቅ ትተዋለች" በማለት ስለሚታዩት ባህሪዎች ያስረዳሉ። የ 'ወንዶች ዓለም' መዘዝ ያለ...አይመዘዝ "አብዛኞቹ ጥቃት አድራሾች የሚያድጉት በአጥቂ አባወራ እጅ ነው" የሚሉት ወ/ሮ ዘሃራ፤ እነዚህ ልጆች በሐይማኖት አባቶች፣ በቅርብ ዘመዶች ወይም በሌላ አካል ጥቃት ማድረስ ተገቢ እንዳልሆነ እየተነገራቸው ካላደጉ ጥቃት አድራሽ ሆነው ይቀራሉ ይላሉ። ወንድ ልጅ ሲያድግ መብቱ እንዲጠበቅ፣ ራሱን እንዲያከብር፣ በጨዋታ ወቅትም ጉልበት የሚፈትኑ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፍ ይደረጋል። በተቃራኒው ሴቶችን ተንከባካቢ በማድረግ ራሳቸውን ችለው ከመቆም ይልቅ ደጋፊ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲያስቡ ይደረጋሉ። • ኢንተርፖል 50 ህጻናትን ከጾታዊ ጥቃት መታደጉን አሳወቀ በጉርምስና ወቅት በሚኖሩ ጓደኞች መካከል ለከፋና ጥቃትን እንደጀብድ መታየታቸው ሌላው ለአጥቂነት የሚገፉ ምክንያቶች ናቸው። 'የደበደብኳት ስለጠጣሁ ነው' የሚሉ ሰዎችን የምንሰማው፤ ጥቃት ያደረሱት ስለጠጡ ሳይሆን ቀድሞውንም የአጥቂነት ባህርይ ውስጣቸው ኖሮ በኋላ በሱስ ገፊ ምክንያትነት ወጥቶ እንጂ፤ መጠጥ በራሱ አጥቂ አድርጓቸው አይደለም" ይላሉ። በትዳር ውስጥ ጥቃት ከመድረሱ በፊት የሚታየውን ባህሪ ሲያስረዱ የወንዱን ቁጠኛነትና ተናዳጅነትን ይጠቅሳሉ። "ወንዱ በር ጓ አድርጎ ሲወረውር፣ እቃ ሲሰብር፣ ሲጮህ እሷ ልጆቿን ይዛ ወደ ጓዳ ትገባለች። ጉዳዩ ወደጥቃት ከተሸጋገረ በኋላ ሽማግሌ ይመጣል። በሽምግልና ወቅትም እግሯ ስር ወድቆ ይቅርታ መጠየቅ፣ ካሳ መስጠት ይከተላል። ይህ ጥቃት ከደረሰ በኋላ የሚመጣ መፍትሄ በመሆኑ ዘላቂነት የለውም" ይላሉ ባለሙያዋ። ሽምግልና መጀመር ያለበት በቤት ውስጥ ውጥረቱ ሲጀምር እንጂ ነገሮች ሲባባሱ አለመሆኑንም ያክላሉ። • ፖፑ የካቶሊክ ቄሶች ሴት መነኮሳትን የወሲብ ባሪያ ማድረጋቸውን አመኑ በሽምግልና ወቅት በእድሜ ከፍ ያሉ፣ ሱሰኛ ያልሆኑ፣ አርአያ የሚሆኑ ሰዎች ግጭት የተፈጠረበት ቤተሰብን ጉዳይ በአንድ ቀን ሳይሆን ለወራት መከታተልና ማረቅ ያስፈልጋቸዋል ሲሉም ይመክራሉ። ይህ ባለመሆኑ ግን የታረቁ ሰዎች ከጥቂት ወራት በኋላ በድጋሚ የሚጋጩ ሲሆን፤ጥቃቱም ከፍ ብሎ እስከሞት ድረስ ይሄዳል በማለት በትዳር ውስጥ የሚፈጠር ግጭት የሚፈታበትን መንገድ ማጤን እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባሉ። የቤተሰብ ድጋፍ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች ማስፈራሪያም ስለሚደርስባቸው ፍትህ እንዳያገኙ ያግዳል። ስለዚህም አንዲት ሴት በሕግ ጉዳይዋን ስትከታተል ደህንነቷ ተጠብቆ የምትቆይበት ማእከል እንደሚያስፈልግ ያነሳሉ። በአገራችን ያሉት ማቆያዎች በቂ አለመሆናቸውንም ያስረዳሉ። ጥቃት የደረሰባት ሴት ጠንካራ የቤተሰብ ድጋፍ ያስፈልጋታል የሚሉት ባለሙያዋ፤ የቅርብ ቤተሰቦች ጥቃት ወዳደረሰባት ሰው እንድትመለስ ከመገፋፋት ይልቅ ሊደግፏት እንደሚገባ ያስገነዝባሉ። በአብዛኛው ጥቃት የሚያደርሱ ወንዶች 'ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ' እንደሚባለው፤ ቤት ውስጥ ክፉ ቢሆኑም ለውጪ ሰው ግን ደግ ስለሆኑ፣ 'ባሌ በደል አደረሰብኝ' ስትል የሚያምናት አታገኝም። • ሀርቪ ዋንስታይን 44 ሚሊየን ዶላር ካሳ ሊከፍል ነው ብዙ ጊዜ ጥቃት የሚያደርሱ ወንዶች የባለቤታቸውን ቤተሰቦች ጥሩ አድርገው ስለሚንከባከቡ፤ የገዛ ቤተሰቦቿም ለሷ ጠበቃ መሆን ይከብዳቸዋል ይላሉ። ስለዚህ ወደባለቤቷ ቤተሰቦችም ሆነ ወደእሷ ቤተሰቦች መሄድ አለመቻሏ ብቻዋን እንድትሆን ያደርጋታል። አንድ ሰው መጀመሪያ ላይ ባህሪውን ሲያሳይ ማመን እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት ወ/ሮ ዘሃራ፤ አንዲት ሴት የፍቅር ወይም የትዳር ጓደኛዋ አንዴ ጥቃት ሲያደርስ ወዲያው ማስቆም እንዳለባት ይመክራሉ። 'ይቀየራል'፣ 'ይሻሻል' እያሉ መቆየት የአካል መጉደልና የሕህይወት ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችልም ያክላሉ።
news-45341290
https://www.bbc.com/amharic/news-45341290
የውጭ ሀገራት ዜጎች በደቡብ አፍሪካዋ ሶዌቶ ጥቃትን እየሸሹ ነው
አንድ ሶማሊያዊ ባለ ሱቅ «ሊዘርፉኝ ሞክረዋል »ያላቸውን ሁለት ታዳጊዎች «ተኩሶ መትቷል» በሚል የተቀሰቀሰው ግጭት ወደለየለት ዝርፊያ እና የውጭ ሀገራት ዜጎችን ወደ ማጥቃት ርምጃ ስለመቀየሩ ተነግሯል።
ከሱቁ ፊት ለፊት ጥቃት የደረሰበት ሶማሊያዊ የሀገሪቱ ፖሊስ እስከ አሁን ድረስ 27 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ጥቃቶቹንም አውግዟል። በ«ዋትስአፕ» የመገናኛ አውታር የአካባቢው ሰዎች ሶማሊያዊ ተከራዮችን ከቤታቸው እንዲያስወጡ ካልሆነ ግን ጥቃቱ ለእነሱም እንደሚተርፍ ቀን ገደብ የተቀመጠለት የዛቻ መልዕክት እንደተሰራጨም ተነግሯል። የአከባቢው ነዋሪዎች የውጪ ሃገር ዜጎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ምርቶች ይሸጣሉ ሲሉ ይወቅሷቸዋል። በሶዌቶ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ሶማሊያዊያን ፣ዚምባብዌያዊያን እና ፓኪስታንያዊያን ሱቆችን ከፍተው ይሰራሉ። ጥቃቱን ተከትሎ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ የነበሩት እኒህ ወገኖች ጓዛቸውን እየሸከፉ ከስፍራው እየለቀቁ እንደሆነ ተሰምቷል።
52479852
https://www.bbc.com/amharic/52479852
ኮሮናቫይረስ፡ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አራት አማራጮች
በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት በነሐሴ ወር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን ምርጫ ማስፈጸም አስቸጋሪ በመሆኑ መንግሥት የምርጫ ጊዜን በማራዘም ምርጫውን ማካሄድ ያስችላሉ ያላቸውን አራት አማራጮችን ማቅረቡ ተነግሯል።
እነዚህም አማራጮች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ ህገ መንግስት ማሻሻል እና የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ ናቸው። ትናንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እነዚህን አማራጮች ካቀረቡ በኋላ አንዳንድ ፖለቲከኞች 'አራቱም አማራጮች ጥሩ አይደሉም ሲሉ ተደምጠዋል'። ቢቢሲ እነዚህ አማራጮች ጥሩ እና መጥፎ ጎናቸው ምንድነው ሲል በኔዘርላንድስ አገር የዲሞክራሲ እና የአስተዳደር አማካሪ የሆኑትን ዶ/ር አደም ካሴን አበባን እና በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዋሺንግተን ኤንድ ሊ የሕግ መምህር የሆኑት ዶ/ር ሔኖክ ገቢሳ ጠይቋል። • እኛ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝቦች. . .? • ትራምፕ ቻይና በምርጫው እንድሸነፍ ትፈልጋለች አሉ • ሰዎች እጃቸውን የማይታጠቡበትን ሥነ ልቦናዊ ምክንያት ያውቃሉ? 1ኛ አማራጭ፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን ዶ/ር አደም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን ማለት በቀላል ቋንቋ የምክር ቤቱ አባላት የሥራ ጊዜ እንዲያበቃ ማድረግ እና መንግሥት ግን የዕለት ተዕለት ሥራውን እያከናወነ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሆነ ይናገራሉ። "የምክር ቤቱ አባላት ይበተኑ እንጂ የመንግሥት ካቢኔ ግን ይቀጥላል" ይላሉ። በኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 60 ጠቅላይ ሚንስትሩ የምክር ቤቱ የሥልጣን ዘመን ከማለቁ በፊት አዲስ ምርጫ ለማካሔድ በምክር ቤቱ ፈቃድ ምክር ቤቱ እንዲበተን ማድረግ እንደሚችሉ ያስታውሳሉ። ዶ/ር አደም መንግሥት ምርጫ ለማስፈጸም አማራጭ ይሆናሉ ብሎ ካቀረባቸው አመራጮች መካከል ይህ የተሻለው አማራጭ ይሆናል ብዬ አላስብም ብለዋል። ለዚህም ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ። የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚንስትሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ከበተኑ በኋላ የሚኖራቸው መንግሥት 'ደካማ' የሚባል ይሆናል። በአንቀጽ 60/5 መሠረት ምክር ቤቱ ከተበተነ በኋላ አገሪቱን የሚመራው የፖለቲካ ድርጅት የመንግስትን የዕለት ተዕለት ሥራ ከማከናወን እና ምርጫን ከማካሄድ በስተቀር አዲስ አዋጆችን፣ ደንቦችን እና ድንጋጌዎችን ማውጣት ወይም ነባር ህጎችን መሻርና ማሻሻል አይችልም። "ለምሳሌ ኮቪድ-19 የሚያመጣው ከባድ የሆነ ፈተና አለ። ከዚህ ኢኮኖሚያዊ ጫና አገሪቱን ሊያወጣ የሚችል አዳዲስ ደንብ እና ድንጋጌዎች መውጣት አለባቸው። መንግሥት ግን ይህን ማድረግ አይችልም። የውጪ ግነኙነታችንንም ብንመለከት ከግብጽ እና ሱዳን ብዙ ጉዳዮች አሉብን። አቅም የሌለው መንግሥት ለውጪ አገር ድርድሮችም የማይመች ነው የሚሆነው" ይላሉ ዶ/ር አደም። • ምርጫ ቦርድ የተራዘመ ቀን ቆርጦ እንዳላቀረበ አሳወቀ ይህ ምክር ቤቱን የመበተን አማራጭ ትክክል ላለመሆኑ ሁለተኛ ምክንያታቸውን ሲያስረዱ፤ "ይህ እንደ አማራጭ ሆኖ መታየቱ የግንዛቤ ችግር እንዳለ ያሳያል። ምክንያቱም ይህ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 60 የፓርላማው እና የመንግሥትን እድሜ ከአምስት ዓመት ለማሳጠር እና ምርጫ ለማካሄድ ታስቦ የተቀመጠ እንጂ የመንግሥትን እድሜ ለማራዘም ታስቦ የተቀመጠ አይደለም" ይላሉ። ይህ አማራጭ ደካማ መንግሥት ከመፍጠሩም በተጨማሪ አንቀጹ ይህን ለማድረግ ታስቦ የተቀመጠ ስላልሆነ ጥሩ አማራጭ ነው ብዬ አላስብም" ይላሉ ዶ/ር አደም። በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዋሺንግተን ኤንድ ሊ የሕግ መምህር የሆኑት ዶ/ር ሔኖክ ገቢሳ በበኩላቸው በአንቀጽ 60 መሠረት ምክር ቤቱ የሚበተነው የሥልጣን ዘመኑ ከማለቁ በፊት አዲስ ምርጫ ለማካሔድ እንጂ መንግሥት የራሱን ስልጣን ለማራዘም በማሰብ አይደለም ይላሉ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መበተኑ አዋጭ አካሄድ አይደለም የሚሉት ዶ/ር ገቢሳ "ምክር ቤቱ ተበተነ ማለት መንግሥት ተበተነ እንደ ማለት ነው። ከመንግሥት ከሶስቱ የመንግሥት መዋቅሮች (ኦርጋንስ ኦፍ ገቨርንመንት) ትልቅ ስልጣን ያለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። ትልቁን የመንግሥት አካል ተበተነ ማለት ሕጎች ማውጣት አይችልም፣ ሚንስትሮችን እና የካቢኔ አባላትን ማስሾም አይችልም" ይላሉ። 2ኛ አማራጭ፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ በኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 93 መሠረት የፌዴራል መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመደንገግ ሥልጣን እንዳለው ዶ/ር አደም ያስታውሳሉ። "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ መንግሥት የሕገ-መንግሥቱን አንዳንድ አንቀጾች ሊገድብ ይችላል። ሊገደቡ ከሚችሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ገደብን ሊገድብ ይችላል" በማለት መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የምርጫ ጊዜን ሊያራዝም የሚችልበትን አማራጭ አስቀምጠዋል። የዜጎች የመምረጥ እና መመረጥ መብትን ጨምሮ የፖለቲካ መብቶች ተገድበው ባሉበት ወቅት ታዓማኒነት ያለው ምርጫ ማካሄድ እንዴት ይቻላል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር አደም ሲመልሱ፤ "ዋናው ጉዳይ ምርጫ በአንድ ቀን የሚፈጸም ድርጊት ሳይሆን በረጅም ጊዜ የሚፈጸም ተግባር መሆኑን መረዳት ይኖርብናል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈለጊ እስከሆነ ድረስ ይሄዳል ከዛ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲቆም ምርጫ ማካሄድ ይቻላል። የግድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምርጫው እስከሚካሄድበት ድረስ መቀጠል አያስፈልገውም" ይላሉ። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? ዶ/ር አደም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ተኩኖ ምርጫ የሚካሄድ ከሆነ ግን የምርጫው ውጤት ላይ የተዓማኒነት እና ነጻነት ጥያቄ ሊነሳበት እንደሚችል ያስረዳሉ። 3ኛ አማራጭ ሕገ-መንግሥትን ማሻሻል መንግሥት ምርጫውን በማራዘም ምርጫ ለመካሄድ ሕገ-መንግሥትን የማሻሻል ሃሳብ ተፈጻሚ መሆን እንደማይችል ዶ/ር ሔኖክ ይናገራሉ። "አሁን ያለው ችግር መንግሥት ያለውን የአምስት ዓመት እድሜ መጨመር እና ምርጫ ማካሄድ ይችላል የሚለው ነው። ሕገ-መንግሥት ማሻሻል ለዚህ ምላሽ አይሰጥም። ለምሳሌ መንግሥት ለተጨማሪ 6 ወራት በሥራ ይቀጥል ተብሎ በሕግ-መንግሥቱ ላይ ማካተት አይቻልም። አንድ ግዜ በሕግ የሚካተት ነገር ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ነው። " ለዶ/ር ሔኖክ፣ ሕገ መንግሥት ማሻሻል የሁሉንም ይሁንታ ማግኘት አይችልም። ሁሉም በሕገ-መንግሥቱ ላይ የራሱ ፍላጎት አለው። ለምሳሌ አንቀጽ 39፣ የብሔሮች ብሔረሰቦች ሕዝቦች መብት፣ እንዲነሳ የሚፈልግ ይኖራል። ሌላው እንዲቆይ የሚፈልግ ይኖራል። በዚህም ግጭት ሊከሰት ይችላል። የማያልቅ እልቂትም ሊያከትል ይችላል። በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 104 እና 105 መሠረት የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሐሳብ በሚመለከተው አካል በበቂ ሁኔታ የሚደገፍ ከሆነ ሕገ-መንግሥቱ ሊሻሻል የሚችልበት አግባብ አለ። "የዚህ አማራጭ መልካም ጎን ግልጽ መልስ ይሰጣል ግን ጥያቄው መፍትሄ ይሰጣል ወይ የሚለው ነው" ይላሉ ዶ/ር አደም። ሃሳባቸውን ሲያብራሩ "ሕገ-መንግሥቱ ይሻሻል ከተባለ በምን መልኩ ነው ሊሻሻል የሚችለው የሚለው ላይ መግባባት ላይ መደረስ አለበት" ይላሉ። • "ትውስታዎቼ መራር ናቸው"- ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሕገ-መንግሥቱ መሻሻል ላይ ህዝቡን ጨምሮ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ማወያየት ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ ጊዜ ይውስዳል ባይ ናቸው ዶ/ር አደም። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ባለበት ወቅት ለመንግሥት ፓርቲዎች እና ህዝቡን በአንድ ላይ ሰብስቦ ማወያየት ቀላል እንደማይሆን ዶ/ር አደም ይናገራሉ። ዶ/ር አደም ጨምረውም "ሕገ-መንግሥት ለማሻሻል መንግሥት በር ከከፈተ በርካቶች እንዲቀየር የሚፈልጉትን ነገር ይዘው ወደፊት ይመጣሉ" ይላሉ፤ ከዚህ ቀደም ድርጅቶች እና ፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ የሕግ መንግሥቱ አንቀጾች ሊሻሻሉ ይገባቸዋል በማለት ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን በማስታወስ። መንግሥት የምርጫ ጊዜን በማራዘም፤ ምርጫ ለማካሄድ ይህን አማራጭ ለመተግበር ቢፈልግ የትኛውን የሕግ-መንግሥት አንቀጽ ሊያሻሽል ይችላል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ በሕገ መንግሥቱ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ነው የሚለውን ክፍል ምክንያት እና በየትኛው አካል መቀየር እንዳስፈለገው በመጥቅስ እንደሚሻሻል ያስረዳሉ። 4ኛ አማራጭ የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሕገ- መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ ማለት ምን ማለት ነው? መንግሥት የሕገ-መንግስት ትርጓሜ በመጠየቅ ምርጫን ሊያራዝም የሚችለው እንዴት ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር አደም ሲመልሱ፤ "የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ ማለት ሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች ሲነሱ፤ ጥያቄዎችን የመፍታት ስልጣን ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው። የፌዴሬሽን ምክር ቤትን የሚረዳው ደግሞ የሕገ-መንግሥት አጣሪ ኮሚቴ የሚባል አለ። 'ዜጎች የመምረጥ እና መመረጥ መብት አላቸው፤ ሕገ-መንግሥቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ነው ብሎ ይገድባል። ይሁን እንጂ አሁን ባለንበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ አልቻልንም ምን ማድረግ አለብን' ብሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ይጠይቃል። የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ ማለት ይህ ነው" ይላሉ። ዶ/ር አደም እንደሚሉት ከሆነ ግን የአምስት ዓመት ገደቡ በፌዴሬሽን ምርክር ቤት ላይም ይሰራል። ይህ ማለት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ የሚጠየቀው በራሱ ጉዳይ ላይ ነው። • እውን የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል? ዶ/ር አደም መንግሥት ካቀረባቸው አራት መፍትሄዎች መካከል "ይሄ የተሻለ ነው" ብሎ መደምደም አስቸጋሪ እንደሆነ በመጠቆም፤ "የፖለቲካ ውሳኔ የቅቡልነት ጉዳይ ነው። ፖለቲካ ፓርቲዎች እና መንግሥት የሚስማሙበት ከሆነ የትኛውም አማራጭ ተግባር ላይ ሊውል ይችላል" ሲሉ ይደመድማሉ። ዶ/ር ሔኖክ መፍትሄ ነው ብለው የሚያስቀምጡት መንግሥት እና ፖለቲካ ፓርቲዎች እንድላይ በመምጣት ሕገ-መንግሥቱ ሳይሸራረፍ ፓርቲዎች መንግሥት ለተወሰነ ጊዜ ማስተዳደር እንዲችል የሚፈቅድ ዲክላሬሽን መስጠት አለባቸው የሚል ነው። ታዲይ መንግሥት በዚህ ወቅት በህገ-መንግሥቱ የተዘረዘሩትን ግዴታዎቹን እየተወጣ መሆን ይኖርበታል ይላሉ።
51677190
https://www.bbc.com/amharic/51677190
የአሜሪካ የዲሞክራት ፓርቲ እጩ በርኒ ሳንደርስን ልዩ የሚያደርጓቸው 18 ነጥቦች
ሽማግሌው በርኒ የቬርሞን ግዛት ሴናተር ናቸው። 78 ደፍነዋል። ቢሆንም ድጋፋቸው በዋናነት የሚመነጨው ከወጣቶች ነው። እርሳቸውም መወዳደር አይሰለቻቸውም። እነሆ የ2ኛ ደረጃ ተማሪ ሳሉ ለክፍል አለቅነት መወዳደር የጀመሩ ዛሬም ድረስ እንደተወዳደሩ አሉ።
በርኒ ሳንደርስ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት እስካሁን በዲሞክራቶች የዕጩ ፉክክር በለስ እየቀናቸው ይመስላል። ባለፈው ምርጫ ጥሩ ሄደው ሄደው በሂላሪ ተረ'ተው ነበር። ዘንድሮ ከጆ ባይደን፣ ማይክ ብሉምበርግ እና ኤልዛቤት ዋረን ጋር አንገት ላንገት ተናንቀዋል። የበርኒ ግራ ዘመም የፖለቲካ ዝንባሌያቸው ለአንዳንድ አሜሪካዊያን ግራ ነው። ለመሆኑ ሳንደርስ ምን ልዩ ያደርጋቸዋል? 18 ነጥቦችን ከታች ዘርዝረናል። ከዚያ በፊት ግን በአንድ አንቀጽ የአጭር አጭር የሕይወት ታሪካቸውን ብንነግራችሁስ? • እያንፀባረቁ ያሉት ኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች በርናርድ ሳንደርስ የተወለዱት በፈረንጆች በ1941 በብሩክሊን፤ ኒውዮርክ ነው። ከመካከለኛም ዝቅ ያለ ገቢ ከነበረው የአይሁድ ቤተሰብ ነው የተገኙት። አባታቸው አይሁዶች ላይ ከተቃጣው የያኔው ጭፍጨፋ አምልጠው ነው ከፖላንድ በ17 ዓመታቸው ቤሳ ቤስቲን ሳይዙ በስደት ወደ አሜሪካ የገቡት። የበርኒ አብዛኛው ቤተሰባቸው በናዚ ተጨፍጭፎ አልቋል። ሳንደርስ ለአጭር ጊዜ አናጢም፣ አስተማሪ ሆነው ሠርተዋል። ወደ ቨርሞንት ግዛት ከሄዱ በኋላ የበርሊንግተን ከተማ ከንቲባ ሆነዋል። ተወዳጅ ከንቲባ ነበሩ፤ አራት ጊዜ ተመርጠው 8 ዓመት አገልግለዋል። ሌላው አስገራሚ ነገር በርኒን ወደ ፖለቲካ የሳባቸው ሰው አዶልፍ ሂትለር መሆኑ ነው። አንድ ሰው በፖለቲካ ይህን ያህል አደጋ ሊያደርስ ከቻለ በበጎም ተጽእኖ ማሳደር ይችላል የሚል እምነት አጎልብተው ነው በርኒ ወደ ፖለቲካ የተወሰወሱት። እነሆ በቀጥታ ወደ 18ቱ ነጥቦች። 6. የጥቁሮች ጉዳይ ያገባኛል፦ ሳንደርስ በአሜሪካ ጥቁሮች ላይ የሚደርሰው በደል የመደብ እንጂ የቀለም ጉዳይ አይደለም ብለው ያምኑ ነበር። አሁን ግን የጥቁሮች ሕይወት ግድ ይለኛል! ("ብላክ ላይቭስ ማተር") የሚለው እንቅስቃሴ መሥራቾች በርኒን ድጋፍ እየሰጧቸው ይገኛሉ። በርኒ ሳንደርስ በባርነት ለተሰቃዩ አፍሪካ-አሜሪካዊያን የልጅ ልጆች ካሳ ይገባቸዋል የሚለውን ሐሳብ ከዚህ ቀደም አጣጥለውታል። ሆኖም ባለፈው ዓመት በባሪያ ንግድና ብዝበዛ አሜሪካ በጥቁሮች ላይ ያደረሰችውን በደል የሚያጠና ኮሚሽን እንዲቋቋም ድጋፍ እንደሚሰጡ ሳንደርስ ተናግረዋል። የሚገርመው ሳንደርስ ወጣት ሳሉ ማርቲን ሉተር ኪንግ በሚያዘጋጃቸው ሰልፎች ይሳተፉ ነበር። የጥቁሮችን መገለል በመቃወማቸውም ፖሊስ አስሯቸው በ25 ዶላር ነው በዋስ የወጡት። • ጆ ባይደን "ቀጣፊ፣ ውሸታም" እየተባሉ ያሉት ለምንድነው? 7• ከእያንዳንዱ እጩ ጀርባ ቢሊየነሮች ለምን?፦ የአሜሪካ ምርጫ ሚሊዮን ብቻ ሳይሆን ቢሊዮን ዶላሮች ሳይዙ የሚወጡት ዳገት አይደለም። ከብዙ እጩዎች ጀርባ ትልልቅ ኮርፖሬሽኖች ያሉትም ለዚሁ ነው። በርኒ ግን ታች ካለው ማኅበረሰብ በሚገኝ መዋጮ ነው ለጊዜው እየተነፈሱ ያሉት ማለት ይቻላል። ገንዘቡን የሚሰበስብላቸው "አወር ሪቮሉሽን" የሚባል ለትርፍ ያልቆመ ፖለቲካ ድርጅት አላቸው። ሆኖም ገንዘቡን የሚያዋጡላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ባለማድረጋቸው በርኒ አልፎ አልፎ ይተቻሉ። 8• ዝቅተኛ ክፍያ በሰዓት 15 ዶላር ይሁን፡ አሁን አሜሪካ በፌዴራል ደረጃ ዝቅተኛው ክፍያ በሰዓት 7.25 ዶላር ነው። በርኒ ግን 15 ዶላር እንዲሆን ይሻሉ። የምጣኔ ሐብት ጠበብቶች ግን እጥፍ ጭማሪ ቢደረግ ትንንሽ ከተሞችንና ትንንሽ ቢዝነሳቸውን ጨርሶውኑ ይገድላል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። 9• ሁለት ግዙፍ ፓርቲ ብቻ ለምን? በርኒ ሳንደርስ ሴናተር የሆኑት በግል ተወዳድረው ነው። አሜሪካ በሪፐብሊካንና በዲሞክራቶች የፖለቲካ ጫፍ መወጠሯ ከድሮም ጀምሮ ምቾት አይሰጣቸውም። ዲሞክራቶችና ሪፐብሊካን በኮርፖሬሽን ገንዘብ ጫንቃ ላይ ነው ያሉት፤ በውለታ ይታሰራሉ፤ በእከክልኝ ልከክልህ የሚሰሩ ፓርቲዎች ሆነዋል ሲሉም ይተቻሉ። 10• የድሆች አባት፦ በርኒ ሳንደርስ የድሆች አባት የሚል ቅጽል ይሰጣቸዋል። በገንዘብ ብክነት አይታሙም። አውሮፕላን ሲሳፈሩ እንኳ ቢዝነስ ክፍል ንክች አያደርጉም ይባላል። ከሕዝብ ጋ ተሰልፈው እንደ ተራ ተሳፋሪ በጭቁን የኢኮኖሚ ክፍል አውሮፕላን ሲበሩ የሚያሳዩ ምሥሎች አሉ። አንድ ቀን ግን ቢዝነስ ክፍል ተንፈላሰው ታይተው "ምነው በርኒ? ምነው ምነው?" ተብለዋል። 11. የጤና መድህን ለሁሉም፦ ሳንደርስ ሁሉም አሜሪካዊ ተጠቃሚ የሚሆንበት መንግሥታዊ የጤና መድህን ሊዘረጋ ይገባል፤ መብትም ነው ሲሉ ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ። ለዚህም 30 ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልገናል ብለው ተነስተዋል። • በቦንጋ ሠርግ አስደግሶ "የሙሽራዬ ቤት ጠፋኝ" ያለው ግለሰብ 12. የአሜሪካ መሠረተ ልማት ላሽቋል፦ በርኒ ሳንደርስና ትራምፕ አንድ የሚያመሳስላቸው ነገር አለ ከተባለ ይህ ነው የሚሆነው። አሜሪካ መሠረተ ልማቷን ማደስ አለባት፤ ለዚህም አንድ ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልገናል ይላሉ። 13• ከሀብታሞች ግብር መሰብሰብ፦ ባርኒ ሳንደርስ ሀብታቸው ከ32 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ ዲታዎች ጫን ያለ ግብር እንዲከፍሉ ይፈልጋሉ። በዎልስትሪት የስቶክ ገበያ ዝውውር ላይ አዲስ ግብር እንዲጣልም ይፈልጋሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን ሥራ ያላቸው ዜጎችም ላይ መጠነኛ ግብር እየተጣለ የጤና መድህን አቅርቦትን ለማገዝ ያልማሉ። 14• ጦርነት ሱስ ሆኖብናል፦ በርኒ ሳንደርስ ድሮም ቢሆን የቬትናም ጦርነትን ይቃወሙ ነበር። አሜሪካ በማያገባት እየገባች ጦርነት ውስጥ መማገዷ ይብቃ ብለው የተነሱት ዛሬ አደለም። በፈረንጆቹ 2002 የአሜሪካ ኢራቅን መውረር ያበሳጫቸው ነበር። ያኔም ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያነሱ ነበር። ኢራቅን መውረራችን በአሜሪካ ታሪክ እጅግ አሳፋሪው የውጭ ፖሊሲ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። የበርኒ ሳንደርስ ደጋፊዎች የሰውየውን ጨብራራ ጸጉር ልዩ መለያቸው አድርገውታል 15. መቆነጃጀት ጊዜ ማባከን ነው፦ ሳንደርስ ለአለባበሳቸው ግድ የሌላቸው ሰው ናቸው። ባለቤታቸው እንዳውም ሲቀልዱባቸው "ምን እሱ'ኮ ሦስት ሹራብ ቢኖረው ራሱ ብዙ ነው ይላል" ብላቸዋለች። ደጋፊዎቻቸው የበርኒ ሳንደርስ መልክ ያልያዘ ጸጉር ቲሸርቶቻቸው ላይ እየሳሉ ለርሳቸው ያላቸውን ፍቅር ይገልጻሉ። በርኒ ጸጉሩዎትን ለምን ያንጨበርራሉ ሲባሉ፡ "ምናገባችሁ? ሚዲያዎች ስትባሉ እዚህ ግባ በማይባል ጉዳይ ጊዜያችሁን ታጠፋላችሁ፤ ስለኔ ጨብራራ ጸጉር ከምታወሩ አሜሪካንን የሚያህል ታላቅ አገር ስለምን የጤና መድህን ላይኖራት ቻለ ብላችሁ አትጠይቁም??" ሲሉ ተሰምተዋል። • የፈረንሳዩ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ የፊልም ቻናል ሊከፍት ነው 16. የፊደል ካስትሮ አድናቂ? በጥቅምት ወር ሳንደርስ በሲቢኤስ ላይ ቀርበው ሁሉም አምባገነን መጥፎ ነው ማለት አይቻልም የሚል አነጋጋሪ አስተያት ሰጥተዋል። የኩባ አብዮት ሁሉም ነገሩ ስህተት ነው ብሎ መናገር አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል። ተቺዎቻቸው ታዲያ ታሪክ ጉርጉረው አወጡባቸው። በ1980ዎቹ በቬርሞን ግዛት የበርሊንግተን ከንቲባ ሳሉ የኒካራግዋ ሶሻሊስት መሪ ዳንኤል ኦርቴጋን "ድንቅ ሰው ነው" ብለው ተናግረው ነበር። ኦርቴጋ ያደርስ የነበረውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ቸል በማለታቸውም ክፉኛ ተችተዋቸዋል 17• እነ ፌስቡክና አማዞን 'አንድ ሊባሉ ይገባል'፦ በርኒ ሳንደርስ ጡንቻቸው የፈረጠሙ አይነኬ ኮርፖሬሽኖች ምቾት አይሰጧቸውም። ኤልዛቤጥ ዋረንም እንደርሳቸው ናት። እነ አማዞን፣ ፌስቡክ እና ጉግል ነገሩን ሁሉ ተቆጣጥረውት "እግዜሩን" ሊሆኑ ምን ቀራቸው? ይላሉ። ስለዚህ ሕግና ደንብ ተበጅቶላቸው፣ ሜዳው ለውድድር ክፍት ሊሆን ይገባል፤ ለነፌስቡክም ልጓም ይበጅ ሲሉ ይሟገታሉ። 18• እስራኤል 'ታበዘዋለች'፦ "በአይሁድነቴ እጅግ ብኮራም..." እስራኤል ግን ዘረኛ ሆናለች፤ አሁን በሥልጣን ያሉትም ሰዎች ጨቋኝ ናቸው ሲሉ ይተቻሉ። ለዚህ ምላሽ የሰጡት የእስራኤሉ ናታንያሁ 'በአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ አልገባም' ሲሉ ተናግረዋል። በርኒ ሳንደርስ ቀንቷቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በአሜሪካ ታሪክ የመጀመርያው አይሁድ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ።
49116177
https://www.bbc.com/amharic/49116177
"እማማ አንቺ በሌለሽበት ደስ አይለኝም አለኝ" የኢዛና እናት
ባለፈው ሳምንት ከማንችስተር ዩኒቨርስቲ በፕላኒንግና ኢንቫይሮንመንታል ማኔጅመንት ፒኤችዲውን ያገኘው ኢዛና ሐዲስ ለምረቃ በዓሉ ክብሩም ሆነ ፀጋው የቤተሰቡ በተለይ የእናቱ በቦታው ላይ መገኘት ነበር።
በህይወቱም ሆነ በትምህርቱ ከሱ በላይ መስዋእትነት የከፈሉለትን እናቱን የምረቃ ጋወኑን አልብሶ ፎቶ ማንሳት ዋና አላማው ነበር። የጋወኑ ምልክትነት ደፋ ቀና ብለው ያሳደጉት፣ እዚህ ቦታ ላይ ለመድረስ ከሱ በላይ እሳቸው መስዋዕትነት ከፍለዋል ለሚላቸው እናቱን ማእረጉ ለሳቸው እንደሚገባ ማሳየት ነበር። • ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ "እናቴ ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍላለች ሰላሳ አመት ልብስ ስትሰፋ ነበር። ጀርባዋ (ስፖይናል ኮርዷ) ተመዛብሏል። የከፈለችው መስዋዕትነት በቃላት የሚነገር አይደለም። ከኔ በላይ ትልቁን መስዋዕትነት የከፈለችው እሷ ናት" ይላል። ነገር ግን ብዙ ሳይጓዝ አላማውን የሚያጨናግፈው ጉዳይ ተከሰተ። በልጃቸው ምርቃት ለመገኘት አስበው የነበሩት እናትና አባቱ ቪዛ ተከለከሉ። በምርቃቱ ላይ የእናቱን አለመገኘት ሊቀበለው ያልቻለው ኢዛና ጉዳዩን ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ በመውሰድ "እናቴ ካልመጣች የምርቃት በዓሉ ላይ አልገኝም" አለ። ትምህርት ላይ ጠንካራ አቋም የነበራቸው እናቱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ በኢዛና ቃል 'ፈንድቶ' ትምህርቱን አቋረጠ። ፎቶ ማንሳት እንደሚፈልግ ቢናገርም እናቱ ሊዋጥላቸው አልቻለም፤ በጭራሽ መስማት አልፈለጉም "መማር አለብህ ብላ አስገደደችኝ" ይላል። በሌላቸው አቅም ገንዘብ ከፍለው ትምህርት ቤት የላኩትም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ማየት ህልማቸው ስለነበር እንደሆነ ኢዛና አበክሮ የሚናገረው ጉዳይ ነው። • “በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ እንዲያው ኢዛና የእናቱ ነገር ስለሚያንሰፈስፈው ነው እንጂ አባቱም "ጫማ ምናምን ለመግዛት ብዙም ፍላጎት የለውም፤ ለመጻሕፍ ከሆነ ግን ግዛ ያልኩትን ይገዛልኝ ነበር" ይላል። እናም ቤተሰቦቹ አይመጡም ሲባል ልቡ ተሰበረ። ከዚህ በፊት ለአራት ጊዜ የተመረቀው ኢዛና መመረቁ ብርቅና ድንቅ አይደለም፤ ነገር ግን ለቤተሰቦቹ ትልቅ ደስታ መሆኑንም በማወቁ ነው። የማስተርስ ትምህርቱን በኧርባን ማኔጅመንትና ዴቨሎፕመንት ከሮተርዳም ዩኒቨርስቲ ያገኘው ኢዛና መጋቢት ወር ላይ የፒኤችዲ 'ዲፌንሱን' (ቫይቫ) ጨርሶ ደስታውንም አጣጥሟል። የምርቃት ፕሮግራም ለቤተሰቦቹ በተለይም ለእናቱ ምን ማለት እንደሆነ ስለገባውም ያለመገኘታቸው ጉዳይ ለሱ ብቻ ሳይሆነ ለቤተሰቡ በተለይ ለእናቱ ወ/ሮ ሮማንም ከፍተኛ ሐዘንን ፈጥሯል። ቢቢሲ ባናገራቸውም ወቅት ድምፃቸው ሐዘናቸውን በሚያሳብቅ መልኩ "በመከልከሌ በጣም አዝኜያለሁ፤ እኔ እዛ ሄጄ የምቀርበት መንገድ የለኝም፤ እድሜየም ትልቅ ነው፤ ኑሮየም ራሴን የቻልኩኝ ነኝ፤ ችግር አልነበረብኝም፤ አሳዘኑኝ፤ በጣም ነው ያዘንኩት፤ እኔ መገኘት እፈልግ ነበር፤ እንድገኝ አላደረጉኝም" ብለዋል። ዱባይ ብዙ ጊዜ ተመላልሰው የሚያውቁት እናቱ በእንግሊዝ ኤምባሲ በጭራሽ ይከለከላሉ ብለው አላሰቡም፤ ከፍተኛ ኃዘን ቢሰማቸውም ዋናው ነገር የልጃቸው መመረቅ ነው "ልጄ እንኳን ተመረቀ" ይላሉ። የአፍሪካውያን ህመም- ቪዛ በቅርቡ የወጣ አንድ ሪፖርት እንደሚያሳየው እንግሊዝ ከሌሎች አገራት በበለጠ አፍሪካውያንን በእጥፍ ቪዛ እንደምትከለክል የሚያሳይ ነው። የዩናይትድ ኪንግደም የፓርላማ አባላት ባጠኑት ጥናት አፍሪካውያን ላይ ያለው የቪዛ አሰጣጥ ስርአት የተሰበረና የዩናይትድ ኪንግደምና የአፍሪካ ግንኙነትንም የሚያበላሽ እንደሆነ ጠቅሰዋል። አፍሪካውያን ላይ ከፍተኛ መድልዎ በሚፈፀምበት በቪዛ አሰጣጥ ስርአት ላይ፤ አፍሪካውያን ሙሉ ወጪያቸውን የሚከፍልላቸው ስፖንሰር ቢኖራቸውም ባንካቸው ውስጥ "በቂ ገንዘብ የለም በሚል ሁኔታ እንደሚከለከሉም ያሳያል። የኢዛና ቤተሰቦችም አፍሪካዊነታቸው፣ ኢትዮጵያውነታቸውና ጥቁርነታቸው በዚሁ የእንግሊዝ ፖርላማ አባላት "በተሰበረ የቪዛ አሰጣጥ" ስርአት ውስጥ እንደሚጥላቸው ኢዛና በበኩሉ በማሰብ የባንክ ማስረጃ፣ ከቤት አከራዩ ፍቃድ፣ ከትምህርት ቤቱ የድጋፍ ደብዳቤ አስገብቷል። ካለው ልምድ በመነሳትም ሙሉ ቀን ወስዶ ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ቢሞላም የቪዛ ጥየቃ ውድቅ ሊሆንበት የሚችል እድል እንዳለ በማሰብም ወደ ቪዛ ማዕከሉ ከመግባታቸው ከአንድ ቀን በፊት ለናቱም ደውሎ ተስፋቸው ከፍ እንዳያደርጉ ነግሯቸዋል። • "ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" አሊ ቢራ የቪዛ ፎርሙን የሞላችው የኢዛና እህት ፌቨን ሐዲስ ከኢዛና ዶክመንቶች በተጨማሪ የቤት ካርታ፣ የጭነት ተሳቢ መኪና ያው ተመልሰው እንደሚመጡ በማስረጃነት ለማሳየት አያይዛ ነበር። ፌቨን ከቤተሰቦቿ እድሜ፣ ካላቸው የገንዘብ አቅም (ፋይናንሻል ስታተስ) እንዲሁም አባትየው ውጭ አገር ተምረው ከመምጣታቸው አንፃር ይከለከላሉ የሚል ግምት አልነበራትም። ከቪዛ ማእከሉ ከወጡ በኋላም መኪና ውስጥ ተረጋግታ ስታየው ማመን እንዳቃታት ትናገራለች። "ሁለት ሶስት ጊዜ ማየት ነበረብኝ፤ ማመን ነው ያቃተኝ" ትላለች። ለኢዛና የቪዛ መከልከሉ ጉዳይ ከቤተቦቹ በላይ መዋቅራዊ ነው በሚለው አሰራር አብረውት የተማሩት አሜሪካውያንና አውሮፓውያን ጓደኞቹ ቤተሰቦቻቸውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመጋበዝ ቀላል መሆኑ የሚያብሰለስለው ጉዳይ ነው። "አሁንም እንደ ዱሮው ታላቅ አገር፣ ታላቋ ብሪታንያ ብለው ነው የሚያስቡት፤ ለዛም ነው የውጭ ጠል ፖሊሲዎች ያላቸው። የብሬግዚት ችግራቸውም እሱ ይመስለኛል" በማለት ይናገራል። በተለይም በከፍተኛ ሁኔታ የሚያበሳጨው እንግሊዝም ሆነ ብዙ የአውሮፓ አገራት የተገነቡበት መንገድ በተበዘበዘ በአፍሪካውያን ጉልበት፣ በቅኝ ግዛት መሆኑን ሲያስበው ነው። "አገራቸውን የገነቡት ከአፍሪካውያን በተሰረቀ ሀብት (ሪሶርስ) ነው፣ በአፍሪካውያን ደምና ላብ ነው" በማለት ትችቱን ይሰነዝራል። የቤተቦቹ መከልከል እንደ አንድ ምክንያት ይሁነው እንጂ ይህንን ሁሉ ስርአታዊ ጭቆናም ለመቃወም ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው የምርቃት ፕሮግራሙ ላይ እንደማይገኝ አቋም የወሰደው። ጉዳዩ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ በተለይም ትዊተር በመሄዱ ብዙዎች በቪዛ አሰጣጡ ስርአት ላይ ኢትዮጵያውያን የሚያልፉበትን "አሳፋሪ አካሄድ" ተችተዋል። በተለይም ታዋቂው ገጣሚ ለምን ሲሳይ በብሎጉ ላይ 'እናትህ ለምረቃህ ስትከለከል' በሚል ርዕስ ስለ ኢዛና አስተዳደግ፣ የኢዛናን ስኬት፣ የትምህርት ዝግጁነቱንና የእንግሊዝን የቪዛ ስርአት 'ኢ-ፍትሐዊ' ሲልም ኮንኖታል። ኢዛናም አገሩ ተመልሶ "ጥሬ ስጋየንና ጠጄን እየጠጣሁ" ከቤተሰቦቹ ጋር አብሮ ለመደሰትም ቀጠሮውንም ያዘ፤ በወቅቱም ለናቱ ምርቃቱ ላይ እንደማይገኝ ነገራቸው። እናቱስ ምን ተሰማቸው? ወ/ሮ ሮማን በሐዘን በተሰበረ ድምፃቸው "ምክንያቱም እናቴ ከሌለች አልገኝም፤ እኔ ምንም ችግር የለም" አልኩት እሱ ግን በምላሹ "ማማ አንቺ በሌለሽበት እኔ ደስ አይለኝም አለኝ" በማለት ይናገራሉ። •"ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ የለምን ሲሳይ በጉዳዩ ጣልቃ መግባት እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በነበረው ጫና ውሳኔው ተቀልብሶ የቪዛቸው ጉዳይ እንደገና እንዲታይ ተወሰነ። የቪዛውን ጉዳይ የሚከታተል ባለሙያ ከደቡብ አፍሪካ በደወለለት ወቅትም ኢዛና በጣም ተናዶ ስለነበር በኃይለ ቃል ተናግሮታል። "እናቴን ደስታዋን ስለነጠቃችኋት በጣም አመሰግናለሁ። የሰባ አመት አዛውንቶች እዚህ አገር ምን ሊሠሩ ይቀራሉ ብላችሁ ነው ያሰባችሁት? ቤት ያላቸው፣ ንብረት ያላቸው፣ ልጆች እንዲሁም የልጅ ልጆች ያላቸው እዚህ አገር መጥተው በሳይክል 'ፉድ ደሊቨሪ' ሥራ እንዲሰሩ ነው?" በተለይም ለኢዛና ያልተዋጠለት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት መደበኛ ያልሆነ (ኢንፎርማል) ኢኮኖሚ በተንሰራፋባቸው ቦታዎች የንግድ ግብይይቶች የሚፈፀሙት እጅ ለእጅ ገንዘብ መሆኑን አፍሪካ ውስጥ ተቀማጭነቱን ያደረገ የቪዛ ባለሙያ አለመረዳቱ ግራ የሚያጋባ ነው። የባንክ አገልግሎት እንደ አውሮፓውያኑ ባልዳባረበት ሁኔታ የቪዛ አሰጣጥ ስርዓቱ የምዕራቡን የንግድ ሥርዓት ማዕከል በማድረግ ግለሰቦች ባንክ ውስጥ ባስቀመጡት የገንዘብ መጠን በቂ ነው አይደለም ተብለው መከልከላቸው ተገቢ እንዳልሆነም ለግለሰቡ አስረድቷል። ግለሰቡም አንዳንድ ጥያቄዎች ኢዛናን ከጠየቀው በኋላ ስህተት መሆኑ እንደገባቸው፤ እንዲሁም ለምርቃቱ ሊደርሱ እንደሚችሉ ነገረው። "የደወሉበት ምክንያት ለምን ሲሳይ በፃፈው ፅሁፍ ምክንያትና ፌስቡክና ትዊተር ላይ ብዙ ሰዎች ስለተጋሩት ነው። ስማቸው በመጥፎ እንዳይነሳ ያደረጉት ነው" ይላል። ይህም ሁኔታ ምረቃ ፕሮግራሙ ላይ አልገኝም የሚለውን ውሳኔውን አስቀልብሶ ለምርቃት ጋወኑ አምሳ ስድስት ፓውንድ ከፍሎ ለመገኘት የወሰነው። ፌቨንም ሁለተኛ ፓስፖርታቸውን አስገቡ በተባለበትና በምርቃቱ ቀንም መካከል የነበረው ልዩነት ጥቂት በመሆኑ ተጣድፋ ፓስፖርታቸውን መልሳ አስገባች። በሁለተኛውም ቪዛውን እንደሚያገኙ በጣም እርግጠኛም ስለነበሩ በረራው እስከ መጨረሻው ቀን ማክሰኞ ሐምሌ 9፣2011 ዓ. ም እንደተያዘ፤ እዛም ሲደርሱ የሚቀበላቸው የታክሲ አገልግሎት፤ ዶሮውንም ሌላውንም ምግብ ተዘጋጅቶ እየጠበቁ ነበር። ነገር ግን እስከ መጨረሻ ሰዓት ድረስ ቢጠብቁም ለምርቃቱ ቀን ሐምሌ 10፣2011 ዓ. ም ፓስፖርታቸው ሳይደርስ ቀርቷል። የኢዛና አስተዳደግ "የምወደው ልጄ ነው፤ ሌሎችም ልጆች አሉኝ ግን ኢዛና የመጨረሻ ልጄ ነው። እሱም ይወደኛል፤ እኔም እወደዋለሁ። በጣም ነው የሚወደኝ" ይላሉ ስለ ልጃቸው ወ/ሮ ሮማን። የኢዛና ምርቃት ላይ ባለመገኘታቸው ልባቸው እንደተሰበረ የምትናገረው ፌቨን "ምክንያቱም ኢዛና ከነበሩት የጤናና የአስተዳደግ እክሎች የተነሳ፤ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶ ማየት በጣም ትልቅ ነገር ነው" ትላለች። ከአስራ አንድ አመቱ እስከ 27 አመቱ 'ኤፕለፕሲ' በተለምዶ የሚጥል በሽታ ምክንያት አስተዳደጉ ቀላል አልነበረም። ኢዛና በፌስቡክ ገፁ እንዳሰፈረው በመጀመሪያ አካባቢ በማይጥለው የኤፕለፕሲ አይነት ለጥቂት ሰኮንዶች በቀን 30 ጊዜ ያህል በመፍዘዝ ይቸገር ነበር። በመካነ እየሱስ ሚሽነሪ አንደኛ ደረጃ ተማሪ በነበረበት ወቅት የተወሰኑ የክፍሉ ተማሪዎች ይስቁበት እንዲሁም ባስ ሲል ስድብም እንደነበር ያስታውሳል። "አንዳንዶቹም ይሰድቡኝ ነበር፣ ዘገምተኛ፣ ፉዞ፣ ወዘተ" በማለት ፅፏል። በማኅበረሰቡ ካለው እምነት ጋር ተያይዞ ህመሙ ከሰይጣን፣ እርግማን፣ መተት ጋር መያያዙ በተለይም አደግ ሲል ፈታኝ እንደነበር ያስታውሳል። የነበረውን ሁኔታ በራሱ አንደበት እንዲህ ይገልፀዋል። "ትንሽ ከፍ ስል 15 ዓመቴ አካባቢ ከመፍዘዙ ባሻገር የሚጥለው አይነት ኤፕለፕሲ ይከሰትብኝ ጀመር፤ ያኔ የሰፈር ሰው ማወቅ ጀመረ። እናቴንም ሰው ማግኘት እስኪያስጠላት ድረስ በሰይጣን እንደተለከፍኩ ይነግሯት እና ያስከፏት ነበር።" "እድለኛ ነኝ" የሚለው ኢዛና እናቱም ሆነ እህቱ እንደ ማንኛውም ህመም ስላዩት ህክምናም አግኝቷል።። መድኃኒቱን በትክክል ከመውሰድ በተጫማሪ ትልቅም ሲሆን የኑሮውን ዘዬ በማስተካከል መጠጥ በደረሰበት ደርሶ አያውቅም። "መጠጥ ከነጭራሹ አልጠጣም ነበር፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጓደኞቼ ለዚህ ነበር ካንትሪ ወይም ቼጉቬራ ውሐ ይዤ ስጨፍር የነበረው" በማለት አስፍሯል። ቤተሰቦቹም ሆነ የኢትዮጵያ ኤፕለፕሲ ማህበር ያደረገለትን አስተዋፅኦ የማይረሳው ኢዛና መፍዘዝም ሆነ መጣል ካጋጠመው ስምንት ዓመት አለፈው። ያ ሁሉ አልፎ ዶክትሬቱን ከሰሞኑ የተቀበለው ኢዛና ቤተሰቡ ባይገኝም ምርቃት ፕሮግራሙ ላይ ጓደኞቹ ተገኝተው ነበር። ማንችስተር ውስጥ የሚገኘው ሁልጊዜም የሚያዘወትሩት የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ልዩ ድግስ በማዘጋጀት፣ ኬክ ቆርሰዋል፣ በሻምፓኝ ተከፍቶላቸዋል፤ በጭፈራም ተደስተዋል። እናቱም ሳይወዱ በግድ የምርቃት ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት በመከታተል የልጃቸውን ምርቃት በትንሹ ለመቋደስ ሞክረዋል። "ልጄ እንኳን ተመረቀ፤ ዝግጅቱም በጣም የሚያስደስት ነው፤ እንዲያው ብገኝ ደስ ይለኝ ነበር" በማለት ወይዘሮ ሮማን የነበረውን ሁኔታ ይናገራሉ። ኢዛናም ከምረቃው በኋላ ደውሎላቸው የነበረ ሲሆን "ተሰብስበው እንዳዩት ነገሩኝ፤ እንደ እግር ኳስ ጨዋታ ነው ሲከታተሉኝ የነበረው" ይላል። እህቱ ፌቨን ወንድሟ በደረሰበት ደረጃ ቤተሰቡ በአጠቃላይ ከፍተኛ ኩራት እንደተሰማቸው ገልፃ ቤተሰቦቿ ቢገኙ ደግሞ የበለጠ ደስታ ከፍ ያለ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ መሆኑን ትገልፃለች። "ቤተሰቦቼ በቀጥታ የሚተላለፈውን ምርቃት እያዩም እያለቀሱ ነበር። በእንግሊዝ ኤምባሲ በጣም አዝነናል" ትላለች።
46617696
https://www.bbc.com/amharic/46617696
የምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ፓርቲዎች እየመከሩ ነው
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም የተረቀቀ አዋጅ ዛሬ ረቡዕ በአዲስ አበባ ለምክክር ቀርቧል። በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ፤ የሕግ እና የፍትህ አማካሪ ጉባዔ ጽህፈት ቤት በተሰናዳው የምክክር መድረክ ላይ በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና ተወካዮች ተገኝተዋል።
አሁን ባለው የኢትዮጵያ የሕግ መዋቅር መሰረት ምርጫን የሚመለከቱ ሦስት ሕጎች ሲኖሩ፤ የምርጫ ሕጉ አንዱ ነው። ሌሎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ሕግ እና የምርጫ ሥነ ምግባር ሕግ ናቸው። • ብርቱካን ሚደቅሳ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንደሚሾሙ ይጠበቃል ዲሞክራሲያዊ፣ ነፃ እና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫን ከማካሄድ አንፃር እነዚህ ሕግጋት ያሉባቸው ክፍተቶች በልዩ ልዩ መስፈርቶች መገምገማቸውን የተናገሩት በጉባዔው የዲሞክራሲ ተቋማት ጥናት ቡድን አባል የሆኑት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሕግን የሚያስተምሩት ዶክተር ሲሳይ አለማው ናቸው። አሁን ለምክክር የቀረበው ግን የምርጫ ቦርዱን ብቻ የሚመለከተውና በአዋጅ ቁጥር 532/99 የተካተተው መሆኑን ዶክተር ሲሳይ ገልፀዋል። "ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት በመንግሥት በኩል ምርጫ ቦርድን እንደገና ገለልተኛ እና ተዓማኒነት ያለው አድርጎ እንዲሁም ለሥራ አፈፃፀም ቅልጥፍና ባለው መልኩ ለማቋቋም ባለው ፍላጎት እና ጥያቄ መሠረት ነው" ብለዋል የጥናት ቡድን አባሉ። • "ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ረቂቅ አዋጁ የቦርዱ አቋም በአጠቃላይ ምን መምስል አለበት፣ አባላቱ እንዴት ሊመለመሉ እና ሊነሱ ይችላሉ፣ ስልጣናቸውስ ምን ይመስላል የሚለውን በዝርዝር የሚያስቀምጥ ይሆናል። ይኖራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ለውጦች መካከል አንዱ በትርፍ ሰዓት ከሚሰሩ አባላት ወደ ሙሉ ሰዓት ማሸጋገር እንደሆነ ዶክተር ሲሳይ ተናግረዋል። በረቂቁ ውስጥ እንደተካተተው ከሆነ የቦርዱ ሠራተኞች የሙሉ ሰዓት ሰራተኛ ሆነው ቁጥራቸው ሊያንስ ይችላል። • ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ? እነርሱም በቦርዱ ሥራ ውስጥ የተሻለ ተሳትፎ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ያስረዱት ዶክተር ሲሳይ፤ ቦርዱ በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ምርጫዎችን እና ሕዝበ ውሳኔዎችን እንደማስተዳደሩ፣ ከዚያም በዘለለ የሥነ ዜጋ ትምህርት የመስጠት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ስልጣናት ስላሉት ዝቅ እስካሉ የአስተዳደር አሃዶች የሚደርስ መዋቅር ቢኖረው ተገቢ ይሆናል ተብሎ እንደታሰበ አትተዋል። ለምክክር የቀረበው ረቂቅ ሕግ የምርጫ ቦርድ በጀቱን ከማስተዳደር አንስቶ የምርጫ አስፈፃሚዎችን እስከ መቅጠር ድረስ ሙሉ ስልጣን እንዲኖረው የሚያስችል ነውም ተብሏል። ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት እና ትልቅ ስፋትም ያላት አገር እንደመሆኗ ምርጫ ቦርድ "በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ስለሚያሰማራ በቂ ጊዜና በጀት አግኝቶ በነፃነትና በገለልተኛነት መስራት የሚችልበት ማዕቅፍ እንዲኖር ነው ይህ ረቂቅ የቀረበው" ብለዋል ዶክተር ሲሳይ። • የሰልፍ "ሱሰኛው" ስለሺ ረቂቅ ሕጉ እንደሚለው የህገ መንግሥቱን መሠረተ ነገር በሚያንፀባርቅ ሁኔታ የቦርዱ አባላት የብሄር ተዋፅዖን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሚመረጡም ተገልጿል። ረቂቅ ሕጉ አንድን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ የተሰናዳ ሳይሆን ረዥም ጊዜን አሻግሮ በማየት የተቀረፀ ነው የተባለ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች በእነዚህ እና በሌሎችም በህጉ በተካተቱ ሃሳቦች ላይ ውይይት አድርገዋል።
49108188
https://www.bbc.com/amharic/49108188
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ 200 ሚሊዮን ችግኞች
አርቲስት ደበበ እሸቱ በቅርቡ ከቢቢሲ ጋር በነበረው አጭር ቆይታ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባዘጋጁት 'ገበታ ለሸገር' የእራት ግብዣ ላይ በሕንድ ተይዞ የነበረውን በመላ አገሪቱ ዛፍ የመትከል ክብረ ወሰን ለመስበር የሚያስችል ዘመቻ ለማካሄድ ማሰባቸውን እነሰለሞን ዓለሙ እንዳጫወቱት ይናገራል።
"ሕንድ 100 ሚሊዮን ዛፍ በመትከል ክብረ ወሰኑን ይዛለች። እኛ በመላ አገሪቱ ሁለት መቶ ሚሊዮን ችግኝ ለምን አንተክልም?" ነበር ያሉት። ያኔ ታዲያ ደበበ ሐምሌ 21/2011 ዓ. ም ይህንን ለማድረግ እንዳሰቡ ጨምሮ ተናግሮ ነበር። • "ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል" ደበበ እሸቱ ይህ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎቹ ሀሳብ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩም ዕቅድ በአንድ ሰምሮ ሁሉም ዶማና አካፋውን እንዲሁም ችግኙን ይዞ በየቦታው ደፋ ቀና እያለ ነው። የአካባቢ፣ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ብሔራዊ የደን ልማት ንቅናቄ የችግኝ ተከላ እንደሚከናወንና ይህም ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ ድረስ እንደሚዘልቅ አሳውቋል። በዘንድሮው የክረምት ወቅትም 4 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መቋቋሙ ተነግሮ ነበር። ሁሉም ነገር ወደ... ዛሬ ሐምሌ 22/2011 ዓ. ም በመላ አገሪቱ ሙሉ ቀን ዛፍ በመትከል ክብረ ወሰን ለመስበር ማለሙን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። በኦሮሚያ 126 ሚሊዮን፣ በአማራ 108 ሚሊዮን፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል 48 ሚሊዮን፣ በትግራይ ዘጠኝ ሚሊዮን ችግኞች ሊተከሉ እቅድ ተይዞ፣ ቦታ ተመርጦ፣ ጉድጓድ ተቆፍሮ መዘጋጀቱ ተነግሯል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ በሁሉም ወረዳዎች 3 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የሚያስችለው ዝግጅት መጠናቀቁን በምክትል ከንቲባው የትዊተር ገፅ ላይ አስፍሯል። ምክትል ከንቲባው በአንድ ቀን ብቻ 1.5 ሚሊየን ጉድጓዶች መቆፈራቸውንም በመግለጽ "ለከተማችን ያለንን ፍቅር በሥራ ብቻ እናሳይ" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። • ብዝኀ ሕይወት ምንድን ነው? ለምንስ ግድ ይሰጠናል? "የአራዳ ልጅ ዛፍ ይተክላል" በትዊተር ላይ የተጀመረ ዘመቻ ነው። የዚህ ዘመቻ አስተተባሪዎች "ዛፍ መትከል ጤናን መገብየት ነው" በሚል በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ዛፍ ለመትከል ጥሪ እያቀረቡ ነው። ሐምሌ 22 ቀን በአንድ ጀንበር 200 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ለተያዘው እቅድ 54 ሚሊየን ብር መመደቡንም የገለፀው ይህንኑ ዘመቻ የሚያስተባብረው ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ ነው። የዛፍ መትከል ዘመቻዎች አቶ ሞገስ ወርቁ የለም ኢትዮጵያ የአካባቢና ልማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ናቸው። ማኅበሩ ከተቋቋመ 28 ዓመት እንደሆነው ጠቅሰው፤ የማኅበሩ መስራቾች ዛፍ ከመትከል አስቀድሞ የሰው አእምሮ ላይ ጤናማ ችግኝ መትከል የተሻለ፤ የተራቆተውንና የተጎዳውን የአገሪቱን መሬት በደን ለመሸፈን ያስችለናል የሚል ጠንካራ እምነት እንደነበራቸው ይናገራሉ። ይህንን ማኅበር የመሰረቱት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ከፍተኛ የዘርፉ ባለሙያዎች መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ወርቁ፤ እነዚህ የችግኝ ተከላ ዘመቻዎች ግንዛቤን በመፍጠር ረገድ የማይናቅ ሚና እንዳላቸው ይገልፃሉ። የመልካ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሠለሞን ከበደ ድርጅቱ ከተመሰረተ ከ10 ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ ተናግረው፤ በአገራችን አካባቢ ተጠብቆ መቆየት የቻለው ማኅበረሰቡ ለአካባቢ ባለው ባህላዊ እሴትና ጥበቃ ነው ብሎ እንደሚያምኑ ይናገራሉ። ይህ የማኅበረሰብ እውቀት ለአካባቢ እንክብካቤ አስተዋፅኦ ስላደረገ እውቀቱ መጠበቅ፣ እንክብካቤ ማግኘትና ማደግ አለበት በሚል ከሳይንሳዊ እውቀት ጋር በማዛመድ ዘላቂ ውጤት ማምጣት በሚያስችላቸው የተለያዩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ይናገራሉ። • ዋሺንግተን ሟቾች ወደአፈር እንዲቀየሩ ፈቀደች ከዚህ ሥራቸው መካከል አንዱ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል የሚያከናውኑት የአካባቢ ልማት እንክብካቤ የችግኝ መትከልን ያጠቃልላል። አክለውም በአሁኑ ወቅት በዘመቻ የሚደረጉ የዛፍ ተከላዎችም ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር አስተዋፅአቸው ከፍ ያለ መሆንን ያስታውሳሉ። ነገር ግን ክረምት በመጣ ቁጥር እየተነሱ ችግኝ መትከል ደግመን ልናጤነው የሚገነባ ጉዳይ መሆኑን የሚጠቅሱት አቶ ሠለሞን፤ እንደ አገር ይላሉ "ፍኖተ ካርታ ያስፈልገናል ምክንያቱም የችግኝ ተከላ ከአንድ ዛፍ ተከላ ያለፈ ነው" ይላሉ። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶች ስላሉ ለዛፍ መጨፍጨፍ ምክንያት የሆኑት ተቋማት ዛፍ የመትከልና የመንከባከብ ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ እነሱን ማሳተፍ ተገቢ መሆኑን ያሰምሩበታል። "እንዲህ በዘመቻ ችግኝ መትከል አዲስ አይደለም" ያሉት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአካባቢ ጥበቃ ላይ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እየሠሩ የሚገኙት አቶ ከድር ይማም መሐመድ ናቸው። በቀድሞው ወታደራዊ መንግሥትም ሆነ ኢህአዴግ ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ዛፍ በዘመቻ መትከል የኖረ ባህል ቢሆንም፤ ከዚያ ይልቅ ማስተዋል የሚኖርብን የምንተክላቸው ችግኖች ምን ያህል ይፀድቃሉ? የሚለው ላይ መሆን እንዳለበት ይናገራሉ። የአቶ ከድርን ሀሳብ የሚጋሩት በአምቦ ዩኒቨርስቲ የግብርና ኮሌጅ የተፈጥሮ ኃብት አያያዝ መምህርና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በአፈር አጠባበቅ ላይ እየሠሩ ያሉት አቶ መሀመድ እንድሪያስ ናቸው። እንደ አገር ለተለያዩ የተፈጥሮ ችግሮች መጋለጣችንን የሚጠቅሱት አቶ መሐመድም ሆኑ የለም ኢትዮጵያው አቶ ሞገስ ለዚህም ምክንያቱ የደን መመናመን መሆኑን ይጠቅሳሉ። ለዚህም መንግሥት አረንጓዴ ልማት በማለት በየዓመቱ ዛፍ መትከሉን በበጎ ያዩታል። • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? ጥያቄው ይላሉ አቶ መሐመድ፤ እንዴት ተደርጎ እየተተከለ ነው? የሚለው ነው በማለት የችግኝ ተከላው ላይ ያላቸውን ስጋት ይሰነዝራሉ። አብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የመሬት መራቆት፣ የአፈር መከላት፣ በብዛት እንደሚታይ አስታውሰው እነዚህ ሁሉ ችግሮች ከደን ሀብት መመናመን ጋር ተያይዞ የመጡ መሆናቸውን ያስረዳሉ። ታዲያ ከሚሌኒየም ጀምሮ በዘመቻ እየተከልን የአገሪቱ የደን ሽፋን መጠን አለመሻሻሉን የሚናገሩት አቶ መሐመድ፤ እንዲያውም "መረጃዎች የሚያሳዩት እየቀነሰ መሆኑን ነው" ይላሉ። በ1990ዎቹ አካባቢ የአገሪቱ የደን ሽፋን መጠን 15 ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አራት ሔክታር ነበር የሚሉት መምህሩ፤ በ2000 ላይ 13 ሚሊዮን ሰባት መቶ አምስት አካባቢ መሆኑን በመጥቀስ፤ በ2010 ላይ አስራ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ስድስት፤ በ2018 ላይ ደግሞ አስራ ሁለት ሚሊዮን 147 ሔክታር አካባቢ ሽፋን መኖሩ ይጠቅሳሉ። በየዓመቱ በዘመቻ እየተከልን የአገሪቱ የደን ሽፋን ግን ከመሻሻል ይልቅ መቀነስ ታይቶበታል። ስለዚህ የተተከለው እየፀደቀ ነውን? ብሎ መጠየቅ ያሻል ይላሉ። አቶ ሠለሞንም የመምህሩን ጥያቄ የሚጋሩ ሲሆን፤ የመንግሥትን መረጃ በመጥቀስ የአገሪቱ የደን ሽፋን በአሁን ሰዓት ከ15 እስከ 20 በመቶ እንደሚሆንና የዘንድሮው ዘመቻ ከተሳካ ወደ 30 በመቶ ከፍ ይላል ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ያስቀምጣሉ። የተከልነው እንዲፀድቅ. . . ሐምሌ 22/2011 ዓ. ም 200 ሚሊዮን ዛፎችን ለመትከል መንግሥት ያለውን እቅድ ይፋ ሲያደርግ፤ በዚህ ክረምት ብቻ 4 ቢሊየን ችግኞችን እተክላለሁ ሲል ሁሉም ክልሎች ዘመቻውን በአንድ ድምፅ ተቀላቅለዋል። ይህ በዘመቻ የሚደረግ ተከላ ግን የአምቦ ግብርና ኮሌጅ መምህሩን ምን ያህል ዝግጅት ተካሂዷል? የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓል። ይህን ያህል ችግኝ ለመትከል፤ ያውም በአንድ ቀን ክብረ ወሰንን ከመስበር ባለፈ ሊነሱ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉበት በማስታወስ የጉድጓድ ዝግጅት፣ የተከላ ቦታ መረጣ፣ አስፈላጊ በጀትና የሰው ኃይል፣ የችግኝ መረጣ እና ማጓጓዝ ቀድሞ ከግንዛቤ ሊገቡ የሚገቡ ነገሮች ናቸው ይላሉ። በዚህ ሀሳብ የሚስማሙት የለም ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጁ አቶ ሞገስ፤ የግንዛቤ እጥረት እንዳለ ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። "መትከል ዝም ብሎ ቁጥር ማስመዝገብ ብቻ አይደለም" የሚሉት አቶ ሞገስ፤ ተቋማት የሚተክሉት ችግኝ ቁጥር ተሰፍሮና ተቆጥሮ ስለተሰጣቸው ብቻ እሱን ለማሟላት መትከል ችግኙ እንዲያድግ አያደርገውም ይላሉ። • የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል አንዳንዱ በዚህ ዘመቻ በመንግሥት መኪና፣ ከባልደረቦቹ ጋር በመሄዱ የደስታ ስሜት ውስጥ የገባ እንጂ የችግኝ መትከልን መሰረታዊ እውቀት ይዞ በሥፍራው አይገኝም ሲሉም ትዝብታቸውን ያጋራሉ። ልክ እንደ አቶ ሠለሞን ሁሉ አቶ መሐመድም የተሳተፉባቸውን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሮች በማስታወስ በዘመቻ ችግኝ መትከል ሳይንሳዊ መንገድን ተከትሎ ለመትከልና አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ እንደማይረዳ ይጠቅሳሉ። "አተካከላችን ሳይንሱን የተከተለ፣ በግንዛቤ እና በጥናት ቢሆን ውጤታማ እንሆናለን" የሚሉት አቶ ሠለሞን፤ የተተከሉባቸው ቦታዎች ላይ መልሶ መትከል፣ ያለ ባለሙያ እገዛ መትከል አዋጭ አለመሆኑን ያሰምሩበታል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በእሳቸው መታሰቢያነት የተተከሉ በርካታ ችግኞች፣ ሌላ ሥፍራ ከተተከሉት በተሻለ ጸድቀዋል ያሉት ደግሞ የአምቦ ዩኒቨርስቲው መምህር አቶ መሐመድ ናቸው። "ይህ የሚያሳየን ችግኝ ተከላው ተቋማዊ ቢሆን ውጤታማ እንደሚሆን ነው" ይላሉ። ችግኝ ተከላ ሳይንሳዊ መንገድን መከተል አለበት በማለትም ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ። እስካሁን ድረስ የሚተከሉ ዛፎች በዘመቻ መሆናቸው ለአቶ መሐመድ ሳይንሳዊ መንገዶችን ስለመከተላቸው ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓቸዋል። "በዘመቻ የሚተከሉ ዛፎች ላይ በቂ የሆነ የሰው ኃይል ማሰማራታችንን፣ በተገቢው ጥንቃቄ ማጓጓዛችንን እርግጠኛ መሆን አለብን" የሚሉት አቶ መሐመድ፤ ስለ አተካከሉም ተሳታፊዎች በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያስታውሳሉ። • "የከተማ መስፋፋት የኢትዮጵያን ብዝሀ ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል" ዶ/ር መለሰ ማርዮ ኢትዮጵያ የተለያየ አግሮኢኮሎጂ እንዳላት የሚያስታውሱት አቶ መሐመድ፤ ችግኞቹን ከመትከላችን በፊት ለተከላ ደርሷል ወይ?፣ ለሚተከሉበት አካባቢ አግሮኢኮሎጂ ተስማሚ ናቸው? የሚለው በሚገባ መስተዋል እንዳለበትም ይናገራሉ። አገር በቀል ዛፎችን መትከል እጅጉን ተመራጭ ነው የሚሉት አቶ መሐመድ የችግኙ ቁመት፣ ከበሽታ የፀዳ መሆኑ ከግምት ቢገባ ለመጽደቅ በጎ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ይላሉ። በተጨማሪም የቦታ መረጣ ላይም ያላቸውን ስጋት ሲያነሱ፤ ዛፎችን የሚተከሉት ብዙ ጊዜ ማኅበረሰቡ በጋራ የሚጠቀመው መሬት ላይ በመሆኑ አርሶ አደሩ ከብቶቻቸውን ለግጦሽ የሚያሰማሩበት ስለሆነ የመጽደቅ እድላቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን የሚያነሱት አቶ መሐመድ፤ ይህ ደግሞ ግብርና እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ያስታውሳሉ። አዳዲስ የሚታረስ መሬት ፍለጋ አንዳንድ አካባቢ ተራራ የሚቧጥጥ፣ ደን የሚያቃጥል አርሶ አደር መኖሩን በማስታወስ የችግኝ ተከላው አርሶ አደሩን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ይመክራሉ። በገጠሩ ክፍል ከደን ሽፋን ይልቅ እርሻ መሬቶች እየተስፋፉ መሆናቸውን በማንሳት ከፊታችን የተደቀነው አደጋ አሳሳቢ ነው የሚሉት ምሁሩ፤ በተለይ የሰሜኑ የአገራችንን ክፍል ሲመለከቱ "ከተሞች በተሻለ አረንጓዴ ለብሰው ይታዩኛል" በማለት ብዙ ሥራ መሰራት እንዳለበት ያብራራሉ። በጎጃምና በትግራይ እየተሠራ ያለው "ዊ ፎረስት" የተባለውን ፕሮጀክት እንደ መልካም ተሞክሮ መውሰድ እንደሚቻልም ያስቀምጣሉ። ፕሮጀክቱ የዛፍ ተከላን 'ጥምር እርሻ' የሚል ጽንሰ ሀሳብ በመጠቀም ከእርሻቸው ጎን ለጎን ለገበያ የሚሆኑ ምርት የሚሰጡ የዛፍ ችግኞችን አፍልቶ በማቅረብ ገበሬው በማሳው ውስጥ ተክሎ በገንዘብ እንዲጠቀም እግረ መንገዱንም የአካባቢ ጥበቃ ላይ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ያነሳሉ። • ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር በችግኝ ተከላ ወቅት በርካታ ጥንቃቄዎች መደረግ አለባቸው የሚሉት አቶ ሞገስም ሆኑ አቶ መሐመድ ጉድጓዱ ከሁለት ሳምንት በፊት መዘጋጀቱን፣ አተካከሉም ላይ ችግኙን ከነላስቲኩ አለመትከልና ሥራቸው አለመታጠፉን እርግጠኛ መሆን አለብን ሲሉ ይመክራሉ። የቦታ መረጣው በሚተከለው ችግኝ አይነት ይወሰናል የሚሉት አቶ መሐመድ፤ ለማገዶ፣ ለአፈር እቀባ፣ ለጥምር እርሻ፣ ለመኖ የሚተከሉ የዛፍ ችግኞች የት ቦታ ይተከሉ የሚለው በሚገባ መስተዋል እንዳለበት ይመክራሉ። ለችግኞቹ የተዘጋጀው ጉድጓድ ውስጥም ውሃና ሌሎች ባዕድ ነገሮች አለመኖራቸውን ማረጋገጥና ከተተከለም በኋላ ውሃ እንዳይተኛበት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑና በአካባቢው ሥነ ምህዳር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የማያሳድሩ ዛፎች መተከል አለባቸው ያሉት ደግሞ የመልካ ኢትዮጵያ ዳይሬክተሩ አቶ ሠለሞን ናቸው። የሚተከሉ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ መሆን አለባቸው በማለት፤ ንብ ማነብ የሚያስችሉ፣ ለከብት መኖ፣ መሬትን ለማልማት የሚሆኑ እና ለመኖና ለማገዶ የሚሆኑትን በመለየት መትከል ተገቢ መሆኑን ይመክራሉ። የሚተከሉት ችግኞች ምን ውጤት እንደሚያስገኙ መታወቅ አለበት የሚሉት አቶ ሠለሞን፤ ይህን ማወቅ የሚተከልበትን ቦታ በመለየት ረገድ አስተዋፅኦ እንዳለው ሳይጠቅሱ አላለፉም። በርግጥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕቅድ ይሳካል? አቶ መሐመድ ለዚህ ምንም ጥርጥር የላቸውም። ዓለም ላይ እንዲህ አይነት ተሞክሮዎች መኖራቸውን በመጥቀስ ጀርመናዊው የዘጠኝ ዓመት ታዳጊን የተከላቸውን 1 ሚሊዮን ችግኞች እንዲሁም ዋንጋሪ ማታይ በኬኒያ የተከሏቸውን 30 ሚሊዮን ችግኞችን በማንሳት ሊሳካ እንደሚችል ይናገራሉ። ነገር ግን ቅድመ ዝግጅቶች ወሳኝ መሆኑን አበክረው የሚናገሩት ጉዳይ ነው። የለም ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ እንደሚሉት፤ ለቀጣይ አስር ዓመት የትኛው ችግኝ የት ቦታ ይተከል? የሚለውን አጥንተው ቢተከል ይሻላል በማለት በአንድ ጊዜም አገሪቷን በአጠቃላይ በደን አለብሳለሁም ብሎ መነሳት ስህተት መሆኑን ያስረዳሉ። ቀስ በቀስ ሊሳካ የሚችል ግብ ማስቀመጥ፣ ሥራዎችን እያጠናከሩ ከስህተት እየተማሩ ለመሄድ ያስችላል በማለትም ምክራቸውን ይለግሳሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ዘመቻ ስኬታማ ለማድረግ ዛፍ በመተከል ኃላፊነት ያላቸውን ዘርፎች በሙሉ ወደ ሥራው ማምጣት ያስፈልጋል የሚሉት ደግሞ የመልካ ኢትዮጵያ ዳይሬክተሩ አቶ ሠለሞን ናቸው። ኢትዮጵያ ያለው የችግኝ ተከላ ዘመቻ ከዘርፉ ተቋማት ጋር ያልተያያዘ ነው የሚሉት ዳይሬክተሩ፤ ይህም ውጤታማነቱ ላይ ወገቡን እንዲያዝ ያደርገዋል በማለት ስጋታቸውን ይገልፃሉ። "ዛፍ ተከላ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚፈልግ ነው" የሚሉት አቶ ሠለሞን መጀመሪያ መሆን ያለበት ዓላማን ግልፅ አድርጎ ማስቀመጥ መሆኑን ያስረዳሉ። "አንድ የጋራ ብሔራዊ ራዕይ ያስፈልገናል" በማለትም ብሔራዊ ራዕዩን ለማሳካት ግልፅ ያሉ ስልቶችንና ግቦች እንደሚያስፈልጉም ያስታውሳሉ። • የማትተነፍሰው ከተማ: አዲስ አበባ ዛፍ ከሚቆረጥበት ዘርፍ አንዱ ግብርና መሆኑን በመጥቀስ፤ ግንባር ቀደሙ ዛፍ ተካይ ተቋም መሆን እንዳለበት ያስረዳሉ። ግብርና ከዛፍ ተከላ ጋር በፕሮግራሙ ውስጥ ካልተቀናጀ፣ "የግብርና ሥራን በየቦታው እንደምንከታተለው የዛፍ ተከላንም ጎን ለጎን ካልተከታተልነው የችግኝ ተከላ ጥረታችን በአንድ እጅ ማጨብጨብ ነው" ይላሉ። አንድ ባለ ሀብት 100 ሺህ ሄክታር አለማለሁ ሲል፣ መቶ ሺህ ሔክታር ደን ይቆርጣል የሚሉት አቶ ሠለሞን፤ ባለሀብቱ ይህንን እንዴት ነው የሚያካክሰው? ሲሉም ይጠይቃሉ። ግብርናው መስኖ አለማለሁ፣ የአፈር መሸርሸርን እከላከላሁ የሚል ፕሮግራም ካለው ደን ተከላ ውስጥ መግባት አለበት በማለት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የችግኝ ተከላ ዘመቻ ውጤታማ ለማድረግ መወሰድ ስላለባቸው ዘርፈ ብዙ ምላሾች ያስረዳሉ። ሌላው ደን የሚጨፈጨፍበት ዘርፍ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫዎች መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ሠለሞን፤ ግድብ ያለበትን አካባቢ በደን በመሸፈን ውሀ እንዲመነጭ ማድረግ፣ ትነትን መቀነስ፣ ወደ ግድቡ የሚገባውን ደለልም መቀነስ ይቻላል ይላሉ። ግልገል ጊቤ ሦስትን ብንወስድ ይላሉ አቶ ሠለሞን ሀሳባቸውን በምሳሌ ሲያስረዱ፣ ውሀ የሚንጣለለው 150 ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ፣ 140 ሜትር ከፍታ ላይ መሆኑን በማስታወስ 150 ኪሎ ሜትር በአጠቃላይ ወይ ደን የነበረበት አልያም ሸለቆ የነበረ መሆኑን ማስታወስ እንደሚገባ ይናገራሉ። የሕዳሴ ግድብም ቢሆን ውሀው የሚጠራቀምበት ቦታ ደን የነበረበት ቦታ ነው የሚሉት አቶ ሠለሞን "ስለዚህ ውሀው የሚተኛበትን ዙሪያ በደን እንዲሸፈን ካላደረግን አንደኛ የተቆረጠው ደን የውሃ አቅርቦቱን ይቀንስበታል። በዙሪያው ችግኝ ብንተክል ግን ሃይድሮ ፓወሩ ከውሀ ተፋሰሱ ዙሪያ ውሀ ያገኛል፤ በዚያውም ወደ ግድቡ የሚገባው ደለል ይቀንሳል" በማለት በአንድ ድንጋይ በርካታ ወፍ መምታት እንደሚቻል ያስረዳሉ። አቶ ሞገስ በአቶ ሠለሞን ሀሳብ በመስማማት በርግጥ አሁን ያለው የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ በውሀ እጥረት የተፈጠረ ብቻ ሳይሆን ግድቦች በደለል በመሞላታቸው ጭምር ሊሆን እንደሚችል በመጥቀስ በግድቦች ዙሪያ ያለውን የደን ሽፋን ማሳደግ እንደሚገባ ያስረዳሉ። • በክረምት ሲዘንብ የመሬት ሽታ ለምን ያስደስተናል? አቶ ሠለሞን የመንገድ ግንባታውንም በማንሳት በከተማም ሆነ በገጠር መንገዶች ሲገነቡ ትልልቅ ዛፎች ተገንድሰው መሆኑን ይናገራሉ። ይህ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ከመንገዱ ግራና ቀኝ የዛፍ ተከላ ፕሮግራምን ማካተት መቻል አለበት ሲሉ እያንዳንዱ ልማት ከዛፍ ተከላ ጋር መተሳሰር እንዳለበት ይጠቅሳሉ። የቤቶች ግንባታም በደን ላይ ተጽእኖ አለው የሚሉት አቶ ሠለሞን "የቤቶች ልማት በከተማ ውስጥ ዛፍ ቆርጦ ቤት ከሠራ፣ በሚሠራቸው ቤቶች በረንዳዎች አገር በቀል ዛፍ እንዲተክል በሕግ ማስገደድ ይቻላል" በየሰፈሩ ውስጥ በሚሠሩ መንገዶች ግራና ቀኝ ዛፍ እንዲተክልም በሕግ ማስገደድ እንደሚገባ ይገልፃሉ። የማኅበረሰብ ተሳትፎ እስካሁን ድረስ በታየው ይላሉ የአምቦ ዩኒቨርስቲው አቶ መሐመድ፤ ችግኝ መትከል ላይ ምንም ችግር እንደሌለ ጠቁመው ከተተከሉ በኋላ ግን መጠበቁ ላይ ድክመት እንዳለ ያስረዳሉ። ላለፉት 10 ዓመታት ችግኝ ተክሎ የደን ሽፋን ከመጨመር ይልቅ መቀነስ የታየው መንከባከብ ላይ ችግር ስላለ ነው የሚሉት መምህሩ፤ "ችግኝ ማለት ልጅ ነው በማለት እንዲፀድቅ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት እንክብካቤ ይፈልጋል" ይላሉ። ችግኝ ለማፍላትና ለመትከል የሚወጣው ጉልበት፣ ገንዘብ ያህል ለእንክብካቤውም ማውጣት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተው የሚናገሩት አቶ መሐመድ፤ በኃላፊነት እና በተጠያቂነት የሚመራና በየክልሉ የፀደቁትን የሚከታተል ተቋም መኖር እንዳለበት ያሰምሩበታል። • ፍርድ ቤት የቀረበው የጤፍ ባለቤትነት ጉዳይ የመልካ ኢትዮጵያው አቶ ሠለሞን በበኩላቸው በአንዳንድ ግምቶች ይህ የመንግሥት ተነሳሽነት 548 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይንም 16 ቢሊየን ብር ገደማ ያስፈልገዋል መባሉን መስማታቸውን ጠቅሰዋል። "ይህንን ያህል በጀት አለ ወይ?" ብለው በመጠየቅ የመንግሥትን ሸክም ለመቀነስ ችግኝ መትከልን የተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ ኢንቨስትመንቶች፣ እንዲወጡት ቢደረግ በበጀት ረገድም የራሱ ሆነ እፎይታ እንደሚኖረው ይናገራሉ። አክለውም የሚተከለው ደን ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ማኅበረሰቡ ለሚያገኘው ጥቅም ሲል እየተንከባከበ ስለሚያሳድገው ሕዝብ አሳታፊ ስልትን ነድፎ መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑን ያስረዳሉ። ይህ የእንክብካቤ ወጪንም ይቀንሳል የሚሉት አቶ ሠለሞን፤ መንግሥት ጫናውን ለሌሎች ማካፈል እንዳለበት ይመክራሉ። አቶ መሐመድ በበኩላቸው የተተተከሉትን ችግኞች ለተከታታይ ሦስት ዓመት መንከባከብ ካልተቻለ አሁን የወጣውን ጉልበትና ገንዘብ ውሃ በልቶት እንደሚቀር ያሳስባሉ። አቶ ሞገስና አቶ ከድር በበኩላቸው የኃይማኖት ተቋማት የማኅበረሰብ ተሳትፎን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸው ሚና ቸል መባል እንደሌለበት በማስታወስ፤ ተቋማቱ በአስተምህሯቸውም ሆነ በእስከ ዛሬ ልምዳቸው ዛፍን መንከባከብ፤ በተለይ የአገር በቀል ዛፎችን ጠብቆ በማቆየት ምስክር ስለሆኑ ከእነሱ ጋር መሥራት ዘላቂ ጥበቃ ላይ አስተዋጽኦ እንዳለው ያስታውሳሉ።
54769005
https://www.bbc.com/amharic/54769005
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማን ናቸው?
ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት በመሆን ተመርጠዋል።
ባይደን የባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል። ደጋፊዎቻቸው ባይደን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ አዋቂ ናቸው ይሏቸዋል። በእርጋታቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛ በግል ሕይወታቸው አሳዛኝ ክስተቶችን አሳልፈዋል። ባይደን የፖለቲካ ሕይወታቸው የጀመረው ከ47 ዓመታት በፊት ነበር። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ጥረት ማድረግ የጀመሩት ደግሞ ከ33 ዓመታት በፊት እአአ 1987 ላይ። ባይደን በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት አላቸው። የቀረቡባቸው ክሶች ከአንድ ዓመት በፊት 8 ሴቶች ባይደን ጾታዊ ትንኮሳ አድርሰውብናል በማለት አደባባይ ወጥተው ነበር። እነዚህ ሴቶች ባይደን ባልተገባ መልኩ ነካክቶናል፣ አቅፎናል አልያም ስሞናል የሚሉ ክሶችን ይዘው ነው የቀረቡት። ይህንን ተከትሎ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ባይደን ከዚህ ቀደም በይፋዊ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ሴቶችን በጣም ተጠግተው ሰላምታ ሲሰጡ የሚያሳዩ ምስሎችን አውጥተው ነበር። በአንዳንድ ምስሎች ላይ ደግሞ ባይደን ሴቶችን በጣም ተጠግተው ጸጉር የሚያሸቱ የሚመስሉ ምስሎችን አሳይተዋል። ከወራት በፊትም ረዳታቸው የነበረች ታራ ሬዲ የተባለች ሴት ባይደን ከ30 ዓመታት በፊት ከግደግዳ አጣብቀው ወሲባዊ ትንኮሳ ፈጽመውብኛል ብላ ነበር። ባይደን በበኩላቸው "ይህ በፍጹም አልተከሰተም" በሚል አስተባብለዋል። ስህተቶችን ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ባይደን በዋሽንግተን ፖለቲካ ውስጥ ረዥም ልምድ አላቸው። 8 ዓመታትን በተወካዮች ምክር ቤት፣ 8 ዓመት ሴናተር በመሆን፣ 8 ዓመት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን አገልግለዋል። ይህ ግን ፕሬዝደንታዊ ምርጫን ለማሸነፍ ሁሌም በቂ አይሆንም። 28 ዓመታትን በሴኔት ውስጥ ያሳለፉት ጆና ኬሪ እንዲሁም 8 ዓመታትን በሴኔት እንዲሁም 8 ዓመታት ቀዳማዊት እመቤት ሆነው ያገለገሉት ሂላሪ ክሊንተር ከነሱ ያነሰ የፖለቲካ ልምድ ባላቸው እጩዎች ተሸንፈዋል። የባይደን ደጋፊዎች ግን ባይደን ይህ እጣ እንደማይገጥማቸው ተስፋ አድርገዋል። ረዥም ታሪክ ባይደን ባለፉት አስርት ዓመታት በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ በተላለፉ ቁልፍ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ውስጥ ተሳትፎ አላቸው ወይም ተሳትፎ እንዳላቸው ይነገራል። ይህ ታዲያ አሜሪካ አሁን ባለችበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ በጥሩ መልኩ የሚታይ አይደለም። ለምሳሌ እአአ በ1970ዎቹ በአሜሪካ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ጥቁር እና ነጭ ተማሪዎችን ለማሰባጠር ተማሪዎች ከሚኖሩባቸው ቦታዎች በአውቶብስ በሟጓጓዝ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመመደብ የተደረገውን ጥረት ተቃውመው ነበር። በዚህም ዘንድሮ ባካሄዱት የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሲተቹ ቆይተዋል። እአአ 1991 ላይ የባህረ ሰላጤውን ጦርነት ተቃውመው እአአ 2003 ላይ አሜሪካ ኢራቅን እንደትወር ደግፈዋል። መልሰው ደግሞ ባይደን አሜሪካ ወደ ኢራቅ መሄዷ ትክክል አልነበረም በማለት ትችት ሲሰነዝሩ ተሰምተዋል። አሳዛኝ ክስተቶች ባይደን ባለቤታቸውን እና ሴት ልጃቸውን በመኪና አደጋ ምክንያት በሞት ተነጥቀዋል። ባይደን የመጀመሪያ የሴኔት ድላቸውን ተከትሎ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ባለቤታቸው የመኪና አደጋ አጋጥሟቸው ነበር። ባለቤታቸው እና ሴት ልጃቸው ሕይወታቸው ሲልፍ ሃንተር እና ቤኡ የተባሉት ሁለት ወንድ ልጆቻቸው ላይ ጉዳት ደርሷል። ቤኡ እአአ 2015 ላይ በአእምሮ ኢጢ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ስልጣን፣ ሙስና እና ውሸት? በሕይወት ያለው ቀሪው ልጃቸው ሃንተር ጠበቃ ሆነ። ገንዘብ ግን ሕይወቱን ከቁጥጥር ውጪ አደረገበት። ከዚያም ሃንተር ከባለቤቱ ጋር ተፋታ። በፍቺው ወረቀት ላይ የሃንተር የቀድሞ ባለቤት ሃንተር አልኮል እና አደንዛዥ እጽ እንደሚጠቀም እንዲሁም የምሽት መዝናኛ ክበቦችን እንደሚያዘወተር ገልጻለች። ሃንተር በተደረገለት ምርመራ ኮኬይን በሰውነቱ ውስጥ በመገኘቱ ከአሜሪካ ጦር ባህር ኃይል ተጠባባቂነት ተሰርዟል። ከዛም ሃንተር ባለፈው ዓመት አንድ ሳምንት ብቻ ካወቃት ሴት ጋር ትዳር መስርቷል። ይህም የመገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። የዩክሬኑ ጉዳይ ሃንተር በዩክሬን ብዙ ገንዘብ የሚያስከፍል ስራ አግኝተው ነበር። ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ ሃንተር በዩክሬን ሙስና ፈጽሟል በሚል ምርመራ እንዲደረግ የዩክሬን መንግሥት ላይ ጫና አሳድረዋል ተብሏል። ትራምፕ የዩክሬኑ አቻቸው ዜሌኔስኪ ጋር ስልክ ደውለው፤ የጆ ባይደን ልጅ ሙስና ስለመፈጸሙ እንዲያጣሩ ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር።
news-53564188
https://www.bbc.com/amharic/news-53564188
ሳይንስ፡ ፅንስን ከማህፀን ውጪ በማሳደግ ፈር የቀደደችው ሳይንቲስት
ፅንስን ከማህፀን ውጭ እንዲዳብር በማድረግ ኢንትሮ ፈርትላይዜሽን የሚባለውን የሥነ ተዋልዶ ዘዴ ለዓለም ያስተዋወቀች የመጀመሪያ ሴት ሳይንቲስት ብትሆንም ስሟን የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው።
ወቅቱ በጎርጎሳውያኑ 1944 ነበር፤ የአርባ ሦስት ዓመቷ የላብራቶሪ ቴክኒሺያን ሚሪያም መንኪን የስምንት ወር ልጇን ስታባብል እንቅልፍ በአይኗ አይዞርም ነበር። ልጇ ጥርስ እያወጣች በመሆኑ ህመሙ እየጠዘጠዛት ህፃኗ መተኛት በመቸገሯ ነው እናቷን ያስቸገረቻት። ሚሪያም ቀደም ባሉት ስድስት ዓመታት እንዳደረገችው ሁሉ ሲነጋ ወደ ላብራቶሪ አቀናች። ዕለቱ ረቡዕ ነበር፤ እንደ ቀድሞው የሴት እንቁላልና የወንዱን ዘር ዘርጋ ባለ የብርጭቆ ሳህን ላይ አዋሃደችውና አንድ እንዲሆኑም ጸለየች። የሃርቫርድ የሥነ ተዋልዶ ባለሙያው ጆን ሮክ እንደሚለው የሚርያም ሙከራ ከማህፀን ውጭ እንቁላሉና ዘሩ ተዋሕዶ ፅንስ የሚሆንበትን ለማየት ነበር። መውለድ ላልቻሉ መካን ሰዎችም መፍትሄ የተጠነሰሰውም በዚህ ወቅት ነው ይላል። በጎርጎሳውያኑ 1944 ከማሕፀን ውጭ የዳበረው ፅንስ አብዛኛውን ጊዜ እንቁላሉንና የወንዱን ዘር ለሰላሳ ደቂቃ ያህል አንድ ላይ በማድረግ ውህደት እንዲፈጥሩ ትጠብቃለች። በዚህች ቀን ግን እንዲያ አልነበረም። ከዓመታት በኋላ ምን እንዳነሳሳት ተጠይቃ በተናገረችበት ወቅት "በጣም ድካም ተጫጭኖኝ ነበር፤ እንቅልፍ እንቅልፍ እያለኝ የነበረ መሆኑንም አስታውሳለሁ። የወንዱ ዘር በእንቁላሉ አካባቢ የሚያደርገውን ምልልስ በማይክሮስኮፑ እያየሁ ሰዓቱን ማየት ዘነጋሁ። ለካ ከአንድ ሰዓት በላይ አልፏል። እናም በሌላ አነጋገር ከስድስት ዓመታት ሙከራ በኋላ የተሳካልኝ ድንገተኛ ዘዴን ፈጥሬ ሳይሆን በሥራ ላይ እንቅልፌ ስለመጣ የተፈጠረ አጋጣሚ ነው" ብላለች። አርብ ዕለትም ወደ ላብራቶሪው ስትመጣ ተአምር የሆነውን ክስተት ተመለከተች። ህዋሳቱ አንድ ላይ ተዋህደው የብልቃጥ ፅንስ ምን ሊመስል እንደሚችልም አየች። የሚሪያም ግኝት በሥነ ተዋልዶ ቴክኖሎጂ ላይ አብዮትን በማምጣት መውለድ ላልቻሉ ሴቶች ፅንስ በብልቃጥ ውስጥ እንዲዳብር እንዲሁም ሳይንቲስቶች የሰውን ልጅ ጥንስስ ከጅምሩ እንዲመለከቱ ፈር ቀዷል። በጎርጎሳውያኑ 1978ም የመጀመሪያዋ የብልቃጥ ልጅ ሊውስ ብራውን በኢንቪትሮ ፈርቲላይዜሽን መንገድ ህይወት ዘራች። ሚርያም ከአስራ ስምንት በላይ ሳይንሳዊ ፅሁፎችን በግሏ እንዲሁም በጋራ አበርክታለች። ከእነዚህም መካከል በመጀመሪያው ከማህፀን ውጪ የሚደረግ ፅንስን በተመለከተ ሁለት ታሪካዊ የሚባሉ ሪፖርቶችንም በሳይንስ ጆርናል ላይ አሳትማለች። ነገር ግን አብሯት ፅሁፉን እንደፃፈው ጆን ሮክ ምንም አይነት እውቅና አልተቸራትም። በሩትገርስ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁርና 'ዘ ፈርቲሊቲ ዶክተር፤ ጆን ሮክ ኤንድ ዘ ሪፕሮደክቲቨ ሪቮሊዩሽን' የፃፉት ማርጋሬት ማርሽ ሚርያም ለጆን ሮክ ከረዳት በላይ እንደነበረች ይናገራሉ። "ጆን ሮክ የህክምና ዶክተር ነው የነበረው። ሚርያም ግን ሳይንቲስት ነበረች። የአዕምሮዋ ምጡቅነት፣ አስተሳሰቧ እንዲሁም እንደ ሳይንቲስት ፕሮቶኮሎች ያላቸውን ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተከትላለች" ብለዋል። ትውልድና እድገት ሳይንቲስቷ ሚርያም በጎርጎሳውያኑ ነሐሴ 8/1901 በላቲቪያ ዋና ከተማ ሪጋ ተወለደች። ገና በጨቅላነቷ ነው ቤተሰቦቿ ወደ አሜሪካ የተሰደዱት። አባቷም ዶክተር ሆነው አገልግለዋል። በሳይንሱ ላይ ከፍተኛ ዝንባሌ በህፃንነቷ ያሳየችው ሚርያም ከኮርኔል ዩኒቨርስቲ በህዋሳት ጥናት እና በሰው ልጅ አካላት አፈጣጠር ዙሪያ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በ1922 አገኘች። በቀጣዩም ዓመት በዘረ መል ጥናት ከኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ የማስተርስ ዲግሪዋን ሰርታለች። በኒውዮርክም ባዮሎጂ እና የአካላት ጥናትን ትምህርቶችን በኒውዮርክ አስተምራለች። የህክምና ትምህርቷን ለመከታተል በወሰነችበት ወቅትም የመጀመሪያው መሰናክል አጋጠማት። ከፍተኛ ስም ያላቸው ሁለት ዩኒቨርስቲዎች አልቀበልም አሏት። ይህም የሆነው ሴት በመሆኗ ነበር። በወቅቱ ሴቶችን ተቀብለው የሚያስተምሩ በጣም ጥቂት ዩኒቨርስቲዎች ሲሆኑ እነሱም ጥብቅ ኮታ ነበራቸው። ትዳር ትምህርቱንም ወደ ጎን በመተው የቀድሞ የክፍል ጓደኛዋና በወቅቱም በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የህክምና ተማሪ የሆነውን ቫሊ መንኪንን አገባች። ሚሪያም ባሏን ጥናቱን እስኪያጠናቅቅ ለመደገፍም በፀሐፊነት ተቀጥራ ትሰራ ነበር። ከአካዳሚው ጋር ቀረብ ብላም በባክቴሪያዎች ላይ እንዲሁም ከሥነ ተዋልዶ ጋር የተያየዙ ኮርሶችን ወስዳለች። ባለቤቷም በሚያደርገው ሙከራም ላይ በላብራቶሪ ሥራዎች ትደግፈው ነበር። በዚህም ወቅት ነበር የሃርቫርዱን የባዮሎጂ ምሁር ግሪጎሪ ፒንከስ የተዋወቀችው። ግሪጎሪ ከጆን ሮክም ጋር ፈር ቀዳጅ የተባለውን የእርግዝና መከላከያን ሰርቷል። ግሪጎሪ ከፒቱታሪ ከተባለው ዕጢ ላይ ሁለት መሰረታዊ ሆርሞኖችን በመውሰድ ሴት ጥንቸሎችን እንድትወጋቸው ትዕዛዝ ይሰጣታል። ይህም ጥንቸሎቹን ተጨማሪ እንቁላሎችን ለውፃት (ovulate) እንዲያዘጋጁ ያስችል እንደሆነም ለማየት ነበር። የፅንስ ማዳበር ሙከራዎች በዚህም ወቅትም ነበር የሥነ ተዋልዶ ስፔሻሊስት ነኝ በሚል ጆን ሮክ የግሪጎሪን ጥናት ወደ ክሊኒክ ምርምር ለማድረግ ሃሳብ ያቀረበው። በየቀኑ ማክሰኞ ጥዋት ሁለት ሰዓትም ሚርያም ማሳቹስተስ፣ ቦስተን በሚገኘው ለሴቶች የነፃ ህክምና አገልግሎት በሚሰጠው ሆስፒታል ቀዶ ጥገና በርም ላይ ታንዣብብ ነበር። እድለኛ ከሆነችም ጆን ሮክ ከህመምተኞች ላይ በቀዶ ጥገና ያስወገደውን የእንቁልጢ አካል (የእንቁላል ከረጢት) ይሰጣት ነበር። እንደምታስታውሰውም በጣም ደቃቃ ከመሆናቸውም አንፃር "ትንሽዬ የኦቾሎኒ ፍሬ ያክላሉ" ትላለች። ከዚያም እንቁልጢውን በመውሰድ ትቀደውና እንቁላል ትፈልጋለች። በየሳምንቱም ማክሰኞ እንቁላል ትፈልጋለች፣ ረቡዕ ከወንዴው ዘር ጋር ትቀላቅለዋለች፣ ሐሙስ ትፀልያለች፣ አርብ ደግሞ ውጤቱን ትከታተላለች። ስድስት ዓመት በሙከራ በየሳምንቱ አርብም ውህዱን የምታስቀምጥበትን መቀፍቀፊያውን ስትመለከት የምታየው ነገር ቢኖር አንድ ህዋስ ብቻ ነው - ያልዳበረ እንቁላልና የሞቱ በርካታ የወንድ ዘሮች። ይህንንም ሙከራ ለስድስት ዓመታት ያህል ለ138 ጊዜ ያህል አከናውናለች። የ1944 የካቲት ወር እድለኛ አርብ ግን ሁኔታዎችን ቀየረች። መቀፍቀፉፊያውን ስታይ ያልጠበቀችው ውህድ ተፈጥሮ አየች፤ በድንጋጤና በደስታ ተውጣም የጆን ሮክን ስም ጠራች። ጆን ሮክ ብቻ ሳይሆን ላብራቶሪው ይህንን ተአምር ለመመልከት በመጡ ሰዎች ተሞላች "ሁሉም ይሄንን ከማህፀን ውጪ የተፈጠረውን ፅንስና የሰው ልጅ ጥንስስ ለማየት እየተሯሯጡ መጡ" ትላለች። ሚርያም በኋላም እንደፃፈችው "ይህንን ድንቅ የሆነ ግኝት፣ ፅንስ ከአይኔ ለደቂቃም ቢሆን ዘወር እንዲል አልፈለግኩም። ለስድስት ዓመታት ያህል የደከምኩበት፤ ብዙ ያልተሳኩ ህልሞችና ቀናት ማስታወሻዬ ነው" በሚል አስፍራለች። ይህ የዳበረ ዕንቁላልም እንዳይበላሽ በሚል ፈሳሽ ጠብ እያደረገች ነበር። ለሰዓታትም ያህል በእንቁላሉ ፈሳሽ ጠብ ከማድረግ ወደኋላ አላለችም። ሲርባትም በአንድ እጇ ሳንድዊች እየበላች በሌላ እጇ ሳታቋርጥ ጠብ እያደረገች ሙሉ ሌሊቱን አደረች። እንዲህ ተግታ ብትሰራም የመጀመሪያዋ ሙከራ ግን አልተሳካም። እሷ እንደምትለው "በብልቃጥ ውስጥ የተከናወነ የመጀመሪያ የፅንስ መጨንገፍ" በማለትም በፀፀት ታስታውሰዋለች። ከዚያ በኋላ ግን ሙከራዋን ሦስት ጊዜ ሞክራዋለች። በዚህም መካከል ድንገትም ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ። ባለቤቷ ሥራውን አጣ። እናም ተከትላው በሰሜን ካሮላይና ወደሚገኘው ዱክ ዩኒቨርስቲ አቀናች። በዚህ ዩኒቨርስቲ ፅንስን ከማህፀን ውጪ ማዳበር እንደ ትልቅ ነውር የሚታይ በመሆኑ ሥራዋን መቀጠል አልቻለችም። ያለ ሚርያምም አስተዋፅኦ በቦስተን የሚገኘው በብልቃጥ ውስጥ የሚደረገው ምርምር ፍሬ ሳያፈራ ቀጥ አለ። የጆን ሮክ ሌሎች ረዳቶች ከማሕፀን ውጪ ፅንስ ማዳበር አልቻሉም። የኑሮ ትግል ላብራቶሪ ማግኘትም ባትችልም ከሩቅ ሆና ከጆን ሮክ ጋር አብራ መስራቷን ቀጠለች። በጎርጎሳውያኑ 1948ም የተገኘውን ግኝት ሚርያም መሪ ፀሐፊ በመሆን ሙሉ ሪፖርቱን በጋራ አሳተሙ። ነገር ግን ምርምሯን ለመቀጠል መሰናክሎች ገጠሟት። ለዓመታት ባለቤቷን ልትፈታ ብታስብም በይደር አቆይታው የነበረ ቢሆንም ችግሮች መጥናት ጀመሩ። ገንዘብ ይከለክላት ነበር ልጆቿ ሉሲና ገብርኤል ፊትም እደበድብሻለሁ እያለ ያስፈራራት ነበር። የባለቤቷን ባህርይ መቋቋም ሲያቅታትም ቤቷን ትታው ወጣች። ነገር ግን ህይወት ቀላል አልነበረም፤ ብቸኛ እናትም ሆና ልጆቿን ማሳደግና ሌሎች ወጪዎችንም መሸፈን ነበረባት። ወደ ቦስተን መልስ በ1950ዎቹ ሚርያም የሚጥል በሽታ ያለባትን ልጇን የተለየ ፍላጎት ትምህርት ቤት ለማስገባት በሚል ወደ ቦስተን ተመለሰች። በቦስተንም ከቀድሞ የላብራቶሪ አጋሯ ጆን ሮክ ጋር ተገናኘች። ነገር ግን ባለፉት አስር ዓመት ብዙ ነገር ተቀይሮ ጠበቃት። የሥነ ተዋልዶ ዋና ትኩረቱ ልጆች እንዲወለዱ መስራት ሳይሆን በርካታ ልጆች እንዳይወለዱ መከላከል ላይ ነበር። ጆን ሮክም ዋና ትኩረቱንም ለሴቶች በቀላሉና ምቹ በሆነ ሁኔታ የሚወስዱትን የእርግዝና መከላከያን መስራት ነበር። የየእርግዝና መከላከያን መጠቀምም በጎርጎሳውያኑ 1960 ፈቃድ አገኘ። ሚሪያም መንኪንና ልጇ ሉሲ ጆን ሮክ ትኩረቱን በሙሉ በሙከራው ውጤት ላይ አድርጎ ሲሰራ ሚርያም ደግሞ ከጀርባ ሆና "እንደ ረዳት" ትሰራ ነበር። የተለያዩ የምርምር ርዕሶችን በማምጣትም በጃፓን የሚደረገውን የወንድ ዘርን በማቀዝቀዝ መካንነትን ለማስቀረት የሚሰራው ሥራም ላይ ፅሁፎችን አበርክታለች። የሴቶች የወር አበባ ዑደት በብርሃን መረጋጋት ይችል ይሆ? እንዲሁም ጠበቅ ያሉ የወንድ ሙታንታዎች በወንዶች ላይ ጊዜያዊ መካንነት ያስከትላሉ በሚሉ ርዕሶችም ላይ ሳይንሳዊ ፅሁፎችን ፅፋለች። ምንም እንኳን እነዚህ ርዕሶች መጀመሪያ ትመራመርበት ከነበረው ፅንስን ከማህፀን ውጪ ማዳበር ራቅ ያለ ቢመስልም የመጨረሻ ግቡ ግን ተመሳሳይ ነው። እንደ ጆን ሮክ በሥነ ተዋልዶ ላይ ያሉ ምስጢራዊ ነገሮችን የሳይንስን ልህቀት በመጠቀም ለመፍታት ሞክራለች። ሚሪያም መንኪን ህይወቷ በተለየ አቅጣጫ ቢሄድ ለምሳሌ ጨቋኝ ባለቤቷን ባታገባ፣ ዶክትሬቷን ለመማር እድል ብታገኝ ከዚህ በበለጠ ማበርከት ትችል ነበር የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ባይቻልም፤ ሳይንቲስቷ የነበራትን የአዕምሮ ምጥቀት በጊዜው በነበረው የሴቶች ቦታ ሊረዷት እንዳልቻሉ ማርጋሬት ይናገራሉ።
news-47772443
https://www.bbc.com/amharic/news-47772443
ሕዝብ ስለመሪው ምን እንደሚያስብ እንዴት እንወቅ?
በኢትዮጵያ የሕዝብ አስተያየት የሚሰፈርበት ዘመናዊ ቁና የለም። በመሆኑም ድምዳሜ ላይ የምንደርሰው በነሲብ ነው። ወይም ደግሞ ከአንዳንድ ኩነቶች በመነሳት…።
ለምሳሌ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች በሚቀነቀን ጯኺ አጀንዳና ምላሹ…፤ ለምሳሌ ከተሳካ የመሪ ቃለ ምልልስ ወይም የመድረክ ላይ ንግግር። አንዳንድ ያልሰመሩ የመሪ ንግግሮች ፖለቲካዊ ጡዘት ያከራሉ፤ አንዳንድ የሰመሩ የመሪ ቃለ ምልልሶች ፖለቲካዊ ትኩሳትን ያበርዳሉ። • በ2018 ጎልተው የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዞሮ ዞሮ የመሪ ቅቡልነት በምን እንደሚመተር የሚያውቅ የለም። "ሕዝቡ'ኮ እያለን ያለው…" ብለው ዲስኩር የሚጀምሩ ፖለቲከኞች ግን እልፍ ናቸው…ፓርቲ ይቁጠራቸው። ሕዝቡን በምን ሰምተውት ይሆን? ቀደም ባለው ጊዜ አውቶቡስና ውይይት ታክሲ ሳይቀር፣ የዕድርና ልቅሶ ድንኳኖችን ጨምሮ ሕዝብ ስለ መሪው እንዴት እያሰበ ነው ለሚለው ረቂቅ ጥያቄ ባህላዊ መስፈሪያዎች ነበሩ። በአያቶች ዘመን ደግሞ "እረኛ ምናለ?" ይባል ነበር፡፡ አሁንስ? የመሪዎቻችንን ተወዳጅነት የምንለካበት አገራዊ ማስመሪያ አለን? ስሙ ማን ይባላል? "የበይነመረቧ ኢትዮጵያ" ኢትዮጵያ ተብላ የምትጠራው አገር ከፌስቡክ እንደምትሰፋ እንዳንረዳ የጋረደን ምንድነው? አንዱ ምክንያት ሁነኛ የሕዝብ የልብ ትርታን መስፈሪያ (Opinion Poll) ማጣታችን ይሆን? አቻ አገራዊ ቃል ያልተበጀለት "ፖሊንግ" ለምዕራቡ የቢሊዮን ዶላር ቢዝነስ ነው። የፖሊንግ ጥናት ማጠንጠኛ ሁልጊዜም አንድ ነገር ነው፤ "ሕዝብ ስለ አንድ ጉዳይ እንዴት ያስባል?" የሚል ምላሽ ማግኘት። ይህ ዳሰሳዊ ጥናት ታዲያ ውጤቱ በዋዛ አይታይም። የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ያስቀይራል፣ ምርጫን ያጎናል፣ ምጣኔ ሀብትን ያዛንፋል፣ በጀት ያስቀይራል፣ ቁልፍ ወታደራዊና ወንዛዊ ጂኦ ፖለቲካን ያተረማምሳል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወታደሮቹ ድርጊት ተበሳጭተው እንደነበር ተናገሩ በተቀረው ዓለም "ፖሊንግ" የመሪዎቻቸውን ቅቡልነት ብቻም ሳይሆን የመራጩን ሕዝበ-ልበ-ትርታ የሚለኩበት ስቴትስኮፓቸው ነው። እኛ ያ የለንም። ሐሳብ ጠፍጥፈው ጋግረው ለገበያ በሚያቀርቡ ጥቂት የማኅበራዊ ትስስር መድረኩ "ጄኔራሎች" ናቸው። በነርሱ ስፌት ልክ አገሪቱን እናያታለን። ስለዚህ ትጠብብናለች፤ ትፈርስብናለች። ከዚያ ተነስተን የእልቂት ነጋሪት የተጎሰመ ያህል እንሸበራለን። አቶ ኢፌራ ጎሳ ምናልባትም ለዚህ "ፖሊንግ" ለሚባለው የዳሰሳ ጥናት ቅርብ ከሆኑ ኢትዮጵያዊን መካከል አንዱ ሳይሆኑ አይቀሩም። ለምን ቢባል ለ26 ዓመታት ማኅበራዊ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የሚታወቀውን ዋስ ኢንተርናሽናል ኩባንያን በምርምር ዳይሬክተርነት መርተዋል። "ኢትዮጵያን መሬት ካልወረድን አናገኛትም" ሲሉ ይደመድማሉ። ለዚህ ድምዳሜ ያበቃቸው ታዲያ በጎ በጎውን ማየት ስለሚሹ ሳይሆን ደረቅ አሐዝ ነው። "ንቁ የኢንተርኔት ተጠቃሚው እኮ ከሕዝቡ ሁለት በመቶም አይሞላም" ይላሉ። እንዴት ሆኖ? "በተጨባጭ ስናወራ ቴሌ 50 ሚሊዮን ስልክ ተጠቃሚ አለ ብሎ ነበር። አሁን ወደ 30 ሚሊዮን አውርዶታል። ከዚያ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚ 20 በመቶው ነው። እኛ በተለያየ መንገድ ባደረግነው ጥናት ግን 10 ከመቶም አይሆንም። ከ10 ከመቶው ውስጥ በየጊዜው ኢንተርኔት የሚበረብር ንቁ (አክቲቭ) ተጠቃሚ 'የ10 ፐርሰንቱ 10 ፐርሰንት' ነው። በዚህ ስሌት ከሄድን እጅግ ትንሹ ቁጥር ላይ እንደርሳለን" ይላሉ አቶ ኢፌራ። የፌስቡኳ ኢትዮጵያ መሬት ላይ ማግኘት እንዴት ከባድ እንደሆነ ሲያስረዱም፣ "እኛ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን በየገጠሩ ሄደን፣ በር አንኳኩተን 'ደህና አደራችሁ?' ብለን ቃለ መጠይቅ ስንሰራ ኢንተርኔት ላይ ያለችውን አስፈሪዋን ኢትዮጵያን አይደለም የምናገኘው።" • የዶክተር ዐብይ አሕመድ 'ፑሽ አፕ' ሰው ፌስቡክ አካውንቱን ሳይሆን ጎረቤቱን ቢመለከት ይበልጥ ኢትዮጵያዊያንን ያውቃል። ያም ሆኖ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፖለቲካዊ ትኩሳት የሚለካ ቴርሞሜትር እስከዛሬም የለንም። ስለዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቅቡልና ልንሰፍረው ይቸግረናል። ለምን ግን "ፖሊንግ" እስከዛሬ ሳይኖረን ቀረ? "ፖሊንግ ማካሄድ ወንጀል ነበር" የዐቢይን አንድ ዓመት የሥልጣን ልደት አስመልክቶ አንዳንዶች "ፖሊንግ" የሚመስል ነገር አሰናድተው መጠይቅ ለማስሞላት ግላዊ ጥረት ሲያደርጉ ታዝበናል። ሌሎች ደግሞ የጠቅላዩን የከፍታና የዝቅታ ነጥቦች በሰንጠረዥ አስፍረው ማኅበራዊ ሰሌዳዎች ላይ ሲለጥፉ ነበር። ይህ ብዙ የሚነግረን ነገር አለ። አንድ አስፈላጊ ነገር ግን ሁሉም ሰው የረሳው ተቋም። የሕዝብ ልብ ትርታን የሚመትር የማኅበራዊ ጥናት ተቋም። ዋስ ኢንተርናሽናል ለትልልቅ ዓለማቀፍ የጥናት ድርጅቶች ጭምር መረጃ የሚለቅም አገር በቀል ኩባንያ ነው። ከእውቁ ጋሎፕ ፖሊንግ ጋር በሽርክና ሠርቷል። ዋስ መሬት ላይ ወርዶ ዘርፈ ብዙ ጥናቶችን በማካሄድ የሁለት አስርታት ልምድ አለው። በዚህ ሁሉ ዘመን ታዲያ የአቶ መለስንም ሆነ የአቶ ኃይለማርያምን ሕዝባዊ ቅቡልነትን ሰፍሮ አያውቅም። ለምን? የዋስ ባለድርሻና ተመራማሪ አቶ ኢፌራ "ፖሊንግ (የሕዝብ ስሜት ዳሰሳ ጥናት) በኢትዮጵያ ክልክል ሆኖ ቆይቷል" ይላሉ። በመሆኑም ለረዥም ዓመታት ፖሊንግ በኢትጵያ እንደ ወንጀል ነበር የሚታየው። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም "እንኳንስ የአገር መሪን መስፈር (rate ማድረግ) ይቅርና ስለ ጤና ሽፋን ወይም ስለመልካም አስተዳደር የዳሰሳ ጥናት ለማድረግም የመንግሥት ፍቃድ ይጠየቃል።" አቶ ኢፌራ ጨምረው እንደነገሩን የጥናት ኩባንያቸው ዋስ ኢንተርናሽናል ለእውቁ "ጋሎፕ ኢንተርናሽናል" በውክልና ማኅበረሰባዊ ጥናቶችን ሲያደርግ የመጠይቅ ወረቀቱ መዘርዝር ሳይቀር ሳንሱር ይደረግበት ነበር። ፖለቲካ ዘመም ጥያቄዎች ተለቅመው "እነዚህን ጥያቄዎች አውጡ እንባል ነበር" ይላሉ። ፖሊንግ ምን ይፈይድልናል? አንድ ፓርቲ ለሕዝብ ቃል ገብቶ ነው ምረጡኝ የሚለው። ምረጡኝ ለማለትም መራጩ ምን እንደሚፈልግ ማወቅን ይጠይቃል። ሕዝቡ ከመሠረታዊ ፍላጎቶች ባሻገር ምን እንደሚፈልግ እንዴት ማወቅ ይቻላል? አንድ ፓርቲ ከተመረጠም በኋላ ሥልጣን ላይ ወጥቶ ከሕዝብ ጋር ሆድና ጀርባ መሆኑን ሳያውቀው ዓመታትን ሊያስቆጥር ይችላል። ጆሮ ለራሱ ባዳ አይደል? ይህን ለማስረዳት እንደ ኢህአዴግ ጥሩ ምሳሌ የለም። በ97 ምርጫ ኢህአዴግ ምን ሰይጣን አሳስቶት ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ እንደወሰነ ባይታወቅም አንዳንድ በድኅረ ምርጫው የተጻፉ መጣጥፎች ግን ፓርቲው ራሱን በሕዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅና ተመራጩ ፓርቲ አድርጎ የማየት ዝንባሌ እንደነበረው የሚጠቁሙ ናቸው። በምርጫው የደረሰበት ስብራት ዛሬም ደረስ ያልጠገገው ለዚያ ይሆናል። "ፖሊንግ" ቢኖር ምናልባትም ያ የዚያን ጊዜ እምነቱ አሸዋ ላይ የተገነባ እንደነበር የማወቅ ዕድል ይኖረው ነበር። • የመደመር ጉዞ ወደ አሜሪካ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ 108 የደረሱት ፓርቲዎች ሕዝባቸው ምን እንደሚያስብ የሚያውቁበት መንገድ አለ ተብሎ አይገመትም። ስላንተ አንተ ከምታውቀው በላይ እናውቅልሀለን የሚሉበት እርግጠኝነት ግን አሳሳቢም አስፈሪም አደገኛም ነው። "ያንተን ጉዳይ ላስፈጽም ነው ሥልጣን ላይ የወጣሁት የሚል መንግሥት፣ ጥያቄህን ለመመለስ ነው የምፎካከረው የሚል ፓርቲ የሕዝቡን የልብ ትርታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይለት ዳሰሳ ጥናት (ፖሊንግ) ሳያካሄድ እንዴት አውቅልሀለሁ ለማለት ይቻለዋል?" ሲሉ ተገርመው ይጠይቃሉ አቶ ኢፌራ። የመጀመሪያዋ "ፖሊንግ" 26 ዓመት ዳሰሳ ጥናት ሲያደርግ የቆየው ዋስ፣ በዓመት በአማካይ ሰማንያ የጥናት ፕሮጀክቶችን የሚያካሄደው ዋስ፣ በዓመት ለመቶ 20 ሺህ ሰዎች መሬት ወርዶ መጠይቅ የሚያስሞላው ዋስ በዚህ ሁሉ የዕድሜ ዘመኑ "ፖሊንግ" የሠራው አንድ ጊዜ ነው። እርሱም የዐቢይን ወደ ሥልጣን መምጣትን ተከትሎ ባለፈው ግንቦት። ፖሊንጉ እንዲሠራ ያዘዙት ራሳቸው ዐብይ አሕመድ ወይም መንግስታቸው ይሆኑ? አቶ ኢፌራ ድርጅታቸው ነገሩን በራስ ተነሻነት እንዳደረገው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። "በአጋጣሚ የሚዲያ ዳሰሳ ጥናት በ12 ከተሞች እያደረግን ነበር" በዚያውም ለምን በነዚሁ ለቃለ መጠይቅ በተመረጡ ናሙናዎች ላይ የዐቢይን የቅቡልነት ከፍና ዝቅ አንመትርም ብለው ተነሱ። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በ100 የሥራ ቀናት የት የት ሄዱ? ምን ምን ሠሩ? ሀሳባችን የነበረው አንድም ስለ ፖሊንግ በኅብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ለመፍጠር ነበር፤ "በዚያ ላይ ለሌላ የሚዲያ ጥናት በተሰናዳ ሪሶርስ ስለነበር መጠይቁን ያደረግነው ብዙም ወጪ አላስወጣንም።" ነገር ግን ያስነሳው አቧራ እግረ መንገድ የተሰራ ፖሊንግ አላስመሰለውም። ብዙ ሰዎች ማናቹ እናንተ? ምን ቤት ናችሁ? ሲሉ የተቿቸው ነበሩ። "በዚያው መጠንም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀሩ የእኛን ጥናት እንደ መነሻ ሲጠቀሙበት ነበር።" በዚህ ዋልታን በረገጠና በሚፋጅ ፖለቲካ ውስጥ ፖሊንግ መስራት ፈታኝ አይሆንም ግን? አቶ ኢፌራ እንደሚሉት አንድ የተማረ ሰው አንድን ሪሰርች ውጤቱን አይደለም የሚጠይቀው፤ ቀድሞ በምን መንገድ ተሰራ ብሎ ነው የሚጠይቀው። ገለልተኝነት፣ የናሙና መረጣ፣ የመዘርዝር ጥያቄዎች ቅንብር፣ ግልጽነትና ይዘት፣ ወደ ውጤት የተኬደበት ቀመር ለፖሊንግ መታመን ወሳኝ ግብአቶች ናቸው። ፖሊንግ መቶ በመቶ ስለ አንድ ሕዝብ ፍላጎት እቅጩን ላያውቅ ይችላል። ሆኖም ሳዊንሳዊነቱን ጠብቆ ከተተገበረ ለእውነታው የቀረበ ነው። በፖሊንግ የተሰሩ የምርጫ ትንበያዎች ከአየር ሁኔታ ትንበያ ባልተናነሰ ሐቀኛ የሚሆኑትም ለዚያ ነው። ሆኖም ይሄ ሕዝብ ቅኔ ነው። ንጉሡን "ሌባ" እያለ በቮልስዋገን የሸኘ፤ አቶ መለስን "አባይን የደፈረ" ከሚለው "ባንዲራን የደፈረ" እስከሚለው ዜጋ ድረስ ከል ለብሶ፣ አንቆለጳጵሶ የቀበረ፣ ያከበረ፤ ዓለም የመሰከረላቸውን አምባገነን "መንጌ ቆራጡ" እያለ የሚናፍቅ ሕዝብ ነው። እንዲህ ሰምና ወርቅ ለሆነ ሕዝብ ‹‹ፖሊንግ›› ምን ያህል የልብ አውቃ እንደሚሆን ማንም አፉን ሞልቶ መናገር አይችል ይሆናል? ቢሆንም. . . !
52287900
https://www.bbc.com/amharic/52287900
ኮሮናቫይረስ፡ ቤት ጥቃት የበዛበት ሲሆን ወደየት ይሸሻል?
በስፔኗ ግዛት አልማሶራ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ተደርጎ እንዲውለበለብና የሶስት ቀናት ሐዘን ታውጇል። ምናልባት ስፔን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በኮሮና ቫይረስ ከመሞቱ ጋር ሊያያዝ ይችላል። ሁኔታው እንደሱ አይደለም የብዙዎችን ልብ የሰበረው የካሪናን አሟሟት ለማሰብ ነው።
በፍቅር ጓደኛዋ የተገደለችው የ27 አመቷ ሎሬና ኳራንታ ካሪና ከሁለት ልጆቿ ፊት ለፊት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችው በባለቤቷ አማካኝነት ነው። ከገደላትም በኋላ እጁን ለፖሊስ የሰጠ ሲሆን ወንጀሉንም ተናዟል። ከኮሮና በፊት ቢሆን ሰው ተሰባስቦ የ35 አመት እድሜ ያላትን ጎረቤታቸውን ይዘክሯት ነበር። አሁን ግን በኮሮና ምክንያት ቤታቸው የዋሉ ግለሰቦች ግን በርቀት በሃዘን አስበዋታል። ደወልም ተደወለ፣ ልብ የሚሰረስር ሙዚቃም በኦርኬስትራ ታጅቦ ቀረበ፤ የአካባቢው ህዝብ መውጣት ባይችልም በመስኮታቸው እንዲሁም የቻሉት ደግሞ ወደ በረንዳቸው ወጣ ብለው በፀሎት አስበዋታል። ከሳኡዲ አረቢያ የሚመለሱት ስደተኞች በኮሮናቫይረስ ምክንያት አይደለም ኮሮናቫይረስ የዓለም የምግብ አቅርቦት ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ አገራት የኮሮና መዛመትን ለመቆጣጠር ቤት የመቀመጥ ውሳኔ ማሳለፈቸውን ተከትሎ ሴቶች ከጥቃት አድራሾቻቸው ጋር በአንድ ቤት እንዲቆለፉ፣ እርዳታ ከሚለግሷቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት አለመኖር እንዲሁም ማምለጥ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ልጆችም ትምህርት ቤት ስለማይሄዱና ጊዜያቸውን በቤት ውስጥ ስለሚያሳልፉ የነዚህ ጥቃቶች ገፈት ቀማሽ ሆነዋል፤ ለማይሽር ስነልቦናዊ ጉዳቶችም እየተጋለጡ ነው። ካሪና በስፔን ውስጥ በዚህ አመት ብቻ በትዳር አጋሮቻቸው ወይም በቀድሞ አጋሮቻቸው ከተገደሉ ሴቶች መካከል 17ኛዋ ናት። ኮሮናን ለመከላከል ውሳኔዎች ከተላለፉ በኋላ በትዳር አጋሯ የተገደለችው የመጀመሪያ ሴት ሆናለች። ከቤት ጥቃት አድራሽ ፍራቻ፤ ከውጭ ቫይረሱን ፍራቻ- የሁለት አለም እሳት አውሮፓ የኮሮና ቫይረስ ማእከል መሆኗን ተከትሎ ቤት የመቀመጥ እወጃን አስተላልፋለች። ምንም እንኳን ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ የደረሱ ጥቃቶችን በተጠናቀረ መልኩ ማግኘት ባይቻልም ባለሙያዎች ከሚደርሳቸው የተበታተኑ መረጃዎች ማየት እንደሚቻለው ቤት ውስጥ የሚደርሱ ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን ነው። ጭንቀት ጥቃት አድራሾችን የበለጠ ጠብ ጫሪ ያደርጋቸዋል፤ ለሴቶቹ ደግሞ ማንም እንደማይደርስላቸው ሲያውቁ ደግሞ የበለጠ ጨካኝነት ያጠቃቸዋል። ከወር በፊት የቤት መቀመጥ ውሳኔው በስፔን ሲተላለፍ እንደ ኪካ ፉሜሩ ላሉ ባለሙያዎች ምን ያህል ሁኔታው አስከፊ ሊሆን እንደሚችል ጠቋሚ ነበር። በካናሪ አይላንድስ ተቋም እኩልነት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ኪካ "ምንም እንኳን ኮሮና ቫይረስ መዛመትን ለማስቆም ጥሩ መፍትሄ ቢሆንም ጥቃት በሚደርስበት ቤት ውስጥ ላሉ ሴቶችና ልጆች የከፋ ጥቃት ሊደርስባቸው እንደሚችል አመላካች ነው" ይላሉ ከዚህ ቀደምም በነበሩ እንደ ጎርፍ ባሉ ሁኔታዎች ሰዎች ቤት ውስጥ መቀመጥ አስገዳጅ በሚሆንበት ወቅት የሚደርሱ ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምሩም አስተውለዋል። ቻይና ከኮሮናቫይረስ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በቅርብ የታዘበው ኢትዮጵያዊ ዶክተር ጣልያን፡ እንደ ስፔን ጣልያንም በኮሮና ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንዷ ናት። ከመቶ በላይ ዶክተሮች ኮሮናን ሲያክሙ ህይወታቸውን አጥተዋል። በፍቅር ጓደኛዋ የተገደለችው የ27 አመቷ ሎሬና ኳራንታ የ27 አመቷ ሎሬና ኳራንታ ዶክተር ለመሆን የቀራት ጥቂት ጊዜ ነበር፤ ህይወቷ በአጭር ባይቀጭ። እንደ ሌሎች ዶክተሮች በኮሮና አይደለም የሞተችው የፍቅር ጓደኛዋ መግደሉንም ለፖሊስ ተናዟል። አስከሬኗም ወደተወለደችበት ሲሲሊ ፋቫራ ከተማ ሲመለስም ብዙዎች በበረንዳቸው ላይ ነጭ አንሶላ ሰቅለው በኃዘን ተቀብለዋታል። የነጩ አንሶላ ምልክትም ከንቲባ አና አልባ ይገልፁታል " የመንፈሷን ፅዳት እንዲሁም ለዘመናት ህልሟ የነበረው ዶክተር ስትሆን የምትለብሰውን ነጭ መለዮ ልብስ የሚያመላክት ነው።" የቤት ውስጥ ጥቃት ማሻቀብ ፈረንሳይ፦ በፈረንሳይ ከጥቃት ጋር ተያይዞ ለእርዳታ የሚደረጉ ጥሪዎች ብዙም አልነበሩም። ነገር ግን የቤት ውስጥ መቀመጥ አዋጁን ተከትሎ የድረሱልኝ ጥሪ በአጠቃላይ በአገሪቷ በሶስት እጥፍ መጨመሩን መንግሥት አስታውቋል። በተለይም በዋና መዲናዋ ፓሪስ ቁጥሩ ከፍተኛ ሆኗል። መስማት ለተሳናቸው መልእክት መላክ የሚችሉ ሲሆን በቀንም 170 መልእክቶች ጥቃት ከደረሰባቸው ሴቶች ይመጣሉ። በስፔንም ጥቃት ለሚደርስባቸው ሴቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች አስፈላጊና መሰረታዊ ተብለው ከተፈረጁት ውስጥ ሲሆን በመንግሥትም ከፍተኛ ድጋፍ ይቸረዋል። ጥቃት ለሚደርስባቸው ሴቶች የእርዳታ የስልክ መስመሮች የተዘረጉ ሲሆን፤ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት 18 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በፈረንሳይ ከስልክና ከመልእክቶች በተጨማሪ በኢሜይል የሚደርሱ መልእክቶች 286 በመቶ፣ እንዲሁም በዋትስአፕ በዘጠኝ ቀናት ብቻ 168 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ተዘግቧል። ህይወትን የሚታደገው 'ማስክ-19' በስፔን ካናሪ አይላንድስ የሚገኘው የእኩልነት ተቋም 'ማስክ 19' የሚል ዘመቻን ጀምረዋል። ይህም ዘመቻ ጥቃት የደረሰባት ሴት ከቤት የመውጣት መብቷ እንዲከበርላት ያለመ ነው። በአሁኑ ሰአት የመድኃኒት መደብሮች (ፋርማሲዎች) ሰዎች በነፃነት ከሚሄዱባቸው ቦታዎች አንዱ ነው። " አንዲት ሴት በቅርብ ወደሚገኝ ፋርማሲ በመሄድ ማስክ 19 የሚለውን የሚስጥር ቃል ብትናገር- ህይወቷ ይድናል" በማለት የዘመቻው ጠንሳሽ ኪካ ፉሜሮ ያስረዳሉ። 'ባሌ ፀጉሬን ይዞ ከግድግዳ ጋር ያጋጨኛል . . . ' እንዲህ አይነት ሴቶች በሚመጡበት ወቅት የፋርማሲው ሰራተኞች ስማቸውን፣ አድራሻና የስልክ ቁጥራቸውን በመመዝገብ ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ያሳውቃሉ። ሴቶቹ ቤታቸው በመሄድ መጠበቅ ይችላሉ ወይም ፖሊስና እርዳታ አድራሾች እስኪመጡ ድረስ ባሉበት ቦታ ሆነው መጠበቅ ይችላሉ። ቴኔሪፍ በሚባል ግዛት ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት ከጥቃት አድራሽ ጓደኛዋ ጋር ለሁለት ሳምንታት የቆየች ሲሆን ፋርማሲው በመሄድ ኮዱን (የሚስጥር ቃሉን) ተናግራ ወደ ቤቷ ሄደች። በወቅቱ ጥቃት አድራሽ ጓደኛዋ ሁኔታውን ሳያውቅ ከፋርማሲው ውጭ ሆኖ እየጠበቃት ነበር። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም ቤቷ በመሄድ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ወስደዋታል። በስፔኗ ግዛት ግራን ካናሪያ የ78 አመት የዕድሜ ባለፀጋ በባለቤታቸው ተገድለዋል። አሮጊቷ በአገሪቷ ውስጥ በትዳር አጋር የተገደሉ ሁለተኛዋ ሴት ሆነዋል። "በእድሜ ተለቅ ያሉ ሴቶች በትዳር አጋሮቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ሪፖርት ለማድረግ እስከ አስራ አምስት አመታት እንደሚወስዱ" በሴቶች ጥቃት ዙሪያ የመንግሥት ተወካይ የሆኑት ቪኪ ሮዜል ገልፀው " እናውግዘው። ለነሱ ድምፅ እንሁናቸው። ይህም ሕይወትን ይታደጋል" በማለት መልእክታቸን አስተላልፈዋል። የማስክ 19 ዘመቻ ከመላው ስፔን አልፎ፣ በፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ኖርዌይና አርጀንቲና ተግባራዊ በመሆን ላይ ነው። በማድሪድ የሚገኘው የአስፓሺያ ፋውንዴሽን መስራች ቨርጂኒያ ጊል ሴቶች ከጥቃት በተጨማሪ፣ በቫይረሱ የመያዝ ሰቀቀን እንዲሁም ከቤት ወጥተው ሪፖርት ቢያደርጉ ጥቃት አድራሾች የበለጠ ሊጎዱዋቸው እንደሚችሉ ማሰብና የትኞቹ ተቋማት እርዳታ እንደሚሰጡ ለይቶ አለማወቅ ተደራራቢ ችግሮች ብለው ከሚጠቅሷቸው መካከል ናቸው። አንዳንድ ጊዜም ጥቃት አድራሾች በፖሊስ ቁጥጥር ሾር አለመዋላቸውና ኢፍትሃዊ በሆኑ ፍርድ አሰጣጥ ሂደቶች በነፃ መለቀቃቸው ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶችን መከራ ከፍ አድርጎታል። ከኮሮናቫይረስ እያገገሙ ያሉ ምን ይላሉ? የ2 ወጣት ሴቶች ታሪክ የአንዳንድ አገራት አመርቂ ስራዎች በሩሲያ፦ ነዋሪነቷን ያደረገችው ማሪያ (ስሟ ተቀይሯል) ጥቃት በደረሰባት ወቅት ከቤት ልውጣ አልውጣ በሚል መንታ ሃሳብ ልቧ ቆመ። ከዚህ በፊት ባለቤቷ ምንም አይነት ጥቃት አድርሶባት ባያውቅም የቤት መቀመጥ ውሳኔ መታወጁን ተከትሎ በአንደኛው ቀን ለአስራ ስምንት ሰአታት የቆየ ጥቃት ፈፀመባት። "በመጀመሪያ ስድብ ነበር። ከዚያም እቃ መሰባበር፣ በኋላም እቃ እያነሳ በኔ ላይ እንዲሁም ልጆቼ ላይ መወርወር ጀመረ" በማለት ለቢቢሲ የተናገረችው ማርያ " ቤት ውስጥ አለ የሚባል እቃ ሁሉ ነው ያደቀቀው። የአሳ ማስቀመጫ እንዲሁም ፍሪጅ አልቀረውም። ልጆቼ ደንግጠው እየተንዘፈዘፉ ነበር" ለዚህ ሁሉ መቀጣጠሉ ምክንያት የሆነው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሾል መስራት አይቻልም የሚለውን ውሳኔ ተከትሎ ገቢው በመቀነሱ ነው ትላለች። እንዲሁ በንዴት ግሎ ቢራ ሊገዛ በወጣበት ወቅት ወደ ፖሊስ ደወለች። "ፖሊሶች ቤቱ የሱ ስለሆነ እንደማያስወጡት ነገሩኝ። ለራሴም ሆነ ለልጆቼ ሌላ መጠለያ ፈልጊ አሉኝ" ብላለች። በዴንማርክም የቤት መቀመጥ አዋጁን ተከትሎ የእርዳታ ጥሪዎች በእጥፍ ጨምረዋል። ይህንንም ተከትሎ መንግሥት ጥቃት ለሚፈሩ ሴቶች መጠለያ የሚሆን 55 ስፍራዎችን ለአራት ወራት ያህል ያዘጋጀ ሲሆን ትምህርት ቤቶችም ለሴቶች መጠለያ በራቸውን ክፍት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። "በማንኛውም መንገድ መጠለያ እንዲኖራቸው እናደርጋለን" ያሉት ሱዛን ላማሃውጌ ሲሆኑ በሴቶች መብት አቀንቃኞች የሚመራ አንድ የድንገተኛ ማእከልም መሪ ናቸው። በቤልጂየም በሴቶችና ቤተሰብ ጥቃት ዙሪያ የሚሰሩት ጂን ሉዊስ ሲሞንስ ሶስት እጥፍ እንደጨመረ ተናግረዋል። "በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ደውላ ባለቤቷ ሲጋራ ሊገዛ እንደወጣና ለማውራት አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ እንዳላት ነገረችኝ። ድምጿ በፍራቻ የተሞላ ነው፤ እየተንቀጠቀጠችም እንደሆነ ያስታውቃል። በፍጥነት አወራን። ስናመጣት በከፍተኛ ሁኔታ ደብድቧታል። ፊቷ አብጧል። አይኗንም መግለጥ አልቻለችም" ቤት የመቀመጥ ሁኔታ ጥቃት አድራሹን የበለጠ ተዳባዳቢ ያደረገው ሲሆን፤ ጂን ሉዊስም ህይወቷ ሌላ አደጋ ውስጥ ከመግባቱ በፊት እንድታመልጥ ረዷት። ቤት መቀመጥ ደህንንት ያልሆነበት ሁኔታ በኮሮና ቫይረስ እያዛለሁ የሚለው ስጋት ጥቃት የሚደርስባቸውን ሴቶች ለመርዳት ከፍተኛ እክል እንደፈጠረ በአውሮፓ የስርአተ ፆታና የሴቶች ጥቃት ጉባኤ ኃላፊ ማርሴሊን ናውዲ ይናገራሉ። ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች በቫይረሱ እያዛለሁ በሚል ስጋት የህክምና አገልግሎት ሳያገኙ ቀርተዋል፤ ህክምና የሚሰጡ ቦታዎችም የተወሰኑ ሆነዋል። "ጥቃት የደረሰባቸው መጠለያ ቦታዎችም ቫይረሱ ይዛመታል በሚል ስጋት ሴቶችን መቀበል አቁመዋል" ይላሉ ከዚህም በተጨማሪ ለወደፊቱም በቫይረሱ ሾል ያጡ ሴቶች በትዳር አጋሮቻቸው ላይ ጥገኛ መሆናቸው ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችልና፤ ከጥቃትም ለማምለጥ አዳጋች እንደሚያደርገው አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። በአስር ሺዎችን ቫይረሱ በገደለበት የአውሮፓ ምድር በህይወት ለመቆየት ቤት መቀመጥ ትልቅ አማራጭ ነው። ነገር ግን ከጥቃት አድራሾቻቸው ጋር በእስርና በስቃይ ላይ ላሉ ሴቶች ግን ቤት መቆየት አደጋ ነው፤ መውጣትም የራሱ አደጋ አለው። በዚህም ምክንያት አማራጭ የሌለው አማራጭ ውስጥ ገብተዋል። በአውሮፓ የምትገኙ ሴቶች ድንገት ጥቃት ቢደርስባቸው እነዚህን ስልኮች በመጠቀም እርዳታ ልታገኙ ትችላላችሁ። ስፔን፡ 016፣ ኢሜይል [email protected]፣ የስነ ልቦና አገልግሎት በዋትስ አፕ፣ +34 682 916 136/+34 682 508 507፣ ፋርማሲ ስትገቡም ማስክ- 19 (ማስካሪላ 19) በማለት እርዳታ ልታገኙ ትችላላችሁ ዩኬ፦ 0808 2000 247 ጣልያን፦1522 ቤልጂየም፦ 0800 30 030፣ በፈረንሳይኛ ወይም በደች ቋንቋ ከሆነ 1712 ፈረንሳይ፦3919፣ ድንገተኛና አስቸኳይ ከሆነ 114 መልዕክት መላክ ትችላላች ወይም 17 ደውሉ ሩሲያ፦8 800 700 06 00 በመላው አውሮፓ ዉሜን ኤጌንስት ቫዮለንስ ዩሮፕ ኔትወርክን (Women Against Violence Europe (WAVE) Network) ልትፅፉ ትችላላችሁ
news-55499861
https://www.bbc.com/amharic/news-55499861
ቴክኖሎጂ፡ የ12 ዓመቷ ታዳጊ ቲክቶክን ልትከስ ነው
የ12 ዓመቷ ታዳጊ ቲክ ቶክን ልትከስ ነው።
ታዳጊዋ ተንቀሳቃሽ ምስልን የሚያጋራውን መተግበሪያ፣ ቲክቶክን የምትከስሰው የሕጻናትን ዳታ [መረጃ] ከሕግ ውጪ ተጠቅሟል በሚል ነው ተብሏል። ፍርድ ቤቱ ክሱ የሚታይ ከሆነ የታዳጊዋን ማንነት ለመደበቅ ተስማምቷል። ጉዳዩ በእንግሊዝ የሕጻናት ኮሚሽነር አኔ ሎንግፊልድ ድጋፍን አግኝቷል። ኮሚሽነሯ ቲክቶክ የዩናይትድ ኪንግደምን እንዲሁም የአውሮፓን የዳታ ሕግ ጥሷል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ቲክቶክ በበኩሉ የሕጻናትን ደኅንነት ለመከላከል "ፖሊሲዎቹን ማሸሻሻሉን" ጠቅሶ፣ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መተግበሪያውን መቀላቀል እንደማይችሉ ተናግሯል። ኮሚሽነር ሎንግፊልድ ይህ ጉዳይ እድሜያቸው ከ16 በታች ለሆኑ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች በእንግሊዝ እንዲሁም ከተቻለ በሌሎች አገራት የተሻለ ጥበቃ ማድረግ ያስችላል ብለዋል። ኮሚሽነሯ የተንቀሳቃሽ ምስል ማጋሪያ መተግበሪያው የሕጻናት ግላዊ መረጃን በመሰብሰብ አልጎሪዝሙ ቪዲዮዎችን እንዲገፋ በማድረግ፣ የተመልካቾችን ቀልብ ለመሳብ እንዲሁም የማስታወቂያ ገበያ ለማግኘት እንደሚጠቀምበት ተናግረዋል። ኮሚሽነር ሎንግፊልድ ለለንደን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቪዲዮ እንደተናገሩት ይህ ጉዳዩ መተግበሪያው የሕጻናትን ግላዊ መረጃ እንዲሰርዝ በማድረግ ለሌሎች ምሳሌ እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል። ነገር ግን በቅድሚያ ፍርድ ቤቱ የ12 ዓመቷ ታዳጊ ማንነቷ ተደብቆ ጉዳዩ ሊታይ ይችላል አይችልም የሚለው ላይ ለመወሰን ውሳኔ መስጠት አለበት ተብሏል። ዳኛው የታዳጊዋ ማንነት ይፋ ከሆነ ለማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች ማንጓጠጥና ስድብ ልትጋለጥ ትችላለች ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም ማንነቷ ከታወቀ "በዚህ ጉዳይ ምክንያት ያላቸው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ጥቅም እና ሌሎች ጉዳዩች አደጋ ላይ ይወድቃል ብለው የሚያምኑ ተጠቃሚዎች ያልተገባ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ" ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ኮሚሽነሯ ቲክቶክን ከመክሰሳቸው በፊት ጎግል ላይ የተመሰረተው የግላዊ መረጃ መከላከል ክስ እስኪጠናቀቅ መጠበቅ ይፈልጋሉ። ቲክቶክ በሕጻናት መራጃ አያያዝ በ2019 በአሜሪካ የፌደራል የንግድ ኮሚሽን ተከስሶ፣ የ5.7 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ተጥሎበት ነበር። መተግበሪያው በ2020 በደቡብ ኮሪያም በተመሳሳይ ጉዳይ ቅጣት ተጥሎበታል። ቲክቶክ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፣ "እኛ ለደኅንነት እና ለግለሰቦች መብት ቅድሚያ እንሰጣለን፤ ለዚህም ሁሉንም ተጠቃሚዎቻችንን ለመከላከል የሚያስችል፣ ቴክኖሎጂያችንን፣ ፖሊሲያችንን አሻሽለናል፤ በይበልጥ ደግሞ ወጣት ተጠቃሚዎችን መከላከል የሚያስችል የፖሊሲ ማሻሻያዎችን አድርገናል" ብሏል። መተግበሪያው እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች ለሆኑ ቲክቶክ መጠቀምን አይፈቅድም። እነዚህ ታዳጊዎች አካውንት ከፍተው ከተገኙም ድርጅቱ እየተከታተለ አካውንታቸውን ይሰርዛል።
news-46651340
https://www.bbc.com/amharic/news-46651340
የኦነግ እና የመንግሥት እሰጣገባ
ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲናጥ የከረመው የኦሮሚያ ክልል፤ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን መምጣትን ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖበት ቆይቷል።
ይሁን እንጂ በምዕራብ ኦሮሚያ የተከሰቱት ግጭቶች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር ላይ የተፈጸሙት ግድያዎች እና መፈናቀል፣ በደቡብ ኦሮሚያ ሞያሌ ከተማ እና አጎራባች ቀበሌዎች በይዞታ ይገባኛል የተፈጠረው ግጭት፣ ይህንንም ተከትሎ ግድያ እና መፈናቀልን ይቁም በማለት በተለያዩ የክልሉ ከተሞችና ዩኒቨርሲቲዎች የተደረጉት የተቃውሞ ሰልፎች የክልሉን ሰላም እና መረጋጋት አደፍርሰውት ቆይተዋል። • ለፖለቲካ ፍላጎት የተጋጋለ ግጭት ነው፡ ሙስጠፋ ኡመር በሞያሌ አካባቢ በኦሮሞ እና ገሪ መካከል ለሚከሰቱት ግጭቶች በሁለቱም ወገን ያሉት ለግጭቾቹ መንስዔ አንዱ አንዱን ተጠያቂ ያደርጋሉ። በኦሮሞ በኩል ያሉት የሞያሌ ድንበር ተሻግረው በከባድ መሳሪያ ህዝቡ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙት የሶማሌ ታጣቂዎች ናቸው ይላሉ። በሶማሌ ወገን ያሉት በበኩላቸው ለግጭቱ፣ ለሞትና መፈናቀሉ የኦሮሞ ታጣቂዎች ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር ላይ ለሚከሰቱት ግጭቶች ደግሞ መንግሥት ''የታጠቁ ኃይሎች'' የሚላቸውን አካላት ተጠያቂ ያደርጋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በምዕራብ ኦሮሚያ ከተከሰቱት አለመረጋጋቶች እና ግጭቶች ጋር በዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም አብሮ በስፋት ይነሳል። በወረሃ ጥቅምት አጋማሽ ላይ ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ውስጥ በመንግሥት እና በኦነግ ሠራዊት አባላት መካከል ግጭት መከሰቱን ቢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል። • "ገዳ የወደፊቱ የፖለቲካ ስርዓት መሆን ይችላል" ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ምንም እንኳ የቄለም ወለጋ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ታመነ ኃይሉ በኦነግ እና በመንግሥት ኃይል መካከል የተደረገ ምንም አይነት ግጭት የለም ያሉ ቢሆንም የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ቄለም በምትባል አነስተኛ ከተማ በሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና በኦነግ ታጣቂዎች መካከል ግጭት ስለመኖሩ አረጋግጠዋል። የደምቢዶሎ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ክብረት ዋቅጋሪም ግጭት ነበረ በተባለበት ምሽት ሦስት የፖሊስ አባላት በቦንብ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታላቸው እንደመጡ ተናግረው ነበር። በወቅቱ የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግሥት እንዲሁም የኦነግ አመራሮች በክስተቱ ላይ አስተያየታቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። • በኦነግ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በምዕራብ ኦሮሚያ ግጭት እንደነበር ተነገረ ከጥቂት ሳምንታትም በፊት በምዕራቡ ክፍል ያጋጠመን የጸጥታ መደፍረስ በሽምግልና ለመፍታት የሃገር ሽማግሌዎች ኦነግን እና መንግሥትን ለማግባባት ወደ ስፍራው አቅንተው ነበር። ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ካቀኑት ሽማግሌዎች መካከል አንዱ የነበሩት ሼክ ሐጂ ከአካባቢው ህዝብ እና በስፍራው ከሚገኙ የኦነግ ወታደሮች እና አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ''ወደ ሃገር ውስጥ ሳንገባ በመሪዎቻችን እና በክልሉ ፕሬዚዳንት መካከል የተደረሰው ስምምነት ለምን ተግባራዊ አልተደረገም?'' የሚል ጥያቄ በኦነግ ወታሮች መነሳቱን ሼክ ሐጂ ከሳምንታት በፊት ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ኦነግ እና መንግሥት አሥመራ ላይ የደረሱት ስምምነት ምን ነበር? ከጥቂት ወራት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የሚመራ ልዑክ ወደ ኤርትራ ተጉዙ ከኦነግ ጋር ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል። መንግሥት እና ኦነግ የደረሱበት ዝርዝር ስምምነት ይፋ ባይሆንም ኦነግ ሰላማዊ ትግልን ለማካሄድ እና ሠራዊቱም በየደረጃው በመንግሥት ሰላም አስከባሪ ኃይል ወይም በሌሎች መስኮች ውስጥ እንዲቀላቀል ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ በወቅቱ የኦነግ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ቶሌራ አደባ ''. . . በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦነግ መካከል የነበረው ጦርነት እንዲያበቃ እና ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ሃገር ውስጥ ገብቶ እንዲሠራ ከስምምነት ላይ ደርሰናል'' ሲሉ ተናግረው ነበር። በኦነግ እና በመንግሥት መካከል የተፈጠረው ልዩነት ምንድነው? ''መንግሥት እና ኦነግ የደረሱበትን ስምምነት ለማስፈጸም በመንግሥት በኩል ቅድመ ዝግጅቱ ከተጠናቀቀ ሰነባብቷል፤ ጉዳዩን እያጓተተ የሚገኘው ኦነግ ነው'' የሚሉት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ ናቸው። በመንግሥት እና በኦነግ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ለማስፈጻም በሁለቱም ወገን ተወካዮች የተዋቀረ ኮሚቴ አለ። የዚህ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኮሚሽነር አለማየሁ፤ የኮሚቴው አባል የሆኑ የኦነግ ተወካዮች 'በተደጋጋሚ ስምምነቱን ከማስፈጸማችን በፊት ከሠራዊታችን ጋር የምንወያይባቸው ጉዳዮች አሉ' በማለት ከአንድም ሁለት ሦስት ጊዜ ጉዳዩን ያጓተቱት እነሱ ናቸው እንጂ መንግሥት አይደለም በማለት ለስምምነቱ ተፈጻሚነት መዘግየት ኦነግን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ''የመንግሥት ተነሳሽነት እንደ ከዚህ ቀደሙ አይደለም'' በማለት ለቢቢሲ የተናገሩት ኦነግን በመወከል የዚሁ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ቦረና ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በቅዳሜው ውይይት ላይ ምን አሉ? እንደ ኮሚሽነር አለማየሁ ሁሉ አቶ ሚካኤልም "መንግሥት ጉዳዩን እያጓተተ ስለሆነ በተግባር ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም" ይላሉ። አቶ ሚካኤል ጨምረውም የኦነግ ሠራዊት አባላት ታሪካዊ እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰከረለት ስለሆነ ሥራዊቱን የሚመጥን ስፍራ ሊያገኝ ይገባል ይላሉ። አቶ አለማየሁ ለዚህ አስተያየት ምላሽ ሲሰጡ ኦነግ ሠራዊቱን ወደ አንድ ካምፓ ሳይሰበስብ፣ በስልጠና ወቅትም የእያንዳንዱ ሠራዊት አባል ማንነት እና አቅም ሳይፈተሽ፤ ለሠራዊቱ የሚመጥነው ስፍራ ይህ ነው ማለት አይቻልም ይላሉ። ሌላው በመንግሥት እና በኦነግ መካከል ቅራኔን የፈጠረው መንግሥት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ የሃገር መከላከያ ኃይልን ማሰማራቱ ነው። በሁለቱ ወገን የተቋቋመው ኮሚቴ ሥራውን በአግባቡ እንዳያከናውን መንግሥት መከላከያ ሥራዊት አሰማራብን በማለት ኦነግ ይከሳል። ኮሚሽነር አለማየሁ በበኩላቸው መንግሥት የጸጥታ ኃይልን የሚያሰማራው የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ ነው ለዚህም ደግሞ መንግሥት ፍቃድ መጠየቅ አይጠበቅበትም ይላሉ። የኦዲፒ መግለጫ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ታህሳስ 11 በወቅታዊ ጎዳዮች ላይ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ መግለጫ አውጥቷል። ክልሉን የሚያስተዳድረው ፓርቲ ''በህዝብ ትግል የተቀዳጀነው ድል በጠላት ሴራ ለሰከንድም ቢሆን አይደናቀፍም፤ ወደ ኋላም አይመለስም'' በሚል ርዕስ ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷል። በክልላችን ላይ በተሸረበው ሴራ በምዕራብ ኦሮሚያ ሕግ ተጥሶ፣ የነዋሪዎች እንቅስቃሴ ተገድቧል፣ ትምህርት እንዲቋረጥ ተደርጓል፣ ባለሃብቶች ሰርተው ሃብት ማፍራት አልቻሉም፣ የመንግሥት ተቋማት ለህዝቡ አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፣ . . . ስለዚህ የሕዝቡን ደህንነት ለማረጋገጥ ካለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የትኛውንም እርምጃ ለመውሰድ ወስኗል'' ሲል የኦዲፒ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ አውጥቷል። • "በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኦነግ ስም ቅመም ነው" የኦነግ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ኦዲፒ ይህን አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሄደው በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎችን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ኮማንድ ፓስት ተቋቁሞ ወደ ሥራ የመግባቱ ዜና ከተነገረ በኋላ ነው። ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል የተባለው ኮማንድ ፖስት የፌደራል፣ የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስን ያቀፈ መሆኑ ተነግሯል። መቀመጫውን በአሶሳ ከተማ የሚያደርገው ኮማንድ ፖስቱ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች የመሸገውን የታጠቀ ኃይል በመደምሰስ የአካባቢውን ሰላም ያስከብራል ተብሏል።
news-54507781
https://www.bbc.com/amharic/news-54507781
ኮሮናቫይረስ፡ በጨርቅ መልኩ የተዘጋጀ የእጅ መታጠቢያ ሳሙናን የሰራው ኢትዮጵያዊ
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሳደረው ተፅዕኖ ባሻገር የሰውን የሕይወት ዘይቤን ለውጦታል። ከዚህ ቀደም ከምናደርገው በበለጠ እጅን መታጠብ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ የምንገለገልባቸውን የእጅ ስልኮችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ዘወትር ማፅዳት ለአፍታ እንኳን የማይዘነጋ ሆኗል።
ከጨርቅ የተሰራው የእጅ መታጠቢያ ሳሙና እጅን መታጠብ ደግሞ ወረርሽኙን ከምንከላከልባቸው መንገዶች አንዱ ነው። በሽታው መጀመሪያ በተከሰተበት ውቅት እጅን ደጋግሞና በሚገባ መታጠብን ለማስተማር በየቦታው ዘመቻዎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ብዙም አልዘለቀም። አንድም በሰው የአጠቃቀም ልምድ ምክንያት ለበሽታው ይበልጥ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች በመስተዋላቸው፤ በሌላ በኩልም በውሃ እጥረት እንዲሁም ለእጅ መታጠቢያ የተቀመጠው ሳሙና ከቦታው እየጠፋ የተቸገሩም ብዙዎች ነበሩ። ታዲያ ይህ ያሳሰበው ፈይሰል ያሲን አንድ ፈጠራ አበርክቷል። ይህ የፈጠራ ሥራ የኮሮናቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከሚያስችሉና በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በአዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ከተመዘገቡ ስምንት የፈጠራ ሥራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የተቋሙ የፓተንት መርማሪ አቶ ጌታቸው ጣፋ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በግል ሥራ የሚተዳደረው ፈይሰል በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቋል። ለፈጠራ ሥራው ማይ ሶፕ [የእኔ ሳሙና] የሚል ስያሜ ሰጥቶታል - ፈይሰል። 'ማይ ሶፕ' ኮሮቫይረስን ጨምሮ ሌሎች ተህዋስያንን ለመከላከል የሚረዳ ሲሆን፤ ሳሙናው ለአንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውሎ የሚወገድ ከመሆኑ በተጨማሪ ለመያዝ አመቺ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ነው። ይህ ሳሙና በፀረ ተህዋስ ኬሚካል የተነከረ ጨርቅ [ዋይፕስ] አይነት የተዘጋጀ ነው። እንዴት ይዘጋጃል? በመጀመሪያ እንደ ፈሳሽ ሳሙና የሚዘጋጅ ውህድ አለ። ውህዱ አልኮል፣ ሶዲየም ላውሮት ሰልፌት [ኤስኤልኤስ] የነጭ ሽንኩርት ጭማቂና ግሪስሊን አለው። ግሪስሊኑ እጃችን እንዳይደርቅና ልስላሴ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ይላል- ፈይሰል። ይህን ውህድ ለማዘጋጀት ከሳይንሳዊ ጆርናል እና ቬትናም ውስጥ ከተደረገ ጥናት ላይ ሃሳቡ እንደተወሰደ የሚናገረው ፈይሰል፤ "ቬትናም ውስጥ የነጭ ሽንኩርት ጭማቂን በመጠቀም የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመቀነስ አገልግሎት ላይ እንደዋለ ጥናቱ ያስረዳል" ይላል። ፈይሰል እንደሚለው የውህዶቹ መጠን የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህንን በላብራቶሪ ለመፈተሽ በሒደት ላይ መሆኑንም ተናግሯል። ከዚያም 'ዋይፕሱን' በተዘጋጀው ውህድ ፈሳሽ ሳሙና ውስጥ በመንከር በእርጥብና በደረቅ መልኩ በማሸግ ለገበያ ይቀርባል። አንድ ሰው ይህንን የእጅ ማፅጃ መጠቀም ሲፈለግ አንዷን የ'ዋይፕስ' ቅጠል በውሃ አርጥቦ እጅን በማሸት መታጠብ ይችላል - ልክ እንደ ሳሙና። ይህ የፈጠራ ሥራ ከሌላ የሚለየው በቀላሉ በኪስ ለመያዝ አመቺ በሆነ መንገድ በመሰራቱ ነው። ፈይሰል እንደሚለው ገበያ ላይ ያሉት 'ዋይፕሶች' ሳሙናነት የላቸውም። የሚዘጋጁትም በእርጥበት መልክ ብቻ ነው። ይህ የፈጠራ ሥራ በደረቅ መልክና በኪስ መያዝ በሚያስችል መልኩ ነው የሚዘጋጀው። ሳሙናን ይዞ መንቀሳቀስ በማይቻልበት ቦታ ላይ ይህ አያያዙን ቀላል ያደርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሳሙናው ለአንድ ሰው አገልግሎት ብቻ የሚውል በመሆኑ፤ ግለሰቡ/ግለሰቧ ለራሳቸው ብቻ የሚሆን ይዘውት የሚንቀሳቀሱት አንድ የግል ሳሙና ይኖራቸዋል ማለት ነው። ፈይሰል እንደነገረን ከሆነ የእጅ ማፅጃው ታሽጎ እስከሚወጣ ድረስም የእጅ ንክኪ የለውም። የመጥረጊያ ጨርቁን [ዋይፕሱን] በደረቅ መልኩ ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ? ደረቅ ሆኖ መዘጋጀቱ ተማሪዎች በቦርሳቸው እንደሚይዙት የመማሪያ ቁሳቁስ ትምህርት ቤት ይዘውት ለመሄድ ምቹ ነው የሚለው ፈይሰል፤ እንደ ሳሙና ስለሚያገለግልም አንዱን እየመዘዙ እጃቸውን ሊታጠቡበት ይችላሉ። አንዱ እሽግም 24 ፍሬ ስለሚይዝ ለብዙ ጊዜ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ተጠቅሞ የሚጣለው ጨርቅም ቧንቧውን ለመዝጋትና ለመክፈትም ሊጠቀሙበት ይችላሉ። የመኪና በርንም በዚያ ለመክፈት ያገለግላል። ከዚህም ባሻገር ላብቶፕና ስልክን የመሳሰሉ የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎችን ለማፅዳት ይውላል። ደረቅ በመሆኑም በቁሶቹ ውስጥ ፈሳሽ ገብቶ በስክሪኖችና ኤሌክትሪክ ገመዶች ላይ የሚያደርሰውን መሰነጣጠቅና የተለያየ አደጋ አይኖርም። በመሆኑም ንክኪ የሚበዛባቸውን የእጅ ስልኮች በደረቁ በማፅዳት ያለ ስጋት በቀላሉ መጠቀም ይቻላል ይላል። ይህን ፈጠራ ለመስራት ምን አነሳሳው? የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እጅን በውሃ እና በሳሙና በሚገባ መታጠብ ወይም ፀረ ተህዋስ ኬሚካል በተነከሩ የእጅ ማፅጃዎች መጠቀም ወሳኝ እንደሆነ የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ። ነገር ግን በርካታ ሕዝብ በሚገኝባቸው ስፍራዎች አንድ ሳሙናን በመጋራት እጅን መታጠብ ከወረርሽኙ አንጻር ስጋት እንደፈጠረበት የሚናገረው ፈይሰል፤ በተጠቃሚው ልክ ሳሙናን በየቦታው ለማስቀመጥ አመቺ አለመሆኑና ሰዎች የራሳቸውን ሳሙና ሲጠቀሙ ልክ እንደ እርሱ ደኅንነት እንደሚሰማቸው በማሰብ ይህንን አማራጭ ለመፍጠር መነሳቱን ይገልጻል። ፈይሰል ይህንን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማምረት የሚያስፈልገውን ጨርቅ በሚፈለገው ሁኔታ ቆርጦ ለማዘጋጀት የሚያስችል ማሽን ያስገጠመ ሲሆን፤ ለዚህ ማሽን ብቻ ወደ 800 ሺህ ብር ገደማ እንዳወጣ ይናገራል። በቀጣይ አምርተው ይህንን የእጅ ንጽህና መጠበቂያ የጨርቅ ሳሙና በስፋት ለማምረትና ለተጠቃሚው ለማቅረብ በተለይም ተማሪዎች የግላቸውን ሳሙና ይዘው መንሳቀስ ስለማይችሉ ይህንን ምርት ትምህርት ቤቶች እንዲጠቀሙ ትኩረት አድርጓል። በተጨማሪም ሰዎች ሆስፒታሎች፣ በምግብ ቤቶችና በመሳሰሉት ቦታዎች ሁሉ ሳሙናውን ይዘው መሄድና መጠቀም እንዲችሉ ምርቱን በስፋት ለገበያ ለማቅረብ እቅድ ይዟል። እስካሁን የመከላከያ ክትባትም ሆነ የፈውስ መድኃኒት ያልተገኘለት የኮሮናቫይረስን መስፋፋት ለመቆጣጠር እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣ ከአንድ በላይ ሰው በሚገኝባቸው ስፍራዎች አፍና አፍንጫን በጭምብል መሸፈን፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅና የሚቻል ከሆነ በርካታ ሰዎች ከሚገኙባቸው ስፍራዎች እራስን ማራቅ በባለሙያዎች ይመከራል። በተለይም ከማንኛውም ንክኪ በኋላ እጅን በአግባቡ በሳሙናና በውሃ ለ20 ሰከንዶች ያህል መታጠብ በንክኪ የሚያጋጥምን በቫይረሱ የመያዝ ዕድልን በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል። በሽታው ከተከሰተ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ቢሆነውም እስካሁን በዓለም ዙሪያ ከ38 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ወደ 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ለሞት ተዳርገዋል። በኢትዮጵያም እስካሁን 86 ሺህ 430 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ የ1 ሺህ 312 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውን የጤና ሚኒስቴር ያሳወቀ ሲሆን ቁጥሩም ከዕለት ዕለት እየጨመረ ይገኛል።
50577878
https://www.bbc.com/amharic/50577878
ከአሰቃቂ የመኪና አደጋ በተአምር የተረፈችው ሴት
የ26 ዓመቷ ወጣት በሕይወት መትረፏ ተአምር ተብሏል።
ክስተቱ በደቡብ አፍሪካ፣ ፖርት ኤልዛቤት በምትባል ከተማ ዛሬ የሆነ ነው። ተጎታች ከባድ መኪና አሽከርካሪው ልጆቹን ከፓርሰንስ ሂል ትምህርት ቤት ሊያወጣ መኪናውን እንደነገሩ አቁሞት ነበር። ሾፌሩ ከባዱን ተሽከርካሪ የቆመበት ቦታ አቀበታማ የሚባል ነበር ይላል ፖሊስ። ልጆቹን ከትምህርት ቤት ሊያወጣ የሄደው ሾፌር እነሱን ይዞ ሲመለስ ከባዱ መኪናው ከቆመበት ቦታ የለም። እንዴት ከባድ ተሽከርካሪ ከዐይን ይሰወራል ብሎ መገረሙን ሳይጨርስ ሾፌሩ የሆነውን ይረዳል። ከባድ ተሽከርካሪው ፍሬኑን በጥሶ፣ ሌላ መኪና ላይ ወጥቶ፣ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የተረዳው ኋላ ነበር። ከባድ ተሽከርካሪው የተጫነው የቤት መኪና እጅግ በመጨፍለቁ ማንም ከዚያች የቤት መኪና ውስጥ በሕይወት ይወጣል አልተባለም ነበር። አራት ሰዓታት በፈጀ እልህ አስጨራሽ ሂደት ግን ሕይወት ተርፏል። ፖሊስ እንደሚለው ከባዱ ተሽከርካሪ ፍሬን በጥሶ ከአቀበት እየተንደረደረ ነው ኦፔል አዳም ሞዴል የቤት መኪና ላይ የወጣው ። ድንገተኛ መአት የተጫናት የቤት መኪና ከአስፋልት ተመሳሰለች በሚባል ደረጃ መጨፍለቋ ነበር የብዙዎችን ተስፋ ያጨለመው። የእርዳታ ሰጪዎች 40 ደቂቃ የፈጀ ጥረት አድርገው ልጅቱን አትርፈዋታል። •በየቤቱ እና በየጎዳናው የሚደፈሩ ሴት የአእምሮ ህሙማን •''እግሬን ባጣም ትልቁን ነገር አትርፌ ለትንሹ አልጨነቅም'' ልጅቱ ትትረፍ እንጂ ከባድ የሚባል የአካል ጉዳቶች እንዳጋጠሟት ተነግሯል። እሷን ከዚያ ለማውጣት መኪናውን መቁረጥ አስፈላጊ ነበር። ፖሊስ የከባድ መኪናውን ሾፌር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገበት ይገኛል።
news-48945353
https://www.bbc.com/amharic/news-48945353
የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሙሉ መግለጫ ምን ይላል?
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ. ም አጠናቆ መግለጫ አውጥቷል። ተጠናቋል።
ህወሐት በመግለጫው፤ "በአሁኑ ጊዜ አገሪቷን ሊበታትን ያለው ከዚህም ከዚያም የተሰባሰበ የትምክህተኞች ቡድን ነው፤ ይህ ኃይል እንደፈለገ እንዲንቀሳቀስ እድል የሰጠው ደግሞ አዴፓ ስለሆነ አዴፓ በአጠቃላይ ስለ ጥፋቱ፤ በፓርቲው አመራር ላይ የተፈፀመውን ግድያ በዝርዝር ገምግሞ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል" ብሏል። • "የመከላከያ ሰራዊትን እንቅስቃሴ የሚያግድ ስራ አንቀበልም" ዶ/ር ደብረፅዮን •"የለውጥ አመራሩን ሳይረፍድ ከጥፋት መመለስ ይቻላል" እስክንድር ነጋ ሲቀጥልም፤ በጄኔራሎቹና በአመራሮቹ ላይ የተፈፀመው ግድያ በሃሳብና በተግባር በቀጥታና በተዘዋዋሪ እጃቸው ያለ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ገለልተኛ በሆነ አካል በአስቸኳይ ሊመረመር ይገባል፤ ውጤቱም ለሕዝብ በየጊዜው በግልፅ መነገር አለበት ሲል ያሳስባል። የተቋሞች ኃላፊዎችና የፀጥታ ተቋማት መሪዎች ተገቢውን ኃላፊነታቸውን ባለመፈፀማቸው ለተፈጠረው ጥፋት ተጠያቂ መሆን አለባቸው ይላልም መግለጫው። ውስጣዊ ችግሮቹን ከመገምገም ይልቅ በነገሩ የሦስተኛ አካል እጅ አለበት በማለት ጥፋቱን ለመሸፋፈን መሞከርና ሕዝቡን ማደናገር ማቆም አለበት ሲልም ህወሐት አዴፓን ይወነጅላል። ስለዚህ አዴፓ ውስጣዊ ችግሮቹን ፈትሾ አቋሙን እንዲያሳውቅም እንጠይቃለን፤ ይህንን ማድረግ ካልተቻለ ግን ህወሐት ከፓርቲው ጋር ለመሥራትና ለመታገል እንደሚቸገርም በመግለጫው በግልፅ አስቀምጧል። •"ብ/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ "እስካሁን ያጋጠሙ መሰረታዊ ችግሮች በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የአሰላለፍ መደበላለቅና ኢህአዴግ ሁሉንም አይነት ጥገኛ አመለካከቶች ተሸክሞ የሚኖር ድርጅት እየሆነ ስለመጣ ነው። ቀድሞ ወደሚታወቅበት ባህል ተመልሶ በሕግና በደንቡ መመራት ይገባዋል" ይላል መግለጫው። ኢህአዴግ እንደ ግንባርም ሆነ እንደ መንግሥት በቀጣዩ ዓመት መደረግ ስላለበት አገራዊ ምርጫ ያለውን ቁርጥ ያለ አቋም እንዲያሳውቅ በመግለጫው ተጠይቋል። በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል እየተነሱ ያሉት ክልል የመሆን ጥያቄዎች ሕገ-መንግስታዊ በሆነ መንገድ ሊፈቱ እንደሚገባ ከዚህ ዉጪ የሕዝብ ጥያቄ በኃይል ወይም በሌላ መንገድ ለመፍታት የሚደረግ ጥረት ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲልም ያስረግጣል መግለጫው። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ያወጣው ሙሉ መግለጫ የሚከተለው ነው የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሐምሌ 2/2011 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፤ በቅርቡ ባጋጠመው የከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎችና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያን መነሻ በማድረግ በአገራችን እያደገ እየመጣ ያለውን ሁለገብ ችግርና እሱን ተከትሎ ወደፊት ሊያጋጥም የሚችለው አጠቃላይ ሁኔታ፤ ለሀገራችን ና ለክልላችን ያለውን ትርጉም በመተንተን በአስቸኳይ ሊፈጸሙ ይቸባቸዋል ያላቸውን ወሳኝ አቅጣጫዎችን እና ውሳኔዎችን አስቀምጧል። በአሁኑ ወቅት የአገራችንን ህልውና ከመጥፎው ወደ ባሰ ሁኔታ ሊወስድ የሚችል በመጠኑና ስፋቱ እጅጉን አሳሳቢ የሆነ ሁኔታ ላይ ደርሰናል። በየጊዜው እየተከማቸ የመጣ፤ በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ የአገራችንን ህልውና አደጋ ውስጥ የሚከት አደጋ እየተበራከተ፣ ከቀን ወደ ቀንም የዚህ አደጋ ፍጥነት እየጨመረ መጥቶ በቅርቡ የተቀነባበረና ረጅም ዝግጅት የተደረገበት በአገራችን ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎችና የአማራ ክልል አመራሮችን በግፍ ወደ መግደል ደረጃ ላይ ደርሷል። ትናንት የሀገራችንን ህልውናና ክብር አሳልፈው የሰጡ፤ የኢትዮጵያን መበታተን እውን ለማድረግ ቀንና ሌሊት አንቀላፍተው የማያውቁ ኃይሎች በለውጥ ስም ግንባር በመፍጠር አሰላለፍ በማይለይ ሁኔታ ሁሉም ተደበላልቆ አንድ ላይ እንዲኖር በመደረጉ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት እየተደራረበ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል። በአንጻሩ ደግሞ፤ ለዚህች ሃገር ክብርና ህልውና ዕድሜ ልካቸውን የታገሉት የሚታደኑበት፣ የሚታሰሩበትና ጥላሸት የሚቀቡበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በሰላም እጦት ህዝቦች እንዲሰቃዩ፣ በማንነታቸው ምክንያት ዜጎች ህይወታቸውን እንዲያጡ፣ እንዲሳቀቁ፣ መጠለያ አጥተው ፀሐይና ብርድ ላይ እንዲጣሉ፣ በዚህች ሃገር ታሪክ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ግጭትና በሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል የተበራከተበት፣ ከማንኛውም ጊዜ በላይ ሕግና ሥርዓት ማስከበር ያልተቻለበት፣ ሃገር ጠባቂ አጥታ የጽንፈኞች መፈንጫ እየሆነች ፀረ ሕገ-መንግሥትና የፌደራል ሥርዓት የሆኑ ጫፍ የረገጡ የትምክህት ኃይሎች እንደፈለጉ የሚፈነጩበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ህወሓት የትምክህት ኃይል ሲል፤ የህዝብን መብትና ጥቅሞችን ረግጠው ስስታም ፍላጎቶቻቸውን ማስፈፀም የሚፈልጉ ኃይሎችን እንጂ የህዝብ ነው ብሎ አያውቅም ሊልም አይችልም። በማነኛውም መመዘኛ ትምክህተኛ የሚባል ህዝብ የለም። የሁሉም ህዝቦች ፍላጎትና ምኞት አንድ ነው። ወዳጅም ጠላትም ማወቅ የሚገባው ህወሓት ትናንትም፣ ዛሬም ሆነ ነገ ለህዝብ ከፍተኛ ክብር የሚሰጥ ህዝባዊ እምነት ይዞ የሚታገል ድርጅት ነው። ባለፉት ጊዜያት ከአማራ ህዝብ ጋር ሆኖ ፀረ ትምክህትና ገዢዎችን በአንድነት የታገለና የበለጠ መስዋዕትነት የከፈለ ድርጅት ነው። ስለሆነም የአማራን ህዝብ ትምክህተኛ ማለት የሚችል ድርጅት አይደለም። ነገር ግን፤ እነዚህ ፀረ ህዝብ የትምክህት ኃይሎች የሚፈልጉትን የድሮ ህልማቸውን ለማስፈፀም ሲሉ የአማራን ህዝብ ትምክህተኛ ተባልክ በማለት እያደናገሩ ነው። በአማራው ህዝብ ስም እየነገዱ ያልተባለውንና ያልሆነውን እንዲህ ተባልክ እያሉ እንደመዥገር ተጣብቀው ሊመጡት ጥረት እያደረጉ ነው። ቢሆንም ግን የአማራ ህዝብ እንደማነኛውም ህዝብ ለሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ ብሎ መስዋዕትነት በመክፈል አዲሲቷን ኢትዮጵያ በመፍጠር ረገድ የማይተካ ሚና የነበረውና ያለው ህዝብ ነው። ተጀምሮ የነበረው ተስፋ የሚሰጥ ልማትና እድገት አሁን መሪ አጥቶ ቁልቁል መውረድ የጀመረበትን ሁኔታ እያየን ነው። የጸጥታና የደህንነት ተቋማት ከማንኛውም ጊዜ በላይ የዚህችን ሃገር ሰላምና ደህንነት መጠበቅ አልቻሉም። የእነዚህ መሪዎች ግድያ የሚያረጋግጠው ሃቅ ቢኖር፤ የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እየተቸገረ፣ በግፍና በጭካኔ የስልጣን ጥማታቸውን ማርካት የሚፈልጉ የትምክህት ኃይሎች እንደፈለጉ የሚፈነጩበት፣ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው የዚህች ሃገር ህዝቦች ዋስትና የሆነውን ሕገ መንግጅትና የፌደራል ሥርዓቱን ለማፍረስ በጠራራ ፀሐይየሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ እየታየ ነው። በእንዲህ ያለ ሁኔታ፡ በየቀኑ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመገመት በሚያስቸግር ደረጃ ላይ ተደርሷል። የአገራችን ሁኔታ እንዲህ ወዳለው ደረጃ መድረሱ እየታወቀ በግልጽ የተፈፀመውን የከፍተኛ መሪዎችን መግደልና በቀላሉ ሥርዓት የማፍረስ ተግባርን የመኮነንም ሆነ የጠራ አቋም በመያዝ ትግል እየተደረገ አይደለም። ይልቁንም ሁሉም የለውጡ መሪዎች ነበሩ እየተባለ ይህን እኩይ ተግባር እንዲቀጥል የሚያደርግና እዚሁ ላይ እጅ የነበራቸው አካላት ተጠያቂ እንዳይሆኑ ሆን ተብሎ ለመሸፋፈን ካለሃፍረት ጥረት እየተደረገ ነው። ሌላው ቀርቶ የዚህችን ሃገር ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሐላፊነት የተሸከሙ የፀጥታና የደህንነት አካላት በተፈፀመው ጥቃት ላይ ያለባቸውን ተጠያቂነትን በሚያረጋግጥ መንገድ እየተሰራበት አይደለም። ይህ ሁኔታ የሃገራችንን ህልውና ወደከፋ አደጋ እያስገባ መሆኑን በመገንዘብ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ቀደም ብሎ ለይቶ ያስቀመጣቸውን የትግል አቅጣጫዎችን በማጠናከር በቅርቡ የተከሰተውን ሁኔታ መነሻ አድርጎ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል። 1. በጀግኖቹ ከፍተኛ የሃገር መከላከያ አመራሮች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀል ከማሰብ እስከ መተግበር በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የነበሩ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ሃገራዊ በሆነ ገለልተኛ አካል እንዲጣራ፣ የጸጥታና ደህንነት አመራሮች በዚሁ ሴራ ላይ በነበራቸው ሚናም ሆነ ተገቢውን ሐላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ባጋጠመው ጥፋት ተጠያቂዎች እንዲሆኑ፣ የዚህ ምርመራ ሂደትና ውጤትም በየጊዜው ለኢትዮጵያ ህዝቦች ግልጽ እንዲሆን የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል። 2. በአሁኑ ወቅት ሀገር እየበተነ ያለው ከዚህም ከዚያም የተሰባሰበው የትምክህት ኃይል ነው። ይህ ኃይል ዕድል አግኝቶ እንደፈለገ እንዲፈነጭ እያደረገ ያለው ደግሞ አዴፓ ነው። በመሆኑም፤ አዴፓ ባጋጠመው ጥፋት ላይ በአጠቃላይ፣ በተለይም ደግሞ በድርጅቱ አመራሮች ላይ ባጋጠመው ግድያ ላይ በዝርዝር ገምግሞ ወደ ተጠያቂነት እንዲሸጋገር እንዲያደርግና አቋም እንዲይዝ ከዚህም ተነስቶ የኢትዮጵያ ህዝቦችን ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል። ከዚህ በተጨማሪም የውስጥ ችግርን ለመሸፈን ሲባል ጥፋቱ የሦስተኛ አካል እጅ አለበት፣ ረጃጅም እጆች ያሉበት ነው እያሉ ህዝብን ማደናገር ሊቆም ይገባል። እንዲህ እያሉ መኖር እንደማይቻል ህዝብም ተገንዝቦታል። ስለዚህም አዴፓ ሁሉንም ውስጣዊ ችግሮቹን በዝርዝር ገምግሞ ግልጽ አቋሙን እንዲያስታውቅ ጥሪ እናቀርባለን። ይህን ማድረግ ካልቻለ እንዲህ ካለው ኃይል ጋር አብሮ ለመስራትና ለመታገል እንደሚቸገር ሊታወቅ ይገባል። 3. እስካሁን ድረስ ያጋጠመው መሰረታዊ ችግር በኢህአዴግ ውስጥ በተፈጠረው የአሰላለፍ መደበላለቅና በጠራ ውግንና ላይ የተመሰረተ ትግል እየተተወ፤ ሁሉም ዓይነት ጥገኛ እና ደባል አመለካከቶችን ተሸክሞ የሚኖር ድርጅት እየሆነ በመምጣቱ ነው። ስለሆነም የሀገራችንን ህልውናና ደህንነት ለማስጠበቅ ኢህአዴግ ወደተለመደውና ወደሚታወቅበት ባህሪና እምነት ተመልሶ፤ ከጎራ መደበላለቅ የጠራና በግልጽ ውግንና ላይ የተመሰረተ ትግል እንዲያካሂድ እና በመጪው ዓመት በሕገ መንግሥታችን መሰረት እንዲካሄድ የሚገባውን አገራዊ ምርጫ በተመለከተ እንደ ግንባርና እንደ መንግሥት አቋሙን ለኢትዮጵያ ህዝቦች ግልጽ እንዲያደርግ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ያሳስባል። 4. የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን እና የሃገር ሉዓላዊነትን ከማነኛውም አደጋ ለመከላከልና ለመጠበቅ የተሰጣችሁን ሕገ መንግጅታዊ ኃላፊነት ከማነኛውም ግዜ በላይ ውስጣዊ አንድነታችሁን በማጠናከር የሃገራችሁን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እያቀረብን፤ ይህን ለመፈጸም በምታደርጉት ትግል ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አሁንም እንደ ሁልግዜው ከጎናችሁ በመሆን በጽናት እንደሚታገል ያረጋግጥላችኋል። 5. ህወሐት እንደ አንድ ሕገ መንግሥታዊና ፌደራላዊ ኃይል ሕዝብንና ሀገርን ለማዳን ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ሕገ መንግሥታዊና ፌደራላዊ ኃይሎች ጋር ሰፊ መድረክ ፈጥሮ ለመታገልና በአስቸኳይ ወደ ተግባር ለመሸጋገር የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ወስኗል። 6. በደቡብ ክልል እየተነሱ ያሉት የክልል እንሁን ጥያቄዎች ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ሊፈቱ ይገባል። ከዚህ ውጪ የህዝብን ጥያቄ በኃይል ወይም በሌላ መንገድ ለመፍታት የሚደረግ ጥረት ፍጹም ተቀባይነት የለውም። 7. የፌደራሉ መንግሥት በዚህች ሀገር አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ፣ ሕግና የሕግ የበላይነት እንዲከበር፣ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጥ፣ ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ሳይሸራረፍ በጥብቅ እንዲተገበር የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አሁንም በድጋሚ ያሳስባል።
news-49218294
https://www.bbc.com/amharic/news-49218294
መንግሥት በምን የሕግ አግባብ ኢንተርኔት ይዘጋል?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ባሳለፍነው ሐሙስ ሐምሌ25 /2011 ዓ.ም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ከጋዜጠኞች ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከልም አንዱ የኢንተርኔት መዘጋት ጉዳይ ነበር።
ጠቅላይ ሚንስትሩም የሰዎችን ሕይወትና ንብረት ከጥቃት ለማትረፍ አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ለሳምንት ሳይሆን እስከ ወዲያኛው ኢንተርኔት ሊዘጋ ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል። ለመሆኑ መንግሥት በምን የሕግ አግባብ ኢንተርኔት ይዘጋል? • የኢንተርኔቱን ባልቦላ ማን አጠፋው? • ጠብ አጫሪና ጥቃት አድራሽ የፌስቡክ ፖስቶችን እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል? የሕግ ባለሙያው አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ፤ በሰብዓዊ መብቶችም ሆነ በሕገ-መንግሥት ድንጋጌዎች መንግሥት የሃገር ደህንነትን ለማስጠበቅ ሲል እንደዚህ ዓይነት እርምጃዎችን ሊወስድ ይችላል ይላሉ። ተመሳሳይ ጥያቄ የሰነዘርንላቸው የ "ግርምተ ሳይቴክ" መጽሐፍ ደራሲና በዓለማችን ላይ በፎርቹን መጽሔት ዝርዝር በዓለም ላይ በ2018 ከፍተኛ ገቢ ካስመዘገቡ 500 ድርጅቶች (Fortune500) መካከል በአንዱ የቴክኖሎጂ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ካሳ በበኩላቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ላይ እንደተቀመጠና የሕዝብን ደህንነትና ሰላም የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት አካል፤ በፌስቡክ የሚሰራጭ መረጃ የሚያደርሰውን ጉዳት ትኩረት ሰጥተው ማየታቸው የሚጠበቅ ነው ይላሉ። መንግሥታት ኢንተርኔት ለምን ይዘጋሉ? በሀገራችን ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ የታየው የኢንተርኔት መዘጋት የዜጎችን መረጃ መቆጣጠሪያ መንገድ በመሆን መንግሥት ያለአግባብ እየተጠቀመበት ነው ይላሉ - የሕግ ባለሙያው አቶ ምስጋናው። አክለውም በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ኢንተርኔትን የሚያቋርጡ መንግሥታት የሚሞግታቸውን ሀሳብ በኢንተርኔት እንዳይንሸራሸር የመከልከያ መንገድ አድርገው እየተጠቀሙበት ነው የሚል ትችት እንደሚሰነዘርባቸው ያነሳሉ። የቴክ ቶክ የቴሌቪዥን መርሀ ግብር አዘጋጅና አቅራቢው አቶ ሰለሞን በበኩላቸው፤ ኢንተርኔትን ማቋረጥ በመላው ዓለም እየተለመደ መጥቷል ሲሉ ከሕግ ባለሙያው ሀሳብ ጋር ይስማማሉ። ምክንያቱ ምንድን ነው? ለሚለውም የተደረጉ ጥናቶችን በመጥቀስ፤ መንግሥት የፖለቲካውና የመረጃ ቁጥጥሩ በእርሱ ሥር እንዲሆን ወይም የፖለቲካ ትርክቱን እርሱ በሚፈልገው መንገድ ለማስኬድ ሲፈልግ ነው ይላሉ። መንግሥታት 'ኢንተርኔት የዘጋነው የተፈጠሩ ችግሮችን ለማስተካከልና ለመቆጣጠር ነው' ቢሉም፤ ጥናቶች የሚያሳዩት ግን መንግሥታቱ የሚሰጡት ምክንያት ሽፋን መሆኑን ነው ይላሉ አቶ ሰለሞን። ኢንተርኔት ለፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በሰፊው ጥቅም ላይ የዋለው እአአ በ2010 በአረብ አብዮት መሆኑን የሚያስታውሱት አቶ ሰለሞን "ከዚያ በኋላ መንግሥታት በንቃት የሚከታተሉት ጉደይ ቢኖር ኢንተርኔትን ነው" ይላሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ የተካሄዱ ጥናቶችንም በመጥቀስ ከአረብ አብዮት በኋላ ከአርባ ሃገራት በላይ ከ400 ጊዜ በላይ ኢንተርኔት መዝጋታቸውን በአስረጂነት ያቀርባሉ። የሕግ ባለሙያው አቶ ምስጋናው በበኩላቸው የምርጫ ወቅት እየደረሰ መሆኑንና የሲዳማ ክልል ለመሆን የሚደረገው ሕዝበ ውሳኔ በቅርብ መሆኑን በማስታወስ "ካለንበት የፖለቲካ ሁኔታ አንፃር፤ በተቻለ መጠን ሀሳቦች በደንብ ተሠራጭተው ሌላ የሚገዳደራቸው ሀሳብ እየቀረበባቸው መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ስልትን ብንጠቀም ነው የሚያዋጣን " ሲሉ አማራጭ ሃሳብ ያቀርባሉ። የዓለም አገራት ራስምታት በፌስቡክ በስፋት የሚሰራጩ ግጭትን የሚያስነሱ መልዕክቶች የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለምና የፌስቡክ ተቋምም ራስ ምታት እንደሆነ አቶ ሰለሞን ይናገራሉ። ችግሩ አራት አይነት ነው። ቀዳሚው ከፍቶ ለማየት የሚያጓጉ ማስፈንጠሪዎችና አሰቃቂ ምስሎች ናቸው። ከታዋቂ ሰዎች ጋር የተያያዙ ሐሰተኛ ወሬዎች፣ እንዲሁም ከጥላቻ፣ ከፖለቲካና ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ጋር የተያያዙ ወሬዎች እንሚገኙበት የቴክኖሎጂ ባለሙያው ያስረዳሉ። ፅንፈኛ ፅሁፎችና ምስሎች ፌስቡክ ላይ እንደሚሰራጩ በማንሳት "እንደዚህ አይነት መረጃዎች የሀሳብ ግጭት ብቻ ሳይሆን የአካል ግጭት ውስጥም ይከታሉ" ይላሉ። • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ • «ኢትዮ-ቴሌኮምን እንከሳለን» የሕግ ባለሙያዎች ሐሰተኛ ዜና ሌላው የዓለም ራስ ምታት መሆኑን የሚያትቱት አቶ ሰለሞን፤ በርካታ ሰዎች በቀላሉ እንዲታለሉ ለማድረግ በሚያስችል ደረጃ ተቀናብሮ የሚቀርብ ነው መሆኑን ያስረዳሉ። የጥላቻ ንግግሮችም የፌስቡክና የመንግሥታት ራስ ምታት መሆናቸውን የሚጠቅሱት አቶ ሰለሞን፤ እነዚህ በዘር፣ በፆታ፣ በሐይማኖት ላይ የሚሰነዘሩ ናቸው ይላሉ። በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ ምህዳር ምክንያት፣ በብሔር፣ በሐይማኖትና በጾታ ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ ዜናዎች ተስፋተው እንደሚታይ የሕግ ባለሙያው አቶ ምስጋናውም ሆኑ አቶ ሰለሞን ይስማማሉ። ኢንተርኔት መዝጋት መፍትሔ ይሆናል? አቶ ምስጋናው እና አቶ ሰለሞን፤ ኢንተርኔትን መዝጋት የብሔር ግጭቶችትንም ሆነ መፈናቀልን አያስቆምም ይላሉ። አቶ ሰለሞን እንደሚሉት፤ ኢንተርኔት ከማቋረጥ ይልቅ ግጭት ቀስቃሽ የጥላቻ ንግግሮችና ሐሰተኛ ዜናዎች በዋናነት የሚሰራጩበትን የፌስቡክ ተቋም ማነጋገር ተገቢ ነው። ይህንን ካደረጉ አገራት መካከል ጀርመንና ፊሊፒንስን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። መንግሥት፤ ከ100 ሚሊየን በላይ ሕዝብ የሚኖርባት አገር ውስጥ ግጭት ቢፈጠርና አለመረጋጋት ቢቀጥል፤ ቀውሱ ለአህጉሪቱ እንደሚተርፍ ለፌስቡክ ቢያስረዳ፤ ከፌስቡክ ጋር የጥላቻ ንግግሮችን በመቆጣጠር ረገድ ትኩረት ሰጥቶ በጋራ መሥራት ይቻላል የሚል ሀሳብ ያነሳሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት የተለያዩ ቋንቋ የሚናገሩ ግለሰቦችን አቅርቦ ከፌስቡክ ጋራ በቅርበት ቢሠራ ውጤት ሊያመጣ የሚችል የቁጥጥር እርምጃ መውሰድ ይቻላል ሲሉም ምክራቸውን ያጠናክራሉ። የሕግ ባለሙያው በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት በአገራችን እየተደረገ ያለው የኢንተርኔት መዝጋት የዘፈቀደ ይመስላል በማለት፤ "አንዳንድ ጊዜ የሕዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ነገሮች ሲከሰቱ ይዘጋል፤ አንዳንዴ ግን ፈተና ለማከናወንም ይዘጋል" ሲሉ ትዝብታቸውን ያጋራሉ። ማን እንደሚዘጋውም የሚታወቅ ነገር እንደሌለ በመጥቀስ "ማን ነው የሚዘጋው? ቴሌ ነው? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው? ወይስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት? ሲሉ በመጠየቅ ይህንን የሚወስን በግልፅ የተቀመጠ መመሪያ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። • በሞባይል ኢንተርኔት መቋረጥ የተገደቡ እንቅስቃሴዎች • ስመ ጥሩ ጋዜጠኛ ሃሰተኛ ዜና በመፈብረክ ከስራው ተባረረ መንግሥት የአገርንና የሕዝብን ደህንነት መጠበቅ ተቀዳሚ ሥራው ስለሆነ ባሻው ጊዜ እየተነሳ ኢንተርኔት እንዲዘጋ የምንፈቅድለት ከሆነ፤ ሕግ ሲጥስ የምንቆጣጠርበት ሥርዐት አይኖረንም በማለት የሕጉን አስፈላጊነት ያስረዳሉ። ኢንተርኔት በመዝጋት የሚደርሱ ኪሳራዎች አቶ ምስጋናው በቅርቡ ቴሌ በሰጠው መግለጫ ላይ በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት የደረሰበትን ኪሳራ መግለፁን በማንሳት፤ የሚኖረውን ምጣኔ ገብታዊ ጉዳት ያሳያሉ። በአሜሪካ ያለ አንድ ተቋም ያወጣው ጥናት እንደሚያሳየው፤ ኢንተርኔት በተዘጋ ቁጥር በአንድ አገር ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት እድገት ላይ በአማካይ 1.9 በመቶ ኪሳራ ያመጣል የሚሉት ደግሞ አቶ ሰለሞን ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ይላሉ አቶ ሰለሞን፤ ገንዘብ የሚለግሱ አገራት የመንግሥት አስተዳዳራዊ ተግባር በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ሲጓተት ተሰላችተውና ተስፋ ቆርጠው ሀሳባቸውን ሊቀይሩ ይችላሉ ሲሉ ያለውን ተፅዕኖ ያስረዳሉ። ኢንተርኔት ከሕክምና አገልግሎት ጋር ተያያዥ መሆኑንም በማንሳት መዘጋቱን እንደቀላል ማየት እንደሌለብን ያሳስባሉ። ኢንተርኔት ሲዘጋ፤ "ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የገነባችውን ምስል በማጠልሸት ጉዳት ማድረሱ አይቀርም" የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ ግጭትን ለማስቆም በሚል ኢንተርኔት ሲዘጋ፤ ግጭት ፈጣሪዎቹ ኢንተርኔት ቢዘጋ ሌላ መንገድ ያጣሉ ወይ? ብሎ መጠየቅ እንደሚያሻ ይገልጻሉ። አቶ ሙሉጌታ በበኩላቸው፤ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ በቀላሉ የሚታለፍ አለመሆኑን ያሰምሩበታል።
news-53148775
https://www.bbc.com/amharic/news-53148775
የሳይበር ጥቃት በማን ይፈጸማል? ምንስ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል?
በዝነኛው የቴድ-ቶክ የዲስኩር መድረክ ላይ ፓብሎስ ቆሟል።
የኮምፒውተር ምስጢር እንዴት ሰብሮ እንደሚገባ እያስረዳ ነው። እርሱ ራሱ የኮምፒውተር መረብ ሰርሳሪ ነበር። በአዳራሹ የታደሙ ሰዎች ስልኮቻቸውን እንዲያወጡ አዘዘ። የግማሹን ታዳሚ የስልክ መክፈቻ የምስጢር ቁጥር ለራሳቸው መልሶ ነገራቸው። ሌሎች ተመልካቾች ደግሞ ክሬዲት ካርዳቸውን ይዘው ወደ መድረክ እንዲመጡ አደረገ። የባንክ ክሬዲት ካርድ የምስጢር ቁጥራቸውን በዚያው መድረክ አጋልጦ ሰጣቸው። "እንበልና…" አለ ፓብሎስ፣ "…እንበልና ያረፍኩበት ሆቴል ከጎኔ የተከራየው ሰው በቴሌቪዥን ምን እየተመለከተ እንደሆነ ልሰልለው ብፈልግ ያ ለእኔ ቀላል ነው…።" "ጎረቤቴ በቴሌቪዥን የወሲብ ፊልም እየተመለከተ ይሆን? ወይስ የዲዝኒ ፊልሞችን…? ከፈለኩ ደግሞ ጎረቤቴ አልጋው ላይ ተጋድሞ የሚመለከተውን ቻናል ከክፍሌ ሳልወጣ ልቀይርበት እችላለሁ።" ተመልካቹ በዚህ ልጅ ድርጊት ተደነቀ። ይህ ልጅ ድርጊቱን የሚፈጽመው እንዲሁ ለጀብዱ ነው። ሁሉም የሳይበር ጥቃቶች ግን ለጀብዱ ብቻ አይፈጸሙም። የመረጃ መረብ ጥቃት ምን ያህል ያሳስባል? መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም ኢንተርኔት ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊዘልቁት ይችላሉ። በግለሰብ ደረጃ ሲከወን ጉዳቱ አስደንጋጭ ላይሆን ይችላል። ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳት ሲያስከትል ነው። አንድ አገር የፋይናንስ መረጃዎቹ ከተጠለፉበት በእንብርኩኩ ሊሄድ ይችላል። አንድ አየር መንገድ መረጃዎቹ ቢጠለፉበት የአውሮፕላኖች መከስከስን ጨምሮ መላ ተግባሩ ሊስተጓጎል ይችላል። በዚህም በቀናት ውስጥ ቢሊዮኖችን ሊያሳጣው ይችላል። አንድ አገር የመብራት ኃይል አቅራቢ ድርጅቱ በመረጃ ቦርቧሪዎች ቢገረሰስበት አገር በድቅድቅ ጨለማ ልትዋጥ ትችላለች። ባንኮች በመረጃ ጠላፊዎች መረጃቸው ቢታወክ አለኝ የሚሉት ገንዘብ፣ ሰበሰብነው የሚሉት አዱኛ ሁሉ በአንድ ጀንበር እንደ ጉም ሊተንባቸው ይችላል። ይህን ሁሉ ተአምር የሚሰሩት መረጃ ጠላፊዎች እነማን ናቸው? በቀድሞ ጊዜ መረጃ ጠላፊዎች ገና ሮጠው ያልጠገቡ ጎረምሶች ነበሩ። ድርጊቱን የሚፈጽሙትም ድርጊቱን መፈጸም እንደሚችሉ ለማረጋገጥና እርካታን ለማግኘት ብቻ ነበር። ልክ ቤት ውስጥ የተበላሸ ቴፕ ፈታትቶ መገጣጠም እንደሚያስደስተው ሰው፤ ልክ የተጣለ ኮምፒውተር አንስቶ ዳግም ሕይወት መዝራት እንደሚያስደስተው ልጅ…ነገሩ ጌም ነው! ጨዋታ ነው! በኋላ ላይ ነው ነገሩ የቢዝነስ ቅርጽ እየያዘ የመጣው። ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ተሰባስበው የአንድን ድርጅት ምስጢር መቦርበር ጀመሩ። ቀጥሎ ደግሞ እንዲህ ያሉ አደገኛ ወጣቶች ተሰባስበው ትልቅ ድርጅት መመስረት ያዙ። የሰው መረጃን በመቦርቦር የጀመሩት ሱስ መረጃ ቦርቧሪዎችን አድኖ ወደመያዝ ተሸጋገረ። ይህ በጎረምሳነቱ ኪስ አውላቂ የነበረ ነውጠኛ በጎልማሳነቱ ጠብ የማያጣው መሸታ ቤት ደንብ አስከባሪ (ጋርድ) ሲሆን ማለት ነው። በዚህ ሂደት የጸረ ጥቃት ተከላካይ ኩባንያዎች መመስረት ያዙ። ይህ ነገር እያደገ ሄደና አገራት ጦርነት የሚከፍቱት የእግረኛ ጦር በመላክ፣ ታንክ በመንዳትና ሚሳይል በማስወንጨፍ መሆኑ እየቀረ የሳይበር ውጊያ ውስጥ ገቡ። ምናልባት በመጪዎቹ ዘመናት "የድሮ ሰዎች ድንበር ድረስ ሄደው ይዋጉ ነበር" ተብሎ የታሪክ መጽሐፍ ይጻፍ ይሆናል፣ ለዚህ ትውልድ። በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠሩትን ጥቃቶች ገታ አድርገን የመረጃ መረብ ደኅንነት ጥሰቶች በአገራት ደረጃ እንዴት ነው የሚፈጸሙት፣ ለምንድነው የሚፈጸሙት፣ ምን ያህል አሳሳቢ ናቸው የሚለውን እንመልከት። ሰሞኑን ኢትዮጵያ መሠረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ሙከራ እንዳደረጉባትና እንዳከሸፈችው ገልጸ ነበር። ምንም እንኳን የተፈጸመባት ጥቃት ኢእተዮጵያ እንደላችው ቀላል ባይሆንም ከአራት ዓመታት በፊት ዩክሬን ተመሳሳይ ክስ በሩሲያ ላይ አቅርባ ነበር። ይህ በታሪክ ትልቁ የመረጃ መረብ ጥቃት ነበር የተባለለትን የዩክሬንን ክስተት ዛሬ መልሰን ብንዳስስ ከወቅቱ ጋር ስሜት የሚሰጥ ጉዳይ ይሆናል ብለን ተስፋ አደረግን። ዩክሬንን በእንብርክክ ያስኬዳት ጥቃት ሰኔ፣ 2009 ዓ.ም ጠዋት። ኦሌዳር ቪያንኮ በዩክሬን የጸረ ሳይበር ጥቃት ኩባንያ ባለቤት ነው። አስቤዛ ለመገዛዛት ወደ ሱፐርማርኬት እየሄደ ሳለ ስልኩ ጠራ። የዩክሬን ትልቁ ቴሌኮሚኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ናቸው የደወሉት። "ቪያንኮ! ጉድ ሆነናል ቶሎ ድረስ" አሉት። ብዙም አልደነቀውም። ምክንያቱም ሳይበር ጥቃት በዩክሬን በሽበሽ ነዋ። እሺ እመጣለሁ ብሎ ሕይወቱን ቀጠለ። አስቤዛውን ገዛዝቶ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ነዳጅ ማደያ ገብቶ ነዳጅ ቀዳ። ሒሳብ ሊከፍል ክሬዲት ካርዱን ሲጠቀም ግን ካርዱ አይሠራም። ደነገጠ። በዚያው ቅጽበት በዩክሬን ግዙፍ ኩባንያዎች ወደእርሱ እየደወሉ ነበር። የሁሉም ጥሪ "እባክህን ቶሎ ድረስ፤ ጉድ ሆነናል" የሚል ነበር። ለካንስ ያን ዕለት ማለዳ የደረሰው ጥቃት የሁልጊዜው አይነት አልነበረም። ጥቃቱ ከዩክሬን ተነስቶ 60 አገራትን ያዳረሰ ስለነበር "አንደኛው (የሳይበር) የዓለም ጦርነት" ብለው የሚጠሩት አልታጡም። ዓለም በታሪኳ እንደዚያ ዓይነት ጥቃት ከዚያ ቀደም በጭራሽ ደርሶባት አያውቅም። ይህ ከመሆኑ ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ የሳይበር ጥቃት መረጃዎችን በመለዋወጥ የሚታወቁትና አምስቱ ዓይኖች (The five Eyes) በሚል የሚታወቁት እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ "ሩሲያ አደገኛ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች" ብለው ፍርሃታቸውን ገልጠው ነበር። የፈሩት ደረሰ። የኤቲኤም ማሽኖች ሥራ አቆሙ ለመሆኑ ሳይበር ጥቃት ሲደርስ ምንድነው የሚሆነው? ሚስተር ቪያንኮ ያን ቀን ክሬዲት ካርዱ አልሰራ ሲለው መኪናውን ባለችበት አቁሞ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ካፌ ገብቶ ላፕቶፑን አውጥቶ ወደ ሥራ ገባ። ጥቃቱን ሊዋጋ፣ አንድ ላፕቶፕ ይዞ መሸገ፤ ካፌ ውስጥ። ወዲያውኑ በየአቅጣጫው ከሚገኙ የጸረ ሳይበር ጥቃት ተከላካይ ጓዶቹ ጋር መነጋገር ጀመረ። እርሱ እንደ ጄኔራል፣ እነርሱ እንደ እግረኛ ሠራዊት ጦርነት ጀመሩ። የሁሉም ጦር መሳሪያ ደግሞ ላፕቶፕ ነው። "ወዲያውኑ ይህ ጥቃት እንደተለመደው ተራ ጥቃት እንዳልሆነ አወቅን" ይላል ቪያንኮ። እንዴት አወቀ? ምክንያቱም ውስብስብ ነው፤ ምክንያቱም ሌሎች ጥቃቶች አንድ መሥሪያ ቤትን ነው ኢላማ የሚያደርጉት። ይህኛው ግን ያስተረፈው ነገር የለም። ከትልልቅ የኤሌክትሪክ አመንጪ ድርጅቶች ጀምሮ ትንንሽ የሱፐርማርኬት ቅርንጫፎች ድረስ መዋቅራቸውን አውኮት ነበር። ባንኮች አልቀሩ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን አልተረፈ፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ፍርድ ቤቶች…ዝርዝሩ የትየለሌ ነው። እንዲህ ዓይነት ጥቃት በተራ የመረጃ ቦርቧሪዎች የሚፈጸም ሊሆን እንደማይችል ሚስተር ቪያንኮም ያውቃል፣ ሰይጣንም ያውቃል…አጥቂም ያውቃል…ተጠቂም ያውቃል። አንድ ሰው ነዳጅ ቀድቶ አልያም ምሳውን ምግብ ቤት ውስጥ በልቶ ሒሳብ መክፈል ካልቻለ ምን ማለት ነው? አንድ ዜጋ ያጠራቀመው ገንዘብ ከባንክ ሒሳቡ ሲሰወር ምን ማለት ነው? አንድ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና የሚፈልግ በሽተኛ በሚታከምበት ሆስፒታል ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት በመፈጸሙ መዳን እየቻለ ሲሞት ምን ይባላል? ሩሲያ መሆኗን ማን አወቀ? እንዴት ታወቀ? በዩክሬን ውስጥ የተፈጸመው ይህ የሳይበር ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኮምፒውተሮችን ከጥቅም ውጭ አደረጋቸው። ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስለ ጥቃቱ ለመዘገብ እንኳ ጊዜ አላገኙም። ዝብርቅርቃቸው ወጣ፣ የአንዳንዶቹ ስርጭትም ተቋረጠ። የቪያንኮ ቡድን ከሰዓታት ምርምር በኋላ አንድ ምስጢር ተገለጠለት። ጥቃት አድራሾቹ ጥቃት በሚያደርሱባቸው ኮምፒውተሮች ላይ የሚልኩት መልዕክት "ገንዘብ ክፈሉን፣ አለበለዚያ ኮምፒውተራችሁን እናወድመዋለን" የሚል ነበር። ጎመን በጤና ብለው ገንዘብ የከፈሉትም ቢሆኑ ግን ከጥቃቱ አላመለጡም። ይህ "ገንዘብ ክፈሉና…" የሚባለው ነገር ብዙውን ጊዜ በግለሰብና በትንንሽ የሳይበር ኪስ አውላቂዎች የሚደረግ ሕገወጥ ወንጀል ነው። ልክ ልጅን አግቶ ማስለቀቂያ እንደሚጠይቅ ሽፍታ በሉት። በእንግሊዝኛ "ራንሰምዌር" ይባላሉ። የኮምፒውተር ማጅራት መቺዎች ይህንን ዘዴ የሚጠቀሙት ለፖለቲካ ግብ አይደለም። ብቸኛ ግባቸው ገንዘብና ገንዘብ ነው። ሚስተር ቪያንኮ እንደሚለው በዚህ ዩክሬን ላይ በደረሰ ግዙፉ ጥቃት ታዲያ ተራ የሚባለው ይህ የገንዘብ ጥያቄ ተካቶበታል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አንድ አገር ጥቃት አድርሳ ሳንቲም ክፈሉኝ ልትል አትችልም መቼስ። "ይህ ዘዴ ሆን ተብሎ ጥቃቱ የተፈጸመው በተራ የኮምፒውተር ሽፍቶች እንደሆነ ለማስመሰል የተቀነባበረ ነበር" ይላሉ ሚስተር ቪያንኮ። ምስጢሩ በኋላ ላይ ተደረሰበት። ሩሲያ ይህንን ጥቃት ስታሰናዳ ሆን ብላ ከገንዘብ ጥያቂ ሽፍቶች ኮድ ሰርቃ የዚህ ጥቃት አካል እንዲሆን አድርጋ ነበር። ሩሲያ ምን ለማትረፍ ጥቃት ታደርሳለች? ይህ ጥቃት በዩክሬን ላይ ፖለቲካዊ ጉዳት ለማድረስ በተቀናቃኝ አገር የተሸረበ የሳይበር ወረራ እንደነበረ ይነገራል። በዚያ ጥቃት ወቅት ባንኮች ገንዘብ ማስተላለፍ አቃታቸው። ይህ ቀላል ጉዳት አይደለም። በእኛ አገር ለአንድ ቀን እንኳ ባንክ 'ሲስተም የለም' ሲባል ምን ያህል ሥራ እንደሚስተጓጎል አስቡት። ነገር ዓለሙ የሚሳለጠው በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ታግዞ በሆነባት ዩክሬን በአገር ደረጃ ጥቃት ሲደርስባት ያቺ አገር በእንብርክክ ብትሄድ ምን ይገርማል? በጥቃቱ በኮምፒውተር ቋት ውስጥ የተጠራቀሙ ጠቃሚ መረጃዎች ተደመሰሱ፤ ሆስፒታሎች የበሽተኞቻቸውን ሙሉ አድራሻና የጤና ዝርዝር መረጃቸውን በአንድ ቅጽበት አጡ። ኃላፊዎች ኢሜይል መላክ ተስኗቸው እንደ ድሮ ዘመን በእስክሪብቶ ጦማር መጻፍ ጀመሩ። እንዲሁም ዩክሬን በኒውክሌር ኃይል ጥገኛ ናት። የአገሪቱ ግማሽ ክፍል ኃይል የሚያገኘው ከኒክሌየር ጣቢያ ነው። ከውኃ የሚመነጨው ኃይል 5 ከመቶም አይሞላም። የአገሪቱ ትልቁ የኒክሌየር ኃይል ማመንጫ በዚህ ጥቃት ዝም ጭጭ እንዲል ተደረገ። ይህ ዝርዝር ጉዳት ከረዥሙ ዘርዝር ትንሹ እንጂ ሙሉው አይደለም። ጥቃቱ "ራንሰምዌር" እንዲመስል ለምን ተፈለገ? በምርመራ ወቅት ሳይበር ቦርቧሪዎቹ የተጠቀሙበትን አንድ ኮድ አገኙ እነቪያንኮ። ይህ ኮድ ሲመረመር የተሰረቀው መረጃን ጠልፈው ገንዘብ ከሚጠይቁ ትንንሽ የሳይበር ሽፍቶች እንደሆነ ተደረሰበት። ይህ ኮድ ተሰርቆ ከዋናውና ግዙፉ የሳይበር ጥቃት ጋር እንዲዋሀድ የተደረገው ሆን ተብሎ ጥቃት አድራሹ ተራ "የሳይበር ኪስ አውላቂ" ለማስመሰለ ነበር። ለዚህም ነበር የዚህ ግዙፍ ጥቃት ስም ኖትፔትያ (Notpetya) የሚል ስም የተሰጠው። "ፔትያ" ከአንድ ዓመት ቀደም ብሎ በዚያው በዩክሬን የደረሰ ጥቃት ሲሆን ገንዘብ ለከፈሉ ብቻ መረጃቸውን ይመልስ የነበረ ጥቃት ነው። ኖትፔትያ ልክ እንደ ፔትያ ገንዘብ የሚጠይቅ ነገር ግን ዓላማው ገንዘብ ያልሆነ ጥቃት ማለት ነው። "ዋናው የጥቃቱ ዓላማ አገሪቱን ማዳከም፣ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ ማድረግ፣ የፖለቲካ መረጋጋት እንዳይኖር መሞከር፣ እንዲሁም በአገሪቱ ላይ ፖለቲካዊና የነዋይ ኪሳራን ማድረስ ነበር" ይላሉ ሚስተር ቪያንኮ። ክሬግ ዊሊያምስና የምርመራ ውጤቱ ክሬግ ዊሊያምስ ገና ልጅ እያለ ነው ከቴክኖሎጂ ጋር የተዋወቀው። በ8 ዓመቱ እጁ የገባ ማንኛውንም ነገር መነካካት፣ አፍርሶ መስራት ይወድ ነበር። የአስተማሪዎቹን ኮምፒውር እየቆለፈ ናላቸውን ሲያዞር ነው ያደገው። አሁን በአሜሪካ፣ ታሎስ ውስጥ አሉ ከሚባሉ የሳይበር ጥቃት ተከላካይ ባለሞያዎች አንዱ ነው። ከሥራዎቹ መካከል ጥቃት ከመድረሱ በፊት ማስቆም፣ የጥቃት ወረዳዎችን መለየት፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስጠት ወዘተ ናቸው። ዩክሬን በጥቃቱ ምስቅልቅሏ የወጣ ዕለት እርሱ መረጃው የደረሰው ገና በጠዋቱ ነበር። ዊሊያምስ ተከላካይ ጦሩን ሰብስቦ ምርመራ ጀመረ። ጥቃቱ ልክ እንደ ሰደድ እሳት ዩክሬንን እየለበለባት እንደሆነ ደረሱበት። ዊሊያምስና ጓደኞቹ የጥቃቱ ምንጭ ከየት እንደሆነ ለመመርመር አንድ ሰበዝ መምዘዝ ያዙ። "የሳይበር ጥቃት የሚመረመረው ልክ እንደ ሬሳ ምርመራ ነው" ይላል ዊሊያምስ። አደጋው ከደረሰ በኋላ የአደጋው ቦታ ይታሸጋል፤ ሬሳው (ኮምፒውተሩ) ይከፈታል። ልክ እንደ ወንጀል ምርመራ ጥቃቅን ምልክቶች ሁሉ ይፈተሻሉ፣ ናሙና ይወሰዳል። የኢንተርኔት አሻራ ምርመራ (ፎረንሲክ) ይደረግበታል። ነገሩ የሳይበር ምርመራ (ዲቴክቲቭ) ሥራ ነው። ዊሊያምስ ያን ማለዳ ሲያስታውስ ጥቃቱ የደረሰው በኢሜይል ነው የሚል ነገር በስፋት ይወራ ነበር ይላል። የእርሱ ኩባንየ በቀን በቢሊዮን የሚቆጠሩ ቫይረሶችን ከኢሜይሎች ይለቅማል። ይህ ጥቃት ግን በመልኩም፣ በቅርጹም፣ በዓይነቱም፣ በአፈጣጠሩም እነዚህን ዕለታዊ ቫይረሶች አይመስልም። ክሬግ ዊሊያምስና የምርመራ ቡድኑ ምርመራቸውን ቀጠሉ። በመጨረሻ አንድ ነጥብ ላይ ደረሱ። ኤሚዶግ የሚባል የግብር አከፋፈል ስሌት የሚሰራ መተግበሪያ ሶፍትዌር በዩክሬን በስፋት ይታወቃል። በርካታ ቢዝነሶች ወርሃዊ ግብራቸውን ለማስላት ይህንን መተግበሪያ ይጠቀሙ ነበር። ይህ ኤሚዶግ የሚባል ኩባንያ ታዲያ ጥቃቱ ከመፈጸሙ ሁለት ወር በፊት አንድ ያልተለመደ ባህሪ በመተግበሪያው ላይ ማስተዋሉን አረዳ። ክስተቱ ሲመረመር ታዲያ የሆነ ሰው የዚህን ሶፍትዌር ማለፍያ ቁጥር አግኝቶ ነገሩን ፐውዞታል። አንድ ዩክሬናዊ ይህን ሶፍትዌር ተጠቅሞ የግብር ክፍያዬን አስላልኝ ሲለው መረጃውን ወደ ዋና ሰርቨሩ ይልከዋል። ነገር ግን ቦርቧሪዎች ማለፍያ ቁጥሩን ከደረሱበት በኋላ ተገልጋዩ የግብር ሒሳብ ስሌት ሲጠይቅ መረጃው ወደ ዋናው ቋት (ሰርቨር) መሄዱን ትቶ ወደ ኮምፒውተር ማጅራት መቺዎች ይሄዳል። ይህ ማለት በእነዚያ ሁለት ወራት ውስጥ መረጃ ቦርቧሪዎች የመቶ ሺህዎ ኮምፒውተሮችን የማለፍያ ቁጥር አግኝተው ነበር ማለት ነው። ለዚህ ነበር ጉዳቱ አስከፊ የሆነው። ይህንን ተከትሎም ልክ ሰኔ 20 ማለዳ ላይ ሁሉንም ከዚህ ኤሚዶግ ከተባለ የግብር መክፈያ ሶፍትዌር ጋር የተነካኩ ኮምፒውተሮች በአንድ ምት ዘረራቸው። ታዲያ ይህን ሶፍትዌር የተቀባበለ ሁሉ ነው ጉድ የሆነው። ጉዳቱ በዩክሬን ብቻ አላበቃም፤ ማንኛውም በዩክሬን ከሚገኝ ኩባንያ ጋር ቢዝነስ የሚሰራ ሁሉ በተዘዋዋሪ ጥቃት ደርሶበታል። ለዚህም ነበር ጥቃቱ በ60 አገራት ጉዳት ሊያደርስ የቻለው። ለምሳሌ በአሜሪካ ፔኒሲልቬኒያ የሚገኘ ሆስፒታል ቀዶ ጥገና ማድረግ ባለመቻሉ በሽተኞች ተንገላተዋል። ለምሳሌ በበርካታ አገራት ባንኮች፣ መርከቦች፣ ኢንዱስትሪዎች ሁሉ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የዚያን ጊዜ የሳይበር ጥቃት ልክ እንደ ኮሮናቫይረስ ነበር ከአገር አገር የተዛመተው። የሚደንቀው ታዲያ ከዚህ ሁሉ ጥቃት በኋላ ፈጻሚዎቹ ማንነታቸውን የሚገልጸውን መረጃን አውድመው ነው የጠፉት። ዊሊያምስ ነገሩን በምሳሌ ሲያስረዳ እንዲህ ይላል፡- "ይህ ማለት ባንክ ዘራፊዎች ወደ ውስጥ በማያሳይ መስታወት በተለበጠ ሚኒባስ መጥተው፣ በጥቁር ጭምብል ፊታቸውን ሸፍነው፣ ባንክ ከገቡ በኋላ ባንኩ ያለውን ገንዘብ ሙልጭ አድርገው ከዘረፉ በኋላ በበር ወጥተው በመስኮት ቦምብ ወርውረው ሲሸሹ እንደማለት ነው።" በ60 አገራት ውስጥ በሺህ የሚቆጠሩ ኩባንያዎችን አዳርሶ በመቶ ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ ጉዳት ያደረሰው ይህ ጥቃት በገንዘብ ሲሰላ ግምቱ ቢሊዮን ዶላሮች አይገልጹትም። "በጥንቃቄ ታቅዶ በጥንቃቄ የተፈጸመ የሳይበር ዘረፋ ነበር" ይላል ዊሊያምስ። ጥቃቱን በትክክል ማን ፈጸመው? እንዴትስ እርግጠኛ መሆን ይቻላል? ሾን ከኑክ የመጀመርያው የአሜሪካ ብሔራዊ የሳይበር ደኅንነት ኃላፊ ነው። እንደአውሮፓውያኑ በ2011 ነው ለዚህ ልዩ ኃላፊነት የተሾመው። ይህ በ60 አገራት የደረሰው ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ሲፈጸም እርሱ በዚያ ወንበር ከተቀመጠ 5 ዓመት ሆኖት ነበር። የሳኡዲው ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያ አራምኮን፣ የሶኒ ፒክቸርስ ኢንተርቴይመንትን የሳይበር ጥቃቶች በሚመለከት በርካታ ምርመራዎችን መርቷል። "መጀመርያ አንድ ጥቃት ሲፈጸም…" ይላል ሾን ከኑክ "…የሚከተሉት ጥያቄዎች መፈተሸ ይኖርባቸዋል።" የጥቃቱ መልክና ስፋት ይታያል፣ ማን ሊፈጽመው ይችላል የሚለው ይገመታል። ሃርድዌርና ሶፍትዌሩ ይበረበራል። ጥቃቱን ያደረሰው ኮድ ተገልብጦ ይነበበራል። ይህም "ሪቨርስ ኢንጂነሪንግ" የሚባለው ነው። ኮዱ የተጻፈበት ቋንቋ ቻይንኛ ነው ወይስ አረብኛ? አልያም የላቲን ቋንቋ…ወይስ ባዕድ ፊደላት ናቸው? የሚለው ይጠናል። በምስጢር ቋንቋ የተቆለፈ ኮድ፣ ይተረጎማል፣ ይተነተናል፡፡ ይህም "ዲ-ኢንክሪፕሽን" (de-encryption) የሚባለው ነው። የወንጀሉ ፈጻሚዎች ማንነትና ጥቃቱ ከየት እንደተነሳም ዱካው ይፈለጋል። እንዲህ ዓይነቱ ጥቃት እጅግ ውስብስብ በሆነ ሁኔታ በአገር ደረጃ ሊፈጸም ይችላል። የትኛው አገር? ለምን ብሎ? በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደራጀ ኃይል ሊፈጽመው ይችላል። አንድ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው አሸባሪ ቡድንም ሊፈጽመው ይችላል። እንዲሁ ለጀብዱ ያህል ጥቃት የሚፈጽሙ ወጣቶችም እንዳሉ ሁሉ እንዲሁ አንድ በድብርት የሚሰቃይ ኮምፒውተር መጎርጎር የሚወድ የ2ኛ ደረጃ ተማሪ ሊፈጽመው ይችላል። ከመጀመሪያው ውጪ ያሉት ሁሉም ማለት ይቻላል ወንጀሉን ከፈጸሙ በኋላ አሻራቸውን መፈቅፈቅ ስለማይችሉ ጊዜው ይርዘም እንጂ በቁጥጥር ሥር ይውላሉ። በቁጥጥር ሥር ባይውሉ እንኳ ዱካቸውን ስለማያጠፉት ከየት ሆነው ጥቃቱን እንደፈጸሙት ይደረስበታል። ከዚህ ባሻገር ጥቃቱ የሚፈጸምበት ኮድ የተቀመረበት ሰዓት፣ ለምሳሌ በሥራ ሰዓት ነው ወይስ ከሥራ ሰዓት ውጪ የሚለው ይጠናል። በየትኛው አገር ሰዓት አቆጣጠር? በየትኛው ንፍቀ ክበብ? በየትኛው የኢንተርኔት አድራሻ (IP Address)? ችግሩ ይላሉ ሾን ካኑክ…ችግሩ ሰባሪዎቹ ላቅ ያለ ችሎታና ጥበብ ካላቸው ይህን ከላይ የተዘረዘረውን ዱካ መሰወር አያቅታቸውም። ለምሳሌ ጥቃቱ የተቀመመበትንና የተፈጸመበትን ሰዓትና ቦታ ሆን ብለው ያዛቡታል። ለምሳሌ ግብጽ የተቀመመ የሳይበር ጥቃት ከኢራን እንደመነጨ ሆኖ በኢራን የሰዓት አቆጣጠር፣ በፋርስ ቋንቋ ሊከሸን ይችላል። ጥቃት አድራሾቹ ዱካቸውን ለመሰወር ሆን ብለው ጊዜ፣ ቦታና ቋንቋን ያመሰቃቅሉታል። በዚህ መንገድ ምንም ፍንጭ ካልተገኘ ወደ ፖለቲካ ትርጉም ይኬዳል። ፖለቲካዊ የሳይበር ጥቃት ለምን? ጂኦፖለቲካዊ ምክንያቶች የሚመረመሩት ለብዙ የሳይበር ጥቃቶች ምላሽ ስለሚሰጡ ነው። ለምሳሌ በዩክሬን ላይ በዚህን ዓይነት ረቂቅ ሁኔታ የሳይበር ጥቃት ሊያደርስ የሚችል አገር ማን ሊሆን ይችላል? ምን ለማትረፍ? ብሎ መጠየቅ የመርማሪዎቹ ሁለተኛ ምዕራፍ ላይ የሚጀመር ተግባር ነው። አንድ ጥቃት ያለ ምክንያት ሊሰነዘር የሚችልበት ዕድል ጠባብ ነው። የንዋይ ግብ ከሌለው ፖለቲካዊ ዓላማ ይኖረዋል። የደኅንነት ተንታኞች የጥቃቱን መልክ ከጂኦፖለቲክስ ጋር አጋብተው የሚተነትኑትም ለዚሁ ነው። በሕግ ወይም በወንጀል ምርመራ ይህ "ሰርከምስታንሺያል ኤቪደንስ" ይባላል። ለምሳሌ አንድ ወንጀለኛን ጥፋተኛ ለማድረግ ቀጥተኛ ያልሆኑ ነገር ግን ተዛማጅ ማስረጃዎች ይቀርባሉ። ሚስቱን ገድሏል ተብሎ የሚጠረጠር ባል ጎረቤቱ ወደ መርማሪዎች ቀርቦ 'ሴትዮዋ የሞተች ቀን ማታ ሲዝትባት ሰምቻለሁ' ቢል ይህ ተዛማጅ መረጃ ሆኖ ይመዘገባል። የሳይበር ጥቃትም ሲመረመር ተመሳሳይ ዘዴን ይከተላል። ሁለት አገራት በአንድ ጉዳይ ክፉኛ ሲቆራቆሱ ከነበረ አንዱ አገር ሌላውን ለጥቃቱ ቢጠረጥር ዘላበደ አይባልም። ይህ በዓለም ትልቁ የተባለው የሳይበር ጥቃት በሰኔ 20/ 2009 ዓ.ም ሲደርስም ሩሲያና ዩክሬን ግንኙነታቸው ቋፍ ላይ ደርሶ ነበር። ስለዚህ ከሩሲያ በላይ ተቀዳሚ ተጠርጣሪ ከየት ይገኛል? ጥቃት የደረሰበት አገር ምን ሊያደርግ ይችላል? ዘ ፋይቭ አይስ (The five eyes) የሚባሉት ብልጹግ አገራት ሩሲያ ከጥቃቱ ጀርባ እንደሆነች ለመደምደም ጊዜ አልወሰደባቸውም። ሩሲያ በበኩሏ "ከእኔ ራስ ውረዱ" አለቻቸው። የሆነስ ሆነና ጥቃት የደረሰበት አገር ምን ማድረግ ይችላል። ለዚህ መልስ የምትሰጠን ሊዝ ፊሂል ናት። ሊዝ የሳይበር ሕግ አዋቂ ናት። ኢስቶኒያ ነው የምትኖረው። ጥቃት የደረሰባቸው አገራት ምን ማድረግ ይችላሉ በሚለው ጉዳይ ላይ ጥናትና ምርምር አድርጋለች። የመጀመርያው እርምጃ ክስ ነው ትላለች ሊዝ። ጠላት አገር ጥቃት ተፈጽሞብኛል ብሎ በይፋ መክሰስ፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይፋ ማድረግ 'ተራ ጉዳይ' አይደለም ትላለች። ሩሲያ ግን ግድ ይሰጣታል ይሄ? ሊዝ ለቢቢሲ ጥያቄ ፈጠን ያለ መልስ ሰጠች፤ "በደንብ ነዋ!" ማንም ሰው ሌባ መባል እንደማይፈልገው ሁሉ አገራትም ወንጀለኛ መባል አይፈልጉም። ምክንያቱም ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ ያስከፍላቸዋል። ከፍ ዝቅ አድርጎ የአጥቂውን አገር ስም እየጠቀሱ ድርጊቱን ለዓለም መንገር ተጠቂው አገር ሊወስደው የሚገባ የመጀመሪያው እርምጃ እንደሆነ ሊዝ ካብራራች በኋላ፤ "ይመስለናል እንጂ አገራት እንዴትም ኬረዳሽ ቢመስሉም ወንበዴ ተደርገው እንዲታሰቡ አይፈልጉም።" ሊዝ ይህን ማድረግ ለአጥቂው አገር የማይታይ ጉዳትም አለው ትላለች። በዚህ ጥቃትም ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተወገዘች በኋላ የዲፕሎማሲ ዋጋን አላስከፈላትም ማለት አይቻልም። ሊዝ እንደምትለው በዓለም አቀፍ ሕግ አንድ አገር የሌላን አገር ንብረት ካወደመ ያ አገር ምላሽ የመስጠት ሕጋዊ መብት አለው። ምላሹ ሲሰጥ ግን ተመጣጣኝ መሆን ይኖርበታል። ዩክሬን ታዲያ ምን ማድረግ ትችል ነበር? በሊዝ አተያይ በዚያ ጥቃት ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ ገብታ እየንዳንዱን ኮምፒውተር ወደ መሬት እየፈጠፈጠች እንደከሰከሰችው ነው የሚቆጠረው። አካላዊም፣ ሰብአዊም፣ የገንዘብም ጉዳት ነው ያደረሰችው። ስለዚህ ዩክሬን ተመጣጣኝ ምላሽ መስጠት መብቷ ነው። ምላሹ ተመጣጣኝ መሆን አለበት ሲባል ግን ተመሳሳይ መሆን አለበት ማለት ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ የሳይበር ጥቃት የደረሰበት አገር፣ ተመጣጣኝ የሳይበር ጥቃት ማድረስ ይችላል። ወይም ደግሞ አንዳንድ ሁነኛ መሥሪያ ቤቶችን በሚስጢር የቁልፍ ጋን በመቆለፍ (encription) "ካሳ ካልተከፈለኝ ቁልፉን አልሰጥም" ማለት ትችላለች። ለምሳሌ ለጥቃቱ ካሳ ካልተከፈለኝ የአየር ክልሌን ለንግድ አውሮፕላኖች ማረፍያም አልከፍትም ልትል ትችላለች። ይህ ሁሉ ስኬታማ የሚሆነው ትላለች ሊዝ "አጥቂና ተጠቂ ተመጣጣኝ የሳይበር ጡንቻ ካላቸው ብቻ ነው።" አሁን ጥያቄው. . . የሳይበር ጡንቻችን ምን ያህል ፈርጥሟል የሚለው ነው።
news-47931844
https://www.bbc.com/amharic/news-47931844
የራሱን የዘር ፍሬ ተጠቅሞ 49 እናቶችን ያስረገዘው የህክምና ባለሙያ
በኔዘርላንድስ የሚገኝ አንድ የስነ-ተዋልዶ ህክምና ባለሙያ የእራሱን የዘር ፍሬ በመጠቀም 49 እናቶችን ማስረገዙ ተረጋገጠ። እናቶቹ ከተለያዩ ፈቃደኛ ከሆኑ የዘር ፍሬ ለጋሾች ለመውሰድ ቢስማሙም ያለእነሱ እውቀት ይህ የስነ-ተዋልዶው ህክምና ባለሙያ የእራሱን የዘር ፍሬ ተጠቅሟል ተብሏል።
ይህ ከሁለት ዓመት በፊት ህይወቱ ያለፈው ዶክተር ኔዘርላንድ ውስጥ በሚገኘው ክሊኒኩ ከ30 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። የዘረምል ምርመራ ውጤት እንዳረጋገጠውም የህክምና ባለሙያው ጃን ካርባት የ49 ልጆች አባት ሆኖ ተገኝቷል። ከ49ኙ ልጆች መካከል አንዷ የሆነችው ጆይ ''ከዚህ በኋላ አባቴ ማነው ስለሚለው ማሰብ ማቆም እችላለሁ። አባቴ ከሁለት ዓመት በፊት ህይወቱ አልፏል'' ስትል እውነታውን ተቀብላዋለች። ''ከ11 ዓመታት ፍለጋ በኋላ አሁን በሰላም ህይወቴን መምራት እችላለው። አሁን ሰላም አግኝቼያለው።'' • ጨው በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ሰዎችን ይገድላል • አራት ንቦች የሰው ልጅ አይን ውስጥ ተገኙ 49ኙን ልጆች ወክሎ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የህግ ባለሙያ ቲም ቡዌተርስ ደግሞ ጉዳዩ በፍር ቤት ተይዞ ለረጅም ዓመታት በመቆየቱ የአሁኑ የምርመራ ውጤትና ፍርድ ቤቱ ማረጋገጫ አስደስቶኛል በማለት ስሜቱን ገልጿል። አብዛኛዎቹ ልጆች የተወለዱት እአአ 1980ዎቹ ውስጥ ነው። አሁን በህይወት የሌሉት ዶክተር ካራባት በፈረንጆቹ 2017 ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦበት ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን በወቅቱ አንደ ተከሳሹን የሚመስል አንድ ልጅ ለፍርድ ቤቱ እንደ ማሳያ ቀርቦ ነበር። ዶክተሩም በ89 ዓመታቸው ነበር በቁጥጥር ስር ዋሉት። • ኢትዮጵያዊያን ቶሎ አያረጁም? • በርካቶች ከምጥ ይልቅ በቀዶ ህክምና መውለድን እየመረጡ ነው በወቅቱም ፍርድ ቤቱ የዘረመል ምርመራ እንዲካሄድ ትእዛዝ አስተላልፎ የነበረ ሲሆን የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ግን ውጤቱ ለህዝብም ሆነ ለ49ኙ ልጆች ይፋ እንዳይሆን ተበይኖ ነበር። ባሳለፍነው የካቲት ወር ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ባሳወቀው መሰረት የዘረ መል ምርመራው ውጤት ይፋ ሆኗል።
50312937
https://www.bbc.com/amharic/50312937
ሦስቱ ሃገራት በዋሽንግተን ምን ተስማሙ?
የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታንና የውሃ አሞላል ሂደትን በተመለከተ ለዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ውይይቶች ውጤት አልባ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።
በዚህም ከግደቡ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ያለው አለመጋባባት እየጎላ መጥቷል። ትናንት የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የልዑክ ቡድናቸውን ይዘው አሜሪካ ከደረሱ በኋላ በጠረቤዛ ዙሪያ ውይይት አድርገው የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። የጋራ መግለጫው ምን ይላል? በውይይቱ ላይ ከሶስቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ባሻገር የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስትር እና የዓለም ባንክ ፕሬዝደንት ተሳታፊ ነበሩ። የሶስቱ ሃገራት ሚንስትሮች በግድቡ አሞላል እና ኦፕሬሽን ላይ የሁሉንም ፍላጎት በሚያረካ መልኩ በትብብር እና በተቀናጀ መልኩ ለመስራት ጽኑ አቋማቸውን ገልጸዋል ይላል ትናንት ምሽት በዋሸንግተን የወጣው መግለጫ። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በየውሃ ሚንስትሮች ደረጃ የሚደረግ አራት መንግሥታዊ የቴክኒክ ስብሰባዎችን ለማካሄድ የተስማሙ ሲሆን፤ የዓለም ባንክ እና አሜሪካ ድጋፍ እንዲሰጡ እና በውይይቶቹ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን መግለጫው ያትታል። በተጨማሪም ሚንስትሮቹ ጥር 6 2012 ዓ.ም. ድረስ ከስምምነት ለመድረስ እንደሚሰሩ እና ኅዳር 29 እና ጥር 4 ዳግም በዋሽንግተን ለመገናኘት እና ሂደቱን ለመገምገም ቀጠሮ ይዘዋል። እስከ ጥር 6 2012 ዓ.ም. ስምምነት ላይ የማይደረስ ከሆነ በ2008 ተፈርሞ የነበረው የጋራ አቋም መግለጫ አንቀጽ 10 ተግባራዊ እንዲሆን ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል። • ሱዳን በህዳሴው ግድብ ጉዳይ አቋሟን ትቀይር ይሆን? • በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም፡ ግብጽ የ2008ቱ ጋራ አቋም መግለጫ አንቀጽ 10 ምን ይላል? ስምምነቱ የተፈረመው በሱዳን ካርቱም ሲሆን፤ የመርሆ መግለጫ አንቀጽ 10 ሶስቱ ሃገራት በአተረጓጓመ ወይም አተገባባር ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶችን በመልካም መንፈስ ላይ ተመስረተው በውይይት ወይም በድርድር ይፈታሉ። ሶስቱ አካላት አለመግባባቶችን በውይይት እና በድርድር መፍታት ቢሳናቸው፤ አደራዳሪ ሊጠይቁ ወይም ጉዳዩ ለየ ሃገራትቱ መሪዎች ወይም ለርዕሳነ ብሔሮቻቸው ሊያሳውቁ ይችላሉ ይላል። የውሃ ሚንስትሩ ሲሌሺ በቀለ (ዶ/ር) የሶስቱ ሃገራት የቴክኒክ ኮሚቴዎች ውይይት እንዲያደርጉ ከመግባባት መደረሱ እንዳስደሰታቸው በትዊተር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል። የዋሽንግተኑ ውይይት፡ ድርድር ወይም ውይይት? በትናንት ውይይት አሜሪካ እና የዓልም ባንክ ተሳትፎ ማድረግ እና በቀጣይ ውይይቶች ላይም በድጋፍ ሰጪነት እና በታዛቢነት በሚኖራቸው ተሳትፎ ላይ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያነሱ አልጠፉም። የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ወደ ዋሽንግተን የምታቀናው ለውይይት እንጂ ለድርድር እንዳልሆነ ገልጿል። • ለህዳሴ ግድብ ግንባታ መዘግየት ምን አይነት መፍትሔዎች እየተሰጡ ነው? • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው የአሜሪካ ግምዣ ቤት ሚንስትር ስቲቭ ማቺን ባደረጉት ግብዣ የሶስቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ወደ ዋሽንግተን ማቅናታቸውን ይጠቁማሉ። "አሜሪካ ይህን ጥሪ ያቀረበችው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ወዳጅ ሃገር ስለሆነች ነው" ያሉ ሲሆን አሜሪካም የአደራዳሪ ሚና እንደሌላት ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ እና የግብጽ መገናኛ ብዙሃን የሶስቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች በዋሽንግተን የከትሙት ለድርድር እንደሆነ በዘገባዎቻቸው ላይ አመላክተው ነበር። ኢጂፕት ቱደይ የተባለው በእንግሊዘኛ የሚታተመው ጋዜጣ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ጋዜጣ የሆነው ገልፍ ኒውስ 'ወደ ድርድር የሚወስደው ወይይት' በአሜሪካው ግምዣ ቤት ሚንስትር ቢሮ ይካሄዳል ሲሉ ዘግበው ነበር። የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ መስከረም 23 እና 24 በህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ የተደረገውን የሦስትዮሽ ምክክር ተከትሎ ግብፅ ዓለም አቀፍ አደራዳሪዎች ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል። የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ፤ አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ላይ ያላት ሚና ከፍ ያለ እንዲሆን ጥሪ አቅርበው ነበር። ኢትዮጵያ በበኩሏ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት፤ በሦስቱ አገራት መካከል የተደረሱ አበረታች ስምምነቶችን የሚያፈርስ ከመሆኑ በተጨማሪ ሦስቱ አገራት እንደ አውሮፓውያኑ በመጋቢት 2017 የፈረሟቸውን የመግለጫ ስምምነቶችም ይጥሳል በማለት የሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል መግለጿ የሚታወስ ነው። ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዋሽንግተን የተካሄደው ውይይት ውጤታማ እንደሆነ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጠቅሰው ነበር። ለምን ወደ አሜሪካ? በናይል ጉዳይ በርካታ ምርምሮችን ያደረጉት ዶ/ር ያእቆብ አርሳኖ ግብፅና ኢትዮጵያ በአሜሪካ ለመገናኘታቸው ምክንያት ሊሆን የሚችለውን ያስቀምጣሉ። እንደ እሳቸው እምነት የአሜሪካ ላወያያችሁ ግብዣ በሶስቱ አገራት በተለይም በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል አለመግባባት እንዳይፈጠር ተቀራርበው እንዲነጋገሩ ለማድረግ ነው። "ምክንያቱም ግብፆች ብዙ ነገሮችን ጮክ አድርገው ቀውስ እንዳለ አድርገው ስለሚያወሩና ስለሚያስወሩ ወዳጅ አገሮች ይህ ያሳስባቸዋል። የአሜሪካም ላወያያችሁ ማለት ለዚህ ይመስለኛል" ይላሉ። በሉንድ ዩኒቨርሲቲ የናይል ተመራማሪ የሆኑት አቶ ወንደሰን ሚቻጎ ኢትዮጵያ ዛሬም በህዳሴው ግድብ ጉዳይ የአቋም ለውጥ እንዳላደረገች ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ለመምከር ወደ አሜሪካ ማቅናቷ የግድቡን ጉዳይ በሰላምና በትብብር ለመፍታት ካላት ፍላጎት የመነጨ እንጂ ትልቅ የአቋም ለውጥ አድርጋ እንደማይሆን አስተያየታቸውን ያስቀምጣሉ። ለምን ወደ አሜሪካ? ለሚለውም አሜሪካ የኢትዮጵያም የግብፅም ወዳጅ ሃገር መሆኗን ነው አቶ ወንደሰን የሚጠቅሱት። አሜሪካ በዚህ መልኩ መንቀሳቀሷ ጉዳዩ ምን ያህል ቦታ እንደተሰጠው የሚያሳይ እንደሆነ፤ ይህም አዎንታዊ እንደሆነም ያክላሉ። "ዞሮ ዞሮ ነገሩ መፈታት ያለበት ግድቡ እንዴት ይሞላ እና ግድቡ እንዴት ይስራ የሚሉ ነገሮችን ከቴክኒክ አኳያ በመመለስ ነው።" የሚሉት አቶ ወንደሰን ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን ከዚህ ቀደምም በዚህ መልኩ አምስት ጊዜ መደራደራቸውን ያስታውሳሉ። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው የሁልጊዜ አቋማ ላይ ትልቅ ለውጥ ያለ አይመስለኝም በማለት የዋሽንግተኑ ውይይት የኢትዮጵያ አቋምን የሚቀይር እንዳልሆነ እምነታቸውን ይገልፃሉ። በሌላ በኩል አሜሪካ ወዳጅነቷ ለግብፅ ያመዝናል፤ ስለዚህም ነገሮች እንደ ግብፅ ፍላጎት ይሄዳሉ የሚል ስጋቶች ስለመኖራቸው የተጠየቁት ዶ/ር ያእቆብ ለአሜሪካ ወሳኙ ብሄራዊ ጥቅሟ እንጂ ሌላ ነገር እንዳልሆነ ይገልፃሉ። በኢትዮጵያ በኩል የህዳሴው ግድብ ግንባር ቀደም ተደራዳሪ የነበሩትና አሁን የምስራቅ ናይል የቴክኒክ አህጉራዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽም በኢትዮጵያ በኩል ምንም የአቋም ለውጥ እንደሌለ ያረጋግጣሉ። እሳቸው እንደሚሉት የኢትዮጵያና የግብፅ መሪዎች የቴክኒካል ስብሰባው እንዲቀጥል ተስማምተዋል። የኢትዮጵያ አቋም አሁንም "የድርድር ነገር ገና ነው" የሚል ነው። "ሁለቱ መሪዎች የቴክኒካል ቲሙ ሥራውን ይቀጥል ልዩነት ካለ እኛ እየተገናኘን እንፈታለን ነው ያሉት" ሲሉም ያክላሉ። አቶ ፈቅአህመድ እንደሚሉት ወደ ድርድር ለመሄድ፤ መጀመሪያ አገራቱ አደራዳሪ ያስፈልገናል ወይ? ድርድሩ በምን ጉዳይ ላይ ነው የሚያተኩረው? በሚሉ ነገሮች ላይ መስማማት አለባቸው። ቀጥሎም የአደራዳሪው ኃላፊነት ምንድን ነው? የሚለውን በጋራ ወስነው አደራዳሪውን በጋራ መምረጥ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ወደ ድርድር ሊኬድ አይቻልም። ወደ ድርድር መሄድ ራሱ ቀላል እንዳልሆነና የራሱ አካሄድ እንዳለውም ያስረዳሉ። ከዲፕሎማሲ አንፃር የአሜሪካን ላወያያችሁ ጥያቄ አለመቀበል ከባድ ስለሚሆን ኢትዮጵያ ከዚህ አንፃር ነገሮችን እንደምታስኬድ ያመለክታሉ አቶ ፈቅአህመድ። የግብፅና የአሜሪካ የቀደመ ንግግር ትናንት ከተካሄደው መርሃ ግብር ቀደም ብሎ የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚህ ሽኩሪ ከፕሬዝደንት ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ ጃሬድ ኩሽነር ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ አስታውቋል። በውይይታቸው ወቅት ሳሚህ ሽኩሪ አሜሪካ እና ግብጽ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውን ወዳጅነት አውስተዋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ግብጽ ባለፉት አምስት ዓመታት የሶስቱንም ሃገራት ፍላጎት ከሚያረካ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት ስታድርግ መቆየቷን እና በኢትዮጵያ በኩል ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ ምክንያት ውጤት አልባ እንደሆነ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሳሚ ሽኩሪ እና ጃሬድ ኩሽነር የመካከለኛውን ምስራቅ እና የፍልስጤም ጉዳይን በማንሳት ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ድረ-ገጽ አስነብቧል።
news-53577597
https://www.bbc.com/amharic/news-53577597
የዓለም ሁለተኛዋ ሴት ቢሊየነር 60 ቢሊየን ብር ለገሰች
ማኬንዚ ስኮት የዓለም 2ኛዋ ሴት ቢሊየነር ናት።
የአማዞን ኩባንያ ባለቤት ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤቱ ወ/ት ማኬንዚ የአማዞን ኩባንያ ባለቤት ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤቱ ማኬንዚ እስከ ዛሬ ለበጎ ተግባር የሚውል 1.7 ቢሊዮን ዶላር ለግሳለች። ይህም በብር ሲሰላ ወደ 60 ቢሊዮን ብር ይጠጋል። ማኬንዚ ይህን አዱኛዋን የለገሰችው በዋናነት የጥቁሮች ኮሌጅ ለሚባሉት የትምህርት ተቋማት፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለሚሰሩ ድርጅቶች እንዲሁም ለጤና ተቋማት ነው። ማኬንዚ ይህንን ድምር የልግስና አሐዝ ይፋ ያደረገችው በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ ሲሆን 'ቤዞስ' የሚለውን የቤተሰብ መጠርያዋ ሆኖ የቆየውን ስም ማስቀየሯን በዚሁ አጋጣሚ ይፋ አድርጋለች። ማኬንዚ ከዓለም ቁጥር አንዱ ቢሊየነር ጄፍ ቤዞስ ጋር ሰማንያቸውን የቀደዱት ባለፈው ዓመት ነበር። ፎርብስ እንደሚለው የማኬንዚ አዱኛ ሲሰፈር አሁን 62 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል። ይህም በዓለም እጅግ የናጠጠች ሁለተኛዋ ሴት ሀብታም ያደርጋታል። የልቦለድ ጸሐፊዋ ማኬንዚ ቤዞስን ያገባችው አማዞንን ከመመስረቱ አንድ ዓመት በፊት ነበር። ያኔ በአማዞን ከተቀጠሩ የመጀመርያዎቹ ሠራተኞች አንዷ ናት። ፍቺ ስትፈጽም ታዲያ የድርጅቱ 4 ከመቶ ንብረት ይገባታል ስለተባለ ይህንኑ አዱኛ ወስዳለች። ማኬንዚ ከቤዞስ ጋር ፍቺ ከፈጸመች በኋላ የመጀመርያ ተግባሯ ያደረገችው የልግስና ቅጽ መሙላት ነበር። በዓለም እጅግ የናጠጡት ዋረን በፌትና የቀድሞው የማይክሮሶፍት አለቃ ቢል ጌትስ ከባለቤቱ ሜሊንዳ ጋር በመሰረቱት የበጎ አድራጎት ድርጅት ቢሊዮኖችን ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። ይህንኑ እየፈጸመች ነው ዛሬ። የቢልጌትስና ሜሊንዳ ድርጅት ባለጸጎች አብዛኛውን ድርሻቸውን ለበጎ ሥራ እንዲያውሉ ለማበረታት የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው። ማኬንዚ ይህን ዓመት በታላቅ ሐዘንና ልብ መሰበር እንዳሰለፈች የገለጸች ሲሆን ይህም የኮሮናቫይረስ ያመጣው ጣጣ እንደሆነ አብራርታለች። ችግሩን ለመቅረፍና ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግም እርዳታ እንደምታደርግ ተናግራለች። በሽታው በድሀና ሀብታም እንዲሁም በጥቁርና ነጭ መሀል ያለውን ልዩነት ያጋለጠ ነበር ያለችው ማኬንዚ የዘር ልዩነትን ለማጥበብ ለሚሰሩ ተግባራት ብቻ ወደ 600 ሚሊዮን ዶላር መለገሷን ገልጻለች። በታሪክ የጥቁሮች ኮሌጅ ተብሎ ለሚጠራው ተስክጊ ዩኒቨርስቲ 20 ሚሊዮን ዶላር መለገሷና ይህም በኮሌጁ ታሪክ ትልቁ ልግስና መሆኑን የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ሊሊ ማክኔይር ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርስቲ የግብረሰናይ ጉዳዮች አጥኚ የሆኑት ፕሮፌሰር ብራይን ሚተንዶርፍ የማኬንዚ እርዳታ ከባለጸጎች ሁሉ ይለያል ይላሉ። "አንዳንድ ልግስናዎች ለሰጪው ገጽታ ግንባታ የሚውሉ ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ የምርም ለውጥ ለማምጣት የሚሰጡ ናቸው። የማኬንዚ ከሁለተኛው ይመደባል" ብለዋል ፕሮፌሰሩ። የማኬንዚ እርዳታ በተለይ አሁን ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ባጋጠማቸው ጊዜ መሆኑ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል ፕሮፌሰር ብራየን።
news-50970108
https://www.bbc.com/amharic/news-50970108
በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ሶስቱ ፓርቲዎች ጥምረት ለብልጽግና ስጋት?
በአገራችን ሕጋዊ እውቅና ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር ብዛት ከ100 በላይ የመሆናቸው ዜና ብዙዎችን አስገርሞ ነበር። የኦሮሞን ህዝብ እና ጥቅም እናስከብራለን ብለው በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ቁጥርም ቢሆን ቀላል የሚባል አይደለም።
ከግራ ወደ ቀኝ፦ከማል ገልቹ (ብ/ጀ)፣ ዳውድ ኢብሳ፣ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)፣ ጀዋር መሐመድ ቁጥራቸው ይህን ያህል ይብዛ እንጂ፤ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑት ጥቂቶቹ ናቸው። በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችና የህዝብ ድጋፍ ካላቸው ጥቂት ፓርቲዎች መካከል፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እንዲሁም የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) ተጠቃሽ ናቸው። • የቤሻንጉል ክልል ምክር ቤት አባል እና የኢኮኖሚ ዘርፍ ሰብሳቢ በታጣቂዎች ተገደሉ እኚህ በክልሉ ተጽእኖ ፈጣሪ ናቸው የሚባሉት ፓርቲዎች፤ ጥምረት ሊፈጽሙ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ኦፌኮን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ መቀላቀላቸው የተሰማው አቶ ጀዋር መሐመድ፣ ለመገናኛ ብዙኀን በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የሶስቱ ፓርቲዎች ጥምረት በቅርቡ እውን ሊሆን እንደሚችል ጥቆማ ሰጥተዋል። አክለውም የሶስቱ ፓርቲዎች ጥምረት ነገ (ዓርብ) ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ይህ ፓርቲ በፕ/ር መረራ ጉዲና ሊቀ መንበርነት የሚመራ ሲሆን፤ እንደ በቀለ ገርባ እና ጃዋር መሐመድን የመሳሰሉ በክልሉ ፖለቲካ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን በአባልነት ይዟል። ኦፌኮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች 'ትልቁ' ፓርቲ ስለመሆኑ የሚናገሩ በርካቶች ናቸው። ኦፌኮ ከዚህ ቀደም በነበሩ ሃገራዊ ምርጫዎች ላይም ተሳትፎ ነበር። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ኦነግ ከተመሰረት ከ40 ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ከዚህ ቀደም 'ሽብርተኛ' ተብሎ ተፈርጆ የነበረው ኦነግ፤ በርካታ ዓመታትን በትጥቅ ትግል፣ ማሳለፉ ይታወሳል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት ዳውድ ኢብሳ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወሳል። • በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ የታገቱት ስድስት ታዳጊዎች ለምን ተገደሉ? ኦነግ ልክ እንደ ኦፌኮ ሁሉ ተጽእኖ ፈጣሪ ስለመሆኑ ብዙዎች የሚስማሙ ሲሆን፣ በመጪው ግንቦት ወር እንደሚካሄድ በሚጠበቀው ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜም ተሳታፊ ይሆናል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) ኦብፓ በብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራ ፓርቲ ነው። ብ/ጀ ከማል ገልቹ ከፓርቲያቸው አባላት ጋር በኤርትራ እንዲሁም በኡጋንዳ መሽገው የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩን ጥሪ ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ይታወሳል። ብ/ጀ ከማል ወደ ሃገር ከተመለሱ በኋላ ለስድስት ወራት ያክል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮን መምራታቸው ይታወሳል። አብፓ የብ/ጀ ከማል ገልቹ የትውልድ ስፍራ በሆነው አርሲ እንዲሁም በአንዳንድ የባሌ አካባቢዎች ድጋፍ እንዳለው ይታመናል። ለመሆኑ ሶስቱ ፓርቲዎች ቢጣመሩ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ብልጽግና ፓርቲ የሚፈጥረው አንድምታ ምንድነው? የኦሮሚያን ፖለቲካ በቅርብ የምትከታተለው የአዲስ ስታንዳርድ መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ የሆነችው ጸዳለ ለማ በዚህ ላይ ለቢቢሲ አስተያየቷን ሰጥታለች። ጥያቄ፡ እነዚህ በክልሉ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ሶስቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች አብረው ለመስራት ቢወስኑ የሚኖረው አንድምታ ምንድነው? ጋዜጠኛ ጸዳለ፡ ባለኝ መረጃ መሠረት በፓርቲዎቾ መካከል ሶስት አይነት ድርድሮች እየተካሄዱ ነው። አንደኛው ከምርጫው በፊት ሊኖራቸው ስለሚችለው ትብብር፣ ሁለተኛው ከምርጫው በኋላ እንዴት ሊሰሩ እንደሚችሉና ሶስተኛው ደግሞ አንድ ላይ ሆነው ከሌሎች 'የፌደራሊስት ብሎክ' ጋር እንዴት ሊተባበሩ እንደሚችሉ በሚመለከት ንግግር ላይ ናቸው። በጣም አስፈላጊ የሚመስለኝ ከምርጫ በፊት የሚኖራቸው ንግግር ነው። ሶስቱም ፓርቲዎች ሃገራዊ ፓርቲዎች ስለሆኑ እጩዎቻቸውን በሁሉም አካባቢ የማቅረብ መብት አላቸው። ይህ ማለት ሶስቱም በአንድ ምርጫ ጣቢያ ላይ ሊወዳደሩ ይችላሉ። ይህ ግን የመራጩን ድምጽ ይበታትነዋል የሚል ስጋት አለ። ያንን ለማስወገድ ነው ንግግሩ እየተደረገ ያለው። • ተጨማሪ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ማደራጀት ለምን አስፈለገ? ሁሉም የየራሳቸው ጠንካራ ድጋፍ ያላቸው የምርጫ ጣቢያዎች አሏቸው። ለምሳሌ የከማል ገልቹ (ብ/ጀ) በአርሲ አካባቢ ጠንካራ ድጋፍ አለው። ኦነግ ደግሞ በምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ቦረና እና ጉጂ ጠንካራ ድጋፍ አለው። ኦፌኮ ደግሞ በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ ጥሩ እንቀስቃሴ አለው። ስለዚህ የመራጮችን ድምጽ ሳይበታተን ፓርቲዎቹ ድጋፍ ባላቸው አካባቢዎች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲወዳደሩ እድል ይሰጣል። ከዚህ በተጨማሪም ከምርጫ በፊትና ከምርጫ በኋላ በደጋፊዎቻቸው መካከል ግጭት እንዳይከሰትም የሚያደርግ ንግግር ነው ሶስቱ ፓርቲዎች እያደረጉ ያሉት። ይህ የሚሳካለቸው ከሆነ አንድምታው ትልቅ ነው። የመጀመሪያው የዲሞክራሲያዊ ምርጫ አንዱ መገለጫ ሰላም ስለሆነ፤ ምርጫውን ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ አስተዋጽኦ የጎላ ነው። ሶስቱ ፓርቲዎች የምርጫ ቀጠናዎችን እየለዩ 'እዚህ አከባቢ ያለኝ ድጋፍ ከዚህ ይበልጣል' በመባባል እርስ በእርስ ከመወዳደር ይልቅ አንዱ ከአንዱ የሚተባበር ከሆነ ይህ ትልቅ ነገር ነው። ከምርጫ በኋላ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በጨፌ [የኦሮሚኣ ክልል ምክር ቤት] ውስጥ ምን አይነት ጥምረት መፍጠር ይቻላል የሚል ንግግርም እየተካሄደ ነው። እነዚህ ከምርጫ በፊት እና በኋላ የሚደረጉ ውይይቶች ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው። • ጃዋር ኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን መቀላቀሉ ተረጋገጠ ጥያቄ፡ የእነዚህ ሶስት ፓርቲዎች ጥምረት መፍጠር የተሻለ ድምጽ ሊያስገኝላቸው ይችላል? ጋዜጠኛ ጸዳለ፡ ያለ ምንም ጥርጥር። ሁሉም በአንድ ምርጫ ጣቢያ ላይ ሲወዳደሩ፤ የመራጩ ድምጽ ይበታተናል። ማንም አሸናፊ ሳይሆን ሊቀር ይችላል። ጥምረቱ እውን የሚሆነ ከሆነ፤ ለፓርቲዎችም ሆነ ለድምጽ ሰጪ አዎንታዊ ነገር እንደሆነ ነው የምገነዘበው። ጥያቄ፡ የሶስቱ ፓርቲዎች ጥምረት ለብልጽግና ፓርቲ አስጊ አይሆንበትም ታዲያ? ጋዜጠኛ ጸዳለ፡ አሁን ባለው የፖለቲካ ግለት ለብልጽግና ፓርቲ ይህ አሉታዊ አጋጣሚ ነው። ነገር ግን አንድ መገንዘብ ያለብን ምንም እንኳ የፓርቲዎቹ ጥምረት፤ የብልጽግና ፓርቲን ድምጽ የማግኘት እድልን ቢያጠበውም፤ የገዢው ፓርቲ መዋቅር በጣም ጥልቅ ነው። ስለዚህ ኦዲፒ (ብልጽግና ፓርቲ) ተጽእኖ ፈጣሪ ፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ ይቀጥላል የሚል ዕምነት ነው ያለኝ። የፓርቲዎቹ ጥምረት ኦዲፒ ድምጽ እንዲያጣ ያደርገዋል። ያ ማለት ግን ኦዲፒ ወሳኝነትን ያጣል ማለት አይደለም። ለኦዲፒ መልካም አጋጣሚው ነበር የመንግሥት መሰረተ ልማት በእጃቸው ነው። ስለዚህ በፈለጉት ጊዜ ይህን ሃብት ለጥቅማቸው ተግባር ላይ ሊያውሉት ይችላሉ። ጥያቄ፡ ከምርጫው በኋላ ፓርቲዎቹ የምርጫውን ውጤት ለመቀበል ዝግጅቱ ያላቸው ይመስልሻል? ጋዜጠኛ ጸዳለ፡ ከምርጫ በፊት የሚያደረጉት ድርድር ፓርቲዎች አቅማቸውን እንዲያወቁት ትልቅ ጥቅም አለው። አንዳንድ ፓርቲዎች የቀደመ ስማቸውን ይዘው ነው እየተወዳደሩ ያሉት። አሁን ለምሳሌ ኦነግ ፖሊስ የለንም ሲሉ ሰምቻለሁ። የቀደመ ዝናቸውን ይዘው ነው እየተወዳደሩ ያሉት። ፓርቲዎች አንድ አካባቢ ላይ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ እርግጠኛ ሆነው መግባት የለባቸውም። ሽንፈት ሊገጥማቸው እንደሚችል አምነው ነው መቀላቀል ያለባቸው። የሚያደርጉት ንግግር ይህንን ማካተት ይኖርበታል። ሌላው ሁሉም አካል የምርጫ ውጤትን እንዲቀበል፤ በምርጫ ቦርድ ላይ እምነት ሊኖረው ይገባል። በአሁኑ ሰዓት በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በምርጫ ቦርድ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች አሉ። አሁን ላይ እኚህ ቅሬታዎች ትንሸና ከባድ ላይመስሉ ይችላሉ። በኋላ ግን መዘዛቸው ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል። • የቢላል መስጂድንና ራጉዔል ቤተ ክርስትያንን የሚያሰሩት ካህን ምርጫ ቦርድም፤ ለእነዚህ ቅሬታዎች ምላሽ እየሰጠ የእርስ በእርስ መተማመን ላይ መደረስ ይኖርበታል። ምርጫው ሰላማዊ ብቻ ሳይሆን ፍትሃዊም መሆን ይኖርበታል። ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆን ሃላፊነቱ የምርጫ ቦርድ ሲሆን፤ ሰላማዊ እንዲሆን ደግሞ ፓርቲዎች ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። ከምርጫ በኋላ ሊከሰት የሚችል ግጭትን መቆጣጠር የሚችል ተቋማዊ አቅም የለንም። ፓርቲዎቹ ከምርጫ በኋላ በሚከሰቱ ግጭቶች ማንም እንደማያተርፍ አውቀው አለመግባባት እንዳይከሰት መስረት አለባቸው። ጥያቄ፡ እኚህ ሶስቱ ፓርቲዎች የሚለዩበት ነገር ምንድነው? ጋዜጠኛ ጸዳለ፡ በሶስቱ ፓርቲዎች መካከል የሰፋ የርዕዮተ ዓለም ልዩነት የለም። ልዩነታቸው ድጋፍ ያላቸው በተለያዩ የምርጫ ቀጠናዎች መሆኑ ነው። ኦነግ የተወለደበት ወለጋ አካባቢ ድጋፍ አለው። ዝና አለው። የመረራ (ዶ/ር) ፓርቲም ቢሆን፤ እርሳቸው ተወልደው ባደጉበት አካባቢ ነው ድጋፍ ያለው። የከማል ገልቹ (ብ/ጀ) ፓርቲ በተመለከተ አንድ መነሳት ያለበት ቁም ነገር አለ። ይህም የኃይማኖት ጉዳይ ነው። የከማል ገልቹ ድጋፍ በስፋት ያለው አርሲ እና ባሌ ነው ስንል የኦሮሞ ሙስሊም ምርጫ ቀጠናዎች አርሲ እና ባሌ በስፋት መኖሩን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል። የኦሮሞ ሙስሊሞች ምስራቅ ሃረርጌም፣ ድሬዳዋም አሉ። ይሁን እንጂ የኦሮሞ ሙስሊም በስፋት በአንድ ቦታ ተሰባስቦ የሚገኘው በአርሲ እና ባሌ ነው። ፓርቲዎቹ ልዩነታቸው ምንድነው ብሎ መፈለጉ የሚያለፋ ይመስለኛል። • የኦሮሞና የሶማሌ ግጭት የወለደው የቴሌቭዥን ጣቢያ ፓርቲዎች የሚያቀርቧቸው ፖሊሲዎች ላይ ተመስርቶ ድመጽ መስጠት የተለመደ ቢሆንም፣ እኛ ሃገር ያለው ባህል ግን ከፖሊሲ ይልቅ በግለሰቦች ላይ ተመስርቶ ነው ድምጽ የሚሰጠው። ኦፌኮ አዲሱን ቢሯችንን ስናስመርቅ የፓርቲ ፖሊሲያችንን ይፋ እናደርጋለን ብለዋል። ኦነግ ከዚህ በፊት ቃለ መጠይቅ ስናደርግላቸው ቀድሞ የነበራቸው 'የሶሻል ዲሞክራት' አካሄዳቸውን ይዘው ወደ ምርጫ እንደሚገቡ ተገንዝበናል። ፓርቲዎች ልለዝቡ ምን ይዘው እንደመጡ መጠየቅ አለባቸው። ሆኖም ግን ከፊታችን ባለው ምርጫ ላይ ህዝቡ ድምጹን የሚሰጠው ፖሊሲዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሳይሆን የሰዎች ማንነት ላይ በመመርኮዝ ነው። ሰው ሰውን ነው የሚመርጠው።
news-42165549
https://www.bbc.com/amharic/news-42165549
የሕወሓት ግምገማና እርምጃ ወዴት ያመራ ይሆን?
ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ የሰነበተው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከሃላፊነታቸው በተነሱትና በተጓደሉት የፓርቲው መሪና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቦታ ላይ ሽግሽግ በማድረግ ተጠናቋል።
በስፋት ሲነገር እንደነበረው ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የድርጅቱ ሊቀመንበር፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ምክትል ሊቀመንበር እንዲሆኑ ተወስኗል። በተጨማሪም አቶ አስመላሽ ወ/ሥላሴ፣ ዶ/ር አብረሃም ተከስተ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነዋል። ከሌላው ጊዜ በተለየ ለሁለት ወራት ያህል ሲገማገም የቆየው ሕወሓት ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ "ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብና አሠራር እንደወረረው፤ የተማረ ወጣት ኃይል አለማካተቱን እንዲሁም እርስበርሱ በመጠቃቃት እንደተጠመደ" አምኗል። በተጨማሪም የተጠበቀውን ያህል ልማትና ዕድገት አለማስመዝገቡና መሰል ጉድለቶች መታየታቸውን መግለጫው ያትታል። ድርጅቱ መሰል ትችቶችን የሚያንፀባርቁ መግለጫዎችን ሲያወጣ የመጀመሪያው አይደለም። ለመጨረሻ ጊዜ ያወጣው መግለጫም ከዚህ በፊቶቹ የተለየ አንድምታ ያለው አልነበረም። ነገር ግን ባለፈው ሰኞ አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳሳወቀው የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አባይ ወልዱና አቶ በየነ ምክሩ ከሥራ አስፈፃሚ አባልነታቸው ተነስተው በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲያገለግሉ ውሳኔ ሰጥቷል። የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ አባል የነበሩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ደግሞ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑም ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ ድርጅቱ ሁለት ስማቸው በይፋ ላልተገለፀ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ማስጠንቀቂያ መስጠቱንም አስታውቋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው በቀሪ አባላቱ ላይ የሚያካሂደው ሂስና ግለ-ሂስ ቀጥሎም ስብሰባውን አጠናቋል። "የዘገየ እርምጃ" የድርጅቱ የቀድሞ አባልና የአየር ኃይል አዛዥ የነበሩት ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ሃገሪቱ ውስጥ የተከሰተው ፖለቲካዊ ቀውስ እልባት ያገኝ ዘንድ ኢህአዴግን የመሠረቱ ድርጅቶች የሚጨበጥ የፖለቲካ ለውጥና የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ እንዳለባቸው በተለያየ ጊዜ ይገልፁ እንደነበር ይታወሳል። ኦህዴድ ያደረገውን የአመራር ለውጥ አድንቀው ሕወሓትና ብአዴን ግን አስፈላጊውን ግምገማና ማሻሻያ ሳያደርጉ ቆይተዋል ሲሉ ይተቻሉ። "ማዕከላዊ ኮሚቴው የወሰደው እርምጃ ቢያንስ ከሁለት ዓመት በፊት መሆን የነበረበትና የዘገየ ነው" በማለት ለቢቢሲ ይናገራሉ። "አዳዲስ ወጣቶች ወደ ድርጅቱ የሚመጡ ከሆነ ትልቅ የለውጥ ምልክት ነው፤ ድርጅቱ ወዴት እንደሚሄድም አመላካች ነው" ባይ ናቸው ጄኔራሉ። "ጉድለታቸውን ማመናቸው አንድ ነገር ነው። ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ ፀረ-ዲሞከራሲያዊ አስተሳሰብ እንዴት እንደሚወጡ መፍትሄ አበጅተዋል ወይ? የሚለው ነው" ሲሉ ይጠይቃሉ። የቀድሞ የድርጅቱ አመራር የነበሩትና በ1993 ዓ.ም. ለሁለት ሲሰነጠቅ የተገለሉት አቶ ገብሩ አሥራት "ማዕከላዊ ኮሚቴው የወሰደው እርምጃ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መካከል የተፈጠረውን ክፍተት ማሳያ እንጂ የለውጥ ምልክት አይደለም" ይላሉ። "እርምጃው የሕዝቡን በተለይ ደግሞ የወጣቱን ጥያቄ ያልመለሰ ነው" ሲሉም ያስረግጣሉ። ከዚህ በፊት እርሳቸውን ጨምሮ በርካቶች ሲባረሩ የቀደሞው የድርጅቱ ሊቀ-መንበር መለስ 'ሙስና' እና 'ፀረ-ዲሞከራሲ' የመሳሰሉ አጀንዳዎችን ተጠቅመው እንደነበር የሚያወሱት አቶ ገብሩ፤ አሁንም 'ፀረ-ዲሞከራሲ' የሚለው ስያሜ የተወሰኑ ሰዎችን ለመምታት የተሸረበ እንደሆነ ያምናሉ። "ለምልክት እንኳን የሚሆን ለውጥ አልታየም። የሥልጣን ሽኩቻ መሆኑን የሚያሳየው ነገር ደግሞ ግልፅ የሆነ ለሃገርና ለህዝብ የሚጠቅም አጀንዳ እንኳን አልተነሳም" ይላሉ። ወዴት ወዴት. . . ? ጄኔራል አበበ ከአቶ ገብሩ በተለየ ቢዘገይም ድርጅቱ ራሱን ካደሰ በሃገሪቱ ውስጥ የሚታዩ የተወሳሰቡ ቀውሶች መፍትሄ ይገኝላቸዋል ብለው ያምናሉ። ጄኔራሉ "ምናልባት ድርጅቱ ለህዝብ ሲታገሉ የቆዩ ወጣቶችን ማካተት ከቻለ ለውጥ ይመጣል" የሚል ተስፋ ሰንቀዋል። ድርጅቱ ውስጥ ያሉም ይሁን ውጭ ያሉ ወጣቶች ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑን ያሰምራሉ ጄኔራል አበበ። ምሁራንና ወጣቶችን ወደ ድርጅቱ ማምጣት ከተቻለ ቢያንስ በግማሽ ያህል እንኳን መዋቅራዊ ለውጥ እንደሚቻል ይናገራሉ። "አረንቋ ውስጥ ነው ያሉት" "ከሁለት ወይም ከሦስት ሰዎች ውጪ በሥራ አስፈፃሚው ውስጥ ንፁህ አባል የለም" ይላሉ ጄኔራል አበበ። "ጭቃ ውስጥ ነው ያሉት። ከዚህ ጭቃ መውጣት ይችላሉ ወይ?" በማለት ይጠይቃሉ። የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለም መብራህቱ በበኩላቸው "ድርጅቱ ውስጥ እየተከናወነ ያለው ትግል የተሻለ ነገር ለማምጣት ነው" ሲሉ ይናገራሉ። "የመጠቃቃት ሳይሆን የመገማገምና መስመርን የማጥራት ሥራ ነው እየተሠራ ያለው" ብለውም ያምናሉ። "አሁንም ብዙ አቅም ያለው አመራር አለ፤ ጠንካራና ቅን ወጣቶች ከድርጅቱ ሸሽተዋል ብዬ አላምንም" ባይ ናቸው። ከዶክተሩ ሃሳብ ሌላ ጫፍ የሚገኙት ጄኔራል አበበ አሁን ያለውን አመራር "የበሰበሰ" እና "ሐሳብ የማያመነጭ" ሲሉ ይገልፁታል። "ድርጅቱ አሁን ባለው አቅም ችግር መፍታት አይችልም" ሲሉ ይደመድማሉ። የህወሓት የሥራ አስፈፃሚ አባላት እነማን ናቸው ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ሽረ ወረዳ የተወለዱት ዶ/ር ደበረፅዮን ከልጅነታቸው ጀምሮ በጣም ጎበዝ ተማሪ እንደነበሩ መረጃዎች ያመላክታሉ። አራት ነጥብ ይዘው ወደ አዲስ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቀላቀሉበት በአጭር ጊዜ ትመህርታቸውን አቋርጠው ነበር ወደ ትጥቅ ትግሉ ያመሩት። ከዝያም በድርጅቱ ወደ ጣልያን አገር ተልከው በመገኛኛ ቴክኖሎጂ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፤ በ1972 ዓ/ም የድርጅቱ ሬድዮ ጣብያ "ድምፂ ወያነ ትግራይ" በማቋቋም ግንባር ቀደም ተዋናይ እንደነበሩ ይነገራል። በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት መረጃ ሰንሰለት ሰብረው በመግባትና በማክሸፍ ይታወቃሉ። እንዲሁም ደግሞ በድርጅቱ "ባዶ ሽድሽተ" በመባል የሚታወቀው የድርጅቱ የደህንነት ክፍልም ውስጥ አገልግለዋል። ግንቦት 20/1983 ዓ.ም. ኢህአዴግ ስልጣን በተረከበበት የደህንነት መ/ቤቱን ይመሩ የነበሩት የአቶ ክንፈ ገ/መድህን ምክትል ሆነውም አገልግሏል። ቀደም ሲል ያቋረጡትን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ተከታትለው የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተቀብለዋል። እንዲሁም ደግሞ የዶክትሬት ድግሪያቸው ከታዋቂው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ለንደን ያገኙ ሲሆን፤ በርካታ ፅሁፎቹን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ማሳተማቸው ይነገራል። በስማቸው የሚታወቅ የሶፍትዌር የፈጠራ ባለመብት ሲሆኑ፤ ሶፍትዌሩ በኣማዞን የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መረብ ውስጥ ሰፍሮ ይገኛል። ። በ1993 ዓ/ም በድርጀቱ ውስጥ በተፈጠረ መሰነጣጠቅ፤ የተሸነፊው ቡድንን ሃሳብ አራምደሃል ተብለው ወደ ወረዳ አስተዳደር ዝቅ ብለው እንዲሰሩ መደረጋቸው ይነገራል። ሆኖም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽንና ኮሙንኬሽን ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ፤ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪ ሆነውም ሰርተዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ማስተባበርያ ብሔራዊ ም/ቤት ሰብሰቢም ናቸው። አሁን ሊቀመንበር ሆነው ከመሾማቸው በፊት ድርጅቱን በምክትል ሊቀመንበርነት ሲመሩት ቆይተዋል። ከሁለት ዓመት በፊት በተካሄደው 12ኛ ጉባኤ ላይም የጉባኤተኛው ከፍተኛውን ድምፅ ያገኙ ሲሆን የድርጅቱ ሊቀመንበር ይሆናሉ የሚል ግምት ተስጥቷቸው ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ በ1965 በአላማጣ ከተማ የተወለዱት አቶ ጌታቸው ረዳ ካሕሳይ፤ በ"ታዳጊዋ ኢትዮጵያ" ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።፥ በ1990 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከህግ የትምህርት ክፍል የተመረቁት አቶ ጌታቸው፤ ከሌላ አሜሪካዊው ዜጋ በመሆን የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የህግ ፋኩልቲ መስራች ናቸው። ከዚያም የህግ አስተማሪ ሆነው ሰርተዋል። በትምህርታቸው በአሜሪካ የሚገኘው አላባማ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጤት ሁለተኛ ድግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፤ ቅርበት ያለቸው ሰው ለቢቢሲ እንደገለፀፁልን ተቋሙ የክብር ዶክተርትም ሰጥቷቸዋል። አቶ ጌታቸው በ1997 ዓ/ም ምርጫ ማግስት ከፍተኛ ተነባቢ በነበረው በአዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ በሚያቀርቧቸው መከራከርያ ሓሰባቦችና ፅሁፎች ብዙዎቹ ያስታውሷቸዋል። ከዚያም ቀጥሎ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና ኮምኒኬሽንስ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ጀነራል ሆነው ሰርተዋል። እንዲሁም ደግሞ 'ኤ ዊክ ኢን ዘ ሆርን' በመባል የሚታወቀው የመስሪያ ቤቱ ድረ ገፅ አዘጋጅና ፀሃፊ ነበሩ። አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ውጭ ጉዳይና ምክትል ጠ/ሚኒስተር ሆነው በተመረጡበት ወቅት ልዩ አማካሪያቸው ሆነው የሰሩ ሲሆን፤ ጠ/ሚኒሰትር ሲሆኑ ደግሞ የእሳቸው ልዩ አማካሪ ሆነው መሾማቸው ይታውሳል። ቀጥለውም የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ለሁለት ዓመት ተቋሙን መርተዋል። በአሁኑ ወቅት የህግ ማሻሻያ ተቋምን በዳይሬክተርነት ይመራሉ። አቶ ጌታቸው በአሁኑ ወቅት በትጥቅ ትግሉ ያልተሳተፉ የሥራ አስፈፃሚ አባል ከሆኑት ጥቂቶች መካከል አንዱ ናቸው። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር (መንጀሪኖ) በውጊያና በፖለቲካ ኣቋማቸው በስፋት ከሚታወቁት ሴት ታጋዮች መካከል አንዷ ናቸው። የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን በኤርትራ መንደፈራና አስመራ ከተሞች "እንዳደናግል" የጣልያን ትምህርት ቤት ተከታትለዋል። ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ በትምህርታቸው ጎበዝና ተሸላሚ ተማሪ እንደነበሩ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ወንደማቸው ይናገራሉ። በ1967 ዓ/ም ወደ ዓድዋ በማምራት የዘጠነኛ ክፍል በንግስተ ሳባ ትምህርት ቤት በመከታተል ላይ ሳሉት ነበር ትምህርታቸውን ኣቋርጠው በ1971 ዓ/ም ወደ ትጥቅ ትግል ያመሩት። የትጥቅ ትግሉን መጠናቀቅ ተከትሎ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መጀመርያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን በግላቸው በለንደን ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝተው በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ፊት ለፊት መናገር የሚወዱና በፖለቲካ ብስለታቸው ብዙ ጓዶቻቸው የሚያደንቋቸው ሲሆኑ በተለይ አቶ መለስን በጣም ከተቹ ጥቂቶች መካከል እንደሆኑ ይነገራል። በዚህም ምክንያት ክድርጅቱ አመራር ጋር መጠነኛ ቅራኔ ውስጥ ገብተው ነበር ። መንጀሪኖ የትግል ስማቸው ሲሆን ወንድማቸው ታጋይ ሰለሞን(ሓየት) እና ሁለት እህቶቻቸው (አልማዝና ረግበ) በትጥቅ ትግሉ ኣጥቷል። መንጀሪኖ በ1999 የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ በ2007 ደግሞ የፖሊት ቢሮ አባል ሆነው ተመርጠዋል። ቀደም ሲል የፌደራል ፋይናንስ ኢንተሊጀንስ ማዕከል ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ቀጥለው ደግሞ የድርጀቱ ህዝብ ግንኙነት ሆነው ነበር። ባለፈው ዓመት ደግሞ በኢህአዴግ ሴክሬታርያት የከተማ ሴክተር ሃላፊ ሀኖው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ወ/ሮ ፈትለወርቅ የመጀመሪያዋ የድርጅቱ ሴት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጧል። አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ በትጥቅ ትግሉ የዓይናቸውን ብርሀን ሙሉ ለሙሉ ካጡት መካከል የሆኑት አቶ አስመላሽ ላለፉት ሁለት ዓመታት በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመንግሥት ተጠሪ ናቸው። አቶ አስመላሽ በለያዩ ወቅቶች በሚሰጧቸው ህግ ነክ ማብራሪያዎች በፓርላማ የሚታወቁ ሲሆን የመጀመርያና ሁለተኛ ዲግሪያቸው በህግ ሰርተዋል። እንዲሁም ደግሞ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በአሁኑ ወቅት የዶክትሬት ድግሪ እጩ ናቸው። ዶ/ር ኣብርሃም ተከስተ የዶክትሬት ድግሪያቸው በኢኮኖሚክስ ከስዊዘርላንድ ያገኙ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በትጥቅ ትግሉ ያልተሳተፉ የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባል ከሆኑ ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። ብሔራዊ ፕላኒንግ ኮሚሽን ለሁለት ዓመታት ሚኒስትር ዲኤታ ሆነውም ሰርተዋል። ቀጥለውም የፋይናነስና ኢኮኖሚ ትብብርን በሚኒስትርነት ዲኤታነት ያገለገሉ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የተቋሙ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም በድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ አባል ሆነው ከተመረጡት አራት አዳዲስ አባላት መካከል አንዷ ሲሆኑ፤ ከዚህ በፊት በክልሉ በተለያዩ የሃላፊነት ስፍራዎች ማገልገላቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። በተለይ ደግሞ በትግራይ ምስራቅዊ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች በተለያዩ ወቅቶች በሃላፊነት ሰርተዋል። እንዲሁም ደግሞ በመቐለ ከተማና በክልል ደረጃ የሴቶች ጉዳይ ቢሮዎች ውስጥ አገልግለዋል። ወ/ሮ ኬርያ እምብዛም በህዝብ የማይታወቁ ሲሆን የእሳቸው መመረጥ በብዙዎች ዘንድ የተጠበቀ አልነበረም።
news-53420113
https://www.bbc.com/amharic/news-53420113
"ጥቁረቴን ለማስለቀቅ ስል ቆዳዬን እፈገፍገው ነበር"
ሴቶች ቆንጆ ብቻ እንዲሆኑ ብቻ በሚጠበቅባት ዓለም ውብ ሆኖ ለመገኘት የማይከፈል መስዋዕትነት የለም። ውበት ወይም ቁንጅና ምንድን ነው? ማኅበረሰቡ የፈጠረው አይደለም ወይ የሚለውን መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳብን ስናጤነው ውበት የሞትና ሽረት ጉዳይ ለምን ሆነ? የሚለው ጥያቄ ግራ ያጋባል።
ቆዳቸውን ለማንጣት ቅባቶችን የተጠቀሙት ካሪሽማ፣ አኑሻና ሳብሪና በጥንታዊት ቻይና ሴቶች እግር ትንሽ መሆን አንድ የውበት መገለጫ በመሆኑ እግራቸው እንዲታጠፍና እንዲሰበርም ይገደዱ ነበር። በዓመታት ውስጥ ማኅበረሰቡ በቻይና እንደሚደረገው እጅና እግር ተጠፍሮ እግር ባይሰበርም ባለንበት ዓለም ማስታወቂያዎች፣ ፊልሞች፣ ሙዚቃዎች በተለያ መንገድ ተፅእኖን ያሳርፋሉ። የጎን አጥንትን ከማስወጣት ጀምሮ፣ ከንፈር፣ ጡትና የተለያየ የአካል ክፍልን ለማስተካከል ቀዶ ጥገና የሚያደርጉ በርካቶች ናቸው። የቁንጅና እሳቤ ኢ-ፍትሃዊ ከሆነው አባታዊ ሥርዓት ጋር ብቻ ሳይሆን ከዘረኝነትም ጋር በፅኑ የተቆራኘ እንደሆነ ተችዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። ከዚህም ውስጥ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚፈስበት ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሆነው የቆዳ ማንጫ ምርቶች ይገኙበታል። ነጭ የቆዳ ቀለም የበላይ ነው በሚል እሳቤም በርካቶች ቆዳቸውን ለማንጣት ፊታቸውን ለጉዳት የሚያጋልጥ ቅባቶችን ይጠቀማሉ። በማንኛውም መንገድ ፊትን ለማንጣትም የሚታገሉ በርካቶች ናቸው። "በየቀኑ ገላዬን ስታጠብ የመጀመሪያ ሥራዬ ጥቁረቴ እንዲለቅ በሚል ቆዳዬን መፈግፈግ ነበር" ትላለች ካሪሽማ ሌክራዝ። ማኅበረሰቡ ቆንጆ ነሽ የሚለውን እንዲያጎናጽፋትም ብዙ መስዋዕትነት ከፍላለች። ቆዳዋን ከመፈግፈግ ጀምሮ ቆዳ ሊያነጡ የሚችሉ ቅባቶችንም መጠቀም የጀመረችው ገና በ13 ዓመቷ ነው። "ነጭ የቆዳ ቀለም ቢኖረኝ ቆንጆ እንደምሆን ይሰማኝ ነበር" ትላለች። "ብዙዎች ልቅም ያልኩ ቆንጆ እንደሆንኩ ይነግሩኛል። ነገር ግን በአሳፋሪ ሁኔታ ቆዳዬ ጥቁር ነው" ትላለች የ27 ዓመቷ ካሪሽማ ከቢቢሲ ሬድዮ ዋን ኒውስ ቢት ጋር ባደረገችው ቆይታ። ካሪሽማ የቆዳ ቀለሟ እንዲነጣ ቅባት ያስጀመሯትም ቤተሰቦቿ ናቸው። የመጥቆሯ ነገር በቤተሰቦቿ ዘንድም ተቀባይነት ስላልነበረው እንድትነጣ ወይም ፈካ ብላ እንድትታይ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። "በባህላችን ዘንድ ስር የሰደደ ጉዳይ ነው። አንድ ሰው ቆንጆ የሚባለው ነጭ የቀለም ቆዳ ሲኖረው ነው" ትላለች። ካሪሽማ ባህሌ የምትለው ነጭ የቆዳ ቀለም ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠውን የደቡብ እስያን እይታ ነው። ከቆዳ ቀለም ማንጣት ጋር ተያይዞ ስሙ የሚጠራው 'ፌር ኤንድ ላቭሊ' አምራቹ ዩኒሊቨር ነው። በነጭ ፖሊስ በግፍ የተገደለውን የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ በተፈጠረው ተቃውሞና የዘር ውይይት ግዙፉ የውበት እቃዎች አምራች ዩኒሊቨር ስምና የማስታወቂያ ሃሳቡን እንዲቀይር ተገዷል። ኩባንያው "ነጣና ፈካ" ያለ ቆዳ የሚለውን አባባል በእስያና በአፍሪካ ገበያዎች ላይጠቀም ቃል ገብቷል። ጋብቻ ፈላጊ ጥንዶችን የሚያገናኘው ሻዲ የተባለው በእስያ ተቀማጭነቱን ያደረገ ድረገፅም እንዲሁ "የቆዳ ማፍኪያ" የሚለውን አገላለጹን አስወግዷል። "ፀሐይ ላይ ብዙ አትቀመጪ" እንደ ካሪሽማ ሳብሪና ማንኩም ስለ ጥቁረቷ አሉታዊ ነገሮችን ከቤተሰቦቿ አንደበት በተደጋጋሚ ስትሰማ ነው ያደገችው። "ህፃን ሆኜ የበለጠ እንዳትጠቁሪ ፀሐይ ላይ አትቀመጪ እባል ነበር" የምትለው የ23 ዓመቷ ሳብሪና፤ አገላለጹ በተለይም በፑንጃቢ ቋንቋ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ጨለምተኛ ትርጉም እንዳለውና "መንፈስንም ስብርብር" የሚያደርግ እንደሆነ ገልፃለች። ሳብሪና ቆዳዋን ፈካ የሚያደርግ ቅባትንም እንድትጠቀም ያደረጓት ገና የአስር ዓመት ታዳጊ እያለች ሲሆን ለስምንት ሰዓታት ያህል ያለማቋረጥ ተጠቅማዋለች። የቤተሰብ አባላት ብቻ ሳይሆኑ ማኅበረሰቡ በአጠቃላይ ስለቆዳ ቀለም ያለው አመለካከት ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚፈጥርም ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ላላቸው ህንዳውያን ፈታኝ መሆኑንም ይናገራሉ። ለአኑሻ ትምህርት ቤት እያለች አቻዎቿ በቆዳ ቀለሟ ላይ ይሰጡት የነበረው አስተያት ስሜቷን እንደጎዳውና ለራሷ ያላትን እይታ በዓመታት ውስጥ እንዳሽቆለቆለው ትናገራለች። "አብዛኛውን ጊዜ ቀላ ካለ የቆዳ ቀለም ካላቸው ሰዎች ጋር የማይሆን አይነት ውድድር እገባ ነበር" የምትለው አኑሻ "ትምህርት ቤት ውስጥ ታዋቂ የሆኑትም ሆነ የተሻለ ቦታ የሚሰጣቸው የተለየ ምክንያት ኖሮ ሳይሆን በቆዳ ቀለማቸው ነበር። ነጣ ያሉት ከፍ ያለ ስፍራን ይይዛሉ" ትላለች። ይህም ሁኔታ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳደረባት አኑሻ ከአቻዎቿ ጋር ፎቶ መነሳትን እርም ብላ አቆመች። ራሷንም በተወሰነ መልኩ መጥላት ጀመረች። "በፎቶው ላይ እኔ ጠቁሬ መታየት አልፈለግኩም" በማለት የተሰማትን ስሜት ትገልጸለች። የቆዳ ቀለም የእርከን ደረጃ በደቡብ እስያ የቆዳ ቀለም የእርከን ደረጃ (ከለሪዝም) በተመሳሳይ ሕዝብ (ማኅበረሰብ) ውስጥ የቆዳ ቀለምን መሰረት በማድረግ የሚመድብ የጭቆና መንገድ ነው። ቆዳን ቀለም መሰረት ያደረገ የበላይነት ከቅኝ ግዛት ጋር በፅኑ የተቆራኘ እንደሆነም አጥኚዎች ይናገራሉ "ቆዳቸው ነጭ የሆኑት እንግሊዛውያን ህንድን በቅኝ ግዛት ገዝተዋታል" የሚሉት የሰብዓዊ መብትና ህግ አጥኚዋ እንዲሁም በደቡብ እስያ ያለውን መድልዎ ያጠኑት ዶ/ር ሪቱሙብራ ማኑቬ ናቸው። "ይህም ሁኔታ ቆዳው ፈካ ወይም ነጣ ያለ ማኅበረሰብ የበላይ ነው የሚለው ስሜት እንዲሰፍን መሰረት ጥሏል" ይላሉ። ከዚህ በተጨማሪ በህንድ የሰፈነው ሕዝብን በደረጃ የመመደብ ሥርዓት እንዲሁ ቆዳቸው ነጣ ያለ ሰዎች በማኅበረሰቡ የተሻለ ቦታ እንዲሰጣቸው አድርጓል። ቆዳቸው ጥቁር የሆኑ ሰዎች በመደቡ የመጨረሻ ስፍራን የያዙ ሲሆን እነሱን መንካትም እንደ አስነዋሪና አስጠያፊ ሁኔታ ይታያል። "በህንድ ባለው የማኅበረሰብ ግንኙነት መዋቅር ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው የቆዳ ቀለማቸው ነጣ ያሉ ናቸው። በጋብቻ ውስጥ ራሱ አስፈላጊ ከሚባሉ መስፈርቶች አንዱ የሙሽሪት የቆዳ ቀለሟ ነጣ ማለት ነው" በማለት ያለውን ያስረዳሉ። በተለይም የቆዳ ማፍኪያ (ማንጫ) ቅባቶች በገበያው ላይ መግነንም የቆዳ ቀለም መንጣት በአሁኗ ህንድ ተቋማዊ በሆነ መልኩ ተቀባይ እንዲኖረው አድርጓል። ባለው ባህልም ነጣ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎችን ከፍተኛ ስፍራ እንዲሰጣቸው አድርጓቸዋል። "በጥንት ጊዜ የነበሩ ተቋማትን ብናይ ለምሳሌ የነፃነት ታጋዮች የቆዳ ቀለማቸው ምንም ስፍራ የሚሰጠው አልነበረም" ይላሉ። ሳብሪና "ታዋቂ ሰዎችን አርአያ አደረግኩ" ለሳብሪና የቆዳ ቀለም ማንጣት ከቤተሰቦቿና በተጨማሪ ውሳኔዋ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳረፈባት የህንድ ፊልም ኢንዱስትሪን የሚመሩት የቦሊውድ ተዋናዮች እንደሆኑ ትናገራለች። "ታዋቂ ተዋናዮች የሚያደርጓቸውን ሁሉ እከታተለሁ እናም እነሱ አርአያ ሆነውኛል" ትላለች። የቦሊውድ ተዋናዮች የቆዳ ቀለምን የሚያነጡ ምርቶችን በማስተዋወቅም በከፍተኛ ሁኔታ የሚተቿቸው አሉ። "የቆዳ ቀለማችን ጠቆር ላልነው እነዚህን ምርቶች መጠቀም ቆዳችንን ፈካ እንደሚያደርገውና ልዩነት እንደሚያመጣ እናምናለን። ምክንያቱም ታዋቂ ሰዎች ብለውታልና" በማለትም ታስረዳለች። አንዳንዶችም ማስታወቂያዎች ላይ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላት ሴት ማንም ሳይፈልጋት ይቀርና እነዚህን የቆዳ ማንጫ ምርቶችን ስትጠቀም ወንዶች በውበቷ ሲሳቡም ያሳያሉ። የቆዳ ቀለም ማንጣት ሁኔታ በማስታወቂያዎች ብቻ የተወሰነ አይደለም። "በፊልሞችም ላይ እንዲሁ የቆዳቸው ቀለም ፈካ ያሉ ሰዎች የበለጠ ውብ ተደርገው ይሳላሉ። እኔም በቴሌቪዥን የማያቸውን ሰዎች የበለጠ መምሰል ፈለግኩ" በማለትም ሳብሪና ታስረዳለች። "አሁንም የቆዳ ማንጫ ቅባት እጠቀማለሁ" ካሪሽማና ሳብሪና የቆዳ ማንጫ ምርቶች ካላቸው የጎንዮሽ ጉዳት ጋር በተያያዘና በዓመታት ውስጥም ጥቁር የቆዳ ቀለማቸውን በፀጋ በመቀበላቸው ምርቶቹን መጠቀም አቁመዋል። የአኑሻ ጉዞ ግን የተለየ ነው። በዓመታት ውስጥ ቤተሰቧና ማኅበረሰቡ የቆዳ ማንጫ ምርቶችን እንድትጠቀም ከፍተኛ ተፅእኖ ቢያሳርፉባትም በአሁኑ ሰዓት ግን እነዚህን ምርቶች ለመጠቀሟ ምክንያቷ ሌላ ነው። አኑሻ "የቆዳ ማንጫ ምርቶችን የሚጠቀም ሰው ሁሉ በቋሚነት ቆዳው እንዲነጣ ይፈልጋል ማለት አይደለም። ምርቶቹ ቆዳን መገርጣትን በማስቀረት የታደሰ ፊት ይሰጣሉ" ትላለች። አኑሻ ሜካፕ ለመጠቀምም እነዚህ ምርቶች አመቺ መሆናቸውንም ታስረዳለች። ሆኖም በህፃንነቷ እነዚህን ምርቶች እንድትጠቀም ባትደረግ ኖሮ ባሁኑ ወቅት ዘወር ብላ ልታያቸው እንደማትችል አልደበቀችም። ቤተሰቧም ሆነ ማኅበረሰቡ ያሳደረባት ተፅእኖ እንዲህ በቀላሉ ትቷት የሚሄድ አልሆነም። በቅርብ ጊዜያት የቆዳን ቀለም መሰረት ያደረገ የማኅበረሰብ የደረጃ አመዳደብም ሆነ እነዚህን ምርቶች በተመለከተ ውይይቶች መኖራቸውን ካሪሽማ ትናገራለች። "ከቤተሶቦችም ጋር ግልፅና ተገቢ በሆነ መንገድ መነጋገር ጀምረናል" ትላለች። በመላው ዓለም "ፌይር ኤንድ ላቭሊ" በሚለው ምርቱ ታዋቂ የሆነው ዩኒሊቨርም ሆነ ሎሬል ስምና የማስታወቂያ ሃሳባቸውን ቢቀይሩም ለሳብሪና ይህ በቂ አይደለም። "የምርቶቹን ስም መቀየር ምርቶቹን ከገበያ አያጠፋቸውም። የቆዳ ማንጫ ምርቶቹ ገበያ ላይ እንዳሉ እናውቃለን። ምርቶቹ ናቸው መወገድ ያለባቸው" ትላለች። ካሪሽማ በበኩሏ "ወደ ልጅነቴ መመለስ ብችል፤ ለህፃኗ እኔ እንዲህ አይነት የቆዳ ማንጫ ምርቶችን አትጠቀሚ፤ አቁሚ እላት ነበርም" ብላለች። "የቆዳሽ ቀለም ውበት ነው እላት ነበር። ጥቁረትሽ ሜላኒን የተሰኘው ንጥረ ነገር ማሳያ እንደሆነም አስረዳት ነበር" በማለት አጠቃልላች።
news-56755326
https://www.bbc.com/amharic/news-56755326
ኮሮናቫይረስ ፡ ሕፃናትን አያጠቃም የሚባለው ኮሮናቫይረስ በርካቶቹን እየገደለ ነው
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ከአንድ ዓመት በላይ ሲሆነው በብራዚል የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ሆኗል።
በኮቪድ -19 ህይወታቸው የሚያልፍ ሕፃናት እምብዛም እንደሆነ ማስረጃዎች ቢኖሩም በብራዚል ግን 1,300 ሕፃናት በቫይረሱ ሞተዋል። አንድ ሐኪም የጄሲካ ሪካርቴን የአንድ ዓመት ልጅ የቫይረሱ ምልክቶች የሉትም በማለት የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርግ ፈቃደኛ አልሆነም ነበር። ከሁለት ወር በኋላ ግን በበሽታው ምክንያት በተፈጠረ ችግር ህይወቱ አለፈ። መምህርት ጄሲካ ሪካርቴ ለሁለት ዓመታት ያደረገችው የማርገዝ ሙከራ ባለመሳካቱ ልጆች አይኖሩኝም ብላ ተስፋ ቆርጣ ነበር። በኋላ ግን ሉካስን ፀነሰች። "ስሙ የመጣው ከብርሃን ነው። እሱም የህይወታችን ብርሃን ነበር። ደስታችን ከገመትነው እጅግ የላቀ መሆኑን አሳይቶናል" ትላለች። ሁሌም ጥሩ የምግብ ፍላጎት የነበረው ሉካስ ፍላጎቱን ሲያጣ አንድ ነገር እንደተፈጠረ ተጠራጠረች። መጀመሪያ ላይ ጥርስ እያወጣ ይሆን ብላ ጄሲካ አስባ ነበር። የሉካስ የክርስትና እናት ነርስ ስትሆን የጉሮሮ ህመም ሊሆን ይችላል የሚል ሃሳብ ሰጠች። በኋላም ትኩሳት፣ ከዚያም ድካም ቆይቶም ለመተንፈስ በመቸገሩ ጄሲካ ወደ ሆስፒታል ወስዳ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርግ ጠየቀች። "ሐኪሙ የኦክስጅን መጠኑን ለካ። ፣ የሉካስ ኦክስጅን 86 በመቶ ነበር። ይህ ማለት ትክክለኛ እንዳልሆነ አውቃለሁ" ትላለች ጄሲካ። ትኩሳት ስላልነበረው ሐኪሙ "አትጨነቂ። የኮቪድ-19 ምርመራ አያስፈልገውም። ምናልባት ትንሽ የጉሮሮ ህመም ብቻ ሊሆን ይችላል" ይላታል። ኮቪድ-19 በልጆች ላይ መገኘቱ እምብዛም መሆኑን ለጄሲካ ነግሮ ጸረ ተህዋሲ መድኃኒቶችን ሰጥቶ ወደ ቤቷ ላካት። ጥርጣሬ ቢኖራትም ሉካስን በግል እንዲመረመር የማድረግ አማራጭ አልነበራትም። ለ10 ቀናት የተሰጠውን አንቲባዮቲክ ሲጨርስ የተወሰኑት ምልክቶቹ ጠፉ። ድካሙ ግን እንደቀጠለ ሲሆን ይህም የኮሮናቫይረስ ጉዳይ ጄሲካን አሳሰባት። "ለክርስትና እናቱ፣ ለወላጆቼ፣ ለአማቴ በርካታ ቪዲዮዎችን ልኬ ነበር። ሁሉም ሰው እያጋነንኩ እንደሆነ ነው የሚያስበው። ብዙ እንዳስብ ስለሚያደርገኝ ዜና ማየቴን ማቆም እንዳለብኝ ይነግሩኛል። እኔ ግን ልጄ ልክ እንዳልሆነ አውቅ ነበር። አተነፋፈሱም ትክክለኛ አልነበረም" ትላለች። ይህ ግንቦት 2020 ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እየጨመረ ነበር። በሰሜን ምሥራቅ ብራዚል ሴአራ በተባለችው መኖሪያ ከተማዋ ታምቦሪል ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በከተማዋ ሁሉም ሰው ይተዋወቃል። በከተማው ድንጋጤ ተፈጠረ።" የጄሲካ ባለቤት የሆነው እስራኤል በበኩሉ በድጋሚ ወደ ሆስፒታል ቢሄዱ እርሷ እና ሉካስ በቫይረሱ የመያዝ ዕድላቸውን ይጨምረዋል የሚል ስጋት አድሮበታል። ሳምንታት ሲያልፉ ሉካስ የበለጠ እንቅልፋም ሆነ። በመጨረሻም በጎርጎሮሳዊያኑ ሰኔ 3 ቀን ሉካስ ምሳ ከበላ በኋላ ምግቡ ሊረጋለት አልቻለም። ጄሲካ ፈጥና እርምጃ መውሰድ እንዳለባት አወቀች። በአካባቢያቸው ወደሚገኘው ሆስፒታል ተመለስው ሄዱ። ሐኪሙ ሉካስን የኮቪድ-19 ምርመራ አዘዘለት። እዚያ የምትሠራው የሉካስ የክርስትና እናትም ውጤቱ ፖዘቲቭ መሆኑን ለባልና ሚስቱ ገለጸች። ጄሲካ በበኩሏ "በወቅቱ ሆስፒታሉ እንኳን አስታዋሽ አልነበረውም" ትላለች። ሉካስ ራቅ ብሎ ወደሚገኘው የሕፃናት ክፍል ተዛውሮ የተለያየ የሰውነት ክፍል መቆጣት (መልቲ ሲስተም ኢንፍላማቶሪ ሲንድረም -ኤም አይ ኤስ) ተብሎ በሚጠራ በሽታ ተያዘ። የጄሲካ ልጅ ሉካስ ኤክስፐርቶች እንደሚናገሩት ልጆች በኮሮናቫይረስ ከተያዙ እስከ ስድስት ሳምንታት ድረስ የሚመጣው ህመም ብዙም ያልተለመደ ነው። የሳኦ ፖሎ ዩኒቨርስቲ ባልደረባው ዶ/ር ፋቲማ ማሪንሆ እንደሚሉት በወረርሽኙ ወቅት የኤምአይኤስ ቁጥር ከፍተኛ ሆኗል። ምንም እንኳን ለሁሉም ሞት ምክንያት ባይሆንም። ጄሲካ ልጇ ሉካስ በነበረበት ክፍል ውስጥ እንድትቀመጥ አልተፈቀደላትም። ራሷን ለማረጋጋት አማቷ ዘንድ ደወለች፡። "ማሽኑ እስኪቆም ድረስ የማሽኑን ድምጽ እንሰማ ነበር። ይህ የሚሆነው ሰው ሲሞት መሆኑን እናውቃለን። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ማሽኑ እንደገና መሥራት ሲጀምር ማልቀስ ጀመርኩ።" ሐኪሙ ሉካስ የልብ ድካም እንደገጠመው ከነገራት በኋላ ግን ሊያነቁት ችለዋል። በሆስፒታሉ ሉካስን ከአንድ ወር በላይ ያከሙት የህጻናት ሐኪሟ ዶ/ር ማኑላ ማኑዌል ሞንቴ አስጊ ሁኔታ ስላልነበረው የሉካስ ሁኔታ በጣም ከባድ መሆኑ ግርምትን ፈጥሮባቸዋል። በግዛቱ ዋና ከተማ በፎርታሌዛ በአልበርት ሳቢን የህፃናት ሆስፒታል ባለሙያ የሆኑት ሎሃንና ታቫረስ እንደሚሉት በኮቪድ-19 የሚጎዱት አብዛኞቹ ህጻናት እንደ ስኳር፣ የልብና የደም ቧንቧ በሽታ ያሉ ነባር ሁኔታዎች ወይም ከመጠን በላይ ክብደት ያላቸው ናቸው። ሉካስ ግን እንደዚያ አልነበረም። በ33 ቀናት ውስጥ ሉካስ በጽኑ ሕክምና ክፍል በነበረ ጊዜ ጄሲካ ለማየት የተፈቀደላት ሦስት ጊዜ ብቻ ነበር። ሉካስ ልቡን ለማከም በጣም ውድ ነው የሚባለውን ኢሞኖግሎቡሊን አስፈለገው።፣ እንደ ዕድል ሆኖ ለራሱ ገዝቶ የተረፈው አንድ ግለሰብ ለሆስፒታሉ ይለግሳል። ሉካስ በጣም ስለታመመ ለሁለተኛ ጊዜ ኢሞኖግሎቡሊን ተሰጠው። ሰውነቱ ሽፍታ በመፈጠሩ የማያቋርጥ ትኩሳት ጀመረው። ለመተንፈስም ድጋፍ አስፈለገው። ሉካስ መሻሻል ሲያሳይ ሐኪሞቹ የኦክስጂን ቱቦውን ለማውጣት ወሰኑ። ራሱን አውቆ እንዳገገመ ብቸኝነት እንዳይሰማው ጄሲካ እና እስራኤልን በቪዲዮ ደውለው አገናኙት። "ድምፃችን ሲሰማ ማልቀስ ጀመረ" ትላለች ጄሲካ። ልጃቸው ምላሽ ሲሰጥ ሲመለከቱ ለመጨረሻ ጊዜ ነበር። በሚቀጥለው የቪዲዮ ጥሪ ወቅት አካሉን ለማንቀሳቀስ የመቸገር ምልክት አሳየ። ከዚያም በሲቲ ስካን በተደረገለት ምርመራ ሉካስ ስትሮክ እንዳጋጠመው አወቀ። ሉካስ ትክክለኛውን እንክብካቤ ካገኘ እንደሚያገግም ለባልና ሚስቱ ከተነገራቸው በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከጽኑ ህሙማን ክፍል እንደሚወጣ ይጠብቁ ነበር። ጄሲካ እና እስራኤል ሊጎበኙት በሄዱ ወቅት ሐኪሟም እንደነርሱ ተስፋ ነበራት ትላለች። "የዚያን ዕለት ምሽት ላይ የሞባይሌን ድምጹን አጠፋሁት። ሉካስ አፍንጫዬን ሲስመኝ በህልሜ አየሁ። ህልሙ ታላቅ የፍቅር፣ የምስጋና ስሜት ስለነበር በጣም ተደስቼ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ሞባይሌን ስመለከት ሐኪሙ ያደረጋቸውን 10 ጥሪዎች አገኘሁ።" ሐኪሟ የሉካስ የልብ ምት እና የኦክስጂን መጠን በድንገት እንደቀነሰና ማለዳ ላይ ማሩን ለጃሲካ ነገረቻት። ሉካስ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ የኮቪድ-19 ምርመራ ቢደረግለት ኖሮ በሕይወት እንደሚቆይ እርግጠኝነት ይሰማታል። "ሐኪሞች ኮቪድ-19 አይደለም ብለው ቢያምኑም ህይወት ለማዳን ምርመራውን ማድረጋቸው አስፈላጊ ነው" ትላለች። "ህጻናት የሚሰማቸውን አይናገሩም ስለዚህ በምርመራዎች ላይ እናተኩራለን።" ጄሲካ እና ባለቤቷ የሉካስን ፎቶ ይዘው ጄሲካ ህክምናው በመዘግየቱ ሁኔታውን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ብላ ታምናለች። "ሉካስ በርካታ ኢንፌክሽኖች ነበሩት። የሳንባው 70 በመቶ ተጎድቷል። ልቡ በ 40 በመቶ አድጓል። ይህ ሊወገድ የሚችል ነበር።" ሉካስን ያከሙት ዶ/ር ሞንቴም በዚህ ይስማማሉ። ኤም አይ ኤስ መከላከል ባይቻልም ሁኔታው ከታወቀ እና ቀድሞ ከታከመ ህክምናው የበለጠ ስኬታማ ነው ይላሉ። "ቀድሞ ህክምና ቢያገኝ ኖሮ የተሻለ ነው። በከባድ ህመም ነው ወደ ሆስፒታል የደረሰው። ቀደም ብለን ማከም ብንችል ኖሮ የተለየ ውጤት ሊኖረው ይችል ነበር ብዬ አምናለሁ።" ጄሲካ ወሳኝ የሆኑ ምልክቶች ያላቸው ሰዎችን ለመርዳት የሉካስን ታሪክ ማካፈል ትፈልጋለች። እንደ ዶ/ር ፋቲማ ማሪንሆ ከሆነ ልጆች ለኮቪድ ያላቸው የአደጋ ተጋላጭነት ዜሮ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ አለ። እጅግ በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሕፃናት በቫይረሱ ተጠቅተዋል። እንደ ብራዚል ጤና ሚኒስቴር ከሆነ ከጎርጎሮሳዊያኑ ከየካቲት 2020 እስከ 15 ሚያዝያ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በኮቪድ-19 ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ 518 ሕፃናትን ጨምሮ እስከ ዘጠኝ ዓመት ዕድሜ ድረስ ያሉ 852 የሚሆኑትን የብራዚል ሕፃናት ሞተዋል። ዶ/ር ማሪንሆ ግን ከዚህ ቁጥር ከሁለት እጥፍ በላይ የሚሆኑት በኮቪድ እንደሞቱ ይገምታሉ። ከኮቪድ ምርመራ እጥረት ጋር ተያይዞ ቁጥሮቹ ዝቅ ብለዋል ይላሉ። ዶ/ር ማሪንሆ በወረርሽኙ ወቅት ባልተገለጸ አጣዳፊ የትንፋሽ ህመም ምክንያት የሟቾችን ብዛት በማስላት ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ እንደሚጨምር ይገልጻሉ። እነዚህን ቁጥሮች በመጨመር ቫይረሱ 1,302 ሕፃናትን ጨምሮ ከዘጠኝ ዓመት በታች የሆኑ 2,060 ሕፃናትን እንደገደለ ይገምታሉ። ይህ ለምን ሆነ? ባለሙያዎቹ እንደሚናገሩት በአገሪቱ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የብራዚል ሕፃናትን የመያዝ ዕድል ይጨምረዋል። "ህጻናትን ጨምሮ ብዙዎች ሆስፒታል ገብተዋል ሕይወታቸውም አልፏል። ቫይረሱን መቆጣጠር ከተቻለ ይህ ሁኔታ ሊቀየር ይችላል" ሲሉ የብራዚል የሕፃናት ሕክምና ማኅበር የክትባቶች የሳይንስ ክፍል ፕሬዝዳንት ሬናቶ ክፉሪ ይገልጻሉ። እንዲህ ዓይነቱ ከፍተኛ የመያዝ መጠን የብራዚልን አጠቃላይ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት አጥለቅልቆታል። በመላ አገሪቱ የኦክስጂን አቅርቦቶች ሲቀንስ የመሰረታዊ መድኃኒቶች እጥረትና በርካታ የጽኑ ህሙማን ክፍሎች ውስጥ አልጋ የለም። የብራዚል ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን መቃወማቸውን የቀጠሉ ሲሆን ባለፈው ዓመት በሰሜን ብራዚል ማኑስ ውስጥ ፒ1 የተባለ የቫይረስ ዓይነት በጣም ተስፋፍቷል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ከወረርሽኝ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር ባለፈው ወር የሞቱት ሰዎች ቁጥር በሁለት እጥፍ ያደገ ሲሆን ይህም እንደቀጠለ ነው። ማሪንሆ እንደሚሉት ብዙውን ጊዜ የኮቪድ ምርመራው ለልጆች የሚደረገው በጣም በጠና በሚታመሙበት ጊዜ ዘግይቶ ነው። "በሽታውን የመለየት ከባድ ችግር አለብን። ለሕዝቡ በቂ ምርመራዎች አናደርግም። የልጆችም ቢሆን አናሳ ነው። የምርመራው መዘግየት ስላለ ለህጻናቱ የሚደረገው እንክብካቤ ላይ መጓተት አለ።" "ልጆች የበለጠ ተቅማጥ፣ በጣም ብዙ የሆድ ህመም እና የደረት ህመም አለባቸው። የምርመራው መዘግየት ስላለ ህጻናቱ ሆስፒታል ሲመጡ በከባድ ሁኔታቸው ተወሳስቦ ሞት ሊከሰት ይችላል" ይላሉ። ድህነት እና የጤና እንክብካቤ ተደራሽ አለመሆንም ሌላው ምክንያት ነው። የበሽታው ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ያሉ ልጆችን መጎብኘት ተከልክሏል። በአልበርት ሳቢን የህፃናት ሆስፒታል ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ሲናራ ካርኔሮ እንዳሉት ይህ እጅግ ፈታኝ ነው። ወላጆች የልጆቻቸውን ስሜት ሊረዱ ስለሚችሉ ነው። እንደ ዶ/ር ካርኔሮ ከሆነ "አንድ ልጅ ወላጆቹን ሳያይ ሲሞት ማየት ያማል" ብለዋል። የአልበርት ሳቢን ሆስፒታል ሠራተኞች በወላጆች እና በልጆቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻልና የቪዲዮ ጥሪዎችን ለማመቻቸት ስልኮችን እና ታብሌቶችን ለመግዛት ተሰባስበዋል። እንደ ዶ/ር ካርኔሮ ከሆነ ይህ እጅግ አግዟቸዋል። "በቤተሰብ አባላት እና በታካሚዎች መካከል ከ100 በላይ የቪዲዮ ጥሪዎችን አድርገናል። ይህ ግንኙነት ጭንቀቱን በእጅጉ ቀንሶታል።" የሳይንስ ሊቃውንት በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሞት አደጋ አሁንም "በጣም ዝቅተኛ" እንደሆነ ይገልጻሉ። አሁን ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከብራዚል 345,287 ሟቾች መካከል 0.58 በመቶ የሚሆኑት ከ 0-9 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ናቸው። መቼ እርዳታ መጠየቅ ያስፈልጋል? ኮሮናቫይረስ በልጆች ላይ ተላላፊ ቢሆንም ከባድ ግን አይደለም። ልጅዎ ጤናማ ካልሆነ ከኮሮቫይረስ ይልቅ በሌላ በሽታ ሊሆን ይችላል። ሮያል የሕፃናት ሕክምና ኮሌጅ ወላጆች ልጆቻቸው ከዚህ በታች ያሉትን ምልክቶች ካሳዩ አስቸኳይ እርዳታ እንዲሹ ይመክራሉ።
news-48446175
https://www.bbc.com/amharic/news-48446175
የዓለም ከትምባሆ ነጻ ቀን: ማጨስ ከጠቃሚ የሕይወት ዘይቤ ወደ ገዳይ ልማድ
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት ትምባሆ ከሚያጨሱ ሰዎች ግማሾቹ በሲጋራ ምክንያት ህይወታቸው ያልፋል። በየዓመቱ 6 ሚሊዮን ሰዎች በቀጥተኛ መልኩ ከትንባሆ ጋር በተያያዘ ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፍ ሲሆን ምንም የማያጨሱ 600 ሺ ሰዎች ደግሞ ለሲጋራ ጭስ በመጋለጣቸው ሳቢያ ለሞት ይዳረጋሉ።
በአውሮፓውያኑ 2016 የአጫሾች ቁጥር ከዓለም ህዝብ 20 በመቶ የደረሰ ሲሆን በ2000 ላይ ግን 27 በመቶ ነበር። ይህ ደግሞ ትልቅ ለውጥ ነው ያለው የዓለም የጤና ድርጅት፤ አሁንም ቢሆን የዓለማቀፍ ስምምነት ከተደረሰበት ቁጥር ላይ ለመድረስ ብዙ እንደሚቀር ያሳስባል። • በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች በዓለማችን 1.1 ቢሊየን አጫሾች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት የሚገኙት መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ውስጥ መሆኑ ደግሞ ነገሮችን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርጋቸዋል። ዛሬ የዓለም ከትምባሆ ነጻ ቀን ነው። ትምባሆ ማጨስ ከየት ተነስቶ እዚህ ደረሰ? ለብዙ ዘመናት ትምባሆ ማጨስ የጤናማ ህይወት መንገድ ዘይቤ ተደርጎ የሚታሰብ የነበረ ሲሆን በትምባሆ ውስጥ የሚገኘው አነቃቂና ሱስ አስያዥ የሆነው ንጥረ ነገር 'ኒኮቲን' ስያሜውን ያገኘው በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነበር። ይህ ንጥረ ነገርም ከፈጣሪ የተሰጠ የህመም ማስታገሻ ተብሎ ይጠራም ነበር። • የሚያስወርዱ ሴቶች ቁጥር ከሚወልዱ ሴቶች የሚበልጥባት ሀገር ጊልስ ኤቨራርድ የተባለው ሆላንዳዊ ተመራማሪ በወቅቱ በነበረው አመለካከት የትምባሆ ጭስ የመድሃኒትነት ባህሪ አለው ከሚል በመነሳት በርካቶች ለተለያዩ ህመሞች የህክምና ባለሙያዎችን ድጋፍ ከመጠየቅ በመራቃቸው የሀኪሞችን ተፈላጊነት እስከ መቀነስ የደረሰ አቅም ነበር። በ1587 በጻፈው መጽሃፍ ላይም እንደጠቀሰው በጊዜው የትምባሆ ጭስ የተመረዘ ሰውን ለማዳንና ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር ጽፏል። በአሁኖቹ ኩባ፣ ሃይቲ እና ባሃማስ በመሳሰሉት ሃገራት የተበከሉ ቦታዎችን ለማጽዳት፣ ድካም ለመቀነስና በሽታ ለመከላከል የትምባሆ ቅጠል ማቃጠል የተለመደ ተግባር እንደነበር ጣልያናዊው አሳሽ ክርስቶፈር ኮሎምበስ በ1492 በጻፈው መፍሃፍ ላይ ጠቁሟል። የትንባሆ ቅጠልን ከኖራ ጋር በመቀላቀል ጥርስን ለማጽዳት የሚያገለግል ሳሙና መስራት በቬኒዙዌላ አካባቢ ይዘወተር የነበረ ሲሆን ህንድ ውስጥ ደግሞ አሁንም ድረስ ጥቅም ላይ ይውላል። ሜክሲኮ ውስጥ አንገት አካባቢ የሚወጡ ቁስሎችን ለማዳን የወቅቱ የህክምና ባለሙያዎች አካባቢውን ከቀደዱ በኋላ ትኩስ የትንባሆ ቅጠል ከጨው ጋር በማቀላቀልና ከላይ በማድረግ ህክምና ይሰጡ ነበር። • በቤታችን ውስጥ ያለ አየር የጤናችን ጠንቅ እንዳይሆን ማድረግ ያለብን ነገሮች በ16ኛውና 17ኛው ክፍለ ዘመን በዶክተሮች፣ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችና የህክምና ተማሪዎች ዘንድ ትምባሆ ማጨስ የተለመደ ነገር ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ባለሙያዎቹ ለምርምር የሚጠቀሟቸው የሰው አስከሬን ሽታን ለመቀነስና ከሞቱ ሰዎች ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን ለመከላከል በማሰብ ነው። እንግሊዝ ውስጥ በ1655 ተከስቶ በነበረው ወረርሽኝ ምክንያት ህጻናት ተማሪዎች በትምህርት ቤት ውስጥ ትምባሆ እንዲያጨሱ ይደረግ ነበር። ትምባሆውን ያጨሱ ህጻናትም ከወረርሽኙ ነጻ ይሆናሉ፤ የተያዙትም ወደሌሎች አያስተላልፉም ተብሎ ይታመን ነበር። የሞቱ ሰዎችን አስከሬን የሚቀብሩና የሚያቃጥሉ ሰዎችም ትምባሆ እንዲያጨሱ ይደረግ ነበር። ነገር ግን የትንባሆን ጎጂነት ቀድመው የተረዱ ሰዎች አልጠፉም ነበር። እንግሊዛዊው ተመራማሪ ጆን ኮታ በ1612 ትንባሆ ካለው ጥቅም በተጨማሪ ለህይወት እጅግ አስጊ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ እንዳለ ጽፎ ነበር። • ጫት የአእምሮ ጤናን እንደሚጎዳ ጥናት አመለከተ ምንም እንኳን የትንባሆ ጎጂነት ቀስ በቀስ እየታወቀ ቢመጣም ተፈላጊነቱ ግን ከምንጊዜውም በበለጠ እየጨመረ ሄዷል። እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የትምባሆ ጭስን ወደ ጆሮ ውስጥ በማስገባት የጆሮ ህመምን ለማከምም ጥቅም ላይ ይውል ነበር። ከ1920 እስከ 1930ዎቹ ባሉት ጊዜያት ትምባሆ ማጨስ ብዙ የጤና እክሎች እንደሚያስከትል መታመን ሲጀምር በወቅቱ ታዋቂ የነበረው 'ካሜል' የተባለ የሲጋራ አምራች ድርጅት 'ዶክተሮች ሲጋራ ማጨስ ጠቃሚ እንደሆነ አረጋግጠዋል፤ እንደውም እራሳቸው ያጨሱታል' በማለት ማስታወቂያ አሰርቶ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ አፋኞች ድምጻቸው ጥርት እንዲልና ጉሮሯቸውን ለማጽዳት ሲጋራ እንዲያጨሱ ይመከር ነበር። በዚህም ምክንያት ታዋቂ ዘፋኞችና የሬድዮ ዝግጅት አቅራቢዎች በብዛት ሲጋራ ያጨሱ ነበር። ባለፉት 30 ዓመታት ግን ሲጋራ በጤና ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት ብዙ ጥናቶች ይፋ መሆን የጀመሩ ሲሆን ሰዎችም ጉዳቱን በመገንዘብ ጥንቃቄ ማድረግ ጀምረዋል። • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች በዚህም ምክንያት ብዙ ሃገራት ህዝብ በተሰበሰበባቸው ቦታዎች ላይ ሲጋራ ማጨስ የሚከለክሉ ህጎችን እንዲያወጡ ግድ ብሏቸዋል። ከዚህ ባለፈም ስለ ሲጋራ ጉዳት የሚያትቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶች በየቦታው መታየት ጀምረዋል። አንዳንድ ሃገራት ከዚህም አልፈው ሲጋራ ማጤስ በሳምባ እና ሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት የሚያብራሩ መልዕክቶች በሲጋራ ማሸጊያዎች ላይ እንዲለጠፍ የሚያስገድድ ህግ አውጥተዋል። እርግዝና ላይ ያሉ ሴቶችም ቢሆን ሲጋራ ማጨስ በጽንሱ ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት መገንዘብ የጀመሩት ከ30 ዓመት በፊት አካባቢ ነበር። ዓለማችን ካጋጠሟት ወረርሽኞች ሁሉ ትልቁ ትምባሆ ነው በማለት የዓለም ጤና ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን ሃገራት የትምባሆ አጠቃም ላይ ጠበቅ ያለ ህግ እንዲያወጡም ይመክራል። በዚህ መሰረትም ሃገራት ወጣቶች ትምባሆ እንዳያጨሱ የሚከለክሉ ፖሊሲዎች እንዲያወጡ፣ የትምባሆ ማስታወቂያዎች እንዲከለከሉና የትምባሆ አምራች ድርጅቶች ላይ ከበድ ያለ ግብር እንዲጣልባቸው ሃሳብ አቅርቧል።
news-49835538
https://www.bbc.com/amharic/news-49835538
የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን?
ሄኖክ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር ወጣት ነው። ከስድስት ወር በፊት በጓደኞቹ ገፋፊነት የጀመረው በስፖርት ውድድሮች ላይ ገንዘብ ማስያዝ መወራረድ ሱስ እየሆነበት እንደመጣ ይናገራል።
''ከገንዘብ ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ መጠን እራስን ለመቆጣጠር ትንሽ ይከብዳል። በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ በተለይ የእንግሊዝና ሌሎች የአውሮፓ ሊጎች ላይ ሳላስይዝ አላልፍም''ይላል። • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ በትንሹ ከ10 ብር ጀምሮ እስከ 200 ብር ድረስ በአንድ ጊዜ እንደሚያስይዝ የሚናገረው ሄኖክ የጨዋታዎቹን ውጤት ለማየትና ምን ያህል እንደበላ አልያም እንደተበላ ለማረጋገጥ ቁጭ ብሎ ሌሊቱን የሚያሳልፍበት ጊዜም እንዳለ ይናገራል። ሌላው ቢቀር ይላል ሄኖክ ''ማህበራዊ ሚዲያዎችን በተንቀሳቃሽ ስልኬ በመመልከት የማጠፋውን ጊዜ እንኳን ቀንሻለው። አጋጣሚው ሲኖረኝ ሁሌም የአቋማሪ ድርጅቱን መተግበሪያ ከፍቼ ማየት ነው የሚቀናኝ።'' በስፖርት ውድድሮች ውጤት ላይ ተመስርቶ መወራረድ በኢትዮጵያ እምብዛም የተለመደ ነገር አልነበረም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እንደ አቢሲኒያ፣ አክሱምና ሃበሻን የመሳሰሉ የስፖርት አወራራጅ ድርጀቶች የብዙ ወጣቶችን ቀልብ መሳብ ጀምረዋል። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው የአቢሲኒያ አወራራጅ ድርጅት መስራችና ባለቤት የሆነው አሸናፊ ንጉሤ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፈቃድ አግኝተው መስራት የጀመሩት ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ መሆኑን ይናገራል። አሸናፊ "ብዙ ሰዎች ከስፖርታዊ ውርርዶች ጋር በተያያዘ የተሳሳተ አመለካከት አላቸው" ብሎ ያምናል። በስፖርታዊ ውድድሮች ገንዘባቸውን ለማስያዝ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናትን በጉጉት ከሚጠብቁት እንደ ሄኖክ ካሉ ተቋማሪዎች በተለየ ሱስ የማስያዝም ሆነ አላግባብ ወጪ ውስጥ አያስገባም ይላል። ''በስፖርት ውድድሮች ይሄኛው ቡድን ያሸንፋል ሌላኛው ይሸነፋል እያሉ መወራረድ የተለመደና ሁሌም የነበረ ነገር ነው'' የሚለው አሸናፊ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ፈቃድ አግኝቶ ተሳታፊዎች ልኩን ባላለፈ መልኩ እንዲወራረዱ ማድረጉ ከጉዳቱ ጥቅሙ እንደሚበልጥ ያስረዳል። ''በአሁኑ ጊዜ ወጣቶች ከሚታሰበው በላይ የስፖርት እውቀታቸው ጨምሯል። በዚህም ምክንያት ገንዘባቸውን ሲያስይዙ እራሱ በእውቀት ላይ ተመስርተው ነው። ገንዘባቸውን ከማስያዛቸው በፊት ሬድዮና ስፖርታዊ ድረገጾችን ተከታትለው ስለሆነ የሚመጡት ከውርርዱ በተጨማሪ መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል'' ይላል። በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴድሮስ ነዋይ በበኩላቸው የስፖርት ውርርድ ድርጀቶች ተገቢውን ቅድመ ሁኔታዎች እስካሟሉ ድረስ ማህበረሰቡ ላይ የሚያሳድሩት ጫና እንደሌለ ይናገራሉ። እስካሁን አስተዳደሩ 28 የሚሆኑ አወራራጅ ድርጅቶችን በህጋዊ መንገድ የመዘገበ ሲሆን 23 የሚሆኑት ፍቃድ ባገኙበት ዘርፍ ሥራቸውን እያከናወኑ ነው። ከነዚህ መካከል አራቱ በያዝነው 2012 ዓ.ም ፍቃድ ያገኙ ናቸው። አቶ ቴዎድሮስ እንደሚሉት የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ከአወራራጅ ድርጅቶች ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢም አግኝቷል። ''በመጀመሪያ መረሳት የሌለበት በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩትን ድርጅቶች አቋማሪ አንላቸውም። የስፖርት ውድድር አወራራጅ ድርጅቶች ብለን ነው የምንጠራቸው'' ይላሉ። ''ቁማር ሲሆን አንዱ የሚጎዳበት አንዱ ብቻ ደግሞ የሚጠቀምት ነው። ስለዚህ ምንም ማህበራዊ ፋይዳ ሊኖረመው አይችልም። እኛ ፈቃድ የምንሰጠው የስፖርት ውርርድ ባህሪው የሎተሪ ነው። ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቶች ጊዜያቸውን በሌሎች ነገሮች ላይ ከሚያሳልፉ እየተዝናኑ እድላቸውን የሚሞክሩበት ነው።'' ''ማህበራዊ ፋይዳ ከሌለው እኛም ፈቃድ አንሰጥም'' የሚሉት አቶ ቴድዎሮስ ለዚህም ድርጅቶቹ ከውርርድ ከሚያገኙት ገቢ 20 በመቶውን በመረጡት ማህበራዊ የበጎ አድራጎት ተቋም ላይ እንዲያውሉ እንደሚገደዱ ጠቅሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከድርጅቶቹ ገቢ 15 በመቶውን በኮሚሽን መልክ የሚወስድ ሲሆን ድርጅቶቹ ከደንበኞቻቸው ግብር ሰብስበውም ለመንግሥት ገቢ ያደርጋሉ። በተጨማሪ ዓመታዊ የግብር ግዴታቸውንም ይከፍላሉ። እነዚህ ሁሉ ሂደቶች ድርጅቶቹ ብዙ ትርፍ እንዳይግበሰብሱና የሚገኘው ገቢ ለተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች መዋላቸውን ማረጋገጫ እንደሚሰጣቸው አቶ ቴድሮስ ይናገራሉ። ሌላኛው ያነጋገርነውና በስፖርት ውድድሮች ገንዘብ ማስያዝ ከጀመረ ብዙ ጊዜ እንዳልሆነው የሚናገረው አሰግድ በሳምንት ቢያንስ አምስት ጨዋታዎች ላይ ገንዘቡን እንደሚያስይዝ ይናገራል። አብዛኛዎቹ ድርጅቶች ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው በአካል ሄዶ ገንዘብ ማስያዝና መቀበል አድካሚ መሆኑን ይገልጻል። ''ብዙ ጊዜ በስሜ ገንዘብ ለማስገባትም ሆነ ካሸነፍኩኝ ገንዘቤን ለመቀበል ወደ አቋማሪ ድርጅቶቹ ቢሮ ድረስ መሄድ አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ ወደ ቢሮው የሚሄድ ጓደኛዬ ካለ ለእኔም እንዲያስገባልኝ የማደርግብትም ጊዜ አለ'' ይላል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ምንም እንኳን ውርርድን በተመለከተ ስለኢትዮጵያ በቂ የሆነ መረጃ ባይበኖርም በኬንያ፣ በደቡብ አፍሪካ ወይንም በናይጄሪያ የሚገኙ እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 የሚደርሱ ሰዎች በአማካይ በቀን እስከ 15 ዶላር ድረስ እንደሚያስይዙ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሚስተዋለው በተለየ ሄኖክ ገንዘቡን የሚያስይዝባቸው ድርጅቶ የሀገር ውስጥ ውድድሮችን እምብዛም እንደማያካትቱና በብዛት የአውሮፓ ሊጎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ይናገራል። እስከ 14 ሺህ ብር ድረስ ሁለት ጊዜ በውርርድ እንዳሸነፈ የሚናገረው ሄኖክ ገንዘቡን ከማስያዙ በፊት የተለያዩ መረጃዎችን እንደሚሰበስብና አማራጮቹን ለማብዛት እንደሚሞክር ነግሮናል። በስፖርታዊ ውድድሮች መወራረድ ጋር አብሮ የሚነሳ አንድ ችግር አለ። እሱም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችና ተማሪዎች በዚሁ ተግባር ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን ሊያጠፉ መቻላቸው ነው። አሰግድ አብዛኛዎቹ አወራራጅ ድርጅቶች ለመወራረድ ከሚመጡት ሰዎች መካከል ምን ያህሉ "እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የሚቆጣጠሩ አይመስለኝም" ይላል። ''እኔ በግሌ ገንዘብ ለማስያዝ ስሄድ ትንንሽ ልጆችን እመለከታለው። ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ተስተናግደው ነው የሚሄዱት። በስልካቸው መተግበሪያዎችን አውርደው ሲጠቀሙም እምለከታለው" ሲል አሳሳቢ መሆኑን ይተቅሳል። የአቢሲኒያ አወራራጅ ድርጅት ባለቤት አሸናፊ ንጉሤ ግን እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በስፖርታዊ ውድድሮች እንዳይሳተፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርጉ ይናገራል። ''ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለማስያዝም ሆነ አባል ለመሆን ወደ ቢሮዎቻችን ሲመጣ መታወቂያ እንጠይቃለን። በድረ ገጽና በስልክ መተግበሪያዎች ለሚጫወቱት ደግሞ የገንዘብ ዝውውር ለማድረግ በባንክ በኩል የሂሳብ ደብተር መክፈት ስላለባቸው የእድሜያቸውን ነገር በዚው እንቆጣጠረዋለን።'' ''ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንዲጫወቱ አንፈቅድም፤ አብረውት ሊመጡ የሚችሉትንም ጉዳቶች ጠንቅቀን እናውቃቸዋለን'' ይላል። • አብረሃም መብራቱ፡ የየመንን ብሔራዊ ቡድን ለትልቅ ውድድር ያበቃ ኢትዮጵያዊ የስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የሚደረግ ውርርድ ዙሪያ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን ድርጅቶቹ እንዳያጫውቱ የሚከለክል መመሪያ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባይኖረውም ውርርዱ ላይ ህጻናት እንዳይሳተፉ ስምምነት እንዳላቸው የአስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ገልጸዋል። ''እድሜያቸው ያልደረሰ ህጻናት የሚጫወቱ ከሆነ ተገቢውን እርምጃ ከመውሰድ ግን ወደኋላ አንልም። ጥቆማ ከደረሰንም የምንከታተል ሲሆን እስካሁን ግን ምንም የደረሰን ቅሬታም ሆነ ጥቆማ የለም'' ይላሉ። ውርርድ ሱስ የማስያዝ ባህሪ ሊኖረው ስለሚችል ወደፊት የዘርፉን አካሄድ በመመልከትና ተያይዘው የሚመጡ ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን አቶ ቴድሮስ ገልጸዋል። ለአሁኑ ግን በኢትዮጵያ ያለው የውርርድ ዘርፍ ገና ጀማሪ በሚባልበት ደረጃ በመሆኑ አካሄዱን መከታተልና ማህበረሰቡ እየተዝናና ሃላፊነቱን የሚወጣበትን መንገድ ማማቻቸት ላይ ትኩረት እንዳደረጉም አክለዋል። ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ መወራረድ ሙሉ በሙሉ መከልክል የለበትም የሚለው ሃሳብ ያሚያስማማቸው አሰግድና ሄኖክ አወራራጅ ድርጅቶችም ሆነ መንግሥት ውርርድ ሱስ ሊያስይዝ እንደሚችል በደንብ መረጃ ቢሰጡና ዘርፉ ጠበቅ ያለ ክትትል ቢደረግብት መልካም እንደሆነ ግን ያምናሉ። ከስፖርታዊ ውርርዶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ ለስፖርታዊ ውድድሮች ያለ ከፍተኛ ፍቅር፣ የላላ የቁማር ህግና ቀላል የተንቀሳቃሽ ስልክ ክፍያ መንገዶች መብዛት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሃገራት ትልቅ ፈተና ሊደቅኑ እንደሚችሉ አንዳንዶች ስጋታቸውን ይገልጻሉ።
news-50065799
https://www.bbc.com/amharic/news-50065799
"ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው" አርቲስት ታማኝ በየነ
ታማኝ በየነ ዘርፈ ብዙ የኪነ ጥበብ ባለሙያ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ፖለቲከኛ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ፣ ኮሜዲያን እንደሆነ ይነገርለታል። ታማኝ በአገሪቷ በነበረው የፖለቲካ ሁኔታ በስደት ወደ አሜሪካ አቅንቶ ለበርካታ ዓመታት የመንግሥትን አስተዳዳር ሲተች፣ ሲቃወም ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ከ22 ዓመታት የስደት ኑሮ በኋላ ታማኝ የአገሩን ምድር መርገጡ ይታወሳል። ለውጡን በመደገፍም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል። በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ የኢሬቻ በዓል ሲከበር የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ አርቲስት ታማኝ በየነ በፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ሃሳብ የተነሳ የበርካቶች መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። • የመደመር እሳቤ ከአንድ ዓመት በኋላ አንዳንዶች 'ተደምሮ ነበር ተቀነሰ' የሚሉ አስተያየቶችንም ሰንዝረዋል። ቢቢሲም ይህንና ሌሎች የአገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካን አስመልክቶ ከታማኝ በየነ ጋር ቆይታ አድርጓል። ሰዎች ፖለቲከኛ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ጋዜጠኛ፣ አርቲስት ይሉሃል። አንተ ራስህን የምታስቀምጠው የትኛው ላይ ነው? እኔ መቼም ራሴን የምገልፀው በኪነጥበብ ውስጥ ነው፤ ግን ሁኔታዎች ገፉ ገፉና ወደ ፖለቲካ መድረኩ አመጡኝ እንጅ የሕይወቴ መነሻውም ገና የሰባት የስምንት ዓመት ልጅ ሆኜ ሙዚቃ ነው ሕይወቴ። በእርግጥ ከ1997 ዓ.ም በኋላ ከኪነ ጥበቡ እየራቅኩ ሄድኩ እንጂ አሁንም ራሴን የማየው የጥበብ ሰው አድርጌ ነው። በእርግጥ ሰዎች የሰጡኝ የተለያዩ ማዕረጎች አሉ፤ ግን ራሴን እንደዛ አድርጌ አልገልፀውም። ወደ ኢትዮጵያ መጥተህ ከተመለስክ በኋላ ብዙም ድምፅህ አልተሰማም። አሁን ምን እየሠራህ ነው? እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በግል ብዙ ይመጣልኛል። ሁለት ጊዜ ነው ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩት። የመጀመሪያው ወደ አገራችሁ ግቡ ሲባል ነው የሄድኩት። 27 ቀን ገደማ ነው የቆየሁት። ያንንም በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወርኩ ሥራ ላይ ነው ያሳለፍኩት። በዚያ ጊዜም የተፈጠሩ ችግሮች ነበሩ - የቡራዩ። እርዳታ ለማሰባሰብ ጥረት አድርጌ ነው ወደ አሜሪካ የተመለስኩት። • ስለተፈፀመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው ተመልሼ አሜሪካ ከመጣሁ በኋላ ደግሞ የጌዲዮና ጉጂ ችግር ተፈጠረ። በዚያ ምክንያት እርዳታ ሳሰባስብ ነበር። እሱ እንዳለቀ ከአሜሪካው ግብረ ሰናይ ድርጅት ወርልድ ቪዥን ጋር በመሆን እርዳታውን ለማድረስ ተመለስኩ። እዚያም ሄጀ በተለያዩ አካባቢዎች ችግር ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ ሳደርስ ነበር። የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ ነበርኩ። እንግዲህ ይህን አድርጌ የተመለስኩት ሰኔ መጀመሪያ ላይ ነው። ጠፋህ የምባለውም ለአራት ወር ያህል ነው። ይሄ አራት ወር ደግሞ በጣም ፈተና ውስጥ ያለፍኩበት ጊዜ ነው። በጣም በቅርብ የማውቃቸው ዶክተር አምባቸውና የሌሎቹም በዚያ መልክ ሕይወታቸውን ያጡት የአማራ ክልል ባለሥልጣኖች ሞት ለእኔ እንደ ሰው በጣም ከባድ ሃዘን ነበር። እንደዚህ ዓይነቱ ሁኔታ በአካባቢው የፈጠረው የፖለቲካ ትርምስም ቀላል አልነበረም። ከዚያ እንደገና በኢሳት ጊዜያዊ ኃላፊነት ላይ ነበርኩና በውስጡ የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ ብዙ ጥረት አድርጌ ነበር። ስመለስ ሁኔታዎች እንደጠበቅኳቸው አልሆኑም። በዚያ ምክንያት እንግዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ዛሬ የምናገረው፤ ኃላፊነቴን ለቅቄ ወጥቻለሁ። በዚህ ምክንያት ተደራራቢ የሆኑ የመንፈስም፤ የስሜት መጎዳትም ደርሶብኛል። ምክንያቱም ያን ሚዲያ በእግሩ ካቆሙት ውስጥ አንዱ ነኝ። ስድስት ዓመት በሙሉ አንድም የእረፍት ቀን ቤቴ አሳልፌ አላውቅም፤ ልጆቼን በአግባቡ በእረፍት ቀን አይቻቸው አላውቅም። ለስድስት ዓመታት ዓለምን እየዞርኩ፤ እየለመንኩም [በዚህ ቋንቋ መናገር እችላለሁ] ያቋቋምኩት ድርጅት ፊቴ ላይ እንደዚህ ዓይነት ችግር ሲገጥመው በጣም ተጎድቼ ነበር እና ኃላፊነቴንም ለቅቄያለሁ። በራስህ ፈቃድ ነው የለቀቅከው? አዎ በራሴ ፈቃድ ነው የለቀቅኩት። እንደማይሆን ሳውቅ መልቀቅ ነበረብኝ። ሌላ ተጨማሪ ጉዳት፣ ሌላ ጭቅጭቅ፣ ሌላ ውዝግብ ላለመፍጠር ስል ነው በዝምታ እስካሁን ድረስ የቆየሁት። አገር ቤት ከመግባታችን በፊት በየጊዜው በአገሪቱ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ በኢሳት ላይ እየወጣሁ ሃሳቤን እገልፃለሁ፣ እከራከራለሁ፣ መረጃዎችን አቀርባለሁ። በተጨማሪም በየቦታው ሄጀ በምናገራቸው ንግግሮች በየጊዜው ሃሳቤን ስለምገልፅ ያ በመቋረጡ ምክንያት ነው ብዙ ሰው ጠፋህ የሚለው። እኔ አሁንም በአገሬ ጉዳይ ላይ አቅሜ የሚችለውን እያደረኩ ነው ያለሁት። ምንም የተደበቅኩበት፤ የጠፋሁበት ምክንያት የለም። አሁንም ስለ አገርህ የሚሰማህ ስሜት ይኖራል ብዬ አስባለሁ፤ ሃሳቤን የምገልፅበት መንገድ አጣሁ ብለህ ታስባለህ? አጣሁ ማለት አልችልም። ለምን አጣለሁ? ግን እንደበፊቱ . . . አየሽ እዚያው ነው የምሠራው፤ አዳሬ ኑሮዬ ማለት ነው። የተፈጠሩ ሁኔታዎችን በየቀኑ በኢሳት ስለምናገር ነው። አጣሁ ለማለት አልችልም። ይሄን ግን በሌላ በኩል እየሄድኩም እባካችሁ አነጋግሩኝ አልልም። እኔ መፃፍ አልችልም፤ ተፈጥሮዬም አይደለም፤ ስሜቴንም አይገልፅልኝም። ግን በሚዲያ ደረጃ በዚህ ሃሳብ፣ በዚህ ጉዳይ. . . ያለኝ ማንም የለም። ስለዚህ በዚያ ምክንያት አልታየሁም እንጅ በየቀኑ የሚለዋወጠውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተደብቄ አይደለም ያለሁት። አሁን ደግሞ አንዳንድ ችግሮች ሲፈጠሩ፤ ተከፍቶ በነበረው በር እየገባሁ ለምን ይሄ ሆነ? እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ? የሚል ጥያቄ አቀርብ ነበር። እስካሁን እሱም አልተዘጋም ነበር ለማለት ነው። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር መምጣት በኋላ ያለውን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ትመለከተዋለህ? እንግዲህ ለውጥ መጥቷል ብሎ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ እ . . . የዛሬ ዓመቱን ሙቀት መለኪያ ባይኖረንም በእርቅና መቻቻል፤ ያለፈውን በመተው ወደፊት ለመራመድ፤ አብሮ ለመጓዝ የሚሉት ሃሳቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተቀብሎት ነበር ማለት እችላለሁ። ሁሉም የሚለው ባያስማማን እንኳን 90 በመቶ ብንል ለእውነት የቀረብን ይመስለኛል። ዶክተር ዐብይ ለዘመናት የሄድንበትን የመበቃቀል ስህተት 'በአዲስ መንፈስ በይቅርታ እንሻገር' ሲል እንደማንኛውም ዜጋ እኔም ደስ ብሎኝ ይሄን ሃሳብ ተቀብያለሁ። ይሄ እንግዲህ የሚሆነው 'ኢትዮጵያ የሄደችበትን የመከራ ዘመን በማሰብ አንድ ቦታ ላይ እንዘጋዋለን' የሚል እንደ አንድ ዜጋ እምነት ስለነበረኝ ነው። አሁን ያሉትን ሁኔታዎች ስንመለከት በብሔር ተኮር ፖለቲካ ያሉ ኃይሎች ጫፍ እየወጡ ኢትዮጵያዊ የሚለውን የዜግነት ሃሳብ እየገፉ፤ ዜጎች እንደልባቸው እንደ ዜጋ የሚኖሩበትን እያፈረሱ የመገፋፋትና የማፈናቀል. . . እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ ሊታረም የሚችልበትን መንገድ እንደ አንድ ዜጋ በግሌ ሞክሬያለሁ ሊሰሙኝ የሚችሉ ባለሥልጣናትን ምን እያደረጋችሁ ነው? ብዬ ጮኼያለሁ፤ አዝናለሁ ይህን ስናገር ግን ተስፋ ሰጪ አይደለም። ያሰብነው ጋር እየሄድን አይደለም። ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ ሥልጣን ሲረከቡ የገቧቸውን ቃል እየፈፀሙ አይደለም ብለህ ነው የምታስበው? መሬት ላይ ባለው ሁኔታ አዎ! ምክንያቱም ዶክተር ዐብይ በኢትዮጵያ ውስጥ አዎንታዊ፤ በተለይ የእናቶችን እንባ የሚጠርግ መንፈስና ሃሳብ ይዞ መጥቷል ብዬ ነው የማምነው፤ የተቀበልኩትም እንደዛ ነው። • የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም አሁን ግን አክራሪ ብሔረተኞች የፈለጉትን የሚያደርጉበት፣ ዜጎች እንደ ዜጋ በነፃነት ሊንቀሳቀሱ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ሲደርሱ ዶክተር ዐብይ ያላቸውን ሥልጣን እና አቅም ተጠቅመው የማስቆም ሥራ እየሠሩ አይደለም። ይሄ ደግሞ አገሪቷን ወደ ከፋ ደረጃ ይገፋታል ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ በእንዲህ ዓይነት ምስቅልቅል ሕይወት ውስጥ ነው ያለችው-አገሪቷ። ትናንት በሙሉ ልብ ሁላችንም ለመደገፍ የቆምነውን ያህል አሁን አብሮ ለመቆም አስቸጋሪ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሠላም ኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው ምን ተሰማህ? ዶክተር ዐብይ የሠላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ ሲባል እኔም እንደ ዜጋ፤ አገሬ በዚያ ክብር ላይ በመጠራቷ ደስ ብሎኝ 'እንኳን ደስ አለዎት' ብያለሁ። 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ደግሞ በዜግነት የሚንቀሳቀሱ ዜጎች 'በአገራችን እኩል ድምፅ የለንም' ብለው ተቃውሞ ለማሰማት ሲንቀሳቀሱ፤ ሲከለከሉና ሲታሰሩ፤ በሌላ በኩል እርሳችውን የሚደግፉ ደግሞ በይፋ . . . ይሄ በፍፁም በፍፁም ሊያኗኑረን የሚችል አይደለምና መስመር ስቷል። ዶክተር ዐብይ እንደገና ቁጭ ብለው አይተው፣ አስበው፤ ለውጡን በምን መልኩ ላካሂድ የሚለውን ከሁሉም የኢትዮጵያ ባለድርሻዎች ጋር መምከር ካልቻሉ በስተቀር ስለኢትዮጵያ ሁኔታ አሁን በተመለከተ መጥፎ ዕይታ ነው ያለኝ። ለውጡ አቅጣጫውን ሲስት ስለተመለከትክ የተለያዩ ጥረቶችን እንዳደረክ ነግረኸኛል። ምን ድረስ ነው ጥረት ያደረከው? ይሄን ነገር መናገር አይከብድም ብለሽ ነው? መቼም በጣም ጥሬያለሁ ብዬ አስባለሁ። እውነቴን ነው የምልሽ ከእርሳቸው ጀምሮ ወደ ታች እስካሉት ባለሥልጣናት ድረስ ምንድን ነው ይሄ ነገር? እያልኩ ጮኼያለሁ፤ በሌላ በኩል ዝም አልክ የሚለኝ ሰው ቢኖርም፤ ዝም ግን አላልኩም። በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ለመናገር ሞክሬያለሁ። • "ለእናንተ ደህንነት ነው በሚል እንዳሰሩን ተገልፆልናል" የባላደራ ምክር ቤት አስተባባሪ አንዳንዴ ተመቸንም ብለን፣ ሁኔታው ስለፈቀደልንም፤ በውጭ ስለምንኖርም በማህበራዊ ሚዲያ የምንሰጣቸው አስተያየቶች አልፈው ሄደው በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ እንደሚችሉ የተረዳንም አይመስለኝም እና ብዙ ውጥንቅጡ የጠፋበት አሠራር ነው ያለው። ይሄ መታረም አለበት። በፍትህ ሥርዓቱ ትናንት ያለቀስነውን ያህል ዛሬም የ28 ቀን ቀጠሮ፣ የ18 ቀን ቀጠሮ እየተባለ ዜጎች እንደዛ ሲሰቃዩ ማየት ከዚህ በኋላ እንዲቀጥል እኔ እድል አልሰጥም። ጠቅላይ ሚነስትሩ ምን ማድረግ አለባቸው ነው የምትለው? በኢትዮጵያዊ መንፈስ እንደ አንድ አገር ዜጎች አብረን እንኖራለን፤ በመከባበር፣ በመፈቃቀድ እና ቂምን በመተው ይሄን መንፈስ ሲያነሱ በአብዛኛው የተቀበላቸው እኮ የዜግነት ፖለቲካን የሚደግፉ ወይም ደግሞ በኢትዮጵያዊነት የሚያምነው ኃይል ነው። ያን ኃይል ይዘው አገሪቷን መስመር ማስያዝ ነበረባቸው ብዬ አምናለሁ። ያ ኃይል አሁን ተገፍቷል። ድምፅ የለውም። ለኢትዮጵያዊነት መብት መታገል የሚያስበው ኃይል የለም። አሁን በብሔር የተደራጁ ኃይሎች ናቸው እንደ ልብ የሚንቀሳቀሱት። ከእሱ ነው የሚጀምረው። ስለዚህ ኢትዮጵያዊው ኃይል ለእርሳቸው ትልቁ ኃይላቸው መሆን ነበረበት። እሱን የተዉት ነው የሚመስለኝ። በሂደት ይታረማሉ ብዬ የማስባቸው ነገሮች ነበሩ ግን እየታረሙ አይደሉም። ሕገ መንግሥቱስ ለምንድን ነው ድምፅ እንዲሰጥበት የማይደረገው? በዚህ ዓይነት ሕገ መንግሥት ልንፈርስ በየቦታው ጠመንጃ መወልወል በተጀመረበት አገር እንደ አገር መቀጠል አይቻልም። የሕዝቡን ድምፅ እየሰሙ አይመስለኝም። እየሰሙ ያሉት የብሔርተኞችን ነው። በመሆኑም በሕገ መንግሥቱና ልዩ ኃይል በሚባለው ላይ ጠንከር ያለ አቋም ይዘው ካልወጡ በስተቀር፤ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ኢትዮጵያን የመምራቱ ነገር አደጋ ውስጥ ይገባል ብዬ ነው የማስበው። በዚህ ዓመት ደግሞ ምርጫ ይጠበቃል፤ አሁን ባለው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ ምርጫ ይካሄዳል መባሉን እንዴት ነው የምታየው? እኔን የሚታየኝ? ባለፈው ሳምንት ውስጥ ከአማራ ክልል የሚመጣ መኪና አዲስ አበባ መግባት የለበትም ተብሎ ወጣቶች መንገድ ዘግተው አትገቡም በሚሉበት፤ በምን ዓይነት መለኪያ ነው በዚያ ክልል ውስጥ እኔ የምፈልገው ሰው ይመረጣል ብዬ የማስበው። በፍፁም ሊሆን አይችልም። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቀጣዩ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ተናገሩ በነፃነት የምትንቀሳቀሽበት አገር አይደለም፤ ከዚያ ብሔር ውጪ ከሆንሽ ነፃነት የለሽም። ዜጎችን በሁለት ዓይነት የሚከፍል - ልዩ ዜጋና መጤ ዜጋ በምንባባልበት. . . ምርጫ ተካሂዶ ዴሞክራሲ ይሰፍናል የሚል ቅዠት የለኝም። በፍፁም ሊሳካ የሚችል አይደለም። ብሔርተኞቹ አንድ ላይ መጥተው በበለጠ አደጋ የሚፈጥሩበት ምርጫ ነው የሚሆነው ብየ ነው የማስበው። እንኳን ምርጫ ማካሄድ ሕግ ማስከበር ይቻላል ወይ? በሕግ የሚፈለጉ ሰዎች ወደ ክልላቸው ሄደው ከተደበቁ እኮ ማውጣት አይቻልም። በምን ዓይነት ዘዴ ነው ምርጫ የሚካሄደው። እንደዚህ ዓይነት ሕግ ባለበት ምን ዓይነት ምርጫ እንደሚካሄድ አይገባኝም። የሕግ የበላይነት ሲባል ዝም ብሎ አይደለም። መንግሥት ሕግ የማስፈፀም አቅም አለው ወይ? የሚለው ነው መታየት ያለበት። እና ለውጡን በመደገፍህ ትቆጫለህ? በፍፁም! ለምን እቆጫለሁ? ምክንያቱም ከማንም በቀረበ ኢትዮጵያ እስር ቤቶች ሲፈፀሙ የነበሩ ግፎችን ከተጎጂዎቹ አንደበት፣ ከተጎጅዎቹ ቤተሰቦች የተካፈልኩ ሰው ነኝ። ዛሬ እነዚያ ተጎጅዎች መፈታታቸው ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። • "እንደምፈታ ያወቅኩት ባለፈው መስከረም ነበር" አንዷለም አራጌ በሌላ በኩል ይነስም ይብዛም፤ በምንፈልገው መልኩ ባይሄድም፤ ዛሬ ሃሳብ መግለፅ የሚቻልባቸው ሚዲያዎች ተከፍተው እያየን ነው። ስለዚህ ለውጡን ብንገፋበትና አጠንክረን ብንሄድ የተሻለ አገር፣ የተሻለ ቦታ መድረስ ስንችል እንደዚህ ወደ ኋላ በመጎተታችን ከመቆጨት በስተቀር ለውጡን በመደገፌ ለአንድ ደቂቃም አልፀፀትም። ይህን ቃለ ምልልስ እንድናደርግ መነሻ የሆነው፤ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት በኢሬቻ በዓል ላይ አደረጉት የተባለውን ንግግር ተከትሎ በአንተ ስም ፌስቡክ ላይ የሰፈረው መልዕክት የአንተ ነው? አዎ! ብዙ ጊዜ አንተ የምትታወቀው ኢትዮጵያዊነትንና ሰብዓዊነትን በማቀንቀን ነው እና በዚህ መልዕክትህ ለአንድ ብሔር ወገነ፤ 'ተደምሮ ነበር ተቀነሰ' የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል። 'እንደራጅ' ስትል ምን ማለትህ ነው? ትክክለኛ ጥያቄ ነው። እኔ እንደራጅ ስል አሁንም ተበታትኖ የሚታየው ስለኢትዮጵያ ግድ የሚሰጠውን ኃይል ነው። እንደ ዜጋ በኢትዮጵያ ውስጥ በእኩልነት መኖር እንችላለን የሚለው ኃይል እየተገፋ ስላለ፤ እየለመንን አይሆንም ተደራጅተን ኢትዮጵያዊነታችንን ማስከበር አለብን የሚል ነው። ነገር ግን ከኦሮሚያው ፕሬዚደንት ንግግር ጋር ተያይዞ አብረው የተነሱ ነገሮች አሉ። በዚህ በለውጥ ሂደቱ ውስጥ ትልቁ ነገር፤ ትናንትን ይቅር ብለን ወደፊት ለመራመድ ስለተነሳን እንጅ አንድን ሕዝብም ሆነ አንድን ግለሰብ በማጥቃት፣ በጠላትነት በመፈረጅ በሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ በምንም መለኪያ ቁጭ ብዬ ላየው አልችልም። ስለዚህ የተደረገው ነገር ስህተት ነው። ማንም ሆነ ማን 'ሰብረናቸዋል . . . እንዲህ አድርገናቸዋል' የሚል የዛቻና የበቀል መንፈስ ያለው ሃሳብ እንኳን የመንግሥት ባለሥልጣን ተራ ዜጋ ሊያደርገው የማይገባ ነው። አንዱ ባለጊዜ ነኝ ብሎ ሰብሬህ እንዲህ አድርጌ የሚል ከሆነ ለማንም አይጠቅምም። ለመጠፋፋት እንዘጋጅ እንደ ማለት ነው። በሌላ በኩል ከአማራነት ጋር አያይዘውታል። ግን አማራስ ቢሆን . . . በማንም ሕዝብ ላይ እንዲህ ዓይነት በጅምላ ያነጣጠረ ነገር፤ በማንኛውም ጊዜ የፈለጉትን ነገር ሊሉኝ ይችላሉ ግን እቃወማለሁ። ኢትዮጵያዊ ዜጋ መብቱ ሲገፈፍ አሁንም ቆሜ አላይም። እንደራጅም ስል 'ኢትዮጵያዊያን' ስላልተደራጁ ነው። የተደራጁት እንዲህ ዓይነት የበቀል ፖለቲካ እያራመዱ ነው የሚሄዱት። አሁንም ተበትኖ ያለው ኢትዮጵያዊ ኃይል እንዲደራጅ እፈልጋለሁ። በአገሪቱ ውስጥ እየታዩ ያሉትን ነገሮች በመመልከት አንዳንዶች የከፋ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። አንተስ ይሄንን ስጋት ትጋራዋለህ? ለሕዝቡ ማመላከት ያለብን ነገር በጎውን ስለሆነ ይህንን ጨለማውን ነገር ባልናገረው እመርጥ ነበር- ሟርት የሚባለው ዓይነት ስለሆነ። ነገር ግን ወደ እውነቱ እየተጠጋን ከሄድን፤ በጣም እውር የሚያደርግ፣ የሚያሰክር የአልኮል መጠኑ የማይታወቅ ነው - ብሔርተኝነት፤ ምንም ጥያቄ የለውም ወደዚያ ሊወስደን ይችላል። አሁንም ጫፍ ጫፉን እያየን ነው። አክራሪ ብሔርተኛ ሲኮን ማሰቢያ አዕምሮን ለሌላ አከራይቶ . . . በቃ ያ ሰው በሚያዘው መንገድ እየሄዱ . . . ግደል ያሉትን መግደል፤ አፍርስ ያሉትን ማፍረስ ነው። እንደ ሰው ቁጭ ብሎ አስቦ በራስ አዕምሮ መከራከር አይኖርምና እኔ አሁን አሁን ያሰጋኛል። ኢትዮጵያዊያን በጋብቻም በማህበራዊ ሕይወትም የተቆራኙ ናቸው እየተባለ ይነገራል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የብሔር ግጭት ይባላል። ምንድን ነው ምክንያቱ ትላለህ? ፖለቲከኞች ናቸው። በጣም ራስ ወዳድ የሆኑ፣ ከራሳቸው በላይ ማየት የማይፈልጉ፣ ከራስ ክብርና ጥቅም በላይ ማየት የማይፈልጉ ፖለቲከኞች እየገፉት ነው እንጂ ሕዝቡ ውስጥ አሁንም አብሮ መኖሩ ገና አልጠፋም። ያ መተሳሰብ፣ መከባበር አሁንም አለ። ያ ባለበት እንዲዘልቅ ውሃ የሚያጠጣው፣ የሚንከባከበው ግን የለም። የሚያጠፋውን መንገድ እየገፉበት ነው ያለው። ቁጠሩ ቢባል እንኳን ሁለት ሺህ የማይሞሉ ፖለቲከኞች ናቸው እኮ ከመቶ ሚሊዮን በላይ የሆነውን ሕዝብ የሚያምሱት። ኃላፊነት የጎደለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምም ለሚደርሰው ውጥንቅጥ ምክንያት ነው። ትልቅ ኃላፊነት በሁሉም ዜጋ ላይ ነው ያለው። ስለዚህ አሁን በምታያቸው ነገሮች ወደ ተቃውሞ ልትገባ ትችላለህ? እንዴ?! በደንብ! እንደ በፊቱ በየኤምባሲው አልጮህም። መደረግ ያለበትን ሠርቶ ማድረግ ነው ብዬ ነው የማምነው እንጂ መቃወሜማ አይቀርም። በዚህ ዓይነት መቀጠል አንችልማ! እና በመሰባሰብ፣ ሥራ በመሥራት፣ በመደራጀት፣ መብታችንን ማስከበር በሚለው በጣም አምናለሁ። የምትደግፈው የፖለቲካ ፓርቲ አለ? አሁንማ የት አለ [ሳቅ] ቢኖር ኖሮ እኔስ መች እንደዚህ መከራዬን አይ ነበር። ችግሩ እኮ ያ ነው። ምንም እኮ ድምፃችንን ሊያሰማልን የቻለ ኃይል ባለመኖሩ እኮ ነው የተበተነው። ሌላኛው የማነሳልህ ትረስት ፈንዱን በተመለከተ ነው። ትረስት ፈንዱ ላይ ያለህ ሚና ምንድን ነው? በመጀመሪያ እንደተቋቋመ፤ እናንተ እንደዚህ ማድረግ ትችላላችሁ ሲባል፤ የደፈረሰ ውሃ የሚጠጣን ወገን ንፁህ ውሃ ማጠጣት ለእኛ በጣም ቀላል ነው። በጣም! ግን ከ5 ሚሊዮን እኮ አላለፍንም። በዚያው ጭቅጭቅ ጀመርን እና አንዳንዶች ገንዘባችን ለመንግሥት ሄዶ ምናምን እያሉ ይጠይቁኛል፤ ግን ለመንግሥት አልሄደም፤ መንግሥት ከፈለገ መዝረፍ የሚችለው በጣም በቂ ገንዘብ አለው። ያ አምስት ሚሊዮን መጣ አልመጣ. . . ኢትዮጵያ እኮ መርከብና አውሮፕላን የሚጠፉባት አገር ናት። ከገንዘቡ በላይ ሕብረተሰቡን አንድ ላይ የማምጣት፣ ኃላፊነት መስጠት፣ ባለ ጉዳይ ነኝ እንዲል የማድረግ ነገር ነበር የነበረው። አጭር ማስታወቂያ ሠርቻለሁ። ነገር ግን ብዙም አልተሳተፍኩም። ለምን? እሱ እንኳን በሥራ መብዛት ምክንያት ነበር እንጅ በመጥፎ አልነበረም። ግን አሁንም በኅብረተሰቡ መካከል የተፈጠረውን የተበታተነ መንፈስ፤ ዶክተር ዐብይ እንዴት እንደሚያስተካክሉት አላውቅም። ካላስተካከሉት ብዙ ውጤታማ ይሆናል ብዬ አላስብም። በዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ [ Global alliance] በተለይ ከምዕራብ ጉጂ ለተፈናቀሉት እርዳታ ስታሰባስብ ነበር። የትብብሩም ሊቀመንበር ነህ። አሁን ምን እየሠራችሁ ነው? በጌዲዮ ጉጂ ዞን ተፈናቅለው ለነበሩት ቤቶች አሠርተናል። ያ እንዳለቀ በይፋ ይመረቃል። ከዚህ በፊት የሠራናቸው ብዙ ሥራዎች አሉ። በቀደመው ሥርዓት ከእኛ ጋር መገናኘትና ስልክ መደዋወል ክልክል ስለነበር በጣም በጥንቃቄ የዜጎችን መብት ለማስከበር በርካታ ነገር እናደርግ ነበር። የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ማሳከም፣ ልጆቻቸውን ላጡ ማቋቋሚያ መስጠት፣ ጋዜጠኞች ሲሰደዱ ለእነሱ ድጋፍ ማድረግ ብዙ ሥራ ሠርተናል። አሁን ምን እናድረግ? በሚለው ላይ ለመነጋገር በሚቀጥለው ወር ላይ ጉባዔ አለን። በኢትዮጵያም ተመዝግበን ለመንቀሳቀስ እየሠራን ነው። እንድንቋቋም መነሻ የሆነን በሳዑዲ በዜጎች ላይ የደረሰው በደል ነበር። አሁን ላይ ጊዜያዊ እርዳታ እየሰጠን መቀጠል እንችላለን ወይ? የሚለውን በደንብ አጥንተን መተዳደሪያ ደንባችንን አስተካክለን ለመንቀሳቀስ እሞከርን ነው።
news-48490483
https://www.bbc.com/amharic/news-48490483
አሜሪካ፡ የሳዑዲ ልዑል በመምሰል 8ሚሊየን ዶላር ያጭበረበረው ግለሰብ ታሰረ
አንቶኒ ጂኒያክ ለዓመታት የንጉሶችን ደረጃ የሚመጥን ቅንጡ ሆቴል ኖሯል። በጣም ውድ የሆኑ ጌጣጌጦችን ያደርጋል፤ በግል ጀቶችና ውድ መኪናዎች ይንቀሳቀሳል፤ የዲፕሎማት መንቀሳቀሻ ፍቃድም ይይዛል፤ የሚይዘው የቢዝነስ ካርድ 'ሱልጣን' ተብሎ የተፃፈበት ነበር።
ይሁን እንጂ ራሱን ልዑል ነኝ ብሎ የሚጠራው ሀሰተኛው ግለሰብ የተጋለጠው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህ የማጭበርበር ወንጀልም 18 ዓመታትን በእስር እንዲያሳልፍ ተወስኖበታል። • ሳዑዲ ልዕልቷን የአሜሪካ አምባሳደር አደረገች • በአዲስ አበባ የኮሌራ በሽታ ምልክት ታየ ውሳኔውን ያሳለፈው የፍሎሪዳ ፍርድ ቤት ዳኛ "የ48 ዓመቱ ጂኒያክ አጭበርባሪ ነው፤ ራሱን የሳዑዲ ልዑል በማስመሰል ከባለሃብቶች 8 ሚሊየን ዶላር ሰብስቧል" ብለዋል። "ላለፉት ሦስት አስርተ ዓመታትም አንቶኒ ራሱን የሳዑዲ አረቢያን ልዑል በማስመሰል በተለያዩ የአለም ክፍሎች ባለሃብቶችን ሲያጭበረብርና በእነርሱ ላይ ያልተገባ ድርጊት ሲፈፅም ቆይቷል" ሲሉ የአሜሪካ አቃቤ ሕግ ፋጃርዶ ኦርሻንም በመግለጫቸው አስታውቀዋል። ግለሰቡ በሀሰተኛ ማንነት ልዑል ካሊድ ቢን አል ሳዑዲን በመምሰል ለበርካታ ሰዎች የማይጨበጥ ተስፋ ሲሰጥ እንደነበርም ተገልጿል። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራቸው፣ አሊያም ለወደፊቱ ሕይወታቸው ያለሙ ግለሰቦችን በተስፋ ሸጧቸዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ ባለሃብቶች ከ8 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ አጥተዋል ሲሉ ኦርሻን አክለዋል። አንቶኒ ጂኒያክ ማነው? አጭበርባሪው ጂኒያክ የተወለደው ኮሎምቢያ ሲሆን የሰባት ዓመት ህፃን ሳለ በጉድ ፈቻ ወደ አሜሪካ ግዛት ሚቺጋን ተወስዷል። የ17 ዓመት ታዳጊ ሲሆን ድርጅቶችን፣ የሱቅ ሠራተኞችንና ባለሃብቶችን ለማጭበርበር የሳዑዲውን ልዑል ገፅታን ለመላበስ ጥረት ያደርግ ነበር። • ኔይማር የቀረበበትን ወሲባዊ ትንኮሳ ክስ አጣጣለ የፍርድ ቤቱ ማስረጃዎች እንደሚያትቱት ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ 11 ጊዜ ታስሮ የነበረ ሲሆን የታሰረው ከልዑል ጋር በተያያዘ ጉዳይም እንደነበር ተገልጿል። ከአራት ዓመታት በፊት ጀምሮ ካሊድ ቢን አል ሳዑዲ የሚለውን ስም ይጠቀምበት እንደነበርም የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ለፍሮሊዳ ግዛት አስታውቋል። የማጭበርበር ድርጊቱን ይረዳው ዘንድም ግለሰቡ ሀሰተኛ የሆኑ የዲፕሎማት ፍቃድ እና መረጃዎችን ለጠባቂዎቹ ይገዛ ነበር፤ ይህም ብቻ ሳይሆን የሳዑዲን ባህላዊ አልባሳት ይለብሳል፤ በጣም ውድ የሆኑ ቀለበቶችንና ሰዓቶችንም ያደርግ ነበር፤ በጣም ውድ የሆኑ የጥበብ ሥራዎችንም ይሰበስብ ነበር። • የቦይንግ 737 ማክስ ደህንነት ስለ ማሻሻል ያለው እሰጣ ገባ ቀጥሏል በአብዛኛው ከባለሃብቶች ጋር ሲገናኝም ራሱን እንደ ልዑል አስመስሎ የሚቀርብ ሲሆን እንደ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች ስጦታ መስጠትንም ያዘወትር ነበር። መርማሪዎች እንደሚሉት ግለሰቡ በዓለም ላይ በተጨባጭ በሌሉ ቦታዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ሲያግባባቸውም ቆይቷል። ይሁን እንጂ የማጭበርበር ድርጊቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ በሚያሚ ቅንጡ ሆቴል ለመገንባት ያደረገው ጥረት ከሽፎበታል። ይህ የሆነው በድርድር ላይ ሳሉ የሆቴሉ ባለቤት ግለሰቡን በመጠራጠሩ ሲሆን የአሳማ ስጋ ለመመገብ ፈቃደኛ በመሆኑም ጥርጣሬው ከፍ እንዲል አድርጎታል። "ምክንያቱም ሙስሊም ልዑል የአሳማ ስጋን አይበላም" ሲል ለሚያሚ ሄራልድ ተናግረዋል። ከዚያ በኋላ በእርሱ ላይ ምርመራ የሚያካሂድ የምርመራ ቡድን ቀጠሩ። ይህም ወደ ፌደራል የምርመራ ቡድን አመራ። በመሆኑም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ጂኒያክ ገንዘብ በማጭበርበሩ፣ ሐሰተኛ ማንነት በመጠቀሙ፣ ዲፕሎማቶችን በማታለሉ ጥፋተኛ መባሉን የፍርድ ቤት ማስረጃዎች አመላክተዋል። ኦሻር በመግለጫቸው ላይ "ፍትህ ለተበዳዮች ትጮሃለች" ሲሉ ተደምጠዋል።
44469215
https://www.bbc.com/amharic/44469215
"ወሎዬው" መንዙማ
መንዙማ የትም ሊኖር ይችላል። ግብፅም የመንም፣ 'ሻምም'
መንዙማ የትም ሊዜም ይችላል፤ ታጃኪስታንም፣ ኡዝቤኪስታንም፣ ፓኪስታንም እንደ ወሎ የሚኾን ግን…እንጃ! የወሎ መንዙማ ቱባ ነው። ኦርጋኒክ! አልተቀየጠ፣ 'አልተከተፈ'፣ 'አልተነጀሰ'። ደግሞም እንደ ዘመነኛ ነሺዳ በ'ኪቦርድ' ቅመም አላበደ…። ለዚህ ምሥክር መጥራት አያሻም። የሼኽ መሐመድ አወል ሐምዛን እንጉርጉሮ መስማት በቂ ነው። 'በጆሮ በኩል ዘልቆ፣ አእምሮን አሳብሮ ወደ ልብ የሚፈስ የድምፅ ፈውስ…።' ይለዋል ወጣቱ ገጣሚ ያሲን መንሱር። የመንዙማው ማማ በዚህ ዘመን ህልቆ መሳፍርት መንዙመኞች አሉ። ሼኽ መሐመድ አወል ሐምዛ ግን ከማማው ላይ ናቸው። ከወሎ የፈለቁት ሼኹ ለመገናኛ ብዙኃን ቃል መስጠት እምብዛም ምቾት አይሰጣቸውም። ለቢቢሲ ጥሪም እንዲያ ነው ያሉት። ኾኖም ታሪካቸውን የዘገቡ ሰነዶች የኚህ ሰው የሕይወት መስመር እንደ መንዙማቸው ልስሉስ እንዳልነበረ ያትታሉ። ደቡብ ወሎ የተወለዱት ሼኹ ገና ድሮ ወደ ሸዋ ገብተው ኑሮ ለማደራጀት ከፍ ዝቅ ብለዋል። የሚያምር የአረብኛ የእጅ ጽሕፈት አጣጣል ስለነበራቸው የሃይማኖት ድርሳናትን በእጅ ከትበው በመስጂዶች ቅጥር ማዞር ጀማምረውም ነበር ይባላል። ወዳጆቻቸው እንደነገሩን በአዲሳ'ባ የመን ኮሚኒቲ በመምህርነት እስኪቀጠሩ ድረስ የወሎ ምድርና ተፈጥሮ አድልተው ያደሏቸውን መረዋ ድምጽ በመጠቀም በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ መንዙማን ያዜሙ ነበር። አንዳንድ መድረኮች ላይ ታዲያ የሼኩ ተስረቅራቂ ድምጽ ለነብዩ ውዳሴ ከሚደረድሩ ጥልቅ መልዕክቶች ጋር ተዳምረው ታዳሚዎችን ስሜታዊ ያደርጓቸው ነበር ይባላል። "የእሱ እንጉርጉሮ እንደሁ ያው ታውቀዋለህ…ልብ ያሸፍታል…አንዳንድ ሼኾች ድምጽ አውጥተው በስሜት ያለቅሱ እንደነበር አስታውሳለሁ" ይላሉ ቆየት ካሉ ወዳጆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ ትዝታቸውን ሲያጋሩ። በመንዙማ ፍቅር የወደቀው ደርግ መንዙመኛው ሼክ መሐመድ አወል ድሮ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ተቀጥረው ነበር አሉ። መንዙማቸውም እንደዋዛ ሬዲዮ ሞገድ ውስጥ ገብቶ ነበር አሉ፤ እንደ ማጀቢያም እንደማዋዣም። ታዲያ ከዕለታት ባንዱ ልበ-ደንዳናዎቹ ደርጎች በሰውየው አንጀት አርስ እንጉርጉሮ ልባቸው ረሰረሰ። ከደርጎቹ በአንዱ ላይ ክፉ አሳብ በልቡ አደረ። እንዲህም አለ፣ 'ይሄ ሰውዬ በነካ እጁ ስለ አብዮቱ ለምን አያዜምልንም?' ሼኪው ተጠሩ። "ድምጽዎ ግሩም ኾኖ አግኝተነዋል፤ እስቲ ስለአብዮታችን አንድ ሁለት ይበሉ…።" ያን ጊዜ "ያ አላህ! አንተው መጀን!" ብለው ከአገር ሾልከው የወጡ ከስንትና ስንት ዘመን ኋላ የሐበሻን ምድር ተመልሰው የረገጡ። 10 ዓመት? 20 ዓመት? እንጃ ብቻ! በዚህ ሁሉ ዘመን ታዲያ እኚህ እንደ ጨረቃ የደመቁ መንዙመኛ የት ከረሙ? ስንል የጠየቅናቸው ወዳጆቻቸው ከፊሎቹ "መሐመድ አወል ሐምዛ ሳኡዲ ነው የኖረው ሲሉ፣ ገሚሶቹ ደግሞ 'የለም! እዚህ ጎረቤት 'ሚስር'፣ አልአዝሃር ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ሲይንበለብለው ነበር' ብለውናል። የቱ ነው ትክክል ብሎ ለመጠየቅ እንኳ ሰውየው ሩቅ ናቸው። ያ ጥኡሙ ድምጻቸው መንዙማን ለማዜም ካልሆነ በቀር አይሰማም። እ…ሩቅ ነው። መንዙማ- የልብ ወጌሻ መንዙማ አልፎ አልፎ መዝናኛ ነው፤ አንዳንዴ የጸሎት ማዳረሻ ነው፤ ብዙዉን ጊዜ የማኅበረሰብን ሰንኮፍ ማሳያም ነው፤ አንዳንዴ የአገር ፍቅር መግለጫም ነው። ብዙዎቹ የመንዙማ ሥንኞች የሥነ-ምግባር ተምሳሌት ተደርገው የሚታሰቡትን ነብዩ ሙሐመድን ያወድሳሉ። አፈንጋጮችን ይገስጻሉ፣ ባሕል ከላሾችን ይኮረኩማሉ። አቶ ተመስገን ፈንታው መቀለ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሥነ-ጽሑፍና ፎክሎርን ለ12 ዓመታት አስተምረዋል። በመንዙማ ዙርያ የተሠሩ በርከት ያሉ ጥናታዊ ወረቀቶችን አማክረዋል። የአጋጣሚ ነገር-ትውልዳቸውም ወልዲያ ነው። 'ሴት አያቴ በመንዙማ ነው ያሳደገችኝ' ይላሉ' ክርስቲያን መሆናቸው መንዙማን ከማጣጣም እንዳላቦዘናቸው ሲያስረዱ። "ወሎ ውስጥ መንዙማ ባሕል ነው። የየትኛውንም ዕምነት ተከታይ ሁን መንዙማን ትሰማለህ፤ በአንድም ሆነ በሌላ…" የወሎ ባሕል ወትሮም ሃይማኖትን ፍዝ ያደርጋል። "አያቴ መንዙማን "የእስልምና" ብላ አይደለም የምትረዳው። እሷ የምታውቀው የወሎዬ መሆኑን ነው። መንዙማ ለእሷ ከአምላክ ጋር መገናኛ፣ መታረቂያ፣ መለማመኛ፣ ስሜቷን መተንፈሻ ነው። ይላሉ። መምህር ተመስገን ይኸው የልጅነት ተጽእኖ ይሁን አይሁን ባያውቁትም አሁንም ድረስ ጥሞናና መመሰጥ ሲያምራቸው ከላፕቶፓቸው ኪስ ያኖሯቸውን እንጉርጉሮዎች ያዘወትራሉ። "አቦ ሌላ ዓለም ነው ይዞኝ የሚሄድ!" መንዙማና 'ፍልስምና' 'ፍልስምና' እስልምናና ፍልስፍናን ያቀፈ ሽብልቅ ቃል መሆኑ ላይ ከተግባባን በመንዙማ ውስጥ ፍልስፍና እንደጉድ እንደሚነሳና እንደሚወሳ ልናወጋ እንችላለን። በመንዙማ ዓለማዊም ኾኑ ዘላለማዊ መጠይቆች በቅኔ ተለውሰው ይዜሙበታል። በግልባጩም የፈጣሪን መኖር የሚጠራጠሩ ኢ-አማንያን ከብርቱ አማኒያን ተሞክሮ እየተጨለፈ በምክር ይረቱበታል። ለነገሩ በመንዙማ ስንኞች ፍልስምና ብቻ አይደለም የሚነሳው፤ ምን የማይነሳ አለና!? ፖለቲካ፣ ግብረ-ገብነት፣ መንፈሳዊነት፣ አርበኝነት…ኢትዮጵያዊነት... በስልክ ማብራሪያ የሰጡን ኡስታዝ አብዱልአዚዝ መሐመድ የነጃሺ መስጂድ ኢማምና የጁምዓ ሶላት ዲስኩረኛ (ኻጢብ) ናቸው። መንዙማ በኢትዮጵያ የኢስላም ታሪክና ፖለቲካ ውስጥ የነበረውን ቦታ ሦስት የመንዙማ ሊቃውንትን በስም በመጥቀስ ይተነትናሉ። በዘመናዊ የኢስላም ታሪክ ውስጥ ሰሜን ወሎ፣ ራያ ውስጥ ጀማሉዲን ያአኒ የተባሉ ሐበሻ ከአጼ ዮሐንስ ጋር ለሦስት ዓመታት ተፋልመዋል። በመጨረሻ አጼው በርትተው ሲመጡባቸው ድል መነሳታቸው እርግጥ ሆነ። ያን ጊዜ ያዜሙት መንዙማ ዛሬም ድረስ ይወሳል። "ዘይኑ ነቢ ዘይኑ ነቢዬ" የሚል አዝማች ያለው ሲሆን የመንዙማው ጭብጥ ደግሞ የአጼውን ጭካኔ ማጉላት ነው። እንዲያውም የአጼ ዮሐንስን ጦርነት አርማጌዶን ሲሉት፤ በምጽአት ቀን (ቂያማ) ይመጣል የሚባለው ሰው ጋር ያመሳስሏቸዋል። ይህ ሰው በኢስላም "ደጃል" በመባል ይታወቃል። አጼው እኔ ላይ ያለ ጊዜው የመጣ ደጃል ሆነብኝ ሲሉም አዚመዋል። በተመሳሳይ በየጁ ግዛት ይኖሩ የነበሩና አሕመድ ዳኒ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ አባት በወቅቱ የነበረው አገረ ገዢ በጣም ቅር እንዳሰኛቸው፣ ዘመኑም እንዳልተመቻቸው ለመግለጽ የሚያንጎራጎሩበት መንዙማ ዛሬም ድረስ ይዜማል። ርዕሱ "ሑዝቢየዲ ያረሱላላህ" የሚል ሲሆን "ከይህ ወዲህ ምድር ላይ መቆየት አልሻም፤ በቃኝ" የሚል መልዕክትን የያዘ ነው። ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መንዙመኞች ደግሞ ሼክ ጫሊ ጎልተው ይወሳሉ። በይዘትም፣ በቋንቋ ልቀትም፣ በቁጥርም፣ በዓይነትም እንደርሳቸው መንዙማን የቀመረ የለም ይባላል። እርሳቸው ታዲያ ከወራሪው ጣሊያን የተፋለሙ ጀግና ነበሩ። ከመንፈሳዊ መንዙማም በላይ ስለ አገር ፍቅር ያዜሙ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። ጣሊያን ወልዲያ፣ ሃራ አካባቢ አባብሎና አግባብቶ ካስጠራቸው በኋላ ተኮሰባቸው፤ በተአምር ተረፉ። እርሳቸውም በመንዙማቸው እንጉርጉሮን አዚመዋል። 'በአገራችን መኖር አትችሉም አሉን፤ ሻምና ሩም ሂዱ አሉን፤ ምን ጉድ ነው ይሄ' የሚሉ ፖለቲካዊ ዜማዎችን አዚመዋል። እንደ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ ገለፃ መንዙማና ሥነ-ቃል እያንዳንዱ መንዙማ ይነስም ይብዛ ታሪክ ተሸክሟል። የመንዙማ ስንኞች ቢያንስ ቀደምት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንዴት እንደኖሩ የመተረክ አቅም አላቸው። አሁን ያሉቱ መንዙመኞች ግን ቀደምት ግጥሞችን በአዲስ ቅላጼ የማዜም ነገር ካልሆነ እምብዛምም አዲስነት አይታይባቸውም። በመንዙማ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ዕውቀትም ተስፋፍቷል። ማንበብና መጻፍ ሩቅም ብርቅም በነበረበት በያ ዘመን መንዙማ የእስልምና ትምህርት መሠረታዊያንን ለገጠሩ ማኅበረሰብ ለማድረስ አስችሏል ይላሉ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ። የመንዙማ ንሸጣ የመንዙማ ግጥሞች ጥልቀትና ከፍታ በታላቅ መነቃቃትና ጥሞና ውስጥ መጻፋቸው ነው። የመንዙማ ደራሲ ድንገት ''ዋሪዳ'' መጣብኝ ካለ ቅኔ ሊዘርፍ ነው ማለት ነው። ንሸጣ ውስጥ ገብቻለሁ እንደማለትም ነው። ድሮ ድሮ በግብታዊነት የሚጻፉ፣ በዘፈቀደ የሚሰደሩ ስንኞች አልነበሩም። አሁን አሁን ካልሆነ። ንፁህ አማርኛን ብቻ የሚጠቀሙ መንዙማዎች የሉም ባይባልም በርካታ አይደሉም። የሚበዙቱ አረብኛን ከወሎ አማርኛ ጋር ያዳቀሉት ናቸው። ለምን? የወሎ አማርኛ ወትሮም አንዲያ ያደርገዋል። "ከአረብኛ ጋር የመጎናጎን ባሕሪው ዘመን የተሻገረ ነው። የወሎ ሕዝብ ችግር መጣብኝ ከማለት "ሙሲባ መጣብኝ" ነው የሚለው። ሙሲባ አረብኛ ነው" ይላሉ ኡስታዝ አብዱልአዚዝ። ይህ ቋንቋን የማዳቀሉ ነገር መንዙማው ላይም ተጋብቶበታል ይላሉ ኡስታዙ። ቢያንስ በሁለት ምክንያት… በኢትዮጵያ የኢስላም ታሪክ የወሎዎች ሚና መጉላቱ አንዱ ነው። ቁርዓን፣ ፊቂህ (ኢስላማዊ ሕግጋት ) የቅዱስ መጻሕፍት ትርጉም (ታፍሲር)፣ አረብኛ ቋንቋ እና የአብነት ትምህርት ቤቶች (ማድራሳ) ከወሎና ሀይቅ አካባቢ ነው የመነጩት። ዛሬም ድረስ የበርካታ መዝጊዶች አሰጋጆችና ሊቃውንት (ሙፍቲሆች) የወሎ ልጆች ናቸው። መንዙማም መንፈሳዊው ሕይወትን የመግለጫ አንድ የጥበብ አምድ መሆኑ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ይልቅ በዚያ አካባቢ እንዲጎመራ የተመቻቸ መስክ ሳያገኝ አልቀረም። ይላሉ ኡስታዙ። የአረብኛ ቃላት በመንዙማው እንዲህ በአያሌው መነስነስ ሌላው ምክንያት ደግሞ፤ አንድም የሃይማኖቱ አንኳር ቃላት በአረብኛ መወከላቸው የፈጠረው ሀቅ ሲሆን፣ አንድም ደግሞ የገጣሚዎቹ የቋንቋ ልኅቀት ማሳያ የይለፍ ወረቀት (poetic license) መሆኑ ነው። ሳኡዲን ያስደመመው የሐበሻ መንዙማ የነጃሸዒ መስጂድ ኢማም ኡስታዝ አብዱልአዚዝ ናቸው ይህን ግርድፍ ታሪክ የነገሩን። የቀድሞው የሳኡዲ ዋናው ሙፍቲህ እጅግ የተከበሩት ሼክ ኢብኒባዝ -አሁን በሕይወት የሉም-ነፍስ ይማር (ይርሃመሁላህ) አንድ ቀን ምን አሉ? 'እስቲ የናንተ ሐበሾች ጻፉት የሚባለውን መንዙማ አምጡልኝ!' በዝና ብቻ ነበር አሉ የሐበሻን መንዙማ የሚያውቁት። ቀረበላቸው። ግጥሞቹን ሰምተው ግን ለማመን ተቸገሩ። "እንዴት እኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋችን አረብኛ የሆንነው ሰዎች ያልቻልነውን በግጥም መራቀቅ እናንተ ቻላችሁበት?" ብለው መደነቃቸው ይነገራል። ሼኸ ኢብኑባዝን ወሎ ነበር ማምጣት...የቅኔ አገር...የደረሶች ማንኩሳ...የመንዙማ ቀዬ...የ'መሳኪን' ሼኮች ማደሪያ...
news-55214480
https://www.bbc.com/amharic/news-55214480
ትግራይ ፡ ጥቅምት 30 ሰኞ ዕለት በማይካድራ ከተማ የተከሰተው ምን ነበር?
በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ውስጥ በምትኘው የማይካድራ ከተማ ጭፍጨፋ ከተፈጸመ ኅዳር 30/2013 ዓ.ም አንድ ወር ሆነው። የሰብአዊ መብት ቡድኖች እንዳሉት በጥቃቱ ከ600 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
በማይካድራ የተገደሉ ሰዎች አስክሬን በዚህ መሰል አልጋዎች ሲሰበሰቡ ነበር በአካባቢው ለአንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ ስለነበረ ቢቢሲ በከተማዋ የሚኖሩ ሰዎችን ለማናገር ሳይችል ቆይቷል። አሁን ግን በአካባቢው የስልክ አገልግሎት በከፊል በመጀመሩ የከተማዋን ነዋሪዎችን ስለክስተቱ ለማናገር ችለናል። ጥቃቱ ጥቅምት 30/ 2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 9፡ 00 ሰዓት ላይ የነበረ ሲሆን አስከሚቀጥለው ቀን ጠዋት ድረስ መቀጠሉን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። ወ/ሮ ትርፋይ ግርማይ የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ ከአማራው ባላቸው ጋር ትዳር መስርተው በማይካድራ ከተማ ውስጥ መኖር ከጀመሩ 12 ዓመታትን እንዳስቆጠሩ ይናገራሉ። አንዲትም ልጅ አለቻቸው። ባለቤታቸው በተለያዩ የግብርና ሥራዎችን በማከናወን የወይዘሮ ትርፋይን እናት ጨምሮ የመላው ቤተሰቡን ሕይወት ለመምራት የሚስችለው ዋነኛ የቤተሰቡ የገቢ ምንጭ ነበር። በትዳር ውስጥ በቆዩባቸው 12 ዓመታት ውስጥ እንደአሁኑ ጥቃት ታይቶ እንደማያውቅ ያስታውሳሉ። ባለቤታቸውና የቤተሰባቸው አስተዳዳሪ አይናቸው እያየ ከቤታቸው ደጃፍ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ይናገራሉ። "ባለቤቴ ምንም የሚያስገድል ወንጀል አልሰራም፤ የተገደለው አማራ በመሆኑ ነው" ይላሉ ወይዘሮ ትርፋይ። የጤና ችግር እንዳለባቸው የሚናገሩት ወይዘሮ ትርፋይ፣ ባለቤታቸውን በዚያ አሰቃቂ ሁኔታ በማጣታቸው ቀጣይ ህይወታቸው መመሰቃቀሉን ይናገራሉ። እናታቸውን እና ልጃቸውን ለማስተዳደር ምን መስራት እንዳለባቸውም ግራ መጋባታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሌላኛዋ የማይካድራ ነዋሪ የሺ ላቀም ባለቤቷን በተመሳሳይ ሁኔታ ማጣቷን ታስረዳለች። የነበረውን ሁኔታ ስታስታውስ "መጀመሪያ ቤታችሁን ዝጉ አሉን፤ ከዚያ ሁለተኛ መጥተው ቤታችንን እየከፈቱ ወንዶቹን መርጠው እየወሰዱ ገደሏቸው" በማለት በምሬት ትናገራለች። የጥቃቱ ዕለት ባለቤቷ የትም እንዳልሄደ የምታስታውሰው ወ/ሮ የሺ፣ "ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ በቡድን የተሰባሰቡ ወጣቶች መጥተው ባለቤቴንና የባሌን ወንድም ከቤት በማስወጣት ገደሏቸው" ብላለች። "ባለቤቴን ተውልኝ ብላቸውም አንቺን ነገ አይቀርልሽም፤ ዛሬ የምፈልገው ወንዶችን ነው በማለት እኔ እና ልጆቼ እያየን ገደሏቸው" በማለት የባሏን ሞት ያየችበትን አጋጣሚ ገልጻለች። "በወቅቱ እኔንም አንዳንዶቹ 'በላት' እያሉ ሌሎቹ ደግሞ ገላግለው አተረፉኝ" ያለችው የሺ ከዚያ በኋላ ወደ ቤት ገብተው አንዳንድ ነገሮችን ዘርፈው እንደወሰዱ ትናገራለች። ወ/ሮ የሺ ከባለቤቷ አየነው ሙላት ጋር ከ10 ዓመታት በላይ በትዳር ኑረዋል። ሁለት ልጆችንም አፍርተዋል። ልጆቻቸውም አባታቸው ሲገደል በቦታው ስለነበሩ አሁን "ሕጻኗ ልጄ ታስቸግረኛለች፤ ሌሊት እየተነሳች 'አባቴ የት አለ' እያለች ትፈልጋለች፤ ይህም ሌላ ችግር ፈጥሮብኛል" በማለት አሁን ያለችበትን ሁኔታ ታብራራለች። የባሌን አሟሟት እያሰብኩ "ኑሮን እንዴት መምራት እንዳለብኝም ለማሰብ ሞራሉ የለኝም፤ ልቤ ተሰብሯል። የነበረው ሁኔታ በጣም ከባድ ተብሎ የሚገለጽበት አይደለም" ትላለች። አቶ ጥላሁን አታላይ ነዋሪነቱ በማይካድራ ግምብ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። "በዕለቱ [ጥቅምት 30] ማሽላ ለማስቆረጥ ስንሰናዳ 7፡00 ሰዓት አካባቢ በቡድን ወደቤታችን በመምጣት መታወቂያ ጠየቁን" በማለት የክስተቱን አጀማመር ያስረዳል። "ይህም ብሔራችንን ለመለየት ነበር።" "ከቀኑ 8፡00 ላይ ወጣቶቹ በከተማዋ ውስጥ እንደሰልፍ ነገር አደረጉ፣ ከዚያ ግን ሰልፉን ሰበብ አድርገው ጥቃቱን ጀመሩ።" ወዲያውም ወደ እነሱ ቤት ሲመጡ "እኛም ሴትና ህጻናትን አያጠቁም የሚል መረጃ ስለሰማን እኔና ወንድሜ ኮርኒስ ላይ ወጣን። ሲያጡን ተመልሰው ሄዱ። ተመልሰው 11፡00 ሰዓት ላይ መጡ እና ድጋሚ ቤቱን ፈተሹ፤ አሁንም እኛ ከኮርኒሱ ስላልወረድን የወንድሜን ሚስት አስፈራርተው ባልሽን ካላመጣሽ እንገድልሻለን በማለት ገልጋይና ተገልጋይ ሆነው ተመልሰው ሄዱ" ይላል። አስደንጋጩ ነገር የተከሰተው ግን ከምሽቱ 1፡30 ነው። ሁለት ጊዜ ወደ ቤት መጥተው አንድም ወንድ ሳያገኙ የተመለሱት ወጣቶች የእነ ጥላሁንን ቤት ለመፈተሽ ለሦስተኛ ጊዜ ምሽት 1፡30 ሰዓት ላይ ተመልሰው መጡ። "በዚህ ጊዜ የወንድሜን ባለቤት ከቤት አስወጥተው 'ባልሽ የት እንዳለ የማትናገሪ ከሆነ አንችን እንገድልሻለን' ብለው ጩቤ አወጡ። በቃ ግደሉኝ ስትላቸው 'እንዲያውም ከአንቺ በፊት ልጅሽን ነው የምንገድለው' ብለው ልጁን ሊወስዱት ሲዘጋጁ ከልጄ በፊት እኔን ግደለኝ ብላ እርሷ ተጠጋች" በማለት በዚያ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ የነበረውን ሁኔታ ይገልጻል። ይህ ሁሉ ሲሆን ጥላሁን ከወንድሙ ጋር ኮርኒስ ውስጥ ተቀምጠው የሚሆነውን ይከታተሉ ነበር። ባለቤቱን ሊገድሏት ሲሉ ግን ወንድሙ ሁኔታውን መቆጣጠር አለመቻሉን ይገልጻል። "ይህንን ወንድሜ ሲያይ 'እኔ ቁሜ አስከሬን አልቆጥርም' ብሎ ወርዶ ወደ እነሱ ሄደ። ከዚያም በያዙት ነገር ሁሉ ሲደበድቡት ባለቤቱ ጩኸት አሰማች፤ እሷንም ትካሻዋ ላይ መትተው አቆሰሏት" በማለት ይህንን ግድያ ለማምለጥ ሰዓታትን አብሮት ኮርኒስ ላይ ተቀምጦ የነበረው ወንድሙን ያጣበትን ክስተት ያስታውሳል። በወቅቱ የነበረውን የሰው ብዛት ሲገልጽ "የሳምሪ ወጣቶች በሙሉ ነው የመጡት፣ ቁጥራቸው ከ150 በላይ ይሆናል። ጥቃቱን ሲፈጽሙ የታጠቁ ሚሊሻ እና ፖሊሶች አብረዋቸው ነበሩ" ብሏል። በወቅቱ ከግድያ በተጨማሪ ዝርፊያም መከሰቱን የሚናገረው ጥላሁን፤ ወንድሙ ከቀናት በፊት ሰሊጥ ሸጦ ባንክ ዝግ ስለነበር በጥሬ 90 ሺህ ብር በቤት ውስጥ አስቀምጦ ነበር። ያንን ብርም እነዚህ ወጣቶች መውሰዳቸውን ገልጿል። ጥቃቱ ተፈጸመ የተባለበት ማይካድራ ከሁመራ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ ትገኛለች ወይዘሮ ሃዳስ መዝገቡም ማይካድራ ውስጥ ግምብ ሰፈር ነው የምትኖረው። ከባለቤቷ ብርሃኑ ጋር በትዳር ተጣምረው 17 ዓመታትን በመኖር ሦስት ልጆችን አፍርተዋል። የማይካድራው ግድያ ሲፈጸም በጅምላ ከተገደሉት መካከል አንዱ የእርሷ ባል ነው። "ከቀኑ 6፡00 መጥተው ሲም ካርድ እና መታወቂያ ለዩ። በ9፡00 ግድያው ተፈጸመ" ያለችው ወ/ሮ ሃዳስ "በአካል የምናውቃቸው ሚሊሻዎችና የሳምሪ ልጆች ናቸው ግድያውን የፈጸሙት" ትላለች። ሌሎች ደግሞ ጥቃት የሚፈጸምባቸው ሰዎች ላይ የሚጠቁሙ ግለሰቦች እንደነበሩ ገልጻለች። "ባሌ ሚሊሻ ነበር፤ ትጥቁን አስወርደው ነው የገደሉት" የምትለው ሃዳስ "ፍተሻውን ለማድረግ የወሰኑት ያለውን የሰው ብዛት ለማወቅ ነው። ባለቤቴ እና የእህቱ ልጁ ተገድለዋል" በማለት አሰቃቂውን ድርጊት ታስረዳለች። ከተገደሉት የቤተሰቧ አባላት በተጨማሪ የሟች ባሏ የአጎት ልጅ ደግሞ ቆስሎ ጎንደር ህክምና ላይ እንደሚገኝ የተናገረችው ሃዳስ "በማግስቱ ተረኞቹ ሟቾች እኛ ነበርን፣ ነገር ግን መከላከያ ደረሰልን። የሞቱት ሰዎች ከሦስት ቀን በኋላ በኅዳር 2 ነበር የተቀበሩት" ብላለች። አቶ ገብረ መስቀል መንግሥቱ ደግሞ ነዋሪነታቸው በማይካድራ ከተማ ሲሆን በእርሻ ኢንቨስትመንት ላይ ተሰማርተው ኑሯቸውን ይመራሉ። በማይካድራ ግድያ ሲካሄድ በቦታው እንደነበሩና ከመጀመሪያ እስከመጨረሻው ተከታትለዋል። እንደአቶ ገብረ መስቀል ገለጻ ከግድያው በፊት በርካታ ወጣቶች በትራክተር 40 እና 50 እየሆኑ ወደ አንድ ቦታ ሲሰባሰቡ መመለክታቸውን ይገልጻሉ። በወቅቱም ሌላው ነዋሪ ስለሁኔታው ምንም የሚያውቀው ነገር ስላልነበረ አንዱን ሰው ከቤቱ አስወጥተው ሲገድሉ ሌላው "ምን እየሆነ ነው ብሎ ከቤቱ ሲወጣ እዚያው ይጨምሩታል" በማለት የሁኔታውን አጀማመር ያስረዳል። ጥቃቱ ከቀኑ ሰኞ ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም 9 ሰዓት ላይ መጀመሩን የሚገልጹት አቶ ገብረ መስቀል እንደሚሉት ጥቃቱ መጀመሪያ ላይ የተፈጸመው በከተማው በነበሩ የጉልበት ሠራተኞች ላይ ነበር። "ድብደባው ሲፈጸም እነሱን [የጉልበት ሠራተኞቹን] ገድለው ሲጨርሱ ወደ እኛ ለምመምጣት ነበር፤ እነሱን መጀመሪያ መግደል የፈለጉበት ምክንያትም ለእኛ ድጋፍ ለመስጠት እንዳይመጡ ነው" ይላል። የቀን ሠራተኞች በአንድ አካባቢ ተሰባስበው ይኖሩ ስለነበር "ከአንድ ቤት እስከ 20 ሬሳ ተሰብስቧል" ያሉት አቶ ገብረመስቀል እስከ ቅርብ ቀን ድረስ ቆይተው የተገኙ አስከሬኖችን ሲቀብሩ እንደነበር ገልጸዋል። ከዚህ አሰቃቂ ጥቃት በፊት "እንደዚህ የከፋ ባይሆንም አልፎ አልፎ ችግሮች በከተማዋ ይከሰቱ" እንደነበር የሚያስታውሱት አቶ ገብረመስቀል "ይህ ግን ያልጠበቅነው መአት ነበር" ይናገራሉ። አሁን በከተማዋ ያለው ስሜት በጣም ይከብዳል፤ ሰው ተረብሿል። በርካቶች ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ በማየታቸው ያንን መርሳት ከባድ እንደሆነባቸው አቶ ገብረመስቀል ይናገራሉ። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው አለመግባባት ተካሮ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ነበር በማይካድራ ከተማ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ የተሰማው። ጥቃቱን በማስመልከት በማኅበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ የተለያዩ አሰቃቂ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ አምነስቲ ኢንትርናሽናል ባደረገው ማጣራት በማይካድራ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ መፈጸሙን የሚገልጽ ሪፖርት አውጥቶ ነበር። በማስከተልም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት በከተማዋ ውስጥ በተፈጸመ ማንነትን መሠረት ባደረገ ጥቃት ቢያንስ 600 ሰዎች እንደተገደሉና በድርጊቱ ውስጥም 'ሳምሪ' የተባለው መደበኛ ያልሆነ የወጣቶች ቡድንና የአካባቢው ፖሊስና ሚሊሻ እጃቸው እንዳለበት አመልክቷል። የፌደራል መንግሥቱም በማይካድራ ለተፈጸመው ጅምላ ግድያው የህወሓት አመራርን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን፤ የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ግን ውንጀላውን "መሰረተ ቢስ" በማለት ጥቃቱ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጥሪ አቅርበው ነበር። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ሚሸል ባሽሌት ጭፍጨፋውን በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ "የግድያው ድርጊት በምርመራ ከተረጋገጠ እንደጦር ወንጀል የሚቆጠር ነው" ነው ሲሉ ማሳሰባቸው የሚታወስ ነው።
news-55279518
https://www.bbc.com/amharic/news-55279518
ክትባት በማዘጋጀት ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት ዓለም የዘነጋችው ግለሰብ
ዋልደማር ሃፍኪን ሞርዴካይ ከፓሪስ ሕንድ እየተመላለሰ በዓለም ቀዳሚ የተባለውን ክትባት ለኮሌራ መከላከያነት ፈበረከ።
ነገር ግን በድንገተኛ መርዝ ሕይወቱ እንዳይሆን ሆነች። በፈረንጆቹ 1984 ዋልደማር ወደ ሕንዷ ካልካታ አመራ። ለኮሌራ ክትባት ፍለጋ። ወቅቱ የፀደይ ወራት ነበር። ኮሌራ በሕንድ የሚፈላበት። ተመራማሪው ወደ ሕንድ ይዞ ያቀናው ክትባት ኮሌራን ከዚህች ምድር ያጠፋል ብሎ አስቦ ነበር። ነገር ግን ተስፋው ከቀን ቀን እየጨለመ መጣ። በወቅቱ ሕንድ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሥር ነበረች። እንግሊዛውያን ቅኝ ገዢዎች ተመራማሪውን ሊያሰሩት አልቻሉም። ዋልደማር የዱር እንስሳት ተመራማሪ ነበር። ዶክተር አልነበረም። ሩስያዊ አይደሁድ ነው። ብዙ ዘመኑን ያሳለፈው ግን ፓሪስ ነበር። ዋልደማር የሕድን አፈር ሲረግጥ 33 ዓመቱ ነበር። ያመረተው ክትባት በሁለት ዙር የሚሰጥ ነው። ለዋልደማርና የሥራ አጋሮቹ ተሳታፊዎችን ፈልጎ ማግኘት እጅግ ከባድ ነበር። በዚያ ላይ የመጀመሪያውን ዙር ተከትበው ለሁለተኛው ዱካቸው የማይገኝ በርካታ ተሳታፊዎች ነበሩ። መጋቢት 1984 ላይ የካልካታ ጤና ቢሮ እስቲ ብቅ ብለህ እዚህ አካባቢ ኮሌራ አለ ወይስ የለም የሚለውን አጣራ ብሎ ጋበዘው። ይህ ለተመራማሪው ምቹ አጋጣሚ ነበር። በሄደበት ሥፍራ ያሉ በርካታ ሰዎች በየቤታቸው ተኝተዋል። የህመም ምልክታቸውም ተመሳሳይ ነበር። ዋልደማር በሽታው የዘለቀበት ቤት ገብቶ ግማሾቹን ከትቦ ግማሾቹን ሳይከትብ ከወጣ ውጤቱን በግልፅ ማየት ያስችለዋል። ሰውዬው ያደረገው ይህን ነው። ከ200 ታማሚዎች መካከል 116 ሰዎችን ከተበ። ከትንሽ ጊዜ በኋላ በበሽታው 10 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ። ሁሉም ሟቾች ካልተከተቡት መካከል ነበሩ። ይህ ውጤት ለግዛቲቱ አስተዳዳሪዎች ፅኑ ማስተማመኛ ነበሩ። ክትባቱን በርከት አድርገው ማዘዝ ይችሉም ነበር። ነገር ግን ስለ ክትባቱ ሰዎችን ማሳመን ራሱን የቻለ ሥራ ነበር። ዋልደማር ከእንግሊዛውያን ሐኪሞች ይልቅ ከህንዳዊያን ዶክተሮች ጋር ተባብሮ መሥራት አዋጭ መሆኑን ተረድቶታል። ሰዎች እምነት እንዲጥሉበት በማለትም አደባባይ ላይ ቆሞ ክትባቱን ተወግቷል። ዋልደማር ካልካታ ውስጥ ቀደምት የተባለ ክትባት ይሞክር፤ ብዙዎችን ያድን እንጂ ስሙ በሕንድም ሆነ በአውሮፓ እንዲሁም በተቀረው ዓለም እምብዛም አይነሳም። ግሰለቡ ዩክሬን ከሚገኘው የኦዴሳ ዩኒቨርሲቲ በዱር እንስሳት ጥናት የተመረቀው በፈረንጆቹ 1884 ነበር። ፕሮፌሰር ለመሆን ቢያመለክትም አይሁድ በመሆኑ ምክንያት ተከልክሏል። የሩስያ ጦር የአንድ አይሁድ ቤተሰብን ቤት ሲያወድሙ ተመልክቶ ሊያስቆም በመሞከሩ ምክንያት ድብደባና እሥር ደርሶበታል። ይሄኔ ነው የትውልድ አገሩን ትቶ ወደ ጄኔቫ ከዚያም ወደ ፓሪስ ያቀናው። እዚያም በዓለም ታዋቂ በሆነ አንድ የባክቴሪያ አጥኚ ተቋም ውስጥ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ መሥራት ጀመረ። በወቅቱ ኮሌራ በነፋስ አማካይነት የሚተላለፍ ተደርጎ ነበር የሚቆጠረው። በኮሌራ ምርምር ላይ ጥናቱን አጠናክሮ የቀጠለው ዋልደማር ሙከራውን በጊኒ ፒግ ጀምሮ። ከዚያም ወደ ጥንቸል። ቀጥሎ ወደ ሰው ማምራት ጀመረ። ሐምሌ 1892 ላይ ዋልደማር ራሱን አውቆ በኮሌራ በከለ። ለቀናት በትኩሳት ተሰቃየ። ነገር ግን ዳነ። ቀጥሎ በርካታ ፈቃደኛ ተሳታፊዎች ላይ መሞከር ጀመረ። አንዱም ተሳታፊ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰበትም። ይሄኔ ተመራማሪው ለሰፊው ሕዝብ የሚሆን ክትባት እንደሰራ አመነ። ነገር ግን በርካታ ፈቃደኛ ሰዎች ያሉበት አገር ማግኘት ነበረበት። ይሄኔ በወቅቱ በፓሪስ የእንግሊዝ የነበሩት ግለሰብ ወደ ቤንጋል እንዲሄድ መከሩት። ሰውዬው ካልካታ ሄዶ ምርምሩ በተሳካላት ጊዜ አሳም ውስጥ ያሉ ሻይ ቅጠል አምራቾች መጥቶ ሠራተኞቻቸውን እንዲመረምርላቸው ጋዘቡት። በደስታ እየፈነደቀ ወደ ሥፍራው ያመራው ዋልደማር በርካታ ሺህ ሰዎችን ከተበ። ነገር ግን በወቅቱ የወባ በሽታ ስለያዘው ወደ እንግሊዝ ተመልሶ እንዲያገገም ተገደደ። የዋልደማር ማሕደር እንደሚያሳየው በወቅቱ ቢያንስ 42 ሺህ ሰዎችን ከትቦ ነበር። ዋልደማር ስለ ክትባቱ ያስተዋለው ነገር ቢኖር መድኃኒቱ በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ቢቀንስም በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ከሞት መታደግ አልቻለም። 1984 ላይ በቻይናዋ ዩናን ግዛት አንድ ወረርሽኝ ተነሳ። ከዚያም ወደ ሆንግ ኮንግ ተዛመተ። እያለም በብሪቲሽ ግዛት ወደ ነበረችው ቦምቤይ ደረሰ። በወቅቱ የብሪቲሽ አገዛዝ ወረርሽኙ እምብዛም አደገኛ አይደለም ሲል አጣጣለው። ነገር ግን በሽታው ጥቅጥቅ ያለችውን ሞምቤይ እየሰረሰረ መዝለቅ ጀመረ። ይህ ወረርሽኝ ገዳይነቱ ከኮሌራ ሁለት እጥፍ ነው። ይሄኔ ዋልደማር ተፈለገ። ዋልደማርም ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ቦምቤይ አመራ። ከሶስት ያልሰለጠኑ ረዳቶቹና ከአንድ ፀሐፊው ጋር በመሆን አንዲት ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ይኖር ጀመር። ለወረርሽኙ መድኃኒት ፍለጋ ይዳክርም ገባ። ክትባት መሥራት ብርቁ ያልሆነው ዋልደማር ለኮሌራ የተጠቀመውን መላ ተከትሎ ለአዲሱ በሽታ መድኃኒት ይፈልግ ጀመር። በፈረንጆቹ ጥር 10/1897 ዋልደማር ከአዲሱ ወረርሽኝ 10 ሲሲ ቀንሶ ራሱን ወጋ። ለወትሮው የሚጠቀመው 3 ሲሲ ነበር። ለጊዜው በከባድ ትኩሳት የተሰቃየው ዋልደማር ከቀናት ሕመም በኋላ አገግሞ ተነሳ። ከዚያም ወደ ሕዝባዊ ሙከራው ተሸጋገረ። ወረርሽኙ አንድ እሥር ቤት መግባቱን ተከትሎ ወደዚያ አቅንቶ ክትባቱን እንዲሞክር ተፈቀደለት። በእሥር ቤት ካሉ ታራሚዎች 147 ሰዎች ክትባት ተሰጣቸው። 172 ደግሞ ያለ ክትባት ክትትል እንዲደረግላቸው ሆነ። ክትባቱ ከተሰጣቸው መካከል ሁለት ሰዎች በሽታው ተገኘባቸው። ካልተሰጣቸው መካከል ደግሞ 12 ሰዎች ተይዘው፤ 6 ሰዎች ሞቱ። ይሄን ስኬት የተመለከተው ዋልደማር ክትባት በብዛት እንዲመረት እና ሰዎች እንዲወጉ ከአንዲት ክፍል ቤተ ሙከራው ሆኖ አዘዘ። በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ክትባቱን ወሰዱ። በዚህም በርካታ ሰዎች ከወረርሽኙ ዳኑ። ታህሳስ 1901 በእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያ የጀግና ኒሻን ሽልማት ተሰጠው። ከዚያም ቦምቤይ ውስጥ 53 ሰዎች ያሉት አንድ ቤተ ሙከራን እንዲያስተዳድር ተሾመ። ነገር ግን ድንገት አደጋ መጣ። መጋቢት 10 ፑንጃብ ውስጥ ባለች አንዲት ግዛት 19 ሰዎች በቲታነስ ምክንያት ሞቱ። ለቲታነሱ ምክንያት ደግሞ የዋልደማር ክትባት ነበር። ጉዳዩ ሲጣራ 53 ኤን የሚል ስያሜ የተሰጠው ጠርሙስ መዘዘኛ ሆኖ ተገኘ። ብልቃጡ ጊዜው ያለፈበት ክትባት ይዞ ነበር። ምርመራው ተጠናክሮ ሲቀጥል ዋልደማር ክትባት የሚሰጥበትን ሂደት መቀየሩ ታወቀ። ተመራማሪው በፊት ክትባት መስጫውን በካርቦሊክ አሲድ ነበር የሚያጥበው። ነገር ግን ፍጥነት ለመጨመር ሲል በግለት ማፅዳት መጀመሩ ለችግሩ መንስዔ መሆኑ ተደረሰበት። በዚህ ምክንያት ተመራማሪው ከቤተ ሙከራ ኃላፊነቱ ተባረረ። ዋልደማርም ሕንድን ጥሎ ወደ እንግሊዝ ተመለሰ። ክትባት በማግኘቱ ምክንያት የጀግና ሽልማት የተሸለመው ዋልደማር የውርደት ማቅ ይከናነብ ገባ። በዋልደማር ሥራዎች ላይ የተመረኮዘ መጽሐፍ ያሳተሙት ዶክተር ባርባራ ሃውጉድ ተመራማሪው በማንነቱ መግለል ይደርስበት ነበር ይላሉ። ሌሎችም ተመራማሪዎች በዚህ ይስማማሉ። ምናልባት እንግሊዛዊ ቢሆን ኖሮ ይሄ አይደርስበትም ነበር ይላሉ። ዋልደማር ከሥራው ከታገደ ከሁለት ዓመታት በኋላ በ1904 ወረርሽኙ ጣራ ላይ ደርሶ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ፈጅቷል። መድኃኒቱ የዋልደማር ክትባት ቢሆንም እሱ ግን እንግሊዝ ውስጥ ቁጭ ብሏል። የሰውዬው ሥራ ካጠኑ መካከል አንዱ የሆኑ ግለሰብ ምናልባትም ዋልደማር ሆን ተብሎ ይሆናል ከሥራው የታገደው ይላሉ። እንደ መከራከሪያ የሚያነሱት ነጥብ ደግሞ በወቅቱ ስለ ቴታነስ በቂ ግንዛቤ አለመኖሩና ጠርሙሱ ሲከፈት ምንም ዓይነት የተለየ ጠረን ያለው አለመሆኑ ነው። ወጣም ወረደ ዋልደማር ብዙ ኢ-ፍትሐዊ መገለሎች ደርሰውበታል የሚሉ በርካቶች ናቸው። ዋልደማር በወርሃ ኅዳር 1907 ከቁም እሥሩ ተለቆ ጉዳዩ በፓርላማ ታይቶለት ወደ ሕንድ ተመልሶ ሥራውን እንዲቀጥል ተፈቀደለት። ነገር ግን ምንም ዓይነት የክትባት ሙከራ እንዳያደርግ ታገደ። ይሄኔ ፊቱን ወደ ኮሌራ በማዞር የተሻሻለ ክትባት ለማምረት መሥራት ጀመረ። ነገር ግን ሙከራ ለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ በሕንድ መንግሥት ውድቅ ተደረገበት። በ1914፤ ዋልደማር በ55 ዓመቱ ሕንድን ጥሎ ወጣ። ከ1897 እስከ 1925 ባለው ጊዜ 26 ሚሊዮን የዋልደማር ፀረ ወረርሽኝ ክትባቶች ከሞምቤይ ወደሌላ ዓለም ተልከዋል። ሙከራዎች እንደሚያሳዩት ክትባቱ ከ50-85 በመቶ ውጤታማነት ነበረው። ነገር ግን ምን ያህል ሰው እንደታደገ የሚሳይ መረጃ የለም። ዋልደማር ወደ ፈረንሳይ ተመልሶ ሕይወቱን ወደ ቤተ እምነት አዞረ። በምዕራብ አውሮፓ የአይሁድ ትምህርትን ለማስፋፋት ብዙ ደከመ። ዋልደማር አላገባም። ስለመውለዱም ምንም ዓይነት መረጃ የለም። ዋልደማር ሃፍኪን ሞርዴካይ በ70 ዓመቱ በስዊተዘርላንዷ ሎውዛን ከተማ ይህቺን ዓለም በሞት ተሰናበተ። ሕንድ እያለ ጥናቱን ሲያካሂድባት የነበረችው ቤተ ሙከራ አሁንም ጥቅም ላይ ትውላለች። ከመቶ ዓመታት በኋላም ዘንድሮ ዓለምን ያሸበረውን ኮሮናቫይረስን በመዋጋት ላይ ትገኛለች። ዋልደማር ሃፍኪን ከመሞቱ አምስት ዓመታት በፊት በ1925 የሕንድ መንግሥት ቤተ ሙራዋን 'የሃፍኪን ተቋም' ሲል በስሙ ሰየመለት። በጊዜው ዜናው የደረሰው ዋልደማር ቂም አልቋጠረም ነበር። "ቤተ-ሙከራዋን በስሜ ስለሰየማችሁልኝ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው" የሚል ደብዳቤ ፅፎ ላከው።
news-50703906
https://www.bbc.com/amharic/news-50703906
የጌዲዮ ዞን የክልል እንሁን ጥያቄ ምን ደረሰ?
የሲዳማ ክልልነት በሕዝበ ውሳኔነት መፅደቁን ተከትሎ፤ በደቡብ ክልል የተለያዩ የክልል እንሁን ጥያቄዎች ተጠናክረው እየቀረቡ ነው። እነዚህ የክልልነት ጥያቄዎች አዲስ ሳይሆኑ ከዚህ ቀደም የተነሱና ምላሽ ሳያገኙ በመንከባለል ላይ ናቸው።
ከሁሉም ጥያቄዎች የሚለየው የጌዲዮ ዞን ጥያቄ ነው የሚሉት የአካባቢው ምሁራንና ተወላጆች በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሳ ዞኑ በደቡብ ክልል ውስጥ መቀጠል አይችልም ሲሉ ያብራራሉ። የጌዲዮ ዞን በይፋ የክልል እንሁን ጥያቄውን ለዞኑ ምክር ቤት ያቀረበው ሕዳር 11፣ 2011 ዓ.ም መሆኑን የምክር ቤቱ አባላት ለቢቢሲ ገልጸዋል። የዞኑ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ የጥያቄውን ተገቢነት በማመን ቡድን አዋቅሮ ጉዳዩን አሳልፎ ሰጥቷል። • ሲዳማ: 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል • የደቡብ ክልል፡ ውስብስቡ የዐብይ ፈተና ይህንን ቡድን የዞኑ ምክር ቤት ሕግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ እንዲያስተባብረው ተደርጎ፣ የብሔረሰቡ ተወላጅ ምሁራን ተካተውበት የጥያቄውን ተገቢነት መርምሮ እንዲያቀርብ ሥራ ተሰጥቶት ነበር። የጌዲዮ ዞን ምክር ቤት የሕግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወደሆኑት ግለሰብ፣ ይህ ጉዳይ ምን ደረሰ ብለን ብንደውልም በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፍላጎት እንደሌላቸው በመናገራቸው አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም። በደቡብ ክልል ምክር ቤት የብሔረሰቦች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና በጌዲዮ ዞን ደግሞ የባህልና ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ ውስጥ የባህል ታሪክና ቅርስ ጥናትና ልማት አስተባባሪ የሆኑትን አቶ ፀጋዬ ታደሰን ይህ የዞኑ ምክር ቤት ወደ ሕግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ የመራው ጥያቄ ምን ደረሰ ብለን ጠይቀናቸዋል። ከሕዳሩ ውሳኔ በኋላ ሚያዚያ ላይ በድጋሚ የዞኑ ምክር ቤት መሰብሰቡን አስታውሰው ሚያዚያ 16፣ 2011 ዓ.ም በተጠራው ጉባዔ የተሰጠው ሥራ ምን ደረሰ በማለት ጉዳዩን መልሶ መገምገሙን ይናገራሉ። ነገር ግን በነበረው የአስፈጻሚው አካል ምክንያት ጉዳዩን ወደ ፊት መግፋት እንዳልተቻለ ቋሚ ኮሚቴው በወቅቱ ሪፖርቱን ማቅረቡን ያስታውሳሉ። በዚህ ስብሰባ ላይ የተወሰነውን ሲናገሩም፣ ሥራ አስፈጻሚው በድጋሚ ይህንን ውክልና ወስዶ እስከ ግንቦት 15፣ 2011 ዓ.ም ድረስ የሚሰራው ሥራ ሰርቶ፣ በአስቸኳይ ለክልል ምክር ቤት ጥያቄው እንዲቀርብ ወስኖ ማስተላለፉን ይናገራሉ። የዞኑ ምክር ቤት በክልል እንዲደራጅ፣ የራሱን አስተዳደር መመስረት እንዳለበት ውሳኔውን አሳልፏል የሚሉት አቶ ጸጋዬ ይህ ጥያቄ ግን እስካሁን ድረስ ለክልሉ አለመቅረቡን አረጋግጠዋል። አቶ ጸጋዬ "ከደህዴን የሥራ አስፈጻሚ አካላት ባለው ግፊት የተነሳ የዞኑ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ይህንን ተልዕኮውን መወጣት አልቻለም" ሲሉ ያስረዳሉ። • የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ሊወያዩ ነው ከጥቅምት 25-28 2012 ዓ.ም ምክር ቤቱ በነበረው ስብሰባ ላይም ይኸው ጉዳይ መነሳቱን የሚያስታውሱት አቶ ጸጋዬ አስፈጻሚው አካል የተሰጠውን ውክልና እየተወጣ ባለመሆኑ እንዲወጣ የሚል ውሳኔ በድጋሜ ተላልፏል ይላሉ። የክልልነት ጥያቄ ለምን አሁን ቀረበ? የጌዲዮ ሕዝብ በተደጋጋሚ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን ለቢቢሲ የገለጹት በዲላ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ታደሰ ኪጤ "ጥያቄው ግን ሲታፈን" መኖሩን ያስረዳሉ። አቶ ጸጋዬ በበኩላቸው ይህ የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለዞኑ ምክር ቤት በይፋ መቅረብ የጀመረው በ2010 ዓ.ም ከዞኑ ውጪ በሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች ላይ የደረሰው መፈናቀልና ሞት በክልሉ መንግሥት ተገቢውን ትኩረት ባመቻሉ መሆኑን ያስቀምጣሉ። በወቅቱ በምክር ቤቱ አባላት ላይ "ስንበደል ቀጥታ የፌደራል መንግሥቱ አባል ብንሆን ኖሮ ጥያቄያችንን ያለ ስማ በለው በቀጥታ ማቅረብ እንችላለን" የሚል ስሜት እንደነበርም ያስታውሳሉ። አቶ ጸጋዬ ለክልልነት ጥያቄው ገፊ ምክንያቶች ናቸው ብለው ካስቀመጧቸው ነጥቦች መካከልም በ2009 ዓ.ም በዞኑ ተፈጥሮ በነበረው ቀውስ ንጹኃን ከጥፋተኞች ሳይለዩ በጅምላ መታሰራቸውን ነው። • ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . . • ወገኖቹን ለመርዳት ጠመኔ የጨበጠው ኢትዮጵያዊው ሐኪም አቶ ጸጋዬ በ2009 በዞኑ ከተሞች የተፈጠረውን ሲያስታውሱ "ጥፋተኞች መጠየቅ ቢኖርባቸውም" ይላሉ፣ "በሥፍራው የነበሩም ያልነበሩም፣ በድርጊቱ የተሳተፉም ያልተሳተፉም፣ ከሀገር ውጪ የነበሩ ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ፣ የዞኑ ተወላጅ ነጋዴዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች በጅምላ ታስረዋል" በማለት ላይ በዚህ የጅምላ እስር ከ3000 ያላነሱ ሰዎች እስር ቤት ቢገቡም ማስረጃ በመጥፋቱ መለቀቃቸውን ይገልጻሉ። በ2009 ዓ.ም መስከረም ወር መጨረሻ በጌዲዮ ዞን ይርጋጨፌ፣ ኮቸሬ፣ ዲላ፣ ወናጎ፣ ፍስሃ ገነትና ጨለለቅቱ አካባቢዎች ግጭቶች ተከስተው የተለያዩ ሰብዓዊ ጥሰቶች መፈፀማቸውን በወቅቱ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ በመግለጫው ላይ አስታውቆ ነበር። በዚያን ጊዜ የተፈጠረው የዞኑን ማህበረሰብ በአንድነት ያስደነገጠ መሆኑን በመጥቀስ፣ በመንግሥት የጸጥታና ደህንነት መዋቅር አካላት የተፈጸሙ ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ግን የዞኑ ብሔረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ፍላጎት ያለማንም ጣልቃ ገብነት የሚለው ሀሳባቸውን እንዲገፉበት እንዳደረጋቸው ይገልጻሉ። በዚህ መካከል በ2010 ዓ.ም ኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት መፈናቀልና ያገኘው ትኩረት ማነስ ለጥያቄው ወደ ፊት መምጣት ሌላ ሰበብ መሆኑን ያብራራሉ። አቶ ጸጋዬ አክለውም "መፈናቀሉ ብቻ ሳይሆን የሕግ የበላይነት ሳይረጋገጥ፣ የተፈናቀሉት ለተራዘመ መከራ መጋለጣቸው ሌላው ምክንያት ነው" ብለዋል። የጌዲዮ ሕዝብ የማንነት ጥያቄዎች ታሪክ የጌዲዮ ሕዝብ ይላሉ ፕሮፌሰር ታደሰ፣ ባሌ የሚባል የራሱ የሆነ ጠንካራ የአስተዳደር ስርዓት ያለው ነው። አቶ ጸጋዬ በበኩላቸው የራሱ የሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ያለው ሕዝብም ነው ሲሉ ያክላሉ። ነገር ግን ይላሉ ሁለቱም፣ ሕዝቡ ከለመደው የአስተዳደር ሥርዓት ውጪ የሆነ ነገር ሲመጣበት ከምንሊክ መስፋፋት ጀምሮ እምቢተኝነቱን ገልጿል። የጌዲዮ ሕዝብ ባህላዊ የሆነ የመሬት ሥሪት፣ ደረባ የሚባል ፣ ያለው ሕዝብ ነው የሚሉት ግለሰቦቹ፣ በ1880ዎቹ መጨረሻ የምንሊክ ጦር ወደ ስፍራው መስፋፋት የጌዲዮን የመሬት ባለቤትነት ሙሉ በሙሉ ነጥቋል ይላሉ። የጌዲዮ ሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ የሚያነሱ አካላት በጋራ የሚጠቅሱት ሌላ ታሪካዊ ክስተት በ1952 ዓ.ም የተካሄደውን የገበሬዎች አመጽ ነው። • ሲፈን ሐሰን፡ ''ለኢትዮጵያ የመሮጥ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም'' ይህ የገበሬዎች አመጽ የተካሄደው 'ምችሌ' ላይ መሆኑን የሚጠቅሱት እነዚህ ግለሰቦች የምችሌ የአርሶ አደሮች አመጽ በጌዲዮ ሕዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ውስጥ ጉልህ ስፍራ እንዳለው ያብራራሉ። ፕሮፌሰር ታደሰ በበኩላቸው ከዚህ ጦርነት በኋላ የኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ከጌዲዮ አካባቢ ሕዝቦችን በማንሳት ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢ ማስፈሩን ይገልጻሉ። በደርግ ጊዜ ቢሆንም ይላሉ ፕሮፌሰር፣ ከ1971 ዓ.ም እስከ 1973 ዓ.ም ድረስ የነበረው አመጽ ዋና ምክንያት የራሱን ምርት ገበያ በሚወስንለት ዋጋ መሸጥ እንዲችል የጠየቀ፣ በራሴ ጉዳይ ራሴ ልወስን የሚል እንደነበረ ያብራራሉ። ይህ አመጽ ከይርጋ ጨፌ ራቅ ብላ በምትገኘው 'ራጎ ቅሻ' ላይ መካሄዱንም ያስታውሳሉ። ይህ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በኢህአዴግ አስተዳደር ወቅት ቀጥሎ የፍትሀዊነት ተጠቃሚነት ጥያቄ፣ የእኩልነት የዲሞክራሲ ጥያቄ እስከዛሬ ድረስ መቀጠሉን ፕሮፌሰር ታደሰም ሆኑ አቶ ጸጋዬ ይናገራሉ። ፕሮፌሰር ታደሰ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን በመጣባቸው የመጀመሪያ ዓመታት፣ የጌዲዮ ሕዝብ ከሲዳማ እና ከምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢ ሕዝቦች ጋር በአንድነት ይኖር ነበር በማለት፣ በአካባቢው በተለይ በኦሮሚያ ጉጂ ዞንና በጌዲዮ መካከል በ1988 በተደረገው ሕዝበ ውሳኔ የተወሰኑ አካባቢዎች ወደ ኦሮሚያ እንዲጠቃለል መደረጉን ይገልጻሉ። ፕሮፌሰር በወቅቱ የተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ሕጋዊውን መንገድ መከተሉ ላይ ጥያቄ እንዳላቸው በመግለጽም፣ በአባያ አካባቢ የሚኖሩ የጌዲቾ ማህበረሰብ፣ በወቅቱ ከጌዲዮ ጋር አንድ ወረዳ የነበሩ ቢሆንም ወደ ኦሮሚያ መካለላቸውን ያስታውሳሉ። ኢህአዴግ ሥልጣን እንደያዘ በመሰረተው ክልል 8 ውስጥ የኮሬ ማህበረሰብም ሆነ ቡርጂ ከጌዲዮ ጋር ነበሩ የሚሉት ፕሮፌሰር እነዚህም ግን ወደ ኦሮሚያ መካለላቸውን ያነሳሉ። እነዚህ ጎረቤቶች በአሁን ሰአት ከጌዲዮ መራቃቸውን በመናገር እንደ ጌዲቾ ያሉ በባህልም በቋንቋ የሚዛመዱት ሕዝቦች ጋር የጌዲዮ ሕዝብ ተራርቋል ይላሉ። ጌዲዮ በዞን ሲካለል ጌዲቼ፣ ኮሬ እንዲሁም በቡርጂ በኢህአዴግ አስተዳደር የመጀመሪያ አመታትም ሆነ ከዚያ በፊት ከእኛ ጋር ነበሩ የሚሉት ፕሮፌሰር ታደሰ በአሁኑ ወቅት የጌዲዮ ዞን ከሲዳማና ከኦሮሚያ ጋር እንደሚዋሰን ያስረዳሉ። • ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ከሦስት ክልሎች ውጪ በወረርሽኝ ደረጃ ነው ያለው በአሁኑ ወቅት በምስራቅና በምዕራብ ጉጂ የሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች ተበታትነው የሚኖሩ ጌዲዮዎች እንዳሉ ገልፀዋል። ክልል የመሆን ጥያቄው ተቀባይነት ባያገኝስ? የጌዲዮ ሕዝብ ፍላጎት ክልል የመሆን ነው የሚሉት ፕሮፌሰር ታደሰም ሆኑ አቶ ጸጋዬ፣ ከኦሮሚያም ጋር ሆነ ከሲዳማ ክልል ጋር የመቀላቀል ፍላጎት እስካሁን ድረስ ከሕዝቡ አለመነሳቱን ይገልጻሉ። ፕሮፌሰር ታደሰ በበኩላቸው፣ የጌዲዮ ሕዝብ ከሲዳማም ሆነ ከኦሮሚያ ሕዝቦች ጋር የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው የሚጋሩት ነገር ቢኖርም የጌዲዮ ሕዝብ የራሱ ባህል፣ ቋንቋ እንዲሁም ማንነት እንዳለው አጽንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። ለዚህም በማስረጃነት የሚያነሱት በአጼ ምንሊክ ወደ ጌዲዮ አካባቢ ሲመጡ እንኳ ከኦሮሚያም ሆነ ከሲዳማም ሕዝብ ጋር አልነበርንም፤ ህዝቡ ራሱን ችሎ ይኖር እንደነበር በወቅቱ የነበሩ መረጃዎችን በማጣቀስ ያስረዳሉ። ፕሮፌሰር አክለውም ከአንድ ትንሽ ቦታ ከፍተኛ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ የሚያቀርበው ጌዲዮ ብቻ ነው በማለት፣ ዞኑ ለፌደራል መንግሥቱም ሆነ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ እንዳለ ያብራራሉ። ኦሮሚያም ሆነ ሲዳማ ቡና ቢያቀርቡም ክልሎቹ ሰፊ ናቸው የሚሉት ፕሮፌሰር፣ ከትንሽ ስፍራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተው የጌዲዮ ዞን ይክልልነት ጥያቄው መታፈኑን ያስረዳሉ። "የራሳችን ኢኮኖሚ አቅም አለን ፤ የራሳችን ሕዝብ ባህል ቋንቋ ታሪክ አለን ሲሉ" ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። • ኢትዮጵያ የካንሰር መከላከያ ክትባት ከሚሰጡ ጥቂት አገራት አንዷ ናት ከማዕከላዊ መንግሥቱ ጋር የጌዲዮ ሕዝብ ቀጥተኛ ግንኙነት እንዲኖረው የሚያደርገው ጥያቄና ትግል "ካድሬዎችና አንዳንድ አካላት ለማፈን የሚሞክሩ ቢኖሩም ሲዳማ ክልልነቱን በሕዝበ ውሳኔ ሲያረጋግጥ ያለ ምንም ውጣ ውረድ ክልል መሆን ነበረብን" ይላሉ። በደቡብ ክልል በአሁኑ ሰዓት ከ50 በላይ ብሔሮች ቢኖሩም አሁን ሲዳማ ክልል ሲሆን በመልከ አምድሩ አቀማመጥ የተነሳ ከቀሪዎቹ የክልሉ ሕዝቦች ጋር መገናኘት እንደማይችሉ በማስቀመጥም፣ ከደቡብ ጋር አንድ ክልል ብሎ ጌዲዮን መጥራት ፈታኝ መሆኑን ያስቀምጣሉ። አቶ ጸጋዬ በበኩላቸው የጌዲዮ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄን ተገቢነት ሲያብራሩ ሕገመንግሥቱን በመጥቀስ ነው። ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 2 በአንድ ክልል ውስጥ ያሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ የራሳቸውን ክልል መመስረት ይችላሉ የሚለውን አንቀፅ በመጥቀስ "ሕገመንግሥቱን ካየን ሰጪና ከልካይ ያለበት አይደለም" ሲሉ ይጠቅሳሉ። ፕሮፌሰር ታደሰ በበኩላቸው የሕዝቡን ጥያቄም ለመንግሥትም ሆነ ለሁሉም አካላት የማቅረብ ሥራው እንደሚቀጥል ተናግረው፣ "ጥያቄያችን በኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች መለስ ዜናዊና ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲሁም አሁን ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ብናቀርብም ታፍኖ ቆይቷል፤ መልስ እስክናገኝ እንቀጥልበታለን" ብለዋል።
news-53533031
https://www.bbc.com/amharic/news-53533031
ኮሮናቫይረስ፡ "በኮሮናቫይረስ አጎቴን አጥቻለሁ፤ አሁን ደግሞ እኔ ተይዣለሁ" ሃና ገብረሥላሴ፡
ሃና ጆይ ገብረሥላሴ የተወለደችው በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ደቡባዊ ግዛት ነው። ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አትላንታ ያቀናችው የአራት ዓመት ልጅ ሳለች ነበር።
ሃና ጋዜጠኛ ናት። የቴሌቪዥን ሪፖርተር ሆና ሠርታለች። ነገር ግን ከአንድ ዓመት ከግማሽ በፊት የራሷን መንገድ መከተል መረጠች። ከቴሌቪዥን ሪፖርተርነት ራሷን ካገለለች ወዲህ በኅብረተሰብ አገልግሎት ሥራ ላይ ተሰማርታ ትገኛለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የሚደርሰውን ጭቆና በመቃወም የመብት ተሟጋችነት መድረክን ተቀላቅላለች። ከዚያም አልፎ ለእናትና ለአባቷ አገራት ኢትዮጵያና ኤርትራ የተለያዩ የእርዳታ ሥራዎችን እንደምትሰራ ትናገራለች። በአሁኑ ወቅት በዩትዩብና ፌስቡክ ገፆቿ ሥራዎቿን ታስተዋውቃለች። ሃና ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኮሮናቫይረስ የቅርብ ዘመዷን እንዳጣች በትዊተር ገጿ ላይ አስፍራ ነበር። ከዚህም አልፎ እሷም ተመርምራ ኮቪድ-19 እንዳለባት ማወቋን በይፋ በመናገር ሌሎች በእሷ ዕድሜ ያሉ ወጣቶች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በተደጋጋሚ መክራለች። ለመሆኑ ሃና ኮሮናቫይረስ እንዴት ሊያገኛት ቻለ? የበሽታውምልክት የበሽታው ምልክት የጀመረኝ ሰኔ 23 [ጁን 30] ገደማ ነው። ከዚያ በፊት ባሉት ሳምንታት የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ስሳተፍ ነበር። ነገር ግን በዚህ ወቅት ምንም ዓይነት የቫይረሱ ምልክት አልታየብኝም። ሁሌም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እጠቀም ነበር። ሳኒታይዘርም ይዤ ነበር የምንቀሳቀሰው። ምልክቱ መጀመሪያ ሲጀምረኝ መካከለኛ የሚባል ነበር። ከዚያ ግን ወዲያው በጣም እየከፋ መጣ። የመጀመሪያው ምልክት ራስ ምታት ነበር። በጣም ከባድ ራስ ምታት። ከዚያ ያቅለሸልሸኝ ጀመር። ጥርሴን ለመፋቅ ብሩሽ ስጠቀም ይሁን አሊያም ምግብ ልመገብ ስል ወደላይ ይለኛል ግን አያስመልሰኝም። ይህ ሁሉ ስሜት የተሰማኝ በአንድ ሌሊት ነው። ከዚያ በኋላ ባሉት ቀናት የተለያዩ ስሜቶችን አስተናግጃለሁ። ሌላኛው ስሜት ደግሞ መፍዘዝ ነበር፤ በጣም ይደክመኝም ነበር። የምግብ ፍላጎቴም እጅጉን ቀንሶ ነበር። አስታውሳለሁ ቁጭ ብዬ ምግብ እየላሁ ከትንሽ ጉርሻ በኋላ የምግቡ ጣዕም እየጠፋብኝ መጣ። ከእነዚህ ሁሉ ምልክቶች ግን የከፋ የነበረው ድንገት ሌሊት ላይ የጀመረኝ ምልክት ነው። ይህም የትንፋሽ ማጠር ነው። በጣም ያስደነገጠኝ እሱ ነበር። ይህን ጊዜ ነው ወደ ሕክምና ተቋም ሄጄ የተመረመርኩት። ከዚያ በፊት ግን የተለያዩ ተቃውሞዎች ላይ ተሳትፌ ስለነበር ምልክቱ ባይኖረኝም ጥቂት ጊዜያት ተመርምሬ ነበር። በዚህኛው ዙር ግን ከተመርመርኩ በኋላ ራሴን አግልዬ ተቀመጥኩ። ይህንን ያደረግኩት ከሰኔ 24 ጀምሮ ነው። ውጤትጥበቃ ከተመረመርኩ በኋላ ያለው ጊዜ በጣም አስጨናቂ ነበር። በተለይ ውጤቱ መጠበቅ እጅግ ግራ አጋቢ ስሜት ነበረው። ምንም እንኳ በሽታው እንደሚኖርብኝ ብጠረጥርም፤ ቢኖርብኝስ የሚል ጥያቄ ሃሳብ ደጋግሞ ይመጣብኛል። ከየት ይሆን ያገኘሁት? ለሰው አስተላልፌውስ ቢሆን? አለብሽ ከተባልኩ ምን እሆናለሁ? ብቻ የተለያዩ ሃሳቦች ወደ አእምሮዬ ይመጡ ነበር። የበሽታው ምልክት ሳይታይብኝ የተመረመርኩ ጊዜ ውጤት የመጣልኝ ወዲያው ነበር። ነገር ግን በሁለተኛው ዙር ይመስለኛል ከአምስት ቀናት በኋላ ነው ውጤቴን የሰማሁት። በጆርጂያ ግዛት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ውጤት ይፋ የሚሆንበት ቀንም እየጨመረ መጥቶ ነበር። በስተመጨረሻ የተመረመርኩ ጊዜ ውጤቴን በፅሑፍ መልዕክት የነገሩኝ ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ነው። ደውለው ውጤትሽ 'ፖዘቲቭ' ነው እና ራስሽይን አግልይ አሉኝ። እንግዲህ ይሄ የሆነው እኔ ራሴን አግልዬ ከቆየሁ በኋላ ነው። ቫይረሱ ሊይዘኝ ይችላል ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ብባል፤ መልሴ "አዎ" ነው። ምክንያቱም በየትኛውም ጊዜ ከቤቴ ከወጣሁ ሊይዘኝ እንደሚችል አስባለሁ። እንዲያውም ወረርሽኙ የገባ ሰሞን ለሦስት ሳምንታት ያክል ከቤቴ ንቅንቅ አላልኩም። በዚያ ላይ ደግሞ ኤፕሪል [ሚያዚያ] ላይ ቺካጎ የሚኖር አጎታችን በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ። ይሄ ቫይረሱ የምር እንደሆነ፤ ወዳጅ ዘመድ እንደሚነጥቅ አሳውቆኝ ስለነበር ሁሌም እጠነቀቃለሁ። እኔን ቢይዘኝ ለቤተሰቦቼ አስተላልፋለሁ የሚለው ነገር ያስጨንቀኝ ስለነበር በጣም እጠነቀቃለሁ። ቢሆንም ውጤቴ 'ፖዘቲቭ' ሆኖ ሲመጣ በጣም ደንግጬ እንደነበር አስታውሳለሁ። 'ኮሮናቫይረስየምርነው' በቅርቡ የሆነ ሰው 'የምር ግን ኮቪድ-19 ነው የያዘሽ?' ሲል ጠየቀኝ። ሌላ ሰው ደግሞ ምንም እንኳ አንድ ዘመድ በበሽታው ቢያጣም ቫይረሱ ገዳይ እንደሆነ ሊያምን አልፈለገም። ይህ የብዙ ሰዎች እይታ ነው። ነገር ግን በሽታው የምር ነው። እኔ የቅርብ ዘመዴን አጥቻለሁ። እኔም በቫይረሱ ተይዣለሁ። ለዚህ ነው የምር ነው የምለው። ወጣቶች በሽታው አይዛቸውም ወይም ምልክቱን አያሳዩም የሚል ፅንሰ-ሐሳብ አለ። ነገር ግን አኔ ወጣቶች እንደሚያዙ ምስክር ነኝ። እርግጥ ነው እኔ በርካታ ተቃውሞዎች ላይ ስሳተፍ ነበር። ምንም እንኳ ጥንቃቄ ለማድረግ ብሞክርም ፍፁም አይደለሁም። በእኔ ዕድሜ ያሉ ሰዎች ላይያዙ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን ምልክቱን ሳያሳዩ ለሌሎች ሊያስተላልፉ ይችላሉ። የእኔ ትልቁ ፍራቻዬ የነበረው ለእናቴ እንዳላስተላልፍ ነበር። ስለዚህ ወጣቶች ተጨማሪ የጤና እክል ላለባቸው ሰዎች ሊያስተላልፉ ስለሚችሉ መጠንቀቅ የግድ ነው። ሌላው ቢቀር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንጠቀም፤ ሰላም ስንባባል ንክኪ አይኑረን። እየተሳሳሙ ሰላምታ መለዋወጥ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ የተለመደ እንደሆነ አውቃለሁ። ነገር ግን ይሄ ሊቆም ይገባል። 'አዲስሕይወት' ወረርሽኙ የሰዎችን የአኗኗር ዘይቤ እጅጉን ቀይሯል። ኮቪድ-19 እንዳለበት ሰው በእኔም ሕይወት ላይ ብዙ ለውጦች አምጥቷል ብዬ አስባለሁ። በጣም ብናፍቃቸው እንኳ ቤተሰቦቼን ማየት አልችልም። አብሬያቸው እንኳን ቢሆንም ያለሁት እኔ በመኖሪያ ቤቱ ሌላ አቅጣጫ ነው ስለሆነ አንተያይም። ወደ መኝታዬ ሳመራ እፈራለሁ። አንዳንዴ ባልነቃስ ብዬ እፈራለሁ። ምክንያቱም አንዳንዴ ጊዜ ትንፋሽ አጥሮኝ ድንገት የምነቃባቸው ሌሊቶች ነበሩ። ሁሌም ወደ መኝታ ከማምራቴ በፊት ጠዋት እንድነቃ እፀልያለሁ። ሌላኛው ፍርሃቴ እናቴ ቢይዛትስ? አባቴ ቢይዘውስ? ወይም ሌላ የቤተሰብ አባል ቢይዘስ? የሚለው ነው። ቤተሰባችን ሐይማኖተኛ ነው። እናቴ ሁሌም ፀበል እንድጠጣ ታደርገኛለች። ምንም እንኳ ቫይረሱ ቢፈትነኝም ብቻዬን አይደለሁም የሚለው እውነታ ይታደገኛል። በዚያ ላይ ሚሊዮኖች ተይዘው ድነዋል። ከቤተሰቦቼ ጋር ቁጭ ብዬ መቼ ነው ምግብ የምቋደሰው? የሚለውን ባላውቅም ሁሉም እንደሚያልፍ አምናለሁ። እስከዚያው ግን ዕድሜ ለቴክኖሎጂ ይሁንና በዚያ በኩል እየተገናኘን ነው። ምግብናእንቅስቃሴ አሁን ላይ በጣም እየተሻለኝ ነው። መካከለኛ የሚባሉት ስሜቶች ከሞላ ጎደል ጠፍተዋል። ማሳልና ሌሎች ምልክቶችን በተለያዩ መድኃኒቶች መቋቋም ችያለሁ። ከበሽታው ከባዱ ነገር የትንፋሽ እጥረት ነው። እሱን ደግሞ የትንፋሽ ስፖርት በመሥራት እያሻሻልኩት ነው። ለምሳሌ ሆዴ [በደረት] እንድተኛ ተመክሬ እሱን በማድረጌ በጣም ለውጥ አይቻለሁ። ከዚያም አልፎ ትንፋሽን እያመቁ መልቀቅም ረድቶኛል። ያልጠጣሁት ዓይነት ጭማቂ [ጁስ] የለም ማለት ይቻላል። በተለይ ደግሞ የብርቱካን ጭማቂ። እንዲሁም በርካታ ቫይታሚኖች ወስጃለሁ። ፈሳሽ ነገር፤ በተለይ ውሃ እንዲሁም ረዘም ያለ እረፍት ማድረግ ይመከራሉ፤ እኔንም እጅጉን አግዘውኛል። የእናቴ ሙያም የሚረሳ አይደለም። ከአገር ቤት የመጡ ቅመማ ቅመሞችን በመደባለቅ ትኩስ ነገር ትሠራልኛለች። እሱም በጣም አግዞኛል። ከዚያ ባሻገር ከቤታችን ጓሮ ወጣ ብዬ እንቅስቃሴ አደርጋለሁ። አሁን ተመርምሬ ውጤቴን እየጠበቅኩ እገኛለሁ። በዚህኛው ዙሪያ እንኳ ምንም ዓይነት ፍርሃት የለብኝም። ውጤቱ 'ኔጌቲቭ' ሆኖ ከመጣ እፎይ ብዬ ድጋሚ እንዳይዘኝ መጠንቀቅ ነው የምፈልገው። ለሁለተኛ ጊዜ የያዛቸው ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ። እንደውም ሁለተኛው ዙር ህመሙ የባሰ ነው ሲሉ ሰምቻለሁ። ለዚህም ነው በቻልኩት መጠን አገር ቤት ላሉ ሰዎች በጣም ተጠንቀቁ ማለት የምፈልገው። ምናልባት አስፈላጊው አቅርቦት ላይኖር ይችላል ግን ባለው ነገር ራስን መከላከል ይበጃል። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት የምናደርገው ጥንቃቄ መፃዒ ዕድላችንን ሊወስን ይችላል። እዚህ አሜሪካ መጀመሪያ አንድ ሰው ነው የተያዘው። ከዚያ በኋላ ይኸው ብዙዎችን አጥተናል። ሁሉም ነገር ቀላል እንዳልሆነ አውቃለሁ ነገር ግን እያንዳንዷ ጥንቃቄ ዋጋ አላት። ውጤት ሃና ጆይ ገብረሥላሴ ከቢቢሲ ጋር ይህንን ቃለ-ምልልስ ካደረገች በኋላ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቷ ኔጌቲቭ መሆኑንና ከበሽታው ማገገሟን ነግራናለች። እንኳን ደስ ያለሽ !
49644838
https://www.bbc.com/amharic/49644838
የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ
ዓውደ ዓመትና ምግብ አይነጣጠሉም። ዶሮው፣ ጥብሱ፣ ዱለቱ፣ ቁርጥ ስጋው፣ ክትፎው፣ ድፎ ዳቦው. . . እነዚህን ሁሉ የዓውደ አመት ደስታ፣ ቄጤማና እጣን፣ የሚትጎለጎል የተቆላ ቡና ሽታ ከዛም ጥዑም ቡና ሲያጅባቸው የበዓል ሞገሱ ይገዝፋል። እኛም ሦስት በምግብ ዝግጅት የሚታወቁ ባለሙያዎችን አነጋግረናል። ሼፎቹ ዩሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ. . .
• አንድ በሞቴ! • የአገልግል ምግብ አምሮዎታል? • 5 ሺህ ጉርሻዎች! ዮሐንስ ኃይለማርያም ምግብ ማብሰልን እንደ ሙያ ከያዘ ዘጠኝ ዓመት አስቆጥሯል። በቅርቡ የምግብ አዘገጃጀት መጽሐፍ አሳትሟል። በቃና ቴሌቭዥን "አዲስ ጓሮ" የተባለ መሰናዶ አዘጋጅም ነው። በኃያት ሬጀንሲ በየወሩ የምግብ አሠራር ትምህርት ይሰጣል። 'ሲድስ ኦፍ አፍሪካ' የተራድኦ ድርጅት ውስጥ ስለልጆች አመጋገብ ያማክራል። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክራለህ? እስኪ ከነአሠራሩ ንገረን። እንፍሌ። አሠራሩ፡-የበግ ወይም የፍየል እግር ሥጋው ከአጥንቱ ሳይለያይ ተፈልቅቆ ይነሳል። ሥጋው ከአጥንቱ ጋር እንደተያያዘ ይዘለዘላል። ልክ እንደ ዶሮ ወጥ በሽንኩርት፣ በበርበሬ፣ በቅመማ ቅመም [ስልስ] ይዘጋጃል፤ ትንሽ ጠጅ ጠብ ይደረግበታል። ከዛ ሥጋው በነዚህ እንፋሎት ይበስላል። እንፍሌ በመላው ኢትዮጵያ ስትዘዋወር ከገጠሙህ የምግብ ግብዓቶች እና የምግብ አሠራር ያስገረመህ የቱ ነው? ጋምቤላ ውስጥ ከአንድ ቅጠል የሚሠራ ጨው ይጠቀማሉ። ቅጠሉ ተቃጥሎ፣ ከውሀ ጋር ይዋሀድና ይጠላል። ከዛ በጸሐይ ደርቆ ጨው ይሆናል። ሶድየም ስለሌለው ለማንኛውም የእድሜ ክልል ተስማሚ ነው። ላሊበላ ውስጥ የአጃ ቂጣ ሲጋገር እንደእንጀራ አይን እንዲያወጣ በምጣዱ ዙሪያ ልጆች ተሰብስበው ያፏጫሉ። በየትኛውም አገር እንዲህ ያለ አሠራር አልገጠመኝም። ጤፍ ስለሚብላላ [በፈርመንቴሽን] እንጀራ ሲጋገር አይን ይሠራል። አጃ ግን ግሉተን ስላለው ውስጡ የሚታመቀውን አየር ለማፈንዳት ይከብዳል። ስለዚህ በፉጨት የድምጽ ንዝረት [ቫይብሬሽን] በመፍጠር አይን እንዲወጣ ይደረጋል። ምግብህ አይጣፍጥም ተብለህ ታውቃለህ? ቆይ አሁን ባይጣፍጥ፤ አይጣፍጥም ብዬ የምነግርሽ ይመስልሻል? (ሳቅ). . . ግን እድለኛ ነኝ ይህ ገጥሞኝ አያውቅም። የምትወደው ምግብ ምንድን ነው? በተለያየ ጊዜ እንደስሜቴ የተለያየ ምግብ ያምረኛል። ሁሌ የሚያስደስተኝ ግን ጥሬ ሥጋ ነው። ምግብ ከመሥራት ሂደት የሚያስደስትህ የቱ ነው? ሁሉንም ሂደት እወደዋለሁ። ከግብዐት መረጣ ጀምሮ እስከ ማብሰል፤ ከዛ አልፎም እንግዶች ምግቡን ቀምሰው አስተያየት እስኪሰጡ ወይም ፊታቸው ላይ የሚነበበውን እስከማየው ድረስ ደስ ይለኛል። ለምትወደው ሰው የምታበስለው ምግብ ምንድን ነው? ሼፍ ስትሆኚ ኃላፊነት አለብሽ። ሁሌም ለምትወጂው ሰው እንደምታበስይ አስበሽ ነው መሥራት ያለብሽ። ግን የሆነ ውድድር ቢኖርብኝ፤ በምን ምግብ አስደምማለሁ? ብዬ ሳስብ ስፔሻሊቲዬ [የተካንኩበት] ስለሆነ 'ሲ ፉድ' [ከባህር ውስጥ እንስሳት የሚዘጋጅ ምግብ] ይመቸኛል። ቆንጆ ምግበ ማብሰል እንደምትችል አምነህ ሼፍ መሆን እችላለሁ ያልክበት ቅጽበት ትዝ ይልሀል? የመጀመሪያ ቀን ምግብ ሰርቼ 'ይጣፍጣል' ብዬ አይደለም ወደሙያው የገባሁት። የመጀመሪያ ዲግሪ የሠራሁት በቪዥዋል አርት [የእይታ ሥነ ጥበብ] ነው። ከዛ ወደ ከልነሪ አርት [ምግብ የማብሰ ጥበብ] ገባሁ። ጥብበ በሸራ፣ በድምፅ፣ በፐርፎርማንስ [ክዋኔ] በብዙ መንገድ ሊገለጽ ይችላል። ብዙ ሰው ጋር ለመድረስ ግን ምግብ የተሻለ ነው። የተማረኩበት ፈረንሳይ የሚገኝ በዓለም እውቅና ያለው ትምህርት ቤት ነው። ጥሩ መሰረት ሰጥቶኛል። እናቴ አንቲካ የሚባል ሬስቶራንት ስላላት ለሙያው ቅርብ ሆኜ ነው ያደግኩት። ምግብህን በልተው ካደነቁህ ሰዎች የማትረሳው ማንን ነው? ለመጽሐፌ ምርቃት ኒውዮርክ ሄጄ ነበር። ሴቮር የሚባል በጣም የታወቀ መጽሔት አለ። እዛ የድርቆሽ ቋንጣ ፍርፍር ሠርቼ ነበር። ምግቡ ቀላል ሆኖ ሰውን ያስደነገጠ ነበር። ከነበረው ምግብ ሁሉ ሰው የወደደው እሱን ነበር። ጆርዳና ከበዶም ምግብ የማብሰል ሙያን ያዳበረችው በሬስቶራንቶች በመሥራት ነበር። ሁለት የምግብ አዘገጃጀት መጻሕፍት ለህትመት አብቅታለች። አሁን በፋና ቴሌቭዥን ላይ የምግብ መሰናዶ መርሀ ግብር እያዘጋጀች ታቀርባለች። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክሪያለሽ? እስኪ ከነአሠራሩ ንገሪን። የአበሻ ዳቦ። አሠራሩ፦ በገብስ ወይም በስንዴም ዱቄት ይቦካል። ከዛ እንዲጣፍጥ ቴምር ወይም ቸኮሌት መጨመር ለሁለት ኪሎ ስንዴ ወይም ገብስ 100 ወይም 150 ግራም ቸኮሌት መሀል መሀል ላይ ጣል ማድረግ። እንዳይቀልጥ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሌላው አማራጭ ቴምር ነው፤ መሀል ላይ ያለው ፍሬ ወጥቶ ጣል ጣል ማድረግ። ከዛ መጋገር። ጆርዳና ከበዶም ሼፎች በቴሌቭዥን የሚያሳዩት ግብዓት ገበያ ላይ በቀላሉ የማይገኝ ወይም ውድ የሆነ ነው ይባላል፤ ምን ትያለሽ? ፍላጎትና አቅርቦት አለ። ፈረንጆች አሁን ያሉት ድሮ በነበሩበት አይደለም። እየተማሩ ሲሄዱ፣ [ግብዓቶች] መፈለግ ሲጀምሩ፤ አቅርቦትም መጣ። እኛም አመጋገባችንን እያሻሻልን ስንሄድ የገበያ አቅርቦት እየተሻሻለ ይሄዳል። የኔን 'ሾው' [መሰናዶ] የሚወቅሱ ሰዎች አሉ። በእኔ እይታ በአቅርቦት ሳይሆን በፍላጎት ይጀምራል። ዛሬ 600 ብር ደሞዝ ያለው ሰው፤ የዛሬ አምስት ዓመት 20 ሺህ ብር ቢያገኝ 'ምን ምግብ ነው የምሠራው?' ብሎ ገንዘቡን ይዞ ቁጭ ይላል። የምትወጂው ምግብ ምንድን ነው? ሁሉንም ነገር እወዳለሁ። በጣም ጥቂት ነገር ነው የማልወደው። ከሁሉም በላይ እንጀራ በጣም አወዳለሁ። በማንኛውም እኔ በምፈላሰፈው 'ዲሽ' [ምግብ] እንጀራ እበላለሁ። በቅርቡ የቅቅል አጥንት ከጎመን ጋር ቀይ ወጥ ሰርቼ ጉድ ነበር። እኔ እንደመጣልኝ ነው የምሠራው። መመራመር ነዋ ደስ የሚልሽ? በጣም! በጣም! ግን ሁሉም ግብዓት አብሮ ይሄዳል? ይጣፍጣል? 'ፋንታሲ' [የምኞት ዓለም] ነው። ጭንቅላትሽ ክፍት መሆን አለበት። ምግብን የሚያጣፍጠው ቅመማ ቅመም ነው። ዝም ብዬ ጎመን ቀቅዬ እበላለሁ የምትይ ከሆነ አይጣፍጥሽም። ግን ከጎመን ጋር የሚሄዱ ነገሮችን አብሮ መሥራት ይቻላል። ብዙዎቻችን ገበያ ላይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩት፣ ካሮትና ድንች ብቻ ነው የምንፈልገው። ከዛ ወጣ ሲል፤ ቀይ ሥር፣ ፎሰልያ፣ ስኳር ድንችም መግዛት ይቻላልኮ። እኔ ወደነዛ ነው የማተኩረው። ያው ባጀቴም እንዳይቃወስ። ሽንኩርቱን ቀንሼ ሌላ ነገር እገዛለሁ። ከምግብ ሥራ ሂደት የቱ ደስ ይልሻል? 'ፍሬሽ' [አዲስ የተቀጠፈ] ጎመን፣ ጥቅል ጎመን፣ ቅመማ ቅመም ገዝቼ ቤት ስሄድ ደስ ይለኛል። ፍሪጅ ውስጥ አስገብቼ፣ አውጥቼ ስሠራውም የሆነ ነገር ይሰማኛል። የኛን አገር የአመጋገብ ባህል መቀየር እፈልጋለሁ። ከምናውቀው ነገር ውጪ መሞከር አንፈልግም። መመራመር አንፈልግም። ይህ መቀየር አለበት። ሬስቶራንትሽ እንዴት ነው? በኪራይ ምክንያት ተዘጋ። ለአምስት ዓመት ቻልኩት። ከዛ ግን ከእጅ ወደ አፍ ሆነ። ማብሰል ብዙ ሰአት ስለሚወስድም ጊዜ ተሻማኝ። ትቼው ወደ ቲቪ እና ወደ መጽሐፌ መሄድ ፈለኩ። ደንበኞቼ ግን አሁንም ይጠይቁኛል። የቲቪ መሰናዶውን ብዙ ሰው እየተማረበት ነው። መለኪያሽ ምንድን ነው? 'ይሄን ሞክረነዋል' ብለው እየመጡ የሚያመሰግኑኝ አሉ። ከኔ 'ሾው' በኋላ ወደ 300 ሰው ይደውላል። 'ይሄን ግብዓት ከየት አመጣሽ?' 'ይሄን ግብዓት በዚህ ልተካ?' እያሉ ይጠይቃሉ። ምግብ ማብሰል ከልጅነቴ ጀምሮ የምወደው ነገር ነው። የእናቴ አክስት የገዳም አብሳይ ነበሩ። ሠርተው ሲጨርሱ እኛ ቤት ይመጡ ነበር። እናቴ ስታበስል 'ነይ ተሳተፊ' እባል ነበር። እናቴ በጣም ባለሙያ ናት። ሙያው ከአክስቷ ወደሷ፣ ከሷ ወደኔ መጣ። እኔ ሼፍ ትምህርት ቤት አልተማርኩም። ወደ ሙያው የገባሁት መብላት ከመውደዴ የተነሳ ነው። ያደግኩት ደሞ ጣልያን ነው። እዛ ምግብ ትልቁ የሕይወት ክፍል ነው። ምግብሽ አይጣፍጥም ተብለሽ ታውቂያለሽ? አውቃለሁ። ብዙ ጊዜ ግን አይደለም። እንደዛ ያሉኝ ልጆቼ ናቸው። 'ይሄ ደሞ ምንድን ነው?' ሲሉኝ ይከፋኛል። ግን ወዲያው አሻሽለዋለሁ። ምግብ የልብ ነገር ነው። ከፍቶኝ ስሠራ የከፋ ምግብ አመጣለሁ። ደስ ብሎኝ ስሠራ ደግሞ ይጣፍጣል። 'ምግብ ሕይወት አለው እንዴ?' እላለሁ። 'ኩክ ዊዝ ላቭ' [በፍቅር አብስሉ] የምለው ለዛ ነው። ምግብሽን በልተው ካደነቁሽ ሰዎች የማትረሽው ማንን ነው? ልጆቼን። ስለምግብ ጥቅምና መጣፈጥ አስተምሬያቸዋለሁ። የትም ሄደው 'ይሄ ጥሩ ነው፤ ይሄ መጥፎ ነው' ማለት ይችላሉ። ምግብ ሳይቀምሱ 'አይጣፍጥም' እንዳይሉም አስተምሬያቸዋለሁ። ለምሳሌ ካንቺ ጋር ቃለ መጠይቅ ከመጀመሬ በፊት ለእንግዶች የሠራሁትን ሱፍ አቀመስኳቸው። 'ልክ አይደለም' አሉኝ። ከዛ በድጋሚ ነጭ ሽንኩርትና ቅመም ጨምሬ አስተካከልኩ። ከዛ 'አሁን ጣዕም አለው' አሉኝ። ዮናስ ተፈራ በሙያው ለ28 ዓመት ቆይቷል። በሆቴል፣ በሬስቶራንት፣ በእንግዳ ማረፊያም ሠርቷል። ከጓደኞቹ ጋር በከፈተው ቤንቬኒዶ የሆቴል ማሰልጠኛ ውስጥ ለአሥር ዓመት አስተምሯል። አምስት የምግብ አዘገጃጀት መጻሕፍት አሳትሟል። በሸገር ኤፍ ኤም ከሠይፉ ፋንታሁን ጋር "ሬሲፔ" በተሰኘ መሰናዶ ላይ ሠርቷል። አሁን በኢትዮ ኤፍኤም ላይ የ "ምሳና ሙዚቃ" መሰናዶ አዘጋጅና አቅራቢ ነው። አንባቢዎቻችን ለበዓል ምን እንዲመገቡ ትመክራለህ? እስኪ ከነአሠራሩ ንገረን። የብረት ምጣድ ጥብስ። አሠራሩ፦ መጀመሪያ ከምንጠብሰው ሥጋ ብዛት ይልቅ የምንጠብስበት እቃ ሁለት እጥፍ ትልቅ መሆን አለበት። የምንጠብሰው ሥጋ እርጥበት ከምንጠብስበት እሳት በላይ መሆንም የለበትም፤ እሳቱ ማሸነፍ አለበት። ሥጋውን በትንንሹ እንከትፈዋለን፤ አጥንቱን ለብቻው በትንንሹ እንሰባብረዋለን። ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል እንከትፋለን፤ የአበሻ ቅቤና ቃሪያ እናዘጋጃለን። ብረት ምጣዱ ከጣድን በኋላ በደንብ ሲግል፤ ትንሽ ዘይት ወይም ጮማውን ብቻ እየተጠቀምን ሥጋውን እየጠበስን ሲበስል ወደ ሌላ እቃ እንጨምራለን። አጥንቱን ለብቻ ሁለት ቦታ ከፍለን እየጠበስን ቡናማ መልክ ሲይዝ በማውጣት የተጠበሰውን ስጋ ወደ አስቀመጥንበት እቃ እንጨምራለን። ባዶ ብረት ምጣድ ላይ ቀይ ሽንኩርት እናደርጋለን። በትንሽ ዘይት ካቁላላነው በኋላ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል ገብቶ ለተወሰነ ሰዓት ይቁላላል። የተጠበሰው ስጋ የተፋውን ውሃ አስቀርተን ከሽንኩሩቱ ጋር በመቀላቀል አብረን እንጠብሳለን። ያስቀረነውን ሥጋው የተፋውን ውሃ ጨምረን ትንሽ እናበስለዋለን። የሀበሻ ቅቤ፣ ቃሪያና ጨው ጨምረን እናወጣዋለን። ዮናስ ተፈራ የኢትዮጵያውያንን የምግብ ዝግጅትና የአመጋገብ ባህል እንዴት ታየዋለህ? ቅባት እናበዛለን (ሳቅ). . . ይሄ ከፍተኛ የጤና ችግር አምጥቶብናል። ዘይት ይበዛል፣ ቅቤ ይበዛል፣ ጮማ ይበዛል። የዚህን ያህል ዘይት አገራችን ከውጪ እንድታስገባም አድርጎናል። በአመጋገብ ስርዓታችን በጎ ነገራችንስ የቱ ነው? የጾም ወራት ስለሚበዛ ሳይወዱ በግድ ከቅባት ይራቃል። ያ የጾም ወቅት ባይኖር ኖሮ እንደ አበላላችን የጤናችን ጉዳይ እጅጉን አሳሳቢ ነበር። የጾም ወራት አትክልትና ፍራፍሬ እንድንመገብ ያግዛሉ። ሳይንሱም እንደሚለው፤ ለተወሰነ ሰዓት ራስን ከምግብ ማራቅ፤ ሰውነታችን መርዛማ ነገሮችን እንዲያስወግድ፣ ውስጡ ያከማቸውን ቅባትና ካርቦኃይድሬት እንዲጠቀም እድል ይሰጣል። ምግብህ አይጣፍጥም ተብለህ ታውቃለህ? እንዴ ቁጭ አድርጎ ያስበላኝ እንግዳ አለ (ሳቅ). . . ግለሰቡ ሼፉን ጥሩት አለ፤ አስተናጋጆቹን። ሄድኩኝ። 'ቁጭ በልና ብላው' አለኝ። 'በሆቴል ሕግ ከእንግዳ ጋር ቁጭ ብሎ መብላት አይቻልም' ስለው፤ 'አልጣፈጠኝም! ቁጭ ብለህ ብላው' አለኝ። ሰውየው ሬስቶራንት ውስጥ ግርግር እየፈጠረ ስለነበር ማረጋጋት ነበረብኝ። ቁጭ ብዬ ያዘዘውን ስቴክ ቀመስኩት። ምንም ችግር አላገኘሁበትም። ግን ሰውየውን ለማስደሰትና ለማረጋጋት 'ትክክል ነህ ጌታዬ፤ ይህ ነገር መቀየር አለበት' አልኩና ስሄድ፣ እኮ! እኮ! ብሎ በጣም ደስ አለው። ወደ ምግብ ማብሰያ ክፍል ሄደን ግማሽ የእሱን ስቴክና ሌላ ስቴክ ጨምረን ላክልነት። ከዛ 'ኪችን' ድረስ ነው ለምስጋና የመጣው። አመስግኖኝ 'ቲፕ' [ጉርሻ] ሄደ። አንተው ሰርተኸው ያልጣፈጠህ ምግብ አለ? አዎ። እኔ ሠርቼው ሳይፍጠኝ፤ ብዙ ሰው የጣፈጠው ምግብ አለ። ውስጤ ስለማይቀበለው 'ሜኑ' [የምግብ ዝርዝር] ላይ እንዲወጣና እንዲሸጥ አልፈልግም። በአንድ ወቅት 'ኪችን' ውስጥ ሾርባ ሠርተን እኔ አልወደድኩትም ነበር። ረዳት ሼፌ ግን በጣም ወደደችው። ሌሎች የ'ኪችን' ሰዎችም ወደዱት። በኋላ ኃላፊውን አቀመስነው። "ዋው!" አለ። 'ሜኑ' ላይ መውጣት አለበት ሲል ወሰነ። እኔ ግን ውስጤ ስላልተቀበለው ፈራሁ። ላንተ ምግብ አዘገጃጀት ሳይንስ ነው ጥበብ? ከባድ ጥያቄ ነው። ሳይንስን ከጥበብ ያቀናጀ ሙያ ነው። ሳይንሱን የማትከተል ከሆነ ተመጋቢ ትጎዳለህ። ተመጋቢ ለመመገብ አፉን የሚከፍተው እኛን አምኖ ነው። ስለዚህ መታመን አለብን። ክቡር ለሆነው የሰው ልጅ የሚቀርበውን ምግብ ለመሥራት ሳይንሱን መከተል ያስፈልጋል። በየትኛው መንገድ ባበስለው ነው ጤናማ የሚሆነው? ብለን ሳይንሱን ካላወቅንና ካልተከተልን ከባድ ነው። ከዚያ ደግሞ መጀመሪያ የሚመገበው ዓይን ነው። ስለዚህ 'አርቲስቲክ' [ጥበብ የተሞላው] ነገር ይፈለጋል። አበሳሰሉ፣ አቀራረቡም ማማር አለባቸው። ስለዚህ ለኔ የምግብ ዝግጅት ሳይንስና ጥበብን ያቀናጀ ሙያ ነው።
48687774
https://www.bbc.com/amharic/48687774
ደቡብ አፍሪካዊቷ የፓርላማ አባል የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባት
ደቡብ አፍሪካዊቷ የተቃዋሚ ፓርቲው የዲሞክራቲክ አሊያንስ ቃል አቀባይና የፖርላማ አባሏ ፑምዚሌ ቫን ዳሜ በኃገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የቱሪስት መናኸሪያ አንዱ በሆነው 'ቪኤ ዋተር ፍሮንት' በተሰኘው ስፍራ የዘረኝነት ጥቃት እንደደረሰባት ገልፃለች።
ፑምዚሌ ቫን ዳሜ በኬፕታውን ከተማ 'ቪኤ ዋተር ፍሮንት' የተባለውን ቦታ እየጎበኘችበት በነበረችበት ወቅት አንዲት ነጭ ሴት እንደሰደበቻት በትዊተር ገጿ አስፍራለች። •ደቡብ አፍሪካ ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ጋዜጣ ሴተኛ አዳሪ ተብላ መሰደቧን ተቃወመች •በደቡብ አፍሪካ በየቀኑ 57 ሰዎች ይገደላሉ •በደቡብ አፍሪካ ዝቅተኛው የሠራተኛ ክፍያ 7ሺ ብር ሊሆን ነው ስድቡ ምን እንደሆነ ግልፅ ያልተደረገ ሲሆን ነጯ ሴት ይቅርታ ጠይቂ ብትባልም በእምቢተኝነቷ እንደፀናች የፓርላማ አባሏ ገልፃለች። "ከስፍራው በወጣሁበትም ወቅት ውጭ ላይ ሴትዮዋ ከቤተሰቦቿ ጋር ተሰባስባ በሚያስፈራራ መልኩ እያየችኝ ነበር፤ እናም ለምንድን ነው እንዲህ የምታይኝ ብየ ስጠይቃትም፤ ጥቁር ስለሆንሽ ነው የሚል መልስ ሰጥታኛለች" ብላለች። •ኤኤንሲ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ 'ዘረኛ' ነው አለ • የፓርላማ አባሉ ሴት ባልደረባቸውን በመምታታቸው ተያዙ ሴትዮዋ ብቻ ሳትሆን ልጇም እንደሰደባትና ጥቁር ስለሆነችም መሳደብ እንደሚችል የነገራት ሲሆን እየቀረፀችበት የነበረውንም ስልኳን መሬት ላይ በመወርወሩ ራሷንም ለመከላከል በቦክስ እንደመታችው ተናግራለች። በቦታው የነበረው የጥበቃ አካል እንዳልደረሰላትም መግለጿን ተከትሎ የቦታው አስተዳደር በተገቢው መልኩ ምላሽ ባለመስጠታቸው ይቅርታ ጠይቀው ምርመራ እንደሚጀመር ገልፀዋል።
news-53520980
https://www.bbc.com/amharic/news-53520980
ለዓመታት የሶሪያን ጦርነት በምስጢር ፎቶ ያነሳው ጋዜጠኛ
ስሙ አቡድ ሀማም ነው። ማንነቱን ሳይገልጽ ለዓመታት በመላው ዓለም ላሉ መገናኛ ብዙሃን ስለሶርያ መረጃ ሰጥቷል።
መጀመሪያ ላይ በፎቶ አንሺነት የቀጠሩት የአገሪቱ ፐሬዝዳንትና ባለቤታቸው በሽር እና አስማ አል-አሳድ ነበሩ። ኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) የድል ሰልፍ ሲያካሂድ ቪድዮ የቀረጸው አቡድ ነው። አሁን ማንነቱን ይፋ አድርጓል። እስኪ ራስህን ግለጽ? ሲባል “ማንነቴን የቀረጸው ዘጠኝ ዓመት የዘለቀው ጦርነት ነው” ብሎ ይመልሳል። “ራሴን በመስታወት ሳይ መሸበቴ ይታወቀኛል። እንዲህ ያደረገኝ ጦርነቱና ጭንቀቱ ነው።” አቡድ 45 ዓመቱ ነው። ሕይወቱ በፍርሃት የተሞላ ነው። ዓለም ስለሶርያ ጦርነት እውነታውን እንዲያውቅ ለማድረግ ለዓመታት ለፍቷል። “ፎቶ ሊገልም ሕይወት ሊያተርፍም ይችላል” ምናልባትም በሁሉም የሶርያ ኃይሎች ስር የሠራ ብቸኛው የፎቶ ጋዜጠኛ ሳይሆን አይቀርም። በአሳድ አምባገነን ዘመን፣ በተቃዋሚው የፍሪ ሲርያን አርሚ፣ በተቀናቃኞቹ የእስልምና ቡድኖች ማለትም በጃብሀት አል-ኑስራ እና በኢስላሚክ ስቴት እንዲሁም የኩርድ አካባቢን በሚቆጣጠረው አካባቢ ስር ሠርቷል። “ፎቶ ሊገልም ሕይወት ሊያተርፍም ይችላል” ይላል ጋዜጠኛው። አማጽያን በደማስቆ ላይ ያደረሱትን ጥቃት የሚያሳይ ፎቶ በድብቅ ካነሳ በኋላ ሕይወቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ሰግቶ ነበር። ሙካሃብራት የሚባሉት ሚስጥራዊ ፖሊሶች ፎቶ ማንሳቱን ቢያውቁ ይገሉት ነበር። ይህ የሆነው ገና አመጹ ሲቀሰቀስ ነው። ያኔ መንግሥት ስለ አማጽያኑ ወታደራዊ አቅም እንዲታወቅ አይፈልግም ነበር። አይኤስ የአቡድን የትውልድ ከተማ ረቃ በቁጥጥር ሥር ካዋለ በኋላ፤ ድሉን በአደባባይ ሲያከብር ፎቶ እንዲያነሳ የተጠየቀው አቡድ ነበር። ፎቶ ማንሳት የጀመረው ረቃ ሳለ ነበር። አባቱ አርሶ አደር ነበሩ። “እውነቱን ለመናገር ያደግኩበት ማኅበረሰብና ቤተሰቤም ለጋዜጠኝነት እና ለፎቶ አንሺነትም ዋጋ አይሰጥም። ፎቶ አንሺነት የማይረባ ሥራ ነው ብለው ያምናሉ። መምህር ወይም ጠበቃ እንድሆን ነበር የሚፈልጉት።” ታላቅ ወንድሙ የሩሲያ ካሜራ ከሰጠው በኋላ በፎቶ ፍቅር ወደቀ። ከደማስቆ የፎቶ ትምህርት ቤት ተመርቋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2011 ላይ አመጽ ሳይቀሰቀስ በፊት በአገሪቱ ብሔራዊ የዜና ተቋም ‘ሳና’ ዋና ፎቶ አንሺ ሆኖ ተቀጠረ። ፕሬዘዳንት አል-አሳድ እና ባለቤታቸው አስማን ፎቶ ማንሳት የሥራው አካል ነበር። ጥንዶቹን ፎቶ ሲያነሳ አንድም ቀን አዋርተውት እንደማያውቁ ያስታውሳል። “ይፋዊ ጉብኝት ሲካሄድ ፎቶ አንሺዎች በከፍተኛ ወታደሮችና የደኅንነት ኃላፊዎች እንታጀብ ነበር። በጣም ነበር የሚያስጠላኝ። እነሱን ማክበር ይጠበቅብናል። እኔ ደሞ እንደዚያ አይነት ሰው አይደለሁም።” አስማ አል አሳድ፤ የፕሬዝዳንት ባሻር አል አሳድ ባለቤት “ብያዝ እንደምገደል ሁሌ አስብ ነበር” ከዘጠኝ ዓመት በፊት በሶሪያ አመጹ ተቀሰቀሰ። በዚህም አቡድ ሁለት አይነት ሕይወት ለመምራት ተገደደ። ቀን ላይ የመንግሥትን ገጽታ የሚገነባ ሥራ ይሠራል። ማታ ደግሞ ተቃውሞውን ይቀርጻል። ፍሪ ሲሪያን አርሚ በመንግሥት ላይ በሚያካሂደው አመጽ የሶርያ መዲና ደማስቆ ላይ ጥቃት ይሰነዝር ነበር። የሚያነሳቸውን የተቃውሞ ፎቶዎች ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የሚልከው ኑር ፉራት የተባለ የብዕር ስም ተጠቅሞ ነበር። ፉራት በራቃ የሚያልፈው የኤፍራጠስ ወንዝ አረብኛ መጠሪያ ነው። አቡድ መንፈሱን ማፍታት ሲፈልግ የሚሄደው ወደዚህ ወንዝ ነው። እስከዛሬ ድረስ ፎቶ የሚልክላቸው መገናኛ ብዙሃን እውነተኛ ስሙን እንደማያውቁ ይናገራል። ከጊዜ በኋላ ለእነዚህ መገናኛ ብዙሃን ፎቶ መላክ አስፈሪ እየሆነ መጣ። “በድብቅ የማነሳቸውን ፎቶዎች የማስቀምጥበትን ሜሞሪ የምይዘው በኪሴ ነው። ብያዝ እንደምገደል ሁሌ አስብ ነበር።” 2013 ላይ ራቃ በአማጽያን ቁጥጥር ሥር የወደቀች የመጀመሪያዋ የሶርያ ከተማ ሆነች። አቡድም ከደማስቆ አምልጦ ረቃ ተመለሰ። ራቃ ውስጥ ፎቶ ጋዜጠኛ መሆንም አስጊ መሆኑ ግን አልቀረለትም። አማጽያኑ የመንግሥት ቅጥረኛ ነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ ብሎ ይፈራ ነበር። “ገለልተኛ ሆኜ የምኖርበት ስልት ቀይሼ ነበር” 2014 አጋማሽ ላይ ነገሮች ተባባሱ። “ጥቁር ሰንደቅ አላማ ያነገቡ ሰዎች በሞተር ሳይክል ሆነው ከተማው ውስጥ ይዘዋወሩ ጀመር” ሲል ያስታውሳል። ከተማዋ ውስጥ የገቡት የአይኤስ አባላት ነበሩ። መግባታቸውን ተከትሎም በርካታ ጋዜጠኞች ከከተማዋ ሸሽተዋል። ቀድሞው በአሳድ መንግሥት ስር ይሠራ የነበረው አቡድ ከማንም በላይ ለአደጋ ተጋላጭ ቢሆንም፤ ከተማዋን አለቀቀም። እንዲያውም ሥራውን ቀጠለ። አይኤስ የድል ሰልፉን በካሜራው እንዲያስቀር ሲጠይቀው ከመቀበል ውጪ አማራጭ አልነበረውም። አይኤስ ለዓለም አቀፍ ተቋማት የላካቸው የፕሮፓጋንዳ ፎቶዎችም እሱ ያነሳቸው ናቸው። አቡድ ሰዎች አንገታቸውን በሚቀሉባቸው ቀናት ከቤቱ አይወጣም ነበር። “አይኤስን ለመደገፍ ቃል አልገባሁም። ገለልተኛ ሆኜ የምኖርበት ስልት ቀይሼ ነበር።” ራቃ ውስጥ ከማኅበረሰብ መሪዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ስላለው ሳይታሰር እንደቀረ ያምናል። መሪዎቹ ኋላ ላይ አይኤስን ተቀላቅለዋል። 2015 ላይ ግን ሁለት የአይኤስ አባላት ሥራውን ካላቆመ ችግር ውስጥ እንደሚገባ ስላስፈራሩት ራቃን ለቀቀ። ወደ ሌላ ሰሜናዊ የሶርያ ከተማ ሄዶ ጦርነቱን መዘገቡን ቀጠለ። እስከ 2017 ወደ ራቃ አልተመለሰም። በዚያ ዓመት አሜሪካ መራሹ ጸረ አይኤስ ኃይል ከተማዋን ከሽብርተኞች ነፃ አውጥቷል። ከተማዋ ነፃ ብትወጣም እንዳልነበረች ሆናለች። “መጀመሪያ ከተማዋን ያየኋት ቀን ምንም መናገር አልቻኩም። በሁለተኛው ቀን ከቤት ወጥቼ ፎቶ ማንሳት ስጀምር አለቀስኩ። ከተማዋን እየዞርኩ አነባሁ።” ለወራት ራቃን እየዞረ ፎቶ አነሳ። ጸጥ ረጭ ባሉት ጎዳናዎች ተመላለሰ። የተበታተኑ ቤተሰቦችን አየ። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፤ 80 በመቶ የሚሆነው የከተማዋ ክፍል ላይመለስ ወድሟል። 90 በመቶ የሚሆኑት ነዋሪዎቿ ደግሞ ሸሽተዋል። ካነሳቸው ልብ የሚሰብሩ ፎቶዎች አንዱ የፈራረሰ ፎቅ ያሳያል። ፎቁ ውስጥ ከነበሩ ቤቶች በአንዱ ደማቅ ቀሚስ ተሰቅሏል። ይህ ፎቶ ለአቡድ ትርጉም አለው። “የሰው ሕይወት እንደተጣሰ ተሰማኝ። ይህን ልብስ ሴቶች የሚያዘወትሩት ቤት ሲሆኑ ነው። ቤቱ ውስጥ ይኖር የነበረው ቤተሰብ የለም። የቤቱ ደስታ ተገፏል። ቀሚሱ ብቻውን ቀርቷል። ንፋስ ቀሚሱን ሲያወዛውዘው ዝም ብዬ አይ ነበር። ተሰቅሎ ለሞት የሚያጣጥር ሰው ነው የመሰለኝ።” የአይኤስ ቡድን የድል ትዕይንት “ራቃን ደግማችሁ ውደዷትና ተመለሱ” ቀስ በቀስ ከተማዋ ሕይወት ስትዘራ የአቡድ ፎቶዎችም ነፍስ ዘሩ። ሱቆች ተከፈቱ። በኤፍራጥስ ወንዝ የሚዋኙ ሰዎችም ይታዩ ጀመር። እሱም ማንነቱን ይፋ ለማድረግ ወሰነ። ፌስቡክ ላይ ‘አቡድ ዊዝአውት ባሪየርስ’ (አቡድ ያለ ሽፋን) በሚል ሥራዎቹን ማሳየት ጀመረ። አላማው ሰዎች ወደ ራቃ እንዲመለሱ ለማድረግ ነው። “ከተማዬን የገጠማትን ክፉ ነገር ማሸነፊያ መንገድ ነው። ሩቅ ያሉ የራቃ ነዋሪዎች ከተማቸውን በተለየ መንገድ እንዲያዩ ማድረግ እፈልጋለሁ። ከተማችን እንደጨለመች አውቃለሁ። ቀለሟ ግራጫ ሆኗል። ግን እንዴት በቀለማት የተዋበች እንደነበረች አስታውሱ። ራቃን ደግማችሁ ውደዷትና ተመለሱ። ፎቶዎቼን ብታዩ በአሳዛኝ ምስል ውስጥ እንኳን ሕይወት ታገኛላችሁ።” በጣም የሚኮራበት ፎቶ አንድ ደማቅ ቀለም ያለው ቀሚስ ያረገች ታዳጊን ያሳያል። ወደ ሳኡዲ አረቢያ ሄዶ የነበረና ከቤተሰቡ ጋር ለመቀላለቀል ወደ ራቃ የተመለሰ ሰው ልጅ ናት። ግለሰቡ ፌስቡክ ላይ የአቡድን ፎቶዎች ከተመለከተ በኋላ በአካባቢው ትምህርት ቤት እንዲሠራ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ሌሎችም ፎቶውን ያዩ ሰዎች ወደ ራቃ ለመመለስ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። አቡድ አሁን ከራቃ ወጥቶ በቱርክ ቁጥጥር ሥር ባለውና በግጭት በሚናጠው ሰሜናዊ ሶሪያ ውስጥ ፎቶ እያነሳ ነው። ወደ ራቃ ቢመለስ በኩርዶች የሚመራው አማጺ ቡድን የቱርክ ሰላይ ነህ እንዳይለው ይፈራል። ብዙ አስፈሪ ነገሮችን አልፏል። ሆኖም ግን ከምዕራባውያን ጋር በመሆን ራቃን ከጽንፈኞች ያላቀቃት ቡድንም ያስፈራዋል። ሶሪያ ውስጥ ጋዜጠኛ መሆን እስከወዲያኛው ከስጋት ጋር መኖር ማለት እንደሆነ የሚያስበውም ለዚህ ነው። “በሕይወቴ በሰላም እና በደስታ ያሳለፍኩት ጊዜ ትዝ አይለኝም። አንድ ጊዜ የአየር ድብደባ ቀርጬ ስጨርስ ከሞቱት አንዱ የአክስቴ ልጅ እንደሆነ ተነግሮኛል። ያነሳሁትን ቪድዮ ተመልሼ ስመለከተው አስክሬኑን አየሁት።” “በጦርነቱ ሳቢያ አላገባሁም” አቡድ እንደሚለው፤ በጦርነቱ ሳቢያ አላገባም፤ ቤተሰብ አልመሰረተም። “45 ዓመቴ ነው። ቤተሰብ የለኝም፤ ሚስት የለኝም፤ ያሳዝናል። ይሄ ካሜራ ባይኖረኝ ሽጉጥ ይኖረኝ ነበር። እኔ ግን በመሣሪያ አላምንም። ምናልባት እንደማንኛውም ሰው ጦርነቱ ውስጥ ብገባ ኖሮ ጉዳቱ ይቀንስልኝ ነበር ብዬ አስባለሁ።” ሶሪያ ውስጥ የሚካሄደውን ነገር ፎቶ ማንሳት መቀጠል ይፈልጋል። “በጎውንም መጥፎውንም ሁሉም ሰው እንዲያየው እፈልጋለሁ። እንደእኔ ምርጫ ቢሆን በሰላማዊ አካባቢ የዱር እንስሳትን ፎቶ አነሳ ነበር። ስዊትዘርላንድ መሄድ እመኛለሁ። ሰላምና ጸጥታው ያስፈልገኛል” ይላል አቡድ።
news-56714419
https://www.bbc.com/amharic/news-56714419
የከተሜውን ህይወት የከተማ ግብርና ያቀለዋል የሚሉት አቶ እስክንድር
አቶ እስክንድር ሙሉጌታ በአዲስ አበባ በሚገኙ አስር የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተለያዩ ችግኞችን በማዘጋጀት ለሽያጭ ያቀርባሉ።
በተጨማሪም በእነዚህ አስር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ድንች፣ ሽንኩርት እና ቲማቲም በማልማት በትምህርት ቤቶቹ ለሚካሄደው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በሽያጭ እያቀረቡ ገቢ እንደሚያገኙ ይገልፃሉ። አቶ እስክንድር ከሚሰሩባቸው አስሩ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል መጋቢት 28 ፣ መቅደላ፣ ደምቦስኮ፣ ብሩህ ተስፋ፣ ቆጣሪ፣ ስብስቴ፣ አቡነ ባስሊዎስ እንደሚገኙበት ተናግረዋል። አቶ እስክንድር ሥራቸውን የጀመሩባቸው ሁሉም የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የሚሰጡ መሆናቸውን ይናገራሉ። በአገር አቀፍ ደረጃ 1.5 ሚሊዮን ተማሪዎች በምገባ ፕሮግራም ውስጥ መታቀፋቸውን የሚናገሩት አቶ እስክንድር በአዲስ አበባ ደግሞ 300 ሺህ ተማሪዎች በዚሁ መረሃ ግብር ውስጥ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል። ይህንን የምገባ ፕሮግራም ለመሸፈን የሚያስፈልገው ገንዘብ ምንጩ በዋነኛነት ከዓለም ባንክ እንደሆነ የተረዱት አቶ እስክንድር ከዚህ አንጻር ሊያከናውኑ ስላሰቡት ሥራ አስፈላጊውን ነገር ማጥናት ጀመሩ። ስለዚህ ይህንን አጋጣሚ እንደ ትልቅ እድል በማየት በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ይዞታ ላይ እንደሰፈሩ ጥናት ማድረጋቸውን ይናገራሉ። እንደ አቶ አስክንድር ጥናት "በአዲስ አበባ አንድ የመንግሥት ትምህርት ቤት 42000 ስኩዌር ካሬ ሜትር ላይ ሰፍሮ ይገኛል።" ይህ በክልል ከተሞች እና በገጠሪቷ የአገሪቱ ክፍል በጣም እንደሚለይ ይናገራሉ። ስለዚህ ይህንን እንደ መነሻ በመውሰድ እና በየትምህርት ቤቱ ከ10 የሚበልጡ ወላጆችን በማደራጀት ወደ ሥራ የጓሮ አትክልት ልማት ሥራውን ማከናወን ጀመሩ። አግሮኖሚስቱ [የአፈር ጥበቃና የአዝርዕት ባለሙያ] አቶ እስክንድር የትምህርት ቤቶቹን የምገባ ፕሮግራም እንዲያግዝ በማሰብ በ10 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የጀመሩት የተለያዩ የጓሮ አትክልቶች ማልማት ውጤት ማሳየት ጀምሯል። በአንድ ትምህርት እስከ 12 ኩንታል ድንች ማምረት ችለናል የሚሉት አቶ እስክንድር፣ በተጨማሪም የዶሮ እርባታ የጀመሩ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል። "በዚህ መልኩ የተማሪዎች ምገባ ራሱን እንዲችል ማድረግ ይቻላል" የሚሉት አቶ እስክንድር፣ አልፎ ተርፎም ከዚያ ላይ በሚገኘው ገቢ ወላጆች እና ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ይናገራሉ። አቶ እስክንድር ማን ናቸው? አቶ እስክንድር በሙያቸው አግሮኖሚስት ናቸው። "ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ነው የመጀመሪያ ዲግሪዬን ያገኘሁት" ይላሉ። ኡጋንዳ ውስጥ ለሰባት ዓመታት በአንድ መንግሥታዊ ባልሆነ ደርጅት ውስጥ ተቀጥረው ሰርተዋል። ከዚያም ውጪ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና በደቡብ ሱዳን በግብርናው ዘርፍ ሰፊ ልምድ አካብተዋል። በኡጋንዳ በነበራቸው ቆይታ ግብርና ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ፣ የከተማ ግብርና ደግሞ እጅጉን ተስፋፋቶ፣ እንዲሁም የሚገባውን ያህል የከተሜው ሕይወት ላይ ለውጥ አምጥቶ ማስተዋላቸውን ይናገራሉ። ኡጋንዳ ውስጥ በየጓሮው ባለው የበሬ ግንባር በምታክል ቦታ አትክልቶችን በመትከል ራሱን የሚመግብ ሕዝብ በርካታ መሆኑን ይናገራሉ። ይህንን ተሞክሮ "በአገራችን ባህል እንዲሆን ፈለግኩ" የሚሉት አቶ እስክንድር፣ ከግብርና ጋር ከፍተኛ የተቆራኘ ሕይወት ያለው ሕዝብ ነገር ግን በምግብ ዋስትና ጥያቄ ላይ መውደቁ ያሳስባቸዋል። አግሮኖሚስቱ እስክንድር በኡጋንዳ ያዩትን መልካም ተሞክሮ ወደ አገር ቤት በማምጣት በትምህርት ቤቶች ላይ መጀመራቸውን ይናገራሉ። ለዚህም እንዲረዳቸው በትምህርት ቤቶች የምግብ አቅርቦት ዙሪያ የሚሰራውን 'ፉድ ሴኪዩርድ ስኩልስ አፍሪካ' [Food Secured Schools Africa (FSSA)] የተሰኘ ድርጅት መሰረቱ። ይህንንም ጽንሰ ሃሳብ ለማስለመድ ዝነኛ ሰዎች በየጓሯቸው አትክልቶችን በመትከል ምሳሌ እንዲሆኑ መሞከራቸውን ገልፀዋል። በአዲስ አበባ የሚኖሩ አብዛኛው ነዋሪዎች ሰፊ ሆነ ግቢ ይዘው እንደሚገኙ የሚያስረዱት አቶ እስክንድር፣ በአግባቡ እነዚህን ስፍራዎች ለከተማ ግብርና በመጠቀም በምግብ እህል ራስን መቻል እንደሚቻል ያስረዳሉ። አክለውም የከተማ ግብርናን የሕይወት ዘዬ በማድረግ፣ ከራስ አልፎ ለሌሎች መትረፍ እንደሚቻልም ይናገራሉ። ግብርናን እንደ ቢዝነስ ማሰብ እንደሚያስፈልግ፣ በግብርና ሰርቼ እበለጽጋለሁ የሚል ትውልድ መፈጠር እንዳለበትም ያምናሉ። "የኢትዮጵያ ግብርና በአግባቡ ከተያዘ የዳቦ ቅርጫት መሆን ትችላለች" የሚሉት አቶ እስክንድር፣ ኢትዮጵያ ከራሷ አልፎ ጎረቤቶቿን መመገብ እንደምትችል ሲናገሩ በልበ ሙሉነት ነው። በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች የክልል ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት፣ የእምነት ቦታዎች፣ ትምህርት ቤቶች ሰፋፊ ቦታዎችን አጥረው መያዛችን በማስታወስ፤ እነዚያን ስፍራዎች ለከተማ ግብርና ማስፋፊያነት በአግባቡ ማዋል ከተቻለ በምግብ እህል ራስን መቻል ቀላል ነው ይላሉ። ይህንን በማድረግ የአርሶ አደሩን ጫና መቀነስ ከቻልን እርሱ ወደ ሐብት ማፍራት ይሄዳል የሚሉት አቶ እስክንድር ይህም በምግብ ዋስትና ላይ እንዳይቆይ ከተሜው ሊያግዘው እንደሚገባ ይናገራሉ። "አርሶ አደሩ ደከመኝ ሰልቸኝ ሳይል ሰርቶ ከተሜውን ጨምሮ ይመግባል" የሚሉት አቶ እስክንድር፣ አሁን ግን በአየር ንብረት ለውጥ፣ የተለያዩ ግብዓቶችና ቴክኖሎጂዎች ባለመሟላት ለራሱም እጅ ሲያጥረው ነው በማለት፤ "ስለዚህ ከተሜው አርሶ አደሩን በከተማ ግብርና ሊያግዘው ይገባል" ይላሉ። "በግብርናም ሚሊየነር መሆን ይቻላል" በማለትም፣ በአስሩ ትምህርት ቤቶች ካሏቸው የከተማ ግብርና ፕሮግራሞች በተጨማሪም በግላቸው ከዚሁ ጋር የተያያዙ ሌሎች ሥራዎች ላይ መሰማራታቸውን ይናገራሉ። በአሁኑ ጊዜ አንድ የአቡካዶ ችግኝ በ40 ብር በመሸጥ ገቢ ማግኘት ይቻላል የሚሉት አቶ እስክንድር፤ በመጋቢት 28 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ 5000 የአቦካዶ ችግኞች አፍልተው ለሽያጭ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል። በዚህ ሥራ ላይ 15 ወላጆች በአማካይ በትምህርት ቤት ውስጥ እየሰሩ ይገኛሉ። በግላቸው ደግሞ በ300 ካሬ ሜትር ላይ 10 ሺህ የአቦካዶ ችግኞችን በማፍላት ለገበያ አቅርበዋል። አቶ እስክንድር ችግኞችን በመሸጥ፣ በጓሮ አትክልት ልማት ላይ ለመንግሥታዊ ድርጅቶች ስልጠናዎችን በመስጠት ገቢ እንደሚያገኙም ይገልጻሉ። የከተማ አርሶ አደር አግሮኖሚስቱ አቶ እስክንድር ከኡጋንዳ መጥተው የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን መልካም ተሞክሮ በአገራቸው ተግባራዊ ለማድረግ ደፋ ቀና ሲሉ የገጠማቸው የመጀመሪያ ፈተና "ግብርና በከተማ እንዴት ሲደረግ?" የሚለው ነበር። መጀመሪያ ሥራውን ሲጀምሩ ትግሉ ከባድ እንደነበር የሚያስታውሱት ባለሙያው፣ የመጀመሪያው ተግዳሮት "ግብርና መሬት ይፈልጋል። ከከተማ ወጣ ተብሎ የሚሰራ ሥራ ነው" የሚለው መሆኑን ይናገራሉ። ግብርናን በትልቅ መሬት ብቻ ማሰብ ከፍተኛ ፈተና ሆኖባቸው እንደነበር አክለው ተናግረዋል። ራስን ለመመገብ በትንሽ መሬት ላይ ምርት ማምረት ይቻላል የሚለው አስተሳሰብ በሂደት እያደገ የመጣ መሆኑንም ይገልጻሉ። የከተማ ግብርና ተገቢው ትኩረት አላገኘም የሚሉት አቶ እስክንድር፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጀመሯቸው የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴዎች እና ኮሮናቫይረስ ሰውን ወደ ጓሮው እንዲመለከት እንዳደረገው ይጠቅሳሉ። ከዚህ በተጨማሪ ግን ያለው የኢንሹራንስና የፋይናንስ ሥርዓት ገበሬውን የሚያበረታተ እንዳልሆነ የራሳቸውን ተሞክሮ በመጥቀስ ያስረዳሉ። አቶ እስክንድር በግላቸው ወደ 10 ሺህ አቦካዶ አምርተው ባንኮች ያንን በመያዝ ብድር እንዲሰጧቸው እንዲሁም ዶሮ እርባታ እና የዶሮ መኖ ማምረት ለመጀመር ቢጠይቁም 10 ሺህ ችግኝ ማስያዣ አይሆንም መባላቸውን ያስታውሳሉ። አገራችን ከተማን ማዕከል ያደረገ፣ ለገበሬውን ትኩረት ያላደረገ "የተዘጋ የፋይናንስ ሥርዓት" ያላት ናት በማለትም ይህ የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ ሥርዓት መስተካከል እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል። አርሶ አደሩን ሰርቶ እንደሚቀየር፣ ሥራ ፈጣሪ መሆኑን በማመን ይህንን ማዘመን እንደሚያስፈልግም ይመክራሉ።
news-51817877
https://www.bbc.com/amharic/news-51817877
የቀድሞው የደኅንነት መስሪያ ቤት ምክትል ይናገራሉ
አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል በ1972 ዓ.ም ወደ ህወሓት የትጥቅ ትግል የተቀላቀሉ ሲሆን ከደርግ ውድቀት በኋላ ደግሞ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ተቋም ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። በሙስና ተጠርጠረው ከተቋሙ በ2003 ዓ.ም እስከወጡበት ጊዜ ድረስ የአገር ውስጥ መረጃና ደኅንነት ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል። እነሆ ከቢቢሲ ጋር የነበራቸው ቆይታ. . . እርስዎ በደኅንነት ተቋሙ ውስጥ በነበሩበት ወቅት መስሪያ ቤቱ በትግራይ ተወላጆችና በ ህወሓት አባላት የተያዘ ነው ይባል ነበር። ምን ይላሉ?
አቶ ወልደሥላሴ፡ የተቋሙ ግዙፍ ክፍል በሆነው የአገር ውስጥ መረጃና ደኅንነት ኃላፊ በመሆን ነው ረጅም ጊዜያት ያሳለፍኩት። ስለዚህም በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ውስጥ የነበረውን አጠቃላይ የሠራተኞችን ብዛት ያየን እንደሆነ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት የአማራ ብሔር ተወላጆች ናቸው። ቀጥሎ ደግሞ የኦሮሞና የትግራይ ተወላጆች ቁጥር ተቀራራቢ ነው። ይህን መረጃ ከተቋሙ የሰራተኞች ፋይል በቀላሉ ማረጋገጥ የሚቻል ነው። በመሰረቱ ይህ አጀንዳ በተደጋጋሚ ይነሳ ስለነበር ጥናት አካሂደንበታል። • መንግሥት በታጣቂዎች ላይ ዘመቻ በሚያካሂድበት ምዕራብ ኢትዮጵያ ህይወት ምን ይመስላል? ታድያ ሐቁ ይህ ከነበረ ለምንድነው ተቋሙ በትግራይ ተወላጆች እንደተሞላ ጥያቄ ሲነሳበትና በጥርጣሬ ሲታይ የነበረው? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በታሪክ አጋጣሚ ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በዘርፉ የተሻለ ተሞክሮና ትምህርት የነበራቸው ከህወሓት ይበዙ ነበር። ከዚህ የተነሳ እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ በኃላፊነት ደረጃ ከነበሩት ሰዎች አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች ነበሩ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ በኃላፊነት ያሉትም ሰዎች መመጣጠን አለበት ተብሎ የማመጣጠን ሥራ ተከናውኗል። ከላይ ለማስመቀመጥ የሞከርኩት ግን ከተቋሙ አጠቃላይ ስታፍ [የሰው ኃይል] አንጻር ያለውን ብዛት ነው። • በመሐል ሜዳ ሚስቱን ለመግደል የሞከረው ግለሰብ የሦስት ሰዎችን ህይወት አጠፋ ሌላኛው በጥራጣሬ ዓይን ይታይ ነበር የተባለውን ግን እኔ አልቀበለውም። ምክንያቱም በምንሰራቸው ሥራዎች በሙሉ የሕዝቡ ተሳትፎ የላቀ ስለነበረ ነው። አብዛኞቹ አገሪቱን የማተራመስ ህቡዕ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ሕዝቡ ቀድሞ መረጃ በመስጠት ይተባበረን እንደነበር አስረግጬ ልነናገር እችላለሁ። ኢትዮጵያ ተጋርጠውባት የነበሩት የደኅንነት አደጋዎችና እነዚህን በማክሸፍ ረገድ የሕዝቡና መንግሥትን ሚና በመጽሐፌ በስፋት ገልጬዋለሁ። የደኅንነት መስርያ ቤቱ በደርግ ግዜ በጣም ተፈሪ ነበር። በኋላ ግን የሚያስመካ እምርታ አስመዝግቧል ባልልም እንኳ በደርግ ጊዜ ከነበረው እጅግ የተሻለና ሕዝብ ወዶ የሚተባበረው ተቋም ነበር ማለት ግን እችላለሁ። የደኅንነት ተቋሙ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጽም እንደነበር በስፋት ሲነገር ቆይቷል። ከዚህ አንጻርስ ምን ይላሉ? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጊዜ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተለያዩ ዘርፎች ጉልህ ጉድለቶች እንደነበሩና ለዚህ ደግሞ ዋናው ተጠያቂ ራሱ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ እንደሆነ ገምግሟል። ስለዚህ ከዚህ በመነሳት የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እንደየተልዕኳቸው በሰብአዊ መብት ረገጣ የየራሳቸውን ድርሻ ይወስዳሉ ማለት ነው። እውነት ለመናገር የአገሪቷን ደኅንነት ለማረጋገጥ ተብሎ በሰብአዊ መብት አያያዝ በኩል ጉድለቶች ሊኖሩ ይችላሉ። እኔ እስከማውቀው ድረስ ግን የደኅንነት ተቋሙ የዜጎችን ህይወት እና ንብረት ለመጠበቅ በታታሪነት ይስራ የነበረ ተቋም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በመገናኛ ብዙሃን በወንድ ብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠልና ጥፍር እስከመንቀል የደረሱ በደሎች ተፈጽሞብናል የሚሉ ሰዎች ቀርበው ታይተዋል። የደኅንነት ተቋሙ በዚህ ውስጥ እጁ የለበትም? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የአገሪቱ የደኅንነት መስሪያ ቤት ሥራው መረጃ ማሰባሰብ ነው። መረጃ አሰባስቦ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ያቀርባል። ከዚያ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያገኘውን መረጃ ተንተርሶ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር ሆኖ እርምጃ በመወስድና ባለመውሰድ ላይ ይወስናል። • ኢትዮጵያ ውስጥ መካኖች ወልደው እየሳሙ ነው እኔ በተቋሙ በኃላፊነት ደረጃ እስከነበርኩበት እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ መረጃ በምርመራ የማግኘት ኃላፊነት የተሰጠው የፌደራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ነው። ስለዚህ የመረጃና ደኅንነት ተቋሙ ሥራና ኃላፊነት የነበረው የሕዝቡን አቅም ተጠቅሞ መረጃ በማሰባሰብ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል መስጠት ነው። ሥራው ራሱ በሕግ የተወሰነ ነው። የምርመራ ሥራ የእኛ ሥራ ስላልነበረ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች ለእኔ ግልጽ አይደሉም። ስለዚህ ተፈጸሙ የተባሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በየትኛው የመንግሥት አካል ነው የተፈጸሙት? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ መረጃው የለኝም። በሙስና ተጠርጥረው ታስረው እንደነበር ይታወሳል። የቀረበብዎን ክስ ተቀብለውታል? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በእኔ የሙስና ክስ ጉዳይ እኔ ባለጉዳዩ ከምናገረው በላይ ከእራሱ ከፍርድ ቤቱ ብትጠይቅ ነው የሚሻለው። በእርስዎ በኩልስ ግን ተቀብለውት ነበር? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ ክሶቹ መሰረተ ቢስ ስለነበሩ አልተቀበልኳቸውም፤ ፍርድ ቤቱም ሁሉንም ውድቅ አድርጓቸዋል። በሁለት ክሶች ግን አልከላከልም ብዬ አልተከላከልኩም። አንደኛው ክስ ሽጉጥና ጠብመንጃ ተገኝቶብሃል የሚለው ነው፤ በነበረኝ የሥራ ኃላፊነት የተነሳ ለምን እንደያዝኩት የሚታወቅ ስለሆነ ለመከላከል ሞራሌ አልፈቀደልኝም። ሁለተኛው ደግሞ በሥራ ምክንያት እንደሆነ እየታወቀ ለአንዲት ሴት የትራስፖርት አገልግሎት ትሰጥ ነበር ተብሎ የቀረብኝን ክስም አልከላከልም ብያለሁ። ታዲያ የተቀጣሁትም በእነዚህ ሁለት ክሶች ነው። • ሦስት ልጆቿን ባሳጣት አሰቃቂ እሳት የተፈተነችው ሄለን በተረፈ ሌሎቹን ማለትም መጽሐፍ አሳትሞ ሲሸጥ ስልጣኑን ይጠቀም ነበር የሚለውንና በአዲስ አበባ ምንጩ ባልታወቀ ገንዘብ ቤት ገንብቷል ተብለው ለቀረቡብኝ ክሶች አስፈላጊውን መረጃዎችን አቅርቤ ፍርድ ቤት ነጻ ብሎኛል። ተከሰው ሲታሰሩ እኮ ከደኅንነት መስርያ ቤቱ ለቀው ነበርና በሚታወቅ የሥራ ባህሪ ምክንያት ነው መከላከል ያልፈለግሁት ያሉት አይጋጭም? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የጠብመንጃውና የሽጉጡ ጉዳይን ለማለት? አዎ አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ ለምን ሽጉጥና ጠብመንጃ እንደያዝኩ፣ ለምን መኪና እንዳሰማራሁ ለማብራራት የሥራው ባህሪና ዲሲፕሊን አይፈቅድልኝም። ሲታሰሩ ግን የትግራይ ልማት ማኅበር የቦርድ ሊቀ መንበር ነበሩ አይደል ?… አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የትግራይ ልማት ማኅበርን ሥራ እሰራ የነበረው በተደራቢነት እንጂ በቋሚነት አልነበረም። ከመታሰሬ ከሁለት ወር ገደማ በፊት ከሥራ ኃላፊነቴ እንደተነሳሁና ሌላ ሥራ ምድባ እየተጠባበኩ ሳለሁ ነበር የታሰርኩት። የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ኃላፊ የነበሩትን አቶ ጌታቸው አሰፋን እንዴት ይገልጿቸዋል? በመካከላችሁስ ምን አይነት ግንኙነት ነበረ? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የነበረው ኃላፊነትና የሥራ ባህሪ ምን እንደነበር ይታወቃል። እንደዚህ አይነት የሥራ ባህሪ ያለውን ተቋም ይመራ የነበረን ሰው ሥራው በሚድያ ወጥቶ መገምገም ፍትሐዊ ነው ብዬ አላምንም። በተጨማሪ ደግሞ እኔ በምሰጠው አስተያየት ላይ ምላሽ በማይሰጥበት ሁኔታ፤ ለዚያውም በዚህ ጊዜ መናገሩ ደግሞ አስፈላጊ አይደለም ባይ ነኝ። በአሁኑ ወቅት የት ነው ያሉት? ምንስ እየሰሩ ነው? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ የማስተማር ፍላጎት ስለነበረኝ ከዚህ በፊት ከሥራዬ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ አስተምር ነበር። የአክሱም ዩኒቨርስቲ መምህራንን ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተወዳድሬ በፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት ክፍል እያስተማርኩኝ ነው። ከእስር ቤት እንደወጡ በቀጥታ ወደ ትግራይ ነበር የሄዱት፤ በዚህም የማዕከላዊው መንግሥት 'ሰላይ' ሆነው እንደሄዱ ይወራ ነበር፤ በዚህ ላይ ምላሽዎ ምንድን ነው? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ ይህ እንኳን ድካም ነው። እንደተባለውም ወሬ ነው ሊሆን የሚችለው፤ ሆን ተብሎ የተወራም ሊሆን ይችላል። ከድንቁርና የሚመነጭ ወሬ ስለሆነ በዚህ ላይ ጊዜያችንን ባናጠፋ ጥሩ ነው። እንደቀድሞ የአገሪቱ የመረጃና ደኅንነት ሹም አሁን ያለውን ተቋም እንዴት ትገመግመዋለህ? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ እውነት ለመናገር መረጃው የለኝም። ምን ዓይነት ፈተናዎች እየገጠሟቸው ነው? እነዚያን ፈተናዎች ቀድመው እየደረሱባቸው ነው ወይ? እንዴት አድርገውስ በአነስተኛ ዋጋ እየመከቷቸው ነው? የሚሉ መረጃዎች ስለሌሉኝ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ለማውራት ይከብደኛል። ወቅታዊው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ የማይገመትና እጅግ የተወሳሰበ እንደሆነ ይነገራል፤ በዚህ ላይ አስተያየትዎ ምንድን ነው? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በእኔ እምነት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተገማች [ፕሪዲክተብል] ነው ባይ ነኝ። ተሳስቼ ልሆን ይችላል፤ ግን በነበረኝ የሥራ አጋጣሚ አገሪቷን አውቃታለሁ የሚል እምነት አለኝ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከ1983 ዓ.ም በኋላ ከስር መሰረቱ ተቀይሯል። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር ጀምረዋል። የራሳቸውን ሀብት በራሳቸው ማስተዳደር ጀምረዋል። በራሳቸው ፖለቲካዊና ማኅበረ ኢኮኖሚ ጉዳይ መወሰን የጀመሩበት ሁኔታ ነው ያለው። አንዳንድ የፖለቲካ ሊሂቃን ካልሆኑ በስተቀር አብዛኛው ሕዝብ በራሱ ጉዳይ ላይ ብቻ የተጠመደ ነው። • የተማሪዎቹ መታገት ከተሰማ 90 ቀናት አለፉ በአሁኑ ወቅት አንዱን ብሔር በሌላኛው ብሔር ላይ ልታነሳሳው አትችልም። ሰለዚህ በዚህ ጉዳይ መሰረታዊ ለውጥ አለ ብዬ ነው እማምነው። ለምሳሌ የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ የወሰድን እንደሆነ ታሪካዊ በደል ደርሶብናል፣ በብሔርተኛ ልጆቻችን ነው መተዳደር የምንፈልገው፣ ከተፈጥሮ ሀብታችን ተጠቃሚዎች አይደለንም፣ ቋንቋችን በሚፈለገው ደረጃ አላደገም የሚሉ ፍትሀዊ ጥያቄዎች ነው የሚያነሳው እንጂ የትግራይ እና አማራ ጉዳይ ጉዳዩ አይደለም። የአማራ ህዝብ ጥያቄም የልማት፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ናቸው። እንደ አጋጣሚ ከትግራይ ሕዝብ ቀጥሎ አውቀዋለሁኝ የምለው ሕዝብ የአማራን ሕዝብ ነው። የትግራይ ጥያቄም ተመሳሳይ ነው። ከዚህ በኋላ ሕገ መንግሥታዊ ፌደራላዊ ሥርዓቱ ልታጎለብተው ካልሆነ በስተቀር ልትቀይረው አትችልም። ስለዚህ የኢትዮጵያ ፖለቲካ 'ፕሪዲክተብል' ነው ባይ ነኝ። በቅርቡ ከህወሓት እውቅና አግኝተዋል፤ ይህ ማለት አሁንም የፓርቲው አባል ነዎት ማለትት ነው? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ እውቅናው ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለብዙ የቀድሞ ተጋዮች የተሰጠ ነበር። እኔ በህይወት እስካለሁኝ ህወሓት ነኝ። ህወሓት 'ዳይናሚክ' እንዲሆን ነው እምፈልገው። ደግሞ ተራማጅ ድርጅት እንደሆነ ነው የማምነው። ተራማጅ እንዲሆን ያደረገው ግን የሕዝቡ ንቃተ ህሊና ነው። አንዳንድ ሰዎች ህወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ አይደሉም ሲሉ እሰማለሁኝ እንደ እኔ ግን አንድ ናቸው ባይ ነኝ። በትግራይ ብዙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ባሉበት ሁኔታ ሕዝቡና ህወሓት አንድ ናቸው ማለት ተገቢ ነው ይላሉ? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በፖለቲካዊ መነጽር ብቻ ካየነው ህወሓት ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅት ነው። ቢሆንም የትግራይ ሕዝብ የህወሓት ፖለቲካዊና ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ስትራቴጂዎችን የእራሱ አድርጓቸዋል። ይህ በጥናትም ሊረጋገጥ የሚቻል ነገር ነው። የትግራይ ሕዝብን ፖለቲካዊ እምነቱን ብትጠይቀው የህወሓትን ንድፈ ሀሳቦች በይበልጥ ነው የሚያብራራልህ። ታዲያ ይህንን ሀሳብ የሚቃወሙ ሰዎች የሉም ማለት ግን አይደለም። የትግራይ ሕዝብና ህወሓት አንድ ናቸው የሚለው ሀሳብ ከህወሓት የተሻለ አማራጭ ለትግራይ ህዝብ ይዘናል የሚሉ ድርጅቶችን ማፈን አይሆንም? ሀሳቡስ ለሕዝቡ ጠቃሚ ነው? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ በትግራይ ሁሉም ዓይነት ሀሳብና ማኅበራት በነጻ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አምናለሁ። የተለይ የፖለቲካ አማራጭ ያላቸው ሰዎች በነጻነት መደረጃት አለባቸው። አንዳች ተጽዕኖ እና ገደብ ሊደረግባቸው አይገባም። እነዚህ መሰረታዊ የዴሞክራሲ ጭላንጭሎች ስለሆኑ ሊሰመረበት ይገባል። የእኔ ሀሳብ ግን ህወሓት የምትመራባቸው ሀሳቦች በአብዛኛው ሕዝብ ተቀባይነት አላቸው ብቻ ሳይሆን በሕዝቡ ዘንድ የሰረጹ ናቸው ብዬ ነው እማምነው። ለዚህም ነው ከድሮ ጀምሮ ህወሓት እንቅፋት ሲገጥማት ሕዝቡ ተረባርቦ የሚያድናት። • የካራማራው ጦርነት ሲታወስ ይህ ማለት ግን ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችና ሀሳቦች መምጣት የለባቸውም ማለት አይደለም። እንደውም ህወሓት ተራማጅ ልትሆን የምትችለው ሌሎች አማራጭ ሀሳቦች ሲመጡ ነው ብዬ ነው የማምነው። በቀጣይነት በመምህርነቱ ይቀጥላሉ ወይስ ወደ ፖለቲካው ይመለሳሉ? አቶ ወልደሥላሴ ወልደሚካኤል፡ አላውቅም፤ ግን ማስተማር በጣም ይመቸኛል። ከታች ያለውን ፖለቲካ ለመረዳት መንግሥታዊ ኃላፊነት ይዞ ሳይሆን በአካዳሚክ ተቋማት ውስጥ ጥናት እያካሄዱ ሲሆን ይበልጥ ጠቃሚ ነው። ለአሁኑ ትውልድ በአካዲሚክ ተቋማት ሆኜ የራሴን ተሞክሮ እያስተላለፍኩኝ አገሩ ራሱን እንዲያስተዳድር በማድረግ ረገድ የምሰራ ይመስለኛል።
news-43992671
https://www.bbc.com/amharic/news-43992671
የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት 20ኛ ዓመት - መቋጫ ያላገኘ ፍጥጫ
የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦርነት የተጀመረበት ሃያኛ ዓመት የፊታችን እሁድ ሚያዝያ 28 ቀን 2010 ዓ.ም ነው። የሁለቱ ሃገራት ጦርነት ሲታሰብ ጦርነቱ እንዴት ተጀመረና ተደመደመ ከሚለው ባሻገር ሌሎች በርካታ ነገሮች ይነሳሉ።
የጦርነቱ መንስኤና ጦርነቱ ያስከተለው የሰው ህይወት ጥፋት ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ኪሳራን የሚመለከቱ ጥያቄዎችም አሉ። ይህ ደግሞ ዛሬ አገራቱ ካሉበት እውነታ ጋር በብዙ መልኩ ይገናኛል። አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኤርትራ ያቀረቡት የሰላም ጥሪን ጨምሮ የአገራቱ የዛሬ ሁለንተናዊ ግንኙነት ከጦርነቱ ጋር ይገናኛል። አስመራን በትዝታ ማቲዎስ ገብረ ህይወት የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳለ ነው የኢትዮጵያና ኤርትራ ግጭትን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያን ከኤርትራ እንዲወጡ ሲደረግ ቤተሰቦቹ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱት። ወላጆቹ አስመራ ውስጥ ለሰላሳ ዓመታት ኖረዋል። እሱን ጨምሮ ስድስቱ ልጆቻቸውም ተወልደው ያደጉት አስመራ ካምፖቦሎ የሚባል ሰፈር ነበር። የደረሰው ማህበራዊ ቀውስ ሲነሳ የእናት ከልጇ፣ የባል ከሚስቱ፣ በአጠቃላይ አስከፊ የቤተሰብ መለያየት ይታወሳል። ኑሯችን ህይወታችን ኤርትራ ነው ያሉ ኢትዮጵያዊን ለዘመናት ረግጠው ወደ ማያውቋት ኢትዮጵያ እንዲሄዱ ሲደረግ የእኔ ካሉት ነገር የመነቀል ያህል ስለነበር ህይወትን እንደገና ከዜሮ ለመጀመር ተገድደዋል። በተመሳሳይ ኑሯችን ቤታችን ኢትዮጵያ ብለው ለነበረ ኤርትራዊያንም መፈናቀል ተመሳሳይ አስከፊ የህይወት ፅዋን እንዲጋቱ ግድ ብሏል። ቤተሰብ ተበትኗል፣ ያፈሩት ሃብት ንብረት ወደ ኋላ ቀርቷል። ለዘመናት የገነቡት ማህበራዊ ህይወት ፈርሷል። በእነማቲዎስ ቤተሰብም የሆነው ይኸው ነው። ታላቅ ወንድማቸው ቀድሞ ሲመጣ እንደ እድል ሆኖ እሱና ቀሪ የቤተሰቡ አባል በ30ኛ ዙር ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል። ያረፉት አዲግራት ከሚገኙ አክስታቸው ጋር የነበረ ሲሆን ለወራት እዚያ እንደቆዩ ማቲዎስ ያስታውሳል። "ሁሉም ነገር ከባድ ነበር። ጦርነቱም ወደ መጠናቀቁ ነበር። ትምህርታችንን ቀድመን ነው ያቋረጥነው። የተወሰነ ንብረታችንን ለመሸጥ ሞከርን። ኑሮ እንደ አዲስ ነው የጀመርነው። ሁሉም ነገር አዲስ ነበር አዲግራት ውስጥ ይነገር የነበረው ትግርኛ በተወሰነ መልኩ የተለየ ስለሆነ ቋንቋ እንኳ ችግር ሆኖብን ነበር" ይላል። የዛሬውን የኢትዮጵያና የኤርትራ እውነታ እንዲሁም በብዙ መልኩ የተሳሰረው የሁለቱ ሃገራት ህዝብ መለያየትን ሲያስብ እንደሚበሰጭ፤ ስለ ጉዳዩ ማውራት እንኳ እንደሚከብደው ማቲዎስ ይናገራል። አስመራ አብረውት ካደጉና ዛሬ የተለያየ አገር ከሚገኙ ኤርትራዊ ጓደኞቹ ጋር በማህበራዊ ድረ-ገፅ ሲገናኙም ስሜታቸውን የሚረብሽ አንዳች ነገር እንዳለ ይገልፃል። "ያሳደገችኝ አያቴ የምትኖረው ኤርትራ ነበር። በቅርቡ የሞተቸውም እዚያው ነው። እኛ እዚህ ነን። መለያየት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ በዚህ ማየት ይቻላል"ይላል በሃዘን። የአዲስ አበባ ናፍቆት ኤርትራዊ በመሆናቸው ከነቤተሰቡ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ የተደረገውና የማቲዎስ እጣ የደረሰው ወጣት ስሙ እንዲገለፅ አልፈለገም። በአሁኑ ወቅት የሚገኘው በስደት እንግሊዝ ሃገር ሲሆን እሱም ሆነ መላ ቤተሰቡ በብዙ ፈታና ውስጥ ማለፋቸውን ይናገራል። ከኢትዮጵያ የወጡት የአስራ ስድስት ዓመት ታዳጊ ሳለ ነበር። "በተለያየ ጊዜ ነው የወጣነው። ግማሹ ቤተሰብ ታሰረ፤ ግማሹ በመጀመሪያ ዙር ሄደ። መጨረሻ ላይ እኔና ታናሽ እህቴ ቀረን" በማለት ወደ ኤርትራ እንዲሄዱ የተደረገበት መንገድ ከባድ እንደነበር ያስታውሳል። እሱ እንደሚለው አንዳንድ ፖሊሶች ቀና አመለካከት የነበራቸው ቢሆንም የጥላቻ ስሜት የነበራቸውም ነበሩ። በዚህ ምክንያትም ተደብድቧል። እሱና ታናሽ እህቱ በእድሜ ትንሽ ስለነበሩ የቤተሰቦቻቸውን ንብረት መሸጥ ወይም ሌሎች ኤርትራዊያን እንዳደረጉት ውክልና ወይም አደራ በመስጠት ነገሩን መልክ ማስያዝ አልቻሉም ነበር። "ከባድና አስቸጋሪ ጊዜ ነበር። ቀላል አይደለም ጠባሳው በህይወታችን እስከዛሬ አለ" ቢልም ዛሬም ኢትዮጵያን እንዲሁም የልጅነት ጓደኞቹን ይናፍቃል። "ተወልጄ ያደግኩበት አገር ስለሆነ ለኢትዮጵያዊያንና ለኤርትራዊያን የሚሰማኝ አንድ አይነት ነገር ነው። የልጅነት ጓደኖቼን እናፍቃለው።ሁሌም በማህበራዊ ሚዲያ ተገናኝተን ስናወራ ሰላም ተፈጥሮ የምንገናኝበት ቀን ቢመጣ ብዬ አስባለሁ" በማለት የመለየትን ከባድነት ይገልፃል። ኤርትራና ኢትዮጵያ በጦርነቱ ዋዜማ የኤርትራን ነፃነት ተከትሎ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ጥሩ ግንኙነት ይኖራል የሚል ግምት በመንግሥት በኩል እንደነበርና ይህን ታሳቢ ያደረጉ ነገሮችም ይከናወኑ እንደነበር በጦርነቱ ወቅት የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዣዥ የነበሩት ሜ/ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት ያስታውሳሉ። እሳቤው ይህ ስለነበርም ድንበር ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ወታደር ቁጥር በጣም ትንሽና ድንበር ላይ ጦር አለ በሚያስብል ደረጃ እንዳልነበርም ያስታውሳሉ። "ጥሩ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ትብብር ይኖረናል ብለን አስበን ነበር። ነገር ግን የኤርትራ መንግሥት የድንበር ጉዳይን ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያን ወረረ። የድንበር ጉዳይን ለማስፈፀም ኮሚሽን ተቋቁሞ ነበር" የሚሉት ጀነራል አበበ እውነተኛው ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ነበር ይላሉ። እሳቸው እንደሚሉት የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጥገኛ የመሆን ፍላጎትና አቀራረብ የነበረው ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ይህ እንዲሆን አልፈቀደም። በተለይም ኤርትራ የራሷን ገንዘብ ናቅፋ ማተሟን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ግብይት በዶላር እንዲሆን መወሰኗ፤ በኤርትራ በኩል ኢትዮጵያ ኤርትራ ላይ እንዳደረሰቸው ትልቅ የኢኮኖሚ ኪሳራ መታየቱም ቁልፍ ነገር ነው ይላሉ ጀነራሉ። የወጣቱ ወኔና የድል ብስራት አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ ከተሞችና ክልሎች የአገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ወጣቱ በወኔ ሆ ብሎ ነበር የዘመተው። ለምሳሌ በአዲስ አበባ በየአካባቢው በየሰፈሩ ወጣቶች ወደ ጦርነት ወደ እሳት ሳይሆን ወደ የደስታ ቦታ የሚሄዱ በሚመስል መልኩ መዝመታቸው ከብዙ ሰዎች የሚያስታውሱት ነው። ግንባር ላይም ወጣቱ በወኔ የተጠመደ ፈንጂ ላይ መስዋዕት እየሆነ ለሌላው መንገድ ይከፍት እንደነበር በተለያዩ የጦር ግንባሮች ለአምስት ወራት የቆየው ጋዜጠኛ መንግሥቱ አበበ ይናገራል። "ለመዝመት በወሰንኩበት ወቅት 18 ዓመት ቢሆነኝ ነው። በአይደር ት/ቤት ላይ የቦንብ ድብደባ የተጎዱ ህፃናትን የሚመለከት ዝግጅት ይቀርብ ነበር። ያንን ስመለከት በተሰማኝ ስሜት ነው ለመዝመት የወሰንኩት" ይላል በ19ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዘምቶ የነበረው ኤፍራታ። አስራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ መከላከያን ተቀላቅሎ ከዚያም በኋላ በጦርነቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባል ሆኖ የዘመተ ጓደኛው ታሪክ የሁለቱ ሃገራት ጦርነት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ከሚያስታውሱት ነገሮች አንዱ ነው። "ጦርነቱ ከመጀመሩ ሦስት ወይም አራት ወራት በፊት ነው መከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀለው (ቤተሰቦቹ ኤርትራዊያን ነበሩ)፣ ከጊዜያት በኋላ ጦርነቱ ተጀምሮ እሱ ዛላምበሳ ተመደበ። ከወራት በኋላ ጦርነቱ ተጀምሮ ኤርትራዊያን ወደ ሀገራቸው ሲባረሩ የእኔ ጓደኛ ግዳጅ ላይ ሆኖ ዛላምበሳ ላይ አገኛቸው። መላ ቤተሰቡን በዚያ ሁኔታ አግኝቶ ሲላቀስ ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዜያት ደግሞ ከኢትዮጵያ ጦር በኩል በጥርጣሬ ሲታይ የደረሰበትን ጭንቀት እያሰብኩ በጣም አዝን ነበር" በማለት ጓደኛው የነበረበትን ሁኔታ ያስታውሳል። ዛሬ ላይ ቆሞ ወደ ኋላ ሲመለከት ጦርነቱ ለሱ ትርጉም አልባ ነው። "በጣም ይቆጨኛል። ለእኔ አላስፈላጊ እና ምንም ውጤት ያልመጣበት ጦርነት ነው" ይላል። «ባድመን መጀመሪያ ከያዝን በኋላ ልቀቁ ተብሎ ስንለቅ፤ እኔ ለሁለተኛ ጊዜ ተመትቼ ሆስፒታል ውስጥ ነበርኩ። በሆስፒታሉ የነበሩ ቁስለኞች ይሄን ሁሉ መስዋዕትነት ለምን አስፈለገ? በሚል ቅሬታ ያሰሙ ነበር። የኋላ ኋላ አመራሮቻቸውን እየላኩ አረጋጉት እንጂ ወታደሩ የሞቱ ጓዶቹን እያሰበ ያለቅስ ነበር።" ጋዜጠኞች በጦር ግንባር አንጋፋው ጋዜጠኛ መንግሥቱ አበበ ጦርነቱን ለመዘገብ የጦር ግንባሮች ላይ ከተገኙ ጋዜጠኞች አንዱ ነበር። የጦርነት ዘጋቢ የመሆን ፍላጎት የነበረው ቢሆንም በወቅቱ ይሰራበት በነበረው ፕሬስ ድርጅት በየሁለት ወር እየተቀያየሩ ወደ ግንባር ለዘገባ መሄድ ግዴታ እንደነበርና እሱም በዚህ መልኩ እንደሄደ ይናገራል። ለሁለት ወር ተብሎ ቢሄድም አምስት ወር ቆይቷል። ነገር ግን እሱን ጨምሮ ግንባር ላይ የተገኙ ጋዜጠኞች ሁሉ ስለ ጦርነቱ እንዲዘግቡ እንዳልተፈቀደላቸው መንግሥቱ ያስታውሳል። ይልቁንም ይዘግቡ የነበረው ሕዝቡ ለሠራዊቱ ስለሚያደርገው የስንቅና ሌሎች ድጋፎች ነበር። "እኛ ጦርነቱን የማንዘግበው ጦርነቱን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚወጡት በመንግሥት ቃል አቀባይ ቢሮ በኩል ነበር" ይላል መንግሥቱ። ምንም እንኳ የጦርነት ዘጋቢ የመሆን ፍላጎት የነበረው ቢሆንም ግምቱ ቦታው ላይ ሆኖ ካገኘው ጋር በመለያየቱ እንዲሁም ጦርነቱ በተጀመረ እለት አብረውት የነበሩ ሦስት ጋዜጠኞች ህልፈት ፍርሃት እንዳሳደረበት ይናገራል። ከሟች ጋዜጠኞች አንደኛው ከወራት በኋላ ሊያገባ እንደነበር መንግሥቱ በሃዘን ያስታውሳል። ባድመን ጨምሮ በተለያዩ ጦር ግንባሮች ላይ የነበረው መንግሥቱ ስምንት ጋዜጠኞች በፈንጂ ፍንጣሪ ሲቆስሉ ሦስት ጋዜጠኞች መሞታቸውን ያስታውሳል። "ስህተቶች" ከ20 ዓመት በኋላ ጦርነቱን ወደ ኋላ ሄደው ሲመለከቱት እንዲህ ወይም እንደዚያ ባይሆን የሚሉት ነገር እንዳለ የተጠየቁት ሜ/ጀነራል አበበ ሲመልሱ "አንድ ጎረቤትህ ልጅና ሚስትህን ሊነጥቅ ሲመጣ ራስን መከላከል የግድ ነው። ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ መንግሥት ወራሪን መከላከል ግዴታና ሃላፊነቱም ነበር። በጦርነቱ አካሄድ በተለይም መጨረሻው ትክክል አልነበረም ብዬ አምናለው" የሚል መልስ ሰጥተዋል። እሳቸው እንደሚሉት ጦርነቱ የኤርትራ መንግሥት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም ለኢትዮጵያ ድንበር ስጋት እንደማይሆን በሚያረጋግጥ መልኩ መደምደም ነበረበት። መጀመሪያም የነበረው እቅድ ይኸው ነበር። ጦርነቱ በታቀደው መልኩ ተደምድሞ ቢሆን ኖሮ ሁለቱ አገራት የዛሬው ሰላምም ጦርነትም የሌለበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አይወድቁም ነበር ይላሉ። ከጦርነቱ በኋላ ሁለቱ አገራት አልጀርስ ላይ ያደረጉት ስምምነት ለእሳቸው ሁለተኛው ስህተት ነው። ''ምክንያቱም የአልጀርስ ስምምነት የኢትዮጵያን ፍላጎት አሳልፎ የሰጠ፤ ኢትዮጵያ ጦርነቱን አሸንፋ ነገር ግን የተሸናፊ ሚና ይዛ ያደረገችው ስምምነት ነው'' በማለት ይጠቅሳሉ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንዲሁም ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር ሰላም ለማውረድ ፍላጎት እንዳላቸው አሳይተው ነበር። አቶ ኃይለማሪያም በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም ለማስፈን ሲሉ አስመራ ድረስ ሊሄዱ ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውም ይታወሳል። ይህ የኢትዮጵያ መሪዎች የሰላም ጥሪ ተገቢ እንደሆነ ሜ/ጀነራል አበበ ይናገራሉ። የኤርትራ ህዝብ የመረጠውን ነፃነት ማክበር እንዲሁም የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያን እስካልነካ ድረስ የሰላም ስምምነት ማድረጉም አስፈላጊ ነው ይላሉ። የሰላም ጥሪው እንዳለ ጎን ለጎን ግን ጥንቃቄ የሚያሻው ነገር አለ ይላሉ። እንደ እሳቸው እምነት የኤርትራ መንግሥት አሁን እያደረገ ያለውንና ፍላጎቱን በጥንቃቄ ሳይመለከቱ ሰላም መፈለግ ብቻውን የሚያዋጣ አይደለም ይላሉ።
51728305
https://www.bbc.com/amharic/51728305
እሽኮኮ ተብሎ ማስታወቂያ ከመስራት ወደ ቴሌቭዥን፡ የውብሸት ወርቃለማሁ የማስታወቂያ ሕይወት
ውብሸት ወርቃለማሁ በማስታወቂያ ሥራ፣ በቴአትር ጽሑፍ፣ በትወና እንዲሁም በሌሎችም የኪነ ጥበብ ዘርፎች ገናና ስም አትርፈዋል። በርካቶች ጋሽ ውብሸት ሲሉ በአክብሮትና በፍቅር ይጠሯቸዋል።
'አቢሲኒያ የትጉሀን መናኸሪያ'. . . ጋሽ ውብሸት በአስገምጋሚ ድምፃቸው ከሚታወሱባቸው ማስታወቂያዎች መካከል ይጠቀሳል። የማስታወቂያ ዘርፍን በማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን በማዘመን እንዲሁም የበርካቶች እንጀራ በማድረግም ፈር ቀዳጅ ናቸው። የሙያ አጋራቸው እንዲሁም ወዳጃቸው አያልነህ ሙላት፤ "ውብሸት ወደ ማስታወቂያ የገባው ገና ቄስ ትምህርት ቤት ሳይገባ ነበር" ይላሉ። አቶ ውብሸት ልጅ ሳሉ በትውልድ ቀያቸው 'በባህላዊ መንገድ' ማስታወቂያ ይነግሩ ነበር። አንድ የታወቀ ትልቅ ሰውን 'እሽኮኮ በለኝ' አሉና ሰውየው ትከሻ ላይ ሆነው ይሄን ያህል ጤፍ መጥቷል፣ ይሄን ያህል በቆሎ ተገኝቷል፣ አትክልትም መጥቶላችኋልና እዚህ ቦታ ግዙ እያሉ ያስተዋውቁ ነበር። "ቄስ ትምህርት ቤት ገብቶ መጻፍ ሲጀምር ሙክት፣ በግ፣ የት እንዳለ ቀለም በጥብጦ ፣ እየጻፈ ትልልቅ ዛፍ ላይ እየሰቀለ ማስታወቂያ ይሰራ ነበር' ሲሉ አያልነህ ያወሳሉ። ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የተቀጠሩት ብሔራዊ ሎተሪ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የብሔራዊ ሎተሪን ማስታወቂያ ሲሠሩ፤ አህያ ላይ ገለባ የሞላው ማዳበሪያ ጭነው፣ ብር ለጥፈውበት ነበር። ከቸርችል ጎዳና ወደ ታች እየወረዱ 'ሎተሪ ብትገዙ ይህን ያህል ብር ታገኛላችሁ' እያሉ ያስተዋውቁ ነበር። • ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ያናገሩና ያነጋገሩ ድርሰቶቹ • ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር "ደፋር ጸሐፊ ነበር" አያልነህ እንደሚሉት፤ ይህን ማስታወቂያ ያየው ፊሊፕስ አቶ ውብሸትን የቀጠራቸው ወዲያው ነበር። ከዚያ በኋላ እጅግ በርካታ ማስታወቂያዎች ሠርተዋል። "የማስታወቂያ ሙያ እንዲታወቅ ያደረገ ታላቅ የኢትዮጵያ ባለውለታ ነው" ሲሉም ይገልጿቸዋል። ጋሽ ውብሸት ከአብነት ትምህርት ቤት ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ መደበኛ ትምህርት ጀመሩ። ከትምህርት ቤት እንደወጡ መዋያቸው አገር ፍቅር ቴአትር ቤት ነበር። የትወና እና የጸሐፌ ተውኔትነት ሕይወታቸውን 'ሀ' ብለው የጀመሩት በዚያው ቴአትር ቤት እንደሆነም አያልነህ ያስታውሳሉ። ያኔ ከቀደምቶቹና ታላላቆቹ እነ ኢዩኤል ዩሐንስ፣ አውላቸው ደጀኔ፣ ጸጋዬ ገብረመድሕን፣ ወጋየሁ ንጋቱ. . . ጋር አብረው ይሠሩ ነበር። ጸሐፌ ተውኔት አያልነህ፤ ጋሽ ውብሸት የተዋጣላቸው ተዋናይና ጸሐፊ እንደነበሩ ይናገራሉ። "ሲተውን መምሰል ሳይሆን መሆን የሚችል ሰው ነበር። ንጉሠ ነገሥቱን ሆኖ ሲጫወት ራሳቸው ንጉሠ ነገሥት [ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ] በጣም ተገርመው ነበር። እንደኔ ለመሆን የሞከርከው በጣም ጥሩ ነው ብለውት ነበር። ውብሸት የሚጽፈው እንደዛሬው ይዘት በሌለው ኮሜዲ ሰውን አስቆ ለመለያየት ሳይሆን፤ መሠረታዊነት የኮሜዲን ሥርዓት ጠብቆ ነው።"ይላሉ ውብሸት እና አያልነህ አጋፔ ቅዱስ ሚካኤል የተባለ የበጎ አድራጎት ማኅበር አባል ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት ለአቅመ ደካማ ቤተክርስቲያኖች ድጋፍ ያደረገው ይህ የጽዋ ማኅበር የሚመራው በአቶ ውብሸት ነበር። "በየወሩ እንገናኝ ነበር። ማኀበሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ያስቻለው ውብሸት ነው። ለአገሩ ያለው ፍቅር፣ በኢትዮጵያዊነቱ ያለው ኩራት ልነግርሽ አልችልም. . . " አቶ ውብሸት በወሎ ረሀብ፣ በድሬዳዋ ጎርፍ ወቅትም ገንዘብ በማሰባሰብ እና ከቀይ መስቀል ጋር በመሥራትም ይታወሳሉ። "ማስታወቂያን 'ሀ' ብሎ ያስተማረኝ ጋሽ ውብሸት ነው" ሙሉዓለም ታደሠ ሙሉዓለም ታደሠ ብሔራዊ ቴአትር የተቀጠረችው በ1984 ዓ. ም. ነበር። ያኔ ተዋናይት ለመሆን ቴአትር ቤቱን ስትቀላቀል፤ አቶ ውብሸት ግን ለማስታወቂያ ሠሪነት ጭምርም አጯት። ወቅቱን "የሕይወት አቅጣጫዬ የተቀየበረበት ነው" ስትል ትገልጸዋለች። ጋሽ ውብሸት ማስታወቂያ ሲሠሩ ታውቃቸው ነበር። በከብት ወይም በሰው ትከሻ ላይ ቆመው 'ስማ፤ የሰማህ ላልሰማ አሰማ'፤ ይህ ሰንጋ ጥሩ ነው' ብለው ማስታወቂያ ይሠሩ እንደነበርም ታስታውሳለች። በድምፅ የምታውቀውን አንጋፋ ሰው በአካል ስታይ "የበለጠ ገዝፎ ታየኝ" ትላለች። በወቅቱ እንኳን ስለ ማስታወቂያ ይቅርና ስለ ቴአትርም እምብዛም እውቀት እንዳልነበራት ሙሉዓለም ታስታውሳለች። ውብሸትን "ማስታወቂያን 'ሀ' ብሎ ያስተማረኝ የሙያ አባቴ ነው" የምትለውም ለዚሁ ነው። በቴአትር ቤቱ ተቀጥራ ገና በአንድም ቴአትር ላይ ሳትተውን ውብሸት የብሔራዊ ሎተሪ ማስታወቂያ እንድትሠራ ጋበዟት። • ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተ መንግሥት የሄደው ደራሲ • የኤልያስ መልካ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኞ ይፈፀማል ሙሉዓለም የምትተውነው ሙሽራ ሆና ነበር። ሁሌም አጠገባቸው ያለን ሰው ፈገግ ማሰኘት የማይሳናቸው ጋሽ ውብሸት ማስታወቂያውን ሲያዘጋጁ ሙሉዓለምን እያሳሳቋት እንደነበር ታወሳለች። 'ዛሬ ባል የሌላት ሙሽራ ደግሼ ልድር ነው' እያሉ ይቀልዱ እንደነበር ታስታውሳለች። ማስታወቂያውን ለመቅረጽ ወደ መናፈሻ ሲሄዱ (ሙሉዓለም ቬሎ እንደለበሰች) ትራፊክ ፖሊስ መኪኖችን አስቁሞ ሲያዩ፤ 'ሙሽራ ክቡር ነው፤ እባክህ አሳልፈን' ብለው ማለፋቸውም አትዘነጋም። በማስታወቂያው ላይ ሙሽራዋ እንደ ሎተሪ ሆና 'እድል የደረሰው ይውሰደኝ' ትል ነበር። ማስታወቂያው ሦስት ጊዜ እንደተላለፈ ግን ከቤተ ክህነት ከባድ ወቀሳ ስለገጠመው እንዲቋረጥ ተወሰነ። ሁለተኛው የሎተሪ ማስታወቂያ ሙሉዓለም ሎተሪ እንደደረሳት ሰው ሆና በጠዋት ተነስታ ዘለግ ላለ ደቂቃ ስትስቅ ያሳያል። ያኔ መንገድ ላይ 'ሳቅ ሳቅ ይለኛል' 'ሳቂልኝ' ትባል እንደነበር ታስታውሳለች። ከዛ በኋላ የአምቦ ማስታወቂያ [ግብዣ ያለ አምቦ ውሀ] እና የፊሊፕስ ማስታወቂያ እንዲሁም ሌሎችም በርካታ ሥራዎች ተከተሉ። "ድራማዊ የሆኑ ማስታወቂያዎችን በመሥራት ለኔና ለሠራዊት ፍቅሬ መነሻችን ጋሽ ውብሸት ነው" ትላለች ሙሉዓለም። ውብሸትን ሁሌም ከምታስታውስበት ነገር አንዱ ጀማሪ ማስታወቂያ ሠሪዎች የሚሰጡትን አስተያየት ለማድመጥ ዝግጁ በመሆናቸው ነው። "እንደ ታላቅነቱ አይደለም። በትህትና ዝቅ ብሎ ይቀርበናል። ምንም የማናውቀው ሰዎች እሱን እንከራከረዋለን። ሲከራከሩት ደግሞ ደስ ይለዋል" ሙሉዓለም ብሔራዊ ቴአትር የተቀጠረችው ከተስፋዬ ገብረሃና፣ ከሰለሞን ሙላት እና ከቴዎድሮስ ተስፋዬ ጋር ነበር። ያኔ ደመወዛቸው 230 ብር ነበር። ውብሸት 'ማስታወቂያ ጥበብ ነው፤ ከዛ ባሻገር ራሳችሁን፣ ኑሯችሁን ትደግፉበታላችሁ' ብለው ወደ ሙያው እንዳስገቧት ታስታውሳለች። ከዛ በኋላ ለዓመታት በዘርፉ ገናና ከሆኑ ባለሙያዎች እንዷ ሆና ዘልቃለች። አቶ ውብሸትንም እንዲህ ትገልጻቸዋለች። "በጣም አገሩን ይወዳል፤ ዓለምን ዞሯል፤ በየሄደበት ደግሞ ኢትዮጵያን ያስተዋውቅ ነበር። ጎርፍም ሌላም ችግር ቢከሰት ቀድሞ ደራሽ ነው። እኛ የሙያ ልጆቹ አንድ ነገር ቢደርስብን የምንደውለው እሱ ጋር ነው። ደከመኝ ሰለቸኝ ከአፉ አይወጣም።" "ጋሽ ውብሸት [ገና ሳያውቀኝ] አበባ ይዞልኝ ቢሮዬ መጥቷል" ሳምሶን ማሞ የማስታወቂያ ባለሙያው ሳምሶን ማሞ ከ25 ዓመታት በፊት የማስታወቂያ ድርጅቱን ሲከፍት ያልጠበቀው እንግዳ ቢሮውን አንኳኳ። ውብሸት ወርቃለማሁ እቅፍ አበባ ይዘው 'እንኳን ደስ አለህ' ሊሉት ቢሮው ተገኝተው ነበር። "ያኔ ጋሽ ውብሸት ሊያውቀኝ አይችልም። እኔ ገና ልጅ ጋዜጠኛ ነበርኩ። ጋሽ ውብሸት እኔጋ ሊመጣ ይችላል ብዬ በህልሜም አላስብም። እንኳን ደስ አላችሁ ብሎ ለኔና ለባለቤቴ አበባ ይዞልን መጣ። በአሁን ሰዓት በጋሽ ውብሸት ደረጃ እንደዚህ የሚያደርግ ሰው አለ ብለሽ ታስቢያለሽ? አንዳንድ ሰው ገበያዬን ነጠቀ ብሎ ሊያስብ ይችላል። ጋሽ ውብሸት ግን እንደዛ አይነት ሰው አይደለም።" ሳምሶን 'ፊሊፕስ የጥሩ እቃ ስም. . .' የሚለውን በሙሉቀን መለሰ ዘፈን የታጀበ ማስታወቂያ ከልጅነቱ ጀምሮ አጥንቶታል። በርካታ የውብሸት ሥራዎችንም ያደንቃል። ሳምሶን እንደሚለው፤ የማስታወቂያ ሙያ እንዲጀመር ብቻ ሳይሆን እንዲጎለብት በማድረግም የአቶ ውብሸት ሚና ቀላል አይደለም። "ባልሰለጠነ ዘመን ቀድሞ የሰለጠነ እና ራሱን የፈጠረ" ሲልም ይገልጻቸዋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ300 በላይ የማስታወቂያ ድርጅቶች ለመፈጠራቸው ምከንያቱ ጋሽ ውብሸት እንደሆነ ያስረዳል። ከሁለት አሰርታት በፊት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የአንድ ደቂቃ ማስታወቂያ ለማስተላለፍ 100 ብር ይከፈል ነበር (ዛሬ ከ15 እስከ 20 ሺህ ያስከፍላል)። በዘመኑ በቴሌቭዥን ማስታወቂያ የሚሠራለት ምርትና አገልግሎት ማንም የማይፈልገው እንደሆነ ይታመን ነበር። • "ፍቃዱ ተክለማርያም የሀገር ቅርስ ነው" • "ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ትምህርት ቤት ሆኖኛል" ደበበ እሸቱ "ማስታወቂያ ማስነገር እንደ ሀጢያት፣ ምርቱም እንደ ርካሽ ይቆጠር ነበር። ይህንን ብቻውን ነው የታገለው። ዛሬ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን የመሳሰሉት ከ100 ብር ተነስተው በአንድ ደቂቃ እስከ 25 ሺህ ብር እየተከፈለ፣ በዓመት ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እስከመሰብሰብ ደርሰዋል" ይላል ሳምሶን። አቶ ውብሸት የዓለም አቀፍ አስተዋዋቂዎች (ኢንተርናሽናል አድቨርታይዚንግ አሶሴሽን) አባል ሲሆኑ፤ በምዕራቡ አገራት ስለ ማስታወቂያ ሥራ ስልጠናዎችም ወስደዋል። በ82 ዓመታቸው የገበያ ድርሻቸው ሳይቀንስ፣ በድምፃቸው ማስታወቂያ በመሥራት መግፋታቸው ሳምሶንን ያስገርመዋል። "እኔ በ82 ዓመቴ ይህንን የማደርግ አይመስለኝም" ይላል። አያልነህ፣ ሙሉዓለምና ሳምሶን ስለ ጋሽ ውብሸት የሚናገሩት ተመሳሳይ ነገር አለ። ይህም አገር ወዳድ፣ ሀይማኖተኛ፣ አስታራቂ፣ በየትኛውም ቦታ (ባለሥልጣኖች የታደሟቸውና ከባድ የሚባል ርዕሰ ጉዳይ የተነሳባቸውን ጨምሮ) ቀልድ ጣል ማድረጋቸው ነው። ያለፈው ቅዳሜ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አንጋፋው ውብሸት ወርቃለማሁ ዛሬ በመስቀል አደባባይ ሽኝት እንደሚደረግላቸው የቀብር ሥነ ሥርዓቱ አስተባባሪ አያልነህ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
48313342
https://www.bbc.com/amharic/48313342
በደቡብ ሱዳን የምሽት ክለቦች ታገዱ
በደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ የሚገኙ የምሽት ክለቦች ሙሉ በሙሉ መታገዳቸውንና መጠጥ ቤቶች ላይ የሰአት እላፊ መጣሉን ቃል አቀባዩ ሜጀር ጀነራል ዳንኤል ጀስቲን ለቢቢሲ ኒውስ ደይ አሳውቀዋል።
" የምሽት ክለቦች ሙሉ በሙሉ እንዲዘጉ የተላለፈው ውሳኔ ተግባራዊ እየሆነ ነው። የከተማው ነዋሪዎች ለከተማው ምክር ቤት የምሽት ክለቦች እየረበሿቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲያማርሩ ነበር" ብለዋል። •"ማህበሩ የማያልፈው ቀይ መስመር የስራ ማቆም አድማ ነው"-ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት የጁባ አስተዳዳሪ አውግስቲኖ ጃዳላ ዋኒ በበኩላቸው ከሳምንት በፊት በፌስቡክ ባስተላለፉት መልዕክት "ያልተገቡ" ተግባራትን ለመከላከል የምሽት ክለቦች እንዲዘጉና በመጠጥ ቤቶችም የሰአት እላፊ አዋጅ እንዲተላለፍ መወሰኑን አሳውቀው ነበር። •የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ? በሰአት እላፊው አዋጅ መሰረት መጠጥ ቤቶች የሚሰሩበት ሰአት ከቀኑ ስምንት ሰአት እስከ ምሽቱ 1 ሰአት ድረስ ብቻ እንደሆነ ሱዳን ትሪቢውን ዘግቧል። •ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? ከዚህም በተጨማሪ በሆቴል መቆየት የሚፈልጉ ጥንዶች ባለትዳር መሆን የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጋብቻ ማስረጃ ሰርቲፊኬትም ሊያሳዩ እንደሚገባም ተደንግጓል።
news-55445099
https://www.bbc.com/amharic/news-55445099
ኮሮናቫይረስ ፡ “በ90 ዓመታችን ፍቅር ጀምረን የኮቪድ-19 ክትባት ተሰጠን”
ሊሊ አቦት እና ትሬቨር ሂስት የተዋወቁት ሲደንሱ ነው።
ሊሊ አቦት እና ትሬቨር ሂስት የተዋወቁት ሲደንሱ ነው ከ30 ዓመት በፊት ብራድፎርድ በተባለ የዳንሰኞች ስብስብ ውስጥ ነበር መጀመሪያ የተዋወቁት። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ክትባት ከተሰጣቸው ሰዎች መካከል እነዚህ በ90 ዓመታቸው የፍቅር ግንኙነት የጀመሩት ጥንዶች ይገኙበታል። ከ30 ዓመት በፊት ከተዋወቁ በኋላ ጥሩ ጓደኛሞች ሆኑ። ሊሊ ከቀድሞው ባለቤታቸው ዊልፍ ጋር፣ ትሬቨርም ከያኔው ባለቤታቸው ሪታ ጋር በየግዛቱ ይዞሩ ነበር። የትሬቨር ባለቤት ከስድስት ዓመት በፊት አረፉ። የሊሊ ባለቤትም ከ14 ዓመት በፊት በሞት ተለዩ። ትሬቨር እና ሊሊ ፍቅር የጀመሩት የትዳር አጋሮቻቸውን በሞት ከተነጠቁ በኋላ ነው። በዚህ ዓመት መባቻ ላይ ሁለቱም 90 ዓመት ሞላቸው። ጓደኞቻቸው ለምን አትጋቡም? እያሉ ይጠይቋቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። "ሁለታችንም ትዳር መስርተን ነበር። ስለዚህ መጋባት አንፈልግም አልኳቸው" ይላሉ ሊሊ። ትሬቨር የሦስት ልጆች አባት፣ ሊሊ ደግሞ የሁለት ልጆች እናት ናቸው። ሊሊ ትሬቨርን በስድስት ቀን በእድሜ ይበልጡታል። ሊሊ አያት፣ ትሬቨር ደግሞ ቅድመ አያት ሆነዋል። ኮሮናቫይረስ ከተከሰተ በኋላ ዩናይትድ ኪንግደም እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ጥላ ነበር። በዚያ ወቅት ሊሊ እና ትሬቨር በእግር ይንሸራሸሩ ነበር። አንድ ቀን ግን ሊሊ ወድቀው ጎናቸው ላይ ስብራት ገጠማቸው። ትሬቨር አብረዋቸው ለመኖር የወሰኑት ያኔ ነው። ሐሳቡን የትሬቨርም የሊሊም ልጆች ደግፈውታል። "መውደቄ አስፈርቶኝ ነበር። 'በየቀኑ ማታ ወደ ቤት ከምትሄድ አብረኸኝ ኑር' አልኩት። በጣም የምንጣጣም ሰዎች ስለሆንን አብሮ ለመኖር ተስማማን" ይላሉ ሊሊ። የኮሮናቫይረስ ክትባት በቅድሚያ የተሰጠው ለአረጋውያን እና ለጤና ባለሙያዎች ነው። 70 በመቶው ሕዝብ ክትባት ካገኘ የጋርዮሽ በሽታን የመከላከል አቅም (ኸርድ ኢሚውኒቲ) እንደሚዳብር ባለሙያዎች ይናገራሉ። ብራድፎርድ ውስጥ ክትባቱን ካገኙ መካከል ሊሊ እና ትሬቨር ይገኙበታል። ጥንዶቹ ሲከተቡ በቦታው የነበሩት ፕሮፌሰር ጆን ራይት ከዚህ ቀደም በኤችአይቪ፣ በኢቦላና በሌሎችም በሽታዎች ላይ ሠርተዋል። ብራድፎርድ ውስጥ ክትባቱን ካገኙ መካከል ሊሊ እና ትሬቨር ይገኙበታል አረጋውያን ለቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚጋለጡ በመጀመሪያ በ80ዎቹ እድሜ ክልል ያሉ ከዚያም በ70ዎቹ እድሜ ክልል ያሉ ክትባት እንደሚሰጣቸው ይናገራሉ። በአረጋውያን እንክብካቤ መስጫ የሚኖሩና የጤና ባለሙያዎችም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው መካከል ናቸው። እሳቸው በሚሠሩበት ሆስፒታል በየሳምንቱ 195 የፋይዘር ክትባት ብልቃጥ ይደርሳል። በየሳምንቱ 975 ሰዎች ይከትባሉ። በቀጣይ በየሳምንቱ ክትባት የሚሰጣቸውን ሰዎች ቁጥር ወደ 1,170 ከዚያም ወደ 2,340 የማሳደግ እቅድ አላቸው። "የማይከተቡ ሰዎች ሞኝ ናቸው" ሊሊ ዘጠኝ እህቶችና ወንድሞች አሏቸው። በ14 ዓመታቸው ከትምህርት ቤት ከወጡ በኋላ ልብስ ሰፊ ጋር ይሠራ የነበረውን ዊልፍ ተዋወቁ። በፍቅር ወድቀውም ትዳር መሠረቱ። እአአ በ1960ዎቹ የፈንጣጣ ወረርሽኝ ሲከሰት፤ እሳቸው በሚኖሩበት ከተማ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ክትባት እንደተሰጣቸው ያስታውሳሉ። "ያኔ ከባድ ጊዜ ነበር። ክትባት ግን ነገሩን አረጋጋው" ይላሉ። አሁንም የኮሮናቫይረስ ክትባት ሲወስዱ የፈንጣጣ ወረርሽኝ ጊዜ ነው ትዝ ያላቸው። "የማይከተቡ ሰዎች ሞኝ ናቸው ብዬ አስባለሁ" ይላሉ ሊሊ። ትሬቨርም የፈንጣጣ ክትባት ሲሰጣቸው ያስታውሳሉ። የ2020ው የኮሮናቫይረስ ክትባት ግን የተሻለ ነው ብለው ያምናሉ። "በዚህ ጊዜ ክትባት ለመውሰድ የተሰለፍኩት ከዳንስ ቡድን ጓደኞቼ ጋር ዘና እያልኩ ነበር" ሲሉ ይገልጹታል። በቅርቡ ወደ ዳንስ እንደሚመለሱ ተስፋ ያደርጋሉ። ባለሙያዎች እንደሚሉት ግን ይህ ተስፋ በቅርቡ እውን የሚሆን አይመስልም። ክትባቱ በመጀመሪያ ደረጃ የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ቢያዳብርም፤ የቫይረሱ ስርጭት ይገታል ማለት ግን አይደለም። እናም ሊሊ እና ትሬዘቨር ሁለተኛውን ዙር ክትባት ካገኙ በኋላም ለበሽታው የመጋለጥ እድል ሊኖራቸው ይችላል። ከጉንፋን ጋር የተያያዙ በሽታዎች ክትባት አረጋውያን ላይ የሚፈጥረው በሽታን የመከላከል አቅም ለረዥም ጊዜ አይቆይም። ፕሮፌሰር ጆን "የሆነው ሆኖ ሊሊ እና ትሬቨር በቅርቡ ዳንስ እንደሚጀምሩ ተስፋ አለኝ" ይላሉ። የጋርዮሽ በሽታን የመከላከል አቅም ዳብሮ፣ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት ቀንሶ የሚያዮበት ቀን ብዙም እንደማይርቅም ያምናሉ።
news-53021266
https://www.bbc.com/amharic/news-53021266
አል ቃኢዳ በጆርጅ ፍሎይድ ሞት አሜሪካዊያን በደንብ እንዲቆጡ አሳሰበ
አል ቃኢዳ ከሰሞኑ ከተደበቀበት ድምጹ ተሰምቷል።
የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ አሜሪካዊያንን በአንድ እንዲቆሙ አድርጓቸዋል በጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ የግፍ ግድያ የተቀሰቀሰው ቁጣ የተስማማው ይመስላል። ለተጨቆኑት የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እቆማለሁ የሚለው አልቃኢዳ ከሰሞኑ ባሰራጨው መልዕክት ሙስሊም አሜሪካዊያንን ብቻ ሳይሆን ሙስሊም ያልሆኑትንም በተቃውሟቸው እንዲገፉበት ሲያበረታታ ነበር። ይህ በአል ቃኢዳ ያልተለመደ አካሄድ ይመስላል። "ኡማህ" የሚባለው የዚህ ቡድን የበይነ መረብ መጽሔት በሰሞኑ ልዩ ዕትሙ የጆርጅ ፍሎይድን ምስል ከፊት ለፊት አውጥቶ አትሞታል። የተጠቀመው ምስል የፍሎይድን የመጨረሻ የጭንቅ ሽርፍራፊ ሰከንዶችን የሚያሳይ ነበር። ምስሉ የተሰራው በጎዳና ላይ የሥዕል ጥበበኛ ባንክሲ ሲሆን አል ቃኢዳ በአሜሪካ ለተነሳው ተቃውሞ የማያወላዳ ድጋፍ እየሰጠ እንደሆነ ያረጋገጠበት ተደርጎ ተወስዷል። ይህ የአል ቃኢዳ ልሳን የሆነው 'ኡማህ' መጽሔት በእንግሊዝኛ መታተሙ በራሱ የሚናገረው ነገር ቢኖር መልዕክቱ እንዲደርስለት የፈለገው ለአሜሪካዊያንን እንደሆነ ነው። በዚህ የመጽሔት መጣጥፉ አል ቃኢዳ "የአሜሪካ መውደቂያ መቃረቡ አይቀሬ" መሆኑን የተነተነ ሲሆን ከሁሉ በፊት ግን የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት እንደሚንኮታኮት ይተነብያል። "የትጥቅ ትግል በአሜሪካ ተቀጣጥሏል፤ የእርስ በርስ ጦርነት ደግሞ አይቀሬ ነው" የሚለው አል ቃኢዳ "ከዚህ ውጥንቅጥ የሚያወጣችሁ ታዲያ ዲሞክራቶች እንዳይመስሏችሁ፤ ከዚህ ቸግር የሚያወጣችሁ አል ቃኢዳ ብቻ ነው" ይላል። የቢቢሲ የሚዲያ ቅኝት ባለሞያ ሚና አልላሚ በዚህ ዙርያ በሰጠችው አስተያየት በአል ቃኢዳና በአይኤስ መካከል የአቀራረብ ልዩነት እንዳለ አስምራበታለች። "አይኤስ አሜሪካ በገጠማት ተቃውሞ እግሩን ዘርግቶ እየሳቀ ሲሆን አልቃኢዳ ግን የአሜሪካዊያንን ቋንቋና የጥቁሮችን ቁስል እየነካካ ወደ ራሱ ርዕዮተ ዓለም ለመማረክ እየሞከረ ነው።" ሚና እንደምታምነው የአል ቃኢዳ 'ኡማህ' መጽሔት የቅርብ ጊዜ ትንታኔ የተጻፈው የአሜሪካንን ፖለቲካ በቅርብ በሚከታተልና ጠንቅቆ በሚያውቅ አባል ነው። አል ቃኢዳ ወደ መድረኩ እየተመለሰ ይሆን? አል ቃኢዳ ባለፉት ዓመታት በአይ ኤስ ተጋርዷል። በለንደኑ ኪንግስ ኮሌጅ የጽንፈኝነት ጥናት ዳይሬክተር ዶክተር ሺራዝ ማሄር ግን በዚህ አይስማሙም። እርሳቸው እንደሚያምኑት አል ቃኢዳ አሁንም ቢሆን ከጀርባ ሆኖ ሥራውን እየሰራ ነው። በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ አሁንም ተሰሚነት ለማግኘትና ወደ መድረኩ ለመመለስ ፍላጎት አለው። "ይህ ከሰሞኑ የተፋፋመው የጥቁሮች የመብት እንቅስቃሴ ዓለም አቀፍ መልክ ሊይዝ የሚችል ጉዳይ እንደሆነ አልቃኢዳ ጠንቅቆ ይረዳል። ለዚህም ነው ዝም ብሎ ቆይቶ አሁን "አለንላችሁ" ማለት የፈለገው" ባይ ናቸው። ምጸቱ ደግሞ በመካከለኛው ምሥራቅ የመብቶች ሁሉ ጨፍላቂ እና የእልቂት ጌታ የሆነው አል ቃኢዳ አሁን ደርሶ ጥቁሮች ላነሱት አጀንዳ ፈውስ አለኝ እያለ የመብት ጠበቃ ልሁን ማለቱ ነው። ኦሳማ ቢን ላደን አል ቃኢዳ በቀድመው መሪው ኦሳማ ቢን ላደን መሪነት በአሜሪካ መሬት ላይ ከፍተኛውን ጥፋት ካደረሰ ሃያ ዓመት ሊደፍን ተቃርቧል። አል ቃኢዳ የሌሎችን መብት ለማክበር ይቅርና በኢራቅ ፋሉጃ ግዛት ውስጥ ሲጃራ አጭሳችኋል ብሎ የወንዶችን ጣቶች በመቁረጥ የቀጣ ቡድን መሆኑ ሲታወስ፤ አሁን የመብት ታጋዮችን አይዟችሁ ማለቱ ወለፈንዲ ይሆናል ሲል የቢቢሲው የደኅንነት ጉዳዮች ዘጋቢ ፍርንክ ጋርድነር* ያትታል። አል ቃኢዳም ሆነ አይኤስ በኒው ዮርክ ከመንትያዎቹ ሕንጻዎች ጥቃት በኋላ በአሜሪካ ምድር ይህ ነው የሚባል ጉዳት አድርሰውም ሆነ ደጋፊም አግኝተው አያውቁም። ለመጨረሻ ጊዜ በ2019 በታኅሣስ ወር የሳኡዲ ዜጋ በፍሎሪዳ ፔንሳኮላ ያደረሰው ጥቃት ተጠቃሽ ነው። ከዚያ ወዲያ አልተሰማም። ደጋፊ በማግኘት ረገድም በአውሮፓ ውስጥ በርካታ አባላትን መመልመል ቢችልም በአሜሪካውያን ዘንድ ግን ይህን ማሳካት አልቻለም። የምዕራቡ ዓለም የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ላለፉት ዓመታት አል ቃኢዳ ጨርሶ እንዳልጠፋና ጉዳት ለማድረስ እየጠበቀ ያለው ትክክለኛ ጊዜና ምቹ ሁኔታን ብቻ ስለመሆኑ ሲያስገነዝቡ ቆይተዋል። አል ቃኢዳም ሆነ አይ ኤስ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአሜሪካና በእንግሊዝ በተለየ ጉዳት ያደረሰው ሁለቱ አገራት በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች ዘንድ ባደረሱት የዘመናት ግፍ የተነሳ ነው በማለት ብዙዎችን ለማሳመን ሞክረዋል። ያም ሆኖ በዚህ ወረርሽኝ እየተጠቁ ያሉት አሜሪካና እንግሊዝ ብቻ ሳይሆን የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትም ጭምር ናቸው። ለምሳሌ ኢራን 175 ሺህ ዜጎቿ ተጠቅተውባታል። ግብጽ በበኩሏ በቀን በአማካይ 2 ሺህ ሰዎች እየተጠቁባት ይገኛሉ። የምዕራቡ ዓለም ደኅንነት ተቋማት ምን ያስባሉ? ዛሬ ሁለቱ ጽንፈኛ ቡድኖች ለጋራ ጠላት የጋራ አቋም የያዙ ይመስላሉ። በአሜሪካ ለእኩልነትና ለጸረ ዘረኝነት ድምጻቸውን እያሰሙ ያሉ አሜሪካዊያንን "ጉዳያችሁ ጉዳያችን ነው" እያሉ ለተጨማሪ ጥቃት እያበረታቷቸው ነው። ለተጨማሪ ተቃውሞ፣ ለተጨማሪ መብት፣ ለተጨማሪ አመጽ ለመቀስቀስ እየሞከሩ ነው። በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን ለእኩልነት በሚታገሉ ሰልፈኞች መሀል የሁለቱ ጽንፈኛ ኃይሎች ጥሪ ትኩረት ያገኛል ማለት ዘበት ነው፤ የሚያስተውለው መኖሩን እንኳ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። አል ቃኢዳ ሽብርተኛ ድርጅት ሲሆን በመስከረም 11ዱ የሽብር ጥቃት 3 ሺህ ንጹህ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ቡድን እንደሆነ ይታወቃል። ለመሆኑ ይህ የአል ቃኢዳ ጥሪ የአሜሪካ ጸረ ሽብር ደኅንነት ሰዎችን ምን ያህል አሳስቧቸው ይሆን? ዶ/ር ማሄር ላለፉት 20 ዓመታት የእነዚህን ጽነፈኛ ቡድኖች አስተሳሰብና ፍልስፍና እንዲሁም የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ሲያጠኑ የቆዩ ጉምቱ ምሁር ናቸው። እንደርሳቸው አመለካከት የአል ቃኢዳ መልዕክት ጥሩ አጋጣሚን ለመጠቀም ከመሞከር ያለፈ አይደለም። "የአልቃኢዳ ሙከራ ለማንኛውም ብሎ መረቡን እንደሚዘረጋ አሳ አጥማጅ ያለ ነው" ይላሉ። *(ይህ ጽሑፍ በቢቢሲው የደኅንነት ጉዳዮች ዘጋቢ ፍርንክ ጋርድነር የተጠናቀረ ነው፡፡)
news-56980750
https://www.bbc.com/amharic/news-56980750
ምርጫ 2013፡ በምርጫ ለመሳተፍ ‘ያልታደለው’ የአላጌ ማህበረሰብ
ነገሩ ግራ ይመስላል። ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በተቃራኒ ምርጫን የተመለከተ እንቅስቃሴ በአካባቢው አይስተዋልም። የእጩዎች ምዝገባ አልተካሄደም። የመራጮች ምዝገባም የለም። ወደ ማህበረሰቡ ቀርቦ "ምረጡኝ" የሚል ፓርቲም የግል ተወዳዳሪም አይታይም።
ይህ ዘንድሮ ብቻ የሆነ አይደለም። ባለፉት አምስት ጠቅላላ ምርጫዎች የዚህ አካባቢ ነዋሪዎች ምንም ተሳትፎ አልነበራቸውም። የሀገሪቱ ህገ መንግስት 18 ዓመት የሞላው ማንኛውም ዜጋ በህግ መሰረት የመምረጥ መብት አለው ቢልም በአላጌ ይህ መብት ተተግብሮ አያውቅም። ለምን? አስተዳደር አልባው ማህበረሰብ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምስራቅ 194 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቡልቡላ የተሰኘች ከተማ አለች። ከቡልቡላ ከተማ አቅራቢያ ወደ ቀኝ ከሚታጠፍና 32 ኪሎ ሜትር ከሚሸፍን አስቸጋሪ መንገድ በኋላ የአላጌ ግብርና ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ ይገኛል። ኮሌጁን ማዕከል አድርገው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም በአካባቢው ኑሯቸውን መስርተዋል ። በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች መካከል የሚገኘው ቦታው በየትኛውም ክልል አስተዳደር ውስጥ አልተጠቃለለም። የዚህ መነሻ ኢህአዴግ ስልጣን ይዞ የክልሎች ወሰን ሲቀመጥ ሁለቱ ክልሎች [በደቡብ በኩል የቀደሞ የሃላባ ልዩ ወረዳ] አካባቢው ላይ የይገባኛል ጥያቄ በማንሳታቸው እንደሆነ ይገለጻል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሶስት ዓመታት በፊት በሰራው ዘገባ 44 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ላይ ያረፈው ስፍራው በፌዴራሉ መንግስት ስር እንደሚተዳደርና ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎች እንዳሉት ጠቁሟል። የአካባቢው ማህበረሰብ የፖሊስ አገልግሎቶችን በደቡብ ክልል- የህግና የፍርድ ቤት ጉዳዮችን ደግሞ በስልጤ ዞን በኩል ይቀርቡለታል። ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተናን የኦሮሚያ ክልል ሲሰጥ ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን የተመለከቱ አገልግሎቶችን ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያመቻቻል - አገልግሎቶቹ በሙሉ በትብብር የሚቀርቡ መሆናቸው ሳይዘነጋ። በአካባቢው ባለፈው ዓመት የመሰናዶ ትምህርት ቤት ስራ ጀምሯል። ይህም የአላጌ ተማሪዎች መሰናዶ ሲደርሱ 'የዚህ ክልል ተማሪ ስላልሆናችሁ አናስተናግድም' ከሚል እንግልት ታድጓቸዋል ይላሉ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች። ሆኖም ወደ መሰናዶ መሸጋገር ያልቻሉ ወይም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያላመጡ የአካባቢው ተማሪዎች የቴክኒክና ሙያ ትምህርትን ለመቀላቀል ሌላ አስቸጋሪ ሁኔታ ይጠብቃቸዋል። "አዲስ አበባ ያለው ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ [ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ] ነው በተወሰነ ደረጃ የሚረዳን። የኮሌጁ ዲን [የአላጌ] ደብዳቤ ተጻጽፎ ክልል እንደሌለን ተረጋግጦ በየዓመቱ ተማሪዎችን ይቀበልልናል።" በማለት ያስረዳሉ የአካባቢው ነዋሪ አቶ ሹሜ። ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ "ኮተቤ ካላገኘ ሌላ ዕድል የለውም። መሃይም ሆኖ መቅረት ነው ይላሉ።" ከምርጫ ጋር የማይተዋወቀው አካባቢ አቶ ሹሜ አሰፋ በአካባቢው 41 ዓመታት ኖረዋል። አምስት ልጆችንም አፍርተዋል። በስፈራው በተለያዩ ወቅቶች በነበሩ መንግሥታዊ ተቋማትም ሰርተዋል። ሆኖም አንድም ጊዜ ምርጫ ላይ አልተሳተፉም። " ምርጫ እዚህ አካባቢ ተካሄደ እዛ አካባቢ ተካሄደ ሲባል እንሰማለን [ግን] ምን ይሁን ምን አናውቅም" ሲሉ ይናገራሉ። ሌላኛው ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ወጣት ነዋሪ ደግሞ "ታዛቢ ሆነን የሚደረገውን ማየት ነው። ሀገራችን ላይ ምን እየተከናወነ ነው የሚለውን ማየት ነው እንጂ ተሳታፊ ሆነን እንደመብት የምንጠቀመው ነገር የለም።...እንደዚህ መሆናችን ያሳዝነኛል" ይላል። ከዚህ ቀደም የኮሌጁ ተማሪዎች የየመጡበትን አካባቢዎች ተወካዮች የሚመርጡበት እድል ተመቻችቶ እንደነበር ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በአላጌ ከአራት አስርት ዓመታት በላይ የኖሩትና ስማቸውን እንዲጠቀስ የማይሹ ሌላ አስተያየት ሰጪ በምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት ቢኖራቸም አንድም ጊዜ ለዚህ አለመታደላቸውን ገልፀዋል። "ዜግነት እንዳለን እንደማይቆጠር ነው የሚሰማን" ብለዋል። በተለያዩ ወቅቶች በነበሩ ስብሰባዎች የምርጫን ጉዳይ "ሳናነሳ አናልፍም" የሚሉት ነዋሪዎቹ 'ጠብ' የሚል ነገር ግን የለም ሲሉ ይደመጣሉ። ከአራት አስርት ዓመታት በላይ የኖሩት አስተያየት ሰጪያችን ነገሩ ተስፍ አስቆርጦናል ሲሉ ይገልጻሉ። በፌዴራል "ስር ስላላችሁ መምረጥ አትችሉም" የሚል ምላሽ ስለመሰጠቱም አስረድተዋል። "ለመጣ ባለስልጣን እንናገራለን። ምላሽ ስለሌለ ሰው ተሰላችቶ ትቶታል...መምረጥ ነበረባችሁ በሚቀጥለው እንነጋገራለን ብሎ የሚሄድ እንጂ ይሄን እናደርጋለን የሚል ሰው የለም" የሚሉት ደግሞ አቶ ሹሜ ናቸው። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘገባ ላይ ተካትተው የነበሩት የኮሌጁ ዲን ከበደ በዬቻ (ዶ/ር) "ስለምርጫውም ለእርሻና ተፈጥሮ ሃብትም [የአሁኑ ግብርና ሚኒስቴር] አሳውቀናል። አንድ ኢትዮጵያዊ ምርጫ ውስጥ መሳተፍ አለበት - መብቱም ስለሆነ" ብለዋል። ሆኖም ተጨማሪ መረጃዎችን ለመጠየቅ ቢቢሲ ዲኑን፣ ምክትል ዲኖችንና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊውን ለማግኘት ከሁለት ሳምንት በላይ (17 ቀን) የፈጀ ተደጋጋሚ ጥረት ፍሬ አላፈራም። የግብርና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበራ ለማ "ተቋሙ [ኮሌጁ] ተጠሪነቱ ለግብርና ሚኒስቴር ነው። የአስተዳደር ጉዳዮች ላይ የማውቀው ነገር የለም...ግብርና ሚንስቴር የሚያስተዳድረው ህዝብ የለም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል ከምርጫ ቦርድም ምላሽ ለማግኘት ላለፉት ሁለት ሳምንታት በስልክ፣ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እንዲሁም በኢሜል ተደጋጋሚ ሙከራ አድርገናል - ነገር ግን ምላሻቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ከህጻናት አምባ እስከ እስከ ግብርና ኮሌጅነት መስከረም 4 1973 ዓ.ም ከኢፌዴሪ መንግስት ምስረታ በፊት በነበረው የኢትዮጵያ አስተዳደራዊ መዋቅር በሸዋ ክፍለ ሃገር ሀይቆችና ቡታጀራ አውራጃ በሃላባ ቁሊቶ ወረዳ አላጌ በተባለ ስፍራ የአብዮታዊ ህጻናት አምባ የተሰኘ ተቋም ተመረቀ። በጦርነትንና በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትን የማሳደግ አላማ የያዘው ተቋሙ በአምስት መንደሮች የተከፋፈለ ነበር። ተቋሙ ግዙፍ ነበር የሚሉት አቶ ሹሜ እያንዳንዱ መንደር አስተዳዳሪ እንደነበረው ይናገራሉ። ሞግዚትነት፣ ምግብ ዝግጅት ህክምናና ሌሎች ተግባሮችን ለመከወን ደግሞ አቶ ሹሜ [በምግብ ቤት ተቆጣጣሪነት]ና ሌላኛው ስሜ አይጠቀስ ያሉትን አዛውንት ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተሰባሰቡ። እናም የተሰባሰቡት ሰዎች ቀስ በቅስ እየተግባቡ ሄዱ። አንዳንዶቹም ተጋቡ። ተዋለዱ። "ሁሉም ከተለያየ አቅጣጫ የመጣ ነው። ትንሿ ኢትዮጰያ ማለት ይቻላል የሌለ ብሄረሰብ የለም" ይላሉ አቶ ሹሜ። ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣም በኋላ አምባው እስከ 1989 ዓ.ም ቆየ። በ1989 ዓ.ም ህጻናቱም ወደ ተለያየ ማዕከላት እንዲዘዋወሩ ተደርጎ አምባው ተዘጋ። የአካባቢው እንቅስቃሴ ተቀዛቀዘ። የተሰወኑ ሠራተኞች ተቀነሱ። ከአመታት በኋላ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲጀመር አላጌ የጦር ጉዳተኞች መንከባከቢያ ማዕከል ሆነ። በህጻናት አምባው ሲሰሩ የነበሩና ኑሯቸውን ያቀኑ ዜጎች በማዕከሉ በተለያዩ መደቦች ስራ ጀምረው ኑሮ ቀጠለ። በ1994 ዓ.ም ደግሞ ማዕከሉ ወደ ግብርና ኮሌጀነት ተቀየረ። አሁንም የተለያዩ ሰራተኞች ቢቀነሱም ቀድሞ በህጻናት አምባና በጦር ጉዳተኞች ማዕከል ሲሰሩ የነበሩ እንዲሁም አዳዲስ ሠራተኞች ስራ ጀመሩ። በሰፋፊ እርሻዎች ላይ በተለያየ ሙያ እንዲሁም የከብት፣ የዶሮና የአሳማ ርባታ ከተሰማሩባቸው መስኮች የሚጠቀሱ ናቸው። አቶ ሹሜ በሶስቱም ተቋማት ከሰሩ ሰዎች መካከል ናቸው። ጡረታ ወጥተው አሁንም በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎችም አሉ። በዚህ ሁሉ መሃል ግን በምርጫና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚጋፈጧቸው ችግሮች መልክ ሳይዙ ድፍን 30 ዓመታት ተቆጥሯል። ታዲያ ይህ ነዋሪዎችን ከመምረጥ መብት የገታና ለውጣ ውረድ የዳረገ አስተዳደራዊ ገጽታ በነዋሪዎቹ ላይ የተለየ ስሜት እየፈጠረ እንደሆነ ማስተዋል ይቻላል። አራት አስርት አመታት የኖሩት ግለሰብ "እንደሮ ዕቃ አስታዋሽ የለንም" ሲሉ ሰሜ አይጠቀስ ያለው ወጣት ደግሞ "እንደ ዜጋ እንዴት ይህን መብት አጣለሁ እያልኩ እቆጫለሁ። መፍትሄው መራቁ ደግሞ በጣም ይሰማል" ይላል። ኑሮ በአላጌ በዚህ መልክ ቢቀጥልም ለነዋሪዎች ያልተመቸው አስተዳደራዊ እንቅፋት ግን መቼ መልስ እንደሚያገኝ ማንም 'ርግጠኛ የሆነ አይመስልም።
news-56509289
https://www.bbc.com/amharic/news-56509289
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ወደ ወታደራዊ ግጭት ያመሩ ይሆን?
በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረስ ያልቻሉት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቃላት ጦርነታቸው የደራ ይመስላል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ፣ ጠ/ሚ አብደላ ሐምዶክ እና ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ አልፎም የሱዳን ጦር የግዛቴ አካል ናቸው ያላቸውና የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ሰፍረውባቸው የነበሩ ለም የድንበር አካባቢ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የድንበር ፍትጫ ተከስቷል። በቅርቡ ሱዳንና ግብፅ የጋራ ስምምነት ደርሰዋል። ስምምነቱ ከወታደራዊ ሥልጠና አንስቶ እስከ ምጣኔ ሃብታዊ ትብብር የሚመዘዝ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ማክሰኞ መጋቢት 14 /2013 ዓ. ም በተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ካነሷቸው ነጥቦች አንዱ የሕዳሴ ግድቡ ጉዳይ ነው። "ኢትዮጵያ ግብፅንም ይሁን ሱዳንን የመጉዳት ፍላጎት የላትም። ሆኖም ግን ጨለማ ውስጥ መኖር አንፈልግም። የእኛ መብራት እነሱን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አይደለም" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለቱን አገራት በማይጎዳ መልኩ መገንባቱን እንደሚቀጥል አስረግጠዋል። ለመሆኑ ሦስቱ አገራት ከሌላው ጊዜ በተለየ ወደ ከረረ ወደ ውዝግብና ፍጥጫ መግባታቸው ለምንድነው? ዋነኛው ምክንያት የሕዳሴ ግድብ ይሆን? ሱዳን በድኅረአልባሽር መቀመጫቸውን ለንደን ያደረጉትና የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አጥኚ የሆኑት አብዱራህማን ሰኢድ አቡሃሽም፤ "አንዱ የጡዘቱ ምክንያት የሱዳን አቋም መቀየር ነው" ይላሉ። "አባይን በተመለከተ የሱዳንና የኢትዮጵያ አቋም አንድ ነበር ማለት ይቻላል። አሁን ሱዳን ያሳየችው የአቋም ለውጥ በፊት ከነበረው በጣም የተለየና ያልተጠበቀም ነው ሊባል የሚችል ነው" ይላሉ። ለዚህ እንደ ምክንያት የሚጠቅሱት በሱዳን ያለው የሽግግር መንግሥት አቋም አንድ አለመሆንን ነው። በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተነሳው የድንበር ፍጥጫ ይህን ያህል የሚያጋጭ ነው ብዬ አላስብም የሚሉት ተንታኙ፤ ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት መግባቷን የተመለከተው የሱዳን የጦር ኃይል ክፍተቱን ለመጠቀም ያሰበ መሆኑን ይጠቅሳሉ። አቶ አብዱራህማን እንደሚሉት፤ የሱዳን ጦር ኃይል የድንበር ጉዳዩን የፈለገው ለውስጥ ጉዳይ መጠቀሚያ ለማድረግና ተቀባይነት ለማግኘት ይሆናል እንጂ ድንበሩን የሚመለከተው የሁለቱ አገራት ኮሚቴ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ሊፈታው ይችል ነበር። ተንታኙ ሱዳን አቋሟን የቀየረችው አሁን ባለው የአገር ውስጥ ሁኔታ ምክንያት ነው ይላሉ። ኔዘርላንድስ የሚገኙት የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች የፖለቲካ ተንታኝ አደም ካሴ (ዶ/ር) በዚህ ጉዳይ ከአቶ አብዱራህማን ጋር ይስማማሉ። "ሱዳን በተለይ በአል ባሽር ጊዜ ከኢትዮጵያ ጋር የሚመሳል አቋም ነበራት። ነገር ግን አል ባሽር ከተወገዱ በኋላ የአገር ውስጥ ሁኔታዋን ስንመለከት ወጥ የሆነ ገዢ የሌላት አገር ሆናለች። የጦር ኃይሉ የሚመራው ክፍል አለ። እዚያ ውስጥ ደግሞ 'ራፒድ ፎርስ' የሚባለው አለ። ከዚያ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ የሚመራው የሲቪል አመራር አለ። ሁለቱ አመራሮች የሚያራምዱት አቋም ተመሳሳይ አይደለም" ይላሉ አደም። እንደ ተንታኙ ከሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይነት ያለው አቋም ሲያራምድ የነበረው በጠቅላይ ሚንስትር ሐምዶክ የሚመራው የሲቪሉ አመራር ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ውስጥ ቀውስ ከተከሰተ በኋላ የሱዳን ጦር ኃይል አቅሙን እያጠናከረ መሆኑን የሚገልጹት አደም (ዶ/ር)፤ "የሲቪሉ ክፍል ደግሞ ቀድሞ ከድርድሩ ማግኘት እንችላለን ከሚሉት የተሻለ ጥቅም አሁን ማግኘት እንችላለን የሚል እሳቤ ያደረባቸው ይመስለኛል" ይላሉ። ሁለቱም ተንታኞች የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ውዝግብ ለግድቡ ድርድር እንደ አዲስ መጦፍ ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አላቸው። ከሱዳንና ግብፅ ግንኙነት አትራፊ ማነው? ሱዳን አቋሟን መቀየሯን ተከትሎ ወደ ግብፅ አድልታለች። ሁለቱ አገራት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከላይ እንደተጠቀሰው የተለያዩ ስምምነቶችን አድርገዋል። ታድያ ከዚህ ስምምነት የበለጠ ተጠቃሚ ግብፅ ወይስ ሱዳን? አደም (ዶ/ር) አሁን ሁኔታው የግድብ ብቻ ሳይሆን የድንበርም ሆኗል ይላሉ። በዚህ ምክንያት ሱዳኖች አሁን ጉዳዩን ነጣጥለው የግድብና የድንበር ብለው ማውራት አይፈልጉም ብለው ያምናሉ። "ሱዳንና ግብፅ የደረሱት ስምምነት ሰፊ ነው። የዲፕሎማሲ ግንኙነትም አለው፤ ሌሎች ሌሎች ስምምነቶችም አሉ። እንግዲህ ኢትዮጵያ ግፊት ደርሶባት በአባይ ላይ ያላትን አቋም ብታቀዘቅዝ ግብፅም ትጠቀማለች፤ ሱዳንም ትጠቀማለች። ስለዚህ ጥቅሙ የሁለቱም ነው" ይላሉ። ነገር ግን ይላሉ አደም. . . "ነገር ግን ጉዳዩ አንዳንድ ሰዎች እንደሚፈሩት ወደለየለት ጦርነት የሚያመራ ከሆነ ሱዳን ከምታተርፈው በላይ ልትጎዳ ትችላለች።" "እንደሚታወቀው ኢኮኖሚዋ የደከመ ነው። በየቦታው ግጭት አለ። ጦርነት ቢጀመር ኢትዮጵያ እንደምትጎዳው ሁሉ ሱዳንም በጣም ትጎዳለች። ነገር ግን ጦርነት ከተጀመረ ዋና ተጠቃሚ የምትሆነው ግብፅ ናት። ጦርነት እስካልተጀመረ ድረስ ግን ሱዳን ከግብፅ ድጋፍ እያገኘች ስለሆነ ተጠቃሚ የሚሆኑት ሁለቱም [ግብፅና ሱዳን] ናቸው።" አቶ አብዱራህማን በበኩላቸው ኢትዮጵያና ሱዳን አለመረጋጋታቸው ለግብፅ ጠቃሚ ይሆናል ቢባልም እሳቸው ግን በዚህ ሐሳብ አይስማሙም። "እርግጥ ነው ሱዳን ለበርካታ ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መቆየቷ ለግብፆች ተስማምቷቸው ነበር። ምክንያቱም ከሚገባቸው በላይ የውሃ ድርሻ ሲያገኙ ነበር። የሱዳንን ድርሻ ጭምር ነው እነሱ [ግብፆች] ሲወስዱ የነበረው። ነገር ግን ይህ ጉዳይ ስትራቴጂክ አልነበረም። ምክንያቱም የአሁን ጥቅምን እንጂ የወደፊቱን ያሰበ አልነበረምና" ይላሉ። "አኔ በግብፅ ሚድያዎች ላይ ቀርቤ በአረብኛ ቃለ መጠይቅ በምሰጥበት ጊዜ እናንተ ዕድል ነበራችሁ። ምክንያቱም እናንተ የምትፈልጉት ውሃውን ሌሎች አገራት የሚፈልጉት ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል ነው። ስለዚህ ይህን ፍላጎታቸውን በሌሎች አማራጮች [የነፋስም ሆነ የፀሐይ] ማሟላት ብትችሉ ኖሮ ይህ አይመጣም ነበር ነው የምላቸው።" አሁን የአባይ ግድብ እውን በመሆኑ ግብፆች ያላቸው አማራጭ ከናይል ተፋሰስ አገራት ጋር የሚያስማማ ስምምነት ገብተው የሁሉም ጥቅም የሚከበርበትን አማራጭ መፈለግ እንጂ የሌሎች አገራት አለመረጋጋት ላይ የተመሠረተ ጥቅም አያዋጣም ይላሉ አቶ አብዱራህማን። እውን የለየለት ጦርነት ይነሳ ይሆን? በአባይ ውሃ አጠቃቀም ምክንያት ጦርነት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው አደም (ዶ/ር) ይናገራሉ። "ጦርነት ውስጥ ለመግባት ፍላጎት ባይኖር እንኳ የተሳሳተ ስሌት ሊኖር ይችላል። ሌላኛው ወገን ምን ሊያደርግ ይችላል እያልክ እያሰብክ ነው እርምጃ የምትወስደው። ሙሉ መረጃ ከሌለህ የተሳሳተ እርምጃ ልትወስድ ትችላለህ። እና እንደዚህ ዓይነት የተሳሳቱ ውሳኔዎች ነገሮችን ከቁጥጥር ውጪ ሊያደርጓቸው ይችላሉ የሚል ስጋት አለኝ" ይላሉ። አደም አክለውም ሁሉቱ አገራት [ኢትዮጵያና ሱዳን] ካላቸው የአገር ውስጥ ችግር አንፃር ጦርነቱን ይፈልጉታል ብለው አያስቡም። "ነገር ግን የጦርነት ድግሱን ይፈልጉታል ብዬ አምናለሁ። በተለይ በሱዳን የጦር ኃይሉ አገሪቱን ለማንቃት ሊጠቀምበት ይችላል። በኢትዮጵያም በኩል እንደዚያው ሊፈለግ ይችላል። ወደ ዋናው ጦርነት የመግባት አቅሙም ፍላጎቱም አላቸው ብዬ አላምንም። ነገር ግን እንዳልኩት ስህተቶች ሊሠሩ ይችላሉ።" የአብደላ ሃምዶክ መንግሥት በሱዳን ጦር ኃይል ላይ ቁጥጥር እንደሌለው እንደ አብነት በመጥቀስ በሱዳንም ሆነ በኢትዮጵያ ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ኃይሎች አሉ የሚሉት አደም (ዶ/ር) "የጦርነት ፍላጎት ባይኖራቸው እንኳ ስህተቶች ሊሠሩ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ።" አቶ አብዱራህማን በበኩላቸው ጦርነቱ ላይነሳ ይችላል የሚል እምነት አለኝ ይላሉ። "በመቶኛ አስቀምጥ ካላችሁኝ ምናልባት ሃምሳ ከመቶ ወይም ከዚያ በታች ነው ባይ ነኝ። አሁን ያለው ጡዘት አንዱ አገር ሌላኛው ላይ ጫና ለማድረግ ነው እንጂ ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት አለ ብዬ አላምንም።" የለንደኑ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ተንታኝ በእርግጥ አሁን ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ጉዳይ ተወጥራ ስላለች ሱዳንና ግብፅ ሁኔታዎቹ አመቺ ናቸው ሊሉ ይችላሉ ይላሉ። "ሱዳንና ግብፅ ይህ ጉዳይ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ካልመጣለት በቀላሉ ሊፈታ እንደማይችል ያውቁታል። ይህ ጉዳይ አሁን ባለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ባይነሳ እንኳ ቀጥሎ በሚመጣው መንግሥት መነሳቱ አይቀርም። ምክንያቱም ይህ ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ወደ ተግባር እስኪገቡ ድረስ ባለፉት መንግሥታትም ሲነሳ ቆይቷል።" ስለዚህ ነገሩ አቅምን የማሳየትና ጫና የመፍጠር ጉዳይ ነው እንጂ ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት የለም ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከሱዳን ጋር ያለውን ሁኔታ በተመለከተ "ወደ ጦርነት ገብተን የማያባራ ነገር ውስጥ አንገባም" ሲሉ ለአገሪቱ ፓርላማ በተናገሩበት ወቅት አገራቸው ፈጽሞ ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸውና "ነገሮችን በውይይት የመፍታት ጥረታችንን እንቀጥላለን" ብለዋል። ጦርነቱ ምን ዓይነት ሊሆን ይችላል? አቶ አብዱራህማን ሱዳንና ኢትዮጵያ የድንበር ጦርነት ውስጥ የሚገቡ ከሆነ ግብፅ ደግሞ ሱዳንን ከመደገፍ አልፋ በቀጥታ ልትሳተፍ ትችላለች ይላሉ። ቢሆንም ግን ሱዳን አሁን ግብፅን ተማምና እንጂ እንኳን በወቅቱ ባለችበት ሁኔታ ቀርቶ በተነፃፃሪ የተረጋጋች በነበረችበት ጊዜ የጦርነት አቅም አላት ብዬ አላምንም ሲሉ ያክላሉ። "ስለዚህ ከጦርነቱ ሱዳን አንዳችም ነገር አትጠቀምም። ነገር ግን ጦርነቱ አይምጣ እንጂ ቢመጣ ሱዳንና ግብፅ አንድ ላይ ይሆናሉ። የኤርትራ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በአሁኑ ወቅት ወዳጅነት አለው። የሁለቱ አገራት ስምምነት እስከ ሴኩሪቲ ስምምነት የሚደርስ ነው። ሱዳንና ግብፅ አንድ ላይ ካበሩ የኢትዮጵያና ኤርትራ ወዳጅነት በዚህ የሚገታ አይመስለኝም።" አደም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ምን እንደሚሆን መገመት ቢከብድም ሁሉም የአቅሙን ከማንቀሳቀስ ወደኋላ አይልም ይላሉ። "ግብፆች አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑ ከሆነ ከአገራቸው ሆነው ሊተኩሱ ይችላሉ። ሱዳንንም በሚያስፈልገው መልኩ በሰው ኃይልም በጦር መሣሪያም ሊያግዙ ይችላሉ። አስፈላጊ ነው ብለው ካመኑ ግድቡንም ሊመቱ ይችላሉ። በአጠቃላይ ጦርነቱ ከተጀመረ ማን ምን ያደርጋል የሚለውን መገመት አስቸጋሪ ነው።" አደም የኤርትራ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር ሊወግን እንደሚችል ግን እምነት አላቸው። "የኤርትራ መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ህወሓትን ማጥፋት እንደመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ትኩረቱ በሱዳን አሊያም በሌላ አገር እንዲያዝ አይፈልግም። ኤርትራ በተቻላት መጠን በተለይ ከሱዳን ጋር ሰላም እንዲፈጠር ነው የምትፈልገው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ መንግሥት ሥራ በበዛበት ቁጥር ህወሓትን የማጥፋት ዓላማቸው አይሳካላቸውም። "ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ደቡብ ሱዳን የሄዱትም ጫና ለመፍጠር ይመስለኛል።" የሌሎች አገራት ሚና ሁለቱ ተንታኞች በሌሎች አገራት ሚና በኩል አይስማሙም። አደም (ዶ/ር) ከትግራይ ክልል ጦርነት ወዲህ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቋም እየተዳከመ ነው ይላሉ። አቶ አብዱራህማን ግን ኢትዮጵያ በተለይ በአፍሪካ ሕብረት ዘንድ ያላት አቋም ከግብፅና ከሱዳን የላቀ ነው ይላሉ። አደም የታችኛው ተፋሰስ አገራት ጦርነት ቢቀሰቀስ ቀጥተኛ ተሳታፊ አይሆኑም። ነገር ግን በግልፅ ወጥተው ለግብፅና ሱዳን ያደላሉ የሚል እምነት የለኝም ይላሉ። "ነገር ግን ለምሳሌ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ብንመለከት ከግብፅ ጋር ስምምነት ማድረግ ከጀመረች ቆይታለች። ምጣኔ ሃብታዊና የጦር ኃይል ድጋፍም ስታደርግ ነበር። እና በዲፕሎማሲ ወደ ሱዳንና ግብፅ ሊያዘነብሉ ይችላሉ። በጦርነቱ ግን ቀጥተኛ ተሳታፊ ይሆናሉ የሚል እሳቤ የለኝም።" አቶ አብዱራህማን ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ከኢትዮጵያ ጋር መልከአ ምድራዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ስላላቸው ከኢትዮጵያ ጋር የሚስማማ አቋም ሊኖራቸው ይችላል ይላሉ። ቢሆንም እነ ኮንጎ ምናልባት ግብፅን የሚደግፉ አሊያም መሀል ላይ ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ አቶ አብዱራህማን። ከታችኛው ተፋሰስ አገራት ባለፈ ሌሎች ኃያላን የዓለም አገራት በሦስቱ አገራት ጉዳይ ቀጥተኛ ያልሆነ ሚና ሊኖራቸው እንደሚችል ምሁራኑ ይስማማሉ። ግብፅ በሦስቱ አገራት ድርድር የአሜሪካ እጅ እንዲኖርበት ትሻለች። ኢትዮጵያ ደግሞ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት አስማሚነት እንዲቀጥል እንደምትፈልግ በግልፅ አሳውቃለች። ከዚህ ባለፈው እንደ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ኳታር በዚህ ጉዳይ ጣልቃ ሊገቡ እንደሚችሉ እምነት አለ። አደም (ዶ/ር) በአረብ ሊግ አገራት ለግብፅ ድጋፋቸውን ሲያሳዩ ቆይተዋል ይላሉ። እርግጥ ነው ቱርክ ከግብፅ ጋር ያላት ስምምነት ሰላማዊ ያልነበረ ቢሆንም አሁን ግን ረገብ ያለ ይመስላል ይላሉ። ስለዚህ ለግብፅ ሊያደሉ እንደሚችሉ እምነት አላቸው። ኢትዮጵያ በድርድሩ ላይ ያላትን ጫና ከፍ ለማድረግ መጀመሪያ አገር ውስጥ ያለውን አለመረጋጋት መቀልበስ እንዳለባት ያምናሉ። አለበለዚያ በድንበሩም ሆነ በግድቡ ዙሪያ የአቋም ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል ይሰጋሉ። ይህ ደግሞ ዞሮ ዞሮ የአገር ቤት አለመረጋጋቱን ያሰፋዋል ባይ ናቸው- አደም። ምሁሩ ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ያላት አንዱ አማራጭ የአገር ውስጥ ፖለቲካውን ማረጋጋት ነው የሚሉት። የተረጋጋች ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲም ረገድ ለውጥ ልታመጣ ትችላለች በማለት ያጠናክራሉ። በሦስቱ አገራት መካከል ያለው የግድብ ድርድር አሁንም መፍትሄ አላገኘም። ምናልባት በሚቀጥሉት ድርድሮች አገራቱ ስምምነት ላይ ይደርሱ ይሆን? ገና ወደፊት የሚታይ ነው።
48999928
https://www.bbc.com/amharic/48999928
የአዲስ አበባ መስተዳደርና የባላደራው ምክር ቤት
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምርጫን ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ የከተማ አስተዳደሩ የምርጫ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑ ይታወሳል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ቻርተርን ባሻሸለበት አዋጅ የከተማው ምክር ቤትን ምርጫ ከማራዘሙ በተጨማሪ፤ ምርጫ ተደርጐ አዲስ አስተዳደር እስኪደራጅ ድረስ በሥራ ላይ ያለው ምክር ቤትና አጠቃላይ የከተማው የአስተዳደር በነበረበት ሁኔታ ይቀጥላል ብሏል። የምክር ቤቱ ውሳኔዎች ሕጋዊ አግባብነት የላቸውም የሚሉ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ተነስተዋል። ምክር ቤቱም ሆነ አጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ ሕጋዊ እውቅና ኖሮት ከተማዋን ሊያስተዳድር አይችልም የሚሉ አካላትም አሉ። • ''አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት'' ከንቲባ ታከለ ኡማ ከእነዚህም መካከል በአዲስ አበባ ከተማ የባላደራ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ አባል እና በሙያቸው ጠበቃ የሆኑት አቶ ሄኖክ አክሊሉ ይገኙበታል። አቶ ሄኖክ በቅድሚያ ባላደራ ምክር ቤትን ማቋቋም ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ''ገፊ የሆኑ ወቅታዊ ሁኔታዎች ይገኙበታል'' ይላሉ። አቶ ሄኖክ ለባላደራ ምክር ቤት መቋቋም ወቅታዊ ጉዳዮች ናቸው የሚሏቸው ''አሁን ያለው አስተዳደር ወደ ሰልጣን ከመጣ ወዲህ የከተማውን ነዋሪ ባገለለ ሁኔታ የጥቂት ሰዎች ፍላጎት ለማሳካት እንቀስቃሴዎችን ያደርጋል፣ እስከታችኛው የስልጣን እርከን ድረስ የእራሱን አመለካከት የሚያራምዱ ሰዎችን ብቻ ወደ ስልጣን ያመጣል . . . '' የሚሉ ምክንያቶች እና ''ከተማዋን እያስተዳደረ ያለው አካል ሕጋዊ እውቅና የለውም'' የሚሉ ምክንያቶች ለባልደራስ ምክር ቤት መፈጠር ምክንያት እንደሆነ ያስረዳሉ። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እና አስተዳደር ''ሕጋዊ እውቅና የለውም'' የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 2 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል የሚለውን አንቀጽና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 365/1995 በማስታወስ አሁን ላይ ያለው አስተዳደር የተቀመጠለትን የሕግ ማዕቀፍ መሰረት ያላደረገ ነው በማለት አቶ ሄኖክ ይከራከራሉ። ''አዲስ አበባ ላይ የሚመረጥ መንግሥት አምስት ዓመት የሥራ ዘመን እንዳለው በግልጽ ተቀምጧል። የከተማው ሥራ አስፈጻሚ አካል፤ የከንቲባ ጽ/ቤትን ጨምሮ የሥራ ዘመኑ አምስት ዓመት ነው። አምስት ዓመት ደግሞ አልፎታል። የሥራ ዘመኑ ካለፈ መፍትሄ የሚሆነው ምርጫ ማካሄድ ነው። ምርጫ ማካሄድ የማይቻል ከሆነ ህብረተሰቡ የእኔ ናቸው የሚላቸውንና የሚያከብራቸውን ወደ ስልጣን ማምጣት ነው'' በማለት አቶ ሄኖክ ይናገራሉ። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው ''የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትና የከተማው አስተዳደር የሥልጣን ዘመን አብቅቷል የሚባለው በአንዳንድ በሰዎች ፍላጎት እንዲስፋፋ የሚደረግ የተሳሳተ መረጃ ነው'' ይላሉ። • «አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7 ወ/ሮ አበበች የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 365/1995ን ማሻሻል በማስፈለጉ ከአንድ ዓመት በፊት በአዋጅ ቁጥር 1094/2010 እንደተሻሻለ ያስታውሳሉ። ''በአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ እንዲራዘም መወሰኑን ተከትሎ፤ ምርጫ ተደርጐ በምርጫው መሠረት አዲስ አስተዳደር እስኪደራጅ ድረስ በሥራ ላይ ያለው ምክር ቤት እና አጠቃላይ የከተማው የአስተዳደር በነበረበት ሁኔታ ይቀጥላል ሲል አውጇል'' በማለት በአዋጅ ቁጥር 1094/2010ን በመጥቀስ ወ/ሮ አበበች ያስረዳሉ። የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 1094/2010 የከተማ አስተዳደሩና ምክር ቤት በሥራ ላይ የሚቆይበትን ቀነ ገደብ እንዳለስቀመጠ የሚናገሩት ወ/ሮ አበበች፤ የማሻሻያ አዋጁ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ከምክር ቤት አባል ውጭ እንዲሾም የሚፈቅድ ስለመሆኑም ይናገራሉ። አከራካሪው አዋጅ ቁጥር 1094/2010 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ ምርጫን ላልተወሰነ ጊዜ ያራዘመውና የአዲስ አበባ ምክር ቤትም ባለበት እንዲቀጥል የወሰነው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 365/1995ን በአዋጅ ቁጥር 1094/2010 በማሻሻል ነው። አቶ ሄኖክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባን ምክር ቤት የሥራ ዘመን የማራዘም መብት የለውም በማለት ይከራከራሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን የሥራ ዘመን የማራዘም መብት ሳይኖረው በዚህ አዋጅ አማካኝነት የከተማ አስተዳደሩን የሥራ ዘመን እንዲራዘም መደረጉ አሁን ያለው የከተማው አስተዳደርና ምክር ቤት የሕግ አግባብነት እንደሌለው ይናገራሉ። ሕገ መንግሥቱ ላይ አንቀጽ 49.2 ከተማ አስተዳደሩ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል ይላል እንጂ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲሰ አበባ ምክር ቤት የሥራ ዘመንን ያራዝማል በሚል የተጠቀሰ ቦታ የለም ይላሉ አቶ ሄኖክ። • በሃገሪቱ የተከሰቱት ቀውሶችና አዲስ አበባ ''ከፖለቲካ አንጻር ብንመለከተው እንኳን ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ ምርጫ እንዲካሄድ የማይፈቅድ ከሆነና ለአንድ ዓመት እንኳ አሸጋጋሪ መንግሥቱን እንቀበለው ብንል፤ ወደ ስልጣን የሚመጣው መንግሥት የከተማው ህዝብ ካለው ራሱን የማስተዳደር መብትና ከሕገ መንግሥቱ ጋር በተጣጣመ መንገድ መሆን ይኖርበታል። ይሁን እንጂ ይህን ከግምት ውስጥ ያላስገባ በመንግሥት የተሰየመበት ሁኔታ የበለጠ ቀውስና ችግር የሚፈጥር ሆኖ አግኝተነዋል'' ይላሉ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤትን የሥራ ዘመን ማራዘም አይችልም፤ አዋጅ ቁጥር 1094/2010 ሕጋዊ አግባብነት የለውም በሚለው ላይ ምላሻቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ ''የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1094/2010 ማጽደቅ አይችልም ከተባለ፤ እሱ ላይ አስተያየት መስጠት አልችልም። እኛ ግን አዋጁን በሕጋዊ መንገድ ተግባራዊ እያደረግን ነው'' ብለዋል። አቶ ኤፍሬም ታምራት የሕግ ባለሙያ ሲሆኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ምክር ቤቱን የሥራ ዘመን ማራዘም እንደሚችል አስረግጠው ይናገራሉ። አቶ ኤፍሬም ሃሳባቸውን ሲያስረዱ ''በሕገ መንግሥቱ ላይ አንቀጽ 49 ስር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌደራሉ መንግሥት መሆኑና የከተማ አስተዳደሩ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን ለመደንገግ ዝርዝር ሕግ ይወጣል ይላል። ዝርዝር ሕግ ተብሎ ከተጠቀሰው መካከል አንዱ ቻርተሩ ነው። በቻርተሩ ላይ ደግሞ በግልጽ የፌደራሉ መንግሥት በራሱ አነሳሽነት ቻርተሩን ሊያሻሽለው እንደሚችል ተገልጿል።" የከተማ መስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 365/1995 ያወጣው የፌደራል መንግሥቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግሥቱ አንደኛ አካል ነው ይላሉ አቶ ኤፍሬም። አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግሥቱ ነው ሲባል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ይመለከታል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ስልጣን የተቀዳለት ከፌደራል መንግሥቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። ምክር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን የሥራ ዘመን ሊያራዝም እንደሚችልም ይጠቅሳሉ። የአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ መቼ ይካሄዳል? የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለው ነባራዊ ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምርጫን ማካሄድ አይቻልም በማለት ምርጫው በ2011 ዓ.ም ላይ እንዲካሄድ ማራዘሙ ይታወቃል። በውሳኔው መሰረትም ዓመቱ ሳይጠናቀቅ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ሊያከናውን እንደሚችል ሲጠበቅ ነበር። ይሁን እንጂ ምርጫ ቦርድ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ምርጫ ማካሄድ እንደማይችል አስታውቋል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግነኙነት ኃላፊ ወ/ሪ ሶሊያና ሽመልስ፤ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደታሰበው ምርጫውን ማካሄድ እንደማይችል ጠቅሶ ምክር ቤቱ ውሳኔ እንዲሰጥበት በደብዳቤ አሳውቋል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ፤ ''የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤቶች ምርጫን ጨምሮ የአካባቢ ምርጫን ለማከናወን የሚያስፈልጉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላና ስልጠና ለመስጠት፣ ተቋማዊ የለውጥ ሥራዎችን በየክልሉ በተዋረድ አጠናቆ ለማስፈጸም ጊዜ አለመኖሩንና ዓመቱ እየተጠናቀቀ በመምጣቱ ምክር ቤቱ ውሳኔ እንዲሰጥበት ደብዳቤ ተልኳል'' ሲሉ ተናግረዋል። የባላደራ ሚና እስከ ምን ድረስ ነው? የአዲስ አበባ ሕዝብ የመረጠው መንግሥት ወደ ስልጣን ቢመጣ የባልደራሱ ሚና ምን ሊሆን እንደሚችል የባልደራስ የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ሄኖክ አክሊሉ ሲናገሩ ''ከሕዝብ የተሰጠ ሁለት አደራ አለ'' የሚሉት አቶ ሄኖክ "የመጀመሪያው ዜጎችን በእኩል ዓይን የማይመለከት አስተዳደርን መታገል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 'የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ድንበር በተመለከተ ሁለቱ አካላት የሚደራደሩበትን ሁኔታ እንድንመለከ ህዝብ የሰጠን አደራ አለ'' ይላሉ። የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ወሰን አለመግባባት የተፈጠረበት ነው የሚሉት አቶ ሄኖክ ''በጠቅላይ ሚንስትሩ በተቋቋመው ኮሚሽን የድንሩን ለማካለል በአዲስ አበባ በኩል በምክትል ከንቲባው በኦሮሚያ በኩል ደግሞ በፕሬዝደንቱ የሚመራ ቡድን እንደተሰየመ ይታወሳል። ሁለቱም ተደራዳሪዎች ተመሳሳይ ፍላጎት ስላላቸው እና የአዲስ አበባን ጥቅም የሚወክል ስለሌለ የከተማዋን ጥቅም እናስከብራለን" ይላሉ። • ሶሪያውያን ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ይህም የከተማው ሕዝብ የሚመርጣቸው ተወካዮቹ የነዋሪውን መብትና ጥቅም በሚያስከብሩበት ሁኔታ እስከሚመረጡ ድረስ ጥኣቄዎቹን በማንሳት ተቀበልናቸው የሚሉትን አደራዎች ለማስፈጸም እንደሚሰሩ ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት ያለው የከተማዋ መስተዳደር የስልጣን ዘመኑ ማብቃትና "ከሕግ ውጪ" ተሾሙ የተባሉት ከንቲባ ጉዳይ እስካሁን እያነጋገረ ቢሆንም፤ አሁንም ምርጫ ለማካሄድና የተመረጠ አስተዳደር ለማቋቋም አመቺ ሁኔታዎች እንደሌሉ እየተገለጸ ነው። ለዚህ ደግሞ በቀጣይ ዓመት ይደረጋል ተብሎ የሚታሰበውን አጠቃላይ ሃገራዊ ምርጫ መጠበቅ የግድ ሳይሆን አይቀርም። ይህ ደግሞ የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ ከቀሪው የሃገሪቱ ክፍሎች ምርጫ ተነጥሎ ለብቻው ሲካሄድ የነበረውን የአዲስ አበባ ምርጫ ወደነበረበት እንዲመለስ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።
news-47879359
https://www.bbc.com/amharic/news-47879359
"ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ
በደርግ ስርዓት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ጉዳዮች ተመራማሪ የሆኑት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ "ኢትዮጵያ በቀውስ አፋፍ ላይ ናት" የሚል ጽሑፍ ፅፈው በተለያዩ ድረ ገፆችና በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሻለቃ ዳዊት የጽሑፋቸው አላማ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ማስረዳት እንደሆነ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ እየወደቀች ነውም ብለዋል።
ሻለቃ ዳዊት፡ የጽሁፌ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ማስረዳት ነው። በሃገሪቱ የሚከናወኑ ብዙ ነገሮች ስላሉ ህዝቡ ተወጥሮ ያለው በዕለት ተዕለት ጉዳዮች ላይ ነው። እነዚህ ሁሉ ግን ተደምረው በጠቅላላ የሃገሪቱ ስእል ምን ይመስላል የሚለውን ለማሳወቅ ነው የፈለግኩት። እናም በደህንነት ረገድ፣ በኢኮኖሚና በአጠቃላይ በአመራር ደረጃ ያለውን ስንመረምረው ጠቅላላ ኢትዮጵያ የከሸፈች ሃገር ( failed state) ወይም ከቁጥጥር ውጪ የሆነች አፍሪካዊ ሃገር እየሆነች ነው። ቁጥሮቹን በሙሉ ጽሁፌ ላይ አስቀምጫለው። • የመደመር እሳቤ ከአንድ ዓመት በኋላ • "የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ" መሐመድ አደሞ እኔ ያደረግኩት በሜዳ ላይ የሚታዩትን ሃቆች አውጥቶና ስእሉ ሲደመር የኢትዮጵያ አቅጣጫ ምን ይመስላል? የሚለውን ለመመለስ ነው የሞከርኩት። አቅጣጫው አደገኛ አቅጣጫ ነው። አመራሩ አስፈላጊና ከባድ ውሳኔ ካልወሰነ በስተቀር አዘቅት ውስጥ ገብታ ምናልባትም የእርስ በርስ ጦርነት ሊያመጣ የሚችል ሁኔታ ይፈጠራል። ይህንን ለማስቀረት መደረግ ስለላባቸው ነገሮችም ጠቁሜያለው። ምናልባት መደረግ ያለባቸው ነገሮች አስቸጋሪና ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን በከባድና አስቸጋሪ ጊዜ ከባድና አስቸጋሪ ውሳኔ መወሰን ያስፈልጋል። በእንደዚህ አይነት ጊዜ ያሉ አመራሮችም መጥፎ ሁኔታ ላይ እንዳለን ሲያውቁ መደረግ ያለበት ውሳኔ መራራ ሆኖ፤ ነገር ግን በረጅም ጊዜ ኢትዮጵያን የሚያድን ይሆናል እንጂ ስለፍቅር በመናገርና ህዝቡን በማባበል፤ ተስፋ በመስጠት ያጋጠመንን ችግር መፍታት አይቻልም ለማለት ነው። ሃገሪቱ አዲሱ አስተዳደር ከመምጣቱ በፊት ከነበረው የባሰ ሁኔታ ውስጥ ናት ማለት ይቻላል? ሻለቃ ዳዊት፡ አዎ፤ በጣም እንጂ፤ በትክክል። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያን በመፈናቀል ደረጃ የወሰድን እንደሆነ፤ ድሮም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከመምጣታቸው በፊትም ነበረ። አሁን ግን በጠቅላላው በጣም እየባሰ መጥቶ በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ በሚባል ደረጃ ብዙ ሰው የተፈናቀለባት ሃገር ኢትዮጵያ ናት። እስከ አራት ሚሊየን ህዝብ ተፈናቅሏል። በጠቅላላው ደግሞ የሃገሪቱ የደህንነት ሁኔታ ስንመለከት አንድ ሃገር ውስጥ በነጻነት መንቀሳቀስ የማይቻልበት ሁኔታ ነው ያለው። እንደዚህ አይነት ነገሮች ደግሞ የሚፈጠሩት እንደ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ማዕከላዊ አፍሪካ ባሉ የከሸፉ ሃገራት ነው። በግለሰብ ደረጃ ስንመለከተው ደግሞ እያንዳንዱ ሰው በስጋት ነው የሚኖረው። ሲወጣም ሆነ ሲገባ በስጋት ውስጥ ሆኖ ነው። የኢኮኖሚውን ዘርፍ ያየነው እንደሆነ ሌላው ቀርቶ መድሃኒትና ነዳጅ ለመግዛት የሚያስችል የውጭ ምንዛሪ ብቻ እንጂ ከዚያ ውጪ ባንክ ውስጥ ምንም መጠባበቂያ እንደሌለ ብሔራዊ ባንክ ተናግሯል። • ሕዝብ ስለመሪው ምን እንደሚያስብ እንዴት እንወቅ? ከዚህ በተጨማሪ አሁን እያስተዋልነው ያለነው መሰዳደብና መዘላለፍ በህዝብ መሃል ያለውን ተቃርኖ እያባባሰው ሄዷል። ይሄ ሁሉ የአመራርና የፖሊሲ ጉዳይ ነው። አመራርና ፖሊሲ እስካልተቀየረ ድረስ ይሄ ሊለወጥ አይችልም። እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው። ሃገሪቱ በእኔ እድሜ በኃይለስላሴም፣ በደርግም ሆነ በኢህአዴግ እንደዚህ አይነት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሳ አታውቅም። ይሄ ችግር ከዚህ በፊት ሲጠራቀም የመጣ እንደመሆኑ አሁን እንዴት በጣም አሳሳቢ ሊሆን ይችላል? ሻለቃ ዳዊት፡ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመምጣት ጋር ተያይዞ የህዝቡ ችግር የነበረውን አስወግዶ አዲስ ምዕራፍ ለኢትዮጵያ ይከፍታል የሚል እምነት ነበር። ስለዚህ ቃል በተገባው መሰረት የተባለው ነገር ስላልተደረገ ችግሩ ቀስ እያለ መፈንዳት ጀምሯል። ይህ ማለት ግን ችግሩ የአንድ ሰው ጥፋት ነው፤ ወይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ችግር ነው ለማለት ሳይሆን እሳቸው ወደ ስእሉ ሲገቡ ችግሩን አስወገደው ሃገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግራሉ የሚል እምነት ነበረ። ቃል የተገባው ነገር አልተፈጸመም። ባለመደረጉ ደግሞ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል። • የጠቅላይ ሚንስትሩን የአንድ ዓመት የስልጣን ዘመን እንዴት ይመዝኑታል? እርሶ የጠቀሷቸው ነገሮች በሽግግር ወቅት የሚያጋጥሙ ናቸው የሚሉ ሰዎች አሉ ሻለቃ ዳዊት፡ አልተሸጋገርንም፤ ለውጥም የለም። ለውጥ ማለት የስርአት ለውጥ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብም የጠየቀው የስርአት ለውጥ ነው። እዚህ ችግር ውስጥም የከተተን የነበረው ስርአት ነው። አብዛኛዎቹ ነገሮች እንዳሉ ናቸው። እስከ ዛሬ ድረስ ተቀየሩ የሚባሉት ነገሮች በስርአት አቅጣጫ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በግል በወሰዷቸው እርምጃዎች ነው። ነገር ግን ይሄ ለለውጡ ሁኔታውን ለማመቻቸት ነው እንጂ በራሱ እንደ ለውጥ ልንመለከተው የምንችለው ነገር አይደለም። እስካሁን ለተፈጠሩት ችግሮች በሙሉ ኢህአዴግን ተጠያቂ ማድረግና ኢትዮጵያ በአዲስ ህገመንግስት አዲስ ምርጫ ውስጥ እንድትገባ ማድረግ ነው ትክክለኛው ለውጥ። ጠቅላዩ በስልጣን ለአንድ ዓመት ቆይተዋል፤ በአንድ ዓመት ውስጥም ምንም ነገር አልታየም። ይህ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፍኖተ ካርታ ስለሌላቸው ወዴት አቅጣጫ እንደሚኬድ አያውቁትም። ሕገ-መንግሥቱ እንዴት እንደሚሻሻልና ወደ አዲስ ምርጫ እንዴት መሄድ እንደምንችል ትክክለኛ አቅጣጫ ማስቀመጥ የሚችል ፍኖተ ካርታ ያስፈልገናል። መሰረታዊ የህግ ለውጦች ካስፈለጉ ሙሉ የህዝብ ውክልና ያለው መንግስት ነው ሕገ-መንግሥቱን መቀየር ያለበት? ሻለቃ ዳዊት፡ በአሰራሩ መሰረት ለውጥ የሚመጣው ወይም ሕገ-መንግሥትን የሚፈጥረው መንግሥት ሳይሆን ሕገ-መንግሥቱ ነው ስልጣን ያለው መንግስት መፍጠር የሚችለው። አሁን ለውጡ ይካሄድ ሲባል ባለው ሕገ-መንግሥትና ባለው መንግሥት ለውጥ ሊካሄድ አይችልም። ለውጥ ሊመጣ የሚችለው አዲስ ሕገ-መንግሥትና አዲስ መሰረታዊ ሃሳቦች ተፈጥረው ሲታዩ ነው። • የዐቢይ ለውጥ፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ? • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ 6 ዋና ዋና ዕቅዶች ያለው መንግሥት እንዳለ ሆኖ ለውጥ ሊመጣ አይችልም። እነዚህን ሁሉ ችግሮች የፈጠረው ጠቅላዩ የሚመሩት ኢህአዴግ ነው። ምናልባት እሳቸው በቀጥታ ላይመለከታቸው ይችላል፤ ነገር ግን ፓርቲው ለብዙ ነገር ተጠያቂ ነው። ስለዚህ ሕገ-መንግሥቱ ፈርሶና አዲስ መንግሥት መጥቶ ነው ለውጥ ልንመለከት የምንችለው። ሁሉንም ሰው የሚያስማማ ነገር ማምጣት ይቻላል? ሕገ-መንግሥቱን ማንሳቱ ወደሌላ ቀውስ አይመራም? ሻለቃ ዳዊት፡ ቀውስማ አሁንም ተፈጥሯል። ከዚህ የባሰ ቀውስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈጠር አይችልም። ስለዚህ ዋናው ነገር ለዘለቄታው ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንድትኖር ከባድ ውሳኔ መሰጠት አለበት። ዋናው ችግራችን የምንከተለው በዓለም ውስጥ የሌለ የብሄር ፌደራሊዝም ነው። ይህ ስርአት በዓለም የለም፤ በአፍሪካም የለም። ትንሽ ተቀራራቢ አሰራር ያለው ኮሞሮስና ናይጄሪያ ውስጥ ነው። እሱም ቢሆን በዋነኛነት በዘር ላይ የተመሰረተ አይደለም። የብሄር ፌደራሊዝሙም ቢሆን ህዝቡን አማክሮ አወያይቶ አልነበረም ተግባራዊ የተደረገው። ሕገ-መንግሥቱን ሲያረቅቁት ትልቅ ስህተት ተሰርቷል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ራሳቸው ተሳስተናል፤ ህዝቡን አላማከርነውም ነበር ብለዋል። እኔ እያልኩ ያለሁት ህዝቡ በደንብ ይመከርበትና አዲስ ሕገ-መንግሥት ይፈጠር ነው። ይህንን የብሄር ፌደራሊዝም ይዘን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ይመጣል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ሰላም አለመገኘት ብቻ ሳይሆን እልቂት ይፈጠራል፤ ምንም ጥርጥር የለውም። አሁን እየጠቀሱት ላለው ችግር መፍትሄው ምንድነው ይላሉ? ሻለቃ ዳዊት፡ መፍትሄው በቀላሉ የሚገኝ ነገር አይደለም። የደፋር እርምጃ ያስፈልጋል። በእንደዚህ አይነት የችግር ጊዜያት የሚመጡ ብዙ መሪዎች ጠንካራ ውሳኔ መወሰን መቻል አለባቸው። ቀላል ነገር ቢሆን ኖሮ ማንም ሰው ያደርገው ነበረ። በጽሑፌ ላይ ለመጠጥቀስ እንደሞከርኩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካልቻሉ፤ አልቻልኩም ብለው ከስልጣን ይልቀቁና አማራ ወይንም ኦሮሞ ያልሆነ ሰው ስልጣኑን ይረከብ። ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት ያለው ችግር በአማራና በኦሮሞ መካከል ያለው ፉክክርና በሁሉም ዘርፍ ያለው ሽሚያ ነው። ወደ ሽግግር ሊያመጣን የሚችል መሪ ያስፈልገናል። ሁለተኛ ያለን አማራጭ ደግሞ፤ እሺ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይቆዩ የሚባል ከሆነ ሕገ-መንግሥቱ ፈርሶና የኢህአዴግ ፓርላማ ተበትኖ እሳቸው በአዋጅ አሸጋጋሪ ሆነው የሃገሪቱን አጀንዳ ይዘው መሄድ አለባቸው። • መፈናቀል፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ዓመት ፈተናዎች አንዱ • ጌዲዮ በዐቢይ ጉብኝት ማግስት አሁን ችግር የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበርም ናቸው። ሁለቱ አብሮ ሊሄድ አይችልም። መምረጥ መቻል አለባቸው። ወይ የኢትዮጵያ መሪ አልያም የኦሮሞ መሪ መሆን አለባቸው። የሁለቱም መሪ ሊሆኑ አይችሉም። የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም አስጠብቃለሁ እያሉ የኢትዮጵያውያንን ጥቅምም አስጠብቃለሁ ማለት አይችሉም። በሌሎች ሃገራት እኮ ሙሉ ሃገሪቱን የሚወክል ፓርቲ ነው ያለው። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይዘው፤ ከዘረኛ ፖለቲካ ወጥተው መምራትና ማሸጋገር ይችላሉ። ግን ይሄንን ለማድረግ ሕገ-መንግሥቱ መፍረስ አለበት። የዘር ድርጅቶች የሲቪክ ድርጅቶች ሆነው የህዝቦቻቸውን መብቶች የሚያስጠብቁበት ሁኔታ መፈጠር አለበት። የፖለቲካ ድርጅቶች መሆን አይችሉም የሚል ህግ መውጣት አለበት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እየሰሩ እንደሆነ አያምኑም? ሻለቃ ዳዊት፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ናቸው። ስለዚህ ፓርቲያቸው የሚፈልገውን ነገር መፈጸም አለባቸው። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያውያንን አጀንዳ መያዝ አለባቸው፤ ይሄ ደግሞ ይጋጫል። አሁን የምናያቸው ችግሮች ሁሉ የተፈጠሩት በሁለቱ ሃላፊነቶች መጋጨት ምክንያት ነው። ይህንን ጠንካራ ውሳኔ ለመወሰን ብዙ ሥራና መነጋገር ይጠይቃል። የኢትዮጵያን አጀንዳ ይዞ በየሃገሩና በየክፍለሃገሩ መናገርና ሰዉን ማሳመን መቻል አለባቸው። መጀመሪያ ላይ እኮ ህዝቡ ከፈጣሪ በታች አድርጎ የተቀበላቸው ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይዘው በመምጣቻው ነበር። አሁን ግን እሳቸው የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብንና የኦዴፓን ጥያቄ ይዘው ነው የመጡት።
47114579
https://www.bbc.com/amharic/47114579
የኩላሊት መድከም የገጠማቸው ሰዎች ተስፋ-ንቅለ ተከላ
የኩላሊት መድከም የገጠማቸው ሰዎች ተቸግረው፣ ሕመማቸው በርትቶ፣ ጎዳና ወጥተው ተመልክተናል፤ በየመገናኛ ብዙሃኑ የድረሱልኝ ጥሪያቸውን ሰምተናል። በአደባባዩች ፎቷቸውን ሰቅለው ለህክምና ምፅዋት ሲጠይቁ አድምጠናል።
ሰርተው ይበሉ የነበሩ እጆች ተይዘው፣ ያስተዳድሩት የነበረው ቤተሰብ ተበትኖ የነገን ፀሐይ ለመሞቅ ማሰብ ቅንጦት ሲሆንባቸው ማጣታቸውን ቆርሰው ያካፈሉ፣ በሙያቸው የቻሉትን አስተዋፅኦ ያበረከቱትንም ተመልክተናል። • "ፍቃዱ ተክለማርያም የሀገር ቅርስ ነው" ድምጻውያን "እኔ ነኝ ደራሽ" ሲሉም አቀንቅነው ልባችንን ነክተው ኪሳችንን እንድንዳብስ አድርገዋል። ይህ ትናንት የሚመስለው የኩላሊት መድከም ወሬ ዛሬ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል። "እኛ ብቻ አይደለንም፤ ዘመዶቻችንም ታመዋል" መሪማ መሐመድ ጦይብ የተሻለ ኑሮን ለመምራት በማሰብ ነበር ወደ አረብ ሀገር ያቀናችው፤ ነገር ግን ብቸኛ ሀብቴ ያለችው ጤናዋ ከዳት። ዘወትር ከብርታት ይልቅ ድካም በጎበኛት ቁጥር ሕክምና ወደ ምታገኝበት ስፍራ ሄደች። የሰማችው ነገር ግን ጆሮን በድንጋጤ ጭው የሚያደርግ ዜና ነበር። "ሁለቱም ኩላሊቶችሽ ከጥቅም ውጪ ሆነዋል" ተባልኩኝ ትላለች። ስለዚህ ቢያንስ ሞቴን በዘመዶቼ መካከል፣ በሀገሬ አፈር ብላ ብላ ጓዟን ጠቅልላ ወደ ሀገሯተመለሰች። • ልብ የረሳው አውሮፕላን አቶ አለነ ወልደማሪያም ደግሞ የስኳር ሕመምተኛ ናቸው። የስኳር ሕመምተኛ ሲኮን ካሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የኩላሊት መድከም አንዱ እንደሆነ ያውቁ ስለነበር ሁሌም ስጋት ሽው ይላቸው ነበር። አንዳንድ የህመም ምልክቶቻቸው ደግሞ ስጋታቸው እውን እንደሆነ እንዲሰማቸው ያደርጉ ጀመር። ወደህክምና ተቋም ሄደው ሲመረመሩ ስጋታቸው ልክ እንደሆነ አረጋገጡ፤ ኩላሊታቸው ደክሟል። የስኳር በሽታው እና የኩላሊት ህመሙ ተደራርቦ አልጋ ላይ ጣላቸው። ሌሎች የጎንዮሽ ህመሞች መደራረብ ደግሞ አልጋ ላይ የሚቆዩበትን ጊዜ አረዘመው። መሪማ ሀገሯ ስትመለስ ዘመድ ወዳጆች ተረባርበው ወደ ግል ሆስፒታል ወሰዷት። የሄደችበት የግል ሆስፒታል ለአንድ ቀን ለመታጠብ፣ ለመድሃኒት፣ ለታክሲና ለአንዳንድ ነገሮች እስከ ሦስት ሺህ ብር ያስወጣን ነበር ትላለች። • ወደ ካናዳ መሄድ አስበዋል? ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ "ይህንን ወጪ በየቀኑ ማሰብ ከሕመሙ በላይ የሚሰማ ሕመም ነው። ይህ የሌላቸው የዘመድ እጅ ወደ ማየት ንብረት ወደመሸጥ ይሄዳሉ" ትላለች መሪማ። አቶ አለነም ቢሆኑ ለእጥበቱ የሚወጣውን ወጪ ለመሸፈን ወደ ጎዳና ላለመውጣት ቤተሰቦቻቸው አግዘዋቸዋል። ለተከታታይ ስምንት ወራት የኩላሊት እጥበት ሲያደርጉ ቤተሰቦቻቸው ያላቸውን ንብረት ለመሸጥ ሃሳብ አቅርበውላቸው እንደነበር ይናገራሉ። ጥሪት አሟጠው፣ ቤተሰቦቻቸውን ያለ መጠለያ አስቀርተው፣ ጤናቸውን መመለስ ግን አልፈለጉም። "ሞት እንኳ ቢመጣ አንድ ነፍሴን ይዤ እሄዳለሁ" በማለት አሻፈረኝ አሉ። መሪማ ሰዎች የኩላሊት እጥበት ለማድረግ የሚያስፈልገውን ወጪ መሸፈን አቅቷቸው ሲሞቱ ስታይ ነገም የእኔ እጣ ይህ ነው በማለት የፍርሃት ቀዝቃዛ ዳና ይሰማት ጀመር። • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና መሪማ ሞትና ሕይወት እጣ እየተጣጣሉባት እንደሆነ ታስብ እንደነበር ትናገራለች። ሐኪሞች በኩላሊት እጥበት መዳን እንደማይቻል፣ ኩላሊት የሚሰጥ ዘመድ ካገኙ ንቅለ ተከላ ማካሄድ ብቸኛ መፍትሄ እንደሆነ ለሁለቱም እንደነገሯቸው ያስታውሳሉ። መሪማ እህቶቿ ወደ ህንድ ሄዳ ንቅለ ተከላ እንድታካሄድ ሃሳብ አቀረቡ። ነገርግን እህቶቿን አስቸግራ፣ አንገት ማስገቢያ ቤታቸውን ሸጠው፣ ወደ ውጪ ሄዶ የመታከም ሀሳብ በጭራሽ አልነበራትም። ስድስት ሰባት ሰው የሚጠለልበትን ቤት ለሽያጭ ማቅረብ ቤተሰቡን እንደመበተን ተሰማት። • የአከርካሪ ቀዶ ጥገና ባልተወለዱ ልጆች ላይ ከዘመዶቿ ውጪም የማንንም እጅ ላለማየት ለራሷ ቃል ገብታለች። ያላት ተስፋ እጥበቱን እያካሄደች ከነገ ማህፀን የሚወለድ ተስፋን መጠበቅ ብቻ ሆነ። ተስፋ ጠፍቶ ሐዘን ባጠላበት አንድ ቀን ጆሮዎቿ መልካም ወሬ ሰሙ። ሕይወት በክር ጫፍ መሪማ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንደሚያካሂድ ስትሰማ ጆሮዎቿን ማመን አልቻለችም። ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት ህክምና ለማግኘት ተመዘገበች። ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ይህንን ዜና ሲሰማ ኩላሊቱን ለመስጠት ተሽቀዳደመ። አብድሩሃማን መሐመድ የመሪማ መሐመድ ልጅ ነው። ኩላሊታቸውን ለመለገስ ከተስማሙ ቤተሰቦች መካከል ቀዳሚው ነበር። ነገር ግን በተደረገለት ምርመራ እንደማይችል ተነገረው። በዚህ ቀን እንኳ ለእናቱ ያለውን ማካፈል ባለመቻሉ አዘነ። አካሏን ከደፍላ ያኖረችው እናቱን አካሉን ከፍሎ ማኖር ባለመቻሉ ከፋው። የአክስት ልጅ የአጎት ልጅ እኛ አለን ሲሉ ተረባረቡ። የሚመረመሩት ሁሉ በአንድም በሌላም ምክንያት መስጠት እንደማይችሉ እየተነገራቸው ተመለሱ። ለመሪማ መሐመድ ኩላሊት የሚለግስ ሳይጠፋ ኩላሊቱ ግን ጠፋ። በዚህ መሀል የአክስቷ ልጅ ሙና መሀመድ ስትመረመር መስጠት እንደምትችል ታወቀ። "ለአክስቴ መዳን ምክንያት በመሆኔ ደስተኛ ነኝ" ትላለች ሙና። መሪማ ግን "ለአቧቷ አንድ ሴት ልጅ፣ ያልወለደች፣ ያልከበደች እንዴት ኩላሊቷን ወስጄ በአንድ አስቀራታለሁ" ስትል አሻፈረኝ አለች። አቶ አለነ ወልደማሪያም ከሐኪማቸው ንቅለ ተከላ በሐገር ውስጥ ማግኘት እንደሚችሉ ሲነገራቸው 'እራሴን ለማኖር የሌላ ሰው ኩላሊት እንዴት እወስዳለሁ' የሚል ሀሳብ ፈትሮ ያዛቸው። በሕይወት መንገድ ላይ ራሳቸውን አስቀድመው ያዩ ስለመሰላቸው አንገራገሩ። ሐኪሙ ግን በአንድ ኩላሊት መኖር እንደሚቻል በመንገር ለማሳመን ሞከሩ። እህት ወንድሞቻቸውም እኛ እያለን ወንድማችን አልጋ ይዞ አይቀርም በሚል ተረባረቡ። የመኖር ዋጋው፣ የነገን ፀሐይ ማየት፣ በወዳጅ ዘመድ መካከል በፈገግታ ታጅቦ የመገኘት ዋጋ ውድ ነው የሚሉት አለነና መሪማ የዘመዶቻቸውን ስጦታ ተቀብለው ንቅለ ተከላው ተካሄደላቸው። ህክምናው ደግሞ በአብዛኛው በነፃ የሚሰጥ መሆኑ የበለጠ ደስታቸውን አድልቦታል። ሁለቱም መድሃኒቱን ለመግዛት ብቻ ገንዘብ እንደሚያወጡ ተናግረዋል። "በአንድ ኩላሊት የሚኖር ሰው ስጋት ሊኖረው አይገባም" ዶ/ር ብርሃኑ ወርቁ የኩላሊት ስፔሻሊስት ሲሆኑ በጳውሎስ ሆስፒታል የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል ይሰራሉ። በሆስፒታሉ ማንም ሰው የኩላሊት መድከም ካጋጠመው መጥቶ በነፃ መታከም ይችላል የሚሉት ዶ/ር ብርሃኑ ነገር ግን ታማሚው ኩላሊት የሚለግሰው፣ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ሊኖረው ይገባል ሲሉ ያስረዳሉ። ዝምድና ካላቸው ሰዎች ብቻ የኩላሊት ልገሳውን የሚቀበሉት በዋናነት ህገወጥ የአካል ሽያጭን ለመከላከል እንደሆነ ያስረዳሉ። የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲካሄድላቸው የሚፈልጉ ሕሙማን ማሟላት ካለባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ኩላሊቱን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ፣ እድሜው በራሱ ለመወሰን የሚያስችለው ደረጃ ላይ የሚገኝ ሰው ማምጣት እንደሆነ ዶ/ር ብርሃኑ ይናገራሉ። ሌላው የኩላሊትም ሆነ ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች የሌሉበት፣ በተለይ በረዥም ጊዜ በራሳቸው የኩላሊት መድከም ሊያመጡ የሚችሉ ህመሞች የሌሉበት ግለሰብ መሆን አለበት ይላሉ። አክለውም ኩላሊት የሚሰጡ ሰዎች ከመስጠታቸው በፊት አስፈላጊው ምርመራ ሁሉ እንደሚደረግላቸውም ያስረዳሉ። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ በአንድ ኩላሊት የሚኖሩ ሰዎች የተለየ ስጋትና ፍራቻ ሊኖራቸው አይገባም የሚሉት ዶ/ር ብርሃኑ ለጋሾችምሆኑ ተቀባዮች ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ መምራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ይመክራሉ። ኩላሊታቸውን የሚለግሱም ሆኑ የሚቀበሉ በአግባቡ የህክምና ክትትላቸውን ማድረግና የሕክምና ባለሙያዎችን ምክር መከተል ያስፈልጋቸዋል የሚሉት ዶ/ር ብርሃኑ፤ ንቅለ ተከላውን ያደረጉ ሰዎች ደግሞ አዲሱ ኩላሊታቸው ከእነርሱ ጋር አብሮ የሚቆየው መድሃኒታቸውን በአግባቡ መውሰድ እስከቻሉ ድረስ ብቻ ስለሆነ የሐኪሞችን ምክር መከተል የግድ ነው ይላሉ። "የኩላሊት መድከም ገጥሟቸው ንቅለ ተከላ የሚካሄድላቸው ሕሙማን የወሰዱት የሌላ ሰው ኩላሊት ስለሆነ ሁሌም አዲሱ ኩላሊት ሰውነታቸው ውስጥ እንግዳ ሆኖ ነው የሚኖረው" የሚሉት ዶክተሩ መድሃኒታቸውን ካልወሰዱ አካላቸው ኩላሊቱን እንደባዕድ ስለሚቆጥረው ይታመማሉ ይላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የኩላሊት ንቅለ ተከላ በብቸኝነት የሚሰጠው የመንግሥት የጤና ተቋም ቅዱስ ጳውሎስ ሲሆን አገልግሎቱን መስጠት ከጀመረ ሦስት ዓመት እንደሆነው ዶ/ር ብርሃኑ ይናገራሉ። እስከ አሁን ድረስ በማዕከሉ አንድ መቶ ያህል ሰዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላውን አካሂደዋልም ይላሉ።
46323991
https://www.bbc.com/amharic/46323991
"የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ የለውጥ መንፈሱን ተከትሎ መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ ወደ አገር ውሰጥ ከተመለሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር አንዱ ነው። በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ አንጋፋ የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ 'ፖለቲካ በቃኝ' እያሉ ነው የሚል መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየወጣ በመሆኑ አቶ ሌንጮ ለታን ስለ ጉዳዩ አነጋግረናል።
የፖለቲካ ሩጫዎን ጨርሰዋል እየተባለ ነው። አቶ ሌንጮ፡- ፖለቲካ በቃኝ ብዬ አላውቅም፤ መረጃውን ከየት እንዳመጡት አላውቅም። ከፓርቲ ኃላፊነትዎ ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል? አቶ ሌንጮ ፡ ገና ፈረንጅ አገር እያለሁ ጀምሮ እየጠየቅኩ ነው።ይህን ለድርጅቴም አሳውቄያለሁ፤ በይፋም ተናግሪአለሁ። ግን ራሴ ፈልጌ ነው። ገና ድርጅቱ መወሰን አለበት። በይፋ በደብዳቤ ድርጅትዎን የጠየቁት መቼ ነው? አቶ ሌንጮ፡- ጥያቄዬን በጽሑፍ አላቀረብኩም። ነገር ግን ለአባላት ስብሰባ ላይ በይፋ ከሚቀጥለው የማእከላዊ ኮሚቴ ምርጫ በኋላ ይሄን ኃላፊነት ተሸክሜ መቀጠል እንደማልፈልግ ተናግሪያለሁ። ፓርቲዎ ለጥያቄዎ ምን ምላሽ እየሰጠ ነው? አቶ ሌንጮ፦ ገና ነው። ነገር ግን አሁን ስብሰባ ሊካሄድ ስለሆነ ውሳኔ ይሰጣል። • በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ • "ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ • የሜቴክ ሰራተኞች እስር ብሔር ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ ተገለፀ ኃላፊነትዎን መልቀቅ የፈለጉት ለምንድን ነው? አቶ ሌንጮ፡- እርጅና እርጅና ከኃላፊነት ብቻ ነው የሚያግድዎት? ቀጣይ ተሳትፎዎት ምን ይሆናል? አቶ ሌንጮ፡- እንደ አንዳንድ ኃላፊዎች እያነከስኩ ስብሰባ መሄድ አልፈልግም። ነገር ግን ሕይወቴ እስካለ ድረስ የፖለቲካ ሥራን መተው አልችልም። ረዥም ዓመታት በውጭ ሃገር ከቆዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር በተያያዘ የዜግነት ጉዳይ ይነሳል። ዜግነትዎ ምንድን ነው? አቶ ሌንጮ፡- የኖርዌይ ፓስፖርት ነው ተሸክሜ የምዞረው። ግን የዜግነቴ ጉዳይ በውሳኔዬ ላይ ምንም ተፅእኖ አልነበረውም። ነገሩ ኃላፊነት መልቀቅ ከመፈለጌ ጋር አይገናኝም። ብፈልግ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ለመመዝገብ ሲቃረብ የኖርዌይን ፓስፖርት ለኖርዌጅያኖቹ መልሼ ኢትዮጵያዊነቴን እንደገና ሥራ ላይ ማዋል እችላለሁ። ይህ ለውሳኔዬ ምክንያት የሆነ ነገር አይደለም። በውሳኔዎ እንደ እርሶ ለረዥም ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እየመሩ ላሉ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልእክት አለ? አቶ ሌንጮ፡- በተለይ ኦነግ ውስጥ ሃምሳ ዓመት ያገለገሉ ሁሉም ኃላፊነት ቢለቁ ጥሩ ነው ብዬ አምናለው። አሁን አዲስ ትውልድ ትግሉን ተረክቧል እና ለእነሱ መተው ነው የተሻለው መንገድ። በቀጣይ ተሳትፎዎት በምን መንገድ ይሆናል? አቶ ሌንጮ፡- ፓርቲውን እያገለገልኩ እቆያለሁ። ከሌሎች ጋር በስፋት ለመሥራትም እቅድ አለኝ። ስለዚህ ቆይታዎ የሚሆነው በኢትዮጵያ ነው? አቶ ሌንጮ፡- አዲስ አበባ
news-45593123
https://www.bbc.com/amharic/news-45593123
ኦህዴድ ስሙን ቀይሮ ኦዴፓ ተባለ
በጅማ ከተማ ድርጅታዊ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስሙን ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) መቀየሩን ይፋ አድርጓል።
ከጥቂት ወራት ቀደም ብሎ ድርጅቱ መለያው የሆኑትን ስያሜውንና አርማውን ለመቀየር እየተዘጋጀ እንደነበር ይታወቃል። በዚህም መሰረት ዛሬ ስያሜውን ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ሲቀይር በተጨማሪም ከቀረቡት መለያ አርማዎች ውስጥ የተመረጠው ላይ ማሻሻያ በመድረግ እግዲቀርብ መወሰኑን ከድርጅቱ የወጣ መረጃ ያመለክታል። • ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን? • ኤርትራ በምሽት ድንበር ማቋረጥን ከለከለች በተጨማሪም ፓርቲው ከመስራችና ነባር አባላቱ መካከል አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ሱለይማን ደደፎ፣ ወ/ሮ ጊፍቲ አባሲያ፣ አቶ እሸቱ ደሴ፣አቶ ድሪባ ኩማ፣ አቶ ጌታቸው በዳኔ፣ አቶ ግርማ ብሩ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ አቶ ደግፌ ቡላ፣ አቶ አበራ ኃይሉ፣ አቶ ተፈሪ ጥያሩ፣ አቶ ኢተፋ ቶላ እና አቶ ዳኛቸው ሽፈራውን በክብር አሰናብቷል ተብሏል።
news-52574818
https://www.bbc.com/amharic/news-52574818
“'ሥልጣንን ያለ ምርጫ ካልሰጣችሁኝ አገር አተራምሳለሁ' በሚል ኃይል ላይ እርምጃ እንወስዳለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በኮቪድ-19 ስጋት ከመራዘሙ ጋር ተያይዘው በሚሰጡ አማራጭ ኃሳቦች ላይ የሽግግር መንግሥት እንመሰርታለን የሚለው አስተያየት ህገ መንግሥታዊ መሰረት የሌለውና በዚህ ወቅት መነሳቱም ኃላፊነት የጎደለው ተግባር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ህገ - መንግሥቱ ከደነገገው ውጭ ያለ ምርጫ እንዲሁም በህገ ወጥ ምርጫ ስልጣን እቆናጠጣለሁ ብሎ የሚያስብ አካል የሃገሪቱንም ብቻ ሳይሆን አለም አቀፍ ድንጋጌዎችን እንደሚጥስ ከመጠቆም በተጨማሪ መንግሥታቸው እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቀዋል። • እውን የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል? • ምርጫ ቦርድ የጃዋር ዜግነትን አስመልክቶ ኢሚግሬሽንን ማብራሪያ ጠየቀ “ ከህግ አግባብ ውጭ ስልጣን ካልሰጣችሁኝ አገር አተራምሳለሁ የሚለውን ማንኛውንም ኃይል አንታገስም፤ በቂ ዝግጅትም አለን።” ብለዋል። የፌደራል መንግሥቱ ዋነኛ ኃላፊነት ህገ መንግሥቱን የመጠበቅና የመከላከል ዋነኛ ኃላፊነት መሆኑንም ገልፀው፤ ይህንን ተግባራዊ በማያደርጉና "የጨረባ" ምርጫ ለማድረግ እንነሳለን በሚሉም ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ መንግስታቸው እንደሚገደደም በአፅንኦት ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት መሰረት መንግሥት ለመመስረት ምርጫ ግዴታ እንደሆነ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምርጫ ሳይካሄድ ስልጣን ላይ መውጣት ህጋዊ መሰረትም የለውም ብለዋል። “የፖለቲካ ፓርቲ ስለሆንኩ ስልጣን ይገባኛል የሚለው ፈሊጥ ዲሞክራሲያዊም ሆነ ህገ መንግሥታዊ አካሄድ አይደለም፤ ያለ ምርጫ እንዲሁ ተጠራርቶ ስልጣን የሚከፋፈልበት ሁኔታም አያስሄድም" ብለዋል። በተለያዩ ሃገራት ውስጥ የተመሰረቱ የሽግግር መንግሥታት እንዴት ተመሰረቱ? የሚለውን ልምድ ያካፈሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአብዛኛውም ከወታደራዊ ወደ ዲሞክራሲያዊ በሚደረግ ሽግግርና ህገ መንግሥትም እስኪፀድቅ ድረስ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታ ለውጥ እንጂ አብዮት ባለመሆኑ የሽግግር መንግሥት ተቀባይነት የሌለው ኃሳብ ነው ብለዋል። “የኮቪድ- 19 ስጋት ባለበትና የቀጠናው ሁኔታው የሃገሪቱን ሉዓላዊነት በሚፈታተንበት ወቅት የሽግግር መንግሥት እመሰርታለሁ ማለት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው፤ ህገ ወጥም ብቻ ሳይሆን አደገኛ ነው” በማለት ተናግረዋል። ከመቶ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተደራድረው በሚያመጡት ፖለቲካዊ መፍትሄ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ማለት ሃገሪቷ እየገነባች ያለቸውንም ዲሞክራሲያዊ ስርአት ወደኋላ የሚመልስ ነው በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። “ህግ በጣሰ ሁኔታ ስልጣን እንደ ድግስ ትሩፋት ይዳረስ የሚለው አካሄድ ትክክል አይደለም፤ ለመሆኑ የተመረጠ መንግሥት እያለ ያልተመረጡ ፓርቲዎች ተሰባስበው መንግሥት የሚመሰርቱት በየትኛው የሞራል፣ የህግና የስርአት አካሄድ ነው” በማለት ይጠይቃሉ። አክለውም “ለወራት ምርጫን ማራዘም ወይስ? ለአመታት ለሽግግር መንግሥት ብሎ የብጥብጥና የሁከት መንግሥት መፍጠር ነው ኢትዮጵያን ለአደጋ የሚያጋርጣት?” ሲሉም ጠይቀዋል። በነሐሴ ወር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረውን ምርጫ በኮቪድ-19 ምክንያት ከመራዘሙ ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎችም መነሳት ጀምረዋል። • ፕሬዝደንት ኢሳያስ በዚህ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ለምን አስፈለጋቸው? • በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ ከሰሞኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሁን ባለው የኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ምርጫውን ማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ የምርጫ ጊዜንም በማራዘም ምርጫው ከሚካሄድበት አራት አማራጮች መካከል ‘ሕገ መንግሥታዊ ትርጓሜ መጠየቅ’ የሚለውን አማራጭ አፅድቋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ህገ መንግሥታዊ ትርጓሚ እንዲሰጥበትና ለህገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ መርቶታል። መንግሥት ያቀረባቸውም አራት አማራጮች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ ሕገ መንግሥትን ማሻሻልና የሕገ መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ ናቸው። መንግሥትም የተለያዩ አማራጮችን በህግ ባለሙያዎች ሲያስጠና እንደነበር የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሃገሪቱንም ሆነ የተለያዩ የህግ ድንጋጌዎችን በማስገባት አማራጭ ያሏቸውን ህጋዊ አግባብ በተመለከተ ያቀረቡ ሲሆን ከባለድርሻ አካላትም ጋር ውይይት ተደርጓል። በህግ አውጭው የሚቀርብ የህገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ በብዙ ሃገራት የተለመደና ህገ መንግሥታዊ ሃሳቦችን ወደ መሬት ማውረጃ መንገድ እንደሆነም በዛሬው ዕለት ተናግረዋል። ከህዝቡም ይሁን ከተለያዩ አካላት የተለያዩ አማራጮች እየቀረቡ እንደሆነ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህግ ባለሙያዎች ምርጫን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማራዘም እንደሚቻልና የተሻለው አማራጭ ይህ እንደሆነ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። በዚህ መልክ ምርጫው በመተላለፉ በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት እስከ ቀጣዩ ምርጫ በስራ ላይ የሚቀጥል እንደሆነ እነዚሁ የህግ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን እንደሰጡም ጠቁመዋል። “መንግሥት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ብቻውን ብዙ ርቀት መሄድ እየቻለ ወይም በቀላሉ ህገ መንግሥታዊ ማሻሻያ ማድረግ እየቻለ ጉዳዩን ለምክክርና ለውይይት ማቅረቡ አሳታፊ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት በግልፅ ያሳያል” ብለዋል። ከበርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራትም ጋር በተደረጉ ውይይቶች ህገ መንግሥታዊ ትርጓሜ የተሻለ አማራጭ መሆኑንም ለማረዳት እንደቻሉ ገልፀዋል። “ይህ አማራጭ የተሻለ ነው የተባለው ዛሬ የገጠመንን ፈተና በማየት ብቻ አይደለም ለወደፊቱም ህገ መንግሥታዊነትን በሃገራችን እንዴት እናጎልብት እንችላለን የሚለውንም በማሰብ ጭምር ነው። ይህ አጋጣሚ እኛም ህገ መንግሥታችንን በትርጓሜ የምናዳብርበት አዲስ ምዕራፍ ይከፍትልናል ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካናዳ፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ አሜሪካና የመሳሰሉ ሃገራት ግንባር ቀደም ህገ መንግሥታዊ ስርአት ተደርገውም የተቆጠሩት በህገ መንግሥት ትርጓሜ ህገ መንግሥቶቻቸውን ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላት ነው ካሉም በኋላ ኢትዮጵያ ከዚህ ትምህርት መቅሰም እንደሚገባት አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ “ሃገሪቷ የገጠማት ህገ መንግሥታዊ ቀውስ ነው፤ ህገ መንግሥቱ ለዚህ ችግር ምንም አይነት ምላሽ፤ ምርጫን የሚያራዝም መንገድ በህገ መንግሥቱ አልተጠቀሰም’ “”ለህገ መንግሥቱ ትርጓሜን መነሻ የሚሆንና ይህንን ጉዳይ የተመለከተ ህገ መንግሥታዊ አንቀፅ የለም” የሚሉ መከራከሪያ ሃሳቦች በተደጋጋሚ ይሰማሉ። ከዚህም ጋርም ተያይዞ ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የህግ ባለሙያዎች አማራጮቹ የተወሰኑ ቢሆንም አሉ እያሉ ጥናት ያላዳረጉ አካላት፤ ህጋዊ መፍትሄ የሌለው ችግር ነው ማለታቸው ምኞታቸውን እንጂ እውነታውን አያሳይም” በማለት ተናግረዋል አክለውም “ህጋዊ መፍትሄ የለም ማለታቸው ህጋዊ መፍትሄ አንፈልግም ማለታቸው ነው፤ ህጉ በአቋራጭ ስልጣን እንድንቆናጠጥ አያደርገንም ማለታቸው ነው” ህገ መንግሥቱ በቀጥታ ባይላቸውም በህገ መንግሥቱ ትርጓሜ የሚመለሱ ጥያቄዎች፤ በተለያዩ አገራትም በትርጓሜ ለወሳኝ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት እንደተቻለ ገልፀው ትርጓሜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም ለሚለው ጥያቄን መመለስ ያለበት ስልጣን የተሰጠው ለገለልተኛ የህገ መንግሥቱ አጣሪ ጉባኤ ሊመልስ ይገባል። “ጉባኤው ወደ ፍርድ ቤትነት የተጠጋ ህገ መንግሥታዊ ተቋም ነው።የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚመራውም በብልፅግና ፓርቲ አይደለም። የትርጓሜው ሂደት በአንድ ፓርቲ ስር ነው ያለ ለማለት አይቻልም” ብለዋል የትርጓሜውንም የሃሳብ ውሳኔ የሚያቀርቡ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና በምክትል የሚመራ ገለልተኛ አካል ነው። “ሁሉም ህገ መንግሥቱን ተርጓሚና የህገ መንግሥት ዳኛ እሆናለሁ ካለ ለዲሞክራሲና ለህገ መንግሥታዊነት የማይበጅ ምስቅልቅል አካሄድ ነው” ብለዋል በህገ መንግሥቱ መሰረት የፓርላማ አባላት የስልጣን ጊዜ ማብቂያ በመጪው መስከረም እንደሆነ ጠቅሰው ከዚያ በኋላ ግን ተቀባይነት የሌለው፣ ህጋዊ መሰረት የሌለውና አለም አቀፍ እውቅናም የማይኖረው መንግሥት ይሆናል የሚል መከራከሪያዎች በተለያዩ አካላት እየቀረቡ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " አሁን ያለው መንግሥት ህግ የሚያወጣ፣ አለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የሚቀበል፣ በጀት የሚያፀድቅ መንግሥት ነው፤ ህጋዊ በሆነ አግባብ የኮቪድ-19 ስጋት እስኪወገድና ቀጣይ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ሃገር መምራት ኃላፊነት ያለበት ፓርቲ ነው” ብለዋል።