id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-44242221
https://www.bbc.com/amharic/news-44242221
ጤፍን ሰዳ የምታሳድደው ኢትዮጵያ
መንግሥት ውልደቱም እድገቱም ኢትዮጵያ በሆነው ጤፍ ላይ በአምስት የአውሮፓ ሃገራት የባለቤትነት መብት ያስመዘገበው የኔዘርላንድ ኩባንያ ላይ በዓለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት ክስ ሊመሰርት እንደሆነ አስታውቋል።
መንግሥት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከኩባንያው ጋር ያለውን ጉዳይ ለመፍታት ያደረጋቸው ጥረቶች ሊሳኩ ባለመቻላቸው መሆኑንም ገልጿል። ውሳኔውን ተከትሎ መንግሥት ክስ በመመስረት የሚጠብቀው ውጤት ምንድን ነው? ከሃገሪቱ የገንዘብና የቴክኒክ አቅም ማለትም ከዓለም አቀፍ ግልግል ዳኝነት ልምድ አንፃር ኢትዮጵያ ይሳካላታል ወይ? የሚሉና መሰል ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ጤፍ እንዴት ከኢትዮጵያ እጅ ወጣ? እንደ አውሮፓውያኑ 2004 ላይ የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲቲዩትና የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ሄልዝ ኤንድ ፐርፎርማንስ ፉድ ኢንተርናሽናል(HPFI) ከተባለ የኔዘርላንድ ኩባንያ ጋር ስምምነት ያደርጋሉ። ስምምነቱ የኔዘርላንዱ ኩባንያ የተለያዩ የጤፍ ዝርያዎችን በመጠቀም ከጤፍ ኬክ ኩኪስና ሌሎችም መሰል ምግቦችን በማምረት ለገበያ እንዲያቀርብና ትርፉን ለኢትዮጵያ እንዲያጋራ እንዲሁም በየጊዜው ለኢትዮጵያ የባለቤትነት መብት ክፍያ እንዲከፍል ነበር። በጤፍ የባለቤትነት መብት ላይ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የጤፍ ዝርያዎች እንዲሁም ከጤፍ አመራረት ጋር የተያያዙ ባህላዊ እውቀቶች ባለቤትነት የኢትዮጵያ ጤፍ አምራቾች ሆኖ እንደሚቀጥል ስምምነቱ ያስቀምጣል። በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ ከተወሰዱት የጤፍ ዘሮች የሚፈጠሩ አዳዲስ ዝርያዎች ባለቤትነት ደግሞ የኢትዮጵያና የኔዘርላንዱ ኩባንያ እንደሚሆን በስምምነቱ ተመልክቷል። ነገር ግን ከዚህ በኋላ ኩባንያው ስምምነቱን በሚፃረር መልኩ መንቀሳቀስ ጀመረ፤ በመቀጠልም ሙሉ በሙሉ ከሚመለከተው የኢትዮጵያ የመንግሥት ተቋም ጋር የነበረውን ግንኙነት አቋረጠ። በማስከተልም መጀመሪያ በኔዘርላንድ ከዚያም በጣሊያን፣ እንግሊዝ፣ ኦስትሪያና ጀርመን የጤፍ ምርት ባለቤትነት መብት ወሰደ። በመጨረሻ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ያደረገው ኩባንያ (HPFI) መክሰሩን አሳውቆ ሲዘጋ በጤፍ ውጤቶች ላያ ያገኘውን የባለቤትነት መብት Vennootschap Onder Firma(VOF)ለተባለ ሌላ ድርጅት አስተላለፈ። በዚህ መልኩ ከኢትዮጵያ እጅ የወጣውን የጤፍ ዱቄት አዘገጃጀት የባለቤትነት መብት ለማስመለስ ለረዥም ጊዜያት የተደረገው ድርድርና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሳይሳካ መቅረቱን ከጥቂት ቀናት በፊት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ጌታሁን መኩሪያ ለተወካዮች ምክር ቤት ገልፀዋል። ስለዚህም መብቱን ለማስመለስ ብቸኛው አማራጭ ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ የፍትህ ተቋም መውሰድና የኔዘርላንዱን ኩባንያ መክሰስ እንደሆነ፤ ይህን ለማድረግም እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ማንን? የት ነው የምትከሰው? በአፍሪካ ዓለም አቀፍ ግልግል ዳኝነት አማካሪ የሆነችው ወ/ት ልዩ ታምሩ መንግሥት ይህን ጉዳይ በዓለም አቀፍ ግልግል ዳኝነት እወጣዋለሁ ካለ ሁለት ነገሮችን ማጤን ያስፈልጋል ትላለች። የመጀመሪያው ጥያቄ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ያደረገው ኩባንያ አሁን ሥራ ላይ ካለመሆኑ ጋር የሚገናኝ ነው። "ስለ ክሱ ዜና ላይ እንደተመለከተው መንግሥት ክሱን የሚመሰርተው መቀመጫውን ፓሪስ ባደረገው በዓለም አቀፉ የግልግል ዳኝነት ማዕከል ነው። እዚህ ቦታ ላይ ሄዶ የሚከስ ከሆነ ደግሞ መክሰስ የሚችለው በውሉ ላይ ስምምነት ያደረገውን ኩባንያ ነው። ያ ኩባንያ ደግሞ በኪሳራ ተዘግቷል። እዚህ ጋር አንድ ትልቅ ችግር ይነሳል" ትላለች ልዩ። የተዘጋና የሌለን ኩባንያ እከሳለሁ ማለት አስቸጋሪ እንደሆነ ትገልፃለች። በሁለተኛነት የምታነሳው ደግሞ መንግሥት ጉዳዩን በዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት እጨርሰዋለው ሲል የግልግል ዳኝነት ተቋሙ ተግባርና ስልጣንን ታሳቢ አድርጎ ነው ወይ? የሚለውን ጥያቄ ነው። ልዩ እንደምትለው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት መብት ያለው፤ ጉዳትን የመመልከትና የማስላት ነው። የባለቤትነት መብትን የመንጠቅ ስልጣን የለውም። የኢትዮጵያ መንግሥት ማድረግ ያለበት የጤፍ ባለቤትነት መብትን ማስመለስ ከሆነ ነገሩ የባለቤትነት መብቱን የሰጠው ማነው? ወደ ሚለው ያመራል። ለኔዘርላንዱ ኩባንያ የጤፍ ባለቤትነት መብቱን የሰጠው ደግሞ የአውሮፓ አእምሯዊ ንብረት ጥበቃ (EPO) ነው። የሚያዋጣው ይህ ተቋም በምን አግባብ ለኩባንያው መብቱን ሰጠው የሚለው ላይ አትኩሮ በዚህ አቅጣጫ መሄድ እንደሆነ ታስረዳለች። የኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃ ከመጀመሩ በፊት እነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ ሊያስብበት ይገባል ትላለች። ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ተሞክሮና አሁን በአገሪቱ ካለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አንፃርም ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቀው ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነትን መምረጥ በቀላሉ ሊታይ እንደማይገባም ታስረዳለች። "ምንም እንኳ ኢትዮጵያዊያን ያሉበትን የጥብቅና ድርጅት መንግሥት ተጠቅሞ ቢያውቅም አብዛኛውን ጊዜ የውጭ ሃገር ሰዎችን ነው የሚጠቀመው" የምትለው ልዩ አሁን ግን መንግሥት ስለ ጤፍ ምንነት የሚያውቅ፣ ስለ አእምሯዊ ንብረት ጥበቃና መብት የግልግል ዳኝነትም እውቀት ያለው ኢትዮጵያዊ የህግ ባለሙያን በጉዳዩ ሊያሳትፍ ግድ ነው የሚል አቋም አላት። የኢትዮጵያ የማሸነፍ እድል ምን ያህል ነው? መንግሥት ክስ ሊመሰርት ስላቀደበት ስትራቴጂ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም፤ በዚህ ነገር ውስጥ ኢትዮጵያ ሦስት ጉዳዩች አሏት ይላሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብሩክ ኃይሌ። የመጀመሪያው ባደረጉት ስምምነት መሰረት በኔዘርላንዱ ኩባንያ ሊከፈላት ይገባ የነበረው ገንዘብ ለኢትዮጵያ አለመከፈሉ። ሁለተኛው በጤፍ አዘገጃጀት ላይ የተገኘው የባለቤትነት መብት ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ ኩባንያው ያገኘው አዲስ የጤፍ ዝርያ ላይ የወሰደው የባለቤትነት መብት ናቸው። ኢትዮጵያ በውሉ መሰረት ከኔዘርላንዱ ኩባንያ ማግኘት የነበረባት ገንዘብ እንዲሁም የምርምር ድጋፍ ጉዳይን ሲያስቡት ነገሩ ሰዶ ማሳደድ እንደሚሆን ዶ/ር ብሩክ ይናገራሉ። "ጤፋችንን ስንልክ ቀድመን ክፍያውን መቀበል እንችል ነበር። ይህ ለምን እንዳልተደረገ አላውቅም። ውሉን ስንገባ ማግኘት ያለብንን የገንዘብ ጥቅም ቀድመን እንድናገኝ መደረግ፤ ኩባንያው የሚያሲዘው ዋስትናም መኖር ነበረበት" ይላሉ። የሚገባንን ክፍያ አላገኘንም ከተባለ እሳቸውም ከኢትዮጵያ ጋር ውል የገባው ኩባንያ በኪሳራ የተዘጋ መሆኑም የክስ ሂደቱን እንደሚያከብደው ይሰማቸዋል። እሳቸው እንደሚሉት ኩባንያው በኪሳራ የተዘጋበትና የባለቤትነት መብቱን ለሁለተኛው ኩባንያ ያስተላለፈበት መንገድ የኔዘርላንድን የኪሳራ ህግ ያልተከተለ ነው የሚል ነገር ላይ ካልተደረሰ በቀር በዚህ ረገድ ያለው ተስፋ የመነመነ ነው። የሚያስኬድ የሚመስላቸው ነገር በጤፍ አዘገጃጀት (እንደ ጤፍ ኬክና ኩኪስ ዝግጅት) ላይ ኩባንያው ያገኘው የባለቤትነት መብትን ማስመለስ ነው። ምክንያቱም ይህ እውቀት በሰፊው የኢትዮጵያ ጤፍ አምራች ዘንድ የሚታወቅ ነውና። በተጨማሪም በጣልያን፣ በእንግሊዝም ሆነ በኔዘርላንድ ህግ የባለቤትነት መብት ለመስጠት አንድ ነገር አዲስ ፈጠራ አዲስ እውቀት መሆን ስለሚገባው ከዚህ የህግ አግባብ ተነስቶ ነገሩን አጠንክሮ መያዝ ይቻላል ብለው ያምናሉ ዶ/ር ብሩክ። "የጤፍ አዘገጃጀት ነባር የአገር ውስጥ እውቀት መሆኑን በማስረጃ በማስረገጥ ኩባንያው የጤፍ ዱቄት አዘገጃጀት ላይ ያገኘውን የባለቤትነት መብት ውድቅ ማስደረግ የሚቻል ይመስለኛል"ሲሉ ያክላሉ። ይህን የባለቤትነት መብት ውድቅ ብታስደርግ ኢትዮጵያ ምን ታገኛለች? ዶ/ር ብሩክ እንደሚሉት የባለቤትነት መብቱን ከኔዘርላንዱ ኩባንያ ብታስነጥቅም ኢትዮጵያ በቀጥታ የምታገኘው የገንዘብ ጥቅም አይኖርም። ምክንያቱም ነባርና የቆየ እውቀት ነው ከተባለ ኢትዮጵያም ዳግም አዲስ ነው ብላ ልታስመዘግብና የባለቤትነት መብት ልትወስድበት አትችልም። "ከኢትዮጵያ የወሰዱትን ዘር በመጠቀም ምርምር አካሂደው ያገኙት አዲስ ጤፍ የባለቤትነት መብትን በማስነጠቅ በኩልም የሚሳካልን አይመስለኝም። ምክንያቱም በአውሮፓ ህግ መሰረት በዚህ አይነት ምርምሮች የሚገኙ አዳዲስ ዘሮች ጥበቃ አያገኙም የሚል ነገር የለምና" ይላሉ። በዚህ ረገድ በብዝሃ ህይወት ዙሪያ የዓለም አቀፍ ህግ ደካማ መሆንና ሃገራት ዓለም አቀፍ ግዴታ የሌለባቸው መሆኑ ኢትዮጵያን ተጋላጭ እንዳደረጋት ያስረዳሉ። በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት የግልግል ዳኝነት ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮሃንስ ወልደ ገብርኤልም የጤፍን የባለቤትነት መብት በማስመለስ ኢትዮጵያ ተስፋ የላትም ሲሉ ይደመድማሉ። ምክንያታቸው ግን ከሌሎቹ አስተያየት ሰጪዎች ለየት ያለ ነው። "እንኳን እንዲህ ያለ የተወሳሰበና ትልቅ አቅም የሚጠይቅ ክስ ቀርቶ፤ ተራ ጉዳዮችን እንኳ በሚገባ መመልከት የማይችል አቃቤ ህግ ባለበት ይህ ክስ ዘበት ነው" በማለት የኢትዮጵያ የኔዘርላንድ ኩባንያን እከሳሁ ማለቷን የሚገልፀውን ዜና እንደ ቀልድ እንደተመለከቱት ይናገራሉ። በጤፍ ይብቃ ረዘም ላሉ ዓመታት በስዊዘርላን በርን ዩኒቨርሲቲ በጤፍ ላይ ምርምር እያደረጉ የሚገኙት ዶ/ር ዘሪሁን ታደለ ከሁለት ዓመታት በፊት የኔዘርላንዱን ኩባንያ በመቃወም ከአሜሪካ ጀምሮ የሚመለከታቸው ሁሉ ፊርማ ሲያሰባስቡ እንደነበርና በዚህ እሳቸውም መሳተፋቸውን ያስታውሳሉ። እሳቸው እንደሚሉት ብዙ ጊዜ እንደዚህ ያለ የባለቤትነት መብት ማጣት ችግር ውስጥ የሚገባው ከትምህርት ተቋማት ሳይሆን ከግል ኩባንያዎችና መንግሥታዊ ካልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ሲገባ ነው ይላሉ። በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የእህል ዘሮችን ለመጠበቅ የሚያስችል ሥራ ለመስራት ጅምሮች መኖራቸውን "እርሻ ምርምር ከሚገኙ የሥራ ባልደረቦቼ ጋር በመሆን ልክ ዲኤንኤ ሰዎችን እንደሚገልፅ ሁሉ የእህል ዘሮችን በዚሁ መንገድ ወደ ኋላ ሄዶ መለየት የሚያስችል ይሆናል ስራው" በማለት እየተደረጉ ያሉትን ጥረቶች አመልክተዋል።
news-48325658
https://www.bbc.com/amharic/news-48325658
በባህር ዳር የእምቦጭ አረምን የሚያጠፉት ጢንዚዛዎች አልጠፉም
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ 'ዊቭል' የተባለ የጥንዚዛ ዓይነት ማራቢያ ይገኛል። ማራቢያው ጢንዚዛዎቹ የሚፈልጉትን ሙቀት የሚሰጥ ማሞቂያ እና ለምግብነት እና ለመራቢያ የሚያስፈልጋቸውን እንቦጭ አረም ይዟል።
ማራቢያው በቀላሉ ከሚበሰብስ ጨርቅ ነው የተሰራው። ከቆይታ ብዛትም ጣሪያው በአንድ በኩል ተቀዶ ነበር። የጣሪያው መቀደድ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ስጋት የሚያጭሩ መረጃዎች እንዲወጡ ምክንያት ሆኗል። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ጌታቸው በነበሩ "በማህበራዊ ሚዲያ የተባለው ከእውነት የራቀ ነው፤ የክልሉን፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲንና የአካባቢ ጥበቃን ገጽታ ለማበላሸት ብቻ ሳይሆን ከኋላም ድብቅ አጀንዳ ያለው ነው፤ እምቦጩ እንዳይጠፋ የሚፈልግ ሰው አለ ወይንም የራሱ የሆነ ትርፍ ለማግኘት ያለመ ሰው አለ" ሲሉም የተሰራጨው መረጃ አሉቧልታ እንደሆነ ያረጋግጣሉ። ፕሮፌሰሩ አክለውም "የዊቭሎቹን (ጢንዚዛዎቹ) ባህሪ ስለማውቅ፤ የእኔ ፍራቻ የነበረው ጦጣዎች ወደ ቦታው ገብተው ማራቢያውን እንዳያበላሹት ነው" ይላሉ። በአማራ ክልል የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በልስቲ ፈጠነም "ሲወጣ የነበረው መረጃ ሀሰተኛ ሲሆን የሚያሳየውም በቦታው ላይ ያለውን ሀቅ አይደለም" ሲሉ የፕሮፌሰሩን ሃሳብ ይጋራሉ። በማህበራዊ ሚዲያ 600 የሚሆኑ ጢንዚዛዎች ከኡጋንዳ በዶላር ተገዝተው መምጣታቸው መገለፁን ያነሳንላቸው ዶ/ር ጌታቸው "ስህተቱ የሚጀመርው ከዚህ ነው" ብለዋል። • የጣና ሐይቅን ሌሎችም አረሞች ያሰጉታል • እምቦጭ የጣና ቂርቆስ መነኮሳትን ከገዳሙ እያስለቀቀ ነው • የቦይንግ 737 ማክስ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? እርሳቸው እንደሚሉት ጢንዚዛዎቹ ከሁለት ዓመት በፊት የመጡት ከወንጂ ስኳር ፋብሪካ የምርምር ተቋም ሲሆን ያመጣቸውም በተቋሙ ለሦስተኛ ዲግሪ ማሟያ ምርምር የሚያደርግ ግለሰብ ነው። ግለሰቡ ምርምሩን ማጠናቀቁን ተከትሎ ፋብሪካው 150 ዊቭሎችን እንደሰጧቸው ይገልጻሉ። "የጸሐይ ብርሃን አይወዱም፤ በዚህም ምክንያት ሌሊት ነው ያጓጓዝናቸው" ይላሉ በወቅቱ ስለነበረው ሲያስታውሱ። በወቅቱም ከጉዞው ይልቅ አስቸጋሪው ሥራ ጢንዚዛዎቹን አዲስ አካባቢ ማላመድ ነበር። በመሆኑም የተለየ አካባቢ ስለሆነባቸው የተወሰኑት ሞተው ነበር። ከሰባት ወራት በፊት በተደረገ ቆጠራም ቁጥራቸው ከሁለት ሺህ በላይ የነበረ ሲሆን አሁን ቁጥሩ እንደሚጨምር ይገምታሉ።ዶ/ር ጌታቸው ጢንዚዛዎቹ መራቢያ ሥፍራቸውን ሙሉ ለሙሉ ለቀው ወጥተዋል የሚባለውም ከእውነት ስለመራቁ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ። ዊቭልሶች መብረር የማይችሉ ከመሆኑም በላይ የሚንቀሳቀሱትም በሌሊት መሆኑ፤ ተንቀሳቀሱ ከተባለም በጣም ጥቂት ሜትር መጓዛቸውና የሚኖሩት የእንቦጭ አረም ባለበት አካባቢ በመሆኑ ለመንቀሳቀስ የውሃ ግፊትን መጠቀማቸው አንደኛው ምክንያታቸው ሲሆን፤ የተከፈተው ጣሪያ ትንሽ ከመሆኑም በላይ በአፋጣኝ ጥገና መደረጉንና በዘላቂነት ለማሰራትም ከአካባቢ ጥበቃ ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ሌላኛው ምክንያታቸው እንደሆነ ገልፀዋል። አቶ በልስቲም በበኩላቸው "ጣሪያው ባይኖርም አይሄዱም፤ ያለ እንቦጭ መኖር አይችሉም፤ በማህበራዊ ሚዲያ የተጻፈው እና ሳይንሱ አይገናኙም" ሲሉ የባለሙያውን ሃሳብ ይደግፋሉ። ዶ/ር ጌታቸው በነበሩ ባለሙያው እንደገለፁልን ከ20 ዓመት በፊት ኡጋንዳ ውስጥ እምቦጭ ተከስቶ ነበር። ይህንን ለመቆጣጠርም የተለያዩ ዘዴዎችን ተግባራዊ አድርገዋል። ከተለያዩ ሙከራዎች በኋላ ዊቭልስን ተጠቅመው ውጤታማ ሆነዋል። ታዲያ ይህንኑ ልምድ ለመቅሰም አምስት ባለሙያዎች ወደ ኡጋንዳ ማቅናታቸውን አውስተው ከዚህ ውጭ በተደጋጋሚ የተደረገ የውጭ ጉዞ አለመኖሩን ዶ/ር ጌታቸው ተናግረዋል። ዊቭልሶቹ ከማራቢያው ቢወጡ በአካባቢው ዕጽዋት ላይ ምን ዓይነት ጉዳት ያስከትላሉ ያልናቸው ባለሙያው "በተለያዩ ወቅቶች የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፤ ነፍሳቱ ወይንም ጢንዚዛው መኖር የሚችለው እንቦጭ ላይ ብቻ ነው" ሲሉ መልሰዋል። በመሆኑም ነፍሳቱ ወደ አርሶ አደሮች ሰብሎች ወይንም ወደ ሌሎች እጽዋት በመሄድ ጉዳት አያደርሱም። "ወደ ሐይቁ ሲገቡ በዚያ አካባቢ ተክሎች ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ለማወቅም ወደ 10 የሚደርሱ ተክሎች ላይ ሙከራ አድርገናል፤ ሸንኮራ አገዳ፣ ጫት፣ ሙዝ፣ ባቄላ እና ሩዝ ላይ ሞክረን ምንም ተጽዕኖ የላቸውም" ሲሉ ዶ/ር ጌታቸው ያብራራሉ። እርሳቸው እንደሚሉት ነፍሳቱ ተክሎቹ ላይ ቢያርፉ እንኳን የመሞት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ተክሎቹን ቢመገቡም እንቁላል መጣል ስለማይችሉ አይራቡም። በመሆኑም ኬሚካልም ሆነ ሌላ ነገር መጠቀም ሳያስፈልግ የሕይወት ዑደታቸው ይቋረጣል። እምቦጭን ለማጥፋት ሦስት ዘዴዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ። የሰው ወይንም የማሽን ጉልበት፤ እንደማንኛውም አረም ኬሚካልን፣ ወይም ሥነ ሕይወታዊ ዘዴን በማስፋፋት ነው። በተለይ በጣና ሐይቅ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሰው እና የማሽን ጉልበት በስፋት ሥራ ላይ ውሏል። ከችግሩ ስፋት አንጻር ውጤቱ ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። "ከሌሎች አረሙን የማጥፊያ ዘዴዎች በተጨማሪ ሥነ ሕይወታዊ ዘዴ ብንጠቀም፤ እምቦጭ የመቆጣጠር እና የመከላከል ሥራ ላይ በአዎንታዊ መልኩ የሚያግዝ ውጤት ይኖረዋል" ይላሉ አቶ በልስቲ።ባለፉት ወራት ጢንዚዛው በማራቢያው ውስጥ እንቦጩን በመራቢያነት ከመጠቀም ባለፈ ለምግብነት በመጠቀምም ጉዳት እያደረሰበት መሆኑን የእስካሁኑ ምርምር ውጤት አሳይቷል። ዶ/ር ጌታቸው እንዳብራሩልን የዊቭል ሕይወት ዑደት እንቁላል፣ ላርቫ፣ ፑፓ እና አደልት የሚባሉ ደረጃዎች አሉት። አደልት የሚባሉት የቅጠሉንና የግንዱን ውጫዊ ክፍል ይመገባሉ። ይህ ክፍል ተጎዳ ማለት ምግብ ማዘጋጀት ስለማይችል ይሞታል። ሴቷ ዊቭል በቀን እስከ 5 እንቁላል የእንቦጭን ግንድ ቦርቡራ ትጥላለች። ከዚያ ወደ ላርቫ ነው የሚቀየረው። በላርቫ ደረጃ ደግሞ ወደ ሁለት ወር ይቆያል። በዚህ ወቅት ላርቫው እስከ ግንዱ ድረስ በመዝለቅ ውስጣዊና ውጫዊ ጉዳት ያደርስበታል። በባህር ዳር የእምቦጭ አረምን የሚያጠፉት ጢንዚዛዎች አልጠፉም ከላይም አደልቱ ይመገበዋል፤ ላርቫው ደግሞ ከውስጥ ይበላዋል። ላርቫው ትልቁን ጉዳት ስለሚያደርስ ተመራጭ ነው። እንቁላሎቹ የሚጣሉት እንደስፖንጅ በሆነው የእንቦጩ ግንድ ውስጥ ነው። በዚህም ግንዱ ስለሚከፈት ውሃ ይገባና ክብደቱን ጨምሮ ወደ ውሃው ውስጥ ገብቶ እንዲበሰብስ ያደርገዋል። "እስካሁን በሥነምህዳሩ ላይ ተጽዕኖ የለውም፤ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲም አጥንቷል፤ በዩጋንዳ የታየውም ይህ ነው" ሲሉ አቶ በልስቲ ያክላሉ። እምቦጭ ጣና ሐይቅን ጨምሮ በሃገሪቱ የተለያዩ የውሃ ክፍሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ባለበት ወቅት ይህ ሥነ ሕይወታዊ ዘዴ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም የሚሉት ዳሬክተሩ በፍጥነት ወደ ሥራ ገብተው ኅብረተሰቡ እፎይ ይላል የሚል ግምት ነበራቸው። "ይህ ባዮሎጂካል ዘዴ ስለማይታወቅ በሚዲያው ብዙ ሰው ተሳልቆብናል፤ ይህቺ ናት ወይ እምቦጭን የምታጠፋው ተብሏል . . . " ይላሉ። ዶ/ር ጌታቸው በበኩላቸው ለልምድ ልውውጡ ኡጋንዳ አቅንተው በተመለሱ ወቅትም ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ 35 ገጽ ያለው ብሔራዊ መተግበሪያ ሰነድ እንዳዘጋጁ ነግረውናል።"የእኛ ሰው ስሜታዊ ነው፤ መጀመሪያ ትልቁም ትንሹም 'ማሽን ማሽን' ብሎ ጮኸ፤ አሁን ደግሞ የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት እኛን መደገፍ ጀምሯል" ብለዋል። "ዊቭል ለመጠቀም ፈቃድ ያስፈልጋል" የሚሉት ዶ/ር ጌታቸው። ጥያቄው ለሚመለከተው አካል የቀረበ ሲሆን ሥራው ሲጀመር ወዲያውኑ ዊቭሎችን ወደ ጣና ማጓጓዝ የለብንም ብለው እንደወሰኑ ያስረዳሉ። በመጀመሪያ በመረጧቸው አራት ቦታዎች በሚሰሩ ኩሬዎች በስፋት ማምረት እንደሚጀምሩ አክለዋል። የካቲት ላይ ሥራ ለመጀመር ቢያቅዱም በግዢ መጓተት ምክንያት እስካሁን መቆየታቸውን ገልፀው በሚቀጥለው ዓመት ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ እንደሚገቡ አቶ በልስቲ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። • የወጣቶች ዘመቻ በእምቦጭ አረም ላይ
41671070
https://www.bbc.com/amharic/41671070
"ችግርን ከመፍታት ይልቅ ጩኸት ማፈን ነው የሚቀናቸው"
ጎንደር ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ምሬቶች የሾፈሯቸው ናቸው የተባሉ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን ካስተናገደች ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ ቢያልፍም፤ ነዋሪዎቿ የሻቱትን ለውጥ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።
በከተማዋ አሁንም የብሔር ተኮር ውጥረት ምልክቶች የሚስተዋሉ ሲሆን፤ በመዝናኛ ስፍራዎች ፖለቲካዊ ይዘት እንዳላቸው የሚታመኑ ዘፈኖችን ማድመጥ እንግዳ አይደለም። ከዚህም ባሻገር ስፖርታዊ ትዕይንቶችን እና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት የሚፈጥሯቸውን አጋጣሚዎች ቅሬታዎቻቸውን ለማንፀባረቅ እንደሚጠቀሙባቸው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ወጣቶች ይገልፃሉ። የመልዕክቶቹ ፖለቲካዊ አንድምታ ብዙም የተደበቀ እንዳልሆነ የሚያወሳው የከተማዋ ነዋሪ ወንድወሰን አለባቸው*፤ ከሳምንታት በፊት የተከበረው የመስቀል በዓል ላይ ይታዩ ከነበሩ አልባሳት ላይ ከታተሙ ጥቅሶች መካከል "የፈራ ይመለስ" እና "የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም" የመሳሰሉትን እንደሚያስታውስ ይናገራል። የፀጥታ ኃይሎች አልባሳትን ለማስወለቅ ሲጥሩ መመልከቱንም ጨምሮ ይገልጻል። "ችግርን ከመፍታት ይልቅ ጩኸት ማፈን ነው የሚቀናቸው" ይላል ወንድወሰን ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። በ2008 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎንደር ተቃውሞ መቀስቀስ ሲጀምር ከሰሜናዊው አዋሳኝ የትግራይ ክልል ጋር የድንበር ጥያቄ በማንሳት እንደነበር ይታወሳል። በሐምሌ ወር መባቻ አዋሳኙ የወልቃይት አካባቢ በአማራ ክልል ስር እንዲጠቃለል ጥያቄ ለማቅረብ የተዋቀረውን ኮሚቴ አባላት በቁጥጥር ስር ለማዋል ሙከራ ተደርጎ በከሸፈበት ወቅት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከአስር በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተዘግቦ የነበር ሲሆን፤ የኮሚቴው ሊቀ መንበር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ክስ ተመስርቶባቸው እስር ላይ ይገኛሉ። ኮሎኔሉን ከመያዝ ለመታደግ ሲጥር በተኩስ ልውውጡ ወቅት ሕይወቱን ያጣ ጠባቂያቸውን በማስታወስ ወደ መቃብር ስፍራው ሲያቀኑ ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ የገቡና እንዲመለሱ የተደረጉ ሰዎችን እንደሚያውቅ ሌላኛው የከተማዋ ኗሪ አንዋር አብዱልቃድር ይናገራል። ባህረ ሰላም ሆቴል ያልተወራረደ ሒሳብ ተቃውሞውን ተከትሎ በተፈጠረው ያለመረጋጋት ጥቃት ከደረሰባቸው የንግድ ተቋማት መካከል ባሕረ ሰላም ሆቴል አሁንም እንደተሰባበረ ተዘግቶ ይገኛል። ሆቴሉ የጥቃት ሰለባ የሆነው የኮሚቴው አባላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የመጡ የደህንነት አባላት ስላረፉበት መሆኑን የስፍራው ኗሪዎች ይናገራሉ። በሆቴሉ አካባቢ በአነስተኛ የችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማራች ወጣት የሆቴሉ ባለቤቶች ከጥቃቱ በኋላ ተመልሰው መምጣታቸውን እንደማታውቅ ትናገራለች። ተቃውሞው በከረረበት ወቅት ከጥቃት ለመሸሽ በርካታ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሐብትና ንብረታቸውን ጥለው ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸው የተዘገበ ሲሆን ከመካከላቸው ጥቂቶቹ ብቻ መመለሳቸውን እንደሚያውቅ አንዋር ይናገራል። በበርበሬ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማራችው ሰናይት መኮንን* እንደምትለው በጎንደር እና በትግራይ ክልል መካከል ያለው የንግድ እንቅስቃሴ መዳከሙ ሥራዋን ክፉኛ ከማወኩም ባሻገር "ግርግሩ ብዙ ገንዘብ አሳጥቶኛል" ትላለች። ሰናይት በርበሬን ከምዕራብ ጎጃም ከገዛች በኋላ የተለያዩ እሴቶችን ጨምራ በሽሬ እና ሑመራ ለሚገኙ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ትልክ እንደነበር ትገልፃለች። "ሁሌም በንፁህ መተማመን ነበር የምንሰራው። ስልክ ደውለው የሚፈልጉትን ያህል መጠን ይነግሩኛል፤ አስጭኜ እልክላቸዋለሁ። እርሱን ሸጠው በሳምንትም በወርም ገንዘቡን ይልኩልኛል" ስትል ለቢቢሲ ታስረዳለች። በዚህም መሰረት ያለመረጋጋቱ ሲከሰት 280 ሺህ ብር የሚገመት በርበሬ ለደንበኞቿ ልካ እንደነበርና ከአንድ ዓመት የሚልቅ ጊዜ ቢያልፍም ገንዘቡን ማግኘት መቸገሯን ትናገራች። "እነርሱም ወደዚህ አይመጡ፤ እኔም ወደዚያ አልሄድ፤ በስልክ ብቻ እየወተወተኩ ነው" ትላለች። ደንበኞቿ በጎንደርና በአካባቢው ሌሎች ከተሞችም ጭምር ልዩ ልዩ የንግድ ሥራዎችን ያከናውኑ የነበረ ሲሆን፤ ያለመረጋጋቱን ተከትሎ ሥራቸውን እንደቀደመው ማከናወን ባለመቻላቸው ለኪሳራ ተዳርገው ገንዘቧን ሊልኩላት እንዳልቻሉ ገልፀውላታል። በዚህ መልኩ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብን ያጡ በተለይ በሕንፃ ሥራዎች ንግድ ላይ የተሰማሩ የሙያ አጋሮቿን እንደምታውቅ የምታስረዳው ሰናይት "እንግዲህ ከእነርሱም ወገን እንዲሁ ገንዘብም ዕቃም የቀረበት ይኖር ይሆናል" ትላለች። "ከዚህ በኋላማ መተማመኑ ጨርሶ ጠፍቷል" የምትለው ሰናይት የወትሮ የንግድ አሰራሯ እንዳከተመለት ትናገራለች። በመምህርነት ሙያ ለተሰማራው ሞገስ አብርሃ* የመተማመን መሸርሸር እጅጉን የሚያሳስብ ጠባሳ ነው። "ፖለቲካው በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ሰርጎ ጥርጣሬን የዘራ ይመስለኛል" ይላል የትግራይ ተወላጁ ሞገስ። ከተማዋ በተቃውሞና በግጭት በምትናጥበት ወቅት በቤተሰባዊ ጉዳይ ትግራይ ውስጥ የነበረው ሞገስ፤ ወደጎንደር እንዳይመለስ ከዘመዶቹ ግፊት እንደነበረበት ያስታውሳል። "ስጋታቸው ገብቶኛል፤ ነገር ግን ትዳርና ልጆች ካፈራሁበት ቦታ እንዲሁ ብድግ ብዬ አዲስ ህይወት ልመሰርት አልችልም" ሲል ለቢቢሲ ይናገራል። ያለመረጋጋቱን መስከን ተከትሎ ወደሥራው ከተመለሰ በኋላ የገጠመው የተለየ ነገር እንደሌለ የሚናገረው ሞገስ ሄደው የቀሩ የሥራ ባልደረቦች እንዳሉት ይጠቅሳል። "የትግራይ ክልል ለተፈናቃዮቹ ድጋፍ አድርጌያለሁ ቢልም [በግለሰብ] ከጥቂት ሺህ ብር በላይ የሰጠ አይመስለኝም።" ከአንድ ዓመት በኋላ የጎንደር ከተማው የባህል፣ ቱሪዝም እና ወጣቶች ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አስቻለው ወርቁ ወደ ከተማዋ ዘላቂ ሰላምን እንዲሁም ተጠቃሚነትን እንዲመለስ ለማድረግ ብዙ ሥራዎች ተከናውነዋል ይላሉ። ለወጣቶች የሥራ ዕድልን ለመፍጠርና ለከተማዋ እና ለአካባቢው ምጣኔ ሃብት የጎላ ሚና የሚጫወተውብን የቱሪዝም ዘርፍ ዳግመኛ ለማነቃቃት መሰራቱን ይገልፃሉ። "በ2009 የውጭ አገር ጎብኝዎች ቁጥር በጣም ቀንሶ የነበረ ሲሆን፤ ይህንን በማካካስ በዘርፉ ላይ የተሰማሩት የኅብረተሰብ ክፍሎች የማይጎዱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ሞክረናል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት ከ45 ሺህ በላይ የሃገር ውስጥ ጎብኝዎች ለመዝናናት፣ ለስብሰባ፣ ስፖርታዊ ትዕይንቶችን ለመታደም እንዲሁም በክብረ በዓላት ላይ ለመሳተፍ ወደ ከተማዋ አቅንተዋል። "በያዝነው ዓመት ግን ከውጭ አገር የሚመጡ ጎብኝዎች ቁጥር ከፍ ያለ ሆኗል" የሚሉት አቶ አስቻለው ከተማዋ በነሐሴና መስከረም ወራት ብቻ ከ3000 በላይ የውጭ አገር ጎብኝዎችን ማስተናገዷን ይገልፃሉ። ቁጥሩ ከዚህ እየተሻሻለ እንደሚሄድም ይጠብቃሉ። በዚህ አባባል የሆቴል ባለቤትና አስተዳዳሪው አቶ ስዩም ይግዛውም ይስማማሉ። "በአሁኑ ሰዓት ካሉን ክፍሎች መካከል ሰባ አምስት በመቶው ያህል ተይዘዋል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጎብኝዎች ቁጥር እና ተያይዞ ያለው ኢንዱስትሪ በወቅት ላይ የተመሰረተ መሆኑን የሚያስረዱት አቶ ስዩም፤ በሥራ ላይ ከቆዩባቸው ስድስት ዓመታት መካከል ያለፈውን ዓመት እጅግ ዝቅ ባለ የሥራ እንቅስቃሴ በተለየ እንደሚያስታውሱት ያወሳሉ። ለዚህም የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ ጉልህ ሚና እንዳለው ይገምታሉ። በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በርካታ ስፍራዎች ተቃውሞዎች እና ግጭቶች መቀጣጠላቸውን ተከትሎ፤ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉ የጎብኝዎች ቁጥር ለማሽቆልቆሉ በምክንያትነት ይወሳል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በመደንገጉ የተለያዩ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ ስፍራው እንዳይሄዱ መምከራቸው አልቀረም። ከዚህም ባሻገር ባለፈው ዓመት አጋማሽ በተከታታይ ያጋጠሙት የእጅ ቦንብ ፍንዳታዎች፤ የተለያዩ ሃገራት ወደ ጎንደር ለማቅናት ላሰቡ ዜጎቻቸው የጉዞ ማስጠንቀቂያ እንዲያወጡ አስገድዷቸዋል። "የጉዞ ማስጠንቀቂያዎቹ ሥራችንን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድተውታል፤ ከየሃገራቸው ለጎብኚዎች ጉዞዎችን የሚያሰናዱ አካላት ስለአካባቢው ያለውን ሁኔታ ከኤምባሲያቸው ማጥናታቸው አይቀርም" ይላሉ አቶ ስዩም። አዋጁ ያለመረጋጋቱን ቢያሰክነውም ለጥያቄዎች መልስ በመስጠት ረገድ ግን መንግሥት በቂ እርምጃዎችን እንዳልወሰደ ተንታኞች ሲያስረዱ ይደመጣሉ። ወንድወሰን ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ "ምንም የተቀየረ ነገር የለም" ባይ ነው። የከተማዋ ነዋሪ አንዋር እንደሚለው፤ ተቃውሞዎቹ ኅብረተሰቡ ያለውን ስሜት እንዲያሳይ እድል ፈጥረውለታል፤ ይሁን እንጅ "ጥያቄያችን ሳይመለስ ችግሩ ተቀርፏል ማለት ራስን ማታለል ነው።" *ስም የተቀየረ
news-55098000
https://www.bbc.com/amharic/news-55098000
ትግራይ ፡ ህወሓት ወደ ሽምቅ ተዋጊነቱ ይመለስ ይሆን?
ለሦስት አሥርታት ለሚጠጋ ጊዜ በተደላደለ ሥልጣን ላይ የነበረው ህወሓት በትግራይ ክልል ገዢ ሆኖ ሲኖር በዚያ ሁሉ የጊዜ ርዝማኔ ይህ ነው የሚባል ተቀናቃኝ አጋጥሞት አያውቅም።
ከክልሉ አልፎም በመላው ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ስንክሳር ውስጥ አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ቆይቷል። አሁን ግን ይህ እድሜ ጠገብ ፓርቲ ዳግም ወደ በረሀ ሊመለስ ይመስላል። በእርግጥ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ለዚህን ያህል ጊዜ ተጽእኖ ፈጣሪ የነበረው ፓርቲ ወደ ሽምቅ ውጊያ ይመለስ ይሆን? ዳግም ወደ በረሃ? የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ይህ እንዳይሆን ነው ፍላጎቱ። በጥቅምት 23/2013 ዓ.ም የተጀመረው የማጥቃት እርምጃ ምናልባትም የህወሓት ግብአተ መሬትን የሚፈጽም ሊሆን ይችላል። በመከላከያ የሚወሰደው እርምጃ የፓርቲውን 70 የሚሆኑ አመራሮችና ወታደራዊ መኮንኖችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚደረግ "ሕግን የማስከበር" ዘመቻ እንደሆነ መንግሥት እገለጸ ነው። ከእነዚህ ማዘዣ ከወጣባቸው ግለሰቦችና ወታደራዊ መኮንኖች መካከል 17 ዓመታት ሙሉ ትጥቅ ትግል አድርገው በ1983 ዓ.ም አዲስ አበባን የተቆጣጠሩ የፓርቲው 'አባቶች' ይገኙበታል። ያን ሁሉ ዘመን የትጥቅ ትግል መርቶ አገሪቱን የተቆጣጠረው የህወሓት ታጣቂ ቡድን ከድል በኋላ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የአገሪቱን ወታደራዊና የደኅንነት መዋቅር ተቆጣጥሮ ቆይቷል። የዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን መምጣት ግን ይህን ሁኔታ ከሥር መሠረቱ ለውጦታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ህወሓት መራሹ ሥርዓት ለሦስት አሥርታት ያህል ጨቋኝና በሙስና የተጨማለቀ ሆኖ እንደቆየ መናገር ጀመሩ። ይህንን ክስ ህወሓት አይቀበለውም። የጠ/ሚኒስትር ዐብይ መምጣትን ተከትሎ የለውጥ ኃይሉ የአገሪቱን ደኅንነት መዋቅር ቀስ በቀስ ከህወሓት መዳፍ ፈልቅቆ በእጁ ማስገባት ቻለ። በተመሳሳይ ህወሓትና ማዕከላዊ አመራሩ ወደ ትግራይ ክልል እያፈገፈገ ነበር። በማዕከላዊ መንግሥቱና በህወሓት መሀል የነበረው መቃቃር እየሰፋ መጣ። ከዚህ በኋላ የመጣው ሁነኛ ክስተት ከሳምንታት በፊት ህወሓት በክልሉ የሚኘውን የሰሜን ዕዝን አጥቅቶ መቆጣጠሩ ነበር። "ለመሞት ዝግጁ ነን" ግጭቶችን ቀድሞ በመተንበይና በመተንተን የሚታወቀው መንግሥታዊ ያልሆነው የዓለም አቀፉ ቀውስ አጥኚ ቡድን (በምህጻሩ ICG) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝን "የፌዴራል መንግሥቱ ጠንካራው ዕዝ" ሲል ይገልጸዋል። ህወሓት ሰሜን ዕዝን ከቆጣጠረ በኋላ ሮኬቶችና ሚሳኢሎችን በእጁ ማስገባት ችሏል። ይሁንና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የአየር ኃይሉ ያይላል። ተዋጊ ጄቶችና የጦር ሄሊኮፕተሮች በእጁ ያስገባ ጠንካራ መከላከያ ጦር ነው። ህወሓት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙ የተሰማው ማዕከላዊው መንግሥት በክልሉ በተናጠል ከተካሄደው ምርጫ ጋር በተያያዘ በመስተዳደሩ ላይ በጀት ዕቀባ ካደረገ በኋላ ነበር። ቀደም ሲል በትግራይ የፌዴራል መንግሥቱ ሕገ ወጥ ያለው ምርጫ ተካሂዶ ነበር። በዚህም በፌደራል መንግሥቱ ና በትግራይ ክልል መካከል አለመግባባቱ እየሰፋ መጥቶ ነበር። የፌዴራል መንግሥት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ምርጫውን አራዝሞ እያለ ትግራይ ተነጥላ ምርጫ ማካሄዷ ማዕከላዊ መንግሥቱን ደስተኛ አላደረገውም። የሕግ መተላለፍ ነውም ብሏል። የህወሓት ባለሥልጣናት በበኩላቸው የሰሜን ዕዝን የተቆጣጠርነው የፌዴራል መንግሥት ወደ ክልላችን መጥቶ ወረራ መፈጸሙ አይቀሬ እንደሆነ በመረዳታችን ነው ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በበኩላቸው በሰሜን ዕዝ ላይ ህወሓት የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ አሁን "ቀዩ መስመር ታለፈ" ብለዋል። ወታደራዊ እርምጃም በአስቸኳይ እንዲጀመርም አዘዋል። መንግሥት በህወሓት አመራሮችና በክልሉ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ ከጀመረ 22ኛ ቀን ሆኗል። ከትናንት [ሐመስ] ጀምሮ ሠራዊቱ የመጨራሻውን ሦስተኛ ምዕራፍ እርምጃ እንዲወስድም ታዟል። ይህ ወታደራዊ ኦፕሬሽን የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ ገብቶ የህወሓትን ከፍተኛ አመራሮችን በቁጥጥር ሥር ማዋልን ግብ ያደረገ ነው። ይህ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በሚቀጥሉት ቀናት ፍጻሜውን እንደሚያገኝ ማዕከላዊው መንግሥት ያምናል። ነገር ግን የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ይህ በቀናት የሚገባደድ ነው የተባለው ጥቃት የተዋጠላቸው አይመስልም። ለዜና ወኪሉ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ባለፈው ሳምንት እንደተናገሩት "እኛ የመርህ ሰዎች ነን። ክልላችንን የማስተዳደር መብታችንን ለማስጠበቅ ስንል ለመሞትም ቢሆን ዝግጁ ነን" ሲሉ ተናግረዋል። የትግራይ ተራራማ መልክአምድር የሠራዊት ብልጫ የዓለም አቀፉ የግጭቶች ምርምር ቡድን ባልደረባና የኢትዮጵያ አጥኚ የሆኑት ዊሊያም ዴቪሰን እንደሚሉት ህወሓት ከ200 ሺህ ባላይ ተዋጊ ሠራዊት ማሰባሰብ ችሏል። ይህም በየአካባቢውና ገጠሩ የሚገኙ ሚሊሻዎችን እና የልዩ ኃይል አባላትን የደመረ አሐዝ ነው። "ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ ምኅዳሩ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ በትግራይ ክልል መጠነ ሰፊ የወታደር ምልመላና ስልጠና ሲደረግ ነበር" ሲሉ አጥኚው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ በምህጻሩ አይሲጂ ተብሎ የሚጠራው የግጭቶች አጥኚ ቡድን የኢትዮጵያን ሠራዊት ግዝፈት በቁጥር ሊገምት አልፈቀደም። ነገር ግን ሮይተርስ ዜና አገልግሎት አንድ ጄንስ የሚባል የደኅንነት አሐዝ መረጃ ሰብሳቢ ቡድንን ዋቢ አድርጎ እንደጠቀሰው መከላከያ ሠራዊቱ 140 ሺህ የሚሆን የታጠቁ፣ የበቁና የነቁ ወታደሮች አሉት ይላል። ይህ ግምታዊ አሐዝ እውነትነት ካለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁጥር ከህወሓት የወታደሮች ቁጥር ያነሰ ነው ማለት ነው። ነገር ግን መዘንጋት የሌለበት አሐዙ ትክክል ነው ቢባል እንኳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከየክልሎቹ የተውጣጡ የልዩ ኃይል አባላትን ማካተቱ ቁጥሩን ያመጣጥነዋል። የኢትዮጵያ ሕግ ክልሎች በክልላቸው ያለውን ሰላም ለማስጠበቅ ኃይል እንዲኖራቸው የሚፈቅድ ነው። ከልዩ ኃይሎች ውስጥ በተለይም የአማራ ክልል ልዩ ኃይል በወታደራዊ ጥቃቱ መጀመርያ አካባቢ በምዕራብ ትግራይ በኩል መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ ቦታዎችን እንዲቆጣጠር አግዞታል። አማራ ክልል በዚሁ አካባቢ ከሚዋሰነው የትግራይ ክልል ጋር የግዛት የይገባኛል ጥያቄዎች እንዳሉት ይታወቃል። "በምዕራብ ግንባር የአማራ ልዩ ኃይልና የፌዴራሉ መከላከያ ሠራዊት ጥምረት የትግራይ ኃይል ላይ ከፍተኛ ብልጫ ስለሚኖረው ቁጥጥሩ ጠንካራ እንደሚሆን ይገመታል" ይላሉ ሚስተር ዴቪሰን። "ሌላው ነጥብ በምዕራቡ የትግራይ ክፍል ሜዳማ የሆነ መሬቶች ስለሚበዙ መደበኛ ውጊያ (conventional army) ለሚያደርገው ማዕከላዊው መንግሥት የተመቸ ዕድል ሰጥቶታል" ይላሉ ባለሞያው። ባለሙያው ይህን የሚያነሱት ሠራዊቱ ወደ ማዕከላዊ ትግራይ በተጠጋ ቁጥር እንዲሁም ወደ ምሥራቅ ትግራይ መቀለ በቀረበ ቁጥር የመልከዓ ምድሩ ተራራማ እየሆነ እንደሚሄድ ለመጠቆም ነው። እንዲህ ዓይነቱ ድንጋያማ፣ ደረቅና ተራራማ መልከአምድር ደግሞ ለሽምቅ ውጊያ እንጂ ለመደበኛ ውጊያ የሚመች አይሆንም። የትግራይ በሮች መዘጋት አቶ አርሄ ሐመድናካ ከቀድሞው የደርግ መንግሥት በተቃራኒ ሆነው በሽምቅ ውጊያ የተሳተፉ ሰው ናቸው። አሁን በስዊድን የሕዝብ እንደራሴ ምክር ቤት አባል ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት የመከላከያ ሠራዊት በምዕራብ በኩል የከፈተው ጥቃት በዋናነት ከሱዳን ጋር ያለውን ድንበር ለመቆጣጠር ያለመ ነበር። ይህ እጅግ ቁልፍ እርምጃ እንደሆነ አቶ አርሄ ይገልጻሉ። ይህ መሆኑ ህወሓት ከ29 ዓመት በፊት በዚያ አካባቢ ጦር ቀጠና አቋቁሞ እንደነበረው ሁሉ አሁን ያን እንዳያደርግ ከልክሎታል ይላሉ። "ለህወሓት ብቸኛው መተንፈሻ፣ ለማምለጥ መውጫ ቀዳዳ፣ እንዲሁም መሳርያ ለማስገባት ያለው ዕድል የሱዳን ድንበር ነበር" ሲሉ የቦታውን ወሳኝነት አስረግጠው ይናገራሉ። ከዚህ ሌላ ህወሓት በደርግ ጊዜ ከሻዕቢያ ጋር ተቆራኝቶ ግዙፉን የደርግ ሠራዊትን ሲታገል የቀይ ባሕር መተለለፊያ ነበረው። አሁን ግን ያ የለም። ይህም የሆነበት ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ሁነኛ ወዳጅ በመሆናቸው ነው። ህወሓት መላ አገሪቱን በሚቆጣጠርባቸው ዓመታት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከኢትዮጵያ ጋር መራር ውጊያ ማድረጋቸው አይዘነጋም። "ጊዜው ተቀየረ። ህወሓት በየት በኩል መተንፈሻ ይኖረዋል። በሰሜን በኩል ያሉት ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው። ለዚያውም የህወሓት ዋንኛ ጠላት" ይላሉ የቢቢሲው የትግርኛ ቋንቋ ኤዲተር አቶ ሳሙኤል ገብረሕይወት። ህወሓት መጪው እጣ ፈንታው ምንድነው? ቢቢሲ ከኤርትራ ያገኛቸው ምንጮች እንደሚያመላክቱት የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኤርትራ በድንበር በኩል ዘልቀው እንደሚገቡ ጠቋሚ ናቸው። የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት በጦርነቱ መሀል ማፈግፈግ ሲኖርባቸው ወደ ኤርትራ ያፈገፍጋሉ። መልሶ ራሳቸውን ለማደራጀት ሲሹም ይህንኑ ያደርጋሉ። የቆሰሉ አባሎቻቸውን ለማከምም የወታደራዊ ሆስፒታሎች ይገባሉ። ይህ የኤርትራ ምንጮች ለቢቢሲ ያቀበሉት መረጃ በኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በኤትራ መንግሥት ተቀባይነት አላገኘም። የኤትርራ መንግሥት በዚህ ጦርነት እጄን አላስገባሁም ይላል፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም በዚህ ይስማማል። "ትግራይ ታጥራለች። የህወሓት ሠራዊት ከዚህ በኋላ መደበኛ ጦርነትን ሊቋቋም አይችልም" ይላሉ የአይሲጂ ተመራማሪው ሚስተር ዴቪሰን። ነገር ግን ይህ ማለት የማዕከላዊው መንግሥት በአንድ ጀንበር ድል ያደርጋል ማለት አይደለም። አቶ አርሄ በጦርነት ታሪክ ሽምቅ ውጊያ ተዋጊዎች በሠራዊት አደረጃጀትና በትጥቅ በአያሌው የሚልቋቸውን ኃይሎች መቋቋም የቻሉበት በርካታ አጋጣሚ ይጠቅሳሉ። "አሜሪካ ያ ሁሉ ውስብስብ ሰው አልባ ተዋጊ ጄትና የጦር መሣሪያ የበላይነት እያላት ታሊባን አልተደመሰሰም" ይላሉ። በተመሳሳይ "የሁቲ ሚሊሻዎች በየመን የኢምሬቶችና የሳዑዲን የመሣሪያ የበላይነትን ተቋቁሞ አለ።" ሚስተር ዴቪድሰን እንደሚሉት መከላከያ ሠራዊቱ ወደ መቀለ በሚገሰግስበት በዚህ ወቅት የትኞቹን ከተሞች እንደተቆጣጠሩ፣ የትኞቹን አልፈው እንደመጡ የተብራራ መረጃ የለም። ያም ሆነ ይህ በርካታ የትግራይ ተዋጊዎች ወደ አቅራቢያ ተራሮችና መንደሮች ማፈግፈጋቸው አይቀርም። ይህም ለሽምቅ ውጊያ ራሳቸውን ለማዘጋጀት የሚያደርጉት ጥረት ነው የሚሆነው። "የፌዴራል ባለሥልጣናት እንደሚሉት ሳይሆን ብዙ የትግራይ ተወላጆች ጣልቃ ገብነቱን ይቃወሙታል። የሚቃወሙትም ይህ ጣልቃ ገብነት በሕጋዊ መንገድ የተመረጠን አስተዳደር ለማስወገድ የሚደረገው አድርገው ስለሚወስዱት ነው።" ከዚህም ባሻገር በርካቶች የክልሉ ተወላጆች ህወሓት በ1983 አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ያመጣውን የፌዴራል ሥርዓተ-አስተዳደር ይደግፉታል። ይህ ዓይነቱ አስተዳደር የፖለቲካ፣ የቋንቋና የባሕል ነጻነታቸውን የሚያስጠብቅላቸውና የተሻለው ሥርዓት እንደሆነም በስፋት ያምናሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ህወሓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሐዳዊ ሥርዓት ሊያሰፍኑ ነው የሚሞክሩት ስትል ትከሳለች። የቢቢሲው ትግርኛ ኤዲትር አቶ ሳሙኤል እንደሚሉት ከሆነ ግን አሁን ባለው ሁኔታ "ምንም እንኳ የትግራይ ብሔርተኝነት መፋፋም ለህወሓት ድጋፍ የሚያስገኝለት መልካም ዜና ቢሆንም፤ ከዚህ ተነስተን በርካቶች (ከህወሓት ይልቅ) የፌዴራል መንግሥትን ሊደግፉ አይችሉም ብለን ልንደመድም አንችልም" ይላሉ። ደርግን በመጣሉ የትጥቅ ትግል ወቅት የትግራይ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ከህወሓት ጋር ይወግን ነበር። ነገር ግን ህወሓት ሦስት አሥርታት ለሚጠጋ ጊዜ በሥልጣን ከቆየ በኋላ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ሥርዓቱ ያመጣው ጭቆናናበሙስና መንሰራፋቱ ድጋፋቸው እንዲሸረሸር አድርጎታል። አቶ ሳሙኤል እንደሚያምኑት የመቀለ ጦርነት መጨረሻ የህወሓትን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ይሆናል። ምናልባትም ህወሓት ሽምቅ ውጊያ እንዲጀምር የሚያደርገው ሊሆንም ይችላል። ይሁንና አቶ ሳሙኤል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የበላይነት ቢይዝም እንኳ በሁሉም ወገኖች ዘንድ የፖለቲካ ንግግር ሳይኖር ህወሓትን በማሸነፍ ብቻ በክልሉ ግጭትን እስከናካቴው ማጥፋት ይቻላል የሚባለው ሐሳብ አይታያቸውም።
news-50603617
https://www.bbc.com/amharic/news-50603617
ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች
ከዙሪክ ኡፊኮን ሰፈር የተነሳቸው BMW X5 ጠይም ቄንጠኛ ተሽከርካሪ እንደ ወፍ ትበራለች፤ ወደ ኒውሼትል። ኒውሼትል ከስዊዘርላንድ 26 ክፍለ አገሮች አንዷ ናት፤ ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች የሚበዙባት።
የመኪናዋ ካፒቴን አቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ናቸው። ባለቤታቸው ወ/ሮ ማክዳ በቀለ ጋቢና ከጎናቸው ተቀምጠዋል። ባልና ሚስት ብዙ ሰዓታቸውን የሚያወሩት ስለ ኳስ ነው፤ እንደ አዲሳባ ኤፍ ኤም። ስለ ልጃቸው ፐርፎርማንስ፣ ስለ ስዊዝ-ሊግ...ስለ ቡንደስሊጋ ያወጋሉ፤ ይስቃሉ፣ አሰላለፍ ይተቻሉ፤ ቴክኒክ-ታክቲክ ያብላላሉ፣ ቦል ፖዚሽን እና ቦል ፖሰስሽን እያባዙ ያካፍላሉ...እየደመሩ ይቀንሳሉ...። ነገረ ሥራቸው ሁሉ ያስቃልም፣ ያስቀናልም። • በምዕራብ ኦሮሚያ በ12 ወራት ቢያንስ 8 የአካባቢው ባለስልጣናት ተገድለዋል ባልና ሚስቱ ኳስ ላይ የሙጥኝ ያሉት ያለምክንያት አይደለም። ከልጆቻቸው 2/3ኛ የሚሆኑት ኳስ ተጫዋቾች በመሆናቸው ነው፤ ለዚያውም ፕሮፌሽናሎች። የስታትስቲክስ ጅራፍ አጮኽኩ እንጂ...፤ ከሦስቱ ልጆቻቸው ሁለቱ ማለቴ ነው። አልፎ አልፎ ታዲያ የኳስ ወሬያቸው ረገብ ሲል በውስጥ ስፖኪዮ ወደኔ እያማተሩ "ተጫወት እንጂ" ይሉኛል። "እሺ...እየተጫወትኩ ነው" 'ዕድለኛ ነህ፤ ጥሩ ጌም ባለበት ቀን ነው ዙሪክ የመጣኸው" "አይደል?! እኔም አጋጣሚው ደስ ብሎኛል።" "በረራህ ጥሩ ነበር?" "ምንም አይል...11 ሰዓት ፈጀ። ከናይሮቢ-ዳሬሰላም፣ ከዳሬሰላም-ዙሪክ" "ው….! ደክሞኻላ!" "ኧረ ደህና ነኝ! ፕሌን ውስጥ መተኛቴ በጀኝ፤ ዳሬሰላም የጀመርኩትን ህልም ስዊዘርላንድ ነው የጨረስኩት" "እውነትህን ነው?" "አዎ! የሕልሜ 'መቼት' ከሞላ ጎደል ሜዲትራኒያን ላይ ነበር ማለት ይቻላል..." ከዚህ በኳስ ፍቅር ካበደ ቤተሰብ ጋር በቀላሉ ለመግባባት እየሞከርኩ ነው። ገና ዙሪክ ደርሼ ሆቴል ከመግባቴ ነበር ‹‹ተነስ የካምቦሎጆ ሰዓት ደርሷል›› ብለው አንከብክበው ይዘውኝ የወጡት፤ ባልና ሚስቱ፤ በኳስ ያበዱቱ። ማረን እና ቅዱስ አቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴና ወ/ሮ ማክዳ በቀለ ሲበዛ ተጫዋቾች ናቸው። ድሮስ ልጆቻቸውን ኳስ እያጫወቱ እነሱ እንግዳ ማጫወት ሊያቅታቸው ነበር'ንዴ? ሦስት ወንድ ልጆች አሏቸው። ማረን ኃይለሥላሴ፣ ቅዱስ ኃይለሥላሴና ቃለዓብ ኃይለሥላሴ ይባላሉ። (ኃይለሥላሴ ቤተሰባዊ ስም በመሆኑ በአገሬው ደንብ የቤተሰቡ ሁሉ ቅጥያ ሆኖ ያገለግላል።) ማረን እና ቅዱስ ታላቅና ታናሽ ናቸው። ሁለቱም እሳት የላሱ ተጫዋቾች ናቸው። ለትንሹ ቅዱስ ኳስ ትታዘዝለታለች፤ ለትልቁ ማረን ኳስ ታሸረግድለታለች...እያሉ ይጽፋሉ 'አሉ፤ የአገሬው ጋዜጦች፣ በአገሬው ቋንቋ። ማረን በተለይ የበቃ የነቃ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሆኗል። አሁን 21 ዓመቱ ነው። እንዲህ ክንፍ አውጥተን ወደ ኒውሼትል የምንበረው ለምን ሆነና! • ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች ታናሹ ቅዱስም የዋዛ አይደለም፤ ለስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከ18 ዓመት በታች ቋሚ ተሰላፊ ነው። አብሮን መኪና ውስጥ አለ። የጎረምሳ ሹራብ ኮፍያ አድርጎ ጸጥ ብሎ ሞባይሉን ይጎረጉራል። "ማረን ዛሬ ወሳኝ ጌም ነው ያለበት።" አቶ ምሥጢረ መሪያቸውን እንደጨበጡ በድጋሚ አስገነዘቡኝ። "ኧረ!?" "አዎ! ተጋጣሚያችን "ያንግ ቦይስ" ይባላል። የዋዛ ቡድን እንዳይመስልህ።" ጉጉታቸው ከአነዳዳቸው ይፈጥናል። "ስሙን ሰምቼው አላውቅም ግን?" "ምናለፋህ የዚህ አገር ማንችስተር በለው? ወይም የኛን ቅ/ጊዮርጊስ ልትለው ትችላለህ" "ኧረ?" "አዎ! የስዊዘርላንድ ዋና ከተማ ቡድን እኮ ነው። ላለፉት ሁለት ዓመታት የስዊስ ሱፐርሊግ ሻምፒዮን ነበር፤ የጥሎ ማለፉን ዋንጫም የወሰደ ክለብ ነው" አቶ ምሥጢረ ጎላ ባለ ድምጽ ተናገሩ። "…በዚያ ላይ ደግሞ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ያውቃል" ወ/ሮ ማክዳ ተደረበች። "ልጃችሁ ማረን ግን ለዙሪክ ኤፍሲ እንደሚጫወት ነበር የሰማሁት...?" "ልክ ነህ! ነገር ግን አንተ ከመምጣትህ ከአንድ አምስት ሳምንት በፊት ነው ወደ ኒውሼትል የተዛወረው…በውሰት።" ከዙሪክ ወደ ኒውሻትል በውሰት የተዛወረው ማረን ከአዲስ'ባ አሰላ…ከዙሪክ-ኒውሼትል አቶ ምሥጢረ በኳስ ስሜት ውስጥ ሆነው ነው መሰለኝ እያሰለሱ መኪናዋን ክንፍ ያስበቅሏታል። ዝግ አሉልኝ ስል... ያፈተልካሉ...፣ልክ እንደ ዎልቭሀምተኑ አዳማ ትራዎሬ....፤ ለዚያውም የጎዳናውን ቀኝ ክንፍ ይዘው፤ ለዚያውም በ140። እኔ ደ'ሞ ፍጥነት ያስፈራኛል። ነፍሴን ይሰውረዋል። ያም ሆኖ የመኪናው ይሁን የአስፋልቱ ልስላሴ አላውቅም…ብቻ...ወትሮ በአገርቤት ‹‹ሃይሩፍ ሚኒባስ›› ስሳፈር እንደማደርገው ለጊዜው ጸሎተ-ንሰሐ አልጀመርኩም። "አይዞህ! በተፈቀደ ፍጥነት ነው የምንሄደው። ይታይኻል ይሄ ማሽን? ከተፈቀደው ፍጥነት ይቺን ታክል ብታልፍ ነገ ቤትህ የቅጣት ወረቀት ነው የሚመጣልህ..." • የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው ለካስ አቶ ምሥጢረ ፍርሃት እንዳኮማተረኝ በውስጥ ስፖኪዮ አሻግረው ተመልክተዋል። የሆነ ቦታ ስንደርስ በግድ ዝግ እንድንል ሆነ። አውላላ የነበረው አውራ ጎዳና ድንገት በተሽከርካሪ ተጨናነቀ። አቶ ምሥጢረ ከፊታችን አንዳች አደጋ መፈጠሩን ተነበዩ። ትንበያቸው ልክ ነበር። አውራጎዳናው ላይ አደገኛ የሚባል ግጭት ተከስቶ አንዱ መኪና አፍንጫው ተጣሞ፣ በበቃኝ የተዘረረ ቡጢኛ መስሏል፤ ቀኝ የወኋላ ቆሟል። ሌላኛውም እንደዚሁ…። ግጭቱን ሾልከን እንዳለፍን ግን አቶ ምሥጢረ መኪናዋን በተለመደው ፍጥነት መጋለብ ጀመሩ፤ ልክ እንደ ፓሪስሴንዣርማኑ ኪሊያን እምባቤ። እርግጥ ነው ኳሱ ሊያመልጠን አይገባም። እኔም ጉጉቴ ሰማይ ነክቷል። የሆነ አውሮፓ አገር ሺህ ተመልካች መሀል ቁጢጥ ብዬ ኳስ ማየት አጓጉቶኛል። እስከዛሬ ኳስ በቴሌቪዥን መስኮት አጮልቄ እንጂ ባይኔ በብረቱ! በአካልወስጋ…!? ከየት ተገኝቶ። "የምንሄድበት ስቴዲየም በጣም ሩቅ ነው እንዴ አቶ ምሥጢረ?" "ያን ያህልም አይደለም…170 ኪ/ሜ ነው። ከአዲስ አበባ አሰላ በለው…" ቼኮሌት…ስዊዝ ባንክ…የአንድ ሚሊዮን ብር የእጅ ሰዓት… ከዙሪክ ተነስተን ዋና ከተማዋን በርንን በግራ አ'ታለን አጋድመናት፣ ኒውሼትል ለመግባት ወደ 2፡00 ሰዓት ግድም ይወስድብናል። አቶ ምሥጢረ ‹‹ቢኤምደብሊው›› መኪናቸውን እየረገጧት ነው፤ ልክ እንደ ማን'ሲቲው ኬይል ዎከር። ከኋላ የማረን ታናሽ ቅዱስ ኃይለሥላሴ እና ወጣቱ አጎታቸው አማኑኤል በቀለ አብረውኝ ተቀምጠናል። ባልና ሚስቱ ጋቢና የራሳቸውን ወግ ሲይዙ እኔም ለነ ቅዱስ ጥያቄ አነሳሁ… "እኔ ምልህ ቅዱስ፤ እየሄድክ ኳስ ታያለህ? ትልልቅ ቡድኖችን?" "ሜሲን፣ ሮናልዶን ሮናልዲንሆን ኔይማርን እየሄድኩ ጌማቸውን ኢመለከታሎ። ምሳሌ ሜሲን ባርሳ ከጁቬንቱስ ሻምፒዯንስሊግ ፋይናል ላይ ነበርኩ። እዚህ ማድሪድ ከዙሪክ ሲጫወት ሮናልዶን አይቼዋለሁ።" የቅዱስ አማርኛ በስዊዘርላንድ ቼኮሌት የተለበጠ ይመስል ይጣፍጣል። "ማነው ግን ይበልጥ የሚማርክህ ተጨዋች" "እኔ ኔማር አንደኛ" • የስፖርት ውርርድ አዲሱ የወጣቶች ሱስ ይሆን? ወጣቱ አጎታቸው አማኑኤል ስለስዊዝ ሊግ ጥንካሬ፤ ሊጉ መሐመድ ሳላህን የመሳሰሉ ድንቅ ተጫዋቾችን ስለማፍራቱ አጫወተኝ። ሞባይሉን አውጥቶ ቅዱሥ ከዚህ ቀደም ያስቆጠራቸውን ጎሎች በተንቀሳቃሽ ምሥል አሳየኝ። ያን ጊዜ ቅዱስ በቴክኒክ የበሰለ 'ፌንተኛ' ተጫዋች መሆኑን መረዳት ቻልኩ። ከአፍታ በኋላ ቀልቤን ወደ ጋቢና መለስኩ። "ቅዱስዬ ለበጋ እረፍት ከባርሴሎና ዛሬ መምጣቱ ነው፤ ትንሽ አመም አድርጎታል። አማርኛ ጎበዝ ነው ግን አይደል?" ወ/ሮ ማክዳ ተቀበለችኝ፤ "በጣም እንጂ…እዚህ ተወልዶ ያደገም አይመስልም!" "አይደል?" "አዎ! ከጠበቅኩት በላይ ጎበዝ ነው" ትንሽ ራሱን አመም ስላደረገው ተጨንቃለች። አሁንም አሁንም የሚጠጣ፣ የሚበላ ታቀብለዋለች።እሱ ግን በጄ አይልም። "እኔምልሽ ማክዳ! ማረን ስንተኛ ጨዋታው ነው የሚያደርገው ዛሬ?" "ማረንዬ ዛሬ ሁለተኛ ጨዋታውን ነው የሚያደርገው...ሱፐርሊጉ ገና መጀመሩ'ኮ ነው..." "የመጀመርያውን ጨዋታ ገብታችሁ ነበር?" "እንዴ! እኛ የትም ቢሆን ጌም ካለው ቀርተን አናውቅም። የትም...! አይደለም ስዊዘርላንድ…የትም...!" የሮቤርቶ ካርሎስን ቅጣት ምት በሚያስንቅ ፍጥነትና አጽእኖት ተናገረች። እናት ማክዳ! ለኪሎ ሜትሮች ያህል በዝምታ ተጓዝን። እነሱ አንድ ጊዜ ፕሪምየር ሊጉን፣ አንድ ጊዜ ላሊጋውን፣ አንድ ጊዜ ቡንደስሊጋውን ሲተነትኑት የኔ ዝምታ መልሶ እኔኑ አስጨነቀኝ። በነርሱ ወሬ ደማቅ ተሳትፎ እንዳላደርግ ደግሞ እግር ኳሳዊ ዕውቀቴ ሳሳብኝ። "የመጀመርያህ ነው ስዊዘርላንድ ስትመጣ?" ዝምታውን ለመስበር ይመስላል፤ ጠየቁኝ። "አዎ የመጀመርያዬ ነው!" ሆኖም ለኔ አንድ ጥያቄ ወርውረው እነሱ ወደ ኳስ ወሬያቸው ይመለሳሉ። የመኪና ወግ ከነ ወ/ሮ ማክዳ ጋር "እንደማየው ለምለም አገር ይመስላል…በዚያ ላይ ተራራማ ነው።" "አታውቅም እንዴ! ኢትዮጵያ የአፍሪካ ስዊዝ እንደምትባል?" አቶ ምሥጢረ ጠየቁኝ። "የሰማሁ መሰለኝ" "የአልፕስ ተራራ ሰንሰለት እንደምታየው ነው። የዚህ አገር ረዥሙ ተራራ ከራስ ዳሽን ይስተካከላል።" "እያየሁት እኮ ነው! ዙሪያ ገባው ተራራ ነው...የተራራ አጥር..." "ሌላ ልንገርህ....ተራራማነቱ የፈጠረው የቋንቋ ብዝኃነት አለ፤ በሁለቱም አገር። ኢትዮጵያ በአንድ ቋንቋ ውስጥ ብዙ ቀዬ (ዳያሌክት) ያላት አገር ናት። ለምን ይመስልሃል? "እኔ እንጃ" "ከዚህ ከተራራማነት ጋ ተያይዞ ነው፤ ከተራራ ማዶና ከተራራ ወዲህ አንድ ቋንቋ አይነገርም። ድሮ ኮሚኒኬሽን እንዳሁኑ አልነበረም፤ የጎንደር፣ የሸዋ፣ የወሎ አማርኛ ዳያሌክት የተፈጠረው...አንዱ በዚህ ምክንያት ነው።" "እዚህም ብዙ ነው ቋንቋው አቶ ምሥጢረ?" "ስዊዘርላንድ እንኳ 4 ቋንቋ ነው ያላት በዋናነት። ግን ብዙ ዳያሌክት ነው ያላት፤ ልክ እንደ ኢትዯጵያ..." "ይሄን የፈጠረው ተራራማነቱ ነው የሚሉኝ" "ትክክል" እንደገና ዝም ዝም። "ለምን እንዲህ አናደርግም?" ድንገተኛ ሐሳብ አቀረብኩ። "ምን?" "ስለስዊዘርላንድ በወሬ የሰማኋቸውን ነገሮች ልንገራችሁና እናንተ ደግሞ እውነት ስለመሆናቸው አረጋግጡልኝ..." "አሁን ጥሩ ሐሳብ አመጣህ፤ እንዳውም መንገዱ ያጥርልናል…" ወ/ሮ ማክዳ ሐሳቤን በሙሉ ድምጽና በምንም ድምጸ ተአቅቦ ደገፈችው። "ስንት ዓመት ሆነዎት ግን እዚህ ከመጡ፤ አቶ ምሥጢረ?" "ዓመቱን እንኳ ተወው! በጣም ድሮ ነው..." (ሳቁ!) አሳሳቃቸው ዙሪክ ከመቆርቆሯ በፊት የመጡ ያስመስልባቸዋል። "አቶ ምሥጢረ አንቱታውን ብተወው ቅር ይልዎታል?" "እንዳውም ገላገልከኝ..."(በድጋሚ ሳቁ)። የስፖርተኛ ተክለሰውነት ነው ያላቸው። አሰልጣኞች በልምምድ ጊዜ የሚለብሱት ቀለል ያለ ቱታ በጅንስ ነው ያደረጉት። ወግ ሆኖብኝ ነው እንጂ ምንም ለአንቱታ የሚሆን ገጽታ አላገኘሁም። ደግሞስ በተቃጠለ የኳስ ስሜት ወደ ካምቦሎጆ የሚሄድ ሰው አንቱ ይባላል እንዴ? "በጣም ቆይተዋል/ቆይተኻል ማለት ነው እዚህ?" (አንቱታው አ'ለቅ አለኝ…) "ኡ! በጣም...!" እሺ በቃ ጥያቄዬን ልጀምር…(ማስታወሻዬን አወጣሁ) "ስዊዘርላንድ ውስጥ ቡና ሲፈላ እንደ ዳቦ ቆሎ የሚቀርበው ቼኮሌት ነው የሚባለው እውነት ነው?" ባልና ሚስት ከት ብለው ሳቁብኝ! የስዊዝ ቼኮሌት፣ የስዊዝ ሰዓት፣ የስዊዝ ባንክ እየተባለ ወሬ ስለሚነዛ ያንኑ ማጋነኔ ነበር...። • እንወራረድ፡- የጦፈው የውርርድ ንግድ በአዲስ አበባ (አንዳንዱ ነገር እንዳሰብኩት ግነት ብቻ አልሆነም፣ ታዲያ። ለምሳሌ በቀጣዩ ቀን 140ሺህ የስዊዝ ፍራንክ ተመን የተቀመጠበት የእጅ ሰዓት በዓለም ላይ ውድ ከሚባሉ ጉሊቶች አንዱ በሆነው ባንሆስትራሰ (Bahnhofstrasse) ጎዳና በአንድ ቄንጠኛ ሱቅ ውስጥ ማየቴን አንባቢ በግርጌ ማስታወሻ ቢይዝልኝ አልጠላም። ሰው እንዴት ‹‹ስንት ሰዓት ነው?›› ሲባል የአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር የእጅ ሰዓቱን ገልጦ ‹‹ለ2 ሰዓት ሩብ ጉዳይ›› ይላል?) "አቶ ሚሥጢረ፣ የስዊዝ ባንክ ግን የቱ ጋ ነው ያለው?" የአህጉሬ አምባገነኖች ብር የሚያከማቹበትን መጋዘን በሩቁም ቢሆን ማየት ጓጉቻለሁ። ከጃንሆይ የልጅ ልጆች የተረፈም ካለ… "ነገ እናሳይኻለን…ግን ስዊዝ ባንክ የሚባል አንድ ባንክ የለም'ኮ። እዚህ አገር የደንበኞቻቸውን ምሥጢር የሚጠብቁ ብዙ ባንኮች ናቸው ያሉት። በተለምዶ ስዊዝ ባንክ እንላለን እንጂ…አንድ ባንክ አይደለም።" "እሺ ሌላ ጥያቄ፡- ስዊዘርላንድ ውስጥ የእንሰሳት የወሲብ ፍላጎት ለማክበር ሲባል አንድን ጾታ ብቻ ለይቶ ማሳደግ አይቻልም። ለምሳሌ ሴት ውሻ ካለ ወንድ ዉሻ...ወንድ ድመት ካለ ሴት ድመት አብሮ ማሳደግ ሕግ ያስገድዳል...እውነት ነው?" ከት ብለው ሳቁብኝ! "አይ ይሄ ሐሰት ነው። የጎረቤታችን የነ እንትና ውሻ ብቻዋን ነው የምታድገው…ሲንግል መሰለችኝ..." ሌላ ጥያቄ፡-"የኑኩሌር ጦርነት ቢከሰት በሚል ሁሉም ስዊዘርላንዳዊ ዜጋ ሊደበቅበት የሚችል ዋሻ በየሰፈሩ አለ የሚባለውስ?" "ልክ ነው፤ ዋሻዎች (Bunkers) በየሰፈሩ አሉ።" ሌላ ጥያቄ፡- "አልበርት አንስታይን የአንጻራዊ ሕግ [ሪላቲቪቲ ቲዯሪን] የቀመረው እዚህ ነበር?" "ይሄም ልክ ነው፤ እዚህ ዙሪክ ዩኒቨርስቲ ያስተምር ነበር። በነገርህ ላይ ኖቤል ካሸነፉት ሰዎች ብዙዎቹ ከዙሪክ ነው የወጡት። ካልተሳሳትኩ 12 የሚሆኑት…ከዙሪክ ዩኒቨርስቲ ናቸው።" መንገዱን እንዲህ እንዲህ እየተጨዋወትን ተሲያት ላይ ኒውሼትል ደረስን። የኤክስማክስ ስታዲየም እዚያም ስታዲየም ሰልፍ አለ ኒውሼትል ከተማ ስንደርስ በጩኸታዊ ዝማሬያቸው ከቡና ደጋፊ ጋር የሚመሳሰሉ፤ በቁመታቸው "የስታዲየም ዳፍ" የሚያካክሉ የያንግ ቦይስ ደጋፊዎች መንገዱን ሞልተውታል። የሚያወጡት ድምጽ ጎርናና በጣም የሚያስፈራ ነው። ቆመን አሳለፍናቸው። ኋላ ቢደበድቡንስ… ማክዳና ምሥጢረ የዓመት መግቢያ ነበራቸው፤ እኔ ግን ስላልነበረኝ ለትኬት መሰለፍ ተገደድኩ። ትኬት በወንበር ቁጥር ጋር መዛመድ ስላለበት ከቤተሰቡ ጋር ለመቀመጥ አስቸጋሪ ሆነ። በኋላ ላይ አቶ ምሥጢረ መላ መታ። "የቢቢሲ ጋዜጠኛ የሚል መታወቂያ ይዘኻል?" "አዎ!" ትኬት ቆራጮቹን በአገሬው ቋንቋ አነጋገራቸው። ተባበሩን። ከቤተሰቡ ጋ እንድመለከት በ82 የስዊዝ ፍራንክ ትኬት ተገዛልኝ። እናትና አባት በኒውሼትል ስታዲየም ልጃቸው ቅዱስ፣ አጎታቸው አማኑኤል፣ እና እኔ በስታዲየሙ ተሰይመናል። በአዲስ አበብኛ ጥላ ፎቅ ነን። ለዚያም ቀኝ ጥላ ፎቅ። አዲስ አበባ ቢሆን ግን አቶ ምሥጢረ በፍጹም ቀኝ ጥላ ፎቅ አይቀመጡም ነበር። ድሮ ቀንደኛ የሳንጃው ደጋፊ ነበሯ። …እንዲያም እነ ማረን ወደ ሜዳ እስኪገቡ ለምን በአጭሩ በርሳቸው የድሮ ታሪክ አናሟሙቅም? "መንግሥቱ ወርቁ ሜሲዬ ነበር" አቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ "አንዳንዴ ጸሎቴ ተሰምቷል እላለሁ። ለምን መሰለህ…ገና ድሮ ሁለት ነገር እመኝ ነበር፤ ወንድ ልጆች እንዲኖሩኝና ኳስ ተጫዋች እንዲሆኑ። ሁለቱም ተሳክተውልኛል።... ...በልጅነቴ ኳስ ወዳጅ ነኝ፤ እንደ ልጆቼ ግን የተመቻቸ ነገር አልነበረም። እንደምታውቀው ድሮ የኳስና የክት ጫማ ብሎ ነገር እንኳ የለም። ወደ ትምህርት ቤት በሄድንበት ጫማ እንጫወታለን። ጫማው ይንሻፈፋል፤ እንገረፋለን። በዚያ ላይ ኳስ መውደዳችን በትምህርት ላይ ተጽእኖ ነበረው። በኛ ጊዜ ትምህርት የሕይወት አልፋና ኦሜጋ ነበር።... ...በኔ ጊዜ ስለ ኢንተርናሽናል ጨዋታ መረጃ ማግኘት በራሱ ከባድ ነበር። በሳምንት አንድ ጊዜ የሚወጣ ‹‹ስፖርት ፋና›› የሚባል ጋዜጣ ትዝ ይለኛል። ስለነፔሌና ጋራንቻ ሞቅ ተደርጎ ይወራ ነበር። .. • .በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ከማስታውሰው ልንገርህ፤ ‹‹ፔሌ የመታው ኳስ ማዕዘን መልሶበት አንግሉ ይለካልኝ አለ›› ተብሎ ይጻፋል። እውነት ነበር የሚመስለን። የዲኤንኤ ነገር ይሆን ታዲያ ዛሬ በሁለት ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች የተባረከው?" ጥያቄ አነሳሁ። "...አላውቅም፤ ሊሆን ይችላል፤ በነገርህ ላይ እዚህ ኳስ ልጆቹን ከአልባሌ ነገርም ይጠብቃቸዋል። ከትምህርት መልስ ልምምድ ነው ቤት ነው። ለአጓጉል ነገር ጊዜም የለም። "ሌላ ምን ትዝ ይልኻል ከድሮ?" "ምን ትዝ የማይለኝ አለና! እንዲያውም ስላለፈው ዓመት ከምትጠይቀኝ የዛሬ 40 ዓመት የነበረውን ብትጠይቀኝ ከነ ደቂቃው እነግርኻለሁ…። በዚያን ጊዜ ጊዮርጊስ ባርሴሎናዬ ነበር። መንግሥቱ ወርቁ ሜሲዬ ነበር። አንዳንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ በድሎታል ብዬ አስባለሁ። አሁን እነ ማረን የሚያገኙትን ልምምድ ቢያገኝ መንግሥቱ የት በደረሰ? መንግሥቱ እኮ የእግዚአብሔር ስጦታ ነበር። በቁመቱ ረዥም አልነበረም፤ የዝላይ ብቃቱ፤ የትኛው የአፍሪካ ተከላካይ ያቆመው ነበር? ንገረኝ…የትኛው…" እነ ሸዋንግዛው አጎናፍር፣ ፍሰሐ ወልደአማኑኤል፤ እነ አዋድ... ለአገራቸው በቀን 5 ብር አበል እየተከፈላቸው የተጫወቱ ባለውለታ ናቸው። ነፍሳቸውን ይማርና ክቡር ይድነቃቸው ያን ጊዜ ፕሮፌሽናሊዝምን ይጸየፉ ነበር። የአማተሪዝም አቀንቃኝ ነበሩ። ለአገርህ ነው የምትዋደቀው። ኳስ ዛሬ የቢሊዮን ዶላር ኢንደስትሪ ሆኗል...እንደምታየው። ያኔ ግን…" "አንተ ግን ለየትኛው ቡድን ተሰልፈኻል ድሮ?" "...የጊዮርጊስ ደጋፊ ብቻ አልነበርኩም፤ የጊዮርጊስ ተጫዋችም ነበሩ። በዚህ ምክንያት በልጅነቴ ስቴዲየም ዘንጬ ነበር የምገባው። "...በዚያ ዘመን ለልጆች ስታዲየም መግባት "ግመል በመርፌ ቀዳዳ..." እንደማለት ነው። ጋሼ ይዘውኝ ይግቡ ተብሎ መለመን የተለመደ ነበር። እኔ ግን ያኔ ቴሴራ የሚባል ነጻ መግቢያ ነበረኝ። ቴሴራውን ወደ ካምቦሎጆ መግባት ላልቻሉ እያቀበልን ሁሉ ገንዘብ ሸቃቅለንበታል፤ ይሄ ታዲያ በ60ዎቹ መጨረሻ ነው። " አቶ ምሥጢረ ያኔ አንተ ያጣኸውን ነገር አሁን በልጆችህ እየተበቀልከው ይመስልኻል? "መበቀል ሳይሆን መ'ካስ ልትለው ትችላለህ" (ሳቀ) ከአቶ ምሥጢረ ጋር እየተጨዋወትን የያንግ ቦይስ ቡድን ለማማሟቅ ወደ ሜዳ ገባ። ስታዲየሙ መሙላት ጀምሯል። የያንግ ቦይሶቹ "አቻኖ" እና «አዳነ» በፈረንሳይኛ ሕዝቡን ያስጨፍሩታል። ዝማሬው የሆነ የሚነዝር ነገር አለው። እነ ማረን ወደ ሜዳ እስኪገቡ ወደ እናቱ ማክዳ በቀለ ዞርኩ። ማረን ኃይለሥላሴ ለአዳጊዎች ፊርማውን ሲያኖር "ልጆቼ ኳስ ሲያቀበል ለማየት ስታዲየም እገባ ነበር" ወ/ሮ ማክዳ "አንድ ነገር ልንገርህ?... "...ማረንና ቅዱስ ኳስ አቀባይ ነበሩ፤ ኳስ ማቀበል ራሱ የሚገኝ ዕድል መሰለህ? ዋናው ቡድን ሲጫወት እነሱ ኳስ ያቀብሉ ነበር፤ ትዝ ይለኛል የመጀመርያ ቀን ማረን በ18 ዓመቱ ለብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ኳስ ያቀብላቸው ከነበሩት ተጨዋቾች ጋር ሲጫወት ሳይ በደስታ አለቀስኩ። አስበው፤ እሱ ቲኒሽዬ ልጅ ነበር። ኳስ ሲያቀብላቸው የነበሩት ጋ ተሰልፎ ሲጫወት ማየት እንዴት አያስለቅስም? አሁን እኮ ተጫውቶ ከሜዳ ሲወጣ የሱን ቲሸርት ለመውሰድ፣ ፊርማውን ለማግኘት ልጆች ሲረባረቡ ስታይ….አስበው... ብቻ እግዚአብሔር የሚሳነው የለም።" ማረን ኃይለሥላሴ በልጅነቱ አስተዳደጋቸውን አጫውችኝ እስቲ… "ማረን ኳስ አካዳሚ የጀመረው በ8 ዓመቱ ነው። ቅዱሥ ደግሞ በ6 ዓመቱ። ቅዱስ ኳስ ሲጀምር ከሚያንከባልላት ኳስ ራሱ በትንሹ ነበር የሚበልጣት። ማረን በ7 ዓመቱ ሰፈር ውስጥ ሲጫወት ተሰጥኦ አዳኞች መጥተው አዩትና ወዲያው ቅድመ-ኳስ አካዳሚ አስገቡት። ቅድመ-አካዳሚ ከ9 በታች የሆኑ ልጆች የሚገቡበት የመሰናዶ ኳስ ትምህርት ቤት ነው። ቅዱስ ግን ያኔ 5 ዓመቱ ነው፤ ኳስ ደግሞ የሚጀመረው በ7 ዓመት ነው፤ ሆኖም ማረንን ለማየት ይሄድ ስለነበር ወንድሙን ማየት ሲሰለቸው ትርፍ ኳስ ይዞ ዳር ላይ እያንጠባጠበ ትኩረት ሳበ። አንድ አሰልጣኝ የዚህን ልጅ ወላጆች አገናኙኝ አለ። አቤት! አልን። ይሄ ልጅ እዚህ እየመጣ እንዲለማመድ እንፈልጋለን፤ አያያዙ ተስፋ የሚሰጥ ነው አሉ። በዚያው የኳስ መዋዕለ ሕጻናት [football Kindergarten] ገባ። • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ በ5 ዓመቱ የጀመረ አሁን ከ18 በታች ለዙሪክ ቡድን ይጫወታል። ያም ብቻ ሳይሆን ለስዊዘርላንድ የታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ይሰለፋል። ቅዱስ ደግሞ 2014 ሻምፒዯንስ ሊግ በርሊን ጁቬንቱስ ከባርሳ ሲጫወቱ ተጋብዞ ሄዶ ነበር። እሱ ብቻ ሳይሆን የሱ ቡድን ያኔ 13 ዓመቱ ነው፤ ሄዶ ነበር። ከእንግሊዝ የቼልሲ የሴቶች ቡድን ጋር ሁሉ ግጥሚያ አድርገዋል። ሕጻናት ነበሩ። የነ ቅዱስ ቡድን 23 ለ 1 በሆነ አስቂኝ ውጤት ሲያሸንፍ ቅዱስ 8 ጎል አግብቶ ጋዜጣ ላይ ሁሉ ወጥቶ ነበር። ከዚያ የነቅዱስ ቡድን 2ኛ ወጥቶ ተሸለመ። ትንሹ ቅዱስ ሽልማቱን ከትልቁ ፍራንስ ቤከን ባወር እጅ ተቀበለ። በአጭሩ ሕይወቴን ልንገርህ? ከሆኑ ዓመታት በፊት ስዊዘርላንድ ለትምህርት ሄድኩ፤ ትዳር መሠረትኩ፤ እነ ማረን ተወለዱ፣ ሕይወቴ እነሱ ሆኑ፤ አብሬያቸው አደግኩ ብልህ ይቀለኛል።" ማረን ኃይለሥላሴ የኳስ መዋዕለ ሕጻናት ወ/ሮ ማክዳ የስፖርተኛ ልጆች እናትም አይደለች? ንቁና ቀልጣፋ ናት። ትንሹን ቃለዓብን አራስ እያለች፤ እሱን በፈረንጅ አንቀልባ (ጨቅላ ጋሪ) እየገፋች፣ ቅዱሥን ደግሞ በጎን ድክ ድክ እያለ (ያኔ እሱ ራሱ ኳስ ነበር የሚያክለው)፣ ወደ መለማመጃ ሜዳ ትሄዳለች። ያን ጊዜ ማረን ተስፋ የሚጣልበት አዳጊ ነበር። በየቀኑ ልምምድ ሜዳ መሄድ አለበት። ያን ጊዜ ትንሽ ልጅ የነበረው ቅዱሥ ታዲያ ታላቅ ወንድሙ ማረን ልምምድ ሲያደርግ ቁጭ ብሎ መመልከት ይሰለቸዋል። ብርር ብሎ ይሄድና ከተደረደሩ ብዙ ኳሶች ውስጥ አንዱን አንስቶ ያንቀረቅባል። (Eis, Zwoi, Dru…) 1...2....3... እያለ፤ በስዊዝ ጀርመንኛ... የማረን አሰልጣኞች ከኳሷ ጋር ቅዥቅዥ የሚለውን ትንሹን ቅዱሥ ይመለከቱታል። በየቀኑ። ይህን ልጅ እስኪ እንየው ብለው ያለጊዜው አስጀመሩት። ስዊዘርላንድ ትምህርት ነጻ ነው፤ ልጅን የእግር ኳስ ትምህርት ቤት ማስተማር ግን በጣም ውድ ነው። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርታቸው ይለያል። ልክ ሙያ ለመማር ተግባረ እድ እንደመግባት ነው። የቀለም ትምህርትና የኳስ ትምህርትን አጣምረው ይሰጣሉ። የነማረን ወላጆች ለዚህ ትምህርት ቤት የሚከፍሉት ፍራንክ ቆንጠጥ ቢያደርጋቸውም አላፈገፈጉም። በነዚህ ትምህርት ቤቶች ተጫዋቾች ለጌም ውጭ አገር ቢሄዱ ልጆቹ ትምህርት አመለጣቸው አይባልም። መጀመርያውኑ የትምህርት መርሃግብሩ ከኳስ የውድድር መርሃግብር ጋር የተስማማ ነው። ማረን ከዚህ ትምህርት ቤት በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ዲፕሎማ ይዟል። ማረን አሁን ለብሔራዊ ቡድን ይጫወታል። ሳምንት ለንደን ቆይቶ ይመጣል። ትምህርት አመለጠው፣ ፈተና አለፈው፤ ወይኔ ጉዱ ፈላ አይሉም፤ ወላጆቹ። ምክንያቱም ‹‹ቢዝነስ ፉትቦል›› ትምህርት ቤት ስለሚማር። 18 ዓመት ሲሞላው ክለቡ በተማረው ትምህርት የሥራ ልምምድ (ኢንተርኒሺፕ) ባንክ ውስጥ ነበር የጀመረው። በኋላ የኤፍሲ ዙሪክ ክለብ ባለቤትና ፕሬዝደንት ማረንን እጅግ ስለሚወዱት እኔ ኩባንያ ውስጥ ይሥራ፤ እንደፈቀደው ወጥቶ እንዲገባ ብለው ፈቀዱለት። አንቺሎ ካሌፓ ይባላሉ።በጣም ነው የሚወዱት ብለውኛል ወላጆቹ። እንዲህ እንዲህ እያለ ማረን አሁን የደረሰበት ደረጃ የደረሰው… ማንቼ ለምን ደጅ ይጠናል ታዲያ? ብዙዎቹ ግዙፍ ክለቦች "ፉትቦል ስካውት" የሚባሉ ተሰጥኦ አዳኝ መኮንኖች አሏቸው፤ በተለይ ባለፈው ዓመት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች እነ ምሥጢረ ጋር ደጅ የጠኑበት ዓመት ነበር። ‹‹ልጃችሁን ለክለባችን›› ተብለዋል። ከአንዴም ሁለት ሦስቴ። ሆኖም የታፈሩ የኳስ ሽማግሌዎችን እምቢኝ ብለው መልሰዋል። ባልና ሚስቱ ይህንን ሲነግሩኝ ለማመን ተቸገርኩ። "እንዴት ለማንቼ እምቢ ይባላል?" በወላጆቹ ድርጊት ተናደድኩ። በአጠያየቄ ትንሽ ስሜታዊ ሳልሆን አልቀረሁም መሰለኝ…የጉዳዩን ውስብስብነት ተረጋግተው ያስረዱኝ ጀመር፤ ባልና ሚስቱ። አንድ ቡድን አንድን ታዳጊ ተጨዋች ፈለገው ማለት ወዲያውኑ ተሰልፎ መጫወት ይጀምራል ማለት እንዳልሆነ፤ ማሳደጊያ ውስጥ ገብቶ በዚያው ቀልጦ መቅረትም እንዳለ…ልጅን አሳልፎ ከመስጠት በፊት ብዙ ጥንቃቄዎች እንደሚያስፈልግ አብራሩልኝ። • ''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ "የምናውቃቸው አንድ ሁለት ልጆች አሉ፤ ማንችስተር የሄዱ የማረን ጓደኞችም አሉ። ብዙም አልተሳካላቸውም፤ ተመልሰው ይመጣሉ።በዚህ ዕድሜያቸው ሄደው ከሚባክኑ ትንሽ እዚሁ ቢያድጉ መረጥን። አሰልጣኞቻቸውንም ስናማክር እንደዚያ ነው ያሉን...።" ከዘረዘሩልኝ ምክንያቶችም ባሻገር እናታቸው ልጆቹ ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ፤ በዕድሜም ትንሽ ከፍ ሳይሉ እንዲርቋት እንደማትፈልግ ተረድቻለሁ። "ከቡንደስሊጋ የመጡና የጠየቁም ነበሩ፤ በየጊዜው ማረንን እኛ ወስደን እናሳድገው ይሉናል…። "አያጓጓችሁም ታዲያ? "እኔ ብሆን ባንዳፍ" ነበር የምላቸው" "በእርግጥ ቡንደስሊጋ አጓጊ ነው። መልማዮቹ ቀስ ብለው እኛን ወላጆቻቸውን ነው የሚያግባቡት፤ ጉጉታችንን ስለሚያውቁ። ብዙዉን ጊዜ ደላሎች ገንዘባቸውን ነው የሚያዩት…" አቶ ምሥጢረ አስረዳኝ። እሱ ሲጨርስ ደግሞ ማክዳ ማብራሪያ አከለች። "ማረንና ቅዱስን ማናጀር እንሁናቸሁ የሚላቸውም ብዙ ነው፤ ያው እነሱም ሲሳካለቸው እንጀራቸውን ለመጋገር ነው። ትልልቅ ክለቦች ለኛ ስጡን ብለው ሲያነጋግሩን እና በራሳችን ብቻ አንወስንም። ከነማረን ማኔጀሮች ጋር በስፋት እንመካከራለን። ለአሁኑ ጊዜው አይደለም በሚል አቆይተናቸዋል። ወደፊት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆነውን ማየት ነው…" ማረን እና ቅዱስ ስለ ኢትዮጵያ ያስባሉ? የጋመ ኢትዮጵያዊ ስሜት ካላቸው ወላጆች የተገኙት ማረንና ቅዱስ ትኩረታቸው ገናና ክለብ ውስጥ ገብቶ ውጤታማ መሆን ነው። ስለኢትዮጵያ በጠየቅኳቸው ጊዜ የኢትዮጵያን ኳስ እንደማያውቁ ተረድቻለሁ። የኢትዮጵያን ማሊያ ለብሰው እንዲጫወቱ ግን የአባትየው ጥልቅ ፍላጎት ነው። የፓስፖርት ጉዳይ ራስ ምታት መሆኑ እንደማይቀር ግን ከወዲሁ ይገምታል። "ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቢጫወት ህልሜ ነው፤ ሆኖም የድርብ ዜግነት ጉዳይ መፍትሄ ማግኘት አለበት። ቀናነትም ያስፈልጋል። ዘንድሮ የአፍሪካ ሻምፒዮን የሆነውን የአልጄሪያን ብሔራዊ ቡድን ውሰድ፤ 90 ከመቶ የሚሆኑት ተጨዋቾች ውጭ አገር ተወልደው ያደጉ ናቸው።" ይላል አቶ ሚስጢረ። ማረን እና ቅዱስ አሁን ጥሩ ተከፋይ ተጫዋቾች ናቸው። ኢትዮጵያ ባይወለዱም ስለ ኢትዮጵያ ያስባሉ። ገና በልጅነታቸው በጎ አድራጎት ውስጥ ገብተዋል።ማረን 2 ልጅ፤ ቅዱስ አንድ ልጅ ወጪ ችለው ያስተምራሉ። በአዲስ አበባ። "እግዚአብሔር በዚህ ዕድሜያችሁ የማይታመን ነገር አደረገላችሁ፤ እንደናንተ የመማር ዕድል ላላገኙ ኢትዮጵያዊ ጓደኞቻችሁ ምን ታስባላችሁ? ስላቸው ነው ይህንን በጎ ተግባር የጀመሩት " ትላለች እናት ማክዳ። ከለላ የሚባል የልጆች ቡድን ደግሞ አለ፤ አዲስ አበባ። በዚህ የሰፈር ቡድን ውስጥ አንዳንዶቹ ልጆች ካለ ጫማ በባዶ እግር ሁሉ ኳስ ይጫወቱ ነበር። እነ ማረን ወደ 40 አዳዲስ ታኬታ የተለያየ ቁጥር አሰባጥረው ላኩላቸው። ልጆቹ በጣም ደስ አላቸው። እሱን ለማመስገን ለማረን ልደቱ ኬክ ቆርሰው ‹‹ሀፒ በርዝደይ ማረን›› እያሉ ቪዲዮ ላኩለት። "ኢትዯጵያዊያን ኳስ ውስጣችን ነው። ያም ሆኖ ትልቅ ደረጃ የደረሰ ተጫዋች አልወጣልንም። የኔ ልጆች የሆነ ቦታ ቢደርሱ ለስንት ልጆች አርአያ ይሆናሉ እያልኩ አስባለሁ። በዚህ ረገድ እግዚአብሔር ቀዳሚ ያደርጋቸዋል ብዬም አስባለሁ።" ይላል አቶ ምሥጢረ። "ትእግስትን የተማርኩት ከቤተክርስቲያንም በላይ ከኳስ ሜዳ ይመስለኛል" ወ/ሮ ማክዳ ባልና ሚስት የልጆቻቸውን ጨዋታ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የጀመርን ሊጎችንም በአንክሮ ይከታተላሉ። ባየርሙኒክና ዶርትሙንድ እና ሌሎች የቡንደስሊጋ ውድድሮችን ከዙሪክ እየነዱ አንዳንዴም በአውሮፕላን በረው እየታደሙ ይመለከታሉ። "እዚህ ያው ጊዜ የለም። ሆኖም ግን ቅዳሜና እሑድ ልጆቻችን ኳስ ግጥሚያ ከሌላቸው ይጨንቀናል።" ትላለች እናት ማክዳ። እሑድ እሑድ ከቤተክርስቲያን መልስ ሁልጊዜም ወደ ኳስ ነው። "አንዳንድ ጊዜ ትእግስትን የተማርኩት ከቤተክርስቲያንም በላይ ከኳስ ሜዳ ይመስለኛል። መሸነፍን የማልቀበል ሴት ነበርኩ። እንዴት ተሸነፍኸው ትመጣለህ ስለው ማረንን፣ "ማሚ እነሱ እኮ በልጠውን ተጫውተዋል" ሲሉኝ " አሃ ለካስ ሽንፈትን መቀበልም አለብኝ ማለት ጀመርኩ። ኳስ ምን ያላስተማረኝ ነገር አለ? ሁሌ ማሸነፍ እንደሌለ..ታጋሽነትን…" "ጀርመን ያልሄድነበትን ቦታ ጠይቀኝ፤ ክረምት የአዳራሽ ጨዋታ አላቸው። ኮሎን ድረስ 14 ሰዓት ደርሶ መልስ እየነዳን ሁሉ እናያቸው ነበር። ሆቴል ነው የምናርፈው ወጪው ብዙ ነው፤ ብዙ ሰዓት ነው የምንነዳው፤ ግን ደስታው ይበልጣል፤ ልጆቻችንን ማየት ትልቅ ፍሰሀ ይሰጣል።" ይላል አባት ምሥጢረ። ማክዳ በበኩሏ "እኔ ማንችስተርን ከማይ ቅዱስ ጌም ሲያደርግ ማየት የበለጠ ደስታን ይፈጥርልኛል፤ አንደኛ ቅዱስ ተአምር ሳይሰራ አይወጣም።" ትላለች። ስዊዝሊግ መጫወት ብርቅ ነው እንዴ? የስዊዝ ሊግ በአውሮፓ ደረጃ መካከለኛ ከሚባሉት ነው። የስዊዝ ብሔራዊ ቡድን በኮካ ኮላ ደረጃ ሰንጠረዥ (ራንኪንግ) እስከ ሆነ ጊዜ ድረስ ከምርጥ አምስት ውስጥ ነበር፤ ለብዙ አመታት። ከነብራዚል ሁሉ ይበልጥ ነበር። በዚህ ዓመት ነው 11ኛ የወረደው ይላል አቶ ምሥጢረ። ለመሆኑ ከዚህ ሊግ ወጥተው ገናና የሆኑ አሉ? "በጣም ብዙ…"ማክዳ መለሰች፤ "ለምሳሌ መሐመድ ሳላህ ከዚሁ ከባዝል ነው የመጣው።" "...ሻኪሪ ብትል፣ ሻካ የአርሴናሉ ከዚህ ነው የሄደው። ኢሚዲ ፣ ራኪቲቺ የባርሴሎናው...ሮልድሪገንስ ሚላን... በተለይ በተለይ ቡንደስሊጋ ውስጥ በጣም ብዙ ተጨዋቾች አሉ። ማረን እያታለለ ነው… ኒውሼትል ስታዲየም ጥላ ፎቅ ተቀምጠናል። እኔና የማረን ቤተሰብ። ሰዓቱ ደርሶ አሰላልፍ በድምጽ ማጉያ ሲገለጽ ማረን ዋና ተሰላፊ እንዳልሆነ ታወቀ። በወላጆቹ ፊት ላይ ቅሬታ ያየሁ መሰለኝ። ወይም አላየሁ ይሆናል…ብቻ አልተሰለፈም። የኔም ድካም አፈር በላ። ‹‹ እንደነገርንህ በተውሶ ስለሆነ የመጣው ገና እየሞከሩት ነው ያሉት…ተቀይሮ መግባቱ አይቅርም…›› አሉኝ፤ እያጽናኑኝ ይሆን? ወይም እየተጽናኑ? እንዳሉትም ከእረፍት መልስ ከተቀያሪ ወንበር ድንገት ብርር ብሎ ተነስቶ ማሟሟቅ ጀመረ። ማክዳ ልቧ ተንጠለጠለ…‹‹ማሪዬ!›› ተጣራች። • ከእግር ኳስ ሜዳ ወደ ኮኛክ ጠመቃ በዚህ ጉጉት መሐል ተከታታይ ጥያቄ መሰንዘር ጀምርኩ። ዐይኗን ከማረን ሳትነቅል ታወራኛለች…. "እኔምልሽ ማክዳ! ልጅሽ ጎል ሲያስቆጥር ምንድነው የሚሰማሽ? "ምን ዓይነት ጥያቄ ነው የምትጠይቀኝ?" በሚል ለአፍታ ዞራ ተመለከተችኝ። "ማለቴ እንደ እናት ከባድ ይመስለኛል..." ራሴን ቶሎ አረምኩ። "በጣም ነዋ የምደሰተው...የሱ ክለብ ኤፍሲ ዙሪክ ትልቅ ቡድን ስለሆነ ማሸነፍ የለመደ ነው። እሱ ገና ኳስ ሲይዝ ደጋፊው በጩኸት ነው የሚያግዘው...ጎ...በዝ ነው ብታይ...።" በድምጽ ማጉያው ‹‹ኃይለሥላሴ….!›› የሚል ድምጽ ሲስተጋባ ደጋፊዎች በታላቅ ጩኸትና ዝማሬ ተቀበሉት። ማረን ተንደርድሮ ወደ ሜዳ ገባ። ‹‹ማርዬ! አይዞን!›› "ለምሳሌ ልጅሽ ማረን ኳስ ሲይዝ ጭንቅ አይልሽም?" ጠልፈው እንዳይጥሉት… ምናምን?" "አሁን'ኮ እንደሱ አይነት ስሜትን አልፌዋለሁ። ድሮ ነበር...ልጅ እያለ። አሁንማ አጣጥፏቸው እንደሚሄድ ስለማውቅ" (ሳቀችና አሳቀችኝ) ከድሮም ኳስ ትወጂ ነበር ግን? "ኧረ እኔ ማንቼ አርሴ ከሚሉት አልነበርኩም! ማረንዬ ኳስ መግፋት ሲጀምር ነው በልጄ ውስጥ 'ፉትቦል' እያፈቀርኩ የመጣሁት..." አሁን ማክዳ የለየላት የኳስ ተንታኝ መሆን ይቃጣታል፤ ተደራቢ አጥቂ አምጥቶ በ 'ካውነተር አታክ' ነበር 'ፈርስት ሃፍ መጨረስ የነበረበት' ምናምን ትላለች። በጨዋታ መሀል ሌላ ጥያቄ ሰነዘርኩ። ልቧ እንደሁ ልጇ ጋ ሄዷል። ጮክ ካላልኩ አትሰማኝም። "ልጅሽ ግን ምነው ኮሰስ አለ፤ እያቸው ጓደኞቹን ምን እንደሚያካክሉ...ማረን ደቃቃ ነው...አታበይውም እንዴ?" በነገር ጎነተልኳት። በግማሽ ልብ ወደኔ ዞራ ተኮሳትራ ካየችኝ በኋላ..."…የኔ ልጆች የጭንቅላት ተጫዋቾች ናቸው እሺ!" አለችኝ። ነገሩ ከነከናት መሰለኝ ኳስ ወደ ውጭ መውጣቱን ተመልክታ ፋታ ስታገኝ ማብራሪያ አከለችልኝ…። "የኔ ልጆች ማረንም ቅዱስም ጥበበኞች ናቸው፤ ፈጣን ጭንቅላት አላቸው፤ ካላመንክ አሰልጣኞቻቸው ጠይቅ። እንደዚያ ነው የሚሏቸው። ኳስ ጉልበት ብቻ አይደለም...።" ማክዳ ከክለብ የዶርትሙንድ፣ ከተጫዋች የሜሲ ደጋፊ የሆነችውም በነርሱ ውስጥ ልጇ ማረን ስለሚታያት ይሆናል። ማረን ቢጫወት ደስ የሚላትም ወይ ላሊጋ ወይ ቡንደስሊጋ ውስጥ ነው። አቶ ምሥጢረም የባለቤቱን መንገብገብ አይቶ ነው መሰለኝ እሷን ደግፎ ተናገረ፤ "በእርግጥ የሰውነት ግዝፈት አስፈላጊ ነው፤ ሆኖም ግን የግድ አይደለም። የኔ ልጆች ለምሳሌ ጥበባቸውና በፍጥነታቸው ከመጀመርያው ረድፍ የሚመደቡ ናቸው፤ እዚህ አገር "እሽፒል ኢንተለጀንስ" ይሉታል። ጨዋታን ቀድሞ ማንበብ። ያን የታደሉ ናቸው። ማረንን በዚህ ረገድ ሁሉም አሰልጣኝ የሚመሰክርለት ልጅ ነው።" የማረን ቡድን አንድ ለባዶ ተሸነፈ ማረን ኃይለሥላሴ መልከ ቀና፣ ለግላጋ ወጣት ነው። ግሩም የግብ ሙከራ አድርጎ፣ አልያም ጎል አስቆጥሮ፣ አልያም ኳሷ ለጥቂት የግብ ማዕዘን ስትገጭበት የሚያሳየው ፈገግታ መለስተኛ የስታዲየም ፖውዛ ነው፤ በእርግጥ ይህ ዓረፍተ ነገር ተጋኗል። የማረን ፈገግታ ግን አልተጋነነም። በኔ እይታ ሜዳ ላይ በቆየበት አጭር ደቂቃዎች እጅግ ማራኪ እንቅስቃሴን አሳይቷል። ደጋፊውም በከፍተኛ ጩኸት ድጋፉን ገልጾለታል። ተደራቢ አጥቂ ነበር። ጨዋታው ሊጠናቀቀ ጥቂት ደቂቃዎች በቀሩት ጊዜም አንድ ያለቀለት ግሩም ኳስ አቀብሏል። ምን ዋጋ አለው…። ልክ 90ኛ ደቂቃው ላይ ፊሽካ ሲነፋ ማረን ሮጦ መልበሻ ክፍል አልገባም። ዓይኖቹ ወደ ክቡር ትሪቡን ያማትራሉ። ወደ ወላጅ እናቱ ማክዳ ይንከራተታሉ። አቶ ምሥጢረና ወ/ሮ ማክዳ ተንደርድረው ከወንበራቸው ይነሱና የትሪቡኑን ደረጃ ጥንድ ጥንዱን እየዘለሉ ተመልካችና ተጫዋችን የሚያግደው አጥር ላይ ይደርሳሉ። • ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ "ማረንዬ! ዛሬ ደግሞ ልዩ ነበርክ" ትለዋለች እናቱ። "አንበሳ የኔ ልጅ" ይሉታል አባቱ አቶ ምሥጢረ። እሱ ምንም አይልም። ፈገግታውን ይመግባቸዋል። ዐይናፋር ሳይሆን አይቀርም። ዐይናፋርነቱ በንኖ የሚጠፋው ከባለጋራ በረኛ ሲገናኝ ብቻ ነው ትላለች እናቱ። እኔም ተከትያቸው ወረድኩ። ከአገር ቤት የመጣሁ ጋዜጠኛ መሆኔን ጠቅሼ አጭር ቃለ ምልልስ እንዲሰጠኝ ጠየቅኩት። ብዙም አልተስማማም። እያቅማማ አማርኛም እየቸገረው ‹‹ጥሩ ጌም ነበር፤ አቻ መውጣት ነበረብን። ያንግ ቦይስ ግን ከባድ ቡድን ነው›› አለኝ። "ለምንድነው 90 ደቂቃ ያልተሰለፍከው? አልኩት። "እሱን የሚመልስ አሰልጣኝ ነው፤ አኔ የለም" አለኝ ከትሁት ፈገግታ ጋር። ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ሕልም አለህ? አንድ ቀን…። "እኔ'ንጃ…እኔ መናገር አላውቅም"። (ምናልባት 'በእኔ ፍላጎት የሚወሰን ነገር አይደለም ማለቱ መሰለኝ) ሁላችንንም ቻው ብሎን ወደ መልበሻ ክፍል እየሮጠ ገባ። ፈገግታውን ታቅፈን ቀረን። ድኅረ ታሪክ ወደ ናይሮቢ የቢቢሲ ቢሮ ተመልሼ ይህን ዘገባ ለድረ-ገጽ ኅትመት ከመስደዴ በፊት ወደ ዙሪክ የመጨረሻ የጽምጽ መልእክት ሰደድኩ፤ ‹‹ምን አዲስ ነገር አለ?›› የሚል። "አንተ ከተመለስክ በኋላ ማረን አስደናቂ አቋም እያሳየ ነው፤ ባለፈው ከFC Thun ቡድን ጋር በነበረው ጨዋታ 3-2 ሲያሸንፉ የማሸነፊያዋን ጎል ማን ያስቆጠረ ይመስልኻል?" "ማረን ኃይለሥላሴ?" "በትክክል!" "ሌላም ዜና አለ፤ ታናሹ ቅዱስ ኃይለሥላሴም ለZurich FC ለመጫወት በይፋ ፊርማውን አስቀምጧል። የአገሬው ጋዜጦችም ይህንኑ ዘግበዋል። ታዲያ ይሄ ደስ አይልም?" "በጣም እንጂ! በጣም!" ማረን የማሸነፊያ ጎሏን ያስቆጠረ "ለታ እናቱ ወ/ሮ ማክዳ እንዴት ሆና ይሆን?
44352206
https://www.bbc.com/amharic/44352206
በቱኒዚያ የ48 ስደተኞች ሕይወት አለፈ
ስደተⶉቹን የጫነቸው ጀልባ በምሥራቅ ጠረፍ ቱኒዚያ ተገልብጣ ነው በትንሹ 48 ስደተኞች የሞቱት። እጅግ ቢበዛ 90 ሰዎችን መጫን የምትችለዋ ጀልባ 180 የሚሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ነበር። ከነዚህም ውስጥ አንድ መቶ የሚሆኑት ቱኒዚያዊያን ወጣቶች ነበሩ።
ሌሎች 67 ስደተኞች ደግሞ የጠረፍ ጠባቂዎች ከሞት ታድገዋቸዋል። ቱኒዚያ አሁን አሁን አማራጭ የስደተኞች ማቋረጫ እየሆነች ነው። ይህም የሆነው በሊቢያ በስደተኛ አስተላላፊዎች ላይ ዘመቻ በመከፈቱ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። አደጋው እንዴት እንደደረሰ የተናገረ አንድ ከሞት ያመለጠ ስደተኛ እንደሚለው የጀልባዋ ሾፌር የጠረፍ ጠባቂዎችን ሲያይ በመስጠም ላይ የነበረችዋን ጀልባ ጥሎ በመጥፋቱ ነው አደጋው የደረሰው። ዋእል ፈርጃኒ የተባለ ሌላ ስደተኛ እንደተናገረው ደግሞ ጀልባዋ ውስጥ ውሀ መግባት በመጀመሩ ነው አደጋው የደረሰው። "ማምለጥ የቻሉት አመለጡ፤ ሌሎች ግን እዚያ መስጠም ጀመሩ" ብሏል። መጀመርያ አሳ አጥማጆች ከዚያም የባሕር ኃይል አባላት እንደደረሱላቸውም ጨምሮ ተናግሯል። ሥራ አጥ ቱኒዚያዊያን እና ሌሎች አፍሪካዊያን ሜዲቴሪያንን ለማቋረጥ መናኛ ጀልባዎችን በመጠቀም ከቱኒዚያ ሲሲሊ ድረስ እጅግ አደገኛ ጉዞን ያደርጋሉ። ይህ የሞት ዜና የተሰማው የኢጣሊያ አዲሱ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ማቲዮ ሳልቪኒ ሲሲሊን በሚጎበኝበት ወቅት ነበር። ሚኒስትሩ "ሲሲሊ የአውሮፓ የስደተኞች ቋት መሆኗ ሊያበቃ ይገባል" ብለዋል።
news-56136264
https://www.bbc.com/amharic/news-56136264
የኑሮ ውድነት፡ በኢትዮጵያ የዋጋ ጭማሪ እንጂ ቅናሽ የማይታየው ለምን ይሆን?
በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት እና በኑሮ ውድነቱ የተማረሩት የቤተሰብ አስተዳዳሪ ሁሌም ለሸቀጦች ዋጋ መጨመር ነጋዴው ምክንያት የሚሰጣቸው የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የዶላር ምንዛሬ ዋጋ መናርን እንደሆነ ለቢቢሲ ይናገራሉ።
"ፈሳሹ ዘይት ተፈልጎ አይገኘም" የሚሉት እኚህ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ከዚህ ቀደም አንድ እንጀራ በ10 ብር ይገዙ እንደነበር አስታውሰው 12 ብር መግባቱን በምሬት ይናገራሉ። የኑሮ ውድነቱ ግን አዲስ አበባን መኖሪያቸው ያደረጉትን ብቻ አይደለም የተጫነው፣ በሐረር ከተማ የሚኖሩት ወ/ሮ ሽርካ አሕመድ ዘንድሮ የገጠማቸው የዕቃዎች ዋጋ መጨመር ከዚህም በፊት ከነበረው ሁሉ የተለየ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ኑሮ እጅግ ተወዶብናል። ለምሳሌ አንድ ኪሎ ቲማቲም 12 ብር የነበረው በአሁኑ ሰዓት 25 ብር ገብቷል። ከጥቂት ቀናት በፊት በ265 ብር ይገዛ የነበረው ዘይት 430 ገብቷል። ከሶስት ወራት ወዲህ ያልጨመረ አንድም ነገር የለም። ከአቅማችን በላይ ሆኗል" ሲሉ ተስፋ በመቁረጥ ይናገራሉ።። ወ/ሮ ሽርካ በሁሉም እቃዎች ላይ የሚታየው የዋጋ ጭማሪ 'ዶላር ስለጨመረ ነው' ሲባል ከመስማት ውጪ ምክንያቱ ይህ ነው ብሎ ያስረዳቸው የለም።። በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት የአጋሮ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ እመቤት ከድር በበኩላቸው፣ በገበያ የሚታየው የዋጋ ንረት "ጠዋትና እና ከሰዓት በኋላ የዋጋ ልዩነት ማሳየት ጀምሯል" ይላሉ። "እኔ የችርቻሮ ነጋዴ ነኝ፤ ከኅብረተሰቡ ጋር በቀጥታ እገናኛለሁ፤ እኛ ደግሞ ከጅምላ አከፋፋዮች እንገዛለን። እኛ እነርሱን ስንጠይቅ፣ የጨመረው ከላይ ነው ይሉናል፤ ግልጽ የሆነ ምክንያት የለም። እኔ አሁን ይህንን የሕዝብ ምሬት መስማት አቅቶኝ ሥራዬን እያቆምኩ ነው" ይላሉ ወ/ሮ እመቤት። አክለውም "አንድም ዋጋው አልጨመረም የምንለው ነገር የለም። አንተ ጠዋት አንድ እቃ ከሸጥክ፣ ከሰዓት በኋላ ዋጋው ጨምሯል። እቃው ግን ያው ጠዋት የነበረው ነው። ተገቢ ቁጥጥር መደረግ አለበት" ሲሉ ለመፍትሄው የመንግሥትን እጅ ይማፀናሉ። የነዳጅ ዘይት እንደ ሰበብ በዚህ ወር ውስጥ ዋጋቸው ከጨመረ ነገሮች መካከል የነዳጅ ዘይት አንዱ ነው። በዚህም ምከንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። ኢትዮጵያ ከውጪ የምታስገባው የነዳጅ ዘይት በሁለት አቅጣጫዎች፣ በሱዳን እና ጅቡቲ በኩል የነበረ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሱዳን በኩል የሚገባው መቋረጡን የቢሮው ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አለማየሁ ፀጋዬ በሱዳን በኩል የሚገባው ነዳጅ ቢቋረጥም፣ አገሪቷ ከውጪ በምታስመጣው ነዳጅ ላይ ግን የታየ ለውጥ የለም ይላሉ። "በነዳጅ አቅርቦት ላይ ከዚህ በፊት በነበረው ላይ ልዩነት የለም። በሱዳን በኩል ይገባ የነበረው ቤንዚን ብቻ ነው። እንደውም በጥገና ምክንያት ይገባ ከነበረው የቀነሰ እና ለተወሰኑት ከተሞች ብቻ ሲቀርብ የነበረ ነው። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ደግሞ ይገባ የነበረው ራሱ ተቋርጦ ነው የቆየው" መሆኑን ገልፀዋል። በሱዳን በኩል ይቀርብ የነበረው ነዳጅ፣ ቀድሞ የተቋረጠ እና በሁለቱ አገራት መካከል ካለው የድንበር ውዝግብ ጋር የማይገናኝ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ነዳጅን ከመካከለኛው ምስራቅ፣ በጅቡቲ በኩል እያስገባች መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው የሚናገሩት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው፣ በሱዳን በኩል የነበረው አቅርቦት ከተቋረጠ ወዲህም የአቅርቦት እጥረት አልተፈጠረም ብለዋል። በኢትዮጵያ ከሰላሳ በላይ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ከውጪ የሚገባውን ይህንን ነዳጅ ለተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያቀርባሉ። በነዳጅ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪም ከዓለም ገበያ ዋጋ ጋር የተያያዘ እንጂ በአቅርቦት መቀነስ ምክንያት እንዳልሆነ ኀብረተሰቡ ሊረዳ ይገባል ሲሉ አቶ አለማየሁ ፀጋዬ ያስረዳሉ። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን የሚወስነው የንግድ ሚኒስቴር በመሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የጨመረበትን ምክንያት ለማጣራት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ የማይታየው የኑሮ ውድነት የምጣኔ ኃብት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ጉቱ ቴሶ አሁን በኢትዮጵያ ለገጠመው የኑሮ ውድነት ምክንያቶቹ በርካታ መሆናቸውን ያስረዳሉ። ቀዳሚዎቹ ግን ከዓመት ዓመት መጨመር እንጂ መቀነስ የማያሳየው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አንዱ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ይህ በየዓመቱ መጨመር ብቻ የሚያሳየው የዋጋ ግሽበት መንስዔው መሠረታዊ የሆኑ የምጣኔ ኃብት መዋቅሮች አለመስተካከል ጋር ተያይዞ መሆኑን ገልፀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ ወቅታዊ የሆኑ እና የአገሪቱን ምጣኔ ኃብት ፈተና ውስጥ የሚጥሉ ክስተቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፥። ዶ/ር ጉቱ የምርት አቅርቦት እየቀነሰ መምጣት፤ የሰላም መታጣት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ መፈናቀሎች ለገበያው ዋጋ መናር ምክንያቶች መሆናቸውንም ይጠቅሳሉ። በአገሪቱ ውስጥ የተካሄዱ ሕዝባዊ አመጾች፣ የተደረጉ ተከታታይ የገበያ እቀባዎች፣ የንግድ ሰንሰለቱን በተጋጋሚ መሰበራቸውን፣ በተለይ ደግሞ ትርፍ አምራች በሆኑ አካባቢዎች በሰላም እጦት ምክንያት ተደራራቢ ጫና መፍጠሩን ያስረዳሉ። ገበሬው በሰላም እጦት ምክንያት ቢያርስ እንኳ አልጎለጎለም የሚሉት ባለሙያው፣ የጎለጎለው መዝራት ሳይችል ሲቀር፣ የዘራ ደግሞ መሰብሰብ አለመቻሉ የእርሻ ምርቶች አቅርቦት እየቀነሰ እንዲመጣ ማድረጉን ይገልጻሉ። የምጣኔ ኃብት ባለሙያው አክለውም በርካታ ኢንደስትሪዎችም ከውጪ አገር ግብዓት ስላላገኙ ወይንም በሰላም እጦት ፍራቻ ምክንያት ምርት መቀነሳቸው ወይንም ማቆማቸው ሌላው ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ ካደረጉ ነገሮች መካከል አንዱ ነው። እነዚህ ማምረት የሚያቆሙ ኩባንያዎች በበዙ ቁጥር ለኑሮ ውድነቱ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የሚገልጹት ዶ/ር ጉቱ፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ተደራርበው የኑሮ ውድነትን ማክበዳቸውን ይገልጻሉ። "ከ2017 እስከ 2021 (እኤአ) የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም በ54 በመቶ ወርዷል፤ በአጠቃላይ ሲታይ በአስር ዓመታት ውስጥ የኢትዮጰያ ብር የመግዛት አቅም በመቶ እጅ ወድቋል" የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ የምግብ አቅርቦትና ሌሎች የዕለት ፍጆታ የሆኑ ምርቶች የብር የመግዛት አቅም በወደቀበት በዚህ ጊዜ ከውጪ ሲገቡ የኑሮ ውድነትን እንደሚያባብሱ ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ምርት የሚያመርቱ አብዛኞቹ ኢንደስትሪዎች ከውጪ በሚገባው ግብዓት ላይ የተንጠለጠሉ በመሆናቸው ይህንን ችግር ለመፍታት ያላቸውን ሚና ማሳነሱንም ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የኑሮ ውድነት ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ከቀጠለ አገሪቷን ውስብስብ ወደ ሆነ ችግር ሊመራት እንደሚችል ባለሙያው ይመለክታሉ። "ሰው በኢኮኖሚ ሲዳከም ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ይሰደዳል። እንደዚህ ዓይነት ስደት ደግሞ በከተሞች ላይ ማህበራዊ ቀውስን ያስከትላል። የሚበላው ያጣ ሕብረተሰብ ደግሞ ወደ ተቃውሞ እና ሽብር ይሄዳል። ይህ ደግሞ አሁንም ምልክቱ እየታየ ነው" ብለዋል። የሥራ ማጣት፣ የኑሮ ውድነት እና ሌሎች ምክንያቶች ችግሮች፣ መጀመሪያውኑ አሁን ካለንበት አዙሪት ውስጥ እንዳንወጣ ያደርጉናል የሚል ስጋት እንዳላቸው ጨምረው ይናገራሉ። መፍትሔው ምንድን ነው? የኑሮ ውድነትን ጨምሮ ለበርካታ የአገሪቱ ችግሮች መነሻ የሆነው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት የመጀመሪያው ምርጫ መሆን እንዳለበት ዶ/ር ጉቱ ያመለክታሉ። "ሰላም ከሌለ ኢንቨስትመንት የለም፣ ወደ ውጪ መላክ የለም፣ ምርትን አጓጉዞ ማከፋፈል የለም። ሰላም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መኖር ያለበት ጉዳይ ነው። ለዚህ ደግሞ መንግሥትና ሌሎች ድርጅቶች አብረው ሆነው መወያየት አለባቸው። ግጭት ከሁሉም ወገን መቆም አለበት" ሲሉ ይመክራሉ። የውጪ ምንዛሬ ላይ በፍጥነት ማስተካከያ መደረግ አለበት የሚሉት የምጣኔ ኃብት ባለሙያው፣ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ ከቀጠለች አስቸጋሪ የምጣኔ ኃብት ቅርቃር ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ገልፀዋል። ብር የመግዛት አቅሙ ከቀን ወደ ቀን መቀነሱ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም እንዳለበትም ይመክራሉ። አሁን ያለው የውጪ ምንዛሬ ከዚህም ባነሰ በ30 እጅ ወደ ኋላ መመለስ አለበት ይላሉ። አሁን የብርን ዋጋ እንዲወርድ ማድረግ በኢንቨስትመንትም ሆነ በውጪ ንግድ አንጻር ለኢትዮጵያ የሚያመጣው ፋይዳ የለውም ብለዋል። የአገሪቷን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ለማድረግ፣ የባህልና ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ አለበትም የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ የህዝቦች የሥራ ባህልም ላይ መሻሻል መደረግ አለበት በማለት ሃሳባቸውን ያጠናቅቃሉ።
45271294
https://www.bbc.com/amharic/45271294
የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል-አቀባይ፡ "ለደቡብ ሱዳን ሰላም የኢትዮጵያን ያህል የባጀ የለም"
የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ቃል-አቀባይ በ2010 የተከናወኑትን አበይት ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶችን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት አንዳንድ እድገቶችን መሰረት አድርገው በመገኛኛ ብዙሃን የሚሰሩ ዘገባዎች ሙሉውን ስዕል አይሰጡም ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ቃል-አቀባይ አቶ መለስ ዓለም የደቡብ ሱዳን የሰላም ሥምምነት የደረሰበትን ደረጃ ኢትዮጵያ ጊዜ ሰጥታ የደከመችበትና የለፋችበት ትልቁ ስራ ነው ማለት ነው የገለጹት። "ዋነኞቹ የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ መሪዎች ሬክ ማቻርና ሳልቫ ኪር ከአንድ ዓመት በላይ ላለመተያየት ወስነው ከቆዩ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሸምግልናና ጫና ነው ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ላይ በአንድ ክፍል በአንድ ጠረጴዛ፤ በአንድ ገበታ ላይ መቀመጥ የቻሉት" ብለዋል። በሬክ ማቻርና ሳልቫ ኪር የቅርቡ ሰላም ስምምነት የተደረገው በሱዳን መዲና ካርቱም መሆኑ ይታወሳል። ከአዲስ አበባው ውይይት በኋላ የተካሄዱት ስብሰባዎች በኢጋድ የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆነችው ኢትዮጵያ የተሰጡ ኃላፊነቶች መሆናቸውን ነው የተናገሩት። • በሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሰቆቃ እስከመቼ? • የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር አልተሳካም ቃል አቀባዩ በአሜሪካ ምክር ቤት የጸደቀውን "የኤች አር 128" የውሳኔ ሃሳብ በማርቀቅ ጉልህ ሚና የነበራቸው ክሪስ ሚዝ አዲስ አበባ እንደሚመጡና ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰብዓዊ መብትና ከዴሞክራሲ አንጻር የተሰሩ ጅምር ስራዎችን በአካል የማየት ዕድል እንደሚኖራቸው አብራርተዋል። ቃል-አቀባዩ ጨምረው እንደተናገሩት የቬትናም ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ።
news-48880777
https://www.bbc.com/amharic/news-48880777
የብ/ጄነራል አሳምነው ፅጌ ሚስት መታሰራቸውን ልጃቸው ገለጸች
መንግሥት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ባህር ዳር ከተማ ለተፈፀመው የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው ያላቸው የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት ወይዘሮ ደስታ አሰፋ በፖሊስ መያዛቸውን ልጃቸው ማኅሌት አሳምነው ለቢቢሲ ገለፀች።
የቡራዩ ከተማ የጸጥታና አስተዳደር ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ወ/ሮ ደስታ በሕግ አግባብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቢቢሲ ያረጋገጡ ሲሆን፤ ተሞክሯል ከተባለው መፈንቅለ መንግሥት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለማግኘት ከሚደረገው ምርመራ ጋር በተያያዘ እንደሆነም ተናግረዋል። ማኅሌት እንደተናገረችው እናቷ በፖሊስ ከቤታቸው የተወሰዱት ትናንት ሐሙስ ዕለት ቡራዩ ውስጥ በተለምዶ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነው። • አዴፓ እነ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን "የእናት ጡት ነካሾች" አለ • "ሌሎችንም ከፍተኛ ባለስልጣናት የመግደል ዕቅድ ነበረ" ማኅሌት እናቷ በመጀመሪያ የተወሰዱት እዚያው አካባቢ ወደሚገኘው አሸዋ ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ጠዋት አያቷ ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሲጠይቁ "ወደ ሌላ ቦታ" መወሰዳቸው እንደተገለፀላቸው ብትናገርም ወ/ሮ ደስታ አሁንም በቡራዩ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ አቶ ሰለሞን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ልጅ ማኅሌት ለቢቢሲ እንደተናገረችው ከጥቂት ቀናት በፊት መላ ቤተሰባቸው ለሃዘን ላሊበላ በነበረበት ወቅት አያቷ (የእናቷ እናት) እና የቤት ሰራተኛ እንዲሁም የጎረቤት ምስክር ባለበት ቤታቸው በፖሊስ ተፈትሾ አንድ የቤት መኪና፣ ላፕቶፕና የተለያዩ ማስረጃዎች መወሰዳቸውን የገለጸች ሲሆን አቶ ሰለሞንም ይህንን አረጋግጠዋል። ማኅሌት ጨምራም እንደተናገረችው ፖሊስ በድጋሚ ለምርመራ በማግስቱም ወደ መኖሪያ ቤታቸው መጥቶ ነበር። ቢቢሲ ስለወይዘሮ ደስታ አሰፋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆንን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃን ከፌደራል ፖሊስም ሆነ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። • "ብ/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን ከዚህ በተጨማሪም የአባቷ ወንድም በብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ቀብር ላይ እንዳልተገኙና እስካሁም የት እንዳሉ ቤተሰብ ባለማወቁ መጨነቁንም አክላለች። ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ተሞክሯል የተባለው መፈንቅለ መንግሥት መሪ እንደነበሩና በክስተቱ ለሞቱት ከፍተኛ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ተጠያቂ መሆናቸው በተደጋጋሚ ተገልጿል። ከጥቃቱ የተረፉ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናትም ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጥቃቱን በአካል ሲመሩ እንደነበር ምስክርነት የሰጡ ሲሆን የእርሳቸው ነው ተብሎ በድምጽ በወጣው ማስረጃም በአመራሩ ላይ እርምጃ መወሰዱን ሲናገሩ ተደምጧል። ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ከግድያው ጥቂት ቀናት በኋላ ከባህር ዳር ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ዘንዘልማ በሚባል ስፍራ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደላቸውን መንግሥት ማስታወቁ ይታወሳል።
news-44672022
https://www.bbc.com/amharic/news-44672022
ክረምትና ንባብ
መፅሀፍ አዟሪዎች ከተመረጡ መፅሀፍ መካከል ምርጦቹን ነው ይዘው የሚዞሩት ይላል መኮንን። "ቢሸጡ ጥቅም ያላቸው፣ አንባቢም ይፈልጋቸዋል የተባለውን ነው ይዘን የምንዞረው።"
መኮንን ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ መነን አካባቢ ነው፤ መፅሀፍ ማንበብ ይወድ እንደነበር ያስታውሳል። ስራ ሲፈታም ፒያሳ መፅሀፍ ዘርግተው የሚሸጡ ጓደኞቹ ጋር እየሄደ መዋል ጀመረ። ጓደኞቹ ጋር ሲውል ያስተዋላቸው ነገሮች ግን የስራ በር ከፈተለት። ወደ ጃፋር መፅሐፍት መሸጫና ማከፋፈያ ሄዶ በአዟሪነት ስራ ጀመረ። በጋሪ አዙሮ መፅሐፍ የሚሸጥ 120 መፃህፍት ብቻ ነው መያዝ የሚችለው የሚለው መኮንን በጀርባው ተሸክሞ ይዞ የሚዞር ደግሞ ከ30 እስከ 50 መፅሐፍት እንደሚይዝ ይናገራል፤ አዲስ መፃህፍትን፣ 'ኮሚሽን' በደንብ የሚገኝባቸውን መርጠው ለምን እንደሆነ ሲያስረዳ። "እጃችን ላይ የማይቆይ መፅሀፍ ነው የምንይዘው።" “ከወጡት ስራዎቼ ይልቅ ገና የሚወጡት ናቸው ትልቅ ቦታ ያላቸው” አለማየሁ ገላጋይ የእለት አንባቢ ፍለጋ በርካታ አዳዲስም ሆነ የጠፉ መፅሐፎች የሚገኙበት ብሔራዊ የእርሱም ማረፊያ ነው። የበድሉ ህንፃ ጀርባን ይዞ የብሔራዊ ቲያትር ጀርባን 'የመፃህፍት ማዕከል' ይለዋል መኮንን። "እዚህ ተፈልጎ ያልተገኘ መፅሐፍ የትም አይገኝም" ሲልም ይወራረዳል። ሥራውን ሲጀምር ጀምሮ ስታዲየም ዙሪያ መፅሐፍ እያዞረ የሚሸጠው መኮንን "እኛ ወደ አንባቢው ሄደን ነው እንዲገዙን የምናግባባው" ሲል ያማራል። "ግሮሰሪ፣ ምግብ ቤት፣ ካፍቴሪያ፣ ስጋ ቤት አንባቢ ፍለጋ ይዞራል። መፅሐፍ ተሸክሞ ከመዞር ይልቅ አንባቢውን መፈለጉ፣ ማስመረጡ ማሳመኑ ከባድ ነው፤ በዚህ ላይ ደግሞ የክረምቱ ዝናብ።" "ድራፍት ለሚጠጣ ቁርጥ ለሚቆርጥ በላተኛ መፅሐፍ ግዙኝ ማለት ፈታኙ ነገር ነው። ከዛ ይልቅ ቆሎ እና በቆልት የሚያዞሩትን ፈገግ ብለው ይቀበሏቸዋል።" "ሌላው አንባቢን በጠዋት ፈልጎ ማግኘት ፈተና ነው፤ ትንሽ ረፈድ ማለት አለበት" ይላል መኮንን ከምሳ በኋላ ደግሞ ቢሆን ፍለጋው የተሳካ ይሆናል ሲል ይናገራል። በደሞዝ ወቅት ገበያው እንደሚደራ የሚናገረው መኮንን ይህንን ስራ ከባድ የሚያደርገው ሌላው ክረምቱ ነው ይላል። ከላይ ሰማዩ እያለቀሰ ከስር ጎርፍ እየወረደ መፅሐፍ ይዞ ከቦታ ቦታ እየዞሩ መሸጡ ፈታኝ መሆኑን በማስታወስ። ሌላው ይላል መኮንን "ቀኑን ሙሉ ስዞር ስውል መፅሐፍ እንዲገዙኝ ከማሳያቸው 100 ሰዎች መካከል አስሩ ይሆናል መፅሐፉን የሚያይልኝ። ከአስሩ ደግሞ አንዱ ነው ለመግዛት ፍላጎት የሚያሳየኝ፤ እርሱ ደግሞ ቀንስልኝ ብሎ ዋጋ እየቆረጠ የሚከራከር ይሆናል ይህ ደግሞ ከሚያለቅስ ሰማይ ስር ያለ ተከራካሪ ደንበኛ የበለጠ ስራውን ከባድ ያደርገዋል።" መኮንን በስራው እጅጉን ይተማመናል። "መፅሐፍ አዟሪ እጅ ያልገባ መፅሐፍ አይሸጥም" ሲል ልቡን ሞልቶ ደረቱን ነፍቶ ይናገራል። የእርሱ ስራ በአንባቢ እና በደራሲ መካከል የተዘረጋ የንባብ የሀሳብ መስመር፣ የገበያ መልህቅ እንደሆነ ያምናል። "አንባቢ ፖለቲካ ነፍሱ ነው" ይላል ደንበኞቹን እያስታወሰ። ልብ ወለድ የስነልቦና መፅህፍት የሕክምና የቢዝነስ የመንጃ ፍቃድ ትምህርት እንዲሁም የታሪክ መፅሐፍት በአይነት ይዞ ይዞራል። ለምን በክረምት? ጃፋር መፅሐፍትን በመሸጥ ስራ ላይ ለ15 ዓመታት ያህል ሰርቷል። እንደ እርሱ ከሆነ በየወሩ እቅድ ይዘው ከሚገዙ አንባቢዎች በተጨማሪ ክረምት ላይ አንባቢዎች ይበዛሉ። የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አበረ አዳሙም ማህበሩ በየዓመቱ ሰኔ 30ን የንባብ ቀን አድርጎ አስቦ የሚውልበት ምክንያት ተማሪዎችና መምህራን ከመማር ማስተማሩ ስራ እረፍት የሚያደርጉበት ወቅት በመሆኑና ይህንን የእረፍት ጊዜ ራሳቸውን ከመፅሐፍት ጋር የሚያገናኙበት እንዲሆን በማሰብ እንደሆነ ያስረዳሉ። በአዲስ አበባ ብቻ 2000 ንቁ አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ሰኔ 30 የንባብ ቀን ተብሎ እንዲታወጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ማቅረቡንም አልሸሸጉም። ይህም ፖለቲከኞችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ መገናኛ ብዙሃን ንባብ ባህል እንዲሆን እንዲሰሩ ያደርጋል ብለው ያምናሉ። "ንባብ የአንድ ወቅት ብቻ እንዳልሆነ የሚጠቅሱት አቶ አበረ ሰኔ 30ን እንደመነሻ በማድረግ ቀሪውን ጊዜ ሁሉ ስለንባብና መፅሐፍት የምንነጋገርበት እንዲሆን በመፈለግ ቀኑ ተመረጠ።" ደራሲ ሕይወት እምሻው 'ፍቅፋቂ' የተሰኘ ሁለተኛው የወግና የልቦለድ ስራዋ በዚህ ክረምት ለገበያ ውሏል። የ60 ደራሲያን ስራዎች የተካተተበት ደቦ መፅሐፍ ላይም አንድ ስራዋ ተካትቶላታል። "መፅሐፌ እንዲወጣ የፈለግኩት ግንቦት ላይ ነበር" ትላለች ሕይወት። "በአጋጣሚ ሲገፋ ሲገፋ አሁን ላይ ደርሷል" በማለት ክረምቱን የመረጠችው ግን በክረምት ተማሪዎች ከትምህርታቸው አርፈው ባለስራውም በዝናቡ ምክንያት ከቤቱ የሚወጣበት ጊዜ ስለሚቀንስ ጥሩ ገበያ ይኖራል በሚል እንደሆነ ትናገራለች። መፅሐፍን ለክረምት ብለው የሚያስቀምጡ አንባቢዎች አውቃለሁ የምትለው ሕይወት 'ንባብ ለሕይወት' የተሰኘው የመፅሐፍ አውደርዕይ ላይ ከአንባቢዎቿ ጋር ለመገናኘት እንዳለመችም አልደበቀችንም። የብራና ሬዲዮ አዘጋጁ በፍቃዱ አባይ በሕይወት ሀሳብ ይስማማል። ክረምት አንባቢን ቤቱ አስሮ ያስቀምጣል ስለዚህ ተመራጭ ነው ይላል። ከመደበኛ ትምህርት መፅሐፍት ውጭ ለማንበብ እድል የሚኖረውም ለዚህ እንደሆነ ይገምታል። ደራሲያንም ይህንን እድል ለመጠቀም በማሰብ ስራዎቻቸውን በዚህ ወቅት እንደሚያሳትሙ ይናገራል። በክረምት ወቅት በርካታ ታዋቂ ደራሲያን በአንድ ላይ ስራዎቻቸውን ለህትመት ማብቃታቸው የመነበብ እድላቸውን ይቀንሰዋል ሲል ስጋቱን ይገልፃል። ስም ያላቸው ደራሲያን በሚያወጡበት ጊዜ መፅሐፍን ለገበያ ማቅረብ ጀማሪ ደራሲዎችንና አዳዲስ መንገድን የሚከተሉ ፀሀፍትን እንዳይነበቡ ያደርጋል የሚል ስጋትም አልተለየውም። በዓመቱ በተለያየ ወቅት መፅሐፍት ቢታተሙ እና ለገበያ ቢቀርቡ ተከታታይነት ላለው የንባብ ባህል ወሳኝ ይሆናል ሲልም ያክላል። ወቅቱ አንባቢን ብቻ ሳይሆን አውደርዕይ አዘጋጆችንም እንደሚስብ የሚናገረው በፍቃዱ የንባብ ለሕይወትን የመፅሐፍት አውደ ርዕይ እንደምሳሌ ይጠቅሳል። የንባብ ለህይወት የመፅሀፍት አውደ ርዕይ አስተባባሪ ቢኒያም ከበደ እነዚህ አውደ ርዕዮች በግድ ክረምት ላይ መሆን አለባቸው ብሎ አያምንም። በበጋ ወቅት በተካሄዱ አውደርዕዮች ግን የጎብኚዎች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነ ታዝቧል። መፅሐፍ እና ቴክኖሎጂ በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን መፅሐፍት ተጠርዘው በእጃችን ሲገቡ ብቻ ማንበባችንን ለበፍቃዱ አባይ የሚደንቅ ነገር ነው። በእጃችን ያለውን ቴክኖሎጂ መጠቀም ጉዳይ ላይ ብዙ እንደሚቀረን ሲያስረዳ "ሞባይል ይዘን እጃችን ላይ ሰዓት ያሰርን፣ ሞባይል ይዘን ሰዓት የምንጠይቅ ሰዎች ብዙ ነን" ሲል ያለውን ክፍተት ያሳያል። ለበፍቃዱ ደካማ የንባብ ባህል መኖሩ እና ቴክኖሎጂውን ለመጠቀም ብዙ ገፍቶ አለመኬዱ ስኬታማነቱን ቀንሶታል። አቶ አበረ አዳሙ በየትኛውም መልኩ ንባብ መዳበሩን ይደግፋሉ። "ማንኛውም ሰው ሳያነብ እንዳይውል እንዳያድር ነው የምፈልገው። የማንበቢያ መንገዱ በየትኛውም መልኩ ቢሆን ንባብ የህይወታችን የዕለት ተዕለት ዘይቤ አንደኛው መልክ ቢሆን እመርጣለሁ።" ለሕይወት እምሻው የመፅሐፍ ሽታ፣ ወረቀቱን እየገለጡ እየዳበሱ ማንበብ በእጅ ዳጎስ ያለውን መፅሐፍ ይዞ መጓዝ ምትክ የማይገኝለት ነው። በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ በላፕ ቶፕ ወይም በታብሌት ላይ ማንበብ ለእርሷ የማይታሰብ ነው። "በርግጥ ዘመኑ በአዳዲስ የቴክኖሎጂ መንገዶች ማንበብ የሚቻልበት ቢሆንም የኔ ምርጫ ግን የሚገለጥ መፅሐፍ ነው" ስትል ሀሳቧን ታስረግጣለች። "መፅሀፍትን እየገለጥኩ ሳነብ ከመፅሐፉ ጋር አንዳች ግንኙነት እንዳለኝ አስባለሁ። በርግጥ አማራጩን ማስፋት ቢቻልና መፅሐፍት በመቀመሪያቸው ላይ ሆነው ማንበብ ለሚፈልጉ መቅረብ ቢችል ጥሩ ነው።" ቢኒያም በአውደ ርዕዮች ላይ እንደታዘበው የኤሌክትሮኒክስ መፅሐፍት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው። "ይህ ነገር ግን በሃገራችን በአግባቡ እንዲሰራ ከኢንፎርሜሽን ዘርፉ ጋር በሚገባ ማስተሳሰር ያስፈልጋል። በመረጃ መረብ ላይ በቀላሉ መፅሐፍቶችን የምናገኝበት በቀላሉ ሰብ ስክራይብ የምናደርግበት መንገድ ቢመቻች ነገሮች አሁን ከምናስባቸው ውጭ ይሆናሉ።" መፅሐፍ ሻጮችን ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያው ጋር ማስተሳሰር እና እነዚህን ሁለቱን በጋራ የሚመራ አንድ አካል ቢኖር መፅሐፍን 'ዲጂታላይዝ' በማድረግ ለአንባቢ ማድረስ ይቻላል ባይ ነው። ይህ ደግሞ ክረምትን ብቻ እየጠበቁ ከማንበብ ያላቅቅ ይሆናል የሚል ግምት አለው። ጃፋር መፅሀፍትን በእጅ ይዞ መንቀሳቀስ ከራስ ባለፈ ለሚመለከተውም የሚተርፍ ነገር አለው ብሎ ያምናል። "ልጆች እያነበብክ መሆኑን ሲያዩ የማንበብ ፍላጎት ያድርባቸዋል። ከጤናም አንፃር እኔ የምመክረው ጥራዝ መፅሐፍትን ማንበብ ነው።"
news-54497816
https://www.bbc.com/amharic/news-54497816
ትግራይ፡ ዐቃቢያነ ሕግ ጥያቄያቸው ምንድን ነው?
የትግራይ ዐቃቢያነ ሕግ በሌላ ክልሎች እና በፌደራል ከሚገኙ ዳኞች እና ዐቃቢያነ ህጎች ጋር ተመሳሳይ ሥራ እየሰሩ በደሞዝ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንደተነጠሉ እንዲሁም ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት፣ ተቋማዊ ነፃነታቸውን በመከልከል ለሥራቸው መሰናክል እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ትግርኛ ገልፀዋል።
ይህንን የመብት እና የፍትህ ጥያቄያቸው ለወራት ለክልሉ ፍትህ ቢሮ ቢያቀርቡም ተገቢ ምላሽ አላገኘንም ይላሉ። የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ ዐቃቢያነ ሕጎቹ ያነሱት የደሞዝ ጥያቄ ትክክለኛ መሆኑን ይናገራሉ። ለደኅንነቱ ሲባል ስሙ የተቀየረው ዐቃቢ ሕግ ዳንኤል በሌሎች ክልሎችና በፌደራል ከሚገኙ ዐቃቢያነ ሕጎችና ዳኞች ጋር ትልቅ የደሞዝ ልዩነት መፈጠሩ አሁን በክልሉ ዐቃቢያነ ሕጎች ዘንድ ለተፈጠረው ቅሬታ ትልቁ መነሻ እንደሆነ ይገልፃል። በሌሎች ክልሎችና በፌደራል ለሚገኙ ዐቃቢያነ ሕጎች "ከ15 ሺህ እስከ 20 ሺህ ብር ድረስ ደሞዝ እየተከፈላቸው እኛ ግን 8700 ብር ብቻ ነው የምናገኘው። ይህ ልዩነት ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ የተፈጠረ ነው" ይላል። በትግራይ ደቡባዊ ምሥራቅ ዞን ዐቃቢ ሕግ የሆነችው ትዝታ ጌታቸውም ይህ ልዩነት እንዲፈታ ቢማፀኑም ሰሚ እንዳጡ ትናገራለች። "ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያ የሚል ቢደነገግም እኛ ግን ዝቅተኛ ክፍያ ነው የምናገኘው። ለወራት የፍትህ ቢሮ ኃላፊን ጠይቀናል፤ እስከኣሁን ጥያቄያችን አልተመለሰም" ትላለች። "ኑራችን ከእጅ ወደ አፍ ሁኗል" ይህ ልዩነት በክልሎችና በፌደራል ካሉት ዳኞች እንዲሁም ዐቃቢያነ ሕግ አንጻር የተፈጠረ ብቻ ሳይሆን፤ በክልሉ ካሉ ዳኞችም ጋር ተፈጥሯል። ዐቃቤ ሕግ ዳንኤል "ለትግራይ ክልል ዳኞች ከ80 እስከ 100 ፐርሰንት የደሞዝ ጭማሪ ተደርጓል። ለዐቃቢያነ ሕጎች ግን በፌደራልና በትግራይ ክልል መካከል ለተፈጠረው ልዩነት ፖለቲካዊ ሁኔታ 'በመመከት ላይ ስለሆንን' አንጨምርላችሁም" የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ይናገራል። "በክልሉ ላሉ ዳኞች ደሞዝ ባይጨመርላቸው 'በመመከት ላይ ነን' ያሉት ምክንያታቸው አሳማኝ ይሆን ነበር" በማለት ለድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ሳይቀር ጭማሪ መደረጉን በመጥቀስ ለአንዱ ተጨምሮ ሌላውን ማግለል በፍፁም ምክንያታዊ ሊሆን አይችልም ይላል። ሌላኛው ዐቃቤ ሕግ ሙዑዝ ፀጋይ ደግሞ የእኩልነት ጥያቄ ቢያነሱም የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ "የዳኞችን ደሞዝ እንቀንሳለን እንጂ የናንተ ደሞዝ አይጨምርም' ከሚል ውጪ ሌላ መልስ እንዳልሰጣቸው በመግለፅ፤ ዐቃቢያነ ሕጎች ተስፋ በመቁረጥ ሥራቸውን እያቋረጡ እንደሆነ ይናገራል። "ዐቃቤ ሕጉ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ህዝብን ለማገልገል ሲል እስከአሁን ሰርቷል። አሁን ግን እንደዚህ አይነት አመለካከት በተፈጠረበት ሁኔታ በተገቢው መንገድ ማገልገል አይችልም" ይላል ሙዑዝ። ጨምሮም ኑሮ እየከበዳቸው በመሆኑ በርካቶች ዐቃቤ ሕግነትን በመተው ወደ ጥብቅና ሞያ እየሄዱ ነው ይላል። "አይደለም ወደ ጥብቅና ወጥተው ማመልከቻ ፅፈውም ከምናገኘው ደሞዝ በላይ ነው የሚከፈላቸው" በማለት ዐቃቢያነ ሕጎቹ ተስፋቸው መሟጠጡን ገልጿል። "ሰጥቶ የሚለምን መንግሥት ነው ያለን" የክልሉ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ የክልሉ ዐቃቢያነ ሕጎች ያነሱት ጥያቄ ትክክለኛ መሆኑ በመግለፅ ጥያቄያቸውን ለመመለስ የዳኞችን ደሞዝ መቀነስ አልያም 'በመመከት ላይ ነን ያለነው' የተባለውን ግን "ውሸት" እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "በመመከት ላይ እንዳለን የሚካድ አይደለም። ዐቃቢያነ ሕጎቹ የሚያነሱት ደሞዝ አይመለከታቸውም ማለት ግን አይደለም። በደሞዝና ጥቅማ ጥቅሞች እንዲጨነቁም አንፈልግም። ጭማሪ ሲነሳ ይህን ያህል ነው መሆን ያለበት እየተባለ ነው፤ እና ምን እንበል? "የመንግሥትን አቅም የምናውቅ እኛ እኮ ነን። አፍሰን መስጠት ብንችል በሰጠናቸው፤ ግን ሰጥቶ የሚለምን መንግሥት ነው ያለን" ይላሉ በአሁኑ ጊዜ የክልሉ ዐቃቢያነ ሕጎች ከኪሳቸው ለክልሉ መንግሥት ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸው በመጠቆም። "መፈናፈኛ የሌለው" የዐቃቢያነ ሕጎች ተቋማዊ ነፃነት የክልሉ ዐቃቢያነ ሕጎቹ ካነሱት የደሞዝና የጥቅማ ጥቅም እኩልነት ጥያቄ በተጨማሪ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትና ፖለቲካዊ ሹመት ተቋማዊ ነፃነት እንዳይኖር በማድረግ ለሥራቸው እንቅፋት እንደሆነ ይናገራሉ። ዐቃቤ ሕግ ከጅምሩ ራሱን የቻለ ነፃ ተቋም ሆኖ መቋቋም ሲገባው፤ ተጠሪነቱ ለክልሉ ካቢኔ እንዲሆን የተደረገው ፖለቲካዊ ጫና እንዲያድርበት ስለተፈለገ ነው የሚሉት የሕግ ባለሙያዎቹ፤ የዐቃቤ ሕግ ተጠሪነት ከካቢኔው ውጪ እንዲሆንም ይጠይቃሉ። ዐቃቤ ሕግ ዳንኤል "ተቋማዊ ነፃነት የሚባል ነገር የለም። ማንም ካቢኔ ወይም ከንቲባ መጥቶ ነው የሚያፈጥብን፤ ይህን አድርግ ይህን አታድርግ ይላሉ። በአጭሩ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት አለ። ስለዚህ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በነፃነት ለመወሰን በጣም አስቸጋሪ ነው" በማለት ከደሞዝ ጥያቄ በተጨማሪ የተቋማዊ ነፃነት ጥያቄም እንዳለ አመልክቷል። "የበላይ ኃላፊ ሊከስ ከፈለገ የሚከስበት ብዙ ክፍተቶች አሉ። የምትወስናቸው ውሳኔዎች ትክክል አይደለም ብሎ ሊከስ አልያም ሊያባርር ይችላል። ነፃነት የሚባል ነገር የለም፤ ምንም አይነት ዋስትና የለም በጣም ከባድ ነው" ይላል። "የህወሓት አባል እንድንሆን እንገደዳለን፤ ደሞዛችንም ይቆረጣል" የክልሉ ዐቃቤ ሕግ መተዳደርያ ደንብ ላይ አንድ ዐቃቤ ሕግ የማንኛውም ፖለቲካዊ ፓርቲ አባል መሆን እንደማይችል ቢደነገግም፤ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የገዢው ፓርቲ አመራር በመሆናቸው ዐቃቢያነ ሕጎቹ የህወሓት አባል እንዲሆኑ ጫና እንደሚደርግባቸው ለቢቢሲ ገልፀዋል። በክልሉ ደቡባዊ ምሥራቅ ዞን ዐቃቤ ሕገ የሆነው ግርማይ ካሕሳይ የገዢው ፓርቲ አባል ሳይሆኑ ከወርሃዊ ደሞዛቸው ከተቆረጠባቸው መካከል አንዱ ነው። "ደሞዛችን በባንክ ገቢ ሲደረግ እየተቆረጠ መሆኑን ካወቅን በኋላ ለምን እንደሆነ ስንጠይቅ የፓርቲው አባልነት ክፍያ ነው ተባልን። እንዲመለስልን ብዙ ጊዜ ብንጠይቅም ሳይመለስልን ከፓርቲው አባላት ጋር ደሞዛችን ሲቆርጥ ሦስት ወር ሆኖናል" በማለት አባል እንዲሆኑ እንደሚጠየቁ ተናግሯል። የፍትህ ቢሮው ኃላፊ አቶ አማኑኤል ግን ይህ ቅሬታ ከእውነት የራቀ መሆኑን በመጥቀስ "አንድን የሕግ ባለሙያ የፓርቲ አባል መሆን መብት ነው ግዴታ የሚለውን ማንም ሰው ሊነግረው አይችልም። ራሱ ወዶ ነው የአንድ ድርጅት አባል የሚኮነው እንጂ ዝም ተብሎ ደሞዝ አይቆረጥም። ደሞዝ በፍቃደኝነት አልያም በህግ ነው የሚቆረጠው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ሙዑዝ ፀጋይ፣ ግርማይ ካሕሳይ፣ ትዝታ ጌታቸው የዐቃቢያነ ሕግ ድምፅ "ያከሰመው" አዋጅ ለወራት ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለማግኘት ሲማፀኑ እንደቆዩ የሚናገሩት የትግራይ ዐቃቢያነ ሕጎች መስከረም 25/2013 ዓ.ም የሥራ ማቆም አድማ ለማካሄድ እንዳሰቡ ተነግረው ነበር። ነገር ግን በተደረገባቸው ጫና ያሰቡትን የሥራ ማቆም አድማ ሳያካሂዱ እንደቀሩ ይገለፃሉ። ዐቃቢያነ ሕጎች በሚተዳደሩበት ደንብ ቁጥር 104/2012 አንቀፅ 68(21) እንዲሁም የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ 421፤ ማንኛውም ሠራተኛ አድማ ማካሄድ እንደማይችል እንደሚደነግግና አድማ ያደረገ ወይም ሌሎች እንዲያድሙ ያደረገ ማንኛውም ሠራተኛ በወንጀል ተጠያቂ ሆኖ አንድ ሺህ ብር እንደሚቀጣ ተፅፎ እንደሚገኝ የሚገልፁም አሉ። ከአሁን በፊት አዲስ ደንብ ሲፀድቅ በክልል ደረጃ ዐቃቢያነ ሕጎች እንደሚወያዩበት የሚገልፁት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ አሁን ግን ለወራት ሲያነሱት የነበሩትን የመብት ጥያቄያቸውንና ድምፃቸውን "የሚያከስምና የሚያፍን" አዲስ አዋጅ እነዙ ሳያውቁ እንዲፀድቅ መደረጉ እንዳስቆጣቸው ዐቃቢ ሕግ ሙዑዝ ፀጋይ ይናገራል። "ይህ አዲስ አዋጅ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ያፀደቁት ነው፤ እኛ ጥያቄ ካነሳን በኋላ ደግሞ አሻሻሉት። ይህም በ2011 በወጣው ደንብ ላይ የተገለፁ ጥቅማ ጥቅሞችን ያስወገደና 'በማኅበራዊ ሚድያ ለዐቃቤ ሕግ ሞያ የሚቃረን ስዕልም ይሁን ፅሁፍ የለጠፈ በሥነ ምግባር ማጉደል ይጠየቃል' የሚል ያካተተ ነው" ይላል ዐቃቤ ሕግ ሙዑዝ። በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና አስተዳደር ኮሌጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር የማነ ካሳ አዲሱን ደንብ ነባራዊ ሁኔታን ግምት ውስጥ ያላስገባና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የተደረገ "የአፈና እርምጃ" በማለት ይገልፀዋል። "ዐቃቢያነ ሕግና ዳኞች ከሲቪል ሰርቪስ ሴክተሮች በተለየ የየራሳቸው የተለየ ባህሪ ስላላቸው በደንብ የሚወጣ የራሳቸው የሥነ ምግባር ደንብ አላቸው። ይሁን እንጂ ማኅበራዊ ሚድያ በመጠቀም በወሳኝ አካል ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሆነ ስላዩ አፋቸውን ለማስያዝ ተብሎ የወጣ እንጂ ከዐቃቤ ሕግ ክብርና ሙያ ጋር የሚቃረን ነገር ከጻፉ፤ በወንጀል ሕግም፣ በራሳው የሥነ ምግባር ደንብም ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል" ይላል። ይህ የሥርዓቱ ዋና ችግር እንደሆነ የሚናገረው ተባባሪ ፕሮፌሰር የማነ ሕግ አጠቃላይ አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ነው የሚወጣው፤ አሁን እየወጡ ያሉት ሕጎች ግን አንድ ቡድንን 'ዒላማ' ያደረገ ይመስላል የሚል ትዝብት አለው። ፖለቲካዊ ሹመት እስከ መቼ? በትግራይ ክልል በመንግሥትና በገዢው ፓርቲ መካከል ያለው የቀረበ ግንኙነት፣ የትግራይ ዐቃቤ ሕግ እንዲሁም የፍትህ ቢሮ በፖለቲካዊ ሹመኛና በህወሓት ከፍተኛ አመራር የሚመራ መሆኑ በሥራቸው ላይ ጫና እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ። ሕጉ ዐቃቢያነ ሕግ የፓርቲ አባል እንዳይሆኑ ቢከለክልም "ኃላፊው የፓርቲ አባል ከሆነ የታችኛው መዋቅር አባል ባይሆንም የሚያመጣው ለውጥ የለም" ይላል ዐቃቤ ሕግ ሙዑዝ። በተጨባጭ ያለው አካሄድ ይላል ዐቃቤ ሕግ ግርማይ፤ እንደ ተማርነውና እንደ ተረዳነው እንዲሁም ኅብረተሰቡን ለማገልገል ቃል እንደገባነው ሳይሆን ዐቃቤ ሕግ የአንድ ወገን አገልጋይ ነው የሚል አስተሳሰብ የሚፈጥር ነው። በተጨማሪም በመንግሥት ጉዳዮች ላይ በተለይም በመንግሥት የፍትሃ ብሔር ጉዳዮች ሲሆኑ ሊከሰሱ የማይገባቸው 'ፍርድ-ቤት የፈለገውን ይበል' እየተባሉ እንዲከሱ እንደሚገደዱ ይናገራል። እንደ ሦስተኛ የመንግሥት አካል ፍርድ ቤት ብቻ ነው ሕገ-መንግሥታዊ የዳኝነት ነፃነት ያለው የሚሉት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ ግን "ፍትህ አንድ የመንግሥት አካል በመሆኑ ፈፃሚው አካል መንግሥት በፈለገው ጊዜ ክስ የማቋረጥ ሕጋዊ ስልጣን አለው" ይላሉ። አክለውም ወንጀል ተፈፅሞ ከሆነም ክስ ይመስረትልኝ በማለት ወደ ሚመለከተው የፖሊስ አካል እንደሚመራ ይናገራል፤ የዐቃቤ ሕግ ስልጣን "መክሰስ ብቻ እንደሆነ" ይናገራሉ። የፍትህ አካላት ከፖለቲካዊና መንግሥታዊ ጣልቃ ገብነት ነፃ መሆን አለባቸው የሚባለው ትክክል ነው የሚሉት ኃላፊው "ፖለቲካዊ ሹመት የፍትህ ሥርዓቱን ያዛባዋል" የሚለውን ግን አይቀበሉትም። "የፍትህ ቢሮን የሚመሩና የሚሰሩ ሰዎች ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሕገ መንግሥታዊ መብት አላቸው። እኔም ሕገ መንግሥታዊ መብቴ ነው። ለፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና ምክትልነት ለሹመት መርጦ የሚያመጣው ፖለቲካዊ ስልጣን የተሰጠው ፓርቲ ነው። በሦስቱ የመንግሥት አካል ውስጥም የፖለቲካ ሹመኛ ያልሆነ ሰው አይገኝም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህ አንጻር ተባባሪ ፕሮፌሰር የማነ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌድዮን ጢሞትዮስ ሹመት እንደ ምሳሌ ይጠቅሳል። በማከልም በክልላዊ ምርጫ ላይ "ለህወሓት ምረጡ" ብሎ ቅስቀሳ ሲያካሂድ የነበረው የህወሓት አመራር፤ በሌላ በኩል ደግሞ የክልሉ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ ሆኖ፤ የዐቃቢያነ ሕጉን ጥያቄዎች ምላሽ ሲነፍግ "ፖለቲካዊ ስልጣን የጨበጠውን ኃይል ፍላጎት ከማሳካት ወደ ኋላ የሚል አይደለም" በማለት ፖለቲካዊ ሹመት ከተቋማዊ ነፃነት ጋር የሚቃረን መሆኑ ያብራራል። በፍትህ ሥርዓቱ ላይ የሚኖረው ጫና በክልሉ በፍትህና በመልካም አስተዳደር ተበድለናል የሚሉ ቅሬታዎች መስማት አዲስ አይደለም፤ ይህ ገዢው ፓርቲ ህወሓትም ሳይቀር ያመነበት ነው። የዐቃቢያነ ሕጉ ቅሬታም አንድ ማሳያ ሊሆን ይችላል። ዐቃቤ ሕግ ዳንኤል እንደሚለው ካለባቸው ተደራራቢ ጫና ጋር ሕዝቡን የማገልግል ፍላጎት ቢኖራቸውም በአንድ መንግሥት ስር ሆነው እኩል አለመታየታቸውና ምላሽ ማጣታቸው የሥራ ሞራሉ እንዲቀንስ በማድረግ በተገቢው መንገድ ለማገልገል እንደሚቸገር ይገልጻል። የትግራይ ዐቃቤ ሕግ ፍትህ እንዲሰፍን ቢታገልም ለራሱ ግን በፍርሃት ወጥመድ ውስጥ የሚኖር እንደሆነ የሚገልጹት ባለሙያዎቹ፤ "ለሕዝቡ ፍትህ ለመስጠት እየታገልን ለራሳችን ግን በቢሮክራሲው እየተጎዳን ነው" ይላል ዳንኤል። "አብዛኛው በትግራይ ያለው ዐቃቤ ሕግ ፍትህ ለመስጠት ቢታገልም ለራሱ ግን ፍትህ የማይጠይቅ፣ ተሸማቆ ወይም ፈርቶ የሚኖር ነው" በማለት ሀሳቡን ይቋጫል። የመቀለ ዩኒቨርሲቲው የሕግ ምሁር ተባባሪ ፕሮፌሰር የማነ ካሳ በበኩሉ "የዐቃቢያነ ሕጎቹን ጥያቄ ማፈንም ሆነ ለማሸማቀቅ መሞከር የፍትህ ችግር ላላት ትግራይ ሌላ ተጨማሪ ችግር መጨመር ነው" በማለት መንግሥት እንዲያነጋግራቸውና ጉዳዩ ቶሎ እንዲፈታ ይጠይቃል። ከዚህ ውጪ ግን ሁኔታው ጊዜ የሚወስድ ከሆነ በትግራይ ያለው የዐቃቢያን ሕግ እጥረት እየባሰ እንዲሄድ፣ ፍትህ እንዲጓተትና እንዲበላሽ የሚያደርግ ነው በማለት አስተያየቱ ይሰጣል።
news-48412621
https://www.bbc.com/amharic/news-48412621
የጉግልና የሁዋዌ ፍጥጫ አፍሪካዊያንን የሚያሳስብ ነው?
ሁዋዌ የአንድሮይድ ሶፍትዌርን እንዳይጠቀም በጉግል በኩል የተጣለበት ዕቀባ አፍሪካ ከአሜሪካ አሊያም ከቻይና ቴክኖሎጂ አንዱን እንድትመርጥ የሚያስገድዳት የቴክኖሎጂ ቀዝቃዛ ጦርነት ሊሆን እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
አፍሪካ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ ስማርት ስልኮች የቻይና ምርቶች ናቸው አብዛኞቹ አፍሪካዊያን በዚህ ዘመን ኢንትርኔትን የሚጠቀሙት ቻይና ሰራሽ በሆኑ ዘመናዊ ስልኮችና በቻይና ኩባንያዎች በተገነቡ የሞባይል አገልግሎት ኔትወርኮች አማካኝነት ነው። ከዚህ ውስጥ ደግሞ ቢያንስ ግማሽ ያህሎቹ አሁን ውዝግብ ውስጥ በገባው ግዙፉ የቻይና የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዌ የተገነቡ ናቸው። "ሁዋዌ በአፍሪካ የቴሌኮም መሰረተ ልማትን በመዘርጋት ሰፊ ድርሻ ያለው በመሆኑ አሜሪካ ኩባንያውን ለማዳከም የምትወስደው እርምጃ ከተሳካላት ውጤቱ በአፍሪካ እያደገ ባለው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የሚያሳድረው ጫና ቀላል የሚባል አይሆንም" ይላሉ፤ ደቡብ አፍሪካ መቀመጫውን ያደረገው የቻይና አፍሪካ ባልደረባ የሆኑት ኤሪክ ኦላንደር። በሁዋዌ ላይ በአሜሪካ የተከፈተውን ዘመቻ የሚመሩት ትራምፕ ሲሆኑ ወዳጆቻቸው ከቻይናው ኩባንያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ የተለያዩ ምክንያቶችን ሰጥተዋል። ከእነዚህም መካከል ኩባንያው የሚያቀርባቸው ቴክኖሎጂዎች ለቻይና መንግሥት ስለላ የሚያመቹ በመሆናቸው የደኅንነት ስጋት ናቸው ይላሉ። ነገር ግን ሁዋዌ ይህንን ክስ በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ቆይቷል። • በእጅ ስልክዎ በኩል እየተሰለሉ ቢሆንስ? • ሳምሰንግ እንደ መጽሐፍ የሚገለጥ ስልክ አመረተ • ዋትስአፕ ሲጠቀሙ እንዴት ራስዎን ከጥቃት መከላከል እንደሚችሉ ያውቃሉ? የጉግል የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሪክ ሽሚት በኢንተርኔት አገልግሎት ዙሪያ ዓለም በሁለት ልትከፈል እንደምትችል ይተነብያሉ። "በቻይና የሚመራ የኢንትርኔት አገልግሎትና በአሜሪካ የሚመራ ኢንትርኔት መምጣቱ አይቀርም" ይላሉ። ይህ ከተከሰተ አፍሪካ ከአንደኛው ወግና መቆም የለባትም ብለው ለቢቢሲ የተናገሩት ደግሞ በአፍሪካና ቻይና ግንኙነት ላይ ባለሙያ የሆኑት ሃሪተ ካሪዩኪ ናቸው። "ፍልሚያው የእኛ ስላልሆነ ለእኛ የሚሻለው ላይ ነው ማተኮር ያለብን" ሲሉ ይመክራሉ። ካሪዩ አክለውም የአፍሪካ ሃገራት በጋራ ሆነው ያላቸውን አማራጮች ለሕዝባቸው በማስረዳት የአውሮፓ ሕብረት ያወጣውን አይነት አፍሪካውያን ተጠቃሚዎችን የሚጠብቅ የመረጃ ጥበቃ ሕግ ለማውጣት መስማማት አለባቸው። • ተማሪዎች አስተማሪያቸውን በመግደል ተጠርጥረው ተያዙ "ይህ ምናልባትም አፍሪካ እንዲሁ ዝም ብላ ገበያው የሚያቀብላትን ከመጠቀም ውጪ ለአህጉሪቱ ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር ጊዜው ሳይሆን አይቀርም። አፍሪካዊያን እየገፋ የመጣውን የዲጂታል ቅኝ ግዛት ለመጋፈጥ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው" ይላሉ። 'ስርሰራ በአፍሪካ ሕብረት ላይ' በአሁኑ ወቅት በሁዋዌ ላይ የሚቀርበው ስጋት ትኩረት የሚያደርገው በምዕራቡ ዓለም ያለውን የመረጃ መረብ ደኅንነት ላይ ይሁን እንጂ፤ ቀደም ሲል አፍሪካ ውስጥ ተፈጸመ ከተባለ የመረጃ ደኅንት ጥሰት ጋር የቻይናው ኩባንያ ስም ተነስቶ ነበር። ሁዋዌን የሚተቹት በማስረጃነት የሚጠቅሱት ባለፈው ዓመት ለ ሞንድ የተባለው የፈረንሳይ ጋዜጣን ነው። ጋዜጣው አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ጽህፈት ቤት ውስጥ በሁዋዌ የተዘረጋው የኮምፒውተር ሥርዓት ለመረጃ ስርቆት ተጋልጧል የሚል ዘገባ ነበር ያቀረበው። መረጃው ጨምሮም ለአምስት ዓመታት ያህል ከሕብረቱ ጽህፈት ቤት ሰርቨር መረጃዎች እኩለ ሌሊት ላይ 8 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቆ ቻይና ሻንጋይ ውስጥ ወደሚገኝ ሰርቨር ይተላለፍ እንደነበር መታወቁን አመልክቷል። • አምስት ካሜራ ያለው ተንቀሳቃሽ ስልክ ነገር ግን በዚህ የጋዜጣ ዘገባ ላይ የቀረበውን ውንጀላ የአፍሪካ ሕብረትም ሆነ የቻይና መንግሥት ባለስልጣናት አስተባብለውታል። የአፍረካ ሕብረት የመረጃ መረብ በሁዋዌ ተመዝብሯል መባሉን አስተባብሏል ሁዋዌ አፍሪካ ውስጥ ዘመናዊ ስልኮች መሸጥ ጨምሮ እጅግ ግዙፍ የቴሌኮም ሥራዎችን የሚያከናውን ኩባንያ ነው። በደቡብ አፍሪካው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኢንስቲቲዩት ውስጥ የቻይናና አፍሪካ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ኮበስ ቫን ስታደን ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአፍሪካ ያሉትን አብዛኞቹን ፎርጂ የኢንትረኔት መረብን የዘረጋው ሁዋዌ ነው። ሁዋዌ አፍሪካ ውስጥ: ምንጭ፡ አውስትራሊያን ስትራተጂክ ፖሊሲ ኢኒስቲቲዩት፣ ሁዋዌ፣ አይዲሲ ሁዋዌ የመጀመሪያውን ጽህፈት ቤቱን በአፍሪካ ውስጥ የከፈተው ከ10 ዓመት በፊት ሲሆን የ5 ጂ ቴክኖሎጂን በአህጉሪቱ ውስጥ ለመጀመር የሚያስችለውን ኮንትራት ለማግኘት ከሚያስችለው ደረጃ ላይ ይገኛል። ሁዋዌ አፍሪካ ውስጥ ላለው ሰፊ ተሳትፎ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገለት በአፍሪካ ውስጥ ያለውን እምቅ የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ኢኮኖሚ አቅም በመጠቀም በኩል የመጀመሪያው ኩባንያ በመሆኑና ይህንንም ለመደገፍ ገንዘብ በማውጣቱ ነው። ለዚህ ደግሞ "ቻይና የምትሰጠው ድጋፍ የአፍሪካ መንግሥታት ከቻይና ኩባንያዎች ጋር እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው መሆኑ የበለጠ ጠቅሞታል" ይላሉ ቫን። የቴክኖሎጂ ምርምር ተቋም የሆነው አይዲሲ እንዳለው በአሁኑ ወቅት ሁዋዌ፣ ቴክኖና ኢንፊኒክስ የተባሉ ምርቶችንና ሳምሰንግን ከሚያመርተው ከሌላኛው የቻይና ኩባንያ ትራንሽን ቀጥሎ በአፍሪካ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የስማርት ስልኮች ሻጭ ነው። አራቱም የስልክ ምርቶች በአሁኑ ጊዜ የሚጠቀሙት የጉግል አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሥርዓትን ነው። ሁዋዌ ቻይና ከአሜሪካ ጋር የገጠመችው ፍጥቻ ወደ ቴክኖሎጂ ቀዝቃዛ ጦርነት የሚያድግ ከሆነና በአፍሪካ ያለውን ሥራውን የሚያሰጋው ከሆነ በአፍሪካ ያለው የበላይነትና ከአፍሪካ መንግሥታት ጋር ያዳበረው ግንኙነት በገበያው ላይ ለመቆት አመቺ እድልን ይፈጥርለታል። • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ • ጃፓን ከቀበሌ መታወቂያ ያነሰች ሞባይል ሠራች ለርካሾቹ የቻይና ስልኮች ምስጋና ይግባቸውና በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ አፍሪካዊያን የኢንተርኔትን አገልግሎት ይጠቀማሉ። አብዛኞቹን አፍሪካዊ ከኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ይልቅ የሚያሳስባቸው ስልኮቹ ባለሁለት ሲም ካርድ መሆን አለመሆናቸውና ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል ባትሪ ያላቸው መሆኑን ጨምሮ የስልኮቹ ዋጋ ውድ መሆን ነው። ፉክክር በአሜሪካና በቻይና የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ በቻይናና አፍሪካ ግንኙነትና ኢንተርኔትን የተመለከቱ ጉዳዮች ጸሃፊ የሆኑት ኢጊኒዮ ጋግሊያርደን እንደሚሉት በአሜሪካና በቻይና መካከል የተፈጠረው እሰጥ አገባ ሁዋዌ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ገበያውን ለመጠበቅ የራሱን ሶፍትዌር እንዲጠቀም ሊገፋው እንደሚችል ገልጸዋል። ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ርካሽና ቀላል እንደማይሆን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቻይና ውስጥ እንደሚደረገው በጉግል ፋንታ ባይዱ፣ ከትዊተር ይልቅ ሲና ዌቦን ለመጠቀም የሚያስችለውን አይነት ዝግ የኢንተርኔት መጠቀሚያ ዘዴን አፍሪካ ውስጥ ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን የማኅበራዊ ሚዲያን፣ የመልዕክት መለዋወጫና የሞባይል ክፍያ መፈጸሚያ ያለውን ዊቻት የተባለው ባለብዙ ግልጋሎት መተግበሪያን በአፍሪካ ተግባራዊ ለማድረግ ይቻላል። ሁዋዌ በአፍሪካ ውስጥ አራተኛው ትልቁ የስማርት ስልክ ሻጭ ነው አፍሪካ እንድትመርጥ ትገደድ ይሆን? "የአፍሪካ ሃገራት ከአንዱ ወገን መቆም የለባቸውም፤ በዚህ የቴክኖሎጂ ፍልሚያ ውስጥ ገለልተኛ የሆነ እንቅስቃሴ በመጀመር የራሳቸውን ጥቅም ማስጠበቅ የሚችሉበትን አጋጣሚ ሊፈጥሩ ይችላሉ" ይላሉ ኢጊኒዮ ጋግሊያርደን። በጥናታቸው ላይ የአፍሪካ ሃገራትን ቁጥጥር የምታደርግበትን የኢንተርኔት ሥርዓት እንዲጠቀሙ ቻይና አጥብቃ ገፍታለች የሚለውን ከጥርጣሬ ውጪ ማስረጃ እንዳላገኙለት ጠቁመዋል። ነገር ግን ኢጊኒዮ ጋግሊያርደን እንደሚያስቡት ቻይና ጥቅሟን ለማስከበር ስትል ከአፍሪካ መንግሥታት ጋር ያላትን ግንኙነት በመጠቀም ኩባንያዎቿ በምዕራባዊያን ተፎካካሪዎቻቸው ላይ የበላይነት እንዲያገኙ የተቻላትን ሁሉ ልታደርግ ትችላለች። • ትውስታ- የዛሬ 20 ዓመት ኢትዮጵያ ሞባይል ስልክን ስትተዋወቅ • ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና በቻይናና በአሜሪካ መካከል ሊቀሰቀስ ከጫፍ የደረሰው የቴክኖሎጂ ቀዝቃዛ ጦርነት ለአፍሪካ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ የሚናገሩት ካሪዩኪ አህጉሪቱም ጎራ ለመምረጥ መገደድ እንደሌለባትም ይመክራሉ። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከሚገኘው የሞጃ ምርምር ኢንስቲቲዩት ባልደረባ የሆኑት ፋዝሊን ፍራንስማን እንደሚሉት "በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ውስጥ ከዳር እስከ ዳር የደረሰው የኢንተርኔት አገልግሎትና ቴክኖሎጂ በአብዛኛው የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ባፈሰሱት መዋዕለ ነዋይ ነው።" ከዚህ አንጻር ተመራማሪዋ ፍራንስማን በእራሷ እይታ ጉዳዩን ስትደመድምም "አፍሪካ በፍልሚያው ከማን ወገን እንደምትቆም ከወሰነች ቆይታለች፤ ቻይናን መርጣለች" ትላለች።
news-55497935
https://www.bbc.com/amharic/news-55497935
ኢትዮጵያ በርካታ ሠራዊት ያበረከተችበት የዳርፉር ሠላም ማስከበር ስምሪት አበቃ
በተባበሩት መንግሥታት ተልዕኮ ስር ኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ወታደሮችንና የፖሊስ ኃይል ያሰማራችበት የዳርፉር ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ተጠናቋል።
በተባበሩት መንግሥታት ስር የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ አባላት በሱዳን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ስር በተለያዩ አገራት ውስጥ ለሚደረጉ የሠላም ማስከበር ተልዕኮዎች ከፍተኛ የሚባለውን ከ8,300 በላይ ሠራዊት የምታበረክት ሲሆን ከዚህም ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር በሱዳን ውስጥ በሚገኙት ዳርፉርና በአብዬ ግዛት ውስጥ የተሰማሩ ናቸው። ዩናሚድ በሚባል የአንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል የሚታወቀው የዳርፉር ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ወታደሮች ካበረከቱ ሦሰት ቀዳሚ አገራት አንዷ ናት። በምዕራባዊ ሱዳን ለ13 ዓመታት በተባበሩት መንግሥታት አማካይነት ሠላም ለማስከበር ተሰማርቶ ለቆየው ሠራዊት በርካታ የዓለም አገራት ወታደሮቻቸውን አዋጥተዋል ከእነዚህም ውስጥ በርካታ የሠራዊቱ አባላትን በማበርከት ሩዋንዳ፣ ፓኪስታንና ኢትዮጵያ ቀዳሚዎቹ ናቸው። በምጽሀረ ቃል 'ዩናሚድ' (UNAMID) ተብሎ የሚታወቀው በዳርፉር ሰላም ለማስከበር የተሰማራው ኃይል ከዚህ በኋላ በሱዳን እንደማይቀጥል የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ማስታወቁ ይታወሳል። ምክር ቤቱ በሱዳን እና በዳርፉር ያለውን አንጻራዊ ሰላም፣ የሽግግር መንግሥቱ ከአማጺያን ጋር ያደረጋቸውን የሰላም ስምምነቶች እንዲሁም አጠቃላይ ለውጦችን ከግምት በማስገባት እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱ ተገልጿል። በዚህ ውሳኔ መሰረትም ዩናሚድ በዳርፉር ከሐሙስ ታኅሣስ 31/2020 በኋላ ምንም አይነት ኃላፊነት አይኖረውም ማለት ነው። ሰላም የማስከበርና ተያያዥ ሥራዎችም ለመጨረሻ ጊዜ የሚካሄዱት በዚሁ ቀን ነው። በሚቀጥሉት ስድስት ወራትም ወታደሮችን ወደ አገራቸው፣ አልያም ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወር፣ እንደ ወታደራዊ መኪና ያሉ ንብረቶችን ለተባበሩት መንግሥታት ማስረከብ የመሳሰሉት ሥራዎች ይከናወናሉ። በዚህ መሰረት ሁሉም የዩናሚድ ሲቪልና ወታደራዊ ሠራተኞች ሰኔ 2021 ላይ ጠቅልለው ይወጣሉ ተብሏል። ዩናሚድ እንዴትና ለምን ተቋቋመ? በአውሮፓውያኑ 2003 ዳርፉር ውስጥ የተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን እስከ ሁለት ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው አፈናቅሏል። በመንግሥት ወታደሮችና በርካታ ታጣቂ ቡድኖች መካከል የሚካሄደውን ውጊያ ተከትሎ በጣም ዘግናኝ የሚባሉ ወንጀሎች እንደተፈጸሙ ይነገራል። በርካቶች ተገድለዋል፣ ሴቶችና ህጻናት ተደፍረዋል፣ ንጹሀን ዜጎች ሰብአዊ መብታቸው ተጥሷል። የእርስ በርስ ጦርነቱን ተከትሎ በዚያው ዓመት የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ጉዳዩን ዓለም አቀፍ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስቦ ነበር። በወቅቱ በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድጋፍ የዳርፉር የሰላም ስምምነት 2006 ላይ ተፈረመ። ነገር ግን ስምምነቱ ላይ የደረሱት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ነበሩ። ይህን ተከትሎም በአፍሪካ ሕብረትና በተባበሩት መንግስታት አደራዳሪነት ኳታር ዶሃ ውስጥ ሁለተኛ ስምምነት ተፈረመ። ወርሃ ኅዳር 2006 ላይ ደግሞ በአዲስ አበባ በተካሄደው ውይይት የተባበሩት መንግሥታት እና አፍሪካ ሕብረት በጥምረት ዳርፉር ውስጥ ሠላም አስከባሪ ኃይል ለማሰማራት ተስማሙ። የወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን እና ሌሎች በርካታ የዓለም መሪዎች ባካሄዱት የማግባባት ስራ፣ ሱዳን ሰኔ 2007 ላይ ይህ ሠላም አስከባሪ ቡድን ወደ ድንበሯ እንዲገባ ፈቀደች። ይህን ተከትሎም የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ሕብረት ጥምር ኦፕሬሽን፣ ሐምሌ 2007 ላይ የተቋቋመ ሲሆን በምጽሃረ ቃል ዩናሚድ ተብሎ እንዲጠራም ተወሰነ። በዳርፉር ተሰማርተው የነበሩት የዩናሚድ ሠላም አስከባሪ ወታደሮች ዋና ዋና ኃላፊነቶቹ ይህ ተልዕኮ ዋና መቀመጫው በሰሜናዊ ዳርፉር ኤል ፋሽር ውስጥ ሲሆን በአምስቱም የዳርፉር ግዛቶች በአጠቃላይ 35 የስምሪት ማዕከላት አሉት። ሐምሌ 2007 ላይ ተልዕኮው 25 ሺ 987 ዩኒፎርም ለባሽ ሰላም አስከባሪዎችን ወደ ሱዳን ለማስገባት ፈቃድ ያገኘ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 19 ሺ 55 ወታደሮች፣ 360 ወታደራዊ ታዛቢዎችና አታሼዎች፣ 3772 የፖሊስ አማካሪዎች እና 2660 የፖሊስ ዩኒቶች ይገኙበታል። ዳርፉር ለምን የጦርነት ቀጠና ሆነች? ዳርፉር የ80 ጎሳዎች መገኛ ስትሆን ነዋሪዎቹም አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ናቸው። አማጺያኑ የሚመጡት ደግሞ ከሶስት ማህበረሰቦች ነው። አካባቢው የአየር ጸባዩም ሆነ ተፈጥሮአዊ አቀማመጡ ለእንቅስቃሴ ምቹ ስላልሆነ ብዙ አማጺያን ይመርጡታል። ለዓመታት አካባቢው ግጭት ርቆት አያውቅም። ሁሌም ነዋሪዎች የጦርነት አካባቢውን ጥለው ይሰደዳሉ። ምንም እንኳን የዳርፉር ቀደምት ነዋሪዎች (ፉር እና ሌሎች ጎሳወፐች) ከአረብ ማህበረሰቦች ጋር ለበርካታ ዓመታት ያለምንም ችግር ተስማምተው የኖሩ ቢሆንም የተፈጥሮ ሀብት እያጠረ ሲመጣ ግን ግጭቶች መከሰት ጀመሩ። እንደውም ይህን ተከትሎ ግጭቱ መልኩን ቀይሮ የዘር ግጭት ሆነ። ዳርፉር ከድሮውም ከሌሎች የሱዳን አካባቢዎች በጣም የራቀና ምቹ ያልሆነ ስፍራ ነው። በደህናው ጊዜ እንኳን መንግሥት፣ እንደ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች እንደልቡ መድረስ የማይችለው በዳርፉር ብቻ ነው። አብዛኛዎቹ የዳርፉር ነዋሪዎች ሙስሊሞች ሲሆኑ በሱዳናዊነታቸው ጠንካራ እምነት እንዳላቸው ይገለጻል። ነገር ግን አንዳንድ የተገፉ ብሄሮች ከሱዳን ይልቅ ከጎረቤት አገር ቻድ ካሉ ብሄሮች ጋር ራሳቸውን ያቆራኛሉ። 2003 ላይ ሁለት የታጠቁ ቡድኖች ዳርፉር ውስጥ የሱዳን መንግሥት ላይ ጦርነት አወጁ። ሁለቱ ቡድኖች የሱዳን ነጻ አውጪ ኃይል (SLA) እና ፍትህ እና እኩልነት እንቅስቃሴ (JEM) ሲሆኑ፣ ጦርነቱን የጀመሩት አንዳንድ ከተሞች፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እና ንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት በመፈጸም ነው። በወቅቱ በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች የተገደሉ ሲሆን፣ 80 የፖሊስ ጣቢያዎችም ወድመዋል። ይህን ተከትሎም የአካባቢው መዋቅር ሙሉ በሙኡ በመቋረጡ ሌሎች ቡድኖችም እንደልባቸው መንቀሳቀስ እንዲችል እድሉን አመቻቸ። በዳርፉር የሚገኙት አማጺያን አብዛኛዎቹ የምንዋጋው በሱዳን መንግሥት በሚደርስብን መገለል ነው ይላሉ። አካባቢው አንዳይለማ ሆን ተብሎ በመንግሥት አሻጥር ተሰርቶብናል የሚሉት አማጺያኑ እንደ አማራጭ የወሰዱት ጦርነትን ነው። የተነሳውን ተቃውሞና አመጽ ለመቆጣጠርም ካርቱም አርብቶ አደር አረቦችን በማስታጠቅ እርምጃ ወሰደች። እነዚህ የታጠቁ አርብቶ አደሮችም 'ጃንጃዊድ' በመባል የሚታወቁ ሲሆን የሱዳን መንግሥት ጠቀም ያለ ገንዘብ ይከፍላቸውም ነበር። የሱዳን ዳርፉር ግጭት ባሳለፍነው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ደግሞ የሱዳን በቀድሞ ፕሬዝዳንቷ ኦማር አል በሺር በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ዳርፉር ላይ የተፈፀመውን ወንጀል መመርመር ተጀምሯል። ከአስር ዓመት በፊት የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዳርፉር ለተፈፀመው የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀልና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በበሺር ላይ የእስር ማዘዣ ቆርጦባቸው ነበር። 30 ዓመት በስልጣን ላይ የቆዩት የሱዳን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አል በሺር በሀገሪቱ በተቀሰቀሰ ሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ ከስልጣን መውረዳቸው ይታወሳል። ሱዳን በአሁኑ ሰአት ከወታደራዊ መሪዎችና የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ይመሩ ከነበሩ አካላት በተውጣጣ የሽግግር መንግሥት እየተመራች ትገኛለች። አል በሺር ከስልጣን ከወረዱ በኋላ የአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቢያነ ሕግጋት በሺር በዳርፉር ለተፈፀመው ወንጀል ችሎት ፊት ቀርበው ጉዳያቸው እንዲታይ ጠይቀው ነበር። በዳርፉር ሰላም ለማስከበር የተሰማራው ኃይል ከዚህ በኋላ በሱዳን እንደማይቀጥል የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ማስታወቁን ተከትሎ የንጹሃን ዜጎች ደኅንነት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል እየተገለጸ ነው። በደቡብ ሱዳን ይደረስበታል የተባለው የሰላም ስምምነት ለ17 ዓመታት የዜጎችን ሕይወት ሲያመሳቅል የቆየው ጦርነት እንዲያበቃና በርካታ ዳርፉራውያን ወደ ቀድሞ ቀያቸው እንዲመለሱ ሊያደርግ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል። በዳርፉር ጦርነት ምክንያት እስካሁን ድረስ ባለፉት 17 ዓመታት 300 ሺህ ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን 2.5 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገድደዋል። የሱዳን መንግሥት ደግሞ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ መሄድን ተከትሎ በቦታው ተክቶ ሊሰራ የሚችል ቡድን ለማቋቋምና ንጹሀን ዜጎችን ለመጠበቅ በዝግጅት ላይ እንደሆነ አስታውቋል።
news-44812413
https://www.bbc.com/amharic/news-44812413
የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን ገለፀ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኤርትራ ቆይታቸው ከኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ድርጅቱ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ ደባ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
በኤርትራ ተቀማጭነቱን ያደረገው ድርጅት ካለው ለውጥጋር ተያይዞ ጦርነት እንደማያስፈልግ መረዳታቸውን ጨምረው ገልፀዋል። መንግሥት ከኦነግ ጋር ካገር ውጭ ሊወያይ ነው በሰላም ትግላቸውንም ለመቀጠል እንደወሰኑ የሚናገሩት አቶ ቶሌራ ከመንግሥት ጋር የሚደረገውም ውይይትም በቅርቡ ይቀጥላል ብለዋል። ግንባሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫም የተጀመሩት ውይይቶች ጥሩ ለውጥ እንደሚያመጡ እምነታቸውን ገልፀው በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል ጊዜያዊ ተኩስ አቁም እንዲተገበር መወሰናቸውን ገልፀዋል። ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ
news-55659542
https://www.bbc.com/amharic/news-55659542
መመጣጠን ያልቻለው የንግድ ሚዛን ጉድለትና የናረው የውጭ ምንዛሪ
ኢትዮጵያ ሚሊኒየም (2000) ዓ.ምን ልትረከብ ወራት በቀሯት ወቅት የኢትዮጵያ ባንኮች አንድ ዶላርን በ8.7 ብር ገደማ ይመነዝሩ ነበር። በዓመታት ከፍተኛ በሚባል ሁኔታ ጭማሬ እያሳየ የመጣው የምንዛሪ ተመን ንሮ አንድ ዶላር በ39.47 (40) ብር እየተመነዘረ ነው።
ይህ የምንዛሬ ተመን በኢትዮጵያ ይፋዊ የባንክ ግብይት መሰረት ነው። ነገር ግን በተለምዶ ጥቁር ገበያ በሚባለው ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ ዶላር 55 ብር እና ከዚያ በላይ እንደሆነ ተሰምቷል። በተለይም አገሪቷ የይፋዊ እና በጥቁር ገበያ የምንዛሪ ተመንን ዋጋ ለማቀራረብ እየሰራችበት ባለችበት ወቅት በጥቁር ገበያና በመደበኛው ገበያ መካከል ያለው ልዩነት አስራ ስድስት ብር ገደማ መሆኑም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችን ስጋት ላይ ጥሏል። ከሰሞኑ በጥቁር ገበያ ላይ የዶላር ምንዛሪ የናረው በትግራይ ክልል ባለው ወታደራዊ ግጭት፣ አገሪቷ ባጋጠማት አለመረጋጋት እንደሆነ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ቢጠቅሱም የብር ከዶላርም ሆነ ከሌሎች የመገበያያ ገንዘቦች አንፃር መድከም በዓመታት ውስጥ የታየ እንደሆነ ተንታኞቹ ይናገራሉ፤ ይህም አገሪቷ እየተከተለችው ካለው የብር ተገቢውን ዋጋ እንዲይዝ (ዲቫሉዌት) ከማድረግ ጋርና በተለይም የአገሪቱ የንግድ ሚዛን ጉድለት ጋር እንደሚያያዝ ያስረዳሉ። ከሰሞኑ የናረው የጥቁር ገበያ ምንዛሬ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለዓመታት የአገሪቱ አንገብጋቢ ችግር ሆኖ ዘልቋል። የአገሪቱ የተዛባ የንግድ ሥርዓት በተለይም የወጪና የገቢ ንግድ አለመመጣጠን ለእጥረቱ መባባስ ምክንያትም ሆኗል። ይህ እጥረት በምጣኔ ሃብቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ በማሳረፉ በርካታ ፋብሪካዎችንና ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዳያመርቱ እንዲሁም ህልውናቸውን ፈተና ላይ ጥሎታል። ኢትዮጵያ በወጪ ንግድ፣ በብድር፣ በእርዳታ እንዲሁም ከውጭ አገራት በሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) የምታገኘው ገንዘብ ተጠራቅሞ ለገቢ ንግድ ከምትፈልገው ዶላር በእጅጉ ያነሰ እንደሆነ የፋይናንስ አስተዳደርና የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ አብዱልመናን መሐመድ ያስረዳሉ። አገሪቷ ለዓመታት ከምትንገታገትበት የንግድ ሚዛን ጉድለት በተጨማሪ ወታደራዊ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ሲፈጠሩ መንግሥት እንደ አንድ አካል የውጭ ምንዛሬ ስለሚፈልግም የፍላጎትና የአቅርቦት ልዩነት እንደሚፈጠር ይናገራሉ። በተለይም በተለይም ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በጥቁር ገበያ ያለው የዶላር ተመን ከፍተኛ በሚባል ሁኔታ ተምዘግዝጓል። ለዚህም እንደ ዋነኝነት የሚጠቀሰው በአገሪቱ ውስጥ ያለው ግጭትና አለመረጋጋት ነው። መንግሥት ለሚያካሂደው ወታደራዊ እርምጃ የዶላር ፍላጎት ስለሚኖረው ከዚህም ጋር ተያይዞ መንግሥት ወጪ የሚያደርገው ዶላር ለሌሎች ገቢ ንግዶች የሚውለውን ስለሚሆን እጥረቱን ያጎላዋል። እንዲህ ባሉ ምክንያቶችም ነጋዴዎች ዶላር ከባንክ የማግኘት ዕድላቸውን ስለሚያጠበውና ከዚህ ቀደም ለነጋዴዎች የሚቀርበው ይፋዊ ዶላር እንደበፊቱ በቂ ስለማይሆን ከፍተኛ እጥረት ሊከተል እንደሚችል ጠቆም ያደርጋሉ። "ያው ግጭቶች ሲኖሩ አገሪቱ የምታወጣቸው የውጭ ምንዛሪ ይኖራልና ነጋዴ የሚፈልገውን ያህል አያገኝም" ይላሉ። "ነጋዴዎች ከባንክ ዶላር ካላገኙ ያላቸው አማራጭ ከባንክ ውጭ ያለ ጥቁር ገበያን እንደ አንድ አማራጭ መጠቀም ነው። በዚህም ምክንያት ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ ነው የሚንረው" ይላሉ አቶ አብዱልመናን። በቀላል ቋንቋም ሲያስረዱ ዶላር እንደ ማንኛውም የሚገዛና የሚለወጥ ሸቀጥ ቢታይ የዶላር ተመንም እንደ ማንኛውም ሸቀጥ በገበያ ዋጋ የሚተመን ይሆናል። መሰረታዊ በሆነው የምጣኔ ሃብት እሳቤ መሰረት ፍላጎትና አቅርቦት በማይመጣጠኑበት ወቅት እንደ ማንኛውም ሸቀጥ መናር ሊፈጠር የሚችል ሲሆን፤ የዶላር እጥረት በገበያው ውስጥ ካጋጠመ የዶላር ዋጋ ሊንር እንደሚችልም ያስረዳሉ። እንዲሁ በተቃራኒው የዶላር አቅርቦት በብዛት ካለ ደግሞ ዋጋው እንዲሁ ያሽቆለቁላል በማለትም በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለውን እሳቤ ያስረዳሉ። ከዚህም በተጨማሪ በገበያው ውስጥ የዶላር አቅርቦት እጥረት ካለ ነጋዴዎችም እቃ የማከማቸትና ዋጋ የመጨመር አዝማሚያም እንደሚኖር በዓመታት ውስጥ ታይቷል። አቶ አብዱልመናንም "አለመረጋጋት በሚኖርበት ወቅት የሸቀጦት አቅርቦት ችግርም ስለሚፈጠር፤ እቃ ማከማቸት እንዲሁም የዋጋ መናርም ይከሰታል" ይላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚ ዲፓርትመንት መምህር የሆኑት ዶክተር ተኪኤ አለሙ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት ውስጥ አለመረጋጋቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ ይኸው ሁኔታ እንደሚፈጠር ታሪክን በማጣቀስ ይናገራሉ። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጀርመን የመገበያያ ገንዘብ (ዶች ማርክ) በመጥፋቱ ዜጎች በሲጋራ ይገበያዩ እንደነበር ያስታውሳሉ። ምንም እንኳን በጥቁር ገበያው ላይ ያለው የምንዛሪ ተመን ፍጥነት በአገሪቱ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ቢሆንም፤ የመደበኛው የብር ምንዛሪ ተመን ነፀብራቅ እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። በመደበኛው ግብይት ላይ የሚታየው የብር መዳከም በጥቁር ገበያውም ላይ የሚታይ ነው ይላሉ። የብር መዳከምና የለጋሾች ጉትጎታ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለዓመታት መንግሥት ብር ከበዶላር ጋር ያለው ምንዛሪ ተመንን መዳከም እንዳለባት ሲጎተጉቱ ነበር። ለአስርት ዓመታት አገሪቱ ስትተዳደርበት የነበረው የውጭ ምንዛሬ የግብይት ሥርዓት (የፊክስድ ፎሬይን ኤክስቸንጅ ማርኬት) አሰራርን በተመለከተ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍ ሲተቸው ነበር። የኢትዮጵያ ብር ካለው መግዛት አቅም በላይ ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው ለዓመታትም ሲያሳስብ ነበር። ባንኩ ሲሰራበት የነበረው ሥርዓት ዶላር የመግዛት አቅምን መሰረት በማድረግ የብር የምንዛሪ ዋጋ ተመን ላልተወሰነ ጊዜ በቋሚነት በአንዴ የሚወሰንበት መሆኑ ይታወሳል። ተቋማቱ ብር ዶላርን የመግዛት አቅሙ ከፍ ያለ በመሆኑም የወጪ ንግድን ለማበረታታት በገበያ ፍላጎት የሚመራ ተለዋዋጭ የውጭ ምንዛሪ የግብይት ሥርዓት ቢዘረጋ አገሪቱ ያለባትን ማነቆ መፍታት እንደሚያስችላት ሲያሳስሰብ ነበር። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ ፍላጎት የሚመራ ሥርዓት እንዲዘረጋ ወስኗል። በሦስት ዓመታት ውስጥም ሙሉ በሙሉ ገበያ መር ይሆናልም የሚል እቅድ ተይዟል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ከሁለት ዓመታት በፊት ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍና የዓለም ባንክ ለሶስቱ ዓመት የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ድጋፍ በተመለከተ ባደረገው ውይይት እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠው በሂደት ብርን ማዳከምና ከጥቁር ገበያው ጋር ማመጣጠን እንደሆነ አቶ አብዱልመናን ይናገራሉ። አገሪቱ ከገባችበት የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ለመውጣት የዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም፣ አይ ኤም ኤፍ 2.9 ቢሊዮን ዶላር ሲያመቻችላትም ከተቀመጡላት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል በዋነኝነት የብር የውጭ ምንዛሪ ተመንን በፍጥነት መቀነስና የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን በሂደት በገበያ ፍላጎት እንዲወሰን ማድረግ የሚሉ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ አገሪቱ ይህንን የብድር ድጋፍ ለማግኘት የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ማዛወር፣ የመንግሥትን ወጪን መቀነስና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችም ተቀምጠውላታል። ኢትዮጵያ በገባችውም ውል መሰረት በቋሚነት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመፍታትና የገበያ ሥርዓቱንም ለማስተካከል እየሰራች ትገኛለች። ከዚህም ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ በይፋዊና በጥቁር ገበያ ላይ ያለውን ሰፊ ልዩነት ለማመጣጠንና የብር የመግዛት አቅም ከውጭ ምንዛሪ አንፃር እንዲቀንስ ለማድረግ መንግሥት ብርን ለማዳከም እየሰራ መሆኑንም አቶ አብዱልመናን ይናገራሉ። በይፋዊና በጥቁር ገበያ ያለውን ልዩነትም ለማጥበብ እየወሰደ ባለው እርምጃ ብር እየተዳከመ መምጣቱንም ያወሳሉ። "ባለፈው ዓመትም ብር ከዶላር ጋር ሲነፃፀር 15 በመቶ በሚባል ሁኔታም ተዳክሟል" ይላሉ። የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን ከዶላር ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎችም የመገበያያ ገንዘቦችም አንፃር ተዳክሟል። "የባለፈው ዓመት ፍጥነቱ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማቱ ያመጡት ጫና የፈጠረው ነው። ይሄም ሆኖ ግን ይፋዊ (መደበኛ) በሆነውና በጥቁር ገበያው መካከል እንደተባለው መጥበብ አልቻለም" ይላሉ አብዱልመናን። ነገር ግን በተቃራኒው ያለው ልዩነት መጥበብ ሳይሆን መንግሥት ይፋዊና የጥቁር ገበያን ለማመጣጠን በሚደረገው ሁኔታ ብር ሲዳከም የጥቁር ገበያውም ከፍ እንደሚል ዶክተር ተኪኤ ይናገራሉ። "መሰራት ያለበት የጥቁር ገበያውን ተመን እንዴት አድርገን ዝቅ እናድርገው በሚለው ላይ መሆን አለበት። ይህም የተሻለው እሳቤ ሊሆን ይገባል" በማለት አፅንኦት የሚሰጡት ዶክተር ተኪኤ አክለውም "የጥቁር ገበያን ልድረስበት ሲባል የባንኩ ተመን ከፍ ማለቱ አይቀርም" ይላሉ። በተለይም የጥቁር ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር የአገሪቱን የዶላር ክምችት ማመናመን እንዲሁም የምታገኛቸውን ገቢ እንድታጣ እንደሚያደርጋትም ይጠቅሳሉ። አገሪቱ ዶላር ከምታገኝባቸውና የዶላርም ክምችቷንም ለማጠናከር ከምትሰራባቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ዲያስፖራው ከውጭ የሚልከው ገንዘብ (ሬሚታንስ) ነው። ይፋዊ በሆነው ገበያና የጥቁር ገበያ ተመን ላይ ባለው ከፍተኛ ልዩነት ምክንያት በርካቶች በባንክ ብራቸውን የመላክ ፍላጎት እንደሚቀንስ ዶክተር ተኪኤ ይጠቅሳሉ። "በአንድ ዶላርና በብር መካከል ከአስር ብር በላይ ልዩነት ካለ ማንኛውም ሰው ባንክን መጠቀም አይፈልግም። ጭማሪ ወዳለበት ነው የሚያመራው" ይላሉ። ይህንንም ሁኔታ ለማስተካከል በቁጥጥርና በማሸግ ሊሆን እንደማይገባም አፅንኦት በመስጠት ይናገራሉ። በባንኮችና በጥቁር ገበያው መካከል የምንዛሪ ዋጋ ልዩነትን ለማጥበብ ብርን ማዳከም ሳይሆን መፍትሄ የሚሉት እነዚህን ነጋዴዎች ሕጋዊ ማድረግና ንግድ ፈቃድ መስጠት ነው። "ሥራው አደጋ ስላለውና መወረስም ስላላ በከፍተኛ ሁኔታ የጥቁር ገበያው ይንራል ይህንን ለማስተካከል ሕጋዊ ቢሆኑ ጤናማ ውድድርም ይመጣል" በማለት ያስረዳሉ። አቶ አብዱልመናንም እንደ ዶክተር ተኪኤ የበለጠ ዘመቻና ማስፈራሪያ በሚኖርበት ወቅት ሥራው የበለጠ አደገኛ ስለሚሆን ተመኑም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር ታዝበዋል። መንግሥት እንዲህ አይነት እርምጃዎችን ቢወስድም "ኢትዮጵያ ውስጥ ዘመቻ ችግር ፈትቶ እንደማያውቅ" አቶ አብዱልመናን ይያሳስባሉ። ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማቱ የምንዛሬ ተመንን ማዳከም ወደ ውጭ አገር ምርታቸውን የሚልኩ ባለሃብቶችን እንዲበረታቱና የንግድ ጉድለቱ እንዲስተካከል፣ አገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝና ያለባትን ማነቆ እንድትቀርፍ ያስችላል ሲሉ ቆይተዋል። ነገር ግን ብሯን ማዳከሟ ከፍተኛ ስጋት እንዳጫረና ለአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ያተረፈው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት እንደተከሰተም የዘርፉ ባለሙያዎች እየተናገሩር ነው። የብር የውጭ ምንዛሬ የመግዛት አቅም መዳከም የተፈለገውን ያህል ውጤት በምጣኔ ሀብቱ ላይ እንዳላመጣ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በተለይም ታስቦ የነበረው የወጪና የገቢ ንግድን ማመጣጠን አልቻለም። አቶ አብዱልመናን እንደሚናገሩት አገሪቱ ከወጪ ንግድ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ስታገኝ በገቢ ንግድ ደግሞ 15 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች። ይህንንም ከፍተኛ ልዩነት ማመጣጠን አለመቻሉ ከፍተኛ ማነቆ ፈጥሯል ይላሉ። ዶክተር ተኪኤ በበኩላቸው ከወጪ ንግዷ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ምርቶች ከውጭ አገር የምታስገባው ኢትዮጵያ የብር ምንዛሬ ማሽቆልቆል ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን አስከትሏል ይላሉ። አገሪቱ በየወሩ የምታስመዘግበው የዋጋ ግሽበት ከ20 በመቶ በላይ በመሆኑ በዜጎች ላይ እያሳረፈ ያለው ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ ሆኗል። ከዋጋ ግሸበትም ጋር ተያይዞ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች ዋጋ መናርም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ኢትዮጵያ ብሯን በዋነኝነት ያዳከመችው አገሪቷቱ የምትሸጠው ምርት ዋጋ ከረከሰ በርካታ ገቢ ይገኛል፤ እንዲሁም የወጪ ንግዱም ይበረታታል በሚል ቢሆንም ከምርታማነት እንዲሁም ከተወዳዳሪነት ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያ እውነታ ይሰራል ወይ? በማለት የሚጠይቁት ዶክተሩ አገሪቱ በዋነኝነት ወደ ውጪ የምትልካቸው የግብርና ምርቶች በዓለም ገበያ ያላቸው ተፈላጊነትም እዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ ይነገራል። ስለዚህ የምትሸጠው ምርት መታየት አለበት ይላሉ። "የኢትዮጵያ ምርት ዋጋው ስለቀነሰ የኛን ምርቶች ይገዛልናል የሚል ነው። አቅርቦታችን በከፍተኛ ሁኔታ አምርተን ለዓለም አቀፉ ገበያ እንድናቀርብ የሚያስችለን አቅም የለንም። ስለዚህ እሱ ይሰራል የሚል እምነት የለኝም" በማለትም ያለውን የገበያ ሥርዓትን ዶ/ር ተኪኤ ያስረዳሉ። ከዚህም በተጨማሪ የአምራች (ማኑፋክቸሪንግ) ዘርፉም አመርቂ የሚባል ውጤት ባለማምጣቱና የአገሪቱ የገቢ ንግድ ከፍተኛ በመሆኑ የንግድ ሚዛኑን አጉድሎታል። ከዚህ በተጨማሪም የገንዘብ ተመኑ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች የመግዣ ዋጋቸውን በመጨመር የገቢ ንግዷን ለመተካትም ቢታሰብ እንኳን፤ አገሪቱ በዋነኝነት ከውጭ የምታስገባው ነዳጅ፣ መድኃኒትና መሰረታዊ ሸቀጦች መሆናቸውን የሚገልፁት ዶክተር ተኪኤ የእነዚህ እቃዎች ዋጋ መናር ከፍተኛ ቀውስ እንደሚያስከትልም ያስረዳሉ። ምርትን ወደ ውጭ የሚልኩ ባለሃብቶችን በማበረታት የሚገኘውን ምንዛሪ ከፍ በማድረግ ያለባትን ማነቆ እንድትቀርፍ የታለመ ቢሆንም ለማምረት የሚመጡት ግብዓቶች ዋጋ በተመኑ መጨመር ምክንያት መናሩ ችግር እንደሆነባቸውም ሲናገሩ ይሰማሉ። በዚህም በብር መዳከም ምክንያት ግብዓቶችን በውድ ዋጋ ገዝተው በተቃራኒው የምርታቸው ዋጋ ስለሚረክስ ላኪዎች ይማረራሉ። ከውጭ የሚገቡ ምርቶች የመግዣ ዋጋቸውን በመጨመር ያለውን ፍላጎት እንዲቀንስ ለማድረግ ቢታለምም ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባው ምርቶች መሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ጭማሪ እንዲኖር አድርጎታል። የሚገቡትም ሸቀጦች በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋ መቀነስ ሳይሆን በከፍተኛ ሁኔታ በመናር የዋጋ ግሸበቱን በማባባስ የኑሮ ውድነቱን እንዳከበደውም ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ የምታመርታቸው ምርቶች ዋጋ ቢቀንስም የአቅርቦቱ መጠን አነስተኛ ከሆነ በተቃራኒው አገሪቱ የገቢ ንግዷ በዚያው መንገድ በመቀጠሉ የተፈለገውን ውጤት ማግኘት እንዳልተቻለም ተነግሯል። የምንዛሬ ለውጡ የገቢውን ንግድ ለመቀነስ እንዲሁም ሸማቾች ከውጭ የሚገቡ እቃዎችን እንዳይገዙ ለማድረግ እንዲሁም የንግድ ሚዛን ጉድለትን ለማስተካከል ያስችላል ቢባልም ፍሬያማ አልሆነም። የብር መዳከምና የምንዛሬ ተመኑ ለውጥ በብድርም ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረም እንደሆነ ይነገራል። ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የኢትዮጵያ ብር ካለው አቅም በላይ ዋጋ ይዟል ብለው ማሳሰባቸው እንዲሁም ብር እንድታዳክም መምከራቸው፤ ለመምህሩ ተቋማቱ አገራት በገበያ መር መተዳደር አለባቸው ከሚለው ርዕዮተ ዓለም ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይናገራሉ። "የአገራቱን የመገበያያ ገንዘብ ማዳከም ወይም በገበያ ፍላጎት እንዲወሰን የማድረግ ምክር ምጣኔ ሃብታዊ ሳይሆን የርዕዮተ ዓለም ጥያቄ ነው" ይላሉ። መፍትሄውምንድን ነው? ኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲሁም በገቢና በወጪ ንግድ ሚዛን መጓደል ችግር የገጠማት ሲሆን፤ በዋነኝነት እንደ መፍትሄ የሚቀመጠውም የወጪውን ንግድ ማሻሻልና በተለይም የአምራች (ማኑፋክቸሪንግ) ዘርፉን ማነቆዎች ለማቃለል መሞከር እንደሆነ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ የሚሰጡት አስተያየት ነው። የብር መዳከሙ ባለበት ሁኔታ የወጪና የገቢ ንግዱ የማይሻሻል ከሆነ በሚቀጥሉት ዓመታት የዶላር ተመን በጥቁር ገበያ መናር ይበልጥ እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል የሚናገሩት አቶ አብዱልመናን ለዚህ የመንግሥት ፖሊሲ ወሳኝ ነው ይላሉ። ለሰሞኑ የምንዛሪ ዋጋ መናር የአገሪቱ አለመረጋጋት ምክንያት ቢሆንም መሰረታዊ ችግሮች ካልተፈቱ በመደበኛወም ሆነ በጥቁር ገበያው የብር መዳከሙ ጉዳይ የሚቀጥል ይሆናል፤ መሰረታዊ የሆነና የወጪ ንግዱን የማሻሻል እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ የመርገብ ሁኔታ እንደማይኖርም ያስረዳሉ። መንግሥት በዋነኝነት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ የፖለቲካ መረጋጋትቱን ማምጣት ቢሆንም፤ ነገር ግን በመሰረታዊነትና ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማምጣት ግን የውጭ ምንዛሪውን እጥረት መፍታት ነው። "አገሪቷ በማንኛውም መንገድ የገቢና ወጪ ንግዷን ልታመጣጥን ይገባል" የሚሉት አቶ አብዱልመናን በተለይም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን አንቀው የያዙትን ችግሮች መፍትሄ ልታበጅለት እንደሚገባ ይጠቁማሉ። ጨምረውም የንግድ ሚዛን ጉድለቷን ለማስተካከል ከግብርና ግብዓቶችና ቁሳቁሶች በመውጣት ወደ ማኑፋክቼሪንግ ዘርፉ መገባት መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራው የሚገባው ጉዳይ ነው ይላሉ። በተለይም ከማኑፋክቼሪንግ ዘርፉ ጋር ተያይዞ ሙስና፣ ብቃት ማነስ፣ የተንዛዛ ቢሮክራሲ፣ የኃይል እጥረት፣ የመሰረተ ልማት ችግር፣ ገንዘብ፣ መሬትና ሌሎችም ተግዳሮቶች ይጠቀሳሉ። በተለይም ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ይገኝባቸዋል ተብለው ታስበው የነበሩት የኢንዱስትሪ ፓርኮች የኃይል እጥረትን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች በሙሉ አቅማቸው ማምረት አለመቻላቸው ይነገራል። መንግሥት የወጪ ንግዱን ለማጠናከር በባለሙያ፣ የፋይናንስ ተቋማቱን እንዲሁም ሌሎች ማሻሻያዎችን በመስራት ችግሩን ሊቀርፍ ይገባል የሚሉት አቶ አብዱልመናን የገቢ ንግድን መተካት አስፈላጊነትንም ያሰምሩበታል። "የገቢ ንግድን መተካትም አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። መንግሥት አገሪቷ በየትኞቹ ምርቶች ላይ የገቢ ንግዷን መተካት ትችላለች የሚለውንም ማጤን ያስፈልገዋል። በአሁኑ ወቅት ስንዴን ጨምሮ ሽንኩርት ሳይቀር ከውጭ ታስገባለች። ይህ የሚያሳዝን ነገር ነው" ይላሉ። በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት መንግሥት መጠነ ሰፊ ማሻሻያ ሊያደርግም እንደሚገባ አበክረው ያሳስባሉ። ዶክተር ተኪኤ ብርን ማዳከም የተሳሳተ ፖሊሲ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚጨምር አይደለም ይላሉ። የብር መዳከም ለከፍተኛ ለሆነ ግሽበት እንደሚያጋልጥ በመጥቀስ የላቲን አሜሪካ አገራትና የዚምባብዌ እጣ እንዳይደርስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ይላሉ። አገሪቱ የሚጠቅማትን ፖሊሲ በደንብ ልታጤን እንደሚገባና ለምጣኔ ሃብቷ የሚስማማው የትኛውን መንገድ መከተል ነው የሚለው በደንብ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም ዶክተር ተኪኤ ይመክራሉ።
news-48824480
https://www.bbc.com/amharic/news-48824480
"በእስክሪብቶ ሳይሆን ክላሽ ተሸክመን ለመዋጋት ዝግጁ ነን'' ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ
የኢትዮጵያ ህልውናና አንድነትን በሚመለከት መንግሥት ከሰላማዊው መንገድ ባሻገር አስፈላጊ ከሆነ የጦር መሳሪያን በማንሳት የሚፈጸሙ አፍራሽ ድርጊቶችን ለመከላከል አስፈላጊውን ሁሉ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት የመንግሥትን የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ሲሆን በዚሁ ጊዜ "ለኢትዮጵያ አንድነት ግንባራችንን እንሰጣለን" ካሉ በኋላ "በኢትዮጵያ ህልውና የሚመጣ ካለ በእስክሪብቶ ሳይሆን ክላሽ ተሸክመን ለመዋጋት ዝግጁ መሆናችንን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ እፈልጋለሁ'' ብለዋል። • "ሌሎችንም ከፍተኛ ባለስልጣናት የመግደል ዕቅድ ነበረ" • "መደናገጥ ባለበት ወቅት ስህተቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ" አቶ ንጉሱ ጥላሁን አክለውም "ለሕዝብ ማስተላለፍ የምፈልገው፤ ይህ ለውጥ እውነተኛ ለውጥ ነው። ይህ ለውጥ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ብልጽግና የሚያወጣ ለውጥ ነው። በልበ ሙሉነት ልነግራችሁ የምፈልገው፤ እውነት ከእኛ ጋር ስለሆነ ማንም አያቆመንም። እውነትን ይዘን ስለምንሰራ የኢትዮጵያ አምላክ ያግዘናል'' ሲሉ ተናግረዋል። የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተው ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ ከኢትዮጵያ ውጪ የሆነው ሐሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ በሚያስተላልፉ ሰዎች ላይ ምሬታቸውን ሲገልጹ ''እኔ እናንተን ለመቆጣጠር የምችልበት መንገድ ስለሌለኝ፤ የእውነት አምላክ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይፍረድባችሁ ብቻ ነው የምለው'' ሲሉ ገልጸዋል። መፈንቅለ መንግሥት ሰሞኑን መንግሥት በብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ነው ማለቱን ተከትሎ በርካቶች እንዴት መፈንቅለ መንግሥት በክልል ደረጃ ይደረጋል፤ ይህን ተግባር መፈንቅለ መንግሥት ብሎ መጥራቱ ትክክል አይደለም ሲሉ የሞገቱት ጥቂት አይደሉም። ጠቅላይ ሚንስትሩም በዛሬው የፓርላማ ውሏቸው የተፈጸመው ጥቃት ''በኢፌዴሪ መንግሥት ላይ የተፈጸመ መፈንቅለ መንግሥት ነው'' ብለዋል። "በየትኛውም የፌደራል ሥርዓቱ ላይ የሚቃጣ ጥቃት የኢፌዴሪ ጥቃት ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ''አመራር ገድሎ እና አግቶ ሲያበቃ፤ የመንግሥት ተቋማትን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ 'ለምን መፈንቅለ መንግሥት ትሉታላችሁ' መባሉ ትክክል አይደለም" ብለዋል። የሰሞኑ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድራጊዎች ከባህር ዳርና ከአዲስ አበባ ውጪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝም ኃይል አሰማርተው እንደነበረ እና ከኦሮሚያ የተመለመሉ ''ገዳዮችን'' ያካተት እንደነበረ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረዋል። • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን • "ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል. . . ግን እናሸንፋለን" በተጨማሪም በመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ ላይ ከወራት በፊት የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ አለን ብለው የመጡ የሠራዊቱ አባላት መኖራቸውንም ተናግረዋል። ''መከላከያ አስሮ ገምግሞ 'እነዚህ ወጣቶች ናቸው ይማራሉ' ብሎ የለቀቃቸው በርካታ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነውበታል'' ብለዋል። ''እንዴት ሰው አምባቸው መኮንን ይገድላል?'' በማለት የጠየቁት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ''አምባቸው እንኳን ልትገድለው፤ ልትቆጣው እንኳን የሚያሳሳ ሰው ነው'' ሲሉ ገልጸዋቸዋል። ''ሰዓረ እንደ ሃበሻ ዳቦ ከላይ እና ከታች እሳት እየነደደበት፤ ጓዶቼን ቀብሬ የመጣሁባትን ኢትዮጵያን አላፈርስም ያለ ጀግናን እንዴት ሰው ይገድላል?" ሲሉ ጠይቀዋል። የመንግሥት ፈተናዎች ጠቅላይ ሚንስትሩ ባለፉት ወራት በመንግሥታቸውና አስተዳደራቸው ላይ ሆን ተብሎ በሌሎች አካላት የተከናወኑ ጥቃቶችንና ፈተናዎችን ዘርዝረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የጥቃቶቹን ዝርዝር በሰኔ 16 የቦንብ ፍንዳታ በማስታወስ ነበር የጀመሩት። ''ገና ሁለት ወራት እንኳ ሳይሆነን የጀመርነውን ለውጥ ለማጨናገፍ በአደባባይ የምታቁት ሙከራ ተደረገ'' ያሉ ሲሆን፤ ከዚህ ሁለት ወር በኋላ ''በሶማሌ ክልል የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተን ገንዘብ እና ትጥቅ ያለው የተደራጀ በሺህዎች የሚቆጠር አባላት ያለው ኃይል ችግር ፈጠረ። . . . እሱን ተሻግረን ሳንጨርስ የተደራጀ ወታደር ቤተ መንግሥት መጣ። በምትውቁት ሁኔታ እነሱን ከመለስን በኋላ በምዕራብ ኦሮሚያ በሦስት ወር መንግሥት እሆናለሁ ብሎ ምዕራብ ኦሮሚያን የሚያተራምስ ኃይል ተፈጠረ'' ብለዋል። • "ከጄ/ል አሳምነው ጋ በምንም ጉዳይ ያወራሁበት አጋጣሚ የለም" እስክንድር ነጋ ''ከቦታ ቦታ ዜጎቻችንን የሚያፈናቅሉ ኃይሎች ተፈጠሩ . . . አፈናቃዮች ብለው ዘፈኑብን። ተፈናቃዮችን ስንመልስ ደግሞ በኃይል መለሳችሁ አሉን'' በማለት ከተፈናቃዮች ጋር የነበረውን የመንግሥትን ፈተና አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ መንግሥት ያጋጠመውን ፈተና መዘርዘር ሲቀጥሉ፤ ''ጥቂቶች አውቀው፤ አብዛኛዎቹ ደግሞ ሳይገባቸው በሁለት እግር እንኳን መቆም ያልቻለችን ሃገር የደሞዝ ጭማሪ በሚል አንዴ መምህር አንዴ ደግሞ ሃኪም እያሉ ተደራጁብን'' ብለዋል። ''ይህ ፖለቲካ ነው። ኢትዮጵያ የደሞዝ ጭማሪ የምትጠየቅበት ጊዜ አልነበረም'' በማለት የደሞዝ ጥያቄው አግባብ አለመሆኑንና ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለው ጠቅሰው አልፈዋል። ቁልፍ ቦታዎች በኦሮሞ ተይዟል ቁልፍ የሚባሉ የመንግሥት የሥልጣን ቦታዎች በኦሮሞ ነው የተያዙት የሚለው አስተያየት ''ውሸት'' ነው ሲሉ አጣጥለውታል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ። ''የተከበረው ምክር ቤት፤ በእያንዳንዱ ተቋም ኦሮሞ ያልተገባ ሥልጣን ይዞ ከሆነ አጣርቶ ከእኔ ጀምሮ እርምጃ መውሰድ ይችላል" ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ "ኦሮሞ በአንድም ቦታ ያልተገባ ሥልጣን አልያዘም" ብለዋል። የክልል እንሁን ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚንስትሩ የክልል እንሁን ጥያቄ በሕጋዊ መንገድ ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል። ''በደቦ እና በጩኽት የሚመለስ ነገር ለማስተናገድ ከእንግዲህ ትዕግስታችን አልቋል። ሁሉም ሥርዓት ጠብቆ ይሄዳል፤ በሥርዓት እንመልሳልን። ያን የማይጠብቅ ከሆነ በተለመደው መንገድ እናስተናግደዋለን።" ሲሉ ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የክልል እንሁን ጥያቄን ለመመለስ ሕገ-መንግሥቱም መሻሻል ይኖርበታል ብለዋል። ምዕራፍ አራት የመንግሥትን አወቃቀር በተመለከተ የሰፈረው መቀየር እንደሚኖርበት ጠቁመዋል። የተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ስለመዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ የወንጀል ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አመልክተው፤ በዚህም መሰረት ከሽብር ቡድን ጋር በተያያዘ 48፣ በተለያዩ ስፍራዎች ከተፈጸሙ ብሔርን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች የተጠረጠሩ 799 አመራሮችና የፀጥታ ኃይል አባላት እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች የተጠረጠሩ 34 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለምክር ቤቱ ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳታፊ ሆነዋል የተባሉ 64 ተጠርጣሪዎችና በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ደግሞ 51 ሰዎች በሕግ አስከባሪዎች መያዛቸውን ጠቁመዋል። የሐገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ስላጋጠሙት መፈናቀሎች አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህም ባለፉት ዓመታት ሁለት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዜጎች እንደተፈናቀሉ አመልክተው ከዚህ ውስጥም ከመጋቢት 2010 ዓ.ም ጀምሮ አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል። ከተፈናቀሉት መካከል አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚሆኑት የተፈናቀሉት በሚኖሩበት ክልል ውስጥ ሲሆን 800 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ይኖሩበት ከነበረው ክልል ተፈናቅለው በሌላ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ከአጠቃላዩ ተፈናቃዮች ውስጥ 400 ሺህዎቹ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ባጋጠሙ ችግሮች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ ተፈናቃዮችን በተመለከተ መንግሥት ያከናወናቸውን ሥራዎች ጨምረው ሲገልጹ ከአጠቃላዩ ተፈናቃዮች ውስጥ ከሁለት ነጥብ አንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ወደ ነበሩባቸው ቦታዎች እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው አክለውም ለእንዲህ አይነቱ መፈናቀል ምክንያት እንደሆኑ የሚጠቀሱትን በተለያዩ ቦታዎች የሚያጋጥሙ ግጭቶችን ለማስቆምና ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር መንግሥታቸው ትኩረት ተሰጥቶ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። የሐገሪቱ ኢኮኖሚ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ሪፖርት ላይ እንዳመለከቱት ከ2008 እስከ 2009 ባለው ጊዜ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 8 ነጥብ 8 በመቶ ማደጉን እንዲሁም ባለፈው ዓመት 7 ነጥብ 7 በመቶ እድገት ማሳየቱን ተናግረዋል። አክለውም በዚህ ዓመት ያለፉትን አስራ አንድ ወራት አፈፃፀም መሰረት በማድረግ በ2011 ዓመተ ምህረት ኢኮኖሚው 9 ነጥብ 2 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
news-42513471
https://www.bbc.com/amharic/news-42513471
በሃገሪቱ የተከሰቱት ቀውሶችና አዲስ አበባ
በሀገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች ለብዙዎች ህይወት መቀጠፍ እንዲሁም በብዙ መቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ መፈናቀል ምክንያት ሆነዋል።
ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች በሀገሪቱ ተንሰራፍተው በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች ህይወት መጥፋት እንዲሁም የመማር ማስተማሩን ሂደት ማስተጓጓላቸው ጭምር ችግሩ ምን ያህል ስር እንደሰደደ አመላካች ነው። በተለይም ከሰሞኑ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ምላሽም የሟቾች ቁጥር እንዲያሻቅብ እንዲሁም ሥርዓቱ ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎችና ትችቶች እንዲያይሉ ምክንያት ሆነዋል። ከባለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ እነዚህ ሀገር አቀፍ ተቃውሞዎች ቢነሱም በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደደረሱ ብዙዎች ይናገራሉ። በተለያዩ ብሔሮችም መካከል ያለው መፈራቀቅና መጠላላትም የሀገሪቷ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን የሚሉ ጥያቄዎች እያስነሱ ነው። በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ግጭት የደረሱ መፈናቀሎችና ሞቶች፣ በተለያዩ ዪኒቨርሲቲዎች ላይ ያጋጠሙ ግጭቶችና የህይወት መጥፋቶች እንዲሁም ተቃውሞችስ በአዲስ አበባ ተፅእኖ መፍጠር ችለው ይሆን? በክልሎች የሚነሱ ጥያቄዎችስ የሀገሪቱ መዲና ነዋሪ ጥያቄዎች ናቸው? አዲስ አበባ እንዴት ናት? በአዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ አካባቢ መኪና አሽከርካሪ የሆኑት አቶ አለማየሁ ተገኘ የሰሞኑ ሁኔታ እንዴት ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ "እኛ ምን እናውቀዋለን፤ ብዙ ከውጭ አገር የሚመጡ ሰዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ላይ እየደረሱ ስላሉ ግጭቶች በበለጠ ይነግሩናል" ብለዋል። የሚሰሟቸው ዜናዎች ለአንዳንዶች መነጋገሪያ ቢሆኑም የከተማው ሁኔታ በተለያዩ ክልሎች ያለው ቀውስ ብዙም ተፅእኖ አልፈጠረም ብለው ያምናሉ። "ሥራም እንደተለመደው ነው፤ ተማሪውም ይማራል። የንግድ ተቋማትም የተለመደ ሥራቸውን ያከናውናሉ። በተወሰነ መልኩ አዲስ አበባ የሀገሪቱ አካል አትመስልም" ይላሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች የአቶ አለማየሁን ሃሳብ የሚጋሩ ሲሆን ህይወት አዳነ የተባለች የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ "ከቀድሞው ጊዜ ለየት የሚያደርገው ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ስላለው ሁኔታ ታክሲ ውስጥ ሲያወሩ እሰማለሁ" ትላለች። ከዚያ ውጭ ግን በምትማርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብዙዎች ሲወራና የመወያያ ርዕስ አጋጥሟት እንደማያውቅ ጭምር ትገልፃለች። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ቀውስ ብዙም የተሰማት በማትመስለው አዲስ አበባ አንዳንዶች ኑሮው እንደ ቀድሞው ነው ቢሉም ስጋቱ እንዳለ ግን አልደበቁም። በአምስት ኪሎ አካባቢ የሚኖሩት ወይዘሮ ወርቅነሽ ደምሴ የተባሉ እናት ሰዎች ቤተ-ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ የፀሎት እና ለሰላም የሚደረጉ መማፀኖች እንዳሉ ይናገራሉ። ምንም እንኳን በተለያዩ ክልሎች በሥርዓቱ ላይ እየተነሱ ያሉትን ጥያቄዎች የአዲስ አበባ ህዝብም በአብዛኛው ይጋራዋል ቢሉም፤ ወገንን የለዩ ግጭቶች ግን "እንደኛ ለተዋለደ፣ ለተዛመደና ለተዋሃደ ህዝብ እንዲህ አይነት ነገር መምጣቱ አሳዛኝ ነው'' በማለት ወ/ሮ ወርቅነሽ ይናገራሉ። ስጋት በ1997 ዓ.ም ምርጫ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ የአዲስ አበባን ሕዝብ ማንቀሳስ ችሎ የነበረው ቅንጅት የቀድሞ አባል የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው በበኩላቸው "አዲስ አበባ ውስጥ ግጭት ላይኖር ይችላል፣ ጥይት ላይተኮስ ይችላል፣ ሰው ላይሞት ይችላል፣ ህዝቡ ግን በውስጡ ሰላም ያለው አይመስለኝም" ይላሉ። ውጥረቱ በከፍተኛ ደረጃ እንዳለ የሚገልፁት አቶ ልደቱ አዲስ አባባ የተለያዩ ሕዝቦች መናኸሪያ መሆኗና በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ላይ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች ብሔርን መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው እንደዚህ አይነት ግጭቶች አዲስ አበባ ላይ የመፈጠር ዕድላቸው ኢምንት መሆናቸውንም ይናገራሉ። "ነገር ግን ከተፈጠረ በጣም አደገኛ ነው፤ ለመቆጣጠርም አስቸጋሪ ይሆናል" በማለት ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ። በአፍሪካ የፖለቲካ ፍልስፍና ምሁር የሆኑት ዶክተር ዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ እነዚህ ግጭቶች በተለያዩ ክልሎች በመከሰታቸው ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውሱን የከተማው ነዋሪ ቢያውቁም ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እንዳልተገነዘበ ይገልፃሉ። ከዚህም በተጨማሪ ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋርም የሚጋሩት የአዲስ አበባ ህዝብ ከብዙ ብሔረሰቦች የተውጣጣ በመሆኑ አሁን እየተፈጠሩ ያሉትን የብሔር ግጭቶች በጎንዮሽ እንዲያየው እንዳደረገም ዶክተር ዮሴፍ ይገልፃሉ። "የተለመደች አባባል አለች፤ የአዲስ አበባ ልጅ ሰፈር እንጂ ብሔር አይጠየቅም የምትል፤ ምንም እንኳን የብሔርም ይሁን የመደብ ጥያቄ ብዙ አስርት ዓመታትን ቢያስቆጥሩም አብዛኛው የአዲስ አበባ ህዝብ ኢትዮጵያ በሚለው እንጂ በብሔር ራስን የመግለፅ ነገር የለውም። ስለዚህም እየገጠሙ ላሉት የብሔር ግጭቶች አትኩሮትን ነፍጓል" በማለት ዶክተር ዮሴፍ ይናገራሉ ። ምንም እንኳን አሁን እየታዩ ያሉት ግጭቶች ከማንነት ጋር የተያያዙ እንደሆኑ ቢነገርም ሥርዓቱ ላይም እንደ ፍትህ ማጣት፣ የወጣቱ ሥራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነትም እንዲሁም ሌሎች ጥያቄዎችም እየተነሱ ነው። ጥብቅ ቁጥጥር መንግሥት ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ማፈንን እንዲሁም ፅንፈኛ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ብዙዎች የሚናገሩ ሲሆን በተለይም እንደ አዲስ አበባ ባሉት ከተሞች የመንግሥት የቁጥጥር መዋቅርም ከሌሎች ከተሞች በበለጠ የጠበቀ መሆኑም ይነጋራል። "አብዛኛው የፀጥታ ኃይል አዲስ አበባ አለ። የመንግሥት መዋቅር በከተማዋ ስር የሰደደ በመሆኑ ሥርዓቱ በከፍተኛ ደረጃ መቆጣጠር ይችላል" በማለት አቶ ልደቱ ይናገራሉ ። በተለይም ከሌሎች ክልሎች በበለጠ በአዲስ አበባ አንድ ለአምስት የሚባለው የገዢው ፓርቲ መዋቅር ስር የሰደደና የማያፈናፍን መሆኑንም ጭምር አቶ ልደቱ ይናገራሉ። አዲስ አበባ ለዘመናት የከተማ የተቃውሞዎች እንቅስቃሴ መነሻ የነበረች ስትሆን ከዚያም በኋላ ግን ወደ ሌሎች ክልሎች የመዛመት ባህርይ ነበራቸው። በ1993 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እንዲሁም በ1997 ዓ.ም ከምርጫ ጋር ተያይዞ የተነሳውም ተቃውሞዎች ተጠቃሽ ናቸው። ከጥቂት ዓመታት በፊት ግን በተለያዩ ክልሎች ተቃውሞዎች ቢነሱም በአዲስ አበባ የተደራጀ እንቅስቃሴ አይታይም። አቶ ልደቱ ለዚህ እንደ ምክንያትነት የሚጠቅሱት ቀደም ባሉት ተሞክሮዎች ህብረተሰቡ ውስጥ የነበሩትን እንቅስቃሴዎችን የሚያደረጁትም የሚመሩትም ተቃዋሚዎች ነበሩ። "ሌሎች ከተሞች ለአዲስ አበባ ድጋፍ ከመስጠት ጋር ተያይዞ ነው የሚቀሰቀሱት አሁን ደግሞ በተቃራኒው ነው" በማለት አቶ ልደቱ ይናገራሉ። የ1997 ምርጫን ተከትሎ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ እንደ ምሳሌ የሚያሱት አቶ ልደቱ፤ ከዚያ በኋላ "በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደሌሉ መቆጠር ይቻላል" የሚሉት አቶ ልደቱም ምናልባት የአዲስ አበባም ሁኔታ ከዚያ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማሉ። በዚህ ይቀጥላል ወይ? በሀገሪቱ ውስጥ የሚታዩት ቀውሶች ወደ አዲስ አበባ ላለመዛመታቸው ምንም አይነት ዋስትና የለም የሚሉት አቶ ልደቱ፤ አዲስ አበባ ውስጥ ቢቀጣጠል ደግሞ የበለጠ አስፈሪ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። "አሁን እየተከሰቱ ያሉት የብሔር ግጭቶች ከቁጥጥር ውጭ ያልወጡትም ችግሩ አዲስ አበባ ላይ ስላልተከሰተ ነው'' ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ አዲስ አበባ ይከሰቱ የነበሩት ተቃውሞዎች በሥርዓቱ ላይ ብቻ የነበሩ ሲሆን፤ አሁን በተለያዩ ቦታዎች እየታዩ ያሉት ግጭቶች ቅርፃቸውና ይዘታቸው ተቀይሯል። "በህዝብና በመንግሥት ብቻ ሳይሆን፣ በህዝብና ህዝብ እንዲሁም በፌደራልና በክልል መንግሥታትም መካከል ፍጭቶች እየተስተዋሉ ነው። የኃይል አሰላለፉም ተቀይሯል" ይላሉ አቶ ልደቱ። ምንም እንኳን ህዝቡ ለውጥ እንደሚፈልግ አቶ ልደቱ ቢናገሩም፤ በተደራጀ መልኩ ለውጥ የማምጣት የፖለቲካ ባህሉ እንደሌለም አቶ ልደቱ ይናገራሉ። "ህዝቡ ለውጥ ይፈልጋል ነገር ግን ለውጥን ከሆነ አካል ነው የሚጠብቀው። በተወሰነ መልኩ መደንዘዝም አለ፤ ይህ አደገኛ ነው። ለውጥ የሚፈልገውም የሚፈራውም ያውነው። ሁሉም ፀጥ ረጭ ብሎ የሚያይበት ሁኔታ ነው ያለው" በማለት አቶ ልደቱ ይናገራሉ። ለዶክተር ዮሴፍ በከተማዋ ላይ እየተንሰራፋ ያለው ጣራ የነካ የኑሮ ውድነት እንዲሁም ከብሄርና ከማንነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ላይ አብዛኛው የአዲስ አበባ ህዝብ በተለየ መንገድ እንደሚመለከተውም ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ ከአቶ ልደቱ ጋር የሚጋሩት ከ1997 በኋላ የፖለቲካው ምህዳር መጥበቡ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተሜነት (ኮስሞፖሊታን) መሆን ለዚህ አስተዋፅኦ እንዳደረገ ያምናሉ።
news-51440665
https://www.bbc.com/amharic/news-51440665
‘በአስራ አራት አመቴ የተደፈርኩበት ቪዲዮ 'በፖርን' ድረገፅ ላይ ነበር'
ሮዝ ካሌምባ በአስራ አራት አመቷ የተደፈረች ሲሆን ይህ ቪዲዮ ታዋቂ የወሲብ ፊልም ድረገፅ ላይ ይኖራል ብላ በህልሟም አላለመችም። ያላሰበችው ሆነና በታዋቂ የወሲብ ፊልም ድረ ገፅ ላይ የመደፈሯን ስቃይ የሚያሳይ ቪዲዮ ለተመልካቹ ይፋ ሆነ።
ይህ ቪዲዮ ከድረ ገፁ እንዲጠፋ ብዙ ትግል አድርጋለች፤ ይህንንም ተስፋ አስቆራጭ ትግል በፅሁፏ አስፍራለች። ፅሁፏ ከወጣም በኋላ ብዙዎች በተመሰሳይ መንገድ የተደፈሩበት ተንቀሳቃሽ ምስል በወሲብ ፊልም ድረገፅ ላይ እንደተቀመጠና እንዲወርድ ለማድረግ እንዳልቻሉ አጋርተዋታል። • የአስገድዶ መደፈር ክሷን ለመከታተል የሄደችው ወጣት በእሳት ተቃጠለች • የተነጠቀ ልጅነት ማስጠንቀቂያ፦ ታሪኩ ጭካኔ የተሞላበት ወሲባዊ ጥቃት አለበት ሮዝ በተኛችበት ሆስፒታል ውስጥ የምታስታምማት ነርስ ቀና ብላ አይታት "ስለደረሰብሽ ነገር በሙሉ በጣም አዝኛለሁ"አለቻት በሚንቀጠቀጥ ድምፅ "ልጄም ተደፍራለች" ነርሷ አከለች ሮዝ ነርሷን ቀና ብላ አየቻት፤ ዕድሜዋ ከአርባ አይበልጥም። ልጇም እንደኔ ትንሽ ልትሆን ትችላለች ብላ አሰበች። በተደፈረች በነገታው ስሜት ካልሰጠው ወንድ ፖሊስና ዶክተር ጋር ያደረገችውን ውይይት አስታወሰች። ሙሉ ሌሊት ጭካኔ በተሞላበት መልኩ የተደፈረችውን "ተጠርጣሪዎቹ" እያሉ ነበር የሰሟት፤ ታሪኳን ስትናገር። የባዳዎቹን ይቅርና ከአባቷና ከአያቷ በስተቀር ዘመዶቿም አላመኗትም። የነርሷ ግን የተለየ ነበር። "አመነችኝ" አለች ሮዝ የደረሰባትንም ጥቃት ያለምንም ጥርጣሬ ስላመነቻት ተስፋ ፈነጠቀላት፤ መጪው መጥፎ ላይሆን ይችላል በሚል። ነገር ግን የወደፊቱ መጥፎ ቅዥት ነበር፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተደፈረችበትን ቪዲዮ ራሳቸው አዩት፤ ምንም ሃዘኔታ አልነበራቸውም። •በህንድ በቡድን ተደፍራ የተገደለችው ዶክተር ጉዳይ ከፍተኛ ቁጣን ቀሰቀሰ ከአስር አመት በኋላ ሮዝ ካሌምባ በመስታወት እያየች ፀጉሯን ታስተካክላለች፤ ከተደፈረችበት ከጥቂት ወራት በኋላ መስታወት መመልከት የሚታሰብ አልነበረም። ቤት ውስጥ ያሉ መስታወቶች በሙሉ በብርድ ልብስ መሸፈን ነበረባቸው። የራሷን ምስል ለማየት አቅሙ አጥሯት ነበር። የሃያ አምስት አመቷ ሮዝ ራሷን ከደረሰባት የማይረሳ ህመም ለማዳን የየቀኑ ጉዳይ ላይ ማተኮር አለባት። ፀጉሯን ማበጠርና መንከባከብ አንዱ ነው። ፀጉሯ ላይ ብቻ እንድታተኩር ያደርጋታል። የሚያምር ፀጉር አላት ብዙዎችም አስተያየት ሰጥተዋታል። በጥዋት ተነስታም ካካዎ ከቸኮሌት ታፈላለች፤ የፈውስ ንጥረ ነገር እንዳለው ታምናለች። ከዚያም እቅዶቿን በዲያሪያዋ ላይ ታሰፍራለች፤ ወደፊት የማሳካቸው በሚል ሳይሆን አሁን እያከናወንኩት በሚል። "በጣም ጎበዝ አሽከርካሪ ነኝ" አንደኛው እቅድ፣ " ከሮበርት ጋር ተጋብተን በሰላምና በደስታ እየኖርን ነው" ሌላኛው እቅድ "መልካም እናት ነኝ" ሮዝ ያደገችው በትንሿ ከተማ ኦሃዮ ውስጥ ነው። ማታ ማታም ከቤት ወጥታ ብቻዋን በእግሯ መራመድ የተለመደ ተግባሯ ነበር፤ ፀጥታውና ንፁህ አየሩ ያስደስተኛል ትላለች። እናም ከአስራ አንድ አመታት በፊትም አንድ ምሽት የአስራ አራት አመቷ ሮዝ በአካባቢዋ ቀስ ብላ እየተራመደች ነበር። •የአንዱ እርግማን ለአንዱ ምርቃን፡ ኢትዮጵያን መጠጊያ ያደረጉ የስደተኞች ታሪክ ሮዝ ህፃን እያለች በድንገት አንድ ግለሰብ ከጨለማው ወጣ ብሎ ወደሷ መጣ። ቢላውን አሳያትና መኪናው ውስጥ እንድትገባ አስገደዳት። ጋቢና ወንበር ላይ 19 እድሜ የሚገመት ሌላ ወንድ ተቀምጧል። ሰውየውን መንገድ ላይ አይታው ታቃለች። ራቅ ብሎ ወደሚገኝ ሰፈርም ወሰዷት፤ የሆነ ቤት ውስጥ አስገቧት ለአስራ ሁለት ሰዓታት ያህል ደፈሯት። ይህንንም የሚሰቀጥጥ መደፈር የሚቀርፅ አንድ ወንድ ነበር። በከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የነበረችው ሮዝ ለመተንፈስ ስትታገል ነበር፤ ክፉኛ ተደብድባለች፣ ግራ እግሯም በጩቤ ተወግቷል፤ ልብሷም በደም ተጨመላልቋል። ራሷንም ብዙ ጊዜ ስትስትና ስትነቃም ነበር። የሆነ ሰዓት ላይ አንደኛው ግለሰብ ሌሎች የተደፈሩ ሴቶች ቪዲዮ አሳያት። "ደፋሪዎቹ በሙሉ ነጮች ሲሆኑ የተደፈሩት ደግሞ ነጭ ያልሆኑ ሴቶች ናቸው እናም ነጭ የበላይ ነው አለኝ" ትላለች። አንደኛው ሰውየ ነቅታ የማታዋራቸው ከሆነ እንደሚገላት አስፈራራት። እሷም በትግል ነቃ ብላ ከለቀቋት ለማንም እንደማትናገር በመለመን ጠየቀቻቸው። እነሱም እንደዛ ካሰቃይዋት በኋላ መኪና ውስጥ አስገቧትና፤ ሰፈሯ አካባቢ ሲደርሱ ጎዳና ላይ ጣሏት። እንደምንም እየታገለች ቤቷ ደረሰች፤ በመስታወት ራሷን ስታየው ከጭንቅላቷ በሚፈስ ደም ፊቷ በከፊል ተሸፍኗል። አባቷ ሮንና አንዳንድ ዘመዶች ሳሎን ተቀምጠው እየተመገቡ ነበር፤ እንደዛ ቆሳስላና በደም ተጨማልቃ ቤት ስትደርስ። •የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት •የታዳጊዋ ሬስቶራንት ውስጥ መደፈር ደቡብ አፍሪቃውያንን አስቆጥቷል ምን እንደተፈጠረ ነገረቻቸው "አባቴ በፍጥነት ፖሊስ ጠራ ፤ አቀፈኝ። ሌሎች ዘመዶቻችን ግን ለምንድነው በማታ ብቻሽን በጨለማ የወጣሽው የሚል ጥያቄ ነው የጠየቁኝ" ትላለች ሮዝ ሆስፒታል ስትደርሰ ወንድ ዶክተርና ፖሊስ ተቀበሏት። "ሁለቱም ቢሆን እውነቱን ለማውጣት በሚል ጥያቄዎች ጠየቁኝ፤ ምንም አይነት ደግነትም ሆነ ሃዘኔታ አይታይባቸውም ነበር" በተለይም ወንዱ ፖሊስ በፈቃደኝነት ላይ የተጀመረ ሆኖ ምናልባት ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሆነው ይሆን አላት። ሮዝ ደነገጠች፤ አላመነችም። "ክፉኛ ተደብድቤ፣ በጩቤ ተወግቼና በደም ተጨማልቄ እኮ ነው የመጣሁት" ሮዝ እንደምንም ታግላ በፈቃደኝነት እንዳልሆነና የደፋሪዎቹንም ማንነት እንደማታውቅ ተናገረች። ፖሊሶቹ ምንም ፍንጭ የለንም አሉ። ሮዝ በነገታው ከሆስፒታልም ስትወጣ ራሷን ልትገድል ሞከረች፤ ወንድሟ በጊዜው ባይደርስ ህይወቷ አልፎ ነበር። ከተደፈረች ከጥቂት ወራት በኋላ በወቅቱ ዝነኛ የነበረው ማይ ስፔስ ማህበራዊ ድረገፅ ላይ ብዙዎች የተጋሩትን የድረገፅ ማስፈንጠሪያ አገኘች፤ ስሟም ተጠቅሶ ነበር። ማስፈንጠሪያውን ስትጫን 'ፖርን ሃብ' ወደሚል የፖርን ድረገፅ ወሰዳት። ራሷን ስትደበደብ፣ ጥቃት ሲደርስባትና ስትደፈር የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ስታይ ወደላይ አላት። አንደኛው ቪዲዮ 'ታዳጊ በጥፊ ስትመታ፣ ስታለቅስና ስትደፈር' የሚል ርእስ 'ሌላኛው ቪዲዮ 'ታዳጊዋ በመደፈር ከጥቅም ውጭ ስትሆን'፣ እንዲሁም 'ራሷን የሳተች ታዳጊ ስትደፈር' የሚሉ ሁሉም የሷን መደፈር የሚያሳዩ ሲሆኑ አንደኛው ቪዲዮን አርባ ሺ ሰዎች ተመልክተውታል። "ከዚህ ሁሉ የሰቀጠጠኝ ራሴን ስቼ የምደፈርበትን ሳይ ነው፤ ራሴን እኮ አላውቅም" ቪዲዮዎቹን አይታ ለቤተሰቦቿ ላለመንገር ወሰነች፤ ምክንያቱም ብዙዎቹ የቤተሰቦቿ አባላት እየደገፏት ስላልነበር፤ መንገር እርባና አልነበረውም። በጥቂት ቀናትም የትምህርት ቤቷ ልጆች አዩት። "ይሰድቡኝ ጀመር፣ ፈልጌ እንደሆነና ሸርሙጣ ነሽ ይሉኝ ጀመር" አንዳንድ ወንዶች በቤተሰቦቻቸው እንዳላሳስታቸው ከኔ እንዲርቁ ተነገራቸው። "ለብዙዎች ተጠቂን ወንጀለኛ ማድረግ ቀላል ነው" ትላለች። የፖርን ሃብ ድረገፅን ለስድስት ወራት ያህል ቪዲዮውን እንዲያወርዱት ለመነቻቸው። "ለመንኳቸው፣ ተማፀንኳቸው። ገና ታዳጊ ነኝ፤ ተደፍሬ ነው! እባካችሁ ከድረገፁ አውርዱት ብላቸውም ምላሽ አልሰጡኝም" "በሚቀጥለው አመት ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቼ ዝም አልኩ፤ ለምንም ነገር ስሜት አልነበረኝም" ቢሆንም ግን አንዳንድ ሰዎች ሲያይዋት ቪዲዮውን አይተውት ይሆን በማለት ራሷን ትጠይቃለች። "የመደፈሬ ቪዲዮ አስደስቷቸው ይሆን? ብዬ እጠይቃለሁ" ራሷን በመስታወት ማየት ከበዳት ለዛም ነው ቤት ውስጥ ያሉ መስታወቶች በብርድ ልብስ የተሸፈኑት። ጥርሷን በቡርሽም ስታፀዳ በጨለማ ማን ቪዲዮውን ተመልክቶት ይሆን እያለች ትጠይቃለች። ከዚያም ድንገት አንድ ሃሳብ መጣላት ራሷን ጠበቃ በማስመሰል ለፖርን ድረገፁ ኢሜይል ፃፈች። ቪዲዮውን ካላወረዱት ህጋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀቻቸው፤ በአርባ ስምንት ሰአታትም ውስጥ ቪዲዮው ከድረገፁ ላይ ተነሳ። ከወራት በኋላም የስነልቦና እርዳታ ሲደረግላት እነማን እንደሆኑ ደፋሪዎቿ ይፋ አደረገች። ለቤተሰቦቿም ሆነ ለፖሊስ ስለ ቪዲዮውም ሆነ ስለ ደፋሪዎቿ ትንፍሽ አላለችም። የስነ ልቦና ባለሙያዎቹ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጋቸውን ተከትሎ ደፋሪዎቿ ፍርድ ቤት ቀረቡ። የደፋሪዎቿ ጠበቃ በፍቃዷ ነው የሚል ክርክር አቅርቦ አሸነፈ። ደፋሪዎቿ በመድፈር ሳይሆን "ከእድሜ በታች ያለችን ህፃን በማባለግ" በሚል ወንጀል ቀለል ያለ እስር ቢፈረድባቸውም፤ የእስሩ ቅጣት ተፈፃሚ አልሆነም። ሮዝም ሆኑ ቤተሰቦቿ የደፋሪዎቿ ቅጣት ከፍ እንዲል ይግባኝ የማለት የገንዘቡ አቅምም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም። ሮን ካሌምባ ልጁ ላይ የነበረውንም ዝርዝር ሁኔታ ቪዲዮም እንደነበር የደረሰበት በቅርቡ ነው። በወቅቱ ቢያውቅ ምን ያደርግ ነበር ራሱን ሁልጊዜም የሚጠይቀው ጥያቄ ነው። ከመደፈሯ በፊት ጎበዝ ተማሪ የነበረች ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ውጤቷ አሽቆለቆለ። ሮንና ልጁ አንዳንድ ጊዜ ፓርክ ውስጥ ሄደው ቢዝናኑም ስላለፈው ነገር ትንፍሽ አይሉም። "መላው አለም ግድ አልሰጠውም፤ የደረሰባት ጥቃትና መደፈር ቀልድ ነበር። ሙሉ ህይወቷ ተቀይሯል" ይላል አባቷ የሮዝ አባት ሮን ካሌምባ ሮን ስለ ቪዲዮው ያወቀው ባለፈው አመት ነው፤ ሮዝ በፃፈችው ፅሁፍ ምክንያት። ፅሁፉን ብዙዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርተውታል። የመደፈሯ ቪዲዮ ይህን ያህል ሰው እንዳየውም ሆነ ትምህርቤት እንደተቀለደባት አያውቅም። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቪዲዮዋን አይተውት ተሳልቀዋል፤ ሌላም ነገር አድርገዋል ። ሮዝ ካሌምባና አባቷ ሮዝ እያደገች ከመጣች በኋላ መፃፍ ላይ አተኮረች፤ በተለያዩ ድረገፆችም ላይ አንዳንድ ጊዜ ትክክለኛ ስሟን በመጠቀም የምትፅፍ ሲሆን ሌላ ጊዜ ደግሞ በብዕር ስም፤ ሆነም ቀረ ስምጥ ብላ ወደ መፃፉ አለም ገባች። በአንድ ወቅትም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፖርን ሃብን የሚያወድሱ አስተያየቶች ተመለከተች፤ ለንብ ጥበቃ ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ፣ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለሚረዳ ድርጅትና ወደ ቴክኖሎጂው መግባት ለሚፈልጉ ሴቶች 25 ሺ ዶላር እርዳታ ማድረጉን አነበበች። በፖርን ሃብ መረጃ ከሆነ በባለፈው አመት ብቻ አርባ ሁለት ቢሊዮን ጊዜ ድረገፁ ተጎብኝቷል፤ በቀን 115 ሚሊዮን ጊዜ ይጎበኛል፤ 1200 ጊዜ በሰከንዶች ድረገፁ ይታያል። ፖርን ሃብ ታዋቂ ድረገፅ ነው፤ ራሳቸውንም እንደ ተራማጅ አድርገው ማስተዋወቋ ገረማት፤ ምክንያቱም የሷ ብቻ ሳይሆን ብዙ ሴቶች የተደፈሩበት ቪዲዮዎች በድረገፁ ስላሉ። ብዙዎች ባጋሩት ፅሁፏም ላይ የመደፈሯን ዝርዝር ሁኔታ፣ቪዲዮውን ከፖርን ሃብ ላይ ለማስወረድ የገጠማትን ፈተና ፃፈች። ብዙዎችም ለፅሁፏ እኛም ጥቃት ደርሶብን እንዲሁ ድረገፁ አላወርድም ብሏል የሚል ምላሽ መስጠት ጀመሩ። ፖርን ሃብ በበኩሉ ለቢቢሲ በሰጠው መግለጫ ይህ የተፈጠረው ከአስራ አንድ አመት በፊት እንደሆነና የድረገፁ ባለቤትም ሌሎች ግለሰቦች እንደነበሩ ነው፤ እናም በወቅቱ የነበሩት ባለቤቶች ምን አይነት ምላሽ እንደሰጡ እንደማያውቁ አስፍረዋል። በአሁኑ ሰዓት ግን እንዲህ አይነት ህገወጥና የህፃናትንም ጥቃት ለመታደግ ፖሊሲ ከማርቀቅ በተጨማሪ የተለያዩ ሶፍትዌሮች እንዳሏቸውም አስረድተዋል። ነገር ግን እንደ ሮዝ የመደፈር ቪዲዮ አይነት "ታዳጊ ተኝታ ባለችበት ሰዓት ጥቃት ሲደርስባት"፣ "የሰከረች ታዳጊ ስትደፈር"፣ "በጭካኔ የተሞላ የታዳጊ መደፈር" በሚሉ ርእሶች ለምን ቪዲዮዎች እንዳሉ በተጠየቁበትም ሰዓት "የትኛውንም አይነት ወሲባዊ ራስን በነፃነት የመግለፅ መብት እንደማይቃወሙና፤ እነዚህ ቪዲዮዎች ለአንዳንዶች አግባብ ባይመስሉም የሚፈልጓቸው አሉ። ይህም ነፃነትን የሚፃረር አይደለም" ብለዋል። ምንም እንኳን ድረገፁ ህገ ወጥ ቪዲዮዎች ሲመጡ ማሳወቂያ መንገድ ከሶስት አመታት በፊት ቢያስተዋውቅም አሁንም ጥቃትንና መደፈርን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ብዙ ናቸው። ባለፈው አመት ክርስቶፎር ጆንሰን የተባለ የ30 አመት ግለሰብ አንዲት የ15 አመት ታዳጊን ወሲባዊ ጥቃት ሲያደርስ የሚያሳይ ቪዲዮ በፖርን ሃብ ወጥቶ ግለሰቡ ለእስር ተዳርጓል። ይህንንም ሁኔታ አስመልክቶ ፖርን ሃብ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ህገ ወጥ መሆኑን ስናውቅ ወዲያው አስወግደነዋል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው አመት እንዲሁ ሃያ ሁለት ሴቶች በወሲብ ባርያነት የተገደዱበትን ቪዲዮዎች በማሳየት ተከሶ የነበረ ሲሆን ቪዲዮውን አስወግደውታል፤ ቪዲዮውን የሰሩት ሰዎችም በህገወጥ የወሲብ ንግድ ተከሰዋል። "ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች በኔ ላይ ከአስር አመት በፊት የደረሰው የማይደርስ ቢመስላቸውም ተሳስተዋል፤ አሁንም ይደርሳል" ትላለች ሮዝ "በከፍተኛ ሁኔታ ፖርን በሚታይባቸው በመካከለኛው ምስራቅና በእስያ ሃገራት የተደፈሩ ሴቶች ቪዲዮዋቸው እንደሚታይ ላያቁ ይችላሉ" ሌላ እንዲሁ በካሊፎርኒያ ነዋሪ የሆነች አንዲት ሴት ስትደፈር የሚያሳይ ቪዲዮ በሌላ የፖርን ድረገፅ እንዳለና አውርዱት ብላ ብትጠይቃቸውም አሻፈረኝ ማለታቸውን ለሮዝ ነግራታለች። ቢቢሲም የድረገፁን ጠበቆች ባናገረበት ወቅት ስለጉዳዩ ምንም አናውቅም ቢሉም ቢቢሲ በምላሹ የቪዲዮውን ማስፈንጠሪያ በላከላቸው በቀናት ውስጥ ቪዲዮውን አውርደውታል። በሮዝ ላይ የተፈፀመው በሌሎች ሴቶችም ላይ እንደሚፈፀም መረጃ እንዳላቸው ኬት አይዛክ የተባለች ተመራማሪ ገልፃለች። "ፖርን ሃብ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ድረገፆች ይህንኑ ያደርጋሉ። በግለሰቦች የተቋቋሙ ትንንሽ ድረገፆች ምንም ማድረግ አንችልም። ፖርን ሃብ ግን ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፤ ይህን የሚያስፈፅም ህግ የለም" ትላለች። ምንም እንኳን በእንግሊዝ ለግለሰቦች ግላዊ የሆነ፣ እርቃንን የሚያሳዩ፣ ወሲባዊ ግንኙነትን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ያለ ፈቃድ ማጋራት እስከ ሁለት አመት እስራት ቢያስቀጣም፤ ድረ ገፆች ግን ተጠያቂ አይደሉም። "የፖርን ድረገፆች የሚረብሹና ፍቃድ የሌላቸው ቪዲዮዎች እንዳሉ ያውቃሉ፤ ፊልምና ትክክለኛውን ነገርስ እንዴት እንለየዋለን ተመሳሳይ ናቸው" ትላለች። ፖርን ሃብ ቪዲዮዎቹን ወደ ግል ኮምፒውተር መጫን (ዳውንሎድ) ማድረግ የሚቻል ሲሆን ይህ ማለት ከድረገፅ ላይ እንኳን ቢጠፉ በሰዎች ንብረትነት ይቆያሉ። ሮዝ መደፈሯን ሙሉ በሙሉ ባትዘነጋውም ከጓደኛዋ ሮበርት ጋር ተወያይተውበታል። ተጋብተውም ሴት ልጅ እንደሚወልዱ ተስፋን ሰንቃለች።፥ " በብዙ መንገድ የዘላለም ፍርደኛ ነኝ፤ አንዳንድ ጊዜ እቃ ልገዛም ወጥቼ ቪዲዮውን አይተውት ይሆን እላለሁ" ትላለች። ነገር ግን አሁን ዝምታዋን ሰብራለች። "ለደፋሪዎች መሳሪያቸው ዝምታችን ነው" ሮዝ ብቻ አይደለችም፣በሰሜናዊ ባንግላዴሽ በአስራ ሶስት አመቷ በቡድን የተደፈረችው ፑርኒማ ሺል መደፈሯን የሚያስታውሳት ጉዳይ አሁንም አለ። ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ አንድ ግለሰብ ስሟንና ስልክ ቁጥሯን የያዘ የፌስቡክ ገፅ ከፍቷል።
news-45764587
https://www.bbc.com/amharic/news-45764587
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ
በሀዋሳ ከተማ ሲካሄድ በነበረው የኢህአዴግ 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከጠቅላላው 177 ድምፅ 176ቱን በማግኘት እንደተመረጡ ታውቋል።
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ አቶ ደመቀ መኮነን ደግሞ በ149 ድምፅ ም/ሊቀመንበር ተደርገው ተሹመዋል። ለምክትል ሊቀመንበርነት በእጩነት የቀረቡት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በበኩላቸው 15 ድምፅ አግኝተዋል። የምርጫው አሰጣጡ ሂደት በ12 የኮሚቴ አባላት የተመራ ሲሆን፤ በአቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አስመራጭ ኮሚቴ መሪነት እና በወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ምክትል መሪነት ተካሄዷል። በተጨማሪም በዕለቱ የድርጅቱ የቁጥጥር ኮሚቴ ተቋቁሟል። ኮሚቴው በአቶ አወቀ ኃይለማሪያም መሪነት፣ በአቶ ጀማል ረዲ (ደኢህዴን) ምክትል ኃላፊነትና በአቶ ብርሃኑ ፈይሳ (ኦዴፓ) ፀሐፊነት እንደሚመራ ተገልጿል። የኢህአዴግ ጉባኤ ነገ ማለዳ በሀዋሳ ስቴዲየም በሚደረግ ስነ ስርዓት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
news-53891757
https://www.bbc.com/amharic/news-53891757
የፍርድ ቤት ውሎ፡ ኢዴፓ የአቶ ልደቱ እስርን በሚመለከት ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ደብዳቤ መጻፉን ገለፀ
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑትና በኦሮሚያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ቢሾፍቱ ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙትን አቶ አቶ ልደቱ በሚመለከት ቅዳሜ ዕለት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ደብዳቤ መጻፉን ፓርቲያቸው አስታወቀ።
ፓርቲው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፈው ደብዳቤ ላይ የአቶ ልደቱ ጉዳይ በፍርድ ቤት እየታየ እንደሆነ በመጥቀስ "አቶ ልደቱ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከወንጀል ጋር የተገናኘ ድርጊት ፈጽመው ሳይሆን በፖለቲካ ታስረዋል ብሎ ፓርቲያቸው እንደሚያምን" መግለፁን አቶ አዳነ ታደሰ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ ገልጸዋል። ፓርቲው በደብዳቤው ላይ አቶ ልደቱ በአሁኑ ሰዓት የታሰሩበት ሁኔታ ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው መንግሥት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት መጠየቁን በተለይ ለቢቢሲ ገልጿል። አቶ አዳነ አክለውም ይህ እየተወሰደ ያለው እርምጃ አጠቃላይ ሰላማዊ ትግሉ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅሬታቸውን ማቅረባቸውን ተናግረዋል። በተያያዘ ዜና አቶ ልደቱ ዛሬ ሰኞ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ አረጋግጠዋል። ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ የሰባት ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ችሎት የቀረቡትም ፖሊስ የደረሰበትን እንዲያስረዳ እንደነበር ተናግረዋል። ፖሊስ ተጨማሪ ነገር ይዞ ሊቀርብ አለመቻሉን የሚናገሩት አቶ አዳነ "የሽግግር መንግሥት ሠነድ እጃቸው ላይ ተገኝቷል፤ በዚህ ሰነድ ሰበብም ብጥብጥና ሁከት ተነስቷል የሚል የፖሊስ ማስረጃ ችሎቱ ተመልክቶ ውድቅ አድርጎ፣ ከስልካቸው ላይ የተወሰዱ የድምጽና የመልዕክቶች ከቴሌ አስገልብጠናል እርሱን አደራጅተን፣ አስተርጉመን ለማቅረብ እንዲመቸን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይፈቀድልን ሲል ፖሊስ ጠይቋል" ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ልደቱም ያሉበትን የጤና ሁኔታን በመጥቀስ የዋስትና ጥያቄ ቢያቀርቡም ችሎቱ በድጋሚ የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ ማድረጉን የተናገሩት አቶ አዳነ፤ አቶ ልደቱ ዛሬ ችሎት ፊት በቀረቡበት ወቅት ከዚህ ቀደም አምስት ጊዜ መታሰራቸውን በመጥቀስ፣ አምስት ጊዜም በነጻ መሰናበታቸውን፤ አሁንም በነጻ እንደሚወጡ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ብለዋል። ጨምረውም አሁን እየታየ ያለው የፍትህ ሂደት ጥርጣሬ ላይ እንደጣላቸው በማስረዳት "ችሎቱ ለፖሊስ ብቻ እድል እየሰጠ እርሳቸውን ግን እያጉላላቸው እንደሆነ" ጠቅሰው ቅሬታቸውን እንዳቀረቡ አቶ አዳነ ተናግረዋል። ችሎቱም ፍርድ ቤቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ተጽዕኖ ነፃ እንደሆነ በመግለጽ፤ ነገር ግን ከቴሌ መጣ የተባለው ድምጽና የመልዕክት ማስረጃ መተርጎምና መቅረብ ስላለበት ለመጨረሻ ጊዜ በሚል የሰባት ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። አቶ ልደቱ አያሌው ለቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ መርማሪ ፖሊስ ለምርመራ ተጨማሪ ሰባት ቀናት እንደተፈቀደለት አቶ አዳነ ገልፀው ቀጣይ ቀጠሮ ለነሐሴ 25 ተሰጥቷል ብለዋል። አቶ ልደቱ አያሌው የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ አመጽና ተቃውሞ እንዲነሳ ሲቀሰቅሱና ሲያስተባብሩ ነበር በሚል ከአዲስ አበባ በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ለኦሮሚያ ፖሊስ ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ ጉዳያቸው በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
news-45192827
https://www.bbc.com/amharic/news-45192827
ልዩ ፖሊስ ማነው? ዕጣ-ፈንታውስ?
የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በተደጋጋሚ የመብት ጥሰት እንደሚፈጽም ክስ ይቀርብበታል።
ዩኒፎርም የለበሱ የታጠቁ የሚሊሻ አባለት መኪና ላይ ተጭነው። ይህ ፎቶግራፍ የተነሳው እአአ2010 ሲሆን ሆብዮ ተብላ በምትጠራ ቦታ ነው። በቅርቡ አምነስቲ ኢንትርናሽናል የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በኦሮሚያና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈፅሟል በማለት የፌደራል መንግሥት ቡድኑን በአስቸኳይ እንዲበትን ጥያቄ አቅርቧል። አምነስቲ ባወጣው መግለጫ ልዩ ፖሊስ ሰዎችን ከመግደል እሰከ መኖሪያ ቤቶችን ማጋየት የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን ይፈጽማል ብሏል። • መንግሥት ልዩ ፖሊስን እንዲበትን አምነስቲ ጠየቀ በቅርቡም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ሙሉ ሙሉቄ ተብላ በምትጠራው ወረዳ ውስጥ ለ41 ሰዎች መሞት፤ የአካባቢው ባለስልጣናት እና ተጎጂዎች ልዩ ፖሊስን ተጠያቂ ያደርጋሉ። የወረዳዋ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ትዝታ አባይ ለ37 ሰዎች ህይወት መጥፋት እና 44 ሰዎች ላይ ለደረሰው ጉዳት ተጠያቂው ልዩ ኃይል ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጠቃት ጉዳት ከደረሰባቸው አንዱ የሆኑት የወረዳዋ ነዋሪ አቶ መሃመድ ሲራጅ ''በቤት ውስጥ ተቀምጠን ባለንበት ወቅት የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊሶች በር ገንጥለው ገቡብን። ባለቤቴን፣ ልጄን እና የሁለት ዓመት የጎረቤት ልጅ አጠገቤ ገደሉ'' በማለት የተፈፀመውን ጥቃት በሶማሌ ልዩ ፖሊስ መፈጸሙን ለቢቢሲ ተናግረዋል። • በምስራቅ ሐረርጌ 37 ሰዎች ተገደሉ ሌላው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዋች ከሳምንታት በፊት ባወጣው ሪፖርት፤ በሶማሌ ክልል በሚገኘው ኦጋዴን እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ታሳሪዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች እና የልዩ ፖሊስ አባላት ድብደባ እና የመደፈር ጥቃት እንዳደረሱባቸው ገልጿል። ራይትስ ዋች ካነጋገራቸው ሴቶች መካከል በእስር ቤቱ ውስጥ ተደፍረው እዚያው በታሰሩበት ክፍል ውስጥ ያለ ህክምና ዕርዳታ ልጆቻቸውን እንደተገላገሉ ገልጸዋል። • "ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች ልዩ ፖሊስ እንዴት ተመሰረተ? የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስን በተመለከተ እስካሁን የሚታወቅ ምንም አይነት ይፋዊ መረጃ የለም። ስለ ልዩ ፖሊስ አመሰራረት እና አደረጃጀት መረጃ እንዲሰጡን የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ የሃገር መከላከያ ባለስልጣንን እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ተቋምን አነጋግረናል። አቶ ጀማል ድሪ ሃሊስ የክልሉ ተወላጅ ሲሆኑ ገላዴ የምትባል ወረዳን ወክለው ሁለት ጊዜ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው ተመርጠዋል። አቶ ጀማል ''የሶማሌ ክልልን እና ፖለቲካውን ጠንቅቄ አውቃለው። እአአ 2007 ላይ በሶማሌ ክልል የሚሰራውን ግፍ በመቃወሜ ሃገር ጥዬ ለመሰደድ ተገድጃለው'' ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት አቶ ጀማል መኖሪያቸውን ጀርመን ሃገር አድርገዋል። አቶ ጀማል የልዩ ፖሊሰን አመሰራርት ሲያስረዱ ''በአካባቢው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በስፋት ይንቀሳቀስ ነበር። ይህን ኃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሥራዊት ለመደምሰስ ብዙ ጥረት አድርጎ ውጤታማ መሆን አልቻለም'' ይላሉ። አቶ ጀማል እንደሚሉት ከሆነ፤ ኦብነግን ሲወጉ የነበሩት የሃገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የአካባቢውን ቋንቋ እና ባህል ስለማያውቁ የአማፂውን ኃይል ከሲቪሉ ህዝብ እንኳን ለየተው ማወቅ አልተቻላቸውም ነበር። ''እአአ 2007 ላይ ግን የክልሉን ፖለቲካዊ ምህዳር የቀየር ሁኔታ ተከሰተ። ኦብነግ ነዳጅ ፍለጋ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ከ70 በላይ ቻይናውያንና በርካታ ኢትዮጵያዊያንን ገደለ። በዚህም የፌደራሉ መንግሥት ኦብነግ ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ተነሳ'' በማለት አቶ ጀማል ያስታውሳሉ። ለዚህም ሁነኛ አማራጭ የነበረው በሶማሌ ክልል ችግር ሆኖ የቆዩትን ሥራ አጥ ወጣቶችን በማደራጀት ሰልጠና ሰጥቶና አስታጥቆ ኦብነግ ላይ ማዝመት ነበር ይላሉ። የአምንስቲ ኢንተርናሸናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ተክሌ፤ ልዩ ፖሊስ የተቋቋመው እአአ ከ2007-2008 ባሉት ዓመታት እንደሆነ አስታውሰው፤ "በአካባቢው ይንቀሳቀስ የነበረውን መንግሥት በወቅቱ የሽብር ቡድን ብሎ የሚጠራውን ኦብነግን ለመቆጣጠር ነው" በማለት ከአቶ ጀማል ጋር ልዩ ፖሊስ ስለተመሰረተበት ምክንያት ተመሳሳይ ሃሳብ ይሰጣሉ። አቶ ፍሰሃ እንደሚሉት ከሆነ ልዩ ፖሊስ ሲቋቋም በክልሉ መንግሥት እንደሚተዳደር እና ለክልሉ መንግሥት ተጠሪ የሆነ አካል ነው ተብሎ ነበር። ጨምረው በሃገሪቱ ሕገ-መንግሥት መሰረት ድንበር ዘለል ታጣቂ ኃይልን የመከላከል ግዴታ እና ሃላፊነት ያለበት የመከላከያ ሠራዊት ነው። ስለዚህ ልዩ ፖሊስ ሊቋቋም የሚችልበት የህግ አግባብ የለም በማለት ያስረዳሉ። ''የልዩ ፖሊስ አደረጃጀትን ስንመለከት በክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ አይደለም ያለው። ልዩ ፖሊስ የራሱ አዛዥ አለው። ያ አዛዥ ደግሞ ተጠሪነቱ ለቀድሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት ለነበሩት አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር ነው'' ይላሉ አቶ ፍሰሃ። አቶ ጀማልም የልዩ ኃይል አወቃቀር ህጋዊ መሰረት የለውም በማለት በአቶ ፍሰሃ ሃሳብ ይስማማሉ። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ ልዩ ፖሊስ የክልሉ ፖሊስ ውስጥም ይሁን የሚሊሻ መዋቅር ውስጥ የለም። በሃገር መከላከያ የኢንዶክትሬኔሽን እና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ተሰማ ግን የልዩ ፖሊስ አመሰራረት ምንም አይነት የሕግ ከለላ የለውም የሚለውን ሃሳብ አይቀበሉም። ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ''ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ሁሉም ክልሎች ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት አለ። መደበኛ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻዎች አሉ። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልም እንደማንኛውም ክልል የልዩ ኃይል ፖሊሶችን አሰልጥኖ እና አቋቁሞ ካሰማራ በኋላ ከፌደራል ኃይል ጋር የፀጥታ ማስከበር ሥራን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም በአካባቢው የተሻለ መረጋጋት ተፍጥሯል። ከህጋዊ ዕውቅና ውጪ የተቋቋመ አልነበረም'' ይላሉ። የልዩ ፖሊስ አወቃቀር ''አብዲ ሙሃመድ ኡምር የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ሆነው፤ እንዲሁም ፕሬዝዳንት ከሆኑም በኋላ ልዩ ፖሊሰ ተጠሪነቱ ለእሳቸው ነበር'' በማለት አቶ ፍሰሃ ይናገራሉ። አቶ ፍሰሃ እንደሚሉት እአአ መስከረም 2017 ላይ ልዩ ፖሊስ ጥቃት አድርሶ በህይወት የተረፉትን አምነስቲ ባነጋገረበት ወቅት የልዩ ፖሊስ አባላት ከፕሬዝዳንት አብዲ ጋር በቀጥታ በስልክ ሲነጋገሩ መስማታቸውን ነግረውና ይላሉ። አቶ ጀማል በበኩላቸው ''ልዩ ፖሊስ በቀጥታ ትዕዛዝ ይቀበል የነበረው ከቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝደነት አብዲ ሙሃመድ ኡመር ነበር። አብዲ ሙሃመድ ኡመር ደግሞ ከምሥራቅ ዕዝ አዛዦች እና አዲስ አበባ ካሉ ባለስልጣናት ትዕዛዝ ይወስዳሉ'' በማለት የዕዝ ተዋረዱን ያስረዳሉ። አቶ ጀማል ጨምረው እንደሚናገሩት ''የልዩ ፖሊስ አባላት ሲመለመሉ ሆነ ተብሎ የትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ እና ሥራ አጥ የነበሩ ወጣቶች ናቸው። በጦር ስልጠናቸው ወቅትም የሰብዓዊ መብት አያያዞችን በተመለከተ የሚሰጣችው ምንም አይነት ስልጠና የለም'' ይላሉ። የልዩ ፖሊስ የሠራዊት ብዛት እና የታጠቀው መሳሪያ አቶ ፈሰሃ ''በሶማሌ ክልል ውስጥ ምንም አይነት ነግር ግልጽ ስለማይደረግ ትክክለኛ አሃዝ ማስቀመጥ አይቻልም'' ይላሉ። በክልሉ ውስጥ ምን ያህል የክልል ፖሊስ፣ ልዩ ፖሊስ እና ሚሊሻ እንዳለ እና በጀታቸውን ማወቅ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። አቶ ጀማል ደግሞ ''አቶ አብዲ ሙሃመድ በተለያየ ወቅት ሲነገሩ እንደሰማሁት ከሆነ፤ የጦሩ ብዛት ከ30ሺ እሰከ 40ሺ ድረስ ሊሆን ይችላል'' ሲሉ፤ የታጠቁት የጦር መሳሪያ አይነትን በተመለከተ ደግሞ አቶ ጀማል ሲያስረዱ ''ተራ ፖሊስ ከሚይዘው መሳሪያ የተሻለ እና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ናቸው'' ይላሉ። አቶ ፍሰሃም በበኩላቸው ''በምሥራቅ ኦሮሚያ ከልዩ ፖሊስ ጋር ግነኙነት ካደረጉ ግለሰቦች በሰበሰብነው መረጃ መሰረት ልዩ ፖሊስ የታጠቀው መሳሪያ የሃገር መከላከያ ከታጠቀው ጋር የሚመጣጠን መሆኑን ተረድተናል'' ይላሉ። ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ደግሞ በሶማሌ ክልል የፀጥታ ችግር እንደነበርና ይህን ችግር ለመቅረፍ ከፌደራል የፀጥታ ኃይል ጋር በመሆን ልዩ ኃይሉን የማጠናከር እና የማዘጋጀት ሥራ መሰራቱን በዚህም ፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍ እንደተቻለ ይናገራሉ። የልዩ ፖሊስ ዕጣ-ፈንታ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ የቀጥታ ትዕዛዞችን የሚቀበለው ከቀድሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር እንደሆነ ይታመናል። የአቶ አብዲ ከስልጣን መውረድ ጋር ተያይዞ የልዩ ፖሊስ ዕጣ-ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል ስንል አቶ ጀማልን ጠይቀናል። እንደ አቶ ጀማል እምነት ከሆነ የልዩ ፖሊስ አባላት አቶ አብዲ ከስልጣን መውረዳቸው እርግጥ መሆኑን ሲረዱ ትጥቅ ለመፍታት ፍቃደኛ ይሆናሉ ይላሉ። ነገር ግን አባላቱ በሕዝብ ላይ የተለያዩ በደሎችን ሲፈጽሙ የቆዩ ስለሆኑ ወደ ሕዝብ እንዲቀላቀሉ ከመደረጋቸው በፊት የተሃድሶ ስልጠና ያስፈልጋቸዋል ባይ ናቸው። አቶ ፍሰሃ ግን በቅርቡ በምሥራቅ ሃረርጌ ልዩ ፖሊስ ፈጽሞታል የተባለውን ጥቃት በማስታወስ ''ምንም እንኳ ለልዩ ፖሊስ ትዕዛዝ ይሰጡ የነበሩት አቶ አብዲ ከስልጣን ቢወርዱም ልዩ ኃይሉ በድርጊቱ እንደቀጠለ ነው። አምነስቲም ጥፋተኛ የሆኑት ለህግ እንዲቀርቡ ይጠይቃል '' ብለዋል። ሜጀር ጀነራል ሞሃመድ ተሰማ ደግሞ ''የፌደራል የፀጥታ ኃይል የሶማሌን ልዩ ኃይል ትጥቅ የማስፈታት ዓላማ ይዞ አልተንቀሳቀሰም። ልዩ ኃይሉ ቀድሞም እንዲታጠቅ እና እንዲሰለጠን ያደረገው የፌደራሉ መንግሥት ነው። ልዩ ፖሊሱ የፀጥታ ማስፈን ሥራ አካል ሆኖ እንዲሰራ የማድግ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው እንጂ እነሱን ትጥቅ የማስፈታት ዓላማም ሆነ ዕቅድ የለም'' ብለዋል።
news-42477708
https://www.bbc.com/amharic/news-42477708
በ2017 አስገራሚ ተግባር የፈፀሙ !
ታራና በርክ- ' #እኔም ' ከተሰኘው ዘመቻ ጀርባ የነበረች ሴት
ፊታቸውን ላታውቁት ትችሉ ይሆናል፣ ልታውቋቸው ግን ይገባል ሁሉም በ2017 ተፅእኖ ነበራቸው። በ2017 ማንም ሳይጠብቃቸው አጃኢብ ያሰኘንን ተግባር ከፈፀሙ ሰዎች መካከል የተወሰኑትን ልናስተዋውቃችሁ ነው። ምክንያቱም እንድንደመም ያደረጉን ነበሩና! ታራና በርክ በ2017 በበርካቶች ዘንድ ተቀባይነትን ካገኘው ዘመቻ ጀርባ ነበረች። እኤአ ኦክቶበር 15 ተዋናይት አሊሳ ሚላኖ የፊልም ፕሮዲውሰሩን ሀርቪ ዊኒስቴይን በፆታ ጥቃት መጠርጠርን ተከትሎ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶችን ለማበረታታት '#እኔም' የሚል የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻ ጀመረች። ነገር ግን ታራና በርክ ለመጀመሪያ ጊዜ 'እኔም' የሚለውን ቃል ለዘመቻ የመረጠችው ከዓመታት በፊት ሃሽ ታግ በሰዎች ዘንድ የዛሬውን ያህል ሳይታወቅ ነበር። ታራና በ2006 በፆታዊ ጥቃት የተጎዱ እና በድህነት የሚኖሩ ጥቁር እናቶችና ልጃገረዶችን ለማገዝ ነበር እንቅስቃሴውን የጀመረችው። 'መረበሽ እንጀምራለን' እውቅና ወደ ታራና መምጣት ጀመረ። የ '#እኔም' እንቅስቃሴ "ዝምታውን ሰባሪዎች" በታይም መፅሔት የዓመቱ ሰው ተብለው ተመርጠዋል። ''የ 'እኔም' ዘመቻ ተመልሶ መምጣት'' ትላለች ታራና ለቢቢሲ "የኔ ትልቁ ግብ ይህ ቅፅበት ሆኖ ብቻ እንዳያልፍ ነው። ይህ በእርግጠኝነት እንቅስቃሴ ነው።" "ድምፃችንን ማሰማት እንቀጥላለን፤ መረበሻችንን እንቀጥላለን፤ ታሪካችንን መናገር እንቀጥላለን።" ጆናታን ስሚዝ- በላስ ቬጋሱ ጥቃት ወቅት የ30 ሰዎችን ህይወት አትርፎ በመጨረሻም በጥይት ተመታ እኤአ ኦክቶበር 1 በላስ ቬጋስ በሺዎች የሚቆጠሩ የሙዚቃ ድግስ ታዳሚዎች ላይ ሲተኮስ ጆናታን ስሚዝ ሌሎችን ለማትረፍ እየሞከረ እያለ አንገቱ ላይ ተመታ። ከአንድ ወር በኋላም ጥይቱ እዛው አንገቱ ውስጥ ነበር። ጆናታን ጥይት እንደዝናብ በሙዚቃ ድግስ ተሳታፊዎቹ ላይ ሲዘንብ ከመኪና ጀርባ ሆኖ ተገን በመያዝ ሁለት ሴቶችን ለማዳን እየሞከረ ነበር። ነገር ግን በጥይት ከመመታቱ በፊት 30 ሰዎችን ማትረፍ ችሏል። አሜሪካ በዘመኗ ሙሉ አይታ ከምታውቀው በመሳሪያ የታገዘ ጥቃት ይኸኛው ትልቁ ነበር። ስቴፈን ፓዶክ ከማንዳላይ ቤይ ሆቴል 32ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ በመተኮስ የ58 ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ 546 ደግሞ አቁስሏል። በመጨረሻም ራሱ ላይ ተኩሶ ህይወቱን አጥፍቷል። "ጥይቱ መውጣት አለበት" ጆናታን በድጋፍ ማሰባሰቢያ ድረ-ገፁ እንዲህ ብሎ ነበር "በዚህ ቅፅበት ጥይቱ ሊወጣ አይችልም...ጠንካራ ለመሆን እና ወደ ጤንነቴ ለመመለስ እየጣርኩ ነው " ስለዚያን እለት ምሽትም "በዚህ አሳዛኝ ወቅት ውስጥ ሆኜ የተገነዘብኩት ነገር ቢኖር ሁላችንም ሰዎች መሆናችንን ነው፤ አስፈላጊ በሆነ ወቅትም አንዳችን በሌላችን ላይ መደገፍ እንዳለብን ነው።" ሔሊ ዲ አብሩ ሲልቫ ባቲስታ-ተማሪዎቿን ከእሳት አደጋ ለማዳን ብላ ሕይወቷን ያጣችው ብራዚላዊት መምህርት አንድ ሰው ከከተማ ርቃ በምትገኘዋ ጃናኡባ ከተማ ባለ አንድ መዋዕለ ህፃናት ውስጥ ተቀጣጣይ አልኮል እየረጨ እያለ ህንፃውን ከመለኮሱ በፊት መምህርት ሔሊ ዲ አብሩ ሲልቫ ባቲስታ ተጋፈጠችው። እኤአ ኦክቶበር 5 ተማሪዎቿን ከጥቃት ለመከላከል ብላ ግለሰቡን ብትጋፈጠውም ሕይቷን ግን አስከፍሏታል። የ43 ዓመቷ መምህርት ዳሚዮ ሶሬስ ዶስ ሳንቶስን እንዳይገባ ወጥራ ያዘችው። መጨረሻም እሷን ጨምሮ 4 ሕፃናት እና ጥቃቱን ያደረሰው ግለሰብ ሞቱ። "የፅናት ተምሳሌት እና ጀግንነት" እሳቱን የለኮሰው ግለሰብ የትምህርት ቤቱ ጥበቃ ነበር። ከዓመት እረፍቱ ሲመለስ ከጤንነቱ ጋር በተያያዘ ከሥራ ተሰናበተ። ወደ ትምህርት ቤቱ የሄደው የሕክምና ማስረጃውን ሊሰጥ ቢሆንም እሱ ግን እሳቱን ለኩሷል። የብራዚል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሚቼል ቴምር ለሄሊ የሀገሪቱን ከፍተኛ ሥራ ለሰሩ የሚሰጠውን ሜዳሊያ ሸልመዋታል። "የተማሪዎቿን ሕይወት ለማትረፍ ስትል የራሷን ሕይወት አሳልፋ የሰጠች ናት፤ የሁላችንንም ልብ የነካ የፅናት ተምሳሌት እና ጀግንነት" ሲሉ አሞግሰዋታል። ማርከስ ሑችኢንስ- ሳይታሰብ ጀግና የሆነው እና የ 'ዋና ክራይን' የሳይበር ጥቃት ያስቆመው በ150 ሀገራት የሚገኙ 300ሺህ ኮምፒውተሮችን ያዳረሰውን የሳይበር ጥቃት ድንገት የሳይበር ደህንነት ባለሙያው ማርከስ ሐቺንስ አስቁሞታል። ዋናክራይ የተሰኘውና ክፍያ የሚጠይቀው ቫይረስ እንደ ባንክና ሆስፒታል ያሉ የትልልቅ ተቋማት መረጃን በመቀየር በምላሹ በቢትኮይን ክፍያ እንዲያካሂዱ መጠየቅ ላይ አነጣጥሮ ነበር። በእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎቱን ከሥራ ውጭ አድርጎት የህሙማንን ሕይወት አደጋ ላይ ጥሎም ነበር። የ22 ዓመቱ ራሱን በራሱ ያስተማረው ሀከር ማልዌሩን ማለትም የቫይረሱን ማከሚያ ዝግ በሆነ ሥርዓት ውስጥ ከሞከረ በኋላ ያልተያዘ የበይነ-መረብ ዶሜን አግኝቶ አስመዘገበው። "የማሸነፊያው ቁልፍ ተገኘ" ድንገት ቫይረሱ የመግደያ ቁልፉን ሲነካው ሶፍትዌሩ ክፍያ መቀበያውን ከመጫኑ በፊት ማልዌሩን እንዲከታተለው ብቻ ሳይሆን ለማስቆምም አስቻለው። ሎስ አንጀለስ መቀመጫውን ላደረገው ክሪፕቶስ ሎጂክ የሚሰራው እና ማልዌር ቴክ በሚል ስም የሚጦምረው ኤናፋሩ ማርከስ መታወቅ አልፈለገም ነበር፤ ነገር ግን ስሞ ሾልኮ ወጣ። ከዚያ በኋላ ያገኘው የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ከጠበቀው በላይ እንደነበር አልካደም። በአሁን ጊዜ ከሰዎች ኮምፒውተር ላይ ወደ ባንክ ሒሳባቸው የመግቢያ ኮድን የሚለይ ክሮኖስ የተሰኘ ማልዌር ላይ በመሳተፍ ተከሶ በዋስ ተለቆ ይገኛል። በርግጥ መሳተፉን ቢክድም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ግን ሀከሮች በማርከስ ዙሪያ አልጠፋ ብለዋል። የፕሬዝዳንት ትራምፕን ቲውተርን የሰረዘው ግለሰብ-ባህቲያር ዱያስክ ሁሉም ሰው በዚህ አይስማማም ነገር ግን የቀድሞው የቲውተር ሰራተኛ ባህቲያር ዱያስክ በ2017 ያልተጠበቀ ነገር አደረገ። ሥራው ላይ በነበረበት የመጨረሻ እለት የፕሬዝዳንት ትራምፕ ቲውተርን ዘጋው። አንድ የቲውተር ተጠቃሚ ኖቬምበር 3 ለአስራ አንድ ደቂቃ ከቲውተር መጥፋት ወዶት ነበር። ምርመራው ቀጥሏል ሁሉም ሰው ግን ደስተኛ አልነበረም። የቲውተር ኃላፊዎች እንዳሉት "ምርመራችንን እንቀጥላለን፤ እንደዚህ አይነት ነገር በድጋሚ እንዳይከሰትም ለመከላለል እንሰራለን፤ እርምጃም እንወስዳለን ብለዋል።" የ28 ዓመቱ ወጣት 44.6 ሚሊየን ተከታይ ያለውን የትራምፕ ቲውተር አካውንት በስህተት እንደሰረዘው ተናግሯል። "የተወሰኑ መንካት የሌሉብኝን ነገሮች ነካክቼ ነው የተዘጋው"ሲል ገልጧል። ቢሆንም ግን የፕሬዝዳንት ትራምፕ አንዳንድ ቲውቶች የማህበራዊ ግንኙነት የጥላቻ ንግግር ደንብን የተላለፈ ነው ብሏል። ፕሬዝዳንት ትራምፕም በትዊታቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል "በመጨረሻም መልዕክቴ ወጥቶ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ ተስፋ አደርጋለሁ" በማለት። ናናማል አማ የ98 ዓመቷ ዮጋ አሰልጣኝ ሕንዳዊቷ ናናማል አማ ሌሎችን ለማነሳሳት በየትኛውም እድሜ ቢሆን እንደማይረፍድ አረጋግጣለች። በ98 ዓመቷም ዮጋ የምታስተምር ሲሆን የማይገመቱ የአካል እንቅስቃሴዎችንም ታደርጋለች። ከታች ያለው ፎቶ ናናማል በሚያዚያ ወር የተነሳችው ነው። በሕንድ ደቡባዊ ግዛት ታሚል ናዱ የምትኖረው ባልቴት ተማሪዎቿን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቧንም አነሳስታለች። ቤተሰቦቿ፣ ልጆቿና የልጅ ልጆቿን ጨምሮ ባጠቃላይ ዮጋ ይሰራሉ። ሳይመን ስሚዝ -በአውቶብስ ከተገጨ በኃላ ተነስቶ ወደ ግሮሰሪ ለመጠጣት የገባው ሰው ሳይመን ስሚዝ ጁን 24 በሬዲንግ ጎዳና ላይ እየተጓዘ እያለ ነበር አውቶቡስ የእግረኛ መንገድ ላይ ወጥቶ የገጨው እና መሬት ላይ ከመውደቁ በፊት በርካታ ሜትሮች የጎተተው። ቀጥሎ የሆነው ግን የማይታመን ነው። ሳይጎዳ ተነስቶ አቧራውን ካራገፈ በኋላ ቀጥ ብሎ ወደ ግሮሰሪ ሄደ፤ መጠጥ አዘዘ- አጃኢብ ነው እንጂ ምን ይባላል። ሳይመን አነስተኛ ጉዳት ያጋጠመው ሲሆን የአውቶቡሱ ድርጅት ምርመራ አካሂዷል፤ ነገር ግን ማንም የታሰረ የለም። አትላስ- ወደኋላ የሚገለበጠው ሮቦት በዚህ ዘመን ተፅዕኖ ለመፍጠር ሰው መሆን አያስፈልግም። ወደኋላ የሚገለበጠው ሮቦት- አትላስም ይህንን ያስረዳል። በሕዳር ወር በቦስተን ዳይናሚክስ ውስጥ በሰው ቅርፅ የተሰራው ሮቦት ወደጀርባ መገልበጥ ተማረ። ዞሎ ተወዛዋዡ ጎሬላ በ2017 እንዲደንሱ ካነሳሳዎት ነገር መካከል አንዱ ጎሬላው ዞላ ሊሆን ይችላል። የ14 አመቱ ጎሬላ በዳላስ መካነ አራዊት ገንዳ ውስጥ ሲደንስ ተቀርፆ የተለቀቀው ቪዲዮ ልብን የሚያቀልጥ ነበር። ያዩት ሁሉ ይቀባበሉት እና በተለየያ ሙዚቃና በተለያየ ስልት ይጫወቱት ጀመር። በርግጠኝነት ዳንሱን ተክኖበታል።
news-52998505
https://www.bbc.com/amharic/news-52998505
ሚሊዮኖችን የጨፈጨፉ፣ የባርያ ፈንጋዮችና የዘረኞች ሃውልቶች መገርሰስ
የጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በነጭ ፖሊስ እጅ መሞቱን ተከትሎ የተቀጣጠለው ተቃውሞ በምዕራባውያን ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸው አሳሾች፣ ጦረኛ ነገሥታት ሃውልቶችን እንዲገረሰሱ አነሳስቷል።
ንጉስ ሊዮፖልድ ሁለተኛ አስር ሚሊዮን የሚሆኑ ኮንጎዎችን ጨፍጭፏል። ምንም እንኳን እነዚህ ሰዎች ለምዕራባውያኑ ትልቅ ቢሆኑም በአፍሪካውያንም ሆነ በደቡቡ ዓለም ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያና መደፈርን ሌሎች አሳፋሪ ታሪኮችን የፈፀሙ ናቸው። የቤልጅየሙ ንጉሥ ሊዮፖልድ ኮንጎ ላይ አስር ሚሊዮኖችን ጨፍጭፏል፣ እጅ ቆርጧል፣ ሰቅሏል። አሳሹ ክርስቶፎር ኮሎምበስም እንዲሁ ቀደምት አሜሪካውያንን ጨፍጭፏል፤ ከምድረገ ፅም እንዲጠፉ ብዙ ጥሯል። ሌሎችም ስመ ጥር የሆኑ ምዕራባውያን በርካታ ናቸው። አውሮፓና አሜሪካ በባርያ ደም እንዲሁም በቅኝ ግዛት በተዘረፈ ንብረት ከመገንባታቸው አንፃር፤ የሚኩራሩበት "ስልጣኔም" ሆነ በጀግንንት የሚያሞካሿቸው ሰዎች ጭቆናን በተጸየፉ የዓለም ሕዝቦች "ዝርፊያና ጭፍጨፋ ስልጣኔ አይደለም" በሚል ተጋልጠዋል። በአፍሪካ ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋም ሆነ ጭቆና ከታሪክ መዛግብት ለመፋቅና አዲስ ትርክት ለመፍጠር ቢሞከርም አልተቻለም። ባርያዎችን በማጋዝ የሚታወቁ፣ በቅኝ ግዛት ወቅት ጭፍጨፋን የፈጸሙ ምዕራባውያን ሃውልቶች በአሁኑ ወቅት እየተገረሰሱና እየወደሙ ይገኛሉ። ከሰሞኑ ከተገረሰሱትና ጉዳት ከደረሰባቸው ሃውልቶችና ከሃውልቶቹ ጀርባ ያሉትን ሰዎች ታሪክ እንቃኝ፦ በአስራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን የባርያ ነጋዴ የነበረው እንግሊዛዊው ኤድዋርድ ኮልስተን ከ80 ሺህ በላይ አፍሪካውያንን ወደ አሜሪካ አግዟል። ከሰሞኑም ከፍተኛ ግፍ የፈፀመውን የኤድዋርድን ሃውልት ተቃዋሚዎች ከትውልድ ቦታው ብሪስቶል በመገርሰስ ውሃ ውስጥ ከተውታል። እንግሊዝም ሆነ የትውልድ ከተማው ብሪስቶል በባርያ ንግድ ሃብትን አከማችታለች፤ በአፍሪካውያን ጫንቃ፣ ላብና ደም በልጽገዋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የሃውልቱ መገርሰስን ተከትሎ የእንግሊዝ መንግሥት ድርጊቱን ቢያወግዝም ተቃዋሚዎች ግን የለውጥ ምልክት ነው ብለዋል። "የሃውልቶች መቆም የሚያመላክተው ታላላቅ ሥራዎችን ላበረከቱ ነው። ኤድዋርድ ግን የባርያ አጋዥና ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ ለእሱ ምልክት መቆሙ አይገባውም በማለት" የታሪክ አዋቂው ዴቪድ ኦሉሶጋ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሄንሪ ዱንዳስ ባርነት እንዳይቆም የታገለው የሄንሪ ዱንዳ ሃውልት በስኮትላንድ መዲና ኤደንበራ ባርነት እንዲወገድ ጥያቄ ቢቀርብም በእምቢተኝነቱ ፀንቶ ያዘገየው ፖለቲከኛ ሄንሪ ዱንዳስ ሃውልት ቆሞለታል። ከሰሞኑም ሃውልቱን በቀለም በመርጨት ጆርጅ ፍሎይድና ብላክ ላይቭስ ማተርስ የሚሉ ቃላቶችም ተፅፈውበታል። በቅዱስ አንድሪው አደባባይ የሚገኘው ሃውልት 46 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በጎርጎሳውያኑ 1823 ነው የቆመው። በ18ኛው እና በ19ኛው ክፍለ ዘመን ተፅእኖ ፈጣሪ የነበረው ፖለቲከኛ "ያልተቀባው ንጉሥ" የሚል ስያሜም እንዲሰጠው አድርጎታል። የባርያ ንግድን የሚያስቆም ረቂቅ ሕግ በጎርጎሳውያኑ 1792 ቢቀርብም ፖለቲከኛው ለአስራ አምስት ዓመታት አዘግይቶታል ተብሏል። በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ሃውልቱ እንዲገረሰስ ፊርማ አሰባስበዋል። ምንም እንኳን ተቃውሞዎች ቢበረክትም ሃውልቱ ላይ ከተማዋ ከባርያ ንግድ ጋር የነበራትን ግንኙነት የሚያንፀባርቅ መግለጫ እንደሚጨመርና፤ ሃውልቱ እንደሚቆይ ገልፀዋል። "በዓለም ታሪክ ውስጥ ኤደንብራ የነበራትን አስተዋፅኦ መንገር አለብን። የምንኮራበትን ታሪክ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ሁላችንንም የሚያሳፍሩ ታሪኮችም ይፋ ሊወጡ ይገባቸዋል" በማለት የከተማዋ ኃላፊ አዳም ማክቬሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ንጉሥ ሊዮፖልድ ሁለተኛ ንጉስ ሊዮፖልድ ሁለተኛ አስር ሚሊዮን የሚሆኑ ኮንጎዎችን ጨፍጭፏል። ቤልጅየምን ለረዥም ዘመናት የገዛው የንጉሥ ሊዮፖልድ ሁለተኛ ሃውልት እንዲገረሰስ ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው። በተለያዩ ድረ ገፆች ላይ የይገርሰስ ፊርማዎች የተሰባሰቡ ሲሆን እስካሁንም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፈርመዋል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች ደግሞ ጥያቄ ከመጠየቅ አልፈው ሃውልቱን በቀይ ቀለም የረጩት ሲሆን እንዲሁም የሃውልቱን ጭንቅላት በጨርቅ ሸፍነውታል። ጨርቁም ላይ በነጭ ፖሊስ በግፍ የተገደለውን የጆርጅ ፍሎይድ ቃላትን "መተንፈስ አልቻልኩም" ተፅፎበታል። በአንትወርፕ ከተማ የሚገኘው የቅኝ ገዥው ንጉሥ ሌላኛው ሃውልትም ተቃዋሚዎች በእሳት ያነደዱት ሲሆን ባለስልጣናቱም እንዲነሳ አድርገው ወደ ሙዚየም አስገብተውታል። በመዲናዋ ብራስልስ የሚገኘው ሃውልት ደግሞ "ነፍሰ ገዳይ" ተብሎ ተፅፎበታል። በጎርጎሳውያኑ 1865- 1909 ቤልጅየምን የገዛው ጨካኙ ንጉሥ በኮንጎ በፈፀመው ግድያና ጭፍጨፋ ይታወሳል። ኮንጎን እንደ ግል ግዛቱ በመውሰድም ዜጎቿን ጎማ እንዲያመርቱ የባርያ ማዕከላትን መስርቷል። ባርነትን እምቢ ያሉት ደግሞ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል፤ የተገደሉትንም ሰዎች እጅ እየተቆረጠም መዘባበቻ አድርጓል። በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ የኮንጎ ዜጎችን ጨፍጭፏል። ግፉ ተቆጥሮ የማያልቀው ንጉሥ የኮንጎ ዜጎችን ወደ ቤልጅየም በመውሰድ እንደ እንስሳ ፓርክ ውስጥ በማስገባት እንዲጎበኙ አድርጓቸዋል። ምንም እንኳን የኮንጎ የንጉሡ ቅኝ ተገዢነት በጎርጎሳውያኑ 1908 ቢያበቃም አገሪቱ ከቤልጅየም ነፃ የወጣችው በጎርጎሳውያኑ 1960 ነው። በቤልጅየም ሃውልቱ እንዳይወገድ የሚቃወሙ አንዳንዶች እንደ ምክንያትነት የሚጠቅሱትም ቤልጅየም የበለፀገችው በንጉሡ ወቅት መሆኑን በመጥቀስ ነው፤ በደም የበለፀገች መሬት። ሮበርት ኢ ሊ የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት ዘረኛ የሚባለውንና ባርነትን ይደግፍ የነበረው የኮንፌደሬት የጦር ጄኔራል ሮበርት ኢ ሊን ሃውልት ለማስወገድ ወስናለች። የጆርጅ ፍሎይድ ግድያን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ሃውልቱ ላይ ጉዳት ደርሶበታል። በጎርጎሳውያኑ 1890 የቆመው ሃውልት አስራ ሁለት ቶን (አስራ ሁለት ሺህ ኪሎ ግራም) የሚመዝን ሲሆን የቨርጂኒያ አስተዳዳሪ ራልፍ ኖርታም "ሐሰተኛ የታሪክ ትርክት ይበቃናል" ብለዋል። አክለውም "ይህ ሃውልት ለረዥም ዘመናት ቆይቷል። የዚያን ጊዜም መተከሉ ስህተት ነበር፤ አሁንም ስህተት ነው። ስለዚህ እንገረስሰዋለን" ብለዋል። በአካባቢውም አምስት የኮንፌደሬት ሃውልቶች የሚገኙ ሲሆን ከሰሞኑ በተከሰተው ተቃውሞ የተለያዩ ቀለሞች ተረጭቶባቸዋል፤ የነጭ የበላይነት ይቁም የሚሉም መልዕክቶች ተፅፎባቸዋል። ሮበርት ኢ ሊ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ባርነት አይቁም በሚል ሲዋጋ የነበረው የደቡባዊው ግዛቶች ጥምረት የሆነው የኮንፌደሬት የጦር አበጋዝ ነበር። የጦር አበጋዙ በቨርጂኒያ ውስጥ የሚታወቁ በባርያ አሳዳሪነት የበለፀጉ ቤተሰቦች ልጅ ሲሆን ያገባው፤ ከጦሩ ከወጣም በኋላ የባርያ አሳዳሪ ነበር። ለነፃነት የሚታገሉ ባርያዎችን በመደብደብም ይታወቃል። የባርያ ቤተሰቦችን በመነጣጠልም ብዙ ግፍ ፈፅሟል። ለበርካታ ጥቁሮች የጦር አበጋዙ የአገሪቱ የባርነት ታሪክና የዘረኝነት ጭቆና ተምሳሌት ነው። ሌሎች እንዲሁ የኮንፌደሬት ሃውልቶች በተቃዋሚዎች ዘንድ ከጥቅም ውጪ ሆነዋል። አንዳንዶች የአሜሪካ ታሪክና የደቡብ ባህል አካል በመሆናቸው ሃውልቶቹ ሊፈርሱ ይገባሉ በማለት የሚከራከሩም አልታጡም። ዊንስተን ቸርችል "በቀደምት አሜሪካውያን ጭፍጨፋም ሆነ አውስትራሊያ በሚገኙ ጥቁር ህዝቦች መገደል መጥፎ ነገር ተፈፅሞባቸዋል ብዬ አላምንም" ያሉት የዊንሰተን ቸርችል ሃውልት በእንግሊዝ መዲና የሚገኘው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ቸርችል ሃውልት በተቃዋሚዎች ዘንድ ዘረኛ የሚል ፅሁፍ ከሰሞኑ ተፅፎበታል። በእንግሊዛውያን ዘንድ አገሪቱን ለሁለተኛ ዓለም ጦርነት ድል ያበቃ መሪ እንዲሁም ድንቅ መሪ፣ ፀሐፊና ተናጋሪ ቢሉትም ከነጭ ዘር ውጪ በነበረው ንቀት አወዛጋቢም ሆኗል። "ያለምንም ጥርጥር ዊንስተን ቸርችል ዘረኛ ነበር። ነጮች የበላይ ናቸው ብሎ ማመን ብቻ ሳይሆን በግልፅም በተደጋጋሚ ተናግሮታል" በማለት 'ቸርችል ሚይዝስ' የተሰኘ መፅሐፍ እየፃፉ ያሉት የታሪክ አዋቂው ሪቻርድ ቶዬ ተናግረዋል። "ስለ ህንዳውያን የሚያፀይፍ ነገር ተናግሯል። ህንዶች አራዊት ናቸው፤ የእንስሳ እምነት ነው ያላቸው ብሏል፤ ስለ ቻይናውያንም እንዲሁ። ስለ ሌሎችም የተናገረው ማለቂያ የለውም" ብለዋል። በጎርጎሳውያኑ 2015 'ቸርችል፡ ዘ ኤንድ አፍ ግሎሪ' ደራሲ ጆን ቻርምሌይ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ዊንስተን ቸርችል በዘር የደረጃ እርከን ያምን እንደነበር ተናግረዋል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የዘር አከፋፈል መሰረት ከላይ የሚቀመጡት ነጭ ፕሮቴስታንቶች፣ በመቀጠል ነጭ ካቶሊኮች ከዚያም ከአፍሪካውያን በልጠው ህንዳውያን ናቸው። አፍሪካውያን የመጨረሻውን ቦታ ሲይዙም ከሰውም ያነሱ ናቸው ብሎ ያምን ነበር። በጎርጎሳውያኑ 1937 ዊንስተን ቸርችል ለፍልስጥኤም ሮያል ኮሚሽን እንደተናገረው "በቀደምት አሜሪካውያን ጭፍጨፋም ሆነ አውስትራሊያ በሚገኙ ጥቁር ሕዝቦች መገደል መጥፎ ነገር ተፈፅሞባቸዋል ብዬ አላምንም። በጠንካራ፣ በላቀና በጠራ ዘር ተሸንፈዋል። ቦታቸውንም ተቀምተዋል" ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በአይሁዶችና በእስልምና ተከታዮችም ላይ በሰጣቸው አስተያቶችም ይወገዛል። በጎርጎሳውያኑ 1943 ሁለት ሚሊዮን ሰዎችን በገደለው የቤንጋል ረሃብ በሰጠው ሰቅጣጭ አስተያየትም ታሪክ በአሉታዊ ገጹ ያስታውሰዋል።
news-42646752
https://www.bbc.com/amharic/news-42646752
ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻን ማገድ አዋጭ ነው?
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀናት በፊት የውጭ ጉዲፈቻን የሚያግድ አዋጅ አፅድቋል። የአዋጁን መፅደቅ ተከትሎ ቀጣዩ እርምጃ ምን ይሆናል? እገዳውስ የሚያዋጣ አካሄድ ነው ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።
ከዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በጉዲፈቻ ወደ ተለያዩ አገራት የሚሄዱ ህፃናት ለማንነት ቀውስና ለተለያዩ ጉዳቶች እየተጋለጡ በመሆናቸው እንደሆነ መንግሥት ገልጿል። ችግሩ በጉዲፈቻ ወደ ውጭ አገራት ከሄዱ በኋላ የህፃናቱ ለማንነት ቀውስ መጋለጥ ብቻም ሳይሆን የሚሄዱበት መንገድም በብዙ ችግሮች የተሞላ መሆኑ ነው። የውጭ አገር ጉዲፈቻ ለብዙ ተቋማትና ግለሰቦች ትልቅ የገቢ ምንጭ ሆኖ ነበር። ልጆች የተሻለ ህይወት ይኖራቸዋል በሚል የሀሰት ተስፋ ወላጆችን አታሎ ህፃናትን በጉዲፈቻ መላክን ሥራቸው ያደረጉ ደላሎችና ኤጀንሲዎችም በርካታ ነበሩ። ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ለመላክ የተሰለፉ ወላጆችም ነበሩ። በዚህ መልኩ ከኢትዮጵያ ይወሰዱ የነበሩ ህፃናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ ነበር። በአንድ ወቅት በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጉዲፈቻ ከሚሄዱ ህፃናት አንድ አራተኛ የሚሆኑት ከኢትዮጵያ የሚወሰዱ እንደነበሩ መረጃዎች ያሳያሉ። ብዙዎች ለትርፍ ተሰማርተውበት የነበረው ይህ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻ የተለያዩ የውጪ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረትም ስቦ ነበር። ህገ-ወጥና ህጋዊ አሰራሮች ተደበላልቀው ህፃናት በገፍ ወደ ውጭ ሃገር የመላካቸው ነገር 'የኢትዮጵያ አዲሱ የወጪ ንግድ ዘርፍ' እስከመባል ደርሶ እንደነበርም ይታወሳል። ከዓመታት በፊትም መንግሥት የውጭ አገር ጉዲፈቻን 90 በመቶ እንደሚቀንስ አስታውቆ ነበር። በአሜሪካ አሳዳጊዎች ተወስዳ በረሃብና በስቃይ የሞተችው የ13 ዓመቷ ሃና አለሙ ታሪክ ደግሞ የውጭ ጉዲፈቻ በምን ያህል ደረጃ ህፃናትን ለስቃይ እየዳረገ እንደሆነ ማሳያ ሆነ። ይህን ተከትሎም መንግሥት በርካታ የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎችን ዘጋ። ከዓመታት በኋላም አሁን የፀደቀው የክልከላ አዋጅ ረቂቅም መጣ። ቢሆንም ግን በጉዲፈቻ ወደ ውጭ የሚሄዱ ህፃናት ሁሉ ለችግር ይጋለጣሉ ማለት አይቻልም። ይልቁንም የተሻለ ህይወትና እድል የሚያጋጥማቸው በርካቶች ናቸው። የአገር ውስጥ ጉዲፈቻ ሦስት ልጆች ወልደዋል። ነገር ግን ከአስራ ሦስት አመታት በፊት መንገድ ላይ ያገኟትን የአራት ቀን ህፃን አራተኛ ልጃቸው አድርገው እያሳደጉ ነው። ይህች ልጃቸው ስለማንነቷ የምታውቀው ነገር ስለሌለ ስማቸው እንዲጠቀስ አልፈለጉም። በወቅቱ የህፃኗ እናት በተወሰነ መልኩ አዕምሮዋ ትክክል ስላልነበር ህፃኗን ትቶ ማለፍ አልቻሉም። "ህፃኗን በዚያ ሁኔት ብንተዋት በጥቂት ቀን ውስጥ ትሞት ነበር" ይላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የትም ቦታ ቢኬድ ችግረኛ ህፃናት አሉ። ጥሩ ኑሮ ያላቸው በርካታ ሰዎች ግን ምናልባትም እነዚህን ህፃናት አንድ ጊዜ መርዳት እንጂ ወስደው እንደማያሳድጉ ይናገራሉ። ይህ የእሳቸው አስተያየት ብቻም ሳይሆን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። "ምንም እንኳን ጉዲፈቻ ከጥንት ባህላችን ነው ቢባልም፤ ሁሉ የሞላላቸው እንኳ ልጅ ሲያሳድጉ አይታይም" በማለት ያስረግጣሉ።በጉዲፈቻ ልጅ የሚያሳድግ የሚያውቁት አንድ ሰው ብቻ እንደሆነም ይናገራሉ። መንገድ ላይ ያገኟትን ህፃን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ያለፉበት የህግ ሂደት ቀና የነበረ ቢሆንም መንግሥት የአገር ውጥ ጉዲፈቻን በሚገባ አስተዋውቆታል ብለው ግን አያምኑም። "በስፋት ካልተዋወቀ የአገር ውስጥ ጉዲፈቻ አለ ቢባል ምን ይጠቅማለ? ማነው ስለዚህ የሚያውቀው?" ሲሉም ይጠይቃሉ።መንግሥት ከዓመታት በፊት ጀምሮ መስፋፋት ያለበት የአገር ውጥ ጉዲፈቻ ነው፤ በዚህ ረገድም የግንዛቤ መፍጠር ስራ እየሰራሁ ነው ቢልም ዛሬም እንደ እሳቸው ተመሳሳይ ጥያቄ የሚያነሱ ብዙዎች ናቸው። ብዙዎቹ የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች በመዘጋታቸው ደስተኛ ቢሆኑም፤ መንግሥት ሙሉ ለሙሉ የውጪ ጉዲፈቻን እንዲቀር ማድረጉ ላይ ግን አይስማሙም። ጊዜው አሁን ነው? ችግር ላይ ያሉ ህፃናትን ለመርዳት የውጭ አገር ጉዲፈቻ የመጨረሻው የማራጭ እንደሆነ መንግሥት ሁሌም ቢናገርም በውጭ ጉዲፈቻ የሄዱ ህፃናት ቁጥር ደግሞ የሚናገረው ተቃራኒውን ነው። በህፃናትና ሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የህግ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ ተክይበሉ የአገሪቱን የህፃናት ፖሊሲ በመጥቀስ፤ ቀጣዩ የአገር ውስጥ ጉዲፈቻ እረምጃ የሚያተኩረው የማህበረሰብ ድጋፍ፣ የአገር ውስጥ ጊዲፈቻና የአደራ ቤተሰብ ላይ መሆኑን ይናገራሉ። ከተቻለ ልጆች በቅርብ ዘመዶቻቸው ባሉበትና በሚያውቁት ማህበረሰብ እንዲያድጉ ይደረጋል። ይህ ካልሆነ በአገር ውስጥ ጉዲፈቻ እንዲያድጉ ይመቻቻል። በአገር ውስጥ ተቋም (በህፃናት ማሳደጊያ) እንዲያድጉ ማድረግ ደግሞ የመጨረሻው አማራጭ ነው። ቀደም ሲል በህጋዊና ህጋዊ ባልሆነ መንገድም ወደ ውጭ ይሄዱ የነበሩ ህፃናት ቁጥር ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም በተለይም ከ2007 ዓ.ም ወዲህ በዓመት ከአራት መቶ የሚበልጥ እንዳልሆነ አቶ ደረጀ ገልፀዋል። በሌላ በኩል ክልሎች ቁጥሩን በመቀነስ ቀድመው የውጭ ጉዲፈቻን ማቆማቸውንም ይናገራሉ። "ከህብረተሰቡ ግንዛቤ፣ ልጆች ለመውሰድ ከሚመዘገቡ ወላጆች ቁጥር አንፃርም የውጭ ጉዲፈቻን አቁሞ በዚያ ሲሄዱ የነበሩ ሦስትና አራት መቶ ልጆችን አገር ውስጥ ማስቀረት ቀላል ነው" ይላሉ አቶ ደረጀ። ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር ችግሩን በአገር ውስጥ አማራጭ ብቻ መፍታት አይቻልም የሚል አስተያየት ያላቸውም አሉ። ከዚህ ባለፈም ውሳኔው የህፃናትን በተሻለ ሁኔታ የማደግ መብትን የሚጋፋ ነው የሚል ሃሳብ ያላቸው አልታጡም።አቶ ደረጀ ደግሞ የአገሪቱ ህግ (የቤተሰብ ህግ) ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻን የመጨረሻ አማራጭ አድርጎ ስለሚመለከት ውሳኔው ትክክል መሆኑን አስረግጠው ይናገራሉ። "ህጉ ታሳቢ የሚያደርገው የህፃናት ጥቅምና ደህንነት ማስቀደምን ነው። ህፃናት ደግሞ በአገራቸው፣ በባህላቻውና በሚያውቁት ማህበረሰብ ውስጥ ማደጋቸው ነው ጠቃሚ ተደርጎ የሚታሰበው።" ህፃናትን በአገር ውስጥ ለማሳደግ የተመዘገቡ ወላጆች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በአገር ውስጥ ጉዲፈቻ መተማመን እንደሚቻልም አቶ ደረጀ ያስረግጣሉ። አቶ ደረጀ እንደሚያስታውሱት በ2001 እና 2002 ዓ.ም ላይ በዓመት አምስት ሺህ የሚሆኑ ህፃናት ወደ ውጪ ይሄዱ ነበር። ባለፉት ሦስት ዓመታት ደግሞ ቁጥሩ ወደ ሦስትና አራት መቶ ወርዷል። በአንፃሩ የአገር ውስጥ ጉዲፈቻስ ባለፉት ዓመታት እየጨመረ ነው? የሚል ጥያቄ ለአቶ ደረጀ ቀርቦላቸው የነበር ቢሆንም መረጃው ከክልሎች ያልተሰበሰበ በመሆኑ ለጥያቄው መልስ ማግኘት አልተቻለም። መዝጋት ወይስ ቁጥጥር ማድረግ? በአገሪቱ ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር ችግሩን በአገር ውስጥ አማራጮች ብቻ መፍታት አዋጭ እንዳልሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሶሻልወርክ ትምህርት ክፍል ሃላፊ ዶ/ር አሸናፊ ሃጎስ ይናገራሉ። ይልቁንም ለእርሳቸው እርምጃው መንግሥት በአቅም ውስንነት ወይም ባለመቻል ከቁጥጥሩ ውጭ የሆነበትን የውጭ ጉዲፈቻ ለማቆም የወሰደው ነው። ስለዚህም የህፃናት ደህንነትና ጥቅምን የሚያረጋግጥ ቁጥጥር ማድረግ ወይስ ሙሉ በሙሉ መዝጋት ያስኬዳል? ሲሉ ይጠይቃሉ። "ለችግሩ መፍትሄ መሆን ያለበት የውጪ ጉዲፈቻን መዝጋት ነው የሚለው አያስማማኝም። ተገቢ ቁጥጥር ማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂ መንደፍ ነው ትክክለኛው ነገር።" በአገሪቱ ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ቁጥር ከፍተኛ ሲሆን በተቃራኒው በአገር ውስጥ ልጆችን ወስዶ የማሳደግ ልምድ እምብዛም እንደሆነ የሚያመለክቱ ጥናቶች መኖራቸውን ዶ/ር አሸናፊ ይናገራሉ። ከዘህ በመነሳት ይህን ከፍተኛ ቁጥር በአገር ውስጥ ጉዲፈቻ ለመሸፈን ማሰብ "ደፍሬ ልበለው በህፃናት ላይ መፍረድ ነው" ይላሉ።
news-45869458
https://www.bbc.com/amharic/news-45869458
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ካማሽ ዞን የመሰረታዊ ፍጆታ እጥረት አጋጠመ
በቅርቡ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አራት የካማሽ ዞን አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ለሰው ህይወት መጥፋት፣ ለአካልና ንብረት ጉዳት እንዲሁም ለበርካቶች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። ይህንንም ተከትሎ በዞኑ የምግብ ግብዓቶች እጥረት ማጋጠሙን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
• በካማሼ ዞን ግጭት እጃቸው አለበት የተባሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ • በፖሊሶች መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ ሕይወት ጠፋ • አፍሪካዊያን ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትን መጎብኘት ለምን ይከብዳቸዋል? ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የካማሽ ከተማ ነዋሪ ምግብና ሸቀጦች ወደ ከተማዋ መግባት ባለመቻላቸው ሱቆች ሁሉ ባዶ ናቸው ይላል። "ከተማው ውስጥ ለመንቀሳቀስ ይቻላል፤ ምንም ችግር የለም፤ ነገር ግን በከተማዋ ውስጥ የሚበላ ነገር የለም። ችግሩ የጀመረው ከደመራ በዓል አንስቶ ቢሆንም ሁኔታዎች ተባብሰው ምንም ዓይነት ነገር ካጣን ዘጠነኛ ቀናችን ነው" ሲል ችግር ላይ እንደወደቁ ተናግሯል። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባየታ ችግሩ ከመስከረም 16 አንስቶ የነበረ ሲሆን በተለይ ከነጆ ካማሽ እና ከጊምቢ ካማሽ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል ይላሉ። ከዚህ ቀደም በአካባቢው የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች የሚደርስን ጥቃት፣ ብሔር ላይ መሰረት ያደረገ ጥቃትን መፍራት፤ አሽከርካሪዎችም ንብረቶቻቸውን ወደ አካባቢው ለመላክ መስጋታቸው ምክንያት ነው ብለዋል። በተለይ ከነጆ ካማሽ መንገዶችም በመቆፈራቸውና በመዘጋታቸው ለመንቀሳቀስ አዳጋች ሆኗል ይላሉ። በካማሽ ዞን የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ለምግብ አቅረቦት እጦት እንደታገለጡ የሚናገሩት ሃላፊው ካማሽ ከተማን ጨምሮ በዞኑ ያሉ ወረዳዎች የዕለት የምግብ ፍጆታ የሚሆኑ ጥሬ እቃዎች እጥረት እንዳጋጠማቸው አስረድተዋል። በዚህም ሳቢያ የክልሉ መንግስት በየአካባቢዎቹ ተገኝቶ ህብረተሰቡን ለማረጋጋት በሄሊኮፍተር ለመንቀሳቀስ እንደተገደደ የገለፁት ኃላፊው አሁንም ከአጎራባች ነጋዴዎች ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ተናግረዋል። አክለውም ከዞኑ በመሸሽ በአዋሳኝ የኦሮሚያ ከተሞች የተጠለሉ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የመመለስ ፍላጎት ቢያሳዩም አብዛኞቹ የመጓጓዣ አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም ይላሉ አቶ አበራ ባየታ። በመሆኑም የክልሉ መንግስት ተፈናቃዮቹን ወደ ቀደመው መኖሪያቸው ለመመለስ የትራንፖርት አገልግሎት ለማመቻቸት መወሰኑንም ጨምረው ተናግረዋል። በግጭቱ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው የሚታወስ ነው።
news-52895720
https://www.bbc.com/amharic/news-52895720
ቢል ጌትስ በክትባት ስም ክንዳችን ውስጥ ሊቀብሩት ያሰቡት ነገር አለ?
ማኅበራዊ ድር አምባው በሴራ ንድፈ ሐሳብ አብዷል። ይህ የሴራ ትብታቦ (Conspiracy theory) በተለይ ከኮቪድ-19 ክትባት ጋር በተያያዘ ከሯል።
የሴራ ንድፎች እንዲሁ ቸል የሚባሉ ጉዳዮች አይደሉም። የሴራ ፈታዮችም ሥራ ፈቶች ሊባሉ አይችሉም። ምክንያቱ ደግሞ ብዛታቸው ነው። ልብ ማለት የሚገባን ስለ ሴራ ትንተና ስናስብ ስለ ብዙሃኑ ሕዝብ አስተሳሰብ እያወራን እንደሆነ ነው። ሴራ ፈታዮች እጅግ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ከመሆናቸው የተነሳ መልዕክታቸው በአጭር ሰዓት ውስጥ ክፍለ ዓለምን ሊያጥለቀልቅ ይችላል። ለምሳሌ ዩጎቭ የተባለ የጥናት ቡድን በአሜሪካ በ1ሺህ 640 ሰዎች ላይ በሠራው ቅኝት 28 ከመቶ አሜሪካዊያን ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ በክትባት ስም ክንዳችን ላይ አንዳች ረቂቅ ዲጂታል ሜሞሪ (microchip) ሊጨምርብን ይፈልጋል ብለው ያምናሉ። ይህ አሐዝ ከሪፐብሊካን ደጋፊዎች ዘንድ ሲደርስ 44 ከመቶ ይደርሳል። ለመሆኑ ቢል ጌትስ ምን ፈልጎ ነው ሚሞሪ ዲስክ ክንዳችን ላይ የሚቀብረው? ይህን ለመመለስ ኮቪድ-19 ቫይረስ እንዴት ሊፈጠር ቻለ? የሚለውን በሴራ ነዳፊዎች መነጽር ማየት ይኖርብናል። በሴራ ነዳፊዎች እስሳቤ ቫይረሱን የፈጠረው የማይክሮሶፍት ፈጣሪ ቢል ጌትስ ነው። የዚህ አንድ ማረጋገጫ አድርገው የሚወስዱት ደግሞ ቢልጌትስ ከዚህ ቀደምም ይህ ቫይረስ ሊከሰት እንደሚችል ያውቅ የነበረ መሆኑን ነው። ቢሊየነሩ ቢልጌትስ ዓላማው የዓለምን ሕዝብ ሁለመናውን መቆጣጠር ስለሆነ መጀመርያ ቫይረስን ፈጠረ፣ ቀጥሎ ደግሞ ክትባቱን ይፈጥራል ይላሉ። ክትባቱ ውስጥ ደግሞ በዓይን የማይታይ ረቂቅ ዲጂታል ሚሞሪ (microchip) ይቀብርብናል በማለት ያስባሉ። ቢቢሲ ይህ ነገር እውነት ነው ወይ? ሲል የቢልጌትስ ፋውንዴሽንን ጠይቆ "ቅጥፈት ነው" የሚል ምላሽ አግኝቷል። ይህ የሴራ ትንታኔ በአሜሪካ ውስጥ ብቻ የሚያጠነጥን አይደለም። የሩሲያ ኮሚኒስትር ፓርቲ መሪ "እነዚህ በሉላዊነት የሰከሩ ሰዎች በክትባት ስም በድብቅ ክንዳችን ውስጥ መቆጣጠርያ ሊከቱብን ይፈልጋሉ" ሲሉ ተሰምተዋል። የቀድሞው የዶናልድ ትራምፕ አማካሪ ሮጀር ስቶን ከሰሞኑ በሰጡት አንድ አስተያየት ደግሞ "አንዳንድ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ መመርመር አለመመርመራችንን ለማጣራት እንዲረዳ አንዳች ነገር እጃችን ውስጥ ይቀበር እያሉ ነው" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። ይሁንና ሚስተር ሮጀር አስተያየታቸው ላይ የቢል ጌትስን በስም አልጠቀሱም። ይህ በቢልጌትስ ዙርያ የተተበተበው ሴራ እየተጠናከረ የመጣው ባለፈው መጋቢት ራሳቸው ቢል ጌትስ የሰጡትን አንድ አስተያየት ተከትሎ ነው። ". . . ወደፊት አንዳች የሆነ ዲጂታል ሰርተፍኬት ሊኖረን ይችል ይሆናል፤ ይህም ቫይረሱ ያለብን እና ነጻ የሆነው ለመለየት የሚያስችለን ነው የሚሆነው. . . ።" ብለው ነበር፤ በንግግራቸው መሀል። "ዲጂታል ሰርተፊኬቱ ማን እንደተመረመረ፣ ማን ቫይረሱ እንዳለበት፣ ማን ክትባት እንደወሰደ አጥርቶ ይነግረናል"› ሲሉም አብራርተዋል። ይህን ተከትሎ ወዲያውኑ አንድ ጽሑፍ ታተመ። የጽሑፉ ርዕስ "ቢል ጌትስ ቫይረሱን ለመዋጋት ረቂቅ ድጂታል ሜሞሪ ክንድ ላይ መቅበር ያስፈልጋል አሉ" የሚል ነበር። ይህ ጽሑፍ ደግሞ ለዘገባው መነሻውን ያደረገው በጌትስ ፋውንዴሽን ትብብር የተሰራ አንድ ጥናትን ነበር። ጥናቱ የሚያወራው ሰዎች ክትባት ስለመውሰዳቸው የሚያሳውቅ የመረጃ ቋት ስለማዘጋጀት ነው። ክትባት ሲወስዱ የመርፌው ጫፍ ቀለም ስለሚኖረው ያን ጊዜ የወሰደውና ያልወሰደውን መለየት ከባድ አይሆንም ብሎ ያምናል። ኾኖም በዚህ ጥናት የተጠቀሰው ቴክኖሎጂ ክንድ ውስጥ የሚቀበር ረቂቅ ሜሞሪ ዲስክ አይደለም። ከዚያ ይልቅ ይህ በየመሸታ ቤቱ ወይ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ሲዘጋጁ የከፈለና ያልከፈለ፤ ትኬት የያዘና ያልያዘን ለመለየት በር ላይ በታዳሚዎች አይበሉባ ላይ የሚታተመው ዲጂታል ቀለም ዓይነት ነው። ወይም ይበልጥ ለመረዳት ንቅሳት ልንለው እንችላለን። ወ/ት አና ጃክሌኒክ የተባለች የዚሁ ጥናት ባልደረባ እንደምትለው ይህ የንቃሳት ሐሳቡ ራሱ ገና ሐሳብ ነው፤ ተግባራዊ እንኳን አልተደረገም። በጭራሽ ሰዎችን ለመከታተልም የሚተገበር ጥናት አይደለም። በርካታ የሴራ ትንተናዎች በአሁኑ ጊዜ ቢል ጌትስ ላይ ያተኮሩ ናቸው ቢል ጌትስ ሊቆጣጠረን ነው የሚሞክረው? የማይክሮሶፍቱ ፈጣሪ፣ በጎ አድራጊና ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ ለሴራ ፈታዮች የተመቹ ሰው ሆነዋል። በእንግሊዝ አንድ ብዙ ተከታዮች ያሉት የትዊተር ሰሌዳ "ቢል ጌትስ በቫይረሱ በአሜሪካ 700 ሺህ ሰዎች እንደሚሞቱ አረጋገጡ" ብሎ ጻፈ። ይህን ካለ በኋላ ጽሑፉን አሌክስ ጆንስ ከተባለ አንድ ቀኝ አክራሪ የሴራ ፖለቲካ አራማጅ ገጽ ላይ ከነበረ ቪዲዮ ጋር አሰናሰለው። ይህ የትዊተር መልዕክት 45 ሺህ ሰዎች ተጋርተውታል። ሰዎች ያልተረዱት ነገር ግን ቢል ጌትስ ያንን አለማለታቸውን ነው። በቪዲዮው ላይ ቢል ጌትስ እያወሩ የነበረው በሕክምናው ዓለም ክትባት ጊዜና ሰፊ ጥናት የሚፈልግ እንደመሆኑ፤ ይህ ሳይደረግ ቢቀር የጎንዮሽ ጉዳቱ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ለማሳየት የተናገሩት ነበር። በተለይም በሽማግሌዎች ዘንድ። ይህንንም ለማስረዳት መላምታዊ ቁጥር አስቀመጡ። "ለምሳሌ እንበልና ከ10 ሺህ ሰዎች በአንዱ አዛውንት ላይ እንኳ ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት ቢያመጣ በአሜሪካ 700 ሺህ ሰዎች ሞቱ ማለት ነው" የሚል። ይሁን እንጂ የሴራ ተንታኞች እንደሚሉት ቢል ጌትስ በዚያ ንግግራቸው በአሜሪካ 700 ሺህ ሰዎች ያልቃሉ አላሉም። ያንን ለማስፈጸምም እየሠሩ አይደለም። ይህንን የሚያረጋግጥ መረጃም የለም። የሚደንቀው ይህ የሴራ ትንተና አራማጆች ቢል ጌትስን በተመለከተ እየፈጠሩ ያሉት ተጽእኖ ከጣሊያን የተወካዮች ምክር ቤት ሸንጎ ድረስ ሰተት ብሎ መግባቱ ነው። ዴንትሮ ላ ኖቲዚያ የተባሉ አንድ የጣሊያን ፓርላማ አባል "ቢል ጌትስን ወስደን በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለምን አንገትረውም" ሲሉ ጠይቀዋል። ከቢል ጌትስ ሌላ ያሉ የክትባት መላምቶች በጣሊያን ጸረ-ክትባት እንቅስቃሴው ተጧጡፏል። አንድ ሚሊዮን ሰዎች ተመለከቱት የተባለ አንድ ተንቀሳቃሽ ምሥል በጣሊያን ዝነኛ ሆኗል። የቪዲዮው ጭብጥ ቫይረሱ ሆን ተብሎ መፈጠሩን የሚያወሳ ነው። የዚህ ቪዲዮ ተራኪ ስቴፋኖ ሞንታናሪ ይባላል። ጣሊያናዊ ተመራማሪ ነው። እንዲያውም በፋርማሲ ቅመማ ዘርፍ ዲግሪ አለው። እሱ እንደሚለው ቫይረሱ የተፈጠረው የሰው ልጆች በግዳጅ ክትባት እንዲወስዱ ለማመቻቸት ነው። ከክትባቱ ጀርባ ደግሞ ቢል ጌትስ አለ ይላል። "ይህ ወረርሽኝ እንዲቀጥል ይደረጋል። እንዲቀጥል የሚደረገው ክትባት እንድንወስድ ለማስፈራራትና ለማሳመን ነው። ከዚያ ሐብታሞች የበለጠ ሀብታም ይሆናሉ" በማለት ሞንታናሪ ለማሳመን ይሞክራል። የዚህ ሴራ ተንታኞች በእሲያም ተበራክተዋል። ሕንድ በየጊዜው አዳዲስ አሉባልታዎች የሚሰሙባት አገር ናት። በዚያ አገርም ቢሆን ከምዕራቡ ዓለም የሚመጣን ክትባት ላለመቀበል እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። ሕንድ ውስጥ ያሉ የሴራ አራማጆች አገራቸው ክትባቱን ከላም ሽንት እንደምታገኝ ያምናሉ። በሕንድ በፌስቡክ ሰፊ ተቀባይነት ያገኘ ዘመቻ ከዚሁ ከላም ሽንት ጋር የተገናኘ ሆኗል። መረጃውን ሺህዎችና ሚሊዮኖች በየቀኑ የሚጋሩት ጉዳይ ነው። ነገሩ 'አህመዳባድ ሚረር' ከተሰኘ ጋዜጣ ዜና ጋር የተያያዘ ነው። ይህ ጋዜጣ በሕንድ ቅዱስ ከሆኑ ላሞች መድኃኒቱ ሊገኝ ይችላል የሚል ይዘት ያለው ዘገባ ሰርቶ ነበር። ክትባቱ የሚቀመመው ታዲያ ከላም ሽንት፣ ከቅቤና አዛባ ይሆናል። ከዚህ ዘገባ ቀደም ብሎም ቢሆን በርካታ ሕንዳዊያን ቫይረሱን ለመከላከል የላም ሽንት መጠጣት ጀምረው ነበር። አሁንም እየጠጡ ነው። በዚያ አገር ለላም ትልቅ ቦታ ይሰጣታል። ላም ቅድስት ናት። የሚገርመው ደግሞ ይህ ሰፊ ተቀባይነትን ያገኘው ሴራና መላምት በጊዜ ሂደት መልኩን እየቀየረ መሄዱ ነው። ነገሩን መጀመሪያ የሴራ ፈታዮች ምንጭ አድርገው የወሰዱት አህመዳባድ ሚረር ከተባለ ጋዜጣ ቢሆንም ጋዜጣው መድኃኒት ከሽንት ይገኛል ብሎ አልጻፈም። ከዚያ ይልቅ ጋዜጣው አንድ ሐኪምን ጠቅሶ የዘገበው "የላም ሽንት መድኃኒትነት ስላለው ለኮቪድ-19 የሚሆን ንጥረ ነገር ሊገኝበት ይችላል" የሚል ጽሁፍን ነበር ያሰፈረው። የሴራ ትንተና አራማጆች ግን ጉዳዩን ከዚህ ብዙ አርቀው ወስደውታል። ቢቢሲ የሕንድ ሕክምና ምርምር ማዕከል ኃላፊ የሆኑትን ዶ/ር ራጂኒ ካንትን ስለ ላም ሽንት ወይም አዛባ ኮሮናቫይረስን ይፈውሳሉ ወይ ሲል ጠይቋቸዋል። እርሳቸው ሲመልሱ "ይህን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት መረጃ የለም፤ የተደረገ ምርምር ስለመኖሩ አላውቅም" ብለዋል። በሕንድ የግብርና ሚኒስቴር ሥር የተቋቋመ አንድ ክፍል ግን ለኮሮናቫይረስ ለጊዜው ክትባት ባይገኝም ምናልባት ክትባቱ ከላም ሽንትና አዛባ፣ እንዲሁም ቅቤም ተቀላቅሎበት መድኃኒት ለማግኘት ሙከራ ይደረጋል ብሏል።
news-52300225
https://www.bbc.com/amharic/news-52300225
"የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም" ዶ/ር ፅዮን ፍሬው
የድንገተኛ ክፍል እና የኅብረተሰብ ጤና ስፔሻሊስቷ ዶ/ር ፅዮን ፍሬው የጤና ጥበቃ አማካሪ ናቸው። በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በሆነባት የአሜሪካዋ ኒው ዮርክ የሚሠሩት ዶ/ር ፅዮን የኮሮናቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።
ዶ/ር ፅዮን ፍሬው የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 ስለ ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም ኢትዮጵያ በሽታውን ለመከላከል እየወሰደች ስላለችው እርምጃ ዶ/ር ፅዮንን ከጥቂት ሳምንታት በፊት አነጋግረናቸው ነበር። የወረሽኙን ስርጭት በመከላከል ረገድ ኢትዮጵያ ምን ላይ ትገኛለች? በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሁለት ሚሊዮን አልፏል። ኢትዮጵያ ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 85 መድረሳቸውን ጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል። ዶ/ር ፅዮን እንደሚሉት፤ በምጣኔ ሃብት እንዲሁም በጤና ሥርዓትም የተሻሉ አገሮችን እየፈተነ ያለው ቫይረስ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ለአቅመ ደካማ አገሮች የበለጠ አስጨናቂ መሆኑ አያጠያይቅም። ነገር ግን ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሰዎች ላይ የቫይረሱ ምርመራ መጀመሩ ጥሩ እርምጃ እንደነበር ያስረዳሉ። በወቅቱ አየር መንገድ ላይ የሰዎች የጉዞ ታሪክ መጠየቁ (ቫይረሱ ወደተሰራጨባቸው አገሮች ሄደው እንደሆነ ለመለየት) የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በሚደረግው ጥረት እንደ ጥሩ ምሳሌ ይጠቅሱታል። የፅኑ ህሙማን ማቆያና ሌሎችም የህክምና መሣሪያዎች ኢትዮጵያም ይሁን ሌሎቹ የአፍሪካ አገሮች በበቂ ሁኔታ የላቸውም። “አሜሪካ እና አውሮፓ ውስጥ እየሄደበት ባለው ፍጥነት አፍሪካ ውስጥ ቢሄድ በጣም ያስፈራል፤ ያስጨንቃል” ይላሉ ዶክተሯ። አህጉሪቱ ውስጥ አብላጫውን ቁጥር የያዙት ወጣቶች መሆናቸው መጠነኛ ተስፋ እንደሚሰጥ ይናገራሉ። ይህ ማለት ወጣቶች በኮሮናቫይረስ አይያዙም ማለት ሳይሆን፤ ቢያዙም ከአዛውንቶች አንጻር የመሞት እድላቸው ዝቅተኛ ነው ማለት ነው። ምርመራን በተመለከተ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በዋነኛነት ምርመራ እየተካሄደ ያለው ከተለያየ አገር ወደ አገሪቱ ለመጡና በቫይረሱ ከተያዙ ወይም ተይዘዋል ተብለው ከተጠረጠሩ ሰዎች ጋር ንክኪ ላላቸው ሰዎች ነው። መመርመሪያው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም በሚፈለገው መጠን አለመኖሩ ምርመራውን ከባድ እንደሚያደርገው የሚናገሩት ዶክተሯ፤ “በሽታው በማኅበረሰቡ ውስጥ እተሰራጨ ሲመጣ ግን በብዛት መመርመር ይኖርብናል” ይላሉ። ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረጉ ነው? በእርግጥ በመላው አገሪቱ በሽታውን ለመከላከል ዜጎች እየወሰዱ ስላሉት እርምጃ አንዳች ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ሰፊ ጥናት ቢያስፈልግም፤ በአደባባይ ከሚታዩ እንቅስቃሴዎች አንጻር፤ ከኮሮናቫይረስ ራስን በመከላከል ረገድ ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረጉ ነው ማለት ይቻላል ወይ? ስንል ዶ/ር ፅዮንን ጠይቀን ነበር። ዶ/ር ፅዮን ፍሬው እሳቸው እንደሚሉት፤ በሽታው ስር ሳይሰድ በፊት መንግሥትና የሚመለከታቸው ተቋሞች (ጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት) የሚያወጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ዜጎች መከተል አለባቸው። “ሰው አላግባብ መደንገጥ ሳይሆን የሚነገረውን ማድረግ አለበት፤ በማኅበራዊም ይሁን በማንኛውም ጉዳይ አትሰብሰቡ እየተባለ ሰው መሰብሰብ ካላቆመ በሽታው ይስፋፋል” ይላሉ። በተለይም በአሁን ወቅት “መዘናጋት ትክክል አይደለም” ሲሉም በአጽንኦት ይናገራሉ። “የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም፤ ቁጥሩ 40 ሺህ ወይም 60 ሺህ እስኪደርስ መጠበቅ የለብንም። በጣም የምወደው ሰው ከዚህ በሽታ ሊሞት ይችላል ብለን ማሰብ አለብን” በማለትም ዶ/ር ፅዩን ያክላሉ። መዘናጋት በበሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከፍ ከማድረጉም ባሻገር፤ ቫይረሱ ስጋት የሚሆንበትን ጊዜም እንደሚያራዝመው ያስረዳሉ። በተጨማሪም ቤት መቀመጥና እጅ መታጠብን የመሰሉ ተግባሮች ቀላል ቢመስሉም የበርካቶችን ሕይወት ይታደጋሉ ይላሉ። ቤት ውስጥ ስለማገገም ዶ/ር ፅዮን እንደሚሉት፤ ወደ ህክምና መስጫ ሳይሄዱ ቤታቸው ማገገም የሚችሉ ሰዎች አሉ። "ሆስፒታል መሄድ የሚያስፈልጋቸው ከ10 በመቶ በታች ናቸው። በእድሜ የገፉ ሰዎችና የተለያየ ህመም ያለባቸው ሰዎች ሆስፒታል መሄድ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን ወጣቶችና ሌላ በሽታ የሌለባቸው ሰዎች ቤት እንዲሆኑ ይመከራል" ይላሉ። በተለይም የህክምና መስጫ ተቋሞች ሁሉንም ሰው ማስተናገድ በማይችሉበት ወቅት ወጣቶችና ሌላ በሽታ የሌለባቸው ሰዎች በቤታቸው እንዲያገግሙ እንደሚደረግ ያስረዳሉ። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በአጠቃላይ ሆስፒታል እየገቡ መሆኑን የሚያጣቅሱት ዶ/ር ፅዩን፤ ቁጥሩ እየበዛ ከሄደ ግን ሆስፒታሎች መቋቋም እንደማይችሉ ይናገራሉ። በአሜሪካ፣ በቻይና እና በአውሮፓ አገራትም አንዳንድ ሰዎች በቤታቸው እንዲያገግሙ የተደረገውም ቁጥሩ በመጨመሩ መሆኑንም ያስረዳሉ። ሆኖም ግን መተንፈስ የሚቸገሩ ሰዎች በሆስፒታል ህክምና እንዲከታተሉ እንደሚደረግም አያይዘው ያነሳሉ። "ቤታቸው ሆነው እንዲያገግሙ የሚጠበቁ ሰዎች ሌላ ጊዜ ጉንፋን ሲይዛቸው ለራሳቸው የሚያደርጉትን እንክብካቤ እንዲያደርጉም ይመከራል። ትኩሳት እና ሳል የሚያስታግስ ነገር በቤታችን ማድረግ እንችላለን" ይላሉ።
51886208
https://www.bbc.com/amharic/51886208
"ባለፉት ሁለት ዓመታት 20 አብያተ ክርስትያናት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል" ማህበረ ቅዱሳን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር የሚገኘው ማህበረ ቅዱሳን ዋና ፀሀፊ የሆኑት አቶ ውብሸት ኦቶሮ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በተለያየ ስፍራዎች በእምነታቸው የተነሳ ብቻ ጥቃት የደረሰባቸውን መልሶ ለማቋቋም ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልገው ለቢቢሲ ገለፁ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በማህበረ ቅዱሳን ጉዳት በደረሰባቸውና መንቀሳቀስ በቻለባቸው አካባቢዎች የደረሰው ጥቃት ምንድን ነው? ምእመናን ምን ዓይነት ጉዳት ደረሰባቸው ? ምን ቢሰራ እነዚህን ሰዎች ማቋቋም ይቻላል የሚለው መጠናቱን ተናግረዋል ዋና ፀሃፊው። • የኮሮናቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ተረጋገጠ • ራስዎን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል እጅዎን ታጥበዋል? ስልክዎንስ? • አውሮፓ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ 'ማዕከል' ሆናለች ተባለ ማህበሩ መንቀሳቀስና ማጥናት በቻለባቸው ስፍራዎች ካገኘው መረጃ በመነሳት ይፋ እንዳደረገው የተለያየ ጉዳት ያስተናገዱ ሰዎችን ለማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ ለማድረግ ከጴጥሮሳውያን የቤተክርስትያን መብትና ክብር አስጠባቂ ህብረት፣ እንዲሁም ከዳንዲ አቦቲ ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ማህበረ ቅዱሳን በጃንሜዳ የገቢ ማሰባሰቢያውን እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜዎች የተደረጉ የለውጥ ሂደቶች ቤተክርስቲያኒቷ እና በአማኞቿ ላይ የተለያየ ጥቃት ደርሷል ያሉት ዋና ጸኃፊው ለዚህም ምክንያቱ በተለያዩ ጊዜያት የሚነገሩ የሀሰት ትርክቶች ናቸው ሲሉ ይናገራሉ። ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቃጠሉና ሙሉ በሙሉ የወደሙ ከ20 በላይ ፣ ከአስር የማያንሱ ደግሞ የተለያየ መጠን ጉዳት የደረሰባቸው አብያተክርስቲያኖች መኖራቸውን ዋና ጸኃፊው ጨምረው ገልፀዋል። ከአብያተ ቤተክርስትያናቱ በተጨማሪ ምዕመናኑ ላይ የተለያየ ጉዳት መድረሱን የገለፁት የማህበረ ቅዱሳን ዋና ጸኃፊ፣ ከሞቱት ባሻገር ቤት ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ የወደመባቸው፣ አካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ ወደተለያየ አካባቢ የተፈናቀሉ ምዕመናን መኖራቸውን ይናገራሉ። የወደሙባቸው አገልግሎት መስጫ ተቋማትና ቤታቸው የሚሰራላቸው 417 ሰዎች፣ ሌሎች በተለያየ መንገድ ድጋፍ የሚደረግላቸው ደግሞ 1ሺህ 700 ሰዎች መሆናቸውን አቶ ውብሸት ተናግረዋል። አቶ ውብሸት አክለውም ንብረቶቹን ብቻ መልሶ ለመተካት 400 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ መገመቱን ገልፀው፤ 200ሚሊዮኑ ለሕክማናና ለስነልቦና ድጋፍ እንደሚውል ተናግረዋል። ጉዳት የደረሰባቸው አብያተ ክርስትያናት በምዕመናኑ ድጋፍ እየታነፁ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ጸኃፊው፣ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ግን አስታዋሽ አጥተው መቸገራቸውን ጠቅሰዋል። እስካሁን የተጎዱ ሰዎችን መልሶ ለመማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የፊታችን መጋቢት 27 ቀን በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ፕሮግራም ማዘጋጀቱንም አቶ ውብሸት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ፕሮግራም ላይ በትንሹ 30 ሺህ የእምነቱ ተከታዮች እንደሚገኙ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከአገር ውጪ የሚኖሩ በዕለቱ በማህበሩ ድረገፅ በቀጥታ በመግባት ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ተናግረዋል። • ሰላም ለመፍጠር የቴሌቪዥን ጣቢያ የከፈተችው አዲሷ ሚኒስትር ማህበረ ቅዱሳን ይህንን ሥራ እንዲሰራ ከጠቅላይ ቤተክህነት በተጻፈ ደብዳቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጠይቆ ፈቃድ ማግኘቱን ጨምረው ገልፀዋል። አቶ ውብሸት በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እንደሚያወግዙ በመጥቀስ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ግን ተገቢውን ትኩረት አላገኙም ሲሉ ይወቅሳሉ። ተመሳሳይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ለማካሄድ ዕቅድ እንዳለ አቶ ውብሸት ጨምረው ገልፀዋል።
50569497
https://www.bbc.com/amharic/50569497
ዛምቢያዊው ፓይለት 'በመብረቅ' የተመታውን አውሮፕላን በሰላም አሳረፉ
ንብረትነቱ ፕሮፍላይት የተሰኘ የግል አየር መንገድ የሆነ ዳሽ 8-300 አውሮፕላን 41 መንገደኞችን አሳፍሮ የቱሪስት ከተማ ከሆነችው ሊቪንግስተን የዛምቢያ መዲና ወደ ሆነችው ሉሳካ በመቃረብ ላይ ሳለ በከባድ ውሽንፍርና መብረቅ መመታቱ ነው የተነገረው።
በ19 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረውና በመብረቅ የተመታው አውሮፕላን አፍንጫው ላይ ጉዳት ቢደርስበትም ፓይለቱ በሰላም መሬት እንዲያርፍ ማድረግ በመቻሉ ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ እያወደሱት ነው። የፕሮፍላይት የበበራ ማናጀር የሆኑት ፊል ሊምባ 41 መንገደኞቻቸው በሰላም በመድረሳቸው ደስታቸውን ገልፅዋል። ዳሽ 8-300 የሆነው ይህ አውሮፕላን በሥሪቱ ምክንያት በመብረቁ አፍንጫው ከመጎዳቱ ባሻገር ምንም ጉዳት እንዳልደረሰበት ማናጀሩ ቢገልፁም አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ ግን አውሮፕላኑ ላይ ጉልህ የሚባል ጉዳት ደርሷል ብሏል። የአየር መንገዱ መግለጫ እንደሚለው እርግጥም አውሮፕላኑ በከባድ ውሽንፍር ተመትቷል። እርግጠኛ ሆኖ በመብረቅም ተመትቷል ለማለት ግን ምርመራ መደረግ አለበት። • ግብጽዊው አርቲስት አውሮፕላን አብራሪውን እስከወዲያኛው ከሥራቸው አሳገደ • ታዳጊዎች በገጣጠሟት አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራቸውን አደረጉ • ደቡብ አፍሪቃ የታንዛኒያ አውሮፕላንን በቁጥጥር ሥር አዋለች
41438845
https://www.bbc.com/amharic/41438845
ካለሁበት 3፡ "ኢትዮጵያ ውስጥ የማውቀው ሁሉም ነገር ይናፍቀኛል"
ለንደን ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ነዋሪዎች መሰባሰቢያ ናት። የተለያዩ ቋንቋዎች፣ የአኗኗር ዘይቤዎችና ባህሎች የሚታዩባትና የተለያየ ተሰጥዖና የተለያየ ልምድ ያላቸው፤ ከዚያም በላይ ደግሞ የተለያ መሠረት ያላቸው ሰዎች አንድ ቦታ ላይ መገኘት የሚችሉባት ከተማ ናት። ይሔም ሁኔታ ከአዲስ አበባ ይለያታል። ስሜ ባህሩ ገዛኸኝ ይባላል። ለንደን የመጣሁት ለጉብኝት ሲሆን እዚህ ከመጣሁ በኋላ በግል ጉዳይ ምክንያት ወደ አገሬ ተመልሼ መሄድ ባለመቻሌ ለንደንን መኖሪያዬ አደረኳት። በአሁኑ ወቅት ደግሞ ትምህርት ቤት ተመልሼ የድህረ-ምረቃ ትምህርቴንም እየተከታተልኩ ነው።
ታዋቂው አሜሪካዊ ገጣሚ ሶውል ዊልያምስና ባህሩ ገዛኸኝ ለንደን ለእኔ ጥሩ ናት። ከኢትዮጵያ የሚናፍቀኝን አንድ ነገር መርጦ ለመናገር ደግሞ በጣም ነው የሚከብደኝ። ቢሆንም ግን የሚናፍቅኝን መርጬ መናገር ግዴታ ቢሆንብኝ የማውቀው ነገር በሙሉ ይናፍቀኛል እላለሁ፤ ምክንያቱም ሁሉን ያጠቃልልልኛልና። ሆኖም ግን ብዙ የሚያስደስቱ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ስለምግብ ብናወራ የለንደን ከተማ ብዙ የምግብ ስጦታዎችን አበርክታልኛለች። ከቺዝ የሚሠራውን ኬክ (ብሉቤሪ ቺዝ ኬክ) በየቀኑ ብበላ አይሰለቸኝም፤ አሁንማ የየቀኑ ምግቤ ሆኗል ማለት ይቻላል። ብሉቤሪ ቺዝ ኬክ ለንደን በተፈጥሮአዊ ውበቷም የታደለች ናት። በማዕድ-ቤቴ መስኮትም በኩል የሚታየኝም አረንጓዴ የሆነ የመናፈሻ ፓርክ ነው። በእኔ ሰፈር ብቻ አይደለም የተለያዩ አካባቢዎችም መንፈስን በሚያድሱ አረንጓዴ ፓርኮችም መሞላቷ ከተማዋን በጣም አስደሳች ያደርጓታል። ከተማዋ ውስጥ በምዘዋወርበት ወቅት ያስደመመኝ ነገር ቢኖር፤ ነዋሪዎች ራሳቸውን የሚገልፁበት መንገድ ነው። በተለይም ከፀጉር ቀለማት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተለመዱ እንደ ወይነ-ጠጅ፣ ሰማያዊና ቀይ ማየት የተለመደ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ግፋ ቢል የሚታየው ቢጫና ቡናማ የፀጉር ቀለሞችን ነው። ከፀጉር በተጨማሪ የልብስ ምርጫቸውም አይን አዋጅ የሚያስብል ነው። በለንደን ጎዳናዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተለመዱና ወጣ ያሉ አለባበሶችም ይታያሉ። ለኔ ዋናው ነገር የአለባበስ ወይም በአጠቃላይ ራስን የመግለፅ ነፃነቱ ነው። አዲስ አበባ እያለሁ በአለባበሴ እቆጠብ ነበር። እዚህ ግን ራሳቸውን በሙሉ ነፃነት ስለሚገልፁ፤ እንዲሁም ማንም ዞር ብሎም ስለማያየኝ እኔም ራሴን በምፈልገው መንገድ ለመግለፅ ነፃነቱ ይሰማኛል። ምንም እንኳን ከተማዋ ብዙ የሚያስደስት ነገር ቢኖራትም ብዙ መቀየር ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ ይሰማኛል። ለምሳሌም ጥቁር ሰዎችን የሚያካትቱ የጥበብ ትዕይንቶችና ፌስቲቫሎች ቢኖሩ ጥሩ ነው። በመጀመሪያ ለንደን ስመጣ ለረዥም ዓመታት እቆያለሁ ወይም እቀራለሁ የሚል ሃሳብ አልነበረኝም ። ለመቆየት ከወሰንኩ በኋላ ነበር ነገሮች መክበድ የጀመሩት፤ ምክንያቱም ለንደን ውስጥ ብዙ ሰው ቢኖርም ብቸኝነትም የሚሰማበት ስፍራ ነው። ሰፋ ካለ ቤተሰብ መምጣቴ፤ ትምህርት ቤት ባለሁበት ወቅት እንዲሁም በማህበራዊ ህይወቴ ብዙ ጓደኞችንም ስላፈራሁ ብቸኝነትን አላውቀውም። እንዲህም ብቸኝነት ተሰምቶኝ አያውቅም ነበር። የባሕሩ "የለንደኗ ካዛንችስ" ከነበርኩበት የማህበራዊ ግንኙነት ተነጥዬ መውጣቴ፤ በስልክ እንኳን ደውዬ የምጠራው ሰው ባለመኖሩ ከብዶኝ ነበር። ከጊዜ በኋላ ጓደኞችም እያፈራሁ እንዲሁም በፊት የማውቃቸው ሰዎችንም ባጋጣሚ በማግኘቴም ቀለል እያለኝ መጥቷል። እንደዛም ሆኖ ግን ኢትዮጵያን የሚያስታውሱኝ እንደ ፊንዝበሪ ፓርክ ያሉ ሰፈሮችም አይጠፉም። በሰሜን ለንደን የሚገኘው ይህ አካባቢ የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን መናኸሪያ ነው። በግዕዝ ፊደላት የተፃፉባቸው የምግብ ቤቶች ወይም ሱቆች ሳይ፤ አማርኛ ወይም ትግርኛ ስሰማ አጠቃላይ የአካባቢው ዕይታ ካዛንችዝ ያለሁ ያህል ይሰማኛል። እንደዛም ሆኖ ግን ያው ለንደን አዲስ አበባ አይደለችም። ምናልባትም ራሴን ኢትዮጵያ መውሰድ ብችል አዲስ አበባ እፎይ በተሰኘው ፒዛ ቤት እየበላሁ የናና ሻይ እያጣጣምኩ አገኘው ነበር። ለክሪሰቲን ዮሐንስ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 4፡ የሰው ሃገር የሰው ነው ካለሁበት 5፡'ኑሮዬን ቶሮንቶ ያደረግኩት በአጋጣሚ ነበር'
news-49202524
https://www.bbc.com/amharic/news-49202524
ከ300ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ቴክቫህ ኢትዮጵያ
አሁን አሁን በኢትዮጵያ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሠራጩ የጥላቻ ንግግርንና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመቆጣጠር በግለሰብ፣ በተቋማት እና በመንግሥት ደረጃ ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ይስተዋላል።
ጉዳዩ ወጣቶችንም ሳያሳስብ አልቀረም ታዲያ። ለዚህም ነው ቴክቫህ ኢትዮጵያ የተጀመረው። አቅሌሲያ ሲሳይ በመላ ሃገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች መረጃን በዋናነት የሚያገኙት ከማህበራዊ ሚዲያ መሆኑን ትናገራለች። የኤሌክትሪካል ምህንድስና እና ኮምፒውተር ተማሪ የነበረችው አቅሌሲያ፤ "በዩኒቨርስቲ ውስጥ ሳለን የምናገኘውን መረጃ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አዳጋች ነበር" ትላለች። በዚህ ሁሉም የራሱ የሆነ ገፅ ከፍቶ የተለያዩ መረጃዎች በሚያሠራጭበት ዘመን፤ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ዐይናቸውን ለቴሌቪዥን ጆሯቸውን ለሬዲዮ ለመስጠት ጊዜ እንዳልነበራቸው ታስታውሳለች - አቅሌሲያ። ሁሉም ሰው ሞባይሉ ላይ ተጥዶ በማህበራዊ ትስስር መድረኮች በኩል የሚያገኘውን መረጃ ይቃርማል። እርሷ በዩኒቨርስቲ በነበረችባቸው የመጀመሪያ ዓመታት ፌስቡክ ለእነዚህ ተማሪዎች መረጃን በማቅረብ አልፋና ኦሜጋ ነበር። በኋላ ግን ቴሌግራም መጥቶ የመረጃ ማቅረቡን መንበር ተቀላቀለ። ያኔ ነው የአቅሌሲያ ጓደኞች ስለቴሌግራም መነጋገር የጀመሩት። አቅሌሲያም ስለ ቴክቫህ ኢትዮጵያ ሰማች፤ ቤተሰብም ሆነች። • ፌስ ቡክ የሳዑዲ አረቢያ የፕሮፓጋንዳ ገጾችን አገደ • የ27 አስደናቂ ፈጠራዎች ባለቤት የ17 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ፀጋአብ ወልዴ ተወልዶ ያደገው ይርጋለም ነው። ሐዋሳ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በጋዜጠኝነትና በተባባሪ አዘጋጅነት መስራቱን ይናገራል። አሁን ደግሞ የቴክቫህ ኢትዮጵያ መስራችና የቤተሰብ አባል ነኝ ብሎ ነው ራሱን የሚያስተዋውቀው። ቴክቫህ ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከ320 ሺህ በላይ የቤተሰብ አባላት ያሉት እና ቴሌግራም በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር መድረክ ላይ መረጃ የሚያቀብል ገፅ ነው። ገፁን የሚቀላቀሉት ሁሉ የቤተሰብ አባላት ተብለው እንደሚጠሩ የሚናገረው ፀጋአብ ቴሌግራምን በስልኩ ላይ ጭኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዚህ ገፅ አባል ያደረጋቸው ስልኩ ላይ የሚገኙ ከሃያ እስከ ሠላሳ ሰዎችን ብቻ መሆኑን ያስታውሳል። እነዚህ ሰዎች በስልኩ ውስጥ ቁጥራቸው የሰፈረ ባልንጀሮቹ ይሁኑ እንጂ የቴሌግራም ተጠቃሚም አልነበሩም። ቀስ በቀስ ግን አንዱ አንዱን እየሳበ፤ ሌላኛው ለጓደኛው እየተናገረ የገፁ ተከታዮች ቁጥር ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ ደርሷል። እነዚህን የቤተሰብ አባላት አንድ የሚያደርጋቸው መረጃ መፈለግ ብቻ ነው? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላት የቴክቫህ ቤተሰብ አቅሌሲያ፤ ፈጠን ብላ "...ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነት ይቅደም የሚለውም አንድ ያደርገናል" ብላለች። ቴክቫህ የት ተጠነሰሰ? ፀጋአብ በሐዋሳ ኤፍ ኤም 100. 9 ላይ፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ የሐዋሳ ድምፅ ላይ ሲሠራ መረጃ አጠናቅሯል፤ አደራጅቷል። ፀጋአብ ዕድሜው ሃያዎቹን ያልዘለለ ወጣት ነው። በርካታ ወዳጆቹ እና የእድሜ አቻዎቹም የሚገኙት በትምህርት ቤት ውስጥ ነው። ታዲያ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት የተነሳ በዩኒቨርስቲዎችም ውስጥ ረብሻ፣ አመፅና ሞት ሁሌም ይሰማል። እነዚህን መረጃዎችን የሚያገኘው ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት መሆኑን ያስታውሳል። ነገር ግን ሁሌም አንድ ክፍተት ይታየዋል። ይህ ለእርሱም ሆነ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ላሉ ጓደኞቹም የሚደርስ መረጃ፤ የብሔር ታፔላ አንጠልጥሎ፣ ስድብ አዝሎ፣ በቀል አንግቦ እንደሚንቀሳቀስ አስተዋለ። "በፌስቡክ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ ዜናዎችን አያለሁ። ይህንን ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ወጣቶችም ያዩታል" ይላል። አቅሌሲያም ይህንኑ ታረጋግጣለች። ተመርቃ ከመውጣቷ በፊት በዩኒቨርስቲ ውስጥ የምትሰማቸው መረጃዎች፣ ተረጋግታ ትምህርቷን እንድትማር የሚያደርጉ ሳይሆኑ ስጋትን የሚያጭሩ፣ መከፋፈልን፣ አለመተማመንን የሚያነግሱ መሆናቸውን አትረሳም። • "ዓላማችን ችግሮችን ፈተን ገንዘብ ማግኘት ነው " የጠብታ አምቡላንስ ባለቤት • የዓለምን ቆሻሻ ወደ ሮቦት የቀየሩ ተመራማሪዎች ጉዳዩ ያሳሰበው ፀጋአብ፤ ከዚህ የማህበራዊ ትስስር መድረክ የመረጃ ቋት ውስጥ ፍሬውን ከገለባ፣ እንክርዳዱን ከፍሬው ለይቶ ለማቅረብ ሁነኛ መፍትሄ ሆኖ ያገኘው ቴሌግራምን ነው። እናም ሐምሌ 19 ቀን 2009 ዓ.ም ላይ ቴክቫህ ኢትዮጵያ ተመሰረተ። ቴክቫህ ኢትዮጵያ የገፅ ስያሜ ነው። ቴክቫህ የሂብሩ ቃል ሲሆን ተስፋ ማለት ነው ሲል ያብራራል፤ ተስፋ ኢትዮጵያ ለማለት መፈለጉንም ይናገራል። ቴክቫህ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እውነተኛ መረጃ ማድረስን ስንቁ አድርጎ ቢይዝም ከዚያ ባሻገር የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይም ወጣቱን ለማሳተፍ እንደሚሰራ ፀጋአብ ይናገራል። ከዚህ ባለፈም ደግሞ በጥላቻና በሐሰተኛ ንግግሮች ዙሪያ በመነጋገር መማማር እንዲፈጠር የተለያዩ ዘመቻዎችን እንደሚያደርግ አቅሌሲያ ትናገራለች። ቴክቫህ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኀን የሚያገኛቸውን መረጃዎችን ከማቅረብ ባሻገር ተከታዮቹ ከያሉበት የሚልኳቸውን መረጃዎችንም ያቀርባል። መረጃዎቹ ከየት መጡ፣ ማን ላከው የሚለውን በማጣራት ኃላፊነት እንዲሰማቸው በሚል ስማቸውን ጠቅሶ ያወጣል። ከተለያዩ መገናኛ ብዙኀን መረጃዎችንም ሲወስድ ያገኘበትን በመጥቀስ የገፁን ተዓማኒነት ለመጠበቅ ይጥራል። ፀጋ አብ እንደሚለው ለየትኛውም አካል ወገንተኛ ሆኖ አይሰራም። ለምን ቴሌግራምን ተመረጠ? ኢትዮጵያ ውስጥ ይፋዊ ጥናት ባይኖርም የማህበራዊ ትስስር መድረክ ተጠቃሚዎች ፌስቡክ ቀዳሚ ምርጫቸው ይመስላል፤ ፌስቡክ ይቅርብኝ ያለ ትዊተር መንደር አይታጣም። ፀጋአብ ግን የመረጠው ቴሌግራምን ነው። ለምን? ፀጋአብ ፌስ ቡክ ብዙ ተከታዮች እንዳለው አልካደም። ነገር ግን በፌስቡክ ላይ የሚንሸራሸሩ የትኛውም ጉዳዮች ላይ [በጎም ይሁኑ መጥፎ] የሚሰጡ አስተያየቶች መከባበር የተሞላባቸው እና የተለያዩ ወገኖችን ስሜት ያገናዘቡ አይደሉም ይላል። ሰዎች አስተያየት የመስጠት መብታቸው የተጠበቀ ቢሆንም የጥላቻ ንግግሮች፣ በስፋት የሚታዮበት መድረክ እንደሆነ ለመናገር አላመነታም። "ፌስ ቡክ ላይ ምንም አይነት ገፅ የለንም" የሚለው ፀጋአብ ገፃችንን ፌስ ቡክ ላይ አድርገነው ቢሆን ኖሮ አንባቢያችን እኛን ብቻ አይቶን ሳይሆን በዙሪያችን የሚርመሰመሱ ሌሎች የመረጃ አቅራቢዎች ጋር ጎራ ብሎ በዚያው መረጃ ሊወሰድ የሚችልበት እድል ሰፊ እንደሚሆን ይናገራል። በቴሌግራም ላይ አንድ ሰው ፈልጎ የተቀላቀለው ካልሆነ በስተቀር ሌሎች ጉዳዮች ስለማይመጡ ተጠቃሚዎቻቸውን ቢያንስ ከስድብና ከጥላቻ ንግግር ለመጠበቅ እንደሚያስችላቸው በመግለፅ የቴሌግራምን ጠቀሜታ ያስረዳል። • «ሰው ሲበሳጭ ማስታወሻ እይዝ ነበር» አዲስ ዓለማየሁ ከዚህ ባሻገርም ቴሌ ግራም እንደ ፌስቡክ አስተያየት በመስጠት ስድብ የመወራወሪያ ዕድል ስለሌለው ራስን ከሐሰተኛ ዜናና ከጥላቻ ንግግር ለመጠበቅ ሁነኛ መላ ሆኖ እንደታየው ይገልጻል። "በቴሌግራም ቢያንስ የተሻለ መደማመጥ የሚችል፣ የሌላውን ሐሳብ አክብሮ የእርሱን ሐሳብ የሚገልፅ ተጠቃሚ ፈጥረን ወደ ሌላዎቹ የማህበራዊ መድረኮች ወደፊት ልንሄድ እንችላለን፣ አሁን ግን ቴሌ ግራም ብቸኛ አማራጫችን ነው" ብሏል- ፀጋአብ። ፀጋአብ ቴክቫህ ኢትዮጵያ በተመሠረተበት በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ አንድ ቀን ብቻ መረጃ ለቤተሰብ አባላቱ ሳያደርስ መቅረቱን ያስታውሳል። ያ- ቀንም ሕመም ገጥሞት እርሱና ሞባይሉ ተራርቀው የነበረበት ነው። በመላው ሀገሪቱ አልያም በትላልቅ ከተሞች ኢንተርኔት ድርግም ብሎ ሲጠፋ እንኳ እርሱ ዋይፋይ ወደሚያገኝበት ጎራ ብሎ መረጃዎቹን ለቤተሰብ አባላቱ እንደሚያደርስ ይናገራል። ፀጋአብ መረጃዎቹ ለመቀበልም ሆነ ለማድረስ ሳምሰንግ ኖት 9ንና ሳምሰንግ ኤ70 ስልኮችን ይጠቀማል። የባትሪ እድሜያቸው ረዥም ስለሆነ ነው የመረጥኳቸው ሲል ያክላል። ቴክቫህ ኢትዮጵያ በአማርኛ ብቻ ለምን? የቴክቫህ የቤተሰብ አባላት በዋናነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ወጣቶች ናቸው። እነዚህ ወጣቶች ደግሞ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡና የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ ናቸው። ፀጋአብ ይህ ጉዳይ በሚገባ ያሳስበዋል። ለዚህም በዚህ ዓመት ቴክቫህን በኦሮምኛ ቋንቋ ጀምሮ እየሞከረ እንዳለ ይናገራል። በሌሎች ቋንቋዎችም ለመጀመር እቅድ ይዟል። በማለት ነገሮች ካሰበው ፍጥነት በላይ በመሄዳቸው ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራትን ለማከናወን አዳጋች እንደሆነበት ያስታውሳል። በሁለት ዓመት ውስጥ ከ300ሺህ በላይ ተጠቃሚዎችን እደርሳለሁ ብሎ አለማሰቡን የሚናገረው ፀጋአብ ሌሎች በርካታ ሀሳቦች እንዳሉትም አጫውቶናል። ፀጋአብ እንደሚለው በርካታ ሰው የሚያውቀው ወቅታዊ መረጃዎችና ዜናዎች የሚቀርቡበትን ቴክቫህ ኢትዮጵያን ብቻ ነው። ይሁን እንጂ የታመሙ ሰዎች የሚያሳክሙበት፣ የተቸገሩ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያደርጉበት 4ሺህ ተከታዮች ያሉት ቴክቫህ ኤይድ የሚባል ገፅ እንዳላቸው ይናገራል። ይህ ብቻም ሳይሆን ተማሪዎች ኦሮምኛ፣ትግርኛና ግዕዝን በቀላሉ በስልካቸው መማር እንዲችሉ የሚያገለግል 24ሺህ ተከታዮች ያሉት ቴክቫህ ኢዱ የተሰኘ ገፅም አለው። እርሱ እንደሚለው ይህ ገፅ በበጎ ፍቃደኞች የቤተሰብ አባላት የተደራጀ ነው። "ወደፊት የቤተሰብ አባላቶቻችንን እያየንና እነርሱ ሊያገለግሉ በሚችሉበት መስክና ቋንቋ መረጃዎችን ለማድረስ መሞከራችን አይቀርም" ይላል -ፀጋአብ። የቴክቫህ ኢትዮጵያ ዘመቻዎች በተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ጥላቻዎች ተሰብከዋል፤ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ልዩነት እንዲሰፋ የሚሰሩ መልዕክቶች በሰፊው ይሠራጫሉ የሚለው ፀጋአብ በማህበራዊ ትስስር መድረክ ላይ የጥላቻ ንግግርን የሚቃወሙ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ መቆታቸውን ይናገራል። የቴክቫህ ቤተሰብ አባላት ግን ይህንን የጥላቻ ዘመቻ ተገዳድሮ የሚቆም የሰላም፣ የመቻቻል መልዕክትን ማስተላለፍ እንደሚቻል ለማሳየት መንቀሳቀሳቸውን ይገልጣል። ባለፈው ዓመት የቴክቫህ የቤተሰብ አባላት በ11 ዩኒቨርስቲዎች በመንቀሳቀስ የጥላቻ ንግግሮችን በተመለከተ ከተቋማቱ ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል። በዚህ ጉዟቸው ከመቀሌ እስከ አርባ ምንጭ፤ ከወልቂጤ እስከ ደብረብርሀን፤ ከዋቻሞ እስከ ወሎ፤ ከሐሮማያ እስከ ወላይታ ዩኒቨርስቲዎች ድረስ ተጉዘዋል። በሄዱበት ሁሉ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው እንዲደጋገፉ፣ አንዱ አንዱን እንዲያውቅ የበኩላቸውን ጥረት ማድረጋቸውን ይናገራል። • ሀና እና ጓደኞቿ የሠሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ "በአንዳንድ ተቋማት ይህንን መልዕክት ይዞ መሄድ አስቸጋሪ ቢሆንም እኛ ግን ሀሳባችንን ደግፎ የሚቆም አንድ ሰው እንኳን ቢገኝ በማለት ሄደናል፤ በመሄዳችንም ውጤታማ ሆነናል።" ይላል። ከተማሪዎቹ ጋር በሚኖር ውይይት በአርባ ምንጭ የሀገር ሽማግሌዎች እንደነበሩ የሚያስታውሰው ፀጋአብ በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ግን በወጣቶች መካከል ብቻ ውይይት መደረጉን፣ በየዩኒቨርስቲዎቹ ባሳለፉትም ሁለት ሁለት ቀን አብዛኛዎቹን ወጪዎች የቴክቫህ ቤተሰብ አባላት መሸፈናቸውን ይናገራል። ሰው በሰውነቱ እንዲከበር ከዚያም ስለሌሎች ጉዳዩች ለመነጋገር የጥላቻ መልዕክቶችን ማስወገድ ተገቢ መሆኑን የምትናገረዋ አቅሌሲያ በሚቀጥለው ዓመትም ተመሳሳይ መልዕክትን በማንገብ እንደሚጓዙ ነግራናለች። ቴክቫህ የቴሌግራም ገፅ አሁን ወጪውን የሚሸፍነው ከሚያስተላልፋቸው ማስታወቂያዎች መሆኑን ፀጋአብ ይናገራል። ቴክቫህ ወደፊት የጥላቻ ንግግሮችን ለማስቀረት፣ ሐሰተኛ ዜናዎችን ለመዋጋት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የመጓዝ፣ በበጎ አድራጎት በሰፊው ለመሰማራትና ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል የመገናኛ ብዙኀን ለማቋቋም ሀሳብ እንዳለው ፀጋአብ ገልፀፆልናል።
news-52491118
https://www.bbc.com/amharic/news-52491118
በኮሮናቫይረስ ከተቀጠፉ ኢትዮጵያውያን መካከል ጥቂቶቹ
ከጥቂት ዓመታት በፊት በቫይረስ ምክንያት የዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ይቆማል፣ ሰዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ቤት ይቀመጣሉ፣ አገራት ድንበሮቻቸውን ይዘጋሉ፣ የአምልኮ ቦታዎች ወና ይሆናሉ፣ የሰው ልጅ የአኗኗር ዘዬውን ይቀይራል፣ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፉ የመጡ ትውፊቶች ቦታ አይኖራቸውም ብንባል ምናልባት ማመን አስቸጋሪ ይሆናል።
በኮሮና ሀይወታቸውን ያጡት ወገኔ ደበሌ፣ አቶ መንግሥቴ አስረሴና አቶ ዮሴፍ ሲቡ ሆሊውድ የሚሰራቸውን ሳይንሳዊ ልብወለድ የፊልም ሃሳቦችን ይመስላሉ ብሎ የሚያጣጥለውም አይታጣም። የኮሮናቫይረስ ግን የሰው ልጅ ባልጠበቀበት ሁኔታ የማንነካ ነን የሚሉ ታላላቅ አገራትን አንበርክኳል፣ የሰው ልጅ ደረስኩበት የሚለውን የሳይንስ ልህቀት ፈትኗል፣ ለዘመናት ሰዎች የእኔ ናቸው የሚሏቸውን ባህል እንዲሁም የባህል መገለጫዎች መቅረት እንደሚችሉ አሳይቷል። ከዚህም በላይ የሰውን ልጅ የወደፊት እጣፈንታ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል፣ በምጣኔ ሃብቱ፣ በማኅበራዊም ሆነ በፖለቲካው ዘርፍ ያለውን አሰላለፍን እንደሚቀይር እንዲሁም አዲስ የዓለም ሥርዓት ያመጣል እየተባለ ነው። በዚህ ሁሉ ውስጥ በርካቶች የሚወዷቸውን ቤተሰቦች አጥተዋል፤ ቤተ ዘመድ ተሰባስቦ ሐዘኑን አላወጣም፣ በክብርም አልቀበረም። ሐዘናቸውን ለብቻቸው በቤታቸው ይዘው በራቸውን ቆልፈው የተቀመጡትን ቤቱ ይቁጠራቸው። በተለይም የተወለዱበትን ቀዬ ለቀው፣ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ፣ ከስር መሰረታቸው ተነቅለው በአሜሪካ ያደረጉ ከመቶ በላይ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በበሽታው ህይወታቸውን ማጣታቸው እየተነገረ ነው፤ በርካቶችም በቫይረሱ ተይዘዋል። ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሰደር አቶ ፍፁም አረጋ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ እንደተናገሩት በአብዛኛው ቁልፍ ተብለው በሚጠሩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ከመቶ የማያንሱ በኮሮናቫይረስ መሞታቸውን ነው። ከእነዚህም መካከል በአብዛኞቹ ነርሶች፣ የአረጋውያን መጦሪያ እንክብካቤ ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ፣ በሥጋ ኢንዱስትሪ፣ በትራንስፖርትና የመሳሰሉ ዘርፎች የተሰማሩ ናቸው። ቢቢሲ አማርኛ በተለያዩ አገራት በኮሮናቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያንን ህይወትና ኑሮ በመዳሰስ ለመዘከር አቅዷል። በዚህም ሳምንት ካገኘናቸው ውስጥ የተወሰኑትን እነሆ፡ የሦስት ሳምንት ልጇን ሳታይ የሞተችው ወገኔ ደበሌ ታሪኳን የሰማ ሁሉ በሐዘን ልቡ ተሰብሯል። እንደወጣች የቀረችውን፣ በተገላገለች በሦስት ሳምንቷ የጨቅላ ልጇን አይን ሳታይ የተነጠቀችውን ወገኔ ደበሌን በማስታወስ። በቀብሯ ላይ የባለቤቷን አቶ ይልማ አስፋውን የመረረ ሃዘን፣ ለቅሶና ዋይታን በቪዲዮ ማየት ልብን ይሰብራል። በሜሪላንድ ታኮማ ፓርክ በተባለ ቦታ ነዋሪ የነበረችው ወገኔ ደበሌ ሳል፣ የምግብ ፍላጎት ማጣትና ድካም ተጫጭኗት ዶክተር ጋር በምትደውልበት ወቅት ምናልባት ኮሮናቫይረስ ሊሆን ስለሚችል ሆስፒታል ሄዳ እንድትመረመር መከሯት። ወደ ሆስፒታልም ብትሄድም የተሰጣት ምላሽ የኮሮናቫይረስ ለመመርመር ብዙ የታመመች ስለማትመስልና እርግዝናው ሊሆን ስለሚችል በሚል ማስታገሻ ሰጥተው ሸኟት። ከቀናት በኋላ መተንፈስ ሲከብዳት ወደ ሆስፒታል መጣች ስትመረመርም በኮሮናቫይረስ መያዟ ተረጋገጠ። ልጇንም መገላገል እንዳለባት ዶክተሮች በመወሰናቸው ከወር በፊት ያለጊዜው ህፃኑ በህክምና ተወለደ። ከሁለት ቀናት በኋላም እየደከመች ስለመጣች ፅኑ ህሙማን ክፍል እንደትገባና ቬንትሌተር እንዲገጠምላት ወሰኑ። ምንም እንኳን ከቀናት በኋላ ጤናዋ ቢሻሻልም ልቧና ኩላሊቷ በቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ በመጠቃታቸው ሚያዝያ 11/ 2012 ዓ.ም ይህችን ዓለም ተሰናበተች። ልጇም ከሦስት ሳምንታት በኋላ ወደ ቤት በተወሰደ በሁለተኛው ቀን ነው ወገኔ የሞተችው። ወገኔ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አሜሪካ ከመጣች ከአስር ዓመታት በላይ አስቆጥራለች። ወገኔ ቤት ውስጥ ሆና ልጆች የምታሳድግ ሲሆን ባለቤቷ አቶ ይልማ ደግሞ የትምህርት ቤት የአውቶብስ አሽከርካሪ ናቸው። ኢትዮጵያ በነበሩበት ወቅት ወገኔ በላብራቶሪ ቴክኒሺያንነት ታገለግል የነበረች ሲሆን አቶ ይልማ ደግሞ የላብራቶሪ ተቆጣጣሪ ነበሩ። ታኮማ ፓርክ በሚባለው አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ ተወዳጅ ነበረቸው ወገኔ ስትሞትም፤ የታኮማ ፓርክ ከንቲባ ኬት ስቲዋርት በሞቷ የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል። በምክር ቤቶች ስብሰባም ላይም የህሊና ፀሎት አድርገውላታል። ቤተሰቦቿም የገንዘብ እርዳታ በማሰባሰብ ላይ ሲሆኑም ከ257 ሺህ ዶላር በላይ ተሰባስቧል። ቸርና ከኢትዮጵያ የሚመጡ ስደተኞችን በመርዳት የምትታወቀው ወገኔ በተቻላት አቅም ከአገሯ በሺህዎች ኪሎ ሜትር ርቃ ትንሿን ኢትዮጵያ ለመፍጠርም ትሞክር ነበር። እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ እንጀራው፣ ቡናው እንዳለ ሆኖ ዘመንና ሰንሰለት የተባሉትን ድራማዎችንም ትወድ እንደነበር ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል። በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበር መስራች- አቶ መንግሥቴ አስረሴ አቶ መንግሥቴ አስረሴ በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበር መስራችና የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብ፣ ለማኅበረሰቡ የቅርብ ደራሽ የነበሩት አቶ መንግሥቴ በቺካጎ የኢትዮጵያውያንን ማኅበር የመሰረቱትም ከ36 ዓመታት በፊት ነበር። በቺካጎ አካባቢ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዋልታ በመሆንና ድጋፍን በመቸር ይታወቁ ነበር የተባሉት አቶ መንግሥቴ፤ ትንሽ፣ ትልቅ ሳይሉ ከሁሉ ጋር በመቀራረብ አንድነትን፣ ህብረትን በማምጣት በብዙዎች ዘንድ መወደድ የቻሉ ናቸው ተብሏል። በብዙዎችም ዘንድ "ጋሽ መንግሥቴ" ተብለው ይጠሩ እንደነበርም ማኅበሩ አስታውሷል። አቶ መንግሥቴ አስረሴ ህዳር 9/1930 በጎንደር ከተማ እንደተወለዱና ገና በለጋነት እድሜያቸውም የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ጀምረው ዲያቆንነትም ማገልገላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያመለክታል። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ትምህርት ቤት ገብተው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሐረር መምህራን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመምህርነት ተመርቀው በወቅቱ ክፍለ ሃገር በነበረችው ኤርትራ ውስጥ በምፅዋና በአሥመራ አስተምረዋል። በተለያዩ የመንግሥት የሥራ ድርሻዎች ላይ የነበሩት አቶ መንግሥቴ በአዲስ አበባም በአገር ግዛት ሚኒስቴር በሕዝብ ደህንነት ክፍል ተመድበው ለበርካታ ዓመታት እንዳገለገሉም በቺካጎ የኢትዮጵያውያን ማህበር በፌስቡኩ ላይ ካወጣው የአጭር የህይወት ታሪካቸው መረዳት ይቻላል። የ1966 የመንግሥት ለውጥንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ሕብረትን ተቀላቀሉ። በኢዲዪ የፖለቲካም ሆነ የትግል ታሪክ ከፍተኛ ስፍራ ነበራቸው የተባሉት አቶ መንግሥቴ በድርጅቱም ውስጥ በአመራርና የኃላፊነተ ቦታም ላይ ነበሩ። አቶ መንግሥቴ ለመፃህፍት በተለይም ለሼክስፒር ድርሰቶች ለየት ያለ ፍቅር ነበራቸው ይባላል። 'ብላክ ኤንድ ዋይት' የተሰኘውን የሲድኒ ኩክና ጋርትሊን ድርሰትንም ወደ አማርኛ ተርጉመዋል። ከቀድሞ ጓደኛቸውና ባለቤታቸው ወይዘሮ ጆርጅጋ ግደይ ጋርም ወደ አሜሪካ ተሰደዱ፤ እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2006 በሞት እስከተለይዋቸውም ድረስ አብረው ኖረዋል። በስደት በመጡበት አሜሪካ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሊረዳዱበት የሚችሉበትን የማሰባሰብና የማደራጀት ሥራ ጀምረው በጎርጎሳውያኑ 1986 በችካጎ የኢትዮጵያውያን ማኅበርን (Ethiopian Community Association of Chicago) ከመሰረቱት አንዱ ናቸው። እስከሞቱባት ዕለት ድረስም በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች በቦርድ ፕሬዚዳንትነት፣ በአማካሪ ቦርድና በበጎ ፈቃደኝነትም አገልግለዋል። ከዚሁ ጎን ለጎንም በቺካጎ በሚገኘው ደብረፅዮን መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያንም ውስጥ በዲቁናና የተለያዩ አገልግሎቶችንም ሲሰጡ ነበር። በፌስቡክ ላይ ሐዘናቸውን የገለፁ የችካጎ ነዋሪዎች ለሰው ችግር ቀድሞ ደራሽ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ አዋቂ፣ ተጫዋች፣ የተጣሉትን አስታራቂ፣ መካሪና አስተባባሪ በማለትም እየዘከሯቸው ይገኛሉ። አቶ መንግሥቴ በኮሮናቫይረስ በመጠቃታቸው በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ82 ዓመታቸው ሚያዝያ 12/2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአንዲት ልጅ አባት የነበሩት አቶ መንግሥቴ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 19/2012 ዓ.ም ከባለቤታቸው ጎን ተቀብረዋል። ካፕቴን ዮሴፍ ሲቡ- የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሰልጣኝ የላስቬጋስ ከተማ ነዋሪ የነበሩትና በደርግ ዘመን በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ በአሰልጣኝነት ያገለገሉት ካፕቴን ዮሴፍ ሲቡ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች አንዱ ናቸው። የ60 ዓመቱ ካፕቴን ዮሴፍ ከፍተኛ ድካም፣ ላብና፣ ሳልም ሲደራረብባቸው ወደ ህክም አምርተው ብሮንካይትስ መሆኑ ተነግሯቸው ነበር። በተጨማሪም የኮሮናቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ሐኪሞች ውጤቱን ከቀናት በኋላ እንደሚያሳውቋቸው ነግረዋቸው ነበር። ቤትም ከተመለሱ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ህመሙ አገረሸባቸው፣ መተንፈስም አዳገታቸው፤ የህክምና እርዳታም ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ወደቤታቸው ግን አልተመለሱም በወጡበት ህይወታቸውም ሚያዝያ2/2012 ዓ.ም በዚያው አለፈ። አስከሬናቸውም በሆስፒታል ውስጥ ይገኛል። ባለቤታቸው ወ/ሮ አበራሽ ኦሮሞም በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በትዳርም ለአስራ ሁለት ዓመታት ቆይተው ሦስት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን ሶስቱም ከአስር ዓመት በታች መሆናቸው ተነግሯል። በስማቸው የተቋቋመው የጎ ፈንድ ሚ ገፅ እንደሚያስረዳው ካፕቴን ዮሴፍ በኢትዮጵያ አየር ኃይል በካፕቴንነት ለዘመናት እንዳገለገሉና በኋላም ላስ ቬጋስ በሚገኘው ቤላጂዮ ሆቴል ለአስራ ሁለት ዓመታት ሰርተዋል። ካፕቴን ዮሴፍን በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎችም በፃፉት መሰረት የተወለዱት ሲዳማ ውስጥ ቦሪቻ በሚባል አካባቢ ሲሆን ከአየር ኃይል ካፕቴንነታቸው በተጨማሪ በተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከላትም ለዓመታት አሰልጥነዋል። ካፕቴን ዮሴፍ "የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ የብሔሮችን ጭቆና የሚፀየፉ እንዲሁም የሲዳማንም ሕዝብ በራስ የመተዳደር መብት በከፍተኛ ሁኔታ ይደግፉ እንደነበርም" ተጽፏል። በኮሮና ህይወታቸውን ያጡት አቶ ዳዊት ግዛው፣ አቶ ሊሻን ወንዳፍራሽ፣ አቶ ምንውየለት መሐሪና አቶ አሸናፊ ተፈራ አቶ ዳዊት ግዛው፡ በዋሽንግተን ዲሲ ካሉት የኢትዮጵያውያን ማኅበራት መካከል የአንዱ ዳይሬክተር የነበሩ ሲሆን፤ በርካታ ሥራዎችን ለማኅበረሰቡ ያበረከቱ በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የጤና ኢንሹራንስ እንዲያገኙ ብዙ የለፉ እንደሆኑም ተነግሯል። አቶ ሊሻን ወንዳፍራሽ፡ የቨርጂኒያ ነዋሪ፣ ባለትዳር፣ በቤተክርስቲያን በርካታ አስተዋፅኦዎችን ያደርግ የነበረ አገልጋይ። አቶ ምንውየለት መሐሪ፡ የአየር ኃይል ቴክኒሺያን፣ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኮሎራዶ በቅርቡ የሄደ፣ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ቤተሰቦቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ። አቶ አሸናፊ ተፈራ፡ የሜሪላንድ ነዋሪ፣ ባለትዳርና የአንዲት ህፃን ልጅ አባት፤ ለንደን ቆይቶ ከተመለሰ በኋላ በኮሮናቫይረስ ተይዞ በቀናት ውስጥ ህይወቱ አልፏል። ምንጭ፦ ዋሽንግተን ፖስት፣ ቪኦኤ አማርኛ፣ የዲሲ ግብረ ኃይል ተወካይ አቶ ጣሰው መላዕከሕይወት፣ በችካጎ የኢትዮጵያውያን ማህበርፌስቡክ፣ ጎፈንድ ሚ ገፆች፣ የተለያዩ ሰዎች የፌስቡክ ገፅ
news-55036271
https://www.bbc.com/amharic/news-55036271
ትግራይ ፡ "ሕግ የማስከበር ዘመቻው የተራዘመው ለንፁሃን ዜጎች ቅድሚያ በመስጠታችን ነው" የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ
በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለው ወታደራዊ ግጭት ሦስት ሳምንት ሊሆነው ተቃርቧል። መንግሥት ሕግ ማስከበር በሚለው ወታደራዊ እርምጃ ጋር ተያይዞ የሽምግልና ጥያቄዎች፣ በግጭቱ ስለተፈናቀሉ ሰዎች፣ ከማንነት ጋር የተያያዙ ናቸው የተባሉ እስሮችና ሌሎችም ጉዳዮች እየተነሱ ነው።
የቢቢሲዋ ካትሪን ባይሩሃንጋ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ጋር ባደረገችው ቆይታ በርካታ ጥያቄዎችን አንሰታላቸዋለች። ቢቢሲ፡ከሰሞኑ ዜና እንጀምር፤ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሲሪል ራማፎሳ የፌደራል መንግሥትንና የህወሓት አመራሮችን እንዲያሸማግሉ በሚል ሦስት የቀድሞ መሪዎችን የአፍሪካ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ አድርገው መሰየማቸውን አስታውቀዋል። የሊቀ መንበሩ መልዕክት ልዑካኑ አዲስ አበባ የሚመጡት ሊያሸማግሉ ነው ቢልም፤ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ግን ድርድርም እንደሌለ ተገልጿል። ይህ ልዩነት እንዴት መጣ? አቶ ማሞ፦ በዋነኝነት አፍሪካውያንን ወንድማቾቻችንና እህቶቻችን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ የተፈጠረባቸውን ስጋት መግለፃቸው የተለየ ነገር አይደለም፤ ስጋታቸውንም እንረዳለን። ይሄንንም ሁኔታ ያው የተለመደው የዲፕሎማሲ አካል አድርገን ነው የምናየው። ነገር ግን ለአህጉራዊ ድርጅታችን እንዲሁም ለሊቀ መንበሩ ካለን ክብር አንፃር ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ልዑካኑን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ እናስረዳቸዋለን፤ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርድሩን አይቀበሉትም። በይፋ እንደተነገረውም ይህ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር አንድ በአንድ የሚደረግ ስብሰባ ነው። ቢቢሲ፡ ልዑካኑ ሁለቱን አካላት ለማሸማገል ከመሰየማቸው አንፃር ትግራይ በመሄድ ከህወሓት አመራር አባላትም ጋር መገናኘት ይፈልጉ ይሆናል። ልዑካኑ ወደ ትግራይ እንዲሄዱ ትፈቅዱላቸዋላችሁ? አቶ ማሞ፦ የልዑካኑን የወቅቱን ጉብኝት በጥልቀት መረዳት ያስፈልጋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ መንግሥት ከህወሓት አመራሮች ጋር ለመነጋገር ብዙ ጥረት አድርጓል። በኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ላይ መምከር የሚያስችሉ ገንቢ ውይይቶችንም ለማድረግ ሞክሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተደጋጋሚ ከትግራይ ክልል አስተዳደር ጋር ጦርነት እንደማይፈልጉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ቢቢሲ፦ እዚህ ጋር ላቋርጥዎትና፤ ልዑካኑ ሁለቱን አካላት የማናገር ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል። ሆኖም ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ በረራዎች ቆመዋል። ታዲያ ልዑካኑ ወደ ትግራይ በመሄድ በግጭቱ የሚሳተፈውን ሌላኛውን ወገን ማግኘት ይችላሉ? አቶ ማሞ፦ በትግራይ ክልል ያለው ሕገወጥ አስተዳደር ጋር ያለው የፖለቲካ ልዩነት አይደለም። ይሄ ሕግን የማስከበር ዘመቻ ነው። በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጠረው አለመረጋጋት ተጠያቂ ወይም ቁልፍ ሚና የተጫወቱትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረግ ነው። ከወንጀለኞች ጋር አንደራደርም። ወደ ፍትህ ማምጣት ነው አላማችን፤ ድርድር የሚባል ነገር የለም። መንግሥትም በተደጋጋሚ የሚገልፀው አቋሙ ይህ ነው። በእኔ አስተሳሰብ አፍሪካውያን ወንድምና እህቶቻችን ህወሓት እጅ እንዲሰጥ ጫና ቢያደርጉ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ፤ ተጠያቂም ሊሆኑ ይገባል። ለወንጀለኞች ድርድር ሳይሆን ተገቢው ነገር ወደ ፍትህ ማምጣት ነው። ቢቢሲ፡ ልዑካኑ ወደ ትግራይ ክልል እንዲሄዱ ካልተፈቀደላቸውና ከህወሓት አመራር አባላት ጋር ውይይት ማድረግ ካልቻሉ የሚሉትንስ ነገር እንዴት ማከናወን ይችላሉ? ወደ መጀመሪያ ጥያቄዬ ልመለስና ልዑካኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ካናገሩ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል እንዲሄዱ ይፈቀድላቸዋል ወይ? አቶ ማሞ፦በትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት ወታደራዊ ዘመቻ እየተካሄደ ነው። ወታደራዊው ዘመቻ በቅርቡ ይቋጫል የሚል እምነት አለን። መንግሥት የሚያደርገው ሕግ የማስከበር ዘመቻ በቅርቡ ከተጠናቀቀ፣ በአገሪቱ አለመረጋጋት ላይ እጃቸው ያለበት የህወሓት አመራሮች ግጭቱ እንዲያቆም ከፈለጉ ማድረግ ያለባቸው ነገር ቢኖር እጃቸውን መስጠት ነው። ይህንን ለማድረግም ሆነ ለህወሓት አመራር አባላት አቋሙን ግልፅ ለማድረግ የትኛውም አካል ቢሆን ትግራይ ክልል መሄድ አያስፈልገውም። ቢቢሲ፦ ስለዚህ የሚሉት ለአሁኑ ልዑካኑ ወደ ትግራይ ክልል መሄድ አይችሉም ነው? አቶ ማሞ፦ እንዳልኩት ልዑካኑ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን ለማግኘት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩም እየተደረገ ስላለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ያስረዷቸዋል። ቢቢሲ፦ ወታደራዊውዘመቻ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ አይደለም በማለት የፌደራል መንግሥት ይገልፃል። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በግጭቱ ምክንያት በርካቶች ተፈናቅለዋል። የተለያዩ የሰብዓዊ ድርጅቶችም በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉና ችግር ውስጥ ያለውን የትግራይ ሕዝብ ለመርዳት የሚያስችል መተላለፊያ እየጠየቁ ነው። ሆኖም መንግሥት ድርጅቶቹ ወደ አካባቢው በመግባት ሰላማዊ ሰዎችን እንዲረዱ ፍቃድ አልሰጠም እያሉ ነው። ለምንድን ነው ይህ የማይፈቀድላቸው? አቶ ማሞ፦ አንዳንድ ነገሮችን ግልፅ ላድርግ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ሕግን የማስከበር ዘመቻ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ አይደለም። በተጨማሪም ይህ ዘመቻ ሁሉንም የህወሓት አባላትን የሚመለከት ሳይሆን በህወሓት ውስጥ ያሉ ወንጀለኞች ላይ ያነጣጠረ ነው። ይሄ ለሁሉም ግልፅ መሆን አለበት። በእነዚህ የህወሓት አመራሮች መወገድ የትግራይ ሕዝብ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ይሆናል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለሌላው ሕዝብ እንደሚጨነቀው ሁሉ ለትግራይ ህዝብም ያስባል። ጥያቄውንም ለመመለስ በተቻለው መጠን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለሕዝቡ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲያደርግም የቻልነውን እያደረግን ነው። በርካታ የትግራይ ክፍሎችም በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ናቸው። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት በአብዛኛው የትግራይ ክፍል የሚያስፈልገውን እርዳታ እንዲያገኙ ለማድረግ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አብሮ ይስራል። በአሁኑ ወቅት መቀለ ብቻ ናት በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ያልሆነችው። የኢትዮጵያ መንግሥት ነፃ ከሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር የሰብዓዊ እርዳታን ለሕዝቡ ለማቅረብ የመስራት እቅድ አለው። በዚህም በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉትም ሆነ ወደ ጎረቤት አገራት ለተሰደዱ ኢትዮጵያውያን የሚደርስ ይሆናል። ቢቢሲ፦ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ሰብዓዊ ድርጅቶች ሰላማዊ ሰዎች የእርዳታ አቅርቦት ለመድረስ የሚያስችል መተላለፊያ እንዲኖር እየጠየቁ ነው። ድርጅቶቹ እርዳታ ለማድረስ ማዕከላዊው መንግሥት የሚያስፈልገውን ሊያመቻች አልቻለም እያሉ ነው። አቶ ማሞ፦ ይሄ ትክክል አይደለም። ይህንን በሁለት መንገድ ልናየው ይገባል። ነፃ ባወጣናቸው አካባቢዎችና በመከላከያ ስር ባሉ አካባቢዎች መንግሥት በአሁኑ ወቅት የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እየሰራ ነው። ለአካባቢው ነዋሪ ምግብ፣ መጠለያና መድኃኒት ለማቅረብ ከተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ጋር እየሰራ ነው። ለምሳሌም ያህል አርብ ዕለት የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ልዑካንን የያዘ ቡድን ወደ ትግራይ ክልል የላከ ሲሆን ይህም በተለያዩ አካባቢዎች የሚያስፈልገውን ቁሳቁሶችና አቅርቦትም ለመረዳት ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ጋር አንሰራም የምንልበት ምክንያት የለንም። በመከላከያ ስር ባልሆኑት አካባቢዎች ጋር ስንመጣ ሰላማዊ ሕዝቦች የሚጠበቁበትን መንገድ ለማረጋገጥም ጦሩ እየሰራ ነው። ይህ ወታደራዊ ዘመቻ ያልተቋጨበት ዋነኛ ምክንያትም መንግሥት ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ በመስራቱ ነው። መንግሥት በመከላከያ ስር ባሉትም ሆነ ባልሆኑትም አካባቢዎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር ይሰራል። ቢቢሲ፡ በግጭቱ ሰላማዊ ሕዝብ እንዳይጎዳ እየሰራን ነው እያላችሁ ነው። ሆኖም በወታደራዊው ዘመቻ የአየር ጥቃት፣ ሮኬትና ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕላኖች) እየተጠቀማችሁ ነው። እንደዚህ አይነት ውጊያዎች ነጥሎ የመምታት አካሄዶች አይደሉምና በርካታ ንፁሃን ሰዎችም እየሞቱ ነው፤ ጉዳትም እየደረሰባቸው ነው። አቶ ማሞ፦ ይሄ ግጭት እንደመሆኑ መጠን ጉዳት መድረሱ አይቀርም። ሆኖም ለመከላከያ ኃይሉ የተላለፈለት ጥብቅ ትዕዛዝ ቢኖር ወታደራዊውን ዘመቻ በተቻለ መጠን ንፁሃን ዜጎችን በመጠበቅ ቅድሚያ እንዲሰጡ ነው። የሰላማዊ ዜጎች ደኅንነትና ጥበቃ ለወታደራዊው ዘመቻው ቁልፍ ጉዳይ ነው። መንግሥት ለንፁሃን ዜጎችም ከፍተኛ ኃላፊነት ስላለበትም ነው ህግ የማስከበር ዘመቻው ይህንን ያህል የወሰደው። ያለበለዚያ በሳምንት ውስጥ ይጠናቀቅ ነበር። የተነሳው የአየር ጥቃት ጉዳይ በዋነኝነት ኢላማው ወታደራዊ ማዕከላትንና የጦር መሳሪያ ቁሳቁሶችን ነው። ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ አያደርግም። ያንንስ ለምን እናደርጋለን? የትግራይ ሕዝብ ዜጋችን ነው። ዘመቻውን የምናድርገው ህፃናትን፣ የዕድሜ ባለፀጎችንና ሌሎችንም ሰላማዊ ሰዎችን በማይጎዳ መልኩ ነው። ቢቢሲ፦ ይሄን ግጭት አስቸጋሪና ፈታኝ የሚያደርገው መሬት ላይ እየተፈጠረ ስላለው ጉዳይ መረጃ ማግኘትና ማጣራት አለመቻል ነው። የትኛውም አይነት የመገናኛ ዘዴ መቋረጡ እንዲሁም ጋዜጠኞች በቦታው እንዳይገኙ መደረጉ ምን እየተከናወነ ነው? የሚለውን ለማወቅ አዳጋች አድርጎታል። ለምንድን ነው ከቀሪው ዓለም መለየት ያስፈለገው? በትግራይ እየተከናወነ ስላለው ቀሪው ዓለም እንዳያየው የማትፈልጉት ጉዳይ ምንድን ነው? አቶ ማሞ፦ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ነጥቦችን ማንሳት እፈልጋለሁ። የመገናኛ ዘዴው በተወሰኑ አካባቢዎች የተቋረጠው ህወሓት ራሱ የመገናኛ ልማቱን ለራሳቸው ወታደራዊ ዘመቻ ሲሉ የተወሰነውን በማውደማቸው ነው። ይሄ አንደኛው ምክንያት ነው። ሌላኛው ምክንያት ትግራይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመሆኗ ወንጀለኛ ቡድኖች ጥቃት እንዳያደርሱና የተለያዩ ቡድን አባላትንም በማነሳሳት በተለያዩ አገሪቷ ክፍል አለመረጋጋትን እንዳይፈጥሩ ለማድረግ መከላከያው እንደዚህ አይነት እርምጃ ሊወስድ ይችላል። ይሄ ካሁን በኋላ ጉዳይ አይሆንም ምክንያቱም ቀደም ብዬ እንዳልኩት አብዛኛው የትግራይ ክፍል በመከላከያ ስር ሆኗል። በሚቀጥሉት ቀናትም ጋዜጠኞች ወደ ክልሉ የመሄድ እድሉ ይኖራቸዋል። ቢቢሲ፦ በትግራይ እየተካሄደ ባለው ነገር ተጠያቂ ላለመሆንና ግልፅነትን በመሸሽ አይደለም? አገሪቱ ውስጥ ግጭት ሲፈጠር ኢንተርኔት መዝጋት ለኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ አይደለም። በኦሮሚያም ላይ የተከሰተውን አይተነዋል። መንግሥት ምርመራ በማይፈልግበት ወቅት ሰዎች መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንዳያውቁ የማድረግ ሁኔታም ነው። አቶ ማሞ፦ በዚህ አባባል አልስማማም። እንዳልኩት ይህ ወታደራዊ ዘመቻ ነው። የወታደሩን የየቀን እቅድና አፈፃፀም መናገር አልችልም። ግን ከዚህም ጋር ተያይዞ መከላከያው እርምጃውን የተሳካ ለማድረግ ማንኛውንም ዘዴ የመጠቀም መብት አለው። ሆኖም ወደ ነጥቡ ስመለስ ምንም መደበቅ የምንፈልገው ነገር የለም። የክልሉ ደኅንነት ከተረጋገጠ፣ ሕግና ሥርዓት ከተመለሰ በኋላ ጋዜጠኞች ወደ ትግራይ ክልል መጥተው መጎብኘታቸውን በደስታ የምንቀበለው ጉዳይ ነው። ምርመራም ሆነ ተጠያቂነቱ በህወሓት ላይ ነው መኖር ያለበት። ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የንፁሃን ጭፍጨፋ የተፈፀመው በህወሓት ነው። ጋዜጠኞች ይህንን ሄደው ሊመረምሩ ይገባል። የአካባቢውንም ነዋሪ ሊያነጋግሩ ይገባል። ምንም የምንደብቀው ነገር የለም። ወታደራዊው ዘመቻ እየተካሄደ ያለው ሕጋዊ በሆነ መንገድ፣ ለንፁሃን ዜጎች ቅድሚያ በመስጠት ነው። ከመንግሥት በኩል የምንደብቀው ጉዳይ የለም። ቢቢሲ፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች፤ በማንነታቸው ብቻ ለእስር ተዳርገዋል እየተባለ ነው። አንዳንዶቹም ያሉበት አይታወቅም። ከዚህም በተጨማሪ በማንነታቸው ቤቶቻቸው እንደተፈተሹ፤ እንዲሁም በብሔራቸው እየተነጠሉ እየተጠቁ እንደሆኑ ሪፖርቶች እየወጡ ነው። ይህ አንድ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ አይደለም የምትሉ ከሆነ፤ እንዴት ይታያል? አቶ ማሞ፦ ይህ መንግሥት መቼም ቢሆን በብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን አይሰነዝርም። በብሔር አይነጥልም። በጣም የሚገርም ነው። ህወሓት ነው ብሔርን መሰረት ያደረገ ሥርዓት የፈጠረው። መንግሥት እያደረገ ያለው ነገር ማኅበረሰቡ እኩል በሆነ መንገድ የሚተሳሰርበትን ራዕይን የመፍጠር ሥራ ነው እየሰራ ያለው። በምንም መንገድ ቢሆን መንግሥት ዜጎችን ትግራዋይ በመሆናቸው ኢላማ አያደርግም። የትኛውም የሕግ ማስከበር እየሰራን ያለነው መረጃን በተመረኮዘ መልኩ ነው፤ ግለሰቦቹ ያላቸውንም ግንኙነትም በማየት የተጠና ነው። ግን ያው ግጭት እንደመሆኑ መጠን ወንጀል ተፈፅሞ ሊሆን ይችላል የሚሉ መረጃዎች ሊወጡ ይችላሉ። ሕዝቡ የተጠራጠሯቸውን ወንጀሎች ሊያሳውቅ ይችላል። በዚህ አጋጣሚ የፀጥታ ኃይሎች ተጨማሪ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። እነዚህን እርምጃዎችንም በምንወስድበት ወቅት በተገቢውና በተጠና መልኩ ለማድረግ እንሞክራለን። ህወሓት ብሔርን መሰረት ያደረገ ፓርቲ ከመሆኑ አንፃር በርካታ አባላቶቹ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ከውጭ ሲታይ መንግሥት አንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ ወይም ኢላማ ያደረገ ይመስላል። ነገር ግን ከፀጥታ ኃይሉ አባላት መካከል ክፍተት ካለ ማስተካከያዎችን እንወስዳለን። ከሕዝቡ ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን እያደረግን ነው። ሕዝቡ ቅሬታውን የሚያሰማበትን ማዕከላት እያቋቋምን ነው። ቅሬታዎችን ስንሰማም ማስተካከያዎችን እናደርጋለን። ኢ-መደበኛ በሆኑ መልኩ የሚገኙ መረጃዎችንም የማጣራት ሥራም እንሰራለን። ችግሮች ካሉ የማስተካከያ እርምጃዎችን እንወስዳለን። ነገር ግን በእርግጠኝነት የምናገረው መንግሥት በተቀናጀ መልኩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እርምጃዎችን አይወስድም። ይህ ዘመቻ በተወሰኑ የህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረ ነው እንጂ በሕዝቡ ላይ አይደለም። ቢቢሲ፦ ወታደራዊው ዘመቻ በተወሰኑ የህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን በትግራይ ክልል አካውንታቸውን የከፈቱ ሰዎች እንዲታገድ ተደርጓል። በአየር መንገዶች ብሔርን ለመለየት ብሔራዊ መታወቂያ እየተጠየቅን ነው የሚሉ አሉ። አንዳንዶችም በማንነታችን መሰረት ተደርጎ እንዳንጓዝ ተደርገናል ይላሉ። ከትግራይ ሕዝብ ጋር ግንኙነት ስለማጠናከር እየተነገረ ይህ ሁኔታ መነጠል አይሆንም? ምንም እንኳን ጦርነቱን ብታሸንፉም ሕዝቡን የምታጡበት መንገድ አይፈጠርም? አቶ ማሞ፦ ለፀጥታ ኃይሎች ግልፅ የሆነ ትዕዛዝ ነው የተላለፈላቸው። የፀጥታ ኃይሉ ባገኘው መረጃ መሰረት ተመርኩዞ እርምጃ እንዲወስድ ነው። ብሔርንና ማንነትን መሰረት ያደረጉ ነገሮችን እንዲህ በቀላሉ የምናየው አይደለም። የምናወግዘውም ጉዳይ ነው። በጭራሽ ይሄ ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው። ሆኖም ከተለያዩ የተሳሳቱ መረጃዎች ልንጠነቀቅ ይገባል። ለምሳሌ ከጥቂት ቀናት በፊት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ 50 ሺህ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች በአዲስ አበባ ታስረዋል የሚሉ መግለጫዎች ወጥተዋል። ይሄ ከእውነት የራቀ መረጃ ነው። ከጠቅላይ አቃቤ ህግ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ300 ያነሰ ነው። ሁሉም ደግሞ ከትግራይ አይደሉም። ከእነዚህ ውስጥ በርካቶቹ ግለሰቦች የታሰሩት ሕገወጥ መሳሪያ በመያዝ ነው። በጣም ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ሐሰተኛ መረጃዎችን የመንዛት ዘመቻዎች እየተካሄዱ ነው። ከመረጃ ጋር ባልተያያዘ የማንንም ባንክ አካውንት አላገድንም መንግሥት ያገደው የባንክ አካውንት ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸውን የተወሰኑ ተቋማትን ነው። ከዚህ በተለየ የትግራይ ተወላጆች ባንክ አካውንት አልታገደም። ይሄ ከእውነት የራቀ ነው። ቢቢሲ፦ የተሳሳቱ መረጃዎችን ሲያነሱ መንግሥት እራሱ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲሰራጩ የሚያደርግ ሁኔታን ፈጥሯል። ጋዜጠኞች በተለያዩ አካባቢዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መዘገብ አይችሉም። ጋዜጠኞችም እየታሰሩ ነው። በትግራይ ያለው የመገናኛ ዘዴም ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል። አቶ ማሞ፦ የመገናኛ ዘዴው የተቋረጠው በትግራይ ክልል ብቻ ነው። በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ጋዜጠኞች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መዘገብ ይችላሉ። ሙያው የሚጠብቅባቸውን ግዴታዎችን ማሟላት አለባቸው። የተለያዩ አገራት ሪፖርተሮችም በአዲስ አበባ በየቀኑ እየሰሩ ነው። የመገናኛ ዘዴው ሙሉ በሙሉ የተቋረጠው በተወሰኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ነው። እንዳልኩት ወታደራዊው ዘመቻ ከተጠናቀቀ በኋላ ጋዜጠኞች ወደተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ቢቢሲ፦ የመጨረሻ ጥያቄ በአየር መንገድ የቀበሌ መታወቂያ ማሳየት ለምን አስፈለገ? አቶ ማሞ፦ለሁሉም ያ አይመስለኝም። የደኅንነት ሠራተኞች በመጀመሪያ አካባቢ የተወሰኑ ሰዎችን መታወቂያ እንዲያሳዩ ያገኙትን መረጃ ተመርኩዘው ጠይቀዋቸው ይሆናል። ይህንንም የሚያደርጉት የሰዎችን መሰረታዊ መብት በጠበቀ መልኩና የመንቀሳቀስ መብታቸውን በማይጋፋ መልኩ ነው። ይሄ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ አይደለም። ቢቢሲ፦ መንግሥት መቼ ነው መቀለን ለመቆጣጠር የሚያስበው? ከዚያ በኋላስ ምን ይፈጠራል? አቶ ማሞ፦ የመንግሥት ሕግን የማስከበር ወታደራዊ ዘመቻ በተያዘለት እቅድ እየተከናወነ ነው። የመከላከያ ኃይል በርካታውን የትግራይ ክፍልን ተቆጣጥሯል። ከእነዚህም መካከል ዋነኞቹ ከተሞች ለምሳሌ አድዋ፣ አክሱምና አዲግራት ይገኙበታል። በመከለከያ ስር ያልሆነችው ዋና ከተማዋ መቀሌ ብቻ ናት። በቅርቡም እንደሚጠናቀቅ እንጠብቃለን።
news-53604867
https://www.bbc.com/amharic/news-53604867
ማርስ ላይ ሕይወት ነበረ? 2 ቢሊየን ዶላር የወጣባት ሮቦት መልስ ይኖራታል
ማርስ ላይ ሕይወት ነበረ? 2 ቢሊዮን ዶላር የወጣባት ሮቦት መልስ ይዛ ትመጣ ይሆናል፡፡
የአሜሪካ የሕዋ ኤጀንሲ 'ፐርሴቪራንስ' ሲል የጠራውን ወሳኝ ሮቦት ወደ ሕዋ አምጥቋል፡፡ ለዚህ ጽሑፍ ምቾት ሲባል እኛ ይቺን ሮቦት ብጤ መሣሪያ ‹ጽናት› እያልን እንጠራታለን፡፡ የ‹ጽናት› ዋና ተልእኮዋ ከቀይዋ ፕላኔት ማርስ ናሙና እየሰበሰቡ አንድ ቦታ ማጠራቀም ነው፡፡ "ጽናት" አንድ ቶን ትመዝናለች፤ 6 ተሸከርካሪ እግሮች አሏት፡፡ የዋዛ እንዳትመስላችሁ፡፡ እጅግ ውስብስብ ናት፡፡ የተወነጨፈችው ሐሙስ ዕለት ከአሜሪካ፣ ፍሎሪዳ በአትላስ ሮኬት ላይ ሆና ነው፡፡ ‹ጽናት› ቀይዋ ፕላኔት የምትደርሰው በሚቀጥለው ዓመት በየካቲት ወር አካባቢ ነው፡፡ ጉዞው 7 ወራት ይወስዳል፡፡ ልክ ማርስ እንዳረፈች ታዲያ እየተሸከረከረች ዐለትና አፈር ቆንጥራ ወደ የቱቦ ቋት በማስገባት ታጠራቅማለች፡፡ እሷ ያጠራቀመችው ተሰብስቦ የሚመጣው ምናልባት ይህን ጽሑፍ የሚያነቡ ሰዎች ሲሶዎቹ ሞተው ሲያበቁ ይሆናል፤ በ2031 ዓ.ም ፡፡ ባለፉት 11 ቀናት ብቻ ወደ ማርስ ከተደረጉ ተልእኮዎች ‹ጽናት› ሦስተኛዋ ናት፡፡ ከሰሞኑ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስም ሮኬት አመንጥቃለች፡፡ ቻይናም ለመጀመርያ ጊዜ በታሪኳ በተናጥል ወደ ማርስ ተልእኮ ያደረገችው ከሳምንት በፊት ነበር፡፡ ‹ጽናት› ከፍሎሪዳ፣ ኬፕ ካናቭራል አየር ኃይል ጣቢያ ጠዋት በአገሬው አቆጣጠር 07: 50 ላይ ነበር ወደ ሕዋ የተመነጠቀችው፡፡ የናሳና የኢሳ ሳይንቲስቶች ‹ጽናት› በሰላም ማርስ ላይ እንድታርፍ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው፡፡ ማርስ ከፍሎሪ ብዙ ትርቃለች? ጎረቤት ማርስ ቅዝቃዜዋ ለጉድ ነው፡፡ በዚያ ላይ ከባቢ አየሯ ከምድር ከባቢ ጋር ሲነጻጸር በመቶ ጊዜ የሳሳ ነው፡፡ በመጠኗ የመሬትን ግማሽ ብታክል ነው፡፡ ከፀሐይ ከኛ ፕላኔት በግማሽ ርቃ ነው የምትገኘው፡፡ ለዚህም ይሆናል የሚበርዳት፡፡ ለዚህም ይሆናል ፀሐይን ለመሾር ከኛ ዘለግ ያለ ጊዜ የሚወስድባት፡፡ ለመሆኑ ማርስ ከመሬት በምን ያህል ኪሎ ሜትር ትርቃለች? እውነት ለመናገር የዚህ ምላሽ ቋሚ አይደለም፡፡ እንደ ወቅቱ ይለያያል፡፡ ምክንያቱም እኛም በምህዋራችን ስንሾር፣ ማርስም ትሾራለች፡፡ መሬትና ማርስ ፀሐይን ሲሾሩ በተለያየ ፍጥነትና በተለያየ ርቀት ነው ታዲያ፡፡ ይህም በመሀላቸው ያለው ርቀት ተለዋዋጭ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አንዳንዴ ማርስ ከኛ 400 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ነው የምትርቀው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ስንቀራረብ ጎረቤት ማርስ በ56 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ትሸሸናለች፡፡ ለዚህ ነው ‹ጽናት› በራሪ ሮቦት ከፍሎሪዳ ማርስ ለመድረስ 7 ወራት የሚወስድባት፡፡ አሁን በብዛት ማርስ ተብሎ የሚታየው ፎቶ፣ ማርስ መሬትን በጣም በቀረበችበት በፈረንጆች በ2003 አካባቢ የሀብል ስፔስ ቴሌስኮፕ ያነሳውን ፎቶ ነው፡፡ ማርስ መሬትን በዚያን ያህል ቅርበት የተጠጋቻት ከ60ሺህ ዓመታት በኋላ መሆኑ አስደናቂ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ማርስ መሬትን በእዚህ ቅርበት የምትጠጋት መቼ ይመስላችኋል? እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2287 ዓ. ም፡፡ ያን ጊዜ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊም ሆነ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ግብአተ መሬታቸው ተፈጽሟል፡፡ በማርስ ወለል ላይ ማረፍ ለምን ፈተና ሆነ? የዚህ መልስ ከመልክአ-ማርስ ጋር ይያያዛል፡፡ መልከአ ምድር እንደምንለው መልከአ ማርስም እንላለን፡፡ ለምን አንል? በማርስ ማረፍ በሳይንቲስቶች ዘንድ ‹‹የ7 ደቂቃ ሽብር›› እየተባለ ይጠራል፡፡ በርግጥም አሸባሪ ስለሆነ ነው፡፡ ለምን መሰላችሁ? አንደኛ ወደ ማርስ የምንልከው መንኩራኩርም ሆነ ሌላ በሰዓት 10ሺዎች ኪሎ ሜትር ይምዘገዘጋል፡፡ ይህ በራሱ ችግር አይደለም፡፡ የማርስ ከባቢ ውስጥ ሲገባ ነው ጭንቅ የሚሆንበት፡፡ የማርስ ከባቢ አየር ሲዘልቅ መንኩራኩሩ ትክክለኛውን አንግል ማግኘት አለበት፡፡ በጣም ቁልቁል ሆኖ ወደ ማርስ ቢገባ ቀልጦ ይነዳል፡፡ ትንሽ በስላሽ ወይም በጎንዮሽ ከሆነ ደግሞ ነጥሮ ይመለሳል፡፡ ሁለተኛ የማርስ ከባቢ አየር ከመሬት ከባቢ ጋር ሲነጻጸር በመቶ እጅ የሳሳ ነው፡፡ ለዚህ ነው ነገሩ ሁሉ ፈታኝ የሚሆነው፡፡ ሮቦቱ ከባቢ አየሩን አልፎ ገብቶም ቢሆን በቀላሉ ለማረፍ መልክአ ማርስ አይመችም፡፡ ለምን አይመችም? አንደኛ ማርስ በጣም አለታማ ነው፤ ሁለተኛ ጠፍጣፋ አይደለም፣ ሦስተኛ በምድር ላይ ያለ ገደል ቢቀጣጠል ማርስ ላይ ያሉ ገደሎችን አይበልጥም፤ በጣም ገደላማ፣ በጣም ሸለቋማ ከመሆኑም በላይ ሐይቅ መሰል ነገር፣ ሽንቁር፣ ስንጥቅጥቅ፣ ዋሻ…ብቻ ምን አለፋችሁ መልክአ ማርስ የሌለ ዓይነት ውጥንቅጥ የለም፡፡ ‹ጽናት› ሮቦት ማርስ የተላከችው ምን እንድትሰራ ነው? ጽናትን እንደ ቆሻሻ ለቃቃሚ አስቧት፡፡ ዐለት ከዚያም ከዚህም ለቃቅማ ግን ይዛው አትመጣም፡፡ በመልክ በመልኩ ትሰድረዋለች፡፡ ውስጡ ትቦ ያለው ሰፊ ቧንቧ ነገር አላት፡፡ የለቃቀመችውን ማስቀመጫ፡፡ ይሄን ማሸጊያ በአለትና ሌሎች ቁሶች እየሞላች መተው ነው፡፡ ይህን ሁሉ ለፍታ ግን የለቃቀመችውን ይዛ አትመጣም፡፡ ባዶ እጇን ነው የምትመጣው፡፡ የ ‹ጽናት› ሥራ መልቀም፣ ለቅሞ መጠቅለል፣ ጠቅልሎ እዚያ አከማችቶ መመለስ ነው፡፡ ናሳ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የ‹ጽናት› ተልእኮ እጅግ ወሳኝ ሆኖበት ቅድሚያ ሰጥቶታል፡፡ ኮሮናቫይረስ አሜሪካንን እያመሰ ባለበት ሰዓት አዲስ የሥራ እቅድና ፈረቃ በማዘጋጀት የ‹ጽናት› ተልእኮ በታሰበለት ጊዜ እንዲሳካ ሆኗል፡፡ ‹‹አልዋሻችሁም፤ ፈታኝ ጊዜ ነበር፡፡ አስጨናቂ ጊዜ ነበር፡፡ ተመልከቱ ምን እንዳሳካን፣ እንዴት እንደኮራን ልነግራችሁ አልችልም፡፡ ይህ እጅግ ደስ የሚል ነገር ነው›› ብለዋል የ ‹‹ጽናት›› ተልእኮ አስተባባሪ ጂም ብራይደስቲን፡፡ ጽናት አሁን ትኩረት እንድታደርግበት የተፈለገው የማርስ ክፍል ‹‹ጀዜሮ ክሬተር›› ይባላል፡፡ አርባ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ስፍራ ነው፡፡ መሬት ላይ ብናስበው ልክ ሀሮማያ ሐይቅ አካባቢ ማንዣበብ ማለት ነው፡፡ ይህ ‹ጀዜሮ› በመልከአ ማርስ ከሚገኙ ቦታዎች ሁሉ ድሮ የዛሬ ቢሊዮን ዓመት ሐይቅ ነበረበት ተብሎ የሚታሰብ ቦታ ነው፡፡ አሁንማ እንኳን ጀዜሮ ዓለማያ ሐይቅም ደርቋል፡፡ ‹ጽናት› ሮቦት የድሮው የማርስ ሐይቅ (ጀዜሮ) አካባቢ እንድታንዣብብ ለምን ተፈለገ? ምክንያቱም ጀዜሮ ሐይቅ መሰል ጎድጓዳ ስፍራ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የተወሰዱ የሳተላይት ምሥሎች ይህ ስፍራ ምናልባት ከቢሊዮን ዓመታት በፊት ሐይቅ እንደነበር ጥቁምታን በመስጠቱ ነው፡፡ ሐይቅ ከነበረ ደግሞ ሕይወት ነበረ ማለት ነው፡፡ ይህን የሚያረጋግጥ ነገር ካለ ሊኖር የሚችለው እዚህ አካባቢው በሚገኙ ዓለቶች ነው የሚሆነው፡፡ አሁን የሳይንቲስቶቹ ተስፋ እዚህ ሐይቅ ነበረ ተብሎ በሚታመንበት ስፍራ የሚገኙ የዐለት ቅሪቶች በዚች ‹ጽናት› ባሏት ሮቦት ተለቅሞ እንዲጠራቀም ነው፡፡ በእርግጥ በማርስ ከአንድ ከቢሊዮኖች ዓመት በፊት ደቂቀ አካላት ኖረዋል? ሕይወትስ ነበረ? ለሚለው አንዳች ፍንጭ ይሰጣል ‹ጽናት› ሮቦት የምትለቃቅመው ነገር፡፡ ጽናት በማርስ አካል ላይ እንደ ሄሊኮፍተር እየተሸከረከረች በዚያ የምትጸናው ለአንድ የማርሻን ዓመት (የምህዋር ዘመን) ይሆናል፡፡ ይህም ማለት በመሬትኛ አቆጣጠር ሁለት ዓመት አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ ናሳ እንደ ጽናት ዓይነት ሮቦት ወደ ማርስ ሲልክ የመጀመርያው አይደለም ታዲያ፡፡ ኾኖም ‹ጽናት›ን ከሌሎቹ ልዩ የሚያደርጋት የተገጠሙላት እጅግ ረቂቅና ውስብስብ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ሕይወት የነበረው ነገር ቅሪት ብታገኝ ‹ቀጨም› ማድረግ ትችላለች፡፡ ያ ማለት ግን በ ‹ጽናት› የተገኘ አካል ሁሉ ሕይወት የነበረው ቅሪት ነው ማለት አይደለም፡፡ ‹ጽናት› ወደፊት ወደ ምድር ተሰብስቦ የሚመጣን የዐለታ ዐለት ቅሪት ከሰበሰበች በኋላ በመልክ በመልክ ሰብስባ እዚያው አሽጋ ታስቀምጠዋለች፡፡ ወደፊት በሌላ ተልእኮ፣ በሌላ ሮቦት ወደ ምድር ተሰብስቦ ይመጣና እዚህ ቤተ ሙከራ ውስጥ ለዓመታት ፍተሻ ይደረግበታል፡፡ ‹ጽናት› ከሌሎች በምን ትለያለች? ጽናት እንዲሁ ስትታይ የዋዛ ነው የምትመስለው፡፡ የዋዛ ግን አይደለችም፡፡ ብዙ ሰዎች ሲያይዋት ይህቺማ በ2012 በፈረንጆች ወደ ማርስ ናሳ የተላከችው ጌል ክሬተር ራሷ አይደለችም እንዴ ይላሉ፡፡ በቅርጽ ስለሚመሳሰሉ ነው እንጂ ‹ጽናት› ከ ‹ጌል› ትለያለች፡፡ ከዚህ በፊት ወደ ናሳ ከተላኩ ሮቦቶች የተራረፉ የሰውነት አካላት ቢገጠሙላትም አዲስ ናት፡፡ ለምሳሌ እጅግ የጠራ ምሥል አንስተው የሚያስቀሩ 23 ካሜራዎች አሏት፡፡ መቅረጸ ድምጽም እንደዚያው፡፡ ‹‹ የተወሰኑ ድምጾችን እናገኛለን ብለን እንጠብቃለን፡፡ ለምሳሌ ‹ጽናት› ሮቦት በማርስ ወለል ላይ ስታርፍና እንደገና ለመብረር ስትነሳ፣ እንዲሁም ወዲያና ወዲህ ስትቅበዘበዝ የሚያሳዩ ምሥሎችም ድምጾችም ይኖሩናል›› ይላሉ የቴክኒካል ጉዳዮች ኃላፊ ጂም ቤል፡፡ ናሳ በማርስ ላይ ሕይወት ነበረ ወይ ከሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ባሻገር ወደፊት በማርስ ላይ ሰፊ ምርመራ አድርጎ ለሌሎች ሰውን ለሚጠቅሙ ጉዳዮች ቀይዋን ፕላኔት ለማሰናዳት ይሻል፡፡ ለምሳሌ ማርስን ከሞላት የካርቦንዳይኦክሳይድ ከባቢ ውስጥ ኦክሲጅንን መፍጠር ይቻላል ወይ የሚለው ይጠናል፡፡ ማርስ 95 ከመቶ ካርቦንዳይኦክሳይድ ነው የሞላት፡፡ ለምሳሌ በዚህች ጽናት ሮቦት ውስጥ የተለያዩ ጠፈርተኛ ቱታዎች ይገኛሉ፤ ቱታ ማርስ ውስጥ ምን ይሰራል ይሉ ይሆናል፡፡ ቱታዎቹ የተያዙበት ዓላማ ለማርስ አስቀያሚ የአየር ንብረት የትኛው የጠፈርተኛ ቱታ የተሻለ ነው የሚለውን ለመመርመር ነው፡፡ ጀዜሮ የማርስ 'ሐይቅ' ሳይንቲስቶች ላይ ለምን የተለየ ጉጉት ፈጠረ? ለመሆኑ ስሙ ራሱ ከየት መጣ? ጀዜሮ በቦስኒያ ሄርዘጎቪኒያ ያለች ከተማ ስም ነው፡፡ በስላቪክ ቋንቋ ጀዘሮ ማለት ሐይቅ ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው ማርስ ላይ ያለው ጎድጓዳ ስፍራ ጀዜሮ የተባለው፡፡ ይህ 500 ሜትር ጥልቀት ያለው ጎድጓዳ ስፍራ ሳይንቲስቶቹን በጉጉት ሊገድላቸው ምን ቀረው? የውሀ ቅንጣት የሚመስል ነገር ትርጉሙ ብዙ ነው፡፡ አንዳች ሕይወት አከል ነገር ነበረ? ካልነበረ እንዴት የውሀ አካል ይኖራል? ተመራማሪዎቹን ያጓጓቸው ይኸው ነው፡፡ ‹ጽናት› በዚህ ስፍራ ነው አብዛኛውን ዘመኗን የምታሳልፈው፡፡ ጀዘሮ ሐይቅ ነበር ካልን እዚያ አካባቢ ሸክላና ካርቦኔትስ ዐለቶች ይገኛሉ ማለት ነው፡፡ እነዚህ አለቶች ደግሞ ሕይወት ያለው ቅንጣትን ጠብቆ የማቆየት ባሕሪ አላቸው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ባለፉት ቢሊዮን ዓመታት ውስጥ በቀይዋ ፕላኔት ሰው አልያም፣ ሰው መሰል ፍጡር ወይም ሌላ አካል ነበረ ወይ ለሚለው ፍንጭ ይሰጣል፡፡ ጥርጥር የለውም፡፡ ‹ጽናት› ሮቦት በማርስ የለቃቀመችው መቼ መሬት ይመጣል? ‹ጽናት› ለቃቅማ የምታመጣቸው ዐለቶች በማርስ በአንድ ወቅት የአንድ የሕይወት መኖር ፍንጭ ከሰጡ በሚል ምድር ላይ የቤተሙከራ ምርመራ ያደርጋሉ ብለናል፡፡ ለዚህም ነው ጽናት የተመረጡ ዓለቶችን ትንሽ ምርመራ እያደረገች አንድ ቦታ እንድታጠራቅማቸው የተፈለገው፡፡ የምታጠራቅማቸው ደግሞ በጀዜሮ ጎድጓዳ ሐይቅ መሰል አካባቢ ባለ ሰፊ ቦታ ይሆናል፡፡ ከዚያ ወደፊት ናሳ (የአሜሪካ የሕዋ ማዕከል) እና ኢሳ (የአውሮፓ የሕዋ ማዕከል) እነዚህን በ ‹ጽናት› የተቆለሉ አለቶችን ሄደው ያመጧቸዋል፡፡ ሌላ ሮቦት ይላካል፡፡ የሚቆለሉት ደግሞ በአንድ ቧንቧ መሰል ሰፊ ትቦ ያለው መሳሪያ ውስጥ ነው ብለናል፡፡ መቼ ነው ጽናት የቆለለቻቸውን የአለት ትቦዎች ለማምጣት የሚኬደው ከተባለ የዛሬ 26 ዓመት ነው መልሱ፡፡ በ2026፡፡ ያን ጊዜ የማርስ ሮኬት እና ሳተላይት ተጣምረው እነዚህን ትቦዎች ወደ መሬት ለማምጣት ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ በ2026 ተሳፍረው ሄደው በ2031 አካባቢ ለመመለስ ነው እቅዳቸው፡፡ የዚያ ሰው ይበለን፡፡ ‹‹ነገሩ ውስብስብ ነው፤ የሚሳተፉት ሮቦቶች ብዛትና ውስብስብነት ስታይ የአፖሎ ጨረቃ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ መርገጥ ዓይነት ልትለው ትችላለህ›› ብለዋል ዴቪድ ፔከር፡፡ ዴቪድ የአውሮጳ የሕዋ ኤጀንሲ የሰውና ሮቦት አሰሳ ዳይሬክተር ናቸ። ናሳና ኢሳ ናሙናዎችን ከማርስ ለማምጣት 7 ቢሊዮን ዶላር ከስክሰዋል፡፡ ይህ ወጪ ለ‹ጽናት› ሮቦት የወጣውን 2.7 ቢሊዮን ዶላርንም ይጨምራል፡፡ ምናልባት ከሁለት ዐሥርታት በኋላ ስለ ጎረቤታችን ማርስ የምናውቀው ነገር ብዙ፣ በጣም ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡ ማርስ እኛን የመሰሉ ጎረቤቶች ኖረውበት ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል?
news-53447244
https://www.bbc.com/amharic/news-53447244
ዐቃቤ ሕግ አምነስቲን በተቸበት ሪፖርት ላይ ከፊል ተዓማኒነት ያላቸው ጉዳዮች አሉ አለ
አምነስቲ ኢንተርናሽናል 'ሕግ ከማስከበር በዘለለ' በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በከፊል ተዓማኒነት ያላቸው ክስተቶች እንዳሉበትና ሪፖርቱ ከመውጣቱ በፊት መንግሥት ለማረጋገጥ ምርመራ ሲከናወንባቸው የነበሩ መሆናቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገለጸ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይህንን ያለው በግንቦት ወር ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ውስጥ ይፈጸማሉ ያላቸው የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ ያወጣውን ሪፖርት በተመለከተ ቅኝት አድርጎ ያገኘውን ውጤት ይፋ ባደረገበት መግለጫው ላይ ነው። በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሪነት መከናወኑ በተገለጸው የማጣራት ሥራ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት "መንግሥት ሕግ ለማስከበር የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ሁሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርጎ የማጠልሸት ዝንባሌ የሚስተዋልበት፣ በአብዛኛው ገለልተኘነት የጎደለው፣ የማስረጃ ምዘና ችግር ያለበት፣ የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታና ዐውድ ያላገናዘበ እንዲሁም መሠረታዊ ግድፈቶች ያሉበት" ነው ሲል ከሷል። ነገር ግን መግለጫው የድርጅቱን ሪፖርት ሙሉ ለሙሉ ውድቅ አላደረገውም በዚህም መሰረት በዘገባው ውስጥ ከተካተቱት የመብት ጥሰት ወቀሳዎች የተወሰኑት በከፊልም ቢሆን ተዓማኒነት ያላቸው ሆነው መገኘታቸውን ገልጾ፤ "ከእነዚህ በከፊል ተዐማኒነት ካላቸው ጉዳዮች መካከል በርካቶቹ በመንግስት ታውቀው ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የምርመራ ሥራ ሲከናወንባቸው የነበሩ ናቸው" ብሏል። መግለጫው በተጨማሪም ሪፖርቱ ገለልተኛነት የጎደለው፣ ተዓማኒነት የጎደላቸው የሆኑ ምስክርነቶችን በመያዝ እጅግ ውስብስብ በሆኑ ግጭቶችና የፀጥታ ችግሮች ዙሪያ የተሳሳቱ መደምደሚያዎች ላይ መድረሱን አመልክቶ፤ በሕግ ማስከበር ሂደት በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎችን የመብት ጥሰት አድርጎ ማቅቡንና "የሌሉ ጉዳዮች እንዳሉ በማስመሰል የሚያቀርብ መሆኑ . . . በአዘጋጆቹ ዘንድ ያለውን የፖለቲካ ወገንተኛነት ያሳያል" ብሏል። በዐቃቤ ሕግ የቀረበው የዳሰሳ ሪፖርት የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት በአምነስቲ የወጣው ሪፖርት ግድፈቶች ያላቸውን የተለያዩ ጉዳዮች በማንሳት ተችቷል እንዲሁም ድርጅቱ የሪፖርቱን አዘገጃጀት እንዲመረምርም ጥያቄ አቅርቧል። ከዚህ ባሻገርም ሪፖርቱ "ጉልህ ስህተቶች የተስተዋሉ ቢሆንም መንግሥት በሪፖርቱ ከተጠቀሱት የመብት ጥሰት ወቀሳዎች መካከል ተዓማኒነት ባላቸው ጥቂት ጉዳዮች ላይ ቀደም ብሎ የጀመረውን ተጠያቂነት የማረጋገጥ ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል። በተያያዘም በኢትዮጵያ ውስጥ ሰብዓዊ መብቶች ይበልጥ እንዲከበሩ ከአገራዊም ሆነ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ትብብር ይቀጥላል ብሏል። ቢቢሲ በዐቃቤ ሕግ የወጣውን ሪፖርት በተመለከተ ናይሮቢ የሚገኘውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጽህፈት ቤት ምላሽ እንዳለው ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፤ ድርጅቱ የወጣውን መግለጫ ተመልክቶ ምላሽ ለመስጠት ዕለቱ የሥራ ቀን ባለመሆኑ እንዳልቻሉና በቀጣይ ቀናት ምላሽ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል።
news-46068720
https://www.bbc.com/amharic/news-46068720
እንግሊዝ ውስጥ ብልትንማወፈር 100 ሺህ ብር ያህል ያስወጣል
የ27 ዓመቱ አብዱል ሃሳን የብልት ማስረዘሚያ መድሃኒቶች ደንበኛ ነው።
በዚህኛው ዙር ብልቱን ማስረዘም ያስፈለገው ለስምንት ዓመት አብራው የቆየችውን የፍቅር ጓደኛውን በምስራች መልክ ለማስደሰት ነው። ባለፈው ጊዜ ብልቱን የሚያስረዝም ፈሳሽ ተወግቶ ቤታቸውን 'በፍስሃ እንደሞላው' ይናገራል። «አንድ ጊዜ ደግሞ ባስረዝም አይጎዳኝ፤ እኔ እንጃ ብቻ ደስታ ይሰጠኛል።» ብልት ማወፈሪያ ፈሳሽ ሲሆን በሲሪንጅ ተደርጎ ስስ በሆነው የወንድ ልጅ መራቢያ አካል በኩል ይሰጣል፤ ኦፕራሲዮን የለ፤ ምን የለ፤ በሰዓታት ውስጥ በአነስተኛ ክሊኒክ ውስጥ ሊከናወን የሚችል ነው። • የዘር ከረጢት ካንሰር ከአባት ጅን ጋር የተያያዘ ነው ቢሆንም. . . ይላሉ ባለሙያዎች፤ ቢሆንም መሰጠት ያለበት በሙያ ጥርሳቸውን በነቀሉ ስፔሻሊስቶች እንጂ እንዲሁ አይደለም። ይህንን ፈሳሽ አንድ ጊዜ ወደ ሰውነት ውስጥ ለማስገባት እንግሊዝ ውስጥ ያሉ ክሊኒኮች 3ሺህ ፓውንድ ይጠይቃሉ፤ ከ100 ሺህ ብር በላይ ማለት ነው። ፈሳሹ የወንድ ልጅ ብልትን በአንድ ወይም ሁለት ሴንቲሜትር ለማወፈር የሚያስችል ንጥረ ነገር አዝሏል፤ እንደሚሰደው መጠን ደግሞ እስከ 18 ወራት ድረስ ሊቆይ ይችላል። ችግሩ ወዲህ ነው። እኒህ ፈሳሽ ብልት ማስረዘሚያዎች ብዙ ቁጥጥር አይደረግባቸውም። ይህ ደግሞ መድሃኒቱ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንዲያይል ያደርገዋል ይላሉ ባለሙያዎች። የእንግሊዝ የመራቢያ አካላት ስፔሻሊስት ማሕበር አባል የሆኑት አሲፍ ሙኒር «ሰዎች ይህን መድሃኒት ከመጠቀም ቢቆጠቡ ይሻላል» ይላሉ። «መድሃኒቱ ብልትን ከማርዘም ይልቅ ኋላ ላይ የሚያመጣው መዘዝ የከፋ ነው» ሲሉ ያስጠነቅቃሉ። ምንም የሚደበቅ ነገር የለም. . . አብዱል በራስ መተማመኑ ዝቅ ማለቱ መድሃኒቱን እንዲጠቀም እንዳስገደደው ይናገራል። ለመጀመሪያ ጊዜ መድሃኒቱ ወደሰውነቱ ሲገባ የራስ መተማመንን ይዞ እንደገባ ይናገራል፤ ኋላ ላይ መዘዝ እንዳይመጣበት ፍራቻ ቢጤ ወረር እንዳደረገው ባይክድም። «ልክ መድሃኒቱን ስወስድ በራስ መተማመን በውስጤ ሲሰራጭ ይሰማኛል፤ ምንም የሚደበቅ ነገር የለም።» እንግሊዝ የመድሃኒቱ ፈላጊ ዜጎቿ ቁጥር ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ከሰባሰበችው ጥናት ማወቅ ችላለች። ከሦስት ዓመታት በፊት በወር ቢበዛ 10 ሰዎች ብቻ ናቸው የሚጠቀሙት፤ አሁን ግን ቁጥር ወደ 700 ገደማ ደርሷል። ባለሙያዎች እጅግ ያስጨነቀው ጉዳይ ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው መውጋት መጀመራቸው ነው። ሙኒር እንደሚሉት ሰዎች ቫዝሊንና ሌሎች መሰል ቅባቶችን በመጠቀም ራሳቸውን ይወጋሉ፤ ይህ ደግሞ መዘዙ የከፋ ነው። «እንዲህ ያደረጉ ተጠቃሚዎች ቁስለት ስለሚያጋጥማቸው ከቀናት በኋላ ወደ ህክምና ጣቢያዎች መምጣታቸው አይቀርም» ይላሉ ባለሙያው። «እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥመን ብዙ ጊዜ የምናደርገው የብልትን ሽፋሽፍት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ከሌላ የሰውነት ክፍል በሚገኝ ቆዳ መተካት ነው።» ስቱዋርት ፕራይስ ይህን ህክምና ወደሚሰጡ ክሊኒኮች ሲያመራ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፤ የ36 ዓመቱ ጎልማሳ ወንዶች ሁሉ እኮ ተለቅ ያለ ብልት ቢኖራቸው ይመርጣሉ ይላል። • አዲሱ የማዋለጃ ቦርሳ የእናቶችን ህይወት እየታደገ ነው «እኔ መድሃኒቱን ባልጠቀመውም ግድ የለኝም፤ ነገር ግን የልብ ልብ እንዲሰጠኝ ነው ልሞክረው የወሰንከት። ትንሽ ተለቅ ቢልልኝ አልጠላም» ይላል። ስቱዋርት በይነ-መረብ ላይ ተተክሎ ፀጉር አሳዳጊ ምርቶችን በመቃኘት ላይ ሳለ ነበር ቀዶ ጥገና የማይጠይቀውን የመድሃኒቱን ጉድ ያነበበው። 2015 ላይ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው የወንድ ልጅ ብልት ለወሲብ ሲነሳሳ መካከለኛ ርዝመት 13 ሴንቲሜትር (5.1 ኢንች) ነው። ጥናቱ በዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 15 ሺህ ወንዶችን አካቶ የተሠራ ነው። የስቱዋርት ፍቅረኛ ካሪስ ስቱዋርት 15 ሚሊ ሌትር ማስረዘሚያ ፈሳሽ ለመወሰድ ተዘጋጅቷል፤ ክሊኒኮችም ቢሆን ከዚህ በላይ ማስረዘሚያ እንዲወሰድ አይመክሩም። የስቱዋርት ፍቅረኛ ካሪስ ጭንቀት ቢጤ ወሯታል፤ እንደው የጓደኛዋ ብልት መጠን ከልክ እንዳያልፍ በማለት። ፈሳሹ ከመጠን በላይ ሆኖ ቢገኝ ወደ ክሊኒክ ተመልሶ ማስቀነስ ይቻላል፤ ያው ሌላ ወጪ ቢሆንም። • ልባችን ከእድሜያችን ቀድሞ ሊያረጅ እንደሚችል ያውቃሉ? ምንም እንኳ ካሪስ በጭንቀት ብትዋጥም ሂደቱ ቀጠለ፤ ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላ ውጤት ለማየት የብልቱ ውፍረት መጠን መለካት ነበረበት። የስቱዋርት ብልት ውፍረት መጠን ከ12.5 ወደ 15 ሴንቲሜትር ደረሰ፤ ስቱዋርትም «ትልቅ የሆንኩ ያህል ተሰማኝ፤ ደስታም ወረረኝ» ሲል ተሰማ። ዶክተሮች የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ከተወጉ በኋላ ቢያንስ ለአራት ሳምንታት ወሲብ እንዳያደርጉ ይመክራሉ፤ ውፍረቱ ከ10 ሴንቲሜትር ወደ 11 የደረሰለት አብዱል «ዋናው መጠኑ መተለቁ ነው እንጂ. . .» ይላል። «መቼም የጤና እውክ እንዲገጥም አትፈልግም» የሚለው አብዱል ከአፍታ ዝምታ በኋላ «በተለይ ደግሞ ከመራቢያ አካል ጋር በተያያዘ» ሲል ያክላል።
news-41252293
https://www.bbc.com/amharic/news-41252293
"በሜዴትራንያን ባህር ልሰምጥ ነበር"
ሽሻይ ተስፋአለም እባላለሁኝ። ነሽነሽ ደግሞ ቅጥያየ ነው። የኤርትራዋ ኣስመራ ከተማ ተወልጄ ያደግኩባት ከተማ ናት። ሳዋ ስለጠና ከወሰድኩኝ ኋላ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኣስተማሪ ነበርኩኝ። በተጨማሪ ሙዚቃ እና ቀልድ እሰራ ነበር። አስተማሪ ሁኜ የማገኘው ደሞዝ ስለማይበቃኝ ከቤተሰቦቼ ተጨማሪ ብር እለምን ነበር።
የሜዲትራንያን ባህር ኣቋርጦ ጀርመን የገባ ኤርትራዊ ስደተኛ፡ ሽሻይ ተስፋኣለም (ነሽነሽ) የኤርትራ ነባራዊ ሁኔታ አገር ውስጥ ለመኖር አልተመቸኝም። እናም ከአገር ለመውጥት ወሰንኩኝ። ከ 2 አመት በፊት እግሮቼ ለስደት ተነሱ። እናም ከከባድ የእግር ጉዞ በኋላ በድንበር ወደ ኢትዮጵያ ገባሁኝ። በኢትዮጵያ ዓዲሓርሽ በሚባል የስደተኞች ካምፕ ለሰባት ውራት ቆየሁኝ። በስደተኞች ካምፕ ብኖርም ካምፑ ለኔ ጥሩ ነበር። ትግራይ ውስጥ በሽረ ከተማ ከሚገኝ የባህል ቡድን በመሆን ለህዝብ ሙዚቃ በማቅረብ፡ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ ፍቅርና ሰላም እንቀሰቅስበት ነበር። በዓዲሓርሽ ስደተኞች ካምፕ በነበርኩበት ጊዜ ኢትዮጵያውያን አስተማሪዎች በሞያ ይረዱን ስለ ነበር፡አንዳንድ ዘፈኖች ሰርቼ ነበር። የኢትዮጵኣ ህዝብ ስታዘብ በጣም እቀና ነበር። ከካመፑ ወጥቼ ስንቀሳቀስ፡ ህዝቡ ማን ነህ የሚለው የለም፡ በነፃነት ይንቀሳቀሳል። ኣኔ የኔው ኤርትራዊ ህዝብ እንዲህ አይነት ነፃነት ቢያገኝ ምን አይነት እፎይታ ማግኘት በቻለ ብየ እቀናለው። እንዲሁ በስደተኞች ካምፕ እኖራለው እንጂ፡ በስደተኞች ካምፕ እንደምኖር አይሰማኝም ነበር። አስተማሪዎቹ ገንዘብ እየከፈሉ ያስተምሩን ነበር። በስደተኞች ካምፕ ሁሌ እየተጦርኩኝ መኖሩን አልመረጥኩትም። እናም ለተሻለ ሂወት ዳግመኛ ወደ ስደት ተነሳሁኝ፡ ኣውሮፓ ለመግባት። ከጓደኞቼ ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ ወደ ሲዳን፡ ከዛም ሰሃራ በረሃ በማቋረጥ ከባድ ዕግር ጉዞ በኋላ ሊቢያ ገባሁኝ። በጣም ከባድ ጉዞ ነበር። ሊቢያ ከገባን በኋላም ከባድ የፈተና ናዳ ይወርድብን ጀመር። ለሶስት ወራት ያክል በደላሎች ተደበደብን። ሁሌ ገንዘብ እንደተጠየቅን ነው። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ለደላሎች ረብጣ ሺዎች በመክፈል በሶስት ጀልቦች ተከፋፍለን፡ ወደ ጣልያን በሜድትራንያን ባህር ጉዞ ጀመርን። እኛ ጋር ከነበሩ አንደኛዋ ጀልባ ጣልያን ገባች። እኛ ግን እፎይ ሳንል በሄድንበት ፈተና ይከተለን ጀመር። ሁለተኛዋ ጀልባ አይናችንን እያየን ከባህሩ መሃል ሰመጠች። የ 500 ኤርትራውያን ስደተኞች ህልምና ሂወት እንደ ውሃ ተነነ፡ ሁሉኑም የባህር ዓሳ ሲሳይ ሆኑ። ስደተኞች የሜዲትራንያንን ባህር በማቋረጥ ወደ ኣውሮፓ ይገባሉ። ዳግማይ ስደት እኛው የያዘችው ጀልባም አንድ ሰዓት ከተጓዝን በኋላ ጭር ባለው ባህር ቆመች። ምንም መንቀሳቀስ አልቻለችም። በአ ንደኛው ጭንቅ ሌላ ጭንቅ አጋጠመን፡ አሁን ሁላችነም ተስፋ ቆረጥን። አትጥፉ ሲለን የሊቢያ የባህር ወደብ ጠባቂዎች ደርሰውብን ወደ ሊቢያ መለሱን። ይህ ሁሉ ሁኖም አሁንም ተስፋ አልቆረጥንም። እንደ አዲስ ለደላሎች ብር ከፍለን ወደ የምናስባት ጣልያን ገባን። ጣልያን አገርም ሌላ የስደጠኞች ካምፕ ነበር የጠበቀን። ግን ነገን የማስበውን ህልሜ እውን ለማድረግ በጣልያን ስደተኞች ካምፕ ለ 11 ወራት ቆየሁኝ። ከኛ በፊት ወደ ጣልያን የሚገቡ ስደተኞች፡ የእጅ አሻራ ላለማድረግ እና በፖሊስ እንዳይያዙ፡በማምለጥ ነበር ወደ ሌሎች ሃገራት የሚገቡት። አጋጣሚ እኛ እድል ስትቀናን ግን ነበረው የስደተኞች ፖሊሲ ተቀየረ። እናም ከ 11 ወራት የስደተኞች ካምፕ ቆይታ በኋላ በህጋዊ መንገድ ወደ ጀርመን እንድገባ ተፈቀደልኝ። አጋጣሚ ሁኖ እኔ እድል በሯን ከፍታልኝ እንጂ፡ የሰሃራ በረሃ አቋርጠው ጣልያን ከገቡ በኋላ የተጣሉ እና መጠለያ ያጡ ብዙዎች ናቸው። ነሽነሽ፡ በምዕራባዊ ጀርመን ሙንስተር ከተማ ፡ ማፐን ዲ በሚባል አካባቢ ይኖራል። የጀርመን ኑሮ አሁን በምእራባዊ ጀርመን ሙንስተር ከተማ በምትገኘው ማፐን ዲ በሚባል አካባቢ እየኖርኩኝ ነው። አሁን 3 ወራት ሁኖኛል። በጀርመን አገር ስራ ለመጀመር፡ ለ 6 ወራት የጀርመን ቋንቋ መማር ግድ ስለ ሆነ ጀርመንኛ እየተማርኩኝ ነው። ህይወት በጀርመን እና በኤርትራ ከቶ ማወዳደር አይቻልም። የፈለግከውን የመናገር መብት አለ። ከደጃፌ ጀምሮ አይንን የሚማርኩ ነገሮችን አያለው። በጣም ንፁህና አረንጓዴ አካባቢ ነው። ኣረንጓዴ አከባቢ፡ ማፐን ዲ፡ ጀርመን ሁሌ እንደምፈልገው ባላገኝም ባይሆንም ኤርትራ እያለው ዶሮ መብላት በጣም እወድ ነበር። እዚህ ግን ሁሌም በቀላሉ ዶሮ እበላለው። እዚህ ሁኜ የሚናፍቀኝ ነገር ቢኖር ኤርትራ እያለው ያሳለፍኩት ጥሩ ጊዜ እና የአብሮ አደጎቼ ፍቅር ነው። ለቀጣይ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ ሰላም በፌስቡክ እኣካሄድኳቸው ኣሉትን እንቅስቃሴዎች እንድሰበስባቸው እና በኤርትራ የነበረኝን የሙዚቃ ስራዎች እንድቀጥል እፈልጋለው። ከሁሉም አንድ የምለይበት ነገር ቢኖር የአማርኛ ፊልሞች በብዛት ከማየቴ የተነሳ፡ ለማታውቀኝ የትግራይ ልጅ ተዋናይት ሰላም ተስፋየ ማፍቀሬ ነው። በሆነ ተኣምር አሁን ካለሁበት ቦታ ነፍሴን ወደ ሌላ ኣካባቢ መላክ ብችል፡ ወደ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ባሳረፍኳት። አዲስ አበባ ህጄ በጣም የማፈቅራት ተዋናይት ሰላም ተስፋየ በማግኘት፡ ያሉኝን የፊልም ድርሰቶች በአማርኛ እና በትግርኛ፡ ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ ህዝብ ሰላምና ፍቅር ኣብርያት እሰራ ነበር።
news-49281159
https://www.bbc.com/amharic/news-49281159
መጻሕፍትን ማንበብና መጻፍ ለአዕምሮ ጤና
ለብዙ ሰዎች ማንበብን እንደ ልማድ ለመያዝ አስቸጋሪ ነገር ነው። ምናልባት ለረዥም ሰዓታት ቁጭ ብሎ መጽሐፍት ማንበብ የሚችሉ ሰዎች የተለየ ችሎታ እንዳላቸው ሊታሰብ ይችላል። ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው። አንድ ጊዜ የማንበብን ጥቅም የተገነዘበ ሰው በንባብ የሚያሳልፈው ጊዜ ላይታወቀው ይችላል።
ቢቢሲ በቅርቡ መጽሐፍ ማንበብን እንደ ህክምና መንገድ የሚጠቀሙ ባለሙያዎችን አነጋግሮ ነበር። 'ቢብሊዮቴራፒስት' የሚባሉት እነዚህ ባለሙያዎች ይህንን መንገድ በመጠቀም የተጨነቀ ሰውን ወደ ጤናማ የአእምሮ አሰራር መመለስ እንችላለን ይላሉ። በተለይ ደግሞ የልብ ወለድ መጽሐፍትን ማንበብ ዓለምን የምንመለከትበትን መነጽር እንድንቀይር እንደሚያደርግ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። • የጥሩ አባትነት ሚስጥሮች ምንድናቸው? • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" በለንደን ስኩል ኦፍ ላይፍ ለሰዎች ግላዊ የንባብ ምክር የምትሰጠውና ቢብሎቴራፒስት የሆነችው ኤላ በርቱድ ለቀድሞዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ምን አይነት መጽሐፍ እንዲያነቡ እንደምትመክር ተጠይቃ ነበር። ''ቀላል ነው፤ አሜሪካዊው ጸሐፊ ሁበርት ሴልቢ በ1978 የጻፈውን 'ሪኩዊየም ፎር ኤ ድሪም' የተባለውን መጽሐፍ እመከራቸዋለው'' ብላለች። ''በተለያየ አይነት የእጽ ሱስ ውስጥ ተዘፍቀው በሚገኙ አራት ሰዎች ህይወት ላይ ነው መጽሐፉ የሚያተኩረው። ዋና መልዕክቱም የህይወት ፍልስፍናችንን መቼም ቢሆን መልቀቅ እንደሌለብን ማሳየት ነው'' ስትል ምክንያቷን አስቀምጣለች። ሌላኛው ልብ ወለድ መጽሐፍት ሊያደርጉልን የሚችሉት ነገር፤ ታሪኩ ውስጥ የመግባት እድልን መፍጠር ነው። ለምሳሌ በቴሌቪዥን አንድ ፊልም ብንመለከት፤ ምስሉና ድምጹ በአንድ ላይ ስለሚቀርብልን ያለ ምንም ጥረት በቀላሉ መረዳት እንችላለን። ነገር ግን መጽሐፍ ሲሆን ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነው። በታሪኩ ውስጥ የምናገኛቸውን ገጸ ባህሪያት በምናባችን ለመሳል ነው የምንሞክረው። ይህ ደግሞ አእምሯችን የሚፈጠሩበትን ጥያቄዎች በሙሉ በራሱ እንዲመልሳቸው ያስችሉታል። • የጄኔራል ደምሴ ቡልቶ ልጅ 'መራር' ትዝታ እጅግ ስለተዋበ ተፈጥሮአዊ ቦታ መጽሐፍ ላይ ስናነብ ሁሌም ቢሆን ጭንቅላታችን ውስጥ ትክክለኛውን ምስል ለማስቀመጥ እንሞክራለን። ታዋቂው ጸሀፊ አሌክስ ዊትል እንደሚለው በልጅነቱ እጅግ ከባድ ጊዜን አሳልፏል። በደቡባዊ ለንደን የልጆች ማሳደጊያ ውስጥ ነው ያደገው። ''በማደጎ ቤት ውስጥ ያጋጥሙኝ የነበሩትን አስፈሪና አስቸጋሪ ጊዜያት አሳልፋቸው የነበረው የምወዳቸውን ልብ ወለድ መጽሐፍት በማንበብና ያለሁበትን ዓለም በመርሳት በገጸ ባህሪያቱ ዓለም ውስጥ በመግባት ነበር'' ይላል። ያነበቡትን መጽሐፍ ደግሞ ማንበብን የመሰለ አስደሳች ነገር የለም ይላሉ ቢብሊዮቴራፒስቶች። ለመጀመሪያ ጊዜ ስናነበው የተሰሙን ስሜቶች፣ በድጋሚ ስናነበው በምናባችን የሳልናቸው ገጸ ባህሪያት ሁሉ ተቀይረው ልናገኛቸው እንችላለን። መጨረሻውን እያወቅን እንኳን ከመጨረሻው በፊት ያለውን መውደቅና መነሳት፣ ደስታና ሃዘንን ለማየት እንጓጓለን። አንዳንዴም የተረዳነው የመሰለን ሃሳብ በድጋሚ ስናነበው መሳሳታችንን ልናውቅ እንችላለን። ታዳጊ ህጻናት መጽሐፍ ማንበብ ሲጀምሩ በተለይ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ እየተስተዋሉ የሚገኙትን የአእምሮ መታወክና ተያያዥ እክሎች ለማዳን አልያም ለመከላከል እጅጉን ይረዳቸዋል። ሁሌም ልጆች በዕለት ተዕለት ኑሯቸውና በአካባቢያቸው የሚገኙ የማይስማሟቸው እንዲሁም ምቾት የሚነሷቸው ሁኔታዎችን ለማምለጥ የራሳቸውን ዓለም ይፈጥራሉ። የሚፈጥሩት ዓለም ደግሞ ከመጽሐፍት ጋር የተገናኙ ከሆነ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። • በባርነት ከመሸጥ የተረፉት 64 ኢትዮጵያዊያን መጽሐፍትን ማንበብ ለአእምሮ ጤና ይህን ያክል ጥቅም ካለው መጻፍስ? አሌክስ ዊትል እንደሚለው በውስጣችን የሚሰሙንን ነገሮች በጽሑፍ ለመግለጽ መሞከር ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳል። የሚያሳስቡንን ነገሮች ለራሳችን ከማስቀረት ይልቅ በወረቀት ላይ ማስፈር ደግሞ ትልቅ ህክምና እንደሆነ ያምናል። በሌላ በኩል በርተን የተባለው ጸሐፊ ደግሞ ደራሲ መሆን ማለት ለሳምንታት፣ ለወራት አንዳንዴም ለዓመታት ከሰዎች ተነጥሎ መቆየትን ሊያስከትል እንደሚችል ያስባል። ነገር ግን ከእነዚያ ሁሉ ጭንቀትና መከራ በኋላ የተጻፈውን መጽሐፍ ሚሊዮኖች ሲያነቡትና ሲጠቀሙበት ማየትን የመሰለ አስደሳች ስሜት እንደሌለ ግን ሁሉም ጸሐፍት የሚስማሙበት ሃሳብ ነው።
news-55328491
https://www.bbc.com/amharic/news-55328491
"ሳሊን ፍለጋ"- የዚያ ትውልድ አሻራ ሲገለጥ
አራት ሴቶች መስዋዕትነት በተከፈለባት በአሲምባ ኮረብታ ላይ ጮክ ብለው ይጣራሉ።
"ሳሊ፣ ሳሊ፣ ሳሊ፤ ሰላማዊት" - ድምፃቸው በተራራው መካከል ይሰማል። የገደል ማሚቶው ድምፅም ሳሊ፣ ሰላማዊት እያለ በከፍተኛ ድምፅ ያስተጋባዋል። ተራራውም ስሟን መልሶ የሚጣራ ይመስላል። እነዚህ ሴቶች ማን ናቸው? ስሟን የሚጠሯትስ ሳሊ ወይም ሰላማዊትስ? በእድሜ ጠና ያሉት እነዚህ ሴቶች ክብረ፣ መንቢ፣ ብሩክታዊትና ፅዮን ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓን) የትጥቅ ትግል ተቀላቅላ ከአርባ አመት በፊት የጠፋችው እህታቸውን ሳሊ (ሰላማዊት ዳዊትን) ስም ነው የሚጠሩት። ከአስርታት በፊት አቆላምጠው እንደሚጠሯት ሳሊ፣ ሳሊ፤ ሰላማዊት ይላሉ። ትግራይ ውስጥ የምትገኘው የአሲምባ ተራራ የወጣቶቹ የፅናትና ቆራጥነት ተምሳሌት፣ የአኬልዳማ መሬት፤ የህልም መነሻና መቀበሪያ፤ ታጋዮችን ውጣ ያስቀረች። "ቢወቀጥ አጥንቴ ቢንቆረቆር ደሜ፤ ለአዲስ ሥርዓት ልምላሜ፤ ፍጹም ነው እምነቴ፤ ትግሉ ነው ሕይወቴ" ብሎ ያ ትውልድ የዘመረባት ቦታ ናት። የአሲምባዋ ታጋይ ሳሊ የሕዝብን ትግል ትግሌ ብላ፣ ለሕዝብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ፣ በጭቆና ለሚማቅቀው የነፃነትን ወጋገን ለማሳየት፣ በእራፊ ጨርቅ እጦት፣ በድህነት አለንጋ ለሚገረፈው፣ ጉርሱን ላጣው የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቤታቸው በወጡበት ካልተመለሱት መካከል አንዷ ናት። በዚህች ተራራማ ስፍራ መሸገው የነበሩ የዚያ ትውልድ የኢሕአፓ አባላትም በመንፈስ እየሰሙ ይሆናል - የእህትማማቾቹን ጥሪ። ከአራት አስርት ዓመታት በኋላ በአሲምባ ተራራ ስር ያለችው የገጠር መንደር፣ በድንጋይ የተሰሩ ህድሞ ቤቶች፣ ጋቢያቸውን ደረብ አድርገው የሚመለከቱ አዛውንት፣ ነጠላቸውን የደረቡ እናቶች፣ በአቧራማው ሜዳ ላይ ኳስ የሚጫወቱ ህፃናትም የሳሊንና የሌሎቹን መስዋዕትነት ያወሱት ይሆን? ለነፃነት ቆርጣ በረሃ የገባችው ሳሊ (ሰላማዊት) ፈገግታ የማይለያትና 'ቀይዋ' በሚል መለዮ ነበር የአካባቢው ነዋሪዎች የሚያውቋት። ልክ እንደ ኢሕአፓ ጓዶቿ ፖለቲካዊ ትምህርት ከመስጠትም ባለፈ ለሴቶች ድጋፍ በማድረግ የታመሙትን በማከም 'ነርሷ' የሚል የቅፅል ስምም አትርፋ ነበር። ለቤተሰቦቿስ? ሳሊ ፈገግታ የማይለያት፣ ሳቂታ፣ ለመቅረብ ቀለል ያለች፣ በጣም ጎበዝ፣ ውይይት የምትወድ፣ ፓርቲ የምታዘወትር፤ ፀጉሯንና ጥፍሯን ተሰርታም ዝንጥ ብላ መውጣትም ትወድ ነበረች። ይህ ግን ትግሉን ከመቀላቀሏ በፊት ነበር። ትግሉን ከተቀላቀለች በኋላስ? የፀረ-ኢምፔሪያሊዝም አቋሟ፣ የማኅበራዊ ፍትህ ጥያቄዋ፣ ደርግን እጥላለሁ ብላ ወደ ትጥቅ ትግል መግባቷ በቤተሰቡ ውስጥ የሚወራም አይደለም፤ ተዳፍኖ የቀረና የማይነሳ ጉዳይ ነው። የሳሊ ደብዛ መጥፋት ለቤተሰቧ ጠልቆ የሚሰማ ህመም ያለው የማይድን ቁስል ነው። የእህታቸውን ትዝታ ተመልሶ መፈለግ የማይሽር የዘመን ጠባሳ መመልከትና በርካቶች መስማት የማይፈልጉትን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የጨለማ ጊዜንም መመልከት ነው። ስለዚህ ትግሉም አይነሳም፤ ሳሊም አትወሳም። ለቤተሰቡ ህመም የሆነው የሳሊ የትግል ታሪክም መቀበር ለወንድሟ ልጅ ታማራ ማርያም ዳዊት፤ ሳሊ የምትባል አክስት እንደነበረቻት ይቅርና እስከነ መፈጠሯ እንዳታውቅ ምክንያት የሆናት። በ30ዎቹም እድሜ ላይ ሆና ነው ሳሊ (ሰላማዊት) የምትባል አክስት እንዳለቻት፣ የኢህአፓ ታጋይ እንደነበረች የተረዳችው። የአክስቷን ታሪክ፣ ማንነት ፍለጋ በዝምታ የተሸበበውን የቤተሰቡን ምስጢራዊ መጋረጃንም 'ፋይንዲንግ ሳሊ' [ሳሊን ፍለጋ] በሚለው ፊልሟ ታሳያለች። ካናዳ ተወልዳ ያደገችው ታማራ ስለ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን መገርሰስ፣ የተማሪዎች እንቅስቃሴ፣ የቀይ ሽብር ጭፍጨፋዎች ብትሰማም ከእሷ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት አለውም ብላ አልጠረጠችም። ነገር ግን ይህ ሁሉ የተቀየረው ከዘጠኝ ወይም ከአስር ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ለእረፍት በመጣችበትና የአንዲት ወጣት ሴት ትልቅ ፎቶ አያቷ ቤት ተሰቅሎ በተመለከተችበት ወቅት ነው። በበርካታ ኢትዮጵያውያን ቤተሰብ ውስጥ የአጎት ልጅ፣ የአክስት ልጅ እንዲሁም ዘመድ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ማደግ የተለመደ ነው። አያቶቿም የሚያስተምሯቸው አምስት ወይም ስድስት የቤተሰብ አባላት ነበሩ። ስታድግም የማታውቃቸው የድሮ ፎቶዎችም ታይ ነበር። የማታውቀው ሰው ፎቶ ማየቷ ብዙ ባያስገርማትም ነገር ግን አያቷ ቤት የተሰቀለው ፎቶ ትልቅና ሳሎን ቤቱ መሃል ላይ መሆኑ ነበር ጥያቄ ያጫረባት። ፎቶው ላይ ያለችው ማን ናት? ብላም አያቷን ስትጠይቅ "እንዴ ማን እንደሆነች አታውቂም? አክስትሽ ናት እኮ አሏት" አያቷ። አክስት ሲባል ምናልባት ዘመድ ትሆናለች ወይ በማደጎ የመጣችም ትሆናለች ብላም አስባ ነበር። "አያቴንም ስለነበር የጠየቅኳት ማን መሆኗን አለማወቄ በጣም ነው ያስደነገጣት፤ ሳሊ የምትባል ሰው በህይወት መፈጠሯንም አለማወቄ በጣምም ነው ያስገረማት" ትላለች ታማራ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ። ታማራ ስለ ሳሊ ማንነት፣ ለአገሯ ያደረገችውንም ተጋድሎና ታሪክ አላወቀችም ማለት መጪው ትውልድ ስለሷ ምንም አያውቅም ማለት ነው። ይሄ ደግሞ የቤተሰቡም ሆነ የኢትዮጵያ ታሪክ አካል ነው፤ መጥፋት እንዲሁም ከታሪክ መዛግብት መፋቅ ማለት እንደሆነም ተረዳች። ከሁሉ በላይ ግን ለታማራ የገረማት፤ ለምንድን ነው ቤተሰቡ ስለ ሳሊ ማውራት የማይፈልገው? ማስታወስስ ለምን አይፈልግም? የሚለው ነው። ታማራ አባቷ ኢትዮጵያዊ ሲሆን እናቷ ደግሞ ካናዳዊት ነጭ ናት። ከእናቷ ጋር ስላደገችና ከአባቷም ጋር የነበራት ቅርበት የተወሰነ በመሆኑም ይሆናል ስለ ሳሊ የማላውቀው የሚል ግምት አላት። ሆኖም ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቻቸው ጋር በቅርበት ያደጉት የአክስትና የአጎት ልጆች የሚያውቁትም በጣም ትንሽ ነው። ህይወቷ ምን እንደነበር? ስለተሳተፈችበት ትግልም ምንም አይነት መረጃ አልነበራቸውም። በቅርቡም ለሰራችው 'ፋይንዲንግ ሳሊ' ለሚለው ጥናታዊ ፊልሟም መነሻ የሆናት ይኸው አጋጣሚ ነው። አያቷን፣ አክስቶቿን እንዲሁም የሳሊን ጓደኞችና ጓዶቿን ወደ ኋላ አራት አስርት ዓመታት እንዲጓዙ ታደርጋቸዋለች። ለዓመታት በዝምታ ተሸብቦ የነበረው ዝምታና ምስጢርም ይገለጣል። 'ፋይንዲንግ ሳሊ' የአገሪቱን ህመም፣ ያልሻረ ቁስል ቤተሰብ፣ ፍቅር፣ የተዳፈኑ ታሪኮች፣ ያልሻራ ጠባሳን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በአያቷ እንዲሁም በአክስቶቿ ላይ ቀይ ሽብር ያሳረፈው ጠባሳ ምን ያህል እንዳልሻረ ፊልሙ ያሳያል። ታሪክን የኋሊት በመመለስም በወቅቱ የነበረችውን ኢትዮጵያ ለመመልከት ሞክራለች- ታማራ። 'ፋይንዲንግ ሳሊ'፣ አክስቷን የመፈለግ ጉዞ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን የኋላ ታሪክና በአሁን ጊዜ ያጠላውን ጥላም ያሳያል። ፊልሙ ሲጀምር በእድሜ የጠገቡ አዛውንት ከመኪና ወጥተው በእድሜ እኩያቸው የሆኑ ሌላ አዛውንትን ለማግኘት ወደ ቤታቸው ሲራመዱ ነው። የእድሜ ባለፀጋዋ ውጭ እየጠበቋቸው ነበር። ተቃቀፉ፣ ጉንጭ ለጉንጭም ተሳሳሙ። እጃቸውንም ተጨባብጠው ተላቀሱ። ወደ ቤትም እየተራመዱ የቀድሞው አልፏል በመባባል ይፅናናሉ። ሁለቱ አዛውንቶች የሳሊ [ሰላማዊት] እና የኢሕአፓ አመራር የነበረው ፀሎተ ህዝቅያስ እናት ናቸው። ሁለቱም ልጆቻቸውን በትግሉ መስዋዕት አድርገዋል። የፀሎተ እናት ለአንድ ወር ያህል ታስረው ልጃቸው ሲሰቃይም እንዲመለከቱ ተገደዋል። ሦስት ልጆቻቸውንም በአብዮቱ አጥተዋል። ሐዘኑ፣ ፀፀቱ፣ ቁጭቱ የፈጠረው ዘመን ያልሻረው ህመምም ይነበብባቸዋል። በርካታ ያልተወሩ፣ ያልተነገሩ ህመሞች በሁለቱ አዛውንት እንባ ውስጥ አለ። "ስንቱ አልፎ እዚህ ደረስን" እያሉ ይጫወታሉ። የሁለቱ እናቶች ብቻ ሳይሆን እህቶቿን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁሉም ማጣትን ያውቁታል። የሚወዱት ሰው ዝም ብሎ ደብዛው ሲጠፋ ምንስ ይደረጋል? በትግል እንደወጡ የቀሩ፣ በቀይ ሽብር የተነጠቁት ሁሉ ሐዘናቸውን በውስጣቸው ደብቀው፣ በፍራቻ ተሸብበው፣ ከባድ ሸክም ተሸክመው ለመኖር ተገደዋል። ከቤተሰቧ ጋር መቆራረጧ በተለይም ልባቸውን ምን ያህል እንደሰበረውም 'ፋይንዲንግ ሳሊ' በሰላማዊት አድርጎ የዚያን ትውልድ ህይወት በር ያንኳኳል። ሳሊ ማን ናት? ሳሊ የዲፕሎማት ልጅ ናት፣ ከላይኛው መደብ የሚመደቡ የሃብታም ልጅ ። አባቷ በአፄ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ ወቅት አምባሳደር ስለነበሩ ሳሊም ሆነ ሌሎች እህቶቿ አዲስ አበባ ቢወለዱም አባትየው በተመደቡባቸው በሌሎች አገራት ነበር ያደጉት። ሳሊም ሆነ ቤተሰቡ በናይጄሪያ፣ በጋና፣ በሱዳንና በሌሎችም አገራት ውስጥ ኖረዋል። ወደ ካናዳም የመጡት በ1968 (እአአ) ነበር። በካናዳ፣ ካርልተን ዩኒቨርስቲ የፖለቲካና የሶሺዮሎጂ ትምህርትን አጥንታለች። ሳቂታ፣ ሙዚቃ የምትወድ፣ በርካታ ጓደኞች ያሏት ነበረች። ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቷም በፊት ኑሮዋ በካናዳ ነበር። አባቷ የአፄ ኃይለ ሥላሴ ማደጎ ልጅና ኢትዮጵያዊ ብሔርተኛ ነበሩ። በተደጋጋሚም "ውጭ አገር የምንኖረው ለኢትዮጵያ መንግሥት እየሰራን ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያንም ወክለን ነው። መመለስ አለባችሁ፤ አገራችሁንም ልታውቁ ይገባል" የሚል ፅኑ አቋም እንደነበራቸው ታማራ ለቢቢሲ ተናግራለች። "መመለስ ብቻ አይደለም ለአገራችሁም ልትሰሩ ይገባል ይሉ ነበር። ምናልባትም አብዮቱ ባይፈጠር ኖሮ ሁሉም ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ያገለግሉ ነበር" ትላለች ታማራ። ኢትዮጵያ የመጣችው በ1973 (እአአ) ነበር። ወቅቱም የሽግግር ጊዜ ወቅት ነበር። ሥነ ጽሁፉ፣ ሙዚቃው፤ የምሽት ክበቡ፣ የዘመናዊነት (ሞደርኒዝም) ፅንሰ ሃሳብ የጎለበተበት፣ ከተሜነት የሚቀነቀንባትና ድምቅ ወዳለችው አዲስ አበባ። ጎን ለጎንም እንዲሁ ሰልፉ፣ ተቃውሞውና ውጥረት የነገሰበት ዘመን። ወቅቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በተለያዩ አገራት ያሉ ትግሎች የተጋጋሉበት ነበር። የዓለም ዓቀፉ ፀረ- ኢምፔሪያሊዝም፣ ፀረ-ቅኝ ግዛት እንዲሁም የፀረ ዘረኝነት ትግሎችም ጎን ለጎን ነበሩ። አሜሪካ በቬትናም ላይ ያደረገችውን ወረራን በመቃወም፣ የፍልስጥኤም ጥያቄ፣ የደቡብ አፍሪካ የፀረ- አፓርታይድ ትግልና በላቲን አሜሪካ ለነፃነት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችም የእነ ሳሊም ጥያቄዎች ነበሩ። ለምሳሌ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር ልሳን ከነበረው 'ታጠቅ' ላይ የሚከተለው ፅሁፍ ሰፍሮ ነበር። "በፊውዳሊዝም እና በኢምፔሪያሊዝም መቃብር ላይ የሁላችን የሆነች ሕዝባዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት ኢትዮጵያውያን የሆንን ሁሉ እፍኝ ከማይሞሉት ጨቋኞችና ደጋፊዎቻቸው በቀር በአንድ የትግል ግንባር ውስጥ ተሰብስበንና ተደራጅተን በአንድነት መራመድ አለብን" ይላል። ካናዳ በነበረችበት ወቅት ማኅበራዊ ፍትህ ላይ ትሰራ የነበረችው ሳሊ አዲስ አበባ ስትደርስ "ፋኖ ተሰማራ ፋኖ ተሰማራ፣ ፋኖ ጫካ ግባ ትግሉን ልትመራ፤ እንደ ሆቺሚኒ እንደ ቼ ጉቬራ" በአዲስ አበባ መንገዶች የሚሰማበት፤ የአብዮት ታሪኮች በወጣቱ ልብ የተቀጣጠሉበት ጊዜ ነበር የተቀበላት። የተንሰራፋው ሥራ አጥነት፣ ረሃብ እንዲሁም ኢ-ፍትሃዊነት መስፈን "መሬት፣ መሬት፣ መሬት ላራሹ፣ ተዋጉለት አትሽሹ" በሚሉ መፈክሮችም፣ ሰላማዊ ሰልፎችና የሥራ ማቆም አድማዎች መካከል ሥርዓቱ ሲንገዳገድ ነበር የመጣችው። ኢትዮጵያ መጣች፤ አልተመለሰችም። እንደወጣች ቀረች፤ አብዮቱን ተቀላቀለች። የ23 ዓመቷ ሳሊ በነፋስ ስልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስተማር ጀመረች። በርካታ የተማሪዎች እንቅስቃሴ አራማጆችን በኋላም የኢሕአፓ መስራቾች ጋር መገናኘት ጀመረች። በጥቂት ወራትም ውስጥ ሳሊ ህይወቷ ከስር መሰረቱ ተቀየረ። ፓርቲ ለፓርቲ የምትሄደው፣ ዝንጥ ብላ ሽቶ የምትቀባባው ሳሊ ኮሚዩኒስት ሆነች። ወደ ትግሉ ዓለም ስምጥ ብላ ገባች። አለባበሷ፣ ሁሉ ነገሯ ተቀየረ። ፊልሙ ለቤተሰቧ የፖለቲካ ህይወቷ እንዴት ሊዋጥላቸው እንዳልቻለ፣ ሁሉን ነገር መስዋዕት ማድረጓ፣ ከቤተሰቧም በላይ ለፖርቲው የነበራት ታማኝነትና ለለውጥ የነበራት ቁርጠኝነትን ያሳያል። የእሷም የሆነ የትውልዱ መፈክር "እዋጋለሁኝ ለመብቴ ላንገብጋቢው የእግር እሳቴ፤ የትግል መርህ ቅኝቴ ትግል ነውና ህይወቴ" የሚል ነበር። በተለይም በ20ዎቹ መጀመሪያ የነበረችው ሳሊ የኢሕአፓ አመራር ከነበረው ፀሎተ ህዝቅያስ ጋር ሊጋቡ መሆኑን ሲያውቁ ቤተሰቡን ግራ እንደተጋባ ፊልሙም ሆነ ታማራ ትናገራለች። በትልቅ ሠርግና ድል ባለ ድግስ ታገባለች ብለው ሲጠብቁ አነስ ባለ የምሳ ሥነ ሥርዓት ነበር ጋብቻቸው የተፈጸመው። የለበሰችውም ሱሪ ነበር። እንደተጠበቀው ትልቅ የኢትዮጵያ ባህላዊ ሠርግም አልነበረም። ፊልሙም ሳሊ የኢሕአፓ አመራር ከነበሩት መካከል አንዱ ከሆነው ፀሎተ ህዝቅያስ ጋርም የነበራቸውን ጥልቅ ፍቅርን ያሳያል። ለእህቶቿም ይህቺ ሳሊ ናት ብሎ መቀበል ቀላል አልነበረም። ከቤተሰቡ ጋር የነበራትንም ግንኙነት መቀነስ ነበረባት። በተለይም አቃቂ በነበረ የሴቶች ምርቃት ላይ ያደረገችው ንግግር መንግሥትን የሚተችና የሚያወግዝም ስለነበር በመንግሥት ጠላት ተብላ ለመፈረጅ ጊዜም አልወሰደባትም። በከተማ ትግል ብቻ አልተወሰነችም አሲምባ የትጥቅ ትግል ለማድረግ ገብታ ጠፋች - እንደወጣች ቀረች። ፀሎተ ህዝቅያስም እንዲሁ። ለዓመታትም ያህል ቤተሰቦቿ በአውሮፓ፣ በተለያዩ አፍሪካ አገራትና በአሜሪካም ፈለጓት። አለችበት የተባለበት ቦታ ሁሉ ፎቶዋን እያሳዩም ዱካውን፣ ጥላዋን ተከታተሉ፤ አላገኟትም። የሳሊ የትግል ህይወት የሳሊ የትግል ህይወት ለቤተሰቡ ድብቅ ነበር። ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታም ግንኙነቷን አቋርጣም ስለነበር ታማራ ከትግል ጓዶቿ በተለይም ከፍቅርተ ጋር በማውራት ነው የትግል ህይወቷን ለማወቅ የቻለችው። በተለይም ከ1975 (እአአ) በኋላም ድብቅ ህይወት ነበራት። ከአንዲት እህቷ ጋር ብቻ የተወሰነ ግንኙነት ነበራት። አሲምባም እያለችም ሁለት ደብዳቤ ፅፋለች። አዲስ አበባም በድብቅ ሬድዮ፣ ገንዘብና የኢሕአፓን አቋም የሚያስተጋቡ መፈክሮች፣ በራሪ ወረቀቶችና መረጃዎች ታዘዋውር ነበር። ለታማራ ያስደነቃትና ከአያቷ የሰማችው ነገር ቢኖር ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ለመግደል በተጠነሰሰው ሴራ ውስጥ አንዷ መሆኗ፤ ከዚህም በተጨማሪ የቦሌ አየር ማረፊያን ለማፈንዳትም በነበረው ሙከራም እንዲሁ መሳተፏ ነው። "ምስጢራዊ የሆኑ በራሪ ወረቀቶችን ማሰራጨትም ሆነ ሌሎች ተግባራት እንዳሉ ሆነው በዚህ መንገድ በትጥቅ ትግሉ ተሳታፊ መሆኗ ለእኔ አስገራሚ ነበር" ትላለች ታማራ። በተለይም በቦሌ አየር ማረፊያ ውስጥ የፍንዳታ ጥቃት ሙከራ ጋር ተያይዞ የደርግ መንግሥት በጥብቅ ከሚፈልጋቸው አንዷ ነበረች። በወቅቱ አሜሪካ የምትኖረውም አክስቷ በፖስታ ሳጥኗ ደብዳቤ ደረሳት። ሳሊ መንግሥት በሞትም ይሁን በህይወት ከሚፈለጋቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መካተቷን የሚጠቅስ ነበር። መረጃውም እንደሚያሳየው ፀረ- አብዮተኛ ተብላ የተፈረጀችው ሳሊ ቦሌ አየር ማረፊያን ለማፈንዳት ሙከራ አድርጋለች ይላል። ይህችው እህቷም ከዚህ ቀደም አርቲፊሻል ፀጉር፣ የቀዶ ጥገና መቀስ ልካላት ነበር። ታማራ ሳሊ ስለነበራት ተሳትፎም በዝርዝር ለማጣራት ባደረገችው ሙከራ፤ 'የአሲምባ ፍቅር' የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ ካሕሳይ አብርሃ ብስራት (አማኑኤል ማንጁስ)ን ጠይቃለች። ካህሳይ በተወሰነ መልኩ ከሳሊ የሰማውን መንግሥቱን ለመግደል ያለመውን ሙከራም ነግሯታል። ከዚህም በተጨማሪ ከሳሊ ጋር በአንድ ህዋስ ውስጥ የነበረውና የፀሎተ ታናሽ ወንድም የተገደለውም መንግሥቱን ለመግደል ካልተሳካው ሙከራ ጋር ተያይዞም እንደሆነም ሰምታለች። በኢሕአፓ ውስጥ መረጃዎች ሲተላለፉ የነበሩት በከፍተኛ ምስጢር በመሆኑ እንዲሁም ይህንንም የሚያውቁት በውጭ አገራት ያሉና አንዳንዶቹም ለመናገር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ስለ ሳሊ ተሳትፎ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ የላትም። ከካህሳይ በተጨማሪ ስለ ሳሊ የሰማችው አሲምባ ሆና እንደ 'ፐብሊክ ዲፌንደር'፣ ጠበቃ ወይም የህግ ባለሙያ መቅጠር ለማይችሉ ሰዎች በመቆምታገለግል ነበር። ለኢሕአፓም ሆነ ለፓርቲው ወታደራዊ ክንፍ ለሆነው ጦር የሚያስፈልገውን የፍርድ ሂደት ለማከናወን ፍርድ ቤትም ተቋቁሞ ነበር። ይሄም ጉዳይ በአሲምባ ፍቅር ውስጥ ተካቷል። በዝምታ የተሸበበ ታሪክ የሳሊ ቤተሰቦች ዝምታ በዘመኑ የደረሱ በደሎችና ግፎች ነፀብራቅ ናቸው። የኢትዮጵያን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎችን ያጠኑ ሰዎች ድብቅነቱ፣ በዝምታ መሸበቡ የአንድ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን የአጠቃላይ የህዝቡ ፍራቻ መገለጫም እንደሆነ ይናገራሉ። ኢትዮጵያን ለዘመናት የገዟት መንግሥታት በጠመንጃ ኃይል አገሪቷን እንደ ሰም አቅልጠው፣ ህዝቡን በጭቆና በመግዛታቸው መንግሥት የሚለው ቃል የሚፈራ ኃይል ከሚለው ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ትርጉም እንዲሰጠው ሆኗል። ለምሳሌ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተደባብሶና በጀግንነት ስም ተለውሶ የሚነገሩ የጭካኔ ታሪኮችን ማንሳት ይቻላል። በ1950ዎቹ ከሚታወቁት የፊውዳል ገዥዎች መካከል ጃራ ተብሎ የሚታወቀው የራስ መስፍን ልጅ በጭሰኛ ገበሬዎች የሽጉጥ ኢላማ መለማመዱ 'በጀግንነቱ፣ በወንድነቱ እንዲሁም በአልሞ ተኳሸነቱ' እንዲሞካሽ አድርጎታል። መሳፍንቱንና ነገስታቱን እንደ አምላክ ማየትና መፍራት የጭቁኑ አርሶ አደር እውነታ ነበር። ከአፄ ኃይለ ስላሴ መገርሰስ በኋላ ስልጣኑን የተቆጣጠረው ደርግም ከጠመንጃ አስተዳደር ባለመውጣቱ እንዲሁም የተከሰተው እልቂት ሽብር አነገሰ። ፍራቻው ዝምታም እንደ ሃገር፣ እንደ ህዝብ፣ የያንዳንዱ ቤተሰብም መገለጫ ሆነ። የደርግ መንግሥትም "የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት፤ እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበት፤ የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ልጆቿም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች" እንደሚለው ተረቱ ወጣቱን"የፍየል ወጠጤ" በማለት በመፈረጅ፣ ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች ቀጠሉ። መንግሥት "የአብዮቱ ጠላቶች' በሚላቸው ብቻ ሳይሆን፤ በሕዝቡም ዘንድ እርስ በርስ መፈራራት፣ መጠራጠርን አነገሰ። ቤተሰብ እርስ በርስ የማይተማመንበት ወቅት፤ እርስ በርስ መጠቋቋምና ማኅበራዊ ትስስሮችም ላሉ። የቤት ለቤት አሰሳው ተጠናከረ፤ 'አብዮት ይፋፋምብን' የሚሉ ጽሁፎች የተለጠፈባቸው በወጣቶች ላይ የሚፈጸሙ የመንገድ ላይ ግድያዎች ተበራከቱ። የአብዮቱ ጠላቶች ተብለው ለተገደሉት ማዘን፣ እርም ማውጣትም የተከለከለ ነበር። ይባስ ብሎ ቤተሰቦቻቸው ለተገደሉባቸው የጥይት ዋጋ መክፈል፣ እንዲሁም ድጋፋቸውን ማሳየት ነበረባቸው። በርካቶች በዝምታ ተዋጡ፤ ፍራቻም ነገሰ፤ ይህም ለትውልድ ተረፈ። ታማራም በፊልሟ በርካታ ሰዎች የተገደሉባቸውን ቪዲዮዎችን እያሳየች ለዘመናት ሐዘናቸውን በውስጣቸው ደብቀው የፈጠረውን ስሜትም አጋርታለች። በባህሉ ውስጥ ያለው ዝምታና ምስጢራዊነት በሳሊ ወይም በሰላማዊት ዙሪያ ባለው በቤተሰብ የሚታየውም በአብዛኛው ቤተሰብ ውስጥም የሚንፀባረቅ ነው። "አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደ ሳሊ ወይም ሰላማዊት አይነት ተመሳሳይ ታሪክ ይኖረዋል። የሞተ፣ የተደበቀ፣ የተንገላታ ወይም ስቃይ የደረሰበት እንዲሁም ሌላ፣ ሌላ አይነት የተደበቀና የማይነገር የቤተሰብ ታሪክ አለ። ራሳቸውም ላይ ቢደርስ ከፍተኛ ህመም ስላለው በርካቶች ከምስጢሩ ጋር መሰቃየትን ይመርጣሉ፤ ታሪኩን መናገር አይፈልጉም" ትላለች ታማራ። ይህ ሁኔታ በቤተሰብ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ "እንደ አገር በጉዳዩ ላይ ከመወያየት በአማራጩ ዝምታን የመረጠ ሕዝብ ነው። ቤተሰቦች ከልጆች ጋር፣ ትምህርት ቤቶችም አይወያዩበትም። እናም ይሄ ህመም ያድጋል፤ ለአገሪቱም በጣም ትልቅ ችግር ነው" በማለትም ታማራ ታሪክን ወደኋላ በመመልከት ምንስ መማር ይቻላል? የሚለውንም አንገብጋቢ ጥያቄ ታነሳለች። አክስቷን ለማግኘት በምታደርገው ሙከራም በወቅቱ የተፈጠሩት ሁኔታዎች ላይ ውይይት እንዲኖር፤ መግባባት እንዲፈጠር፤ በአገር ደረጃም ሕዝቡ ከህመሙ እንዲድንም ለማድረግ ፊልሙን ሰርታለች። በመቶ ሺዎች ባለቁበትም በዚህ ጭፍጨፋ ኢትዮጵያውያንን አስደንግጦ በዝምታ የሸበባቸውም የሳሊ ቤተሰቦች እውነታ የአገሪቱንም እውነታ ያንፀባርቃል። ሳሊን ፍለጋ የእናቷን ናፍቆት፣ የእህቶቿ ህይወትና የሳሊ መጉደል የፈጠረው ክፍተት፣ የዘመን አሻራን ያስቃኛል። ከቤተሰቡ የተገኙ የቀድሞ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ አዲስ አበባ በወቅቱ ምን ትመስል ነበር? ለሚለውም 'ፋይንዲንግ ሳሊ' ምላሽ አለው። ማን ናት ሳሊ? ሳሊ እንዴት አብዮተኛ ሆነች የሚለው በቀይ ሽብርና በዚያን ወቅት አብዮትና ትግል ህይወታቸውን ያጡ የመቶ ሺዎችም ታሪክ ነው። ታማራ ዳዊት ኢትዮጵያዊ ካናዳዊ የፊልም ባለሙያ ናት፤ በርካታ ሙዚቃዎችን፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ፕሮዲውስ አድርጋለች፤ ለምሳሌም ያህል ለሲቢሲ፣ ለብራቮ፣ ለኤምቲቪ፣ ለሬድዮ ካናዳ ከሰራችላቸው መካከል የተወሰኑት ናቸው። በአዲስ አበባም 'ጎበዝ' ሚዲያ የሚባል የፕሮዳክሽን ኩባንያ አላት። ከዚህ ቀደም 'ግራንድ ማ ኖውስ ቤስት' የሚልም አጭር ፊልም ሰርታለች። በአሁኑ ወቅትም 'ቄሮ' የሚል ጥናታዊ ፊልም እየሰራች ነው።
44052351
https://www.bbc.com/amharic/44052351
"የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ
"ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃ የቆየች ሀገር ስንል እኮ ዝም ብለን እንዲያው በጠመንጃ ብቻ አይደለም። በጠመንጃ የቆሰለውንም፤ በሳንጃ የተወጋውንም የሚያክሙ አዋቂዎች ሀገር ናት" የሚሉት ከግማሽ በላይ ዕድሜያቸውን በባህል መድኃኒት ጥናት ላይ ያሳለፉት ዶክተር አሰፋ ባልቻ ናቸው።
"የኢትዮጵያ ባህላዊ መድኃኒትና ሕክምና የምዕተ-ዓመት ጉዞ" ('Acentury of Magico-Religious Healing: The African, Ethiopian case (1900-1980)) በሚለው መፅሀፋቸውም በባህል ህክምና ዘርፍ በፅሁፍ የሰፈሩ ጥንቅሮችን፣ የቁጥርና የፊደላት ማስላት፣ መናፍስት፣ ዕፅዋትን፣ ማዕድናትን እንዲሁም የእንስሳት ተዋፅኦ ፈውስን ማግኘት ኢትዮጵያውያን እንዴት ልቀውበት እንደነበር ዳስሰዋል። አሁንም ቢሆን ለራስ ህመም ጠንከር አድርጎ ማሰር፣ ለጉንፋን ዝንጅብል በማር፣ ለሆድ ድርቀት ተልባን በጥብጦ መጠጣት ብዙ ኢትዮጵያውያን ለራሳቸው ሆነ ለወዳጆቻቸው ፈውስ ብለው የሚመክሯቸው ናቸው። በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በከተማም በሽታ ባስ ካለለ ወደ ህክምና ተቋማት መሄድ የተለመደ አይደለም። "ባህላዊ መድኃኒት ትልቅ ስፍራ ነበረው አሁንም እየተሰራበት ነው። የዘመናዊ ህክምና አቅርቦት ዝቅተኛ መሆን እንዲሁም መወደድ አማራጩን ወደ ባህል መድኃኒት እንዲያዞር አድርጓል" ይላሉ። ትውልድና እድገታቸው ደሴ ከተማ የሆነው ዶክተር አሰፋ የባህል መድኃኒት ምርምራቸውን በዚችው ከተማ ነው የጀመሩት። ለዚህ ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን እውቀት ለመቅሰምና ለባህል ህክምና ቅርብ ከሆኑት ከእናታቸው በላይ ሰው አላገኙም። በታሪክ መምህርነታቸው በደሴ ወይዘሮ ስሒን ትምህርት ቤት ከፍተኛ ዝናን ያተረፉት ዶክተር አሰፋ፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ጥናት እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም በባህል መድኃኒት ላይ ሰርተዋል። "በመንግሥት ፍቃድና ትዕዛዝ እንደ እድል ሆኖ የታሪክ ትምህርት ደረሰኝ እናም እጣ ፈንታዬ ተወሰነ" ይላሉ። በዩኒቨርስቲው ከነበሩት ትልልቅ ምሁራን መካከል ስለ ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይ አውርተው አይጠግቡም። የኢትዮጵያ የባህል መድኃኒት ጅማሬ የኢትዮጵያ የባህል መድኃኒት ምርምራቸውን ሲጀምሩ "ታሪክ እንዴት ይፃፋል? እንዴትስ መደምደሚያ ላይ ይደረሳል?" የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ የሚያስችሉ መሰረትም አስይዟቸው ነበር። የባህል መድኃኒት ውርሳችን ዝም ብሎ በኢትዮጵያዊያን ብቻ የበቀለ ነው? ወይስ ከሌላ ሃገር ተፅእኖ አለበት? እሰከ መቼስ ወደኋላ መውሰድ ይቻላል የሚሉትንም ጥያቄዎችንም ለመመለስ ብዙ ፅሁፎችን ዳስሰዋል። የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ ከፍተኛ ክፍተት አለበት የሚሉት ዶክተር አሰፋ፤ ያንንም ለመሙላት ፅሁፎቹን ከመዳሰስ በተጨማሪ አዋቂዎቹን በማናገር እንዲሁም ስለእፅዋቶቹ በዝርዝር ማወቅ እንደሚያስፈልግ ዶክተር አሰፋ ይገልፃሉ። መድኃኒቶቹም ሆነ ዕውቀቱ ይጠበቅበታል የሚባሉት ቤተ-ክርስቲያን እንዲሁም መስጊዶችን ፈትሸዋል። ኢትዮጵያ በባህል መድኃኒት ረዥም ታሪክ እንዳላት ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ ያደረጉ የተጓዦችን ማስታወሻ እንዲሁም የሪቻርድ ፓንክረስት ፅሁፎችን ያጣቅሳሉ። "ከቀላል ስብራት ጀምሮ ውስብስብ ተውሳክና እንደ ካንሰር ወይም በተለምዶ መጠሪያው ነቀርሳ የመሳሰሉ የውስጥ በሽታዎችን ማከም ይሞክሩ የነበሩበት አገር ሰዎች መኖሪያ ለመሆኗ፤ በአረብኛ፣ በግዕዝ፣ የማጣቀሻ ፅሁፎችም አሉ" ይላሉ። የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ የፖለቲካ ታሪኩ ብቻ ነው የሚሉት ዶክተር አሰፋ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ውትድርና፣ የሥርዓተ-ፆታና ሌሎች የታሪኮችን መንገር እንዳልተለመደ ያስረዳሉ። "እኛ የምናውቀው የእፅዋት ስብስቡን ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለመድኃኒትነትም ይጠቀሙባቸው የነበሩ የማዕድኖች ስብስብ ነበራቸው" የሚሉት ዶክተር አሰፋ "ከነበረባቸው ተፈጥሯዊ ችግርና ጦርነት ኢትዮጵያዊያን ረዥም እድሜ ኖረዋል፤ ይህም በመድኃኒት ምን ያህል የላቁ እንደነበር ማሳያ ነው" ይላሉ። ክፍተቱ እንዴት ተፈጠረ? ባለፉት ዘመናት የሀገር በቀሉን የመድኃኒት ህክምና ጥበብ በሐገሪቱ ሰፍኖ ከቆየው ከፊል የፊውዳል ሥርዓትና ከጥቁር አስማትና መጥፎ መናፍስት ጋር አያይዞ መመልከት የተለመደ በመሆኑ የባህል መድኃኒትን ታሪክ ጥላሸት እንደቀባው ያወሳሉ። ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ታሪክ ጋር ተያይዞ የመጣው የዘመናዊነት (ሞደርኒዝም) ታሪክ በባህል መድኃኒት እውቀትም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳሳረፈበት ዶክተር አሰፋ ይናገራሉ። በተለይም በአፄ ምኒልክ ዘመነ-መንግሥት የተጀመሩት ከውጭ ሀገራት የሚመጡ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች በህክምናው ዘርፍም በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቶ እንደነበር ይናገራሉ። መጀመሪያ አካባቢም የምዕራቡ ህክምና ተቀባይነት ያገኘው በአፄ ምኒልክና በመሳፍንቱ አካባቢ ቀጥሎም በመኳንንቱ፣ በአጠቃላይ ደግሞ በዋና ከተሞችና በፖለቲካ የሥልጣን ማዕከሎች በሚገኙ ህዝቦች ዘንድ መሆኑንም ሪቻርድ ፓንክረስትን ጠቅሰው ፅፈዋል። በተለይም የአባላዘር በሽታዎችን ፈውስ ለመፈለግ ከውጭ ሀገር በሚመጡ ሳርሳፓራሊና ካሎሜል ወይም የሜርኩሪ ክሎራይድ መድኃኒቶች መስፋፋትንም ይጠቅሳሉ። ሆኖም ግን አፄ ምኒልክ የባህል ሐኪሞችን ክህሎት ከመጠቀም ወደ ኋላ እንዳላሉም ጨምረው ይናገራሉ። ሆኖም ግን በወቅቱ የባህል መድኃኒቶችን መጠቀም በማህበረሰቡ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ የሰረፀ እንደነበር ይገልፃሉ። የህዳር በሽታ ተብሎ የሚጠራው ኢንፍሉዌንዛ በተከሰተበት ወቅት የባህር ዛፍ ቅጠልና ነጭ ሽንኩርት እንዲሁም የባህላዊ የአልኮል መጠጦች እንደ መከላከያ ወይም ፈውስ ጥቅም ላይ እንደዋሉ የተለያዩ የታሪክ መዛግብቶች እንደሚያትቱ ይናገራሉ። የባህል መድኃኒት ከፍተኛ ክፍተት የተፈጠረው ጣልያን አምስት ዓመት ኢትዮጵያን ይዛ በነበረችበት ወቅት እንደሆነ ዶክተር አሰፋ ይናገራሉ። "ጣልያን የኃገረ-ሰብ መድኃኒትና ህክምና አዋቂዎች ናቸው ባለቻቸውና በተለይም ደግሞ የቤተ-ክህነት ትምህርት በቀሰሙ የመስኩ ባለሙያዎች ላይ በሰነዘረችው ጥቃትና የዘመናዊ ህክምናን ለማስፋፋት ባደረገችው ጥረት የተነሳ በቀደሙት ዘመናት የበላይነት የነበረው የባህል ህክምና መዳከመ ጀመረ"ይላሉ። ከነፃነት በኋላም የባህል መድኃኒቶች ተጠናክረው መውጣት ያልቻሉ ሲሆን በደርግ ጊዜም ከዕምነት ጋር ከተያያዘ ትምህርት ጋር በመጣመሩ የህክምናውን ዕውቀት ያዳበሩ ባለሙያዎች ችግሮች እንደገጠሟቸው ዶክተር አሰፋ ይናገራሉ። ኢህአዴግም ስልጣን ከያዘ በኋላ የባህል መድኃኒትን ማሳደግ፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ማዘጋጀት እንዲሁም የባህል መድኃኒት አዋቂዎችን መመዝገብና ቀስ በቀስም የባህልና ዘመናዊ የሕክምና መስኮችን ስለማዋሃድ በተመለከተ የ1985 ጤና ፖሊሲው ውስጥ ቢካተትም ምንም ሥራ እንዳልተሰራ ዶክተር አሰፋ ይናገራሉ። "ይህን የዕውቀት ሃብት እንደማይረባና እንደማይጠቅም አድርገን ነው የምናየው። የእኛን ሀገር የባህል ህክምና ለምን እንደተጠየፍነው አላውቅም፤ ትውልድ በተላለፈ ቁጥር ትልቅ ሃብት እያጣን ነው። በጣም የሚከበሩ አዋቂ ሰዎችን እያጣን ነው። የአንድ በሽታ መድኃኒት ማወቅ ማለት እኮ በአንድ ዩኒቨርስቲ 20 ዓመት የሰለጠነ ሰው ከአንድ አካል በላይ የሚያውቀው የለም'' ይላሉ። ለስምንት ዓመታት በአትላንታ በሚገኘው በኤምሪ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ማጥናታቸው የኢትዮጵያንም ሆነ የተለያዩ ሀገራትን የባህል መድኃኒቶች በጥልቀት ለማየት እንዳስቻላቸው ይገልፃሉ። ከአሜሪካ ከተመለሱም በኋላ የጤና ጥበቃን እንዲሁም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚሏቸውን ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ለዘርፉ ትኩረት ሰጥተው የባህል መድኃኒት ጥናትና ምርምር የሚደረግበትና ቀጣይነቱን የሚያረጋግጥ ተቋም እንዲኖር ቢጎተጉቱም "ከከንፈር መምጠጥ በላይ ምላሽ አልተሰጠኝም" ይላሉ። "ይህን ያህል ዓመት ተጉዘን አንድ የባህል መድኃኒትን የሚመለከት ተቋም የለም" የሚሉት ዶክተር አሰፋ ያናገሩዋቸው አዋቂዎች በዕድሜ እየገፉ መሆኑና እውቀታቸውን ሳያስተላልፉ እንዳይቀር ስጋት አላቸው። "አንተ ማዕከሉን ክፈተው እንጂ እኛ ያለንን የመድኃኒት ዕውቀትን በነፃ እንሰጥሀለን ብለውኝ ነበር። እሱንም ማድረግ አልቻልኩም" ይላሉ። ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ነበር የሚሉት ዶክተር አሰፋ ተመልሰው ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ መምህርነት እንዲሁም በምርምሩ ክፍል ኃላፊነት ለሁለት ዓመታት ያህል አገልግለዋል። በመቀጠልም የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በመሆን ሦስት ዓመት ከሰሩ በኋላ ካለው ሥርዓት ጋር ባለመስማማታቸው በፍቃዳቸው ከሥራቸው ለቀዋል። በአሁኑ ወቅት በግላቸው ተማሪዎችን ማማከር፣ ምርምሮችን ማድረግ እንዲሁም አዲስ መፅሀፍ ለማሳተም በሂደት ላይ ናቸው።
news-51646826
https://www.bbc.com/amharic/news-51646826
"ዘራፊው ለሕዝብ ጥቅም እየተባለ ክሱ እንዲነሳ ከተደረገ ውርደቱ ለአቃቤ ሕግ ነው" አቶ ዮሐንስ ወልደገብርኤል
ከሙስናና ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያዘ እስር ላይ የነበሩ ስልሳ ሦስት ሰዎች ክሳቸው ተቋርጧል። ክስ ለማቋረጥና ሰዎቹን ከእስር ለመልቀቅ የተሰጠው ምክንያት የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት የሚል ከመሆኑ አንፃር፤ ፍትህን ማስፈን እና እንዲህ ዓይነቱ ውሳኔ እንዴት አብሮ መሄድ ይችላል? የሚልና ሌሎች ከግለሰቦቹ ክስ መቋረጥ ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎችም እየተነሱ ነው።
የደርግ ከፍተኛ አመራሮችን ለመክሰስ ተቋቁሞ በነበረው ልዩ አቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት፣ በኋላም በሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአቃቤ ሕግነት ከዚያም በቀድሞው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕግ ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ ዮሐንስ ወልደ ገብርኤልን በዚህ ጉዳይ ላይ አነጋግረናል። አቶ ዮሐንስ፦ የእነዚህ የሙስና ድንጋጌዎች እንደ ማንኛውም የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ መታየታቸው ከቀረ ከሃምሳ ዓመት በላይ ሆኗቸዋል ብዬ ነው የማምነው። እነዚህ የሙስና ወንጀል ህግ ድንጋጌዎች በመጀመሪያ ደረጃ መደበኛው አቃቤ ሕግ፣ መደበኛው ፖሊስ የሚያስፈፅሟቸው አይደሉም። የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች ምርመራ ፖሊስ ነው የሚያጣራው ከማንም ትእዛዝ አይቀበልም። በተሰጠው ስልጣን፣ በተሰጠው ኃላፊነት ጥቆማ ሲደርሰው ወይም በራሱ ክትትል ሲረዳ ምርመራ አጣርቶ ለአቃቤ ሕግ ይልካል። አቃቤ ሕግም እነዚህን ምርመራዎች ይዞ ወደ ፍርድ ቤት ያቀርባል። ፍርድ ቤትም እንደ ማንኛውም የወንጀል ድንጋጌ አይቶ፣ መዝኖ ውሳኔ ይሰጣል። የሙስና የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች ላለፉት ሃምሳ ዓመታት፣ ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ የመደበኛው አቃቤ ሕግ፣ የመደበኛው ፖሊስና የመደበኛው ፍርድ ቤት እጅ ውስጥ መሆናቸው ቀርቷል ብዬ አምናለሁ። እንደ ቀድሞ አቃቤ ሕግ የምናገረው እነኚህ የሕግ ድንጋጌዎች መደበኛው ፖሊስ፣ መደበኛው አቃቤ ሕግና ፍርድ ቤት አይደለም ውሳኔ የሚሰጥባቸው። ይህ መሰረታዊ ጉዳይ በራሴ በምርምር የደረስኩበት ነው። በፊት በመርማሪ ኮሚስዮን ጊዜ እነ አክሊሉ ኃብተወልድ የተያዙት እኮ ሙስና ፈፀሙ ተብለው አይደል፤ እነሱ ከተያዙ በኋላ ምርመራ ተጀመረ። ከዚያ በኋላ ግን ሂደቱ ተቋረጠና ወደ ፍርድ ሳይቀርቡ ቀሩ። እና የመንግሥት ኃላፊዎች በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ይሄንን ፈፀሙ፣ ይሄንን አደረጉ የሚባል የወንጀል ክስ ከእነ አክሊሉ ኃብተወልድ ጊዜ ጀምሮ ከመደበኛው የወንጀል ሕግ ሥርዓት ወጥቷል በሕግ ሳይሆን በተግባር። ይህ በደርግ ጊዜ ያው ነው፤ በኢህአዴግ ጊዜም ያው ነው፤ አሁንም ያው መሆኑን ነው የማውቀው። የመንግሥት ባለስልጣናት በሙስና ተብሎ ሲከሰሱ ጉዳዩ ከወንጀል ይልቅ እንደ ፖለቲካ ጉዳይ ነው የሚታየው እያሉ ነው? አቶ ዮሐንስ፦ እነዚህ ወንጀሎች ከመደበኛው የፖሊስ ተግባርና ኃላፊነት፤ ከመደበኛው የአቃቤ ሕግ ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም ከመደበኛው የፍርድ ቤት ተግባርና ኃላፊነት ውጭ ባለ አካል ነው ውሳኔ የሚሰጥባቸው። እኔ ያለፉትን አርባ ዓመታት ሁኔታዎች ስገመግም በብዙዎችም ተሳትፌያለሁ በፍፁም ተራው ፖሊስ ሄዶ፣ አጣርቶ ለአቃቤ ሕግ አቅርቦ፣ ፍርድ ቤትም ወስኖ የሚኬድበት ነገር አደለም። ሲጀመርም እነዚህ ወንጀሎች ፖለቲካዊ የተደረጉ ወንጀሎች ናቸው፤ የፖለቲካ ተሿሚ የፖለቲካ ስልጣን ከፖለቲካ ስራዎች፣ ከመንግሥት ሥራዎች ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት ያላቸው የወንጀል ድርጊቶች ናቸው። ከዚህ አንፃር አሁን ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር የተለቀቁትን 63 ሰዎችን ጉዳይ እንዴት ይገመግሙታል? አቶ ዮሐንስ፡ በተመሳሳይ መንገድ ነው የምመለከተው፤ አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ አስፈፃሚ አካላት ለምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክስ የማንሳት ስልጣን አለው፤ ጠቅላይ ሚነስትሩ አንድ የወንጀል ክስ፣ ከመደበኛ የወንጀል ጉዳይ ባሻገር፤ ክሱ ቢነሳ ተመራጭ ነው ብሎ ሊወስንና ለአቃቤ ሕግ ሊያስተላልፍ ይችላል። ይሄ በወንጀለኛ የመቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ያለ ነው። የወንጀል ክስ ባለቤት መንግሥት ነው። ስለዚህ መንግሥት ሲወስን ክሱን ማንሳት ይቻላል። ክሱን የሚያነሳው አቃቤ ሕግ ሲሆን ያቀረብከውን ክስ አንሳ ከተባለ በምንም ምክንያት ይሁን ይሄ የመንግሥት ውሳኔ ነው እንዲነሳ ማድረግ ይቻላል፤ ይሄም በሕጉ ላይ የተቀመጠ ነው። በመንግሥት ውሳኔ እነዚህ፣ እነዚህ ሰዎች ይፈቱ ተብሎ ከተወሰነ፤ በፖለቲካዊ ምክንያት ይሁን ለሌላ፤ እነዚህን ሰዎች በወንጀል ክስ ከምንሄድ እና በሕግ አስፈርደን በፍትህ ሥርዓቱ ማግኘት ከምንችለው ውጤት ይልቅ ክሱ ቢነሳ ይሻላል ብሎ መንግሥት ካመነ ማድረግ ይችላል። ከዚህ አንፃር የመንግሥት የ63 ቱን ሰዎች ክስ ማቋረጥ ትክክል ነው ማለት ነው? አቶ ዮሐንስ፦ ይቻላል በፖለቲካዊ ምክንያቶች ነገር ግን ከዚህ ውጭ አቃቤ ህግ በመግለጫው ሲሰጥ የነበረው ምክንያት ከመንግሥትን ውሳኔ ጋር ለመጣጣም የተደረገ ጥረት ነው። ነገሩ የአቃቤ ሕግ ተቋም ድክመትን ነው የሚያሳየው። ከመንግሥት እነ እከሌ ይፈቱ ተብሎ ከታዘዘ ይቻላል፤ ለውሳኔው ምክንያት በማስቀመጥ የግለሰቦቹ መለቀቅ ተገቢነትን ለማረጋገጥ መሞከር አይገባውም። አቃቤ ህግ በዚህ በዚህ እያለክሱ የተቋረጠበትን ምክንያት ማስቀመጥ አይጠበቅበትም እያሉኝ ነው? አቶ ዮሐንስ፦ የሰጠው ምክንያት በራስ ላይ የመፍረድ ያህል ነው። በቀላሉ መንግሥት በሰጠው አቅጣጫ ወይም አመራር ክሳቸው እንዲነሳ ተደርጓል ከሚል በስተቀር ሌላ ምክንያት ለመደርደር እውቀቱም፣ ችሎታውም አቅሙም ሊኖር አይገባም። የክሱ መቋረጥ ተገቢነትን ላብራራ ካለ እንዴት አድርገህ መዝገብ ከፈትክ? ምንድን ነው የማስረጃው ብቃት? ወደሚል ሊመጣ ነው። መንግሥት እነዚህን ሰዎች አስሮ በፍርድ ሂደት አስፈርዶ፤ ፍትህን አስፍኖ ከማመጣው ውጤት ይልቅ እነዚህን ሰዎች በመልቀቅ የማመጣው ውጤት ይበልጣል ብሎ ሲያምን ሊወስን እንደሚችል በህግ የተቀመጠ ነው ብለዋል። ምናልባት ይሄ የመንግሥት ስልጣን፤ገደብ ውስጥ የሚወድቅበት ምክንያት አለ? አቶ ዮሃንስ፦ ገደብ የለውም፤ አንድ ክስ ይነሳ ብሎ ከታዘዘ ገደብ የለውም። አንድ ክስ ይነሳ ብሎ ካዘዘ ይፈጸማል ነው የሚለው ሕጉ። ክሱ ምንም ሊሆን ይችላል? ጊዜው መቼም ሊሆን ይችላል? ምንም አይነት ገደብ የለም? አቶ ዮሐንስ፦ገደብ የሌለው ስልጣን ነው፤ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የሚል ነገር ግን አለው። ይሄ የእኛ አገር ሕግ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገሮች አለ። የፍትህ ሥርዓትን የሚያሽመደምድ ነገርም አደለም። ነገር ግን እጅግ ጥንቃቄ ባለው ሁኔታ የሚከናወን ነው። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ይህን ትዕዛዝ በሚቀበልበት ጊዜ እንደማንኛውም አሽከር ዝም ብሎ ተቀብሎ ይፈጽማል ማለት አይደለም። የአቃቤ ሕግ ተቋምን ሊያጠለሽ እና ተዓማኒነቱን ሊያሳጣው የሚችል ቆሻሻ ውሳኔ ከመንግሥት ሊመጣ ይችላል። አቃቤ ህግ የሙያ ተቋም፤ ሕዝብን ወክሎ የሕዝብን ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው። ስለዚህ ሥራው ሙያዊ መሆን መቻል አለበት። የዚህ ዓይነት ትዕዛዝ ተቀብሎ ተግባራዊ በሚያደርግበት ጊዜ የእሱ ምክር በጣም ጠቃሚ ነው። አቃቤ ህግ የፌደራል መንግሥትም ህጋዊ አማካሪ ነው። ቁመናው፣ ብቃቱ፣ አስተማማኝ ያልሆነ የአቃቤ ሕግ ተቋም የፖለቲከኞች ውሳኔ አስፈጻሚ ነው የሚሆነው። የአቃቤ ሕግ ሙያ በጣም የተከበረ ነው። በሕዝብ ዘንድ መሳቂያ፣ መሳለቂያ የማያደርገውን ምክር ለመንግሥት ሰጥቶ ነው እንጂ እንዲህ ያለውን ውሳኔ መፈፀም ያለበት ዝም ብሎ ዘራፊውም ሌባውም ለሕዝብ ጥቅም እየተባለ ክሱ እንዲነሳ ከተደረገ የመጨረሻ ውርደቱ ለአቃቤ ሕግ ተቋም ነው። ተአማኒነቱን ያጣዋል። የማን ክስ ነው የሚቋረጠው?እነማን ናቸው የሚለቀቁት? የሚለውስ? መንግሥት ክሶች እንዲቋረጡና ሰዎች እንዲለቀቁ የማድረግ ገደብ የሌለው ስልጣን ካለው፤ አቃቤ ሕግ በምን መልኩ ምክር ሊሰጥ፤ ምን ድረስ ተገቢላይሆኑ የሚችሉ ውሳኔዎችን አይሆንም የማለት፣ የማንገራገር ወይም የመቃወም ስልጣን አለው? በተለይም ከአገሩቱ የተቋማት ጥንካሬ አንፃር፤ አቶ ዮሐንስ፦ለመገዳደር ይችላል፤ ነገር ግን ጀርባ ያለው አቃቤ ሕግ ሲሾም፤ በሙያ፣ በእውቀቱ እና በችሎታው መንግሥትን መምራት የሚችል አቃቤ ሕግ ተቋም ሲኖር ነው። ግልጽ የሆነ ማዕቀፍ ላይ ተመስርቶ የማይሰራ የአቃቤ ሕግ ተቋም ከሆነ ደግሞ ይሄ አሁን እንደሆነው ነው የሚሆነው። በዚህ ረገድ አንዱ እየተፈተነ ያለው የአቃቤ ሕግ ተቋም ነው። ስለዚህ የሰዎቹ አለቃቀቅ፣ የሰዎቹ ስብጥር፣ ምን አይነት ሰዎች ናቸው እየተፈቱ ያሉት የሚለው ጉራማይሌ ነገር ከተገኘ የአሰራር ችግር አለ ማለት ነው። አሁን ለምሳሌ የፖለተካ ምህዳሩን ለማስፋት በሚል እና ለህዝብ ጥቅም ከተባለ በርግጥም የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያሰፋው ምን አይነት ሰዎችን፣ ምን አይነት ፖለቲካዊ ክሶችን አቅርበናል? እነማንን ነው መልቀቅ የሚገባን? የሚሉት በደንብ መታየት አለባቸው። አንድ ክስ የቴክኒክ ማስረጃ ክፍተት ከተገኘበት በመንግሥት ስልጣን ሳይሆን አቃቤ ሕግ በራሱ ስልጣን ክሱን እንዲቋረጥ ማድረግ ይችላል። ቴክኒካል የሆነ ማስረጃው በቂ ነው ወይስ አይደለም፣ ደካማ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጉዳይ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ስልጣን ነው። ደካማ ክስ፣ አጓጉል ክስ፣ ባለበት ሁኔታ መወሰን ይገባው የነበረው አቃቤ ሕጉ እንጂ መንግሥት አይደለም፤ የመንግሥት ውሳኔ ለአቃቤ ህግ ደካማ ክሶች ሽፋን መሆን የለበትም። አቃቤ ህግ በቂና አሳማኝ ባልሆነ ማስረጃ ክስ መመስረት የለበትም። ክስ ለመመስረት የማያበቁ አካሄዶችን አቃቤ ሕግ በራሱ ስልጣን ቀድሞ ሊያስቆማቸው ይገባል? አቶ ዮሐንስ፦አዎ ማድረግ ነበረበት፤ በትክክል። ይሄ ግን ብዙ ጊዜ ሲተገበር አናይም እንዲያውም የሚታየው ልፍስፍስ ክሶች ሁሉ እንዲስተናገዱ ሲደረግ ነው። ብዙዎች ውሳኔ ማሰጠት የማይችሉ ደካማ ክሶችን ፍርድ ቤት እያቀረቡ፤ ነገር ግን መንግሥት ለህዝብ ጥቅም ብሎ የሚያቋርጣቸው ናቸው። የመንግሥት ትኩረት መሆን የነበረበት ግን በደንብ ለፍርድ ሊቀርቡ፣ ሊፈረዱ የሚችሉ ጉዳዮችን ተመልክቶ ለህዝብ ጥቅም ነው ብሎ ካመነ መወሰን ነበር። አሁን የተቋረጡት ክሶች ማስረጃ ክስ ወደ መመስረት የማያበቁ ነበሩ ብለውያምናሉ? አቶ ዮሐንስ፦ ማመን አይደለም፤ እገምታለሁ ምክንያቱም መዝገቡን ስላላየሁ እንደዛ ብዬ እንደ ቀድሞ አቃቤ ሕግ አፌን ሞልቼ ልናገር አልችልም። ነገር ግን መንግሥት ለህዝብ ጥቅም ብሎ እንዲነሱ የሚያደርጋቸው በጣም የተሟላ መረጃ ባላቸውና በማያጠራጥር ሁኔታ ፍርድ ቤት ፍርድ ሊያሳርፍባቸው የሚችሉ ጉዳዮች መሆን አለባቸው፤ በተረፈ ግን እነዚህ 63 ክሶች በእኔ እምነት ብዙዎቹ የመንግሥት ውሳኔ ሊያርፍባቸው ይገባል ብዬ አላምንም። አብዛኞቹን ምናልባት አቃቤ ሕግ አስቀድሞ እንደ ክስም አድርጎ ሊያቀርባቸው የማይገቡ የነበሩ ናቸው የሚዲያ ሪፖርቶች ስሰማ፤ አሁን ለምሳሌ ተመሳሳይ ሊቀርቡ የማይገቡ ክሶች በፍርድ ቤት ሂደት ላይ አሉ። ነገር ግን እነዚህ ክሶች በዚህኛው የክስ መቋረጥ ውሳኔ ውስጥ አልተካተቱም። ይሄን ያህል ቁጥር ያለው ተከሳሽ በመንግሥት ውሳኔ ይስተናገዳል ብዬ አላስብም፤ አብዛኞቹ ጉዳዮች አቃቤ ሕግ ዝም ብሎ አድፈንፍኖ ያቀረባቸው ናቸው ብዬ እገምታለሁ። እና አሁን መንግሥት ይህንን ውሳኔ ሲሰጥ በዚያ ውስጥ ተካተው እንዲስተናገዱ አደረጉ ብዬ ነው የማስበው፤ አቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት አለ ብዬ አላምንም ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ።
news-54267354
https://www.bbc.com/amharic/news-54267354
ፍትህ፡ የጎልያድና የዳዊት ፍልሚያ ነው የተባለለት የፍርድ ቤት ክርክር
ኢንዶኔዥያዊት የቤት ሠራተኛ ናት፤ ለተሻለ ኑሮም ቀዬዋን ለቃ ኑሮዋን በሲንጋፖር አደረገች።
ፓርቲና አሰሪዋ ሊየው ሙን ሊዮንግ በናጠጡ የሲንጋፖር ቱጃር ቤተሰቦች ተቀጥራም ትሰራ ነበር። በየወሩም ስድስት መቶ ዶላር (23 ሺህ ብር ገደማ) ይከፈላታል። አሰሪዋ በአገሪቱ ውስጥ አሉ የሚባሉ ሃብታም ሲሆን፤ የተለያዩ ኩባንያዎችን መስራች፣ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅም ናቸው። ዕቃ ሲጠፋ የቤት ሠራተኞችን መወንጀል በብዙ ቦታዎች እንደሚያጋጥመው ሁሉ የዚህ ግለሰብ ቤተሰብም እቃዎችን "ሰርቀሻል፣ ዘርፈሽናል" አሏት። ዘርፈሽናል ብለው ብቻ አልቀሩም፤ ፓሊስ ደውለው ጠሩ። የፍርድ ሂደቱም ባልታሰበ ሁኔታ የሚዲያዎችንም ሆነ የሕዝቡን ቀልብ የገዛና ታሪካዊ መሆን ችሏል። ፓርቲ ሊያኒ ውድ የእጅ ቦርሳዎችን፣ የዲቪዲ ማጫወቻን በመስረቅ የተወነጀለች ሲሆን ከዓመታት ተስፋ አስቆራጭ የፍርድ ቤት ውጣ ውረድ በኋላ በዚህ ወር ነው ነፃ የወጣችው። "በመጨረሻም ነፃ በመሆኔ ተደስቻለሁ" በማለት በአስተርጓሚዎቿ አማካኝነት ለሪፖርተሮች ተናግራለች። "ለአራት ዓመትም ያህል እየታገልኩ ነበር" ብላለች። ሆኖም የፍርድ ሂደቱ በርካታ የፍትህ ጥያቄዎችን አስነስቷል። በተለያየ የኑሮ ደረጃ ያሉ ሰዎች በሲንጋፖር የፍትህ ሂደት ምን ያህል በእኩል ደረጃ እንደማይታዩም ያሳየ ነው ተብሏል። በተለይም ጥፋተኛ ሆና መገኘቷ የሥርዓቱን መበስበስ ያሳየ ነው በማለትም ተችተውታል። ፓርቲ ሊያኒ በአሰሪዋ የተቀጠረችው በጎሮጎሳውያኑ 2007 ነበር። አሰሪዋ ሊየው ሙን ሊዮንግና በርካታ የቤተሰቦቹ አባላት የሚኖሩት በአንድ ቤት ውስጥ ይኖሩ ነው፤ ልጁ ካርልም ከቤተሰቡ ጋር በዚሁ ቤት ይኖር ነበር። የሥራ ድርሻዋም እነዚህን ሁሉ ሰዎች መንከባከብና ለእነሱ ምግብ ማብሰል፣ ልብስ ማጠብ፣ ማፅዳትና እንዲሁም ሌሎች ኃላፊነቶች ነበሩባት። በ2016 ልጅየው ካርል ሊየው ከባለቤቱና ከልጆቹ ጋር ሆኖ ከአባቱ ቤት ወጥቶ ሌላ ቤት ይኖር ጀመረ። ልጅየው ሌላ ቤት መኖር ሲጀምርም የእሷ የሥራ ድርሻ ባይሆንም የልጁን ቤትም ሆነ ቢሮውን እንድታፀዳ በተደጋጋሚ ትጠየቅ እንደነበረ ለፍርድ ቤት የቀረበው ማስረጃ ያስረዳል። ይህ ሁኔታ የአገሪቱን የአሰሪና ሠራተኛ ህግ የጣሰ ሲሆን እሷም በተደጋጋሚ ቅሬታዋን አቅርባለች። ከጥቂት ወራት በኋላም የአሰሪዋ ቤተሰቦች ሰርቀሻል በሚል ውንጀላ ከሥራ አባረሯት። ልጅየው ካርል ሊው ከሥራ መባረሯን ሲነግራትም "ለምን እንደተባረርኩ አውቃለሁ፤ ሽንት ቤትህን አላፀዳም በማለቴ ነው" ብላው ነበር። ያላትን ጓዝ ጠቅልላ እንድትወጣም የተሰጣት ሁለት ሰዓት ነበር። ሆኖም እቃሽን ወደ አገርሽ እንልክልሻለን አሏት። እሷም በዚያኑ ቀን ወደ ኢንዶኔዥያ ተመለሰች። ሆኖም እቃዋን እያስተካከለች እያለም ለሲንጋፖር ባለስልጣናት ያልተዋወለችበትን የልጁን ቤት አጽጂ መባሏን በመጥቀስ እከሳለሁ አለች። ፓርቲም ከቤት ከወጣች በኋላ የጠቀለለችውን ጓዝ ሲያዩ የእሷ ያልሆነና የሰረቀችው ዕቃ እንዳገኙ ለፖሊስ ሪፖርት አደረጉ። ፓርቲ ስለዚህ ጉዳይ የምታውቀውም አልነበረም። ከአምስት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ሌላ ሥራ ፈልጋ ወደ ሲንጋፖር ተመልሳ ስትመጣ በቁጥጥር ስር ዋለች። የፍርድ ሂደቷም ተጓተተ፤ በነበረባት የወንጀል የፍርድ ሂደት ምክንያት መስራት ስላልቻለች በስደተኛ ሠራተኞች መጠለያ ውስጥም ለመቆየት ተገደደች። ኑሯዋንም ለማሸነፍ የእነሱን ድጋፍ ማግኘት ነበረባት። ሰረቀች የተባለችው ምንድን ነው? ፓርቲ አሰሪዎቿ ሰረቀች ብለው የሚወነጅሏት 115 ልብሶች፣ ውድ ቦርሳዎች፣ የዲቪዲ ማጫወቻና ጌራልድ ጌንታ የተሰኘ ስያሜ ያለው ሰዓት ነው። የእነዚህ እቃዎች ዋጋም ሲገመት 34 ሺህ ዶላር (1.3 ሚሊዮን ብር) የሚያወጣ ነው አሉ። በፍርድ ሂደቱም ወቅት የእሷ መከራከሪያ የነበረው አንዳንዶቹ እቃዎች እነሱ እንደሚሉት የተሰረቁ ሳይሆኑ ተጥለው የተገኙ፣ የራሷ እቃዎችና እሷ ከቤታቸው ከተሰናበተች በኋላ ሻንጣዎቿ ውስጥ ሆን ተብለው የተከተቱ ናቸው ትላለች። ሆኖም በ2019 የአንድ ግዛት ዳኛ ጥፋተኛ መሆኗን የበየኑባት ሲሆን ሁለት ዓመት ከሁለት ወርም እንድትታሰር ወሰኑባት። ሆኖም ፓርቲም ዝም አላለችም ይግባኝ ጠየቀች። ጉዳዩ እየተጓተተ ወደ ሲንጋፖር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደረሰ ሲሆን በመጨረሻም ባለንበት የመስከረም ወር ነው ፍርድ ቤቱ በነፃ እንድትሰናበት ወሰነ። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ቻን ሴንግ ኦን እንዳሉት ከአሰሪዎቿ ክስ ጀርባ ድብቅ ሴራ እንዳለ ጠቅሰው፤ ከዚያም በተጨማሪ በጉዳዩ ላይ የተሳተፉ ፖሊሶች፣ ዐቃቤ ሕግና የግዛቲቷ ዳኛም ላይ ጣታቸውን ጠቁመዋል። አሰሪዎቿ ለፖሊስ ሪፖርት ያደረጉት የአሰሪና የሠራተኛ ሕግን በመጣስ የቤት ሠራተኛቸው የልጃቸው ካርል ቤት እንድትሰራ ማዘዛቸውን በመጥቀስ እንዳትከሳቸው ለማድረግ ነበር ብለዋል ዳኛው። ፓርቲ ሰርቃለች ተብሎ በአሰሪዎቿ የቀረቡት ቁሶች ማለትም ሰዓቱም ሆነ ሁለት ስልኮች ከጥቅም ውጪ የሆኑና የማይሰሩ ናቸው ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ አሰሪዎቿ አይሰራም ብለው የወረወሩት የዲቪዲ ማጫወቻን ሰርቀሻልም ተብላ እንደ ማስረጃ ቀርቦባታል። በኋላ ላይ ዐቃቤ ሕግ የዲቪዲ ማጫወቻው እንደማይሰራ ያውቁ እንደነበር ቢገልፅም፤ በፍርድ ሂደቱ ግን እንደ አንድ ማስረጃ ሆኖ ቀርቦ ነበር። ይህም ሁኔታ የፍርድ ሂደቱን ያዛባ ነው በሚል ዳኛ ቻን ተችተውታል። ከዚህም በተጨማሪ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ሆኖ የቀረበው የባለሐብቱ ልጅ ካርል ያቀረባቸው ማስረጃዎችም ታማኝነት በዳኛው ዘንድ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ፓርቲ ሰረቀቻቸው የተባሉ በርካታ የሴት ልብሶች የነበሩ ሲሆን የማን እንደሆኑ በተጠየቀበት ጊዜ ካርል "የእኔ ናቸው" ብሏል። በፍርድ ሂደቱም ወቅት አንዳንዶቹን ማስታወስ ካለመቻሉ በተጨማሪ "የሴት ልብሶች ለምን ኖሩት?" ለሚለው ጥያቄ "እንደ ሴት መልበስ እንደሚወድ" ቢናገርም ዳኛ ቻን "የሚታመን" ሆኖ አላገኙትም። ፖሊስ በበኩሉ ወንጀሉ ተፈፅሞበታል የተባለውን ቤት ያየው ሪፖርት ከተደረገ ከአምስት ሳምንታት በኋላም መሆኑ ጥያቄን በዳኛው በኩል አጭሯል። ፓርቲ የምትናገረው ቋንቋ አንደኛው የኢንዶኔዥያ ቢሆንም ፖሊስ በፍርድ ሂደቱ ወቅት አስተርጓሚ አላቀረበላትም። እሷ የማትናገረውን ማሌይ የተባለውን ቋንቋ አስተርጓሚ ነው የቀረበላት። "ፖሊስ ምርመራውን ያካሄደበት መንገድ በጣም የሚያሳዝንና አሳሳቢ " በማለት በሲንጋፖር ማኔጅመንት ዩኒቨርስቲ የሕግ ፕሮፌሰር የሆኑት ኡጅን ታን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የግዛቲቱ ዳኛም ቢሆኑ ቀድመው ነው ውሳኔ ላይ የደረሱት። ፖሊስም ሆነ ዐቃቤ ሕግ የፈፀሟቸውን ስህተቶች ማየት አልቻሉም" ይላሉ። የዳዊትና ጎልያድ ትግል የበርካቶችን ቀልብ መግዛት የቻለው ይህ የፍርድ ሂደት በቱጃሩና በቤተሰቦቹም ላይ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ምን ያህል ሃብታሞች ከሕግ በላይ እንደሆኑና ደሃዎችና መጠጊያ የሌላቸውን ቢያሰቃዩና ቢበድሉም የሚደርስባቸው ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው፤ ይህንንም አሳዛኝ እውነታ ያጋለጠ ነው ተብሏል። ምንም እንኳን መጨረሻ ላይም ቢሆን ፓርቲ ፍትህ ብታገኝም በአጠቃላይ ሥርዓቱ ላይ ጥያቄ አስነስቷል። "በቅርብም እንዲህ አይነት የፍርድ ሂደት አስታውሳለሁኝ" የሚሉት ፕሮፌሰሩ "በብዙዎች ጭንቅላት ይመላለስ የነበረውም በእሷ ቦታ እኔ ብሆንስ? ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ምርመራው ይካሄድ ይሆን? የተዛባ ዳኝነት ያጋጥመኝ ይሆን የሚለው ነው።" አሰሪዎቿ ፖሊስንና ፍርድ ቤቱን ሐሰተኛ በሆነ ክስ መቆጣጠር ችለዋል፤ ይህም የአገሪቱ አጠቃላይ የፍትህ ሥርዓት ላይ ጥያቄ አስነስቷልም ተብሏል። ይህ ሊዋጥላቸው ያልቻለው ሲንጋፖራውያን ቁጣ ተከትሎ ሊየው ሙን ሊዮንግና ሥራ አስኪያጅ ከሆኑባቸው በርካታ ኩባንያዎች ራሳቸውን በጡረታ እንደሚያገሉ አስታውቀዋል። የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብሩና በሲንጋፖር የፍትህ ሥርዓትም እምነት እንዳላቸው ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ሆኖም የቤት ሠራተኛቸውን ለፖሊስ ሪፖርት በማድረጋቸው ግን ምንም እንደማይፀፀት አሳውቀዋል። "ከልቤ የማምነው ነገር ቢኖር ወንጀል ተፈፅሟል ብለን የምንጠራጠር ከሆነ ለፖሊስ ማሳወቅ የዜግነት ግዴታችን ነው" ብለዋል። ልጅየው ካርል በበኩሉ በሁኔታው ላይ ዝምታን የመረጠ ሲሆን፤ ምንም አይነትም መግለጫ ከመስጠትም ተቆጥቧል። ፓርቲና ጠበቃዋ አኒል ባልቻንዳኒ ይሄ ጉዳይም የፓርቲ ብቻ ሆኖ አልቀረም የፖሊስና ዐቃቤ ሕግ ምርመራቸውን የሚያካሂዱበት ሁኔታ መገምገም አለበት ተብሏል። የሕግና የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኬ ሻንሙጋም ቢሆኑ በፍርድ ሂደቱ ስህተት እንደተፈፀመ አምነው መንግሥት በቀጣይነት የሚያደርገውንም በጥብቅ እንከታተላለን ብለዋል። ገንዘብና ስልጣን ምን ያህል የተቆራኘ መሆኑንና ሃብታም ሰዎችም ሕግን እንደፈለጉ ማሽከርከር ይችላሉ የሚለውን እሳቤ ከማጉላቱም በተጨማሪ ስደተኛ ሠራተኞች ፍትህን ለማግኘት ያለባቸውን ፈተና አጋልጧል ተብሏል። ፓርቲ መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጅት ድጋፍ በሲንጋፖር ቆይታ ወንጀለኛ አይደለሁም በሚል ተከራክራለች። ጠበቃው አኒል ባልቻንዳኒም 150 ሺህ ዶላር የሚያስከፍለውን የጥብቅና አገልግሎቱን በነፃ ሰጥቷታል። "ጠበቃዋ ከመንግሥት ጋር ተናንቆ ነው የታገለላት፤ የዳዊትና የጎልያድ ትግልም ይመስላል፤ በመጨረሻም ዳዊት አሸነፈ" ይላሉ ፕሮፌሰር ታን። ፓርቲ በበኩሏ በአሁኑ ወቅት ወደ ትውልድ አገሯ ለመመለስ ዝግጁ ናት። "ችግሮቼ ሁሉ ተቀርፈዋል እናም ወደ ኢንዶኔዥያ መመለስ እፈልጋለሁ" በማለት ለአንድ ሚዲያ የተናገረችው ፓርቲ "አሰሪዎቼን ይቅርታ አድርጌላቸዋለሁ። በሌሎች ሠራተኞች ላይ እንዳይደግሙት ብቻ መንገር እፈልጋለሁ" ብላለች።
56916800
https://www.bbc.com/amharic/56916800
ምርጫን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የሶማሊያ ውዝግብ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ያመራ ይሆን?
በሶማሊያ ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ መዘግየቱ አለመግባባትን እና በፖለቲከኞች መካከል አለመተማመንን አባብሷል።
ይህንንም ተከትሎ በመዲናዋ ሞቃዲሾ የሰዎች ሕይወት የጠፋበት አመጽ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አገሪቱን ወደ ከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። በመዲናዋ ሞቃዲሾ በፌዴራል ኃይሎች እና በታጠቁ የተቃዋሚ ታማኝ ኃይሎች መካከል ከቀናት በፊት በተነሳ ግጭት ቢያንስ አስር ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ይቀጥላል በሚል በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች 'ሠላማዊ' ወደሚሏቸው መንደሮች ተሰደዋል። ክፍተቱ ለአል-ሻባብ የአፍሪካ ቀንዷን አገር የበለጠ ለማተራመስ መልካም አጋጣሚ ሊሆነው ይችላል። ታጣቂዎቹ ከቅርብ ወራት ወዲህ ብቻ በምርጫው ዙሪያ ውይይቶች በተካሄዱባቸው ቦታዎች ላይ በርካታ ጥቃቶችን አካሂደዋል። የአገሪቱ የታችኛው ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆን የስልጣን ዘመን በሁለት ዓመት ይራዘም ሲል ወሰነ። ከሁለት ሳምንት በፊት ከተላለፈው ውሳኔ በኋላ የአገሪቱ የፖለቲካ ክፍተቶች ተባብሰዋል። ከወራት ውይይቶች በኋላ ውሳኔው ሲጸድቅ የፌዴራል መንግሥቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሕዝባዊ ምርጫዎችን እንዲያደራጅ ቢያዝም የአገሪቱን የምርጫ ቀውስ ማስቆም አልቻለም። የሶማሊያ ዓለም አቀፍ አጋሮች እና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች የሥልጣን ማራዘሙን ውድቅ በማድረግ ፋርማጆን ሥልጣንን የሙጥኝ ብለዋል ሲሉ ከሰዋል። የተነሳባቸው ተቃውሞና ሊከተል የሚችለው ቀውስ ያሰጋቸው ፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመናቸውን የማራዘም ፍላጎታቸውን እንዲተዉ አስገድዷቸዋል። ነገር ግን ውጥረቱ በጎሳ ፉክክር ይበልጥ እየከረረ ነው። ከአስርት ዓመታት የእርስ በእርስ እና የታጣቂዎች ግጭት በኋላ የተገኘውን አንፃራዊ መረጋጋት ሊቀለበስ የሚችልም ነው። ቁልፍ ተዋናዮች እና ምላሾች ተቃዋሚዎች የፋርማጆ ሥልጣን የካቲት 8 ስላበቃ ከእንግዲህ ለፕሬዝዳንትነታቸውን እውቅና አንሰጥም ብለዋል። ናሽናል ሳልቬሽን ፎረም (ብሔራዊ አገርን የማዳኛ መድረክ እንደማለት ነው) ተቋቁሟል። ፎረሙ ተሰሚ በሆኑ ተቃዋሚዎች የተቋቋመ ነው። የፋርማጆ ቀንደኛ ተቃዋሚ የሆኑት የምክር ቤት አፈ ጉባኤ አብዲ ሀሺ አብዱላሂ፣ የጁባላንድ እና ፑንትላንድ መሪዎችን ያካተተ ጥምረት ነው። ሕገ መንግሥታዊ ባልሆነው የሥልጣን ማራዘሚያ ላይ "አስፈላጊ እርምጃዎችን እንወስዳለን" ሲሉም ዝተዋል። የሴኔቱ አፈ ጉባኤ አብዱላሂ እንዳሉት፤ ፕሬዚዳንቱ የውሳኔ ሐሳቡን ለማጽደቅ የላይኛውን ምክር ቤት ሳያቀርቡ ማራዘማቸው ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነው። የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒ እና የጁባው አቻቸው አህመድ መሐመድ ኢስላም በሞቃዲሾ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ነበር። "ሶማሊያን ከማይቀረው የትርምስ አዘቅት ውስጥ እንዳትገባ እንዲያድኑ" ጠይቀዋል። የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ምክር ቤት ፋርማጆን ለመተካት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው የፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ጥምረት ነው። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሻሪፍ ሼህ አህመድ የሚመራ ሲሆን ፕሬዚዳንቱን "የጦር አበጋዝ" ብለዋቸዋል። የሃውያ ንዑስ ጎሳ አባላት ተደማጭነት ካላቸው ጎሳዎች መካከል ነው። ለአንድ ቀን በመዲናዋ ሞቃዲሾ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ሥልጣን የማራዘሙን ውሳኔ ውድቅ አድርገውታል። አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና የአውሮፓ ሕብረት ሥልጣን የማራዘሙ ውሳኔ ሶማሊያ ወደ ሰላምና መንግሥት ግንባታ የምታደርገውን ጉዞ የሚያደናቅፍ ነው ብለዋል። ግንኙነታቸውን በድጋሚ እንደሚያጤኑትም አስጠንቅቀዋል። አሜሪካ "ሰላምና መረጋጋትን በማደናቀፍ" በሥልጣን ማራዘሙ በተሳተፉት ላይ ማዕቀብ እንደምትጥል ዝታለች። የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት ሥልጣን ማራዘሙን ውድቅ አድርጎታል። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ መሪዎች በምርጫ ውዝግቡ ዙሪያ ውይይት እንዲቀጥሉ ያቀረበውን ሐሳብ እንደሚደግፍ አስታውቋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም በታችኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴዎች እና በጋልሙዱግ፣ በሂውማሌ እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች ሰፊ ድጋፍ አላቸው፡፡ በቋፍ ላይ ያለ የፌዴራል ሥርዓት የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሥርዓት ሥር የሰደደውን የጎሳ ግጭት ለማቆም እና የአንድነት መንግሥት ለመመስረት የሚደረገውን ጥረት በመሰናከሉ የተመሠረተ ነው። ይህን ተከትሎም የተቆራረጠ እና ደካማ ቢሆንም ብሔራዊ ደኅንነት ግንባታው እያዘገመም ቢሆን እንዲጓዝ መንገዱን ጠርጓል። አገሪቱ ከ30 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት ሥርዓት ለመቀላቀል የፋይናንስ ተቋማቷን እንደገና አደራጅታለች። ምርጫው ያስከተለው አለመረጋጋት በማዕከላዊ መንግሥት እና ቀድሞውንም የፋርማጆን ሥልጣን 'በሚያኮስሱት' አንዳንድ የክልል መንግሥታት መካከል ውዝግቡን አጡዞታል። እአአ በመስከረም 2018 አምስት የአገሪቱ የክልል ፕሬዚዳንቶች በሥልጣን እና በሀብት ክፍፍል አለመግባባት ምክንያት ከፌዴራል መንግሥት ጋር እንደማይተባበሩ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ፋርማጆ ለምላሽ አልዘገዩም። ክልሎችን በራሳቸው ቁጥጥር ስር ማድረግ ጀመሩ። ተቀናቃኝ ሊሆኑ የሚችሉትን በመንቀል አጋሮቻቸውን በጋልሙዱግ እና በደቡብ ምዕራብ ግዛቶች አስቀመጡ። የፌዴራሉ መንግሥት በፑንትላንድ እና በጁባላንድ ባሉ ምርጫዎች ላይ ተመሳሳይ ተጽዕኖ ማሳደር አልቻለም። የእነዚህ አካባቢ መሪዎች ፋርማጆ እንደገና እንዳይመረጡ እየሠሩ ነው። የፖለቲካ ህልውናቸው የተመሠረተው በዚሁ ላይ ነው። የመስከረም 17ቱ ስምምነት ብሔራዊው የምርጫ ኮሚሽን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያለው ሕዝባዊ ምርጫ ለማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል። ተዓማኒነት ያለው ምርጫ ለማዘጋጀት እስከ 13 ወር ድረስ እንደሚያስፈልገው እአአ ሰኔ 2020 ለሕዝብ እንደራሴዎች ገልጿል። የጁባላንድ፣ ፑንትንትላንድ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን መዘግየት ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆኑም። እአአ ሐምሌ 2020 አስደንጋጭ ነበር የተባለለት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ኬይሬ ከሥልጣን መነሳት በምርጫው ሂደት ላይ ያላቸውን እምነት ይባስ ሸረሸረው። የጁባላንድ እና የፑንትላንድ መሪዎች በማዕከላዊው ዱሳማሬብ ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። በስብሰባው ላይ ከምርጫ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ስምምነት ተደርሷል። የአማጺያኑ አመራሮች አድሏዊ ነው ሲሉ የምርጫ ኮሚሽኑ እንዲፈርስ ጠይቀዋል። እአአ መስከረም 17 ቀን 2020 ከሳምንታት የዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ በምርጫ ሁኔታዎች ላይ ስምምነት ተፈረመ። በስምምነቱ መሠረት ሁለት የምርጫ ክልሎች በእያንዳንዱ ክልል ይኖራሉ። ምርጫዎች የሚካሄዱት በየክልል ተሰብሳቢዎች ላይ ተመስርቶ ሲሆን በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ውስጥ 101 የምርጫ ልዑካን ድምጽ ይሰጣሉ። በአማጽያን ጥያቄ መሠረት ምርጫውን በበላይነት የሚቆጣጠር ብሔራዊ እና ክልላዊ የምርጫ ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙ ተወሰነ። የጁባላንዱ ማዶቤ እና የፑንትላንዱ ዴኒ በፌዴራል መንግስት የተቋቋመውን የምርጫ ኮሚሽን ባለመቀበላቸው የስምምነቱ ትግበራ እንቅፋት ገጠመው። የጸጥታ አዛዦች እንዲነሱ እና ፓርላማው እንዲበተንም ጠይቀዋል። የምርጫውን መዘግየት አስቀድሞ የገመተው የፌዴራሉ ፓርላማ እአአ ኅዳር 2020 አዲስ ተመራጮች እስኪተኩ ድረስ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል። የዘር ፖለቲካ እና ግጭት በምርጫው ላይ በተፈጠረው ክፍፍል ላይ ብሔራዊ ማንነት እና የጎሳ ማንነት ልዩነትም ሚና ተጫውተዋል። አለመተማመን እየጠነከረ ሲሄድ ፖለቲከኞች እና ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናት ወደ ጎሳቸው መመሸግ ጀመሩ። እነዚህም በጎሳ ሚሊሻዎች፣ በጎበዝ አለቆች እና በቀድሞ የጦር መሪዎች የሚጠበቁ ናቸው። የተወሰኑ የተቃዋሚ የፓርቲ አመራሮች ለትጥቅ ትግል መዘጋጀት ያዙ። የጦር መሣሪያዎችና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የገዙም አሉ። በመዲናዋ ሞቃዲሾ የዘገየውን ምርጫ የሚቃወሙ ሰልፈኞችን በሚደግፉ ወታደሮች እና በፖሊስ መካከል መጋቢት 15 ቀን ግጭት ተፈጥሯል። የፖሊስ መኮንኖቹ በቱርክ የሰለጠነው ልዩው የሃርማድ የፖሊስ ኃይል አባላት ነበሩ። ከዚህ በፊት መንግሥት ፍላጎቱን በክልል መንግሥታት ላይ ለመጫን ልዩ ኃይሉን ይጠቀም ነበር። የቀድሞው የሞቃዲሾ የፖሊስ አዛዥ ሳዲቅ ኦማር ሃሰን (ሳዳቅ ጆን) በምርጫ ውዝግብ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀውን የፓርላማ ስብሰባ በማገድ እአአ ሚያዝያ 13 ፊታቸውን መንግሥት ላይ አዞሩ። ከኃላፊነት ተነስተው ማዕረጋቸውም ተገፈፈ። የቀድሞው የፖሊስ አዛዥ ከቀናት በኋላ በጎበዝ አለቆች እና ከጎሳቸው በተገኙ ሚሊሺያዎች እየተጠበቁ በከተማው በዳይናል አካባቢ ካምፕ መሠረቱ። መንግሥት የታጠቁ የጸጥታ ኃይሎችን በአቅራቢያው ወደሚገኙ አካባቢዎች በማሰማራቱ ውጥረቱ ዋና ከተማዋን አዳርሷል። በኋላ ላይ ሁኔታው ተረጋጋ። በፋርማጆ ላይ የተጀመረው አዲስ አመጽ የጎሳ ጦርነት ቀስቅሶ አገሪቱን በቀላሉ ወደ የእርስ በእርስ ግጭት እንዳያስገባ ያሰጋል። የፖለቲካ እና የደኅንነት አንድምታዎች የአልሻባብ ታጣቂዎች በ2011 ከሞቃዲሾ ከተባረሩ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦርነት ድባብ በከተማዋ ሰፍሯል። ጂሃዳዊው ቡድን ከአብዛኞቹ ዋና ዋና ከተሞች ተጠራርጎ ተባሯል። ብሔራዊው ጦር፣ በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ልዑክ እና በአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ ጥረት ቢያደረጉም ቡድኑም አሁንም በማዕከላዊ እና በደቡባዊ ክልሎች ኃይሉ እንዳለ ነው። አል-ሸባብ በሞቃዲሾ በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል። የተፈጠረውን ሁከት በመጠቀምም እንቅስቃሴዎቹን ለማጠናከር ሊጠቀምበት ይችላል። እንደመገናኛ ብዙሃን ከሆነ አዲስ ጉዳት የደረሰባቸው ሕንፃዎች፣ ታንኮች እና የጦር ተሽከርካሪዎች ላይ የታጠቁ ወታደሮች እና ዋና ዋና መንገዶች ተዘግተዋል። በግል በሚተዳደረው ራዲዮ ኩልሚዬ የሚሠራ አንድ ጋዜጠኛ እንደተናገረው፤ ትራፊክ እና የማዘጋጃ ቤት ፖሊሶች በጎዳናዎች የሉም። የአል-ሸባብ ጥቃትን ለመከላከል በዋና ዋና መንገዶች ላይ የተተከሉ የደኅንነት ካሜራዎችም ወድመዋል። በትጥቅ የተደገፈው አመጽ የፕሬዚዳንት ፋርማጆን የእውቅና ጥያቄ የከድጡ ወደ ማጡ የወሰደው ሲሆን፤ በምርጫ ውዝግብ ላይ የተከፈተውን የውይይት መስኮትም የሚዘጋ ነው።
news-45228202
https://www.bbc.com/amharic/news-45228202
ካለሁበት 44፡ "በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም መኖሩን ሳረጋግጥ ነው ወደ ሃገሬ የምመለሰው’’
ስሜ ካሚል አህመድ አደም ይባላል።
ተወልጄ ያደግኩት በምስራቅ ሀረርጌ ጨርጨር ወረዳ ነው አግብቼ አንድ ልጅ አፍርቻለሁ። በወቅቱ ባጋጠመኝ ችግር ከመሞት መሰንበት በማለት የትውልድ ስፍሪያዬን ለቅቄ ከሀገር ወጣሁ። በአሁኑ ወቅትም በየመን ሀገር ኤደን በሚትባል ከተማ ነው የምኖረው። ስደትን ሀ ብየ የጀመርኩትም በሀገር ወስጥ እያለሁ ወደ ኢሉባቦር ዞን በመሸሽ ነበር። እዚያም ሄጄ የንግድ ስራ ጀመረኩ እንዲሁም ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ የባህር ዛፍ ችግኞችን ተክየ ነበር። ይሁን እንጂ በማላውቀው መንገድ ብዙም ሳልቆይ ንብረቴን በሙሉ በመውስድ ችግኞቼንም በማውደም እኔን እስር ቤት ወርውረው ያሰቃዩኝ ጀመር። ካለሁበት 41: ከባሌ እስከ ቻድ የተደረገ የነጻነት ተጋድሎ እኔም በደረሰብኝ መከራና ችግር የተነሳ መደበኛ ስራዬን መስራት ባለመቻሌ ተቸገርኩኝ፤ በዚህም የተነሳ ቤተሰቦችን ትቼ ከሀገር ለመውጣት ተገደድኩኝ። ከአምስት አመት በፊትም ከኢሉባቦር በመነሳት በጂቡቲ በኩል የመን ኤደን ገባሁ። ካለሁበት 42 : ''የጠበቀ ቤተሰባዊ ፍቅራቸውና ትስስራቸው ከኢትዮጵያውያን ጋር ያመሳስላቸዋል'' ሌላ አማራጭ ከማጣት የተነሳ እንጂ የመን የሚሸሽበት ሀገር አይደለችም። የየመን ዜጎችን ጨምሮ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ድጋፍ አያደርጉልንም፤ ፍትህን ነስተውናል። በዚህ ሀገር የስደተኛ መብት የሚጠበቅላቸው ለሱማሊያ ስደተኞች ብቻ ነው። ሶማሌዎች ወደዚህ ሀገር መምጣት ከጀመሩ 40 አመት በላይ ስላስቆጠሩ በሀገሪቷ የበለጠ እውቅናን አግኝተዋል። ስለዚህ እንደ ምግብ ፤ የጤና እንክብካቤ፤ ወደ ሶሰተኛ ሀገር መላክም ሆነ በየመን ሀገር ውስጥ መኖር እኩል ተጠቃሚ አይደለንም። ከሀገሩ ህዝብ ጋር ተመሳስሎ መስራትና መኖር ለሱማሌዎች የበለጠ ይቀላል። የኢትዮጵያ ስደተኞች ኑሮ ፈታኝና ብዙ ጥሰት ስለሚደርስብን በዚህ ሀገር እየተፈፀመብን ያለውን ነገር አለም እንዲያውቅልን እንፈልጋለን። ከሶስት አመታት በፊት በሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት የአረብ ኤምሬት የመንን በጥምረት በአየር በደበደቡበት ወቅት በዚህ ከተማ ውስጥ የቀረነው እኛና አሞራዎች ብቻ ነበርን። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ትራንስፖርት በመላክ ከጦርነቱ እንደያስወጣን ቢንጠይቅም የሚደርስልን አካል አላገኘንም። በወቅቱ በተደረገው ጦርነትም የየመን ዜጎችን ጨምሮ ብዙ ህዝብ ሞቷል። እኔም ለትንሽ ነው የተረፍኩት። የመን ብዙ ባህላዊ የምግብ አይነት አላት። በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያለው እኔም የምወደው ኩፍዚ የሚባል ባህላዊ ምግብ አለ። ከስንዴ ዱቄት በተዘጋጀ ቂጣ፣ በአሳ ስጋ ከሚሰራ ማባያ ጋር ይበላል፤ጣፋጭም ነው። ከሀገሬም ብዙ ነገሮች ይናፍቁኛል ለምሳሌ ተራራዎቹ እና ወንዞቹ ሁሌም አልረሳቸውም። የድድሳ እና ደባና ወንዞች እንዲሁም የአባስና ተራራን ሁሌ በሀሳቤ ሽው ይሉብኛል። አሁን በምኖርበት የየመን ኤደን ከተማ ውስጥ አንድም ደስ የሚያሰኝ ቦታ የለም። የሀገሪቱ መሰረት ልማት አውታሮች በሙሉ በጦርነቱ ወድመዋል። በዚያ ላይ የሽንት ቤት ፍሳሾች በየመንገዱ ስለሚፈሱ የከተማውን ሽታ ለውጦታል። በዚህም ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በከተማው አንድም የሚስብ ቦታ የለም። ስልጣን ቢኖረኝ በዚህ ሀገር ሰላምና መረጋጋትን ማምጣት የመጀመሪያ ስራዬ ይሆን ነበር። በተጨማሪም እንደኛ ያሉት ጥቁር ሰዎች መብት እንዲከበር እሰራ ነበር። በዚህ ሀገር ካጋጠሙኝ ችግሮች መካከል ከስድስት አመታት በፊት የተለያዩ የ12 ሀገራት መንግስታት የመንን በጋራ በደበደቡበት ጊዜ በጣም አስቸጋሪው ወቅት ነበር። ብዙ ሰዎችም ከአጠገባችን ስለሞቱ ያን ጊዜ ፈታኝ ነበር። በሀገራችን እየታየ ያለው ለውጥ እንደ አንድ ሰው ደስ ይለኛል። ነገር ግን አሁንም ገና የሚቀሩ ነገርች እንዳሉ ይሰማኛል። ብዙ ቦታዎች ላይ አሁንም ሰላም የለም። ይህንን እየሰማሁ እንዴት ልመለስ? ተገቢው መፍትሄ ለህዝባች ከተሰጠና ዘላቂ ሰላም መረጋገጡን ባወኩኝ ግን በደስታ ወደ ሀገሬ እመለሳለሁ። ለጫሊ ነጋሳ እንደነገረው
news-42241865
https://www.bbc.com/amharic/news-42241865
እኛ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝቦች. . .?
የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን ማክበር ከተጀመረ እነሆ አስራ ሁለት ዓመት ሞላው፡፡ ሁሌም ግን ሕገ-መንግሥቱ ላይ ስለተቀመጠው እና "እኛ የኢትዮጵያ ብሔር ፣ ብሔረሰብና ሕዝቦች" ስለሚለው አገላለፅ ጥያቄ ይነሳል።
የኢትዮጵያ ባንዲራ ለህግ ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት ይህንን ጥያቄ ስናቀርብ "ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ" ሦስት ቃላት እንጂ አንድ ትርጉም ብቻ ያለው ሐረግ አይመስልም፡፡ እንደሳቸው አባባል ይህንን በትክክል ለመረዳት በሕገ-መንግሥቱ አርቃቂዎች የተዘጋጀውን አጭር ማብራሪያ ማየቱ በቂ ነው፡፡ በማብራሪያው ላይ "በ'ብሔር' 'ብሔረሰብ'ና 'ሕዝብ' መካከል የመጠንና የስፋት ልዩነት ያለ ቢሆንም…" ይላል፡፡ ስለዚህ ልዩነታቸውን በማብራሪያው ላይ ባይዘረዝርም በደፈናው "የመጠንና ስፋት" ልዩነት እንዳላቸው አስቀምጧል በማለት ያስረዳሉ፡፡ ሀሳባቸውን ለማጠንከርም ፤ በአማራ ክልል ውስጥ የሚኖሩትን በተመለከተ አማራን "ብሔር"፣ አገውን "ብሔረሰብ" እንዲሁም ኦሮሞን "ሕዝብ" በማለት በአንቀጹ ማብራሪያ ላይ በመግለጽ በሦስቱ መካከል የመጠንና የስፋት ልዩነት እንዳላቸው ይጠቁማል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን በጠቅላላው እንደምሳሌ ኦሮሞን "ብሔር"፣ አፋርን "ብሔረሰብ"፣ ኮሎን "ሕዝብ" በማለትም ማሳያውን ያጠናክራለሉ፡፡ የታሪክ ምሁሩ አቶ አበባው አያሌው የህግ ባለሙያውን ሃሳብ ይጋራሉ። ብሔር አንድ ትርጉም አለው፣ ብሔረሰብም ሌላ ትርጉም አለው ህዝብም እንደዚሁ በማለት። ሕገ-መንግሥታችን ግን ሶስትን ቃላት አንድ ላይ ሰብስቦ የኢትዮጵያን ነገር ቸል ብሎ 'ስታንሊናዊ' ብያኔ ይሰጠዋል ሲሉ ያክላሉ አቶ አበባው። በሕገ-መንግሥታችን ላይ ለሦስቱም አንድ ወጥ የሆነ ትርጉም ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይኸውም፡- "ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልውና አለን ብለው የሚያምኑና የሥነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛው በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው" ይላል፡፡ አቶ አበባው የጋራ ጠባይ ለግለሰብ እንጂ ለብሄር የምንጠቀምበት አልነበረም ሲሉ ይሞግታሉ። የአንድ ብሄረሰብ ጠባይ እንደምን ያለ ነው? ሲሉም ጥያቄ ያቀርባሉ። እንደ አቶ ውብሸት ገለፃ ደግሞ የክልል ሕገ-መንግሥቶች ላይ ትርጉም የተሰጠው በአጠቃላይ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በማለት ሳይሆን የብሔሩን ስም በመግለጽ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የአተረጓጎም ልዩነት አይታይባቸውም፡፡ አቶ አበባው በበኩላቸው ብሔረሰብ የሚለውን በአንድ አካባቢ የሰፈረ የሚለውን ወስደን ለመረዳት የአይሁድ ህዝብን ማየት በቂ ነው። የተለያየ የዓለም ክፍል ላይ እየኖሩ ተመሳሳይ ቋንቋ መናገሩ እና አንድ አይነት ባህል መጋራቱ ብቻ ብሔረሰብ ያሰኘዋል። የግድ በአንድ አካባቢ መስፈር አይጠበቅባቸውም። የተለያየ አካባቢ ሊኖር ይችላል ነገር ግን ተመሳሳይ ባህልና ቋንቋ ይጋራል። ብሄር ግን ልንለው አንችልም ይላሉ። ሕዝብ የሚለውን ብንወስድ ደግሞ ከቀለም እና ከቋንቋ ባሻገር አንድን ህዝብ አንድ የሚያደርገው አንድ ሉአላዊ አገር መኖሩ ነው። ሕገ-መንግሥታችን እነዚህን ለያይቶ አላስቀመጠም በማለት ሀሳባቸውን ያጠቃልላሉ። ታሪካዊ አመጣጡን በጨረፍታ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገ-መንግሥቱ ሲረቀቅ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳሉ። "መጀመሪያ ሕገ-መንግስቱ ውስጥ መግባት ያለባቸው ምንድን ናቸው ብለን 73 ጥያቄዎች አዘጋጀን። ጥያቄዎቹ በምርጫ መልክ ተዘጋጅተው ወደ ሕዝቡ ወረዱ።" ጥያቄዎቹ ላይ ሕዝቡ ከተወያየ በኋላ በየቀበሌው የተሰጠው ሃሳብ በየክልሉ ከተሰበሰበ በኋላ ጥያቄዎቹን በሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች መሰረት ከፋፈሏቸው። አንቀፆቹ ሲከፋፈሉ 106 ሆኑ። ሕገ-መንግሥቱን በማርቀቅ ሂደት ውስጥ የደርግ ሕገ-መንግሥትን ያረቀቁ እና ሌሎች ባለሙያዎች በጋራ ተሳትፈዋል በማለት ያክላሉ። ነገር ግን ይህ የሕገ-መንግሥቱ አገላለፅ መብራራት እንዳለበት መጠየቁን አያስታውሱም። አቶ ውብሸትም በወቅቱ የሕገ-መንግሥት አርቃቂ ጉባኤውን በሊቀ መንበርነት የመሩት አቶ ክፍሌ ወዳጆ "ሕገ- መንግሥቱ በሚረቀቅበት ወቅት በሰፊው ተቃውሞ ከነበረባቸው ክፍሎች መካከል መግቢያው አንዱ ነው፡፡ ከአርቃቂዎቹ ውስጥ የነ ክፍሌ ወዳጆ ቡድን በእዚህ መንገድ እንዳይጻፍ ተቃውሞ ነበር" በማለት ያስታውሳሉ ። ሁሉም እንደሚሉት ግን ሕገ-መንግሥቱ መነሻም መድረሻም በመሆን ያገለገለው 'ስታንሊናዊነት' ነው። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ ብሔር ፣ ብሔረሰብ እና ሕዝብ እንደ አቶ ውብሸት ገለፃ ሶቪየቶች ''ብሔርን በታሪክ ሂደት ውስጥ የተከሰተ የሰዎች ስብስብ ነው'' ይላሉ፡፡ አንድ ብሔር በመጀመሪያ ደረጃ የሚለየው ባሉት የወል ቁሳዊ የኑሮ ሁኔታዎች ነው፡፡ በአንድ መልክአ-ምድራዊ ክልል ውስጥ መኖር በኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች መተሳሰር፣ በአንድ ቋንቋ መጠቀም በጋራ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የወል ሥነ-ልቡናዊ ገጽታዎችና ባህላዊ አመለካቶች መከሰት የብሔር መሠረቶች እንደሆኑ ይገልጻሉ፡፡ በሶቪየቶች አተረጓጎም ''ብሔረሰብ ከደም አንድነት ይልቅ የተመሠረተው በክልል፣ በቋንቋና በባህል አንድነት ላይ ነው፡፡ ብሔረሰብ የነገድ ከፍተኛ ደረጃ የሆነ የብዙ ነገዶች ውህደት ውጤት ነው፡፡'' በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ምርምር ማዕከል፣ ያሳተመው የ"አማርኛ መዝገበ-ቃላት" ስለብሔረሰብ ምንነት በሰጠው ትርጓሜ ላይ 'ከደም አንድነት ይልቅ የብዙ ነገዶች ውጤት አድርጎ ነው፡፡' በሶቪየቶች አረዳድ ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማሳየት የሚጥር፣ በማኅበራዊ ሥርዓት ከፍተኛ ጫና ውስጥ የገባ ማኅበረሰብ ነው፡፡ በሂደት የኢኮኖሚ ለውጥ እየተከሰተ ሲሔድ፣ ሰፋ ያሉ የኢኮኖሚ ግንኙነቶችን ሲፈጥር የብሔረሰብ ማንነቱን እየተወ ከፍ ወዳለ ደረጃ በመቀየር ብሔር ይሆናል ይላሉ፡፡ እንደ አቶ ውብሸት ገለፃ የብሔርና የብሔረሰብ ልዩነቶቹ ቀጭን ቢሆኑም በዋናነት መለያቸው ግን የፖለቲካዊ አቋምን የመወሰን ፍላጎት መኖርና አለመኖር ነው፡፡ እንደ ሶቪየቶች አረዳድ ሕዝብ በመጠንና በስፋት ከብሔረሰብ በታች ነው፡፡ የነገድ ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡ በቁጥርም ያንሳል፤ በሥነ-ልቦና ረገድም እንደብሔረሰብና ብሔር ጥብቅነት ወይንም አንድነት የለውም፡፡ በመሆኑም ብሔር ከፍተኛ፣ ብሔረሰብ መካከለኛና ሕዝብ ደግሞ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥትም የተቀመጠው ከዚሁ አረዳድ አንጻር ነው የሚሉ አሉ፡፡ ሕገ-መንግሥቱን ስለማሻሻል ለዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሕገ-መንግሥቱ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝቦች የሚለውን በደፈናው ማስቀመጡ ችግር አይደለም። ከዛ ይልቅ ሕገ-መንግሥቱ ላይ በተደጋጋሚ ጭቅጭቅ ከሚያስነሱት መካከል አንቀፅ 39፣ የፌደራሊዝም እና የባንዲራ ጉዳይ፣ የምርጫ ቦርድ ጉዳይ፣ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግሥቱን የማየትና የመተርጎም ስልጣን የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ያገባኛል የሚሉ አካላት በሙሉ ተሰባስበው ቢመለከቷቸው እና ቢሻሻል ጥሩ ነው ብለው ያስባሉ። አቶ አበባው እና አቶ ውብሸትም ሕገ-መንግሥቱ መሻሻል ቢኖር ጥሩ ነበር ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይላሉ አቶ ውብሸት "ይህንን ማሻሻል ሕገ መንግሥቱን እንደመቀየር ይሆናል፡፡ መግቢያው፣ አንቀጽ ስምንት፣ አንቀጽ 39፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አወቃቀርን መለወጥ ይሆናል" ሲሉ ያጠናቅቃሉ። አቶ አበባው በተጨማሪም "በሕገ-መንግሥቱ የቋንቋ አጠቃቀም ዘፈቀዳዊ ነው። ሕገ-መንግሥት የሚያረቅ አካል በተቻለ መጠን ግልፅ መሆን አለበት።" "ሕገ-መንግሥቱ ሉአላዊነትን ሲበይን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ባለቤቶች ናቸው ይላል ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝቦች በቂ ነበር። የሕዝብን የመንቀሳቀስ ፣ እኩል የመዳኘት መብት እየገደበ ያለው አንዱ ይሄ ስለሆነ መከለስ ካለበት አንዱ ይሄ ነው ይላሉ።
49902829
https://www.bbc.com/amharic/49902829
ከ57 ዓመታት በኋላ የተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ምን አዲስ ነገር ይዟል?
የኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሻሻያ ቢደረግበትም፤ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህጉ ግን ምንም አይነት መሻሻያ ሳይደረግበት 57 አመታትን አስቆጥሯል። በቅርቡም ይህ ከአምስት አስርት አመታት በላይ ያስቆጠረው የሥነ ሥርዓት ህጉ ተሻሽሎ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርቷል። የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ህግ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ረቂቅን ለማዘጋጀት አስራ አምስት አመት እንደወሰደ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላይሁን ይርጋ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል። ከአምሳ አመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህ ግ ሊሻሻል ነው ። ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት ምንድን ነው ?
የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሥርዓት ህጉ የተደነገጉ የወንጀል ድንጋጌዎችን ማስፈጸሚያ መሣሪያዎች ናቸው። ከምርመራ ጀምሮ እስከ ፍርድ ማስፈጸም ወይም ታራሚዎችን እስከማረምና ማነጽ ያለውን ሂደት ይመራሉ። ምርመራ እንዴት ይጀመራል? የተጠርጣሪዎች መብት ምንድን ነው? ከዋስትና ጋር ተያይዞ ያለው ነገር ምንድን ነው? ፖሊስ ማድረግ የሚችለው ምንድን ነው? የሚሉ ዝርዝር ነገሮችን የሚመሩት በሥነ ሥርዓት ሕጎች ነው። •“ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ •"ፍቅር እስከ መቃብርን አልረሳውም" ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በ1954 ዓ. ም. የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ማሻሻል ያስፈለገባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ። በ1949 ዓ. ም. ወጥቶ የነበረው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በ1996 ዓ. ም. ተሻሽሏል። የ1954 ዓ. ም. የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ በ1949 ዓ. ም. የወጣውን የወንጀል ሕግ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አይነት ሥርዓት ያለው ከሆነ፤ የ1949ኙ ሕግ ከተሻሻለ የግድ የ1954ቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ መሻሻል ይኖርበታል ማለት ነው። ስለዚህ አንዱ ምክንያት ይሄ ነው። ሁለተኛው ምክንያት የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕጉ ሲረቀቅ አገራችን አሁን ያላትን ቅርጽ የያዘች አልነበረችም። ያን ጊዜ የነበረው አሃዳዊ ሥርዓት ነው። ፌደራላዊ ሥርዓት አልነበረም። ስልጣን በክልልና በፌደራል መንግሥቶች የተከፋፈለ አልነበረም፤ ስለዚህ ሕጉ ሲረቀቅ አሀዳዊ ሥርዓትን ታሳቢ ያደረገ ነው። አሃዳዊ ሥርዓትን ታሳቢ ያደረገ ከመሆኑ አንፃር አሁን የፌደራል ሥርዓት ሲደራጅ፤ የፌደራል መንግሥቱ ሥልጣን ምንድን ነው? የክልሎች ሥልጣን ምንድን ነው? የሚለውና የፍርድ ቤቶቻችን አደረጃጀት በ1954 ዓ. ም. እንደነበረው አይደለም። ያን ጊዜ አውራጃ፣ ወረዳ የሚባል አደረጃጀት ነው የነበረው። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ ፍርድ ቤቶች አሉ። የነዚህ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ምንድን ነው? ከዚህም በተጨማሪ የክልልና የፌደራል መንግሥት ሥልጣን ምን መሆን አለበት የሚለው መሰረታዊ ለውጥ ይፈልጋል። ከዛ ውጪ አሁን ከደረስንበት የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ሥርዓት አንጻር፣ ከደረስንበት ዘመናዊ ዓለም አንጻር በ1954ቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ውስጥ ያልተካተቱ አዳዲስ መሰረታዊ ፅንፀ ጽንሰ ሀሳቦች መካተትና መሻሻል ስለነበረባቸው ነው። •የጤፍ ቢራ አሜሪካ ውስጥ ገበያ ላይ ዋለ ምን ያህል አዳዲስ ሕጎች ናቸው የተጨመሩት? ምን ያህሉስ ተሻሽለዋል? ጥፋተኝነት ድርድሩንም እስቲ ዘርዘር አድርገው ይንገሩኝ? አጠቃላይ የተሻሻለው ሕግ ምን ያህል ነው የሚለውን ብዙ ነው እዚህ መዘርዘር ትንሽ አስቸጋሪ ይሆናል። ረቂቅ ህጉን ከሰራን በኋላ ሕግ አውጪውም ሌላውም አካል እንዲረዳው በሚል ሠንጠረዥ አዘጋጅተናል። በዚህም መሰረት አንደኛ ከነባሩ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ እንዳሉ የተወሰዱ ድንጋጌዎች፤ ነባሩ ወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ የነበሩና ግን በተወሰነ መልኩ ተሻሽለው ወይም ደግሞ አገላለፃቸው፣ ሃሳባቸው ተስተካክሎ የገቡና አዳዲስ የመጡ ፅንሰ ሀሳቦች (ድንጋጌዎች) ይዟል። ብዙ አዳዲስ ፅንሰሃሳቦች ገብተዋል፤ ለምሳሌም ያህል አንዱ የጥፋተኝነት ድርድር (Plea bargain) ነው። አቃቤ ሕግና ተከሳሽ የሚደራደሩበትና በብዙ አገሮች ለምሳሌ በአሜሪካ፣ በካናዳ = ተግባራዊ የሚደረግ ሥርዓት ነው ለምሳሌ 15፣ 20 ክሶች የሚመሰረቱባቸው ተከሳሾች አሉ እነርሱ ጋር አቃቤ ሕግ ሊደራደር ይችላል። በዚህም መሰረት ይህን ያክል ወንጀል ፈፅመኻል፤ በዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ማስረጃ አለኝ። ይህንን ይዘን ወደ ፍርድ ቤት ብንሄድ ክርክሩ እና የፍርድ ቤት ውጣ ውረዱ ብዙ ዓመት ይፈጃል፤ ማስረጃ ማሰማቱ እና ሌሎች ሌሎችም። ስለዚህ የቀረቡብህ ማስረጃዎችንና መሰል ጉዳዮችን እይና የምታምነው አለ ወይ? ካመንክ ከዚህ ውስጥ፣ ለምሳሌ በ15 ክስ የሚከሰስ ተከሳሽ ከሆነ፣ አምስቱን ክስ እተውልህና በአስር ብቻ እከስሃለሁ ሊለው ይችላል። ጥፋትህ ተደምሮ ተቀንሶ ይህን ያህል ዓመት የሚያስቀጣ ነው። ነገር ግን ይህን ያህል ዓመት እንድትቀጣ ልንስማማ እንችላለን ብሎ ይደራደራል ማለት ነው። ስለዚህ አንድ ዓመት ሁለት ዓመት የሚፈጅ ጉዳይ በአንድ ቀን ያልቃል ማለት ነው።ፍርድ ቤት ስምምነታቸውን ሲያፀድቅ ወዲያውኑ ቅጣት ይፈፀማል። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያላት አገር ከመሆኗ አንፃር ለዘመናት ወንጀልን ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን መፍትሔ የሚሰጡባቸው የራሳቸው ሥርዓቶች አሏቸው። እነዚህ ባህላዊ ሥርዓቶች መደበኛ የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት ከሚሰጠው የተሻለ እልባት መስጠት የሚችሉ ከሆነ ባህላዊ ስርዓቶች እውቅና መስጠት ያስፈልጋል። ባህላዊ ስርአቶችም ተካትተዋል። እስካሁን ሲሰራበት የነበረው ተጠርጣሪ ይያዛል፣ ምርመራ ይደረጋል፣ ፍርድ ቤት ይሄዳል፣ ይቀጣል፣ ማረሚያ ቤት ይሄዳል፤ አማራጭ መፍትሄ የሚባል አልነበረም። ነገር ግን ሱስ ውስጥ ያሉ፣ የአዕምሮ ችግሮች ያሉባቸውና እንዲሁም ለሌሎች ብዙ አደጋዎች የተጋረጡ ግለሰቦች አሉ። እነዚህን ግለሰቦች ማረሚያ ከመላክ ይልቅ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን ወደ ማገገሚያ ወይንም በማህበራዊ ግንባታ ውስጥ አስተዋፅአ የሚያደርጉበት መንገድ በረቂቁ ውስጥ ተካቷል። ይህ አሰራር በተለያዩ ሃገራት ይጠቀሙበታል። ከዚህም በተጨማሪ አሁን ያለው የዕርቅ አሰራር የሚያሻሽል የመንግሥት ጥቅም የሌለባቸውን እስከ 3 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት በሚያስቀጡ የወንጀል ጉዳዮች ላይ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የማሻሻያ ሀሳብ ቀርቧል፡፡ እርቅ ማስጨረስ ቢቻል የተሻለ ውጤት መምጣት እንደሚችል በተግባር አይተነዋል። የመጨረሻ ፍርድን (ብይንን) እንደገና ስለማየት ፤ አሁን ባለው የፍትህ ስርአት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ የሰጠው ውሳኔ መሆኑ በተጨባጭ ቢረጋጋጥ፤ ለምሳሌ ሰው ሞቷል ተብሎ በግድያ ሰዎች ከተፈረደባቸው በኋላ ሞተ የተባለው ሰው በአካል ቢመጣ ፍርድ ቤቱ ያንን ጉዳይ መልሶ የሚያይበት ስርዓት የለም። ውሳኔውን ለማስቀልበስ በይግባኝ ነው መሄድ ያለበት፤ አንዳንዴ ይግባኝ ሊያልፍ ይችላል። የተፈረደበት ግለሰብ ከእስር ሊወጣበት የሚችል ምንም አይነት አሰራር የለም። በሌሎች ሀገሮች ግን የዳበረ ፅንሰ ሀሳብ አለ። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድን እንደገና ማየት የምንለው ማለት ነው። ሌላኛው የሞት ፍርድ አፈፃፀምን በተመለከተ ነው። በረቂቁ መሰረት ውሳኔ ከተሰጠ ጀምሮ ከተቀመጠለት ከሁለት አመት በላይ ከቆየ ወደ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት ይቀየራል። ከዚያ ውጪ በእኛ ሀገር የሞት ቅጣት አፈፃፀም ተፈርዶባቸው 20 ዓመት ለ15 ዓመት አስር አመታት ያለምንም ውሳኔ የተቀመጡ ሰዎች አሉ። •ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም መቆየታቸው ጥሩ ቢሆንም፣ አንዳንዴ ግን ሳይኮለጂካል ቶርቸርም [የስነልቦና ስቃይ] ነው። ከአሁን አሁን ተፈፀመብኝ እያለ ሲሰጋ ይኖራል። መፈፀሙ የሚመረጥ ላይሆን ይችላል። ግን የሆነ መፍትሔ ሊኖረው ይገባል። በረቂቁ ያስቀመጥነው ወደ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት መቀየር ትልቅ 'ፓራዳይም ሺፍት' [ለውጥ] ነው ይኼ። ከዚህ በተጨማሪ አሁን ባለው አሰራር ሞት ቅጣት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከፈረደ እና ለምሳሌ ግለሰቡ ይግባኝ ካልጠየቀ እንደሚፈፀም ነው። ይህ ደግሞ በጣም አደገኛ አካሄድ ነው። በርግጥ እኛ ብዙም እየፈፀምን ስላልሆነ አሁን ስጋት ላይ ላይከተን ይችላል። ግን ከሞተ በኋላ ሰውየው ተመልሶ ስለማይመጣ የተፈረደበት ግለሰብ ራሱ የይግባኝ ባይጠይቅ ፍርድ ቤቱ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ነው መላክ ያለበት ብለን አካትተናል። የግድ በይግባኝ መታየት አለበት። በአምስተኛ ወይንም በሰባተኛ ተሰይሞ ማፅደቅ አልያም መሻር አለባቸው። የባህላዊ ስርዓቶችን በምን መንገድ ነው የተካተቱት? የባህላዊ ስርዓቶች ለምሳሌ አፋር ክልል ላይ ብንሄድ የግድያ ወንጀል ቢፈፀም የሟች ዘመዶችና የገዳይ ዘመዶች ቁጭ ብለው የሚነጋገሩበት፣ የሚካካሱበትና የመጨረሻውን ዕልባት የሚሰጡበት ስርዓት አላቸው። የገዳ ስርዓትም እንዲሁ ለምሳሌ የወንጀል ጉዳዮች ላይ ራሱ እልባት ይሰጣል። ወደ ወሎ አካባቢ፣ ደቡብ ውስጥ ብንሔድ ትልልቅ ጉዳዮችን ዕልባት የሚሰጡባቸው ስርዓቶች አሏቸው። የወንጀል ጉዳይን ጨምሮ ማለት ነው። ስለዚህ ባሕላዊ ስርዓቶች ስንል የዳበሩ ባህላዊ ስርዓቶችን ዕውቅና መስጠት ነው። እዚህ ጋር ጥንቃቄ የሚደረጉባቸው የሉም ማለት አይደለም። አንዳንዶቹ ስርዓቶች ሰብዓዊ መብትን የሚጥሱ፣ ለምሳሌ አንዳንድ ቦታ ላይ ስናይ ባልና ሚስት ተጣልተው ሲያስታርቁ 'ምንም አትናገሪ፣ ዝምብለሽ ተስማምተሽ ቤትሽ ግቢ' የሚል ዓይነት ወደ አንድ ጎን ያጋደለ ሽምግልና አለ። ይህ ትክክለኛ ያልሆነኛ የሴቶች መብትን የሚጎዳና ሰብዓዊ መብትንም የሚጥስ ነው። ይህ ሲከናወን ከጥንቃቄ ጋር ነው፤ በባህላዊ ስርዓቶች የማይታዩ ወንጀሎችም አሉ። ረቂቅ ሕጉ ከዚህ በፊት ይነሱበት የነበሩ ለምሳሌ ከተጠርጣሪዎች አያያዝ እንዲሁም ተደጋጋሚ ቀጠሮዎችና የመሳሳሉ ቅሬታዎችን ይደፍናል? አዎ በደንብ አድርጎ ክፍቱን ይሞላል። በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓቱ ላይ ግን ከዋስትና ጋር ተያይዞ፣ ከጊዜ ቀጠሮ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ሰብዓዊ መብትን የሚጥሱ ድንጋጌዎች አሉ። ባልተለመደ ሁኔታ በተደጋጋሚ አስራ አራት ቀን በማለት ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም እያለ በርካታ ጊዜ እንደሚገፋ ነው በተግባር እየታየ ያለው። በዚህ አሰራርም ለአመታት የሚቆይ ምርመራ አለ። አስራ አራት ቀን ለምን ያክል ጊዜ? መጨረሻ ገደብ ሊኖረው ይገባል፤ ሰብዓዊ መብትን ይጥሳል። ያው በረቂቅ ደረጃ ነው ያለው የሚሰጠው ጊዜ ቀጠሮ ለቀላልና ለከባድ ሊለያይ ይችላል። በረቂቁ የተካተተው ለከባድ ወንጀል አራት ወራት ብለናል። በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ካልጨረሰ ፍርድ ቤት 'አውቶማቲካሊ' [ወዲያውኑ] ተጠርጣሪውን ይለቅቀዋል ነው የሚለው። የተያዘ ንብረትም ካለ ይለቀቃል። ቶሎ ለፖሊስ ክስ እንዲመሰርት ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል ካልሆነ ግን ይለቅቀዋል። ሌላኛው የዋስትና መብትን በተመለከተ ነው። የድሮው አሻሚ ነው በአሁኑ ግን ግልፅ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በመርህ ደረጃ ሰው በዋስትና መለቀቅ ነው ያለበት። በልዩ ሁኔታ በጣም ውስን ከሆኑ ጉዳዮች በስተቀር ህገ መንግሥቱም ሆነ አለም አቀፍ የመብትና የህግ ማዕቀፎች ይህንን መብት ሰጥተዋል። የተረቀቀው ሕግ ከስያሜው ጀምሮ ከዚህ ቀደሙ ይለያል። የአሁኑ ሕግ ስያሜው 'የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዐትና የማስረጃ ሕግ' ሲሆን በይዘትም ደረጃ የማስረጃ ጉዳዮችንም አካትቶ ይዟል። ይህ ትልቅ ለውጥ ነው። ከዚህ ቀደም ማስረጃን በተመለከተ የተደራጀ ህግና ዝርዝር ሁኔታዎች አልነበሩም። በአሁኑ ግን ማስረጃ ሆነው የሚቀርቡት ምንድን ናቸው? ተቀባይነት ያለው መረጃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃና የመሳሰሉት ላይ ዝርዝር ጉዳይ በረቂቁ ተቀምጧል። ስለዚህ እነዚህን ክፍተቶች ይሞላል። •“ጭኮ እወዳለሁ” ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሥነስርዓት ህጉን ለማሻሻልለምንድን ነው ይህን ያህል ረዥም ጊዜ የወሰደው? እኛ አሁን አሻሽለን እያቀረብን ነው ስንል፤ እኛ አሁን ተነስተን ያረቀቅነው ሕግ አይደለም። ከዚህ በፊትም በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ በርካታ ባለሙያዎች አሉ። የማርቀቅ ስራው የቆየ ስራ ነው ወደ አስራ አምስት አመታትም ወስዶበታል። ዛሬ ሲባል፣ ነገ ሲባል፣ ይጀመራል እንደገና ይተዋል፣ በባለቤትነት መንፈስ በአግባቡ ይኼ መጠናቀቅ አለበት በሚል ስሜት የራሱ የሆነ ባለሙያ ተመድቦለት እንደ ተቋምም የሞት የሽረት ጉዳይ ነው ተብሎ በባለቤትነት ስላልተያዘ ይመስለኛል። ዞሮ ዞሮ ግን እንደ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ይህንን ሕግ አርቅቆ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቀረብን ስንል ከዚያ ጀምሮ የነበሩትን ግብዓቶች እየወሰድን እያሻሻልን፣ እየጨመርን፣ እየቀነስን ነው፤ የዛ ሁሉ ውጤት ነው። ተግባራዊም ለማድረግ ጊዜ ይወስዳል፤ ቀላልም ስላልሆነ ፤ የጁሪዚዲክሽን (ስልጣን ክፍፍልን) ለውጥ ያመጣል። ፌደራል ላይ የነበሩ ወደ ክልል ይኼዳሉ። ክልል ላይ የነበሩ ወደ ፌደራል የሚሳቡ አሉ። በቀጣዩ የሚወጡ መመሪያዎችና ደንቦች ይኖራሉ፤ ተቋማትም ጭምር ይቋቋማሉ። ይህ ህግ ፀደቀ ማለት በፍትሕ ስርዓቱ ላይ ትልቅ ለውጥ ይመጣል። የፍትሕ ስርዓቱ በጣም ዘመናዊ እንዲሆን ያስችላል ብዬ አስባለሁ። የፌደራል ስልጣን ወደ ክልል ሊሄድ ይችላል ሲሉ.... በ1996 ዓ.ም የወጣው የወንጀል ሕግ አለ። እዚያ ላይ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን በሙሉ ለቅመን ይህኛው የፌደራል ነው ይህኛው የክልል ነው፤ ይህኛው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፤ ይህኛው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፤ ይህኛው የጠቅላይ ነው ብለን በዝርዝር አስቀምጠናል። አሁን ባለው አሰራር ክልሎች የወንጀል ጉዳይን በቀጥታ የማየት ስልጣን የላቸውም። የፌደራል መንግሥቱ የሚያወጣቸውን ሕጎች በፌደራል መንግሥቱ ስር ነው የሚወድቁት። ስለዚህ አሁን ባለው አሰራር እኮ ክልሎች በውክልና ነው እየሰሩ ያሉት የሚል አንድምታ ነው ያለው። ነገር ግን አሁን በዚህኛው ረቂቅ ላይ ለክልል ተብሎ በግልፅ ተዘርዝሮ ተሰጥቷቸዋል።
news-42692159
https://www.bbc.com/amharic/news-42692159
ኦሮሚያና አማራ የሚፈቱ እስረኞችን እየለዩ ነው
ዛሬ የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ 528 እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ እንደሚለቀቁ ተናግረዋል። ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ከሚፈቱት እስረኞች መካከል 115 በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሥር እንደሚገኙ ጠቁመዋል። የተቀሩት 413 ደግሞ የደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል ስም ዝርዝር አቅርቦ ክሳቸውን እንዲቋረጥ ተወስኗል ብለዋል።
የተቃውሞ ሰልፈኞች ከደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል በተጨማሪ የኦሮሚያ እና አማራ ክልል በጉዳዩ ላይ ምን እየሰራ ነው ስንል ጠይቀናል። የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ኮሚኒኬሽን ሃለፊ አቶ ታዬ ደንደዓ ክልሉ ''የክስ መዝገቦችን እያጣራን ነው። እሰከ ጥር 12 ድረስ አጣርተን እንጨርሳለን'' ብለዋል። ''የፖለቲካ ተሳትፎ የሚባል ወንጀል የለም። ከፖለቲካ ተሳትፎ ጋር ተያይዞ የታሰሩ በሙሉ ይፈታሉ።'' እንደ አቶ ታዬ ከሆነ ክልሉ እስረኞች የሚፈቱበት ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የለም። ''በሽብር፣ ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን ለመናድ ሙከራ አድርገዋል ተብለው ክስ የተመሰረተባቸውም ይፈታሉ'' ይላሉ አቶ ታዬ። ይሁን እንጂ በግል ጸብ የሰው ህይወት ያጠፉ ወይም አካል ጉዳት ያደረሱ ግን ይህ ምህረት አይመለከታቸውም ብለዋል። አቶ ማሩ ቸኮል የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው ክልሉ ኮሚቴ አዋቅሮ እየሰራ ነው ብለዋል። ክልሉ ልክ የፌደራል አቃቤ ሕጉ እንዳስቀመጣቸው ያሉ መስፈርቶች የሚኖሩት ሲሆን "እኛም የምንከተለው አካሄድ ተመሳሳይ ይሆናል" ብለዋል። "ክሶችን የፌደራል ወይም የክልሉ ስልጣን የሆነውን የመለየት ስራም ይሰራል። ከዛ በኋላ የሚለቀቁትን እስረኞች ለሕዝቡም ለመገናኛ ብዙሃንም ይፋ እናደርጋለን" ብለዋል። በክልሉ የተዋቀረው ኮሚቴ ከርእሰ መስተዳድሩ፣ ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ እና ከሌሎች አባላት ጋር በመሆን ተወያይቷል ያሉት አቶ ማሩ በዚህ መግለጫ ወቅት የሚፈቱ ታራሚዎች ስም ዝርዝር ለምን አልደረሰም ለሚለው ጥያቄ የደቡብ ክልል ቀድሞ ተዘጋጅቶ ካልሆነ በስተቀር ታራሚው በርካታ ስለሆነ እና የማያዳግም ስራ ለመስራት እንዲያስችል እየሰራን ነው። "ከዚህ በላይ ባይዘገይ እኔም ደስ ይለኛል ታራሚዎቹ ተለይተው እንዳለቁም ይፋ እናደርጋለን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
news-44288532
https://www.bbc.com/amharic/news-44288532
"አጭሩ የሥልጣን ቆይታ የእኔ ነው" ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር)
የኢንጂነሩ የፓርቲ ቅብብሎሽ አስር ዓመትን ይሻገራል። ከነበሩባቸው ሁለት ፓርቲዎች ወጥተው ሌሎች ሁለት ፓርቲዎችን አዋልደዋል።
ከ"አንድነት ለነፃነትና ለዲሞክራሲ" ውስጥ "መርሕ ይከበር" የሚለው ቡድን ሲፀነስ ፊታውራሪ ነበሩ። መርሕ ይከበር ሠማያዊ ፓርቲን ሲፈጥር ሊቀመንበር ሆኑ። የኋላ ኋላ ከሠማያዊ ፓርቲ ማኀጸንም አዲስ ፓርቲ ተጸንሷል። በአጭር ጊዜ ተቀባይነት ካገኘው ሠማያዊ ፓርቲ ጀርባ የእርሳቸው ጠንካራ አመራር ነበር። ፓርቲው ሲሰነጠቅም እጃቸው አለበት። ከሰሞኑ አዲስ ፓርቲ ይዘው ብቅ በማለታቸው ብዙዎችን አስገርመዋል። የኢትዮጵያዊያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ ወይም በምኅጻረ ቃሉ 'ኢሃን' የሚል ስም የተሰጠው የኢንጂነር ይልቃል አዲሱ ፓርቲ በይፋ መመሥረቱ የተገለጸው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ቢቢሲ ለምን አዲስ ፓርቲ መመሥረት አስፈለገዎ? ሲል ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር። እርሳቸው እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሕዝብ የለውጥ ፍላጎት እየተቀጣጠለ መምጣቱና የሕዝቡን ፍላጎት አደራጅቶ በትግልና በሐሳብ የመምራት ውስንነት በመኖሩ ይህን ኃላፊነት ሊሸከም የሚችል ፓርቲ መመሥረት የግድ ሆኗል። ጨምረው እንደሚያብራሩትም ''ሥርዓቱ ከሚከተለው የአውዳሚነት ፖለቲካና ተቀናቃኞችን አንደ ጠላት ስለሚመለከት አንድም ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የሚችል የፖለቲካ ማኅበር አንዳይፈጠር አድርጎ ቆይቷል'' ኢሃን ይህን ክፍተት እንደሚሞላ ኢንጂነር ይልቃል ተስፋ ያደርጋሉ። 'በገቢር አናሳ በቁጥር "መቶ አምሳ" የሚሆኑ ፓርቲዎች በአገሪቱ እያሉ የእርስዎ አዲስ ፓርቲ ይዞ መምጣት ምን ይፈይዳል?' በሚል ቢቢሲ ላነሳላቸው ጥያቄ ኢንጂነር ይልቃል ጥያቄውን በመኮነን ምላሻቸውን ይጀምራሉ። "ጥያቄው መሆን ያለበት ምን ያህል ትሠራላችሁ? ምን ያህል ተዘጋጅታችኋል? ምን ታሳካላችሁ እንጂ በዚህ አገር የፖለቲካ ማኀበር ምሥረታ አስፈላጊነት ላይ እንዴት ጥያቄ ይነሳል?" ሲሉም ጥያቄ በጥያቄ ይመልሳሉ። አፍቅሮተ ሥልጣን? ኢንጂነር ይልቃል ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ ከመሠረቱት አንድነት ለነፃነትና ለፍትሕ ፓርቲ ጀምሮ በገቡበት ፓርቲ ሳይጸኑ ቆይተዋል። እንደ አመራርም እንደ አባልም በቆዩባቸው ፓርቲዎች ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ አምባጓሮ አልተለያቸውም። ከዓመት ተኩል በፊት ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የገቡት ቅራኔ ለገላጋይም አስቸጋሪ ነበር። "በሚመሠርቷቸው ፓርቲዎች ውስጥ ለምን አይረጉም?" ሲል ቢቢሲ ላቀረበላቸው ጥያቄ ኢንጂነር ይልቃል ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥተዋል። "ይልቃል ፓርቲዎችን ሲቀያይር ምን ነበር ምክንያቱ። በአጠቃላይ የተቃዋሚ ፖለቲካ ውስጥ የይልቃልን ልዩ የሚያደርገው ምንድነው? ብሎ መጠየቅ አይቀድምም?" የሚሉት ኢንጂነር ይልቃል ከጅምሩ ይህን ጥያቄ የሚያነሱት አብረዋቸው የተዋደቁ፣ የታሠሩ፣ የተገረፉ ቢሆኑ ትኩረት ይሰጡት እንደነበር ያወሳሉ። "እኔን የሚያውቁ ሥልጣን ፈላጊ ብለውኝ አያውቁም" ካሉ በኋላ "ይህ ሩቅ ካሉና ከማላውቃቸው ሰዎች የሚነሳ ነገር ነው" ይላሉ። "ለመሆኑ...ፓርቲ አካባቢስ ምን ጥቅም አለ?" ሲሉም ይጠይቃሉ። "በአሁኑ ጊዜ ባለሙያ ሆኖ መሥራት በጣም ብዙ ገንዘብ የሚገኝበት ነው። የፖለቲካችን አለማደግና ፍረጃ ነው እንጂ አውነት ለመናገር አንድ የግል ሕይወቱን ለመምራት የሚፈልግ ሰው [ለጥቅም ሲል] የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ይገባል ብዬ አላስብም።" "አጭሩ የሥልጣን ቆይታ የእኔ ነው" ኢንጂነር ይልቃልን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ሦስት ፓርቲዎችን መቀያየራቸውን ተከትሎ፤ በአመራርነት ካልሆነ ፓርቲ ውስጥ ለመሥራት ፈቃደኝነታቸው ጥያቄ ውስጥ እየገባ እንደሆነ ከቢቢሲ ለተነሳላቸው ጥያቄ ከሌሎች የፓርቲ አመራሮች ጋር ራሳቸውን በማነጻጸር ምላሽ ሰጥተዋል። "ብርሃኑ ነጋ በትወስድ እንደምሳሌ ከኢህአፓ ጀምሮ፣ ከቀስተ ደመና ጀምሮ፣ ከቅንጅት ጀምሮ ስንት ዓመት አለ? የኢዴፓ መሪ ዶ/ር ጫኔ ሁለት "ተርም" ሙሉ አለ። ልደቱ በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ዋና ፖለቲከኛ ነኝ ብሎ አለ። ይልቃል ግን የቆየው ሦስት ዓመት ብቻ ነው። ከዚያም በኋላ ስሙ ጠፍቶና ሌባ ነህ ተብሎ ተባሮ መጥፋት ነበረበት?" "እንዲያውም በኢትዯጰያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም አጭር ጊዜ በኃላፊነት የቆየው ማን ነው ብለህ ብትጠይቅ ይልቃል ነው።" ኤርትራን ያካተተው አርማ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲተች የነበረው የአዲሱ ፓርቲያቸው መለያ አርማ (ሎጎ) የኢትዮጵያና የኤርትራን ካርታ አጣምሮ የያዘ ነበር። "አንዲት ሉአላዊት አገርን በካርታ ማካተቱ አግባብ ነው ወይ" ተብለው የተጠየቁት ኢንጂነር ይልቃል፤ አርማው የኤርትራንና የኢትዮጵያን የሕዝቦች ትስስር ለማጉላት ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑና ሆኖም በችኮላ በመሠራቱ በተለይም ሁለቱን አገራት የሚለይ መስመር በጉልህ አለመታየቱ ለትችት እንዳጋለጠው አምነዋል። "ችቦዎቹ 14 ነበሩ። በኋላ አራት እንዲሆኑ አድርገናል። የኢትዮጵያ ልጆች ከአራቱም አቅጣጫ ለነፃነትና ለእኩልነት በአንድነት ሲቆሙ የሚያሳይ ምልክት ነው። ሆኖም አርማው በጉባኤ ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶበት እንዲስተካከልና መስመሩ ግልጽ ሆኖ እንዲወጣ ውሳኔ ተሰጥቶበታል" ብለዋል። ስለ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ምን ያስባሉ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየመድረኩ የሚሰጡትን ተስፋ በጥንቃቄ እንደሚመለከቱት የሚናገሩት እንጂነር ይልቃል አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር በተለየ ሁኔታ የሚያዩበት ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል። "ፓርቲያቸው ነው የሰየማቸው። በሊመንበርነት የመረጧቸው የፓርቲው አራት ግንባሮች ናቸው። የሕዝብ ስሜትን ይይዝልኛል ብለው የሚያስቧቸው ነገሮች ላይ ብቻ አትኩረው እየሄዱ ስለሆነ እኔ እንደውም [የጠ/ሚሩ ንግግሮች] ከማዘናጋት ያለፈና የአገሪቷን ችግር እንዲከማች ከማድረግ ያለፈ ሆኖ አይታየኝም" ይላሉ። "ፖለቲከኛ በመሆኔ በስሜታዊ ንግግሮች ወይም ደግሞ የፖለቲካ ትኩሳት ለማብረድ በሚወሰዱ ትናንሽ እርምጃዎች አላምንም፤ [አንድን መሪ] በመዋቅር በሚሠራው ሥራ ነው የሚለካው" ብለዋል። ከአቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) ጋር ከተደረገ ቃለ ምልልስ ውስጥ የተወሰደ " 'ኢንጂነር' በሚለው የማዕረግ ስም ለምን ይጠራሉ?" ከደቡብ ዩኒቨርስቲ በእርሻ ምሕንድስና በመጀመርያ ዲግሪ የተመረቁት ኢንጂነር ይልቃል በመጨረሻ ስለሚጠሩበት ማዕረግ ዙርያ ከቢቢሲ ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር። "ቀኛዝማች፣ ግራዝማች ባላንባራስ እየተባለ በኖረ አገር ይህንን ነገር ቁምነገር ያደርጋል ብዬ አላስብም። እኔ በበኩሌ ብዙ አልወደውም። ዞሮ ዞሮ ግን ከውሀ ሀብት ልማት የሞያ ፍቃድ ወስጄ ነው ያለሁት። እኔም ማዕረጉን አልወደውም። ደስተኛም አይደለሁም። ቢቢሲ፦ ይህንን ቃለመጠይቅ ስናደርግልዎ ኢንጂነር እያልኩ ነው የቆየሁት፤ በዚህ ማዕረግ አትጥሩኝ ብለው ያውቃሉ? ኢንጂነር ይልቃል፦ እንደነገርኩህ መመጻደቅ እንዳይሆን እንጂ መድረክ ላይ ስብሰባም ስናደርግ እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም። ለምሳሌ አሜሪካን አገር ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ጋር አንድ መድረክ ላይ ስብሰባ ተቀምጠን እኔ ይሄንን ነገር እንደማልወደው መቅረትም እንዳለበት ተናግሪያለሁ።" "...ኦባማ በከንስቲትዩሽናል ሎው ፒኤችዲ አላቸው። ነገር ግን "ዶ/ር ኦባማ" ብለናቸው አናውቅም። ሰው ታይትል ኦሪየንትድ ነው። እኔም አልፈልገውም። እንዲሁ መመጻደቅ እንዳይሆና ከሌሎች ሰዎች ላለመለየት ነው ዝም የምለው።" ቢቢሲ፦ ግን እኮ ኢንጂነር ይልቃል! የሚጠራው ሰው ዝም ካለ ወይም በዚህ ማዕረግ አትጥሩኝ ካላለ ፈቅዶታል አያስብልም? ኢንጂነር ይልቃል፦ በቃ ከዛሬ ጀምሮ ይልቃል ብለህ ጥራኝ።
49041905
https://www.bbc.com/amharic/49041905
የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ኃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስብሰባ ተቀምጠው በነበረበት ሰዓት የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው የኔትወርኩ የዜናና ፕሮግራሞች አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ብርሀኑ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ጌታሁን ደጉዬ እና ምክትላቸው አቶ ታሪኩ ለማ የሚባሉ ሲሆን ሌሎች የመገናኛ ብዙሀኑ ባልደረቦች ግን ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገልፀዋል። ትናንት ጠዋት ወደ 6 ሰዓት አካባቢ ወደ ቢሯቸው የፀጥታ አካላት መምጣታቸውን እና ጥበቃ ሰራተኞቹ የቢሮውን ቁልፍ እንዲሰጧቸው መጠየቃቸውን ያስታወሱት አስተባባሪው፤ ነገር ግን የጥበቃ ሰራተኞቹ ቁልፍ እንደሌላቸው በመግለፅ እንዳሰናበቷቸው ተናግረዋል። • ከሐዋሳ ተነስቶ በሌሎች አካባቢዎች ጉዳት ያደረሰው ሁከት • "አሁንም እያጣራን ማሰሩም፤ መፍታቱም ይቀጥላል" ኮሚሽነር አበረ ማታ ወደ 4 ሰዓት የሲዳማ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ ሽማግሌዎችና፣ ኤጀቶዎች በታቦር መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የምርጫ ቦርድን ሃሳብ ለመቀበል በንግግር ላይ ባሉበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ተናግረዋል። እነዚህ ኃላፊዎች ከወጣቶቹ ጋር የተሰበሰቡት ኤጀቶ ውስጥ በነበሯቸው ተሳትፎ ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። • የአዲስ አበባ መስተዳደርና የባላደራው ምክር ቤት ሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ ሥራ የጀመረው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ሲሆን እስካሁን የሚገኘው የሙከራ ስርጭት ላይ ነው። የሚዲያ ተቋሙ ፕሮግራሞቹን የሚያስተላልፈው ሐዋሳ ከሚገኘው ቢሮውና ደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ውስጥ ከሚገኘው ማሰራጫው እንደሆነ አስተባባሪው ተናግረዋል። በአሁን ሰዓትም ምንም ዓይነት ስርጭት ከሐዋሳ የማይተላለፍ ሲሆን ነገር ግን ከጆሀንስበርግ የሚተላለፉ ዝግጅቶች ብቻ በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ እንደሚታዩ ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር ውለዋል ስለተባሉት ግለሰቦች የእስር ምክንያትና ስላሉበት ሁኔታ ለመጠየቅ ይመለከታቸዋል የተባሉ የደቡብ ክልልና የሐዋሳ ከተማ ባለስልጣናትን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ በሲዳማ ተወላጅ ዳያስፖራዎችና ባለሀብቶች የተቋቋመ ቴሌቪዥን ሲሆን ድርጅቱ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ጨምሮ አርባ አንድ ሰራተኞች እንዳሉት ተገልጿል።
news-52845064
https://www.bbc.com/amharic/news-52845064
በሕንድ የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ለምን ማዕድቤት እንዳይገቡ ይከለከላሉ?
በሕንድ የወር አበባ እያየች ያለች ሴት ሁሉን አቀፍ መገለል ይደርስባታል። እንደጎደፈች ትቆጠራለች። ከማኅበራዊና መንፈሳዊ ሕይወት ትገለላለች። ቤተ መቅደስ አትገባም፤ እንኳን ቤተ መቅደስ ማዕድቤት ምግብ ለማብሰልም እንዳትገባ ትደረጋለች። ይህ በዚያች አገር አሁንም ድረስ ያለና በስፋት የሚታይ ሀቅ ነው።
የዓለም የወር አበባ ቀንን አስመልክቶ ዝነኛው የፎቶግራፍ ጥበበኛ ኒራጅ ጌራ የወር አበባ ውብ ተፈጥሮ እንጂ ነውር እንዳልሆነ ለማሳየት ሞክሯል። እነዚህ የፎቶግራፍ ሥራዎቹ ቀጥተኛና ሀቁን የሚያፍረጠርጡ በመሆናቸው ማንኛውም ተመልካች እንዲሁ አንደዋዛ አይቶ የሚያልፋቸው አይደሉም። በሕንድ በወር አበባ ጉዳይ ላይ ግልጽ ውይይት ስለማይበረታታ 71 ከመቶ የሚሆኑ ልጃገረዶች የመጀመርያውን የወር አበባ የሚያዩት "ፔሬድ" ምን እንደሆነ ጨርሶዉኑ ሳይረዱ ነው። በጉዳዩ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚሠሩ ትጉሃን እንደሚናገሩት ከሆነ በሕንድ ወላጆች ለልጆቻቸው ስለ ወር አበባ ለማስረዳት ስለሚያፍሩ ወይም ስለማይደፍሩ ወይም ተገቢ ነው ብለው ስለማያስቡ ሴት ልጆቸውን ለመሸማቀቅ፣ ለድንጋጤና ለፍርሃት ይዳርጓቸዋል። የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ እንደልብ ማግኘት በሕንድ ሌላ ትልቅ ራስ ምታት ነው። ከሁለት ዓመት በፊት የመብት ተሟጋቾች ለወራት የዘለቀ እልህ አስጨራሽ ዘመቻ በማድረግ መንግሥት በወር አበባ የንጽህና መጠበቂያ ላይ ጥሎት የነበረውን የ12 ከመቶ ግብር እንዲያነሳ ማስገደድ ችለዋል። የመብት ተሟጋቾች በወቅቱ ያነሱት አንኳር ነጥቦች ሁለት ናቸው። አንዱ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ እንደ ቅንጦት ዕቃ ተደርጎ መታሰብ እንደሌለበት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የወር አበባ ሴቷ ተፈጥሮ የሰጣት ጸጋ እንጂ ሲሻት እንዳይመጣ የምታደርገው ነገር አለመሆኑን ነው። ያም ሆኖ የመብት ተሟጋቾቹ ያስገኙት የ12 ከመቶ የግብር ቅነሳ ገና የመጀመሪያው ሂደት እንጂ የመጨረሻው ግብ አይሆንም። በአገሪቱ ሁሉም ሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ የማግኘት ሙሉ መብትን ሊጎናጸፉ ይገባል። ይህን ለመገንዘብ አንዳንድ የቁጥር መረጃዎችን ማጤን ያሻል። ሴቶች የወር አበባ ንጽህናን ለመጠበቅ የተለያዩ ነገሮችን ለመጠቀም ይገደዳሉ በሕንድ የወር አበባ ከሚያዩ 355 ሚሊዮን ሴቶች ውስጥ 36 ከመቶ ብቻ ናቸው መሠረታዊ የንጽህና መጠበቂያን የሚያገኙት። የተቀሩት ግን እንደ አፈር፣ ጭቃ፣ ብጣሽ ጨርቅ፣ ገለባ፣ ቅጠላ ቅጠልና ሌሎች ለጤና ጠንቅ የሆኑ ነገሮችን ነው የሚጠቀሙት። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ደግሞ በተለይ አሁን በኮሮናቫይረስ ምክንያት የንጽህና መጠበቂያ ምርትና አቅርቦት እንደልብ ባለመኖሩ በርካታ የሕንድ ሴቶች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ነው። ድህነት ለዚህ ችግር ሌላው ምክንያት ነው። የፕላን ኢንተርናሽናል ዩኬ ጥናት እንደሚያስረዳው ከሆነ በሕንድ ከ10 ሴቶች አንዷ ከ21 ዓመት በታች ያለች ሴት መሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ማግኘት ስለማትችል ጋዜጣ ወይም የሽንት ቤት ሶፍት አልያም ካልሲን በምትኩ ለመጠቀም ትገደዳለች። በሕንድ ሴቶች ገና በወጣትነታቸው ከእንደዚህ ዓይነት መሳቀቅና ህመም ጋር መኖርን ተላምደውታል፤ ወይም ለማላመድ ተገደዋል። ከዚህ ችግር ለመውጣትና ለመወያየት ሲጥሩ እምብዛምም አይታዩም። አሁን አሁን ግን ከማኅበራዊ ሚዲያው መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሴቶች ከወር አበባ ጋር የተያያዘ ታሪካቸውን በድፍርት ማጋራት ጀምረዋል። የሚገርመው ሴቶች ታሪካቸውን በማጋራታቸው ብቻ የሞራል ፖሊስ ነን ባዮች ያንጓጥጧቸዋል፤ ስሜታቸውን የሚጎዱ ቃላትን ጭምር እየተናገሩ ሊያሳፍሯቸው ይሞክራሉ። ሺህዎች የበይነ መረብ ጥቃትና ዛቻን ያደርሱባቸዋል። በሕንድ አሁንም ድረስ ሚሊዮኖች የንጽሕና መጠበቂያ አያገኙም። ድህነት የወር አበባ ንጽህናን በተመለከተ ከባድ ፈተና ሆኗል ከዚህ በላይ በሚታየው ምሥል ላይ በቀን ሠራተኝነት የሚተዳደር ቤተሰብ ልጅ የንጽህና መጠበቂያ አስፈልጓት ነገር ግን ቤተሰቧን መጠየቅ ጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቷት ስትጨነቅ ይታያል። ለቤተሰቧ ምርጫው ከባድ ነው፤ የእርሷን የንጽህና መጠበቂያ ፍላጎት ማሟላት ይሻላል ወይስ የሚላስ የሚቀመስ ማቅረብ? ይህ የብዙ ቤተሰቦች ሕይወት ነው። ይህ የፎቶግራፍ ጥበበኛ በመሠረተው ሂዩማኒቲ ፋውንዴሽን አማካኝነት ሁሉም ከድህነት ወለል በታች ለሚኖሩ የሕንድ ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ማግኘት መብት እንዲሆን እየታገለ ይገኛል። በሕንድ በየዓመቱ 23 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች የወር አበባ ካዩ በኋላ ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ። ለዚህም አንዱ ምክንያት በቂ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ አለመኖር ነው። በርካታ ሴቶች በወር አበባ ምክንያት ትምህርት ያቋርጣሉ ልጃገረዶች የወር አበባ መጠበቂያ ማግኘት ስለማይችሉ ልብሳቸው ላይ ደም ሲታይ በጓደኞቻቸው መንጓጠጥ ስለሚደርስባቸው ያን በመፍራት ከትምህር ቤት ይቀራሉ። ሌላ ጥናት እንዳስረዳው ወንዶች ብቻ ሳይሆን በርካታ ሴቶች የወር አበባ ማለት መጉደፍ ወይም አለመንጻት መሆኑን አምነው እንዲቀበሉ ሆነዋል። በወር አበባ ጊዜ ከማኅበራዊ ሕይወት መገለላቸውንም ተገቢና ትክክለኛ አደርገው ያዩታል። ሆኖም ይህ ጉዳይ የሕንድ ችግር ብቻ አይደለም። "የወር አበባም ተፈጥሯዊና ጤናማ ነገር አድርገን መመልከት ይኖርብናል። በወር አበባ ዙርያ ያሉ አሉታዊ አመለካከቶች ቀስ በቀስ ሊጠፉ ይገባል" ይህ የሚሆነው ደግሞ ተፈጥሮን ስንቀበል ነው" ይላል የፎቶግራፍ ጠቢቡ ጌራ። ጌራ የመጨረሻ መልእክት አለው። "ስለ ወር አበባ በግልጽ መነጋገር የመፍትሄዎች ሁሉ ቁልፍ ነው።"
news-52859906
https://www.bbc.com/amharic/news-52859906
ከቦምብ ሠሪነት ወደ ሰላም ሰባኪነት የተሸጋገረው አሊ ፋውዚ
አሊ ፋውዚ ከአል ቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው ጀማ ኢስላሚያ ቡድን ቁልፍ አባል ነበር። ይህ ቡድን እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2002 ኢንዶኔዥያዋ ባሊ ላይ ከፍተኛ የቦምብ ጥቃት ሰንዝሯል። የ200 ሰዎች ሕይወትም ተቀጥፏል።
“የባሊውን የቦምብ ጥቃት ያደረሱት ወንድሞቼ ናቸው። በቱሪስት መናኸሪያዋ ከተማ የተጣለው ትልቅ ፈንጂ ነበር” ቡድኑ በኢንዶኔዥያ ሌሎችም ጥቃቶች አድርሷል። ሆቴሎች፣ የምዕራባውያን ኤምባሲዎችም ኢላማው ነበሩ። ምሽጋቸው የኢንዶኔዥያዋ ምሥራቅ ጃቫ ውስጥ የምትገኘው ተንጉሉን ነበረች። “ጎበዝ ቦምብ ሠሪ ነኝ። በአምስት ደቂቃ ውስጥ ቦምብ ሠርቼ እጨርሳለሁ” የሚለው አሊ ዛሬ ላይ የሕይወት መርሁን ለውጧል። • ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ዝሆኖች በታጣቂዎች ተገደሉ • በምዕራብ ኦሮሚያ ነጆ አራት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች ተገደሉ በደቡብ ምሥራቅ እስያ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ጂሀዲስቶች ሕይወታቸውን እንዲለውጡ ያግዛል። ከነውጥ እንዲወጡ፣ አዳዲስ ታጣቂዎች መመልመል እንዲታቀቡም ይደግፋቸዋል። “ሰዎች የአሸባሪ ቡድን እንዲቀላቀሉ መመልመል ቀላል ነው። አንድ ጥይት ተኩሰው በርካቶች ይከተሏቸዋል። በተቃራኒው አንድን ሰው ከጽንፈኛ አመለካከቱ ማላቀቅ (ዲራዲካላይዜሽን) ጊዜ ይወስዳል” ይላል አሊ። ሰዎችን ከጽንፈኛ አመለካከት ለማላቀቅ መሞከር ቀላል ነገር አይደለም። አሊ ብዙ ጊዜ የሞት ማስፈራሪያ እንደደረሰው ይናገራል። “ቢሆንም አልፈራም። የማደርገው ነገር ትክክል እንደሆነ አውቃለሁ። ለዚህ ተግባሬ ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” ሲል አቋሙን ያስረግጣል። “የቦምብ ጥቃታችን ያስከተለውን አስከፊ ጉዳት ማየቴ ሕይወቴን እንድለውጥ አደረገኝ” አሊና ወንድሞቹ በሚኖሩበት መንደር በአፍጋኒስታን፣ ቦስንያና ፍልስጤም ያሉ ጦርነቶችን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በስልካቸው ይመለከቱ ነበር። ታጣቂ ቡደን ለመቀላቀል የወሰኑትም ለዚህ ነው። “ንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጭካኔ የተሞላው ጥቃት አይተናል። በጂሀድ ሙስሊሞችን ለመታደግ ቆረጥኩ። በወጣት፣ ሙቅ ደሜ ለመታገል ወሰንኩ።” ወንድሞቹ ለትግል ወደ አፍጋኒስታን ሲሄዱ እሱ በፊሊፒንስ ያሉ ታጣቂዎችን ተቀላቀለ። “እዛው መሞት እፈልግ ነበር። ሞቴን ብዙ ጊዜ አስቤዋለሁ። ትግል ላይ ሳለሁ ከሞትኩ ቀጥታ መንግሥተ ሰማያት እንደምገባ አምን ነበር። መሪዎቻችን በየቀኑ ይህንን ደጋግመው ይነግሩን ነበር” ይላል። ወንድሞቹ ከአፍጋኒስታን ሲመለሱ የተማሩትን ተገበሩ። በዓለም አቀፍ ጎብኚዎች በሚዘወተረው ባሊ ላይ በ2002 ጥቃት አደረሱ። • የደረሱበት ያልታወቀው ተማሪዎች ስድስት ወር ሆናቸው • በአማራ ክልል ሁለት አመራሮች እና አንድ የፖሊስ አባል ተገደሉ “ጥቃቱን በቴሌቭዥን ሳይ ደነገጥኩ። ብዙ አስክሬን ነበር። ባለሥልጣኖችም የት እንዳለን አውቀው ነበር” ሲል ያስታውሳል። ሁለቱ ወንድሞቹ ተገድለዋል። ሌላው ወንድሙ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል። አሊ በባሊው የፈንጂ ጥቃት እንዳልተሳተፈ ይናገራል። ከሌላ የሽብር ጥቃት ጋር በተያያዘ ሦስት ዓመት ታስሯል። ሕይወቱ የተለወጠውም በዚህ ወቅት ነው። “ፖሊሶቹ ለሰው በሚገባ ክብር ነበር የያዙኝ። አሰቃይተውኝ ቢሆን ኖሮ እስከ ሰባት ትውልዴ ድረስ የኢንዶኔዥያን መንግሥት ይታገል ነበር።” ፓሊሶች “ሰይጣን ናቸው” ተብለው ይማሩ እንደነበር ይናገራል። እውነታው ግን ከዛ የተለየ ሆኖ አግኝቶታል። በሱ ቡድን አባላት የደረሰ የቦምብ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ሲያገኝ የተሰማውን ሀዘንም እንዲህ ይገልጻል. . . “አለቀስኩ። ልቤ ተሰበረ። የቦምብ ጥቃታችን ያስከተለውን አስከፊ ጉዳት ማየቴ ሕይወቴን እንድለውጥ አደረገኝ። ከጦርነት አጋፋሪነት ወደ ሰላም አርበኛነት ለመሸጋገር ወሰንኩ።” ሌሎች አሸባሪዎችም እንዲቀየሩ እረዳቸዋለሁ” ተንጉሉን በተባለችው መንደር በሚገኘው ዋና መስጊድ አቅራቢያ አሊ የመሠረተው ተቋም ይገኛል። ‘ሰርክል ኦፍ ፒስ’ ወይም የሰላም ክበብ ይባላል። ከአራት በፊት ነበር ተቋቋመው። ሰዎችን ከጽንፈኝነት ለማላቀቅም ይሠራል። አንድ ምሽት ላይ በዋናው መስጊድ የተካሄደው የምሽት ጸሎት የተመራው በሁለት የቦምብ ጥቃት ሰለባዎች ነበር። መንደሩ የሁለቱን ሰዎች ሕይወት ያመሰቃቀሉት ታጣቂዎች ምሽግ ነበር። አሊ እንደሚለው፤ የቦምብ ጥቃት ሰለባዎችን ወደ ማኅበረሰቡ ይወስዳቸዋል። “አመለካከቴን የለወጠው እነሱን መተዋወቅ ነው” ይላል። በመስጊዱ ውስጥ በኢንዶኔዥያ የደረሰ የቦምብ ጥቃት ያስከተለው ጉዳት በተንቀሳቃሽ ምስል ይታያል። በመስጊዱ በሽብር ጥቃት ታስረው የነበሩ ሰዎች እንዲሁም ያሰሯቸው ፖሊሶችም በጋራ ተሰባስበዋል። የቦምብ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ሰቆቃቸውን እያለቀሱ ሲናገሩ ያደምጣሉ። በመስጊዱ ከተገኙት አንዱ የ33 ዓመቱ ዙሊያ ማህንድራ ነው። አባሩ አምሮዚ ሲታሰር ዙሊያ ወጣት ነበር። አባቱ ከባሊው የፈንጂ ጥቃት ጋር በተያያዘ በሞት ተቀጥቷል። አምሮዚ ቅጣቱን ሲቀበል አንዳችም ጸጸት አላሳየም ነበር። ስለዚህም መገናኛ ብዙሀን “የሚስቀው ገዳይ” ይሉት ነበር። የአምሮዚ ልጅ ዙልያ የመስጊዱ ጸሎት ካለቀ በኋላ፤ የቦምብ ጥቃት የደረሰባቸውን ሁለት ሰዎች አግኝቶ፣ አቅፏቸው ደጋግሞ ይቅርታ ጠይቋቸዋል። • ሩሲያና ቱርክ የሚፎካከሩባት ሊቢያ • የጆርጅ ፍሎይድ የመጨረሻዎቹ 30 ደቂቃዎች “ይቅርታ የምለው እኔ ስላጠፋሁ አይደለም። በአባቴ ድርጊት የተጎዱ ሰዎችን ይቅርታ የመጠየቅ ኃላፊነት ስላለብኝ ነው” ይላል ዙልያ። ዙልያ አባቱ ሲገደል ለበቀል ተነሳስቶ ነበር። ቦምብ መሥራት መማር ፈልጎ እንደነበርም ይናገራል። አጎቱ አሊ ግን ሀሳቡን አስቀይሮታል “አጎቴ አሊ ፋውዚ እና አሊ ኢምራን ስህተት ውስጥ ልገባ እንደነበር አሳይተውኛል። የነሱን ፈለግ ተከትዬ ሌሎች አሸባሪዎችም እንዲቀየሩ እረዳቸዋለሁ። ዛሬ የሆንኩትን ሰው ለመሆን ብዙ ርቀት ተጎዣለሁ። ጂሀድ ሰዎችን መግደል ወይም መዋጋት ሳይሆን ለቤተሰብ መትጋት መሆኑን ተደርቻለሁ” ይላል። የዙልያ ጓደኞች ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያለው የኢንዶኔዥያ ታጣቂ ቡደን መቀላቀላቸውን ይናገራል። አንዳንድ ሰው በድህነት ሌሎች ደግሞ ሥራ በማጣት መሰል ቡድኖችንን ይቀላቀላሉ ይላል። አጎቱ አሊ ከጽንፈኛ ሀሳብ የሚያላቅቃቸውን ሰዎች ከማረሚያ ቤት ይመለምላል። “የምመክራቸው ከሕይወት ተሞክሮዬ ተነስቼ ነው። ታጋይ፣ አሸባሪ ነበርኩ። ስለዚህ ማረሚያ ቤት የምሄደው እንደ ጓደኛቸው ሆኜ ነው።” ታራሚዎችን ማሳመን ግን ቀላል አይደለም። አንዳንዶች የፖሊሶች ቅጥረኛ ነው ብለው ያስባሉ። “ከፖሊሶች በላይ ኢ-አማኒ (ካፊር) ነህ ይሉኛል። በድረ ገጽ ማስፈራሪያም ይደርሰኛል። ግን እችለዋለሁ” ይላል አሊ። ያስተምራቸው ከነበሩ 98 ሰዎች መካከል ሁለቱ ከእስር ቤት ከተለቀቁ በኋላ በድጋሚ ታጣቂዎችን ተቀላቅለዋል። በሰዎች አዕምሮ ሰርጾ የገባን ሀሳብ ማስለወጥ ቀላል እንዳልሆነና ሁሌ እንደማይሳካም አሊ ያስረዳል። “የጥፋት ሕይወትን እተዋለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ከአሊ ተማሪዎች አንዱ ሱማርኖ ነው። ቀድሞ ከታጣቂዎች ጋር መሣሪያ ይሠሩበት የነበረውን ቦታ ለአሊ አሳይቶታል ሱማርኖ ከሦስት ዓመት እስር ሲለቀቅ በአሊ ድጋፍ የጎዞ ወኪል ቢሮ ጀምሯል። ቢሮው አማኞችን ወደ መካ ይወስዳል። “በዚህ የጉዞ ወኪልነት ሥራ የጥፋት ሕይወትን እተዋለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ይላል ሱማርኖ። • በአሜሪካ እየተበራከተ የመጣው የፖሊስ ጭካኔ እና የተገደሉ ጥቁሮች ለደንበኞቹ ስለቀደመ ሕይወቱ ሲነግራቸው ስጋት ይገባዋል። ሆኖም ግን ሥራው አዕምሮውን ነፃ እንደሚያወጣው ያምናል። “ለደምበኞቼ ባሊ ቦምብ አፈንድተው የተገደሉት አሊ ጉፍሮን እባ አምሮዚ ዘመድ ነኝ እላቸዋለሁ። የአሸባሪ ቡድኑ አባል ነበርኩ አሁን ግን አላህ ምስጋና ይግባውና ከክፉ አስተሳሰቤ ነጽቻለሁ እላቸዋለሁ። ወደ መካ የምወስዳቸው አስጎብኛቸው እንደሆንኩም እነግራቸዋለሁ።” “አሁንም ታጥቀው ያሉ ሰዎች አይወዱንም” የአሊ ባለቤት ሉሉ ታዳጊዎችን ቁርዓን ከሚያስተምሩ አንዷ ናት። ከምታስተምራቸው ታዳጊዎች ያንዳንዶቹ ቤተሰቦች በሽብርተኝነት ተከሰው ቢታሰሩም “ሁሉም ሰው አንድ አይነት አይደለም” ስትል ልጆቹን ትመክራለች። “ማኅበረሰባችን ውስጥ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች አሉ። ሀይማኖታችንን እስካላደናቀፉ ድረስ ልናከብራቸው ይገባል” ትላለች ሉሉ። ነገር ግን በሀሳቧ የሚስማማ እንዳለ ሁሉ የሚቃወማትም አለ። “አሁንም ታጥቀው ያሉ ሰዎች አይወዱንም። ከኛ ይርቃሉ። በአንድ ቡድን ለአንድ አላማ የቆምን ነበርን። የባሊው ፍንዳታ ብዙ ሙስሊሞችን ጨምሮ ንጹሀንን ከቀጠፈ በኋላ እኛ ተለውጠናል። ያልተቀየሩም አሉ።” ባለፈው ዓመት የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ አጥፍቶ ጠፊዎች ሦስት ቤተ ክርስቲያኖችን በቦምብ አጋይተዋል። • በትግራይ ክልል የተፈጠረው ምንድን ነው? አጥቂዎቹ ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያለው ጀማ አንሽሩት ዱላይ ቡድን አባላት ናቸው። በኢንዶኔዥያ የጸጥታ ኃይልና ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። አሊ በፈጠረው የሰላም ክበብ ውስጥ ሴቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳተፉ መሆኑ ሉሉን ያስገርማታም። “ባለቤቴ የቀድሞ አሸባሪዎች ከእስር ሲለቀቁ ወደ ሽብር እንዳይመለሱ ለማድረግ ደፋ ቀና እያለ ነው። የብዙ ሰዎችን ሕይወት ቢለውጥም አሁንም በርካቶች ጽንፈኛ ናቸው። ሙሉ በሙሉ ልናጠፋው አንችልም” ትላለች።
54557174
https://www.bbc.com/amharic/54557174
የሴቶችና ሕጻናት ጥቃትን ለመከላከል የተቋቋመው የፖሊስ ግብረ ኃይል እንዴት ይሠራል?
የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በዓሥር ዓመት መሪ እቅዱ ካካተታቸው መካከል የጸረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ኃይል እንዲሁም ብሔራዊ የጥቃት አድራሾች መረጃ ሥርዓት ይገኙበታል።
ተቋሙ ከነዚህ በተጨማሪ የሕጻናት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና የሕጻናት ማኅበራዊ አገልግሎት ኤጀንሲ የመዘርጋት ሐሳብም እንዳለው አስታውቋል። የአፍሪካ ሴቶች አመራር ማዕከል፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ካውንስል እና የሴቶች የልማት ፈንድ ማቋቋምም ከእቅዶቹ መካከል ይገኙበታል። በዋነኛነት ስለ ጸረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ኃይል እና ብሔራዊ የጥቃት አድራሾች መረጃ ሥርዓት ምንነት ከመሥሪያ ቤቱ ማብራሪያ ጠይቀናል። የጸረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ኃይል የሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ሚንስትር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አድነው አበራ እንደሚሉት፤ በዚህ ግብረ ኃይል ከፍትሕ፣ ከጤና እና ማኅበራዊ ጉዳይ የተውጣጡ አካላት ይካተቱበታል። የፖሊስ ግብረ ኃይሉ ሕጻናት እና ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን በሚመለከት ብቻ ይሠራል። "ጥቃት ከመከሰቱ በፊት ይከላከላል። ጥቃት ሲከሰትም ጉዳዩን እስከ ፍርድ ቤት መረጃ በማጠናቀር ይሠራል" ብለዋል አቶ አድነው። ግንዛቤ በመስጠትና በንቅናቄ ሥራዎች ብቻ ጥቃትን መከላከል ስለማይቻል ሥርዓቱ መዘርጋቱን አስረድተዋል። "የተለያዩ ተቋሞች በቅንጅት ካልሠሩ አንድ ተቋም ብቻ በአሸናፊነት አይወጣውም" የሚሉት አቶ አድነው፤ አሁን ላይ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ እና ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር እየተወያዩ እንደሆነና የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅዱ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚተገበር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ብሔራዊ የጥቃት አድራሾች መረጃ ሥርዓት ብሔራዊ የጥቃት አድራሾች መረጃ ሥርዓት ወይም ናሽናል ሴክስ ኦፌንደርስ ሬጅስትሬሽን ጥቃት አድራሽ ወንጀለኞች የሚመዘገቡበት ሥርዓት ነው። "በሴቶችና ሕጻናት ላይ ጥቃት የሚያደርስ በሕግ ብቻ ተጠይቆ የሚወጣበት ሳይሆን፤ በሕይወቱ ባጠቃላይ ተጠያቂ የሚሆንበት፣ የሚሸማቀቅበት ሥርዓት ነው" ሲሉ የሕዝብ ግንኙነቱ ያስረዳሉ። ሥርዓቱ፤ ወንጀለኞች ከእስር ከወጡ በኋላ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ያግዳል። አሠራሩ ወንጀለኞችን ለመቅጣት፣ ጥቃት አድራሾችን ለመግታት እንዲሁም ኢትዮጵያም የሴቶችና ሕጻናት ጥቃትን የምትጠየፍ አገር መሆኗን ለማሳየትም እንደሚያገለግል አቶ አድነው ገልጸዋል። እንዴት ይሠራል? በአብዛኛው ጾታዊ ጥቃት የሚደርሰው በቤተሰብ፣ በዘመድ፣ በጎረቤት ወይም በሌላ የቅርብ ሰው እንደመሆኑ ጥቃት የደረሰባቸውን ሕጻናት እንዴት ትለያላችሁ? በሚል ለአቶ አድነው ጥያቄ አቅርበን ነበር። እሳቸው እንደሚሉት፤ ሰፈር ውስጥ ወይም በትምህርት ቤቶች ከመምህራን መረጃ በመሰብሰብ ይሠራሉ። "ተማሪዎች የሚያሳዩትን ባህሪ መምህራን ያውቁታል። ትካዜ፣ ትምህርት በቀላሉ መቀበል አለመቻል ወዘተ. . . ይጠቀሳሉ" ብለው ግብረ ኃይሉ ከተቋቋመ በኋላ ሌሎች ዝርዝር የአሠራር መንገዶች እንደሚወጡ አክለዋል። ሌላው የሕጻናት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት (ዩኒቨርሳል ቻይልድ ቤነፊት) ነው። ጥቃት፣ ያለ እድሜ ጋብቻና ድህነት በሰፋበት አካባቢ ከ0 እስከ 2 ወይም እስከ 5 ዓመት ልጆች እናቶች የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ ፕሮጀክት ነው። "ጥቃትን ለመከላከል ቀጥተኛ ያልሆነ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። እናትን በኢኮኖሚ ለማሳደግና አመጋገብ፣ ጤናና የአእምሮ እድገትን ጨምሮ ለሕጻናት ሁለተንተናዊ እድገት ድጋፍ ለማድረግ ይውላል" ይላሉ። በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም የነበረው ጥቃት የደረሰባቸው እንዲያገግሙ የመደገፍ (ሪሀብሊቴሽን) ሂደት እንደሚቀጥል አቶ አድነው ተናግረዋል። አዳማ እና አዲስ አበባ ላይ ፍቃድ እንዳገኙና የነበሩትን ማዕከላት ከማጠናከር ጎን ለጎን፤ አዲስና ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከላት ለመገንባት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አክለዋል። አያይዘውም፤ "ማንኛውም ችግር ሲከሰት በቅድሚያ የሚጎዱት ከተጠቃሚነትም ወደ ኋላ የቀሩት ሴቶችና ሕጻናት ናቸው። ይህን ለመፍታት ቋሚ አሠራር እንጂ ጊዜያዊው አይረዳም። ተደራርበው የሚመጡ ማኅበራዊ ቀውሶች በዘላቂ ሥርዓት እየተቀረፉ እንደሚሄዱ እናምናለን" ብለዋል። የሴቶች መብት ተሟጋቾች ምን ይላሉ? የጸረ ጥቃት ፖሊስ ግብረ ኃይል እና ብሔራዊ የጥቃት አድራሾች መረጃ ሥርዓትን በተመለከተ በተለያዩ የጾታ እኩልነት ላይ የሚሠሩ ማኅበሮች አባላት ምን አስተያየት እንዳላቸው ጠይቀናል። የ 'የሎ ሙቭመንት' አባል የሆነችው ሩት ይትባረክ፤ ግብረ ኃይሎቹ መቋቋማቸው መልካም ቢሆንም፤ ተቋቁመዋል ለሚል ፍጆታ ከመዋል ባሻገር ተግባራዊ ለውጥ ማምጣት እንዳለባቸው ትናገራለች። ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ወደ ፍትሕ እንዳይሄዱ ከሚያደርጋቸው አንዱ ከፍትሕ አካላት አዎንታዊ መልስ አለማግኘት መሆኑን በመጥቀስ፤ "በጥቃት ላይ ጥቃት የሚያደርሰው አንዱ የፍትሕ አካሉ ነው። ስለዚህ የፍትሕ አካሉ መፈተሽ፣ መሻሻል፣ ለጾታ ጉዳዮች ስሱ መሆን እና ለእውነተኛ ፍትሕ የቆመ መሆን አለበት" ትላለች። ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን አላስፈላጊ ጥያቄ የሚጠይቁ የፍትሕ አካላት ታርመው ጥቃት የደረሰባትን ሴት በምን መንገድ ማስተናገድ እንዳለባቸው መገንዘብ እንዳለባቸው ታሳስባለች። "ዳይሬክቶሬት ማቋቋም ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ሥራ ያስፈልጋል። ታች ካለ ፖሊስ እስከ መጨረሻ የፍትሕ አካላት ድረስ ጥቃት የደረሰባትን ሴት እንዴት እንደሚያስተናግዱ መገንዘብ አለባቸው" ትላለች። ከጾታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የመረጃ ክፍተት እንዳለ የምትገልጸው ሩት፤ ስንት ሴቶች ላይ ጥቃት ይደርሳል? የሚለውን ጨምሮ ሌሎችም ተያያዥ መረጃዎች ተቀናጅተው ቢገኙ ጥሩ እንደሆነ ታክላለች። "ይህ የተዳፈኑ ጉዳዮችን ለመያዝ፣ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትም በጣም ጥሩ ነው። ብዙ ጊዜ የሴቶች መብት ተሟጋቾች እስኪጮሁ ድረስ ምንም አይሠራም። ፍርድ ይጓተታል። ተዳፍኖ ይቀራል። መደራደር ይባላል። ይህንን የሚከታተል መቋቋሙ ጥሩ ነው።" ጾታዊ ጥቃት ሲደርስ ከደፋሪው በበለጠ ተጎጂዋ እንድትሸማቀቅ እንደሚደረግ በመጥቀስ፤ ብሔራዊ የጥቃት አድራሾች መረጃ ሥርዓት መጀመሩን በበጎ ታየዋለች። አሠራሩ፤ ተጎጂዎች እንዲሸማቀቁ የሚያደርገው ማኅበረሰባዊ ትርክት እንዲቀየር እንደሚረዳ ታምናለች። "እከሌ እንዲህ አድርጓል መባል አለበት። መታወቅ አለባቸው። ማኅበረሰቡ ጣቱን ከተበዳይ ወደ በዳይ መቀሰር እስኪጀምር መቀጠል አለበት" ብላለች። የ'ዝም አልልም' ንቅናቄ መሪዎች አንዷ የሆነችው ድምፃዊት ፀደንያ ገብረማርቆስም የሩትን አስተያየት ትጋራለች። "ወሲባዊ ጥቃት ላይ ብቻ አተኩሮ የሚሠራ ግብረ ኃይል መቋቋሙ ትልቅ ነገር ነው" ትላለች። መደፈርና ሌሎችም ወሲባዊ ጥቃቶች ከሌሎች ወንጀሎች በተለየ መንገድ መታየት እንዳለባቸው አለመረዳት በአጠቃላይ የፍትሕ ሥርዓቱ እንደሚስተዋል በማጣቀስ፤ የግብረ ኃይሉ መኖር የለውጥ ጅማሮ እንደሚሆን ተስፋ ታደርጋለች። "በፊት በአፈጻጸም፣ በሕጉና የአቅምም ውስንነት ነበረ። ወሲባዊ ጥቃትን ላይ [በመግታት ረገድ] እስካሁን ለውጥ ያላየነውም ለዚሁ ነው። ከዚህ በኋላ በተወሰነ ደረጃ ለውጥ ይመጣል ብዬ አስባለሁ" ስትል ፀደንያ ታስረዳለች። ብሔራዊ የጥቃት አድራሾች መረጃ ሥርዓት፤ ጥቃት ፈጻሚዎችን ወደ አደባባይ በማውጣት፤ እንዲሸማቀቁ፣ ማኅበረሰቡን እንዲያፍሩም እንደሚያደርግ ትገልጻለች። "እስከዛሬ ጥቃት የደረሰበትን እንጂ ጥቃት አድራሽን አናውቀውም ነበር። ፍርዳቸው የት እንደደረሰ እንኳን አጣርተን አናውቅም። የሰረቀ፣ የገደለና ሌላም ወንጀል የሠራ በአደባባይ ይታያል። ጥቃት አድራሾችስ ለምን አደባባይ አይታዩም? ወጥተው በአደባባይ መታየት አለባቸው።" ማኅበረሰቡ ወሲባዊ ጥቃትን እንደ ወንጀል ገና እንዳልተረዳው የምትናገረው ፀደንያ፤ ጥቃት መፈጸም ከፍተኛ ወንጀል እንደሆነ ግንዛቤ መፍጠር ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ የጥቃት አድራሾችን ማንነት በማጋለጥ ማሸማቀቅ እንደሆነ ትናገራለች። "በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል"
news-53719606
https://www.bbc.com/amharic/news-53719606
ኤርትራ ፡ ኤርትራዊያንና የሌላ አገር ዜጎች ለምን በጀልባ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ያቋርጣሉ?
በዩናይትድ ኪንግደም ኬንት አውራጃ ሙቀቱ አይሏል። የተረጋጋው የባሕር ወጀብ በንፋስ ወዲያ ወዲህ ይላጋል፤ በዝምታ።
ኤርትራዊያንና ሌሎች አምባገነን መሪዎቻቸው ፊታቸውን ያዞሩባቸው ዜጎች በተመሳሳይ ጸጥታውን ተገን አድርገው ይሻገራሉ፤ በዝምታ። እንግሊዝ ባሕር ሰርጥን. . . ። የእንግሊዝ ባሕር ሰርጥ፤ ዩናይትድ ኪንግደምንና ፈረንሳይን የሚያገናኘው አጭሩ የባሕር ላይ አቋራጭ ነው። ይህ ስፍራ ወደ እንግሊዝ ለመሻገርና አዲስ ኑሮ ለመጀመር ላቆበቆቡ ስደተኞች ተመራጩ ነው። ለምን? አንደኛ ይህ የባሕር ሰርጥ በርካታ የመርከቦች እንቅስቃሴ ያለበት በመሆኑ ትኩረት አይስብም። ሁለተኛ አየሩ ምቹ ነው። አየሩ ምቹ ሲሆን የባሕሩ ወጀብ ዝግ ያለ ነው። የኬንት ነዋሪዎች ጠዋት ሲነሱ ባሕር ዳርቻው አካባቢ ቤሳቤስቲ የሌላት እርጉዝ ሴት ያገኛሉ። ከወጀቡ ተገፍታ የወጣች ሴት። መሽቶ በነጋ ቁጥር ስደተኞችን የሚተፋው ይህ ባሕር በርካታ በጦርነትና በድህነት ከሚታመሱ አገሮች የሚነሱ ስደተኞችን አስተናግዷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዚሁ መንገድ ከአውሮፓ አገራት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ገብተው አዲስ የጥገኝነት ጥያቄ የሚያቀርቡ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው። ቁጥሮች በራሳቸው ብዙ ይናገሩ ይሆናል። በዚህ ዓመት ብቻ 4ሺህ ሰዎች በሦስት መቶ ትንንሽ ጀልባዎች ቁጢጥ ብለው ተሻግረዋል። ባለፈው ሐሙስ ዕለት ብቻ 235 ሰዎች ተመዝግበው እንግሊዛዊያን ጉድ እያሉ ነበር። እንዲህ ዓይነት ቁጥር በአንድ ቀን ተመዝግቦ አያውቅም። በነገራችሁ ላይ የፈንሳይ የባሕር ተቆጣጣሪዎች አደን ስለሚወጡና ጀልባዎችን በአካባቢው ስለሚያስቆሙ እንጂ ከዚህ ቁጥር እጥፍ የሆኑ በርካታ ጀልባዎች በየቀኑ ኬንት በደረሱ ነበር። ብዙዎቹ ጀልባዎች በጣም ትንንሽና ለአደጋ የሚያጋልጡ ሆነው በዚያ ላይ በሕጻናትና አቅመ ደካሞች ይታጨቃሉ። በዚያ ላይ ያ መስመር እጅግ ብዙ መርከቦች የሚመላለሱበትና አደገኛ ነው። በዓለም አቀፍ የባሕርና የውቅያኖስ ሕግ በባሕር ላይ ሕይወታቸው አደጋ ላይ ያለ ሰዎችን ከአደጋ መታደግ ለአገሮች ግዴታ ነው። ባለፈው የፈንጆች ዓመት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የገቡ የውጭ ዜጎች (ለሥራና ለትምህርት) 677ሺህ ናቸው። 49 ሺህ ሰዎች ደግሞ የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከቻ አስገብተዋል። ከዚህ ቁጥር ውስጥ በእንግሊዝ የባሕር ሰርጥ (English Channel) በጀልባ ተሳፍረው የመጡት አንድ እጅ ቢሆኑ ነው። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄ ከዩናይትድ ኪንግደም ይልቅ በሌሎች የአውሮፓ አገራት ይበዛል። ለምሳሌ ያለፈውን ዓመት አሐዝ ብቻ ብንመለከት 165ሺህ 600 ሰዎች በጀርመን የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበዋል። በፈረንሳይ ደግሞ 129ሺህ የተለያዩ አገራት ዜጎች አስጠጉን ብለዋል። በስፔን ደግሞ 118ሺህ ሰዎች ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል። ከዚህ አንጻር ዩናይትድ ኪንግደም ጥብቅ ድንበር፣ ጥብቅ የጥገኝነት ፖሊሲ እንዳላት መገመት ይቻላል። አንድ ሰው የእንግሊዝን ምድር ሳይረግጥ የጥገኝነት ጥያቄ ለማሳካት በጣም ፈታኝ ይሆንበታል። ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ወደ አገሪቱ ለመግባት ይሞከራል። ቀደም ሲል ስደተኞች በከባድ መኪናና በጭነቶች ውስጥ ተደብቀው ነበር ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የሚገቡት። ባለፈው ዓመት 39 ቬትናማዊያን እንደ ማቀዝቀዣ በሚያገለግል ከባድ ተሸከርካሪ ውስጥ ታጉረው ወደ አገሪቱ ሲገቡ እዚያው መኪናው ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ደንጋጤን ፈጠረ። ክስተቱን ተከትሎ ጥብቅ ቁጥጥር ተጀመረ። በከባድ መኪና ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መግባት እጅግ አደገኛ እየሆነ ሲመጣ ትንንሽ ጀልባዎች አማራጭ ሆኑ። ካለፈው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ በጀልባ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ከገቡት ውስጥ ወደመጡበት የአውሮፓ አገር የተመለሱት 155 ሰዎች ብቻ ናቸው። በቀጣይ 600 የሚሆኑትን በተመሳሳይ ወደመጡበት ለመመለስ ሐሳብ አለ። ዩናይትድ ኪንግደምን የሚናፍቁት የየትኞቹ አገራት ዜጎች ናቸው? ባለፈው ቅዳሜና እሑድ ብቻ 200 ሰዎች በጀልባ ገብተዋል፤ ኬንት፣ ዩናይትድ ኪንግደም። ስደተኞቹ በብዛት የምን አገር ዜጎች ናቸው? ብለን ከጠየቅን የሚከተለውን መልስ እናገኛለን። የመን፤ ሰነዓ ውስጥ በዝናብ ፈረሰ ህንጻ ፍርስራሽን የሚያጸዱ ሠራተኞች 1ኛ፡የመን ከዓለም እጅግ ካጡ ከነጡ ድሀ አገራት ተርታ የምትመደበው የመን በእርስ በርስ ጦርነት ደቅቃለች። ጦርነት በአጥንቷ አስቀርቷታል። በደቡባዊ የአረቢያ ሰላጤ የምትገኘው የመን ላለፉት 10 ዓመታት ሳኡዲ አረቢያና አጋሮቿ ያላዘነቡባት የቦምብ ዓይነት የለም። በዚህ ዘመን በዓለም ላይ እንደ የመን ሕጻናት በጦርነት ያለቀበት ስፍራ የለም። ለተወሰነ ጊዜ ረገብ ብሎ የነበረው ጦርነት ድጋሚ እያገረሸ ይመስላል። ኢራን በአንድ በኩል የሁውቲ ሚሊሻን ደግፋ፣ ሳኡዲና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በሌላ በኩል የሱኒ መንግሥትን ደግፈው በየመን ላይ ጡንቻቸውን እየፈተኑ ይገኛሉ። ይህ ጦርነት ዜጎቿ አገር ጥለው እንዲጠፉ አድርጓል። የሚላስ የሚቀመስ ቀርቶ ቦምብ የማይረብሸው ንጹህ እንቅልፍ ካላገኙ እንዴት በዚያች አገር ሊጸኑ ይችላሉ? ኤርትራና ኢትዮጵያ ለ20 ዓመታት በድንበር ፍጥጫ ውስጥ ቆይተዋል 2ኛ፡ኤርትራ ቀይ ባሕርን ተደግፋ ከሳኡዲ አረቢያ ማዶ፣ ከኢትዮጵያ በስተሰሜን የምትገኘው ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኤርትራ በአፍሪካ እጅግ ድሀ ከሚባሉ አገራት ተርታ ትሰለፋለች። ከአንድ ሚሊዮን ተኩል በላይ ኤርትራዊያን ከገዛ አገራቸው ኤርትራ ውጭ ነው የሚኖሩት። ይህ አሐዝ የዚያችን ትንሽ አገር ጠቅላላ ሕዝብ አንድ አምስተኛ ያክላል። የኤርትራ ዜጎች አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱበት አንዱ ምክንያት የግዴታ የውትድርና አገልግሎትን በመሸሽ ነው። ማንኛውም ዕድሜው ከ18 እስከ 50 ዓመት ያለ ዜጋ በማንኛውም ጊዜ ተጠርቶ ለዓመታት በወታደርነት እንዲያገለግል ሊገደድ ይችላል። የኤርትራ ምጣኔ ሃብት ክፉኛ ደቋል። ለዚህም ምክንያቱ ለዓመታት ቆይቶ የነበረው የድንበር ፍጥጫና የአምባገነን አገዛዝ መኖር ናቸው። ከነጻነት ጀምሮ ለሦስት አስርታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቱን በፈርጣማ ክንዳቸው እየመሩ ያሉት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በዚህ ሁሉ ቁምስቅል ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት የጣለባት ማዕቀብ ኤርትራን አፍረክርኳት ቆይቷል። አሁን ለአገሪቱ እንደ ተስፋ የሚነገርላት ነገር ቢኖር ከጎረቤቷ ኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት በመጀመሯ ምጣኔ ሃብቷ ሊነቃቃ ይችላል የሚል ነው። የኤርትራ ዜጎች በብዙ ቁጥር በዩናይትድ ኪንግደም ይኖራሉ። በአሁን የበጋ ወቅትም ወደዚያው የሚያመሩት ከየመኖች ቀጥሎ ኤርትራዊያን ናቸው። ቻድ ነዳጅ ማስተላለፊያ ትቦ 3ኛ፡ ቻድ ቻድ የባሕር በር የላትም። ወደ ሰሜን በሚጠጋው የማዕከላዊ አፍሪካ ክፍል ነው የምትገኘው። በረሃማ አገር ናት። እዚያም እንደ ኤርትራ ሁሉ መንግሥትን መቃወም አይፈቀድም። ቻድ ወርቅና ዩራኒየም አላት። በቅርቡም ከነዳጅ ላኪ አገሮች ተርታ ተመድባለች። ሆኖም ከፈረንሳይ ነጻነቷን ከተቀዳጀች ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት እንደታመሰች አለች። የእርስ በእርስ ጦርነቱ አረብ-ሙስሊሞች ነን በሚሉ ሰሜናዊያንና ክርስቲያን በሆኑ ደቡቦች መካከል ነው። ቻድ የረባ አውራ ጎዳና እንኳን የላትም። መሠረተ ልማቷ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በርካታ ሕጻናት በቻድ በበሽታ ይሞታሉ። ድህነት ጥላውን እንዳጠላ ነው። ረሀብ ቶሎ ቶሎ ይጎበኛታል። የዚህች አገር ሕዝቦች ከየመንና ከኤርትራ ቀጥሎ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በጋውን እየጠበቁ በጀልባ ይጎርፋሉ። ግብጽ ኢኮኖሚዋ በቱሪዝም ላይ የተመሰረተ ነው 4ኛ፡ ግብጽ 85 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ግብጽ በመካከለኛው ምሥራቅ ጉልበተኛ አገር ናት። የሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ግብጽ የስዊዝ ካናል ባለቤትና ከአፍሪካ ወደ እስያ የሚወስደው መስመር ላይ መተላለፊያ ሆና ታገለግላለች። ስዊዝ ካናል በዓለም በጣም ብዙ መርከቦችን በማስተላለፍ የሚታወቅ ወደብ ነው። ፖለቲካዋ ስክነት የለውም። በተለይም የፀደይ አብዮትን ተከትሎ አብዱልፈታህ አልሲሲ ከመጡ ወዲህ የተቃውሞ ድምጾች ታፍነዋል። ባለፉት 10 ዓመታት በግብጽ ፖለቲካ ውስጥ ብዙ ሆኗል። አሁን ደግሞ ወረርሽኙ በቱሪዝም ላይ የተንጠለጠለውን ኢኮኖሚዋን ክፉኛ ተፈታትኖታል። ይህም በመሆኑ ሕዝቦቿ ከአውሮፓ ከተሞች እየተነሱ በዩናይትድ ኪንግደም አዲስ ሕይወት ለመመስረት ይታትራሉ። ጦርነትና ተቃውሞ ባለፉት ዓመታት ሱዳንን ጎድቷታል 5ኛ፡ ሱዳን ሱዳን በአፍሪካ አህጉር ትልቅ የቆዳ ስፋት ካላቸው አገር አንዷ ናት። ለወራት የዘለቀ ተቃውሞ አምባገነኑን አልበሽርን ከሥልጣን አስወግዷል። ሱዳን ለዘመናት ከጦርነት አልወጣችም። አንድ ነጥብ ተኩል ሚሊዮን ሕዝቧን የበላው የደቡብና የሰሜን ሱዳን ጦርነት በዚህ ረገድ ይጠቀሳል። በምዕራብ ሱዳን ዳርፉር ግዛት 2 ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ደግሞ ተገድለዋል። እንደ አውሮፓዊያኑ በ2011 አገሪቱ ለሁለት ተከፈለች፤ ደቡብ ሱዳን አዲስ አገር ሆና ወጣች። መንግሥት ነጻ ሚዲያዎችን እንደልብ አያሰራም። የመናገር ነጻነት የተገደበ ነው። አማካይ የመኖርያ ዕድሜ 63 ነው። የአገሪቱ ዜጎች ስደት ሊያስመርጣቸው የሚችል ብዙ ምክንያት አላቸው። ኢራቃዊያን ባግዳድ ውስጥ 6ኛ፡ ኢራቅ ኢራቅ ታላቅ አገር ነበረች። የአሜሪካኖች ወረራ ከአገርነት ወደ የጦርነት አውድማ ቀየራት። ከሳዳም ወዲህ ኢራቅ ቁምስቅሏን አይታለች። 37 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት ኢራቅ ከቡሽ ወረራ በኋላ አገሪቱ በሐይማኖቶች ተከፋፍላ ሰላም ርቋታል። ሰላም አለመኖሩ ምጣኔ ሀብቷ እንዳያንሰራራ አድርጎታል እንጂ ሀብታም መሆን የምትችል አገር ናት። በዓለም የነዳጅ ክምችት 2ኛ መሆኗ ሳይዘነጋ ዜጎቿ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለመግባት ብዙ ይቆፍራሉ። የእንግሊዝ መንግሥት በቀጣይ ምን አስቧል? አሁን በጀልባ ወደ ግዛቱ የሚያቋርጡ ስደተኞች ቁጥር እያሳሰበው ያለው መንግሥት፤ ፈረንሳይ ጀልባዎቹ ከመነሳታቸው በፊት ቁጥጥር እንድታደርግ፣ ጉዞ ከጀመሩ በኋላም ጉዟቸውን እንድታስተጓጉል እየጠየቀ ነው። በእንግሊዝ ፓርላማ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ልዩ ኮሚቴ ሁለቱ አገራት ትብብራቸው ምን እንደሚመስልና ምን መደረግ አለበት በሚለው ዙሪያ እየመከረ ነው። መንግሥትን የሚተቹ ወገኖች እንደሚሉት ሁለቱ አገራት ስደተኞችን የሚያቀባብሉ ደላሎችን አይቀጡ ቅጣት እንዲቀጡ ማድረግ አለበት ይላሉ። ለስደተኞች መብት ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ድርጅቶች ደግሞ መንግሥት ደንበሮቹን ቢከፍትና የጥገኝነት ጥያቄን በአግባቡ ማየትና መቀበል ቢጀምር በሕገ ወጥ ጀልባ ጉዞ የባሕር ድንበርን በማቋረጥ የድሀ ዜጎች ነፍስ አይቆረጥም ነበር ይላሉ።
49367332
https://www.bbc.com/amharic/49367332
ከ125 በላይ የተጠፋፉ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦችን ያገናኘችው አሜሪካዊት
አሜሪካዊቷ አንድርያ ኬሊ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ልጆች አሏት። የአብራኳ ክፋይ ባይሆኑም እናታቸው ናት።
አንድርያ ከጉዲፈቻ ልጆቿና ከባለቤቷ ጋር ከ19 ዓመት በፊት እሷና ባለቤቷ ወንድ ልጅ በማደጎ ተረከቡ። ልጁን ወደቤታቸው የወሰዱበት ቀን ከአንድርያ ህሊና አይጠፋም። ልክ ልጁን ስትታቀፈው በደስታ ብዛት ትንፋሽ አጠራት። ቀናት ሲገፉ፤ ልጁን አምጣ የወለደችው እናት የት ትሆን? ብላ ታስብ ጀመር። አንድ እናት የዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ልጇ የት እንደደረሰ ሳታውቅ እንዴት ሕይወት ይገፋላታል? የዘወትር ጥያቄዋ ነበር። • ለዓመታት የተጠፋፉት የወላይታ ሶዶዋ እናትና የኖርዝ ኬሮላይናዋ ልጃቸው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2002 ላይ ከባለቤቷ ጋር ሁለተኛ ልጅ በጉዲፈቻ ለመውሰድ ወሰኑ። አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ የህጻናት ማሳደጊያ ውስጥ 'ወላጅ አልባ' ተብላ የተመዘገበች ኢትዮጵያዊት ልጅን ተረክበው ወደ ቤተሰቡ ቀላቀሏት። አንድርያ ስለሁለቱ የጉዲፈቻ ልጆቿ እናቶች ማሰብ ማቆም አልቻለችም። ነገሩ በጣም ሲያስጨንቃት የጉዲፈቻ ልጆቿን ቤተሰቦችን መፈለግ ጀመረች። "ልጆቹ ደህና እንደሆኑ ለወላጆቻቸው ማሳወቅ እንዳለብኝ ወሰንኩና ፍለጋ ጀመርኩ" ትላለች። "የልጆቼን ወላጆች ስፈልግ 'ቤተሰብ ፍለጋ' ተመሰረተ" አንድርያ የጉዲፈቻ ልጆቿን ቤተሰቦች መፈለግ የጀመረችው በምትኖርበት አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን 'ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው የሚገኘው እንዴት ነው?' እያለች በማጠያየቅ ነበር። የአንድርያ የጉዲፈቻ ልጅ፤ ወላጅ እናቷን ኢትዮጵያ ውስጥ ስታገኝ የተነሳ ፎቶግራፍ እድለኛ ሆና አንድ ኢትዮጵያዊ ሊረዳት ፈቀደና ሴት ልጇ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ስትወሰድ የተሰጧትን ሰነዶች አዲስ አበባ ለምትኖር እህቱ ላከ። እህቱም፤ ልጅቷን ለማደጎ የሰጠችው የልጅቷ እናት ጓደኛ እንደሆነች፤ እናትና ልጅን ማገናኘት እንደሚቻልም አሳወቀችው። በወቅቱ ልጅቷ ሁለት ዓመት ሞልቷት ነበር። የአንድርያ የጉዲፈቻ ልጅ ስድስት ዓመት ሲሆናት ወደ ኢትዮጵያ ሄዳ ከወላጅ እናቷ ጋር ተዋወቀች። አንድርያና የልጅቷ እናት በቋንቋ ባይግባቡም አንዳቸው የሌላቸውን ደስታ ከፊታቸው ለማንብ እንዳልተቸገሩ ታስታውሳለች። • "በኤችአይቪ የምሞት መስሎኝ ልጄን ለጉዲፈቻ ሰጠሁ" "ያኔ የጉዲፈቻ ልጄ ህጻን ስለነበረች ነገሩ ብዙም ስሜት አልሰጣትም ነበር። ከፍ እያለች ስትመጣ ግን ከእናቷ ጋር መጠያየቅ፣ መቀራረብም ጀመረች።" ልጇ አሁን 17 ዓመቷ ነው። የ11ኛ ክፍል ተማሪ እና ቫዮሊን ተጫዋች ናት። እናቷን ወደ ኢትዮጵያ እየሄደች ትጠይቃለች፤ አዘውትረውም በስልክ ያወራሉ። ከዚህ በተቃራኒው የአንድርያ የጉዲፈቻ ወንድ ልጅ ቤተሰቦቹን እስካሁን አላገኘም። አንድርያ እና ባለቤቷ ልጁን ማሳደግ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ወላጆቹን ቢያፈላልጉም አልተሳካላቸውም። "ቤተሰቦቹን ፍለጋ ደጋግመን ወደ ኢትዮጵያ ሄደናል፤ አፈላላጊ ቀጥረናል፤ በቴሌቭዥን፣ በራድዮ፣ በጋዜጣ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥተናል. . . ያልሞከርነው ነገር የለም. . . የወላጅ አልባ ህጻናት ድርጅት፣ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ፣ ፖሊስ ጣቢያ፣ ፍርድ ቤት. . . ያልረገጥነው ቦታ የለም. . . ወደ 19 ሺህ ዶላር አውጥተናል።" እስካሁን ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቹን ማግኘት ያልቻለው የአንድርያ የጉዲፈቻ ልጅ ህጻን ሳለ የተነሳው ፎቶግራፍ ላለፉት 19 ዓመታት የጉዲፈቻ ልጃቸውን ቤተሰቦች ለማግኘት ያደረጉት ጥረት ውጤት ባያስገኝም፤ አሁንም ተስፋ አልቆረጡም። አንድርያ የጉዲፈቻ ልጆቿን ቤተሰቦች ስታፈላልግ፤ በኢትዮጵያውያን ወላጆች እና በጉዲፈቻ በሰጧቸው ልጆች መካከል ሰፊ ክፍተት መኖሩን አስተውላለች። • ከ43 ዓመት በኋላ የተገናኙት ኢትዮጵያዊ እናትና ስዊድናዊ ልጅ ለሀያ፣ ለሠላሳ ዓመታት እና ከዚያም በላይ ቤተሰብን መፈለግ፤ የአንድርያ የጉዲፈቻ ልጅ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሺዎች ታሪክ ነው። ልጄ የት ናት? ልጄን መቼ አየው ይሆን?. . . የበርካታ ወላጆችን ልብ የሚሰቅል ጥያቄ ነው። "ወላጆች ስለልጆቻቸው፤ ልጆችም ስለወላጆቻቸው ማወቅ ይገባቸዋል። ከራሴ ተሞክሮ ተነስቼ 'ቤተሰብ ፍለጋ' የተባለ ወላጆችና ልጆችን የሚያገናኝ ድርጅት ያቋቋምኩትም ለዚህ ነው።" ቤተሰብ ፍለጋ ወይም Ethiopian Adoption Connection በተለያየ ምክንያት በጉዲፈቻ የተሰጡ ልጆችና ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቻቸውን ማገናኘት ከጀመረ አምስተኛ ዓመቱን አስቆጥሯል፤ ከ125 በላይ የተጠፋፉ ቤተሰቦችንም አገናኝቷል። ፍለጋ. . . ልጇን የምትፈልግ እናት፣ እህቱን የሚፈልግ ወንድም. . . ብዙዎች ፍለጋውን ከየት እንደሚጀምሩ ግራ ይገባቸዋል። ልጆችን ለጉዲፈቻ የሚሰጡ ድርጅቶች፤ ልጆቹ ከኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ ስለልጆቹ መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ ላይሆኑ ይችላሉ። ልጆቹን የሚቀበላቸው ድርጅት ወይም አሳዳጊ ቤተሰብ መረጃ መስጠት የሚያቋርጡበት አጋጣሚም አለ። አንዳንድ ቤተሰቦች፤ ልጆቻቸው በምን መንገድ ከኢትዮጵያ እንደወጡ፣ የት አገር እንደሚኖሩ እና እንዴት ሊያገኟቸው እንደሚችሉም አያውቁም። 'ቤተሰብ ፍለጋ' ይህንን ክፍተት ለመሙላት ጥረት እያደረገ ይገኛል። ልጅ፣ እህት፣ ወንድም ወይም የቅርብ ዘመድ የመፈለግ ሂደቱ እንዲህ ነው. . . በመጀመሪያ ቤተሰቦች ስለልጁ/ልጅቷ ያላቸውን መረጃ ባጠቃላይ ለ'ቤተሰብ ፍለጋ' ይሰጣሉ። ልጆቹ ሲወለዱ የወጣላቸው ስም፣ ለጉዲፈቻ የተሰጡበት ዓመተ ምሕረት፣ የልጅነት ፎቶ፣ በጉዲፈቻ የተወሰዱበት አገር፣ ለጉዲፈቻ የሰጣቸው ድርጅት መጠሪያ ወዘተ. . . ከዚያም በጉዲፈቻ ስለተወሰደው ወይም ስለተወሰደችው ልጅ የተሰበሰበው መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ ይሰራጫል። በዋነኛነት በ'ቤተሰብ ፍለጋ' የፌስቡክና የትዊተር ገጽ ላይ ልጆቹ ይፈለጋሉ። አሜሪካ እና አውሮፓ የሚሠሩ ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች በማፈላለግ ሂደቱ ድጋፍ ያደርጋሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ቤተሰብ መረጃ የሚያቀብሉ ኢትዮጵያዊ ማኅበራዊ ሠራተኞችም አሉ። • ለ20 ዓመታት ዴንማርካዊት እህቱን የፈለገው ኢትዮጵያዊ ሀኪም የልጆቹን የጉዲፈቻ ቤተሰቦች አልያም ልጆቹን ለማግኘት ከሳምንታት እስከ ዓመታትም ሊወስድ ይችላል። ሁሉንም ሰው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማግኘት አይቻልምና የሚፈለጉት ልጆች ወይም የጉዲፈቻ ቤተሰቦቻቸው አንድ ቀን መረጃውን እስኪያዩት መጠበቅ ግድ ይላል። 'ቤተሰብ ፍለጋ' ባዘጋጀው የመረጃ ቋት (ዳታቤዝ) ላይ የልጆቹ መረጃ ተመዝግቦ ስለሚቀመጥ በየትኛውም ጊዜ 'ጉግል' ሲያደርጉ ያገኙታል። አንድርያ እንደምትናገረው፤ እስካሁን በ 'ዳታቤዝ' ውስጥ 700 የሚደርሱ 'ኬዞች' (የተጠፋፉ ቤተሰቦች) ተመዝግበዋል። ከ43 ዓመት ፍለጋ በኋላ ልጇን ያገኘችው ሀሊማ ሀሰን ከልጇ ሁሴን ፈይሰል እና አንድርያ ኬሊ ጋር "ዳታቤዝ ውስጥ ያለው መረጃ ልጆቹ እስከሚገኙ ድረስ አይጠፋም። አንዳንድ ቤተሰቦች ልጆቹ የት አገር እንደተወሰዱ ስለማያውቁ ፍለጋው ዓመታት ሊወስድ ይችላል። ብዙ አገሮች ውስጥ የሚያግዙን በጎ ፍቃደኞች አሉ።" "ፍለጋው ስሜታዊ ነው፤ እንቅልፍ ይነሳኛል" ከማን ማህጸን ተፈጠርኩ? ማንን ነው የምመስለው? ወላጆቼ ለምን ለጉዲፈቻ ሰጡኝ?. . . ልጄ በሕይወት አለችን? ልጄን በዓይነ ሥጋ ሳላየው ብሞትስ?. . . የልጆችም የወላጆችም ሕይወት በእነዚህ ጥያቄዎች መዋጡ አይቀርም። ልጆች ቤተሰቦቻቸውን፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ለዓመታት ይፈልጋሉ. . . ፈላጊዎች ከተፈላጊዎች ወገን ስለሚኖረው ምላሽ ባያውቁም ከመፈለግ አይቦዝኑም። የፍለጋ ሂደቱን የምታስተባብረው አንድርያ እናቶች፣ አባቶች፤ 'ፈጣሪ ይመስገን! ልጄ በሕይወት አለ!' ሲሉ እንደመስማት የሚያስደስታት ነገር የለም። ደስታዋን የሚያደበዝዙ ታሪኮችም ብዙ ናቸው። "የምደሰትበት ጊዜ እንዳለ ሁሉ የማዝንበት ወቅትም አለ። ሥራዬ ቀላል አይደለም። የአንዳንድ ቤተሰቦች ጉዳይ እንቅልፍ ይነሳኛል።" አንዳንድ የጉዲፈቻ ቤተሰቦች የልጆቻቸው ወላጆች እየፈለጓቸው እንደሆነ ሲያውቁ ይበሳጫሉ። ልጆቹን ከወላጆቻቸው ጋር ለማገናኘትም አይፈቅዱም። በሌላ በኩል፤ ልጅ ፍለጋው ገንዘብ ማሳደድ እንደሆነ የሚሰማቸው ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር መገናኘት አይሹም። "ከሁሉም በጣም የሚከብደው ልጆች ወላጆቻቸውን 'አንፈልግም' ሲሉ ነው። 'ልጅሽን አፈላልገን አግኝተነዋል፤ ነገር ግን ሊያገኝሽ አይፈልግም' የሚል ዜና ለወላጅ መንገር አስጨናቂ ነው" ትላለች። የየቤተሰቡ የፍለጋ ታሪክ ይለያያል. . . ውጤቱም እንደዚያው። • ዓለም አቀፍ ጉዲፈቻን ማገድ አዋጭ ነው? አንዲት ሴት 'የጉዲፈቻ ልጅሽ ወላጅ እናት እየፈለገችው ነው' የሚል መልዕክት ሲደርሳት፤ 'የልጄን ቤተሰቦች ማግኘት ብፈልግ እኔው እፈልጋቸው ነበር፤ እናንተ ምን ጥልቅ አደረጋችሁ!' ብላ መቆጣቷን አንድርያ ታስታውሳለች። የኋላ ኋላ ልጁ ስለ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦቹ መጠየቅ ጀመረ። የጉዲፈቻ እናቱ ነገሩ ባይዋጥላትም 'ልጄ ስለወላጆቹ እየጠቀኝ ነውና የእናቱን አድራሻ ስጪኝ' ብላ ለአንድርያ ኢሜል ላከች። ሁለት ልጆቻቸው በጉዲፈቻ ወደ አውሮፓ ተወስደው ለዓመታት በፍለጋ የባዘኑ የአንድ አዛውንት ታሪክም አይረሳትም። አኚህን አባትም ከልጆቻቸው ጋር ማገናኘት መቻሏ ያኮራታል። ከዓመታት በኋላ ወላጅ እናቷን ያገኘችው አማረችና አንድርያ "ልቤን ከሰበሩት ታሪኮች አንዱ የእነዚህ ጥንዶች ነው. . . ጥንዶቹ ልጅ የወለዱት ወጣት ሳሉ ነበር። ለቤተሰቦቻቸው መናገር ፈሩ፤ እንዳያሳድጓት ደግሞ ገንዘብ አልነበራቸውም። ሕይወታቸውን ፈር አስይዘው ማሳደግ እስኪችሉ ድረስ ልጃቸውን ለህጻናት ማሳደጊያ ሰጧት። "ከጥቂት ጊዜ በኋላ ልጃቸውን ለመውሰድ ወደ ህጻናት ማሳደጊያው ሲመለሱ ልጃቸውን አጧት። የማሳደጊያው ሠራተኞች የጥንዶቹን ፍቃድ ሳይጠይቁ በጉዲፈቻ ሰጥተዋት ነበር. . . ". . . ጥንዶቹ ልጃቸውን እንድንፈልግላቸው ከነገሩን ቀን ጀምሮ እናትየዋ በየቀኑ ቢያንስ ሦስቴ ትደውልልኝ ነበር። ከብዙ ልፋት በኋላ የልጅቷን የጉዲፈቻ ቤተሰቦች አገኘናቸው። ነገር ግን ከወላጆቿ ጋር ሊያገናኟት ፍቃደኛ አልሆኑም። በጣም ተናደድኩ፤ ለሳምንታት ተጨነቅኩ፤ ታመምኩ። እናትየዋ 'የልጄ አሳዳጊዎች ልጄን የሚወዷት ከሆነ ለምን እኔን መቀበል ከበዳቸው? እኔ'ኮ የልጄ አካል ነኝ!' ስትለኝ የምመልስላት ነገር አጣሁ. . ." አንድርያ ይህን መሰል ታሪኮች የሚፈጥሩባትን ሀዘን፤ ለዓመታት ሲፈላለጉ የነበሩ ቤተሰቦች ተገናኝተው፣ ጥሩ ግንኙነት መስርተው ስታይ በሚሰማት ደስታ እየሻረች ሕይወትን ተያይዛዋለች. . .
news-57238327
https://www.bbc.com/amharic/news-57238327
የአሜሪካ ማዕቀብ በቀጣናው ስትራቴጂያዊ ለውጥን ያስከትል ይሆን?
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ግንቦት 15/2013 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ካለው ግጭት ጋር እየተፈፀሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ጥቃቶች አገራቸው በተደጋጋሚ ስጋቷን ብታሰማም ትርጉም ያለው ምላሽ ባለመኖሩ አገራቸው የጉዞ እቀባ መጣሏን አስታውቀዋል።
በዚህም በኢትዮጵያና በኤርትራ የቀድሞ እና የአሁን ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ እና ደኅንነት ኃላፊዎች እንዲሁም የአማራ ክልል መደበኛና ኢ-መደበኛ የጸጥታ አባላትና ግለሰቦች፣ ሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ባደናቀፉ የህወሓት አባላት ላይ የቪዛ እቀባ አሜሪካ ጥላለች። ይህ በግጭቱ ላይ እጃቸው ያለበት ወይም ተባባሪ የሆኑትን የሚመለከት ሲሆን እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦቻቸውም ጭምር እቀባው ተግባራዊ ሊሆንባቸው እንደሚችል የወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ከጉዞ እቀባው በተጨማሪ አሜሪካ የምታደርገውን የምጣኔ ሀብትና የደኅንነት እገዛ እንዲቋረጡና ግጭቱ ካልቆመና መሻሻሎች ካልታዩ፤ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደምትወስድም አስጠንቅቃለች። ሌሎችም አገራት የአሜሪካን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪ አድርጋለች። ይህ የማዕቀብ ሁኔታ አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገው ያልተገባ ጫና አካል ነው በሚልም ኢትዮጵያን አሳዝኗል። ምንም እንኳን አሜሪካ ለግጭቱ መፍትሄ ለማምጣት ትርጉም ያለው እርምጃ ሊወሰድ አልተቻለም ብትልም ኢትዮጵያ በበኩሏ ከአሜሪካ አስተዳደር ጋር ገንቢ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ እየሰራች ነበር ብላለች። ኢትዮጵያ በትግራይ የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በጥምረት ሆነው ለመመርመር እየሰሩ መሆናቸውንና ተጠያቂ የሚሆኑበትንም ስራ እያከናወነች እንደሆነ አስታውቃለች። እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ በአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ በመጥቀስ ቀውሱን ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች። አሜሪካ ያሳለፈቻቸው እርምጃዎች የሁለቱንም አገራት የዘመናት ግንኙነት የሚጎዳ ነው ትላለች ኢትዮጵያ። የአሜሪካንን እርምጃዎች በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነት ነው የምትለው ኢትዮጵያ፤ አሜሪካ በዚሁ የምትቀጥል ከሆነ ግንኙነታቸውን የምታጤነው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የማዕቀቡ አንድምታ፤ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ይሆን? ኢትዮጵያና አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ውስጥ እየተደረጉ ስላሉ እርምጃዎች ተመሳሳይ አረዳድ የላቸውም። በቀጣናው ከአልሻባብ መግነን ጋር ተያይዞ ሸብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል የአሜሪካ ቀኝ እጅ የነበረችው ኢትዮጵያና አሜሪካ በትግራይ ባለው ቀውስ ምክንያት ግንኙነታቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ለአስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአሜሪካ የደኅንነት አጋር ነበረች የሚሉት የአሜሪካ የቀድሞ ዲፕሎማትና በአትላንቲክ ካውንስል የደኅንነት ኃላፊ የሆኑት ካሜሮን ሀድሰን ናቸው። ለረጅም ጊዜያት ፖለቲካዊ ድርድሮችንና ሽምግልናዎችን በዋነኝነት በመምራት፣ በሰላም በማስከበር ስምሪት እንዲሁም በአጠቃላይ መረጋጋት በሌለባቸው የቀጣናው አካባቢዎች መረጋጋትን በማምጣት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና መጫወቷን ካሜሮን ይናገራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ራሷ መረጋጋት የሌለባት አገር ናት የሚሉት ዲፕሎማቱ፤ አሜሪካም ይሄንን ለመቆጣጠር የራሷን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባት ይላሉ። በተለይም ከማዕቀቡ ጋር ተያይዞ በሁለትዮሽ ግንኙነቱ ላይ አዲስ የሆነ ግንኙነትን የሚያሳይ ነው፤ እንዲሁም አሜሪካ ስትራቴጂያዊ ለውጥን ማድረጓን ጠቋሚ ነው ይላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም ዳይሬክተርና መምህር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው በዲፕሎማቱ ሃሳብ አይስማሙም፤ የአሁኑን ማዕቀብ በአገራቱ መካከል መሰረታዊ የሚባል የርዕዮተ ዓለም ልዩነት የሌለበት ስለሆነ "ጊዜያዊ ነው" በማለት። ኢትዮጵያ ካላት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ አንጻር ስትራቴጂክ ቦታ ላይ ከመሆኗም ጋር ተያይዞ አሁንም በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በቀጣናው ካሉ አገራት ከኢትዮጵያ የተሻለ ወዳጅ ለአሜሪካ ማግኘት ያስቸግራል ብለው እንደሚያምኑ ምሁሩ ይናገራሉ። ለዚህም እንደ ዋቢ የሚጠቅሱት የሶማሊያ በአልሻበብ ቁጥጥር ስር መውደቅ፣ የሶማሌላንድና የፑንትላንድ ዕውቅና አለማግኘት፣ በኬንያና በሶማሊያ መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት፣ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ትርምስ ውስጥ መሆኑ ኢትዮጵያ አሁንም ለቀጣናው የተሻለች የአሜሪካ አጋር ናት እንዲሉ አስችሏቸዋል። በተለይም አሜሪካ የምጣኔ ሀብትና የደኅንነት ድጋፍ እቀባ ማድረጓን ተከትሎ አገራቱ ሽብርተኝነትን በጋራ እንዋጋለን የሚሉትን ፕሮጀክት እንዲቆም አያደርገውም ወይ? ብለው በርካቶች ጥያቄ ያነሳሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ በኩልም በሰጠው መግለጫ እርምጃው ቀጣናውን ችግር ላይ የሚጥል እንዲሁም ኢትዮጵያ በፀረ-አልሻባብ የሽብር መከላከል እና በሰላም ጥበቃ ላይ ያላትን ሚና በጉልህ የሚጎዳ ሲሉ ተችተውታል። ዶክተር ዮናስም በተመሳሳይ መልኩ "ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ለአሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ቀኝ እጅ ነበረች አሁንም ናት" ብለው ያምናሉ። የዲፕሎማቱ ካሜሮን ሀድሰን እይታ ግን ከውጭ ጉዳይ መግለጫም ሆነ ከምሁሩ አስተያየት ለየት ይላል። አገሪቱ በአሁኑ ወቅት በውስጧ ካለው ቀውስ የተነሳ ለዓመታት የሚጠበቅባትን በቀጣናው የተጫወተችውን ሚና በአሁኑ ወቅት መጫወት አትችልም ይላሉ። "ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በሕዝቡ ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማካሄድ አዳዲስ የደኅንነት አጋሮችን እንደነ ሩሲያ፣ ቻይናና የባሕረ ሰላጤው አገራትን አገራትን አጋርነትን እየተመለከተች ነው። ሁኔታዎች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ እነዚህን የመሳሰሉ የደኅንነት ግንኙነቶች በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የምዕራባውያን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ያስከትላል" ይላሉ። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ከፀረ-ሽብር ጋር በተገናኘ ለኢትዮጵያ ስልጠናዎችን፣ እንዲሁም የደኅንነት መረጃዎችን በመለዋወጥ ይሰሩ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የቀድሞው የሲአይኤ አባል የነበሩት ዲፕሎማት ሀድሰን እንደሚሉት አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር መሳሪያም አቀባይ ነበረች። በቅርቡ ያወጣችው የጉዞ እቀባና 'ዲፌንስ ትሬድ ኮንትሮል ፖሊሲ' ያለችውን ተግባራዊ እንደምታደርግም አሜሪካ አስታውቃለች። ይህ ፖሊሲ ምንን ያካትታል? ለዲፕሎማቱ ቢቢሲ ያቀረበላቸው ጥያቄ ነው። እሳቸውም በምላሹ የትኛውም እርምጃ በሕዝብ ላይ ጥፋት የሚፈፀምበት የቴክኖሎጂ ግብአት ላይ ከሚደረግ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይናገራሉ። ሰፋ ያለ ይዘት ያለው ይህ ፖሊሲ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን ጨምሮ፣ ሶፍትዌሮች፣ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቁሳቁሶችና ረቀቅ ያሉ ወታደራዊ ቴክኖሎጂን ያካትታል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተለገሱ በአሜሪካ የተሰሩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን መጠገን አስፈልጎ መለዋወጫ ቢያስፈልግ በዚህ እቀባ መሰረት ኢትዮጵያ ይሄንን ማካሄድ አትችልም ይላሉ። የሁለቱ አገራት ግንኙነት መበላሸት ኢትዮጵያና አሜሪካ ከመቶ ዓመታት በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በሊግ ኦፍ ኔሽንም ሆነ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምስረታ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የሚሉት ዶክተር ዮናስ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማት ከአሜሪካ ጋር ትስስር አላቸው ይላሉ። የሁለትዮሽ አጋርነታቸውም ነፀብራቅ የሚባሉት በትምህርት ተቋማት እንዲሁም የአሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበራትን ሚና እንደ ምሳሌ በማንሳት አሜሪካ ለዘመናት የኢትዮጵያ የልማት አጋር ሆና ቀጥላለች ይላሉ። ለዚያም ነው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማዕቀቡን የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥንና የመቶ ሃያ ዓመታቱንም ግንኙነት "በዜሮ ያባዛው" ያለው። በአገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ዳራ በምንመለከትበት ወቅት ሻክሮ የነበረው ደርግ ኢትዮጵያን ያስተዳድር በነበረ ወቅት ነበር። ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን ግንኙነታቸው ጠንካራ የሚባል እንደሆነ ይነገራል። ዲፕሎማቱም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እንዲህ አይነት እርምጃ ወስዳ አታውቅም ይላሉ። በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የተወሰነ ውጥረት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ በአሜሪካ የቀረበው የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በሁለቱ አገራት መጣሉን ተከትሎ እንደሆነ ያወሳሉ። አሜሪካ በማንኛውም በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን አጋርነት አልተወችም የሚሉት ዶክተር ዮናስ ይህ እቀባ "ማስደንገጥ የለበትም" ይላሉ። ለምሳሌ ያህልም ኢህአዴግ በ2002 ምርጫ መቶ በመቶ አሸንፌያለሁ ብሎ የፓርላማ ወንበሩን ከተቆጣጠረ በኋላ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነው ብለው ማፅደቃቸውን በማውሳት ነው። "ይህ ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነ ነበር" ይላሉ። በአፍሪካ ውስጥ "ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፖለቲካ መዲና ናት" የሚሉት ዶክተር ዮናስ "ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት እቀባም አሜሪካንም ሆነ ኢትዮጵያን ይጎዳል" ይላሉ። በተለይም ኢትዮጵያ የራሷን አፀፋዊ እርምጃዎች የምትወስድ ከሆነ ሁኔታዎች ሊጋጋሉና ቀጣናው የአሸባሪዎች መፈንጫ ሊሆን እንደሚችል ምሁራዊ እይታቸውን ይሰጣሉ። በተለይም በቀጣናው የደኅንነት ስጋት ቢፈጠር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድም ሆነ ወደ ሌሎች አካካቢዎች አንደሚዛመትና ጉዳቱም ሰፋ ያለ መልክ ሊኖረው እንደሚችል በአፅንኦት ያስረዳሉ። "በነገራችን ላይ የደኅንነትና የሰላም ጥናት ድንበር አይከፋፍልም። አንድ አካባቢ ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከተጎዳ መላው ዓለም ነው የሚጎዳው። ለምሳሌ ከዓመታት በፊት በአሜሪካ ላይ ተፈጸመው የመስከረም 11ዱን ጥቃት ብንወስድ፤ ባደጉም ይሁን ባላደጉ አገራት ውስጥ ከፍተኛ ትርምስ ነው የፈጠረው" የሚሉት ዶክተር ዮናስ የአንድ አገር ደኅንነት ወይም ሰላም የሚባል የለም በማለት የአገራቱ እጣ ፈንታ በከፍተኛ ሁኔታ የተሳሰረ እንደሆነ ይተነትናሉ። ዲፕሎማቱም በበኩላቸው ማዕቀቡ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር በነበራትን ግንኙነት ላይ ስትራቴጂያዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ጠቁመው፤ ይህም ሁኔታ አሜሪካ በቀጣናው ላይ ያላትን ስትራቴጂያዊ ፍላጎቶችም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚያደርስ አልደበቁም። በተለይም ኢትዮጵያ በውስጧ ሰላም ካልሰፈነባትና አጋርነቷ ከቀረ አሜሪካ በቀይ ባሕር ዙሪያ ደኅንነትንም ሆነ መረጋጋት ለማምጣትም እንዲሁም ተፅእኖ ለመፍጠር ፈተና እንደሚሆንባት ያስረዳሉ። የአሜሪካ ስጋት ምንድን ነው? በትግራይ ካለው ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ጥቃትና አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ችግር በተጨማሪ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ክልል እንዲሁም በአገሪቱ ላይ የተጋረጡት የሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ አንድነትና የግዛት ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብኛል ይላል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎች እርዳታ እንዳይደርስ እክል መፍጠር፣ በክልሉ ውስጥ ያሉ ግድያዎች፣ በአስገዳጅ ሁኔታ መፈናቀል፣ መዋቅራዊ የሆነ ወሲባዊ ጥቃት፣ ሆስፒታሎችና የህክምና ተቋማት መውደም አሜሪካ እንዳሳሰባት ትገልጻለች። እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ቀጥለዋል የምትለው አሜሪካ ተደጋጋሚ ጉትጎታዎችን ባደርግም ለቀውሱ ፖለቲካዊም ሆነ ሰላማዊ መፍትሄ መምጣት አልተቻለም ትላለች። በዚህም ምክንያት የወሰደችው እርምጃ አስፈላጊ ነው ትላለች። ዶክተር ዮናስ በበኩላቸው ሁለቱንም አገራት ይጎዳል ያሉት ይህን ማዕቀብ በተሳሳተና በደንብ ባልተጠና መረጃ ላይ ተመስርቶ የተወሰደ ነው ይላሉ። ምሁሩ በአውሮፓውያኑ 2003 አሜሪካ ኢራቅን መውረሯን እንደ ምሳሌ በማንሳትም በወቅቱ አሜሪካ ምክንያት ያደረገችው ኢራቅ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አላት የበሚል ነበር። ነገር ግን መሳሪያው አለመኖሩ የታወቀው ኢራቅ ከፈራረሰችና ከዘገዬ በኋላ መሆኑን ታሪክን ያጣቅሳሉ። በተመሳሳይም አፍጋኒስታንን በማንሳት ከቀደመ ስህተት መማርና ማገናዘብ እንደሚገባ ያወሳሉ። "በስሜት የሚደረጉ ነገሮች የሚያሳዝኑ ይሆናሉ። በዚህ ትብብር ወቅት ኢትዮጵያን በግድ አንበረክካታለሁ ብሎ ማሰቡ በተለይም በጣም ካደጉ አገራት የሚጠበቅም አልነበረም። በተለይም የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ከመሆኑ አንፃር። ይሄንን በድጋሚ ያጤኑታል ብዬ አስባለሁ" ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግሥትም በተለይም አሜሪካ ከምታወጣቸው መግለጫዎች ጋር በተያያዘ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተው ጫና ለመሞከር የሚሞክሩ መንግሥታት ተቀባይነት አይኖረውም ሲል መደመጡ ይታወሳል፟። ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ ክልል ቀውስና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ምዕራባውያን እንዲሁም አሜሪካ ከፍተኛ ጫና እያሳደረች ነው ያሉ ተቃውሟቸውን በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች አገራት በበይነ መረብ አሰምተዋል። የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የሕግ እና የውሃ ጉዳይ የቴክኒክ ባለሞያዎች በዋሽንግተን ዲሲ ሲደራደሩ በነበረበት ወቅት፤ በዓመታት የተራዘመ ድርቅ እንዲሁም በተራዘመ ዓመታት አነስተኛ የውሃ ፍሰት ላይም መሰረታዊ መግባባት ተደርሷል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ያለምንም ውጤት መቋረጡ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረውንም ድርድር ያቋረጠችበት ምክንያት በግብጽ ፍላጎት ታዛቢ እንዲሆኑ የገቡት አሜሪካና የዓለም ባንክ ለግብጽ ከመወገን አልፈው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ላይ ጫና ለማሳደር ሞክረዋል በማለት ኢትዮጵያ መውቀሷ የሚታወስ ነው። አሜሪካ፣ የዓለም ባንክ ከግብጽ ጎን ቆመው ነበር በተባለው በዚህ ድርድር ላይ ከመጀመሪያው ሙሌት በኋላ ኢትዮጵያ ለምትጠቀመው ውሃ ለግብጽ የተጠራቀመ የውሃ ጉድለት ማካካሻ እንድትሰጥ የሚያስገድድ እንደሆነም ተገልጾ ነበር። ከዚህም ጋር በተያያዘ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሕዳሴ ግድቡ ድርድር ምክንያት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደማይሰጥ ገልፀው ነበር። ከዚህም ጋር ተያይዞ የአሜሪካ የአሁኑ ማዕቀብ የትግራይ ግጭት ብቻ አይደለም የሕዳሴ ግድብም ነው የሚሉ አልታጡም። ነገር ግን የአትላንቲክ ካውንስሉ ካሜሩን ሀድሰን በበኩላቸው "የአሜሪካ ዋነኛ ስጋት በትግራይ ያለው ጦርነት እንዲሁም በአገሪቱ ያለው አለመረጋጋት አገሪቷን አንዳይበታትናት የሚል ፍራቻ ነው" ይላሉ። ምንም እንኳን የተጣለው ማዕቀብ አገሪቱን የበለጠ እንዳያዳክማት አሜሪካ ብትሰጋም "በትግራይ ውስት እየተፈፀመ ካለው የመብት ጥሰት ክብደት አንፃር ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆና አግኝታዋለች" ይላሉ። እቀባው ጣልቃ ገብነት ወይስ? ዲፕሎማቱ ጠንከር ያለ እርምጃ ቢሉም ለዶክተር ዮናስ በአገራት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባትና በጉልበት ለመፍታት መሞከር "ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ አካሄድ ነው" ይላሉ። "ሁላችንም እንደ መረብ የተያያዝን ዓለም ላይ ስለምንኖር አንዱ ሌላውን ገፍትሮ፣ አንዱ የሌላው የበላይ፣ አዛዥና ናዛዥ ሆኖ፤ ሌላኛው ታዛዥ ሎሌ ወይም ባርያ ሆኖ ለመኖር ጊዜው አልፏል" የሚሉት ዶክተር ዮናስ "21ኛው ክፍለ ዘመን አገራት ችግሮቻቸውን በአንድነት ተባብረው የሚፈቱበት ዘመን እንጂ አንዱ ሌላኛውን አስፈራርቶ ችግር ሊፈታ አይችልም" ይላሉ። ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዘመናት የቆየው ግንኙነት እንዳይበላሽና ዘላቂው ጥቅም እንዲጠበቅ ውሳኔው መጤን አለበት በማለትም ምክር ይለግሳሉ። "አሜሪካ ለራሷም ጥቅም ለራሷም ክብር ሲባል የወሰደችውን አቋም እንደገና ማጤንና መገምገም አለባት" በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ለመሆኑ አሜሪካ ኢትዮጵያ እቀባውን የጣለችውም ሆነ ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ አገሪቷ ምን እንድታደርግ የሚጠይቅ ነው? ጥሰቶችን በገለልተኛ አካላት ተጣርተው ጥፋተኞቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዲጠበቁ፣ የሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም እክል እንዲደርሱ እንዲሁም የኤርትራ መንግሥትም ሠራዊቱን በአስቸኳይ ከክልሉ እንዲያስወጣና ዓለም አቀፍ እውቅና ወዳለው የኤርትራ ግዛት እንዲመለሱ የሚጠይቅ ነው። ግጭቱ እስካልቆመና ሰብዓዊ እርዳታዎችን ማቅረብ ካልተቻለ ያለው የምግብ ደኅንነት ስጋት ወደ ረሃብ ይቀየራል ይላል። የትግራይን ቀውስ ማስቆም የማይችሉ ከሆነ ከአሜሪካም ሆነ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሌሎች እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል የሚለው የአሜሪካ ሐሳብ በኢትዮጵያ ላለው ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲመጣ አገራቸው እንደምትሰራ ዘርዝሯል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በክልሉ ተፈፀሙ የተባሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመመርመር ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራች እንደሆነና በተመሳሳይም የሰብዓዊ እርዳታም ባልተገደበ ሁኔታ እርዳታ እንዲቀርብ እየሰራሁ ነው ብላለች። ነገር ግን ያላት አቅም ውስን መሆኑንም አስታውቃለች። ኢትዮጵያ ባወጣችው በዚሁ መግለጫ ላይ አሜሪካ በዋነኝነት ስለምትጠቅሰው የኤርትራ ሠራዊት መውጣት ጉዳይ የተጠቀሰ የለም። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች በቅርቡ እንደሚወጡ አስታውቆ ነበር። አሜሪካ የምታወጣው መግለጫዎችን በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው እያለ ሲወቅስ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት እቀባውን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዩ በኩል በሰጠው መግለጫ "የኢትዮጵያ ነፃነትና ሉዓላዊነት በገንዘብ የማይቀየር ቀይ መስመር ነው" ብሎታል። በተለይም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ኃይሎች ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው የሚለው ጥረት በመንግሥት በኩል ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ተገልጿል። እቀባውንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ሽብርተኛ ተብሎ ከተሰየመው ህወሓት ጋር ድርድር ማድረግ እንደማይቻል ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል" በማለት ቡድኑ መልሶ እንዲያንሰራራ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ አሉታዊ ውጤት የሚኖረውና የማይሳካ መሆኑ ተጠቅሷል። ዶክተር ዮናስም በበኩላቸው ከህወሓት ጋር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በተለያዩ አካላት ወደ ድርድር ለማምጣት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አስታውሰው በወቅቱ አሜሪካም የራሷን ድርሻ መጫወት ትችል ነበር ይላሉ። "የኢትዮጵያ ምክር ቤት ተሰብስቦ ህወሓትን በሽብርተኝነት ከፈረጀው በኋላ እንደገና ህወሓትን ከዚያ ውስጥ ለማውጣትና እንደ መንግሥት ሁለቱን እኩል አድርጎ ለድርድር ግቡ ማለት ቅንነት ያለው አይመስለኝም" ብለዋል። የአሜሪካ መንግሥት በአገሪቱ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ሽብርተኛ ቡድን" ተብሎ የተሰየመውን ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በእኩል የመመልከት ዝንባሌ እንዳስቀየመው አስፍሯል።
news-47634986
https://www.bbc.com/amharic/news-47634986
"የሠራዊቱ ሁኔታ ከፍተኛ የህሊና መረበሽ ውስጥ ከቶኛል" አቶ ነአምን ዘለቀ
ላለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩት የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ከፍተኛ አመራርና ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ነአምን ዘለቀ ከፓርቲ መልቀቃቸውን ተከትሎ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፡ የአርበኞች ግንቦት 7 የ ሠ ራዊ አባላት አሁን ያሉበት ሁኔታ ትንሽ ያስጨነቀዎት ይመስላል። ግን ደግሞ ለመልቀቅ ከወሰኑ ቆይተዋል፤ እርስዎም በጽሑፍዎ እንደጠቀሱት። እና ዝም ብሎ ከመውጣት ፣ መልቀቅዎን ከአንድ ጉዳይ ጋ ሆን ብለው ለማያያዝ የሞከሩ ይመስላል ።
አቶ ነአምን ዘለቀ አቶ ነአምን፡ (ዘለግ ካለ ሳቅ በኋላ ) ምን እላለሁ እንግዲህ። አንተ የመሰልህን (ማሰብ ትችላለህ). . .። መጀመሪያ (ከጽሑፌ) አንተ ይሄን ብቻ ነጥለህ ለምን እንዳወጣኽው አላወቅኩም። እዚያ ላይ ሠራዊቱን በሚመለከት የተደረገው ጥረት በዝርዝር ተቀምጧል። እስካሁን ድረስ እነኚህ የሠራዊት አባላት በከፍተኛ ችግር ላይ ነው ያሉት፤ ላለፉት ሰባት ወራት። • «የሠራዊታችን አባላት በክብር ይሸኛሉ» ግንቦት 7 መንግሥት የእነርሱን ጉዳይ በተደረገው ስምምነት መሠረት (ማለትም) ቶሎ በሁለትና በሦስት ወር ውስጥ መልሰው ይቋቋማሉ፣ ድጎማ ይሰጣቸዋል አለ፤ የጀርመን መንግሥት ገንዘብ ለመስጠት ቃል ገባ፤ ነገር ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው ቢሮ ምንም አቅም ስላልነበረው እስካሁን ድረስ ሲጓተት ቆይቶ አሁን ገና ወደ ኮሚሽን ጉዳዩ ተመርቶ ያው ኮሚሽኑ ኃላፊነት ተሰጥቶት በብሔራዊ አደጋ መከላከል ኮሚሽን በኩል የእነርሱ ጉዳይ እንዲካሄድ ነው እየተደረገ ያለው። ቢቢሲ፡ ለመሆኑ የሠራዊቱን አባላት በአካል አግኝተዋቸዋል? አቶ ነአምን፡ የዛሬ ሁለት ወር ወረታ ካምፕ ሄጄ አይቻቸው፤ ችግራቸውን መርምሬ ለሥራ አስፈጻሚውም ሪፖርት ያደረግኩበት ሁኔታ ነው ያለው። ቢቢሲ፡ሁሉም ወረታ ካምፕ ነው ያሉት? አቶ ነአምን፡ ሁሉም አይደሉም። ግማሾቹ እዚያ ናቸው፤ ግማሾቹ የመልሶ ማቋቋሚያ እርዳታ ታገኛላችሁ ተብለው ከካምፑ ውጪ ናቸው። ከካምፑ ውጪ ያሉት በሺህ የሚቆጠሩ ናቸው። በተለይ ደግሞ በጣም የተቸገሩት ከኤርትራ በረሃ የመጡት ናቸው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ናቸው፤ ካምፕ ውስጥ ያሉት ደግሞ ወደ 150 የሚጠጉ ናቸው። ቢቢሲ፡ እና ለመልቀቅ ያበቃዎ ምኑ ነው? አቶ ነአምን፡ እነዚህ ልጆች፤ እነዚህ የሠራዊት አባላት፤ የአርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊት አባላት፤ ከኤርትራ የተመለሱትን ወሮታ ሄጄ አነጋግሬያለው። ችግራቸውን ተገንዝቤያለሁ። በአፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያገኙ በሁለት ወር ውስጥ ቃል ገብቼ ነው ጥር ላይ የተመለስኩት። አቶ አንዳርጋቸውም ይህንኑ አድርጓል። ያ ሁለት ወር አለቀ። • አርበኞች ግንቦት 7 ፈርሶ አዲስ ፓርቲ ሊመሰረት ነው እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት እርዳታ አላገኙም። እንዳልኩት ገና የዛሬ ሳምንት ኃላፊነት የተሰጠው ኮሚሽን አለ፤ በዚያ ኮሚሽን በኩል ይሄ በመንግሥት በኩል ቃል የተገባው የመልሶ የማቋቋም እርዳታ ተግባራዊ ይሆናል የሚል ግምት አለን። ግን ጉዳዩ ካልተፋጠነ ደግሞ ትልቅ አደጋ አለው። እነሱ እራሳቸው በሁለት በሦስት ሳምንት ውስጥ እርዳታ ካላገኙ ወደ ሚዲያ እንደሚሄዱ፤ ሌላም እርምጃ እንደሚወስዱ የተናገሩበት ሁኔታ ነው ያለው። በአንጻሩ የሌላ ድርጅቶች፤ የብሔር ድርጅቶች፤ በአማራ በኦሮሞ የተደራጁ ደግሞ በየክልላዊ መንግሥቱና ጸጥታ ኃይል ውስጥ እንዲካተቱ ተደርገዋል።...ይሄን እያዩ… ቢቢሲ፡ ላቋርጥዎት አቶ ነአምን፤ እሱን እንመለስበታል። አሁን የእርስዎ መልቀቅ እንዴት ነው ይህን ነገር ወደፊት የሚያራምደው? የጀርመን እርዳታ የእርስዎን መልቀቅ ተከትሎ አይመጣ? የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት እርስዎ ስለለቀቁ ተደናግጦ እርዳታውን አይቀጥል? በእርስዎ መልቀቅ የሚመጣ ለውጥ ይኖራል ብለው ነው? አቶ ነአምን፡ የእነሱ መቸገር፣ የእነሱ ለከባድ ማኅበራዊ ችግር መዳረግ፣ በቀን ሥራ ከዚያም ውጪ በረሃብና በጉስቁልና ሕይወታቸውን እንዲገፉ መደረግ፤ የእኔ መልቀቅ የበለጠ አሁን የተወሰነውን ውሳኔ እንዲያፋጥነውና ትኩረት እንዲያገኝ ያደርጋል ብዬ እገምታለው። ቢቢሲ፡ ውስጥ ሆነው ቢታገሉ አይቀልም ነበር ግን? አቶ ነአምን፡ ይሄ እኮ የትግል ጉዳይ አይደለም። እኔ ጽሑፌ ላይ እንደገለጽኩት የንቅናቄው አመራር፤ ዶክተር ብርሃኑ፤ ዋና ጸሐፊው ጥረት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩንም በተለያየ ደረጃ ያሉት ሰዎችንም አነጋግረዋል፤ ግፊት አድርገዋል። አንዴ አይደለም ብዙ ጊዜ። • "በአንድ ሀገር ውስጥ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ክልሎች ሊኖሩ አይገባም" ፕሮፌ. ብርሃኑ ነጋ ጉዳዩ ከሚገባው በላይ ተጓቶ አንድ ውሳኔ የመስጠት አቅም ያለው ጽህፈት ቤት ማቋቋም ስላልተቻለ፤ ጀርመኖቹም ቃል ከገቡ በኋላ ድጋፉን ያልሰጡበት ምክንያት አምባሳደሩን ስናነጋግር ይሄ የተቋቋመው ጽሕፈት ቤት አቅም የለውም። ፕሮጀክትና ፕሮግራሞችን ቀርጾ ማሠራት የሚችል የሰው ኃይል የለውም ብለው እኮ በግልጽ ነግረውናል። ምንድነው ለማድረግ የሞከርነው? ይሄ ጽሕፈት ቤት አቅም ከሌለው ወይ ለሌላ ስጡት። ወይ ደግሞ ይሄንንን የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት በአግባቡ ፕሮግራምና ፕሮጀክት የሚቀርጹ ባለሙያዎች ይመደቡ። አንድ ግለሰብና አንድ ጸሐፊ ብቻ ነው እዚያ ያሉት ብለን እኮ ብዙ ጊዜ ተናግረናል። ይሄ ጉዳይ ስላልተፈጸመና ስለተጓተተ ነው እዚህ ደረጃ የደረስኩት። ነገሩ ገና የዛሬ ሳምንት ውሳኔ አግኝቷል። ያ ደግሞ ምን ያክል ተግባራዊ እንደሚሆን እናያለን። በዚህ ሁሉ ሂደት እኛ (ለሠራዊታችን) ቃል የገባነው ጊዜ አልቋል። ያ ሁለት ወር ከማብቃቱ በፊት ለሠራዊቱ ቃል የገባነው፤ እንደውም ሁለት ወይም ሦስት ወር ነው ከኤርትራ ከገቡ በኋላ፤ አሁን ስምንተኛ ወር ሊመጣ ነው። ያ ከሆነ በኋላ ነው በዚህ ጉዳይ ላይ ጫና ለመፍጠር፣ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ ብዬ የለቀቅኩት። ቢቢሲ፡ እርስዎ በመልቀቅዎ የሠራዊቱ አባላት የተሻለ ድምጽ የተሻለ መሰማት ያገኛሉ ብለው የምር ያምናሉ ማለት ነው? አቶ ነአምን፡ እኔ መጀመሪያውኑም እለቃለሁ ብዬ ደብዳቤው ላይ በዝርዝር አስቀምጫለሁ። እኔ በፖለቲካ ድርጅት አባልነት አልቀጥልም። የእኔ ኃላፊነት ከፖለቲካ ድርጅት አመራርነት ወይም አባልነት ነው የሚያበቃው፤ በኢትዮጵያና በሃገር በሕዝብ ጉዳይ ላይ ተሳትፎዬ በተለያየ መንገድ ይቀጥላል። እስካሁን ድረስ 26 ዓመት ያልተቋረጠ ትግል አድርጌያለው፤ ብዙ አስተዋጽኦ አድርጌያለው፤ ከሚጠበቅብኝ በላይ። ለኢትዮጵያ ሕዝብ አሁንም የሚጠቅሙ፣ የሚበጁ፣ ለሀገር ደኅንነት፣ ለሰላም፣ ለዴሞክራሲ፣ ለፍትህ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ እንደግለሰብ፣ እንደዜጋ አስተዋጸኦ አደርጋለሁ። ግን በኃላፊነት ላይ ተቀምጬ እንዲህ ዓይነት በጣም ህሊና የሚቆጠቁጥና እንቅልፍ የሚነሳ ሁኔታ ውስጥ እራሴን ማግኘት አልፈልግም። አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን ከዚያ ከሚመጣው ጭንቀት፣ መከራና ስቃይ፤ ልመናና ተማጽኖ ብትሰማ ታዝናለህ። ቢቢሲ፡ አሁንም ያልተመለሰልኝ ጥያቄ፣ አልታይህ ያለኝ ነገር ሠራዊቱን ከእርስዎ መልቀቅ ጋ ያያዙበት ገመድ ነው? አቶ ነአምን፡ ምክንያቱንና ውጤቱን አታመሰቃቅለው። እኔ ያልኩት መጀመሪያ ቀደም ሲል ለውጡ ከመጣ በኋላ ተናግሬያለሁ፤ እኔ አልቀጥልም። የቆየሁበት ምክንያት አቶ አንዳርጋቸውም ሌሎቹም እንድቆይ ስለጠየቁኝ ነው። በዚህ በቆየሁበት ጊዜ ዋናው ማሳካት የፈለግኩት የሠራዊቱ ሰላማዊ ሕይወት እንዲቋቋም ያንን መስመር ማስያዝ ነው። በዚያም መሠረት ብዙ እንቅስቃሴ ተደርጓል። አቶ አንዳርጋቸውም አድርጓል፤ ዶክተር ብርሃኑም አድርጓል፟፤ እኔም አድርጌያለሁ። • ስለ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጥቂቱ ግን በፈለግነው ፍጥነት አልሄደም። በዚህ መካከል ሠራዊቱ ከፍተኛ የማኅበራዊ ችግር ውስጥ ነው ገባ። ከካምፕ ውጪ ያሉትም፤ ካምፕ ውስጥ ያሉትም ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ናቸው። እኛ ደግሞ ቃል ገብተናል፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ብለን። ያ ጊዜ ደግሞ አለቀ። አሁንም ሥራው ገና አልተጀመረም፤ በዚህ መካከል ከፍተኛ ችግር አለ። በየቀኑ አዲስ አበባ ሆኜ ስልኮች ይመጣሉ፣ ሰዎች ይመጣሉ፤ ብዙ ነገር ነው የምሰማው። ይሄ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የህሊና መረበሽ ነው በእኔ ላይ ያመጣው። ቢቢሲ፡ ከእንግዲህ በፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ ምንም ተሳትፎ ማድረግ አይፈልጉም። የመጨረሻዎ ነው ይሄ? አቶ ነአምን፡ አዎ! እኔ ለዚህ ትግል ሁሉ ነገሬን ሰጥቼ ስለነበር የቤተሰቤንም፣ የራሴንም የድርጅቴንም ሁሉ ነገሬን ነበር የሰጠሁት። አሁን ራሴ ላይ ማተኮሪያ ጊዜ ነው። ግን የኢትዯጵያ ጉዳይ፣ የዲሞክራሲ ጉዳይ፣ እኔ የማምንባቸው መርሆች፣ አገሬ ውስጥ እንዲኖሩ የምፈልጋቸው በጎ ነገሮች ውስጥ አስተዋጽኦዬን እንደ አንድ ዜጋ እቀጥላለሁ። ነገር ግን ፓርቲ ውስጥ ወደፊት እሳተፋለሁ አልሳተፍም የሚለውን አሁን የምናገረው አይደለም። ቢቢሲ፡ ችግር ውስጥ ናቸው የሚሏቸው የሠራዊቱ አባላት እርስዎ ጥለዋቸው ወደ ግል ሕይወትዎ ሊያተኩሩ እንደወሰኑ ሲሰሙ የሚያዝኑብዎ አይመስልዎትም? አቶ ነአምን፡ እነሱም እኮ ብዙዎቹ ወደ ግል ኑሯቸው (እንዲመለሱ)፣ ሕይወታቸው እንዲስተካከል ነው ጥረቱ። አሁን እኮ የትጥቅ ትግሉ አልቋል። አሁን የሚደረው ትግል ፖለቲካዊ ትግል ነው። በተለያዩ መንገዶች ለውጡን የማስቀጠል ነው ትግሉ። ይህ ደግሞ በአንድ ድርጅት የሚሳካ አይደለም። ቢቢሲ፡ ለሠራዊቱ ቃል የተገቡ ነገሮች ምን ምን ነበሩ? አቶ ነአምን፡ በቅድሚያ ኤርትራ ጉባኤ ተደረገ። ሠራዊቱ አገር ወስጥ እንደሚገባ፣ ከዚያ ደግሞ በሁለት በሦስት ወራት ወስጥ መልሶ እንደሚቋቋም፣ ድጎማ፣ ድጋፍና ስልጠና ተሰጥቶት ሁሉም ሰላማዊ ኑሮ የሚገፋበትን ሁኔታ እንደምናመቻች ነበር ቃል የተግባባነው። ይህን ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጋር ዋሺንግተን ውስጥ ተነጋግረንበት ነበር። እኛም አስተዋጽኦ እንድናደርግ ተስማምተን ነበር። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ብዙ የተደረገ ጥረት ነበር፤ ይህ የሚካድ አይደለም። ነገር ግን ሄዶ ሄዶ ሁለት ሦስት ወር ወስጥ ትቋቋማላችሁ የተባለው ቃል ሊከበር አልቻለም። ከዚያም አልፎ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ እኔ ራሴ ካምፕ ሄጄ አነጋግሪያቸው ሁለት ወር ጊዜ ስጡን ነው ያልናቸው። ያ ሁለት ወር አለፈ። ቢቢሲ፡ ሠራዊታችሁን በቁጥር ማስቀመጥ ይቻል ይሆን? አቶ ነአምን፡ ቁርጥ ያለ አኀዝ ባልሰጥህም አሁን አገር ውስጥ ካሉ ከተለያዩ በረሃዎች የገቡት ከ2ሺህ በላይ ናቸው። ከኤርትራ በረሃ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ናቸው። ቢቢሲ፡ ስለዚህ እያወራን ያለነው ከ3ሺ ስለማይበልጥ ሠራዊት ነው? አቶ ነአምን፡ አዎ። ቢቢሲ፡ መልቀቂያዎ ተቀባይነት አግኝቷል? አቶ ነአምን፡ ቀደም ብዬ ለሥራ አስፈጻሚው መልቀቂያዬን አቅርቢያለሁ፤ ከዚያ ለሕዝብ ይፋ አድርጊያለሁ። ቢቢሲ፡ ተቀባይነት አግኝቷል ግን? አቶ ነአምን፡ በርግጥ ይሄ የእኔ ውሳኔ ነው። ነገር ግን ሊቀመንበሩ እስከ ጉባኤ እንድቆይ ጠይቆኛል። የራሴን ምክንያት ሰጥቻለሁ። ይሄ ጉዳይ ጉባኤም ለማድረግ የማንችልበት ደረጃ ይደርሳል። ስለዚህ ይህ ጉዳይ ወደ ሕዝብ መሄድ አለበት። አንዳርጋቸውም ብርሃኑም በዚህ ላይ ብዙ ሠርተዋል፤ ግን በተጨባጭ እስካሁን የተወሰደ እርምጃ የለም። ይሄ ጉዳይ የሚያስፈልገውን ትኩረት አግኝቶ በሁለት ሦስት ሳምንት ውስጥ ሠራዊቱ መረዳት ካልተጀመረ የሚፈጠረውን ለፓርቲም ሆነ ለጉባኤው አስቸጋሪ ይሆናል። እንዲውም ታገሱን እያልን ነው እንጂ ወደ ሚዲያም መውጣት ይፈልጋሉ። ቢቢሲ፡ ቅድም አቋረጥኮት እንጂ "ሌሎች ከትጥቅ ትግል የተመለሱ ብሔር ተኮር ድርጅቶች ቃል የተገባላቸው ሲፈጸምላቸው፣ የእኛ ተዘነጉ" ሲሉኝ ነበር ልበል? አቶ ነአምን፡ ሆን ተብሎ ይሁን ሳይታወቅ፤ ብቻ ምንድነው ስሜቱ፣ ወሮታ ካሉ የሠራዊት አባላት ጋር ባደረግነው ውይይት የተረዳነው፤ በብሔር የተደራጁ ኃይሎች በአማራም በኦሮሞም ከኤርትራም የገቡትም አገር ውስጥም የነበሩት በጸጥታም በአስተዳደርም ከአመራር እስከ አባላት ተገቢ በሆነ ሁኔታ እንዲካተቱ አድርገዋል። እኛ ግን ለኢትዮጵያ ብለው የታገሉ፣ ኅብረ ብሔር የፖለቲካ ዓላማን አንግበው የታገሉ፣ ለአንድ ብሔር ሳይሆን በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ብለው የታገሉ፣ ልክ አባት እናት እንደሌለው (ኦርፋን እንደመሆን) ነው የተሰማቸው። ይሄ ደሞ ጥሩ አይደለም። አሁን ባለው አክራሪ ብሔርተኝነት ለኢትዮጵያ መቆም እንደ ነውር እንዲታይ የሚያደርግ ነው። ያኔ ሳናግራቸው እንደዚህ ዓይነት ድርጅቶች፣ የብሔር ድርጅቶች (ስም መጥቀስ አልፈልግም) የእነሱ ታጋዮችም አመራሮችም እንደዚህ ሆነዋል። 'እኛ ለኢትዮጵያ ብለን ሕይወታችንን ለመስጠት በረሃ በወረድን ለምን ተጣልን' የሚል ስሜት ነው ያላቸው፣ የሠራዊቱ አባላት። ቢቢሲ፡ አቶ ነአምን፣ ከአመራሩ ጋር መጠነኛም ቢሆን ቁርሾ ወይ መቃቃር ውስጥ ገብተዋል እንዴ? አቶ ነአምን፡ አንዳንዶች የእኔን መልቀቅ በሌላ እየተረጎሙ እየጻፉ ነው። እኛ በጣም ወፍራም መተማመን ያለን ነን። ብንጋጭም ለዓላማችን ለዓመታት አብረን በጋራ ሠርተናል። ሁልጊዜ በድርጅት ውስጥ ችግር ይኖራል። ነገር ግን በዋናው በኢትዯጵያ ጉዳይ ላይ ተማምነን ተከባብረን ነው የሠራነው። ዛሬ ለምሳሌ ከአንዳርጋቸውም ከብርሃኑም ጋር በጽሑፍ ተነጋግረናል። ምንም ዓይነት ቅራኔ የለም፤ ይህን ላረጋግጠልህ እወዳለሁ።
48918665
https://www.bbc.com/amharic/48918665
"ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" አሊ ቢራ
በቅርቡ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ለአንጋፋው ድምጻዊ አሊ ቢራ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል። አሊ ቢራ ለዓመታት ባስደመጣቸው ነጻነትና ፍቅርን በሚሰብኩ ሙዚቃዎቹ ይታወቃል። ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ማግኘቱን ተከትሎ ከአፍረንቀሎ ባንድ እስከ ዛሬ ስላለው የሙዚቃ ጉዞ ከቢቢሲ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል። የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ሰጥቶሃል፤ ምናልባት የትውልድ ቦታህና ሙዚቃ የጀመርክበት ስለሆነ የተለየ ስሜት ነበረው?
አሊ ቢራ፡ ይሄ ከሰዎች የምሰማው ነው እንጂ ለኔ ለየት ያለ ክብርና ደስታ የተሰማኝ አለመሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ። ምክንያቱም ጅማም፣ ጎንደርም ሆነ ጎጃም የትኛውም ያከበሩኝ ቦታ አንዱን ካንዱ አብልጬ አይደለም የማየው ማለቴ ነው። አንድ ፎቶ ከብዙ ሺ ቃላቶች የበለጠ ራሱን ይገልፃል ይባላል። እጄን ዘርግቼ የተነሳሁትን ፎቶግራፍ አይተው፤ ከጅማ ዩኒቨርስቲ የበለጠ ደስታ እንደተሰማኝ አድርገው ሲያወሩ ነበር፤ እኔ የሚሰማኝ ሁለቱም እኩል ነው ያከበሩኝ፤ እግዚአብሔር ያክብራቸው። እጁን ስለዘረጋ የተለየ ደስታ ያሳያል የሚለውን ነገር አላውቅም። ከዚህ ቀደም የክብር ዶክትሬት የሰጡህ ዩኒቨርስቲዎች የትኞቹ ናቸው? አሊ ቢራ፡ ዩኒቨርስቲዎች አይደሉም፤ አንድ ዩኒቨርስቲ ነው። የጅማ ዩኒቨርስቲ ነው ያከበረኝ፤ እግዚአብሔር ያክብራቸው። ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት ነበር የሰጡኝ፤ ሁለተኛው ያው ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በቅርቡ የሰጠኝ ነው። እስቲ ወደ ኋላ ልሂድና በ14 ዓመትህ አፍረንቀሎ የሚባል ባንድ መስርተህ ነበር፤ በወቅቱም የተወሰኑ ሰዎች ታስረዋል። አንተም ተሰደህ ነበር፤ በሙዚቃውም በትግሉም የመጣህበትን ጉዞ አጫውተን። አሊ ቢራ፡ በአፍረንቀሎ ባንድ ውስጥ ከመስራቾቹ አንዱ ነኝ እንጂ መስራች አይደለሁም። በእድሜ ከነሱ አነስ እላለሁ። አፍረንቀሎን ከመሰረቱት ውስጥ አሊ ሸቦ የሚባል እሱም ከሃረማያ ዩኒቨርሰቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጥቶታል። እኔ ከነሱ ጋር ተቀላቅዬ አፍረንቀሎን መሰረትኩ። ስሜቱ በጣም ትልቅ ደስታን ይሰጣል በተለይም ባሁኑ ጊዜ ስናየው። • ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" ባንዱ የተመሰረተው ከ57 ዓመት በፊት ነው። ባንዱ የነበረው ራዕይ ለተነሳው ትግል [ማለትም]፤ በዛን ጊዜ ማንነታችን፣ ኦሮሞነታችን፣ ቋንቋችንና ህልውናችን ተደምስሶ በነበረበት ወቅት ነው። እኛም ታግለን እንትን እናደርጋለን በማለት ተነስቶ፤ እንግዲህ የዛሬ 57 ዓመት ፍሬ እያፈራ፤ ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል እየታየ፤ ዛሬ እንግዲህ ፈጣሪ ይመስገን ብሔር ብሔረሰቦች እኩል የሆኑበት፤ ሁሉም የየራሱን ማንነት እያስከበረ የሚኖርበት ዘመን ተፈጥሯል። የአፍረንቀሎ መነሻውና መድረሻው በጣም የሚያስደስት ነገር ነው። ነገር ግን ከብዙ መራራ ትግል በኋላ ነው። እስር፣ ግድያ ነበረው፤ ያው እዚህ ጋ መድረሳችን ተመስገን የሚያስብል ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣሁት ከአሥራ አራት ዓመት በፊት ነው። ይህም ከብዙ ዓመት ስደት በኋላ ነው። አሁን ሙሉ በሙሉ ከተመለስኩኝ አምስት፣ ስድስት ዓመት ሆኖኛል። ተመስገን ነው። "አባ ለፋ" የሚለውን አልበምህን ዶሚኖ ሬከርድስ የሚባል ኩባንያ ሙዚቃህን ለማተም ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው። ሙዚቃው ታተመ? አሊ ቢራ፡ አዎ ታትሟል። የመጀመሪያ እትም በዚሁ በአገራችን ስፖንሰር የሚያደርጉት አኬፋ የሚባል ኩባንያ እዚሁ አትሞታል። ሌላኛው ደግሞ የድሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን እንደነ ጥላሁን ገሰሰ፣ ማህሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሸቴ የመሳሰሉት የታተሙበት ኢትዮፒክስ የሙዚቃ አልበሞችን ያተመው ቡዳ ሬከርድስ አትሞታል። አባ ለፋ የራሱ ታሪክ አለው። ሙዚቃው ከነበረው የመሬት ከበርቴዎች ሥርአት በሕዝቡ ላይ ያደርሱ የነበረው 'አትሮሲቲ' [ግፍ] ለማስቀረት ምን መደረግ አለበት የሚል መልዕክትን የያዘ ነው። መልዕክቶቹ ለሕዝቡ፣ ለአራሹ፣ ለተማሪውና ለሠራተኛውም የሚሆን ነው። ጊዜውን ጠብቆ ነው ያ ዘፈን የተዘፈነው። ወደ ዶሚኖ ኩባንያ ልመለስና መጀመሪያ ጠይቀው ነበር። ቀጥታ ከኛ ጋር ሳይሆን ኢትዮፒክስን ከሚያሳትመው ከቡዳ ሬከርደስ ጋር ተነጋገሩ ብለናቸው ነበር። በኋላ ላይ ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም፤ ዝርዝሩን ባለቤቴ ነች የምታውቀው። • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን በኦሮምኛ ቋንቋ ብትዘፍንም፤ ቋንቋውን የሚረዳውም ሆነ የማይረዳው ሙዚቃህን ያውቀዋል። እንዲህ ቋንቋን አልፎና ትውልድን የሚያገናኝ ሙዚቀኛ ከመሆንህ አንፃር፤ ሙዚቃህ ያለውን ተፅእኖ እንዴት ታየዋለህ? አሊ ቢራ፡ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው። ንፁህ ሆኖ ለሀቅና ለትክክል የሚሠራ ሰው እግዚአብሔርም ከላይ ሆኖ ያየናል፤ ምድርም ጭንቅላት ያለውን ሰው ይረዳል። እኔ በሙዚቃዬ አቀነቅን የነበረው ስለ ሀቅ፣ መብትና ሰላም ነው። አንዳንዱ በኦሮምኛ ስለዘፈንኩኝ እንዴት በሶማሊኛ አልዘፈነም? ብሎ ሶማሌውን እኔ ላይ የሚያነሳሳ ሊኖር ይችላል። አማርኛ፣ እንግሊዝኛና ሌሎችም ቋንቋዎች ለምን አልዘፈንክብ ብለው የሚጠይቁ [አሉ]. . . ቋንቋው ኦሮምኛ ይሁን እንጂ መልዕክቱ ዓለም አቀፍ ነው። በሰው ልጅ ላይ የሚደርስ ግፍ፣ ጭቆና፣ ሞት በየትኛውም አገር አለ። በኦሮምኛ ቋንቋ ስለተዘፈነ ወደ ኦሮምኛ ብቻ ጥግ የሚያስይዙኝ አሉ። ግን እኔ የማውቀውና የማስበው የሰውን ልጅ መብት መጋፋት እግዚአብሔር አላደረገውም፤ የሰው ልጅ ነው የሚያደርገው። • በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች አካሄዴ፣ መነሻና መድረሻዬ በዛ ላይ የተመሰረተ ነው። ሙዚቃው ከሌላ ሙዚቃ የተሻለ ተብሎ አይደለም። 'ሪዲንግ ቢትዊን ዘ ላይን' የሚሉት አለ አይደል? [ግጥሞቼ በመሀል የማይታዩና የማይነበቡ መልዕክቶች አሉት]። እናም ቀና የሆኑ ሰዎች ሙዚቃዬን ይሰሙታል ቀና ያልሆኑ ሰዎች አንድ ጥግ ሊወስዱኝ ይችላሉ እንደ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ሙዚቃዬን እንዲወድልኝ እወዳለሁ። ይሆናል ብየም ሳይሆን፤ ስለ መሬት አራሹ፣ ስለ መብት፣ ስለ አካባቢም ከዘፈንኩ ከልቤ ነው፤ ለበጎም ነው። እናም በጎ አስተሳሰብ ያለው ሰው እየሰማ ያደንቅልኛል። ሌላውም እንዳልኩት በሆነ መንገድ ጥግ ሊወስዱኝ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ለኔ የፈጣሪ ፀጋ ነው ሙዚቃዎቼ እንዲወደዱ ያደረገልኝ። ዋናው መልዕክቱ ነው። • ተፈራ ነጋሽ፡ "በነገራችን ላይ ሙዚቃ አልተውኩም" ለምሳሌ በኦሮምኛ "ሲን ጃለዳ" ካልኩ በአማርኛ እወድሻለሁ ማለት ነው። በእንግሊዘኛ "አይ ላቭ ዩ" ማለት ነው። በኦሮምኛ "ሲን ጃለዳ" ስለሆነ በሌሎች ቋንቋዎች መተርጎም አይችልም ማለት አይደለም። ተተርጎሞ 'ግሎባል' [ዓለም አቀፍ] ይሆናል። በፈረንሳይኛ፣ በቻይንኛም ይሁን በፈለገው ቋንቋ እወድሻለሁ፣ እወድሻለሁ ነው። አንድ ጊዜ አፍረንቀሎ ውስጥ ሳለን ሳንሱር ተደርጎ ነበር። ዘፈን በአማርኛ ተርጉሙና አምጡ ተብለናል። እኛ ማታ ለኮንሰርት ተዘጋጅተናል። እና ሁሉንም ነገር (ወደ 30 ዘፈን) በአማርኛ ተርጉሙ ተባልን። በኦሮምኛ "ጃለላ" ፍቅር ማለት ነው። ዘፈኑ ውስጥ ለአንዲት ልጅ ወይም ለፈለገው ነገር ፍቅር ሊኖረው ይችላል። ሰውየው "ጃለላ" ማለት ምንድን ነው? ሲለኝ ፍቅር ነው እላለሁ። 'አዎ፤ [ፍቅር ማለት እንደሆነ] እናውቃለን፤ ግን እናንተ የምትሄዱበት መንገድ ይህ ፍቅር ምን አይነት ነው?' አለኝ። ይታይሽ እንግዲህ አንድን ቃል በሁለት ቦታ ለመክፈል አይደለም "ጃለላ" የተባለው። "ጃለላ" ፍቅር ነው። የእናት፣ የአባት፣ የአገር [ሊሆን ይችላል]። ሙዚቃ መልዕክቱን ለሰው የሚያደርሰው የአንድ ቋንቋ ብቻ ሆኖ አይደለም። የዓለም ነው። በጎም መጥፎም ቢሆን። ሁሉም ቦታ ስላለ [ነው]። አሊ ቢራ ታሪክ ነጋሪ ነው፣ ሙዚቀኛ ነው፣ የነጻነት ታጋይ ነው ይሉሀል፤ አንተስ ራስህን ምን ብለህ ነው የምትጠራው? አሊ ቢራ፡ እኔ ተማሪ ነኝ። እኔ ብቻ ሳልሆን ምድር ላይ ወደ 7 ቢሊዮን ከምናምን ተማሪዎች አሉ። ከነዛ መሀል አንዱ ነኝ። ራሴን የማየው በዛ አይነት መንገድ ነው። ዛሬም እማራለሁ፤ ነገም እማራለሁ፤ ትላንትም ተማርኩኝ። ፈጣሪ በመዘነው አይነትና በሰጠኝ ያችን ብቻ ነው የማውቀው። እንጀራ እንጀራ ነው። ዳቦ ዳቦ ነው። እንደዚህ እንደዚህ ብሎ ከዚህ በላይ ከፍ እያለም የማውቀው ነገሮች አሉ። ስለ ትምህርት ከሆነ እድለኛ አይደለሁም። እንደ ብዙሃን የአገራችን ተጨቋኞች እና የደሀ ቤተሰብ ልጅ ስለሆንኩኝ እስከዚህም የመማር እድል አላገኘሁም። ግን በየቀኑ ትምህርት ቤት ሄጄ የምማረው ነገር አለ። እኔ የዓለም ተማሪ ነኝ። አንቺም፣ እሱም፣ እሷም ሁሉም [ተማሪ ነው]። በቀላሉ ራሴን የምገልጸው እንዲህ ነው። • ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች የነጻነት ታጋይ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ለሚሉህስ? አሊ ቢራ፡ ያ የተመልካቹና ስለኔ የሚያወራ ሰው የሚያውቀውን ነው የሚያወራው። ታጋይ መሆኔን ወይም እምቢተኛ ከሆንኩኝ የሰው ትርጓሜ ነው። ስለ አሊ ቢራ የዛ ሰው ትርጓሜ ነው። ስለዚህ እኔ ሰዎች አሁን እንዳልሽኝ ታጋይ ነው ሲሉ፤ እርግጥ ታጋይ ማለት ትልቅ ነገር ነው። ስለ ሀቅ የሚታገል ከሆነ። እኔ የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው ራሴን የምፈርጀው። አንዳንድ ሰዎችም እንደዛ ይሉኛል። በተቃራኒውም የሚሉኝም አሉ። የሀቅ፣ የመብት፣ የሰላም፣ የበጎ ነገር ታጋይ ነኝ እላለሁ። እንግዲህ ለ56 ዓመት ዘፍነሀልና ላንተ ለየት ያለ ዘፈን የምትለው የትኛውን ነው? አሊ ቢራ፡ እኔ 'ኮምፖዝ' ያደረኳቸው [ያቀናበርኳቸው] 267 ዘፈኖች ናቸው። ሁሉም የኔ ልጆች ናቸው። እኔ ልጆችም የሉኝም። ያለኝ 267 ዘፈኖች ናቸው። እና ከነሱ የትኛውን ትመርጣለህ? ቢባል በየጊዜው የራሳቸው ስሜት አላቸው። ስሠራቸው የሚሰማኝ ስሜት። ስለ ፍቅር፣ ስለ ቆንጆ ልጅ፣ ከዘፈንኩ በዛን ጊዜ የተሰማኝ ስሜት አለ። ስለ 'ኢንቫይሮመን'ት [አካባቢ] ከዘፈንኩ በዛ ጊዜ ስለዘፈንኩት የሚሰማኝ ስሜት አለ። ስለ ፖለቲካም ከዘፈንኩ [እንደዛው]። እውነቴን ነው። ብዙ ሰዎች ይጠይቁኛል. . . ለዚህ ጥያቄ ግን የኔ 'ፌቨራይት' [ምርጥ] ይሄ ነው የምለው የለኝም። 267ቱንም በደንብ እንወዳቸዋለን። ለአድማጭ 'ሪፈር' የማደርገውም [የምጋብዘውም] 267ቱን ነው። አሁን ምን እየሠራህ ነው? ሙዚቃ አቁመሀል? ትዘፍናለህ? አሊ ቢራ፡ አሁን ጡረተኛ ነኝ። በጥበብ ዉስጥ 57 ዓመት ሳገለግል ነበር። እግዚአብሔር በሰጠኝ 'ኢነርጂ' [ጉልበት] ተጠቅሜበታለሁ። እስካሁን ድረስ ፈጣሪ ይመስገን ብዬ። ከዚህ በኋላ እንግዲህ ብዙ ወጣቶች አሉ። ብዙ ታጋዮች አሉ። ብዙ ስለ መብት የሚከራከሩ አሉ። አሁን 'ሪላክስ' አድርጌ [ዘና ብዬ] እንደ 'አድቫይዘር' [አማካሪ] ሆኜ ለወጣት ሙዚቀኞች የማውቀውን አካፍልላሁ። የበለጠ ጊዜዬን [የማሳልፈው በዚህ ነው]። እናንተ ወጣቶች እንድትጦሩን ብዬ ነው። ግን አልፎ አልፎ ትልልቅ ኮንሰርቶች ባሉበት ጊዜ እታደማለሁ። አንድ፣ ሁለት እዘፍናለሁ እንጂ 'ፕሮፌሽናሊ' [እንደ ሙያ] እንደ በፊት ሙዚቃ ሠርቼ እኖራለሁ የሚለውን በቃ አቁሜያለሁ። የጤናህስ ሁኔታ እንዴት ነው? አሊ ቢራ፡ ጤናዬ የተጠበቀ ነው። በብዙ ዶክተሮች። ባለቤቴ የኔ ዶክተር ነች። ባለቤቴ አለ አይደል ወደ ሆስፒታል ትልከኛለች። የእድሜ ነገር ነውና ስኳር፣ የደም ግፊት ምናምን ነገሮች አሉ። እሷ መድሀኒቶቼን አስተካክላልኝ. . . ተቀጥራ የምትሠራ ነርስ ይመስልሻል። በጣም ጎበዝ ስለሆነች። ፈጣሪ ይመስገን እሷ ትረዳኛለች። በቃ በተቻለኝ መጠን ከፈጣሪ የሚሰጠኝን ጸጋ እየተቀበልኩ መኖር ነው።
54348246
https://www.bbc.com/amharic/54348246
ባህል፡ በዋቄፈና እምነት ሀጥያት፣ ገነትና ገሃነም አሉ?
ዋቄፈና የቀደምት ኦሮሞ ሕዝቦች እምነት ሲሆን የእምነቱ ተከታዩች ሁሉን በፈጠረ አንድ አምላክ እንደሚያምኑ ይናገራሉ።
አቶ አስናቀ ተሾመ ኢርኮ፣ ላለፉት 20 ዓመታት ስለ ዋቄፈና እምነት አጥንተዋል። አሁንም በዓለም አቀፍ የዋቄፈና እምነት ምክር ቤት በአመራርነት እያገለገሉ ይገኛሉ። በዋቄፈና እምነት ዙሪያ የአገር ሽማግሌዎች እና ካደረጉት ጥናት የተረዱትን ለቢቢሲ እንዲህ በማለት አካፍለዋል። አቶ አስናቀ ቦረና አካባቢ በመሄድ ጥናታቸውን እንዳደረጉ ገልፀው "ፈጣሪ ስሙ መቶ፣ ሆዱ እንደ ውቅያኖስ ሰፊ፣ ሃሳቡ ደግሞ ንጹህ ነው፤" ድሮ ድሮ ሰው ሃጥያት መስራት ሳይጀምር በፊት የፈጣሪን ድምጽ የሰሙ ሰዎች ነበሩ ይባላል ይላሉ። ስሙ መቶ ነው የሚለው ደግሞ ፈጣሪ "አንድ" እና ከሁሉ በላይ የሆነ መሆኑን እና ሀይማኖቶች ወይንም እምነቶች ግን ብዙ መሆናቸውን ለማሳየት መሆኑን አቶ አስናቀ ያብራራሉ። ይሁንና ፈጣሪን በዓይኑ ያየው ሰው የለም በማለት ነው ኦሮሞ የሚያምነው ሲሉ ያስረዳሉ። ኦሮሞ 'ፈጣሪ ጥቁር ነው' ይላል። የኦሮሞ ፈጣሪ ጥቁር ነው ሰንል ግን ይኼ የሚታየውን መልክ ወይም የቀለም ጉዳይ ሳይሆን፣ "ፈጣሪ ጥልቅ ነው፤ ፈጣሪን ማየት፤ መለየት አይቻልም የሚለውን ለመግለጽ ነው። ማንም ተመራምሮ ሊደርስበት አይችልም።" ብለዋል። "ፈጣሪ ምስጢር ነው፤ ከሰው አእምሮ በላይ ነው የሚለውን ለማሳየት ነው በጥቁር መልክ የሚገለፀው።'' ዘፍጥረት እንደ ዋቄፈና እምነት፤ ፈጣሪ ሁሉን ነገር የፈጠረው በቀደመ ዘመን ከነበረ ውሃ እንደሆነ ይታመናል። ፈጣሪም ይህንንም ውሃ 'የላይኛውና የታችኛው ውሃ' በማለት ለሁለት ከፈለው የሚሉት አቶ አስናቀ፣ የላይኛው ውሃ ጠፈር ውስጥ የሚገኙ አካላትን ሰማይን እንዲሁም ፀሀይንና ከዋክብትን ይይዛል። የታችኛው ውሃ ደግሞ፣ የውሃ አካላትን እንደ ውቅያኖስ፣ ባህርን፣ ደረቅ መሬትን ይይዛል። ዋቄፈና በዚህ ምድር ላይ ያሉ ፍጥረታት በሙሉ በ27 ቀናት ተፈጠሩ ብሎ ነው የሚያምነው። መጀመሪያ ሰውን ፈጠረ፣ ከዚያም ወንድና ሴት ብሎ እኩል ለሁለት ከፈላቸው። ሌሎች ፍጥረቶችንና ተክሎችን እንደዚሁ በቅደም ተከተል ፈጠራቸው። ፈጣሪ ምድርን ሲፈጥር ሰው በስነ-ስርዓት እንዲኖር ሕግንም አብሮ ፈጠረ። እነዚህም ሕጎች የሰው ሕግ፣ የከብቶች ሕግ፣ የፈረሶች ሕግ፣ የዱር አራዊት ሕግ፣ የእጽዋትና የፀሀይና የከዋክብት ሕግ ይሰኛሉ። 'ሰፉ' የማይቀየር የፈጣሪ ሕግ ነው። ይህም ክልክል የሆኑትን ሰውን መግደል፣ መስረቅ፣ ዝሙት እና መዋሸትን ተላልፎ መገኘት ነው። ፈጣሪን፣ ምድርን እንዲሁም ሌሎችን ፍጥረቶች ሁሉ ማክበር የፈጣሪን ሕግ መጠበቅ ነው። ክልከላዎች 'ለጉ' የሚባሉት የማህበረሰቡን አይነኬ ተግባራት ለመጠበቅ የወጡ ናቸው። አንድ ሰው ሀጥያት ሰራ የሚባለው እነዚህን የፈጣሪን ሕግና ክልከላዎች ሲጥስ/ ሲተላለፍ ነው። ከሞት በኋላ ሕይወት? ቀደምት የኦሮሞ ሕዝቦች ሰው ሲሞት ነፍሱ ወደ ፈጣሪ ወይንም ደግሞ ወደ እውነት ቦታ ትሄዳለች ብለው ነው የሚያምኑት። እንደ ዋቄፈና እምነት ሰው ከውሃ፣ ከነፋስ፣ ከእሳት እና ከአፈር በአንድ ላይ ተበጅቷል። ስለዚህ ሰው ሲሞት አካሉ ከአፈር ይቀላቀላል፣ ደሙ ወደ ውሃ ይሰርጋል። ነፍሱ ደግሞ ወደ ፈጣሪው ይሄዳል። "እንደ ሌሎች እምነቶች ዋቄፈና ሰው ከሞተ በኋላ ይነሳል ወይንም በሕይወት ይኖራል ብሎ አያምንም። እንዲሁም በሴጣን መኖርና ፈጣሪን የሚገዳደር ሌላ ኃይል አለ ብሎ አያምንም። ሰዎችንም ኃጥያት እንዲሰሩ የሚያስገድዳቸው ኃይል የለም ብሎ ነው የሚያምነው" ይላሉ አቶ አስናቀ። ይኹን እንጂ "ክፉ መንፈስ አለ ብሎ ያምናል" በማለት፣ ሰው የማይቀየረውን የፈጣሪን ሕግ ከተላለፈ፣ ስለሚጠየቅ እና ርግማንም ወደ ሰባት ትውልዱ ስለሚተላለፍ ኃጥያት መስራት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ሕዝቡም ይህንን ይፈራል። ለምሳሌ አንድ ሰው፣ ነፍስ አጥፍቶ ሳይናገር ከሞተ በፈጣሪ ዘንድ ስለሚጠየቅ ቤተሰቦቹ ወይንም ዘመዶቹ የሙት መንፈስን የሚያናግሩ "አዋቂዎች" ዘንድ ይሄዱና ካሳውን "ልክ በሕይወት እንዳለ ሰው" ይጠይቃሉ። በዚህ እምነት ገሃነም ወይንም ገነት የሚባል ነገር የለም። እንዲህ ማለት ግን ሰው የፈለገውን እያደረገ ይኖራል ማለት አይደለም። በእነዚያ በፈጣሪ በማይቀረው ሕግ ስር መመላለስ አለበት። በዚህ መንገድም በፍጥረታት እና በሰዎች መካከል ያለ ሚዛን ተጠብቆ በሰላም መኖር ይቻላል ብሎ ያምናል፤ ዋቄፈና። አቶ ተሻገር የአገር ሽማግሌዎች 'እዳየነው እንደሰማነው' በማለት ሲናገሩ፣ ኦሮሞ ፈጣሪን ሴት ወይንም ወንድ ብሎ ለይቶ አይጠራም። ነገር ግን ሲጠሩት በወንድ ጾታ ነው። ይህ ግን ጾታውን ለማመለክት አለመሆኑን.ይናገራሉ። የዋቄፈና እምነት ተከታዮች አቶ ደሳለኝ ደሜ በቢሾፍቱ ሆረ አርሰዴ የዋቄፈና ቤተ እምነት "ዋዩ" ናቸው። ዋዩ ማለት የዋቄፈና ቤተ እምነት ውስጥ ያሉ የአስተዳደር ጉዳዮችን የሚሰበስብና የሚመራ ሰው ነው። አቶ ደሳለኝ ዋቄፈና ከአባቶቻችን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣ እምነት ቢሆንም፣ እኛ የአሁኖቹ ትውልዶች ደግሞ ስርዓት እና ባህሉን ሳይለቅ ለአሁኑ ዘመን በሚመች መልኩ በ1990ዎቹ ቤተ እምነት መስርተን ኃይማኖቱን አቋቁመናል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እኛ እንደ እምነታችን ሁሉን በልጦ የሚያስተምር መምህር የለንም ያሉት አቶ ደሳለኝ ደሜ፣ ምክንያቱን ሲያስረዱ ስለዚህ እምነት ጉዳይ ሁሉም ከአባቱ ወርሶ ተምሮ መምጣቱን ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጂ የውይይት ጥላ የሚባል ዝግጅት እንዳላቸው ገልፀዋል። በዚያም ስለፈጣሪ ተነጋግረን ፈጣሪን ለምነን እንገባለን ሲሉም ያክላሉ። "በአጠቃላይ ግን እምነቱን በበላይነት የሚመራው 'ቃሉ' ነው።" በአሁኑ ጊዜ በቢሾፍቱ ከተማ ብቻ አራት የዋቄፈና ቤተ እምነቶች አሉ። ከቢሾፍቱ በተጨማሪ በአዳማ፣ ባቱ ፣ ሰበታ እና ወሊሶ እንዲሁ ቤተ እምነቶች ይገኛሉ። በየዓመቱ ደግሞ አንድ ቤተ እምነት እንደ ክብረ በዓል ያዘጋጅና ሁሉም በአንድነት ያከብራሉ። የሆረ አርሰዴ ቤተ እምነት በግምት ከ5000 በላይ አባላት እንዳሉት አቶ ደሳለኝ ይናገራሉ። አብዛኛዎቹ አባላት ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ሰራተኞችና በተለያየ የኑሮና የስራ ዘርፍ የሚገኙ ሰዎችም አባላት ናቸው። የዋቄፈና የአምልኮ መርሃ ግብር ቤተ እምነቱ ሁሌም ለሁሉም ሰው ክፍት ቢሆንም ዘወትር እሁድ ግን አባላቶች በአንድነት ተገናኝተው የአምልኮ ስነ ስርዓት ያካሄዳሉ። ጠዋት ሲገናኙ ማንኛውም ስነ ስርዓት ከመጀመሩ በፊት አንዱ ለአንዱ ይቅርታ የማድረግ ስርዓት ይፈፀማል። "በዚያ ቤተ እምነት ውስጥ የሚገኝ ሰው እርቀ ሰላም ካላወረደ፣ ፈጣሪ አይሰማም ተብሎ ስለሚታመን እርቀ ሰላም ይቀድማል" የሚሉት አቶ ደሳለኝ፣ ከዚህ በመቀጠል በእድሜ ታላቅ የሆኑ እና አካባቢን መሰረት በማድረግ የምርቃት ስነ ስርዓት መርሃ ግብር ይካሄዳል። ከዚህ በኋላ ዋቄፈናን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በማንሳት በውይይቱ ጥላ ስር ያሉ አባላቶች ይማማራሉ። አሁን ፀሎትና ምስጋና ይቀጥላል። በዚህም ጊዜ የቡና ማፍላት ስርዓት ይከናወናል። የታመመ ሰው ይፀለይለታል፤ ቤተሰቦቹ የፈጣሪን ሕግ ጥሰው ከሆነ ፈጣሪ እንዲታረቃቸው ይለመናል። ከዚህ በፊት ፀሎታቸው የተመለሰላቸው ሰዎች ካሉ ደግሞ ምስጋና ያቀርባሉ። በዚህ ሁሉ መካከል 'ጄከርሳ' መዝሙር ይዘመራል። ይህ መዝሙር በስነ ስርዓቱ መክፈቻና መዝጊያ ላይ የሚካሄድ ሲሆን ከመጨረሻው መዝሙር በፊት ግን አንድ "ባልቻ" የሚባል የመባ መስጠት ስርዓት ይካሄዳል። ይህ ስርዓት የቤተ እምነቱ አባል የሆነ ሰው የገንዘብ የሃሳብና የንብረት ድጋፍ የሚያደርግበት ነው። በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥት በኩል እውቅና የማግኘትና የአምልኮ ስፍራ ለማግኘት ትልቅ ችግር እንዳለባቸው አቶ ደሳለኝ ጨምረው አስረድተዋል።
49686048
https://www.bbc.com/amharic/49686048
ከ22 ዓመት በኋላ በ 'ጉግል ማፕ' አስክሬኑ የተገኘው ግለሰብ
ፍሎሪዳ ውስጥ ከ22 ዓመት በፊት ጠፍቶ የነበረ ዊልያም ሞልድት የተባለ ግለሰብ አስክሬን በ'ጉግል ማፕ' አማካይነት ተገኘ። የግለሰቡ አስክሬን የተገኘው 'ጉግል ማፕ' [የተለያዩ አካባቢዎችን የሚያሳይ የስልክ ካርታ] መኪናው ያለበትን ሥፍራ ካሳየ በኋላ ነበር።
ዊልያም ሞልድት • በጠርሙስ በላኩት መልዕክት ሕይወታቸው የተረፈው ቤተሰብ • ኦክስፎርድ ከዓለማችን ቀዳሚው ዩኒቨርስቲ ተባለ • የአእምሮ ጤና ሰባኪው ፓስተር ራሱን አጠፋ ዊልያም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1997 ነበር የጠፋው። በወቅቱ 40 ዓመቱ ነበር፤ የምሽት ክለብ ውስጥ ሲዝናና ካመሸ በኋላ ለዓመታት የት እንደደረሰ አልታወቀም። ፖሊስም ዊልያምን ፈልጎ ማግኘት አልቻለም ነበር። 'ጉግል ማፕ' ያሳየውን የመኪና ምስል ተከትሎ፤ ፖለሶች ወደ ሥፍራው ሲሄዱ የዊልያምን አስክሬን አግኝተዋል። መኪናው የሚገኝበት ቦታ የታወቀው አንድ ግለሰብ 'ጉግል ማፕ' ላይ ያደረጉትን አሰሳ ተከትሎ ነበር። 'ጉግል ማፕ' ላይ የሚታየው የመኪና ምስል ፓልም ቢች የተባለው ግዛት የፖሊስ ኃላፊ ተሬሳ ባርባራ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ዊልያም ከ22 ዓመት በፊት መኪናውን እያሽከረከረ ሳለ፣ መኪናው ከቁጥጥሩ ውጪ ሆኖ ወደኩሬ ሳይገባ አልቀረም። "ከዚ ሁሉ ዓመታት በፊት የተፈጠረውን በውል ለማወቅ ያስቸግራል" ብለዋል። ዊልያም ከ22 ዓመት በፊት ሄዶበት ከነበረው የምሽት ክለብ ከመውጣቱ በፊት ብዙም አልኮል እንዳልጠጣ በወቅቱ የተሰበበሰው መረጃ ያሳያል። በምሽቱ ዊልያም ለፍቅረኛው ወደቤት እንደሚመለስ ቢነግራትም፤ ዳግመኛ አላየችውም። አስክሬኑ መገኘቱን ፖሊስ ለቤተሰቦቹ አሳውቋል።
41310617
https://www.bbc.com/amharic/41310617
የፀረ ሙስና ዘመቻው አንድምታዎች
በቢሊዮን ብር የሚቆጠር የህዝብ ሐብትን በማጉደል ወንጀል ተጠርጥረዋል የተባሉ 34 ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ደላሎች እና ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ፤ ከሙስና ጋር በተያያዘ የሚታሰሩ ባለስልጣናት እና የንግድ ሰዎች ጉዳይ ከባለፈው ዓመት መገባደጃ ጀምሮ ከ ዐብይ የመነጋገሪያ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ሆኖ አሁን ድረስ ዘልቋል።
የግንባታ ሥራዎች ለሙስና ከተጋለጡ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ገደማ የተጀመረው የመንግሥት በሙስና የተጠረጠሩ ባለሥላጣናትና ነጋዴዎችን የመያዙ ዘመቻ አሁንም ያበቃ አይመስልም። በተለያዩ ጊዜያት ከመንግሥት ተቋማትና ከሌሎችም ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች እየተያዙ ከምርመራ ባሻገር ወደ ፍርድ ቤት እቀረቡ ነው። ከነዚህም መካከል በከፍተኛ የመንግሥት የሥልጣን እርከን ላይ ከሚገኙ ሃላፊዎች መካከል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ዓለማየሁ ጉጆ አንዱ ናቸው። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ አለማየሁ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ነበር በቁጥጥር ሥር የዋሉት። አሁንም በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ከዚያም ለፍርድ የሚቀርቡ ተጠርጣሪዎች ቁጥር እየጨመረ የሄደ ሲሆን፤ መንግሥት ቃል ስገባ የቆየሁትን የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ዘመቻ በከፍተኛ ደረጃ መጀመሬን የሚያሳይ ሰፊ ጥናት እና በቂ ዝግጅት አድርጌ የወሰድኩት እርምጃ ነው ይላል። ከስልጣን ጋር በተያዘዘ የተሳሳተ አመለካከት መኖሩን የሚያምነው የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በወቅቱ ያወጣው መግለጫ፤ ተጠያቂነትን ለማስፈን ብሎም አጥፊዎቹን ከህግ ፊት ለማቅረብ በመስራት ላይ መሆኑን ይናገራል። ይሁንና ተችዎች በፌደራል ፖሊስ ምርምራ ቢሮ እና በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ትብብር እየተወሰደ ነው በተባለው እርምጃ ላይ ያላቸውን ጥርጥሬ ይገልፃሉ። የዘመቻው ውጤታማነት ላይ ጥያቄ የሚያነሱ እንዳሉ ሁሉ፤ ገፊ ምክንያቱን ከአገሪቱ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር የሚያይዙት አልጠፉም። ግንባታ የሙስና ፈተና ከሰባ በላይ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ኦዲት በማድረግ ልምድ ያካበቱት የሒሳብ አያያዝና የፋይናንስ ባለሙያው አብዱልመናን መሃመድ በሥራ ላይ በቆዩባቸው ባለፉት ሰባት ዓመታት ሙስና እየተንሰራፋ ሲሄድ አስተውያለሁ ይላሉ። ይህም አነስተኛ ጉቦን ጨምሮ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ድረስ ያለውን እንደሚያካትት ይናገራሉ። በከፍተኛ ደረጃ ምዝበራ ከሚፈፀምባቸው ዘርፎች መካከልም የሥራ ውል አሰጣጥ እና አስተዳደር፣ የመሬት አስተዳደርና ግብር ይገኙበታል ብለዋል። ዋነኛ ዓላማውን ሙስናን እና ተያያዥ ወንጀሎችን መታገል ያደረገው ዓለም አቀፉ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት በበኩሉ፤ በአዲስ አበባ የሚገነቡ ጥራታቸው የወረደ የመንገድ ሥራ ፕሮጄክቶችን ነቅሶ ዓይነተኛ የብልሹ አሰራር ማሳያዎች መሆናቸውን ያስረዳል። መንግሥት በዘመቻው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣንን በር ማንኳኳቱንም "የሚያበረታታ" ነው ብሏል። የገንዘብና ኢኮኖሚ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቤቶች ልማት አስተዳደር እንዲሁም የስኳር ኮርፖሬሽን ሌሎች በርከት ያሉ የሥራ ኃላፊዎቻችው ሞስነዋል ተብለው የታሰሩባቸው ናቸው። የተጠርጣሪ ባለሃብቶች ንብረቶች የታገዱ ከመሆኑም በላይ በተለያዩ ክልሎችም በመቶዎች የሥራ ኃላፊዎች በጥርጣሬ እንዲታሰሩ ሆነዋል። ጽህፈት ቤቱ ጨምሮም ኢትዮጵያ በሙስና እየተፈተነች ያለች አገር ለመሆኗ እ.ኤ.አ የ2016ቱን የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የሕዝብ የሙስና እይታ መለኪያን በማስረጃነት ያቀርባል። በመለኪያው መሰረት ኢትዮጵያ ከ176 አገራት መካከል 108ኛ ደረጃን በመያዝ "በሙስና የተዘፈቁ" አገራት ተርታ ውስጥ ትገኛለች። በሙስና ንፅህና ከመቶ ነጥብ ማስመዝገብ የቻለችውም 34 ብቻ ነው። በመለኪያው መሰረት ያለፉት አስራ አምስት ዓመታት የአገሪቱ አማካይ ደረጃ 109ኛ አካባቢ ነው። አብዱልመናን እንደሚሉት ለሙስና ከዕለት ወደ ዕለት መንሰራፋት አንደኛው ምክንያት መንግሥት በምጣኔ ሐብት ውስጥ በሰፊው እጁን ማስገባቱ ሲሆን የሕዝብን ሃብት የማስተዳደርና የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለባቸው ተቋማት እጅጉን ደካማ መሆናቸውም እንዲሁ ትልቅ ሚና አለው። "በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ውስጥ ያለው ተገቢ ያልሆነ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትም" ለሙስና መንገድ ጠራጊ ነው ይላሉ። "ፉከራ ብቻ" አዲስ አበባ ውስጥ በግል የንግድ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው ብሩክ ዘላለም መንግስት ሙስናን የመቅረፍ ልባዊ ፍላጎት አለው ብሎ እንደማያምን ይገልፃል። "ሁሌም ችግራችን እንደሆነ ለይተነዋል ሲባል እንሰማለን፤ አንድ ሰሞን ሆይ ሆይ ይባልና ከዚያ ደግሞ ይረሳል" ይላል። ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ ሲጋጋል የነበረው ሙስናን የመመንጠር ዘመቻ ከአንድ ወር በኋላ መቀዛቀዙ ጉዳዩን "ፉከራ ብቻ" እንዳስመስለውም ይናገራል። አብዱልመናን ሥር የሰደደውን የአገሪቱን የሙስና ችግር በዘመቻ መቅረፍ መቻሉ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ አትኩሮቱን ሙሰኞችን መመንጠርን ያደረገ የምርምራ ቡድን መቋቋሙን ባሳውቁበት ወቅት፤ መንግሥታቸው ሥልጣናቸውን ያላግባብ ለግል ጥቅም ባዋሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተው ነበር። በወቅቱም እንዲሁ ወደ 130 የሚጠጉ ግለሰቦች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው ይታወሳል። እነዚህ እርምጃዎች ከወትሮው በተለየ ውጫዊ ገፊ ምክንያቶች እንዳላቸው የሚከራከሩት አብዱልመናን፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቱ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተቀስቅሰው የነበሩ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መንግሥት ላይ ጫና እንዳሳደሩ ያምናሉ። ሙስና የስራ ፈጠራን፣ ታታሪነትን እና ሃቀኛ ፉክክርን በማቀጨጭ በአገሪቱ ምጣኔ ሐብት ላይ ትልቅ አደጋ መደንቀር ይዟል የሚሉት ባለሞያው፤ ተቋማዊ ድክመት እና ፖለቲካዊ ወገንተኛነት መገለጫቸው የሆኑ ፍርድ ቤቶችን፣ የመንግሥትና የፓርቲ ወሰን መምታታትን በመፍጠር ፖለቲካውን ማወኩም እየተስተዋለ ነው ባይ ናቸው።
51905321
https://www.bbc.com/amharic/51905321
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የመንግሥት ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲዘጋጁ ጠየቀ
የኢትዮጵያዊያን የአኗኗር ዘዬ ለኮሮናቫይረስ በቀላሉ መሰራጨት ምቹ በመሆኑ ምዕመናን ይህን ልማድ ለጊዜው በመግታት የጤና ተቋማት የሚሰጡትን ምክር ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጸ።
ጉባኤው ምዕመናን የቫይረሱ ምልክቶችን በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ላይ ሲመለከቱ መረጃውን በአፋጣኝ ለሚመለከታቸው የጤና ተቋማት እንዲያሳውቁም ጠይቋል። ምዕመናን በየቤተ እምነታቸው ተገኝተው የአምልኮ ሥነ ሥርዓቶችን ሲካፈሉም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፤ ይህንንም ሲያደርጉ የሌሎችን ስሜትና ሥነ ልቦና በማይጎዳ መልኩ እንዲሆን አሳስቧል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው። በሌላ በኩል የንግድ ማኅበረሰቡም የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚያስፈልጉም ሆነ በሌሎች የፍጆታ እቃዎች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ጭማሪ ከማድረግ እንዲታቀቡም ጠይቋል። የመንግሥት ኃላፊዎች አስፈላጊውን ጥረትና ዝግጅት እንዲያደርጉ፤ መገናኛ ብዙሃንም ትክክለኛ መረጃን በወቅቱ በማድረስ ወገናቸውን የመርዳት ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አሳስቧል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ።
news-45873864
https://www.bbc.com/amharic/news-45873864
ሞባይልዎ ላይ ችግር የሚያስከትሉ መተግበሪያዎች የትኞቹ ናቸው?
መቼስ በዚህ ወቅት ጫኑኝ የማይል የስልክ መተግበሪያ የለም። ዓለም ራሷ የስልክ መተግበሪያዎች ውስጥ ተከናንባ እየገባች ይመስላል። የደም ግፊት መጠንን ከሚለኩት ጀምሮ ቋንቋ መማሪያዎች፣ ቀን መቁጠሪያዎች፣ ቁርስ ምሳ ማዘዣዎች፣ ታክሲ መጥሪያዎች፣ ባንክ ሂሳብ ማንቀሳቀሻዎች፤ ብቻ የሌለ ዓይነት የስልክ መተግበሪያ የለም።
• ሞባይል ለእናቶችና ለህፃናት ጤና ፈተናው ሐሰተኛውን ከእውነተኛው መለየት ነው። በዚህ በኩል እኛ እንርዳዎት! የሚከተሉት ሦስት የስልክ መተግበሪያዎችን ጫኑ ማለት መከራን ስልክዎ ላይ ጫኑ እንደማለት ነው። ስልክዎን ለጤና መቃወስ የሚያጋልጡ ሐሰተኛ መተግበሪያዎች (Apps) የሚከተሉት ናቸው። 1.የባትሪ ዕድሜን እናራዝማለን የሚሉ የሞባይል ባትሪ እንደ ቋንቋ ነው፤ ይወለዳል፣ ያድጋል ይሞታል። ልዩነቱ በምን ፍጥነት ይሞታል የሚለው ነው። በዚህ ረገድ የባትሪው ኦሪጅናልነትና የአገልግሎት ዘመን ቁልፍ ጉዳይ ነው። አንዳንድ ጊዜ ባትሪ ቶሎ እየሞተ ሲያስቸግር ያነጫንጫል። በዚህ ጊዜ የባትሪዎን ዕድሜ ላራዝምልዎ የሚል መተግበሪያ ሲመጣ ያጓጓል። ጫኑኝ ጫኑኝ ይላል። አይቸኩሉ! የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛ የሆነው ኤሪክ ሄርማን "የባትሪ ዕድሜን የሚያቆይ ምንም ዓይነት መተግበሪያ የለም" ይላል። • የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም ይልቅ የባትሪ ዕድሜን ለማራዘም መፍትሄው ብዙ ዳታ የሚያሟጥጡ መተግበሪያዎችን ለጊዜው ዝም ማሰኘት ነው። እምብዛምም የማያስፈልጉ መተግበሪያዎች ከጀርባ ሆነው ባትሪን ይመዘምዛሉ። የስልክዎ የብርሃን ድምቀት፣ የኢንተርኔት ዳታ፣ የዋይ ፋይ ማብሪያ ማጥፊያ ባትሪን ይመገባሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ስልክዎን "ናይት ሞድ" ወይም "ባትሪ ቆጥብ" የሚለው ማዘዣ ላይ ያድርጉት። ሌላው መፍትሄ ባትሪ ኮንፊገሬሽን ላይ ገብቶ የባትሪን እድሜ እየበሉ ያሉትን ዝርዝሮች ማየትና ያንን ለይቶ ዝም ማሰኘት ነው። 2.ስልክዎን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች ስልክዎትን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች በአመዛኙ ውሸት ናቸው። እንዲያውም ለቫይረስ ያጋልጣሉ። "ክሊን ማስትር" የሚባለው መተግበሪያ ዋንኛው ነው። ስፔናዊው የቴክኖሎጂ አዋቂ ጆስ ጋርሺያ እንደሚለው "ክሊን ማስተር" የተባለው መተግበሪያ የስልክን ፍጥነት ይቀንሳል፣ የራሱን ገበያ ለማድመቅም ብዙ መተግበሪያዎችን እንድንጭን ያባብለናል። የሞባይል ስልክን ፀሐይ ላይ አለመተው ስልክዎ ትኩሳት ከተሰማው ችግር አለ ማለት ነው። የስልክ ትኩሳት በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል። ለረዥም ሰዓት ለፀሐይ ብርሃን ከተጋለጠ፤ በቫይረስ ከተጠቃ፤ ወይም ደግሞ ጤናማ ያልሆነ ባትሪ ከተገጠመለት አልያም ደግሞ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት አገልግሎት ላይ ከዋለ ስልክ እንደ ብረት ምጣድ ይግላል። • በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? ይህን ችግር እንቀርፋለን የሚሉ የስልክ መተግበሪያዎች ሐሰት ናቸው። መፍትሄም አያመጡም። እንዲያውም ትኩሳቱን ያብሱበታል። ስልክዎ በአዲስ መንፈስ እንዲሰራ ከፈለጉ አጥፍተው ያሳርፉት። ለስልክዎ ጠቅላላ ጤና የሚከተሉትን ያስታውሱ • መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ምንነታቸው ከተረጋገጠላቸው ሁነኛ የስልክ መደብሮች ብቻ ያውርዱ። አፕል ስቶር እና ጉግል ስቶር የታወቁት ናቸው። • የፋይል ስማቸው በኤፒኬ ፊደል እንደሚጨርስ (.apk) ከሚታዩ መተግበሪያዎች ይጠንቀቁ • ራሳቸውን ተአምራዊ ሥራ እንሠራለን እያሉ ከሚያሞካሹ መተግበሪያዎች ይጠንቀቁ • ስልክዎትን በየጊዜው "አፕዴት" በማድረግ ያድሱ
news-55469566
https://www.bbc.com/amharic/news-55469566
የሱዳንና እስራኤል ስምምነት ስጋት የሆነባቸው ስደተኞች
የሱዳኗ ዋና ከተማ ካርቱም በተለያዩ ብሄሮች መከፋፈል የሚታይባት ከተማ ናት። የከተማዋ ዙሪያ የዳርፉር ጦርነትን ሸሽተው የመጡ፣ የኑባ ተራሮችና ሌሎች የተገፉ ማህበረሰቦች የሚኖሩበት ሲሆን የከተማው መሀል ላይ ደግሞ አረብኛ ተናጋሪዎች በብዛት የሚኖሩበት ነው ትላለች ጋዜጠኛዋ ዛይነብ መሀመድ ለቢቢሲ በጻፈችው ደብዳቤ ላይ።
ካርቱም ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፓውያኑ 1967 የአረብ ሊግ ስብሰባን ካስተናገደች ወዲህ የአረብ ስምምነት ማዕከል ተደርጋ የምትቆጠር ሲሆን በዚህ ስምምነት መሰረት የአረብ አገራት ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማቋረጥ ተስማምተዋል። በስብሰባውም ላይ ከእስራኤል ጋር ምንም አይነት ሰላማዊ ግንኙነት ላለማድረግ፣ እውቅና ላለመስጠትና ላለመደራደር ተስማምተዋል። በካርቱም የሚኖሩ በርካቶችን የሚያማርር አንድ ነገር አለ። በየዓመቱ የናይል ወንዝ እየሞላ በርካታ ቤቶችን ያፈርሳል፣ ጠራርጎ ይወስዳል፣ የሰዎች ሕይወትንም እስከመቅጠፍ ይደርሳል። ታዲያ በዚህ ወንዝ አቅራቢያ ከሚኖሩት ሰዎች መካከል ጥቂት የማይባሉት ቤታቸውን መልሰው የሚገነቡት በእስራኤል ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩ ዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው በሚልኩላቸው ገንዘብ ነው። በቅርቡ በአሜሪካው ተሰናባች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አደራዳሪነት በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው ስምምነት ደግሞ በጊዜያዊነት ጥገኝነት ለተሰጠቻቸው በርካታ ሱዳናውያን አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ሱዳን ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ደፋ ቀና ስትል የነበረው አሜሪካ አሸባሪነትን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትሰርዛት ለማድረግ እንደሆነ በርካቶች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። ቃላቸውን ጠብቀውም ፕሬዝዳንቱ ሱዳንን ከዚህ ዝርዝር ውስጥ አስወጥተዋታል። እአአ 1948 ላይ እስራኤል አገር መሆኗን ካወጀች ወዲህ ሱዳን ከአገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ወስና ነበር። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ባህሬንም ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ነው። በተመሳሳይ እስራኤልና ባህሬን ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ ለማሻሻል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይፋ ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነበሩ። ለበርካታ አስርታት በርካታ የአረብ አገራት እስራኤልን የፍልስጥኤም ጉዳይ ከተፈታ በኋላ ግንኙነታቸውን እንደሚቀጥሉ በመግለጽ አግልለው ነበር። የሱዳንና የእስራኤልን ስምምነት ተከትሎ በሱዳን መንግስት መከራ ይደርስብናል ብለው በእስራኤል ጥገኝነት ጠይቀው ይኖሩ የነበሩ በርካታ ሱዳናውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ከተደረጉ በኋላ በሱዳን የደህንንት ሰራተኞች እንደተገረፉ ይናገራሉ። የሱዳንና የእስራኤልን ስምምነት ተከትሎ የእስራኤል የደህንነት ሚኒስትሩ ኤሊ ኮሀን የሱዳን ጥገኛ ጠያቂዎች ወደ አገራቸው መሄድ እንዳለባቸው ተናግረው ነበር። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ጥገኝነት ጠያቂዎች በሱዳን ያለውን ግጭት ሸሽተው ነው እስራኤል የገቡት። የተባበሩት መንግስታት እንደሚለው ከ6 ሺ በላይ ሱዳናውያን ስደተኞች በእስራኤል የሚገኙ ሲሆን በእዛኛዎቹ ደግሞ እስካሁን ድረስ ሕጋዊ የስደተኛ ሰነድ እንኳን ማግኘት አልቻሉም። እንደውም በቅርብ ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂዎች መጠለያ ካምፖች ውስጥ እንዲኖሩ አልያም እንደ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ ባሉ ሁለተኛ አገራት እንዲኖሩ ምርጫ እየተሰጣቸው እየተባረሩ ይገኛሉ። በአውሮፓውያኑ 2014 ወደ ሱዳን እንዲመለስ የተደረገ አንድ ግለሰብ የመመለስ ውሳኔው እንደሚያስቆጨው ይናገራል። ምክንያቱም ተመላሾች በደህንነት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ክትትል የሚደረግባቸው ሲሆን ፓስፖርታቸውም ቢሆን ለአምስት ዓመታት በኃላፊዎች ይያዝባቸዋል። በአሁኑ ሰአት ታናሽ ወንድሙ እስራኤል ውስጥ የሚገኘው ይሄው ግለሰብ ወንድሙ ፋብሪካ ውስጥ ስራ አግኝቶ ቤተሰቡን እየደጎመ እንደሚገኝ ይናገራል። አዝራ ኤል ኑር የምትኖረው በእስራኤሏ አራድ ውስጥ ሲሆን ከዚህ በኋላ ወደ ሱዳን የመመለስ ምንም አይነት ፍላጎት የላትም። በኑባ ተራሮች የሚደረገውን ጦርነት ሸሽታ ነው በሰባት አመቷ ከቤተሰቧ ጋር ወደ እስራኤል የተሰደደችው። በመጀመሪያ ወደ ግብጽ ነበር ያመሩት። የመጀመሪያዎቹን ሰባት ዓመታት በግብጽ በስደተኝነት ያሳለፉ ሲሆን ወደ ሌላ አገር የመዘዋወር እድል እንኳን እንዳልነበራቸው ትናገራለች። ''በመጨረሻም አባቴ ወደ እስራኤል መሄድ እንዳለብን ወሰነ። ወደ እስራኤል ለመሄድ ግን በጣም ከባድ ነበር።'' በአሁኑ ሰአት አዝራ የ27 ዓመት ወጣት ናት። ሁለት ልጆች ያሏት ሲሆን ሁለቱም ልጆቿ መናገር የሚችሉት ኢብራኢስጥኛ ብቻ ነው። ነገር ግን ማንኛቸውም እስራኤል ውስጥ ተረጋግቶ ለመቆየት እንኳን የሚያስችላቸው የስደተኛ ሰነድ አልተሰጣቸውም። አዝራ ወደ ሱዳን እንዲመለሱ የሚገደዱ ከሆነ እሷና ልጆቿ ለበርካታ ዓመታት የሱዳን ጠላት ተደርጋ ትሳል በነበረችው እስራኤል ኑሯቸውን አድርገው በመቆየታቸው መገለልና መድልዎ ሊደርስባቸው እንደሚችል ትሰጋለች። ''ሁለቱም ሴት ልጆቼ ስለ ሱዳን ምንም የሚያውቁት ነገር የለም። እኔ እንኳን ስለ አገሬ የማውቀው ነገር በጣም ውስን ነው። ሱዳንን ለቅቄ ስወጣ በጣም ትንሽ ልጅ ነበርኩ። ከዚህ የምንባረር ከሆነ እንዴት አድርጌ መኖር እንደምችል ያማውቀው ነገር የለም'' ትላለች። ሌላኛው ስደተኛ የ32 ዓመቱ ባሺር ባብኪር ወደ ዳርፉር ተመልሰህ ሂድ እንዳይባል ከፍተኛ ስጋት አለበት። ቤተሰቦቹ አሁንም መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን እሱም እዛው እያለ መጠለያቸው ውስጥ ጥቃት ደርሶበት ነበር። ''ከጥቃቱ በኋላ እዛ ምንም የቀረ ነገር አልንበረም። ወፎች እንኳን ሸሽተው ሄደዋል። ካርቱም ዘመድ ያላቸው ወደዛው ሲሄዱ ምንም ዘመድ ያልነበራቸው ግን ካሳብ የሚባል መጠለያ ውስጥ ቀርተዋል።'' እሱ ከዚህ ክስተት በኋላ በግብጽ በኩል አድርጎ ለአዘዋዋሪዎች ገንዘብ ከፍሎ እስራኤል መግባት ቻለ። ነገር ግን አሁንም ድረስ ወደ አገሩ ሱዳን የመመለስ ከፍተኛ ስጋት አለበት። ምክንያቱም ለበርካታ ሱዳናውያን አሁንም ድረስ እስራኤል ጠላት አገር ናት። ለዚህ ትልቅ ማሳያ ደግሞ የሁለቱ አገራት ስምምነት ይፋ ከተደረገ በኋላ በርካቶች በአደባባይ በመሰብሰብ ተቃውሟቸውንና ቁጣቸውን መግለጻቸው ነው። በእስራኤል አፍሪካ ግንኙነት ላይ ምርምር የሚያካሄዱት ዮታም ጊድሮን እንደሚሉት እስራኤል ለበርካታ ዓመታት የካርቱም መንግስትን የሚቃወሙና በደቡብ በኩል ያሉ አማጺያንን ስትደግፍ ቆይታለች። አሁንም ድረስ ግጭት ባልራቀው የዳርፉር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አማጺያን የተወካይ ቢሯቸውን እየሩሳሌም ውስጥ ከፍተውም ይንቀሳቀሳሉ። ነገር ግን እስራኤል ውስጥ ለሚገኙት ሱዳናውያን ሁኔታው እጅግ የተወሳሰበ ነው። እዛው እስራኤልም ስጋት ያለባቸው ወደ አገራቸው ቢሄዱም ምን አይነት ሁኔታ እንደሚጠብቃቸው አያውቁም። እስራኤል ለጊዜው ወደ ሱዳን መሄድ የሚፈልጉ ብቻ ናቸው የሚሄዱት ብላለች። ነገር ግን ስደተኞቹ በእጅ አዙር ከእስራኤል እንዲወጡ እየተገደዱ እንደሆነ ነው የሚያስቡት። ለምሳሌም በአውሮፓውያኑ 2017 የወጣውን ረቂቅ ሕግ ይጠቅሳሉ። በዚህ ሕግ መሰረት ስደተኞች ወደ አገራቸው እስከሚመለሱባት ቀን ድረስ አሰሪዎች የስደተኞችን 20 በመቶ ደሞዝ እንዳይከፍሏቸው የሚል ሀሳብ ቀርቧል። ነገር ግን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሚያዝያ ወር ላይ ውድቅ አድርጎታል። ''ወደ ዳርፉር እንድንመለስ የሚደረግ ከሆነ ልንሞት እንችላለን፤ እስራኤል አሁንም ለበርካታ ሱዳናውያን ጠላት አገር ነው። ነገር ግን እዚህም ያለው ሁኔታ በጣም አሰቃቂ ነው'' ይላል ባሺር ባብኪር።
news-47565672
https://www.bbc.com/amharic/news-47565672
"እስካሁን ሙሉ የሰውነት ክፍል ማግኘት እንደተቸገርን ለቤተሰብ እያስረዳን ነው" አቶ ተወልደ ገ/ማርያም
ባለፈው እሁድ ከቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ኬንያ ሲያቀና ቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው አውሮፕላን የምርመራ ሂደትና ኢትዮጵያ በአውሮፕላኑ ላይ የጣለችውን የበረራ ዕገዳ በተመለከተ ቢቢሲ ከአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡
"እሁድ ዕለት እኔ አደጋ የደረሰበት ቦታ ስደርስ አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ ከመሬት በታች ነበር፤ ከላይ ሲታይ ምንም ዓይነት የአውሮፕላን ማመልከቻ ነገር አልነበረም " ይላሉ አቶ ተወልደ፡፡ እናም አስከሬኖቹንም ሆነ የአውሮፕላኑን ክፍሎች ለማግኘት ከመቆፈር ውጪ ምንም አማራጭ እንዳነበረ ይገልጻሉ፡፡ • "እናቱ ስታየኝ ልጄ ያሬድ ይመጣል፤ እያለች ታለቅስ ነበር"- በናይሮቢ የካፒቴኑ ጸጉር አስተካካይ "በጣም የሚሳዝነው ነገር እስካሁንም በጣም የተወሰኑትን የሰውነት ክፍሎች እንጂ ሙሉ የሰውነት ክፍል አላገኘንም፤ ይህ ደግሞ ለቀሪ ሥራዎችም ትልቅ ፈተና እንደሚሆንብን እንጠብቃለን ፤ ለሃዘንተኛ ቤተሰቦችም ይህን ችግር እያሰረዳናቸው ነው" ዋና ስራ አስፈጻሚው የአውሮፕላን አደጋ ሊፈጠርባቸው የሚችሉባቸው ምክንያቶች በርካታ በመሆናቸው መላምቶችን ማስቀመጡ ተገቢ ባይሆንም አደጋው ከኢንዶኔዢያው የአውሮፕላን መከስከስ ጋር የሚመሳሰልባቸውን መንገዶች እንዳሉ ጠቅሰዋል. "ሁለቱም ተመሳሳይ የአውሮፕላን ሥሪት ነበሩ፤ከመሬት ተነስተው ብዙም ሳይቆዩ ነው የተከሰከሱት፤የ በረራ ጊዜያቸው በጣም አጭር ነበረ፤ የእኛው አውሮፕላን በ6 ደቂቃ የኢንዶኔዥያው ደግሞ በ 8 ደቂቃ ነው የተከሰከሱት" እናም እነዚህን መረጃዎች መነሻ በማድረግና ለመንገደኞች ህይወት ቅድሚያ ለመስጠት አውሮፕላኙን ከበረራ ማገድ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡ • ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው "እኔ በግሌ እስካሁን ባስተዋልናቸው መመሳሰሎች ምክንያት እንደዚያ መሆን አለበት ብዬ ነው የማምነው፡፡ በቴክኖፖሎጂ የተራቀቁ ሃገራትም እኛን ተከትለው አውሮፕላኖቹን ከበረራ ለማገድ የወሰኑትም በቂ ምክንያት ቢኖራቸው ነው ፡፡እኛም ለደህንንት አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ በማሰብ ነው ወዲያውኑ አውሮፕላኑ ላይ አገዳ የጣልነው፡፡ ይህም ትክክለኛው ነገር እንደሆነ አስባሁ፡፡" አቶ ተወልደ ይህ ለጉዳዩ ካላቸው ቅርበት የመነጨ ነው ባይ ናቸው፡፡ እርሳቸው ይህን ባሉበት ወቅት ቦይንግም ሆነ የአሜሪካ አቪየሽን ተቋም አውሮፕላኑ አስተማማኝ እንደነበር ገልፀው የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ ትናንት የአሜሪካ ሲቪል አቪየሽን ዛሬ ደግሞ ቦይንግ ኩባንያ ራሱ አውሮፕላኑ ከበረራ እንዲታገድ ወስነዋል። "ቦይንግ የአውሮፕላኑ አምራች በመሆኑ ደህንነነቱ የተጠበቀ ነው እንደሚል ይጠበቃል፡፡ለአውሮፕላኑ ፈቃድ ለማገኘትም በተቆጣጣሪው አካል በኩል ማለፋቸው ስማይቀር ይህን ለማለት የራሳቸው ምክኒያ ሊኖራቸው ይችላል፤ ነገር ግን አዲስ አውሮፕላኖች፤ በአምስት ወራት ውስጥ፤ በተለያየ የዓለም ክፍል ውስጥ ፤ ሁለት ከፍተኛ አደጋዎች ማሰተናገዳቸውን ስናይ አውሮፕላኑን ለማገዳችን በጣም በቂ የሆነ ማብራሪያ መስጠት ይችላል" • ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል ዋና ስራ አስፈጻሚሚው የኢንዶኔዥያው ላየን ኤይር አውሮፕላን ከተከሰከሰ በኋላ ቦይንግ አገዳውን ለመከላከል ያስችላል ያለውን መመሪያ ማስተለፉንና አየር መንገዱም ይህንኑ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጉን ነው የገለፁት፡፡ "በዛ መሰረት አብራሪዎቻችንን አሰልጥነናል፤ መመሪያውንም በሁሉም የስልጠናና የስራ ማስኬጃዎቻችን ላይ አካተናል፤ ነገር ግን ይህ በቂ የነበረ አይመስልም" አየር መንገዱ የተከሰከሰውን የአውሮፕላን ዓይነት ለመግዛት እቅድ እንደነበረው የገለጹት አቶ ተወለደ አሁን ግን የአደጋ መርማሪ ቡድኑ ሪፖርት እስሚወጣ ድረስ እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡ "አሁን መልስ ያላገኘንላቸው በጣም ብዙ ጥያቄዎች አሉን ፤ ነገር ግን ምላሽ ሊያገኙ የሚችሉት ከምርመራው ብቻ ነው ። እሰከዚያም ቢሆን ለቅድመ ጥንቃቄ ሲባል አውሮፕላኑ ላይ እገዳ እንዲጣል እመክራሁ"
49041904
https://www.bbc.com/amharic/49041904
ከሐዋሳ ተነስቶ በሌሎች አካባቢዎች ጉዳት ያደረሰው ሁከት
ትናንት ሐዋሳ ውስጥ ከተቀሰቀሰው ግርግር ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት አብቅቶ ዛሬ አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ።
በሐዋሳ ከተማ ውስጥ የጸጥታው ስጋት እንዳለ ቢሆንም በዛሬው እለት አንዳንድ የንግድ ተቋማት መከፈታቸውንና የተወሰኑ ባጃጆች በመንገዶች ላይ እንደሚታዩ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከትናት ጀምሮ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን የዋይፋይ ኢንትርኔት አገልግሎትም መቋረጡን በከተማዋ ከሚገኙ ሁለት ሆቴሎች ለማረጋገጥ ችለናል። የተፈጠረውን ችግር ተከትሎም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው መታሰራቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የከተማዋ ፖሊስ አባል፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ትናንትና ማታ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ወጣቶችን ለማስፈታት ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ የተናገሩት አንድ የሀገር ሽማግሌ ትናንት ከነበረው የተሻለ ሰላም በከተማዋ እንደሚታይ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር በከተማዋ ውስጥ ከወትሮው በተለየ የተሰማሩት የክልሉ ልዩ ኃይል፣ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት በብዛት እንደሚገኝ የተናገሩት ነዋሪዎች ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን አልሸሸጉም። • በሐዋሳ ለግርግሩ ተጠያቂ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸው ተገለፀ ክስተቱ ከሐዋሳ ከተማ ባሻገር በሌሎች ቦታዎችም ጉዳትን አስከትሏል። ከእነዚህም መካከል ይርጋለም፣ አለታወንዶ፣ በንሳና ለኩ አካባቢዎች ችግር እንደነበረ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በንግድ ሥራ ለረዥም ዓመት በአለታ ወንዶ ይተዳደሩ የነበሩ አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ትናንትና ከተማዋ ላይ የተፈጠረውን ሲያስረዱ "አላታ ወንዶ የሆነውን አይደለም ተነግሮ በቪዲዮ ብታየው አታምነውም" ይላሉ። በአለታወንዶ በተለምዶው አረብ ሰፈር በሚባለው አካባቢ በሚገኙ የጣቃ ጨርቅ መሸጫ ሱቆች ላይ እንዲሁም ታእዋን ሰፈርና መናኽሪያ አካባቢ የሚገኙ ሱቆች እንዲሁም ከመናኽሪያ ጀርባ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች መውደማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። እርሳቸው እንደሚሉት ከከተማዋ አጎራባች ቀበሌ የመጡ ወጣቶች ከተወሰኑ የከተማዋ ወጣቶች ጋር አንድ ላይ በመሆን የነጋዴዎችን የስም ዝርዝር ይዘው ንግድ ቤታቸውና መኖሪያ ቤታቸው ላይ ጥቃት አድርሰዋል ይላሉ። ግለሰቡ አክለውም የተደበደበ ወይንም የሞተ ሰው መኖሩን ባያውቁም እያንዳንዱ ከሌላ አካባቢ የመጣ ነጋዴ ቤትና የንግድ ስፍራ እየተገባ ንብረቱ፣ ገንዘቡ እየወጣ ሲቃጠል እንደተመለከቱ ተናግረዋል። ወጣቶቹ ንብረት ከማቃጠል ውጪ ዘረፋ እንዳልፈጸሙ ገልፀው በከተማዋ አሉ የሚባሉ ንግድ ቤቶች ላይ በአጠቃላይ ጉዳት መድረሱን አብራርተዋል። የአስናቀ ገብረኪዳን ሆቴል የመኝታ ክፍሎችና የግለሰቡ መኪና መቃጠሉን እንዲሁም በተለምዶ ታይዋን የሚባለው አካባቢ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ንብረት በአጠቃላይ መቃጠሉን ይናገራሉ። የከተማዋ ወጣቶች ከቀኑ አራት ሰዓት ጀምረው ንብረት ማውደም መጀመራቸውን በማስታወስ ቀኑን ሙሉ የከተማዋ ፖሊስ ምንም እንዳልረዳቸው በምሬት ያስረዳሉ። ማታ ተኩስ እንደነበርና ዛሬ ማለዳ ግን የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት ወደከተማዋ መግባቱን፣ የከተማዋ እንቅስቃሴም ሙሉ በሙሉ መገታቱን ገልጸው፤ የከተማዋ ፖሊስም እየተዘዋወረ ሰዎች ከቤት እንዳይወጡ እያሳሰበ እንዳለ ተናግረዋል። የአለታወንዶ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍሬው ዓለሙ ትንናት በከተማዋ አለመረጋጋት ተከስቶ እንደነበር ለቢቢሲ አረጋግጠው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመድረሱንና ዛሬ የመከላከያ ሠራዊት ስለገባ ዛሬ ከተማዋ በአንጻራዊነት ሰላም መሆኗን ገልፀዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አንድ የይርጋለም ነዋሪ ከተማዋ ትላንት ከረፋድ ጀምሮ ሰላም እንደራቃት ተናግረዋል። "ትላንት ከአራት ሰዓት በኋላ ነገሮች ቀስ በቀስ እየተለወጡ መጡ፤ ሰዎች ተደብድበዋል፣ የተዘረፉና የተቃጠሉ ቤቶች አሉ፣ ሁለት የከተማ አስተዳደር መኪናዎችና አንድ የዱቄት ፋብሪካም ተቃጥሏል" ሲል የተፈጠረውን ገልጿል። • በሐዋሳ ውጥረት ነግሷል ተባለ በይርጋለም ከተማ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ደኢህዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ባጢሶ ባቲሶ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በከተማው ከትናንት ማለዳ ጀምሮ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አረጋግጠዋል። በዚህም አራዳ በሚባል አካባቢ የሰባት ግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች፣ በሌላ ስፍራ ደግሞ ሦስት ቤቶች መቃጠላቸውን፣ የዱቄት ፋብሪካ መቃጠሉን፣ የከንቲባውና የድርጅት ጽህፈት ቤቱ መኪኖች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት መኪና፣ የአረጋሽ ሎጅ ሦስት መኪኖች መቃጠላቸውን ጨምረው ተናግረዋል። ዛሬ ረብሻ ባይኖርም ውጥረቱ እንዳልረገበ ያነጋገርነው ነዋሪ ተናግሯል። አክሎም በከተማዋ ውስጥ የመከላከያ ሠራዊት እንደሚገኝም ገልጿል። በከተማዋ ውስጥ የመጓጓዣ አገልግሎት ካለመኖሩ ባሻገር የንግድ ተቋማትም መዘጋታቸውን ነዋሪው የተናገረ ሲሆን፤ "ባንክ ዝግ ነው፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም እንደተዘጉ ናቸው" ብሏል። ትላናት በነበረው ተቃውሞ አንድ ሰው መሞቱ እና ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን መስማቱም ነዋሪው ገልጿል። የሞተው ግለሰብ የተቃውሞው አካል የነበረ ሳይሆን ለንግድ ከገጠር ወደ ከተማ የሄደ ሰው መሆኑንም አክሏል። ስጋት ያጠላበት የሲዳማ የክልልነት ጥያቄና የሀዋሳ ክራሞት ለዓመታት ሲንከባለል የመጣው የክልልነት ጥያቄ ሐምሌ 11/ 2011 ዓ. ም ምላሽ ያገኛል ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅትና የሃገር ሽማግሌዎች ከመንግሥት ጋር ሲደራደሩ ቆይተው ሳለ ምርጫ ቦርድ፣ የክልሉ ፕሬዝዳንትና የዞኑ አስተዳዳሪ በስተመጨረሻ የሰጡት መግለጫ የፈጠረው ፍጥጫ የግጭቱ መንስኤ እንደሆነ ነዋሪው ተናግሯል። ነዋሪው እንዳለው፤ ትላንት "ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ይከበር"፣ "መንግሥት ለጥያቄያችን መልስ ይስጥ" የሚሉ መፈክሮች ወደ ጉዳና ከወጡት ሰልፈኞች ይሰሙ ነበር። የድርጅት ኃላፊው በግጭቱ ከገጠር ቀበሌ የመጣ ነው የተባለ ግለሰብ ከፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መሞቱን አረጋግጠው አስክሬኑ ወደ መኖሪያ አካባቢው መሸኘቱንም ጨምረው አረጋግጠዋል። በከተማዋ ቤት ንብረታቸው የተቃጠለባቸው ከሌላ አካባቢ የመጡ ሰዎች ናቸው ይባልል ተብለው ማብራሪያ የተጠይቀው ሲመልሱ፤ ንብረታቸው ያልተነካባቸው የሌላ ብሔር ተወላጆች መኖራቸውን የሚናገሩት አቶ ባጢሶ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ሰዎች ክልል እንዳይሰጠን ያደረጉ ሰዎች ናቸው የሚሉ ሰዎች መኖራቸውን መስማታቸውን ተናግረው በርግጥም ጥቃት አድራሾቹ መርጠው ማቃጠላቸውን ተናግረዋል። ከትናንትና ማታ ጀምሮ ወደ ከተማው ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል መግባቱን የተናገሩት ኃላፊው ትናንት ጥፋት ካደረሱ ወጣቶች መካከል የተያዙ ስለመኖራቸው እንደማያውቁ ተናግረዋል። • ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው? ከሐዋሳ እስከ ዲላ ያለው አንዲሁም እስከ አለታ ወንዶ የሚወስደው መንገድም ስለተዘጋ የመከላከያ ሠራዊት አንደልብ መንቀሳቀስ አልቻለም ያሉት ደግሞ የከተማው ነዋሪ ናቸው። የድርጅት ኃላፊውም መንገዶች ዝግ መሆናቸውን አልሸሸጉም። "ይርጋለም ዛሬ በአንፃራዊነት ሰላም ናት" ያሉት ኃላፊው ከገጠር ከተሞች ወደ ከተማዋ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመከላከያና ከቀበሌ አስተዳደሮች ጋር በመነጋገር ለጊዜው መገታታቸውን ገልጠዋል። በአጠቃላይ በሲዳማ ዞን ስላለው ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የደወልንላቸው የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በሥራ መደራረብ ምክንያት ለጥያቄያችን ምላሽ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጠውልናል። በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ሁከት መጠኑ በውል ያልታወቀ ንብረት መውደሙን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችና የአካባቢ ባለስልታናት ያረጋገጡ ሲሆን በሰው ላይ ደረሰን ጉዳት በተመለከተ አሃዞች ከተለያዩ ወገኖች እየወጡ ቢሆንም ለማረጋገጥ አዳጋች ሆኗል።
54297292
https://www.bbc.com/amharic/54297292
ዶናልድ ትራምፕ፡ "አሜሪካ የዓለም ጤና ድርጅትን ጥላ የምትወጣበት በቂ ምክንያት የላትም" ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት መውጣቷን በማስመልከት፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ጥሎ ለመውጣት በቂ ምክንያት የላቸውም" ሲሉ የድርጅቱ የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ተናገሩ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነቷ መውጣቷን ያስታወቁት በግንቦት ወር ሲሆን፣ ድርጅቱን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ቻይናን ተጠያቂ ማድረግ ተስኖታል የሚል ስሞታ ያሰሙ ነበር። ከታይም መጽሔት ጋር በነበራቸው ቆይታ " እውነቱን ለመናገር በመጀመሪያ አላመንኩም ነበር" ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም " አሁንም ቢሆን የአሜሪካ አስተዳደር ከዓለም ጤና ድርጅት ጥሎ ለመውጣት በቂ ምክንያት የለውም ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። በ2019 አሜሪካ የዓለም ጤና ድርጅትን አጠቃላይ በጀት 15.18% በመቶ ትሸፍን ነበር። ይህም ከፍተኛ መዋጮ ከሚያዋጡ አገሮች መካከል ብቸኛው ያደርጋታል። ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴድሮስ የኮቪድ-19 ክትባት ተገኝቶ ክፍፍል ሲጀመር ዳግም አሜሪካ ያላት ትብብር ይሻሻላል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። "ክትባትን ማከፋፈል ላይ አሁን የምንከተለው መሰረታዊው መርሆ፣ በተወሰኑ አገራት ለሁሉም ሰዎች ሳይሆን፣ በሁሉም አገራት ለተወሰኑ ሰዎች ክትባቱን መስጠት ነው።" ብለዋል።
45726550
https://www.bbc.com/amharic/45726550
አቶ ጌታቸው አሰፋ የሀዋሳውን ጉባኤ ይታደማሉ?
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ያደርጋል። አራቱ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶችም ከድርጅታዊ ጉባኤው በፊት የፓርቲዎቻቸውን ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበር፣ የማዕከላዊ እና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን አካሂደዋል።
የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) መጠሪያውን ወደ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) በተመሳሳይ መልኩ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ደግሞ ወደ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) መቀየራቸው ይታወሳል። ሁለቱ ፓርቲዎች ከስማቸው ባሻገር የአርማ ለውጥም አድርገዋል። በሌላ በኩል ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የቀድሞ ስማቸውን እና አርማቸውን ይዘው ቀጥለዋል። • አቶ መላኩና ጄነራል አሳምነው ለማዕከላዊ ኮሚቴ ተመረጡ • «አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7 • «ማስተር ፕላኑ ተመልሶ ይመጣል» አቶ ኩማ ደመቅሳ ኦዴፓ፣ አዴፓ እና ዴኢህዴን በርካታ የቀድሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎቻቸውን በአዲስ እና ወጣት አባሎች ተክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ህውሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አድርጎ የመረጣቸው ግለሰቦች ነባር እና ከሞላ ጎደል የድርጅቱ ታጋዮች መሆናቸው አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል። በተለይ ደግሞ የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ ከዐሥራ አንዱ የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ ሆነው መመረጣቸው ብዙዎች ህወሓት ከለውጡ ራሱን ገሽሽ እያደረገ ስለመሆኑ እንደ አንድ ማሳያ አድርገው ወስደውታል። ለመኾኑ አቶ ጌታቸው አሰፋ ወደ ሥራ አስፈጻሚ መምጣታቸው አሁን ባለው የለውጥ አውድ ምን ፖለቲካዊ ትርጉም ይሰጣል? በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የህወሓት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የነበሩትን አቶ ጌታቸው ረዳን በስልክ አነጋግረናቸው ነበር። ''ጌታቸው አሰፋ ጎበዝ መሪ መሆኑን አውቃለሁ። ጎበዝ ኢህአዴግ መሆኑን አውቃለሁ። ጎበዝ ህወሓት መሆኑን አውቃለሁ። ህወሓት ሲወስን በሚዲያ ሃሜት ላይ ተመሥርቶ አይደለም የሚወስነው'' በማለት በቀድሞው የደኅንነት ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ የሚቀርቡ ወቀሳዎችን አጣጥለዋል። አቶ ጌታቸው ጨምረውም ''ይፋዊ መግለጫ ሳይኖር ሚዲያዎች ሃሜት ሲያወሩ ነበር። ሃሜት ላይ ተወስነን ውሳኔ የምናስተላልፍ ቢሆን ኖሮ ሃገር ይጠፋል። ክስ ስለመመስረቱም የማውቀው ነገር የለም። አቶ ጌታቸው አሰፋን ፈልጎ ህውሓት ጋር የመጣ አካል የለም።'' በማለት አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይ ክስ አለመመሥረቱን አመላክተዋል። አቶ ጌታቸው አያይዘው እንደሚሉት ከሆነ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ የመመረጥ ፍላጎት አልነበራቸውም። ''ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ መግባትም አልፈለገም፤ ሲሪየስሊ [አጥብቆ] ነው የተከራከረው። ጉባኤው ግን ከማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እንዲገባ ወሰነ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ውስጥ መግባት አለበት ብሎ ወሰነ።'' ይላሉ አቶ ጌታቸው ረዳ። "አቶ ጌታቸው አሰፋ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀዋሳ ይሄዳሉ ወይ?" ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ ጌታቸው ረዳ ሲመልሱ ''የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በጉባኤው እንዲሳተፍ ይጠበቃል። እንደማንኛው የኮሚቴ አባል ሀዋሳ ላይ ልታይዋቸው ትችላላችሁ። እንደማንኛውም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ተሳትፎ ማድረግ ስላለብን አንዳንዶቻችን ያው መንገድ ላይ ነን። ለምሳሌ አውሮፕላን ካመለጠኝ ልቀር እችላለሁ'' ብለዋል። ይህ አገላለጽ 'አቶ ጌታቸው አሰፋ ላይገኙ ይችላሉ' የሚለውን ያመላክት እንደሆነ ከቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ፣"እኔ የእያንዳንዱ ሰው ስኬጁል አላወጣም። ሁላችንም ተበትነን ነው ወደ ሀዋሳ እየሄድን ያለነው፤ ጌታቸውም በራሱ ጊዜ ስኬጁሉን አሬንጅ ያደርጋል፤ ካገኘሁት እነግራችኋለሁ" ሲሉ በቀልድ የታጀበ ምላሽ ሰጥተዋል። ነገ በሚጀመረው የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ማን ሊሆን ይችላል ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ''አሁን ያሉት ሊቀ መንበር ላለፉት 5 ወይም 6 ወራት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። እስካሁን የሠሩት ሥራ ተገምግሞ ለውጥ ማድረግ ያስፈልገናል ወይስ አያስፈልገንም የሚለው የጉባኤው ውሳኔ ነው የሚሆነው'' በማለት መልሰዋል። ህወሓት ማንን በእጩነት ለማቅረብ እንደተሰናዳ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲዎች እንደማይመርጡ አስረድተዋል። ''ህወሓት፣ ብአዴን ወይም ኦህዴድ ዕጩዎችን አያቀርቡም። ፓርቲዎች አይደሉም ዕጩዎችን የሚጠቁሙት። ከ180ዎቹ የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ግለሰቦችን ለሊቀ መንበርነት ለጉባኤው ጥቆማዎችን ይሰጣሉ። ከዚያም ምርጫ ይካሄዳል። ድምጽ ያገኘ ያሸንፋል።'' ብለዋል። በግንባሩ ጉባኤ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፤ ''የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ አፈጻጸም ላይ መቀዛቀዝ ይታያል። ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት እሱን እንዴት አድርገን ነው በፍጥነት የምናስቀጥለው የሚለው ትልቁ አጀንዳ ነው። ወደ ሃገር እንዲገቡ የተደረጉ ተፎካካሪ፣ ተቃዋሚ የሚባሉ ፓርቲዎች ወደ ሃገር ከገቡ በኋላ አንዳንዱ 'አሸንፌ ነው የመጣሁት' ይላል። ሌላኛው 'ወደሽ ሳይሆን ተገደሽ ነው የተቀበልሺኝ' ይላል። ይህ ዓይነት ስሜት የሚፈጥረው የሰላም እና የመረጋጋት ዝብርቅርቅ አለ። ይህን ለመሰሉ ጉዳዮች ጉባኤው ምላሽ ይሰጣል። ይህ የሁላችንም አጀንዳ ነው'' ብለዋል።
news-55458663
https://www.bbc.com/amharic/news-55458663
በተስፋ መቁረጥና በስጋት ውስጥ የሚገኙት የኢትዮ-ሱዳን ድንበር አርሶ አደሮች
በምዕራብ ጎንደር ዞን በተለይም መተማና ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች የሱዳን ወታደሮች ዘልቀው በመግባት በአርሶ አደር ማሳዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውንና ሰዎች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናትና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለቢበሲ እንደተናገሩት 200 የሚደርሱ አርሶ አደሮች ንብረት የወደመባቸው ሲሆን ከ1700 በላይ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል። የሱዳን የማስታወቂያ ሚንስትር ፋይሳል ሳሊህ የአገራቸው ወታደሮች በሁለቱ አገራት አዋሳኝ የድንበር አካባቢ በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ተይዞ የቆየ ነው ካሉት መሬት ውስጥ አብዛኛውን መቆጣጠራቸውን ባለፈው ቅዳሜ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በዚህ የድንበር ላይ ፍጥጫ ሳቢያ ጉዳት ከደረሰባቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች መካከል የተወሰኑትን ስለገጠማቸው ሁኔታ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በመተማ ወረዳ 400 ሄክታር የሚሆን የእርሻ መሬትን በመውሰድ ሲያለሙ መቆየታቸውን የሚናገሩት አቶ ከሰተ ውበቱ፤ በስፍራው ከ12 ዓመት በላይ የግብርና ሥራ ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ይናገራሉ። ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ግን "የሱዳን ወታደሮች ወደ እኔ እርሻ አካባቢ እየመጡ አልፎ አልፎ ጥቃት ያደርሱ ነበር" የሚሉት አቶ ከሰተ፤ በዚሁ ምክንያትም ከእርሻ ሥራ ለተወሰነ ጊዜ ወጥተው ነበር። ነገር ግን ሥራቸውን ማቆማቸውን የተገነዘበው የአካባቢው አስተዳደር ወደ እርሻ ልማታቸው መመለስ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ተከትሎ "ወደ ቦታዬ ተመልሼ በመግባት ማረስ ጀምሬ ነበር" ይላሉ። ይሁንና በተለያዩ ጊዜያት የሱዳን ወታደሮች በአካባቢው የሚሰማሩ የቀን ሠራተኞችን እያባረሩ በማስቸገራቸው፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በስፍራው እንዲሰፍር ተደርጎ የግብርና ሥራቸውን ማከናወን እንደቻሉ ገልጸዋል። ጥቅምት 29/2013 ዓ.ም ጠዋት ግን፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአካባቢው መውጣቱን ተከትሎ ማታ እነሱ [የሱዳን ወታደሮች] መምጣታቸውንና እርሳቸው "ወረራ" ያሉት ክስተት መጀመሩን አስረድተዋል። "በዘጠኝ መኪና ነው ተጭነው የመጡት" የሚሉት አቶ ከሰተ፣ "መትረየስ የጫኑ መኪኖች፣ ከኋላ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎችን [ሱዳናውያን] በማስከተል በእርሻ ቦታችን ላይ ወረራ ፈጸሙብን" ይላሉ። አቶ ከሰተ በማሳቸው ላይ ሱፍ፣ ጥጥ እና ሰሊጥ ዘርተው እንደነበርና ሁሉም ለመሰብሰብ ደረሰው እንደነበር በመጥቀስ ለጥቃቱ የተሰማሩት "የቻሉትን እየሰበሰቡ ጭነው በመውሰድ ቀሪውን በማቃጠል አውድመውታል" ብለዋል። "በማሳ ላይ እየሰራን እንዳለ እየተኮሱ መጡብን። ከዚያ የተወሰነ ለመከላከል ብንሞክርም አቅም ስላጣን ሁሉንም ነገር ጥለን ወጣን" ብለዋል። በተለምዶ የሁለቱ አገራት ድንበር ጓንግ ወንዝ ቢሆንም አሁን ግን ያንን ተሻግረው ወረራ መፈጸሙን ገልጸዋል። "ቢያንስ የ3 ሰዓት የእግር ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ተጉዘው ነው ወረራ የፈጸሙብንም" ብለዋል። አቶ ከሰተ በተወሰነው የማሳቸው ክፍል ላይ በአማካይ እስከ 500 ኩንታል ሰሊጥና እስከ 200 ኩንታል ማሽላ ያመርቱበት እንደነበር ገልጸዋል። የእርሻ ሥራውን "ተበድሬ ነበር የምሰራው፣ አሁን ግን ይህ አደጋ በመከሰቱ እንኳን ለማትረፍ ብድሬንም ለመክፈል ተቸግሬያለሁ፣ በዛሬው ዕለት ራሱ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ብድርህን የማትመልስ ከሆነ ቤትህ ይሸጣል የሚል ማስታወቂያ ቤቴ ላይ ለጥፈው ሂደዋል" በማለት ያሉበትን ሁኔታ አስረድተዋል። አክለውም "አሁን ባደረግኩት ማጣራት 89 ኩንታል ሰሊጥ፣ በርካታ የሱፍና ጥጥ ምርት ወስደውብኛል" ብለዋል። በአሁኑ ገበያ የአንድ ኩንታል ሰሊጥ ዋጋ 5 ሺህ ብር አካባቢ ደርሷል ያሉት አቶ ከሰተ፣ ይህም 450 ሺህ ብር አካባቢ እንደሚገመት ገልጸዋል። በተጨማሪም "ማሳውን ስናሰራው የነበረው በቀን ሰራተኛ ነበር፤ ነገር ግን ደመወዛቸውን መክፈል ባለመቻላችን እስከ 250 የሚደርሱ ሠራተኞችን አሰርተን አሁን እየከሰሱን ነው" ብለዋል። ሌላኛው በዚሁ ወረዳ [መተማ] ደለሎ በሚባል የእርሻ ቦታ ጉዳት ከደረሰባቸው አርሶ አደሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ይበይን ይባላሉ። በክረምቱ ወቅት የጸጥታ አካል አብሮን በመኖሩ ምንም ጉዳት አልደረሰብንም፤ "ነገር ግን ጦሩ አካባቢውን ለቅቆ ወደ ትግራይ መሄዱን ተከትሎ የሱዳን ወታደር ተከታትሎ መጥቷል" ብለዋል። ወታደሩን ተከትለው ደግሞ በቅርብ የሚገኙ ሁለት የሱዳን ከተማ ነዋሪዎች በመምጣት ዘረፋና ውድመት መፈጸማቸውን ገልጸዋል። የሱዳን ወታደሮች ወደ አካባቢው ሲገቡ ጥቃት እየፈጸሙ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ይበይን፣ በዚሁ የተኩስ ልውውጥም "ሁለት የጉልበት ሠራተኞች ተገድለውብኛል፣ ሌሎች ሁለት ሠራተኞች ደግሞ በከባድ ተጎድተውብኛል" ብለዋል። ከእዚህም በተጨማሪ በርካታ የካምፕ ቁሳቁስ አውድመዋል የሚሉት አቶ ይበይን፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ምርት ጭነው ሲወስዱ ቀሪውን ደግሞ አውድመውታል ብለዋል። አርሶ አደሩ አቶ ይበይን በዘንድሮው የእርሻ ዘመን ሙሉውን ማሳቸውን የማሽላ ሰብል ዘርተው እንደነበርና ከእዚህ ውስጥም አብዛኛው እንደተወሰደ ቀሪውም እንደወደመ በመግለጽ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብና ንበረት ኪሳራ እንደደረሰባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነገር ግን አካባቢው ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ የሱዳን ወታደሮች በሁሉም ቦታዎች በቋሚነት ሰፍረው አይቀመጡም የሚሉት አቶ ይበይን፤ ሰሞኑን ድጋሚ ወደ ማሳቸው በመሄድ 400 ኩንታል ያህል ማሽላ ለመሰብሰብ መቻላቸውን ይገልጻሉ። ይህንን ማሳ ከ15 ዓመት በላይ እንዳረሱት የተናገሩት አቶ ይበይን፣ በአማካይ በዓመት በብር ደረጃ ሲተመን ከ3 እስከ 4 ሚሊዮን ብር ከወጭ ቀሪ ያገኙበት እንደነበር ገልፀው፤ በተፈጸመው ጥቃት ሳቢያ በዚህ ዓመት ከባድ ኪሳራ እንደገጠማቸው አመልክተዋል። ሙላት ነጋሽ ነዋሪነታቸው ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት የድንበር አካባቢ በምትገኘው ምድረ ገነት ውስጥ ሲሆን በግብርናው ዘርፍ ተሠማርተው ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። አሁን ግን የሱዳን ጦር የኢንቨስትመንት ቀጣና ወደሚባለው የምዕራብ አርማጭሆ በጣም ሰፊ ቦታ ላይ በመግባት ከማሳቸው እንዳፈናቀላቸው ይናገራሉ። በአካባቢው የነበረው የመንግሥት ሠራዊት ወደ ትግራይ ክልል ለሌላ ተልዕኮ መሰማራቱን ተከትሎ፣ የድንብር አካባቢውን ለቅቆ ሲሄድ ቀጠናው ክፍት መሆኑን ተከትሎ፣ የሱዳን ኃይሎች ሰፊ የግብርና ልማት ወደሚካሄድበት ቦታ ዘልቀው መግባታቸውን አስታውቀዋል። "አብዛኛው በአካባቢው በግብርና ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው ሰው ከሥራ ውጪ ሆኗል። ማሽላውንም እየጫኑት ነው። ቁጥራቸው በምዕራብ አርማጭሆ ከ200 በላይ፣ በመተማ ደግሞ ቁጥሩን [በትክክል ባላውቀውም] እስከ 50 ገበሬዎች ተፈናቅለዋል። በኢንቨስተመንት ቀጠናዎች መኪናና የእርሻ መሣሪያ የተወሰደባቸው አሉ" ብለዋል ለቢቢሲ። "ሉግዲ አካባቢ ወደ ስምንት ኮምባይነር [ማጨጃ ማሽን] አስገብተው ነበር። ኃይላቸው ከፍ ስላለ መግባት አልቻልንም። ኮምባይነሩ ትልቅ ጉልበት ስላለው ማሳ ላይ ያለውን ማሽላ ለመውሰድ በስፋት እየሰበሰቡ ነው" ብለዋል። በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ምድረ ገነት ከተማ አስተዳደር ውስጥ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፋሲል አሻግሬም "የሱዳን ጦር ወደ ድንበር ገብቷል። እነሱ ተጠናክረው ስለመጡ በተኩስ ለመቋቋም አልተቻለም። ኮምባይነር ይዘው መጥተው ምርቱን ሰብስበው እየጫኑ ነው። ቆርጠን የከመርነውን ሁሉ እየጫኑ ሲሆን አካባቢያችንን በሙሉ ተቆጣጥረውታል" ሲሉ ያለውን ሁኔታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በማሳ ላይ ካለው ሰብል በተጨማሪ ለግብርና ሥራው የሚውሉ ንበረቶችንና የተለያዩ የእርሻ መሣሪያዎችን መውሰዳቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። "እኛ ቁጭ ብለናል። እጅ እና እግራችን ታስሮ ምን እናድርግ? ምን አቅም አለን? መንግሥት አዝመራው ተዘርፎ ሳያለቅ ይድረስልን ብንልም መልስ የለም። እኛ ከሞትን ደግሞ የምናመጣው ለውጥ የለም" ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል። "መንግሥት ትንሽ ትንሽ ኃይል ያቀርባል። ይህም መከላከል ብቻ ነው የሚሠራው። አገር አደጋ ላይ ነች። ለእኔ ሳይሆን አገር እንደ አገር በከፋ አደጋ ላይ ነች። ከ200 በላይ ገበሬ ተዘርፏል" ብለዋል። የሱዳኑ የማስታወቂያ ሚንስትር ፋይሳል ሳሊህ የአገራቸው ወታደሮች በድንበር አካባቢ በኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ተይዞ ከሚገኘው መሬት ውስጥ "በአሁኑ ጊዜ ከ60 አስከ 70 በመቶ የሚሆነውን የሱዳን መሬትን መልሶ ይዟል" በማለት ከቀናት በፊት ለሮይተርስ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ጨምረውም "ማንኛውም ችግር በውይይት ይፈታል ብለን እናምናለን" ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲም በአዋሳኝ የድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመቅረፍ የተጀመረውን ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። ለረጅም ጊዜ ሁለቱን አገራት ሲያወዛግብ የቆየው የድንበር አካባቢን በተመለከተ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ የሚያስችል ኮሚሽን ተቋቁሞ ካርቱምና አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ውይይት ቢያደርግም ሁለቱንም የሚያስማማ ውጤት ላይ ሳይደረስ ቆይቷል።
news-52308072
https://www.bbc.com/amharic/news-52308072
ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት ድርጅት ሥራው በትክክል ምንድነው? አገሮችንስ የማዘዝ ሥልጣን አለው?
ዶናልድ ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅትን ኮንነዋል። ሁለተኛ ገንዘብ አንሰጠውም ብለዋል። እንደ ትራምፕ አስተያየት ድርጅቱ አፍቃሪ-ቻይና ሆኗል፤ ኃላፊነቱንም በአግባቡ አልተወጣም።
ለመሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊነት ምንድነው? አገራትን ይህን አድርጉ፣ ያን አታድርጉ ብሎ የማዘዝስ ሥልጣንስ አለው? ማማከር እንጂ ማዘዝ አይችልም ስዊዘርላንድ ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አሉባት። ከነዚህ ውስጥ ሲሶው በጄኔቫ ነው የሚገኙት። የዓለም ጤና ድርጅት ገና ወደ ቅጥር ሲገባ አረንጓዴና ማራኪ ነው። በየትኛው የግቢው ክፍል ማጨስ አይፈቀድም። ወደ እንግዳ መቀበያው አዳራሽ ሲዘልቁ የሚያገኙት ብን ብን የሚሉ ባንዲራዎችን ነው፤ ለዓይን ይማርካሉ። ከኮርኒሱ ቁልቁል የሚወርዱት 194 ባንዲራዎች ንፋስ ያወዛውዛቸዋል። ከነዚህ መሀል የአሜሪካ ባንዲራ የመውረጃው ጊዜ ተቃርቦ ይሆናል። ይህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካል የሆነው መሥሪያ ቤት የተመሰረተው በ1948 ነው። ራሱን "የዓለም ማኅበረሰብ የጤና ዘብ" ሲል ይጠራል። ዋንኛ ግቡ የሰው ልጆች ሊያገኙት የሚገባውን የመጨረሻ የጤና ደረጃ እንዲያገኙት መትጋት ነው። ትልቅ ኃላፊነት ይመስላል። የ72 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ የሆነው የዓለም ጤና ድርጅት ባለፉት 11 ዓመታት ብቻ 6 ለዓለም ሥጋት የሆኑ ወረርሽኞችን በመቆጣጠር የተሳካ ሥራን ሠርቷል። ከነዚህ ውስጥ በምዕራብ አፍሪካ በ2014 የተቀሰቀሰው ኢቦላ፣ ከሁለት ዓመት በፊት የተነሳው ዚካ ቫይረስ እና አሁን ደግሞ በቻይና ዉሃን ከተማ የተነሳው ኮቪድ-19 ይጠቀሳሉ። የዓለም ጤና ድርጅት፡- በሽታዎች ወደተቀሰቀሱባቸው ሥፍራዎች ባለሞያዎችን ፈጥኖ ይልካል፤ መረጃ ይሰበስባል፤ ያጠናቅራል። ከነዚህ ጥቅል የወል ተግባራቱ ባሻገር ድርጅቱ ፡- ከዚህ በኋላ ነው ትልቁ ጥያቄ የሚነሳው። ለመሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት አገራትን የማስገደድ፣ መመሪያዎቹን እንዲፈጽሙ የማዘዝ ጉልበትና ሥልጣን አለውን? መልሱ የለውም ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ሥራው ማማከር ነው፤ ማገዝና መደገፍ ነው። ማዘዝ አይደለም። ለአገሮች በጤና ዙርያ ሐሳብ አስተያየት ይሰጣል፤ አቅጣጫ ያስቀምጣል፤ የዜጎቻቸውን ጤና እንዲጠብቁ ያማክራል፣ አዳዲስ ወረርሽኞች እንዳይቀሰቀሱ ያበረታል፣ ይከላከላል መረጃ ያቀባብላል እንጂ በአገራት የጤና ጉዳይ ገብቶ ይህን ለምን አደረጋችሁ/አላደረጋችሁም ብሎ የመቅጣትም ሆነ የማዘዝ መብቱ የለውም። የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ላይ ተዘናግቶ ነበር? መልሱ በመላሹ ማንነት ላይ ይወሰናል። መላሹ ዶናልድ ትራምፕ ከሆኑ ድርጅቱ የሰነፍ ሥራ ነው የሠራው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸው በወረርሽኙ መባቻ ፈዘው ነበር፣ መፍዘዝ ብቻ ሳይሆን አፊዘው ነበር፣ ማፌዝ ብቻ ሳይሆን የአሜሪካዊያንን ሕይወት ለአደጋ አስጥተው ሰጥተዋል ተብለው እየተብጠለጠሉ ነው፡፡ እነሆ በእርሳቸው መፋዘዝ 600ሺ ዜጎች በተህዋሲው ተይዘዋል፤ 30ሺ ሞተዋል ይላሉ ተቺዎቻቸው፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩትን ድርጅት በእንዝላልነትና በቻይና አፍቃሪነቱ ሲወነጅሉት ነበር፡፡ ጉዳዩን በቅርበት የተከታተሉ ጋዜጠኞችና ተንታኞች ግን ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸው ቻይና ወረርሹን የተቆጣጠረችበት ፍጥነትና መንገድ አሞካሽተዋል፡፡ ይህም በትዊተር ሰሌዳቸው ዛሬም ድረስ አለ ይላሉ፡፡ ሆኖም ዶ/ር ቴድሮስ ቻይናን በማሞገሳቸው ዶናልድ ትራምፕ ዛሬም ድረስ የዓለም ጤና ድርጅትን ይወቅሳሉ፡፡ ይህ ብዙም ስሜት የሚሰጥ አይደለም፡፡ የዶናልድ ትራምፕ ከቻይና ጋር ያለባቸው ቁርሾ ፖለቲካዊ እንጂ ጤናዊ አይደለም ይላሉ፡፡ ይህን ካልን ዘንዳ የዓለም ጤና ድርጅት በኮቪድ-19 አያያዝ ጉዳይ ሲተች ትራምፕ የመጀመርያው አይደሉም፡፡ ለምሳሌ ወረርሽኙ ሲቀሰቀስ ጀምሮ መረጃ የነበራቸው የጤና ባለሞያዎችን ቻይና አፋቸውን እንዲይዙ ቅጣት ስትጥልባቸው ጭምር እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህ ብቻውን የዓለም ጤና ድርጅት ቻይናን እንዳያሞገስ ሊያደርገው አይገባም ነበር ወይ ሲሉ የሚጠይቁ አሉ፡፡ ቻይናዊያኑ የጤና ባለሞያዎቹ ስለ ወረርሽኙ የሰጡት ቅድመ ጥንቃቄ ቸል ተብሎ ሳለ እንዴት ቻይና በዓለም ጤና ድርጅት ሙገሳ ይገባታል? የድርጅቱ አለቃ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም ገብረየሱስ ግን አሁንም በአቋማቸው እንደጸኑ ነው፤ በተደጋጋሚ ቻይና ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ያደረገችው ፈጣን እርምጃ አድናቆት ይገባዋል ይላሉ፡፡ ምክንያቱም እንደ ዶ/ር ቴድሮስ አመለካከት ቻይና በሽታው ላይ ፈጣን እርምጃ በመወሰዷ ቀሪው ዓለም ለዝግጅት የሚሆን ጊዜን ገዝቷል፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረው እንደሚሉት ቻይና ከበጎ ፈቃድ ተነስታ ያለማቅማማት የተህዋሲውን ዘረመላዊ ቅንጣተ-ፍጥረት(ጄኔቲካል ኮድ) በፍጥነት ለዓለም አጋርታለች፤ ይህም አገራት ጊዜ ሳይወስዱ ክትባት የመፍጠርና ምርመራ የማድረግ ዕድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ያደረገችው ቻይና ብትደነቅ ምንድነው ክፋቱ? ዶ/ር ዴቪ ሲዳሃር በኤደንበርግ ዩኒቨርስቲ የዓለም የኅብረተሰብ ጤና ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ እርሳቸው በዶ/ር ቴድሮስ አረዳድ አይስማሙም፡፡ "ወረርሽኙ የመጀመርያ ምዕራፍ ላይ ቻይና ዘግይታለች፤ ቻይና ስኬታማ ሥራ ሰርታለች ለማለት እቸገራለሁ፤ መዘግየቶች ነበሩ፤ መጀመርያ አካባቢ እንዲያውም ነገሩን አቅለው ነበር ያዩት…" ይላሉ፡፡ ፕሮፌሰሯ በተለይ ድርጅቱ በምዕራብ አፍሪካ ለኢቦላ ወረርሽኝ ያሳየው ዳተኝነትን በተመለከተ አምርረው ሲተቹ የነበሩ ሴት ናቸው፡፡ "እርግጥ ነው ሁሉንም ችግሮች ድርጅቱ ላይ መደፍደፍ ይከብዳል፤ ምክንያቱም አገራት ሁሉ በእኩል ወረርሽኙ ለይ እንዲዘምቱ በማድረግና ሁሉንም በተመሳሳይ ደረጃ እንዲገኙ መጠበቅ ፈታኝ ነው፤ ሆኖም…" የዓለም ጤና ድርጅት ሲታሰብ ትልቁ መዘንጋት የሌለበት ነጥብ ድርጅቱ የማዘዝ ሥልጣን የሌለው መሆኑ ነው፡፡ አብዛኛው ሥራው በአባል አገራት በጎ ፈቃድ የሚመሰረት ነው፡፡ ስኬቱም በዚያው መጠን በሌሎች መልካምነት የሚለካ ነው፡፡ አብዛኛው ሚናው የጤና ዲፕሎማሲ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ዶ/ር ቴድሮስ የድርጅቱ አለቃ ስለሆኑ የቻይና መንግሥት ስለ ወረርሽኙ መረጃ እንዲያጋራ ሊያስገድዱት አይችሉም፡፡ አገራት ናቸው ወደ ድርጅቱ በፈቃዳቸው ቀርበው ሊያግዙ የሚችሉት፡፡ የኅብረተሰብ ጤና ፕሮፌሰሯ ዶ/ር ዴቪ የድርጅቱ ተቺ ቢሆኑም ዶ/ር ቴድሮስና ድርጅታቸው ያለባቸውን ውስንነት እንዲሁም አጣብቂኝ ፍንትው አድርጎ የሚገልጽ ነገር ተናግረዋል፡፡ " ዶ/ር ቴድሮስ (ትራምፕ እንደተመኙት) ቻይናን አምርረው ቢያወግዙ ኖሮ በደቂቃዎች የዓለም ጤና ድርጅት ዝናው ይናኝ ነበር፤ ሆኖም ያን ቢያደርጉ ኖሮ በኮቪድ-19 ዙርያ ለመከላከል የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ጥረት ዜሮ ያስገባው ነበር" ዶ/ር ዴቪ እንደምትለው ዶ/ር ቴድሮስ ቻይናዊያን በመጀመርያው የወረርሽኙ ምዕራፍ ስለ በሽታው የሚያውቁትን መረጃ እንዲያጋሩት ጠይቋቸዋል፤ ይህ ግን ከመጋረጃ ጀርባ የሆነ ነው የሚሆነው፡፡ "እኔ እንደሚገባኝ አንድን ነገር በይፋ በሚዲያ ፊት ማድረግና ነገሩን ከሚዲያ ጀርባ ማድረግ ልዩነት አለው፤ ለሚዲያ ፍጆታ አንድን ነገር ማድረግ ትወና ነው " ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ ከሚዲያ ጀርባ ጠንካራ ጥረት እንዳደረጉ ያላቸውን እምነት ይገልጻሉ፡፡ ድርጅቱ እንዲህ ሲብጠለጠል ዶ/ር ቴድሮስ የመጀመርያው ናቸው? የዓለም ጤና ድርጅት መብጠልጠል የጀመረው በኮቪድ-19 አይደለም፡፡ በምዕራብ አፍሪካ ኢቦላ የተነሳ ጊዜ ከዚህ በባሰ ተተችቷል፡፡ ልዩነቱ ያን ጊዜ ተቺው ዶናልድ ትራምፕ ስላልነበሩ ብዙ ሚዲያ አላራገበው ይሆናል፡፡ የ2014ቱን የኢቦላ ወረርሽኝ የዓለም ቀውስ አድርጎ ለማወጅ ድርጅቱ 5 ወራት ወስዶበታል፡፡ በ2009 ደግሞ ድርጅቱ ስዋይን ፍሉን የዓለም ወረርሽን ብሎ ለማወጅ ተጣድፏል ሲባልም ይተቻል፡፡ ምናልባት ይህ ድርጅት አገራት የውስጥ ችግሮቻቸውን የሚያላክኩበት ተቋም ሆኖ ሳይታይ አይቀርም፡፡ በእርጋታቸውና ግርማ ሞገሳቸው የሚታወቁት ዶ/ር ቴድሮስ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት "ከእንግዲህ ገንዘብ ላንሰጣች እንችላለን" ሲሏቸው፤ "ነገሩን በፖለቲካ ባንለውስ ደስ ይለኛል" ሲሉ ጤናን ለፖለቲካ ፍጆታ እንዳያውሉት መክረዋቸው ነበር፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረውም ድርጅታቸው መተቸቱን በጸጋ እንደሚቀበሉት፤ ከስህታቸው እየተማሩ ጥንካሪያቸውን እያዳበሩ ወደፊት ብቻ እንደሚመለከቱ ተናግረው ነበር፡፡ ዶ/ር ቴድሮስ ያን ሳምንት ሐሳባቸውን ሲያሳርጉ "አሁን ቅድሚያ ማሰብ ያለብን ስለ ቫይረሱ ነው" ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ የትራምፕ እርዳታ ጥንቅር ብሎ ቢቀርስ? አሜሪካ ሁነኛዋ የድርጅቱ ደጋፊ ናት፡፡ ይህ አያጠያይቅም፡፡ የትኛውም አገር የአሜሪካንን ያህል ድርጅቱን በገንዘብ አይደግፍም፡፡ አገራት የሚያዋጡት ገንዘብ የሚወሰነው በበጎ ፈቃድ፣ በሕዝብ ብዛትና በሀብት መጠናቸው ነው፡፡ በበጎ ፈቃድ ወደ ድርጅቱ ካዝና የሚገባው የገንዘብ መጠን 2.2 ቢሊዮን ዶላር ከሚጠጋው የድርጅቱ አመታዊ በጀት ትልቁን ይይዛል፡፡ ባለፈው ዓመት ለምሳሌ አሜሪካ 400 ሚሊዮን ዶላር ነበር የሰጠችው፡፡ የእንግሊዝ ዌልካም ትረስት የተባለ በጎ አድራጎት ዳይሬክተር ዶ/ር ጄርሚ ፋራር "በዚህ ወቅት ድርጅቱ ገንዘብ የሚፈልግበት ጊዜ ነበር ብለዋል፡፡ "በዘመናቸውን ትልቁን የጤና ፈተና እየተጋፈጥን ነው፤ ይህን የሚያግዝ ሌላ ዓለም አቀፍ ድርጅት የለም፤ አብረን ማገዝ በሚገባን ጊዜ መከፋፈላችን ያሳዝናል" ብለዋል ዶ/ር ጄርሚ፡፡ ፕሮፌሰር ዴቪ የአሜሪካ ገንዘብ አላዋጣም ማለት ኮቪድ-19 ብቻም ሳይሆን ወባን፣ፖሊዮን እና ሌሎች በርካታ በሽታዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዳንዋጋ የሚያደርግ ነው፡፡
news-56701293
https://www.bbc.com/amharic/news-56701293
ልዑል ፊሊፕ፡ የንግሥት ኤልዛቤት ባለቤት የኤደንብራው መስፍን ልዑል ፊሊፕ
ልዑል ፊሊፕ በግሪኳ ደሴት ኮርፉ ውስጥ እንደ አውሮፓውያኑ ሰኔ 10/1921 ነበር የተወለዱት።
የልዑሉ አባት የሄለኒስ ንጉሥ ቀዳማዊ ጆርጅ የመጨረሻ ልጅ የነበሩት የግሪክና የዴንማርክ ልዑል አንድሩ ነበሩ። እናታቸው ልዕልት አሊስ የሎርድ ልዊስ ሞንትባተን ሴት ልጅ እና የንግሥት ቪክቶሪያ የልጅ ልጅ ነበሩ።
44723896
https://www.bbc.com/amharic/44723896
ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በመደበኛ ስብሰባው ኦነግ፣ኦብነግና ግንቦት 7 ሽብርተኛ መባላቸው ይሰረዝ ዘንድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የላከለትን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከተወያየበት በኋላ አፅድቋል።
ምክር ቤቱ ከዓመታት በፊት እነዚህን የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲሁም አልቃይዳንና አልሻባብን አሸባሪ ማለቱ ይታወሳል። በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ዛሬ በ2011 ዓ.ም በጀት ላይ የተወያየ ሲሆን በነገው እለት በቀረበለት በጀት ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2011 ዓ.ም በጀት 346 ቢሊየን 915 ሚሊየን 451 ሺህ 948 ብር እንዲሆን ወስኖ ደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል።
news-50709714
https://www.bbc.com/amharic/news-50709714
የደረሰባቸውን ጥቃት በመንገድ ላይ የሚጽፉት የኬንያ ሴቶች
በአፍሪካ ዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች በጣም ትልቅ ከሚባሉት አንዱ የሆነው በኬንያ መንደር በሚገኘው 'ኪቤራ' መንደር የሚኖሩ ሴቶች ወንዶች ያደረሱባቸውን ጥቃቶች በመንገዶች ላይ እየጻፉ ነው። ማስጠንቀቂያ : አንዳንድ አንባቢዎች በዚህ ጽሁፍ ያሉ ቃላት ሊያስደነግጧቸው ይችላሉ
ዙቤይዳ ዩሱፍ በኬንያዋ ዋና ከተማ በሚገኘው ኪቤራ ሙሉ ህይወቷን ያሳለፈች ሲሆን በሴትነቷ የሚደርስ ጥቃትና መዋረድ ሁሌም አብረዋት እንዳሉ ትገልጻለች። ''ወንዶች ሁሌም በጣም ወፍራም ነሽ፤ እናትሽ ስጋ ቤት ነው እንዴ የምትሰራው? መቀመጫሽን እና ጡቶችሽን ፈጣሪ ከምንድነው ሰራቸው? በጣም ትልቅ ናቸው'' እንደሚሏት ትገልጻለች። • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና • ሳዑዲ ምግብ ቤቶች በጾታ የተለየ መግቢያ በሮችን መጠቀም የለባቸውም አለች የ 22 ዓመቷ ዙቤይዳ በኪቤራ መንደር መንገድ ላይ ለአንዲት ሴት ብቻዋን መራመድ በጣም አስፈሪ ነው ብላለች። ከጊዜ ብዛት ዙቤይዳ ስትሰደብ ዝም ብሎ ማለፍን የምትቃወም ሲሆን በኪቤራ የሚገኙ ሴቶችም መፍራት እንዲያቆሙና ድምጻቸውን እንዲያሰሙ በማበረታታት ላይ ትገኛለች። ቾክና ማርከሮችን በመጠቀም 'ቾክ ባክ' የሚል ዘመቻ የጀመረች ሲሆን ዙቤይዳ እና መሰል ሴቶች በሴትነታቸው የደረሱባቸውን መዋረዶችና ጾታዊ ጥቃቶች በመንገድ ላይ እየጻፉ ነው። ይህ ተግባርም ሰዎች ስለጉዳዩ እንዲወያዩበትና ሴቶች በነጻነት ሃሳባቸውን መግለፅ እንዲጀምሩ ያደርጋል ብለው ያስባሉ። ''አሁን አሁን ወንዶች ስድብና መሰል ነገሮች ሲናገሩኝ ቆም ብዬ እጋፈጣቸዋለሁ፤ ለምን እንደሚሰድቡኝም እጠይቃቸዋለው። ነገር ግን ለታዳጊ ሴቶች ይሄ በጣም አስፈሪ ነገር ሊሆን ይችላል።'' ''ለዚህም ነውእንደዚህ አይነት ዘመቻዎች በጣም አስፈላጊ የሆኑት። ወንዶች እንዲህ አይነት ነገር ሲናገሩ ትክክል እንዳልሆነና መብትን የሚጋፋ መሆኑን ልናሳውቃቸው ይገባል።'' ብላለች። ''ለአካሌ ክብር ይኑራችሁ" ይላል በአንድ ጥግ በኩል የተጻፈ መልእክት። በስዋሂሊ የተፃፉ ሌሎች መልእክቶች ግን ሴቶቹ የተባሉዋቸውን ነገሮች ሲሆኑ በጣም አፀያፊና አስደንጋጭም ናቸው። "ቹራ ሂ" የሚለው ሌላኛው ጽሁፍ ይታያል። በስዋሂሊ እንቁራሪት ማለት ሲሆን በወጣቶች ዘንድ ግን ሌላ ትርጉምም አለው፤ 'ሴተኛ አዳሪ' እንደማለት ነው። ካሮሊን ምዊካሊ የ 20 ዓመት ወጣት ነች፤ በኪቤራ ተወልዳ ሲሆን ያደገችው ወንዶቹ የሚናገሩት ነገር አንዳንድ ጊዜ ለቀናት ከጭንቅላቷ እንደማይጠፋና በጣም እንደሚረብሻት ገልጻለች። '' በእነዚህ መንገዶች ላይ የሆነ ወንድ መጥፎ ነገር ሳይናገረኝ አልፌ አላውቅም። አንዳንድ ጊዜ ከእንስሳት ጋር ሁሉ ሊያወዳድሩን ይችላሉ።" '' በራስ መተማነኔን በጣም ነው የሚጎዳው። ብቻዬን ቁጭ ብዬ ሳስበው ግራ ይገባኛል። ይህን ያህል የማልረባና የማልጠቅም ሰው ነኝ ግን? ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ'' ብላለች። • ፈጣን ለውጥና ጭቆና በሳኡዲ አረቢያ • በኔፓል የወር አበባ የሚያዩ ሴቶች ጽዩፍ ተደርገው ይታያሉ በያዝነው ዓመት ፕላን ኢንተርናሽናል የተባለው የተራድኦ ድርጀት ባወጣው መረጃ መሰረት የመንገድ ላይ ጥቃት ከደረሰባቸው 10 ሴቶች አንዷም እንኳን ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዳላደረገች ያሳያል። ይህም የሚሆነው ሴቶቹ ወደ ሃላፊዎች ቢሄዱ ምን ሊያደርጉላቸው እንደሚችሉ እርግጠኛ ስላልሆኑ እንደሆነ መረጃው ይጠቁማል። ሌላው ቀርቶ እንደዚህ አይነት ትንኮሳና ጥቃቶች ወንጀል መሆናቸውን እንኳን የሚያውቁት በጣም ጥቂት ናቸው። ዙቤይዳ ዩሱፍና ጓደኞቿ ያጋጠሟቸውን ስድቦችና ጥቃቶች በመንገዶች ላይ መጻፍ መጀመራቸው ደግሞ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች እየተቀየሩ እንደሚመጡና ሀሳባቸውን ለመግለጽ የሚፈሩ ሴቶች ደግሞ ድፍረት እንደሚሰጣቸው ታምኖበታል።
news-47194866
https://www.bbc.com/amharic/news-47194866
ቀራፂ በቀለ መኮንን ስለ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት ይናገራል
ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መመስረት ጉልህ ሚና ከነበራቸው መሪዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የመታሰቢያ ሐውልት በአፍሪካ ሕብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የካቲት 03/2011 ዓ.ም ተመርቋል።
ሠዓሊና ቀራፂ በቀለ መኮንን በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአፍሪካ ሕብረት አዲስ አበባ ውስጥ በሚያካሂደው 32ኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የመጡ የሃገራት መሪዎች እና የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል። የእርሳቸው ሐውልት መቆሙንም ተከትሎ በርካቶች ሲነጋገሩበት ነበር። • ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ ሐውልቱን ከቀረፁት ቀራፂያን መካከል በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱትን ሰዓሊና ቀራፂ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት መምህር የሆነውን ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንንን አነጋግረናል። ቢቢሲ፡ የቆመው ሐውልት ጃንሆይን አይመስልም የሚሉ አስተያየቶች ሲሰሙ ነበር። ለዚህ ያለህ ምላሽ ምንድን ነው? በቀለ፡ አንድ ሥራ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ብዙ ዓይነት ሃሳብ እንደሚመጣ ይጠበቃል። ሃሳቦቹ ትክክል ናቸው ማለት ግን አይቻልም፤ እኔም ሰምቻቸዋለሁ። ስለዚህ ይህንን አስተያየት የሰጡት በሙሉ ንጉሡንም ሐውልቱንም አይተዋቸው አያውቁም። ይህንን ሃሳብ ይዘው ሲጨቃጨቁ የነበሩት አንድ ተማሪ በስርቆሽ ያነሳውን የሐውልቱን ፎቶ ይዘው ነው፤ ዛሬ ላይ ሳይ ቀረብ ብለው ሐውልቱን የጎበኙ ሰዎች 'አፉ በሉን! 'እያሉ ሲለጥፉ አይቻለሁ። (ሳቅ) ፎቶ ሲነሳ ጥንቃቄና ሙያ ይጠይቃል፤ እንግዲህ ንጉሡ አልፈዋል (ሳቅ) የቢቢሲው ጋዜጠኛ ያነሳውን ፎቶግራፍ ገፃችሁ ላይ አይተው በእርሱ መዳኘት ይችላሉ። የንጉሡ ቤተሰቦችም በእያንዳንዱ ሒደት ይጎበኙት ነበር፤ አሁን ባለውም ደስተኞች ናቸው። ቢቢሲ፡ ሐውልቱን ለመሥራት እንደ ሞዴል የተጠቀማችሁት ፎቶ ግን የትኛውን ነው? በቀለ፡ ከ300 ፎቶግራፎች በላይ ከተለያዩ ቦታዎች ተሰብስበው ስናጠና ነው ቆየነው፤ ቅርፅ ለመስራት አንድ ፎቶ ብቻ መጠቀም አይቻልም፤ በእርግጥ እርሳቸውን መግለፅ ይኖርበታል። አንድ እንግሊዛዊ ቀራፂ ንጉሡ በሕይወት እያሉ እንግሊዝ በቆዩበት ጊዜ አጠገባቸው ሆኖ እያየ ሁለት ሦስት መልክ ያለው ሐውልት ሠርቷል። የጥበብ ሥራ በመሆኑ ቅርፁን ስታይው ጃንሆይን አይመስሉም። • የሁለቱ የቀድሞ ርዕሰ ብሔሮች ወግ በመሆኑም በአፍሪካ ኅብረት ምስረታ ጊዜ የነበሩ ፎቶግራፎች ብዙ ናቸው። ወደ 100 የሚሆኑ በአፍሪካ ሕብረት ምስረታ ወቅት የነበሩ ፎቶዎችን ሰብስበናል። እንግዳ ሲቀበሉና ስብሰባ ሲያደርጉ የሚለብሷቸው ልብሶችና የሚገልጿቸው አካላዊ ገለፃዎች ላይ ተመስርቶ ተሠራ እንጂ የአንድ ፎቶግራፍ ውጤት ብቻ አይደለም። ቢቢሲ፡ የተጠቀምከው ጥበባዊ ግነት አለ? በቀለ፡ በትክክል! እጃቸውና ደረታቸው ላይ፤ ደረታቸው አካባቢ ገነን ለማድረግ ሞክረናል። የጠቢቡ ነፃነት የሚባል ነገር አለ አይደል? በማይበላሽና ከሥርዓት በማይወጣ መንገድ ገነን ለማድረግ ሞክረናል፤ ሌላው ሰውነታቸው መለስ ይላል። በእርግጥ በአካልም እንደዚህ ነበሩ። እጃቸውንም ሲፅፉ እንደሚታየው፤ እኛም ዳቦ ስንቀበል እንዳየነው ሎጋ፣ ቀጠን ቀጠን ያሉ ጣቶችን በማድረግ የምንችለውን ሁሉ አድርገናል። ቢቢሲ፡ ሐውልቱ ከምንድን ነው የተሠራው? በቀለ፡ የተሠራው ከነሃስ ነው። ቢቢሲ፡ በቀላሉ በዝናብና በፀሀይ እንዳይበላሽ የተለየ ጥበብ ተጠቅማችኋል? በቀለ፡ ነሃስ የሚመረጠው ለዚህ ነው፤ ዓለም ላይ ለልዩ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር የሕዝብ ሐውልቶች ብዙ ጊዜ የሚሰሩት በነሃስ ነው። በነሐስ እንዲሠሩ የሚፈለገው በውስጣቸው ያለው አብዛኛውን የሚይዘው መዳብ ነው፤ መዳብ ደግሞ ኦክስጅን ስለሚይዝ አሮጌ ሲሆኑ የሻገተ አረንጓዴ ይሆናሉ። ልክ መዳብ ያላቸው ሳንቲሞች ሲቆዩ እንደሚፈጥሩት ቀለም ዓይነት። • አራት ልጆች የወለዱ እናቶች ከግብር ነፃ ሊሆኑ ነው እናም ኦክስጅን እንዲስብ አድርገን ነው የሠራነው ይህም አካባቢውን እንዲመስልና በጊዜ ሂደት መልኩ እንዲለወጥ ይፈለጋል... ያ እንዲሆን አድርገን ነው የሠራነው። ጠንካራ ብረትም ስለሆነ አይሰበርም፤ አይሸማቀቅም። ቢቢሲ፡ ቀመቱና ክብደቱ ምን ያህል ነው? በቀለ፡ ከነመቆሚያው ወደ ሦስት ሜትር ነው። ይህም የእርሳቸውን ቁመት ሁለት እጥፍ ይሆናል ማለት ነው። ክብደቱ ደግሞ ከ650 እስከ 680 ኪሎግራም ይመዝናል። በትክክል ይታወቃል፤ ነገር ግን ሲበየድ የተጨመሩ የብየዳ ብረቶች ኪሎ ስለሚጨምር ነው 30 ኪሎ ግራም እንደ ግምት የተቀመጠው። ቢቢሲ፡ የት ነው የተሠራው? በቀለ፡ የሸክላ ሞዴሉ አዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ሲሆን ቀሪው ሥራ የተከናወነው እንግሊዝ ኤምባሲ አካባቢ በተከራየነው ቤት ነው። ቁርጥራጮቹን ይዘን የመጨረሻውን ሞዴል የሠራነው ግን በእኔ ስቱዲዮ ውስጥ ነው። በአፍሪካ ሕብረት የቆመው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቢቢሲ፡ ሐውልቱ ተቀርፆ ለመጠናቀቅ ምን ያህል ጊዜ ፈጀ? በቀለ፡ እንደሌሎች አገራት ለጥበብ ሥራዎች የሚሆኑ ግብዓቶች የማግኘት እድሉ ባለመኖሩ ረዘም ያለ ጊዜ ፈጅቶብናል ... ስድስት ወር አካባቢ ነው የፈጀው። ቢቢሲ፡ ሥራው ወደ እናንተ የመጣው እንዴት ነበር ? በቀለ፡ እኔ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው የማስተምረው፤ እኔን ቢያነጋግሩኝም በዩኒቨርሲቲው ያሉ ባለሙያዎች በቡድን ነው ስንሰራ ቆየነው። ረዳቶች ነበሩኝ። እንደ ፕሮፌሰር ዘይኑ፣ ተመራቂ ተማሪ የሆነው አቶ ሔኖክ አዘነና ሌሎች በነሃስ ጥበብ ላይ ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። • አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ቢቢሲ፡ ምን ያህል ገንዘብ ወጣበት? በቀለ፡ ብዙ ነው የፈጀው... እ... እስካሁን አልደመርኩትም ግን ብዙ ገንዘብ ነው የወጣበት። ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ተፈላጊውን ውጤት ለማምጣት የሰው ጉልበትም በጣም የበላ ነው። ቢቢሲ፡ እንደው ገንዘቡን ከእዚህ እስከዚህ ብሎ ማስቀመጥ ይቻላል? በቀለ፡ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ነው፤ ለሂደቱ የሚያስፈልጉ ኬሚካሎች አሉ አገር ውስጥ የሌሉ... ቁሳቁሶች አሉ ... በጣም ብዙ ነገሮች አሉ... ቢቢሲ፡ እንደው በትክክል ባይሆንም ስንት አወጣ ማለት እንችላለን? በቀለ፡ ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ ነው ለማቴሪያል ብቻ የወጣው። ቢቢሲ፡ ምን ያህል ነው የተከፈላችሁ? በቀለ፡ ታክስ ይኖራል... ገና ነው ...ሰርተን ያስረከብነውም ሰሞኑን ስለሆነ ቀስ ብለን የምናየው ነው የሚሆነው ...ብዙ ገንዘብ አይኖረውም ትንሽ ስለሆነ፤ የሥራውን ጥበባዊም ሆነ የሰው ኃይል ዋጋውን እንደማይመልስ ግን አረጋግጣለሁ። ቢቢሲ፡ የገጠማችሁ ተግዳሮት ምንድን ነው? በቀለ፡ ብዙ ነገር የተሳካ ነበር ማለት ይቻላል፤ የግብዓት ጉዳይ ግን እጥረት ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ጠፋ ማለት ይቀላል። ከእርሳስ አቅም እራሱ አላሰራ እስኪል ድረስ ... ልክ የጋፋት የቴዎድሮስ ሰዎች አፈር አቅልጠው ብረት ሥሩ እንደተባሉት ዓይነት ነገር ነው። ብቻ በጥንታዊው መንገድም ቢሆን ብዙ የሰው ኃይል በመጠቀም ወደሚፈለገው ነገር መጥተናል። ቢቢሲ፡ የሐውልቱን ወጪ የሸፈነው ማነው? በቀለ፡ ኢትዮጵያን ወክሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው። ቢቢሲ፡ ሌላ ተባባሪ አካል የለም? በቀለ፡ እኛ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ነው የምንገናኘው ቢቢሲ፡ ከዚህ በፊት በሌሎች አገራት ከተሠሩት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሐውልቶች ይህን ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው? በቀለ፡ በዚህ መጠን ሙሉ ነሃስ ተሰርቶ አያውቅም። የትም አገር፤ የትም ቦታ! የእርሳቸውን መጠን ሁለት እጥፍ ተሰርቶ አያውቅም እሱ ነው ለየት የሚለው። ቢቢሲ፡ ሐውልቱ መቆሙን ተከትሎ የተቃውሞና የድጋፍ ሀሳቦች እየተንሸራሸሩ ነው፤ ይህንን እንዴት ትመለከተዋለህ? በቀለ፡ ኖርማል ነው... ጤና ነው ብዬ ነው የማስበው። ሰው አንድ ዓይነት አይደለም። አንድ ዓይነት አለመሆኑም ጥሩ ነው፤ አንዳንዴ የኛ የሚከፋው እ... ነገራችንን ሁሉ የክፋት የክፋት መንገዱን ሁሉ እየነቀስን እየነቀስን.. እዚች አገር አንድም ጥሩ፣ አንድም ደግ፣ አንድም አዋቂ፣ አንድም ፃድቅ እንዳይኖር እስከማድረስ ድረስ እንሄድና ፅንፋዊ ሆነን ራሳችን ማጥፋታችን ነው እንጂ የሚከፋው... እየሱስም ተቃዋሚ ነበረው አይደል ? ተቃዋሚ መኖሩ አይደለም ክፋቱ እኔ ከሌለሁበት ሁሉንም ነገር ይጥፋ የሚል ነገር አለብን፤ እሱ ነው ክፉ ነገር እንጂ የተወሰኑ ሰዎች ቢቃወሙ ጤነኛ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ። በተለይም እርሳቸው ከሄዱ በኋላም ብዙ የሠራናቸው ያጠፋናቸው ነገሮች አሉ። እነርሱን የምንቆጥር ከሆነ እንዳልኖርን ነው የሚቆጠረው፤ ቢያንስም ቢበዛ ደግ ደጉን ስናነሳ ነው እንደ እድሜ የምንቆጥረው ጊዜውን... ቢቢሲ፡ ሐውልቱ በመቀረፁ እንደ ግለሰብ ምን ተሰማህ? በቀለ፡ ልጅም ሆኜ ቢሆን አስታውሳቸዋለሁ ከእጃቸው ዳቦና ብር ተቀብያለሁ፤ ብዙ ጊዜ አይቻቸዋለሁ። ታሪካቸውንም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ አውቃለሁ፤ ትልቅና ኢትዮጵያን ያኮሩ ሰው እንደሆኑ፣ በተለይ ከእርሳቸው በኋላ ኢትዮጵያ ምን እንደሆነች እንደኛ ኖሮ ለሚያውቅ ሰው ቢመለከት ከእርሳቸው ምን እንደታጣ ማመዛዘን ስለሚችል ይህን ሁሉ ስታስቢ እንዴት ደስ ላይል ይችላል? ቢቢሲ፡ ስለ እርሳቸው ምን ትውስታ አለህ? በቀለ፡ እንግዲህ ተወልጄ ያደኩት ደብረዘይት ነው፤ አሁንም ከደብረዘይት አልተነጠልኩም፤ ጃንሆይ ደብረ ዘይት በየሳምንቱ ይመጡ ነበር። ለመዝናኛ ይመርጧታል። ያኔ ከዘጠኝ ዓመት አንበልጥም። ያን ጊዜ ሕፃናት ተሰልፈን ስንጠብቃቸው እንግዳ ያዙም አልያዙም ይቆማሉ፤ ቆመው ብርና ዳቦ ይሰጡናል። አርብ አርብ ደብረዘይት ቅዳሜና እሁድን ለማሳለፍ እንዲሁም ለማስቀደስ ይመጣሉ፤ እንጠብቃቸዋለን። የእጃቸው ስስነት ያ የሚነገርላቸው ግርማ ሞገስ በተለየ ዓይን ነበር የምንመለከታቸው። እቤት ደግሞ... ገንዘቡን ስንሰጥ የብዙ ልጆች እናት ገንዘቡ በረከት እንዲኖረው ተብሎ ከእንጀራ ሥር ይቀመጣል። ይህ ሕብረተሰቡ ምን ያህል ለንጉሡ ታማኝ እንደነበረ የሚያሳይ ነው። ዓለምም እንደዚህ ነው የሚያያቸው፤ ምንም ይሁን ምን ብዙ ታሪክ ያላቸው ሰው ናቸው።
49671695
https://www.bbc.com/amharic/49671695
"የአምባቸው ሕልም የተጠናከረ አማራን፣ የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት ነበር" አቶ ቹቹ አለባቸው
ሰኔ 15፣ 2011 ዓ. ም በአማራ ክልል በተካሄደው የ "መፈንቅለ መንግሥት" ሙከራ የተገደሉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን በሥራ ገበታቸው ላይ ምን ዓይነት ሰው ነበሩ? በአንድ ወቅት በአማራ ክልል የከተማ ልማት ምክትላቸው ሆነው ያገለገሉትን አቶ ቹቹ አለባቸውን ጠይቀናቸዋል። ከዶ/ር አምባቸው ጋር መቼ ነው የተዋወቃችሁት?
ዶ/ር አምባቸው መኮንን በትክክል ጊዜውን ባላውቀውም 80ዎቹ አጋማሽ ላይ፣ ከደርግ ውድቀት በኋላ ነው ሁላችንም የተገናኘነው። በክልል አካባቢ በሚደረጉ መድረኮች ላይ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅነው። ከ84. . . 85 እስከ 87 ካሉት ዓመታት መካከል በአንዱ ነው የተዋወቅነው። ትውውቃችሁ ወደ ጓደኝነት ያደገበትን አጋጣሚ ያስታውሱታል? እንደ ታጋይ የተዋወቅነው በአልኩህ ዓመተ ምሕረት ነው። ከ84 በኋላ ከስድስት እስከ ሰባት ባሉት ዓመታት። ያኔ የምንገናኘው እንደ ማንኛውም ታጋይ ነበር። እንደውም ከደርግ ድምሰሳ በኋላ እኔ ጎንደር ስመደብ እርሱ አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው ሸዋ ስለሆነ ብዙ የመገናኘት እድል የለንም። የምንገናኘው እንዲሁ አልፎ አልፎ ትልልቅ መድረኮች ሲመጡ፤ እርሱም ተናጋሪ ስለነበር፣ እኔም በመድረክ ላይ የዚያ ዓይነት ባህሪ ስላለኝ መተዋወቅ ጀመርን። ከዚያ በኋላ በ1990ዎቹ አካባቢ እርሱም እኔም ለትምህርት ሄድን። ከዚያ በኋላ ብዙም ተገናኝተን አናውቅም። • "ስተዳደር የቆየሁት በዋናነት ለመለስ በሚሰጠው የጡረታ ገቢ ብቻ ነው" ወ/ሮ አዜብ መስፍን ወደመጨረሻ የተገናኘነው 2001 ዓ. ም. ጉባዔ ላይ ይመስለኛል። ያኔ እንግዲህ በቅርበት መነጋገር ጀመርን። አንድ ትልቅ መድረክ ነበረ። ከዚያም በኋላ እንደገና እርሱ ወደ ውጪ ሄደ። ፒ ኤች ዲውን ጨርሶ ሲመጣ ሥራ ተመደበ። በዋናነት ጓደኛ የሆነውና በቅርብ መሥራት የጀመርነው ከ2006 ጀምሮ የእርሱ ምክትል ከሆንኩ በኋላ ነው። ከተማ ልማት ላይ። ከዚያ በኋላ የቅርብ ጓደኛሞች ሆነን ቀጠልን። በከተማ ልማት በዋናና ምክትልነት ስትሠሩ የነበራችሁ ግንኙነት ምን ይመስል ነበር? በዚህ ደረጃ ተቀራርበን እንትን ባንልም በሀሳብ ደረጃ እኔና አምባቸው በመድረክ እንግባባለን። ሀሳቤን ያውቀዋል፤ ሀሳቡን አውቀዋለሁ። ድሮም በመከባበር ላይ የተመሰረተ ወንድማዊና ጓዳዊ ግንኙነት ነበረን። ቢሮም ላይ በጋራ መሥራት ከጀመርን በኋላ የቀጠለው ይኸው ነው። ስለ እውነት በዚህ ጉዳይ ላይ ከድርጅት ጋር ተጋጭቼ ጎንደር ላይ ከኃላፊነት ተነስቼ ነበር። ከኃላፊነት ተነስቼ እርሱ ወደ ከተማ ልማት ሲመጣ ነው እኔ እንደገና ወደ ክልል የመጣሁት። እና እርሱ እዚያ ቢሮ ባይሆን ኖሮ እኔ አልመጣም ነበር። ዶ/ር አምባቸው እርስዎ እንዲመደቡ ጫና አድርገዋል ወይስ? አጠቃላይ ውሳኔው የድርጅቱ ነው። ድሮም በስህተት ስለተነሳን፣ የተነሳንበት አግብብ ትክክል አይደለም ብሎ ድርጅቱ ሲወስን፣ ይህ ውሳኔ በተወሰነበት አጋጣሚ ሳምንት ወይ ወር አይሞላውም አምባቸው ከተማ ልማት መጥቶ ነበር። ከዚያ በኋላ የሆነ ቦታ ሲፈለግ ከኔ ሙያ ጋርም በቅርበት ሊሄድ የሚችለው የአምባቸው ቢሮ ሆኖ ተገኘ። በርግጥ ለእኔ መጀመሪያ አልነገሩኝም ነበር፤ ግን ጠርጥሬያለሁ። • የሼፎች የበዓል ምግብ ምርጫ፡ ሼፍ ዮሐንስ፣ ጆርዳና እና ዮናስ እንደሚመልሱኝ ሲነግሩኝ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ተነጋገርኩ። ያሉት ክፍት ቦታዎች ሁለት ናቸው፤ አንዱ ባህር ዳር ላይ ሥራ አስኪያጅና ሁለተኛው ከተማ ልማት። ከተማ ልማት የሚሆን ከሆነ ከአምባቸው ጋር እንደሚሄድ፣ ያ ጓደኛዬ 'እርሱ ጋር ከሆነ ሂድ፤ ሌላ ጋር ከሆነ ግን አትሂድ' አለኝ። እሺ ብዬ ቆየሁና በመጨረሻ ሲነገረኝም የተመደብኩት ከአምባቸው ጋር እንድሠራ ነበር። በኋላ እንደተረዳሁት አምባቸውም የእኔን መምጣት በጽኑ ነው የደገፈው። በሥራ አጋጣሚ ተጣልታችሁ ታውቃላችሁ? [ሳቅ] እኔና አምባቸው. . . አየህ፤ አንዳንዴ የምታከብረው ሰው አለ አይደል? እርሱም እኔን ማስከፋት አይፈልግም፤ እኔም እርሱን ማስከፋት አልፈልግም። ግን ምንድን ነው? በውሳኔዎች ላይ፣ በተለይ ከመሬት ጋር በተያያዘ ብዙ ጊዜ በልዩነት ነው የምንወጣው። መጨረሻ ላይ ትክክል የሚሆነው ሀሳብ የኔ ነው። እርሱ በቅንነት እንሥራ ነው [የሚለው]። እኔ ደግሞ የሕጎች ትንሽም ቢሆን ግንዛቤ ስላለኝ አይሆንም ነው። ያኔ አምባቸው ቅንነት ብቻ ሳይሆን አልፎ አልፎ የሚበሳጭም ሰው ነው። በነገራችን ላይ መታወቅ ያለበት አንደኛው ባህሪው ይኼ ነው። የአምባቸውን ብስጭት ከእኛ የሚለየው ምንድን ነው? ከአምስት ደቂቃ በላይ በኩርፊያ አይቆይም። እና አይሆንም ስንለው ወዲያው ትንሽ የማኩረፍ፣ በስጨት የማለት ነገር አለበት። በአምስት ደቂቃ ውስጥ እዛው መድረክ ላይ እንዳለን ወርዶ 'ወንድማለም አስቀየምኩህ አይደል?' ብሎ እንደገና ይመለሳል፤ አጀንዳችንን እንቀጥላለን። እና ብዙ ጊዜ በመሬት ጉዳዮች፣ በተለይ ውሳኔ ላይ አለመግባባት ነበር። እኔ እሱን መሸፈን ነው። አሠራሩንም መጠበቅ ነው። እርሱ ግን ሁል ጊዜም የሚታየው ሥራ ብቻ ነው። ሥራ፣ የሕዝብን ጥያቄ መመለስ፣ አገልግሎት መስጠት። እኔ ደግሞ ይህንን ማድረግ የምንችለው በአሠራር ውስጥ ስንሆን ነው ስል የተወሰኑ መድረክ ላይ ገጭ ገጭ አለ። ያው የወንድም ግጭት ማለት ነው። በወንድም ሀሳብ አለመግባባት እንዲህ አይነት ጉዳዮች በተደጋጋሚ ገጥመውናል። ግን አንድም ቀን እኔ ለእርሱ ክፉ፣ እርሱ ለእኔ ክፉ ድርጊት ውስጥ ገብተን አናውቅም። እንኮራረፋለን፤ ግን እዚያው መድረክ ላይ እንተራረባለን፤ ብዙ ጊዜ የእርሱ ባህሪ 'ወንድማለም አስቀየምኩህ? ይቅርታ' ብሎ እንደገና መድረኮችን እንቀጥላለን። በዚህ መልኩ የሚገለፁ ብዙ ጉዳዮች አሉ፤ ነበሩ። • "ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በትንሳኤ በዓል ነበር" የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ እናት በተለይ የሚያስታውሱት የተጋጫችሁበት ጉዳይ ይኖራል? በርከት ያሉ ናቸው ሌላ ጊዜ ለመጻፍ እሞክራለሁ። ግን ምንድን ነው? አሁን የማስታውሰው. . . በ2006 ወይንም 2007 ይመስለኛል ሕገወጥ ቤት በፈረሰ ጊዜ. . . በክልሉ ወደ 19ሺህ ቤት ፈርሷል። በዚህ ላይ ልዩነቶች ነበሩን። በእኔም በእርሱም በኮሚቴያችንም ውስጥ። እና የእርሱ ሃሳብ ገዢ ሆኖ፣ እርሱም በርግጥ መነሻ ነበረው፣ ከዚያ በፊት የተወሰደ እርምጃ ስለነበረ ዘንድሮ ሳናፈርስ ብንቀር አግባብ አይሆንም የሚል አቋም ነበረው። የክልሉም መንግሥት የእርሱን ሀሳብ ደግፎ እርምጃ ተወሰደ። ቤት ፈረሰ። ቤት ከፈረሰ በኋላ በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ተፈጠረ። ሰዎችም ሞቱ። ቤታቸው ሲፈርስ። የዚያኔ የክልሉ መንግሥት ሲቸግረው በሕገ ወጥ መሬት የፈረሰባቸውን ሰዎች መሬት እንስጣቸው አለ። ይኼ ሕገ ወጥ አሠራር ነው። ይህንን አምባቸው ከእነ አቶ ገዱ ጋር ከተወያየ በኋላ ከተማ ልማት እንዲያስፈፅም ተብሎ አምባቸው ይዞ መጣ። ወደ ከተማ ልማት ሲመጣ ደግሞ ይህንን ሥራ የግድ የምፈፅመው እኔ ነኝ። ቀጥታ ሚመለከተኝ እኔን ስለሆነ ማለት ነው። • 2011፡ በፖለቲካና ምጣኔ ኃብት አምባቸው ይህንን ጉዳይ ይዞ መጣ። አልፈጽምም አልኩ። እንደማይፈፀምም ነገርኩት። ይህንን ስለው እርሱም ጉዳዩን ወደ ትልልቆቹ አመራሮች ይዞት ሄዶ እነርሱም 'ይህንን ማስፈፀም ያልቻልክ' አይነት ነገር ገጭ አደረጉት መሰለኝ፤ እንደገና ይዞት መጣ፤ እናም አንፈፅምም አልን። በዚህ መካከል ትንሽ መደባበር ነበረ። መጨረሻ ላይ ግን እኔ እምቢ በማለቴ እርሱንም ከስህተት ጠብቄዋለሁኝ። ሌላም ገጠመኝ አለ ይህች ግን የምትጠቀስ ናት። ከሥራ ውጪ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች አብራችሁ የምትሆኑባቸው ጊዜያት ነበሩ? በዚህ መልኩ ብዙ የእረፍት ጊዜ የምንለው፣ የምንጫወትባቸው ጊዜያት የሉም። እርሱም ወደ አዲስ አበባ ከሄደ በኋላ እኔም ወደ አዲስ አበባ ከሄድኩ በኋላ ለብቻ አንድ ቀን ተገናኝተን ያወራናቸው ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ ጉዳዮች አሉ። እንጂ እዚህ ሥራ ላይ እያለን እርሱም ጊዜ የለው፤ እኔም ጊዜ የለኝ። እንደዚህ የምንዝናናበት ጊዜ ብዙም አልነበረም። ከተማ ልማት ላይ እያለን ትርፍ ጊዜ አልነበረንም። ጊዜ አግኝተን ሻይ ቡና በምንልበት ወቅት አምባቸው ተጫዋች ነው። በኢህአዴግ ውስጥ በሦስት ጉዳዮች እንደ አምባቸው የተሳካለት ሰው ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ። የመጀመሪያው ነገር ከታች ተነስቶ የደረሰበትን ትምህርት ደረጃ ስታየው እጅግ በጣም የሚገርም ነው። ከታች ነው የተነሳው። ከታች መነሳት ብቻ ሳይሆን ያለፈባቸው መንገዶች እጅግ መሰናክል የበዛባቸው ናቸው። ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተነስቶ፣ በኢህአዴግ ውስጥ ታግሎ፣ የኢህአዴግን ፈተና ተቋቁሞ፣ ፒኤችዲ ደረጃ መድረስ. . . ያለፈበትን መንገድ ለምናውቀው ሰዎች እጅግ በጣም የተሳካለት ሰው ነው፤ በትምህርት መስኩ። • በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ ሌላው አምባቸው የተሳካለት ነው የምለው የአመራር ዘይቤ ነው። አምባቸው በበርካታ ቢሮዎች ሠርቷል። ሁሉም ቢሮዎች ተወዳጅ ሆኖ ነው የወጣው። በማኔጅመንቱም፣ በሠራተኛውም አምባቸውን የሚነቅስ፣ አምባቸውን በክፉ የሚያየይ ገጥሞኝ አያውቅም። ይሄ በአመራር ዘይቤ ይዞት የወጣው ትልቅ ድል ነው ብዬ አስባለሁ። ሶስተኛው ማኅበራዊ ሕይወቱ ነው። አምባቸው ከማንኛውም ጋር ተግባቢ ነው። በሐዘን ደራሽ፣ በደስታ ደራሽ፣ ችግር ተካፋይ ነው። በእነዚህ ሦስት ጉዳዮች በኢህአዴግ ውስጥ እንደ አምባቸው የተሳካለት ሰው አለ ወይ? ብዬ ሁልጊዜ ሳይ፤ ብዙ ያለ አይመስለኝም። ካሉም ግን አንዱ አምባቸው መሆኑ ነው። እነዚህ ሦስቱ ግን እኔ ሁሌም የምቀናባቸው የአምባቸው የተለዩ ባህሪያት ናቸው። ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ሲማሩ፤ ከድርጅቱ ጋር በነበረ አለመግባባት ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ ያደረጉት ጓደኞቻቸው ገንዘብ አዋጥተው ነው ሲባል እሰማለሁ። ስለዚህ የሚያውቁት ጉዳይ አለ? እውነት ነው። [ፈገግታ በተሞላው ድምጽ] እርሱ እንዲማር የሄደው ሁለተኛ ዲግሪውን ነበር፣ ለንደን ወይም ኮሪያ ይመስለኛል። ድርጅቱ ተምሮ ይመጣል ብሎ ሲጠብቅ፤ በዛው በራሱ ጥረት ሦስተኛ ዲግሪውን ለመቀጠል እድል አገኘ። እርሱ ወዶት ብቻ ሳይሆን ሁኔታዎችም ናቸው ወደዚያ ያስገቡት። ያኔ የነበሩት የድርጅቱ አመራሮች ይህንን ሲያውቁ፤ 'ከፈለግህ ትተህ ና እንጂ አናስተምርም' ተባለ። ቤቱንም ለመሸጥ፣ ለሌላም ነገር ለመዘጋጀት ጥረት አድርጎ ነበር። ጓደኞቹ የምንችለውን ያህል. . . በርካታ ጓደኞቹ በማዋጣት ተሳትፈዋል። በመጨረሻም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ መማሩ እንደማይቀር ሲያውቁ ወጪውን ሸፍነውለታል፤ እውነት ነው። ርዕሰ መስተዳደር ከነበሩ በኋላ ትደዋወሉ ነበር? ርዕሰ መስተዳድር ከሆነ በኋላ እንኳ ብዙ አንደዋወልም። ትንሽ ተኮራርፈን ነበር። የተኮራረፍንበት ምክንያት ባለፈው እንዳነሳሁት [የፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ የፃፉትን ለመጥቀስ ነው] አዲስ አበባ ላይ ለብአዴን ሊቀመንበርነት ታጭቶ፤ በሆነ ምክንያት መክሸፉን መረጃ ይኖርሃል። አዲስ አበባ ተገናኝተን በዚህ ጉዳይ ላይ አውርተን ነበር ለብቻችን። እንደጥሩ አጋጣሚ ወስዶት፤ ካሁን በኋላ የሚፅፋቸው ነገሮች ካሉ እንዲፃፍ፣ ተረጋግቶ እንዲቀመጥና ወደራሱ እንዲመለስ፣ በፍፁም ወደ አማራ ክልል ፖለቲካ ተመልሶ እንዳይሄድ ብዙ ውይይት አደረግን። እኔና እርሱ በዚህ ተስማምተናል። በተለይ ወደ ክልል ፕሬዝዳንትነት እንደማይሄድ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰን ነበር። እንደ ወንድም። ሳይነግረን፣ ምን ሳይል መጥቶ ፕሬዝዳንት ሆነ። ከዚያ ትንሽ ተደባበርን። አንደኛ እንደዚያ ተነጋግረን፣ ሁለተኛ ሀሳቡን ሲቀይር እንኳ አልነገረንም ብዬ እርሱም ደብሮት፣ እኔም ደብሮኝ አንገናኝም ነበር። በመጨረሻ ከመገደሉ አንድ ሳምንት ምናምን ቀደም ብሎ ተደዋወልን፤ አንድ የግድ የምንገናኝበት ጉዳይ ስለነበርን። እዚያ ፕሮግራም ላይ በትራንስፖርት ምክንያት ሳንገናኝ ቀረን። በምን ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ነበር ቀጠሮ ያዛችሁት? ቀጠሯችን በሁለት ጉዳይ ነው። አዲስ አበባ ነበር የተቀጣጠርነው። ምንድን ነው? የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውይይት ነበርና በዚያ እንድሳተፍ ጋበዙኝ። ውይይቱ ውጪ ጉዳይ ነው የነበረው። እርሱም እኔም የምንወቃቀስበት ነገር አለ። ያ ሁለተኛ አጀንዳችን ነበር። በል ሁሉንም እዚያ እናውራው ብለን ነበር ቀጠሮ የያዝነው። እኔም በትራንስፖርት ምክንያት ሳልገኝ ቀረሁ። ሌላ ጊዜ እንገናኝ ብለን ቀጠሮ እንደያዝን አደጋው ደረሰ፤ ቀረ። ዶ/ር አምባቸው ሕልማቸው ምን እንደነበር እንደጓደኛ አካፍሎዎት ካወቁ፤ ምን ነበር የሚያልሙት? ብዙ ጊዜ ስንገናኝ የሚያነሳው. . . ቁጭት አለው ታውቃለህ። የአማራ ሕዝብ ያሳለፋቸው በደሎች ላይ ቁጭት ነበረው። ትልቁ እይታው የነበረው ከማኅበረሰብ አንጻር ነበር። ሁል ጊዜ የሚያስበው የተጠናከረ፣ በተለይ በኢኮኖሚ አቅም ያለው አማራን ማየት ነበር። ያለፈው ሥርዓት በዚህ ሕዝብ ላይ ጥሎ የሄደው ነገር ሁል ጊዜ ይቆጨዋል። ከዚያ የተላቀቀ፣ በራሱ የሚተማመን፣ አቅሙ የዳበረ የአማራን ማኅበረሰብ ማየት የአምባቸው የዘወትር ሕልሙ ነበር። ይኼ ሁልጊዜ የማልረሳው፤ ሁልጊዜ የሚያነሳው ጥያቄ ነበር። በታሪክ ላይ ብቻ ተመስርተን እንደማንኖር፤ የቴዎድሮስ ልጅ. . . የማንም ልጅ እያልን መኖር እንደማንችል። ይህንን ለማስቀጠል፣ ከድህነት ተላቀን ሁለንተናዊ አቅም [እንዲኖር]፤ በተለይ 'ኢኮኖሚክ ኢምፓወርንመንት' [በምጣኔ ሀብት ራስን መቻል] ላይ ትኩረት ይሰጥ ነበር። የበለፀገ አቅም የፈጠረ አማራን የማየት ፍላጎት ነበረው። ከዚያም በላይ ራዕዩ አገራዊ ነው። በዚሁ ልክ የምትለካ፣ የበለፀገች ኢትዮጵያን. . . የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጎ. . . ይህችን ኢትዮጵያ ማየት ፍላጎቱ ነበር [በረዥሙ ተነፈሱ]።
news-52821801
https://www.bbc.com/amharic/news-52821801
ኮሮናቫይረስ፡ አንዳንዶች በኮሮናቫይረስ ሌሎች ደግሞ በሐሳዊ ዜና ወረርሽኝ እየሞቱ ነው
የቢቢሲ የምርመራ ጋዜጠኞች ግብረ ኃይል በሐሳዊ ዜና (fake news) ምክንያት ሰው ይሞታል? ሲል ጠየቀ።
ሚስቱና ራሱ እስኪያዙ ድረስ ቫይረሱ የለም ብሎ ያስብ የነበረው ብሪያን ሊ የማኅበራዊ ሳይንት ተመራማሪዎች ሐሳዊ ዜና፣ መላምታዊ ድምዳሜ፣ የሴራ ወሬ ብዙዎችን ዋጋ እያስከፈለ ነው ብለው ይደመድማሉ። ምን ያህል እውነት ነው? አሁንም ድረስ ኮሮናቫይረስ አውሮፓዊያን የሸረቡት ሴራ እንጂ እውነት አይደለም ብለው የሚያምኑ ሺህዎች ናቸው። አሁንም ድረስ ኮሮናቫይረስን የወለደው 5ጂ ኔትዎርክ ነው የሚሉ አሉ። አሁንም ድረስ 'አረቄ ኮሮናቫይረስን ድራሹን ያጠፈዋል' ብለው ጉሮሯቸው እስኪሰነጠቅ የሚጨልጡ በርካቶች ናቸው። ከኢትዮጵያ እስከ ማዳጋስካር፣ ከታይላንድ እስከ ብራዚል፣ ከአሜሪካ እስከ ታንዛኒያ በሐሳዊ ወሬ ያልናወዘ፣ መድኃኒት ያልጠመቀ የለም። ሳይንስ መፍትሔ የለውም ብለው ከደመደሙት ጀምሮ አምላክ ያመጣው መቅሰፍት ነው ራሱ ይመልሰው ብለው ሕይወታቸውን በተለመደው መልኩ የቀጠሉ የዓለም ሕዝቦች ብዙ ናቸው። የሐሳዊ ዜና ምስቅልቅል ለምሳሌ ብሪያን ሊን እንውሰድ። 46 ዓመቱ ነው። ፍሎሪዳ በሚገኝ ሆስፒታል አልጋ ላይ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ላይ ሆኖ ለቢቢሲ ሲናገር ኮሮናቫይረስ መንግሥት ዜጎቹን ሊያዘናጋ የፈጠረው የፖለቲከኞች ሴራ ነው ብሎ ያምን እንደነበር ገለጧል። "ሁለት ነገር ይሆናል ብዬ ነበር የገመትኩት፤ አንዱ እንዳልኩት የመንግሥት ማስቀየሻ ዘዴ ሆኖ ነበር የታየኝ። በኋላ ደግሞ 5ጂ ኔትዎርክ ነው በሽታውን ያመጣው ብዬ በጽኑ አመንኩ፤ ቀጥሎ በጽኑ ታመምኩ።" ብሪያን ብቻውን አይደለም። ባለቤቱም እንደዛ ነበር ያመነችው። በኋላ ሁለቱም የአልጋ ቁራኛ ሆኑ። ቫይረሱ ውሸት ነው ብላችሁ እንድታምኑ ያደረጋችሁ ምንድነው? ተብለው ሲጠየቁ "በፌስቡክ ያነበብነው ሐሳዊ ዘገባ ነው ጉድ ያደረገን" ብለዋል በአንድ ድምጽ። ቫይረሱም ይገድላል፤ ሐሳዊ ዜናም ይገድላል። የቢቢሲ የምርመራ ቡድን የሐሳዊ ዘገባዎችና የሴራ ሽረባዎች ያደረሱትን የጉዳት መጠን ለማወቅ በርካታ አገራትን አስሷል። ችግሩ ዓለም አቀፋዊ ስለመሆኑም ተረድቷል። ለምሳሌ በሕንድ በኢንተርኔት የተለቀቀ ወሬ ሰው ተደብድቦ እንዲገደል አድርጓል። በኢራን በሐሰተኛ ወሬ ምክንያት መርዝ የጠጡ ብዙ ናቸው። በ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ላይ በተነዛው ወሬ የቴሌኮሚኒኬሽን ኢንጂነሮች ተደብድበዋል፣ የስልክ እንጨቶች በእሳት ተለኩሰዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ እየወሰድኩት ነው ያሉት ሀይድሮክሲክሎሮኪን የፕሬዝዳንት ትራምፕ ምክር በአሜሪካ አሪዞና የዓሳ ገንዳ ማጽጃ ኬሚካል ኮሮናቫይረስን ይፈውሳል የሚል ዜና ያነበቡ ጥንዶች ኬሚካሉን ጠጥተው ሆስፒታል ገብተዋል። ለዚህ አንዱ ተጠያቂ የሚሆኑት እንደመጣላቸው ይናገራሉ የሚባሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሳይሆኑ አይቀሩም። ዋንዳና ጌሪ ትራምፕ ስለሚያሻሽጡት ሀይድሮክሲክሎሮኪን በመጋቢት መጨረሻ ላይ ነበር የሰሙት። ቤታቸው ውስጥ አንድ ተመሳሳይ ስም የተጻፈበት ጠርሙስ አገኙ። ሀይድሮክሲክሎሮኪን አንዳች ተስፋ የሚሰጥ መድኃኒት እንደሆነ ቢነገርም የዓለም ጤና ድርጅት በዚህ መድኃኒት ላይ የሚደረገው ምርምር እንዲቆም አዟል። ለዚህ ውሳኔ ያበቃው በቅርብ የተደረጉ ምርምሮች እንዲያው በሽታው ገዳይ መሆኑን ስላመላከተ ነበር። የዚህ መድኃኒት ፈዋሽነት ወሬ የተነዛው በመስከረም መጨረሻ በኢንተርኔት ላይ ነበር። አንዳንድ የቻይና ሚዲያዎች ይህ መድኃኒት ጸረ-ቫይረስ ስለመሆኑ የድሮ ያልታደሰ መረጃ ይዘው አራገቡት። ከዚያ ቀጥሎ አንድ የፈረንሳይ ሐኪም ይህንኑ የሚያጠናክር ነገር ተናገሩ። ቀጥሎ የቴስላ መኪና መስራች ኤሎን መስክ ስለ መድኃኒቱ አዳንቆ አወራ። ዶናልድ ትራምፕ ተከተሉት። ወሬው ወደ ላቲን አሜሪካ ሄደና የአእምሮ ጤናቸው ያጠራጥራል ወደሚባሉት የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጄየር ቦልሶናሮ ጋር ደረሰ። ከሁሉም የከፋ ጥፋት የሰሩት ግን ዶናልድ ትራምፕ ሳይሆኑ አልቀሩም። በጋዜጣዊ መግለጫቸውም ሆነ በትዊተር ሰሌዳቸው ስለ ሀይድሮክሲክሎሮኪን ሳይናገሩ ማደር አቃታቸው። "ቆይ! ብትወስዱት ምን ትጎዳላችሁ?" ሲሉ አበረታቱ። "አንዲት ሴትዮ የእኔን ምክር ሰምታ ዳነች" አሉ። ጋዜጠኞች በጥያቄ ሲያጣድፏቸው ደግሞ "ከመሞት መድኃኒቱን ወስዶ መሰንበት አይሻልም?" ማለት ጀመሩ። ግንቦት ላይ ደግሞ ትራምፕ መድኃኒቱን ራሳቸው እየወሰዱት እንደሆነ ተናገሩ። ይህን ሁሉ ንግግራቸውን ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ሰፊ ሕዝብ ሰምቶ ያጋራዋል። ሚሊዮኖች ይነጋገሩበታል። ሺህዎች ይተገብሩታል። በናይጄሪያ ይህን መድኃኒት ተከትሎ በርካታ ሰዎች ታመው የሆስፒታል አልጋ በማጣበባቸው የጤና ሚኒስቴር መግለጫ እስከማውጣት ደርሷል። በሚያዚያ ወር በቬትናም የ43 ዓመት ጎልማሳ ይህንኑ መድኃኒት ወስዶ መርዝ ሆኖበት በሃኖይ ሆስፒታል እየተሰቃየ ይገኛል። አይኑ ቀልቶ፣ ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ፣ የሚያየው ነገር ጨልሞት ነበር የመጣው ይላሉ የክሊኒከኩ ዳይሬክተር ዶ/ር ጉይን። "ሰውየው እድለኛ ነው፤ ቶሎ ወደ ክሊኒካችን ባይመጣ ሕይወቱ አትተርፍም ነበር" ብለዋል። ባልና ሚስቱ ጌሪና ዋንዳ እድለኞች አልነበሩም። ቤታቸው ጓሮ ሀይድሮክሲክሎሮኪን የሚል አይነት ጽሑፍ የነበረበትን ኬሚካል የትራምፕን ምክር ተከትለው በመጠጣታቸው ወዲያውኑ ነበር ራሳቸውን የሳቱት። መተንፈስ አቃታቸው። ጌሪ ሞተ፤ ዋንዳ ግን ሆስፒታል ተኝታለች። ዋንዳ ካገገመች በኋላ እንደተናገረችው ለዚህ የዳረጋቸው ዶናልድ ትራምፕ ስለ ሀይድሮክሲክሎሮኪን መድኃኒት አብዝተው በመናገራቸው ለምን አልንሞክረውም በሚል ተበረታተው ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በየዕለቱ ስለወረርሽኙ መግለጫ ይሰጣሉ የአልኮል መርዝና ኢራን በኢራን ደግሞ በመቶዎች የገደለው የአልኮል መርዝ ነው። የአልኮል መርዝ በሽታውን ሙልጭ አድርጎ ያጠፋል ሲባል ሰምተው ብዙዎች ለምን አንሞክረውም አሉ። ያድናል የሚለው ነገር ከየት እንደተነሳ ባይታወቅም ብዙዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች እንዳነበቡት ተናግረዋል። ካምቢዝ ሱልጣኒጃድ የተባሉ የኢራን ባለሥልጣን እንደተናገሩት በዚህ የአልኮል መርዝ የሟቾች ቁጥር 800 ይጠጋል። ሁሉም ታዲያ ፌስቡክ ላይ ባነበቡት ነገር ተበረታተው ነው መርዙን የጠጡት። ይህ የሆነው የአልኮል መጠጥ በሚከለከልባት ኢራን መሆኑ ደግሞ ሌላው አስገራሚ ምጸት ነው። ቢቢሲ ባደረገው ተጨማሪ ምርመራ መርዛማው አልኮል ያድናል የሚለው ወሬ መጀመርያ የተሰራጨው በቴሌግራም ነበር። ሻያን ሳንዳሪዛድ የቢቢሲ የጸረ-ሐሳዊ ዜና ቁጥጥር ግብረ ኃይል አባል ናት። እሷ እንደምትገምተው ነገሩ የኢራን ባለሥልጣናትን አሳፍሯቸው ነው እንጂ የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ በብዙ እጥፍ የበዛ ሊሆን ይችላል። የቢቢሲ መርማሪ ቡድን ባረጋገጠው ሌላ ዜና እዚያው ኢራን ውስጥ የ5 ዓመት ልጅ በሐሳዊ ዜና ምክንያት አይነ ስውር ሆኗል። ወላጆቹ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚል አረቄ መሰል አደገኛ መጠጥ አይኑ ላይ አፍስሰው ነው የገዛ ልጃቸውን ብርሃን ያጠፉት። ክፉኛ በበሽታው ከተጠቁት አገራት መካከል የሆነችው የኢራን ፕሬዝዳንትን ጨማሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጓደኛዬ ሳሙና ጎርሷል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሀይድሮክሲክሎሮኪንን ብቻ አይደለም ሲያሻሽጡ የከረሙት። በሚያዚያ መጨረሻ ደግሞ የአልትራቫዮሌት ጨረር ቫይረሱን ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው እንደሚችል ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሚሰነዝሩት የግብር ይውጣ አስተያየቶች ኃላፊነት ወስደው አያውቁም። ሲሻቸው ፈርጠም ብለው በሐሳቡ ይገፉበታል። ሲሻቸው ደግሞ እንደዛ አላልኩም ብለው ሽምጠጥ አድርገው ይክዳሉ። አንዳንዴ ደግሞ እረ እኔ የቀልዴን ነው እንደዛ ያልኩት ይላሉ። ዞሮ ዞሮ እያንዳንዱ ንግግራቸው የነፍስ ዋጋ ያስከፍላል። ለምሳሌ የንጽህና ኬሚካል ኮሮናቫይረስን ይከላከላል ከሚለው የትራምፕ ንግግር በኋላ በካንሳስ ያሉ አንድ ባለሥልጣን አንድ ዜጋ አንድ ሳሙና እንደዋጠ መስማታቸውን ተናግረዋል። ዶ/ር ዱንካን ማሩ በኒውዮርክ ኤልመሀረስ ሆስፒታል ሐኪም ናቸው። የትራምፕን ንግግር ተከትሎ የንጽሕና ኬሚካል የጠጡ በርካታ ህሙማንን ማከማቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ባለፈው ወር ብሪታኒያ ውስጥ በእሳት እንዲቃጠል የተደረገ የሞባይል ሰልክ ኔትወርክ ማማ 5ጂ የሞባይል ቴክኖሎጂ ቫይረሱን ያመጣል የሚለው ሴራ ሐሳዊ ዜናዎችና የሴራ ትንተናዎች የንብረት ጉዳትም አድርሰዋል። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም 70 የሚሆኑ የሞባይል ስልክ ኔትወርክ ማማዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ 5ጂ ቴክኖሎጂ ነው ቫይረሱን ያመጣው የሚለው ወሬ ነው። በሚያዝያ ወር ኢንጂነሩ ዳይላን ፋረል ቫን መኪናውን ከተርማስተን ወደ ሌስተር እየነዳ ነበር። በሥራ የተወጠረበት ቀን በመሆኑ ትንሽ የሻይ እረፍት ለማድረግ እያሰበ ሳለ የተቃውሞ ድምጽ ወደሰማበት አቅጣጫ ዞር አለ። መጀመርያ ያሰበው ተቃውሞው ወደ ሌላ ሰው ያነጣጠረ እንደነበረ ነው። ለካንስ "5ጂ ይውደም" የሚለው ተቃውሞ ወደሱ የሥራ መኪና ያነጣጠረ ነበር። "አንደኛው ተቃዋሚ ወደእኔ ተጠግቶ ዘለፈኝ፤ አንተ ሞራል የሌለህ ሰው ነህ፤ 5ጂ ሕዝብ እየጨረሰ ነው" አለኝ። በጣም አስፈሪ ነበር፤ ሊደበድቡኝ ሲሉ ፈጣሪ ነው ያተረፈኝ፤ የመኪናዬ በር ዝግ ነበር።" በ5ጂ ቴክኖሎጂ ዙርያ ብዙ የሴራ ትንተናዎች በድረ ገጾች ለዓመታት ሲነገሩ ነበር፤ ይህ ነገር ሄዶ ሄዶ ከኮሮናቫይረስ ጋር መገናኘቱ ግን አስገራሚ ነው። ኮሮናቫይረስና የዘር ጥቃት በመጋቢት ወር ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም በሰጡት መግለጫ ወረርሽኙ ወደ ዘር ጥቃት ሊዛመት እንደሚችል ገምተው ነበር። የፈሩት ደርሷል። በርካታ እሲያዊያን በበርካታ የአሜሪካ፣ የአፍሪካና የላቲን አሜሪካ አገራት ውስጥ ጥቃት ደርሶባቸዋል። በሽታውን ያመጣችሁብን እናንተ ናችሁ በሚል። ለምሳሌ በሚያዚያ ወር ሦስት የሕንድ ሙስሊሞች በዴልሂ በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ ሙስሊሞች በሽታውን አሰራጭተውታል የሚል ሐሳዊ ዜና ማኅበራዊ ሚዲያውን ሞልቶት ስለነበረ ነው። ሌላ አንድ ወጣት በተመሳሳይ በሐሰተኛ ዜና የተነሳ ሲገደል ጓደኛው ቆስሏል። በእንግሊዝ ደግሞ ነጭ ያልሆኑ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች አልጋ አይሰጣቸውም፤ ባሉበት እንዲሞቱ እየተደረገ ነው የሚል ወሬ በመወራቱ ብዙ ችግር ተፈጥሮ ነበር። ሕንድ ውስጥ በኢንዶር ከተማ ሐኪሞች አንድ ቫይረሱ እንዳለበት የተገመተን ሰው ለመውሰድ በሄዱበት በድንጋይ ተደብድበው ሕይወታቸው ለጥቂት ተርፏል። ምክንያቱ ደግሞ በዋትስአፕ የተሰራጨ ሐሰተኛ ወሬ ነው። ሐኪሞቹ የመጡት ጤነኛ የሆኑ ሙስሊሞችን ለመውሰድ ነው የሚል ነበር። ከሐኪሞቹ መሀል ሁለቱ አካል ጉዳተኛ ሆነው ቀርተዋል። ብሪያንና ባለቤቱ ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት አንድ ድግስ ላይ ታድመው "አታካብዱ!" ሲል የነበረው ብሪያን የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች አደገኛነታቸው ብቻ ሳይሆን ጥቅማቸውም የትየለሌ ነው። ለምሳሌ ብሪያንን እንውሰድ። ብሪያን እንደ ሌሎች ሰዎች ቫይረሱ ውሸት ነው ብሎ አላመነም። ወይም በ5ጂ የመጣ በሽታ ነው ሲል አላሰበም። እሱ ያሰበው ቫይረሱ እውነት ሆኖ ሳለ ነገር ግን መገናኛ ብዙሃን ነገሩን ከሚገባው በላይ አጋነውታል። ማኅበራዊ ሚዲያውም እያካበደ ነው ብሎ አሰበ። ባለቤቱ የአስም በሽተኛ ናት። እርሱ ሾፌር ነበር። ሱፐርማርኬት እየሄደ በነጻነት እቃ ገዝቶላት ይመጣል። ራሱን ማግለል አስፈላጊ ሆኖ አላገኘውም። ድንገት ቫይረሱ ያዘው። ደነገጠ። ባለቤቱንም ለአደጋ አጋለጣት። በነገሩ በማዘኑ ወደ ፌስቡክ ገጹ በመሄድ ተናዘዘ። እኔን ያያችሁ ተቀጡ ሲል ጻፈ። ባለሙያዎች እንደሚሉት በትልልቅ ሚዲያዎች ከሚነገሩ ማስጠንቀቂያዎች ይልቅ እንደ ብሪያን ያሉ ተራ ዜጎች የሚጽፏቸው ነገሮች የተሻለ ውጤትን ያስገኛሉ፤ ተአማኒነታቸውም ከፍ ያለ ነው። በሐሳዊ ዜና ሕይወት ይጠፋል ሲባል ሐሰት አይደለም በዚህ ጽሑፍ የተነሱት ምሳሌዎች እንጂ ጠቅላላ ጉዳትን አያስቃኙም። ኢንተርኔት የመረጃ ሱናሚ ነው። ፍሬውን ከገለባ መለየት አይቻልም። የመቆጣጠሪያ መንገዱም ቀላል አይደለም። ትዊተር በትራምፕ ሰሌዳ ላይ ሐሳዊ መረጃ ምልክት ማድረጉ አንድ እርምጃ ቢሆንም ነገሩ ውቅያኖስን በጭልፋ እንደማለት ነው። ለዚህም ነው ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ሐሰተኛ መረጃን ኢንፎዴሚክ ሲል የሰየምው። ራሱን የቻለ በሽታ፤ ራሱን የቻለ ወረርሽኝ ሆኗል ለማለት ነው። ባለፈው ዓርብ ሁለት ወጣቶች ወደ ኒውዮርክ ኩዊንስ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል በአምቡላንስ መጡ። አብረው ነበር የሚኖሩት። "ከአንድ ሰዓት በኋላ አንደኛው ወጣት ዓይኔ እያየ ሞተ" ይላሉ ዶ/ር ፈርናንዶ። ሌላኛው በቬንትሌተር ነው እየተነፈሰ ያለው። "ለምን ቶሎ ወደ ሐኪም ቤት እንዳልመጡ ስጠይቃቸው የሰጠኝ መልስ 'ፌስቡክ ላይ ቫይረሱ ተራ ጉንፋን ነው' የሚል ነገር በማንበባችነው ነው ብሎኛል።" ክትባት አንወስድም የሚሉ ዜጎች ሊፈጠሩ ይችላሉ ቀጣዩ ስጋት እንደው ተሳክቶ ለተህዋሱ ክትባት ቢፈጠር እንኳ ሚሊዮኖች ለመከተብ ፍቃደኛ ላይሆኑ እንደሚችሉ ተገምቷል። አንዱ ምክንያት በፌስቡክ ገና ከወዲሁ የሚነዛው ወሬ ነው። መንግሥታት የሕዝብ ቁጥርን ለመቀነስ ፈልገው ነው ቫይረሱን የፈጠሩት፤ አሁን ደግሞ በክትባት ሊጨርሱን ነው ብለው የሚያምኑ በርካታ ናቸው። 'ቢልጌትስ ሀብቱን ለመጨመር ሲል ነው ቫይረሱን ፈጥሮ ክትባቱን ያመጣው' ሊሉ የሚችሉ ሺህዎች አሉ። በሴራ ትንታኔ ያምን የነበረው የፍሎሪዳው ብሪያን ከሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ መልዕክት አለኝ ይላል። "አትጃጃሉ፤ እኔን አይታችሁ ተቀጡ!"
news-52708217
https://www.bbc.com/amharic/news-52708217
ኮሮናቫይረስ፡ ክትባቱ ቢገኝ አፍሪካ ከሃብታም አገራት እኩል ተጠቃሚ ትሆን ይሆን?
ከዚህ ቀደም በአፍሪካውያን ላይ ስለተሞከሩ የክትባት ዓይነቶች በርካታ አስፈሪ ታሪኮች ሲነገሩ ይሰማል። ቢሆንም ግን ተመራማሪዎች አፍሪካውያን በዚህ የክትባት ምርምር ላይ መሳተፋቸው ወሳኝ ነው ሲሉ ይደመጣሉ። ለዚህም ምክንያታቸው በመላው ዓለም የሚሰራ ክትባት ለማምረት የሁሉም የዓለም ሕዝቦች ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ነው።
የኮሮናቫይረስ እስካሁን ድረስ ፈዋሽ መድሃኒት ወይም ክትባት ባይገኝለትም ነገር ግን ክትባት መገኘቱ የቫይረሱ ስርጭትን ለመግታትም ሆነ ሕሙማንን ለማከም ወሳኝ ሚና እንዳለው የዓለም ጤና ድርጅት ይናገራል። አክሎም የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም በማለማመድ ቨይረሱን በመዋጋት እንዳይታመሙ ያደርጋል ይላል። በአፍሪካ ውስጥ እስካሁን ድረስ የክትባቱ ሙከራ እየተካሄደ ያለው በደቡብ አፍሪካ ሲሆን ኬንያዊያንም ሙከራውን ለማድረግ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ነገር ግን አሁንም ቢሆን የክትባት ሙከራ ጉዳይ አፍሪካውያንን እያከራከረ ነው። በክርክሩ ገበታ ከፊት የሚሰየመው ደግሞ "የቅኝት ግዛት አስተሳሰብ" የሚለው ነው። ይህ መከራከሪያ የተሰማው ሁለት ፈረንሳውያን የሕክምና ባለሙያዎች የክትባቱን ሙከራ በአውሮፓ እና በአውስትራሊያ ስለማድረግ በቴሌቪዥን ቀርበው ሃሳብ ከሰጡ በኋላ ነው። በዚህ የቴሌቪዥን ክርክር ላይ ታዲያ በአፍሪካም ሙከራው መደረግ እንዳለበት በመግለጽ ተስማሙ። በወቅቱ የሕክምና ባለሙያዎቹ ለክርክራቸው ያቀረቡት አስረጅ ያለ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ያለ በቂ ሕክምና በአፍሪካ እንዴት ቫይረሱ ሳይስፋፋ ቀረ የሚለው ነው። ከዚያም ሙከራው አፍሪካ ውስጥ መደረግ እንዳለበት ሃሳብ ሰጡ። ይህ የሕክምና ባለሙያዎቹ ንግግር ግን ከተለያዩ ወገኖች ተቃውሞን አስተናግዷል። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከአንድ ተመራማሪ እንዲህ አይነት አስተያየት መስማት አሳፋሪና አፀያፊ ነው" ያሉት የዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ናቸው። "ይህንን ሃሳብ በቻልነው መጠን ሁሉ እናወግዘዋለን፤ እናም የማረጋግጥላችሁ ነገር አይሆንም፤ የቅኝ ግዛት የዞረ ድምር መቆም አለበት" ነበር ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ በወቅቱ። በዚህ እሰጥ አገባ ውስጥ ድምጻቸው የተሰማው ሌሎች ታዋቂ አፍሪካውያን ደግሞ ዲዲየር ድሮግባና ሳሙኤል ኤቶ ናቸው። ድሮግባ በትዊተር መልዕክቱ ላይ "አፍሪካውያንን እንደ ጊኒ ፒግ መሞከሪያ ለማድረግ አትቋምጡ፤ ያስጠላል" ብሏል። ይህ የተለያዩ ሰዎች ቁጣ መሰረተ ቢስ አይደለም። ዘረኝነትና የምጣኔ ሃብት ልዩነት በጤና ተቋማትም ውስጥ እንደሚታይ በሚገባ ተሰንዶ የተቀመጠ ነው። የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች በአፍሪካ ለሰው ልጅም ሆነ ለሙያው ስነምግባር ግድ ሳይሰጣቸው ሙከራ ማድረጋቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ይገኛሉ። ለምሳሌ እአአ በ1996 ግዙፉ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ፋይዘር በናይጄሪያ ሰሜናዊ ግዛት ካኖ የመድሃኒት ሙከራ አድርጎ ነበር። ፋይዘር የመድሃኒት አምራች የመድሃኒት ሙከራ ያደረገባቸው የናይጄሪያውያን ሕፃናት የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል በዚህም የተነሳ ረዥም ጊዜ የፈጀ የሕግ ክርክር ተደርጎ ግዙፉ የመድሃኒት አምራች በመድሃኒት ሙከራው ላይ ለተሳተፉ የተወሰኑ ልጆች ወላጆች ካሳ እንዲከፍል ተደርጓል። በዚህ ምርምር ላይ በተሰጣቸው የፀረ ባክቴሪያ መድሃኒት የተነሳ 11 ልጆች ሲሞቱ በርካቶች ደግሞ የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል። በወቅቱ ልጆቹ በምርምር ላይ እንዲሳተፉ ኩባንያው ከቤተሰቦቹ ስላገኘው ፈቃድ ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ከሁለት አስርታት በኋላ፣ በኡጋንዳ ከሚገኙ ተመራማሪዎች መካከል አንዷ የሆነችው ካትሪን ኪዮቡቱንጊ ነገሮች ስለመቀየራቸው ያስረዳሉ። አሁን ምርምር ለማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም አካል ጥብቅና ግልጽ የሆነ ሂደት ማለፍ አለበት ይላሉ። የአፍሪካ ስነ-ሕዝብ እና ምርምር ማእከል ኃላፊ ዶ/ር ኪዮቡቱንጊ "የግለሰቦችን ደህንንት ለመጠበቅ የሚሰራ ስራ አለ" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እኚህ ግለሰብ ሰዎች ሙያዊ ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን የራሳቸውን የሙያ ህይወት አደጋ ላይ መሆኑን ያስረዳሉ። "በክትባት ሥራ ውስጥ የተሰማራ አንድ ተመራማሪ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ሰዎችን የሚገድል እንዲሆን አይፈልግም" በማለትም "የሰዎች ሕይወትና የሥራ ታሪክ አደጋ ላይ ነው፤ ሰዎች በሙያቸው ላይ ከፍተኛ ጊዜና ገብዘብ አጥፍተዋል" ብለዋል። አክለውም የግለሰቦችን ደህንንት ለመጠበቅ በአገርና በተቋማት ደረጃ የሚሰራ ሥራ መኖሩን ገልፀዋል። አገራት የመድሃኒት ምርምሮችንና ሙከራዎችን ቁጥጥር የሚያደርጉ አካላት እንዳሏቸው ይገልፃሉ። "የክትባት ምርምሮችን ሁሉንም የክትባት ደህንነት ቅደመ ሁኔታዎች ሳይከተሉና ሳያሟሉ ለእርሱም ማረጋገጫ ሳያገኙ ማካሄድ አይቻልም" ሲሉ ያስረዳሉ። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት በዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ የሚካሄዱ የመከላከልና ክትባት ምርምሮችን የሚከታተሉት ሪቻርድ ሚሂጎ ናቸው። "በምርምር ስርዓት ውስጥ አፍሪካውያን ደህንነታቸው ባልተጠበቁ ምርቶች እንዳይጎዱ የሚያደርግ የደህንነት ጥበቃ እንዲሁም ማበረታቻዎች አሉ" ካሉ በኋላ ምርምር የሚያደርጉ አካላት ማንኛውንም መድሃኒትም ሆነ ክትባት በመሸጥም ሆነ በማምረት ውስጥ እንዲሳተፉ እንደማይፈቀድ ገልፀዋል። ይህ ማረጋገጫ ግን የብዙ አፍሪካውያንን ልብ እንዳያሳርፍ እንቅፋት የሆነው የሐሰተኛ መረጃ ዘመቻዎች ናቸው። ጥቁር ሕዝቦችን ለማጥፋት ያለሙ ጎጂ ክትባቶች እየተሰሩ ነው የሚል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እዚህም እዚያም ይሰማል። ለምሳሌ ሰባት ሴኔጋላዊ ሕፃናት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ተሰጥቷቸው ሞቱ የሚለው የፌስቡክ ሐሰተኛ ወሬ በርካቶችን አሸብሮ ነበር። ይህ ወሬ ደግሞ የተሰማው የፈረንሳውያኑ የሕክምና ባለሙያዎች አስተያየት ከተሰማ በኋላ መሆኑ ጉዳዩን አባብሶት ነበር። የዓለም ጤና ድርጅትም ኮሮናቫይረስን ከመከላከል ጎን ለጎን የሐሰተኛ መረጃዎችንም መዋጋት እንደሚያስፈልግ አስታውቆ ነበር። በአፍሪካ ያለው በቂ ትኩረት ያላገኘው ችግር ደግሞ የጤና ስርዓቱ ተገቢው ድጋፍ ሳይሰጠው መቆየቱ ነው። የአፍሪካውያን መሪዎች እአአ በ2001 የጤና ስርዓቱን ለማሻሻል ከዓመታዊ በጀታቸው ቢያንስ 15 በመቶ ለመመደብ ቃል ገብተው ነበር። ነገር ግን ከ54 አፍሪካ አገራት ይህንን ማሳካት የቻሉት አምስት ብቻ ናቸው። አፍሪካ የምሁራን እጥረት ባይኖርባትም አብዛኞቹ ወደተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ተቋማት በመሄድ ምርመራቸውን ማካሄድ ይመርጣሉ። ለዚህም ምክንያታቸው በቂ የሆነ በጀት አለመኖሩ መሆኑ ይገለፃል። በዚህም የተነሳ የአፍሪካውያን የጤና ችግሮች በሚገባ አልተዳሰሱም። በአገራቸው የምርምር ስራቸውን ለማካሄድ የወሰኑም ቢሆኑ ደጋፊ አካላትን ለማግኘት ፈተና ይሆንባቸዋል፤ በዚህም የተነሳ በርካታ ምርምሮች በደቡብ አፍሪካና በግብጽ ብቻ ይደረጋሉ ማለት ነው። በተጨማሪም በርካታ የክሊኒክ ሙከራቸውን አልፈው የሚወጡ መድሃኒቶች ሙከራ የሚደረግባቸው በአደጉ አገራት ይሆናል። በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ሙከራ ተደርጎላቸው ለገበያ የሚቀርቡ መድሃኒቶች በአፍሪካ ፈዋሽነታቸው አልተረጋገጠም ማለት ነው። ምስራቅ አውሮፓ፣ እስያ እንዲሁም መካከለኛው ምስራቅ ምንም እንኳ የሕዝብ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢሄድም የመድሃኒት ምርምርና ሙከራዎች ላይ ሲሳተፉ አይስተዋልም። ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በመላው ዓለም የሚሰራ የኮቪድ-19 ክትባት መሰራት እንዳለበት ይስማማሉ። አክለውም አፍሪካ ከምርምር ስራዎች ራሷን ማግለሏ ከዚህ ቀደም የነበራትን የመገለል ታሪክ ማስቀጠል ነው ብለዋል። "ክትባቱ በዩናይትድ ኪንግደም ሙከራ ተደርጎበት አፍሪካውያንን ለማከም ቢውል ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም የተለያዩ ሁኔታዎች ናቸው ያሉን፣ የዘረመል ዓይነታችን ክትባቱ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል" ይላሉ ዶ/ር ኪዮቡቱንጊ። "የተለየ ዝርያ እንዲሁም የተለየ የበሽታ ታሪክ አለን፤ በርካታ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎችም የሚገኙት እዚህ አፍሪካ ውስጥ ነው" ነገር ግን ተመራማሪዋ አሁንም ፍራቻቸው አፍሪካ ምንም ቢሆን መገለልዋ ላይቀር ይችላል የሚል ነው። ምክንያቱ ደግሞ አህጉሪቱ አሁንም የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ ላይ ችግሮች ያሉባት መሆኑ ነው። " አፍሪካ የምትጋፈጠው ትልቁ ችግር ክትባቱ ቢገኝም ሃብታም አገራት ሁሉንም ገዝተው ለአፍሪካውያን የሚቀር ላይኖር ይችላል" ይላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያዩ የዓለም አገራት መሪዎች ክትባቱ ሲገኝ አገራት በእኩልነትና በፍትሃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠይቀዋል። የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶችና እንዳይዘን ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ
47810951
https://www.bbc.com/amharic/47810951
ከኢቲ 302 አደጋ ጋር በተያያዘ ኬንያውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድንና ቦይንግን ሊከሱ ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ 302 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ተሳፍረው በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ኬንያውያን ቤተሰቦች ከአደጋው ጋር በተያያዘ አየር መንገዱንና ቦይንግን እንከሳለን አሉ።
ከሟቾቹ 157 ሰዎች መካከል 32ቱ ኬንያውያን ነበሩ። የሟቾች ቤተሰቦች እንደሚሉት ከሆነ አየር መንገዱ እና ቦይንግ ለመሞታቸው ኃላፊነቱን መውሰድ አለባቸው። የሟች ቤተሰቦች ኬንያ እና አሜሪካ በሚገኙ የጠበቃ ቡድን የተወከሉ ሲሆን ክሱም የሚመሰረተው በሃገረ አሜሪካ እንደሚሆን ታውቋል። • ET 302 የተከሰከሰበት ምክንያት ቅድመ-ሪፖርት ዛሬ ይወጣል • አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 የገጠመው ምን ነበር ? ከዚህ ቀደምም በአደጋው ህይወቱ ያለፈው ሩዋንዳዊ ጃክሰን ሙሶኒ ዘመዶች በአሜሪካ ቦይንግን መክሰሳቸው ይታወሳል። በክሳቸው ላይ አደጋ የደረሰበት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በአውቶማቲክ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓቱ ላይ የዲዛይን ችግር አለበት ሲሉ አመልክተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአደጋው በኋላ ቦይንግ ከኢንዶኔዢያው ላየን አየር መንገድ ጋር በተያያዘም ከሟች ቤተሰቦች በርካታ ክሶች ቀርበውበታል።
news-53758756
https://www.bbc.com/amharic/news-53758756
የኮሮናቫይረስ ክትባት ፡ የ"ቭላድሚር ፑቲንን ክትባት" እንዴት እንመነው?
ሳይንስ አቋራጭ አያውቅም። በድግግሞሽና በሙከራ የሚፈተሽ ነው። ለዚያም ነው ሳይንስ የተባለው።
ምናልባት ጀብደኝነትና ሳይንስ አብረው አይሄዱ ይሆናል። አሁን ቭላድሚር ፑቲን እየተተቹ ያሉትም በዚሁ ነው። ብሔራዊ ኩራት ሌላ፤ ሳይንስ ሌላ እየተባሉ። ምናልባት ይህ ትችት ምዕራቡ ለፑቲን ያለውን ጥላቻ በሳይንስ አስታኮ እየገለጠው ይሆን? ምናልባት መቀደም ያመጣው መንፈሳዊ ቅናት ይሆን? አገራት ክትባቱን በማግኘት ረገድ ቀዳሚ ለመሆን ድምጽ አጥፍተው በሚራኮቱበት ወቅት ፑቲን 'ተቀድማችኋል' ቢሏቸው ምዕራባዊያን እንዴት ላይከፋቸው ይችላል? ሌሎች ደግሞ መሀል ገብተው "ተው እንጂ! ይሄ የምሥራቅ የምዕራብ ጉዳይ አይደለም፤ ይሄ ሳይንስ ነው፤ ነገሩን በሳይንስ መስፈሪያ ብቻ እንስፈረው፤ ነገሩን በሳይንስ መነጽር ብቻ እንመልከተው" ይላሉ። ለመሆኑ የፑቲን ክትባትን እንዴት እንመነው? ሳይንሳዊ ሥነ ዘዴዎችን መዝለልና ፍቱን ክትባት ማግኘትስ ይቻላል? ይህን ለመመለስ የሳይንስ መነጽራችንን መደቀን ሳይኖርብን አይቅርም። ክትባቱን አግኝተነዋል የዘላለም የሩሲያ ፕሬዝዳንት የሆኑ የሚመስሉት ቭላድሚር ፑቲን ለዓለም አዲስ ብስራት አሰምተዋል። በአገር ውስጥ በተደረገ ምርምር አገር በቀል ክትባት አግኝተናል፤ ሰዎች ላይ አገልግሎት እንዲውልም ይፋዊና ብሔራዊ ፍቃድ ሰጥተናል ብለዋል። በዚህ ረገድ የትኛውም የዓለም አገር ለየትኛውም ክትባት ሙሉ ዕውቅና ሰጥቶ ስለማያውቅ ፑቲንና አገራቸው በዚህ ረገድ የመጀመሪያው ይሆናሉ። አሁን ሳይንቲስቶችን እያነጋገረ ያለው ነጥብ የትኛውም መድኃኒት ወይም ክትባት ሲፈጠር ሦስት ጥብቅ ምዕራፎችን ማለፍ እያለበት ፑቲን በሁለት ምዕራፍ ብቻ መድኃኒቱ ተፈጠረ ማለታቸው ነው። ክትባት ሲፈጠር ሰው ላይ ለሁለት ወራት ብቻ ተሞክሮ ውጤታማ ነው ማለት አይቻልም። ፑቲን ግን ክትባቱ ሁሉንም የሙከራ ደረጃዎችን በአጥጋቢ ሁኔታ ማለፍ ችሏል ነው የሚሉት። ፑቲን የሰው ልጅን የቤተ ሙከራ አይጥ አድርገዋል በሚል እንዳይወነጀሉ ሊሆን ይችላል ክትባቱ ከተሰጣቸው ዜጎች መሀል ሴት ልጃቸውን አስገብተዋታል። አሁን ነገሩ ሁሉ ስለተጠናቀቀ በመጪው ኅዳር ክትባቱን በገፍ ማምረት እንጀምራለን ብለዋል። በዚህ ዜና በቅድሚያ ከደነገጡት መሀል ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩት የዓለም ጤና ድርጅት ነው። ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት ይህ ዜና ገና ይፋ ከመሆኑ በፊት "ሩሲያ እባክሽን በክትባት ምርምሩ ሂደት እኛ ያስቀመጥናቸውን ሒደቶች ተከተይ" ሲል ተማጽኗታል። ማክሰኞ ደግሞ ድርጅቱ እንዳለው ከሩሲያ የጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ንግግር ጀምሯል። ስፑትኒክ-5 ጥድፊያ ከሳይንስ ይልቅ ለብሔራዊ ኩራት ቅድሚያ እንደሰጠ አንድ ማሳያ ሆኖ የቀረበው ለክትባቱ የተሰጠው ስም ነው። ስፑትኒክ-5 (Sputnik-V) የሚል የቁልምጫ ስም ነው የተሰጠው። ስፑትኒክ ወደ ጨረቃ ያቀናችው በዓለም የመጀመሪያዋ የሩሲያ ሳተላይት ናት። ስፑትኒክ በሩስኪ ቋንቋ ሳተላይት ማለት ነው። ነገሩ የቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ በአሜሪካና በሶቭየት ኅብረት መካከል የነበረውን የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የጦር መሣሪያ ምርት ትንቅንቅና ፉክክር ለማስታወስ ይመስላል። የሚገርመው ይህ ተሳካ የተባለው ክትባት በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዝርዝር ውስጥ ምዕራፍ ሦስት ከደረሱ ስድስት ተስፋ ሰጪ ክትባቶ አንዱ ሆኖ እንኳ አልተመዘገበም ነበር። ምዕራፍ ሦስት የክትባት ሙከራ ማለት ክትባቱ በምዕራፍ ሁለት በተመረጡ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ከተሞከረ በኋላ አጥጋቢ ውጤት ሲያሳይ በርከት ባሉ ሰዎች ለመጨረሻ ዙር ሙከራ የሚያልፍበት ደረጃ ነው። በክሊኒካል ደረጃ አሁን መቶ የኮቪድ-19 ሙከራዎች በመላው ዓለም ቤተ ሙከራዎች ውስጥ ይገኛሉ። የፈለገ ፈጣንና ቀልጣፋ አሰራር ቢዘረጋ አስተማማኝ የኮቪድ-19 ክትባት እስከ ሚቀጥለው የፈረንጆች 2021 አጋማሽ ድረስ እውን ሊሆን አይችልም ይላሉ እውቅ የጤና ጉዳይ አዋቂዎች። ይህም ማለት አሁን ካለንበት ብንቆጥር ገና 10 ወራትን መጠበቅ ማለት ነው። እስከዚያ ድረስ ስንቶቻችን በሕይወት እንቆይ ይሆን? ማነው ይህን ክትባት ያመረተው? በዓለም የመጀመርያው የተባለው ይህ ስፑትኒክ-5 ክትባት ሞስኮ የሚገኘው ጋማሊያ ኢንስቲትዩት ነው ያመረተው። ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ክትባቱ አስተማማኝ የመከላከል አቅም ይሰጣል። ፑቲን በበኩላቸው ገና ቀደም ብሎ "ይህ ክትባት አስተማማኝ እንደነበር አውቅ ነበር" ብለዋል። "ሁሉንም ሳይንሳዊ ሂደቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማለፍ ችሏል" ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል። ፑቲን ከልጆቻቸው ለአንዷ ክትባቱ ተሰጥቷት ትንሽ አተኮሳት እንጂ ምንም አልሆነችም ብለዋል። ፑቲን የትኛዋ ልጃቸው ክትባቱን ወስዳ እንዳተኮሳት ግን በስም አልገለጹም። ሩሲያዊያንን ያስገረመው ታዲያ ፑቲን በታሪካቸው ስለ ሴት ልጆቻቸው ማሪያ ቮሮንዞቫ እና ካተሪና ቲኮኖቫ በሚዲያ ሪፖርት ላይ ተናግረው አለማወቃቸውና አሁን ግን ይህን ማድረጋቸው ነው። የሩሲያ ሳይንቲስቶች የመጀመሪያ ዙር ሙከራዎች ተደርገው ሁሉም ድንቅ ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል። ሳንቲስቶቹ ሰዎች ላይ ጉንፋንን የሚያመጣው አዲኖቫይረስ የተሰኘውን የተላመደ የተህዋስ ቅንጣት ተጠቅመው ነው ክትባት ሰራን ያሉት። ይህን ለማዳ ተህዋሲ አዳክመው ወደ ሰውነት በማስገባት ሕዋስ በማቀበል ክትባቱ ሰውነት ኮቪድ-19 ተህዋሲ ሲገባ ነቅቶ እንዲዋጋ ያደርገዋል ብለዋል። አሁን የሩሲያ የጤና ባለሥልጣናት ለዚህ ክትባት እውቅና የሰጡት ክትባቱ በብዙ ሺህ ሰዎች ሳይሞከር መሆኑ ነው ጥያቄ ያስነሳው። በተለመደው አሰራር ምዕራፍ ሦስት የደረሰ ክትባት ወደ ገፍ ምርት ከመገባቱ በፊት በሺህዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ይሰጣል። በዚህ ሂደት ክትባቱ የሚሰጣቸው በተለያየ የዕድሜና የጤና ሁኔታ ላሉ ሰዎች ይሆናል። ይህም ክትባቱ የማይታወቅ አሉታዊ ጎንዮሽ ጉዳት ሰዎች ላይ እንዳያደርስ ለመቆጣጠር ነው። ባለሙያዎች አንድ ክትባት ምዕራፍ ሦስት ላይ የሚገኘውን ሙከራ በብዙ ሺህ ሰዎች ላይ ካላደረገ እንደ ፍቱን ክትባት አይቆጠርም ይላሉ። ገለልተኛ የጤና ባለሙያዎች ይህን ይበሉ እንጂ የሩሲያ የጤና ሚኒስትር ያገኘነው ክትባት ፍቱን ነው፤ ምንም ስጋት አይግባችሁ ብለዋል። ጨምረውም "ይህ ለሩሲያ ብቻ ሳይሆን ለሰው ዘር በሙሉ ትልቅ ድል ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የሩሲያው ጤና ሚኒስትር (በስተግራ) በክትባቱ ላይ የተነሳውን ጥርጣሬ መሰረተ ቢስ ብለውታል የሩሲያና የሌሎች አገራት ሙከራ ከዚህ ቀደም ዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካና ካናዳ፤ ሩሲያ የክትባት ግኝት ምስጢሮችን ልትሰርቀን ሞክራለች ሲሉ ተችተዋታል። ሩሲያ ክትባቱን ለመፍጠር የሄደችበት ፍጥነት በሕክምና ምርምር ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። የመጀመሪያው የክሊኒካል ሙከራዋን ያደረገችው እጅግ ዘግይታ በሰኔ 17 ነበር። በቻይና፣ በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ ሳይንቲስቶች ከዚህ ቀን እጅግ ቀደም ብለው ነበር የጀመሩት። ሌላው የፑቲንን ክትባት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው የጋማሊያ ኢንስቲትዩት ከክትባቱ ጋር በተያያዘ ያሉ እጅግ ጠቃሚ ዳታዎችን (መረጃዎችን) ለማንም አለማጋራቱ ነው። ይህ ገለልተኛ ሳይንቲስቶች በክትባት ውጤቱና ስኬታማነቱ ዙርያ ምንም አስተያየት እንዳይሰጡ አድርጓቸዋል። ምክንያቱም ምንም መረጃ በእጃቸው ስለሌለ ነው። ፑቲን ለዓለም አንድ ጥርት ያለ መልዕክት ማስተላለፍ የፈለጉ ይመስላል። የሩሲያ ሳንቲስቶች እጅግ የላቀ ብቃት እንዳለቸውና አገራቸው ልዕለ ኃያል እንደሆነች። ነገር ግን ይህ አገራዊ ጀብደኝነት ለሳይንስ የሚጥም አይደለም። እስካሁን የትኛውም የኮቪድ-19 ክትባት በሽታውን መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ አልተከላከለም። አሁን ጥያቄው የፑቲን ክትባት ይህን ያደርጋል ወይ ነው። ይህ በእንዲህ እያለ መቀመጫውን ሞስኮ ያደረገው የክሊኒካል ትራያልስ ኦርጋናይዜሽን የተባለውና በሩሲያ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎችን የሚወክለው ቡድን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ምዕራፍ ሦስት የሙከራ ደረጃን ሳያጠናቅቅ የክትባቱን ስኬታማነት ይፋ እንዳያደርግ ተማጽኖ ነበር። የቡድኑ ሥራ አስፈጻሚ ስቬትላና ዛቪዶቫ እንደሚሉት አንድ መድኃኒት ምዕራፍ አንድና ሁለትን ስላለፈ ፍቱን ነው ተብሎ አይታወጅም። የፑቲን ክትባት ደግሞ በ76 ሰዎች ላይ ነው የተሞከረው። በምንም ሁኔታ በ76 ሰዎች ላይ የተሞከረን ክትባት ፍቱን ነው አይደለም ልንል አንችልም ብለዋል። የፑቲን የክትባት ሰበር ዜና ከሳይንስ ይልቅ ብሔራዊ ኩራትን ያስቀደመ ነበር የሚባለውም ለዚሁ ነው። ፍቱኑን ክትባት ለማግኘት አንድ 10 ወራት ያስፈልጉ ይሆናል። እስከዚያው ግን ተስፋም ዕድሜ ነው። ፑቲን ክትባት ሳይሆን ተስፋን ይሆናል ለዓለም ያበሰሩት። በክትባቱ ላይ የተሰነዘረው ትችት "መሰረተ ቢስ ነው" ማክሰኞ ዕለት ሩሲያ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ካሳወቀች በኋላ በሕክምናው ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች ጉዳዩ በጥንቃቄ መያዝ እንዳለበት በመግለጽ በክትባቱ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ሩሲያ በሰጠችው ምልሽ ከየአቅጣጫው እየተሰነዘረ ያለው ስጋት "መሰረተ ቢስ" ነው ስትል በክትባቱ ላይ ያላትን መተማመን ገልጻለች። የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር ሚኻይል ሙራሽኮ እንዳሉት "በውጭ አገራት ያሉ ባልደረቦቻችን ያገኘነው ክትባት ከሌሎች አንጻር ተፎካካሪ የበላይነት እንዳለው ተገንዝበው ፍጹም መሰረት ቢስ አስተያየት ለመስጠት እየሚከሩ ነው" ሲሉ ኢንትርፋክስ ለተባለው የዜና ወኪል ተናግረዋል። ጨምረውም ክትባቱ በቅርቡ ለአገልግሎት እንደሚቀርብ ጠቅሰው "የመጀመሪያው ጥቅም ላይ የሚውለውን ክትባት በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት ውስጥ እንረከባለን. . . በቀዳሚነት ለሐኪሞች የሚሰጥ ይሆናል" ብለዋል ሚኒስትሩ። አሁንም ክትባቱ ላይ ከተለያዩ ወገኖች ጥያቄዎች እየተነሱበት ቢሆንም የሩሲያ ባለስልጣናት እንዳሉት በመጪው ጥቅም ት ላይ ክትባቱን በስፋት ለሕዝቡ ለመስጠት ዕቅድ ይዘዋል።
news-45394406
https://www.bbc.com/amharic/news-45394406
መስከረም ኃይሌ፡ ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት
ይህንን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እርሷን ማነጋገር ከጀመርንበት የአውሮፓውያኑ ሰኔ፣ አሁን እስካለንበት መስከረም ወር በጀርመን፣ ቦን የተካሄደውን ዓለም አቀፍ የሚዲያ ጉባዔን ታድማለች።
በሰሜን አሜሪካ ዳላስ፣ ቴክሳስ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ባዘጋጀው የባህል ትዕይንተ-ሕዝብ ላይ ተገኝታለች፤ ዋሽንግተን፣ ቨርጂኒያና ካሊፎርኒያ ተጉዛለች። በሶማሊላንድ ሃርጌሳ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ላይ ከተፍ ብላለች። በቅርቡ በጀርመን በአውሮፓ የኢትዮጵያ ስፖርትና የባህል ፌደሬሽን ባሰናዳው የባህል ፌስቲቫል ላይ 'ኮይልን' ላይ አልታጣችም። በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በሚካሔደው የመጻሕፍት ፌስቲቫል ላይ ለመታደም እንደበረረች ከግል የፌስቡክ ገጿ ለመረዳት ችለናል። ይህ ሁሉ ጉዞ ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ የሆነ ነው። "ሁልጊዜም በውስጤ የሚመላለስ የሆነ ድምጽ ነበር፤ የሚያጓጓ፣ ደስ የሚል፣ የሚያስፈራ፣ የሚያረጋጋ፣ የሚያበረታታ። ከራሴ ጋር አወራለሁ ፤ እሟገታለሁ፤ ከሐሳቤ ጋር እጨቃጨቃለሁ። ብቻ እውን ሆኖ እንዳየው እጓጓ ነበር" ትላለች መስከረም ኃይሌ ልጅነቷን ዞር ብላ ስታስታውስ። ህልሟን እንኳን በውል ማስረዳት አትችልም፤ ህልሟ ለማንም የማትነግረው ምስጢር ነበር። "የአምስት ወይም የስድስት ዓመት ልጅ ነበርኩ። ትንሿ እኔነቴ፤ ህልሜ ከዕድሜዬና ከኑሮዬ እጅግ የገዘፈ እንደነበር ታውቃለች፤ ነገር ግን በድብቅ ጉዳዩን አብዝቼ አስብበት ነበር። በምስጢር ነበር የማስብበት፤ ለምወዳት እናቴ እንኳን አልተናገርኩም" ትላለች። ከፍ እያለች ስትመጣ ከህልሟ ጋር መለማመድ ጀመረች። ከሰዎች ጋር የመገናኘት፣ የመማማር፣ ዓለምን የመዞር ፍላጎቷ አየለ። ህልሟ ወለል ብሎ ይታያት ጀመር። ከአንታርክቲካ በስተቀር የዓለማችንን ሁሉንም አህጉሮች አዳርሳለች። አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ ኤዥያ፣አውስትራሊያ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ደቡብ አሜሪካ፤ ከመቶ በላይ የዓለማችን አገራትም እንግዳ ሆናለች። ከአፍሪካ ሶማሌ ላንድ፣ ታንዛኒያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ፣ ቦትስዋና፣ ዝምባብዌ አገራትን አዳርሳለች። ካልሃሪ በርሃ፣ የካልሃሪ በርሃ ፈርጥ ነው የሚባለውን ኦኮቫንጎ በርሃ፣ ቪክቶሪያ ፏፏቴ፣ በታንዛኒያ የሚገኘውን ንጎሮንጎሮ አስደማሚ ቦታ ትንፋሿን ሰብስባለች፤ በአባይ ወንዝ ታንኳ ቀዝፋለች፤ ቀይ ባሕርን ጠልቃ ዋኝታለች፤ በግብጽ የንጉሦች በር (Valley of the Kings) ገብታለች። በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ከቤተሰቡ ከተረፈው ብቸኛው ፓትሪክ ጋር ተጨዋውታለች። በኬንያ ማሳይ ማራ የዱር እንስሳትን የቡድን ፍልሰት ተመልክታለች። ከእግር እስከ ግመል፤ ከአውቶብስ እስከ ባቡር፤ ከመርከብ እስከ አውሮፕላን ተጓጉዛለች። ተራራ ወጥታለች፤ ቁልቁለት ወርዳለች፤ ባሕር ተሻግራለች፤ ከአንበሳ ጋር ሰላምታ ተለዋውጣለች፤ ከዱር እንስሳት ጋር ተዋውቃለች። የተለያየ ባህል ካላቸው ማኅበረሰቦች ጋር ቤተሰብ ሆናለች ፤ ባህላቸውን ተጋርታለች፤ አብራቸው ማዕድ ቆርሳለች፤ ሕይወታቸውን አጣጥማለች። ከበርካታ ባህሎች ጋር ተዋውቃለች፤ በርካታ ወዳጆችን አፍርታለች። • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ነው። በአስር የተለያዩ አገሮች ኖራለች፤ ሰርታለች። በአሁኑ ሰዓት የካናዳዋን -ሞንትሪያል ዞራ ማረፊያዋ አድርጋታለች። 'አቢሲኒያን ኖማድ' የተሰኘ የሕይወት ታሪኳና የጉዞ ማስታወሻዎቿ የተካተቱበት መጽሐፍ ለንባብ አብቅታለች። የጉዞዋ ጥንስስ በልጅነቷ የጠነሰሰችውን ዓለምን የመጎብኘት ህልም በአቅራቢያዋ ያሉትን ቦታዎች በመጎብኘት ተብላላ። ለቤተሰቧ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው መስከረም የእናቷ የሥራ ባህሪ ከቦታ ቦታ የሚያንቀሳቅስ ስለነበር የተለያዩ ቦታዎችን የመጎብኘት እንቅስቃሴዋን ሀ ብላ ጀመረች። የመጽሐፍት ወዳጅ መሆኗም የአዕምሮዋ ከፍታ ከአካባቢዋ አሻግራ ማየት እንድትችል አድርጓታል። ለዚህ ሁሉ አስተዳደጓ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው። በቤተሰባቸው መካከል የነበረው በግልጽነት የተሞላ ውይይት እርካቧ ነበር። ከጉዞ መልስ ያዩትን፣ የወደዱትን፣ ያልወደዱትን ፣ የተማሩትን መነጋገራቸውና መጠያየቃቸው የምትጓዝበትን መንገድ ክፍት አድርጎ ኪሎ ሜትሩን እያራቀው መጣ። ህንድ አገር ለትምህርት ባቀናችበት ወቅትም በህንድ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎችን በማየት የረጅም ርቀት ጉዞዋን ጀመረች። • ታይዋናዊ ቱሪስት ፎቶ ሊያነሳው በነበረው ጉማሬ ተነክሶ ሞተ "ሰዎች በተለያየ ምክንያት ጉዞ ያደርጋሉ፤ የእኔን ለየት የሚያደርገው ተጋብዤ ወይም ለትምህርት አሊያም ለስራ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሆነ ብዬ ለማየት ስለምሄድ ነው። በየጊዜው አንዳንድ ቦታ እየሄድኩኝ፤ በራስ መተማመኔ እየተሻሻለ ፤ እውቀቴ እያደገ መጥቶ እየቀለለኝ ሄደ እንጂ ባንድ ጊዜ እዚህ አልደረስኩም።"ትላለች። መስከረም እንደምትለው ሴቶችን የመርዳት ፍላጎት ያደረባትም ከልጅነቷ ጀምሮ ነው፤ ለዚህም ደግሞ ተጓዥ መሆኗ ጠቅሟታል። በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረገቻቸው ጉዞዎች በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ልጆች ትምህርት ቤት እንደማይሄዱ ስታውቅ ፤ ሴቶች የተሸከሙትን የሥራ ኃላፊነት ስትረዳ የእነርሱ ጉዳይ የቤት ሥራዋ ሆነ። "ሌሎች ህልማቸውን እንዲያሳኩ ለማበረታታትና የሚከተሉኝን አፍሪካውያን ሴቶች፤ ማህበረሰቡ በልምድ ካስቀመጠው አስተሳሰብ ወጥተው ራሳቸውን እንዲመለከቱ የማድረግ ምኞት አለኝ" ትላለች። ፈታኝ አጋጣሚዎች እናቷ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ ትሰራ ነበር። ሁልጊዜም የልጇን የጉዞ ታሪኮች የሚያሳዩ ፎቶግራፎች በአጠገቧ በሚገኝ ሰሌዳ ላይ ትለጥፋቸዋለች። ይህ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሰሩ ሠራተኞች የቤተሰባቸውን ፎቶ በዚህ መልክ ማስቀመጥ የተለመደ ነው። ከከፍታ ላይ ስትዘል፣ አንበሳ ስትዳብስ ፣ ተራራ ስትወጣ ፣ ጀልባ ስትቀዝፍ ፣ ደክሟት አረፍ ስትል የተነሳቻቸውንና ሌላም ሌላም። ለሥራ ባልደረቦቿ ታስጎበኛቸዋለች። እጅግም ትኮራባቸው ነበር። • ጤፍን ሰዳ የምታሳድደው ኢትዮጵያ "የኋላ ኋላ እድሜዋ በሃያዎቹ መጨረሻ ሲደርስ በለጠፈቻቸው ምስሎች መደሰት አቆመች" ትላለች መስከረም። ምክንያቱ ደግሞ የእርሷ ባልደረቦች የተሞሸሩ ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ፎቶ ሲቀይሩ የእርሷ ግን ያው ነበርና ነው። ይህ ሃሳብ በእናቷ ብቻ የተገደበ አልነበረም። አያቷም እንዲሁ በዚሁ ጉዳይ ይነዘንዟት እንደነበር ታስታውሳለች። "እንደው ያንች ነገር!" ይሏታል በጨነቀው አንደበታቸው። • ጥቁር ገበያውን ማሸግ መፍትሄ ይሆን? በአንድ ቦታ ተወስና፣ አግብታ፣ ልጆች ወልዳ ልጆቿን እያሳደገች እንድትኖር የቤተሰቦቿ ምኞት ነበር። በምትሻገርበት ድንበር ሁሉ ይሄው ጉዳይ ፈተና ይሆንባታል። "እኔን ለማግባት ጥያቄ የሚያቀርቡ አሉ፤ የሚያገባኝ ያጣሁ ይመስል" ትላለች እርሷ ዓለምን በመመርመር ፍላጎት ተይዛለች። ይህ ሁሉ ከአላማዋ አላደናቀፋትም። ሉልን [የአለም ክብ ካርታ] እንደ ልጇ ስትዳብሰው፤ ስትዳስሰው ደስ ይላታል። ይሁን እንጂ የምታደርጋቸው ጉዞዎች አልጋ ባልጋ እንዳልሆኑም ትናገራለች። ከኬፕታውን እስከ ካይሮ ከኬፕታውን እስከ ካይሮ ያደገችውን ጉዞ በፈታኝነቱ የማትረሳውና ሁል ጊዜም ማንሳት የምትፈልገው ነው። ይህ ጉዞ ባልጠበቀችውና ባልገመተችው መልኩ እናቷ በጡት ካንሰር መያዟን የሰማችበት አጋጣሚ ነው። 'በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ' እንዲሉ ጥቁር አፍሪካዊት ሴት ሆኖ ተጓዥ መሆን በራሱ ፈታኝ ሆኖ እያለ የእናቷ ህመም ደግሞ ሌላ ራስ ምታት ነበር። "እናቴን በጡት ካንሰር ህመም አጣት ይሆን? በሚል ስጋት ተሰቅዠ የልጅነት ህልሜ ዕውን እንዲሆን የተጋፈጥኩበት ነበር" ስትል አጋጣሚውን ትገልጸዋለች። በውስጧ ከያዘችው ጭንቅ ባሻገርም በጉዞዋ የሚገጥማትም ቀላል አልነበረም። አብዛኛው የጉዞ መፃህፍት የተፃፉት አፍሪካውያን ባልሆኑ የምዕራባውያን ፀሐፍት ነው። ይህ ሁኔታ አፍሪካውያን በተለይ ሴት ጥቁር አፍሪካውያን ሊገጥማቸው የሚችለውን እውነታ የሚያንፀባርቅ እንዳልሆነ ታምናለች። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እናም እንደ አፍሪካዊና እንደ ሴት እኔን የገጠመኝ ግን ከተጻፈው በተቃራኒ ነበር ፤ ብዙ ጊዜ አፍሪካዊ ሴት ጉዞ ማድረግ ስህተትና ተቀባይነት የሌለው ተደርጎ ነው የሚወሰደው" ስትል ለአፍሪካውን ሴቶች የተሰጠውን ቦታ ደጋግማ ታነሳለች። እንደ አፍሪካዊት ሴት ጉዞ ስታደርግ በቦታው መገኘቷ ለሰዎች ምቾት አይሰጣቸውም። እዚያ መከሰቷ ትክክል እንዳልሆነ የሚያስቡት በርካቶች በመሆናቸው ያበሳጫት ነበር። ድንበር በተሻገረች ቁጥር አፍሪካዊ ሴት በመሆኗ ብዙ ጊዜ ጥያቄዎች ይዥጎደጎዱባታል። ለእርሱ ማብራሪያ መስጠት ልቧን ያዝለዋል። ሶማሊ ላንድ በዚህ ጉዞዋ ሶማሊ ላንድ ድንበር ልትደርስ ትንሽ ኪሎ ሜትር ሲቀራት በኢትዮጵያ ጉምሩክ ጣቢያ ሁሉም ተሳፍረውበት ከነበረው አውቶብስ ለፍተሻ ወረዱ። አንድ ሰው ወደርሷ ቀርቦ መታወቂያ ጠየቃት። ፓስፖርቷን አሳየችው። እያንዳንዱን ገጽ አገላብጦ ተመለከተ። ምን እየፈለገ እንደሆነ አልገባትም። በርካታ አገራት የተጓዘችበት ቪዛ ተመቶበታል። ኢትዮጵያዊ እንደሆነችና ፓስፖርቷ ላይ የተመታውን ማህተም ልታሳየው ሞከረች፤ ነገር ግን ይህ ሁሉ አላስጣላትም፤ የተሳፈረችበት አውቶብስ ጥሏት ሊፈተለክ ሆነ፡፡ በዚያ ላይ የያዛት ጉንፋን እየደቋቆሳት ነበርና እንግልቱ የባሰ አዳከማት። • "ቤቶቹ በማንኛውም ሰዓት ሊደረመሱ ይችላሉ" ሰላይ ነሽ ተባለች። ሻንጣዋን እያነሱ ወረወሩት። እቃውን ሁሉ እየዘረገፉ መበርበር ጀመሩ። ምንም ባያገኙባትም ከብዙ እንግልትና ጭቅጭቅ በኋላ እንደተፈታች የምትረሳው ጉዳይ አይደለም። ሌላው ፈተና አካላዊ ድካም ነው። አንዳንዴ ውሃና ምግብ የማይኖርበት አካባቢ አለ። ያኔ ችግር ነው። ረጅም መንገድ በአውቶብስ ወይም ተራራ ወጥታ ስለምትሄድ አካላዊ ድካሙም ቀላል አይደለም። በምታደርጋቸው ጉዞዎች ብዙ ነገሮች ይገጥመኛል የምትለው መስከረም የተለያየ አገራት ያላቸው የተለያየ ባህል፣ ልማድና የአኗኗር ዘይቤ በተለይ ለሴት ልጅ ፈታኝ ነው ትላለች። "ከአለባበስ ጀምሮ እስከ አቀማመጣችን ፣ አመጋገባችን ሳይቀር ደንብ መኖሩ ፈታኝ ነው። ቀድሞ ማወቅና መገንዘብ ያስፈልጋል። ቢሆንም ግን ሁሌም የሚታየኝ ዓለም እንዴት ውብ እንደሆነ፣ የሰዎች የአኗኗር ዘይቤ ፈጠራ ድንቅ እንደሆነ ነው። ተግዳሮት ቢኖረውም ለእኔ ግን ሽልማት ነው" በማለት ትገልጸዋለች። ተጓዥ መሆን በአጠቃላይ አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ የሆኑ ተግዳሮቶች እንዳሉት ትናገራለች። "ራሴን እጠይቃለሁ፤ ችግሮቹን እንዴት መፍታት አለብኝ እላለሁ ፤ ግቤን አስባለሁ ፤ ከዚም እቀጥላለሁ" ትላለች። 'የሺህ ተራራዎች' ከተማ ውለታ ከእናቷ ጋር የጠበቀ ቁርኝት ነበራት፤ የማይላላ፤ የማይፈታ። እናቷን በጡት ካንሰር አጣች፤ ሞት ለያያቸው። እናቷን ለሞት ስለዳረገው የካንሰር ህመም አስመልክቶ ጥያቄያችንን ያቀረብንላት መስከረም በዝምታ ተዋጠች፤ ሐዘን ውስጧ ሰረጎ ሲገባ ያስታውቅ ነበር። ካንሰር ልቧን ያደማው ጉዳይ ነው። በመጽሐፏም ስለ ህመሙ ጽፋለች ፤ የመነጋገር ባህል መዳበር አለበት ትላለች። "ስለ ካንሰር የማውራቱና እንደ ቤተሰብ ቁጭ ብሎ የመነጋጋሩ ልምድ የለም፤ እንደ መጥፎ ነገር ነበር የሚታየው፤ ቁጭ ብለን መነጋጋር አልቻልንም" በማለት የሆነውን ሁሉ ታስታውሳለች። የመጀመሪያ ጉዞዋን ሳትጨርስ ወደ እናቷ ተመለሰች፤ እናቷን በሞት ካጣች በኋላ ያቋረጠችውን ጉዞ እንደገና ጀመረች- ወደ ሩዋንዳ። ''እናቴ ሞታለች፣ እናቴ ሞታለች...' ይህንን እውነት ለራሴ ደጋግሜ እነግረዋለሁ፤ በአእምሮዬ ይመላለሳል፤ በመደጋጋም እውነታውን ለመቀበል ሞከርኩ። ደግሜ ሕይወቴን ማስቀጠል ታተርኩ። ነገሮች ሁሉ ተለዋወጡ። ሕይወቴን የሚካፈለኝ ማንም አልነበረም፤ በጉዞዬ የሚገጥመኝን ደስታና ሐዘን የምነግራት እናቴ ከጎኔ የለችም። እንደገናም 'ለካ በገፍ የምልክላቸውን የኢሜል መልዕክት የሚጠባበቁ ብዙ ጓደኞች አፍርቻለሁ' እላለሁ፤ ብርታት ይሰማኛል ቢሆንም ግን በሕይወቴ ተሰምቶኝ የማያውቅ ብቸኝነት በላየ ላይ ያንዣብብኝ ነበር። ይህ የኔ አዲስ ሕይወት ነው፤ ሁሉም ነገር አሁን መጀመር አለበት" ትላለች። ከእናቷ እረፍት በኋላ ወደ ሩዋንዳ - ኪጋሊ ጉዞ ጀመረች፤ ባልተረጋጋና ባልተጽናና መንፈስ ጉዞ ማድረጓ ያልተዋጠላቸው አባቷ አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ተከትለዋት እንድትመለስ ቢያግባቧትም አልተስማማችም። አውሮፕላን ውስጥ ገባች። በሃዘን የተሰበረ ልቧን ይዛ አንገቷን ደፋች። አውሮፕላኑ ውስጥ ማንም ያናገራት አልነበረም፤ ራሷን ማስተዋወቅ ፈለገች። "መስከረም እባላለሁ ..እናቴ ሞታለች…" የምታስበው ይህንን ብቻ ነው፤ የእናቷን ሞት አምና መቀበል ከብዷታል፤ ሳታስበው የወረደባት ዱብ እዳ ነበር ፤ ከራሷ ጋር እየተነጋገረች ኪጋሊ ደረሰች። "ኪጋሊ ጉዞዬን ለመቀጠል ጥሩ አገር ሆና አገኘኋት" ትላለች። "የሺህ ተራራዎች ከተማ ያሰኛትና ዙሪያዋን የከበቧት ተራራዎች ቀልብን ይስባሉ ከዚህ ቀደም እንዳየኋቸው ሌሎች የአፍሪካ አገሮች አይደለችም፤ የተረጋጋችና ንጹህ ናት- ኪጋሊ ራሴን የማዳማጥበትና ለራሴ ጊዜ የሰጠሁባት ከተማ ሆነች።" የምትለው መስከረም ኪጋሊ ቀልቧን የምትሰበስብበት ከተማ ሆና አግኝታታለች። ለምን ትጓዛለች? የጉዞዋን ወጭ የምትሸፍነው በግሏ ነው። ባጠራቀመችው ገንዘብና አንዳንዴም ከወዳጆቿ በሚቀርብላት ግብዣ ጉዞዋን ታከናውናለች። ያላትን ዕቃ ሽጣም ሆነ ሠርታ የምታገኘውን ሁሉ በአመዛኙ የምታውለው ለጉዞ ነው። አዲስ ጫማና ልብስ ልግዛ አትልም። ደስ ብሏት ገንዘቧን ጉዞ ላይ ታጠፋለች። ለምን? እያንዳንዱ አገርና ጉዞ ያደረገችበት ቦታ በሕይወቷ ላይ አንድ ነገር መጨመር አለበት ብላ ታምናለች። በራሷና በህልሟ ላይ እምነት እንዲኖራት፤ ሰውን እንድታምንና ነጻ አስተሳሰብ እንዲኖራትም አድርጓታል። "ሰዎችንና ባህሎችን በጅምላ ከመፈረጅ ይልቅ ነገሮችን እንዳሉ እንድመለከት፣ ከዚያም የምፈልገውን እንድወስድና የማልፈልገውን እንድተው አስተምሮኛል" ትላለች። የሰው ሐብታም እንድትሆን አድርጓታል፤ ብዙ ጓደኞችን አፍርታለች፤ ከሰዎች ጋር በቀላሉ እንድትግባባ ረድቷታል። "ዓለም ሰፊ ነው። በጣም ብዙ ነው። ብዙ እንደማላውቅ ይሰማኛል። ይህም ትሁት እንድሆን አድርጎኛል። ብዙ የሚመረመሩ ነገሮች አሉ፤ ብዙ ላያቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፤ በመሆኑም ያለኝንም እንዳደንቅ ፤ ሌሎችንም እንዳከብር ... አስተሳሰቤን አሳድጎታል" በማለት የጉዞዋን አበርክቶት ትገልጻለች። እንደ ማሳረጊያ "አፍሪካን የማቆራረጥ ህልም ካላችሁ ትችላላችሁ፤ ነገርግን ህልማችሁ የራሳችሁ መሆኑን እመኑ፤ ምክንያቱም አፍሪካ ውስጥ ጉዞ ማድረግ ህልማችሁ ላይ ያላችሁን እምነት ይፈታተናችኋል፤ አፍሪካ በየቀኑ የሚኖራችሁን መንፈሳዊና አካላዊ ጥንካሬ ይፈልጋል፤ ቢሆንም ግን ባልተነካና በሚማርክ ተፈጥሯዊ ውበት፣ በዱር እንስሳት፣ በተራራዎቿ ፣በአስደናቂ የባህል ህብር፣ ለጋሽ በሆኑት ህዝቦቿ ትክሳችኋለች፤ ይህም ብቻ አይደለም ሕይወታችሁን ትቀይሩበታላችሁ" ትላለች።
48048287
https://www.bbc.com/amharic/48048287
የአቶ ታደሰ ካሳ ባለቤት፡ «የእሥር ውሳኔውን ያስተላለፉት የተወሰኑ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንደሆኑ አውቃለሁ»
በትግል ስማቸው 'ጥንቅሹ' ተብለው የሚታወቁት እና የጥረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳ ከአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ የታገዱት ከወራት በፊት ነበር። ይህ ተሰምቶ ብዙም ሳይቆይ አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት ስምዖን መታሠራቸው ተዘገበ።
አቶ ታደሰ ካሳ አሁን አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት ከባህርዳር ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ። ጥር 15፣ 2011 ዓ. ም. የተፈጠረውን የሚያስታውሱት የአቶ ታደሰ ካሳ ባለቤት ወ/ሮ ነፃነት አበራ፤ «የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ሆነ አቶ ደመቀ እኛም ብንፈተሽ ብዙ ችግር አለብን ማለታቸውን አውቃለሁ» ይላሉ። ሙሉ ቃለ ምልልሱ እነሆ። ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ያስውሱታል? ወ/ሮ ነፃነት፦ ንጋት 1፡45 ገደማ ነበር። ፖሊሶች መጥሪያ ይዘው መጡ። በወቅቱ የት ነው የምሄደው? ብሎ ጠይቋቸው ነበረ። ያው ታደሰ በሥራ ብዛት ምክንያት የተለያዩ በሽታዎች አሉበት። የልብ ሕመም አለበት። ለማንኛውም ለዝግጅት እንዲሆን የት ነው የምሄደው? አማራ ክልል ነው ወይስ ፌዴራል ነው? የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር። እዚሁ ፌዴራል ነው ጉዳያችሁ የሚታየው ነው ያሉን። ልብስ መያዝም አልፈቀዱለትም። ምናልባት ለዛሬ የሚሆን መድኃኒት መያዝ ትችላለህ ነው ያሉት። ስናረጋግጥ ግን ቻርተር አውሮፕላን አዘጋጅተው ነበር። በቀጥታ ወደቦሌ ነው የወሰዱት። ቢቢሲ፦ ባህርዳር ከገቡ በኋላ የነበረውን ሁኔታ አቶ ታደሰ ነግሮዎታል? ወ/ሮ ነፃነት፦ በግዜው እኔ አልሄድኩም። የአቶ በረከት ባለቤት እና ልጄ ነበር የሄዱት። ወደ ባህርዳር ዘጠነኛ ፖሊስ ጣብያ ነበር የሄዱት። እዚያ ሰብዓዊ መብታቸውን የሚጥስ ሁኔታ ነው የተፈፀመባቸው። መያዛቸውን ያወቁ ሰዎች በስድብ እና ዛቻ ነው የተቀበሏቸው። ሌቦች፣ ፀረ-አማራዎች እና የመሳሰሉ ስድቦች ሲሰደቡ ነበረ። ፖሊስ ወጣቶቹ ገለል እንዲሉ ጥረት አድርጓል፤ ግን ብዙ ሊርቁ አልቻሉም። በዚህም ምክንያት በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊቀርቡ አልቻሉም። በእኔ እምነት ዘጠነኛ ፖሊስ የነበረውን ወከባ ለመቀነስ የፖሊስ ኃይል በመጨመር መካላከል ይቻል ነበር። ከእነሱ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር አለ የሚል እምነት የለኝም። እንዲሰደቡም ጭምር የአሣሪው አካል ፍላጎት አለ የሚል እምነት ነው ያለኝ። • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ በሕግ ጥላ ሥር ከመዋላቸው በፊት ይህ ቀን ሊመጣ ይችላል ብለው አስበው ያውቃሉ? አውርታችሁ ታውቃላችሁ ስለዚህ ጉዳይ? ወ/ሮ ነፃነት፦ የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ አባል ነበርኩ። የፓርቲው የሁለት ዓመት ተኩል አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ነበር ብዬ አልወስድም፤ በወቅቱ ስለነበርኩ ማለት ነው። በረከት እና ታደሰ ላይ ያተኮረ ስድብና ዛቻ ነው የነበረው። ጉባዔተኛው፤ «እነዚህ ፀረ-አማራ ናቸው፤ ታደሰ ትግሬ ነው፤ በረከት ደግሞ ኤርትራዊ ነው፤ ሰርገው የገቡ ናቸው፤ ጥረት ለብክነት የዳረጉ ናቸው፤ የሕወሓት ተለጣፊ ናቸው» እና የመሳሰሉ ነገሮች ሲነሱ ነበር። ማጠቃለያ ላይ፤ የተነገረው ነገር ተገቢ አይደለም ብሎ የተናገረ፣ ሥነ ስርአት ያስያዘ ከፍተኛ አመራር ግን አልነበረም። ስለዚህ በጉባዔ ደረጃ የመጨረሻ መደምደሚያ የሆነው በሕግ እንጠይቃቸዋለን ነበር። ሁለቱም [አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት] ይህንን ያውቁታል። ቢሆንም ታደሰ እታሠራለሁ የሚል እምነት አልነበረውም። ምክንያቱም በጥረት ጉዳይ የአሠራር ግድፈት ሊኖር ይችል ይሆናል፤ ይህ ደግሞ አስተዳደራዊ በሆነ መልኩ ሊታይ የሚችል እንጂ የሙስና ወንጀል ሆኖ እስከ አሥራት ሊያደርስ የሚችል አይደለም የሚል ፅኑ እምነት ነው የነበረው። እኔ ግን የስም ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄ ነው፤ በሕዝቡ ዘንድ ስማችሁ ጠፍቷል እና ይህን ማስታገስ የሚችሉት እናንተን በማሠር ነው የሚል እምነት ነበረኝ። እሱ ግን ምንም ዓይነት ጥርጣሬ አልነበረውም። ጥር 15፤ በግምት 1፡45 አካባቢ ሲይዙትም ሳይገርመው አልቀረም። ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ተከፍቷል እያሉኝ ነው። ይህን የጥላቻ ዘመቻ ማነው የከፈተባቸው ብለው ያስባሉ? ወ/ሮ ነፃነት፦ በስም እከሌ ብዬ መጥራት አልፈልግም። መሆንም የለበትም። እንደ ኮሚቴ የተሠራ ሥራ ነው ብዬ አስባለሁ። ሁሉም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በታደሰም ሆነ በአቶ በረከት መታሠር ፈቃደኛ ነበሩ ብዬ አላስብም። እንደሰማሁት እንግዲህ፤ መረጃው ያው ምስጢር አይደለም፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ ላይ መታገድ አለባቸው እና የለባቸውም በሚል ክርክር ተደረገ። ውሳኔው ደሞ አቶ በረከትን ያካተተ አልነበረም። ታደሰ እና አቶ ምትኩ በየነ [የአምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃላፊ] ላይ ነው የነበረው። በድምፅ ብልጫ ከማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲታገዱ ተወሰነ። እዚህ ውሳኔ ላይ አቶ ገዱ የነበራቸው አቋም፤ ከአሠራር ክፍተት አኳያ ሁላችንም እንፈተሽ ከተባልን፤ ጥረት ላይ ከተፈጠረው በአሥር እጥፍ የሚበልጥ ግድፈት ሊገኝብን ይችል ይሆናል። ልዩነቱ ጥረት ላይ ሰው አሰማርተን መረጃ የማጥራት ሥራ መሥራታችን ነው። በዚህ ደረጃ ብንሄድ የሚቀር ሰው የለም የሚል አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ። አቶ ደመቀም ተመሳሳይ አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ። ቢቢሲ፦ በሕግ ጥላ ሥር እንዲውሉ በመወሰኑ ላይስ? ወ/ሮ ነፃነት፦ እንዲታሠሩ በመወሰኑ ላይ የእያንዳንዱ ሰው ሚና ምንድነው? የሚለውን በዝርዘር ባላውቅም፤ 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተሰብስበው ነበር። በነገራችን ላይ 25 የብአዴን [አዴፓ] ሕጋዊ የማዕከላዊ ቁጥርም አይደለም፤ የአባላቱ ቁጥር 65 ነው። ከዚያ 13 ሰዎች ይታሠሩ፤ 12 ሰዎች ደግሞ አይታሠሩ የሚል ድምፅ ሰጡ። ስለዚህ በውሳኔ ነው የታሠሩት። ከከፍተኛ አመራሩ ማን ምን ብሎ ድምፅ እንደሰጠ ግን በውል አላውቅም። ቢቢሲ፦ የኮሚቴው አባላት 65 ከሆኑ ለምን 25 ሰዎች ብቻ ተሰበስበው ይህን ውሳኔ ሊያስልፉ እንደቻሉ የምታውቁት ነገር አለ? ወ/ሮ ነፃነት፦ እኔ ይህን አላውቅም። ሕጋዊ ነው የሚልም እምነት የለኝም። የኮሚቴው አባላት ቁጥር 65 ነው። ምናልባት በአንዳንድ ምክንያቶች የተወሰኑ ሰዎች ቢቀሩ 60 ወይ 50 ሊሆን ይችላል እንጂ በዚህ ደረጃ ዝቅ ያለ የማዕከላዊ ኮሚቴ ቁጥር አላውቅም። ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰን እየሄዱ የሚጠይቋቸው መች መች ነው? ሲያገኟቸውስ ምን ጉዳዮች አንስታችሁ ታወራላችሁ? ወ/ሮ ነፃነት፦ እኔ በየሁለት ሳምንቱ እሄዳለሁ። ልጄ ግን ሁሌም ችሎት ባለ ቁጥር ትሄዳለች። ስንገናኝ ብዙ ጊዜ የምናወራው ስለ ፍርድ ሂደቱ ነው። እንደሚታወቀው ጠበቃ የላቸውም። ማግኘት አልቻሉም። ሁለት ጠበቆች አግኝተን ነበር። ነገር ግን ማስፈራሪያ ከደረሳቸው በኋላ ጉዳዩን መከታተል እንደማይችሉ ነገሩን። በሕግ ነው የተያዙት፤ ስለዚህ ጉዳዩ በሕግ ማለቅ አለበት። አስፈፃሚው አካል፤ ሕግ አውጭውም ጭምር የአማራ ማስ ሚድያን ተጠቅመው ጠበቃ እንዳይቆም እየተደረገ ያለው ነገር ትክክል እንዳልሆነ በይፋ መግለጫ መስጠት አለባቸው ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ እዚህ አዲስ አበባ ላይ ያማከርናቸውን ጠበቆች ሐሳብ እነግረዋለሁ። ችሎት ላይ የተባለውን ነገር መነሻ በማድረግ እዚህ ካሉ ጠበቆች ጋር እንመክራለን። ሌላው የምናወራው ጉዳይ የጤንነቱ ጉዳይ ነው። ጤናው በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። የልብ በሽተኛ ነው። የመተንፈሻ መሣሪያ ካልተገጠመለት ተኝቶ ማደር አይችልም። ሌላኛው ጉዳይ ያው የቤተሰብ ጉዳይ ነው። ስለልጆቻችን እንመካከራለን ማለት ነው። • «ወይዘሮ ጎሜዝ፤ እርስዎ አያገባዎትም! አርፈው ይቀመጡ በልልኝ» ቢቢሲ፦ የሚያስፈልጋቸውን ሕክምናና የምግብ አገልግሎት እያገኙ ነው? ወ/ሮ ነፃነት፦ ያው እሥር ቤት ውስጥ እንደማንኛውም ሰው የምግብ አቅርቦት ነው ያለው። ባለው ርቀት ምክንያት የሚያስፈልገውን ነገር ልናደርግ አልቻልንም። እዚያው ማረሚያ ቤት ውስጥ አንድ ካፌ አለ እዛ ነው የሚጠቀመው። የጤና ጉዳይ እዚያ ባለው ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል መፍትሄ ማግኘት የሚችል አይደለም። ነገር ግን አስፈላጊው መድኃኒት እንዲቀርብላቸው እናደርጋለን። ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ ያለፈውን ነገር ዞር ብለው ሲያዩት ምን እንደሚሰማቸው ጠይቀዋቸው ያውቃሉ? ወ/ሮ ነፃነት፦ በአንድ በኩል መታሠሩ ግፍ እንደሆነ ያየዋል። ታደሰ የጥረት ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ ሲገባ 4 ድርጅቶችን ነው የተረከበው። በስምንት ዓመታት ውስጥ በሱ አመራር ሥር ድርጅቶቹ ከ4 ወደ 21 አድገዋል። ይሄ በግልፅ የሚታወቅ ነገር ነው። አማራ ውስጥ ስለ ኢንዱስትሪ ጉዳይ ሲነሳ ጥረት በታደሰ እየተመራ የሠራቸው ሥራዎች ናቸው የሚነሱት። ይሄን ለሠራ ጀግና፤ ይሄን ለሠራ የልማት አርበኛ ሽልማት ሲገባው በአሠራር ጉድለት፤ በተለይ ደግሞ የፖለቲካ ልዩነትን መነሻ በማድረግ እሥር ቤት መግባቱ፤ ይህን ደግሞ ያደረጉት አብረውት የታገሉ፤ የሚያምናቸው ሰዎች መሆናቸው በጣም ያሳዝነዋል። በአንድ በኩል ይሄ ነው። በሌላ በኩል ግን ጀግንነት ይሰማዋል። እኔ ታደሰ ካሳ በሕይወት ታሪኬ በሙስና የምታወቅ አይደለሁም። እንደውም አይበላ አያስበላ ነው የምባለው። ስለዚህ እውነተኛ ፍትህ ካለ የጠፋውን ስሜን አጠራለሁ። ነገ ከነገ ወዲያ የአማራ ሕዝብ እውነታውን ይረዳል ብሎ ያስባል። ቢቢሲ፦ የሚቆጫቸው ነገርስ ይኖር ይሆን? ባደርገው ወይም ባላደርገው ኖሮ የሚሉት? ወ/ሮ ነፃነት፦ ብዙም የሚቆጨው ነገር የለም። የሚያስቆጭ ሥራ አልሠራም። የሚቆጨው ይሆናል ብዬ የማስበው ከሐምሌ ጀምሮ የተደረገ የስም ማጥፋት ዘመቻ አለ። ምናልባት ራሱን ግልፅ ለማድረግ የሚያስችል መድረክ አለማግኘቱ ነው። ብዙ ጊዜ የስም ማጥፋት ዘመዛ ሲደረግ በዝምታ አልፏል። በዝምታ ከማለፍ ማን ምን እንደሆነ መናገር ነበረብኝ ይላል። ይሄ ይቆጨዋል ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ፦ ከሃገር የመውጣት ሃሳብስ አልነበራቸው ይሆን? ወ/ሮ ነፃነት፦ ታደሰ ከሃገር የመውጣት ፍላጎት የለውም። ሃሳቡ ጡረታ ከወጣ በኋላ አዲስ አበባ ሳይሆን ቢሆን ሰቆጣ ወይ ደግሞ ወልዲያ እሄዳለሁ የሚል ነበር። እውነት ለመናገር ከሃገር መውጣት ቢፈልግ መውጣት የሚያስችሉ ብዙ አማራጮች ነበሩት። የሁለት ዓመት የአሜሪካ ቪዛ አለው። የእንግሊዝም አለው። ነገር ግን በተገኘው አጋጣሚ ሕዝቡን የማገልገል ሃሳብ ነበር የነበረው። ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ የተመሠረተባቸው ክስ ውድቅ ሆኖ በቅርቡ እለቀቃለሁ ብለው ያስባሉ? ወ/ሮ ነፃነት፦አ. . . አዎም አይደለም ነው የዚህ ምላሽ። እውነተኛ ፍትህ ኖሮ፤ ዳኞች እና አቃቤ ሕጎች የአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ከሌለባቸው፤ ወደ ክስ መከራከሪያ ሳንገባ በክስ መቃወሚያችን ብቻ ይሄ አያስከስስም ተብሎ፤ ውድቅ ተደርጎ ልንወጣ እንችላለን [አቶ ታደሰና አቶ በረከትም] የሚል ሃሳብ አለ። ምክንያቱም በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሁሉም ከአሠራር ግድፈት ጋር የተያያዘ ስለሆነና የአሠራር ግድፈት ደግሞ የሙስና አንቀፅን መጥቀስ ስለማይችል ዳኞች ያቀረብነውን መቃወሚያ አይተው ውድቅ ሊሉት ይችላሉ። ይህ ግን ፍትህ ካለ ነው። የአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ከሌለበት ይህ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት አለው። ነገር ግን እየተደረገ እንዳለው ጠበቃ ሊቆምላቸው ካልቻለ፤ የስም ማጥፋት ዘመቻ በሚድያ ከተደረገባቸው፤ ይህ ደግሞ በዳኞች እና በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ከሆነ በነፃ መውጣት የሚቻልበት ሁኔታ የማይታሰብ ነው የሚል እምነት አለው። ቢቢሲ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአቶ በረከትን ቤተሰቦችን እንዳናገሩ ሰምተናል። በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ፤ ነገር ግን ፍትህ እንዳይጓደል እንደሚያሳስቡ ሰምተናል። የአቶ ታደሰን ቤተሰብስ አግኝተው ነበር? ወ/ሮ ነፃነት፦ አዎ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጋራ ነው ያገኙን። የአቶ በረከት ባለቤትንም፤ እኔንም ጠርተው ነው ያናገሩን። ስላሉበት ሁኔታ፤ ስለደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ እሥሩ ፖለቲካዊ እንደሆነ፤ በተለይ ደግሞ ጠበቃ የማጣታቸው እና የጤንነታቸው ጉዳይ እንደሚያሳስበንና በፍትህ እንዲዳኙ እንደምንሻ ነግረናቸዋል። ከምንም በላይ ፍትህ ብቻ እንዲዳኛቸው እኔም አናግሬያቸዋለሁ። • አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ወደ ባህር ዳር ተወሰዱ
48659634
https://www.bbc.com/amharic/48659634
በኬንያ ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ያለባት ታማሚ ተገኘች
በደቡብ ምዕራብ ኬንያከፍተኛ ሙቀት፣ ራስ ምታት፣ የመገጣጠሚያ ችግሮች፣ የጉሮሮ መቁሰል እንዲሁም ማስመለስ ምልክቶች የታዩባት አንዲት ታማሚ ኢቦላ ሊሆን ይችላል በሚል ግምትም ምርመራው ቀጥሏል።
በመጀመሪያ ወባ ነው በሚል በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል እየታከመች የነበረ ሲሆን፤ ውጤቷ ግን ወባ እንደሌለባት እንዲሁም ሁኔታዋ በመባሱ ወደ ሌላ ሆስፒታል ተዛውራለች። ለብቻዋም ተገልላ እንድትታከም እየተደረገች ነው። •ኢቦላ ዳግም አገረሸ •ኢቦላ ወደ ኡጋንዳ እየተዛመተ ነው •ሕይወት ከኢቦላ ወረርሽኝ በኋላ ወደ በኋላም ተቅማጥ የታየባት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ጤናዋ እየተሻሻለ እንደሆነ ተገልጿል። መጀመሪያ የታየችበት የግል ክሊኒክ ኢቦላ ተከስቶበታል ወደ ተባለው ኡጋንዳ ድንበር ጉዞ አድርጋ ነበር በሚል በጥንቃቄ እንድትያዝ የገለፀ ቢሆንም እሷ የሄደችበት የምስራቅ ኡጋንዳ ክፍል ምንም ነገር እንዳልተከሰተ ተገልጿል። በባለፈው ሳምንት በኡጋንዳ ኢቦላ የተከሰተው በምዕራብ የኃገሪቱ ክፍል ሲሆን ይህም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በሚያዋስናት ድንበር እንደሆነ ተገልጿል። የደም ናሙናዋ ለኢቦላ ምርመራ ወደ ናይሮቢ ተልኳል ተብሏል።
news-41588871
https://www.bbc.com/amharic/news-41588871
ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ?
በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ምክንያት የብዙ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል፤ ከ75 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያ ተወላጆች አካባቢያቸውን ጥለው መፈናቀል እንዲሁም ለሺህዎች ንብረት መውደምም ምክንያት ሆኗል።
የክልሎቹ መንግሥታት ግን እርስ በርስ መወነጃጀልን መርጠዋል። ምንም እንኳን ይሄ እሰጥ እገባ እየቀለለ የመጣ ቢመስልም ግጭቶቹ እንዳልበረዱም፤ የሚፈናቀልም ሰው ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ በቅርቡ አሳውቀዋል። የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የድርጅቱ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ማዕከላዊው መንግሥት ችግሩ በተከሰሰበት አካባቢ በፌዴራል አካላት፣ በመከላከያና በፖሊስ ኃይል አማካኝነት ዋና ዋና መንገዶችን በመቆጣጠር ችግሩን አብርዷል። እርሳቸው ይሄንን ቢሉም በክልሎቹ መካከል እስካሁን ግጭቱ ያልተፈታ መሆኑ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነው። ባስ ሲል በቅርቡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ ከስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውም ግርምት ፈጥሯል። አቶ ሽፈራው ኢህአዴግ ከያዘው የመተካካት ስርዓት ጋር የተያያዘ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከመንግሥት የስልጣን ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ልልቀቅ ማለታቸው ያልተለመደ መሆኑንም አቶ ሽፈራው አልደበቁም። ምንም እንኳን አባ ዱላ ለመልቀቅ የጠየቁበትን ምክንያት ለወደፊቱ እገልፃለሁ ቢሉም፤ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በተነሳው ግጭትና መፈናቀል ማዕከላዊው መንግሥት የሰጠው አዝጋሚ ምላሽም ቅር እንዳሰኛቸው የቅርብ ሰዎች እየተናገሩ ነው። አገራዊ ተቃውሞዎች በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች አገሪቷን ያናወጠ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቷል። ከዓመት በላይ የዘለቀው ይህ ተቃውሞ የተነሳው ጊንጨ አካባቢ ሲሆን፤ ይሄም የጪልሞ ጫካ ወደ ግል ይዞታ በመዛወሩ የተነሳ ነበር። ይሄም በአገሪቱ ላይ አከራካሪ የሆነውንና ለዘመናት መመለስ ያልተቻለውን 'መሬት የማን ነው?' የሚለውን ጥያቄ ከኋላ አንግቦ የተነሳ ነው። በርካታ ገበሬዎች በልማት መነሳት ያመጣቸውንም ቀውሶች ያጋለጠ ነበር። የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ወረዳዎች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሊያመጣቸው የሚችሉ ከፍተኛ መፈናቀሎችን በመቃወምም ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ከመሬት ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ብሄርን መሰረት ያደረገው ፌደራላዊ ሥርዓት ያልመለሳቸው ጥያቄዎች ናቸው። በተመሳሳይ በአማራ ክልልም ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ችግሩም እሳካሁን መፍትሄ አልተገኘም የሚሉ ሰዎች ጥያቄውን በማንሳት ላይ ናቸው። ሥርዓቱ የክልል መንግሥታት ራሳቸውን የሚያስተዳድሩበት፣ የራሳቸውን ተወካዮች የሚመርጡበት፣ የራሳቸውን ቋንቋ የሚናገሩበትን ሥርዓት መመስረት፣ ቀድሞ የነበረውን የዜግነት እሳቤን መቀየር የሚል ቢሆንም የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች በትክክል ተግባራዊ እንዳልተደረገ ይተቻሉ። ታዋቂው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና ተንታኝ ጆን ማርካኪስ "ይሄ ሁሉ ግን የተደረገው ህዝቡን ፀጥ ለማስባል እንጂ ስልጣንን ለማጋራት አልነበረም፤ ፌደራሊዝሙ በኢህአዴግ የተሰላ ጥረት ነው" ይላሉ። "ስልጣን አሁንም በማዕከላዊው መንግሥት ቁጥጥር ስር ነው፤ ፌደራል መንግሥቱ ስልጣንንም ሆነ ሀብትን በቁጥጥር ስር አድርጎ ለማከፋፈልም ሆነ በጋራ ለመጠቀም ዝግጁ አይደለም። ይኼ አካሄድ ደግሞ ለሥርዓቱ ትልቅ ጠንቅ ነው፡፡ የአንድን አገር ህልውና ለመጠበቅ ኃይል ብቻውን በቂ አይደለም፡፡" በማለት ይጨምራሉ። ሕዝቦች ራሳቸውን የሚያስተዳድሩበት፤ ስልጣንና ሀብትን የሚጋሩበትን ሥርዓትን ይህ መንግሥት መፍጠር አልቻለም የሚሉት የመድረክ ምክትል ሊቀ-መንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙላቱ ገመቹ ናቸው። "ራስን በራስ የማስተዳደር መብት አልተሰጠም፤ አሁንም ለይምሰል ነው እንጂ ለሥርዓቱ ታማኝ የሆኑ ሰዎች ከላይ በማስቀመጥ በተዘዋዋሪ አሃዳዊ በሆነ መልኩ በጠመንጃ የሚተዳደሩበት ሥርዓት ነው።" ይላሉ። የዲሞክራሲ እጥረት የተለያዩ ምሁራን እና የፖለቲካ ተንታኞች የችግሩን ምንጭም ሆነ መፍትሄውን በተለያየ መነፅር ይመለከቱታል። የቀድሞ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ) "ፈተና የሌለበት ሥርዓት የለም" በማለት በአገሪቷ የተከሰተውን አመፅና ግጭት በአሉታዊነቱ ብቻ አይመለከቱትም። በአገሪቷ የተተገበረው የፌደራሊዝም ሥርዓት ፍሬ ነው ብለው ያምናሉ። ጆን ማርካኪስ ራስን የማስተዳደር ጥያቄና ነፃነትን ከመፈለግ የሚመነጭ እንደሆነ ከሚያነሱት ሃሳብ ጋር ይዛመዳል። "ኢህአዴግ 'ትምክህተኞችና ጠባቦች' እያለ በጠላትነት የሚፈርጃቸው ወገኖች ጊዜና ፋታ እየጠበቁ ጥያቄ ማንሳታቸውን አያቆሙም" ይላሉ። "ችግሩም ያለው ከጠያቂዎቹ አይደለም፤ ከመላሹ እንጂ" በማለት ጨምረው ይናገራሉ። አቶ ሙላቱም ሆነ ጀኔራል አበበ እንደ መፍትሄ የሚጠቁሙትም ትልቅ ህዝባዊ ውይይትና መነጋገርን ነው። "ኢህአዴግ የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ መሆኑን አምኖ ካልተቀበለ አገሪቷን ትልቅ ዕድል ያስመልጣታልም" ይላሉ። እሳቸው እንደሚሉት ጥያቄ እየተነሳ ያለው ኢህኣዴግ በጠላትነት ከሚፈርጃቸው ወገኖች አይደለም። በተቃራኒው ከህዝብ እንጂ። እንደ ምሳሌም የሚያነሱት በአማራ ክልል ሲውለበለብ የተሰተዋለውን አርማ የሌለበት ሰንደቅ ዓላማ "ህዝቡ ነው ያውለበለበው" ይላሉ። በቅርቡም የኦነግን ሰንደቅ አላማ የሚያውለበልቡ የኢሬቻ በአል ታዳሚዎች በኦሮሚያ ክልል ተስተውለዋል። "እነዚህ ሰንደቅ ዓላማዎች ምን ማለት ናቸው?" ሲሉ ጀኔራሉ ይጠይቃሉ። "እኩልነትን ያመጣል ተብሎ የታመነበት አዲሱ ሰንደቅ ዓላማ ከ25 ዓመታት በኋላ ይሄን ያህል ተቃውሞ የሚገጥመው ከሆነ፤ አንድም ህዝቡ አልተቀበለውም ወይም የማስረዳት ችግር አለ ማለት ነው" ይላሉ። ጥያቄው መነሳቱ ተገቢ መሆኑን አምነው። "የኢህኣዴግ አመራር ጥያቄዎቹን ማፈን እንጂ መመለስ አልቻለም በተቃራኒው አስተዳደራዊና የኃይል እርምጃ መውሰድን መርጧል" ይላሉ። ቀይ መብራት የቀድሞው የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው በበኩላቸው ቀውሱን ከዚህ በተለየ መንገድ ይረዱታል። አገሪቷ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር ባለችበት ሁኔታ እንዲህ ዓይነት ቀውስ ተከስቶ የጋራ ነገር እየጠፋ መሄዱ አደገኛነቱ ያመዝናል ይላሉ። "በዚህ ሥርዓት ስር የተለያዩ ፖሊሲ ያላቸው ፓርቲዎች በምርጫ አሸንፈው የተለያዩ ክልሎችን ቢያስተዳድሩ፤ ምን ይውጠን ነበር?" በማለት ስጋታቸውን ይገልፃሉ። በፖለቲካ ቀውሱ ምክንያት ተቃውሞና አመፅ እየተቀጣጠለ አገሪቷ ወደባሰ ደረጃ እየሄደችም እነደሆነ አቶ ልደቱ ይጠቅሳሉ። ይሄንን ሃሳብ አቶ ሙላቱም የሚጋሩት ሲሆን ሥርዓቱ መውደቅ ብቻ ሳይሆን አገሪቷ ወደበለጠ ማጥ ውስጥ እየገባችም ነው ብለው ያምናሉ። "ኢትዮጵያዊ ነኝ በሚል የሚታወቀው አማራ፤ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ደረጃ ብሄርተኝነቱ እየጎለበተ መምጣቱ፤ ሁሉም የጋራ አገርን እየዘነጋ ወደ እየራሱ ማየት መጀመሩ ትልቅ ምልክት ነው" ይላሉ አቶ ልደቱ። አቶ ልደቱ ብሔርን መሰረት ያደረገው ፌደራሊዝም ችግሮቹን አባብሷቸዋል ብለው የሚያምኑ ሲሆን የመገንጠልም ጥያቄዎችም ተጧጡፈዋል ይላሉ። የዚህ ሥርዓት ሌላኛው ፈተና የተለያዩ ብሔር ተወላጆች በተለያዩ ክልሎች ተንቀሳቅሰው የመስራት እክሎች እያጋጠማቸው እንዲሁም "ከክልላችን ውጡ" በሚሉ መፈክሮች ብዙዎች መፈናቀላቸው አገሪቷ የመበታተን ጥላ እንዳጠላባት ተንታኞች ይናገራሉ። በተቃራኒው ጀኔራል አበበ ከዚህ በፊት በ1966 እና በ1983 መንግሥት ባልነበረበት ታሪካዊ ቅፅበቶች እንኳን አገሪቷ አለመበተኗንና አሁንም ህዝቡ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት እንዳለ ይናገራሉ። "ሥርዓቱ ይሆናል እንጂ አገር አትበታተንም" ብለዋል። መፍትሔው ምን ይሆን? ለተነሱት ከፍተኛ ተቃውሞዎች መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ እንዲሁም ብዙዎችን በማሰር መልስ የሰጠ ቢሆንም፤ ይህ የኃይል እርምጃ ቀውሱን ከማብረድ ውጭ እንዳልፈታው ቢቢሲ ያነጋገራቸው እነዚህ ተንታኞች ይናገራሉ። "እንደ ቀድሞዎቹ መንግሥታት ኢሕአዴግም ተመሳሳይ ቀውስ ገጥሞታል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ እንደ ቀደሙት መንግሥታት ችግሮቹን ለመፍታት ሠራዊቱን ማሳተፍን መርጧል" በማለት ጆን ማርካኪስ ይናገራሉ። አቶ ሙላቱ እንደ መፍትሄ የሚጠቁሙትም እውነተኛ ፌደራሊዝምን መፍጠር፣ ህዝቡ የፈለገውን እንዲመርጥ መፍቀድ፣ የመናገርና የመፃፍ ነፃነትን ማክበር፣ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት እንዲሁም የአንድ ፓርቲ የበላይነት የሚያበቃበትን ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል። አቶ ልደቱ በበኩላቸው ስርዓቱ ራሱን መፈተሽ እንዳለበትና አሁንም አገራዊ ውይይት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል። "መንግሥት ወዶና ፈቅዶ መዋቅራዊ ለውጥ ካላመጣ፤ በኃይል ተገዶ ለውጥ መምጣቱ አይቀርም" ብለዋል።
44224289
https://www.bbc.com/amharic/44224289
"ልጅ" ማይክል በ30 ዓመቱ ከወላጆቹ ጋር በመኖሩ ክስ ተመሠረተበት
ልጅ በስንት ዓመቱ ከቤት ወጥቶ ራሱን መቻል ይኖርበታል?
ማይክል ሮቶንዶ ማክሰኞ ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ በኒውዮርክ በ30 ዓመቱ የወላጆቹን ቤት የሙጥኝ ያለው ጎልማሳ በገዛ ወላጆቹ መከሰሱ ተሰምቷል። አባትና እናት ልጃቸው ራሱን ችሎ ከቤት እንዲወጣ ያደረጉት ውትወታና ተከታታይ ጥረት ፍሬ አላፈራም። የመጨረሻው አማራጭ ለፍርድ ቤት መክሰስ በመሆኑ ይህንኑ ጨክነው አድርገውታል። ልጃቸው 30ኛ ዓመቱን ቢደፍንም አሁንም ከወላጆቹ ጋር ነው የሚኖረው። የፍርድ ቤት መዝገብ እንደሚያስረዳው የ30 ዓመቱ "ልጅ" ማይክል የቤት ኪራይ አይከፍልም። በዚያ ላይ ደግሞ ቀለል ያሉ የቤት ውስጥ ሥራዎችን (እገዛዎችንም) አያደርግም። ወላጆቹ ራሱን ችሎ ቤት እንዲከራይ የድጎማ ገንዘብ ቢሰጡትም በጄ አላለም። ወላጅ እናቱ ወይዘሮ ክርስቲና እና አባቱ አቶ ማርክ ሮቶንዶ እንደሚሉት ልጃቸው ቤታቸውን እንዲለቅ አምስት ግልጽ ደብዳቤዎችን በተለያየ ጊዜ ሰጥተውታል። "ልጅ" ማይክል ግን "ከቤት እንድለቅ በቂ ጊዜ አልተሰጠኝም" ይላል። ለኦኖንዳጋ አውራጃ ፍርድ ቤት ክስ የመሠረቱት ወላጆቹ ልጃቸውን ከቤት ወጥቶ ራሱን እንዲችል ያደረጉት ሙከራ ውጤት ሊያመጣ ስላልቻለና ሌላ ምን ማድረግ እንደሚቻል ግራ ስለገባቸው ነው ወደ ፍርድ ቤት ያቀኑት ተብሏል። "እኛ አባትና እናትህ ይህንን የወላጆችህን ቤት በአስቸኳይ እንድትለቅ ወስነናል" ይላል በየካቲት 2 የተጻፈ የመጀመርያው ደብዳቤ። ማይክል ይህን ደብዳቤ ችላ ካለ በኋላ ወላጆቹ በጠበቃቸው አማካኝነት ለልጃቸው ሌላ መደበኛ ደብዳቤ እንዲደርሰው አድርገዋል። "ልጄ ሆይ! ከዚህ በኋላ ከዚህ ቤት ተባረሃል" ይላል በየካቲት 13 በእናቱ ፊርማ የወጣ አንድ ደብዳቤ፤ ይህን የማያደርግ ከሆነ ግን በሕግ እንደሚጠየቅ ከሚገልጽ ማስጠንቀቂያ ጋር። ወላጆቹ ከዚህ ደብዳቤ በኋላ ለልጃቸው መቋቋሚያ እንዲሆነው በሚል 1100 ዶላር ያበረከቱለት ሲሆን እሱ ግን ገንዘቡን ለመውሰድም ፍላጎት አላሳየም። በመጋቢት ወር ወላጆቹ ወደ ክፍለ ከተማው ፍርድ ቤት ሄደው ጉዳዩን ያሳወቁ ሲሆን የፍርድ ቤቱ የመዝገብ ቤት ኃላፊዎች ማይክል ልጃቸው በመሆኑ ውሳኔያቸውን ለማስፈጸም የከፍተኛ ፍርድ ቤት ደብዳቤ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጾላቸዋል። ደብሊው ኤቢሲ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው "ልጅ" ማይክል የወላጆቹን ክስ "የበቀል ስሜት ያዘለ" በሚል አጣጥሎታል። ፍርድ ቤቱም እንዳይቀበለው አሳስቧል። ወላጆቹ ግን ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ቀጠሮ ይዘዋል። ይህ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በሚመለከትበት ወቅት "ልጅ" ማይክል 31ኛ ዓመቱን ለመድፈን ይቃረባል።
42778164
https://www.bbc.com/amharic/42778164
ወልዲያ ትናንትም በውጥረት ውስጥ ውላለች
ዛሬ ሰኞ ማለዳ መናኸሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በከተማዋ የሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለቀው ይወጣሉ ሲሉ ቃል ቢገቡም ዛሬ ጠዋት ተጨማሪ ኃይል ወደ ከተማዋ በመግባቱ ለሌላ ተቃውሞ መቀስቀስ ምክንያት ሆኗል።
በወልዲያ ከተማ በጥምቀት በዓል ማግስት የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ በርካቶች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል። መንግሥት የሟቾች ቁጥር ሰባት ነው ቢልም የከተማዋ ነዋሪዎች ግን የሟቾችን እና የቁስለኞችን ቁጥር ከፍ ያደርጉታል። ወልዲያ ውስጥ 7 ስዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆሰሉ ቅዳሜ የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ እሁድ ዕለት የበርካታ ነጋዴዎች፣ የአካባቢው ባለስልጣናት እና የመንግሥት ደጋፊዎች ናቸው በተባሉ ግለሰቦች የንግድ ተቋማት እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሰኞ ጠዋትም የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከከተማዋ እንዲወጡ አልተደረጉም በሚል ምክንያት በመንግሥት ተቋም ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከትናንት ጀምሮ የከተማዋን ነዋሪዎች ሰብስበው እያወያዩ ነው። የውይይቱ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አንድ ወጣት በስልክ እንደነገረን፤ ትናንት በነበረው ውይይት የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአስቸኳይ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ተሳታፊዎች ጠይቀው ነበር። አቶ ገዱም በበኩላቸው የሠራዊት አባላቱ ከተማዋን ለቀው እንደሚወጡ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት ገደማ ተጨማሪ የመከላከያ ኃይል ወደ ከተማዋ ገብቶ በወልዲያ ጎዳናዎች እና አቋራጭ መንገዶች ላይ ተሰማርቷል ሲሉ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህም የተቆጡ የከተማዋ ወጣቶች የወልዲያ ከተማ ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ላይ ዛሬ ከምሳ ሰዓት በኋላ ጥቃት ፈጽመዋል። ወጣቱን በስልክ እያነጋገርን በነበረበት ወቅት የተቃውሞ ድምጽ ይሰማ ነበር። ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በነበረው ውይይት ተሳታፊ ከነበረ ሌላ ወጣት እንደሰማነው፤ ርዕሰ መስተዳድሩ የሃይማኖት አባቶችን ጨምረው ስብሰባው፤ ተሳታፊዎች የሥርዓት ለውጥ እንፈልጋለን ከሚሉ ጥያቄዎች አንስቶ ፍትህን፣ ሥራ አጥነትን እና ከማንነት ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎችን ለክልሉ መስተዳድር አቅርበዋል። የጥቃቱ ኢላማ ግጭቱ ከተከሰተበት ዕለት አንስቶ በሰው ሕይወትና አካል ላይ ከደረሰው ጉዳት ባሻገር በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። የዚህ ጥቃት ኢላማ እነማን እነደሆኑ ለማወቅ ያነጋገርናቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች ጠይቀን ነበር። ከአነጋገርናቸው መካከል እንዱ፤ ''በቤት እና ንብረታቸው ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው የአካባቢው ባለስልጣናት እና ወጣቶችን በመጠቆም የሚያሳስሩ የመንግሥት ደጋፊዎች ላይ ነው'' ብሏል። ''የከተማዋ ከንቲባ መኖሪያ ቤት ላይ እና ባለቤትነቱ የክልሉ ተወላጅ በሆነው መቻሬ ሆቴል ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። እንዲሁም የመንግሥት ደጋፊ በሆኑ የግለሰብ ንብረቶች ላይ ጥቃት ደረሰ እንጂ የሌላ ክልል ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ ምንም አይነት ጥቃት አልደረሰባቸውም'' ሲል ይሞግታል። በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ተወላጆች ንብረት ላይ ጨምሮ በአካባቢው ባለስልጣናት እና የመንግሥት ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል ሲሉ ሌላ የከተማዋ ነዋሪ ነግረውናል። በአሁኑ ሰዓት በወልዲያ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት እንቅሳቀሴ አይታይም። በርካታ ነዋሪዎችም ለደህንነታቸው በመስጋት ከመኖሪያ ቤታቸው ከመውጣት መቆጠባቸውን ነግረውናል።
48442485
https://www.bbc.com/amharic/48442485
ባህር ዳር፡ ለተጎዱ ህጻናት ሴቶች መጠለያ የሆነው ማዕከል
ሰላም (ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ስሟ የተቀየረ) ባህር ዳር የደረሰችው ከዘጠኝ ወራት በፊት ነበር። የ14 ዓመቷ ታዳጊ ከቤት ለመውጣት የተገደደችው ከአባቷ ጋር አለመግባባት በመፈጠሩ ነው።
ጓደኛዋ፤ ከመኖሪያ ቀያቸው ጠፍተው ባህር ዳር ቢሄዱ ሥራ እንደሚያገኙና ራሳቸውን ችለው መኖር እንደሚችሉ ደጋግማ ነግራታለች። "ጓደኛዬ እንጥፋ ስትለኝ ስለነበር፤ አባቴ 'ትምህርት ተማሪ' ሲለኝ አልማርም ብዬው ነበር" ትላለች። ጓደኛዋ ባህር ዳርን ስለምታውቃት አብረው ወደ ባህር ዳር ከኮበለሉ በኋላ ሰው ቤት በሞግዚትነት የመቀጠር ሀሳብ እንደነበራቸው ትናገራለች። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ውሳኔዋ ትክክል አለመሆኑን በመረዳት ሃሳቧን ቀየረች። • "በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ" "አባቴን ልማር ስለው መልሶ እምቢ አለኝ" ስትል አለመግባባታቸው እንዴት እንደተጀመረ ታስረዳለች። አለመግባባታቸው አይሎም ከጓደኛዋ ጋር የተስማማችበትን ሀሳብ እንድትተገብር አስገደዳት። ውሳኔዋን ከግብ ለማድረስ እንዲረዳትም ከቤት ገንዘብ ይዛ ወጣች። "ብሩን ይዤ ከጓደኛዬ ጋር ከአካባቢዬ ጠፋሁ፤ ጓደኛዬ ደግሞ ብሩን ይዛብኝ ጠፋች።" የምትለው ሰላም በዚህ ሁኔታ አጣብቂኝ ውስጥ ገባች። ወደ ቤተሰቦቿ እንዳትመለስ ገንዘብ ወስዳ መውጣቷ ሊያመጣባት የሚችለው መዘዝ አስፈራት። ወደ ባህር ዳር እንዳትሄድ ደግሞ ለመጓጓዣ የሚሆን ገንዘብ ስለሌላት አውጥታ አውርዳ የቀራትን ብቸኛ አማራጭ ለመጠቀም ወሰነች - ወደ ሌላ ከተማ ሄዶ ሥራ መቀጠር። ሌላ ከተማ ሄዳ ሥራ መሥራት ጀመረች፤ እየሰራች ገንዘብ በማጠራቀም ከቤተሰቦቿ ይዛ የተሰወረችውን ገንዘብ በገበያተኛ በኩል መልሳ ላከችላቸው። ሰላም አሁን ከእዳ ነፃ መሆኗ እፎይታን ሰጥቷታልና ስለቀጣይ ጉዞዋ ማውጠንጠን ጀመረች። ለትራንስፖርት የሚበቃ ገንዘብ ካጠራቀመች በኋላ ጉዞዋን ስታልማት ወደነበረችው ባህር ዳር አደረገች። ባህር ዳር የምታወቀው ሰው አልነበራትም። ከተማዋን እንደምታውቅ የነገረቻት ጓደኛዋም ገንዘቧን ይዛ ተሰውራለች። ብቸኛ ተስፋዋ ሲወራ እንደሰማችው በደላላ በኩል ሥራ መቀጠር ነው። "ባህር ዳር እንደመጣሁ ደላላው ወደ ቤቱ ወሰደኝ፤ በዚያው በመጀመሪያ ቀን ማታ አስገድዶ ደፈረኝ" ስትል በሃዘን ተሞልታ የደረሰባትን መከራ ትገልጻለች። ደላላው ለማንም ምንም እንዳትናገር አስጠንቅቆ በቀጣዩ ቀን ሥራ አስቀጠራት። እሷም የሆዷን በሆዷ አድርጋ ሥራዋን መሥራት ጀመረች። ምግብ ቤት ውስጥ ለሁለት ወራትና በግለሰብ መኖሪያ ቤት ደግሞ ለሦስት ወር መሥራቷን ትናገራለች። • "በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል" ሥራው እንዳሰበችው ቀላል አልነበረም። በ14 ዓመት ታዳጊ አቅም የሚቻል አልሆነም። በተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት የሚደርስባት ስቃይ ከድጡ ወደ ማጡ ሆነባት። "ሥራው በጣም ከባድ ነው፤ ታስርበኛለች፤ ለምን እንደሆነ አላውቅም" ትላለች ስለአሠሪዋ ስትገልጽ። ሥራ ለመቀየር አስባ ቀጣሪዋ የሠራችበትን ገንዘብ እንድትሰጣት በተደጋጋሚ ብትጠይቅም በምላሹ ትደበድባት እንደነበረ ትናገራለች። "ካስፈለገ ለፖሊሶች 'ብሯን ሰጥቻታለሁ' ብዬ አስመሰክራለሁ" አለችኝ የምትለው ሰላም ቀጣሪዋ ለአንድ ሾፌር ከፍላ 'ወደማታውቀው ቦታ ውሰዳት' ብላ እንደነገረችው ትገልፃለች። እሱ ግን የወሰዳት ፖሊስ ጣቢያ ነበር። ፖሊስም ቃሏን ከተቀበለ በኋላ በከተማው የሚንቀሳቀሰው የጎዳና ተዳዳሪ ሴት ህጻናት መከላከያ፣ ተሃድሶና መቋቋሚያ ድርጅት አስገባት። ድርጅቱ ሰላምን ጨምሮ የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸው ህጻናትን እና ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ ሴቶችን ማገዝ ከተጀመረ ከ10 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። ሰላም ወደ ድርጅቱ ከገባች በኋላ የልብስ፣ የምግብ፣ የመኝታ እና የሥነ ልቦና ድጋፍ እየተሰጣት ነው። "እዚህ እንደመጣሁ በጣም ጨንቆኝ ነበር፤ ለቤተሰቦቼ ሲደወልም 'አንፈልጋትም' ብለዋል አሉ፤ እኔ ይህንን አላወቅኩም። 'አይወስዱሽም' ብለው ሲነግሩኝ ልጠፋ አስቤ በመስኮት ዘልዬ ወጥቼ ሁሉ አውቃለሁ" ትላለች እንባ እየተናነቃት። • የተነጠቀ ልጅነት በድርጅቱ የሚሰጣት የማማከር አገልግሎት ድርጅቱ ውስጥ ተረጋግታ እንድትኖር ከማድረግ ባለፈ፤ የደረሰባትን አስገድዶ መደፈር ለመጀመሪያ ጊዜ እንድትናገር አድርጓታል። ከማማከሩ በተጨማሪ በመደፈሯ ያጋጠማት የጤና እክል ካለ በሚል ምርመራ ተደርጎላታል። "አስመርምረውኝ ጤነኛ ነሽ ተብያለሁ" ትላለች። ወይዘሪት ሠናይት ገዳሙ የጎዳና ተዳዳሪ ሴት ህጻናት መከላከያ፣ ተሃድሶና መቋቋሚያ ድርጅት ውስጥ በአማካሪነት ያገለግላሉ። ያለዕድሜ ጋብቻና ወሲባዊ ትንኮሳ የደረሰባቸው ሴቶች በብዛት ወደ ድርጅቱ እንደሚሄዱ ያስረዳሉ። "ያለዕድሜያቸው የተዳሩ ልጆች ቤተሰቦችን በማስመጣት እናማክራለን። ህጻናት መማር እንዳለባቸው ነግረን፣ ቤተሰቦቻቸው እንዳይድሯቸው ቃል አስገብተን ልጆቹን ከቤተሰቦቻቸው ጋር አንቀላቅላቸዋለን። ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ህጻናት የሕግ ከለላ አግኝተው ፍትህ አንዲያገኙ እናደርጋለን። ሴቶቹን በማጽናናትና በማማከር ጉዳዩን ረስተው የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ እናግዛለን።" ሲሉ በድርጅቱ የሚያከናውኗቸውን መሰረታዊ ሥራዎች ይጠቅሳሉ። ወይዘሪት ሠናይት እንደሚሉት ክትትሉ በማዕከሉ ብቻ አይቆምም። ወደ ቤተሰቦቻቸው አሊያም አሳዳጊዎቻቸው ከተቀላቀሉ በኋላም ልጆቹ ትምህርት ስለመጀመራቸውና ስላሉበት ሁኔታም ክትትል ያደርጋሉ። ከጥር ጀምሮ ባሉት ሦስት ወራት ብቻ 38 ሴቶች ወደ ድርጅቱ የሄዱ ሲሆን፤ በዓመት በአማካይ እስከ 150 ሴቶችን ተቀብለው ያስተናግዳሉ። ህጻናቱን ወደ ድርጅቱ የሚወስደውም ፖሊስ ነው። • ቀኝ እጇን ለገበሬዎች የሰጠችው ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሴቶች ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ ወገኖች ድጋፍና እንክብካቤ አስተባባሪ የሆኑት ዋና ሳጅን መለሰ ዓለሙ እንደሚሉት፤ ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን በተመለከተ የሚሠሩ ሴት ፖሊሶች በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች አሉ። "በሕገ ወጥ ዝውውር ሲመጡ የምናገኛቸውን ህጻናትም ሆነ ህብረተሰቡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሚልካቸውን ወደ ድርጅቱ እንልካቸዋለን፤ በድርጅቱ የሚሠራው ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማቀላቀል ሥራ ነው" ይላሉ። ዘመድ የሌላቸው ልጆች በማዕከሉ ትምህርት እንዲከታተሉ የሚደረግ ሲሆን፤ ዕድሜያቸው ለሥራ የደረሱ ግለሰቦች ለአደጋ በማይጋለጡበት ቦታ እንዲሠሩ ምክር ይሰጣቸዋል። በጎዳና ተዳዳሪ ሴት ህጻናት መከላከያ፣ ተሃድሶና መቋቋሚያ ድርጅት የባህር ዳር ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ግዛው ድርጅቱ ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ የህጻናቱን መሠረታዊ ፍላጎት ከማማሏት ባለፈ የሥነ ልቦና ድጋፍ እንደሚሰጥ ይናገራሉ። "ዋናው ግብ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ህጻናትን ከአካባቢያቸው ሳይርቁ ድጋፍ መስጠት ነው። በዚህም ከ2 ሺህ በላይ ህጻናትን መታደግ መቻል ትልቅ ለውጥ ነው" ይላሉ። • ታሪክ እየቀየሩ ያሉት ሴቶች ጉዳት የደረሰባቸው ህጻናት ጉዳይ በሕግ እንዲታይ ድርጅቱ ድጋፍ ያደርጋል። በዚህ ረገድ ሰላም ዕድለኛ አልሆነችም። ደላላው የት እንዳለ ባለማወቋ ግለሰቡን ሕግ ፊት ማቅረብ አልተቻለም። በድርጅቱ በኩል ከቤተሰቦቿ ጋር እንድትቀላቀል ጥረት እየተደረገ ነው፤ ውጤቱንም በጉጉት እየጠበቀች ትገኛለች። "የምመለስበትን ቀን እየጠበቅኩ ነው፤ እናቴ በጣም ትናፍቀኛለች" የምትለው ሰላም ወደ አካባቢዋ ስትመለስ ትምህርቷን መማር እንደምትፈልግ ያላትን ተስፋ ትገልጻለች።
52889061
https://www.bbc.com/amharic/52889061
ዙም መሰብሰቢያ ብቻ ሳይሆን ከሥራ ማባረሪያም ሆኗል
ኮሮናቫይረስ ብዙዎች ቤታቸውን ቢሮቿው እንዲያደርጉ አስገድዷል። ስብሰባዎች በዙም መካሄድ ከጀመሩም ወራት ተቆጥረዋል። ዙም ስብሰባ ማከናወኛ ብቻ ሳይሆን ከሥራ ማባረሪያም ሆኗል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ‘ፓና’ የተባለ ድርጀት ነው። የድርጅቱ ኃላፊዎች ሁለት ስብሰባ እንደሚካሄድ አስታወቁ። የመጀመሪያው ስብሰባ 3፡00 ላይ ሁለተኛው ደግሞ 3፡45 ላይ።
የሦስት ሰዓቱ ስብሰባ ከተቋሙ ጋር ለሚቀጥሉ ሰዎች ነበር። ቀጣዩ ስብሰባ ደግሞ ለሚባረረሩ ተቀጣሪዎች። ሠራተኞቹ ለየትኛው ስብሰሰባ እንጠራ ይሆን? ብለው ተጨንቀው ነበር። ከነዚህ አንዷ የሽያጭ ኃላፊዋ ሩቲ ታውንሰንድ ናት። በጣም ከመጨነቋ የተነሳ የ3 ሰዓቱና የ3፡45ቱ ስብሰባ ትምታታባት። “ከሥራ የሚባረሩ ሰዎች አሉ የሚለው ዜና አስደንግጦኝ ስለነበር ስብሰባዎቹ ተምታቱብኝ። የሦስት ሰዓቱን ስብሰባ በዙም ከተቀላቀልኩ በኋላ ልባረር እንደሆነ ሲገባኝ ቪድዮውን አቋረጬ ወጣሁ።” • የፌስቡክ ሠራተኞች በመሥሪያ ቤታቸው ድርጊት ተበሳጩ • የጆርጅ ፍሎይድ የአስከሬን ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ ዴንቨር የሚገኘው የጉዞ ድርጅቱ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ገቢው ስለቀነሰ ሠራተኞችን ለማሰናበት ተገዷል። ሌሎች ኪሳራ የገጠማቸው ድርጅቶችም ተመሳሳይ እርምጃ ከመውሰድ ውጪ አማራጭ አጥተዋል። ቀድሞ ቀጣሪና ተቀጣሪ ፊት ለፊት ተገናኝተው ያወሩ ነበር። አሁን ግን ሠራተኞች የሚባረሩት እንደ ዙም እና ማይክሮሶፍት ቲም ባሉ ቴክኖሎጂዎች ሆኗል። ክሪስ ማሎን መርሀ ግብሮች የሚያዘጋጀው የዩኬው ‘ስፓርክ’ የተባለ ድርጅት ውስጥ ይሠራ ነበር። የድርጅቱን የማይክሮሶፍት ቲም የቪድዮ ስብሰባ ከሰው ኃይል ክፍል ተቀጣሪዎች ጋር እንደሚያካሂድ ሲነገረው፤ ከሥራ ሊባረር እንደሆነ ጠርጥሮ ነበር። የፈራው አልቀረም ስብሰባው ላይ ከሥራህ ተሰናብተሀል ተባለ። “በስልክ ቢሆን የሚያባርርህን ሰው ፊት አታየውም። ለቪድዮ ስብሰባ ብለህ የክት ልብስህን አድርገህ በተቀመጥክበት መባረር ግን ምቾት ይነሳል። ከሚያባርረው ሰው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ብትሆን ከሰውነት እንቅስቃሴው ምን ለማለት እንደፈለገ ስለምትረዳ እንግዳ ስሜት አይሰማህም።” ክሪስ እንደሚለው፤ የአንድ ድርጅት ሠራተኞች ባጠቃላይ በቪድዮ በተሰበሰቡበት ከመባረር ይልቅ ቀጣሪ ለተቀጣሪው ለብቻው ደውሎ ቢያሰናብተው ይመረጣል። ሩቲ ሥራዋን ከማጣቷ በፊት በተሳተፈችበት የመጨረሻ ስብሰባ 15 ሰዎች ነበሩ። • በምዕራብ ኦሮሚያ ነጆ አራት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች ተገደሉ • “ኮሮናቫይረስን ለሦስት ሳምንታት በሦስት ሆስፒታሎች ታገልኩት” “እኔና አለቃዬ ብቻ ብንሆን ስሜቴን መረዳት ይችላል። የቡድን ስብሰባ ስለነበረ መጠየቅ የምፈልጋቸውን ጥያቄዎች ሳላነሳ ነው ስብሰባውን ያቋረጥኩት።” ጄኤምደብሊው የተባለ የሕግ አማካሪዎች ተቋም ውስጥ የምትሠራው ሣራ ኢቫንስ እንደምትለው፤ ሥራ ቦታ ላይ የሚከናወኑ ነገሮችን ለተቀጣሪዎች ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ነው። “በዙም ትልቅ ስብሰባ ጠርቶ ለሁሉም ሠራተኞች ምን እንደተፈጠረ ማሳወቅ ያስፈልጋል” ስትል ታስረዳለች። ሠራተኞች ከተሰናበቱ በኋላ ምን እንደሚጠብቃቸው እንዲሁም ተቋሙ ስላለበት ሁኔታም ለማወቅ ግልጽነት የተሞላቸው ስብሰባዎች መካሄድ አለባቸው ትላለች። ሣራ እንደምትለው፤ ለአንድ ሰው ስልክ ደውሎ ተባረሀል ማለት ይሻላል? ወይስ በቪድዮ ስብሰባ ከሥራ መሰናበቱን ማሳወቅ? የሚሉት ጥያቄዎች በሕግ ማዕቀፍ ምላሽ ያላቸው አይደሉም። ተቀጣሪ እንዴት ይባረር የሚለው ጉዳይ የሥነ ምግባር ጥያቄ ነው። አሜሪካ ውስጥ በቡድን የቪድዮ ስብሰባዎች ላይ ተቀጣሪዎችን ማባረር ቢቻልም፤ በዩናይትድ ኪንግደም ግን ሕገ ወጥ ነው። ሩቲ የዩኬ ዜጋ ብትሆን፤ አለቃዬ ያባረረኝ ፍትሐዊ ባልሆነ መንገድ ነው ብላ መክሰስ ትችል ነበር። ቪድዮ ስብሰባዎች ሲካሄዱ መቅረጽ ይቻላል ወይ? ሌላው ጥያቄ ነው። • ከስልክዎ ጋር ጨክነው ለመለያየት አምስት መንገዶች ኮርከር ቢኒንግ የተባለው የሕግ አማካሪዎች ድርጅት አጋር መስራች ፒተር ቢኒንግ እንደሚለው፤ ማንም ሰው የስብሰባ ቪድዮ ከመቅረጹ በፊት በይፋ ማስታወቅ አለበት። አንድ ሰው በቪድዮ የተባረረው ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ መሆኑን ለማሳየት የቪድዮ ማስረጃ ለመጠቀም ቢፈልግም፤ ሕጋዊነቱ ላይ ጥያቄ ሊነሳ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ ባሙያው ያስረዳል። ቪድዮ የሰው ለሰው ግንኙነትን ለውጧል። ይህም በሥራ ቦታ ላይ ማጥላቱ አልቀረም። የሥነ ልቦና አማካሪዋ ፐርን ካንዶላ እንደሚሉት፤ አንድ ሰው ከሥራ ሲሰናበት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ግልጽ መረጃ ሊሰጠው ይገባል። “የአንድን ሰው አይን እያዩ ማባረር ምቾት ሊነሳ ይችላል። ንዴቱና ቁጣው ፊቱ ላይ ይነበባልና። ሆኖም ግን ግልጽ ሆኖ መነጋገር ያዋጣል።”
news-46538976
https://www.bbc.com/amharic/news-46538976
ኦባንግ ሜቶ ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ተስፋና ስጋት አለ
ልክ የዛሬ 17 ዓመት ጋምቤላ ውስጥ በአኙዋኮች ላይ የተፈፀመው ግድያ ወደ ሰብአዊ መብት ተከራካሪነት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት የሆነው ኦባንግ ሜቶ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ለውጥ ተስፋና ስጋትን ይዟል ስለዚህ መስተካከል ያሉባቸውን ነገሮች ልናከናውን ይገባል ይላል። ቢቢሲ፡ ከአስራ ስድስት ዓመታት የውጭ ቆይታ በኋላ ወደኢትዮ ጵ ያ ተመልሰሀል ። ምን ስሜት ፈጠረብህ?
ኦባንግ ሜቶ፡ የተሰማኝማ ብዙ ነገር ነው። እኔ የምሰራው የሰብዓዊ መብት ሥራ ነው። ለአስራ ስድስት ዓመት ያህል ሰርቻለሁ። እና ሁሌም የምሟገተው ለኢትዮጵያዊያን መብት ነው። ሰብዓዊ መብት ስንል ለኢትዮጵያዊያን መብት ማለት ነው። የብሄር መብት አይደለም። የአንድ ጎሳ፣ የአንድ ኃይማኖት ወይንም ክልል አይደለም። የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብት ማለት ነው። እና ወደ አገር ቤት መመለሴ ትልቅ ደስታ ነበር የፈጠረብኝ። ሰው ሞቶ፣ የሰው አካል ጎድሎ ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ ነው ለዚህ የበቃነው። እነዚህ ሰዎች መስዋዕትነት ባይከፍሉ ኖሮ እዚህ ልሆን አልችልም ነበር። በራሴ እኔ ያደረግኩት ነገር የለም። እነርሱን ማመስገን በጣም አስፈላጊ ነው። ለውጡ የሁሉም ቢሆንም የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት የሞቱት ሰዎች ናቸው፣ የቆሰሉ ሰዎች ናቸው። እስር ቤት የነበሩ ሰዎች ናቸው። ይሄንን አስታውሳለሁ። • በእስር ቤት ውስጥ ሰቆቃና ግፍ ለተፈጸመባቸው ካሳ ሊጠየቅ ነው • ቴሬዛ ሜይ ሥልጣናቸውን እንዳያጡ ተሰግቷል ቢቢሲ፡ ለመጨረሻ ጊዜ ወደኢትዮጵያ በመጣህ ጊዜ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አልነበርክም። ወደዚያ የወሰደህ መንገድ ምን ዓይነት ነበር? ኦባንግ ሜቶ፡ ለሰብዐዊ መብት ተከራካሪ ወደመሆን እገባለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ከዚህ በፊት በጋምቤላ ግጭት ነበር። ያኔ የሞቱ 424 ሰዎች ነበሩ። ዛሬ ሐሙስ አስራ ሰባት ዓመት ሞላው። ከዚያ በኋላ ነው ለሰብዓዊ መብት መታገል የጀመርኩት። ያኔ ሰዎቹን የገደለው የመከላከያ ሠራዊት ነበር። አሁንም ወደኢትዮጵያ ስንመለስ የሰብዓዊ መብት ላይ የሚከራከር ቡድን አለን። ከዚያ ቡድን አስራ ስድስት ሆነን ነው የመጣነው። ከአስራ አራት የተለያዩ ብሄሮች ነው የተገኘነው። ቡድኑን የምትመራው ኤድና አለማየሁ ናት። ስድስቱ ሴቶች ናቸው። ስንመጣ ዋነኛ ዕቅዳችን የነበረው ወደ ጋምቤላ ለመሄድ ነበር። የእኔ መገኛ ከዚያው ስለሆነ። ሄደንም መልዕክት ስናስተላለፍ፤ በቀል አይደለም የሚያስፈልገው ነው ያልነው። እና እኛ ያሰብነው ጋምቤላ የእርቅ ምንጭ እንዲሆን ነው። የእርቅ ሒደቱ የሚጀመርበት ማዕከል እንዲሆን ነው። ግድያው ሲፈፀም የተነጣጠረው በአኙዋክ ብሄረሰብ አባላት ላይ ነበር። እነርሱ አሁን በቀለኞች ሊሆኑ ይችላሉ። ግድያው የተፈፀመው በመከላከያ ሰራዊት አባላት ስለነበረ ምሬት ሊኖር ይችላል። እኔ ግን ያሰብኩት፤ መጥፎን ነገር በመጥፎ ነገር ማስተካከል አይቻልም። ስለሆነም ሰዎቹን ሰበሰብን፤ ከዚህ በፊት ያልተሞከረ ነገር አደረግን። ከዚህ ቀደም ስለሞቱት ሰዎች ምንም አይነሳም። ምንም ማስታወሻ የለም። ትንሽ ቪዲዮ ነበረን እርሱን አሳየን። የሞቱት ሰዎች የእያንዳንዳቸው ስም ተነበበ። መታሰቢያ እንዲኖር ነው የፈለግነው። ለበቀል ሳይሆን ከዚህ በኋላ እንዳይደገም። እንዲህ መሰል ነገር ዳግመኛ መኖር የለበትም። ይሄንን አድርገን ወደ አዲስ አበባ ተመለስን። • የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች • ፈረንሳይ 'አላሁ አክበር' ብሎ ተኩስ የከፈተውን ግለሰብ በማደን ላይ ናት • ኻሾግጂ የዓመቱ ምርጥ ሰው ዝርዝር ውስጥ ተካተተ ቢቢሲ፡ ከውጭ እንደመጣህ የመጀመሪያ ጉዞህን ያደረግከው ወደጋምቤላ ነበር። በዚህ ሳምንት አጋማሽ ተመልሰህም ትሄዳለህ። ለምን ጉዳይ ነው? ኦባንግ ሜቶ፡ አዎ። አሁን አርባ ሁለት ዓመቴ ነው። ሃያ ስምንት ዓመት ያህል በውጭ ነው የኖርኩት። እ.ኤ.አ በ2001 ገደማ ወደጋምቤላ ሄጄ የኗሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያግዝ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አቋቁሜ እንቀሳቀስ ነበር። ከዚያ እ.ኤ.አ. 2003 በክልሉ ሆስፒታል ለማቋቋም እየጣርን ነበር። ሆኖም ያኔ በክልሉ እና በፌዴራል መንግሥት መካከል ውጥረት ነበር። የጋምቤላ አስተዳዳሪ እና ሌሎችም ሰዎች ሲታሰሩ ውጥረቱ ይበልጡ ከረረ። በታህሳስ ወር ወደ ሱዳን የስደተኞች ጣብያ በማቅናት ላይ የነበረ ተሽክርካሪ ጥቃት ደረሰበት። በውስጡ የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች አለቁ። ጋምቤላ የነበረው የሃገር መከላከያ ሠራዊት ታዲያ ጥቃቱን የፈፀሙት የአኙዋክ ብሄረሰብ ታጣቂዎች ናቸው በማለት እርምጃ መውሰድ ጀመሩ። ሂውማን ራይትስ ዋች በዚህ ጉዳይ ላይ ጥሩ ሪፖርት አጠናቅሯል። ከተገደሉት ሰዎች መካከል የተወሰኑትን አውቃቸዋለሁ። ከዚያ በኋላ ነው ፍትህን ፍለጋ የጀመርኩት። የአኙዋክ ፍትህ ጉባዔ የሚሰኝ ተቋም መሰረትኩ። ከዚያም ለሰብዓዊ መብት ወደ መታገል ገባሁ። እነርሱ ባይሞቱ ኖሮ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችም አልሆንም ነበር። መንግሥት ክስተቱን ሲያስተባብል ነው የኖረው። አሁን ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎች ማውራት የጀመሩት። ሐሙስ አስራ ሰባተኛ ዓመት ይሆነዋል። ከዚያን ሁሉ ጊዜ በኋላም ግን ትናንትና የተከናወነ ነው የሚመስለኝ። አዕምሮዬ ውስጥ አሁንም ለጋ ነው። እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሞታቸው የተደበቀ አይሆንም። እርሱን በሚያስታውስ ዝግጅት ላይ ለመገኘት ነው የምሄደው። ቢቢሲ፡ ከዚያ በኋላም ወደተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ተጉዘሃል። ምንድን ነበር ዓላማህ? ኦባንግ ሜቶ፡ ወደ ሌሎች ስድስት ክልሎች ተጉዘናል። ዋናው ዓላማችን ከሰዎች ጋር ለመገናኘት እና ሃሳባቸውን ለመስማት ነበር። ሕዝቡ ምን እያለ ነው? ብለን ለማዳመጥ። የሰብዓዊ መብት ሥራ የአዲስ አበባ ወይንም የከተማ ብቻ አይደለም። ዓላማችንም በመጀመሪያ አገሩን እስካሁን ካቆዩ ሽማግሌዎች ጋር ለጥቆም ነገ የሚረከቧት ወጣቶችን ለማግኘት ነው። የኃይማኖት አባቶችም ጥበብን ፍቅርን የማስተማር ኃላፊነት አለባቸው። ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የተከናወነው ነገር ቀላል አይደለም። ሌላው ቀርቶ ምግባር (ሞራል) የሚባል ነገር ከልጆቻችን ተወስዷል። ብዙዎች ስለኢትዮጵያዊነታቸው ቀርቶ ስለማንነታቸው የማያውቁ አሉ። ከማኅበረሰብ ውስጥ የሰዎችን ሥነ ምግባር ስትወስድ ገደልካቸው ማለት ነው። አንደኛው በየቦታው የታዘብኩት ነገር ብሔራዊ ስሜት የሚባል ነገር ያለመኖሩን ነው። ሁሉም በየብሔሩ ነው። ይሄንን ትውልድ እንዴት ነው መቀየር የሚቻለው? ብዙ ሥራ ያስፈልጋል። ከከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ስንገናኝም ያነሳነው ይሄንን ነው። የእኛ ተቋም የሚለው ከዘር በፊት ሰብዓዊነት ይቅደም ነው። ሰው በሰውነቱ በቂ ነው ነው። ሁላችንም አብረን ነፃ ካልወጣን አንዳችንም ነፃ ልንወጣ አንችልም ነው። በየቦታው እንደተመለከትነው ትልቅ ተስፋ አለ። ግን ደግሞ ስጋትም አለ። ይሆናል ተብሎ የማይታሰበው ሲሆን ያመጣው ተስፋ ትልቅ ነው። ያ ደግሞ እኔንም ጨምሮ ማለት ነው። ተስፋ ደግሞ ያለተግባር ዋጋ የለውም። በጊዜም ይወሰናል። እስከመቼ ድረስ? እነዚህ ወጣቶች ጥሩ ትምህርት ያገኛሉ ወይ? ጥሩ ሥራ ያገኛሉ ወይ? በየቦታውስ ያለው ግጭት? ብዙ ሰዎች ይፈናቀላሉ። በብሄር ፖለቲካ ምክንያት ነው። ይህን ችግሩ ፖለቲካ ነው ያመጣው። በእኔ አመለካከት ዋናው ችግር ሌላ ሳይሆን በብሔር የተቃኘው የፌዴራሊዝም ሥርዓት ነው። ለምን ቢባል ሥርዓቱ ሲተገበር ለአገሩ ዕድገት አይደለም፣ ለሰላም አይደለም፣ ለእኩልነት አይደለም፣ ለፍትህ አይደለም። አገር የሚመሩ ሰዎችን ለመጥቀም ነው። ቢቢሲ፡ አንዴ ላቋርጥህና. . . አሁን ያለው ብሔር ተኮር ፌዴራላዊ ሥርዓት የተለያዩ ፍላጎቶችን ለማመቻመች፣ ልዩነቶችን ለማቻቻል እና ብዝሃነትን ለማክበር ያለው ብቸኛ መንገድ ነው ሲሉ የሚከራከሩ ወገኖች አሉ። ኦባንግ ሜቶ፡ መወያየት አለብን። ምናልባት የብሔር ፌዴራሊዝሙን አጥብቀው የሚደግፉ ሰዎች የራሳቸውን ጥቅም የሚያሰሉ ሊሆኑ ይችላሉ። በዚህ ሥርዓት ጥሩ ቦታ እናገኛለን ብለው ያሰቡ ሊሆን ይችላሉ። ቢሆንም መወያየት አለብን። ሥርዓቱ ሲፀድቅ ሕዝቡ አልተወያየም እኮ። የየክልሉ ድንበር ሲወሰን የተወያየ የለም። ለመምራት እንዲመች ነው። ለፍትህ፥ ለእኩልነት አልነበረም። ብሔር ብሔረሰቦች ብለን እዚህ እንጨፍራለን። በኋላ ሲገናኙ መገዳደል። ችግር እንዳለ ሁላችንም ማመን አለብን። ካመንን በኋላ እንዴት እንፈታዋለን ብሎ ማሰብ ነው። ሃቀኛ ሰዎች ከሆነን። በእኛ ተቋም ጥናት መሠረት አስራ ስድስት ቦታዎች የብሔር ግጭቶች የተስተውሎባቸዋል። ኢትዮጵያ እኮ ሰማንያ ብሄር ብሄረሰቦች አሏት። ሁሉም እኩል ውክልና አላቸው? አንዳንዶቹ ስማቸው ተጠቅሶ ክልል ሆነዋል። ሌሎቹስ? በዚያ ላይ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ አፋር፣ ሱማሌ አጋር ናቸው ይባላል። መገለል ነው ይሄ። ቢቢሲ፡ ስለዚህ በተለምዶ መሃል አገር (ሴንተር) በሚባሉት እና ዳር አገር (ፔሪፌሪ) በሚባሉት አካባቢዎች መካከል ውጥረት ወይንም የአያያዝ ልዩነት አለ ብለህ ታምናለህ? ኦባንግ ሜቶ፡ አገሪቷን ከመሩት ሰዎች ድንቁርና የመጣ ነው። የአራቱ ክልሎች ፓርቲዎች ናቸው ገዥውን ፓርቲውን የፈጠሩት። ሌሎቹስ አጋር ብቻ? ምንድን ነው ይሄ መገለል ካልሆነ? እነዚህ ክልሎች ሲገለሉ ነው የኖሩት። እኛ ሁላችንም ከሌላው እኩል ለአገራችን ስንደማ፣ ስንሞት ነው የኖርነው። ስድብ ነው ለእኛ። ቢቢሲ፡ በየሄድክባቸው ቦታዎች ሁሉ ሰዎች እየመጡ ሰላም ሲሉህ፣ ሲያቅፉህ፣ ፎቶ አብረውህ ሲነሱ በማኅበራዊ ሚዲያ አይተናል። እንዴት አየኸው? ኦባንግ ሜቶ፡ ከምንም በላይ ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። ይች አገር የጎደላት ነገር ፍቅር ነው። እና ራስን ማክበር ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ ብሔሩን፣ ኃይማኖቱን የት እንደተወለደ የማላውቀው ኢትዮጵያዊ መጥቶ ልክ እንደማውቀው ወንድም ሲያቅፈኝ ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው ብቸኛው ነገር ለአንድ ብሔር ሳይሆን ለሰብዓዊነት ለመታገል መወሰኔ ልክ እንደነበር ነው የሚያረጋግጥልኝ። ለምሳሌ ጎንደር ላይ የተደረገልኝ አቀባበል ጋምቤላ ላይ ከነበረውም አቀባበል የበለጠ ነው። እንዲያውም ለጓደኞቼ 'አሁን የማንነት ዘመን ላይ ነው ያለነው። እኔም ማንነቴን አገኘሁት፤ በአያቴ ጎንደሬ ነኝ' እያልኩ ስቀልድ ነበር። የኢትዮጵያን ውበት ኖሬበት አይቼዋለሁ ነው የምለው። ለምሳሌ ወደ ሐረር አካብቢ የሄድን ጊዜ ከገበሬዎች ጋር ተገናኝቼ ነበር። አንዳንዶቹ 'ከዚህ በፊት ከጋምቤላ የመጣ ሰው አይተን አናውቅም ነበር፤ አንተ የመጀመሪያው ነህ' ብለውኛል። ሆኖም ግን ከእነርሱ አንዱ እንደሆንኩ አድርገው ነበር የተቀበሉኝ።
50673671
https://www.bbc.com/amharic/50673671
ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል?
ሃምሳ የሚሆኑ ከተለያዩ ከማኅበረሰብ ክፍሎች የተወጣጡና በኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ሚና ይኖራቸዋል የተባሉ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ለ11 ቀን አብረው ውለው፣ 8 ቀን አብረው አድረው ስለኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ መክረዋል።
እነዚህ በኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ቁልፍ ሚና አላቸው የተባሉ አካላት ምክክራቸውን ሲያደርጉ መገናኛ ብዙኀን እንዳይገኙ፣ ታዛቢ እንዳይኖር ተደርጎ አንደነበርም ሰምተናል። • ኢህአዴግ እዋሃዳለሁ ሲል የምሩን ነው? 50 የሚሆኑትን ተሳታፊዎች ለመምረጥም ስድስት ወር ፈጅቷል ያሉት አዘጋጆቹ፤ 150 ሰዎችን ማነጋገር አስፈልጎ እንደነበርም ጨምረው ለቢቢሲ ገልጸዋል። እነዚህ የምክክሩ ተሳታፊዎች በመጨረሻም ኢትዮጵያ የዛሬ 20 ዓመት ሊገጥማት ይችላል ያሏቸውን አራት እጣ ፈንታዎች ማስቀመጣቸውንም ተነግሯል። የተለዩት ዕጣ ፈንታዎች ምንድን ናቸው? በዚህ ወርክሾፕ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ምን ምን ዓይነት ዕጣ ፈንታዎች ይጠብቋታል የሚለው ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል ያሉት የወርክሾፑ አዘጋጆች ከሆኑት መካከል አንዱ አቶ ንጉሡ አክሊሉ ናቸው። ዝም ብለን ብንቀጥል ምንድን ነው የምንሆነው? ዝም ብለን ጊዜ የሚያመጣውን ከምንጠብቅ እየገነባን ብንሄድ የት ጋ ልንደርስ እንችላለን? የሚለውን 50ዎቹ ተሳታፊዎች ከተነጋገሩ በኋላ አራት እጣ ፈንታዎችን ለይተው አውጥተዋል ይላሉ አቶ ንጉሡ። ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት ግን የወርክሾፑ አዘጋጆች ሀሳብም ሆነ አስተያየት አይሰጡም ያሉት ደግሞ አቶ ሞኔኑስ ሁንደራ ናቸው። አቶ ሞኔኑስ ከወርክሾፑ አዘጋጆች መካከል ሲሆኑ ውይይቱም ሆነ ሀሳቡ ከራሳቸው ከፖለቲከኞቹ የሚመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ጨምረውም የአዘጋጆቹ ድርሻ የነበረው የስብሰባውን ሪፖርት መጻፍ፣ ለሁሉም ተሳታፊዎች መላክና እነርሱ በሚሰጡት አስተያየት መሰረት የተስማሙበት እየቀጠለ እንዲሄድ ማድረግ እንደነበር ያብራራሉ። ተሳታፊዎች ኢትዮጵያ በመጪዎቹ 20 ዓመታት ይገጥማታል በማለት የለይዋቸውን ዕጣ ፈንታዎችና መጨረሻ የሚሉት ነጥብ ላይ ለመድረስ መንገዱ ምን ይመስላል? ስያሜዎቹ መዳረሻዎቹና እዚያ የሚያደርሱት መንገዶችን የቀየሱት እራሳቸው መሆናቸውን ከአዘጋጆቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጠቅሰዋል። • "ኢህአዴግ ተዳክሟል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ይህ ሁሉም የተስማሙበት ሰነድ ከ20 ጊዜ በላይ አስተያየት በመስጠት መመላለሳቸውን፣ በስህተት የገቡ እንዲወጡ፣ የተዘነጉ እንዲገቡ እየተደረገ የሁሉም ሀሳብ ተካትቶ የመጨረሻው ሰነድ መውጣቱ ይናገራሉ። በዚህም የውይይቱ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያን የዛሬ 20 ዓመት ሊገጥማት ይችላል ያሏቸውን እጣ ፈንታዎች በሰባራ ወንበር፣ በአጼ በጉልበቱ፣ በየፉክክር ቤትና በንጋት መስለው አቅርበዋል ያሉት ደግሞ አቶ ሞኔኑስ ሁንደራ ናቸው። የእነዚህ የእጣ ፈንታዎቹ ስያሜዎችን ሲያብረራሩም፤ ሰባራ ወንበር ተብሎ የተሰየመው ኢትዮጵያ አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠለች የዛሬ 20 ዓመት የመንግሥት ሥልጣን ቢኖርም ሀገርን ወደ ሚፈልገው ጎዳና ለመምራት አስቸጋሪ ይሆናል በሚል መሆኑን ያስረዳሉ። የፖለቲካ ኃይሎች፣ ብሔር ብሔረሰቦችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ሀገርን ወደ ቀና ጎዳና መምራት የሚያስችል ፍላጎት ቢኖራቸውም አቅም ግን አይኖራቸውም ሲሉ ይተነብያሉ። በዚህም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ማህበራዊና ደህንነት ሁሉ ይሽመደመዳል ሲሉ ይገልጻሉ። አቶ ሞኔኑስ በመቀጠል፣ 'አጼ በጉልበቱ' ተብሎ የተሰየመውን እጣ ፈንታ ሲያብራሩ በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት እየታየ እንዳለው ዜጎች የተለያየ ጥያቄ እያነሱ ነው ብለዋል። መንግሥት እነዚህን ጥያቄዎች ለመፍታት የሚሠጠው ምላሽ ወሳኝ ነው በማለትም፤ አሁን ያለው ስጋት ጥያቄዎቹ እየበዙ ሲሄዱ መንግሥት ጥያቄዎቹን ለማፈን ጠመንጃ ቢጠቀም፣ ቢያስር ወደ የኃይል አገዛዝ የማምራት ዕጣ ፈንታ ይኖራል ሲሉ ማስቀመጣቸውን ያብራራል። 'የፉክክር ቤት' በሚል በተቀመጠው እጣ ፈንታ ሊከሰት የሚችለው ይላሉ አቶ ሞኔኑስ፤ ብሔር ብሔረሰቦች ከአጼ በጉልበቱ አገዛዝ ለመውጣት የሚያደርጉት እና መብታቸውን ለማስከበር በሚወስዱት ርምጃ ነው ይላሉ። ብሔር ብሔረሰቦች በየግል የራሳቸውን አገር ለመመስረት ይንቀሳቀሳሉ። አገራዊ አስተሳሰብ እየቀረ ሁሉም በየብሔሩ እያሰበ የሚሄድበት ሁኔታ፤ በዚህም አተካሮና ፉክክር ውስጥ ተገብቶ የጋራ አገር ይረሳል፤ አገርም ወደ መፍረስ ትሄዳለች በማለት ማስቀመጣቸውን ያብራራል። በመጨረሻ የተቀመጠው ዕጣ ፈንታ 'ንጋት' የሚል ሲሆን አሁን አገር ያለችበትን ሁኔታ ተሳታፊዎቹ በጨለማ መስለውታል ብለዋል። በዚህ ወቅት እስር፣ ግድያ፣ መከፋፈል፣ እርስ በርስ መጠራጠር እና ሌሎች ስጋቶች ተጋርጠው ይታያሉ ሲሉ የተቀመጠውን እጣ ፈንታ ይገልጻሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ጥያቄዎች በሂደት እየተመለሱ መተማመን እየተፈጠረ መነጋገር ከተቻለ ፌደራሊዝምና እርሱን የሚያጠናክሩ ተቋማት እየዳበሩ ጨለማው ተገፍፎ ብርሃን ይወጣላታል ሲሉ ማስቀመጣቸውን ይናገራሉ። ከእነዚህ ከአራት እጣ ፈንታዎች መካከል ሦስቱን ተሳታፊዎቹ እንደማይፈልጓቸው ማስቀመጣቸውን የሚናገሩት አቶ ንጉሡ፤ 'ንጋት' ግን ሁሉንም የሚያስማማ ነው በማለት በንጋት ውስጥ ሊያይዋት የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ ለመስራት እና ለቀጣይ ትውልድ ለማውረስ እንደሚሰሩ በመግለጽ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ የአቋም መግለጫ ማውጣታቸውን ገልጸዋል። • "ኢህአዴግ ነፃ ገበያም፣ ነፃ ፖለቲካም አላካሄደም" ፀደቀ ይሁኔ (ኢንጂነር ) 'ንጋት' የተሰኘው እጣ ፈንታ እንዲሁ በቀላሉ ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ መነጋገር፣ መደማመጥ ብሔራዊ መግባባት እንደሚያስፈልገው አቶ ንጉሡ ያስረዳሉ። የትብብር መንፈስ መፍጠር፣ እየሰጡ መቀበልና ማመቻመች ስለሚያስፈልግ በቀጣይ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚኖሩ ድርድርና እርቆች እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። የፓርቲ አመራሮች እዚህ የወሰኑትን የ'ንጋት' እጣ ፈንታ ለአባላቶቻቸው በመንገር የማስረጽ ሥራ እንደሚሰሩ ይናገራሉ። 'ንጋት'ን ወደ ሕዝቡ ለማስረጽ የተለያዩ ሥራዎችን እንደሚሰሩ የሚናገሩት አቶ ንጉሡ፤ የስብሰባው 50 ተሳታፊዎችም ይህንኑ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውን ይናገራሉ። አዘጋጆቹ እነማን ናቸው? ዘጠኝ ጓደኛሞች ናቸው። በተለያየ የህይወት አውድ ውስጥ የሚውሉ ቢሆንም ሲገናኙ ግን ስለ አገራቸው ዘወትር ያወራሉ። እነርሱም ሆኑ ሌሎች ስለኢትዮጵያ በሚያወሩት ጉዳይ ግን ደስተኞች አልሆኑም። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ሕዝባዊ ተቃውሞና በነበረው ብሔር ተኮር ግጭት ምክንያት ብዙዎች የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ ከሊቢያና ከሶሪያ ጋር እያዛመዱ የሚያወሩ በረከቱ። እነርሱ ግን የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ ከሶሪያና ከሊቢያ ከማመሳከር ይልቅ እንዲህ ዓይነት ሕዝባዊ ተቃውሞና ግጭት ገጥሟቸው በድል የተሻገሩ አገራትን ማሰስ ጀመሩ። የገጠማቸውን ችግር አልፈው ወደ ተሻለ ጎዳና የሄዱ አገራት ያደረጓቸውን ነገሮች ሲመረምሩም አንድ ቁልፍ ነገር ማግኘታቸውን አቶ ንጉሡ ይናገራል። • "ኢትዮጵያ የኢህአዴግ አባት እንጂ፤ ኢህአዴግ የኢትዮጵያ አባት አይደለም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አቶ ንጉሱ ራሳቸውን ከገጠማቸው ችግር ውስጥ ያወጡና ሕዝባቸውን ወደ ዲሞክራሲ ያሻገሩ አገራት ያደረጉ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሪዎች እንዲሁም የተወሰኑ የቁልፍ ተዋንያን የሚያደርጉት ዝግ ውይይትና ንግግር እንደሆነ ከንባባቸውና ከአሰሳቸው ማግኘታቸውን ይናገራሉ። እነዚህ ዝግ ውይይቶች ለመገናኛ ብዙኀንም ሆነ ለታዛቢዎች ዝግ እንደሚሆኑም ማስተዋላቸውን ይጠቅሳሉ። እንዲህ አይነት ንግግሮች እርስ በእርስ መቀራረብ፣ መግባባትና መተማመንን እንደሚፈጥሩ መረዳታቸውን እንዲሁም በጋራ መነጋገር ከጀመሩ በኋላ አንድ የጋራ ሰነድ ይዘው ሊወጡ እንደሚችሉ ተረድተዋል። እንዲህ አይነት ልምድ በደቡብ አፍሪካ፣ በኮሎምቢያ፣ በሜክሲኮ፣ በአየርላንድና በካናዳ ተሞክሮ ሸጋ ውጤት ማሳየቱንም ይገልጻሉ። ድርድርም እርቅም ያልሆነ መርሃ ግብር እነዚህ በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዋነኛ የፖለቲካ ተዋናዮችን አቀራርቦ ሀሳባቸውን እውን ለማድረግ ይበጃል ያሉትን ያወጡ ያወርዱ ጀመር። በቅድሚያ ለዚህ ጥረታቸው "ዴስቲኒ ኢትዮጵያ 2040" የሚል ስያሜ ሰጥተዋል። ሀሳባቸውን ይዘው በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ጉምቱ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ደጃፍን ማንኳኳት ጀመሩ። በመጀመሪያ እናንተ ማናችሁ የሚል ጥያቄ ከተሳታፊዎቹ መቅረቡን ያስታውሳሉ። ዘጠኙ ጓደኛሞች በተለያየ የሙያ መስክ የተሳካላቸው ቢሆኑም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን ስማቸው ተነስቶ ዳናቸው ተገኝቶም አያውቅም። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ሊወያዩ ነው • ህወሓት ከኢህአዴግ ለመፋታት ቆርጧል? ይህ እንደ ድክመት ቢነቀስባቸውም ነገር ግን ገለልተኛ ለመሆናቸው እንደ አስረጅ ሊቀርብ የሚችል መሆኑን አቶ ንጉሡ በኩራት ያስረዳሉ። የወርክሾፑ ተሳታፊዎችን ለመመልመል በዙሪያቸው የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ማነጋገር፣ ዓላማውን ማስረዳት እንደነበረባቸው ይናገራሉ። በመጨረሻም ከተሳታፊው ጋር በቀጥታ ከመገናኘታቸው በፊት የተሳታፊው የቅርብ ወዳጆች ስለዚህ ወርክሾፕ አስቀድመው ነግረውት ስለሚጠብቃቸው እምነት ለማግኘት እንዳልከበዳቸው ያብራራሉ። 50 ሰው ለመመልመል ከ150 በላይ ሰዎችን ማነጋገር አስፈልጓቸው እንደነበር የሚገልጸው ንጉሡ፣ እነዚህ 150 ሰዎች ወደ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አድራሽ እንጂ በራሳቸው መዳረሻ አልነበሩም ይላል። እነዚህን ሰዎች ማነጋገር በራሱ ስድስት ወር መፍጀቱን በማስታወስም ወርክሾፑ መካሄድ ከመጀመሩና ደጋፊ አካላትን ገንዘብ ልገሳ ከመጠየቃቸው በፊት የተሳታፊዎቹን ይሁንታ ማግኘትን ማስቀደማቸውን ያስረዳሉ። አንዳንድ ተሳታፊዎች በመካከል የሚወጡ፣ የሚጠራጠሩና እንዲህ ዓይነት ውይይት የተለመደ ነው በማለት ማጣጣል እንደነበር ያስታውሳሉ። ተስፋ ባለመቁረጥ ይሁንታቸውን ከሰጡ በኋላ በሚወጡ ሰዎች ምትክ እየተኩ፣ ካልሆነ እንዲተኩ በማድረግ ወርክሾፑን ማስጀመራቸውን ይናገራሉ። ወርክሾፑን መሳተፍ ከጀመሩ መውጣት አይታሰብም የሚሉት አቶ ንጉሡ፣ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ጉዳይ መሳተፋቸውን ይጠቅሳሉ። "ይህ ፕሮግራም ድርድር አይደለም፤ እርቅ አይደለም። ይህንን በወርክሾፑ ላይ የተሳተፉ አካላትም ቀድመው እንዲያውቁ ተደርጓል" በማለትም ከተለያየ የፖለቲካ አመለካከት እና አስተሳሰብ የሚመጡ ፖለቲከኞች በታሪክ የማይግባቡባቸው ነጥቦች መኖራቸውን ያነሳሉ። እነዚህ አለመግባባቶችና ልዩነቶች እየሰፉ ሄደው ስለዛሬና ስለነገ እንኳ እንዳናስብ እያደረጉን ነው በማለት፤ የዚህ ወርክሾፕ ዋነኛው ዓላማ ሰዎችን ከትናንትናና ከዛሬ አውጥቶ፣ በትናንትና በዛሬ ላይ በመመስረት ነገን እንዲያዩት ማድረግ መሆኑን ይገልጻሉ። "ነገን አብረው እንዲገነቡት በነገይቱ ኢትዮጵያ ላይ እየተወያዩ የምንፈልጋት ኢትዮጵያ እንደዚች ዓይነት መሆን አለባት ብለው፤ የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ በሀሳብ መገንባት ቢችሉ ከዚያ በኋላ በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እየተነጋገሩ መግባባት ይችላሉ" ይላሉ አቶ ንጉሡ። የጉባዔው ተሳታፊዎች እነማን ናቸው? እነዚህ ዘጠኝ ጓደኛሞች ይህንን ወርክሾፕ ለማካሄድ አንድ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚሰራ ድርጅት አግኝተው በማናገር ምክር ጠይቀዋል። ከድርጅቱ ጋር የኢትዮጵያን ተጨባች ሁኔታ ካወሩ በኋላ መልካም ምክር ማግኘታቸውን አቶ ንጉሡ ያስታውሳሉ። ይህንን ዘዴ ከኢትዮጵያ ተጨባች ሁኔታ ጋር አንዴት እናላምደዋለን በሚል መወያየታቸውን አንስተው፤ በመቀጠል የወሰዱት እርምጃ የኢህአዴግ አራት አባል ድርጅቶችን፣ ዋና ዋና የፖቲካ አስተሳሰብን ይወክላሉ ያሏቸውን የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ ክልሎችን፣ አክቲቪስቶችንና፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን፣ ነጋዴዎችን፣ ሲቪል ማህበረሰቡ ተወካዮችን፣ ጋዜጠኞችንና ምሁራንን በማሰባሰብ መስራት መጀመር መሆኑን ይናገራሉ። ይህንን ሀሳብ ወደፊት ሊያራምድ የሚችል ተቋም እንደሚያስፈልግም ከተነጋገሩ በኋላ፤ ተቋም በገዢው ፓርቲና በተፎካካሪ ፓርቲዎች ሙሉ እምነት የሚጣልበት እንዲሆን በማለትም የካናዳውን "ፎረምስ ኦፍ ፌዴሬሽንስ" በመምረጥ ከስምምነት ላይ ደረሱ። • "ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደትን ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" አቶ ጌታቸው ረዳ • ኢህአዴግን ያጣበቀው ሙጫ እየለቀቀ ይሆን? በአጠቃላይ ሂደቱ ሦስት ወርክሾፖች ይካሄዱበታል የሚሉት አቶ ንጉሡ፤ እነዚህ ወርክሾፖች የመገናኛ ብዙኀን የማይገኙባቸው፣ ሶሻል ሚዲያ ላይ የማይጻፍበትና ታዛቢ የሌለባቸው መሆናቸውን ያስረዳሉ። ይህንን ደግሞ ተሳታፊዎችም ያከብራሉ በማለት፤ በዚሁ መሰረት በአርባምንጭና በቢሾፍቱ ወርክሾፖቹን ማካሄዳቸውን ያስረዳሉ። እነዚህ ወርክሾፖች በአይነታቸው ለየት ይላሉ የሚሉት አቶ ንጉሡ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወርክሾፖች፤ ወርክሾፖቹ አራት አራት ቀን ብቻ የሚካሄዱ ሲሆን ለሦስት ቀናት ተሳታፊዎች አብረው ያድራሉ ሲሉ ያስረዳሉ። በሦስተኛው ወርክሾፕ ደግሞ ሁለት ቀን አብረው ያድራሉ ሦስት ቀን አብረው ይቆያሉ ይላሉ። ፖለቲከኞች ከጉባኤው በኋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ረዥም ዓመት እንደቆዩ የተናገሩት አቶ ፀጋዬ ማሞ አንዳንዶቻችን ከሌላው የበለጠ ስለኢትዮጵያ የሚያገባን የሚመስለን አለን በማለት በዚህ ሂደት በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ 50ዎቹ ተሳታፊዎችም እኩል ስለኢትዮጵያ እንደሚያገባቸው መማራቸውን ተናግረዋል። አክለውም አንዳንዶቻችን አውሬ አድርገን ከሳልናቸው አካላት ጋር ቁጭ ብለን ስንወያይ በትክክልም ሰው መሆናቸውን ተረድተናል ብለዋል። ከእኛ በላይ የተጣላ የኢትዮጵያ ሕዝብ የለም በማለትም በመነጋገርም ሁሉንም ችግር መፍታት እንደሚቻል መማራቸውን መስክተዋል። ዶ/ር በድሉ ዋቅጂራ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ችግር በጠመንጃ ሳይሆን በመነጋገር፣ በይቅርታና በፍቅር ብቻ የሚፈታ መሆኑን መረዳታቸውን ተናግረዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው ፖለቲካ ውስጥ ሁሌም ችግሩ ምክንያታዊነት መጥፋቱ ነው፤ በማለት በተካሄዱት የተለያዩ ወርክሾፕ የተረዱት ሰዎች በምክንያታዊነት ቁጭ ብለው ከተወያዩ መፍታት የማይችሉት ነገር እንደሌለ መረዳታቸውን ተናግረዋል። እነዚህ 50 የወርክሾፑ ተሳታፊዎች በተደጋጋሚ እየተገናኙ ኢ መደበኛ የሆኑ ውይይት ለማድረግ መስማማታቸውንም ተገልጿል። የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ደግሞ በበኩላቸው የምንወዳት አገራችን ንጋት እንዲነጋላቸት የምችለውን አደርጋለሁ ብለዋል።
news-51425053
https://www.bbc.com/amharic/news-51425053
"የኤርትራ ሉዓላዊ መሬት ያልተመለሰው በህወሓት እምቢታ ነው" ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቱ ቴሌቪዥን ቀርበው ከሚሰጡት ቃለ ምልልስ አንዱ በሆነውና የመጀመሪያው ክፍል ትናንት አርብ ምሽት በሰጡት ማብራሪያ ላይ በተለይ ኤርትራ ከኢትዮጵያና ሌሎች ጎረቤት አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት አስመልክተው ሰፋ ያለ ምላሽ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዚህ ንግግራቸው ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለሁለቱ አገራት ግንኙነት መበላሸት ምክንያት ስለሆነው የድንበር ጥያቄ አንስተው በተለይ በባድመ ጉዳይ ስምምነቱ እንዳይፈጸም ህወሓት እንቅፋት መሆኑን ጠቅሰዋል። "በወረራ የተያዘው የኤርትራ ሉዓላዊ መሬት ያልተመለሰው ህወሓት እምቢ በማለቱ ነው" ብለዋል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ። ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ የተደረገው የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላም ስምምነት እልባት ይሰጣል የተባለውን የድንበር ጉዳይ በማስመልከት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ትናንት ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ህወሓት በድንበሩ ጉዳይ የወሰደውን አቋም ተችተዋል። "ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የተናገሩት የስምምነት ሃሳብ ሳይተገበር የባድመ የድንበር ሁኔታ እንደምናየው ድሮ ከነበረበት ደረጃም በላይ በከፋ ሁኔታ ነው ያለው። "ሕጋዊ ውሳኔ ተሰጥቷል፤ በዚሁ መሰረት ውሳኔው ተከብሮ የተወረረው ሉዓላዊ መሬት ወደ ኤርትራ መካለል ነበረበት። አሁን ግን አልተቻለም። "ለምን አልተመለሰም ያልን እንደሆነ፤ የከሰረው ስብስብ [ህወሓት] የድንበርን ጉዳይ በአንድ በኩል እንደ ማስፈራሪያና በሌላ በኩል ደግሞ እንደ መቋመሪያ ስለያዘው በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በባድመ ጉዳይ ምን ሰራን ካልን፤ ዝርዝር ጉዳይ ውስጥ ሳንገባ በአጭሩ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል" ብለዋል። "በአሁኑ ወቅትም ለጦርነቱ መነሻ በነበረችው ባድመ መሬት እየተሸነሸነ እየታደለ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ይህ ደግሞ የድንበሩን ጉዳይ እልባት ላለመስጠት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። "ለኤርትራ በተወሰነው መሬት ላይ መሬት ለማን እየታደለ እንደሆነ መረጃ አለን።" ከህወሓት በበኩሉ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት የተወሰነውን የድንበር ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ እንደሚቀበሉ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ውሳኔውን በተመለከተ ግልጽ ምላሽ አልሰጠም። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ ውሳኔውን እንደሚቀበሉ ካሳወቁ ከአንድ ዓመት በኋላ የድንበሩን ጉዳይ ለመፍታት የተሰራ የሚታይ ነገር የለም። ለኤርትራ የተወሰነው የባድመ መሬት አሁንም በኢትዮጵያ እጅ ነው የሚገኘው። "እጃችንን አጣምረን ቁጭ አንልም" ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አስመልክተው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ "በባድመ ድንበር ብቻ ሳንታጠር፤ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በሁሉም አቅማችን እንደግፋለን" ብለዋል። "ሰላም ሰርተህ የምታመጣው እንጂ እንደመና ከሰማይ የሚወርድ አይደለም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ ጋር የጀመሩትን የሰላም ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ስምምነት ከፍተኛ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን በመጠቆም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም ፖለቲካዊ ለውጥም ኤርትራን እንደጎረቤት ሳይሆን ራሷን በቀጥታ ስለሚጎዳት "እጃችንን አጣምረን ቁጭ አንልም" ብለዋል። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ለሦስት ትውልድ የተደረገው ጦርነት "ትርጉም አልባ ነበር" በማለት ጦርነቱም የውጭ ኃይሎች ጉዳዩን ስላወሳሰቡት የመጣ ጣጣ እንደነበርም ገልጸዋል።
42743092
https://www.bbc.com/amharic/42743092
''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው"
ከአምሳ ሁለት ዓመታት በፊት ኒውዮርክ ባለች በትንሽ ስቱዲዮ ውስጥ የተፈጠረው ኢትዮ-ጃዝ ከአይፎን 8 ማስተዋወቂያነት በጀርመን ውስጥ እስካለ መንደር ስያሜ ሊሆን ችሏል።
የሰሩት ሙዚቃ ለአይፎን 8 ማስተዋወቂያ ከመሆን ጋር ተያይዞም የተወሳሰቡ ጉዳዮች እንዳሉና ከእሳቸው ፈቃድ ውጭ ሙዚቃው እንደተሰጡ የሚናገሩት ሙላቱ ከወኪሎቻቸው ጋር በድርድር ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ ቢሆንም ለአይፎን 8 ማስተዋወቂያነት መብቃቱ ኢትዮ-ጃዝ የፈጠረውን ተፅዕኖ ማሳያ ነው የሚሉት አቶ ሙላቱ "ለሙላቱ ወይም ለኢትዮ-ጃዝ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ትልቅ ነገር ነው" በማለት ይናገራሉ። በመላው ዓለም ተደማጭነትን ማግኘት የቻለው ኢትዮ-ጃዝ እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ ያደረገው ትግሉ ግን ቀላል አልነበረም ይላሉ አቶ ሙላቱ። የሙላቱ ስኬቶች በተለያዩ ትላልቅ መድረኮችም ላይ የመታየት እድልን አግኝቷል። ከነዚህም መካከል የኢትዮ-ጃዝ ውጤት የሆነው የሙዚቃ ሥራ ለኦስካር ሽልማት ታጭቶ ለነበረው "ብሮክን ፍላወርስ" ለተሰኘው ፊልም ማጀቢያነት ውሎ ነበር። በተጨማሪም በሂፕ ሆፕ ሙዚቃ ታላቅ ስፍራ ያላቸው አሜሪካዊው ናስና የሬጌ ሙዚቃ ተጫዋቹ ዴሚየን ማርሌይ "የግሌ ትዝታን" ''ዲስታንት ሪላቲቭስ'' በሚለው አልበማቸው ውስጥ አካትተውታል። ሙላቱ አስታጥቄ በሙዚቃ ትምህርት ታላቅ በሚባለው በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬትም ያገኙ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ ናቸው። "በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ ለጃዝ ሙዚቃ ታላቅ ዩኒቨርሲቲ ነው። በዚህ ዩኒቨርሲቲም ተቀባይነትንና ዕውቅናን ማግኘት ክብር ነው። በጃዝ ውስጥ ከፍተኛ ስም ካላቸው እንደነ ዱክ ኤሊንግተን፣ ኩዊንሲ ጆንስ፣ አሪታ ፍራንክሊን ያገኙትን አንድ አፍሪካዊ ማግኘት ትልቅ እውቅና ነው" ይላል ሙላቱ። በቅርቡም ጃፓን ውስጥ በተደረገው የፉጂስ ኮንሰርት ላይ ከ120 ሺህ ሰዎች በላይ በተገኙበት ሥራቸውን ያቀረቡ ሲሆን ስኮትላንድ በሚገኘው ታላቁ ፌስቲቫል ግላስተንቤሪ ከ140 ሺህ ሰዎች በላይ በታደሙበት መድረክ ላይ ተሳትፈዋል። ከዚህ በተጨማሪ በጀርመን ሀገር በፖፕ ሲቲ በኢትዮ-ጃዝና በሙላቱ አስታጥቄ ስም መንደር ተሰይሟል። ከእሳቸው ሌላም ለሙዚቃ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ለሚባሉት ለእነ ኤልቪስ ፕሪስሊ፣ ማይክል ጃክሰን እንዲሁም ማሪያ ማኬባም ዕድሉ ደርሷቸዋል። እነዚህ ሁሉ የኢትዮ-ጃዝ ትሩፋት ናቸው የሚሉት ሙላቱ፤ ከዚህም በተጨማሪ የዘመናዊው ጃዝ ፈጣሪ በሆነው ቻርሊ ፓርከር ስም በየዓመቱ ኒውዮርክ ውስጥ በሚካሄድ ፌስቲቫል ላይ መጫወታቸው ለኢትዮ-ጃዝ ያገኘውን ትልቅ ክብር ማሳያ እንደሆነ ይናገራሉ። "ይሄ ሁሉ ለኢትዮ-ጃዝ ትልቅ ዕውቅና ነው፤ ሁልጊዜም እምፈልገውና የማልመው ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው። የትም ቦታ ብሄድ ያለው የህዝቡ ፍላጎትና ፍቅርም ትልቅ ነው'' ይላሉ። ጥናቶችና አዳዲስ ሥራዎች ሁልጊዜም ቢሆን አዳዲስ ሥራዎችን ከመፍጠር አላቆምም የሚሉት ሙላቱ፤ በአሁኑ ወቅትም በኢትዮጵያዊው የዜማ ቀማሪ በቅዱስ ያሬድ ሥራዎች ላይ የኦፔራ እያዘጋጁ ነው። ይህ ሥራ ኢትዮጵያ በባህል ዘርፍ ለዓለም ያበረከተችውን አስተዋፅኦ የሚዘክር ነው። በዚህም ጥናት ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በምትጠቀመው መቋሚያ ላይም ምርምሮችን አድርገዋል። ይህንን ምርምራቸውን እያካሄዱ ያሉት በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የማሳቹሴትስ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ ስር ነው። "ሙዚቃን መምራት ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው አስተዋፅኦ ነው" (ኮንደክቲንግ ኢዝ ኢትዮፕያን ኮንትሪዩብሽን ቱ ዘ ወርልድ) በሚል ርዕስ የጥናት ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ኢትዮጵያ ከሌሎች ቀድማ መቋሚያን በመጠቀም ሙዚቃን መምራት እንዳስተማረች ይዘረዝራል። መቋሚያን ብቻ ሳይሆን ፀናፅሉን፣ ከበሮውን በአጠቃላይ ንዋየ-ማህሌት ተብሎ የሚጠራውን ሥርዓት እንዳጠኑም ይናገራሉ። "ይህ ክላሲካል ሙዚቃ ተብሎ ለሚጠራው የሙዚቃ ሳይንስ መሰረት ነው፤ ይህም ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችውን ያሳያል እላለሁ" ይላሉ። ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎችን የፈጠሩትንና "የሙዚቃ ሳይንቲስቶች" ብለው በሚጠሯቸው እንደነ ደራሼ ባሉት ህዝቦች ሙዚቃም ላይ ምርምር እያደረጉም ነው። "በታሪክ ስናጠናው እነዚህ ሕዝቦች ለበርካታ የአውሮፓውያን የሙዚቃ መሳሪያዎች መሰረቶች ናቸው። ትራምፔትንና ትሮምቦንን የሚመስሉ የሙዚቃ መሳሪያዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ አንዱ የቤኒንሻንጉል የሙዚቃ መሳሪያ የሆነው ዙምባራ ነው" ይላሉ። ሸራተን አዲስ ተደርጎ በነበረው የሙላቱ የሙዚቃ ኮንሰርትም ላይ ሙዚቀኞቹንና እነዚህን የሙዚቃ መሳሪያዎች አካተዋል። በብዙ አጋጣሚዎች ስለደራሼ ህዝብ ሙዚቃ ጥልቀትም ሆነ ጥበብ አውርተው የማይጠግቡት ሙላቱ የደራሼ ሙዚቃ ከኢትዮጵያ ቅኝት ውጭ የሆነ ሙዚቃ ነው በማለት ይናገራሉ። ከአውሮፓውያኑ በላይ እንደ ደራሼ ላሉ አገር በቀል ሙዚቃዎች ክብርም ሆነ ዕውቅና መስጠት ይገባል ብለው የሚያምኑት ሙላቱ፤ "ምንም እንኳን ለቀረው ዓለም የጃዝ ሙዚቃ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ቢሆንም በኢትዮጵያ ውስጥ ሥራዎቻቸው ላይ ጥናትና ምርምር የለም። ይህ ሁኔታ ደግሞ ሊቀየር ይገባል'' ይላሉ። ኢትዮ-ጃዝ እንዴት ተፈጠረ? ሙዚቃን በበርክሌይ ያጠኑት ሙላቱ "ወደራስ መመልከት ወይም ማየት" ለሚለው መነሻቸውም የሆነው በዚሁ ትምህርት ቤት የሙዚቃ መምህር በነበረ ሰው አማካኝነት እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ መምህር "ራሳችሁን ሁኑ" የሚል ምክርም በተደጋጋሚ ለግሷቸው እንደነበር ያስታውሳሉ። ከትምህርት ቤት ወጥተውም ኒውዮርክ በሚኖሩበት ወቅት ስለኢትዮጵያ መመራመራቸውን ቀጠሉ። "እነዚህ ቅኝቶች ላይ ተመስርቼ ቀለምና መልካቸውን ሳይቀይር ከአውሮፓውያኑ አስራ ሁለት ድምፆች ጋር እንዴት አዋህጄ አዲስ ድምፅ መፍጠር እንደምችል እየተመራመርኩ ነበር" ይላሉ ሙላቱ። ከብዙ ጥናትና ምርምር በኋላም የሁለቱ ጥምረት ኢትዮ-ጃዝን መፍጠር ቻለ። ይህንንም ጥምረት ሙላቱ ''የቅኝቶች ፍንዳታ" (ኢምፕሮቫይዜሽንን) ይሉታል። ወደ ኢትዮጵያም ሲመለሱ ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ አልነበረም። ከሚያስታውሱትም አንዱ የፀጋየ ገብረ-መድህን ቲያትር ድርሰት ለሆነው 'ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት' ሙዚቃ በገናን፣ ፒያኖን፣ጊታርና ሌሎች ሙዚቃ መሳሪያዎችን በመጠቀም ቅንብሩን ሰሩ። በዚያን ወቅት የጥላሁን ገሰሰ "ኩሉን ማን ኳለሽ" በጣም ታዋቂ ዘፈን የነበረ ሲሆን ይህንን ሙዚቃ እንዲጠቀሙ ብዙዎች ቢፈልጉም የራሴን ቅንብር ነው የምጫወተው በማለት ሙላቱ በሀሳባቸው እንደፀኑ ይናገራሉ። በአምባሳደር ቲያትር ቤት ዝግጅታቸውን አቀረቡ። "መቼም ቢሆን አልረሳውም፤ ሙዚቃውም ከበገና ወደሌሎች ሙዚቃ መሳሪያዎች ሲሄድ ብዙዎች ውረድ አሉኝ። ውረድ የሚለው ድምፅ ቢበረታም ሳልጨርስ አልወረድኩም" የሚሉት ሙላቱ "ሁልጊዜም ቢሆን የምናገረው ያን ጊዜ ተስፋ ቆርጨ ሙዚቃ ማቆም እችል ነበር፤ መታገልን የመሰለ ነገር የለም። እንዲያውም እሱ የበለጠ ብርታትና እልህ ሰጥቶኛል። 'ተስፋ አትቁረጡ ሁልጊዜም ታገሉ፤ አዲስ ነገር ፍጠሩ' በማለት እመክራለሁ'' ይላሉ። ከዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮ-ጃዝ ታዋቂነትን እያገኘና ተከታዮችን እያፈራ ቢመጣም አሁንም ቢሆን በከፍተኛ ደረጃ ተቀባይነት ያለው በአውሮፓና በሌሎች ሀገራት እንደሆነ ሙላቱ ይናገራሉ። ስለአዝማሪዎች ኢትዮ-ጃዝ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነ የሚናገሩት ሙላቱ በዓመታት ውስጥ ብዙ የምርምር ሥራዎች እንደተጨመረበት ይናገራሉ። "አሁን ደግሞ ዋናው የኢትዮ-ጃዝ አላማ የሙዚቃ ሳይንቲስቶቻችንና ፈጣሪዎቻችን ላይ ተመስርተን፤ ያሉን መሳሪያዎች መልካቸውና ዲዛይናቸው ሳይቀይር እንዴት አድርጎ የሌላውን ዓለም ሙዚቃ መጫወት ይችላል የሚል ነው" ይላሉ። ''አዝማሪዎቻችን የሙዚቃ ሳይንቲስቶች ናቸው" የሚሉት ሙላቱ፤ ያሉትን የኢትዮጵያ ሙዚቃ መሳሪያዎችንና ሙዚቃን ፈጥረው እዚህ ካደረሱ ቀጣዩ ትውልድ ደግሞ ሊያሻሽለው እንደሚገባ ይናገራሉ። ሥራዎቻቸው መካከልም አዝማሪን ወደ 21ኛው ክፍለ-ዘመን ማምጣት በሚል በክራር ላይ የሰሩት ይገኝበታል። "እነዚህ ሥራዎች ቀላል አይደሉም። ማድመጥና መውደድን የሚፈልጉ ሰዎችን ይጠይቃል። በግለሰብ ደረጃ ብቻ የሚሰራ አይደለም'' ይላሉ ሙላቱ። ከምርምርና ከሙዚቃ ሥራው በተጨማሪ አፍሪካን ጃዝ ቪሌጅ (የአፍሪካ ጃዝ መንደር) የሚባል የሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ የሬድዮ ፕሮግራም የነበራቸው ሲሆኑ ለሀርቫርድ ጥናት በሄዱበት ወቅት ተቋረጦ የነበረ ቢሆንም የሬድዮ ፕሮግራሙ አሁን ወደ አየር ተመልሷል።
news-57230086
https://www.bbc.com/amharic/news-57230086
የሴቶች ጥቃት፡ በጀርመን ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ ከሁለት ዓመት ልጇ ጋር ተገደለች
በጀርመን ባየርን ክሮናህ ከተማ በሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት ከእነ ሁለት ዓመት ልጇ መገደሏ ተሰማ።
የሟች ሐይማኖት ገ/እግዚአብሔር የቅርብ ጓደኞች ለቢቢሲ እንደገለጹት እናትና ልጅ የተገደሉት ባለፍነው እሁድ ግንቦት 15 ቀን 2013 ዓ.ም አመሻሽ 11፡00 ሰዓት አካባቢ ነው። እናትና ልጅን በስለት በመውጋትና በላያቸው ላይ እሳት በመለኮስ የተጠረጠረው በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኘው ሞሮኳዊ የሟች የቀድሞ የፍቅር አጋር እንደነበር ጓደኞቿ ትህትና ጸጋውና ወንድወሰን ፋንታሁን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ግለሰቡ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ በራሱም ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። በ30ዎቹ መጀመሪያ እድሜ ላይ የነበረችው ሟች ሐይማኖት ላለፉት ሰባት ዓመታት ገደማ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ ኖራለች። በጀርመን የሚታተመው 'ፍራንክንፖስት' ዕለታዊ ጋዜጣ ከትናንት በስቲያ ባወጣው ዕትም የኮበርግ የወንጀል ምርመራ ፖሊስና ዐቃቤ ሕግ በእናትና ልጅ ግድያ የ34 ዓመቱ ሞሮኳዊ ግለሰብ ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ዘግቧል። ግለሰቡ በአስጊ የጤና ሁኔታ ላይ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱን ጋዜጣው ጽፏል። 'ፍራንክንፖስት' ጋዜጣ የ31 ዓመቷ ሴትና የሁለት ዓመት ልጇ እሁድ ምሽት 11:45 በመኖሪያ ክፍላቸው ውስጥ መሞታቸውን አስነብቧል። ጋዜጣው የኮበርግ ወንጀል ምርመራ ቡድንና ዐቃቤ ሕግን ጠቅሶ እንደዘገበው ግለሰቡ እናትና ልጅ ወደሚኖሩበት ቤት ህንጻ በማምራት በቢላ ወግቶ ሳይገላቸው እንዳልቀረ ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ። በወቅቱ በህንጻው ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሦስት ሴቶች ተሯሩጠው በመውጣት ለፖሊስ እንደደወሉ ጋዜጣው ጠቅሷል። በእናት ልጅ መኖሪያ ቤት ውስጥ እሳት የተነሳውም በዚህ ጊዜ ነበር። ግለሰቡ ሆነ ብሎ እናትና ልጅ ላይ እሳት እንደለኮሰ ፖሊስ ጥርጣሬ እንዳለው 'ፍራንክንፖስት' ዘግቧል። የእናትና ልጅ አስክሬንም የተገኘው በእሳት አደጋ ሠራተኞች ነበር። እንደ ጋዜጣው ከሆነ ግለሰቡም በእሳቱና ከበረንዳ ላይ ዘሎ ለማምለጥ በመሞከሩ ለሕይወቱ አስጊ የሆነ ጉዳት ደርሶበታል። የእናትና ልጅ የአስክሬን ምርመራ ውጤት የሁለት ዓመቷ ህጻን በቢላ በመወጋቷ ሕይወቷ ሲያልፍ፤ እናቷ ግን በስለቱ ጉዳት ቢደርስባትም እሳቱ ከተነሳ በኋላ ሕይወቷ ማለፉን ያሳያል ተብሏል። የመኖሪያ ሕንጻው በእሳቱ የደረሰበት ጉዳትም በ50 ሺህ ዩሮ [ከ2 ሚሊየን 600 ሺህ ብር በላይ] እንደሚገመት ጋዜጣው አክሏል። የቅርብ ጓደኞቿ ምን ይላሉ? ትህትና ጸጋው የሐይማኖት የቅርብ ጓደኛ ናት። የምትኖረውም በጀርመን ባየርን ክሮናህ ከተማ ነው። መኖሪያዋም ከስደተኞች ካምፑ 5 ደቂቃ ያህል ቢያስኬድ ነው። ሐይማኖትና ልጇ ተገደሉ ከተባለበት ሰዓት 5 ሰዓታት ቀደም ብሎ ማለትም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ገደማ ተደዋውለዋል። በወቅቱም ልጇን ይዛ ስትወጣ "እገልሻለሁ!" ሲል እንደዛተባት አጫውታት ነበር። ነገር ግን እስከምታውቀው ድረስ ግለሰቡ የአዕምሮ ጤና ችግር ስለሌለበት ይህንን ይፈጽማል ብላ አላሰበችም ነበር። "እንዲህ የከፋ ነገር ያመጣል ብዬ ስላላሰብኩ በፖሊስ የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ 'አትፍሪ! አይዞሽ!' ብዬ አጽናናኋት" ትላለች። ከሰዓታት በኋላ የሄሊኮፕተርና የእሳት አደጋ መኪና ድምጽ ሰማች። ብቅ ብላ ተመለከተች። ሁኔታው ግራ ቢያጋባትም በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ለማንሳት ነበር የመሰላት። ወደ ቤት ተመልሳ ሰትገባ የጽሁፍ መልዕክቶች ደረሷት፤ "የስደተኞች ካምፕ እሳት ተነስቷል" የሚል። ወደምታውቃቸው ስልክ መታች። "ጉድ ሰራን!" የሚል መልስ መልስ ነበር ያገኘችው። በቀጥታ ወደ ሥፍራው አመራች። በቦታው ስትደርስ ፖሊሶች የእናትና ልጅን አስክሬን እያወጡ ነበር። "ግለሰቡ እናትና ልጅን ቤታቸውን ሰብሮ ገብቶ በጩቤ ደረታቸው ላይ ወግቶ ነው የገደላቸው። ከዚያም እሳት ለኮሰ። ግን ሟቾቹ የመለብለብ አደጋ ነው የደረሰባቸው። እርሱም ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን አቃጥሏል" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ትህትና እንደምትለው ግለሰቡ የሐይማኖት የፍቅር አጋር ነበር- ለወራቶች የዘለቀ ግንኙነት ነበራቸው። በካምፑ ውስጥ ሁለቱም ለየብቻ ነበር የሚኖሩት። እርሷ በሴቶች ክፍል፤ እርሱም በወንዶቹ። ነገር ግን ጎረቤት ነበሩ። ግንኙነታቸው ግን አልዘለቀም። በባህልም፣ በባህርይም ልዩነት ባለመግባባታቸው ተለያዩ። እርሱ ግን ከእርሷ ጋር መለያየት አልፈለገም። ሁኔታው ያሰጋት ሐይማኖትም ለሕይወቷ እንደምትፈራ በተለያዩ ጊዜያት ለፖሊስ እያለቀሰች አመልክታለች። "አልቅሼ ሳስረዳቸው የአዕምሮ ሕክምና ያስፈልግሻል ወደዚያ ሂጂ አሉኝ" በማለት በአንድ ወቅት እንደነገረቻት ጓደኛዋ ትህትና ታስታውሳለች። እንደ ትህትና ከሆነ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ፖሊስ ጣቢያው አማርኛ ተናጋሪ አስተርጓሚ ቀጥሮ በዚሁ ጉዳይ ላይ ሁለት ሰዓታት የፈጀ መጠይቅ አድርገውላትም ነበር። ነገረ ግን መንግሥት ቦታ ካልቀየረ በስተቀር በበግል ፍላጎት ሌላ ቦታ መሄድ ባለመቻሉ ሐይማኖት እዚያው ለመቆየት ተገድዳለች። ትህትና እንደምትለው በግድያው የተጠረጠረው ሞሮኳዊ በቅርቡ ያቀረበው የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ በሥራ ላይ ነበር። በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የተለያየ የአዕምሮ ጤና ችግር አሊያም የባህል ልዩነቶች ያሉባቸው ሰዎች በአንድ ላይ ስለሚኖሩ መሰል አደጋዎች እንደሚከሰቱ ትህትና ትናግራለች። ከዚህ ቀደም አንድ አፍጋኒስታዊ መገደሉንም ታስታውሳለች። "ከ20 ደቂቃ በፊት ደውላልኝ ነበር" ሌላኛው የሐይማኖት የቅርብ ጓደኛ ወንድወሰን ፋንታሁን ነዋሪነቱ በጀርመን ሙኒክ ከተማ ነው። ትውውቃቸው ሟች ጀርመን ከገባችበት ጊዜ ይጀምራል። ላለፉት አምስት ወይም ስድስት ዓመታት የዘለቀ። ወንድወሰን ለዓመታት በዚያው መጠለያ ካምፕ ውስጥ ነበር የሚኖረው። መጠለያ ካምፑ የገባው ከእርሷ ቀደም ብሎ ነበር። ጥሩ ጓደኛሞች ነበሩ። ተገደለችበት ከተባለው ሰዓት 20 ደቂቃ ቀደም ብሎም ደውላለት ነበር፤ ነገር ግን መንገድ ላይ በመሆኑ ስላልተመቸው ስልኩን አላነሳውም። ለመጨረሻ ጊዜ ግን ቅዳሜ ዕለት ነበር ያወሩት። ያለችበትን የስደተኛ ካምፕ ለመቀየር ደብዳቤ ማስገባት እንዳለባት ነበር የተመካከሩት። ሐይማኖት ስጋት እንዳላት ለእርሱና ለሌሎች ጓደኞቿ ትነግራቸው እንደነበር የሚናገረው ወንድወሰን፤ ቦታ ለመቀየር ለፖሊስ ማመልከቻ አስገብታ በሂደት ላይ ሳለች ነው የተገደለችው ይላል። ወንድወሰን በካምፑ የእሳት አደጋ መነሳቱን ዜና እንዳነበበና ለማጣራት ጓደኞቹ ጋር ሲደውል "ገደላቸው!" የሚል መልስ እንዳገኘ ይናገራል። "እነርሱ እንደሆኑ አልተጠራጠርኩም ነበር። ምንም የማታውቅ የሁለት ዓመት ልጅ ግን ይህ ይደርስባታል ብዬ አልገመትኩም" ይላል ወንድወሰን። "ሐይማኖት ለሰዎች የተሰጠች መልካም ሰው ነበረች፤ ጥሩ ጓደኛዬ ነበረች" ይላል። ወንድወሰን ከሞሮኳዊው ግለሰብም ጋር በእርሷ አማካኝነት ትውውቅ ነበረው። "ልጁ መልካም ሰው ነበር፤ ልጇን ይንከባከባል። ግን የባህል ልዩነቶች ነበሩ። 'ሴት ሌላ ሰው ማየት የለባትም ይል ነበር' እና በመሃል 'ተቀየረብኝ' አለችኝ" ሲል የነበራቸውን ግንኙነት ያስታውሳል። በዚህ ምክንያት ሁለቱም አብረው መኖር እንደማይችሉ ተነጋግረው ተለያይተው ነበር። ይሁን እንጂ ግለሰቡ ከአንድም ሁለት ሦስቴ ድብደባ ፈጽሞባት እንደነበር ወንድወሰን ይናገራል። "በመጀመሪያ ለፖሊስ ስታመለክት ፖሊሶች ልጁ አጠገቧ እንዳይደርስ ማድረግ ወይም ሌላ መፍትሔ መፈለግ ይችሉ ነበር፤ በማይገባ የፖሊሶች ቸልተኝነት እርሷንና ልጇን አሳጥቶናል" ሲል ይወቅሳል። አሁን ጓደኞቿ የሐይማኖትንና የልጇ ሃናንን አስክሬን ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ገንዘብ እያሰባሰቡ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ክሮናህ ትንሽ ከተማ ናት። ካምፑ ለፖሊስ ጣቢያው ቅርብ ነው። በእግርም ቶሎ የሚደረስበት ነው። ነገር ግን ፖሊሶች ከ20 ደቂቃ በኋላ እንደደረሱ ነው የሰማነው" የሚለው ወንድወሰን፤ ፖሊሶቹ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው በሕግ እንዲጠየቁ ማድረግ ቀጣይ ሥራቸው እንደሆነ ገልጿል። ስለጉዳዩ በጀርመን የኢትዮጵያን ኤምባሲን ለመጠየቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
news-57164708
https://www.bbc.com/amharic/news-57164708
የቤኒሻንጉል ክልልና የታጣቂው የጉሙዝ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ስምምነት ይዘት
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥትና ታጣቂው ቡድን በትናንትናው ዕለት የፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ በክልሉ በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ የሚከሰቱ ጥቃቶችን ለመቀነስ ያለመ መሆኑን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር ለቢቢሲ ተናገሩ።
የክልሉ አስተዳደርና ታጣቂ ቡድኑ የመግባቢያ ስምምነት የፈረሙት በተደጋጋሚ ጥቃት በሚከሰትበት የመተከል ዞን ያለውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት መፍትሔ ለማምጣት መሆኑንም የመተከል ዞን ኮሚዩኒኬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ካወጣው መረጃ መረዳት ተችሏል። ክልሉን ወክለው ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሃሰን እና የታጣቂ ቡድኑ ተወካይ አቶ አጀግናማው ማንግዋ የስምምነት ሰነዱን መፈረማቸው ቢገለፅም የታጣቂው ቡድን ስም በዞኑ መግለጫው ላይ አልሰፈረም። ለመሆኑ ስምምነቱ የተደረሰው ከየትኛው ታጣቂ ቡድን ጋር ነው? ብሎ ቢቢሲ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድርን ጠይቋል። የታጣቂው ቡድን ማንነት ታጣቂው ቡድን በአካካቢው ንጹሃን ዜጎችን ግድያ ይፈጽሙ የነበሩና ከማኅበረሰቡ ወጥተው ወደ ጫካ ገብተው የሚዋጉና በአብዛኛው የጉሙዝ ብሔረሰብ ተወላጆች ናቸው ይላሉ። ኃላፊው እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት ታጣቂዎቹ መንግሥት ያደረገውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉና የተሃድሶ ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከእነዚህ እጃቸውን የሰጡ ታጣቂዎችም መረዳት የተቻለው የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባላት መሆናቸውን እንደሆነ ኃላፊው ይናገራሉ። "ድርጅቱን ወክለን እየታገልን ያለነው የሚሉ ነገሮችን ያነሳሉ። በተጨባጭም የድርጅቱ መታወቂያዎችን ይዘናል። በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ታጣቂዎቹ ከተደመሰሱ በኋላ ኪሳቸው ውስጥ መታወቂያዎችን አግኝተናል" ይላሉ። ታጣቂዎቹ በዋነኝነት የህዳሴ ግድብ በሚገነባበት አካባቢ የነበሩ ሲሆን በትጥቅ ትግልም ከዓመት በላይ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ መሆናቸውንም አቶ ኢስሃቅ ያስረዳሉ። ፓርቲው ከዚህ ቀደም ዕውቅና አግኝቶ ሲንቀሳቀስ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በዚህ ዓመት ታኅሣሥ ወር ላይ ከሰረዛቸው 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው። በወቅቱም ምርጫ ቦርድ እንዳሳወቀው በተለያዩ ምክንያቶች ማብራሪያ እንዲሰጡ ወይም መስፈርት አሟልተው እንዲያቀርቡ የተወሰነ እና የማጣራት ሂደታቸው ያልተጠናቀቀ በሚል መሰረዙን ማስታወቁ የሚታወስ ነው። ኃላፊው በበኩላቸው "ምርጫ ቦርድ አንድ ድርጅት በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ብሎ ፍቃድ ከወሰደ በኋላ ሕጋዊ በሆነ መንገድ መታገል ሲገባው የታጠቀ ኃይል በመሆኑ ሊሰረዝ ችሏል" ይላሉ። ድርጅቱ ዕውቅና እንደሌለው አስታውሰው በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ይህንን ኃይል እንወክላለን የሚሉ ታጣቂዎች ናቸው ይላሉ። ክልሉ የሚያውቀው በጉሙዝ ሕዝብ ዴሞከራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ስም የሚንቀሳቀሱ የታጣቂ አባላትን ብቻ እንደሆነ የሚናገሩት ኃላፊው፤ ከውጭ ኃይሎችና ከውስጥ ባሉ ኃይሎች ከፍተኛ ድጋፍ የሚደረግላቸው እንደሆነ ጠቅሰው በሱዳን በኩልም ይገባሉ ይላሉ። "በዋነኝነት የህዳሴ ግድብ አካባቢን የግጭት ማዕከል ለማድረግ በተደራጀ እየተሰራ እንደሆነም" ኃላፊው ያስረዳሉ። አካባቢው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ለዓመታት የሚወዛገቡበት የህዳሴ ግድብ ያለበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ "በርካታ ኃይሎች እጃቸውን የሚያስገቡበትና እነዚህን ታጣቂዎች ከኋላ ሆነው በሎጅስቲክም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች የሚደግፉበት ሁኔታ አለ" ይላሉ። "ወጣቶቹ በተለያየ ምክንያት ተታልለው ነው ጫካ ገብተው ሲታገሉ ነበር። ትግላቸው ይሄንን ያህል የጎላ አልነበረም። በክልሉ መንግሥት መመለስ የሚችሉ ጥያቄዎችን ይዘው ነበር" የሚሉት አቶ ኢስሃቅ "ነገር ግን ያንን ባለመረዳት ጫካ ገብተው ንፁሃን ዜጎች ላይ በተለያየ መንገድ ጥቃት ሲፈፅሙ የነበሩ መሆናቸውን" ያስረዳሉ። የመተከል ዞን ነዋሪ የነበረው አለሙ በየነ፣ ቤተሰቡን ለመታደግ በአውቶብስ ወደ ቻግኒ ከተማ በታኅሣሥ 3 2013 ዓ.ም ይልካቸዋል። ታጣቂዎች ግን ባለቤቱን እና ሦስት ልጆቹን ጨምሮ 44 ተሳፋሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ የክልሉ መንግሥትና የታጣቂው የጉሙዝ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ስምምነት ይዘት በአሁኑ ወቅት የተደረሰው የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመውም እጃቸውን በሰላም ከሰጡ ታጣቂዎች ጋር ሲሆን ስምምነቱ በዋነኝነትም በክልሉ ይስተዋላሉ የሚሏቸውና ታጣቂዎቹ የሚያነሷቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፈታት አለባቸው የሚል አለበት ይላሉ። ኃላፊው የመልካም አስተዳደር የሚሏቸውና ታጣቂዎቹ ከሚያነሷቸውም መካከል ትምህርታቸውን ጨርሰው የቅጥር ምደባ ያላገኙ፣ በተለያየ መንገድ አድሏዊ አሰራር ተፈፅሞብናል ብለው ያመለከቱም አለበት ከነዚህም መካከል አንዳንዶቹ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያልገቡና ያኮረፉ እንዳሉም ይጠቅሳሉ። በስምምነቱም መሰረት በተለያየ መንገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑና በምጣኔ ሀብቱ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ መዋቅሮች እንዲሳተፉ የማድረግ ሥራም ይሰራል ተብሏል። "ከዚህ በኋላ ትጥቃችሁን አስቀምጣችሁ በሰላማዊ መንገድ ከሕዝቡ ጋር መኖር አለባችሁ" በሚልም በመግባቢያ ሰነዱ ስምምነት ላይ የተደረሰው ይላሉ። በዚህ ሰነድ ከተካተቱት ዋነኛ ጉዳዮች መካከል እነዚህ ኃይሎች የኃላፊነት ቦታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ የከተማ የቤት መስሪያ ቦታ፣ የገጠር የእርሻ መሬት እንዲኖራቸው ማድረግ ይገኙባቸዋል። በኃላፊነት ቦታ የሚመደቡት አቅምና የትምህርት ደረጃቸውን ባማከለ መልኩ እንደሆነ የጠቆመው መግለጫው በክልል ደረጃ ሁለት፣ በዞን ደረጃ ሦስት እና በወረዳ ደረጃ ደግሞ አራት ሰዎች ይቀመጣሉ ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ልምድ ያላቸው የቡድኑ አባላት በክልሉ ውስጥ ባሉ የፀጥታ መዋቅሮች መመደብ፣ ሴቶችን አካታች ያደረገና በተለያዩ ማኅበራት እንዲደራጁ ማስቻል፣ በተማሩበት የሙያ መስክ እንዲመደቡ ማድረግና የብድር አገልግሎት እንዲመቻች ማድረግ የሚሉ ሃሳቦች በሰነዱ ውስጥ መካተታቸውን ቢቢሲ ከዞኑ መግለጫ መረዳት ችሏል። መግለጫው አክሎም የክልሉ መንግሥት ስምምነት ላይ የደረሰው መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበልና ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መፍትሄ ለመስጠት ሰልጠና የሚወስዱ ናቸው ተብሏል። በትናንትናው ዕለት የስምምነት ሰነዱ ሲፈረም ርዕሰ መስተዳድሩ በሰላም የገቡትን የታጣቂ ቡድን አባላት "የሰላም አምባሳደር" ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን ሌሎች ወደ ሰላም ያልመጡ የታጣቂ ቡድን አባላት ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥረት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል። ይህም ከታጣቂው ቡድን ጋር የተፈፀመው የመግባቢያ ሰነድ ሌሎች አባላትንም ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ሊያበረታታ እንደሚችልም አቶ ኢስሃቅ በበኩላቸው ይናገራሉ። በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች ከዚህ ቀደም በታጣቂዎች በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ሰዎች ከሞትና ለመፈናቀል ሲዳረጉ መቆየታቸው ይታወሳል። ከእነዚህም መካከል ለረጅም ጊዜ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሲፈጸሙበት የቆየው የመተከል ዞን በዋናነት የሚጠቀስ ሲሆን፤ ይህንንም ለመቆጣጠር በሚል የክልሉና የፌደራል መንግሥት የጸጥታ አካላት በጥምረት የሚመሩት የዕዝ ማዕከል (ኮማንድ ፖስት) በዞኑ ውስጥ ከተቋቋመ ወራት ተቆጥረዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በክልሉ የተለያዩ ዘመቻዎች እየተካሄዱ ሲሆን ታጣቂዎችን ወደ ሰላማዊ መንገድ ማምጣቱ የዚህ ዘመቻ አካል እንደሆነም ኃላፊው ይናገራሉ። ከሚካሄዱ ዘመቻዎች መካከል መከላከያ የሚወስደው እርምጃ አንዱ እንደሆነ ጠቅሰው "የታጣቂ አባላቱን መደምሰስ" የሚገኝበት ሲሆን "ጎን ለጎንም ወደ ሰላም መምጣት የሚፈልጉ ታጣቂዎችም እድል እንዲያገኙ ለማድረግ ነው" ይላሉ። በአሁኑ ወቅት 500 የሚሆኑ አባላት የስልጠና ተሃድሶ እየወሰዱ መሆኑን ገልፀው በጫካ ያሉት የታጣቂ አባላት ቁጥር ሙሉ መረጃ እንደሌላቸው ይናገራሉ። የክልሉ መንግሥት ለተገደሉት ንፁሃን ዜጎችና ጥቃቶች ኃላፊነቱ የታጣቂዎቹ ነው ከማለቱ ጋር ተያይዞ እጅ የሰጡት ታጣቂዎት በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ? የሚል ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኃላፊው በቀጣይነት በሕግ አካላት የሚታይ ይሆናል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግሥት በዋነኝነት እየሩ ያሉት አካባቢውን የማረጋጋትና "በሞት ላይ ዳግሞ ሞት እንዳይመጣ ነው" ይላሉ። "እነዚህ ታጣቂዎች ጫካ ውስጥ የሚቀመጡ ከሆነ አሁንም ሞት ይቀጥላል። ሰው ማፈናቀሉ ይቀጥላል። ይሄ መቆም ስላለበት የክልሉ መንግሥት እየሰራ ያለው ይሄንን ለማስቆም ነው" ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ከሆነ "በተጨባጭ ሰው እየገደለ፣ ወንጀል መስራቱ በማስረጃ የተደገፈ ካለ" የሕግ አካላት ተከታትለው የተጠያቂነት ሥራ የሚሰሩት ይሆናል ይላሉ። "እነሱ የራሳቸውን ሕግ የማስከበር ሥራ ያከናውናሉ። በአሁኑ ወቅት እናንተ ሰው አፈናቅላችኋል፣ ገድላችኋል፣ መታሰር ይገባችኋል የምንል ከሆነ ነገሮች ይባባሳሉ እንጂ አይበርዱም። ስለዚህ መሆን ያለበት የሞተ ሞቷል፤ ተጨማሪ ሞት እንዳይከሰትና ሌላ ነገር እንዳይመጣ መሰራት አለበት" ብለዋል። ታጣቂዎቹ በክልሉ ውስጥ ካሉ ሶስት ዞኖች በካማሺ ውስጥ የሚገኘውን የሴዳል ወረዳ፣ ዲዛን ተቆጣጥሮ እንደነበር በባለፈው ወር ተገልጿል። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ምስጋናው እንጂፋታ በወቅቱ እንደገለፁት ከሱዳን 25 ኪሎ ሜትር በሚርቅ ስፍራ ላይ 'መርሾ' የሚባል ቀበሌ ውስጥ እነዚህ ታጣቂዎች የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ እንዲሁም ሦስት ንፁሃን ዜጎች ገድለው እንደነበር በወቅቱ መናገራቸው የሚታወስ ነው። ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለእርሻ የሚውል ሰፊ ለም መሬት ያለበት አካባቢ ሲሆን ለዓመታት የዘለቀው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽን እያወዘገበ ያለው በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ግዙፉ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚገኝበት ክልል ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ከሁለት ዓመት በፊት ባወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በክልሉ ወደ 1.1 ሚሊዮን እንደሚጠጋ ሕዝብ ይገኛል።
44355105
https://www.bbc.com/amharic/44355105
በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው በአዞ ተገደሉ
በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በላንቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ "መርከብ ጣቢያ" በተባለ ስፍራ ከሀይቅ ዳር ቆመው መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩ ፓስተር በአዞ በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው ፖሊስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ፓስተር ዶጮ እሸቴ የተባሉት የሃይማኖት አባት እሁድ ጠዋት 2 ሠዓት ተኩል አካባቢ ቁጥራቸው በግምት ሰማኒያ አካባቢ የሆኑ ተከታዮቻቸውን በሃይቁ ውሃ እያጠመቁ በነበረበት ሰዓት አደጋው እንደደረሰባቸው አቶ ከተማ ካይሮ የተባሉ የከተማው ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ከተማ ስለ ክስተቱ ሲያስረዱ ''አጥማቂው የመጀመሪያውን ሰው አጥምቀው ሁለተኛውን ማጥመቅ ሲጀምሩ አዞው በድንገት በመውጣት የሚጠመቀውን ሰው ገፍትሮ ሲጥለው አጥማቂውን ግን ጎትቶ ወደ ውሃው ይዞት ሄዷል'' ብለዋል። የወረዳው ፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን እውነቱ ካንኮ በበኩላቸው ክስቱት መፈጠሩን አረጋግጠው፤ በወቅቱ በአካባቢው የነበሩ ዓሳ አስጋሪዎችና ወጣቶች በአዞው ጥቃት የተፈፀመባቸውን ግለሰብ ከአዞው ለማስጣል ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ እንደቀረ ተናግረዋል። ዋና ሳጅን እውነቱ ምንም እንኳን የፓስተሩን ህይወት ማዳን ባይቻልም የአካባቢው ማህበረሰብ የሟች አስከሬን ከአዞው ለማስጠል እንደተቻለ ጨምረው አስረድተዋል። የሟቹ ፓስተር ዶጮ እሸቴ የቀብር ሥነ-ሥርዓትም ሰኞ እለት ተፈፅሟል።
news-46313415
https://www.bbc.com/amharic/news-46313415
ከሁለት ወር በፊት ሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ሰው 'ዳግም' ሞቱ
ከሁለት ወራት በፊት የሞትን ብርቱ ክንድ አሸንፈው ተነሱ የተባሉት አቶ ሂርጳ ነገሮ ሞተው ሳሉ የገጠማቸውን ለቢቢሲ አጫውተው የነበረ ሲሆን ከ70 ቀናት በኋላ ትናንት 'ዳግም' ማረፋቸውን ከሁለት ጊዜ ገናዣቸው ሰምተናል።
አቶ ሂርጳ ነገሮ መቃብር ፈንቅለው ከወጡ በኋላ ጤናማ የነበሩት አቶ ሂርጳ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ግን በፅኑ ታመው ከፈሳሽ ውጭ ምንም ነገር ይወስዱ እንዳልነበር ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችለናል። እሳቸው አይሆንም ቢሉም ቤተሰቦቻቸው ነቀምት ሆስፒታል ወስደዋቸው ነበር። ቤተሰቦቻቸው አቶ ሂርጳ ዳግም መቃርብር ፈንቅለው ይነሳሉ የሚል ተስፋ እንደሌላቸው ገልፀዋል። አቶ ሂርጳና ገናዣቸው አቶ ኢታና ቀንአን አነጋግረን የሰራነው ዘገባ የሚከተለው ነበር። ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች የሚባለው መቼ ነው? ምን ሲሆን? አቶ ሂርጳ ነገሮ ለዚህ ፍንጭ ሊሰጡን የሚችሉ ሁነኛ ሰው ናቸው፤ የቅርብ ጊዜ ምሥክር። ትውልዳቸው ከወደ ምሥራቅ ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳ ነው። ዘለግ ላለ ጊዜ በጽኑ ታመው ቆይተዋል። ከ2 ዓመት በፊት ሆድ ዕቃቸው ተከፍቶ በቀዶ ጥገና ታክመዋል። የጤና ታሪካቸው በአጭሩ ይኸው ነው። ማክሰኞ ረፋድ ላይ ግን ድንገት ደካከሙ። በዚያው ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ሞቱ [ተባለ]። ጥሩምባ ተነፋ፣ ጥይት ተተኮሰ፣ ድንኳን ተጣለ፤ ለቀስተኛ ተሰበሰበ፤ ሬሳ ተገነዘ። • በደቡብ ኢትዮጵያ አጥማቂው በአዞ ተገደሉ • ባህልን በኤሌክትሮኒክ ሙዚቃ የቀመመው ሮፍናን • ሰባኪው አውሮፕላን ግዙልኝ አለ ከአራት ተኩል ሰዓታት በኋላ ግን አቶ ሄርጳ[ሳጥን ፈንቅለው ወጡ]፤ 'ኢጆሌ ኢጆሌ እያሉ....'። ይህ የኾነው ማክሰኞ 'ለታ ተሲያት ላይ ነው። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከእርሳቸው ጋር የስልክ ቆይታ አድርጓል። በ'ሞቱበት' ሰዓት ያለ ቀጠሮ ያገኙት 'መልአክ' ምን ሹክ እንዳላቸው ጭምር አብራርተዋል። ኾኖም መቅደም ያለበትን እናስቀድም። አቶ ኢታናን፤ ገናዣቸውን። ቢቢሲ፦ ሳይሞቱ እንዳይሆን አጣድፋችሁ ሳጥን ውስጥ የከተታችኋቸው። አቶ ኢተና፦ "ዛሬ አይደለም እኮ ሰው የገነዝኩት [ቆጣ አሉ]። ስንትና ስንት ሰው ገንዣለሁ። ስንትና ስንት..." ቢቢሲ፦ እና ሳጥን ውስጥ ሲከቷቸው ትንፋሽ አልነበራቸውም? እርግጠኛ ኖት? አቶ ኢታና፦ "[ምን ነካህ!] ስንትና ስንት ሰው ሲሞት ዐይቻለሁ። ስንትና ስንት አው ገንዣለሁ። መሞቱን አረጋግጬ ነው ሳጥኑ ውስጥ ያስገባሁት። ዝም ብዬ እከታለሁ እንዴ። [የምር እየተቆጡ መጡ] ቢቢሲ፦ ታዲያ እንዴት የሞቱ ሰውዬ ሊነሱ ቻሉ? አቶ ኢተና፦ እንጃ! እንዲህ ዓይነት ነገር ሆኖ አያውቅም። ይሄ ከእግዛቤር የሆነ ነው እንጂ...። እሑድ ሊናዘዙ ቀጠሮ ነበራቸው "ሞቼ ተነሳሁ" የሚሉት አቶ ሂርጳ በሽታቸውን በውል አያውቁትም። ኾኖም እምብርታቸው አካባቢ ለረዥም ጊዜ ይቆርጣቸው ነበር። ነገርየው የጉበት ሕመም ሳይሆን እንዳልቀረ ይጠረጥራሉ። ሐኪምም ዐይቷቸዋል። የፈየደላቸው ነገር ባይኖርም። መጀመርያ ነቀምት ሆስፒታል፣ ከዚያ ደግሞ ጥቁር አንበሳ 'ሪፈር' ተብለው ሄደዋል። ደንበኛ ምርመራ አድርጊያለሁ ነው የሚሉት። ኾኖም የምርመራ ውጤቱ አልተነገራቸውም። በታኀሣስ 1፣ ሊነገራቸው ቀጠሮ ተይዞ ነው በዚያው 'ያሸለቡት'። በዚያ ላይ ለመዳን ከነበረ ጽኑ ፍላጎት የተነሳ በሬ ሽጠዋል። ዘመድ አዝማድ ተቸጋግሯል። ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄዶ ለመታከም። ከሰሞኑ ጉልበት ሲከዳቸው ታዲያ እንደማይተርፉ ጠረጠሩ። ያለቻቸውን ጥሪት ለአምስት ልጆቻቸው ሊናዘዙ ፈለጉ። ሰኞ ሊሞቱ እሑድ ዕለት ለመናዘዝ ቀጠሮ ተይዞ ነበር። ያጋጣሚ ነገር ኾኖ በዕለቱ የበኩር ልጃቸው ስላልነበረ ኑዛዜው ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ። ማክሰኞ 'ለት 'ሞቱ'። "ሬሳ ሳጥን የሰጠሁት እኔ ነኝ" ገናዥ አቶ ኢታና ቤተሰብም ናቸው፤ ጎረቤትም ናቸው። 'ሟች' የወንድማቸው ልጅ ናቸው። 3ሺህ የሚያወጣ ሬሳ ሳጥን በታላቅ ቸርነት ያበረከቱትም የገነዙትም እርሳቸው ናቸው። "ጋዜጠኞች ትናንት መጥተው ዐይተዋል። የወንድሜ ልጅ ስለሆነ የራሴን ሳጥን ሰጠሁት" ይላሉ። ቤተሰቡን ከወጪ ለመታደግ ነው ታዲያ ይህን ያደረጉት። ሳጥኑ ውስጥ ልብስ ምናምን ነበር የሚቀመጥበት። ምናምኑን ሁሉ ወለል ላይ ጣጥለው፣ አራግፈው፣ የወንድማቸውን 'ሬሳ' በክብር አኖሩበት። "ነጭ ልብስ የለበሰ መልአክ 'ተመለስ' አለኝ" እጅግ በተረጋጋ ሁኔታ የሚያወጉት አቶ ሄርጶ በሰማይ ቤት ቆይታቸው የተመለከቱትን ለቢቢሲ አጋርተዋል። እርግጥ ነው አንዳንድ ነገሮች ተዘንግተዋቸዋል። አንዳንዶቹ ትውስ ይሏቸዋል፣ ኾኖም በጠራ መልኩ አይደለም። አንዳንዶቹን ነገሮች ግን አጥርተው ማስታወስ ይችላሉ። ልክ ዛሬ የኾነ ያህል። ለምሳሌ በሰማይ ቤት በብረት ሰንሰለት የሚታጠር ግቢ ብዙ ሺ ሰዎች ተሰብስበው ተመልክተዋል። አጥሩ ከምን እንደተሠራ ግን አያስታውሱም፤ በሩ የብረት ይሁን የሳንቃ ትዝ አይላቸውም። አካባቢው ደጋና ልምላሜ የወረሰው እንደነበር ያስታውሳሉ። ኾኖም የሰማይ ቤቱ መልከዐምድር አይከሰትላቸውም። ከሁሉ ከሁሉ ያልዘነጉት ግን ከባድ ንፋስ ይነፍስ እንደነበረ ነው። ክብደቱን ሲገልጹ ድምጻቸውን ሁሉ ይበርደዋል። ሰዎች ተሰብስበውበታል ከሚሉት ከዚያ ግቢ ታዲያ ማንንም አያውቁም። ከሦስት ሰዎች በቀር። እነርሱም ከ2 ዓመት በፊት የሞቱትን አባታቸው፤ ከዓመታት በፊት የሞቱትን አማቻቸውን እና አንድ ሌላ አጎት ናቸው። ከሦስቱ ጋር ምን እንዳወጉ በውል አያስታውሱም። የሚያስታውሱት "እኛን ተከተለን" ብለዋቸው ቢከተሉ፣ ቢከተሉ፣ በፍጥነት ቢራመዱ፣ ቢሮጡ ሊደርሱባቸው እንዳልቻሉ ነው። ነገሩ የሕልም ሩጫን ይመስላል። ቀዩን መልአክ ግን መቼም አይረሱትም። በሁለተኛው ምዕራፍ የሕይወት ዘመናቸውም የሚረሱት አይመስልም። ቢቢሲ፦ መልአኩ ቀይ ነው ጥቁር? አቶ ሂርጶ፦ ነጭ ነው፤ ቀይ ነው...ጌታን ኢየሱስንም ይመስላል። ቢቢሲ፦የሰው መልክ ነው ያለው ወይስ የመልአክ? አቶ ሄርጶ፦ፊቱ በደንብ አላየሁትም። ወደ አጥሩ ቆሞ እኔ ውጭ ነበርኩ። መልኩ ቀይ ነው፣ ነጭ ልብስ ይለብሳል። ሰዎቹን ወደ ውስጥ አስገባና ይዟቸው ሄደ። ቢቢሲ፦ሌላ መልአክ አልነበረም አጠገቡ? አቶ ሄርጶ፦ አላስታውስም፤ እሱን ብቻ ነው ያየሁት። ቢቢሲ፦ምን አሎት? አቶ ሄርጶ፦ 'አንተ የት ትሄዳለህ? ተመለስ!' አለኝ። ቢቢሲ፦በምን ቋንቋ ነው ያናገርዎት? አቶ ሄርጶ፦ በኦሮምኛ። ቢቢሲ፦ አልፈሩም? አቶ ሄርጶ፦ አቅም አጣሁ እንጂ አጥሩን ኬላውን አልፌ ብገባ ደስ ባለኝ ነበር። "ኢጆሌ ኢጆሌ..." ማክሰኞ ተሲያት ላይ ከሬሳ ሳጥኑ ውስጥ ድምጽ ሲሰማ የአጋጣሚ ነገር በቅርብ የነበሩት የ'ሟች' እናትና ባለቤቱ ነበሩ። "ኢጆሌ ኢጆሌ..." ይላል ድምጹ። ሚስትና እናት ራሳቸውን አልሳቱም፤ በርግገው ከአካባቢው ተሰወሩ እንጂ። ድምጹ አልቆመም። "ኢጆሌ ኢጆሌ ነምኒ ሂንጂሩ?..." ለቀስተኛው ግማሹ እግሬ አውጪኝ አለ። ግማሹ የሚይዘው የሚጨብጠውን አጣ። የሰሙት ሬሳው እየጮኸ እንደሆነ ተናገሩ። ለመጠጋት የደፈረ አልነበረም። ከገናዣቸው በስተቀር። "ወንዶቹ ሁሉ ጥለው ጠፉ" ይላሉ አቶ ኢታና። ቢቢሲ፦ እርስዎ ግን አልፈሩም? አቶ ኢታና፦ ለምን እፈራለሁ፤ ሬሳውን ማስቀመጤን አውቃለዋ... "ከዚህ በኋላ የምኖረው ትርፍ ሕይወት ነው" ያን 'ለታ ፀሐይ ስታዘቀዝቅ ሚሪንዳ ቀመሱና ነፍሳቸው መለስ አለች። ሲረጋጉ ዘመድ አዝማድ መሰብሰቡን አስተዋሉ። እልልታና ለቅሶም ሰሙ። "ምንድነው ይሄ?"። 'ሞተው ነበረኮ' ተባሉ። "እንኳን በሰላም ገባህ፤ እንኳን በሰላም ተመለስክ ብለው ተደሰቱ" ይላሉ የወቅቱን የለቀስተኛውን መደነቅና ደስታ ለቢቢሲ ሲያስረዱ። "ተጸጸቱ እንዴ ግን? ወደ ሕይወት በመመለስዎ?" ብለናቸው ነበር። "እዛ ብሆን ጥሩ ነበር...። ግን አሁን ቅር የሚለኝ ነገር የለም። ወደ ልጆቼ፣ ወደ ቤተሰቤ በመመለሴ በጣም ደስ አለኝ።" ከዚህ በኋላ ምን ለማድረግ እንዳሰቡ ሲጠየቁ ጊዜያቸውን የሃይማኖት ትምህርት በመስጠትና የተጣሉ ሰዎችን በማስታረቅ ለማሳለፍ እንዳሰቡ ተናግረዋል። ለቀስተኞች ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳ እነ አቶ ሄርጳ ቤት ዛሬም ለለቅሶው ሲባል የተተከለው ድንኳን ባለበት አለ። "ሰዎች በብዛት እየመጡ ነው። እንደለቅሶ ነው የሚመጡት" አሉ ገናዡ አቶ ኢታና። ጥቁር አንበሳ ቀጠሮ አላቸው "ከመሞቴ በፊት ከነሐሴ ጀምሬ እንጀራ በልቼ አላውቅም" የሚሉት አቶ ሄርጳ "አፌም እንደዚህ መናገር አይችልም ነበር" ይላሉ። ከሬሳ ሳጥን ከወጡ በኋላ ግን ሕመማቸው ሙሉ በሙሉ ድኖ በሶም እንጀራም መቀማመስ ጀምረዋል። ድምጻቸው ደከምከም ይበል እንጂ ዘለግ ላለ ሰዓት እንደልብ ያወራሉ። የተዘነጋው ጉዳይ! ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቀጠሮ አላቸው። ለታኅሣሥ አንድ። ለውጤት ነው የተቀጠሩት። ከዚህ በኋላ ሐኪም ዘንድ ይሄዳሉ? ተብለው ሲጠየቁ ታዲያ መልሳቸው አጭርና ፈጣን ነው። "ለምን ብዬ!"
news-55156380
https://www.bbc.com/amharic/news-55156380
በትግራይ ልዩ ኃይል ተይዘው የነበሩ የሠሜን ዕዝ አባላት ምን ይላሉ?
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የትግራይ ልዩ ኃይል በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዛ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ መንግሥት ሕግ የማስከበር ያለውን ርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በመቋረጡ በአብዛኛው የትግራይ አካባቢ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ለማወቅ እድል አልነበረም።
ከሳምንታት በፊት የህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ከ10 ሺህ በላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን መያዛቸውን ገልጸው ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት ከታገቱት የሠራዊት አባላት መካከል 7 ሺህ የሚጠጉትን ማስለቀቁን መግለጹ የሚታወስ ነው። በተመሳሳይ መቀለ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ከገባች በኋላ በህወሓት ተይዘው የነበሩ የሠሜን ዕዝ አባላትን መልቀቁን ድርጅቱ ማስታወቁ ይታወሳል። በሠሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰውና ከሦሰት ሳምንታት በላይ በቆው ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ህይወት መጥፋቱ እየተነገረ ነው። በሠራዊቱ ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ጊዜ በክልሉ ልዩ ኃይል ተይዘው ለሳምንታት የቆዩ የሠራዊቱ አባላት ምን እንደተፈጠረና አስካሁን የቆዩበትን ሁኔታ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በትግራይ ልዩ ኃይል ተይዘው ከነበሩት መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከቀናት በፊት በዋግኽምራ እና በሰሜን ጎንደር በኩል ወደ አማራ ክልል መግባታቸው ተነግሯል። ከእነዚህ ውስጥም በዋግ ኽምራ በኩል የተከዜ ሰው ሰራሽ ሐይቅን ተሻግረው ሰቆጣ ከገቡትን የሠራዊቱን አባላት ውስጥ ቢቢሲ የተወሰኑትን አናግሯል። በምዕራብ ትግራይ አዲ ሀገራይ ከተባለችው ከተማ በሰባት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንዳሸተናይ በሚባል ስፍራ ውስጥ በ31ኛ አድዋ ክፍለ ጦር ውስጥ የክፍለ ጦር አባል የሆነው አምሳ አለቃ አብርሐም ባየ 22 ቀናትን በትግራይ ልዩ ኃይል አባላት በቁጥጥር ስር ቆይቶ ወደ ዋግኽምራ ከገቡት መካከል ነው። አምሳ አለቃ አብርሐም እንደሚለው የበታች ወታደሮች ስለተከተው ሁኔታ የሚያውቁት ነገር አልነበረም። ከሌሊቱ 6፡15 አካባቢ የመጀመሪያዋ ጥይት ስትተኮስ ነው ከእንቅልፋችን የነቃነው ይላል። "ስንነቃ ገደብ በሌለው ተኩስ እየተናጥን ራሳችንን በትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ተከበን አገኘነው" የሚለው አምሳ አለቃ አብርሐም የመሳሪያ መጋዘኑም ከቁጥጥራቸው ውጪ ሆኖ ስለነበረ እራሳቸውን የሚከላከሉበት ተጨማሪ መሳሪያ ማግኘት እንዳልቻሉና ተኩሱም ቀጥሎ የሚደርሰው ጉዳት እየደረሰ ሌሊቱ መንጋቱን ያስታውሳል። በአቅራቢያ የነበረው ሌላው የሠራዊቱ አሃድም በተመሳሳይ ጦርነት ተከፍቶበት ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 4፡00 እንደቀጠለ ይናገራል። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ራስን ለመከላከል የሚያስችል መሳሪያ በመጨረሳቸው "አማራጭ ስላልነበር አጠገባችን ብዙ ወንድሞቻችን ከሞቱ በኋላ እኛ ተያዝን" በማለት የውጊያውን ፍጻሜ ያብራራል። በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በጥቅምት 27 ወደ አከሱም ዩኒቨርሲቲ 10 ሺህ የሚሆኑ ወታደሮችን አንድ ላይ በማድረግ እንደወሰዷቸው ይገልጻሉ። ከቀናት በኋላ በኅዳር አንድ ደግሞ ከአክሱም በመነሳት ወደ አብይ አዲ እንደተወሰዱ አምሳ አለቃ አብርሐም ይናገራል። ምርኮኛ ሆነው በቆዩባቸው ቀናት በሚሊሻ እና በማረሚያ ቤት ጠባቂዎች ሲጠበቁ መቆየታቸውን የሚናገረው አምሳ አለቃ አብርሃም፣ "ምንም አይነት ንግግር አልነበረንም። በተለይ አብይ አዲ በነበርንበት ወቅት ሚሳኤሎች ሲተኮሱ በቦታው ሆነን እየተመለከትን ነበር። ከባድ መሳሪያዎች ወደ ስፍራው ሲጓጓዙ ስንመለከት በቀሪው የአገራችን ክፍል ውስጥ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ስለማናውቅ በጣም ጭንቀት ውስጥ ነበርን፣ እንቅልፍም አልነበርንም" በማለት የነበራቸውን ቆይታ ይገልጻል። መቀሌ በቁጥጥር ሥር መዋሏ በተነገረበት ዕለት አዳሩን እጅግ ብዙ የሆነ ከባድ መሳሪያ ወደ ስፍራው ሲመጣ አደረ፤ በማግስቱ ኅዳር 20 ሂዱ ብለው ለቀቁን ሲል የቆይታቸውን ፍጻሜ ያስታውሳል። ከእገታ እንዲለቀቁ ከተወሰነ በኋላ በኅዳር 20 ወደ ተከዜ የኃይል ማመንጫ ጫፍ አድርሰዋቸው እንደተመለሱ የሚናገረው አምሳ አለቃ አብርሐም ከዚያም ወደ አማራ ክልል በመሻገር አበርገሌ ከምትባል ቦታ መግባታቸውን ገልጿል። "የአካባቢው ማኅበረሰብ ተንከባክቦ አሳደረን ከዚያም መኪና ተልኮልን ወደ ሰቆጣ ገባን" ብሏል። ሃምሳ አለቃ አብረሐም ተከዜ ጫፍ በመኪና ከተሸኙ በኋላ ሠራዊቱ በሁለት ቀጠና መሄዱን ይገልጻል። የተለቀቁት ከ50 አለቃ በታች ማዕረግ ያለካቸው ወታደሮች መሆናቸው በመጥቀስም "ሴት ወታደሮችና ከ50 አለቃ በላይ ማዕረግ ያላቸው የት እንዳሉ አናውቅም። በሌላ በኩል ከባድ ቁስል የደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላትም ነበሩ" ብሏል። ከ50 አለቃ በታች ያለነው ከ4 ሺህ በላይ እንሆናለን ያለው ሃምሳ አለቃ አብረሐም ይህም ኃይል ተከዜ ጫፍ ከደረሰ በኋላ የጀልባ ከፍሎ የተከዜን ሰው ሰራሽ ሐይቅ መሻገር የቻለው ወደ ሰቆጣ፣ ገንዘብ የሌለው ደግሞ በእግሩ በበየዳና ደባርቅ አድርጎ ወደ ጎንደር መጓዙን ይገልጻል። "የነበርንበት ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪ ነበር፣ የተባልነውን ከማድረግ ውጭ ከባድ ቁስል ላይ ሆነን እንኳ የምንታከምበት እድል አልነበረም፣ ያንን ማየት አስቸጋሪ ነው" ይላል። ሌላኛው የሠራዊቱ አባል አስር አለቃ ኢብራሂም ሃሰን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የመከላከያ ሠራዊቱን በመቀላቀል እኣገለገለ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል። መጀመሪያ ወደ ትግራይ ሲመጣ ስምሪቱ በአክሱም ከተማ ነበር። ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ አዲግራት ከተማ ነበረ። እሱም ሆነ ባልደረቦቹ ጥቅምት 24 የተከሰተው ነገር ይሆናል ብለን ፈጽመው አስባው እንደማያውቁ ይናገራል። ስለዚህም ከቀን ውሏቸው መልስ ሁሉም በየክፍሉ አረፍ ብሎ እንዳለ ከሌሊቱ 5፡30 ላይ ተኩስ ተከፈተ። "ከዚያም መሳሪያ አምጡ፤ እጅ ስጡ አሉን። እኛ ትጥቅ የሚያስፈታን የፌደራል መንግሥት እንጂ የክልል መንግሥት አይደለም አልናቸው። እንዴት እጅ እንሰጣለን፤ እጅ አንሰጥም ስንላቸው ነበር።" ነገር ግን ኋላ ላይ በከበቧቸው የትግራይ ኃይል እና ሚሊሻ አባለት መያዛቸውን የሚናገረው አስርአለቃ ኢብራሂም "ጥቅምት 25 እና 26 ውለን ዓርብ በ27 እዳጋ ሐሙስ ወደሚባል ቦታ ወሰዱን። እዳጋ ሐሙስ ለአንድ ሳምንት ያክል ከቆዩን በኋላ አብይ አዲ ወደምትባል ቦታ ተወሰድን" ይላል። ኢብራሂም ተይዘው የቆዩባቸው ቀናት እጅግ አስቸጋሪ እንደነበሩ በመግለጽ ይራቡ እንደነበረም ያስታውሳል "ጠዋት አንድ ዳቦ ይመጣል። ለምሳም አንድ ዳቦ ነው የሚሰጠን። አንዳንዴ ጠዋት ከበላን ምሳ ላይሰጠን ይችላል።" ከቀናት ቆይታ በኋላም የተለያዩ አማራጮች ቀረቡልን ይላል "የትግራይ ልዩ ኃይልን መቀላቀል፣ ሲቪል ሆኖ ትግራይ ውስጥ መቆየት ወይም ወደ አገሬ መግባት ነው የምፈልገው የሚል ካለ መሄድ ይችላል አሉን። አብዛኞቻችን ወደ አገራችን መመለስ የሚለውን መረጥን" ሲል ተናግሯል። ከዚያም ከሠራዊቱ መካከል የተለያዩ ሙያ ያላቸውን እንደ ኦፕሬተር እና መድፍ ተኳሾችን በመለየት አስቀሩና ሌሎቻችንን በሲምንቶ መጫኛ ተሳቢ መኪና ጭን እንድንወጣ አደረጉን ይላል አስር አለቃ ኢብራሂም። ሌላኛው ስሙን ያልገለጸልን የ11ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ አባል፣ እርሱ በነበረበት ቦታ ተኩሱ ምሽት 5፡30 አጉላ ላይ መጀመሩን ይገልጻል። "እንደዚህ አይነት ኦፕሬሽን እንደሚኖር በግርድፉ ጥርጣሬ ቢኖርም መቼ እንደሆነ ግን አላወቅንም" የሚለው ይህ የሠራዊቱ አባል በወቅቱ ለጥበቃ የሚሆኑ 3 ክላሽንኮቮች ብቻ ነበሩ ለጥበቃ የወጡት። ሌላው መሣሪያ መጋዘን ውስጥ ተቆልፎ እኛም ተኝተን ነበር" ይላል ጨምሮም "ተኩሱ ሲጀመር መሳሪያ ለማውጣት ወደ መጋዘኑ ብናመራም ቀድመው ስለከበቡት ሊያስጠጉን አልቻሉም።" እራሳቸውን የሚከላከሉበት መሳሪያ ለማግኘት ጥረት ማድረጋቸውን እንደቀጠሉና ከመካከላቸው አንድ ቁልፍ የያዘ አባል ወደ መጋዘኑ ተጠግቶ ለመክፈት ሲሞክር ተመትቶ በመውደቁ ድጋሚ መቅረብ አለመቻላቸውን ይገልጻል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ "የራሴ የግል መሳሪያ በቅርብ ስለነበረኝ፣ እያየሁ ዝም አልልም በሚል አውጥቼ ለመታኮስ ስወጣ ገና 30 ሜትር እንደተጓዝኩ ተመትቼ ወደቅኩ" በማለት ለጉዳት የተጋለጠበትን አጋጣሚ ይገልጻል። "ለተወሰነ ጊዜ ራሴን ስቼ ስለነበር እነሱም ሞቷል ብለው ዝም አሉኝ። ከዚያ እንደምንም ተጎትቼ በአጥር በመሹለክ የሠራዊቱ መኝታ ክፍል ውስጥ ገባሁ" ይላል። ነገር ግን በቦታው ሰው እንዳላገኘ ገልጾ "ወደ ሌላኛው ቦታ ስሄድ ሰው ቤት ውስጥ ተቀምጧል። መመታቴን ስነግራቸው ቁስሌን አስረው አስቀምጡኝ። ተኩሱም እስከ ማግስቱ ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ቀጠለ። ሌላ ኃይል እኛን ሊከላከለን ሞክሮ ነበር፣ ነገር ግን ጥይት ሲጨርሱ ከፍተኛ ጥቃት ደርሶባቸው ተማረኩ። እኛም ተያዝን" በማለት በትግራይ ልዩ ኃይል ቁጥጥር ስር የወደቁበትን ክስተት አስረድቷል። ከተማረኩ በኋላም ግማሻቸውን ወደ ውቅሮ፣ ሌሎቻቸውን ደግሞ ወደ አጉላ መወሰዳቸውን በማስታወስ፤ በውቅሮ ሆስፒታል ለሦስት ቀን ሕክምና እንደተደረገለት የሚናገረው አባሉ ከአንድ ሳምንት በኋላ ወደ አብይ አዲ መወሰዱን ገልጿል። ወደ አብይ አዲ ከመወሰዳቸው በፊት ግን ሹፌር፣ ቴክኒሻን፣ መሃንዲስና የመረጃ ባለሙያ የመሳሰሉትን ባለሙያዎች እየለዩ ለብቻቸው እንደሳስቀሯቸውና ከዚያ በኋላም የተለያየ ፎርም እያስመጡ እንደሞሉ የሚናገረው ይህ የሠራዊቱ አባል "ሦስት ጓደኞቻን ከተማረኩ በኋላ ተገድለዋል" ብሏል። ከቀረቡላቸው ፎርሞች መካከል ብሔርን የሚጠይቅ እንዳለ በማስታወስ በመጨረሻ የቀረበላቸው ፎርም ግን ሦስት አማራጮችን የያዘ ነበር ይላል። "አንደኛው ከትግራይ ልዩ ኃይል ጋር በመሆን ትግራይን ነጻ እንድናወጣ፣ ሁለተኛ በትግራይ ውስጥ ሰላማዊ ሰው ሆነን እንድንኖርና ሦስተኛው ደግሞ ከትግራይ ወጥተን ወደ ቤተሰብ እንድንሄድ የሚፈቅዱ ናቸው" ይላል። "እኛም ተመካክረን ሦስተኛውን አማራጭ መርጠን እንሄዳለን አልናቸው። እነሱም ከንፈራቸውን እየነከሱ እና ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ ተቀበሉን" በማለት ከምርኮኛነት የወጡበትን ሁኔታ አብራርቷል። ከአብይ አዲ ወደ አማራ ክልል የተሸኙት የሠራዊት አባላት በሁለት አቅጣጫ መሸኘታቸው የሚታወስ ነው፤ በዋግኽምራ እና በሰሜን ጎንደር በኩል። እስካሁን ትክክለኛ ቁጥራቸው ባይታወቅም በሁለቱም አቅጣጫ በሺዎች የሚቆጠሩ የሠራዊት አባላት በሰላም መግባታቸው ይነገራል። ከእነዚህ መካከል በዋግኽምራ በኩል እስከ ትናንትናው ዕለት ድረስ ከ1240 በላይ የሰሜን ዕዝ የሠራዊት አባላት መግባታቸውን በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በላይ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየው አለመግባባት ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ መካረሩ ይታወሳል። ተከትሎም የፌደራል መንግሥቱን ውሳኔ ባለመቀበል ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል የተካሄደው የተናጠል ምርጫ የፌደራል መንግሥቱን ተቀባይነት ካለማግኘቱ በተጨማሪ በአገሪቱ ምክር ቤቶች ሕገ ወጥ ተብሎ ውድቅ ተደርጓል። የክልሉ ባለስልጣናትም በበኩላቸው ፌደራል መንግሥቱ በኮቪድ ሰበብ ምርጫን ማራዘሙ "ሕገመንግስቱ ከሚፈቅደው ውጭ ነው ስልጣኑን አራዝሟል" በማለት የፌደራሉን መንግሥት "ሕገወጥ" ብለው እውቅና መንፈጋቸው አይዘነጋም። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የክልሉን አስተዳዳሪዎች ሕገ መንግሥቱን በመጣስና ከሕግ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በማለት የፌደራል መንግሥቱ ከትግራይ ክልል ክልል አስተዳደር ጋር የነበረውን የቀጥታ ግንኙነት አቋርጦ የበጀት ዕቀባ ጥሎ ነበር። አለመግባባቱና መካሰሱ ያለማቋረጥ በቀጠለበት ሁኔታ ጥቅም 24/2013 ዓ.ም ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በትግራይ ክልል በነበረው የፌደራሉ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የፌደራሉ ሠራዊት በትግራይ ክልል ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ይታወሳል። መንግሥት "ሕግ የማስከበር" ባለውና ከሦሰት ሳምንታት በላይ በተካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል። ባለፈው ቅዳሜ የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ሰር ከዋለች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሳውቀዋል።
48062361
https://www.bbc.com/amharic/48062361
እስልምናን የሚቃወሙ ሰልፈኞች ፊት ፎቶ የተነሳችው ሙስሊም ሴት መነጋገሪያ ሆናለች
የ24 ዓመቷ ሻይማ ኢስማኤል የምትኖረው አሜሪካ ነው።
ሻይማ ኢስማኤል የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮችን የሚያጥላሉ ሰልኞች ፊት ለፊት የተነሳችው ፎቶ የማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ አድርጓታል። ሰልፈኞቹ ሙስሊሞችን የሚያንቋሽሹ ጽሁፎች አንግበው ነበር። ሻይማ ደግሞ በተቃራኒው ፈገግ ብላ በእጇ የድል ምልክት (V) እያሳየች ፎቶ ተነሳች። • የቻይና ሙስሊሞች ምድራዊ 'ጀሐነም' ሲጋለጥ ፎቶው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከ200,000 በላይ ወዳጅ ወይም 'ላይክ' ያገኘ ሲሆን፤ ሻይማ "ፎቶውን የተነሳሁት ጥላቻቸውን በፍቅርና በፈገግታ ማሸነፍ ስለምፈልግ ነው" ብላለች። ሻይማ የምትሠራው የአእምሮ ዝግመት ካለባቸው ህጻናት ጋር ነው። ዋሽንግተን ውስጥ የተካሄደ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ኮንፈረንስ እየተሳተፈች ነበር። ለሦስት ቀናት የተሰናዳው መድረክ የሀይማኖቱ ተከታዮች እንዲገናኙ፣ እንዲወያዩ የተሰናዳ ዓመታዊ መርሀ ግብር እንደነበረ ትናገራለች። "ኮንፈረንሱ ውስጥ ደስ የሚል ድባብ ነበር። ስንወጣ ግን እኛን የሚቃወሙ ሰልፈኞች አየን። በመጀመሪያው ቀን ሳንጠጋቸወ አለፍን።" ሀይማኖቱን የሚያጥላላ ንግግር በድምጽ ማጉያ እያሰሙ ነበር። 'እስልምና የጥላቻ ሀይማኖት ነው'፤ 'የስብሰባው ተሳታፊዎች ጥላቻ እየተሰበኩ ነው' የሚል ጽሁፍ ይዘውም ነበር። • "መንግሥት የሚደግፈው የሙስሊሙን ሕብረተሠብ ነው" ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ • ፀረ ሙስሊም ደብዳቤ በእንግሊዝ ሻይማ በተቃራኒው "እኔም ድምጽ ማጉያ ኖሮኝ ኮንፈረንሱ ውስጥ የምናወራውን ባሰማቸው ብዬ አሰብኩ" ትላለች። ሰልፈኞቹን ለሦስት ቀናት ካየች በኋላ በስተመጨረሻ እሷም አቋሟን ለመግለጽ ወሰነች። "ነቢያችን ፈገግታ ቸርነት ነው ይላሉ። እኔም ሳቂታ ነኝ። ሰልፈኞቹ ፈገግ ብዬ እንዲያዩኝ ስለፈለግኩ ጓደኞቼ ስስቅ ፎቶ እንዲያነሱኝ ጠየቅኳቸው።" ሻይማ እንደምትለው ፎቶው ላይ ያሉት ሰልፈኞች በድርጊቷ መበሳጨታቸውን አይታለች። በተቃራኒው ፎቶውን ያዩት ሌሎት ሰዎች ከጠበቀችው በላይ ድጋፍ ሰጥተዋታል።
news-56021562
https://www.bbc.com/amharic/news-56021562
በትግራይ ከተሞች ላይ በዘፈቀደ የጦር ድብደባ መፈፀሙን ሂውማን ራይትስ ዋች ገለፀ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ከተሞች ላይ ልዩነት ባላደረገ መልኩ፣ በዘፈቀደ ድብደባ እንዳደረሰና ይህም የጦርነት ሕግን የሚጥስ እንደሆነ ሂውማን ራይትስ ዋች በዛሬው እለት ባወጣው ሪፖርቱ አስታወቀ።
ሪፖርቱ በተለይም ግጭቱ በተጀመረበት ወቅት በከባድ መሳሪያዎች ቤቶች፣ ሆስፒታሎችና፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የገበያ ቦታዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል ብሏል። ሪፖርቱ እነዚህ ድብደባዎች የደረሱት በመቀለ፣ ሁመራ፣ ሽረ እንዳስላሴ ከተሞች እንደሆነ ጠቅሶ ህፃናትን ጨምሮ 83 ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል፤ እንዲሁም 300 ሰዎችም ቆስለዋል ይላል። መንግሥት ለሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት እስካሁን የሰጠው ምላሽ ባይኖርም፤ ከዚህ ቀደም "በሕግ የማስከበር እርምጃው" በሲቪሎች እና በቅርሶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ መደረጉን አስታውቋል። "ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት የኢትዮጵያ ፌደራል ኃይሎች በከባድ መሳሪያ ከተሞች ላይ ልዩነት ባላደረገ መልኩ፣ በዘፈቀደ ደብድበዋል። ይሄም ማለት የሲቪሎች መሞትና የንብረት መውደም ማስከተሉ የማይቀር ነው" ይላሉ የድርጅቱ የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላይቲታ ባዴር። አክለውም "እነዚህ ጥቃቶች የንፁኃን ዜጎችን ህይወት አደጋ ውስጥ ጥለዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ነዋሪዎችን አፈናቅሏል። እነዚህ ህጋዊ ያልሆኑ ጥቃቶች እንዲቆሙና ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው አካላት ወደ ፍትህ ይቅርቡ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ህዳር 21፣ 2013 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የፌደራል መንግሥት ሰራዊት "በህግ ማስከበር ዘመቻው አንድም የንፁህ ዜጋ አላጠፋም" ማለታቸው ይታወሳል። ግጭቱን አስመልክቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ እንዲሁ በትዊተር ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ የፌደራል ኃይሎች "በከተሞችና ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ውጊያ አላካሄዱም" ብሏል። ማጣሪያው አክሎም "መከላከያ ኃይሉ ንፁኃን ዜጎች እንዳይሞቱና ውድመትን ለመካከል ፈታኝ መልክዓ ምድሮችን ለማቆራረጥ ተገዷል። እስካሁንም ባለው የመከላከያ ሠራዊቱ ለንፁኃን ዜጎችን ከፍተኛ ጥበቃ በማድረግ የተሳካ ስራ ሰርቷል" በማለት አስፍሯል። ጥቅምት 24፣ 2013 የትግራይ ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለውን ሁኔታ የገመገመው የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት፤ ግጭቱን ተከትሎ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች በቂ ምግብ የላቸውም፣ የውሃ፣ የነዳጅና የመድኃኒት ዕጥረት አጋጥሟቸዋል። ከ200 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በዚያው በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው የሚገኙ ሲሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ሸሽተዋል ብሏል። ሂውማን ራይትስ ድርጅት 37 የአይን እማኞችን እንዲሁም በመንግሥት ኃይሎች ጥቃት ደርሶብናል ያሉ የሁመራ፣ ሽረ እንዳስላሴና መቀሌ ነዋሪዎችን፣ ዘጠኝ ጋዜጠኞችን፣ የረድዔት ድርጅት ሰራተኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችንና የፎረንዚክ ባለሙያዎችን አናግሮ ይሄንን ሪፖርት እንዳጠናቀረ አስታውቋል። ድርጅቱ ከዚህም በተጨማሪ የሳተላይት ምስሎችን እንዲሁም ጥቃት ከተፈፀመባቸው ስድስት ቦታዎች የተገኙ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን እንደመረመረ አስታውቆ፤ ከአይን እማኞቹ ምስክርነት ጋርም ተመሳሳይነት እንዳለው በሪፖርቱ አካቷል። ድርጅቱ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ለኢትዮጵያ መንግሥት ቢያሳውቅም ምላሽ እንዳላገኘ እንዲሁ አስፍሯል። በሌላ በኩል የአይን እማኞችን አባሪ አድርጎ ድርጅቱ እንዳሰፈረው የፌደራል ሰራዊቱ የሁመራ፣ ሽረና መቀለ ከተሞችን ለመቆጣጠር በከፍተኛ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ማድረሱን ነው። እነዚህ ጥቃቶች ወታደራዊ (የጦር ሰፈሮችን) ኢላማን ያደረጉ ሳይሆኑ በርካታ ነዋሪዎች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ላይ የተፈፀሙ መሆናቸውን አስረድተዋል። እንደነዚህ አይነት ተመሳሳይ ድብደባ በአክሱም እንደደረሰም ከ13 ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ተረድቻለሁ ብሏል። በሁመራ ደረሰ የተባለው ድብደባ በምዕራባዊ የሁመራ የድንበር ከተማ ጥቅምት 30፣ 2013 ዓ.ም ከኤርትራ ሠራዊት የተሰነዘረ ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ያደረሰ ሲሆን፤ በርካቶችም እንደሸሹ ሪፖርቱ አስፍሯል። በጥቃቱ ቀበሌ 2 የሚባለው አካባቢ የነዋሪዎች ቤት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን እንዲሁም ጥቃቱ በቤተ ክርስቲያንና መስጊድ አካባቢ የደረሰ ነው ብለዋል። በቀበሌ 01 የደረሰው ጥቃት በከተማዋ ዋነኛ ሆስፒታል አካባቢ ላይ ጥቃት ማድረሱን ድርጅቱ ነዋሪዎቹን ዋቢ በማድረግ ሪፖርቱ ያትታል። በከተማዋ ዋነኛው ካህሳይ አበራ ተብሎ በሚጠራው ሆስፒታል የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች ደግሞ በሟቾች አስከሬንና ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው ህሙማን ምክንያት ሆስፒታሉ ድንገተኛ መጨናነቅ አጋጠመው በማለት ለድርጅቱ መናገራቸው ተገልጿል። አንደኛው ዶክተር በጥቅምት 30 ቀን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 46 ይገመታል ያለ ሲሆን የቆሰሉ ደግሞ 200 ናቸው ማለቱን ድርጅቱ አስፍሯል። በሽረ እንዳስላሴ ደረሰ የተባለው ጥቃት በሰሜን ምስራቅ ሽረ እንዳስላሴ ከተማ ህዳር 8፣ 2013 ዓ.ም ጥቃት የተጀመረ መሆኑን ያመላከተው ሪፖርቱ በከተማዋ ማዕከል የሚገኙ ህንፃዎችን እንዲሁም የኢንዱስትሪ ስፍራዎችም ጥቃት ደርሶባቸዋል። "በነዚህም ድብደባዎች ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ሸሽተዋል" ይላል። በዚያኑ ቀን የአይን እማኞች የኢትዮጵያ ሰራዊትና የኤርትራ ጦር በከተማው ሲያልፉ ማየታቸውን ተናግረዋል። በተለያዩ ሪፖርቶች የኤርትራ ወታደሮች መሳተፋቸው የተጠቀሰ ሲሆን በቅርቡ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል በአስቸኳይ እንዲወጡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) የአውሮፓ ህብረት መጠየቃቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በተደጋጋሚ በትግራዩ ግጭት የኤርትራ ጦር አለመሳተፉን ማሳወቁ የሚታወስ ነው። በመቀለ ደረሰ የተባለው ጥቃት በመቀለ ከተማ ህዳር 19፣ 2013 ዓ.ም በደረሰው ከፍተኛ ድብደባ ልጆችን ጨምሮ 27 ንፁኃን ዜጎች ተገድለዋል እንዲሁም ከመቶ በላይ ቆስለዋል ይላል ሪፖርቱ። በመቀለ አይደር ክፍለ ከተማ በገበያ አካባቢ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት በደረሰ የቦንብ ጥቃት አራት የቤተሰብ አባላትን ገድሏል ያለው ሪፖርቱ ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ ህፃናት ልጆች ሲሆኑ አምስት ትልልቅ ሰዎችና አንድ የ9 አመት ልጅም ቆስሏል። "የዘፈቀደ ወይም ደግሞ ያልለየ ጥቃት የምንለው በአንድ ወታደራዊ ኢላማ ያላደረገ ዝም ብሎ የደረሰ ጥቃት ነው። ከዚህም በተጨማሪ በከተሞችና ህዝብ በሚኖርባቸው ቦታዎች ላይ ወታደራዊ ኢላማ ላይ ያነጣጠሩ የቦንብ ድብደባዎች የዘፈቀደ ጥቃት ይባላሉ። እነዚህን የጦር ህጎች በቸልተኝነትም ሆነ ዝም ብለው የጣሱ ግለሰቦች ለጦር ወንጀሎች ተጠያቂ ይሆናሉ" በማለት ሪፖርቱ አፅንኦት ሰጥቷል። ሁሉም ኃይሎች ቢሆኑ የንፁኃን ዜጎችን ህይወት አደጋ እንዳይጥሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው በማለት አስምሯል። በትግራይ ክልል ያለው ውጊያ አሁንም በቀጠለበት ሁኔታ ሁሉም ኃይሎች ለጦር ህግጋት እንዲታዘዙ አሳስቧል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል። "የኢትዮጵያ የፌደራል ሰራዊት ልዩነት ካላደረገ ጥቃት እንዲታቀቡ፣ ተፈፀሙ የተባሉ የጦርነት ህግ መጣስን እንዲመረምርና ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ባለባቸው ቦታዎች ላይ ተቀጣጣይ መሳሪያዎችን ከመጠቀም መቆጠብ አለበት" በማለት ጥሪውን አቅርቧል። ከዚህም በተጨማሪ በአካባቢው የሰብዓዊ ረድዔቶች እርዳታ ያለ ምንም እክል እንዲገባ ሊመቻች ይገባል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ ደረሱ የተባሉ የጦርነት ህግ ጥሰቶችን የሚያጣራና መረጃዎችን የሚሰበስብ አንድ ቡድን የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ሊልክ ይገባል ብሏል። "የኢትዮጵያ መንግሥት የተባባሩት መንግሥት መርማሪዎች በክልሉ ገብተው እንዲመረምሩ እንዲፈቅድና ሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ውስጥ የከተተው ጦርነት ችላ ሊባል አይገባም ብሏል።
news-49793799
https://www.bbc.com/amharic/news-49793799
ኢትዮጵያን ጨምሮ 130 አገራትን የጎበኘው ዓይነ ስውር
በቅርቡ ኢትዮጵያን የጎበኘውና ከ130 በላይ ሃገራት የተጓዘው ዓይነ ስውሩ ቶኒ ጊልስ በዓለም ላይ ያሉ ቦታዎችን በተለየ መንገድ እንደሚመለከታቸው ይናገራል።
ቶኒ ጊልስ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የዞማ ቤተ መዘክር ውስጥ "ቀዝቃዛውን አንታርክቲካን ጨምሮ፤ ሁሉንም አህጉራትን ጎብኝቻለሁ። አላማዬም በዓለም ላይ ያሉትን ሁሉንም ሃገራት ተዘዋውሬ መጎብኘት ነው" ይላል ቶኒ። ቶኒ ዓይነ ስውር ሲሆን ሁለቱም ጆሮዎቹ አይሰሙም። ነገር ግን ይህ ወደተለያዩ ስፍራዎች ተጉዞ ጉብኝት ከማድረግ አላገደውም። በዚህም ከ130 በላይ ሃገራት በመጓዝ ጉብኝት አድርጓል። "አንዳንዶች ጉብኝት ለእኔ የሚታሰብ እንዳልሆነ ይናገራሉ። ነገር ግን ዓለምን በሌላ መንገድ ላያት እንደምችል እያሳየሁ ነው" ይላል የ41 ዓመቱ እንግሊዛዊ ተጓዥ። በቆዳዬ በኩል ስሜቱን እረዳለሁ "ሰዎች ሲናገሩ እስማለሁ፣ ተራራዎችን እወጣለሁ እወርዳለሁ፤ በቆዳዬ በኩል ሁሉንም ስሜት አገኘዋለሁ። በዚህ መንገድ ነው ሃገራትን የምጎኘው" ሲል ስፍራዎችን እንዴት እንዴት እንደሚጎበኝ ይገልጻል። ቶኒ ባለፉት 20 ዓመታትን ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመጓዝ አዳዲስ ስፍራዎችን ሲጎበኝ ቆይቷል። • ዓይናሞችን ዓይነ ስውር የሚያደርገው እራት እንደሱው ዓይነ ስውር የሆነችውን ግሪካዊት የሴት ጓደኛውን ያገኘውም ለጉብኝት ከተጓዘባቸው በአንዱ ቦታ ነው። ባለፈው ዓመትም ከጓደኛው ጋር ወደ ሩሲያ ተጉዘው ነበር። እዚያም የዓለማችንን ትልቋን ሃገር በባቡር በመጓጓዝ ጎብኝተዋል። ነገር ግን በአብዛኛው የጉብኝት ጉዞው ግን ብቻውን ነው የሚሆነው። የጉዞ ፍቅር ቶኒ ለጉዞው የሚሆነውን ወጪ የሚሸፍነው ከአባቱ ጡረታ ላይ በሚያገኘው ገንዘብ ሲሆን ጉዞውን ቀደም ብሎ በማሰብ ያቅዳል። የአብዛኞቹ አየር መንገዶች ድረ ገጽ እንደሱ ላሉ ለዓይነ ስውራን አጠቃቀም አመቺ ስላልሆኑ እናቱ የአውሮፕላን ጉዞ ትኬቶቹን በመቁረጥ እንደሚረዱት ይናገራል። እሱም ኢንትርኔትን በመጠቀም በሚጓዝባቸው ሃገሮች ውስጥ ሊረዱት ሚችሉ ሰዎችን ፈልጎ በማግኘት ቀድሞ ይዘጋጃል። "እንዲሁ ብድግ ብዬ አንድ መጽሐፍ በማንሳት 'እዚህ ወይም እዚያ ልሄድ' ብዬ አልወስንም። ቀድሜ ስለቦታው ማወቅ ይኖርብኛል። ጥሩ የማስታወስ ችሎታ አለኝ። ለዚህም ጉዞዬን ቀድሜ አቅዳለሁ" ይላል። • ዐይነ ስውሩ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ሕንፃ ከሰባተኛ ፎቅ የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ሞተ ካሰበው ቦታ ደርሶ በማያውቀው ከተማ ውስጥ ሚፈልገውን ቦታ ለማግኘት በራሱ የሚያደርገው ጥረት የተለየ ደስታን ይፈጥርለታል። "አንዳንድ ጊዜ ማንን እንደማገኝና ምን ሊከሰት እንደሚችል የማውቀው ነገር የለም። ይሄ ለእኔ የተለየና ጀብድ ነው።" አካል ጉዳተኝነት ቶኒ የማት ችግር እንዳለበት የታወቀው ገና የዘጠኝ ወር ህጻን እያለ ነበር። ከዚያም አስር ዓመት ሲሆነው የዓይን ብርሐኑን ሙሉ ለሙሉ አጣ። ዓይነ ስርው ከመሆኑ በፊት ስድስት ዓመቱ ላይ መስማት የሚችለው በከፊል እንደሆነ ታውቆ ነበር። አሁን መስማት እንዲያስችለው ከፍተኛ ኃይል ያለው ዘመናዊ የመስሚያ መርጃ መሳሪያ ቢጠቀምም ሁሉንም ድምጾች ግን ለመስማት አይችልም። "በአስራዎቹ እድሜ ውስጥ እያለሁ ዓይነ ስርው መሆኔ በእጅጉ ያሳስበኝ ነበር።" ቶኒ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ትምህርት ቤት ነበር የተማረው፤ እዚያም የ16 ዓመት ታዳጊ እያለ በትምህርት ቤቱ አማካይነት በተዘጋጀ ጉዞ ላይ በመሳተፍ ወደ አሜሪካዋ ቦስተን በመሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጪ ሃገር የመጓዝ ተሞክሮን ለማግኘት ቻለ። ነገር ግን አሁን ድረስ የሚገጥመው የጤና ችግር ጥልቅ በሆነው የመጓዝ ፍላጎቱ ላይ እንቅፋትን እየፈጠረበት ነው። ለምሳሌም ከ10 ዓመት በፊት የኩላሊት ችግር አጋጥሞት ከእንጀራ አባቱ በተለገሰው ኩላሊት ንቅለ ተከላ ተደርጎለታል። ቶኒ ላሊበላን ሲጎበኝ የአልኮል ሱስ ቶኒ ከታዳጊነቱ ጀምሮ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመውታል። በ15 ዓመቱ አባቱን ያጣ ሲሆን 16 ዓመት ሲሆነው ደግሞ አካል ጉዳተኛ የነበረውና የቅርብ ጓደኛው በሞት ተለየው። በገጠመው ሐዘን ሳቢያም "ለስድስት ወይም ለሰባት ዓመታት የአልሆል ሱሰኛ እንድሆን አደረገኝ። 24 ዓመቴ ላይ የመጠጥ ሱሰኛ ነበርኩ" ይላል። አባቱ የንግድ መርከቦች ላይ ይሰሩ ስለነበረ ከባሕር ማዶ ስላሉ እሩቅ ቦታዎች ይነግሩት የነበሩ ታሪኮች በታዳጊው ቶኒ ልብ ውስጥ ትልቅ ፍላጎትን ፈጥረው ነበር። የጉዞው ጅማሬ የቶኒ ዓለምን ዞሮ የመመልከት የጀመረው የዛሬ 19 ዓመት የመጀመሪያ ጉዞውን ወደ አሜሪካ ኒው ኦርሊያንስ በመሄድ ካደረገ በኋላ ነው። "እዚያ ስደርስም የት እንደምሄድ ስላላወቅሁ ደርቄ ነበር የቀረሁት። ከዚያም ሁለት ጊዜ በጥልቁ ከተነፈስኩ በኋላ እራሴን 'ቶኒ ካልፈለግህ ወደ ቤትህ ተመለስ' አልኩት።" ከዚያም ጉዞውን አቋርጦ ላለመመለስ ወስኖ ጉዞውን ቀጠለ። አስከትሎም ሁሉንም የአሜሪካ ግዛቶችን ተዟዙሮ ለመጎብኘት ቻለ። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" ቶኒ እንደሚለው "መጓዝን እንድመርጥ ካደረጉኝ ምክንያቶች መካከል አንዱ ሽሽት ነው። በውስጤ ካለው ስሜት ለመሸሽ የማደርገው ነበር" ይላል። ወደ አዳዲስ ቦታዎች መጓዙ ለቶኒ አብዝቶ የሚፈልገውን የስሜት መነቃቃትን እንዲያገኝ አስችሎታል። "የተለያዩ ሰዎችን ማግኘት ስጀምር፤ ዓይነ ስውር ስለሆንኩ ሳይሆን በሰብዕናዬ ምክንያት አብረውኝ መሆን እንደሚፈልጉ ለማወቅ ችያለሁ።" የታቀደ ጉዞ ጉዞውን ሲያደርግ ወጪውን ቆጥቦ ነው። ለመጓጓዣም የህዝብ ትራንስፖርትን ሲጠቀም መኝታም አዲስ አበባ ውስጥ እንዳደረገው ቅንጡ ያልሆኑ ነገር ግን መሰረታዊ አገልግሎት ያላቸው ቦታዎችን ይመርጣል። ያስተናገደው ግለሰብም ቶማስ ከአካባቢው ገበያ ገዝቶ ባመጣለት ነገር ምግብ ለማዘጋጅት እጅጉን ፈቃደኛ ነበር። "በዙሪያዬ ያለውን ነገር እስማለሁ፣ አሸታለሁ እንዲሁም እዳስሳለሁ" ይላል። ቁሶችን መንካትና መዳሰስ የሚወደው ቶማስ ከሰዎች ጋር ሲያወራና የሚሉትን ሲያዳምጥ በአእምሮው ውስጥ ስለነገሮች ምስል ለመፍጠር እንደሚያስችለው ይናገራል። አዲስ አበባ ውስጥም የጥበብ ኤግዚቢሽን ወደ ሚታይበት ቦታ ሄዶ የቀረቡትን ስዕሎች በእጁ እንዲዳስስ ተፈቅዶለት ነበር። በዚህም ከሌሎቹ ሙዚሞች በተለየ ለእሱ ፍላጎት ምላሽ በማግኘቱ ከሌሎቹ እኩል ቦታ እንደተሰጠው ተሰምቶታል። ቶኒ ኢትዮጵያ ውስጥ በጉዞ ላይ መጥፋት ብዙ ጊዜ ሌሎች ከሄዱበት መንገድ ውጪ ለመጓዝ ይደፍራል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሳለ ቱሪስቶች ብዙም ወደ ማይሄዱበት አንድ ሐይቅ በመሄድ በውሃው ላይ ላሉት አእዋፋት አሳ እየወረወደ ሲመግብ እንደነበር እናገራል። ቶኒ በጉዞው ላይ አንዳንድ ጊዜ የሚመራው ሰው የሚቀጥር ሲሆን በአብዛኛው ግን ጉዞውን የሚያደርገው ብቻውን ነው። በዚህም በጉዞው ላይ መጥፋት አጋጣሚዎች እንደነበሩት ይናገራል። • በዓይነ ስውሯ የተሠራው የሚያይ ሻንጣ ነገር ግን በመንገድ ላይ ሲጠፋ ብዙም አይሸበርም። በእርጋታ በመንገዱ የሚያልፉ ሰዎችን ጠብቆ እንዲረዱት ይጠይቃል። "አስር አልፈው የሚሄዱ ሰዎችን ልታገኝ ትችላለህ፤ ከመካከላቸውም አንዱ ቆም ብሎ 'መንገድ ጠፍቶህ ነው? እርዳታ ትፈልጋለህ?' ብሎ ይጠይቅሃል። ቶኒ እንደሚለው በጉዞው ላይ ያገኛቸው የማያውቃቸው ሰዎች ወደ ቤታቸው ወስደው ምግብ እንደጋበዙትና በመንገዱም ላይ እንደረዱት ይናገራል። የማያውቁት ላይ እምነት መጣል ወደ ተለያዩ ሃገራት ባደረገው ጉዞ ወቅት ገንዘብ ከማሽኖች ማውጣትና የተለያዩ የገንዘብ ኖቶችን መለየትና በአግባቡ ማውጣት ትልቁ ፈተናው ነበር። "ለዚህ አንድ የማምነው ሰው ማግኘት አለብኝ። ለዚህ ደግሞ ስለሰዎቹ ማጣራት ነበረብኝ። ታሪካቸውንም እጠይቃለሁ" ይላል። ስለሰዎቹ የሰማው ነገር እምነት እንዲጥልባቸው ካደረገው ከማያውቀው ሰው ጋር ወደ ኤቲኤም ማሽኖች በመሄድ ገንዘብ ያወጣል። "ገንዘቡን ካወጣሁ በኋላም አብረውኝ ያሉትን ሰዎች ገንዘቦቹ ምን ምን ያህል መጠን እንዳላቸው እጠይቃቸዋለሁ።" ሙዚቃ ቶኒ በሚያደርጋቸው ጉዞዎቹ ሁሉ የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለመጫወት ሙከራ ያደርጋል። "ከማፈቅራቸው ነገሮች መካከል አንዱ ሙዚቃ ነው። እራሴን ከሙዚቃ ጋር ማጣታም እችላለሁ። ምቶቹን በደንብ እረዳቸዋለሁ። ሙዚቃ ሁሉንም ድንበር ይሻገራል።" የሰዎች ጥያቄ ቶኒ ባደረጋቸው ጉዞዎች ውስጥ በርካታ ድንቅ ገጽታ ያላቸውን ቦታዎች ጎብኝቷል፤ ፎቶግራፎችንም አንስቷል። ፎቶዎቹን አይቶ ሊደሰትባቸው ባይችልም በእራሱ ድረ ገጽ ላይ እንዲወጡ በማድረግ ሌሎች አይተውት እንዲደሰቱበት ያደርጋል። ቶኒ በጉዞው አንዳንድ ጊዜ እርሱ ለጉብኝት ባለው ጥልቅ ፍቅር ግራ የሚጋቡ ሰዎች ያጋጥሙታል። "ዓይነ ስውር ሰው ስለምን ዓለምን ለመጎብኘት ይፈልጋል?" ሲሉ ይጠይቃሉ። እርሱም ቀላል ምላሽ አለው። "መልሱም፤ ለምን አይፈልግም?" የሚል ነው ይላል።
news-56201583
https://www.bbc.com/amharic/news-56201583
ትግራይ ፡ የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም ከተማ ከ200 በላይ ሰዎች መግደላቸውን አምነስቲ ገለጸ
በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች በኅዳር ወር በሁለት ቀናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደላቸውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት አመለከተ።
በኅዳር 19 እና 20/2013 ዓ.ም የተፈጸመው የጅምላ ግድያ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን እንደሚችል ሪፖርቱ ገልጿል። አንድ የዓይን ምስክር ለቢቢሲ እንደገለጹት በከተማዋ በተፈጸመው ግድያ በየመንገዱ አስከሬኖች ለቀናት ሳይነሱ መቆየታቸውን ገልጸው በርካቶቹ በጅብ መበላታቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያና ኤርትራ ትግራይ ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች መግባታቸውን በይፋ ያስተባበሉ ሲሆን በአምነስቲ ሪፖርት ላይ የሰጡት ምላሽ የለም። ትግራይ ውስጥ የሚገኘውን የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት የሠሜን ዕዝ ላይ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ነበር ጥቅም 24/2013 ዓ.ም ወታደራዊ ግጭቱ የተቀሰቀሰው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለአገሪቱ ፓርላማ በዚህ ዘመቻም አንድም ሰላማዊ ዜጋ እንዳልተገደለ ቢገልጹም፤ አብዛኞቹ ያልታጠቁ ልጆችና ወንዶችን በጉዳና ላይ ወይም ቤት ለቤት በተደረጉ አሰሳዎች በኤርትራ ወታደሮች የተገደሉ ሰዎችን ስለመቅበራቸው የዓይን እማኞች ገልጸዋል። የአምነስቲ ሪፖርት በጥንታዊቷና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ስፍራ በሆነችው አክሱም ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቤተክርስቲያናት ውስጥ የቀብር ቦታዎችን የያዙ የተቆፈሩ ስፍራዎችን የሚያመለክቱ ከፍተኛ የምስል ጥራት ያላቸው የሳተላይት ምስሎችን አካቷል። የኮምዩኒኬሽን መስመሮች መቋረጥና ወደ ትግራይ ለመግባት አለመቻል በግጭቱ ወቅት ስለተከሰቱ ጉዳዮች በወቅቱ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። በአክሱም የነበረው የኤሌክትሪክና የስልክ አገልግሎት ግጭቱ በጀመረ በመጀመሪያው ዕለት ተቋርጦ ነበር። ከሪፖርቱ ጋር በተያያዘ ይህንን የአምነስቲን ሪፖርት በተመለከተ መንግሥታዊው የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳለው ምንም እንኳን ያልተጠናቀቀ ቢሆንም በአክሱሙ ክስተት ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል። የኮሚሽኑ የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቱ ጥቂት ነዋሪዎችና የህወሓት ታጣቂዎች ለፈጸሙባቸው ጥቃት የኤርትራ ወታደሮች በወሰዱት የበቀል እርምጃ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰላማዊ ሰዎች በከተማዋ ውስጥ ተገድለዋል ሲል አመልክቷል። ኮሚሽኑ ጥቃቱ በኤርትራ ወታደሮች የተፈጸመው የህወሓት ወታደሮች አካባቢውን ለቀው ከወጡ በኋላ መሆኑንም ገልጿል። በተማሪም በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ተፈጽመዋል ስለተባሉ በርካታ የከባድ መሳሪያ ድብደባዎች ምርመራዎችን እያካሄድኩ ነው ብሏል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአክሱም ከተማ ተፈጽሟል ያለውን ይህንን የሰብአዊ መብት ጥሰት የምርመራ ውጤት የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርና የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይል ቃል አቀባይ ለሆኑት ለአምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ማቅረቡንና በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዳላገኘ በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል። ቢቢሲም ይህንን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከተመለከተ በኋላ ከኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ በኢሜይል ጥያቄ ቢያቀርብም ለጊዜው ምላሽ አላገኘም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ረቡዕ ለተካሄደው በ46ኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አገራቸው አሉ በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ አስፈላጊውን ማጣራት እንደምታደርግ ገልጸዋል። አቶ ደመቀ በንግግራቸውም ወሲባዊ ጥቃትን ጨምሮ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የመንግሥታቸው ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች እንደሆኑ አመልክተው "በዚህ ዙሪያ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ የድርጊቶቹን ፈጻሚዎች ተጠያቂ እንዲሁኑ ለማድረግ ቁርጠኛ ነን" ሲሉ ተናግረዋል። አክሱም ከተማ። አምነስቲ በሪፖርቱ ከግድያው ባሻገር ሰፊ ዝርፊያ በኤርትራ ወታደሮች ተፈጽሟል ብሏል። አክሱም እንዴት ተያዘች? በምዕራባዊው የአክሱም ክፍል ላይ በኢትዮጵያና በኤርትራ ኃይሎች የከባድ ድብደባ የተጀመረው ኅዳር 10/2013 ዓ.ም እንደነበረ የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። "ይህ ጥቃትም ያለማቋረጥ ለአምስት ሰዓታት ቀጥሏል። በወቅቱ በቤተክርስቲያናት፣ በካፍቴሪያዎች፣ በሆቴሎችና በመኖሪያ ቤታቸው የነበሩ ሰዎች ሞተዋል። ለጥቃቱ በከተማው ከነበረ የታጠቀ ኃይል የተሰጠ ምላሽ አልነበረም፤ ጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ ነበር" ሲሉ አንድ በከተማው ያሉ የመንግሥት ሠራተኛ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ ጋር የሚመሳሰሉና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ተከታታይ የከባድ መሳሪያ ድብደባን በተመለከተ አምነስቲ ኢንትርናሽናልም የበርካታ ሰዎችን ምስክርነት አሰባስቧል። ከተማዋ በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላም የኤርትራ እንደሆኑ የተገለጹ ወታደሮች የህወሓት ወታደሮች ወይም "መሳሪያ የታጠቃ" ምንኛውንም ሰው ለማግኘት ፍለጋ አካሂደዋል ይላል የአምነስቲ ሪፖርት። "ቤት ለቤት በመሄድ በርካታ ግድያዎች ተፈጽመዋል" ስትል አንዲት ሴት ለሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገልጻለች። የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች "አክሱምን ለመቆጣጠር ባካሄዱት ጥቃት በርካታ የጦር ወንጀሎች መፈጸማቸውን" የሚያመለክት መስረጃ አለ ሲሉ የአምነስቲ ኢንትርናሽናል ባለስልጣን ዴፕሮስ ሙቼና ተናግረዋል። ለግድያው ምክንያቱ ምንድን ነው? የዓይን እማኞች እንዳሉት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ወታደሮች አክሱም ውስጥ ነበሩ፤ የኤርትራ ወታደሮች ደግሞ ወደ አድዋ ከተማ ሄደው ነበር። አንድ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ እንደተናገረው የኢትዮጵያ ወታደሮች ባንኮችን ሲዘርፉ መመልከቱን ገልጿል። አምነስቲ እንደሚለው ከአንድ ሳምንት በኋላ የኤርትራ ወታደሮች ተመልሰው በመጡበት ጊዜ በደንብ ያልታጠቁ የህወሓት ተዋጊዎች በፈጸሙት ጥቃት ውጊያ ተቀስቅሷል። በዚህም ከ50 አስከ 80 የሚደርሱ አክሱም ውስጥ የነበሩ ታጣቂዎች በከተማዋ አቅራቢያ ባለ ኮረብታ ላይ በሰፈሩ የኤርታራ ወታደሮች ላይ ነበር ጥቃት የፈጸሙት። በጥቃቱ ላይ የተሳተፈ አንድ 26 ዓመት ወጣት ለአምነስቲ እንደተናገረው "ከተማችንን በተለይ ከኤርትራ ወታደሮች ለመከላከል ፈልገን ነበር... እነሱ እንዴት እንደሚተኮስ ያውቃሉ የግንኙነት ሬዲዮም አላቸው... እኔ መሳሪያ አልነበረኝም ዱላ ብቻ ነበር የያዝኩት" ብሏል። ውጊያው ለምን ያህል ጊዜ እንደቆየ ግልጽ ባይሆንም ከሰዓት በኋላ የኤርትራ የጭነት መኪኖችና ታንኮች ወደ አክሱም ከተማ መግባታቸውን የአምነስቲ ሪፖርት ያመለክታል። የዓይን እማኞች እንዳሉት የኤርትራ ወታደሮች ያገኙትን ማጥቃት ጀመሩ፤ ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎችንና በጉዳና ላይ ያገኟቸውን ወንድ ልጆችን በጥይት እየመቱ እስከ ምሽት ድረስ ቀጠሉ። በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ አንድ ግለሰብ በከተማዋ መንገዶች ላይ ስለተፈጸሙት ግድያዎች ለአምነስቲ እንደተናገረው "በአንድ ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ሆኜ በመስኮት በኩል የኤርትራ ወታደሮች ወጣቶችን በጎዳና ላይ ሲገድሉ አይቻለሁ" ብሏል። ወታደሮቹ የኤርትራ መሆናቸው የተለየው በለበሱት የደንብ ልብስ ወይም በመኪኖቻቸው የሰሌዳ ቁጥር ብቻ አልነበረም። ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሳ ወቅት በሚናገሩት የአረብኛ ቋንቋና የትግረኛ ዘዬ ነበር። ግድያው "የበቀል እርምጃ ነው እላለሁ" ሲል አንድ ወጣት ለቢቢሲ ተናግሯል። "ያገኙትን ሰው ሁሉ ገድለዋል። በር ተከፍቶ ወንድ ካገኙ ይገድላሉ፤ በር ካልተከፈተላቸው በር ላይ ይተኩሳሉ" ብሏል። በአንድ የምሽት ክለብ ውስጥ ተደብቆ በነበረበት ጊዜ የኤርትራ ወታደሮች አንድ ግለሰብን አግኝተው ሲገድሉት መመልከቱን የሚናገረው ግለሰብ "ሰላማዊ ሰው ነኝ፤ የባንክ ሠራተኛ ነኝ' እያለ ሲለምናቸው ነበር" ሲል ተናግሯል። ሌላ ግለሰብ ደግሞ ኅዳር 20 አብነት ሆቴል አቅራቢያ ከሚገኘው ቤቱ ውጪ ስድስት ሰዎች ርሸና በሚመስል ሁኔታ ሲገደሉ መመልከቱን ለአምነስቲ ገልጿል። "በአንድ መስመር እንዲቆሙ አድርገው ከጀርባቸው ነበር የተኮሱባቸው። ሁለቱን አውቃቸዋልሁ። የእኔ ሰፈር ነዋሪዎች ናቸው… 'መሳሪያችሁ የታለ' እያሉ ሲጠይቋቸው 'እኛ ሰላማዊ ሰዎች ነን መሳሪያ የለንም' በማለት ሲመልሱላቸው ነበር።" የቀብር ሥርዓቱ ከተፈጸምባቸው ቤተ ክርስትያናት አንዷ የሆነችው አርባአቱ እንሰሳ ቤተ-ክርስተያን ስንት ሰዎች ተገደሉ? የዓይን እማኞች እንደሚሉት መጀመሪያ አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች በመንገዶች ላይ ወደ ወደቁት አስከሬኖች ማንም እንዳይቀርብ ከልክለው ነበር፤ ለመቀረብ የሚሞክሩት ላይ ይተኩሱ ነበር። የ29 እና የ14 ዓመት የቅርብ ዘመዶቿ የተገደሉባት አንዲት ሴት "መንገዶች በአስከሬን ተሞልተው ነበር" ስትል ተናግራለች። አምነስቲ እንዳለው የአካባቢው ሽማግሌዎችና የኢትዮጵያ ወታደሮች ጣልቃ ከገቡ በኋላ የተገደሉትን ሰዎች ለቀናት መቅበር ተጀመረ። ነዋሪዎች በአንድ ጊዜ አስከ 10 የሚደርሱ አስከሬኖችን በፈረስና በአህያ በሚጎተቱ ጋሪዎች በመጫን እያመላለሱ የበርካታ ሰዎች ቀብር የተፈጸመው ኅዳር 21 ነበር። የመንግሥት ሠራተኛ የሆነው አንድ የዓይን እማኝ ለቢቢሲ እንደተናገረው በአብነት ሆቴል የነበሩ አስከሬኖች አስከ አራት ቀናት ድረስ ሳይነሱ ቆይተዋል። "አብነት ሆቴልና ሲያትል ሲኒማ አካባቢ ወድቀው የነበሩ አስከሬኖች በጅብ ተበልተው አጥንት ብቻ ነበር ያገኘነው። አጥንት ነው የቀበርነው። "አክሱም ውስጥ 800 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል ብዬ መነገር እችላለሁ።" ይህንን ምስክርነት ለአሶሺየትድ ፕሬስ የተናገረ አንድ ዲያቆንም የሚጋራው ሲሆን፤ በርካታ አስከሬኖች በጅብ መበላታቸውን ተናግሯል። ዲያቆኑ የሟቾችን የመታወቂያ ወረቀት የሰበሰበ መሆኑንና በጅምላ ሲቀበሩም እንዳገዘ ይናገራል። ጥቃቱ በተፈጸመባቸው ቀናት 800 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለዋል ብሎ እንደሚያምን ገልጿል። አምነስቲ ያናገራቸው 41 ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች የተገደሉ ናቸው ያሏቸውን ከ200 በላይ ሰዎች ስም ሰጥተዋል። ከቀብር በኋላ ምን ተፈጠረ? የዓይን እማኞች እንዳሉት ከግድያው በኋላ በርካታ ሰዎች ከተማዋን ለቀው በመሄዳቸው የኤርትራ ወታደሮች በስፋትና ዘዴ በተሞላበት መንገድ ዝርፊያ ፈጽመዋል። ዩኒቨርስቲ፣ የግል መኖሪያ ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የእህል መጋዘኖች፣ ጋራዦች፣ ባንኮች፣ መደብሮች፣ ዳቦ ቤቶች ሌሎች ሱቆች የዝርፊያ ኢላማ ነበሩ ተብሏል። አንድ የወንድሙ ቤት የተዘረፈበት ግለሰብ የኢትዮጵያ ወታደሮች በኤርትራ ወታደሮች የተፈጸመውን ዝርፊያ እንዴት ማስቆም እንዳልቻሉ ለአምነስቲ ተናግሯል። "ቴሌቪዥን፣ መኪና፣ ፍሪጅ፣ ስድስት ፍራሾች፣ የምግብ ሸቀጦችና ዘይት፣ የጤፍ ዱቄት፣ የማዕድ ቤት መደርደሪያ፣ ልብሶች፣ ፍሪጅ ውስጥ የነበረ ቢራ፣ የውሃ ፓምፕና ላፕቶብ ወስደዋል" ብሏል። አንድ የከተማዋ ወጣት ለቢቢሲ እንደተናገረው በከተማዋ ያሉ ነጋዴዎች ንብረት የሆኑ 15 መኪኖች እንደተወሰዱ አውቃለሁ ብሏል። ይህም የአክሱም ከተማን ለቀው የሄዱ ሰዎችን በህይወት ለመቆየት የሚያስችል የምግብና የመድኃኒት አቅርቦት በማሳጣት ለከባድ ችግር ዳርጓቸዋል ሲል አምነስቲ ገልጿል። በውሃ መሳቢያ ፓምፖች ላይ የተፈጸመው ዝርፊያ ነዋሪዎች የወንዝ ውሃን ለመጠጥነት እንዲጠቀሙ እንዳስገደዳቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል። አክሱም ታሪካዊቷ የአክሱም ከተማ ከጥንታዊዎቹ ሐውልቶች ባሻገር መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ለሙሴ የተሰጠውን አስርቱን ትዕዛዛት እንደያዘ የሚታመነው የቃል ኪዳን ታቦት የሚገኝባት የአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ይገኝባታል። በዚህም አክሱም ከመላው ኢትዮጵያና ከዓለም ዙሪያ ተሰባሰቡ በርካታ ቁጥር ያላቸው የዕምነቱ ተከታዮች የሚታደሙበት ሐይማኖታዊ በዓል በየዓመቱ ኅዳር 21 ይካሄድ ነበር። በክልሉ ውስጥ በነበረው ግጭት የተነሳም በዚህ ዓመት በዓሉ በተለመደው ሁኔታ ሳይካሄድ ቀርቷል። በአክሱም ከተማ የመንግሥት ሠራተኛ አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ እንደተናገረው የኤርትራ ወታደሮች ኅዳር 24 ወደ ቤተክርስቲያኗ በመሄድ "ቄሶችን በማስፈራራት ከወርቅና ከብር የተሰሩ መስቀሎችን እንዲሰጧቸው አስገድዷቸው ነበር።" ነገር ግን ዲያቆኖችና ሌሎች ወጣቶች የቃል ኪዳን ታቦቱን ለመከላከል ወደ ቤተክርስቲያኑ ሄደው ነበር ብሏል። "ከፍተኛ ብጥብጥ ነበር የተፈጠረው። ወንዱም ሴቱም ተቃውሟቸዋል። እነሱም ተኩሰው ጥቂቶችን የገደሉ ቢሆንም ቅርሶቻችንን ለማስጣል በመቻላችን ደስተኞች ነን።" የኤርትራ ወታደሮች የተለያዩ አገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ግጭት መሳተፋቸው የተጠቀሰ ቢሆን ይህንን ኢትዮጵያም ሆነ ኤርትራ መንግሥታት ማስተባበላቸው ይታወሳል። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የአገሪቱ ሠራዊት ትልቁ ክፍል በሆነው የሠሜን ዕዝ ላይ በህወሓት ኃይሎች ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ሕግ የማስከበር ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን በመግለጽ በዚህም የኤርትራ ጦር አለመሳተፉን ሲያስተባብል ቆይቷል። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን ቢገልጽም በአንዳንድ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች እንዳሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
news-44924335
https://www.bbc.com/amharic/news-44924335
ይህ የአፍሪካ ዋነኛው የፈጠራ አካባቢ ይሆን?
በርናንድ ኪዊያ ከብስክሌት እጅግ ብዙ ነገር መስራት ይችላል።
በርናርድ ኪዊያ የታንዛንያው የፈጠራ ትምህርት ቤት ትዌንዴ መስራች ነው መጀመሪያ የታወቀው በብስክሌት የሚሰራ የተንቀሳቃሽ ስልክ ባትሪ መሙያ (ቻርጀር) በመፍጠር ነው። በርናንድ ከብስክሌት መለዋወጫ እቃዎች በርካታ ተጨማሪ ነገሮችን መስራት እንደሚችል በኋላ ላይ ቢገነዘብም ሥራ የጀመረው የብስክሌት መካኒክ ሆኖ ነው። "አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የምፈጥረው ቤተሰቤን እና ማህበረሰቡን የሚጠቅም ነገር መሆኑን ስለምገነዘብ ነው" ይላል በርናንድ፡፡ ነገር ግን ብስክሌቶች ብቻ አይደለም። የቻይና ግዙፍ ማሽኖች የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ ሊውል ነው የእርሱ የፈጠራ ውጤት የሆነውና በንፋስ ኃይል የሚሰራው የልብስ ማጠቢያ ማሽን የቤተሰቡን አልባሳት ንፋስ በሚበረታበት ጊዜ በአንዴ ስለሚያጥብላቸው ልፋትና ጊዜያቸውን ቆጥቦላቸዋል። የበርናንድ ፈጠራ አሁን ከራሱ ቤትና ጓሮ አልፎ ለማህበረሰቡ ተዳርሷል። ትዌንዴ የተባለውን እና እርሱ የጀመረውን የፈጠራ ሰርቶ ማሳያ 800 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው የፈጠራ ሰዎች ተጠቅመውበታል። በታንዛንያ "የገጠር የፈጠራ ውጤት አባት" እየተባለም ይጠራል። "ለሰዎች ማሳየት የፈለገነው ሁሉም ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ራሳቸው ሊጠግኑት የሚችሉት እና የሚፈልጉትን መለዋወጫ ሊያገኙለት የሚችል የራሳቸውን ቴክኖሎጂ ለመፍጠር ክህሎቱ እንዳላቸው ነው" ይላል ብርናንድ። "የሀገሬው ሰዎች ሁሌም ገቢያቸው ትንሽ ሲሆን በየሱቆቹ የሚሸጡት መሳሪያዎች ደግሞ ውድ በመሆናቸው ለእነዚህ ሰዎች አይሆኑም። ለዚያም ነው በአካባቢዬ በማገኛቸው ነገሮች ላይ ያተኮርኩት።" ፍራንክ ሞሌል ማዳበሪያ ከሚያሰራጭበት ጋሪ ጋር ማዳበሪያን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ፈጠራ ፈራንክ ሞሌል ከአካባቢው የፈጠራ ሰዎች አንዱ ሲሆን ማዳበሪያ እና ከከብቶች የሚወጣን ፍግ በእጅ ለመበተን የሚወስደውን ጊዜ ለማሳጠር የሚረዳውን የተሻሻለ ጋሪ 'ፈርት ካርት'ን ፈጥሯል። የፍራንክ የፈጠራ ሃሳብ ተሻሽሎ የተሰራውን ጋሪ ለመግዛት በቂ መሬት እና ገቢ ለሌላቸው አርሶ አደሮች ማከራየትን ይጨምራል። ትዌንዴ በሰርቶ ማሳያቸው ውስጥ ያሉ ሁሉ ጥሩ የንግድ ልምዶችን መቅሰማቸውን እና የንግድ እቅድ ማዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል። ከደንበኛቹ መካከል አንዱ ይህን መሳሪያ መጠቀሙ ለልጆቹ የትምህርት ቤት የመክፈል አቅምን እንደፈጠረለት ይናገራል። ሬሳን ከሞት አስነሳለሁ ያለው 'ነብይ' የሟች ቤተሰብን እንዴት አሳመነ? "ተሻሽሎ የተሰራው ጋሪ 'ፈርት ካርት' በእርሻ ተግባራት የሚጠፋውን በቢሊዮን የሚቆጠር ሰዓት ቀንሶታል" ይላል ፍራንክ። "አፍሪካ በተለይ ደግሞ በታንዛኒያ አርሶ አደሮች ምርታማነታቸው እንዲጨምር እና አነስተኛ እርሻ ያላቸው ገበሬዎች ገቢያቸው እንዲያድግ የሚረዳቸውን ይህን ድንቅ ቴክኖሎጂ ትፈልገዋለች።" የጄሲ ኦሊጃንጌ የአቮካዶ ዘይት መጭመቂያ በትዌንዴ ሰርቶ ማሳያ ለስድስተኛ ጊዜ እየተሰራ ነው አረንጓዴ ወርቅ የጄሲ ኦሊጃንጌ አቦካዶ መጭመቂያ የማበረሰቡን ህይወት እየቀየረው ነው። "ትዌንዴ እራሱ ማህበራዊ የፈጠራ ግኝት ነው" ይላል ጄሲ። "በአንድ ክፍል ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ ሰዎች አሉ። እናም ችግር ቢገጥምህ ከመካከላቸው አንዱን በመጠየቅ መፍትሄውን ታገኛለህ።" አርሶ አደሮቹ በገበያው ላይ የተሻለ ዋጋ ስለማያገኙ ዘይቱ ከመጨመቁ በፊት አቦካዶዎች በረገፉበት ቦታ ይበሰብሱ ነበር። አሁን በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ሴቶች አቦካዶውን የሚሸጡትን ዘይት ለማውጣት ይጠቀሙበታል፡፡ ጄሲ እንደሚለው ትዌንዴ ውስጥ መሳተፉ ሰርቶ ማሳያውን እንደ እናት ድርጅት በመጠቀም የገንዘብ ድጋፍ ለመጠየቅም አስችሎታል። የገንዘብ ድጋፍ እና የመንቀሳቀሻ ገንዘብ ማግኘት እንደ ጄሲ ላሉ የአካባቢው የፈጠራ ሰዎች ሁለቱ ተግዳሮቶች ናቸው። በአብዛኛዎቹ በርናርድን የመሳሰሉ የሚያግዟቸው አማካሪዎች አሏቸው። "ችግር ካጋጠመህ ጭንቅላትህ ሊዞር አይገባም ለበርናርድ ትነግረዋለህ። ለሁለት ደቂቃዎች ያህል አስቦ በዚህ መንገድ ሥራው ይልሃል። እኛም ብዙ የምናማክረው አለን" ይላል ጄሲ። የማግሬት ኦማሬ የሳሙና መቁረጫ ግኝት የብዙዎችን ሰዎች እጣ ፈንታ ቀይሮታል የሳሙና እገዛ የማገሬት ህይወት ትዌንዴ ሰርቶ ማሳያ ውስጥ በፈጠረችው የሳሙና መቁረጫ ማሽን ምክንያት ተቀይሯል። የእራሷን የሳሙና ንግድ እንድትጀመር ከማስቻሉም ባሻገር ማሽኗን በከተማው ውስጥ ላሉ ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች በማጋራት ገቢ እንዲያገኙ ታደርጋለች። "ልጆቼ ከዚህ በኋላ በክፍያ እጦት ምክንያት ከትምህርት ቤት ስለማይባረሩ ደስተኛ ነኝ" ትላለች። ቀላል የፈጠራ ውጤት የብዙዎችን ህይወት እንዴት ሊቀየር እንደሚችል አስረጂ ነው። በርናርድ ኪዊያ በአካባቢው የሚገኙ ትምህርትቤቶችን በማዳረስ አዲስ የፈጠራ ትውልድ ለማፍራት ተስፋ ያደርጋል ምን ትምህርት ተቀሰሙ "የወደፊት ህልሜ ታንዛንያዊያን በዘወትር እንቅስቃሴዎቻችን የምንጠቀምባቸው የራሳችን ምርቶች ኖረውን ማየት ነው" ይላል በርናርድ። ይህ እንዲሆንም በአካባቢው ከሚገኙ ትምህርትቤቶች ልጆችን ወደ ትዌንዴ በመጋበዝ ለምርጥ የፈጠራ ውጤቶች እንዲበረታቱ ያደርጋል። ሰርቶ ማሳያው ልጆቹ መስሪያ እቃዎችን ይዘውም ሆነ ለስልጠና ወደ ገጠራማ መንደሮች የሚሄዱበት አነስተኛ መኪና አለው። "ትዌንዴ ውስጥ ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ የፈጠራ ሥራዎች እንሰራለን። በመሆኑም ማህበረሰቡን የሚፈታተኑ ተግዳሮቶችን በማየት እሱኑ ለመወጣት ጥረት በማድረግ ችግሩን እንፈታለን" ይላል ተማሪው ላይትነስ ሲምኦን ኪኒሳ። ብየዳን ለመሳሰሉ ትምህርቶች እንደሚያደርገው የተግባር ልምምድ ሁሉ በትዌንዴ ትምህርት ቤት አነስተኛ ንግድን እንዴት ማስኬድ እንደሚቻል እና የበጀት ዝግጅትን የተመለከቱ ሰርቶ ማሳያዎችም አሉ። "በርናርድ ኪዊያ በጣም የተለየ ሰው ነው" ይላል ከታንዛኒያዊን የፈጠራ ሰዎች እና ቴክኖሎጂ አመንጪዎች ማህበር የመጣው ኢሳ ካንጉኒ። እሱ እንደሚለው "በአፍሪካ ወይም በታንዛኒያ የፈጠራ ሰው መሆን በጣም ከባድ ነው። ምክንያቱም የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሰዎች የሚተገብሩበት ሀብት የላቸውም።" በርናንድ ኪዊያ በትዌንዴ ሀብትን በመጋራት ማህበረሰቡ ለራሱም ሆነ ከእነሱ ውጪ ላለው ዓለም መፍትሄ የሚሆን አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብ ማመንጨቱን እንዲቀጥል ለማነቃቃት ተስፋ ያደርጋል። "አንዳንድ ጊዜ ላይሳካልህ ይችላል፤ ስለዚህ እንደገና ትሰራዋለህ ይላል በርናርድ። አንዳንድ ጊዜ በድጋሚም ላይሳካልህ ይችላል፤ አሁንም እንደገና ትሰራዋለህ። ነገር ግን በመጨረሻ ጥሩ ነገር ላይ ትደርሳለህ።"