id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
49671693
https://www.bbc.com/amharic/49671693
“ትርጉም ያለው ሕይወት የምንለው ለሌሎች አገልግሎት ሲኖር ነው” ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
ባለፈው ዓመት ጥቅምት ውስጥ ከተሾሙት ሃያ ሚኒስትሮች መካከል የገቢዎች ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አንዷ ናቸው። ወደ ሚኒስትርነት ቦታ ከመምጣታቸው በፊት በአዳማ ከንቲባነት እንዲሁም የኦዴፓ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አርሲ ዞን የተወለዱት ወ/ሮ አዳነች የትምህርት ዝግጅታቸው ሲታይ በመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ተምረው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት የነበሩ ሲሆን እያስተማሩም ዲፕሎማቸውን እንዲሁም ዲግሪያቸውን በሕግ ይዘዋል። በኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ በአቃቤ ሕግነት፣ እንዲሁም በ1997 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው ከተመረጡ በኋላ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። ለስድስት ዓመታትም ያህል የኦሮሚያ ልማት ማኅበርን መርተዋል። ቢቢሲ አማርኛ ከገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዓልንና ሌሎች ጉዳዮችንም በተመለከተ ቆይታ አድርጓል። • ከነፍስ የተጠለሉ የዘሪቱ ከበደ ዜማዎች አብዛኛውን ጊዜ በዓልን እንዴት ነው የሚያሳልፉት? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ በዓል እንደሁኔታው ነው። የበዓል ዝግጅት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይዘጋጃል። ከዛ ውጭ አንዳንድ ጊዜም ሥራ ሊያጋጥም ይችላል። ቤትም ውስጥ ዝግጅት እያለ ሥራ ቦታ አቻችየ ያለፍኩበት ጊዜ አለ። ከዛ ውጭ ከቤተሰብም፣ ከዘመድ ጋር ብዙ ጊዜ አሳልፋለሁ። ሚኒስትር እንደ መሆንዎ መጠን እርስዎን የሚፈልጉ አስቸኳይ ሥራዎች ይኖራሉ። የበዓላትና የቤተሰብ ጊዜን የሚሻማበት የለም? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ ይኖራል። በሚኖርበት ሰአት አንደኛ ቤተሰብ ራሱ ሁኔታውን እንዲረዳ የማድረግ ሥራ ቀድሜ ሰርቼያለሁ። ሰው ወደ ኃላፊነት ሲመጣ የቤተሰብ ብቻ አይደለም፤ የሕዝብም ጭምር ስለምትሆኝ፤ እንዲህ አይነት ሁኔታ በሚያጋጥመን ሰአት አብረን የምንገኝባቸው ከሆኑ ቤተሰቤን ይዤ እገኛለሁ። ነገር ግን ደግሞ ድንገተኛ ምክክር አጋጥሞ ከሆነ ደግሞ ሄጄ ተገኝቼ ያንን ጨርሼ ከቤተሰብም ጋር ማምሻችን ቢሆን አብረን እናከብራለን። ለርስዎ የተለየ በዓል የትኛው ነው? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ አዲስ ዓመትን በተለየ ሁኔታ ነው የምወደው ለምን ይሆን? ከልጅነትዎ ጋር የተያያዘ ይሆን? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ በርግጥ አዲስ ዓመት ከልጅነት ጋር ይያዛል። አዲስ ዓመት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሴት ልጆች የእንቁጣጣሽ ዘፈን ዘፍነናል፣ አደይ አበባ ወጥተን ለቅመናል። እሱን ደግም ለዘመድ አዝማድ ለጎረቤት እንኳን አደረሳችሁ እያልን አበባየሆይ እየዘፈንን እንሰጣለን። • የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ ሁልጊዜ አዲስ ዓመት በሚመጣበት ሰአት ሁሉ ነገር አዲስ ነው። ቤተሰብም አዲስ ልብስ ያለብሳል። ሁሉን ነገር አዲስ አድርገን እንድናየው የሚያደርግ አጠቃላይ የማኅበረሰብ እንቅስቃሴ ስላለ አዲስ ዓመትን በተለየ ሁኔታ እወደዋለሁ። ብዙ ሰው አዲስ ዓመት ሲመጣ ያቅዳል። እርስዎስ? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡አዎ! ማኅበረሰባችን ውስጥ የሚደረገውን በልጅነቴ የማውቀውን አንድ ጉዳይ ላንሳ። ጳጉሜ ወር ላይ የጳጉሜ ውሃ ሳያልፍ፤ ብለው በየእለቱ ማለዳ ሌሊት እየተነሱ ገላቸውን ይታጠባሉ፣ ገላችንንም እንድንታጠብ ያደርጋሉ። ለምንድን ነው? ባለፈው ዓመት የነበረ መልካም ያልሆነ፣ ቆሻሻ የሆነ ጥሩ ያልሆነ ነገር አብሮን ወደ አዲሱ አመት አብሮን ሊሻገር አይገባም። አዲስ ሆነን ነው ማለፍ ያለብን የሚል አስተሳሰብና እምነት አለ። ባለፈው አመት የነበረብን ድክመት አብሮ መሻገር የለበትም። እንዴት አድርገን መፍታት እንዳለብን ከባለፈው አመት ተምረን ለሚቀጥለው አመት በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ድካሞቻችንን ለማረም፤ ጠንካራ ጎናችንን አጠናክረን ለመቀጠል የምናቅድበት ጊዜ ስለሆነ ሁልጊዜም አዲስ አመት በሚመጣበት ሰአት አዲስ መንፈስ፣ መነቃቃት ያድራል። ከዚህ የተነሳ እኔም አቅዳለሁ። ሌሎችም እንደዛ የሚያደርጉ ይመስለኛል። በዓል ሲነሳ ብዙ ጊዜ የሚነሳው ምግብ ነው እና እርስዎ የሚወዱት ምግብ አለ? በአጠቃላይ የሚወዱት ምግብ ምንድን ነው? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ ያው ለበአላት ባህላዊ ምግቦች ይዘጋጃሉ። ያው በግሌ ከመውደድ አንፃር ጭኮና ጨጨብሳ እወዳለሁ። ጭኮ በምን? ጭኮ ነው ያልኩት ቆጮ አላልኩም (ሳቅ) በአል ሲሆንና ጊዜ ሲኖር ገባ ብዬ እሳተፋለሁ። ከሰአት አንፃር ካልሆነ በስተቀር ማዘጋጀት የማልችል እንዳይመስልሽ (ሳቅ) በትርፍ ጊዜዎ ምን ማድረግ ደስ ይልዎታል? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ የተለያዩ ነገሮች ነው የማደርገው፤ ያው በዚህ ደረጃ በኃላፊነት ስትቀመጪ፤ ሁልጊዜ ሥራሽን እያያሻሉ መሄድም ያስፈልጋል። መረጃዎች ያስፈልጋሉ። አነባለሁ። ሁለተኛ ነገር ደግሞ እግዚአብሔርን ማምለክ በጣም እወዳለሁ። ያለኝን ትንሽ ሰአት ለሁለቱ አካፍላለሁ። ከቤተሰቤ ጋር ቡና መጠጣት፣ ማውራት፣ ውሏችን፣ ሕይወታችን አንዳንድ ነገሮች እናወራለን። በወቅቱ እያነበቡት ያለ መጽሐፍ አለ? ወይም የሚወዱት መጽሐፍ? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡የማነበው መጽሐፍ አለ። ከሥራዬ ጋር ግንኙነት ባለውና መረጃ ስፈልግ የማነበው አለ። ከሥራዎ ውጭስ ያሉ ልብወለድ ወይም ታሪካዊ መጻሕፍትን ያነባሉ? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ ሁልጊዜ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ የሚነገርለት መጽሐፍ ያጋጥምሻል። ታሪኩን ቀንጨብጨብ ባለ ሁኔታ ስሰማ ሙሉውን ማንበብ እፈልጋለሁ። በእንደዛ አይነት ሁኔታ አነባለሁ። በህይወትዎ ትልቅ ስፍራ የሚሰጡት መፅሀፍ ይኖር ይሆን? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ "Inspiration and the wisdom for challenging times" የሚለው የማርቲን ሉተር ኪንግ መፅሀፍ፣ ' A king on leadership' አጠቃላይ ለመንግሥት ሥራ መምራት ብቻ ሳይሆን የራስንም ሕይወት ጭምር አስተዋፅኦ ሊያደርግ የሚችል ፅሁፍ ነው ብዬ በግሌ ተጠቅሜበታለሁ። ፊልም ያያሉ? ሙዚቃ ያዳምጣሉ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ እዛም ላይ ብዙ አይደለሁም። የሚወዱት ጥቅስ አለ? እንደ ሕይወት መርህ የሚከተሉት? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ የምወደው ጥቅስ አለ። በተለይ የህንዱን ማህተመ ጋንዲ "ትርጉም ያለው ሕይወት የምንለው ለሌሎች አገልግሎት ሲኖር ነው" ውስጤን ይነካኛል። መኖር ከራስ በላይ መሆን እንዳለበት ብዙ እንዳሰላስልና እንዳስብ፤ ከራስ በላይ መኖር ምን ማለት ነው? ለሌሎች አገልግሎት መኖር የሚለውን ፈልጌ የበለጠ እንድረዳውና እንዳነበውም ያደረገኝ ጥቅስ ነው። ያዘኑበትና የተደሰቱበትን ቀን የሚያስታውሱት አለ? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡በተለየ ሁኔታ የማልረሳው ብየ እንደዚህ የማስታውሰው የለም። በህይወት ውስጥ ያው ውጣ ውረድ አለ። በራስሽ ጉዳይ ብቻ አታዝኚም፤ በራስሽ ጉዳይ ብቻ አትደሰችም። እንደማንኛውም ሰው የማዝንበትም የምደሰትበትም ያጋጥመኛል፤ እያጋጠመኝ ነው የኖርኩት፤ የተለየ ሁኔታ ፈጥሮብኝ ያለፈ አሁን የማስታውሰው የለኝም። በሕይወትዎ ምን ሲያዩ ያስደስትዎታል? በስራም፣ በቤተሰብም እንዲሁ በአጠቃላይ ባለው? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ በአጠቃላይ ባለው እንደ ፍትህ የሚያስደስተኝ ነገር የለም። የተዛባ ነገር፣ አረዳድ ሊሆን ይችላል። በፍርድም እጦት ሊሆን ይችላል። ያ ነገር ሲፈታ የተለየ ነገር ይፈጥርብኛል፤ የተለየ ስሜት የሚሰጠኝ እሱ ነው። • መከላከያ የሶሪያ እና የየመን ዜጋ የሆኑ የአይኤስ አባላትን በቁጥጥር ሥር አዋልኩ አለ ለኢትዮጵያ ምን ይመኛሉ? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ ለኢትዮጵያ ካለብኝ ኃላፊነት የራሷን ወጪ በራሷ መሸፈን የምትችል ሃገር እንድትሆንና እንደገናም እዛ ላይ መድረስ እንድንችል እመኛለሁ። እንደ አጠቃላይ እንደ ሃገር ጥንታዊ ታሪክ ያላት ብትሆንም ነገር ግን እድገቷም ዛሬ ያለችበትን በምናይበት ሰአት ወደኋላ ከቀሩ ሃገራት ተብላ የምትጠቀስ ሃገር ናት። ስለዚህ ለሃገሬ እድገትና ብልፅግና የዜጎቿን መበልፀግና መለወጥ ማየት እፈልጋለሁ። ለበአሉ የሚያስተላልፉት መልእክት ካለ? ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፡ አዲሱ አመት የለውጥ በግላችንም በማህበረሰቡም ሆነ በኢትዮጵያም፣ በአስተሳሰባችንም ሆነ በተግባራችንም ተለውጠን አዲስ ነገር የምናይበት አመት ይሁንልን። አዲስ ውጤት የምናስመዘግብበት፣ ፍቅራችን፣ አንድነታችን የሚለመልምበት አመት እንዲሆንልን እመኛለሁ። መልካም አዲስ ዓመት!
news-55663925
https://www.bbc.com/amharic/news-55663925
ትግራይ ፡ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም (አምባዬ) መስፍን
በትግራይ ውስጥ የተከሰተውን ወታራዊ ግጭትን ተከትሎ በተፈላጊነት የስም ዝርዝራቸውን ካወጣው ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን በአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች ረቡዕ ጥር 05/2013 ዓ.ም መገደላቸው ተገልጿል።
አቶ ስዩም መስፍን ከፍተኛ የህወሓት አመራር ሆነው ከሃያ ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የአገሪቱ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን ከህወሓት የትጥቅ ትግል ጀምሮ ከፍተኛ ተጽእኖ የነበራቸው ግለሰብ እንደነበሩ ይነገራል። ስዩም (አምባዬ) መስፍን ስዩም መስፍን በ1940ዎቹ መጀመሪያ ትግራይ ውስጥ አዘባ ተብሎ በሚጠራ የአጋሜ አውራጃ ቀበሌ ነው የተወለዱት። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲ ግራት ከተማ አግአዚ ትምህርት ቤት በመከታተል፤ በባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የዲፕሎማ ምሩቅ ናቸው። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገቡት አቶ ስዩም፤ በዩኒቨርሲቲው የትግራይ ተማሪዎች ማኅበርን ካቋቋሙት መካከል አንዱ ናቸው። በ1965 ዓ.ም ማኅበሩ በድብቅ ወደ ተመሰረተው የትግራይ ብሔር የፖለቲካ ቡድንነት ሲሸጋገር ስዩም ፓርቲውን ከመሰረቱት ሰባት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አንዱ ነበሩ። የንጉሡ ሥርዓት መውደቅን ተከትሎ በርካታ ወጣቶች የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመመስረት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ፤ የትግራይ ብሐር ፓርቲ አባላትም "የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች በትጥቅ ትግል ነው የሚፈቱት" በማለት ጠመንጃ አንስተው ትግል ለመጀመር ወደ ትግራይ በረሃማ አካባቢዎች ሄዱ። አቶ ስዩም መስፍንም የዚህ ውሳኔ አካል ሆነው ከጓዶቻቸው ጋር ወደ ትግራይ አቀኑ። ስዩም - በትጥቅ ትግል የትግራይ ሕዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ ትጥቅ ትግል እንዲጀመር ከተወሰነ በኋላ የንቅናቄው አመራር በሦስት የተለያዩ መንገዶች የተሰጠውን ዓላማ እንዲፈጽም ተወሰነ። አንዱ ቡድን ወደ ደደቢት በረሃ በመሄድ የትጥቅ ትግሉ መጀመርን ይፋ እንዲያደረግ፣ ሁለተኛው ወደ ኤርትራ በመሄድ የትጥቅ ትግል ተሞክሮ እንዲወስድ፣ ሦስተኛው ደግሞ በከተማ ውስጥ ፖለቲካዊ ሥራዎች እንዲመራ ተደረገ። በዚህም አቶ ስዩም መስፍን ወደ በረሃ በመሄድ የትጥቅ ትግሉን ከጀመሩት አስራ አንድ ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ቤተሰባቸው አምባዬ ብሎ መጠሪያ ስም ያወጣላቸው አቶ ስዩም፤ ወደ ትጥቅ ትግል ከሄዱ በኋላ ግን ሁሉም ስማቸውን ሲቀይሩ አብረዋቸው ከነበሩት ጓዶች መካከል አንዱ የሆነው ታጋይ ስሑል 'ስዩም' የሚለውን ስም ሰጣቸው። በ1970ዎቹ አጋማሽ ድርጅቱን ከሚመሩት አንዱ በመሆን የተመረጡት አቶ ስዩም፤ አድያቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከመንግሥት ሠራዊት ጋር በተደረገው ከባድ ውጊያ ጭንቅላታቸውን ተመትተው ኤርትራ ውስጥ ህክምና እንደተደረገላቸው "ጽናት" በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል። ታጋይ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) ከኤርትራ ህወሓት ወደ ሚመራው የትጥቅ ትግል ከተቀላቀሉት ጥቂት ቀደምት ታጋዮች በመንግሥት ተይዞ በሽረ እንዳሥላሴ ከታሳረ በኋላ፤ ስዩም ሙሴን ጨምሮ የታሰሩትን ታጋዮች ለማስፈታት የተዘጋጀውን "የሙሴ ኦፕሬሽን" ለመፈጸም የአዕምሮ ህመምተኛ በመምሰል ስለላ ላይ ተሰማርተው እንደነበር ታሪካቸው ያትታል። ስዩም- የህወሓት መልዕከተኛ አቶ ስዩም ከ1969 ዓ.ም መጨረሻዎቹ ጀምሮ የህወሓት የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው ለ15 ዓመታት በሱዳን የሰሩ ሲሆን፤ በካርቱም ቆይታቸውም ስማቸው ወደ 'ሙሳ' ተቀይሮ እንደነበረም ይነገራል። አቶ ስዩም በ1983 ዓ.ም ከመለስ ዜናዊና ከብርሃነ ገብረክርስቶስ ጋር በመሆን በለንደን ከመንግሥት ጋር ሲደረግ በነበረው ድርድር ላይ ተሳትፈዋል። ህወሓት/ኢህአዴግ የደርግ ሥርዓትን ጥሎ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የወቅቱ የሱዳን ፕሬዝደንት የነበሩት ኦማር አልበሽር ባዋሷቸው አውሮፕላን ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙበት ጊዜ የቴክኒክ ችግር አጋጥሟቸው ነበር። በዚህ ምክንያት አውሮፕላኑ ከባድ አደጋ እንደገጠማት በተረዱ ጊዜ ለ17 ዓመታት የመሩት ትግል በድል ተጠናቆ ማየት አለመቻላቸው ከባድ ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸው እንደነበር ይነገራል። ነገር ግን የፈሩት ሳይደርስ በሰላም አዲስ አበባ ገቡ። ስዩም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በህወሓት መሪነት ኢህአዴግ የአገሪቱን ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ አንስቶ አቶ ስዩም መስፍን ለ20 ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን በቁልፍ የመንግሥት ሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ከኢትዮ ኤርትራ የድንበር ጦርነት ማብቃት በኋላ በ1993 ዓ.ም በህወሓት አመራሮች መካከል ክፍፍል ሲፈጠር አቶ ስዩም ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጎራ ከተሰለፉት መካከል አንዱ ነበሩ። ከድንበር ጦርነቱ ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት ለደም አፋሳሹ ጦርነት ዋነኛ ምክንያት የነበረችው ባድመን ለኤርትራ ወስኖ እያለ ለኢትዮጵያ እንደተወሰነ አድርገው በቴሌቪዥን መግለጫ በመስጠት ሕዝብ የድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ በማድረጋቸው በተአማኒነታቸው ላይ ዘወትር የሚጠቀስ ጠባሳ ጥሏል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ካሉ ጎረቤት አገራት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖራት ለማድረግ አስችለዋል ቢባልላቸውም፤ ከኤርትራ ጋር ግን የድንበር ግጭቱ ሳይፈታ እንዲቆይ በማድረግ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያደረጉት ጥረት የለም ተብለው ይተቻሉ። በተጨማሪም ህወሐት በኢሕአዴግ ውስጥ በነበረው ጠንካራ የበላይነት ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂ ናቸው ተብለውም ይከሰሳሉ። በሌላ በኩል አቶ ስዩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በቆዩባቸው ዓመታት የእስያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸው እንዲያፈሱ ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ እንደነበረ ይነገራል። በዚህም ምክንያት የሚኒስትርነት ቦታቸውን ሲለቁ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ለስድስት ዓመታት ሰርተዋል። ስዩም - ከለውጡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ አቶ ስዩም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተመልሰው ማገልገል ጀምረው ነበር። ነገር ግን በተመደቡበት ክፍል ደስተኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ ወደ መቀለ እንደሄዱ ይነገራል። በፌደራል መንግሥቱና በህወሐት መካከል የተፈጠረው መካረር በበረታበት ወቅት፤ አቶ ስዩም በተለያዩ አጋጣሚዎች በመገናኛ ብዙሃን ላይ በመቅረብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አጥብቀው ሲተቹ ቆይተዋል። በአንድ ቃለ ምልልሳቸውም የኖቤል ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጠው የሠላም ኖቤል ሽልማት ላይ እየተወዛገበ መሆኑን በመግለጽ ሽልማቱን ለማንሳት እያሰበ መሆኑን በመግለጻቸው መነጋገሪያ ሆነው ነበር። የሽልማት ኮሚቴውም በእንዲህ አይነቱ ጉዳይ ላይ እንዳልተነጋገረና አንድ ጊዜ የተሰጠ የኖቤል ሽልማት እንደማይመለስ ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ሠራዊት የክልሉን ዋና ከተማ መቀለን በቁጥጥር ስር ከማስገባቱ ቀደም ብሎ እስካለው ጊዜ ድረስ አቶ ስዩምና የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች በከተማዋ የቆዩ ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ግን ከተማዋ ወጥተው ወደ ተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች መሄዳቸው ተነግሮ ነበር። የእስር ማዘዣ ከወጣባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የነበሩት አቶ ስዩም መስፍንና ሌሎች ጓዶቻቸው ያሉበት ቦታ በጸጥታ ኃይሎች ተከቦ እጅ እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል ጥር 05/2013 ዓ.ም በተወሰደባቸው እርምጃ መገደላቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። መቀለ በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ከነበሩት ጥቂት ቀናት ውጪ የህወሓት አመራሮች ለየትኛውም የመገናኛ ብዙሃን ምንም አይነት መግለጫ ሰጥተው ስለማያውቁ ስለተገደሉት አመራሮቹ ከቡድኑም ሆነ ከሌላ ወገን የተሰማ ነገር የለም።
news-50984853
https://www.bbc.com/amharic/news-50984853
የምርጫ ቅስቀሳ ወጎች
የዘውዳዊው ሥርዓት ተገርስሶ፤ ደርግ 'ኢምፔሪያሊዝምን የማንበርከክ' የመሬት ከበርቴውን የማንቀጥቀጥ የቡርዧውና ፊውዳሉ ሥርዓትን የማውገዙ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች የሚሰበክበት ወቅት፤ በአንድ ወቅትም በሰሜን ኢትዮጵያ በምትገኝ ደሃና በምትባል አካባባቢ የደርግ ካድሬዎች የአካባቢውን ሕዝብ ሰብስቦ "የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ይውደም" በማለትም ጮክ ብለው መፈክሮችን ያሰማሉ።
ያው የተሰበሰበውም ሕዝብ " እኛ ምን አውቀን የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ይውደም እንጂ" አሉ እየተባለ በአካባቢው ይወሳል። ኢምፔሪያሊዝም፣ አናርኪስት፣ ቡርዧ፣ ሶሻሊዝም እንዲሁም ሌሎች ይደጋገሙ የነበሩ ቃላት ለሰው ባዕድ እንደሆኑ ዘመናትን ቀጥለዋል። • ምርጫ ፡ የተቃዋሚዎችና የመንግሥት ወግ? የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ መንግሥት የሚከተሏቸው ርዕዮተ ዓለማት፤ የሚያወጧቸው ፖሊሲዎች ወይም በተደጋጋሚ የሚሰሙ ቃላት እንደ ዴሞክራሲ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ግብርና መርህ ኢንዱስትሪ፣ ኒኦ ሊበራሊዝም እና ሌሎችም ከቃላት በላይ ምን ያህሉ ኢትዮጵያዊ ፅንሰ ሃሳቦቹን በጥልቀት ይረዳቸዋል? በተለይም ምርጫዎች ሲቃረቡ በተለያዩ ሚዲያዎች በሚደረጉ ክርክሮች እነዚህን ፅንሰ ሃሳቦችና የተለያዩ የፖለቲካ ፕሮግራሞች መስማት የተለመደ ነው፤ እነዚህን ሃሳቦች ለሰፊው ሕዝብ እንዴት ይወርዳሉ? በምንስ መንገድ ይሰርፃሉስ? ድጋፍስ የሚያሰባስቡት እንዴት ነው የሚሉ ጥያቄዎችን ሊያጭሩ ይችላሉ። የነዚህ ቃላትም ሆነ ፅንሰ ሃሳቦች ተመሳሳይ አገርኛ እሳቤስ የለም ወይ፤ ቃላቶቹ የተዋሱ ከመሆናቸው አንፃርና ገና ሲሰሙ ፊደል ያልቆጠረውን ማህበረሰብ የማግለል ስሜትስ አይፈጥሩም ወይ? ካፒታሊዝም፣ ሶሻሊዝም የመሳሰሉ ሃሳቦችን፤ የፍራንዝ ፋኖንም ሆነ ማኦን ፅሁፎች ከልሂቃኑ በስተቀር አብዘኛው ማህበረሰብ ባያውቋቸውም የተማሪዎች እንቅስቃሴ 'መሬት ለአራሹን' በዋነኝነት አንግቦ መምጣቱ አርሶ አደሩንና በወቅቱ የነበረውን የተማረ ክፍል በአንድ ጎራም ያሰለፈ እንደነበር በወቅቱ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ የነበሩት ዶ/ር ታዲዮስ ቦጋለ ያወሳሉ። ከዘውዳዊው ስርአት መገርሰስ በኋላም ዕድገት በህብረት ዘምተው በነበረበት ወቅት በተወሰነ መልኩ የሕዝቡን ሥነ ልቦና ለማወቅ ዕድል ያገኙ ሲሆን የኢህአፓን ርዕዮተ አለም ለማስረፅ በሚሞክሩባቸው ወቅት ያጋጠማቸውን አሁንም ያወሱታል። • ህወሓት፡ ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች የቦረና ማህበረሰብ በተለይም ጉጂ ስለ ሶሻሊዝም ሆነ ኮሚዩኒዝም ርዕዮተ ዓለም ሲነግሯቸው ቃላቶቹን ባያውቋቸውም ፅንሰ ሃሳቦቹ አዲስ እንዳልሆኑ የነገሯቸውን በመጥቀስ። "አብሮ መኖር ለኛ አዲስ አይደለም፤ ተሰባስቦ መኖርም ሆነ ያለውን ተካፍሎ መብላት፤ አብሮ መንቀሳቀስና ችግር ሲኖር ተሰባስበን ችግራችንን የመፍታት እነዚህ ቀድመው የነበሩ ባህሎቻችን ስለሆኑ የምትሉት ነገር አዲስ አይደለም። ለኛ ስለዚህ ጉዳይ ከምትነግሩን እኛ ኑሯችን እንዴት እንደሚሻሻል፣ መንገድ እንዴት እንደሚሠራ፣ ትምህርት ቤት እንዴት እንደሚሠራ፣ እነዚህን ነገሮች ነው በአብዛኛው የምንፈልገው እያሉ ነው ይሞግቱን የነበሩት" ይላሉ። አንዳንድ ጊዜም እንዲህ ከተወሳሰቡ ሃሳቦች ሌላ ማሳካት የማይችሏቸውን ጉዳዮች ቃል በመግባት ብዙዎች ደግሞ የሚያወሷቸው ቀልዶች አሉ፤ በኃይለ ሥላሴ ጊዜ ወቅት አንድ ሹም ሕዝቡን ምረጡኝ እያሉ ይቀሰቅሳሉ፤ እናም ከተመረጥኩ ይህን አደርጋለሁ፤ ይህን አደርጋለሁ ብለው ከሚዘረዝሯቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ "ድልድይ አሠራለሁ" ነበር። የአካባቢው ሕዝብም ደግሞ "ድልድዩ ለምን ይሆን?" ብሎ መጠየቅ "ያው እንድትሻገሩበት ነው አሉ"፤ "ወንዝ እኮ በአካባቢው የለም" ሲሉ "ወንዙንም አመጣለሁ" ብለው መልሰዋል እየተባለ ፖለቲከኞች በምርጫ ወቅት ለመመረጥ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ይላሉ። ብዙዎች የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላትም የሚስማሙበት ጉዳይ ኢህአዴግ ምርጫ ሲቃረብ፤ የምርጫ ቅስቀሳው ወቅት እንዲሁ ለመመረጥ የማይሄድበት መንገድ እንደሌለ ነው። ሕዝቡን በጥቅማ ጥቅም ከመያዝ ጀምሮ፣ ማስፈራሪያዎች፣ መደለያዎችና እና እንዲሁም ሌሎችም፣ ሌሎችም። ኢህአዴግ ስልጣን መያዝ ተከትሎ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ከሽግግር መንግሥቱ 1983 ዓ. ም. ጀምሮ በተቃዋሚነት የቆዩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በባለፉት ዓመታት ያደረጓቸውን ለፓርቲያቸው የሚደረጉ የድጋፍ ጥሪዎችንም ሆነ የምረጡኝ ቅስቀሳዎች ፈታኝ ነበሩ ይላሉ። ይህ ፈታኝ ጉዞ የተጀመረው፤ በሽግግሩ ማግስት እንደሆነ የሚናገሩት ፕሮፌሰር በየነ በሽግግሩ ወቅት የቻርተሩን ጉባኤ አከናውነው የድጋፍ ጥሪ ለማድረግ ወደ ሆሳዕና ከተማ አቀኑ። በወቅቱም መቀስቀስ አትችሉም ተባሉ በዚህም ምክንያት ከመንግሥት ጋር ያላቸው ፍጥጫዎችና እሰጣ ገባ ሀ ተብሎ ተጀመረ። የአካባቢው ማህበረሰብም አሻፈረኝ አለ መጀመሪያ ታስቦ የነበረው በአንዲት ጠባብ አዳራሽ ሊደረግ ታስቦ የነበረው ውይይት በትልቅ ስታዲየምም ተከናወነ። በቦታውም ምንም እንኳን የሽግግር ጊዜ ከመሆኑ አንፃር ግድያዎችና ግጭቶች ከመበራከታቸው አንፃር የሰላምና የመረጋጋት ሁኔታ አስፈላጊነትን ቢያምኑበትም የኢህአዴግን ርዕዮተ ዓለምን በመቃወምና የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን አስፈላጊነት ለሕዝቡ አስረዱ። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቀጣዩ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ተናገሩ የተቃዋሚነትም ሕይወታቸውም ሀ ተብሎ ተጀመረ፤ ፖርቲያቸው እንዴት ከኢህአዴግ እንደሚለይ በፕሮግራማቸውም ሆነ በርዕዮተ ዓለማቸው ለማስረዳትም ከፍተኛ ሥራ መስራት ተጀመረ። ሰፊውንም ሕዝብ በሚያገኙበት ሰዓት ለልሂቃኑ ብቻ የሚገቡ ፅንሰ ሃሳቦችንም ወደ ጎን በመተው የሚከተሉት ሶሻል ዴሞክራሲ (ማህበራዊ ዲሞክራሲ) ስለ ማኅበራዊ ፍትህ፣ የኃብት ክፍፍል፣ ዜጎች መሰረታዊ የሆነ ፍላጎታቸው እንዲሟላ፤ ሕዝቡ በሚገባው ቋንቋ በጤና፣ በትምህርት፣ በምግብ፣ በመኖሪያ ቤት ተደራሽነትን ማዕከል በማድረግ፤ የሕዝቡን ፍላጎትና ጭንቀቱን በዚያ መልክ እንደሚያቀርቡ ይናገራሉ። "ያንን እምነት ወደ ሕዝቡ ማስተላለፉ ከባድ አልነበረም፤ ያኔም አልነበረም፤ አሁንም አይደለም" ይላሉ። ከከተሜው አጀንዳዎች በተጨማሪ አርሶ አደሩ የምርት መጠኑን የሚያሳድጉባቸውን የምርጥ ዘር እንዲሁም የመሬትና ማዳበሪያ ጥያቄዎች ምርጫ ወቅት ላይ የሚነሱ ዋነኛ ጉዳዮች ናቸው። በተለያዩ ጊዜያትም በአርሶ አደሩ ዘንድ ማዳበሪያና ምርጥ ዘርን እንደ መያዣ በማድረግ የምረጡኝ ቅስቀሳ ኢህአዴግ ይጠቀምበት እንደነበር የፕሮፌሰር በየነ ፓርቲም ሆነ ሌሎች ተቃዋሚዎች ሲሉ በተደጋጋሚ ይሰማሉ። "ተቃዋሚውን ከመረጣችሁ ምርጥ ዘርንም ሆነ ማዳበሪያ አንሰጥም ከሚሉ ማስፈራሪያዎች አልፈው፤ ሳይዘሩ መሬታቸው ፆሙን ያደረበት ሁኔታዎች፤ በጥቁር ገበያ እያወጡ እየሸጡ በብዙ እጥፍ ለመግዛትም የተገደዱ አሉ። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? "የምትደግፉት የበየነ ጴጥሮስ ፓርቲ ሲመጣና ስልጣን ሲይዝ እናንተ ታገኛላችሁ፤ እንዲያውም በሄሊኮፕተር መጥቶ ያወርድላችኋል የሚሉና ወደ ኋላ የቀሩ መንግሥትን የማይመጥኑ ዘዴዎች ሁሉ ይጠቀሙ ነበር" ይላሉ። ከዚህም በባሰ እርዳታንም ለምርጫ ቅስቀሳ ይጠቀሙባቸውም ነበር ይላሉ፤ በተለያዩ ጊዜ በሚከሰት የዝናብ እጥረት ምክንያት በሚከሰት የምግብ እጥረት የሚመጣው እርዳታ ለተቃዋሚ የድርጅት አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች አይደርሳቸውም በማለት ይወነጅላሉ። "በየነ ፓርቲ ሲያሸንፍ ያኔ ነው የምትበሉት ተብለው የእርዳታ እህል የሚከለከሉበት ኢሰብአዊ የሆነ ከሞራል መሰረት ውጭ ተግባራት ውስጥ ይገቡ ነበር" የሚሉት ፕሮፌሰር በየነ የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃት እንዲሉ እንዲህ አይነት "በደሎች" ድጋፍ ለማሰባሰብም ያመቻቸው ወቅት ነበር። ማዳበሪያ እንዲሁም ምርጥ ዘር አንሰጥም የሚሉ ጉዳዮችም ህዝቡን እልህ አጋብተውትም እሳቸውም ሆነ ፓርቲያቸው የፖለቲካ ስራ ከሰሩበትና ከቀሰቀሱበት ሃድያ ዞንና ከምባታ ጠምባሮ 1992 ምርጫ ላይ ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ እንዲሸነፍበት ምክንያት የሆነው። በ1992 ዓ. ም. ያሸነፉበትም የምርጫ ቅስቀሳም ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘርን ለመስጠት ቃል በመግባት፤ ረኃብና የእህል ምግብ እጥረት ሲከሰት ደግሞ ያለው እርዳታ በፍትኃዊነት እንዲከፋፈል፤ የትምህርት ጥራት፣ ጤና ማዕከላት እንዲቋቋሙ የሚሉ ጉዳዮችን አንግበው ነበር። በምርጫ ቅስቀሳቸውም ወቅት ሕዝቡም እሮሯቸውን ይነግሯቸው የነበረ ሲሆን፤ በተደጋጋሚም "ልማት አምጡልን፤ የመሬት እጥረትን ቅረፉልን፤ ኑሯችንን አቅልሉንም" ይሉ ነበር። ምንም እንኳን የሕዝቡን ኑሮ በሚነካ መልኩና የገዥውን ፓርቲ ስህተቶች እየነቀሱ በማውጣት የምርጫ ቅስቀሳቸውን ቢያካሂዱም አባላቶቻቸው ከፍተኛ መዋከብ፣ ቀስቃሾች መታሰር፣ መገረፍ እንዲሁም በሌሎች ጥሰቶች ውስጥ መሆኑንም ፕሮፌሰር በየነ ምሳሌዎችን በማንሳት ይጠቅሳሉ። አብዛኛውን ጊዜ ለምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጓቸው የስብሰባ አዳራሾች ሕዝብ እንዳይገባ መከልከል፤ በታጠቀ ኃይል መበተን አንዳንዴም ረዥም ኪሎ ሜትር ተጉዘው ሆቴሎች አታድሩም ተብለው መከልከል አጋጥሟቸዋል። • የ31 ዓመቱ ኢሕአዴግ ማን ነው? "ለምርጫ ቅስቀሳ በሚል ቀድመን ሆቴል ይዘን ልክ እኛ መሆናችንን ሲያውቁ የለም፤ ተከራይቷል ይሉናል። እኔም ይህ ሁኔታ አጋጥሞኛል። ማደሪያ አጥተን ደጋፊዎቻችን ደሳሳ ጎጆዎቻቸውን የለቀቁበት አጋጣሚም አለ፤ ምን ይባላል ትውስታዎቼ መራር ናቸው" ይላሉ። ብዙዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በቅስቀሳዎቻቸው ወቅት ይደርስብናል የሚሏቸውንም ግፎችም በተደጋጋሚ መስማት የተለመደ ነው። የኢህአዴግን መምጣት ተከትሎ በአማራው ሕዝብ ከሌላው ብሔር በተለየ መልኩ በደል ይደርስበታል የሚል አላማን አንግቦና ይህንንም ለመቅረፍ እታገላለሁ ሲል የነበረውና በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የተቋቋመው የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ) አባል የነበሩት ዶ/ር ታዲዮስ መጀመሪያ አካባቢ ለድጋፍ መውጣት የማይቻል ነበር ይላሉ። አብዛኛውን ጊዜ መአህድ የድጋፍ እንቅስቃሴው የተገደበ እንደነበር የሚናገሩት ዶ/ር ታዲዮስ ፕሮፌሰር አስራትም የተወነጀሉት አስፈቅደው ደብረ ብርሃን ላይ ባደረጉት ስብሰባ መሆኑንም በማስረጃነት ይጠቅሳሉ። ባገኟትም አጋጣሚዎችም ለድጋፍ በወጡበት ወቅት ከደጋፊዎቻቸው ዘንድ በብሔር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝምን እንደማይደግፉ፣ ፓርቲያቸውንም ህብረ ብሔር ማድረግ እንደሚገባ ስለወተወቷቸውም የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያሰባስብ ፌደራሊዝም ለምን አይቀየስም በሚል ድርጅቱም ውስጥ ከፍተኛ ውይይት ካደረጉ በኋላ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን መሰረቱ። ከኢህአዴግ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚውም ሆነ በሌሎች ዘርፎች የሚለዩባቸውን ሁኔታዎች በጥልቀት ቢሰሩበትም ህዝቡ ተረድቶታል ላይ የሚለው ላይ ጥያቄ አላቸው። "ስንቱ ነው ስለ መንግሥት አደረጃጀት፣ የፖለቲካ አወቃቀር የሚያውቀው፣ የሰብአዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ ስለ ብሄረሰቦች እኩልነት ፅንሰ ሃሳቦች ብዙዎች ጠንቅቀው አያውቁም፤ የመሬትና ሌሎች የተፈጥሮ ባለሃብት ባለቤትነት፣ የልማት አካሄድ፣ የውጭ ፕሮግራምና ሌሎችም አሉ፤ ምን ያህሉ ያውቀዋል ማለት ከባድ ነው።" ይላሉ ፕሮግራማቸውንም ሆነ ፖሊሲዎቻቸውን ለሰፊው ሕዝብ ግልፅ አለመሆናቸው እንዲሁም የሰው ልጅ ኑሮው እንዴት መሻሻል ይችላል የሚለው በነዚህ ርዕዮተ ዓለማት ሲተገበር ምን ይመስላል? በሚልም ከፅንሰ ሃሳብ በዘለለ መንገድ ለማስረዳትም እንደሚሞክሩ ዶ/ር ታዲዮስ ይገልፃሉ። መነሻቸውም ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ላይ ያሉ ጉድለቶችን ነቅሶ ማውጣት እንደመሆኑ መጠን ለምሳሌ የመሬት ባለቤትነት ለአርሶ አደሩ ማረጋገጥ፣ ማዳበሪያ በቀላሉ የሚገኝበት ሁኔታ እንደሚያሳልጡ ያነሳሉ" እኛ ለምሳሌ ብንመረጥ ማዳበሪያ ፋብሪካ እናቋቁማለን፤ ለሕዝቡም በቀላል ዋጋ እንዲሰራጭ ይደረጋል እንላቸዋለን" ይላሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ ድህነት አረንቋ ውስጥ ያለ ሕዝብ ከመሆኑ አንፃር የሰውን ችግርና ቁስል የሚነኩ ነገሮችንም በሚናገሩበት ወቅት የሕዝቡ ስሜትም ወደነሱ ቢሆንም ያ ቀጣይነት እንደሌለውም አስተውለውታል። "ዋነው ነገር ለሕዝቡ ካለበት ድህነት እንዴት ነው የምወጣው የሚለው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። እናም በሚደረጉ ስብሰባዎች ስሜታዊ የመሆንና ያንን ነገር የመከተል፤ ያ ወቅት ደግሞ ሲያልፍ የመተው፤ ቦግ፣ ብልጭ የማለት የመተው ነገር አለ" ይላሉ። ፕሮፌሰር በየነም ሆነ ዶ/ር ታዲዮስ አፅንኦት ሰጥተው የሚናገሩት የምርጫ ቅስቀሳቸውም ሆነ የድጋፍ ጥሪያቸው ወከባ የተሞላበት መሆኑን ነው። የሕዝብ መሰብሰቢያ አዳራሾች ተከራይተው ሊገቡ ሲሉ ተይዟል መባል፣ ሕዝቡ ወደ አዳራሾቸ በሚመጣበት ጊዜ የሚመዘግቡ ካድሬዎች ማቆም፤ ቀበሌ ትፈለጋለህ ብሎ ከስብሰባ አዳራሹ መውሰድና ሌሎችንም ይጠቅሳሉ። "አዳራሹም እንደምንም ተብሎ ከተገኝም ካድሬዎች ይረብሹና ስብሰባው እንዲቋረጥ ይደረጋል፤ በተለያየ ዘዴ፤ እኛም ይህንኑ ዘዴያቸውን ስለምናውቅ ተዘጋጅተን ነው የምንጠብቃቸው፤ ሕዝቡም ያውቃል፤ ቀበሌ አዳራሸ ላይ ውይይቶች ሲበተኑ ህዝቡ ቅሬታውን እየተናገረ ይወጣል" ይላሉ። • "ምርጫው እንዲራዘም እንፈልጋለን" አቶ አንዷለም አራጌ ሆኖም በአዳራሽም ሆነ፣ በራሪ ወረቀቶችን በማደል፣ በመኪናም እየዞሩ የመኖሪያ ቤቶችን ችግሮች እንደሚቀርፉ፣ የግል ባለቤትነትንም እንደሚያረጋግጡ በሰፊው ሰርተዋል። ሕዝቡም በምርጫ ቅስቀሳ ወቅታቸው ወቅት ይሰጣቸው የነበረው ድጋፍም ከፍተኛና ተስፋቸውንም ያንሰራራ ነበር። በአንድ ወቅት ወደ ጋሞጎፋ ሳውላ የሚባል ቦታ ስብሰባ ለማድረግ ባቀኑበት ወቅት ባነራቸውም ከተማው መሃል ተሰቅሎ ስለነበር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ወጥቶ በዘፈን ያቀልጠው ጀመር "መኢአድ ለዘላለም ይኑር፤ መኢአድ ያሸንፋል፤ መኢአድ የኛ ነው " የሚሉ መፈክሮችን ያሰሙበትን ሁኔታ አሁንም ዶ/ር ታዲዮስ ትናንት የተፈጠረ በሚመስል መልኩ ያስታውሱታል። ምንም እንኳን የሕዝብ ድጋፍ ከፍተኛ ቢሆንም ኢህአዴግ በከፍተኛ ሁኔታ በሚያደርጋቸው መደለያዎችም ጫና እንዳሳደሩባቸውም ዶ/ር ታዲዮስ ይናገራሉ። በገጠር ያለ የማዳበሪያና ምርጥ ዘር እንዲሁም በከተማውም ላሉ ደሃ እናቶች ለቡና ተብለው የሚሰጥ ብር እንዲሁም ተደጋጋሚ ግብዣዎች ለውጥ እንዳለው ነው። "ያው እንግዲህ ምርጫ ሲመጣ እናቶች ያው አንቺ የምታራምጅውን አላማ አይደለም የሚመለከቱት፤ እነሱ የሚያዩት ካለው የኑሮ ችግር የቡና መግዣ ማግኘታቸውን ነው" ይላሉ። የኢዜማ ሥራ አስፈፃሚና በአንድ ወቅት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህን ወክለው ብቸኛ ተቃዋሚ የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው ኢህአዴግ በምርጫው ሰሞን ወቅት ኢህአዴግ በእያንዳንዱ ጓዳ ጎድጓዳ መግባት እንደቻለ ነው። "ጋዝ የምትፈልግ ከሆነ ጋዝ፤ ለዛ ሰሞን ምንም ችግር የለውም። አንዷ ሴትዮ አስታውሳለሁ መርጠው ሲወጡ 'የታለ የጋዙ ገንዘብ' ብለው በሳቅ ገድለውናል እና በደንብ ነው የሚደርሷቸው" በማለት ተቃዋሚዎች ህዝቡን ይደርሳሉ ወይ? ለሚለው ጥያቄም "እንዴት አድርገው ነው የሚደርሱት ሊደርሱ አይችሉም" ይላሉ። "በያንዳንዱ ቤት ውስጥ የሚመርጣቸውንም ስለሚያውቁ ተንከባክበው ነው የሚይዙት፤ የቀበሌ ሰዎችም እነማን እንደሚመርጡ በዝርዝር ያወቃሉ" ብለዋል። ምንም እንኳን እንዲህ በየቤቱ መድረስ ባይችሉም በዓመታት ውስጥ ለየትኛው አካባቢ ምን አይነት መልእክት ነው በሚልም ሰፊ ከሆነ መልዕክት ወደታች በሚወርድ መንገድ በያንዳንዱ ቤት ውስጥ ሊገባ በሚችል መልኩም ቅስቀሳ አድርገዋል። ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከሆነ በራሪ ወረቀቶች ያዘጋጃሉ፣ ምርጫው እየተቃረበ ሲመጣ በመኪና ላይ የሚደረጉ ቅስቀሳዎቸን ለማከናወን የተቀዱ የድምፅ መልእክቶች ይተላለፋሉ። "መድረክን ምረጡ፤ መድረክን ስትመርጡ ነፃ ትወጣላችሁም" ይላሉ። ጠጅ ቤቶች የመሳሰሉ የሕዝቡ ቦታዎች ፎርማል የሆነ ቅስቀሳ ባይኖርም በራሪ ወረቀቶች ሰጥተው ይመለሳሉ ምናልባት ቤታቸው ሆነው ቢያነቡት በሚል ቢሆንም፤ አንዳንዶች ግን እዛው አይተው ወዲያው ጥያቄ እንዲሁም ንግግሮችን ይጀምራሉ፤ ውይይቶችም ቦታው ላይ ይጦፋሉ፤ ከግል ጉዳይ ጀምሮ እሰከ የአገሪቱ ፖለቲካ ውጥንቅጦች ይነሳሉ። በተቻለ መጠን በሰውኛ ቋንቋ፣ ሰው በሚረዳው መንገድ ቢያስረዱም የአገሪቱን አጠቃላይ የፖለቲካ ሁኔታ በማየት ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ይበዛባቸዋል ይላሉ። "በኛ አገር እንዳለመታድደ ሆኖ ስለ ፌደራሊዝምና የብሔር ብሄረሰቦች ጥያቄ ብዙውን ነገር ይሸፍነዋል፤ ተጨባጭ የማይሆኑና ለሕዝቡ ውስብስብ የሆኑ የልሂቃን ውይይቶች ይደረጋሉ። በሚዲያዎችም ላይ ሕገ መንግሥታዊ የሚል ጠቅላላ ርዕስ ይመጣና ሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጭቅጭቆች ውስጥ በመግባት፤ ሰብአዊ መብት እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ ግንባታ የሚሉ የፅንሰ ሃሳብ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ይካሄዳሉ" ይላሉ። ለምሳሌ ለአዲስ አበባው ነዋሪ ትኩረት መሰጠት የሚገባቸው ጉዳዮች የመጠጥ ውሃ ችግር፣ የትምህርት ቤት ዋጋ ማነት፣ ራስ ምታት የሆነው የቤት ኪራይ ብዙ ጊዜ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋና መከራከሪያ ሲሆኑም አይሰሙም። ከተወሳሰቡ ሃሳቦች በተጨማሪ የአካል ጉዳተኞች፣ የኤች አይ ቪ ህሙማን እንዲመዘገቡና እንዲመርጡ፤ ለሕይወታችሁ ዋጋ ስጡ የሚሉ መልእክቶች ያሉበት በራሪ ወረቀቶች ሊበተኑ ሲሉ ስማቸውን መጥራት የማይፈልጉ አንድ ፖለቲከኛ እንዲህ አይነት መልዕክት አይተላለፍም አሻፈረኝ ብለው ሁሉንም ሰዎች በእኩል የማስተናገድ ቦታ እንደሌላቸውም ያሳያቸውን ጊዜም ያስታውሳሉ። • "ምርጫ ቦርድ ከጨዋታ ውጭ ሊያደርገን ይፈልጋል" መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በምርጫ ቅስቀሳዎች ውስጥ ለሚደረጉ የትራንስፖርት፣ በራሪ ወረቀቶችን እንዲሁም ሌሎች ወጭዎች የብዙ ፖለቲካ ፓርቲዎች ራስ ምታት እንደመሆኑ መጠን ፓርቲዎችም ወጭዎቻቸውን ለመሸፈን ከመገደዳቸው አንፃር በአንዳንድ አጋጣሚዎችም ፈረሱን ሽጦ የተወዳዳረ እጩና የእርሻ በሬውን ሽጠው የተወዳደሩ እንዲሁም ሌሎችንም መስዋዕትነቶችን መከፈላቸውን ፕሮፌሰር በየነ ይጠቅሳሉ። በሌሎች አገራት በሚደረገው አቅም ያላቸው ሰዎች ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ እንደማያደርጉም ፕሮፌሰር በየነ ይናገራሉ። "የኢትዮጵያ ሃብታሞች ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ አያደርጉም፤ ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቁ ብለው ነው የሚፈሩት፤ ሌላው ቀርቶ እኛን በአደባባይ ቆመው ሰላምታ እንኳን መስጠት ያስፈራቸዋል። አይደፍሩም" ይላሉ የ1997 ምርጫ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የ1997 ዓ. ም. ምርጫ እንደ ትልቅ ምዕራፍ ይታያል በነበሩት የጦፉ ውይይቶችና መድረኮች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣምረው በአንድ ግንባር መምጣትና በምርጫ ቅስቀሳዎች። በ1992 ዓ. ም. የነበረውን የሃድያ ድል አንድ ተሞክሮ ሆኖ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ቢያስተባብሩ በአገር አቀፍ ደረጃ ኢህአዴግን ማሸነፍ ይቻላል በሚል በውጭ አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ክልል አቀፋዊና አገር አቀፋዊ ፓርቲዎቸን በማስተባበር የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ህብረት በሚልም አስራ አምስት ፓርቲዎች በአንድ መድረክ የመጡት በ1997 ዓ. ም. ነበር። በመኢአድ አስተባባሪነት አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘውን ቅንጅት የተፈጠረውም በዚሁ በ1997 ዓ. ም. ነበር። ወቅቱም አብዛኛው የአለም አቀፍ ማህበረሰቡም የመድብለ ፓርቲ ስርአት እንዲገነባ ብዙ ከመጣሩ አንፃር፤ ኢህአዴግ የምርጫውን ሜዳ ክፍት ማድረግ አለበት የሚሉ ግፊቶችም እንደነበሩ የሚያወሱት ፕሮፌሰር በየነ የተለያዩ አለም አቀፍ መንግሥታት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ብዙ ድጋፎችን አድርገዋል። በ1997ቱም ምርጫ መላውን ኢትዮጵያ ለማዳረስ ተንቀሳቅሰዋል። ሶማሌ ክልል የተወሰኑ ችግሮች ስለነበሩ በዛ በኩል መንቀሳቀስ ባይችሉም በትግራይ፣ አማራ ክልል፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ወጭዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው መኪኖች ተከራይተው፤ ትልልቅ 'ሜጋ ፎን' ከላዩ ላይ አድርገው፤ በየከተማው ስብሰሰባዎችን በመጥራት ቅስቀሳዎችን አድርገዋል። ከአለም አቀፉም ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግ ስለነበር የምርጫ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ለሁለት ወራትም ያህል ቀን ተሌት ሳይሉ ቀስቅሰዋል። ተፋዞና በፍርሃት ተሸብቦ የነበረው ፖለቲካ ያንሰራራበት ክርክሮች ባልተለመደ መልኩ ቀደም ብለው የተጀመረበት ጊዜም ነው። በተቀናጀ መልኩ ከፍተኛ ቅስቀሳ የተደረገበትም ጊዜ እንደሆነም ሶስቱም ፖለቲከኞች ይስማማሉ። በዚህም ውጤታማ መሆን እንደቻሉ ፕሮፌሰር በየነም ሆነ ዶ/ር ታዲዮስ አስምረው የሚናገሩበት ነው። እንደ ምሳሌም ደ/ር ታዲዮስ ከተወዳደሩበት ልደታ ክፍለ ከተማ ከተመዘገበው 26ሺ መራጭ ሲሆን እሳቸውም ወደ 24 ሺ አካባቢ አግኝተዋል። መጪው ምርጫ ከአስራ ስምንት ወራት በፊት የመጣው ለውጥ እንደ አንድ እመርታ የሚያዩት ዶ/ር ታዲዮስ በምርጫው ሃገሪቱ አሁን ባለችበት ሁኔታ ሊካሄድ አይገባም ከሚሉ ወገኖች ናቸው። በየቦታው ግጭቶችና ግድያዎች ተበራክተዋል፣ መንቀሳቀስ አይቻልም፣ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ሕዝብን በአዳራሽ መሰብሰብ፤ ሕዝብን ማግኘት እንደሚያስፈልግም ሳይታለም የተፈታ በመሆኑ እሱን ማድረግ ከባድ ነው ይላሉ። "ሕዝቡን ለማግኘት የፀጥታው ሁኔታ ከባድ ስለሆነ፤ ፕሮግራም ሳይነገር፣ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊሠራ የሚገባው ጉዳይ ምንም ሳይባል ምርጫው እንዴት ሊካሄድ ይችላል?" የሚል አቋም ነው ያለን ፕሮፌሰር በየነ በበኩላቸው አሁን ካለው የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተያይዞ አለመረጋጋቶች በመኖራቸው እንቅስቃሴያቸውን የገደበው ሲሆን የምርጫ ቅስቀሳቸውም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚፈጥር ያስባሉ። ከዚህ በተጨማሪ ግን አለም አቀፍ ማህበረሰቡና መንግሥታት በአሁኑ ሰዓት ስልጣን ላይ የወጣውን ቡድን ያለ ጥያቄ ድጋፍ የሚያደርግበት ጊዜ ፈተና እንደሚሆንባቸውና ከዚህ ቀደም የነበሩ ድጋፎች በሙሉ ታጥተዋል ይላሉ። • ኢሕአዴግ እዋሀዳለሁ ማለቱን የፖለቲካ ተንታኞች እንዴት ያዩታል? "1997ን ብንወስድ በወቅቱ የነበረው የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ለውጥ ይፈልግ ስለነበር ይደግፈን ነበር፤ እንዳሁኑ ስልጣን ላይ ያለውን አካል በጭፍን መደገፍ አልነበረም" ይላሉ ኢዜማ በበኩሉ በተለየ መልኩ ለአዲስ አበባ ማኒፌስቶ እያዘጋጀ ሲሆን በዚህ ዘመን የምርጫ ቅስቀሳውን ደግሞ ለየት የሚያደርገው ማኅበራዊ ሚዲያን በሰፊው ለምርጫ ቅስቀሳ ሊጠቀሙ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ነው። እያንዳንዱ እጩ የራሱም ገፅ ይኖረዋል፤ በፌስቡክም የምረጡኝ ቅስቀሳ መልዕክትም የሚያስተላልፍ ይሆናል።
news-45899024
https://www.bbc.com/amharic/news-45899024
"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት የመከላከያ ሚኒስትር ሾማለች።
በዚህ ታሪካዊ ቀንም የቀድሞዋ የኮንስትራክሽን ሚንስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመጀመሪያዋ ሴት የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ መሾም በጭራሽ ያልጠበቁትና ለመናገርም ቃላት እንደሚያጥራቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። በተለይም የመከላከያ ሚኒስትርን ጨምሮ ቁልፍ የሚባሉ የመንግሥት ቦታዎች ሴቶች ተሹመውም ሆነ ተወክለው ስለማያውቁም፤ በዚህ ቦታ ላይ መሾምን እንዲህ ይገልፁታል። •ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ለመግደል በመሞከር የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ቀጠሮ ተጠየቀ •"የመሰረታዊ ፍጆታ እጥረት ካጋጠመን ዘጠነኛ ቀናችን ነው" •ከጄኔራሎቹ ሹመት ጀርባ? "ለኢትዮጵያ ሴቶች ክብር ነው፣ እኔ ለተወለድኩበት አካባቢ ክብር ነው፣ ለግሌም ክብር ነው።የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብር ትልቅ ግዙፍና ታሪካዊ ኃይል ከመምራት በላይ ክብር የለም ብየ ነው የወሰድኩት" ይላሉ። ወደ መከላከያ ከመምጣታቸው በፊት ወደ ሚዲያው አይን የገቡት የኮንስትራክሽን ሚኒስትርነት በነበሩበት ወቅት ላይ ሲሆን፤ በሚኒስትርነት ቦታ ከመምጣታቸው በፊት በአፋር ብሔር ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የአደጋ መከላከል ቢሮ አመራር ነበሩ። በአፋር ክልል የተለያዪ የስልጣን ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን፤ በ2008 ዓ.ም በተደረገው የመንግሥት ምደባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል። ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት ሶስት ሴቶች ሆነው የተመደቡ ሲሆን የነበረውንም ሁኔታ እንዲህ ያስታውሱታል። " ሶስታችንም የኢትዮጵያ ሴቶች ምሳሌ ሆነን መስራት አለብን በሚል መንፈስ ነበር የምንሰራው፤ ስህተት እንኳን ብንሰራ ያ ስህተት የመጣው ባለመቻሏ ነው ከሚል ጋር ነው የሚያያዘው። ሴት ስንሆን ስህተት መስራት ካለመቻል ጋር ነው በቀጥታ የሚያያዘው" ይላሉ። በቀጣዩ ዓመትም በ2009 በተደረገው የሚኒስትሮች ሹመት ኮንስትራክሽን ሚኒስትር በመሆን ለሁለት ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን፤ ግዙፍ ኢንዱስትሪና የሀገሪቱን ትልቅ በጀት የሚይዝ ከመሆኑ አንፃር ኃላፊነቱም ቀላል እንዳልነበር ይናገራሉ። "ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ያለች ሀገር ናት። ያስፈልጋሉ የሚባሉ ነገሮችን ለማደራጀትም ሆነ አስፈላጊ የሚባሉ ነገሮችን የማስተካከል ስራዎችንም እየሰራሁ ነበር" ብለዋል የሁለት ሴት ልጆችና የአንድ ወልድ ልጅ እናት የሆኑት ኢንጂነር አይሻ ተወልደው ያደግኩት ሰሜን አፋር አካባቢ በምትገኝ ትንሽ መንደር ሲሆን አባታቸው በመንግሥት ሰራተኝነት አሰብ ወደብ ተቀጥረው ይሰሩ ስለነበር ወደ አሰብ የመጡት በልጅነታቸው ነው "ነፍስ ያወቅኩት አሰብ እያለሁ" ነው ይላሉ። አባታቸው ወደ ዋናው ቢሮ አዲስ አበባ ሲዛወሩ እሳቸውም አብረው መጡ፤ ሁለተኛ ደረጃንም አዲስ አበባ ነው የተማሩት። ከልጅነታቸው ጀምሮ መሐንዲስ መሆን ይፈልጉ የነበሩ ሲሆን ህልማቸውንም አምስት ኪሎ ዩኒቨርስቲን ተቀላቅለው በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ዘርፍ በመመረቅ አሳክተዋል። "ከሁለተኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርስቲ የተማርኩት አዲስ አበባ ስለሆነ፤ በምህንድስና ሙያም ተቀጥሬ በተለያዩ ቦታዎች ስለሰራሁ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ ማለት ይቻላል" በማለት በሳቅ መልሰዋል። ወደ ፖለቲካ ህይወታቸው ከመግባታቸው በፊት በምህንድስና ሙያ የተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉት ኢንጂነር አይሻ ስራን ሀ ብለው የጀመሩት የቀድሞው ጂአይዜድ (ጂቲዜድ) ውስጥ ነው፤ በመቀጠልም ሰመራ ዪኒቨርስቲ ሲገነባ ሳይት ማኔጀርም ነበሩ። ወደ ፖለቲካው እንዴት ገቡ? ከመሐንዲስነት ወደ ፖለቲካ ፓርቲ እንዴት ተቀላቀሉ ለሚለው ጥያቄ ኢንጂር አይሻ ሲመልሱ በመጀመሪያ የአፋርን ህዝብ ጥያቄን በቅርበት ለማየት ወደ አፋር በሔዱበት ወቅት እንደተጠነሰሰ ይናገራሉ። "አፋር ስለሆንኩኝ አካባቢ ያለውንም የህዝቡን ሁኔታንም ሆነ ኑሮን ለማገዝ ክልሉ በሰጠኝ ዕድል መሰረት ወደ አፋር ተመለስኩኝ" ይላሉ በአፋር ውስጥ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ አናሳ መሆንና የሴቶች የስራ መደራረብ ጫና ከፍተኛ መሆን ብዙ ያሳስባቸው የነበረ ሲሆን በተደራጀ ሁኔታ ለመታገል የተወሰነ ጊዜ ጥናት እንዳደረጉም ይናገራሉ። መሰረታዊና መዋቅራዊ የሆኑ የሴቶችስ ጥያቄ በፖለቲካዊ መንገድ እንዴት ይመለሳል? የአፋር ሴቶችን ትግል ወደፊት ለመግፋት፣ ማስተካከያም ለማምጣት የኢህአዴግ አንዱ አጋር ፓርቲ የሆነውን የአፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ። ማዕከላዊ ኮሚቴም አባል የተቀላቀሉት ወዲያውኑ ነበር። "ህዝቡን ማገልገል እንዳለብኝ ነው የሚሰማኝ ምክንያቱም ህዝብ ሲኖር ነው እኛም የምንኖረው የሚል እምነት አለኝ። ህዝብ ለመኖር ደግሞ የሚያስፈልገውን ነገር ማግኘት አለበት፤ በተለይ ሴቶች ደግሞ ያለብን ድርብርብ ጭቆናዎች በተወሰነ መልኩ መቀረፍ ስላለበት ያንን ለማድረግ ተፅእኖ ፈጣሪ መሆን ስችል ብቻ ነው የሚል እምነት ስላለኝ ነው የፖለቲካ ፓርቲውን የተቀላቀልኩት" ብለዋል። ለባለፉት አስርት ዓመታት የብሔር፣ የመደብና ሌሎች ጥያቄዎች እንደ ፖለቲካ ጥያቄዎች ከመነሳት አልፎ የተለያዩ ምላሾችንም ለመስጠት ተሞክራል። ምንም እንኳን ሴቶች በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳታፊ ቢሆኑም ጥያቄያቸው እንደ ፖለቲካ ጥያቄ አለመታየቱ፣ ሴቶች ኮታን ከሟማላት ውጭ በመንግሥት የስልጣን መዋቅር ውስጥ አለመካተታቸውና እንዲሁም በስልጣን ቦታ ላይም ከተቀመጡ ለሴቶች ተብለው የተያዙ ቦታዎች ላይ ይቀመጡ ነበር። ሰሞኑን በነበረው የካቢኔዎች ሹመት ላይ የነበረው አሰራር ተቀይሮ አምሳ ፐርሰንቱ ለሴቶች ከመሰጠት በተጨማሪ የመንግሥት ቁልፍ ቦታዎችንም አግኝተዋል። ይህንን በተመለከተ ኢንጅነር አይሻ የሚሉት አላቸው። "ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ባህል ሴቶችን ዝቅ የሚያደርግና፣ የሚነገሩትም ተረት ምሳሌዎች ብዙዎች ሴቶች ልጆች ላይ ሰርፆ ስለሚያድጉ "አንችልም" የሚለውን ስነልቦና ይዘው እንደሚያድጉ ይናገራሉ። "እኛ ራሳችንም አንችልም የሚል ስነ ልቦና ስላለን፤ እነሱም አይችሉም የሚለውን ይዘው ይመስለኛል እነዚህ ቁልፍ ቦታዎች የማይሰጡት" ይላሉ ነገር ግን ማንኛውም ቦታ ላይ የሚሰራ ስራ አለ ብለው የሚያምኑት ኢንጅነር አይሻ " ያደግንበትን አይችሉም ወይም እኛም አንችልም የሚለውን ባህል ያለመተው አለ። ዋናውም ችግሩ እሱ ነው" ይላሉ። በዓመታት ውስጥ መንግሥት ሴቶችን "ለማብቃት" በሚለው ፕሮግራም ለሴቶች ልዩ ድጋፍ (አፈርማቲቭ አክሽን) እንደ እቅድ አስቀምጦ የሰራ ሲሆን ሴቶችን በፖለቲካው፣ በትምህርቱ፣ በኢኮኖሚው ራሳቸውን እንዲችሉ ቢሰራም ውጤታማነቱ ላይ ጥያቄ አላቸው። በርካታዎቹም ስራዎችም ውጤታማ እንዳልነበር ይናገራሉ። ይህ ሴቶችን በሆነ አካል ድጋፍ ማብቃትና ከሚለው አስተሳሰብ ወጥቶ በሚኒስትርነት ደረጃ መሾማቸው ለየት ያለ እንደሆነ የሚናገሩት ኢንጅነር አይሻ " እኛ እንደምንችል ማሳየት አለብን ብየ ነው የማምነው" ይላሉ። አምሳ ፐርሰንት የካቢኔው ሹመት ሴቶች የተሾሙበትን ምክንያት ሴቶች ከሙስና የፀዱ በመሆናቸውና ስራቸውንም አክብረው ይሰራሉ በሚል ምክንያት እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ መናገራቸው በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያን የፈጠረ ሲሆን በዚህ ላይ ኢንጅነር አይሻ የሚሉት አላቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስራ ሂደቶች የሚያገኟቸው ሴቶች ባህርይ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚናገሩት ኢንጅነር አይሻ "ሴቶች በባህርያቸው ትርፍ ፈላጊ ናቸው ብየ አላምንም፤ ነገር ግን የማህበረሰቡ አካል እንደመሆናቸው መጠን ሁሉም ሴቶች መልአክ ነው ብየ አልወስድም። ሴቶች ባየኋቸው ቦታዎች ላይ ተጠንቅቆ የመስራት፣ በሌብነትም ምሳሌ ሲሆኑ አይታይም። ይህ ማለት ሌቦች የሉም ማለት አይደለም። ኃላፊነት ሲሰጣቸው የቻሉትን ያህል ማድረግ እንጂ በጥፋት ሲወገዙ አልሰማሁም፤" በማለት ኢንጅነር አይሻ ይናገራሉ ለዓመታት የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ አናሳ መሆን በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳ ከመቆየቱ አንፃር፤ ሹመቱም ሆነ ውክልናው እንደ መልካም ጅማሮ ብዙዎች ቢያዩትም መስረታዊና መዋቅራዊ የሚባሉ የሴቶችን ችግር ሊቀርፍ ይችላል ወይ የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሳሉ። የኢትዮጵያን ሴቶች ችግር መቶ በመቶ ይቀረፋል ብለው ኢንጂነር አይሻም የማያምኑ ሲሆን "የሴቶች ችግር በኛ ብቻ የሚቀረፍ እንዳልሆነ አውቃለሁ። አይችሉም የሚለውን አስተሳሰብ ግን ግን ሊቀርፈው ይችላል ብየ አስባለሁ " ይላሉ። ይህንን ያህል ቁጥር ያለው ሚኒስትሮች መሆን ለወደፊቱ ለሚመጡት ህፃናት ሴቶች አርዓያ እንደሚሆኑና የሴቶችንም ጥያቄ የመግፋት ጅማሮ ከመሆኑ አንፃር እንደ ቀላል መታየት እንደሌለበት ይናገራሉ። ሴቶች በባህርያቸው የማስተዳደር ስጦታ አላቸው ብለው የሚያምኑት ኢንጅነር አይሻ መንግሥታት ሴቶችን ወደ አስተዳደርና ወደፊት ቦታ ሊያመጡ እንደሚገባም ይመክራሉ። የመከላከያ ሚኒስትሩን እንዴት ሊመሩት አስበዋል ለሴቶች ሊሰጡ አይገቡም የሚባሉ ቦታዎች ሊኖሩ እንደማይገባ የሚያምኑት ኢንጅነር አይሻ የመከላከያ ሚኒስትርነት ከባድ እንደሆነ ቢታሰብም ያላቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ ናቸው። "ይህንን ግዙፍ፣ ታሪካዊና በአፍሪካ ደረጃ ትልቅ ዕውቅና ያለው ተቋም መምራት ቢቻል የተሻለ አድርጎ ለመምራት፣ ያንን ማድረግ ቢያንሰኝ ግን ካለበት ዝቅ እንዳይል ተቋሙን ለመምራት መዘጋጀት አለብኝ ብየ ነው የማስበው" ይላሉ። በዋነኝነትም የአገሪቷን ዳር ድንበር ማስጠበቅ፣ የአገሪቷን ፀጥታና ሰላም ማስከበርና የዜጎችን ልማትን ማገዝ ዋና አፅንኦት የሚሰጠው ስራ ነው ብለው የሚያምኑ ሲሆን " የህዝብን ጥያቄን ለመመለስ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መምራት አለበት ብየ አምናለሁ። ከዚያም በተጨማሪ አገሪቷ ያለችበትን የጂኦ ፖለቲካል ሁኔታንም በብልህነት ካለው አመራር ጋር መምራት ያቅታል ብየ አላምንም፤ ሲሆን በተሻለ መልኩ መምራት እችላለሁ" ይላሉ። ምንም እንኳን ያለውን የመከላከያ አሰራር ማስቀጠል ዋና አላማቸው ቢሆንም አሁን ሀገሪቷ እየሄደችበት ካለው ለውጥ ጋር ለማጣጣም የተወሰነ ማሻሻያ እንደሚኖር አልደበቁም። በተለያዩ ቦታዎች በሀገሪቷ ግጭት በተለይም በብሔር ግጭት እየተናጠች ከመሆኗ አንፃር ያንን እንደ አንድ ፈተና ቢያዩትም ያንን በኃላፊነት የሚያይ የሰላም ሚኒስትር የተቋቋመ ሲሆን ከዛ የተረፈው ወደ መከላከያ ሚኒስትር እንደሚመጣም ተናግረዋል። "በዋናነት የሀገራችንን ውስጣዊ ሰላም ማስጠበቅ አለብን። የምታሰባስበን፣ የማንነታችን መገለጫ ኢትዮጵያ እስከሆነች ድረስ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አድርገን ማቆየት የምንችለው ሰላማዊ ፣ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ የሆነ ስርዓት በአገራችን ሲኖር ነው። ነገር ግን በርካታ ልናስባቸው የሚገቡ ስጋቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ብየ አምናለሁ። በተቻለ መጠን በዲፕሎማሲ መንገድ ለመፍታትና በሰላም አሁን እንደጀመርነው ከጎረቤቶቻችን ጋር መኖር መቻል አለብን። " ይላሉ
news-56596284
https://www.bbc.com/amharic/news-56596284
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሦስት ዓመታት ጉዞ፡ ከኖቤል ሽልማት እስከ ትግራይ ግጭት
በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭትና ተቃውሞች መበራከታቸውን ተከትሎ 'የመፍትሄው አካል ለመሆን' በሚል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን ለቀቁ።
በዚህም ምክንያት መጋቢት 24/2010 ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። በተመሳሳይ ቀን ባደረጉት 35 ደቂቃ የፈጀ የመጀመሪያ ንግግራቸው በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በውጪ ግንኙነት [ከኤርትራ ጋር 20 ዓመታት ተቋርጦ የቆየውን ግንኙነት ማደስን ጨምሮና በማኅበራዊ ጉዳዮች መጠነ ሰፊ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ቃል ገቡ። በዚህ ንግግራቸው "የሃሳብ ልዩነት እርግማን አይደለም" ያሉት ዐቢይ "በተለያየ ጊዜ መስዋዕትነት ለከፈሉ የመብት ተከራካሪዎች፣ ፖለቲከኞች፣ በቅጡ ሳይቦርቁ ህይወታቸው ለተቀጠፈ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ለሥነ ልቦናዊና አካላዊ ጉዳት ለተዳረጉ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ።" ሲሉም ተደምጠዋል። ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሄ በመስጠት ህዝባችንን እንክሳለንም ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ሁሉ ከሆነ ዛሬ ሶስት ዓመታት ተቆጠረ። እናም ያለፉትን ሶስት ዓመታት ከተለያዩ ጉዳዮች አንጻር በወፍ በረር እንቃኘው። የሚዲያ ነጻነት እና የፖለቲካ እስረኞች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጀመሪያዎቹ የስልጣን ወራቶች በፖለቲካዊ ምክንያቶች የታሰሩ ግለሰቦች ከእስር ተፈትተዋል። ከሀገር ውጪ ነፍጥ አንግበው ሲታገሉ የነበሩና 'በአሸባሪነት' የተፈርጁ ፓርቲዎች 'ከአሸባሪነት መዝገብ ተፍቀው' ወደ ሃገር እንዲገቡ ተደርገዋል። ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩን 'መልካም አደረጉ፣ አበጁ!' ያስባላቸው ነበር። በመገናኛ ብዙሃን ነጻነትም እንዲሁ። ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ከለላ ተቋም (CPJ) እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2019 ባወጣው ሪፖርት ከመገናኛ ብዙሃን አንጻር በኢትዮጵያ ያለውን ለውጥ 'ተአምራዊ' ሲል ነበር የገለጸው። ተቋሙ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምንም አይነት ጋዜጠኛ በእስርቤት የለም ሲል አሳውቆ ነበር። ከ260 በላይ የታገዱ ድረ ገጾች እንደተለቀቁና ውጪ የነበሩ መገናኛ ብዙሃን ወደ አገር ቤት እንዲገቡ መደረጉን ገልጾ ይህም አበረታች እርምጃ ነው ብሎት ነበር። በተመሳሳይ ዓመት ኢትዮጵያ በዓለም የፕሬስ ነጻነት ያላትን ቦታ 40 ደርጃዎችን አሻሽላ ከ150ኛ ወደ 110ኛ ከፍ ያለችበት ነበር። ሆኖም ነገሮች እንደመጀመሪያው የቀጠሉ አይመስልም። ወደሃገር ተመልሶ የነበረው OMN አሁን ላይ አዲስ አበባ ላይ የነበረው ቢሮው ተዘግቷል። በተለያዩ ወቅቶች ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገዋል። ድምበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሞጋች (Reporters without borders) አሁን ላይ በኢትዮጵያ መረጃ የማግኘት መብት ጥስት ጋር በተያያዘ በርካታ ሪፖርቶችን እየተቀበለ እንደሆነ ገልጾ ይህም ያለፉትን አስመስጋኝ እርምጃዎች 'አደጋ ላይ' የሚጥል ነው ብሎታል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን በመጡ በጥቂት ወራት የፖለቲካ እስርኞችን በመፍታታቸው እንደተመሰገኑ ሁሉ አሁን ላይ በእስር ላይ አሉ በሚባሉት ፖለቲከኞች ወቀሳም ይቀርብባቸዋል። የኦነግ፣ የኦፌኮ፣ የባልደራስና የኦብነግ አመራሮች 'አባሎቻችን ታስረውብናል'፣ 'ቢሮዎቻችን ተዘግተውብናል'፣ 'ወከባና ማስፈራሪያ ይደርስብናል' የሚል ቅሬታ በተደጋጋሚ ያቀርባሉ። በተለይ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስርኞች ቁጥር ከፍ ብሏል የሚለው ደግሞ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዋች ነው። ክስ ሳይመሰረትባቸው እስር ላይ የሚገኙ እንዳሉም ገልጿል። ከዚህም ባለፈ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያየ ወቅቶች ባወጣቸው መግለጫዎች ፍርድ ቤቶች የሚያሳልፉት ውሳኔዎች [በተለይ የፓለቲካ ተሳትፎ ያላቸውን እስረኞችን በተመለከተ] ያልተከበሩባቸውን ጊዜያት ጠቅሶ ችግሩ እንዲታረም በተደጋጋሚ አሳስቧል። ሰላምና መረጋጋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ባሉት ሶስት ዓመታት ውስጥ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ንጹሃንን ዒላማ ያደረጉ በርካታ ጥቃቶች ተሰንዝረዋል። ከአራት ወራት በፊት [ኅዳር 21-2013] በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ማዕከላዊ መንግስቱና ህወሃት የገቡበትን ግጭት ሳይጨምር በሁለት ዓመት ተኩል ውስጥ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች በድምሩ 113 ግጭቶች [ከትግራይ ክልል በስተቀር] መከሰታቸውን ገልጸዋል። እነዚህ ግጭቶች የሰው ህይወት የጠፋባቸውና ንብረት ያወደሙ እንደነበሩም ጠቁመዋል። "በእያንዳንዱ ሳምንት የጦርነት ድግስ ነበር። የመንግሥት ስራ እዚህ ማልቀስ መቅበር - እዚህ ማልቀስ መቅበር! ከአንደኛው ለቅሶ ሳይነሳ ወደ ሌላው ለቅሶ መሄድ ነበር።" ሲሉም ተደምጠዋል። ለዚህም ተጠያቂው ህወሓት እንደሆነ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ይበሉ እንጂ ህወሓት አቅሙ እንደተዳከመ ከተገለጸ በኋላም ንጹሃን ላይ ያተኮር ጥቃት ተፈጽሟል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ድባጤ ወረዳ ከሁለት ወራት በፊት [ጥር 4-2013] 82 ንጹሃን ሰዎች መገደላቸውን በወቅቱ እማኞች ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ከዚህ ጥቃት አንድ ወር ቀደም ብሎ ደግሞ በተመሳሳይ ዞን ቡለን በተባለ ወረዳ 207 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል። በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን በተለያየ ወቅት ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ ያደርጉ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። ከትግራይ ግጭት በፊት በነበሩ አለመረጋጋቶችም እንዲሁ በርካታ ንጹሃን ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል። ለአብነት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ የተፈጠረውን ቀውስ በተመለከተ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን 'መንግስት ያለ አይመስልም ነበር' በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ከአርቲስቱ ግድያ በኋላ በነበሩት 3 ቀናት ብቻ 123 ሰዎች በጸጥታ አካላትና በሁከቱ በተሳተፉ ሰዎች መገደላቸውን አትቷል። በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች በተከሰቱ ግጭቶችም የሰው ህይወት ጠፍቷል። ከዓመት በፊት በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተዘግቦ ነበር። ሲዳማን በክልል ከመደራጀት ጋር ተያይዘው በተነሱ ግጭቶችም የሰዎች ህይወት ጠፍቷል አካል ጎድሏል ንብረት ወድሟል። በደቡብ ክልል በጌዲዮ፣ በወላይታ፣ በኮንሶና በጉራጌ ዞኖች በተለያየ መነሻ የተፈጠሩ ግጭቶች የንጹኀንን ህይወት ቀምተዋል። በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች እንዲሁ። ከዚህም ባለፈ ወታደራዊና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት የተገደሉትም ዐቢይ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ነው። በተለያዩ ወቅቶችም ከክልል በታች ያሉ መንግስታዊ መዋቅር አመራሮችም የተገደሉባቸው ወቅቶች ነበሩ። እናም የዚህ ሁሉ ድምር መንግስት ባለፉት ሦስት ዓመታት የዜጎችን ደህንነት በመጠበቅና ሰላምና መረጋጋትን ከማስፈን አኳያ በተለያዩ አካላት ክፉኛ አስተችተውታል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥቅምት 24-2013 በነበራቸው መደበኛ ስብሰባ ባልተለመደ መልኩ በእንባና በቁጣ ታጅበው መንግሥት የዜጎቹን ደህንነት እንዲጠብቅ አሳስበው ነበር። ከብልጽግና ምስረታ እስከ ትግራይ ግጭት 30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በስልጣን ላይ የነበረው ኢህዴግ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ የቆየው ዘጠኝ ወራት ብቻ ነው። ከህወሃት በስተቀር ስምንቱን ክልሎች የሚያስተዳድሩ ገዢ ፓርቲዎች ከስመው ብልጽግና የተሰኘ ፓርቲ ተመሰረተ። ፓርቲው በተለይ ክልሎች ላይ ያለው መዋቅር ከቀድሞ በምን እንደሚለይ ግልጽ አይደለም የሚል አስተያየት ይቀርብበታል። ታዲያ የፓርቲው መመስረት ህወሓት ቀድሞ ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር የነበረውን የሻከረ ግንኙነት ይበልጥ እንዳካረረው ይነገራል። የህወሓት ሊቀ መንበር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከፓርቲ ውህደት በፊት ሊታዩ የሚገቡ አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉና የውህደት ሂደቱም ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዳልተፈጸመ ገልጸው ነበር። በሌላ በኩል የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ በድምፀ ወያኔ ቴሌቪዥን ቀርበው "አገሪቱ ወደማይሆን ጣጣ እየገባች ባለችበት ሁኔታ ስለውህደት ብቻ ማውራት ምናልባት የሀገሪቱን ሁኔታ የመዘንጋት ስለሃገሪቱ ሁኔታ ያለመጨነቅ ነገርን ነው የሚያሳየው" ብለው በዚህም ምክንያት ህወሃት የተለየ አቋም መያዙን ገልጸዋል። ይህ ከሆነ ከወራት በኋላ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርጫ 2012 እንዲራዘም በህዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሲወሰን ሃሳቡን የትግራይ መንግሥት ባለመቀበል በክልሉ ምርጫ ለማድረግ ወሰነ። ምርጫውም ተደርጎ ህወሃት እንዳሸነፈ ተገለጸ። ይህም የሁለቱን አካላት የሻከረ ግንኙነት ይበልጥ አጋጋለው። "ትግራይ ክልል የሚደረገው የጨረቃ ምርጫ ነው።... ልክ እንደጨረቃ ቤት ነው ህጋዊ አይደለም። ..." ያሉት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ነበሩ። የሁለቱ አካላት በቃላት ጦርነት የታጀበ መቃቃር በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወደ ግጭት ተሸጋገረ። የትግራይ መንግሥት ለፌዴራሉ መንግሥት እውቅና ሲነፍግ የፌዴራሉ መንግስት ደግሞ ለክልሉ የሚሰጠውን በጀት ማቋረጡን አስታወቀ። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ሁለቱ አካላት ወደለየለት ወታደራዊ ግጭት አመሩ። በግጭቱ የተሳተፉ አካላት በሙሉ የከፋ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ማድረሳቸውን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ገልፀዋል። ግጭቱን ተከትሎ በማይካድራ ከ600 በላይ ዜጎች በህወሓት ኃይሎች ለሞት እንደተዳረጉና በሌላ በኩል ከ100 በላይ ሰዎች በአክሱም በኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውን የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ ወቅቶች ገልጿል። ይህ ግጭት በርካቶችን ለአካላዊ ጉዳት፣ ለስደትና መፈናቀል ዳርጓል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉልህ ሚና የነበራቸውን አንጋፋ ፖለቲከኞችን ለሞትና ለእስርም የተዳረጉበት ነው። በትግራይ ባለው ግጭትም የኤርትራ ስም ተደጋግሞ ይነሳል። የኤርትራ ወታደሮች በውጊያ በቀጥታ ከመሳተፍ አልፈው ንጹኀንን በአክሱም 'በአሰቃቂ' ሁኔታ መግደላቸውን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገልጿል። ሌሎች አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ደግሞ ቁጥሩን ከዚህም ከፍ ያደርጉታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በመጨረሻው የተወካዮች ምክር ቤት ቆይታቸው 'ኤርትራ ባለባት የብሄራዊ ደህነነት ስጋት ' ምክንያት ወታደሯቿ 'የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው' እንደሚገኙ ከገለጹ ከቀናት በኋላ ኤርትራ ወታደሮቿን ለማስወጣት መስማማቷ ተሰምቷል። ኢኮኖሚ: የዋጋ ግሽበቱ ከሦስት ዓመታት በኋላ ሲቃኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በያዙ የመጀመሪያው [ሚያዚያ 2010] ማዕከላዊ ስታቲክስ ባወጣው መረጃ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.7 በመቶ ነበር። ይኸው ተቋም ባወጣው ሪፖርት ከሶስት ዓመታት በኋላ የባለፈው ወር [የካቲት 2013] አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 20.6 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በያዙ የመጀመሪያ ወራት ኢትዮቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ 13 የስኳር ፋብሪካዎች፣ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ድርጅቶችን እንዲሁም ሌሎች በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ የልማት ተቋማትን በከፊል ለማዞር መወሰኑ ተሰማ። ይህም የተለያዩ ግብረ መልሶችን አስከተለ። አንደኛው ወገን መልካም እርምጃ ነው የሚል ሲሆን ሌላኛው ግን "ያለ በቂ ጥናት የተደረገና የተጣደፈ ነው "የሚል ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮ ቴሌኮም ከሌሎቹ የልማት ድርጅት በተለየ የተወሰነውን ድርሻ ለመሸጥ የሚኣስችለው ሂደት በፍጥነት እየተከናወነ ነው። ሂደቱንም የሚከታተል የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የተባለ ተቆጣጣሪ ተቋም ተመስርቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድን የተወሰነ ድርሻ ወደ ግል የማዞሩን ሃሳብ መንግሥት 'ለጊዜው እንደተወው' ገልጿል። የስኳር ፕሮጀክትና የባህር ሎጀስቲክስ የተወሰነ ድርሻን የመሸጥ ሂደት እንደቀጠለም የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከወራት በፊት ገልፀው ነበር። የተቀሩትን ተቋማት በተመለከተ ግን የተባለ ነገር የለም። ኤርትራ፡ ለዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ምስጋናና ወቀሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተሾሙ የመጀመሪያ ቀን ለኤርትራ የሰላም ጥሪ ማቅረባቸው በበርካቶች ያልተጠበቀ ነበር። "በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል ልዩነታችንን በጋራ ለመፈታት ያለንን ዝግጁነት እየገለጽኩ፣ የኤርትራ መንግሥትም ተመሳሳይ አቋም እንዲወስድ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለው።" ሲሉ ከምክር ቤቱ አዳራሽ 'ሞቅ' ያለ ጭብጨባ ተቀባላቸው። ይህንን ካሉ ከአራት ወራት በኋላ ወደ አሥመራ አቀኑ። ይህም ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ኤርትራን የጎበኙ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሪ አደረጋቸው። በርከት ያለ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ተቀበላቸው። የአየር መንገድና የስልክ አገልግሎቶች ዳግም ተጀመሩ። ከሳምንት በኋላ ደግሞ ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ሲገቡ ተመሳሳይ አቀባበል ተደረገላቸው። በጦርነቱ ምክንያት ረጅም ዘመናት ተለያይተው የነበሩ ቤተሰቦች ተገናኙ። ድንበሮች ተከፈቱ። ይህም ዐቢይን እጅግ አስመሰገናቸው የተለያዩ ዓለምአቀፍ ተቋማት አድናቆታቸውን ገለጹ። የዚህ ሁሉ ድምር እንደ አውሮፓውያኑ የ2019 የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ አደረጋቸው። ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ግን ግልጽ ባልሆነ መንገድ የሁለቱ አገራት ድንበሮቹ ዳግም ተዘጉ። የሁለቱ አገራት ግንኙነት 'ግልጽ መርህ የለውም' የሚል ወቀሳም ተከተለ። በአንድ ወቀቅ ትግራይ ቲቪ ላይ ቀረበው ስለሁለቱ ሃገራት ግንኙነት አስተያየት የሰጡት አምባሳደር ስዩም መስፍን ግንኙነቱ 'የጠላቴ ጠላት ወደጄ ነው' በሚል መርህ የቆመ ነው ሲሉ ገልጸው ነበር። ይህ ግንኙነት ለሁለቱ አገራት ህዝቦች የፈየደው ነገር የለም ሲሉም ተናግረዋል። በሌላ ቀን ደግሞ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እንዲጥሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፈቅደዋል ሲሉ ተደምጠዋል። በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተያዘው ዓመት መግቢያ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የሁለቱ አገራት ግንኙነት መርህ የሌለውና ህወሓትን ለማጥቃት የዋለ ነው ይባላል የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ ይህንን የሚሉ አካላት ማምጣት ያልቻሉትን የዲፕሎማሲ ድል አግኝተናል፣ የዚህ ድል ትርፍ ደግሞ ሰላም ነው ብለዋል። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደግሞ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ "በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ሁኔታ የቻልነውን ያህል ለማበርከት እየሞከርን ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የትግራይ ግጭት በተጀመረ ሰሞን ሱዳን ወደ ኢትዮጵያን ግዛት ዘልቃ መግባቷ ተሰምቷል። እነዚህ ሁለቱ ሀገራት ከበርካታ አመታት በኋላ የከፋ ዲፕሎማሲያዊ ግጭት ውስጥ ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ይህም ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በተመለከ የእርሳቸውን ድርሻ የተቃረኑ ገጾች እንዲኖሩት ያደረገ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን በሱዳን ያለው የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ባደረጉት አስተዋጾ በ'ባለውለታነት' ሲነሱ ድንበር አከባቢ ባለው ውጥረት በተለየ አይን ይታያሉ። ግብጽ፣ ሱዳንና ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት ሦስት ዓመታት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲነሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሁለት መልኩ ነው አስተያየት ይቀርብባቸዋል። በግንባታው ሂደት በበጎ ሲነሱ በድርድሩ ግን ስህተቶችን ሰርተዋል ተብለው ይወቀሳሉ። የግድቡን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችን ይዞ የነበረውና ለግንባታው መጓተት ምክንያት እንደነበር ሲጠቀስ የነበረው ሜቴክ በግንባታው የነበረው ጉልህ ተሳትፎ የተቋረጠው እርሳቸው ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነው። "ፕሮጀክቱ በነበረው አመራር በነበረው አካሄድ ቢቀጥል ምንም አትጠራጠር እንኳን ዘንድሮ በሁለት ሶስት ዓመታት ውሃውን መያዝ አይችልም። ግድቡም አይገደብም ስራውም አይሰራም" ብለውም ነበር። እናም ተደረጉ በተባሉ ማስተካከያዎች ባለፈው ዓመት ግደቡ 4.9 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ያዘ። ይህም ዐቢይን ያስመሰገናቸው ነበር። በዚያው ዓመት ግን በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና ግብጽ መካከል ሲደረግ በነረው ድርድር የአሜሪካን ገንዘብ ሚኒስቴርና የዓለም ባንክን ተሳትፎ መፍቀዳቸው ክፉኛ ሲያስተቻቸው ነበር። ታዛቢ የተባሉት አካላት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጻረር ስምምነት እንዲፈርም ጫና ማሳደራቸውን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ስምምነቱን ባለመቀበሏ ለማዕቀብ ተዳርጋለች። ድርድሩ ኢትዮጵያ ከግብጽና ሱዳን ጋር ያላትን ግንኙነትንም እንዳሻከረው ይገለጻል።
47689767
https://www.bbc.com/amharic/47689767
በቤት ውስጥ ግርዛት የአምስት ወር ልጅ ሞተ
በጣልያን ሰሜናዊ ሪጊዮ ኢሚሊያ ግዛት ወላጆች የአምስት ወር ሕፃን ልጃቸውን በቤት ውስጥ ለመግረዝ ሲሞክሩ ሕፃኑ ለድንገተኛ የልብ ህመም በመጋለጡ ወደ ቦሎኛ ሆስፒታል ቢወሰድም ወዲያው ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
ሕፃኑ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ሕይወቱ በዚያው ያለፈው ባለፈው አርብ ዕለት ነበር። የግዛቲቱ ባለሥልጣናት ትውልደ ጋናዊያን ናቸው የተባሉት የሕፃኑ ወላጆች ላይ ምርመራ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ ላይም በጣልያን መዲና ሮም በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ የሁለት ዓመት ሕፃን በተመሳሳይ የግርዛት ሙከራ ሕይወቱ አልፏል። • "አደጋውን ስሰማ ክው ነበር ያልኩት..." አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በጣልያን በዓመት በአማካይ አምስት ሺህ ግርዛቶች የሚካሄዱ ሲሆን ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆነው በህገወጥ መንገድ የሚካሄድ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። በካቶሊካዊቷ ጣልያን የግርዛት አገልግሎት በሕዝብ የጤና ተቋማት አይሰጥም። በአገሪቱ የሚገኙ በርካታ ስደተኞች ደግሞ ግርዛት በተለምዶ ከሚካሄድባቸው እስልምናን ከሚከተሉ አገራት የሄዱ ናቸው። ምንም እንኳ ግርዛት ቀላል የሚባል ህክምና ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ግን አደጋን የማያስከትል አደለም። • የገጠር አስተማሪው አንድ ሚሊዮን ዶላር አሸነፉ
news-49606277
https://www.bbc.com/amharic/news-49606277
የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ማን ነበሩ?
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1924 የተወለዱት ሮበርት ሙጋቤ የእንጨት ሠሪ ልጅ ናቸው። የተማሩት በሮማን ካቶሊክ ሚሽነሪ ትምህርት ቤት ነበር።
ሮበርት ሙጋቤ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ፎርት ሀሬ ዩኒቨርስቲ ነፃ የትምህርት እድል አግኝተው ከተማሩ በኋላ፤ ጋና ውስጥ መምህር ነበሩ። ጋና ሳሉ በፓን አፍሪካዊው ክዋሜ ንክሩማ አስተሳሰብ እጅግ ይማረኩ ነበር። የመጀመሪያ ባለቤታቸውም ጋናዊት ነበሩ። በ1960 ወደ ትውልድ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ መጀመሪያ ላይ ከጆሽዋ ንኮሞ ጋር በጋራ ሠርተዋል። ኋላ ላይ ግን 'ዚምባብዌ አፍሪካን ናሽናል ዩኒየን' ወይም ዛኑን መሰረቱ። የጆሽዋ ንኮሞ ፓርቲ ከሆነው 'ዚምባብዌ አፍሪካን ፒፕልስ ዩኒየን' ወይም ዛፑ ፓርቲ ጋር በቅርበት ይሠሩ ነበር። ዛኑን በመሰረቱ በአራተኛው ዓመት ጠቅላይ ሚንስትር ኢን ስሚዝና አስተዳደራቸውን በመሳደባቸው ታሠሩ። እሥር ላይ ሳሉ ልጃቸው ቢሞትም ቀብሩ ላይ ለመገኘት ፍቃድ አልተሰጣቸውም ነበር። በጎርጎሳውያኑ 1973 ላይ እዛው እሥር ቤት ሳሉ የዛኑ ፕሬዘዳንት ሆነው ተመረጡ። ከእሥር ከተለቀቁ በኋላ ወደ ሞዛምቢክ አቅንተው ያኔ 'ሮዴዢያ' ትባል ወደነበረችው የአሁኗ ዚምባብዌ የጎሪላ ተዋጊዎች ልከው ነበር። • የሮበርት ሙጋቤ ጥቅሶች • ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣን ለቀቁ ሮዴዢያ ነፃነቷን እንድታገኝ ያደርጉት በነበረው ጥረት ወለም ዘለም የማያውቁ፣ ቆፍጣና ሰው መሆናቸውን አስመስክረዋል። ሙጋቤ (በስተግራ) ጆሽዋ ንኮሞ (በስተቀኝ) 1960ዎቹ አካባቢ የሙጋቤ የመደራደር ብቃት ተቺዎቻቸውን ሳይቀር በአድናቆት ያስጨበጨበ ነበር። 'ዘ ቲንኪንግ ማንስ ጉሬላ' እየተባሉም ተሞካሽተዋል። ሙጋቤ በአመራር በህመም ሳቢያ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሙጋቤ ዚምባብዌ ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የመጀመሪያው መሪ ናቸው። ሙጋቤ አገራቸው ዴሞክራሲ የሰፈነባት እንደምትሆን ቃል ገብተው ነበር። ያሉት ግን አልሆነም። ዚምባብዌ በግጭት የምትናጥ፣ በሙስና የተጨመላለቀች፣ ኢኮኖሚዋ የተናጋ አገር ሆነች። ሙጋቤ ምዕራባውያንን አጥብቆ በመተቸት ይታወቃሉ። በተለይ የቀድሞው የዚምባብዌ ቅኝ ገዢ ዩናይትድ ኪንግደምን "ጠላት አገር" ይሏት ነበር። ምንም እንኳን ሙጋቤ ለተቀናቃኞቻቸው ርህራሄ አልባ ቢሆኑም የአፍሪካ አገራት መሪዎችን ድጋፍ ለማግኘት አልተቸገሩም። ማርክሲስት ነኝ የሚሉት ሙጋቤ ሥልጣን እንደያዙ፤ ደጋፊዎቻቸው ሲፈነድቁ ነጮች በተቃራኒው ከዚምባብዌ ለመውጣት ሻንጣቸውን ሸክፈው ነበር። ሆኖም ሙጋቤ ይቅር መባባልን ያማከሉ ንግግሮች በማድረግ ተቀናቃኞቻቸውን ለማጽጽናት ሞክረዋል። ሙጋቤ አብረዋቸው ይሠሩት ከነበሩት ጆሽዋ ንኮሞ ጋር በምርጫ ፉክክር ወቅት ቅራኔ ውስጥ ገብተው ነበር። ዛኑ አብላጫ ድምፅ ሲያገኝ ምርጫው ተጭበርብሯል ተብሎም ነበር። • ለዘመናት በስልጣን ላይ ያሉት ስድስቱ መሪዎች • ሙጋቤ ከሥልጣን አልወርድም እያሉ ነው የዛፑ ንብረት በሆኑ አካባቢዎች መሣሪያ ከተገኘ በኋላ ጆሽዋ ንኮሞ በካቢኔ ሽግሽግ ከሥልጣናቸው ዝቅ ተደርገዋል። ሙጋቤ ደጋግመው ስለዴሞክራሲ ቢናገሩም፤ በ1980ዎቹ የንኮሞ ደጋፊዎች ናቸው የተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተጨፍጭፈዋል። በሰሜን ኮሪያ በሰለጠኑት አምስተኛ ብርጌድ የዚምባብዌ ጦር ጭፍጨፋ ሙጋቤ እጃቸው እንዳለበት ቢነገርም፤ ሕግ ፊት ቀርበው ግን አያውቁም። የዛፑ ፓርቲ መሪ ጆሽዋ ንኮሞ በደረሰባቸው ከፍተኛ የሆነ ጫና ምክንያት፤ ከዛኑ ጋር ለመቀላቀልና በጣም ጠንካራ የሆነውን 'ዛኑ ፒ-ኤፍ' የተባለ ፓርቲ ለመመስረት ተስማምተው ነበር። ይሁን እንጂ በ1987 ሙጋቤ የአገሪቷ ፕሬዝደንት ሆነው ተሾሙ። ከዚያም በ1996 ለሦስተኛ ጊዜ የሥልጣን ዘመን ለፕሬዚደንትንት ተመረጡ። ባለቤታቸው በካንሰር በሽታ በሞት ከተለየቻቸው በኋላ በዚያው ዓመት መጀመሪያ ከግሬስ ማሩፉ ጋር ትዳር መሰረቱ። ሙጋቤ አርባ ዓመት ከሚበልጧት ባለቤታቸው ግሬስ ሁለት ልጆችን አፍርተዋል። ሦስተኛውን ልጃቸውንም የወለዱት የ70 ዓመት የዕድሜ ባለ ፀጋ ሳሉ ነበር። ሙጋቤ ከዘረኝነት አስተሳሰብ ነፃ የወጣ ማኅበረሰብ ለመፍጠር በርካታ ተግባራት አከናውነዋል። በጎርጎሳውያኑ 1992 ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመሬት ባለቤት መሆን የሚያስችል የመሬት ይዞታ ደንብ አስተዋወቁ። የደንቡ ዓላማ የነበረው ከ4500 በላይ በሚሆኑ ነጭ ገበሬዎች ተይዞ የነበረውን መሬት የዚምባብዌ ባለቤት ለሚሏት ጥቁሮች እንደገና ለማከፋፈል ያለመ ነበር። በዚህ ምክንያት በ2000 መጀመሪያ አዲስ የተመሰረተው ለዲሞክራሲዊ ለውጥ ንቅናቄ [ሙቭመንት ፎር ዲሞክራሲ ቼንጅ] መሪ በነበሩት ሞርጋን ፅፋንጊራይ በሚመራው እንቅስቃሴ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ነበር። ሙጋቤ ከአርሶ አደሮቹ ጎን ባለመቆማቸው የእንቅስቃሴው ደጋፊ ተደርገውም ይቆጠሩ ነበር። የቀድሞ ወታደሮች በነጮች ተይዞ የነበረውን መሬት የግላቸው ያደረጉ ሲሆን፤ በወቅቱም በርካታ ገበሬዎችና ጥቁር ሠራተኞች ተገድለዋል። 2008 አካባቢ የኤምዲሲ የመብት ተሟጋቾች ጥቃት ደርሶባቸው ነበር የዚምባብዌ የፖለቲካ ሽኩቻ በ2000 ምርጫ የዚምባብዌ ምክር ቤት 57 መቀመጫዎች በኤምዲሲ ፓርቲ ቢወሰዱም፤ የዛኑ ፒ-ኤፍ ፓርቲ ሥልጣን ላይ እንዲቆይ ለማድረግ ሲባል 20 መቀመጫዎችን በቀጥታ ሙጋቤ ሰይመዋል። ከሁለት አመት በኋላ በተደረገ ምርጫ ደግሞ ሙጋቤ 56.2 በመቶ ሲያሸንፉ ተፎካካሪያቸው ሻንጋራይ 41.9 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል። ነገር ግን በርካታ የገጠር አካባቢ ሰዎች እንዳይመርጡ ክልከላ ተደርጎባቸው የነበረ ሲሆን፤ ከምርጫ በኋላም በመላ አገሪቱ ተቃውሞ ተቀጣጥሎ ነበር። ኤኤምሲ ፓርቲን በመደገፍም አሜሪካ፣ እንግሊዝና የአውሮፓ ህብረት ምርጫው ተጭበርብሯል በማለትና ቀጥሎ የመጣውን ሕዝባዊ ተቃዉሞ በመደገፍ ዚምባብዌንና ሙጋቤን ያለደጋፊ ብቻቸውን አስቀርተዋቸዋል። • ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለምን ዘጋች? • ለጉብኝት ክፍት የተደረገው የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት በፎቶ የጋራ ብልጽግና መድረክ ዚምባብዌ የዴሞክራሲ መሻሻል እስከምታሳይ በማለት ከማንኛውም ጉባዔ አግዷት ነበር። ጥቁር ገበያን ለመቆጣጠር በሚል በ2005 የተደረገው ንቅናቄ በአገሪቱ ሕገ ወጥነትን የበለጠ አባብሶታል። 30 ሺህ የሚደርሱ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች ሲታሠሩ፤ በርካታ ትንንሽ ከተሞች ወድመዋል። 700 ሺህ የሚጠጉ ዚምባብዌያውያን ቤት አልባም ሆነዋል። 2008 ላይ ሙጋቤ ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ የመጀመሪያው ዙር ላይ ቢረቱም፤ በመጨረሻ ተስቫንጊራይ ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ ሥልጣን ይዘዋል። በተስቫንጊራይ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ከመሰንዘሩ አስቀድሞ ተስቫንጊራይ በዚምባብዌ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ ማድረግ አይታሰብም ብለው ነበር። ከዛ በኋላ ዚምባብዌ በኑሮ ውድነት ትናጥ፣ ምጣኔ ሀብቷም ያሽቆለቁል ጀመር። መንግሥት የውሀ ማከሚያ ከውጪ ለማስገባት አቅም ስላልነበረው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኮሌራ ምክንያት ለሞት መዳረጋቸውን ተከትሎ፤ ሙጋቤ ከተቀናቃኛቸው ጋር ሥልጣን ለመጋራት ፍቃደኛነት አሳይተዋል። ለወራት ከዘለቀ ድርድር በኋላ 2009 ላይ ሙጋቤ ተስቫንጊራይን ጠቅላይ ሚንስትር አድርገው ሾሟቸው። ሆኖም የመብት ተሟጋቾች ሙጋቤ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ያሰቃያሉ ሲሉ ይከሷቸዋል። ሮበርት ሙጋቤ ገደብ የለሽ ሥልጣን የታየበት ምርጫ ወቅቱ በዚምባብዌ ገደብ የለሽ ሥልጣን የታየበትና የ89 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋው ሙጋቤ በተወዳዳሪነት የቀረቡበት ነበር። ሆኖም ሙጋቤ እድሜያቸው እየገፋ ሲመጣ ለተለያዩ የጤና ችግሮች መጋለጣቸው አልቀረም። በወቅቱ ማን ሊተካቸው ይችላል? የሚል ስጋትም ነበር። ሁኔታው የሙጋቤ አስተዳደር ሕዝቡ ላይ ጫና እንዳሳደረ አሳይቷል። የዚምባብዌ አስተዳደር ምን ያህል የተከፋፈለ እንደሆነ የሚያሳዩ ነገሮች ቀስ በቀስ መገለጥም ጀምረዋል። በወቅቱ ሙጋቤ ምንም ተቀናቃኝ እንዳይገጥማቸው፤ ተከታዮቻቸው እርስ በርሳቸው እንዲጠላለፉ ሆነ ብለው ፖለቲካዊ ጨዋታ ይጫወቱ ነበር ተብሏል። ሙጋቤ ቢሞቱ እንኳን ባለቤታቸው ግሬስ እሳቸውን በመተካት ሥልጣን እንደሚይዙ ወሬዎችም ይናፈሱ ነበር። • "የሞራል ባቢሎን ውስጥ ነው ያለነው፤ በጎና እኩይ መለየት አቅቶናል" ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ • የስድስት ቀን ጨቅላ በቦርሳዋ ይዛ የተገኘችው ሴት ተከሰሰች እሳቸውም የዋዛ አልነበሩም 2015 ላይ በ2018 በሚደረገው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ። 2016 ላይም ፈጣሪ ወደ ማይቀርበት ሞት እስከሚጠራቸው ድረስ ሥልጣን ላይ እንደሚቆዩ ተናገሩ። ታዲያ ያኔ ሙጋቤ ቢመረጡ ኖሮ የ94 ዓመት አዛውንት ፕሬዚደንት ይሆኑ ነበር። የሆነው ሆኖ ከፈጣሪ የተላከ ሞት ሳይሆን የዚምባብዌ ብሔራዊ ጦር ወደ ሮበርት ሙጋቤ ገሰገሰ። ሕዳር 15፣ 2017 ላይ በቁጥጥር ሥር ውለው ለአራት ቀናት በቁም እስር ከቆዩ በኋላ የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የዛኑ ፒ-ኤፍ መሪ ሆነው ሙጋቤን ተኩ። ሙጋቤ 'ሥልጣኔን ምን ሲሆን እለቃለሁ?' ብለው ቢያንገራግሩም፤ ከስድስት ቀናት በኋላ የዚምባብዌ ፓርላማ ሮበርት ሙጋቤ ከሥልጣናቸው መነሳታቸውን አበሰሩ። ሙጋቤ ሥልጣናቸውን የለቀቁት እሳቸውም ሆነ ቤተሰባቸው ወደፊት ከሚደርስባቸው ማንኛውም ችግር እንዲጠበቁና በሚፈልጉት የንግድ ዘርፍ ለመሰማራት እንዲችሉ ከተደራደሩ በኋላ ነበር። ቤት፣ ሠራተኞች፣ ተሽከርካሪዎች እና ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ሥልጣንም ተሰጥቷቸዋል። ሙጋቤ በግል ሕይወታቸው ሙጋቤ በአለባበሳቸው 'ወግ አጥባቂ' የሚባሉ ነበሩ። የአልኮል መጠጦችን የማይቀምሱ፤ ወዳጆቻቸውንና ጠላቶቻቸውን ለይተው የሚያውቁ ነበሩ ይባላል። አፍሪካን ከቅኝ አገዛዝ ለማውጣት ሲታገሉ 'የአፍሪካ ጀግና' ተደርገው የሚወሱት ሮበርት ሙጋቤ፤ ወደ ጨቋኝ መሪነት በመለወጣቸው ይተቻሉ። አገሪቷንም ወደ ባሰ ድህነት እንዳሸጋገሯትም ይነገራል። ራዕያቸው ግን በዚምባብዌ ታሪክ ሲዘከር ይኖራል። በሙጋቤ ሕይወት ወሳኝ የሚባሉ ዓመታት- እንደ ጎርጎሳውያን አቆጣጠር 1924፡ የተወለዱበት ዓመት 1964፡ በሮዲዥያ መንግሥት የታሠሩበት 1980፡ ከነጻነት በኋላ ያለውን ምርጫ አሸነፉ 1996፡ ግሬስ ማሩፉን አገቡ 2000፡ በሕዝበ ውሳኔ ተሸነፉ። በዚህ ምክንያት ደጋፊ ሚሊሻዎቻቸው በነጭ የተያዘውን እርሻ ቀምተው፤ በተቃዋሚ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት አደረሱ። 2008፡ በመጀመሪያ ዙር ምርጫ ከሻንጋራይ ቀጥሎ ሁለተኛ ሆኑ። ቢሆንም በደጋፊዎቻቸው ላይ በመላ አገሪቱ በደረሰ ጥቃት ሻንጋራይ ምርጫውን አቋረጡ። 2009፡ የአገሪቱ ምጣኔ ሃብት መዳከሙን ተከትሎ ሻንጋራይን ጠቅላይ ሚንስትር አድርገው ሾሙ። 2017፡ ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ እንዲተኳቸው መንገድ ለመጥረግ ሲባል ምክትላቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከሥልጣን አገዱ። ሕዳር 2017፡ ወታደሩ ጣልቃ በመግባት ከሥልጣን አወረዳቸው
news-55191616
https://www.bbc.com/amharic/news-55191616
የትራምፕ የጉዞ ገደብ: "በመጨረሻም ልጆቼን ላያቸው ነው"
በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ዘመን አወዛጋቢ ከሚባሉ ውሳኔዎች መካከል ለአሜሪካ የደኅንነት ስጋት በሚል ከተወሰኑ አገራት የሚመጡ ሰዎችን ጉዞ ማገድ ነው።
በበርካቶች ዘንድ ቢወገዝም አሻፈረኝ ያሉትን የዶናልድ ትራምፕን መንበር በቅርቡ የሚረከቡት ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የመጀመሪያ የሚቀለብሱት ፖሊሲም እንደሆነ ቃል ገብተዋል። 13 አገራት ላይ ተግባራዊ የሆነው የጉዞ እግድ በተደጋጋሚ የፍርድ ሙግቶች ቢቀርቡበትም እስካሁን ዘልቋል። ለአንዳንድ ቤተሰቦች ደግሞ የዓመታት መለያየት መከራን ሰንቋል። 'የልጄ አምስተኛ ዓመት ልደት ትናንት ተከበረ። ሙሉ ህይወቱን ተለያይተን ነው የኖርነው" አፈቃብና ባለቤቱ አፈቃብ ሁሴን ሶማሊያዊ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ነው። ለዓመታትም ከልጁም ሆነ ከባለቤቱ ጋር ተለያይቶ ነው ኑሮውን እየገፋ ያለው። ወደ አሜሪካ፣ ኦሃዮ በጎሮጎሳውያኑ 2015 ሲመጣ፣ በቀጣዩ ዓመት ነፍሰ ጡር ባለቤቱ ወደ አሜሪካ እንደምትመጣ አቅደው ነበር። ባለቤቱና ልጆቹ ነዋሪነታቸው በኬንያ ቢሆንም ዜግነታቸው ግን ሶማሊያዊ ነው። የጉዞ እግዱ መጀመሪያ ከተጣለባቸው አገራት መካከል ሶማሊያ የመጀመሪያዋ አገር ናት። አሜሪካ ከመጣም በኋላ ቤተሰቡን ለማየት የተወሰኑ ጉዞዎች ቢያደርግም መቆየት የቻለው ለአጫጭር ጊዜያት ብቻ ነው። ይባስ ብሎም ሁለቱ ህፃናት ልጆቹ ሲወለዱም ከባለቤቱ ጎን አልነበረም። "የባለፉት ዓመታት በህይወቴ ፈታኝ የምለው ጊዜ ነው የገጠመኝ። በጣም ፈታኝ ነው" የሚለው አፈቃብ "መቼም ቢሆን ያለፉትን አራት ዓመታት አልረሳቸውም" ይላል። ከባድ መኪና ማሽከርከር እንዲህ ቀላል አይደለም፣ ረዥም ሰዓት መስራትና ብቻ መሆንን ይጠይቃል። በ40 የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥም ነው የሚያሽከረክረው። ባለቤቱን በቻለው መጠን በስልክ ያዋራታል ሆኖም በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የስምንት ሰዓታት ልዩነት ፈታኝ አድርጎታል። እሱ ከሥራው እፎይታ አግኝቶ ሰላም ለማለት ቢደውልም አብዛኛው ጊዜውን ተኝተው ነው የሚያገኛቸው። በልጆቹ ህይወት ውስጥ ወሳኝ የሚባሉ ምዕራፎች አምልጠውታል "ትናንትና የአንደኛው ልጄ አምስተኛ ዓመት የልደት ቀን ነበር፤ እናም አብሬው አልነበርኩም" በማለት በሐዘን በተሰበረ ልቡ ይናገራል። አፈቃብ ፈታኝ የሚባሉ ጊዜዎችን ቢያሳልፍም ጆ ባይደን በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ስልጣን በያዙ በመቶ ቀናት ውስጥ ገደቡን አነሳዋለሁ በማለት ቃል መግባታቸውን ተከትሎ መጪውን በተስፋ እንዲያይ አድርጎታል። በካሊፎርኒያ የቪዛ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጠበቃ የሆነው አሊ ቦሉር ገደቡ እንደሚነሳና የተለያዩ ቤተሰቦችም እንደገና እንደሚገናኙ ተስፋ ቢኖረውም፤ ከጉዞ እግዱም በፊት ቢሆን እንደ አፈቃብ ያሉ ሙስሊም ወጣቶችን የአሜሪካ የቪዛ ሥርዓት መድልዎ ይፈፅማባቸዋል ይላል። የአፈቃብ ባለቤትና ልጆቹ "ከትራምፕ በፊትም በባራክ ኦባማ ዘመን ይህ ሁኔታ ከፍተኛ ችግር ነበር" ይላል አሊ። "ዋናውን ይቅርና በአሜሪካ ያሉ ስደተኞች፣ የስደተኞች ተብሎ የሚጠራውን ቪዛ ለማግኘት ወደ ቆንስላው የሚያመሩ ግለሰቦች እንኳን ሙስሊም መሆናቸው ከታወቀ የኋላ ታሪካቸው መጠናት አለበት በሚል ዓመታትን ይወስዳል። በተለይም ወንዶችና የሆነ እድሜ መካከል ካሉና የመጡትም እነሱ ከማይቀበሏቸው አገራት ከሆኑ ችግሩ የበለጠ ይወሳሰባል" ይላል። "ዶናልድ ትራምፕ ያደረገው ነገር ቢኖር ከዚህ ቀደም የኦባማም ሆነ ሌሎች መንግሥታት ሲከተሉት የነበረውን ጉዳይ በማጠናከር የጉዞ እግድ በማለት በፖሊሲ ደረጃ ማውጣቱ ነው" በማለት ያስረዳል። አንዳንዶች የጉዞ እገዳው ሽብርን በመዋጋት ደረጃ አመርቂ ውጤት አምጥቷል ቢሉም ለተለያዩ ቤተሰቦች ግን የማያቋርጥ ቅዠት ሆኖባቸዋል። "እናቴ አጠገቤ እንደማትሆንና- እንዲህ አይነት ነገር እንደሚፈጠር ባውቅ ኖሮ ልጅ አልወልድም ነበር" ሚና ማህዳቪ ከልጇ ጋር ሚና ማህዳቪ፣ ከካምፕቤል ካሊፎርኒያ ብትሆንም ኢራናዊ እናቷ ወደ አሜሪካ መምጣት አልቻሉም። የልጅ ልጃቸውንም ለማየትና 'እንኳን አይንሽን በአይንሽ አሳየሽ' ለማለትም አልታደሉም። የመጀመሪያ ልጇን ነፍሰጡር በነበረችበት በ2016 ሚና ለእናቷ በቱሪስት ቪዛ ከኢራን እንዲመጡ አመለከተች። ልጇን ለመውለድም ሆነ እንዲያርሷትም ስለፈለገች የእናቷን ድጋፍ አጥብቃም ትሻ ነበር። ቪዛውን ባመለከተች በአንድ ወርም ውስጥ ፕሬዚዳንት ትራምፕ አብዛኛው ሙስሊም የሕዝብ ቁጥር ያላቸው አምስት አገራት ላይ በፍፁማዊ ትዕዛዝ ገደብ ጣሉ። ከእነዚህም አገራት መካከል አንዷ ኢራን ናት። "ዜናውን ልክ ስንሰማ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ጆሯችንን ማመን አልቻልንም። ኧረ በጭራሽ አይሆንም፤ አይፈጠርምም አልን። እኔ በአሜሪካ ሕጋዊ ዜጋ ነኝ እሷም የምትመጣው በቱሪስት ቪዛ ነው ብዬ ተረጋጋሁ።" ነገር ግን እንዳሰበችው አልሆነም የቪዛ ሂደቱ እየተጓተተ መጣ ልጇም ተወለደ፣ "በጣም ከባድ ወቅት ነው" ትላለች። ምንም እንኳን የቪዛው ሂደት የተጀመረው እግዱ ከመታወጁ ቀድሞ ቢሆንም መልስ ለመስጠት አንድ ዓመት ወስዷል። ከዚያም በኋላም ጥያቄያቸው ውድቅ ተደርጎ አሜሪካ መግባት እንደማይችሉ ተነገራቸው። አሁን ልጇ ሦስት ዓመት ተኩል ሆኖታል እስካሁንም ድረስ እናቷ መምጣት አልቻሉም። ልጇን ያለ እናቷ ማሳደጓ ከፍተኛ የሆነ የብቸኝነት ስሜት፣ ጭንቀትና ድብርትም ውስጥ ከቷታል። "ልጄን በመውለዴ ደስተኛ ነኝ። ነገር ግን እውነቱን ንገሪኝ ካላችሁኝ እናቴ እንደማትመጣ ባውቅ ኖሮ ልጅ በጭራሽ አልወልድም ነበር" ትላለች። አላስችልም ብሏት አጠር ላለ ቆይታ ወደ ኢራንም ሄዳ ነበር። ከካሊፎርኒያ ኢራን ድረስ ያለው ርቀት ከመርዘሙ ጋር ተያይዞ በረዥሙ በረራ ወቅት ልጇ እንዳለቀሰና እንደተነጫነጨ ነበር የደረሰው። እናቷ አሜሪካ መጥተው ከእሷም ጋር ቢቆዩ ምን ያህል ደስታ እንደሚሰማት ብታውቅም "ያንን ድጋፍ እንደማላገኘው ራሴን ማሳመን አለብኝ፤ ወላጆቼ እንደፈለግኩት ሊመጡና ሊመለሱ አይችሉም" በማለትም ታስረዳለች። ምንም እንኳን የጉዞ እግዱ በተዘረዘሩት አገራት ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎች ቢሆንም አንዳንዶች ግን ውሳኔው የሚቀለበስበትን መብታቸውን ማስከበር ችለዋል። የሚና እናት ግን ውሳኔው የሚቀለበስበት ቦታም አልተሰጣቸውም። በካውንስል ፎር አሜሪካን ኢስላሚክ ሪሌሽንስ በተባለው ድርጅት የስደተኞች መብት ጠበቃ ብሪትኒ ሬዛይ እንደሚሉት ለደንበኞቻው ውሳኔውን ማስቀልበስ ከፍተኛ ፈተና ሆኖባቸዋል። "መንግሥት በየትኞቹ ሁኔታ ነው ውሳኔ መቀልበስ የሚቻለው የሚለው ላይ ግልፅ ያለ መመሪያ አላወጣም። እናም እኛም ለደንበኞቻችን ሂደቱንንና መመሪያውን በተመለከተ ማስረዳት አልቻልንም" ይላሉ። ሚና እናቷ አሜሪካ እንዲመጡ ያልፈነቀለችው ድንጋይ የለም። ቢጨንቃት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ጉዳዩን ወስዳው ነበር ነገር ግን እግዱ እስከ 2025 ሊቆይ እንደሚችል አረዷት። "ልጄ ስምንት ዓመት እስኪሆነው አያቱን በቃ ላያይ ነው? እያልኩ በጣም እያዘንኩ ነበር" የምትለው ሚና የባይደንን መምጣት ተከትሎም እናቷ አሜሪካ መጥተው የልጅ ልጃቸውን በየቀኑ የማቀፍ እድል ይኖራቸዋል የሚልም ብሩህ ተስፋን ሰንቃለች። 'ልጄከባህሉ በፍፁም ተነጥሏል' ጉልናራ ኒያዝና ልጇ ከአራት አመታት በፊት ጉልናራ ኒያዝ በቦስተን ተቀማጭነቷን ያደረገች የፎቶ ባለሙያ ናት። ልጇ ስር መሰረቱንና ባህሉን እንዲረዳ ቤተሰቦቿ አጠገቧ መኖር ነበረባቸው ትላለች። የጉልናራ ቤተሰቦች ትውልዳቸውም ሆነ መኖሪያቸው በማዕከላዊዋ እስያ ኪርጊስታን ነው። ኪርጊስታን ከጉዞ ገደቡ ዝርዝር የተካተተችው ባለፈው ዓመት ጥር ወር ነበር። የጉዞ ገደቡ በከፍኛ ሁኔታ ያበሳጫት ጉልናራ ልጇ ከወላጆቿ ባህሉንና አመጣጡን እንዳይማርም ደንቃራ ሆኖበታል ትላለች። "ከባህላችን ፍፁም ተነጥሏል። ገና ታዳጊ በነበረበት 12 ወይም 13 ዓመት እድሜ ላይ እያለ ማማ እንደ አንቺ አይነት አስተዳደግ ያለው እናት እንዴት ከባድ እንደሆነ አትረጂም። አንቺ እኮ ትለያለሽ እንደ ሌሎቹ አይነት እናት አይደለሽም ይለኝ ነበር" ትላለች ጉልናራ። ጉልናራ ተወልዳ ያደገችው በገጠራዋማ ኪርጊስታን ሲሆን ያደገችበትም ማኅበረሰብ አንድ ቦታ ሰፍሮ የመኖር ሳይሆን ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚኖሩ ናቸው። ከአስተዳደጓም ጋር ሆነ ከባህሏ ጋር ፅኑ ቁርኝት ያላት ጉልናራ በቦስተንም ይህንኑ የሙጥኝ ብላ ይዛለች። በተለይም ምግብ ላይ ሲመጣ አትደራደርም። የራሷን ሽንኩርት ስታበቅል ሲያይ ልጇ ይደንቀዋል። "ስለ ባህላችን ቢማር በጣም ጥሩ ነው። ወይ የሩሲያ ቋንቋን ወይም የአፍ መፍቻ ቋንቋችን የሆነውን ኪርጊዝን ቢማር ጥሩ ነው" በማለት ትናገራለች። ቤተሰቦቿ ወደ አሜሪካ ቢመጡና ለተወሰኑ ወራትም አብረዋቸው ቢቆዩ ከማንነቱና ከባህሉ ጋር ቁርኝት እንዲፈጥር ያረጉት ነበር ነገር ግን የጉዞ ገደቡ ኑሯቸውን ትግል አድርጎባቸዋል። አንዳንድ ነጥቦች ስለ ትራምፕ የጉዞ ገደብ፦
news-51297716
https://www.bbc.com/amharic/news-51297716
የአድዋ ድልና ዘንድሮ ለ80ኛ ጊዜ የሚከበረው የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር ምና ምን ናቸው?
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢዎች ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክዋኔዎች ቀዳሚ ሚና የሚጫወተው ፈረስ ነው።
ፈረስ እርሻ በማረስ የነዋሪዎችን ገቢ ያሳድጋል፣ በአካባቢው እንግዳ ከመጣ የሚታጀበው በፈረስ ነው፣ ዓመታዊ ኃይማኖታዊና ዓለማዊ በዓላት የሚደምቁት በፈረስ ነው፣ ሠርግና ለቅሶ በአዊ ያለፈረስ የማይከወኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ናቸው። • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን በየዓመቱ ጥር 23 የሚከበረው "የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር" ደግሞ የአዊ ብሔረሰብና ፈረስ ያላቸውን ዘመን ያስቆጠረ ቁርኝት የሚያንጸባርቅ ኩነት ነው። ማኅበሩ ታዲያ እንዲሁ "በማኅበር እናቋቁም" ምክክር የተመሰረተ አይደለም። ታሪካዊ ጅማሮውን 120 ዓመታትን ወደኋላ ተጉዞ ከአድዋ ጦርነት ይመዝዛል። አለቃ ጥላዬ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት በ1888 ዓ.ም በተደረገው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ወደ አድዋ የተጓዙትም የተዋጉትም በፈረስ ነው። በሁለተኛው የጣሊያን ወረራም ወቅትም ፈረስ ተመሳሳይ የአርበኝነት ተጋድሎ ውስጥ ተሳትፎ፤ ከአምስት ዓመታት ፍልሚያ በኋላ ጣሊያንን ድል መንሳት ተችሏል። በዚህ ሂደት ታዲያ ፈረስ በብዛት ለጦርነቱ ከተሳተፈባቸው ስፍራዎች መካከል የአዊ አካባቢዎች አንዱ ነበር። ይህ በመሆኑም "የፈረስና የአርበኛ ውለታው ምን ይሁን" የሚል ሃሳብ ተነስቶ የአካባቢው አረጋዊያን ምክክር አድርገው "በአድዋ፤ በኋላ በነበረውም የአምስት ዓመት የአርበኝነት ዘመን አጥንታቸውን ለከሰከሱት አርበኞችና ፈረሶች እንዲሁም በድል ለተመለሱት መታሰቢያ ለማድረግ ሲባል ማኅበሩ በ1932 ዓ.ም በሃሳብ ደረጃ ተጠንስሶ በዓመቱ 1933 ዓ.ም በይፋ ተቋቋመ" ይላሉ አለቃ አሳዬ። የፈረስ ጉግስ በአካባቢው ለዓመታት የተለመደ ቢሆንም በኃይማኖታዊ በዓላት ላይ ወጣቶች ውድድር አድርገው ታዳሚውን ያስደምማሉ፤ በግልቢያ ችሎታቸው ጉልምስናቸውን ያሳያሉ እንጂ በተደራጀ መልኩ የሚደረግ ዓመታዊም ሆነ ወርሃዊ ውድድር እንዳልነበረው አለቃ ጥላዬ ይናገራሉ። የ75 ዓመቱ አዛውንት አለቃ አሳዬ ተሻለ ከታዳጊነት የእድሜ ዘመናቸው ጀምረው አብዛኛውን እድሜያቸውን በአገው ፈረሰኞች ማኅበር ውስጥ አሳልፈዋል። አባታቸው ግራዝማች ተሻለ የማኅበር ምስረታ ሃሳቡን በማመንጨትና ማህበሩን በማቋቋም ረገድ ስማቸው ከሚነሳ ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን ያስታውሳሉ። የአዊ ፈረሰኞች በወቅቱ የአሁኑ አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባንጃና አንከሻ የሚባሉ ሁለት ወረዳዎች ነበሩት። አርበኞች ጣሊያንን ካባረሩ በኋላ የፈረስንና የአርበኞችን ገድልና ውለታ ለመዘከር ከባንጃ ወረዳ 16 ሰው፤ ከአንከሻ ወረዳ 16 ሰው በድምሩ 32 ሰው ሆነው የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማህበርን በ1933 ዓ.ም መመስረቱን ይገልጻሉ። "በጊዜው በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲከበር ተወስኖ የነበረ ሲሆን ሚያዚያ 23 እና ጥቅምት 23 ደግሞ በዓሉ የሚከበርባቸው ቀናት ነበሩ" በማለት አለቃ አሳዬ የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበርን ታሪካዊ ዳራውን ይተነትናሉ። ማኅበሩ በተቋቋመበት ወቅት የፈረስ ጉግስ በማድረግና የቅዱስ ጊዮርጊስን ማሕበር በመጠጣት እንደተጀመረ የሚናገሩት አለቃ አሳዬ፤ ማህበሩን ያቋቋሙትም ከባንጃ ወረዳ አለቃ መኮንን አለሙና ግራዝማች ንጉሤ፤ ከአንከሻ ወረዳ ደግሞ ቀኛዝማች ከበድ ንጉሤና ግራዝማች ተሻለ (የአለቃ አሳዬ አባት) መሆናቸውን ይናገራሉ። በበዓሉ የተመረጡ ሰጋር ፈረሶች በተለያዩ አልባሳት አሸብርቀው ይቀርባሉ። ፈረሶቹ ለበዓሉ ማድመቂያ ብቁ መሆናቸው በአካባቢው ሰዎች ተረጋግጦ የተሻሉት ብቻ ለበዓሉ ይጋበዛሉ። ከሁሉም አካባቢዎች የመጡ ልምድ ያላቸው ጋላቢዎች ደግሞ በጉግስ፣ ሽርጥና በሌሎች የውድድር ዓይነቶች እነዚህን ፈረሶች በመጋለብ፤ በታዳሚው ፊት ልክ በጦርነት ወቅት ፈረሶች እንደነበራቸው ሚና በማስመሰል ትርዒት ያሳያሉ፤ በውድድሩ አሸናፊ የሆኑትም ሽልማት እንደሚበረከትላቸው የማኅበሩ ሊቀመንበር አለቃ ጥላዬ ያስረዳሉ። የአዊ ፈረሰኞች በዓሉ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዓመታት በዓመት ሁለት ጊዜ እየተካሄደ ከቀጠለ በኋላ፤ የማኅበሩ አባላት እየበዙ በመምጣታቸውና በዝግጅቱ ውበትም ብዙ ሰው እየተማረከ በመምጣቱ ሰፋ ባለ ዝግጅት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲከበርና ቀኑም ጥር 23 እንዲሆን ተወስኖ በየዓመቱ በዚሁ ዕለት እየተከበረ እንደሚገኝ አለቃ ጥላዬ ለቢቢሲ በሰጡት መረጃ አረጋግጠዋል። በታሪክ በዓሉ የተከበረባቸው ሦስቱም ቀናት በተለያዩ ወራት ቢሆንም '23' በመሆናቸው ግን ልዩነት የለም። ለዚህ ደግሞ አለቃ ጥላዬ ዋነኛ ምክንያት ብለው የሚያስቀምጡት፤ በአድዋ ጦርነት ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ወደ ቦታው ተጉዞ ነበር ስለሚባል፤ ቀኑ የተመረጠው የቅዱስ ጊዮርጊስን መታሰቢያ ዕለት ምክንያት በማድረግ ነው ይላሉ። በ32 አባላት የተጀመረው የፈረሰኞቹ ማኅበር ዘንድሮ በ80ኛ ዓመቱ የአባላት ብዛቱን 53 ሺህ 2 መቶ 21 ማድረሱን ሊቀ መንበሩ አለቃ ጥላዬ ተናግረዋል። የማኅበሩ አባል ለመሆን ጾታ የማይለይ ሲሆን በእድሜ በኩል ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና በአካባቢው ማሕበረሰብ ዘንድ የተመሰከረላቸውና ምስጉን መሆን ብቻ ብቁ ያደርጋል። ከአባልነት የሚጠየቀው መዋጮም በዓመት 8 ብር ብቻ ነው ይላሉ አባላቱ። የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በዘጠኝ ወረዳዎችና በሦስት ከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረ ነው። ሁሉም ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች "የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር" አባል መሆናቸውን የአዊ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መለሰ አዳል ያስረዳሉ። • ጣልያን በተሸነፈችበት አድዋ ቆንስላዋን ለምን ከፈተች? በዓሉ በእነዚህ ወረዳዎች በየዓመቱ በየተራ ይዘጋጃል የሚሉት አቶ መለሰ ተረኛ የሆነ ወረዳ ለበዓሉ ታዳሚ ባህላዊ ምግቦችንና በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ተሳታፊ የሚቀመጥበትና ተወዳዳሪዎች የሚጋልቡበት የመጫወቻ ሜዳንም ያዘጋጃል ብለዋል። ዛሬ እየተከናወነ ያለው 80ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓልም በተለያዩ የብሔረሰቡ አካባቢዎች ሲካሔድ ቆይቶ የማጠቃለያ ፕሮግራሙ በ2 ሺህ ፈረሶች አማካኝነት በእንጅባራ ከተማ እየተከበረ መሆኑን ኃላፊው አስታውቀዋል። የአካባቢው ሕዝብ በዓሉን በጉጉት ይጠብቀዋል። በበዓሉ የሚታዩ ትርኢቶች ተመልካችን ያስደምማሉ። ፈረስ ጋላቢዎች በሺዎች ለሚቆጠሩ ታዳሚያን ችሎታቸውን ለማሳየት ብቸኛዋ ቀን ጥር 23 ናት። የአዊ ፈረሰኞች አምና በውድድሩ የተሸነፈው ዘንድሮ ለማሸነፍ፣ አሸናፊው ደግሞ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል የሚያደርገው ትንቅንቅ፤ ፈረሶች በኋለኛ ሁለቱ እግሮቻቸው ብቻ ቀጥ ብለው ሲቆሙ ማየት ታዳሚያን በዓሉን እንዲናፍቁ ከሚያደርጉ ትዕይንቶች መካከል አንዱ ነው። አለቃ አሳዬ አባታቸው በመሰረቱት የፈረስ ማኅበር ውስጥ ተወዳዳሪም የማህበሩ የበላይ ጠባቂም በመሆን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ አሳልፈዋል። ዘንድሮም በ75 ዓመት የእድሜ ዘመናቸው፤ 80ኛ የማህበሩን በዓል ለማክበር እንጅባራ ተገኝተዋል። በ1962 ዓ.ም አለቃ አሳዬ መኖሪያቸውን ከአንከሻ ወደ ቻግኒ ቀይረዋል፤ በአዲሱ የመኖሪያ አድራሻቸውም ላለፉት 50 ዓመታት በበዓሉ ግንባር ቀደም ፈረስ ጋላቢ በመሆንና ማኅበሩን በማጠናከር የማይተካ አስተዋጽዖ ሲያበረክቱ ቆይተዋል። እርሳቸው ከሚኖሩበት ቻግኒ ከተማ በዓሉ እስከሚከበርበት እንጅባራ ያለው ርቀት 60 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ነው። ይህንንም ርቀት ፈረሳቸውን ጭነው ባለፉት 50 ዓመታት ሲጓዙት ኖረዋል። ዘንድሮም ዕድሜ ሳይገድባቸው ይህንን 60 ኪሎ ሜትር ርቀት በ4 ሰዓታት በሰጋር ፈረሳቸው ተጉዘው እንጅባራ ተገኝተዋል። "ሚሊዮን ብር ሰጥተው ከፈረስ ማኅበሩ በዓል እንድቀር አማራጭ ቢሰጠኝ ዝግጅቱ ላይ መገኘትን እመርጣለሁ" የሚሉት አንድም ቀን ከበዓሉ ተለይተው የማያውቁት አለቃ አሳዬ ዛሬም ለውድድር ባይሆንም ፈረስን እንዴት በቄንጥ መጋለብ እንደሚቻል በማሳየት ታዳሚን ጉድ ሊያስብሉ ተዘጋጅተዋል። • በአውስትራሊያ ፈረሶች እየታረዱ ነው በሚል ውንጀላ ላይ ምርመራ ተጀመረ በአሁኑ ወቅት የበዓሉ አድማስ ከአካባቢው ማህበረሰብ አልፎ በአገር አቀፍ ደረጃ ቦታ የሚሰጠው ሆኗል። በየዓመቱ በርካታ የአማራ ክልል ባለስልጣናትና ነዋሪዎች በዓሉን ለመታደም ወደ አካባቢው ይተማሉ። ከክልሉ ውጭ የሚገኙ ነዋሪዎችና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበዓሉ ተማርከው ጥር 23ን በአገው ምድር እንጅባራ ማሳለፍን ምርጫቸው እያደረጉ ነው። በዘንድሮው በዓልም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣ የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) እና ሌሎች በርካታ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናትም የበዓሉ ተሳታፊዎች ናቸው።
news-46601907
https://www.bbc.com/amharic/news-46601907
ለፖለቲካ ፍላጎት የተጋጋለ ግጭት ነው፡ ሙስጠፋ ኡመር
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ኡመር የግጭቱን መንስዔ ሲያስረዱ፤ በግጦሽ መሬት ሰበብ ከኃይለስላሴ መንግሥት ጀምሮ በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰቱ እንደነበረ አስታውሰው፤ ''ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ግን ሆነ ተብሎ የፖለቲካ ፍላጎት ተጨምሮበት የተጋጋለ ግጭት ነው'' ይላሉ።
ከጥቂት ዓመታት በፊት ተቀስቅሶ የነበረውን የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ለማዳከም በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች የሶማሌ ፖሊስን አንቀሳቅሰው በኦሮሚያ እና ሶማሌ ደንበር አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድረሰዋል ይላሉ አቶ ሙስጠፋ ኡመር። • ፓርቲዎች የምርጫ ቦርድን በሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከሩ ነው ከዚህ በፊት የነበረው ግጭት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነበረ። በግጭቱ የተጎዱ በሁለቱም በኩል ያሉት ኃይሎች ቁጭት እና ንዴት ስላለባቸው ግጭት እንዲቀጥል እያደረጉ ነው። አሁንም ግጭቱ እንዲቀጥል የሚያደርጉት እነርሱ ናቸው ይላሉ ሙስጠፋ ኡመር። ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር በሚያዋስነው አካባቢ ዋነኛዋ ከተማ በሆነችው ሞያሌ፤ የግጭት፣ የሞት እና የመፈናቀል ዜና መስማት እየተለመደ የመጣ ይመስላል። ነዋሪዎቿም በፍርሃት እና በሽብር መኖር ከጀመሩ ወራትን አስቆጥረዋል። መንግሥት ''በስህተት የተፈጸመ ነው'' ብሎ ከ10 በላይ ንጹሃን ነዋሪዎቿ ህይወታቸውን ያጡባት፤ በከተማዋ የሚኖሩ የኦሮሞ እና ሶማሌ ወጣቶች በሞያሌ ከተማ አስተዳደር ባለቤትነት ጥያቄ በድንጋይ የሚወጋገሩባት፤ ከፍ ሲልም በይዞታ ይገባኛል ምክንያት በጦር መሳሪያ የታገዙ ኃይሎች የሚፋለሙባት ግጭት፣ ሞት እና መፈናቀል የማያጣት ከተማ ሆናለች። እንደ አዲስ ከሁለት ሳምንታት በፊት በተቀሰቀሱ ግጭቶችም በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቆስለዋል፣ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። • "በምን ማስተማመኛ ነው የምንመለሰው" የሞያሌ ተፈናቃዮች ከዓይን እማኞች፣ ከጎሳ መሪዎች እና ከአካባቢው ባለስልጣናት እንደሰማነው ከሆነ ቢያንስ እንደ አዲስ ባገረሹት ግጭቶች እስካሁን ከ20 ሰዎች በላይ ተገድለዋል። የሰሞኑ ግጭት የተቀሰቀሰው ኦሮሚኛ ቋንቋ ተናገሪ በሆኑት ገሪ ተብለው በሚታወቁት የሶማሌ ጎሳ አባላትና በኦሮሞዎች መካከል በይዞታ ይገባኛል ምክንያት ነው። በኦሮሞ በኩል ያሉት የሞያሌ ወረዳ ኃላፊዎች ድንበር ተሻግረው በከባድ መሳሪያ ህዝቡ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙት የሶማሌ ታጣቂዎች ናቸው ይላሉ። በሶማሌ ወገን ያሉት በበኩላቸው ለግጭቱ፣ ለሞትና መፈናቀሉ የኦሮሞ ታጣቂዎች ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ኡመር የግጭቱን መንስዔ ሲያስረዱ፤ በግጦሽ መሬት ሰበብ ከኃይለስላሴ መንግሥት ጀምሮ በተደጋጋሚ ግጭቶች ይከሰቱ እንደነበረ አስታውሰው፤ ''ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ግን ሆነ ተብሎ የፖለቲካ ፍላጎት ተጨምሮበት የተጋጋለ ግጭት ነው'' ይላሉ። • በሞያሌ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ የሰው ህይወት ጠፋ ከጥቂት ዓመታት በፊት ተቀስቅሶ የነበረውን የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ለማዳከም በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች የሶማሌ ፖሊስን አንቀሳቅሰው በኦሮሚያ እና ሶማሌ ደንበር አዋሳኝ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድረሰዋል ይላሉ አቶ ሙስጠፋ ኡመር። ከዚህ በፊት የነበረው ግጭት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነበረ። በግጭቱ የተጎዱ በሁለቱም በኩል ያሉት ኃይሎች ቁጭት እና ንዴት ስላለባቸው ግጭት እንዲቀጥል እያደረጉ ነው። አሁንም ግጭቱ እንዲቀጥል የሚያደርጉት እነርሱ ናቸው ይላሉ ሙስጠፋ ኡመር። ''ሞያሌን እንደ ሞቃዲሾ'' አቶ አሊ ጠቼ የሞያሌ ወረዳ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ ናቸው። አቶ አሊ ሞያሌ ከተማ ከዘርፈ ብዙ ችግሮቿ ጋር ብዙ ዓመት ተሻግራለች ይላሉ። አቶ አሊ ከሳምንታት በፊት ለተቀሰቀሰው ግጭት ጽንፈኛውን ቡድንን አልሸባብን ጭምረው ተጠያቂ ያደርጋሉ። ''አልሸባብ እንዲሁም ከሶማሌ ልዩ ፖሊስ እና ከሃገር መከላከያ ያፈነገጠ ኃይል ከባድ የጦር መሳሪያ በመጠቀም ሞያሌን እንደ ሞቃዲሾ አደረጓት'' ይላሉ። • በርካታ ሰዎች ከሞያሌ በመሸሽ ወደ ኬንያ ገብተዋል ጉዳዩን ለክልል እና ፌደራል መንግሥት ቢያሳውቁም በቂ ምላሽ አለማግኘታቸውን እና በሞያሌ ሰፍሮ የሚገኘውም የሃገር መከላከያ ሠራዊት ግጭቱን ማስቆም እንዳልቻለም ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከአምስት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ግጭቱ እንዲከሰት የሚያደርጉት የሁለቱን ክልሎች መረጋጋት የማይሹ ኃይሎች ናቸው፤ ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብሏል። መግለጫው አክሎም በግጭቱ ለተጎዱ ሰዎች አስፈላጊው እርዳታ እየተሰጠ መሆኑን አመልክቷል። ''የፖለቲካ ጦርነት'' የሶማሌ ገሪ ጎሳ መሪ የሆኑት ሱልጣን ሞሐመድ ሃሰን በበኩላቸው ''ሁለቱ ህዝቦች [ገሪ እና ኦሮሞ] ከዚህ ቀደምም በይዞታ ይገባኛል ይጋጩ ነበረ። ይህ አዲስ አይደለም። ይህ ግጭት ግን የይዞታ ይገባኛል ሳይሆን የፖለቲካ ጦርነት ነው'' ይላሉ። ሱልጣን ሞሐመድ እየደረሰ ላለው ጥፋት የኦሮሞ ታጣቂዎችን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ''ድንበር ተሻግረው እየወጉን ያሉት እነሱ [የቦረና ኦሮሞ] ናቸው። እኛ እራሳችንን መከላከል ነው የያዝነው። መብታችንን እየተጋፉ ነው። በትልልቅ ጦር መሳሪያዎች የሚወጉን፣ ቤታችንን የሚያቃጥሉት እነሱ ናቸው።'' ይላሉ። • የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች ሱልጣን ሞሐመድ እንደሚሉት ከሆነ፤ የፌደራል እና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት ግጭቱን በውይይት ለመፍታት ሞያሌ ላይ ስብሰባ ቢጠሩንም በስብሰባው ላይ የኦሮሞ ተወካዮች በእምቢተኝነት ሳይገኙ ቀርተዋል ይላሉ። ''ምንም እንኳ እነሱ ስበሰባው ላይ ባይገኙም፤ እኛ ሰላም ነው የምንፈልገው ስንል ተናግረናል። ከዚያ በኋላም አዲስ አበባ ላይ ለስብሰባ ተጠርተን አባ ገዳው [የቦረና አባ ገዳ] ሳይገኝ ቀረ። የመጡትም ተወካዮች [የኦሮሞ ተወካዮች] ሰላም አንቀበልም ብለው ሄዱ'' ይላሉ። የቦረና አባ ገዳ ምን ይላሉ? ''የቦረና መሬትን የሸጠው መንግሥት ነው። የግጭቱ መንስዔ መንግሥት ነው። ችግሩን መፍታት ያለበትም መንግሥት ነው'' የሚሉት የቦረና አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ናቸው። ''ሞያሌ ውስጥ ሁለት ባንዲራዎች [የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል ባንዲራዎች] እስከተውለበለቡ ድረስ በከተማዋ ሰላም ሊሰፍን አይችልም።'' አባ ገዳ ኩራ፤ ሶማሌዎች ዳዋ የሚባል ወረዳ መስርተው ሞያሌን የወረዳው ከተማ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት ማቆም አለባቸው ይላሉ። "በ1997 ዓ.ም ላይ ተካሂዶ የነበረው ህዝበ ውሳኔ ሳይሆን የመሬት ዘረፋ ነበረ" የሚሉት አባ ገዳ ኩራ መንግሥት ታሪክ ተመልክቶ ውሳኔዎችን ያስተላልፍ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በግጭቱ በመኖሪያ ቤቶች፣ በመንግሥት ቢሮዎች እና ባንኮችን ጨምሮ በንግድ ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱንም የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
news-53634447
https://www.bbc.com/amharic/news-53634447
ኢኮኖሚ፡ የብር የምንዛሪ ዋጋ በገበያ መወሰኑ ምን ይዞ ይመጣል?
ብሔራዊ ባንክ የብር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የብር ዋጋ በገበያ ተመን እንዲወሰን ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብርን ወደ ፍሎቲንግ ካረንሲ ሥርዓት (የገንዘብን ተመን በገበያ ዋጋ ላይ መመስረት) እንደምትሸጋገር ተገልጿል።
ለመሆኑ ፍሎቲንግ ካረንሲ ምንድነው? ኢትዮጵያ ፊቷን ወደዚህ ሥርዓት ማዞሯ ምን ያስከትላል? በንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ላይ የሚያሳድረሰው ተጽዕኖ ምንድነው? በተራው ዜጋ ህይወት ላይስ ምን አንድምታ አለው? ለእኒዚህ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡን የምጣኔ ሃብት ባለሙያ የሆኑቱን እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) እና አቶ ዋሲሁን በላይን ጠይቀናል። የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቶች የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ የተለያዩ አይነት የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቶች እንዳሉ ይጠቅሳሉ። የገንዘብን ዋጋ በገበያ መሠረት መተመን (Floating Exchange Rate)፣ የገንዘብ ዋጋ መጠን በማዕካለዊ ባንክ የሚወሰንበት (Fixed Exchange Rate) እና ማዕከላዊ ብንኩ እንደ አስፈላጊነቱ ጣልቃ የሚገባበት (Managed Floating Exchange Rate) ይጠቀሳሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ሁሉም አይነት የውጪ ምንዛሪ ሥርዓቶች የራሳቸው የሆነ አውንታዊና አሉታዊ ውጤቶች እንዳላቸው ይስማማሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ፤ አገራት የተወሰነ የውጪ ምንዛሪ ሥርዓትን ስለመረጡ ብቻ ውጤታማ ይሆናሉ ማለት አይደለም ይላሉ። እንደምሳሌም ሳዑዲ አረቢያ ምንዛሪው በማእከላዊ ባንክ የሚወሰን የተመን ሥርዓትን እየተከተለች ውጤታማ መሆኗን በማስታወስ፤ "ዋናው ቁምነገሩ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቱን በነጻ ገበያ ወይም በመንግሥት የሚወሰን አይደለም። የአገር ውስጥ ምርታማነትን በማሳደግ ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ማሳደግ ነው" ይላሉ። በገበያ ከሚወሰነው ምንዛሪ ኢትዮጵያ ምን ታተርፋለች? ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። አቶ ዋሲሁን የብር የመግዛት አቅም ሲቀንስ ኢትዮጵያ የምታመርታው ምርት ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ርካሽ ይሆናል ይህም የአገር ውስጥ አምራቾችን ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል ይላሉ። "ለምሳሌ 1 የአሜሪካ ዶላር 25 ብር ነው ብለን እናስብ። አንድ አሜሪካዊ 1 ዶላር ይዞ ቢመጣ፤ 25 ብር ዋጋ ያለውን እቃ በ1 ዶላር ይገዛናል። የብር የመግዛት አቅምን በቀነስን ቁጥር ከውጪ የሚመጣ ሰው በርካሽ ዋጋ እንዲገዛን እያደረግን ነው። የዚህ እሳቤ ምንድነው ብዙ ምርት ለገበያ ባቀረብን ቁጥር ብዙ ዶላር እናገኛለን ማለት ነው።" አቶ ዋሲሁን በሌላ በኩል ደግሞ የዚህን ተገላቢጦሽ እንመልከት ይላሉ። "የ1 ዶላር ወደ 33 ከፍ ተደረገ ብለን እናስብ። አሁን የ1 ዶላር እቃ ለመግዛት 33 ብር መያዝ ያስፈልገናል። በፊት ግን 25 ብር ነበር የሚያስፈልገው" ብለዋል። በዚህም ይህ የሚያሳየን ብር ከዶላር ጋር ያለውን ልዩነት በሰፋ ቁጥር ኢትዮጵያዊ እቃ ከውጪ ለመግዛት ይወደድበታል። የአገር ውስጥ ምርትን ግን ውጪ ለመሸጥ ተወዳዳሪ ይሆናል። ይህ ማለት የአገራችን የውጪ ምንዛሪ ክምችት ያድጋል፤ ምርትና ምርታማነት ይጨምርልናል ሲሉ ሊኖረው የሚችለውን ውጤት ይናገራሉ። ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላል በአሁኑ ጊዜ ብር ከሚገባው በላይ ዋጋ እንደተሰጠው የሚናገሩት እዮብ (ዶ/ር)፤ የብር የዋጋ በገበያው መሠረት ሲተመን ከውጪ አገራት ገንዘብ ጋር የሚኖረው ልዩነት እንደሚሰፋ ይገልጻሉ። ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ዶላር ዛሬ ላይ በባንኮች 35 ብር የሚመነዘር ከሆነ፤ በትክክለኛው የገበያ ዋጋ ይተመን ቢባል አንድ ዶላር እስከ 45 ብር ድረስ ሊመነዘር ይችላል። "በዚህም ወደ በገበያ ዋጋ በሚወሰን የምንዛሪ ተመን ስንሸጋገር የብር ዋጋ በከፍተኛ ዋጋ ሊያሽቆለቁል ይችላል፤ ይህም የዋጋ ግሽበትን ይከሰታል። ሌሎች እክሎችም ሊከሰቱ ይችላሉ" ይላሉ እዮብ (ዶ/ር)። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደዚህ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓት ሽግግር ሲደረግ ከሚያጋጥሙ አሉታዊ ተጽዕኖዎች መካከል ዋነኛው የዋጋ ግሽበት ሊሆን ይችላል ይላሉ። "ለምሳሌ ከሰሞኑ መንግሥት የ1 ዶላር ምንዛሬን ከ32 ወደ 35 ብር ከፍ ብሏል። ይህ ከ5 እና 6 ወራት በኋላ እስከ 24 በመቶ ድረስ በእቃዎች ላይ ጭማሪ ያመጣል" ሲሉ ይናገራሉ። አለማየሁ (ዶ/ር) በሱዳን የተከሰተውን እንደምሳሌ ያነሳሉ። 1 የአሜሪካ ዶላር 29 የሱዳን ፓወንድ ሳለ ሱዳን የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቷን በገበያ ወደ ሚወሰነው አሰራር መቀየሯን ያስታወሳሉ። "በዚህም ሱዳን ውስጥ የ1 ዶላር ምንዛሪ 48 የሱዳን ፓወንድ ገባ። በሕገ-ወጡ ገበያ ደግሞ 1 ዶላር 58 የሱዳን ፓወንድ ደረሰ። በዚህን ጊዜ ሰዎች በሱዳን ፓወንድ ላይ እምነት አጡ" በዚህም ሁሉም ሰው ወደ ኤቲኤም በመሄድ ገንዘብ ማውጣት ላይ ተረባረበ፤ ባንኮች ደግሞ የሚከፍሉት ማጣታቸውን አለማየሁ (ዶ/ር) ይናገራሉ። "ከዚያም ችግሩ ተባብሶ ሄዶ እንደ ዳቦ ባሉ መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ ጭማሪ ታየ። ተቃውሞ ተቀስቅሶ አሁን ለመጣው የመንግሥት ለውጥ ምክንያቶች መካከል አንዱ ሆነ " ይላሉ። የውጪ ምንዛሬ ስርዓት ከ3 ዓመት በኋላ ይቀየራል መባሉ 'ግራ አጋቢ ነው' ብሔራዊ ባንክ የብር ዋጋ በገበያው የሚተመነው በሦስት ዓመት ውስጥ ነው ማለቱ ይታወሳል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓቷን በዚህ ጊዜ ውስጥ መቀየር ይቻላታል? እዮብ (ዶ/ር) በበለጸጉ አገራት ዘንድ የውጪ ምንዛሬ ሥርዓታቸውን በሦስት ዓመት ውስጥ የመቀየር ልምድ እንዳለ አውስተው፤ በብሔራዊ ባንክ በኩል ግን ቅድሞ ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች እያሉ "ከሦስት ዓመት በኋላ የተባለው ከምን ተነስቶ እንደሆነ 'ግራ አጋቢ' ነው" ይላሉ። በኮቪድ-19 ምክንያት የዓለምና የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት እየተጓተት መሆኑን ያስታወሱት እዮብ (ዶ/ር)፤ በወረርሽኙ ሳቢያ የተወሰነው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ክፍል ክፉኛ መጎዳቱን ይናገራሉ። "ከእነዚህ ጫናዎች ሳንላቀቅና የኮቪድ-19ን ሙሉ ጫና ሳንረዳ ከአሁኑ ሦስት ዓመት ብሎ መወሰን ለእኔ ግራ አጋቢ ነው። በበኩሌ የምቀበለው ነገር አይደለም" ሲሉ ይሞግታሉ። እዮብ (ዶ/ር) እንደሚሉት ወደዚህ አይነት የውጪ ምንዛሬ አስተዳደር ለማምረት የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እንደሚያስፈልጉ በማውሳት፤ ኢትዮጵያ ወደዚህ ከመሸጋገሯ በፊት "የማክሮ ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ያስፈልጋል፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ያስፈልጋል፣ በቂ የውጪ ምንዛሬ ክምችት መኖር ይኖርበታል እንዲሁም የንግድ ሚዛን ጉድለት መጥበብ ይኖርበታል" ሲሉ ይመክራሉ። እንደ እዮብ (ዶ/ር) አመለካከት በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ሥርዓት ከመሸጋገራችን በፊት የዋጋ ግሽበት መጠንን ወደ አንድ አሃዝ ማምጣት "እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።" "በገበያው ላይ በቂ የሆነ የውጪ ምንዛሪ መኖር ይኖርበታል። ይህ እንዲሆን ደግሞ በቂ የውጪ ምንዛሪ ክምችት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያም የውጪ ምንዛሪ የምታገኘባቸውን መንገዶች መጨምር ይኖርባታል። ከውጪ የሚላክ ገንዘብ እንዲጨምር ማበረታቻ ማድረግ፣ ቱሪዝምና ኤክስፖርት ማደግ ይኖርባቸዋል" ይላሉ። ይህን የውጪ ምንዛሬ ሥርዓት ለመተግበር የተማረ ሰው ኃይልና ተቋማዊ ለውጥ የግድ እንደሚልም እዮብ ተስፋዬ (ዶ/ር) ያሳስባሉ። አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ግፊት ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ገንዘቧ በገበያ ዋጋ እንዲተመን ግፊት እንደሚያሳድሩ ይነገራል። እዮብ (ዶ/ር) ለዚህ አንዱን ምክንያት ሲያስረዱ፤ አይኤምኤፍ ከተመሰረተባቸው ምክንያቶች አንዱ የዓለም አገራት የመገበያያ ገንዘብ ዋጋ እንዲረጋጋ ለማድረግ በመሆኑ ነው። "በእነሱ ፍልስፍና የምንዛሪ ተመን የተረጋጋ የሚሆነው ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሲሆን ነው። ምክንያቱም ምንዛሪ እንደማንኛውም ሸቀጥ ዋጋ አለው። እንደ ሌሎች ሸቀጦች ሁሉ ይህ ዋጋ በገበያ ኃይል መወሰን አለበት ብለው ያምናሉ" ሲሉ ያስረዳሉ። አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልከው ምርት በላይ ከውጪ የምታስገበው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ በመሆኑ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ይህንን ልዩነት ለማጥበብ የብር ዋጋ በገበያ ቢወሰን በተሻለ መልኩ የውጪ ምንዛሪ እንዲገኝ ይረዳል የሚል እሳቤ ስላለ አገሪቱ ወደዚህ ሥርዓት እንድትገባ ጫና እንደሚደረግ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አለማየሁ (ዶ/ር) እንደሚሉት በኢትዮጵያዊያን ላኪዎች እንደችግር ከሚቀርቡት መካከል የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት እጥረት ትልቁ ራስ ምታት አይደለም ባይ ናቸው። "እኔ ከመቶ በላይ ላኪዎችን አነጋግሬ የደረስኩበት ነገር፤ ለእኛ አገር ላኪዎች መሠረታዊ ችግር የሆነው የጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት፣ የመሬትና የፋይናንስን አቅርቦት ችግር፣ ሙስናና ጉምሩክ ላይ ያለው ውጣ ውረድ ነው እንጂ የዶላር እጥረት የላኪዎች ትልቁ ችግር አይደለም" ይላሉ። "ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት በትይዩ ገበያ [ጥቁር ገበያ] እና በባንክ መካከል ያለው ልዩነት እንዲሁም ወደ አገር በሚገባውና ወደ ውጪ በሚላከው መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ነው።" በእነዚህ መካከል ልዩነቱ የሰፋበት ዋነኛ ምክንያት ወደ ውጪ የሚላከው ምርት ስላላደገ እንደሆነ የሚናገሩት አለማየሁ (ዶ/ር) "በእኔ ስሌት ወደ አገር በሚገባውና ከውቺ በሚመጣው መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ወደ ውጪ የምንልካቸው ምርቶች በአማካይ በዓመት 20 በመቶ ለስምንት ተከታታይ ዓመት ማደግ ይኖርበታል" ይላሉ። ስለዚህም የመንግሥት ትኩረት መሆን ያለበት "ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች የሚጨምሩበትን መንገድና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት አምራቾችን ማበረታት ላይ ነው" ይላሉ አለማየሁ (ዶ/ር)። አዋጭ ነው? የባለሙያዎቹ ጠቅላላ ግምገማ ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር የዋጋ ተመን በገበያ እንዲወሰን ብታደርግ ያዋጣታል? የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ማጠቃለያ ሃሳብ የሚከተለው ነው። እዮብ (ዶ/ር) - የምንዛሪ ሥርዓት መቀየርና በገበያ ዋጋ መወሰን እንዳለበት አምናለሁ። አካሄዱ ግን ቀስ በቀስ በሂደት መሆን አለበት። ብሔራዊ ባንክ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ መከናወን ያለባቸው ነገሮችን መሰራት ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያና ተቋም ያስፈልጋል። አለማየሁ (ዶ/ር) - ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። የውጪ ምንዛሪ ሥርዓታችንን ከመቀየራችን በፊት ቀድሞ መከናወን ያለባቸው የቤት ሥራዎች አሉ። አቶ ዋሲሁን - በጠቅላላው አዋጭ ነው ብዬ አስባለሁ። ሥርዓቱ በራሱ ጊዜ ወደ ዚያው እየወሰደን ይገኛል። በመጪው ሦስት ዓመታት ውስጥ የሚጠበቅብንን የቤት ሥራዎች ማከናወን የምንችል ከሆነ የሚየቀሩ ነገሮች ቢኖሩም ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር ዋጋ በገበያ እንዲተመን ማድረጉ ትክክለኛ አካሄድ ነው።
news-52975845
https://www.bbc.com/amharic/news-52975845
ጥቁር ሰው በነጭ ፖሊስ ጉልበት ተደፍቆ ሲሞት ማየት እንዴት ይቻለኛል?
በሚኒያፖሊስ አንድ ነጭ ፖሊስ በሦስት ባልደረቦቹ ታግዞ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድን እጁ ከኋላ እንደተጠፈረ አንገቱን ከመሬት ላይ አጣብቆ በጉልበቱ ደፍቆ ሲገድል የሚያሳየው ቪዲዮ ዓለምን አስደንግጧል።
መረበሽና መጨነቅ ፊቱ ላይ የሚታይበት ጆርጅ ፍሎይድ የመጨረሻ እስትንፋሱም ስትወጣ፤ ህቅታውንም ዓለም ግድያውን በማየት ምስክር ሆኗል። "መተንፈስ አልቻልኩም" እያለ ሲለምን፤ የሞቱትን እናቱን እንዲደርሱለት ሲማፀን የነበረው ጆርጅ "እባክህ፣ እባክህ፣ እባክህ" በማለት ህይወቱ እንዲተርፍም ነጩን ፖሊስ ጠየቀ። ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው ፖሊስም አልሰማም ለዘጠኝ ደቂቃ ያህልም በጉልበቱ እንደተንበረከከበት ቆየ፤ በመጨረሻም የጆርጅ ፍሎይድ ህይወት አልባው ሰውነቱ ተወሰደ። የቴክኖሎጂ ሁለት ገፅታ፤ ግድያን ወደድንም ጠላንም በአይናችን ሲያሳየን በሌላ መልኩ ግፉንም አጋልጧል። የጆርጅ ፍሎይድ መማፀን የብዙዎችን ልብ ሰብሯል፤ ይህንን ቪዲዮ ለቀረፀችው ለአስራ ሰባት ዓመቷ ታዳጊስ በወቅቱ ምን ተሰምቷት ይሆን? ለጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወዳጅስ የህይወቱን መጨረሻ በቪዲዮ ማየት የሚፈጥረው ስሜት በቃላት መግለፅ ይቻል ይሆን? ይህንን ቪዲዮ አላይም ያሉም በርካታ ናቸው። ከእነዚህም መካከል ጥቁሯ ጋዜጠኛ ሳንድሪን ሉንጉምቡ አንዷ ናት ለምን ቪዲዮውን እንደማትመለከት በእራሷ አንደበት ትተርካለች። የሌሎችንም ልምድ ታጋራለች። እንደ ጥቁር ሴት ይህንን ቪዲዮ ማየት አልችልም። መሳሪያ ያልያዘ አንድ ጥቁር ሰው በነጭ ፖሊስ ጉልበት ተደፍቆ ሲሞት ማየት እንዴት ይቻለኛል? አድካሚ ነው፤ የማያቋርጥ ቅዠት፣ ህመምን ይፈጥራል። ቪዲዮው ግፍን በማጋለጡ፤ ለዘመናት የሰፈነውን ማኅበራዊና መዋቅራዊ ዘረኝነት እውነታም ይፋ በማድረጉ ልደሰት እንደምገባ ብዙዎች ነግረውኛል። እንዲህ ዝም ብዬ ሳስበው ለአንድ ጋዜጠኛ ከእውነት በላይ ምን አለ? ነገር ግን በዓመታት ውስጥ እንዲህ አሰቃቂ እውነታን በማጋለጥና የአዕምሮዬን ጤና በመጠበቅ መካከል ልዩነት እንዳለ ተረድቻለሁ። በተለይም ከራሴ ማንነት፣ ልምድ ጋር በፅኑ የተቆራኘ ከመሆኑ ጋር እንዴትስ መነጠል ይቻላል? እንዲህ አይነት ቪዲዮዎችን ለሚመለከት ለማንኛውም ሰው አስጨናቂ ቢሆንም እንደእኔ ላሉት ጥቁር ሰዎች ደግሞ ከአስደንጋጭም በላይ ነው። ሌሎች ህመሞችን ይቀሰቅሳል። የማያቋርጥ ቅዠት ኒያ ዱማስ ገና ሃያ ዓመቷ ነው፤ ሩጣ ያልጠገበች፤ ነገር ግን ጥቁር መሆን ከዕድሜ በላይ ያደርጋል። ከነጮች እኩዮች በላይ ማደግን፣ መብሰልን እንዲሁም መጠንቀቅን ይጠይቃል። የጆርጅ ፍሎይድንም ግድያ ካየች በኋላ አልቅሳ አላባራችም፤ ስታዋራኝም ሳግ እየተናነቃት ነበር። "ካየሁት በኋላ ቢያንስ በቀን አራት ጊዜ አለቅሳለሁ። መቼም ቢሆን ከህሊናዬ አይጠፋም" ትላለች። በክሊቭላንድ ኦሃዮ ያደገችው ኒያ ለግድያም ሆነ ለግጭቶች አዲስ አይደለችም። በህፃንነቷም ወቅት ጥቁሮች ሲሞቱ ማየት የህይወቷ አካልም ነበር። "ጆርጅ ፍሎይድ ባይሆን ሌላም ጥቁር ይገደላል። ዋናው ጥቁር ሆኖ መገኘት ነው። ጥቁር መሆን ወንጀል ይመስል፤ ለጭንቅላትም ከባድ ነው። የማያቋርጥ ቅዠት" ትላለች። የጆርጅ ፍሎይድም መገደል በነጭ የአካባቢ ጥበቃ ህይወቱ የጠፋውን ታዳጊውን ትሬይቮን ማርቲንን አሟሟት አስታወሳት። "ትሬይቮን ሲገደል አስራ አንድ አመቴ ነበር። ከዚያ በኋላም ለዓመታት በርካታ ጥቁሮች ሲገደሉ አይቻለሁ። ደክሞኛል። አሞኛል" ብላለች። የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነችው ኒያ ዱማስ በአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት ነዋሪ ናት 'ብላክ ላይቭስ ማተር' [የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አለው] እንቅስቃሴ በአሜሪካ ሳይወሰን በመላው ዓለም ለሚገኙ ጥቁሮችም የፀረ ዘረኝነት እንቅስቃሴን አቀጣጥሏል። ከትውልድ ትውልድ የተላለፈ ትግልን መቀጠል ለብዙዎች አድካሚ ነው። የ27 ዓመቱ ቶኒ አዴፔግባ ዘረኝነት ካደከሙት ውስጥ አንዱ ነው። ጥቁር እንግሊዛዊው ቶኒ በተለይ የዚህ ወር ጫናው ከብዶታል። "የተፈተንበት ወር ነው። አህመድ አርበሪ ግድያን ቪዲዮ በቅርቡ አየን፤ ቀጠለ ሌላ ጥቁር ሰው ጆርጅ ፍሎይድ ተከተለ።" የ25 ዓመቱ አህመድ አርበሪ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ በወጣበት ወቅት ነው በዘረኛ አባትና ልጅ ጥይት ህይወቱ የጠፋው። ለቶኒ በተለይ የጆርጅ ፍሎይድን የመጨረሻ እስትንፋስና መማፀንን ማየት ከዘግናኝም በላይ ነው። "የተሰማኝን ህመም በቃላት መግለፅ ይከብደኛል። መንፈሴ እንደተሰበረ ይሰማኛል። ጥቁር ሰው መሆን ብቻ ኢላማቸው መሆኑ ጋር ተያይዞ እኔም እሆን ነበር። አድካሚ ነው" ብሏል። በማያቋርጠው የዘረኝነት ትግልም በዚያኑ ሳምንት በኒው ዮርክ ሴንትራል ፓርክ ወፎችን ሊያይ የመጣ አንድ ጥቁር ሰው አንዲት ነጭ ግለሰብን እፅዋትን እንዳያበላሽና ወፎቹንም እንዳያስደነብር 'ውሻሽን እሰሪ' በማለቱ ለፖሊስ እደውላለሁ "ጥቁር አሜሪካዊ ለህይወቴ እያሰጋኝ ነው እላለሁ" በማለት ማስፈራቷንም አይቷል ። ግለሰቧ ፖሊስ ያለውን ጭካኔ ለጥቁሮች ምህረት እንደሌለው በማወቅ እንደ መሳሪያነትም ልትጠቀም ማሰቧ ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሎባታል። በእንግሊዝ ነዋሪ የሆነው ቶኒ አዴፔግባ "በጣም ነው የሰቀጠጠኝ። በቆዳዋ ቀለም ያላትን የበላይነት ታውቃለች። ያንን በመጠቀምም የጥቁሩን ህይወት አደጋ ውስጥ መክተት እንደሚቻል ተረድታዋለች። ከዚህም በላይ ያለውን የኃይል ተዋረድ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው" የሚለው ቶኒ። "ግለሰቡን በአንድ ስልክ ማሳሰርም ሆነ ማስገደል እንደምትችል ታውቃለች" ብሏል። ከፍተኛ ግፍና ስቃይ በጥቁሮች ላይ ማየት ያደከመው ቶኒ የጆርጅ ፍሎይድንም ሙሉውን ቪዲዮ ለማየት አንጀቱ አልቻለም። "መጀመሪያ እንዲሁ ተቀንጭቦ ሳየው ለምንድን ነው ቆመው የሚያዩት የሚል ጥያቄን አጫረብኝ" ነገር ግን ብዙዎቹ በእሱ ቦታ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስለተረዱ ነው። በቅርብ ሳምንታት እነዚህን ቪዲዮዎች በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ማጋራት ላይ ስላለው ፋይዳም የተለያዩ ውይይቶችን አድርጌያለሁ። የዘር ግንዷ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚመዘዘውና ፓሪስ የተወለደችው የ28 ዓመቷ ላይቲታ ካንዶሎም ብትሆን በመጀመሪያ ቪዲዮውን ማየት አልቻለችም። "በርካታ ስሜቶች ተፈራረቁብኝ እናም ዜናውን ስሰማ ላለማየት ወስኜ ነበር። ከሰዓታት በኋላ ግን ቪዲዮውን ሲቀባበሉት እኔም አየሁት። እርዳታ የሌለው ሰው ነበር። እኔም እንደሱ እርዳታ ቢስ እንደሆንኩ ተሰማኝ።" ፈረንሳይና ኮንጎ የምትሰራው ላይቲታ ካንዶሎ "ዘረኞችን ሥራቸው የሚጋለጥበትን ተግባር ሁሉ ማከናወን አለብን" የምትለው ላይቲታ "እንደዚህ አይነት ቪዲዮዎች በቆዳቸው ቀለም የተለየ ቦታ ያገኙ ሰዎችን ቆም አድርጎ የሚያሳስባቸው ከሆነ ለሕዝብ ይፋ መሆን አለባቸው።" "ማስታወስ ያለብን ነገር ነጮች እነዚህን ቪዲዮዎች ያያሉ፤ ለእኛ ግን የየቀኑ የህይወታችን አካል ነው" በማለት ታስረዳለች። በተለይም ጥቁር ያልሆኑ ሰዎች እነዚህን ቪዲዮዎች በተለያዩ ሚዲያዎች ሲያጋሩ ማየት የጥርጣሬ መንፈስን ያሰፍናል። ኒያ በተለያዩ ድረገፆች ላይ ያለው ድጋፍ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ አላት። በተለይም እነዚህ ድጋፎች መዋቅራዊ የሆነውን ዘረኝነትን የመንካት ሚናቸው ምን ያህል ነው በሚልም ጥያቄ ታነሳለች። "በርካታ ነጭ ታዋቂ ሰዎች ቀድመው የተዘጋጁ የሚመስሉና ከላይ ከላይ ብቻ ዝም ብለው የሚያወሩ አርቲፊሻል መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ" አያለሁ ትላለች። የተወሰኑ ሰዎችም እውነተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን ብትወደውም "አሳ ስለዋኘ አታጨበጭብም" በማለት መስራት የሚገባቸውንና ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን የሚያስጨበጭብ ሥራ እንዳልሆነ ታስረዳለች። "በዘረኝነት ጉዳይ ላይ የሰውየውን አስተሳሰብ፣ አቋምና ለማጥፋትስ ምን እያደረገ ነው የሚለው ነገር ትኩረት ልንሰጠው የሚገባው ጉዳይ ነው። በማኅበራዊ ሚዲያ ፅሁፎችን፣ ቪዲዮዎችን ስላጋራን ድጋፍ የሚመስለን ብዙ አለን። ተሳስተናል። ከእሱ አልፈናል" በማለትም መሰረታዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግም ትገልፃለች። "ከአዕምሮዬ መቼም ቢሆን አይጠፋም" ጥቁር ሰዎች እንደነዚህ አይነት ቪዲዮዎችን በሚመለከቱበት ወቅት ራሳቸውን ወይም የቤተሰባቸውን አንድ አካል እንዲሁም ከባርነት ጀምሮ ሲሰቃዩ የነበሩ የቅድመ አያቶቻቸው ምስል ድቅን ይልባቸዋል። "የአህመድ ቪዲዮ ሲወጣ ብዙ ጊዜ እሮጥ ነበር እናም ስሮጥ ያዩኝ ወንጀል ሰርቼ የምሸሽ መስሏቸው ፖሊስ ጋር ሊደውሉ ይችላሉ የሚለው ሃሳብ በአዕምሮዬ ይመላለሳል። አሜሪካ ብሆን ደግሞ የእሱ እጣ ፈንታ ሊደርሰኝ እንደሚችል አስባለሁ" በማለት ቶኒ የፈጠረበትን ስሜት አጋርቷል። "እያንዳንዱ ጥቁር ሰው ጥቁርነቱን ሲረዳና እንዲህ አይነት ክስተቶችም በዓለም ላይ ያለው ፀረ- ጥቁርነትና ያለህን ቦታ ያሳዩሃል" የምትለው ላይቲታ በአስራ ስምንት ዓመቷ ወደ ፋሽን ትምህርት ቤት ለመግባት ባቀደችበት ወቅት ከአባቷ ጋር የነበራትን ውይይት ታስታውሳለች። "አባቴ አንቺ ጥቁር ነሽ፤ እንደ ጥቁርነትሽም በምዕራቡ ዓለም የጥበብ ቦታ ለመግባት ቀላል አይሆንም። ትግል ነው የሚሆንብሽ። ከነጭ እኩዮችሽ በበለጠ መስራት ይጠበቅብሻል የሚለውን እውነታ አረዳኝ። ተሰበርኩኝ ማለት ይቻላል። አለቀስኩ" ብላለች። "የጆርጅ ፍሎይድ ታሪክ የእኔም ነው" በዓለም ላይ የምንገኝ ጥቁር ሕዝቦች ዘረኝነትን በየቀኑ ነጮች ፊታቸውን ከሚያከፉብን ጀምሮ፣ መዋቅራዊ እንዲሁም ታሪካዊ ዳራውን እንረዳለን። በምሥራቅ ለንደን በአፍሪካ ብዝሃ ባህል ከማደጌ አንፃር መጀመሪያ በፍቅር ነው ያደግኩት። ከዚያ ግን ዩኒቨርስቲ ጋዜጠኝነት ለማጥናት ስገባ እውነተኛው ዓለም ምን እንደሆነ ተረዳሁ። አፍሮ ፀጉሬ የመወያያ ርዕስ ነበር። በፀጉሬም መዘባበት እንዲሁም መወልወያ ይመስላል፤ ሥራም አታገኝም እያሉ ነጮች ቀልደውብኛል። እንዲህ አይነት ዘረኛ ቪዲዮዎችን ስናይ ለብዙ ጥቁሮች የራሳችንን አስከፊ ትዝታ ወይም ደግሞ እንደ ህዝብ እየደረሱብን ያሉ ግፎችን ይቆሰቁሳሉ። ፀረ-ዘረኝነት ሰልፎችን የሚያስተባብረው ትሪስተን ቴይለን ለጆርጅ ፍሎይድ ሞት ተቃውሞ ላይ የተሰማውን ስሜት በእንባ ገልፆታል "ለጥቁሮች በሙሉ የጆርጅ ፍሎይድ ታሪክ የእኛ ነው፣ የእኔ ነው። ጥቁሮች በሙሉ በአንድም በሌላ መንገድ የምንጋራቸው በርካታ ነገሮች አሉ" ትላለች ላይቲታ። "እነዚህ ምስሎችም ሆነ ቪዲዮዎች ታሪካዊ የሆነ ቦታ አላቸው። በቅኝ ግዛት ወቅት ቤልጅየማውያን ኮንጎዎችን ሰቅለዋቸዋል፣ አንቀው ገድለዋቸዋል፣ እጃቸውንም ቆርጠውታል። በሰው ልጅ ላይ ዘግናኝ ነገሮችን ፈፅመዋል። "ለዘመናትም ገድለውናል፤ ሊገድሉንም እየሞከሩ ቢሆንም አልጠፋ አልናቸው፤ በህይወት አለን። ነገር ግን እንዲህ አይነት ግድያዎች አድካሚ ናቸው። እስከመቼስ ነው የሚቀጥለው? በአዕምሮ ጤናችን ላይ የሚያደርሰውም ጫና ቀላል አይደለም" ብላለች። ለበርካታ ዓመታትም ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ዘረኝነትን መቃወም፣ የፖሊስ ጭካኔን ብታወግዝም የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ግን ከምትቋቋመው በላይ በመሆኑ ለአዕምሮዋ ጤንነት ቦታ መስጠት እንዳለባት ተሰማት። "ለአእምሮ ጤናችን ቅድሚያ ልንሰጠው ይገባል" የቶኒም ልምድ ከዚህ የተለየ አይደለም አዙሪቱ በማያልቀው የዘረኝነት ትግል ውስጥ መግባትና የአዕምሮ ጤንነቱን መጠበቅን አብሮ ማስኬድ አለበት። "ጆርጅ ፍሎይድ እንዳይረሳ ማድረግ፤ ስሙንም ማንሳት የእኛ ተግባር ነው። ነገር ግን ለብዙ ጥቁር ሰዎች የምመክረው ቪዲዮውን ለማየት መገደድ የለባቸውም። ማጋራትም አይጠበቅባቸውም። ለአዕምሮ ጤንነታችን ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል" ብሏል። "ጥቁርና ነጭ መባባል አቁመን እንደ ሰው መተያየት ስንጀምር። የእነሱ ችግር ነው ብለው መጠቆም ሲያቆሙና ሁላችንም የምንረባረብበት ሲሆን ችግር መሆኑ ያቆማል" ብሏል።
news-44312635
https://www.bbc.com/amharic/news-44312635
አልጄሪያ አንድ ኮንቴይነር ሙሉ ኮኬይን ያዘች
የአልጄሪያ ባለሥልጣናት 700 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን በኮንቴይነር ተጭኖ በመርከብ ሊያልፍ ሲል ደርሰውበት በቁጥጥር ሥር አውለውታል። ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አስተላላፊ ናቸው የተባሉ 20 ሰዎች ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
የአልጄሪያ የባሕር ኃይል አባላት መርከቧን ኦራን በተሰኘችው ወደብ ታግታ እንድትቆይ አድርገዋል መርከቡ "ሀላል ሥጋ" የሚል ምልክት የተደረገባቸው ኮንቴይነሮችን ከብራዚል ወደ ስፔን ቫሌንሺያ በማጓጓዝ ላይ ነበር ተብሏል። ኦራን የተሰኘችው የአልጄሪያ ምዕራባዊ ወደብ ሲደርስ ግን የተወሰኑ ኮንቴይነሮችን ማራገፍ ነበረበት። ካፒቴኑ ግን ለ3 ቀናት ይህን ለማድረግ አለመፍቀዱ ጥርጣሬን ጫረ። ይህን ተከትሎ ለአልጄሪያ ፖሊስ ጥቆማ በመድረሱ መርከቡን በአስገዳጅ ወደ ወደቡ በመውሰድ ዘለግ ያለ ፍተሻ ተደርጎበታል። በፍተሻውም በላይቤሪያ ስም የተመዘገበችው ቬጋ ሜርኩሪ በምትባል መርከብ ውስጥ "ሃላል ሥጋ" የሚል ምልክት ተለጥፎበት ተገኝቷል።
news-48718892
https://www.bbc.com/amharic/news-48718892
እዩ ጩፋ፡ ማን ነው ነብይ ያለህ?
ነብይ እዩ ጩፋ ነብይና ሃዋርያ ተብለው ከተነሱ ብዙዎች አንዱ ነው። ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል የተሰኘ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያን መስርቶ በርካታ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል። ክራይስት አርሚ በተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያው በሚተላለፉ የፈውስ ትዕይንቶች ፣ 'አጋንንትን በካራቴ በመጣል'ና በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች አነጋጋሪና አወዛጋቢ ስለመሆኑ ጠይቀነው ምላሽ ሰጥቷል። ደቡብ ውስጥ ነብያትና ሃዋርያት በዝተዋል ይባላል ፤ በዚህ ውስጥ ራስህን እንዴት ነው የምታየው?
ነብይ እዩ ጩፋ፡ እውነት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያገለግሉ የብዙ ነብያትና ሃዋርያት መነሻ ደቡብ ነው፤ እኔም ከዚያው ነኝ። ምናልባት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሊኖረው ይችላል። ደቡቡም ሰሜኑም የእግዚአብሔር ነው። ነገር ግን እኔ የተወለድኩበት ወላይታ አካባቢ ብዙ ዋጋ የከፈሉ የወንጌል አባቶች የነበሩበት በመሆኑ ከዚያ ጋርም ሊያያዝ ይችላል ብዬ አምናለሁ። ሐሰተኛ ነብያት በብዛት የሚነሱበት ጊዜ እንደሚመጣ በመፅሃፍ ቅዱስም ተፅፏል።እነዚህ ነብያትና ሃዋርያት ሁሉም እውነተኛ ናቸው? እዩ ጩፋ፡ በዚህ ጊዜ ሐሰተኛም እውነተኛም ነብያት አሉ። የሚታወቁት ደግሞ በሥራቸው፤ በፍሬያቸው ነው። እኔ ግን የእግዚአብሔብርን ወንጌል እያገለገልኩ የምገኝ የእግዚአብሔር ነብይ ነኝ ብዬ አምናለሁ። ግን አንተም ገንዘብ ከፍሎ ምስክርነት ያሰጣል፤ ወደ ንግድነት ያደላ ሐይማኖታዊ አካሄድ ይከተላል ትባላለህ? እዩ ጩፋ፡ እውነት ነው ገንዘብ ከፍሎን ነው የሚል ነገር ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተለቆ ነበር። ገንዘብ ከፍሎ የሚለው ነገር ፈጽሞ ውሸት እንደሆነ ግልፅ ማድረግ ስለነበረብኝ እኔም አንዴ መልስ ሰጥቼ ነበር። አጋንንት እስራት ውስጥ ያሉትን ነፃ ለማውጣት ነው የተቀባሁት። ከፍዬ አጋንንት ማስጮኸው ለምንድን ነው? ከፍዬ የማስጮህ ከሆነ የቀን ገቢዬ አስር ሚሊዮን እንኳ ቢሆን አያዋጣኝም። ሰው ደግሞ የማያዋጣውን አይሰራም። ማነው ነብይ ብሎ የሾመህ? እዩ ጩፋ፡ በዚህ ዓለም ሰው ሰውን የሚሾም ቢሆንም እውነተኛ ሿሚ እግዚአብሔር ነው። በቤተክርስትያን ከእኛ የቀደሙ ሰዎች በእኛ ላይ የተገለፀውን ፀጋ አይተው ወንጌላዊ፣ ዘማሪ ወይም ነብይ ብለው ይሾማሉ። እኔም በጣም በማከብራቸውና በምወዳቸው ቄስ በሊና ነው ሃዋርያ ተብዬ ሹመት የተሰጠኝ። ነገር ግን ከእሳቸው በፊት ቦዲቲ በሚባል ቦታ በማገለግልበት ወቅት ነብይ ሆኜ በቤተክርስትያን ሰዎች ተሹሜአለሁ። እንጂ እራሴን ነብይ ብዬ አልሾምኩም። በአንተ ቤተክርስትያን የሚያመልኩ ባለስልጣናት ወይም ታዋቂ ሰዎች አሉ? እዩ ጩፋ፡ ስማቸውን መጥራት ባያስፈልግም እስከ ሚኒስትር ደረጃ ያሉ አሉ። ግን ሰው ስለሚበዛ የስልጣን ደረጃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቅለው እንዲገቡ የማይፈቅድላቸው አሉ። እነዚህን ሰዎች በተለይ እንደ ሰዉ አጠራር ቪአይፒ አግኝቼ የማገለግልበት ጊዜ አለ። • ኤርትራ በቤተ ክርስቲያን ስር ያሉ የጤና ተቋማትን ወሰደች የእግዚአብሔር ክብር ከእኔ ይበልጣል ብለው ቦታ ተይዞላቸው ከሰው ጋር ተጋፍተው የሚገለገሉም አሉ። ከአገር ውጪም ለትልልቅ ሰዎች ጸልዬ አውቃለሁ። ለምሳሌ ባለፈው ሱዳን ሄጄ ለፕሬዘዳንት ሳልቫኪር ቤተ መንግሥት ገብቼ ጸልያለሁ። ትልልቅ ሰዎችንም ወደ ቤተ ክርስትያን ጋብዤ አውቃለሁ። አጋንንት ማውጣትና ካራቴን ምን አገናኛቸው? ካራቴ ታበዛለህ። እዩ ጩፋ፡ ካራቴ የተማርኩት አጋንንት ለማውጣት አይደለም። የለየለት ካራቲስትም አደለሁም። እኛ ጋ ከባህልና ከሁኔታዎች ጋር የተለመደ ነገር አለ። ከተለመደው ውጪ ሌላ አቅጣጫ ይዘሽ ስትነሺ ያስገርማል። አዲስ ነገር ነውና ካራቴው ያስገረመው፣ ያደናገረውና ያስደሰተውም አለ። ሁሌ ካራቴ ሁሌ አጋንንትን ጩኸና ውጣ አልልም። መንፈስ እንዳዘዘኝ ነው ማደርገው። በጌታ በእየሱስ ስም ጩኸና ውጣ ብዬ አዝዤ የወደቀውን መንፈስ አንስተው ሲያመጡ በካራቴ መታሁት፣ በቴስታ መታሁት ምን ጉዳት አለው? በእጅም በእግርም ጥዬ አውቃለሁ ይህን የማደርገው አጋንንት የተመታና የተዋረደ መሆኑን ለማሳየት ካለኝ ፍላጎት የተነሳ ነው። እግዚአብሔር መላ ሰውነቴን እንደሚጠቀም ማሳያም ነው። እኔ በካራቴ ከእኔ በኋላ ደግሞ በሌላ ስታይል አጋንንትን የሚመቱ ሊነሱ ይችላሉ፤ ይህ የራሴ ስታይል ነው። አንዳንዶች ካራቴውን የሚቃወሙት በቅናት፣ ሌሎች ደግሞ ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው በማለት ነው። ከካራቴም የተሻለ አሰራር ያላቸው ካሉ ግብዣዬ ነው። በቀይ ቦኔቶች ተከበህ ስትንቀሳቀስ ይታያል። እንዴት ነው እንዲህ በወታደሮች የምትጠበቀው? እዩ ጩፋ፡ አንድ ሚሊዮን ሁለት ሚሊዮን ሰዎች በሚገኙበት የሜዳ ላይ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ ለህዝብ ደኅንነት ሲባል መንግሥት የጥበቃ ኃይል ያሰማራል። አንዱ ተጠባቂ እኔ ነኝ፤ ከጌታ በታች እኔን ይጠብቃሉ። ብዙ ሰው ግን እኔ ከፍዬ ያመጣኋቸው ይመስለዋል። ብዙ የፖሊስና የወታደር ልብስ የለበሱን ከኋላህ አሰልፈህ "የእየሱስ ወታደር ነኝ"ን ስታዘምር የሚታይበት ቪዲዮም አለ? እዩ ጩፋ፡ እሱ እኔ በክልል ባዘጋጀሁት ኮንፈረንስ ከመንግሥት የተቀበሉትን ሃላፊነት ሦስት ቀን በሥራ ላይ በታማኝነት በማሳለፋቸው በመዝጊያው ቀን ኑ ፖሊሶች ብዬ ጠርቼ የፀለይኩበት ነው። ምክንያቱም ለመንግሥት ለአገርም መፀለይ ስላለብን። እነሱም የመንግሥት አንድ አካል ናቸው። ወደ አገር ጉዳይ ከመጣን፤ በአሁኑ ወቅት በርካታ ፕሮቴስታንቶች በመንግሥት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ናቸው ይባላል። ይህ ላንተ የተለየ ትርጉም አለው? እዩ ጩፋ፡ በአሁኑ ወቅት በጠላት አይን አገር እየፈረሰ ያለ ይመስላል በእኔ እይታ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከመጣ በኋላ አገር እየተገነባ ነው። ትልቅ ለውጥ መጥቷል። አንደኛው ለውጥ እግዚአብሔርን የሚያውቅና የሚፈራ መሪ ኢትዮጵያ ላይ መምጣቱ ነው። • ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት እግዚአብሄር በትንቢታዊ መንገድ የሰጠኝን መልእክት አስተላልፌ ነበር። ዩ ቲውብ ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚመጡ ቀድሞ እግዚአብሄር ተናግሮኝ ተናግሬአለሁ።የፖለቲካ መናጋቱና መናወጡ በየትኛውም ዘመን አለ። ኢትዮጵያ ከመቼውም በላይ ወደ ተነገረላት ከፍታ እየሄደች ያለችበት ጊዜ ላይ ነን። ስለ ኢትዮጵያ ብልፅግና ካነሳህ የልምላሜ ተስፋ የተጣለበት የህዳሴው ግድብ ተሰርቶ የሚያልቅ፤ እውን የሚሆን ይመስልሃል? እዩ ጩፋ፡ በእምነት የምትናገሪው ነገር አለ። እኔም የእምነት ቃል መስጠት እችላለሁ። በግሌ እንደ ቤተክርስትያን የጀመርናቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች አሉ። ሰው ሲያይ የማያልቅ የሚመስለው እኔ ግን እንደሚያልቅ አምናለሁ። ያልቃል የምለው ገንዘብ ስላለ ወይም በሌላ ምክንያት ሳይሆን አማኝ ሰው ስለሆንኩና እምነት የሁሉ ነገር ተስፋ ስለሆነ ነው። እንደዚሁ በእምነት አባይም ተገድቦ ያልቃል ብዬ አምናለሁ። የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆኑ ባለስልጣናት ስለመብዛታቸው ጠይቄህ ነበር . . . ? እዩ ጩፋ፡ ፕሮቴስታንት ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን የሚያውቁና የሚፈሩ በሚለው ብናገር ደስ ይለኛል። ከዚህ በፊት የነበሩት ባለስልጣናት እግዚአብሔርን ካለማወቃቸው የተነሳ ስልጣናቸውን ሰዎችን ለመጉዳት ተጠቅመውበታል። አሁን ግን ፕሮቴስታንት ባለስልጣናቱ ጌታን ስለሚፈሩ ጥሩ ሥራ ይሰራሉ ብዬ አምናለሁ እየሰሩም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ቤተክርስትያንህ ጋብዘሃቸው ታውቃለህ? እዩ ጩፋ፡ አንድ ጊዜ ጋብዣቸው ነበር ግን በጊዜው ለሥራ ወደ ውጪ ሃገር ሄዱ። ከዚህ በኋላ ግን አንድ ፕሮግራም አለ እዚያ ላይ እንዲገኙ ደግሜ እጋብዛቸዋለሁ፤ እንደሚገኙም ተስፋ አደርጋለሁ። ከጥቂት ዓመታት በፊት አትታወቅም ነበር።ያጣህ የነጣህ ደሃ ሆነህ ታውቃለህ? እዩ ጩፋ፡ እዚህ ደረጃ ከመድረሴ በፊት ሰው በሚያልፍበት መንገድ አልፌአለሁ። ከመታወቄ በፊት ስለ እኔ ሰምተው የማያውቁ በሦስት በአራት ዓመት ወደ ስኬት እንደመጣሁ አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን እጅግ አስቸጋሪና ዋጋ በሚያስከፍል መንገድ ነው የመጣሁት። ብዙ ተከታዮች አሉህ ብዙ ሰዎች የተማሩና በኢኮኖሚም ጥሩ ቢሆኑ ይህን ያህል ተከታይ የሚኖርህ ይመስልሃል? እዩ ጩፋ፡ እንደ አሜሪካ የሰለጠነና የበለፀገ አገር ላይም ቢሆን ተከታይ ይኖረኛል ብዬ ነው ማስበው። በጥረቴም በፍልስፍናም አይደለም ሰው የሚከተለኝ። ህዝቡ እንዲከተለኝ የሚያደርግ የእግዚአብሄር ሞገስ ስላለ እንጂ። ሰዎች ድሃ ስለሆኑና ስላልተማሩ ይከተሉኛል ብዬ አላስብም። ጥግ ድረስ የተማሩና ባለፀጎችም አብረውኝ አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያዘጋጁት "ገበታ ለሸገር" ላይ ጋብዘውህ ነበር? እዩ ጩፋ፡አልሰማሁም አጋጣሚ አገር ውስጥም አልነበርኩም። አረቦች ለፈውስ ወደ አንተ እንደመጡ የሚያሳዩ የተለያዩ ቪዲዮዎችን አይቻለሁ። የሶሪያ ስደተኞች ናቸው ወይስ አንተን ብለው የመጡ? እዩ ጩፋ፡ እስከማውቀ እኔ ጋር እግረ መንገዱን የመጣ የውጭ አገር ሰው የለም። ፕሮግራም አስይዘው ትኬት ቆርጠው ነው የሚመጡት። ከኢራን፣ ኢራቅ፣ ዱባይና ኦማን ፕሮግራም አስተርጉመው የሚሆነውን ተአምራት እያዩና እየሰሙ ይመጣሉ። ምን ያህል ሃብት አለህ? እዩ ጩፋ፡ ሃብቴ የማይመረመር የማይቆጠር ሰማያዊ በረከት ነው። በዓለማዊው የባለጠጋ መለኪያ ራሴን እንዴን እንደምገልጽ ግን እንጃ። አገልጋይ ነን ቤተክርስትያንን የምናንቀሳቅስበት ብር ይመጣል። መባ፣ አስራትና ስጦታ እያገኘን ያንን ደግሞ መልሰን ለአገልግሎት እናውላለን። እንደሚታወቀው በአንድ ጊዜ አስራ አራት ሺህ ሰው የሚያስተናግድ 97 ሚሊዮን ብር የሚያስወጣ የአዳራሽ ግንባታ እያካሄድን ነው። በአንድ ዓመት ውስጥ ያልቃል። በግል ያለህ ምድራዊ ሃብትስ? እዩ ጩፋ፡ እስካሁን ያለኝ የማሽከረክረው መኪና ነው። ወንጌልን ከመስበክ ይልቅ ፈውስና ተዓምራት ላይ ያተኩራል እየተባልክ ትተቻለህ? እዩ ጩፋ፡ ቅድሚያ የምሰጠው ለወንጌል ነው። ተዓምራት ወንጌል ከሌለ የለም። ቃል ለወጣበት ዘይት(የተፀለየበት ዘይት) እስከ ሁለት ሺህ ብር ታስከፍላለህም ይባላል? እዩ ጩፋ፡ የተፀለየበት ዘይት(አኖይንቲንግ ኦይል) ሰዎች እኔ መድረስ የማልችልባቸው ቦታዎች እየወሰዱ እንዲፈወሱበት ነው ያዘጋጀነው። አሜሪካ፣ አውሮፓና አረብ አገር እየገባ ነው። አገር ውስጥም በየሰው ቤት እየገባ ነው። እኛ ቤተ ክርስትያን የገባ ሁሉ ይውሰድ የሚል መመሪያ ግን የለም። በነፃ ግን አይሰጥም ምክንያቱም ቤተክርስትያናችን የዘይት ፋብሪካ የላትም። ዘይቱ የሚመጣው ከውጭ ተገዝቶ ነው። ዘይቱ የሚታሸግበት ጠርሙስም የሚመጣው ከውጭ ነው። የጠርሙስ ክዳን፣ ጠርሙስ ላይ የሚለጠፍ ስቲከርም ማምረቻ ፋብሪካ የለንም። ይህን ሁሉ በገንዘብ ስለምናገኝ ነው በገንዘብ የምንቀይረው። የምትጠይቁት ብር የተጋነነ አይደለም ወይ? እዩ ጩፋ፡ አልተጋነነም እንዲያውም እኛ እንደ ቢዝነስ ሰው ብናስብ፤ ዶላር ስለጨመረ ዘይት ጨምሯል ብለን ዋጋ መጨመር እንችላለን። ለቲቪ በወር እስከ 640 ሺህ ብር እንከፍላለን። የቤተክርስትያን ኪራይ፣ የወንበር ኪራይ፣ የአገልጋዮች ክፍያና የሳውንድ ሲስተም የመሰሉ ወጪዎችም አሉ። 'ወንጌላይ' የተሰኘው መዝሙር ክሊፕህ፤ ይህንኑ መዝሙር መድረክ ላይ ስትዘምረውም እንቅስቃሴው የወላይተኛ ጭፈራ ነው። እንዴት ነው እንዲህ ፈጣሪ የሚመሰገነው? የሚሉ ሰዎች አሉ። እዩ ጩፋ፡ ጨፋሪዎች ናቸው ከእኛ የኮረጁት። የወላይታ ባህል ጭፈራ ምን እንደሆነ ሳላቅ ለእግዚአብሔር ጨፍሬአለሁ። በቤተክርስትያን ሰው የለመደው ሽብሸባ[ተነስቶ እያሸበሸበ] ስለሆነ ነው። ይሄኛው እንቅስቃሴ ለዘፈን፤ ያ ለእግዚአብሄር ተብሎ የተፃፈ ነገር የለም፤ ሁሉም የእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ እኛ ወደፊት የዘፋኞችን እንቅስቃሴ ሁሉ ለእግዚአብሔር ገቢ እናደርጋለን። አለባበስህ ለየት ያለ ነው የልብስ ዲዛይነር አለህ? እዩ ጩፋ፡ አዎ ዲዛይነሮቼ ግብፃዊያን ናቸው ልብሴ እዚያ ነው የሚሰራው።
news-47147898
https://www.bbc.com/amharic/news-47147898
ውክልናን በቪድዮ፡ የውክልና ሂደትን በ20 ደቂቃ
ኬብሮን ነዋሪነቱ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሲሆን ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቹ ውክልና ለመስጠት አስቦ ሂደቱን በአሜሪካን ሃገር ቢጀምርም ነገሮች እንዳሰባቸው ቀላል ሆነው አላገኛቸውም። በዚህ ምክንያት የተነሳም የውክልና አሰጣጥ ሥርዓቱን ለመቀየር ቆርጬ ተነሳሁ ይላል፤ ኬብሮን ።
ኬብሮን ደጀኔ ከአምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ጋር እንዳለውም አደረገው። የውክልና ሥርዓቱን በማዘመን የሚወስደውን ጊዜ ከወራት ወደ ደቂቃዎች ለማሳጠር ችሏል። እንዴት? ኬብሮን ደጀኔ 'ሲሊከን ቫሊ' በመባል የሚታወቀው የአሜሪካ ቴክኖሎጂ እምብርት ውስጥ 'ቪዲቸር' የሚባል ድርጅት ካቋቋመ አምስት ዓመት ሊሆነው ነው። አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የውልና ማስረጃን አሠራር ለማፋጠን ትልቅ ሚና ለመጫወት በቅቷል። በዛሬው ዕለት በ'ቪዲቸር' የተደገፈው የውክልና አሠራር በዋሺንግተን ዲሲ ባለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመርቋል። ለሕዝብ አገልግሎትም ሥራ ላይ እንዲውል ይፋ ተደርጓል። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና የተጓተተ የውክልና ሂደት ከሁለት ዓመት በፊት ነበር ከውክልና አሠራር ጋር ኬብሮን ግብ ግብ የገጠመው። በኢትዮጵያ ያለን የንግድ ተቋም ዘመድ እንዲያንቀሳቅስለት በማሰብ የውክልና ሂደቱን ቢጀምርም በካሊፎርኒያና በአካባቢው ውክልና የሚጽፍለትም ሆነ የሚያረጋግጥለት ማግኘት ሳይችል ቀረ። ከስድሰት ሰዓታት የአየር ጉዞ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ ሂደቱን አስጀመረ። ውክልና የመስጠት ተግባሩ ግን ቀላል አልነበረም። 11 የተለያዩ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቅ እንደነበር እንዲሁም በሕግ ባለሙያ አረጋግጦ ቢያንስ 40 ቀናት መጠበቅ ግድ እንሆነ ይናገራል። ከስንት ወጣ ውረድ በኋላ ኢትዮጵያ የደረሰው የውክልና ወረቀት ስህተት አለበት በመባሉ በድጋሚ ለማሠራት መገደዱንም ኬብሮን ይናገራል። እንደዚህ ዓይነት ችግሮች መኖራቸውን ከዚህ ቀደም ከብዙ ሰዎች ይሰማ የነበረ ቢሆንም በእርሱ ላይ ከደረሰበት በኋላ አሠራሩን ለመቀየር ቆርጦ እንደተነሳ ይናገራል። በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና 'ቪዲቸር' መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት የውልና ማስረጃን አሠራር ለመቀየርና 'ዲጂታላይዝ' ወይም 'አውቶሜት' ለማድረግም 'ቪዲቸር' ለተሰኘው የኬብሮን ተቋም ፈቃድ ተሰጠ። የሲሊከን ቫሊ ልጆች ትልቁን ኢትዮጵያዊ የመረጃ ቋት የመፍጠር ህልምን ሰንቀዋል እነ ፌስቡክ ግላዊ መረጃዎትን ያለአግባብ እንደሚጠቀሙበት ያውቃሉ? ለመሆኑ 'ቪዲቸር' ምንድን ነው? 'ቪዲቸር' ማለት የእንግሊዘኛውን 'ቪድዮ' እና 'ሲግኒቸር' (ፊርማ) ቃላት በማጣመር የመጣ ቃል ሲሆን ስሙ እንደሚገልፀውም እራስን ቪድዮ በማንሳት መፈረም ማለት ነው። "በብዕር ጫር ጫር የሚደረገው ፊርማ" የሰውን ደህንነት ይጠብቃል ብዬ አላምንም የሚለው ኬብሮን፤ አንድ ሰው ውክልና ለሚሰጠው ሰው በሰነዱ መስማማቱን እየገለፀ እራሱን በቪድዮ ይቀርፃል። ቪድዮውም በሰነዱ ይካተታል ስለዚህም ለማረጋገጥ ቀላል ይሆናል ሲል ያስረዳል። "ጥሩነቱ ማንኛውም ባለ ጉዳይ ካለበት ሆኖ መተግበሪያውን በስልክ በመጫን ቪድዮውን ቀርፆ መላክ መቻሉ ነው። ለጊዜው ግን በአሜሪካ ላሉ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነው የጀመርነው" በማለት ሂደቱን ያብራራል። "በመጀመሪያ ንግግሬን ከአምባሳደር ግርማ ብሩ ጋር ነበር የጀመርኩት ከዚያ በኋላ ከአምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ጋር ወደ ስምምነት አደረስነው። አምባሳደር ካሳም የቴክኖሎጂውን ሃሳብ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በመላክ ወደ ውሳኔ አደረሰው በማለት ወደ ሥራ እንዴት እንደገባ ያስረዳል። ከውጪ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ የሚላክ የውክልና ሂደት ምን ይመስል ነበር? 1) ወካይ በአቅራቢያው ባለ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማምራት የውክልና ሰነዱን ያጽፋል 2) ኤምባሲው ውክልናውን ተረክቦ ከገመገመ በኋላ ፊርማና ማህተም አስፍሮ ለአመልካች ያስረክባል 3) አመልካች ሰነዱን ከኤምባሲ ተረክቦ ወደ ፈጣን የፖስታ አገልግሎት ወይም ወደ ፖስታ ቤት በመሄድ ሰነዱን ለተወካይ ይልካል 4) ተወካይ ከፖስታ ቤት የውክልናውን ሰነድ ይረከባል 5) ተወካይ ሰነዱ በቆንሱላ ጽሕፈት እንዲረጋገጥ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ይወስዳል 6) በቆንሱላ ጽሕፈት ቤት ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ውልና ማስረጃ በመውስድ በሰነዶች ማረጋገጫ እንዲረጋገጥ ያደርጋል ይህ ሁሉ ሂደት በትንሹ ከ20 እስከ 40 የሥራ ቀናት ሊፈጅ ይችል እንደነበርና በ'ቪዲቸር' ግን ሙሉ ሂደቱ ወደ 20 ደቂቃ እንዲያጥር መቻሉ ተነግሯል። እስራኤል ዮሐንስ በቆንሱል ጽሕፈት ቤት ቢሮ ካሉት 2 ሠራተኞች መካከል አንደኛው ሲሆን "መተግበሪያው ለተጠቃሚም ሆነ ለእኛ በጣም ቀላልና ፈጣን ነው" በማለት የማረጋገጫውን ሂደት እንደሚያቃልል ይናገራል። በኢትዮጵያ የቪዲቸር አማካሪ የሆነችው ጺዮን ትርሲት አክሊሉ ከውጪ የሚመጡ ብዙ የውክልና ሰነዶች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩና ሂደቱን ለማፋጠን መሞከሩ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ትናገራለች። • ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች • ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም የሌለብዎት ሰአት መቼ ነው? የቆንሱላ ጽሕፈት ቤት 'ቪዲቸር' መሥራያ ቤት ውክልናን ከ40 ቀን ወደ 20 ደቂቃ "አንድ የቅርብ ጓደኛዬ በጋምቤላ የኮንስትራክሽን ሥራ ጀምሮ ነበር። ሥራውን ለማስፈፀም ውክልና መስጠት ፈልጎ ሂደቱን ካገባደደ በኋላ ለሚመለከተው አካል ቢያስረክብም የሰነዱን እውነተኛነት ማመን ባለመቻላቸው ለሦስት ሳምንታት ወደ መቶ ሠራተኛ ደምወዝ እየከፈለ መጠበቅ ግድ ሆኖበት ነበር። ይህ ልክ አይደለም። ብዙ ነገር ያስተጓጉላል። እኛም ይህን የማረጋገጫ ሂደት ቢበዛ ቢበዛ ወደ 20 ደቂቃ መቀነስ ነው የምንፈልገው" ይላል ኬብሮን። • ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መልዕክት ማጋራትን አገደ • ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ የሚመጡ የሙያ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው? "እያንዳንዱ የውክልና ቪድዮ ለተፈለገው ሰነድ ብቻ የሚሠራ ነው" የሚለው ኬብሮን ይህ አሠራር ወንጀለኞችን ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው ይላል። "ማንም ሰው የውሸት ፊርማ በሰነድ ላይ አስፍሮ ለማጭበርበር ሊሞክር ይችላል። ግን በቪድዮ መልክ እየታየ ማንም ለማጭበርበር አይደፍርም" ይላል።
41606727
https://www.bbc.com/amharic/41606727
ህመሙ እየከፋ የሚገኘው ዓባይ፡ ከጣና ሃይቅ እስከ ታላቁ ህዳሴ ግድብ
የዓለማችን ረዥሙ ወንዝ ከመታመም በላይ ህመሙ እየከፋ ነው።
እየተመናመነ የመጣውን ውሃ ለመጠቀም የሚደረገው ፉክክር በአካባቢው ሃገራት መካከል ግጭት ሊፈጥር ይችላል ክፍል 2 ፡የህዝብ ብዛት መጨመርና የአካባቢ ብክለት ሌሎቹ የዓባይ ስጋቶች ክፍል 3 ፡የዓለማችን ረጅሙ ወንዝ መፃኢ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? የህዝብ ቁጥር መጨመር ውሃውን እያቆሸሸው እና እያደረቀው ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥ ደግሞ መጠኑን እየቀነሰው ይገኛል። አንዳንዶች ደግሞ እየተመናመነ የመጣውን ውሃ ለመጠቀም የሚደረገው ፉክክር በአካባቢው ሃገራት መካከል ግጭት ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። በዓባይ ዙሪያ በሦስት ክፍሎች ከምናቀርበው ዘገባ፤ በመጀመሪያው ክፍል ወንዙ ስለገጠመውን ፈተና፣ ስለተፈጥሮ ሃብቱ እና ስለአካባቢው ህዝቦችን ዕጣ ፈንታ እንመለከታለን። ዝናብ ችግሩ የሚጀመረው ከወንዙ መነሻ ነው። የዓባይ ወንዝ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የውሃ መጠን በኢትዮጵያ ከሚጥለው ዝናብ ያገኛል። ከጣና ሐይቅ በስተደቡብ ከሚገኘው ጫካ ውስጥ የሚነሳው ጥቁር ዓባይ በመጠኑ እያደገ ይሄዳል። ከቪክቶሪያ ሃይቅ የሚነሳው ነጭ ዓባይ በበኩሉ አነስተኛ መጠን ያለው ውሃ ይዞ ካርቱም ላይ ከኢትዮጵያው ጥቁር ዓባይ ጋር ይቀላለቀላል። በኢትዮጵያ ዝናብ እንደዚህ ቀደሙ እየዘነበ አይደለም። ይህ ደግሞ ዓባይ ሙሉ ለሙሉ እንዲሞት ሊያደርገው ይችላል። ከረዥም የበጋ ወቅት በኋላ በየዓመቱ የሚኖረው አጭር የዝናብ ወቅት አንዳንዴ አነስተኛ ዝናብ ብቻ ይዞ ይመጣል። "ዝናቡ አሁን ይበልጥ የማይገመት ሆኗል። አንዳንዴ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ አነስተኛ መጠን ያለው የዝናብ ወቅት ይሆናል። መጠኑ ሁሌም የተለያየ ነው" ይላል የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ መምህሩና የአየር ንብረት ለውጥ ተመራማሪው ላዕከማርያም ዮሃንስ። የዓባይ ወንዝ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የውሃ መጠን በኢትዮጵያ ከሚጥለው ዝናብ ያገኛል ከባድ የሆነ የክረምት ወቅት ሲኖር ወንዙ በቢሊዮን ቶኖች የሚቆጠር ለም አፈርን ከኢትዮጵያ በየዓመቱ ይዞ ይሄዳል። ይህ ደግሞ ግድቦችን የሚገድልና አርሶ አደሮች የሚያስፈልጋቸውን ለም አፈር የሚያሳጣ ነው። ይህ ችግር በህዝብ ቁጥር በፍጥነት ማደግ ምክንያት ተባብሷል። የቤተሰብ መስፋፋትን ተከትሎ ሰዎች መኖሪያቸውን ለመቀለስ የሚረዳቸውን ቦታ እና ቁሳቁስ ለማግኝት ዛፎችን እየቆረጡ ነው። ከፍተኛ አደጋ የሚያስከትሉ ጎርፎችም በተደጋጋሚ መከሰት ጀምረዋል። የሰብሎች ምርታማነት እየቀነሰ እና የምግብ ዋጋ ደግሞ እየጨመረ ይገኛል። በዚህም ወንዞችን በመስኖ ከመጠቀም ይልቅ ዝናብ ላይ የተመሰረተ ግብርና ላይ የሚተዳደሩ የገጠር መንደሮች ወደ ድህነት እየተሸጋገሩ ይገኛሉ። አንዳንድ የገጠር ነዋሪዎች የግብርና ሥራቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ወደ ክልሉ ርዕሰ መዲና ባህር ዳር ወይንም በማደግ ላይ ወደምትገኘው የአገሪቱ መቀመጫ አዲስ አበባ ማቅናትን መርጠዋል። አብዛኛዎቹ ሰዎች ዝናቡ እንደቀድሞው ይሆናል በሚል ተስፋ ያገኙትን ውሃ በመጠቀም ህይወታቸውን ለመግፋት ተገደዋል። ለአንዳንድ ታዳጊዎች ግን ተስፋ አስቆራጭ ሆኗል። ቤተሰቦቹን በእርሻ ሥራቸው ለመደገፍ ትምህርቱን አቋርጦ ያለችውን ብስክሌት በመሸጥ አዲስ ምርጥ ዘር የገዛው የ17 ዓመቱ ጌትሽ አዳሙ በስደት ሜድትራኒያንን ስለማቋረጥ እያሰበ ይገኛል። "ቆም ብዬ ሳስበው ከቤተሰቤ ጋር መኖር እፈልጋለሁ። ነገር ግን ዝናቡ እንዲህ ሆኖ የሚቀጥል ከሆነ እዚህ ስፍራ መቆየት አልችልም" ይላል። አንዳንድ የመንደሩ ነዋሪዎች የግብርና ስራቸውን እርግፍ አድርገው ትተዋል የግድብ ውዝግብ ዓባይ ብዙ በተጓዘ ቁጥር ያለበትም ችግር እየጨመረ ይሄዳል። 30 ማይሎችን ያህል ከጣና ሃይቅ ከራቀ በኋላ አስደማሚውን የዓባይ ፋፏቴን አልፎ በጠመዝማዛው ገደላ ገደል ውስጥ ጉዞውን ይቀጥላል። ገባሮቹን ወንዞች ተጠቅሞ የሚያገኘውን ውሃ እየጨመረ ጉልበቱን እያጠናከረ በመሄድ ከከፍተኛ ቦታ የጀመረውን ጉዞ ወደ ዝቅተኛ አካባቢዎች ያደርጋል። ይህም እጅግ በጣም ቆንጆ፣ የተነጠለ እና ምናልባትም በጣም ያልተረጋጋው የውሃው መንገድ ይሆናል። የህዳሴው ግድብ ሰባት ጌጋ ዋት ኃይል ያመነጫል በአፍሪካ ትልቁ ከሆነው የኤሌክትሪክ ግድብ ጀምሮ እስከ ወንዙ አቅራቢያ የሚኖሩና መሬቶቻቸው በግብርና ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ትላልቅ የውጭ ባለሃብቶች ተሰጥቶባቸው እስከተፈናቀሉ ሰዎች ድረስ ብዙ ያልጠራ ነገር አለ። ከስፍራው ሆኖ መዘገብ ማለት የፈሩ ቃለመጠይቅ ሰጪዎችና ውስብስብ የሆኑ የፍተሻ ቦታዎች ያሉት የማዕድን ቦታዎችን እንደመጎብኘት ነው። "የማንናገራቸው ጉዳዮች እንዳሉ ልትረዳ ይገባል" ይላል በእንጅባራ የምግብ ቤት ባለቤት ሆነው ሳሙኤል። "እነዚህ ጥያቄዎች ችግር ውስጥ ሊከቱህ ይችላሉ" ሲል ያክላል። ንግግሩ ግነት የለበትም። ከቀናት በኋላ የደህነነት ሃይሎች የሆቴሌን ክፍል ወረው ማስታወሻ መያዣ ደብተሬን ብቻ ወስደዋል። በሌላ አጋጣሚ ደግሞ ስለተወረሱ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ለመዘገብ ስጓዝ ቻግኒ አቅራቢያ በሚገኝ የፖሊስ ፍተሻ ጣቢያ ላይ ወደ ኋላ እንድመለስ ተነግሮኛል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የህዳሴው ግድብ ሰባት ጌጋ ዋት ኃይል የሚያመነጭ እና ለበርካቶች ኩራት ከመሆን ባለፈ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የአሌክትሪክ ኃይል ያስገኛል ተብሎም ተስፋ ተጥሎበታል። ከታችኛው የውሃው ተፋሰስ ሃገራት አንዷ ሆነችው ግብጽ፤ ግድቡ የዓባይን ውሃ ይቀንሳል የሚል ስጋት አላት። አብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል በረሃማ ከመሆኑም በላይ በየዓመቱ የሚጥለው ዝናብ ጥቂት በመሆኑ፤ ሃገሪቱ 95 በመቶ የሚሆነውን የውሃ ፍላጎቷን ከዓባይ ታሟላለች። ምንም እንኳ ኢትዮጵያ እና ሌሎች የታችኛው የተፋሰሱ ሃገራት ህጋዊነቱን ቢቃወሙትም፤ እ.ኤ.አ በ 1959 የተደረሰው ስምምነት የዓባይን ውሃ ሙሉ ለሙሉ ለግብጽ እና ለሱዳን ሰጥቷል። ይህን ግን አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ጉዳይ የነበራቸው ሚና አነስተኛ በነበረበት በቅኝ ግዛት ዘመን ነው የተደረገው በሚል ነው የሚቃወሙት። እ.ኤ.አ በ 1959 የተደረሰው ስምምነት የዓባይን ውሃ ሙሉ ለሙሉ ለግብጽ እና ለሱዳን ሰጥቷል ከካይሮ የጦርነት ዛቻዎች እየተወረወሩ ሲሆን በሁለቱም በኩል ጠንካራ የቃላት ልውውጦች ነበሩ። ውሃን ምክንያት በማድረግ በአካባቢው ግጭት ቢከሰት፤ ይህ በጣም አስገራሚ ወንዝ ቀዳሚው ምክንያት ሊሆን ይችላል። "ሠላም ይሆናል? አይሆንም" ይላል ጣና ዳር በሚገኘው ባህር ዳር ተብሎ በሚጠራው ግሮሠሪ ቢራ ስጠጣ ያገኘሁት ሞሰስ የተባለ የባሕር ኃይል መኮንን። "ሁላችንም የጦር ግንባር ላይ እንደሆንን እንረዳለን። ውሃው፣ ግድቡም፣ ምርጡም መሬት እዚሁ ነው" ይላል። ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር እ.አ.አ በ1991 ከተለያየች በኋላ የባህር በር ባይኖራትም ጣና ሐይቅ ላይ ያላትን የባሕር ኃይል ተቋም ጠብቃ አቆይታለች። "ተቋሙ ወደፊት ሊጠቅመን ይችላል" ሲል ሞሰስ ይገልጻል። ክፍል 2 ፡የህዝብ ብዛት መጨመርና የአካባቢ ብክለት ሌሎቹ የዓባይ ስጋቶች ክፍል 3 ፡የዓለማችን ረጅሙ ወንዝ መፃኢ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? ተጨማሪ ፡ጣና ሐይቅ የተጋረጡበት ፈተናዎች
47664122
https://www.bbc.com/amharic/47664122
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፡ በእርግጥ ስልጠናው ከአደጋው ጋር ይያያዛል?
ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ግዙፍ አየር መንገዶች ብቻ ያላቸው እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላን ነው። ነገር ግን አውሮፕላኑ ባጋጠመው አንዳች ውሉ ያልታወቀ እክል ሁለት አሰቃቂ አደጋዎች ከገጠሙት በኋላ ለጊዜውም ቢሆን ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን ተደርጓል።
ባለፈው ጥቅምት ወር የኢንዶኔዢያ ላየን አየር መንገድ ንብረት የሆነ ተመሳሳይ አውሮፕላን ለበረራ ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ በከፍተኛ ፍጥነት ቁልቁል ወደ ባህር በመከስከሱ የ189 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል። ከዚህ አደጋ አምስት ወራት በኋላም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ መከተሉ የዓለም አቪየሽን ኢንዱስትሪን ከዚህ ቀደም ሆኖ በማያውቅ ደረጃ ንጦታል። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? ከአደጋው በኋላ ለምርመራ ወደ ፈረንሳይ ተወስዶ የነበረው የአውሮፕላኑ የበረራ መረጃ ማስቀመጫ የያዛቸው መረጃዎች በተገቢው ሁኔታ መገልበጣቸውን፣ ምርመራውን እያካሄደ ያለው ቢኢኤ ለጊዜው ያገኘውን መረጃ ለኢትዯጵያ አደጋ ምርመራ ቢሮ እንዳስረከበም ተዘግቧል። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚኒስትር በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያውና በኢንዶኔዢያው የአውሮፕላን አደጋዎች መካከል "ግልጽ መመሳሰል" እንዳለ ጠቁመዋል። የአውሮፕላኖቹ ስሪት፣ ለበረራ ከተነሱ ከደቂቃዎች በኋላ አደጋው መድረሱ፣ የአወዳደቃቸው ሁኔታና ገጥሟቸዋል የተባለው ሁለንተናዊ ችግር በእጅጉ መመሳሰል ሲታይ ለአሰቃቂዎቹ አደጋዎች መከሰት የአብራሪዎቹ ችግር ሳይሆን አዲሱ አውሮፕላን ምርትና ስሪቱ አንዳች ቴክኒካዊ እክል ሳያጋጥመው እንዳልቀረ ፍንጭ ሰጥቷል። • በቦይንግ 737 ማክስ ፈቃድ ላይ ምርመራ ሊደረግ ነው በተለይም የአሜሪካ የአቪየሽንት ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት (FAA) የቦይንግ ምርቶችን ደረጃና ጥራት በመቆጣጠርና በማጽደቅ ሂደት ላይ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ለቦይንግ አሳልፎ መስጠቱ ዓለምን አስደንግጧል። ባጋጠመኝ የፋይናንስ አቅም መመናመን የአውሮፕላኑ አምራች ራሱ የአዳዲስ አውሮፕላኖችን ብቃት በከፊል እንዲያረጋግጥ አድርጊያለሁ ሲል አምኗል፥ ባለሥልጣኑ ባሳለፍነው ሳምንት ለሲያትል ታይምስ የምርመራ ዘገባ በሰጠው ቃል። ለዚህም ነው ይህ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ያላቸው ሃገራት በአውሮፕላኑ ላይ ያለው ችግር ተጣርቶ መፍትሄን እስኪያገኝ ድረስ ከበረራ ውጪ እንዲሆኑ ያደረጉት። የአውሮፕላኑ አምራች የሆነችው አሜሪካም ለአውሮፕላኑ አገልግሎት ላይ መዋል የተሰጠውን ፍቃድ በተመለከተ ምርመራ እንዲደረግ አዛለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመገኛኛ ብዙኃን የኢትዮጵያው አየር መንገድ አብራሪ ይህን አውሮፕላን ለማብረር የሚያስፈልግን ተጨማሪ ስልጠና እንዳልወሰደ በመጥቀስ ያቀረቡት ዘገባ ከተለያዩ ወገኖች ቁጣንና ተቃውሞን አስከትሏል። • ሁለቱን የአውሮፕላን አደጋዎች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ ዘገባው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ለአየር መንገዱ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ አደጋው የደረሰበት አብራሪ ለዚህ አውሮፕላን ያስፈልጋል የተባለ በምስለ በረራ (ሲሙሌተር) የሚደረግ ልምምድ አላደረገም ሲል አስፍሯል። ይህን ልምምድ ለማድረግ ፕሮግራም የተያዘለትም በዚህ ወር መጨረሻ ነበር ይላል ዘገባው። ይህን ተከትሎ በተለይ ከኢትዮጵያዊያን በኩል ዘገባው ቦይንግን ለማዳን የተረደረገ ሴራ በሚል ቅሬታ እየቀረበበት ይገኛል። በተለይም ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ይህንን ዘገባ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ላይ ካጋራ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ አንባቢዎች ዘገባውን ክፉኛ ተችተዋል። ዘገባውን መሠረታዊ ቴክኒካል ችግርን ገሸሽ አድርጎ በአብራሪዎች ለማላከክ ቦይንግን ለማዳን የተደረገ ነውር አድርገው የቆጠሩት ጠቂት አይደሉም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ወልደማሪያም በአደጋው ስፍራ የምስለ በረራ ስልጠናና አደጋውን ምን አገናኛቸው? የኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ በቦይንግ 737 ላይ በቂ ልምድ ያላቸው ካፒቴኖች ማክስ ኤይት የተባለውን ዘመነኛ አውሮፕላን ለማብረር የተወሰነ ልምምድ ብቻ እንደሚያስፈልጋቸው ይጠቅሳል። ነገር ግን ቦይንግም ይሁን ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቶች የምስለ በረራ ስልጠና ማክስ-8ን ለማብረር እንደ ግዴታ አላስቀመጡም። ብዙዎቹ የአሜሪካ የዚህ አውሮፕላን አብራሪዎችም ቢሆኑ ከ737 አውሮፕላን ወደ ማክስ 8 አብራሪነት የተሸጋገሩት የአንድ ሰዓት ስልጠና በአይፓድ በመውሰድ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ስለምን የምስለ በረራ ስልጠና ጉዳይ ጎልቶ እንዲሰማ ተፈለገ የሚለው ለብዙዎች ግራ ሆኗል። በርካታ የተለያዩ በቦይንግ ኩባንያ የተሠሩ ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘገባውን "የተሳሳተ እና የተዛባ" መሆኑን ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። • "እናቱ ስታየኝ 'ልጄ ያሬድ ይመጣል' እያለች ታለቅስ ነበር"- በናይሮቢ የካፒቴኑ ጸጉር አስተካካይ ጨምሮም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አብራሪዎች አውሮፕላን አምራቹ ባወጠው እና በአሜሪካ የአየር ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተቀባይነት ባለው መንገድ ተገቢውን ስልጠና መውሰዳቸውን አረጋግጧል። በአቪዬሽን ጉዳዮች ላይ ዘጋቢ የሆነው ቃለየሱስ በቀለ "የአሜሪካ አብዛኞቹ 737 ማክስ አውሮፕላን ያላቸው አየር መንገዶች የምስለ በረራ መለማመጃ የላቸውም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ለስልጠናው የሚያገለግለው ይህ ዘመናዊ መሣሪያ ባለቤት ነው" ይላል። ምስለ በረራ (ሲሙሌተር) እጅግ ውድ ዋጋ የሚያወጣ ቢሆንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እነዚህን ሞዴል ማሰልጠኛዎች ቀደም ብሎ የመግዛት ባህል እንዳለው ብዙዎች ይመሰክሩለታል። ቃለየሱስ እንደሚለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማክስ ኤይትን በምስለ በረራ መለማመጃ ከጥር ወር ወዲህ ማሰልጠን የጀመረ ሲሆን አብራሪዎቹም በየስድስት ወሩ ልምምድ ያደርጋሉ፤ ይህን ልምምድ ተከትሎም ፈተና ይወስዳሉ። ይህ ለኢትዯጵያ አየር መንገድ አዲስ ነገር አይደለም በተጨማሪም ከ737 800 ኤን ጂ (ኔክስት ጄኔሬሽን) ከተባለው አውሮፕላን ወደ ማክስ 8 አውሮፕላን ሲኬድ ልዩነታቸው የተወሰነ ስለሆነ አብራሪዎች ልዩነቱን እንዲወስዱ ቦይንግ እንደሚመክር የሚናገረው ቃለእየሱስ፤ "ይህንን ስልጠና ደግሞ አደጋው የደረሰበት አውሮፕላን አብራሪ ወስዷል" ሲል ይናገራል። • ስለምንጓዝበት የአውሮፕላን አይነት እንዴት ማወቅ እንችላለን? ነገር ግን ከቦይንግ 737 ማክስ ቀደም ያለውን ስሪት ያበሩ የነበሩ አብራሪዎች በሁለቱ አውሮፕላኖች መካከል ያለው ልዩነት ጉልህ የሚባል ባለመሆኑ በምስለ በረራም ባይሆን በቀላል ስልጠና ክፍተቱን ማሟላት ይችላሉ። "ይህንን የሚለው ደግሞ እራሱ አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ነው። ቦይንግ ይህን ባይል ኖሮማ ልምምዱን ያላደረጉ ሁሉ ማክስን ማብረር አይችሉም ነበር" ይላል ቃለየሱስ። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ባወጣው መግለጫ ላይ በኢንዶኔዥያው አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ አስፈላጊ የሆኑ ተጨማሪ መመሪያዎች አብራሪዎቹ እንዲያውቁ መደረጉን አመልክቶ የመመሪያው ይዘት ሙሉ በሙሉ በስልጠና ማኑዋል፣ በኦፕሬሽን ዝርዝር መመሪያዎች እና በዕለት ተዕለት ሥራዎች ዝርዝር መመሪያዎች እንዲካተት አድረጌአለሁ ብሏል። የምስለ በረራ መለማመጃውን በተመለከተም አየር መንገዱ እንደሚለው "የቦይንግ 737 ማክስ ምስለ በረራ አሁን አከራካሪ የሆነውንና ለተከሰተው አደጋም ዋና ምክንያት ይሆናል ተብሎ የሚገመተውን የአውሮፕላኑ ሥርዓት መቆጣጠሪያ (MCAS) ላይ አለ የተባለውን ቴክኒካዊ ችግር ለማሳየት ታስቦ የተሠራ አይደለም" ይላል። ይህም ማለት የምስለ በረራ ስልጠና መውሰድና የቴክኒክ ችግሩ አራምባና ቆቦ ናቸው። • "በመጨረሻ ላይ ሳትስመኝ መሄዷ ይቆጨኛል" እናት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ የአውሮፕላኑ ደህንነት ጥያቄ ላይ በመውደቁ አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ፈተና ውስጥ ገብቷል። ድርጅቱ ይህንን አስቸጋሪ ሁኔታ ለማለፍ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ቢያሳውቅም ሁለት ሳምንት ለሚደርስ ጊዜ ጉዳዩ ከእራሱ ላይ ሊወርድ አልቻለም። ስለአደጋው ምክንያት የተሟላና ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በፈረንሳይ የተጀመረው ምርመራ መጠናቀቅ የሚኖርበት ሲሆን ይህም ከስድስት ወራት በላይ ጊዜን እንደሚጠይቅ ባለሙያዎች አሳውቀዋል። ይህ ውጤት ሳይገለጽ የአደጋ መላምት ማስቀመጥ የአቪየሽን ሥነምግባር አይፈቅድም። ያም ሆኖ ኩባንያዎች ህልውናቸውን ላለማጣት በእጅ አዙር የሚዲያ ጦርነት መክፈታቸው የሚጠበቅ ነው። ቃለየሱስ እንደሚለው የእራስን ስምና ዝናን ለመታደግ ሲባል "እውነት የሚመስሉ ወይም የተወሰነ እውነት ያላቸው ግን ደግሞ ብዥታን የሚፈጥሩ መረጃዎች በቀጣይነትም መውጣታቸው አይቀርም። ዋናው ነገር መሆን ያለበት ግን የተጣሰ ነገር አለ ወይ የሚለው ነው? በዚህም የቦይንግን የአሰራር መመሪያን ከጣሱ ቦይንግ ራሱ ዝም አይልም" ይላል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋውንና ሠራተኞቹን በተመለከተ የሚወጡት የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳሳዘኑት ገልጾ፤ "ምርመራው የዓለም አቀፍ የአደጋ ምርመራ ሥነ ሥርዓትና ሕጎች መከተል ስላለበት ውጤቱን በትዕግስት እየተጠባበቀ" መሆኑን ጠቅሶ የመገናኛ ብዙኃን ስለአደጋው መንስዔ በግምት ላይ የተመሠረቱ ምክንያቶች በመስጠት የተሳሳተ መረጃ እንዳያቀርቡ ጠይቋል።
news-45703284
https://www.bbc.com/amharic/news-45703284
ታምሩ ዘገዬ፡ በክራንች ተገልብጦ በመሄድ የ100 ሜትር የክብረወሰን ባለቤት
ታምሩ ዘገዬ ተገልብጦ በክራንች በመሄድ 100 ሜትርን በ57 ሰከንድ በማጠናቀቅ ከአራት ዓመታት በፊት በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ስሙ ሰፍሯል።
የአንደኛ ክፍል ተማሪ እያለ አንድ እንግዳ በቴሌቪዥን ቀርቦ ተመለከተ፤ ቀልቡን ሳበው፤ ራሱን በእንግዳው ቦታ አድርጎ ደጋግሞ አሰበው። ሲነሳም ሲቀመጥም፤ ሲበላም ሲጠጣም ይህንኑ ማሰላሰል ያዘ። ጉዳዩን ከራሱ ጋር በሚያደርገው የሃሳብ ትግል ብቻ ሊተወው አልሻተም። በእግሩ እያዘገመ ወደ ቴሌቪዥን ጣቢያው አመራ። • አቶ ጌታቸው አሰፋ የሀዋሳውን ጉባኤ ይታደማሉ? • ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ድጋፍ አገኘች ገና ሲቃረብ በር ላይ ለሚሰሩ ጥበቃዎች ምን እንደሚላቸው አላወቀም። ብቻ በውስጡ እንደ ደራሽ ጎርፍ የሚገፈትረው ህልም አለ። ማንም ሊያስቆመው እንደማይችል ውስጡ ነግሮታል። በሩ ጋር ሲደርስ ያው ደንብና የሥራ ኃላፊነት ነውና ጥያቄው አልቀረለትም- ማነህ? ከየት ነህ? ወዴት ነህ? የተለመዱ ጥያቄዎች። በጥያቄዎቹ አልተደናገጠም። በጨዋ ደንብ አስረዳቸው። እንዲገባም ፈቀዱለት። ደስታው ወደር አልነበረውም። ወደ ጣቢያው እንደገባ ከአንድ ጋዜጠኛ ጋር ይተዋወቃል። "ምን ሆነህ ነው የመጣኸው?" ሲሉ ይጠይቁታል። " ችሎታየን ለማሳየት ፈልጌ ነው!"ሲል በጉጉት ይመልሳል። "ምን ዓይነት ችሎታ ነው ያለህ?" በዝርዝር አስረዳቸው። "አሳየና! " ይሉታል። የት ላይ እንደሚያሳያቸው ቦታ ለመምረጥ ዙሪያውን ማማተር ጀመረ። በርግጥ በቴሌቪዥን መስኮት ያየው ሰው በእጁ ተገልብጦ በመሄድ 21 የፎቅ ደረጃዎችን በመውረድ ነበር ተመልካቹን አጃኢብ ያሰኘው። ዙሪያውን ገልመጥ ገልመጥ ብሎ ተመለከተ በወቅቱ የነበረው የቴሌቪዥን ጣቢያ ቢሮ 12 ፎቅ ብቻ ነበረው። 'ከሰውየው የበለጠ መስራት እችላለሁ' እያለ ከቤቱ ቢወጣም ችሎታውን የሚሳይበት ቦታ አነሰበት፤ ግራ ተጋባ። "ግድ የለም አሳየን" አሉት ግራ እንደተጋባ የተረዱት ጋዜጠኞቹ። በደስታ እየቦረቀ በወቅቱ ጣቢያው ያለውን 12 ፎቅ በእጁ ተገልብጦ ወረደ። "ያኔ በቴሌቪዥን የተመለከትኩትና በድንቃ ድንቅ መዝገብ ስሙ የተጻፈው ግለሰብ 21 ፎቅ ነበር የወረደው፤ ጣቢያው ከዚያ በላይ ፎቅ ቢኖረው እኔም ከ12 ፎቅ በላይ የመሄድ አቅሙ ነበረኝ" ሲል ያስታውሳል። • «ማስተር ፕላኑ ተመልሶ ይመጣል» አቶ ኩማ ደመቅሳ • «የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ አሁን አሁን ብዙዎች በእግር ቀስ እያሉ ለመውረድ እንኳን ተስኗቸው 'አሳንሰር' የሚያዙለትን ደረጃ ታምሩ ግን እግሮቹን ወደላይ አንጨፍርሮ በእጆቹ የእግር ያህል ተራመዳቸው። ሲመለከቱት የነበሩት ጋዜጠኞችም መዳፋቸውን አፋቸው ላይ ጫኑ፤ ተደመሙ። ከዚያም እርሱን በጠራው የቴሌቪዥን መስኮት እሱም ከተመልካች ጋር ተዋወቀ። ህልሙን የማሳካት ፍላጎቱም እያየለ መጣ - ታምሩ ዘገዬ። "በተፈጥሮዬ በእጄ በመሄድ የሚያክለኝ የለም" ታምሩ ትውልዱ ሰሜን ወሎ ላሊበላ አካባቢ በሚገኝ ጋዝጊብላ ቀበሌ ሲሆን ከአካል ጉዳት ጋር ነው የተወለደው። ባጋጠመው ጉዳት ሳቢያ ሁለቱን እግሮቹን ያለ ክራንች መጠቀም አይችልም። የተወለደበት አካባቢ ገጠር በመሆኑ በወቅቱ ማህበረሰቡ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያን ያህል ግንዛቤው አልነበራቸውም። እንኳንስ ስለ ህክምናና ቴክኖሎጂ፤ መኪና እንኳን ማየት ብርቅ ነበር ይላል። ይህም በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አካል ጉዳተኛ መሆኑ ፈተናውን አባብሶበታል። የገጠመውን ችግር ከባዕድ አምልኮና ከእርግማን ጋር ያያይዙታል። ወላጆች በልጆቻቸው የሚያፍሩበትና የሚሳቀቁበትም አጋጣሚ ብዙ እንደሆነም ይናገራል። ይህም ልጅነቱን ፈታኝና ጎዶሎ አድርጎበታል። ይሁን እንጂ ነገሮችን ወደ ቀልድና መዝናኛነት መለወጥ የሚቀናው ታምሩ ውሃ ለመቅዳት አልያም ከብት ለመጠበቅ ወደ መስክ ሲሄዱም ሆነ ሲመለሱ ዳገቶችን ተገልብጦ በእጁ በመራመድ ጓደኞቹን ያስደምማቸው እንደነበር ያስታውሳል። ፈተናዎቹን በሳቅ ለማለፍ ይሞክራል። "በተፈጥሮዬ በእጄ በመሄድ የሚያክለኝ የለም፤ ተራራውን ለመውጣት ጤነኞች በእግራቸው ሲሄዱ፤ እኔ ግን በእጄ ተገልብጨ ተራራውን እወጣ ነበር" ይላል። የቄስ ትምህርቱን እስከ ቅኔ ድረስ ተከታትሏል። ከዘመናዊ ትምህርት ጋር የተዋወቀው ግን ዘግይቶ በ16 ዓመቱ ነበር። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታተለ። በኢንፎርሚሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም በቱሪስት በማስጎብኘት (Tour Guide) ዲፕሎማውን አገኘ። አዲስ አበባ በሚኖርበት ጊዜም ከጉዳቱ ያገግም ዘንድ የእግር ቀዶ ጥገና አድርጎ ነበር። ቢሆንም ሙሉ በሙሉ እግሮቹን መጠቀም ባያስችለውም ክራንች ግን አልከለከለውም። ጥያቄ የወለደው ህልም ይህ ሁሉ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ በአእምሮው የሚያብሰለስለው ጉዳይ አልጠፋም፤ ይባስ ብሎ አቅጣጫውን ለወጠ። ጥያቄዎች እየተግተለተሉ በአዕምሮው ይመላለሱ ጀመር። "ለምንድን ነው ሰዎች በክራንች እያነከሱ የሚሄዱት?" የሚል ጥያቄውን ከቂላቂልነት የጣፉትም ነበሩ። እርሱ ግን የምሩን ነበር። "ለምን በክራንቹ ላይ ተገልብጨ በእጄ አልሄድበትም? አልኩ" የሚለው ታምሩ ገጠር በሚኖርበት ጊዜ ተገልብጦ በእጁ የሚሄደውን ልምዱን ማዳበር ፈለገ። ውሳኔው ራሱን ለማዝናናት፣ ለመቀለድ፣ ፌስቡክ ላይ ፎቶውን ለመለጠፍ ሲል እንጂ በዚህ መልክ ለዚህ ደረጃ እበቃለሁ ብሎ ግን አላሰበም። እግሩን ቢያመውም ሙከራውን አጠናክሮ ቀጠለ፤ እየወደቀ ተነሳ ፤ ደጋግሞ ሞከረው ከዚያም እግሮቹን ወደ ላይ ዘርግቶ ክራንች ላይ ተገልብጦ በእጁ መቆም ሆነለት። • አቶ መላኩና ጄነራል አሳምነው ለማዕከላዊ ኮሚቴ ተመረጡ • ስለአዲሱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጥቂት እንንገርዎ እንቁላል ቀስ በቀስ በእግሩ ይሄዳል እንደሚባለው በክራንቹ ላይ መቆም ከቻለ የማይራመድበት ምንም ምክንያት እንደሌለ ራሱን አሳመነ። ልምምዱንም በተንቀሳቃሽ ምስል ቀርፆ አስቀመጠ። በቴሌቪዥን መስኮት ከተመለከተው እንግዳ የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ…የሚለው ቃል በአዕምሮው ይንሸራሸር ያዘ። በርሱ ችሎታ በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ የሰፈሩ ሰዎች እንዳሉ ለማየት መዝገቡን አገላበጠ። በእርሱ ችሎታ የተመዘገበ አለመኖሩንም አረጋገጠ። ይህንኑ ለማድረግ ተግቶ መስራቱን ቀጠለ። በእጁ ተገልብጦ ደረጃዎችን በመውረድና በመውጣትም ብዙዎችን አስደነቀ። በክራንች ተገልብጦ ወደ 70 ሜትር በመሄድ ችሎታውን አሳደገ። በሥራ አጋጣሚ ያገኛቸው ሰዎችም እርሱን በማስተዋወቅ የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ እንደነበር ይናገራል። ማስታወቂያ አስነገሩለት ፤ የሚዲያ ሽፋንም ማግኘት ጀመረ። የስኬት ጎህ ሲቀድ በወቅቱ የነበሩት የሰርከስ ደብረብርሃን አሰልጣኝ ሥራውን ስለወደዱለትና አካል ጉዳተኞችን ማሳተፍ በሚለው መርህ የሰርከስ ቡድኑን መቀላቀል ቻለ። በዚያ ቆይታውም የተለያዩ ትዕይንቶችን ከቡድኑ ጋር ያቀርብ ነበር። 14 ከሚሆኑትና የተለያየ ችሎታ ካላቸው የሰርከስ ቡድኑ አባላት ጋር በመሆን 'ካርጎ' በሚል የሰርከስ ትርኢት ለሦስት ወር ያህል ለማሳየት ወደ ስዊድን ተጓዙ። " ካርጎ ያልነው ብዙ አፍሪካውያኖች በኮንቴነር ተጭነው ወደ አውሮፓና ሌሎች አረብ አገራት ይሄዳሉ፤ ይሁን እንጂ በኮንቴነር ውስጥ ታሽገው እንደ ዋዛ የሚሄዱት ስደተኞች የራሳቸው ችሎታና ብቃት እንዳላቸው ለማሳየት ያለመ በመሆኑ ነው " ይላል። • በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች • ኤርትራ ካሳ ጠየቀች በስዊድን በነበራቸው ቆይታም ብዙ አድናቆትን እንደተቸራቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታው ነው። ይሁን እንጂ "በተለያየ ችግር ምክንያት ከአሰልጣኜ ጋር አልተስማማሁም ነበር" የሚለው ታምሩ ወደ ጀርመን አቅንቶ ጥገኝነት ጠየቀ። በጀርመን ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ አግኝቶ ኑሮውን መሠረተ። በሥራው ምክንያት ብዙ አገራት እንደተጓዘ የሚናገረው ታምሩ ጀርመን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆኑን ይናገራል፡፡ ይህም ህልሙን ዳር ለማድረስ ሁኔታዎችን ምቹ እንዳደረገለት ይናገራል። የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ አድራሻ ፈልጎ የተቀረፀውን ተንቀሳቃሽ ምስሎች ላከላቸው፤ እነርሱም ወደዱት። ጥረቱና ህልሙ ተሳክቶለት ከአራት ዓመታት በፊት በክራንች ተገልብጦ 100 ሜትርን በ57 ሰከንድ በመሄድ በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሙን አሰፈረ። ወደፊት ትዝ ሲል ታምሩ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን አግኝቷል። ከሽልማቶቹ መካከልም ወርልድ ሪከርድ አሲስታንስ (ASSIST WORLD RECORDS) እና ወርልድ ሪከርድ አካዳሚ (world record academy) ይጠቀሳሉ። በራሱ ተይዞ የቆየውን የራሱን ሰዓት ለማሻሻል ተግቶ እየሰራ ይገኛል። አሁን ባለው ብቃቱም 100 ሜትሩን ከ45- 50 ባሉት ሰከንዶች መጓዝ እንደሚችል ይናገራል። ከዚህ ባሻገርም ሌሎች ያልተለመዱ ሥራዎችን ለማስመዝገብ በልምምድ ላይ ይገኛል። በእጆቹ ተገልብጦ 50 ፑሽ አፕ በመሥራት ልምምዱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ታምሩ በአሁኑ ሰዓት ጀርመን ባየር ኑረምበርግ የሰርከስ አርቲስት በመሆን ሕይወቱን እየመራ ነው። ያለፈበት የሕይወት መንገድ አስተምሮታልና የአካል ጉዳተኛ ማህበር የመመስረት እቅድ አለው፤ በተለይ ከ 5- 18 ያሉና ትምህርት ያላገኙ አካል ጉዳተኛ ህጻናትን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ማህበር የመመስረት ዕቅድ ይዟል። ከሚኖርበት ጀርመን ሆኖ የአካል ጉዳትን የሚረዳ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለማድረግ ሃሳብ አለው። አካል ጉዳተኛው ታምሩ በክራንች ተገልብጦ በመሄድ በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሙ ሰፍሯል
45899604
https://www.bbc.com/amharic/45899604
ዛሚ ሬዲዮ ይዘጋ ይሆን? ከሜቴክ ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት አቶ ዘሪሁን ተሾመ ይናገራሉ
በሃገር ውስጥ ቀዳሚ ከሆኑት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነው ዛሚ 90.7 በችግር ውስጥ እንደሆነና ሊዘጋ እንደሚችል በስፋት እየተወራ ነው። በዚህና ጣቢያውን በሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑትን አቶ ዘሪሁን ተሾመን አነጋግረናል። የፋይናንስ ችግር አጋጥሟችኋል እየተባለ ነው
ምን እኛ ብቻ ነን እንዴ፤ አገርም ችግር አጋጥሟታል እኮ! እንዴት? ኢንደስትሪያል ፓርኩም ኢንቨስተር ካልተገኘ ቆርቆሮ ነው አይደለም እንዴ? የአገር ኢኮኖሚው ቀዝቅዟል። የአገር ኢኮኖሚ ከቀዘቀዘ የአንዳንድ ሴክተሮችም ኢኮኖሚ ይቀዘቅዛል። ሁለተኛው በየትኛውም የቢዝነስ [ሽክርክሪት] ውስጥ እኛ አገር ብርቅ ሆኖ ነው እንጂ መነሳት፣ መውደቅ፣ መሞት፣ እንደ አዲስ መፈጠር ያለ ነው። ስለዚህ ችግር አጋጥሞናል እያሉኝ ነው፣ አቶ ዘሪሁን? ቆየኝ...ቆየኝ! እነዚህ የተባሉት ነገሮች ሁሉ እውነት ናቸው ቢባሉ ሊገርም አያስችልም፤ ግን እንደዜና ሊቀርብ ይችላል። የሚገርም ነገር እና ዜና የሚሆን ነገር ይለያያል። ስለዚህ ቢቢሲም የሚገርም ዜና ብሎ ሳይሆን ምናልባት የአገሪቱ ኢኮኖሚ የተለያዩ ሴክተሮችን 'አፌክት' እያረገ ነው በሚል ሊቀርብ ይችላል። ስለዛሚ ሬዲዮ ትኩረት አድርገን እናውራ፣ አቶ ዘሪሁን? ልመጣልህ ነው! ስለዛሚ እናውራ ከተባለ ዛሚ በሠራተኛ ደረጃ የዘገየ ደመውዝ የለም። የዘገየ ደሞዝ ቢኖር የዚህኛው ወር፣ እሱም የዘገየው ሁለት ቀን ነው። ስለዚህም ሁልጊዜ ወር በገባ በ30 እንከፍላለን። የአሁኑ ወር ላይ ወር በገባ በ30 ሳይሆን በ2 እና በ3 ተከፈለ። ምክንያቱም ደመወዝ የምንከፍለው ከምናገኘው የማስታወቂያ ገቢ ነው። ከምናገኘው የማስታወቂያ ገቢ የምንሰበስበው ደግሞ ማስታወቂያ [አምጪዎች] ሲከፍሉን ነው። እሱን በጊዜው ሊከፍሉን አልቻሉም። ደንበኞቻችን ናቸው። ስለሆነም እነሱን መጠበቅ ነበረብን። ያም ሆኖ ግን ተወጥተናል። በአጋርነት በጣቢያችሁ የሚሠሩትም እየሸሹ ነው የሄደው ኢትዯፒካሊንክ ነው። 6 ዓመት እኛ ጋር ቆይቷል። የራሱ ሬዲዮ ለመጀመር አሳብ አለው። እስከዛ ድረስ ለመሟሟቅ ወደ ፋና ሄጃለሁ ብሏል። ይሄ ምርጫቸውን እኛ ልናቆመው አንችልም። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወታደሮቹ ድርጊት ተበሳጭተው እንደነበር ተናገሩ • "ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው" ማስታወቂያ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ የገቢ ማነስ ሊሆን ይችላል፤ ቁጭ ብላችሁ ተነጋግራችኋል? አውርተናል። በቃ ልንሄድ ነው ምናምን ብለው ነግረውኛል። ከፋና ጋር በፊት ባለመግባባት ነው የተለያዩት። አሁን የይቅርታና የመደመር ዘመን ስለሆነ ይቅርታና መደመር አግኝተው ሄደው ሊሆን ይችላል። (ሳቅ) እሱም የኔ ችግር አይደለም። ምርጫቸውን ግን አከብራለሁ፡፡ ወዳጆቼ ናቸው። የ"ዛሚ ክብ ጠረጴዛ"…"ቆይታ ከሚሚ ስብሐቱ ጋ" ተቋርጧል እየተባለ ነው። የ"ዛሚ ክብ ጠሬጴዛ" መቼ ነው የተቋረጠው የሚለውን እናንተ ፈትሹ። አልተቋረጠም ነው የሚሉኝ፣ አቶ ዘሪሁን? አልተቋረጠም ሳይሆን ላስረዳህ። የ "ቆይታ ከሚሚ ስብሐቱ" ፕሮግራም ሚሚ አገር ውስጥ የለችም፤ ወደ ውጭ ሄዳለች። ለምን ሄደች? ለግል ጉዳይ ሄደች። የግል ጉዳይዋ ምንን ይመለከታል? ራሷን ማስደሰት ሊሆን ይችላል፤ መታከም ሊሆን ይችላል መብቷ ነው። አንደኛው ይሄ ነው። ይሄም ከሆነ በኋላ እሱን ለመተካት ሞክረናል። የሞከርነው ቤት ውስጥ ባሉ ጋዜጠኞች ነው። ስለሆነም አንድ ሳምንት ይቀርባል፤ አንድ ሳምንት አይቀርብም። እንደዚህ እያለ ሄዷል። በአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ ሁሉ ነገር ቢቀጥል በጣም አሪፍ ነው ቢቻል። እረፍት ሲወጡ የሚተካቸውና የእነሱን ካሊበር [ቁመና] የሚመጥን ሰው ቢኖር ሳይቋረጥ ቢሄድ አሪፍ ነው። • "የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከተለው ዲፕሎማሲ ቀለም አልባ ነው" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ ይሄ [ክስተት] የተገጣጠመበት ሁኔታ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መጥቶ ነበር። አቧራ በአቧራ ነው። ማጨብጨብ ነው። ወዴት ነው የምንሄደው? እንዴት ነው የምንሄደው? ከጥቅል ነገሮች ውጭ ምንም ነገር የለንም። ስለሆነም በእንደዚያ ዓይነት ፕሮግራሞች ላይ የሚቀርብ ቀጥተኛ ንግግሮች፣ ዜጋ የሚሳተፍበት መድረክ ነው የሚሚ ፕሮግራም። ማንም የፈለገውን የሚያወራበት ላይቭ ነው። "ዊ ዲዲንት ዎንት ቱ ቴክ ዘ ሪስክ" [ኃላፊነት መውሰድ አልፈለግንም]። በአንድ በኩል ለውጥ አለ ብሎ ተስፋ ያደረገውን ኅብረተሰብም እና ለውጥ አለ ብሎ ያመነውንም የዚህች አገር ገዢ መደብ ምንድነው ለውጡ ብሎ ግልፅ ባለዳረገበትም፤ እሱን ኮንትሮል የሚያደርግ መልስ የማይሰጥ ተሳታፊ የሚኖርበት መድረክ ላለመፍጠር ነው፡፡ ምን ማለትዎ ነው አቶ ዘሪሁን? ግልጽ ያድርጉልን። ሰዎች ነጻ ሆነው አየር ላይ እንዲናገሩ ትክክለኛጊዜው አሁን አይደለም፤ የጠራ ነገር የለም ነው የሚሉት? አላልኩም! አላልኩም፤ ሰዎች በግልጽ መናገር ይችላሉ። ሰዎች በግልጽ ተናገሩ ማለት ግን የሚናገሩትን በሙሉ ያውቃሉ ማለት አይደለም። አንድ ሚዲያ ላይ የሚተላለፍ ነገር በእንዲህ ዓይነት ወደ ግራ ይሂድ ወደ ቀኝ፣ ወደፊት ይሂድ ወደ ኋላ በማይታወቅ ሁኔታ ላይቭ ከፍተህ እሱን የምታስተናግድና አንጻራዊ በሆነ ደረጃ አቅሙ አላት የምትላት ሆስት በሌለችበት ከፍቶ መልቀቅ አንድም ማምታታት ነው። ሁለተም ማዘባረቅ ነው። ሦስትም መደበላለቅ ነው። ስለሆነም... ይቅርታ ግን፤ ይህን ፕሮግራም መምራት የሚችሉት ወይዘሮ ሚሚ ብቻ ናቸው እንዴ? ናቸው። ቆይታ ከሚሚ ስብሀቱ ጋ ነው የሚለው። ከእሷ በፊት የነበረችው የምትችል መስታወት ነበረች። መስታወት ደግሞ ለቃለች። ከዚያ ውጭ ያሉት አዳዲስ ናቸው። መቼም አንተ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ነህ። ስቲቨን ሳከርን የምትተካው ዘይናብ በዳዊ ናት። ሌላ ማንም አይተካም። ስለዚህ ባለቤትዎ ወይዘሮ ሚሚ እስኪመለሱ ድረስ ያ ቦታ ክፍት ነው የሚሆነው? በተቻለ መጠን እኮ ተሞክሯል። ሌላ የምትጠይቀኝ ጥያቄ ካለ ጠይቀኝ። አዎ ሚሚ ትመለሳለች፤ አንድ። ፕሮግራሙ ይጀምራል፤ ሁለት። ጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ ይጀምራል? አዎ ይጀምራል። መቼ? የሚቀጥለው 15 ቀን። ከዚያ በኋላ ሚሚ ትመጣለች? አዎ ትመጣለች፡፡ ዛሚ ይዘጋል ወይ? አይዘጋም። በፋይናንስ እጥረት? አይዘጋም። ፋይናንስ ችግር ግን የገጠማችሁ ይመስላል፤ እንዴት ነው የምትወጡት? ቢበዛ የምናደርገው ስታፍ እንቀንሳለን። ካልቻልን። ጋዜጠኞቻችሁ ቁጥራቸው ስንት ነው? ተመናምነዋል እየተባለ ነው አሁን ላይ? በግምት ወደ 6 አለን። በቅርቡ ሠራተኛቀንሳችኋል? እኛ ቀንሰን ሳይሆን ራሳቸውም የሄዱ ልጆች አሉ። በነገራችን ላይ ዛሚ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ሁሉም ጣቢያ ላይ አሉ። አሀዱ ብትሄድ የእኛ ልጆች አሉ። የጋዜጠኝነት ብኩርናቸውን ከእኛ ጋር የቀደሱ። ሸገር ብትሄድ አሉ። ፋና ብትሄድ አሉ… ከሰሞኑ ችግር ጋር በተያያዘ የቀነሳችሁት ሠራተኛ ግን የለም? አንድ ነገር ልንገርህ። ዛሚ ዛሚን መዝጋት ካለበት በሶሻል ሚዲያ ስለተወራ አይዘጋም። ዛሚ ዛሚን አይዘጋም። በሦስትም ሰው በአራትም ሰው ከዚያ ውጭ ያለውን በአጋር መሙላት ይቻላል። ስለዚህ የፕሮግራም ትኩረታችን አስተካክለን አንድ ነገር ማድረግ እንችላለን። አማራጩ ክፍት ነው ማለቴ ነው። ዛሬ ላይ ካንተ ጋር እየተነጋገርኩ ዛሚ እራሱን ለመዝጋት እቅድ የለውም። እራሱን አይዘጋም። ሊዘጉት የሚሞክሩ ካሉ አትችሉም ይላቸዋል። ከቻሉ ደግሞ ያኔ እናያለን። ችግር ላይ ያላችሁ ይመስላል። ጫና እየደረሰባችሁ ይሆን እንዴ? ከመንግሥት አካባቢ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ? እስካሁን ድረስ ከአዲሱ መንግሥት ጋር በጫናም በፍቅርም የተገናኘነው ነገር የለንም። ከድሮውም ጋር ብዙ የለንም። ጫና የነበረብን ባለፈው ጊዜ ነው ከብሮድካስት ባለሥልጣን፤ እሱ ደግሞ የሚታወቅ ነው። ስለዚህ ምነም ጫና አልደረሰባችሁም? መንግሥትነት ግን በሚገርምህ ደረጃ እኮ ቢሮ የያዘ ብቻ አይደለም። ቢሮ የያዘውንም እኔ ነኝ ባለቤቱ የሚልም ሊመጣ ይችላል። ምናልባት ሶሻል ሚዲያ ላይ [ዛሚ ሊዘጋ ነው] ያ መረጃ አለን የሚሉ ሰዎች ከዚያ አካባቢ የመጡ ከሆነ አንተ አጣራቸው። አሁን ባለው የለውጥ ሁኔታ ይሄ ጣቢያ ምቾት የማይሰጣቸው ሰዎች ጫና ያደርሱብናል ብላችሁ ትሰጋላችሁ? ለምን እንሰጋለን? ትናንትም የማይወዱን ሰዎች ነበሩ። ዛሬም የማይወዱን ሊኖሩ ይችላሉ። ትናንትም የሚወዱንም ነበሩ፤ ዛሬም የሚወዱን አሉ። በተደራጀ መልኩ መንግሥት ሆነው ይሄንን የሚሞክሩ እስካሁን ድረስ በፊት ለፊት ያገኘናቸው የሉም። ከመጡ ደግሞ እንደ አመጣጣቸው ስማቸውን ጠርተን እንናገራለን። ሜቴክ ዋንኛ ደጋፊያችሁ ነበር ልበል? እንኳን ይሄንን ነገር ጠየቅከኝ። በደንብ ስማ። የሚገርም ብዥታ አለ። እስከዛሬ ተናግሬው አላውቅም ይሄንን ነገር። አንደኛ! እኛ ከሜቴክ ጋር ግንኙነት ነበረን? አዎ። ሁለት፤ ምን ዓይነት ግንኙነት ነበረን? ሜቴክ ለዛሚ ሬዲዮ ጣቢያ በብር የሚቆጠር አንድ ብር፣ አ...ንድ ብ…ር ሰጥቶ አያውቅም። ትሰማኛለህ? አ…ንድ ብር! እኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ ጣቢያ ነበረን፤ ስለሆነም ከሜቴክ ጋር የነበረን የዓይነት ልውውጥ ነው። የዓይነት ልውውጥ ምንድነው በለኝ፤ ሜቴክ ጄኔሬተር ሰጠን። ምክንያቱም ፉሪ ላይ ከፍተኛ የኃይል መቆራረጥ ችግረ ነበረብን። ገዝተን የነበረን አቅሙ አነስተኛ የሆነ ጄኔሬተር ተቃጠለ። በ2007 ዓ.ም ማለት ነው። ስለሆነም እኛ የሜቴክን ማስታወቂያዎች እናስተላልፍ፤ እናንተ ጄኔሬተር ስጡን፤ በሰዓት ማስታወቂያ የምናስተላልፍበት ዋጋ ይኸውና፤ ይሄ ጄኔሬተር በዚህ ወቅት የሚያወጣው ዋጋ ይኸውና፤ ስለሆነም በአገልግሎት ልውውጥ እናጣጣው ተባባልን። አ…ንድ ጄኔሬተር ነው ሜቴክ የሰጠን። ከዚያ ውጭ አስክሜቴክ፤ አስክ ማንንም ሰው ለዛሚ ፐብሊክ ኮኔክሽን ሜቴክ ይሄንን ሺህ ከፈለ የሚል ካገኘህ ይዘህ ና። ለአንድ ጄኔሬተር ስንት የአየር ሰዓት አገኙ? 162 ሰዓት! ኢንፋክት አሳልፈን ሰጥተናቸዋል። ሌላ ጥያቄ ካለህ ጠይቀኝ ከቀድሞው የደኅንነት መሥሪያ ቤት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አልነበራችሁም? ሊዘጋ ነው ከሚል ጀምረህ ነው አሁን ይህን የምትጠይቀኝ፣ አይደል? ቢኖረን ኖሮ እስካሁን ሳይወጣ የሚቆይ ይመስልኻል? አንተው መልሰው፤ ቢኖረን ኖሮ እስካሁን ዝም የሚባል ይመስልኻል? የለንም። አልነበረንም። እንደ ማንኛውም አንተ ዛሬ ከማንም መረጃ እንደምትሰብስበው እኛም በጊዜው ከማንም መረጃ እንሰበስባለን፤ ከማንኛውም መረጃን እንቀበላለን፤ እሱም የኢትዮጵያ ደኅንነት መሥሪያ ቤትን ይጨምራል፡፡ ዕድሉ ካለን ነገም እንወስዳለን። ዛሚ ከዐብይ በፊት ከነበረው አመራር ጋር በቅርብ የሚሞዳሞድ ጣቢያ እንደሆነ ነው የሚነገረው፤ አሁን ደግሞ ሥልጣን ላይ ያሉት ዛሚ በብዛት ሲተቻቸው የነበሩ ናቸው፤ እነሱን እየተቻችሁ ትቀጥላላችሁ? ምንድነው የደገፍነው ቆይ እኛ…? ዛሬ ላይ በሥልጣን ላይ ያሉ ባለሥልጣኖቻችንን እነሱንም የሚደግፉ፣ በጥቅምም በሌላ መልኩም የሚደግፉ ሰዎች ካሉት ውጭ ምን አልን? ማለቴ ሕገ መንግሥት አለ በዚች አገር፤ ሕገ መንግሥት ይከበር፣ የሕግ የበላይነት ይከበር፣ ብጥበጣ አይበጀንም፣ ሰዎች አይገዳደሉ ነው ያልነው፤ አይደለም እንዴ? ዛሬም እሱ ነው እኮ ጩኸቱ…። አዎ ይሄ ከሆነ መለኪያው እንደ ሁሉም ሰው ደጋፊ ነን ማለት ነው። ከዚያ ውጭ ግን አገሌ ከፍሎን አገሌ ሰጥቶን... ማለቴ እኛ እቃ አይደለንም እኮ። ስለዚህ ስናጠቃልለው አቶ ዘሪሁን፤ የፋይናንስ ችግሮች የሉባችሁም፤ ቢኖሩም አዲስ ነገር አይደለም። ስፖንሰር ክፍያ መዘግየት ካልሆነ ስፖንሰር መዘግየት፣ ስፖንሰር መቀነስ፣ የፋይናንስ ችግር አዎ አሉብን። አጋጥመውናል። አጋጥመውንም ያውቃሉ። ዛሬ ብቻ አይደለም። አቶ ዘሪሁን ይህ ክስተት ለውጡን ተከትሎ የመጣም አይደለም ነው የሚሉኝ አይደለም? የስፖንሰሮቹ መሸሽ ለውጡን ተከትሎ የመጣ እንዳይሆን? ድሮም እኮ ያንን ያህል የቀረቡ የሉም፤ ዘንድሮም ያንን ያህል የሸሹ የሉም። ለምን እንደሚቀርቡ፣ ለምን እንደሚሸሹ አናውቀውም። በመንግሥት ነው ስላልከው፣ ነገርኩህ እኮ! ገንዘብ የምታገኙት ከደኅንነት ነበር ላልከው ከደኅንነት ያገኘነው አምስት ሳንቲም የለም፤ መረጃ ካላችሁ አውጡት፤ ሜቴክ ጋር በተመለከተ አምስት ሳንቲም የገንዘብ ክፍያ የለንም። የወሰድነው ጄኔሬተር ነው፤ ይህንን ሜቴክ ያውቃል። አገልግሎት ሰጠነው፣ በሚመጥነው ዋጋ፤ አበቃ! አሁን ዛሚ እንደማይዘጋ ማረጋገጫ ይሰጡኛል? ቆይ በግልጽ ላስቀምጥልህ! እንዴ ዛሚ ሊዘጋ ይችላል እኮ! ወይ እኔ ልሞት እችላለሁ? ወይ አንዱ ተነስቶ ዝጋው ሊለን ይችላል ወይ… ነገርኩህ የሁለት ቀን የደመወዝ መዘግየት አጋጠመ፤ ከዚያ ውጭ እንግዲህ ለመዝጋት ያሰቡ ካሉ እናያለን። ትናንትም በማስጠንቀቂያ ተሞክሮ አልተዘጋም፤ ነገም በማስጠንቀቂያ ተሞክሮም ወይም ተገፍቶም እንዝጋቸው እስካላሉን አንዘጋም። ወይዘሮ ሚሚ ስብሐቱ የት ናቸው በትክክል? ወደ ጣቢያውስ ይመለሳሉ ወይ? እንዲያውም ልንገርህ፤ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የ"ጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ" እንደሚጀምር እናስታውቃለን፤ የሚቀጥለው እሑድ እንዲያውም የመጀመርያ እንግዳችንን ከቢቢሲ እና ከሌሎችም ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ሚዲያ ውስጥ የመሥራትን ጥቅምና ጉዳት እንዲያወሩን እንጋብዛለን። ምናልባት አንተ ወይም አለቃህ እንግዳችን ይሆናሉ፤ ኦኤምኤንን ጨምሮ… ወይዘሮ ሚሚ ይመሩታል? የአሁኑ ሳምንት [ሆስት የማደርገው] የማስተናብረው እኔ ዘሪሁን ተሾመ ነኝ፤ ከጥቅምት [ኦክቶበር] መጨረሻ በኋላ ወይዘሮ ሚሚ ይሆናሉ። ወይዘሮ ሚሚ ላለፉት ጊዜያት ያልነበሩበት ምክንያት ግን አልነገሩኝም? የግል ጉዳይ ነው፤ የጤንነት ጉዳይ ነው፤ ዋናው ደግሞ የዓይን ጉዳይ ነው፤ ስለዚህ ዓይኗን መታከም ነበረባት፤ ዓይኗን ታክማ ተደጋጋሚ ነገር መደረግ ነበረበት፤ በእሱ ሁኔታ መብረር አይፈቅድም ከዚያ ደግሞ አቧራው ትንሽ የቀነሰ ቦታ መቆየት ነበረባት፤ እናም አሜሪካ ነው የቆየችው። ላለፉት ስድስት ወራት? ስድስት ወር አይሆንም አምስት ወራት ቢሆን ነው፤ ግንቦት መጨረሻ ነው የሄደችው። ሕይወትን የሚያህል ነገር በተለይ ዓይን ከዚያ በላይ ቢወስድም የሚገርም ነገር የለውም፤ እንዳልኩህ ነው ተደጋጋሚ ሰርጄሪ ያስፈልግ ነበር፤ ሁለተኛው [ህመሟ] አቧራ አይፈልግም፤ በዚህም ምክንያት እዚያ መቆየት ነበረባት፤ ይሄን አቧራ የፖለቲካ አቧራ ብላችሁ ከተረጎማችሁትም እኔ የለሁበትም፡፡ (ሳቅ) ስለጊዜዎ እናመሰግናለን አቶ ዘሪሁን ምንም አይደል፡፡
news-44679024
https://www.bbc.com/amharic/news-44679024
የዶክተር ዐብይ አሕመድ ፊልም
ወታደርም፣ አርሶ አደርም፣ ላብ አደርም ነበሩ። ብዕረኛ ስለመሆናቸው ግን የሚያውቅም ያለም አይመስልም…። ምናልባት ቴዎድሮስ ተሾመ?
እርሱ እንደሚለው ከቀዝቃዛ ወላፈን ውጪ ሁሉም ሥራዎቹ ላይ የዶክተር ዐብይ አሻራ አለ። ይህን አባባል ካፍታታነው ደራሲ ዐብይ ‹‹አባይ ወይስ ቬጋስ››፣ ‹‹ፍቅር ሲፈርድ››፣ ‹‹ቀይ ስህተት›› እና ሌሎች 8 የቴዎድሮስ ፊልሞች ላይ በኅቡዕ አንዳች የሐሳብ መዋጮ ሳያደርጉ አልቀሩም። ይህ ነገር የሰውየውን መግነን ተከትሎ ራስን ከዚያው ተርታ ለማሰልፍ የተቀነባበረ የዝና ሻሞ ይሆን ወይስ ሰውየው የምርም ጸሐፊ ናቸው? ከሆኑስ የኚህ ጠቅላይ ሚኒስትር የፈጠራ ድርሻ እንዴት ይመተራል? በ‹‹ሦስት ማዕዘን›› ውስጥ እርሳቸው ስንት ማዕዘናትን አሰመሩ? ይህን ለመረዳት ያስችለን ዘንድ ከሴባስታፖል ሲኒማ ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ ጋር አወጋን፡፡ ፊልም የሚጽፍ ጠቅላይ ሚኒስትር? ፊልም የሚመርቅ ሚኒስትር አጋጥሞን ሊሆን ይችላል። ፊልም የሚጽፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን…? እንጃ! ሐሳቡ ራሱ ወለፈንድ ይመስላል። ዐብይ አሕመድ በቅድመ ንግሥና ወይም ከ4 ኪሎ ደጅ ፊልም ለመጻፍ የመጀመርያው መሪ ሊሆኑ ይችሉ ይሆን እንጂ በብዕር ሥም መጽሐፍ ለማሳተም ብቸኛው ጠቅላይ አይደሉም። የቀድሞው የመለስ ዜናዊ ‹‹ምኩሕኳሕ ዘይፍለዮ ማዕፆ›› የሚል ልቦለድ መጽሐፍ ተስፋዬ የኋላሸት በሚባል የብዕር ሥም መጻፋቸው ይነገራል። ‹‹ማንኳኳት ያልተለየው በር›› እንደማለት ነው ርዕሱ በአማርኛ ሲመነዘር። ‹‹ገነቲና›› የሚል ሌላ መጽሐፍ እንዳላቸውም በገደምዳሜ ይወራል። ዐብይ አሕመድ ደግሞ ‹‹ዲራዐዝ›› በሚል የብዕር ስም ‹‹እርካብና መንበር›› እንዲሁም ‹‹ሰተቴ›› የተሰኙ መጻሕፍን አበርክተዋል እየተባለ መወራት ከጀመረ ሰነባበተ። ‹‹ዲራዐዝ›› ቢያንስ የርሳቸውና የባለቤታቸው ምህጻር መያዙን መጠርጠር ይቻላል። ቀሪ ሆሄያት የልጆቻቸው ስሞችን የሚወክሉ ይሆኑ? ቴዎድሮስ በዚህ ጉዳይ ምንም ማለት አይፈልግም። ትውውቃቸው ከጅማ ይሁን ከአጋሮ፣ ከተማሪ ቤት ይሁን ከጉልምስና ፍንጭ ሰጥቶም አያውቅም። ከቢቢሲ ለቀረበለት ተመሳሳይ ጥያቄም ‹‹ይለፈኝ›› ሲል መልሷል። ባይሆን ሁለቱ የጥበብ ሥራዎቻቸውን ከድሮም ጀምሮ እንደሚገማገሙ ይናገራል። ‹‹በሥራዎቼ ውስጥ ዐብይ አለ፣ በዐብይ ሥራዎቹ ውስጥ እኔ አለሁ።›› በደራሲ ዐብይ መጻሕፍት ጀርባ የቴዎድሮስ የሽፋን አስተያየት (blurb) መጻፉም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው። የዐብይ አሕመድ ‹‹ሰተቴ›› ሌላው መጽሐፍ ነው። ጅማ ውስጥ የነበረ ‹‹ከድር ሰተቴ›› የሚባል ሰው ታሪክ ነው። የመናገር ነጻነት ባልነበረበት በደርግ ወቅት በጅማ አደባባይ መንግሥትን ልክ ልኩን የሚናገር ነበር አሉ። በዚህ የተነሳ ደርጎች በየጊዜው የሚቀፈድዱት ሰው እንደነበረና በመጨረሻም ከሰዋራ ቦታ እንደገደሉት ቴዎድሮስ ‹‹የደራ ጨዋታ›› ለተሰኘው የራዲዮ ፕሮግራም ተናግሮ ነበር። ዶክተር ዐብይ ታዲያ በዚህ አማጺ (Rebel) ስም ለምን መጽሐፍ መጻፍ ፈለጉ? ለምንስ ዲርዐዝ በሚል የብዕር ስም አሳተሙት? ብለን ብንጠይቅ ከመልስ ይልቅ ተጨማሪ ጥያቄን እንቆሰቁሳለን። ‹‹ከድር ሰተቴ የነጻነት ታጋይ ስለነበረ ለመጽሐፋቸው የመረጡት ለዚሁ ይመስለኛል›› ይላል ቴዎድሮስ፡፡ ምን ማለቱ ይሆን?. . . ዶክተር ዐብይ የደበቁን መጽሐፍ አለ? ለቴዎድሮስ ተሾመ ዐብይ አሕመድ የቀንተሌት ትጉህ አንባቢ ብቻ አይደሉም። ለመሪነት የተቀቡ ደግ ሰው ብቻም አይደሉም። ብዙ ነገሩ ናቸው። ከሁሉም በላይ ግን ‹‹ነፍሱ ለጥበብ የቀረበች ናት›› ይላል። ለዚህም ነው ‹‹ከርሱ ጋር አንድ ሰዓት መቀመጥ አንድ ዓመት ትምህርት ቤት የመግባት ያህል የሚሆነው›› ሲል ምስክርነቱን የሚሰጠው። ሌሎች የጥበብ ሥራዎችን አሳይተውት ከሆነ ከቢቢሲ የተጠየቀው ቴዎድሮስ ‹‹አያዎ›› ምላሽ ከሰጠ በኋላ ሕዝብ የማያውቃቸው ሥራዎች እንዳሏቸው ግን አልሸሸገም። ምናልባት የግጥም መድብሎች፣ ምናልባት የቴአትር ቃለ ተውኔቶች፣ ምናልባት አጫጭር ልቦለዶች? ምናልባት የፊልም ስክሪፕት? ቴዎድሮስ ለዚህ ምንም ፍንጭ አልተውልንም። በ‹‹ሦስት ማዕዘን›› ግን የዶክተሩ ድርሻ 50 እጅ እንደሚይዝ ይናገራል። ርዕሱ እና የመጀመርያው ረቂቅ የርሱ እንደሆነ ካተተ በኋላ ‹‹ስሱ (sensitive) የሆኑና ፊልሙ ላይ የሚገኙ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እሱ ነው ያስተካከላቸው›› ይላል። ‹‹ብዙ ሰው የሱን ሥራ በስሜ ያወጣሁ አድርጎ ይተቸኛል፡፡ የሱን ስም ያልጠቀስኩት መጠቀስ ስለማይፈልግ ነው፤ ሆኖም ግን እኔና እሱ በምንግባባበት መንገድ አመስግኜዋለሁ›› ይላል ቴዎድሮስ። ለካንስ ፊልሙ ሲጠናቀቅ ከሚመሰገኑ ሰዎች ዝርዝር ‹‹ዐብይ ወንድሜ›› የሚለው ውክልና ለአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበር። የሦስት ማዕዘን ክብነት በፍቅራቸው ተነድፈናል የሚሉ ዜጎች በበረከቱበት፣ የተናገሯቸው ቃላት እንደ ቆሎ በሚቆረጠሙበት፣ ከአፋቸው ማር ጠብ ይላል በሚባልበት፣ በዚህ የሰበር ዜና ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በገደምዳሜም ቢሆን ‹‹ፊልም ጽፌ ነበር›› ሲሉ ሕዝቡ እንደ ዋዛ ያልፈዋል ተብሎ አይጠበቅም። የሆነውም ይኸው ነው። ‹‹ሦስት ማዕዘን›› ከሲኒማ ከወረደ ዘመን የለውም። አሁን ግን ፊልሙን ወደ ሲኒማ ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ ነው። ለምን ከተባለ ‹‹ብዙ ሰዎች ያን እንዳደርግ እየጠየቁኝ ነው። እኛም እየተዘጋጀን ነው›› ይላል ቴዎድሮስ። እስከዚያስ? መታገስ ያልቻሉት በይነመረብ ላይ ተኮልኩለዋል። የተመልካቾ ቁጥር ባለፉት ሳምንታት ብቻ በእጥፍ ጨመሮ ታይቷል። ይህ ሒሳዊ ሐተታ እስሚዘጋጅበት ዕለት ድረስም ለግማሽ ሚሊዮን የተጠጉ የበይነ መረብ ታዳሚያን ፊልሙን ደጋግመው አጫውተውታል። ከነዚህ ወስጥ ገሚሶቹ በፊልሙ ላይ የዶክተር ዐብይን ተሳትፎ በመስማታቸው ብቻ ፊልሙን ለመኮምኮም ዳግም የመጡ ናቸው። ይህንኑ አስያየታቸውን እዚያው ከፊልሙ ሥር በተሰጣ የበይነመረብ አስተያየት መስጫ ሰሌን ገልጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ፊልሙ እንዲታይላቸው መፈለጋቸውን አልሸሸጉም። ‹‹…ሦስት ማዕዘንን ያላያችሁ ሰዎች በደንብ እንድታዩት በዚህ አጋጣሚ እመክራችኋለው›› ነበር ያሉት፣ በዚያች ምሽት የእራት ግብዣ። ‹‹…አትናገር ብዬው እኔው ራሴ አፈረጥኩት›› ዶክተር ዐብይ ድርሰቱን ስለመጻፋቸው ይፋ ያደረጉበት አጋጣሚ የሰውየውን ቀደምት ትልም እንድንመረምር ይጋብዛል። የአስመራን ልዑክ እራት በጋበዙበት ምሽት የአገራቱን ወንድማማችነት እያጎሉ በመናገር ላይ ነበሩ። ሊያውም በተፍታታ ስሜት። በእያንዳንዱ ዐረፍተ ነገር ማሳረጊያ ጭብጨባ ያጅባቸው እንደነበር ልብ ይሏል። ‹‹…እነ ጥሩዬ በአስመራና በምጽዋ ለመሮጥ በጣም ጓጉተዋል።›› ካሉ በኋላ የኛ በርካታ አርቲስቶች በፊልም በሙዚቃ የሁለቱን አገራት ወንድማማችነት ለማሳየት ጥረት ማድረጋቸውን ጠቀሱ። ቀጥለው ይህን ያደረጉ አርቲስቶችን በስም ይጠቅሳሉ ብለን ስንጠብቅ ራሳቸውን አስቀድመው አስገረሙን። ‹‹እኔም በተወሰነ ደረጃ በደራሲነት የተሳተፍኩበት ሦስት ማዕዘን የሚያስተላልፈው አንዱ መልዕክት የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች ወዳጅነት በችግር ጊዜ ምን እንደሚመስል ነው።›› ለዓመታት በምስጢር የያዙትን ጉዳይ ይፋ በማድረግና ባለማድረግ ቀልባቸው መወላወሉን በሚያሳብቅ ድምጽ እንዲህ አሉ፣ ‹‹ለረዥም ጊዜ ቴዲን አትናገር ብዬው ዛሬ እኔው ራሴ አፈረጥኩት።›› ቀዝቃዛ ትንቢት ሦስት ማዕዘን ከተደረሰ ሰባት ዓመታት አልፎታል። ያኔ የፊልሙ ገሚስ-ደራሲ ዐብይ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ። ያኔ 'ዐብይ' የሚለው ቃል ተውላጠ ስም እንጂ የ 'ንጉሥ' ስም መሆን አልጀመረም ነበር። ቴዎድሮስ እንደሚያስታውሰው ከሆነ ሰውየው መሪ እንደሚሆኑ ገና ድሮ ያውቁ ነበር ‹‹ (ለመሪነት) እየተዘጋጀ እንደነበር አውቃለሁ።›› ያኔ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉትም ምናልባት ለዚሁ ይሆን? ለነገሩ ፎቶ መነሳት የማይወዱትም ለዚሁ እንደነበር ተናግረው ያውቃሉ። ሩዋንዳ ሰላም አስከባሪ ሳሉ አንዲት ፈረንሳዊት አፍቅራቸው ይዤህ ልጥፋ ስትላቸው እንዴት ብትንቀኝ ነው ብለው ማልቀሳቸውን ልብ ይሏል። ‹‹አንተስ ጓደኛህ ዐብይ አንድ ቀን መሪ እንደሚሆን ሽው ብሎህ ያውቃል?›› በሚል ከቢቢሲ የተጠየቀው ቴዎድሮስ ‹‹የማላውቅ መቼ የሚለውን ብቻ ነበር›› የሚል ምላሽ ሰጥቷል። የደራሲ ዐብይ የንግርት ቴክኒክ (Foreshadow) ንግርት በፈጠራ ሥራዎች በተለይም በተንቀሳቃሽ ምስልና በልቦለድ ጽሑፍ ውስጥ የሚገኝ የጎበዝ ደራሲዎች መለያ ቴክኒክ ነው። ሁሉም እግር ኳስ ተጫዋቾች ጎል ያስቆጥሩ ይሆናል። እንደ ሮናልዲኒሆ ጎቾ ግን በኳስ ቅኔ አይቀኙም። ሁሉም ደራሲ ሊሞነጫጭር ይችላል። ንግርትን የሚችሉት ግን ጥቂቶች ናቸው። በፊልሙ ውስጥ ወይም ከዚያም ባሻገር ባለ የእውን ዓለም ወደፊት ስለሚሆነው ነገር በስሱ ጠቆም አድርጎ የሚያልፍ ጥበባዊ ትንቢት ነው-ንግርት። ደራሲዎች እንደ ባሕታዊ ሲሰራራቸው ታይቶኝ ነበር የሚሉባት አትሮንስ ናት-ንግርት። ደራሲ ዐብይ ስለ ኢትዮጵያና ኤርትራ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመተንበይ እንዲያ ያለ ቴክኒክ ሳይሞካክሩ የቀሩ አይመስልም። የሞከሩበት መንገድ ግን ግልብ ነው፤ አልሰወሩትም። አጻጻፋቸውም ቢሆን ደርዘኛና አማላይ ኾኖ አይታይም። ይህ ጨለም ያለ ድምዳሜ በሦስት ነገረ ማገሮች (Core Points) ሊፍታታ ይችላል። አንደኛው ቴዎድሮስ ተሾም ረቂቁን ሲያሳያቸው አፍርሰው መሥራታቸው ነው። እርሱ እንደሚለው የመጀመርያው ረቂቅ እንደተለመደው እኩይና ሰናይ ገፀ ባሕርያት ሰዋዊ ሆነው የቀረቡበት ነበር። ወይም ደግሞ ኤርትራና ኢትዮጵያዊያን በፊልሙ ውስጥ አንዱን ሰናይ ጀግና ሌላው እኩይ ባላንጣ (hero and villain) ሆነው ነበር የተሰለፉት። ዶክተር ዐብይ ‹‹የለም ይሄ መሆን አይገባውም›› አለ። ሁለቱን አገሮችማ እርስበርስ ጠላት አናድርጋቸው። ‹‹ባይሆን በጋራ በሚደርስባቸው ችግር ሲፈተኑ ነው ማሳየት ያለብን ብሎ ስክሪፕቱን እንደገና ጻፈው›› ይላል ቴዎድሮስ። በፊልሙ ውስጥ ታዲያ ጥበባዊ ውበት በራቀው መንገድም ቢሆን ሁለቱ አገሮች መቼም ወንድማማች እንደሆኑ፣ ብሎም ዐሐዳዊነት እጣ ፈንታቸው እንደሚሆን ለማሳየት ደራሲ ዐብይ ብዙ ለፍተዋል። በፊልሙ እንደ ኤርትራዊት ፍልሰተኛ ሆና የምትተውነው ማኅደር አሰፋ በጉዞ ላይ ችግር ሲያጋጥማት የሚደርሱላት ኢትዮጵያዊያን ሆነው ተስለዋል። በተለይም በፍቅሯ የተነደፈው ሌላው ፍልሰተኛ ሰለሞን ቦጋለ ኢትዮጵያን ወካይ ገጸ ባሕሪ ኾኖ ተጫውቷል። ኤርትራዊቷ ማኅደር አሰፋ ጨርቆስ አካባቢ የተወለደች ስትሆን ነጻነት ተከትሎ ኤርትራ የአፍሪካ ሲንጋፖር ልትሆን ነው በሚል ተስፋ ቤተሰቦቿ ወደ አስመራ ይዘዋት እንደሄዱ በፊልሙ ትተርካለች፡፡ ያ ተስፋ ከንቱ ሲሆን ስደትን ትመርጣለች፡፡ ማኅደር በፊልሙ ላይ ስትሳል አማርኛ የማትችል መስላ ብትቆይም የኋላ ኋላ ቅኔ መቀኘት የሚያስችል አማርኛን ስታቀላጥፈው እንመለከታለን፡፡ ደራሲ ዐብይ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ይዘገይ ይሆናል እንጂ መደመራችን አይቀርም ማለቱ ይሆን? ላይ ላዩን እያስመሰልን ነው እንጂ ውስጣችን አንድ ነው ማለቱ ይሆን? ሁለት ቋንቋ በመናገር የተቀናነስን እንመስላለን እንጂ ለመደማመር የተፈጠርን ሕዝቦች ነን ለማለት ይሆን? ማኅደር አሰፋ በሊቢያና በሜክሲኮ በረሃ ስትወድቅ የደረሰላት ኢትዮጵያን እንዲወክል የተደረገው ሰለሞን ቦጋለ ነው። ለምሳሌ ሜክሲኮ በሞት አፋፍ ላይ ለነበረችው ማኅደር ደም ለጋሽ ጠፍቶ ጀማል የሚባለው ገጸ ባሕሪ ደም በመስጠት ሕይወቷን ይታደጋታል። ማኅደር አሰፋ ከሰመመን ስትነቃም ‹‹ለማላውቃት ለኤርትራዊ ደም ሰጠሁ›› ይላል፤ ኢትዮጵያዊው ጀማል። ጀማል የጅማ ልጅ ሳይሆን አይቀርም። ቴዎድሮስም የጅማ ልጅ ነው። ዶክተር ዐብይም ከዚያው አካባቢ ነው። ሦስት ማዕዘን። ከዚህም ሌላ ንግርት የሚመስሉ በግልብ ቋንቋም ቢኾን በዐብይ አሕመድ በተሳሉ ገጸ ባሕርያት የሚነገሩ ‹‹የአንድ ነን›› ትርክቶች በፊልሙ ላይ እዚህም እዚያም ይገኛሉ። ማኅደርን የሊቢያ ንዳድ አዝለፍልፎ ሲጥላት ሰለሞን ቦጋለ (ኢትዮጵያ) ከተቀረው ስደተኛ (ከአካባቢው አገራት) ሁሉ ተለይቶ ማኅደርን ጥዬ አልሄድም ይላል። ጓደኞቹ ‹‹እርሷ እኮ ኤርትራዊት ናት›› ቢሉትም ‹‹ለኔ ያ ልዩነት የለውም›› ሲል ይሟገታል። በአረብ የባሪያ አስተላላፊዎች ልትደፈር ስትል የሚደርስላትም ይኸው ኢትዮጵያዊ ነው። ነገሩ የአካባቢውን ጂኦፖለቲክስ በፊልም ጥበብ ለመነካካት ይመስላል። ይልቅ አጨራረሱን ችለውበታል። ሜክሲኮ ድንበር ላይ ማኅደር አሰፋ (ኤርትራዊት) እና ሰለሞን ቦጋለ (ኢትዮጵያዊ) ቃል ኪዳን ያስራሉ። ቃል ኪዳን ያሰሩበት መንገድ ለጥጠን ከተረጎምነው ‹‹አሰብ›› የሚል ፖለቲካዊና ፍካሪያዊ ትርጉም ሊሰጠን ይችላል። ማኅደር አሰፋ፡- ‹‹ነፍሴን አትርፈክልኛል ከዚህ በኋላ ነፍሴ የኔ አይደለችም፤ ያንተ ናት›› ካለች በኋላ ከዞማ ጸጉሯ ጫፉን ሳትሰስት ቆርጣ በሰለሞን ቦጋለ ጣት ከጸጉሯ የተገመደ የጋብቻ ቀለበት ሠርታ ታጠልቅለታለች። ደራሲ ዐብይ አሕመድ በዚህ ንግርት ምን ሊተነብዩ እየሞከሩ ይሆን? ዶ/ር ዐብይ ጎበዝ ጸሐፊ ናቸው? ፊልምን ፊልም የሚያደርገው የፊልም ጽሑፉ ብቻ ቢሆን ኖሮ መራር ሐያሲያን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ‹‹ለዛሬ አልተሳካሎትም›› ባሏቸው። ለምን? ደራሲው እንዲሆኑ የሚመኝዋቸውን ሕልሞች ሁሉ ሳይመሰጥሩ እንዲሁ እንደነገሩ ያዘንቧቸዋል። እርግጥ ነው ፖለቲካዊ ምኞታቸው የሚያማልል ነው። ኾኖም ምኞቱ የተጻፈው በኑዛዜ ቋንቋ ነው። በጥበብ ቅመም አልታሸም። በውብ ቋንቋ አልተዋዛም። ጥፍጥ፣ ክሽን፣ ምጥን አልተደረገም። ፊልሙ ብዙ የሚወደሱለት ሙከራዎች ቢኖሩትም ብዙ ፊልሞቻችንን የሚያስነጥሱ ጉንፋኖች እሱም ላይ በርትተው ይታያሉ። ምናልባት በፊልሙ መጨረሻ የምንማረው ስደት ብቻ ሳይሆን ፊልም መሥራትም አስቸጋሪ መሆኑን ነው። ሁሉንም ኩነት በተራዘመ ቃለ ተውኔት ለተደራሲ ለማተት ይሞክራል። ከድርጊት ድርጊት ቶሎ ስለማይሸጋገር አንድ ታዳሚ ፊልሙን አቋርጦ ውልና ማስረጃ ጉዳይ ጨርሶ ቢመለስና ፊልሙን ማየት ቢቀጥል እምብዛምም የሚያጣው ነገር የለም። እርግጥ ነው ይህ ገለጻ ተጋኖ ሊሆን ይችላል። ውልና ማስረጃ ፈጣን አገልግሎት ሰጪ መሥሪያ ቤት መሆኑንም መዘንጋትም አያሻም። ፊልሙ ላይ የሚተውኑ ሌሎች ፀጉረ ልውጥ የሜክሲኮና የአረብ ዝርያ ያላቸው ተዋንያን ለምን በተሻለ እንደተወኑ ሆኖ እንደሚሰማን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። ምናልባት እነ ሰለሞን ቦጋለን፣ እነ ማኅደር አሰፋን፣ እነ ሳምሶን ታደሰ ቤቢን፣ እነ ሰላም ተስፋዬን እጅግ ተላምደናቸው ይሆን? ለዚያ ይሆን በየበረሃው እንግልታቸውን እያየን ነገር ግን የማናምነው? በሌላ አነጋገር ፊልም እየሠሩ እንደሆነ ሳናስብ ፊልሙን አንጨርሰውም። አንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ሐያሲ ‹‹ፊልሙን ከመጨረስ በረሀውን ማቋረጥ ሳይቀል አይቀርም›› ያለው ነገር ርሕራሄ ያጣ ሂስ ሊባል ይችላል እንጂ እውነትነት የለውም የሚባል አይደለም። ያም ሆኖ ፊልሙ በርከት ባሉ አገራት እየተንሸራሸረ አክሊል ደፍቷል። በደቡብ አፍሪካ ‹‹አፍሪካን ሙቪ አካዳሚ አዋርድ››፣ ለዚያውም በሦስት ዘርፍ አሸንፏል። በፓን አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል እንዲሁ ሌላ ዋንጫ ወስዷል። በሩዋንዳ ‹‹ቤስት ኦዲየንስ ፊልም አዋርድም›› እንዲሁ። ፊልሙ በተጫነበት የዩቲዩብ መስኮት ሥር የተሰጡ አያሌ አስተያየቶች ይህን ሲኒማ እያነቡ ጭምር እንደተመለከቱት የሚናዘዙ ናቸው። ስለዚህ እንደ ስውሩ ደራሲ ዶክተር ዐብይ ሁሉ ፊልሙም ሰፊ ሕዝባዊ ቅቡልነት ያገኘ እንደሆነ ሊካድ አይገባም። ቴዎድሮስ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ፊልሙ በሐያሲያን ዘንድ ደካማ እንደሚባልና ለድክመቱ ምናልባት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃላፊነት ይወስዱ እንደሁ ሲጠይቅ ‹‹ያ የዳይሬክተሩ እንጂ የደራሲው ችግር አይደለም›› ሲል ተከራክሯል። ‹‹ፊልም እኮ የድርሰት ውጤት አይደለም፡፡ እንዲያውም ለፊልም ውድቀትም ሆነ ስኬት ተጠያቂ መሆን ያለበት ዳይሬክተሩ ነው፡፡ ስለዚህ ችግር አለ ከተባለም የእኔ የዳይሬክተሩ ነው እንጂ የሚሆነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አይደለም።››
news-51276518
https://www.bbc.com/amharic/news-51276518
በአንድ ቀን 1 ቢሊዮን ዶላር ያተረፈው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው?
አንድ የደበተው ሰኞ ከሰዓት፤ በ2019 ኅዳር ወር ላይ መሆኑ ነው፣ ምንነቱ ያልታወቀ የፖስታ ጥቅል በኒውዮርክ የባለጸጎች መንደር በሚገኝ አንድ ግዙፍ ቤት ተቀመጠ፤ ደጅ የፖስታ ሰንዱቅ ውስጥ።
ጆርጅ ሶሮስ ከብዙ አመጾች ጀርባ እጁ እንዳለ የሚታሰበው ለምንድነው? ጥቅሉ አጠራጣሪ ነገሮች ነበሩት። አንደኛ የተመላሽ ስም በትክክል አልተጻበትም። ሁለተኛ በተላከበት ቀን ነው የደረሰው። ፖሊስ ተጠራጠረ፤ ኤፍቢአይ ተጠራ። የጆርጅ ሶሮስ ቪላ ተወረረ። • የዓለማችን ቁጥር አንድ ሃቀኛዋ ሃገር በዚያ ጥቅል ውስጥ የሶሮስ ፎቶ ነበር፤ ከፊት ለፊት የይገደል ምልክት ተጽፎበታል። 6 ኢንች የሚረዝም የፕላስቲክ ጎማ፣ ቁልቁል የሚቆጥር ሰዓት፣ ባትሪና የኤሌክትሪክ ሽቦዎች ነበሩበት፤ በጥቅሉ ፖስታ። ተመሳሳይ ጥቅል ወደ ኦባማና ሂላሪ ቤት ተልኳል። ደግነቱ አንዱም አልፈነዳም፤ ፖሊስ አክሽፎታል። እነዚህን ጥቅሎች የላከው ማን ነበር? ቀኝ ዘመም የአሜሪካ ሚዲያ ቶሎ ጣቱን የቀሰረው ወደ ሶሮስ ነበር። ራሱ ሶሮስ የሸረበው ሸር ነው በሚል። ሶሮስ እንዴት አድርጎ ወደ ራሱ ቦምብ ይልካል? ጥሩ ጥያቄ ነው። ነገር ግን የትራምፕ አክራሪ ደጋፊዎች በአመዛኙ ለርትዕ ፊት አይሰጡም ይባላል፤ ለፖለቲካ ተዋስኦ ክፍት አይደሉም፤ አመክንዮ ይቀፋቸዋል። የትራምፕ ደጋፊዎች የሚቀናቸው ሴራ ነው። የአሻጥር ፖለቲካ የነጭ አክራሪዎች ኦፒየም ነው። ስለዚህም አደባባይ ወጡ። ጆርጅ ሶሮስን ሊያወግዙ። "ትራምፓችን ሆይ! ሶሮስን እሰር! ሶሮስን ዘብጥያ አውርድልን" የሚል ድምጽ በዋይት ሃውስ ደጅ ላይ አስተጋባ። ደግነቱ ፖሊስ ቦምቦቹን በጥቅል የላከውን ሰው ደረሰበት። የ56 ዓመቱ የፍሎሪዳ ነዋሪ ሲዛር ሳዮክ ነበር። ሰውየው እንዲያውም ብዙዎች እንደገመቱት ሪፐብሊካን አልነበረም። ቤት ለቤት ፒዛ አዳይ እንጂ። • በትራምፕ የድጋፍ ደብዳቤ ወደ አሜሪካ ያቀናችው የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ኢትዮጵያዊት ሆኖም አእምሮው በሴራ ፖለቲካ ናውዞ ነበር። እንደ ብዙዎቹ ቀኝ አክራሪዎች። ከሁሉም ፖለቲካ ጀርባ ጆርጅ ሶሮስ የሚባል ሰው አለ ብሎ ያምን ነበር፤ ሶሮስ የነጭ የበላይነትን ሊያጠፋ የተነሳ ጠላት ነው ብሎ ያስብ ነበር፤ የትራምፕ ጠላት ነው ብሎ ያምን ነበር፤ ስለዚህ መገደል አለበት በሚል ነው ቦምቡን በፖስታ የላከው። የዚህ ወንጀለኛ ፌስቡክ ሲበረበር ደግሞ ሌላ ጉድ ተገኘ። "ዓለም ከእንቅልፉ ሲነቃ የሶሮስን አሳዛኝ ዜና ይሰማል!" ይህ ግለሰብ ለጊዜው 20 ዓመት እስር ተከናንቧል። ጆርጅ ሶሮስ ግን አሁንም የሴራ ፖለቲካ ገፈት ቀማሽ እንደሆነ አለ። ከሁሉም የዓለም ፖለቲካ ለውጥ ጀርባ የሶሮስ እጅ አለ የሚል አስተሳሰብ ናኝቷል። ለመሆኑ ሶሮስ እንደሚገመተው የዓለም የአሻጥር ፖለቲካ ሾፌር ነው? የጆርጅ ሶሮስ አጭር የሕይወት ታሪክ ጆርጅ ሶሮስ ከፖለቲከኞች አፍ የሚጠፋ ስም አይደለም። አምባገነኖች በተለይ ይፈሩታል። የእነዚህ አምባገነኖች መቀመጫ እሲያም ይሁን አፍሪካ፣ ምሥራቅ አውሮፓም ይሁን ደቡብ አሜሪካ ወይም መካከለኛው ምሥራቅ... ብቻ መንግሥታቱ ከሚነሳባቸው ተቃውሞ ጀርባ የቢሊየነሩ ጆርጅ ሶሮስ እጅ እንዳለበት ይገምታሉ። እውነት አላቸው? ለመሆኑ ይሄ ለግራ ዘመም ፖለቲከኞች ብር ይረጫል የሚባለውና በልግስናው ስመ ገናናው ጆርጅ ሶሮስ ማን ነው? ትውልደ ሀንጋሪያዊ-አሜሪካዊው ሶሮስ የተወለደው በቡዳፔስት በ1930 ዎቹ መጀመርያ ከአይሁድ ቤተሰብ ነበር። እንዲያውም "ጆርጂዮ ሽዋትዝ" ነበር የቀድሞ ስሙ። በጊዜው በአውሮፓ በአይሁዳዊያን ላይ በነበረው ሥር የሰደደ ጥላቻ ምክንያት አባቱ ከግድያ ለማምለጥ፣ ቤተሰባቸውንም ለመታደተግ እንዲረዳቸው ሲሉ ነው የቤተሰባቸውን ስም ከሽዋትዝ ወደ "ሶሮስ" የቀየሩት። ስሙን መቀየር ብቻም ሳይሆን በተለይ ለጆርጅ አዲስ ማንነትና መታወቂያ ተዘጋጅቶለት ልክ አይሁድ ያልሆነ ሌላ አንድ ተራ የቤተሰብ አባል ተደርጎ እንዲኖር ተደረገ። በዚህም ያንን አስቸጋሪ ዘመን መሻገር ቻለ። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ሶሮስ በ14 ዓመቱ የአንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ልጅ እንደሆነ ተደርጎ መታወቂያ ወጥቶለት ለጥቂት ሳይገደል ቀርቷል። ሶሮስ ከግድያዎች ያምልጥ እንጂ በዚህ ወቅት የአይሁዶች ንብረት ሲዘረፍ፣ ክብራቸው ሲገፈፍ ዓይኑ በብረቱ ተመልክቷል። በዚያ ዘመን፣ በተለይም በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ግማሽ ሚሊዮን የሀንጋሪ አይሁዶች እንዲገደሉ የሆነው 8 ሳምንታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር። እንዲያውም በመላው ዓለም ካሉ አገራት እንደ ሀንጋሪ አይሁዶች በአጭር ጊዜ በስፋት የተረሸኑበት አገር የለም ይባላል፤ ወላ በጀርመንም ቢሆን። ሶሮስ ከናዚዎች ግድያ ተርፎ እፎይ ብሎ መኖር ሲጀምር ሀንጋሪ ወደ ኮምኒስት አገርነት ተለወጠች፤ ሌላ ፈተና። በዚህ ጊዜ ነበር ገና በ17 ዓመቱ ከቡዳፔስት ወደ ለንደን የሸሸው። ቀኝ አክራሪዎች ሶሮስን ሲያወግዙ የእንግሊዝን ባንክ ያንበረከከው ሶሮስ ጎረምሳው ሶሮስ እንግሊዝ እንደገባ የሻይ ቤት አስተናጋጅ ሆነ። ከዚያም የባቡር አውራጅና ጫኝ ሆነ። ቀጥሎ ዩኒቨርስቲ ገባና ከዝነኛው የለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ በምጣኔ ሀብት ዘርፍ ዲግሪ ያዘ። እዚያ ዩኒቨርስቲ ሳለ ነበር አስተሳሰቡን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የለወጠለትን ሰው ያገኘው። ይህ ሰው ፈላስፋው ሰር ካርል ሬይመንድ ፖፐር ነበር። ፈላስፋው ፖፐር ልክ እንደ ሶሮስ ሁሉ አይሁድ ስደተኛ ነው። ኦስትሪያዊ አይሁድ። ጆርጅ ሶሮስ አስተሳሰቡ የተጠረበው በዚህ መምህሩ እንደሆነ ይታመናል። • ሐኪሞች ለቀዶ ህክምና የሚጠቀሙበት የናዚ መፅሐፍ የዚህ መምህሩ በፖለቲካ ፍልስፍና ዓለም የናጠ ሥራው "The open society and its enemies" ይሰኛል። ከዚህ ከመምህሩ የጥናት ሥራ በተወሰደ ስም ነው ኋላ ጆርጅ ሶሮስ ዓለም ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ ድርጅቱን የመሠረተው፤ ስሙም "ኦፕንሶሳይቲ ፋውንዴሽን" ይባላል። ብቻ ከዚህ በኋላ ጆርጅ ሶሮስ በ1970 የሶሮስ ፈንድን አቋቋመ። እሱን ዓለም የሚያውቀው ግን በሁለት ነገር ነው፤ አንዱ እሱ አምጦ በወለደውና ቀደም ሲል በጠቀስነው "ኦፕን ሶሳይቲ" በሚባለው ድርጅቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የእንግሊዝን ባንክ በእንብርክክ በማስኬዱ ነው። ከሁለተኛው እንጀምር... አንድ ቢሊዮን በአንድ ቀን በ1992 እንግሊዞች "ጥቁሩ ረቡዕ" (ብላክ ወይንስዴይ) ብለው የሚያውቁት ታሪክ አለ። ብሪታኒያ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የገባችበት አስገራሚ ቀን ነው። ይህ ቀን ለብሪታኒያ ጥቁር ነበር ካልን ለጆርጅ ሶሮስ ግን ነጭ ነበር፤ የእርሱ የብልጽግና በር የተከፈተው በዚች ቀን ነበር ማለት ይቻላል። ነገሩን በአጭሩ ለማስረዳት፡ ብዙዎቹ የአውሮፓ አገራት ዩሮን ወይም እሱን የሚመስል የጋራ ገንዘብ ለመፍጠር እያለሙ ነበር።ይህን መንገድ የሚጠርግ The European Exchange Rate Mechanism (ERM) የሚባል ህብረት ነበራቸው። ይህንን ለማሳካት ደግሞ አባል አገራት የገንዘባቸው ጥንካሬ ከተወሰነ መጠን ዝቅ እንዳይል ይጠበቅባቸው ነበር። የብሪታኒያ መንግሥት የሚገበያይበት ፖውንድ ስተርሊንግ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል የወለድ ምጣኔን ከፍ በማድረግ ጭምር ሞከረ። ሆኖም አልተሳካም። በዚህ ታሪካዊ ቀን እንግሊዝ ገንዘቧን ፓውንድን ከመውደቅ ማዳን አቃታት፤ ስላቃታትም ከአውሮፓ አገራት የውጭ ምንዛሬ መወሰኛ ኅብረት (ERM) ለመውጣት ተገደደች። ይህ "ጥቁሩ ረቡዕ" ብሪታኒያ ብሔራዊ ኪሳራን በአገር ደረጃ ያወጀችበት ዕለት ነበር። ጆርጅ ሶሮስ ከዚህ ቀን ቀደም ብሎ የፓውንድ መውደቅ አይቀሬ እንደሆነ በመተንበይ ፓውንድ አብዝቶ ከባንኮች ይበደር ነበር። በርካታ ፓውንድ እየተበደረ መልሶ ከባንክ ውጭ በርካሽ ይሸጠዋል። በተከታታይ ፓውንድ ዝቅ ባለ ዋጋ በመሸጥ ሌላ የገንዘብ ኖት በማከማቸቱ (በተለይም የጀርመን ማርክን) ብቻ በትንሹ በአንድ ቀን 1 ቢሊየን ዶላር ማትረፍ ችሏል። በዚህም የተነሳ ጆርጅ ሶሮስ "የእንግሊዝን ባንክ የያንበረከከው ሰው" በመባል ይታወቃል። ጆርጅ ሶሮስ በዚያ ዓመት እንግሊዝን 3.3 ቢሊዮን ፓውንድ አክስሯታል፤ በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ እንግሊዛዊ በተናጥል 15 ፓውንድ ለሶሮስ ከፍሏል ማለት ነው። በእንዲህ ዓይነት አስቀድሞ የገንዘብ ጥንካሬን በመተንበይ በዓመታት ውስጥ በበርካታ አገራት ውስጥ ቢሊዮን ዶላር ማጋበስ እንደቻለ ይነገርለታል፤ ሶሮስ። ሶሮስ ስደተኞችን ያበረታታል፤ ዓለም ድንበር አልባ እንድትሆን ይሠራል በሚል ክስ ይቀርብበታል ኦፕን ሶሳይቲና ሶሮስ እንደ ፈረንጆቹ በ1979 የተመሠረተው ኦፕን ሶሳይቲ በአሁኑ ጊዜ በ120 አገራት እየሠራ ነው። በኢትዮጵያም ቢሮ ለመክፈት በሂደት ላይ እንደነበር አንድ ሰሞን መዘገቡ ይታወሳል። የአገር ቤቱ ሪፖርተር ጋዜጣ የእንግሊዝኛው ቅጂ በፈረንጆች ኅዳር 30 እትሙ እንደዘገበው ደግሞ ኦፕን ሶሳይቲ እገዛ ሊያደርግላቸው ካሰባቸው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች መሀል አዲስ ስታንዳርድ የድረገጽ ጋዜጣና አዲስ ፎርቹን የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ይገኙበታል። ሁለቱ ሚዲያዎች ከ160 እስከ 200ሺህ ዶላር እንደሚለገሳቸውም ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። ሪፖርተር በዚሁ ዘገባው የድርጅቱን ኃላፊ ሩት ኦሜንዲን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ ኦፕንሶሳይቲ በቅርብ ጊዜ ቢሮውን አዲስ አበባ ይከፍታል። እስከዛሬ እውን አልሆነም። • የወንድ የዘር ፍሬን ልክ እንደ ዓይን፣ ኩላሊት መለገስ ይቻላልን? ሊበራል ዲሞክራሲን በማስፋፋት የተጠመደው ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን የብዙ አገሮች ራስ ምታት መሆኑ አልቀረም። በተለይ አገራት ወደ ዲሞክራሲ እንዲሸጋገሩ "አመጾችን ለማቀጣጠል የሚውል ገንዘብ ይረጫል" የሚባለው ኦፕን ሶሳይቲ በሰብአዊ መብትና በትምህርት ላይ ያሳደረው የላቀ አስተዋጽኦ የሚካድ አይደለም። ጆርጅ ሶሮስና የሴራ ፖለቲካ ሚስተር ጆርጅ ሶሮስ ለሴራ ፖለቲካ ለመጀርመያ ጊዜ የተጋለጠው በ1990ዎቹ መጀመርያ ቢሆንም በተለይ በ2003 የኢራቅ ጦርነትን መቃወሙ በሪፐብሊካኖች ዘንድ ጥርስ እንዲነከስበት ሆኗል። "ያለኝን ሀብት በሙሉ ጆርጅ ቡሽን ለማስወገድ ብጠቀምበት አይቆጨኝም" ማለቱ ብዙ ሲያነጋግር ነበር፤ በዚያ ዘመን። ሶሮስ በ2018ቱ የአሜሪካ ምርጫም በተመሳሳይ ገንዘቡን ረጭቷል ተብሎ ይነገራል። ከባራክ ኦባማ መመረጥ ጀርባ ትልቁ ገንዘብ የሶሮስ ነው ተብሎም ይታመናል። እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት ፍቺ እንዳትፈጽም ለሚተጋ ቡድን ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር ለግሷል። የጆርጅ ሶሮስ ስምን ገናና ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የቅርቡ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የነበረው ፍጥጫ ነው። ዶናልድ ትራምፕን የሚያወግዙ ማናቸውም ሰልፎችን በከፍተኛ ገንዘብ ይደግፋል የሚባለው ሶሮስ፤ ከሆንዱራስ ተነስተው በሜክሲኮ አድርገው ወደ አሜሪካ በእግር የዘመቱ ሥራ አጦችን ያዘመተብን እሱ ነው የሚል ክስ ይቀርብበታል። ውግንናው ለትራምፕ እንደሆነ የሚነገርለት ፎክስ ኒውስ በተከታታይ በሰራቸው ዘገባዎች ጆርጅ ሶሮስ ሁሉም የአገራት ድንበሮች እንዲከፈቱና በሕዝቦች መካከል ያልተገደበ ዝውውር እንዲኖር ይሻል ሲል ከሶታል። ዶናልድ ትራምፕም በትዊተር ሰሌዳቸው ገንዘብ ለስደተኞች ሲታደል የሚያሳይ ቪዲዮ በመለጠፍ የገንዘቡ ምንጭ ሶሮስ እንደሆነ ለማመላከት ሞክረዋል። "ዱርዬዎች የአሜሪካንን ድንበር እንዲሰብሩ እየተከፈላቸው ነው" በሚል። በኋላ ጋዜጠኞች እንዳጣሩት ከሆነ ግን ትራምፕ ያጋሩት ቪዲዮ በጭራሽ በሆንዱራስ እንዳልተቀረጸና የቪዲዮው ምንጭም ጓቲማላ እንደሆነች ማረጋገጥ ችለዋል። ትራምፕ ግን ይህ ግድ አልሰጣቸውም። ከዚህ ትራምፕ ካራገቡት የሴራ ፖለቲካ በኋላም በአይሁዳዊያን ላይ የደረሰውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ የሶሮስ ስም በድጋሚ አንሰራራ። በዚህ ጥቃት አንድ ነጭ የአይሁዶች ምኩራብ ውስጥ ገብቶ 11ዱን ከፈጀ በኋላ ግለሰቡ ጆርጅ ሶሮስ የላከው ተደርጎ ሲዘገብ ነበር። ኋላ ላይ ሲጣራ ግን እንዲያውም ወንጀለኛው የጆርጅ ሶሮስ ቀንደኛ ጠላት እንደሆነ ተደርሶበታል። • በኢትዮጵያ ካምፕ ውስጥ ባለ2 ፎቅ መኖሪያ የገነባው ስደተኛ ይህ አክራሪ ነጭ ሽብርተኛ ጽፎታል በተባለ ምሥጢራዊ ሰነድ ማወቅ እንደተቻለው "ጆርጅ ሶሮስ ቀስ በቀስ የነጮችን የበላይነት በአሜሪካና በአውሮፓ ለማጥፋት የሚሰራ ጠላት ነው" ብሎ ያምን ነበር። ይህ አክራሪ ነጭ ሽብርተኛ የታወረበት የሴራ ፖለቲካ እንደሚያትተው ዓለም ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ነጮችን የማዳከምና የነጮችን አገር በጥቁር ስደተኞች ቀስ በቀስ የመሙላት ሐሳብ አለ፤ ይህን ሐሳብ በገንዘብ የሚደግፈው ሰው ደግሞ ጆርጅ ሶሮስ ይባላል። ያንን ጥቃት እንዲያደርስ የተገፋፋውም ይህንን የጆርጅ ሶሮን እንቅስቃሴ ለመግታት ነው። ጆርጅ ሶሮስን የሚያወግዙ የመንገድ ላይ ማስታወቂያዎች በሀንጋሪ ተሰቅለው ይታያሉ የዶናልድ ትራምፕ ሰዎች እጅግ ከማይወዷቸው ቢሊየነሮች ግንባር ቀደሙ ጆርጅ ሶሮስ ነው። በትራምፕ ወዳጆች ዘንድም ሶሮስ ላይ ከባድ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶበት ነበር። "ሶሮስ ናዚ ነው"፤ "ኦባማና ሂላሪ የሶሮስ አሻንጉሊቶች ናቸው"፤ "አሜሪካን ለማፍረስ የሚተጋው አይሁድ ጠሉ ጆርጅ ሶሮስ ነው" የሚሉ ወሬዎች ኢንተርኔቱን ሞልተውት ነበር አንድ ሰሞን። • የወንድ የዘር ፍሬን ልክ እንደ ዓይን፣ ኩላሊት መለገስ ይቻላልን? የጦር መሣሪያ ቁጥጥር እንዲጠብቅ፤ ጸረ ትራምፕ ሰልፎች እንዲፋፋሙ እንዲሁም የፍሎሪዳ ጥቃትን ተከትሎ የተደረገው "ማርች ፎር አወር ላይቭስ ሙቭመንት" በሶሮስ ገንዘብ የተቀነባበሩ እንደሆነ ይታመናል። የትራምፕ ተቺዎችን ለመግደል ያለመ የጥቅል ፖስታ ቦምብ እደላ በተደረገበት ወቅትም በቁጥር አንድ የትራምፕ ጠላትነት የተፈረጀው ሶሮስ ነበር። ሶሮስ ድንበር ይጠላል? ከመካከለኛው አሜሪካ ኑሮ መረረን ያሉ ስደተኞች ወደ አሜሪካ የእግር ጉዞ ሲጀምሩ ትራምፕ የግምብ አጥሩን ቶሎ እንገንባው በሚሉበት ወቅት ይህንን የሕዝቦች ስደትን የሚደግፈው ጆርጅ ሶሮስ ነው የሚሉ ወሬዎች መነዛት ጀምሩ። ትራምፕም ይህንኑ እንደሚጠረጥሩ ተናግረዋል። "እሱ ነው ቢሉኝ አልደነቅም፤ እሱ ስለመሆኑ አላውቅም፤ እሱ እንደሚሆን ግን እገምታለሁ፤ አያስደንቀኝም" ብለው ነበር ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች። የትራምፕ ልጅ በተዋናይት ሮሰን ባር የትዊተር ሰሌዳ ስለ ሶሮስ የተጻፈውን መራር ጥላቻ ማጋራቱም ምን ያህል ሶሮስ በነ ትራምፕ ቤተሰብ የማይወደድ ቢሊየነር እንደሆነ መገመት አስችሏል። ተዋናይት ባር የጻፈችውና የትራምፕ ልጅ ያጋራው ጽሑፍ እንዲህ ይላል። • ወደ ለንደን የሚሄደው አስደናቂው የትራምፕ ጓዝ "በነገራችሁ ላይ ጆርጅ ሶሮስ ናዚ ነው። የገዛ አይሁድ ጓደኛውን በጀርመን ማጎርያ ካምፕ ውስጥ አስገድሎ ገንዘቡን የዘረፈ ናዚ" ይህን ተከትሎ የሶሮስ ቃል አቀባይ "እንዲህ ዓይነት መሠረተ ቢስ ክሶች በሶሮስ ሳይሆን በመላው አይሁድ ሕዝብ ላይ የተቃጡ ስድቦች ናቸው፤ በተለይም በጅምላ ፍጅቱ ተጠቂዎች ላይ..." ብሏል። እርግጥ ነው ሶሮስ አገሮች ነጻ እንዲሆኑ፤ የሕዝቦች ነጻ እንቅስቃሴ እንዲኖር ይተጋል። ይህ ግን አገሮች ድንበር አይኑራቸው ከሚል ጽንሰ ሐሳብ የሚመነጭ አይደለም። የሶሮስ ትውልድ አገር ሐንጋሪ ስደተኞች እንዳይገቡባት የሽቦ አጥር አጥራለች "የነጮች አህጉር የሆነችውን አውሮፓን በስደተኛ ልታጥለቀልቃት ነው ሀሳብህ" የጆርጅ ሶሮስ ተቺዎች ሶሮስ በአገራት የውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ ይገባል፤ እጁም ረዥም ነው ይሉታል። እርግጥ ነው ለሂላሪና ለኦባማ የምርጫ ዘመቻ ትልቁን ገንዘብ ስለመስጠቱ የሚካድ አይደለም። ይህ ተግባሩ ግን በአሜሪካ ብቻ የሚወሰን አልሆነም። ሶሮስ በ1980ዎቹ የሀንጋሪ ኮምኒስቶችን ለማዳከም ገንዘቡን አውሎታል። ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን ለዲሞክራሲ እሴቶች የሚተጋ ነው። በዓመታት ውስጥ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር ለዚህ ድርጅቱ ፈሰስ አድርጓል ሶሮስ። ይህ ገንዘብ በምንም መለኪያ ትንሽ አይደለም። • ትራምፕ ስለስደተኞች በተናገሩት ወቀሳ ደረሰባቸው "ይህን ድርጅት ያቆምኩት አስተማማኝ ዲሞክራሲን በመላው ዓለም ለመዘርጋት ነው" ይላል፤ እሱም ቢሆን። ሶሮስ በትውልድ አገሩ ሀንጋሪ ቢሊዮን ዶላሮችን በማፍሰስ የሰብአዊ መብት ፕሮጀክቶችንና በትምህርት ቤቶች ነጻ የምግብ እደላዎች እንዲኖሩ አስችሏል። ከሁሉም በላይ በኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ጭምር ዝነኛ የሆነውና የውጭ የትምህርት ዕድል በመስጠት የሚታወቀው የሴንትራል ዩሮፒያን ዩኒቨርስቲን (CEU) የመሠረተው ጆርጅ ሶሮስ ነው። "አንዳንድ ጊዜ ትልቅ ለማይመስሉ ነገር ግን ለምናምንባቸው ነገሮች መቆም አለብን" ይላል ሶሮስ። ከእነዚህ መሀል አንዱ በስደተኞች ላይ ያለው አቋሙ ነው። በአውሮፓ የሚገኙ ስደተኞችን ለማገዝ የሚተጋው ሶሮስ ከበርካታ አገራት መንግሥታት ጥላቻን አትርፏል። "የነጮች አህጉር የሆነችውን አውሮፓን በስደተኛ ልታጥለቀልቃት ነው ሀሳብህ" የሚል ክስ ይነሳበታል። እሱም "በስደተኛ ላይ ያለኝ አቋም ብዙ ጠላት አፍርቶልኛል" ይላል። • ማሽተት አለመቻል ምን ይመስላል? ለምሳሌ የገዛ ትውልድ አገሩ ሀንጋሪ ለሶሮስ ያላትን ጥላቻ በጎዳና ላይ ቢልቦርድ ጭምር ሰቅላዋለች። አሁን ያለው የሀንጋሪያዊያን መንግሥት በአመዛኙ ጥቁር ጠል የሚባል ነው። በሀንጋሪ ለስደተኞቸ ድጋፍ የሰጠ ዜጋ በእስር ይቀጣል። የሚደንቀው ታዲያ የዚህን የቅጣት ሕግ ስም ሳይቀር የሃንጋሪ መንግሥት "ስቶፕ ሶሮስ" ብሎ ነው የሚጠራው። ያው ስደተኞችን እያጋዘ የሚያመጣብን ጆርጅ ሶሮስ ነው በሚል። የሀንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የሶሮስ ቀንደኛ ጠላት ናቸው። በስሎቫኪያ የጋዜጠኛ መገደልን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ የተደናገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት ባደረጉት ንግግር፡ "ይሄ የጆርጅ ሶሮስ እጅ ነው። በስሎቫኪያ የተነሳው ነውጥ የሶሮስ ሥራ ነው። እሱ ስደተኛ እንዳይመጣባቸው ለሚፈልጉ አገራት አይራራም። የጎዳና ላይ ነውጥ እያስነሳ ይገለብጣቸዋል" ብለው ነበር። ሶሮስ ስለሱ ስለሚባለው ምን ይላል? ጆርጅ ሶሮስ ከአፍሪካ እስከ ምሥራቅ አውሮፓ፣ ከትራምፕ እስከ ሞዲ ስለሱ የሚባለውን ሲሰማ ምን ይላል? በእርግጥ የዓለም ፖለቲካን የሚዘውረው ሰው ጆርጅ ሳሮስ ነው? "የእኔ እጅ ረዥም እንደሆነ የሚነገረው የተጋነነ ነው። እንደሚባለው የእንግሊዝ ባንክን አላንኮታኮትኩትም። ገበያው ነው ያንኮታኮተው። እንደሚባለው ስደተኛን እያጋዝኩ ወደ አውሮፓና አሜሪካ አላስኮበልልም። ኦፕን ሶሳይቲን የመሠረትኩት ዲሞክራሲንና የዲሞክራሲ ተቋማትን ለማጎልበት ነው" ይላል። ጆርጅ ሶሮስ እና ዶናልድ ትራምፕ ጆርጅ ሳሮስ እንደ ትራምፕ የሚንቀው ሰው ያለ አይመስልም። "ትራምፕ አታላይና በራሱ ፍቅር የናወዘ ሰው ነው" ይላል። ትራምፕን ብሔራዊ ጥቅምን ሳይቀር ለግል ስምና ዝናው አሳልፎ ለመስጠት የማይሳሳ ነው ይለዋል። የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዠን ፒንግን ደግሞ በቴክኖሎጂ መላ ሕዝቡን ለመቆጣጠር የሚሞክር አምባገነን ይለዋል። ዓለማችን ሁለቱን መሪዎች ብታስወግድ የተሻለ እንኖር ነበር ይላል ሶሮስ። ሶሮስ መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው ይላል ሶሮስ በስዊዘርላንድ ዳቮስ በቅርቡ ባደረገው ንግግር ዘረኝነት በአገራት እየተስፋፋ መምጣቱ እንደሚያሳስበው ተናግሯል። ጥላቻ እንዳይነግስ ለሚሰሩ፣ የመቻቻል ፕሮጀክቶችን ለማጎልበት ደግሞ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 1 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ቃል ገብቷል። በዘረኞችና በሀሰት ወሬ አራጋቢዎች የምትሾረው ዓለም ለሶሮስ ታሳስበዋለች። ክሪቲካል ቲንኪንግ ወይም ምክንያታዊነትን ቶሎ ካላስፋፋን መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው ይላል ሶሮስ። ከመሞቴ በፊት ማድረግ ይመፍልገውም ይህንን ነው።
news-48425801
https://www.bbc.com/amharic/news-48425801
ሲኤንኤን ለዓመቱ ምርጥ ያጫት ኢትዮጵያዊት ፍረወይኒ መብራህቱ
ፍረወይኒ መብራህቱ በዘንድሮው የሲኤንኤን 'ሂሮ ኦፍ ዘ ይር' (የዓመቱ ምርጥ) ውድድር ውስጥ ለመጨረሻው ዙር ከደረሱ አስር እጩዎች አንዷ ናት።
የውድድሩ አሸናፊ የፊታችን ሕዳር 28 ቀን 2012 ዓ. ም. ይፋ የሚደግ ሲሆን፤ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለፍረወይኒ ድምጻቸውን እሰጡ ይገኛሉ። ትዊተር እና ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ለፍረወይኒ ድምጽ እንዲሰጥ ቅስቀሳ እተካሄደም ነው። ቢቢሲ በአንድ ወቅት ስለፍረወይኒ መብራህቱ 'ማርያም ሰባ'፡ ፍረወይኒ 'የወር አበባ አሁንም እንደ ነውር ይቆጠራል' በሚል ርዕስ የሠራው ዘገባ እነሆ፦ በዚህ በሰለጠነ ዓለም እስከ ዛሬ ድረስ የወር አበባ አንዱ የሴት ልጅ ተፈጥሮአዊ ክስተት እንደሆነ የማይቀበሉ ኃይማኖቶችና ባህሎች ያላቸው አገራት ጥቂት አይደሉም። በበርካታ የአፍሪካ አገራትም ሆነ በሌሎች ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ወቅት ከኃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ተከልክለው ነጻነታቸው በኃይማኖታዊው ወይም ባህላዊው ትምህርት እንዲገዛ ይደረጋል። ህንድ የወር አበባ እንደነውር ከሚቆጥሩበት አገራት አንዷ ነች። 70 ከመቶ በህንድ የሚገኙ የገጠር ሴቶች በግንዛቤ ችግር፣ በድህነትና ሀፍረት የወር አበባ በሚያዩበት ወቅት ንጽህናቸውን በአግባቡ ስለማይጠብቁ ለሞትና በሽታ የተጋለጡ ናቸው። በዚህ ምክንያት ቆሽሸዋል ተብለው ስለሚፈረጁ 28 በመቶ ታዳጊዎች ከትምህርት ገበታቸው ይቀራሉ። • "ጥቃት የደረሰባት ሴት ከግንኙነቱ ለመውጣት 10 ዓመት ይፈጅባታል" የጋና ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ወቅት ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ እንዳይሻገሩት የሚከለከል 'ኢፊን' የሚባል ወንዝ አለ። ለምን ቢባል በወር አበባ ጊዜ ሴቷ ስለ ምትረክስ ወንዙ ላይ የሚመለኩ አማልክትን ታረክሳለች ተብሎ ስለ ሚታመን ነው መልሱ። የኢትዮጵያ ገጠር አካባቢዎችም ሴቶች የተለያዩ ችግሮች ይገጥሟቸዋል። ዩኒሴፍ እንደሚለው 75 በመቶ ሴቶች በቂ የንጽህና መጠበቂያ አያገኙም፤ 50 በመቶ የሚሆኑትን ደግሞ በዚህ ምክንያት ከትምህርታቸው ይቀራሉ። የግል ሕይወትን ተሞክሮን ለማህበረሰብ ለውጥ በዚህ ችግር አንድም ሴት ከትምህርት ገበታ መቅረት የለባትም የሚል አቋም ያላት ፍረወይኒ መብራህቱ "የወር አበባ በየወሩ የሚመጣ ስለሆነ ይህ ችግር ለመፍታት ማድረግ ስላለብኝ አንድ ነገር በየወሩ የሚያስታውሰኝ ነገር ነበረኝ" ትላለች። ወይዘሮ ፍረወይኒን በየወሩ የሚቀሰቅሳት ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባ ያየችበትን እድሜ ስታስታውስ ነው። "የትኛዋ ሴት ናት ለመጀመርያ ጊዜ የወር አበባ ስላየችበት ቀን ሳትሸማቀቅ የምታወራ?" በማለትም ትጠይቃለች።። "ኅብረተሰባችን ስለ ወር አበባ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ በመሆኑ፣ ታላላቅ እህቶቼና ወላጆቼም የማያወሩት ጉዳይ ስለ ነበር፣ እኔም የወር አበባ ምን እንደሆነ ሳላውቅ ነው ያደግኩት" ስትል በልጅነቷ የነበረውን ሁኔታ መለስ ብላ ታስታውሳለች። • መአዛን በስለት ወግቶ ከፖሊስ ያመለጠው አሁንም አልተያዘም የወር አበባ ያየችበትን የመጀመሪያ ቀን በማስታወስም "የወር አበባዋን ያየች ሴት ባልጋለች ይባል ስለነበረ ጊዜው ደርሶ ቢመጣም፣ ምን ሆኜ ይሆን ይህ ነገር የተከሰተው ብዬ ነበር" ትላለች ወይዘሮ ፍረወይኒ። ፍረወይኒ እድሜዋ በአርባዎቹ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን በመቀሌ ከተማ ማርያም ሰባ የተሰኘ የሚታጠብ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያን በማምረት ሥራ ላይ ተሰማርታለች። በዚህ ሥራዋ ሲ ኤን ኤን "ጀግና ሴት" ብሎ የሰየማት ወይዘሮ ፍረወይኒ በአሜሪካ በኬሚካል ኢንጅነሪግ ዲግሪዋን ሰርታለች። ፍረወይኒ ዘመናዊ የንጽህና መጠበቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየችው ለትምህርት በሄደችበት አሜሪካ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1983 ነበር። "ለትምህርት ወደ አሜሪካ እንደሄድኩ ታላቅ እህቴ መጀመርያ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) እንድገዛ ወደ ሱፐር ማርኬት ወሰደችኝ። ያኔ ነበር አገር ቤት ትቼያቸው የመጣሁት ሴቶችስ መች ይሆን ይሄንኑ አይነት አማራጭ የሚያገኙት የሚል ሀሳብ አእምሮዬ ላይ የቀረው" በማለት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ሴቶች የሚቀርብ የንፅህና መጠበቂያ በርካሽ ዋጋ ማቅረብ የሚል ሀሳብ የተጠነሰሰው አሜሪካ ሳሉ መሆኑን ያስረዳሉ። • “አንቺሆዬ”፡ የኢትዮጵያዊያት ታሪክን መናገር በ1983 ዓ.ም የመንግሥት ለውጥን ተከትሎ ሁኔታዎች ተቀይረው እንደሆነ በማለት ወደ ሀገራቸው ቢመለሱም ልጅ ሆነው ነውር ሲባል ይሰሙትና ያዩት የነበረው ነገር አሁንም ጥዩፍ እንደሆነ፣ መገለል እንዳለ አስተዋሉ። ሰዎች ስጠይቅ ይላሉ ወይዘሮ ፍረወይኒ "ለምንድነው ስለዚህ ጉዳይ የምትጠይቂኝ ይሉኝ ነበር" በማለት የወር አበባ አሁንም እንደ ነውር እንደሚቆጠር ያስረዳሉ። ማንኛዋም ሴት የወር አበባ በምታይባቸው ቀናት የምታሳልፋቸው ጊዜያት ከባድ መሆናቸውን የሚጠቅሱት ፍረወይኒ "በገጠር አካባቢዎች ጉድጓድ ቆፍረን እንቀመጣለን አሉኝ። ያኔ የሚፈሰው ደም ልክ እንደተከፈተ የውሃ ቧንቧ መቆጣጠር የማይቻል መሆኑን ሳስብ ከእግር ጥፍሬ እስከ ራሴ መጥፎ ስሜት ነበር የተሰማኝ" ይላሉ። በአቅም ማነስ ምክንያት በርካታ ሴቶች የወር አበባቸውን በሚያዩበት ወቅት አንሶላ ቀድደው፣ እራፊ ጨርቅ አጥበው ጸሐይ ላይ እያሰጡና እያደረቁ ነው የሚጠቀሙት። ከዚህ በከፋ ደረጃ ግን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እስከ አሁን የሙታንታንና የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያን ጥቅም የማያውቁ ሴቶች መኖራቸውን ይጠቅሳሉ። ይህንን የሴቶች ችግር ከእኛ ሴቶች ውጪ ተረድቶት መፍታት የሚችል ሰው የለም በማለትም ያስረዳሉ። ለአለፉት 10 ዓመታት 'ማርያም ሰባ' ብላ በልጃቸው በሰየሙት ድርጀት ስም የሚታጠብ ሞዴስ በማምረት በዝቅተኛ ዋጋ በትግራይ እና አፋር ገጠር አካባቢዎች ለሚገኙ ሴቶች ያቀርባሉ። ማርያም ሰባ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ታጥቦ መልሶ አገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን ከ18 ወራት እስከ ሁለት ዓመት ማገልገል ይችላል። በምቾትና ፈሳሽ በመያዝ አቅም አንዴ ጥቅም ላይ ውሎ ከሚወገደው የንጽህና መጠበቂያ የሚለየው ነገር እንደሌለ የሚናገሩት ወ/ሮ ፍሬወይኒ ግማሹ ጥሬ እቃ በአገር ውስጥ ከሚመረት ጨርቅና ጥጥ እንደሚጠቀሙ ይገልጻሉ። • በጃፓን በተፈጸመ ጥቃት ሦስት ሰዎች ሞቱ ከንጽህና መጠበቂያ ጨርቁ ጋር ለንጽህና መጠበቂያው የሚሆን ሙታንታም አብሮ ይሰራል። ተቋሙ ንጽህና መጠበቂያውን ማምረት ሲጀምር በዓመት 200 ሺህ ያመርት የነበረ ሲሆን አሁን ወደ አንድ ሚሊዮን ማሳደግ እንደቻለ ወ/ሮ ፍረወይኒ ይናገራሉ። ውጣ ውረዶች በ2014 የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ከባለቤቱ ጋር ወደ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የመጣው ዶክተር ልዊስ ዎል የማርያም ሰባን ፋብሪካ ማገዝ እንዳለበት አምኖ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሰባት ወር ወስዶበታል። ከዚህ በኋላ ግን "ዲግኒቲ ፔሬድ" የሚል ፕሮጀክት በመጀመር የድርጅቱን ምርቶች በመግዛት 150 ሺህ የሚደርሱ ሴቶች ተጠቃሚዎች እንዲሆኑና በወር አበባ ዙርያ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች ለመፍታት የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን እየሰጠ ይገኛል። ድርጅቱ ሴቶችና ወንዶች ስለ ወር አበባ ማወቅ ያላቸው እውቀት ከፍ እንዲል ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን በትግራይ ከ800 ሺ በላይ ሴቶች የዚህ ንጽህና መጠበቂያን እንዲያገኙ በማድረግ ትምህርታቸው ያቋረጡ ሴቶች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ይናገራሉ። "ይህ መሰረታዊ ችግር ካልተፈታ ሴት ልጅ ልትደርስበት የሚገባ ቦታ መድረስ አትችልም" የሚሉት ወ/ሮ ፍረወይኒ ሥራውን ለመጀመር የባንኮችን ደጅ በጠኑበት ወቅት የገጠማቸውን ያስታውሳሉ። ባንኮች ለማሳመን ሁለት ዓመት እንደወሰደባቸው የሚናገሩት ወ/ሮ ፍሬወይኒ "እኔ ደፍሬ ካልጀመርኩት የወር አበባ ለዘላለም የሚያሳፍር ነገር ሆኖ ይቀራል" በሚል ቆራጥነት በእቅዳቸው በመግፋት እንዳሳኩት ይገልጣሉ። • በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀሰ ረብሻ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ ማንም በልጁ አይጨክንም፤ ይህ ፕሮጀክት ለእኔ ልጄ ነበር። እስከ መጨረሻው መውሰድ አለብኝ ብዬ የሚገጥሙኝ ፈተናዎችን በጽናት ተወጥቻለሁ። "የሴት ልጅ ውበትዋ ደግሞ ጥንካሬዋ ነው" ይላሉ። አክለውም የወር አበባን በሚመለከት ያለው ግንዛቤና አመለካከት ለመቀየር ግን አሁንም ትልቅ ሥራ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው በማለት የችግሩን ግዝፈት ይናገራሉ።
56495526
https://www.bbc.com/amharic/56495526
ማኅበራዊ ሚዲያ፡ ቲክቶክ ‘እንጀራ’ የሆነላቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
ሃያት የአባቷንና የእናቷን አልባሳት ተጠቅማ በኩል ጺም ሰርታ የሰራቻቸው ቪዲዮዎች በበርካቶች ተወዶላታል። በሚሊዮን የሚቆጠር እይታም አግኝተዋል። የትናየትም እንዲሁ - ቤት ውስጥ ባሉ ቁሳቁሶችና አልባሳት በርካታ ቀልብ የገዙ ቪዲዎች ሰርታለች።
ቲክቶክ ላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሏቸው ሃያት ናስር እና የትናየት ታዬ አዝናኝና 'ቀለል' ያሉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራሉ። የትናየት ዘንድሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮንስትራክሽን ማኔጅምንት ተመርቃ በኢንቴሪየር ዲዛየን መማር ጀምራለች። ሃያት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፒውተር ሳይንስ የ3ኛ ዓመት ተማሪ ነች። ዳንሶች፣ ከተለያዩ ቪዲዮዎች የተወሰዱ ድምጾችን በከንፈር እንቅስቃሴና በትወና መልክ መስራት (lip-sync) በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰዎች ሊያሳዩ የሚችሉትን ስሜት ማንጸባረቅና መሰል ጉዳዮች በብዛት የሰሯቸው ቪዲዮዎች ይዘቶች ናቸው። ለነገሩ - በአለም ዙሪያ ያለው ልምድም ይሃው ነው። ተጠቃሚዎቹ 'ዘና' ለሚያደርጉ እንጂ ፖለቲካን ለመሰሉ ጠንካራ ጉዳዮች ብዙም ቦታ የሚሰጡ አይመስልም። 'ኢንፍሎይንሰር ሜኪንግ ሃብ' የተሰኘ ድረ ገጽ በቲክ ቶክ ተወዳጅነት ከሚገኙ ሥራዎች በነ ሀያት የሚሰሩትን ጨምሮ 21 የቪዲዮ አይነቶችን ዘርዝሯል። የቤት እንስሳት አስገራሚ እንቅስቃሴዎች፣ ከተለያዩ ቁሳቁሶች የሚሰሩ የጥበብ ስራዎች፣ የፍራፍሬዎች አቆራረጥ፣ የተለያዩ ሳይንሳዊ ሙከራዎች፣ የቱቶሪያል/ማስተማሪያ ቪዲዮዎች፣ መተግበሪያው የሚያቀርበው አስቂኝ ገጽታን የሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች፣ የዕለት ውሎን የሚያስቃኙና መሰል ቪዲዮች በቲክቶክ ተጠቃሚዎች እጅግ ተወዳጅ ስለመሆናቸው አትቷል። 'ቢዝነስስ ኦፍ አፕ' የተባለ ሌላ ድረ ገጽ ደግሞ አዝናኝና ቀልድ አዘል ይዘቶች ከየትኛውም ማህበራዊ ሚዲያ በላይ በቲክቶክ ሰፊ ተወዳጅነት እንዳላቸው ይጠቁማል። ተጠቃሚዎች አስቂኝ ቪዲዮዎችን በፌስ ቡክ ማጋራት ልምዳቸው 36 በመቶ በኢንሰታግራም 42 በመቶ ሲሆን ቲክቶክ ላይ 48 በመቶ ይደርሳል። "ቲክቶክ ላይ የሚያመዝነው ይዘት መዝናኛ ነው" የምትለው የትናየት "ከ'ሆነ ጊዜ በኋላ ፖለቲካዊ ጉዳዮችም አሉ። ግን ብዙም ትኩረት አያገኝም" ስትል ገልጻለች። የኮሮናቫይርስ ሲሳይ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይርስ መከሰት በስፋት ካስተዋወቃቸው ጉዳዮች አንዱ ቲክቶክ ሳይሆን አይቀርም። የትናየትም በዚህ ሃሰብ ትስማማለች። የትናየት የኮሮናቫይርስ በኢትዮጵያ ከመከሰቱ በፊት የነበሯት ተከታዮቿ 2 ሺህ አካባቢ እንደነበር ትገልጸለች። ከቫይረሱ መከሰት በኋላ ግን የተከታዮ ቁጥር 200 ሺህን ተሻግሯል። ሀያት ደግሞ ከቫይረሱ መከሰት 1 ወር በፊት ቲክቶክን ተቀላቅላ ከዛ በኋላ ባሉት ጊዜያት ከ306 ሺህ በላይ ተካታዮችን አፍርታለች። የኮሙኒኬሽን ባለሙያው አቶ ነጻነት ተስፋዬ በቫይረሱ ምክንያት ብዙዎች ቤት ለመዋል መገደዳቸውና ትምህርትን ጨምሮ ሌሎች ክንውኖች በኢንተርኔት አማካኝነት እንዲሰጥ መደረጉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከፍ እንዳደረገው ይናገራሉ። ይህም ቲክቶክን ጨምሮ የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎች በኢትዮጵያ ያሏቸውን ተጠቃሚዎች እንዳሰደገም ገልጸዋል። ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱና መደበኛ እንቅስቃሴዎች ወደነበሩበት ሲመለሱ የተመልካቾች ቁጥር እየቀነሰ እንደመጣ ገለጻለች። በተቀረው ዓለምም ኮሮና ለቲክቶክ 'ሲሳይ' ይዞ የመጣ ይመስላል። ቲክቶክ የፈጠረው 'እንጀራ' ሃያትም ሆነ የትናየት ቲክቶክ ያላቸውን ተሰጥኦ ለማውጣት ምቹ መድረክ እንደሆነላቸው ተናግረዋል። "ያለኝን አቅም እንዳውቅና ከብዙ ሰው ጋር እንድተዋወቅ ያደረገኝ ቲክቶክ ነው' የምትለው የትናየት የስራ ዕድሎችም እንደፈጠረላት ገልጻለች። የተለያዩ ድርጅቶች ያላቸውን ምርትና አገልግሎቶችን እያስተዋወቀች ትገኛለች። "በተለይ ወጣቱ ማግኘት ከሚፈልጉት ድርጅቶች ጋር እየሰራሁ ነው። የማገኘው ገቢ ትልቅ ነው ባልልም ራሴን እንድችል አድርጎኛል" ስትል ታሰረዳለች። ሀያት በተመሳሳይ የተለያዩ ድርጅቶችን ምርት ከማስተዋወቅ አልፎ አንድ ፊልም ላይ በትወና እንድትሳተፍ ቲክቶክ በር ከፍቷል። በሌላ ፊልም ላይም እንድትተውንና የቲቪ ማስታወቂያ እንድትሰራ ግብዣ ቀርቦላታል። ይህም የፊልሙን ዓለም ለመቀላቀል ከልጅነቷ ጀምሮ የነበራትን ምኞት አሳክቷል። "እኔ ሂጃብ አደርጋለሁ። እሱን [ሂጃብ] አድርጌ ፊልም እሰራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም። ቲክቶክ ስለመጣ እንጂ ማን አይቶ ያሰራኝ ነበር" ብላለች ሃያት። ከዚህም ሲዘል የቲክቶክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን የሌላውን ዓለም እንዲያዩ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን ባህል፣ አለባበስ፥ መልክዓ ምድርና መሰል ጉዳዮች እንዲያስተዋወቁ በር ከፍቷል ደግሞ የሚሉት የኮሚኒኬሽን ባለሙያው አቶ ነጻነት ናቸው። ቲክቶክና ወጣቶች በዓለም ዙሪያ ከቲክቶክ ተጠቃሚዎች 42 በመቶ የሚሆኑት ከ18-24 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። የኮሚኒኬሽን ባለሙያው አቶ ነጻነት ቲክቶክ ያለው ይዘትና ለአጠቃቀም ምቹ መሆኑ በወጣቶች የሚወደድ እንዲሆን አድርጎታል ይላሉ። ተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎች በዚህ መስመር ተገናኝተው መረጃ እንዲለዋወጡ እንድል እንደሰጠም ጠቁመዋል። የትናየት በቲክቶክ መተገበሪያዋ በኩል ባገኘችው መረጃ ከአጠቃላይ ተከታዮቿ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከ18-24 ዕድሜ ላይ የሚገኙ ናቸው። 'ቀለል' ያሉ ይዘቶችን በብዛት ማስተናገዱ በወጣቶች የሚመረጥ ሳያደርገው እንዳልቀረ የኮሙኑኬሽን ባለሙያውም ይሁን የቲክቶክ ተሳታፊዎቹ ጠቁመዋል። "ፌስቡክ ላይ ፖለቲካ ነው። ቲቪ ላይ ፖለቲካ ነው። እዚህ ላይ [ቲክቶክ] ላይ ግን መዝናኛ ነው። ለዛ ይመስለኛል ወጣቱ በደንብ የሚከታተለን" ስትል ገልጻለች ሃያት። የቲክቶከሮቹ ቀጣይ ዕቅድ የ3ኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪዋ ሃያት በቲክቶክ ምክንያት ያገኘችውን ፊልም የመሥራት ዕድል አጠናክራ መቀጠል ትፈልጋለች- በተለይ በድርሰት። 'በቲክቶክ ብቻ መገደብ አልፈልግም። በጣም አሪፍ ፊልም ሰርቼ መሸለም ነው የምፈለገው ብላለች። የትናየት ከምርቃት በኃላ የጀመርችውን ትምህርት አጠናቃ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ የመሰማራት ዕቅድ አላት። የቲክቶክ ተሳትፎዋንም መቀጠል እንዲሁ። "ይህን ያህል ተከታይ ማግኘት ቀላል ዕድል አይደለም" የምትለው የትናየት ይህንን ዕድል ባለማባክን ለወጣቶች መልካም ተምሳሌት ለመሆን እንደምትሰራ ገልጻለች። ወጣቶች ያላቸውን አቅም ለማሳየት ቲክቶክ ሁነኛ መድረክ ነው የሚሉት ድግሞ አቶ ነጻነት ናቸው። እናም ወደፊት ስራ ሊያገኙበት የሚችሉባቸውን ቪዲዮዎች ፈጠራ በተሞላበት መንገድ እንዲያቀርቡ መክረዋል። በመዝናኛ፣ በፋሽን፣ በዕደ ጥበብ፣ በጉብኝትና ጉዞ ዘርፎች ላይ መሰማራት የሚፈለጉ ወጣቶች ቲክቶክ ላይ ስራዎቻቸውን ቢያቀርቡ ወደ ገበያው ለመቀላቀል መልካም ዕድል ሊሆን ይችላል ብለዋል የኮሚኒኬሽን ባለሙያው። ቲክቶክን በምን ይነቀፋል? የቲክቶክ 'የተጠቃሚዎችን ፍላጎት የሚገነዘበው ቀመር ' ወይም algorism በሚስጥር የተያዘ እንደሆነ ይገለጻል። ቀመሩ ተጠቃሚው መጀመሪያ የወደደውን 'ላይክ' ያደረገው ቪዲዮ ብቻ በመውሰድ ተመሳሳይ ይዘቶችን በብዛት ያቀርባል። ይህ መሆኑ ደግሞ ተጠቃሚዎች ለረዥም ጊዜ ቲክቶክ ላይ እንዲያጠፉ ምክንያት ይሆናል። በሌላ በኩል የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ይሰጣል ተብሎ ይተቻል። ህንድ ለብሄራዊ ደህንነቷ አደጋ እንደሆነ በመግለጽና 'ተጠቃሚዎች በማያውቁት መንገድ መረጃዎቻቸውን ይሰርቃል' በሚል ቲክቶክ በምድሯ እንዳይሰራ አግዳዋለች። የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ቲክ ቶክ ላይ 'ጥርስ ነክሰውበት' ሊያግዱትም ተቃርበው ነበር - ለብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ነው በማለት! በተመሳሳይ ምክንያት መተግበሪያው በአሜሪካው የመከላከያ ተቋም በሚገኙና ለስራ በሚውሉ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ አገልግሎት እንዳይሰጥ ታግዶል። ዩናይትድ ኪንግደምና አውስትራሊያም ስጋታቸውን ገልጸዋል። ቲክቶክ ግን ይህንን ትችት አይቀበለውም። የሆነው ሆኖ፣ ቲክቶክ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ወጣት ኢትዮጵያውያንን ቀልብ እየገዛና በሌላው ማህበራዊ ሚዲያዎች 'ከሚያነታርኩ' ጉዳዮች ለመሽሽ እየዋለ ያለ ይመስላል። ለሀያትና የትናየት አይነት ተጠቃሚዎች ድግሞ አሁንም የዕድልና የገቢ ምንጭ መሆኑ ቀጥሏል። "በቲክቶክ የገቢ ምንጭን ጨምሮ ሦስት ዕድሎች አግኝቸበታለሁ" የትናየት ታዬ
news-52378452
https://www.bbc.com/amharic/news-52378452
ኮሮናቫይረስ፡ "ከሞትኩ መላዕክትስ ስሜን ለምን አይጠሩም እል ነበር" ከኮሮናቫይረስ ያገገመችዋ
የአርባ ዘጠኝ ዓመቷ ኤልዛቤት በህይወት መቆየትን፣ መተንፈስን እንደ ቀላል አታየውም። እድለኛ እንደሆነችም ታውቃለች። በኮሮናቫይረስ በጠና ታማ ሆስፒታል የገባችውም በዚህ ወር ነበር። ለማገገም ያያችውን ስቃይ፣ ሆስፒታል ውስጥ ስለተደረገላት ድጋፍ ለቢቢሲ ጋዜጠኛ አጫውታዋለች። የመጀመሪያዎቹ ቀናት
አስታውሳለሁ ቀኑ አርብ ነበር፣ ከሌላው ጊዜ በተለየ ድካም ተጫጫነኝ። አልጋ ላይ ስወጣ ድካሙን መቋቋም አልቻልኩም ነበር። በመጪዎቹ ቀናት ቅዳሜና እሁድም እንዲሁ በማላውቀው ምክንያት በድካም ተወጥሬ ነው ያሳለፍኳቸው። ሰኞ ዕለትም ድካሙ ቀጠለ፣ እግሬ መዝለፍለፍ እንዲሁም መቋቋም የማልችለው ህመም ይሰማኝ ጀመር። ምናልባት የጡንቻ መኮማተር ይሆን ብዬ ህመሙንም ለማስታገስ ፓራሲታሞል ዋጥኩኝ። •በሴቶች የሚመሩ አገራት ወረርሽኙን በተሳካ ሁኔታ እንዴት ተቆጣጠሩት? •ፌስቡክ ከእንግሊዛውያን የጤና መረጃ ሊሰበስብ ነው ሳል ነበረኝ ግን ከባድ አልነበረም። ለሳምንት ያህልም ከአልጋዬ መውጣት አልቻልኩም። አካባቢዬ ወደሚገኝ የነዳጅ ማደያ በትግል እቃ ለመግዛት ሄድኩ። ስመለስ ያንቀጠቅጠኝ ያንዘፈዝፈኝ ነበር፤ ሰውነቴ በረዶ የሰራ ይመስል ቀዘቀኝ። ሙቀት እንዴት ላግኝ? የሞቀ ውሃ በአራት ጠርሙሶች አድርጌ፣ ሁለት ብርድ ልብስ ብደርብም ምንም ሊሞቀኝ አልቻለም። ከዚያም ትንሽ ቆይቶ ሙቀት አይደለም ትኩሳት ለቀቀብኝ። ሰውነቴ እንደ እሳት ነደደ፣ የራስ ምታቱ ጭንቅላቴን ለሁለት የሚከፍል እስኪመስል ድረስ በቃላት መግለፅ የማልችለው ህመም ይሰማኝ ጀመር። መብላት አልቻልኩም፣ ያስመልሰኛል፣ ሰውነቴ በላብ ተጠመቀ፣ ትንፋሼም መቆራረጥ ጀመረ እናም ትንሽ ቆይቶም መተንፈስ አልቻልኩም። የአስም ህመምተኛ በመሆኔ የትንፋሼ ሁኔታ ትንሽ ቢያሰጋኝም ቤት ሆኜ ማገገም እንደምችል ተስፋ ነበረኝ። ነገር ግን ከጥቂት ቀናት በኋላ ራሴን መሳት ጀመርኩ፣ ያለሁበትን መዘንጋት ጭራሽ የ15 ዓመት ልጄ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት ለእርዳታ እንደደወለ ሲነግረኝ እንደ ህልም ነው ትዝ የሚለኝ። የህክምና ባለሙያዎቹ መጥተው የአምቡላንስ ሾፌሩ "በጣም ደክማለች፤ ይዘናት ልንመጣ ነው" ሲልም ከርቀት ይሰማኛል። የኦከስጅን መተንፈሻ ማሽን ገጠሙልኝና ወደ አምቡላንሱ ውስጥ አስገቡኝ። አንደኛው ልጄ እናቴን ጠርቷት ስለነበር ስታየኝ የወላድ አንጀቷ ተብረከረከ። ለእኔም በዚያ ሁኔታ ሆኜ ፊቷ ላይ ያለውን ተስፋ መቁረጥ ማየት ከባድ ነበር። የልብ ህመም ስላለባት ተጠግታ ልታየኝም አልቻለችም። ሆስፒታል ስንደርስም የእኛ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አምቡላንሶችም ህመምተኞችን ለማውረድ ተራቸውን እየጠበቁ ነበር። ተራዬም እስኪደርስ ለሦስት ሰዓታት ያህል ጠበቅኩ። ተራዬ ሲደርስም በተሽከርካሪ ወንበር እየገፉ ለብቻ የተለየ ክፍልም ሆነ ቦታ እንደሌለና ሆስፒታሉም ከአፍ እስከ ገደፉ መሙላቱን ሰማሁ። •የኮሮናቫይረስ ፅኑ ህሙማን እንዴት ያገግማሉ? •መንግሥታት ከተሜውን ከኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲታደጉ ጥሪ ቀረበ አይኖቼን ጨፍኜ የሚሉኝን እሰማለሁ፣ ሰዎች ይጣደፋሉ፣ ስልኮች ይጮሃሉ፤ ሆስፒታሉ በረሻ የተሞላ ነበር። ትንሽ ቆይቶም አንድ ነርስ "አፍሺን ክፈቺና ከጉሮሮሽ ናሙና እንወስዳለን" አለኝ ህመም ነበረው፤ ከዚያም ከአፍንጫየም እንዲሁ በተመሳሳይ ናሙና ተወሰደ። የደም ምርመራ፣ የደረት ራጅ ያልተደረገልኝ ምርመራ የለም። ምን እየተከናወነ እንደሆነ አልገባኝም፤ ከአሁን አሁን ራሴንም የምስት መስሎኝ ነበር። በመቀጠልም አንዲት ነርስ መጥታ ኮሮናቫይረስ እንደሆነና 24 ሰዓትም በኦክስከጅን በመታገዝ መተንፈስ እንዳለብኝ አስረዳችኝ። ደረቴ ላይ ያለው ህመም ይህ ነው የሚባል አይደለም፤ የድንጋይ ክምር የተጫነኝ ይመስለኛል። ማስታገሻ መርፌም ቢወጉኝ፤ ህመሙ አልቀነሰልኝም። ሆዴን የመውጋት ስሜት ተሰማኝ፤ ከባድ የሚባለውን የምጥ አይነት ስሜትም ይሰማኝ ቀጠለ። ጮክ ብዬም ማልቀስ ቀጠልኩ አልቻልኩም፤ በዚህ ሁኔታ መቀጠል አይቻለኝም እያልኩ ነበር። በሞት ጥላ ስር ከእኔ ጋር አራት አልጋዎች ነበሩ፤ ሁሉም ህመምተኞች ኮሮናቫይረስ ያለባቸው ሲሆን በተጨማሪም ተደራራቢ የጤና እክል ነበረባቸው። ሁለት ተለቅ ያሉ ሴቶች የስኳር ህመምተኞች ነበሩ። ሌላኛዋ ሴትዮ እኔ ከገባሁ ከቀናት በኋላ ስለመጣች ብዙ አላስታውስም። የመጀመሪያዎቹ ቀናቶች እንደ ሰመመን ነው የሚታወሱኝ፤ ነርሶች ይገባሉ ይወጣሉ። ፅዳት ሠራተኞች በየጊዜው እየመጡ ያፀዳሉ። የውሃ ጥም ያነደዳቸው ህሙማን ደወሉን በተደጋጋሚ ይደውሉታል። ነርሶቹ ያለመታከት ቢያንስ ከአስራ ሁለት ሰዓት በላይ ያለማቋረጥ ይሰራሉ። ድካማቸው በፊታቸው ላይ ይነበባል፤ በከፍተኛ ሁኔታ ዝለዋል። አንድ ምሽት ላይ አንድ ወንድ በክፍላችን ውስጥ አየሁ። የሴቶች ብቻ በሆነው የህሙማን ክፍል ወንድ ምን ይሰራል? ብዬ ነርሷን ጠራሁ። ነርሷም ከእኔ በተቃራኒ ያለችው ሴትዮ ልጅ እንደሆነና ልትሞት እያጣጣረች መሆኑን ነገረችኝ። ልቤ ተሰበረ፤ አዘንኩላቸው ግን ለራሴም ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ተሰማኝ "እንደእኔ አይነት ሙሉ ሰው በአይኔ እያየሁ እንዴት ትሞታለች?" እያልኩ በተደጋጋሚ እጠይቃለሁ። ግራም ተጋብቻለሁ። መጋረጃውን ከለል ቢያደርጉትም ድምፅ ይሰማኝ ነበር። "ሞቻለሁ ወይስ አለሁ?" ከዚያ በኋላ መቃዠት ጀመርኩ። በህይወቴ የማውቃቸው ሰዎች ጋር እያወራሁ ይመስለኛ፤ የት እንደሆነ አላውቅም። "ሞቻለሁ ወይስ አለሁ?" ራሴንም እጠይቅ ነበር። እነዚህን ሰዎች የማናግረው ወደ ሞት እየተሻገርኩ ስለሆነ ነው? ሰዎች ወደሞት ሲቃረቡ ሙሉ ህይወት በጨረፍታ ትመጣለች ሲሉ ይህንን ማለታቸው ነው። ከዚያም ደግሞ ከእራሴ ጋር ያለኝ ሙግት ይቀጥላል "አይ አልሞትኩም! ከሞትኩ ነጩ ብርሃን የታለ? መላዕክትስ ስሜን ለምን አይጠሩም?" ሲነጋጋ አንድ ነርስ ሴትየዋ መሞቷን አረዳን። አስከሬኗን በፍጥነት ያነሱታል ብለን ብንጠብቅ ምንም የለም። ለሰዓታት ያህልም ሬሳዋ እንደተንጋለለ ማየት አሰቃቂ ነበር። ከዚያም አስከሬኑን አፀዳድተው በፕላስቲክ ጠቀለሉት፤ እቃ የሚያሽጉ ነው የሚመስሉት። አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት ብለውም ለአስከሬን ወደተዘጋጀው ትልቅ ሻንጣ መሰል ነገር ውስጥ አስገቡት። አስከሬኑ ከሻንጣው ብረት ጋር ሲጋጭ ያወጣው ድምፅ እስካሁን ይዘገንነኛል፤ እስከ ህይወቴ መጨረሻ አልረሳውም። የሞተችበት አካባቢ ተፀዳ፣ የሎሚ መአዛ ባለው ሽታ ተረጨ። አልጋው ባዶ ሆነ። የሰው ልጅ ታይቶ ጥላ ይሉ እንዲህ ነው፤ ባንዴ መሞት አለ። ሰው ነበረች አሁን አፈር። ይህ ሁኔታ ህይወቴን ነው የቀየረው። ከእኔ ትይዩ የተኛችውም ሴትዮ ድንገት እራሷን ሳተች ልጇም "እማማ፣ እማማ፤ እኔ ነኝ" እያለች ስትጣራ ይሰማኛል። ልጇ አላወቀችም ግን ሞታለች። ለሁለት ቀናትም ያህል ስትሰቃይ ነበር። ከእኔ አጠገብ ያለችው ሴት እየተሻላት ነበር እኛ አካባቢ ያሉ የህመምተኛ ክፍሎች ውስጥ ያሉ ህሙማን ግማሹ ተርፎ ግማሹ በመሞቱ እድለኛ ነን ትለኛለች። በሞትና በመኖር መካከል የሚደረግ ትግል በህይወት ለመቆየትም ታገልኩ። ተስፋ ልቆርጥ ስል እንደገና ራሴን አይዞሽ ግፊ፣ ገና አርባ ዘጠኝ ዓመትሽ ነው። ለመሞት ዝግጁ አይደለሽም። ቀንሽ ገና ነው እላለሁ። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለልጆቼ፣ ለቤተሰቦቼ፣ ለጓደኞቼ ስል መኖር እንዳለብኝ ተሰማኝ። እህቴ ሎሬን፣ ወንድሜ ሪቻርድ በተደጋጋሚ ፍቅርና ድጋፍ የተሞላበት መልዕእክቶች ልከውልኛል፤ መንፈሴንም ጠግነውታል። የመኖር ተስፋዬንም አንሰራርተውታል። መጋቢት 30/2012 ዓ.ም ሙሉ ጨረቃ ወጣች። በጨረቃ ለሚቆጥሩ አዲስ ወቅትም ነው። ወቅቱንም የማገገሚያየ ምልክት እንደሆነ አድርጌ ወሰድኩት። በተስፋ ባለሁበት ሁኔታ የተረፈችው ሦስተኛዋም ሴት ዓለምን ተሰናብታ ሄደች። ተመሳሳይ ሂደቶች ተስተናገዱ። ምናልባት ለህይወቴ መትረፍ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው አንድ ነርስ ነው፤ በተደጋጋሚም "ዶክተሮች ደህና ነሽ ወደቤት መሄድ ትችያለች ካሉሽ ያለምንም ማወላወል ወደቤት መሄድ ነው። ብዙዎች ህሙማን የሰሩትን ስህተት አንቺም እንዳትደግሚ። አብዛኛዎቹ ተሽሏችኋል ሲባሉ ሙሉ በሙሉ አላገገምንም ብለው ሆስፒታል ይቆያሉ እናም ሁሉም ህሙማን እንደገና በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል። ሁሉም ሞተዋል" ይለኝ ነበር። አንድ ቀንም ዶክተሩ በደሜ ውስጥ ያለውን የኦክስጅን መጠን በማየት "ደህና ነሽ፣ ልትሄጂ ትችያለሽ" አለኝ። በጣም ተደሰትኩ፣ የማይታመን ነው ቤቴ ልሄድ ነው። ውጭ ስወጣ የብርዱ ውሽንፍር ተቀበለኝ። የሆስፒታል ጋወንና ሸበጥ አድርጌያለሁ። ብርዱ ፊቴን ለበለበው፤ ምንም ግን አልነበረም። አሁን የአምቡላንሷን ሹፌር ስሟን አላስታውሰውም ግን መልአክ ናት። ጠዋት አስራ ሁለት ሰዓት የጀመረች እኔን ከሆስፒታል ስትወስደኝ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ከሃያ ነበር። አስራ ስምንት ሰዓታት ሰርታለች። እንዲህ ነው ሰዎች እያገለገሉ ያሉት። ነርሶችና ዶክተሮች ብቻ አይደሉም። አምቡላንስ የሚነዱት፣ በሆስፒታሉ ውስጥ ያሉ የአስተደዳር ሠራተኞች፣ አስከሬን የሚያፀዱት፣ ወደ መካነ መቃብር የሚወስዱት ስንቱ ተቆጥሮ፤ ሁሉም መስዋዕትነት ከፍሎ እየሰራ ነው። የአምቡላንስ አገልግሎት ለሚሰጡት እንዲሁም ለሆስፒታሉ ሠራተኞች ለፅናታቸው፣ ለእንክብካቤያቸው አመስግኜ ደብዳቤ ፅፌያለሁ። አሁንም ቢሆን በማገገም ላይ ስለሆንኩ ለሳምንታት ያህል አልጋ ላይ ነኝ። የሳንባ ምቹ እስኪሻለኝ ከሦስት እስከ ስድስት ወር እንደሚወስድ ዶክተሩ ነግሮኛል። ከሆስፒታል ከወጣሁ በኋለ እናቴ ምግብ እየሰራች ደጃፌ ላይ ታስቀምጣለች፤ ምስጋናው ይድረሳትና፤ ህይወቴን ቀጥላዋለች። ሞትን ነክቻታለሁ እናም በህይወት በመቆየቴ ደስተኛ ነኝ። ለወደፊቱ ህይወትን እንዲህ እንደ ቀልድ አልወስድም። ቁሳቁስ፣ ሃብት፣ ንብረት ምንም ጥቅም የለውም። አሁን የሚናፍቀኝ ውጭ ወጥቼ መተንፈስ፣ ወፎችን መመልከት፣ ተፈጥሮን ማድነቅ ነው። በህይወት ለመኖር ሁለተኛ እድል ተሰጥቶኛል።
44195925
https://www.bbc.com/amharic/44195925
የቢላል አዛን የናፈቃቸው ሀበሾች
የረመዳን ፆም ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ይፀናል። ፀሐይ ስትጠልቅ ደግሞ 'ማፍጠር' ይከተላል። ግን ቆይ! ፀሐይ በጄ ብላ ባትጠልቅስ? እምቢኝ አሻፈረኝ ብትልስ? ሌሊቱ ብራ እንደሆነ ቢነጋስ? ሳይበላ ሊቀር!?
ራውዳ አሰፋ፣በክሪስቲያንሳንድ፣ ክሪስቲያን IV ጋታ መንገድ, የረመዳን መባቻ፣ የኖርዌይ ብሔራዊ ቀን ለማክበር የኢትዮጵያን ሸላይ ፀሐይ ብቻ እየሞቀ ያደገ ሀበሻ "ያ አኺ! ምንድነው ምታወራው?" ሊል ይችላል። አትፍረዱበት። አንድ ፀሐይ ነው የሚያውቀው። ምድር ላይ ስንትና ስንት 'ዐዛ' የሚያደርጉ ፀሓያት እንዳሉ አያውቅም። የአገር ቤት ፀሐይ እንደ እንጀራችን ክብና ገራገር ናት። በ12 ግድም ወጥታ፣ በ12 ግድም ትጠልቃለች። መዓልትና ሌቱ ስምም ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ሙስሊምም የቀኑን እኩሌታ ፆሞ፣ እኩሌታውን ይፈስካል። ኻላስ! ይህ ግን ሁሉ አገር አይሠራም። በየዓለማቱ እንደ አሸዋ የተበተነው ሕዝባችን እስከ አርክቲክ ተረጭቷል። ፀሐይ እስከማትጠልቅበት አፅናፍ ድረስ። ከ'ቢላዱል ሀበሺ' ብዙ ሺህ ማይሎችን ርቀው፣ የምድር ድንበር ላይ የሚኖሩ፣ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ምዕመናንን ጠይቀናል፤ "ኧረ ለመሆኑ ፆሙ እንዴት ይዟችኋል?" ስንል። ግሪንላንድ፣ አይስላንድ፣ ቻይና፣ ሰሜን ራሺያ፣ ሰሜን ስዊድን፣ ሰሜን ፊንላንድ፣ ምዕራብ ካናዳ፣ ደቡብ ኖርዌይ እንዲሁም መካከለኛው አውሮፓ ከሚኖሩትና በስልክ ካነጋገርናቸው ውስጥ የጥቂቱን ብቻ ለዛሬ 'መርሃባ!' ብለናል። "በቀን ለ21 ሰዓት እንፆም ነበር" ራውዳ አሰፋ (ከኖርዌይ) በኖርዌይ መንገዶች ባለሥልጣን የዊንዶስ ሲስተም ባለሞያ ነኝ። ኖርዌይ መኖር ከጀመርኩ 10 ዓመት ሆነኝ። አሁን ክሪስቲያንሳንድ የምትባል ከተማ ነው የምኖረው። ከኦስሎ በመኪና የአራት ሰዓት መንገድ ቢሆን ነው። እኔና ባለቤቴ አሁን ለ18 ሰዓት ነው እየፆምን ያለነው። የምንጾምበት ሰዓት በየቀኑ 6 ደቂቃ ስለሚጨምር በወሩ መጨረሻ ለ19 ሰዓት እንፆማለን ማለት ነው። እዚህ ደቡባዊ ኖርዌይ መኖር ከመጀመሬ በፊት ቡዶ (Bodø) የምትባል ከተማ ነበር የምኖረው። ከአርክቲክ ሰርክል በሰሜናዊ አቅጣጫ የምትገኝ ትንሽዬ የኖርዌይ ከተማ ናት። እዚያ እያለሁ ለ21 ሰዓታት እንፆም ነበር። ቡዶ ፀሐይ ስትጠልቅ ዐይተናት አናውቅም። ከሌሊቱ 10 ሰዓት ፀሐይ ፍጥጥ ብላ ትታያለች። በዚህን ጊዜ 'ፉጡር' እና 'ሱሁር' አንድ ይሆናሉ። *('ፉጡር'-ጦም መግደፊያ ሲሆን 'ሱሁር' ግን አዲስ ጦም ለመጀመር ሲባል ከንጋት በፊት የሚቀመስ አፍ-ማሟሻ ነው።) በጁን 21 ደግሞ ፀሐይ ጭራሽ ሳትጠልቅ ቀኑ ይቀየራል። እኔ ወደ ክሪስቲያንሳንድ ከመጣሁ በኋላ እንደሰማሁት ደግሞ በኖርዌይ ቡዶ ጀምበር ስለማትጠልቅ የ'ኢፍጣር' ሰዓታቸውን በቅርብ ከሚገኝ ሙስሊም አገር አስማምተው መፆም እንደጀመሩ ነው። ዊንተር (የፈረንጆቹ ክረምት) ላይ በተቃራኒው ፆሙ ለአጭር ሰዓት ይጸናል። ፀሐይዋ አረፋፍዳ ስለምትወጣ ሱብሂ ሶላት (*ለወትሮ ማለዳ ወፍ ጭጭ ሳይል የሚደረግ ስግደት) የምንሰደግደው ሥራ ገብተን ነው። ፆም የምንገድፈው ደግሞ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው። እውነቱን ለመናገር ማጠሩን "ሰለብሬት" አላደርገውም። ብዙም ምቾት አይሰጠኝም። አጅሩ ( *መለኮታዊ ሽልማቱ) በዚያ መጠን የሚቀንስ ስለሚመስለኝ ይሆን ይሆናል። እዚህ ኖርዌይ ለረዥም ሰዓት ስለምንፆም አገር ቤት እንደለመድነው ዘይት የሚበዛባቸው ምግቦችን፤ እነ ሳንቡሳን፤ ብዙም አንወስድም። ከዚያ ይልቅ ፕሮቲን ያላቸው፣ ሳይፈጩ መቆየት የሚችሉ ምግቦችን እናዘወትራለን። እንቅስቃሴያችንም የተገደበ ይሆናል። ለምሳሌ እኔና ባለቤቴ ልጆቻችንን ለብስክሌት ግልቢያ መስክ ይዘናቸው አንወጣም። ኖርዌይ ከባለቤቴ ጋር ተጋግዘን ነው የምንሠራው። እሱ ቤት ማጽዳት፣ ልብስ ማጠብ፣ ልጆቹን ቁርስ ማብላትና መንከባከብ ላይ ያተኩራል። እኔ ምግብ ማዘጋጀቱን እመርጣለሁ። አልፎ አልፎ ኢትዮጵያ ስንሄድ ግን ባለቤቴ "ኢትዮጵያዊ ባል" ነው የሚሆነው። (ሳቅ) ረመዳን በኢትዮጵያ የሚናፍቅ ነገር አለው። በተለይ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እያለን ከእኩዮቼ ጋር አብረን እያፈጠርን፣ ለሱሁር አብረን እየተነሳን፣ ተራዊህ ( *ምሽት ከእቅልፍ በፊት የሚሰገድ ዘለግ ያለ ስግደት) አብረን እየሰገድን የማይረሳ ጊዜ አሳልፈናል። ከሁሉ ከሁሉ የረመዳን የመጨረሻዎቹን አስር ቀናትን እናዘወትርበት የነበረው ሸጎሌ የሚገኘው ሼክ ሆጀሌ መስጊድ እጅግ አድርጎ ንፍቅ ይለኛል። በከሪ ኑሪ እና ሱረያ ዲኖ በጀርመን ፍራንክፈርት "ረመዳን በካናዳ ምንም ደስ አይልም" ጋልማ ጉዮ ተወልጄ ያደኩት ቦረና ነው፤ ያቤሉ ውስጥ። አሁን የምኖረው ምዕራብ ካናዳ ነው፤ ኤድመንተን-አልበርታ። ኢትዮጰያ 12 ሰዓት ጀምረህ ማታ 12 ሰዓት ታፈጥራለህ። ደስ ይላል። እዚህ ግን ሌሊት 2፡50AM (በኢትዮጰያ ሌሊት 8 ሰዓት፡ከ50) ፆም መያዝ የጀመርን ማታ 10፡00 PM (አራት ሰዓት በኢትዮጵያ) ነው የምንፈታው። በመሐል ያለው 4 ወይም 5 ሰዓት ብቻ ነው። እኛ እዚህ ስናፈጥር ኢትዮጰያ 'ተራዊህ' እየተሰገደ ነው። እኛ 'ተራዊህ' ሰግደን እንደጨረስን የአዲሱ ቀን ፆም ይጀምራል። ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ረመዳንን በካናዳ ፆሜያለሁ። በቀን ከ20 ሰዓት በላይ ነው የምንፆመው። እዚህ ሁሉንም ነገር ገዝተህ ታገኛለህ። ግን ደስ አይልም። ኢትዮጵያ ብሆን ይሻለኛል። ኢትዮጵያ ቤተሰብ አለ፣ ጎረቤት አለ፣ ፍቅር አለ። እዚህ ምን አለ? ሥጋ ራሱ ቦረና "ኦርጋኒክ" ነው፤ እዚህ ካናዳ ግን "ፍሮዝን" ነው። ከትውልድ አገሬ ቦረና ኡጂና ሳምቡሳ እጅግ ይናፍቁኛል። "ኡጂ" ታውቃለህ? "ከኤርትራዊያን ጋር ነው የምናፈጥረው" በክሪ ኑሪ እና ሱረያ ዲኖ በክሪ እባላለሁ። ባለቤቴ ሱረያ ትባላለች። ጀርመን ፍራንክፈርት እሷ 10 ዓመት፣ እኔ 6 ዓመት ኖረናል። እዚህ ረመዳንና Summer በመገጣጠሙ ወደ 17/18 ሰዓት ነው የምንፆመው። ሌሊት 10 ሰዓት መፆም የጀመርን ማታ 21 ሰዓት (ምሽት 3፡00 ሰዓት) ነው የምንበላው። እዚህ በበጋና በክረምረት መፆም ልዩነት አለው። በጋ ላይ ረዥም ሰዓት መፆሙ ብቻ ሳይሆን ሙቀቱ እስከ 35 ዲግሪ ስለሚደርስ ይደክማል። በክረምት ግን ለአጭር ሰዓት ነው የሚፆመው፤ ኾኖም በጣም ይርባል፡፡ በክረምት አጭር ሰዓት ከመፆም በበጋ ረዥም ሰዓት መፆም ነው የሚሻለው። አንድ ሁለት ጊዜ ረዥም ሰዓት መፆም አቅቶኝ አቋርጬ አውቃለሁ። ለረዥም ሰዓት ምግብ ስለማልበላ ጨጓራዬ ተቀሰቀሰብኝና አቋረጥኩት። ቢሆንም ግን በክረምት መፆም የባሰ ነው፤ በጣም ይርባል፤ ሰዓቱ ማጠሩን ማየት የለብህም። ብርዱ በጣም ነው የሚያስርበው። ሕጻን ዩኑስ እና ሕጻን መሐመድ ከአባታቸው በክሪ ኑሪ ጋር ሶላት በመስገድ ላይ፣ ፍራንክፈርት "ማድቤት ገብቼ ሳንቡሳ የምሠራው እኔ ነኝ" በክሪ ሾርባ፣ ሳንቡሳ፣ የሞሮኮ ምግቦችን ሁሉ ልቅም አድርጌ አበስላለሁ። ከባለቤቴ ይልቅ ማድቤት ገብቼ የምሠራው እኔ ነኝ። እዚህ ጀርመን እንደኛ ቤተሰብ ያለው ቤቱ ያፈጥራል። ላጤ የሆነ ደግሞ መስጊድ ሄዶ በነፃ ማፍጠር ይችላል። እዚህ ፍራንክፈርት ብዙ መስጊዶች ነው ያሉት። ሞሼ ይባላሉ። መስጊድ ማለት ነው በጀርመንኛ። "ሀበሾች ግን መስጊድ የለንም" ጀርመን ብዙ መስጊድ ቢኖርም ሀበሾች ግን መስጊድ የለንም። እዚህ መስጊዶች በአገሮች ነው የሚሰየሙት። የሞሮኮ፣ የቱርክ፣ የአፍጋን፣ የግብፅ፣ የፓኪስታን መስጊዶች አሉ። ለእኔ የሚቀርበኝ የሞሮኮዎቹ 'አቡበከር ሞሼ' የሚባለው መስጊድ ነው። ሀበሻ የሚበዛበት መስጊድ ግን 'ዶቼ-ሞሼ' የሚባለው ነው። እኛ ሀበሾች የራሳችን መስጊድ ስለሌለን ዶቼ-ሞሼ ነው የምንሰግደው። ረመዳን ደስ ይላል። የተጠፋፋን ጓደኛሞች የምንገናኝበት ወር ነው። ከኤርትራዊያን ጋር በወር አንዴ ተገናኝተን አብረን እናፈጥራለን። "የፉርኖ ዱቄት እንጀራ" እንጀራን ኢትዮጵያ የምናውቀው በጤፍ ነው። እዚህ በገብስና በፉርኖ ዱቄት ነው የሚሠራው። ኢትዮጵያ ሾርባ መሥሪያ ትክክለኛ የገብስ ቅንጬ አለ። እዚህ ግን ከአጃ ነው የምናዘጋጀው። ሳምቡሳውም፣ ሾርባውም ሁሉም አለ። ግን ኦሪጅናሉን የኢትዮጵያውን አታገኝም። ጣዕሙስ ካልከኝ በአጭሩ እንደ አገርቤት አይጣፍጥም። "ጀርመን…ቶሎ ቶሎ የሚሰገድባቸው መስጊዶች" ከ'ኢፍጣር' በኋላ የሚኖረወን ሰዓት በጣም የተጠጋጋ ስለሆነ ቶሎ አፍጥረን፣ ቶሎ ተራዊህ ሰግደን፣ ቶሎ 'ሱሁር' በልተን ፆሙን መጀመር አለብን። ጀርመን ቶሎ ቶሎ የሚሰገድባቸው መስጊዶች አሉ። ቀስ ተብሎም የሚሰገድባቸው አሉ። ቀጠሮ ያለበት ሰው ምናምን በፍጥነት በመስገድ ወደሚታወቁት ቱርኮች መስጊድ ሄዶ ይሰግዳል። የበክሪና የሱረያ ብላቴና መሐመድ በክሪ፣ በፍራንክፈርት "ለሙከራ አብረውን የሚፆሙ ጀርመኖች አሉ" እዚህ በሥራ ቀልድ የለም። ረመዳን ነው ብለህ ሥራ መቅረት አትችልም። ኾኖም የዓመት እረፍትህን፣ (እዚህ "ኡርላፕ"/Urlaub/ ይሉታል) ረመዳን ላይ እንዲሆን አድርገህ ትሞላና ፆም ላይ ትንሽ ታርፋለህ፡፡ የእኛ መፆም ጀርመኖችን በጣም ነው የሚገርማቸው። በተለይ ውሀ አለመጠጣታችን በጣም ይገርማቸዋል። እንሞክረው ብለው አብረውን የሚፆሙም አሉ። በተለይም በውፍረት የሚቸገሩ "ይሄ ነገር አሪፍ ሳይሆን አይቀርም" ብለው አብረውን ይፆማሉ። "የአገሬ አዛን ይናፍቀኛል" ኮልፌ ነበር ሰፈ። ኮልፌ ተራራማ አካባቢ ነው። ፀሐይ ስትወጣም ስትገባም ማየት ትችላለህ። ፍራንክፈርት ግን ፀሐይ ስትገባም ሆነ ስትወጣ አይተናት አናውቅም። እዚህ አገር መስጊዶች ቢኖሩም ድምፅ ማሰማት አይችሉም። በጣም ክልክል ነው። ኮሽታ ከተሰማ ነዋሪዎች ቅሬታ ያሰማሉ። ዐዛን የሚሰማው መስጊዱ ውስጥ ላለ ሰው ብቻ ነው። ነዋሪዎችን መረበሽ አትችልም። ምንድነው መሰለህ የሚደረገው መስጊዶች ካላንደር ይሰጡሃል። ስንት ሰዓት እንደሚሰገድ፣ ስንት ሰዓት እንደሚፈጠር። ሰዓቷን አይተህ ትሄዳለህ እንጂ ዐዛን የሚባል ነገር የለም። ለዚህ ነው የአገሬ ዐዛን ይናፍቀኛል የምልህ… "የአንዋር መስጊድ ግርግር አይረሳኝም" የበክሪ ባለቤት ሱረያ ዲኖ በበኩሏ ጀርመን ረዥም ሰዓት ብፆምም እንደ ኢትዮጵያ ግን አይርበኝም ትላለች። ምክንያቱን ስታስረዳ "እዚህ በሥራ ተወጥሬ ስለምቆይ ሰዓቱ አይታወቀኝም።" "...አገር ቤት እኮ 'ፍጡር ሰዓት አይደርስም እንዴ?፣ አዛን አይልም እንዴ?' እያልክ ደጅ ደጁን ታያለህ፤ እዚህ ግን 'ወይኔ ጉዴ ፍጡር ሰዓት ደረሰብኝ!' ብለህ ነው የምትሯሯጠው።" ሱረያ ከኢትዮጵያ ረመዳን ጋር ተያይዞ የምትናፍቀው የመስጊድ ግርግር ነው። "…መርካቶ አንዋር መስጊድ ታክሲው፣ ሳምቡሳው፣ ቴምሩ፣ ግርግሩ በጣም ያምራል፤ ወሩን ሙሉ ኢድ ነው የሚመስለው። ሆኖም እኔ መሳለሚያ ቢላል መስጊድ ነበር የማዘወትረው።" ትላለች የፍራንክፈርቷ ሱረያ ዲኖ። የቢላል ዐዛን ናፋቂ ሀበሾች በኢስላም ታሪክ የመጀመርያውን ዐዛን (የሶላት ጥሪ) ያሰማው ሰው ደምፀ-መረዋው ቢላል-አል-ሀበሺ ነበር። የዚያ ዘመን ስደተኛ!? ይኸው ከ1ሺህ 439 ዓመታት በኋላም እንደ ቢላል የተሰደዱ፣ የእርሱን ዐዛን በአገራቸው መስማት የናፈቁ ሀበሾች ዛሬም እልፍ ናቸው። ተዘርተዋል፤ እንደ ከዋክብት፤ እንደ እንጀራ ዐይኖች። እንጀራ ፍለጋ…እስከ አርክቲክ…እስከ ሰሜን ዋልታ…
news-56353675
https://www.bbc.com/amharic/news-56353675
ማትሪክ፡ አራስ ልጇን እያጠባች ማትሪክ የተፈተነችው ሚሊዮን
ባለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመፈተን እየተጠባበቁ የነበሩ ተማሪዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፈተናው ተራዝሞባቸው ቆይቷል።
በዚህ የተነሳ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ገብተው ነበር፤ በተደጋጋሚ በመራዘሙም "የምንፈተን አልመሰለንም ነበር" ይላሉ። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለረዥም ጊዜ ቤት ውስጥ መቀመጥ ድብርት ውስጥ ከትቷቸው፣ ተዘናግተ እንደሁም መሰልቸት የተፈጠረባቸውም እንደነበረም ተፈታኞቹ ሲናገሩ ተሰምቷል። በመጨረሻም እንዲህ ሲጠበቅ የነበረው ፈተና ከሰኞ የካቲት 29 2013 ዓ.ም ጀምሮ የ2013 ሀገር አቀፍ ተሰጥቶ በትናንትናው ዕለት ተጠናቅቋል። ፈተናቸውን በትናንትናው ዕለት ካጠናቀቁ ተፈታኞች መካከል ደግሞ ሚሊዮን አንዷ ናት። ሚሊዮን ተካልኝ ገና ወገቧ ያልጠናከረ 'እርጥብ አራስ' ናት። ሁለተኛ ልጇን የተገላገለችው ቅዳሜ፣ የካቲት 27 2013 ዓ.ም እለት እንደነበር ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ ተናግራለች አራስ ልጇ የእርሷን ጡት አሁንም አሁንም ይፈልጋል። ያማጠችበት ወገቧ ረዥም ሰዓት አያስቀምጣትም። የረዥም ጊዜ ሕልሟን ደግሞ የሚወስነው ይህ ፈተና ነው። እናም ልጇን ታቅፋ፣ እንደ ሌሎቹ በዩኒፎርም ሳይሆን ጋቢ ተከናንባ ወደ መፈተኛ ክፍል አምርታለች። በነቀምቴ ከተማ የምትኖረው ሚሊዮን፣ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በሆስፒታል የወለደች ሲሆን፣ እሁድ ከሰዓት ከሆስፒታል ወጥታ ሰኞ ጠዋት ለፈተና ተቀምጣለች። እንደ አራስ ትኩስ ትኩሱ እየቀረበላት፣ በአልጋዋ ላይ አረፍ ብላ ጠያቂ መልካም ምኞቱን እየገለፀ ቢንከባከቧት አትጠላም ነበር። ነገር ግን እርሷ ልታሳካው የምትፈልገው ሌላ ግዳጅ ከፊቷ ተደቅኗል። እናም ሰኞ ማለዳ እርሳሷን ቀርጻ፣ ልጇን ሸክፋ፣ ወገቧን አጥብቃ አስራ ወደ ምትፈተንበት ትምህርት ቤት አመራች። "ዛሬ ወልዶ ነገ መፈተን በጣም ይከብዳል" የምትለው ሚሊዮን " ለመተው አስቤ ነበር። ነገር ግን ያለሁበት ሁኔታ እንድተወው አላስቻለኝም" ብላናለች። በትምህርት ቤት የሚጠብቃት "እንኳን ማርያም ማረችሽ" የሚል ጠያቂ አይደለም፤ ሰዓት አልቋል የሚል ፈታኝ አንጂ። ቢሆንም ነገ ሩቅ አይደለም ለእርሷ ስለዚህ የነገዋን እያሰበች ለመፈተን ቆርጣ ሄደች። ሚሊዮን ትምህርቷን የተማረችበት አልጋ በአልጋ ላይ በሆነ ሁኔታ አይደለም በተቃራኒው በአነስተኛ እና ጥቃቅን ከጓደኞቿ ጋር ተደራጅታ ቡናና እና ሻይ እየሸጠች ነው የተማረችው። "የጉልበት ሥራ እየሰራሁ ነው የተማርኩት፤ ቡናና እና ሻይ እየሸጥኩ ነው ራሴን ያስተማርኩት። በዚህ ላይ ደግሞ ትዳር መስርቻለሁ። በዚህ ስራ ላይ የቤተሰብ ኃላፊነት ተደርቦ ትምህርቴን መከታተሌ አስቸጋሪ ነበር።" ትላለች ሚሊዮን አሁን ወልዳ ለመሳም የበቃችው ሁለተኛ ልጇን ነው። የመጀመሪያ ልጇን ስታሳድግ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፋለች። ልጇ ታምሞባት ሆስፒታል ተኝቶ በሚታከምበት ወቅት አጠገቡ እያደረች ቀን ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ትማር እንደነበር ታስታውሳለች። በዚያ ላይ የዕለት ጉሮሮን ለማሸነፍ፣ ቡናና ሻይ ትሸጣለች። በሌላ በኩል በስራ ላይ እያለች የቡና መፍጫ ማሽን እጇን ቆርጧት በጣም ታማም እንደነበር ለቢቢሲ ተናግራለች። በአንድ በኩል የሚጠዘጥዝ ቁስል፣ በሌላ በኩል የሚያለቅስ ልጅ፣ ዞር ሲሉ የጎደለ ማጀት የእርሷ የትምህርት ዘመን ፈተናዎች ነበሩ። የትዳር አጋሯ ደግሞ የመኪና አሽከርካሪ ስለሆነ፣ አብዛኛውን ጊዜ ቤት ስለማይገኝ ከጎኗ መቆም አልቻለም። "እነዚህ ገጠመኞች ናቸው እንግዲህ ጥንካሬ የሆኑኝ፤ ለዚህም ነው አልቀርም በማለት በእልህ ፈተና ላይ የተገኘሁት።" ትላለች። ምንም እንኳን እንዲህ በጥንካሬ እዚህ ደረጃ ላይ ብትደርስም እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ሲደራረቡባት ትምህርቷን ማቋረጥ አስባ እንደነበር ትናገራለች። " ነገር ግን እዚህ እቀራለሁ የሚለው ሃሳብ ያስጨንቀኝ ነበር። እስከመቼ ይህንን ቡና ይዤ በየበረንዳው እንከራተታለሁ የሚለው ሃሳብ ጭንቀት ይፈጥርብኛል። ይህ ሁኔታ የቆሰለው እጄን ይዤ ትምህርቴን እንድከታተል አድርጎኛል" በማለት ጥንካሬ ስለሆናት ጉዳይ ትናገራለች ሚሊዮን ትዳር የመሰረተችው በ2008 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱም የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነበረች። ሚሊዮን ቡናና እና ሻይ መሸጥንም በዚያው ዓመት ነው የጀመረችው። በዚያው ዓመት ኑሮ ከብዷት ትምህርት አቋርጣ ነበር። በ2009 ዓ.ም ተመልሳ ትምህርቷን ጀምራ የነበረ ቢሆንም እንደገና ለመቀጠል ሳትችል ቀርታ ዳግም አቋርጣለች። የመጀመሪያ ልጇንም የወለደችው በ2009 ዓ.ም ነው። ከዚያ በፅናት እንደገና በ2010 ዓ.ም ዳግም ትምህርት ቤት ተመልሳ የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ተፈተነች። በተደጋጋሚ ትምህርቷን በማቋረጧ ከጓደኞቿ በሁለት ዓመት ወደኋላ መቅረቷ የሚያብሰለስላት ጉዳይ ነው ስለዚህ የዚህን ዓመት የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና አለመውሰድ ለእርሷ በሕይወቷ የምታመክነው ሶስተኛ እድል መሆኑ እንደማታባክነውም ወሰነች። በዚያ ላይ የቡና ማሽን እጇን የቆረጣት 12ኛ ክፍል መማር እንደጀመረች ነው። እና በዚህ ከሕመም ጋር የሚታገለው ልጇ፣ በሌላ በኩል አልሞላ ብሎ ያስቸገራት የእለት ሕይወትን ለማሸነፍ፣ በሌላ ወገን ከጀማው ወደ ኋላ የመቅረት እልህ ወጥሮ ይዟት ትምህርቷን ተከታተለች። በዚህ ሁሉ መሃል አለም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማዕበል ተመታች። የነበረው እንዳልነበር ሆነ። ሁሉም ያቀደውን ሁሉ ጣጥሎ ቤቱ ተከተተ። ፈተናዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘሙ። "ከዚያ በኋላ ፈተና መቼ ይሆናል በሚል በጉጉት ስጠብቅ ነበር። የፈተና ጊዜ መተላለፉን ስሰማ ልጅ መውለድ እንዳለብኝ ወሰንኩ፤ ነገር ግን ፈተና ለመሰጠት ይህ ያህል ጊዜ ይቆያል የሚለውን አስቤ አላውቅም" ትላለች። ከመውለዷ በፊት ፈተናው ይሰጣል ብላ ተስፋ ያደረገችው ሚሊዮን፣ እያጠናች ቆየች። ነገር ግን ፈተናው በጥር ወር ይሰጣል ቢባልም ዳግም ተራዘመ። ይኼኔ በእርግዝናው ላይ ሌላ ጭንቀት ሚሊዮንን ጎበኛት። "ፈተናው በ29 ነው መባሉን ስሰማ በጣም ነው የደነገጥኩት" "እኔ የምወልደው የካቲት 27 መሆኑ ተነግሮኛል" የምትለው ሚሊዮን" ፈተና ደግሞ በ29 ይሰጣል መባሉን ከመገናኛ ብዙኀን ስሰማ በጣም ነው የደነገጥኩት ምን ማድረግ እንዳለብኝም ግራ ተጋባሁኝ" ትላለች ለመምህራኖቿ አማከረች። በአገር አቀፍ ደረጃ የተቆረጠውን ቀን ማንም ማጠፍ አይችልም። ሁሉም በርቺ አሏት። "ተስፋ አልቆረጥኩም፤ ምጥ እንኳን ቢይዘኝ ሄጄ እፈተናለሁ። ብዬ ራሴን አሳምኜ ነበር" በማለት በወቅቱ የነበራትን ቁርጠኝነት ታስታውሳለች። በዚህ መካከል የዋህ ሃሳብ አእምሮዋን ሽው ብሎት ነበር። ከወለደች በኋላ በጣም ደክሟት ስለነበር "ቤት አልጋዬ ላይ ይፈትኑኛል ብዬ አስቤ ነበር" ያለችው ሚሊዮን፣ እነርሱ ግን በምጥ ላይ እያለሽ እንደሆነ እንጂ ከወለድሽ በኋለ ተማሪዎች መካከል ሆነሽ ነው መፈተን አለብሽ አሉኝ" ብላናለች። ሰኞ እለት፣ የካቲት 29 2013 ዓ.ም አራስ ወገቧን ሸብ አድርጋ፣ ጋቢ ለብሳ፣ ከጡት የማይነጠለውን ልጇን በመያዝ ወደ ፈተና መስጫው አመራች። ሚሊዮን ሁለተኛ ልጇን አምጣ በሰላም ስትገላገል የተሰማት ደስታን ያህል በፈተና ክፍል መገኘቷም አስደስቷታል። በዚህ የፈተና ክፍለ ንፋስ እንዳይነካሽ አትገላለጭ የሚል ቤተሰብ የለም። መኮራረጅ ክልክል ነው የሚል መምህር እንጂ። እዚህ ልጁ ጠብቷል፤ አንቺስ በልተሻል የምትል እናት የለችም። መልሱን አጥቁራችኋል፤ ስማችሁን መጻፍ አትርሱ፤ ሰዓት አልቋል። እርሳሳችሁን አስቀምጡ የሚል ፈታኝ እንጂ። ለእርሷ ግን ይህ ደስታ ከምንም በላይ ነው። ቢሆንም የስጋት ቀጭን ነፋስ በአእምሯ ውስጥ መንፈሱ አልቀረም። "በተቀላቀለ ስሜት ውስጥ ነበርኩኝ" የምትለው ሚሊዮን በፈተና ላይ መገኘቷ ቢያስደስታትም ጨቅላ ልጇን ይዛ ከተማሪዎች መካከል ሆና መፈተኗ የአእምሮ ጫና እንደፈጠረባት ትናገራለች። "አብሬ የተፈተንኳቸው ልጆች አብረን የተማርናቸው ስላልሆኑ አንተዋወቅም። ይህም ሲያስጨንቀኝ ነበር።" ራሷን ችላ ለመሄድ አቅም እንዳልነበራት የምትናገረው ሚሊዮን፣ በቅርብ ስለወለደች ደም እንዳይፈሳት እንዳስጨነቃትም አልሸሸገችም። በዚያ ላይ ደግሞ ፈታኞቿ ወንዶች መሆናቸው፣ ሴት ልጆች አጠገቧም ስላልነበሩ በመናገር ስጋት ውስጥ ሆና መፈተኗን ትናገራለች። ፈተናው የተጀመረ ዕለት እነዚህ ስጋቶች ቢኖርባትም እያደር ግን ቀለል ብሏት ፈተናዋን ማጠናቀቋን ትናገራለች። በስተመጨረሻም "ፈጣሪ ከፈቀደ እና የመግቢያ ነጥብ ማስመዝገብ ከቻልኩኝ፣ ዩኒቨርስቲ መግባት እፈልጋለሁኝ ፤ ነገር ግን ልጆቼን ስለማሳድግ ርቄ መሄድ አልፈልግም።" ብላለች። እኛም ለአራስ የሚገባውን ይዘን፣ ለጨቅላው ጥብቆ ገዝተን ባንጠይቃትም መልካም እድል እንዲገጥማት ተመኘን።
50415010
https://www.bbc.com/amharic/50415010
ተኪ፡ መስማት በተሳናቸው የሚንቀሳቀሰው ተቋም
ሚሚ ለገሰ፤ አልፋ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት ውስጥ ሳለች ከአንድ ኢትዮጵያዊና ስዊዘርላዳዊ ጋር ተገናኘች። በሦስት ሚሊዮን ብር መነሻ በጀት መስማት የተሳናቸውን ያካተተ ድርጅት የመመስረት አላማ አንግበው ነበር።
ተኪ በ18 መስማት የተሳናቸው ሠራተኞች ይንቀሳቀሳል በሕጻናት ማሳደጊያ ያደገችው ሚሚ፤ ከሁለቱ ግለሰቦች ጋር በመሆን የወረቀት ቦርሳ የማምረት ሀሳብን ጠነሰሱ። መስማት የተሳናቸውን ያካተተ የሥራ ዘርፍ ለመፍጠር፣ ጎን ለጎንም አካባቢን ከፕላስቲክ ብክልት ለመከላከል። ሚሚ ከሕጻናት ማሳደጊያ ከወጣች በኋላ በክር ሹራብ፣ ኮፍያና ቦርሳ ትሠራ ነበር። ሙያውን እንደሷው መስማት ለተሳናቸው ታስተምርም ነበር። ሆኖም የዳንቴል ሥራ ገበያው እንዳሰቡት አመርቂ አልነበረም። ማኅበራዊ አገልግሎት የመስጠት ከፍተኛ ፍላጎት ያላት ሚሚ፤ ሙሉ ጊዜዋን ከሹራብ ሥራው ወደ ወረቀት ቦርሳው አዞረች። ከሦስት ዓመት ተኩል በፊትም 'ተኪ' የተባለው የወረቀት ቦርሳ አምራች ድርጅት ተመሰረተ። • የኢትዩጵያውያን አካል ጉዳተኞች ፈተናዎች ምን ድረስ? • በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት መስማት ከተሳናቸው ልጆች ጋር ያደገችው መስከረም በየነ፤ የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ ናት። መስማት ከተሳናቸው ጋር በቅርበት የምትሠራው መስከረም፤ ተኪን የተቀላቀለችው ከአንድ ዓመት ከስምንት ወር በፊት ነበር። ሚሚና መስከረም የተኪ ሥራ አስኪያጆች ናቸው። ሚሚ ከምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ ጋር በመሆን በተለያዩ ሥፍራዎች እየተዘዋወረች የወረቀት ቦርሳቸውን ታስተዋውቃለች፤ መስከረምም የድርሻዋን ትወጣለች። [ሚሚ ከቢቢሲ የቀረቡላትን ጥያቄዎች በምልክት ቋንቋ ስትመልስ፤ መስከረም እያስተረጎመች ስለድርጅታቸው አውግተውናል።] ሚሚና መስከረም የተኪ ሥራ አስኪያጆች ናቸው የአካታችነት ጥያቄ ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግሥትም ይሁን የግል ድርጅቶች አካል ጉዳተኞችን አካታች ባለመሆናቸው ይተቻሉ። አካል ጉዳተኞችን ለመቅጠር ካለመፈለግ አንስቶ ቢቀጠሩም ምቹ የሥራ ሁኔታ አለማዘጋጀት ዋነኛ ችግሮች ነው። ተኪ ይህንን ለመለወጥ የተነሳ ድርጅት ሲሆን፤ በዋነኛነት ሴት መስማት የተሳናቸውን ቀጥሮ ያሠራል። መስከረም እንደምትለው፤ የድርጅቶች አካታች አለመሆን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ችግር ነው። "ድርጅቶች አካል ጉዳተኞችን መቅጠር ሲያስቡ ፍርሀት ያድርባቸዋል። መስማት ለተሳነናቸው የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ መቅጠር ተጨማሪ ወጪ ይሆንባቸውል። ነጋዴውም፣ ቀጣሪውም ማኅበረሰቡ ጋርም የግንዛቤ ክፍትተ አለ፤ አካል ጉዳተኞች እንደ ጉዳት አልባ ይሠራሉ ተብሎ ስለማይጠበቅ ማካተቱ አይታሰብም" • የዓመቱ የቢቢሲ የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ 100 ሴቶች • ዐይነ ስውሩ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ሕንፃ ከሰባተኛ ፎቅ የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ሞተ ችግሩ የሥራ ቅጥር አካታች አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ መሥሪያ ቤቶች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አለመሆናቸው ጭምርም ነው። ምን ያህሉ መሥሪያ ቤት ወይም ህንፃ ራምፕ (የአካል ጉዳተኞች መወጣጫ) አለው? ምን ያህል መሥሪያ ቤትስ ለአካል ጉዳተኞች አሳንስር ያዘጋጃል? ሚሚ እንደምትለው፤ በተለይ መስማት በተሳናቸው ዘንድ ችግሩ የሚጀምረው ከቤተሰብ ነው። የምልክት ቋንቋ የሚችል ሰው እምብዛም ስላልሆነ መስማት የተሳናቸው ልጆች ከመረጃ ተገልለው ያድጋሉ። በሥራ ቦታም እንዲሁም። "መስማት የተሳናቸው ይገለላሉ፤ ብቻቸውን የመሆን አዝማሚያም አለ። ተኪ ውስጥ ግን አንዱ አንዱን እያየ ለካ ብቸኛ አይደለሁም ብሎ ጉዳቱን አቅልሎ እንዲመለከተው ይደርጋል። መረጃም እንለዋወጣለን። መረጃ ማግኘት ደግሞ በራስ መተማመንን ይጨምራል" ከሦስት ዓመት በፊት የተመሰረተው 'ተኪ' የወረቀት ቦርሳ አምራች ድርጅት ነው ምን ይደረግ? ከ60 በመቶ በላይ አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሠራ ድርጅት ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ነጻ ይሆናል የሚለው ድንጋጌ አካታችነትን ቢያበረታታም አተገባበሩ ላይ ክፍተት እንዳለ መስከረም ትናገራለች። "ከ60 በመቶ በላይ አካል ጉዳተኞች ስለቀጠርን የተጨማሪ እሴት ታክስ እፎይታ ለማግኘት ስንጠይቅ ረዥም ቢሮክራሲ ገጠመን። ለሰባት ወር፣ በረዥም ኦዲት አልፈን አሁንም አልጨረስንም" መንግሥት የድንጋጌውን ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ ሂደቱን ቀላል ማድረግ እንዳለበት ሚሚም ትናገራለች። ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ከማድረግ ባሻገር ከውጪ የሚገባ ጥሬ እቃን ከቀረጥ ነጻ ማድረግና ሌሎችም ማበረታቻዎች ቢኖሩ፤ ድርጅቶች አካል ጉዳተኞችን ለመቅጠር እንደሚነሳሱ ታምናለች። • ካለሁበት 45፡''የጽዳቷ ነገር እንጂ አዲስ አበባ ትሻለኛለች'' • የዓለማችን ሃብታም ሴቶች ብዙ ድርጅቶች አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ተቋም ከፍተው፤ በሥራ ቦታ አለመመቻቸትና በኪራይ ዋጋ መናር ሳቢያ ሲዘጉ እንደሚስተዋል የምትናገረው መስከረም፤ መንግሥት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ ቢያደርግ ለውጥ እንደሚመጣ ታስረዳለች። አካል ጉዳተኞች ለአንድ ክፍት የሥራ ቦታ የሚጠየቀው የትምህርት ማስረጃና ሙያዊ ብቃት ቢኖራቸውም ቀጣሪዎች እድሉን አይሰጧቸውም። ቀጣሪ ድርጅቶችና ኃላፊዎች ስለ አካል ጉዳተኞች ያላቸውን ግንዛቤ ማስፋት፣ አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ሰው መሥራት እንደሚችሉ መረዳት እንዳለባቸውም ታክላለች። ጉዞ ወደ አካባቢ ጥበቃ ኢትዮጵያ፤ ከሦስት ዓመት በኋላ እንደሚተገር በተነገረለት ድንጋጌ፤ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የፕላስቲክ ምርትን የማገድ እቅድ እንዳላት ይፋ አድርጋለች። በዚህ ረገድ ጎረቤት አገር ኬንያን ጨምሮ በርካታ አገሮች ፕላስቲክ ምርትን ከዓመታት በፊት ማገዳቸው ይታወቃል። ተኪ ከድንጋጌው ቀድሞ ለአካባቢ ጥበቃ የሚበጀውን የወረቀት ቦርሳ ለማስተዋወቅ እየሞከረ ነው። በኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ ረግድ ግንዛቤ እንዳልዳበረ የምታስረዳው ሚሚ፤ ሥራቸው ፈታኝ እንደሆነ ትገልጻለች። ለምሳሌ የመደብር ባለቤቶች በቅናሽ የሚሸመተውን ፕላስቲክ ይመርጣሉ። "በነጻ ለምሰጠው ነገር ለምን [ውድ የወረቀት ቦርሳ ገዝቼ] ጥቅሜን አሳልፌ እሰጣለሁ ብለው ቅር ይላቸዋል" ትላለች። የወረቀት ቦርሳ ከፕላስቲክ አንጻር ዋጋው ቢጨምርም ለአካባቢ ጥበቃ ያለው አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑን ለማስረዳት ጥረት ያደርጋሉ። ምርታቸውን ግዙፍ ተቋሞች ሲገዙ በማየት በወረቀት ቦርሳ ለመገልገል ፍቃደኝነት ያሳዩ እንደተበራከቱ መስከረም ትናገራለች። • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች • ለዓመቱ ምርጥ የታጨችው ኢትዮጵያዊት በዋነኛነት በብዛት ለድርጅቶች ቢያከፋፍሉም፤ በግላቸው የሚገዟቸውም አሉ። በእርግጥ ከትርፍ አንጻር አዋጭ ባይሆንም ለወደፊት ነገሮች እንደሚለወጡ ተስፋ እንዳላቸው ሚሚ ትገልጻለች። "ትርፋችን ትንሽ ሆኖ ብንሠራም ነገ የሰው ግንዛቤ ሲያድግ የተሻለ እንሸጣለን። የተነሳነው የአካባቢ ጥበቃን እና ማኅበራዊ አገልግሎትንም ይዘን ነው" በአንድ ወቅት ከስዊዘርላንድ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በሴት ሥራ ፈጣሪዎች ለተመሰረቱ ድርጅቶች በነጻ የወረቀት ቦርሳ አከፋፍለው ነበር። ከዚህም የተሻለ ተቀባይነት የተገኘው በባልትና ምርቶች መደብረና በፋርማሲዎች ነበር። ተኪ እስካሁን 395 ሺህ የወረቀት ቦርሳ አምርቷል ሽሮ፣ በርበሬ ሲሸምቱ በካኪ መሸፈን የሚመርጡ እንዲሁም የቲቢ እና ኤችአይቪ መድሀኒትን በሚስጥር ለመያዝ የወረቀት ቦርሳ የሚገዙም ብዙ ናቸው። ለወደፊት የፕላስቲክ ምርት ሲታገድ የገንዘብ አቅም ያላቸው ግዙፍ ተቋሞች ከፕላስቲክ ወደ ወረቀት ቦርሳ ምርት ሊዘዋወሩ ይችላሉ። ይህም እንደ ተኪ ያሉ ተቋሞች ህልውናን ጥያቄ ውስጥ ይከታል። ሚሚ እንደምትለው፤ በወረቀት ቦርሳ ምርት ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ቢሰጥ ብዙ ሺህ ሥራ አጥ አካል ጉዳተኞችን መደገፍ ይቻላል። "ይሄ ዘርፍ ለአካል ጉዳተኞች ቢሰጥ በከፍተኛ ሁኔታ የአካል ጉዳተኞችን ሥራ አጥነት ይቀርፋል። ማሽን ሳያስፈልግ፣ በቀላሉ ማንኛውምም አካል ጉዳተኛ ሊሠራው ይችላል። የሰውን አስተሳሰብም ለመቀየርና መንግሥትን ለማሳመንም ግንዛቤ መስጫ መድረክ ለማዘጋጀት አስበናል" በቅርቡ ግንዛቤ ማስጨበጫና የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ 'ክራውድ ፈንዲንግ' የማካሄድ እቅድ እንዳላቸው ሚሚና መስከረም ይናገራሉ። የተኪ ጅማሮ ተኪ በ18 መስማት የተሳናቸው ሠራተኞች ይንቀሳቀሳል። እስከአሁን 935ሺህ የወረቀት ቦርሳ አምርቷል። ለመዋዋቢያ ማስቀመጫ፣ ለምግብ ማጓጓዣ እና ለተለያዩ ቁሳቁሶች የሚሆን የወረቀት ቦርሳ በተለያየ ዋጋ ያቀርባሉ። ሚሚ እና መስከረም እንደሚሉት፤ የጥሬ እቃ ውድነት ዋነኛ ተግዳሮታቸው ነው። ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ቢሆኑ ይህ እንደሚለወጥም ያስረዳሉ። "እስካሁን ከቫት ነጻ ብንሆን፤ የምርታችንን ዋጋ ቀንሰን ሰው በቀላሉ እንዲገዛው ማድረግ እንችል ነበር። ገበያውን ሰብረን ገብተን ተወዳዳሪ እንሆንም ነበር" ትላለች ሚሚ። ቀድሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተረፈ ምርት ዳግመኛ የተሠራ ወረቀት ይጠቀሙ ነበር። የውጪ ምንዛሬ እጥረት ወረቀቱ የሚሠራበት ኬሚካል እንደልብ እንዳይገኝ ስላደረገ የምርታቸው ጥራት ቀንሶ ነበር። ስለዚህም ለተወሰነ ጊዜ ምርት ለማቆም ተገደዋል። ለዚህም መፍትሔው የመንግሥት ድጋፍ እና ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መደረግ እንደሆነ ሚሚ ታስረዳለች። ሌላው መሰናክል ምቹ ቦታ አለማግኘት ነው። ቀድሞ የሚሠሩበት ቦታ ከአዲስ አበባ እምብርት ስለሚርቅ ምርታቸውን ለማጓጓዝ ተቸግረው ነበር። ቦታው ለመኖሪያ ተብሎ የተዘጋጀ ስለሆነ ምርት ማከማቻ አልነበራቸውም። ተጨማሪ መስማት የተሳናቸው ለመቅጠርም አልቻሉም ነበር። • "ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን ወደ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ማምጣት ፈታኝ ነው" ዘረሰናይ መሐሪ • ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት ተኪ የአካባቢ ጥበቃን እና ማኅበራዊ አገልግሎትን አጣምሯል ዓመት ከወሰደ ሂደት በኋላ፤ ጎተራ አካባቢ ለጥቃቅንና አነስተኛ የተመደበ ህንፃ ላይ፣ በአነስተኛ ኪራይ መንግሥት ቦታ ሰጥቷቸዋል። ለድርጅቶች ምርት ለማመላለስ ቅርብ ቢሆንም፤ ፎቅ ላይ በመሆኑ ዊልቸር ወይም ክራንች የሚጠቀሙ ሰዎች ምቹ አይደለም። ሚሚ እና መስከረም በቀጣይ ሦስት ዓመታት፣ 5 ሚሊዮን የወረቀት ቦርሳ በአዲስ አባበ የማሰራጨት፣ ለ100 ሰዎች የሥራ እድል የመፍጠር እቅድም አላቸው።
news-56765791
https://www.bbc.com/amharic/news-56765791
ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ፡ በሃጫሉ የፍርድ ሂደት ቅሬታ እንዳላቸው ገለጹ
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ቤተሰብ ከዘጠኝ ወራት በላይ ከቆየ ዝምታ በኋላ በወንጀል ምርመራው እና በፍርድ ሂደቱ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
ታናሽ ወንድሙ ሲሳይ ሁንዴሳ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ "ላለፉት ዘጠኝ ወራት ምንም ካለመናገር የተቆጠብነው ማንኛውም አካል ግድያውን ለፖለቲካ ትርፍ እንዳይጠቀምበት በማሰብ ነበር" ይላል። ከሃጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞ ያለው የወንጀል ምርመራ እና አሁን ያለው የፍርድ ሂደት "የፖለቲካ ጨዋታ ነው። ቤተሰብ ይህንን ጠንቅቆ ያውቃል" ይላል ሲሳይ። ከዘጠኝ ወራት በላይ ያስቆጠረው የምርመራ እና የፍርድ ቤት ሂደት ችሎት እንዳይገቡ መከልከልን ጨምሮ የተለያዩ መከልከሎች ሲያጋጥማቸው እንደነበር ይናገራል። ጉዳዩን የያዙት የፌደራሉን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በበኩላቸው የወንጀል ምርመራውም ሆነ የፍርድ ቤት ሂደቱ የአገሪቱን ሕግ መሰረት ባደረገ እና በገለልተኝነት እየተካሄደ መሆኑን ይናገራሉ። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ባለፈው ዓመት ሰኔ 22/2012 ምሽት ላይ አዲስ አበባ ውስጥ መኪናው ውስጥ ነበር የተገደለው። ግድያውን ተከትሎ አራት ሰዎች ተጠርጥረው የተያዙ ሲሆን ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውም በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ተከሳሽ ላምሮት ከማል፣ በነጻ እንድትሰናበት ሦስተኛ ተከሳሽ አብዲ አለማየሁ በ10 ሺህ ብር የዋስ መብቱ ተጠብቆ እንዲወጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። አንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ በቀጥታ የሃጫሉ ግድያ መፈፀሙን የሚያረጋግጥ በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ስለተገኘ ራሱን እንዲከላከል ብሎ ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ይታወቃል። በዚህ መዝገብ ውስጥ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው ከበደ ገመቹ፣ ከአንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ ጋር በመሆን ግድያውን በመፈፀሙ እንዲከላከል ተወስኗል። ነገር ግን ከበደ ገመቹ ከአንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ ጋር " ጉዳት አድርሰን እንዝረፈው" በማለት፣ ዝርፊያ ለመፈፀም በመስማማት አብሮ እንደሄደ መረጋገጡ ተነግሯል። ስለዚህ ይህንን ድርጊት የፈፀመው አስቦበት እንዳልሆነ በመጥቀስ ጉዳዩ በ1996 የወንጀል ሕግ 540 አንቀጽ ስር እንዲታይ ብይን ተሰጥቷል። ሶስተኛ ተከሳሽ አብዲ አለማየሁ ደግሞ በሃጫሉ ግድያ ውስጥ በቀጥታ እጁ እንዳለበት የሚያሳይ መረጃ የለም በማለት፣ ነገር ግን ወንጀሉን አይቶ ባለመናገር የዋስትና መብቶ ተጠብቆለት ጉዳዩን ከውጪ እንዲከታተል ተወስኖለታል። ቤተሰብ እና ዐቃቤ ሕግ ምን ይላሉ? ከመጀመሪያው አንስቶ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ "ገለልተኛ በሆነ ሦስተኛ አካል" እንዲመረመር ቤተሰብ ፍላጎት እንደነበረው የሃጫሉ ሁንዴሳ ወንድም ሲሳይ ሁንዴሳ ተናግሯል። ነገር ግን ይህንን ፍላጎታቸውን የሚያመለክቱበት አካል እንዳልነበረ እና መንገዱም ዝግ እንደነበር ይናገራል። የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ አቶ አወል ሱልጣን ለዚህ የቤተሰቡ ቅሬታ ምላሽ ሲሰጡ፣ አገሪቱ ካላት ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግ ውጪ ይህንን ማጣራት የሚችል ሌላ ገለልተኛ አካል የለም ይላሉ። በእርግጥ ውስብስብ የሆኑ እና ከአገሪቱ የመመርመር አቅም በላይ የሆኑ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ሌሎች አቅሙ ያላቸው ወዳጅ አገራትን መጋበዝ እና ድጋፍ እንዲያደርጉ ማድረግ ይቻላል ሲሉ ያክላሉ። ነገር ግን በዚህ ምርመራ ይሄ የሚያስፈልግበት አግባብ የለም ብለዋል። "የሃጫሉ ቤተሰብ ይህንን እንደ ጥያቄ ማንሳታቸው ስህተት ላይሆን ይችላል" የሚሉት አቶ አወል ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስችል የሕግ አግብ እንደሌለ ግን ያስረዳሉ። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ወንጀል ምርመራ ለየት ባለ መልኩ ፈጣንና ጠንካራ የሆነ ምርመራ መደረጉ ምንም የሚያጠያይቅ አይደለም የያሉት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ አቶ አወል ሱልጣን፤ የምርመራ ሂደቱን የሃጫሉን ቤተሰብ ጨምሮ ለምርመራው ያስፈልጋሉ የተባሉ ሰዎችን ሁሉ ያሳተፈ እንደነበር ይናገራሉ። "በወንጀል ምርመራ ሂደቱም ሆነ በፍርድ ቤት የክርክር ሂደት ከሃጫሉ ቤተሰብ ጋር የነበረን የሥራ ግንኙነት ጠንካራ ነበር" ብለዋል። "የምርመራ ሂደቱ ጠንካራ እንደነበር ሲያስረዱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው ባለሙያዎች፣ ከጠቅላይ አዐቃቤ ሕግ ደግሞ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክተሮችን ሳይቀር ያሳተፈ ቡድን ተዋቅሮ ነው ምርመራው የተካሄደው። "በዚህም ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው ወንጀሉን መፈጸማችን የሚያሳይ እና ፍርድ ቤቱንም ሊያሳምን የሚችል ማስረጃ ቀርቦባቸው ወንጀሉን ይከላከሉ መባሉ የተደረገው ምርመራ ጠንካራ እንደነበር ማሳያ ነው" ይላሉ። ከሃጫሉ ጋር በአንድ ቤት ይኖር እንደነበር የሚናገረው ሲሳይ፤ ሃጫሉ በተገደለበት ምሽት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ እስር ቤት እንዳደረ፣ እናም ጠዋት ላይ እንደተለቀቀ ለቢቢሲ ተናግሯል። ከተለቀቀ በኋላ የዚያን ዕለት ምሽት ምን እንደተፈፀመ ያየውን የጠየቀው አካል እንደሌለ፣ በአጠቃላይም የወንጀል ምርመራው ሂደት ቤተሰብን በበቂ ሀኔታ ያሳተፈ እንዳልነበር እና ትክክለኛ የሆነ ምርመራ ተደርጓል ብሎ ቤተሰቡ እንደማያምን ሲሳይ ጨምሮ ያስረዳል። "ለምሳሌ፣ ሙሉ መረጃ ያለበት እና ሃጫሉ ከሰዎች ጋር ለመገናኘት የሚጠቀምበት የእጅ ስልኩ፣ በእነርሱ [መርማሪዎች] እጅ ነው ያለው። ኤግዚቢት ነው ብለው ሲመልሱልን 480 ሺህ ብር እና ሌላ ተለዋጭ የሚጠቀምበትን ስልክ ሰጥተውናል። "ነገር ግን ሙሉ መረጃ ያለበት የእጅ ስልኩ እና ሽጉጡ አልተመለሰልንም። ይህ የእጅ ስልኩ አለመመለስ ያለ ምክንያት አይደለም ብለን ነው የምናስበው።" ቤተሰብ አርቲስት ሃጫሉ ተገድሏል በተባለበት ስፍራ መገደሉን ጥርጣሬ እንዳለውና አሁን ባለው ሂደት "ፍትህ እናገኛለን ብለን አናምንም" ብሏል። የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የእጅ ስልኩና ሽጉጡን እንዲሁም ሌሎች መኪና ውስጥ የተገኙ መሳሪያዎች በሙሉ በሚገባ መመርመራቸውንም ይናገራሉ። ቤተሰብ አልተመለሰልንም በማለት ያቀረበውን ስልክ እና ሽጉጥ በተመለከተ በፍርድ ቤት የክርክር ሂደት ውስጥ አስፈላጊ ናቸው ተብሎ ከታመነባቸው እቃዎች ውጪ በሙሉ ለቤተብ መመለሱን ይናገራሉ። የሃጫሉ ወንድም ቅሬታውን ለቢቢሲ ሲገልጽ "እኛ ተስፋ የቆረጥነው በነጋታው፣ እርሷ [አራተኛ ተከሳሽ ላምሮት ከማል] መክሰስ አያስፈልግም የምታውቀውን ነገር ከነገረችን ልትለቀቅ ትችላለች ተብሎ መግለጫ የተሰጠ ጊዜ ነው" ሲልም ያክላል። ሲሳይ እንደሚለው ከሆነ የሃጫሉ ቤተሰብ አራተኛ ተከሳሽ የሆነችው ላምሮት ከማል ከአርቲስቱ ግድያ ላይ ተሳትፎ አላት ብሎ ያምናል። ነገረ ግን "እርሷ ተጠያቂ እንዳትሆን ድራማ ሲሰራ ነበር" ይላል። "ሂደቱ ድራማ ነው፤ በጣም አስቀያሚ ድራማ፣ ደካማ በሆኑ ሰዎች የተጻፈ፣ ደካማ የሆኑ ሰዎች የሚተውኑበት፣ እኛ ተጎጂዎቹ ቀርቶ ሌላ ከውጪ ተመልካች የማይመስል ነገር ብሎ የሚንቀው ድራማ ነው" ይላል። "በአጠቃላይ አሁን ባለው ሂደት ሄዶ ሄዶ አንደኛው ተከሳሽ ላይ አላኮ ድራማውን እርሱ ላይ ለመጨረስ ነው እየተሄደ ያለው።" በፍርድ ቤት በኩልም ገለልተኛ ሆኖ ጉዳዩን እያየ እንደሆነ ቤተሰብ እምነት እንደሌለው በመጥቀስ፤ ቦታ ሞልቷል ተብሎ ከችሎት መከልከልን ጨምሮ "ሰው እውነቱን ከመጠየቅ ወደ ኋላ እንዲል እንዲፈራ ብዙ ነገር ተደርጓል" ይላል ሲሳይ። "ሰው አይኑ እያየ ድራማ ከሚሰራበት ተትቷል ወይም ቀርቷል ቢባል ይሻላል" የሚለው ሲሳይ "ፍርድ ቤት ከጉዳዩ ላይ እጁን ያውጣ" ሲል ይጠይቃል። "ይህ ማለት ግን ሙሉ ለሙሉ ጉዳዩን ጥሎ ይውጣ ሳይሆን አሁን እየሄደ ካለው የፖለቲካ ጨዋታ ይውጣ፣ ጉዳዩ ገለልተኛ በሆነ አካል ተጣርቶ ወንጀሉ አንድ በአንድ ከተመረመረ በኋላ ፍርድ ቤትም ገለልተኛ ሆኖ ይይልን" ማለት እንደሆነ አብራርቷል። የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ በበኩላቸው ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሳሾች እንዲከላከሉ የተባለበት ወንጀል አንቀጽ መቀየሩን በተመለከተ አሁንም በፍርድ ሂደት ላይ ያለ ስለሆነ ምናመልባት ውሳኔ ሲያገኝ ይግባኝ የሚያስጠይቅ ከሆነ ያኔ የሚገለጽ መሆኑን አመልክተዋል። አራተኛ ተከሳሽ ላምሮት ከማል በነጻ እንድትሰናበት ፍርድ ቤት መወሰኑን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ጉዳዩ በቀጠሮ ተይዞ እንዳለም ተናግረዋል። እስከዚያ ድረስ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ትፈታ ብሎ ስለወሰነ እርሱ ውሳኔ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጎ፣ ተከሳሿ አሁንም በፖሊስ ቁጥጥጥር ስር እንደምትገኝ አቶ አወል አስረድተዋል። ተከሳሿ መጀመሪያ ላይ ስለግድያው የምታውቀውን ከተናገረች እርሷን እንደምስክር በመቁጠር ዋነኛ ወንጀል ፈጻሚዎች ላይ ክስ የመመስረት የተለመደ አሰራር እንደሆነ እና አቃቤ ሕግም በዚሁ መሰረት መግለጫ ሰጥቶ እንደነበር ይናገራሉ። ነገር ግን በምርመራ ሂደት እርሷ ወንጀሉ ውስጥ ተሳትፎ እንዳላት የሚያሳዩ መረጃዎች ስላገኘን እርሷንም ተከሳሽ አድርገን ፍርድ ቤት አቅርበናታል ይላሉ አቶ አወል። ስለዚህም እርሷ እንዳትከሰስ ለማድረግ ወይንም እርሷ ነጻ እንድትወጣ ዐቃቤ ሕግ የሚሰራበት ምንም አግባብ አለመኖሩን ይናገራሉ። በዚህ ዘገባ ላይ የላምሮት ከማልን ወይንም የጠበቃዋን ሃሳብ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ነገር ግን በማንኛውም ወቅት ምላሻቸውን ለማካተት ዝግጁ ነን። ፍርድ ቤቱ ምን ይላል? የአርቲስት ሃጫሉን ግድያ እያየ ያለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ብርሃነ መስቀል ዋቅጋሪ ቤተሰብ በሚያነሳቸው ቅሬታዎችና ትችቶች ዙሪያ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ብርሃነመስቀል እንደሚሉት ፍርድ ቤቱም ሆነ ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ ዳኞች ከየትኛውም ወገን ገለልተኛ ሆነው ጉዳዩን እያዩ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን "በፍትህ ሥርዓት ውስጥ ፍርድ ቤት ብቻውን አይደለም የሚሰራው፤ ፖሊስ ይመረምራል፣ ዐቃቤ ሕግ ክስ ይመሰርታል ከዚያ በኋላ ነው ፍርድ ቤት የሚመጣው" ይላሉ። "ከመጀመሪያ ጀምሮ ፖሊስ እንዴት ነው የመረመረው፤ አቃቤ ሕግ በምን አግባብ ነው ክስ የመሰረተው፤ እንዴትስ ነው ክስ የመሰረተው የሚሉ ነገሮች የመጨረሻ ውጤቱ ፍርድ ቤት ላይ ስለሆነ የሚንፀባረቀው ትችቱ ፍርድ ቤት ላይ ይበዛል" ይላሉ። ነገር ግን በፍርድ ቤት በኩል "ዳኞች ነጻና ገለልተኛ ሆነው ሕግና ሕግን ብቻ መሰረት ባደረገ፣ በጥሩ ሞራል እና መንፈስ ነው ሥራቸውን እየሰሩ ያሉት" ይላሉ። አራተኛ ተከሳሽ ላምሮት መለቀቋን ተከትሎ ቤተሰብ የሚያነሳውን ቅሬታ በተመለከተ "ፍርድ ቤት የቀረበለትን ነገር ነው የሚመዝነው፤ ሚዛን የሚደፋ ነገር ከቀረበለት ፍርድ ቤት ምን ሊያደረግ ይችላል?" የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን የፍርድ ቤት ሂደት በተመለከተ ለፍርድ ቤቱ የቀረበ ምንም ዓይነት ቅሬታ እንደሌለ "ነገር ግን ቅሬታ ካለ ነገም ከነገ ወዲያም በራችን ክፍት ነው" ይላሉ አቶ ብርሃነ መስቀል። ቤተሰብ በገለልተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩ እንዲታይልን ሲሉ የጠየቁትን በማስመልከት "ፍርድ ቤት አንድ ነው ሌላ አዲስ የሚቆም ገለልተኛ ፍርድ ቤት የለም ሊኖርም አይችልም፤ ባለው ፍርድ ቤት ላይ እምነት ማጣት የለብንም" ይላሉ።
44393752
https://www.bbc.com/amharic/44393752
አሜሪካዊው በሞተ እባብ ተነደፈ
መኖሪያውን ቴክሳስ ግዛት ያደረገ አንድ ግለሰብ 25 ያክል የእባብ መርዝ መከላከያ መድሃኒት እንዲወስድ ግድ ሆኖበታል። ይህም የሆነው ቀጥቀጦ እና ቆራርጦ የጣለውን እባብ ከመኖሪያ ቤቱ እያራቀ ሳለ በሞተው እባብ ጭንቅላት በመነደፉ ነው።
የተነዳፊው ባለቤት ለአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ስትናገር ባለቤቷ የአትክልት እርሻውን በማሰማመር ላይ ሳለ ነበር 1.25 ሜትር ርዝማኔ ያለውን እባብ የተመለከተው። ከዚያም መከላከያውን መዥለጥ በማድረግ እባቡን እንዳልነበር ካታትፎ ይጥለዋል። ለጥቆም የተቆራረጠውን የእባቡን አካል ይዞ በመውጣት ላይ ሳለ የእባቡ ጭንቅላት የነደፈው። ወዲያውም ሰውየውን ይንዘፈዘፍ ያዘ። ይህን የተመለከትችው ባለቤቱ ደርሳ አምቡላንስ ትጠራለች። የአካባቢው የጤና ባለሙያዎችም የእባብ መርዝ ማርከሻ ካለበት ሥፍራ በሄሊኮፕተር በመውሰድ ሕይወቱን ሊያተርፉት ችለዋል። ግለሰቡ ኩላሊቱ አካባቢ ከሚሰማው የሕመም ሰሜት በቀር አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተነገሯል። በሕክምና መስጫው ያሉ አንዲት ባለሙያ አንዳንድ የእባብ ዝርያዎች ጭንቅላታቸው ቢቆረጥ እንኳ ለሰዓታት ሳያሸልቡ ሊቆዩ እንደሚችሉ አስገንዝበዋል። የዓለም የጤና ድርጅት በቅርቡ በእባብ መነደፍ ከአንገብጋቢ የጤና እክሎች መካከል መመደቡን አሳውቆ እንደነበር አይዘነጋም።
news-54003525
https://www.bbc.com/amharic/news-54003525
2012 ፡ ኮሮናቫይረስ ያጠላበት የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ፡ “አርቲስቶች ቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቸዋል”
ነሐሴ 17 ቀን 2012 ዓ. ም ከሰዓት “ንጋት” የተሰኘ ኮንሰርት ነበር።
ዘሪቱ ከበደ፣ ኃይሌ ሩትስ፣ ፍቅርአዲስ ነቃዓጥበብ፣ ጌቴ አንለይ፣ ሔኖክ መሐሪ፣ ቤቲ ጂ እና ሌሎችም ድምጻውያን ያለ ታዳሚ ሙዚቃቸውን አቅርበው በኢቢሲ፣ በዋልታና በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ተላልፏል። ታዳሚዎች ቤታቸው ሆነው ኮንሰርቱን በቴሌቭዥን እየተከታተሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሐሳብ ሲለዋወጡ ነበር። የኮሮናቫይረስ ባስከተለው ተጽእኖ በበርካታ አገሮች ኮንሰርቶችና የአደባባይ ፌስቲቫሎች ቆመዋል። በኢትዮጵያም ቴአትር፣ የሙዚቃ መሰናዶ፣ ዓውደ ርዕይ ወዘተ. . . ከተገቱ ከአምስት ወራት በላይ ተቆጥረዋል። የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች ለወትሮው እንደሚያደርጉት በመቶዎች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ሥራቸውን እንዲያዩ መጋበዝ አልቻሉም። በበይነ መረብ ኮንሰርት እንዲሁም የሥዕል ዓውደ ርዕይ ያካሄዱ ጥቂት ሙዚቀኞችና ሠዓሊዎች አሉ። ሆኖም ግን አጠቃላይ የሥነ ጥበብ ዘርፉ 2012 ላይ እጅግ ተቀዛቅዞ ከርሟል። ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳደረ? የጥበብ ሰዎችስ ዓመቱን እንዴት አሳለፉ? ስንል ወደኋላ መለስ ብለን ቃኝተናል። ሙዚቃ "ሙሉ በሙሉ የመድረክ ሥራ ላይ ለተመረኮዘ ሙዚቀኛ በጣም ከባድ ነው" ሔኖክ መሐሪ "ንጋት" በዓመቱ ከወጡ አልበሞች አንዱ ነው። ከአልበሙ የሚገኘውን ገቢ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ለሚያደርው ጥረት እንዲውለው በሙዚቀኞቹ ተሰጥቷል። አልበሙ ከወጣ በኋላ ደግሞ "ንጋት" የተባለው ታዳሚ አልባ ኮንሰርት ተካሂዷል። ሙዚቀኛ ሔኖክ መሐሪ እንደሚለው፤ ኮንሰርቱ የተዘጋጀው ሕዝቡ ቤቱ ሆኖ መዝናናት እንደሚችል ለማሳየትና ቫይረሱ ያስከተለውን ድብርት ለመቀነስ ነው። "ሙዚቃ የሚሰማው በድግስ ብቻ ሳይሆን በሀዘን፣ በድብርት ወቅትም ነው" የሚለው ሔኖክ፤ ሙዚቃ አንዳች መጽናኛ እንደሚሆን ያስረዳል። በሌላ በኩል ሙዚቀኞችን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በገንዘብ ለመደገፍ ተሞክሯል። ከተለያዩ ከተሞች በተወጣጡ ሙዚቀኞች ሌሎች ተመሳሳይ ኮንሰርቶች የማዘጋጀት እቅድም አላቸው። "በኮንሰርቱ አማካይነት ወደ 24 የሚሆኑ በህመምና በሌላም ምክንያት ችግር ውስጥ ያሉ ሙዚቀኞች ቤተሰቦችን ደግፈናል" ይላል። ኮንሰርቶችና ፌስቲቫሎች እንዲሁም ሌሎችም ሙዚቃን ያማከሉ መሰናዶዎች በመሰረዛቸው ድምጻውያን፣ የመድረክ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አዘጋጆች ወዘተ. . . ተጎድተዋል። መደበኛ ተቀጣሪ ያልሆኑና ገቢያቸውን ከሙዚቃ ዝግጅቶች የሚያገኙ ከፍተኛ የገንዘብ ቀውስ እንደገጠማቸው እሙን ነው። እንዲሁም የቅጂ መብት ጥሰት ጫና ያሳደረበት ሙዚቃው፤ ኮሮናቫይረስ ሲጨመርበት ለባለሙያዎች ፈታኝ እንደሆነ ሔኖክ ይናገራል። "ኮንሰርት፣ የምሽት ክለብ ሥራና ሌላ መሰናዶ ቆሟል። ሙሉ በሙሉ የመድረክ ሥራ ላይ ለተመረኮዘ ሙዚቀኛ በጣም ከባድ ነው። ተቀማጭ፣ ጡረታ የለውም። ዘፋኙ ስቱድዮ ሲሄድም በኪስ ገንዘቡ ነው የሚሠራው።” ወረርሽኙ ካመጣው የምጣኔ ሀብት ጫና ባሻገር ግን ለፈጠራ ሰዎች የጽሞና ጊዜ መስጠቱ አይካድም። ሔኖክም የመጀመሪያዎቹን አራት ወራት ከቤተሰብ ጋር ዘለግ ያለ ጊዜ በመቆየት፣ ሙዚቃ በመሥራት አሳልፏል። ወራት በወራት ላይ እየተደራረቡ ሲመጡ አብዛኛው ሰው ድብርት እየተጫጫነው መምጣቱንም፤ "ሰዋዊ የሆነውን ሰላምታ፣ መተቃቀፍና በነጻነት መተንፈስ ቀማን" በማለት ይገልጻል። በሌሎች አገራት ሙዚቀኞች ሥራቸውን በተለያዩ መተግበሪያዎች ያቀርባሉ፣ ይሸጣሉም። ይህ ግን የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ እውነታ አይደለም። ገቢያቸውን በምሽት ክለቦች፣ በኮንሰርቶችና በፌስቲቫሎች የሚያገኙ ሙዚቀኞች ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደወደቁ የሰላም ኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ሲሳይ መንግሥቴ ያስረዳል። አዝማሪዎች በየዕለቱ ይሠሩባቸው የነበሩ የባህል ቤቶችና የምሽት ክበቦች አሁን ላይ ተቀዛቅዘዋል። አሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ሲከበር በአማራ እንዲሁም በትግራይ ክልል ድምጻውያን ያለ ታዳሚ ተቀርጸው በአማራ ቴሌቭዥንና በድምጺ ወያነ እንዲሰራጭ ማድረጋቸውን ሲሳይ ይናገራል። "አርቲስቱ ያለበት ሁኔታ አሳዛኝ ነው። ለምሳሌ በአማራ ክልል ወደ ዶሮ እርባታ የገቡ አርቲስቶች አሉ" ሲል ሁኔታውን ይገልጻል። ኮሮናቫይረስ ያሳደረውን የምጣኔ ሀብት ቀውስ በመጠኑም ለማቃለል ለአዲስ ዓመት ሙዚቀኞችን ያለ ታዳሚ ቀርጾ የማስተላለፍ እቅድ አላቸው። "በቴሌቭዥን የሚተላለፈው መንግሥትም አርቲስቶቹን እንዲደግፍ ለማነሳሳት ነው።" ሲሳይ እንደሚለው፤ ቨርችዋል ኮንሰርት [የበይነ መረብ ኮንሰርት] ሲዘጋጅ ለመድረክ፣ ለመብራት፣ ለባንድ የሚወጣው ወጪ ከመደበኛ ኮንሰርት እኩል ነው። ሙዚቀኞቹ ግን የሚከፈላቸው እንደሌላው ኮንሰርት አይደለም። "አርቲስቶቹ ቁጭ ከሚሉ፣ ከሚቸገሩ፣ ከሚጨነቁ በሚል ነው እንጂ ገቢው ያን ያህል አይደለም። መሠረታዊን ወጪ ከመሸፈን አያልፍም። ማሳተፍ የሚቻለውም ጥቂት አርቲስቶች ብቻ ነው። ይህ በድርጅት ብቻ የሚሸፈን አይደለም" በማለትም ድጋፍ ሰጪ እንደሚያሻ ይጠቁማል። ሥነ ጥበብ "ገበያው ዜሮ ሆኗል" ኑሩ አበጋዝ ላፍቶ ዘመናዊ የሥነ ጥበብ ጋለሪ በወራት ልዩነት ዓውደ ርዕዮችን የሚያስተናግድ፣ የሥነ ጥበቡን ማኅበረሰብም የሚያስተሳስር ነበር። ላለፉት ስድስት ወራት ግን እንቅስቃሴው ተገቷል። ሠዓሊና የጋለሪው ኪውሬተር ኑሩ አበጋዝ እንደሚለው፤ ዓውደ ርዕዮች መቆማቸው ሠዓሊዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ቀላል አይደለም። አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች መቋረጣቸው እንዲሁም ሆቴሎች ኪሳራ ውስጥ መግባታቸው የሥነ ጥበብ ገበያውን አዳክሞታል። "የጋለሪ ሥራ ጥበቡን ወደ ገበያ ማውጣት ነው። አሁን ግን ገበያው ዜሮ ሆኗል። ዓውደ ርዕይ ማካሄድ ስላልተቻለ ግን ቨርችዋል ኤግዚብሽን [የበይነ መረብ ዓውደ ርዕይ] አዘጋጅተናል።" ጋለሪው በድረ ገጹ ላይ 'ስታግናንት ታይም' የተባለ ዓውደ ርዕይ ያሳያል። የዳዊት አድነው፣ የሰይፉ አበበና ሌሎችም ሠዓሊዎች ሥራዎች ስብስብ በተንቀሳቃሽ ምስል ይታያል። "ዓውደ ርዕይ እንደማሳየት አይሆንም። ግን ያሉትን ሥራዎችን ያስተዋውቃል። በድረ ገጹ ስልክ ቁጥር አስቀምጠናል። ሥዕሎች ሲሸጡ በዲኤችኤል መላክም ይቻላል" ይላል። ዓውደ ርዕይ፤ ባለሙያዎች የሚገናኙበት፣ አንዳቸው ሌላቸውን የሚያነሳሱበት፣ ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ ሥራቸውን የሚሸጡበት፣ እርስ በእርስ የሚወያዩበትም ነው። "ይህ ሲቀር ብዙ ነገር እንዳጣን ይሰማናል። ብዙ ሠዓሊ ራሱን ነው የሚያስተዋውቀው። ሰው አለማግኘት ትስስሩን መስበር ማለት ነው። ተጓዳኝ ሥራ የሌለውና ሥዕሉ ላይ ብቻ ለሚያተኩር ባለሙያ ተስፋ ሊያስቆርጥ ይችላል።” ሠዓሊዋ ሮሻን ሁኒሀንኒም የኑሩን ሐሳብ ትጋራለች። ሥዕል አልፎ አልፎ ካልሆነ እንደማይሸጥና ተጓዳኝ ሥራ ከሌለ ነገሮች ከባድ መሆናቸውን ትናገራለች። "ወቅቱ ለሁሉም ሰው አዲስ ነው። ዓለምን ሁሉ በጥብጦ ኑሯችንን የቀየረው ነገር ምንድን ነው? በቀጣይስ ወዴት እንሄዳለን? የሚለው ያሳስበኛል። ከሌሎች አርቲስቶች ጋር መገናኘት የሚቻለው በኢንተርኔት ብቻ ሆኗል" ትላለች። ቴአትር "ቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቸው ወደ ዘመድ ቤት የሄዱ አሉ" ማንያዘዋል እንደሻው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤትን ጨምሮ ሌሎችም ሰው የሚሰበሰብባቸው አዳራሾች ሥራ ያቆሙት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ነበር። የብሔራዊ ቴአትር ተቀጣሪዎች ደሞዝ አልተቋረጠም። ሆኖም ደሞዙ ትንሽ ነው። ተዋንያን፣ ሙዚቀኞች፣ ተወዛዋዦች የሚተዳደሩባቸውን ተጨማሪ ሥራዎች በማጣታቸው ከፍተኛ ችግር እንደገጠማቸው የቴአትር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ማንያዘዋል እንደሻው ይናገራል። "የቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቸው ወደ ዘመድ ቤት የሄዱ አሉ። በተጋባዥነት የሚሠሩ፣ ሁለት ሦስት መድረክ የሚሠሩ ተቸግረዋል። በኢ መደበኛ ሁኔታ ከውጪ ገንዘብ አሰባስቤ ባከፋፍልም በቂ አይደለም" ሲል ችግሩን ይገልጻል። ማስወቂያና ፊልም በመሥራት ራሳቸውን የሚደግፉ ተዋንያን እንዲሁም በምሽት ክለቦችና ኮንሰርቶች ላይ የሚሠሩ ድምጻውያንና ተወዛዋዦች አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር "የማገገሚያ ስልት" የሚል የዘርፉን ባለሙያዎች ሊደግፍ የሚችል ሐሳብ ቢያቀርብም ገና እንዳልተተገበረ ይናገራል። "በጣም ዘግይቷል። ቶሎ መድረስ አለበት። የቴአትር ባለሙያዎችና ሙዚቀኞችም ደሞዛቸው ትንሽ ነው። ድጋፍ ይፈልጋሉ። አሁን ባሉበት ሁኔታ ከቀጠሉ አስጊ ነው። የእኛ ሐሳብ ከመስከረም ወዲያ ተዋንያንም ተመልካቾችም ርቀታቸውን ጠብቀው ሥራ መጀመር ነው።" ሌላው አማራጭ ሐሳብ ተመልካች በሌለበት ተውኔቶችን መድረክ ላይ ቀርጾ በቴሌቭዥን እያስተላለፉ ሙያተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል ነው። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ሥነ ጥበብን በዚህ ወረርሽኝ ወቅት እንዴት ይቀጥል ብሎ ያቀረበውን በመውሰድ በዙም [የኢንተርኔት መድረክ] ውይይት መደረጉን ማንያዘዋል ያስታውሳል። ከሐሳቦች በዘለለ ለባለሙያዎች አፋጣኝና ተጨባጭ መፍትሔ የሚሰጥ ነገር አለ ለማለት ግን ይቸገራል። "በሕይወቴ እንዲህ ያለ ነገር ገጥሞኝ አያውቅም። ለብዙዎቻችን አዲስ ነው። መፍትሔው እየተሞከረ ያለው ችግሩ ጉዳት እያደረሰ ሳለ ነው” ይላል። ማንያዘዋል ከኮቪድ-19 ጋር ሚገናኝ "የእሳት አደጋ" የተባለ ቴአትር ወደ አማርኛ ተርጉሟል። በቴሌቭዥን ለማስተላለፍ ያነጋገራቸው ጣቢያዎች እንዳሉም ይናገራል። ሥነ ጽሑፍ "የሰው ትንፋሽ ሕይወቱ የነበረ ከያኒ ተቋርጦበታል" እንዳለጌታ ከበደ በ2012 ዓ. ም ላይ ለንባብ ከበቁ መጻሕፍት መካከል የሕይወት ተፈራ "ምንትዋብ" የዓለማየሁ ገላጋይ "ሐሰተኛው፡ በእውነት ስም"፣ የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ "የራስ ምስል"፣ የታደለች ኃይለሚካኤል "ዳኛው ማነው" እና የእንዳለጌታ ከበደ "መክሊት" ይገኙበታል። በእርግጥ የመጻሕፍት ህትመት ባይቋረጥም፤ የመጽሐፍ ምርቃቶችና የሥነ ጽሑፍ መሰናዶዎችም ከቆሙ ወራት ተቆጥረዋል። ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ እንደሚለው፤ ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞችም ተበራክተው የነበሩ የሥነ ጽሑፍ መድረኮች መቋረጣቸው እንደ ክፍተት ይነሳል። ከሥነ ጽሑፉ በተጨማሪ በሐይማኖት፣ በፖለቲካና በሌሎችም ዘርፎች የሚታወቁ ሰዎች ሐሳባቸውን የሚያንጸባርቁባቸው የግጥምና የዲስኩር መድረኮች በርካታ ታዳሚ ያስተናግዱም ነበር። "የሥነ ጽሑፍ ምሽቶቹ ቋሚ ደንበኛ ነበራቸው። አዳራሾች ይሞሉ ነበር። ኮሮናቫይረስ ሲመጣ ግን እነዚህ መድረኮች ተዘጉ። አዘጋጆቹ፣ አቅራቢዎቹ፣ አጃቢ ሙዚቀኞቹ፣ መድረክ አጋፋሪዎቹ ባጠቃላይ ገቢያቸው ተቋርጧል።" መጻሕፍት ምርቃት መቅረቱም ዘርፉ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አልቀረም። በእርግጥ ወረርሽኙ ሌሎች የጥበብ ዘርፎች ላይ ያሳደረው ጫናን ያህል ሥነ ጽሑፉ አልተጎዳም። እንዳለጌታ ወቅቱን የሚገልጸው ከገቢ አንጻር ብቻ ሳይሆን ከተፈጠረው ድባብም ጭምር ነው። "የሰው ትንፋሽ ሕይወቱ የነበረ ከያኒ ተቋርጦበታል። የመድረክ ሰው የሰው ጭብጨባ ሲቋረጥበት ሥነ ልቦናዊ ጫና ያድርበታል። መስመር ላይ ያለነው ሰዎች ምንም ባንሆንም አንጋፋ ባለሙያዎች ቤት ኪራይ የሚከፍሉት ሲያጡ፣ የእለት ጉርስ ሲያጡ ይታያል። መንግሥት ድምጻውያንን እና ተወዛዋዦችን በዓል ማድመቂያ አድርጎ ጓዳችሁ እንዴት ነው? አይልም" ይላል። ታዳሚ አልባ መሰናዶዎች፣ ኢቡክ [በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ መጻሕፍት የሚገኝባቸው] እና ሌሎችም ከወቅቱ ጋር የሚሄዱ አማራጮች መጠቀም የግድ እንደሆነም ያሰምርበታል። በሌላ በኩል ወቅቱ ለጸሐፍት እና ለአንባቢውም ፋታ፣ የጽሞና ጊዜ እንደሰጠ ያምናል። ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ከሚመጣ ጭንቀት መጻሕፍት እፎይታ የሰጧቸውም ጥቂት አይደሉም። በአዳራሽ ይካሄዱ ከነበሩ የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች ብዙዎቹ ሲቋረጡ፤ መሰናዷቸውን በቴሌቭዥን ማሰራጨት የጀመሩም አሉ። እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው ሰምና ወርቅ የሥነ ጽሑፍ ምሽት ነው። የሥነ ጽሑፍ ምሽቱ ባለቤትና የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር የሬድዮ መሰናዶ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ዓለሙ እንደሚለው፤ ታዳሚ አልባ መሰናዶዎችን በቴሌቭዥን ከማስተላለፍ ውጪ አማራጭ የለም። "መጻሕፍት ቢታተሙም የሥነ ጽሑፍ ምሽቶች፣ የመጻሕፍት ውይይቶችም እየተካሄዱ አይደለም። አንድ ሁለት ደራሲያን ዩቲዩብ ላይ ቻናል በመክፈት ሥራቸውን ሲያቀርቡ አይቻለሁ" ሲል ያስረዳል። ፊልም "በነፃ የሚሠራው የጥበብ ሰው ሆኖ ድጋፍ ያጣውም የጥበብ ሰው ነው" ደሳለኝ ኃይሉ ሲኒማውም እንደ ሌሎች የጥበብ ዘርፎች በኮቪድ-19 ሳቢያ ተጎድቷል። ፊልሞች በብዛት እየወጡ አይደለም። ሲኒማ ቤቶች ከተዘጉም ሰነባብተዋል። ካለፉት ዓመታት አንጻር በ2012 ዓ. ም የወጡት ፊልሞች ውስን እንደሆኑ የኢትዮጵያ ፊልም ሠሪዎች ማኅበር ፕሬዘዳንት ደሳለኝ ኃይሉ ይናገራል። "ፊቸር ፊልም ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ ተቋሞች ጋር የሚሠሩ ዘጋቢ ፊልሞችም ቆመዋል። ተዋንያን፣ አዘጋጆች፣ ፕሮዲውሰሮች ወዘተ. . . ሥራቸውን አቋርጠዋል። ስንቶች ቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቸዋል። ዘርፉ አሳዛኝ የኢኮኖሚ ድቀት ገጥሞታል። ባለሙያዎች ከዚህ ተርፈው ላይወጡም ይችላሉ።" አንዳንዶች ሥራቸውን በዩቲዩብ ቢለቁም ያን ያህል ገቢ ያስገኛል ብሎ ለመናገር አያስደፍርም። የፊልም ሠሪዎች ማኅበርና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ማኅበራት ከባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ጋር እንዴት ባለሙያዎች ማገገም ይችላሉ? በሚለው ዙርያ ተነጋግረው፤ እቅድ ቢነደፍም "እስከአሁን በተጨባጭ የአርቲስቱ ችግር ተፈቶ አላየንም" ይላል ደሳለኝ። "ለሆቴልና ቱሪዝም የገንዘብ ድጋፍ ሲሰጥ በሚያሳዝን ሁኔታ የባህልና ጥበብ ዘርፉ ተረስቷል። መድሏዊ ነው። ይሄ አርቲስቱን አስከፍቶታል፤ አማሮታል።" ስለ ኮቪድ-19 ግንዛቤ የሚሰጡ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች፣ የቴሌቭዥን እና የራድዮ ድራማዎች በነፃ ለሚያዘጋጁ ባለሙያዎች አንዳችም ድጋፍ አለመደረጉ እንደሚያሳዝን "ሕይወቱን አደጋ ውስጥ ከቶ በነፃ የሚሠራው የጥበብ ሰው ሆኖ ድጋፍ ያጣውም የጥበብ ሰው ነው" በማለት ይገልጻል። በቀጣይ ወራት ሲኒማ ቤቶች እና ቴአትር ቤቶች ተከፍተው፤ ባለሙያዎችና ታዳሚዎችም አካላዊ ርቀት ጠብቀው፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል አድርገው ሥራ የሚጀምሩበት መንገድ መመቻቸት እንዳለበት ደሳለኝ ይናገራል። "ማንም ስድስቱን ወር መቋቋም አልቻለም። አርቲስቱ የሚበላው እየተቸገረ ነው። ከዚህ በላይ መቆየት ስለማይቻል ከጤና ሚንስትር እና ከጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ጋር እየተነጋገርን ነው። ጥንቃቄ እየተደረገ ሥራ መጀመር አለበት።"
41627680
https://www.bbc.com/amharic/41627680
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ተለቀቀ።
የተዛባ መረጃን በማሰራጨትና ሕዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳት ተከሶ የ3 ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ቤት ወጥቷል፡፡ አርብ ዕለት የእስር ጊዜውን ጨርሶ እንደሚፈታ ሲጠበቅ የነበረው ተመስገን ደሳለኝ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እንደማይፈታ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ተነግሮት ለተጨማሪ ቀን እስር ቤት ቆይቷል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በአመክሮ ይፈታል ተብሎ ቢጠበቅም የተፈረደበትን የሦስት ዓመታት እስር አጠናቆ ነው የተፈታው። ተመስገን በማረሚያ ቤት ቆይታው በወገቡና በአንድ ጆሮው ላይ የጤና መታወክና ስቃይ አጋጥሞት እንደነበር ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። ባለፈው ዓመት ኅዳር ወር ማብቂያ ላይ ተመስገን በዝዋይ ማረሚያ ቤት ውስጥ እንደሌለ ለቤተሰቦቹ ተነግሯቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከቀናት ፍለጋ በኋላ ግን እዚያው ማረሚያ ቤት እንዳለ ታውቋል። ተመስገን በጋዜጣና በመፅሔት ባለቤትነትና ዋና አዘጋጅነት በቆየባቸው ጊዜያት መንግሥትን በሚተቹ ጽሁፎቹ ይታወቃል። በተደጋጋሚ ጊዜያት የህትመት ሥራዎቹ እንዲቋረጡ ተደርግዋል።
news-47863332
https://www.bbc.com/amharic/news-47863332
መሐመድ አዴሞ "የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ"
አቶ መሐመድ አደሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር ወደ ስልጣን እንደመጣ ቀድመው ወደ ሀገር ቤት ከገቡ የዳያስፖራ አባላት መካከል አንዱ ናቸው። ከዚያም በኋላ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ የክልሉን መገናኛ ብዙሃ ድርጅትን በኅላፊነት እንዲመሩ ኅላፊነት ሰጥቷቸዋል።
ይህ ግን ረጅም ጊዜ አልቆየም፤ ከኅላፊነታቸው መነሳታቸው ተሰማ። የአቶ መሐመድ ከስልጣን መነሳትን ተከትሎ በሌሎች ኅላፊነቶች ሊመደቡ እንደሚችል ሲወራ ከርሟል። እኛም ናይሮቢ በሚገኘው ቢሯችን በተገኙበት ወቅት በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ አጭር ቆይታ አድርገናል። ወደ ሀገር ቤት ሲመጡምን ጠብቀው ምን አገኙ? ከሀገር ርቆ ሲኖር ይላሉ አቶ መሐመድ "ሁሉንም ነገር በወሬ ነው የምትሰማው። ስለሀገርህ የምታየውና የምትሰማው ነገር የተለያየ ነው" በማለት ወደ ሀገራቸው ሲመጡ አእምሯቸውንም ልባቸውንም ከፍተው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለማየት መምጣታቸውን ያስረዳሉ። "ብዙ ለማውራት ሳይሆን ብዙ ለማድመጥ ወስኜ ነበር ጓዜን ጠቅልዬ ሀገር ቤት የገበሁት" ሲሉም ያጠናክሩታል። • "ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት አዲስ አበባ እግራቸው ሲረግጥ ይሰሙ ከነበረው ነገር በተቃራኒውን ማግኘታቸውን የሚናገሩት አቶ መሐመድ፤ ከዚህ በፊት የሚያውቋቸው ነገሮች በአጠቃላይ ተቀይረው በአዲስ መልክ፣ አዲስ ስሜት ተላብሰው እንዳገኟቸው አልሸሸጉም። "አዲስ አበባ የሚቀበለኝ ሰው ባይኖር ኖሮ፣ የት እንደምሄድ፣ የት እንደምገባ ማወቅ በጭራሽ አልችልም ነበር" ሲሉ በጊዜው የተፈጠረባቸውን አግራሞት አጋርተውናል። ይህ የለውጥ መንፈስ ግን መናገሻ ከተማዋን ብቻ ሳይሆን ክልሎችንም ያዳረሰ እንደነበር በተጓዙበት ሁሉ አስተውለዋል። "ብዙ ሰው ተስፋ ማድረግ ጀምሮ ነበር" ያሉት አቶ መሐመድ እርሳቸው አዲስ አበባ ሲደርሱ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር የጫጉላ ጊዜው አለማለቁን ያስታውሳሉ። በወቅቱም ዜጎች ደስተኛ ሆነው ከደስታቸው በላይ ደግሞ ብዙ ተስፋ ኖሯቸው ማየታቸው ልባቸውን ሳያሞቀው አልቀረም። ከደስታው ባሻገር በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አንደበትና ልብ ውስጥ አይተው የሚመሰክሩት ተስፋ ማድረግና ብሩህ ነገር የማሰብ ጅማሮንም አይዘነጉም። • የዓለማችን ሃብታም ሴቶች "ዜጎች ተስፋ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ትልቅ መነሳሳት ነበራቸው" በማለት የኢትዮጵያ ወጣት ለረጅም ጊዜ ያጣው ሁለት ነገሮችን እንደሆነ በማስረጃ አስደግፈው ያስረዳሉ። ቀዳሚው ተስፋ የሚሰጠው ሲሆን ተከታዩ ደግሞ ተስፋ ሰጥቶት ለተሻለ ነገር የሚያነሳሳው መሪ በማለት። "ወደ ሥራ፣ ወደ አንድነት የሚመራው ነበር የጠፋው። ይህ አሁንም አለ። ያኔ እኔ በመጣሁበት ወቅት ደግሞ ገና ትኩስ ስለነበር የሚደንቅ ጊዜ ነበር፤ ለእኔ። ከጠበኩት በላይ ነበር የሰዉ ነፃነት" ይላሉ አቶ መሐመድ። የመንግሥት ስልጣን አቶ መሐመድ ከተሰጣቸው ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክን የማስተዳደር ኅላፊነት በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ከተነሱ በኋላ አሁን እረፍት ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ። ከተሾሙበት ለምን እንደተነሱ ሲጠየቁም ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር ተነጋግረውና ተማምነው መሆኑን ይጠቅሳሉ። በርግጥ ኅላፊነቱ ሲሰጣቸው ሚዲያውን የሕዝብ ድምፅ ለማድረግ፣ ተሰሚነት እንዲኖረው ለማድረግ አልመው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ላለፉት አራት ዓመታት የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክን በቦርድ ሊቀመንበርነት ከመሩ ወዲህ ጥሩ ሥራ ተሰርቶ ነበር የሚሉት አቶ መሐመድ ያንን ለማስቀጠል ብርቱ ፍላጎት ነበራቸው። ብዙ ሥራም ሰርተናል ሲሉ በስልጣን ላይ የቆዩበት ጊዜ ማጠር ከውጤታማነት እንዳላናጠባቸው ይጠቅሳሉ። በምሳሌ ሲያስረዱም በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪዎች በክልሉ ውስጥ የሚሰራውን እና እየሆነ ያለውን በተሻለ መንገድ እንዲረዱ ለማድረግ፤ አሁን የአንድ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ የሆነውን ፕሮግራም ወደ ሦስት ሰዓት ለማሳደግ፤ ከዚያም ወደ ስድስት ሰዓት፤ በዓመት ውስጥ ደግሞም ራሱን የቻለ የሙሉ ቀን የቲቪ ፕሮግራም ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ሰርተናል" ይላሉ። ገዢው የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋውረው ቢሰሩ ከዚህ ቦታ የተሻለ ሊያበረክቱት የሚችሉት አስተዋፅኦ መኖሩን ጠቅሶ እንደነገራቸው የሚያስረዱት አቶ መሐመድ ቀጣይ መዳረሻቸው በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ስር በዲፕሎማትነት መሆኑን አልሸሸጉም። • በወሲብ ፊልሞች ሱሰኛ የሆኑ ወጣት ሴቶች የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርን በወጣት ኃይል የተደራጀ፣ ብዝኀነት በሚታይበት፣ ሙያው ያላቸውና ከዚህ በፊት ከሀገር ወጥተው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ልምድ ባላቸው ሰዎች የማዋቀር ሀሳብ ስላለ ነው ወደዚያ እንድዘዋወር የጠየቁኝ በማለት ከኃላፊነታቸው ፈልገወው ሳይሆን በፓርቲው ጥያቄ እንደተነሱ አቶ መሐመድ ይናገራሉ። "በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ዲፕሎማት ሆኜ እንድሰራ ፍላጎት አለ። ለዚያ ነው ከቦታው የቀየሩኝ። በርግጥ ስምምነት ላይ አልደረስንም። እኔ ጋዜጠኝነቱ ላይ የመቆየት ፍላጎት አለኝ። የእነርሱም መከራከሪያ ግን አሳማኝ ነው። የትምህርት ዝግጅቴም ለዚያ ይረዳኛል። ገና እየተነጋገርን ስለሆነ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል ስለዚህ በጊዜ ሂደት ማየት ይሻላል" ሲሉ ያለውን ሁኔታ ይገልፁታል። ከኅላፊነት ሲነሱ ተከዳሁ የሚል ስሜት ተሰምቷቸው እንደሆነ ተጠይቀው በጭራሽ ሲል መልሰዋል። "ኢትዮጵያ ሽግግር ላይ ናት። የሽግግር ወቅት ደግሞ ብዙ ችግሮች አሉበት" የሚሉት አቶ መሐመድ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በሚገባ መነጋገራቸውን ከእርሳቸውና በዙሪያቸው ካሉት አመራሮች ጋር ምንም ችግር እንደሌለ ያስረዳሉ። ከኋላ ያሉ ያሏቸው ግለሰቦች አንዳንድ ፍራቻዎች እንደነበሯቸው ነገር ግን ከኅላፊነት መነሳታቸውን አንደ ክህደት እንዳላዩት ያረጋግጣሉ። • የጠቅላይ ሚንስትሩን የአንድ ዓመት የስልጣን ዘመን እንዴት ይመዝኑታል? "እዚያ ብቆይ በጣም ደስተኛ ነበርኩ፤ እቅዶቼ ብዙ ነበሩ። ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያዊ የምፈልገው ዐብይ ሲሄድ የሚኖር ተቋም መገንባት ነው። አሁን የሚያስፈልገን ተቋም መገንባት ነው። እዚያ ላይ ደግሞ ግልፅ ውይይት አድርገን ስለተለያየን እንደመከዳትና እንደ ክፋትም አልቆጠርኩትም።" የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በአቶ መሐመድ አይን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ከቀጠናው አንፃር እንኳ ቢታዩ ከደረጃ በታች ነው የሚገኙት የሚሉት አቶ መሐመድ የመንግሥት ልሳን ሆኖ መኖሩንና ነፃ ሚዲያ ገንብቶ ለመስራትም መወዳደሪያ ሜዳው ምቹ እንዳልነበረ ይጠቅሳሉ። "ለግል መገናኛ ብዙሃንም ማስታወቂያ ማግኘት ፈተና ነው። ስለዚህ የግል ሚዲያው ቀጭጮ ነው ያለው" የሚሉት አቶ መሐመድ ዶ/ር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከአክቲቪስትነትና ከጋዜጠኝነት አንዱን መርጠው እንዲሰሩ በግልፅ ጥሪ ማቅረባቸው እስከዛሬ ከነበሩት መሪዎች በተለየ የመጀመሪያው መሪ ያደርጋቸዋል ሲሉ ይጠቅሳሉ። • የመደመር እሳቤ ከአንድ ዓመት በኋላ ከዚያም አልፎ ይላሉ የሕዝብ ሚዲያውን ጨምሮ ከመንግሥት ቁጥጥር ወጥቶ የሕዝብን ጥያቄ የሚያነሳ፣ የሕዝብ ልሳን ሆኖ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል በማለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር የታዩ በጎ ነገሮችን ይጠቅሳሉ። አስተዳደሩ የመገናኛ ብዙሃን በዚያ አቅጣጫ እንዲሄዱ እየሰራ እንደሆነ የሚያምኑት አቶ መሐመድ የሚዲያ ሕግ እየተረቀቀ መሆኑን፣ የሚዲያ ካውንስል ለማቋቋም መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ እንደቀረበለት በመጥቀስ ለውጡን ታሪካዊ ሲሉ ያሞካሻሉ። አቶ መሐመድ 'የእኔ ስጋት' የሚሉት ግን አላጡም። ስጋቴ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እየተጠቀምንበት ነወይ የሚል ነው? በማለት ራሳቸውን ከጠየቁ በኋላ "በተለይ በግል ሚዲያው አካባቢ" ሲሉ ለጥያቄያቸው አፅንኦት ይሰጣሉ። የመንግሥት ሚዲያ አካባቢ ያለው ችግር ለውጥና ቀጣይነት መካከል ያለ ነው የሚሉት አቶ መሐመድ "ነገሮችን ለመቀየር ጊዜ ይወስዳል። በዚያ ውስጥ ሰዎች ምን ያህል ተቺ ዘገባ ማቅረብ እንደሚችሉ? ምን ያህል በነፃነት መስራት እንደሚችሉ፤ ስርአቱን እየፈተሹ እየሄዱ ይመስለኛል" ሲሉ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ላይ ያላቸውን ግምገማ ያቀርባሉ። "የግሉ ሚዲያ ላይ ግን ይህ የነፃነት አየር ሲከፈት ሁሉም ሰው አንድ ጥግ ይዞ በወሬ፣ በሐሰተኛ ዘገባ ሕዝቡን ጠርዝ እንዲረግጥ እያደረገው ይመስለኛል" ሲሉ ይተቻሉ። • ሕዝብ ስለመሪው ምን እንደሚያስብ እንዴት እንወቅ? አቶ መሐመድ የእነዚህ የግል የመገናኛ ብዙሃን ተግባር ላይ ያላቸውን ስጋት ሲያቀርቡም "ወደ መንግሥት ቁጥጥር እንዳይመልሰን" ይላሉ። አክለውም የግል መገናኛ ብዙሃን ራሳቸውን ቢፈትሹ ተገቢ መሆኑን ያሰምሩበታል። በተለይ ደግሞ ይላሉ አቶ መሐመድ "የመገናኛ ብዙሃን ራስን ሳንሱር ማድረግ ሳይሆን የአቻ ግምገማ ወይም ራስን መፈተሽ ያስፈልጋቸዋል። ጥግ ሳይረግጡ፣ መረጃና እውነታ ላይ ተመስርተው ቢሰሩ መልካም ነው። ከአስተያየት (opinion) ሰጪ ጋዜጠኝነት መውጣት ያስፈልጋል" ሲሉም ይመክራሉ። ማንም ሰው አንድ ነገር መቃወም ከፈለገ ጋዜጣ ከፍቶ፣ የፓርቲ ወይም የአንድ አስተሳሰብ አልያም የብሔር ጥግ ይዞ እርስ በእርስ ከመነቋቆር ይልቅ በመደማመጥ መነጋገርና መወያየት ያስፈልጋል ይላሉ አቶ መሐመድ። እንደሚዲያ ሰዎች ቁጭ ብሎ መነጋገርን፣ መወያየትን የሚመክሩት አቶ መሐመድ "መንግሥትን ወደ አንድ ጥግ ከገፋነው ጨቋኝ እየሆነ እንዳይሄድ ስጋት አለኝ" በማለት የመገናኛ ብዙሃን ፎረም ወይም ካውንስል ቢፈጠር ከመንግሥት ቁጥጥር ራስን በራስ መፈተሹ እንደሚሻል ይመክራሉ። ሌላው መገናኛ ብዙሃኑ ላይ ያይዋቸውን ህፀፆችንም ሲዘረዝሩ "አሁን ያለው ችግር የልሂቃኑ ችግር ነው። ልሂቃኑ በጋራ መግባባት ሳይችሉ ነው የቀሩት። ይህንን ወደ ህዝቡ እያመጣነው ይመስለኛል" በማለት እዚህ ላይ ማህባራዊ ሚዲያውም ድርሻ አለው ሲሉ ይገልፃሉ። ወደ ቀድሞው መመለስ ቀላል ነው የሚሉት አቶ መሐመድ "አሉባልታ፣ ሹክሹክታ፣ ወሬ ላይ የተመሰረተን ዘገባ እየሰሩ መተማመንን ከማጥፋት እና ሀገራችንን ከምናጠፋ ሙያዊ ሥነ ምግባሩን የጠበቀ ጋዜጠኝነት በመተግበር የሚያግባቡንን ነገሮች ፈልገን እርሱ ላይ ካተኮርን ወደፊት መሄድ እንችላለን" ሲሉ ይመክራሉ።
49297780
https://www.bbc.com/amharic/49297780
"የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ
ክራር አናጋሪው ሙዚቀኛና የአካባቢ ተቆርቋሪው ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) ለ17ኛው የኢትዮጵያ ባሕልና ስፖርት ፌስቲቫል ስዊዘርላንድ ዙሪክ በተገኘበት ሰሞን ክሎተን በተባለ ቀበሌ፣ አንድ የሕዝብ መናፈሻ ውስጥ አግኝተነው ዘለግ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገናል። በአመዛኙ ያወጋነው ከሙዚቃ ይልቅ በወቅታዊ አገራዊ፣ ፖለቲካዊና ከተማዊ ጉዳዮች ላይ ነበር ማለት ይቻላል። ዙሪክ ብዙ ችግኝ ተተክሏል መሰለኝ.. ፣ እንደምታየው ዙሪያ ገባው ሁሉ አረንጓዴ ነው...(ሳቅ)
[እውነትህን ነው] አራት ቢሊየኑ እዚህ የተተከለ ነው'ኮ የሚመስለው (ሳቅ) •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ይሄን ይሄን አይተህ ቁጭት አንገብግቦህ ነበር እንዴ ያኔ ጠቅልለህ ወደ አገር ቤት ገብተህ አገሩን በዘመቻ ያመስከው? አዲስ አበባን ጄኔቭ የምታደርግ መስሎህ ነበር? (ሳቅ) እም...ይሄን አይቼ ሳይሆን በፊት ልጅ በነበርንበት ጊዜ፤ ከዚያ በፊት በአያት በቅድም አያቶቻችን ጊዜ ኢትዮጵያ 60 እና 65 እጅ ያህል ደን የነበረበት አገር ነበር [የነበረን]። ለም የሆነ አገር። ከዚያ በኋላ የተለያዩ ሥርዓቶች ያንን ሊያስጠብቁ አልቻሉም። የሕዝቡ ቁጥር እየጨመረ መጣ፤ ልቅ የሆነ ሥርዓት ተከተለ። ከሥርዓቱ የሚመጡ አስከፊ ሁኔታዎች ድርቅ አስከተሉ። የአየር ንብረቱ ተዛባ። ሕዝቡም ደኑን መጠቀሚያ አደረገው... ላቋርጥህ ጋሽ አበራ...ከኋላህ አንድ ወጣት ውሻው መንገድ ላይ ስለተጸዳዳ እሱን ጎንበስ ብሎ እያጸዳ ነው፤ እንደምታየው በእጁ የላስቲክ ጓንት አጥልቆ...ይህን አጋጣሚ አልለፈው ብዬ ነው። የት እንደሚጥለው እንመልከት...(ጋሽ አበራ ፊቱን አዙሮ መታዘብ ጀመረ)፣ እንዳየኽው በቅርብ ርቀት መጣያ አለ። በስተቀኝህ ደግሞ የሕዝብ መጸዳጃ አለ። እዚህ አጠገባችን እጅግ ያማረ ሌላ ቆሻሻ መጣያ ይታያል...። አንተ እነዚህን ነገሮች በአገር ቤት ለመሥራት በተወሰነ ደረጃ ሞክረህ ነበረ። የገነባኻቸው ሽንት ቤቶች ፈርሰዋል። መናፈሻዎችህ የቆሻሻ መጣያ ሆነዋል? ለመሆኑ ራስ መኮንን ድልድይ ስትሄድ ምንድነው የሚሰማህ? መሸነፍ? ተስፋ መቁረጥ? አይ ተስፋ አልቆርጥም ግን ለምን ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ። የምታገኘው ምላሽ ምንድነው? መጀመርያ አካባቢ ለምን እንደዚህ ሆነ? ምንድነው ችግሩ እያልኩ እብሰለሰል ነበር። ግን መጨረሻ ላይ ያገኘሁት መልስ ምንድነው፣ አንደኛ ባህሪያችንን መለወጥ አልቻልንም፤ በዕውቀት ማደግን አላወቅንበትም። ለአንድ አገር ሥርዓት ወሳኝ ነው። መልካም ሥርዓት ለአንድ ከተማ ምን እንደሚያስፈልግ [ጠንቅቆ ይገነዘባል]። አሁን ተመልከት...መንገዱን ያየኸው እንደሆነ፣ መሻገሪያውን ያየኸው እንደሆነ፣ ምልክቶችን ያየኸው እንደሆነ [እያንዳንዷ ነገር ታስባ የተሠራች ናት]። • ተነግረው ያላበቁት የ'ጄል' ኦጋዴን የሰቆቃ ታሪኮች ተመልከት ይሄን ቆሻሻ መጣያ...ተመልከተው በደንብ... ሲጋራ መተርኮሻ ሁሉ አለው [በቅርብ ርቀት የተተከለ የቆሻሻ መጣያን እያመላከተ]። በዚህ ደረጃ ታስቦበት ነው የሚሠራው። ይሄን አግዳሚ የሕዝብ መቀመጫን ተመልከተው። ይሄን የእግረኛ መንገድ እይ፣ እዛ ጋ ተመልከት የሆነ በዓል አለ..ድንኳን ተክለዋል...ተመልከት ሕጻናት ሲቦርቁ ወዲያ ደ'ሞ...እያንዳንዱ ነገር ታስቦበት ነው። ሁሉ ነገር በሕግ፣ በደንብና በሥርዓት ነው ያለው። ለምን ይሄ ሆነ ብለህ ጠይቅ። የሥርዓቱ ችግር ነው እያልክ ነው? እንግዲህ ምንድነው፤ የሰለጠነ አስተሳሰብ ያስፈልጋል። አንድ ባለሥልጣን ስንል ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣኑን ከያዘ በኋላ የእሱ ምቾትና ሥልጣኑን ማስቀጠል እንጂ [ሌላው አያሳስበውም።] ሥልጣን የሚለው ቃል ሥልጣኔ ማለት ነው። አንድ ባለሥልጣን እዚህ ቁጭ በል ሲባል ስለሠለጠንክ ሥልጣኔህን ተጠቅመህ ሕዝብ አስተዳድር እንደማለት ነው። እሱ ግን የሚመስለው በቃ ገዢ ሆኖ፣ የበላይ ሆኖ፣ አዛዥ ሆኖ፣ ቁጭ ብሎ፣ መኪና ነድቶ፣ ቁርጥ በልቶ፣ ውስኪ ጠጥቶ መኖር ነው። ሥልጣን ይዘው የተቀመጡ ሰዎች የሥልጣኔ ባህሪውም የላቸውም። ካልሠለጠነ አእምሮ ሥልጡን የሆነ ሥርዓትን እንዴት ትጠብቃለህ? የቅድሙን ጥያቄ መልሼ ላምጣው። ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ ስትሄድ አበቦቹ ደርቀው፣ ችግኞቹ ከስመው፣ አረንጓዴ ያደረከው ቦታ የቆሻሻ ቁልል ሆኖ ስታይ ምን ይሰማኻል? ዕድሜህን ያባከንክ አይመስልህም? ነገርኩህ እኮ ያን ያደረጉ ሰዎች አልሠለጠኑም፤ ከአፍንጫቸው አርቀው አያስቡም። ለእኔ አይደለም መታዘን ያለበት፤ ለእነሱ ነው እኔ የማዝነው። እነዚህን ሰዎች እንዴት ማሠልጠን ይቻላል? ነው ጥያቄው። በአጠቃላይ ሕዝቡን ሳይሆን ሥርዓቶች ናቸው። አንድ ሥርዓት ወድቆ ሌላ ሥርዓት ሲመጣ የተሻለ ነገር ይዞ ከመምጣት ይልቅ በድንቁርና ላይ የተመሠረተ አመራር ነው [የሚከተለው]... ሕግን፣ ደንብን፣ ሥርዓትን ተከትሎ የሚሠራ አስተዳደር ነው የሚያሻው። በመሀል የሆነ ጊዜ ላይ ጨርሶኑ ጠፍተህ ነበር።በሥርዓቱ አኩርፈህ ነበር ልበል? "ጋሽ አበራ ሞላ ጋሽ አበራ ሞላ፤ አበደ ይሉኻል ጉዳይህ ሳይሞላ..." የምትለው ነገር ባንተም የደረሰች ይመስልኻል...? እንደዚያ አይደለም። ሁኔታውን ታየውና ዘዴህን ትቀይራለህ። መንግሥት በዚህ ነገር ካልተሳተፈ እንዴት ግለሰቦችን ታሳትፋለህ? ባለሀብቱን እንዴት ታሳትፋለህ? ተማሪዎች ስለጽዳት እንዴት ግንዛቤያቸው ሊያድግ ይችላል እያልክ ታስባለህ። ዘዴ ለውጠህ ትሠራለህ። ተስፋ ቆርጬ የተቀመጥኩበት ጊዜ አልነበረም። ቅድም እንዳነሳኸው የደከምንባቸውን ቦታዎች ቆሻሻ መጣያ ሆነዋል። መሬቱን ለመሸጥ፣ ለሆነ ካድሬ ለማስተላለፍ፣ ወይም ደግሞ እከሌ ሠራው የተባለ እንደሆነ መንግሥትን አሳጣ ከሚል መጥፎ ሐሳብ የመነጨ ስለነበረ እኛ በየጊዜው ዘዴያችንን እየለወጥን ቆይተናል። ለዚያም ነው ብዙ እውቅና ያገኘነው። • የወንድሙን ገዳይ ለመበቀል ወደ ፈጠራ ሥራ የገባው ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝ ፓርላማ ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛ ወጥቼ ግሪን ጎልድ አዎርድ አግኝቻለሁ። ከዚያም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሽልማትን አገኘን። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቀመጫ ከአዲስ አበባ መነሳት አለበት። አዲስ አበባ ቆሻሻ ናት፤ ተስቦ፣ ማሌሪያ፣ ኮሌራ፣ ታይፈስ፣ ታይፎይድ ከጽዳት ማነስ የሚመጡ በሽታዎች ስላሉ የአፍሪካ ከተማ ከዚህ ተነስቶ ትሪፖሊ መሆን አለበት ብለው እነ ጋዳፊ ዘመቻ በከፈቱበት ሰዓት ነው እንግዲህ ያን ያህል እየታገልን የነበረው። እንዳልኩህ ግፊያው አለ፤ ምቀኝነቱ አለ፤ ሥርዓቱ ተጨመላልቋል። ያም ሆኖ ተስፋ አልቆረጥንም። ከተማውን ያስተዳደሩ የነበሩ ሰዎች ላይ ቅሬታ ያለህ ይመስላል። የከተማው አስተዳዳሪዎች በጣም በሚገርም ሁኔታ ለየት ያሉና ዕውቀቱ የሌላቸው፣ ከተማን የማስተዳደር ባህሪ ጨርሶውኑ ያልነበራቸው ነበሩ። እነሱ ሲመጡ የሠራነው ሁሉ እየፈራረሰ መታየት ጀመረ። አርቆ አለማሰብ አለ፤ ትንሽ ነበር አስተሳሰባቸው፤ መኪና፣ ልብስ፣ አጊጦ መታየት ከዚህ ያልራቀ ዓይነት አመለካከት እያለ ይሄ ይሄ ነው እንግዲህ ችግሮችን ይዞ የቆየው። ይሄ የሰሞኑ ችግኝ ተከላ፤ በችግኝ ቁጥር ክብረ ወሰን መሰበሩ ወዘተ ሰሞነኛ ሆይሆይታ ሆኖ ነው የሚሰማህ ወይስ? አነሳሱ ጥሩ ነው፤ ቀጥሎ ምን ይሆናል የሚለው ነው የሚያሳስበኝ። በእርግጥ 4 ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል ወይ የሚለው አንድ ትልቅ ጥያቄ ነው። 4 ቢሊዮን ችግኝ ሁለት ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሐሳብ ታስቦ ተተከለ ለማለት ያስቸግራል። • ለ20 ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም በዚህ ላይ እኛ ልምዱ አለን፤ ብዙ ተክለናል፤ አገሩን ማስተባበር ችለናል። ይሄን በተለያየ ጊዜ ለመንግሥት ሰዎች እንነግራቸዋለን። ነገር ግን የመስማትና የመቀበል ሁኔታቸው ዝቅተኛ ነው። እንኳን አብሮ ለመሥራትና ዕውቅና ሊሰጡህም ፍቃደኛ አይደሉም። ሕዝቡ ምንድነው የሚለው "ይሄንን ነገር የጀመርከው አንተ አይደለህም ወይ?" ይላል። ይሄ ሁሉ እየሆነ በማማከር ደረጃ እንኳ አብረን እንሥራ የሚልህ የለም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አካባቢ እንድታማክር ወይ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ አልቀረበልህም? ቅሬታ ያለህ ይመስላል። አንድ መንግሥት ሲመጣ አማካሪ ሆነው አብረው መሥራት የሚፈልጉን ሰዎችን ያየኻቸው እንደሆነ...አሁን አንዱ ትልቁ ቅሬታዬ ትናንትና የነበሩ ሰዎች ናቸው ዛሬ ያሉት። ትናንትና በተለያየ ቦታ ላይ ሲያስቸግሩኝ የነበሩ ሰዎች ዛሬም አሉ፤ ትናንት ቀይ ኮት ለብሰው ነበር፤ ዛሬ አረንጓዴ ኮት ለብሰው ቁጭ ብለዋል። ከእነኚህ ሰዎች ምንድነው የምጠብቀው? በአርቱ አካባቢም ብታይ ትናንትና ሆይ ሆይ ሲሉ የነበሩ ዛሬ 'ቅኝት ቀይረው' ምናምን ብለው እያዜሙ ነው። እና ይሄ 'ህልም ነው ቅዠት ነው?' ምናምን ትላለህ። ዕውቅና ስላልተሰጠህ ቅሬታ ያለህ ይመስላል። ምንድነው መንግሥት እኔን "ሪኮግናይዝ ባለማድረጉ" [ዕውቅና ባለመሥጠቱ] እኔ ምንም እንትን አይሰማኝም። እኔን 'ሪኮግናይዝ' ባለማድረጉ የራሱን ሥራ 'ሪከግናይዝ' እንዳይደረግ አድርጎት ይሆናል እንጂ እኔን ምንም እንትን ያለኝ ነገር የለም። የጋሽ አበራ ሞላን ሥራ ሰዉ ቀርቶ ጅቡም ያውቃል። መንግሥት ዕውቅና ሰጠኝ አልሰጠኝ ብዬ አልልም። ምን እያሰብክ ነው በቀጣይነት? ከጥቂት ወራት በኋላ ትልቅ ፕሮጀክት ይኖረናል። ሲቪል ሶሳይቲ ይኖረናል። እኛ ከወጣቱ ጋር ከሰሜን፣ ደቡብ፣ ምሥራቅ፣ ምዕራብ ጥሩ ግንኙነት አለን። ለእኛ ቅን አስተሳሰብ አላቸው። በብሔር በጎሳ የተጠረነፉ ሳይሆኑ ይህቺን አገር ትልቅ ለማድረግ ቁጭቱ ያላቸው ብዙ ጉልበት ያላቸው ሰዎች አሉ። ስለዚህ ምንድነው ፕሮጀክትህ ማለት ነው? ሲቪል ሶሳይቲ [መመሥረት] ነው የሚሆነው። አገሪቱ እንዲህ የሆነችው ለምንድነው ያልክ እንደሆነ ኢህአዴግ አንድ ፓርቲ ነው። አጣኙም፣ ቀዳሹም፣ ቄሱም ዘማሪውም እሱ ነው። ኢህአዴግ እንዲህ አደረገ ተብሎ ለሰው ይነገረዋል እንጂ ሰው ይህ ይደረግ አይልም። በዚህ በኩል መንገድ ይውጣ ከተባለ፣ ሰው ተማክሮ ነው እንጂ ማዘጋጃ ቤት ስለፈለገ መሆን የለበትም። የሕዝብ ተሳትፎ መቅደም አለበት። ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ይሄ የለም። የሕዝብ ተሳትፎን ካነሳህ አይቀር አሁን ይሄ ማዘጋጃ ቤት አጠገብ ያለው ሜዳ መጀመርያሜድሮክ ፎቅ ሊሠራበት ነበር። አሁን ደግሞ አድዋ ፓርክ ሊደረግ ነው፤ መልካም ተነሳሽነት ቢሆንም ቅሉ ከዲዛይኑ ጀምሮ የሕዝብ ተሳትፎ አያሻውም ወይ? የከተማ ፈርጥ የሚሆን ነገር እንዲሁ ማዘጋጃው ስለፈለገ... እሱን ነው የምልህ። አንተ ያልከው ነገር ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ከተማው ውስጥ ያሉ ግንባታዎች። አምጥቶ እብድ የሚያህል ፎቅ ይገደግድብኻል። ለእግረኛ ማለፊያ የለው፤ መኪና ማቆምያ የለው፤ አረንጓዴ ቦታ የለው...የዛሬ 40 እና 50 ዓመት ያለው ሕዝብ አይደለም አሁን ያለው። ክፍት ቦታ የለም። ፎቅ መገጥገጥ ነው...ያስጨንቅሃል። ይሄው ተመልከት (አንዲት ሴት ልጇን በተንቀሳቃሽ አንቀልባ እየገፋች ታልፋለች) ይቺ ሴትዮ ጋሪውን ከእግረኛው ጥርጊያ ለማውረድ ትንሽዬ (ራምፕ) ተሠርቶላታል። ተመልከት እንግዲህ...ይቺ ሁሉ ሳትቀር ታስባ ነው። • የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት የፓርላማውን ውሳኔ ተቃወመ ይኸን ተወው...ይቅር። አሁን አንዱ ተነስቶ ሕንጻ ሲሠራ ባለቤቱ ይመጣና ጠጠሩን አሸዋውን ይደፋል፤ ትራኩ ምኑ.. ትርምስ ነው፤ የእግረኛ ማለፊያ የለ፣ ምን የለ፣ ፎቅ ብቻ...ሕግ ደንብና ሥነ ሥርዓት ያለው አገር አይመስልም። እኛ ጋር ዝም ተብሎ ነው የሚሠራው። ቀበሌው ምን ይሠራል? ክፍለ ከተማው ምን ይሠራል? ከተማውን አስተዳድራለሁ የሚለው አካል የት ነው ያለው? ግራ ነው የሚገባህ። አረንጓዴ የነበረው ቦታ ቆሻሻ መጣያ ሲሆን፣ አገር ጉድ ሲል፣ እዚያ የአረንጓዴ ልማት ቢሮ የተቀመጠው ሰው ቁጭ ብሎ ያያል። ስለዚህ ምን ማለቴ ነው፣ ሕዝቡ ይሄ ያንተ ከተማ ተብሎ ድርሻ እየተሰጠው እየተሳተፈበት፣ የእኔ ነው እያለ ሲሆን ነው ነገሩ መልክ የሚይዘው። እስካሁን ስናወራ የተረዳሁት በአገሪቱ ብቁ አመራር እንደሌለና ይህም ያሳሰበህ ይመስላል። አንተ ከዚህ በፊት ሕዝብን ማንቀሳቀስ ችለሃል። ተምሳሌት መሆንም ችለሃል። አንዳች ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ፍላጎት አይብሃለው። ለምን ለከንቲባነት አትወዳደርም? ምንድነው ችግሩ? ትፈራለህ ፖለቲካ? አይ አይ እኔ እንኳን ይሄ ሥልጣን ምናምን አይሆነኝም። ግን እኮ ለውጥ ለማምጣት የምር የምትሻ ከሆነ... አይ...!አይ..! አይሆንም። አንደኛ እኔ እንደዛ ዓይነት ነገር አልወደውም፤ መሆንም አልፈልግም። ቢሮ ውስጥ ተቀምጬ የወረቀት ሥራ ምናምን ለዚያ የምሆን አይደለሁም። ምን መሰለህ? ሐሳቦች አሉ። ሐሳቦችን ማፍለቅ ነው ዋናው። ከሁሉም በላይ የሚልቀው ሐሳብ ነው። ሐሳብህን ወደ ዲዛይን የሚለውጥ አለ። ዲዛይኑን ወደ ተግባር የሚለውጥ አለ። ለዚህ ነው ቅድም ሲቪል ማኅበረሰብ መኖር አለበት ያልኩህ። • "እራት ለመመገብ አይደለም የምንሄደው" በላይነህ ክንዴ በአንድ አገር የሲቪል ማኅበረሰብ ከሌለ ማንኛውም ነገር ሊሠራ አይችልም። መንግሥት አጣኙም እሱ፣ ቀዳሹም እሱ፣ ሰጪውም እሱ፣ ነሺውም እሱ፣ ተጠያቂውም እሱ ይሆናል። በአዲሱ አስተዳደር እነዚህ ሁሉ ነገሮች መልክ መያዝ አለባቸው ነው እያልኩህ ያለሁት። ለዚህ ነው የሲቪል ማኅበረሰብ የሚያስፈልገው። ባለፈው የኢህአዴግ ጊዜ የሲቪል ማኅበረሰብ ለማቋቋም ብለን እነ ብርሃኑ ነጋ፤ ክቡር ገና አንድ አራት አምስት የምንሆን ሰዎች በጋሽ አበራ ሞላ ተነሳሽነት ከተማዋን ለማጽዳት፤ ለማልማት ሲቪል ሶሳይቲ ብንመሰርት ገንዘብ ይዋጣል፤ በእውቀት መንግሥትን ያግዛል ብለን አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ውስጥ ትልቅ ስብሰባ ተደረገ። ማታውኑ...! ማታውኑ መለስ ዜናዊ ጠርቷቸው "እናንተ ምንድናችሁና ነው [እኔን አልጠራኝም] ምን አግብቷችሁና ነው ሲቪል ሶሳይቲ ብላችሁ እንደዚህ የምትሰባሰቡት? ሕዝብ ልታሳምጹ ነው?" ተብለው እነኛን ሰዎች ማታውኑ አስፈራርተው ሰደዷቸው። አንተ ለምን አልተጠራህም? እኔ ስብሰባ ውስጥ ተጠራሁ። እሱ ያመጣው ሐሳብ ትልቅ ሐሳብ ነው። በአንድ ግለሰብ የመጣ ሐሳብ አገር ለውጧል። ይሄ ሁሉ ኅብረተሰብ ደግሞ ቢሳተፍበት ምን ያህል ለውጥ ሊመጣ ይችላል በሚል... ስለዚህ የሲቪል ማኅበረሰብ የሆነ አካል ሲኖር የበለጠ ብዙ ነገር ሊሠራ ይችላል። ይሄንን እናዳብረው ነው እንግዲህ። ዲያስፖራው ይመጣል። ዕውቀት ያለው ይመጣል፤ ጉልበት ያለው ይመጣል፤ እነዚህ እነዚህ በሙሉ ታሰባስብና ለውጥ የሚመጣበትን ሁኔታ ታመቻቻለህ። እና የዚያን ጊዜ እንደዚያ ሆኖ [ከሸፈ]። አሁንም መታወቅ ያለበት ሕዝብ ተዋናይ እንጂ ተመልካች መሆን የለበትም። አንተ አብዝተህ በእግር ስለምትንቀሳቀስአሁን መገናኛና ሜክሲኮ አካባቢ ስትሄድ ምንድነው የሚሰማህ? [ምን አ'ርግ ነው የምትለኝ? በሚል ስሜት በረዥሙ ተነፈሰ]...ምን እኮ... ያው እንደምታየው ነው። መገናኛና ሜክሲኮ ብቻ ሳይሆን የትስ ቦታ ብትሄድ...! ጉድ ነው እኮ! የሕዝቡ ብዛት፣ ውጥንቅጡ...ትርምሱ...ቅድም እኮ አወራን...። እዚህ ተመልከት፤ እያንዳንዱ ነገር እኮ በቀመር ነው የተሠራው፤ በአጋጣሚ አይደለም። አገሩ በሙሉ ነቅሎ ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምሥራቅ፣ ከምዕራብ፣ ገበሬው፣ ወጣቱ፣ እናቱ፣ ምኑ ምኑ ሳይቀር በየቀኑ ይገባል ወደ አዲስ አበባ። እኔ የሚገርመኝ እነዚህ በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በዚህ እየተጋፉ ነው የሚሄዱት፤ ግን መኪና ውስጥ ናቸው። መኪና ውስጥ ቢሆኑ አሁን የከተማው አስተዳዳሪዎች ይሄን ሁሉ ትርምስ ሲያዩ ምንድነው የሚሰማቸው? እላለሁ። እኔ እውነት ለመናገር አንድ እግዚአብሔር የነሳን አንድ የሆነ ነገር አለ? እንዳናይ ያደረገን? • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች እንጂ ዓለም እዚህ በደረሰበት ሰዓት እኛ እንዲህ ትርምስምስ ባለ ጎሳዊ፣ ጎጣዊ፣ ግላዊ አመለካከት ውስጥ እንሆን ነበር? ምን ለማለት ፈልጌ ነው...መንገዱ ላይ ስትሄድ የለማኙ ብዛት ቁጥር ስፍር የለውም። አልፎ ተርፎ ልጅ እየወለዱ መንገድ ላይ ሺህ የሚሆኑ አራሶች ግራና ቀኝ ተደርድረው ይታያሉ። ሽማግሌዎች ሲለምኑ ታያለህ። ቅድም እንዳልከው መገናኛና ሜክሲኮ ስትሄድ ከሆነ ፕላኔት ላይ የወረድን ሰዎች እንጂ የምንመስለው እውነት በምጣኔ ላይ ተመሥርተን ተወልደን በሥርዓት አድገን ለመኖር የመጣን ሰዎች አንመስልም። የሳልቫጁ እቃ ራሱ አብሮ ከሰማይ የወረደ ነው የሚመስለው፤ ሻጩም አብሮ የወረደ ይመስላል፤ ገዢውም አብሮ የወረደ ይመስላል። ዱብ ዱብ ብለው የወረዱ ነው የሚመስለው። ማታ ደግሞ ስታያቸው የሉም። ከሌላ ስፔስ የመጡ እኛን የሚመስሉ ሰዎች ናቸው ወይስ? ትርምሱ እየገረመኝ እተክዛለሁ። እና እኔ'ንጃ...ደንብ፣ ሕግ ሥርዓት ያለን ሕዝቦች አንመስልም ብቻ... እንደምታየው እንዲህ እያወጋን አዛውንቶች፣ ሕጻናት እዚህ መናፈሻ ላይ ደስ የሚል ጊዜ እያሳለፉ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ አረጋዊያን የት ይሂዱ፤ ሕጻናት የት ይጫወቱ? አረጋዊያኑ ቤት ይዋሉ፤ ሕጻናቱም ቤት ነው የሚቀመጡት፤ ምናልባት ለወደፊት ቤቱ ሲሞላ ጣሪያም ላይ ሊቀመጡ ይችላሉ (በምጸት ዓይነት)። ምክንያቱም ቦታ የሚባል ነገር የለማ። ቅድም እንዳልኩህ ነው። በየቦታው [የበሬ ግንባር] በምታህል ቦታ እንኳ ስትገኝ ፎቅ ነው። መሬትን መሸጥ ነው የተያዘው። በተሸጡ መሬቶች መሀል እንኳ ምናለ እንደው 50 ካሬ እንኳ ለአዛውንት ለሕጻናት ተብሎ ቢተው። አሁን እንደዚህ ከሆንን ከዚህም በላይ ቁጥራችን እየበዛ በሚሄድ ጊዜ ምን ልንሆን ነው ብዬ አስባለሁ። የወንዝ ዳር ልማቱ ተሳክቶ አንተ በእነዚያ መናፈሻዎች የእግር ጉዞ የምታደርግ ይመስልሃል? ቢሊዮን ችግኞች ጸድቀው በሕይወትህ የምታያቸው ይመስልሃል? አሁን ያልናቸው ነገሮች የሚሳኩ ከሆነ፤ ሕዝቡን የምታሳትፍ ከሆነ ለምን አይሆንም? አሁን በዚህ በወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት አለሁበት። የአካባቢዎቹን ታሪኮች የጻፍኩት እኔ ነኝ። እንጦጦ ምንድነው? አፍንጮ በር ምንድነው? 6ኪሎ፣ ቃሊቲ፣ አቃቂ የሚሄደው ይሄ ሁሉ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት በአካባቢው ስም፣ በአካባቢው ምሳሌ፣ በአካባቢው ተረት፣ ያንን ወዙን፣ ያንን ለዛውን፣ ያንን ማዕረጉን፣ ያንን ታሪኩን፣ ዘይቤውን፣ እንቆቅልሹን ይዞ የሚሄድ እንዲሆን በሚያስችል መንገድ ነው የጻፍኩት። • ችግኝን በዘመቻ መትከል መቼ ተጀመረ? ጠቅላይ ሚኒስትሩም ደስ ብሏቸው ተጀምሯል። ትልቅ ፕሮጀክት ነው። የጨርቆስም ትልቅ ፕሮጀክት ነው። እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሩ ህልም አላቸው። ግን እዚህ ላይ የሚያማክሩ አብረው የሚሠሩ ሰዎችን ቅድም እንዳልኩህ ሲቪል ማኅበራት ያስፈልጋሉ። ወጣቱ አዛውንቱ ሁሉ መሳተፍ ይኖርበታል። ችግኙም እንደዚሁ። ዝም ብሎ ይሄንን ያህል ተተከለ ለማለት ሳይሆን ችግኝ ስትተክል አእምሮ ውስጥ ነው መጀመርያ የምትተክለው። እኔ እንደሚመስለኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ 4 ቢሊዮን ችግኝ ሲል የሕዝብ አእምሮ ላይ ለመትከል ያሰበው እቅድ ነው የሚመስለኝ። እንጂ ዝም ብሎ የችግኝ ቁጥር አይመስለኝም። የአረንጓዴነት ስሜቱንና አስተሳሰቡን ሰው አእምሮ ውስጥ ለመትከል ያሰበ ነው የሚመስለኝ። እስኪ ጋሽ አበራ አሁን ደግሞ በአጫጭር ጥያቄዎች እረፍት እናድርግ። ለመጨረሻ ጊዜ ሱፍ የለበስከው መቼ ነው? ለብሼ አላውቅም እኔ። አንድ ቀን ብቻ ኦፕራህ ዊንፍሬይ የመጣች ቀን ልበስ ተብዬ ለበስኩ። ከዚያ ሰዎች ሲፈልጉኝ አጡኝ። እኔኮ አጠገባቸው ተቀምጫለሁ። ለካስ እነሱ በሱፍ አያውቁኝም። (ሳቅ) መኪና አለህ ጋሽ አበራ ሞላ? መኪና ይኖራል ግን... ምንድነው አቅም ማነስ ነው? ሕዝቡ ማዋጣት ካለበትም ይነገረው... (ሳቅ) አይ እኔ መኪና የሌለኝ ስለምቸኩል ነው። በቀን ውስጥ ምን ያህል ኪሎ ሜትር በእግር ትጓዛለህ፣ በአማካይ? ለምሳሌ አያት አካባቢ ነው ሰፈሬ። እንግዲህ ቦሌ መሄድ ካለብኝ ጠዋት እነሳለሁ፤ አንድ 15 ወይ 20 ኪሎ ሜትር በየቀኑ? ሥጋ ...ቁርጥ እንደዚህ ነገር ትበላለህ? ሥጋ እበላለሁ ግን እስከዚህም ሥጋ በላተኛ አይደለሁም። አልፎ አልፎ ከሰዎች ጋር ካልሆነ...ብዙም... ታዲያ የምታዘወትረው ምግብ ምንድነው? እኔ ከምግብና ከገንዘብ ጋር ብዙም ግንኙነት የለኝም። ብዙ ጊዜ እስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን ፊትለፊት ካፌ ቁጭ ብለህ እመለከትሃለሁ፤ ጥሞና ታበዛለህ። ምንድነው የሕይወት ፍልስፍናህ? ያው እንግዲህ እኔ ምድር ላይ ብኖር 575 ዓመት ነው። ለዚህች አጭር ዕድሜዬ ብዬ ብዙ አልጨነቅም (ሳቅ)፤ እናንተ 70/80 ዓመት ለመኖር ነው የምትጨነቁት። እኔ ቀስ እያልኩ ነው የማረጀው፤ እናንተ ቶሎ ታረጃላችሁ። የምር ፍልስፍናህን ንገረኝ.. አየህ ሰዎች ሱስ ውስጥ ይገባሉ። ምን ዓይነት ሱስ መሰለህ... ማቴሪያል የመውደድ ሱስ። ወይ መኪና የመውደድ፣ ወይ ኑሮ ማለት ለነሱ ገንዘብ የማከማቸት። አእምሯቸውን፣ ልባቸውንና አጠቃላይ ሕይወታቸውን ወደ ውጭ አውጥተው እዚያ ላይ ያስቀምጡታል። ሕይወት ግን ወደ ውስጥ ነው። • የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ? መጀመሪያ ሕይወት ያለው አንተ ውስጥ ነው። ያንን ሕይወት፣ ሕይወት ልታደርገው የምትችለው አንተ ነህ እንጂ፣ ውጭ ያለው ነገር አይደለም ላንተ ሕይወት የሚሰጥህ። ራስህን አውጥተህ ስትሰጥ ማንነትህን እያጣህ ትመጣለህ። ውስጥ ያለው መንፈስህ እየወጣ፣ እየደከምክ አቅም እያጣህ ትመጣለህ። ከዚያ ጭንቀት ይቆጣጠርሃል። ተጠራጣሪና ፈሪ ትሆናለህ። ከሰው ጋር ለመግባባት ትቸገራለህ። ስለ ገንዘብ ምን ታስባለህ? እኔ ገንዘብን ብዙም አላቀርበውም፤ እዚያ ጋ ይቀመጣል፤ ከዚያ ስፈልግ "ና እዚህ ጋ" እለዋለሁ። ቤት ኪራይ ይከፍላል፤ ይሄዳል። ገንዘብ ይታዘዝልኛል እያልከን ነው? አዎ! (ሳቅ) ገንዘብ አልሰበሰብ እያለ አስቸግሮህ፤ ሩቅ ሆኖብህ እንዳይሆን? ሩቅ ሆኖብኝ አይደለም። በአንድ በኩል ሩቅም ነው። አሁን እነዚህ ሚሊዮን ብር ያላቸው...አንድ ሰው ይሄን ብር ከየት ያመጣል? ካልሰረቀ ካልዘረፈ በስተቀር። ሠርቶ የሚያገኘው ምናልባት ጥቂት ሰው ነው የሚሆነው። አእምሮን መንፈስን ኮራፕት አድርገን ተላምደን ኖረናል ለብዙ ጊዜ። ይሄንን ኖርማል አድርገን ይዘነው ነው ብዙዎች ሀብታም ነን የሚሉት። [እንጂ] ከየት ያመጣሉ? የትኛው ዕውቀታቸው ነው ይሄን ያህል ገንዘብ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው? የትኛው ነጋዴ ነው? እንዴ እናውቃለን እኮ...እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እኮ ያውቃል። ማን ብሩን እንዴት እንዳገኘው። ሀበሻ ፍልስፍናው በተረት ውስጥ ነው ያለው። አንድ ተረት ልንገርህ... ሰጎን አሉ... መሀል በረሃ ላይ ይቺን የምታክል አፏን አሸዋ ላይ ቀብራ አንገቷና ሰውነቷ ውጭ ነው ያለው። ኋላ ሰው ሄደና "ሰጎን! ሰጎን! ምን እያረግሽ ነው? አፍንጫና ዓይንሽን ቀብረሽ ሰውነትሽ ዝሆን አክሎ ቢሏት... 'ሰው እንዳያየኝ ተሸሽጌ ነው አለች' አሉ። እነኚህ ሰዎች ይሄንን ሚሊዮን ብር ከየት እንዳመጡት የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል። ነገር ግን አንገቱን የቀበረው ሰውዬ ስለ'ኔ ሰው አያውቅም ብሎ አንገቱን እንደ ሰጎን አሸዋ ውስጥ ቀብሮታል። በንጽሕና የተገኘ ሀብት የለም እያልኩህ ግን አይደለም። ጥቂት ነው። ስዊዘርላንድ፤ ዙሪክ ኅብረተሰባችን የሞራል ልዕልናው እየተሸረሸረ ይመስልሃል? በጣም እንጂ! ህልውናውን ያጣበት ዘመን ነው፤ ታዲያ ህልውናውን ባያጣ በሄድክበት... ከዚህ በፊት ሐዋሳ [መሄድ ስታስብ] ኤጀቶ እንደዚህ ያደርገኛል፤ ኦሮሚያ ብትሄድ ቄሮ እንዲህ ይለኛል፣ አማራ ብትሄድ ፋኖ ምናምን ይለኛል [ትላለህ እንዴ?] ወጣቱ ሁሉ በዘር በሃይማኖት በጎሣ ተበጣጥሶ እያንዳንዱ ሰው እየጠበበ፣ ዱላ እየያዘ እርስ በርሱ ይደባደባል እንዴ? ከዚህ የበለጠ ህልውና ማጣት ምን ይኖራል? ምን ያልሆነው አለ እስቲ አሁን? ሰው እየሰቀልን? ሰው እየቆራረጥን፤ ሰው እየገደልን፤ ሺህ ሰው እያፈናቀልን! ምን ያልሆነው አለ?! እስቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንድነው ያልተሆነው? ንገረኝ? እንዴት በአንድ ጊዜ እዚህ ደረስን ግን? በአንድ ጊዜ አይደለም። ትንሽ ዓመት ነው እንዴ? እስኪ አስበው። በደርግ ጊዜ ተጀመረ። በኢህአዴግ ጊዜ አለቀ። 30 ዓመት በለው የኢህአዴግን ዕድሜ። ያ 17 ዓመት...ወደ 50 ዓመት ሊሆን እኮ ነው። ግማሽ ክፍለ ዘመን ቀላል ነው እንዴ ታዲያ? 50 ዓመት ጆሮው ላይ ስለክፍፍል ሲጮኽበት የነበረ ሰው እንዴት አድርጎ ነው ልዕልና የሚኖረው? ተጠላልፈን በድንበር ተከፋፍለን፣ 99 ባንዲራ አሲዘውን......አእምሯችን ላይ ድንበር ሠርተው፣ በሃይማኖት አጥረውን፣ በክልል አጥረውን፣ በጎሣ አጥሮን አንተ እንዴት እኔን ትወደኛለህ? ይሄ ኅብረተሰብ ቪክቲም (ሰለባ) ነው። የዚህ ድምር ሥርዓት ውጤት ነው። ታዲያ በምን ሂሳብ ነው የተሻለ ነገር የምትጠብቀው? አረም ዘርተህ ስንዴ ትጠብቃለህ እንዴ? ትሰጋለህ? ይቺ አገር እልቂት ውስጥ ትገባለች ብለህ? [ዘለግ ካለ ትካዜ በኋላ....] ሶሪያ ምን ሆነ? የመን ምን ሆነ? ሶማሌ ምን ሆነ? ጎረቤትህ እኮ ነው። የግድ አንተ ቤት መምጣት አለበት እንዴ? ጎረቤትህ ምን እየሆነ እንዳለ እያየህ አንተ "ምን ሆንን እኛ?" ብለህ የተቀመጥክ እንደሆነ የት ይቀርልሃል? አፈር ድሜ ትበላለህ...ቀልድ እንዳይመስልህ። የሚመጣውን መገመት የማትችል ከሆነ ሲኦል ነው የምትገባው። ማነው ተጠያቂው ግን? አሉ የዘር በሽታ የያዛቸው። ኦሮሞ በል፣ አማራ በል፣ ትግሬ በል..[በለው!] እያሉ በቃ በዘር የተለከፉ በሽተኞች አሉ፤ እነኚህን በሽተኞች መለየት ያስፈልጋል። አሉ እዚህ... ምንም የማይሻሻሉ፤ እዚህ የሰለጠነ ዓለም እየኖሩ እንኳ ያልሰለጠኑ ሰዎች አሉ። እነኚህን በሽተኞች ወደዚያ አግልለህ... ወዴት? በሕግ፣ በደንብ በሥነ ሥርዓት ጠፍንገህ ታስረዋለሃ። [ቆጣ ባለ ስሜት] ምን ያረጋል መንግሥት? ኃላፊነቱ ይሄ አይደለም እንዴ? ይሄን ሁሉ መከራና አመጽ የሚያመጡ ሰዎች እኮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አይደሉም። ጥቂት ሰዎች ናቸው። እዚህና እዚያ...ጥቅማቸው እንዳይቀርባቸው ነው ክብሪት እየለኮሱ ብዙኃኑን የሚያፈናቅሉ። እነኚህ ሰዎች በደንብ ይታወቃሉ። ምንጫቸው ይታወቃል። ምንጩን ማድረቅ አለብህ። እነዚህ የምትላቸውን ማሰር ወደ ባሰ ቀውስ አይከተንም? ብዙ ወጣት ተከታይ አላቸው እኮ እሱ ልክ ነህ፤ ሁለት ነገር አለ። ዛሬ ስንት እጁ ነው ወጣት? ምን ያህሉ ነው ሥራ ያለው። ሁሉም ቦዘኔ ነው። ትግራይ ብትገባ ያ ሁሉ ወጣት ሥራ የለውም፤ ግን እዚያ ያለው ሥርዓት ምን ይለዋል ልክ እሱ አርበኛ እንደሆነ፣ ጀግና እንደሆነ፣ በወሬ እያሞካሸ አንተ እንደዚህ ነህ እያለ ዝም ብሎ ያወጣዋል ያንን ወጣት። አዲስ አበባም በለው የትም የትም እንደዚህ ነው የሚያደርጉት። ጀሌውን የሚመራውን ነው መያዝ፤ ፋኖ ነኝ፣ ኤጄቶ ነኝ፣ ቄሮ ነኝ ምንድነኝ የሚለው ሌሎች ይጠቀሙበታል እንጂ ሥራ ነው የሚፈልገው። ድሃ በመሆኑ ነው ሊጠቀሙበት የሚፈልጉት፤ ድሃ ባይሆንማ ዝም ብሎ አይነሳላቸውም። ግን ጋሽ አበራ ነጻና እውነተኛ ዲሞክራሲ ቢኖር ምርጫ አትወዳደርም? እርግጠኛ ነህ? አይ አላደርገውም፤ እውነት ለመናገር እኔ እዚያ ነገር ውስጥ ብገባ እኔነቴን አጣዋለሁ። ሁሉም ሰው ሥልጣን አይዝም። ሁሉም ሰው ቤት አይሠራም፤ አንዱ ቤት ይሠራል፤ ሌላው ቤት ይከራያል።
news-44519676
https://www.bbc.com/amharic/news-44519676
በየቀኑ ወደ ምድር የሚመጡ እንስሳት ቁጥር ሲሰላ ስንት ይሆን?
አእዋፍት፣ ንቦችም፣ ትሎችም ሳይቀሩ ይዋለዳሉ።
ምድራችን ወደ 7.7 ሚሊየን የሚሆኑ እንስሳት መኖሪያ ናት። እነዚህ እንስሳት እንደ ሰው ልጆች በፍቅር ክንፍ ሲሉ ባይታዩም ይዋለዳሉ። ዘር ይቀጥላሉ። ለመሆኑ በየቀኑ በአለም ዙሪያ ስንት እንስሳት ይወለዳሉ ብለው ያስባሉ? ቢቢሲ 'ሞር ኦር ለስ' የተሰኘ መርሀ ግብር አለው። ታዲያ ከዝግጅቱ አድማጮች አንዱ አለም በየቀኑ ስንት እንስሳትን ትቀበላለች? ሲል ጠየቀ። ዘር በመተካት ረገድ ጥንቸሎች ተወዳዳሪ የላቸውም። ከየትኛውም እንስሳ በላቀ ይዋለዳሉ። እንግሊዝን እንደምሳሌ ብንወስድ የእንግሊዝ የዱር ጥንቸሎች ርቢ 40 ሚሊየን ይደርሳል። አንዲት ጥንቸል ከሶስት ወደ ሰባት ጥንቸሎችን ታፈራለች በሚለው ስሌት በየቀኑ 1,917,808 ጥንቸሎች ይወለዳሉ ማለት ነው። ሆኖም ከጥንቸሎች ውስጥ ተወለወደው ብዙም ሳይቆዩ የሚሞቱ አሉና አለም ከምትቀበላቸው ጥንቸሎች ብዙዎቹን ታጣለች። በአንዳንድ አካባቢዎች ብቻ ተወሰወነው የሚኖሩ ብርቅዬ እንስሳትን ደግሞ እንመልከት። በቺሊና ፔሩ የሚኖሩት ሀምቦልት ፔንግዊኖች ጥሩ ምሳሌ ናቸው። እነዚህ እንስሳት የሚራቡት እንቁላል በመጣል ነው። በአንዴ የሚጥሉት ሁለት እንቁላል ሲሆን፣ እያንዳንዳቸው በአመት ሁለት እንቁላል ይጥላሉ። ስለዚህም በቀን 40 ሀምቦልት ፔንግዊኖች እንዲሁም በአመት 14,400 ይጣላሉ። ወደ ዶሮ አለም እንዝለቅ። የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ዘርፍ ክፍል በቀን 62 ሚሊየን ዶሮዎች ወደ ምድር ይመጣሉ ይላል። በአንጻሩ ንቦች በሞቃትና በቀዝቃዛ ወቅት ዘራቸውን የሚተኩበት ፍጥነት ይለያያል። በሞቃት ወራት ንግስቲቷ ንብ በየቀኑ 1,500 እንቁላል ትጥላለች። ባጠቃላይ ሞቃታማ ጊዜ ላይ 371,191,500 እንቁላል ይጥላሉ። በለንደን ዙስ ኢንስቲትዪት ኦፍ ዙኦሎጂ የምትሰራው ሞኒካ ቦሀም እንደመሚሉት የእንስሳትን አለም ከሀ እስከ ፐ ማወቅ አልተቻለምና ስለሚራቡበት መንገድ የተሟላ መረጃ የለም። የክዊን ሜሪ ዩኒቨርስቲው ፕሮፌሰር ኣክሰል ሮስበርግ በበኩሉ የእንስሳት አካል ግዝፈት ከሚራቡበት መጠን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው ይላሉ። ጥቃቅን እንስሳት በብዛት ሲራቡ ግዙፎቹ የሚወዋለዱበት ፍጥነት ዝግ ይላል። በፕሮፌሰሩ ስሌት መሰረት በምድር ላይ ካሉ ዝሆኖች የንቦች መጠን ይበልጣል ማለት ነው። ለምሳሌ ኔማቶድ የተባሉት አነስተኛ ትሎች ከመጠናቸው ትንሽነት አንጻር በአንድ ካሬ ሜትር ሶስት ሚሊየን ይገኛሉ። በአንድ ካሬ ሜትር ሶስት ሚሊየን ኔማቶዶች ይገኛሉ ከትሉ ዝርያዎች መሀከል በአንድ ሰአት አምስት እንቁላል የሚጥለው ይጠቀሳል። ከ100 እንቁላሎች አንዱ ስለሚፈለፈል በየቀኑ 600 ካትሪልየን ይወለዳሉ ማለት ነው። የተለያዩ ዝርያዎች በየቀኑ ወደ ምድር የሚያመጧቸውን እንስሳት ብንደምር ያጠቃላይ እንስሳት ቁጥር ላይ መድረስ ይቻላል።
44211605
https://www.bbc.com/amharic/44211605
መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ
ኮ/ል መንግሥቱ ደርግን ኮትኩተው አሳድገውት ይሆናል። ነገር ግን አልወለዱትም። የደርግ እናትም አባትም ኮ/ል አጥናፉ ናቸው። ኾኖም ደርግ ፈጣሪውን መልሶ ለመብላት የወሰደበት ጊዜ ከ5 ዓመት ያነሰ ነበር፡፡ ኅዳር 3/ 1970 በዕለተ ቅዳሜ አጥናፉ ተገደሉ። "አብዮት ልጆቿን በላች" ተባለ።
መስከረም 2/1967 የአብዯት በዓል- ከግራ ወደ ቀኝ መንግሥቱ ኃይለማርያም (ሻለቃ)፣ ተፈሪ በንቲ (ብ/ጄኔራል)፣ አጥናፉ አባተ (ሻለቃ) ሲያልቅ አያምር ሆኖ እንጂ መንጌና አጥናፉ ጎረቤት ነበሩ። ሚስቶቻቸው ውባንቺና አስናቀች በአንድ ስኒ ቡና ጠጥተዋል። ትምህርትና ትዕግስት ከነሱራፌል አጥናፉ ጋር ኳስ ሲራገጡ፣ መሐረቤን ያያችሁ ሲጫወቱ ይውሉ ነበር። ጨርቆስ፣ መሿለኪያ፣ 4ኛ ክፍለ ጦር ግቢ የሟችም የ'ገዳይ'ም ቤት ነበር። • ፍርድ ቤት የቀረበው የቀይ ሽብር ተከሳሽ ምስክሮችን ተማፀነ • ፍቅርና ጋብቻ በቀይ ሽብር ዘመን መንጌ ቀኝ እጃቸው፣ ጎረቤታቸውና ለአጭር ጊዜም ቢሆን አለቃቸው በነበሩት ሻለቃ አጥናፉ ላይ ድንገት "ሲጨክኑ" ሐዘኑ ከባድ ሆነ። የሟች ልጅ ሱራፌል አጥናፉ እንደሚያስታውሰው ከሆነ ገራገሯ ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው ለቅሶ ደርሰዋቸዋል። "ትዝ ይለኛል እማዬ ወይዘሮ ዉባንቺን 'ባልሽ ባሌን ገደለው!' እያለቻት ተቃቅፈው ሲላቀሱ" ይላል ሱራፌል። ለመሆኑ ከኮሎኔል አጥናፉ አባተ መገደል በኋላ ልጆቹ እንደምን ኖሩ? ከ8ቱ ልጆች 5ኛው ሱራፌል አጥናፉ "መንጌ አባቴን ካስገደለ በኋላ እኛን እንዳሮጌ ዕቃ ከቤት አውጥተው ጣሉን..." ሲል ረዥሙን ቤተሰባዊ ምስቅልቅ በአጭር ዐረፍተ ነገር ይጀምራል፡፡ "ሁለቱ ወንድሞቼ በብስጭት ሞቱ" ሱራፌል አጥናፉ አባተ እባላለሁ። የኮ/ል አጥናፉ 5ኛ ልጅ ነኝ። አሁን እኔ ራሴ አምስት ልጆች አሉኝ። የምተዳደረው በሹፍርና ነው። የአጥናፉ ልጆች 8 ነን። አሁን በሕይወት ያለነው ግን አምስት ስንሆን ሦስቱ በሕይወት የሉም። የሁለቱ ሞት ከአባታችን መገደል ጋር የተያያዘ ነው። አባታችን አጥናፉ የተገደለው ሁለቱ ወንድሞቼ ራሺያ በሄዱ ልክ በ10ኛው ቀን ነበር። የታላቄ ታላቅ ሰለሞን አጥናፉ ይባላል። ራሺያ ለከፍተኛ ትምህርት እንደሄደ ያባታችንን ሞት ሲሰማ በዚያው የአእምሮ በሽተኛ ሆነ። እዚህ መጥቶ አማኑኤል ሆስፒታል ተሞከረ፤ አልተቻለም። እናታችን ብዙ ደከመች። አልሆነም። • "ወሎዬው" መንዙማ • የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ በጣም ይበሳጭ ነበር፤ በአባታችን ሞት። ለምሳሌ እንደማስታውሰው ድንገት ተነስቶ በእግሩ ጎጃም ድረስ ይሄድ ነበር። አእምሮው ታወከና በመጨረሻ ብዙም አልቆየ ራሱን አጠፋ። የሁላችንም ታላቅ ዶክተር መክብብ አጥናፉ ይባላል። እሱም እንዲሁ በአባታችን አላግባብ መገደል በጣም ይበሳጭ ነበር። ራሺያ ሕክምና ተምሮ ከተመለሰ በኋላ ብዙ ዓመት ሆሳዕና "መንግሥቱ ኃይለማርያም ሆስፒታል" ሠርቷል። አባቱን በገደለው ሰው ስም በተሰየመ ሆስፒታል ውስጥ መሥራት ምን ስሜት እንደሚሰጥ አስበው። ከሆሳዕና ሕዝብ ዶክተር መክብብን የማያውቅ የለም ማለት ይቻላል። ተወዳጅ ሐኪም ነበር። ግን በአባታችን ሞት እጅጉኑ ይበሳጭ ነበር። እኔ እጨቃጨቀው ነበር። 'በቃ አባታችን የሚያምንበትን ሠርቶ አልፏል። እኛ የራሳችንን ሕይወት ነው መኖር ያለብን' እለው ነበር። እሱ ግን ብዙ ምስጢር ያውቅ ስለነበር አይሰማኝም፤ በጣም ብስጩ ሆነ። በመጨረሻ እሱም ጭንቅላቱ ተነካና ሞተ። ሟች ወንድሞቻችን ሰለሞንና ዶክተር መክብብ አባታችን ነገሌ፣ 4ኛ ክፍለ ጦር እያለ የተወለዱ ነበሩ። ሌሎቻችን ግን እዚህ መሿለኪያ 4ኛ ክፍለ ጦር ግቢ ውስጥ ነው የተወለድነው። ቴድሮስ፣ ጌታሁን፣ ሳምሶን፣ እንዳለ፣ እህታችን አብነት፣ እኔን ጨምሮ- ሁላችንም የመሿለኪያ ልጆች ነን፡፡ ከመንጌ ልጆች ጋር አብረን ነው ያደግነው እኛ ቤት ነበር እኮ የሚያድሩት። መንጌ ከሐረር 3ኛ ክፍለ ጦር አባቴ ሲያስጠራው እኛ ቤት ነበር ያረፈው። ደርጉን ያሰባሰበው እኮ አባቴ ነው። በየጦር ክፍሉ እየደወለ፣ ተወካይ ላኩ እያለ…። በኋላ ነው ነገር የመጣው። እንጂማ ጎረቤት ሆነን ነው የኖርነው። ውባንቺና እናቴ አስናቀች እኮ ቡና ሲጠጡ ነው የሚውሉት። እኛ ግቢ ቅዳሜና እሑድ ኳስ ስንራገጥ ነበር የምንውለው። የኮ/ል ነጋሽ ዱባለ ልጆች ምሥራቅ ነጋሽ፣ ገብረየስ ወልደሀና የሚባል ነበር፣ የደርጉ ዋና ፀሐፊ ተብሎ የተመረጠ፣ ከ3ኛ ክፍለ ጦር፤ እሱ 2 ልጆች ነበሩት፣ ስማቸው ተረሳኝ። እኛ ግቢ ነበር ኳስ የምንጫወተው። ደግሞ ሁላችንም ፈለገ ዮርዳኖስ ነበር የምንማረው። ያኔ ፈለገ ዮርዳኖስ የግል ነበር፤ በወር 6 ብር ይከፈል ነበር። ከመንጌ ሴት ልጅ ጋር አብረን ነበርን። ልክ መንግስቱ ግድያ ሲሞከርበት አባቴን 'ቤተ-መንግሥት እንግባ' አለው። አባቴ 'እኔ 4ኛ ክፍለ ጦርን አለቅም' አለ። ያኔ እሱ ጥበቃ የለው ምን የለው...። አንድ አቶ ኤፍሬም የሚባሉ ሾፌር ብቻ ነበሩት። ቤተ-መንግሥት ያልገባነው አባቴ ባለመፈለጉ ብቻ ነበር። ኮ/ል አጥናፉና ባለቤታቸው ወይዘሮ አስናቀች ከበደ ከልጆቻቸው ሳምሶን፣ ቴዎድሮስ፣ ሱራፌል፣ ጌታሁን፣ ሰለሞንና መክብብ አጥናፉ ጋር የአጥናፉ ኑዛዜዎቹ በየክፍለሃገሩ የኢትዮጵያ ትቅደም ባንዲራን የሰጠ፣ ሚሊሻን ያደረጀ አባቴ ነው። በየሄደበት ማስታወሻ የመያዝ ልምድ ነበረው። መአት ማስታወሻ ነው ትቶ ያለፈው። ፎቶዎች፣ ካሴቶች…መአት..መአት ቅዳሜ ገድለውት እሑድ ቤታችን መጥተው በርብረው ብዙ ነገር ወስደዋል። ይሄ ሁሉ ከዚያ እንዴት እንደተረፈ አላውቅም። ለምሳሌ በ20/10/69 ዓ.ም የፃፈው የግል ማስታወሻ ላይ "ለጊዜው ብቻዬን ብቀርም እውነትን መከተልና መናገር ምንጊዜም እምነቴ ነው" ይላል። እነ ተፈሪ በንቲ፣ ኮ/ል ሻምበል ሞገስ፣ ሌ/ኮ/ል ዳንኤል አስፋውና ሌሎችም እሱ ወለጋ ጊምቢ ወታደር ሊያስመርቅ በሄደበት ነው የተገደሉት። ተደውሎ መረሸናቸው ተነገረው። "እንዴት እንዲህ ይደረጋል። አሁንም ይሄ መግደል አልቀረም? ትናንት አማንን ገደልን፣ ዛሬ ተፈሪን ገደልን፤ ይሄ መግደል የት ነው የሚያበቃው?" ሲል "ና እሱን እዚህ እንነጋገራለን" አለው መንጌ። ያኔ በ27/5/69 ዓ.ም ጠዋት ከጊምቢ አዲስ አበባ እየመጣ የጻፋት ማስታወሻ እነሱ በተረሸኑ ማግስት መሆኑ ነው። ላንብብልህ፤ "የተገደልኩ እንደሆን" ይላል ርእሱ።"…በጎሰኞችና በሥልጣን ጥመኞች በሀሰት የተገደልኩ እንደሆን ተመልሻለሁ፤ለጭቁኑ እውነተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ እነሆ ኑዛዜዬን በሐቅ አረጋግጣለሁ። ስለሆነም ቤተሰቦቼ የጭቁኑ ወገን ስለሆኑ በሐሰት ታሪክ ታሪካቸውና ሕይወታቸው እንዳይበላሽ፤ እንዳይንገላቱ ለኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝብ አሳስባለሁ" አሁን ሳስበው ከነሱ ጋር ቀላቅለው የገደሉኝ እንደሆን ብሎ ነው የጻፈው። እዛው ማስታወሻ ላይ "…ጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! እኔ እዚ አድርሼሃለሁ። ታገልና ራስህን ነፃ አውጣ!" ይላል። አባቴ ሁሉን ነገር ልቅም አድርጎ ማስታወሻ የመያዝ ልምድ ነበረው። የየቀኗ ሪፖርት አለች። ብዙ ማስታወሻዎችን፣ ፎቶግራፎችን፣ በካሴት የተቀረፁ ድምፆችን በሙሉ ትቶልን ሄዷል። እንዲያውም ይሄ ነገር በኢትዮጵያ መንግሥት ማኅደር ውስጥ ቢቀመጥ ለመጪው መንግሥት ትምህርት ይሆናል ብዬ አስባለሁ… እዚሁ የግል ማስታወሻው ላይ ያገኘሁትን ላንብብልህማ… "እኛ የምናካሄደው አብዮት ነው። በስህተት ንብረት ተወርሻለሁ የሚል ካለ ፍርድ ቤት ይሂድ፤ የተበደለ ካለ ለኛ ሳይሆን ለፍርድ ቤት ይናገር። ማንኛውም ሰው ያለ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዳይገደል አሳስባለሁ" በቀይ እስክሪብቶ ነው የጻፈው። የመንግሥቱ ልጆች ዶክተር ሆነዋል። እኛ ደግሞ ሾፌሮች ሆንን እንደነገርኩህ አብረን ነው ያደግነው። ግን እኛ መንጌ አባቴን ከገደለው በኋላ ያላየነው መከራ የለም። ንፋስ ስልክ አጠቃላይ የትምህርት ቤት ክፍያ አቅቶን ተባረናል። አስታውሳለሁ አንዴ የስፖርት 8 ብር አጥተን ከትምህርት ቤት ስንባረር፣ ልኡል ሰገድ ዘካሪያስ የሚባል ነበር ዲሬክተሩ ያኔ አግኝቶን ሁኔታውን ነገርኩት፤ "ይሄ ክፉ...! ለመሆኑ ጡረታ ሰጥቷችኋል?" ብሎ አዝኖ፣ "ከአሁን በኋላ የአጥናፉ ልጆች ማንም እንዳያባራቸው፤ እኔ አለሁ" ብሎ ወደ ትምህርት ቤት መልሶናል። ጀርባቸው ይጠና ተብሎ የቀበሌ መታወቂያ ሁሉ የተከልክለንበት ጊዜ ነበር። እናታችን 3በ5 በሆነች አንዲት ክፍል ቤት ነው ኖራ የሞተችው፤ እሱንም እግዚአብሔር ይስጠው አቶ ወንድሙ የሚባል የከፍተኛ 19 ሊቀመንበር "መንጌ ቢገድለኝም ይግደለኝ" ብሎ ነው ያሰጠን። እዛች ክፍል ተደራርበን ነበር የምንተኛው። ከፍ ስንል ረዳት ሆንን፣ ከዚያ እንደምንም መንጃ ፍቃድ አወጣን። አባታችን ቢኖር እኛም ዶክተር እንሆን ነበር…ብቻ መንግሥቱ ያላስደረገን ነገር የለም። በመጨረሻ እንዲህ አገር ጥሎ ሊሄድ… ኮ/ል አጥናፉ ከሊቢያው መሪ ሞአመር ጋዳፊ (ከ1970 ዓ ም በፊት ቢሆንም ትክክለኛ ቀኑን ዓመተ ምህረቱ ያልተገለጸ።) ጄ/ል ጃጋማ ኬሎና አጥናፉ አባተ በንጉሡ ጊዜ ጃጋማ ኬሎ አለቃው ነበሩ፤ ነገሌ 4ኛ ክፍለ ጦር። በኋላ ከ60ዎቹ ጋር ሊገደሉ ተብሎ እንዳይገደሉ ያደረገው አባቴ ነው። ይሄን ራሳቸው ነው የተናገሩት። እንኳን መገደል፣ እንዳይታሰሩ ብሎ ነው አባቴ ያዳናቸው። ይወዳቸው ነበር። አሁን በቅርብ ጊዜ ነው የሞቱት። እንደመሰከሩለት ነው የኖሩት። በተደጋጋሚ 'እኔ ከደርግ የተረፍኩት በኮ/ል አጥናፉ ነው' ሲሉ ተናግረዋል። መንግሥቱ ግን ሥልጣን እንደያዘ የ3ኛ ክፍለ ጦር አለቃውን ማዕረግ ከልክሎኛል ብሎ ወዲያው ነበር ያስረሸነው። ቂመኛ ይመስለኛል መንግሥቱ። አባቴ ግን እንደዛ አልነበረም። አባቴ ስለሆነ አይደለም እንደዚያ የምልህ፤ በተደጋጋሚ ማስታወሻውን አይቻለሁ፤ አንብቢያለሁ፤ "እኛ ያመጣነው ለውጥ እኮ ሰው ለመግደል አይደለም" ሲል ጽፏል በተደጋጋሚ፤ ግድያን ተቃውሟል። ያስገደለውም ይኸው አቋሙ ነበር። ያኔ ከደርጎቹ መሐል ትንሽ ትምህርት የቀመሰውም እሱ ነበር። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም፣ አሜሪካም ድረስ ሄዶ ተምሯል።በቁጣም በችኮላም የሚያምን ሰው አልነበረም። ሰከን ያለ ሰው ነበር። ሁለት ነገር ነው በዋናነት ጥርስ ውስጥ ያስገባው። ሶሻሊዝም አይሆነንም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይማኖተኛ ነው። ታሪኩም፣ ባሕሉም አይፈቅድለትም። ሶሻሊዝም ብለን ባዕድ ነገር አንጫንበት። ሶሻሊዝም ለእኛ አይሆነንም ነበር ያለው። ሌላው ደግሞ 'እኛ ወታደሮች ነን፤ ሥልጣን ለሕዝብ አስረክበን ወደ ካምፓችን እንመለስ' የሚል አቋም ነበረው። ያኔ ነው ጥርስ የተነከሰበት። ኮሚቴ አዋቅረው "ባንተ ጉዳይ እስክንወስን ጠብቅ" አሉት። አጥናፉ ያቺን ሰዓት ሕዳር 3/1970 ዓ.ም ቅዳሜ ነበር፤ አስታወሳለሁ። ዝም ብሎ ቁጭ ብሎ ሲጽፍ ትዝ ይለኛል። ሦስት ቀን ከቤት አልወጣም። እኔ ጉንፋን አሞኝ ይመስለኛል ቤት ነበርኩ ያን ሰሞን። ሐሙስ አርብ ቅዳሜ ቤት ነው የዋለው፤ ሲጽፍ። ቅዳሜ ጠዋት ሲወጣ ትዝ ይለኛል። ቶሎ ላንደሮቨሩ ውስጥ አልገባም። አቶ ኤፍሬም አሉ ሾፌሩ። ዝም ብሎ በረንዳ ላይ ቆመ። ኳሴን ይዤ እሱ ጋር ቆምኩ። ጭንቅላቴን እየዳበሰ ለእማዬ፤ "...በይ እንግዲህ ካልመጣሁ የልጆቼን ነገር አደራ" እያለ ተናገራት። መኪና ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሁላችንንም እየጠራ ሳመን። ትንሽ ቆይታ እናቴ በቢሮው ስልክ ደጋግማ ስትደውልለት እያነሳ "አለሁ፣ ደህና ነኝ" እያላት ነበር። የሆነ ሰዓት ላይ መልሳ ስትደውል አንድ ሌላ ወታደር ስልኩን አንስቶ "ጓድ አጥናፉ የለም፤ ካሁን በኋላ መደወል አይቻልም፤ ማታ በቴሌቪዥን ተከታተይ" አላት። ታውቋታል። ማታ በቴሌቪዥን "አብዮቱን ለመቀልበስ ሲሞክሩ… ምናምን…" እያሉ አወሩ። ለቅሶ ጀመርን። የመንግሥቱ ሚስት ወይዘሮ ውባንቺ ቢሻው ጠዋት ለቅሶ መጣች። የእማዬ ወዳጅ ነበረች። ማልቀስ ጀመረች። እናቴ እሷን አቅፋ "ባሌን ባልሽ ገደለው" እያለች ተያይዘው ተላቀሱ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም በኮ/ል አጥናፉ ላይ አብዮታዊ እርምጃ መወሰዱን የገለጹበት ደብዳቤ (ኅዳር 4፥ 1970 ዓ ም) የወይዘሮ አበበች መታፈሪያ ውለታ ሬሳውን አልሰጡንም። ለቅሶ እንዲለቀስ ያስፈቀዱልንም…ኮ/ል ነጋሽ ዱባለ ይመስሉኛል። ለቅሶው እንዳለቀ ብዙም አልቆየንም፤ የመንግሥት ቤት ነው ልቀቁ ተባልን፤ ከ4ኛ ክፍለ ጦር። የት እንግባ? እናታችን 8 ልጆች ይዛ ወዴት ትሂድ? ማን ያስጠጋን? ምናለ አባታችንን እንደሁ ገድለውታል፣ አይመለስ…ለውለታው፣ ለዚህ ስላበቃቸው እንኳ የቀበሌ ቤት ቢሰጡን? የአገሩን ሰው ሁሉ የመሬት ባለቤት ያደረገ ሰው ነው፤ እኛ ቤተሰቦቹ የምንቆምበት መሬት ማጣት ነበረብን? በኋላ እዚህ ሐኪም ማሞ ሰፈር በፍቃዱ ተሰማ የሚባል የእናታችን ዘመድ እሱ "ከገደሉኝም ይግደሉኝ" ብሎ አስጠጋን። አቶ በፍቃዱ 12 ልጅ አለው፤ እኛ ስምንት ነን፤ ሃያ ሰው ሆነን አንዲት ቤት ውስጥ መኖር ጀመርን። 20 ሰው አንድ ቤት እንግዲህ አስበው። ብቻ በእንዲህ አይነት ሁኔታ አደግን፤ ችግሩ ምግብ ምናምን ነበር። አንዲት አይዳ በቀለ የምትባል የእናት ያባቷን ቤት የወረሰች ልጅ ታሪካችንን ታውቅ ስለነበር አስጠጋችን። እማዬ እሷ ቤት ምግብ መሥራት ጀመረች። እዚህ ዮሴፍ ቤተ-ክርስያን ጋር አንድ ድርጅት ነበረ። የድርጅቱ ሠራተኞች ሽሮ እናቴ ጋ እየመጡ በኮንትራት መብላት ጀመሩ። ያችን እየሸጥን እንደምንም አደግን። በመሐል ምን ይሆናል መሰለህ! አንድ ቀን ወይዘሮ አበበች መታፈሪያ የሚባሉ ሴትዮ የተጠለልንበትን ቤት አፈላልገው ይመጣሉ፤ የለገሀር ሚኒ ባለቤት ናቸው። ያኔ ዝነኛ ካፌ ነበር፤ ትዝ ይለኛል በሬኖ መኪና ነበር የመጡት። 'የኮ/ል አጥናፉን ልጆች አሳዩኝ' ብለው ገቡ፤ እማዬ 'ይቅርታ አላውቆትም' አለቻቸው። "አዎ አታውቅኚም፤ እኔ ታስሬ ሞት የተፈረደብኝ ሰው ነበርኩ፤ አንድ ስድስት ሰባት እንሆናለን ሞት ተፈርዶብን (አየህ! ያኔ ኮ/ል አጥናፉ በየእስር ቤቱ በየክፍለ አገሩ ይጎበኝ ስለነበር ድንገት ደርሶ ሲገባ ያያቸዋል)፤ 'ደግሞ እናንተ ምን አድርጋችሁ ነው?' ሲላቸው፣ 'አይ እኛ ሞት ተፈርዶብን ነው' ይሉታል። 'ምን አድርጋችሁ?' 'ኢዲዩ ናችሁ ተብለን…' 'እንዴ! እኛ እኮ ለውጥ ያመጣነው ሕዝቡን ገድለን ለመጨረስ አይደለም፤ ማነው ይሄን ያዘዘው…? አንቺ ምንድነሽ? አለኝ፤ 'እኔ የለገሐር ሚኒ ባለቤት ነኝ'፤ አልኩት፤ 'በሉ እሺ ፍቷቸው…' ብሎ ከሞት ያስጣለን ያንቺ ባለቤት ነው…" ብላ ለእማዬ ነገረቻት። እሳቸው ተከታትለው፣ አፈላልገውን ነው እንግዲህ የእሱን ውለታ ለመመለስ የመጡት። "በሉ እንግዲህ! እኔ ካሁን በኋላ አልመጣም፣ ለማንም ትንፍሽ እንዳትሉ ብለው አስጠንቅቀውን፤ በወር 300 ብር ተቆራጭ አድርገውልን ሄዱ። 71/ 72 ዓ.ም ይመስለኛል። 300 ብር በዚያን ጊዜ አስበው፤ አባታቸን አገር ሲመራ እኮ ደመወዙ 800 ብር አይሞላም። እሷንም 500 ለቤት ተቆራጭ ያደርጋል፣ ሌላውን ለኪሱ ይወስዳል። እሳቸው ግን 300 ብር በየወሩ በዚያን ጊዜ በጣም ብዙ ብር ነው። እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ በሳቸው 300 ብር ነው ያደግነው። አጥናፉ አባተ ከቀኝ ሁለተኛ ዮጎዝላቪያ በጉብኝት ላይ አፅሙን ፍለጋ ያልሄድንበት የለም። ያልጠየቅነው የለም። እኔ እንዲያውም በየሳምንቱ ከርቸሌ እየሄድኩ የደርግ ባለሥልጣናትን ብስኩትና ውሃ እየያዝኩ እጠይቃቸው ነበር። 85 ላይ ይመስለኛል፤ ሳሌም የምትባል መጽሔት ላይ ደበላ ዲንሳ እጃቸውን ወደላይ አድርገው "ያስገደልኩትም የገደልኩትም የለም" በሚል የወጡባት መጽሔት ገዝቼ ሳነብ ጋዜጠኛው መጨረሻ ላይ "እንደው በከንቱ ሞተ የምትሉት ሰው አለ ወይ?" ብሎ ጠየቃቸው። እሳቸው ሲመልሱ "አጥናፉ ያሳዝነኛል። አስታውሳለሁ ለምሳ ስንነሳ አንዴ የምናገረው አለ ቁጭ በሉ ወንድሞቼ ብሎን አንዲት ወረቀት አውጥቶ ንግግር አደረገ። 'ካምፕ የምንገባበት ቀን ትወሰን፤ ሚክስድ ኢኮኖሚ እናድርግ፤ ሶሻሊዝም የማይሆነን ነገር ነው' ብሎ ተናገረ። እሱ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ሰው ነበር በከንቱ ሞተ የምለው እሱን ነው" ብለው የተናገሩትን አንብቤ ከርቸሌ ሄጄ አገኘኋቸው። "የእሱ ልጅ ነህ? አሉኝ። "አዎ!" ስላቸው ገረማቸው። ደጋግሜ ጠይቂያቸዋለሁ። ስለአባቴ ይንገሩኝ እያልኩ...። ደኅንነቱ ተስፋዬ ወልደሥላሴንም አገኝቼዋለሁ። እሱን እንኳን ሥልጣን ላይ እያለም አግኝቼዋለሁ። ቤቱ እዚህ ሩዋንዳ ነበር። ከእማዬ ጋር አምድ ቀን በጠዋት ሄደን "አባቴን አጥቻለሁ፤ ሥራ አስቀጥረኝ" ብዬው አውቃለሁ። "ሹፍርና ትችላለህ?" ብሎኝ አልችልም ስለው ያኔ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ለሽመልስ አዱኛ ደውሎ የሥራ አጥ ወረቀት አሰጥቶኝ ነበር። ሽመልስ የአጥናፉ ልጅ መሆኔን ሲያውቅ አክብሮ ተነስቶ ነው የሥራ አጥነት ወረቀት የሰጠኝ። (ኢህአዴግ ከገባ በኋላ)ተስፋዬን እስር ቤት ሳገኘው በቀኝ ጎኑ ፓራላይዝድ ሆኖ ነበር። ከአባቴ ጋር የአንድ ኮርስ ሰልጣኞች ነበረ።፡ እሱና አጥናፉ 17ኛ ኮርስ ነበሩ። መንጌ 19ኛ ኮርስ ነው። ብቻ አሳዘነኝ። ከዚያ በኋላማ ቅዳሜና እሑድ ቤቴ ከርቸሌ ሆነ። ደርጎችን ተራ በተራ እያስጠራሁ ውሃና ኩኪስ እየገዛሁ ላዩ ላይ "ከኮ/ል አጥናፉ አባተ ቤተሰቦች" ብዬ አጽፍበትና እሰጣቸዋለሁ። አንድ ጊዜ ለገሰን አስጠራሁትና ሱራፌል አጥናፉ እባላለሁ አልኩት። 'የኮ/ል አጥናፉ ልጅ ነህ?' አለኝ። 'አዎ!' አልኩት። ብዙ አወራን ከለገሰ ጋር። 'ምናለ አባዬን ባትገድሉት?' ስለው 'እኔ አይደለሁም እኮ! መጽሐፍ አንብበህ ነው የመጣኸው?' አባትህን እኔ አላስገደልኩትም" አለኝ። ሁሉም እንደዛ ነው የሚሉህ። (ከግራ ወደ ቀኝ) ኮ/ል አጥናፉ ከሱዳኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኑሜሬ ጋር፣ ሱራፌል አጥናፉ፣ ሻለቃ አቡል ጋሲም ከሻለቃ አጥናፉ ጋር "እዚህ ጋ ነው ከነወታደር ጫማው የቀበሩት" የተገደለ ቀን ከቤት ሲወጣ ሁለት መቶ ብር ኪሱ ውስጥ ነበረች። የጋብቻ ቀለበትና ሌላ አንድ የጉልላት ቀለበት ነበረ ያደረገው። እሱን ወስደው መቶ ብሩን ወስደው መቶ ብር ብቻ ነው ለእማዬ የመለሱላት። 100 ብሩ የጥይት መሰለኝ። የት እንደቀበሩት ለማወቅ ብዙ ጣርኩ። ኢህአዴግ ሲገባ እኔና እማዬ ሆነን ዊንጌት ሄድን። አፅሙን ፍለጋ። ዊንጌት የሄድነው ምስክርነት የሚባል መጽሐፍ ላይ "አጥናፉን መንጌ ራሱ ዊንጌት ድረስ ሄዶ ቆሞ ቀብሮታል" የሚል ነገር አንብበን ስለነበረ ነው። የቀይ ሽብር ሬሳ በጅምላ ሲወጣ እኛም እድላችንን እንሞክር ብለን ነው የሄድነው። አንድ የግቢው ጠባቂ ነገር ነው ጠቆር ያለ ቀጭን ሰውዬ፤ "እኔ ኮ/ል አጥናፉን ሲቀብሩት አስታወሳለሁ' ብሎ፤ 'እዚህ ጋ ነው የቀበሩት፤ ከነወታደር ጫማው፤ ከነምኑ" ብሎ አሳየን። እንግዲህ ምንም ምልክት የለም። እንዴት ሊያውቅ ቻለ…? ሰውየውንም ማመን ተቸገርን…ለነገሩ ማስቆፈርያም አልነበረንም ያኔ…በቃ ተውነው። ዞሮ ዞሮ ለሱ ይሄ አይገባውም ነበር። እነሱን ታግሎ ለዚህ ያበቃ ሰው፣ ሶሻሊዝም ለኢትዮጵያ አይሆንም ባለ፣ የኢትዮጵያን ገበሬ የመሬቱ ባለቤት ባደረገ፣ ሰው ዝም ብለን አንግደል ባለ፣ ስልጣን ለሕዝብ መልሰን ወደ ካምፕ እንመለስ ባለ፤ እንዲህ መሆን አልነበረበትም። ምናለ ከሚገድለው ቢያሰድደው፣ ምናለ ጡረታ ቢያስወጣው…! "ነበር"ን የጻፈው ገስጥ የሚባል ሰው አንዴ በአካል አግኝቼው ምን አለኝ…"ቆጥ ላይ አንድ አውራዶሮ ነው የሚሰፍረው፤ ለዚያ ነው እንጂ አባትህ ከእሱ አንሶ አይደለም...።" የሟችና 'ገዳይ' ልጆች ወዳጅነት ሱራፌል ለቢቢሲ እንደተናገረው ታናሽ ወንድሙ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከጓድ መንግሥቱ ሴት ልጅ ጋር ይደዋወሉ፣ ለሰዓታትም ያወጉ ነበር። ጥሩ የበይነ-መረብ ወዳጆች ሆነው ቆይተዋል፤ ግን ወንድሜ እየቆየ ሆድ ይብሰዋል። በተለይ አባቷ አባቱን 'እንዳስገደለ' ሲያስብ…። አንድ ቀን እንደተለመደው በበይነ-መረብ ሲያወጉ ይቆዩና "ታውቂያለሽ ግን እኛ ቤት እኮ አንቺ፣ መንጌ፣ የእናትሽ ዉባንቺና የእኔ ወንድሞች ድሮ 4ኛ ክፍለ ጦር አብራችሁ የተነሳችሁት ፎቶ አለ…" ይላታል። "እውነትህን ነው? በናትህ ላክልኝ?" ትለዋለች፤ "...እማማ ብታየው በጣም ደስ ይላታል፤ እንደውም ሃራሬ ልሄድ ስለሆነ ላክልኝ…" ትለዋለች። ፎቶውን እልክልሻለሁ ግን እኮ… አባትሽ አባቴን ካስገደለው በኋላ እኛ ጎዳና ወጥተን፣ የሚላስ የሚቀመስ አጥተን፣ የትምህርት ቤት መክፈል አቅቶን ነበር…"አባትሽ ግን እንዴት ጨካኝ ሰው ናቸው? ይላታል። ከሀራሬ ወደ ለንዶን ስትመለስ ታዲያ መልሳ ትደውልለታለች… "አባቴን እኮ አናገርኩት፤ ከአባታችሁ ሞት በኋላ ይሄን ያህል መቸገራችሁን በፍፁም አያውቅም። እውነቴን ነው የምልህ…በጣም ነው የገረመው ስነግረው...። "ውሸታም በይው! ሁሉንም ያውቃል፣ እሱ የማያውቀው ነገር የለም…። ሁሉንም ያውቃል" የመንጌ ልጅ የአባቶች ጦስ ወደ ልጆች እንዳይወርድ የሰጋች ይመስላል። ለምሳሌ ለአጥናፉ አንደኛው ልጅ "ለልጆቹ ኮምፒውተር እንደምትልክለት፣ ሕክምና ትምህርት ከጀመሩ ደግሞ በርከት ያሉ መጻህፍት እንደምትልክለት ቃል ገብታለትም ነበር" ይላል ሱራፌል። ሱራፌል ጨምሮ እንደመሰከረው የመንግሥቱ ሴት ልጅ ከሐራሬ ስትመለስ ለወንድሙ እንዲህ ብለዋለች። "አባቴ በሕይወቱ ባደረገው ነገር አንዴም ሲፀፀት ሰምቼው አላውቅም። ነገር ግን በአባታችሁ አጥናፉ ሞት ያዝናል። 'እሱን ከጎኔ ካጣሁ በኋላ ነው ነገሮች የተበላሹት' ሲል ሰምቼዋለሁ።"
news-49288873
https://www.bbc.com/amharic/news-49288873
መፈናቀል በኢትዮጵያ፡ በአገር ውስጥ ያለው መፈናቀል ሕገ ወጥ ስደትን አባብሷል?
በሕገ ወጥ መንገድ ባሕር ተሻግረው ለመሄድ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ይነገራል። በተለያየ ጊዜ ባህር ለመሻገር ሲሞክሩ ሕይወታቸው የሚያልፉ ዜጎችን ዜና መስማት የተለመደ ሆኗል።
ከሳምንታት በፊትም ከትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ ከሊቢያ ተነስተው ሜዲትራንያንን ሲያቋርጡ የነበሩ 15 ወጣቶች ሕይወታቸው ማለፉንም ሰምተናል። • ህገወጡ የአረብ አገራት ጉዞ በአዲሱ አዋጅ ይገታል? • ኢትዮጵያዊያን በህጋዊ መንገድ ለሥራ መሄድ የሚችሉባቸው ሃገራት የትኞቹ ናቸው? በአማራ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሰው ኃይል ጥናትና የሥራ ስምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ጌታሰው መንጌ፤ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተጋላጭ ከሆኑ ክልሎች አንዱ የአማራ ክልል መሆኑን ይናገራሉ። የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር በድብቅ የሚፈፀም በመሆኑ ቁጥራቸው ይህን ያህል ነው ብሎ ማስቀመጥ ባይቻልም ሊሻገሩ ሲሉ በድንበር አካባቢ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ግን መጥቀስ እንደሚቻል ያስረዳሉ። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ዓመት ብቻ በሰመራ በኩል ወደ ጂቡቲ ሲሄዱ 545 ሰዎች ተይዘው ወደ አካባቢያቸው ተመልሰዋል። በመተማ መስመርም የስደተኛ ማቆያ ማዕከል ስላለ በየጊዜው በርካቶች ተይዘው ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ ይናገራሉ። "በአብዛኛው ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበትን የመተማን መንገድ ለመሸሽ የአብርሃጂራን መንገድ ይመርጡታል" የሚሉት ኃላፊው በዚህ ዓመትም 290 የሚሆኑ ሕገ ወጥ ስደተኞች ድንበር አካባቢ ተይዘው ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸውን ያስታውሳሉ። እነዚህ ስደተኞች ከአማራ ክልል ብቻ ሳይሆኑ ከደቡብ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአዲስ አበባ እና ሶማሌ ክልል የመጡ መሆናቸውንም ዳይሬክተሩ አክለዋል። ስደተኞቹ በአብዛኛው ሴቶች ሲሆኑ 40 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ህፃናት ናቸው። እንደ ዳይሬክተሩ ከሆነ በክልሉ ካሉ አካባቢዎች በአብዛኛው የሚሰደዱት ከምሥራቁ የአማራ ክፍል [ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሚያ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ] ነው። ይሁን እንጂ "ከሌሎች አካባቢዎች የሉም ማለት አይደለም" ብለዋል። የፓስፖርት ክልከላን ጨምሮ ሕገ ወጥ ስደትን ለመቀነስ የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም አሁንም በሥራ አጥነት እና በአገር ውስጥ ባለው መፈናቀል ምክንያት ቁጥሩ እየጨመረ እንደመጣ ዳይሬክተሩ ያብራራሉ። "በሕጋዊ መንገድ የሥራ ስምሪት ለማድረግ፤ ያውም በቂ ቅስቀሳ ሳይደረግ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ተመዝግበዋል። ይህም ዜጎች ሕጋዊ በሆነ መንገድ የመሄድ ፍላጎት እንዳላቸው ያየንበት ነው" ሲሉ፤ ይህ ባይሆን ኖር ይህን ያህል ቁጥር ያለው ሰው በሕገ ወጥ መንገድ ሊሄድ ይችል እንደነበር ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። እስካሁን ከአማራ ክልል በሕገወጥ መንገድ ሄደው ሕይወታቸው ያለፉ ስደተኞች ምን ያህል እንደሆኑ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸውም አክለዋል። • የዘንድሮ ተመራቂዎች እንዴት ሥራ ያገኛሉ? በትግራይ የደቡብ [ራያ] እና ምሥራቅ ዞኖች [አዲግራት፣ ውቅሮ፣ ኢሮብ... ] በሕገ ወጥ ስደት በስፋት የተጠቁ ዞኖች መሆናቸው ከክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊና ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የትግራይ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ክትትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን ገ/ሕይወት እንዳሉት አብዛኞቹ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ስደት የሚያቀኑት ወጣቶች ሲሆኑ ከእነዚህ መካከልም የሴቶቹ ቁጥር ከፍ ያለ ነው። እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሁሉ በኦሮሚያ ክልልም አብዛኛው ለዚህ ሕገ ወጥ ጉዞ ተጋላጭ የሆኑት ታዳጊዎችና ወጣቶች ናቸው። በኦሮሚያ ክልል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ጠይቡ፤ ከክልሉ ለሕገ ወጥ ስደት የሚዳረጉት እድሜያቸው ከ12 ዓመት ጀምሮ ያሉ ታዳጊዎች መሆናቸውን ይናገራሉ - በቅርቡ ወደ አረብ አገራት ሲሰደዱ ተይዘው ከተመለሱት መካከልም ስልሳዎቹ ህፃናት መሆናቸውን በመጥቀስ። አቶ መሐመድ እንደሚሉት በክልሉ በአብዛኛው የሚሰደዱት ከስድስት ዋና ዋና ዞኖች ሲሆን እነሱም ጅማ፣ ባሌ፣ አርሲ እና የምዕራብ አርሲ ዞኖችን በዋነኛነት ይጠቅሳሉ። "በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሌሎች አገራት የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ይሄ ነው ተብሎ ባይታወቅም ቁጥሩ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው" ብለዋል- አቶ መሐመድ። መውጫ በሮች... ከትግራይ ክልል በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ባህር ማዶ ለመሻገር የሚሞክሩት የሚጠቀሙበት የአፋር-ጅቡቲ መስመር አንዱ ሲሆን፤ ወደ አውሮፓ ለመሄድ ያሰቡ ደግሞ በሁመራ-ሊቢያ እንዲሁም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋን እንደ አማራጭ በመጠቀም ወደ ሳዑዲ አረቢያና የመን እንደሚያቀኑ አቶ ሰለሞን ይናገራሉ። አቶ ጌታሰውም ከአማራ ክልል በሕገ ወጥ መልኩ ሰዎች ከሚሰደዱባቸው መስመሮች መካከል ሦስት መውጫ በሮችን በዋናነት ይጠቀሳሉ። አንደኛው በጅቡቲ አድርጎ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚያደርስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በመተማ በኩል ሱዳን - ሊቢያ ከዚያም ወደ አውሮጳና ሳዑዲ አረቢያ ጉዞ የሚደረግበት ነው፤ በዚህ ድንበር ከፍተኛ ቁጥጥር ስለሚደረግ ሕገ ወጥ ስደተኞች እምብዛም አይደፍሩትም። ሌላኛው አዲስ የተከፈተው የአብርሃጂራ መንገድ ነው። አቶ መሐመድ በበኩላቸው ከኦሮሚያ ክልል የሚሰደዱትም ሁለት ዋና ዋና መንገዶችን እንደሚጠቀሙ ያስረዳሉ። አንደኛው በአማራ ክልል በኩል በማቋረጥ በመተማ አድርገው ወደ ሱዳን እስከ ሊቢያ የሚደረግ ጉዞ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጅቡቲ በኩል ወደ የመንና ሌሎች የአረብ አገራት ለመጓዝ ጥቅም ላይ የሚውለው መንገድ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በሕገ ወጥ መንገድ ኬንያንና ታንዛኒያን አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረግ የስደት ጉዞ እንዳለም አቶ መሐመድ ገልፀዋል። የአፍሪካ የስደተኞች መውጫ መንገዶች ለምን ይሰደዳሉ? ዜጎች በሕገወጥ መንገድ የሚሰደዱባቸው ምክንያቶች የተለያዩ ናቸው የሚሉት አቶ ጌታሰው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አገር ውስጥ ያለው መፈናቀል ቁጥሩን እንዳባባሰው ይናገራሉ። ሥራ አጥነትም ሌላው ዐብይ ምክንያት ነው። ዜጎች ተምረው፤ ተመርቀው ሥራ የሚያጡበት ሁኔታ በመኖሩና በሥራ ፈጠራ ዘርፍ ላይ አመርቂ ሥራ ባለመሰራቱ ዜጎች ስደትን እንደ አማራጭ ይወስዱታል ብለዋል። ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያት ያቋረጡና አማራጭ የለንም ብሎ የሚያስቡ፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን የሚሸሹ፣ የሕገ ወጥ ደላሎች አቅጣጫና ስልቱን የለወጠ ቅስቀሳም ሰበብ ናቸው። "ችግሩን ለመፍታት የውጭ አገር ሕጋዊ የሥራ ስምሪትን ጨምሮ የተለያዩ መፍትሄዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ" የሚሉት ዳይሬክተሩ ሕብረተሰቡ ችግሩን እንዲገነዘብ እየሰሩ ቢሆንም ይህን ለማድረግ የሚመደበው በጀት አነስተኛ በመሆኑ በርካቶችን መድረስ አለመቻሉን ይናገራሉ። አቶ ሰለሞን ገ/ሕይወት በበኩላቸው 'የተሳሳተ' ብለው በሚገልጹት ወጣቶቹ በሚሄዱባቸው የውጭ አገራት የተሻለ ነገር ይገኛል በሚል እምነት፣ በአቻና ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ግፊት ከአገር ለመውጣት የሚገደዱባቸው ምክንያቶች እንደሆኑ ያስቀምጣሉ። "ሁሉም ትምህርት የጨረሰ፤ ተመርቆ ሥራ ይቀጠራል ማለት አይደለም። ሥራ አጥነት፣ ማጉላላትና አስፈላጊውን አገልግሎት አለመስጠት የለብም አንልም። በተቻለ መጠን ግን በአገራቸው ሰርተው የሚቀየሩበት እድል አለ" በማለት አብዛኛዎቹ በሕገ ወጥ መንገድ ለመሄድ ሲሉ የሚይዟቸው ሰዎች ማንነት በሚጣራበት ጊዜ መኪና እና ቤት ያላቸው መሆናቸውን ያስረዳሉ። "የሚጠቀሙት መንገድ የተወሳሰበ ሲሆን ሰፊ ኔትዎርክ አላቸው። ይህ ትልቁ ችግራችን ነው። ሲያዙም የሚገጥማቸው ቅጣት አስተማሪ አይደለም፤ አንዳንዶቹ በዋስ ሁሉ ይፈታሉ። የፍትህ አካላት አስተማሪ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ግን ሥራው ራሱ ያሳየናል" ሲሉ ለሕገወጥ ስደት ትልቁ ችግር የሕገወጥ ደላሎች ጉዳይ እንደሆነ ያሰምሩበታል። • ህገወጡ የአረብ አገራት ጉዞ በአዲሱ አዋጅ ይገታል? • ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም? በዚህም ምክንያት በየጊዜው ከክልሉ የሚወጡ፣ አደጋ የሚደርስባቸውና የሚሞቱ ስደተኞች በውል ማወቅ እንደማይቻል በመግለጽ ቁጥሩ የማይናቅ ወጣት ግን ከአገር ለመውጣት ሕጋዊ ያልሆኑ መንገዶች እንደሚጠቀም ገልጸዋል። የኦሮሚያ ክልል ሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ኃላፊም የተለየ ሃሳብ የላቸውም። ለሕገወጥ ስደቱ እንደ ምክንያት የሚያነሱት ሥራ አጥነትን ሲሆን ሌሎች ደግሞ የተሻለ ሕይወትንና ሐብትን ፍለጋ አልመው የሚሄዱ እንዳሉም ተናግረዋል። በተለያዩ ጊዜያት በሕገ ወጥ መንገድ የሚጓዙት ዜጎች በባህር ሰጥመው ሕይወታቸው ሲያልፍ በመንገድ ላይ የተለያየ ችግር ሲገጥማቸው ሪፖርት እንደሚደርሳቸውም ኃላፊው አክለዋል። ለችግሩ እልባት ለመስጠት ምን እየተሰራ ነው? በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ 50 ሺህ የሚጠጉ ሠራተኞችን ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለመላክ እቅድ እንደተያዘ አስታውቀው ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን ወደ ኤዥያና አውሮፓ ሃገራትም የሠለጠነ የሰው ኃይል በሕጋዊ መንገድ ለመላክ እንደታሰበ መናገራቸው ይታወሳል። ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሥራ ስምሪት መጀመሩንና ወደ እስያና አውሮፓም የሠለጠነ የሰው ኃይል ለመላክ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ዳይሬክተር ብርሃኑ አበራ ለቢቢሲ ገለፀዋል። ይህንኑ አስመልክተን የጠየቅናቸው አቶ ጌታሰው ከአማራ ክልል ምን ያህል ሥራ ፈላጊዎች በዚህ ስምሪት ውስጥ እንደሚሳተፉ ለጊዜው ባያውቁም ለዚህ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ይናገራሉ። በክልሉ ካሉ 125 የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎችም ብዙዎቹ የሥራ ውል እያፀደቁ ነው። እስካሁን በአንድ ኤጀንሲ አማካኝነት ከ16 በላይ ሴቶች ወደ ሳዑዲ በቤት ሠራተኝነት በሕጋዊ መልኩ መላካቸውን ያስታውሳሉ። በክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ መዋቅር 20 ሺህ ሰዎች ተመዝግበው 10 ሺህ 434 ሰዎችን አሰልጥነው ማጠናቀቃቸውን ይናገራሉ። 20 ሺህ ሰዎችን ለማሰልጠን በመንግሥት የተመረጡ የሥልጠና ማዕከላት ከአንድና ሁለት በላይ የሙያ ዘርፍ ሥልጠና የመስጠት አቅም ስለሌላቸው የግል ማዕከላትን አካቶ በ48 የሥልጠና ማዕከላት ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል። በመሥሪያ ቤቱ ባሉት መዋቅሮች ፍላጎት ያላቸውን ሥራ ፈላጊዎች አዋጁ በሚፈቅደው መሠረት ምዝገባ ማካሄዳቸውን ሳይጠቅሱ አላለፉም። ዳይሬክተሩ እንደገለፁልን የሥራ ዘርፎቹ፤ የቤት ውስጥ ሠራተኝነት፣ የቤት ውስጥ ሥራና የቤት አያያዝ፣ ሹፌር፣ ነርስ ሲሆን ተፈላጊ ብቃቱ እንደ ሥራ ሁኔታው ቢለያይም ለቤት ውስጥ ሠራተኛነት ቢያንስ ስምንተኛ ክፍል ያጠናቀቁ፣ በሰለጠኑበት ዘርፍ የሙያ ብቃት ወስደው ያለፉ፣ የጤና ምርመራና አሻራ ጨርሰው እንዲሄዱ ይደረጋል ብለዋል። በነርስነት ሙያ አሰሪዎችና በተቀባይ አገራት ያለው ፍላጎት በሚያቀርቡት መሠረት እንደሚከናወንም ገልጸዋል። ስደትን ጠቅልሎ ማስቆም እንደማይቻል የሚናገሩት አቶ ሰለሞንም ቢያንስ በሕጋዊ መንገድ ወደ 'ሚፈልጉት አገር ሄደው በክህሎት እና በብቃት ሠርተው ተጠቃሚ የሚሆኑበት አማራጭ መኖሩን መገንዘብ አለባቸው ባይ ናቸው። መንግሥት ስምምነት ከደረሰባቸው አገራት ጋር ሠራተኞችን በሕጋዊ መንገድ አሰልጥኖ መላክ የሚያስችለው አሰራር በመተግበሩ በአሁኑ ሰዓት በቤት አያያዝ፣ ህጻናት እንክብካቤ እና በሾፌርነት በመንግሥት እና በግል ተቋማት ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን አቶ ሰለሞን ይጠቅሳሉ። አቶ መሐመድ እንደሚሉት ይህንን ሕገ ወጥ ስደትን ለመቀነስ እና ዜጎችም በሕጋዊ መንገድ ሰርተው ለራሳቸውና ለአገሪቱ እንዲተርፉ ለማድረግ መንግሥት አዲስ ሕግ በሥራ ላይ እያዋለ ይገኛል ብለዋል። ከዚህም ባሻገር በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያዘዋውሩ ደላሎች ላይ እርምጃ መውሰድን ለማጠናከርና ለማህበረሰቡ የግንዛቤ መስጫ ሥራዎችን በስፋት ለመስራት መታሰቡን ለቢቢሲ ተናግረዋል። • ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው ሚክስድ ማይግሬሽን ሴንተር የተባለ የመረጃና የጥናት ተቋም በድረ ገጹ ላይ በ2019 ሁለተኛው ሩብ ዓመት ባወጣው ሪፖርት ከሦስት ወራት በፊት ወደ ጎረቤት አገር ሶማሊያ የሚገቡና የሚወጡ ስደተኞች ቁጥር [የመን፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ጂቡቲ] በ41 በመቶ ጨምሯል። ከአምስት ወራት በፊት ደግሞ ወደ 19 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያን የመን መግባታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል። በግንቦት ወር መጨረሻ የመን የገቡ ስደተኞች ቁጥርም 74 ሺህ በላይ እንደሆነ አመልክቷል። በሪፖርቱ እንደተገለፀው በሚያዚያ ወር በትንሹ 40 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን በየመን የባህር ዳርቻ ላይ ሕይወታቸው ሲያልፍ ይህ መንገድ በተለይ ከምሥራቅ አፍሪካ የሚመጡ ስደተኞች የመን ለመድረስ የሚጠቀሙበትና እጅግ አደገኛው ነው። አብዛኞቹ ስደተኞች በሊቢያ ተይዘው እስር ቤቶች ስለሚገቡ የሜደትራኒያንን ባህር አቋርጠው የአውሮፓን ምድር የሚረግጡት ስደተኞች ቁጥር ቀንሷል። በዘንድሮው ዓመት ከምሥራቅ አፍሪካ ወደ አውሮፓ የገቡት ስደተኞች ቁጥር ከ50 የሚያንስ መሆኑን ሪፖርቱ ጠቅሷል። ከተጠቀሱት ክልሎች ውጪ ባሉ የሃገሪቱ አካባቢዎችና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ስላለው በሕገ ወጥ መንገድ የሚደረገውን ስደት በተመለከተ ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።
news-52635913
https://www.bbc.com/amharic/news-52635913
የመቅመስና የማሽተት ስሜት ሳይኖር ሼፍ መሆን ይቻላል?
በዓለም ላይ በሙዚቃ ታሪከ አዋቂዎች ዘንድ ከሚዘከሩትና ሊቅ ከሚባሉት መካከል አንዱ ቤትሆቨን ነው።
ቤትሆቨን በሙዚቃው መጠበቡ ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን የሚያስደንቀው ከ28 ዓመቱ በኋላ የመስማት ችገር አጋጥሞት 44 ዓመቱም ላይ ሙሉ በሙሉ መስማት አይችልም ነበር። መስማት ሳይችል እንዴት ሙዚቃን አቀናበረ? የሚለው ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ብዙዎችም በህይወት የሚያጋጥም ተቃርኖ ይሉታል። በካናዳ ውስጥ ታዋቂ የምግብ አብሳይ (ሼፍ) የሆነችው ጆሽና ማሃራጅም ይሄው ተቃርኖ ሊባል የሚችል ጉዳይ ገጥሟታል። ለአምስት ዓመታትም ያህል የማሸተትም ሆነ የመቅመስ ስሜቷን እንዳጣችም ከወራት በፊት ይፋ አድርጋለች። •"ሞትን ተሻገርኳት" ከኮሮናቫይረስ ያገገመች ሴት •በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ ያጣችውንም የስሜት ህዋሷን ለመመለስ እንዲሁ እየደከመች ነው። በመጀመሪያ ያጣችው የማሽተት ስሜቷን ሲሆን እንዲሁ በአንድ ሌሊት አይደለም። ቀስ በቀስ ነበር። በመጀመሪያው ላይ ምግብ ማሳረር ጀመረች፤ የኮክ ኬክ እየጋገረች፣ ቀምበር ማለት ቢኖርበትም ማሽተት ባለመቻሏ አሮ ወጣ። "አንዳንዴ ያረረውን ቆርሶ ማቅረብ ይቻል ይሆናል። በዚህ ወቅት ግን ሙሉ በሙሉ በማረሩ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ተጣለ" ትላለች። በሌላ አጋጣሚም እንዲሁ ከጓደኞቿ ጋር ታዋቂ የሥጋ ጥብስ የሚሸጥበት ሬስቶራንት እያለፉ፤ ጓደኞቿ በሥጋው ጥብስ መዓዛ ሲደመሙ እሷ ግን ምንም ማሽተት አልቻለችም። "መጀመሪያ አልገባኝም ነበር ችግሩ፤ በኋላም ሁኔታዎችን ስከታተል፤ አፍንጫዬ ማሽተት አይችልም የሚለው ተገለፀልኝ" ትላለች። "እውነቱን ለመናገር በወቅቱ መንፈሴ በሙሉ ነው የተረበሸው። ማሽተት ሳልችል እንዴት ሼፍ እሆናለሁ የሚለውም ያስጨንቀኝ ጀመር። ሥራዬን ላቁመው የሚለውም ሃሳብ ይመላለስብኝ ነበር" ትላለች። ሆኖም የሆዷን በሆዷ ለማድረግ ወሰነች "ምስጢርሽን ትደብቂያለሽ፤ ማንም ቢሆን መስማት የለበትም" በማለትም ከእራሷ ጋር ንግግር አድርጋ ወሰነች። ቶሮንቶ ተወልዳ ያደገችው ጆሽና፤ የሥርዓተ ምግብ መብት አቀንቃኝ፣ ደራሲ ስትሆን በዓለም ላይ ካሉ ታዋቂ የሕዝብ ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎችና ሆስፒታሎች ምግብ በምን መንገድ ማብሰል እንዳለባቸውና ለአቀራረቡም የተለየ እሳቤ በማምጣት ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ችላለች ይሏታል። በአሁኑ ወቅት ግን 'አኖሶሚያ' በሚባል በሸታ ተጠቅታለች፤ በሸታው ሙሉ በሙሉ የማሽተት የስሜት ህዋስን የሚያጠፋ ነው። በዓመታት ውስጥ ምግብ መድረስ አለመድረሱን በሽታ መለየት ትችል የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ወደ ሰዓት መሙላትና የቅመም መጠናቸው ከፍተኛ ወደሚባሉ ምግቦችም ተሸጋገረች። ጠንካራና ሸታ ያላቸውን ቅመሞች መጨመር፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል እንዲሁም በቅመም ያበደውን የህንዱን ከሪ ማብሰል ጀመረች። የማሽተትና የመቅመስ ስሜት ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን ተከትሎ የመቅመስ ስሜቷንም ያጣችው ወዲያው ነው። አኖሶሚያ የሚባለው ህመም በተለያዩ ምክንያቶች ይመጣል፤ በቀላሉ በቫይረስ ከመጠቃት ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የአዕምሮ ጉዳት አኖሶሚያን ያስከትላል። በቅርቡም ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ውስጥ ብለው ከጠቀሷቸው ውስጥ የመቅመስና የማሽተት ስሜትን ማጣት ይገኙበታል። ጆሽና ማሃራጅም ለዓመታት ያህል በሳይነስ አለርጂ ትሰቃይ ነበር፤ በተደጋጋሚም ከአንገቷ በላይ ባለው የመተንፈሻ አካሏ ችግርም መፍትሄ ልታገኝለት አልቻለችም ነበር። አፍንጫዋም ስለሚታፈን መተንፈስም ከባድ ነበር። "ያልሞከርኩት አይነት ህክምና የለም። የቻይና የአገር በቀል መድኃኒት፣ ምግብ መቀየር፣ አኩፓንክቸር እንዲሁም በተደጋጋሚ በአፍንጫ የሚወሰድ መድኃኒት ወስጃለሁ" ትላለች። በባለፈው ዓመትም ይህንኑ ለማስተካከል ቀዶ ጥገና አድርጋ በወራት ውስጥም የማሽተት ስሜቷ ትንሽ ተመለሰ። የህንዷን ባንጋሎር ግዛት እየጎበኘች ባለችበት ወቅት ድንገት የማንጎ ሽታ ሸተታት፤ ራሷን ተጠራጠረች። ሆቴሏም ስትመለስ በእንግዳ መቀበያው አካባቢ የአበባ ሽታ ሸተታት። ሆኖም በሚያሳዝን ሁኔታ ማሽተትም ሆነ መቅመስ የቻለችው ለሁለት ሳምንታት ብቻ ነበር። በተለይም ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ክሮሺያ በሄደችበት ወቅት ሁኔታው በጣም ከብዷት ነበር። ቤተሰቧ ጋር የተለያዩ ሬስቶራንቶች ሄደው የምግቡን ጣዕም ሲያመሰግኑ፣ በምግብ ሽታ ሲደመሙ ለእሷ ግን ሁሉ ነገር ባዶ ነበር። ያልናፈቀችው አይነት ሽታ የለም። ነጭ ሸንኩርት፣ ዝንጅብል ቁሌት፣ የአራስ ልጅ ሽታ... "ጓደኛዬ ከወራት በፊት ስትወልድ ፊቴን አስጠግቼ ጨቅላውን ለማሽተት ሞከርኩ። ምንም ነገር አልሸተተኝም። በጣም ነው ልቤ የተሰበረው፤ ሐዘኔ ጥልቅ ነው" ትላለች። ይባስ ብሎ ማሸተት ከተለያዩ የሰው ልጅ ስሜቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው አንድ ጓደኛዋ ነግሯት ጠለቅ ብላም የተለያዩ ምርምሮችን ማንበብ ጀመረች። የማሽተት ስሜት ማጣት ለድብርት፣ ጭንቀት እንደሚያጋልጥም መረጃዎችን አገኘች። ይህንኑም ተከትሎ ስለህመሟ ለሌሎች ሰዎችም መናገር እንዳለባትና መፍትሔም መፈለግ እንዳለባት ተረዳች። በኢንስታግራም ገጿም ላይ ስለ ችግሯ ፃፈች። በመቀጠልም እንደ አዲስ የማሽተት ስልጠናንም መውሰድ ጀመረች፤ አዕምሮዋንና አፍንጫዋን የሚያገናኘውንም መስመር ለመጠገንም ህክምና እንደገና ጀመረች። በለንደን ተቀማጭነቱን ያደረገና የሽታና የመቅመስ ስሜታቸውን ላጡ እንደገና የሚመልሱበትን፤ እንዲሁም ግንዛቤ በማዳበር ላይ የሚሰራ 'አብሰንት' የሚባል ድርጅትም አገኘች። በዓለም ላይ 5 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ የማሽተት ስሜት በማጣት እንደሚሰቃይ መረጃዎች ይጠቁማሉ። "የተለያየ ምግብ መብላትና መጠጥ መጠጣት ለሚወዱ፤ ማብሰልን ለሚናፍቁ ሰዎች የማሽተትና የመቅመስ ስሜትን ማጣት ማለት ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ መግባት ነው" ትላለች። ከዓመታት በፊት ማሽተትን ብዙም ልብ ብላ አስባው አታውቅም ነበር። ነገር ግን ስታጣው የቤቷ ሽታ ይናፍቃታል፣ የታጠበ ልብስ. . . ምን የማይናፍቃት ነገር አለ። የተለያዩ ምርምሮች እንደሚጠቁሙት ምንም እንኳን የማሽተት ስልጠና ሙሉ በሙሉ ማሽተትን ባይመልስም የአእምሮ ነርቮችን በማነቃቃት እንዲያገግሙ ለማድረግ ይቻላል። ለአፍንጫ የቴራፒ ህክምና እንደመውሰድ ማለት ነው። ስልጠናውም ሽታቸው ጠንካራ የሆኑ ዘይቶች፣ በተለይም የፍራፍሬ ዘይት ያላቸው በመጠቀም የሚሰጠጥ ነው። አራት አይነት ዘይቶችን፤ እያንዳንዱን ለሃያ ሰከንዶች በቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ማሽተት። በተቻለ መጠን የማሽተቱን ስሜትን መመለስ ብቻ ሳይሆን አእምሮንም ከዚህ ቀደም ያንን ሸታ እንዲያስታውስ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል። ጆሽና ማሃራጅም የባህር ዛፍ፣ ሮዝ አበባ፣ ሎሚና ቅርንፉድ ዘይቶችን መረጠች። ቁጭ ብላም መጀመሪያ የባህር ዛፉን ዘይት እያሸተተች በጭንቅላቷ ስቲም የሚወሰድበት ክፍልን ታስባለች፤ ሎሚን ስታስብ ደግሞ ሎሚ ሲጨመቅ የነበረውን ሽታ አእምሮዋ እንዲያስታውሰው ትጥራለች። የሮዝ አበባንም ከዓመታት በፊት ያሸተተችውን ጣዕሙ ለስለስ ያለውን ለማስታወስ በጭንቅላቷ እያሰላሰለች ትሞክራለች። ለጆሽና ማሃራጅ ሸታም ሆነ መቅመስ ከትዝታዋ ጋር በጣም የተቆራኘ ነው። የቅርንፉድ ሽታ ከልጅነቷ የገና ወቅት እንዲሁም ለክረምት ምግብ ሲቁላላ የነበረው የቅመሙን ሽታ፣ ትንሽ የሚያቃጥል ጣዕምን በጭንቅላቷ ለማስታወስ ከፍተኛ ትግል ታደርጋለች። ለአንድ ወርም ያህል ምንም ነገር ማሸተት አልቻለችም። በቅርቡ ግን የባህር ዛፍም ሳይሆን የቅርንፉድ የሆነ ሽታ ብልጭ አለላት። ሽታው ምን እንደሆነ ለመለየት ብትታገልም ማወቅ አልቻለችም። ቀስ በቀስም የማሸተት ስሜቷ ቢመለስም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ጠፋ። 'አብሰንት' እንደሚለው የሽታን ስሜት ጭላንጭሉን ለማምጣት ቢያንስ አንድ ወር ይፈጃል። ሆኖም ለጆሽና የማሽተት ስሜት ባይኖራትም የቅምሻ ጣዕሟ በትንሹም ቢሆን ተመልሷል። በተለይም ታበስል የነበረው በትዝታ ከመሆኑ አንፃር አሁንም ትንሽም ቢሆን ማጣጣም መቻሏ አስዳሳች ሆኖላታል።
49274621
https://www.bbc.com/amharic/49274621
ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ
ዘሩባቤል ሞላ፤ እንፋሎት በተሰኘ አዲስ አልበም ብቅ ብሏል። እንፋሎቱ ደግሞ ከአዲስ አበባ እስከ ናይሮቢ፤ ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ ሁሉን እያዳረሰ ነው።
አልበሙ 15 ሙዚቃዎችን ይዟል። ሃገርን፣ ፍቅርን፣ ጉበዝናን፣ ሕይወትን፤ በመንፈሳዊ ቃና ይዳስሳል፣ ያነሳሳል፣ በግጥም ብቻ ሳይሆን በዜማም ይፈውሳል፤ እንፋሎት። እንፋሎት መቼ ተፀነሰ? ቢቢሲ አማርኛ ለዘሩባቤል ሞላ ያቀረበው የመጀመሪያው ጥያቄ. . . «ያው እንግዲህ አርቲስት ስትሆን፤ ወይም ደግሞ ጊታር ይዞ እንደሚጫወት አንድ ዘፋኝ ራስህን ካየህ አንድ ዓላማ ይኖርሃል፤ አልበም የሚባል። ነጠላ ዜማም ሊሆን ይችላል። ይህንን ሥራ ለመሥራት ወደ አምስት ዓመት ገደማ ፈጅቶብናል። ወደ መጨረሻ አካባቢ ላይ የገቡ አዳዲስ ሥራዎችም አሉ። ሙዚቃዎቹን ከሠራን በኋላ አሁን በቅቷል፤ እንፋሎቱ ወጥቷል፤ ሰው ሊመገበው ወይም ሊሰማው ይገባል ብለን ስናስብ ነው ይህንን አልበም ያወጣነው። ግን በጠቅላላው አምስት ዓመት ገደማ ፈጅቶብናል፤ ያው አንዱን ስንጥል አንዱን ስናነሳ።» • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች የመካኒሳ ሴሚናሬ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ልጅ ነው ዘሩባቤል። መቅረዝ የተሰኘው የፕሮቴስታንት እምነት የሙዚቃ ቡድን አባልም ነበር። ሚካኤል በላይነህ 'የነገን ማወቅ' ብሎ ባቀነቀነው ሙዚቃ ቪድዮ ክሊፕ ላይ ጊታሩን ይዞ ሲወዛወዝ ብዙዎች ተመልክተውታል። ወገኛ ነች፣ እስከመቼ፣ እንደራሴ፣ ልብሽ ይፋካ. . . ከዘሩባቤል ቀደምት ሥራዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። «ሙዚቃን በሥርዓቱ የያዝኩት፤ ወይም የእኔ የተሰጠኝ ችሎታዬ ይሄ ነው ብዬ ያመንኩበት ሰዓት መቅረዝ የሙዚቃ ቡድን ውስጥ እያለን ነው፤ ረዘም ያለ ጊዜ ነው። አስራምናምን ዓመት ገደማ መሆኑ ነው።» «ሁሉም ሥራዎቼ መንፈሳዊ ናቸው. . .» ዘሩባቤል ሙዚቃን 'ሀ' ብሎ የጀመረው መቅረዝ ውስጥ ነው፤ መንፈሳዊ ሙዚቃ በመጫወት። 'መንፈሳዊ ተብሎ ከሚታወቀው የሙዚቃ ዘርፍ ወደ ዓለማዊው መጥቻለሁ ብለህ ታስባለህ?' «እውነት ለመናገር ለእኔ ሁሉም መንፈሳዊ ናቸው። ዓለማዊ ተብሎ የሚታሰበውም መንፈሳዊ ነው። የሚያስተላልፈው መልዕክት ምንድነው የሚለው ነው። ዓለማዊ የተባለውም እኮ ዓለማዊ ያስባለው ከበስተጀርባው ያስተላለፈው ደስ የማይል መልዕክት አለ ማለት ነው።» እንፋሎት፤ መነሳሳትን የሚሰብኩ፤ ጥንካሬን የሚያጋቡ፤ መልካምነትን የሚያስተጋቡ ሙዚቃዎች ስብስብ ነው። እንደው ይህ መንፈስ የመጣው ሥራዎቼ መንፈሳዊ ናቸው ብለህ ከማሰብህ ነው ወይ? ለዘሩባቤል ያነሳንለት ጥያቄ። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን «አዎ። ሰው አልበምህን ሰምቶ ያዘነ እንዲፅናና፣ የደከም እንዲበረታ፣ የወደቀ እንዲነሳ፣ በአንተ ዘፈን፤ አንተ በሠራኸው ሙዚቃ ይህንን መልዕክት ማስተላለፍ ካልተቻለ. . .እንግዲህ ምንድነው መፈጠራችን ዋናው ዓላማው። ሰው ሲሰማው መፅናናትን ካላገኘ፤ የአልበም ማውጣት ምንድነው ጥቅሙ? ይሄ የእኔ እምነት ነው ከድሮም ጀምሮ። አንድ የሆነ ይዘት ያለው ሙዚቃ ይዘህ መጥተህ ሰው ሲስቅ፣ ሲዝናና፣ ሲነሳሳ ማየት በጣም ትልቅ ደስታ ነው፣ ዕድልም ነው፤ እውነት ለመናገር።» ዘሩባቤል ከአልበሙ በፊት የለቀቃቸው ነጠላ ሥራዎቹ በቪድዮ ክሊፕ ተቀምረዋል። ታድያ እኒህ ቪዲዮዎች በጎ መልዕክትን ለማስተላለፍ ያለሙ ናቸው። «አንዳንዴ ቤት ቁጭ ብዬ ከቤተሰብ ጋር የማያቸው የሙዚቃ ክሊፖች እጅግ በጣም የሚያሳፍሩና አባቴን ቀና ብዬ እንዳላየው የሚያደርጉ ናቸው። እኔ የምሠራቸው ክሊፖች ማንም ሰው ሊያያቸው የሚችሉ፤ እናት ከልጇ ጋር ቁጭ ብላ፤ አባት ከልጁ ጋር ቁጭ ብሎ ሊያያቸው የሚችላቸው መሆን አለባቸው ብዬ ነው የማምነው። ቤተ-ዘመድ እያየው የማያፍርበት ቪዲዮ መሆን አለበት። መልዕክት ያለው ቪዲዮ መሥራት ነው የሚያስደስተኝ።» መንፈሳዊና ዓለማዊ ሙዚቃን የምትለየው ቀጭን መስመር ዘሩባቤል 'አባቴ ዘፈን ሐጥያት ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ነው' ሲል አጫውቶኛል። ይህ እምነታቸው ደግሞ የመጣው ከመፅሐፍ ቅዱስ ነው። ከእንደዚህ ዓይነት ቤተሰብ ውጥቶ 'ዓለማዊ' ተብሎ ወደሚታሰበው ሙዚቃ መምጣት ነገሩን አያፈርሰውም ወይ? በመንፈሳዊ እና ዓለማዊ ሙዚቃ መካከል ያለችው ቀጭን መሥመር ምንድን ነች? ለዘሩባቤል የቀረበ ጥያቄ። «እኔ ምንድነው የማምነው. . . ዘፈን ሐጥያት አይደለም እያልኩ አይደለም። ለምሳሌ አመፅን የሚያነሳሱ ዘፈኖች፣ አድመኝነት የሚያነሱና ዝሙትን የሚያበረታቱ ሐጥያት የሆኑ ዘፈኖች አሉ። ግን መልካም ነገር ዘፍነህ፤ ፍቅርን ሰብከህ፤ የዋህነትን አስተምረህ ሐጥያት የሚሆንበት መንገድ እኔ አይታየኝም። ሳነብም በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የሚቃወመኝ ቦታ የለም። ማንም ሰው የሠራው ሥራ የሚያንጽ ከሆነ ይሄ መልካም ዘፈን ነው።» • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ «ይህን ቀጭን መስመር የሆነ ቀን ሳነብ ገባኝ፤ ተረዳሁ። አንደኛው የአንደኛውን ጎሣ የማይነካበት፤ አንደኛው የአንደኛውን ሚስት የማይነካበት፤ አመፅ የማያስነሳበት የትኛውም ዘፈን ልክ ነው ማለት ነው።» «'እንደ ቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ' ሲል ምክር እየሰጠ ነው፤ ሌላውን እንዳትመኚ እኮ እያላት ነው። አንድ ሰው ይሄ ሐጥያት ነው ሲኦል ያስገባሃል ካለ አንድ የሆነ የሳተው ነገር አለ ማለት ነው። 'ተማር ልጄ እያለ' የሚመክርህን ይህ ሐጥያት ነው የሚል ከሆነ አሁንም ችግር አለ ማለት ነው። አባቴ ባይቃወመኝም እኔ ማለት የፈለግኩት ሃሳብ እየገባው የመጣ ይመስለኛል።» ባቲና ብሉዝ ብሉዝ [ስም ቀየርንለት እንጂ ባቲ እኮ ነው ይላል ዘሩባቤል]፣ ጃዝ፣ ለስለስ ያለ ሮክ. . .እንፋሎት ውስጥ ከምናደምጣቸው ቀለመ-ብዙ ዜማዎች ጥቂቶቹ ናቸው። እኒህ ዜማዎች ለኢትዮጵያዊ ጆሮ እምብዛም የተለመዱ አይደሉም። ዘሩባቤል ግን ይዟቸው ብቅ ብሏል፤ ለዚያውም በመጀመሪያ አልበሙ። መሰል ዜማዎችን ይዞ በመጀመሪያ አልበም መምጣት እንደው ድፍረት አይጠይቅ ይሆን? • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" «እውነት ለመናገር ይህንን ነገር አንትም ሆነ ሌሎች አድማጮች ሲሉት ነው የሰማሁት እንጂ እኔ አላውቀውም። እውነት ለመናገር ለእኔ የምዘፍነው አዘፋፈን ሃገርኛ፣ ኢትዮጵያዊኛ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። ብሉዝን ለመሥራት ስፈልግ ብሉዝ አድርጌ እሠራለሁ። ለምሣሌ 'ውሃና ዘይት' የተሰኘወ ሥራዬ የኢትዮጵያ ዜማ ሆኖ 'ሳውንዱ' ግን ብሉዝ እንዲሆን አድርገነዋል። ለእኔ ግን ባቲ ነው። ስሙን ቀያየርነው እንጂ ባቲ ስትሰማ ብሉዝ ሰማህ ማለት ነው። እኔ ኢትዮጵያዊኛ አድርጌ ለመዝፈን የማስበውም፤ አድርጊያለሁ ብዬ የማምነውም እንደዚያ ነው።» «ሳድግም እንደዚህ ዓይነት ሙዚቃ እየሰማሁ ነው ያደግኩት። አጎቴ እንዲህ ዓይነት ዜማ ይከፍት ነበር። ጋሽ ጥላሁንን፣ እነ ጋሽ መሃሙድን፣ እነ ጋሽ አለማየሁን . . .ሌሎችንም ትልልቅ አርቲስቶችን ይከፍት ነበር። ወታደር ነበር፤ ዶክተርም ነው። ካርታ እየተጫወተ እኒህን ሙዚቃዎች ያደምጥ ነበር። ኢትዮጵያዊ ቃና እየሰማሁ ነው ያደግኩት፤ እኔም ደግሞ አሁን ሠራሁት ብዬ የማስበው ይህንኑ ነው።» ጊታር ተጫዋቹ ዘሩባቤል 'ኢትዮጵያዊያን ዘፋኞች መዝፈን ብቻ እንጂ የሙዚቃ መሣሪያ አይጫወቱም' በአለፍ ገደም የምንሰማው ትችት ነው። ይህ ሃሳብ ጊታር አሳምሮ ለሚጫወተው ዘሩባቤል አንድ ጥያቄ እንዳነሳ አስገደደኝ። የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት ነገሮችን ቀለል ያደርጋል? «ምንድነው መሰለህ እያየህ ማከም እና ዓይንህን ጨፍነህ እማከም ማለት ነው፤ ለእኔ። አንድ የሙዚቃ መሣሪያ አወቅክ ማለት የዜማው አካሄድ ይገባሃል። የሚያቀናብርልህ ሰው የሚናገረው ቋንቋ ምን እንደሆነ ይገባሃል። ታላላቅ የሚባሉ ዘፋኞች፤ ትልልቆቹን ጨምሮ ከብዙ ሂደት በኋላ የሙዚቃው ቋንቋ፤ የሙዚቃው አካሄድ ስለገባቸው ነው በሰሉ የሚያስብላቸው። የሙዚቃ መሣሪያ ማወቅ ይህንን ነገር ያሳጥርልሃል። መዝፈን የሚፈልግ ሰው የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት ቢማር በጣም ይጠቅመዋል ብዬ አምናለሁ። ለምሳሌ እኔ ጊታሬን ይዤ ቁጭ ባልኩበት ዜማ ይመጣልኛል። ጊታሬን ባልይዝ ላይመጣልኝ ይችላል። ቢመጣም ያ ነፍስን የሚነካ፤ ውስጡ ነፍስ ያለውን ነገር ላትሠራ ትችላለህ። ይሄ የእኔ አመለካከት ነው።» የልፋትን ውጤት ማየት የዘሩባቤል እንፋሎት ኢትዮጵያ ውስጥ በሲዲ በውጭ ሃገራት ደግሞ በበይነ መረብ ባሉ እንደ 'አይቲዩንስ'፣ 'ስፖቲፋይ' እና 'ሳውንድክላውድ' ዓይነት የሙዚቃ ሥራዎች ማጋሪያ ላይ እየተኮመኮመ ይገኛል። እንደው አንድ ነገር መረዳት ፈለግኩና ለዘሩባቤል ሃሳቤን ጀባ አልኩ። 'አዲስ አበባ ውስጥ መኪና ውስጥ ሆነህ፣ አልበምህ በሲዲ ሲዞር ስታይ፤ ሰዎች ሲዲህን እያገላበጡ ሲመለከቱ ስታይ፤ ምን ዓይነት ስሜት ተሰማህ ይሆን?' • ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ? «እህ. . . እውነት ለመናገር ብዙ ልፋት፣ ትግል፣ የሰው ፊት ማየት፣ ንቀት ማየት. . .እንግዲህ ይህን የምናገርበት ምክንያት ለማነፃፀርና ሰውን ስለሚያስተምር እንጂ አሁን እዚያ መንፈስ ውስጥ ሆኜ አይደለም። ካለፍክበት መከራ ወይም ደግሞ ከተራራው ትልቅነት አንፃር ስታየው፤ አልበሙ ሰዎች እጅ ላይ ደርሶ፤ ሰዎች አገላብጠው ወደዉት ስታይ በጣ...ም የተለየ ስሜት አለው። እንደውም ለተወሰነ ጊዜ ስሜታዊ አድርጎኝ ነበር። ሲዲውን አዟሪዎች እጅ ላይ ሳይ፣ ፖስተሮች ተለጥፈው ሳይ፣ በቃ እግዚአብሔርን አደንቅኩ። ለሁሉም ጊዜ አለው የሚባለውን በፊት በመስማት ነበር የማውቀው አሁን ግን በዓይኔ አየሁት። ለእኔ በጣም ለየት ያለ ስሜት ነው ያለው።» እንፋሎት አልበም ብዙ የሙዚቃ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በያምሉ ስቱዲዮ የተሠራው እንፋሎት ዘሩባቤል፤ ከግጥምና ዜማ ደራሲነት በተጨማሪ ጊታር በመጫወት ተሳትፎበታል። ሚክሲንግ፣ ማስተር እና ቅንብሩን የዘሩባቤል ወንድም የሆነው ወጣቱ የሙዚቃ ሰው ያምሉ ሞላ ተወጥቶታል። ሌላኛው ጉምቱ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ደግሞ በዜማ በግጥም እና በማቀናበር እንፋሎት ላይ አሻራውን አሳርፏል። ዳዊት ተስፋዬ ሌላኛው የዜማና ግጥም ደራሲ ነው። ሳክፎኑን አብይ፣ ማሲንቆውን ደግሞ ሃዲንቆ ተጫውተውታል። ከፍ. . .የሚያደርጉ ዜማዎች እንፋሎትን ማድመጥ አለብኝ ብሎ የመጀመሪያውን 'ትራክ' የከፈተ ሰው አንድ ነገር ማስተዋሉ ግድ ነው። የዘሩባቤል ግጥሞች ብቻ ሳይሆኑ ዜማዎቹም ጭምር መንፈሳዊ መነቃቃትን ለመስበክ ቆርጠው እንደተነሱ። • አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ «ለምሳሌ ክትፎን መብላት የለመድነው በጣባ ነው አይደል? ግጥሙን እንደ ክትፎ እይልኝ [ብዙዎቻችን ክትፎ እንወዳለን ብዬ ነው ክትፎ ያልኩት]፤ ጣባውን ደግሞ እንደ ዜማ አስብልኝ። አንድ የምትወደውን ምግብ በተገቢው ሁኔታ ሲቀርብ የመብላት ስሜትን ከፍ ያደርጋል። ልክ እንደዚያው የሚያምር ግጥም ሠርተህ ለዜማው ካልተጨነቅክ አድማጭህ ይጨነቅብሃል። ዜማ ውስጥ ነብስ አለች፤ ያንን ተረድተህ መሥራት መቻል አለብህ። ዘፈኑ ሳይጨንቅህ ጀምሮ፤ ሳታስበው ከፍታ ላይ ወጥተህ ሳታስበው ማለቅ አለበት።» ዘሩባቤል እኔ ሙዚቃዬን የሠራሁት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው ይላል። ዘፈኖቹ ማንም በዕድሜም ሆነ በሌላ መለያ ሳይገደብ እንዲያደምጣቸው ይፈልጋል። እስካሁንም ሥራዎቹን በመግዛት እያደመጡ ላሉት ሰዎች «ጎንበስ ብዬ ምሰጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ፤ እግዚአብሔር ይስጥልኝ!» ይላል።
news-47387850
https://www.bbc.com/amharic/news-47387850
መንትዮቹ ዶክተሮች፡ እየሩሳሌም ጌታሁንና ቃልኪዳን ጌታሁን
መንትዮቹ ዶ/ር ቃልኪዳን ጌታሁንና ዶ/ር እየሩሳሌም ጌታሁን ተወልደው ያደጉት በሻሸመኔ ከተማ ነው። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉትም እዚያው ነው። ከዚያም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል።
ዶ/ር እየሩሳሌም ጌታሁን (በግራ) እና ዶ/ር ቃልኪዳን ጌታሁን (በቀኝ) በአዲስ አበባ ሃያት ሜዲካል ኮሌጅ ገብተው ህክምና አጥንተዋል። አሁንም በማዕረግ ነበር የተመረቁት። ሻሸመኔ መልካ ወረዳ ሪፈራል ሆስፒታል ተመድበው የተወሰነ ጊዜ አገልግለዋል። በአሁን ሰዓት 'ትዊንስ ክሊኒክ'ን ከፍተው እየሠሩ ይገኛሉ። • ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች በትዊንስ ክሊኒክ ከህክምናው ባሻገር ዶ/ር እየሩሳሌም ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቃልኪዳን ደግሞ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ያገለግላሉ። ዶ/ር እየሩሳሌም ለዶ/ር ቃልኪዳን የ5 ደቂቃ ታላቅ ናት። ድምፃቸው፣ ቁመታቸው፣ ክብደታቸው፣ የትምህርት ውጤታቸው፣ ስሜታቸው፣ ፍላጎታቸው፣ የጫማ ቁጥራቸው በጣም ይመሳሰላል። ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው፣ ታካሚዎቻቸውና ሌሎችም እነርሱን ለመለየት ይቸገራሉ። እኩል ይደሰታሉ፤ እኩል ያዝናሉ፤ አንደኛቸው ህመም ሲያጋጥማቸውም ስሜቱ ለሌላኛቸውም ይተርፋል። አለባበሳቸው፣ የፀጉር አሠራራቸው እንዲሁም የሚያደርጉት ጌጥ ተመሳሳይ በመሆኑ መምታታቱን ጨምሮታል። እነርሱ እንደሚሉት የባህርይ ልዩነትም የላቸውም። የማያመሳስላቸው ምንድን ነው? አምጠው የወለዷቸው እናታቸው እንኳን በቀላሉ አይለዩዋቸውም። ብዙ ጊዜ ከስህተት በኋላ ነው ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚያረጋግጡት። ከአገር ውጭ የሚገኙ እህትና ወንድሞቻቸው በስልክ ሲያናግሯቸው ማንነታቸውን ካልገለፁ በስተቀር አንደኛቸው ሌላኛቸውን ወክለው መልስ ቢሰጡ አይነቃባቸውም። በጣም የጎላ መለያየትና የማያመሳስላቸው ባይሆንም በንፅፅር ሰዎች የሚለዩባቸው መንገዶች ግን መኖራቸው አልቀረም- ያም ቢሆን ለቅርብ ሰው ነው። "ቃል ኪዳን ከእኔ በተለየ ተግባቢ፣ ተጨዋችና ሳቂታ ናት፤ እኔ ደግሞ ኮስታራና ዝምተኛ ነኝ" ትላለች ዶ/ር እየሩሳሌም ልዩነታቸውን ነቅሳ ስታወጣ። ዶ/ር ቃልኪዳን በበኩሏ"ብዙም ባይሆን በክብደት እኔ እበልጣለሁ፤ እርሷ ከእኔ ቀጠን ትላለች፤ ባህርያችን ተመሳሳይ ቢሆንም እኔ ትንሽ የመቸኮል፤ በተቃራኒው እየሩስ ደግሞ የመረጋጋትና ጊዜ የመስጠት ሁኔታ አለ" ትላለች። በዚህም አንዳንድ ሰዎች እንደ ምንም እንደሚለዩዋቸው ይናገራሉ- መንትዮቹ። "አንገቴ ላይ ጥቁር ነጥብ አለኝ፤ እየሩሳሌም ላይ ግን ይህች ምልክት የለችም" የምትለው ቃልኪዳን ይህ ካልሆነ በስተቀር በአካላቸው ላይ አንዳቸውን ከአንዳቸው የሚለይ ምልክት የለም። • ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ እነርሱ እንደሚሉት አብዛኛውን ጊዜ አንድ ላይ ነው የሚውሉት፤ ተለያይተው የሚውሉበት አጋጣሚ እምብዛም ነው። ይሁን እንጂ በልጅነት ጊዜያቸው ከእህትና ወንድሞቻቸው ጋር የመሸዋወድ አጋጣሚዎች እንደነበሩ እየሩሳሌም ታስታውሳለች። ቃልኪዳንም የማትረሳው አጋጣሚ አላት። እርሷ እንደምትለው እናታቸው ለእየሩሳሌም የማዳላት ነገር እንዳለ ይሰማታል። ሁኔታው የከነከናት ቃልኪዳንም እውነቱን ከእርሳቸው ለመስማት ፈለገች። እናም እናቷ በተኙበት እየሩሳሌምን ሆና ቀስ ብላ ሄደች። ቃልኪዳን፡ "ግን ለምንድን ነው እኔን ከቃልኪዳን የምታስበልጭው?" እናት፡"ሁለታችሁም ለእኔ እኩል ናችሁ፤ አንድ ዓይነት ናችሁ፤ አለያችሁም " ሲሉ ይመልሳሉ። ቃልኪዳን፡"እርሷን ግን ትንሽ ታስበልጫለሽ?" እናቷ የምትጠይቃቸው ቃልኪዳን እንደሆነች አልለዩምና እውነቱን መናገር ጀመሩ። እናት፡"እየሩስዬ፣ ትንሽ ወደ አንች የማደላውና የማጋድለው ስለሚያምሽ ነው" ሲሉ በራራ የእናት አንደበት ይመልሳሉ (በእርግጥ በጊዜው እየሩስን ትንሽ ያማት ነበር)። በኋላ ላይ ማንነቷን ሲለዩ በጣም ነበር የደነገጡት፤ ይህን አጋጣሚ እናታቸውም አይረሱትም፤ ሁልጊዜም በቤታቸው ይነሳል። ታካሚዎቻቸውም ዶክተሮቹን ለመለየት ይቸገራሉ፤ ነገርግን መንታ መሆናቸውን ሲያውቁ አንዳቸውን ከአንዳቸው ለመለየት ምልክት ማጥናት ይጀምራሉ። መንትዮች አንድ ዓይነት አለባበስና አጊያጊያጥ ለምን ይከተላሉ? ቃልኪዳን እንደምትለው ፍላጎታቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ተመሳሳይ ስለነበር የሚገዛላቸው ነገር ሁሉ ተመሳሳይ ነው። እንደውም ልጅ እያሉ ትንሽ መለያየት ሲኖረው እንኳን ደስተኛ አይሆኑም። አሁንም ያላቸው ፍላጎት ተመሳሳይ ነው። ተመሳሳይ አልባሳትና ጌጣጌጥ ለማግኘት የሚችሉትን ያህል ይሞክራሉ። ብዙ ጊዜ የሚፈልጉትን ለማግኘት አይቸገሩም። የእየሩሳሌም ሐሳብም ተመሳሳይ ነው። "በልጅነታችን ልብሳችን ላይ አንዳች ልዩነት ስናይ እናለቅሳለን፤ እናታችን እንደገና ሄዳ ትለውጣለች" ስትል ትውስታዋን አጋርታናለች። ፍላጎትም ብቻ ሳይሆን የሰዎችም ግፊት አለበት። የተለያየ ልብስ ሲለብሱ ጥያቄ ይበዛባቸዋል። ጥያቄው የሚበዛው ሲለያዩ እንጂ ሲመሳሰሉ አይደለም። ፎቶግራፍ የሚጠየቅባቸው የትምህርት፣ የሥራና ሌሎች የሕይወት እንቅስቃሴዎች መለየት ስለሚያዳግት የአንደኛቸውን ፎቶ በሌላኛዋ መረጃ ላይ አሳስተው ይለጥፉታል። "ብዙ ጊዜ አንድ ዓይነት ስለምንለብስ መለየት አይችሉም" ይላሉ። በዚህም ምክንያት ፎቶግራፋቸው ጀርባ ላይ ስማቸውን እንዲፅፉ ይጠየቃሉ። • የሙያውን ፈተና ለመጋፈጥ ከከተማ ርቆ የሄደው ሐኪም የመንትዮቹ የትምህርት መስክም ሆነ የትምህርትና ሥራ ምደባ ተመሳሳይ መሆኑ በአጋጣሚ የሆነ እንጂ እነርሱ ያደረጉት ጥረት የለም። ይሁን እንጂ የሥራ ምደባ ሲደረግ እንለያይ ይሆን የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር። የፈሩት አልቀረም ታዲያ እየሩሳሌም በጂማ ኒቨርሲቲ እንድታስተምር ተመደበች። ሥራ ከመጀመሯ አስቀድሞ ለሥልጠና ወደ አዳማ ዩኒቨርስቲ አቀናች- ለሁለት ሳምንታት ብቻ። ያኔ ቃልኪዳን አዲስ አበባ ነበረች። ይህ ወቅት ለቤተሰቡ ሁሉ ፈተና ሆኖ ማለፉን ሁለቱም አይዘነጉትም። 'መለያየት ሞት ነው'ን የዘፈኑት ያኔ ነው ማለት ይቻላል። አሁን ግን የልባቸው ሞልቶ አንድ የሥራ ገበታ ላይ ተሰይመዋል። መንትዮቹ ራሳቸውን በበጎ ሥራ ጠምደዋል። መንትዮቹ ማኅበርን (Twins Association) አቋቁመዋል። የፌስቡክ ገፅ ከፍተው በማንኛውም ዕድሜ የሚገኙ መንትዮችን ማሰባሰብ ጀምረዋል። ዓላማው ብዙ ቢሆንም መንትዮችን ማሰባሰብ፣ የመንትዮችን ቀን ማክበር፣ ልምዳቸውንና ተግዳሮቶቻቸውን የሚጋሩበትና የሚተወቃወቁበት ማኅበር ነው። ይህንን ዓላማ ለማሳካትም በሂደት ላይ እንደሚገኝ ለቢቢሲ ገልፀዋል -መንትዮቹ ዶክተሮች። እንደ ጨዋታ... ቢቢሲ፡ መንትዮች የፍቅር ግንኙነት ላይ አንዳቸው ባንዳቸው ቅናት ያድርባቸዋል ይባላል? እየሩሳሌም፡ መስፈርታችን ተመሳሳይ ስለሆነ የምንፈልገው ተመሳሳይ መሆኑ አይቀርም (ረዥም ሳቅ) እንዲያውምመንትያ ሲኾን መንትያ የሕይወት አጋር ቢኖር ይባላል፤ ያ ደግሞ አያጋጥምም። ሁለታችንም በጎ ነገር ከገጠመን አንዳችን ላንዳችን ደስተኛ ነው የምንሆነው። እንዲህ ዓይነት ስሜት እኛ ጋ የለም። ቃልኪዳን፡መንታ ይምጣ ነዋ የምንለው (ሳቅ)... ቅናቱን በተመለከተ ግን ሰዓት መሻማቱ ስለሚኖር ትንሽ ቅር የሚል ነገር ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ያንዳችን ደስታና ስኬት ስለሚያይልብን ያን ያህል የከፋ ነገር አይኖርም።
news-52541182
https://www.bbc.com/amharic/news-52541182
ህወሓት ክልላዊ ምርጫ ቢያከናውን "ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም" ወ/ት ብርቱኳን
የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህወሓት በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል የሕግ ድጋፍ እንደሌለው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ገለጹ።
ህወሓት ለቀናት ሲያደርግ የነበረውን ስብሰባ ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው መግለጫ ላይ መንግሥት የሥራ ዘመኑን በማራዘም ምርጫ ለማካሄድ ያቀረበውን አማራጭ በመቃውም፤ በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት አደርጋለሁ ማለቱ ተከትሎ ነው ሰብሳቢዋ ይህንን ያሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ት ብርቱኳን ሚደቅሳ ይህንን በተመለከተ "የክልሉ መንግሥትም ሆነ ክልሉን ሚያስተዳድረው ፓርቲ ምርጫ ማካሄድ ሕጋዊ አሆንም" ሲሉ ለብሔራዊው ቴሌቪዥን ኢቢሲ ተናግረዋል። ህወሓት ምርጫውን በክልል ደረጃ ለማካሄድ ስለመወሰኑ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አለማሳወቁን ወ/ት ብርቱኳን "ለእኛ በይፋ የደረሰን ነገር" የለም በማለት አስረድተዋል። "ክልላዊ ምርጫውን ለማካሄድ አስበው ከሆነ ትክክለኛ አካሄድ አይሆንም። ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንም" ያሉት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102 የተቋቋመው እርሳቸው የሚመሩት ምርጫ ቦርድ በፌደራል፣ በክልል እና በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የማስፈጸም ብቸኛ ስልጣን የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰዋል። ከዚህ ውጪ የክልል መንግሥታትም ሆኑ የፌደራል አስፈጻሚ አካል ተስቶ ምርጫን በተመለከተ ውሳኔ ቢያስተላልፍ ሕገ-መንግሥታዊ አይሆንምም ብለዋል። ወ/ት ብርቱኳን ከአጠቃላይ ምርጫ በተለየ ጊዜ የአንድ አካባቢ ምርጫ ሊካሄድ እንደሚችል ግን ጠቁመዋል። እንደ ምሳሌም፤ ከዚህ ቀደም በሶማሌ ክልል አብዛኛው ድምጽ ሰጪ በኑሮ ዘያቸው ምክያት በድምጽ መስጫ አካባቢ የማይገኙበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበረ በማስታወስ ከአጠቃላይ ምርጫ በኋላ በክልሉ ምርጫ እንደተከናወነ አስታውሰዋል። መንግሥት የምርጫ ጊዜን በማራዘም ምርጫውን ማካሄድ ያስችላሉ ያላቸውን አራት አማራጮች ማቅረቡ ይታወሳል። ከቀረቡት አማራጮች መካከል ደግሞ ዛሬ ረፋድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ ሚለውን አማራጭ አጽድቋል። ህወሓት ምን አለ? የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከሚያዝያ 23-25 በክልሉ እና በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል። መንግሥት ምርጫውን በቀጣይ ለማካሄድ ካስቀመጣቸው አመራጮች አንዱ የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚለው አንዱ ነው። ህወሐት በመግለጫው "የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-መንግስቱን ለመተርጐም በሚል ሰበብ የጀመረውን ገሀድ የወጣ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆም" ሲል ጠይቋል። ህወሐት የትግራይ ህዝብ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዳለው በማስታወስ፤ ለትግራይ ህዝብ ሙሉ እውቅና ከሚሰጡ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር በመሆን ክልላዊ ምርጫን ለማካሄድ ዝግጅት እንዲደረግ ውሳኔ ተላልፏል ብሏል። ለመሆኑ ህወሓት የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል? ህወሓት ምርጫ የማይካሄድ ከሆነ በክልል ደረጃ ምርጫ እንዲካሄድ ዝግጅት አደርጋለሁ ብሏል። በእርግጥ የትግራይ ክልል የራሱን ምርጫ ማካሄድ ይችላል? ዶ/ር አደም ካሴ በኔዘርላንድስ የአስተዳደር እና ዲሞክራሲ አማካሪ ናቸው። ምርጫን የማካሄድ፣ የምርጫ ሕግን የማውጣት፣ የወጣውን ደግሞ ማስተዳደር ሥልጣን ያለው የፌደራሉ መንግሥቱና ምርጫ ቦርድ ነው ሲሉ ይናገራሉ። ከዚያ ውጪ የህወሐት አመራሮች ሕጉን ተከትለው ካልተቃወሙ በስተቀር በራሳቸው ዝም ብሎ መሄድ ስልጣኑም የላቸውም ይላሉ። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት ደግሞ የሕግ አማካሪው አቶ ኤፍሬም ታምራት ናቸው። አቶ ኤፍሬም "ምርጫን በሚመለከት ሊጠሩ የሚገቡ ነጥቦች አሉ ብዬ አስባለሁ" ካሉ በኋላ ምርጫ በዋናነት አላማው ዜጎች በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ራሳቸው በቀጥታ ወይንም በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሳተፍ መብት ከሚለው እሳቤ መመንጨቱን ያስረዳሉ። በዚህም የተነሳ የምርጫ ሥርዓት መዘርጋቱን፣ ዜጎችም መምረጥና የመመረጥ መብት እንደሚኖራቸው ይገልፃሉ። "መንግሥት የሕዝቦች ፈቃድ ነው ስለሚባል ዜጎችን በመምረጥና በመመረጥ ማሳተፍ ብቻ ሳይሆን ምርጫው ነፃና ገለልተኛ መሆን አለበት" የሚሉት አቶ ኤፍሬም፤ በዚህም የተነሳ በሕገ መንግሥቱ ምርጫ ቦርድ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ መቋቋሙን ይናገራሉ። "ይህ ምርጫ ቦርድ የፌደራል የዲሞክራሲያዊ ተቋም ነው። በክልል ጽህፈት ቤቶች አሉት። አገር አቀፍ ምርጫ ባልተደረገበት በክልል ምርጫ እንደርጋለን ማለት፣ የፌደራል ዲሞክራሲያዊ ተቋም ባልተሳተፈበት፣ ባልታዘበበት ምርጫ ማድረግ የምርጫውን ሕጋዊነት፣ ነፃና ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል" በማለትም ክልሉን የሚያስተዳድረው ፓርቲ ህወሐት፤ ምርጫ ማካሄድ እንደማይችል ያብራራሉ። "ምርጫ ሲባል ዝም ብሎ አንድ ቀን ሄዶ መምረጥ አይደለም" የሚሉት ዶ/ር አደም በበኩላቸው "በቅድሚያ የምርጫ ወረዳዎች መወሰን አለባቸው። ያለውን እንኳ ይጠቀማሉ ቢባል ያም እንደገና መወሰን አለበት። ከዚያም ሲያልፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መመዝገብ ያስፈልጋቸዋል" በማለት ሂደቱን ያብራራሉ። የፖለቲካ ፓርቲዎች ከተመዘገቡ በኋላ ምልክታቸውን ማሳወቅ፣ መራጮች መመዝገብ፣ ቅስቀሳ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ በማስታወስ ህወሐት "ሁሉን ነገር የማድረግ የሕግ ሥልጣን ብቻ ሳይሆን በተግባር አቅምም፤ ተቋማዊ ዝግጅትም አለው ብዬ አላስብም" ይላሉ። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? የሕግ ባለሙያው አቶ ኤፍሬም በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ አገራዊ ምርጫውን ሲያራዝም አገሪቱ በኮሮናቫይረስ ውስጥ ስላለች ነው በማለት "አሁን ባለንበት ሁኔታ የተለያዩ የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች ይገደባሉ" ይላሉ። እነዚህ መብቶች መካከል ደግሞ የመመረጥና የመምረጥ መብት እንደሚገኝበት በመግለጽ ይህ ጉዳይ ሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈረ፣ ምርጫ ቦርድም በሕገ መንግሥቱ መነሻነት ያንን ውሳኔ ማሳለፉን ይገልፃሉ። "ስለዚህ ሁኔታዎች ተሻሽለው ወደ መደበኛው ሕይወት እስክንመለስ ድረስ ስለምርጫ የምናወራበት ሕገ መንግሥታዊ መሰረት ያለን አይመስለኝም" ይላሉ። ዶ/ር አደም በበኩላቸው የክልሉ መንግሥት ወይንም ህወሓት ምርጫውን አደርጋለሁ ብሎ እርምጃ ቢጀምር ያ ተቋም ነፃነት አለው ወይ? በሌሎቹ ይታመናል ወይ? እንደምርጫ ቦርድ ሆኖ የሚያገለግል ተቋማዊ መዋቅር ይኖረዋል? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት "እኔ ግን አለው ብዬ አላምንም" ይላሉ። መፍትሔው ታዲያ ምንድን ነው? የሕግ ባለሙያው አቶ ኤፍሬምም ሆኑ የአስተዳደርና ዲሞክራሲ አማካሪው ዶ/ር አደም ለተፈጠረው ፖለቲካዊ አለመግባባት ከመነጋገር የተሻለ ሌላ አማራጭ አይታያቸውም። "የዚህ ችግር ምንጩ በአዲሱ የብልጽግና ፓርቲና በህወሓት ወይንም በነባሩ ኢህአዴግ መካከል ያለ የፖለቲካ ግጭት ነው" የሚሉት ዶ/ር አደም "የተወሰዱ እርምጃዎችና ውሳኔዎች ሕጉን ይጥሳሉ ወይም ይቃረናሉ የሚሉ ከሆነ፤ አይ እኔ ምርጫ አካሄዳለሁ ማለት ሳይሆን . . . ወደ ሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚቴ፣ ከዚያም አልፎ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት ሄዶ ለመፍታት መሞከር ይሻላል" በማለት ይመክራሉ። "ምናልባት እነርሱ ሕጉን ጥሰዋል እኛም ሕጉን እንጥሳለን ከሆነ፤ የአንድ ጥሰት ሌላኛውን ጥሰት ትክክል አያደርገውም" በማለትም እንዲህ አይነት ቅራኔ ምንጩ ፖለቲካዊ ግጭት በመሆኑ ከሕግ ይልቅ ፖለቲካዊ ውሳኔ መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ይጠቁማሉ። ጉዳዩ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቋም ምን እንደሆነ ለማወቅ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እና የቦርዱ ቃል አቀባይ የእጅ ስልክ ላይ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም።
news-52499205
https://www.bbc.com/amharic/news-52499205
ኮሮናቫይረስ፡ "ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ በርሃብ ልናልቅ ነው"
የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመግታት አንዳንድ አገራት እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ መዝጋትን አማራጭ አድርገዋል።
በእነዚህ አገራት የቫይረሱ ስርጭት በአንጻራዊ ሁኔታ መገታቱ እንዳለ ሆኖ ዜጎቻቸው ግን በርሃብ አለቅን እያሉ ነው። በተለይ ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ የሆኑ የዜጎች የገቢ ምንጭ ሙሉ በሙሉ በመድረቁና የመንግሥታት ድጋፍም ዝቅተኛ በመሆኑ ችግር ላይ መውደቃቸውን ይገልጻሉ። በተመሳሳይ ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ከአንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ከሥራቸው እንደሚፈናቀሉ አስታውቋል።
news-56117870
https://www.bbc.com/amharic/news-56117870
አዲሱ የቪድዮ መደዋወያ ሕፃናትን ለወሲብ ጥቃት አሳልፎ እንደሚሰጥ ቢቢሲ አጋለጠ
ማስጠንቀቂያ፡ ይህ ፅሑፍ ሊረብሹ የሚችሉ ይዘቶች አሉበት።
ቢቢሲ የሠራው የምርመራ ዘገባ አንድ ኦሚግል የተሰኘ የቪድዮ መደዋወያ ድረ-ገፅ ሕፃናትን ለወሲባዊ ጥቃት እንደሚያጋልጥ ተደረሰበት። ኦሚግል የተሰኘው የቀጥታ ቪድዮ መደዋወያ መተግበሪያ [አፕሊኬሽን] የማይተዋወቁ ሰዎች እየተያዩ እንዲደዋወሉ የሚያስችል ነው። ድረ-ገፁ ይዘቶቼን እቆጣጠራለሁ ቢልም ተጠቃሚዎች ያልተጠበቀ ድርጊት ሲፈፅሙበት ታይቷል። ዓለም አቀፍ የሕፃናት መብት ተቋርቋሪዎች ወሲባዊ ጥቃት አድራሾች ገፁን ተጠቅመው ሕፃናትን እየበዘበዙ ነው ሲል ይከስሳሉ። የገፁ መሥራች ሊፍ ኬ ብሪክስ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ይዘት የምንቆጣጥርባቸውን መላዎች እያሰፋን ነው ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ሴምራሽ የተሰኘው መረጃ ሰብሳቢ ቡድን በቅርቡ ያጠናው ጥናት እንደሚያመልክተው የገፁ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርክቷል። በፈረንጆቹ ጥር 2020 34 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች የነበሩት ኦሚግል አሁን 65 ሚሊዮን ሰዎችን ያስተናግዳል። በተለይ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩናይትድ ስቴትስና ሜክሲኮ የተጠቃሚዎች ቁጥር እጅጉን ጨምሯል። በዩኬ ብቻ ባለፈው ታኅሣሥ 3.7 ሚሊዮን ሰዎች ገፁን ጎብኝተውታል። ከእነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ ከ34 ዓመት በታች ሲሆኑ በርካታ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ጥናቱ ይጠቁማል። ቲክቶክ በተሰኘው የቻይና ማሕበራዊ ድር-አምባ ላይ ብቻ 9.4 ቢሊዮን 'ሃሽታግ' ኦሚግል የሚሉ ቪዲዮዎች ታይተዋል። የቻይናው ቲክቶክ ቢቢሲ በሠራው የምርመራ ዘገባ ምክንያት የኦሚግልን ቪድዮዎች ገፁ ላይ እንዳይጫን አግዷል። የቲክቶክ ሰዎች እንዳሉት ምንም እንኳ እስካሁን ጎጂ የሚባል ይዘት የኦሚግል ቪድዮዎች ላይ ባያገኙም ቁጥጥራቸውን ግን ይቀጥላሉ። የወንዶች አፀያፊ ድርጊት "ሁሉም ሰው ቲክቶክ ላይ ሲያደርገው ዓይተን እኔና ጓደኞቼም እንሞክረው ተባባልን" ትላለች የ15 ዓመቷ አሜሪካዊት ኬይራ። "ነገር ግን በብዛት የሚታየው ወንዶች አስፀያፊ ድርጊት ሲፈፀሙ ነው። ቁጥጥር ቢደረግበት መልካም ነው። ድብቅ ድረ-ገፅ ነው የሚመስለው። ግን ለሁሉም ክፍት ነው።" ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ የፖሊስ ተቋማትና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችነድረ-ገፁን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል። ይህን ካደረጉ ሃገራት መካከል ዩኬ፣ ዩኤስ፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳና አውስትራሊያ ይጠቀሳሉ። ቢቢሲ የምርመራ ዘገባውን ለማድረግ ድረ-ገፁ ላይ በተገኘበት ወቅት በርካታ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተጠቃሚዎችን ተመልክቷል። አልፎም ዕድሜያቸው ከሰባት ወይም ስምንት የማያልፍ ሕፃናት ድሩን ይጠቀሙታል። ድረ-ገፁ ተጠቃሚዎች ቢያንስ 18 አሊያም ከዚያ በላይ እንዲሆኑ ቢመክርም የተጠቃሚዎችን ዕድሜ መቆጣጠሪያ መንገድ ግን የለም። የቢቢሲ ምርመራ ቡድን በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዓታት ብቻ ግለ-ሩካቤ [ማስተበርቤት] ከሚያደርጉ 12 ወንዶች ጋር ተገናኝቷል። ከዚህ በተጨማሪ ስምንት ራቁታቸውን ያሉ ወንዶችና ሰባት የወሲብ ድረ-ገፅ ማስታወቂያዎች ተመልክቷል። የወሲብ ድርጊት የሚፈፅሙ ሕፃናት የምርመራ ቡድኑ ሁለት ጊዜ ግለ-ሩካቤ እያደረጉ ካሉ ታዳጊዎች ጋር መገናኘት ችሏል። ከእነዚህ መካከል አንደኛው የ14 ዓመት ታዳጊ እንደሆነ ይፋ አድርጓል። የምርመራ ቡድኑ እኒህን ይዘቶች አልቀዳም። ሕፃናቱ ይህን ድርጊት በሚያደርጉበት ወቅትም የቪድዮ ግንኙነቱ ወዲያውኑ እንዲቋረጥ ተደርጓል። የድርጅቱ መሥራች የሆነው ግለሰብ ገፁ አሁን መሰል ይዘቶች እንዳይሰራጩ አድርጓል ቢልም ቢቢሲ ይህን ማጣራት አልቻለም። ሕፃናት ጥቃት ሲደርስባቸው የሚያሳዩ ምስሎችን ከበይነ መረብ በማስወገድ የሚታወቅ ኢንተርኔ ዎች ፋውንዴሽን የቢቢሲ ዘገባ አስደንጋጭ ቢሆንም እውነታን ያሳየ ነው ብሏል። ድርጅቱ ሕፃናት ወሲባዊ ድርጊቶች ሲፈፅሙ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ከኦሚግል ተገኝተው በትላልቅ ሰዎች አማካይነት በይነ መረብ ላይ እንደተበተኑ ደርሼበታለሁ ብሏል። ቢቢሲ ያናገራት ዩኬ ውስጥ ያለች እናት የስምንት ዓመት ሴት ልጇን አንድ ትልቅ ሰው ወሲባዊ ድርጊት እየፈፀመች ገፁ ላይ እንድትታይ እያሳመናት ሳለ እንደደረሰች ተናግራለች። "ልጄ ቲክ ቶክ ላይ ሰዎች ስለዚህ ገፅ ሲያወሩ ሰምታ ነው ወደ ድሩ ያመራችው። ይህን ገፅ መመዝገብ [ሎግ ኢን] እንዲሁም የዕድሜ ገደብ አያሻም" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። "ገፁ ላይ ያሉ ሰዎች ልጄን ቆንጆ ነሽ፣ ታሳሻለች እያሏት ነበር። እሷ ገና ስምንት ዓመቴ ነው ብትልም ችግር የለውም ብለዋታል። ይባስ ብሎ አንድ ትልቅ ሰው ግለ-ሩካቤ ሲፈፅም ተመልክታለች።" ቢቢሲ ለሶስት ወራት ያክል ኦሚግል የተሰኘውን ገፅ እንዲሁም መሥራቹ ሊፍ ኬ ብሩክስን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት አድርጓል። የድረ-ገፁን አስተዳዳሪዎች ለማግኘት የሚያስችል ምንም ዓይነት መንገድ ድሩ ላይ አልተቀመጠም። መሥራቹን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ ብሩክስ የተሰኘው የድረ-ገፁ መሥራች ለዓመታት በይፋ ስለ ኦሚግል ምንም ዓይነት አስተያየት አልሰጠም። ቢቢሲ መሥራቹ ከሌሎች ጋር ላቋቋመው ኦክቴን ኤአይ የተሰኘ መሥሪያ ስድስት ጊዜ ኢሜይል ልኮ በስተመጨረሻ ምላሽ አግኝቷል። በሰጠው ምላሽ ድረ-ገፁ የይዘት ቁጥጥር እንደሚደርግለትና ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ተጠቃሚዎች 'እንደሚታገዱ' ተናግሯል። አልፎም በፈረንጆቹ 2020 የይዘት ቁጥጥር ሥራዎች እንደተጠናከሩ ተናግሯል። "ምንም እንኳ ፍፁም መሆን ባይቻልም የኦሚግል የይዘት ቁጥጥር ገፁ ንፁህ እንዲሆን አስችሏል። አላስፈላጊ ድርጊቶች የፈፀሙ ሰዎች ተይዘው ለሕግ ተላልፈው እንዲሰጡም አድርገናል" ይላል በኢሜይል የሰጠው ምላሽ። ሰውዬው በምላሹ ገፁ ላይ የሚታዩት የወሲብ ገፅ ማስታወቂያዎች የሚለቀቁት ዕድሜን ተገን አድርገን ነው ቢልም ተጠቃሚዎች ዕድሜያቸው ካልተመዘገበ ይህ ሊሆን እንደሚችል ግን ማብራሪያ አልሰጠም። ብሩክስ ለሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል።
48672477
https://www.bbc.com/amharic/48672477
ኮሎኔል መንግሥቱን ትግል ለመግጠም ቤተመንግሥት የሄደው ደራሲ አውግቸው ተረፈ
አውግቸው ተረፈ የብዕር ስሙ ነው። ወላጆቹ ያወጡለት ስም ኅሩይ ሚናስ ነው። የብዕር ስሙ ግን ይህ ብቻ እንዳልሆነ ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ ለቢቢሲ ይናገራል።
በአጫጭር ልብወለድ፣ በትርጉም፣ እንዲሁም በአርታኢነት የሚታወቀው ኅሩይ ሚናስ ውልደቱ አዲስ አበባ አይደለም። ከጎጃም ደጀን ነው፤ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ አይነ ስውራንን ይመራ ነበር። ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ ራሱን ለማኖር በረንዳ ላይ አድሯል። ቀስ በቀስ የፀሎት መጻህፍትን ወደ መሸጥ ከዚያም በሂደት የትምህርትና የልብ ወለድ መጻህፍትን ሸጧል። • “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ መጻህፍት ንግድን ያስተማራቸው እነ አይናለም ዛሬ በጥሩ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ መጻህፍት ሻጮና አከፋፋይ ሆነዋል ይላል እንዳለ ጌታ ከበደ። አውግቸው መጻህፍት ሻጭ በነበረበት ወቅት እርሱ እያነበበ ተመሰጦ ሳለ የመግዛት ፍላጎት ያለው ሰው ሲመጣ ውሰደው ብሎ በነጻ እንደሚሰጥ ይነገርለታል። ለደራሲ አበረ አዳሙ ከአውግቸው ስራዎች "ወይ አዲስ አበባ"ን የሚያክል የለም። "ወይ አዲስ አበባ" የአውግቸው የራሱ ታሪክ ነው ይላሉ። ለአቶ አበረ አውግቸው ጭምት ደራሲ ነው። በዚህ ሀሳብ የ"አለመኖር" ደራሲው ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝም ይስማማሉ። ሁለቱም ደራሲያን ብዙ ማውራት አይወድም። በጥልቀት ያስባል ሲሉ አቶ አበረ አክለው የመርህ ሰው ነው ብለዋል። አቶ አበረ ለአውግቸው የመርህ ሰውነት የሚጠቅሱት በ19 87ና 88 ዓ.ም አካባቢ የሆነውን በማስታወስ ነው "በዚህ ዓመት የማነበው መዝገበ ቃላት ነው ካለ አመቱን ሙሉ ቃሉን ጠብቆ የሚያነበው ያንኑ ነው።" አቶ አበረ "እንደው ለመሆኑ አውግቸው ጓድ መንግሥቱን ትግል እገጥማለሁ ብሎ ቤተ መንግሥት መሄዱን ታውቃላችሁ?" አሉን። "አረ በጭራሽ" የኛ መልስ ነበር። አውግቸው አንድ ዕለት ወደ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ሄዶ ኮሎኔል መንግሥቱን ጥሩት አለ። "ለምን?" ሲሉት "ትግል እገጥመዋለሁ መልሱ ነበር። "ይህንን ... "ብሎም እላፊ ተናገረ። እኔን ትግል ገጥሞ መጣል ሳይችል አገር መግዛት ይችላል መከራከሪያው ነበር። ወታደሮቹ አፈፍ አድርገው ደበደቡት። ከዚያም እስር ቤት ወርውረውት ለበርካታ ጊዜ ታስሮ ነው የወጣው ይላሉ አቶ አበረ። "ይህ መቼ ነው የሆነው አልናቸው?" ሰባዎቹ መጀመሪያ ይመስለኛል አሉ በመጠራጠር። "ኅሩይ ርትዑነት ያረበበበት ቀና ሰው ነበር የሚለው" እንዳለጌታ አሮጌ መጻህፍትን እየሸጠ የጻፋቸው አጫጭር ልብ ወለዶች የካቲት መጽሔት ላይ ታትመው መነበብ መጀመራቸውን ይናገራል። ለዚህ ደግሞ ምክንያት የሆነው መፅሐፍት ከእርሱ እየገዛ ያነብ የነበረው ስብሀት ገብረ እግዚያብሄር እንደሆነ እንዳለ ጌታ ያስታውሳል። ያኔ አሮጌ መጻህፍት እየሸጠ ሲጽፍ ጓደኞቹ አንተን ብሎ ደራሲ ብለው እንዳይዘባበቱበት ስለፈራ በብዕር ስም ነው ትረካው መጽሔት ላይ እንዲወጣ ያደረገው። • "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7? አውግቸው ብዙ የብዕር ስሞች አሉት የሚለው እንዳለጌታ፣ ራሱ ነገረኝ በማለት አዳነ ቸኮል የእርሱ የብዕር ስም መሆኑን አጫውቶናል። በዚህ የብዕር ስም፣ በአዳነ ቸኮል 'የአማልክትና የጀግኖች አፈ ታሪክ' የሚል ሥራ ታትሞ ለንባብ በቅቷል፤ አዳነ ቸኮል የአያቱ ስም ነው። የአውግቸውን በርካታ ሥራዎች ከተመለከተና ካነበበ በኋላ "የአደፍርስ ደራሲ ዳኛቸው ወርቁ አውግቸውን ኩራዝ አሳታሚ ወስዶ በአርታኢነት አስቀጥሮታል" የሚለው እንዳለጌታ ኩራዝ አሳታሚ በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል ሲል ምስክርነቱን ይሰጣል። ከአሮጌ መጽሐፍ ሻጭ ወደ ደራሲነት አውግቸው መርካቶ አሮጌ መጽሐፍትን ከመሸጥ ተነስቶ፣ ከ20 በላይ መጽሐፍት በድርሰት እና በትርጉም ለአንባቢዎች አበርክቷል። እንዳለ ጌታ ከበደ ስለ ሥራዎቹ ሲጠቅስ 'ወይ አዲስ አበባ' ይጠቀሳል። በ1974 ዓ.ም ገደማ ከነሲሳይ ንጉሡ ጋር በጋራ በመሆን ያሳተመው 'ጉዞው' የተሰኘው የአጭር ልብ ወለድ ስብስብ "እያስመዘገብኩ ነው" የሚልው የኅሩይን ሥራ ይዟል። ይህ የአውግቸው ሥራ በበርካታ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች ይጠቀሳል። እንደ እንዳለ ጌታ ከበደ ከሆነ ደግሞ ይህ ሥራ ለዛሬው 'እያዩ ፈንገስ' ደራሲም መሰረት እንደሆናቸውም ይጠቅሳል። ከ'ወይ አዲስ አበባ' ውጪ በዓለም ላይ የታወቁ ደራሲዎችን ሥራዎች በመተርጎምም ይታወቃል ኅሩይ ሚናስ። 'የአንገት ጌጡ' በዓለም ላይ የሚታወቁ ደራሲዎች ሥራ ስብስብ ነው የሚለው እንዳለጌታ የባልዛክ ሥራ የሆነውን 'ምስኪኗ ከበርቴ'ን በመተርጎምም ዝናን ማትረፉን ይናገራል። "አውግቸው ክላሲካል የሆኑ ሥራዎችን ማስነበብ ላይ ያተኩራል" ያለው እንዳለ ጌታ በኋላ ላይ ያሳተመው "እብዱ" የተሰኘው መፅሐፍም ተጠቃሽ ነው። • የ2010 የጥበብ ክራሞት በኢትዮጵያ ውስጥ የአእምሮ ህመም ችግር ካጋጠመው በኋላ ያንን በመጻፍ ያስነበበ አንድም ሰው የለም የሚለው እንዳለጌታ አውግቸው ግን ያንን በማድረግ ቀዳሚ ነው ይላል። በዚህ ሥራው የተነሳ የአማኑኤል ሆስፒታል አንዱን የህክምና ክፍሉን በእርሱ ስም ሰይሞ ምስሉን ቀርጾ በግድግዳው ላይ አኑሮታል። የአእምሮ ህመምና ኅሩይ አውግቸው በ70ዎቹ ውስጥ አእምሮው ታውኮ ነበር። እርሱም ለምን እንደሆነ አያውቅም። ወዳጆቹም በእርሱ አይነት ችግር የገጠማቸው ሰዎች የመትረፍ እድላቸው በጣም የመነመነ ነው ይላሉ። የአእምሮ ሐኪሙ ዶ/ር ዳዊት በዚህ ሀሳብ ባይስማሙም ለደራሲ አውግቸው "እብዱ" ስራ ግን ያላቸውን አድናቆት አልሸሸጉም። አውግቸው ስለ ህመሙ ሲናገር ለበርካታ ጊዜያት በር ዘግቶ መፅሐፍ ስለሚያነብ፣ ስለሚቆዝም እንዲሁም ያለማቋረጥ ይቅም ስለነበር መታመሙን የእነዚህ ነገሮች ሁሉ ድርብርብ ውጤት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ ይል እንደነበር እንዳለጌታ ይናገራል። አውግቸው አእምሮው በታወከበት ወቅት የሆነች ሴቴ መንፈስ ታዝዘው እንደነበር ይናገራል። ያቺ መንፈስ ማሪያም ነኝ ትለኛለች። ጩቤ ይዘህ ዙር ራስህን ተከላከል እንደምትለው ይናገር ነበር። • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" • የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ ይህንንና በወቅቱ ያለፈበትን በማስታወሻው ላይ አስፍሮ ካቆየ በኋላ ነበር ያሳተመው። ለእንዳለጌታ ይህ ሥራ ልብ ወለድ ኤይደለም ማስታወሻ ነው። የኅሩይ የግል ሕይወት ገጠመኝ ነው። "ይህንን የአውግቸው ተረፈ ሥራ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆኑ የሥነ ልቦና ባለሙያዎችም ያጣቅሱታል" ይላል እንዳለ። ለዚህም በዋቢነት የሚጠራው የ'አለመኖር' ደራሲን ዶ/ር ዳዊትን ነው። ዶ/ር ዳዊት በዚህ ሀሳብ ይስማማሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ አይነት የተኖረ ህይወት በአእምሮ ሕክምና ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም መስኮች ተፅፎ አይገኝም ይላሉ። "እብዱ" የተሰኘው የአውግቸው መጽሐፍ ለስነ ልቦና ባለሙያዎች ለማስተማሪያም ሆነ ለማጣቀሻ ያገለግላል ሲሉ ይመሰክራሉ። መጽሐፉ ከአእምሮ ህክምና ውጪ ያሉ ባለሙያዎች፣ በማህበራዊ ዘርፍም ሊጠቀስ የሚገባው ነው ሲሉም ይከራከራሉ። ስራው ለእኔ ክላሲካል ነው ሲሉ የሚየያስረዱት ዶ/ር ዳዊት ዘመን ተሻጋሪ ስራ መሆኑን ሲጠቅሱ የአእምሮ ህመምን፣ የአእምሮ ህክምናንና ሥነጽሑፍን የሚያጠና ቢኖር ይህ ስራ ከፊት እንደሚቀመጥ ጥርጥር የለኝም በማለት ነው። የአውግቸው የመጨረሻ ዘመናት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መርካቶ መሳለሚያ ይኖር የነበረው አውግቸው ኮንዶሚኒየም ደርሶት ቃሊቲ ገላን ኮንዶሚኒየም ይኖር ጀመረ። የፕሮፌሰሩ ልጆች የሚል ቤሳ ልብወለድ፣ አረቢያን ናይት ሦስተኛውን ክፍል እንዲሁም እብዱን አሻሽሎ ለማሳተም በዝግጅት ላይ ነበር። ከቤቱ መራቅ ከጤንነትም ሁኔታ ጋር በተያያዘ ብዙ መንቀሳቀስ እና ከሰዎች ጋር መገናኘት ያዳግተው እንደነበር ያስታወሰው እንዳለጌታ አውግቸው ባለትዳርና የልጆች አባት እንደሆነ ይናገራል። አውግቸው አንገቱ ሊታዘዝለት አይችልም ነበር፤ ያለው እንዳለ ጌታ ይህ ህመሙ ከምን እንደመነጨ አይታወቅም በማለት የነበረበትን የጤና እክል ያስታውሳል። አውግቸው በ2008 ዓመተ ምህረት የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ነበር።
news-52695853
https://www.bbc.com/amharic/news-52695853
ኮሮናቫይረስ: ታይዋን ከአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ወሳኝ ጉባኤ ለምን ተገለለች?
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ካጠላበት ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ላይ ያሉ የጤና ኃላፊዎች በሚቀጥለው ሳምንት ወሳኝ በተባለው የአለም ጤና ጉባኤ አለምን ከቀውሱ እንዴት እንታደጋት? በሚል ይመክራሉ። ጉባኤውን ያዘጋጀው የአለም ጤና ድርጅት ሲሆን በኢንተርኔት አማካኝነት የሚካሄድ ይሆናል።
በአለም ላይ የወረርሽኙን አካሄድ በመቀልበስ፣ ቫይረሱን በመግታት ከፍተኛ እመርታ አሳይታለች የምትባለው ታይዋን ግን በዚህ በርካታ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል በተባለው ጉባኤ ላይ እንድትሳተፍ በአለም ጤና ድርጅት አልተጋበዘችም። ሃያ ሶሰት ሚሊዮን ህዝብ ባላት ታይዋን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 440 ሲሆን፤ ሰባት ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል። ታይዋን የቫይረሱን መዛመትም ለመግታት ቀድማ ድንበሯ ላይ ጥብቅ ቁጥጥርን፣ የውጭ ሃገራት ዜጎች ወደ ሃገሯ እንዳይገቡ መከልከል እንዲሁም ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ዜጎቿ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ አድርጋለች። ታይዋን የወረርሽኙን መዛመት በፍጥነትና ውጤታማ በሆነው አካሄዷ አለም አቀፉን ውደሳ ማግኘቷን ተከትሎ ለአለም ሃገራትም ልምዷን ማካፈል አለባት የሚሉ በርካቶች ናቸው። ሆኖም ቻይና የግዛቴ አካል ናት ብላ የምትከራከርላትን ታይዋን ከጎርጎሳውያኑ 2016 ጀምሮ የአለም አቀፉ ድርጅት ስብሰባዎች ላይ እንዳትሳተፍ እግድ ጥላለች። በባለፉት ሳምንታት አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ ጃፓንና የተለያያዩ ሃገራት ታይዋን ቢያንስ እንደ ታዛቢ ትሳተፍ በሚልም ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉላት ነው። የቫይረሱ መነሻ ናት የምትባለው ቻይና የወረርሽኙን ሁኔታ ባግባቡ ለአለም አላሳወቀችም እንዲሁም መረጃዎችን ደብቃለች በሚል በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ትችት እየደረሰባት ያለችው ቻይና ግን ታይዋን ትሳተፍ የሚለውን አካሄድ በከፍተኛ ሁኔታ ተችታዋለች። ከዚህ ቀደም ከታይዋን ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጉዳዮችን የሃገር ውስጥ ጣልቃ ገብነት የምትለው ቻይና በቅርቡ ግን ታይዋን የአለም አቀፉ ጤንነት ድርጅት ትሳተፍ የሚለው የመገንጠልና የነፃነት ጥያቄ ላይ ያነጠጣረ ነው በማለት ተችታለች። የሃገሪቱ ሚዲያ ዢኑዋም አሜሪካን ወርፎ አንድ ፅሁፍ አትሟል። "በአለም ላይ ያለችው አንድ ቻይና ናት። የቻይናን ሪፐብሊክም ሆነ ግዛቶቿን የሚያስተዳድረው አንድ የቻይና ህጋዊ መንግሥት ነው። ታይዋን ደግም የቻይና አካል ናት" ያለው ፅሁፉ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለወረርሽኙ እየሰጠ ያለውን ምላሽ አሜሪካዊ ፖለቲካዊ ማድረጓን ታቁም ብሏል። የታይዋን ግዛት ይገባኛል ቅራኔዎች ረዥም ዘመናትን እንዳስቆጠረ በዴቪድሰን ኮሌጅ የፖለቲካል ሳይንስ ፕሮፌሰሯ ሼሊ ሪገርስ ይናገራሉ። በጎርጎሳውያኑ 1949 ቻይናን በወቅቱ ያስተዳድር የነበረው መንግሥት በኮሚዩኒስት ፓርቲ መወገዱን ተከትሎ ታይዋን ራሷን እያስተዳደረች ትገኛለች። ይህ ሁኔታ ለቻይና ያልተዋጠላት ሲሆን፤ የታይዋን ህጋዊ መንግሥት በቻይና መንግሥት መጠቃለል አለበት ከማለት አልፋ፤ ግዛቷ በማንኛውም መንገድ በቻይና ስር እንደምትሆንና ፤ ሃይልን በመጠቀም ሊሆን እንደሚችልም ገልፃለች። በአሁኑ ሰአት ታይዋንን እያስተዳደረ ያለው የፕሬዚዳንቷ ትሳይ ኢንግ ዌን ዲሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ መንግሥት የግዛቷን ነፃነትን የሚደግፍ ሲሆን ከቻይና ጋር ያለውንም ግንኙነት የበለጠ አሻክሮታል። •በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ •"ለሃያ ዓመታት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስዘጋጅ ነበር" የንፅህና ሱሰኛው ፕሬዚዳንቷ ትሳይ ኢንግ ዌን ቻይና በታይዋን ላይ አለኝ የምትለውንም የሉዓላዊነት ጥያቄ በጭራሽ አይቀበሉትም። ታይዋን የራሷ የሆነ ሰራዊት እንዲሁም የመገበያያ ገንዘብ ያላት ሲሆን በአንዳንድ መንግሥታትም እንደ 'ዲፋክቶ' ሃገርም ትታያለች። ግሎባል ታይምስ ባሳተመው ርዕሰ አንቀፅ ቻይና በታይዋን ላይ ሃይልን ልትጠቀም እንደምትችል አመላክቷል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝም ከመከሰቱ በፊት ታይዋንና ቻይናን በሚከፍለው የታይዋን ስርጥ በርካታ ጦር ማስፈሯ ተነግሯል። በባለፉት ሶስት ወራትም እንዲሁ የጦር አውሮፕላኖችና ጄቶች በአካባቢው ሲያንዣብቡ እንደነበርም ተገልጿል። ቻይና በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ታይዋንን ይደግፋሉ የምትላቸውን ሃገራትም ኢኮኖሚያዊ ማስፈራሪያዎች ታደርጋለችም ይባላል። ታይዋን የአለም አቀፉን የጤና ጉባኤ እንድትሳተፍ ኒውዚላንድ ድጋፍ መስጠቷን ተከትሎ ቻይና የሁለቱን ሃገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያበላሽ ነው ብላለች። የታይዋን ፕሬዚዳንት ትሳይ ኢንግ ዌን በቻይና ግፊት ምክንያት አስራ አምስት ሃገራት ከታይዋን ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያቋረጡ ሲሆን ታይዋን በበኩሏ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች እውቅና እንድታገኝ እየሰራች ነው። በአለም አቀፉ ማህበረሰብም ዘንድ የሃገርነት እውቅናም ማግኘትም ዋና አላማዋ ነው። የተለያዩ ሃገራት ከቻይና ጋር ያላቸውን ግንኙነት ላለማበላሸት የታይዋንን ጉዳይ ወደ ጎን ገፋ አድርገውት ነበር። ሆኖም በአለም አቀፉ ጤና ድርጅት 'የቻይናዋ ታይፔይ' በሚል የታዛቢ ቦታ ነበራት። ነገር ግን በጎርጎሳውያኑ 2017 የፕሬዚዳንት ትሳይ ኢንግ ዌን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ እንዳትሳተፍ ተደርጋለች። ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ታይዋን እንድትካተም ከፍተኛ ግፊት እያደረገች ነው። ሆኖም በዚህ አመት በርካታ ሃገራት እንድትሳተፍ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ከዚህ ቀደም ቻይናን ማስቀየም የማይፈልጉ ሃገራትም ለታይዋን ድጋፋቸውን የሰጡ ሲሆን ይህም የሆነው በኮቪድ- 19 ምክንያት ነው ተብሏል። የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ታይዋንን መጋበዝ ይችላል ወይ የሚሉ ጥያቄዎችም በመነሳት ላይ ናቸው። ድርጅቱ የታይዋን አባልነትም ሆነ ተሳትፎ የሚወሰነው በአባላት ሃገራቱ እንደሆነ አሳውቋል። ከዚህም በተጨማሪ የታይዋንን የጤና ሃላፊዎችም ጋር መነጋገሩንም አሳውቋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማይክ ፖምፔዮ በበኩላቸው የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ታይዋንን የመጋበዝ ስልጣን አላቸው ቢሉም፤ የድርጅቱ የህግ ቢሮ ኃላፊ ስቴቨን ሰለሞን በበኩላቸው ዳይሬክተር ጄኔራሉ መጋበዝ የሚችሉት አባላቱ ድጋፍ ሲያሳዩ ነው ብለዋል። እስካሁንም ባለው የአባላት ሃገራቱ ድጋፍ ላይ ግልፅ የሆነ ነገር የለምም ብለዋል። ሆኖም ፕሮፌሰር ሼሊ ሪገርስ ከዚህ ቀደም ታይዋን ትሳተፍ እንደነበር ጠቅሰው እንዲሁም የሃገርነት እውቅና ያላገኙ ፍልስጥኤምና ቫቲካንም በታዛቢነት ይሳተፋሉ ብለዋል። ታይዋን የተገለለችበት መንገድ ምከንያት አለው የሚሉት ፕሮፌሰሯ የታይዋን ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ሌሎች ሃገራት ከቻይና ጋር የሚያደርጉትን የውክልና ፍልሚያ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
news-52975226
https://www.bbc.com/amharic/news-52975226
በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ፍርድ የቀረበው የቀድሞ ፖሊስ ባልደረባ 1.25 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ዋስ ተጠየቀ
በሚኒያፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን እጁ ከኋላ እንደተጠፈረ ከመሬት ላይ አጣብቆ አንገቱን በጉልበቱ ለዘጠኝ ደቂቃ የተጫነው ነጭ ፖሊስ የሰው ህይወት በማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርቧል። በወቅቱም 1.25 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ዋስ እንዲያቀርብ ተጠይቋል።
አቃቤ ሕግ እንደጠቀሰው ወንጀሉ ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር እንዲሁም በበርካታ ግዛቶች የተነሳው ተቃውሞና ቁጣን ተከትሎም ነው ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ዋስ እንዲያቀርብ የተጠየቀው። ዴሪክ ቾቪን በሁለተኛ ደረጃ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል ክስ የሚቀርብበት ሲሆን ሦስቱ ፖሊሶች ደግሞ በግድያ ወንጀል በመተባባር ይከሰሳሉ። በሦስት ባልደረቦቹ ታግዞ አንገቱን ከመሬት ላይ አጣብቆ በጉልበቱ ደፍቆ ሲገድል የሚያሳየው ቪዲዮ ዓለም አቀፍ ተቃውሞዎችን እንዲሁም በአሜሪካ ውስጥ ያለውን መዋቅራዊ ዘረኝነት እንዲቆም ጥያቄዎችን አስነስቷል። ዴሪክ ቾቪንን ጨምሮ ሦስቱ ፖሊሶች ከሥራም ተባረዋል። በፖሊስነት ለአስራ ዘጠኝ አመታት ያገለገለው ዴሪክ ቾቪን በትናንትናው ዕለት በኢንተርኔት አማካኝነት በተደረገ የፍርድ ሂደት ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርቧል። ለአስራ አምስት ደቂቃ ያህል በነበረውም የፍርድ ሂደት ላይ አንድም ቃል ያልተነፈሰ ሲሆን እጁ በሰንሰለት ታስሮ ብርቱካናማ የመለዮ ልብስ አጥልቆ አነስ ባለች ጠረጴዛ ትይዩ ተቀምጦ ነበር። ዳኛዋ ጂኒስ ኤም የጆርጅ ፍሎይድን ቤተሰቦች በምንም መንገድ እንዳያገኝ፣ የጦር መሳሪያውን እንዲያስረክብና የፍርድ ሂደቱም እስኪጠናቀቅ ከፀጥታ ኃይል አባልነቱ እንዲሰናበት የሚሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ 1.25 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ዋስ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ጠበቃውም የገንዘብ ዋሱን አልተቃወሙም። ፖሊሱ ሶስት ክሶች የቀረቡበት ሲሆን እነዚህም ያልታሰበበት ሁለተኛ ደረጃ ነፍስ ማጥፋት፣ ሦስተኛ ደረጃ ነፍስ ማጥፋት እንዲሁም ለግድያ ማድረስ የሚሉ ሲሆን፤ በእነዚህም ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ በያንዳንዳንዳቸው 40፣ 25ና አስር ዓመት የተቀመጠው ከፍተኛ ቅጣት ተፈፃሚ ይሆንበታል። ፍርድ ቤቱም ለሰኔ 22/2012 ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል። የአርባ አራት ዓመቱ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በሚኒሶታ በሚገኝ እስር ቤት ያለ ሲሆን ለበርካታ ጊዜያትም ተዘዋውሯል። ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች ክሶች ይቀርቡበታል እየተባለ ሲሆን፤ ነገር ግን በመጀመሪያ ደረጃ የግድያ ወንጀል ላይጠየቅ የሚችልበት እድል በጣም ከፍተኛ ነው ተብሏል። ለዚህም እንደምክንያትነት የቀረበው አቃቤ ሕጉ ፖሊሱ የግድያውን ወንጀል ለመፈፀም ሆን ብሎ ማቀዱን፣ ነፍስ ለማጥፋት የነበረውን ፍላጎት እንዲሁም ምክንያት ማምጣት ሊኖርባቸው እንደሚችል አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የሚኒያፖሊስ ከተማ በበኩሉ የፖሊስ አባላት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያደርጉትን አንገትን ጠምልሎ መያዝ አንዲሁም ማነቅ ያገደ ሲሆን ዲሞክራቶችም በፖሊስ ተቋም ላይ ለውጥ እንዲመጣ አዲስ የሕግ ረቂቅ አቅርበዋል። በአሜሪካ ውስጥ የሚደረጉ የፀረ ዘረኝነት ተቃውሞዎች የቀጠሉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ሚኒያፖሊስ ከመምጣቱ በፊት ጆርጅ ፍሎይድ በኖረባት ቴክሳስም አስከሬኑ ለስድስት ሰዓታት ያህል እንዲሰናበቱት በፋውንቴይን ኦፍ ፕሬይዝ ቤተክርስቲያን ቀርቧል። በትናንትናው ዕለት በሂውስተን፣ ህይወቱ ባለፈባት ሚኒያፖሊስና በትውልድ ቦታው ሰሜን ካሮላይና የሐዘን ሥነ ሥርዓትም በትናንትናው ዕለት ተደርጓል። ብዙዎችም ሐዘናቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው። ባለፈው ሳምንት ቅዳሜም አስከሬኑ ወደ ቴክሳስ ተሸኝቷል። የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦች ጋር ተገናኝተው ሐዘናቸውን ገልፀዋል። "አዳምጠውናል፤ ህመማችንን ሰምተዋል እናም በተቻለ መጠን ተጋርተውናል" በማለት የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ ቃለ አቀባይ ቤንጃሚን ክራምፕ ከፎቶ ጋር በትዊተር ገፁ አጋርቷል።
news-53690902
https://www.bbc.com/amharic/news-53690902
ኮሮናቫይረስ፡ የብሪቲሽ ኤርወይስ ሠራተኞች ቁርጣቸውን የሚያውቁት ዛሬ ነው
የሠራተኛ ማህበራት 'ጥቁሩ አርብ' ሲሉ ሰይመውታል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ለዓመታት ብሪቲሽ ኤርዌይስን ያገለገሉ የበረራ ሠራተኞች ቁርጣቸውን የሚያውቁበት ቀን ነው ዛሬ [አርብ]። ከሥራ መባረር ቢቀርላቸው እንኳ ድመወዛቸው አናቱን ተመቶ ነው የሚደርሳቸው። ከቀጣሪ ድርጅታቸው ጋር ያላቸውም ግንኙነት እንደ ቀድሞ የሚሆን አይመስልም። ኢንጂነሮችና ሌሎች የየብስ ስራውን የሚያከናውኑትን ጨምሮ የቢሮ ሠራተኞችም ከአየር መንገዱ ጋር መፃዒ ዕድል ይኑራቸው አይኑራቸው ቁርጡ የሚለየው ዛሬ ነው። ብሪቲሽ ኤርዌይስ በበረራ ኢንዱስትሪ መቀጠል ካለብኝ ሠራተኞችን መቀነስ የግድ ይለኛል ያለው ከሳምንታት በፊት ነበር። ነገር ግን ይህን ለማድረግ የወሰነበር መንገድ ብዙዎችን አስቆጥቷል። "ከደመወዜ ላይ ግማሽ ያህሉ ሊቆረጥብኝ ይችላል" ትላለች የበረራ አስተናጋጇ ቪኪ። "ብቻዬን ነው ልጅ የማሳድገው። እንዴት አድርጌ ነው 50 በመቶ ደመወዜን ዓይኔ እያየ የምሰጠው?" ለዚህ ዘገባ ሲባል ስሟን የቀየረችው ቪኪ በ30ዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ ሲሆን ብሪቲሽ ኤርዌይስን [ቢኤ] ከ15 ዓመታት በላይ አገልግላለች። ምንም እንኳ የምትኖረው ከአየር ማረፊያው ራቅ ብሎ በሰሜን ምስራቅ ለንደን ይሁን እንጂ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ሄትሮ ወደ ሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ተቃውሟቸውን ለማሰማት ካቀኑ ሠራተኞች መካከል ነበረች። "ይህ ለኔ በጣም አስጨናቂ ጊዜ ነው። እጅግ በጣም ተበሳጭቻለሁ።" ብላለች። የዚህ ሁሉ ጣጣ መንስዔ ኮሮናቫይረስ ነው። ብሪቲሽ ኤርዌይስ ልክ እንደ ሌሎች አየር መንገዶች ሁሉ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የምጣኔ ሃብት ድቀት ደርሶበታል። እስከ ባለፈው ሰኔ ድረስ ብቻ የ700 ሚሊዮን ዩሮ ኪሳራ ደርሶበታል። በተለይ እንግሊዝና አውሮፓ የእንቅስቃሴ ገደብ በጣሉበት ወቅት ለሳምንታት ያክል በቀን በጣት ከሚቆጠሩ በረራዎች በላይ ማከናወን አልቻለም። ኩባንያው የበረራ ኢንዱስትሪ እስከ ፈረንጆቹ 2023 ድረስ አያገግምም ይላል። አየር መንገዱ ባለፈው ሚያዚያ ነው ሠራተኞችን ሊቀንስ እንደሚችልና የማይቀነሱ ሠራተኞች ደግሞ ደመወዛቸው እንደሚቆርጥ ይፋ ያደረገው። ኩባንያው ከሠራተኞች ማሕበራት ጋር ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ዕቅዱን እንደሚገፋበት አስታውቆ ነበር። ይህን የሚያደርገውም ለሠራተኞች ቁርጣቸውን የሚያሳውቅ ደብዳቤ በመበተን መሆኑን ተናግሯል። የሠራተኞ ማሕበራት ይህ የአየር መንገዱ ውሳኔ አስቆጥቷቸዋል። በርካታ የሕዝብ እንደራሴዎችም የአየር መንገዱን ውሳኔ ሲተቹ ነበር። ወግ አጥባቂው ሃው ሜሪማን 'ይህ ግንባር ላይ ሽጉጥ እንደመደገን ነው' ሲሉ ተደምጠዋል። ነገር ግን እስካሁን ድረስ የአየር መንገዱን ሠራተኞች በሚወክሉ ማሕበራትና በአየር መንገዱ መካከል ስምምነት አልተደረሰም። አየር መንገዱ ደግሞ በዕቅዴ መሠረት ደብዳቤ ልበትን ነው እያለ ነው። ጆን [ስሙ የተቀየረ] በ50ዎቹ ዕድሜው የሚገኝ ለብሪቲሽ ኤርዌይስ የሚያገልግል ኢንጂነር ነው። የጆን ጭንቀት ደግሞ ከተባረርኩ እንደ እኔ ዕድሜው የገፋ ሰውን የሚቀጥር ሌላ ድርጅት የለም የሚለው ነው። ጆንም ሆነ ቪኪ ቁርጣቸውን ዛሬ ያውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። አየር መንገዱ በዕቅዴ መሠረት እገፋበታለሁ ይበል እንጂ የሠራተኛ ማህበራት ደግሞ እርምጃ እንወስዳለን በማለት እየዛቱ ነው።
news-48313496
https://www.bbc.com/amharic/news-48313496
የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ
ከግንቦት 1981'ዱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጠንሳሾች ኹነኛው የነበሩት ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ናቸው። ልጃቸው አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ አሁን በአሜሪካን አገር የሕግ አዋቂና ጠበቃ፣ በማሳቹሴት የወንጀል ጉዳይ ጠበቆች ማኅበር ፕሬዝዳንትም ናቸው።‹‹አባቴ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ የነበረው ፍቅር ወደር አልነበረውም›› የሚሉት አቶ ደረጄ የልጅነት ውብ ትዝታቸውን፣ ልክ የዛሬ 30 ዓመት የሆነውን በግርድፉ ለቢቢሲ እንዲህ አጋርተዋል።
በኩርኩም እንወራረድ! ልጅ እያለሁ… ከአባቴ ጋር ሰፈር ውስጥ አዘውትረን ‹‹ዎክ›› እናደርግ ነበር። በተለይ ምሽት ላይ…ቦሌ መንገድ ላይ… ትዝ ይለኛል አባቴ ቀጥ ብሎ፣ ደግሞም አንገቱን ቀና አድርጎ ነበር የሚራመደው። እኔ ደግሞ ብርቱካኔን እያሻሸሁ፣ ከሥር ከሥሩ እየተራመድኩ በጥያቄ አጣድፈዋለሁ… "በጦርነት ላይ እንዴት ነው መድፍ የሚመታው?" "አስተኳሹ አለ፤ እሱ የርቀቱን መጠን ለክቶ በሚሰጠው ምልክት ነው የሚተኮሰው። አንዳንድ ጊዜም ግምት መጠቀም የሚገደድበት ሁኔታ አለ" "ርቀት ሳይለካ እንዴት ማወቅ ይቻላል? "ዘዴ አለው…" • ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት • ''ኢትዮጵያን ወደተሻለ ስፍራ ሊወስዳት የሚችል ሌላ መሪ የለም'' የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት "እንዴት በግምት ይሆናል…አባዬ? ለምሳሌ አንተ ከዚህ እስከዚያ ፎቅ ድረስ ያለውን ርቀት መገመት ትችላለህ?" "በሚገባ" "ስንት ሜትር ይሆናል?" "መቶ ሀምሳ" ፈርጠም ብሎ መለሰልኝ። "አይሆንም! መቶ ከሞላ ይገርመኛል" አልኩት። "ትወራረዳለህ?" አለኝ ቆም ብሎ፣ በአባታዊ ፈገግታ እየተመለከተኝ። "እንወራረድ!" አልኩ የእርምጃ ልኬቱን ለመጀመር ቆም ብዬ… "በምን ትወራረዳለህ?" አለኝ ሳቁን እየታገለ… "በኩርኩም" አባቴ ከት ብሎ ሳቀና፣ "እንዴ! በፈለኩት ሰዓት ጠርቼ ልኮረኩምህ ስችል ለምን በኩርኩም እወራረዳለሁ?'' አለኝ። "እሺ ታዲያ በምን ይሁን?" "እንግዲያውስ ከተሸነፍክ የያዝካትን ብርቱካን እበላለሁ፤ ካሸነፍክ ግን ትኮረኩመኛለህ" አለኝ እየሳቀ። ተስማማሁ። እያንዳንዱ እርምጃ ወደ አንድ ሜትር እንዲቀርብ ረዘም እያደረክ ቁጠር ብሎ ከቆምንበት ቦታ እርምጃውን እየሳቀ አብሮኝ መቁጠር ጀመረ። ቤታችን ስንደርስ ለብዙ ሰዓት ያሟሟኋትን ብርቱኳኔን ልጣጯን ልጦ፣ አንዳንዴም በማብሸቅ መልክ ፈገግ ብሎ ቁልቁል እየተመለከተኝ፣ ሳቁ አፍኖት እየበላት ነበር። በወቅቱ በልጆች ሳይቀር ይዘወተር የነበረው የሰላምታ አሰጣጥ። ‹‹ማታ ማታ ጄኔራል ፋንታ እኛ ቤት ይመጡ ነበር›› ድሮ ቦሌ ድልድይ አካባቢ ‹‹ካራማራ›› የሚባል ሆቴል ነበር። የኛ ቤት በዚያ ገባ ብሎ ነው፤ ሶማሌ ኤምባሲ ፊት ለፊት። አባቴ በየአውደ ግንባሩ ውሎ ቤት ሲመጣ እጅግ ደስ ይለናል። እንቦርቃለን። ትምህርት ቤት በሄድንበት ቤት ገብቶ ወጥቶ ከሆነ በሚል ቁምሳጥን ከፍተን ከልብሶቹ ጠረኑን ፍለጋ እናሸታለን። ከዚያ በፊት ግን በሱ የሥራ ባህሪ ምክንያት ብዙ ቦታ ኖረናል። ለምሳሌ ሐረር። እንዲያውም አባቴ ከጄኔራል መርዕድ ጋ በደንብ የተቀራረቡት ያኔ ይመስለኛል። ለነገሩ እነሱ ድሮ ካዴት እያሉም ይተዋወቃሉ። • የዛሬ 30 ዓመት... የኮ/ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም? • በኤርትራ የማህበራዊ ድረ ገጾች አገልግሎት ተቋረጠ ጄ/ል መርዕድ ንጉሤ ለተወሰነ ጊዜ ከሠራዊቱ ወጥተው የሐረርጌ ክፍለ አገር አስተዳዳሪ ሆነው ነበር። ያን ጊዜ ክረምት ነበር። እኔም ካባቴ ጋ ሐረር ነበርኩ። እና ጋሽ መርዕድ የተመደበላቸው ቤት እየታደሰ ስለነበር እኛ ቤት ይኖር ነበር። ማታ ማታ አብረው ሲጫወቱ እኔም እዛ የሚጠጣ ምናምን እያቀረብኩኝ ቁጭ እላለሁ። ጋሽ መርዕድ ልጆች ይወዳል። በጣም ያቀርበን ነበር። የሚነጋገሩትን ነገሮች በሙሉ እሰማ ነበር። ብዙውን ጊዜ የአገሪቷን ችግር ነበር የሚያወሩት። የጦርነት ሁኔታ እንደረበሻቸው፣ በሰሜኑ ጦርነት የሚያልቀው ሠራዊት ቁጥር ያንገብግባቸው እንደነበር አስታውሳለሁ። እርግጥ ስለመፈቅለ መንግሥት ወይም እንደዚያ የሚመስል ነገር እኔ ፊት ሲያወሩ ትዝ አይለኝም። የጄ/ል ፋንታ በላይ እና የኔ አባት ግንኙነት እየጠነከረ የመጣው ደግሞ ‹‹የባህረ ነጋሽ›› እና ‹‹የቀይባህር ዘመቻ›› ጊዜ ይመስለኛል። አባቴ ከሐረር ምሥራቅ እዝ አዛዥነት ለተወሰነ ጊዜ ኤርትራ ሄዶ እነዚህን ሁለት ዘመቻዎች በአስተባባሪነት መርቶ ነበር። በዚያ ጊዜ ጄኔራል ፋንታ የአየር ኃይል አዛዥ ነበሩ። እንዲያውም በባሕር ኃይልና በአየር ኃይል የተቀነባበረ ጥቃት ለአንድ ጦርነት ሲደረግ ለመጀመርያ ጊዜ ይመስለኛል። በዚያ ጦርነት ገፍተው ሄደው ናቅፋን ለመያዝም ጥረት አድርገው ነበር። ከዚያ በፊት ባሬንቱን ጭምር አስለቅቀው ነበር። ያ ጦርነት አባቴንና ጄ/ል ፋንታን አቀራርቧቸዋል ይመስለኛል። ለምን መሰለህ እንደዚያ የምልህ…ከዚያ በኋላ ማታ ማታ ጄኔራል ፋንታ እኛ ቤት ይመጡ ጀመር። የኔ አባት ከመጣ ጄ/ል ፋንታም ይመጡና ረዥም ሰዓት ያወራሉ። እኛ ቤት ማንኛውም ሚኒስትርም ሆነ ጄኔራል ከመጣ እኛ ልጆች ውጡና ውጭ ተጫወቱ አንባልም፤ ቁጭ ብለን ማዳመጥ ይፈቀድልን ነበር፤ ምንም ችግር አልነበረውም። ጄ/ል ፋንታ ከመጡ ግን እንደሱ ብሎ ነገር የለም። ለብቻቸው ነው የሚያወሩት፤ ሳሎን ማንም አይገባም። ደግሞ ሳሎን አውርተው ሲበቃቸው አልፎ አልፎም በአንድ መኪና ወጣ ብለው ይመለሳሉ። አስታውሳለሁ ጄ/ል ፋንታ ቶዮታ ነበረቻቸው። • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች አሁን መለስ ብዬ ሳብሰለስል ያ ጊዜ 'ስለ መፈንቀለ መንግሥት መወጠን የጀመሩበት ጊዜ ይሆን?' እላለሁ። ጋሽ መርዕድና ጄኔራል አበራ እኛ ድሮ ገና ከልጅነታችን ቤታችን ሁልጊዜ ሲመጡ የምናያቸው ጄ/ል መርዕድን ነበር። ከጄ/ል መርዕድ ጋ እኮ በጣም ቅርብ ነበርን። እንዳውም አባቴ የጋሽ መርዕድ የመጀመርያ ወንድ ልጅ የክርስትና አባት ሲሆን እናቴ ደግሞ የትልቋ ሴት ልጃቸው የክርስትና እናት ናት። ያን ያህል ቅርብ ነበርን። ጄ/ል መርዕድ ቤታቸው ጎፋ ቄራ ነበር፡፡ ቢሆንም እኛ ቤት ብዙ ጊዜ ይመጡ ነበር፡፡ ከጄ/ል አበራ ጋ ደግሞ አባቴ የምሥራቅ ዕዝ አዛዥ እያለ እሳቸው ምክትል ነበሩ። ከአየር ወለድ ጀምሮ ከአባቴ ጋር ይተዋወቃሉ። ጄ/ል አበራ ብዙ ልምድ ያላቸው አዋጊ አዛዥ ነበሩ። እና ይቀራረቡ እንደነበር አስታውሳለሁ። እንግዲህ መርዕድ፣ ፋንታ፣ አበራና አባቴ በዚህ ሁኔታ ተቀራርበው መፈንቅለ መንግሥቱን የወጠኑት ይመስለኛል፡፡ ከቀኝ ወደ ግራ ኤዲ አሚን ዳዳ፣ ተፈሪ በንቲ፣ መንግሥቱ ኃይለማርያም። ጥር 1፣ 1968፥ አዲስ አበባ። "የአገሪቱ ኢኮኖሚ ኮዳ መግዛት አይችልም ነበር" እንግዲህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስሰማቸው አገሪቱ ውድቀት ላይ እንደነበረች ነበር የሚያወጉት ብዬኻለሁ። በኤርትራ የሚደረገው ጦርነት በንግግር መፈታት እንዳለበት፥ በትግራይ የነበረው የፖለቲካ ችግር ለመሀል አገርም እንደሚተርፍ ወዘተ...፤ በነዚህ ነጥቦች ላይ ተቀራራቢ አመለካከት የነበራቸው ይመስለኛል። ለነገሩ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ጦርነቱ ከብዶት ነበር። ከቆርቆሮ ኮዳ አቅም እንኳ ፕላስቲክ ኮዳ መግዛት የሚከብደው ነበር። የተራበ ጦር ነበር። ሠራዊቱ ኮቾሮ እየበላ ያን ሁሉ ዓመት መዋጋቱ ራሱ የሚገርም ነው። የቆረቆዘ ኢኮኖሚ ይዞ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጋ ጦር ሠራዊት ማስተዳደር እንደማይቻል አባቴና ጓደኞቹ የተረዱ ይመስለኛል። በተለይ ሠራዊቱ የሚከፍለው የተጋነነ የሕይወት ዋጋ በየጦር አውድማው ሲመለከቱ እየተበሳጩ እንደመጡ መገመት ይቻላል። ይህን ይህን እያዩ መተኛት ሲያቅታቸው ይመስለኛል ወደ መፈንቅለ መንግሥት ሐሳብ የደረሱት። ነገር ግን ቀደም ሲልም እንደነገርኩህ እዚህ የደረሱት በአንድ ቀን አይደለም። አሁን ወደ ኋላ ተመልሼ ሳስበው... እኔ ነፍስ አወቅኩ ከምልበት ጊዜ ጀምሮ ነው የምልህ...የሰሜኑ ጦርነት መቆም እንዳለበት ነበር የሚያወሩት። መቼስ መፈንቅለ መንግሥቱ የዚህ ሁሉ ድምር የወለደው ነው የሚሆነው....፡፡ "አባቴን የማገኘው ጦር ሜዳ እየሄድኩ ነበር" ከልጅነቴ ጀምሮ ከጦሩ ጋር ነው ያደጉት። ምክንያቱ ደግሞ አባቴ ነው። ሕይወቱ በየአውደ ውጊያው ነበር።፡ እንዲያውም በሦስት የኢትዮጵያ ግንባር የኢትዮጵያን ጦር ለመምራት ዕድል ያገኘ ብቸኛው ጄኔራል አባቴ ይመስለኛል። ምሥራቅ፣ ደቡብና ሰሜን። • እናት አልባዎቹ መንደሮች መጀመርያ ሐረር አካዳሚ እንኖር ነበር ብዬኻለሁ። አባቴ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የጦር ስልጠናና ትምህርት ዳይሬክተር ነበር። በዚህ ረገድ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ዳይሬክተር መሆኑ ነው። ከዚያ በፊት እንግሊዞችና ሕንዶች ነበሩ የሚያስተዳድሩት። እዚያ የመኮንኖች መኖርያ ካምፕ ነበረ፤ ሐረር አካዳሚ ፊት ለፊት። መንገድ ተሻግረን ካዴቶች ሰልፍ ሲሰለፉ ነው የምናየው። እግር ኳስ እንጫወታለን። "ተስፋዬ ቼንቶ" የሚባል በጣም የሚታወቅ ተጫዋች ነበር። ኳስ ያጫውተን ነበር። አባቴ ደቡብ እዝ እያለ ደግሞ ጦር ሰፈር እንውላለን። ያየነውን በጨዋታ መልክ እንናገራለን። ከዚያ በኋላ የመድፈኛ የታንክ ትርኢቶች፣ የወታደር ምረቃ አንድም አያመልጠንም። ወንድሜ ለምሳሌ ባሌ ዶሎ ፊልቱ ጦር ሜዳ ሄዷል፤ ከአባቴ ጋር። እጅግ ከባድ ጦርነት የተካሄደበት ቦታ'ኮ ነው። እኔ ደግሞ ጭንአቅሰን፣ ከረን ከዚያ እስከ አፋቤት፣ ግዝግዛ፥ መሳአሊት ሄደናል። በጣም መጥፎ ቦታዎች ነበሩ። ሬሳ እያየህ፣ ጦርነት እየተካሄደ ነው ታዲያ...። መድፍ ወደፊት እየተተኮሰ ሁሉ አባቴ ይዞኝ ይሄድ ነበር። ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ፥ ቁምላቸው ደጀኔ እዛ እንዳገኘናቸው ትዝ ይለኛል። ኮ/ል አምሳሉ ገብረዝጊም ነበረ። እንዳውም የጦር ሜዳ መነጽር ሁሉ ከሱ ተቀብዬ ተራራ ላይ የሚካሄደውን ጦርነት ሁሉ አይቻለሁ። እና ከልጅነታችን ጀምሮ አባቴ ስለ ኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት እንድናውቅ፤ የአገር ፍቅር እንዲያድርብን ይፈልግ ነበር። ለምሳሌ አንደኛው ብሔራዊ ውትድርና ጥሪ ሲደረግ የማንም ጄኔራል ልጅ ብሔራዊ ውትድርና የሄደ አልነበረም። የኔ አባት ግን "ይሄ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የመጣ ሕግ ነው፤ የኔ ልጅ ከተጠራ መሄድ ነው ያለበት" ብሎ ወሰነ። በዚህም ምክንያት ወንድሜ ብሔራዊ ውትድርና ዘምተ። እረፍት በማይሰጠው ጦርነት የተነሳ አባቴ እቺን ታህል ፋታ አልነበረውም። እኔ ለምሳሌ በአንድ ወቅት አሥመራ ልጠይቀው ሄጄ ላገኘው አልቻልኩም። እኩለ ሌሊት ነው ወደ ቤት የሚመጣው። ማልዶ ነው ቢሮ የሚገባው። አንዳንድ ጊዜም ቢሮ ያድራል፤ እዛው ታጣፊ ፍራሽ አለችው። በተደጋጋሚ ብሞክርም ላገኘው ስላልቻልኩኝ መልእክት ላኩበት፤ • ኢትዮጵያ ሀይቆቿን መጠበቅ ለምን ተሳናት? «አባዬ! እዚህ አሥመራ ድረስ መጥቼ ሳንገናኝ ልመለስ ነው ወይ?» ስለው ‹‹እንግዲህ በዚህ ወቅት ሥራ ትቼ ወዳንተ አልመጣም፤ ወይም ለምን የሚሊተሪ ልብስ ለብሰህ ከኔ ጋ ጦር ሜዳ አትመጣም፤ ያለው ዕድል እሱ ብቻ ነው…›› አለኝ። እንዳለው አደረኩ። ያኔ ምጽዋ እንዳይያዝ የሚደረጉ ጦርነቶች ነበሩ። ጄ/ል ዋሲሁን ንጋቱ ታንከኛ ያሰለጥኑ ነበር፤ እዛ ሄድን። ከረን ጄ/ል ታደሰ ተሰማ የሚመሩት መምሪያ ነበር፤ ተራራ ላይ ያለ። እዛም ሄደን ነበር። ብቻ ምን ለማለት ነው...ጦር ሜዳ ሄጄ የአባቴን ናፍቆት ተወጥቼ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ እልኻለው። የሐረር አካዳሚ ምረቃ በዓል፤ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ (ቀኝ) የጦር ትምህርትና ስልጠና የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዳይሬክተር "መፈንቅለ መንግሥቱን ያካሄዱት ለሥልጣን ነው የሚሉ ሰዎች ይገርሙኛል" አባቴን በደንብ ስለማውቀው ነው ይህንን የምናገረው። በጦርነቱ የሚያልቀው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ሁልጊዜም ይረብሸው ነበር። የሰሜኑ ችግር በፍጹም በጦር እንደማይፈታ ጠንቅቆ የተረዳ ይመስለኛል። አንዳንዶች ያንን ዘመን በአሁን መነጽር እያዩት የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ይደርሳሉ። እውነት ለመናገር አባቴን ጨምሮ ብዙዎቹ የገንዘብ፣ የጥቅም ሰዎች አልነበሩም። "ለሥልጣን ነው" የሚሉ ሰዎች ደግሞ ይበልጥ ያስገርሙኛል። ብዙዎቹ የመፈንቅለ መንግሥቱ አቀናባሪዎች እኮ በአገሪቱ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ሥልጣን የነበራቸው ናቸው። መንግሥት ቢገለበጥም ከያዙት ሥልጣን በላይ ሥልጣን አያገኙም። ከየት መጥቶ? መቼስ በአንድ አገር መሪ የሚሆነው አንድ ሰው ብቻ ነው። የቀሩት ሚኒስትርና የጦር አዛዦች ነው ሊሆኑ የሚችሉት። ናቸውም። አንዳንዴ ጉዳዩን ፍትሐዊ ሆነን በሚዛን መመልከት ጥሩ ነው። አንድ በአንድ እንየው ካልከኝም እሰየው። ጄ/ር መርዕድ የኢትዮጵያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ናቸው። ፋንታ በላይ ሚኒስትር ናቸው። አባቴ ኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፉን የሰሜን ጦር የሚመራ ጄኔራል ነው። ጄ/ል ኃይሉ የምድር ጦር አዛዥ ናቸው፤ አድሚራል ተስፋዬ የባሕር ኃይል አዛዥ ናቸው፤ ጄ/ል አመኃ አየር ኃይል በእጃቸው ነው። ሌሎቹም እንደዚያው። ሰከን ብለን፣ ወቅቱን አገናዝበን፣ ነገሩን ካሰብነው እያንዳንዳቸው ይሄን አገኛለሁ ብለው አይደለም እንዲህ ዓይነት እሳት ውስጥ የገቡት። በፍጹም የገንዘብ፣ የሥልጣን ሰዎች አልነበሩም ነው የምልህ። መንግሥት ያኔ በነጻ አምስት መቶ ካሬ ሲሰጥ እኮ ያልወሰዱ ናቸው። ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ ቤት አልባ የሆኑና የተበተኑ ብዙ ናቸው እኮ። በኔ እምነት ያን ሙከራ ያደረጉት የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ እንቅልፍ ነስቷቸው ነው። በፍጹም ስለገንዘብ የሚያስቡ ሰዎች አልነበሩም። ያደጉትም እንደዚያ አልነበረም። ብዙ ጊዜያቸውን አገሪቷ እንዴት አንድነቷ እንደሚጠበቅ ነበር የሚጨነቁት። እንዲያውም ብዙዎቹ ጄኔራሎች ልጆቻቸውን ካስተማሩ ያ በቂያቸው ነበር። ቆይ እንደውም፣ የኮ/ል ግርማ ተሰማን ታሪክ ታውቀዋለህ? የሚገርሙ ሰው ናቸው… በመፈንቅለ መንግሥቱ ጊዜ በናቅፋ እስርቤት ውስጥ ነበሩ፤ ተማርከው። የምርኮኞች ተጠሪ ነበሩ። ኩዴታው በማስመልከት የተኩስ ማቆም ስምምነት ተደርጎ ነበር። እሳቸው ጦሩ ወክሏቸው አሜሪካ ድረስ እየሄዱ ንግግር ያደርጉ ነበር። ታዲያ አሜሪካ መጥተው ጥገኝነት አልጠየቁም። እየቻሉ። "የወከለኝ ጦር እዛ እስር ቤት እያለ እኔ እነሱን ጥዬ አልቀርም" ብለው አሜሪካን አገር ሥራቸውን ሠርተው ተመልሰው ናቅፋ እስር ቤት ነው የገቡት። ማን ነው ይሄን የሚያደርግ? [ይሄ የወቅቱን ሰዎች ሥነልቦና በተወሰነ መልኩ ይወክል እንደሁ አላውቅም።] ኮ/ል ግርማ ኤርትራ የራሷን መንግሥት ስትመሠርት ተፈተው፣ አዲስ አበባ ሄደው፤ የድሮ ጡረታቸውን እየበሉ ኖረው በቅርብ ነው ያረፉት። ያን ጊዜ ብዙዎቹ የጥቅም ሰዎች አልነበሩም የምልህ ለዚህ ነው። እነ ደረጀ ደምሴ "ያቺን ሰዓት" ግንቦት 8 ድንገት ቤታችን ተንኳኳ፡፡ ደጅ የወታደሮችን ሁኔታ ሲያዩ ነው መሰለኝ ዘበኞች በሩን መክፈት ፈሩ። ሄጄ በሩን ከፈትኩ። ከአሥመራ የመጡ ወታደሮች ናቸው። ከወታደሮቹ መሐል የአባቴን አጃቢ ዐሥር አለቃ ጌታቸውን ስላየሁት ተረጋጋሁ። ከነሙሉ ትጥቁ ቆሟል፡፡ «ተልከን ነው የመጣነው» አለኝ፤ ከአሥመራ ሁለቱ የአባቴ አጃቢዎች፣ ሁለቱ ደግሞ ያን ጊዜ የአባቴ ምክትል የነበሩት የጄ/ል ሁሴን አጃቢዎች ናቸው፡፡ «ምንድነው ምን ተፈጠረ?» ብለን ስንጠይቃቸው አውሮፕላኑ ውስጥ የነበረውን ሁኔታ አስረዱን። እነሱ በቀጥታ ከአሥመራ ስለመጡ መንግሥቱ መገደሉን ነው የሚያውቁት። በኔ አባት አመለካከት ደግሞ መፈንቅለ መንግሥቱ በታቀለደለት ሁኔታ እየሄደ ነው። ከአሥመራም ይህንኑ የሚያሳካ ጦር ተልኳል። መንጌም አብቅቶለታል። በዚህ ሁሉ ግርግር የተለያዩ ሰዎች ወደኛ ቤት ሊሄዱ ይችላሉ ብሎ ገምቷል። ለዚህ ነው ወታደሮችን የላከው ይመስለኛል። በዚያ ላይ ሰፈራችን ብዙ ሹማምንት ያሉበት ነው። ከኛ ቤት አለፍ ብሎ የፍቅረሥላሴ ወግደረስ ቤት አለ። በጀርባም በኩል ሌሎች የደርግ አባሎች አሉ። እና ያው አባቴ አጃቢዎቹን የላከልን የተወሰነ ከለላ ከሰጧቸው ብሎ ይመስለኛል። ነገሩ አላማረንም፡፡ ሁኔታዎች እስኪጠሩ ድረስ ከቤት ወጥተን ማረፍ እንዳለብን ተነጋግረን፤ እናቴም፣ እኔም፣ ወንድሜም ሁለት እህቶቼም ሌላ ቦታ ሄደን አደርን። ዘመድ ቤት ሊደረስበት ስለሚችል ዩሱፍ ዘከሪያ የሚባል የቤተሰብ ወዳጅ ጋ ሄደን ተደበቅን። የኤርትራ ነጻ አውጪ ተዋጊዎች በናቅፋ አካባቢ ጦርነት ላይ ሳሉ፤ ሐምሌ 3/1970 ማክሰኞ ግንቦት 8 ምሽት፣ 1981 አዳር አትበለው። አስጨናቂ ምሽት ነበረ። ሬዲዮ ስንጎረጉር ስንጎረጉር…። የአሥመራ ሬዲዮ ምን እንደሚል ለመስማት ነበር ሙከራችን። ጆሯችን ሬዲዮ አይናችን ቴሌቪዥን ላይ ተክለን ቆየን። እንደሚባለው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ ከሆነ አባታችን ከየትኛው ወገን እንደሚሆን እርግጠኞች ስለሆንን ነው ጭንቀታችን የበዛው። ምሽት አራት ሰዓት ገደማ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በጥቂት ሰዓቶች ውስጥ የማስተላልፈው ሰበር ዜና አለኝ አለ። የሁላችንም ልብ ቆመ። ቆይቶ ዜና አንባቢው መጣና በጥቂት ጄኔራሎች መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ መክሸፉን ተናገረ። የጄ/ል መርዕድና የጄ/ል አመሓን ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ጠቀሰ። ክው ብዬ ቀረሁ። እናቴና እህቴ ተንሰቅስቀው ማልቀስ ጀመሩ። የአባቴ ሁኔታ ምን ሊሆን እንደሚችል በማሰብ ጭንቅላቴ እረፍት አጣ። የአሥመራ ሬዲዮ በበኩሉ የመንግሥቱ ኃይለማርያም የ15 ዓመታት አምባገነን አገዛዝ ማክተሙን ያወራል። አባቴ መቼስ እዚህ ሙከራው መክሸፉን ሲያውቅ አውሮፕላን እስነስቶ ከአገር ይወጣል። ይሄ ለሱ በጣም ቀላሉ ነገር ነው። ራሴን ማጽናናት ጀመርኩ። እናቴንም እንዲሁ ማጽናናት ጀመርኩ… ረቡዕ፤ ግንቦት 9፣ 1981 በነገታው እሮብ ሁላችንም አንድ ቦታ ማደር እንደሌለብን ተነጋገርን፡፡ መለያየትማ የለብንም አሉ እህቶቼ፡፡ እኛ ደሞ በፍጹም አልን… እጅህን ካልሰጠህ እንገድላቸዋለን ቢሉትስ፡፡ በዚያ ላይ ትናንት ወደዚህ ቤት ስንመጣ ያየን ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ሌላ የማይጠረጠር ቤት ተበታትነን መቆየት ነው የሚሻለው፡፡ ተስማማን፡፡ እኔና ወንድሜ ሽመልስ የሚባል ጓደኛዬ ጋ፤ እናትና እህቶቼ ባላምባራስ ጥበቡ የሚባሉ ቤተሰብ ጋ ተበተንን፡፡ ባላምባራስ ጥበቡ ባለውለታችን ናቸው፡፡ አሁንም በሕይወት አሉ፡፡ ማታ ከጓደኛዬ ሽመልስ ጋ እናወራለን፤ ጭንቀቱን ለማቅለል፡፡ አባቴ ሙከራው እዚህ አዲሳባ ከከሸፈ ለምን ቶሎ ከአገር አልወጣም እያልኩ እብሰለሰላለሁ፡፡ ረቡዕ ማታ መንግሥቱ ኃይለማርያም ጉብኝታቸውን አቋርጠው ተመለሱ፡፡ የአሥመራ ሬዲዮን ስጎረጉር ግን አሁንም የመንግሥቱ አምባገነን አገዛዝ ማክተሙን፤ የተለያዩ የጦር ክፍሎች ደግሞ ድጋፍ ስለመስጠታቸው ነው የሚያትተው፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ አባቴ በዚህ ሁሉ መሀል የት ነው ያለው? ሐሙስ ግንቦት 10፣ 1981 ሐሙስ ማታውኑ የአሥመራው ሙከራ መክሸፉን ሰማን። ስለ አባቴ ግን ምንም የሰማሁት ነገር አልነበረም። ጠዋት አካባቢ ድንገት እንዲህ ነው የማልለው ከፍተኛ የስሜት መረበሽ ደረሰብኝ። ምንም የሰማሁት ነገር የለም'ኮ፣ ግን በበዛ ሐዘን ራሴን መቆጣጠር ተሳነኝ። የመጣው ይምጣ ብዬ ከጓደኛዬ ቤት ወጥቼ ወደ ቤታችን መሄድ ጀመርኩ። ቤታችን አካባቢ ጄ/ል ግዛው በላይነህን አየኋቸው። አባቴን በጣም ይወዱት የነበሩ ሰው ናቸው። ሌሎች ሰዎችም ቤታችን አካባቢ ይንቀሳቀሳሉ። ደስ አይልም። በቃ ሁኔታውን ገባኝ። (ከግራ) ሜ/ጄነራል አበበ ወ/ማሪያም፣ ሌ/ጄነራል ጃጋማ ኬሎ እና አቶ ደረጀ ደምሴ ድኅረ-ደምሴ ቡልቶ በመጀመርያ ደረጃ የኔ አባት የኢትዮጵያን ጦር ለ37 ዓመታት ነው ያገለገለው። በደርግ 15 ዓመት፣ ከዚያ በፊት 22 ዓመት። ያልተዋጋበት የለም። ደቡብ አዛዥ ሆኖ ሲሄድ የሶማሌ ጦር አዋሳን ለመያዝ 60 ኪሌ ሜትር ላይ ነበር። እዚያ ተዋድቋል። ተወው ብቻ… ግን ከመንግሥት ለቤተሰብ አንድ ደብዳቤ እንኳ አልደረሰንም። ተወው ደብዳቤውን…አስክሬኑ አልተሰጠንም። እንዲያውም ያኔ በግልጽ ሐዘን መቀመጥ መቻላችንን እንደ ዕድል ተደርጎ ነበር የሚወራው። መንግሥቱ አገር ጥሎ ወደ ዚምባቡዌ ከሸሸ በኋላ ነው የአባቴን ሬሳ ያገኘነው። እናቴ አዲሱን መንግሥት አስፈቅዳ፣ የኤርትራ መንግሥትም ፈቅዶ፣ የተቀበረበትን በአገሬው ሰው ተመርታ አውጥታ ነው የቀበረችው። እዛ ያኔ አምጸው የነበሩትና በኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቀጥተኛ ትእዛዝ የተገደሉትን በሙሉ በአንድ ጉድጓድ አሥመራ መንደፈራን አልፎ ያለ አንድ ቦታ ላይ ነበር ቆፍረው የቀበሯቸው። እናቴ የሁሉንም ቤተሰቦች አስተባብራ አጽማቸውን አስወጥታ በክብር ዮሴፍ ቤተክርስቲያን እንዲያርፍ አስደርጋለች። "መንግሥቱ ኃይለማርያም ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል" እሱኮ ኢትዮጵያ ለደረሰችበት ውድቀት ቀጥተኛ ተጠያቂ ሰው ነው። ሰውየው ቤተሰቡን አሽሾ አንድ ቦታ ተጠልሎ ዛሬም ድረስ ይኖራል። ከዚህ ሁሉ ወንጀሉ ጋ ዛሬም ድረስ ከሕሊናው ጋር ተስማምቶ ይኖራል። አስደናቂ ነው። አሁን ዕድሜው ገፍቷል። በትንሹ ሊያደርግ የሚችለው የኢትዮጵያ ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ ነው። ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላም፣ "ይቅርታ፣ ያኔ የነበረኝ ዕውቀት አገሬን ለማስተዳደር በቂ አልነበረም። ያኔ ሥልጣኑን መቀበል አይገባኝም ነበር። ባለማወቅ ያደረኩት ስለሆነ ይቅርታ አድርጉልኝ" አላለም። እውነት ለመናገር ታሪክን መለስ ብለህ ስታይ ኢትዮጵያን የመሰለች ትልቅ አገር በሱ ጭንቅላት መመራት አልነበረባትም። እንደ ተፈሪ በንቲ ያሉ የሰከኑ ሰዎች የሰከነ አመራር ለማምጣት ይሞክሩ ነበር። እነ አማን አምዶም ገና ከመነሻው ሰላም ለማምጣት ጥረዋል። በጎ ያሰቡ ሰዎችን በሙሉ ነው አንድ በአንድ የጨረሳቸው። ያም ሆኖ ግን እሱም ሆነ የሱ የነበሩ ሌሎች ባለሥልጣናት ይቅርታ አልጠየቁም። በየቤተክርስቲያኑ እየሄዱ፣ የድሆችን እግር እያጠቡ ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ ሲገባቸው ሁሉም ‹‹እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ›› እያሉ፣ አልፎ ተርፎም መጽሐፍ እየጻፉ በየመድረኩ ያስመርቃሉ፤ ንግግር ያደርጋሉ። የሚገርም ሕሊና ነው ያላቸው። እቺን ታህል እንኳ ጸጸት አይሰማቸውም፤ እቺን ታህል…፡፡ "የአባቴ አሟሟት የማይገኝ ነው" አዲስ አበባ የከሸፈው ማክሰኞ ግንቦት 8 ማታ ላይ ነው። እሱ የተገደለው ግንቦት 10 ሐሙስ ነው። የኔ አባት አውሮፕላን አስነስቶ መሄድ የሚከለክለው ምን ነገር ነበር? እስከመጨረሻው ድረስ በሕይወቱ ቆርጦ የገባበት ነገር ስለሆነ ነው እንጂ ያን ማድረግ ለሱ በጣም ቀላሉ ነገር ነው። የሱ ምክትል የነበሩት ጄ/ል ሁሴን አሥመራ ከመያዟ በፊት '83 ላይ አውሮፕላን አስነስተው ነው ወደ ሳኡዲ የሄዱት። እሱም ያን ማድረግ አያቅተውም ነበር። ጄ/ል ንጉሤ መክረውት ነበር። "ነገሩ ከተበላሸ በኋላ ምን ትሠራለህ?" ብለውት ነበር። ይሄን ሁሉ ሰው ጥዬ የትም አልሄድም ነው ያላቸው። ኮ/ል መንገሻ ነበሩ ያኔ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ትእዛዝ እየተቀበሉ ሄሌኮፕተር የሚልኩት። ‹‹ጄ/ል ደምሴ ቢፈልጉ እዛው ቢሯቸው ፊትለፊት አንድ ሄሊኮፕተር ቆሞ እንዲጠብቃቸው ማድረግ ይችሉ ነበር። አልፈለጉትም እንጂ›› ብለውኛል። ምንድነው ለኔ ትልቅ ትምህርት የሆነህ ካልከኝ የርሱ ዓይነት አሟሟት አይገኝም። ለምን በለኝ…ያመነበትን አድርጓል። ጦሩን አልከዳም…አገሩን አልከዳም…። ከሱ በተቃራኒ የቆሙት እኮ ሞት አልቀረላቸውም። የህወሓት ጦር ሲገባ ብዙዎቹን ተሰልፈው እጅ ሰጥተው፣ ለዚያውም ዘርህን ጥራ እየተባሉ፤ ስለ ብሔር ትምህርት ደግሞ ያስፈልግሃልና ተማር እየተባሉ፣ ስለ ዘር ልዩነት ተማር እየተባሉ፣ ትናንትና ሽፍታ ይሉት የነበረው ሰው በአርጩሜ ሂድ እዛ ተሰለፍ እያላቸው። ከዚያም አልፎ ግማሾቹ እዚያው እስር ቤት ሞተዋል። የኔ አባት ያን ሳያይ ማረፉ ለሱም ትልቅ ግልግል ነው። እኛም ልጆቹ በጣም የምንኮራበት ሥራ ነው የሠራው። ለልጅ ልጅም የሚያኮራ ነው። የአባቴ ዓይነት አሟሟት አይገኝም። እውነተኛ የአገር አንድነት፣ የሕዝብ ፍቅር የነበረው ሰው ነው አባቴ። እንወደዋለን፡፡ እንኮራበታለን።
news-55068598
https://www.bbc.com/amharic/news-55068598
ትግራይ ፡ የትግራይ ተወላጆች በማንነታችን የተነሳ እንግልት እየደረሰብን ነው አሉ
ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች በማንነታቸው እንግልት፣ መገለልና እስር እየደረሰባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ማንነታቸውን መሠረት ባደረገ ሁኔታ መልከ ብዙ እንግልቶችን እያስተናገዱ እንደሆነም ያብራራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል የሚደረገው ጦርነት ሕግን የማስከበር ተልእኮ ያለው ነው ይላሉ። ዓለማውም ንጹሐን ላይ ጉዳት ሳይደርስ በወንጀል የሚፈለጉ የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ሥር ማዋል እና ለሕግ ማቅረብ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህን በእንዲህ እንዳለ እየወጡ ያሉ የተለያዩ ሪፖርቶች ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ በተለያዩ ስፍራዎች ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች እና ፍጥጫዎች መበራከታቸውን ይጠቁማሉ። በተመሳሳይ የትግራይ ተወላጆችም ማንነትን መሠረት ያደረጉ እንግልቶች እያደረሱብን ነው ይላሉ። 110 ሚሊዮን የሚገመት የሕዝብ ብዛት ባላት ኢትዮጵያ፤ የትግራይ ተወላጆች ከጠቅላላ ሕዝብ 6 በመቶ ይሸፍናሉ። ከክልላቸው ውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚኖሩባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ከማንነት ጋር በተያያዘ ለእስር እያተዳረግን ነው፤ ከሰር መገለል እየገጠሙን ነው ይላሉ። መንግሥት በበኩሉ እንዲህ ዓይነት ዘርን ያማከለ ተግባር አይፈጸምም ሲል ያስተባብላል። ሰዎች በማንነታቸው ሳይሆን ከደኅንነት ጋር በተያያዘ በግለሰብ ደረጃ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ ሲል ይናገራል። በደኅንነትና ፀጥታ መሥሪያ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ግን ለቢቢሲ እንደተናገሩት ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ከሥራ ታግደናል፣ ቤት እንድንውልም ተደርገናል ይላሉ፡፡ መሣሪያችሁን አስረክቡ 'መሣሪያ መልሺ' ከተባሉ የትግራይ ተወላጆች አንዷ በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ አባል ናት። ላለፉት 20 ዓመታት አገልግላለች። ከዚያ ቀደም ብሎ ግን የህወሓት አባል ነበረች። እሷ እንደምትለው ግጭቱ በተጀመረ በሁለተኛው ቀን ከአለቃዋ የስልክ ጥሪ ደርሷታል። በነገታው በአስቸኳይ ቢሮ ሪፖርት እንድታደርግ አለቃዋ አሳሰባት። በተባለችው ቀን ቢሮ ስትደርስ ወዲያውኑ ትጥቅ እንድትፈታ እንደተደረገች ትናገራለች። ‹‹ማንኛውንም እጄ ላይ የሚገኝ ንብረት እንዳስረክብ፣ የጦር መሣሪያም እንዳስረክብ ተደረኩ›› ትላለች። እሷ ብቻ ሳትሆን ሌሎች በፖሊስ ሠራዊቱ ውስጥ የነበሩ ከፍተኛ ኃላፊዎችም ጭምር የትግራይ ተወላጅ ስለሆኑ ብቻ በእጃቸው ያለውን ሁሉ አስረክበው ቤት እንዲያርፉ ተደርጓል ብላለች ለቢቢሲ። መንግሥት በሠራዊቱ ውስጥ ትግራዊያን በመሆናቸው ብቻ ትጥቅ እንዲፈቱ ስለተደረጉ ዜጎች ያለው ነገር የለም። ሆኖም ዘርን ባማከሉ ጠቅላላ ጉዳዮች ዙርያ በቅርቡ አስተያየት የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ማሞ ምሕረቱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "መንግሥታቸው በማንነት ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችንም ሆነ መገለሎች ካሉ በዋዛ እንደማያልፋቸውና አጥብቆ እንደሚያግዛቸው" ጠቅሰው "ይህ በፍጹም ተቀባይት የሌለው ነገር ነው" ብለዋል። "ሆኖም…" ይላሉ ከፍተኛ አማካሪው፤ ለጸጥታና ደህንነት ተቋማት ግልጽ መመርያ ተላልፎላቸዋል። ማንኛውም የሚወስዱት እርምጃ የደኅንነት ስጋትና መረጃን መሠረት ያደረገ እንዲሆን፤ እርምጃዎች ትኩረት ያደረጉትም የደህንነት ስጋት የደቀኑ አክራሪና ያኮረፉ የህወሓት ርዝራዦች ላይ ብቻ ነው ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ የሕዝቦችን እኩልነት እንደሚያስጠብቁ፣ ብሔራዊ አንድነትን ለመፍጠር እንደሚሰሩ ቃል ገብተው ነበር። ለዚህም ተግባራዊነት ባለፉት ዓመታት ጥረት ሲያደርጉ እንደቆዩ እሙን ነው። ሆኖም በአገሪቱ እዛም እዚህም የግጭቶች መፈጠር ይህ ህልማቸው ብዙም እንዳልተሳካላቸው የሚያሳይ ሆኗል። ቢቢሲ 14 ዓመት በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ አገልግሎት ከሰጠና ስሙ እንዲጠቀስ ከማይሻ አንድ ግለሰብ እንደሰማው የግጭቱን መቀስቀስ ተከትሎ እሱና ሌሎች ተጋሩ የሆኑ የሥራ ባልደረቦቹ መገለልና አስደንጋጭ የሆነ ያልተጠበቀ እንግልት ደርሶብናል ይላል። እሱ እንደሚለው በሰሜን ኢትዮጵያ ችግር መፈጠሩን ተከትሎ በገዛ ባልደረባው መጋዘን ውስጥ እንዲታሰር መደረጉን ይናገራል። 90 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሠራዊቱ አባላት ከሱ ጋር በእስር ላይ እንደነበሩ ይናገራል። በቅድሚያ የእጅ ስልካቸው መቀማቱንና በእስር ላይ ሳሉም ልክ እንደ ምርኮኛ ይታዩ እንደነበር ያስረዳል። "መሣሪያ እንድንመልስ ተደርገን የታሰርነው ሁላችንም ተጋሩዎች ነበርን። አንድም የሌላ ብሔረሰብ አባል መሀላችን አልነበረም። እስሩ በማንነታችን ምክንያት እንደሆነ ከዚህ በላይ ማስረጃ ሊኖር አይችልም" ይላል። አሳሪዎቻችንን ለምን እንዲህ ታደርጉናላችሁ ብለው በሚጠይቁበት ጊዜ 'ህወሓት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት አድርሶብናል። እናንተን እንድናስር ትእዛዝ የመጣው ከበላይ ነው' የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ይናገራል። ማንነትን ሸሽጎ ስደት በዚህ ሁኔታ ከግለሰቡ ጋር ለእስር ተዳርገው ከነበሩት መካከል የህወሓት ቀደምት አባላት ይገኙበታል። ህወሓት የተራዘመ የትጥቅ ትግል አድርጎ የአምባገነኑን የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ማርክሲስት ቡድን በ1983 ዓ.ም በኃይል አሸንፎ ስልጣን ከያዘ ወዲህ በአገሪቱ የፖለቲካ ኩነቶች አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል። እነዚህ እስርና መገለል ገጥሞናል ብለው ለቢቢሲ የተናገሩት የትግራይ ተወላጆች የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስተዳደር መምጣቱን ተከትሎ ግን ከፖለቲካ መድረኩ እየተገለሉ መምጣታቸውን ያወሳሉ። ሌሎች ተመሳሳይ ቅሬታ ለቢቢሲ ያቀረቡት በመከላከያ ሰራዊቱ ባልደረባ የነበሩ ናቸው። ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ መኮንኖች ይገኙበታል። አንዳንዶቹም በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ተካተው ሶማሊያ የዘመቱ ናቸው። "አገራቸውን ለነዚህ ሁሉ ዓመታት ደከመን ሰለችን ሳይሉ ያገለገሉ የሠራዊቱ አባላት በዚህ መልኩ በገዛ አገራቸው ይጉላሉ ብዬ በፍጹም አስቤ አላውቅም" ይላል ለቢቢሲ ቃሉን የሰጠው ይህ የትግራይ ተወላጅ። ይህ የሠራዊት አባል በመጨረሻ ታስሮ ከነበረበት መጋዘን አምልጦ ተራ ግለሰብ በመምሰል ወደ ጎረቤት አገር ሸሽቷል። ይህንን መረጃ የሰጠውም በስደት ከሚገኝበት አገር ሆኖ ነው። ድንበር በሚያቋርጥበት ጊዜ ትግራዋይ መሆኑ እንዳይታወቅበት የቋንቋ ዘዬውን ጭምር ለመለወጥ እንደተገደደ ያስረዳል። ይህን ያደረኩት በኔ ላይ ጥርጣሬ እንዳይፈጠር ሰግቼ ነው ይላል። ይህ ስደተኛ አገር ውስጥ ሳለ ጥሏቸው ለመጣውና መጋዘን ውስጥ ታስረው ለሚገኙትና የአገሩ ልጆች ይጨነቃል። ሌሎች ለቢቢሲ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የመከላከያ ሰራዊቱ (የቀድሞም ሆነ የአሁን) አንዳንድ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ አባላት ላይ መገለል ደርሶባቸዋል። የተወሰኑት ታስረዋል፣ በተወሰኑ ላይ ደግሞ ብርበራ ተፈጽሟል። አንዳንዶቹም በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ተረድተናል። በዚህ ሁኔታ ላይ አስተያየታቸውን ከቢቢሲ የተጠየቁት ኢታማዡር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ ‹‹ይህ የፖለቲካ ጉዳይ ነው›› በማለት ምላሽ ለመስጠት ጉዳዩ እሳቸውን እንደማይመለከት ተናግረዋል፡፡ ዘርን ያማከለው መገለልና እስር በፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት ብቻ ላይ ያጋጠመ ጉዳይ እንዳልሆነ ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡት ያስረዳሉ። ሾፌሩ አባቴን ከሰሱት ማንነቷን ለመግለጽ ደኅንነት እንደማይሰማት ለቢቢሲ የተናገረች አንዲት ሴት ባለፈው ሳምንት ያጋጠማትን ስትናገር ቤታቸው በድንገት በታጠቁ ሰዎች እንደተወረረና ብርበራ እንዳደረጉ ከዚያም ቤት ውስጥ የሚገኙ የባንክ ደብተሮችን እንደወሰዱ ተናግራለች፡። በመጨረሻም በሾፌርነት የሚተዳደሩት አባቷንም ፖሊሶች ይዘዋቸው እንደሄዱ ለቢቢሲ አስረድታለች። አባቷ ከተወሰዱ በኋላ ለ2 ቀናት መታሰራቸውን ተናግራለች። የደኅንነት ሰዎች አባቷ 6 ሚሊዮን ብር ይዘው ወደ ትግራይ በቅርቡ መሄዳቸውንና የጦር መሣሪያ ይዘው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን በመጥቀስ እንደከሰሷቸው አስረድታለች። ይህ የፈጠራ ክስ ነው የምትለው ይህች ሴት፤ አባቷ ቱሪስቶችን ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚያመላልሱ ሾፌር እንደሆኑ ተናግራ በአሁኑ ወቅት አባቷ የተመሰረተባቸው ክስ ተነስቶላቸዋል ትላለች። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት በሰጡት መግለጫ፤ ህወሓት በአዲስ አበባ እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ጥቆማ ለመንግሥት መድረሱን ተከትሎ የተለያዩ ምርመራዎች መደረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም 343 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን እና ከእነዚህም መካከል 160 የሚሆኑት በዋስ መለቀቃቸውን ተናግረዋል። እንዲህ ዓይነቱ ዘርን ያማከለ ፍተሻና ብርበራ በመንግሥት መዋቅር ሥር ባሉ አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ መስተዋሉን ቢቢሲ ተረድቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም አንዱ ነው። የጦርነቱን መከሰት ተከትሎ በርካታ ትግራዋይ የአየር መንገዱ ሰራተኞች ተጨማሪ ጥሪ እስኪደርሳቸው ድረስ የግዴታ እረፍት እንዲወስዱ ተደርገዋል፡፡ አልያም ደግሞ ከቤት ሆነው እንዲሰሩ ሆነዋል። ቢቢሲ ይህን መረጃ ያገኘው እዚያው ከሚሰሩ ሰራተኞች ነው። ይህ ቅሬታ ምን ያህል እውነት ነው በሚል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ ማግኘት አልቻለም። ከመንግሥታዊ መዋቅር ውጭ ባሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ቢሆን ይህ ዘርን መሠረት ያደረገ ልዩነት ተስተውሏል። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በቅርቡ እንዳለው አማራ ክልል በሚገኘው ቢሮው የፖሊስ መኮንን ሰራተኞቹን ስለማንነታቸው ጥያቄ አቅርቦላቸዋል፡፡ የትውልድ ስፍራቸውንም ጠይቋል፡፡ የዐለም ምግብ ድርጅት እንዲህ ዓይነቱ መረጃ በእጁ እንደማይገኝ የመለሰ ሲሆን፣ የተጠየቀው መረጃም የመንግሥት ፖሊሲ እንዳልሆነ ከክልሉ ጸጥታ ቢሮ አረጋግጧል የፌዴራል መንግሥት በበኩሉ ይህንን በአማራ ክልል የዓለም የምግብ ፕሮግራም ቅርንጫፍ ቢሮ የተፈጸመውን ሁኔታ ‹‹የክስተቱን ሌላ መልክ መስጠት ነው›› በሚል አስተባብሏል፡፡ የፌዴራል መንግሥት እንደሚለው የፖሊስ መኮንኑ ቅርንጫፍ ቢሮ የሄደው የደህንነት መረጃን መሰረት አድርጎ ነው፡፡ የህወሓት ሰዎች በአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ተሰግስገው እንዳሉ ለማጣራት የደኅንነት መረጃ በመያዝ የተደረገ መጠይቅ ነው ብሏል፡፡ ጨምሮም የፖሊስ መኮንኑ በቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱ ሲገኝ ስም ዝርዝሮችን ይዞ ነው፡፡ ከያዛቸው ስም ዝርዝሮች ውስጥ በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ የሚሰሩ ካሉ ለማጣራት ነው የሄደው ብሏል መንግሥት፡፡ የደኅንነት ሰዎች በትግራይ እየሆነ ባለው ሁኔታ በተቀረው የአገሪቱ ክፍል ከህወሓት ደጋፊዎች ሊፈጸም የሚችለው የደህንነት አደጋ ስጋት እንደሚያሳስባቸው እሙን ነው፡፡ ነገር ግን ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡ የትግራይ ተወላጀጆች እየደረሰባቸው ያለው እንግልት የሚመነጨው የህወሓት ደጋፊ ከመሆን አለመሆን ሳይሆን ከብሔር ማንነታቸው ነው፡፡. አገራዊ ስሜቱ ይመለስ ይሆን? ይህ የሰሜኑ ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ከሆነ በብሔሮች መካከል ያለው ውጥረት ሊረግብ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጦርነቱ እየተራዘመ ከመጣ ከክልሉ ውጭ ለሚኖሩ ተጋሩዎች ሕይወት ፈታኝ ሊሆንባቸው ይችላል የሚል ስጋት አለ፡፡ ምንም እንኳ ህወሃት ሀገራዊ አንድነትን ለማምጣት ለተያዘው ዕቅድ መሰናክል ተደርጎ ቢታይም፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሀገሪቱን አንድ ለማድረግ ላላቸው ራዕይ እንዲህ ያሉ ግጭቶች ትልቅ ፈተና ሊደቅኑ ይችላሉ። ‹‹መንግሥት እያደረገ ያለው አንድ አንኳር ተግባር ቢኖር ሁሉንም ዜጋ የሚያስተሳስር አንድ ማኅበረሰብን መፍጠር ነው›› ብለዋል የጠቀልይ ሚኒስትሩ አማካሪ ለቢቢሲ፡፡ ነገር ግን በትግራይ ያለው ጦርነት ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ግብ የሚያወሳስብ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡
news-52766783
https://www.bbc.com/amharic/news-52766783
ኮሮናቫይረስ፡ በሞት የተደመደመው የልደት በዓል
ዓለም በዚህ ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ከተከሰቱ ነገሮች ታገግም ይሆን? "ያ ክፉ ወቅት" ተብሎስ ይወራለት ይሆን?
ማን ያውቃል? ይሆን ይሆናል። በብራዚል እንዲህ ሁኔታው ሳይከፋ ልደት ለማክበር የተሰባሰቡት ቤተሰቦች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሦስት አባላታቸውን በሞት ተነጥቀዋል። የልደት በዓሉ አከባበር በሞት ይደመደማል ብለው ያላሰቡት ቤተሰቦች እዝንም አላወጡም፣ ሃዘናቸውን ለብቻቸው በቤታቸው ይዘው የእግር እሳት ሆኖባቸዋል። ከሦስቱ የቤተሰብ አባለት መቀጠፍ በተጨማሪ አስሩ ደግሞ መታመማቸውን የብራዚል ባለስልጣናት አስታውቀዋል። የልደት አከባበሩሽርጉድ የልደቱ በዓል በሳኦፖሎ በምትገኘው ኢታፔሪካ ዴ ሴራ ከተማ ነበር መጋቢት 4/2012 ዓ.ም። በዚያን ወቅት በብራዚልም በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር እንደ ዛሬው በመቶ ሺህዎች አልነበረም፤ ገና 98 ነበር። የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው ሞትም አልተከሰተም። በወቅቱም በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 60ዎቹ በዓለማችን ከፍተኛ ሕዝብ ይኖርባቸዋል ከሚባሉት ከተሞች መካከል አንዷና የ21 ሚሊዮን ሕዝብ መኖሪያ በሆነችው ሳኦ ፖሎ ነው። ከሦስት ሳምንታት በኋላ መጋቢት 30/2012 ዓ.ም በብራዚል በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 16 ሺህ ያህል ደረሰ፤ 800 ዜጎቿንም አጣች። ቬራ ሉሺያ ፔሬራ የኮሮናቫይረስ ብራዚል መግባቱንና እየተስፋፋም መሆኑን ታውቃለች። 59ኛው የልደት በዓሏን ለማክበር ሽር ጉድ እያሉ በነበረበት ወቅት፤ እንዲያውም "ልደቴ ባይከበርስ?" የሚል ሃሳብም ብልጭ ብሎላት ነበር። "ጥርጣሬዎች ነበሩን፤ ሆኖም አይ እናክብር በሚል ገፋንበት" ትላለች። በወቅቱም በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ባለመኖራቸው እንዲሁም አገሪቱም አስገዳጅ ቤት ውስጥ የመቀመጥ አዋጅም ካለማውጣቷ አንፃር ጥርጣሬዎች ቢኖሩም የከፋ ይሆናል ተብሎ አልታሰበም ነበር። 28 የቤተሰብ አባላት የተሳተፉበት የልደት በዓል ቀኑም ተቆረጠ በግቢዋ ውስጥ በሚገኘው ጓሮ ውስጥ 28 የቤተሰብ አባላቱ ተሰባሰቡ። ለልደቷ ከተጋበዙትም መካከል የባለቤቷ ፖውሎ ቪየራ ወንድምና እህት ይገኙበታል። ፓውሎ ከወንድሙ ክሎቪስና ከእህቱ ማሪያ ጋር ሆነው ነገ አማን ይሆናል በሚል ተስፋም ልደት እያከበሩ ነበር። በኮሮናቫይረስ ተይዘን እንሞታለን የሚል ሃሳብ በጭራሽ አልታያቸውም። ቬራ ሉሺያም እህቶቿን፣ የእህቶቿን ልጆች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቿንም ጠርታ ነበር። ቤቱም በቤተሰቡ ሳቅ ደስታ ደመቀ፤ "መልካም ልደት" ብለው ለቬራ ዘመሩላት፤ በዓመቱም አብረን እናከብራለን ብለው ቃል ገቡ። ስለነገው ተስፋ የተደረገውና የተገባውን ቃል እውን ስለመሆኑ ማን ያውቅ ይሆን? ከቬራ ልደት ጥቂት ቀናት በኋላም ግማሹ እንግዳ የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን ሳል፣ ትኩሳትና ትንፋሽ ማጠር ያሳዩ ጀመር። የአብዛኛዎቹ መካከለኛ የሚባል ምልክት ስለነበር ወደጤና ማዕከላት መሄድ አላስፈለጋቸውም። ነገር ግን የቬራ ባለቤት እንዲሁም ወንድምና እህቱ በሳምንቱ ህይወታቸው አለፈ። የቬራ ሉሺያ የልደት ፓርቲ ላይ 28 የቤተሰብ አባላት ተገኝተው ነበር ሁሉም የሞቱት በኮቪድ-19 ነው ቢባልም የቬራ ባለቤት እህት ማሪያ አሟሟት ግን በኮሮናቫይረስ መሆኑ ተረጋግጧል። ልጇ ራፋኤላ ለቢቢሲ እንደተናገረችው "እናቴ በኮሮናቫይረስ መሞቷን እርግጠኞች ነን" ብላለች። "በሽታው ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ ያሳያል። ምንም እንኳን እናቴ ሆስፒታል ሄዳ ቬንትሌተር ቢገጠምላትም ህይወቷን ማትረፍ አልቻሉም" ብላለች። እናቷ ማሪያ የስኳር ህመም ያለባት ሲሆን የጤናቸውም ሁኔታ ያሽቆለቆለው ከልደቱ ጥቂት ቀናት በኋላ ነው። ቤተሰቡ አሁንም ቢሆን የፓውሎና ክሎቪስን የምርመራ ውጤት እየጠበቀ ነው። "ያዩዋቸው ዶክተሮች ኮቪድ-19 መሆኑን 99 በመቶ እርግጠኛ ናቸው" በማለት ቬራ ሉሺያ ተናግራለች። የተረፈው ልጅ ቬራ ሉሺያ ምንም እንኳን እሷም ሆነ ልጇ የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው የነበረ ቢሆንም ሁለቱም አገግመዋል። "አካላዊ ሁኔታዬ ደህና ነኝ፤ ትንሽ ሳል ብቻ ነው ያለብኝ። ነገር ግን ፈታኝ የሚባል ወቅት ላይ ነን ያለነው። በሽብር ውስጥ እየኖርን ነው" ብላለች። ቬራ ሉሺያ ከባለቤቷ ፓውሎና ከልጇ ጋር እንዴት ይታመናል? በመጀመሪያ ሁሉም የቤተሰብ አባላት በኮሮናቫይረስ እንጠቃለን የሚል ስጋት አልነበራቸውም። "በወቅቱ በብራዚል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በጣም ጥቂት ነበረ። ቫይረሱ እኛ ላይ ይደርሳል ብለን አላሰብንም። ገና በርቀት ላይ ነው ያለው ብለን ገምተን ነበር" በማለት ከተረፉት አንዱ ገልጿል። በፓርቲው ላይ የነበሩት በሙሉ ጤንነታቸው ደህና ይመስል ስለነበር፤ ማን በቫይረሱ እንደተያዘ ለመገመት ፈጽሞ አይቻልም። "ለነገሩ አሁን ማን መጀመሪያ እንደተያዘ ማወቅ አለማወቁ ምንም የሚቀይረው ነገር የለም" ብሏል። ማሪያ ከሞተች በኋላ የ62 ዓመት ወንድሟ ክሎቪስ የጤናው ሁኔታ እየከፋ መጣ። ክሎቪስ ከባለቤቱና ከልጆቹ ጋር "ከልደቱ ሦስት ቀናት በኋላ አባቴን በከፍተኛ ሁኔታ ያስለው ጀመር" በማለት የክሎቪስ ልጅ አርተር ለቢቢሲ ተናግሯል። "ራስ ምታት እንዲሁም ከፍተኛ ትኩሳት ነበረው። ከዚያም በተጨማሪ የማሽተት እንዲሁም የመቅመስ ስሜቱንም ሙሉ በሙሉ አጥቶ ነበር።" ከእህቱ ማርያ በተቃራኒ ክሎቪስ ምንም አይነት ተደራራቢ ህመም አልነበረበት። ህመሙ ሲብስበትም አርተር አባቱን ወደ ህክምና ማዕከል መውሰድ እንዳለበት ተረድቶ ቢወስደውም ሆስፒታሉ ወደ ቤቱ መለሰው። "ዶክተሮቹ በጭራሽ ኮሮናቫይረስ ነው ብለው አላሰቡም" ብሏል። በፅኑ ህክምና ላይ የቬራ ሉሺያ ባለቤት ፓውሎም ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ነው የተነገረው። ከዚህ ቀደም በየቀኑ ስፖርት ይሰራል እንዲሁም ተራራ ይወጣም፣ ብስክሌትም ይነዳ ስለነበር ሲታይ ደህና ነበር። ፓውሎም ሆስፒታል በገባበትም ወቅት ጤናውን ሲገመግሙት ደህና እንደሆነና የትንፋሽ ማጠር አጋጥሞኛል ማለቱንም ባለቤቱ ትናገራለች። "ከሁለት ቀናት በኋላ ፅኑ ህሙማን ክፍል ገባ" በማለት ያልተጠበቀችው እንደሆነ ቬራ ታስረዳለች። ክሎቪስና አርተር ሁለቱ ወንድማማቾች ክሎቪስና ፓውሎ ከህፃንነታቸው ጀምሮ የማይነጣጠሉ ነበሩ፤ በሞትም አልተነጣጠሉም። መጋቢት23/2012 ዓ.ም ማሪያ ስትሞት በተከታዩ ቀን ክሎቪስ እንዲሁም መጋቢት 25/2012 ዓ.ም ፓውሎ ይህችን ዓለም ተሰናብተዋል። በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ለተረጋገጡ ወይም ለተጠረጠሩ ሰዎች በሚደረገው የቀብር ሥነ ሥርዓት መሰረት ማሪያና ፓውሎ በተዘጋ የሬሳ ሳጥን ተቀብረዋል። ክሎቪስ ለቤተሰቦቹ በተናዘዘው መሰረት አስከሬኑ ተቃጥሏል። የሦስቱም የቀብር ሥነ ሥርዓት የተፈፀመው በተለያዩ ቀናት ነው። የሐዘኑ ሥነ ሥርዓትም ከጥቂት ደቂቃዎች እንዳያልፍ በተሰጠ መመሪያ መሰረት ከአስር ያነሱ ሰዎችም ብቻ ሐዘናቸውን ውጠው ተሰናብተዋቸዋል። በልደቱ ቀን ታድመው የተረፉት ደግሞ ራሳቸውን ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያስገቡ ሲሆን፤ ኡን ሁሉም አገግመዋል ማለት ይቻላል። በአሁኑ ሰዓት ሁሉም "እኛን ያየ ይቀጣ" እያሉ ነው። ቸልተኝነት እንደማያስፈልግ እንዲሁም በተቻለ መጠን ቤት ውስጥ ሰዎች እንዲቀመጡም እየመከሩ ነው። 'ጄይር ቦልሶናሮ የማይረቡ ነገሮችን ይቀበጣጥራል' የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ጄይር ቦልሶናሮ አካላዊ ርቀት የመጠበቅ ሕጎች ላይ ሲዘባበቱ እንዲሁም ህመሙንም "ቀላል ጉንፋን" ነው በማለት በማጣጣላቸው አወዛጋቢ ሆነዋል። የፕሬዚዳንቱም ድርጊት እንደ ቬራ ሉሺያ ላሉት ብዙ ህመም ለተሸከሙ እንዲሁም ቤተሰብ ላጡ ሰዎች ከመጠን በላይ የሚያበሳጭም ነው። "ጄይር ቦልሶናሮ የማይረቡ ነገሮችን ይቀበጣጥራል። በስልጣን ላይ ያለ ሰው እንደመሆኑ መጠን ያለበትንም ኃላፊነት ልብ ሊል ይገባል" ብላለች። በአሁኑ ጊዜ ለቬራ ፈታኙ ነገር ያለ የህይወት አጋሯ በብቸኝነት ህይወትን መግፋቱ ነው። "ምንም ቢፈጠር ያው እንኖራለን። ማንኛውም ቤተሰብ የእኛ እጣ ፈንታ እንዲያጋጥመው አልፈልግም" በማለትም በሐዘን ተናግራለች።
news-56755321
https://www.bbc.com/amharic/news-56755321
ቡና ለመጠጣት መንገድ ሲያቋርጥ ባጋጠመው አደጋ ህይወቱ የተመሳቀለው ወጣት
የከባድ መኪና አሽከርካሪው አዲስ ዘመን እግረኛ ሆኖ መንገድ ሲያቋርጥ የገጠመው የትራፊክ አደጋ አምስት ዓመታት በሆሰፒታል አልጋ የስቃይ ጊዜያትን እንዲያሳልፍ አስገድዶታል።
አዲስ ዘመን የደረሰበትን ጉዳት አስራ አራት ጊዜ ከባድ ቀዶ ህክምና እንዲያደርግና ለህክምና ገንዘብ ተቸግሮ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ለልመና እንዲቀመጥም ምክንያት ሆኗል። የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበረው አዲስ ከባድ መኪና እያሽከረከረ በሚያገኘው ገቢ 15 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ህይወቱን መርቷል። ከስድስት ዓመታት በፊት ያጋጠመው ክስተት ግን የህይወቱን መሰመር እስከ ወዲኛው የቀየረ ነበር። ኅዳር 15/1999 ዓ.ም በመቶች የሚቆጠር ኪሎ ሜትሮችን ተጉዞ ከደሴ በቅርብ ርቀት ወደምትገኘው ኩታበር ከተማ ሲደርስ ለእርፍት አቆመ። እንደእሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ከሆነው ጓደኛው ጋር ሲጫወቱ ቆይተው ቡና ለመጠጣት በእግራቸው መንገድ ማቋረጥ ጀመሩ። እናም በመንገዳቸው መካከል ያልታሰበው ሆነ። "በአጋጣሚ ዞር ስል አንድ ፒክ አፕ መኪና መሪው ግራና ቀኝ እየዋለለ በቅጽበት ሲመጣ አየሁ። ከእኔ ጋር የነበረውን ሹፌር ጓደኛዬን ገፈተርኩትና እኔም በተቃራኒ አቅጣጫ ሸሸሁ። ከአስፓልቱ ከአስር ሜትር በላይ ሩጫያለሁ። ግን አላመለጥኩም መኪናው ሦስት ቦታ ላይ መታኝ" ሲል የነበረውን አሰቃቂ ክስተት አዲስ ያሰታውሳል። በአደጋውም መጀመሪያ እግሩን የመኪናው የፊተኛ ክፍል ሲመታው ወደቀ ከዚያም የእጎተተ ሲወስደው ደርቱና አንገቱ ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰበት። "ከዚያ በኋላ የሆነውን አላውቅም" ይላል። "እሰኪ አስነዳኝ!" ያስከተለው መዘዝ አዲስ ላይ ይህንን አደጋ ያደረሰው አሽከርካሪ በቂ ልምድ ያልነበረው ሲሆን "እስኪ አስነዳኝ!" በሎ ከሾፌሩ ተቀብሎ መሪ የጨበጠ የመኪና ባለቤት ነው። ልምድ ያለው አሽከርካሪ ቢሆን ኖሮ "ብዙም ጉዳት አይደርስብኝም ነበረ" ሲል የሚናገረው አዲስ፤ ለአደጋው መባባስ የአሽከርካሪውን ልምድ ማነስ ዋናኛ ምክንያት ነው ይላል። "መለማመድ ካለበት እኮ ትምህርት ቤቶች አሉ። አደጋ ማይበዛበት ቦታ ላይ ከፍሎ መንዳት ይችል ነበር። የእኔን ህይወት ያየ ድጋሚ ልምድ ለሌለው ሰው መኪና ይሰጣል ብዬ አላምንም" ሲል ተናግሯል። ለአምስት ዓመታት በሦስት ሆስፒታሎች ህክምናውን ሲከታተል የቆየው አዲስ 14 ጊዜ ቀዶ ህክምና ተደርጎለታል። በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የሰውነቱ ክፍሎች ውስጥ 'ብረት' ወይም Plate ተደርጓል። ጉልበቱ አይታጠፍለትም፣ ረጅም መንገድ መጓዝ አይችልም፣ ሲራመድም ያነክሳል። ከአደጋው ጋር በርካታ ነገሮቹ ተመሰቃቅለዋል "እግሬ ኢንፌክሽን ፈጥሮ መንገድ ዳር ቁጭ ብዬ የአዲስ አበባን ሕዝብ አንድ ብርና ሃምሳ ሳንቲም ለምኜ ታክሜያለሁ" የሚለው አዲስ፤ ጉዳቱን ያደረሰበት ግለሰብ በሌላ ሰው አማካይነት ሁለት ጊዜ የህክምና ወጪውን ቢሸፍንለትም ከዚያ በኋላ ተሰውሮበታል። ከአደጋው ጋር በተያያዘ የመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት 40 ሺህ ብር ቢከፍለውም የህክምና ወጪውን ከዚህም በላይ ሆኖ አቅሙን ፈትኖታል። 17 አዳሪ ት/ቤቶችን ሊገነባ የሚችል ንብረት ወድሟል በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋዎች ሳቢያ የተፈጠሩ ከአዲስ ዘመን ጋር የሚመሳሰሉ ታሪኮች በርካታ ናቸው። ቁጥራቸውም ከዕለት እለት እየጨመረ የሚሄድ ነው። በመገናኛ ብዙሃን በየቀኑ ከሚደመጡ የትራፊክ አደጋ ዘገባዎች ጀርባ የተናጉ ቤቶች፣ የተመሰቃቀሉ ህይወቶችና ከህመም ስቃይ ጋር እያንዳንዱን ቀን የሚያሳልፉ ዜጎች በርካቶች ናቸው። ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው በተያዘው ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የትግራይና የሲዳማ ክልልን ሳይጨምር በመላው አገሪቱ 1 ሺህ 849 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አልፏል። ይህ ቁጥር ከቫቲካን ከተማ ጠቅላላ ሕዝብ በእጥፍ የሚልቅ ነው። ከ 2 ሺህ 600 በላይ ሰዎች ከባድ ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የወደመው ንብረት ግምት ደግሞ ከ495 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነው። ይህ ገንዘብ በቅርቡ ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ በደሴ ከተማ የተገነባውን አይነት 17 ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን መገንባት የሚስችል ነው። በትራንስፖርት ሚኒስቴር የመንገድ ደኅንነት ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ በለጠ የትራፊክ አደጋ 'አምራችና የተማረ' የሚባለውን የኅብረተሰብ ክፍል በብዛት እየቀጠፍ እንደሚገኝ ይናገራሉ። በሌላ በኩል በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ክፍል ኃላፊውና የአጥንትና አደጋዎች ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ብሩክ ላምቢሶ የትራፊክ አደጋ በጤና ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ያስረዳሉ። "72 በመቶው በትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች የተያዘ ነው" ዶ/ር ብሩክ የትራፊክ አደጋ በህክምናው ላይ ያለውን ተጽእኖ ሲያስረዱ ከለጋሾች የሚሰበሰበውን ደም በመጠቀስ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውስጥ ያለውን ስርጭት ለአብነት ያነሳሉ። በወሊድ ወቅት የሚያጋጥም እጥረትን ለማቃለል የሚቀርበው ደም "በአባዛኛው የመኪና አደጋ ተጠቂዎችን ህይወት ለማትረፍ ነው የምንጠቀመው" ይላሉ። በቁጥር በበረከቱ አደጋዎች ምክንያት የሚደርሰው ጫና አምቡላንስ ከመሻማት ጀምሮ በህክምና ክፍሉ ቀድመው የተያዙ የቀዶ ህክምና ቀጠሮዎችን እስከ ማሰረዝ ደርሰዋል። "እኛ ባለን አሃዝ መሠረት በዓመት ውስጥ ከምንሰጠው የህክምና አገልግሎት ውስጥ 72 በመቶው የመኪና አደጋ ተጎጂዎች ናቸው። ስለዚህም ካለን ሃብት፣ ሙያ እና ጊዜ ውስጥ ሦስት አራተኛ የሚሆነው በመኪና አደጋ ተጎጂዎች ላይ የሚውል ነው።" ይህ አሃዝ ደግሞ የአንድና የሁለት ወይም የጥቂት ዓመታት መረጃን መሠረት ያደረገ ሳይሆን በ30 ዓመታት የህክምና ሥራን የተከናወኑ አገልግሎቶችን በማስላት የተገኘ እንደሆነ ዶ/ር ብሩክ ገልጸዋል። በቅርቡ ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ ደርሶ ከ30 በላይ ሰዎች የሞቱበት አደጋ የቀረውን ድርሻ ደግሞ የዲስክ ህመም ላለባቸው፣ በካንሰር ምክነያት ለአጥንት ችግር ለተጋለጡ፣ በስፖርትና በመውደቅ አደጋ ለተጎዱና መሰል ችግሮች የተተወ ነው። "የመኪና አደጋው ሃብት ሰለሚሻማ ሌሎቹ [ከትራፊክ አደጋ ወጪ ያሉ የህክምና ክፍሉ ታካሚዎች] አልጋ የለም፣ ድንገተኛ ሞልቶበታል ይባላሉ - ይንከራተታሉ" ሲሉ አደጋው የፈጠረውን የዕለት ከእለት ጫናን ይገልጻሉ። "የሞቱት ይሻላሉ እስኪባል ድርስ በስቃይ የሚያልፉ ተጎጂዎች አሉ።" "በእውነቱ ተርፏል ወይ የሚያሰኙ አደጋዎች ይገጥሙናል" ሲሉ የአንዳንዶቹን ጉዳት የሚያስረዱት ዶ/ር ብሩክ "ወጣት ዕድሜ ላይ ያሉ፣ የት ይደርሳሉ የተባሉ ልጆች እጃቸው ወይም እግራቸው ተቆርጦ፣ ጭንቅላታቸው ተመቶ አዕምሯቸው መስራት ሲያቆም ገጥሞናል። "በትራፊክ አደጋ ምክንያት በሚደርስ ጉዳት መናገር ያቃታቸው፣ መራመድ የተሳናቸውና ፓራላይዝድ የሆኑ [ሰውነታቸው አልታዘ ሲላቸው]፤ ልጆች አባታቸው ጠዋት በሰላም ወጥቶ ዊልቼር ላይ ሆኖ ሲያዩት ሥነ ልቦናቸው እንዴት እንደሚጎዳ እናያለን። አንዳንዴ እንዲያውም የሞቱት ይሻላሉ እስኪባል ድርስ በስቃይ የሚያልፉ ተጎጂዎች አሉ" ይላሉ። በትራፊክ አደጋ የሚደርሱ የእለት ከዕለት ሰቆቃዎችን የሚመለከቱት እንደ ዶክተር ብሩክ ያሉ ባለሙያዎችም የችግሩን ገፈት ይቀምሳል። የአደጋዎቹ ምክንያት ምንድን ናቸው? አቶ ዮናስ እንደሚሉት ከ40 በመቶ በላይ የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት በፍጥነት ማሽከርከር ነው። የሌሊት ጉዞ እንዲሁም ጠጥቶና አደንዛዥ ዕጽ ተጠቅሞ ማሽከርከር ሁለተኛው ምክንያት ሆኖ ተቀምጧል። እነዚህ ዋነኛ የአደጋ መንሰሄዎች ደግሞ ከሽከርካሪው ጋር በቀጥታ የሚያያዙ ናቸው ብለዋል። ሌላኛው ደግሞ የመንገዶች ምቹ አለመሆንን ይጠቅሳሉ። እናም 10 አደጋ ይበዛባቸዋል የተባሉና 2000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ መንገዶችን 'የምህንድስና መፍትሄ' እንዲያገኙ "ጥናት አድርገን ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስተላፈናል" የሚሉት ሃላፊው "ዋናው ጉዳይ ግን አሽከርካሪው ላይ ትልቅ ስራ መስራት እንደሚያስፈልገን ተረድተን ተከታታይ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየሰራን ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በለማጅ አሽከርካሪ ተገጭቶ ለዓመታት በስቃይ ውስጥ ያለፈው የቀድሞው ሾፌር አዲስ ዘመን አሁን በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ሥራ ጀምሯል። ሆኖም በእያንዳንዱ ቀን የሚሰማው ህመም ያለፉትን ጊዜያት ያስታውሰዋል። "አንድ ሰው ላይ የትራፊክ አደጋ ስታደርስ ለአካል ጉዳት፣ ለስቃይ ወይም ለሞት የምታበቃው አንድን ሰው ብቻ አይደለም።ከእርሱ ባሻገር የሚረዳቸውን እናቱን ወይም አባቱን፤ የሚሳሳላቸውንና የሚለፋላቸውን ልጆቹን፣ እህት ወንድሞቹን ነው" ይላል። በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በአንድ ሰው ላይ የሚደርሰው የትራፊክ አደጋ ከጀርባው የበርካቶችን ተስፋ ያጨልማል፣ የሞቀ ቤትን ያቀዘቅዛል እንዲሁም ፈርጀ ብዙ ጉዳትን ያስከትላል። "ለእራሳችንም ለሌሎችም ደኅንነት ስንል በኃላፊነት እናሽከርክር" ይላል የትራፊክ አደጋ ህይወቱን ያመሳቀለበት አዲስ።
44439785
https://www.bbc.com/amharic/44439785
በጃንጥላ ተከልሎ ቀዶ ህክምና? በችግር የተተበተበው ፈለገ ህይወት ሆስፒታል
በቅርቡ የባሕር ዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ፎቶግራፍን በማህበራዊ ድረ ገጾች ያዪ ሰዎች ጥያቄ ነው። የቀዶ ህክምና ክፍሉ ጣሪያ ቀዳዳ ኖሯል። በጣሪያው ሽንቁርም ዝናብ ይገባል።
የባሕር ዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ሀኪሞች ቀዶ ህክምና ሲያደርጉ ዝናብ እንዳያውካቸው በጃንጥላ ይከላከላሉ። ነፍሳቸውን በሀኪሞቹ እጅ ጥለው አልጋው ላይ ያሉ ታካሚዎችም በጥላው ይጋረዳሉ። ነገሩን በፎቶግራፍ መመልከትና ቦታው ሆኖ የሁነቱ አካል መሆን ይለያያሉ። በጃንጥላ ስር ቀዶ ህክምና ማድረግ ምን አይነት ስሜት ይኖረው ይሆን? ስሜ አይጠቀስ ብሎ አስተያየቱን የሰጠን የህክምና ባለሙያ በቀዶ ህክምና ክፍሉ ጃንጥላ ተይዞለት ህክምና የሰጠው ከአንዴም ሁለቴ መሆኑን ይናገራል። ባለሙያው እንደሚለው የቀዶ ህክምናውን ሂደት የሚያስተባብሩ ነርሶች ሁለት ወይም ሦስት ጥላ ይዘረጋሉ። ከቤታቸው እስከ ሆስፒታሉ የተጠለሉበት ጃንጥላ ሁለተኛ ዙር አገልግሎት እየሰጠ ይመስላል። ሁኔታው ለህክምና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ለህሙማንም ምቾት አይሰጥም። "በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ቀዶ ህክምና ከሚደረግልን ቢቀርብንስ? የሚሉም አሉ። ደህንነት አይሰማቸውም" ይላል ሀኪሙ። ያነጋገርናቸው የሆስፒታሉ ሰራተኞች ጣሪያው ማፍሰስ ከጀመረ ሁለት ወር እንደሆነውና ቅሬታቸውን ደጋግመው ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ይናገራሉ። "ዝናብ ጠብ ባለ ቁጥር ሁለት ወይም ሦስት ጥላ ተይዞ ነው የሚሰራው። ዝናብ በመጣ ቁጥር ለእኛ ሰቀቀን ይሆንብናል። ለታካሚዎችም አስቸጋሪ ነው። የቀዶ ህክምና ክፍል በጣም የፀዳ መሆን አለበት። ህሙማንን እናድናለን ሲሉ ሁለት ሰዎች ለኢንፌክሽን ተጋልጠዋል። ሞትም ሊከሰት ይችላል። ስለ ችግሩ ብንናገርም ከጤና ቢሮ ጀምሮ የሚመለከታቸው ሰዎች መፍትሄ አልሰጡንም" ይላሉ። ሆስፒታሉ በዘርፈ ብዙ ችግሮች የተበተበ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያው ማህበረሰቡን ለማገልገል ከመፈለግ በመነጨ ፍላጎት ቢሰሩም በሆስፒታሉ ደስተኛ አለመሆናቸውን ያመለክታሉ። ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የፈለገ ህይወት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ ባዬ እንደሚሉት የቀዶ ህክምና ክፍል ዝናብ ያፈሰሰው ያሳለፍነው ሰኞ ብቻ ነው። ችግሩን በጊዜያዊነት ለመቅረፍ ያፈሰሰውን ቦታ መርጠው እንደጠገኑና በዘላቂነት መፍትሄ ለመስጠት ሙሉ እድሳት እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። ሆስፒታሉ እድሜ ጠገብ መሆኑ ለችግሩ መንስኤ መሆኑን ተናግረው "በጤና ቢሮ የሚሰራው አዲስ ህንጻ ሲጠናቀቅ መፍትሄ ይሰጠናል" ይላሉ። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባው ገበየ በበኩላቸው "በሆስፒታሉ ጥላ ተይዞ ቀዶ ህክምና አልተካሄደም። በማህበራዊ ድረ ገጽ የሚወራው ውሸት ነው" ባይ ናቸው። በእርግጥ የሀኪሞቹና የዳይሬክተሩ ምላሽ የዶ/ር አበባውን ይቃረናል። ጥላ ተይዞ ቀዶ ህክምና ሲካሄድ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ብዙዎች ከማክሰኞ አንስቶ በማህበራዊ ድረ ገጽ እየተቀባበሏቸው ነው። አርብ እለት ያነጋገርናቸው ስማቸውን ያልጠቀሱት ሀኪምና አንድ እጩ ሀኪም "ችግሩ ሁለት ወራት አስቆጥሯል" ይላሉ። ሜዲካል ዳይሬክተሩ የአንድ ቀን አጋጣሚ ነበር ተፈቷል ሲሉ፤ የጤና ቢሮ ኃላፊው ሀሙስ በፈለገ ህይወት ሆስፒታል ተገኝቼ እንዳየሁት የቀዶ ህክምና ክፍሉ አንድ ቀን ቢያንጠባጥብም ተጠግኗል። "የቀዶ ህክምና ክፍሉ እንደሚያፈስና በወቅቱ እየሰሩ የነበሩ ሃኪሞች ጣሪያው ሲያፈስባቸው የወሰዱት አማራጭ ጥላ መዘርጋት እንደሆነ ሰምቻለሁ" ያለን የስድስተኛ ዓመት የህክምና ተማሪና በፈለገ ህይወት ሆስፒታል በቀዶ ህክምና ክፍል ልምምድ የሚያደርግ እጩ ሃኪም ነው። ሆስፒታሉ አራት የቀዶ ህክምና ክፍሎች ሲኖሩት ጣሪያው ያፈሳል የሚባለው ሁለተኛው ክፍል ነው። ክፍሉ ጠባብ በመሆኑ ልምምድ የሚያደርጉ የህክምና ተማሪዎች ክፍሉ ውስጥ ገብተው ለመመልከት የሚቆሙበት ቦታ እንኳን አያገኙም። "ይህም የወደፊቶቹ ሃኪሞች በቂ የልምምድ እውቀት እንዳያገኙ ፈታኝ አድርጎባቸዋል" ሲል ያክላል። የጣሪያው ማፍሰስ እንደጊዜያዊ ችግር ተቆጥሮ እንደቆየ የገለፀልን ተማሪው "በክልል ደረጃ እንደሚገኝ አንድ ትልቅ ሪፈራል ሆስፒታል በርካታ ህሙማንን የሚያስተናግድ ቢሆንም ያለበት ችግር ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም" ሲል ይጨምራል። የኦክስጅን እጥረት ከዚህ ቀደም ሆስፒታሉ የኦክስጅን እጥረት ገጥሞት ነበር። ከአራት ወር በፊት በኦክስጅን እጥረት ስምንት ህጻናት መሞታቸውን ዳይሬክተሩ ዶ/ር መልካሙ ይናገራሉ። ታካሚዎች ኦክስጅን ገዝተው ይጠቀሙ መባሉ አነጋጋሪ ነበረ። "ለኦክስጅን የሚወጣው ገንዘብ ከፍተኛ በመሆኑ በሽያጭ አድርገነዋል ማለታቸው፤ ገንዘብ ያላቸው ብቻ እንዲጠቀሙ የሌለው አማራጩ ሞት ብቻ እንዲሆን አስገድዷል" ሲል ተማሪው ይናገራል። በሀገሪቷ የነበረው አለመረጋጋት ያስከተለው የመንገድ መዘጋት በሆስፒታሉ የኦክስጅን እጥረት ማስከተሉን ዳይሬክተሩ ጠቁመው፤ ሲያነጋግር የቆየው የኦክስጅን ችግር በቅርቡ እልባት አግኝቷል ይላሉ። "ከአራት ወር በኋላ ሆስፒታሉ የራሱ ኦክስጅን ማዘጋጃ ይኖረዋል" ብለውም ተስፋ ሰጥተዋል። የኦክስጅን እጥረት በእጅጉ ከጎዳቸው አንዱ የህጻናት ክፍል ነው። ክፍሉ በእንቅርት ላይ... እንዲሉ የማሞቂያ እጥረትም አለበት። ስማቸውን የማንጠቅሰው ዶክተር፤ የህጻናት ህክምና ክፍል ውስጥ ጨቅላ ህጻናት የሚሞቁበት ኢንኩቤተር ቁጥር ከሚወለዱ ህጻናት ጋር እንደማይመጣጠን ያስረዳሉ። "በአንድ ግዜ ሙቀት የሚያገኙት አምስት ህጻናት ናቸው። አንድ ማሞቂያ ለአንድ ህጻን ብቻ መሆን ነበረበት" ይላሉ። ድንገተኛን በቀጠሮ የጤና እክል አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታሉ የሚሄዱ ታካሚዎች ለሳምንት ወይም ለወራት ቀጠሮ ይሰጣቸዋል። ባለቤታቸው ታማባቸው ከፍኖተ-ሰላም ወደ ሆስፒታሉ ያመሩ አስታማሚ እንደነገሩን ችግሩ አገልግሎት ለማግኘት ሳምንታት መጠበቃቸው ብቻ አይደለም። "ላብራቶሪ ለማሰራት ሳምንት ሆነኝ። እንኳን አገልግሎት ሊሰጡን ወደ ላብራቶሪው ስንጠጋ እየገፈተሩ ነው የሚያባርሩን" ሲሉ ያማርራሉ። በርካታ ታካሚዎችን በሚያስተናግደው ሆስፒታል አልጋ እንኳን የማያገኙ አሉ። መሬት ላይ ሆነው መድሃኒት የሚወስዱ ህሙማንን ማየት የተለመደ ነው። ልጅ ወልደው ብዙም ሳይቆዩ ወለል ላይ የሚተኙ እናቶች ጥቂት አይደሉም። እናቶች ወልደው የሚጠብቃቸው እንክብካቤ ሳይሆን ቀዝቃዛና ጎርባጣ ወለል መሆኑን ማሰብ ያሰቅቃል ይላሉ ተገልጋዮች። የቀዶ ህክምና የተደረገላቸው ህሙማንም ከቀዶ ህክምና ክፍል ከወጡ በኋላ ለማገገም የሚተኙበት ክፍል ባለመኖሩ አብዛኞቹ በረንዳ ላይና በየኮሪደሩ ለመተኛት ይገደዳሉ። በሆስፒታሉ ሁለት ዓመት ተኩል የሰራው የአጥንት ህክምና ክፍል ነርስ አዳነ ከበደ* "አንድ ሰው በድንገት አጥንቱ ተሰብሮ ቢመጣ ህክምና የሚያገኘው ከሦስት ወራት በኋላ ነው" ይላል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የመኪና አደጋ ደርሶባቸው የሚያክሙበት ቦታ ያጡበትን ወቅትም ያስታውሳል። በወቅቱ ተጎጂዎቹን ኮሪደር ላይ አስተኝቶ ለማከም እንኳን ቦታ ታጥቶ ነበር። ያነጋገርነው ተማሪ እንደሚለው ሆስፒታሉ የቦታ ጥበት ችግርን ለመቅረፍ ሰፋፊ ክፍሎችን በማጥበብና ለሁለት በመክፈል እንዲሁም በረንዳን ወደ ክፍል መቀየር ሞክሯል። ሆኖም ይህም መፍትሄ ሊሆን አልቻለም። 'ካልተከፈለን ሥራ እናቆማለን' ነርሱ አዳነ ከበደ* እንደሚለው የህክምና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከየካቲት ጀምሮ ለአራት ወራት አልተሰጣቸውም ነበር። በዚህ ምክንያትም በተለያየ እርከን ያሉ የህክምና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ ለመምታት የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ ሲያደርጉ ሆስፒታሉ የአንድ ወር ክፍያ ለመስጠት ወሰነ። ባለሙያዎቹ የሚያማርሩት በክፍያ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ አስፈላጊ የህክምና መሳሪያዎች ባለመሟላታቸውም ጭምር ነው። ህክምና መስጫ መሳሪያዎች ሲበላሹ ለመጠገን የሚወስደው ጊዜም ሌላ የራስ ምታት ሆኖብናል ይላሉ። በተለያየ ክፍሎች የሚገኙ ሀኪሞች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ 'አድማ እንመታለን' ሲሉ ማስፈራራትን እንደ አማራጭ እየወሰዱ ነው። ይህንን ለማድረግ የተገደዱትም ለጥያቄዎቻቸው አፋጠኝ ምላሽ ስለማያገኙ መሆኑን ያመለክታሉ። "ጥያቄ ተጠይቆ መልስ ስለማይሰጥ እጩ ሀኪሞች፣ ነርሶች፣ ሬዚደንት ሀኪሞች በየተራ አምጸዋል። ለእዚህ የበቃነው ሰሚ ስለሌለን ነው" ይላል አዳነ። ፈለገ ህይወት የአማራ ክልል ሪፈራል ሆስፒታል ቢሆንም ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የሚያውኩ ክፍተቶችም ይስተዋሉበታል። እንደ ምሳሌ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክቶች አለመኖራቸው ይጠቀሳል። ከባህር ዳርና ከአቅራቢያዋ ወደ ሆስፒታሉ የሚያቀኑ ታካሚዎች አንድ የህክምና ክፍልን ለማግኘት ለደቂቃዎች መንከራተትት ግድ ይላቸዋል። ያነጋገርናቸው በተለያዩ ክፍሎች ያሉ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አብዛኞቹን ችግሮች የሆስፒታሉ አስተዳዳሪዎችና የክልሉ ጤና ቢሮ በቀላሉ ሊፈቷቸው ቢችሉም ቸል ብለዋል ይላሉ። ህሙማን በረንዳ ላይ የዘገየው የማስፋፊያ ህንጻ ግንባታ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተርና የጤና ቢሮ ኃላፊው ከቢቢሲ ለቀረቡላቸው አብዛኞቹ ጥያቄዎች እየተገነባ ያለው የሆስፒታሉ ማስፋፊያ ህንጻ ለችግሮቹ መፍትሄ ይሰጣል የሚል ምላሽ አላቸው። ሆኖም ማስፋፊያ ግንባታው ይጠናቀቃል ከተባለበት በአራት ዓመት ዘግይቷል። ግንባታው መሀል ላይ ተቋርጦ ዳግም የተጀመረውም በቅርብ ነው። "ችግሩ ከጨረታ ጋር የተያያዘ ነበር። ለግንባታው በቂ ገንዘብ ተመድቧል። የተቋራጩ ፍጥነት ህንጻው የሚያልቅበትን ግዜ ይወስነዋል" ይላሉ የጤና ቢሮ ኃላፊው። በሌላ በኩል ዶ/ር መልካሙ ሆስፒታሉ ወደ ሰባት ሚሊየን ህዝብ ከማስተናገዱ አንጻር የሚመደብለት በጀት በቂ እንዳልሆነ ይናገራሉ። ለችግሮቹ መንስኤ የሚሉትም የክልሉ ጤና ቢሮ ለሆስፒታሉ ትኩረት መንፈጉን ነው። በስድስት ወር ውስጥ 127ሺህ ተመላላሽ ታካሚዎች ህክምና ተሰጥቷቸዋል፤ 5ሺህ ከፍተኛ ቀዶ ህክምናም ተደርጓል። ዳይሬክተሩ ፈለገ ህይወት እንደ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልነቱ መስጠት የሚጠበቅበትን አገልግሎት እየሰጠ ስላለመሆኑ በጀት ያስከተለው የግብአት እጥረትን በምክንያትነት ያነሳሉ። የሰራተኞች ክፍያ ለሦስት ወራት የዘገየውም በጀት ስላልነበረ ነው ይላሉ። "ለ2010 ዓ.ም ያስፈልጋል ብለን የያዝነው 316 ሚሊዮን ብር ቢሆንም የጤና ቢሮ መስጠት ከሚችለው በላይ ነው" የሚሉት ዳይሬክተሩ አፈጻጸማቸውን ሲመዝኑ ከእቅዳቸው ወደ ኋላ መቅረታቸውን ያክላሉ። የጤና ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር አበባው በአንጻሩ "በከፍተኛ የክልሉ ካቢኔ ጥናት ተሰርቶ የሆስፒታሉ ችግሮች ተለይተው ታውቀዋል። ለአገልግሎት ጥራት ማነስና የሰው ኃይል እጥረት መፍትሄ የሚሆን ሰነድ እየተገበርን ነው" የሚል ምላሽ አላቸው። "ለሆስፒታሉ የሀገሪቷንና የክልሉን ስሌት መሰረት ያደረገ በጀት እንሰጣለን" ቢሉም ፈለገ ህይወት ከሚያስተናግደው ሰው አንጻር በጀቱን መከለስ ሊያስፈልግ ይችላል ይላሉ። ኃላፊው "ስለ ክፍያ መቋረጥ ሪፖርት አልደረሰንም። የሰራተኞች ዲውቲ አንድም ቀን አልተቋረጠም" ይላሉ። የሰራተኞቹና የዳይሬክተሩ ምላሽ ግን ይህን ይቃረናል። *ስም የተቀየረ
news-52932158
https://www.bbc.com/amharic/news-52932158
በአሜሪካ ፖሊሶች ነፍስ አጥፍተው የማይከሰሱት ለምንድነው?
አሜሪካ ውስጥ "ሰማይ አይታረስ፣ ፖሊስ አይከሰስ" የሚል አባባል ቢኖር ተገቢ ይመስላል። በዚያ አገር ፖሊስ አልፎ አልፎ ካልሆነ ነፍስ በእጁ አጥፍቶም አይከሰስም የሚለው ስሞታ በስፋት ይነገራል።
ለፖሊሶች የሚሰጠው የሕግ ከለላ አወዛጋቢ ሆኗል እርግጥ ነው ቁጣን የቀሰቀሰው የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ይለይ ይሆናል። ተጠርጣሪው ነጭ ፖሊስ ዴሪክም ተከሷል፤ አብረውት የነበሩት ሌሎች ሦስት ፖሊሶችም ከብዙ ውትወታና ተቃውሞ በኋላ እንዲሁ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ይህ ማለት ግን አብዛኞቹ ጥቁር አሜሪካዊያን ተስፋ እንደሚያደርጉት በግድያው የተከሰሱት ፖሊሶች ጥፋተኛ ሆነው ከባድ ቅጣት ይቀምሳሉ ማለት ላይሆን ይችላል። የጆርጅ ፍሎይድ የመጨረሻዎች ደቂቃዎች በቪዲዮ ተቀረጹ እንጂ ክስተቱ ለአሜሪካ ብርቅ አይደለም። በአሜሪካ በየዓመቱ ብዙ ንጹሐን ዜጎች በፖሊስ ይገደላሉ። ሟቾቹ ደግሞ በብዛት ጥቁሮችና ስፖኒሾች ናቸው። በአመዛኙ ገዳይ ፖሊሶች ከሥራ ይባረሩ ይሆናል እንጂ መደበኛ ክስ ተከፍቶባቸው ይፈርድባቸዋል ለማለት ያስቸግራል። አሐዞች የሚመሰክሩትም ይህንኑ ነው። በአሜሪካ በየዓመቱ በአማካይ 1200 ዜጎች በፖሊሶች ይገደላሉ። ከእነዚህ ግድያዎች ውስጥ ታዲያ 99 ከመቶ የሚሆኑት ገዳይ ፖሊሶቹ ጭራሽ ክስ እንኳ ሳይቀርብባቸው፤ የፍርድ ቤት ደጅ እንኳ ሳይረግጡ ነው የሚታለፉት። ለምን? የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ በመላዋ አሜሪካ ከባድ ተቃውሞን ቀስቅሷል ኳሊፋይድ ኢሚዩኒቲ፡ ለአሜሪካ ፖሊሶች ከለላ የሚሰጠው ሕግ በአሜሪካ ሕግ ጸጥታ አስከባሪዎች ከወንጀል ክስም ሆነ ከፍትሐ ብሔር ክስ የሚጠብቃቸው ፍጹም ልዩ የሆነ የሕግ ከለላ አላቸው። በማስረጃ እናስደግፈው። የፖሊስ እርምጃዎችን በመመዝገብ የሚታወቀው ማፒንግ ፖሊስ ቫዮለንስ ፕሮጀክት ከ2013 እስከ 2019 ድረስ በፖሊሶች የተገደሉ 7 ሺህ 666 አሜሪካዊያንንና አገዳደላቸውን ሰንዷል። ከእነዚህ ውስጥ ታዲያ በፖሊስ ክስ የተመሰረተባቸው 99 ፋይሎች ብቻ ናቸው። ይህም ከጠቅላላው 1.3 በመቶው ብቻ መሆኑ ነው። የሚገርመው ከእነዚህ 7 ሺህ 666 ግድያዎች ውስጥ ፖሊስ ላይ ክስ ተመስርቶ የጸጥታ ኃይል አባል አጥፊ ተደርጎ ፍርድ የተሰጠው በ25 ጉዳዮች ላይ ብቻ ነው። ይህም ማለት በእነዚህ ዓመታት ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ያለው የፖሊስ ቁጥር 25 ብቻ ነው ማለት ነው። በዋሺንግተን ካቶ ኢንስቲትዩት የወንጀል ጉዳዮች ጥናት ቡድን ምክትል ፕሬዝዳንት ክላርክ ኔይሊ እንደሚሉት ፖሊሶችን በወንጀል የመክሰስ እድሉ ጠባብ ስለሆነ አብዛኛዎቹ ክሶች የወንጀል ሳይሆኑ የካሳ ጥያቄዎች ለመሆን ተገደዋል። ለፍትሐ ብሔር የካሳ ክስም ቢሆን አብዛኞቹ ፍርድ ቤቶች በራቸው ዝግ ነው የሚሉት ሚስተር ክላርክ ይህም የሆነው በአሜሪካ ኳሊፋይድ ኢሚዩኒቲ (Qualified Immunity Doctrine) የሚባል ነገር በመኖሩ ነው። ኳሊፋይድ ኢሙዩኒቲ የሕግ አስከባሪዎች የሰዎችን መብት ቢገፉም እንኳ ተጠያቂ እንዳይሆኑ የሚያደርግ ልዩ መብት ነው። ይህ መብት ሊነሳ የሚችለው ተጎጂው በፍጹም በማያሻማ ሁኔታ ፍርድ ቤትን ሊያሳምን የሚችል ግፍና ጥፋት በፖሊስ ሆን ተብሎ እንደተፈጸመበት ማስረዳት ሲችል ብቻ ነው። ሚስተር ክላርክ ይህ ለተጎጂዎች ተገቢ ካሳ እንኳ ሊያስገኝ የሚችለውን የፍትሐ ብሔር ክስ ለመመስረትና ፍርድ ለማግኘት እስከዛሬ በታሪክ እንደታየው አስቸጋሪና ሩቅ ብቻም ሳይሆን የማይታሰብ ነው። ለጊዜው ሁለት ምሳሌዎችን እንውሰድ። የጸጥታ አስከባሪዎችን ለመክሰስና ለማስቀጣት ፈታኝ እንደሆነ ይነገራል በገዛ ቤቷ ገብቶ ሕጻን ልጇ ላይ የተኮሰው ፖሊስ በ2014 አንድ ፖሊስ አሚ ኮርቢት የተባለች እናት ግቢ ውስጥ ዘሎ ይገባል። ወንጀለኛ እያሳደደ ነበር። ስድስት ልጆቿ በግቢ ውስጥ እየተጫወቱ ፖሊሱ ሽጉጡን እንደደቀነ ሁሉም መሬት ላይ በሆዳቸው እንዲተኙ አዘዘ። ልጆቿም ይህንን አደረጉ። በዚህ መሀል ብሩስ እያለች የምትጠራው ውሻዋ ድንገት ዘሎ በዚህ ውጥረት መሀል ገባ። ፖሊስ ውሻው ላይ አከታትሎ ተኮሰበት። በኋላ ላይ እንደታየው ውሻው ፖሊሱ ላይ ምንም የደቀነው ስጋት አልነበረም። ብቻ ሁለት ጥይት ተኮሰበት። ሆኖም ጥይት ውሻውን ሳተው፤ ብሩስ የተባለውን ውሻ የሳተው ጥይት ግን መሬት አላረፈም። ተወርውሮ የአሚን የ10 ዓመት ልጇን እግሩ ላይ መታው። ዳኮታ ይባላል የዚህ ልጇ ስም። እንደ እድል ሆኖ ዳኮታ በዚያች ጥይት ባይሞትም አካል ጉዳተኛ ሆነ። በዚያ ዕድሜው ላይ በጥይት ሲመታ የደረሰው የሥነ ልቦና ጉዳት ደግሞ ለዘልዓለሙ አብሮት የሚኖር ረቂቅ ቁስል ነው። ለዚህ ፖሊስ ታዲያ ክስ አይገባውም? እናት ፍርድ ቤት ክስ መሰረተች። ፖሊስ የገዛ ግቢዬ ውስጥ ገብቶ የ10 ዓመት ልጄን ተኩሶ አቁስሎታል ብላ የፍትሐ ብሔር ክስ መሰረተች። ፖሊስ ላይ የወንጀል ክስ የማይታሰብ ነው ብለናል። ፍርድ ቤት ክሷን ውድቅ አደረገው። የ8 ወር እርጉዝ ሆና አስፋልት ለአስፋልት በፖሊስ የተጎተተችው ማላይካ ማላይካ ብሩክስ እርጉዝ ነበረች። ፖሊስ በድንገት ሦስት ጊዜ በፖሊስ ማደንዘዥ ዱላ ገረፋት፣ ከመኪናዋ ጎትቶ አስፋልት ላይ ጣላት፣ ከዚያ ጭንቅላቷን ቁልቁል ደፍቶ የፊጥኝ አሰራት። ይህ ሁሉ ሲሆን የ11 ዓመት ልጇ ቆሞ ይመከለት ነበር። እርሷም የ8 ወር ነፍሰ ጡር ነበረች። ይህን ሁሉ የተደረገቸው ከተገቢው ፍጥነት በላይ መኪናሽን አሽከርክረሻል ተብላ ነው። እርሷም የክስ ወረቀት ለመውሰድ ፍቃደኛ አልሆነችም። የክስ ወረቀት ከወሰደች ለጥፋተኝነቷ ማስረጃ ተደርጎ እንዳይቀርብባት ሰግታለች። ኋላ ላይ ለደረሰባት ግፍና እንግልት ፖሊሱን ፍርድ ቤት ከሰሰችው። ፍርድ ቤቱም ክሷን ውድቅ አደረገው። ማላይካ ከስንትና ስንት እንግልት በኋላ፤ 10 ዓመት መንከራተት በኋላ ከመደበኛ ፍርድ ቤት ውጪ የ45 ሺህ ዶላር ካሳ ስምምነት አድርጋ ጉዳዩ በዚሁ ተቋጨ። ሚስተር ክላርክ እንደሚሉት ፍርድ ቤት በፖሊስ ላይ የሚመሰረትን ክስ ወደ ፊት ለመውሰድ እጅግ ግልጽ የሆነና የማያሻማ ጥፋት መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃን ይሻል። ያ ማስረጃ ከሌለ ፖሊስ ምንም ዓይነት ጥፋት ቢሰራ እጅ በኪስ አድርጎ ከፍርድ ቤት አዳራሽ ይወጣል። በፖሊስ እጅ ህይወቱ ያለፈው ጆርጅ ፍሎይድ ጉዳይ በዓለም ዙሪያ ቁጣን ቀስቅሷል የጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ ይፈረድበት ይሆን? ሚስተር ክላርክ እንደሚሉት ለፖሊስ በሕግ የተሰጠው ልዩ መብት "ኳሊፋይድ ኢሙኒቲ" (Qualified immunity) የሟች ጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰቦች ተገቢውን ፍትህ እንዳያገኙ ሊያደርጋቸው ይችላል። "ኳሊፋይድ ኢሚይኒቲ" ቀደም ሲል እንዳብራራነው በአሜሪካ የጸጥታ አስከባሪዎች ሕግን ለማስከበር ሲሉ በሚወስዷቸው እርምጃዎች ተጠያቂነት ሊመጣባቸው አይገባም ሲል የሚደነግግና ለፖሊሶች ከለላ የሚሰጥ ልዩ መብት ነው። ፖሊሶቹ ተጠያቂ የሚሆኑት በግልጽ የተቀመጡ ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን በማያሻማ ሁኔታ ጥሰው ሲገኙ ብቻ ነው። "የጆርጅ ፍሎይድ ጠበቆች አንድ ነገር ካገኙ ብቻ ክሳቸው ዋጋ ያገኛል" ይላሉ ሚስተር ክላርክ። ". . . ይኸውም ከዚህ በፊት በፍርድ ቤት የተወሰነ ተመሳሳይ ድርጊት ተፈጽሞ ፍርድ የተሰጠበት ጉዳይ ካለ. . . ማለትም አንድ ፖሊስ አንድ ተጠርጣሪ ላይ አንገቱ ላይ ቆሞ ትንፋሹ እስኪቆም ድረስ አፍኖ መግደሉ ሕጋዊ አይደለም" የሚል ውሳኔ ካላገኙ በስተቀር ክሱ ውድቅ ይሆንባቸዋል። ለምን ቢባል ፍርድ ቤቱ የኳሊፋይድ ኢሚዩኒቲ መርህን በመጥቀስ "እንዲህ ያለ ክስ የጸጥታ አስከባሪዎች ተከሰውበት አያውቁም፤ ስለዚህ ፖሊስ ላለመከሰስም ልዩ መብቱን ፍርድ ቤቱ ይጠብቅለታል ብሎ ጉዳዩን ይዘጋዋል" ይላሉ። የጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ ፖሊስ ነጻ ሰው ሆኖ ያለምንም ፍርድ ሊንቀሳቀስ የሚችልበት ዕድል መኖሩ ለብዙዎች እጅግ አስገራሚ ጉዳይ ነው። ቢቢሲ ለዚህ ጥንቅር የአሜሪካ ብሔራዊ ፖሊሶች ማኅበርን ሐሳብ ለማካተት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ይህ ጽሑፍ እስኪታተም ድረስ ምላሸ ማግኘት አልቻለም። ሆኖም የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ማይክል ማኬል ከዚህ ቀደም በዚሁ ጉዳይ እንተናገሩት "ጆርጅ ፍሎይድ ላይ የሆነው ነገር በሕግም፣ በሞራልም፣ ይቅር የሚባል አይደለም።" የሕግ ማሻሻያ ካልተደረገ ያ ሁሉ ተቃውሞ ውሃ ይበላዋል ብዙ ዜጎች በተቃውሞና በመፈክር ሕግ ሸብረክ እንደሚል ያስባሉ። ሆኖም የሕግ ማሻሻያና የፍትሕ ሥርዓት ለውጥ እስከሌለ ድረስ ፖሊሶች ያጠፉትን ቢያጠፉም ጥቁሮች እየሞቱ ይቀጥላሉ። ታዲያ ምን ይደረግ? የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኳሊፋይድ ኢሚዩኒቲ የሚባለውን ለፖሊሶች ከለላ የሚሰጠውን ደንብን የሚረዳበትን መንገድ እንዲቀይር ማድረግ አንዱ መፍትሄ ነው። የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸው የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ፒስ አክት (Peace Act) የተሰኘውን ረቂቅ እንዲያጸድቁ እየወተወቱ ነው። ሕጉ የፖሊስ አካላት እርምጃ በሚወስዱበት ጊዜ የሚጠቀሙት ኃይል ተመጣጣኝ እንዲሆንና ሰላማዊ በሆኑ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ የሚያዝ ነው። ፖሊሶች የግድ እስካልሆነ ድረስ ሕግን ለማስከበር በሚል ብቻ በሰላማዊ ሁኔታ ያልተመጣጠነ ጉልበት እንዳይጠቀሙ የሚያስገድድ ረቂቅ ነው። አንዳንድ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት ለዚህ ረቂቅ ከወዲሁ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ኦዲ ኦፈር የአሜሪካ ሲቪል ሊበርቲ ዩኒየን ዳይሬክተር ናቸው። "ሕግ ማውጣት ብቻውንም ምንም የሚፈይደው ነገር የለም" ይላሉ። በሕግ አስከባሪዎች ዙርያ ያለው አመለካከት በአሜሪካ ካልተለወጠ ችግሩ እንደሚቀጥል ያምናሉ። ለምሳሌ በአሜሪካ በአንዳንድ ግዛቶች ለፖሊስና ተያያዥ ጉዳዮች የሚወጣው ወጪ የግዛቱን 40 ከመቶ ወጪ ይሸፍናል። "በዚያ ላይ የታጠቁ ፖሊሶች በአሜሪካ አስፈላጊ ባልሆኑ ቦታዎች ሁሉ ይሰማራሉ፤ ይህ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ለምሳሌ ትምህርት ቤቶች ውስጥና ሥርዓት ያጡ ተማሪዎችን ልክ ለማስገባት ሁሉ ታጣቂ ፖሊስ ይሰማራል።" በአሜሪካ በየሦስት ሰከንዱ አንድ ሰው በፖሊስ ይታሰራል። እንደ አሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መረጃ ከሆነ በ2018 ብቻ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ዜጎች ብዛት 10.3 ሚሊዮን ይሆናሉ። የሚገርመው ከእነዚህ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ውስጥ ሲሶዎቹ ላይ እንኳ ክስ አይመሰረትም። ለምሳሌ ጆርጅ ፍሎይድ በቁጥጥር ሥር የዋለውና ለሞት ያበቃው በአንድ መደብር ውስጥ ሐሰተኛ ዶላር ለማስተላለፍ ሞክሯል በሚል ነበር። ለእንደነዚህ ዓይነት ወንጀሎች የጦር መሣሪያ የታጠቀ ፖሊስ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል። "ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለፖሊስና ተያያዥ ወጪዎች መመደብን ጤናማ አይደለም" ይላሉ ኦዲ ኦፈር። ይልቅ ለፖሊስ የሚወጣው ቢሊየን ዶላር በታሪካዊ ሁኔታዎች የተነሳ ለወንጀል የቀረቡ ናቸው ለሚባሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሰጥቶ ቁም ነገር ቢሰራበት ወንጀል ይቀንሳል። አሁን በአሜሪካ የተቀጣጠለው ተቃውሞ በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚከስም ይጠበቃል። በጥቁር አሜሪካዊያን ላይ የሚደርሰው በደልስ? ለዚህም ነው የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ የተቀሰቀሰውን ቁጣ ከመብረዱ በፊት ብልህ የመብት ተሟጋቾች ወደ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲያመራ እየሰሩ የሚገኙት። ኦዲ ኦፈር እንደሚሉት ግለሰቦችን በመክሰስ የፖሊስን የጭካኔ ወንጀል መቀነስ አይቻልም። ተቃውሞው ሲበርድ ሁሉም ነገር ወደ ቦታው ይመለሳል። ተቃውሞው ተቋማዊና መዋቅራዊ ለውጥ ካላመጣ ከንቱ ድካም ነው።
news-50178711
https://www.bbc.com/amharic/news-50178711
"ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው" ቸኮለ መንበሩ
ለመማር ምን ያህል ዋጋ ከፍለዋል? ምን ያህልስ ስኬታማ ነኝ ብለው ያስባሉ? የልፋትዎትን ያህልስ አግኝቻለሁ ብለው ያስባሉ?
የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ምሩቁ ሊስትሮ ዛሬ የአንድ ወጣትን የትምህርት ጉዞ እናጫውታችኋለን። ቸኮለ መንበሩ ይባላል። የተወለደው ናበጋ ጊዮርጊስ በምትባል ቦታ ነው። በህጻንነቱ ነበር አባቱን በሞት ያጣው። እናቱም ሌላ በማግባቷ ታዳጊው ቸኮለ ከአያቶቹ ጋር መኖር ጀመረ። ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ መማር እንደሚፈልግ ለአያቱ ቢነገርም 'ማን ያስተምርሃል?' በሚል ውድቅ ተደረገበት። • ከስደት ወደ ባለሃብትነት ወደ አጎቱ ቤት በማቅናት በእረኝነት ማገልገል ጀመረ። ጓደኞቹ ትምህርት ቤት መግባታቸው በድጋሚ "አስተምሩኝ?" ብሎ እንዲጠይቅ ምክንያት ሆነው። ካልተማረ አብሯቸው መኖር እንደማይፈልግ ገልጾ ነው ጥያቄውን ያቀረበው። አያቱ ሁለተኛውን ጥያቄ ግን ውድቅ አላደረጉበትም። ትምህርቱንም ጀመረ። ሁለት ዓመት ያህል አያቱ ዘንድ ተቀምጦ ከተማረ በኋላ መግባባት ባለመኖሩ ምክንያት ከአያቱ ቤት እንዲወጣ ሆነ። ትምህርት እስኪጀመር ክረምቱን እናቱ ጋር እንዲያሳልፍ ተደረገ። 'እስከመስከረም ድረስ የት ይክረም?' በሚል ሽማግሌዎች ወደ እናቱ ተልከው በመጠየቃቸው "ከእናቴ ጋር 2 ማድጋ ከረምኩ" ይላል። በዚህም ምክንያት "ከእናቴ ጋ ሁለት ክረምት ያሳለፍኩ ብቸኛው ልጅ እንደሆንኩ አስባለሁ" ሲል ያስታውሳል። የሚረዳው ሰው ባለመኖሩ ራሱን ማስተማር ብቸኛው አማራጭ ሆነ። አንድ ጫማ የሚጠርግ ጓደኛውን ሲያወያየው አብሮት እንዲሠራ መከረው። አባቱ የተከሉትን ባህር ዛፎች በሃያ ብር ሸጦ ጫማ ለመጥረግ የሚረዱትን ቁሳቁሶችን ገዝቶ ሥራ ጀመረ። "ከዚያ በኋላ መማር ጀምርኩኝ" ይላል ቸኮለ። ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ከትምህርት ሰዓቱ ውጭ ጫማ እየጠረገ ትምህርቱን መከታተሉን ቀጠለ። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" "ለመማር የተሻለ ያግዘኛል ብዬ ያሰብኩት ሥራ ጫማ መጥረግ ነው። ግማሽ ቀን እየሠራሁ ግማሽ ቀን ለመማር ማለት ነው። [የሞባይል] ካርድም ሸጫለሁ። አብዛኛውን ሊስትሮ ነው የሠራሁት። [በወቅቱ] ኑሮም ከባድ ስላልነበረ ሊስትሮ ሠርቼ መማር እችል ነበር። አንዳንድ የሚያውቁኝ ሰዎች እያበረታቱ 'እነእከሌ እኮ እንደዚህ ተምረው ነው ዶክተር እና መሃንዲስ የሆኑት' እያሉ ስለሌሎች ስለሚነግሩኝ ከኋላ ያለው ስቃይ አይታየኝም ነበር። የወደፊቱን ነበር የሚታየኝ። " "ትምህርት ዋጋ ነው ያስከፈለኝ" የሚለው ቸኮለ "ትምህርት ዋጋ ነው ያስከፈለኝ። ስቅይት ብዬ ነበር የተማርኩት። በተለይ በዓል ሲደርስ የነበረው ስሜት ይከብድ ነበር። ዳቦ በልቼ አድር ነበር። ለነገም ከዳቦው ለቁርስ አስተርፍ ነበር። በተለይ 7ኛ እና 8ኛ ከፍል እያለሁ" ሲል ይገልጻል። የደንብ ልብስ ለመግዛት ጫማ መጥረጉ ብቻ ስለማይበቃው ሥራ ፍለጋ ወደ በረሃ አቅንቷል። ሥራ ስላልነበረ ወደ ሁመራ ያደረገው ጉዞ ስኬታማ አልነበረም። ከጓደኛው ጋር አንድ ሱሪ እና ቲሸርት ብቻ ገዝተው ተመልሰዋል። ብዙ አስቸጋሪ ወቅቶችን ቢያሳልፍም 8ኛ እና 10ኛ ክፍልን ሲያልፍ አዲስ የደንብ ልብስ ማሰፋት ስለሚያስፈልገው እንዲሁም ዩኒቨርሲቲ ሲገባ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟላት ፈተናው ከባድ ነበር። "እነዚህ ሦስቱ [ክፍሎች] ለእኔ ልዩ ናቸው። ማለት በጣም የተጨናነቅኩባቸው ጊዜያቶች ነበሩ" ሲል ያስረዳል። ከ3ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ድረስ ጫማ በመጥረግ ተምሮ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚያስገባውን ውጤት በማምጣቱ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ገባ። ህይወት "ግቢ [ዩኒቨርሲቲ] ውስጥ የተሻለ ነበር" የሚለው ቸኮለ "ከቀበሌ ረዳት የሌለው የሚል ማስረጃ አጽፌ በወር 200ም ሆነ 100 ብር እየተሰጠኝ፤ ክረምት ደግሞ እዛው [ዩኒቨርሲቲ] እየሠራሁ ተከፍሎኝ እከርም ነበር። ጓደኞቼም አብዛኛውን ይሸፍኑልኝ ነበር። ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተሻለ ነበር። ጥሩ ጓደኞች ነበሩኝ። ደብተር ጭምር ይገዙልኝ ነበር። ስመረቅም ሱፌ እንደተጀመረ ማስጨረሻ ብር ስላጣሁኝ የዶርም ልጆች አግዘው አሰፉልኝ።" ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላ የትምህርት ክፍል ለመምረጥ መስፈርት ያደረገው 'ቶሎ የሚያስቀጥረውን' ነበር። በዚህ መሠረትም ኤሌክትሪካል ምህንድስና የመጀመሪያ ምርጫው ነበር። በሁለተኛነት ደግሞ ኬሚካል ምህንድስና። በውጤት እና በተለያዩ መመዘኛዎች መሠረት ሁለተኛ ምርጫው የሆነውን የኬሚካል ምህንድስና የትምህርት ክፍልን ተቀላቀለ። • ከድምፃዊት ቤቲ ጂ እና ቸሊና ጀርባ "የኢንዱስትሪ ወሬ ነበር። በሃገሪቱ ይህን ያህል መሐንዲስ ያስፈልጋል ሲባል ስለነበር ጥሩ ይሆናል ብዬ ነበር የመረጥኩት። " "ስለሥራ ዕድልም ማንም የሚነግርህ የለም። ቀደም ሲል የተዘጋጅቼ የመጣሁት ለመቀጠር ነው። . . . ሥራ አለው የለውም አልተነገረንም። የዲፓርትመንት [ትምህርት ክፍል] ምርጫ ጊዜ ሁሉም የውጭ ዲዛይን ያመጣና ኬሚካል ይሄን ይሠራል ስለሚባል በዚያ እየተሳብን ነው የምንገባው።" "እውነት ለመናገር እኔ የተቀረጽኩትም ሆነ ሊስትሮ ስሠራም ሳስበው የነበረው የመቀጠር ነው አባዜ የነበረኝ" የሚለው ቸኮለ "እሠራለሁ ብልም ገንዘብ ስለሌለኝ ሃሳቡም የለኝም። መቀጠር እና መሥራት ነው የምፈልገው" ይላል። ዩኒቨርሲቲ ሲገባ የነበረውን ደስታ ያህል መመረቂያው ሲደርስ ደግሞ "ጭንቀቴ ጨመረ" ይላል። ምክንያቱ ደግሞ "ምን እሠራ ይሆን?" በሚል ነው። ቀድመዋቸው ከተመረቁት ተማሪዎች ብዙዎቹ ሥራ አለማግኘታቸው ስጋቱን ከፍ አንዳደረገው ቸኮለ ያስረዳል። "ግቢ ስገባ የተደሰትኩትን ያህል ልመረቅ አካባቢ ጭንቀቴ እየጨመረ ነው የመጣው። ምክንያቱም ነገ ደግሞ ሥራ አጥቼ ከዚያ ሊስትሮ ድጋሚ ልቀመጥ ነው። ያሰብኩት ላይሳካ ነው። ተመርቄ ቶሎ ሥራ ላልይዝ ነው። ይኼን ሳስብ ይጨንቀኝ ጀመር" ይላል። የመጨረሻ ዓመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ እያለ ብዙዎች ድጋፍ ያደርጉለት ነበር። "አኔና ጓደኛዬ ሰዎች በሚሰጡን ብር ተመርቀን ስንወጣ [ሊቸግረን ይችላል] በሚል ለአንድ ዓመት የሚበቃ ልብስ ገዝተናል።" • የዘንድሮ ተመራቂዎች እንዴት ሥራ ያገኛሉ? በ2010 ዓ.ም ከተመረቀ በኋላ ቀጣዩ ሥራ መፈለግ ነው። "አዲስ አበባ ሥራ ለመፈለግ 3 ወር ነበርኩኝ። በየኢንዱስትሪ ፓርኩ በእግሬ እየዞርኩ ሥራ ስጠይቅ የነበረው።ወልዲያ እና አዲስ አበባ ድረስ ሄጃለሁ። አንድ ፋብሪካ ውስጥም በሃያ ዘጠኝ ብር የቀን ሥራ ጀምሬ ነበር። ግን አላዋጣኝ አለ" ይላል። ከመጀመሪያ ዲግሪ በታች የሚጠይቁ ሥራዎች ላይም አመልክቶ ያውቃል። ቀጣይ እድገት ይጠይቃል በሚል ማመልከቻው በተደጋጋሚ ውድቅ ሆኗል። ሥራ አጥ ወጣቶች ተደራጅተው በየቀበሌው የሚከፈትላቸውን የሥራ ዕድል ለመጠቀም ከጓደኞቹ ጋር ቢያመለክትም "በኬሚካል ምህንድስና የተመረቃችሁ አትመደቡም' ቢባሉም ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ አዎንታዊ ምላሽ ተሰጣቸው። ሥራውን ለማግኘት ዕጣ ስላልወጣለት በዕድሉ መጠቀም ግን አልቻለም። የተወሰኑት አብሮ አደጎቹ እና የትምህርት ክፍል ጓደኞቹ ሥራ አግኝተዋል። ከወራት ሥራ ፍለጋ በኋላ ሥራ ባለማግኘቱ ያለው አንድ አማራጭ ብቻ መሆኑን አወቀ። "አማራጭ ሳጣ ሊስትሮ መሥራት ጀመርኩኝ።" • ሴት ተመራቂዎች ለምን ሥራ አያገኙም? ጫማ እየጠረገም ቢሆን አሁንም ሥራ መፈለጉን አልተወውም። "ጫማ እየጠረግኩም ሥራ እፈልጋለሁ። የምጠርገውን ጫማ ጨርሼ ማስታወቂያ ለማየት እጓጓለሁ። ማስታወቂያ መለጠፊያው አካባቢ ስለሆንኩኝ አሁንም እፈልጋለሁ። እየዞርኩኝም ሥራ እፈልጋለሁ" ይላል። ሥራ ያላገኘው ባለው አነስተኛ ነጥብ ምክንያት እንደሆነ ለቀረበለት ጥያቄ "ውጤቴ ለእኔ ምንም አይልም። ወደ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ብቻ የተላከ ይኖራል። እኔ ግን ከትምህርት በተጨማሪ የኑሮ ውጣ ውረድ ስለነበረብኝ የተመረቅኩበት ነጥብ ለእኔ ጥሩ ነበር" ብሎ ምላሽ ሰጥቷል። ለዚህም ነው "ለእኔ ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበት ዋጋ ያላገኘሁበት ቢኖር ትምህርት ነው ብዬ አስባለሁ" የሚለው። ከዚህ ይልቅ በፖለቲካው አለመረጋጋት ምክንያት የመንግሥት ትኩረት ወደ ፖለቲካ መዞሩ፤ ክፍት የሥራ ቦታዎች በዝምድና መያዛቸው እና ያሉት የሥራ ዕድሎች እና የተመራቂዎች ቁጥር አለመጣጣምን በምክንያትነት ያነሳል። • የወንድሙን ገዳይ ለመበቀል ወደ ፈጠራ ሥራ የገባው ኢትዮጵያዊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ይዞ ጫማ ሲጠርግ ብዙ አስተያየቶች ይሰጡታል። " የሚያውቁኝ መምህራኖቼ ከእኔ ይልቅ እነሱ ናቸው የሚደነግጡት። ሲያገኙን አንገታቸውን ደፍተው ከእኔ በላይ በጣም ስቅቅ ብለው ይሄዳሉ።አንዳንዶቹ ደግሞ ቀርበው አይዞህ ብለው አበረታተውኝ የተወሰነ ገንዘብ ሰጥተውኝ ይሄዳሉ። ጓደኞቼ ሲያገኙኝ ሳይፈልጉም ቢሆን አሠርተው ያላቸውን ሰጥተውኝ ይሄዳሉ። ይህን ትውልድ ተስፋ ታስቆርጣለህ ከዚህ ተቀምጠህ የሚሉም ሰዎች አሉ።" በመጨረሻም ቸኮለን 'ለምን ተማርኩ ብለህ አስበህ ታውቃለህ?' ብለን ጠይቀነዋል። "ብዙ ጊዜ ባልማር አልናደድም ብዬ አስባለሁ። ይህን ያህል ዋጋ መክፈል አልፈልግም። ምን አሰቃየኝ?። አንደኛዬን የለየልኝ ጥሩ ወይም መጥፎ ሰው እሆናለሁ ብዬ የማስብበት አጋጣሚ አለ" ሲል ስሜቱን አጋርቶናል።
news-49274399
https://www.bbc.com/amharic/news-49274399
የዓለምፀሐይ ወዳጆ፣ የዘነበ ወላና የሕይወት እምሻው ምርጥ መጻሕፍ የትኞቹ ናቸው?
ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር የዓለም የመጽሐፍ ሳምንት ተከብሯል። ዛሬ ደግሞ ኦፊሴሊያዊ ባይሆንም የመጻሕፍት ወዳጆች (አፍቃሪያን) ቀን ይከበራል። ይህ ቀን ለመጽሐፍ ቀበኞችና ወዳጆች ክብር የሚሰጥበትና የሚደነቁበት ነው።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት መጽሐፍ ማንበብ ለተዝናኖት ብቻ ሳይሆን ጤንነትን ለመጠበቅም ጠቀሜታዎች አሉት። ማንበብ ጭንቀትን ለመቀነስ፣ አዕምሮን ለማስላት፣ ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ፍቱን መድኃኒትም ነው ይላሉ አጥኚዎች። • ማንበብ ስፓ ከመግባት ይሻላል? • ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ ተመራማሪዎች እንደሚሉት የሚያነቡ ሰዎች ከማያነቡት በተሻለ የሌሎችን ስሜት የመረዳት ብቃታቸውም ከፍተኛ ነው። ታዲያ ይህ ቀን በመጻሕፍት አፍቃሪ ዘንድ የመጽሐፍ ስጦታ በመለዋወጥ፣ በመገባበዝ፣ በመደናነቅ ይከበራል። የመጻሕፍት መደርደሪያዎችን በማጽዳት እና የመጻሕፍትን አደራደር በቅጡ በማድረግ ለመጽሐፍ ያላቸውንም ፍቅርም ይገልጹበታል። ከዚህም ባሻገር ቤተ መጻሕፍትን በመጎብኘት፤ የቤተ መጻሕፍት መግቢያ ካርድ የሌላቸው በመመዝገብ፣ የንባብ ክለቦችን በመቀላቀልም ሲያከብሩ ይስተዋላል። በዚህ ቀን ሕፃናትና ወጣቶች መጽሐፍ እንዲያነቡም ይበረታቱበታል። የእርስዎ ምርጡ መጽሐፍ የትኛው ነው? ከወራት በፊት የዓለም የመጽሐፍ ቀንን አስመልክቶ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የመጽሐፍ ወዳጆች ለእነርሱ ምርጥ የሚሏቸውን መጽሐፍ ነግረውናል። ካነበቧቸው መጻሕፍት መካከል አንድ መምረጥ ጭንቅ ቢሆንባቸውም ይህንን ጋብዘውናል። 'እኔ የምለምነው መጽሐፍና ቆሎ ነው" ይህን ያለችው ታዋቂዋና አንጋፋዋ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆ ናት። ዓለምፀሐይ ከልጅነቷ ጀምሮ በኢትዮጵያ የአማርኛ መጻሕፍት ውስጥ ታትሞ የወጣ እና እርሷ ያላነበበችው መጽሐፍ ስታገኝ ትበሳጭ እንደነበር ትናገራለች፤ ይህን ያህል ነው ለንባብ ያላት ፍቅር። ታዲያ ለእርሷ በልብወለድ አጻጻፍ ስልት የደራሲ በዓሉ ግርማ አድናቂ ስትሆን በጋዜጣዊ የድርሰት አጻጻፍ ደግሞ ብርሃኑ ዘሪሁንን ታደንቃለች። በግጥም ዘርፍ የሎሬት ፀጋየ ገ/መድህንን 'እሳት ወይ አበባ' ለእሷ ወደር የለውም። " ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀጥሎ ከራስጌዬ የማልነጥለው መጽሐፍ ነው" ትላለች። እንዲህ እንዲህ እያለች ትዘረዝራለች። እኛ ግን አንድ ብቻ እንድትመርጥ እድል ሰጠናት። [አንዱን ካንዱ ማወዳደር ጭንቅ ነበር ለእሷ።] • የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ መጻሕፍት ዘርፈ ብዙ በመሆናቸው ለመምረጥ ብትቸገርም ከአማርኛ መጻሕፍት ውስጥ ፍቅር እስከ መቃብርን ትጠቅሳለች። "የደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁን ድርሰት 'ፍቅር እስከ መቃብር'ን አንብቦ የኢትዮጵያን ታሪክ አለማወቅ አይቻልም" ትላለች። ምክንያቷ፤ የኢትዮጵያን የፍቅር፣ አርበኝነትን፣ የባላባት ሥርዓትን፣ ጀግንነትን፣ የታሪክና ባህልን የሚየሳይ በመሆኑ ለእርሷ ምርጡ መጽሐፍ ነው። ዓለምፀሐይ ፍቅር እስከ መቃብርን የመጀመሪያ ዕትሙ እንደወጣ [በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1958 ዓ.ም] እንዳነበበችው ትናገራለች። ከዚያ በኋላ ግን ሦስት አራቴ በተደጋጋሚ ያነበበችው መጽሐፍ ነው - ፍቅር እስከ መቃብር። መጽሐፍ ማንበብ ከመውደዷ የተነሳ፤ በስደት አሜሪካ አገር ሆና እንኳን ከሃገር ቤት እንዲላክላት የምትጠይቀው መጽሐፍና ቆሎ ነው ትላለች። • "የመጀመሪያውን ድራማ አንተ፤ ሁለተኛውን እኔ እፅፈዋለሁ" ኤርሚያስ አመልጋ • ዕድሜ ጠገቧ የጥድ መፃሕፍት ቤት መደብር ትውስታ ዓለምፀሐይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴያትር እና በራስ ቲያትር፤ የቬነሱ ነጋዴ፣ ሐምሌት፣ ሮሜዮና ዡልየት፣ ማክቤዝ፣ 12ቱ እብዶች በከተማ፣ ሀሁ በስድስት ወር፣ ዋናው ተቆጣጣጣሪ እና ሌሎችም በርካታ የመድረክ ተውኔቶች ላይ በመሪ ተዋናይነት ተውናለች። ስግብግብ ምላሴ፣ የኑዛዜው መዘዝ፣ ጤና ይስጥልኝ ዶክተር፣ ያልተከፈለ ዕዳ በተሰኙ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመሪ ተዋናይነት ተጫውታለች። በተውኔት እና በፊልም ፀሐፊነትና አዘጋጅነት ደግሞ አማቾቼ፣ ደማችን፣ የሞኝ ፍቅር፣ ህልመኞቹ እና ሌሎች በርካታ ሥራዎች ይጠቀሳሉ። አምስት የግጥም መጻሕፍትን ለንባብ አብቅታለች። ከ400 በላይ የዘፈን ግጥሞቿ ቁጥራቸው ከ48 በላይ በሚሆኑ በአንጋፋና ወጣት ድምጻዊያን መዜማቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። "ከ10 ወዳጆችሽ አንዱ አንብቤዋለሁ ካለ እድለኛ ነሽ" አብዛኛውን የሕይወቱን ክፍል በባሕር ላይ ያሳለፈው ባህረተኛና ደራሲ ዘነበ ወላም የራሱ የመጽሐፍ ግብዣ አለው። ጋዜጠኛና ደራሲ ዘነበ ወላ ማስታወሻ፣ መልህቅ፣ ልጅነት፣ ሕይወት በባህር ውስጥ እና "21 ዓመታት ፈጅቶብኛል" ያለውን የምድራችን ጀግና (Champion of the Earth) በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያጠነጥን እና በዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሔር የሕይወት ታሪክ ላይ ትኩረት አድርጎ የተጻፈ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ አብቅቷል። ለንባብ ባህል አብዝቶ የሚቆረቆረው ዘነበ ይህንኑ የሚሰብክ የቴሌቪዥን ፕሮግራምም ያዘጋጃል። "የረጅም ጊዜ የንባብ ሕይወት ካሳለፍሽ አንድ መጽሐፍ መምረጥ አስቸጋሪ ነው" የሚለው ዘነበ በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ገብረሕይወት ባይከዳኝ የጻፉት 'መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር' የሕይወት ዘመን መጽሐፉ እንደሆነ ይናገራል። ሌላው የተክለሃዋሪያት ተክለማሪያም ግለ ታሪክ የሆነውን መጽሐፍ "ለልጅ ልጅ መተላለፍ የሚገባው መጽሐፍ ነው" ይላል። ዘነበ በርካታ መጻሕፍትን ስም መዘርዘር ጀምሮ ነበር። ይሁን እንጂ ለእርሱ ምርጥ የሆነውን አንድ መጽሐፍ እንዲጋብዘን ጠየቅነው፤ እርሱም እንዲህ አለ። • ክረምትና ንባብ "አንድ አማርኛ ቋንቋ ማንበብና መጻፍ የሚችል ሰው፤ ላንብብ ቢልና አዋቂ ልሁን ቢል፤ ዓለም አቀፍ ዕውቀት እንዲኖረው የሚያስችሉ ሥራዎች በአማርኛ ተሠርተዋል" ሲል ይንደረደራል። ነገር ግን ለዘነበ ወላ የገብረ ሕይወት ባይከዳኝን 'መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደርን' የሚያህልበት ግን የለም፤ ሁልጊዜም የእርሱን ያስቀድማል። 'መንግሥትና የሕዝበ አስተዳደር' ከዛሬ መቶ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ የሥራ ፈጠራ፣ በኢትዮጵያ የመንግሥት አስተዳደር ላይ እንዲሁም በሌሎች ጠንካራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ መጻፉ ደራሲው በዚያ ዘመን ምን ያህል ሰፊና ጥልቅ ሕሊና እንዳለው ስለሚያሳየው መጽሐፉን ይመርጠዋል። ገብረሕይወት ሕይወቱ ሲያልፍ "ገብረሕይወት አረፈ፤ እንደ እሱ ዓይነት አስተሳሰብ ያለው ሰው፤ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ 10 ሰው እንኳን አልነበራትም" ሲሉ ልዑል ራስ እምሩ መጻፋቸውን ዘነበ ያወሳል። "መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር በትምህርት ሥርዓት ውስጥ መካተት ያለበት ሐሳብን የያዘ ነው" የሚለው ዘነበ ወደፊት ጠንክሮ ከሚሠራባቸው ጉዳዮች አንዱ እንደሆነም ነግሮናል። መጽሐፉንም እንድታነቡት ጋብዟል። "መምረጥ ከባድ ቢሆንም ፤ ከልብ ወለድ አለንጋና ምስርን እመርጣለሁ" ሕይወት እምሻው 'ነቆራና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር' በተሰኘ የፌስ ቡክ ገጿ በምትፅፋቸው ጽሑፎች ትታወቃለች። በዚህ ገጿ የግል ምልከታዋን፣ ማህበራዊ ትዝብቷንና ልብ ወለድ ሥራዎችን ታቀርብበታለች። በርካታ ተከታዮችን ማፍራትም ችላለች። ባርቾ፣ ፍቅፋቂ እና ከሰሞኑ ደግሞ ማታ ማታ የሚሉ መጻሕፍትንም ለንባብ አብቅታለች። እንደሌሎቹ ሁሉ ሕይወት እምሻውም መጽሐፍ ዘርፈ ብዙ በመሆኑ አንደኛውን ከአንደኛው ለመምረጥ ብትቸገርም በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ የሕይወት ዘመን ምርጥ ደራሲ አዳም ረታ እንደሆነ ገልጻልናለች። ከአዳም ረታ ሥራዎች መካከልም 'አለንጋና ምስር'ን ታስቀድማለች። ምክንያቷ ደግሞ የሰውን ልጅ ኑሮ፤ በተለያየ ደረጃና ዘመን ያሉ የኢትዮጵያዊያንን ኑሮ በተለያዩ ታሪኮች በአንድ መጽሐፍ ውስጥ አካቶ ስላቀረበ ነው ትላለች። • 'ደራሲ ያደረገኝ ማኅበራዊ ሚዲያው ነው' የእናንተስ ምርጡ መጽሐፍ የትኛው ነው? . . . ለምን?
news-47897843
https://www.bbc.com/amharic/news-47897843
በኢትዮጵያ ለሰዎች መገደል ምክንያት የሆነውን የጥላቻ ንግግር፣ ህግ ይገድበው ይሆን?
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በማህበረሰቡ ዘንድ መጠራጠርና ፍራቻ ነግሶ የሰው ልጅ በአደባባይ የተሰቀለበት፣ ለምርምር የወጡ የዩኒቨርስቲ ምሁራን ተወግረው የተገደሉበትና እንዲሁም ሌሎች ለመስማት የሚሰቀጥጡ ዜናዎች የተሰሙበትና በአገሪቱም ላይ ጠባሳን ትቶ አልፏል።
በተለያዩ በይነ መረቦችና ማህበራዊ ገፆችም ላይ የተለያዩ ማህበረሰቦችን ለጥቃት የሚያነሳሱ፣ የግድያንና የመፈናቀልን የሚቀሰቅሱ መልዕክቶች በተለያዩ ጊዜያት ይስተዋላሉ። በዚህ ደግሞ ተራ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ማህበረሰቡን የሚመሩ የመብት አራማጆች ማህበረሰቡን እርስ በርስ በማጋጨት በመወቀስ ላይ ናቸው። •መከፋፈል ያጠላበት ጉዞ አድዋ •"የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ" መሐመድ አደሞ የአንዳንድ የመንግሥት ኅላፊዎችም ንግግር ከአውድ ውጭ እየተወሰደ በተፈጠረው መከፋፈል ላይ ቤንዚን በእሳት ላይ እንደ ማርከፍከፍ ሆኖ ለአንዳንድ ጥላቻዎችና መፈራቀቆች መቀጣጠል ምክንያት ሆኗል። ለተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መልሶች በሙሉ ጥላቻንና ጥቃትን ምላሽ ያደረጉና ሃይ ባይ ያጡ መልዕክቶች ለፖለቲካዊ ቀውስ ምክንያት እንዳይሆኑ ያሰጋል። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ግድያ፣ ጦርነት፣ ዘር ማጥፋት እንደተለመደ ነገር ተደርጎ መቀስቀሱ ቀጥሏል። በዚህም ምክንያት ሀገሪቷ ውስጥ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ተፈናቅለዋል፤ በርካቶች ለሞት ሲዳረጉ እንዲሁም ለብዙዎች በስጋት ውስጥ ለመኖር ምክንያት ሆኗል። • ብሔርን ከመታወቂያ ላይ ማስፋቅ. . . የተለያዩ ሰብአዊ መብት ድርጅቶችና እንዲሁም የጠቅላይ አቃቤ ህግ ጥናት እንደሚያሳየው ለዚህ ሁሉ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የጥላቻ ንግግር እንደሆነ ያሳያል። ይሄንንም በጄ ለማለት ከሰሞኑ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ረቂቅ አዋጅ ወጥቷል። ረቂቅ ህጉ ምን ይዟል? ረቂቅ አዋጁ የጥላቻ ንግግር ትርጉም ብሎ ሲያስቀምጥ "ሆን ብሎ የሌላ ግለሰብን፣ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሔርን፣ ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ፆታን አካል ጉዳኝነትን ዜግነትን፣ ስደተኝነትን፣ ቋንቋን፣ ውጫዊ ገፅታን መሰረት በማድረግ ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል የሚያንኳስስ፣ የሚያስፈራራ፣ መድልዎ እንዲፈፀም፣ ወይም ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል መልዕክቶችን በመናገር፣ ፅሁፍ በመፃፍ፤ በኪነ ጥበብ እና እደ ጥበብ፣ የድምፅ ቅጂ ወይም ቪዲዮ፣ መልእክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨትን ይመለከታል።" ከዚህም በተጨማሪ ረቂቅ ሕጉ የሐሰት መረጃን በተመለከተም "የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው፤ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልፅ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ መረጃን ሆን ብሎ በማንኛውም መንገድ ማሰራጨትና ለህዝብ እንዲደርስ ማድረግ" እንደሆነ አስቀምጧል ። እነዚህን ድርጊቶች የፈጸመ ሰው በህጉ በተቀመጠው አግባብ መሰረትም በእስራትና በገንዘብ መዋጮ እንደሚቀጣ አስቀምጧል። ምንም እንኳን የጥላቻ ንግግር አደገኛነት ሳይታለም የተፈታ ነው ቢባልም መፍትሄው አዲስ ህግ ማውጣት ነው ወይ? ለሚለው ብዙዎች የራሳቸውን ጥርጣሬ ያስቀምጣሉ። አዲስ ህግ ያስፈልግ ይሆን? በተለይም ህግ አውጪውና፣ ህግ አስፈፃሚው ወይም የፍትህ ሰጪ መዋቅሮች ነፃ ባልሆኑበት መንገድ እንዲህ አይነት አዲስ ህግ ማስተዋወቅ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚበልጥ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነትን የሚመለከተውን አንቀፅ 19ን ከመፈረም በተጨማሪ ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብትን አስመልክቶ አንቀፅ 29 በሕገ መንግሥቱ ተካቷል። እንደ አንቀፅ 29 ከሆነ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በፅሁፍ ወይም በህትመት፤ በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ሀሳብ የመሰብሰብ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን የሚያካትት ነው። በዚሁ አንቀፅ ላይ ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ ቅስቀሳዎችን እንዲሁም ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትም አንዱን ከአንዱ በማጋጨት ሌሎችንም ሰዎች አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ከተገኘ በህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል በግልፅ አስቀምጧል። •"ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት ይሄን ህግ ማስከበር እንዲሁም ማሻሻል እየተቻለ ለምን አዲስ ህግ ማውጣት አስፈለገ? የህግ ባለሙያውና ጋዜጠኛ አቶ አብዱ አሊ ሒጂራ ጥያቄ ነው። "አንቀፅ 29 የጥላቻ ንግግር ባይለውም ፕሮፓጋንዳን ሰውን ማንኳሰስን፤ ለዘር ማጥፋት የሚያነሳሳን 'በለው በለኝና ላሳጣው መድረሻ' የሚልን ነገር አልታገስም ይላል። የህጎቹ መሰረት የተደላደለ ቢሆንና ያሉትን ህጎች ህይወት የሚሰጥ ፍርድ ቤት ቢኖረን እንኳን ለራሳችን ለሌላ በተረፍን ነበር" ይላሉ። የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ በበኩላቸው ይህ ህግ የተረቀቀው በዘፈቀደ ሳይሆን አገሪቷ ያለችበትን ውጥንቅጥ ምክንያት መሰረት በማድረግ ጥልቅ ጥናት ከተደረገ በኋላ ነው ይላሉ። የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት ጠንቅ ነው የሚሉት አቶ ዝናቡ "የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ተከትሎ በርካታ የሃገራችን ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው፤ በርካታ ንብረት ወድሟል፤ ህይወትም ጠፍቷል። ይሄ መከላከልም ይጠይቃል" ይላሉ። ከዚህም በመነሳት ከዚህ በፊት የነበሩት ህጎች የወንጀል ጉዳይን የሚያመላክቱ ስላልነበሩ የዚህን ረቂቅ ህግ አስፈላጊነት አበክረው ይናገራሉ። አቶ አብዱ በዚህ አይስማሙም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ህግ በቂ ነው ባይ ናቸው። "ካወቅንበት አሁን ያለው ህግ ይበቃናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር አዲስ መፍትሄ ማምጣት አያስፈልገንም" በማለት። ረቂቁ ሕጉ ነፃነትን ይገድብ ይሆን? ምንም እንኳን በሀገሪቱ የሰፈነውን የጥላቻ ንግግር አስፈሪነት አቶ አብዱ ባይክዱትም ይሄንን የሚከላከል ሕግ ለማውጣት በምታደርጋቸው ጥረቶች ኢትዮጵያ በዘርፉ የተሳካላት ሆና እንደማታውቅ አጥብቀው ይከራከራሉ። እንደ ምሳሌነትም የሚያነሱትም ብዙዎችን ለእስር የዳረገውና፤ ብዙ ጋዜጠኞችንም የመናገርም ሆነ የመፃፍ ነፃነታቸውን ሸብቦ ያሸማቀቀውን የፀረ ሽብር ህጉን ነው። "የፀረ ሽብር ህጉ ቦርቃቃ ነው፤ ለትርጉም የሚመች ነው" የሚሉት አቶ አብዱ የጥላቻ ንግግሩም ለትርጉም ክፍት የሆነና አደገኛም እንደሆነ ይገልጻሉ። "የፈለገው ፖሊስ ወይም አቃቤ ህግ ጋዜጣ አንስቶ ይሄማ የጥላቻ ንግግር ነው ቢል ፍርድ ቤት 'እልል' ብሎ የሚቀበልበት ሁኔታ ነው ያለው" ይላሉ። በተለይም የፀረ ሽብር ሕጉ ፕሬሱን የማጥቂያ መንገድ አድርገው የሚወስዱት ባለሙያዎችም የፀረ ሽብር ሕግ ከመውጣቱ በፊት አሸባሪነትን የሚከላከል ሕግ ቢኖርም አጠቃላይ ሂደቱ ሚዲያን ዝም የማሰኘት ነበር ባይ ናቸው። "ሽብር ማለት እኔን የጠላ ሁሉ አሸባሪ ነው የሚል ትርጉም ተሰጥቶት፤ አንድ ቦታ ላይ ያለ ሰው ድንገት ሊቆጣ ይችል ይሆናል፤ ሌላው ሰው እንዲህ ይተረጉምብኝ ይሆን እንዴ? ብሎ እስከመሸማቀቅ በሚል ነፃነትን የገደበ፤ ፕሬሱንም ያሸማቀቀ ነው" ይላሉ የሕግ ባለሙያው አብዱ። የጥላቻ ንግግር ህግ ወጣም አልወጣም ማንኛውም የንግግር ነፃነት ገደብ እንዳለው የሚናገሩት አቶ አብዱ ከኢትዮጵያ ልምድ በመነሳትም "ገደብ ይጣልበታል ሲባል ገደቡ ገደብ የሌለው ይመስላቸዋል" ይላሉ። ለአቶ አብዱ ዋነኛው አስጊ ነገር የንግግር ነፃነትን የሚገድብ መሆኑ ነው። የንግግር ነፃነት የተፈጠረው ሰውን ለማወደስ ብቻ ሳይሆን ለማስቀየምም ወይም ለማስደንገጥ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አብዱ ኢትዮጵያ በጣሊያን በተወረረችበት ጊዜም ሞሶሎኒ ለዘላለም ይኑር፤ ጣልያን ጥሩ ናት የሚሉ ንግግሮች እንደነበሩ ያወሳሉ። "ሞሶሎኒ ለዘላለም መኖር የለበትም፤ ሞሶሎኒ ፋሽስት ነው ለማለት ነው የንግግር ነፃነት የሚገባው። የንግግር ነፃነት ሰው ሊያስቀይም ይችላል ይህ ግን አደጋ እንዳያስከትል ይሄንን ከህግ ይልቅ በወግ በባህል ነው ልንገነባው የምንችለው" ይላሉ። አቶ ዝናቡ በበኩላቸው የተወሰኑ ግለሰቦችንም ሆነ የተወሰነ ህብረተሰብን ክፍል ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ለመገደብ ታስቦ የተዘጋጀ ምንም መነሻ መሰረት የሌለውና ከፀረ ሽብር ሕጉ ጋር በምንም እንደማይገናኝ ይናገራሉ። "ይህ ረቂቅ ህግ ዜጎች ሰብአዊ ክብራቸው እንዲጠበቅ የዜጎች አብሮ በመኖር፣ በእኩልነት፣ በአንድነት፣ በሰላማቸው ላይ አደጋ እያመጣ ያለውን ነገር እንዲጠብቅ የሚያስችል አቅም ያለው ነውም" ይላሉ። አቶ አብዱ ግን በተለይም የሕግ አውጭ፣ ተርጓሚውና አስፈፃሚዎች ነፃ ባልሆኑበትና "ለይተው የማያውቁትን ሕግ ማስታጠቅ ማለት ትክክል አይደለም፤ ሕግ የሚያወጡ አካሎቻችን ሁሉ አንካሶች ናቸው። ህግ የማውጣትም፤ ህግ የማስፈፀምም ህመምተኞች ነን፤ መጀመሪያ ከእሱ መፅዳት ያስፈልጋል" ብለዋል። የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት የተለያዩ ግብአቶችን በመሰብሰብ ላይ እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ ዝናቡ በሰከነ መልኩ በደንብ ግብአት ተወስዶ እንደሚፀድቅ ይናገራሉ። የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ጠንቅ እንደሆነ በመረዳትም የሌሎች ሃገራትን መነሻ አድርገው ሕጉ እንደተረቀቀ አቶ ዝናቡ ይናገራሉ። ምንም እንኳን የረቂቅ ህጉ መነሻ የተወሰደው ከተለያዩ ሃገራት ስለሆነ ጥሩ ነው የሚል መከራከሪያ ቢያቀርቡም አቶ አብዱ በበኩላቸው "አፋኝ ተብሎ የሚጠራውም የፀረ ሽብር ሕጉም የተወሰደው ከእንግሊዝ ነው" ይላሉ። መፍትሄ ለአቶ አብዱ ከህግ በላይ ዋነኛው መፍትሄ ንግግር ነው ይላሉ። "ጋዜጠኞችና የመብት አራማጆች ነፃነቱ የሚጠይቀውን ኅላፊነትና ጨዋነት ሊኖራቸው ይገባል። ዝም ተብሎ አፍ ያመጣው ነገር ሁሉ አይነገርም። ስንናገር የምንናገረው ነገር ምን ተጨማሪ እሴት አለው መባል አለበት ይላሉ። በከፍተኛ ሁኔታ ማህበረሰብ በተፈራቀቀበት ሁኔታ ዋነኛው ነገር ህዝብን ማቀራረብ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አብዱ መከባበርና መቻቻል ባህል ከሆነ በኋላ ሕግ ማውጣት እንደማያስፈልግም አፅንኦት ሰጥተው ይሞግታሉ። •ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰዎች ምን ይጠብቃሉ? "ጨዋነት የሚፈጠረው ህግ በማውጣት አይደለም። ማክበር፣ መከባበርና መቻቻል ባህል ከሆነ በኋላ ሕግ ማውጣት አያስፈልግም። ወደ ህግ የሚኬደው እኮ ሌሎች ማህበራዊ ተቋማት ሲከሽፉ ነው" ብለዋል። አቶ ዝናቡ በበኩላቸው የጥላቻ ንግግርንም ሆነ ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት በህግ ብቻ የሚገታ ሳይሆን ህዝቡ ያሉትን መልካም የጋራ እሴቶች ማዳበርና ከዚህ ባሻገር ሲሆን የህግ ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባ ይናገራሉ። የኦፕራይድ መስራች፤ የቀድሞ የአሜሪካ አልጀዚራ ኤዲተር መሐመድ አደሞ በበኩሉ ዲሞክራሲ ሂደት እንደመሆኑ መጠን ሁሉ ነገር በአንድ ምሽት እንደማይመጣ ይናገራል። ያለውን የዲሞክራሲ ሂደት ለማስቀጠል የጥላቻ ንግግር ሕግ ሊበጅለት እንደሚገባ የሚያስረዳው አቶ መሐመድ ሁሉን የሚያስማማና ሁሉም የእኔ ነው የሚለውና ተቀባይነት ያለው ህግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን ያሰምርበታል። "ሁሉንም ነገር ለመንግሥት መተው ግን ተገቢ አይደለም። መንግሥት ሁሉን አካታቶ፣ ረቂቁ ላይም የሲቪል ማህበራቱ፣ ጦማርያን፣ ጋዜጠኞችና የሕግ ባለሙያዎች ቢወያዩ፤ መንግሥት እንደመጨቆኛ መሳሪያ እንዳይጠቀምበት መከታተል ያስፈልጋል" ይላል። ይህም ሁኔታ ሕጉን የመንግሥት ብቻ ነው ብሎ ከመግፋት እንደሚታደገውና የሁላችንም ነው የሚል ስሜት እንዲኖረው እንደሚያደርግ ይናገራል።
50430105
https://www.bbc.com/amharic/50430105
ኢትዮጵያ፡ የሞት አደጋ የሚያንዣብብባቸው አውራ ጎዳናዎች
ወ/ሮ ሳሙኔ አሊ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ የድሬ ሂንጪኒ ነዋሪ ናቸው። በደህናው ቀን የሞላቸው የተረፋቸው "እመቤት" ነበሩ። መኪና ስላላቸው ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድሩ ነበር።
በዚህ መካከል ልጃቸው ከባለቤቱ ጋር በጉዞ ላይ እያለ በደረሰበት የመኪና አደጋ ከነባለቤቱ ሕይወቱ አልፈ። ወ/ሮ ሳሙኔ የልጃቸውን ልጆች ወስደው ማሳደግ ቢጀምሩም አቅም አጠራቸው። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ባለቤታቸውም ከአምቦ ለንግድ ወደ አዲስ አበባ እየሄዱ እያለ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ነው። የልጅ ልጅ ታቅፈው ሕይወትን ለመምራት ቢፍጨረጨሩም አልሆነላቸውም። ወ/ሮ ሳሙኔ በአጠቃላይ 15 ቤተሰባቸውን ጎሮሮ ደፍኖ ማደር አቃታቸው። ያኔ "ልጆቹ እናትና አባታቸውን ስላጡና ጥሪት ስለሌለኝ ለባዕድ አሳልፌ ሰጠሁ" ሲሉ የልጅ ልጆቻቸውን በጉዲፈቻ ወደ አውሮፓ መላካቸውን ይናገራሉ። የባህር ዳር ነዋሪ የሆኑት የሰባተኛ ክፍሉ ተማሪ እስክንድርና (ስሙ የተቀየረ) እና አባቱ ማለዳ ከቤታቸው የወጡት አብረው ነው። ዘወትር አባትና ልጅ ወደ ጉዳያቸው የሚሄዱት ብስክሌታቸውን በማሽከርከር ጎን ለጎን እየተጨዋወቱ ነው። ዕረቡ ዕለትም የሆነው እንደዚያው ነው፤ ቤት ያፈራውን ቀማምሰው፤ ልጅ ወደ ትምህርት ቤቱ፤ አባቱም ከእርሱ ጋር እየተጨዋወቱ ወደ ሥራ ገበታቸው ይሄዳሉ። አዝዋ ሆቴል አካባቢ ሲደርሱ ግን እርሳቸውን አንድ ግለሰብ ያስቆማቸዋል። ልጁ ትምህርት ቤት እየረፈደበት መሆኑን ተናግሮ ቀድሟቸው ይሄዳል። በልጅ እግሩ ብስክሌቱን እየጋለበ፣ ወደ ትምህርት ቤቱ ሲያቀና የደረሰበት የትራፊክ መብራት እንዲያልፍ አረንጓዴ አሳየው። • "ዓላማችን ችግሮችን ፈተን ገንዘብ ማግኘት ነው " የጠብታ አምቡላንስ ባለቤት • ስልክዎ ጥሩ አሽከርካሪ ሊያደርግዎ እንደሚችል ያስባሉ? እርሱ በመልዕክቱ መሰረት ብስክሌቱን ወደ ፊት ገፋ። በሌላ መስመር ግን ቀዩን መብራት ጥሶ የመጣ ሕዝብ ማመላለሻ ገጨው። በወቅቱ ሾፌሩ መኪናውን አቁሞ አምልጧል ይላል እስክንድር። አሁን በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ሕክምና የሚደረግለት ተማሪ እስክንድር ጭኑና ጭንቅላቱ ላይ ጉዳት አጋጥሞታል። እስክንድር ታሞ በተኛበት ያገኘናቸው ዶ/ር አዲሱ መለሰ፣ በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል የኬዝ ማናጀር ነው። ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ወደ 300 ሰው በትራፊክ አደጋ ምክንያት ተጎድተው ወደ ድንገተኛ ክፍል መምጣታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። እነዚህ 300 ሰዎች መንገድ ላይ የሞቱትን፣ ከነጉዳታቸው ወደ ቤታቸው የሄዱትንና ወደ ሌላ ጤና ተቋም የተወሰዱትን ሳይጨምር መሆኑን ይናገራሉ። ይህ የሚያሳየው ይላሉ ዶ/ር አዲሱ፣ በመኪና አደጋ የሚጎዱ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንና አደጋው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሄዱን ነው። የድንገተኛ ክፍሉ በሰው ኃይልና ቁሳቁስ አቅርቦት የተሟላ ባለመሆኑ በትራፊክ አደጋ ወደ ክፍላቸው የሚመጡ ሕሙማን የሚደርስባቸው ጉዳት በሚገባው ለማከምና በተገቢው ሰዓት የሕክምና ርዳታ ለመስጠት ፈታኝ እንደሆነባቸው ጨምረው ያስረዳሉ። እነዚህ የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች አደጋው ከደረሰበት ስፍራ ሆስፒታል እስኪደርሱ ድረስ የሚደረግላቸው ሕክምና ርዳታና ድጋፍ አለመኖሩን በማንሳት በዚህም ደረጃ በሀገር ደረጃ ያለው ተሞክሮ አነስተኛ በመሆኑ የአደጋው ተጎጂዎች ጉዳት እንደሚባባስ ይጠቅሳሉ። አክለውም በመኪና አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ሆስፒታል በአንቡላንስ ርዳታ እያገኙ መምጣት ቢኖርባቸውም ይህ ሲሆን እንደማይመለከቱ የሚገልፁት ዶ/ር አዲሱ፣ ተጎጂዎቹ በርካታ ደም ሊፈሳቸው፣ ምላሳቸው ታጥፎ መተንፈሻ አካላቸውን ሊዘጋው እንደሚችል፣ በመጥቀስም በቀላሉ ለመርዳት የሚቻሉ ጉዳቶች ወደ ሞት ሊያደርሱ ይችላሉ ሲሉ ያለውን ችግር ይገልጻሉ። በመኪና አደጋ የተጎዱ ግለሰቦች የሕክምና ርዳታ ማግኘት የሚጀምሩት ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ መሆኑን በማስታወስ ይህ በሕይወት የመትረፋቸውን ዕድል እንደሚያጠበው ያስረዳሉ። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ደህንነት መምሪያ ተወካይ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ሙሉጌታ በዜ ለቢቢሲ እንዳሉት ከአመት ዓመት የትራፊክ አደጋው እየጨመረ የሄደ ሲሆን፣ በክልሉ ካለው የአደጋ ስጋት የተነሳ ባልና ሚስት ወደ አንድ ጉዳይ በተመሳሳይ ተሽከርካሪ ለመሄድ በመፍራት 'አንዳችን ብንተርፍ በሚል' የተለያየ መኪና እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል። በአማራ ክልል በ2012 ሩብ አመት ብቻ 618 አደጋዎች መድረሳቸውንኮማንደር ሙሉጌታ አስረድተዋል። በዚህ አደጋ 183 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል። 105 ከባድ፣ 114 ቀላል አካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን በማስታወስም እዚህ ውስት ቁጥራቸው ያልተካተተ ሊኖርአእንደሚችልም ገልጸዋል አቶ ይበልጣል ታደሰ በአማራ ክልል የመንገድ ትራንስፖርት የኮሙኑኬሽን ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር ናቸው። በአማራ ክልል ከመስከረም ወዲህ ያለው የትራፊክ አደጋ እየጨመረ መሆኑን ያስረዳሉ ይላሉ። ከፍተኛ የሆነ የሰው ሞት ያስከተሉ አደጋዎች ከመስከረም ወዲህ መመዝገባቸውን ገልፀው በ2011 አጠቃላይ የአደጋው ብዛት 2591 መሆኑን ያስታውሳሉ። ከእነዚህ መካከል 1109 ሰዎች ሞተዋል የሚሉት አቶ ይበልጣል የደረሰው የጉዳት መጠን በንብረት ሲሰላ ደግሞ ከ97 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙንም ያስረዳሉ። በኦሮሚያ ትራንስፖርት ቢሮ የትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አዲሱ ተመስገን አንደሚሉት በ2012 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ 1095 የትራፊክ አደጋ መከሰቱን የደረሰ ሲሆን፣ የ433 ሰዎችም ሕይወት አልፏል። በዚህ ዓመት በደረሰው የትራፊክ አደጋ የወደመው ንብረትን በገንዘብ አስልተው ሲናገሩም 63.7 ሚሊየን ይገመታል ይላሉ። የትግራይ ክልል ትራፊክ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ብርሃነ መስቀል በበኩላቸው በክልላቸው በ2011 ብቻ 1512 አደጋዎች ማጋጠማቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ አደጋ 386 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ 79 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ብለዋል። ኮማንደር ሙሉጌታ በዜ እንደሚሉት ከሆነ በክልላቸው አጠቃላይ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ አቅደው እየሰሩ መሆኑን ተናግረው፣ የትራፊክ አደጋ ሲሰላ ከትራፊክ ፍሰቱ ጋር በንጽጽር እየተሰላ መሆን እንዳለበት በመጥቀስ የትራፊክ ማናጅመንቱ ካለው የትራፊክ ጋር አብሮ እንደማይሄድ ጠቅሰዋል። አቶ አዲሱ ተመስገን የኦሮሚያ ክልል ብዙ የትራፊክ ፍሰት ያለበት እንደመሆኑ መጠን የትራፊኩ አደጋ በዛው ልክ እንደሚበዛ ያብራራሉ። በክልሉ ለሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች ብዙ ጊዜ ከአሽከርካሪዎች ስነምግባር ጉድለት ጋር የተያያዘ መሆኑን ቢሯቸው በጥናት ማረጋገጡን የሚናገሩት አቶ አዲሱ፣ ሌሎች ምክንያት ናቸው ያሉትን ሲጠቅሱም ለቁጥጥር የሚሰማሩት ፖሊሶች በትክክል አለመቆጣጠራቸውን፣ በፍጥነት ማሽከርከር፣ ከመጠን በላይ መጫን እና ሱስ አስያዥ ነገሮችን እየተጠቀሙ ማሽከርከር እና ተገቢውን እርፍት ሳይወስዱ ማሽከርከር ናቸው ይላሉ። ኮማንደር ሙሉጌታ በበኩላቸው በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር የሚጓዙ መኪኖች እየገቡ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት የቁጥጥር ስርዓቱ በቴክኖሎጂ አለመደገፉን በማንሳትም የያለውን ክፍተት ያሳያሉ። በእግሩ እየሄደ ህግ የሚያስከብር የትራፊክ ፖሊሱ አባል መኖሩ፣ በየትልልቅ ከተሞች ላይ የትራፊክ መብራት የተሟላ አለመኖር፣ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ካሜራ፣ ፍጥነት መቆጣጠሪያ ራዳር አለመኖራቸውን በማንሳትም የትራፊክ ማናጅመንቱ ጉዳይ በሚጠበቀው ደረጃ አይደለም ሲሉ የችግሩን ስፋት ያሳያሉ። ትልልቅ መንገዶች ሲገነቡ የእግረኛ መንገድ በሚፈለገው ደረጃ አለመገንባት፣ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ የመንገድ ስርዓት አለመኖር፣ የብስክሌት ማሽከርከሪያ መስመር አለመከለልንም ለትራፊክ አደጋ መበራከት ምከንያት ከሆኑት መካከል ይጠቅሳሉ። ወደ ሀገሪቱ የሚገባው የተሽከርካሪ ብዛት ካለን የሕዝብ ቁጥር አንጻር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑን በየሚናገሩት ኮማንደር ሙሉጌታ፣ የሚደርሰው አደጋ ግን ከፍተኛ መሆኑን ይስማሙበታል። ለዚህ ሁሉ አደጋ የትራፊክ ማኔጅመንቱ ያለውን የትራፊክ ስርዓት ለመምራት በሚችል መልኩ የተዘረጋ አለመሆኑን ይገልጻሉ። ዋና ዋና የትራፊክ አደጋዎች አሽከርካሪም እግረኛም የሚፈጽሙት ስህተት መሆኑን አንስተው፣ የማሽከርከር ስራ ያለውን ከባድ ኃላፊነት ያለመገንዘብ ለአደጋ ምክንያት መሆኑን ያስታውሳሉ። የመንገድ ችግር፣ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር ከሚደርሱ የመኪና አደጋዎች ጥቂቱን እንደሚይዙ በመጥቀስ አብዩን ድርሻ የሚይዘው የእግረኛና የአሽከርካሪ ስህተት መሆኑን አጽንኦት ይሰጡታል።
news-52106876
https://www.bbc.com/amharic/news-52106876
ኮሮና ቫይረስ፡ "ከቫይረሱ በላይ የሚያስጨንቀን ረሃብ ነው?" የናይጄሪያዋ ጉሊት ቸርቻሪ
የኮሮና ቫይረስ መዛመትን በመፍራት ብዙ አገራት የከተሞቻቸውን እንቅስቃሴ የመገደብ እርምጃን እየወሰዱ ሲሆን ናይጄሪያም ዋና ዋና ከተሞቿ ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉ ወስናለች።
ሃያ አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ ናይጄሪያውያን እንቅስቃሴያቸው ተገድቧል። በተለይም በተጨናነቁ መንደሮች ለሚኖሩት ሁኔታው ዱብ እዳ ነው የሆነባቸው፤ የማይወጡት አዘቅት፤ እንደ ሰማይ ከባድ ሆኖባቸዋል። የቢቢሲ ጋዜጠኛ ንዱካ ኦሪጅንሞ ከናይጄሪያዋ ንግድ ማዕከል ሌጎስ የተወሰኑትን አናግሯል። "ይሄን የምትሉትን ለእጅ መታጠቢያ የሆነውን ውሃ ከየት ነው የምናገኘው" በማለት የ36 ዓመቷ ዴቢ ኦጉንሶላ ትጠይቃለች። •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ •በኮሮናቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነታቸው የጨመረ 6 ምርቶች የንግድ ማዕከል የሆነችውን ሌጎስ፣ አጎራባቿን ኦጉን እንዲሁም ዋና መዲናዋን አቡጃን ለሁለት ሳምንታት ያህል የመዝጋት ውሳኔ የተላለፈው በትናንትናው ዕለት ሲሆን፤ የአገሪቱም ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የቫይረሱን መዛመት ለመከላከል ብቸኛው አማራጭ ይሄ ነው ካሉ በኋላ "ይህ የሞት የሽረት ጉዳይ ነው" ብለዋል። ምንም እንኳን ፕሬዚዳንቱ ይህንን ይበሉ እንጂ እንደ ዴቢ አጉንሶላ ላሉ ሰዎች ቤት ውስጥ መቀመጥ ፈታኝ ነው። እሷም ሆነ ቤተሰቦቿ በአንድ ቤት ውስጥ ሆነው ተጨናንቀው ነው የሚኖሩት፤ በተለምዶም ቤቶቻቸው ካላቸው መጠጋጋት የተነሳ 'ፊት ለፊት' የሚል ቅፅል መጠሪያ ተሰጥቷቸዋል። የቢቢሲ ጋዜጠኛም በቦታው በተገችበት ወቅት የመብራት አገልግሎት ያልነበረ ሲሆን በቤቱ ውስጥ ጭላንጭል ብርሃን ይገባል። በአካባቢው የሚኖሩ 20 ቤተሰቦችም የሚጋሩት ሁለት መፀዳጃ ቤትና መታጠቢያ ቤት አላቸው። "የምንፈራው ረሃብን ነው፤ ቫይረሱን አይደለም" ዴቢ በምትኖርበት አላፔሬ የውሃ መስመርም ሆነ ውሃ ባለመኖሩ በአቅራቢያዋ ካለ አምሳ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የተሰበረ የህዝብ ቧምቧ ሄዳ ትቀዳለች። "ከኔ በላይ የምጨነቀው ለልጆቼ ነው" ትላለች። ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ እየጣለ ቢሆንም አራቱም ልጆቿ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። "ወጥቼ አትክልትና ፍራፍሬ መንገድ ላይ ካልሸጥኩ ልጆቼ ምን ይበላሉ? እንዴትስ ይተርፋሉ" ትላለች ጉሊት በመቸርቸር የምትተዳደረው ዴቢ። እጇን የምትታጠብ ልጅ ባለቤቷ በደቡብ ናይጄሪያ በምትገኘው ዋሪ የነዳጅ ማውጫ ውስጥ ተቀጥሮ ነው የሚሰራው፤ ቤቱም የሚመጣው በየወሩ ነው። ሆኖም በአሁኑ ወር ላታየው ትችላለች፤ ናይጄሪያ በተለያዩ አካባቢ የሚገኙትን ሪቨርስ፣ ዴልታ፣ ካኖ፣ ባዬልሳ ድንበር ከተሞች መዝጋቷ፤ ከአንድ ግዛት ወደ አንድ ግዛት የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንዲገደብ አድርጎታል። የከተሞች መዘጋት ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ባለቤቷን የምታይበትን ጊዜ ሩቅ ያደርገዋል። "የሚያስጨንቀኝ ረሃብ ነው፤ ቫይረሱ አይደለም። ቫይረሱ ህፃናትን እንደማይገድል ሰምቻለሁ" ትላለች ኦጉንሶላ ። ምንም እንኳን ቫይረሱ ክፉኛ የሚያጠቃውም ሆነ የሚገድለው በዕድሜ ከፍ ያሉትን እንዲሁም ተደራራቢ የጤና እክል ያላቸውን ቢሆንም ዴቢ እንደምትለው ሳይሆን ህፃናትም በቫይረሱ እየሞቱ ነው፤ ቫይረሱንም ከሰው ወደ ሰው ያስተላልፋሉ። •በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው ቤሳ ቤስቲን በሌለበት ሁኔታ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የዴቢ ብቻ አይደለም፤ የጎረቤቶቿ እንዲሁም ድንበር፣ ወንዝ፣ ባህልን ተሻግሮ በድህነት የሚኖሩባት የዓለም ሁኔታ ነው። የዴቢ ጎረቤት ተለቅ ያለ በረንዳ ያላቸው ሲሆን ሁለት በእድሜ ገፋ ያሉ ሴቶች ቁጭ ብለው ያወራሉ። በእድሜ ተለቅ ያሉ ቤተሰቦች እንደ ልጆች ጠባቂ ሆነው ከልጆቻቸው እንዲሁም ከዘመዶች ጋር መኖር የከተሜው እውነታ ነው። በዚህም ሁኔታ ቫይረሱ ቢዛመት በእድሜ ለገፉት ከፍተኛ ስጋት ነው። "አሁንም ቢሆን ሰብሰብ ብለው ቤት ይቀመጣሉ። አንድ ሰው በቫይረሱ ቢያዝ በአካባቢው ያሉ ሰዎች የመያዛቸው እንዲሁም የመዛመቱ ሁኔታ በጣም ከፍተኛ ነው" ይላሉ የጤና ባለሙያው ዶ/ር ኦየዋሌ ኦዱባንጆ። •በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው በጣልያንም የአኗኗር ሁኔታቸው ለቫይረሱ መዛመት ምክንያት ነው። አያቶች፣ አጎት፣ አክስት፣ አባት፣ እናት፣ ልጆች፤ የተለያየ ትውልድ ተሰባስበው ይኖሩባት የነበረችው ጣልያን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ህይወት አጥታለች። ናይጄሪያም የሌሎች አገሮችን ፈር በመከተል እንቅስቃሴዎች የተገደቡ ሲሆን፤ የግሉም ይሁን የመንግሥት ሰራተኞች ከቤት እንዲሰሩ ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል። መብራት በሚቆራረጥበት እንዲሁም ደካማ ኢንተርኔት ባለበት ሁኔታ ከቤት ሆኖ ሥራ ይሰራል ማለት አስቸጋሪ ነው። የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ከተሞች መዘጋታቸውን ባወጁ ማግስት በትልልቅ መደብሮች ላይ ምግብ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቁሶችን ለመሸመት ተሰልፈውም ታይተዋል። ነገር ግን ይሄ የብዙ ናይጄሪውያን እውነታ አይደለም። ከእጅ ወደ አፍ ለሆነው ናይጄሪያዊ፣ ቤሳ ቤስቲን ለሌለው ናይጄሪያዊ የነገን ምግብ ማከማቸት አይደለም ዛሬን በልቶ ማደር ቅንጦት ነው። •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች ብዙ ናይጄሪያውን የዚህ ወር ደመወዝ እየጠበቁ ከመሆናቸውም አንፃር የኑሮ ሁኔታቸውን አጣብቂኝ ውስጥ ከትቶታል። ይህንን ሸክም ለማቃለል በሚል ፕሬዚዳነት ሙሃማዱ ቡሃሪ የደሃ ደሃ ተብለው ለተለዩ ሰራተኞች 420 ብር ቅድሚያ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ቢወስኑም ኢ-መደበኛ በሆነ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሚሊዮኖች ናይጄሪያውያን ከአርዳታው ውጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል በማለትም እየተተቹ ነው። "የሚሸምተውም ሆነ የሚያከማቸው ገንዘብ ያለው ነው። ገንዘብ ከሌለ ምን ማድረግ ይቻላል?" ይላል ከአንደኛው ትልቅ መደብር ውጭ የቆመ የታክሲ አሽከርካሪ። ሌላኛው ፍራቻ ደግሞ በከተሞች ያሉ ችግሮች ከተባባሱና ከፍተኛ የምግብ እጥረት የሚያጋጥም ከሆነ ብዙዎች ምግብ ለማግኘት ገጠር ወደሚገኙ ዘመዶቻቸው ለመሰደድ ይገደዳሉ። ይህም ሁኔታ በመጀመሪያ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የእድሜ ባለፀጎች ለቫይረሱ ያጋልጣል፤ በተለይም የጤና አገልግሎት ደካማ በሆነባቸው በነዚህ ስፍራዎች መሆኑ ደግሞ ችግሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ያደርገዋል። በኮሮናቫይረስ የተያዘው የመጀመሪያው ጣልያናዊ ሲገኝ የናይጄሪያ ባለስልጣናት ግለሰቡን ለይቶ ማቆያ ውስጥ በማስገባት፤ ከእሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን እንዲሁም ንክኪ ያላቸውን ክትትል በማድረግ ከዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ምስጋና ተችሯቸው ነበር። ነገር ግን አሁን ቫይረሱ እንዳይዛመት ያደረገችው ጥረት እንዲሁም ወረርሸኙን ለመቆጣጠር ያላት የጤና ሥርዓት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። "ይህንን ጊዜ እናልፈዋለን" አገሪቷ ያሏት መመርመሪያዎች ጥቂት ቢሆኑም ምልክቱ ያልታየባቸው የመንግሥት ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎች መመርመራቸው የፍትሃዊነት ጥያቄን አጭሯል። ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ስልጣን ሲረከቡ ለህክምና የሚደረጉ ማንኛውም የውጭ ጉዞዎችን እንደሚያስቀሩ ቃል ቢገቡም እሳቸውም ሆነ ሌሎች ባለስልጣናት ለህክምና የሚያደርጉትን የውጭ ጉዞ አላቆሙም ነበር። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ግን ይህ የሚሆን አይደለም። ሌጎስም ሆነ ሌሎች ከተሞች ስብሰባዎችንም ሆነ ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ቢያግዱም፤ ፓስተሮችን ጨምሮ ብዙዎች አካላዊ ርቀት መጠበቅ የሚለውን እየጣሱት ይገኛሉ። አላፔሬ በሚገኘውና በተጨናነቀው የአውቶብስ መናኸሪያ ጉሊት ቸርቻሪዎች፣ እንዲሁም ጌጣጌጥና ልብሶችን መንገድ ላይ የሚሸጡ ግለሰቦች መሸጫ ቦታ ይፈልጋሉ። ከቫይረሱ በላይ የእለት ጉርሳቸው ያስጨንቃቸዋል። "ሁሉም ሞት ሞት ነው" ትላለች በሁለት አውቶብሶች እየተመላለሰች በትሪዋ ላይ አሳ እየሸጠች የነበረች ሴት። "ቤቴ ብቀመጥ በረሃብ እሞታለሁ፤ እዚህ መጥቼ የዕለት ጉርሴን ለማግኘት ብሞክር በቫይረሱ እንደምሞት እየነገራችሁኝ ነው" "በህይወታችን ብዙ ፈተና አይተናል፤ ያላየነው ነገር የለም። አሁንም አለን፤ ነገን እናያለን፤ ይህንንም ጊዜ እናልፈዋለን"ብላለች።
news-51147381
https://www.bbc.com/amharic/news-51147381
የሊቢያ የእርስ በእርስ ጦርነት፡ የሌሎች ሃገራት ጣልቃ ገብነት
የሊቢያ ጉዳይ የዓለም ትኩረትን እንደሳበ ነው። በብዙ ፍላጎት የተወጠሩ የሊቢያ ኃይሎች እና ሌሎች ሃገራት ሊቢያን ሰላም ነስተዋታል።
በአሁኑ ሰዓት በሊቢያ ሁለት ዋነኛ ተቀናቃኝ ኃይሎች ይገኛሉ። በተባበሩት መንግሥታት እውቅና የተሰጠው በጠቅላይ ሚንስትር ፋዬዝ አል-ሴራጅ የሚመራው መንግሥት እና በጀነራል ካሊፍ ሃፍታር የሚመራው አማጺ ኃይል ናቸው። • "በሜዴትራንያን ባህር ልሰምጥ ነበር" • ጀነራሉ ወታደሮቻቸው ትሪፖሊን እንዲቆጣጠሩ አዘዙ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ እውቅና ባለው መንግሥት እና በአማጺያኑ መካከል በነበረ ግጭት ቢያንስ 2 ሺህ ሊቢያውያን ሕይወታቸውን አጥተዋል። 146ሺህ የሚሆኑት የመኖሪያ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። አሁን ላይ ሁለቱ ኃይሎች በቱርክ እና ሩሲያ ጫና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይሁን እንጂ የተኩስ አቁሙን ስምምነት ለመፈረም ሲያመነቱ የቆዩት ጀነራል ካሊፍ ሃፍታር ስምምነቱን ሊጥሱት ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ሊቢያውያን በሙዓመር ጋዳፊ አምባገነናዊ ሥርዓት ሥር ሳሉ፤ ይክፋም ይልማም የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ነበሩ። ነጻ ትምህርት እና ነጻ የህክምና አገልግሎት አይለያቸውም ነበር። ዛሬ ላይ አምባገነኑ ሙዓመር ጋዳፊ ከሥልጣን ከተባረሩ 9 ዓመታት በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሊቢያውያን ሰላም ናፍቋቸዋል። የዳቦ ዋጋ ተወዶባቸዋል። የጀነራል ካሊፍ ሃፍታር ጦር አባል በቤንጋዚ ከተማ ለመሆኑ ሊቢያውያን እዚህ አጣብቂኝና ውስብስ ነገር ውስጥ እንዴት ገቡ? ልክ እንደ ሶሪያ ሁሉ፤ የሊቢያውያን ሰቆቃ የጀመረው የአርብ አብዮቱን ተከትሎ ነው። እአአ 2011 ላይ በምዕራባውያኑ ኔቶ (የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት) ድጋፍ የረዥም ጊዜ የሊቢያ መሪ የነበሩት ሙዓመር ጋዳፊ ከሥልጣን ተባረሩ። አምባገነኑ ሙዓመር ጋዳፊ በሊቢያውያን ለውጥ ናፋቂ ወጣቶች መንገድ ላይ ተጎተቱ፤ አይደፈሬው ተዋረዱ፤ ከዚያም በጥይት ተመትተው ተገደሉ። በሊቢያ አዲስ ለውጥ መጣ ተባለ። ሊቢያውያን ግን አምባገነናዊ ሥርዓቱን በሕዝባዊ አብዮት ሲገረስሱት፤ ነጻነትን እና የተሻለ ሥርዓትን አልመው ነበር። የሙዓመር ጋዳፊ ሞት ግን ሊቢያውያን የተመኙትን ለውጥ ሳይሆን፤ መግቢያ መውጫ ያሳጣቸውን የእርስ በእርስ ጦርነት ነው ያስከተለው። የተባበሩት መንግሥታት በጠቅላይ ሚንስትር ሰርጀ የሚመራ መንግሥት መቀመጫውን በትሪፖሊ እንዲያደርግ አመቻቸ። ሁሉም በዚህ አልተስማማም፤ ጀነራል ሃፍታ ሥልጣን ፈለጉ። • አቶ ለማ ለምን ዝምታን መረጡ? • ከኢትዮጵያ ለአረብ አገራት በሕገ ወጥ የሚሸጡት አቦ ሸማኔዎች ጀነራሉ በምስራቅ ሊቢያ በሚገኙ ቶበሩክ እና ቤንጋዚ ከተሞች መቀመጫቸውን አድርገው የራሳቸውን ጦር አደራጁ። ተጽእኖ ፈጣሪው ጀነራል፤ የሊቢያ ብሔራዊ ጦር የተሰኘ ኃይል አቋቁመው ካለ እኔ ለሊቢያ የሚፈይድ የለም፤ እኔ እንጂ ማንም "እስላማዊ አሸባሪዎችን" አያስወግድም አሉ። ከዚያም በተመድ እውቅና ያለውን መንግሥት መውጋት ተያያዙት። ትሪፖሊን ለመቆጣጠር የጦር እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ 9 ወራት ተቆጠሩ። ከጀነራሉ ጦር በተጨማሪ በሊቢያ ''ነጻ'' አውጪ ነን የሚሉ ኃይሎች በርካቶች ናቸው። ከየመሸጉበት እየወጡ፤ አንዱ አንዱን ይወጋል። በሊቢያ ''እስላማዊ መንግሥት'' መመሠረት አለበት ብለው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችም ብዙ ናቸው። ተጽዕኖ ፈጣሪው ጀነራል ካሊፍ ሃፍታር የእጅ አዙር ጦርነት በሊቢያ የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች የራሳቸውን ብቻ ሳይሆን የሌሎች የውጪ ሃገራት ፍላጎትን ለማሳካት ነፍጥ አንግበዋል። በቀጠናው የሚገኙ ሃገራት በተለያየ አሰላለፍ የእጅ አዙር ጦርነት ወይም የውክልና ጦርነት ያካሂዳሉ። ጀነራል ሃፍታር "እስላማዊ አሸባሪዎችን" እዋጋለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እና ጆርዳን ጽንፈኞች ከቀጠናው መጽዳት አለባቸው በማለት አጋርነታቸውን ከጀነራሉ ጋር አድርገዋል። ጆርዳን እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ከድጋፍም አልፈው የጀነራሉን ጦር አስታጥቀዋል፤ በተመድ እውቅና ባለው መንግሥት ላይ ጥቃት ሲሰነዘር የአየር ላይ ድጋፍ ያደርጋሉ። በግጭቱ ወቅት የተገደሉት ንጹሃን ዜጎች ለሞት ያበቃቸው የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ጦር መሳሪያ ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት ይከሳል። ከእነዚህ ሃገራት በተጨማሪ፤ ጎረቤት ሃገር ግብጽም የጀነራሉ አጋር ነች። አል ሲሲ ለጀነራል ሃፍታር ጦር የሎጂስቲክ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ። ከአካባቢው ሃገራት በተጨማሪም ሞስኮ በሊቢያ እጇን እያስገባች እንደሆነ እየተነገረ ነው። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት በሩሲያ መንግሥት ተከፋይ የሆኑ የሌሎች ሃገራት ወታደሮች ከጀነራሉ ጎን ሆነው እየተዋጉ ይገኛሉ። የክሬምሊን መንግሥት ግን ቀጥተኛ ተሳትፎ የለኝም ይላል። የቱርክ የሕዝብ እንደራሴዎች፤ ቱርክ ጦሯን ወደ ሊቢያ እንድትልክ በአብላጫ ድምጽ ወስነዋል። በሌላኛው በኩል ደግሞ ቱርክ የተመድ እውቅና የተሰጠውን መንግሥት ትደግፋለች። ከጥቂት ቀናት በፊትም ቱርክ ወደ ሊቢያ የትሪፖሊን መንግሥት ለመደገፍ ጦሯን ልካለች። የቱርክ መንግሥት ጦሩን ወደ ሊቢያ የላከው "የሥልጠና እና የምክር አገልግሎት" ለመስጠት ታስቦ ነው ብሏል። በሊቢያ መንግሥት ውስጥ የሚገኝ የቢቢሲ ውስጥ አዋቂ ግን በቱርክ በኩል ወደ ሊቢያ ከመጡ ወታደሮች መካከል በቱርክ የሚደገፉ የሶሪያ አማጺያን ይገኙበታል ብሏል። በመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ ውስጥ ብዙውን ግዜ ተገልላ የምትገኘው ኳታር፤ በሊቢያ ጉዳይ ከተባበሩት መንግሥታት እና ከቱርክ ጎን ተሰልፋለች። የምዕራባውያን ሃገራት ፍላጎቶች ሌላ የሊቢያ ጉዳይ ያገባኛል የምትለው ፈረንሳይ፤ የቱርክን አሰላለፍ ተቀላቅላለች። ፈረንሳይ የተባበሩት መንግሥታት እውቅና ያለውን መንግሥት እደግፋለሁ ትበል እንጂ ልቧ ያለው ከጀነራሉ ጦር ጋር ነው ተብሎ ይታመናል። የቀድሞ የሊቢያ ቅኝ ገዢ የሆነችው ጣሊያን፤ ፓሪስ ለጀነራሉ ጦር የምታደርገውን ድጋፍ አጥብቃ ካወገዘች በኋላ፤ ሮም ሁልጊዜም ተመድ እውቅና ለሰጠው መንግሥት ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። • ጃፓናዊው ቢሊዬነር ወደ ሕዋ አብራው የምትጓዝ 'ውሃ አጣጭ' እየፈለገ ነው • ሶሪያዊያን በበርሊን በምስጢር የሰላም ጉባዔ አካሄዱ በርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች በሊቢያ በኩል አድርገው ሜደትራኒያን ካቋረጡ በኋላ የመጀመሪያው መዳረሻቸው ጣሊያን ነች። በዚህም ጣሊያን የስደተኞችን ፍሰት ለማስቆም በሊቢያ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አለብኝ ባይ ነች። ኃያሏ ሃገር አሜሪካም በሊቢያ በቀጥታ እጇን አስገብታለች። በደቡብ ምዕራብ ሊቢያ የሚገኙ የአይኤስ ሚሊሻዎች ላይ እርምጃ ትወስዳለች። ይህ ሁሉ ሃገር በሊቢያ ጉዳይ እጁን የሚያስገባው ለምን ይሆን? በሊቢያ የእርስ በእርስ ጦርነት እጃቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያስገቡት ሃገራት ቁጥር ከፍተኛ ነው። ለዚህም የመጀመሪያው ምክንያት ሰሜን አፍሪካዊቷ ሊቢያ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት ሃገር ነች። በተፈጥሯዊ ጋዝ ገበያ ላይም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሃገር መሆን ትችላለች። ሌላኛው ምክንያት መዳረሻቸውን አውሮፓ ለማድረግ ከአፍሪካ የሚሰደዱ ወጣቶች መነሻቸውን የሚያደርጉት ከሊቢያ ነው። ሊቢያ ከ2ሺህ ኪ.ሜትር በላይ ከሜድትራኒያን ባህር ጋር እንደምትዋሰን እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። ከኢራቅ እና ሶሪያ ድል የተመታው ጽንፈኛው አይኤስ በሊቢያ በረሃዎች ላይ እግሩን እየከተተ መሆኑ ተነግሯል። ይህ ለሊቢያ እና ጎረቤት አገሮች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ደህንነት ስጋት ነው።
news-52370898
https://www.bbc.com/amharic/news-52370898
ኮሮናቫይረስ፡ የነዳጅ ዋጋ መውደቅ ምርቱን በነጻ እንድናገኝ ያስችለናል?
አሜሪካ የምታመርተው የነዳጅ ዘይት በታሪክ ባልታየ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋጋው አሽቆልቁሎ ዜሮ ገብቷል። የአሜሪካ የነዳጅ ምርት ማነጻጸሪያ ዋነኛው የዋጋ መተመኛ የምዕራብ ቴክሳስ ተመን እንደሚያመለክተው የአንድ በርሜል ነዳጅ ዘይት ዋጋ ከዜሮ በታች ቁልቁል ወርዷል እየተባለ በመዘገብ ላይ ነው።
ይህም ነዳጅን እየገዙ በሚጠቀሙ አገራት ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ ደስታን የፈጠረ ይመስላል። አንዳንዶች እንዲያውም ኢትዮጵያን የመሰሉ ነዳጅ የማያመርቱ አገራት ምርቱን በነጻ ካልሆነም እየተከፈላቸው እንዲወስዱ ሊደረግ ይችላል የሚል ግምት አሳድረዋል። ይህ ግን አውነት አይደለም። ታዲያ የአንድ ምርት በተለይም የነዳጅ ዘይት ዋጋ ከዜሮ በታች ሲወርድ ምን ማለት ነው? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። በአሁኑ ጊዜ የዓለማችን የነዳጅ ዘይት ፍጆታ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነሱ አምራቾች እስከ ግንቦት ድረስ የነዳጅ ማከማቻ ቦታ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል የሚል ስጋት ስላደረባቸው በወደቀ ዋጋ ነዳጁን እንዲወስዱላቸው እየለመኑ ነው ማለት ይቻላል። ይህም ማለት ነዳጅ አምራቾች ምርታቸውን ለመሸጥ ካለመቻላቸው በተጨማሪ ያመረቱትን ለማጠራቀም የሚሆን ስፍራ ለመከራየት በመገደዳቸው ከገቢ ይልቅ ወጪው በዝቶባቸዋል። ይህም ሆኖ የነዳጅ ዋጋ በዓለም ላይ ዝቅ እያለ ቢሆንም ፍጆታው ከመጨመር ይልቅ እየቀነሰ ነው። ስለዚህ ምርቱ ፈላጊ አጥቷል ማለት ነው። በአፍሪካ አገራትም ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክስተትን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ቢቀንስም ፍጆታው ሊያድግ ይቀርና ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ የሚውለውን ያህል የሚገዛ አልተገኘም። በአጠቃላይ በበርካታ የአፍሪካ አገራት ውስጥ በበሽታው ምክንያት የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብን ተከትሎ የነዳጅ ፍጆታው ስለቀነሰ ፍላጎቱ እያሽቆለቆለ መሆኑ ተነግሯል። ለምሳሌም የአውሮፕላን ትራንስፖርት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፣ ፋብሪካዎች የምርታቸውን መጠን ቀንሰዋል አሊያም አቁመዋል፤ እንዲሁም በከተማና በአገር አቋራጭ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚጠመዱት ተሽከርካሪዎች ከእንቅስቃሴ ተቆጥበዋል። በዚህም የነዳጅ ፍላጎት አሽቆልቁሏል። ስለዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከየትኛውም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አንጻር የነዳጅ ፍጆታ ይጨምራል የሚል ግምት ለአሁኑ በቅርበት አይታይም። በአሁኑ ጊዜ ምንም እንኳን የነዳጅ ዋጋ ቢወርድም የማምረት ሂደቱ ግን ቀጥሏል። ለዚህም ምክንያቱ የነዳጅ ማውጫ ጉድጓዶችን ከመዝጋት ይልቅ ነዳጁን እያመረቱ ለምርት ማጠራቀሚያ ቦታ ኪራይ መክፈል አዋጪ በመሆኑ ነው። መቀመጫቸውን ኬንያ ያደረጉት በነዳጅ ዘይት ዙሪያ በግል የሚያማክሩት ፓትሪክ ኦባት እንደሚሉት "በአሁኑ ጊዜ የሚታየው ነዳጅ አምራቾች ምርታቸውን መሸጥ አልቻሉም፤ በተጨማሪ ደግሞ ነዳጁን ለሚያከማቹበት ቦታ መክፈል አለባቸው። ስለዚህም ነዳጅ ማውጫዎችን ከመዝጋት ወጪ እያወጡ በምርታቸው መቀጠልን መርጠዋል። ለዚህ ነው በዋጋ ላይ ከዜሮ በታች የሆነ ውጤት የሚታየው" ብለዋል። ስለዚህም የዋጋው መውደቅ ምርቱን ለፈላጊው በነጻ የማግኘት ዕድልን የሚፈጥር ሳይሆን፤ አምራቹ ላይ የተፈጠረውን የወጪ ጫና ለማመልከት ነው። በቀላል ምሳሌ ነዳጅ አምራቹ ምርቱን የያዘውን በርሜል ከመሸጥ ይልቅ ምርቱን ለማጠራቀም የሚሆን ቦታን ለመከራየት የሚያወጣው ወጪ ነው ዋጋው ላይ ትልቅ ለውጥ ያሳየው። ስለዚህ ማንም ነዳጅ ዘይትን በነጻ ሊያገኝ አይችልም። በአሁኑ ጊዜ ገበያው ምላሽ እየሰጠ ያለው በዓለም ዙሪያ ላለው የነዳጅ ፍላጎት ማሽቆልቆልና በወረቀት ላይ ለሚታየው ዋጋ ነው። ይህ በዚህ ከቀጠለ በየብስ ላይ የሚገኙት የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች ሞልተው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የውሃ አካላት ላይ በሚንቀሳቀሱ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ሳይቀር ማከማቸት ሊቀጥል ይችላል፥ እስከዚያም ያለው ሁኔታ ተስተካክሎ እንቅስቃሴው ወደነበረበት ሊመለስና የነዳጅ ፍጆታውም ከምርቱ ጋር በተቀራረበ ሁኔታ ሊስተካከል ይችላል። "ምንም እንኳን የተትረፈተፈ ምርት ቢኖርም ማምረቱ ቀጥሏል በዚህም ምክንያቱ ዋጋው የበለጠ ማሽቆልቆሉ አይቀርም። በቀጣዮቹ ወራት የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ ከ15 እስከ 20 ዶላር ይሆናል" ሲሉ ኦባት ተንብዋል። ናይጄሪያና አንጎላን የመሳሰሉ የምጣኔ ሃብታቸው ከነዳጅ ዘይት ምርት ጋር የተቆራኘ የአፍሪካ አገራት ከባድ ጫና ይገጥማቸዋል ተብሎ ይገመታል። ከሌሎች ጋር ተወዳድረው ምርታቸውን በበርሜል እስከ 10 ዶላር መሸጥ ከቻሉ እድለኞች ሊባሉ ይችላሉ ተብሏል።
47783067
https://www.bbc.com/amharic/47783067
በዛምቢያ አባቶች ከትዳር ውጪ ለሚወለዱ ልጆቻቸው የወሊድ ፈቃድ ሊያገኙ አይገባም ተባለ
በዛምቢያ የአሰሪዎች ማህበር መንግሥት ለወንዶች የሚሰጥ የአባትነት የወሊድ ፈቃድ ገደብ እንዲደረግበት ጠየቀ። ማህበሩ ጥያቄውን ያቀረበው ወንዶች የትዳር አጋሬ ብለው ካስመዘገቧት ሴት ውጪ ለሚወልዷቸው ልጆች ፈቃድ እንዳያገኙ በሚል ነው።
ይህ የዛምቢያ የአሰሪዎች ፌዴሬሽን አላማ ያደረገው ወንዶች የሚወስዱትን የወሊድ ፈቃድ ለመገደብ ነው። • በወሲብ ፊልሞች ሱሰኛ የሆኑ ወጣት ሴቶች የማህበሩ መሪ የሆኑት ሀሪንግተን ቺባንዳ እንዳሉት አንድ ያገባ ወንድ ምን ያህል ጊዜ የአባትነት እረፍት መውሰድ እንዳለበት ገደብ ሊጣልበት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የማህበሩ ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ከፀደቀ ያላገቡ ወንዶች እረፍት አያገኙም ማለት ነው። • ሴተኛ አዳሪነት ባህል የሆነበት ማህበረሰብ ወንዶች ከፈለጓት ሴት ሊወልዱ እና አሰሪዎቻቸውን እረፍት ሊጠይቁ ይችላሉ። ነገር ግን አሰሪዎች እረፍት ሊሰጧቸው የሚገባው የትዳር አጋሬ ብለው ካስመዘገቧት ሴት ሲወልዱ ብቻ ነው ብለዋል። "የሴቶቹ የተለየ ነው እርግዝናቸው ስለሚታይ አያስቸግርም፤ የወንዶቹን ግን ማጣሪያ መንገድ የለንም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ ሀሳብ አግላይ አይሆንም ወይ ተብለው ሲጠየቁም "አንድ ወንድ ድንገት ብድግ ብሎ 'ልጅ ወልጃለሁ' ብሎ እረፍት ይሰጠኝ የሚለውን ለመከላከል ነው ምክንያቱም ከሥራ በቀረ ቁጥር ሥራ ይበደላል" ብለዋል። • ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት "ከአንድ በላይ የትዳር ጓደኛ ያላቸውም ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል" ሲሉ አክለዋል። የዛምቢያ የሠራተኞች ህግ ማሻሻያ እየተገደረገበት ሲሆን የሰራተኛ ሚኒስትር ጆይሴ ሲሙኮኮ መንግስት ጉዳዩን እያጤነው እንደሆነ ተናግረዋል።
51556381
https://www.bbc.com/amharic/51556381
ከማዕከላዊ ስልጣን የተገፋው ህወሓት ከዬት ወደዬት?
ከሰሞኑ ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበት 45ኛ አመት ክብረ በዓል በትግራይ በደማቅ ሁኔታ በመከበር ላይ ነው።
የደርግን ስርአት ገርስሶ ስልጣን ከተቆጣጠረ ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ከማዕከላዊ መንግሥት ስልጣንም ገሸሽ ተደርጎ ክልሉን እያስተዳደረ ይገኛል። ለመሆኑ ህወሓት ከዬት ተነስቶ የት ደረሰ? በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ያደረጋቸው አስተዋፅኦዎች ምን ይመስላሉ? ስህተቶቹስ ምን ይመስላሉ? በጨረፍታ እንመለከተዋለን። • መጠየቅ ካለብን የምንጠየቀው በጋራ ነው፡ አባይ ፀሐዬ • "ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደትን ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" አቶ ጌታቸው ረዳ ደደቢት፣ የህወሓት የትጥቅ ትግል መነሻ፣ የደርግን ጭቆና የተፀየፉና ነፃነትን የናፈቁ ወጣቶች፣ የብዙ ወጣቶች ደም የተገበረባት ቦታ። የነገን ተስፋ የሰነቁባት ወጣቶች የደርግን ስርአት ለመገርሰስ ተነሱ፤ ትግሉም እልህ አስጨራሽና ብዙዎችም የተሰውበት ነው። በድርጅቱ የተለያዩ ሰነዶችም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደሚነገረው የትግሉ ዋና ዓላማ የልማትና የዴሞክራሲ ዕንቅፋት ሆኗል ብሎ ያመነውን የደርግ ስርዓት አስወግዶ ወደ ዴሞክራስያዊ ስርዓት ለመሸጋገር ነበር። ከአስራ ሰባት አመታት ትግል በኋላ የደርግ ስርአትም ተገረሰሰ፣ ህወሓት ከብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ኢህዴንና ሌሎች አጋር ፓርቲዎች ጋር በመሆን ስልጣን ተቆናጠጠ። የሽግግር መንግሥት በማቋቋም ለሶስት አመታት ያህልም ቆይቷል፤ በዚህ ወቅት ነው አገሪቱ አዲስ ህገ መንግሥት እንዲኖራትና ፌደራላዊት፣ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ የሚል መጠሪያ እንዲኖራትም የተወሰነው። ህወሓትና ህገመንግሥቱ ህዳር 29፣ 1987 ዓ.ም በወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተፈርሞ የፀደቀው ህገ መንግሥት ለብሄር ብሄረሰቦች የተለየ መብት የሚሰጥ እንዲሁም በመርህ ደረጃ ለህዝቡ የስልጣን ባለቤትነትን የሚያጎናጽፍ ነው። ህገ መንግሥቱ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ፤ የዜጎች የመጻፍ፣ በነጻነት ሃሳብ የመግለጽ፣ የመሰባሰብና የመቃወም መብቶችን አካቶ የያዘ ሰነድ በመሆኑ ድጋፍ ተችሮት ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ህገ መንግሥቱንም በማርቀቅ የተለያዩ ሃሳብ ያላቸውን ኃይሎችንም በማሰባሰቡ ህገ መንግሥቱ በመርህ ደረጃ ብዙዎች ደግፈውታል። • "ሕገ-መንግሥቱ ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትርን በሚመለከት ክፍተት አለበት" ውብሸት ሙላት ምንም እንኳን ህገ መንግሥቱ ከተለያዩ ሃይሎች ድጋፍ ቢቸረውም አንዳንድ አንቀፆች አሁንም ድረስ ያልተቋጨ ውዝግብን አስነስተዋል። ለምሳሌም ያህል አንቀፅ 39 ላይ የሰፈረው 'ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እስከ መገንጠል ድረስ' የሚለው ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሃገር ሆና እንዳትቀጥል ህልውናዋን የሚገዳዳራት ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ እስካሁን ላሉ የብሄር ጥያቄዎችን ራሳቸውን የማስተዳደር ታሪካዊ ጥያቄ የመለሰ ነው የሚሉም በሌላ ወገን አልታጡም። በህወሓት/ኢህአዴግ ፊት አውራሪነት የጸደቀው አዲሱ ሕገ መንግስት፤ ከዚህ በፊት የነበረውን በአሃዳዊነት ላይ የተመሰረተውን የኢትዮጵያ አገር ግንባታ አፍርሶ ሌላ መልክ የሰጠ ነው ተብሎ ይተቻልም እንዲሁም በተቃራኒው ይሞካሻል። የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርበት ሲከታተሉ ለቆዩት የግጭት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮ በወቅቱ በኢትዮጵያ የነበረው ሁኔታ የሚያንጸባርቅና በአብዛኛው የህዝቡ ስሜት የሚገልጽ እንደነበር ያስረዳሉ። እሳቸው እንደሚሉት የኢህአዴግ ስርዓት ትልቁ ችግር ራሱ ህገ-መንግስቱ ሳይሆን፤ አተገባበር ላይ የነበሩ ክፍተቶችና ጉድለቶች እንደሆኑ ያስረዳሉ። ምርጫ 1997፡ የዴሞክራሲተስፋ መፈንጠቅ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የ1997 ምርጫ እንደ ትልቅ ምዕራፍ ይታያል። በነበሩት የጦፉ ውይይቶችና መድረኮች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣምረው በአንድ ግንባር መምጣት፣ በምርጫ ቅስቀሳዎች እንዲሁም ህዝቡ ይሆነኛል የሚለውን የመምረጥ ተስፋን ያመጣ ነበር። ከዛ በፊት በነበረው የመጀመሪያው ምርጫ ከጠቅላላ 547 የፓርላማ ወንበሮች ውስጥ ኢህአዴግ 481 አሸንፎ ነበር ስልጣኑን ከሽግግር መንግስቱ የተረከበው። በወቅቱ እነ ዶክተር መረራ ጉዲና የመሳሰሉ ነባር የተቃዋሚ አመራሮች ጥቂት መቀመጫ አግኝተው በምክር ቤቱ የተለዬ ሃሳባቸውን ለመግለጽ ዕድል አግኝተው ነበር። የተሻለ የዲሞክራሲ ጭላንጭል የታየበት የ1997ቱ ምርጫም፤ ብሔርን ከብሔር የሚያጋጩ ፅሁፎች ነበሩባቸው ተብለው ቢተቹም፤ የግል ሚድያዎችና ሲቪክ ማህበረሰቦች እንደልባቸው የተንቀሳቀሱበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር። • ህወሓት ከኢህአዴግ ለመፋታት ቆርጧል? • ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም" በተለይም የተቃዋሚዎች ተጣምረው አንድ ላይ መምጣት ለምርጫው ሌላ መልክ ነበር። በወቅቱ ቅንጅትና ህብረት ኢህአዴግን ተገዳድረውታል፤ ተንታኞች እንደሚሉት ኢህአዴግ ባልጠበቀው መልኩ የሃገሪቱን ማዕከል አዲስአበባን በተቃዋሚዎች አጥቷል። ሆኖም በምርጫው ውጤት ተቃዋሚዎችና ኢህአዴግ ስለልተስማሙ ወደ እስርና ደም መፋሰስ ነበር ያመራው። የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች ህገመንግሥቱን በኃይል ለማፍረስና በሃገር ክህደት ተወንጅለው ዘብጥያ ወረዱ። ምንም እንኳን ብዙዎቹ ከመንግሥት ጋር በተደረገ ድርድር ከእስር ቢፈቱም በርካቶች በሰላማዊ ትግሉ ተስፋ ስለቆረጡ ስደትን ምርጫ ለማድረግ ተገደዱ። ብዙዎቹ በውጭ ሆነው ሲታገሉ ቆይተው ዶክተር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የተደረገውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ነበር ወደ አገር ቤት የመጡት። በ1997 ምርጫ ስልጣኑ ለመጀመርያ ግዜ የተነቃነቀው ገዢው ፓርቲ ከፍቶት የነበረውን ጭላንጭልም ተዘጋ፤ ይህንንም የሚያጠናክርና በተቋማዊ መልኩ የሚያደርጉ ህጎች ፀደቁ። ከነዚህም መካከል በብዙዎች ዘንድ አፋኝ ተብለው የሚጠሩት የጸረ ሽብር፣ የፕሬስ፣ የሲቪል ማህበረሰብ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምዘገባ አዋጆች ይገኙበታል። ብዙዎችንም በፍርሃት እንዲሸበቡ አድርጓቸዋል፤ የፖለቲካ ምህዳሩን አጥብበውታል በማለት በተደጋጋሚ የተለያዩ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሪፖርቶችንም ያወጡ ነበር። የቀድሞ የህወሓት አመራር አባል አቶ ገብሩ አስራትም አስተያየት ከዚህ ብዙ የተለየ አይደለም፤ በወቅቱ ገዢው ፓርቲ የወሰደውን እርምጃ የአገሪቱ የዴሞክራሲ ዕድገት ወደኋላ የጎተተ ክስተት ይሉታል። • 'የአልባኒያ ተቃዋሚዎች' በትግራይ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችንም ከማሽመድመድ ሌላ የምርጫ ውዝግቡን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ አዳዲስ አባላትን መመልመል ጀመረ። ከምርጫ 1997 በፊት ከአንድ ሚልዮን በላይ አባላት ያልነበሩት ቢሆንም የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎ 7 ሚሊዮን አዳዲስ አባላትን መልምሏል። በሚሊዮኖች የተመለመሉት አባላት የኢህአዴግን ርዕዮተ አለም፣ ፕሮግራም እንዲሁም ለሃገሪቱ አስቀመጥኩት የሚለውን አቅጣጫ አምነውበት ሳይሆን፣ ከመንግሥታዊ ጥቅማ ጥቅም ጋር የተያያዙ እንደሆኑም በቅርበት ግንባሩን የሚከታተሉ በተደጋጋሚ ይናገሩት የነበረ ጉዳይ ነው። ግንባሩን ሳያምኑበት በአባልነት የተመለመሉ ወጣቶች በመጨረሻ ድርጅቱ አደጋ እንደሚያስከትል ስጋታቸውን የገለጹም ብዙዎች ነበሩ፤ ግንባሩም መሸርሸሩ አይቀርም በማለትም ተንታኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። "የተራበው ህዝብ መሪውን ይበላል" በሚልና በሌላ መረር ያሉ ንግግሮቻቸው የሚታወሱት መረራ ጉዲና (ዶ/ር) "የኢህአዴግ መጨረሻው ከአገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጭ ሊሆን ይችላል በሚለው እንጂ በህዝባዊ ዓመጽ እንደሚሆን አውቅ ነበር" ይላሉ ከቢቢሲ ጋር በባደረጉት ቆይታ። ነጻ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ክፍተት? ኢትዮጵያ ውስጥ እምነት የሚጣልበት የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ አለመኖር እንደ አንድ ለስርአቱ ችግር ተብለው ከሚነሱ ምክንያቶች አንዱ ነው። ምንም እንኳን በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ አንዱ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ምሰሶ የሆነው የተቋማት እርስ በርስ የመቆጣጠር እና ሚዛን መጠበቅ ቢሆንም አገራዊ እና መንግሥታዊ መዋቅሮች ከኢህአዴግ ነፃ አልነበሩም። ለዘመናትም መንግሥታዊና የህዝብ ተቋማት የፓርቲው መሳሪያ ሆነው ከፍተኛ ክፍተትን አስከትለዋልም ተብለው ይተቻሉ። ለዚህም የፍትህ አካላት፣ የፀጥታና ደህንነት አካላት ኢህአዴግ እንደ ግል ንብረቱ የሚጠቀምባቸውና የሚያሽከረክራቸው ናቸው ይባላሉ። ለምሳሌም ያህል የመንግሥት ሚዲያ ለአስርት አመታት ያህል የገዢው ፖርቲ ፕሮፓጋንዳ መንዢያ ናቸው ይላሉ፤ ከዚህም በተጨማሪ ፍርድ ቤትም ሆነ አስፈፃሚው አካል ፓርቲው ጣልቃ እየገባ እንደፈለገ የሚያዛቸው ናቸው ይላሉ ተችዎች። በተደጋጋሚ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ ተጠርጣሪዎችን በመንግሥት ሚድያ እንደ ወንጀለኞች ተደርገው የተለያዩ ዘገባዎች የሚቀርቡባቸው አካሄድ ነበር፤ ይሄ ሁኔታ ባለፉት ሁለት ዓመታትም ቀጥሏል። ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም እንደነበረው ይህንን ሲያስቆምም አይታይም ይላሉ። በባለፉት ሶስት አስርት አመታት ያሉትን ክፍተትም በመታዘብ በኢትዮጵያ የከፋው ነገር ነፃ የዲሞክራሲ ተቋማት መፍጠር አለመቻል እንደሆነ ፕሮፌሰር ትሮንቮል ይናገራሉ። "ገዢው ፓርቲ ራሱን ከመንግሥት ተቋማት ጋር አጣብቆ፤ ተቋማቱ ራሳቸውን ችለው እንዳይቆሙ አድርጓቸዋል"ይላሉ። ፕሮፌሰር ትሮንቮል እንደሚሉት ለዚህ ችግር ዋነኛው ምክንያት በሶስቱም የመንግሥት አካላት- ህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሚውና አስፈጻሚው መካካል የእርስ በርስ ሚዛናቸውን ጠብቀው፣ ተለያይተውና አንዱ ሌላውን ሊቆጣጠር ስላልቻለ ነው ይላሉ። የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ- አብዮታዊ ዴሞክራሲ? ምንም እንኳን የኢህአዴግ "አፋኝ እርምጃዎች፣ ፈላጭ ቆራጭ መሆን የጀመረው ምርጫ 97ን ተከትሎ፤ በውጤቱ ተደናግጦ ነው የሚሉ ቢኖሩም አቶ ገብሩ አስራት ግን በዚህ ሃሳብ አይስማሙም። ለሳቸው ዋነኛውና መሰረታዊው ችግር የግንባሩ ርዕዮተ ዓለም ነው። • "አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ነገ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንደሚገባ ግልጽ ነው" አቦይ ስብሃት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፅንሰ ሃሳብ ከህገ መንግሥቱ ጋር ይጻረራል የሚሉት አቶ ገብሩ " ስርዓቱ ሁሉንም ዜጎች እኩል አይመለከትም፤ ወዳጅና ጠላት ብሎ ዜጎችን ለሁለት ይከፍላል" ይላሉ። እንደ ማስረጃነት ድርጅቱ ይጠቅሳቸው ከነበሩትም መካከል "ለሰራተኞችና ለአርሶ አደር እቆማለሁ ይላል። ምሁር ወላዋይ ነው ብሎ ያምናል።" በማለት ይናገራሉ። ምንም እንኳን ይህ አስተሳሰብ ለህወሓትም ሆነ ኢህአዴግ በትጥቅ ትግል ወቅት ህዝቡን ለማንቀሳቀስ ጠቃሚ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ገብሩ፣ ሆኖም ትግሉ ተጠናቆ ስልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ የተቀመጠ አቅጣጫ እንደሌለ ይጠቁማሉ። "እንዴት እንቀጥልበት የሚለው ላይ አልተነጋገርንም" ይላሉ አብዮታዊ ዴሞክራሲ በአቶ ገብሩ አስራት ብቻ ሳይሆን በብዙ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ተንታኞችና ምሁራንም ሲተች ይደመጣል፤ እንደ ርዕዮተ አለምም የማያዩት አሉ። "ኢሕአዴግ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮግራም የሚመራና በፕሮግራሙ ላይ ለሰፈሩት ዓላማዎች የሚታገል ድርጅት ነው። ያነገባቸው ዓላማዎች ዴሞክራሲያዊና አብዮታዊ በመሆናቸው በተግባር ላይ ከዋሉ ኅብረተሰባችንን ከሚገኝበት ድህነትና ኋላ ቀርነት አላቀው ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲና ለብልፅግና ያበቁታል። " ይላል ከኢሕአዴግ መተዳደሪያ ደንብ መግቢያ አንቀጽ ላይ የተወሰደው ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ አመራርን መሰረት ያደረገው አብዮታዊ ዴሞክራሲን ለማስፈን የህዝብ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል የሚል ሲሆን፤ በጥቅሉ የዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት ጠንካራ የመካከለኛ ገቢ ያለው መደብ መፍጠር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚያስፈልገው ነውም ይላል። ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው "የኢትየጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች፡ የኢህአዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ" በሚለው ፅሁፋቸው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና መሰረት ስልጣን ላይ መምጫው መንገድ የማኦው ፍልስፍና የሆነው "ስልጣን የሚመጣው ከጠመንጃ አፈሙዝ ነው" የሚለው ነው ይላሉ። አክለውም ይህንን የኢህአዴግ አስተሳሰብ ራሱ በህገ መንግስቱ ውስጥ ከገባው ቃል ይጻረራል ሲሉ ያስረዳሉ። ጠንካራ ፖርቲ በመመስረት የሚያምነው ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን እንዲኖሩ የሚፈልገው በወሳኝ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ ሳይሆን ለይስሙላና ለለጋሾች ተብሎ እንደሆነም ትችቶች ከሚቀርቡባቸው ጉዳይ አንዱ ነው። የልማታዊ መንግሥት ጥያቄ ኢትዮጵያ ባስመዘገበችው የኢኮኖሚ እድገት የጤና አገልግሎት ሽፋን፣ የትምህርት ተደራሽነት፣ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መንግሥት የሚያራምደው የልማታዊ መንግሥት ርዕዮት ውጤት ነው ብለው ብዙዎች ያምናሉ። በተቃራኒው የዚሁ ልማታዊ መንግሥት መገለጫም የተለየ እይታዎችን የያዙ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች በእስር መማቀቅ ነው። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ተቀረፀ የሚባለው የኢትዮጵያ ልማታዊ መንግሥት መገለጫዎች የሚባሉት ጠንካራ እና ጣልቃ ገብነት ያለው፣ ለሰው ሐብት ልማት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት፣ የሀገርን ሐብትን በማስተባበር ቀጥተኛ ሚና በመጫወት ትልልቅ ሀገር አቀፍ የልማት ሥራዎችን ለመተግበር እንዲችል በማመቻቸት ለውጥ ማምጣት ነው ይላሉ። ልማታዊ መንግሥቱ ያለ ሌሎች ተፅእኖ ራሱን የሚያስተዳድር እና በሃገር ውስጥ የበላይነት ያለው በምርጫ ሂደት የማይስተጓጎሉ ሲሆኑ የእስያ ሃገራቱ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን እንደ አብነት ይጠቀሳሉ። ከምዕራባውያኑ ተቋማት አለም ባንክ እና አይኤምኤፍ "ያረጀ ያፈጀ" አካሄድ ነፃ በመሆን በፍጥነት እመርታዊ ኢኮኖሚ ማስመዝገብ የሚልም አካሄድ ነበረው። በዚህ አካሄድ ብዙ አስርት አመታትን በስልጣን የሚቆዩ ሃገራት ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ አምጥተዋል ቢባልም ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን ይደፈጥጣሉ ተብለው ይተቻሉ፤ ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያን በማስገባት ይተቿታል። የሲቪል ማሕበራትንና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽን በማፈን በተቃራኒ ወደ አምባ ገነንነትና ፈላጭ ቆራጭነት አምርተዋል ቢባልም ይህንን አስተሳሰብ ለዘመናት ኢህአዴግ በተለይ መለስ ዜናዊ ሲሞግቱት ነበር። የመጡ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች የመጡ ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን በተመለከተ እንደ አለም ባንክ ያሉ መረጃዎች ሲፈተሹ በተከታታይ አመታት በዓለማችን ከፍተኛ ዕድገት ካሳዩ አገራት አንዷ ሆናለች፤ በአለም በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አምስት ሀገራት መካከልም ሁና ነበር። አዳዲስ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መጀመር ለምሳሌ የህዳሴ ግድቡን ጨምሮ በርካታ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች ተሰርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሴፍቲኔት መርሐ ግብር የሚጠቀስ ሲሆን በአለም ባንክ መረጃ መሰረት በጎርጎሳውያኑ በ2011፣ 30 % ህዝብ ከድህነት ወለል በታች የነበረ ሲሆን በ2016 ወደ 24% ቀንሷል። የትምህርት ቤት ተደራሽነትም እንዲሁ በ2006 97%፣ በ2016 ደግሞ ወደ 99% እንዳደገ መረጃው ያመለክታል። ምንም እንኳን እነዚህ የመጡ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች በተለያዩ አለም አቀፍ ሚድያዎች ከፍተኛ መወደስን ቢያመጡም መንግሥት ያደረጋቸውም ጫናዎችና ጭቆናዎች በብዙዎች ዘንድ ተተችቶበታል። ስልጣን ላይ ለመቆየት የማያደርገው ነገር የለም የሚሉት ዶክተር መረራ በተለይም በ2002 በነበረው ምርጫ 99 በመቶ አሸነፍኩ ማለቱን እንደ ምሳሌ ያነሳሉ። ምክር ቤቱን ጠቅልሎ የሚቆጣጠርበት ዘዴም ያበጀ ሲሆን 'የምርጫ ሰራዊት' የሚባል ከእርዳታ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በማስተሳሰር አንድ ለአምስት "የሚጠረነፉበትን" ሁኔታም ተቀየሰ። የምርጫው ውጤት ያልተቀበሉ ተቃዋሚዎችም እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ቢሄዱም ለውጥ ግን አላገኙም። የሥርዓቱ ፈላጭ ቆራጭነት ከሰላሳ ዓመታት በላይ የህወሓት እና ኢህአዴግ ሊቀ መንበር ሆነው የቆዩት አቶ መለስ ዜናዊ በትልልቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች ባመጡት የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር ተያይዞ ስማቸው ቢነሳም ባገሪቱ ውስጥ ግን በነበረው ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓትም ይወቀሳሉ። "ግንባሩ የመበስበስ አደጋ እንዳይገጥመው" በሚል ጀምረውት የነበረውን የመተካካት ፖሊሲም ከግብ ሳያደርሱ በ57 ዓመታቸው አረፉ። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአፍሪካ ተቀባይነት ያገኙ መሪዎች ውስጥ ቢካተቱም እንዲሁም "ባለ ራዕይ እንዲሁም ሞጋች ተደርገው ቢታዩም በሌላ መልኩ ዘኢኮኖሚስት መፅሄት ግን 'The man who tried to make dictatorship acceptable' (አምባገነንት ተቀባይነት እንዲያገኝ የሞከሩ ሰው) በማለት ይገልፃቸዋል። ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ አገሪቱን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም በቀደመው ራዕይ ቀጠሉበት፤ ፈላጭ ቆራጭነቱም ቀጥሎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች መታሰር ብዙዎችን ተስፋ ያስቆረጠ ነበር። የህወሓት የቀድሞ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ብርሃነ ፅጋብ 'የኢህአዴግ ቁልቁለት ጉዞ' በሚለው መጽሐፋቸው ከመለስ ሞት በኋላ የግንባሩን አካሄድ የፈተሹት ሲሆን በሳቸውም አስተያየት "በግምገማ፣ ራስን በመተቸት የሚታወቅ ፓርቲ በመተዛዘል (እከከኝ ልከክህ) ዳዴ ማለት ጀመረ፤ ሺዎች ደማቸውን የከፈሉበት ሥርዓት፣ የፓርቲው መሪዎች የግል ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁበት ሆነ" በማለት ያስረዳሉ። የኢህአዴግ የሥርዓት መበስበበስም መገለጫ የሆነው ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና የሕዝቡ ቁጣ ናቸው። በኢህአዴግ ላይ የሚንፀባረቁት ከፍተኛ ተቃውሞዎች በተለይም ግንባሩን በአካሉና በአምሳሉ ከሠራው ህወሓት ጋር በከፍተኛ ሁኔታ ያነጣጠረ ነው። ህወሓት ላይ የሚያጋጥሙ ማንኛውም እክሎች ግንባሩንም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ነበራቸው። ለዚህም በህወሓት ያጋጠመው መከፋፈል በአገሪቱ ውስጥ ላለው መከላከያ እንዲሁም ሌሎች ተቋማትን የከፋፈለ እንዲሁም የአገሪቱን ደህንነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነበር። ኢህአዴግ ወይም ህወሓትም ላይ ያነጣጠረው ተቃውሞም የትግራይ ሕዝብ ላይ የወረደ ሲሆን የትግራይ ሕዝብ በተለየ የሥርዓቱ ተጠቃሚ ተደርጎም ተስሏል። ይህ ሁኔታም ከራሱ ከፓርቲው ሲወጡ የነበሩ ሃሰተኛ ሪፖርቶችና ፕሮፖጋንዳዎች ሁኔታውን አባብሶታል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤ ይህንንም ሁኔታ ዶ/ር ደብረፅዮን ወደ ፓርቲው ኃላፊነት ሲመጡ ያመኑበት ጉዳይ ነው። መቋጫ በህወሓት አካሄድ ያልተደሰቱ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ የሆነው አብርሃ ሃይለዝጊ አይነት ግለሰቦች ፓርቲውን ለቀው ለመውጣት ብዙ አልወሰደባቸውም። ለሶስት ዓመት የፓርቲው አባል የነበረ ሲሆን፤ ፓርቲውን ጥሎ ለመውጣት ግን አራት ዓመትም አልሞላም። "ፓርቲው ከሕዝባዊነት ወጥቶ ለሕዝብ ጥቅም ሳይሆን ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉት አስተዋልኩኝ። በፓርቲው ውስጥ ሆኜ ለመታገል የሚያስችል ቦታም እንዳልነበረም ተረዳሁ" በማለት ከፓርቲው ደብዳቤ በመፃፍ እንደተሰናበተ ያስታውሳል። አብርሃ በፓርቲው ውስጥ ሆኖ ለመንቀፍ የሞከረ ሰው ከሥራ የመባረር፣ በሕይወቱ የማስፈራራት እና ሌሎችም ችግሮች ይደርሱበት ነበር ይላል። "ጥያቄ የጠየቀ እንደ ጠላት ይታያል። ጠባብ፣ ትምክህተኛ የሚሉ የአፈና መሣርያ ቃላትን በመጠቀም ያሸማቅቃሉ" ይላል። በወቅቱ ትክክለኛ ውሳኔ እንደወሰነ የሚሰማው አብርሃ በኋላም ህወሓት ባደረገው ጥልቅ ግምገማ ስህተት መሆኑ ታምኖበት ነበር ይላል። ህወሓት በ2010 ዓ.ም ባካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ጥልቅ ግምገማ ዜጎች ሕገ-መንግስታዊ መብታቸው እንደታፈነ፣ በፓርቲው ሥርዓት አልበኝነት እንደነገሰ፣ፀረ-ዲሞክራሲያዊ አሠራር እና መጠቃቃት የፓርቲው መገለጫ እንደነበር በማመን ለሕዝብ ይቅርታ ጠይቋል። ባለፉት 27 አመታት ድህነት፣ ሲፈፀም የነበረ ግፍ እና ሕገ-መንግስታዊ ጥሰት፣ የዜጎች ሰብኣዊ መብት ጥሰት በትግራይ የከፋ እንደነበርም ተንታኞች ይናገራሉ። "ለረዥም ጊዜ በስልጣን የቆየ ገዢ ፓርቲ መጨረሻው ሙስና እና ሥርዓት አልበኝነት ነው" የሚሉት ፕሮፌሰር ሼቲል ትሮንቮል፤ ህወሓት እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ ግንባር ከታገለበት መስመር ወጥቷል በማለት ሀሳቡን ያጠናቅቃል። ዶክተር መረራም ስለ ህወሓት/ ኢህአዴግ የሚያስታውሱት ጥሩ ነገር ካለ ተጠይቀው "ከሰይጣኑ ደርግ ነፃ ስላወጣን ብቻ አመሰግነዋለው" ብለዋል።
news-54239240
https://www.bbc.com/amharic/news-54239240
ኮሮናቫይረስ፡ ለ15 ዓመት በወሲብ ንግድ ላይ የቆየችው ሴት ኮቪድ-19 ሕይወትን አክብዶብኛል ትላለች
ሩሐማ አበበ እባላለሁ። ትውልዴ ደቡብ ጎንደር አርብ ገበያ የሚባል ቦታ ነው። * (ለዚህ ጽሁፍ ሲባል ስሟን ጨምሮ ማንነቷን ሊያሳውቁ የሚችሉ ነገሮች ተቀይረዋል ወይም እንዲቀሩ ተደርጓል።)
አርብ ገበያ ብወለድም አላደግኩበትም። አባቴ እኔ እንደተረገዝኩኝ ከእናቴ ጋር በመለያያቱ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ። በስም ብቻ የማውቀው አባቴ በኋላ ላይ ህይወቱ እንዳለፈ ሰማሁ። እናቴ ደግሞ የሦስት ዓመት ልጅ ሆኜ ነው ህይወቷ ያለፈው። ሰባት ዓመት እስኪሆነኝ ድረስ አያቴ ዘንድ እዚያው አርብ ገበያ ነው ያደግኩት። በኋላ ላይ አክስቴ 'እኔ ላሳድጋት' ብላ ወደ ባህር ዳር ከተማ ይዛኝ መጣች። ባህር ዳር በሁሉም ነገር የተሻለ ነበር። ትምህርቴንም ጀመርኩኝ። አንደኛ ክፍል እያለሁ የደረሰብን ጉዳት ግን ህይወቴን እሰከወዲያኛው ለወጠው። እንጥሌ ወድቃ ጎሮሮዬ በማበጡ ምክንያት ወደ ሐኪም ቤት ይዘውኝ ሄዱ። መርፌ የወጋኝ ሐኪም የሠከረ ይመስለኛል። ህጻን ስለሆነበርኩ በደንብ ባላስታውስም መርፌ ሲወጋኝ የአክስቴ ልጅ 'ኧረ ቸኮልክ' ስትለው ትዝ ይለኛል። አንዴ ሲወጋኝ ቀጭ ነው ያለው አጥንቴን ሲያገኘው። መርፌው ተሰብሮ የቀረ ይመስል አመመኝ። የወጋኝ ቦታ ጎደጎደ። ሌላው ሰውነቴ ደግሞ አበጠ። ስራመድ እግሬን እየሳበኝ መሄድ ጀመረ። በአንድ ወሩ ቀኝ እግሬ አጠረ። እስከ አንድ ወር ድረስ በስርዓቱ እሄድ ነበር። መርፌ የተወጋሁበት ቦታ ጎድጉዶ ጣት ያስጋብል። አሁን መኝታም ሲጎዳኝ ያመኛል። አሁንም መርፌው ተሰብሮ ቀርቷል ብዬ ነው የማስበው። አሞኝ ይቀራል ብዬ በፍጹም አላስበኩም ነበር። ካበጠም በኋላ እግሬ እያጠረ መሬት መርገጥ አስቸገረኝ። በሁለተኛ ወሩ ወደ ሐኪም ቤቱ ስንሄድ ሐኪሙ የለም። እያዛለሁ ብሎ ሸሽቷል። ግማሹ አዲስ አበባ ሄዷል የሚል አለ። ሌሎች የት እንደሄደ አናውቅም አሉ። በዚህ ምክንያት ራሴን አላጠፋም። እግሬን አልገዛውም። ምንም። ምን እላለሁ። [ረዥም ዝምታ] በወቅቱ አንደኛ ክፍል እማር ነበር። ብቻ ብዙ ነገሮችን አጥቻለሁ። [ማልቀስ ጀመረች]። ቤተሰብ የለኝም ሁለተኛ ራሴን ሳጣ . . . [ከእንባዋ ጋር እየታገለች ቀጠለች] ብዙም ሳትቆይ አክስቴ ሞተች። ከልጇ ጋር አብረን መኖር ጀመርን። እሷ ስታገባ ግን አማራጭ አጣሁ። ሰው ራሱን ለማዳን ልመና ይቆማል። እኔ ግን አልመኘውም። የታክሲ እንኳን ሰው እንዲከፍልልኝ አልፈልግም። ትምህርት ቤት አንዲት ጓደኛ ነበረችኝ። አበበች ትባላለች[ስሟ የተቀየረ]። አሁን አረብ ሃገር ነው ያለችው። ባህር ዳር ቀበሌ 5 ብትኖርም ሌላ ቦታ ነው ትውልዷ። 'ቤተሰብ አለሽ?' ስላት 'የለኝም' ትለኛለች። ወዳጅነታችን ሳይጠነክር በፊት 'ቆሎ እሸጣለሁ' ትለኝ ነበር። 'በምሸጠው እኖራለሁ' ስትለኝ 'ቆሎ እየሸጥሽ እንዴት ያዋጣሻል?' ስላት ትስቅብኛለች [ፈገግ አለች]። ሁሌም ትምህርት ቤት እያረፈደች ነው የምትገባው። አለቃ ይገርፋታል። 'ለምን ትተኛለሽ?' እላታለሁ። አንድ ቀን ግን 'ብዙ ነገር አለ። ስንወጣ እናወራለን' አለችችኝ። ከትምህርት ቤት ስንወጣ 'ምን ነበር አወራሻለሁ ያልሽኝ?' ስላት። 'እንደዚህ እንደዚህ ነው የምሰራው' አለችኝ። 'ከወንድ ጋር እወጣለሁ። ከብዙ ሰዎች ጋር' አለችኝ። ብዙ ነገር ነገረችኝ። አለቀስኩ። 'ሩሐማ ቤተሰብ ይሄን እንደምሰራ አያውቅም' አለችኝ። መጀመሪያ ላይ 'እንዴት? የሚያውቅሽ ወይም መምህርሽ ቢመጣስ?' ስላት 'ላይለየኝ' ይችላል አለችኝ። 'መብራቱ ቀይ አምፖል ነው' ብላ አሳየችኝ ቤቱን ወስዳ። ማታ ላይ ከቤት አድረን አይቼዋለሁ። ቀይ ቀለም በተቀባው አምፖል በቀላሉ እንደማትለይ እኔ እንኳን ቤቷ ድረስ ሄጄ አይቼዋለው። 'እኔ መሆኔን ሳያውቅ አንድ ጊዜ አብሮን የሚማር ልጅ ጠይቆኝ ያውቃል' አለችኝ። በወቅቱ ጥልፍ እየሠራሁ ነበር የምተዳደረው። የምሠራው ጥልፍም ሳጣ አወያያታለሁ። 'ነይ እኛ ጋር ነገ ሌላ ሰው እንሆናለን። ቀን ሲያልፍ ሌላ ቦታ ሄደን እንኖራለን' ትለኛለች። 'እኔ ቀን ቢወጣልኝም አልተውሽም' ትለኛለች። በኋላ አንድ ክፍል ቤት 30 ብር ተከራየችልኝ። አልጋ እና አንዳንድ ዕቃዎችን አሟላችልኝ። የመጀመሪያ ቀን ምሽት አንድ ትልቅ ሰው መጣ። 'ለስብሰባ ነው ከአዲስ አበባ የመጣሁት' አለኝ። ሁኔታዬን አየና 'ለምን ወደ ሥራው ገባሽ?' ሲለኝ ነገርኩትና አዘነ። 'ቤቱን ስንት ተከራየሽ?' ሲለኝ '30 ብር' አልኩት። ማደር ቢፈልግም ሂድ አልኩት። 'ልትሠሪ አይደለም?' አለኝ። ጓደኛዬን ጠራትና አናገራት። 'ውጣ አለችኝ' አላት። እሷ 'ልትሠሪ አይደል አንዴ?' አለችኝ። ለሊቱንም ሙሉ 'ይህ ህይወት ላንቺ አይደለም' እያለ ሲያወራኝ አደረ። 'ሌላ ሥራ' አለኝ። ምንም ሳናደርግ አደርን። 'በዚህ ህይወትሽና በዚህ ፍርሃትሽ በሽታም አለ' አለኝ። ጓደኛዬ እንኳን ያልነገረችኝን ብዙ ነገር ነገረኝ። ስለኤድስ አንኳን እውቀቱ አልነበረኝም። ሲሄድ ስልክ ስላልነበረኝ የተከራየሁበትን ቤት ስልክ ሰጠሁት። መጀመሪያ ሦስት ሺህ ብር፤ ቀጥሎ ሁለት ሺህ ብር ከዚያም 1500 ብር ላከልኝ። ቤት በመቀየሬ እና የሰውየው ስልክ ስላልነበረኝ በኋላ ላይ ግንኙነታችን ተቋረጠ። ወደ ወሲብ ንግድ የገባሁት የ15 ዓመት ልጅ ሆኜ ነው። አሁን 30 ዓመቴ ነው። 15 ዓመታት በዚህ ሥራ አሳለፍኩ ማለት ነው። እየሠራሁም ትምህርቴን እከታተል ነበር። ከ6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የተማርኩት እየሠራሁ ነው። የመጀመሪያ ቀን ያደርኩት ከፖሊስ ጋር ነው። አንገራግሮኝ ነው ያደረው። ገንዘብ እንኳን አልከፈለኝም። አዲስ መሆኔ ገብቶታል። ከባልደረቦቹ ጋር ሲዞር ቆይቶ ተመልሶ መጣ። መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር። መጥቶ 'ላድር ነው' ሲል 'አይቻልም' ስለው አንገራገረኝ። ገንዘብም አልጠየኩትም። እንዴት እንደሚጠየቅም አለውቅም። አሁን ለራሴ ሳይሆን ሌላም አስተምራለሁ። አደረና ጠዋት 'ማታ እመጣለሁ እሺ' ብሎኝ እንደ ባል ወጥቶ ሄደ። ለጓደኛዬ 'ያደረው ሰውዬ ማታ እመጣለሁ ብሎ ሳይከፍለኝ ሄደ' ስላት፣ ሳቀችና ከአሁን በኋላ ገንዘብ ቀድመሽ ተቀበይ አለችኝ። የመጀመሪያውን ቀን ሳስበው ይዘገነንነኛል። አንዳንዴ ምን ቀን ነበር እላለሁ። እንደዚያ ከሆነ በኋላ ከሥራው ብወጣ እል ነበር። ሆኖም የተሻለ ሰው ሲመጣ መላመድ ይመጣል። ልውጣ ስል ደግሞ የገቢ ጥያቄ ይመጣል። ገንዘብ እያገኘሁ አይደለም በሚል መላመድም አለ። አሁን ከመላመድ እንደ ቤተሰብ ነኝ። ግን ከባድ እና ከባድ ሸክም እንደዚህ ሥራ የሚከብድ የለም። ተነጋግረው ገብተው ገንዘብን አብልጠው ገንዘብ ልጨምርና ያለምንም ኮንዶም ልጠቀም የሚሉ አሉ። ሰውን በገንዘብ እንደሚገዙ። ገንዘብ የነገር ማስፈጸሚያ ነው። ማመኚያ የሚያደርጉት አሉ። እነሱ በገንዘብ አምነው አንተን ጥለው በገንዘብ ቀይረው ሊገዙ ይፈልጋሉ። የተለያየ ነገር መሥራት እችላለሁ ብዬ ጓደኛዬ ጋር ልብስ ስፌት ተለማመድኩ። ጥልፍም እችላለሁ። ግን የስፌት መኪናውን መግዛት አልቻልኩም። ገንዘቡ አይጠራቀምም። የቤት ኪራይ ሁለት ሺህ ብር ነው። የቤት ኪራይ ቅድሚያ እከፍላለሁ። ብዙ ወጪ አለ። እየሰለቸኝም ዛሬ ካገኘሁ ሁለት ወይም ሦስት ቀን እተኛለሁ። አንዱ ጠጥቶ ይመጣል። ሰክሮ፣ ቅሞና መርቅኖ ይመጣል። እኔን በገንዘብ ሊገዛ ይፈልጋል። እናም በጣም ከባድ ነው። ለመናገርም ከባድ ነው። የተለያየ ነገር ይጠይቅሃል። ዛሬ ከሠራሁ ካገኘሁ ሁለት ወይም ሦስት ቀን እተኛለሁ። ዛሬ 300 ብር ባገኝ ነገም ላገኝ እችላለሁ። በ100 ተጠቅሜ ሌላውን መቆጠብ እችላለሁ። ግን መሥራት ስለማልፈልግ በቀጣይ ቀናት አልሠራም። [ወሲብ] ከባልም ጋር ቢሆን እንኳን ሁልጊዜ የሚደብር ይመስለኛል። ሰው ወዶት አይደለም ወደዚህ ህይወት የሚገባው። አካል ጉዳተኛ መሆኔ ደግሞ ሌላ ተጽዕኖ ይፈጥራል። አንዳንዱ አብሮኝ ለማደር ሊጠይቀኝ ፈልጎ ተመልሶ ይሄዳል። 'እንዳይሰማሽ' የሚሉም ብዙ ሰዎች አሉ። 'አንቺ ለምን እንደዚህ ትሠሪያለሽ?' የሚሉኝም አሉ። ሥራው አስጠላኝ። መጀመሪያ ላይ ሁሉ ነገር ሲምታታብኝ ኮብልስቶን እሠራ ነበር። ኮብልስቶን ሰልጥኜ ተቀጥሬ እየሠራሁ ነበር። ሥራው ድንጋይ መፍለጥም ቢሆን ማህበሩ ሲበታተን አቆመ። ዞሬ ቀጠልኩበት። አንድ ቀን ኮብልስቶን አብሮኝ ሲሠራ የነበረ ልጅ ግብት አለና አይቶኝ አማተበና ምንም ሳይለኝ ዞሮ ሄደ። ሌላ ቀን ደውሎ ሰደበኝ። 'ለምን ትሠሪያለሽ? ሲለኝ 'ሃብታም ስለሆንኩ ነው' አልኩት። አሁንም አልፎ አልፎ እየደወለ 'አልወጣሽም? በናትሽ ውጪ' ሲለኝ 'አንተ ሁለት መኪና አለህ። አንዷን ሽጥና ገንዘቡን ስጠኝ ልሥራበት' እለዋለሁ። ይስቃል። ብዙ ነገር ይከብዳል ብቻ። ብዙ ገጠመኝ ይገጥማል። አንዱ አካል ጉዳተኛ መሆኔን አላወቀም። መጽሐፍ እያነበብኩ ገባ። ተነጋገረን። ቤቷ ጠባብ ነች። አልጋ አነጣጥፌ ተኛን። ከተኛን በኋላ የሆነ ነገር ሲፈልግ ልሰጠው ስል 'እንዴ ምን ማለት ነው?' አለ። 'አካል ጉዳተኛ ነሽ እንዴ?' አለ። 'አዎ' ስለው ልብሱን ለበሰና 'ገንዘቤን' አለ። 'ለምን እሰጥሃለሁ? ጊዜ አቃጥለሃል። ሥራ ልሰራ ነው የተቀመጥኩት። ደልቶኝ ወይም ሞልቶኝ አይደለም' አልኩት። 'ምን ልትሠሪ ተቀመጥሽ?' ሲለኝ 'ያንተን ጸጉር ላበጥር' አልኩት። ካልሆነ 'ሂድ' ስለው 'ለምን ጉዳተኛ ነኝ አላልሽኝም?' አለ። 'እንደውም ፖሊስ ጥሪ' አለኝ። ጠራሁና ፖሊስ መጣ ብሬን ሳልይዝ ከቤት አልወጣም አለ። ጃኬቱ አልጋ ላይ ነበር። ፖሊስ ጣቢያ ሄድን። ተቀመጠን ፖሊሱ 'ብር መልሺ ነው የምትላት" ሲለው 'አዎ' አለ። 'ብር ብትመለስልህ ይዘህ ትሄዳለህ?' ሲለው 'አዎ' አለ። 'መታወቂያህን አሳየኝ?' አለው። ከጃኬቱ ኪስ ሊያውጣ ከትከሻው ላይ ጃኬቱን ሲያወርድ ለካ ጃኬቱ መስሎት ትከሻው ላይ ጣል አድርጎት ከእኔ ቤት የወጣው የራሴን ፒጃማ ነበር [ሳቀች]። ውርድ አድርጎ ሴያየው ፒጃማ ነው። አፈረ ምን ይበል። 'ብሩንም አልፈልግም እሄዳለሁ' ሲል ፖሊሱ በነገሩ ሳቀ። 'መታወቂያህን ካላሳየሀኝ አትሄድም' ሲለው 'አንዴ ከተነቃ ይታለፋል' አለ። ጃኬቱ ከቤት ቀርቷል። ፒጃማውን ሰጠኝ ብሩን ተወልኝ። ጃኬቱን በነገታው ወሰደ። ብቻ የጠጣ ሰው ትክክል አይደለም። አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ኮሮና መጣ። ኮሮና በጣም አስከፊ እና አሰቃቂ ነው። ለኤድስ ኮንዶም እጠቀማለሁ። ባለፉት ሰባት ዓመታት በየሦስት ወሩ እመረመራለሁ። ኮሮና ግን ከባድ ነው። ልሥራ ካልኩን ለበሽታው መጋለጥ ይኖራል። አይ ይቅርብኝ ብዬ እንዳልቀመጥ በረሃብ ልሞት ነው። ብዙ ባይሆንም አሁንም እየሠራሁ ነው። ኮሮኖ ሰውና ሰው አያገናኝም። አብሮ ለመተኛት እንደ ኮንዶም ዓይነት የምንጠቀመው ነገር የለም። ከተከራየንባቸው ሰዎችም እየለየን ነው። እኛ የቀዳንበትን ቧንቧ እያጠቡት ነው የሚጠቀሙበት። ምክንያቱም እኛ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ስለምንገናኝ 'እነሱ ከነኩት ዝም ብላችሁ አትንኩት' እየተባለ ከሰው የተገለለንበት ሰዓት ነው። ለኤች አይቪ ኮንዶም አለ። ለዚህ [ለኮሮና] ምንም የለም። ከሰው ነጥሎን በሬን ዘግቼ እውላለሁ። ከሰው አያገናኝም። በሽታው እንደመጣ ኮሮና ኮሮና ሲባል አንደ ሰው መጣ ማስክ (የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል) አድርጌ ስለነበር 'ምንድነው አለኝ?'። 'ባህር ዳር አይደለም የምትኖረው? የሚወራውን አትሰማም?' አልኩት። 'አላወቅኩም ሌላ ነገር ልናደርግ ነው አይደል?' አለኝ። ውሃ አቀረብኩ 'ታጠብ ሳኒታይዘርም አለ ተጠቀም' አልኩት። 'አብሬሽ ልተኛ እያልኩ ነው። ካላወለቅሽው አልተኛም 'አለ። ብሩን ስለፈለግኩኝ 'አበድሩኝ' እና 'ስጡኝ' ብሎ ከመለመን እጄን ታጠብኩ ሳኒታይዘር እኔም እሱም ተጠቀምን። ተኛን። ፊቴን ዞሬ ተኛሁ። ግማሽ ለሊት ላይ 'አንቺን ፈልጌ እንጂ ዞረሽ ከተኛሽስ ልሂድ' ሲል 'እሺ ሂድ' ብዬ የሰጠኝን ብር ሰጠሁት። ወጥቶ ሄደ። ሌላ ጊዜ ደግሞ አንዱ እየሳለ ገባ። ገብቶ ሲስል ሸሸሁት። 'ምን ፈልገህ ነው?' ስለው 'ፈራሽኝ እንዴ?' አለ። 'እያሰላክ ነው' እኮ ነው አልኩት። ያስነጥሳል፤ ያስላል። ወጥቶ ሄደ። '[የጓደኛዋን ስም ጠቅሳ] አንቺ' አልኳት። 'እኔም ጋር መጥቶ ሲያስለው ውጣ አልኩት' አለች። ሰውየው ተመለሰና 'ኮሮና አንቺን እንጂ እኔን አይዘኝም' አለ። በቀላሉ የሚለይበት ምልከት የለውም። ኤድስ ማለት ነው። ምልክት ወይም ቁስል ቢሆን እሸሻለሁ። እያስነጠሰ ግን አላስገባውም። ሁሌም ማስክ እጠቀማለሁ። ግን ብዙዎች 'ለምን ትጠቀሚያለሽ?' ይላሉ። እኔ ከቤት ወጥቼ ስሄድም ሁሌም እጠቀማለሁ። ማንንም በእጄ አልነካም። ደንበኞች አሉኝ። ግን በኮሮና ምክንያት አይመጡም። ብዙ ሰው ራሱን ይፈልገዋል። አሁን ምንም አንሠራም። በወር 400 ብሠራ ጥሩ ነው። አንድ ጓደኛዬ ካላት እሷ ጋር ምሳ በልቼ ቡና ጠጥቼ ልውል እችላለሁ። እሷም እኔ ዘንድ። ቤት ኪራይ ምናምን እያሉ የአካባቢው ወጣቶችም እየሰበሰቡ ካለው እያዋጡ የአንድ ወር የቤት ኪራይ ከፍለውልናል። የምሠራው ነገር ባገኝ ከዚህ ህይወት እወጣ ነበር። ብዙ ነገር አስብ ነበር። ተቀማጭ ቢኖረኝ እቁብ ገብቼ እንደዚህ ባደርግ እላለሁ። ዕቁብ እንዳልገባ ማህበረሰቡ በየራሱ ጭንቅ ላይ ነው። ያላቸው ጋር ደግሞ እንዳልገባ ደግሞ ማን ዋስ ይሆነኛል። 'በልታ እልም ብትልስ?' ይላሉ። ወር ደሞዝተኞች አሉ፤ ከእነሱ ጋር ልግባ ለማለት ደግሞ ያላቅም መንጥጠል ነው። የሚያበረታታም የለም።
49651467
https://www.bbc.com/amharic/49651467
"ሰዓረ ሙዚቃ በጣም ያዝናናው ነበር" ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ
ሰኔ 15፣ 2011 ዓ. ም. የደረሰው ጥቃት፤ ከተሾሙ አንድ ዓመት ከጥቂት ቀናት ብቻ የሆናቸውን የአገሪቱን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን ሕይወት ቀጥፏል። ከሳቸው በተጨማሪ በጡረታ የተገለሉትና በወቅቱ በጄኔራል ሰዓረ ቤት የነበሩት ሜጄር ጄኔራል ገዛዒ ከጠባቂያቸው በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የሚመለከታቸው አካላት አስታውቀዋል።
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ጥቃቱ በደረሰባቸው ሰዓት አማራ ክልል የ"መፈንቅለ መንግሥት" ሙከራን ለማክሸፍ ሲሠሩ እንደነበርም ተገልጿል። በተመሳሳይ በአማራ ክልል በዛኑ ቀን በደረሰ ጥቃት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንንና አማካሪያቸው አቶ እዘዝ ዋሴና የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ምግባሩ ከበደም ሕይወታቸውን አጥተዋል። ኢትዮጵያ ብዙ ክስተት የተከናወነበትን 2011 ዓ. ም. ለማገባደድ አንድ ቀን በቀራት በዛሬው እለት፤ በድንገት ሕይወታቸው የተቀጠፈውን የአገሪቱን ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ቢቢሲ አስታውሷቸዋል። የሚቀርቧቸውን በመጠየቅ ከውትድርና ጀርባ ያለውን ሕይወታቸውን ቃኝቷል። ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ • በሃየሎም ይምሉ የነበሩት ጄነራል ሰዓረ መኮንን ማን ናቸው? የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ- ጓደኛና የትግል አጋር ከጄኔራል ሰዓረ መኮንን ጋር ትውውቃችሁ እንዴት ተጀመረ? ጄኔራል ፃድቃን፡ ከጄኔራል ሰዓረ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው እኔና ጄኔራል ሃየሎም የምንመራት ኃይል 73 የምትባል ሻምበል ነበረች፤ እሱ እዛው ተመድቦ መጥቶ ነው። እኔ የሻምበሏ ኮሚሳር ነበርኩ፤ ጄኔራል ሃየሎም ደግሞ ኮማንደር ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅነውም በዚሁ አጋጣሚ ነበር። ከጄኔራል ሃየሎም ጋርም በጣም ጥሩ የሚባል ግንኙነት ነበረው። የሃየሎምን አመራርና ወታደራዊ ብቃት በጣም ነበር የሚያደንቀው። የአስከሬን ሽኝት በተደረገበት እለት • የጄነራል ሰዓረ ቀብር አዲስ አበባ ሳይሆን መቀሌ ይፈጸማል • ራሱን አጥፍቷል የተባለው የጄነራል ሰዓረ ጠባቂ ሆስፒታል እንደሚገኝ ተገለፀ በትግል ወቅት ግዳጅ ላይ ካልሆኑ ምን ያዝናናቸው ነበር? ጄኔራል ፃድቃን፡ልክ እንደ ሁላችንም ሙዚቃ በጣም ያዝናናው ነበር። የትግርኛ ሙዚቃ ደግሞ መስማት ያስደስተዋል። በረሀ ላይ በነበርንበት ወቅት፤ እንዲሁም ከትግል በኋላ አዲስ አበባ መንግሥት ከመሰረትን በኋላ የተለያዩ በአሎች እናዘጋጃለን፤ በዚህ ወቅት ወደ መድረክ መጥቶ መጨፈርም ይወድ ነበር። ሁሌም ቢሆን አዎንታዊ አስተሳሰብ ይዞ ነው የሚንቀሳቀሰው። ልክ እንደ ማንኛውም ታጋይ እግር ኳስም ይወድ እንደነበር አስታውሳለው። ምንም እንኳን አብዛኛውን ጊዜያችንን በወታደራዊ ኃላፊነቶች ብናሳልፍም፤ አንዳንዴ ሰብሰብ የማለት እድሉን ስናገኝ ኳስ የምንጫወትባቸው ጊዜያት ነበሩ። በሬድዮም ቢሆን ስፖርታዊ ውድድሮችን የመከታተል እምብዛም እድሉ አልነበረንም። የትግል ሕይወታቸውስ ምን ይመስል ነበር? ጄኔራል ፃድቃን፡ ጄኔራል ሰዓረ የሚሰጠውን ማንኛውም አይነት ኃላፊነት በትልቅ መነሳሳትና ፍላጎት በአግባቡ የሚወጣና ከእሱ በኩል ምንም አይነት ጉድለት እንዳይኖር አድርጎ ጥንቅቅ አድርጎ ነበር የሚሠራው። ከዚህም ባለፈ ከእሱ ሥራ መስክ ባለፈ በተጓዳኝ ሥራ መስኮች ችግር እንዳይፈጠር ቅድመ ዝግጅት የሚያደርግ ወታደር ነበር። ሰዓረ ገና ተራ ወታደር እያለ ነው የማውቀው እና ሁሌም ቢሆን ነገሮችን ቀድሞ በጥልቀት ለማወቅ የሚጥርና ጥንቅቅ አድርጎ የሚዘጋጅ፤ ምንም አይነት ነገር ለእድል የማይተው ወታደር ነው። ጦርነት ውስጥ ከገባ በኋላ ደግሞ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውም ጉዳይ በማንኛውም ሰአት ማከናወን የሚችል ሰው ነው። ያልተጠበቀ ነገር እንኳን ቢያጋጥም ሰዓረ በምንም ሁኔታ ሳይደናገጥ ነው እርምጃ ለመውሰድ የሚሞክረው። መደንገጥ የሚባል ነገር አልፈጠረበትም። በቃ ጀግና ወታደር ነው። ትልቅ የአመራር ብቃት ያለው ወታደራዊ መሪም ነው። የጄኔራል ሰዓረ መኮንን ባለቤት የምግብ ምርጫቸውስ? ጄኔራል ፃድቃን፡ በረሃ ላይ እያለን የምንመርጠው ምንም አይነት ምግብ አልነበረም። ያገኘነውን ነበር የምንበላው። ነገር ግን ደርግን ጥለን ወደ ሥልጣን ከመጣን በኋላ በተለይ ደግሞ ባህላዊ ምግቦችን ያዘወትር ነበር። አንድ የማልረሳው ግን በተለይ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት እሱ ወደነበረበት ግንባር በምመላለስበት ወቅት ሰብሰብ ብለን ጥብስ እንበላ ነበር። ጠዋትም ማታም ጥብስ ብንበላ ግድ አይሰጠንም ነበር። የእንጀራ ፍርፍር እና እንቁላል ፍርፍርም የምንበላባቸው ጊዜዎችን አስታውሳለሁ። ከትግል በኋላ ግን ሁሉም የየራሱ ምርጫ ሊኖረው ይችላል። በትግል ወቅት የማይረሱት አጋጣሚ ምንድን ነው? ጄኔራል ፃድቃን፡በአግአዚ ኦፐሬሽን ወቅት እጅግ አስገራሚ ተልዕኮ ነበር የተወጣው። በ1976 እና 1977 ዓ. ም. አንድ ሻለቃ ምሽግ ይዞ ተቀምጦ በጣም ተቸግረን በነበረበት ወቅት፤ ሻለቃውን ለመደምሰስ ከፍተኛ ጀግንነት በማሳየት ትልቅ ሥራ ሠርቷል። ከሁሉም በላይ ግን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ቡሬ ግንባር ላይ በሃገር ደረጃ አጋጥሞ የነበረውን አደጋ በአስገራሚ ሁኔታ የፈታ ትልቅ ጀግና መሪ ነው። • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን ሰላም (አሸናፊ)- የጄኔራል ሰዓረ የታላቅ እህት ልጅ ጄኔራል ሰዓረ በቤተሰቡ ውስጥ እንዴት ይታያሉ? አሸናፊ፡ ከቤተሰቡ ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው። ሳቅ እና ጨዋታ የሚወድ ሰው ነው። ማንኛውም ሰው ሊጠይቀው ሲመጣ እንደ አንድ ትልቅ መሪ ሳይሆን እንደ እኩያ ነው የሚያጫውተው። ቀልድ ማውራት ይወዳል፤ በጣም አዝናኝ ሰው ነበር። ወደ 9ኛ ክፍል እንዳለፈ የ15 አመት ልጅ ሆኖ ነው ትግሉን የተቀላቀለው። እሱ በ1969 ዓ. ም. ወደ ትግል ሲሄድ እኔ ደግሞ በዓመቱ በ1970 ዓ. ም. ተወለድኩኝ። ነገር ግን ስለሱ ከወላጆቼ ከሰማሁት ልጅ እያለ ከጓደኞቹ ጋር ጠመንጃ በ25 ሳንቲም እያስያዙ ተኩስ ይለማመዱ ነበር ብለውናል። የጄኔራል ሰዓረን ስብዕና እንዴት ትገልፀዋለህ? አሸናፊ፡ ለአላማው ታማኝ፣ ግለኝነት የማይወድ፣ መጥፎ ነገር ሲያይ የሚበሳጭ አይነት ሰው ነው። ለአላማው ጽኑ፣ ለማይዋሽና ማይሰርቅ ሰው ደግሞ ትልቅ ክብር ይሰጣል። ለእኔ፣ አጎቴም ወንድሜም ነው። እሱ ነው ደብተር እና ልብስ እየገዛ ያስተማረኝ። የሁልጊዜም ምኞቱ ኢትዮጵያን ሰላማዊ እና ታላቅ አገር ሆና ማየት ነበር። ሕዝቡ ከድንቁርና፣ ድህነት እና ኋላ ቀርነት ተላቆ እንዲበለጽግም ይመኝ ነበር፤ ያ ነበር የትግላቸው ትልቁ አላማም። እሱ የኔ የሚለው አንድም ኃብት አላፈራም። ለልጆቹ የተወላቸው ነገር ቢኖር ጡረታውን ነው። • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን የሚታወቁት በወታደርነታቸው ነው። ሌላ ሙያ ይመኙ ነበር ብለህ ታስባለህ? አሸናፊ፡ ወታደር ከመሆን ውጪ የሚመኘው ወይም የሚወደው ሙያ ይህ ነው ማለት አልችልም። ልጅ እያለ ነው ትግሉን የተቀላወለው። እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ የመጣ ሰው ነው፤ እንደ እድል ሆኖ እሱ በሕይወት ተርፎ የደረሰበት ደረጃ ደርሶ ነበር። ትግሉን ከተቀላቀለ በኋላ ከነበረው ፈታኝ ሁኔታ አንጻር እዚህ ደረጃ ይደርሳል የሚል እምነት አልነበረንም። ያዘኑበትን ቀን ታስታውሳለህ? አሸናፊ፡ በከፍተኛ ሁኔታ ያዘነበት ቀን ቢኖር ጄነራል ሃየሎም ሞተ ተብሎ የተረዳበትን ቀን ነው። ሁሉንም የሕወሃት ታጋዮችን ያደንቃል፤ በይበልጥ ግን ለነሃየሎም፣ ኩሕለን እና ዳንቡሽ የተለየ ቦታ አለው።
news-49800373
https://www.bbc.com/amharic/news-49800373
የቀድሞ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የሞቱት "በካንሰር" ነው ተባለ
የቀድሞ የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ለካንሰር ህክምና ይደረግላቸው የነበረው የኬሞቴራፒ ህክምና ሲቋረጥ እንደሞቱ የአገሪቱን ፕሬዝዳንት ኤመርሰንን ምናንጋግዋንን ጠቅሶ የአገሪቱ ሄራልድ ጋዜጣ ዘግቧል።
ሙጋቤ ይታከሙበት የነበረው የሴንጋፖሩ ሆስፒታል ዶክተሮች የሙጋቤ ኬሞቴራፒ እንዲቋረጥ ያደረጉት በሁለት ምክንያቶች እንደሆነ ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ገልፀዋል። እሳቸው እንዳሉት ሮበርት ሙጋቤ እንድሜአቸው የገፋ በመሆኑና ካንሰሩም በሰውነታቸው ተስፋፍቶ ስለነበር ኬሞቴራፒው ብዙ ጠቀሜታ ስላልነበረው እንዲቆም ተወስኗል። ዚምባብዌን ከነፃነት ጀምሮ ለ37 ዓመታት የመሩት የ95 ዓመቱ ሮበርት ሙጋቤ በመፈንቅለ መንግሥት ከስልጣን የተወገዱት እአአ በ2017 ነበር። ለወራት ተኝተው ይታከሙ በነበረበት የሴንጋፖር ሆስፒታል ህይወታቸው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነበር። ከዚምባብዌ መዲና ሃራሬ ወጣ ብሎ በሚገኝና በግንባታ ላይ በሚገኝ የነፃነት ታጋዮች የመቃብር ስፍራ እንደሚቀበሩም ተገልጿል። • ሮበርት ሙጋቤ ሆስፒታል ከገቡ ወራት እንዳለፋቸው ተነገረ • ትናንት ሕልፈታቸው የተሰማው ሮበርት ሙጋቤ ጥቅሶች
53424326
https://www.bbc.com/amharic/53424326
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ መያዝ በባለሙያ እይታ
ከህዳሴ ግድቡ አካባቢ የተገኙ ሳተላይት ምስሎች የግድቡ የውሃ መጠን እየጨመረ መሆኑን ያሳያሉ፤ በርካቶች ግድቡ ውሃ መሞላት ጀምሯል ሲሉ ጥያቄ ቢያቀርቡም የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ግን በይፋ የተጀመረ ነገር የለም ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
አዲሱ የሳተላይት ምስል የተወሰደው ሰኔ 20/2012 እና ሐምሌ 5/2012 ሲሆን ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን በተከታታይ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል። የግድቡ ውሃ መጨመርንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በውሃ ፖለቲካ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን ያደረጉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ በላቸው አነጋግረናቸዋል። ግድቡ ውሃ መያዙን ማረጋገጣችንን ተከትሎ ከግብጽ በኩል የተለየ ምላሽ መጠበቅ እንችላለን? ምንም የተለየ ምላሽ አይኖርም። ያው ሌላ ጊዜም እንደሚሉት ማስፈራራት የተለመደው ካልሆነ በስተቀር ምንም ማድረግ አይኖርም። ያው በአረብ አገራት በኩል ጫና ሊያሳድሩብን ይሞክሩ ይሆናል። ድንበር አካባቢ የሚኖሩ ግጭቶችን በማባባስ ወደዚያ ውጥረት ሊያስገቡን ይሞክሩ ይሆናል። አገር ውስጥ ያሉትን አንዳንድ የተቃዋሚ ድርጅቶችን ደግሞ አሁን ያለውን ሁናቴ ተጠቅመው እርስ በእርሳችን ማተራመስ ይፈልጉ ይሆናል። ከዚያ በተረፈ ግን በቀጥታ ጥቃት የሚባል ነገር ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም። እርሱ በተግባር ሲታይ የማይቻል ነው። ኢትዮጵያና ግብጽ ግን ግድቡን በተመለከተ ስምምነት ለይ መድረስ አይችሉም? አሁን የሚያጣላው ነገር እኮ ግድብ ውሃ መሙላቱ አይደለም። ከተሞላ በኋላ የሚለቀቀው ውሃ ነው ትልቁ ችግር። እነርሱ የሚፈልጉት ከተሞላ በኋላ የሚለቀቀው ውሃ መጠኑን አሁኑኑ እንወቀው ነው። እኛ ደግሞ ይህንን ግድብ ብቻ አይደለም የምንሰራው ከግድቡ በላይ ሌሎች ወደ ፊት ለምንሰራቸው ፕሮጀክቶች ውሃ ሲያስፈልገን መጠቀም አለብን ስለምንል አሁኑኑ ይህን ያህል ውሃ እንለቅላችኋለን ብለን ቃል መግባት የለብንም ነው። ለነገሩ እርሱ የኛ የሱዳንና የግብጽ ጉዳይም አይደለም። የ11 የተፋሰስ አገራት ጉዳይ ስለሆነ ብቻችንም የሚለቀቀው ውሃ ላይም መስማማት አይገባንም። ሌሎቹ የተፋሰሱ አገራት ከጎናችን የቆሙትም ማግለልና ማስቀየም ስለሚሆንብን እርሱንም አሁን ቃል መግባት የለብንም። ድርቅ ሲኖር የሚለቀቀው የሚሉት ጉዳይም እርሱም ለሚፈጠረው ድርቅ እኛ ኃላፊነት አንወስድም። ለነገሩ ድርቅ የሚፈጠረው ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ እነርሱ ጋር አይደለም። ስለዚህ ድርቅ በተፈጠረ ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ የሚቀንሰው ውሃ የእነሱን ውሃ ለማካካሻ እንድናደርገው ነው የሚፈልጉት። እርሱ ራሱ ነው እንጂ የሚያጣላን መሙላቱ አይደለም። ከአራት እስከ ሰባት አመት መሙላቱም አይደለም የሚያጣላን። ከተሞላ በኋላ ያለው የውሃ አለቃቀቅ ነው የሚያጣላን። እርሱ ደግሞ ከብሔራዊ ጥቅማችን አንጻር ልናደርገው የምንችለው አይደለም። ወደፊት በአባይ ወንዝ ላይ ያለንን ነገር ሁሉ የሚገድብ ነገር ስለሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በጎርጎሳውያኑ 1959 የፈረሙትን፣ ብቻችንን እንጠቀማለን የሚሉትን፣ እውቅና መስጠት ነው የሚሆነው እና ኢትዮጵያ ወደዚህ መግባት አትፈልግም አሁን። ኢትዮጵያግድቡን መሙላት መጀመሯ ግብጽ እንድትለሳለስ ያደርጋል ብለው ያስባሉ? አዎ። የዘንድሮው ውሃ መሙላት ምንም ማለት አይደለም። አንደኛ 4.9 ቢሊዮን ኪዮቢክ ሜትር ነው የምንሞላው። ይህ ደግሞ ከአባይ ዓመታዊ ፍሰት አንድ አስረኛው ነው። ይህ ማለት ደግሞ ዘንድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንጀምራለን ማለት አይደለም። ምክንያቱም የሚቀጥለው ዓመት የምንጠብቀው ሌላ 13.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር አለ። የሁለቱ ድምር ውጤት ነው የኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም የሚፈጥርልን። እና እኛ አሁን የምናደርገው ያለው በሚቀጥለው አመት ብዙ ውሃ ከምናስቀርባቸው ትንሽ ትንሽ በማድረግ በሁለት ዓመት ከፍለነው ነው። እነርሱን የሚጠቅም ነው። ሁለተኛ ግብጾች አሁን የሚቸግራቸው ለህዝባቸው የገቡት ቃል ነው። እኛ ታሪካዊ መብት አለን፣ ይህ ግድብ እኛ ስልጣን ላይ እያለን አይሞላም በሚል የገቡት ቃል ነው የሚያስቸግራቸው። እንዳውም ግድቡ ውሃ መሞላቱን በአደባባይ እንዲነገር የሚፈልጉት አይመስለኝም። ምክንያቱም ግድቡን እስኪሞሉት ድረስ ምን ትሰሩ ነበረ የሚል ጥያቄ ሕዝቡ ያነሳባቸዋል። እናም እነርሱ ፊት ለፊት እያሳወቁ ባይሆን ዘንድሮ የሚያዘው ውሃ ብዙ የሚጎዳን አይደለም እያሉ ሕዝባቸውን ቢያረጋጉ ነው የሚሻላቸው። መሙላታችን የማይቀር ስለሆነ እነርሱንም ችግር ውስጥ እንዳያስገባቸው የሚሞላው ውሃ ብዙም ለውጥ የሚያመጣ አይደለም በማለት ሕዝባቸውን ማረጋጋት እና ይህንን መቀበል ነው የሚያዋጣቸው። በዚህ በሁለቱ አገራት ድርድር መካከል የሱዳን ሚና እየተረሳ መጥቷል የሚሉ ሃሳቦች ይነሳሉ፤ ሱዳን ትልቅ ሚና እንዳላት ብዙዎቹ ስለሚያምኑ እርሶ በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ? ድሮም ቢሆን ግብጾች የሚሞክሯቸው ነገሮች ነበሩ። ዋናው የውሃ ተጠቃሚ ግብጽ ናት። ዋናው ውሃ አመንጪ አትዮጵያ ናት።እና ትልቁ ጉዳይ በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ስለሆነ ያለው እናንተ መካከል ላይ ሆናችሁ አደራድሩን ነው የሚሏቸው። እርሱ አደገኛ ጉዳይ ነው። እንደ ባለጉዳይ ያለማየት ነገር ነው። በአባይ ተፋሰስ ሱዳን አይደለችም ሩዋንዳም፣ ብሩንዲም፣ አስራ አንዱም አገራት ባለጉዳይ ናቸው። ስለዚህ ሱዳን ተመልካች የምትሆንበት ጉዳይ የለም። እነርሱም አይቀበሉትም። ምንድን ነው አሁን ሱዳን ውስጥ ያለው የጥምር መንግሥት ስለሆነ ያለው፣አንድ አይነት አቋም ስለማይዝ የተደላደለ እና በሁለት እግሩ የቆመ መንግሥት ስላልሆነ፣ እዚህ መንግሥት ላይ ደግሞ ጫና መፍጠር ስለሚችሉ እርሱን እያገለሉ መቀጠል ይፈልጋሉ። ግን ሱዳን አደራዳሪ መሆን አትፈልግም፤ መሆንም አይገባትም። ግን የቆየ ፍላጎት ነው። ግብጾች በተደጋጋሚ ሲሞክሩት የነበረው ነው። በተናጠል ከኢትዮጵያ ጋር ለመገናኘት ሲሞክሩ ኢትዮጵያ አይሆንም እያለች የቆየችው ነገር ነውና ሱዳን ባለጉዳይ ናት። ኢትዮጵያና ሱዳን አንድ አይነት አቋም የሚይዙ ከሆነ ይጠነክሩብናል ስለሚሉ ነው ለመከፋፈል እንደተደራዳሪ ሳይሆን እንደ አደራዳሪ ሊያይዋት የሚፈልጉት። ግብጽም ሆነ ኢትዮጵያ የራሳቸው የሆነ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት አላቸው። ግብጽ ሊቢያ ድረስ በመሄድ ከቱርክ ጋር ግጭት ውስጥ እንዳለች ይሰማል። ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰሞኑ የተፈጠረውን ሁኔታ መጥቀስ ይቻላል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ለግብጽ እንደ እድል ሊቆጠር የሚችል ይሆናል ብለው ያስባሉ? ማሰባቸው አይቀርም። ለነገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ጀርባ ሁል ጊዜ ግብጾች እጃቸው አለበት። የኤርትራ ነጻ አውጪ መመስረት ላይ፣ ከድሮ ጀምሮ ከ1950ዎቹ፣ 60ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥቱ ነዋይ ወቅት የነበረው መፈንቅለ መንግሥት ላይ ወታደር እስከ መላክ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሁሉ እጃቸው እንዳለበት እሙን ነው። እኛ የአገራችንን ጉዳይ በአገራችን መፍታት ነው። የውስጣችን ጉዳይ የውስጥ ነው፤ እኛው ራሳችን መፍታት አለብን። ለእነርሱ ግን መግቢያ ቀዳዳ መፍጠር የለብንም። እና ይህንን ለመጠቀም መፈለጋቸው ምንም ጥርጥር የለውም። በተለያየ መንገድም ይሞክሩታል። . . .የራሳችን ችግር በራሳችን ከፈታን የእነርሱ ተላላኪ የሚሆን ኃይል ማሳጣት ይቻላልና በውስጣችን ያለውን ነገር ነው መስራት ያለብን። አላስፈላጊ ጉዳዮችን እየመዘዝን፣ እርሱን እያጎላን፣ ለእነርሱ ቀዳዳ መክፈት አይገባንም። እርሱን ነው መከላከል ያለብን በአገራችን። የውስጥ ጥንካሬ ነው ዋናው ነገር፤ እነርሱ እጃቸውን የሚያስገቡበትን ቀዳዳ መዝጊያው መንገድ። የተፋሰሱ አገራት በቅርብ አመታት ውስጥ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ብለው ያምናሉ? አሁን እኛ ትንሽ ጠንክረን መስራት ያለብን ነገር የላይኛው ተፋሰስ አገሮች በተለይ ብሩንዲንና ኬንያን የተስማሙበትን ነገር በአገራቸው ፓርላማ ቢያፀድቁትና የአራቸው ህግ አካል ቢያደርጉት፣ የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን ቢቋቋም፣ የውሃ ድልድሉ ይጀመራል። እርሱ እንግዲህ አስገዳጅ ዓለም አቀፍ ህግ ውስጥ የሚካተት ነው የሚሆነው።ያ መፍትሄ ይሆናል። አሁን ግብጾች እየተከላከሉ ያሉት ወደዚያም እንዳንደርስ ነው። ምክንያቱም እኛ ውሃ የማያስቀር ኃይል ማመንጫ እየሰራን እንኳ እንዲህ ከጮሁ የውሃ ድርሻ የሚያስቀር ነገር ከተፈጠረ ምን ሊሉ እንደሚችሉ ከአሁኑ መገመት ይቻላል። መፍትሄው ግን የላይኛው የተፋሰስ አገራት የጀመሩትን ነገር አጠናክረው እነዚህ ብሩንዲና ኬንያ በፓርላማ አፀድቀው የአገራቸው ህግ ቢያደርገት፣ የግብጾች ጫና ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ አይደለም ከሌሎቹ የላይኛው የተፋሰሱ አገራት ጋር ይሆናል ቅራኔያቸው። Interactive A large reservoir is beginning to form behind the dam 12 July 2020 26 June 2020 ስለዚህ ያኔ በአፍሪካ ሕብረትም የተሻለ ተሰሚነት ይሰጠናል። የሚያሳዝነው አሁን አፍሪካ ሕብረት ድረስ መጥተውም የቅኝ ግዛት ውሎችን እንዲፀድቅላቸውና በዚያ እንዲጠቀሙ መሞከራቸው ነው። ይኼ ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን ያላቸውን ንቀት ማሳያ ተደርጎ ነው የሚታየው እና አፍሪካውያንን በዚህ ጉዳይ ማነሳሳት በጣም ቀላል ጉዳይ ነው። ስለዚህ በተፋሰሱ አገራት በኩል በፓርላማ አፀድቀን አስገዳጅ ሕግ አድርገን ከጨረስነው ይኼ ሁሉ አካኪ ዘራፍ ይቆማል። ግብጽ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት ሄዳ ጥያቄዋን አቅርባ ነበር ፤ ምክር ቤቱ ግን ወደ አፍሪካ ሕብረት መምራቱን መርጧል። የዚህንስ ጥቅም እንዴት ልንተረጉመው እንችላለን? የፀጥታው ምክር ቤት እኮ ይኼ ለአካባቢው ስጋት አይደለም ብሎ ስለሚያምን ነው ወደ አፍሪካ የመለሰው። ሁለተኛ ወደ አፍሪካ ሕብረት ቢመለስም አሜሪካና የዓለም ባንክ አሁንም በታዛቢነት እየተሳተፉ ናቸው። ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ወደ አፍሪካ ተመልሷል ማለት አይቻልም። ግን እስከዛሬ በአረብ አገሮች፣ በአውሮጳ አገራት፣ በአሜሪካ ሲንጠላጠሉ የነበሩትን በተወሰነ ደረጃ አስጥለናቸዋል። እና ለእኛ ይህ ትልቅ ነገር ነው። አሁንም ግን አፍሪካውያንን ማስተባበር፣ የላይኛው ተፋሰስ አገራትን በማስተባበር ወደ ተሻለ ደረጃ መውሰድ የምንችልበት እድል ይከፍታል። ከዚህ በኋላ የፀጥታው ምክር ቤትም ይህንን ጉዳይ ለማየት ፈቃደኛ አይሆንም። እዚያው ጨርሱ ነው የሚሏቸው። እዚህ ደግሞ እኛ የተሻለ አቋም ላይ ነው ያለነው። የቅኝ ግዛት ውሎች የአፍሪካ ሕብረት እንዲያፀድቅላቸው አይጠበቅም። የኢትዮጵያ መንግስት የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ፣ የታችኛውና የላይኛው ተፋሰስ አገራትን በማስተባበር ረገድ ምን ማድረግ ነው ያለበት ይላሉ ታድያ? አሁን በተለይ አሜሪካ የነበረችበትን ድርድሩ ከተቋረጠና ኢትዮጵያ ያንን ስምምነት አልፈርምም ካለች በኋላ ያለው አቋም ጥሩ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥትን የምመክረው ባለሙያዎቹ ተደራዳሪዎቹ የሚሉትን በሙሉ ቢሰማና በዚያ መንገድ ቢንቀሳቀስ ነው። . . . እስከዛሬም ድረስ ጠንክረው እዚህ ያደረሱት ጥሩ ጥሩ ባለሙያዎች አሉን። [መንግሥት]እነርሱን ምክር መስማት አለበት። ወሳኙ ነገር እዚያ ላይ ነው ያለው።
news-49577800
https://www.bbc.com/amharic/news-49577800
ኢትዮጵያ፡ የግብረ ገብ ትምህርት ለምን ያስፈልገናል?
በቅርቡ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያስነሱና ሲያከራክሩ የነበሩ ምክረ ሃሳቦችን ይዞ በወጣው የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ በዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ቆይታ ግብረ ገብ፣ ክሪቲካል ቲንኪንግ፣ ኢንተርፕርነርሽፕ፣ .... እና ሌሎችም የትምህርት ዓይነቶች እንዲሰጡ በምክረ ሃሳብ ደረጃ ቀርቧል።
እነዚህ የትምህርት ዓይነቶች ሊሰጡ መታሰባቸውን በበጎነት ያነሱት እንዳሉ ሁሉ የትምህርት ዓይነት ከማብዛት ውጭ ፋይዳ የላቸውም ሲሉ የኮነኑትም አሉ። ማን ነው የሚሰጣቸው? በምን ያህል ጥልቀት ነው የሚሰጠው? ለምን ያህል ጊዜ ነው መሰጠት ያለባቸው? ከየት ነው መጀመር ያለበት? የሚሉትም በጉዳዩ ላይ ከተነሱ መሠረታዊ ጥያቄዎች ውስጥ ይገኙበታል። በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታው ሊሰጡ ከታሰቡ የትምህርት ዓይነቶች አንዱ ደግሞ ባለፉት ዘመናት ሲሰጥ የነበረው የግብረ ገብ ትምህርት ነው። • ሥነ-ምግባር የተላበሱ ሮቦቶች • ወላጆች ለልጆቻቸው የሚመኟቸው ኢትዮጵያዊ መምህር 'The role of civic and Ethical education in democratization process of Ethiopia: challenge and prospects'በሚል በዘንድሮው ዓመት የታተመ ጆርናል እንደሚያስረዳው የሥነ ምግባር ትምህርት 'የሞራል ትምህርት' በሚል ለመጀመሪያ ጊዜ በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ተካቶ መሰጠት የጀመረው በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነው። ፅሁፉ ላይ እንደተጠቀሰው በወቅቱ የነበረው የሞራል ትምህርት ዓላማ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን ኃይማኖት ሥርዓትን መሠረት በማድረግ በሥነ ምግባር የታነፁ ትውልዶችን መፍጠር ነበር። ንጉሱን የሚያከብሩ፣ የሚያገለግሉ 'ፈሪሃ እግዚሃብሔር' ያደረባቸው ተማሪዎችን ለማውጣትም የሚያንፅ እንጅ የዲሞክራሲ ሥርዓት ላይ ትኩረት ያደረገ እንዳልነበር በጥናቱ ላይ ተወስቷል። ከዚያም የደርግ መንግሥት በ1966 ዓ.ም ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ የማርክሲስት - ሌኒኒስት ርዕዮተ ዓለም ሥር የተለያዩ ፖሊሲዎች ተቀርፀው በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ተካተው ይሰጡ ነበር። በዘመኑ 'የፖለቲካ ትምህርት' በሚል ይሰጥ የነበረው የትምህርት ዓይነት የሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለምን የማስረፅ ዓላማ ነበረው ይላል- ጥናቱ። ጥናቱ ይሰጡ በነበሩት የትምህርት ዓይነቶች ውስጥም ሰብዓዊ መብት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ነፃነት የመሳሰሉ ሃሳቦች የተካተቱበት እንዳልነበር በመግለፅ በሁለቱም መንግሥታት የነበረው የሥነ ምግባር ትምህርት የርዕዮተ ዓለም ትምህርት እንጂ ዲሞክራሲያዊ የሆኑ የሥነ ምግባር ትምህርት አልነበሩም ሲል ያትታል። ከዚያ በኋላ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላም 'የሥነ ምግባርና ሥነ ዜጋ ትምህርት' በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ተካቶ እየተሰጠ ይገኛል። ይሁን እንጂ የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ተማሪዎችን በሥነ ምግባር በማነፅ ረገድ ውጤታማ እንዳልሆነ ጥናቱ ከነ ምክንያቶቹ ነቅሶ ያሳያል። የዲሞክራሲ በተግባር አለመኖር፣ የባለሙያዎች እጥረት፣ ለትምህርቱ ያለው አመለካከት፣ የትምህርቱ ይዘት እና ሌሎች ተግዳሮቶች ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናቸው። በመሆኑም ይህም እንደ ቀደመው ዘመን ርዕዮተ ዓለምን የማስረፅ እንጅ ተማሪዎችን በሥነ ምግባርና በሞራል አንፆ ማውጣት የሚያስችል አይደለም የሚል ትችት የሚስተናገድበት ሆኗል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋም የሥነ ምግባርና ሥነ ዜጋ ትምህርት[ሲቪክ ኤዱኬሽን] ትምህርት መልካም ቢሆንም ግብረ ገብነትን ሊተካው አይችልም ሲሉ ከሚሟገቱት አንዱ ናቸው። "የግብረ ገብ ትምህርት ድሮ ልጅ እያለን ከሁለተኛ ክፍል ወይም ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ እንማር ነበር ፤ በመሆኑም ተመልሶ መሰጠት አለበት " ሲሉ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ ቀረበውን ምክረ ሃሳብ ይደግፉታል። ይህም ብቻ ሳይሆን ክሪቲካል ቲንኪንግ እና ሌሎችም የትምህርት ዓይነቶች መካተታቸው ጥሩ ነው የሚል አቋም አላቸው። "የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታው በጎ በጎ ነገሮች ተካተውበታል" ሲሉም አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ሥነ ባህሪ ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መስከረም ለቺሳም በሃሳቡ ላይ ተቃውሞ የላቸውም። ነገር ግን ግብረ ገብ በትምህርት ቤት ውስጥም ሆነ በከፍተኛ ተቋም ውስጥ በየትምህርት ዓይነቶቹ ውስጥ ገብቶ፣ አኗኗራችንም ውስጥ የሚገለፅ እየሆነ መሰጠት አለበት የሚል አቋም አላቸው። ግቡን እንዲመታም ከተለያየ አቅጣጫ በጥንቃቄ መታየት እንዳለበት ይመክራሉ። የግብረ ገብነት ትምህርት ለምን አስፈለገ? "አሁን ያለነው ባቢሎን ውስጥ እኮ ነው፤ በጎና እኩይ የሆነን ነገር መለየት አቅቶናል" የሚሉት ዶ/ር ዳኛቸው የግብረ ገብ ትምህርት እንደገና መተዋወቅ እንደነበረበት በማንሳት በምክረ ሃሳቡ መቅረቡን በጥሩ መልኩ ይመለከቱታል። "የተበላሸው ተበላሽቷል፤ ነገር ግን ከሥር ጀምሮ እንደ አዲስ መማር አለባቸው፤ ሥነ ምግባር ወሳኝ ነው፤ ለአንድ ማህበረሰብ ሕልውናም መሰረት ነው" ሲሉ ምክንያታቸውን ያስረዳሉ። ዶ/ር መስከረምም ይህንን የትምህርት ዓይነት መልሶ ለመስጠት የታሰበው በሥነ ምግባር ያለውን ክፍተት የሚሞላ ስላጣን ነው ይላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ክፍተቶቹ በባህል መላላት፣ በሥርዓተ ትምህርቱ አጥጋቢ አለመሆን፣ በማህበራዊ ትስስር መበጣጠስ፣ ሉላዊነት እና ሌሎች ውስጣዊና ውጫዊ ተፅዕኖዎች አማካኝነት የሚፈጠሩ ናቸው። ይህም ብቻ ሳይሆን ራስን ማወቅ፣ አዎንታዊ አስተሳሰብ አለመልመድ፤ በዚያኛው በኩል ግፊት ሲመጣ የሚቋቋሙበት ብቃት እና እውቀት አለመኖሩን እንደ ተጨማሪ ምክንያት ያስቀምጡታል። የባህል፣ የኃይማኖት፣ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የፆታ እኩልነትን ማክበር አለባችሁ እየተባለ በሚደረገው ውትወታ ብቻ ግብረ ገብነት ሊጎለብት ይችላል የሚል እምነት የላቸውም። ይህንን ንግግር በመርህ ደረጃ ሁሉም ሰው ያውቀዋል የሚል ሃሳብ ያላቸው ዶ/ር መስከረም በተግባር ይህንን ለማድረግ የሚያስችል አኗኗር ውስጥ ነን ወይ? የሚለው ላይ ግን ጥያቄ አላቸው። ዶ/ር መስከረም በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ይሰጥ የነበረውን የግብረ ገብ ትምህርት መለስ ብለው ያስታውሳሉ። በወቅቱ ይሰጥ የነበረው ትምህርት ይሞላ የነበረው ክፍተት ትንሽ ነው ይላሉ። ምክንያቱም ግብረ ገብነት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ የሙያ ሥነ ምግባር ሆኖ በመቀመጡ የእያንዳንዱን ሙያ ሥነ ምግባር በደንብ ይማሩት ስለነበር ነው። • የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፖለቲካ ጥያቄ እንዴት ይመለስ? "አባቴ በአፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ ተግባረ ዕድ ትምህርት ቤት ነው የተማረው፤ ለአለባበሳቸው እንኳን ትኩረት ይሰጣል። ማሽን ክፍል ውስጥ ሲገቡ ምን መልበስ እና እንዴት መልበስ እንዳለባቸው፣ ራሳቸውንና ሰውነታቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው፣ የሚፅፉበት ደብተር፤ የእጅ ፅሁፋቸው በጣም ጥንቃቄ ያደርጉ እንደነበር ነግሮኛል" ይላሉ። ቅልጥፍናቸው፣ ታዛዥነታቸው፣ አመጋገባቸውን፣ ሁሉንም ሥነ ምግባር ይማሩ ነበር። የዚያን ትምህርት ነፀብራቅም በአባታቸው ላይ መታዘብ እንደቻሉ ያስረዳሉ። "የማንኛውም ትምህርት ዓላማ ወደ ሥነ ምግባራዊ አስተሳሰብ ማምጣት ነው" በማለት የአንዳንድ ፈላስፋዎችን ንግግር የሚያጣቅሱት ዶ/ር መስከረም አሁን ላይ ያለው የትምህርት ሥርዓት ወደዚህ አቅጣጫ እየመራን ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ ውስጥ ነው ሲሉ ያክላሉ። በሌላው ዘርፍ የጎደለውን በአንድ ትምህርት ለማካካስ መሞከር የበለጠ ክፍተቱን ሊያሰፋው ይችላል የሚል ስጋትም አላቸው። ዶ/ር ዳኛቸው በበኩላቸው በየትምህርት ዓይነቱ የሚሰጡት የሥነ ምግባር ትምህርቶች ከግብረ ገብነት ተመዘው የወጡ ናቸው፤ በመሆኑም ዋናው ግንድ መኖር አለበት ሲሉ ይሟገታሉ። በመሆኑም መሠረታዊ የሆነው ግብረ ገባዊ አስተምሮት ያስፈልጋል የሚል ፅኑ አቋም አላቸው። "ልጆቻችንን በሞራል ማነፅ አለብን" የሚሉት ዶ/ር ዳኛቸው "በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ሰው ነው ወሳኙ፤ የበጎና የመጥፎ ነገር ዓለም አቀፋዊ የሆነ መለኪያ የለም የሚለው መሻር አለበት" ይላሉ -ዶ/ር ዳኛቸው። በቀደመው ሥርዓት የግብረ ገብ ትምህርት መኖሩ በጣም በጎ አስተዋፅኦ እንዳሳረፈም ሳይጠቅሱ አላለፉም። አንድ ሃገርና ማህበረሰብ ያለ ግብረ ገብና ሞራል እሴት ሊኖር እንደማይችል ያስረዳሉ። በመሆኑም ይህ እሴት ከልጅነት ጀምሮ መሰጠት እንዳለበት፣ የግብረ ገባዊ ጥያቄዎችን እያነሱ መለማማድ እንዳለባቸው፣ ፍትሃዊነትን ከሥር ከሥር መማር እንዳለባቸው ይመክራሉ። ግብረ ገብነትን በመደበኛ ትምህርት መላበስ ይቻላል? ምንም እንኳን ግብረ ገብነትን የሚያላብሱ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በመደበኛ ትምህርት ውስጥ ተካቶ መሰጠት እንዳለበት ዶ/ር ዳኛቸው የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ዶ/ር መስከረምም ቤተሰብ ያላስተካከለውን ትምህርት ቤት የማነፅ ኃላፊነት እንዳለበት ያሰምሩበታል። አንዳንዴ ከቤተሰብ አቅም በላይ የሆኑ ነገሮች ይኖራሉ የሚሉት ዶ/ር መስከረም የተጣመመውን ለማስተካከል ትምህርት ቤቶች ሁለተኛ እድል ይሰጣሉ ይላሉ። የመምህራን ተነሳሽነት፣ በቂ ሥልጠና፣ በቂ ዝግጅት፣ ብልሃቱና ባህሉም ስለሌለ እንጂ በትምህርት ቤት ጥሩ ዘር መዝራት ይቻላል ባይ ናቸው። "ተሞክሮ አልወሰድንም፤ ግድ የለሾች ሆነናል፤ ትኩረታችን ገንዘብ፣ ፖለቲካ፣ ብሔር ላይ ነው ይህን ማን ይስራ? ይህ ነው ክፍተቱ" ሲሉም ተግዳሮቱን ይነቅሳሉ። የአሁኑ ትውልድ ምን ጎድሎታል? ዶ/ር መስከረም ጎዶሎ ስለመኖሩ ጥርጣሬ የላቸውም። ነገር ግን የአሁኑ ትውልድ ብቻ ነው ወይስ የቀደመው? ሲሉ በመጠየቅ በዚህ ትውልድ ብቻ ጣታቸውን መቀሰር አይፈልጉም። "የተሳሳተ መስመር ላይ የቆመ ትውልድ፤ ተከታዩም የተሳሳተ መስመር ላይ ቆሞ ይገኛል፤ እናም የዚህ ትውልድ ሞግዚት ማን ነበር? የሚለውን ማየት ያስፈልጋል" ይላሉ። በእርግጥ በዚህ ትውልድ ላይ በአለባበስ፣ በአነጋጋር ፣ ለሰው ስሜት አለመጠንቀቅ መታየቱን ባይክዱም ተስፋ ግን ያደርጋሉ - ተንከባሎ የመጣ ብዙ ሸክም ያለበት ትውልድ በመሆኑ የሚያይዋቸው የግብረ ገብነት ችግር ከዚህም ብሶ አለማየታቸውን በማድነቅ። እዚህም ላይ የአባታቸውን ተሞክሮ ይመዛሉ። "የግብረ ገብ አስተሳሰቡ ከብዙ ነገር የተቃኘ ነው፤ ከባህሉ ውስጥ ያሉትን ጥሩ ነገሮች ከራሱ ጋር አዋህዶታል። ትምህርት ቤት ሲገባ መምህር ሲያስተምር፤ ጃንሆይ መጥተው ሲጎበኙ፤ ትምህርት ቤቱን እንደ ቀላል አያየውም፤ ትልቅ ኢንቨስትመንት እየተደረገብኝ ነው ብሎ ያስባል" በማለት አሁንም ድረስ የዘለቀ ትዝብታቸውን ያጋራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት አባታቸው የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ወድቆ የደርግ ዘመንም ሲመጣም ጥሩ ነገር እንዳለ ለማየት ይችሉ ነበር። የፆታ እኩልነት፣ የሥነ ምግባሩ፣ የሥራ ባህሉ ፣ አንድ ሰው ብዙ መስራት እንዳለበት እንዲሁም ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰቡ ማሰብ እንዳለበት ያምናሉ። በመሆኑም ቤተሰብም፣ ሁለቱም መንግሥታት በአንፃራዊ መልኩ ስለ ሃገር የሚያስቡበትና የሚቆረቆሩበት ትውልዶች በነበሩት ወቅት በመሆኑ፤ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚወራውና ውጭ ላይ ያለው የተስማማላቸው እንደነበር ይናገራሉ። "አሁንም ድረስ በሚሰራው ሥራ ከፍተኛ ገንዘብ በማስከፈል አያምንም፤ ምክንያቱም ኅብረተሰቡ ድሃ ነው፤ የሚመጥነውን ዋጋ ነው የማስከፍለው የሚል አቋም አለኝ ይላል። ይህም መሰረት እንዳለው አንዱ ማሳያ ነው።" ይላሉ- ዶ/ር መስከረም። በመሆኑም ግብረ ገብነት ከሁሉም አቅጣጫ ነው መሰጠት ያለበት፤ የትምህርት ቤት ብቻ ሸክም መሆን የለበትም ሲሉ ያስረግጣሉ። • 1550 ተማሪዎች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን ለውጠዋል " ይህ ትውልድ መሪ የለውም፤ የሚጨነቅለት የለውም፤ የኃይማኖት ተቋም ሄዶ 'የኃይማኖት አባቶች ስለ እኔ ግድ የላቸውም' ብሎ ያምናል። የመጥፋት ስሜት፤ እናት አባት የሌለው ትውልድ የመሆን ስሜት ይታይበታል" ሲሉም ትዝብታቸውን ያካፍላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት "ባለሥልጣናትን በቴሌቪዥን እያየ አባቶቼ ናቸው ብሎ እንዲያምን የሚያስችለው ሁኔታ ላይ አይደለም። ፖለቲካውም ምኑም እንደዚያ እንዲያስብ አያስችሉትም። መሪ የሌለው ትውልድ ደግሞ ለሥነ ምግባር ችግር የመጋለጥ እድሉ ሰፊ ነው"ይላሉ። አክለውም "በየትም ሆነ በየት ተገፋፍተህ፤ በሌላው ላይ ተረማምደህም ቢሆን ራስህን አድን ዓይነት አስተሳሰብ ውስጥ ነው የምንገባው፤ በመሆኑም ይህ ትውልድ መሪ አጥቷል" ሲሉ ይተቻሉ። ጨለምተኛ አስተሳሰብ ውስጥ መግባት እና ብርሃን እንዳለ አለማሰብም ይታያል የሚሉት ዶ/ር መስከረም "አዕምሮን ጨለማ ከወረሰው ምክንያታዊነት አይታሰብም ግን ጨለማን ያወረሰው ማን ነው? በግለሰባዊ ደረጃ ማን ነው ጉዳቱ ያለበት? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። በቴሌቪዥን ወጥቶ ማውራት አይለውጥም።" ሲሉ መፍትሔ አመንጭ ጥያቄያቸውን ይሰነዝራሉ። " ተቆሳስለን መራራቅ፤ ከዚያ እንታረቅ መባባል ነው አሁን ያለው፤ ብዙ ያልተሰራ ነገር አለ፤ በሳል ሰው ያላየ ራሱ በሳል ሊሆን አይችልም" ሲሉም ጠንከር ያለ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ትምህርቱ መሰጠቱ ምን ይለውጣል? ግብረ ገባዊነት የኅብረተሰብና የአገር መሠረት ከመሆኑ አንፃር ከታች ጀምሮ የግብረ ገብ ትምህርት መሰጠት አለበት የሚል አቋም አላቸው- ዶ/ር ዳኛቸው። ዶ/ር መስከረም በበኩላቸው "የሚያመጣውን ለውጥ አሁን ማየት አስቸጋሪ ቢሆንም ተማሪዎች እንዲነጋገሩ፤ መምህራንም ክፍተት ያለበትን ቦታ እንዲረዱ እና ራሳቸውን እንዲፈትሹ እድል ይከፍትላቸዋል" ይላሉ። ነገር ግን በቅርፅ ላይ ሳይሆን ግለሰብ ላይ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራ ሥራ ነው ለውጥ የሚያመጣው የሚል እምነትም አላቸው።
news-53967064
https://www.bbc.com/amharic/news-53967064
ትዳር ፡ የጃፓን ወንዶች በሚስቶቻቸው ላይ ለምን ሰላይ ይቀጥራሉ?
እንደው ነገር ለማድመቅ ነው እንጂ ነገሩስ ወንዶች ብቻ አይደለም ሰላይ የሚቀጥሩት። በጃፓን ሴቶችም ባሎቻቸው ላይ ሰላይ ይልካሉ።
ወጣቶች ፍቅረኞቻቸውን ያሰልላሉ። ቀላል ብር እንዳይመስልዎ ታዲያ የሚከፈለው። የአንድ ሰላይ ዋጋ እስከ 400 ሺህ የን [የጃፓን ብር] ሊደርስ ይችላል። እርግጥ ነው ይህ ብር እንደ ዜሮዎች ብዛት አስደንጋጭ አይደለም። ይህን ጽሑፍ አንብበው እስኪጨርሱ የምንዛሬ ዋጋ እንዳይጨምር እንጂ በአገር ቤት ይህ ገንዘብ ስንት እንደሚሆን ቆየት ብለን እንነግርዎታለን። በቅድሚያ ይቺን ታሪክ ያንብቧት። ሰላዩ ፍቅር ያዘው ነገሩ 2010 (እንደ አውሮፓዊያኑ) የሆነ ታሪክ ነው። ሰላዩ ፍቅር ያዘው። የሰው ሚስት ለመሰለል ተቀጥሮ በዚያው ፍቅር ያዘው ነው የምንልዎት። ከዚያ ሴቲቱ የገዛ ባሏ የቀጠረው ሰላይ እንደሆነ ደረሰችበትና ተጣላችው። ከዚያ በቃ አንተንም ባሌንም አልፈልጋችሁም አለች። ከዚያ በሲባጎ አንቆ ገደላት። ይህ ታሪክ ትንሽ ግነት ያለበት የቦሊውድ ፊልም ከመሰላችሁ ይቅርታ። ነገር ግን እውነት ነው። እንዲያውም ሰላዩ ወንጀለኛ በ15 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጥቷል። ታሪኩ ትንሽ እንዲብራራ ፈለጋችሁ? እነሆ፡- ታኬሺ ኩዋምባራ ይባላል ሰላዩ። ሰላይ ታኬሺ ኢሶሃታ የምትባል ቆንጆ እመቤት እንዲሰልል በኢሶሃታ ባል ይቀጠራል። ከዚያም ኢሶሃታን ተከታትሎ ተከታትሎ አንድ ቀን ሱፐርማርኬት ውስጥ አማለላት። ሲተዋወቃት ብቻውን የሚኖር የኮምፒውተር ባለሙያ ነኝ ብሎ ነበር። ደግሞ ይመስላል። ቀጭን ፊቱ፣ በሰልካካ አፍንጫው ላይ መነጽሩ ሲታይ ፈረንጆች (ነርዲ) የሚሏቸውን እነዚያ የኮምፒውተር አባዜ የተጠናወታቸውን ወጣቶች ይመስላል። ብቸኛ ነኝ ሲላት አመነችው። ሚስትና ልጆች አሉት እኮ፤ ውሸቱን ነው ላጤ ነኝ የሚላት። "አንቺስ?" አላት። "እኔማ ባለትዳር ነኝ" አለችው። የደነገጠ መሰለ። "ውይ! ምን አስቸኮለሽ ግን? ምነው ሳታገቢ አውቄሽ ቢሆን?" አላት። አውቆ እኮ ነው። ውሸቱን ነው። ሲያማልላት… በሰላዩ ታኬሺ ማለለች። ባለትዳርነቷ ከሰላዩ ታኬሺ ጋር የደብብቆሽ ፍቅር ከመጀመር አላገዳትም። እራት በሉ፣ እያመሸች ከእሱ ጋ መሳቅ መጫት ጀመረች። ደስ አላት። ተሳሳተች። ተሳሳቱ። የሚገርመው ሰላዩ ታኬሺ ሥራውን ረስቶ እሱ ራሱ ፍቅር ከእሷ ጋር አይዘውም መሰላችሁ! የሰላዩ ሁናቴ ያልጣመው ባል በሰላይ ላይ ሰላይ መቅጠር። የሆነ ቀን ከሆቴል ሲወጡ አዲሱ ሰላይ በፎቶ አነጣጥሮ ቀለባቸው። ጉድ የፈላው ከዚህ በኋላ ነበር። ባልየው የሚፈልገውን መረጃ አገኘ። ባልየው ድሮም ሰላይ የቀጠረው ሚስቱን ስለሚወዳት ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። መፋታት ፈልጎ ነበር። በጃፓን መፋታት ቀላል አይደለም። መረጃ ያስፈልጋል። የፎቶ መረጃ። የቪዲዮ መረጃ። ሚስት መማገጧን የሚያሳይ ፍርድ ቤትን የሚያሳምን ሁነኛ መረጃ። በመጨረሻ ፍቺው ተሳካና ተፋቱ። እድሜ ለአዲሱ ሰላይ። ነገር ግን ሚስት ከባሏ ጋር ብትፋታም ከመጀመርያው ሰላይ ጋር ፍቅር ላይ ነበረች። የታኬሺን ሰላይነት ግን ዘግይታ ደረሰችበት። በጣም አናደዳት። ካንተ ጋር አልኖርም አለችው። ቢል፣ ቢሰራት፣ ተንበርክኮ ቢለምን…ወይ ፍንክች ያባ ቢላ ልጅ። ሰላዩ በዚህን ጊዜ አመረረ። ምክንያቱም እሱ ራሱ ትዳር አለው፤ ልጆች አሉት። ሁሉን ትቶ ነበር ፍቅር የያዘው። እሷ እሄዳለሁ ስትል "አንቺ ከሄድሽ የእኔ መኖር ታዲያ ምን ትርጉም አለው?" በሚል በሲባጎ አንቆ ገደላት። ጃፓናዊያን ደነገጡ። በዚህ የተነሳ የትዳር ሰላዮች ቢዝነስ ቀዘቀዘ። ሰላይ ታኬሺም ለወንጀሉ በ15 ዓመት ፍርድ ዘብጥያ ወረደ። ስቴፋኒ ስኮት በዚህ የስለላ ተግባር ላይ ሰፊ ጥናት አድርጋ መጽሐፍ ጽፋለች "በአዲስ መልክ ባልና ሚስት መሰለል ጀምረናል" የኢሶሃታ ሞትን ተከትሎ በጃፓን የትዳር ሰላዮች ጉዳይ መነጋገርያ ሆነ። ለጊዜው የተዳፈነ መሰለ። ለጊዜው ባለትዳሮች በሰላዮች እምነት ያጡ መሰሉ። ከዓመታት በኋላ ግን የስለላ ቢዝነስ ዛር ቆመ። ጃፓኖች የትዳር ሰላዮችን ዋካሬሳሴያ ብለው ነው የሚጠሯቸው። ቢዝነሱም ዋካሬሳሴያ ነው የሚባለው። ቢዝነስ ብቻ አይደለም ታዲያ። ኢንዱስትሪ ሆኗል ማለት ይቻላል፤ ለጃፓን። ለምሳሌ 270 የሚሆኑ ኩባንያዎች ሕጋዊ ፍቃድ አውጥተው ትዳር ይሰልላሉ። ይፋ ድረ ገጽ አላቸው። ሚሊዮኖችን ይከሰክሳሉ፤ ለማስታወቂያ። ይህ በጣም ብዙ ቁጥር አይደለም ታዲያ? በምዕራቡ ዓለም የግል ወንጀል ምርመራ ቢሮዎች የተለመዱ ናቸው። በጃፓን ደግሞ ዋካሬሳሴያ። "የትዳር ሰላዮች ዋጋ የሚቀመስ አይደለም" ይላል ሞሺዙኪ። ሞሺዙኪ ቀድሞ ሙዚቀኛ ነበር። አሁን የግል መርማሪ ሆኗል። የትዳር ስለላ ቢሮም አለው። ለአንድ ስለላ እስከ 400 ሺህ የን ያስከፍላል። ይሄ ወደ ዶላር ሲመነዘር 3 ሺህ ዶላር ይጠጋል። ወደእኛ ብር ስንመታው ወደ አንድ መቶ ሺህ ብር አካባቢ ነው። ነገር ግን ይሄ ትንሹ ክፍያ ነው። ሚስቱ ወይም ባሏ እንዲሰለልለት የፈለገ በጣም ብዙ መረጃ ከሰጠ/ከሰጠች ነው ይህ ዋጋ የሚሰጠው። በታላቅ ቅናሽ። የዘመድ ዋጋ ነው ይሄ። ለምሳሌ ሚስቱ የት እንደምትውል፣ ምን እንደምትወድ፣ የጓደኞቿ አድራሻና ማንነት፣ የፌስቡክ ማለፊያ የምስጢር ቃል እና ደካማ ጎኗ ወዘተ. . . ይሄ ዋጋ አንዳንድ ጊዜ እስከ 20 ሚሊዮን ከፍ ሊል ይችላል። መቼ ከተባለ የሚሰለለው ባል/ሚስት/ፍቅረኛ ለምሳሌ እውቅ፣ ስመ ጥር፣ ዝነኛ ሰው ከሆነ/ከሆነች፣ ፖለቲከኛ ከሆነ/ከሆነች ዋጋው ይወደዳል። የሚጠየቀው ክፍያ ከመቶ ሺህ ዶላር በላይ ይዘላል። በጣም ብዙ ብር ነው ይሄ። አንዱ ምክንያት በጣም ብዙ ሰላዮችና በጣም ውስብስብ ቴክኖሎጂን ማሰማራት ስለሚያስፈልግ ነው። በለንደን መቀመጫዋን ያደረገችው ስቴፋኒ ስኮት የልቦለድ ሥራዎቿ ብዙዎቹ በዚህ በጃፓኖቹ ስለላ ላይ ያተኮሩ ናቸው። "ዋት ኢዝ ሌፍት ኦፍ ሚ ኢዝ ዩርስ" የሚል መጽሐፍ ጽፋለች። ታሪኩ በአመዛኙ በሰላዩ ታኬሺ የተገደለችው በቆንጅየዋ በኢሶሃታ ላይ ያተኮረ ነው። ደራሲ ስኮት ለቢቢሲ እንደተናገረችው ከሆነ የትዳር ሰላይ መቅጠር ከትዳር አጋር ጋር የሚኖረውን የተንዛዛ ፍጥጫና የተራዘመ ፍቺ ያሳጥራል። አንደኛ ሰላይ የተቀጠረባት ሚስት ሰላዩ ተሳክቶለት ፍቅር ካስጀመራት ፍቺ ስትጠየቅ ደስ ብሏት ትፈጽማለች። አለበለዚያ ግን ፍቺው ቀላል አይሆንም። ፍቺ ሲራዘም ደግሞ ባልና ሚስት ጊዜና ጉልበታቸው ይሟጠጣል። በስሜት ይጎዳሉ። ሕይወት ይቃወሳል። አንዳንድ ጊዜ ሰላዮች የሚቀጠሩት ፍቺን ለማፋጠን ብቻ ሳይሆን ሕይትን ለማቅለል ነው። ነገር ግን ሰላዮች ሁልጊዜ ፍቺን ለማሳለጥ አይደለም የሚቀጠሩት። አንዲት ሚስት ባሏ በጣም እንዲጎዳ ስትፈልግ ሆን ብላ ሰላይ ቀጥራ ፍቅር እንዲይዘው ታደርግና ከዚያ ሰላይዋ ማንነቷን ሳትገልጽ ድንገት ግንኙነቷን በማቋረጥ ከፍተኛ የስሜት ጉዳት እንድታደርስበት ይከፈላታል። በተመሳሳይ 'ሚስቴ አቃጥላ ልትደፋኝ ነው' ያለ ባል ጠንበለል የጃፓን ሰላይ ይቀጥራል። ሰላዩ በዚህም በዚያም ብሎ የሰውየውን ሚስት ያጠምዳል። ፍቅር ያስጀምራታል። ከዚያ በድንገት ስሜቷ እንዲጎዳ አድርጎ ፍቅሩን ይቆርጠዋል። ለዚህ ተግባሩ ከፍ ያለ ገንዘብ ይከፈለዋል፤ ከቀጣሪ ባል። "ይህ ቀላል ተግባር አይደለም፤ አንድ የስለላ ተግባር ከወራት እስከ ዓመታት ሊወስድ ይችላል" ይላል ሞቺዙኪ። ሰላዮች በብዛት በሕግ የሰለጠኑ ናቸው። ሥራቸውን ሲሰሩ የጃፓንን ሕግ መጣስ አይኖርባቸውም። ለምሳሌ ዛቻ መፈፀም፣ ማስፈራራት፣ አካላዊ ጥቃት አይፈቀዱም። እንደዚህ የሚያደርጉ የትዳር ሰላዮች ድርጅታቸው ከሥራ ሊያባርራቸው ይችላል። ችግሩ ከሥራ ሲባረሩ በድብቅ ፍቃድ ሳያወጡ የሚሰማሩ ሕገወጥ ሰላዮች ሆነው መቀጠላቸው ነው፤ አሁን አሁን አሳሳቢ እየሆነ የመጣው። እነዚህ ሕገወጥ ሰላዮች ቀይ መስመር በማለፍ ይታወቃሉ። ለምሳሌ ባለትዳር ሴትን ካማገጡ በኋላ የወሲብ ድርጊትን በድብቅ ቪዲዮ በመቅረጽ ለባል አሳልፎ መስጠት። በጃፓን ይህ የትዳር አጋርን የማሰለል ቢዝነስ ሞቅ ያለ ገበያ አለው ማለት ማኅበረሰቡ በድርጊቱ ይኩራራል ማለት ግን አይደለም። በዚህ ድርጊት ውስጥ ተሳታፊ ሆኖ መገኘት በጃፓን ባህል አሳፋሪ ነው። ሰዎች በፍጹም ከድርጊቱ ጋር ራሳቸውን ማቆራኘት አይሹም። ሆኖም አገልግሎቱን ይወዱታል። በጃፓን የቲቪና የሬዲዮ ፕሮዲዩሰር ኒሺያማ ለቢቢሲ ስትናገር "በጃፓን ለሁሉም ነገር ገበያ አለ" ትላለች። ለምሳሌ የውሸት ሙሉ ቤተሰብ አባል መከራየት የፈለገ ይህንኑ ማድረግ ይችላል። ለምሳሌ ልጁን ከሴት ፍቅረኛው ፈልቅቆ ለመውሰድ የሚፈልግ ወንድ ለዚህ ተግባር ሰላይ ሊያሰማራ ይችላል። የትዳር ሰላይ ኩባንያዎች ሰዎችን በማለያየት ብቻ አይደለም የሚሰማሩት፤ አንዳንድ የተሰበረ ትዳርን በመጠገንም ይታወቃሉ። የተሰበረ፣ የወለቀ፣ ወለምታ የገጠመው ትዳር ሲጠግኑ ታዲያ በነጻ አይደለም። ሞቅ ያለ ሒሳብ በማስከፈል እንጂ።
news-48376792
https://www.bbc.com/amharic/news-48376792
ማሚቱ፡ ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ
ማሚቱ ትዳር የመሰረተችው በ14 ዓመቷ ነበር። ከዚያ በፊት ቤተሰቦቿን በሥራ የምትረዳ፣ ከእኩዮቿ ጋር የምትጫወት ታዳጊ ነበረች። ትዳር መስርታ ሁለት ዓመት ከቆየች በኋላ ግን ያልጠበቀችው ሆነ።
ትዳሯን ስትመሰርት በሀገሩ ባህል መሰረት ወደ ቤተሰብ ሽማግሌ ተልኮ የወጉ ሁሉ ተሟልቶ ነው። ያኔ ከተማ ምንድን ነው የሚለውን እንኳ አስባው አታውቅም። ህልሟ የነበረው ወልጄ ከብጄ እቀመጣለሁ የሚል ብቻ ነበር። ማሚቱ እንደምትለው በወቅቱ እድሜው 25 የሚገመት ወጣት ስታገባ ትዳሯ ሁሉ ነገር የሞላው ነበር፤ ከልጅ በስተቀር። • የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እጩ ሐኪሞች ግቢውን ለቅቀው ወጡ • ለወሲብ ባርነት ወደ ቻይና የሚወሰዱት ሴቶች ባሏም ደግና አዛኝ፤ ሁሌም እርሷን ለመርዳት ወደኋላ እንደማይል ትናገራለች። በትዳር ሁለት ዓመት ከቆዩ በኋላ የማሚቱ ህልም እውን የሚሆንበት አጋጣሚ ተፈጠረ፤ ፀነሰች። እርሷም ለልጇ መታቀፊያ ልብስ ገዝታ መጠባበቅ ጀመረች። የስምንት ወር ነፍሰጡር ሳለች አዲስ አበባ ትኖር የነበረች ታናሽ እህቷ ልትጠይቃት መምጣቷን ታስታውሳለች። ከተማን እህቷ ከምታወራላት ውጪ አታውቀውም። የአራት ቀን ምጥ ምጧ ሲፋፋም ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ 'ማርያም ማርያም' ቢል ሕፃኑ ግን ሊወለድ አልቻለም። አንድ ቀን አለፈ መሸ፤ ነጋ ሁለተኛም ቀን ሆነ። ማሚቱ በላብ ተነክራ ጥርሷን ነክሳ አማጠች፤ ምንም የለም። አራት ቀን ሙሉ እንዳማጠች የምትናገረው ማሚቱ በአራተኛው ቀን ራሷን ሳተች። ስትነቃ ዘመድ ጎረቤቱ ከቧታል። ከሄደችበት ሰመመን ስትነቃ ከበው በጭንቀት ሲያይዋት የነበሩ ሰዎችን የተፈጠረውን ጠየቀቻቸው። 'ልጄ' አለች በደከመ ድምፅ፤ ልጇ ሞቶ ስለነበር ወጌሻ ተጠርቶ ተጎትቶ እንደወጣ ነገሯት። ለማልቀስ አቅም አጣች፤ ሐዘን ልቧን ሰበረው። በኋላ ግን ሌላ ችግር በጤናዋ ላይ አስተዋለች፤ ሽንቷንና ሰገራዋን መቆጣጠር አለመቻሏን። • ሰማይ ላይ ወልዳ አሥመራ የምትታረሰው ኢትዮጵያዊት • በፆም ወቅት ሰውነታችን ውስጥ ምን ይካሄዳል? ከቀን ቀን ይሻልሻል እየተባለች እናቷና እህቶቿ እያገላበጡ፣ እያጠቡ ተንከባከቧት ለውጥ የለም። እኔም ለውጥ ይኖራል ብዬ ተስፋ እያደረኩ ነበር የምትለው ማሚቱ ለውጥ ስታጣ ተስፋ ቆረጠች። ራሷንም ለማጥፋት ትፈልግ እንደነበር ትናገራለች። "ሰዎች ሲወልዱ አንደዚህ አይነት ነገሮች አይደርስባቸውም። ልጅ ብሆንም፣ አያለሁ እሰማለሁ። እንዴት እንዲህ አይነት ነገር እኔ ላይ ሊደርስ ቻለ?" በሚል አዘነች። በአካባቢዋ ያሉ ሰዎች በተኛችበት "ጠገግ አልጋ" ላይ ሆና ሲመለከቷት ሳይሻላት ሲቀር ደሴ እንውሰዳት አሉ። ማንም ስለበሽታዋ ምንነት አያውቅም። የተኛችበት ክፍል በመጥፎ ጠረን ታውዶ ሲመለከቱ ማስታገሻ እንኳን እንድታገኝ በሚል ነበር ሀሳቡን ያቀረቡት። ማሚቱ ሀፍረት ውጧት ነበር። እናቷ፣ እህቷና ወንድሞቿ ቢያገላብጧትም፣ ቢያፀዷት ቢያጥቧትም እርሷ ግን የወደፊት ሕይወቷ አሳሰባት። ከሰው ተራ እንደጎደለች ተሰማት፤ መብላትና መጠጣቴን ማቆም አለብኝ ብላ እንዳሰበች ትናገራለች። ያኔ ቤተሰቦቿን ወደ እህቴ፣ አዲስ አበባ ውሰዱኝ በማለት ጠየቀች። ከዚህ በኋላ ነው በወሬ በወሬ አዲስ አበባ ሕክምና እንዳለ የሰሙት። ወዲያው አዲስ አበባ ያሉ ዘመዶች ይቆጠሩ ጀመር። የእህቷ የክርስትና እናትና እህቷ አዲስ አበባ እኖራሉ። ዘመድ አዝማድ ፈውስ እንድታገኝ ተረባረበ። ዘመድ ለመቼ ነው! ሕይወት የሚለወጥበት የደስታ መንደር አዲስ አበባ የእህቷ ክርስትና እናት ይሰሩበት ወደነበረው ዘውዲቱ ሆስፒታል አመራች። ዘውዲቱ ለ15 ቀን ተኝታ የሕመም ማስታገሻ እየተሰጣት ቆየች። ከዚያም የእህቷ ክርስትና እናት በወቅቱ ልዕልተ ፀሐይ ይባል ወደነበረው ሆስፒታል ሄደው ጠይቀው ወደዚያው ወሰዷት። በሆስፒታሉ ደግሞ ዶ/ር ካትሪን ሐምሊንና ባለቤታቸው ዶ/ር ሬጅ ሐምሊን ለፌስቱላ ታማሚዎች ቀዶ ጥገና ይሰጣሉ። ወደ ሆስፒታሉ ከደረሰች በኋላ አቀባበላቸው እና እንክብካቤያቸው ራሱ በሽታዋን እንድትረሳ እንዳደረጋት ታስታውሳለች። ሆስፒታሉ ስትደርስ በሆስፒታሉ አስር የሚሆኑ ሴቶች እንደነበሩ እና የእርሷ አይነት ሕመም ታምመው እያገገሙ መሆናቸውን ሲነግሯት ፈውስ ተሰማት። ሌላ ክፍል ታመው የታከሙ እና እያገገሙ ያሉ ሴቶችም ወደ እርሷ እየመጡ መዳን እንደሚቻል ይነግሯት ጀመር። የተወሰኑ ቀናት ተኝታ መጠንከር ስትጀምር ቀዶ ህክምና ተደርጎላት ተሻላት። "እኔ ሞቴን ተመኘሁ ፈጣሪ ግን ረዥም እድሜን ሰጠኝ" የምትለው ማሚቱ ታማሚዎች እየታከሙ ወደ መጡበት አካባቢ ሲሄዱ እና ስለሆስፒታሉ ሲናገሩ በርካታ ታካሚዎች መምጣታቸውን ትናገራለች። ማሚቱ ሲሻላት ለእርሷ ይደረግ የነበረውን እንክብካቤ ለሌሎች ማድረግ ጀመረች። "የሌሎች ታካሚዎችን አልጋ በማንጠፍ ነው የጀመርኩት" የምትለው ማሚቱ ከዳነች በኋላ ወደ ትውልድ ቀዬዋ ለመመለስ አላሰበችም። ቤተሰቦቼን በማንኛውም ጊዜ ሄጄ መጎብኘት እነርሱም መጥተው ሊጎበኙን ይችላሉ እዚህ ብቆይ ግን እንደኔው ታማሚ የሆኑትን ብረዳ ብላ ወሰነች። ባለቤቷ ለህክምና ሁለት ዓመት በቆየችበት ጊዜ መጥቶ ይጎበኛት ነበር፤ እርሷ በደንብ እስኪሻላት እንደምትቆይ ገልጣ እርሱ የራሱን ሕይወት እንዲመራ ነገረችው። ጉዞ ወደ ቀዶ ህክምና ባለሙያነት ከዚህ በፊት ታካሚዎቹን ትረዳ የነበረችው ጓደኛዋ ለእረፍት ስትሄድ እርሷን ተክታ መስራት ጀመረች። መርዳት ጀምራ ስታየው እኔ እርዳታ አግኝቼ ሌሎችን ብረዳ ደስተኛ ነኝ በሚል እዚያ ቆይታ መስራት መጀመሯን ትናገራች። በኋላም እረፍት የሄደችው ሰራተኛ ስትመለስ እርሷ ወደ ማገገሚያ ክፍሏ ተመለሰች። ይኼኔ ዶ/ር ሬጅ ሐምሊን የት ሄደች? ብለው በመጠየቅ እንዳስመጧት ታስታውሳለች። ዶ/ር ሬጅ ሐምሊን ኦፕራሲዮን ሲሰሩ እንድትመለከት ያደርጓት ነበር። የቀዶ ጥገና ልብሷን ለብሳ ከስር ስር እየተከተለች ሙያቸውን እንድትመለከት በማድረግ አነስተኛ ቀዶ ጥገናዎችን እንድትሰራ እድል ይሰጧት ጀመር። "እነርሱ ሰርተው ያጠናቀቁትን ቀዶ ህክምና እንድጨርስ እንዲሁም ቀለል ያሉ ቀዶ ህክምናዎችን እነርሱ ባሉበት እንዳከናውን ያደርጉኝ ነበር።" አዲስ ሆስፒታል ገንብተው ወደዚያ ሲዘዋወሩም ይህንን ተግባር ቀጠሉበት። ዶ/ር ሬጅ ሐምሊንን 'አባዬ' ካትሪን ሐምሊንን ደግሞ 'እማዬ' የምትለው ማሚቱ ሥራዬን በጣም ነው የምወደው ትላለች። "እንደእኔ የተሰቃዩትን ከዚያ ስቃያቸው መፈወስ ደስታ ይሰጠኛል።" ከተማ የማታውቀው፣ ሆስፒታል፣ መድሀኒት በቅጡ የማትረዳ የነበረችው ማሚቱ ለፌስቱላ ታማሚዎች የተሳካ ቀዶ ጥገና ብቻዋን ማድረግ ጀመረች። "ለማከምም የበቃሁት በእነርሱ ተይዤ ነው፣ እንግሊዝኛ ብናገር ከእነርሱ የለመድኩትን ነው። አማርኛ ማንበብ እና መፃፍ ያስተማሩኝ እዚህ ግቢ ውስጥ ነው።" ማሚቱ ለትምህርት ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡትን የሕክምና ተማሪዎችንም ትረዳለች። ዓለም አቀፍ እውቅና አንድ ሰንበት ከእንግሊዝ ሮያል ኮሌጅ የመጡ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ማሚቱን አገኟት። በወቅቱ እነሐምሊን በግቢው አልነበሩም። በዚያ ሰንበት የቀዶ ህክምና ሥራውን የምትመራው ደግሞ ማሚቱ ነበረች። ይህንን ድርጊቷን በድጋሚ መጥተው በዶ/ር ሬጅ ሐምሊን ረዳትነት ሙሉ ቀዶ ጥገና ስታከናውን ሲያይዋት ተደነቁ፤ ከዚያም እውቅናን ሰጧት። በዚህ ተግባሯም ዶ/ር ሬጅ ሐምሊንም እንደኮሩባት የምትናገረው ማሚቱ "እኔም በሥራዬ ኮራሁ" ትላለች። እስካሁን ለምን ያህል ሰዎች ቀዶ ህክምና እንዳደረገች አታውቅም። ነገር ግን በርካታ ሐኪሞችን መርዳቷን በርካታ ታማሚዎችን ማከሟን ታስታውሳለች። ከእንግሊዝ ሮያል ኮሌጅ እውቅና በኋላ ወደ አሜሪካ ተጠርታ ከኢትዮጵያዊያንም እውቅና ተሰጥቷታል። ማሚቱ የምትሰራበት ሆስፒታልን ለየት የሚያደርገው በርካታ ሰራተኞች በፌስቱላ ታመው የነበሩና ታክመው የዳኑ መሆናቸው ነው። እነዚህ ሴቶች ከነርሶቹ ስር በመሆን የሚረዱ ሲሆን በሽታውን ስለሚያውቁት ለሕመምተኞቹ ብርታት ይሆኗቸዋል። ይህም በማስተማ ሂደቱም ውስጥ በጎ አስተዋፅኦ እንዳለው ይናገራሉ። ማሚቱ "ለእኔ የተደረገውን ያህል ለሌሎች በበቂ ሁኔታ ያደረኩ አይመስለኝም" ስትልም ዛሬም በርካቶችን የመርዳት ፍላጎቷን ታስረዳለች።
news-56249158
https://www.bbc.com/amharic/news-56249158
በኢትዮጵያ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው አምስት የዱር እንስሳት ዝርያዎች የትኞቹ ናቸው?
ኢትዮጵያ በዱር እንስሳት ሀብት ስብጥር ስሟ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የምትነሳ አገር ናት። በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በሚገኙ የዱር እንስሳቶች፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አራተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗን የዱር እንስሳት ባለሙያው አቶ ጨመረ ዘውዴ ያስረዳሉ።
የዚህ ስብጥር ምክንያት ያሉትንም ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ ሲያስረዱ የአገሪቱ የመሬት አቀማመጥ፣ አዋሳኝ አገራት፣ ከደጋ እና ቆላ መካከል የምትገኝ አገር መሆኗ የዱር እንስሳት ስብጥር በርከት ብሎ የሚገኝባት እንዳደረጋት ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም ቀጭኔን ኢትዮጵያ ውስጥ ማየት ቀላል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ፈተና ሆኗል። ቀይ ቀበሮዎች በሰሜንና በባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርኮች፣ በሰሜን ወሎ አቡነ ዮሴፍ ተራራ ላይ እና በመንዝ ገሳ አካባቢ ይገኝ ነበረ ቢሆንም አሁን ግን ቁጥሩ ተመናምኖ የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው እንስሳት መካከል ስሙ ሰፍሮ ይገኛል። ኢትዮጵያን በዓለም ላይ ስሟን ሊያስጠራ የሚችል የዱር እንስሳት ሀብት ቢኖርም የአብዛኞቹ ይዞታ ግን ከጊዜ ወደጊዜ እየተመናመነ መምጣቱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ። የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሙያ እና አማካሪ የሆኑት ዶ/ር መኮንን በኢትዮጵያ የዱር እንስሳቱ የመኖሪያ አካባቢያቸው በትክክል ባለመጠበቁ እና በመረበሹ የመራባት ዕድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱም ለመጥፋት የተጋለጡ እንዳሉ ያስረዳሉ። ለመሆኑ በኢትዮጵያ የመጥፋት አደጋ ከተደቀነባቸው የዱር እንስሳት መካከል አምስቱ የትኞቹ ናቸው? የስዋይን ቆርኬ የስዋይን ቆርኬ (የኢትዮጵያ ቆርኬ) ይህ እንስሳ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ የዱር እንስሳ ነው። ቀደም ሲል በአምስት የተለያዩ ጥብቅ ስፍራዎች ይገኝ ነበር ያሉት አቶ ጨመረ፤ በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፣ ያቤሎ የዱር እንስሳት መጠለያ፣ ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የነበሩት ሙሉ በሙሉ መጥፋታቸውን ተናግረዋል። የስዋይን ቆርኬ (የኢትዮጵያ ቆርኬ) አሁን በደህና ቁጥር የሚገኘው በሻሸመኔ አቅራቢያ ስንቅሌ በሚባል ቦታ በሚገኝ የቆርኬ መጠለያ ውስጥ ነው። በደቡብ ክልል በሚገኘው ማጎ ብሔራዊ ፓርክም እንደሚገኝ አቶ ጨመረ ጠቅሰዋል። ትልቁ የሜዳ አህያ (ግሬቪ ዜብራ) በኢትዮጵያ ሦስት አይነት የአህያ ዝርያዎች አሉ የሚሉት አቶ ጨመረ ከሦስቱ የአህያ ዝርያዎች መካከል ትልቁ የሜዳ አህያ አንዱ ነው። ይህ የአህያ አይነት ዝርያው በከፍተኛ ሁኔታ እየተመናመነ መሆኑንም ባለሙያው አክለው ገልፀዋል። በዓለም ላይ የዚህ አህያ ዝርያ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ውስጥ ብቻ እንደሚገኝ ተናግረው፣ በኢትዮጵያ ቁጥሩ በጣም እየተመናመነ አነስተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ይላሉ። እነዚህ እንስሳት የተለየ ጥበቃ እስካልተደረገላቸው ድረስ "ከአለን ወደ ነበረን" የምንሸጋገርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ሲሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ጥቁር አውራሪስ በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት የአውራሪስ ዝርያ (ነጭና ጥቁር) እንደሚገኝ የሚናገሩት ዶ/ር መኮንን፤ ለቀንዱ በሚል ብቻ ከፍተኛ ጥቃት እንደሚደርስበት ያስረዳሉ። በኢትዮያ ውስጥ ጥቁር አውራሪስ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ግን "አለ ከማይባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል" ይላሉ። አቶ ጨመረ ስለ አውራሪስ ሲናገሩ "ስሙ ብቻ ነው የቀርን እንጂ እንስሳው የለም" በማለት ነው። ባለፉት ሰላሳ እና አርባ ዓመታት አውራሪስን አጥተናል የሚሉት አቶ ጨመረ በተደረጉ በርካታ ጥናቶች አንድም ቦታ ላይ ሊገኝ አልቻለም ብለዋል። ይህንን ሃሳብ የሚያጠናክሩት ዶ/ር መኮንን፣ አውራሪስ ኢትዮጵያ ውስጥ ታየ የሚባለው በኦሞ ሸለቆ ውስጥ እኤአ በ1985 መሆኑን ይናገራሉ። በርግጥ አሁንም በዚህ አካባቢ አለ የሚል ወሬ ቢኖርም ተጨባጭ መረጃ እንደሌለ በመግለጽ፣ በዚህም ምክንያት አውራሪስ ከኢትዮጵያ እንደጠፋ ነው የምንገምተው ይላሉ። ቀይ ቀበሮ (አቢሲኒያ ዎልፍ) ቀይ ቀበሮ (አቢሲኒያ ዎልፍ) ቀይ ቀበሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ የዱር እንስሳ ነው። ይህ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ የቀበሮ ዝርያ በዓለም ደረጃ ለመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው ሥጋ በል የዱር እንስሳት መካከል አንዱ ነው። ቀይ ቀበሮ በኢትዮጵያ ሰባት ስፍራዎች ላይ ይገኝ የነበረ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየተመናመነ መጥቶ፣ በአሁኑ ሰዓት ከ450 የማይበልጥ ብቻ እንደሚገኝ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ባለሙያዎቹ ገልፀዋል። እንደ ዶ/ር መኮንን ከሆነ ለእነዚህ እንስሳት መጥፋት በቀዳሚነት የሚጠቀሰው በሽታ ነው። ምንም እንኳ እነዚህን የቀበሮ ዓይነቶች አምስት አይነት በሽታ ቢያጠቃቸውም፣ በተለይ የእብድ ውሻ በሽታ በአካባቢው ከሚኖሩ ውሾች በቀላሉ ወደ እንስሳቱ እንደሚተላለፍ እና ለሞት እንደሚዳርጋቸው ተናግረዋል። ቀይ ቀበሮዎች አኗኗራቸው በሕብረት ስለሆነ ከመካከላቸው አንድ ቀበሮ በበሽታው ከተያዘ ቀሪዎቹ ለበሽታው በቀላሉ ይጋለጣሉ ሲሉም ያክላሉ። ዝሆን ዝሆን ዶ/ር መኮንን ዝሆን በመላው አፍሪካ በሰው ልጆች አማካኝነት ጥቃት ከሚደርስባቸው የዱር እንስሳ መካከል አንዱ ነው ይላሉ። ኢትዮጵያ ባለፉት 100 ዓመታት ካሏት የዝሆን ሀብት መካከል 80 በመቶ ያህሉን ማጣቷን ጥናቶች ያመለክታሉ ሲሉ አቶ ጨመረ ይናገራሉ። ይህንን ሃሳብ የሚያጠናክሩት ዶ/ር መኮንን ኢትዮጵያ ከ1980ዎቹ ወዲህ 80 በመቶ ያህል የሚሆነውን የዝሆን ሀብቷን አጥታለች ብለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አይነት የዝሆን ንዑስ ዝርያ አለ እንደሚባል የሚገልፁት አቶ ጨመረ፤ የባቢሌ የዱር እንስሳት መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዝሆኖች በየዓመቱ ቁጥራቸው እየቀነሰ መሆኑን ያሰታውሳሉ። በኦሮሚያ ጉጂ ውስጥ ከ20ዎቹ በታች በሆነ ቁጥር ዝሆኖች እንደሚገኝ በመግለጽ፣ በዚህ ሳምነት እንኳ ሦስት ዝሆኖች እንደተገደሉ መስማታቸውን ተናግረዋል። በዝሆን ሀብቱ የሚታወቀው ኦሞ ማጎ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥም ከዕለት ወደ ዕለት የዝሆኖች ቁጥሩ እየተመናመነ መምጣቱንም ይጠቅሳሉ። ዝሆኖች አሁን በተሻለ ቁጥር ይገኛሉ የሚባለው ትግራይ ውስጥ ቃፍታ ሽራሮ እንዲሁም ባቢሌ እንዲሁም በትንሽ ቁጥር ኦሞ ማጎ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ መሆኑን ይናገራሉ። አእዋፋት የአቢያታ ሻላ ሐይቆች ፓርክ ከሰሜን ዋልታ የሚመጡ አእዋፋት የሚታዩበት ስፍራ መሆኑን ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ። በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚመጡ ወደ 241 ያህል ገደማ ተጓዥ አእዋፋት መኖራቸውን፣ ወደ 20 የሚጠጉ ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ አእዋፋት እንደሚገኙ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ከ30 ዓመት ወዲህ በደረሰው የሰው ሰራሽ ጫና የሐይቆቹ የውሃ መጠን እየቀነሰ በመምጣቱ አእዋፋቱ መኖሪያ እና የሚመገቡት እያጡ ቁጥራቸው ቀንሶ ነበር። ነገር ግን ከሁለት ዓመት ወዲህ የሐይቆች ውሃ እየጨመረ በመሆኑ አእዋፋቱ እየተመለሱ ነው ይላሉ። መፍትሄ የዱር እንስሳት ቁጥር መመናመን በዓለም ላይ ያለ ክስተት ነው። በዚህም የተነሳ በአህጉራችን አፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ሀብት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ የተለያየ ምክንያቶች ያሉት ሲሆን ቀዳሚው የሕዝብ ብዛት ጨመር መሆኑን ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። ሌላው ለዱር እንስሳቱ ቁጥር መቀነስ እንደምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ መኖሪያቸው እየተጣበበ መምጣቱ ነው። ሕገወጥ አደን ያለባቸው አካባቢዎችም ለዱር እንስሳቱ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መመናመን እና መጥፋት ተጠቃሽ ምክንያት ሆኖ ይገኛል። የኢንቨስትመንቶች መስፋፋት፣ የዱር እንስሳት አካባቢዎች መበጣጠስ እንዲሁ ለእንስሳቶቹ ቁጥር መመናመን እና ብሎም መጥፋት የራሳቸውን ሚና ይጫወታሉ ይላሉ ባለሙያዎቹ። "የዱር እንስሳትን የምንጠብቀውና የምንንከባከበው ስለሚያምሩ ወይንም ፍጡር ስለሆኑ ብቻ አይደለም" የሚሉት አቶ ጨመረ "ለሰው ልጆች ሕልውና መቀጠል አስፈላጊ በመሆናቸው ነው" ብለዋል። የዱር እንስሳት መኖር ለሰው ልጅ ህልውና ወሳኝ መሆኑን ተገንዝቦ፣ መንግሥት በመላ አገሪቱ ወጥ የሆነ የመሬት አጠቃቀም ፖሊሲ እንዲያበጅም ይመክራሉ። ወጥ የሆነ የመሬት ፖሊሲ ሲኖር ለደን፣ ለልማት፣ ለዱር እንስሳት መኖሪያ የሚለውን በአግባቡ መከለል ይቻላል ሲሉ ይመክራሉ። የዱር እንስሳቱ በሚኖሩበት ስፍራ የሚገኙ ማኅበረሰቦችንም የመሰረታዊ ፍላጎት ማሟያ አማራጭ መንገዶችን ማመቻቸት ያስፈልጋል ሲሉም ይናገራሉ። "የዱር እንስሳት የአገር ቅርስ የትውልድ ውርስ ናቸው" የሚሉት አቶ ጨመረ በገንዘብ የማይተኩትን እነዚህን የተፈጥሮ ቅርሶች እንዳይጠፉ በመጠበቅና በመንከባከብና ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ አሁን ካለው ትውልድ ይጠበቃል ይላሉ። ከዓለማችን ላይ ሊጠፉ የተቃረቡ 5ቱ እንስሳት የትኛዎቹ ናቸው?
news-53864759
https://www.bbc.com/amharic/news-53864759
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ምን እንደሆነ አናውቅም የሚሉት 10 አገራት
ኮቪድ ዓለምን አምሷል፡፡ እኛ ግን አናውቀውም የሚሉ 10 አገሮች አሉ ብንላችሁስ፡፡
ለመሆኑ እነዚህ አገሮች እነማን ናቸው? የማያውቁት ኮቪድ እንዴት እያደረጋቸው ይሆን? 1.ፕላው (Palau) ይቺ አገር የት ያለች ትመስልዎታለች? ሩቅ ምዕራብ ፓስፊክ ነው የምትገኘው፡፡ ማይክሮኒዢያ ሪጂን በሚባለው አካባቢ ከነ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኒዢያ ነጠል ብላ በባትሪ ተፈልጋ የምትገኝ ጢኒጥ ደሴት ናት፡፡ እዚያ ፕላው የሚባል ሆቴል አለ፡፡ ድሮ በ1982 ነበር የተከፈተው፡፡ ያኔ የአገሩን ስም የያዘው ይኸው እስከዛሬ አለ፡፡ በአገሩ ሌላ ሆቴል የሌለ ይመስል፡፡ በፓስፊክ ውቅያኖስ ሰማያዊ ቀለም ውሀ ውስጥ ጠብ ያለች ነጥብ የምትመስለው ይቺ አገር የቱሪስት አገር ናት፡፡ ያለፈውን ዓመት ብቻ አሐዝ ብንወስድ፣ ወደ ፕላው ደሴት 90ሺህ ቱሪስት ገብቷል፡፡ ይህ አሐዝ ከፕላው ጠቅላላ ሕዝብ አምስት እጥፍ ይበልጣል ብንላችሁስ? 40 ከመቶ የአገሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት ገቢ በቱሪዝም የሚታለብ ነው፡፡ ይህ ግን ከኮቪድ በፊት ያለ ታሪክ ነው፡፡ ኮቪድ ድንበሯን ሲያዘጋት ፕላው ደሴት ጉሮሮዋ ተዘጋ፡፡ እንኳን ሌላው መዝናኛ ይቅርና የአገሪቱን ስም የያዘው ሆቴል ሳይቀር ተዘጋ፡፡ ‹‹ለውድ ደንበኞቻችን፡- ኮቪድ የሚባል በሽታ በተቀረው ዓለም ስለተከሰተ ፕላው ሆቴል ለጊዜው ዝግ መሆናችንን ለውድ እንገልጻለን›› ብለው በር ላይ ሳይለጥፉ አልቀሩም፡፡ ፕላው አገር አንድም ዜጋ በቫይረሱ ባይያዝባትም ቫይረሱ ግን ቱሪዝማዊ ኢኮኖሚዋን ደም እያስተፋው ነው፡፡ 2. የማርሻል ደሴቶች 4ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ መሀል፣ ከምድር ወገብ ሰሜን፣ ብጥስጥስ ብለው ከሚገኙት የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ውስጥ የማርሻል ደሴቶች ይገኙበታል፡፡ በሀዋይ እና በፊሊፒንስ መሀል ነው የሚገኙት፡፡ በውስጣቸው 1200 ጥቃቅን ደሴቶችና የጎመራ ፍንጥቅጣቂ የሆኑ የሰመጡ ደቂቀ ደሴቶች (ኮራል አቶልስ) ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የአሜሪካ የሩቅ ግዛት ሆነው የቆዩ ቢሆንም ከ1986 ወዲህ ራሳቸውን ችለዋል። ደህንነቱና መከላከያን እንዲሁም ጠቀም ያለ ድጎማን ግን አሁንም ከአሜሪካ ነው የሚያገኙት። የሕዝብ ብዛት 55ሺህ ሲሆን ዋና ከተማቸው ማጁራ ትባላለች፡፡ እነዚህ ደቂቀ ደሴቶችና የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ ስብስቦች ማርሻል ደሴቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ኮቪድ ምን እንደሆነ ባያውቁም ምጣኔ ሀብታዊ ቁንጥጫው ግን ፓሲፊክን አቋርጦ ተሰምቷቸዋል። ታዲያ አንድ ፕላው በቱሪዝም በኩል አይደለም ቁንጥጫው፡፡ በዓሣ ማጥመድና መላክ ጥሩ ገንዘብ ያገኙ ነበር፡፡ ኮቪድ ይህንን አስተጓጎለባቸው፡፡ በኮቪድ ምክንያት 700 ሰዎች ሥራ አጥተዋል፡፡ ይህ ትንሽ ሕዝብ ላላት ማርሻል አይላንድስ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ 3. ቫኑዋቱ የሕዝብ ብዛቷ 300ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ዋና ከተማዋ ፖርትቪላ ይባላል፡፡ በ1ሺህ 300 ኪሎ ሜትር ላይ የተሰፉ የሚመስሉ 80 ደሴቶች የፈጠሯት አገር ናት፡፡ ከፈረንሳይና እንግሊዝ ቅኝ ነጻ የወጣችው ገና በ1980 ነበር፡፡ አብዛኛው ሕዝቧ ገጠር የሚኖር ገበሬ ነው፡፡ የብዙ አገር ህዝቦች ድንበር ክፈቱልን ሥራ እንስራበት እያሉ ነው የሚያስቸግሩት፡፡ ቫኑዋቱ ብትሄዱ ግን በተቃራኒው ነው የምትሰሙት፡፡ ዶ/ር ሌን ታሪቮንዳ የኅብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር ናቸው፣ የቫኑዋቱ ደሴት፡፡ ዶ/ር ሌን የመጡባት ደሴት አምባኡ ደሴት ትባላለች፡፡ 10ሺ ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ‹‹እኔ የመጣሁበት ደሴት ሄዳችሁ ድንበሩ ይከፈት ወይ ብትሏቸው አረ እንዳታስጨርሱን ነው የሚሏችሁ›› ይላሉ ለቢቢሲ፡፡ መታመም አንፈልግም ነው የሚሉት፡፡ 80 ከመቶ የታሪቮንዳ አገር ሕዝብ ገጠር ነው የሚኖር፡፡ የኮቪድ ሕመም ብዙም አልተሰማቸውም፡፡ እርሻ እንጂ ቱሪዝም ላይ ስላልተንጠላጠሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ዶር ሌን ድንበር ለመክፈት አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ጎረቤት ፓፓዎ ጊኒ ለወራት ከቫይረሱ ነጻ ሆና ቆይታ ሐምሌ ላይ እንዴት ጉድ እንደሆነች ሰምተዋል፡፡ ስለዚህ ድንበር መክፈቱ ይቆየን ብለዋል፡፡ 4. ቶንጋ ቶንጋን የፈጠሩት ደግሞ 170 ደቂቀ ደሴቶች ናቸው፡፡ እዚያው ደቡባዊ ፓስፊክ ነው የሚገኙት፡፡ ቶንጋ ደሴቶቿን ብትሰበስብ በስፋት ከጃፓን አታንስም፡፡ ለ165 አመታት ንጉሣዊ የፊውዳል አስተዳደር ነበራት፡፡ ከዚህ ፊውዳላዊ ሥርዓት የወጣችው በ2010 ዓ. ም ነበር፡፡ ጥብቅ ክርስቲያን አማኞች ያሏት ቶንጋ ከእንግሊዝ ነጻ የሆነችው በ1970 ዓ.ም ነበር፡፡ ቶንጋ ምን አይነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሌላት አገር ተደርጋ ትታያለች፡፡ ማዕድን አልባም ናት ይባላል፡፡ ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ማዕድን ሀብት ባይኖራትም በዓሣ ሀብት ራሷን ትደጉማለች፡፡ ሌላው የገቢ ምንጭ እርሻ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቶንጋዊያውን ከውጭ አገር የሚልኩት ገንዘብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ቶንጋዊያን ያሉት በኒዊዚላንድ ነው፡፡ በአገሪቱ የሥራ አጥ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ ያም ሆኖ የውጭ ምንዛሬዋን የምታገኝበት አንዱ ቀዳዳ ቱሪዝም ስለነበር ኮቪድ ባይደርስባትም ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ 5. ሰሙዋ በፓስፊክ ውቅያኖስ የምትገኘው ሰሙዋ እስከ 1961 ዓ. ም ድረስ በኒውዚላንድ ሥር ነበር የምትተዳደረው፡፡ 9 የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ነው የፈጠሯት ይቺን አገር፡፡ ሆኖም 99 ከመቶ ሕዝቧ የሚኖረው በኡፖሉና ሳቫይ ደሴቶች ነው፡፡ ዋና ከተማዋ አፒያ ይባላል፡፡ ምጣኔ ሀብቷ በእርሻና በዓሣ ሀብት የተንጠለጠለ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቱሪዝም ሞቅ ደመቅ ብሎላት ነበር፡፡ በተለይ ያማሩ የባሕር ዳርቻዎቿ ተወዳጅ ሆነውላታል፡፡ ከቱሪዝም ጋር የባሕር ማዶ ዓለም አቀፍ ኦፍሾር የባንክ አገልግሎት በማሳለጧ ሀብታሞች ሸሸግ ማድረግ የፈለጉትን ገንዘብ ይዘው እዚያ ይሄዳሉ፡፡ አንድም ለመዝናናት፣ አንድም ለባንክ አገልግሎት፡፡ 200ሺህ የማይሞላው ሕዝቧ የወግ አጥባቂ ባህልና የጥብቅ ክርስትና ተከታይ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ዜጎቿ ወደ ኒውዚላንድና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ገንዘብ ወደ ቤተሰብ ይልካሉ፡፡ ኮሮና በሌሎች አገሮች ያደረሰው ጉዳት ሕመሙ ተሰምቷል፣ ሩቅ በምትገኘው በሰሙዋ ደሴት፡፡ 6.ቱቫሉ ቱቫሉን የፈጠሩት 9 ደሴቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 5ቱ እሳተ ገሞራ ወልዶ፣ አሳብጦ፣ በድጋሚ አስምጦ ዳግም የወለዳቸው (ኮራል አቶልስ) ናቸው፡፡ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ሕዝብ በደንብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቱቫሉ በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ ነው የምትገኘው፡፡ ፉናፉቲ ይባላል ዋና ከተማዋ፡፡ በቱቫሉ ተራራ አይታሰብም፡፡ ከባሕር ጠለል በላይ ከ4.5 ሜትር ከፍ ያለ ቦታ የለም፡፡ የአየር ንብረት በቱቫሉ ትልቁ ጉዳይ ቢሆን የማይገርመውም ለዚሁ ነው፡፡ የባሕር ጠለል ከፍታ ከምድረ ገጽ ከሚያጠፋቸው አገሮች አንዷ ቱቫሉ ነው የምትሆነው፡፡ በቱቫሉ ወንዝም ምንጭም ስለሌለ ኑሮ የዝናብ ጥገኛ ነው፡፡ የኮኮናት ተክል የአገሪቱ ገቢ ምንጭ ነው፡፡ ይህ ገቢ እንዲታወክ ምክንያት በመሆኑ ኮቪድ ቱቫሉ ባይገባም ገብቷል፡፡ 7. ናውሩ በዓለም ትንሽዋ አገር ናውሩ ናት፡፡ ይቺ ደሴት ስሟ በቅርብ ጊዜ ይነሳ የነበረው አውስትራሊያ አገሪቱን እንደ ጓሮ እየተጠቀመቻት ነው በሚል ነው፡፡ ናውሩ ስደተኞች ማጎርያ አለ፤ ንብረትነቱ የአውስትራሊያ የሆነ፡፡ ይሄ ማጎርያ ታዲያ ለናውሩ አንድ የገቢ ምንጭ መሆኑ ይገርማል፡፡ ናውሩዎች አንዱ ሥራ ቀጣሪ ኢንደስትሪያችሁ ምንድነው ቢባሉ የአውስታራሊያ የስደተኛ ካምፕ ብለው ሊመልሱ ይችላሉ፡፡ ከ2013 ጀምሮ አውስትራሊያ በጀልባ ወደ አገሯ ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞችን በሙሉ ወደ ናውሩ ነው የምትወስዳቸው፡፡ ካልሆነም ፓፓው ኒው ጊኒ፡፡ ከአውስትራሊያ 3ሺህ ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን ምሥራቅ ፓስፊክ አቅጣጫ የምትገኘው ናውሩ የዜጎቿ ብዛት 10 ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ናውሩን የሚያኖራት እርዳታ ነው፡፡ ሌላው ብቸኛ ሀብቷ ፎስፌት ማዕድን ነው፡፡ በናውሩ የውጭ ጋዜጠኛ ሄዶ መዘገብ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በካምፖቹ ውስጥ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ያጋልጣል፡፡ ይህ ደግሞ ናውሩ የገቢ ምንጬን ሊጎዳብኝ ይችላል ትላለች፡፡ ናውሩን በዓመት የሚጎበኛት ሰው ከ200 አይበልጥም ይባላል፡፡ ቴሌግራፍ በአንድ ዘገባው በናውሩ እስከዛሬ የገባው ቱሪስት ቢደመር ከ15ሺህ አይበልጥም ሲል ጽፏል፡፡ በስፋት ቫቲካን ሲቲና ሞናኮ ብቻ ናቸው የሚበልጧት፤ ለዚህም ነው የዓለም ትንሽዋ ሪፐብሊክ ደሴት የምትባለው፡፡ ቱሪስት የአገሪቱ ገቢ ምንጭ አለመሆኑ በኮቪድ-19 አልተጎዳችም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለጊዜው ከ10ሺህ ዜጎቼ አንድም ሰው ኮቪድ-19 አልያዘውም ብትልም ሕመሙ ግን ናውሩም ደርሷል፡፡ 8. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የብጥስጣሽ ደሴቶች አገር በመሆኗ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ 4ሺህ ኪሎ ሜትር፣ ከሰሜን ደቡብ ደግሞ 2ሺህ ኪሎ ሜትር ታስኬዳች፡፡ ይህ ማለት ግን ይህ ሁሉ ርቀት ሰው የሚኖርበት ደረቅ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነጻነቷን ያገኘችው ከእንግሊዝ በ1979 ዓ.ም ነው፡፡ በ1960ዎቹ ይቺ አገር አንዳንድ ደሴቶቿ ለእንግሊዝ የኑክሌር መሞከሪያ ሆነው አገልግለዋል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የፓስፊክ ደቂቀ ደሴቶች ሁሉ ኪሪባቲም የዓለም ሙቀት መጨመር ከምድረ ገጽ ሊያጠፋት እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኪሪባቲ ከፊጂ ደሴት መሬት ተከራይታ ምግብ ታመርታለች፡፡ ኢኮኖሚዋ ደካማ ሲሆን ኮኮናትና ኮፕራ በመላክ ነው የምትታወቀው፡፡ የዓሣ ማጥመድ ፍቃድ ለውጭ ኩባንያዎች እየቸበቸበች ኢኮኖሚዋን በከፊል ትደጉማለች፡፡ 9ኛ የሰለሞን ደሴቶች፤ 10ኛ ማይክሮኒዢያ በዝርዝሩ 9ኛ እና 10ኛ ላይ ያሉት የሰለሞን ደሴቶች እና ማይክሮኒዢያ ናቸው፡፡ ሁለቱም አገራት በዓሣ ምርትና በቱሪዝም ይታወቃሉ፡፡ ሁሉም በኮቪድ-19 የተጠቃ ዜጋ የለባቸውም፡፡ ይህ ዝርዝር ታዲያ ሰሜን ኮሪያና ቱርከሜኒስታን አላካተተም፡፡ ሆኖም እነዚህ ሁለት አገራት በይፋ ከኮቪድ-19 የያዘው ዜጋ አለም የለምም ብለው አያውቁም፡፡ ወይም አይታመኑ ይሆናል፡፡
45784502
https://www.bbc.com/amharic/45784502
የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ
ስደት ክፉ ነው። ወደ ሀገር መመለስ በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ መኖር ደግሞ የክፉ ክፉ።
ከሀገር ከመሸሽ ውጪ አንዳችም አማራጭ አጥተው ኢትዮጵያን የተሰናበቱ ስፍር ቁጥር የላቸውም። በየደረሱበት ሕይወት ቢጤ ቢጀምሩም፤ ጥለውት ስለሄዱት ዓለም አዘውትረው ማሰባቸው አይቀርም። ቤተሰብ በሞት ሲለይ. . . ሕጻናት ተወልደው ቤተሰቡን ሲቀላቀሉ. . . ቤተሰቡ ከሌላ ቤተሰብ በጋብቻ ሲተሳሰር. . . የሚወዱትን ሰው አፈር አለማልበስ. . . አይዞሽ፣ አይዞህ ባይ በሌለበት ለብቻ ማንባት. . . የዘመድ አዝማድን ስኬት በስልክ ገመድ መስማት. . . • የ2010 የጥበብ ክራሞት • 2010 ለታምራት ላይኔ፣ ለእስክንድር ነጋ፣ ለሃጫሉ ሁንዴሳ . . . • "ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆን ነው የምፈልገው" አንድ ቀን ለሀገሬ መሬት እበቃለሁ ብለው በተስፋ የተሞሉ ነፍሶች በአንድ ወገን፤ በሌላ ጽንፍ ደግሞ ቁረጥ ልቤ ባዮች። ባለፉት ሳምንታት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ያስተናገደችው እኒህን ነው። ቢቢሲ ከሦስት ኢትዮጵያውያን ጋር ቆይታ አድርጓል። ሁለቱ ከዓመታት በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን፤ አንደኛው በቅርቡ ሀገር ቤት የሚገባ ነው። ዐሥርታት ወደ ኋላ መለስ ብለው ሀገር ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ የደረሱበትን ቅጽበት፣ ስደት ያሳጣቸውን እንዲሁም ዳግመኛ ኢትዮጵያን ማየት የፈጠረባቸውን ስሜት አጋርተውናል። • "ሀገሬ ራሱ በድንቅ ተቃርኖ ውስጥ ተዛንቃ ስላለች ሥራዎቼም እንደዛ ናቸው" • "በሰው ሃገር አገኘሁ የምለው ነገር ስደተኛ በሚል ስም መጠራትን ብቻ ነው።" • ካናዳን በጥበብ ሥራው ያስዋበው ኢትዮጵያዊ "እናቴን፣ አባቴን፣ ባሌን አልቀበርኩም" ዓለምፀሐይ ወዳጆ የኪነጥበብ ሰው ዓለምፀሐይ ወዳጆ ከኢትዮጵያ የተሰደደችው ከ27 ዓመታት በፊት ነበር። ኢህአዴግ ሥልጣን ሲጨብጥ። የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቿ ከአመራሩ ጋር እንደማያኗኗሯት ለመረዳት ጊዜ አልወሰደባትም። "የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በሚመለከት፣ የኤርትራን ጥያቄ በሚመለከት እጽፋቸው፣ እተውናቸው፣ አቀርባቸው የነበሩትን ነገሮች፤ በነሱ የሬድዮ መቀስቀሻ ጣቢያ ላይ ያፌዙባቸው ነበር" ትላላች። ኢትዮጵያ ውስጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ምርጫ ተደርጎ ሕዝቡ በፈቀደው የምትመራ ሀገር እንጂ አንድ ብሔር ላይ የተመሠረተ አገዛዝ የሚሰፍንባት አትሆንም የሚል ጽኑ አቋም ነበራት። ደርግ ሲያበቃለት የመጣው መንግሥት የተሻለ እንደሚሆን አላመነችም። ዕለቱ ማክሰኞ ነበር። ከኪነ ጥበብ ጓዷ ታማኝ በየነ ጋር ራድዮ እያዳመጡ ነበር። ኮለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ከሥልጣን መውረዳቸውን ሰሙ። የዛኑ ዕለት ከሀገር ለመውጣት ወስና፤ አርብ ልጇቿን ይዛ ወደ አሜሪካ በረረች። የሁለት ዐሥርታት የስደት ኑሮ ለዓለምፀሐይ ቀላል አልነበረም። በግል ሕይወቷም፣ በሙያዋም ብዙ አጥታለች። "እናቴን አልቀበርኳትም፤ አባቴን አልቀበርኩትም፤ የምወደውን ባሌን አልቀበርኩትም። ከዚህ የበለጠ በሰው ላይ ሊደርስ የሚችል በደል ያለ አይመስለኝም" እህቶቿ፣ የእህቶቿ ልጆች፣ የአክስቶቿና የአጎቶቿ ልጆች ሲዳሩ፣ ሲወልዱ ከጎናቸው አልነበረችም። ደስታም ሀዘንም እንዳመለጣት ስትናገር ሀዘን በሰበረው ድምጽ ነው። ባዕድ ቋንቋ በሚናገሩ ሰዎች መካከል መኖር እንደ ጥበበኛ ዋጋ አስከፍሏታል። ከምትጽፍለት፣ ከሚወዳት ሕዝብ ርቆ መሥራት እንደከበዳት ስትገልጽ "በጽናቴና በጥንካሬዬ ጥርሴን ነክሼ ሙያዬ ውስጥ ለመቆየት ቻልኩ እንጂ፤ እጅግ አንገትጋች የስደት ሕይወት ነው የመራሁት" ትላለች። የኢትዮጵያ የጥበብ መድረክ ያለሷ ወደፊት መጓዙም ያስቆጫታል። በየጽሑፉ፣ በየትወናው፣ በየዝግጅቱ ውስጥ ብትሆን ኖሮ ልምዷን ለወጣቶች ታካፍል ነበርና። በገዛ ሀገሯ ስለ ሥራዎቿ ማውራት፣ ጽሑፎቿን ማንበብ እንደ ወንጀል መቆጠሩም ይቆጠቁጣታል። "ከተመልካቼ ጋር አብሬ፣ ተውቤ የማድግበት፤ ለኅብረተሰቤ ስለ እውነት፣ ስለ እኩልነት፣ ስለ ፍቅርና ሰላም የምዘምርበት መድረኬን ተነፍጌያለሁ።" ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ዓለምፀሐይ አንድም ቀን ተስፋ አልቆረጠችም። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ እንደሚለወጥ፣ ወደ ትውልድ ሀገሯ እንደምትመለስም ታምን ነበር። እሷ እንደምትለው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ የነበረው ግፍና በደል በፈጣሪ እገዛ እንዲሁም የኅብረተሰቡ መስዋእትነት አክትሞ፤ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን የመጀመሪያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ንግግርን ስታዳምጥ ከመቼው በላይ ተስፋዋ ለመለመ። "በኢትዮጵያ መሪዎች ያልተለመዱ ቋንቋዎችን ስሰማ..." ትላለች ቅጽበቱን ስታስታውስ። አሜሪካ ሳለች ኢትዮጵያና ኤርትራ እርቀ ሰላም ሲያወርዱ ከሥራዎቿ አንዱ የሆነው የማሕሙድ አሕመድ "ሰላም" መድረክ ላይ ሲቀርብ ፊቷ በእንባ ይታጠብ ነበር። ልጅ ሳሉ ትታቸው የሄደቻቸው የሕጻናት አምባ ታዳጊዎች ዛሬ ጎልምሰው ለዓመታት በናፈቀችው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ሲያወድሷት፤ ዕድሜና ሙያ ሳይለይ ሕዝብ በነቂስ ሲቀበላት የደስታ ሲቃ ተናነቃት። ከስብራት ለቅሶ ወደ ደስታ እንባ ተሸጋገረች። «ቤተሰቦቼን ባገኝም ዘግይቻለሁ»ፍስሃ ተገኝ የ97ቱን ምርጫ ተከትሎ አዲስ አበባ ተናጠች። የተቃውሞ ሰልፎች ይካሄዱም ጀመር። ሰልፎቹን ተከትሎ ስለተገደሉ ሰዎች ዜና ማንበብ የፍስሃ ተገኝ ድርሻ ነበር። "አብዛኞቹ ሰዎች የተገደሉት ባንክ ሊዘርፉ ሲሉ ነበር" የሚል ዘገባ ቀረበለት። ምላሹ "ህሊናዬ ስለማይፈቅድ ዜናውን አላነብም" የሚል ሆነ። ውሳኔው ከኤፍኤም አዲስ 97.1 ብቻ ሳይሆን ከሀገር እስከ መሰደድ አድርሶት ለ13 ዓመታት በእንግሊዝ ኖረ። የዜና አላነብም ውሳኔውን ተከትሎ ማስፈራሪያ ይደርሰው ነበር። በወቅቱ ሊቀጥረው ፍቃደኛ የነበረ መገናኛ ብዙኃንም አልነበረም። ለሦስት ሳምንት ያህል ስለ ሁኔታው ከጓደኞቹ ጋር ይመክር ነበር። ከራስ ሆቴል አካባቢ ብዙም የማይጠፋው ፍስሃ፤ ማክሰኞ ለንባብ ለሚበቃው ኢትዮ-ስፖርት ጋዜጣ ቅዳሜ ቃሉን ሰጠ። አስከትሎም ጋዜጣው ሳይወጣ በግብጽ አየር መንገድ አድርጎ ሀገሩን ተሰናበተ። "ቅጽበታዊ ውሳኔ ነበር፤ ጓደኞቼ ወደ እንግሊዝ የሚሄድ ተሳፋሪ ትኬት ቀይረው ሰጡኝ። ትኬቱን እንዴት እንዳገኙልኝ አላውቅም፤ ብቻ ከኪሴ አምስት ሳንቲም አላወጣሁም፤" ኤስኦኤስ ውስጥ ያደገው የስፖርት ጋዜጠኛው፤ ዘመድ አዝማዶቹን የማፈላለግ ፍላጎት ቢኖረውም፤ ባህር ማዶ ሆኖ የሚያሳካው ነገር አልነበረም። ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለመቻሉ ቤተሰቦቹን እንዳያፈላልግ ብቻ አይደለም ያገደው፤ ሙያዊ እድገቱንም ገታው እንጂ። በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2013 ላይ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈችበትን ጨዋታን ስቴድየም ተገኝቶ አለማየቱ፣ አለመዘገቡ ያስቆጨዋል። "አዲስ አበባ ስታዲየም ከሱዳን ጋር የተደረገውን የመልስ ጨዋታ፤ ጋዜጠኛ እንኳን ባልሆን እንደተመልካች ገብቼ አየው ነበር" በአውሮፓውያኑ 2007 ጥሩነሽ ዲባባ በኦሳካ የአለም ሻምፒዮና በ10ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች። ድሉን ለተቀዳጀችው ሯጭ ቃለ መጠይቅ ቢያደርግ ከምንም በላይ ይደሰት ነበር፤ አልሆነም እንጂ። ቤተሰቦቹን ፈልጎ ለማግኘት የግድ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንዳለበት ስለሚያውቅ፤ በአውሮፕላን መመለስ ባይችልም አማራጭ መንገዶች ያሰላስል ያዘ። በኤርትራ በኩል ልግባ? ወይስ በሱዳን አድርጌ? እያለ ሲያወጣና ሲያወርድ ኢትዮጵያ በተቃውሞ እየታመሰች ነበር። ከዛም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ሥልጣን ይዘው ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ንግግር ያደረጉበት ቀን መጣ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በንግግራቸው "ሀገሪቱን በአንድነት ለማቆየት፣ ድንበሯን ለማስጠበቅ መስዋእትነት ከተከፈለባቸው መካከል ካራማራ ይገኝበታል" ሲሉ ጆሮውን ማመን አቃተው። ለሱ ያ ንግግር "ሀገርህ መግባት ትችላለህ" የሚል ቀጥተኛ ጥሪ ነበር። ስሙ የማይጠቀስ ቦታ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲነገርለት የአውሮፕላን ትኬቱን ለመቁረጥ ወሰነ። የፖለቲካ ስደተኞች ሀገራችሁ ተመለሱ የሚለው ጥሪ ከመተላለፉ በፊትም ልቡ ተነሳሳ። «ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ያገኛቸው ድሎች ሲነሱ፤ በደርግ ጊዜ የተገኙ ድሎች በሙሉ ከደርግ አምባገነን ሥርዓት ጋር ብቻ ስለሚያያዙ ተሰርዘው ነበር። ጠፍተው ነበር» ይላል። የሀገሩን መሬት እንደረገጠ የቤተሰብ ፍለጋውን ተያያዘው። ፍለጋው የተጠናቀቀው በድል ነው። ዛሬ ላይ የዘር ሀረጉን አውቋል። ሆኖም ስደት ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀል የሚሰጠውን ሀሴት አዘግይቶበታል። "ከ 13 ዓመት በኋላ ስመለስ ቤተሰቦቼን ፈልጌ አግኝቻለሁ። የተወለድኩበትን ቦታ አውቄያለሁ፣ ዐይቻለሁ፤ ነገር ግን ዘገይቷል" ካሳሁን አዲስ ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር "ሕይወቴን እስር ቤት የማሳለፍ ፍላጎት አልነበረኝም" ካሳሁን አዲስ ካሳሁን አዲስ እንደ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኛነት በአውሮፓውያኑ ከ2005 እስከ 2009 ባሉት ዓመታት ተፈትኗል። ዘገባዎቹን ተከትሎ ማስፈራሪያና ማዋከብ ደርሶበታል። ቢሯቸው አስጠርተው ማስጠንቀቂያ የሰጡት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ነበሩ። Open Letter to Bereket Simon [ግልጽ ደብዳቤ ለበረከት ስምኦን] በሚል ርእስ ባለፈው ነሐሴ ላይ ያስነበበው ጽሑፍ መነሻም ያሳለፈው ውጣ ውረድ መሆኑን ይናገራል። "የሥራ ፍቃድ አይታደስልህም"፣ "የዋሽንግተን ፖስት ፈቃድ እያለህ ለታይም መጻፍ አልነበረብህም"፣ "የሀገር ገጽታ ታጠፋለህ"፣ "አዘጋገብህ ትክክል አይደለም..."ብዙ ተብሏል። በስተመጨረሻ ከሀገር ለመውጣት ውሳኔ ላይ የደረሰው የክስ መዝገብ እየተዘጋጀበት እንደሆነ ከታማኝ ምንጭ መረጃ ሲደርሰው ነበር። ሰኞ ዕለት የፍርድ ቤት መጥሪያ እንደሚደርሰው ሲሰማ ዓርብ ዕለት ወጣ። «ክሱ የፖለቲካ ስለነበረ አንዳንድ ቁርጠኞች እንዳደረጉት ፍርድ ቤት ሄጄ ለመታገል ወይም ሕይወቴን እስር ቤት ለማሳለፍ ፍላጎቱ አልነበረኝም» ሲል የያኔውን ውሳኔ ይገልጻል። ካሳሁን ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የብዙ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የስደት መዳረሻ ወደ ሆነችውና «አክስት ሀገር» ወደሚላት ኬንያ ሸሸ። ኬንያ ውስጥ ሥራ ቢጀምርም "ደኅንነቶች እየተከታተሉህ ነው" የሚል መረጃ ደረሰውና ሁለተኛ ሽሽቱ ወደ አሜሪካ ወሰደው። ብዙም ባይሆን በሙያው ሠርቷል። «የመብራትና ውሀ የሚከፍሉ» የሚላቸው ከጋዜጠኝነት ጋር የማይያያዙ ሥራዎችን ለመሥራት የተገደደበት ጊዜ ነበረ። ቀድሞ ኢትዮጵያ ነክ ጉዳዮችን ይተነትንላቸው የነበሩ የውጪ ሀገር ሚዲያዎች ከሀገሩ በመራቁ እንደ መረጃ ምንጭ ሊጠቀሙበት አልቻሉም። ስለ ኢትዮጵያ የሚያወሱ ድረ ገጾች መክፈት ቢሞካክርም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ታግደው ነበርና ነገሩ ሁሉ ትርጉም አልባ ሆነበት። ስደት ያጠላው በሥራው ላይ ብቻ አይደለም። የቤተሰብ፣ የጓደኛ ትስስሩ ላልቶበታል። በሱ አነጋገር "ከሀገር ስወጣ የሃያዎቹን አጋማሽ አልፌ ነበር። ስለዚህ የዛን ያህል ሕይወት ትቼ ነው የወጣሁት። " ያሳደጉት አያቱ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ መቅበር አለመቻሉ አሳምሞታል። ለመጨረሻ ጊዜ ዐይናቸውን አለማየቱ ሁሌም ይቆጨዋል። ሀገር ቤት ሳለ እናቱን አልፎ አልፎ ቢጠይቅ ነው። ዛሬ ዛሬ ግን ዘወትር በናፍቆት ይቆዝማል። ለጥቂት ጊዜ አሜሪካ ሄደው ቢያያቸውም በቂ አልነበረም። በተለይም አሁን በመታመማቸው ሁሌም ከጎናቸው ቢሆን ይመኛል። ኢትዮጵያ ቢኖር ፍሬያማ ሊሆን ይችል የነበረ የፍቅር ግንኙነት በመሰደዱ ሳቢያ ተቀጭቷል። ጓደኞቹን በስልክ ቢያገኛቸውም የልቡን አያደርስለትም። በግንባር ቀደምነት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ሕይወታቸውን ያጡ ብዙ ናቸው። ሞት ሳያስፈራቸው ለተቃውሞ ወደ አደባባይ የሚወጡትን ሰዎች ቁጥር ግን አልቀነሰውም። "አገዛዙ ብዙ አይቆይም፤ መቀየሩ አይቀርም፤ እኔም ሆንኩ ከኔ በፊትና በኋላም ከሀገራቸው ተገፍተን የወጣን ሰዎች መመለሳችን አይቀርም የሚል እሳቤ ያደረብኝ ያኔ ነው" አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር ሲፈታ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ)፣ አርበኞች ግንቦት 7 እንዲሁም ሌሎችም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች "ሽብርተኛ" ከሚለው ዝርዝር ሲወጡ ሀገሩ እንደሚገባ አገጋገጠ። ኢትዮጵያ፣ ኬንያ ብሎ አሜሪካን ሦስተኛ ሀገሩ ቢያደርግም፤ እንደ እናት ሀገር የሚሆን የለምና የያዝነው የፈረንጆች ዓመት ሳያልቅ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለስ ተስፋን ሰንቋል። ዳግመኛ ላያገኛቸው ያመለጡትን የሚክስ ምን ተዐምር ሊጠብቀው ይችላል?
news-52734564
https://www.bbc.com/amharic/news-52734564
በጥሬ ገንዘብ ዝውውር ላይ የተጣለው ገደብ ለምን አስፈለገ?
በኢትዮጵያ ከባንኮችና ከማክሮ ፋይናንስ ተቋማት በሚወጣ የጥሬ ገንዘብ ላይ የተጣለው እገዳ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። ብሔራዊ ባንክ ያወጣው መመሪያ ተቋማትና ግለሰቦች ከባንኮች በቀንና በወር ውስጥ በሚያወጡት የጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ገደብ ጥሏል።
በዚህም መሰረት አንድ ግለሰብ በቀን እስከ 200 ሺህ ብር እንዲሁም በወር እስከ 1 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ከባንኮች ማውጣት የሚችል ሲሆን፤ ተቋማት ደግሞ በቀን እስከ 300 ሺህ ብር እና በወር እስከ 2.5 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶክተር) ይህንን እርምጃ መውሰድ ያስፈለገው "የገንዘብ ዝውውርን ሥርዓት በማስያዝ ወንጀልንና የግብር ስወራን ለመከላከል ይረዳል" በሚል ነው ብለዋል። ይህን የብሔራዊ ባንክ እርምጃን በተመለከተ የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች አሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይ አንድ አገር ላይ የኢኮኖሚ ፖሊስ ሲወጣ፣ ምጣኔ ሃብቱ እንዲረጋጋ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚው ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ሲፈለግ ሁለት ዓይነት ኃይለ ፖሊሲዎችን እንደሚከተሉ ያስረዳሉ። በጀት ምን መምሰል አለበት፣ ሰዎችና የንግድ ተቋማቶች መክፈል ያለባቸው ግብር ምን ይመስላል ተብሎ የሚወሰንበትን እና የገቢዎች ሚኒስቴርና የገንዘብ ሚኒስቴር የሚቆጣጠሩት ፊሲካል ፖሊሲ አንዱ ሲሆን፣ ሞኒተሪ ፖሊሲ ደግሞ የብሔራዊ ባንክ የሚቆጠጣረው መሆኑን ያስረዳሉ። ብሔራዊ ባንክ ሲቋቋም ጀምሮ የአገሪቱ የገንዘብ አቅርቦት ምን መምሰል አለበት? ምን ያህል ገንዘብ ታትሞ በገበያ ውስጥ መሰራጨት አለባቸው? የሚለውን የመቆጣጠር የሥራ ድርሻው እንዳለው ያብራራሉ። በተጨማሪ ደግሞ በባንኮች በኩል ያለውን የወለድ መጠን፣ የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዋሲሁን፣ ብሔራዊ ባንክ በትናንትናው ዕለት ካሉት ሁለት ትልልቅ ስልጣኖች መካከል በመጠቀም የገንዘብ አቅርቦት በገበያው ምን መምሰል እንዳለበት ወስኗል ሲሉ ያስረዳሉ። የመንግሥት ውሳኔ መነሻ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? እንደ ምጣኔ ሃብቱ ባለሙያ አስተያየት ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የገንዘብ መጠን ላለፉት ብዙ ዓመታት በእርግጠኝነት ማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው። "በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከ700 እስከ 800 ቢሊየን ብር ድረስ በገበያው መሰራጨቱ ይታወቃል የሚሉት የምጣኔ ሃብቱ ባለሙያ እርሱንም ቢሆን በእርግጠኝነት ለማወቅ አስቸጋሪ ነው" ሲሉ ያለውን ፈተና ያብራራሉ። ስለዚህ እዚህ ገበያ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ማወቅ እንደሚያስፈልግ በማንሳት "የገንዘብ መጠኑ የማይታወቅ ከሆነ የተለያዩ ሕጋዊ ያልሆኑ የንግድ ሥርዓቶች ሊበራከቱ ስለሚችሉ ብሔራዊ ባንክ ያንን ለማወቅ አስቦ እንደወሰነው እገምታለሁ" ይላሉ። ሌላው መንግሥት ባይጠቅሰውም የገንዘብ እጥረት የአገሪቱ አንዱ ችግር መሆኑን ይጠቅሳሉ። "ጥሬ ገንዘብ አቅርቦት በጣም እያነሰ ነው። የኮሮናቫይረስ ክስተትን ተከትሎና በሌሎችም ምክንያቶች ሰዎች ያላቸውን ገንዘብ በእጃቸው መያዝ ይፈልጋሉ" የሚሉት ባለሙያው ለመንግሥት የገንዘብ እጥረት ገጥሞኛል ብሎ መናገር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ ከባድ መሆኑን ይናገራሉ። "ወረርሽኙን ተከትሎ ሰዎች ለመድኃኒት፣ ለሕክምናና ለምግብ የሚሆኑ ወጪዎችን ብቻ ነው እያወጡ የሚገኙት" የሚሉት ባለሙያው በተጨማሪም ነገ በሚሆነው ነገር ላይ ተስፈኛ መሆን አለመቻል ገንዘብን በባንክ ለማስቀመጥ ፍላጎት እንደሚያሳጣ ይጠቅሳሉ። "አሁን በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ ከባንክ ቤቶች እየወጣ መሆኑ ግልጽ ነው" በማለትም ከበሽታው በፊትም ቢሆን የልማት ባንክ ያልተመለሱ የተበላሹ ብድሮች እንዳሉት ሲናገር በርካታ ባለሃብቶች ብድር ወስደው መክፈል አልቻሉም ማለት እንደሆነም ያስረዳሉ። ኢንቨስትመንት ላይ ያሉ ሰዎች ራሳቸው ብድራቸውን መክፈል እንዲችሉ ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ሰዎች ያስቀመጡት ገንዘብ ባንክ ቤት ውስጥ የለም ማለት መሆኑን በማስረዳት ለገንዘብ እጥረቱ የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ያብራራሉ። "መንግሥት ግን ይህንን ውሳኔ የወሰንኩት እጥረት ስለገጠመኝ ነው ብሎ ሊል አይችልም" በማለትም የገንዘብ እጥረቱ እየገጠመ ነው ወደፊት ደግሞ በፍጥነት ሊገጥም መቻሉ ገሃድ መሆኑን ያስረዳሉ። "ምክንያቱም ወደ በሽታው [ኮሮናቫይረስ] ገና እየገባንበት ነው ይላሉ። ወረርሽኙ እየተስፋፋ ሲመጣ፣ የሰዎች እንቅስቃሴ ሲገደብ፣ አሁን ገበያ ላይ ያሉት ነጋዴዎች አቅማቸው ሲዳከም፣ ገንዘባቸውን በእጃቸው ይዘው መጠቀም ሲመርጡና ለአስፈላጊ ነገሮች ብቻ ሲያወጡ፣ የባንክ ቤት ሰልፍ ጠልተው እያወጡ ሲያስቀምጡ ወደፊትም ቢሆን እጥረት መፈጠሩ አይቀርም ይላሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይ። "ዜጎች በመጪው ጊዜ ላይ እርግጠኛ መሆን የማይችሉ ከሆነ ብራቸውን ስለሚይዙ የመቆጠብ አቅማቸው ደካማ ስለሚሆን የገንዘብ አቅርቦት እያነሰ ስለመጣ እርሱንም አስታኮ የወሰነው ይመስለኛል።" በተጨማሪነት ግን ኢንቨስትመንት እንዲያድግ ቁጠባን ለማበረታታት አስቦ መንግሥት የወሰነው እንደሚመስላቸው ባሙያው ጠቅሰው "ገንዘብ ከባንክና ከፋይናንስ ሥርዓት ውጪ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ አይፈቀድም።" ብዙ አገራቶች ይህንን ነገር እያስቀሩ መምጣታቸውን ገልጸው "ስለዚህ ብሔራዊ ባንክም የሆነ ቦታ ላይ ለጥሬ ገንዘብ ዝውውሮች ሥርዓት ማበጀት ነበረበት" ብለዋል። አቶ ዋሲሁን በላይ እና ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) "ተጻራሪ የምጣኔ ሃብት ፖሊስ" የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱ ቴሶ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ሲሉ እርምጃውን አጥብቀው ይተቻሉ። "ይሄ ይዞት የሚመጣው ነገር በጣም አደገኛ ነው። ከዚህ በኋላ ባለሃብቱ የሚከፈለውን ክፍያ በጥሬ ገንዘብ ይቀበልና ወስዶ ቤቱ ያስቀምጣል። ይህ ደግሞ ገንዘብ ወደ ባንክ ገብቶ እንቅስቃሴ እንዳይፈጠር ያደርጋል። ይሄ እርምጃ ከሚያመጣው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል" ይላሉ። ግብር ስወራን በተመለከተ ጉቱ (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ በኢትዮጵያ የሚጠበቅባቸውን ግብር ላለመክፈል 'ኪሳራ ደርሶብኛል' እያሉ ሪፖርት በማድረግ ግብር የሚያሸሹ በርካታ ነጋዴዎች መኖራቸው አይካድም ይላሉ። "ነገር ግን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ሰዎችን አሳደን የሚጠበቅባቸውን ግብር እንዲከፍሉ ማድረግ እንችላለን ወይ? ይህ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣል ወይ?" ሲሉ ይጠይቃሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው እንደሚሉት ከሆነ ይህ ዓይነት የመንግሥት ውሳኔ፤ "ከባንክ ውጪ ሊደረግ ወደ የሚችለው ልውውጥ ስለሚወስድ ምጣኔ ሃብቱን በአፍጢሙ ሊደፋ ይችላል" ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ጉቱ (ዶ/ር) ይህ የመንግሥት ውሳኔ አገሪቱ ኮሮናቫይረስ ከሚያስከትለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ በኋላ ለማንሰራራት በምታደርገው ጥርት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ያነሳሉ። "ከኮሮናቫይረስ ስርጭት በፊት የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የሚያበድሩት በቂ ገንዘብ አልነበራቸውም። ብሔራዊ ባንክ ራሱ ከተቀማጭ ገንዘቡ ማሻሻያ እያደረገ ለባንኮች ገንዘብ የሚለቅበት አጋጣሚዎች ነበሩ" ይላሉ ባለሙያው። አክለውም ከወረርሽኙ በኋላ ደግሞ እንደሚስተዋለው የዓለም ምጣኔ ሃብት እጅጉን ተጎድቷል፤ በኢትዮጵያም የፋይናንስ ተቋማት ለመደገፍ መንግሥት በብሔራዊ ባንክ በኩል 15 ቢሊዮን ብር እንዲቀርብ ማድረጉን አስታውሰዋል። "መንግሥት ይህን ያደረገው አበዳሪዎች ለተበዳሪዎች ጊዜ እንዲያራዝሙ፣ የወለድ መጠን እንዲቀንስ፣ ተጨማሪ ብድር የሚፈልጉ ብድር እንዲያገኙ፣ አምራቾች ምርታቸውን እንዲያስፋፉ ነው። "ለዚህ ደግሞ ጥሩ የገንዘብ አቅርቦ ወደ ኢኮኖሚው መፍሰስ አለበት እያልን አያሰብን ባለንበት ሰዓት ላይ የገንዘብ ዝውውር ላይ ገደብ መጣል ከተባለው ነገር ጋር የሚቃረን የምጣኔ ሃብት እርምጃ ነው የሚሆነው" ይላሉ። መልካም ጎኑ? መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ከተገደደብ ምክንያት አንዱ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት በማሰብ ነው። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ጉቱም (ዶ/ር) አሁን ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ወጪ በሚደረግ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ መጣል የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ጠቀሜታ አለው በማለት ይስማማሉ። ይህንንም ሲያስረዱ "ከወረርሽኙ በፊት የሰው እንቅስቃሴ እንደልብ ነበር። ሰዎች ገንዘብ በማዳበሪያ ጭነው ሃርጌሳ ይወስዳሉ፤ ወደ መተማ ይሄዳሉ። አሁን ግን በቫይረሱ ምክንያት ሰዎች እንደፈለጉት መንቀሳቀስ አይችሉም። ስለዚህ ባንክ ለመጠቀም ይገደዳሉ" ይላሉ። ይህንንም በምሳሌ ሲያስረዱ "አንድ ሰው ወደ ባንክ ገቢ የተደረገውን ገንዘብ ላውጣ ቢል፤ ወጪ የተጠየቀው ቅርንጫፋ ብዙ ገንዘብ ስለተጠየቀ ሥራ መስራት አቆመ ማለት። ግለሰቡም ይህን ያክል ገንዘብ ከየት አመጣህ ተብሎ ይጠየቃል። በዚህ መልኩ መቆጣጠር ይችላል" በማለት እርምጃው ሊኖረው የሚችለውን ጠቀሜታ ያስረዳሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዋሲሁን በላይበበኩላቸው የመንግሥት ውሳኔ መጥፎ አለመሆኑን ያስረዳሉ። "የገንዘብ አቅርቦቱን በጣም በጣም መቆጣጠር አለበት። ምክንያቱም የዋጋ ንረት ከሚቀጣጠልባቸው ነገሮች አንዱ ከፍተኛ ብር በገበያው ሲሰራጭ ነው። ሐሰተኛውን በር ከትክክለኛው መለየትም በጣም አስቸጋሪ ነው" በማለት መንግሥት እነዚህን ለመቆጣጠር አስቦ እንደሆነ ያምናሉ። "ውሳኔው ጥሬ ገንዘብ የመያዝ እንጂ ሰዎች ገንዘብ ማንቀሳቀስ የለባቸውም" የሚል አይደለም የሚሉት ባለሙያው፣ ከጥሬ ገንዘብ ውጪ ዲጂታላይዝ በሆነ ገንዘብ ግብይት ማከናወን የሚቻልበት ሥርዓት ካለ በሞባይል መገበያየት፣ በኤቲኤም፣ በቼክ፣ በፖስ ማሽን መገበያየት የሚችሉ ከሆነ ግብይቶች እንዲቆሙ አልተደረገም ይላሉ። ስለዚህም የመሸመት መጠኑን የሚገደብ ምክንያት አለ ብለው እንደማያስቡ የሚናገሩት አቶ ዋሲሁን፤ ከፍተኛ ገንዘብ ገበያ ላይ ተረጭቶ ገንዘቦቹ ምርትና ምርታማነት ላይ የማያርፉ፣ ፍላጎትን የሚያሳድጉ ከሆነ የዋጋ ግሽበትን የማቀጣጠላቸው እድል በጣም ከፍተኛ መሆኑን ያሰምሩበታል።
news-54198844
https://www.bbc.com/amharic/news-54198844
ኮሮናቫይረስ ፡ በኢትዮጵያ የሚካሄደው የኮቪድ-19 መድኃኒቶች ምርምር ምን ላይ ደረሰ?
የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት ዓለም ላይ ታች እያለ ነው።
ሁሉም አለኝ ባለው ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ መድኃኒት ላይ ምርምር ያካሄዳል። የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ከሆነ፣ በተለያዩ የዓለም አገራት ወደ 150 ክትባቶች ላይ ምርምር እየተካሄደ ነው። ነገር ግን እስካሁን ድረስ አንድም ፈዋሽ ነው የተባለ ክትባት አልተገኘም። በኢትዮጵያም በአሁኑ ወቅት 'ኮሮናቫይረስን ሊያክሙ ይችላሉ' ተብለው በቀረቡ አምስት መድኃኒቶች ላይ ምርምር እየተደረገ መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ተቋም የባህልና ዘመናዊ መድኃኒት ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ወርቁ ገመቹ ለቢቢሲ ገልፀዋል። አቶ ወርቁ እንዳሉት ከባህል መድኃኒት አዋቂዎች ማኅበር በኩል 'ለኮቪድ-19 ይሆናሉ የተባሉ' ከ50 በላይ መድኃኒቶች ለተቋሙ ቀርበዋል። ነገር ግን በአቅምና በሰው ኃይል ውስንነት ምክንያት ከእነዚህ መካከል 5 ያህሉን መርጠው መመልከታቸውንና ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ባህላዊ መድኃኒቶቹ በጭስ መልክ የሚታጠን፣ በሻይ መልክ የሚጠጣ፣ በቅባት መልክ የቀረበ፣ በምግብ መልክ የሚወሰዱ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ምርምር እንዲደረግባቸው መቅረባቸውን ገልፀዋል። ይሁን እንጂ በጭስ መልክ የቀረበውን በላብራቶሪ ደኅንነቱን ለማጥናት ስለማይቻል ሳይቀበሉት ቀርተዋል። በመሆኑም የተመረጡት አምስቱ ባህላዊ መድኃኒቶች በሻይ መልክ፣ በምግብ መልክ፣ በቅባት መልክ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መሆናቸውን አቶ ወርቁ ተናግረዋል። እስካሁን ባለው የጥናት ሂደትም ለመድኃኒቶቹ ጥቅም ላይ የዋሉትን የእፅዋት ዓይነቶችና ዝርያቸውን መለየታቸውንና ተያያዥ የጽሁፍ ዳሰሳ [Literature Review] በማድረግ መረጃው ተሰንዶ ወደ ቀጣይ ሂደት ለመሻገር ዝግጅት ላይ መሆናቸውን አቶ ወርቁ አስረድተዋል። መድኃኒቶቹ ከአምስት ሰዎች የመጡ ቢሆንም ከ30 በላይ እፅዋት እንደተካተቱበት የጠቀሱት አቶ ወርቁ፤ ለ30ዎቹ የእፅዋት ዓይነቶችም የተያያዥ ጽሁፍ ዳሰሳ መስራታቸውን ተናግረዋል። በዳሰሳውም "የእፅዋቱን ምንነት፣ ተመሳሳይ ስም ያላቸውን የመለየት፣ አካባቢያዊ ስም መኖር አለመኖሩን የማጥራት፣ በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም ዙሪያም የእፅዋቶቹ መገኛ የት እንደሆነና ለምን እንደሚጠቀሙባቸው የማጥናትና የመለየት ሥራ ተከናውኗል" ብለዋል። ሰዎች እነዚህን እፅዋቶች ለምግብነት የሚጠቀሙባቸው መሆን አለመሆናቸውንም በዳሰሳው አረጋግጠዋል። እፅዋቶቹ በውስጣቸው ምን ዓይነት ኬሚካሎች ይዘዋል የሚለውን በተመለከተም በሳይንሳዊ መንገድ ጥናት ተካሂዶባቸው መሆን አለመሆኑ፤ እንዲሁም ደኅንነታቸውንና የጎንዮሽ ጉዳት ካላቸው መለየትና ሰው ላይ ተሞክሮ እንደሆነ በዳሰሳቸው ተመልክተዋል። ነገር ግን እስካሁን ሰው ላይ የተሞከረ አለማግኘታቸውን አቶ ወርቁ ተናግረዋል። በዚህ ጥናት ምን ተገኘ? አቶ ወርቁ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አስካሁን በተደረጉት የጽሁፍ ዳሰሳ ጥናታት የደደረሱበት እነዚህ ባህላዊ መድኃኒቶች የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ወይም ለማከም የሚጠቅሙ ሆነው አለማግኘታቸውን ነው። ይሁን እንጂ የተለያዩ በሽታዎችን ለመፈወስ በባህላዊ መልክም ጥናትን የተካሄደባቸው አሉ። ለምሳሌ የሰውነት ሙቀትን የሚቀንሱ፣ በሽታ የመከላከል አቅምን የሚጨምሩ፣ የምግብ ፍላጎትን የሚጨምሩ ሆነው እንዳገኟቸው ገልፀዋል። ምርምሩ ማንን ያሳትፋል? በምርምር ሂደቱ እየተሳተፉ ያሉት በዋናነት የባህል መድሃኒት አዋቂዎቹ፣ የተቋሙ ተመራማሪዎች እና ናዲክ (ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ምርምርና ጥናት ማዕከል) ናቸው። በመድኃኒት ምርምሩ ላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተወጣጡ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን፤ በውጭ ከሚገኘው ናዲክ የምርምር ተቋም ያሉ ባለሙያዎችም በዚህ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ እንደሆኑ ዳሬክተሩ አስረድተዋል። ምርምሩ ምን ያህል ተስፋ ሰጪ ነው? በዚህ የምርምር ደረጃ ላይ ሆኖ ኮሮናቫይረስን ማዳን አለማዳኑን እርግጠኛ ሆኖ መናገር እንደማይችል ዳሬክተሩ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም የተለያዩ እፅዋቶች የተለያዩ በሽታዎችን ይፈውሳሉ ተብለው ሙከራ መካሄዱን ጠቅሰው፣ ቢሆንም ግን በሽታውን ሳይሆን የበሽታውን ምልክቶች ላይ ለውጥ ያመጡ እንደነበሩ አስታውሰዋል። ከመካከላቸው ግን የሚፈውሱም እንደነበሩ ገልጸዋል። በመሆኑም መድኃኒቶቹ "የበሽታ ምልክቶችን ሊያጠፋ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ በሳይንሳዊ መንገድ መረጋገጥ አለበት። በመሆኑም ተስፋ የለውም ወይም አለው ማለት ይከብዳል" ብለዋል አቶ ወርቁ። የምርምሩ ቀጣይ ሂደት ምንድን ነው? አቶ ወርቁ እንደገለፁት ከሆነ ከቤተ ሙከራ ውጪ ያሉ ሥራዎችን አጠናቀው ወደ ቤተ ሙከራ ምርምር ለመግባት የቤተ ሙከራ እንስሳትን እያራቡ መሆኑን አመልክተዋል። በመሆኑም እነዚህ እንስሳት አካለ መጠናቸውና እድሜያቸው ለላብራቶሪ ሙከራ ብቁ ሲሆን እነርሱ ላይ ሙከራ መደረግ ይጀመራል ብለዋል። ስለዚህ በሕብረተሰብ ጤና ተቋም ውስጥ የደኅህንነት ሥራው የሚሰራ ሲሆን የመድኃኒቶቹ የፈዋሽነት ወይም የፍቱንነት ሥራው ግን በሽታው አዲስ ከመሆኑና ከዚህ በፊት በተቋሙ ተሰርቶ ስለማይታወቅ 'ናዲክ' ከተባለ የምርምር ተቋም ጋር በጋራ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል። ዳይሬክተሩ እንዳሉት ይህ የሚሆነው መጀመሪያ ላይ የመድኃኒቱ የደኅንነት ሁኔታ [ምን የጎንዮሽ ጉዳት አለው የሚለው] ሲጠናቀቅ ነው። ምርምሩ ምን ያህል ጊዜ ሊወስድ ይችላል? እንደ አቶ ወርቁ ገለፃ በመድኃኒት ጥናት የሚደረገው የደኅንነት ፍተሻ አኪዩት (Acute) ለቤተ ሙከራ እንስሳቱ መድኃኒቱ ከተሰጠ በኋላ የሚደረግ ክትትል 14 ቀናትን ይወስዳል። ሌላው የደኅንነት ጥናት ሰብ አኪዩት (Sub Acute) ደግሞ 28 ቀናት ይፈጃል። ሌላኛው ሂደት ክሮኒክ የሚባል ሲሆን 90 ቀናት ወይም ሦስት ወራትን ይጠይቃል። ከዚህ ባሻገርም 6 ወራትም የሚያስፈልገው ሂደት ይኖራል። በዚህ ሂደት እንስሳቱ ላይ የታየው የጎንዮሽ ጉዳት ይጠናል። "አንድ ሰው በኮቪድ-19 በሽታ ከተያዘ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይድናል ወይም ይሞታል። በመሆኑም 28 ቀናት የሚወስደውን ሰብ አኪዩት የተባለ የደህንነት ጥናት መርጠናል" ብለዋል ዳይሬክተሩ። በዚህ ሂደትም ለእንስሳቱ ብቻ 28 ቀናት ይሰጣል። ከዚያም እነርሱን ለማጥናት እስከ 40 ቀን እንደሚወስድ ጨምረው ገልጸዋል። ይህ ከሆነ በኋላ ውጤቱ ታይቶ ፍቱንነቱ ወይም ፈዋሽነቱ ወደሚረጋገጥበት ደረጃ ይሸጋገራል። በዚህ ሂደት ጥራቱና ደረጃው ከተጠበቀ በኋላ ወደ ክሊኒካል ሙከራ እንደሚያመራ ሂደቱን አብራርተዋል። አንድ መድኃኒት ከመጀመሪያው ጀምሮ ለሰው ጥቅም እስከሚውል ድረስ ከ3 አስከ 14 ዓመታት ድረስ እንደሚፈጅ አመልክተው "ሳይንስ ስለሆነ አቋራጭ መንገድ የለም፤ ስለዚህ በዚህ ሂደት ማለፍ አለበት" ብለዋል። የኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መጋቢት ወር ገደማ የባህል ሕክምና አዋቂዎችን ከዘመናዊው ጋር በማጣመር ለኮሮናቫይረስ ሕክምና የሚያገለግል ተስፋ ሰጪ አገር በቀል መድኃኒት እየተዘጋጀ መሆኑን አስታውቆ ነበር። መድኃኒቱም መሠረታዊ የምርምርና ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሂደቶች ማለፉን በወቅቱ ተገልፆ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ለበርካቶች ተስፋ የሰጠ ቢሆንም "ምንም ባልተያዘበት ሰው ራሱን እንዳይጠብቅ ያዘናጋል" ሲሉ ብርቱ ትችቶች መሰንዘራቸው አይዘነጋም። በኢትዮጵያ እስካሁን ከ66 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረሱ ተያዙ ሲሆን 1060 ሰዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።
55737484
https://www.bbc.com/amharic/55737484
"ሱዳን ድንበራችንን አልፋ እንድትገባ የተደረሰ ስምምነት የለም" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር አልፋ እንድትጠብቅም ሆነ መሬት እንድትይዝ የተደረሰ ስምምነት እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጥር 12/ 2013 ዓ. ም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
መንግሥት ህግ ማስከበር በሚለው ወታደራዊ ዘመቻ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ባቀናበት ወቅት ድንበር አካባቢ ሊከሰቱ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን በተመለከተ ከሱዳን ጋር መግባባት ተደርሶ ነበር ብለዋል። "ድንበር አካባቢ የሁለቱን አገሮች ደህንነት የሚጎዳ እንቅስቃሴ እንዳይኖር በኛ አመራር ለሱዳን መንግሥት አደራ ተሰጥቷል" ያሉት ቃለ አቀባዩ አክለውም ሆኖም "ድንበሩን አልፈው አገራችን ግቡ መሬት ይዛችሁ ጠብቁልን የሚል አይነት ሊኖር የሚችል አይደለም፤ አልነበረም" ብለዋል። ከሰሞኑ የሱዳን ምክር ቤት ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ሱዳን ሰራዊቷን ወደ ድንበር ያስጠጋችው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብይ አህመድ ጥያቄና ፈቃድ ነው መባሉ ተዘግቧል። ለዚህም ምላሽ የሰጡት ቃለ አቀባዩ "ቅዠት ነው" ካሉ በኋላም "አጥፊ ኃይሎች የናንተን ድንበር ተጠቅመው ወደኛ ድንበር እንዳይገቡ ማለት ኑና ገብታችሁ ጭራሽ ያልተከለለና መቶ አመት በዚሁ ሁኔታ ይሁን ተብሎ የቆየውን መሬት ድንበር የኛ ነው በሉ ማለትም አይደለም" ብለዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በአመራር ደረጃ የተደረሰ ስምምነት እንዳለ መነገሩ ስህተት ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል የድንበር ይገባናል ውጥረት እየተጋጋለ ነው በተባለበት ወቅትም የመንግሥታቸውን አቋም ያስረዱት አምባሳደር ዲና፤ ሱዳን በትግራይ ክልል ግጭት ከተነሳበት ከሶስት ቀናት በኋላ፣ ከጥቅምት 27፣ 2013 ዓ.ም ያላግባብ የያዘችውን መሬት ትልቀቅና ወደ ንግግር እንግባ የሚል ነው። የሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት የአገራቸው ሠራዊት ግዛቴ ነው ከሚላቸው ቦታዎች ውስጥ አብዛኛውን መቆጣጠሩንና ይህም የማይቀለበስ እርምጃ መሆኑን መግለፃቸው የሚታወስ ነው። ሁለቱን አገራትን በተመለከተም የድንበር፣ የቴክኒክና ከፍተኛ ኮሚሽኖች ያሉ ሲሆን በየጊዜው ውይይቶችም ሲደረጉ እንደነበር አንስተዋል። ሁለቱን አገራት ለማስታረቅና ለማሸማገል የተለያዩ አካላትም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የጠቀሱት አምባሳደር ዲና "አገሮቹን እናደንቃቸዋለን፤ ይኸንን ያሰቡትን ጥሩ ነው እንላለን። ነገር ግን እኛ እኮ እምቢ አላልንም። እንነጋገር ነው እያልን ነው ያለነው። ያስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ ግን ወደነበራችሁበት ተመለሱና እንነጋገር የሚል ነው" ብለዋል። ጉዳዩ ያሳሰባት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኢትዮጵያና ሱዳን ያላቸውን የድንበር ላይ ውዝግብ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እንዲፈቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ ጠይቃለች። ቃለ አቀባዩ በመግለጫቸው ወቅት አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት ሱዳን የያዘችውን መሬት እንድትለቅ ኢትዮጵያ በቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧንና ይህ ከተሳካ ሁለቱ አገራት በዋናነትም ችግራቸውን ተነጋግረው መፍታት እንደሚችሉም አስረድተዋል። የሱዳንና የኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ምጣኔ ኃብት፣ ባህላዊና የህዝቦች ትስስርና ቁርኝት በመጥቀስም አገራቱ ወደ ግጭት ቢገቡም የሁለቱም ህዝቦች እንደሚጎዱ አፅንኦት ሰጥተዋል። በታሪካቸውም እንዲሁ ከመደጋገፍና ከመረዳዳት በስተቀር ይህ ነው የሚባል ግጭት ተከስቶ እንደማያውቅ የተናገሩት አምባሳደር ዲና በተለይም በሰላም ጥበቃ፣ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላቸውን ግጭት ለመፍታትና በአጠቃላይ የሱዳንና ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት ኢትዮጵያ ጉልህ ሚና ተጫውታለች ብለዋል። የህዝቦቹን ቁርኝትና የአገራቱንም እጣ ፈንታ አንድ መሆኑን አፅንኦት በመስጠትም አሁን ሱዳን እያደረገችው ያለችው ከህዝቡ የመነጨ አይደለም ይላሉ። "የሁለቱ አገራት ጥቅም ይተሳሰራል ስንል ግጭቱ ሁለቱንም አገራት እንደሚጎዳ እናውቃለን። ነገር ግን ሁለቱን አገሮች አባልቶ የራሳቸውን ጥቅም በመሃል መፍጠር የሚፈልጉ ወገኖች እንዳሉ እናቃለን።" ብለዋል። ቃለ አቀባዩ ሶስተኛ ወገን የሚሉትን አካል ባይጠቅሱም ሁለቱን አገራት በማበጣበጥ የሚጠቀሙ ኃይሎች አሉ በማለት የተናገሩ ሲሆን ግጭቱ የሱዳን ፍላጎት አይደለም ብለዋል። አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግሥት "አጥፊ ኃይሎች" ያላቸው አካላት በሱዳን ድንበር በኩል እንዳይገቡ ሲል አገራቱ ካላቸው ትስስር አንፃር እምነት በመጣል እንደሆነም ጠቆም አድርገዋል። "የፌደራሉ መንግሥት እምነት በሱዳን አለው እንጂ ከኋላ ይወጉናል የሚል እሳቤ በኢትዮጵያ በኩል እንዳልነበረ ነው። እንዲህ አይነት ተግባር ከጀርባ ይፈፅማሉ ብለንም ከኢትዮጵያ በጭራሽ ግምት አልነበረም። ያየነው ግን ተቃራኒውን ነው" ብለዋል። ስለ ኤርትራና ሶማሊያ ሰራዊት በዚሁ መግለጫ ላይ ትግራይ ላይ በተደረገው ወታደራዊ ግጭት የኤርትራ ሰራዊት ተሳትፏል ስለመባሉም ምላሽ ሰጥተዋል። ሁኔታውንም "ፕሮፓንዳና መሰረተ ቢስ ነው" ብለውታል። ከኤርትራም በተጨማሪ የሶማሊያ ሰራዊት ተሳትፏል መባሉን ሃሰት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአገሩን ዳር ድንበር ማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን በሶማሊያ፣ በሩዋንዳ፣ በብሩንዲና፣ ኮንጎ "ትልቅ ገድል የሰራ ኃይል ነው" በማለትም የሰራዊቱን ጥንካሬ አስረድተዋል። "የውስጥ የህግ በላይነትን ለማስከበር ማንንም አገር የሚጠራ አይደለም፤ የሚጠራም አገር የለም፤ ሊጠራም አይችልም፤ አይገባም፤ አይፈልግምም፤ አስፈላጊም አልነበረም" በማለት አፅንኦት በመስጠትም ነው የተናገሩት። ቢቢሲ ያናገራቸው የትግራይ ክልል ነዋሪዎች፣ አዲስ የተሾሙት የመቀሌ ከንቲባም ሆኑ፣ የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች አካላት የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸውን ቢናገሩም አምባሳደሩ በበኩላቸው ግጭቱን ቀጠናዊ ለማድረግና ጣልቃ ገብነትን ለመጋበዝ የተቃጣ ነው ብለውታል። ወደ አስመራ የተወነጨፉት ሮኬቶችም ይህንኑ ለማገዝና የኤርትራ ሰራዊት እንዲገባ በሚል ታቅዶም ነው ብለዋል። ነገር ግን ወደ ኤርትራ ሚሳይል ሲወነጨፍ አገራቱ ካላቸው ርቀት አንፃር የኤርትራ ሰራዊት ድንበር አካባቢ ድንበሩን ለማስከበር ሊታይ እንደሚችል ጠቁመዋል። "ይህንን ወስዶ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እየተዋጉ ነው ማለት ስህተት ነው። የኤርትራም የሶማሊያም ሌላ ኃይል አልነበረም። ብቃት አለው በራሱ ነው የጨረሰው" ብለዋል። ነገር ግን የአውሮፓ ሕብረት በከፍተኛ ዲፕሎማቱ ጆሴፕ ቦሬል በሰጠው መግለጫ " ግጭቱ ወደ ቀጠናዊ ወደ መሆን የመሸጋገር እድል አለው፣ ለምሳሌ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ግጭት ውስጥ መሳተፋቸው፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ መውጣታቸው" በማለት መጥቀሳቸው የሚታወስ ነው። አምባሳደር ዲና በበኩላቸው በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ሚዲያውም ሆነ የምዕራቡ አለም ግጭቱን ቀጠናዊ ለማድረግ ሲሰሩ የነበሩ ኃይሎች ነበሩ ብለዋል። በርካታ የጦር መሳሪያ አምራችና ሻጮች ጠመንጃ ከመሸጥ ጀምሮ እንዲሁም ግጭቶችን ሰበብ በማድረግ እርዳታ እስከማሰባሰብ ድረስ በአፍሪካ ከሚከሰቱ ጦርነቶች የሚጠቀሙ ኃይሎችም እንዲሁ ግጭቱ የቀጠናዊ መልክ እንዲኖረው ጥረዋል ብለዋል። "ንግድ ስለሆነ በየሚዲያውም ቀጠናዊ ለማድረግ እያራገበ ይገኛል፤ የምዕራቡ አለም ከግጭቱ መጠቀም ለሚፈልጉ በርካታ አገራት እንዲበጣበጡ ይፈልጋሉ ያሉት ቃለ አቀባዩ "ግጭቱ ቀጠናዊ ሳይሆን ከሽፏል" በማለትም ያለውን ፖለቲካ አስረድተዋል። ስለ ህዳሴ ግድቡ ሌላኛው ከሶስትዮሽ ህዳሴ ግድቡ ጋር ተገናኝቶ የተናገሩት አምባሳደር ዲና በህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ተጠቃሚዋ ሱዳን ናት ብለዋል። የህዳሴ ግድብ መሰረት በተጣለበት ወቅት ከሶስቱ አገራት የተውጣጣ ነፃ አለም አቀፍ የባለሙያዎች ጉባኤ ቡድን ግድቡ በከባቢ፣ ምጣኔ ኃብትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚለውን አጥንቶ በግምገማው መሰረትም አይጎዳም የሚል ማጠቃለያ ላይ መድረሱንን አስታውሰዋል። ሱዳን የህዳሴ ግድብ በደለልና በጎርፍ መጥለቅለቅን ከማስቀረት በተጨማሪ፣ ርካሽ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚነት፣ የዳበረ እርሻ እንዲሁም ደለል ለመጥረግ ከምታወጣው ወጪም እንደምታተርፍ ሱዳን ታውቃለች የሚሉት አምባሳደር ዲና፤ "የሚያነሷቸው ነገሮች የነሱ አይደሉም፤ ሌላ አካል ወክለው ነው እየሰሩ ያሉት" ይላሉ። በኢትዮጵያ በኩል አሁንም የተቀየረ ነገር እንደሌለና ድርድሩም ሆነ ግንባታና ሙሌቱ ተያይⶋ ይቀጥላልም በማለት የመንግስታቸውን አቋም አስረድተዋል።
54894546
https://www.bbc.com/amharic/54894546
የአሜሪካ ምርጫ፡ በ152 አመታት ውስጥ ለኦስቲን ምክር ቤት በመመረጥ ታሪክ የሰራው ትውልደ ኢትዮጵያዊ
ከሰሞኑ የአሜሪካ ምርጫ ጋር ተያይዞ የትራምፕና የባይደን ትንቅንቅ አሜሪካውያንን ብቻ ሳይሆን የመላው አለምን ቀልብ ሰቅዞ ይዞ ነበር።
ከዲሞክራቱ ባይደን ከፍተኛ ድምፅ አግኝቶ በፕሬዚዳንትነት ከመመረጣቸው በተጨማሪ የሚኒሶታ ግዛት ኦስቲን ከተማ በታሪኳ ጥቁር፣ አፍሪካዊ፣ ኢትዮጵያዊ እንዲሁም ስደተኛ በከተማ ምክር ቤት አባልነት መርጣለች። የ27 አመቱ ኦባላ ኦባላ ትውልዱ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ ነው። በስደት ወዳቀናባት አሜሪካ ዜግነቱን ያገኘው ከአንድ አመት በፊት ነው። ኦባላ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት በዩኒቨርስቲ ካምፓሶች ላይ ያለው የምግብ ደህንነትና የኤሌክትሮኒክስ መፅሃፎችን አቅርቦት በተመለከተ ከፍተኛ ቅስቀሳ ማድረጉ የተነገረ ሲሆን በምርጫውም ተፎካካሪውን በ481 የድምፅ ብልጫ እንዳሸነፈ ተዘግቧል። ስለ ምርጫው፣ በምክር ቤት አባልነቱ ስለሚያከናውናቸው የወደፊት እቅዶች፣ የስደት ጉዞውና ሌሎች ጉዳዮችም ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል። ቢቢሲ፦ በሚኒሶታ ግዛት፣ ኦስቲን ከተማ፣ የከተማዋ ምክር ቤት አባልነትን መቀመጫ ማሸነፍ ችለሃል። ማሸነፍህን ስትሰማ ምን አይነት ስሜት ተሰማህ? በወቅቱስ ምን አልክ? እንዴትስ ገለፅከው? ኦባላ፦ከመጠን በላይ ደስታ ነው የተሰማኝ! ምክንያቱም ይሄ ታሪካዊ ነው። በ152 አመታት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሚኒሶታ በከተማው ምክር ቤት አባልነት ጥቁር ስትመርጥ እኔ የመጀመሪያው ነኝ ። ከኔ በፊት የተመረጠ ጥቁር አልነበረም። የምረጡኝ ቅስቀሳ በማደርግበትም ወቅት አሸንፋለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር ምክንያቱም የምወዳደርበትና የወከልኩት አካባቢ (ዲስትሪክት) በሙሉ ነጮች ስለሆኑ። ነገር ግን ማሸነፌን ሳውቅ ከመጠን በላይ ደስታ ተሰማኝ። በከተማው ምክር ቤትም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሆኜ መመረጤ ከፍተኛ ደስታ ነው የሰጠኝ ቢቢሲ፡ እስቲ ወደ ምርጫ ቅስቀሳህ እንመለስና፤ መቼ ነው በምርጫው ለመወዳደር የወሰንከው? የምረጡኝ ቅስቀሳውስ ምን ይመስላል? የተወዳደርክበት አካባቢ የህዝቡ መዋቅርስ ምን ይመስላል? ኦባላ፡ የወከልኩት (የተወዳደርኩበት) አካባቢ 99 በመቶ ነጮች ናቸው። አፍሪካውያንና ሌሎች አናሳ ህዝቦች በጣም ዝቅተኛውን ስፍራ 0.05 ይሆናሉ። በከተማዋ ሌሎች ክፍሎች ስደተኞች ቢኖሩም እኔ የወከልኩትና ያሸነፍኩበት አካባቢ የነጮች ቦታ ነው። የምረጡኝ ቅስቀሳዬን የጀመርኩት ባለፈው አመት ግንቦት ወር አካባቢ ሲሆን በጣምም ፈታኝ ነበር፤ ምክንያቱም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ጋር ተያያይዞ በርካታ ዝግጅቶችን ማዘጋጀትም አልቻልንም። ሆኖም በመጨረሻ ሁሉ ነገር በሰላም ተጠናቀቀ። ቢቢሲ፡ የአሜሪካ ዜግነትህን ያገኘኸው ከአንድ አመት በፊት መሆኑን ሰምተናል? መረጃው ትክክል ነው? ኦባላ፦አዎ ልክ ነው። የአሜሪካዊ ዜግነቴን ያገኘሁት ታህሳስ 7 2012 ዓ.ም ነው። ቢቢሲ፦ ታዲያ መቼ ነው ለመወዳደር የወሰንከው? ኦባላ፦ለመወዳደር የወሰንኩት በግንቦት ወር፣ ከጥቂት ወራት በፊት ነው። ቢቢሲ፦ በተወዳደርክበት አካባቢ ዋነኛ ተቀናቃኝህ (ተፎካካሪ ) የነበሩት እነማን ነበሩ? ኦባላ፦ዋነኛ ተቀናቃኜ የነበረችው ሄለን ጃር የምትባልና የ66 አመት ግለሰብ ናት። ግለሰቧ እዚሁ ኦስቲን ከተማ የተወለደች ናት። ሙሉ ህይወቷንም በዚሁ ከተማ ነው የኖረችው። በምርጫው ወቅት ከፍተኛ ተፎካካሪዬም ነበረች ሆኖም የኦስቲን ህዝብ እኔን ለመምረጥ ወሰነ። ቢቢሲ፦ ወደኋላ እንመለስና እስቲ ስለ ልጅነትህ፣ አስተዳደግህና እዚህ ስለደረስክበት ጉዞ እናውራ። በኬንያ ውስጥ ባለው የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ እንደነበርክ እናውቃለን። በዳዳብ በነበርክበት ጊዜ አንድ ቀን በአሜሪካ ባለ ምክር ቤት አሸንፋለሁ ብለህ አስበህ ታውቃለህ? በዚያን ጊዜስ ህልምህ ምን ነበር? ኦባላ፦በአሜሪካ ምክር ቤት አሸንፋለሁ የሚል ሃሳብም ሆነ ህልሙም አልነበረኝ። ነገር ግን በዳዳብ ካምፕ ውስጥ ስደተኛ እያለሁ አንድ ቀን አሜሪካ ሄጄ የተሻለ ህይወት እኖራለሁ፤ እንዲሁም ጥሩ ትምህርትም አገኛለሁ የሚል ነበር እንጂ በአሜሪካ ፖለቲከኛ እሆናለሁ ብዬ አላለምኩም። አስቤውም አላውቅ። ቢቢሲ፡ ጋምቤላ በነበርክበት ወቅት በህፃንነትህ ከፍተኛ ፈተናዎች እንዳጋጠሙህ አንብበናል እናም ምን ነበር ያጋጠመህ? እስቲ ስለ አስተዳደግህ ትንሽ ንገረን። ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ያደረግከው ጉዞስ ምን ይመስላል? ኦባላ፦የተወለድኩት በኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ ነው። ታህሳስ 3/1996 ዓ.ም በጋምቤላ በደረሰው የዘር እልቂት (ጂኖሳይድ) ከ420 በላይ የአኝዋክ ህዝቦች ተገድለዋል። ያንንም ፍራቻ ነው ለመሰደድ የተገደድነው። ሸሽተንም ኬንያ በስደተኝነት መጣን። ከዚያ በፊት የነበረው የልጅነት ጊዜዬ መልካም ነበር። ቢቢሲ፦ ከዚያስ ኬንያ ነው የደረስከው? ኦባላ፦ከጋምቤላ ሸሽተን ለሁለት ሳምንት ያህል በእግራችን ተጉዘን የደቡብ ሱዳንን ድንበር ተሻገርን። ደቡብ ሱዳን ቆየን ከዚያም ወደ ኬንያ። በኬንያ የስደተኞች ካምፕም ውስጥ ለአስር አመት ያህል ቆይተናል። በ2013 (በጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር) የአምላክ ፈቃድ ሆኖ ወደ አሜሪካ አቀናን ቢቢሲ፦ አንድ ዜና ላይ ወደ ከንቲባው ቢሮ ዘው ብለህ ሄደህ በምን መንገድ አስተዋፅአኦ ማድረግ እችላለሁ? የሚል ነገር ተናግረህ ነበር የሚል አንብበናል፤ እስቲ በዝርዝር ስለ ጉዳዩ ንገረን ኦባላ፦አሜሪካ ከመጣሁ በኋላ በሳውዝ ዳኮታ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቀቀቅኩ። ከዚያም እናቴ ሚኒሶታ ከተማ ኦስቲን ግዛት መኖር ጀምራም ስለነበር ወደዚህ መጣሁ።ነዋሪነቴን በኦስቲን ካደረግኩ ከሶስት ወራትም በኋላ ከተማው ጥሩ እንደሆነ ተረዳሁ። እናም በኦስቲን የሚኖሩ የአኝዋክ ጓደኞቼን ሳዋራም ' የኦስቲንን ከንቲባ ታውቃላችሁ ?" እንዲሁም እነማን መሪዎቻችን እንደሆኑ ለምሳሌ የፖሊስ ኃላፊው ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ ብዬ ስጠይቃቸው። ሁሉም አናውቅም አሉኝ። ከንቲባ እንዳለ እናውቃለን ግን አግኝተናቸው አናውቅም አሉኝ። የከንቲባውን ፅህፈት ቤት አድራሻ በጉግል ፈለግኩና ወደቢሮአቸው ሄድኩኝ። ከንቲባውን እንዳየሁዋቸውም ስሜ ኦባላ ኦባላ ይባላል። በቅርብ ከሶስት ወራት በፊት ነው ወደ ኦስቲን ሚኒሶታ የመጣሁት። አሁን ተማሪ ነኝ። የኦስቲንን ከተማም ሆነ ነዋሪውን ለማገዝ ማድረግ የሚያስፈልግ ነገር ካለ አለሁኝ፤ የኦስቲንን ከተማ ለማገዝ በየትኛውም መንገድ አለሁ። ምክንያቱም ኦስቲንን በጣም ነው የምወዳት ከንቲባውም አዩኝና ማን ነህ አሉኝ? ከዚያም ያልኩዋቸውን ደግሜ ከስሜ ጀምሮ ነገርኩዋቸው። ከንቲባው ሳቁና ያሉኝ ነገር ቢኖር ቢሮዬ መጥተህ በምን መንገድ አስተዋፅኦ ላድርግ? በማህበረሰቡስ ልሳተፍ ያልከኝ የመጀመሪያው ስደተኛ ነህ። በኔና በከንቲባው መካከል ያለውም ግንኙነት እየጠነከረ መጣ። ከዚያም ከአመት በኋላ፣ በጎሮጎሳውያኑ 2016 የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ውስጥ ሾሙኝ፤ በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቦርድም ከ2016 ጀምሮ አገልግያለሁ። ቢቢሲ፦ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት ለህዝቡ እሰራለሁ ብለህ የገባሃቸው ጉዳዮች ይኖራሉ። ምንድን ናቸው ቅድሚያ ሰጥተህ የምትሰራባቸው? ኦባላ፦ዋነኛ ቅድሚያ ሰጥቼ የምሰራው የመኖሪያ ቤቶችን ችግር ነው። በኦስቲን በርካታ ቤቶችን፣ አፓርትመንቶችን መገንባት ይኖርብናል። ስደተኞች ወደ አሜሪካ በሚመጡበት ወቅት ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ቤት መከራየት አይችሉም። ሁለተኛው ደግሞ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ማግኘት ነው። በኦስቲን ተመጣጣኝ ዋጋ በሆነም ማቆያ ባለመኖሩ ብዙዎች ይቸገራሉ። ከዚያም በተጨማሪ ከሁሉ ነገር በላይ በኦስቲን በርካታ የስራ እድልን መፍጠር ነው። ከሁሉ ነገር በላይ የሚያነሳሳኝ ጉዳይ በማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ነው። እንደ ወጣት መሪም መሳተፍ፤ ድምፄንም ለየት ባለ መንገድ በዚህች ከተማም ሆነ ነዋሪውን ለማገዝ መጠቀም እፈልጋለሁ። ቢቢሲ፦ ስደተኛ ሆነህ ማሸነፍህ ለህፃናት በተለይም ሌሎች ስደተኛ ህፃናትን በማነቃቃት ደረጃ እንዴት ታየዋለህ? ኦባላ፦በኔ አስተሳሳብ ለየትኛውም ህፃን የማስተላልፈው መልዕክት በኢትዮጵያም፣ በደቡብ ሱዳን፣ ታንዛንያ በየትኛውም የአፍሪካ አገራት ለሚኖሩ ስደተኞች ይሁኑ ሌላ ህልማችሁ ትክክለኛ፤ ተገቢ ነው። በህፃንነታችሁ አሜሪካም መጥታችሁ ከሆነ በትልቅነታችሁም ከሆነ ጠንክራችሁ ከሰራችሁ የአሜሪካ ህልማችሁን ታሳካላችሁ። አሜሪካ ታላቅ ከሆኑ አገራት አንዷ ናት። በርካታ እድሎችም አሉባት። እነዚህ እድሎችም በቀላሉ አይመጡም፤ መውጣት መውረድ ያስፈልገዋል። የተሻለ ሰውነትም ይፈልጋል። ይሄንን መንገድም ነው ለነዚህ ህፃናት እየከፈትኩላቸው ያለሁት። በተለይም ማድረግ አልችልም ብለው ለሚያስቡ ህፃናት፤ አሜሪካም መጥቼ ይሄንን መፈፀም አልችልም ለሚሉ ነው። ትችላላችሁ! የሚል መልእክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። በአሜሪካም በህይወት መቆየት ከቻላችሁ የምታልሙትን ነገር በሙሉ ማከናወን ትችላላችሁ። ቢቢሲ፦27 አመትህ ነው። ገና ወጣት ነህ። ቀጣዩ የፖለቲካ ህይወትህ ምን ይሆናል? ኦባላ፦ብዙም ሩቅ አላስብም። በአሁኑ ወቅት በሚቀጥሉት አራት አመታት ዋናው አትኩሮቴ የኦስቲንን ከተማ መቀየር እንዲሁም ማሸጋገር ነው። ኦስቲን ሁሉን ተቀባይ እንደትሆን ማድረግና ሁሉም የሚበለፅግባት ከተማ እንድትሆን መስራት ነው። ከዚያ በኋላ የወደፊቱ ምን እንደሚሆን አላውቅም፤ ይሄ በራሱ ትልቅ ሃላፊነት ነው። በሚቀጥሉት አራት አመታት ለህዝቡ ቃል የገባሁትን በሙሉ መስራት አለብኝ።የአምላክ ፈቃድ ሆኖም ሌላ እድል ከመጣም እሱንም ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። በሚቀጥሉት አመታት ኦስቲን ለህፃናትና ለነዋሪዎቿ የተሻለች ቦታ ማድረግ እፈልጋለሁ።
news-48892878
https://www.bbc.com/amharic/news-48892878
ቆዳን ለማንጣት የሚከፈል ዋጋ፡ የሴቶች የቆዳ ክሬሞች የደቀኑት አደጋ
በርካታ ሴቶች የፊትን ቆዳ የሚያፈኩ ክሬሞችን ይጠቀማሉ። እነዚህ ክሬሞችም ሆኑ ቅባቶች ሕጋዊና ጤንነታቸው የተጠበቁ ካልሆኑ በቆዳና በአጠቃላይ ጤና ላይ ጠንቅን እንደሚያስከትሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ሚሊዮኖች በአፍሪካና በእስያ ቆዳቸውን ለማንጣት የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ በተለይ በአፍሪካና በእስያ አህጉራት የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በርካታ ሴቶች የቆዳቸውን ገጽታ ለማፍካት ብዙ ርቀት ተጉዘው ጉዳትን የሚጋብዙ ነገሮችን ይጠቀማሉ። በዓለም ዙሪያ ያሉ ቆዳን የሚያፈኩ ምርቶችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች በፈረንጆቹ 2017 ላይ 4.8 ቢሊዮን ዶላር ገቢን ያገኙ ሲሆን ይህ አሃዝም ከሃያ ዓመታት በኋላ በእጥፍ እንደሚያድግ ይጠበቃል። ለእነዚህ ምርቶች ከፍተኛው ፍላጎት ያለው ደግሞ በአፍሪካና በእስያ ባሉና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሰዎች ዘንድ ነው። • ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር እነዚህ ምርቶች ሳሙናን፣ ክሬሞችን፣ እንዲሁም በሰውነት ውስጥ የቆዳ ቀለምን የሚቆጣጠሩ የተፈጥሯዊ ንጥረ ነገሮች መመንጨትን ለማዘግየት ያስችላሉ የተባሉ የሚዋጡ እንክብሎችንና በመርፌ የሚደሰጡ ምርቶችንም ያካትታል። የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ 10 ሴቶች 4ቱ ቆዳን የሚያፈኩ ምርቶችን ይጠቀማሉ። በዚህ በኩል ናይጄሪያ ከሁሉም ሃገራት ቀዳሚ ስትሆን 77 በመቶ የሚሆኑ የሀገሪቱ ሴቶች ቆዳን የሚያፈኩ ምርቶችን ይጠቀማሉ። ቶጎ በ59 በመቶ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ በ35 በመቶ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል። በአህጉረ እስያ ውስጥ ደግሞ ከህንድ ሴቶች 61 በመቶዎቹ፤ ከቻይና ሴቶች ደግሞ 40 በመቶዎቹ ምርቶቹን በስፋት ይጠቀማሉ። ዓለም አቀፋዊ ፈተና እነዚህ ምርቶችን በተመለከተ የሰዎች ፍላጎት በጨመረ ቁጥር አብሮት ያለው ተግዳሮትም ከፍ ይላል። ጋናዊያን ሴቶች በማህጸናቸው ውስጥ ያለን ጽንስ ቆዳ ያፈካዋል በሚል ተስፋ ሲወስዱት የነበረውን እንክብል፤ ባለፈው ዓመት የጋና ባለስልጣናት እንክብሉ በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገር ምክንያት ነፍሰጡር ሴቶች እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቂያ አውጥተው ነበር። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች ቆዳን ያፈካሉ ከሚባሉ ምርቶች አንጻር ጠንካራ ሕግ ካላቸው ጥቂት የአፍሪካ ሃገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ ናት። ጋምቢያ፣ ኮትዲቯርና በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ደግሞ ሩዋንዳ ሜላኒን የተባለውን በሰውነታችን ውስጥ የሚመረት ንጥረ ነገር እንዲቀንስ የሚያደርግ ይዘት ያላቸውና በቆዳ ላይ ዘላቂ ጉዳትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ቆዳን ሚያፈኩ ምርቶች ወደ ሃገራቸው እንዳይገቡ ከልክለዋል። ሜላኒን የተባለው ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገር ቡናማ ወይም ጥቁር ሲሆን ለቆዳችን የሚሆነውን ቀለም ያመነጫል። ቆዳን የሚያነጡ ክሬሞች የሚሰሩባቸው ኬሚካሎች ጉዳትን ሊያስከትሉ ይችላሉ የባለሙያዎች ሚና የብሪታኒያ የቆዳ ጤና ተቋም እንዳለው ለቆዳ ቀለም ተብለው ጥቅም ላይ ከሚውሉት ምርቶች ውስጥ በባለሙያ ትዕዛዝና ክትትል የሚሰጡ እንዳሉና አንዳንድ የቆዳ ማፍኪያ ምርቶችም እንዲሁ የሚወሰዱ እንዳልሆነ አመልክተዋል። የተቋሙ ቃል አቀባይ የሆኑት አንተን አሌክሳንድሮፍ እንደሚሉት "አንዳንዶቹ የቆዳ መፍኪያ ምርቶች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን በቆዳ ሐኪም መታዘዝና የቅርብ ክትትል ሊደረግባቸው ይገባል። ካልሆነ ግን ውጤታቸው አደገኛ ነው።" • ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ? የብሪታኒያ የቆዳ ጤና ተቋም እንደሚለው ደግሞ የቆዳ ቀለምን በማፍካት በኩል እውቅና የተሰጠውና አስተማማኝ የሆነ ዘዴ የለም። ያለሃኪም ትዕዛዝ ጥቅም ላይ የሚውሉ ክሬሞች ጠቃሚ መሆናቸውን የሚያመለክት ነገር የለም። ምናልባትም ከሚጠበቀው ተቃራኒ ውጤትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፤ የሚሉት ቃል አቀባዩ "ቆዳን ተፈጥሯዊ ከሆነው ውጪ ሊያነጡ ወይም ሊያጠቁሩ ከመቻላቸው በተጨማሪ የቆዳን ተፈጥሯዊ ውበትን ሊያጠፉ ይችላሉ" በማለት ያስጠነቅቃሉ። የጎንዮሽ ጉዳት ከባለሙያ ትዕዛዝና የቅርብ ክትትል ውጪ ቆዳን የሚያፈኩ ምርቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች የሚከተሉትን የመሳሰሉ ከበድ ያሉ የጎንዮሽ ውጤቶች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። የቆዳ መንደብደብና እብጠት የማቃጠልና የመቆጥቆጥ ስሜት ማሳከክና የቆዳ መሰነጣጠቅ (ምንጭ፡ ኤንኤችኤስ ዩኬ) የሃገራት አቋም ቆዳን በማቅላት በኩል ፈጣን ውጤትን እንደሚያስገኙ የሚነገርላቸው አንዳንድ ምርቶች ደግሞ ጎጂ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዙ ናቸው። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በውስጣቸው የሜርኩሪ ንጥረ ነገርን የያዙ ቆዳን የሚያፈኩ ምርቶች ለጤና በጣም አደገኛ ናቸው። ጨምሮም ሜርኩሪ በውስጣቸው የሚገኙ ምርቶችን በቻይና፣ በዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ በሌባኖስ፣ በሜክሲኮ፣ በፓኪስታን፣ በፊሊፒንስ፣ በታይላንድና በአሜሪካ ውስጥ እንደሚመረቱ ጠቁሟል። የአውሮፓ ሕብረትና በርካታ የአፍሪካ ሃገራት ሜርኩሪን በውስጣቸው የያዙ የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች ላይ እገዳ የጣሉ ሲሆን፤ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ፊሊፒንስና ሌሎች ጥቂት ሃገራት ደግሞ በዝቅተኛ መጠን እንዲኖር ይፈቅዳሉ። ሜርኩሪ ሜርኩሪ የተለያዩ የጤና ችግሮችን የሚያስከትል "መርዝ ነው" ይላሉ ቃል አቀባዩ አሌክሳንድሮፍ፤ ቆዳን በሚያፈኩ ክሬሞችና ሳሙናዎች ውስጥ በሚገኝ ሜርኩሪ ሳቢያ ከሚከሰቱ ተጓዳኝ ችግሮች መካከል (ምንጭ: የዓለም ጤና ድርጅት) ጥንቃቄ በፊንበርግ የህክምና ትምህርት ቤት መምህርና የውበት መጠበቂያ ምርቶች በሚያስከትሉት አሉታዊ ውጤት ላይ ምርምር ያደረጉት አሜሪካዊው የቆዳ ሃኪም የሆኑት ዶክተር ሹይ ዡ እንደሚሉት "አንዳንድ የቆዳ ክሬሞችን በአግባቡ ካልተጠቀምንባቸው በውስጣቸው የሚይዟቸው ንጥረ ነገሮች ጉዳትን ያስከትላሉ።" ገበያው ተመሳስለው በተሰሩ ምርቶች የተጥለቀለቀ በመሆኑ ሃሰተኞቹን ከትክክለኛው ለመለየት አስቸጋሪ ነው። አስመስለው የሚሰሩትን፣ የሚያጓጉዙበትንና የሚሸጡበትን መንገድ መለየት ለትክክለኞቹ አምራቾች አዳጋች እንደሆነም ይነገራል። • ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን ለዚህ ደግሞ ጠንካራ የመቆጣጠሪያ ደረጃዎችን ማዘጋጀት አደገኛ ምርቶችን ወደ ገበያ እንዳይገቡ ለማድረግ እንደሚያስችል ዶክተሩ ይመክራሉ። ጨምረውም ከበድ ያለ ውጤት ያላቸውን ምርቶች ተጠቃሚዎች ሲገዙ የባለሙያ ምክርና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል። የተዛባ አመለካከት በተለያዩ ማህበረሰቦች ባህልና ቋንቋ ውስጥ ነጭ ቀለም በአብዛኛው ከሰላም፣ ከውበት፣ ከአዋቂነት ጋር የተዛመደ ትርጉም ሲሰጠው ጥቁር ደግሞ ከሞት፣ ከአደጋ፣ ከመጥፎ ገጽታና ስሜት ጋር ተመሳሳይ ተደርጎ ይወሰዳል። ከውበት አንጻር ዘወትር እንደሚባለው ዋነኛው ውበት ውስጣዊ ነው፤ ነገር ግን በቆዳ ቀለም አንጻር ያለው የተሳሳተ አመለካከለት እጅጉን ስር የሰደደ ነው። ይህ ደግሞ በርካቶች የቆዳ ቀለማቸውን 'ለማስተካከል' ጤንነታቸውን ለጉዳት እስከሚዳርግ እርምጃ ድረስ እንዲሄዱ እየገፋቸው ነው። አመለካከትን መለወጥ የመዝናኛው ኢንደስትሪም የተወሰነ አይነት የሰውነት ቅርጽና የቆዳ ቀለምን ተቀባይነት እንዲያገኝ በመስራቱ ከመወቀስ አልፎ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሴቶች ላይ በጎ ያልሆነ ስሜትን ፈጥሯል። የቁንጅና ውድድሮችና ማስታወቂያዎች ላይ የፈካ የቆዳ ቀለም ከፍ ያለ ትኩረት የሚሰጣቸው በመሆኑ በርካቶች ቆዳን የሚያፈኩ ምርቶችን አንዲጠቀሙ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጽእኖ ሲፈጥሩ እንደቆዩ ይገመታል። • ሙንጭርጭር ሥዕሎች ይህንንም አመለካከት ለመለወጥ የተለያዩ የማህበረሰብ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። ከእነዚህም መካከል ህንዳዊያን ሴቶች ያላቸውን የቆዳ ቀለም ተቀብለው ለማንጣት የሚያደርጉትን ጥረት እንዲተዉ "ጥቁር ውብ ነው" በሚል የተጀመረው ዘመቻ አንዱ ነው። ፓኪስታን ውስጥም "ቆንጆ ለመባል የነጣ ቆዳ አያስፈልግም" የሚል እንቅስቃሴ አለ። በአሜሪካም በሶማሊያ ስደተኞች ላይ ትኩረት በማድረግ ቆዳን የሚያፈኩ ተግባራትንና ለተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች ያለውን ተጋላጭነት ለማስወገድ ተመሳሳይ በአንድ ቡድን አማካይነት ጥረት እየተደረገ ነው። ህንድ ውስጥ ከእምነት አንጻር የሚወከሉ የአማልክት ምስሎች ነጭ የቆዳ ቀለም ስላላቸው ይህንን ለመቀየር ጥቁር ገጽታ እንዲኖራቸው በማድረግ "ጥቁር መለኮታዊ ነው" የሚል እንቅስቃሴም ተጀምሯል።
45036021
https://www.bbc.com/amharic/45036021
የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝና የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በዚምባብዌ መዲና ሃራሬ ተገናኝተዋል።
በርካቶች ሁለቱ ግለሰቦች አንድ ላይ የሚታዩበትን ፎቶግራፍ በማህበራዊ ድረ ገፅ ከተጋሩት በኋላ አቶ ሃይለማሪያም በፌስቡክ ገፃቸው በአገሪቱ ሰላማዊ ሽግግር ከተደረገ በኋላ የቀድሞ የአገሪቱ መሪዎች በተለያየ መልኩ በአገራቸው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎ ቢኖራቸው ምኞታቸው እንደሆነ በመግለፅ ፎቶግራፉን ለጥፈውታል። ኢህአዴግ ሥልጣን ሲቆጣጠር ወደ ዚምባብዌ የሸሹት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ለ17 ዓመታት ያህል መርተዋል። ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በሌሉበት ክስ ተመስርቶባቸው የሞት ፍርድ እንደተፈረደባቸው ይታወሳል። ሌሎች የደርግ ባለስልጣኖች ከዓመታት እስር በኋላ በምህረት መለቀቃቸውም እንዲሁ ይታወቃል።
news-55984483
https://www.bbc.com/amharic/news-55984483
ትግራይ፡ ጥቅምት 24 በሰሜን ዕዝ ላይ ደረሰ የተባለው ጥቃት ምን ነበር?
የትግራይ ክልልን ያስተዳድር የነበረው ሕወሓት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈፅሟል መባሉን ተከትሎ የፌደራል መንግሥቱ "የሕግ ማስከበር" የሚለውን ወታደራዊ ዘመቻ መውሰድ ከጀመረ መቶ ቀናት ሊሞላው የቀረው በጣት የሚቆጠር እድሜ ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በህወሓት ኃይሎች ላይ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያዘዙት በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል። በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት ኃይሎች መካከል በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ተካሂዶ የፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት ዋና ከተማዋ መቀለን ጨምሮ የተለያዩ የትግራይ ከተሞችን በሦስት ሳምንት ውስጥ መቆጣጠር መቻሉ ይታወሳል። ኅዳር 19/2013 ዓ.ም የፌደራሉ ሠራዊት መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ ጦርነቱ መጠናቀቁን እና ቀጣይ የመንግሥታቸው ተግባር በሕግ የሚፈለጉ የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ሥር ማዋል እና ትግራይን መልሶ መገንባት መሆኑን አስታውቀዋል። ከዚያ በኋላም ከፍተኛ የሕወሓት አመራሮች በመከላከያ ቁጥጥር ስር ሲውሉ የተወሰኑት ደግሞ ተገድለዋል። ምንም እንኳን የፌደራል መንግሥቱ መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ውጊያው ተጠናቋል ቢልም የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ የተለያዩ አካላላት በገጠሪቷ የትግራይ ክፍል ውጊያው እንደቀጠለ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። የአገር መከላከያ ሠራዊት መቀለ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ከተማዋ አቀንተው ከከፍተኛ የጦሩ አዛዦች ጋር ውይይት ባደረጉትበት ወቅት፤ የአገር መከላከያ ሠራዊት የተልዕኮ አፈጻጸም "የየትኛውም አገር ወታደር አይደግመውም" ብለው ነበር። የአገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሰጧቸው ቃለ መጠይቆች ሠራዊቱ "አስደናቂ" የሚባለውን ድል በአጭር ጊዜ መቀዳጀት የተቻለው በሁለት ዋነኛ ምክንያቶች ነው ይላሉ። እነዚም ሠራዊቱ "በእልህ" በመዋጋቱ" እና የሎጂስቲክ አቅርቦቱ የተሟላ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ ለዘመቻው ስኬት ወሳኝ ነበሩ ያሉትን ጠቅሰዋል። የሰሜን እዝ በወፍ በረር ሲቃኝ የሰሜን እዝ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተካሄደውን ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነትን ተከትሎ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ጀምሮ በትግራይ ክልል ውስጥ የሰፈረ ሲሆን አገሪቱ ካላት ሠራዊት ውስጥ በሰው ኃይልና በታጠቀው መሳሪያ አንጻር ግዙፉ እንደሆነ ይታመናል። የሕወሓት ተዋጊ ኃይል በበኩሉ በርካታ ድል ያስመዘገበ ጦር ነው። በ1993 ዓ.ም ወታደራዊውን መንግሥት ከሥልጣን ያስወገደና ለረዥም ዓመታት የተካሄደ ጦርነትን በድል አጠናቅቋል። በ1990 ዓ.ም ደግሞ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር የነበረው ጦርነት ላይ የኢትዮጵያ ጦር የሰሜን እዝ ተሳትፏል። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለውጊያ ዝግጁ የሆኑ እስከ 200 ሺህ ገደማ ወታደሮች እንዳሉት ይነገር ነበር። የሕወሓት ታጣቂ ኃይሎች የህወሓት ኃይሎች ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በገጠሙት ጦርነት የክልሉን ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ማሰለፋቸው ይታመናል። ነገር ግን የትግራይ ልዩ ኃይል ወታደሮችና የሚሊሻ ብዛት በትክክል አይታወቅም። እንዲሁም ይህ ወታደራዊ ኃይል የሚታጠቀው መሳሪያ ብዛት እና ዓይነትም በግልጽ አይታወቅም። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ የአገር መከላከያ ሠራዊት መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በከተማዋ ተገኝተው ከአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት የህወሓት ኃይል ብዛት ወደ 80 ሺህ ይገመት እንደነበር ተናግረዋል። ህወሓት ፈፀመ የተባለው ጥቃት በሰሜን እዝ ላይ ምን ያህል ጉዳት አደረሰ? በብአዴን አባልነታቸው እና በሕወሓት ደጋፊነታቸው የሚታወቁት ሴኩ ቱሩ በህወሓት ሥር ይንቀሳቀስ በነበረው የቴሌቪዥን ጣብያ ላይ ቀርበው የሕወሓት ኃይሎች ሰሜን እዝን ስለማጥቃታቸው ተናግረው ነበር። በዚህ በክልሉ ይተላለፍ በነበረው ቴሌቪዥን ላይ ሴኩ ቱሬ ቀርበው ሲናገሩ " ትግራይን ለማንበርከክ በሁሉም አቅጣጫ የተሸረበው ሴራ ሊጠናቀቅ መቅረቡን ደርሰንበታል፣ በፍጥነት መወሰን ያስፈልግ ነበር. . . ለዚያም ነው የሰሜን እዝን በፍጥነት በ45 ደቂቃ ለመቆጣጣር እርምጃ የተወሰደው" ብለዋል። የሕወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረፂዮን ገብረሚካዔል በበኩላቸው የሕወሓት ታጣቂዎች የሰሜን እዝን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውንና የመከላከያ አባላት ከትግራይ ወገን መቆማቸውን በወቅቱ ተናግረው ነበር። የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ በሰነዘሩት ጥቃት በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ምን ያክል እንደሆነ በመንግሥት በይፋ የተነገረ ነገር የለም። ይሁን እንጂ በሰሜን ዕዝ ሥር ከሚገኙ ቢያንስ በአራት ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሮች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የጦር አዛዦች ለመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል። 7ኛ ሜካናይዝድ በሰሜን ዕዝ ስር ከሚገኙት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የ7ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ግርማ ከበበው በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ላይ በተላለፈው ቃለ መጠይቃቸው፤ በሚመሩት ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል። መድፍ፣ ታንክና ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን እንደታጠቁና "የህወሓት ኃይሎች የጦር መሳሪያ ለመዝረፍ" በክፍለ ጦራቸው ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ብርጋዴር ጀነራል ግርማ ተናግረው፤ ጥቃቱን ሲከላከሉ ቆይተው ከ8ኛ ሜካናይዝድ ጋር ወደ ኤርትራ መሸሻቸውን ገልጸዋል። "ሁለቱ ክፍለ ጦሮች (7ኛ እና 8ኛ) አንድ ላይ ሆነው ትልቅ መሰዕዋትነት ነው የተከፈለው። እነዚህ ሁለት ሜካናይዝድ ጦሮች የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው። ከባድ መሳሪያዎችን ይዘን ባንወጣ ኖሮ ከባድ አደጋ ይደርስ ነበር" ሲሉ ተናግረዋል። 8ኛ ሜካናይዝድ የ8ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ናስር አባዲጋ በተመሳሳይ በሰጡት ቃል "የህወሓት ኃይሎች በእዙ ስር በሚገኙ ክፍለ ጦሮች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ጥቃት መፈጸማቸውን" ተናግረዋል። ብርጋዴር ጀነራል ናስር የጥቃቱ ዓላማ "የጦር መሳሪያዎችን ለመዝረፍ ያለመ እንደነበረ" ተናግረው፤ እርሳቸው ከሚመሩት ክፍለ ጦር "ምንም አይነት መሳሪያ አለመዘረፉን" ተናግረዋል። 5ኛ ሜካናይዝድ በሰሜን ዕዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱም በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ የሚመሩት ጦር በህወሓት ኃይሎች ለሦስት ቀናት ተከቦ መቆየቱን ገልጸዋል። ማዘዣውን ዳንሻ ከተማ ባደረገው 5ኛው ሜካናይዝድ ጦር ላይ ጥቅምት 24 ጥቃት የተከፈተው "ሠራዊቱ ታጥቆ የሚገኘውን ከባድ መሳሪያዎች ለመዝረፍ" እንደሆነ ብርጋጄር ጀነራል ሙሉዓለም ተናግረዋል። "የጥቃቱ አላማ የዕዙን ትጥቅ ለመንጠቅ ነበር። ትጥቆቻችን በእጃችን ነው ያሉት። ምንም ትጥቅ አልተዘረፈም" ብለዋል። ብ/ጀ ሙሉዓለም ለሦስት ቀናት ያክል ተከበው ሲታኮሱ ከቆዩ በኋላ "ከበባውን ሰብረን ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረናል" ብለዋል። 4ኛ ሜካናይዝድ በመቀለ ከተማ የሚገኘው 4ኛው ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የህወሓት ኃይሎች ተቆጣጥረውት እንደነበረ በሰሜን ዕዝ የ4ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የጦር መሳሪያ ክፍል ኃላፊ ሻለቃ አድማሱ ደመቀ በኢቢሲ ላይ በተላለፈ ቃለ መጠይቅ ተናግረው ነበር። የህወሓት ኃይሎች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5፡30 ላይ ከሜካናይዝዱ አመራሮች መካከል ከተወሰኑት ድጋፍ በማግኘት ክፍሉን ከተቆጣጠሩ በኋላ ጦር መሳሪያዎቹንና ሰነዶችን መውሰዳቸውን ሻለቃ አድማሱ ተናግረዋል። እንደ ኢትዮጵያ መንግሥት ከሆነ በአገሪቱ ትልቁ እንደሆነ በተነገረው የሰሜን እዝ ላይ የደረሰው ጥቃት በሚገባ ታስቦበትና ታቅዶ የዕዙን ጦር መሳሪያዎች ለመቆጣጠር ያለመ ነበር። በርግጥ በዚህ ጥቃትም ሆነ ተከትሎ በነበረው ግጭት ዕዙን ምን ያህል እንደጎዳው ይፋዊ የሆነ መረጃ የለም። ግልጽ የሆነው ነገር ቢኖር ለወራት የዘለቀው የፌደራል መንግሥቱና ትግራይን ሲያስተዳድር የነበረው ሕወሓት በበርካታ ጉዳዮች አለመግባባት፣ ወደ ሰሜን እዝን ማጥቃት እና በኢትዮጵያ የቅርብ ታሪክ ውስጥ ከተደረጉ ጦርነቶች መካከል አንዱና ቁልፉ ሆኖ መመዝገቡ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከጥቅምት 24 ጥቃት በኋላ ሕወሓት ቀዩን መስመር በማለፍ የፌደራል መንግሥቱን ምርጫ በማሳጣት እርሳቸው "የሕግ ማስከበር" ያሉትን ዘመቻ ለማካሄድ ተገድዷል ብሏል። በክልሉ የከሰተው ግጭት በርካቶች ቀያቸውን ጥለቀው እንዲሰደዱም አድርጓል። ከ2 ሚሊዮን በላይም በዚያው በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው ይገኛሉ። ከ50 ሺህ በላይ ደግሞ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ሸሽተዋል። የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢዎች ከትግራይ ክልል እየተሰደዱ ያሉ ዜጎችን ለመድረስ እንዲቻል ያለገደብ አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። በክልሉ ያለው ሁኔታም ወደ ሰብዓዊ ቀውስ ሊሸጋገር ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በትግራይ ክልል በተከሰተው ግጭት ምን ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም።
news-54435795
https://www.bbc.com/amharic/news-54435795
ልደቱ አያሌው፡ “አቶ ልደቱ በፍትሕ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጧል”
የአቶ ልደቱ አያሌው የመቶ ሺህ ብር የዋስትና መብት እንዲጸና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ያስተላለፈውን ማዘዣ ለቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቢሰጡም፤ ፖሊስ አቶ ልደቱን አልለቅም ማለቱን የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዘዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለቢቢሲ ገለጹ።
"ፖሊስ አለቅም በማለቱ ተስፋ ቆርጠን ወደ አዲስ አበባ ተመልሰናል። አቶ ልደቱ ምንም እንዳይደረግ ብሎ በመከልከሉ እኛም ጠበቆቹም ከዚህ በኋላ በፍትሕ ሥርዓቱ በኩል ተጨማሪ እንቅስቃሴ አናደርግም። እሱም ከልክሎናል እኛም አናምንበትም" ብለዋል አቶ አዳነ። አቶ ልደቱ በፍትሕ ሥርዓቱ ተስፋ እንደቆረጡ ገልጸው፤ "ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ከመጠበቅ ውጪ የትም አትሂዱ ብሎናል" ብለዋል። የፍርድ ቤት ውሳኔ በአስፈጻሚው አካል እየተሻረ እያዩ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ በኋላ "ፍርድ ቤት አቅም አለው ብለን አንሄድም። የፍርድ ሂደቱን በፈለጉት መንገድ ያስኬዱታል። የፖለቲካ ውሳኔ ነው" ሲሉ አክለዋል። ስለጉዳዩ ትላንት ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት እንዳደረጉ ገለጸዋል። ኮሚሽነሩ ከፖሊስ ጋር እንደሚነጋገሩ እንደገለጹላቸውም አስረድተዋል። በተጨማሪም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ደብዳቤ ማስገባታቸውንም ገልጸዋል። "ማንኛውም አካል ለፍርድ ቤት ውሳኔ ተገዢ መሆን አለበት። የሕግ የበላይነት እየተጣሰ ከሄደ ሥርዓት አልበኝነት በአገሪቱ ነግሷል። አስፈጻሚው አካል ከማንም ቁጥጥር በላይ ሆኗል። ይህን እያደረገ ያለው የፖለቲካ ሥርዓቱ ነው" ሲሉም አቶ አዳነ ተናግረዋል። አቶ አዳነ እንዳሉት፤ ፖሊስ ከፍርድ ቤት የተላለፈውን ውሳኔ ያልተቀበለው ለሦስተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት በነፃ ሲያሰናብታቸው፣ ከዛ ደግሞ የመቶ ሺህ ብር ዋስ ሲወስንላቸው፣ አሁን ደግሞ ዋስትናው እንዲጸና ውሳኔ ሲተላለፍም ፖሊስ አቶ ልደቱን ከእስር እንዳልፈታቸው አስረድተዋል። "አቶ ልደቱ ከጤናቸው አንጻር ውጪ ቢወጡም ከፍትህ ይርቃሉ፣ ይጠፋሉ ብለን አናምንም ስለዚህ ውጪ ወጥተው ይከራከሩ ብሎ እንዲለቀቁ ብሎ ነበር" ያሉት የፓርቲው ፕሬዘዳንት፤ አቶ ልደቱ በዛሬው ችሎት "ይህን ብትወስኑም ፖሊስ እንደማይለቀኝ አምናለሁ። ስለዚህ ከዚሁ ልሰናበት" እንዳሉም አክለዋል። ፍርድ ቤቱ የዋስትናው መብት እንዲጸና ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፍ ለአቶ ልደቱ ቢገልጽም፤ "እኛም እንደፈራነው፣ አቶ ልደቱም እንደፈሩት ፖሊስ አለቅም ብሏል" ብለዋል። የትናንቱ የፍርድ ቤት ውሳኔ ምን ይላል? የድምፃዊ ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ልደቱ ከዚህ ቀደም ተፈቅዶላቸው የነበረው የመቶ ሺህ ብር ዋስትና እንዲፀና በትናንትናው ዕለት፣ ማክሰኞ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት መወሰኑን የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አቶ አዳነ ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ማክሰኞ ዕለት፣ መስከረም 26፣ 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የዋስትና እግድን በተመለከተ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ሲሆን፣ የአቶ ልደቱ የዋስትና ጥያቄ እግድ አይገባውም፣ ዋስትና ሊፈቀድላቸው ይገባል የሚለውን የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመቶ ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ የሚለውን ውሳኔ አፅንቶ እንዲፈቱም ትዕዛዝ አስተላልፏል። ከዚህ ቀደም አቶ ልደቱ ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከራከሩና፣ የዋስ መብታቸው እንዲከበር የምስራቅ ሸዋ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳልፎ የነበረ ሲሆን የቢሾፍቱ ፖሊስ በበኩሉ አቶ ልደቱ "በአደራ ነው" ያሉት በማለት አልለቅም ማለቱ ይታወሳል። ይህንንም ጉዳይ ማክሰኞ የዋለው ችሎት ላይ አቶ ልደቱ ስጋታቸውን መግለፃቸውን አቶ አዳነ ይናገራሉ። "ከዚህ በፊት የነበረውን ሁኔታ በመጥቀስ ፖሊስ አልለቅም ሊል ይችላል፤ ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ከዚሁ በነፃ ያሰናብተኝ የሚል ጥያቄ አንስተው ፍርድ ቤቱ ግን ለፖሊስ በአስቸኳይ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ የ100 ሺህ ብር ዋስትናውን ለወሰነው ለምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ትዕዛዙ እንዲደርስ በሚል ወስኗል" ብለዋል አቶ አዳነ። ከዚህ ቀደም የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ በመቶ ሺህ ብር ዋስ ወጥተው ጉዳያቸውን ውጭ ሆነው እንዲከላከሉ በሚል ለመስከረም 20፣ 2013 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፎ ቀጠሮ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ያንን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ወስደው እንዲያስፈፅም በጠየቁበትም ወቅት ፖሊስ አልፈታም ማለቱ ይታወሳል። አቶ ልደቱም በእስር ለሁለት ቀናት ከቆዩ በኋላ የአቶ ልደቱ ዋስትና የሚታገድበት ክስ (አቤቱታ) አቃቤ ህግ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት አቅርቧል። ፍርድ ቤቱ መስከረም 20፣ 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎትም አቃቤ ህግ አቶ ልደቱ በዋስትና መውጣት የለባቸውም በሚል እንደ ምክንያትነት ያቀረባቸውን መከራከሪያ ሃሳቦች ሰምቷል። አቃቤ ህግም አቶ ልደቱ ዋስትና እንዲከለከሉ ካቀረባቸው ምክንያቶች መካከል በዋስትና ቢወጡ የውጭ የህክምና ቀጠሮ ስላላቸው ሄደው ሊቀሩ ይችላሉ፣ ምስክሮችን ያስፈራራሉ፣ በደጋፊዎቻቸው አማካኝነት ውጭ ሆነውም ተፅእኖ ይፈጥራሉ፤ እንዲሁም የተከሰሱበት የጦር መሳሪያ ክስ ከ18-20 አመት የሚያስፈርድ ነው የሚል ነው። አቶ ልደቱ በበኩላቸው ውጭ ወጥተው ይቀራሉ ለሚለው "ከመጀመሪያውም ውጭ የህክምና ቀጠሮ እንዳላቸው የተናገርኩት እኔ ነኝ ይህንን በተናገርኩበት ሁኔታ አቃቤ ህግ እንደራሱ የክስ ጭብጥ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም፣ ውጭ ወጥቼም የምቀር አይደለሁም፣ ባለኝ ቀጠሮ ለመምጣት እንዲያመቸኝ ነው የውጭ ቀጠሮዬን የተናገርኩት።፡" ማለታቸውንም አቶ አዳነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቃቤ ህግ እንደ መቃወሚያ ላቀረበው " ምስክሮቹን ያስፈራሩብኛል' ለሚለው ምስክሮቹን ለማስፈራራት ምክንያት እንደሌላቸውና ምስክሮቹ መሳሪያው እጃቸው ሲገኝ ከተገኘ የታዘቡ ሰዎች መሆናቸውን ጠቅሰው እሳቸው ደግሞ መሳሪያው በእጃቸው መገኘቱን ባልካዱበት ሁኔታ ምስክሮችን ሊያስፈራሩ እንደማይችሉም ተከራክረዋል። በሶስተኛ ደረጃ ደጋፊዎች ለተባለው" የፖለቲካ ፓርቲ ነው የምመራው ደጋፊዎች ይኖሩኛል፣ ደጋፊዎች ተፅእኖ ያሳድራሉ ብሎ የፖለቲካ አመለካከቴን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ የመብት ጉዳይ መነሳት የለበትም።" ብለዋል በህገ ወጥ መሳሪያ ክስና ከ18-20 አመት ስለሚያስፈርድ በዋስ ሊለቀቁ አይገባም ብሎ አቃቤ ህግ ላቀረበውም መሳሪያውን የሰጣቸው መንግሥት መሆኑን የተናገሩት አቶ ልደቱ እየከሳሳቸውም ያለውም መንግሥት መሆኑንም ተናግረዋል። ይህንን ደግሞ እለመካዳቸውን ጠቅሰው "በኦሮሚያ ባለው ህግም ደግሞ ህጋዊ አድርግ ተብሎ ነው መጠየቅ ያለብኝ እንጂ ሊያስከስሰኝም የሚችል ስላይደለ በዚህ የዋስትና ጥያቄዬ መልስ ማግኘት አለበት" ብለው ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱ የግራና ቀኝ ክርክሮቹን ከሰማም በኋላ ገምግሞ ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ልደቱ ውጭ ሆነው ቢከራከሩ ከፍርድ አደባባይ፣ ከፍትህ ይርቃሉ ብሎ እንደማያምን ፣ ከዚህ በፊት የነበራቸውም የፖለቲካ ተሞክሮ፣ ያላቸው ተደማጭነት፣ አሁንም ቢሆን ህግን አክብረው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በማየቱ ስለዚህ ቢወጡም ሊቀሩ እንደማይችሉ በማመን የአቃቤ ህግን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን አቶ አዳነ ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ የመሳሪያው ክስም ከ18-20 አመት የሚል ቢሆንም በመሳሪያው የሞተም ሆነ ለመግደልም የታሰበ ሰው ስለሌለ፤ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የክሱን ከባድነት ፍርድ ቤት ስላላመነበት ከዚህ በፊት የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሰነው ውሳኔን አፅንቶታል። የልብ ህመምተኛ የሆኑት አቶ ልደቱ ጤና ስጋት ላይ እንደጣላቸው የሚናገሩት አቶ አዳነ ሆኖም በቢሾፍቱ ያለው የፖሊስ ጣቢያ አያያዝም መልካም እንደሆነ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ ቢሾፍቱ ፖሊስ ጣቢያ እያመሩ ሲሆን ስጋቱ እንዳለ ሆኖ ፖሊስ የሚወስነው ውሳኔ ያለውን የፍትህ ስርአትም የሚያሳይ ይሆናል ብለዋል።
news-47849679
https://www.bbc.com/amharic/news-47849679
"ሐዘኑ አንደበቴን ሰብሮታል፤ አእምሮዬን አቃውሶታል" የካፒቴን ያሬድ አባት ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ
ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ የሰማኒያ አመት አዛውንት ናቸው። የቢቢሲ ባልደረቦች ያገኟቸው ወቅት ከደረሰባቸው ሐዘን መፅናናት አቅቷቸው ፊታቸው ላይ በሚያሳብቅ ሁኔታ ስሜታቸው ተሰብሮ ነበር። እንዴት ነው አባት በረቱ? ተብለው ሲጠየቁም "ምርኩዜን ነው ያጣሁት" አሉ።
እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ጠዋት ላይ 149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረው አውሮፕላን ቢሾፍቱ አቅራቢያ ነበር የተከሰከሰው። ዜናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በትዊተር ገፃቸው ላይ ነው። ሁኔታውም ብዙ ኢትዮጵያውያን ከማስደንገጥ በላይ ብዙዎችም አንብተዋል። ለመሆኑ አውሮፕላኑን በዋና አብራሪነት ሲያበር የነበረው ካፒቴን ያሬድ አባት ዶክተር ጌታቸው ተሰማ የሰሙበትን ቅፅበት እንዴት ያስታውሱታል? ዶ/ር ጌታቸው፡ ባለቤቴ ደወለችልኝ። ያሬድ እመጣለሁ ብሎ ደውሎልኝ ነበር፣ እስካሁን ግን አልደረሰም። የሰማኸው ነገር አለወይ አለችኝ። የሰማሁት ነገር የለም ብያት ወደ አየር መንገዱ ደወልኩ። መጀመሪያ ላይ ሊነግሩኝ አልፈለጉም። በኋላ ግን ሊደበቅ የሚችል ነገር ስላልሆነ የደረሰውን አደጋ ነገሩኝ። ለባለቤቴም ነገርኳት። እና ጠዋት ወደ አራት ሰዓት ግድም ነው የሰማሁት አደጋውን እንደሰማሁ ራሴን ስቼ ወደቅኩ። አፋፍሰው ሆስፒታል ወሰዱኝ። ስነቃ በሆስፒታል አልጋ ላይ ኦክስጂን ተሰክቶልኝ ነው የነቃሁት። ከአደጋው በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኛችሁት መቼ ነበር? ዶ/ር ጌታቸው፡ ከሶስት ቀን በፊት ይሆናል። ብዙ ጊዜ ሲመለስ ነው የሚደውልልኝ። አንዳንድ ጊዜም ጠዋት ሲሄድ ይደውልልኛል። አንድ ወይም ሁለት ቀን ካለው ደግሞ አዳማ ያለው ቤቴ መጥቶ ይጎበኘኛል። ታዛዥ እና ቅን ልጅ ነበር። ሌሎችም ልጆች አሉኝ። ያሬድን የሚተካ ግን አንድም የለም። አንዳንድ ጊዜ አዲስ አበባ ሄጄ ያመሸሁ እንደሆን እርሱ ቤት አድራለሁ። ማለዳ ስነሳ የሚንከባከበኝ እርሱ ነበር። ብዙ ልጆች ቢኖሩኝም ብዙዎቹ ውጪ ስለሆኑ በሀሳብ፣ በመግባባት ቀረብ ያለኝ እርሱ ነው። ሐዘኑ አንደበቴን ሰብሮታል። አእምሮዬን አቃውሶታል። የሆነ ሆኖ ሞቱ በሀገር ደረጃ ስለሆነ ኩራትም ክብርም ይሰማኛል። ዛሬ ጊዜ ሞት ሰበቡ ብዙ ነው። ያሬድ ለመሆኑ ምን አይነት ልጅ ነበር? ዶ/ር ጌታቸው፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ስፖርት ወዳድ ነበር። በተለይ በዋና በርከት ያሉ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል። በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የነበረው ስሜትና ፍላጎት በአጠቃላይ ስፖርት ነበር። እያደገ ሲሄድ ከመሰናዶ በኋላ አውሮፕላን አብራሪ የመሆን ፍላጎት እንዳለው ይናገር ጀመር። እኔም እናቱም በሕክምና ዘርፍ ውስጥ ስላለን፤ ቢያንስ ያሉኝን መፅኃፍት የሚያነብልን ስለምፈልግ፤ ወደ እኔ ወይም ወደ እናትህ ሙያ ብትመጣ ደስ ይለኛል ብለው እርሱ ግን የምትችሉ ከሆነ ፓይለትነት ብታስተምሩኝ ፍላጎቴ እርሱ ነው የሚል ሀሳብ አቀረበ። እንግዲህ ስሜት ካለህ አንከለክልህም በማለት ፍላጎቱን ተቀበልን። • አውሮፕላኑ 'ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ነበር' • የበረራ አስተናጋጆች ከአደጋው በኋላ በነበራቸው በረራ ምን ተሰማቸው? መጀመሪያ ፍላጎታችን ደቡብ አፍሪካ ሄዶ እንዲማር ነበር። በኋላ ላይ ግን፤ ለኔም ወደ ሀገሬ መመላለሻ ምክንያት እንዲሆነኝ በማሰብም፤ ኢትዮጵያ ሄዶ እንዲማር የሚል ሀሳብ ለባለቤቴ አቀረብኩላት። የአየር መንገዱ ትምህርት ቤት የታወቀ እና በርካታ ኢትዮጵያውያንንና አፍሪካውያንን ያፈራ ስለሆነ እዚያ ሄዶ እንዲማር ፍላጎቴ ነበር። ሌላው ልጆቼ በሙሉ የሚኖሩት ውጪ ሀገር ነው። አንድ ልጅ እንኳን በአስራት ደረጃ ወደ ሀገር ይመለስ በማለት ከቤተሰቡ ጋር ከተወያየን በኋላ ስለተስማማን አዲስ አበባ ሄዶ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ተማረ። ስንት ልጆች አለዎት? ዶ/ር ጌታቸው፡ ስድስት ያሬድ ስንተኛ ልጅዎ ነው? ዶ/ር ጌታቸው፡አምስት አብራሪ ለመሆን ለምን ፍላጎት እንዳደረበት አጫውቶዎት ያውቃል? ዶ/ር ጌታቸው፡ ልጆቼ ሁሉ የሚሉት እንዳንተ ሐኪም እንሆናለን ነበር። ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያሉ ሀሳባቸውን እየቀየሩ መጡ። እርሱም ሁለተኛ ደረጃ ላይ እያለ ነው ሀሳቡን የቀየረው። ይመስለኛል በትምህርት ቤታቸው የቀድሞ ተማሪዎች ፓይለት ሆነው እየመጡ ንግግር ያደርጋሉ። እርሱም መሰናዶ እየተማረ እያለ ፍላጎት አደረበት። እኛም አልከለከልነውም። • አደጋው ስፍራ በየቀኑ እየሄዱ የሚያለቅሱት እናት ማን ናቸው? ስለሚያበረው አውሮፕላን ዘመናዊነት አጫውቶዎት ያውቃል? ዶ/ር ጌታቸው፡ ብዙ አውሮፕላኖችን በረዳትነት ጭምር አብሯል። ድሪም ላይነር እና ሌሎች ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ጨምሮ። የተለያየ ሀገራትም በሯል። በስራው ደስተኛ ነበር። ፍላጎትም ጭምር ነበረው። መብረር ብቻ ሳይሆን በስራው የተሻለ ለመሆን ጥረት ያደርግ ነበር። በእረፍት ጊዜው ያነብ ነበር። ወደ አሜሪካም በራሱ በመሄድ የንግድ አውሮፕላን ማብረር የሚያስችለው ስልጠና ሁለት ጊዜ ወስዷል። ምስክር ወረቀትም አግኝቷል። በእድሜው ምንም እንኳ ትልቅ ሰው ባይሆንም በስራው ከፍ ያለ ግምትና አስተሳሰብ የነበረው ልጅ ነበር። እንደነገሩኝ በርካታ ስልጠና ወስዷል። አደጋው ከደረሰ በኋላ የአብራሪዎቹ ጥፋት ይሆን የሚል ትንሽ ጥርጣሬ አላደረብዎትም? ዶ/ር ጌታቸው፡ አላደረብኝም። ምክንያቱም እነደነገረን አብዛኞቹ አውሮፕላኖች ዘመናዊ ናቸው። አንድ ጊዜ ግን ምን ብሎኛል..'በዚህ አውሮፕላን ስንሄድ ስንሰራ አንዳንድ ጊዜ ችግር ይታያል' ሲል በትንሹ ነግሮኛል። ግን የትኛው እንደሆነ አላውቅም። ብዙ ቅሬታ አያቀርብም። በወር ውስጥ በርካታ ሰዓታትም ይሰራ ነበር። በአደጋው ቦይንግን ይወቅሳሉ? ዶ/ር ጌታቸው፡ አዎ፤ በጣም፤ ምክንያቱም ስለምን በኢንዶኔዢያ ከደረሰው አደጋ በኋላ ይህ አውሮፕላን እንዳይበር አላደረጉም። ስለምን እንዲበር ፈቀዱ? ምክንያታቸው ከሌላ አምራቾች ጋር ያላቸው ውድድር ሊሆን ይችላል። ብዙ መሸጥ ፈልገውም ይሆናል። በአንዳንድ ያደጉ ሀገራት ክቡር የሰው ልጅ ዋጋ የለውም። በአውሮፕላኑ ላይ ተገቢው መሳሪያ ባለመገጠሙ ልጄን አጥቻለሁ። ለዚህ ደግሞ መሪር ሀዘን ተሰምቶኛል። ነገር ግን በስራው ላይ እያለ ነው የተሰዋው። ያ ቀጣዩ ትውልድ የሚያስታውሰው ይሆናል። ለዚህ ነው ሀገር ሁሉ ጀግና ሲለው የምትሰማው። የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። •"እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም እቅዱን አጫውቶዎት ያውቃል? ዶ/ር ጌታቸው፡ አዎ ምን አለዎት? ዶ/ር ጌታቸው፡ እጮኛ ነበረችው። እርሷም ካፒቴን ናት። በሚቀጥለው አመት ትዳር ለመመስረት እቅድ ነበራቸው። እኔም አዲስ አበባ ቤት ስላለን ያንን ቤት መኖሪያ እንደሚያደርጉ ቃል ገብቼለት ነበር። የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ላይ ፓይለቶቹ አውሮፕላኑ እንዳይከሰከስ የተቻላቸውን ማድረጋቸውን ጠቅሷል። እርስዎ እንደአባት ይህንን ሲሰሙ ምን ተሰማዎት? ዶ/ር ጌታቸው፡ ኩራት ነው ያደረብኝ። መስሪያ ቤቱም የፖለቲካ ግፊት ሳያድርበት ትክክለኛውን ነገር በማድረጋቸው አመሰግናቸዋለሁ። ከዚህ በፊት ሊባኖስ ላይ የደረሰው ተልከስክሶ ነው የቀረው። በአሁኑ ሰዓት ግን የደረሰው ሁኔታ በገለልተኞች ተጠንቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለአለም በማቅረባቸው ትልቅ ምስጋና አቀርባለሁ። አየር መንገዱም እንኮራባቸዋለን በማለቱ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሌላውም አለም ምሳሌ ነው ብዬ አስባለሁ። የተሰጠው ምስክርነት ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለወደፊት በአየር መንገዱ ወደፊት ፓይለት ለመሆን ፍላጎት ላለው ወጣት ሁሉ ትልቅ ምሳሌ ነው ብዬ ነው የማምነው። የቦይንግ አምራች የሆነው ኩባንያ በአደጋው ማዘኑን ገልፆ ይቅርታ ጠይቋል። ከቦይንግ የተሰማው ይቅርታ በቂ ነው ብለው ያስባሉ? ዶ/ር ጌታቸው፡ ከዚህ በፊት ይሰጡ የነበሩ አስተያየቶችን ስከታተል ነበር። በጋዜጦች የሚሰጡትንም ጨምሮ። ያበረሩበትን ሰአት ጨምሮ አስቀያሚ አስተያየቶች ይሰጡ ነበር። ይህ ከባድ ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው። ያሬድ ከ8 ሺህ ሰአቶች በላይ በሯል። ረዳት አብራሪውም እንደዛው። ሁለቱም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል። ቦይንግ ግን በርካታ የፈጠራ ታሪኮችን ይነግረን ነበር። ራሳቸውን መከላከል እንደፈለጉ ይገባኛል። እነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች ትንንሾቹን መደቆስ ይፈልጋሉ። አሁን እውነቱ ወጥቷል። እነርሱም ይቅርታ ጠይቀዋል። ነገር ግን በጣም የዘገየና እዚህ ግባ የማይባል ነው። •"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን በካሳ ክፍያ በኩል ያናገራችሁ አለ? ዶ/ር ጌታቸው፡ እስካሁን ድረስ የተደረጉትን ያስረዱኛል። ነገሩ ተጀምሯል ወደፊት እየተጣራ ሲሄድ ያለውን ነገር እናሳውቅሀለን ብለውኛል። በአሜሪካ ቦይንግን የከሰሱ አሉ። ኬንያውያንም ቦይንግንና ኢትዮጵያ አየር መንገድን እንደሚከሱ ተሰምቷል። እርስዎ ይህ ሀሳብ አለዎት? ዶ/ር ጌታቸው፡ ሬሳ ባለበት አሞራ ይበዛል ነው የአሜሪካኖቹ ነገር። አሜሪካውያን ጠበቆች እዚህ ናይሮቢ ድረስም መጥተዋል። ኢትዮጵያም ሄደዋል። ለእኔም በማግስቱ ነው የደወሉልኝ። በጣም ነው ቅር ያለኝ። አርባው እስኪወጣ፣ የእኛም እንባችን እስኪደርቅ ድረስ መታገስ ማንን ገደለ? ግን አሜሪካኖቹ የእኛ ስሜትና አስተሳሰብ የላቸውም። እኔ አሁንም ቢሆን ለኢትዮጵያኖቹ የምለው ሰብሰብ ብሎ በአንድነት መነጋገር ጥቅም ይኖረዋል ነው የምለው። አንደኛ ተሰሚነት ይኖረዋል። የጠበቆቹም ኮሚሽንም ይቀንሳል። ስለዚህ መሰባሰቡ ክፋት አለው አልልም። እስካሁን ግን ክስ ለመመስረት አላሰቡም? ዶ/ር ጌታቸው፡ አላሰብኩበትም። ካናዳ ጠበቃ የሆነ ልጅ አለኝ። አሜሪካም ፈቃድ አለው። እርሱም እየደወለ አንዳንድ ነገሮችን ይጠይቀኛል። እስካሁን ነገሩን እናስብበት የሚል ነገር ላይ ነኝ። ኢትዮጵያ መንግሥት በቋሚነት ማሰቢያ ቢያቆምላቸው የሚል ሀሳብ ተሰምቶዎት ያውቃል? ዶ/ር ጌታቸው፡ እነዚህ ፓይለቶች ሳይሆንላቸው ቀረ እንጂ አውሮፕላኑን ለማትረፍ የተቻላቸውን ሁሉ ሙከራ አድርገዋል። መቼም ለሀገር በጦርነት ዘመን ብቻ ሳይሆን በሰላሙ ጊዜም መስዋዕት ይቀርባል። ስለዚህ ይህ መስዋዕት ለመጪው ትውልድ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማስታወሻ እንዲሆን የረገፉበት ቦታ አንድ ሀውልት ወይንም መቃብር ስፍራ ቢሰራ እና መጪው ትውልድ ያለፈው ትውልድ ምን እንዳበረከተ እንዲያውቀው ቢደረግ ደስተኛ ነኝ። ይህንን ነው የምለው።
news-45623802
https://www.bbc.com/amharic/news-45623802
''አሁንም ቢሆን አርበኞች ግንቦት 7 አልፈረሰም'' አቶ ኤፍሬም ማዴቦ
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ከግንቦት 7 ጋር በይፋ መለያየቱን የተለያዩ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የፓርቲው ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ይህንን "የተለመደ የማኅበራዊ ሚዲያ" አሉባልታ ነው ማለታቸውን ከዚህ በፊት ዘግበን ነበር።
ነገር ግን የአርበኞች ግንባር አባላት የሆኑ ሰዎች ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግንባሩ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ንቅንቄ አካል መሆኑ ቀርቶ ለብቻው ለመንቀሳቀስ ማስታወቁን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃኑ ዘግበዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ንቅንቄ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦን ቢቢሲ በድጋሚ አነጋግሯቸው ነበር። ''እኔም ጉዳዩን የሰማሁት ከመገናኛ ብዙሃኑ ነው።'' መረጃውም ፍጹም ሃላፊነት በጎደለው መልኩ መዘገቡን ለመግለጽም ከሚመለከታቸው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሃላፊዎች ጋር በስልክ መገናኘታቸውንና በደንብ ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸውን ገልጸውልናል። • አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ • የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ኮሚቴ አባል ፍርድ ቤት ቀረበ ''አርበኞች ግንቦት ሰባት በይፋ ወደ ሃገር ቤት ተመልሷል። ከድርጅቱ ተገንጥያለሁ የሚል ''መንገደኛና ወንጀለኛ'' አካል አቅርበው እኛን ሳያናግሩና ሳያሳውቁ አርበኞች ግንቦት 7 ለሁለት ተከፍሏል የሚለውን ዜና ያስተላለፉ የመገናኛ ብዙሃን በሙሉ ፍጹም ተጠያቂነት የጎደላቸው ናቸው'' ብለዋል። አክለውም ''አርበኞች ግንባር የሚባል ድርጅት የለም። ግንቦት 7 የሚባልም ድርጅት የለም። አሁንም ቢሆን ያለው አርበኞች ግንቦት 7 ብቻ ነው።'' ''እ.አ.አ በ2001 ዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና ግንቦት 7 ተዋህደው፤ በስብሰባቸው ወቅት የመረጧቸው አመራሮች ድርጅቱን እ.አ.አ እስከ 2017 ድረስ ሲመሩ ቆይተዋል። በዚሁ ዓመት የንቅናቄው ጠቅላላ ጉባኤ ኤርትራ ውስጥ አካሂዶ አዲስ አመራር መርጧል።'' ሲሉ ምስረታው እንዴት እንደተካሄደ ያስረዳሉ። በዚህ ሂደትም የቀድሞ አመራሮቹ በድጋሚ መመረጥ አልቻሉም። ይህ መሆኑ ያላስደሰታቸው ሰዎች ናቸው ግንባሩ ፈርሷል በማለት የተለያዩ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ የሚገኙት ብለዋል አቶ ኤፍሬም። በተጨማሪም ''አቶ መንግስቱ ወልደስላሴ እና አቶ ክፈተው አሰፋ የተባሉት ግለሰቦች ድርጅቱን የማይወክሉና ምንም አይነት ኃላፊነት የሌላቸው የግንባሩ አባላት ናቸው ብለዋል። እንደውም በድርጅቱ ስም መግለጫ ሲሰጡ የነበሩት አቶ መንግስቱ ወልደስላሴ ግልጽ በሆነ መንገድ ከድርጅቱ በወንጀል ተባርረው የወጡና ላለፈው አንድ ዓመት ተኩል የድርጅቱ አባል ያልነበሩ ሰው ናቸው'' በማለት ከመባረርም አልፎ ሰውዬው በወንጀል ታስረው እንደነበረ ቃል አቀባዩ ይናገራሉ። • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ስጋት • ስደተኞችን የምትታደገው መርከብ ፈቃዷ ተነጠቀ ከአቶ ኤፍሬም ሃሳብ በተቃራኒው የአርበኞች ግንባርን በመወከል ሲያስተባብሩ የነበሩትን አቶ አቶ ክፈተው አሰፋን ቢቢሲ አነጋግሯቸው ነበር። ድርጅቱ ይፋዊ ጉባኤውን አካሂዶ አመራሮቹን እስኪመርጥ ድረስ አቶ መንግስቱ ወልደስላሴ ከተባሉ ግለሰብ ጋር በመሆን በማስተባበር ላይ እገኛለሁ ያሉት አቶ ክፈተው አሰፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለመለያየታቸው ዋነኛው ምክንያት የድርጅታዊ መርህ መጣስ ነው። መጀመሪያውኑ ስንዋሃድ ይላሉ አቶ ክፈተው፤ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ተስማምተንባቸው የነበሩት የውህደት ህጎች ስላልተከበሩና የአርበኞች ግንባር አመራሮችና አባላት በጎ ገጽታ እንዳይኖራቸው መደረጉ አርበኛውን ስላስቆጣ እዚህ ውሳኔ ላይ ደርሰናል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ''ከ1993 ጀምሮ ለ17 ዓመታት ስንታገል የቆየን ቢሆንም፤ ትግሉ የዛሬ አስር ዓመት የተጀመረ በማስመሰል ከእዛ በፊት የተሰዉትን አርበኞች ክብርና ጥቅም የማያስከብር ሆኖ ስላገኘነው አማራጩ ከእነሱ መለየት ነው ብለን መግለጫ ሰጥተናል'' በማለት አቶ ክፈተው አክለዋል። ወደ ኋላ መለስ ብለውም ''ውህደቱ ሲካሄድ የሁለቱም ድርጅቶች አባላትና አመራሮች ነበሩ የመሰረቱት። ነገር ግን በውህደቱ ወቅት የነበሩት የአርበኞች ግንባር የምክር ቤት አባላትና የስራ አስፈጻሚዎች በተለያዩ ምክንያቶች እንዲወገዱ ተደርገው አሁን ላይ በቦታቸው የሉም። ስለዚህ የግንቦት ሰባት ብቻ ስብስብ ሆኗል፤ እኛን አይወክሉንም'' ብለዋል። ''ከዚህ በኋላ ግንቦት ሰባት እንጂ አርበኞች ግንቦት 7 የሚል ድርጅት የለም'' ሲሉ አቶ ክፈለው አቋማቸውን ገልጸዋል። • የባህር ላይ ወንበዴዎች መርከበኞችን አገቱ ከዚህ በኋላስ ግንባሩ ዕጣፈንታው ምን ይሆናል? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ አቶ ክፈለው ሲመልሱ፤ በመጀመሪያ ድርጅታዊ ጉባኤ ያደርጋል፤ በመቀጠልም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር አብሮ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል። ይህንን ለማሳካትም ከወልቃይት የማንነት ኮሚቴ፤ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች ጋር ውይይት በማድረግ ኢትዮጵያዊ መንፈሱን ያልለቀቀ አንድ ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅት ለመመስረት ማሰባቸውን ይናገራሉ። አሁን እያነሳችኋቸው ያሉት ጥያቄዎች ቢመለሱ ተመልሳችሁ የመቀላቀል ሃሳብ ይኖራችኋል ወይ? የቢቢሲ ጥያቄ ነበር። ''ከግንቦት 7 ሰባት ጋር በድጋሚ የምንቀላቀልበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖርም'' የአቶ ክፈለው ምላሽ ነው።
45480896
https://www.bbc.com/amharic/45480896
2010 ለታምራት ላይኔ፣ ለእስክንድር ነጋ፣ ለሃጫሉ ሁንዴሳ . . .
ባለፈው ዓመት በአገሪቱ ያልተጠበቁ በርካታ ነገሮች ሲከሰቱ በተቃራኒው ይሆናሉ የተባሉ ሳይሆኑ የቀሩ ብዙ ነገሮችም ይኖራሉ። የስልጣን ማማ ላይ የነበሩ ሲወርዱ እስከ ዛሬ የት ነበሩ የተባሉም ስልጣን ተቆናጠዋል።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተፎካካሪ፣ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ግለሰቦችና ተቋማት የለውጥ አጋር ናችሁ ወደ አገራችሁ ግቡ ቤት ለእንቦሳ ተብለዋል። መንግሥትን በመቃወም ቅኝት ውስጥ የነበረው ዲያስፖራ ለመንግሥት አለኝታነቱን ሲያሳይ፤ የረዥም ጊዜ ባላንጣ ኤርትራ የኢትዮጵያ መሪዎች በተደጋጋሚ ጎራ የሚሉባት ሁነኛ ጎረቤት የሆነችበት ዓመት ከመሆኑና ከሌሎችም ነገሮች አንፃር ዓመቱ አገሪቱ በለውጥ ማዕበል ውስጥ የነበረችበት ነው ሊባል ይችላል። • የዓመቱ የቢቢሲ አማርኛ ተነባቢ ዘገባዎች ብዙ ነገር በሆነበትና ብዙ በተባለበት ባለፈው ዓመት በተለያየ ምክንያት የህዝብ እይታ ውስጥ የገቡ ሰዎች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ የተወሰኑትን ዓመቱ ለእናንተ እንዴት ነበር? ብለናቸዋል። "የአሮጌው ፖለቲካዊ አመለካከት ሞት የተበሰረበት ነው" የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ታምራት ላይኔ ያለፈው 2010 ዓ.ም ብዙ ነገሮች የተከናወኑበት ነው። ያለፈው ሥርዓት ከነችግሮቹ ማለፍ መሞት እንዳለበት ህዝቡ በግልፅ ሃሳቡን ፍላጎቱን የገለፀበት ነበር። የአሮጌው ፖለቲካ አስተዳደር ዘይቤዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች መሞት እንዳለበት የተበሰረበት ዓመት ነበር። አዲስ ነገር በተስፋ ደረጃ የፈነጠቀበት፤ መልካም ጅማሮ የታየበት ዓመት ነው። ከሁሉም በላይ አዲሱ ጅማሬ ፈነጠቀ የምለው ህዝብ ያለምንም መደናቀፍና ክልከላ ወጥቶ በነፃነት ሃሳቡን የሚገልፅበት እድል መፈጠሩን ነው። ይህ አዲስ ፋናና ተስፋ ነው። ግን ገና ጅማሮ ነው። ሃሳብን በነፃነት በመግለፅ ረገድ የተጀመረው ነገር በሌሎች ነገሮችም እየቀጠለ ለውጡ እየጎለበተ የሚሄድበት ተስፋ ነው ብዬ ነው የማምነው። አዲስ ዓመት ከቤተሰብ ጋር ሆኜ ኢትዮጵያ ውስጥ ሳከብር ከ22 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያዬ ነው። 12 ዓመታትን እስር ቤት ከዚያም አስር ዓመታትን አሜሪካ ነው ያሳለፍኩት። እስር ቤት እያለሁ ለብቻዬ ሻማ አብርቼ ቀኑን አስብ ነበር። አሁን ግን ከቤተሰቦቼ ፣ እናቴም አለች ከዘመድ ከጓደኞቼ ጋር ነው የማሳልፈው። በአዲሱን ዓመት ካለፉት ዓመታት ስህተቶቹ ተምሮ፤ ጠንካራ ጎኑም ጠንክሮ ወጥቶ የፊቱን የሚያይ ሰው እሆናለሁ ብዬ ነው የማምነው። • የ2010 የጥበብ ክራሞት በዚህ የወደፊቱ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ለኢትዮጵያ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ የሚጠቅም ነገር መስራት የሚፈልግ ለመስራት የሚተጋ ሰው እሆናለው። አዲሱን ትውልድ ከስህተቴም ከጥንካሬዬም የማስተምር ሰው እሆናለው ብዬ አምናለው። አዲሱን ዓመት ሳስብ አሁን የታየው ተስፋ ስር ሰድዶ አዲስ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መነቃቃት መንፈስ ሰፍኖ ይቺ ሃገር የመጣችበት የድቀት፣ የመከራና የችግር መንገድ ማክተሚያ የመጀመሪያ እርምጃ ይሆናል ብዬ እገምታለው። በዚህ ውስጥ በተለይም አዲሱ ትውልድ ከሁለት የብሄርተኝነት ፅንፍ እንዲጠበቅ አፅንኦት መስጠት እፈልጋለው። ሚዛናዊ አስተሳሰብና ሚዛናዊ ግንኙነት እንዲሆር እመኛለሁ። እቺ አገር እንደ ኢትዮጵያ አንድ ህዝብ አንድ ሃገር ሆና ጠንክራ እንድትወጣ ባለቀለትና በሞተ አስተሳሰብ ውስጥ ያሉ የኢህአዴግ የቀድሞ መሪዎች ልብ እንዲገዙና ሁኔታውን ቆም ብለው እንዲመለከቱ እፈልጋለው። "እነዚህ ሰዎች የሚያዞሩኝ ከንቲባ ሊያደርጉኝ ነው እንዴ?" የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ለአገራችን የተለየ ዓመት ነው የሚል እምነት አለኝ። ምክንያቱም ፍቅር ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን አጥብቀን የያዝንበት፤ በፍቅር የተያያዝንበት ነው። ነፃነት የተንፀባረቀበትም ነበር። አዲስ አበባ ማደግ መኖር ደግሞ በራሱ ፍቅር ነው ብዬ አምናለው። ከተማችን አዲስ አበባ የተለያየ የህብረተሰብ ክፍል ያለባት ሁሉም እንደ አቅሙ ወቶ የሚገባባት በመተባበር የሚኖርባት አስተዋይ ሰላም ወዳድ ህዝብ ያለባት ከተማ ናት። እናም አዲስ አበባ መወለድ፣ ማደግና መኖር እነዚህን ስብዕናዎች ተላብሶ ለማደግ እድል እንደሚሰጥ አምናለሁ። ባለፉት አስር ዓመታት ከክፍለ ከተማ ጀምሮ ከተማውን ሳገለግል ወደ አምስት የሚሆኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶችን የመምራት እድል አግኝቼ ነበር። አንዱን ሴክተር አውቄ የተሻለ ውጤት ማምጣት ምችልበት ደረጃ መድረሴን ሳምን ወደ ሌላ ቢሮ መዘዋወር አለብሽ የሚል ጥያቄ ይነሳ ነበር። • ያልተጠበቁ ክስተቶች የታዩበት ዓመት አንዳንዴ አዝኜም ባለቅ እል ነበር። ወደ ሚቀጥለው ቢሮ ስሄድ ያለ ምንም ችግር ቶሎ ሥራውን እለምድ ነበር። ቶሎ ቶሎ የተለያዩ ቢሮዎችን እንድመራ ሲደረግ እንዴት ነው እነዚህ ሰዎች ከንቲባ ሊያደርጉኝ ነው እንዴ የሚያዞሩኝ ሁሉ እል ነበር። ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ግን በሆነው ነገር ደስተኛ ነኝ። 2011 ዓ.ምን ሳስብ ትልቅ ተስፋ ይታየኛል እንደ አገር። የህዝባችን ልብ ከመሪዎቹ ጋር ስላለ እጅግ ትልቅ ነገር ይታየኛል። "ህወሃት በ2010 ዓ.ም የበላይነቱን ያጣል ብዬ አልተበቅኩም" ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ህወሃት በ2010 ይወድቃል ብዬ በፍፁም አላሰብኩም ነበር። እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎች አልጠበቁም ስለዚህም ትልቅ ክስተት ነው። የኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ጥያቄ ግን በህወሃት መውረድ ብቻ የሚፈታ አይደለም። ምንም እንኳ ተስፋ የተጣለበት ዓመት ቢሆን በጣም ብዙ ያላለቀ ነገር አለ። ስለዚህ ያለኝ ቁጥብ ተስፋ ነው። ትልቁ የዲሞክራሲ ጥያቄ አልተመለሰም ወደዛ መግባት ካልቻልን ከለውጡ በፊት ወደ ነበርንበት ከዚያም ወደ ከፋ አደገኛ ነገርም ልንገባ እንችላለን። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አዲሱ ዓመት የሽግግር መንግሥት የሚመሰረትበት እንዲሆን ነው ምኞቴ። ምክንያቱም ሰላማዊ የዲሞክራሲ ሽግግር ማድረግ የምንችለው በሽግግር መንግሥት ብቻ ነው ብዬ ስለማምን ነው። ለዚህ ዓይነቱ ከአምባገነናዊ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሽግግር ደቡብ አፍሪካ ጥሩ ምሳሌ ናት ብዬ አምናለው። ይህን ሂደት የማንከተል ከሆነ እናበላሸዋለን ብዬ እሰጋለሁ። በተጨማሪም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ህዝብ የሚተማመንበት የምርጫ ሂደት ይኖራል ብዬ አልገምትም። የሁላችንንም የዲሞክራሲ ጥያቄ የሚመልሰው የምንተማመንበት ምርጫ ነው። ስለዚህ ምኞቴ አዲሱ ዓመት የሽግግር መንግሥት መስርተን፣ የምንተማመንበት መንግሥት ለመመስረትና ነፃ ተቋማት ለመገንባት የሚያስችለን ከዚያም ምርጫ የምናደርግበት መንገድ ውስጥ የምንገባበት እንዲሆን ነው። "የገባው አሜን፤ያልገባውም ለምን ብሏል" አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አሁን ያለው ለውጥ እንዲመጣ የአገራችን ህዝቦች መራር ትግል ያደረጉበትና መጨረሻውም ያማረበት ዓመት ነበር። እኔም ከህዝብ ውጭ ስላልሆንኩ እንደ አንድ የኦሮሞ አርቲስት፤ በሚሊኒየም አዳራሽ ከሶመሌ ክልል ለተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች እርዳታ ማሰባሰቢያ ፤ ከዚያም ደግሞ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንኳን ደህና መጡ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተጋብዤ ነበር። በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ ከህዝቤ ጎን መቆም የምችለው በሙያዬ ስለሆነ የማምንበትን መልዕክት ለመሪዎች አስተላልፌአለሁ። ያን ደግሞ የኮነኑኝና ሊጎዱኝ የተንቀሳቀሱ ነበሩ። በተቃራኒው ሃላፊነት ተሰምቷቸው የተከላከሉልኝ የመንግሥት ሃላፊዎችም ነበሩ። ለፕሬዘዳንት ኢሳያስ የተዘጋጀው ፕሮግራምም እንኳን ደህና መጡ ለማለት ቢሆንም ዜጎች በሐረር አካባቢ በግፍ እየተገደሉ ስለነበር እዚያ ቦታ ላይም መልዕክቴን በማስተላለፍ ሙያዊ ግዴታዬን ተወጥቻለው (ያልተጠበቀ ነበር አድርጌያለሁ)። በሁለት መድረኮች ላይ ያደረግኩትን የገባው እንደገባው አሜን ሲል ያልገባውም ለምን ብሏል። ሁሉም ሃሳቤን ይወደዋል አይወደውምም አልልም። አዲሱን ዓመት ሳስብ አሪፍ ነገር ነው የሚታየኝ። መንግሥት በዚሁ ከቀጠለ ህዝብም የሚደማመጥና የሚቻቻል ከሆነ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለአገራችን ህዝቦች ተስፋ የሚሰጥ ነው። ከጥቂት ወራት በፊት መንግሥት እንደ መንግጅት ተስፋ የሚጣልበት ሳይሆን የሚፈራ ነበር። ህዝብ እንደፈለገው ሃሳቡን የሚገልፅበት እምነቱን የሚያንፀባርቅበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ይህ ደግሞ ያስደስተኛል ግን ለዘለቄታው የመንግሥት አምባገነንነትን ስንፈራ ህዝብ አምባገነን እንዳይሆን እሰጋለሁ። "የእግዚአብሄርን እጅና መልካምነትን ያየሁበት ጊዜ ነው" የቀድሞ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክትር አቶ መላኩ ፈንታ ዓመቱን ለሁለት ከፍዬ ነው የማየው። ከግንቦት ወር በፊት እስር ቤት የነበርኩበትን እና ከወጣሁ በኋላ ያለውን ማለት ነው። ብዙ ሰዎች እስር ቤት ያለ ሰው ምንም የማያደርግ ቢመስለውም አንድ አይነት ቢሆንም የፀሎት፣ የስፖርት፣ የንባብ እንዲህ እንዲህ እያለ ለሁሉም እቅድ አለው። የእስር ጊዜዬን እንደዚያ ነበር ማሳልፈው። አልፎ አልፎ ውጭ የሚካሄደውን ነገር መስማት ተስፋ የሚሰጥ ነበር። ከተፈታሁ በኋላ ያለው ለእኔ ባብዛኛው የእግዚአብሄር እጅና መልካምነትን ያየሁበት ጊዜ ነው። የህዝብን ፍቅር፣ መልካምነትና ፈራጅነትም ያየሁበት ነው። ከሚገባኝ በላይ የህዝብን ፍቅርና ክብርም ያገኘሁበት ነው። ዓመቱ ከአገር አንፃርም ታሪካዊ ክስተት የታየበት ነው ብዬ ነው የማምነው። ህዝብ በተለይም ወጣቱ ለዲሞክራሲንና ለፍትህ ቆርጦ የተነሳበትም ጊዜ ነበር። ለውጡ በህዝብ የመጣ ስለሆነ በአዲሱ ዓመት ተስፋ ነው የሚታየኝ። የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት የሚደረገው ጥረት ወደ ፍትሃዊ ምርጫ እንዲያመራ የሚደረግበትና የሃሳብ የበላይነት የሚነግስበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው። በልማትም እኩልነትና ተጠቃሚነት የምናይበት ይሆናል ብዬ ነው ተስፋ የማደርገው።
50856029
https://www.bbc.com/amharic/50856029
የጃንሆይ ቮልስዋገን ዛሬ በቦሌ ትታያለች
ዛሬ በቦሌ ጎዳና ቮልስዋገኖች ተግተልትለው ያልፋሉ፤ ከነሙሉ ክብርና ሞገሳቸው፡፡ በቁጥር 160 ይሆናሉ፡፡ ከነዚህ መካከል ቢያንስ አንዷ ታሪካዊ ናት፡፡ የጃንሆይ ቮልስ!
አቶ ሀብታሙ ኤርሚያስ አባታቸው ቮልስ ነበራቸው። እርሳቸውም ከጉርምሳና ዕድሜያቸው ጀምሮ ቮልስ ነድተዋል። ወንድማቸውም ቮልስ ነው የሚነዳው። ማን ያውቃል? በፎቶ የሚታየው ልጃቸውም ቮልስ ይነዳ ይሆናል። ለ46 ዓመታት ኢትዮጵያን ‹‹የሾፈሯት›› ጃንሆይ በመለዮ ለባሾቹ ከዙፋናቸው ሲገረሰሱ ከሞቀው ቤተ መንግሥት ‹‹ተሾፍረው›› የወጡት በዚች ቮልስዋገን ነበር፡፡ ያን ጊዜ ሾፌራቸው የነበሩት ጄኔራል ሉሉ እንግሪዳ ይባላሉ፡፡ እርሳቸው በሕይወት የሉም ዛሬ፡፡ ባለቤታቸው እማማ አጸደ ግን ቮልስዋገኗን ወርሰዋታል፡፡ • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሊያድኑት የነበረው ለገሰ ወጊ ማን ነበሩ? ይቺ ቮልስ የታሪክ ድር እያደራች ዛሬም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሽር ትላለች፡፡ ምናልባት በመኪና ቋንቋ ‹‹ቀሪን ገረመው›› እያለችን ይሆን? የአዶልፍ ሂትለር ደግ መኪና እንደ ጎርጎሮሲያዊያኑ በ1930ዎቹ መጨረሻ አዶልፍ ሂትለር ቀጭን ትእዛዝ ሰጠ። የእርሱ ትእዛዝ ይፈጸማል እንጂ ወለም ዘለም የለም። ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ የሚሸጥ፣ ማንም የአርያን ዘር ነኝ የሚል ኩሩ ጀርመናዊ ባልተጋነነ ዋጋ ሊገዛው የሚችል የደስተኛ ቤተሰብ መኪናን የሚወክል የተሽከርካሪ ፋብሪካ እንዲቆቋም አዘዘ፡፡ ይህን ቀጭን ትእዛዝ ተከትሎ አንድ በወቅቱ ግዙፍ ሊባል የሚችል የመኪና ማምረቻ ተቋቋመ። ሆኖም ምርቱ በገፍ ከመጧጧፉ በፊት የ2ኛው የዓለም ጦርነት ተጀመረና ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ተባለ። ቮልስ ሊያመርት የተባለው ፋብሪካም የጦር መሣሪያ ማምረት ያዘ። የማያልፉት የለም ጦርነቱ ሂትለርን ይዞ አለፈ። የዓለም ጦርነቱ ሲያባራ በዓለም ዝነኛ ለመሆን እጣ ፈንታዋ የሆነች አንዲት መኪና ተመረተች፡፡ • የማትተነፍሰው ከተማ: አዲስ አበባ • የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ በዋጋ የሚያንራቸው ምርቶች ለመኪናዋ ስያሜ ለመስጠት ብዙም ያልተቸገሩ የሚመስሉት አምራቾቿ ስሟን ቮልስዋገን አሏት። 'የሕዝብ መኪና' እንደማለት፡፡ ጢንዚዛ የመሰለችው ቮልስ መኪና ተወለደች። በምድር ላይ እንደርሷ በተወዳጅነት ስኬታማ ሆኖ የቆየ የመኪና ዘር የለም። የአውቶሞቲቭ ተንታኞች ቮልስ ቢትልን ልዩ የሚያደርጋት በሀብታምና ሀብታም ባልሆነ ሕዝብ በእኩል መወደዷ ነው ይላሉ። ምርቷ ሙሉ በሙሉ እስኪቆም ድረስ በጀርመን፣ በብራዚልና በሜክሲኮ 21 ሚሊዮን 529ሺህ፣ 464 ያህል ተመርተዋል። ስንት ሺዎቹ ወደኛ አገር እንደመጡ ግን በውል አይታወቅም። "ቮልስዋገን ኢትዮጵያ" ማኅበር በሕግ ሲመሠረት አንዱ ሥራው የቆሙና በሕይወት ያሉ ቮልሶችን በትክክል መቁጠርና አባላትን መመዝገብ ይሆናል። ይቺ ፈጣሪዎቿ "የሕዝብ" ያሏት የብዙኃን መኪና እኛ ዘንድ መጣችና የጥቂቶች ብቻ ሆነቸ፡፡ ቮልስ በአዲስ አበባ ጎዳና ገናና በነበረችበት ዘመን ቮልስና ዴክስ የነዳ የየሰፈሩ ፈርጥ ነበር። "ደህና ዋሉ ጋሼ" ተብሎ ቆብ ከፍ የሚደረግለት። መኪና እንደ ቆሎ ከውጭ አገር በሚዘገንበት በዚህ ዘመንም ቢሆን ቮልስ ዐይነ ግቡ ናት። ምንም እንኳ አንዳንዶች ሊሳለቁባት ቢሞክሩም። ጃንሆይ ከቤተ መንግሥት በመለዯ ለባሾች የተሸኙባት ቮልዋገን አቶ ሀብታሙ ኤርሚያስ ለምሳሌ ለ16 ዓመት ባሽከረከሯት ቮልስ ያልተባሉት ነገር የለም። በቀደም ለታ ለምሳሌ መገናኛ ጋር አንድ ዘናጭ ዘመነኛ መኪና የሚያሽከረክር ሰው መስኮት አውርዶ "አንተ ሰውዬ! ምናለ ይቺን ሸጠህ ደህና ጫማ ብትገዛ?" ብሏቸዋል። እርሳቸው ግን ውድድ ነው የሚያደርጓት። • ኢትዮጵያ ሳተላይት አስወነጨፈች አቶ ሀብታሙ ሰፈራቸው አንቆርጫ ነው። በርሳቸው ቮልስ ምክንያት የሰፈራቸው ታክሲ መዳረሻ "ቮልስ ግቢ" ተብሎ ነው ዛሬም ድረስ የሚጠራው። ታክሲ የሚጭነው። ኮተቤ ብረታ ብረት 02 ጋ ታክሲ ሲጭን "የቮልስ ግቢ" እያለ ነው። የአቶ ሀብታሙ ሕጻን ልጆች ቮልሳቸውን "ቮልስ" ብለው አይደለም የሚጠሯት። ውቤ እያሉ ነው የሚያቆላምጧት። አቶ ሀብታሙ በአንድ የቻይና የነዳጅ አውጪ ኩባንያው ውስጥ ነው የሚሰሩት። ቻይኖቹ ራሱ ቮልሷን "ውቤ" ነው የሚሏት። ታዲያ ለአቶ ሀብታሙ ቮልስ የኩራታቸው ምንጭ ብትሆን እንዴት ይገርማል? ጥሎባቸው አንዳንድ ነገሮች እንደ ዋይን ናቸው። እያረጁ ይጣፍጣሉ፡፡ ቮልስም እንዲያ ናት፡፡ ፈጣሪዋ አቶ ፈርዲናንድ ፖርሻ ቮልስን ሲነድፋት በጢንዚዛ ቅርጽ መሥሎ ነው፡፡ እነሆ ከዚያ ዘመን ጀምሮ ሁሌም ዝንጥ እንዳለች አለች፡፡ ደክርታም ዘናጭ ናት፡፡ ዕድሜ ተጭኗትም አፍላ ኮረዳ ነው የምትመስል፡፡ ለዚህም ይመስላል የቮልስ ወዳጆች እልፍ የሆኑት፡፡ እንዲያውም በብዙ አገራት ማኅበር አላቸው፡፡ የቀልድ ሳይሆን ሕጋዊ ማኅበር፡፡ ‹‹የቢትልስ ወዳጆች ማኅበር›› ይባላሉ፡፡ እኛም አገር ይህ እውን ሊሆን ተቃርቧል፡፡ ነገ የሚከፈተውን የቮልሶች አውደ ርዕይን ከሚያስተባብሩት አንዱ የሆነው ወጣት ሚካኤል ጌታቸው ነው እንዲያ የነገረን፡፡ ኸረ እንዲያውም አባላቱ ቮልሶቻቸውን እየነዱ ሱዳን ለመሄድ ሁሉ ያስባሉ፡፡ • መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ የቢትልስ ወዳጆች ማኅበር እዚያም አለ፤ ኻርቱም፡፡ በመላው ዓለም የቢትልስ ወዳጆች እንደቤተሰብ ነው የሚተያዩት፡፡ ኻርቱምና አዲሳባም እንዲሁ፡፡ ‹‹ወይ እነሱ ይመጣሉ፤ ወይ እኛ እንሄዳለን›› ይላል ሚካኤል፡፡ የሆነስ ሆነና፣ በቮልስ ካርቱም ድረስ ይኬዳል እንዴ? ቮልስ እንኳን የኡምዱርማንን በረሃ ልታቋርጥ ይቅርና መቼ የቸርችልን አቀበት ለመውጣት ወገቧ ጠና? ሚካኤል ጌታቸው ሳቀብኝ፡፡ ቮልስዋገኖች እጅግ ፈጣን መኪኖች ናቸው ሲልም ሞገተኝ፡፡ ችግራቸው በሾፌሩ በኩል ያለ ባትሪ ነው፡፡ እሱ ከተጠገነ "ከቪ8 እኩል ይሮጣሉ" ይላል፡፡ "ጓደኞቼ ለቮልሶቻቸው የውድድር መኪና ሞተር ገጥመውላቸው እንዴት ክንፍ አውጥተው እንደሚበሩ ብታይ…!" አልተዋጠልኝም፡፡ እንደኔ ሰፈራችን በነበሩ የቮልስ ባለቤት ሰውዬ የ'ግፉልኝ' ጥያቄ የተማረሩ አንባቢዎችም ሚካኤልን አያምኑትም። እሱም ይህን አላጣውም። ተጨማሪ ማስረጃ አቀረበው። "ከ6 ወር በፊት ድንበር ሲከፈት አንድ ኤርትራዊ ሙሉ ቤተሰቡን ይዞ ከአስመራ አዲስ አበባ በቮልስ ዋገን እየነዳ ገብቷል "ሲል አስረዳኝ፡፡ ቤተሰቡ ሶደሬና ሐዋሳ ሽር ብትን ብሎ መመለሱን በፎቶ አስደገፈልን፡፡ ይሄ ማለት 1078 ኪሎ ሜትር ደርሶ መልስ ማለት ነው። በ'ነርሱ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ መሠረት ይህን ጉዞ ያደረጉት ሰው አቶ ኒኮዲሞስ ናቱ ይባላሉ። በአውሮጳ አቆጣጠር በ1996 ቮልስ ይዘው መጥተው ነበር፣ ወደ አዲስ አበባ። 2ኛው ጉዟቸው ከ25 ዓመት በኋላ የተደረገ ነው። የቮልሳቸው እድሜ ደግሞ 42 ዓመት አልፎታል። የቮልስ ኢትዮጵያ አስተባባሪው አቶ ሚካኤል ጌታቸው እንደሚለው ቮልስ የጤና ክትትል ከተደረገላትና በሾፌር በኩል ያለው ባትሪዋ ከተቀየረላት ዕድሜዋ የማቱሳላ ነው፡፡ ቮልስዋገን ባለቤቶች መኪናዬ "ትኩሳቷ ተነሳባት" ሲሉ ቢሰሙም ሚካኤል በዚህ አይስማማም የቮልስ ወዳጆች እንዴት ተገናኙ? ዛሬ የሚገናኙት የቮልስ ባለቤቶች ብቻ አይደሉም። የቮልስ ጋራዥ ባለቤቶች፣ የቮልስ አካል መለዋወጫ ነጋዴዎች፣ የቮልስ ኤልትሪሻኖች ሁሉ አሉበት። ለመሆኑ የቮልስዋገን ባለቤቶች እንዴት ይሆን የተገናኙት? እንዴት ተጠራሩ? ምናልባት "ግፋልኝ እባክህ" ሲባባሉ በዚያው ተቀራርበው ይሆን? ምናልባት ቀይ የትራፊክ መብራት የቮልሳቸውን የልብ ትርታ ቀጥ ባደረገበት ቅጽበት "እኔን" ሲባባሉ በዚያው ተወዳጅተው ይሆን? ነገሩ ሚካኤል ጌታቸውን ፈገግ አሰኝቶታል፡፡ የቮልስዋገኖችን ስም ለማጥፋት በቪትሶች የሚሰራጭ አሉባልታ አድርጎ ሁሉ ሳይወስደው አልቀረም፡፡ በነገራችሁ ላይ ቮልስዋገን አፍቃሪዎች ራሳቸውን ልክ እንደ አንድ "የፋሽን ጎሳ" መሰለኝ የሚመለከቱት፡፡ የእርስ በርስ ቅርርባቸው የሚያስቀናም የሚያስደንቅም ነው፡፡ አንድ ቮልስ ነጂ መንገድ ዳር እክል ገጥሞት ቢቆም ከማንም በፊት የሚደርሱለት ሌላ ቮልሳዊ ወንድሞቹ ናቸው፡፡ 'ስኮርት' ያቀብሉታል፣ 'ክሪክ' ያውሱታል፡፡ ይሄ የበዛ መቀራረብ ከምን የመነጨ ይሆን? ሲባል አቶ ሚካኤል ያው ቮልስዋገን ‹‹የሕዝብ መኪና›› ማለትም አይደል?›› ይላል፡፡ እንደ አንድ ሕዝብ እንቀራረባለን ማለቱ መሰለኝ፡፡ ይህን 'ቮልስወገናዊ' ፍቅር ብንለውስ። 'ቮልስወገናዊ' ፍቅር ቮልስ ፍቅር ያጎበጣት መኪና ትመስላለች። አንዳች አዚም አላት፤ የመወደድ፡፡ ሰዎች አንድ ጊዜ ቮልስ ከነዱ ገንዘብ ስላገኙ ብቻ ቮልሳቸውን አሳልፈው አይሰጡም፡፡ ከቤተሰብ ተማክረው፣ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ፣ ቤተሰብ ጉባኤ ተጠርቶ ...። እንጂ እንዳገለገለ ባልዲ በቀላሉ አይጥሏትም። የወለዱትን የመጣል ያህል የሚሆንባቸው ሁሉ አሉ። ብዙዎች ቮልስን በቀላሉ ከልባቸው ማውጣት የማይሆንላቸው ግን ለምን ይሆን? ቮልስ ብዙውን ጊዜ የቤተሰብ አባል ሆና ቁጭ ትላለች። ሚካኤል ለዚህ የሚሰጠን ምሳሌ አንድ በቅርብ የተቀላቀላቸውን ወጣት ታሪክ በመግለጽ ነው፡፡ "ባለፈው የተዋወቅነው ወንድማችን" ይላል ሚካኤል "አባቱ የዛሬ 50 ዓመት የገዟትን ቮልስ ነው ይዞ የመጣው፡፡ ሴፌሪያን የሚባል ቮልስ መሸጫ ነበር ድሮ ሜክሲኮ ጋ፡፡ 00 (ጭራሽ ያልተነዱ) ቮልሶችን የሚሸጥ ኩባንያ ነበር። ከዚያ የተገዛችው መኪና ከትውልድ ስትተላለፍ ቆይታ እርሱ እጅ ገብታ እንዴት እንደምታምር…" ቢቢሲ፡-የቤተሰብ አባል ነበረች በለኛ! ‹‹አዎና! ቮልሶች 'ሴንትመንታል ቫሊይዋቸው' ከፍተኛ ነው፡፡ እንዲያውም እኮ አንዳንድ ቤት ግቢ ውስጥ ቆመው ታያቸዋለህ፡፡ ዝገት እንዳይነካቸው ከፍ የሚያደርግ ድንጋይ ተነጥፎላቸው፤ በየቀኑ እየታጠቡ ግቢ ውስጥ ለዘመናት ቆመው ያሉ አሉ፡፡ የማይነዱ፡፡›› • በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች ደግሞ የድሮ ታርጋ ያላቸው አሉ፡፡ ሚካኤል እንዲያውም ወደ ፒያሳ ጳውሎስ በብዛት የምትነዳ ታርጋ ቁጥሯ የአማራ ክልል የሆነ 00001 መኪና እንዳለች አስተውሏል፡፡ "በዚያ ላይ ከርቫቸው ያምራል፤ በተለምዶ ደማቅ ቀለም ነው የሚቀቡት ከኋላ ብታያቸው ከፊት በሁሉም ጎናቸው ቆንጆ ናቸው፡፡" ይላል። ነገ ለተጋባዦች ብቻ ክፍት በሚደረገውና ኮላብ ሲስተምስ ፒኤልሲ ጋር በመቀናጀት በተሰናዳው በዚህ የቢትልስ ቮልስ የእንትዋወቅ መርሐግብር በሺ የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ይጠበቃሉ። ከታዳሚዎቹ መካከል ታዲያ በእድሜ ገፋ ያሉና ቮልስን ለሩብ ክፍለ ዘመን ያሽከረከሩ ይገኙበታል። የበዓሉ ግርማ ቮልስ በአገራችን እንደ ቮልስ በታዋቂ ሰዎች የተዘወረ መኪና ይኖር ይሆን? በዚህ ዘመን እንኳ ኮሜዲያን ደረጀ ኃይሌ ብቻ ቀርቷል መሰለኝ። ባይነዷቸውም ታዲያ የቮልስ ወዳጆች እልፍ ናቸው። ባለማቀፍ ደረጃ ዕውቋ ትውልደ ኢትዯጵያዊት ጸሐፊ መዓዘ መንግሥቴ ለምሳሌ ትዊተር ሰሌዳዋን ለጎበኘ የቢትልስ ወዳጅ መሆኗን ይመሰክራል፡፡ • ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ያናገሩና ያነጋገሩ ድርሰቶቹ ከቀድሞዎቹ የሥነ ጽሑፍ ሰዎች ደግሞ በዓሉ ግርማ ይጠቀሳል፡፡ ከአገራችን አውራ ደራሲያን አንዱ የነበረው በዓሉ በሕይወቱ የመጨረሻ ዓመታት የሚያሽከረክራት ቮልስ ነበረችው፡፡ እስከዛሬ ድረስ ውሉ ባ'ለየለት የደራሲው መሰወር ታሪክ ውስጥ ቮልስዋ አብራ ትነሳለች፡፡ በዓሉ ከተሰወረ ከጥቂት ቀናት በኋላ ቃሊቲ መንገድ ቆማ የተገኘቸው ይቺ ቮልስ በሞተር ፈንታ አንደበት ቢኖራት ኖሮ የዘመናት ምሥጢርን በገለጠችል ነበር። የበዓሉ ቮልስ ግን የት ትሆን ያለችው?
news-52293790
https://www.bbc.com/amharic/news-52293790
ኮሮናቫይረስ፡ የፅኑ ህሙማን ፈታኙ የማገገም ሂደት ምን ይመስላል?
ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ (ቬንትሌተር)፣ የፊት ጭምብል እንዲሁም የፅኑ ህሙማን ክፍል ማቆያ የሚሉ ቃላትን በተደጋጋሚ መስማት የዓለማችን አዲሱ እውነታ ሆኗል።
አንድ ሃኪም ጣሊያን ውስጥ የኮሮናቫይረስ ጽኑ ህመምተኛን ሲንከባከቡ በኮሮናቫይረስ የታመሙ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እየታከሙም ይገኛሉ፤ ብዙዎችም በሞትና በህይወት መካከል ናቸው ። በሆስፒታሎች በሚገኙ የፅኑ ህሙማን ክፍሎች ውስጥ በህይወት ለመቆየት ትግሉ ቀጥሏል። በራሳቸው መተንፈስ ያዳገታቸው ሰዎች በተራቀቁ ማሽኖች በመጠቀም በህይወት ለመቆት የሚያስችላቸው ትንፋሽ ተቀጥሎላቸዋል። የተለያዩ የሰውነት ተግባራትን በማሽኖች በመጠቀምም ነው አካላቸው እየሰራ ያለው። መድኃኒቶችም እንደአስፈላጊነቱ ይሰጣቸዋል። • ቢልጌትስ የኮሮናቫይረስ ሊከሰት እንደሚችል እንዴት ቀድመው ሊያውቁ ቻሉ? • ከሚስታቸውና ከልጃቸው ጋር ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት የአዳማ ነዋሪ ወደ ቤታቸው ተመለሱ ለኮሮናቫይረስ መድኃኒት አልተገኘም። በአሁኑ ሰዓት በፀና ለታመሙ ህሙማን በሳንባቸው ውስጥ በቂ ኦክስጅን እንዲያገኙ ማድረግና በሽታን የመቋቋም አቅማቸው እንዲጠናከርና ቫይረሱን አካላቸው እንዲታገል የማድረግ ሥራ ነው በጤና ባለሙያዎች እየተሰራ ያለው። ይህ ግን የማገገማቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በፅኑ ህሙማን ማከሚያ ክፍል ማገገም የቻሉ ህሙማን የጤና ችግራቸው ማብቂያ አይደለም። በቀጣይነት የጤና ሁኔታቸው የተወሳሰበ ይሆናል። ከሆስፒታልም ከወጡ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለመዳን ዓመታትን ሊፈጅ ይችላል። የማይሽር የሥነ ልቦና ጠባሳም ሊያስከትል ይችላል። ታካሚዎች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ፍርሃትና ጭንቀት ሊያጋትማቸው ይችላል መተንፈስን መማር ለረዥም ጊዜያት በፅኑ ህሙማን ክፍል የቆዩ ህሙማን ከወጡ በኋላም በራሳቸው መተንፈስ ስለሚያዳግታቸው የቴራፒ ህክምና ይሰጣቸዋል፤ በራሳቸው መተንፈስን እንደገና እንዲማሩ። ከወጡም በኋላ የነበሩበት አሰቃቂ ሁኔታ እንዲህ በቀላሉ የሚጋፈጡት አይሆንም፤ ፍራቻም ያጠላባቸዋል። በተለይም ረዘም ያለ ጊዜ ለቆዩት እንደገና ወደነበሩበት ህይወት መመለስ ፈተና ነው፤ ወደቀድሞ ማንነታቸውም ለመመለስ ከፍተኛ ትግል ይገጥማቸዋል። "ታመው የፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የገቡ ከሆነ ህይወትዎ እንደሚቀየር ይወቁ። ቢሻልዎት እንኳን ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍልዎ መሆኑን ማወቅ አለብዎት" በማለት በዩናይትድ ኪንግደም የሮያል ግዌንት ሆስፒታል የፅኑ ህሙማን አማካሪ ዶክተር ዴቪድ ሄብበርን ይናገራሉ። • ትራምፕ "ቫይረሱ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል የሚችልበትን ጊዜ አልፏል" አሉ • የመጀመሪያውን ኮሮናቫይረስ ስላገኘችው ሴት ያውቃሉ? "የፅኑ ህሙማን አገግመው በሚነቁበት ወቅት በጣም ስለሚደክሙ ያለድጋፍ መቀመጥ አይችሉም። እጃቸውን እንኳን ከተኙበት አልጋ ማንሳት አይችሉም፤ ጉልበታቸው ይክዳቸዋል" ይላሉ። በህክምናው ወቅት ምግብ በቱቦ አማካኝነት ይገባላቸው ከነበረም የመናገርም ሆነ የመዋጥ እክሎች ከተሻላቸው በኋላ የሚያጋጥሟቸው ናቸው። "ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ፤ ራሳቸውን ማወቅም ሆነ የነበራቸውን እውቀት መመለስ ችግር ይገጥማቸዋል" ብለዋል ዶክተር ሄብበርን በትዊተር ገፃቸው። "ከጊዜ ጋር ይሻላቸዋል። በቴራፒ የታገዘ የህክምና አገልግሎት፤ የቋንቋና የንግግር ክህሎትን የሚያሰለጥኑ ባለሙያዎች፣ የሥነ ልቦናና ሌሎች ተጨማሪ እርዳታዎች ማግኘት አለባቸው። ይህም አንድ ዓመት ወይም ከዚያ የረዘመ ጊዜ ይወስዳል" ይላሉ። ባለሙያዎች አፅንኦት ሰጥተው የሚናገሩት በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ማገገም የመጀመሪያው ደረጃ ቢሆንም፤ አገገምኩ ተብሎ መዘናጋት የለባቸውም ለረዥም ጊዜ የተቀናጀ የባለሙያዎች ክትትል መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ዴቪድ አሮኖቪች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ያሳለፈውን ያስታውሳል በፅኑ ህሙማን የሚያጋጥም የአዕምሮ መረበሽ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ካሉ ህሙማን ውስጥ ሩብ የሚሆኑት ከፍተኛ የሆነ የአዕምሮ መረበሽ ያጋጥማቸዋል። የብሪታኒያው ጋዜጠኛ ዴቪድ አሮኖቪች ለቢቢሲ እንደተናገረው ከዘጠኝ ዓመት በፊት በሳንባ ምች ህመም ምክንያት ራሱን የፅኑ ህሙማን ክፍል ሲያገኘው የተሰማውን እንዲህ ይናገራል። "እንዲህ ግልፅ ባለ ቋንቋ ለመናገር፤ ስነቃ ከቀን ወደ ቀን እያበድኩ እንደሆነ ይሰማኝ ነበር። የሌለ ድምፅ እንዲሁም ሰዎች ሲያወሩ ይሰማኛል" ብሏል። "ብዙ ነገሮች እየተፈፀሙብኝ እንደሆኑ ይሰማኝ ነበር። ይባስ ብሎ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ወደ ሙት መንፈስ ቀይረውኛል ብዬ አመንኩኝ። ከዚያም በሚያሳዝን ሁኔታ ሊበሉኝ እያዘጋጁኝም ነው ብዬ መፍራት ጀመርኩ" በማለት የነበረውን ስሜት አጋርቷል። • አሜሪካ ጥላ የወጣቻቸው የዓለም ድርጅቶች እነማን ናቸው? ጋዜጠኛው በማከልም በህይወቱ ውስጥ አሰቃቂ የሚላቸውን ሦስትና አራት ቀናትም ያሳለፈበት ሁኔታ እንደሆነ ይናገራል። እሱ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ህሙማንም በዚሁ መንገድ አልፈዋል። ክስተቱም በስልሳዎቹ ውስጥ በፅኑ ህሙማን ላይ ያለውን የአእምሮ መረበሽ ይፋ ያደረገ ነው። በዘርፉ ያሉ ተመራማሪዎች ይህ የሚፈጠረው በአእምሮ ውስጥ ያለ የኦክስጅን እጥረት፣ ለማደንዘዣ የሚጠቀሙት መድኃኒቶች፣ የእንቅልፍ እጥረት ሲያጋጥም እንደሆነ ያስረዳሉ። ሆኖም ዴቪድ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚያጋጥመው የአዕምሮ መረበሽ ብዙ የሚወራለት አይደለም። ህሙማን የአእምሮ ህመምተኛ የሚል ስያሜ እንዳይሰጣቸውም በመፍራት በሚስጥር ይይዙታል። ከፅኑ ህሙማን ክፍል ሚወጡ ሰዎች የተለያዩ ድጋፎች ያስፈልጓቸዋል ወደቤት መመለስ ምንም እንኳን የጤና ባለሙያዎች የሰለጠኑና የተረጋጉ ቢሆንም፤ የፅኑ ህሙማን ክፍል የሚረብሽ ቦታ ነው። "የሰውን ልጅ ለማሰቃየት የሚደረጉ ዘዴዎችን በምናስብበት ወቅት የሚመጡልን ሃሳቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የምታልፉባቸው ሁኔታዎች ናቸው" የሚሉት በለንደን ኮሌጅና በዊቲንግተን ሆስፒታል የፅኑ ህሙማን ህክምና ፕሮፌሰር ሂውግ ሞንቶጎሞሪ ናቸው። ህሙማን ራቁታቸቸውን ይሆናሉ፣ በተለያየ ሰዓትም የሚሰሙ የጥሪ ድምፆች አሉ፣ እንቅልፋቸው በጤና ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ይቋረጣል፣ ሙሉ ሌሊቱንም መድኃኒት ይሰጣቸዋል በማለት ፕሮፌሰር ሂውግ ለጋርዲያን ጋዜጣ ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ ምቾት የማጣት ሁኔታ፣ ግራ መጋባት፣ ፍራቻና ጥቃት የሚያደርስባቸው አካል እንዳለ የማሰብ ሁኔታ የፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የገቡ ሰዎች የሚያልፉባቸው አሰቃቂ እውነታዎች ናቸው። ለዚያም ነው ግለሰቦቹ ከፅኑ ህሙማን ክፍል ወጥተው ወደ የቤታቸው በሚሄዱበት ወቅት የነበረው ስቃይን በቀላሉ መላቀቅ ስለማይችሉ ለቤተሰባቸውም ይተርፋል። እንቅልፍ አይወስዳቸውም፣ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ መቆየታቸውን ሁሉ ሙሉ በሙሉ ሊረሱት ይችላሉ። • የኮሮናቫይረስን በመቆጣጠር በኩል እየተሳካላት ያለችው አገር ይህንንም ለመከላከል ሲል የእንግሊዝ የጤና አገልግሎት በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የቆዩ ቤተሰቦች ማስታወስ ይረዳቸው ዘንድ ማስታወሻ ቢያስቀምጡላቸው ጥሩ ነው ይላሉ። መላው የሰውነታቸው ተግባር ይከናወን የነበረው በማሽን ታግዞ ስለነበር ካገገሙም በኋላ የሰውነት አካላት ወደ ቀድሞ ተግባራቸው በፍጥነት አይመለሱም። የጡንቻ መዛል እንዲሁም የማያቋርጥ ድካም ለረዥም ጊዜ አብረውት ለመኖር የሚታገሉት እውነታ ይሆናል። ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘ ጥናት እንደሚያሳየው በአሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ፅኑ ህሙማን ከ3-11 በመቶ የሚሆን የጡንቻ ጥንካሬን እያጡ ይሄዳሉ ይላል። ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ማገገም ለብዙ የኮቪድ-19 ህመምተኞች በራሳቸው መተንፈስ አለመቻልና ሳንባቸው ከጥቅም ውጭ መሆን ለመሻል ረዥም ጊዜን እንደሚወስድ ማሳያ ነው። የትንፋሽ መሳሪያ (ቬንትሌተር) ለህሙማኑ ኦከስጅን ወደ ሳንባ ለመውሰድና ካርቦንዳይኦክሳይድ ወደ ውጭ ለማስወጣት ይጠቅማል። ቬንትሌተሩም እንዲሰራ በአፍ ወይንም በአፍንጫ የሚገባ ቱቦ ይገጠማል፤ በከፍተኛም ሁኔታ ማደንዘዣ ይሰጣቸዋል። አንዳንዶቹም ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ቱቦው በመተንፈሻ አካላቸው ውስጥ ይገጠማል። ይህም የህሙማኑን የመዳን ጉዞ የበለጠ ያወሳስበዋል። በእንግሊዝ፣ ዌልስና ሰሜናዊ አየርላንድ በተደረገ ጥናት ፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የገቡ ህሙማን በአማካኝ ከአራት እስከ አምስት ቀናት ያሳልፋሉ። • ቤት ጥቃት ሲበዛ ወደየት ይሸሻል? የህሙማኑ ቁጥር 2 ሺህ 249 ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 15 በመቶ የሚሆኑት እንዲወጡ ተደርገዋል፤ ሌሎች 15 በመቶውን ደግሞ ሞት ነጥቋቸዋል። 1 ሺህ 600 የሚሆኑት ደግሞ አሁንም በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ናቸው። ይህ ግን አጠቃላይ አገሪቷ ውስጥ ያለውን መረጃ አያሳይም። ከዩናይትድ ኪንግደም የተገኘ ሌላ መረጃ እንደሚያሳየው ተጨማሪ የላቀ የመተንፈሻ ድጋፍ ከተደረገላቸው የኮሮናቫይረስ ህመምተኞች መካከል 67 በመቶ ሞተዋል። በቻይና ደግሞ ቬንትሌተር የተገጠመላቸው ህሙማን ውስጥ መትረፍ የቻሉት 14 በመቶ ብቻ ናቸው። ከኮሮናቫይረስ ያገገሙት ሂልተን መሪይ ፊሊፕሰን ከሆስፒታል ሲወጡ ሃኪሞቻቸው ሲሸኟቸው 'ቀስ በቀስ የመዳን ተስፋ' የ61 ዓመቱ ሂልተን መሪይ ፊሊፕሰን በኮሮናቫይረስ ከተያዙ በኋላ በቬንትሌተር በመታገዝ ነበር ሲተነፍሱ የነበሩት። ይመገቡ የነበሩትም በቱቦ አማካኝነት ስለነበር 15 በመቶ የሚሆነውን የሰውነት ክብደታቸው ቀንሷል። አገግመው ከሆስፒታል ከወጡም በኋላ እንዴት መራመድ እንዳለባቸው መማር ነበረባቸው። የማገገማቸውንም ሁኔታ "ደረጃ በደረጃ ነው፤ ቀስ በቀስ ነው" ብለዋል። "ለሦስት ሰዓት ያህል በጀርባዬ ሳልንጋለል በወንበር ላይ መቀመጤን እንደ ትልቅ ድል ነው ያየሁት። በጣም ነው ደስ ያለኝ" በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከሌሲስተር ፅኑ ህሙማን መታከሚያም ክፍል ሲወጡ የሆስፒታሉ ሠራተኞች በጭብጨባና በደስታ ሸኝተዋቸዋል። ይህንኑ የሚያሳየውን ቪዲዮ ብዙዎች ያጋሩት ሲሆን፤ በሕይወትም "ሁለተኛ እድል በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብለው ብዙ ነገር እንደተማሩና ህይወትንም እንደገና እንዲያጤኑ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል። "የወፎች ጫጫታ፣ ሰማዩ፣ አበቦች፣ በሆስፒታል ውስጥ ሆኜ እያስታወስኳቸው ነበር። ሁሉ ነገር ይታወሰኛል፤ ቀላሉ ነገር ለምሳሌ ዳቦና ማርማላታ ፊቴ ላይ ድቅን እያሉ ነበር" ብለዋል። "ያው ፈሳሽ ምግብ ነበር ሲሰጠኝ የነበረው፤ እግዚኦ ነው የሚያስብለው የሆስፒታል ምግብ፤ በተለይም የድንቹ ሾርባ ለመቅመስም ይከብዳል። የህይወቴ መጨረሻ ይሄ መስሎኝ ነበር" በማለት አስረድተዋል።
news-54347636
https://www.bbc.com/amharic/news-54347636
ምርጫ 2013 ፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ሚና ምንድነው?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ካሉት አምስት የቦርድ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) ሰኞ ዕለት [መስከረም 18] በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸው ይታወሳል።
ብርቱካን ሚደቅሳ (ወ/ሪ)፣ አበራ ደገፉ (ዶ/ር)፣ ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ት) ፣ አቶ ውብሽት አየለ እና ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) ብርቱካን ሚደቅሳ (ወ/ሪት) የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ ቦርዱ ተጨማሪ አራት አባላት አሉ። ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር)፣ አቶ ውብሽት አየለ፣ ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ሪት) እና አበራ ደገፉ (ዶ/ር) የምርጫ ቦርድ አባላት በመሆኑ ሰኔ 2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሾማቸው ይታወሳል። የቦርዱ አባላት ሚናቸው ምንድነው? አምስት አባላት ያለው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔን በተመለከተ ከፍተኛውን የመወሰን ኃላፊነት የያዘ አካል ነው። በዚህም ቁልፍ ውሳኔን የማሳለፍ ስልጣን እንዳለው ይነገራል። በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 መሠረት ቦርዱ በሕገ መንግሥቱ እና በምርጫ ሕግ መሠረት የሚካሄድን ማንኛውንም ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ በገለልተኝነት ያስፈጽማል። የምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ደግሞ በምርጫ ሂደት የምርጫ ውጤትን የሚያዛንፍ የሕግ ጥሰት ተከስቷል ብለው ሲያምኑ ውጤቱን መሰረዝና ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የመወሰን ስልጣን አላቸው። የሥራ አመራር ቦርዱ የምርጫ ቦርድ የመጨረሻው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አካል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የምርጫ ውጤቶች ይፋ ከመደረጋቸው በፊት የምርጫ ውጤቶችን ያጸድቃል። የምርጫ ሕጎችን ማስፈጸም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መቆጣጠር፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ ማከፋፈል፣ ለምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ መስጠት እና መቆጣጠር፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ማሰናዳት እንዲሁም በጀት አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ማዋል የሚሉት ከቦርዱ ስልጣን እና ተግባር መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የቦርዱ አባላት እንዴት ይመረጣሉ? የቦርድ አባላት የሚመረጡት ዝርዝር ሥነ-ሥርዓቶችን ተከትሎ ነው። በቅድሚያ ጠቅላይ ሚንስትሩ እጩ የቦርድ አባላትን የሚመለምል ኮሚቴ ያቋቁሟሉ። የዚህ ኮሚቴ አባላት ደግሞ ከተለያዩ የሕብረተሰቡ ክፍል የሚወጣጡ እና ገለልተኛ የሆኑ ግለሰቦችን ያቀፈ መሆን ይኖርበታል። ከሐይማኖት ተቋማት፣ ከሳይንስ አካዳሚ፣ ከሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን፣ ከንግድና ማኅበራት፣ ከሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም ከሲቪል ማኅበራት እና ከአገር ሽማግሌዎች የሚመረጡ ሰዎች የኮሚቴው አባላት ይሆናሉ። ከዚያም ይህ ኮሚቴ የምርጫ ቦርድ አባል ሊሆኑ የሚችሉ እጩዎችን ጥቆማ ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች እና ከሲቪል ማኅበራት ይቀበላል። ኮሚቴው ከተጠቆሙት ሰዎች ውስጥ የቦርድ አባላት ሊሆኑ የሚችሉ እጩዎችን በመለየትና ፍቃደኝነታቸውን በማረጋገጥ የእጩዎቹን ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀርባል። ጠቅላይ ሚንስትሩም የእጩዎቹ ስም ዝርዝር ከኮሚቴው ከደረሰባቸው በኋላ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በቀረቡት እጩዎች ላይ ምክክር ያደርጋሉ። ከምክክሩ በኋላ ጠቅላይ ሚንስትሩ እጩዎቹን ለሹመት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ። ምክር ቤቱም የቀረቡት እጩዎችን በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቅ እጩዎቹ የቦርዱ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሆነው ይሾማሉ። የምርጫ ቦርድ አባላት እነ ማን ናቸው? ብርቱካን ሚደቅሳ (ወ/ት) የቦርዱ ሰብሳቢ ሲሆኑ ቦርዱ ተጨማሪ አራት አባላት አሉ። ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር)፣ አቶ ውብሽት አየለ፣ ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ሪት) እና አበራ ደገፉ (ዶ/ር) የምርጫ ቦርድ አባላት በመሆኑ ሰኔ 2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሾማቸው ይታወሳል። ብርቱካን ሚደቅሳ- የቦርድ ሰብሳቢ ከሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሕዝብ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት ብርቱካን ሚደቅሳ ቀደም ሲል የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው አገልግለዋል። ብርቱካን ወደ ስደት ከመሄዳቸው በፊት በተቃዋሚ ፓርቲ አባልነት በፖለቲካው ውስጥ ይንቀሳቃሱ እንደነበረ ይታወቃሉ። ብዙ የተባለለትን የ1997 ዓ.ም ምርጫን ተከትሎም ከተነሳው ውዝግብ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ለእስር የተዳረጉ ሲሆን የዕድሜ ልክ እስራትም ተፈርዶባቸው ነበር። ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘው ጥናቶችን አድርገዋል። ከሰባት ዓመታት ስደት በኋላም በ2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን እንዲመሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሹመው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በሊቀ መንበርነት እየመሩ ይገኛሉ። አቶ ውብሸት አየለ - የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ምሩቅ ናቸው። በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በዳኝነት አገልግለዋል። ከዳኝነት ሥራቸው ለቀው የራሳቸውን ቢሮ በመክፈት የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ ሆነው ሠርተዋል። አቶ ውብሸት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን በማማከር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ውይይት በማስተባበር እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ እንቅስቃሴዎች ላይ በሙያቸው ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተጠቅሷል። አቶ ውብሸት በሲቪክ ማኅበራት እና ማኅበረሰባዊ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል። አበራ ደገፋ (ዶ/ር) - የቦርድ አባል አበራ ደገፋ (ዶ/ር ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሶሻል ወርክ እና ሶሻል ዴቨሎፕመንት ከአ.አ.ዩ አግኝተዋል። በተጨማሪም፣ በኔዘርላንድስ ከሚገኘው ኢንስቲትዩት ፎር ሶሻል ስተዲስ፣ በዓለም አቀፍ ሕግ እና ልማት የድኅረ ምረቃ ዲፕሎማ አላቸው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመደበኛው የመምህርነት ሥራቸው ባሻገር በልዩ ልዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች በሙያቸው እንዳገለገሉ የሚነገርላቸው አበራ (ዶ/ር)፤ በዘመን ባንክ፣ በፍትሕ ሚኒስቴር የጠበቆች አስተዳደር ጉባኤ እና በኦሮሚያ የሕግ ጆርናል የቦርድ አባል በመሆን መስራታቸው ይጠቀሳል። የምርጫ ቦርድ አባል ሆነው ከመሾማቸው በፊት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ እና የፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ እንዲሁም የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባል ሆነዋል። ብዙወርቅ ከተተ (ወ/ሪት) - የቦርድ አባል ብዙርቅ ከተተ(ወ/ሪት) የከፍተኛ ትምህርታቸውን ከኩባ ሐቫና ዩኒቨርሲቲ የውጪ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል በሥነ ቋንቋ የሁለተኛ ደረጃ ዲግሪ አግኝተዋል። ብዙወርቅ (ወ/ሪት) በልዩ ልዩ ተቋማት አገልግለዋል። ከእነርሱም መካከል የቀድሞው የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ አክሽን ኤይድ ኢንተርናሽናል ይገኙበታል። በግጭት አፈታት እና መከላከል ላይ በሚሠራው የጀርመን አማካሪ ድርጅት ውስጥም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፕሮጄክት አስተባባሪ ሆነው ሠርተዋል። ብዙወርቅ (ወ/ሪት) በመልካም አስተዳደር፣ በአቅም ግንባታ እና ሲቪክ ተሳትፎን በማበረታታት ላይ የሚሠራ፤ 'ዜጋ ለዕድገት' የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት መሥራች እና የቦርድ ሊቀ መንበር ሆነው አገልግለዋል። ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) - የቦርድ አባል ከቦርዱ ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት በ2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው። ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። በትግራይ ክልል የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ፣ በአዲስ አበባ እና በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር እና ዲን፣ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል። ጌታሁን (ዶ/ር) የተለያዩ የምርምር ጽሑፎችን በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የኅትመት ውጤቶች ላይ ማሳተማቸውም ተጠቅሷል። ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባል ሆነው ከተሾሙ በኋላ በኃላፊነታቸው ላይ ከአንድ ዓመት ብዙም ባልበለጠ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ነው በፈቃዳቸው ሥራቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸው የተነገረው። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ የቦርዱ ዋነኛ ሥራ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ስድስተኛ አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ወደዚህኛው ዓመት መሸጋገሩ ይታወሳል። ከሳምንት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አገራዊው ምርጫ በዚህ ዓመት እንዲካሄድ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግ ከወሰነ በኋላ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚጠበቅበትን ለመወጣት ዝግጅት በሚጀመርበት ወቅት ከቦርድ አባላቱ አንዱ የሆኑት ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸው ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) ከቦርድ አባልነታቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን በመግለጽ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ከማቅረባቸው ውጪ ምክንያታቸው ምን እንደሆነ የገለጹት ነገር የለም።
55814355
https://www.bbc.com/amharic/55814355
በብሪታኒያ ፌስቡክ የዜና አምድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
በብሪታኒያ ፌስቡክ የዜና አምድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
ኩባንያው በብሪታኒያ 'ፌስቡክ ኒውስ' የሚል አምድ ከፍቷል። ይህ አግልግሎት በስልኮች በሚጫኑ የፌስቡክ መተግበሪያዎች እንደ አንድ አማራጭ ዜናና ተያያዥ መጣጥፎችን ለማንበብ የሚያስችል ነው። ፌስቡክ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ የዜናና ሌሎች ጠቃሚ አምዶችን በይዘቱ በይፋ ሳያካትት ቆይቶ ነበር። አሁን ግን ተጠቃሚዎች ፌስቡክ ሲጠቀሙ ዋና ዋና የዜና አውታሮችን አብረው መቃረም ያስችላቸዋል። ፌስቡክ ይህን የዜና አምድ አገልግሎት ሲሰጥ ብሪታኒያ 2ኛዋ አገር ናት። ከዚህ ቀደም ይህ አገልግሎት በአሜሪካ መጀመሩ መዘገቡ ይታወሳል። ፌስቡክ ይህን የዜና አገልግሎት ለመስጠት ከቻናል4፣ ስካይኒውስ እና ዘ ጋርዲያን ጋዜጦች ጋር ልዩ ስምምነት አድርጓል። ተጠቃሚዎች እነዚህን ይዘቶች ባነበቡ ቁጥር ፌስቡክ ለዜና አውታሮቹ/ጋዜጦቹ ተገቢውን ክፍያ ይፈጽማል። ጉግል ባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ስምምነት በአውስትራሊያ መፈጸም አለብህ መባሉን ተከትሎ አገልግሎቴን ሙሉ በሙሉ በዚያ አገር አቋርጣለሁ ብሎ ሲዝት እንደነበር አይዘነጋም። አውስትራሊያ እነዚህ የኦንላይን መተግበርያዎች ዜናና ዜና ነክ ይዘትን ለሚያመርቱ ሚዲያዎች ተገቢውን ክፍያ መፈጸም አለባቸው በሚል ጫና እያሳደረችባቸው ይገኛል። የጉግል አውስትራሊያን ለቅቄ ከናካቴው እወጣለው የሚለው ማስፈራሪያ የመጣውም ይህን ተከትሎ ነው። የፈረንሳይ ዜና አውታሮች በተመሳሳይ ከጉግል ጋር በዚሁ ጉዳይ በመነጋገር ላይ ናቸው። ፌስቡክ አሁን በብሪታኒያ የጀመረው የዜና አገልግሎት ይህንን በዜና አምራቾችና በዲጂታል መተግበሪያዎች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማርገብ የተወሰደ የተናጥል እርምጃ ነው ተብሏል። ፌስቡክና ጉግልን የመሰሉ መተግበሪያዎች በገቢ ደረጃ ከፍተኛ ትርፍ የሚያጋብሱ ሆነው ሳለ በገቢ ማጣት የሞት ሽረት ትግል ውስጥ ላሉ የዜና አውታሮች የሚከፍሉት ሽራፊ ሳንቲም አለመኖሩ ፍትሐዊ አይደለም በሚል ሲተች ቆይቷል። አሁን በብሪታኒያ አዲስ የተጀመረው የፌስቡክ የዜና አምድ ትናንት ከሰዓት ነው በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረው። አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻለው የፌስቡክ መተግበሪያን ከከፈቱ በኋላ 'ሞር አፕሽን' የሚለው ውስጥ ገብቶ የዜና አገልግሎት ሰጪ ቴሌቪዥኖችናና ጋዜጦችን ዝርዝር በማየት ነው። ፌስቡክ የግለሰቦችን እለታዊ ፍላጎትና የልማድ አዝማሚያ በአልጎሪዝሙ አማካኝነት እያጠና ለግለሰቡ ተስማሚ ዜናዎች ሲመጡ ያንን የማቅረብ አሰራርን ይከተላል። ዜና አውታሮቹ በፌስቡክ መካተታቸው ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል ተብሏል። አንዱ ከፌስቡክ በቀጥታ መደጎማቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እያወቋቸው እንዲመጡና በሂደትም ደንበኛ እንዲሆኑ ሊያበረታታቸው ይችላል፤ አዲስ ገበያም ይፈጥርላቸዋል ተብሏል። ይህ ፌስቡክ የወሰደው እርምጃ ግብአተ መሬቱ እየተፈጸመ ነው ለሚባለው የፕሮፌሽናል ጋዜጠኝነት እንደ ትንሳኤ እየታየ ነው።
news-46823810
https://www.bbc.com/amharic/news-46823810
"ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም" ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ
ጫት 'የኢኮኖሚ ዋልታ' ተብሎ የተዘፈነለት ቡናን ከተካ ረዥም ጊዜያት ተቆጥረዋል። ገበሬዎች የቡና መሬታቸውን ወደ ጫት ማሳነት በመቀየር ጫትን የኑሮ ዋልታቸው ካደረጉ ቆይተዋል።በጥቅሉ በጫት የተሸፈነ መሬት ተስፋፍቷል ፤ የጫት ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ቁጥርም ጨምሯል። ጫት እንደ ነውር ይታይ የነበረባቸው አካባቢዎች ቀዳሚ ጫት አምራችና ወደ ውጭ ላኪ እየሆኑም መጥተዋል።
በቅርቡ ጫት የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ቡናን መተካት ብቻም ሳይሆን ከቡና ይገኝ የነበረውን ገቢ በእጥፍ ማስገኘቱም ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት አራት ሚሊዮን የሚሆኑ ጫት አምራቾች እንዳሉም መረጃዎች ያሳያሉ። በተቃራኒው ግን ጫት ከሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባሻገር እያስከተለ ያለው ማህበራዊ ቀውስም የአገሪቱ እራስ ምታት ሆኗል። በዚህ ምክንያትም በቅርቡ የአማራ ክልል ጫትን ማገድ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ማውጣቱ የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በክልሉ ገበሬዎች ጫትን ከማሳቸው መንቀል መጀመራቸውም እየተነገረ ነው። • ጫትን መቆጣጠር ወይስ ማገድ? በማምረት፣ በመጓጓዝ፣በማከፋፈልና በመሸጥ የበርካቶች ኑሮ የተመሰረተው ጫት ላይ መሆኑ በአንድ በኩል፤ የጫት ሱስ እያስከተለ ያለው ማህበራዊ ቀውስ በሌላ በኩል ጫትን ማገድ የሚለውን ጉዳይ ለብዙዎች አከራካሪ አድርጎታል። ጫት ላይ የተለያዩ ጥናቶችን ያደረጉት እንዲሁም በጫት ላይ በተካሄዱ አገራዊ የውይይት መድረኮች ላይ ጥናቶቻቸውን ያቀረቡት ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድን አነጋግረናል። ዶ/ር ዘሪሁን ጫት ላይ የተሰሩ በርካታ ጥናቶችን ለህትመት ባበቃው የፎረም ፎር ሶሻል ስተደስ(FSS) አጥኚ ናቸው። •በኢትዮጵያ የአዕምሮ ህሙማን ሰብዓዊ መብት እየተጣሰ ይሆን? ቢቢሲ፦ ጫትን በሚመለከት ምን አይነት እርምጃ ነው መወሰድ ያለበት? ዶ/ር ዘሪሁን፡ በአሁኑ ወቅት ጫትን በሚመለከት ሁለት ፅንፍ የያዙ አቋሞች አሉ። ጫት እያስከተለ ያለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የጤና ጉዳት በመመልከት ጫት ይታገድ የሚል አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ጫት ለብዙዎች እንጀራና የኑሮ መሰረት በመሆኑ መነካት የለበትም የሚል ሌላ ፅንፍ አለ። ስለዚህ መከተል የሚኖርብን በሁለቱ መሃከል ያለውን መንገድ ነው። ጫት የሚያስከትለው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የጤና ጉዳት በብዙ ጥናቶች የተረጋገጠ ሲሆን ለጉዳቱ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ የመንግስትና የማህበረሰቡ ግዴታ ነው። በአንፃሩ ደግሞ ጫትን የሚያመርተው ክፍል ያለው አማራጭ ምንድን ነው? ጫት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያመጣ ያለ በመሆኑ የሚተካውስ በምንድን ነው? የሚሉትን ነገሮች በጥልቀት መመልከት ያስፈልጋል። ቢቢሲ፦መሃከል ላይ ያለው መንገድ ምንድን ነው? ዶ/ር ዘሪሁን፡ መሃከል ላይ ያለው ጫትን እንዲሁ መልቀቅ ወይም ማገድ ሳይሆን መቆጣጠር ነው። ምናልባት መቆጣጠር የሚለው በትክክል ካልገለፀው Regulate ማድረግ ማለት ነው። የምንቆጣጠረው በምን መንገድ ነው? አሁን ባለው ሁኔታ ሲታይ ጫትን ማገድ በተለያዩ ምክንያቶች ፈፅሞ የሚቻል አይደለም። በተለያዩ አገራት እንደ ካናቢስ ያሉን ማገድ ኮንትሮባንድን እንዳስከተለ ጫትን ማገድ ከዚህ የዘለለ ውጤት አያመጣም። ምን አይነት አማራጮችን አቅርበን ነው የምናግደው? ጫት በአንዳንድ ቦታዎች ለምእተ አመታት ከባህልና ከማንነት ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ማገድ ፖለቲካዊ ተፅእኖ ሊኖረውም ይችላል። ቁጥጥር ማድረግም ቀላል አይደም ሰዎች በቀላሉ ጫት እንዳያገኙ ከፍተኛ ቀረጥ መጣል የሚል ሃሳብ የሚሰነዝሩ አሉ። በተቃራኒው ደግሞ ለምን ?ትንባሆና አልኮል ላይ ምን ያህል ቀረጥ ነው የሚጣለው በማለት ጥያቄ የሚያነሱም አሉ። ዞሮ ዞሮ በአጥኚዎች ዘንድ ክርክሩ በአመዛኙ ቁጥጥር ማድረግ ወደ ሚለው መጥቷል። ቁጥጥሩ ፣ እንዴት ይመረት? እንዴት ይጓጓዝ? እንዴት ጥቅም ላይ ይዋል? በሚለው ላይ የሚያተኩር ነው። ቢቢሲ፦ መንግሥት የጫት ፖሊሲ ስለሌለው ጫት ላይ አቋም የለውም? ዶ/ር ዘሪሁን፡ በጫት ላይ ፖሊሲ አለመኖር ብቻ ሳይሆን በጫት ላይ ውይይት ከጀመርን ራሱ ብዙ ዓመት አልሆነም። ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ ብሄራዊ የጫት ውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ቀዳሚው ተቋም ነው። ብዙ ውይይቶችም ተካሂደዋል ቢሆንም ግን ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ ተጨማሪ ምርምሮችና ውይይቶች ያስፈልጋሉ። ጫትን በሚመለከት ባሉ ፅንፍ አቋሞች የጫት ፖሊሲ ማውጣት ቀላል እንደማይሆን ይሰማኛል። ፖሊሲው ባንድም ይሁን በሌላ መንገድ የብዙ አያሌ ሰዎችን ህይወት እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ጉዳይን የሚመለከት መሆኑም ጉዳዮን እጅግ ከባድ ያደርገዋል። በፖሊሲ ማውጣት ሂደት ጫት እየተቃመ ያለው በምን አይነት አውድ እና ባህል ነው ?የሚለው መታየት የሚኖርበት ሲሆን በሁሉም ክልሎችና አካባቢዎች እኩል ተፈፃሚ የሚሆን ፖሊሲ እናውጣ ማለት ግን አስቻጋሪ የሚሆን ይመስለኛል። ጫት መጀመሪያ ተገኝቶባቸዋል የሚባሉና ለረዥም ጊዜ ሲቃምባቸው የኖሩ አካባቢዎች እና ጫት ማብቀል ከጀመሩ አስር ዓመታት ብቻ ያስቆጠሩ አካባቢዎች አንድ አይነት መመሪያ ሊከተሉ አይችሉም። ስለዚህ አንዱ አማራጭ ሊሆን የሚችለው ክልል አቀፍ አማራጮችን ማውጣት ነው። ይህም ቢሆን ራሱ ጫት ክልል ተሻጋሪ ነው። ጫት ላይ ጥናት ሰራን የምንል ሰዎች ብቻ ሳንሆን እታች ድረስ ያሉ ሰዎች የሚሳተፉበት ሰፊ ውይይት ያስፈልጋል። ከታች ያሉ ሰዎች አመለካከት በጣም ጠቃሚ ነው። ያኔ ነው የነጠረ ሃሳብ ይዘን መውጣት የምንችለው። ቢቢሲ፦ጫትን ለመቆጣጠር የሚሞከረው አቅርቦት ላይ በማተኮር ነው? ዶ/ር ዘሪሁን፡ አዎ አብዛኞቹ እርምጃዎች አቅርቦት ተኮር ናቸው። የዚህ አይነቱ እርምጃ ደግሞ ብዙ አያስኬድም። ዋናው ፍላጎት ላይ መስራት ነው።አሁን ያለውን ከፍተኛ የጫት ገበያ የፈጠረው ፍላጎት ነው። ይህ ፍላጎት ባይኖር ኖሮ ገበሬው ጫት ለማምረት ነጋዴውም ለማቅረብ አይበረታታም ነበር። መቆጣጠሩ እንዳለ ሆኖ መጣር ያለብን ጫት ወደ መቃም የሚገባውን ሰው ቁጥር ለመቀነስ ነው። ይህ ደግሞ ህፃናትን ከጫት በመጠበቅ ነው። የጫትን አደገኝነት በመንገርና በማሳመን ወደ ሱስ እንዳይገቡ ማድረግ ነው። ለምንድን ነው ጫት መቃም እንደዚህ የተስፋፋው? የሚለውም መታየት አለበት። በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ተያያዥ የሆኑ ነገሮች አሉ። ምን ያህል የአካል ብቃት ማዘውተሪያ ቦታዎችና ቤተ መፃህፍት አሉን? ቢቢሲ፦ማን ነው ከጫት እየተጠቀመ ያለው? ዶ/ር ዘሪሁን፦እዚህ ጋር ጥቅምስ ጉዳትስ የገንዘብ ብቻ ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ መነሳት አለበት። የገንዘብን ብቻ ከተመለከትን በአሁኑ ወቅት አራት ሚሊዮን የሚሆኑ ጫት አምራቾች እንዳሉ ጥናቶች ያመለክታሉ። በጫት የተሸፈነው መሬትም ምን ያህል እንደሆነ የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ ያመለክታል። ይህ የጫት አምራቾች የኢኮኖሚ ጥቅም እያገኙ እንደሆነ ግልፅ ያደርጋል። ጫት በብዛት የሚመረትባቸው እንደ ሀረርጌ ፣ ጉራጌ አካባቢና ሲዳማና የተወሰኑ የጌዲኦ አካባቢዎች ሲታዩ ከፍተኛ የህዝብ ጥግግት ያለባቸውና ከፍተኛ የእርሻ መሬት እጥረት ያለባቸው ናቸው። ስለዚህ ጫት በአነስተኛ ቦታ ላይ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ የሚመረት በመሆኑ ገቢው ቤተሰብ ለማስተዳደር ያስችላል። በዚህ የአምራቹ ተጠቃሚነት ጥያቄ የለውም። በሌላ በኩል ከጅምላ ሻጩ ጀምሮ እስከ ቸርቻሪው ድረስ ያለው ሰንሰለት ሲታይ አንድ ጥናት 18 የሚሆኑ ባለድርሻዎችን ይዘረዝራል። ጫት ቆራጭ፣ አደራጅ፣ አመላላሽ(ትራንስፖርት)፣ መጠቅለያ የእንሰት ቅጠል የሚያቀርቡና ሌሎችም። ስለዚህ ስለ ጫት ሲወራ ጫትን ስላመረተውና ስለተጠቃሚው ብቻ አይደለም። ይልቁንም በመሃከል ሰፊ የንግድ ትስስር አለ። ክልልና ፌደራል መንግስትም እየተጠቀሙ ነው። በክልሎች ትንንሽ ኬላዎች ላይ ከጫት የሚሰበሰበው ቀረጥ ለአካባቢ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጋል። እንግዲህ ይህ ከቀረጥ ብቻ የሚገኝ ጥቅም ነው። ቢቢሲ፦ ገዥው ምን ይጠቀማል? ዶ/ር ዘሪሁን፦ ለአንዳንድ ሰው መዝናኛ ነው።በአንዳንድ ማህበረሰብ ደግሞ ጫት በማህበራዊ ትስስር ትልቅ ዋጋ አለው። ስለዚህ ይህም ጥቅም ነው። ከሃይማኖት ጋርም የሚያያዝበት ሁኔታ አለ። በተቃራኒው ጫትን አላግባብ የሚጠቀሙ በጣም ይጎዳሉ።ቤተሰብ ይፈርሳል ማህበረሰብና አገር ይጎዳል።በጫት የሚደርሰው የአእምሮ ጤና ጉዳትም ከፍተኛ ነው።
54769253
https://www.bbc.com/amharic/54769253
ውጤታማ የአፍሪካ ገበሬ በመባል የተሸለመችው ሃረጉ ጎበዛይ
ወይዘሮ ሃረጉ ጎበዛይ፤ በአንድ ወቅት በገጠራማ የትግራይ ወረዳዎች ትዳር መስርተው፣ ልጆች ወልደው፣ የባለቤታቸውን የወር ገቢ እየተጠባበቁ በዝቅተኛ የህይወት ደረጃ ከሚኖሩት ሴት ገበሬዎች መካከል አንዷ ነበረች።
በወቅቱ፤ የራሴ የምትለው መውደቂያ ያልነበራትና በእናቷ ስር ተጠግታ የምትኖር ባለ ትዳር ሴትም ነበረች። ይሁን እንጂ፤ ባለቤቷ በሚያገኘው አነስተኛ ገቢ ከእጅ ወደ አፍ የሆነን ኑሮ ሳይቀይሩ እንቅልፍ ለወይዘሮ ሃረጉ የሚታለም አልነበረም። "ግብርና እሞክር ነበር፤ ግን ደግሞ የሚያጠግብ ምርት አላገኝበትም። አካባቢያችን ቆላ ስለሆነ ከአንድ ሄክታር ከሁለት እስከ ሦስት ኩንታል ምርት ብቻ ነው የሚገኘው። በጦርነት የተጠቃ ድንበርም ስለሆነ ምድረ በዳ ሆኖ ነበር" ትላለች። አርሶ አደር ሃረጉ፤ በትግራይ ክልል ማእከላይ ዞን ወረዳ መረብለኸ ከተማ ራማ ዓዲ አርባዕተ ኗሪ ናት። በትምህርት ብዙም አልገፋችም፤ አራተኛ ክፍል ግን ደርሳለች። ስለዚህ ከዚህ የድህነት ኑሮዋ የሚቀይራት ትምህርት ሳይሆን ድንጋይ የበዛበት መሬትዋን ማልማት ብቻ ነው። የነበራት መሬትም ብዙም የምትመካበት አይደለም፤ 1.5 ሄክታር ብቻ ናት። በ1997 ዓ. ም፤ ያቺን መሬትዋ ይዛ ወደ እርሻ ልማት መግባት ወሰነች። ይሁን እንጂ በቀላሉ ታርሶ የሚለሰልስ መሬት አይደለም የያዘችው። ከላይ እሰከ ታች ድንጋይ ብቻ የወረረው መሬት ነው። "በእስራኤል አፈር ከሌላ አካባቢ መጥቶ ነው መሬት የሚለማው ሲባል በቴሌቪዥን ስሰማ፣ እኔም መሬቱን ለመለወጥ በድፍረት ጀመርኩት። አፈር የሚባል አልነበረውም፤ ስለዚህ አንድ ሜትር ከግማሽ ቆፍሬ፣ ከሌላ ቦታ አፈር አምጥቼ ሞላሁት። ከዛ በኋላ ቋሚ አትልክቶች ተከልኩ" ትላለች። በአካባቢው የመስኖ ልማት የተለመደ እንዳልነበረ የምትናገረው አርሶ አደር ሃረጉ፤ እንደ ማሽላ፣ ዳጉሳና ሽምብራ የመሳሰሉት አዝዕርቶች ይዘወተሩ እንደነበር ታወሳለች። "ትግራይ ድንጋይ እንጂ ፍራፍሬ የሚገኝ የማይመስለው ብዙ ነው፤ ከተሰራ ግን የማይቀየር የለም። ለዚህም ነው ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት ከኤርትራ መጥተው በአካባቢያችን መሬት ተከራይተው በመስኖ ልማት ቋሚ አትክልቶች ሲያለሙ ከነበሩት ኤርትራውያን ልምድ ወስጄ የእኔን ድንጋያማ መሬት መቀየር የቻልኩት" በማለት ትገልጻለች። "እያበደች ነው ይሉኝ ነበር" ይህ አፈር ያልነበረው መሬት ለም አፈር በማልበስ በመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ቃርያና ሌሎች ገቢ ሊያስገኙላት የሚችሉ አትክልቶች በመትከል ስራ ጀመረች። እንዲህ እያለች፤ መሬቱንም ወደ 12 ሄክታር በማሳደግ አፕል፣ ኬንት፣ ቶሚ፣ ኪት፣ ዳዶ የሚባሉ የማንጎ አይነቶች የሚገኙባቸው ሰባት የማንጎ ዝርያዎች ተከለችበት። "የእኔ መሬት ልዩ የሚያደርገው ዐለት እንጂ የሚታረስ መሬት አይደለም የነበረው። በ1982 ዓ. ም ለገበሬዎች ታድሎ ማንም ሰው ሳይጠቀምበት የቆየ ነው። በኋላ በ1997 ዓ. ም ትንሽም ቢሆን ልሞክረው ብዬ ድንጋይና እሾህ እያጸዳሁ ማልማት ጀመርኩ። ያኔ ይህች ሴት በየበረሃው የምትሄደው እያበደች ነው፣ ሌላ ስራ አትሰራም የሚሉኝ ነበሩ። አሁን ህይወቴ ተቀይሮ ሲያዩ ደግሞ ያኔ ከእሷ ጋር ብንሮጥ ኖሮ ይላሉ" ስትል ትውስታዋን ታጋራለች። ዓለትም ፈንቅላ ይሁን እሾህ ለቅማ አፈር የሌለው መሬት አለማለሁ ብላ ስትነሳ የሳቁባትና 'የሴቶች ስራ አትሰራም' ሲሉ ያንቋሸሽዋት ጥቂቶች እንዳልነበሩ የምትናገረው ሃረጉ፤ የልማት አርበኛ ሆና ለሌሎች አርአያ የሆነችበት ደረጃ በመድረሷ ደስተኛ ናት። በአንድ ቀን የመቀለ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ተማሪዎችን ይዞ በመሄድ ይሄንን ስራዋን የተመለከተ የተፈጥሮአዊ ሃብትና የደረቅ መሬት ልማት ኮሌጅ አስተማሪ ዶክተር ዳዊት ገብረእግዚኣብሄር፣ "ድንጋይ ወደ ፍራፍሬ የቀየረች ሴት" የሚል ስያሜ ሰጥቷታል። እሷም "ስንስቅባት የነበረው ለዚህ ለውጥ ነበር ለካ ያላሉ የሉም። ባለቤቴም ፖሊስ ስለነበረ በተለያዩ አካባቢዎች ስለሚንቀሳቀስ ለብቻዬ ነበር የምኖረው። እሱም ስራዬን ከሚቃወሙት አንዱ ነበር። 'በረሃ ለበረሃ ከምትሮጪ ሌላ ስራ አትሰሪም . . . መቼ ያልፍልኛል ብለሽ ነው?' ይለኝ ነበር" በማለት ያለፈችውን ታስታውሳለች። "በራሴ ትግል ብቻ ነው እዚህ የደረስኩት" ትላለች። ከጊዜ በኋላ ደጋፊዋ የሆነው ባለቤቷም ስራውን ትቶ ከእርሷ ጋር በግብርና ስራ ከተሰማራ አመታት አስቆጥሯል። የእርሻ ማሳ ወደሚገኝበት ቦታ የሚያደርስ መንገድ የለም፣ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ያለበት አካባቢ መሆኑም ሌላ ትልቁ ፈተና ነበር። አርሶ አደሯ ግን በእነዚህና ሌሎች አዳጋች ችግሮች ተስፋ በመቁረጥ እጅና እግር አጣጥፎ መቀመጥን አልመረጠችም። ይልቁንስ፤ 1.2 ሚሊየን ብር በማውጣት የመስኖ መስመር ስትዘረጋ የሚያጋጥማትን የውሃ ችግር ፈታች። ቀጥላም 820 ሺ ብር ወጪ በማድረግ ምርቶችዋን በቀላሉ ወደ ገበያ የሚያደርስላትና ስራዋን ለመጎብኘት የሚመጡት ሰዎች በመኪና የሚሻገሩበት ድልድይ ሰራች። ይህንን በማድረግ ራስዋን ጨምሮ በአካባቢዋ የሚገኙ 80 አባወራዎች ከበፊት ችግሮቻቸው እረፍት እንዲያገኙ በማድረግ፤ በህይወትዋም ትልቅ ስኬት የምትለውን ለማስመዝገብ የበቃች አርሶ አደር መሆን ችላለች። "ከዚህ በፊት መንገድ ስላልነበረ የእርሻ ባለሞያዎች በእግራቸው ነበር የሚመጡት። እኔም በዚህ ሁሉ ችግር ተስፋ አልቆረጥኩም፤ አንድ ቀን ይህ ጨለማ ተገልጦ ይበራልኛል የሚል ተስፋ ነበረኝ። እነሆ በርቶልኛል" በማለት በጥረቷ ደስተኛ መሆንዋን ትገልጻለች። ሃረጉ ማሳ ላይ ምን ይገኛል? በአሁኑ ወቅት ሰባት የማንጎ ዝርያዎች ለገበያ ታቀርባለች። በዋናነት አፕል ማንጎን በብዛት ታመርታለች። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ፤ ዴስሞሲየም፣ የዝሆን ሳር፣ የግጦሽ ሳር፣ ተፈጥሮአዊ ጸረ ተባይ ሆኖ የሚያገለግለው የኒም ቅጠልና ሌሎች አትክልቶች ያሉት ሰፊ ማሳ ይገኛል። ለዚህ ሁሉ ዘመናዊ ማዳበሪያም ሆነ ጸረ ተባይ አትጠቀምም። ከባለፈው አመት ጀምሮ አርሶ አደሯ ያላት 12 ሄክታር መሬት በሙሉ ምርት መስጠት ስለ ጀመረ ከ6700 ቋሚ ተክል በአመት ወደ 2500 ኩንታል የሚጠጋ ፍራፍሬ እንደምታገኝ ትናገራለች። "አብዛኛዎቹን ደምበኞቼ በስልክ እንጂ በአካል አላውቃቸውም። በትግራይና አዲስ አበባ ግን ብዙ ደንበኛ እንዳለኝ አውቃለሁ አፕል ማንጎ ጥሩ ገበያ ያለው ሲሆን፤ በዚህ አመት አዲስ አበባ ያሉትን ናቸው በብዛት የወሰዱልኝ" ትላለች። ራማ፤ ኢትዮጵያ ኤርትራ ከሚገናኙባቸው ድንበሮች አንዱ ሲሆን፤ ከሁለት አመት በፊት በሁለት አገራት የሰላም ስምምነት በኋላ ሲከፈት ጥሩ ገበያ እንደነበራትም ገልጻለች። "በወቅቱ በኪሎ 80 ብር ስሸጥ ነበር፤ ጊዜው አጭር ቢሆንም ጥሩ ነበር። የድንበሩ መከፈት ለሁላችንም ጠቅሞን ነበረ፤ ሁሌም ሰላም ቢሆን እላለሁ። በዚህ የገበሬውም ህይወት ይቀየራል፤ ተጠቃሚውም በቀላሉ የሚፈልገውን ማግኘት ይችላል" የሚል እምነት አላት። ይሄንን ስራ ከጀመረች በኋላ ባሉት አመታት የነበረው ጉዞ ቀላል እንዳልነበረ ግን አትዘነጋም። በየጊዜው የሚያጋጥም የሞተር መሰበር፣ መክሰርና ገበያ ማጣት በተደጋጋሚ የተጋፈጠቻቸው ችግሮች ናቸው። "ሲከስር ያጣሁትን ቶሎ እተካለሁ በማለት የሚሰደድ አለ፤ እኔ ግን ያንን አልመረጥኩም። ሁሉንም ችዬ ስላለፍኩትም በኑሮዬ ምንም ያልነበረኝ ሰው አሁን ሦስትና አራት ቦታ ላይ ቤት ሰርቼ ጥሩ ህይወት እየመራሁ ነው" ስትል ልፋት የሚጠይቅ ስራ እንደሆነ ትገልጻለች። ወይዘሮ ሃረጉ የስድስት ልጆች እናት ናት። ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ገብተው የሚማሩ መኖራቸውንም ትናገራለች። ታዲያ ሁሉም የቤተሰብ አባል በዚህ ማሳ የራሱ የስራ ድርሻ ይዞ ለተጨማሪ እድገት ይተጋል። በተጨማሪም ለ16 ሴቶችና ለ16 ወንዶች ቋሚ የስራ እድል ፈጥራለች። በገንዘብ እጥረት ትምህርታቸውን ማቋረጥ የለባቸውም ብላ ለምታምንባቸው ከ50 እስከ 60 ለሚሆኑ ወጣት ተማሪዎችም በሰአት ሰርተው ገቢ በማግኘት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ታደርጋለች። ይሄንን ጥረትና ትጋት ሲከታተል የቆየው ዶክተር ዳዊት፤ ጥቅምት ወር ላይ ውጤታማ የአፍሪካ ገበሬ ተብላ እንድትሸለም በ 'አፍሪካን ፋርመርስ ስቶሪስ' ላይ አመለከተላት። መሸለምዋንም የነገራትም እሱ ነው። "በዚህ ሁኔታ አንዲት ሴት ራስዋን ቀይራ ፍራፍሬዎች በማምረት ሌሎችን ለመለወጥ ስትጥርና ስትሸለም ከማየት በላይ የሚያስደስት የለም" ይላል። ወይዘሮ ሃረጉ በበኩሏ፤ "በየጊዜው ስሸለም ብርታት ነው የሚሆነኝ። አሁን ግን ትግራይን በመወከል ይሄንን ሽልማት ማግኘቴ ኩራት ይሰማኛል። በዚህ ልጆቼም ደስተኞች ናቸው። እኛም እንዲህ ሌላ እንሰራልን፣ ወደ ፋብሪካና ኢንዳስትሪ እናሳድገዋለን ይሉኛል" በማለት የወደፊት ምኞትዋን ታጋራለች። "እኔ ስጀምር አካባቢዬ ላይ ብድርና ባንክ ስላልነበረ በ1700 ብር ብቻ ነው የጀመርኩት። አሁን ግን በተለያየ መልኩ ብድር ስለሚገኝ የምትቀየርበት ነገር ሩቅ አይደለም" በማለት ሁሉም በስራ እንዲተጋ ታበረታታለች።
42869384
https://www.bbc.com/amharic/42869384
ለናይጄሪያዊቷ ፀሃፊ ባቀረበችው ጥያቄ የተጋለጠቸው ጋዜጠኛ
ካሮላይን ሙህ የተባለች የፈረንሳይ ጋዜጠኛ በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘችው ናይጄሪያዊቷ ፀሃፊ ችማማንዳ አዲቼን "ናይጄሪያ ውስጥ ቤተ መፃህፍት አሉ? መፅሃፎችሽስ ይነበባሉ?" ስትል መጠየቋን ተከትሎ 16 ሺህ ሰዎች ስለጉዳዩና ስለ ቺማማንዳ ትዊት አድርገዋል።
13 ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ጉዳዮን በማስመልከት ችማማንዳ ፌስቡክ ገጿ ላይ ላሰፈረችው ፅሁፍ በተለያየ መንገድ ምላሽ ሲሰጡ ሦስት ሺህ አስተያየቶችም ተሰጥተዋል። ባለፈው ሃሙስ ፓሪስ ላይ በተደረገ የቀጥታ ስርጭት ቃለ-ምልልስ ነበር ቺማማንዳ ከጋዜጠኛዋ ጥያቄው የቀረበላት። የቺማማንዳ መልስ "በጣም በሚያስገርም መልኩ ያነባሉ" የሚል ነበር። መፅሃፏ በናይጄሪያ ብቻም ሳይሆን በመላው አፍሪካ እንደሚነበብም ጨምራ ገልፃለች። በምርጥ ፀሃፊነቷ ዓለም ለሚያውቃት፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ላገኘቸውና በአሜሪካና በአውሮፓ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ለተሰጣት ቺማማንዳ የዚህ አይነት ጥያቄ ማቅረብ የጋዜጠኛዋን ዝግጅት ከማድረግ ይልቅ ግምቷን ይዛ ወደ ቃለ መጠይቁ መግባቷን አጋልጧል። ጋዜጠኛዋ ፈረንሳይ ውስጥ ስለ ናይጄሪያ የሚነገረው ሁሉ ስለ ቦኮ ሃራምና ብጥብጥ ብቻ እንደሆነ በመጥቀስ ጥያቄዋን መሰረት ለማስያዝም ጥራ ነበር። ጋዜጠኛዋ ስለ ናይጄሪያ ሥነ-ፅሁፍና የንባብ ባህል ግምቷን መሰረት አድርጋ ያቀረበችው ጥያቄ የፈረንሳይ ህዝብን ገፅታ የሚያበላሽ እንደሆነ ቺማማንዳ ተናግራለች። በጋዜጠኛዋ የተበሳጩ ናይጄሪያዊያን እውቅ ፀሃፊ ዎሌ ሾይንካ፣ ቺንዋ አቼቤንና ቤን ኦርኪን በመጥቀስ ስለ ናይጄሪያ የሥነ-ፅሁፍ ከፍታ ለማስታወስ ተገደዋል። በዚህ ዘመን አንብቦ ከመዘጋጀት ይልቅ ግምቱንና የራሱን ውስን የዓለም አተያይ መሰረት አድርጎ የሚሰራ ጋዜጠኛ መኖር አሳዛኝ እንደሆነ አስተያየታቸውን የሰጡም በርካቶች ናቸው። ከቺማማንዳ መፅሃፎች አሜሪካና እና ፐርፕል ሄቢስከስን መጥቀስ ይቻላል። "ዊ ሹድ ኦል ቢ ፌሚኒስትስ" የሚለው የቴድ ኤክስ ንግግሯ ደግሞ ወደ መፀሃፍ ተቀይሮ ስዊድን ውስጥ ለ16 ዓመት ልጆች በሙሉ ተሰጥቷል። የንግግሩን ሃሳብ ቢዮንሴም በአንድ ዘፈኗ አካታዋለች።
news-55349589
https://www.bbc.com/amharic/news-55349589
ኪነ ጥበብ፡ አንጋፋው የጥበብ ሰው ተስፋዬ ገሰሰ በሚያውቋቸው አንደበት
መተከዣ ፣ ዕቃው፣ የሺ፣ አባትና ልጆች፣ ላቀችና ደስታ፣ ተሐድሶ የተሰኙ ተውኔቶችን ደርሰዋል።
የሼክስፒር ድርሰት የሆነውን ሐምሌትና ትያትርን ጨምሮ በርካታ ተውኔቶች ላይ በመተወን እና በማዘጋጀት ለመድረክ አብቅተዋል። የዑመር ኻያምን ልቦለዳዊ የሕይወት ታሪክና ሩብ አያቴ የትርጉም ሥራ ለአንባቢያን አድርሰዋል። 'ሽልንጌን' ጨምሮ በርካታ የአጭር ልቦለድ ሥራዎችን ለአንባቢያን አበርክተዋል። በተለያዩ ፊልሞችና ድራማዎች ላይ ተውነዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር እና ጥበባት ኮሌጅ ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል። የብሔራዊ ትያትር ቤት ዳሬክተር በመሆንም ሰርተዋል። ለኢትዮጵያ ኪነጥበብ ትልቅ አሻራ ካሳረፉ አንጋፋ የጥበብ ሰዎች አንዱ ናቸው። ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ። እኝህ አንጋፋ የጥበብ ሰው በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው ትናንት ነበር። በርካቶች ተስፋዬ ገሰሰን "ራሳቸውን ሆነው ለጥበቡ ዘርፍ የበኩላቸውን አበርክተው ያለፉ ሰው" ሲሉ ይገልጿቸዋል። "በግለሰቦችም ሆነ በአገርም ላይ ብዙ ውጤቶች ያፈራ ሰው ነው" አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) ከተስፋዬ ገሰሰ የቅርብ ወዳጆች አንዱ ናቸው። ለአስርት ዓመታትም በጥበቡ ዘርፍ አብረው ደፋ ቀና ብለዋል። ሁለቱ ተስፋዬ ትውውቃቸው የሚጀምረው በ1965 ዓ.ም ነበር። እርሳቸው አገር ፍቅር ትያትር ክበብ ሲመሰርቱ፤ ተስፋዬ ገሰሰ ደግሞ የትያትር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ነበሩ። "ተስፋዬ ገሰሰ ልዩና ጨዋ ሰው ነበር" የሚሉት ተስፋዬ አበበ፤ "በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትያትር ጥበብ መምህር ሆኖ ወደፊት ተተኪ የሆኑ ተዋንያንን ፈጥሯል" ይላሉ። በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንድ የትያትር አዳራሽ 'ተስፋዬ ገሰሰ የኪነ ጥበባት ማዕከል' ተብሎ ተሰይሞላቸዋል። "ተስፋዬ ገሰሰ በግለሰቦችም ሆነ በአገር ላይ ብዙ ውጤቶች ያፈራ ሰው ነው" ይላሉ። ለዚህም 'ጋሻ ዳምጤ' የተሰኘውን ሙዚቃዊ ተውኔት ለአብነት ያነሳሉ። 'ጋሻ ዳምጤ' በሳንሱር የተከለከለና የወሎ ረሃብን የሚያሳይ ሙዚቃዊ ድራማ ነው። በዚህ ተውኔት ላይ የተስፋዬ የትወና ብቃት የሚገርም እንደነበር ያስታውሳሉ። "ተዋንያኑም በደስታ ተነስተው ይቀበሏቸው ነበር" ይላሉ- በሙያቸውም ሆነ በጥበበኞች ዘንድ ምን ያህል ተወዳጅ እንደነበሩ ሲገልፁ። 'ጋሻ ዳምጤ' የተሰኘው ሙዚቃዊ ተውኔት ሙዚቃው በተስፋዬ አበበ የተሰራ ሲሆን ዳይሬክት የተደረገው በተስፋዬ ገሰሰ ነበር። የጥበቡ ሰው ተስፋዬ ገሰሰ ለኪነ ጥበብ ዘርፉ እንደየ ዘመኑ ዋጋ ከፍለዋል። በደርግ ዘመነ መንግሥት 'ዕቃው' የሚል ተውኔት ጽፈው ለእስራት ተዳርገው እንደነበር አርቲስት ተስፋዬ ያስታውሳሉ። በዚያው ዘመን 'ደማችን ትግላችን' የሚል ሙዚቃዊ ድራማ ላይ በትወና እና በዝግጅት ሰርተዋል። በዚህም በዝምታ አልታለፉም ነበር። ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ነበር። "አገራዊና ሕዝባዊ የሆኑ ሥራዎች ላይ በድፍረት እየገባ፤ ጥበብን በድፍረት እየተወጣ የነበረ ሰው ነበር" ይላሉ አርቲስት ተስፋዬ። እርሳቸው እንደሚሉት ተስፋዬ ገሰሰ በግድ ፖለቲካ ውስጥ ገብተው የሰሯቸው ሥራዎች አልነበሩም። አንዳንድ ነገሮች ከበላይ አካል ሲመጡም 'ይህን አልሰራም!' የማለት አቅም የነበራቸው ሰው እንደነበሩ ይመሰክራሉ። በወቅቱ ከነበረው ጫና ጋር ተያይዞ ገጣሚና ፀሐፈ ተውኔት አያልነህም አንድ አጋጣሚን እንዲህ ሲሉ ያስታውሳሉ። "በደርግ ዘመነ መንግሥት የሱዳን መሪ ኢትዮጵያ መጥተው ከኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም ሙዚቃ ለማየት ትያትር ቤት ገብተው ሳለ፣ ማን እንዳደረገው ሳይታወቅ መብራት ጠፋ። የዚያን ጊዜ 'ሆነ ተብሎ ነው የተደረገው' በሚል ወቀሳ ቀርቦባቸው ነበር። በዚህ ምክንያትም በወቅቱ የነበሩት የባህል ሚኒስትር ከሥልጣናቸው ተነስተዋል" "በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለዲግሪ ተዋናይ ነበር" በንጉሱ ዘመን አፄ ኃይለሥላሴ ተስፋዬ ገሰሰን አንድ ተውኔት ሲሰራ አይተውት በሥራው በመደሰታቸው የትምህርት ዕድል ሰጥተውት ነበር። ከዚያም ወደ አሜሪካ አገር አቅንቶ ትያትር አጥንቶ ተመልሷል። "በኢትዮጵያ የኪነ ጥበባት ታሪክም የመጀመሪያው ባለዲግሪ ተዋናይ ተስፋዬ ገሰሰ ነው" ይላሉ አርቲስት ተስፋዬ። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በፊልሞች ላይ በርካታ ሥራዎችን ሲሰሩ እንደነበር በመጥቀስም "እርጅና እንኳን አልበገረውም። በጥበብ የተገዛ፣ በጥበብ የኖረ እና በጥበቡ መስዋዕትነት የከፈለ ሰው ነው" ይላሉ። አርቲስት ተስፋዬ፤ የተስፋዬ ገሰሰ የገፀ ባሕርይ አለዋወጥ፣ የሥነ ቃላት አጠቃቀማቸው ልዩ ነበር ይላሉ። "ዑመር ኻያምን ማንም እንደሱ አድርጎ አይተውነውም፤ ዑመር ኻያም ማን ነው? የሚለውን ብዙዎቻችን የምናውቀው በተስፋዬ ገሰሰ ነው" ሲሉም አድናቆታቸውን ይገልፃሉ። ይህንን ሃሳብ የሚጋሩት ብዙዎች ናቸው። ገጣሚና ፀሐፈ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ከተስፋዬ ገሰሰ ጋር የተዋወቁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳሉ ነበር። እርሳቸውም "የጥበብን ፍቅር 'ሀሁ' ብሎ ያስተማረኝ ተስፋዬ ነው" ይላሉ። የጥበብን ከፍታ ያዩትም ያኔ ተስፋዬ ገሰሰ በብሔራዊ ትያትር 'ሐምሌትን' ሲጫዎት እንደነበር ይናገራሉ። ይህም በሕይወት ዘመናቸው ትልቅ ተፅእኖ እንዳሳደረባቸው ተናግረዋል። ደራሲ እንዳለጌታ ከበደም የሕልፈታቸውን ዜና ከተሰማ በኋላ በፌስቡክ ገጹ ተስፋዬን " በባህርይውም በሥራውም ተለይቶ የወጣ ሰው ነበር፤ በሥራዎቹ መድረክ የቤተመቅደስ ያህል ክቡር እንደሆነ ኖሮ አሳይቶናል" ሲል ገልጿቸዋል። "አርቲስቶች ቋሚ ደመወዝ እንዲኖራቸው ያስፈቀድነው ከተስፋዬ ገሰሰ ጋር ሆነን ነው" ፀሐፈ ተውኔት አያልነህ ከተስፋዬ ገሰሰ ጋር በርካታ ሥራዎችን የሰሩት ተስፋዬ የብሔራዊ ቲያትር ቤት ዳሬክተር በነበሩነት ጊዜ ነበር። ከእነዚህ መካከል የአርቲስቶች የደመወዝ ጉዳይ ነበር። አቶ አያልነህ እንዳጫወቱን በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን አርቲስቶች ቋሚ ደመወዝ አልበራቸውም። በኮንትራት ክፍያ ነበር የሚሰሩት። "ይህን አሰራር ለመለወጥ ጥናት አጥንተን ለመንግሥት በማቅረብ፤ አርቲስቶቹ ቋሚ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ያስፈቀድነው ከተስፋዬ ገሰሰ ጋር ነበር" ይላሉ። የጥበብ ሥራዎችንም አብረው እንደሰሩ ይናገራሉ። ከእነዚህ መካከል በናይጀሪያ ሌጎስ የጥቁር አፍሪካ ፌስቲቫል ላይ የቀረበው 'ትግላችን' የተሰኘው ሙዚቃዊ ድራማ አንዱ ነበር። ይህ ድራማ በናይጄሪያ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ ተዘዋውሮ እንደታየ አቶ አያልነህ ይናገራሉ። ድራማው ኩባም ድረስ ተጋብዞ በወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ለዕይታ በቅቷል። በዚያም ድራማ ላይ በአያልነህ ተጽፎ ተስፋዬ ገሰሰና ሃይማኖት አለሙ የተሳተፉበት የ20 ደቂቃ 'ትንሳኤ ሰንደቅ አላማ' የሚል ውዝዋዜ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮት እንደነበር ያስታውሳሉ። በደርግ ዘመንም በብሔራዊ ትያትር የሚወጡት ሥራዎች የሚደነቁ እንደነበሩ አቶ አያልነህ አውስተዋል። " 'ሻጥር በየፈርጁ'፣ 'መንታ እናት' ፣ የጋዜጠኛ ነጋሽ ገብረ ማሪያም ሥራዎች 'የአዛውንቶች ክበብ'፣ 'ሀሁ በስድስት ወር'፣ 'የከርሞ ሰው' ፣ 'ጠያቂ እና ሌሎችም በሰው ሕሊናው ውስጥ የማይጠፉ ወጣቱን ትውልድ ሊቀርፁ የሚችሉ ሥራዎች ይወጡ የነበሩት ተስፋዬ ገሰሰ የትያትር ቤቱ ዳሬክተር ከሆኑ በኋላ ነው" ይላሉ። አቶ አያልነህ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ በትያትር ቤት የሚቀርቡት ትያትሮች ትርጉም ነበሩ በማለትም፤ ይህ የተቀየረው በተስፋዬ ጥረት እንደነበር ይመሰክራሉ። "ጋሽ ተስፋዬ ራሱን ሆኖ የኖረ ሰው ነው" በርካቶች የጥበቡ ሰው ተስፋዬ ገሰሰን የግል ባህርይ፤ "ግልፅ ፣ ተጨዋች፣ ያመነበትን የሚናገር፣ ለማንም የማያሸረግድ፣ ራሱን ሆኖ የኖረ ነው" ሲሉ ይገልጿቸዋል። አርቲስት ተስፋዬ አበበ "በጣም ልዩ ሰው ነው። በመድረኩም በውጭም አርቲስት ነው። ለፍንደቃ የተፈጠረ ሰው ነው። ምንም ነገር ቢሆን አይከፋውም። ሁሉንም ሰው አስደስቶ፣ አጫውቶ ማናገር ይፈልጋል። መድረክ ላይም ዳይሬክት የሚያደርገው ተዋንያንን ከገፀ ባህሪያቸው እንዳይወጡ እያሳሳቀ ነበር" በማለት ተናግረዋል። ፀሐፈ ተውኔት አያልነህ በበኩላቸው " በትወናውና በአስተዳደሩ እውነተኛ የአርቲስት መንፈስ የያዘ ነው። ቂም አያውቅም፤'ተጣልተናል' ሲባል እንኳን 'መቼ?' ብሎ የሚጠይቅ ሰው ነው። ቅን ልቦና ያለው ነው። ሕዝባዊ አመለካከት ያለው፣ የሕዝብ ወገን የሆነ ሰው ነበር" ብለዋል። ደራሲ እንዳለጌታም በፌስቡክ ገፁ እኝህን አንጋፋ የጥበብ ሰው በዘከረበት ፅሁፉ "ራሱን ሆኖ የኖረ ሰው" ሲል ገልጿቸዋል። አንዳንዴ ደግሞ እንግዳ በሆነ ተግባር ሲሳተፍ እንግዳ ነገር ሲያደርግ እናየዋለን ይላል። ለዚህም ከአብነቶቹ አንዱን ያነሳል። በአንድ ወቅት ከተስፋዬ ጋር ለጨዋታ ተገናኝተው ሦስት ድራፍት እንዳዘዙና እና አንዱ ለማን እንደሆነ በጠየቃቸው ጊዜ በሞት ለተለየው ወዳጁ ደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚያብሔር መሆኑን እንደገለፀለት በጽሁፉ አውስቷል። የአንጋፋው ደራሲና ተዋናይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
42562514
https://www.bbc.com/amharic/42562514
የእስረኞች መፈታትና የማዕከላዊ መዘጋት ውሳኔ አንድምታዎች
በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተከሰቱት ተቃውሞዎችን ተከትሎ ለውጦች ሊደረጉ ይችላል ተብሎ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ ቆይቷል። በተለይ ለሳምንታት የቆየው የገዢው ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ አዲስ ነገርን ይዞ ይመጣል ተብሎ ነበር።
የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መግለጫ ግን ጥቅል የሆኑ የመሻሻል እርምጃዎች ይወሰዳሉ ከማለት ያለፈ ነገር ስላልነበረው ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ነበር። በተከታይ ቀናት የጋራ መግለጫ ይሰጣሉ የተባሉት የኢህአዴግ አባል ፓርቲ መሪዎችም ከዛሬ ነገ እየተባለ፤ ረቡዕ ለተወሰኑ የመንግሥት መገናኛ ተቋማት በሰጡት መግለጫ ግን አዲስ ነገር ተሰምቷል። በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ከሌላው ጊዜ በተለየ ተከታታይ ፎቶግራፎችንና አነጋጋሪ የሆነውን ውሳኔ ለሕዝብ ሲያቀርቡ ነበር። በቀዳሚነት የተላለፈው ባለ ሃያ ቃላቱ መልዕክት "በአቃቢ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የመሚገኙ የተለያዩ ፖለቲከኞች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ ተወስኗል::" የሚል ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ቃላት እየተቀየሩና እየተጨመሩ ለሰባት ጊዜ ያህል ለውጥና መሻሻል ተደርጎበታል። ይህም በተለይ ፖለቲከኞችን በተመለከተ የሰፈሩት አገላለፆች ጥርጣሬን አጭሯል። ለሰባተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የቀረበው መልዕክትም 46 ቃላትን ይዞ "በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወይም ደግሞ ወንጀል በመፈፀም ድርጊት ተጠርጥረው በአቃቢ ህግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዲሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በምህረት ህግና ህገመንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ እንዲፈቱ ይደረጋል::" የሚል ነበር። እስካሁን ውሳኔው መቼ ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለፀ ነገር ባይኖርም በርካቶች ግን ትክክለኛ እርምጃ እንደሆነ እየገለፁ ነው። መልካም ጅምር በኪል ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ለሆኑት ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ የመግለጫው መንፈስ ጥሩና የሚያበረታታ ነው። ነገር ግን ለሁሉም የሕዝብ ጥያቄዎች መልስ እንደሆነ ሳይሆን መንግሥት ሊወስዳቸው ካሰባቸው እርምጃዎች መካከል እንደ አንድ ተደርጎ የሚወሰድ ከሆነ ጥሩ ዜና ነው ይላሉ። የመብቶች ተከራካሪ እና ጋዜጠኛ ለሆነው አቶ ጌታቸው ሽፈራው ደግሞ ኢህአዴግ የ17 ቀኑን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ መሰረታዊ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን ማለቱ ምን ሊወሰድ ይችል ይሆን የሚል ጥያቄ ፈጥሮበት ነበር ። "ምክንያቱም አብዛኛው ሰብአዊ መብቶች የሚመለከቱት እስረኞችን ነው። ያ ደግሞ መሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄ ስለሆነ አሁን ባሉት መልኩ አልጠበኩም።" አቶ ገብሩ አስራት እንደሚሉት መጀመሪያም የፖለቲካ እስረኛ የሚባል ነገር መኖር አልነበረበትም። ማንም በፖለቲካ አመለካከቱ ሊታሰር እንደማይገባ በማመልከትም ሕገ-መንግሥቱን ይጠቅሳሉ። "ስለዚህ እርምጃው ቀድሞም ፖለቲከኞች ላይ የተከፈተ ጥቃት ነው። ማዕከላዊም የዚህ ጥቃት አካልና መሳሪያም" ነው ብለዋል። ውሳኔውን እንደ አንድ አዎንታዊ እርምጃ ቢመለከቱትም የዘገየና ከብዙ ጥፋት በኋላ የተወሰደ መሆኑን ግን ይናገራሉ። ይህ ውሳኔ መልካም ጅምር ነው፤ የሚሉት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በቂ የሚባል ግን እንዳልሆነ ይናገራሉ። "ለዚህች ሃገር ሰላም የሚሆነው ኢህአዴግ አሁን ያለበትን ሁኔታ መልሶ አይቶ ከሕዝቡ ጋር ተወያይቶ የሽግግር መንግሥት መመስረት ሲችል ብቻ ነው'' ይላሉ። "ላለፉት 26 ዓመታት ብዙ ሕይወት ጠፍቷል፣ ደም ፈሷል፣ የሰዎች ኑሮ ተመሰቃቅሏል፣ በርካታ ሰዎች ሃገር ጥለው ተሰደዋል። ስለዚህ ይህን ጥያቄ ብቻ በመመለስ እርቅ ይፈጠራል ብለን አናምንም'' የሚሉት አቶ ሙላቱ የአሁኑ የመንግሥት ውሳኔ ሰላም ለማስፈን መልካም ጅምር በመሆኑ መቀጠል እንዳለበት ይጠቅሳሉ። መንግሥትን ለዚህ ያበቃው ምንድን ነው? ለዶ/ር አወል ኢህአዴግ የወሰደውን እርምጃ እንዲወስድ ያስገደደው፤ ''የነበረው ሕዝባዊ ጥያቄ በአባል ፓርቲዎች ላይ ያሳደረው ጫና እና ያም የፈጠረላቸው እድል ነው። ያንን ተጠቅመው እስከዛሬ ማድረግ ያልቻሉትን ነገር አሁን እያደረጉ ነው።'' "ሕዝቡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሳያቋርጥ ያደረገው ትግል ፍሬ ነው"ይላሉ። ለዶ/ር አወል የፖለቲካ እስረኞች መፈታት ትልቁ ጉዳይ ነው፤ ''ያለምንም ጥፋት ሕገ-መንግሥቱ የሚሰጣቸውን መብት ተጠቅመው ሕገ-መንግስቱ ይከበር ያሉ ሰዎችን መፍታት ከፍትህና የሕዝብ ጥያቄን ከመመለስ አንፃርም ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል'' ባይ ናቸው። "የሕዝብን ድምፅ እናሰማለን ብለው የቆሙ ሰዎችን ሕግን እና የሕግ-ሥርዓቱን ተጠቅሞ አስሯቸዋል። መንግሥት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶች አሰፍናለሁ ካለ መደራደርም ካለበት፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት ካለበት፣ ዲሞክራሲያዊ እሴቶች እንዲያድጉ እንዲበለፅጉ ማድረግ ካለበት የመጀመሪያ እርምጃ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት ነው።" አቶ ጌታቸው ደግሞ ውሳኔው ከህዝቡ ጫና ባሻገር ኢህአዴግ ካርዱን የመጨረሱ ውጤት ነው ይላሉ። "ከዚህ በፊት የሰንደቅ አላማ ቀን፣ ከዚያም የሚሌኒየም ክብረ በዓልን በመቀጠል ደግሞ አባይን በማንሳት የሕዝቡን ጥያቄ ለማዳፈን ሞክሯል። " አሁን ያለው እና ሕዝብ በቀዳሚነት የሚያነሳው ጥያቄ ደግሞ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ስለሆነ ''እፈታለሁ'' በማለት የፖለቲካ እስትንፋሱን ለማራዘም ይጠቀምበታል ሲሉ ይገልፃሉ። "ከበቀለ ገርባ፣ ከመረራ እስከ አንዳርጋቸው ፅጌ ድረስ ያሉት እዛው እስርቤት ውስጥ ነው። ስለዚህ ለእኔ ህዝቡ እነዚህ እስር ቤት ውስጥ ያሉ ግለሰቦችን ጥያቄ ነው ተቀብሎ ሲያሰማ ነበረው። አሁን ድምፁን የሚያሰማለት አካል ስለሌለ እሱ ራሱ አደባባይ ወጣ፤ ይህም ትልቅ ጫና ፈጠረ" ሲሉ ያስረዳሉ። ስለዚህ የእነዚህ ሰዎች መፈታት የታሰረውን ለውጥ መፍታትና የሌሎች ጥያቄዎችም መፈታት ስለሆነ ከነሱ መፈታት በኋላ ጥያቄው ይቀጥላል ሲሉ አፅንኦት ይሰጣሉ። ማዕከላዊ ለአቶ ጌታቸው ማዕከላዊ ከሕግ ውጭ ከ4 ወር በላይ ታስሮ በኋላም የእስር ቤቱን ኃላፊዎች ከሶ የወጣበት ቦታ ነው። ማዕከላዊንም ሲገልፀው "ሰማይ የሚናፈቅበት እስር ቤት ነው። እስረኛ 24 ሰዓት የማይከፈትለት፣ ፀሃይ ለ5 ወይም ለ10 ደቂቃ ብቻ የሚፈቀድበት፣ መፀዳጃ ቤት ጠዋት 11 እና ማታ 11 ሰዓት ብቻ የሚኬድበት ነው። በዚህ ላይ ድብደባው እና ሌሎች ማሰቃየቶችም አሉ።" ይላል። በማዕከላዊ ሰቆቃ የደረሰባቸው ከሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆኑነ ጋዴዎችና አርሶ አደሮች አሉ የሚሉት አቶ ጌታቸው በመግለጫው መሰረት የፖለቲካ እስረኞች ብቻ የሚፈቱ ከሆነ የእነዚህ ሰዎች እጣ ፈንታ ያሳስባቸዋል። "ጥፍራቸው የተነቀለና የተኮላሹ ሰዎች ፍርድ ቤት በደላቸውን ተናግረዋል። እነዚህ ሰዎች ደረጃውን ወደ ጠበቀ እስር ቤት ይዛወራሉ ከማለት፤ የተሰቃዩና ያለጥፋታቸው የታሰሩ ግለሰቦች መፈታት አለባቸው።" ኢህአዴግ ማዕከላዊን መዝጋት የነበረበት የዛሬ ሃያ አምስት ዓመት ነው የሚሉት አቶ ገብሩ የዘገየ ቢሆንም ውሳኔው አንድ እርምጃ ነው ይላሉ። ለዓመታት ፖለቲከኞችን እያሰሩ በአገሪቱ የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት የማይታሰብ ነገር መሆኑን ተቃዋሚዎች ሲወተውቱ መቆየታቸውንም የሚያስታውሱት አቶ ገብሩ፤ ኢህአዴግ ግን ላለፉት በርካታ አመታት ማዕከላዊን አስቀጥሎታል። የፖለቲካ እስረኞችን መፍታትና ማዕከላዊን መዝጋት በአገሪቱ ከሚነሱ አጠቃላይ የፖለቲካ ጥያቄዎች አንዱ መልስ ብቻ መሆኑም ሊተኮርበት እንደሚገባም አቶ ገብሩ ያሳስባሉ። ለአቶ ጌታቸው በሃገሪቱ ማዕከላዊ ብቻ አይደለም ማሰቃያ እና መመርመሪያ ሆኖ እያገለገለ ያለው። "በማረሚያ ቤት ቃጠሎ ተጠርጥረው የተከሰሱት ሰዎች የተመረመሩትና የተሰቃዩት ሸዋ ሮቢት ነው።" የሚሉት አቶ ጌታቸው በሃገሪቱ የተለያየ ስፍራ ያሉ እንዲህ አይነት ማሰቃያዎች በአጠቃላይ መዘጋት አለባቸው ይላሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ማህበራዊ ድረ-ገፅ ለዶ/ር አወል የፖለቲካ እስረኞች እነማናቸው የሚለውን የሚወስነው መንግሥት ነው። "አሳሪም ፈቺም እሱ ስለሆነ እዚያ ምደባ ውስጥ የሚወድቁትን ራሳቸው ናቸው የሚወስኑት። " የፖለቲካ እስረኛ ብያኔ ሰፊ ነው የሚሉት ዶ/ር አወል "የፖለቲከኛ እስረኛ የምንለው ፖለቲካዊ በሆኑ ጉዳዮች የሚሳተፍና መንግሥት ያንን ግለሰብ ከፖለቲካ ምህዳር ውጭ ለማድረግ የተከሰሰ እና የታሰረ እንደሆነ ነው። ከዚህ ተነስተን ታዲያ እኒህ ሰዎች ሁሉ ይፈታሉ የሚለውን በሂደት የምናየው ነው" ይላሉ። ዶ/ር አወል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የማህበራዊ ድረገፅ በተደጋጋሚ መታረም ከዚህ አንፃር ተግባራዊ ልዩነት የሚያመጣ አይመስላቸውም፤ ''ዋናው መለቀቃቸው ነው'' ይላሉ። ለአቶ ጌታቸው መንግሥት እስረኞች መኖራቸውን ማመኑ ጥሩ ቢሆንም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ገፅ ላይ የፖለቲካ እስረኞች ላለማለት ተደጋጋሚ ማስተካከያ መደረጉን በጥርጣሬ ይመለከተዋል። መጀመሪያ ይነገር የነበረው እና በኋላ ላይ የሰማነው የተለያየ መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ ነው ይላል። "በዚህ አገር የፀረ-ሽብር አዋጁ ራሱ አንዱ የፖለቲካ መሳሪያ ነው። ለኔ በዚህ አዋጅ የታሰሩ ሰዎች የፖለቲካ እስረኞች ናቸው።" ከ1500 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ እስረኞች አሉ የሚለው አቶ ጌታቸው፤ የመንግሥት መግለጫ ግን እነዚህን ሁሉ ያካትታል ብዬ አላስብም ሲል ያስረዳል። ይልቁንም ይህንን ጉዳይ ለማስተንፈሻ ይሆናል ብለው ከሚያወጧቸው ነገሮች መካከል እንደ አንዱ ነው የሚመለከተው። " ቃላቸውን ያከብራሉ ብዬ አላስብም" ይላል። ምን ይጠብቃሉ? ዶ/ር አወል ሕገ-መንግሥቱ ላይ የተቀመጡ ሰብአዊ መብቶች ይከበሩ፣ ፌደራላዊ ሥርዓቱ በትክክል ይስራ በማለታቸው ብቻ የታሰሩ ሰዎች የሚፈቱ ከሆነ ከአሁን በኋላ ሰዎች አመለካከታቸውን ስለገለፁ ብቻ መታሰራቸው ይቆማል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። አቶ ጌታቸው ደግሞ የፖለቲካ እስረኞች በአንዴ ይፈታሉ ብሎ አይጠብቅም። "ከዚህ በፊት ካለው ልምድም ስናይ ቀስ እያሉ ይፈቱ ይሆናል እንጂ፤ ጠንቅቆ የሚያቃቸውን የለውጥ ኃይሎች በአንዴ መፍታት የሚፈልጉ አይመስለኝም" ይላል። ዶ/ር አዎል ግን ከእስረኞቹ መፈታት በተጨማሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ፕሮግራማቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ ደጋፊዎቻቸውን የሚያደራጁበት፣ የመገናኛ ብዙሃን በነፃነት የሚሰሩበት፣ ፍርድ ቤቶች ያለምንም ጣልቃ ገብነት በነፃነት የሚዳኙበት፣ የመንግሥት ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ፓርላማ እና ምርጫ ቦርድ መስራት ያለባቸውን በአግባቡ የሚሰሩበት መንገድን ያበጃል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። አለምአቀፍ ተቋማት ምን አሉ? አምነስቲ ኢንተርናሽናል የእስረኞች መፈታትና የማዕከላዊ መዘጋት ዜና እንደተሰማ የኢትዮጵያ አጥኚውን ፍሰሃ ተክሌን ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ ''ዜናው የአስከፊው የጭቆና ዘመን ማብቃት ምልክት ሊሆን ይችላል። በፖለቲካዊ ምክንያቶችና በሃሰት በተቀነባበሩ ክሶች ዓመታትን በእስር ላሳለፉ እስረኞች ግን እጅጉን የዘገየ ነው'' ብሏል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ታሳሪዎቹን በመልቀቅ ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲያደርጉት እንጠይቃለን። በተጨማሪም መንግሥት የፀረ-ሽብር ሕጉን ጨምሮ ለእስሩ ምክንያት የሆኑትን ሌሎች ጨቋኝ ሕጎች እንዲሰርዝ ካልሆነም በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል አለበትም ብሏል። "የማዕከላዊ እስር ቤት መዘጋት እዚያ የተፈፀሙትን አሰቃቂ ድረጊቶች መሸፈኛ መሆን የለበትም። ማዕከላዊ ለዓመታት ሰላማዊ ተቃውሞን ባሰሙ ግለሰቦች፣ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ላይ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት አሰቃቂ ምርመራ የተካሄደበት የሰቆቃ ማዕከል ነው። ስለዚህም አዲስ የሰብዓዊ መብቶች መከበር ምዕራፍን መጀመር የሚቻለው ተፈፀሙ የተባሉት ሁሉም ሰቆቃዎችና የከፉ አያያዞች ምርመራ ተደርጎባቸው ፈፃሚዎቹ ለፍርድ ሲቀርቡ ብቻ ነው።'' የሚለው አምነስቲ ''የት እንደደረሱ ያልታወቁ ሰዎች እጣ ፈንታ ግልፅ ባልሆነበት ሁኔታ የተወሰኑ ሰላማዊ ተቃውሞ ያሰሙ እስረኞችን መልቀቅ ብቻውን በቂ አይደለም'' ብሏል። ''ምንም እንኳን መንግሥት ውሳኔውን እንዴትና መቼ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ባያሳውቅም ለረጅም ጊዜ የቆየውን ፖለቲካዊ ጭቆና ለማብቃት ወሳኝ እርምጃ ነው።'' ያለው ደግሞ ሂዩማን ራይትስ ዋች ነው። ማዕከላዊ ተዘግቶ ታሳሪዎቹ ወደሌላ ቦታ የሚዘዋወሩ ከሆነና ተመሳሳይ ስቃይ ሚገጥማቸው ከሆነ ውሳኔው ትርጉም የለሽ ይሆናል የሚለው ተቋሙ፤ መንግሥት በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ የደህንነት ሃላፊዎች እስረኞችን ማሰቃየት የተከለከለና የሚያስቀጣ መሆኑን መንገር አለበት። ሂውማን ራይትስ ዋች ጨምሮም መንግሥት በቀጣይ ሰላማዊ ተቃውሞን መፍቀድና ጨቋኝ ህጎችን በማሻሻል ተጨማሪ ለውጦችን በማድረግ ይኖርበታል ብሏል። በተመሳሳይም በዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት በማቆም ከውጪ የሚተላለፉ የሬዲዮና የቴሌቪዥን እንዲሁም የኢንተርኔ አገልግሎትን ማገዱን እንዲተው ሂውማን ራይትስ ዋች ጠይቋል። የፖለቲካ እስረኛ ማን ነው? ቁርጡ ያልታወቀው የታሳሪ ቤተሰቦች ጥበቃ
news-54078239
https://www.bbc.com/amharic/news-54078239
"ብልጽግናን የሚቀላቀሉ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ይኖራሉ" ነብዩ ስሁል
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ ወጥና ተቀባይነት የሌለው ነው ያለው በትግራይ ክልል የታቀደው ምርጫ ዛሬ እየተካሄደ ነው። አገሪቱን እየመራ የሚገኘው ፓርቲ ብልጽግና የትግራይ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል ምርጫው ሕጋዊ አይደለም ይላሉ።
አቶ ነብዩ በትግራይ ክልል ስለሚካሄደው ምርጫና ፓርቲያቸው በክልሉ ውስጥ ስላለው እንቅስቃሴ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ ዋዜማ ላይ ነን። ብዙ ሲባል ነበር፤ ሁሉን አልፎ እውን ሊሆን ነው። ትልቅ መነጋገሪያ ለመሆን በቅቷል። እናንተ ምርጫው ሕገ ወጥ ነው ብትሉም ለመካሄድ ጫፍ ላይ ደርሷል። ታዲያ በዚህ ወቅት ከሕዝባችሁ የመነጠል ስሜት አይሰማችሁም? ምርጫ እየተካሄደ አይደለም። ህወሓት እያካሄደ ያለው ምርጫ ሳይሆን እንዲሁ የዲሞክራሲ ልምምድ እያደረገ እንደሆነ ነው እኛ የምናየው፤ የምንገመግመው። ምክንያቱም አንድን እንቅስቃሴ ምርጫ ለማለት መስፈርቶች አሉ። ምርጫው ደግሞ እነዚያን መስፈርቶች አያማሏም። ከመሠረታዊ ነገር ስንጀምር ሕጋዊ አይደለም። ሕጋዊ ያልሆነው ደግሞ ሕገ መንግሥቱ ስለማይፈቅደው ነው። ሁለተኛ ደግሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ አለ። በተደጋጋሚ ነው ይሄንን ውሳኔ ያሳለፈው። ከቀናት በፊትም አጽድቆታል። ስለዚህ አንድ ምርጫ፤ ምርጫ እንዲባል የመጀመሪያው መስፈርቱ ሕጋዊ መሆኑ ነው። ስለዚህ ሕጋዊ ስላልሆነ ምርጫ ብለንም መጥራት የለብንም። በሌላ በኩል ምርጫ የይስሙላ ምርጫ ነው። ህወሓት አጀንዳ ስላጣ እያደረገው ያለው ቀቢጸ ተስፋዊ ሂደት ነው። ይሄ ደግሞ ምንም ዋጋ የለውም። አብዛኛዎቹን መስፈርቶች አላሟላም፣ የሕዝባችንም ፍላጎት አይደለም፣ እውነተኛ የምርጫ ሂደትን የተከተለና ተአማኒ አይደለም። ስለዚህ በዚህ መልኩ ስናየው ምርጫ ብለን መጥራት አንችልም። እኛ ህጋዊ ምርጫ እስከሚመጣ ድረስ እየጠበቅን ነው። ከሕዝባችን የመለየት ስሜት ፍጹም ሊሰማን አይችልም። ሕዝባችንም ሕጋዊ ምርጫ እየጠበቀ እንደሆነ ነው እኛ የምናውቀው። የትግራይ ሕዝብም ሕግ አክብሮ፣ ሐሳቦች በትክክል ተንሸራሽረው፣ እውነተኛ ምርጫ ተካሂዶ፣ በሕዝብ የተመረጠ ፓርቲ መንግሥት ሆኖ እንዲመራው ነው የሚፈልገው፤ ለዚህም ነው የታገለው። ከትግራይ ሕዝብ ታሪክም አንጻር ስናየው የትግራይ ፍላጎት ይሄ ነው እንጂ በጨረባ ምርጫ፣ የውሸት ምርጫ አድርጎ መንግሥት መሰየም አይፈልግም። ስለዚህ የመነጠል ስሜት አይሰማንም። የሕዝባችን ፍላጎት አይደለም የሚል ነገር አንስተዋል፤ እንደምናየው ከሆነ ሕዝቡ በንቃት ተሳትፎ እያደረገ ነው። ክርክሮች እየተካሄዱ ነው፤ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መነቃቃት አለ፡፡ እርስዎ ደግሞ የህዝባችን ፍላጎት አይደለም እያሉ ነው፡፡ መቼስ ሁለት የትግራይ ሕዝብ የለም፡፡ እና የሕዝባችን ፍላጎት አይደለም ሲሉ ምን ማለትዎ ነው፡፡ መለኪያችሁ ምንድነው? ሕዝቡ ተገደን ነው የምንመርጠው ሲል አልሰማነው'ኮ፡፡ እንግዲህ ስትጨቆን ተጨቁኛለሁ ለማለት እንኳን ነጻነት ያስፈልግሃል። የትግራይ ሕዝብ አይደለም በዚህ ደረጃ ወጥቶ ይሄ ምርጫ ሕጋዊ አይደለም ብሎ ለመውጣት ይቅርና ለመኖርም ለሕይወቱም እየሰጋ ያለበት ከፍተኛ አፈና ውስጥ ያለ ሕዝብ ነው። ስለዚህ ነጻነቱ ተረጋግጦለት የትግራይ ሕዝብ ምን እንደሚፈልግ ቢጠየቅ በትክክል ይሄንን ሊፈልገው አይችልም። ምክንያቱም የታገለለትና የኖረለት ዓላማ ይሄ አይደለም። የትግራይ ሕዝብ የታገለውና የኖረው ኢትዮጵያ የምትባል አገር ጸንታ እንድትኖር፣ በሕግና በሥርዓት እንዲተዳደር፣ ዴሞክራሲና ልማት እንዲጎናጸፍና ከኢትዮጵያዊ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ለመኖር ነው። ነገር ግን በዚህ መልኩ ተነጥሎ የጭቆና ገፈት እየቀመሰ፣ አገር ይበዘብዝና ይመዘምዝ የነበረ አንድ ቡድን መፈንጫ ሆኖ ባለበት ሁኔታ የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት እየተንጸባረቀ ነው ለማለት በጣም አስቸጋሪ ነው። ያየናቸው የፖለቲካ ክርክሮችም እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም። አብዛኛዎቹ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከህወሓት ጋር የጥገኝነት ግንኙነት ያላቸው፣ እንዲሁም አቅም ፈጥረው መገዳዳርና መወዳደር የማይችሉ፣ በቅርብ ጊዜ በደም ፍላትና በአንዳንድ ጊዜያዊ ቅሬታዎች የተፈጠሩ ናቸው። እናም ይሄ የትግራይ ሕዝብን የሚመጥን አይደለም። ያየኸው የሚዲያ ድራማ የትግራይን ሕዝብ ፍጹም የማይመጥን ነው። አብዛኞቹ ፓርቲዎች ያኮረፉ በጣም ጽንፈኛ ብሔርተኞች ናቸው። የትግራይ ሕዝብ ደግሞ እንዲህ አይነት ብሔርተኝነት አይፈልግም። የትግራይ ሕዝብ እራሱን አክብሮ ሌላውንም አክብሮ በትብብር መኖር እንጂ በዚህ መልኩ ከፈጠራት አገር ተነጥሎ መኖር አይሻም። ስለዚህ የታየው ነገር በሙሉ ከትግራይ ሕዝብ ታሪክና ፍላጎት አንጻር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ሕጋዊ ምርጫ ሲካሄድ የተሻለ እንቅስቃሴ፣ የተሻለ የዴሞክራሲ ምህዳር እንደሚፈጠር ምንም ጥርጥር የለውም። መቀሌ ቢሮ ከፍታችኋል ሲባል ነበር። በዋነኛነት የምትንቀሳቀሱትና ቢሯችሁ የሚገኘው ግን በአዲስ አበባ ነው። እርስዎ አሁን ስለ ሕዝቡ ስሜትና ፍላጎት ሲያወሩኝ ከፍ ባለ የእርግጠኝነት ስሜት ነው። የሕዝቡን ስሜት በዚያ ደረጃ ለማወቅ ቀረብ ማለት ያለባችሁ አይመስላችሁም? ለመሆኑ ወደ ምትወክሉት ሕዝብ የማትገቡት ለምንድነው? ስለሕዝብ እንዲህ በርቀት ሆኖ ማውራት ድፍረት አይሆንባችሁም? ሲጀመር እኛ ትግራይ ውስጥ አለን። ትግራይ ውስጥ በጣም ብዙ አመራሮች አሉን፤ ደጋፊዎችም አሉን፤ ቢሮዎችም አሉን። አንድ ሁለት ቢሮ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በላይ የሚሆኑ ብዙ ቢሮዎች አሉን። እኛ አሁን በሚፈለገው ደረጃ መንቀሳቀስ ያልፈለግነው ከኮቪድ ጋር ተያይዞ ነው። ይቅርታ ላቋርጥዎ፤ የሚጨበጥ የሚዳሰስ አድራሻና ቢሮ አላችሁ? እዚህ ቦታ እዚያ ቦታ ብለው ሊነግሩኝ ይችላሉ? አዎ አሉ፤ ምን መሰለህ። እና አሁን በሚፈለገው ደረጃ መንቀሳቀስ ያልቻልነው እንደነገርኩህ በኮቪድ ምክንያት ነው። እንዲህ ዓይነት ወረርሽኝ ባጋጠመበት ጊዜ እንደሚታሰበው እንቅስቃሴ አድርጎ አባላት ለመመልመል በምናስበው ደረጃ በሰፊው እንዳንሄድ እራሳችንን ገታ ያደረግነው ነገር ነው። ነገር ግን ብዙ አመራሮች መቀለ ውስጥ ናቸው። አመራሮቹ እንግዲህ አዲስ አበባ ለስልጠና ይመጣሉ፡፡ ከዚህም ወደዚያ ይሄዳሉ። ይቅርታ በድጋሚ ላቋርጥዎ፡፡ የሚሉኝ አመራሮች በኅቡዕ ነው የተሰማሩት? እንቅስቃሴያቸው የኅቡዕ ነው ወይስ በይፋ? ይንቀሳቀሳሉ ግን ምን መሰለህ። አባሎቻችን ብዙ እክል ይደርስባቸዋል ብዙ ተጽእኖ አለባቸው። ለመንቀሳቀስም ነጻነት ያስፈልጋል። በአጠቃላይ የስምሪቱ ጉዳይ የኛ ጉዳይ ነው። ሁለተኛ በምንፈልገው ደረጃ እየሄደ ነው ያለው። እክሎች ግን አሉ። ከህወሓት ጠብ አጫሪነት ጋ ተያይዞ፣ ግን በቂ ነው። ትግራይ ውስጥ ያለን እንቅስቃሴ በቂ የሚባል ነው። ለጊዜው አባሎቻችንና ቢሯቸው በደንብ እንዲታወቅ አንፈልግም። ምክንያቱም ብዙ አደጋዎች ሊደርሱ ስለሚችሉና ከጊዜ ወደጊዜም አንዳንድ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እየተፈጠሩ ስለሆነ፤ የአባሎቻችንና የአመራሮቻችን ደኅንነት ከመጠበቅ አንጻር ግልጽ እንዳይሆኑ የምንፈልጋቸው ነገሮች አሉ። ነገር ግን እንቅስቃሴያችን አሁንም በቂ ነው ብለን ነው የምናምነው። ትግራይ ውስጥ ያሉ አመራሮች አሉ በቂ እንቅስቃሴም እያደረጉ ነው። ሁለተኛ ነገር ደግሞ የትግራይ ሕዝብ ትግራይ ክልል ውስጥ ብቻ አይደለም የሚገኘው። አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ 1.5 ሚሊየን የሚሆኑ ትግራዋይ አሉ። በሌሎች አካባቢዎችም በርካታ የትግራይ ተወላጆች አሉ። ስለዚህም እናገናቸዋለን፣ አባላትን እንመለምላለን፣ በአጠቃላይ ፓርቲውን ስናየው ደግሞ ብልጽግና አገራዊ ፓርቲ ነው። ስለዚህ ለትግራይ ሕዝብ ብቻ አይደለም የምንታገለው። ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ነው የምንታገለው። ስለዚህ ሁሉም አገራችን ነው፤ ሁሉም ትግራዋይ ያለበት፣ ኢትዮጵያዊ ሀሉም የኢትዮጵያ ክፍል ይመለከተናል። በቀጥታ ከሚመለከተን የትግራይ ሕዝብም ጋር በቂ ተደራሽነት አለን። አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ደግሞ ያሉ መዋቅሮች ምን እንደሚመስሉና ያለውን የአባላት ብዛት በትክክለኛው ጊዜ ግልጽ የምናደርግ ይሆናል። ይቅርታ አቶ ነብዩ፣ ቀደም ሲል በትግራይ ክልል እንደልብ እንዳንንቀሳቀስ ያደረገን የኮቪድ-19 ወረርሽን ነው ብለው ነበር፤ ነገር ግን ኮቪድ-19 አዲስ አበባም አለ። እናንተ ደግሞ በአዲስ አበባ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጋችሁ ነው። ኮቪድ-19 ሁሉም ጋር ያለ ችግር ነው። አዲስ አበባ ኮቪድ የለም አላልኩህም። ሁሉም ጋር አለ፤ በመላው ዓለም አለ። እናም ወረርሽኙ የሚያሳድረው ተጽእኖ የታወቀ ነው። ትግራይ ውስጥ አንድ ልዩነት ላስቀምጥ፣ ለምሳሌ ወደ ክልሉ ለመግባት ወደ ለይቶ ማቆያ እንድትገባ ትደረጋለህ። ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ ቫይረሱን ለመቆጣጠር ሳይሆን ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር ነው። አዲስ አበባ ላይ ግን ከውጭ አገር ካልሆነ በስተቀር ከክልል የሚመጣ ሰው ለይቶ ማቆያ እንዲገባ አይደረግም። ነገር ግን ከየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ወደ ትግራይ ስትገባ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት አለ። ይሄ ሆን ተብሎ ጫና ለመፍጠር የሚደረግ ነው። ምንም እንኳን ወረርሽኙ በሁሉም ቦታ ያለ ቢሆንም በትግራይ ግን እንዲህ አይነት ለየት ያሉ ሁኔታዎች አሉ። ከዚህ በፊት በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ የህወሓት ከፍተኛ አባላት የብልጽግና ትግራይ አባላት ሆነዋል ብለው ተናግረው ነበር። እነማን እንደሆነ መግለጹ አደጋ ስለሆነ ነው ወይስ እንዲሁ ለፕሮፓጋንዳ የተጠቀማችሁት ነገር ነው? በይፋ ወጥተው የተቀላቀሉ አሉ፤ በየጊዜው ቃለ መጠይቅ ይደረግላቸዋል። ትከታተላቸዋለህ ብዬ አምናለው። ሌሎችም ያ ፍላጎት ያላቸው፤ በግልጽ አባል መሆን እንደሚፈልጉ የሚገልጹ ብዙ የህወሓት አመራሮችና አባላት አሉ። እኛንም ኮሚኒኬት እያደረጉን ያሉ አባላት አሉ። እነዚህ በከፍተኛ የህወሓት አመራርነት ላይ ያሉ ናቸው? አዎ አሁንም ያሉና ወደእኛ መምጣት የሚፈልጉ፣ ፍላጎት ያላቸው አሉ። ምክንያቱም ታውቀዋለህ በህወሓት ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት በሚል ተጨምድዶ የተያዘ ብዙ ለውጥ የሚፈልግ ካድሬ አለ። ምናልባት የዴሞክራሲ ባህል ቢመጣ ፓርቲው ውስጥ ስንት ሰው የተለየ ሀሳብ ሊያራምድ እንደሚችልና ወደ ብልጽግና ሊሄድ እንደሚችል፤ ሌላው ቢቀር ድርጅቱን ለቆ የራሱን ሕይወት መኖር የሚፈልግ ምን ያህል እንደሆነ መገመት ይቻላል። ፓርቲው ውስጥ አምባገነንነት ስላለ ካድሬው ፍላጎቱን እንዳይገልጽ እንደሚደረግ ለሁላችንም ግልጽ ነው። እናም ይህንን ስንል ፕሮፓጋንዳ አይደለም፤ በተጨባጭ ብዙ የተቀላቀሉን አሉ። አሁን በቀጣይነትም እንደውም በቅርቡ ቃለ መጠይቅ በመስጠት ወደ ብልጽግና መቀላቀላቸውን በይፋ የሚገልጹ ከፍተኛ አመራሮችም አሉ። ከፍተኛ ሲሉ አቶ ነብዩ በማዕካዊ ኮሚቴ ደረጃ እንደዚያ ማለትዎ ነው? አዎ። ከላይ ጫፍ ላይ ካሉትም ሊሆን ይችላል። ይሄ ትልቅ ዜና ነው የሚሆነው መቼስ… አዎ! ብልጽግናን መቀላቀል የሚፈልጉና የሚቀላቀሉ በቅርቡ ይኖራሉ። እንዳልኩህ ህወሓት ውስጥ ትንሽ የዲሞክራሲ ቅንጣት ቢኖር ብዙ ነገር ይታይ ነበር። ነገር ግን እንደደምታውቀው ህወሓት የአፈና የሴራ ሥርዓት ነው። ብዙ አመራሮች ብዙ አመራሮች ከድርጅቱ እንዳይወጡ ጫና እንደሚደረግባቸው አንዲሁም እስከመታገትና ወደሌላ እንዳያማትሩ በቤተሰብ ማስፈራራትን የመሳሰሉ በጣም ብዙ ጫናዎች በማድረግ ነው እንጂ አመራሩን ተቆጣጥረው የያዙት፤ ዴሞክራሲ ቢኖር ምናልባት ህወሓት ፈርሶ ሊያድር የሚችል ፓርቲ ነው። አቶ ነብዩ እርስዎ ላይ ግን በቀጥታም ሆነ በቤተሰብዎ ላይ የደረሰ ዛቻ ወይንም ማስፈራራት አጋጥምዎት ያውቃል? እኔ ጣጣዬን ጨርሼ መጥቻለሁ። ከዚህ በፊት የግራስሩት እንቅስቃሴ ስለነበረ እዚያ ላይ ብዙ ወከባዎች፣ እስር፣ እንግልትና እስከ 18 ዓመት የሚያስቀጣ ክስ አሁንም ድረስ አለ። እኔ ያው በዚያ እንቅስቃሴ በመቀሌና በዙሪያዋ ሁለት ዓመት ሙሉ እንቅስቃሴ ነበረ እና እዚያ ብዙ ነገር እኔ ላይ ነው የደረሰው። ቤተሰቤ ላይ የደረስ ብዙም ነገር የለም። እንቅስቃሴውም ጠንከር ያለ ስለነበረ ፈትነውም እንደማያሸንፉ ስለሚያውቁ ነገርየው ብዙም አልተለጠጠም። ነገር ግን አንዳንድ ተጽእኖዎች ይኖራሉ። ሌላው ቢቀር የሥነልቦና ተጽእኖ ይኖራል ቤተሰብ ላይ። እኔ ላይም ብዙ ነገር ደርሷል። እስከመደብደብ ደርሻለው፤ ታስሬ ወጥቻለው፤ ክስም አለብኝ። እሱ በሚዲያም ይታወቃል። እሱን ማለቴ አልነበረም አቶ ነብዩ፤ ወደዚህ ወደ ብልጽግና ከመጡ ወዲህ ማለቴ ነው። የትለየ ነገር አለ? ወደ ብልጽግና ከመጣሁ በኋላ ብዙም አይደለም ጫናው። ይመስለኛል ተስፋ ቆርጠዋል። መግቢያም ስላጡበት፣ የእኔን አያያዝም፣ የእኔን የትግል ስልትም ስለሚያውቁት ነገርየውን ለመንካት የደፈሩ አይመስለኝም። ሌላው ጋ በጣም ብዙ ጫና ይደርሳል፤ እኔ ጋ ግን እስከዚህም አይደለም። ወይም ደግሞ ለተራ ትንኮሳ እኔን የሚፈልጉኝም አይመስለኝም። ምናልባት ከዚያ በላይ ሌላ ኮንስፓይረሲ ሊኖራቸው ስለሚችል መነካካት አልፈለጉ ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም ይሄ ትግል ነው። የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲከበር ነው እየሰራን ያለነው። ይሄ ደግሞ ቅዱስ አላማ ነው። ይዘነው የተነሳነው ዓላማ ትልቅ ስለሆነም ነው ምንም ማድረግ ያልቻሉት። ሕዝብም ስለሚያየው፣ ብዙ ደጋፊም ስላለው ምንም ማድረግ ስላልቻሉ ይመስለኛል…። ይህ ማለት አንዳንድ ጫናዎች የሉም ማለት አይደለም። እኔ ጋ ጎልቶ የወጡ ነገርኦች ግን ለጊዜው የሉም። ጎልተው የወጡ ጫናዎች ከሌሉ ታዲያ አቶ ነብዩ፤ መቼ ነው ወደ ትግራይ የሚሄዱት? መቼ ነበር ለመጨረሻ ጊዜስ ትግራይ የነበሩት? ያው ቀኑን የመወሰኑ ሥራ የእኛ ነው። የግድ ለሚዲያ መናገር ግዴታም የለብንም፤ ትክክልም አይደለም። ምክንያቱም የደኅንነት ጉዳይም አለበት። ትልቅ የሰኪዩሪቲ ጉዳይ ነው። ከአምባገነን ጋር ነው እየታገልን ያለነው እና በዚህ ሰዓት እንዲህ እናደርጋለን እያልን ሚዲያ ላይ መረጃ መስጠት አይጠበቅብንም። ዞሮ ዞሮ ግን ሥራ ላይ ነን ያለነው። አዲስ አበባ ላይ አለህ ማለት ሥራ እየሰራህ አይደለም ማለት አይደለም። ትግራይ ተግባራዊ ሥራ የሚሰሩ የዘርፍ አመራሮች አሉ። እኛም የምንሰራውን እዚህ ሆነን እንሰራለን። አስፈላጊ ሆኖ ባገኘነው ጊዜ ደግሞ በይፋ ወደዚያ እንንቀሳቀሳለን። እዚያ ቤዝ እናደርጋለን። ይሄ ማለት ግን እስካሁን ሥራ እየተሰራ አልነበረም ማለት አይደለም። ከበቂ በላይ ሥራ እየተሰራ ነው። እንዲያውም እኔ እዚህ መቆየቴ በጣም ብዙ ጥቅሞች ነበሩት። እንቅስቃሴ በቦታው ላይ ከመገኘት አንጻር ብቻ መያያዝ የለበትም። አሁን የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዘመን ነው። እንዳይሄዱ የሚያደርግዎ ግን ምንድነው፤ ስጋት ነው፤ አይደለም እንዴ? ስጋት አይደለም። ስጋት ሳይሆን ስትራቴጂና የአስፈላጊነት ደረጃ ነው። አሁን ስለሄድክ ያቀድከውን ነገር ታሳካለህ ማለት አይደለም። የተፈጠረውን የፖለቲካ ድባብ [ክላይሜት] ታውቀዋለህ። ሕዝባችንም እንዲሰጋ አንፈልግም። እኛ ከሄድን ብዙ ሥራ መስራት ስለምንጀምር በተለይ ሕዝቡንም በብዙ ስጋት መወጠር ነው የሚሆነው። ይደርሳል። ሁሉም ነገር ይደርሳል። የትግሉ ሙሉ ቁመናም ጊዜውን ጠብቆ ይደርሳል። ድሉም ይደርሳል። ሁሉም ነገር እጃችን ውስጥ ነው ያለው። ሕዝባችንም እንዳይጎዳ ማሰብ ስላለብን ነው…። ነገሮችን ካከረርናቸው ዞሮ ዞሮ ሕዝብ ነው የሚጎዳው። ለሕዝብ አስበን ነው እንጂ ሰግተን አይደለም የምለው ለዚህ ነው። የፌደሬሽን ምክር ቤት ምርጫውን ሕገወጥ ነው ብሎታል እናም ማዕከላዊው መንግሥት ምን ዓይነት እርምጃ እንደሚወስድ ብዙዎች የሚጠብቁት ነው። ለመሆኑ መንግሥት ሊወሰዱ ስለሚችሉ ቀጣይ እርምጃዎች የትግራይ ብልጽግናን ያማከረው ነገር አለ? ያቀረባችሁትስ አማራጭ አለ? በመጀመሪያ ብልጽግና አንድ ወጥ አገራዊ ፓርቲ ነው። ስለዚህ በፓርቲያችን በተለይ በቀጥታ ከትግራይ ህዝብ ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ የእኛ ሐሳብና ምክር ብዙ ነው ማለት ይቻላል፤ እንደውም እኛ ነን የምንመራው። ፓርቲና መንግሥት የሚለያዩት መስመር እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። የግድ ሁሉን ነገር እኛ እንወስናለን ማለት አይደለም። የፌደሬሽን ምክር ቤት የራሱ የሆነ አሰራር አለው፤ የራሱ የሆነ ቁመናም አለው። በዚያ ደረጃም መንግሥትና ፓርቲ ተከባብረን ነው የምንሰራው። ስለዚህ ጉዳዩ በዋነኛነት የፌደሬሽን ምክር ቤት ነው። የእኛ ሐሳብም በተለያየ መልኩና መንገድ ይጠየቃል። በተለያየ ውይይት ይነሳል። ሁሌም ሐሳባችን እየተዋሀደ ሄዶ ነው ወደ ውሳኔ የሚደርሰው። ጦርነት አያስፈግም፤ ለሕዝባችንም ሰላም፣ ጤንነትና ብልጽግና እንጂ ጦርነት ልናሰማው፤ አሁንም ወደ መሰዋዕትነት ልናስገባው አያስፈልግም። የእርስ በርስ ጦርነት ደግሞ ድሮ ያበቃለት ነገር ነው መሆን ያለበት እንጂ አሁንም ኢትዮጵያውያን እርስ በራሳችን የምንዋጋበት ምንም ምክንያትም የለንም። እንደ ብልጽግናም፤ አይደለም ጦርነት ተብሎ የሚገለጽ ይቅርና ተራ ግጭት እንኳን አስፈላጊ አይደለም ብለን ነው የምናምነው። በተለይ ደግሞ ለትግራይ ሕዝብ ጦርነት ወይም ግጭት እንዲገጥመው አንፈልግም። የትግራይ ሕዝብም ለነጻነት የታገለው ከመሰዋዕትነት ወደ መሰዋዕትነት እየተገላበጠ ለመኖር አይደለም። ፓርቲያችንም በሰላም፣ በአንድነት፣ የተሻለና አካታች የሆነ ሥርዓት ተፈጥሮ እንዲኖር ነው የሚፈልገው። የፌደሬሽን ምክር ቤትም የወሰነው ውሳኔ ተቋሙን የሚመጥን፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ወኪልነቱን የሚያረጋግጥ፣ በጣም የበሰለና የሰከነ ሰላማዊ ነው። ምናልባት ሰዎች የጠበቁት ሌላ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ምክር ቤቱ መወሰን ያለበትን ነገር ወስኗል። ከዚያ በኋላ ግን ሲተነተን ምን ሊሆን እንደሚችል አስፈጻሚው አካል ምን እንደሚወስን፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደግሞ ምን አይነት ውሳኔ እንደሚወስን አብረን የምናየው ይሆናል። በእናንተ በኩል ለሕዝባችን ይሄ ቢሆን፣ በህወሓት ላይ ይሄ ቢደረግ ብላችሁ ያቀረባችሁት ምክረ ሐሳብ ግን የለም? አኛም ብንሆን ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት ነው ያሰመርነው። ነግር ግን ሰላም አንድ ወገን ስለፈለገው ብቻ ላይሳካ ይችላል። የማይሳካ ከሆነ በኋላ አይተን፣ ተወያይተን የምንወስነው ነገር ነው የሚሆነው። ዞሮ ዞሮ ግን ሰላምና ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ውሳኔ መወሰን አለበት ብለን ነው የምናምነው። እንግዲህ ነገሮች በጣም እየከፉ የሚሄዱ ከሆነ ከዚህ በላይ እያየን ደግሞ ተገቢ የሆነ ሕጋዊ የሆነ ውሳኔ እየተወሰነ ነው የሚሄደው፤ እሱን ሁላችንም አብረን የምናየው ይሆናል።
44654343
https://www.bbc.com/amharic/44654343
የሶፊያ ንብረት የሆነ አንድ ሻንጣ ጠፋ
በጀርመን በርሊን ኤክስፖ ቆይታ ያደረገችው ሮቦት ሶፊያ ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ብትደርስም በፍራንክፈርት የአውሮፕላን ማረፊያ የተወሰነ ክፍሏን የያዘው ሻንጣ መጥፋቱ ታውቋል።
ይህም በእርሷ ላይ የተወሰነ ጉድለት የሚፈጥር ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አይኮግ ላብስ የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ባለሙያዎች ለማስተካከልና የጠፋውን ለመተካት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ እንደሆነ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሶፊያ ከአብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች ለደኅንነትና ግርግርን ለማስወገድ በሚል ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ያደረጉላት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ብቻ ነበሩም ተብሏል። ቀደም ባለው መርሀ ግብር በአቀባበሉ ላይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንደሚገተኙ ተነግሮ ነበር። ዛሬ ቀትር ላይ 'ከድንቅነሽ እስከ ሶፊያ' በሚል ርዕስ በብሔራዊ ሙዚየም የሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እየሄዱ እንደሆነ ሚኒስትሩ ከደቂቃዎች በፊት ለቢቢሲ በስልክ ተናግረዋል። የአይኮግ ላብስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት አሰፋ በበኩላቸው ሻንጣው በጀርመን ፍራንክፈርት የአውሮፕላን ማረፊያ እንዸጠፋ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎቹ የጎደለውን ለመሙላት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
44530484
https://www.bbc.com/amharic/44530484
1 ቢሊየን ዶላሩ ስንት ችግር ያስታግሳል?
በእዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ውስጥ የጀበና ቡና እፉት እያሉ የሚያወጉ የኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ መሪዎችን ምስል የተመለከተ አንዳች መልካም ድባብ በመሪዎቹ መካከል እንዳቆጠቆጠ ይገምታል፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የተባባሩት አረብ ኤምሬትስ ልዑል ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ቆይታ በሰናይ ውጤት ለመደመደሙ የተሻለ ፍንጭ የሚሰጠን ግን ከኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ሺዴ በኩል የተሰጠው የድህረ - ምክክር መግለጫ ነው፡፡ የተባባሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢትዮጵያ የ3 ቢሊየን ዶላር እርዳታ እና መዋዕለ-ንዋይ ድጋፍ ለማድረግ ፈቅዳለች፡፡ ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊየን ዶላሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ እንደሚደረግ እና ሀገሪቱ የገባችበትን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማረጋጋት አንደሚውል የመንግስት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አህመድ ሺዴ ለውጭ ሀገራት የዜና አውታሮች አስታውቀዋል፡፡ የችግሩ ግዝፈትና የተባባሩት ዓረብ ኤምሬትስ ችሮታ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያዋ ከዕለት ተዕለት እየመነመነ በመምጣቱ መሠረታዊ እና አንገብጋቢ ግብዓቶችን ከውጭ ሀገራት ለማስገባት ለቸገራት ኢትዮጵያ፣ የተባባሩት ዓረብ ኤምሬትስ ሰሞነኛ "ደራሽነት" የተወሰነ እፎይታን እንደሚሰጥ ይታመናል፡፡ ለምጣኔ ሃብት ጉዳዮች ተንታኙና የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረባ አቶ ዘሪሁን ተስፋዬ የተገኘው ገቢ በቋፍ ላይ ላለው ምጣኔ ሃብታችን ማስታገሻ ነው፤ ‹‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከወር ብዙም ላልተሻገረ ጊዜ ብቻ ከውጭ ሀገራት ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ ሸቀጦችን መግዣ ተቀማጭ እንዳላት ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ የአሁኑ ገንዘብ ለዘላቂነት ከሙሉ ችግሯ ሙሉ በሙሉ እንደማያወጣት የሚናገረው አቶ ዘሪሁን "መድኃኒትን የመሳሰሉ እጅግ አስፈላጊ ሸቀጦችን ለማስገባት አቅም ይሆናታል፤ እንደ ጥቃቅን ወጪዎች መሸፈኛ ወይንም ማነቃቂያ ብናየው ይሻላል›› ይላል ፡፡ በርግጥም ባሳለፍነው ጥር ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ይፋ ባደረገው ሪፖርት በ2016/17 የበጀት ዓመት ማብቂያ ኢትዮጵያ የነበራት የውጭ ምንዛሬ ተቀማጭ 3.2 ቢሊየን ነበር፡፡ የአሁኑ የኤመሬቶች ድጋፍ እና የመዋዕለ-ንዋይ ድጋፍ ተጠቃሎ ሲገባ ተቀማጩን በእጥፍ ያሳድጋል፡፡ የምጣኔ ሐብት ጉዳዮች ተንታኝና አጥኚ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ ከአቶ ዘሪሁን ጋር የሚስማማ ምልከታ አላቸው፡፡ በአሁኑ ገንዘብ የተወሰኑ ወራት የገበያ ዕድሜ መግዛት ይቻል ይሆናል ፤ሆኖም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚን መታደግ የሚቻለው ለሁለት አበይት ችግሮች መፍትሄ ሲገኝ እንደሆነ ይዘረዝራሉ፡፡ በዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ምልከታ፣ የሀገሪቱ የተሳሳተ የፋይናንስ ሥርዓትና አመራር ሀገሪቱን ለምጣኔ ሀብታዊ አጣብቂኝ ካበቁ ምክንያች አንዱ ነው፡፡ የፋይናንስ አስተዳደሩ በአጠቃላይ የተያዘው በብሔራዊ ባንክ ነው የሚሉት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፣ "ለዓመታት ማሻሻያ ባልተደረገለት ሥርዓት ውስጥ የውጪ ባንኮች ተቀማጭ ይዘው የሚገቡበት ዕድል የለም፡፡በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ ስትጠቀምበት የነበረው (ዶላር) ከዲያስፖራው (ሀዋላ)እና ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በብድር የተገኘ ነበር" በማለት ያስገነዝባሉ፡፡ የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ቤት ገብተው እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ፣ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ "በነፃ ሀገራቸውን ለማገልገል ፈቃደኛ እስከ መሆን ፍላጎት ያላቸውን" ውጤታማ ኢትዮጵያዊ የምጣኔ ሀብት ሊቆችን አስተባብሮ አዲስ እና የተሻለ የፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ማስተዋወቅ መፍትሔ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ ቁጥራቸው የበዙት ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ከሚፈጁት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ አንጻር ሌላኛ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፈተና መሆናቸውን ተንታኙ በሁለተኛ ችግርነት ያነሳሉ፡፡ የአንዳንዶቹ ግንባታ መልካም መሆኑን የሚጠቅሱት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ የብዙ ግንባታዎች ክንውን ግን የብክነት ምንጭ ስለመሆኑ ፣ይሄም በተራው ሀገሪቱ የነበራትን የዶላር ክምችት አሟጣ እንድትጠቀም እንዳስገደዳት ሲያስረዱ "ለምሳሌ 11 የስኳር ፋብሪካዎች ይሰራሉ ተብሎ ነበር"ይላሉ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ። በቢሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ ፈስሶባቸው የውሃ ሽታ ሆነው የቀሩ ‹ፕሮጀክቶችን› እያስታወሱ፣ "እነዚህ ግንባታዎች አልተሳኩም፡፡ በእነዚህ ግንባታዎች ላይ የሚወጣው ገንዘብ ካለ ውጤት በደፈናው የሚፈስ ከሆነ ቢቆሙ ይሻላል፡፡ እንዲያው ቀደም ብሎ ነበር ይሄ ርምጃ መወሰድ ያለበት፡፡ በተመሳሳይ ውጤት ያላሳዩ የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታን ጋብ ማድረግ ያስፈልጋል" ይላሉ። የፋይናንስ አስተዳደሩን የሚመሩት ሰዎች ብቃት ሌላው ቁልፍ ነጥብ ነው። የፋይናንስ ተቆጣጣሪ አካል ውስጥ ብቃት ያላቸው ዜጎችን ማሳተፍ ያሻል ይላሉ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ። "ብዙ ብቁ ዜጎች አሉን። አምስት ኢትዮጵያዊያን የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ጸሐፊ ናቸው። የአይኤምኤፍ የአፍሪካ ዳይሬክተር ኢትዮጵያዊ ናቸው። አሜሪካ አገር ትልልቅ ኮርፖቴሽኖችን የሚመሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ለአንድ ዓመት ለሁለት ዓመት አገራችን ያለ ደመወዝ እንኳ ሥሩ ቢባሉ ደስ የሚላቸው ናቸው።" የመዋዕለ-ንዋይ ድጋፍ እና የሰጥቶ መቀበል ጥያቄ አቶ ዘሪሁን ኢትዮጵያ ከሰሞኑ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ያገኘችውን መዋዕለ-ንዋይ ድጋፍ የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ተቋም ዛሬ በኢኮኖሚ ለበረቱ የትናንት ታዳጊ ሀገራት ከጥቂት ዐስርት ዓመታት በፊት ሲያደርጉ እንደነበረ ያወሳል። "የልማት ብድር ተደረገ የሚባለው ተቋማት ወይንም ሀገራት ለአንድ የተወሰነ ጉዳይ አሊያም የልማት ሥራ አንደኛው ለሌላኛው ወገን ከገበያ ምጣኔ በወረደ ወለድ ሲያቀርቡ ነው፡፡" ይላል። በተለይ በአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ እና 80ዎቹ ህንድና ቻይናን ለመሰሉ የእስያ ሀገራት፤ ከ1990ዎቹ ወዲህ ደግሞ የአፍሪካ ሀገራትን ምጣኔ ሃብት ለማበረታት በሥራ እንደዋለ የሚጠቅሰው አቶ ዘሪሁን ይሄ ብድር ከሌሎች ብድሮች ለየት ባለ መልኩ ለሀገራት የሚሠጠውን አንጻራዊ እፎይታ ያነሳል፡፡ ሆኖም ብድር በተፈጥሮው በሀገራት ላይ ከሚተወው የወለድ እና ፖለቲካዊ ጫና ጋር ተያይዞ አሁንም ፍቱን አማራጭ እንዳልሆነ ያስረግጣል፡፡ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት ለኢትዮጵያ በሰጠችው ብድር እና ድጋፍ ምትክ በሰጥቶ መቀበል ብሂል ልትጠይቃቸው በምትችላቸው ጉዳዮች ላይም አቶ ዘሪሁን መላምቶችን ያጋራል። የምጣኔ ሃብት እና ፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ በወዳጅነት ብቻ የሚደረግ ምንም ነገር የለም የሚለው አቶ ዘሪሁን፣ "የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በአፍሪቃ ቀንድ ቀጠና እና በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ተደማጭነትን መፍጠር ትፈልጋለች፡፡ ተጽዕኖዋን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያላት ፍላጎት ባለፉት ዓመታት ታይቷል፡፡" ይላል። የኢትዮጵያ መንግስት ይሄንን ብድር በምን ሁኔታ እንደወሰደ ዝርዝር ማብራሪያዎች ባይሰጡም በደግነት እንዳልሆነ ግን ያስረግጣል። ኢትዮጵያ በጊዜያት ውስጥ የየተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቋም እንድትደግፍ ልትጠየቅ እንደምትችል ግምቱን ያስቀምጣል፡፡ በዳረጎትና በብድር እስከመቼ? የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ኢትዮጵያ በብድር እና ችሮታ ከገባችበት የኢኮኖሚ አጣብቂኝ ለዘለቄታው መውጣት እንደማትችል ያስረግጣሉ፡፡ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ አሁን በሀገሪቱ የተጀመሩ አንዳንድ እርምጃዎች ቀስ በቀስ ሀገርን አትራፊ እንደሚያደርጉ ዕምነት አላቸው፡፡ ከእነዚህ ርምጃዎች በመንግሥት እጅ ሥር ያሉ ንግድ ተቋማት ወደ ግል ባለሀብቶች የማዘዋወር ጅማሬ አንዱ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ "ይሄ እርምጃ ለግንባታዎች የሚሆን በቂ ገንዘብ በማስገኘት፣ በራሳቸው በድርጅቶቹ ውስጥ የተሻለ ትርፋማነት እና የሥራ ውጤታማነት ያስገኛል" ሲሉ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ አቶ ዘሪሁን በበኩሉ ኢትዮጵያ በነባር ዕዳ ላይ ዕዳን ከማከል ታቅባ የፖለቲካ ተሰሚነቷን በማሳደግ በተለያዩ የምዕራብ እና ሩቅ ምሥራቅ ሀገራት መዝገብ ላይ የሰፈረ ውዝፍ ዕዳዋን ለማሰረዝ ጥረት ብታደርግ ይመርጣል፡፡ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በበኩላቸው "ኢትዮጵያ ከፍተኛ የእርሻ መሬት አላት። ወደ 72 ሚሊዮን ሄክታር የሚታረስ መሬት አላት። ወንዞቻችን ወደ 122 ቢሊየን ኩዩቢክ ሊትር ዉሃ ይዘው ነው የሚወጡት። እኛ ይሄን ይዘን አርሰን ማምረት አልተሳካልንም። ቢሳካልን ኑሮ የገቢ ወጪ የንግድ ሚዛኑም ይስተካከል ነበር።"ይላሉ። ከእነዚህ የመፍትሄ ሀሳቦች በተጨማሪ ግን ኢትዮጵያ በገፍ ከውጭ ሀገራት ሸቀጦችን ከማስገባት ድና ምርቶቿን በከፍተኛ መጠን ለሌሎች ሀገራት መሸጥ የምትጀምርበትን፣ የወጪ እና ገቢ ንግዶች የሚመጣጠኑበት መላ እንዲበጅ የኢኮኖሚ ልሂቃኑ ይመክራሉ፡፡ አነሰም በዛም ዕዳም ሆነ ችሮታ እንደየ ሁኔታው ወደ ዜጎች የሚሻገር የተዋረድ ጫና አለውና፡፡
news-53935478
https://www.bbc.com/amharic/news-53935478
ኮሮናቫይረስ ፡ ልጆቻችንን ትምህርት ቤት ባንልካቸውስ?
እስኪ ስለ ተማሪዎች ከማውራታችን በፊት ስለ አስተማሪዎች በአጭሩ እናውራ።
መምህራን ከሌላው በላቀ ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ ናቸው? አጭሩ መልስ 'አይደሉም' ነው። ይህንን በተመለከተ የእንግሊዝ የኅብረተሰብ ጤና ማዕከል ጥናት አድርጎ ነበር። ድምዳሜው አንድ አዲስ ነገር አለው። መምህራን ከትምህርት ቤት ውጭ ወይም ከባልደረቦቻቸው በሚያደርጉት መስተጋብር እንጂ ከትንንሽ ተማሪዎቻቸው ጋር አብሮ በመሆን ቫይረሱን የመቀበል እድላቸው እጅግ አነስተኛ ነው። በአጭሩ መምህራን ከልጆች ጋር እየዋልኩ ቫይረሱ ያዘኝ ቢሉ አይታመኑም። እናም ጥናቱ በመጨረሻ መምህራንን ምን ይመክራል መሰላችሁ፤ ልጆች በቫይረሱ ይለክፉኛል ከምትሉ ይልቅ ራሳችሁን ከሌሎች ጠብቁ፤ ለምሳሌ ከባልደረቦቻችሁ። ጥናቱ ዝም ብሎ ወደዚህ ድምዳሜ አልመጣም። ትንንሽ ልጆች በኮቪድ-19 የመያዝ፣ ተይዞ የመታመም እድላቸው በጣም አነስተኛ መሆኑ ስለተደረሰበት እንጂ። አንዲት የመዋዕለ ሕጻናት መምህርት ከምታስተምራቸው ልጆች ቫይረሱ ሊይዛት የሚችለው በስንትና ስንት እጥፍ ከመምህራን ቢሮ፣ ወይም ከትምህርት ቤቱ ኮሪደር ወይም ወደ ትምህርት ቤት ከመጣችበት አውቶቡስ ሊይዛት የሚችልበት እድል ሰፊ ሆኖ ታይቷል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ለወረርሽኝ አደገኛ ቦታዎች፣ ወይም የወረርሽን መፈልፈያዎች አድርጎ አይፈርጃቸውም። ነገር ግን ትምህርት ቤቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ጠቃሚ መመርያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ አስቸጋሪ ቦታዎች እንደሆኑ ይታመናል፤ ለምሳሌ ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅ። ልጆችን አራርቆ ክፍል ውስጥ ማስቀመጥ ይቻል ይሆናል። ልጆችን አራርቆ ተጫወቱ ማለት ግን ይቻላል? ልጆችን ያን አትንኩ፣ ይህን አትንኩ እያሉ ማስቆምስ ይቻላል? ልጆች ለቁጥጥር ፈታኝ የሆኑ ፍጥረታት ናቸው። ለዚህም ነው ትምህርት ቤቶች ፈታኝ ቦታዎች የሚሆኑት። ኮሮናቫይረስ ለልጆች ምን ያህል አስጊ ነው? ከሕጻናት እስከ አዳጊዎች ሁሉም የልጆች ዕድሜ ላይ ያሉ ለኮሮናቫይረስ የሚበገሩ አልሆኑም። ይህ መልካም ዜና ይመስላል። ሊይዛቸው ቢችል እንኳ የመታመም እድላቸው አናሳ ሆኖ ተገኝቷል። ይሄም ጥሩ ዜና ነው። ከልጆች ይልቅ አዋቂዎች በተለይም ጎልማሶችና ሽማግሌዎች ቫይረሱ በሚመርጠው ዕድሜ ላይ ያሉ ፍጡራን ናቸው። ሽማግሌዎች ሌላ ተጨማሪ በሽታ ስለማያጣቸው ቫይረሱ ሲያገኛቸው አፈፍ አድርጎ ወደ ሞት ሊያደርሳቸው ይችላል። የዩናይትድ ኪንግደም ዋናው የመንግሥት የጤና አማካሪ ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲ እንደሚሉት ሕጻናት በኮሮናቫይረስ ተይዘው የመሞት እድላቸው ሲበዛ ዝቅተኛ ነው። ይህንን በስታትስቲክስ እንደግፈው ከተባለ በአገሪቱ የብሔራዊ ስታትስቲክስ ቢሮ በእንግሊዝና በዌልስ በመጋቢትና በሰኔ የሟቾችን ቁጥር የሰነደበትን ዶሴ ማየት ይበቃል። የሟቾችን ዕድሜ ዘርዝሮ ያስቀምጣል። በሁለቱ ወራት ማለትም በመጋቢትና በሰኔ የሞቱ ሕጻናት ጠቅላላ ቁጥር 10 ብቻ ነው። ከ20 ዓመት በላይ ያሉ ሟቾች ደግሞ እስከ ዛሬ 46 ሺህ 725 ደርሰዋል። ይህ የሚያሳየን የፕሮፌሰር ክሪስ ዊት ድምዳሜ ልክ መሆኑን ይሆን? ልጆች ለኮቪድ-19 እጅ የማይሰጡ ትንንሽ ጀግኖች ይሆኑ? በሌላ ጊዜ ደግሞ በሆስፒታሎች ውስጥ የሚገኙ 55ሺህ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ላይ ጥናት ተደርጎ ነበር። ከታማሚዎቹ ውስጥ ምን ያህሉ አደጋ ውስጥ ናቸው ብትባሉ ስንት ትላላችሁ? 10ሺህ? ዕድሜያቸው ከ19 ዓመት በታች የነበሩት ከ55ሺዎቹ 1 እጅ አይሞሉም፡፡ የ55ሺህ አንድ ፐርሰንት ስንት ነው? አንዳንድ ልጆች ደግሞ አንዳንድ ምልክቶችን እያሳዩ መሆኑ የጤና ባለሙያዎችን እያነቃ መጣ። ትንሽ ጉሮሯቸው አካባቢ የመከርከርና የካዋሳኪ ዓይነት የሕመም ምልክቶች የሚያሳዩ ልጆች በዝተው ነበር አንድ ሰሞን። ካዋሳኪ ከ5 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ላይ የሚታይ ምንነቱ የማይታወቅ ትኩሳትን የሚያበረታ በሽታ ነው። ይህን ምልክት ልጆች እያሳዩ ያሉት ምናልባት የኮቪድ-19 ቫይረስ ተተናኩሏቸው ነገር ግን ሰውነታቸው ተከላክሎት ሲያበቃ የዚያ ግብግብ ርዝራዥ ዘግይቶ የሚያሳየው ምልክት ይሆናል በሚል የሕክምና ሰዎች ይህን ጠርጥረው ነገሩን አስፍተው መመራመር ጀምረዋል። ልጆች ቫይረሱን ያጋባሉ? ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ኦፍ ለንደን እና ለንደን ስኩል ኦፍ ሐይጂን እና ትሮፒካል ሜዲስን ተባበሩና አንድ ጥናት አጠኑ። ጥናቱም ያው ከዚሁ ከቫይረሱና ከልጆች ጋር የተያያዘ ነው። የደረሱበት ድምዳሜ ልጆች ከአዋቂዎች ይልቅ 50 እጅ በቫይረሱ የመያዝ ዕድል ብቻ እንዳላቸው ነው። ይህ በሌላ ቋንቋ ምን ማለት ነው? የማስተላለፍ እድላቸውም በዚያው መጠን አናሳ ነው ማለት ነው። ይህ የሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች ጥናት በዓለም ላይ የተሰሩ 6ሺህ ምርምሮችን ፈትሿል። ነገር ግን 18ቱ ብቻ ጠንከር ያለ የጥናት መርህን የተከተለ ውጤት ሰንደው አግኝቷቸዋል። ከእነዚህ ወረቀቶች ተነስቶ ነው እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው። ብቻ ወደ ሁሉም የጥናት ድምዳሜዎች ስንመለስ ሁሉም ጥናቶች ውጤት ያመላከተው ልጆች በአስተላላፊነትም፣ በታማሚነትም እዚህ ግባ የሚባል ስጋት እንደማይፈጥሩ ነው። ሌላው በቫይረሱ የተያዙ ቤተሰቦች ላይ የተደረገ ምርመራም ነበረ። በቻይናና በፈረንሳይ። ምርመራው ማጣራት የፈለገው የተያዙ ሰዎች ቫይረሱን መጀመሪያ ከማን ተቀበሉት ብሎ ምንጩን መፈተሸ ነበር። ከእነዚህ በአንድ ቦታ በድንገት ከተከሰቱ በርከት ያሉ ወረርሽኞች ውስጥ አንዱም ታዲያ ልጆች አልጀመሩትም። የሁሉም ምንጭ አዋቂዎች ነበሩ። ሌላም ምርምር ተደርጎ ነበር፤ በአይስላንድ፣ በደቡብ ኮሪያና በጣሊያን። ድምዳሜው አሁንም ሕጻናት በሽታውን በመቀበልም ሆነ በማቀበል፣ በመያዝም ሆነ በመታመም ዕድላቸው አነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ግሎባል ቲም የተሰኘ የአጥኚዎች ቡድን ደግሞ ቫይረሱን በማስተላለፍ የሕጻናት ሚና ለጊዜው ግልጽ አይደለም ይላል። ሆኖም ግን ቫይረሱን ወደ ቤተሰብ በማምጣትም ሆነ በቫይረሱ ተለክፎ አልጋ በመያዝ ሕጻናት በፍጹም አይታሙም። የሆነስ ሆኖ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት ባንልካቸውስ? ቢቀርባቸውስ? ምንም እንኳ ልጆች በቫይረሱ የመያዝ፣ ተይዞ የማስያዝ፣ ተይዞ አልጋ የመያዝ ዕድላቸው ከአዋቂዎች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቢሆንም ለምን በትንሹም ቢሆን ተጋላጭ እናደርጋቸዋለን? ይህ የአብዛኛው ወላጅ ድምዳሜ ይመስላል። የእንግሊዝ መንግሥት ዋናው የጤና አማካሪ ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲ ትንሽ ወጣ ያለ አተያይ አላቸው። ልጆች ትምህርት ቤት ባለመሄድ የበለጠ ይጎዳሉ ብለው ነው የሚያምኑት። እንዴት? ምክንያቱም ዞሮ ዞሮ "ከተጋላጭነት ነጻ የሆነ ቦታና ሁኔታ የለም" ባይ ናቸው ፕሮፌሰሩ። ስለዚህ የትምህርት ቤቶች ተመልሶ መከፈት ወላጆችም መምህራንም አምነውበት፣ ሙሉ ጥንቃቄ እያደረጉ ሊፈጸም የሚገባው ተግባር ነው ይላሉ። ትምህርት ቤት ያልሄዱ ልጆች በሥነ ልቡና መጎዳታቸው አይቀርም፣ አእምሯዊ እድገታቸውን ይጎትተዋል፣ "ስለዚህ ቤት ማስቀረት አንዱ ጉዳት ቀንሶ ሌላ ጉዳት መጨመር ማለት ነው" ብለው ያምናሉ አማካሪው ፕሮፌሰር። ትንንሽ ልጆች ቤት ከሚማሩት ይልቅ ትምህርት ቤት መማራቸው ከፍተኛ ልዩነትን ያመጣል። የትምህርት ሂደቶች በጥንቃቄ መካሄድ ከቻሉ ለልጆች አደጋ አይሆኑም፤ አደጋው እንዲያውም ቤት ሲመለሱ ሥራ ውለው ከሚመለሱ ወላጆቻቸው ነው የሚጋረጥባቸው። ይህ ጽሑፍ ሙሉ በሙሉ መሰረት ተደርጎ የተጻፈው የእንግሊዝን ትምህርት ቤቶች፣ የተማሪ ቁጥር፣ የተማሪ ቤት ስፋትና መሠረተ ልማትን ግምት ውስጥ አስገብቶና ተመርኩዞ ነው። ሁኔታዎች ወደእኛ አገር ሲመጡ ፍጹም መልካቸው እንደሚቀይሩ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።
news-56353673
https://www.bbc.com/amharic/news-56353673
ምዕራብ ጎንደር ዞን፡ መንገደኞችን በማገት በመቶ ሺህዎች የሚጠይቁት ሽፍቶች
ከሳምንታት በፊት የምዕራብ ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የዞኑን የህዝብና ሰላምና ደኅንነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አራጋው አዛናውን ጠቅሶ በአካባቢው እገታ መፈጸሙን አስታውቆ ነበር።
"በቀን 16/06/13 ከጧቱ ሁለት ሰአት አካባቢ ከሽንፋ ወደ ገንዳ ውሃ ሲጓዝ የነበረን ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ በመተማ ወረዳ በለምለም ተራራና ጉባይ ቀበሌዎች አዋሳኝ ቦታ ሽፍቶች የዝርፊያ እና የእገታ ወንጀል ፈጽመዋል።" ብሏል። አጋቾቹ አንድ የፖሊስ አባል ገድለው፤ ግለሰቦችን አግተው በመቶ ሺህ ብሮች እየጠየቁ ነው ፤ በርካታ ንብረትም ዘርፈዋል ሲል አስታውቋል። ቢቢሲ በወቅቱ ታግተው ከነበሩ ግለሰቦች መካከል ሶስቱን አግኝቶ ስለነበረው ሁኔታ ማናገር ችሏል። "እያገላበጡ እንደገብስ ወቁኝ" ከአራቱ ታጋቾች አንዱ የሆነው መለሰ የኔዓለም "መረጃ ስላላቸው እኔ ባልሄድ እነሱም አይያዙም ነበር" ሲል የነበረውን ሁኔታ ማስረዳት ይጀምራል። አጋቾቹ ሰኞ ይመጣል የሚል መረጃ እንደነበራቸው እና ሰኞ ሲቀር ማክሰኞ እንደጠበቁት ይገልጻል። ከፊት ለፊታቸው ሲሄዱ የነበሩ ስድስት መኪኖችን አልፈው እነሱን ማስቆማቸውንም መረጃ አላቸው ብሎ እንዲደመድም ምክንያት ሆኖታል። "ጠንካራ መረጃ እዚህ [ሸንፋ ከተማ] አላቸው። ከቤቴ ስወጣም የሚከታታለኝ አለ። [ተይዘን] ሹፌሩን አስወርደው ካበቁ በኋለ ከሴቶች በስተጀርባ ሲፈትሽ ሲያጣኝ ወረደ። ሁለተኛ ጊዜም ሲያጣኝ በስልክ ጠይቆ ነው መጋረጃውን መንጥቆ የወሰደኝ" ብሏል። ተቀጥሮ እንደሚሠራ በተደጋጋሚ ቢነግራቸውም ነጋዴ መሆኑን እና ለዚህ መረጃ እንዳላቸው በመግለጽ ደጋግመው ገርፈውታል። " ሾፌሩም ተገርፏል፤ ግን ልዩነት አለው። ግርፋታቸው ብዙ አይደለም እንደኔ የጠነከረ ግርፋት የላቸውም። ነጋዴ ነው ብር አለው በሚል ነው" ብሏል መለሰ። "በሰደፍም መትተውኛል። እንደገናም ሌዛ የሚባል እንጨት አለ ያንን ቆርጠው ለቁም እያገላበጡ ወቁኝ። እንደገብስ እንደኑግ አለ አይደል? 'ስላንተ የተለየ መረጃ እየሰማን ነው። መረጃህ እንደዚህ [ነጋዴ ነው። ገንዘብ አለው] እያለን ነው አንተ እንዴት ትደብቀናለህ? እኔ ተቀጥሬ እሠራለሁ ትላለህ። የሚነግረን መረጃ ንብረቱ ያንተ ነው እንጂ ተቀጥረህ በውክልና እየሠራህ አይደለም የሚል ነው' በሚል ነው የገረፉኝ።" ከመኪና ካስወረዷቸው በኋላ ገንዘብ፣ ስልክ፣ ቀለበት እና የአንገት ማህተብ ጭምር ወስደውበታል። "ሽርጤንም 'የሰው ነው ብዬ ነው' ያስቀረሁት- በሙሉ የቀረ ነገር የለም ከኪሴ" ብሏል። መኪናው ላይ ተጭኖ የነበረው የጓደኛው አኩሪ አተር ነበር። እህሉንም ምንም አላዳረጉም። "በመረጃ የኔን መሄድ ነው እንጂ የሚፈለጉት ከእህሉ አይደለም ጉዳዩ። ከዚህ [ከከተማ] ያለው መረጃ እኔ ባለሃብት መሆኔን 'ብር ያለው እሱ ነው' በማለት ይነግራቸው ነበር" ሲል ያስረዳል። በሌላ መኪና ውስጥ የነበረ የጸጥታ አባል ከቦታው ደርሶ ከአጋቾቹ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የአንድ አጋች ህይወት ሲያልፍ የጸጥታ አባሉም ሞቷል። ቢቢሲ መለሰን ለማናገር በመጀመሪያው ቀን ያደረገው ሙከራ ግርፊያው ባደረሰበት ህመም ምክንያት ሊሳካ አልቻለም። በሁለተኛው ቀን ቃለ መጠይቁን ሲያደርግ በተደጋጋሚ ህመሙን ቻል አድርጎ መረጃውን ለመስጠት ካለው ፍላጎት ማውራቱን ገልጿል። ትከሻው እና ኩላሊቱ አካባቢ በደረሰበት ምት በሚሰማው ህመም ምክንያት በሆዱ እንደሚተኛ ገልጿል። ከአጋቾቹ ጋር ያሳለፉትን አራት ቀናት "ማደሪያ የለንም። መንገድ ነው የምናድረው። ቀን ምሽግ ነው የምንውል። አለ አይለደል ዋሻ ውስጥ ነው የሚያውሉን" ሲል ያስታውሳል። "ለእነሱ ለምለም እንጀራ ይመጣላቸዋል። ለእኛ የሠርግ ኮሾሮ [የእንጀራ ድርቆሽ] በኩባያ ይሰጡናል። በቀን አንድ ጊዜ አንድ ኩባያ ለአራት ይሰጡናል" ይላል። እንደ መለሰ ከሆነ አጋቾቹ ያሉበት ቦታ እንዳይታወቅም ሱዳን ድንበር አካባቢ መሆናቸውን በመጥቀስ ለቤተሰቦቻቸው ሲነግሩ ነበር። ቤተሰቦቹ እንዲለቀቅ ከፈለጉ ከ450 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል። ቤተሰቦቹ ጉዳዩን ለህግ አካላት ለማሳወቅ ሲንቀሳቀሱም አጋቾቹ መረጃው ይደርሳቸው ስለነበር እየገረፉ ቤተሰቦቹ አርፈው እንዲቀመጡ እንዲነግራቸው አድርገዋል። "'ወደ ፖሊስ ከህግ አካል እየሄዱ ነው ተመለሱ በላቸው። ለምንድነው የሚሄዱት? ምን ሊያመጡ ነው? አሁን እጃችን ላይ ነክ። ምን ሊያደርጉ ነው? ከህግ አካልም መረጃ አለን። ከመከላከያ እስከ ፖሊስ ድረስ ምን ሊያደርጉ ገቡ?' አሉኝ። 'ተመለሱ እኔን እኮ ሊገሉኝ ሰኮንድ አልቀራቸውም' እያልኩ ወንድሜን እያወራሁትም ይደበድቡኛል" ብሏል። ቤተሰቦቹ ያላቸውን ሰብስበው እና ተበድረውም 410 ሺህ ብር ከፍለው እንዲለቀቅ አድርገዋል። "ለእኔ ብቻ ነው 410 ሺህ የተከፈለው። ቤተሰብም ተጨናንቆ ነበር እንገለዋለን እያሉ ስለነበር" ብሏል። ገንዘቡን ለማሰባሰብ ለሥራ የሚጠቀምባቸውን እንደ ሚዛን ያሉ ቁሳቁሶችን ጨምሮ መጋዘን ውስጥ ያለውን ንብረት ለመሸጥም መገደዱን ይናገራል። "ከደልጊ እስከ ባህር ዳር ድረስ ያሉ ጓደኞቹ" ያቅማቸውን አዋጥተው ስለረዱኝ ነው የተጠየቀውን ገንዘብ ለመክፈል የተቻለው። አሁን "ምንም ተስፋ የለኝም" የሚለው መለሰ "ምንም የማስበው የለም አንደኛ ህይወቴን አጥቻለሁ። ሁለተኛ ሠርቼ አገኛለሁ የሚል ዓላማ እስከሌለኝ ድረስ በህይወት ካለሁ ተቀጥሬም ቢሆን እሠራለሁ። ጓደኞቼም ካላቸው ይረዱኛል። ከሌላቸውም ተቀጥሮ መኖር ነው ውሳኔዬ" ሲል ተስፋ በቆረጠ ስሜት ይገልጻል። መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት ይገባዋልም ይላል። "ነገ ተቀጥሬም አንዱ ሥራ ቢያዘኝ እንዲሁ ታግቼ ህይወቴን መገበር እንጂ ለውጥ የለውም። መንግሥት ለሌሎችም ለህብረተሰቡም ለውጥ ቢያመጣ ጥሩ ነው" ሲል ፍላጎቱን አስታውቋል። መለሰ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም ህክምናው በመከታተል ይገኛል። ገንዘብ ብቻ ነው የሚፈልጉት ከመለሰ የኔዓለም ጋር የነበሩት ሌሎች ሁለት ታጋቾችም ተመሳሳይ ምስክርነታቸውን ለቢቢሲ ሰጥተዋል። ሁለቱም ታጋቾች ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቀም ጠይቀውናል። ከታጋቾች መካከል አንዱ የሆነው ግለሰብ አግተው ይዘዋቸው የሄዷቸውን ሰዎች እንደማያቋቸው ለቢቢሲ ይገልጻል። "ማክሰኞ ጭነት ጭነን ከሽንፋ ወደ ገንዳ ውሃ ስንሄድ ነው የያዙን። . . . ሁሉም የጦር መሣሪያ ይዘዋል" ይላል ይህ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ግለሰብ። ሌላኛው ግለሰብ ደግሞ በተለምዶ ኤፍ ኤስ አር ተብሎ በሚጠራው መኪናቸው ላይ ከተጫነው አኩሪ አተር በተጨማሪ ሁለት ሴቶች እና አራት ወንዶች በድምሩ አራት ሰዎች ተጭነው እንደነበር ተናግሯል። ከሽንፋ ወደ ገንደ ውሃ እየሄዱ ሳለም 11 ጦር መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች እንዳስቆሟቸው ያስታውሳሉ። በአጋጣሚ ፖሊስ የጫነ መኪና ደርሶ ተኩስ መከፈቱን ለቢቢሲ አስረድተዋል። በተኩስ ልውውጡ ወቅት ከአጋቾቹ ወገን አንድ እንዲሁም አንድ የፖሊስ አባል ተገደለ። ሁለቱን ሴቶች ያላቸውን ቀምተው ከመኪናው ጋር ትተዋቸው ሲሄዱ ወንዶቹን ግን ወሰዷቸው። አጋቾቹ የወሰዷቸው ሰዎች የመኪናው አሽከርካሪ ከእነ ረዳቱ፣ አኩሪ ተሩን የጫነው ግለሰብ እና ሌላ መንገደኛ መሆናቸውንም ግለሰቦቹ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ከአጋቾቹ ጋር አራት ቀናት አብረው መቆየታቸውን የሚናገሩት ግለሰቦቹ መኪናው ላይ ምንም ጉዳት አለማድረሳቸውን ይናገራሉ። "'ብር አምጡ? ብር ካላመጣችሁ እንገላችኋለን' እያሉ ነው ያቆዩን" ሲል የተናገረው አንደኛው ግለሰብ፣ እነሱ እየተደበደቡ ጓደኞቻቸው ደግሞ ብር እያዋጡ እና ከሰዎች እየለሙኑ ቀናቶች አለፉ። "በመጨረሻም ብር ተከፍሎ ወጣን። ለእኔ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብር ነው የተከፈለው። [ግለሰቡ የገንዘቡን መጠን ለቢቢሲ የገለጸ ቢሆንም ማንነቱን ሊያሳውቅ ይችላል በሚል አስቀርተነዋል] ብሩ በአካል ተሂዶ ነው የተሰጣቸው። ሲከፈላቸው ሂዱ አሉን" ይላል። ገንዘቡ ተከፍሎ ከተለቀቁ በኋላ ጥለውት የሄዱትን መኪና እዚያው እንዳገኙት ገልጾ "አጋቾቹ ብር ብቻ ነው የሚፈልጉት። ብር ነው የሚሉት።. . ." ሲል ይገልጻል። "ህዝቡ አዋጥቶ እና ለምኖ ነው ገንዘቡን የከፈለልኝ። ብሩን ስንከፍል ሁላችንንም አንድ ላይ ለቀቁን። አምስቶቹ አጋቾች ብሩን ሄደው ሲቀበሉ ቀሪዎቹ ይዘውን ደበቅ ያለ ቦታ ቆዩ። ገንዘቡን መቀበላቸውን ሲያረጋግጡ በስልክ ተነጋግረው ለቀቁን። መንደር አካባቢ ነበር የለቀቁን" ብሏል ሌላኛው ስሙ እንዳይጠቀስ የገለፀ ታጋች። ከእገታው እንዲለቀቁ መንግስት ምንም እንዳላደረገላቸው ለቢቢሲ ገልጿል። "እርምጃም እንወስዳለን" የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደሣለኝ ጣሰው እገታው በተፈጸመበት ወቀት የጸጥታ መዋቅር ደርሶ አንድ የፖሊስ አባል መገደሉን አረጋግጠዋል። "ከአጋቾችችም አንድ ሰው ሞቷል" ሲሉም ያክላሉ። አጋቾች በቁጥር ከአስር በላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ሰዎቹን ከእገታው ለማስቀረት አለመቻሉን አስታውቀዋል። ሰዎቹን ከእገታው ለማስለቀቅ ስምሪት ከመደረጉም በላይ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በጥርጣሬ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል ለቢቢሲ። ". . .የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው አካላት ይህን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይታወቃል። እገታ አዲስ አይደለም አልፎ አልፎ በወርም በሁለት ወርም የጸረ ህዝብ አመለካከት ያላቸው ያግታሉ፤ ህይወትም ይጠፋል። ከወራት በኋላ ይሄ ተፈጥሯል። መፈጠር አልነበረበትም አሳዛኝ ነው" ሲሉ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል። "[የእገታው] ዓላማ አንደኛው ግጭት እና ብጥብጥ ለመፈጠር እና ሁለተኛው ደግሞ ሳይሰሩ ለመበልጸግ ስለሚፈልጉ ነው። ምንጊዜም ብር ስጡን ነው የሚሉት" ብለዋል። ህይወቱ ካለፈው ሰው በተገኘው መረጃ መሠረት እገታው የተፈጸመው ከአካባቢያቸው ውጭ በመጡ ሰዎች መሆኑ ታውቋል ብለዋል። "ድሮም የባዳ ተልዕኮ ነው አሁንም ይሄው ነው። ይህ እንዳይሆን እየሠራን ነው። እርምጃም እንወስዳለን" ሲሉ አቶ ደሣለኝ ተናግረዋል። ቢቢሲ በጉዳዩ ዙሪያ አማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን ሃሳብ ለማካተት ያደረገው ተደጋጋሚ ትረት አልተሳካም።
news-53021267
https://www.bbc.com/amharic/news-53021267
የኮሮናቫይረስ ውጤት መዘግየት ስጋት እየፈጠረ ነው
የአስከሬን ምርመራ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ በስፋት እየተካሄደ ነው። ቀደም ሲል በተለየ ምክንያት ካልተፈለገ በስተቀር ምርመራው አይካሄድም ነበር።
ምርመራው የቫይረሱን የስርጭት መጠን ለማወቅ ይረዳል። ሌሎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያግዝ ነው። ከበሽታው እየተስፋፋ ከመምጣት አንጻር የምርመራው ውጤት ከመዘግየት ጋር ተያይዞ ችግሮች እየተከሰቱ ነው። ሁለቱን እንመልከት። አዲስ አበባ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ቢኒያም አሸናፊ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አብነት አካባቢ ነዋሪ ነው። ከሳምንታት በፊት በሰፈሩ የተፈጠረውን መቼም አይረሳውም። የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ አንዲት ግለሰብ በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው ያልፋል። "እኛ አካባቢ የተፈጠረው ነገር ህክምና ላይ የነበሩ የሰፈራችን ነዋሪ ሴት ውጤታቸው ሳይታወቅ በመሞታቸው አስከሬናቸው ለቤተሰብ ተሰጠ። በአጋጣሚም ውጤቱ የታወቀው አስከሬን ከወጣ በኋላ ነበር" ሲል ቢኒያም ያስታውሳል። ግለሰቧ የህይወታቸው አልፎ ግብዓተ መሬታቸው ከተፈጸመ በኋላ ውጤታቸው ታወቀ። የኮሮናቫይረስ እንደነበረባቸው ተረጋገጠ። ይህም በአካባቢው ብዙ መዘዝ ይዞ ነበር የመጣው። "ብዙ ንኪኪዎች ነበሩ። በአኗኗራችን ምክንያት ድንኳን ውስጥ ለለቅሶ የተቀመጠ ሰው ስለነበረ በጣም ብዙ ሰው ነው በቫይረሱ የተያዘው። በቁጥር ደረጃ ይህ ያህል ነው ማለት ባልችልም። ነገር ግን በንክኪ የተነሳ ብዙ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቂ ነበሩ።" በኮሮናቫይረስ ምርመራው ውጤት መዘግየት፣ የአካባቢው ነዋሪ የተጠጋጋ አኗኗር ስላለው እና በለቅሶ ሥነ-ሥርዓት ወቅት በነበረው ንክኪ ምክንያት ብዙዎች ቫይረሱ እንዲይዛቸው ዕድል ፈጥሯል። የጤና ጥበቃ ሚንስቴር ከቫይረሱ በኅብረተሰቡ ውስጥ መስፋፋት ጋር ተያይዞ አንዳንድ አካባቢዎችን ከእንቅስቃሴ ሊዘጋ እንደሚችል በዚያው ሰሞን አስታውቆ ነበር። የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ነዋሪዎች ግን በወጣቶች አስተባባሪነት አካባቢውን ለሁለት ሳምንት ከእንቅስቃሴ ውጪ ለማድረግ በመወሰን ቀድመው ተገበሩት። "የተዘጋበት ምክንያት መንደር ውስጥ ቁጥሩ እየበዛብን ሲሄድ እዚው ያለን ወጣቶች በጎ ፈቃደኞች ሌላው አካባቢ እና ማኅበረሰብ እንዳይጠቃ በማሰብ ከጤና ባለሙያዎችና እና ከመንግሥት አካላት ጋር በመነጋጋር ራሳችንን ነው ኳራንቲን ያደረግነው" ብሏል ቢኒያም። በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎችም የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው የሁለት ሳምንቱን ጊዜ አጠናቀው አሁን ወደ መደበኛ ሥራቸው ተመልሰዋል። ከሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ ደረጃ በቫይረሱ ስርጭት ቀዳሚ የነበረው ልደታ ክፍለከተማ ነው። አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ወይዘሮ ጸዳለ ሰሙንጉሥ የሰሜን ሰዋ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ ኃላፊ ናቸው። የዚህም ታሪክ መነሻ አዲስ አበባ። ሸገር ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ወድቀው ወደ ግል ሆስፒታል ለህክምና ያቀናሉ። በህክምና ወቅትም የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል። ውጤቱ ይፋ ከመሆኑ በፊት ግን ህይወታቸው ያልፋል። "የአስከሬን ምርመራ ውጤቱ ቶሎ አልደረሰም ነበር። ቤተሰብ አና ወዳጅ ዘመድ አስከሬን ተቀብሎ ወደ ትውልድ ቀዬው እንሳሮ ያቀናል። በዚያም ሥረዓተ ቀብሩ ሲካሄድ በርካታ ሰው ተገኝቶ ነበር። ስለዚህ እንደማንኛውም ሰው የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ተካሂዷል" ይላሉ ወይዘሮ ጸዳለ። የህክምና ማዕከሉ ውጤቱ የደረሰው የግለሰቡ አስከሬን ከአዲስ አበባ ውጪ ተጓጉዞ አንደባህሉ ሰው ተሰብስቦ ግብዓተ መሬት ከተፈጸመ በኋላ ነበር። ውጤቱም ሟች የኮሮናቫይረስ ህመምተኛ እንደነበሩ የሚያረዳ ነበር። ከዚያም መልዕክት ለአካባቢው የጤና ኃላፊዎች ደረሰን። ሟች ኮሮናቫይረስ ስለነበረበት አስፈላጊው የበሽታ አሰሳና ንኪኪ የነበራቸውን ሰዎች የመለየት አስፈላጊው ሥራ እንዲከናወን ትዕዛዝ ተላለፈ። ወ/ሮ ጸዳለ እንደሚሉት "ከእንሳሮ ወረዳ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ርብርብ አድርገን 53 የሚሆኑ ሰዎችን የመለየት እና ቀደም ተብሎ ወደተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ አደረግን። ተጨማሪ 20 ሰዎች ደግሞ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ወደሚገኘው ለይቶ ማቆያ ገብተዋል።" ወደ ለይቶ ማቆያው እንዲገቡ የተደረጉት ሰዎች አብዛኛዎቹ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኙ ናቸው። ውጤቱ ቀደም ተብሎ ቢታወቅ ኖሮ ይህ ሁሉ ሰው ተጋላጭ እንደማይሆን ባለሙያዎቹ ያምናሉ። "የቅርብ ቤተሰቦቹን ስናስገባ ከእሱ ጋር ማን ተገናኝቷል የሚለውን ነገር እየለየን ነው። የለየናቸው ከአስከሬኑ ጋር ንኪኪ የነበራቸው እና በቀብሩ ላይ የነበሩ ናቸው" ምክትል ኃላፊዋ። ወይዘሮ ጸዳለ እንደሚሉት የምርመራ ውጤት መዘግየት የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ላይ የእራሱ ተጽእኖ አለው። "የላቦራቶሪ ውጤት በአንድ ቀን መድረስ ካልቻለ መዘግየት ኖሮ ሁለት እና ሦስት ቀን የሚቆይ ከሆነ በዚያ መካከል ብዙ ንክኪ ሊፈጠር ይችላል። የተመረመረ ሰው ውጤት እስኪታወቅ በተለየ ቦታ ማቆየት ቢቻል ለሌላ ሰው የማስተላለፍ ዕድሉ ይቀንሳል" ይላሉ። በአካባቢው የውጤት መዘግየት ሲከሰት ግን ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ቀደም ሲልም ከቫይረሱ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ሁለት ሰዎች አዲስ አበባ ናሙና ሰጥተው ውጤታቸውን ሳያውቁ ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን አቅንተው ነበር። ዘግይቶም ቢሆን በደረሰው ውጤት የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። "ከተለያዩ ሰዎች ጋር ተገናኝተዋል። አንደኛው ከቤተሰቦቹ ጋር እያለ ነው ተደውሎ ውጤት የተነገረው። እንግዲህ በሽታውን ወደ ቤተሰቦቻቸው የማስተላለፍ ዕድል አላቸው" ሲሉ ይናገራሉ። በዚህም ምርመራው የሚደረግላቸው ሰዎች ንክኪ ያላቸው ወይም ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ በመሆናቸው ውጤት እስኪታወቅ ድረስ ባሉበት እንዲቆዩ ማድረግን እንደ አንድ መፍትሄ ያቀርባሉ ወ/ሮ ጸዳለ። በአስከሬን ላይ የሚደረገው ምርመራም ናሙና ተወስዶ ውጤት እስኪታወቅ ድረስ አስከሬን ካልተሰጠ በተለያዩ አጋጣሚዎችና በቀብር ሥነ ሥርዓት ጊዜ በሚደረግ ንክኪ ቫይረሱ ወደ በርካታ ሰዎች እንዳይሻገር በማድረግ የወረርሽኙን መስፋፋት መቀነስ ይችላል ይላሉ። ወይዘሮ ጸዳለ ካላቸው ልምድ በመነሳት የመርመሪያ ማሽኑ ናሙና ማዘጋጀትን ጨምሮ ናሙናውን ለመመርመር የሚፈጀመውን ጊዜ አካቶ የአንድ ሰውን ውጤት በአንድ ቀን ማደረስ እንደሚቻል ይናገራሉ። ለዚህም ነው "ቢዘገይ ቢዘገይ በአንድ ቀን ውጤት መነገር ግዴታ መሆን አለበት" የሚሉት። የበሽታውን ምልክት አላሳዩም ብሎ ናሙና የሰጡ ሰዎችን ወደ ፈለጉበት እንዲሄዱ መልቀቅ የአቅም ጉዳይ ይመስለኛል የሚሉት ምክትል ኃላፊዋ ውጤቱ በቶሎ እንዲታወቅ ከተደረጋ በዚህ በኩል ያለውን ችግር መቅረፍ ይቻላል ይላሉ። "ወደ ቀያቸው የሄዱት ሁለቱ ሰዎች ከታወቀ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራቸው። እነሱም ከብዙ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራቸው። ውጤቱ ባይዘገይ የመከላከል ሥራ ለመስራት ዕድል ይፈጥርልናል" ሲሉም ያስረዳሉ። የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ ከሄደ አይደለም የተመረመሩ ሰዎች ቫይረሱ ኖሮባቸው ምልክት ያላሳዩትም በቤታቸው ሆነው ራሳቸውን በማግለል እስኪድኑ እንዲቀመጡ ሊደረግ ይችላል ይላሉ። በምሳሌነት ደግሞ ቫይረሱ በተስፋፋባቸው ያደጉት ሃገራት ተመሳሳይ ነገር እየተካሄደ መሆኑን ይገልጻሉ። ኅብረተሰቡም በምንም ምክንያት ይሁን ተመርምሮ ውጤቱ እስኪታወቅ ራሱን ለይቶ በመቀመጥ ውጤቱን በመጠበቅ ቤተሰብንም ሆነ ሌሎችን ከቫይረሱ ለመታደግ ወሳኝ ነገር እርምጃ ነው ይላሉ። በኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት መዘግት ዙሪያ የጤና ጥበቃ ሚንስቴርንና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ሃሳብ ለማካተት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።
news-48634128
https://www.bbc.com/amharic/news-48634128
በሠርግ ዕለት ማታ የሚጠበቀው 'የደም ሻሽ (ሸማ)' ምንን ያመላክታል?
በሕይወታችሁ ከምትደሰቱበት ቀን አንደኛው የሠርጋችሁ ዕለት ነው። ይሁን እንጂ የወንዶች የበላይነት ተንሰራፍቶ ባለባቸው ሃገራት ለሚኖሩ ሴቶች ምሽቱ አስፈሪ ቅዠት ይሆንባቸዋል። በጥንታዊው ልማድ ዕለቱ ሴቶች የሥነ ልቦናና አካላዊ ስቃይን የሚያስተናግዱበት ነው። አንዳንዴ ችግሩ የረጅም ጊዜ የጤና ቀውስ ሆኖም ይቀጥላል።
ኤልሚራ (ለዚህ ታሪክ ሲባል ስሟ የተለወጠ) "ልክ የሠርጋችን ምሽት ከፊት ለፊቴ ቆሞ ልብሱን ማወላለቅ ሲጀምር በጣም ፈርቼ ነበር" ትላለች ከሠርጓ በኋላ ስለተፈጠረው ስታስታውስ። "ምንም እንኳን እንዳገባሁ ራሴን ለማሳመን ብሞክርም፤ ይህንኑ ለራሴ ደግሜ ደጋግሜ ብነግረውም ሊያረጋጋኝ ግን አልቻለም፤ ማሰብ የቻልኩት ልብሴ ማውለቅ እንደነበረብኝ ነው" ትላለች። • ተጭበርብራ የተሞሸረችው ሴት አፋቱኝ እያለች ነው • ቻይና ቅጥ ያጡ ሰርጎችን ልትቆጣጠር ነው ኤልሚራ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን ስታጠናቅቅ የ27 ዓመቷ የነበረ ሲሆን የራሷን ሥራ በመፍጠርም ትሰራ ነበረ። ባሏን የመረጡላት ቤተሰቦቿ ሲሆኑ እርሷም ጋብቻውን ለመፈፀም ተስማማች። ምክንያቷ ደግሞ እናቷን ማስደሰት ነበር። "ጎረቤታችን ነበር፤ ነገር ግን ምንም የሚያመሳስለን ነገር አልነበረም፤ እሱ አልተማረም፤ በቃ አንድ የሚያደርገን ምንም ነገር የለም" ስትል ስለ ባሏ ትናገራለች። ኤልሚራና ባሏ የተዋወቁት በወንድሟ አማካኝነት ነው፤ ጥሩ ባል ሊሆናት እንደሚችልም ተነግሯታል። እናቷም ጎረቤታቸውን በማግባቷ ደስታቸው ወደር አልነበረውም። ይሁን እንጂ ኤልሚራ ቤተሰብ መመስረት እንደማትፈልግ ለእናቷ በተደጋጋሚ ነግራቸዋለች። በዚህን ጊዜ ይህች ልጅ 'ጎጆ መቀለስ አሻፈረን አለች' ሲሉ ለቅርብ ዘመዶቻቸው አልሚራን እንዲያግባቧት ስሞታ ተናገሩ። ጋብቻውን እምቢ ማለቷ ድንግል አይደለችም የሚል ጥርጣሬን ፈጠረባቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ያደረገችው የሠርጓ ዕለት ነበር። "ባሌ ይህንን እያወቀ ስሜቴንና ክብሬን ለመጠበቅ ቅንጣት ታህል አልተጨነቀም ነበር" በማለት ዕለቱን ታስታውሰዋለች። " ብር አምባር ሰበረልዎ፣ ጀግናው ልጅዎ ! " ተብሎ እንደተዘፈነው እርሱም ጀግነቱን በወንድነቱ ለማስመስከር ተጣድፏል። እርሷ እንደምትለው ተነስቶ ከላይዋ ላይ ተከመረባት፤ በሁኔታው እጅግ ተደናገጠች ። ከሚቀጥለው ክፍል የመንኳኳትና 'ቀስ በል! ምን ዓይነት ጭካኔ ነው' የሚል የሴት ድምፅ ሰማች። • ድብቅ የህጻናት ጋብቻዎች • ኬንያዊው በአንድ ሰርግ ሁለት ሚስቶች አገባ ከበሩ በስተጀርባ የነበሩት እናቷ፣ ሁለት አክስቶቿና ሌሎች ዘመዶቿ ነበሩ። ሲጮሁና በሩን ሲያንኳኩ የነበሩትም እነርሱ ናቸው። በዚያ ሁኔታ ከበሩ ሥር የተኮለኮሉት ከባለቤቷ ጋር የምታደርገውን አካላዊ ግንኙነት ለመከታተልና የእርሷን ድንግል መሆን ለማረጋገጥ ነበር። "እስኪ አምጡት ደሙን ሸማ - እንዳንታማ፣ እስኪ አምጡት የደሙን ሻሽ- እንዳንሸሽ..." በሚለው ዘፈን በኩራት ለመውረግረግ ጓጉተዋል። "የሚያወሩት እያንዳንዱ ድምፅ ይሰማን ነበር" የምትለው ኤልሚራ ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥና በግንኙነቱ ምክንያት የተፈጠረው ህመም ሲበረታባት ጋብቻ ማለት ይህ ነው? ስትል ራሷን እንድትጠይቅ አድርጓታል። አብዛኞቹ ያገቡ የሴት ዘመዶች ሙሽሮቹ ካሉበት ቀጣይ ክፍል በመሆን አዲስ ያገባች ሴትን ተከትለው በመሄድ 'ኢንጊ" የተባለውን ሚና ይወጣሉ። የእነዚህ ሴቶች አንደኛው ሚናቸው የግብረ ሥጋ ግንኙነት በማድረግ ልምድ የሌላትን ሙሽራ ማማከር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ 'የደሙን ሻሽ' ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ግንኙነት የፈፀሙበትን አንሶላ ማንሳት ነው። "የሠርጌ ምሽት በጭንቀት የተሞላ ድራማ ነበር" በካውካሰስ ባህል ከሠርጉ ማግስት ጠዋት አንሶላ ይዞ ወጥቶ ማሳየት የተለመደ ነው። ለዘመድ አዝማዱ ደሙን ማሳየት ድንግል የመሆኗ እና የክብር ማሳያ ነው። ከዚያም በአንሶላው ላይ ደሙን ያዩ ቤተሰቦች አዲሶቹን ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ ይሏቸዋል፤ ደስታቸውንም ይገልፃሉ። "ለዚህ ነው የሠርግ ምሽት በእስጨናቂ ድራማ የሚሞላው፤ በሠርጉ ማግስት አንሶላው ምንን ነው የሚያመለክተው?" ሲሉ በአዘርባጃን የሴቶች መብት አጥኚ የሆኑት ሻክህላ ኢስማኢል ይጠይቃሉ። አንሶላው ላይ ደም መታየት ካልቻለ ሴቷ ትገለላለች ወደ ቤተሰቦቿም በሃፍረት ተሸማቃ እንዲትመለስ ይደረጋል። ከዚያም ከባሏ እንደተፋታች ስለምትቆጠር በድጋሚ ለማግባት ትቸገራለች። ከቤተሰቦቿ ቁጣና ስድብን ለማስተናገድም ትገደዳለች። በአዘርባጃን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት ይህ ልማድ አሁንም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎችም እንደተስፋፋ ነው። አንዳንዴ እንደውም ከጋብቻው በፊት ሴቷ ድንግል መሆን አለመሆኗ በሃኪም እንዲረጋገጥ ይደረጋል። ይህ ድርጊት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተወገዘ ነው፤ ይህ በትንሹ በ20 አገራት ተግባራዊ የሚደረገው ልማድ እንዲያከትም የተባበሩት መንግሥታትና የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቅርበው ነበር። ድርጊቱ የሴቶችን መብት የሚጥስና ለሥነ ልቦና ችግር የሚዳርግ ነው ሲሉም አውግዘውታል። በመግለጫቸው ላይም የህክምና ሳይንስ ድንግልና የሚባል ፅንሰ ሃሳብ እንደሌለና ይህ ሃሳብ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊና እና ማህበራዊ አስተሳሰብ እንደሆኑነ ጠቅሰዋል። 'ቀይ አፕል' በጎረቤት አገር አርሜኒያ፣ ጆርጂያ እና በሰሜናዊ ካውካሰስ እንዲሁም በሩሲያ ሪፐብሊክ ተመሳሳይ ልማድ አለ። በአሜሪካ ከበር ባሻገር የሚቀመጡ የዐይን እማኞች አይኖሩም። ልማዱ ቀይ አፕል (red apple) ይባላል። ስያሜው በአንሶላ ላይ የሚፈስን የደም ጠብታ ለማመላከት የተሰጠ ነው። ከዋና ከተማዋ የሬቫን ውጭም ድርጊቱ በተመሳሳይ መልኩ ይፈፀማል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ኒና ካራፔሺያን እንደሚሉት አንዳንድ ጊዜ የሙሽራዋ ዘመዶች እና ጎረቤቶች ልጃቸው ንፁህና ያልተነካካች መሆኗን እንዲያረጋግጡ ይጋበዛሉ። በመሆኑም በመንደሩ ያሉ ሰዎች በሙሉ በልማዱ ምክንያት የተገኘውን ደስታ ይጋራሉ። በገጠር አካባቢዎች ሴቶች ዕድሜያቸው 18 ሲሞላ ወዲያውኑ ይዳራሉ። አብዛኞቹ ምንም ዐይነት ሥራም ሆነ ሌላ ክህሎት የላቸውም። በመሆኑም እነዚህ ሴቶች የቀይ አፕሉን ምርመራ ካላለፉ ምን አልባት ቤተሰቦቻቸው ሊክዷቸውም ይችላሉ ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ አክለዋል።
news-55391886
https://www.bbc.com/amharic/news-55391886
የዝሆን ልጅ [ኤልሞሌ] ከሞት የታደገው ታይላንዳዊ
በአንድ ምሽት ታይላንድ ውስጥ የዝሆን መንጋ መንገድ እያቋረጠ ነበር። ከመንጋው መካከል ግን አንዱ ኤልሞሌ፣ የዝሆን ልጅ፣ እየከነፈ ሲመጣ በነበረ የሞተር ብስክሌት ተገጭቶ ተዘረረ። በዚህ ወቅት በመደበኛ ሥራው ላይ ያልነበረ ታይላንዳዊ የአደጋ ሠራተኛ ለኤልሞሌው የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ መስጠት ጀመረ።
ይህንን የግለሰቡን ተግባር በተንቀሳቃሽ ምስል ያስቀሩ ሰዎች ዜናውን ለዓለም አዳረሱት። ኤልሞሌውንም በተሰጠው የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ መትረፍ የቻለ፣ ግለሰቡም ለዝሆን እርዳታ በመስጥ ወሬያቸው ናኘ። የሕክምና እርዳታው የኤልሞሌው ትንፋሽ እንዲመለስ ደረቱን በአግባቡ ጫንጫን ማለትን ያካተተ ነበር ተብሏል። ማና ስሪቫቴ ይባላል ታይላንዳዊው የአደጋ ጊዜ ሠራተኛ። እንደ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገባ ከሆነ ይህ የአደጋ ጊዜ ሠራተኛ በሥራ ሕይወቱ በርካታ የሕይወት ማትረፍ ሥራዎችን ቢያከውንም የዝሆን ሕይወትን ከሞት ሲታደግ ግን ለመጀመሪያ ጊዜው ነው። በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ በስፋት ሲሽከረከር የሚታየው የተንቀሳቃሽ ምስል ላይ በአንድ አውራ ጎዳናው በምሽት በጎኑ ለወደቀው ኤልሞሌ፣ የዝሆን ልጅ፣ ግለሰቡ የሁለት እጅ መዳፎቹን አቆላልፎ ደረቱን ሲጫን ይታያል። ከአስር ደቂቃ በኋላም ዝሆኑ ተነስቶ ቆመ። የዝሆኑ ልጅ፣ ኤልሞሌ፣ በምሥራቃዊ ታይ የቻንታቡሪ አውራጃ ከሌሎች በርካታ ዝሆኖች ጋር አውራ ጎዳናውን እያቋረጠ ነበር። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የማና ባልደረቦች ዝሆኑን ገጭቶ የተዘረረውን የሞተር ብስክሌቱን አሽከርካሪ ሲረዱ ይታያል። አሽከርካሪው ለወሬ የሚበቃ ጉዳት አልደረሰበትም ተብሏል። ማና ላለፉት 26 ዓመታት በነፍስ አድን ሠራተኝነት ማገልገሉን፣ አደጋው ስፍራ የደረሰው ከሥራ ሠዓቱ ውጪ እየተንሸራሸረ ባለበት ወቅት እንደሆነ ለሮይተርስ ገልጿል። "ሕይወትን ማትረፍ በደመነፍሴ ውስጥ ያለ ነገር ነው። ነገር ግን የኤልሞሌውን ሕይወት ለማትረፍ በምጥርበት ሰዓት ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ነበርኩ። ምክንያቱም እናቱ እና ሌሎች የመንጋው አባላት ሲጠሩት ይሰማኝ ነበር" ሲል ለዜና ወኪሉ በስልክ አስረድቷል። አክሎም "የዝሆኑ ልብ የት ስፍራ ሊገኝ እነደሚችል በአንድ የኢንተርኔት ቪዲዮ ላይ ባየሁት እና በሰው ልጅ አፈጣጠር ላይ ተመስርቼ ገምቻለሁ፣ ኤልሞሌው መንቀሳቀስ ሲጀምር እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም" ብሏል። ኤልሞሌው ወደ እናቱ እና ሌለች የመንጋው አባላት ከመመለሱ በፊት ለአስር ደቂቃ ያህል ከቆመ በኋላ ተጨማሪ ሕክምና እንዲያገኝ ወደ ሌላ ሥፍራ ተወስዶ ነበር ሲል የሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ኤልሞሌው ከእናቱ እና ከመንጋው ጋር በሰላም መቀላቀሉም ተሰምቷል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኛው ማና ደግሞ ኤልሞሌው መተንፈስ እንዲችል የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ የሰጠው ብቸኛው እንስሳ መሆኑን ተናግሯል። ኤልሞሌው የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ከተሰጠው በኋላ
news-55585440
https://www.bbc.com/amharic/news-55585440
ከ10 በላይ ዋሻዎችን ያቆራረጠው የአዋሽ ወልዲያ የባቡር ሃዲድ
ኢትዮጵያ የባቡር ግንባታን ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ እንደገና ስትጀምር ከተጠነሰሱ ፕሮጀክቶች አንዱ መነሻውን አዋሽ አድርጎ መዳረሻውን ሃራ ገበያ [ወልዲያ] ያደረገው የባቡር መንገድ ነው።
የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ የባቡር መንገዱ አጠቃላይ ርዝመቱ 392 ኪሎ ሜትር ሲሆን ግንባታው በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተከናወነ ይገኛል። የመጀመሪያው ምዕራፍ ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ የሚደርስ ሲሆን 270 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ነው። ከኮምቦልቻ ሃራ ገበያ ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ 122 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። ግንባታው በሁለት ምዕራፍ እንዲከፈል የተደረገበት ምክንያት በወቅቱ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆን ሙሉ በጀት ባለመገኘቱ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር አብዱልከሪም ሞሐመድ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የባቡር መንገዱን ግንባታ ለማከናወን በ2012 [እአአ] ስምምነት ተደርሶ በ2014 ደግሞ የምዕራፍ አንዱ ግንባታ ተጀመረ። 1.235 ቢሊዮን ዶላር የተያዘለት በጀት ነበር። የዚህ የባቡር መንገድ ግንባታ [ምዕራፍ አንድ] በአሁኑ ወቅት 99 በመቶ ሥራው ተጠናቅቆ አገልግሎት ለመስጠት የኃይል አቅርቦት ብቻ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ሁለተኛው ምዕራፍ ዘግይቶ ፋይናንሱ ስለተገኘለት በቅርቡ የተጀመረ ነው። ከዚያም ባለፈ በኮሮናቫይረስ፣ በወሰን ማስከበርና በተለያዩ ምክንያቶች ተስተጓጉሏል። በአሁኑ ወቅት ግንባታው 82 በመቶ መድረሱን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል። በፍጥነት አጠናቅቆ አገልግሎቱን ለማስጀመር እየተሰራ ቢሆንም "ነገር ግን አሁንም የኃይል አቅርቦት ይዘገያል ብለን እንሰጋለን" ይላሉ ኢንጂነር አብዱልከሪም። የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ ባቡር ፍሬን ስለሌለው ይጨርሰናል. . . ግንባታው ከመጀመሩ በፊት ትልቁ ፈተና የአካባቢው መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ነበር። ከአዋሽ ሃራ ገበያ ያለው አካባቢ ተራራማና ለባቡር ሃዲድ ግንባታ አመች ስላልነበር ዲዛይኑን በየቦታው እየሄዱ ማስተካከሉ ፈታኝ ሥራ ነበር ይላሉ ሥራ አስኪያጁ። እነዚህን ተራራማ አካባቢዎች በአፈር ቆረጣ፣ በዋሻ እና በድልድይ ማስተካከል ዋነኛ የፕሮጀክቱ የትኩረት ነጥቦች ነበሩ። በአካባቢው የባቡር መንገድ ግንባታ ሲከናወን ይህ የመጀመሪያ ነው። በዚህም ምክንያት ሕብረተሰቡ ስለባቡር መንገድ ግንባታና አገልግሎት እውቀት አልነበረውም። እናም የሚናፈሱ ማናቸውንም አሉባልታዎች እንደወረዱ እውነት አድርጎ የመቀበል ችግር እንደነበርም ኢንጂነር አብዱልከሪም ያስታውሳሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንደኛውና አስቸጋሪ የነበረው አሉባልታ "ባቡር ፍሬን የለውም፤ ወደእዚህ ከመጣ ሕዝቡን ይጨርሳል" የሚለው ነበር። ሕብረተሰቡ በቂ መረጃ ስላልነበረው የተነገረውን ሁሉ እውነት አድርጎ ይወስድ ስለነበር የዚህን መረጃ ስህተትነት ለማስገንዘብ ረዘም ያለ ጊዜ መውሰዱን ስራ አስኪያጁ ነግረውናል። ሌላኛው፤ ምናልባትም በሁሉም ግንባታው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች ያጋጥም የነበረው የወሰን ማስከበርና የካሳ ችግር ነው። ባቡሩ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የሚሄድ ስለነበር ሁኔታውን በጣም አስቸጋሪ አድርጎታል። የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ በአሁኑ ወቅት የምዕራፍ አንድ ሥራውና የካሳው ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል። አንዳንድ ለአፈር መድፊያና ለተለያዩ ሥራዎች ሲያገለግሉ የነበሩ ቦታዎችን ወደነበሩበት መመለስና ለሕብረተሰቡ መልሶ የማስረከብ ሥራ እየተሰራ ነው። በምዕራፍ ሁለት ግን የካሳ ሁኔታው መቋጫ ያገኘው በቅርቡ ነው። የኮሮናቫይረስን መከሰት ተከትሎ ሥራው ለተወሰነ ጊዜ ቁሞ ስለነበር ከካሳ ጋር ተያይዞ በተለይ ተሁለደሬ ወረዳ አካባቢ ከፍተኛ ችግር አጋጥሟቸው እንደነበር ኢንጅነር አብዱልከሪም ይናገራሉ። ካሳ አንሶናል በሚል ከ2 ዓመት በፊት የተነሳ ቅሬታ ነበር። ካሳው ከተከፈለ በኋላ ቅሬታው በመነሳቱ ውሳኔ ለማሰጠት ረዥም ጊዜ ወስዷል። በቅርቡ ግን በትራንስፖርት ሚንስትርና በክልሉ ፕሬዛዳንት [የአማራ ክልል] አማካኝነት ልዩ ውሳኔ ተሰጥቶ የካሳው ሁኔታ መስተካከሉን ገልጸዋል። ነገር ግን ከዚያ በፊት በካሳው ምክንያት ለረዥም ጊዜ የ55 ኪሎ ሜትር ሥራውን ማከናወን ሳይቻል ቆይቷል። "እነዚህን ችግሮች ከቀረፍን በኋላ ግን የሕብረተሰቡ ተሳትፎና በፕሮጀክቱ ላይ ያሳደረው የእኔነት ስሜት ሥራችንን እንድናሳልጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቶልናል" የሚሉት ሥራ አስኪያጁ፤ መጀመሪያ አካባቢ በማሕበረሰቡ ዘንድ ስለባቡር መንገዱ ግንባታ የነበረው ብዥታም ሆነ የካሳ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ መስተካከሉን ይገልጻሉ። 10 ኪሎ ሜትር ዋሻዎች እና70 ድልድዮች. . . በአገራችን እስካሁን የዋሻ ቁፋሮ ሥራ ብዙም የተለመደ አይደለም። በተለይ ለትራንስፖርት በጣም አስፈሪ የነበረና ለመገንባትም ልዩ ክህሎትና ልምድ የሚፈልግ ነበር። በእዚህ ፕሮጀክት ግን በተለየ ሁኔታ የዋሻና የድልድይ ሥራዎች የፕሮጀክቱ ልዩ ገጽታ በመሆን ተከናውነዋል። በፕሮጀክቱ ድልድዮች፣ ወንዝን ለማሻገር ብቻ ሳይሆን ተራራን ከተራራ ጋር ለማገናኘትም ተገንብተዋል። ይህ ሲደረግም እስከ 53 ሜትር የሚረዝሙ ድልድዩን የሚሸከሙ ምሰሶዎች ተገንብተዋል። የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ ድልድዮቹና ዋሻዎቹ በርካታ ቴክኖሎጅዎችን በማጠናቀር የተገነቡ ናቸው ያሉት ኢንጅነር አብዱልከሪም፤ በተለይ ካራቆሬ አካባቢ የተገነቡት ድልድዮች በአካባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ ይነሳል ተብሎ ስለሚታሰብ፣ በአሰራር፣ በባሕሪና በቴክኖሎጅ አጠቃቀምም ከፍተኛና ልዩ ክህሎት የታከለባቸው ናቸው ብለዋል። ፕሮጀክቱ 12 ዋሻዎችን ያካተተ ሲሆን ረዥሙ የሚገኘው ከፕሮጅክቱ መዳረሻ ሃራ ገበያ [ወልዲያ] ትንሽ ቀደም ብሎ ነው። 2 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። በአጠቃላይ የአስራ ሁለቱም ዋሻዎች ርዝመት ሲደመር ደግሞ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነ ኢንጅነር አብዱልከሪም ገልጸዋል። ይህም አካባቢው ምን ያክል ለባቡር መንገድ ግንባታ አስቸጋሪ እንደነበርና የታለፈበት ሂደት ውስብስብ መሆኑን የሚያሳይ ነውም ብለዋል። የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ በተለይ ከ1.5 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ዋሻዎች ልዩ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ታክሎባቸው የተሰሩ መሆናቸውን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ በአጋጣሚ በእነዚህ ዋሻዎች ውስጥ ባቡሩ ብልሽት ቢገጥመው ሰዎች ራሳቸውን ማዳን የሚችሉባቸው ሌሎች የተለዩ ዋሻዎች በዋናው ዋሻ ውስጥ እንደተሰሩ አብራርተዋል። በፕሮጀክቱ ከ70 በላይ ድልድዮች ተገንብተዋል። በአጠቃላይ ከ6 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝሙ ናቸው። ትልቁ የግንባታው ድልድይ ካራቆሬ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፤ 1 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። ድልድዩ የተሰራበት ምሰሶ ከፍታም 53 ሜትር የሚረዝም ነው። ፕሮጀክቱን በበላይነት ኮንትራት ወስዶ የሚያከናውነው ያፒ መርከዚ የተባለ የቱርክ ኩባንያ ነው። ኢትዮጵያውያን ንዑስ ተቋራጮች እና ሞያተኞችም በግንባታው ተሳታፊ ናቸው። በፕሮጀክቱ ከ6 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ሞያተኞች በተለያዩ ጊዜዎችና የሥራ ዘርፎች ተሳትፈዋል የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ በተለይ በባቡር ምህንድስና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተማሩ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ሙያዊና ቴክኒካዊ በሆኑ ጉዳዮች መሳተፋቸውን የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ፤ ከፍተኛ ልምድ የቀሰሙበት ሂደት ስለነበር ነገ ኢትዮጵያ በራሷ ተመሳሳይ ፕሮጀክት መገንባት ብትጀምር እነዚህ ሞያተኞች ከፍተኛውን ድርሻ ለመወጣት የሚያስችል ክህሎት አዳብረዋል ብለዋል። የፕሮጀክቱ መጓተት. . . ምዕራፍ አንድ በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቁን ሥራ አስኪያጁ ይናገራሉ። ነገር ግን የኃይል አቅርቦት ስላልተሟላ አገልግሎት መስጠት አልጀመረም። በፈረንጆቹ 2012 የመጀመሪያው ኮንትራት ሲፈረም በጀቱ ወዲያው የሚገኝ ከሆነ ሙሉ ፕሮጀክቱ [392 ኪ/ሜ] በ42 ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ ኮንትራት ተፈርሞ ነበር። ነገር ግን የምዕራፍ ሁለት በጀቱ በወቅቱ ባለመገኘቱ ምክንያት የጊዜ ገደቡ እንደገና ተከልሶ በ72 ወራት ለማጠናቀቅ እቅድ ተቀምጦለታል። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆናቸውን የሚገልጹት ኢንጅነር አብዱልከሪም፤ እንዲያም ሆኖ የኃይል አቅርቦት በጊዜው ስለመሟላቱ እርግጠኛ አይደሉም። "ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ኃይል እንዲለቀቅ ጥያቄ አቅርበን ነበር" የሚሉት ኢንጅነር አብዱልከሪም፤ በተለይ የምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ከተጠናቀቀ አንድ ዓመት ስላለፈው "በተደጋጋሚ ጥያቄውን አቅርበናል፤ የባለቤትነት ችግር ነበር" ብለዋል። የኃይል አቅርቦቱን ማን ያቅርብ? የሚለው ኃላፊነት የተሰጠው አካል አልነበረም፤ በመሆኑም ከብዙ ውይይት በኋላ መንግሥት ጣልቃ በመግባት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃይል እንዲያቀርብ ውሳኔ አስተላልፏል። በዚሁ መሰረትም ኃይል ለማቅረብ ኮንትራት ተሰጥቷል። በቅርቡ ኃይል ሲቀርብ የባቡር አገልግሎቱ ወዲያውኑ ይጀመራል ብለዋል ሥራ አስኪያጁ። የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ የዋሻ ሥራውን አቁሙ. . . ፕሮጀክቱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች ከባቡር ግንባታው ባሻገር ሌሎች የተለያዩ ሥራዎች ይካሄዳሉ። በፕሮጀክቱ ምክንያት በተለይ ማሳቸው ከ25 በመቶ በላይ የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች የተሰጣቸውን ካሳ ወደ አዋጭ ቢዝነስ እንዲቀይሩ ስልጠና መስጠታቸውን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል። በፕሮጀክቱ የተሠሩ 400 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ የማሳለጫ መንገዶች እና በከተማ ውስጥ የተሠሩ 70 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በመሥራት ለማሕበረሱቡ ማስረከባቸውንም ተናግረዋል። በፕሮጀክቱ የሥራ ጉዞ ተሁለደሬ ላይ ተቢሳ የምትባል ቀበሌ ውስጥ የማይረሱት ገጠመኝ ማስተናገዳቸውን ኢንጅነር አብዱልከሪም ያስታውሳሉ። በአካባቢው የዋሻ ቁፋሮ ሥራ ያከናውናሉ። ዋሻው 1.9 ኪሎ ሜትር ይረዝማል። አካባቢው ከፍተኛ የውሃ ችግር ያለበት በመሆኑ ለፕሮጀክቱ ሠራተኞች ውሃ የሚመጣው ከሌላ ቦታ ነበር። በውሃ እጥረት ምክንያትም ግማሹ ነዋሪ አካባቢውን ለቆ ወደ ሌላ ቦታ የሚሄድበት ቀሪው ደግሞ እስከ 10 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ውሃ የሚያመጣበት አካባቢ ነው ይላሉ ሥራ አስኪያጁ። የዋሻ ቁፋሮ በሚሠራበት ወቅት ግን ያልተጠበቀ ነገር ተፈጠረ፤ ውሃ መፍሰስ ጀመረ። ይህንን ተከትሎም ትልቅ የውሃ ጋን እንዳለ ተረዳን ያሉት ኢንጅነሩ "ተጨማሪ ጥናቶችን አካሂደን ውሃውን በማውጣት ስንለቀው፣ ሕብረተሰቡ ላይ የተፈጠረው ደስታ ልዩ ነበር" ይላሉ። ነገር ግን ሕብረተሰቡ ውሃውን ከተመለከተ በኋላ ያልተጠበቀ ምላሽ ሰጠ፤ "የዋሻ ሥራውን አቁሙልን ውሃችንን ያጠፋብናል" የሚል ነበር። ውሃው የማይቆም መሆኑን በማስረዳት ከነዋሪው ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ውሃውም እንዲወጣ ዋሻውም እንዲገነባ በመስማማት ሥራው ቀጠለ። አሁን የዋሻ ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። የአካባቢው ነዋሪም ለዘመናት ችግር ሆኖበት የነበረው የውሃ አቅርቦት በዋሻ ግንባታው ሳቢያ እንደተቀረፈለት ሥራ አስኪያጁ ገልጸውልናል። ከጀማሪ ሲቪል መሃንዲስ ወደ የባቡር ፕሮጀክት ሃላፊ. . . ኢንጅነር አብዱልከሪም ሞሐመድ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የተመረቁት በሲቪል ምህንድስና ነው። ሥራ የጀመሩት ደግሞ በአማራ ትራንስፖርት ባለስልጣን ውስጥ ነበር። የመጀመሪያ ሥራቸው ከመተማ ገለጎ [ቋራ] በሚሰራው የጠጠር መንገድ ግንባታ ላይ በመሃንዲስነት ነበር። በዚሁ የምህንድስና ሙያ ለተወሰነ ጊዜ ካገለገሉ በኋላ የፕሮጀክቱ ማናጀር መሆናቸውን ይገልጻሉ። ኢ/ር አብዱልከሪም ሞሐመድ ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ወደ ወሎ ገጠር መንገድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሃላፊነት ተመድበው ሠርተዋል። የተወሰነ ከሠሩ በኋላ ወደ ባህር ዳር በመመለስ የአማራ ክልል መንገዶች ባላስልጣን ምክትል ሃላፊ ሆነው አገልግለዋል። በሥራ ዘመናቸው በተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳታፊ ነበሩ። በመጨረሻም የክልሉ መንግሥት በሰጣቸው ሃላፊነት መሰረት "የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት" የተባለ ተቋም መስርተዋል። በ2003 ዓ. ም የኢትዮጵያ መንግሥት በቀጣይ ለሚገነቡ የባቡር መንገዶች ትልቅ ሚና የሚጫወቱ መሃንዲሶችን ወደ ውጭ አገር ልኮ ለማሰልጠን ምልመላ አካሄደ። በብዙ የመንገድ ሥራዎች ላይ አሻራቸውን ያሳለፉት ኢንጅነር አብዱልከሪም ከተመረጡት 18 መሃንዲሶች መካከል አንዱ በመሆን ወደ ሩሲያ፣ ሴይንት ፒተርስበርግ ትራንስፖርት ዩኒቨርሲቲ ተልከው ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በባቡር ምህንድስና ለሦስት ዓመታት ተከታትለው ተመልሰዋል። በፈረንጆቹ 2014 የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ የባቡር መንገድ ፕሮጀክት ሥራ ሲጀመር ፕሮጀክቱን በሃላፊነት እንዲመሩ ተመደቡ። ሃላፊነቱን ሲረከቡ ሦስት ነገሮችን ለማሳካት አቅደው እንደነበር ያስታውሳሉ። ፕሮጀክቱን በሚፈለገው ጥራት ማከናወን፣ በተያዘለት በጀት ማጠናቀቅና በታቀደው ጊዜ ፕሮጀክቱን ለፍጻሜ ማብቃት። ከእነዚህ እቅዶች መካከል የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ሙሉ በሙሉ የተሳኩ መሆናቸውን የሚገልጹት ኢንጂነር አብዱልከሪም፤ በተለያዩ ምክንያቶች የፕሮጀክቱ መጠናቀቂያ ጊዜ ግን መራዘሙን ይናገራሉ። የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ የባቡር መንገዱ ሥራ ሲጀምር. . . ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የባቡር መንገዱ 26 ባቡሮችን ያስተናግዳል። 20ዎቹ ባቡሮች የእቃ ማጓጓዣዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ስድስቱ ደግሞ የሰው ማጓጓዣዎች ናቸው። ሁሉም ባቡሮች በቀን ቢሰሩ ከ4300 በላይ ሰዎችን ከአዲስ አበባ ወይም ከወልዲያ ጂቡቲ ማመላለስ ይችላሉ። አንድ ባቡር እስከ 1 ሺህ 350 ቶን የመጫን አቅም አለው። በቀን ሁሉም ባቡሮች ሥራ ላይ ቢውሉ እስከ 27 ሺህ ቶን እቃ ማጓጓዝ ይችላሉ። በአጭር ሰዓትና በአንድ ጊዜ ወደቦች ላይ የሚገኙ እቃዎችን የማንሳትና ወደ ወደቦች የማድረስ ሥራን ያሳልጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የባቡር ፕሮጀክቱ ከአዋሽ እስከ ሃራ ገበያ [ወልዲያ] ባለው የ392 ኪሎ ሜትር ርዝመት ውስጥ 4 ዋና እና 6 ንዑስ ጣቢያዎች አሉት። አዋሽ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ኮምቦልቻ እና ሃራ ገበያ ያሉት ዋና ጣቢያዎቹ ናቸው። ከእዚህ በተጨማሪ የባቡር ብልሽት ቢያጋጥም ጥገና የሚደረግበት በአንድ ጊዜ ብቻ ስምንት ባቡሮችን መጠገን የሚችል ጋራጅ ኮምቦልቻ ላይ ተገንብቷል። የአዋሽ ወልዲያ የባቡር መንገድ በቀጣይ የኢትዮጵያ መንግሥት ተጨማሪ የባቡር መንገድ ፕሮጀክቶችን ሲሰራም ይህ ፕሮጀክት መነሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ከታጁራ ወደብ ይነሳል ተብሎ የሚጠበቀው የባቡር መንገድ ግንባታ መዳረሻው ሃራ ገበያ ነው። በጥናት ላይ ያለው ከወልዲያ ወረታ፣ ከወረታ መተማ የባቡር መንገድም የዚሁ የባቡር መንገድ አካል ነው።