doc_no
int64
1
12.6k
doc_text
stringlengths
81
395k
relevant_topic_nos
sequencelengths
0
1
relevant_topic_titles
sequencelengths
0
1
relevant_topic_descriptions
sequencelengths
0
1
relevant_topic_narratives
sequencelengths
0
1
301
የአርብቶ አደሩ በመንደር መሰባሰብ የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ አስችሎታል, - ; .._2015_26. 0 261 145 ; 5; አዲስ አበባ ፣ ጥር 182007 (ዋኢማ) - አርብቶ አደሩን በመንደር የማሰባሰቡ ፕሮግራም በስኬት ለማጠናቀቅ ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሃይለ ማርያም ደሳለኝ አሳሳቡ፡፡ - ; 15ኛ የአርብቶ አደሮች ቀን በዓል የአርብቶ አደሩ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለህዳሴያችን በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትላንት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተከብሯል፡፡ - ; ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ ሃይለማያም ደሳለኝ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር  አርብቶ አደሩን በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተደረጉት ጥረቶች ውጤታማ ሰራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ - ; መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች የሚከተለው የልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ የዉሃና እንስስት ሃብትን መሰረት በማድረግ በየክልሎቹ አቅም የሚሰሩት እንደተጠበቁ ሆነው በፌዴራልና በአጎራባች ክልሎች ትብብር የሚከናወኑ  የተፋሰስ ልማትና በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የመንደር ማሰባሰብ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ - ; ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በአፋርና በሱማሌ ክልሎች የምዕተ አመቱን የልማት ግብና የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ግቦችን  የሚያሳኩ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡ - ; በተጨማሪም አርብቶ አደር በሚገኝባቸው የደቡብና የኦሮሚያ አካባቢዎች ጭምር ውጤታማ የልማት ስራዎች  መከናወናቸውን አመልክተዋል፡፡ - ; ይሁንና አርብቶ አደሩን በመንደር  የማሰባሰብ ተግባር ያላስደሰታቸው  አንዳንድ የወስጥና የውጭ ሃይሎች  ከመንግስት በላይ ለህዝብ የተቆረቆሩ በመምሰል ልማቱን ለማደናቀፍ ቢጥሩም  እናንተ አርብቶ አደሮቹ በሰራችሁት ስራና በተገኘው ውጤት ተራ አሉባልታና መሰረተ ቢስ መሆኑን ለማረጋገጥ ችላችዋል ብለዋል፡፡ - ; የመንደር ማስባሰቡ ፕሮግራም ተጠናክሮ በመቀጠል አርብቶ አደሩ የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ እንዳስቻለውም  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ - ; በአርብቶ አደር አካባቢ የተመዘገቡት የልማት ዉጤቶችና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት በተለይ አርብቶ አደሩን በመንደር የማሰባሰቡ ፕሮግራም በስኬት ለማጠናቀቅ  ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ - ; የፌዴራል መንግስት አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሰፊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በማካሄድ የአርብቶ አደሮች አካባቢን ልማት እያቀላጠፈ ይገኛል ብለዋል የአርብቶ አደር አከካባቢዎች መዳረሻና ከአጎራባች ክልሎች ጋር ሊያስተሳስሩ የሚችሉ የመንገድ ፣ የስልክ ፣ የኤሌክትሪክና አዉሮፕላን ማረፊያ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውንም ገለጸዋል፡፡ - ; በልማቱም አካባቢዎቹ የኢንቨስትመንትና ቱሪስት መዳረሻ መሆናቸውን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ሀገሪቱ የእኩል ተጠቃሚነት መርህ የምትከተልና ሁሉም ህዝቦች የህዳሴዉ ጉዞ አካል መሆናቸውን እንደሚያሳይ አብራርተዋል፡፡ - ; የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር  አቶ እስማኤል ኢሊሴሮ በበኩላቸው መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዋና የኑሮ መሰረቱ በሆነው የእንስሳት ሃብቱ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን በርካታ ስራዎች ማከናወኑን  ገልጸዋል፡፡ - ; የተጀመረዉ የተፋሰስ ልማትና በመንደር ማሰባሰብ ፕሮግራም አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ በማድረግ  የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ ምቹ ሁኔታ የፈጠረለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ - ; ባለፉት 3 አመታት ዉስጥ በክልሉ16 ሺህ አርብቶ አደሮች በመንደር ተሰባሰቡ የልማቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጠይነትም ህብረተሰቡን በመንደር የማሰባሰቡ ስራ ተጠናክሮ እንደሚጠጥል ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት አስርተ አመታት የአፋር ክልል ከምንም ተነስቶ የንጽሁ መጠጥ ውሃ ፣ትምህርት ፣ የጤና አገልግሎቶች ተደራሽ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ - ; በግብርና መስክም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስተናችን ለማረጋገጥ የሚያስችለው አቅም በመገንባት ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ - ; የፌደራል መንግስትና የአጎራባች ክልሎች የልማት ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጠልም ጠይቀዋል - ; በስራቸው የተሻለ ውጤት አስመዝግበው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዳሊያ ሽልማት ከወሰዱት አርብቶ አደሮች መካከል ከኦሮሚያ ክልል የመጡት አቶ ኢብራሂም አሊ ይገኙበታል፡፡ - ; ሽልማቱ ለበለጠ የስራ ውጤት መነሳሳት እንደፈጠረላቸውና በቆይታቸውም  ከተለያዩ ክልሎች ከመጡ  አርብቶ አደሮች ጠቃሚ ልምድ ማግኘታቸውን እኚሁ ተሸላሚ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡ - ; ከአፋር ክልል ተሸላሚ የሆኑት አርብቶ አደር አቶ ሃመዱ ሁመድ በበኩላቸው ያገኙት ሽልማት ለቀጣይ የልማት ሰራቸው ማደግ እንደሚያበረታታቸው ጠቁመው  ሌሎችንም  ለዉጤት ለማብቃት እንደሚጥሩ ተናግረዋል በበዓሉ ላይ የፌዴራል መንግስትና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በውጤታማነታቸው ከየክልሉ የተመረጡ 229 አርብቶ አደሮች ሜዳሊያ ተሸልመዋል፡፡ (ኢዜአ)),
[ 102 ]
[ "አርብቶ አደሮች" ]
[ "በአርብቶ አደሮች ስለተከናወኑ ክንውኖች የሚያመለክቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "በአረሶ አዶሮች አርብቶ አደሮች ህይወት, ላይ ስለተሰሩ ስራወች, ስለተሰሩ ጥናቶች, ስለ ታቀዱ እቅዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ስለአረሶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
302
በጉጂ ዞን ባለፈው ዓመት አንድ ሚሊዮን ለሚሆኑ አርብቶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደሮች የጤና አጠባበቅ ትምህርት መሰጠቱን የዞኑ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱያ ኃላፊ አቶ ጎዳና አሬሮ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ትምሀርቱ የተሰጠው በዞኑ 12 ወረዳዎች የጤና አገልግሎት ባልተዳረሰባቸው አርብቶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደሮች አካባቢዎች ነው፡፡ በግልና በአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ፣ በስነ ተዋልዶና ቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት፣በወባ፣ በኤች አይ ቪ/ኤድስና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች መከላከል ዙሪያ ትምህርቱ የተሰጠው በ500 የጤና ባለሙያዎች አማካኝነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ትምህርቱን የተሰጠወ በዞኑ በሚገኙ ጤና ድርጅቶች፣ በቀበሌ ጽህፈት ቤቶች፣ ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ማህበራዊ ተቋማትና ቤት ለቤት በመዘዋወር እንደሆነ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ በዞኑ በወሊድ ዕድሜ ክልል ለሚገኙ 260 ሺህ ያህል ሴት አርብቶ አደሮች በስነ ተዋልዶ ጤናና በቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመሰጠቱ ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮች እየቀነሱ መምጣታቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ በዞኑ የጤና አገልግሎትን ችግር በሚታይባቸው ወባማ ቀበሌዎች ለሚገኙ አርብቶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደሮች ለማዳረስ በመንግስትና በሕዝብ ትብብር 20 ጤና ኬላዎች መገንባታቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ ትምህርቱ በመሰጠቱ ቀደም ሲል 69 በመቶ የነበረው የዞኑ የጤና አገልግሎት ሽፋን በአሁኑ ወቅት 74 በመቶ መድረሱን አቶ ጎዳና አስታውቀዋል፡፡
[ 102 ]
[ "አርብቶ አደሮች" ]
[ "በአርብቶ አደሮች ስለተከናወኑ ክንውኖች የሚያመለክቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "በአረሶ አዶሮች አርብቶ አደሮች ህይወት, ላይ ስለተሰሩ ስራወች, ስለተሰሩ ጥናቶች, ስለ ታቀዱ እቅዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ስለአረሶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
303
የፈላታ አርብቶ አደሮች በጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑ ተገለጸ ጋምቤላ መጋቢት 17/2010 ድንበር ዘለል አርብቶ አደሮች ወደ ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የቀንድ ከብቶቻቸውን ይዘው በመግባት በፓርኩ የብዝሃ ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን የፓርኩ ጽህፍት ቤት አስታወቀ። የክልሉ የጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ ከአርብቶ አደሮቹ የጎሳ መሪዎች ጋር በመነጋገር ወደ መጡበት አካባቢ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል። በጽህፈት ቤቱ የዱር እንስሳት ኤክስፐርት ወይዘሮ ማሚቱ አበበ ለኢዜአ እንደገለጹት ድንብር ዘለል የፈላታ አርብቶ አደሮች ወደ ፓርኩ ክልል በርካታ የቀንድ ከብቶችን ይዘው በመግባታቸው በፓርኩ የዱር እንስሳት መጠለያ እና ብዝሃ ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው። አርብቶ አደሮቹን ወደ ፓርኩ ይዞታ እንዳይገቡ ለመከለካል ጥረት ቢደረግም ከአቅም በላይ እንደሆነ ነው ወይዘሮ ማሚቱ የተናገሩት። ለክልሉ ጸጥታ አካላትና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በደብዳቤ ማሳወቃቸውንም አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት አርብቶ አደሮች በፓርኩ የዱር እንስሳት መጠለያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸው ምክንያት በአካባቢው የነበሩት የዱር እንስሳት ከአካባቢው መሰደዳቸውንም ወይዘሮ ማሚቱ ገልጸዋል። ''የፈላታ አርብቶ አደሮች ከፍተኛ የግጦሽ እጥረት እየፈጠሩብን ነው፤ በአሁኑ ወቅት ለከብቶቻችን የምናበላው ሳር ጭምር እያጣን ነው'' ያሉት ደግሞ በላሬ ወረዳ የንብንብ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ኦቶል ሎንግ ናቸው። የሚመለከተው አካል ተገቢ ትኩረት ሰጥቶ የፈላታ አርብቶ አደሮችን ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመልስላቸውም ጠይቀዋል። "አርብቶ አደሮቹ በየዓመቱ ወደአካባቢያችን ይመጣሉ፤ ብዙ ከብት ይዘው ስለሚመጡ የእንስሳት መኖ ይሻሙብናል። በአሁኑ ወቅት ለከብቶቻችን የምናበላው ሳር እያጣን በመሆኑ አርብቶ አደሮቹ ወደመጡበት እንዲመለሱልን እንፈልጋለን። መንግስት መፍትሄ ይስጠን"ብለዋል፡፡ ''ወደ አካባቢው የመጣነው ለከብቶቻችን ሳርና ውሃ ፈልገን ነው ፣ ለሌላ ጉዳይ አይደለም'' ያሉት ደግሞ በፓርኩ ይዞታ ገብተው ከተገኙ ድንብር ዘለል አርብቶ አደሮች መካከል አቶ ጅማ ሙሃመድ ናቸው። "በአካባቢው የገባነውም ዝም ብለን ሳይሆን መሪዎቻችን የአካባቢውን ማህበረሰብ አነጋገረው ነው፣ አካባቢው የተከለከለ የፓርክ ይዞታ ስለመሆኑ አናውቅም፤ ብናውቅ ኑሮ አንገባም ነበር። የተከለከለ ቦታ ስለመሆኑም የነገረን አካል የለም'' " ብለዋል። የክልሉ ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡኩኝ ኦኬሎ በበኩላቸው፣ ድንበር ዘለል አርብቶ አደሮቹ በፓርኩም ሆነ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም አርብቶ አደሮቹ ከህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መረጃ መገኘቱን ነው አቶ ኡኩኝ የገለጹት ። እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ አርብቶ አደሮቹ በፓርኩም ሆነ በአካባቢው አርብቶ አደሮች ላይ እያደረሱት ያለውን ችግር ለመከላከል በአሁኑ ወቅት ከጎሳ መሪዎቻቸው ጋር በመነጋገር ወደ መጡበት የመመለስ ሥራ ተጀምሯል። መነሻቸው ከናይጄሪያ እንደሆነ የሚነገርላቸው እነዚህ አርብቶ አደሮች በመከካለኛው አፍሪካና በደቡብ ሱዳን በኩል አድርገው ከ600 ሺህ በላይ የሚገመት የቀንድ ከብቶችን በመያዝ ወደ ጋምቤላ ክልል መግባታቸው ይነገራል ።
[ 102 ]
[ "አርብቶ አደሮች" ]
[ "በአርብቶ አደሮች ስለተከናወኑ ክንውኖች የሚያመለክቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "በአረሶ አዶሮች አርብቶ አደሮች ህይወት, ላይ ስለተሰሩ ስራወች, ስለተሰሩ ጥናቶች, ስለ ታቀዱ እቅዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ስለአረሶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
304
የደቡብ ክልል የአርብቶ አደሩ የእንስሳት እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጀ በደቡብ ክልል ከሚገኙ 12 የአርብቶ አደር ወረዳዎች መካከል የአራቱን የእንስሳት እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱ ተገለጸ። የሀመር፣ ኛንጋቶም፣ ሱርማና ዳሰነች ወረዳዎችን እንስሳት እንቅስቃሴ የሚያሳየው ፍኖተ ካርታ በክፍለ አህጉራዊ የድርቅ መቋቋሚያና የአርብቶ አደር ኑሮ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ነው የተሰራው። ፍኖተ ካርታው ለእንስሳቱ የሚሆን ውሃና ግጦሽ ያለበትን ስፍራ ለመጠቆም፣ ለእንስሳቱ የጤና አገልግሎት ለማቅረብና የግብይት ስርዓቱን ለማዘመን መነሻ ይሆናል ተብሏል። በፍኖተ ካርታው ጥናት ላይ ከእንስሳትና ዓሣ ሀብት፣ ከንግድና ኢንዱስትሪና ከውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ቢሮዎች የተውጣጡ አካላት ተሳትፈውበታል። የፕሮጀክቱ የእንስሳት ሀብት ልማት ባለሙያ ዶክተር ጉልላት ገዛኸኝ በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጥናቶች ባለመካሄዳቸው ህብረተሰቡ ከእንስሳቱ ሀብት በሚፈለገው ልክ ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ፍኖተ ካርታው የእንስሳትን እንቅስቃሴ መስመር እንደሚያሳይና ለእንስሳቱ የጤና አገልግሎት ለመስጠትና ወደ ገበያ ለማስገባትም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። የክልሉ የአርብቶ አደርና ልዩ ድጋፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ከተጠናቀቁት ፍኖተ ካርታዎች በተጨማሪ በሰባት ከፊል አርብቶ አደር ወረዳዎች በአፍሪካ ልማት ባንክ የፕሮጀክት ድጋፍ ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ጥናት መጀመሩን ገልጸዋል። ጥናቱ የአርብቶ አደሩን ህይወት ለማሻሻል፣ ከእንስሳቱ የሚፈለገውን ጥቅም በተገቢው ወቅት እንዲያገኝ ለማስቻልና የገበያ ጊዜውን ለማወቅ ይረዳዋል ብለዋል። በተካሄደው የዳሰሳ ጥናት በዞኑ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የቀንድ ከብቶች እንደሚኖሩ ተመላክቷል።
[ 102 ]
[ "አርብቶ አደሮች" ]
[ "በአርብቶ አደሮች ስለተከናወኑ ክንውኖች የሚያመለክቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "በአረሶ አዶሮች አርብቶ አደሮች ህይወት, ላይ ስለተሰሩ ስራወች, ስለተሰሩ ጥናቶች, ስለ ታቀዱ እቅዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ስለአረሶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
305
የአርብቶ አደር አካባቢዎች የልማት ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስና የተመጣጠነ እድገት ለማምጣት የሚያግዝ የአርብቶ አደር አካባቢዎች የልማት ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን የፌደራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ እየተዘጋጀ ያለውን ረቂቅ ፖሊስ ለማዳበርና የአርብቶ አደር አካባቢዎች ልማት ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት በሰመራ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ወቅት በሚኒስቴሩ የአርብቶ አደር ክልሎችና አካባቢዎች ተመጣጣኝ ልማት ማረጋገጥ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ሰውነት ቸኮል እንዳሉት በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ሲካሄዱ የቆዩት የልማት ስራዎች በሀገሪቱ የገጠር ልማት ፖሊሲዎች ውስጥ ተካተው ነበር፡፡ በዚህም የአርብቶ አደሩ አካባቢ ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል፡፡ በአካባቢዎቹ እየጨመረ የመጣውን የድርቅ ተጋላጭነት ችግር ለመቀነስና የተመጣጠነ እድገት ለማምጣት የአርብቶ አደር አካባቢዎች የልማት ፖሊሲ መቅረጽ አስፈላጊ መሆኑን ዳይሬክተር ጀነራሉ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የድህነት ቀናሽ መስሪያ ቤቶች የተካተቱበት አደረጃጀት በመፍጠር ከአርብቶ አደሮች አካባቢ የተደረጉ ጥናታዊ ጽሁፎችን በመፈተሽ ረቂቅ የፖሊሲ ማዕቀፉ በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ በፖሊሲ ማዕቀፍ ውስጥ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ፣ የእንስሳት ሀብት ልማት፣ ውሃን መሰረት ያደረገ መንደር ማሰባሰብ እንዲሁም ማህበራዊ አገልግሎትን ይበልጥ ማጠናከርና ሌሎች የስራ መስኮች የሚካተቱ ይሆናል፡፡ አቶ ሰውነት እንዳመለከቱት ረቂቅ ፖሊሲውን ለማዳበር የአርብቶ አደሩ ልማት ጉዞና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም የፖሊሲ ክፍተት የዳሰሳ ጥናትም እየተካሄደ ነው፡፡ በሁሉም ክልሎች የሚካሄደው ይሄው ጥናት ከአለም ባንክና ከአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ በጥናቶች መሰረት የማዳበሪያ ግብአቶችን ለማካተት ሰመራ ላይ የተጀመረው አውደ ጥናት በሌሎችም ክልሎች የቀጠለ ሲሆን በቀጣይም ረቂቅ ፖሊሲው እስከ ህብረተሰቡ ድረስ አውርዶ ከዳበረ በኋላ በሚቀጥለው ዓመት ጸድቆ ስራ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡ የአፋር ክልል አርብቶ አደርና ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢብራሂም መሃመድ በበኩላቸዉ ረቂቅ የፖሊሲ ማዕቀፉ በአርብቶ አደሩን አካበቢዎች የሚስተዋሉ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ "ባለፉት ዓመታት ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ የአርብቶ አደሩ ህብረተሰብ እራሱን የቻለ የልማት ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲዘጋጅለት በየመድረኩ ሲያቀርብ የነበረውን ተደጋጋሚ ጥያቄ መልስ የሰጠ ነው" ብለዋል፡፡ በክልሉ በኩል ለረቂቅ ፖሊሲው የሚሆኑ የማዳበሪያ ግብአቶችን ለማቅረብ ድጋፍ እንደሚደረግም አመልክተዋል፡፡ ለሁለት ቀናት የተዘጋጀውና ትናንት በተጠናቀቀው አውደ ጥናት ከክልሉ የተለያዩ የዘርፍ መስሪያ ቤቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተውጣጡ ከ100 በላይ የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡ አውደ ጥናቱ የተዘጋጀው የፌደራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር ከአፋር ክልል ጋር በመተባበር ነው፡
[ 102 ]
[ "አርብቶ አደሮች" ]
[ "በአርብቶ አደሮች ስለተከናወኑ ክንውኖች የሚያመለክቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "በአረሶ አዶሮች አርብቶ አደሮች ህይወት, ላይ ስለተሰሩ ስራወች, ስለተሰሩ ጥናቶች, ስለ ታቀዱ እቅዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ስለአረሶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
306
በጉጂ ዞን በሊበን ወረዳ የአርብቶ አደሩን ልጆች በአዳሪ ትምሀርት ቤት ማስተማር የሚያስችል ሕንጻ መገንባት የሚያስችል ከግማሽ ሚሊዮን ብር የሚበልጥ የእርዳታ ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን ከኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ልማት ድርጅት ጋር የተፈራረሙት የነገሌ ቦረና ከተማ አስተዳደር የሊበን ወረዳ አርብቶ አደርና ዱባፍ የተባለ የልማት ማህበራት መሆናቸውን አቶ ቦሩ ገልገሎ የነገሌ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገልጠዋል፡፡ ለተማሪዎቹ የማደሪያ ህንጻ መገንባት ያስፈለገው ትምሀርታቸውን ሳያቋርጡ እንዲከታተሉ ለመርዳት መሆኑን ገልጠው በነገሌና ሀረቀሎ ከተሞች የሚገነቡት ሕንጻዎች ሲጠናቀቁ ከ360 በላይ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንደሚኖራቸው አስታውቀዋል፡፡ ድርጅቱ የዞኑን አርብቶ አደር ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል ባለፉት ሁለት ዓመታት ባደረገው የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተለያዩ የልማት ስራዎች ማከናወን ከመቻሉም ሌላ በአዶላና ሀረቀሎ ከተሞች የሚገኙ 160 ሴቶች ከድርጅቱ ባገኙት ብድር ኑሮአቸው እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ አርብቶ አደር ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ጉዩ እንዳስታወቁት በከተሞቹ የሚገኙ ሴቶች በአነስተኛና ጥቃቅን ንግድ ስራ ተሰማርተው አትራፊ በመሆናቸው የወሰዱትን ብድር ሙሉ በሙሉ መልሰዋል፡፡ በአቅም ማነስ የተነሳ ትምህርታቸውን ለሚያቋርጡ ሴት ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አመልከተው በአቅም ማነስ የተነሳ ትምሀረታቸውን ሊያቋርጡ የነበሩ የአርብቶ አደር ልጆችን ተቀብሎ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና በዩንቨርስቲ እያስተማረ መሆኑን ገልጠዋል፡፡ ድርጅቱ የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል በሰባት ሚሊዮን ብር የልማት ስራዎች ለማከናወን እቅድ እንዳለው አቶ ኤልያስ አስታውቀዋል፡፡

307

308
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የመስኖ አጠቃቀም ዘዴዎችን ለአርሶ አደሮች እያስተዋወቀ ነው , .._2011__. 0 214 161 ; 5; ሀዋሳ፤ ህዳር 302004ዋኢማ - ዘመናዊ የመስኖ አጠቃቀም ዘዴዎችን ለአርሶ አደሩ ለማስተዋወቅ የሚያስችለውን ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲው የመስኖ ልማትና ውሃ አጠቃቀም ምህንድስና ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ወሰኑ ለማ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ፕሮጀክቱ ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ በደቡብ ክልል በተመረጡ ዝናብ አጠር አካባቢዎች ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል። ዘመናዊ የመስኖ አጠቃቀም ዘዴ ፕሮጀክቱን ለአርሶ አደሩ የማስተዋወቅ ሥራ የሚሰራው ከኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አጠቃቀም ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ አርሶ አደሩ የጎርፍ ውሃን በማሰባሰብና የከርሰ ምድር ውሃን በቀላሉ በማውጣት ለእርሻ ሥራዎች ሊያውል የሚችልባቸውን ዘዴዎች እንደሚያስተዋውቅ የትምህርት ክፍል ኃላፊው አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ እየተካሄደ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሥሩ ባቋቋማቸው ስድስት የቴክኖሎጂ መንደሮች አማካኝነት መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ይህም አርሶ አደሩ በፕሮጀክቱ አማካኝነት በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጡ ሥልጠናዎች በቅርበት ለመከታተል እንደሚያስችለው ተናግረዋል። ለሦስት ዓመት የሚቆየው ይኼው ፕሮጀክት በ14 የገበሬዎች የሕብረት ሥራ ማህበራት ሥር የተደራጁ ከ8ሺ በላይ አባወራ አርሶ አደሮችን የመስኖ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ አስረድተዋል። ፕሮጀክቱ በዝናብ አጠር አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የመስኖ አማራጮችን ተጠቅመው፤ በዓመት ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ በማምረት በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸው የምግብ እጥረት ለመቅረፍ እንደሚያስችላቸው ኃላፊው አመልክተዋል። ዩኒቨርሲቲው ከመደበኛ የመማር ማስተማር ሥራዎቹ በተጨማሪ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር ችግር ፈቺና የአርሶ አደሩን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የቴክኖሎጂ ትውውቅና የምርምር ሥራዎችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ጠቁመዋል። ዩኒቨርሲቲው ከ23ሺ በላይ ተማሪዎችን በቀን በማታና በተከታታይ ፕሮግራሞች በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በ2004 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ደግሞ ከ5ሺ በላይ አዳዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን ከኃላፊው ገለጻ ለመረዳት መቻሉን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
309
 በምስራቅ ሸዋ በቀጣዩ የምርት ዘመን ከ122 ሺ የሚበልጡ አርሶ አደሮች በኤክስቴንሽን መርሀ-ግብር ይሳተፋሉ ። የምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ በቀጣዩ የምርት ዘመን ከ122ሺ የሚበልጡ አርሶአደሮችን በሰባት የኤክስቴንሽን ማእቀፎች እንደሚያሳትፍ አስታወቀ ። በዞኑ የ1993/94 የምርት ዘመን የመደበኛና አክስቴንሽን መርሀግብር አፈጻጸምን ለመገምገም ዛሬ በአዳማ ከተማ በተጀመረ ስብሰባ ለይ የመምሪያው ሃላፊ ዶክተር ዳኛቸው በየነ እንደገለጹት በመጪው የምርት ዘመን አርሶአደሮቹን በሰብል ፣ ትራጥሬ ፣ ምርጥ ዘር ማባዛት ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ፣ በገጠር ቴክኖሎጂ ፣ በእንስሳት እርባታና በስራተምግብ ማእቀፎች ለማሳተፍ ዝግጅቱ ተጠናቋል ። በምርት ዘመኑ በተለይም በመኸርና በበልግ እርሻ ከ48ሺ ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት በዘር እንደሚሸፈን ሃላፊው ተቁመው ፤ በማእቀፉ እንዲሳተፉ የተመረጡት አርሶአደሮች ካለፈው የካቲት ወዲህ የማሳ ዝግጅት በማካሄድ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል ። ለአርሶአደሮቹ የሚያስፈልጉ የማዳበሪያና የምርጥ ዘር ግባቶች በወቅቱ ለማቅረብም መምሪያው ከየወረዳው ግብርና እህፈት ቤቶች ጋር በመነጋገር ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ በማካሄድ ላይ መሆኑን ተናግረዋል ። በተጠናቀቀው የምርት ዘመን በመርሀግብሩ የተሳተፉ 166ሺ አርሶአደሮች በወቅቱ አስፈላጊ የምርት ግባቶችና የባለሙያዎች ክትትል በማግኘታቸው 9 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን ተቁመው ፤ ይህም ከእቅዱ 12 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስታውቀዋል ። ይህንኑ የአርሶአደሩን ምርታማነት ለቀጣዩ የምርት ዘመንም ተብቆ ለማስቀጠል መምሪያው ከወዲሁ አስፈላጊ የባለሙያዎች ክትትልና የምክር አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ ታውቋል ። ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ስብሰባ 250 ያህል የወረዳ ግብርና ልማት ሰራተኞችና የቴክኒክ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው ።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
310
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሙዝ ምርት በሳውዲ አረቢያ ገበያ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ ነው, .._2012__. 0 303 228 ; 5; አርባምንጭ፤ መጋቢት 12 2004 ዋኢማ - በጋሞ ጎፋ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሙዝ ምርት በሳውዲ አረቢያ ገበያ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱ ተገለፀ። የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሙዝ አምራች አርሶአደሮችም ለምርቶቻቸው የተሻለ የገበያ አማራጭ ማግኘት መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡ በወረዳው በሙዝ ምርት የተሠማሩ አርሶአደሮች በሥፍራው ለተገኘው የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ሪፖርተር እንደገለፁት በአሁኑወቅት ባቋቋሙት የሙዝ አማራቾች መሠረታዊ የሕብረት ሥራ ማህበርና በመንግሥት ድጋፍ ለምርቶቻቸው  በአገር ውስጥና በውጪ የሚገኙ አማራጭ ገበያዎችን ማግኘት ጀምረዋል፡፡ በተለይ በወረዳው የቆላ ሻራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶአደር መንግሥቱ ኦዳ ቀደምሲል ለሙዝ ምርት የተመቻቸ የገበያ ሁኔታ ባለመኖሩ ምርታቸውን ከዋጋ በታች በመሸጥ ቤተሰቦቻቸውን ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ ሲያስተዳድሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል  ፡፡ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ ግን ምርቱ በአዲስ አበባና በውጪ አገር በሚገኙ የአትክልትና የፍራፍሬ ገበያዎች ውስጥ ቀርቦ በመሸጡ ቀደምሲል ያገኙ ከነበረው ከሁለት እስከ ሦስት እጥፍ በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡በተለይ ከቀበሌያቸው ወደ ሳውዲ አረቢያ መላክ ለተጀመረው ምርት 326 ኪሎ ግራም ጥሬ ሙዝ በማቅረባቸው ከፍተኛ ገቢ ለማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል ፡፡ይህም በኑፘቸው ላይ መሻሻል ከማሳየታቸውም በላይ በቀጣይ ምርታቸውን በተሻለ ጥራት ለማቅረብ ትልቅ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው አርሶአደር መንግሥቱ አስረድተዋል፡፡በደቡብ ክልል የግብይትና ሕብረት ሥራ ቢሮ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ አያና አበቶ በበኩላቸው በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ሙዝ አምራች አርሶአደሮች ምርቶቻቸውን ከአገር ወስጥ አልፈው ለውጭ ገበያ ማቅረብ በመጀመራቸው የበለጠ ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡እስከአሁን ሦስት ኮንቴይነር ጥሬ ሙዝ ከአርባ ምንጭ ወደ ሳውዲ አረቢያ ተልኮ ከፍተኛ ተቀባይነት ከማግኘቱም በላይ በአሁኑወቅት ተጨማሪ የምርት ጥያቄዎች ቀርበው ቀጣይ ዙር ለመላክ ዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡የክልሉ ግብይትና ሕብረት ሥራ ቢሮ ተጨማሪ የአትክልትና ፍራፍሬ የገበያ መዳረሻዎችን በማፈላለግ ለአምራች ማህበሩና ለአርሶአደሩ መረጃዎችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡በደቡብ ክልል በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ የግብርና ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የክልሉ ቆላማና ደጋማ አካባቢዎች ከፍተኛ መጠን ያለው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለማምረት የሚያስችሉ የውሃ ተፋሰሶችና ለም መሬት ጨምሮ የበርካታ  የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ነው፡፡),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
311
ኢንስቲትዩቱ የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ምርታማነት የሚያሳድጉ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን እያሰራጨ ነው, .._2012__. 0 239 179 ; 0; 5; አዲስ አበባ፤ መጋቢት 282004ዋኢማ - የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማሰራጨት ላይ መሆኑን አስታወቀ። በኢንስቲትዩቱ በምርምር የሚወጡ የሰብልና የእንስሳት ቴክኖሎጂዎች የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ምርታማነት በሶስትና በአራት እጥፍ በማሳደግ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን አሰፋ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ኢንስቲትዩቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰብል፣ በእንስሳት፣ በአፈርና ውሃ ጥበቃ 736 አዳዲስና ችግር ፈቺ የሆኑ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማውጣት ለአርሶ አደሩ አሰራጭቷል። ኢንስቲትዩቱ በዕፅዋት ምርምር ዘርፍ 620፤ በእንስሳት 61 እንዲሁም በአፈርና ውሃ ጥበቃ 55 ያህል ቴክኖሎጂዎችን በማውጣት ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ ማድረጉን የጠቆሙት ዶክተር ሰለሞን ቴክኖሎጂዎቹ በብሔራዊ አፅዳቂ ኮሚቴ ፀድቀው ከአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ መድረሳቸውን አስረድተዋል። በኢንስቲትዩቱ በምርምር የሚወጡ የሰብልና የእንስሳት ቴክኖሎጂዎች የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ምርታማነት በሶስትና በአራት እጥፍ በማሳደግ ላይ መሆናቸውንም  ጠቁመዋል። ኢንስቲትዩቱ በመላ ሀገሪቱ ባሉት 16 የምርምር ማዕከላት በመታገዝ በሽታን የሚቋቋሙና ምርታማነትን ሊያሻሽሉ በሚችሉ የበቆሎ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ሩዝ፣ አኩሪ አተር፣ ሽንብራ፣ ነጭ ቦሎቄና ሌሎች የሰብል ዝርያዎች ላይ የሚያደርገውን ምርምር በተጠናከረ ሁኔታ እያካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ ከዚህ ቀደም በሄክታር በአማካይ ከዘጠኝ ኩንታል የማይበልጥ ምርት ይሰጥ የነበረውን የጤፍ ምርት ለማሻሻል ባካሄደው ምርምር ቁንጮ የተባለ የጤፍ ዝርያ ማግኘቱን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ከዚህ የጤፍ ዝርያ በሄክታር ከ25 እስከ 30 ኩንታል ማግኘት መቻሉን ጠቁመዋል።     ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ዋና ግብዓት የሆነውን የጥጥ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ኢንስቲትዩቱ ልዩ ትኩረት መስጠቱን የተናገሩት ዶክተር ሰለሞን ገበያው የሚፈልገውንና የተለያየ የጥራት ደረጃ ያላቸውን የጥጥ ዝርያዎች በስፋት አላምዶ ለማቅረብ ኢንስቲትዩቱ በተጠናከረ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል። እንደ ዳይሬክተሩ ማብራሪያ ኢንስቲትዩቱ በአርብቶ አደሩ አካባቢም ተጨማሪ የምርምር ማዕከላትን በመክፈት በሰብል፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት ላይ  የምርምር ስራዎችን እያካሄደ ይገኛል። የተሻሻለ የወተትና የስጋ ምርት ያላቸውን የከብት ዝርያዎች በምርምር ለማውጣትም በአዳዲስ የመኖ ቴክኖሎጂዎች ላይ የምርምር ሥራዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ዶክተር ሰለሞን ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመደገፍ በሰብል፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት ላይ ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምር ስራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑንም ዶክተር ሰለሞን ገልፀዋል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
312
በበጋው ወራት 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር የሚጠጋ መሬት በስነ አካላዊ፣ በአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ ተከናውኗል, .._2012__. 0 304 228 ; 5; አዲስ አበባ ሰኔ 292004ዋኢማ - በዘንድሮው ዓመት 5 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር የሚጠጋ መሬት በተለያዩ ስነ-አካላዊ፣ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራዎች መሰራቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በዘንድሮው ዓመት በበጋ ወራት በተደረገ ሁለገብ የህዝብ ንቅናቄ 3 ነጥብ 77 ሚሊየን ሄክታር መሬት በስነ አካላዊና የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራዎች እና 1 ነጥብ 39 ሚሊየን የተራቆቱና የተቦረቦሩ መሬቶችን ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ ከልሏል። የአየር ንብረት ለውጥን በማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት የሚቻለው በበጋ ወቅት በህዝብ ንቅናቄ የተሰሩ ስነ አካላዊ እርከኖችን በስነ ህይወታዊ ዘዴ ማጠናከር ሲቻልና ችግኞችን ተክሎ ማልማት ሲቻል መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፤ የዕፅዋት ሽፋን ማሻሻል የአካባቢ ሥርዓተ-ምህዳር በዘላቂነት እንዲጠበቅ ማድረግ በአየር ንብረት መለዋወጥ ምክንያት የሚፈጠረውን የአካባቢ የአየር መዛባት በማስተካከል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁሟል። በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ሙያተኞች መላውን ህብረተሰብና የልማት ደጋፊ አካላትን በማስተባበርና በማንቀሳቀስ በበጋ ወቅት በአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራ የታየውን የህዝብ መነሳሳት በችግኝ ተከላና እንክብካቤ ማስቀጠል ይገባል። በመሆኑም አካባቢዎችን በስነ ህይወታዊ ዘዴ ለመሸፈን በዘንድሮው ክረምት ከ5 ቢሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል መዘጋጀቱን መግለጫው ገልጿል። ይህም ከሁለት ነጥብ ስድስት ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ይሸፈናል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤  ችግኞቹ የሚተከሉትም መልሰው እንዲያገግሙ በተከለሉ አካባቢዎች፣ በበጋ ወቅት በተፋሰስ ልማት በተሰሩ ስነ አካላዊ የአፈርና ውኃ ጥበቃ እርከኖች፣ በእርሻ ማሳ ላይና የደን ልማትን ለማስፋፋት በሚውሉ አካባቢዎች ነው። የችግኝ ተከላው እንደየአካባቢው የእርጥበት ሁኔታ መተከል የተጀመረ ሲሆን፤ እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ ከ199 ሚሊየን በላይ ችግኞች መትከል ተችሏል። በመሆኑም በአፈርና በውኃ ጥበቃ ስራው የታየውን የህብረተሰብ መናሳሳት በችግኝ ተከላና እንክብካቤ ወቅት እንዲደገም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳሰቡን መግለጫው ጠቁሟል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
313
በ7ኛው የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ፌስቲቫል 920 ግለሰቦች ይሸለማሉ, .._2015. 0 263 198 ; 5; አዲስ አበባ ፤ የካቲት 19 2007 (ዋኢማ) - ከካቲት 20 እስከ 22 በደቡብ ክልል ሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው 7ኛው አገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ፌስቲቫል ላይ 920 ለሚሆኑ ሞዴል አርሶአደሮች ፣ አርብቶ አደሮችና ድጋፍ ሠጪ አካላት የዕውቅና ሽልማት እንደሚሠጥ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አስራት ተክለፃዲቅ ለዋልታ እንደገለጹት ሽልማቱ የሚሰጠው በልማት ቡድን ተደራጁና የተለያዩ የግብርና ግብዓቶችን፣ ቴክኖሎጂዎችንና አሠራሮችን ተግባራዊ አድርገው ውጤት ያመጡ የአንድ ለአምስት አደረጃጀቶች ናቸው። በአጠቃላይ ከ1ነጥብ5 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ያፈሩ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በሽልማቱ እንደሚካተቱ የጠቆሙት አቶ አሥራት ከተሸላሚዎቹ ውስጥ 30 በመቶ ሴቶች 20 በመቶ ደግሞ ወጣቶች እንደሚሆኑ ተናግረዋል። የሽልማቱ ዓለማ በአገር አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ አርሶ አደሮችን እውቅና በመስጠት ወደ ባለሃብትነትና ወደ ኢንዱስትሪ ልማት እንዲሸጋገሩ እንዲሁም የግብርና ዘረፉ እንዲያድግ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው። የአገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ፌስቲቫል በ1999 ዓም የተጀመረ ሲሆን እስካሁን 4ሺ 510 አርሶ አደሮች ፤ አርብቶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች እውቅና እና ሽልማት ማግኘታቸው ታውቋል። ),

314
የአርሶ አደሩ ውጤታማነት የግብርናው ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው, - ; .._2015. 0 187 196 ; 5; አዲስ አባባ የካቲት 242007 (ዋኢማ) - አርሶ አደሩ እያከናወነ ያለው ውጤታማ ተግባር የግብርናው ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡ - ; ሰባተኛው አገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን እምርታዊ ለውጥ በምርታማነትና በአመራረት ዘይቤ በሚል መሪ ቃል በሃዋሳ ከተማ ተከብሯል። - ; በበዓሉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመከተል አርሶ አደሩ ገበያ ተኮር ምርት አያመረተ ተጠቃሚነቱን ማሳደግ ችሏል፡፡ - ; አርሶ አደር መሆንና በግብርና ሙያ መሰማራት ኋላቀርነት ተደርጎ ከሚታይበት የአስተሳሰብ ድህነት በመላቀቅ ፋና ወጊ መሆናችሁና ለበርካቶች መለወጥና ማደግ ምክንያት የሆናችሁት በግል ጥረታችሁና በልማታዊ መንግስታችን ድጋፍ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ - ; በርካታ አርሶ አደሮች ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮ በመላቀቅ ዛሬ ለአለም ገበያ ተፈላጊ የሆነ ምርት ማምረት ስራ ውስጥ መግባታቸው በግብርናው መስክ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ትክክለኛና ፈር ቀዳጅ ጉዞ መጀመራቸውን እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ - ; የሀገሪቱ የግብርና ስራ ውጤታማ መሆን የቻለው የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን መቀበልና መተግበር በመቻላቸው መሆኑንና ይህ ተጠናክሮ  እስከቀጠለ ድረስ ዘርፉን ሌሎች ከደረሰሰቡት ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ - ; በአለም አቀፍ ደረጃ የስንዴ ምርታማነት በሄክታር 180 ኩንታል መድረሱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በሞዴል አርሶ አደሮች በአማካይ 60 ኩንታል መሆኑ ሲታሰብ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ በአርሲ ዞን ሲሬ ወረዳ ሞዴል አርሶ አደር የሆኑት በሄክታር 120 ኩንታል ላይ ለመድረስ በትጋት መስራት እንዳለባቸው አቶ ኃይለማርያም አሳስበዋል፡፡ - ; የግብርና ምርታመነት የሚያኮራ ደረጃ ላይ አልደረስንም፤ በበሌሎች ሰብሎችና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍም ቢሆን መድረስ ከሚገባን አንጻር ብዙ ይቀረናል ብለዋል፡፡ - ; እንደ ኢዜአ ዘገባ ለዚህም ምክንያቱ ሞዴል አርሶ አደሮች ከደረሱበት ደረጃ አብዛኛው አርሶ አደር ያልደረሰ መሆኑን በመረዳት በቀጣይ ጥቂት አመታት ሞዴል አርሶ አደሮች ደረጃ ለማድረስ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ - ; ሞዴል አርሶ አደሮቹ በሚያከናወኑት የግብርና ልማት ስራ ሌሎችን ለማብቃት ተግተው እንዲሰሩና ይህን ተግባር ለማገዝ መንግስት ምንጊዜም ከጎናቸው እንደሚቆም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ - ; በተጨማሪም የግብርና ምርቶችን በማቀነባበር፤ የአርሶ አደሩን ምርት በመረከብና አርሶ አደሮችን በማስተባበርና በማደራጀት የተሻለ የገበያ ስርዓት በመዘርጋት ረገድ የህብረት ስራ ማህበራት የሚያከናውኑት ተግባር ከፍተኛ በመሆኑ ማህበራቱን የማጠናከር ስራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ - ; የግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው ያለፉት ዓመታት የአርሶ አደሮች የሽልማት ስነስርዓት በአርሶ አደሮች መካከል ጠንካራ የውድድር መንፈስና መነሳሳት እንዲፈጠርና የበለጠ ተግተው በመስራት የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስችላል ብለዋል፡፡ - ; በርካታ አርሶ አደሮች ራስን ከመቻል ባለፈ ወደ ባለሀብትነት ጎራ እንዲቀላቀሉና ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ እሴት ወደሚጨምሩ ስራዎች በመሸጋገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ ሚናም አሻራቸውን ማሳረፍ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ - ; በዓሉ መከበር ከጀመረ ወዲህ የውጤታማ ሞዴል አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቁጥር እያደገ በመምጣቱ የዛሬ ተሸላሚዎች 920 መድረሱን ገልፀዋል፡፡ - ; በዘንድሮው ሽልማት በልማት ቡድን ተደራጅተው የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና የተሻሻሉ አሰራሮችን በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ በመተግበር ውጤት ያመጡ የልማት ቡድኖችና አንድ ለአምስት ትስስሮች መካተታቸውን አቶ ተፈራ አስረድተዋል፡፡ - ; ከሞዴል ተሸላሚ አርሶ አደሮች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ስሬ ወረዳ የመጡት አርሶ አደር አበበ ትርፌ እንዳሉት በስንዴ ልማት መስክ ለተወሰኑ አመታት ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በገበያ ተፈላጊ ወደሆነው የሽንኩርት ልማት በመሰማራት በሄክታር ከ300 ኩንታል በላይ እያመረቱ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ካፒታላቸውን ወደ 20 ሚሊዮን ብር ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ - ; መንግስት በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ በሰሩት ስራ ከግብርና ስራቸው በተጨማሪ በሆቴል ስራ በመሰማራት በሲሬ ከተማ ባለሁለት ፎቅ ህንጻ በመገንባት እየሰሩ አንደሚገኙና በቀጣይ የግብርና ስራቸውን በማጠናከር የበለጠ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ ባከናወኑት ውጤታማ ስራ አሁን ወደ ባለሀብትነት ደረጃ አድገው እውቅና ማግኘታቸው እንዳኮራቸው ተናግረዋል፡፡ - ; ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ማኦ ኮሞ ወረዳ የመጡትና ወደ ባለሀብትነት ደረጃ አድገው በበዓሉ ላይ እውቅና የተሰጣቸው አርሶ አደር ጅብሪል ኢሳ በበኩላቸው በቡና፣ በማሽላና ሌሎች የአገዳና ቅባት ሰብሎች ልማት ተሰማርተው ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ - ; የግብርና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክር በመቀበልና ባለፉት አመታት የተከናወኑ በዓላት በአርሶ አደሩ መካከል የልማት ፉክክር በማምጣቱና እሳቸውም የበለጠ በመስራታቸው ሀብታቸውን ማሳደግና ሌሎችንም ወደ ባለሀብትነት ደረጃ እንዲያድጉ ማብቃት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ - ; በሰባተኛው አገርዓቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን ላይ 920 አርሶ አሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ ባለሀብቶችና ሌሎች አጋዥ አካላት ተሸልመዋል፡፡ - ; ሽልማትና እውቅና ከተሰጣቸው መካከል 580 አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ሲሆኑ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ወጣቶች ናቸው፡፡ - ; የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ስድስት የአርሶ አደሮች ቀን 5 ሺህ 430 አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ - ; የአርሶ አደሩ ውጤታማነት የግብርናው ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው አዲስ አባባ የካቲት 242007 (ዋኢማ) -  አርሶ አደሩ እያከናወነ ያለው ውጤታማ ተግባር የግብርናው ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡ - ; ሰባተኛው አገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን እምርታዊ ለውጥ በምርታማነትና በአመራረት ዘይቤ በሚል መሪ ቃል በሃዋሳ ከተማ ተከብሯል። - ; በበዓሉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመከተል አርሶ አደሩ ገበያ ተኮር ምርት አያመረተ ተጠቃሚነቱን ማሳደግ ችሏል፡፡ - ; አርሶ አደር መሆንና በግብርና ሙያ መሰማራት ኋላቀርነት ተደርጎ ከሚታይበት የአስተሳሰብ ድህነት በመላቀቅ ፋና ወጊ መሆናችሁና ለበርካቶች መለወጥና ማደግ ምክንያት የሆናችሁት በግል ጥረታችሁና በልማታዊ መንግስታችን ድጋፍ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ - ; በርካታ አርሶ አደሮች ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮ በመላቀቅ ዛሬ ለአለም ገበያ ተፈላጊ የሆነ ምርት ማምረት ስራ ውስጥ መግባታቸው በግብርናው መስክ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ትክክለኛና ፈር ቀዳጅ ጉዞ መጀመራቸውን እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ - ; የሀገሪቱ የግብርና ስራ ውጤታማ መሆን የቻለው የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን መቀበልና መተግበር በመቻላቸው መሆኑንና ይህ ተጠናክሮ  እስከቀጠለ ድረስ ዘርፉን ሌሎች ከደረሰሰቡት ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ - ; በአለም አቀፍ ደረጃ የስንዴ ምርታማነት በሄክታር 180 ኩንታል መድረሱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በሞዴል አርሶ አደሮች በአማካይ 60 ኩንታል መሆኑ ሲታሰብ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ በአርሲ ዞን ሲሬ ወረዳ ሞዴል አርሶ አደር የሆኑት በሄክታር 120 ኩንታል ላይ ለመድረስ በትጋት መስራት እንዳለባቸው አቶ ኃይለማርያም አሳስበዋል፡፡ - ; የግብርና ምርታመነት የሚያኮራ ደረጃ ላይ አልደረስንም፤ በበሌሎች ሰብሎችና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍም ቢሆን መድረስ ከሚገባን አንጻር ብዙ ይቀረናል ብለዋል፡፡ - ; እንደ ኢዜአ ዘገባ ለዚህም ምክንያቱ ሞዴል አርሶ አደሮች ከደረሱበት ደረጃ አብዛኛው አርሶ አደር ያልደረሰ መሆኑን በመረዳት በቀጣይ ጥቂት አመታት ሞዴል አርሶ አደሮች ደረጃ ለማድረስ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ - ; ሞዴል አርሶ አደሮቹ በሚያከናወኑት የግብርና ልማት ስራ ሌሎችን ለማብቃት ተግተው እንዲሰሩና ይህን ተግባር ለማገዝ መንግስት ምንጊዜም ከጎናቸው እንደሚቆም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ - ; በተጨማሪም የግብርና ምርቶችን በማቀነባበር፤ የአርሶ አደሩን ምርት በመረከብና አርሶ አደሮችን በማስተባበርና በማደራጀት የተሻለ የገበያ ስርዓት በመዘርጋት ረገድ የህብረት ስራ ማህበራት የሚያከናውኑት ተግባር ከፍተኛ በመሆኑ ማህበራቱን የማጠናከር ስራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ - ; የግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው ያለፉት ዓመታት የአርሶ አደሮች የሽልማት ስነስርዓት በአርሶ አደሮች መካከል ጠንካራ የውድድር መንፈስና መነሳሳት እንዲፈጠርና የበለጠ ተግተው በመስራት የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስችላል ብለዋል፡፡ - ; በርካታ አርሶ አደሮች ራስን ከመቻል ባለፈ ወደ ባለሀብትነት ጎራ እንዲቀላቀሉና ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ እሴት ወደሚጨምሩ ስራዎች በመሸጋገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ ሚናም አሻራቸውን ማሳረፍ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ - ; በዓሉ መከበር ከጀመረ ወዲህ የውጤታማ ሞዴል አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቁጥር እያደገ በመምጣቱ የዛሬ ተሸላሚዎች 920 መድረሱን ገልፀዋል፡፡ - ; በዘንድሮው ሽልማት በልማት ቡድን ተደራጅተው የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና የተሻሻሉ አሰራሮችን በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ በመተግበር ውጤት ያመጡ የልማት ቡድኖችና አንድ ለአምስት ትስስሮች መካተታቸውን አቶ ተፈራ አስረድተዋል፡፡ - ; ከሞዴል ተሸላሚ አርሶ አደሮች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ስሬ ወረዳ የመጡት አርሶ አደር አበበ ትርፌ እንዳሉት በስንዴ ልማት መስክ ለተወሰኑ አመታት ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በገበያ ተፈላጊ ወደሆነው የሽንኩርት ልማት በመሰማራት በሄክታር ከ300 ኩንታል በላይ እያመረቱ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ካፒታላቸውን ወደ 20 ሚሊዮን ብር ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ - ; መንግስት በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ በሰሩት ስራ ከግብርና ስራቸው በተጨማሪ በሆቴል ስራ በመሰማራት በሲሬ ከተማ ባለሁለት ፎቅ ህንጻ በመገንባት እየሰሩ አንደሚገኙና በቀጣይ የግብርና ስራቸውን በማጠናከር የበለጠ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ ባከናወኑት ውጤታማ ስራ አሁን ወደ ባለሀብትነት ደረጃ አድገው እውቅና ማግኘታቸው እንዳኮራቸው ተናግረዋል፡፡ - ; ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ማኦ ኮሞ ወረዳ የመጡትና ወደ ባለሀብትነት ደረጃ አድገው በበዓሉ ላይ እውቅና የተሰጣቸው አርሶ አደር ጅብሪል ኢሳ በበኩላቸው በቡና፣ በማሽላና ሌሎች የአገዳና ቅባት ሰብሎች ልማት ተሰማርተው ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ - ; የግብርና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክር በመቀበልና ባለፉት አመታት የተከናወኑ በዓላት በአርሶ አደሩ መካከል የልማት ፉክክር በማምጣቱና እሳቸውም የበለጠ በመስራታቸው ሀብታቸውን ማሳደግና ሌሎችንም ወደ ባለሀብትነት ደረጃ እንዲያድጉ ማብቃት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ - ; በሰባተኛው አገርዓቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን ላይ 920 አርሶ አሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ ባለሀብቶችና ሌሎች አጋዥ አካላት ተሸልመዋል፡፡ - ; ሽልማትና እውቅና ከተሰጣቸው መካከል 580 አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ሲሆኑ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ወጣቶች ናቸው፡፡ - ; የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ስድስት የአርሶ አደሮች ቀን 5 ሺህ 430 አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡),

315
አርሶ አደሩ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂን በመጠቀሙ የግብርናው ዘርፍ ውጤታማ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ገለፁ, .._2014. 0 260 196 ; 5; አዲስ አበባ፤ የካቲት 242006ዋኢማ -ሀገሪቱ ተግባራዊ ባደረገችው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ አርሶ አደሩ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂን በመጠቀሙ የግብርናው ዘርፍ ውጤታማ መሆን መቻሉን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በግብርናው ዘርፍ ለተገኘው ውጤት መንግስት በእቅድ ዘመኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መሰራት በመቻሉ ነው ብለዋል። መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ወደ አርሶ አደሩ በማስረፅ ረገድም በርካታ ስራዎች መሰራቱን ጠቁመው፤ ቴክኖሎጂዎቹን ወደ ተግባር በመለወጥ ስራ ላይ መዋሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ኢህአዴግ በባህርዳር ከተማ ባካሄደው ዘጠነኛው ጠቅላላ ጉባዔ የግብርናው ዘርፍ ውጤታማ የሚሆንበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ማስቀመጡን ጠቁመው፤ በአቅጣጫው መሰረትም አርሶ አደሩ የግብርና ምርታማነቱን የሚያረጋግጥበት ሁኔታ በመፈጠሩ ስኬታማ መሆን ተችሏል ብለዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ አርሶ አደሩ አመቱን በሙሉ ውጤታማ ስራን ለመስራት እንዲችልም የመስኖ ስራዎች በበጋ ወራቶች እንደሚካሄዱም ገልፀዋል። በመኸር ወቅትም ዝናብ በሚዘገይባቸው አንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመስኖ በአመት ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችሉበት ሁኔታ ተመቻችቷል በማለት ጠቁመው፤ ይህም የሀገሪቱ የግብርና ምርት እድገት ዘላቂ በሆነ ሁኔታ እንዲቀጥል ያስችለዋል ብለዋል። የተገኘውን ውጤታማ ተሞክሮ በማስፋትም ለሚቀጥለው የግብርና የምርት ዘመን እንደ ግብዓት በመጠቀም ምርታማነቱን ይበልጥ ለማሳደግ ከወዲሁ ሁኔታዎች መመቻቸቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ድህነትን ታሪክ ለማድረግና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ዋነኛ አማራጭ የሆነውን የግብርና ዘርፍ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመኑ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል በማለት መግለፃቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
316
ክልሉ 4 ሺሕ 90 አርብቶ አደሮችን በመንደር ማሰባሰቡን አስታወቀ, .._2013_. 0 262 192 ; 5; አዲስ አበባ፤ ሰኔ 212005 (ዋኢማ) - የአርብቶ አደሮችን ህይወት ለመቀየር በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት 4 ሺሕ 90 አርብቶ አደሮችን በመንደር ማሰባሰቡን የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። በክልሉ የአርብቶ አደር ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ኩይሳ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት ባለፉት ሁለት ዓመታት በመንደር ለተሰባሰቡት አርብቶ አደሮች አስፈላጊውን የማህበራዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ 83 ተቋማት በግንባታ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። የአገልግሎት መስጫ ተቋማቱ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ኬላዎች፣  የባለሙያ መኖሪያ ቤቶች፣  የእህል ወፍጮዎች፣  መጋዘኖች፣  የቀበሌ ጽህፈት ቤቶችና  የአርብቶ አደር ማሰልጠኛዎችን እንደሚያካትቱ ሃላፊው  ተናግረዋል። በክልሉ በሶስት ዞኖች በሚገኙ 12 ወረዳዎች የሚኖረው ግማሽ ሚሊየን አርብቶና ከፊል አርብቶ አደርን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሉ መንግስት እየሰራ መሆኑንም ሃላፊው ተናግረዋል። ያለፉት ስርዓታት ለአርብቶ አደሮቹ ምንም ዓይነት ትኩረት እንዳልሰጡ የጠቆሙት አቶ ዳዊት  መንግስት የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ  የተቀናጀ የአርብቶ አደሮች የልማት ፓኬጅ ነድፎ  ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል። የአርብቶ አደሩን ህይወት ለመቀየር ከተወሰዱ እርምጃዎች አንዱ በሰፈር ማሰባሰብ መሆኑን የገለጹት አቶ ዳዊት በቀጣይ  ዓመታትም በመንደር የማሰባሰቡ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። አርብቶ አደሩ በመንደር ማስፈር ጋር ተያይዞ እየተነሳ ያለው አሉባልታ የአርብቶ አደሩ  ህይወት እንዲቀየር በማይፈልጉ ግለሰቦች የመሚነዛ  መሆኑን ሃላፊው ጠቁመው ፕሮግራመሙ እየተፈጸመ ያለው ፈቃደኝነትን  መሰረት አድርጎ መሆኑን  አስረድተዋል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
317
አርሶ አደሮች በቲማቲም ላይ የተከሰተው ቅጠል ሰርስር በሽታ ለመከላከል የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ እንዳለባቸው ግብርና ሚኒስቴር አስገነዘበ , .._2013. 0 260 195 ; 5; አዲበባ፤ ሐምሌ 102005 (ዋኢማ) - አርሶ አደሮች በቲማቲም ላይ የተከሰተው ቅጠል ሰርስር ፍሬ ቦርቧሪ ተባይ ቱታ አብሱሉታ ለመከላከል በበሽታው በተጠቃው ቲማቲም የሚደርሰውን ጉዳት የሚቀንሱ እርምጃዎች መውሰድ እንደሚገባቸው የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ። ሽታውን ለመከላከል የተጀመረው እንቅስቃሴ አበረታች ውጤት እያሳየ ነው። የሚኒስቴሩ የእንስሳትና ዕፅዋት ጤናና ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፍቅሬ ማርቆስ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስረዱት አርሶ አደሮች በምርቱ ላይ አደጋ እያስከተለ ያለውን በሽታ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ ይገባቸዋል። በዚህም የተቀናጀ የተባይ መከላከያ ዘዴዎችን ከተባዩ የጸዳ ችግኝ በመጠቀም፣ለተባዩ መራቢያ የሚሆኑ አረሞችን በማስወገድ፣ቲማቲሙ በመደብ ላይ እያለ ጀምሮ በመከታተልና በተባዩ የተጠቁትን በጥንቃቄ ማስወገድ ያስፈልጋል። ከምርት ለቀማ በፊትም ሆነ በኋላ በበሽታው የተጎዱ ፍሬዎችን ከማሳ ውስጥ ለቅሞ በፕላስቲክ ከረጢት ሰብስቦ በደንብ ማሸግና ለሁለት ወራት ያህል በማስቀመጥ ተባዩ እንዲሞት ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል። በተጨማሪም ማሳውን አጽድቶ ደጋግሞ ማረስ፣ማገላበጥና ኩብኩባውን ለፀሐይና የተፈጥሮ ጠላይ ማጋለጥ፣ለሁለት ወራት አቆይቶ አዲስ ቲማቲም መትከል እንዲሁም ቲማቲም ከሌላ ከቤተሰቡ ውጭ ከሆነ ሰብል ጋር ማፈራረቅ እንደሚገባም አቶ ፍቅሬ አሳስበዋል። ተባዩ በኢትዮጵያ ውስጥ የካቲት 152005 ጀምሮ የትግራይና የኦሮሚያ ክልሎች ግብርና ቢሮዎች በቲማቲም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መከሰቱን በመጠቆማቸውና በተካሄደው ቅኝት ተረጋግጧል። ተባዩ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚሰራጨው በሰዎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ በመሆኑ ከሱዳን ድንበር አካባቢ በሚደረገው የግብርና ምርቶች ግብዓት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ ይገመታል። ተባዩ አነስተኛ መጠን ካላቸው የእሳት ራት ዝርያዎች ውስጥ እንደሚመደብ ምከትል ዳይሬክተሩ ገልጸው፣ ከፍተኛ የመባዛት ችሎታ ያለውና ለተባዩ ተስማሚ በሆኑ ሞቃታማ አካባቢዎች በአንድ ዓመት ጊዜ እስከ 12 የሚደርሱ ትውልዶች ይፈጠራሉ። ተባዩን በአጭር ጊዜ የመባዛትና ፀረ ተባይ የመላመድ ባህሪ ስላለው የመቆጣጣሪያ እርምጃ ካልተወሰደ በአንድ ማሳ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ እሣት ራቶች ይፈጠራሉ። ችግሩን ለመፍታት በአገሪቱ ፀረ-ተባይ መድኃኒት የተሞከሩና ውጤታቸው የታወቁት ጥቂት ቢሆኑም፤ ሌላው ዓለም የተጠቀመባቸው ፀረ -ተባይ መድኃኒት አገር ውስጥ ገብተው ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ናቸው። የእሳት ራቷ ትሉን የምትጥለው ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እሷን በሁሉም ቦታ ደርሶ መከላከል በጣም አስቸጋሪ ስለሚሆን በፀረ-ተባይ መድኃኒት ከመጠቀም ባሻገር ሌሎች የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል። በዚህም የሌሎች አገሮችን ልምድ በመውሰድ በአገሪቱ የሚገኙ ባለሃብቶች እሳት ራቷን ማጥመጃ ፌርሞን የተባለ መሣሪያ በመጠቀም በተደረገው ሙከራ አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸው፣ በማጥመጃው መሣሪያ መወደድ ምክንያት አነስተኛ ገበሬዎች ሊጠቀሙበት እንዳልቻሉ ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር የበሽታውን ምንነትና መከላከያ ዘዴዎች ግንዛቤ ለመፍጠር የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል። በተጨማሪም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በግብርና ሚኒስትር ዴኤታው የሚመራ የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች፣የሆርቲካልቸር ልማት ኤጀንሲና የሆርቲካልቸር ፕሮዲዩሰር ኤክስፖርተር ማህበር ያሉበት የቴክኒክ ኮሚቴ መቋቋሙንና በቅርቡም ብሔራዊ ዐውደ ጥናት እንደሚካሄድ ተናግረዋል። በቀጣይም የጥናትና ምርምር እንዲሁም የክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። በምሥራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ የጎልባ አሉቶ ቀበሌ አርሶ አደር መቶ አለቃ ኤዳኦ መንገሻ በሽታው ፍሬው ላይ ጉዳት በማድረስ ቅጠሉ እንዳያቆጠቁጥ በማድረግና ግንዱን ከርክሮ በመጣል አበባ እንዳያፈራ በማድረግ ጉዳት እያደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል። በዚሁ ዞን ዱግዳ ወረዳ የግራር ቆርኪ የኦዳ ቀሎ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ኅብረት ሥራ ማህበር አባል አርሶ አደር ዋቅጅራ ሮባ በበኩላቸው ተባዩ ቅጠሉንና ፍሬው ውስጥ በመብላት እንደሚያበላሸው አስታውቀዋል። በሽታውን ለመከላከል በተደጋጋሚ ኬሚካልም ቢጠቀሙ በሽታው ሊጠፋ እንዳልቻለም አርሶ አደሮቹ አመልክተዋል። ቅጠል ሰርስር ፍሬ ቦርቧሪ ተባይ ቱታ አብሱሉታ በሽታ በደቡብ አሜሪካ አገሮች በተለይ በፔሩ የተከሰተ ሲሆን፣ስያሜውም የደቡብ አሜሪካ የቲማቲም እሳት ራት ነው። በሽታው ባለፉት ሰባት ዓመታት ወደ ስፔንና ሌሎች ደቡብ አውሮፓ አገሮች ከተዛመተ በኋላ ሰሜን አፍሪካንና ሜዲትራንያን አገሮችን በስፋት ማጥቃቱን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
318
በአማራ ክልል በአርሶአደሮች ይዞታነት የተረጋገጠ የእርሻ መሬት ወደ ኮምፒዩተር የማስገባት ስራ ተከናወነ , .._2013. 0 260 197 ; 5; አዲስ አበባ፤ 292005 (ዋኢማ) - በአማራ ክልል በአርሶአደሮች ይዞታነት የተረጋገጠ ከ6 ሚሊዮን በላይ የእርሻ ማሳ መረጃን ወደ ኮምፒውተር የማስገባት ስራ መከናወኑን የክልሉ አካባቢ ጥበቃ፣ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ገለጸ። የቢሮ ሃላፊው አቶ ከበደ ይማም እንደገለጹት የባለይዞታዎችን መሬት በኮምፒተር መረጃው እንዲገባ መደረጉ በቀጣይ የካዳስተር ቅየሳ ስራ ለማከናወንና የሁለተኛ ደረጃ ማረጋገጫ ደብተርን ለአርሶአደሩ ለመስጠት ያስችላል። ከባለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በክልሉ በተመረጡ 69 ወረዳዎች በሚገኙ ከ1ሺ በላይ ቀበሌዎች የአርሶአደር፣ የተቋማት፣ የወል፣ የመንግስትና የድርጅት መሬቶች መረጃ ወደ ኮምፒተር የማስገባት ስራ መካሄዱንም ገልጸዋል። የመሬት መረጃን በክልሉ ወደኮምፒዩተር የማስገባት ስርዓት ተግባራዊ መሆኑ በቀጣይ የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተርን ለአርሶአደሩ ለመስጠትና ለሚካሄደው የካዳስተር ቅየሳ ስራ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ይህም በአርሶአደሩ ዘንድ ከመሬት ጋር ተያይዞ በየጊዜው የሚነሱ አለመግባባቶች፣ ግጭቶችና የሚስተዋሉ የመልካም ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እንደሚያስችልም አመልክተዋል። በተለይም ሴቶች፣ ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን በውስጣቸው የመሬት ባለቤትነት መንፈስን በአስተማማኝ ሁኔታ እንደፈጠር የሚያደ ርግ ከመሆኑም በተጨማሪ የመሬታቸውን ለምነት በመጨመር ምርታማነትን እንዲያሳድጉ እንደሚያስችላቸውም አስታውቀዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ እንዲሁም በበጀት ዓመቱ በህገወጦች ተይዞ የነበረ ከ19ሺ ሄክታር በላይ የወል መሬት እንዲመለስ መደረጉን አመልክተው በተጭበረበረ ማስረጃና በሀሰት ምስክር በፍርድ ቤት የተነጠቁ ግለሰቦችም መሬታቸውን በህዝቡ በማስተቸት እንዲመለስ ተደርጓል ብለዋል፡፡),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
319
በግብርና ናሙና ጥናቱ ከ68 ሺ በላይ አርሶአደሮች ይካተታሉ , .._2013. 0 260 195 ; 5; አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 302005 (ዋኢማ) - በ2006 በጀት ዓመት በግብርናው ዘርፍ በሚካሄደው የግብርና ናሙና ጥናት በመላው ሃገሪቱ ከ68 ሺ በላይ አርሶአደሮች እንደሚካተቱ የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ገለጸ። በኤጀንሲው የግብርና፣የተፈጥሮ ሃብትና አከባቢ ስታስቲክስ ዳይሬክተር አቶ ሃበክርስቶስ በየነ እንደገለጹት በ2006 በዋና መኽር ሰብል ትንበያ ፣የድህረ ሰብልና የቤተሰብ እንስሳት ቆጠራ ጥናት ለማካሄድ 68 ሺ 700 አርሶአደሮች ይካተታሉ። ኤጀንሲው በመላው ሃገሪቱ ለሚያካሂደው ጥራት ያለው፣አስተማማኝና ወቅታዊ መረጃን ለሚመለካታቸው አካላት የናሙና ጥናት ለማቅረብ   የሚያስፈልጉ የሰው ሃይልና የሎጂስቲክስ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ተናግረዋል። በናሙና ጥናቱ ላይም ከ2 ሺ በላይ የመረጃ ሰብሳቢዎች፣800 የመስክ ተቆጣጣሪዎችና 250 ከፍተኛ የስታስቲክስ ባለሙያዎች እንዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል። ኤጀንሲው በሚያካሂደው የናሙና ጥናት ላይ ከዚህ በፊት በጥናት ውስጥ ተካትተው የማያውቁና ያልተዳሰሱ የጥናት መስኮችን ጨምሮ በግብርናው ዘርፍ ያለው ስኬትና አጠቃላይ ሁኔታ ምን እንደሚመሰል እንደሚጠናም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በጥናቱ  ላይ የአርሶአደሮችን ማደበሪያ አጠቃቀም መጠን፣የእንሰት ተክል ብዛት፣የመስኖ ተጠቃሚ አርሶአደሮች ብዛትና በግብርናው ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ በጥናቱ ትኩረት ይሰጣቸዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ ከመስከረም እስከ  ሰኔ አጋማሽ 2006 የሚካሄደው የግብርና ናሙና ጥናት ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ስኬት በግብአትነት እደሚያገለግልም ተጠቁሟል፡፡),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
320
ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች በድንች ተክል ህይወታቸውን እየለወጡ ነው፡ ዘ ጋርዲያን, .._2013. 0 260 195 ; 5; አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 72006 (ዋኢማ) - የደሴ ዙርያ ወረዳ አርሶ አደሮች ለዘመናት የአካባቢው መልከአምድራዊ አቀማመጥ አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳና የአፈር ለምነቱ ለአዝርዕት የማይመች እንዲሁም ከፍተኛ የአፈር መከላት የነበረነበት አካባቢ በመሆኑ ዜጎች ለችግር የተገላጡ ነበሩ  ሲል የእንግሊዙ ዘጋረዲያን ጋዜጣ አትቷል፡፡ በዚህ የተነሳ በአከባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች  ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ሊገፉ ተገደው ነበር፡፡ እንዲያውም አንዳንድ አርሶ አደሮች ያላቸውን ትንሽ ጥሪት ሽጠው ወደ ከተማ የቀን ስራ ለመስራት ለመሄድ እየተዘጋጁ ባሉበት ቅፅበት የድንች ተክልን እንዲተክሉ በተዘረጋው ፕሮጀክት ህይዎታቸውን እየቀየሩ ይገኛሉ ይላል የዘጋርዲያን ዘገባ፡፡ በድንች ተክልም በበዙ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ ወደ ኪሳቸው በማስገባት ከእጅ ወደ አፍ የነበረው ህይዎታቸውን ቀይርው የተንደላቀቀ ህይዎት እይገፉ ይገኛሉ፡፡ በፕሮከጅቱ እስካሁን ድረስ 10ሺ ዜጎች ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን የወረዳው አስተዳደር በቀጣይ 7ሺ አርሶ አደሮችን የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደታሰበ ተናግሯል፡፡ ከዚህ ቀደም አርሶ አደሮች ከ1 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ 75 ኪሎግራም ገብስ ብቻ እንደሚያገኙ የገለጸው የዘጋርዲያን ዘገባ በአሁኑ ሰዓት ግን በተመሳሳይ የሄክታር ሰፋት ላይ 20 ኩንታል ድንች እያገኙ አንዱን ኩንታል ድንች  በ340 ብር በመሸጥ ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውን ያትታል ሲለ ዘ ጋረዲያንን ጠቅሶ ኢሬቴድ ዘግቧል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
321
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የአርሶ አደሮችን አቅም ማጠናከር ተገቢ ነው- የመንግስታቱ ድርጅት ተቋማት , .._2013. 0 261 196 ; 5; አዲስ አበባ ታህሳስ 42006ዋኢማ - በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፉን ለማሳደግ ለሚደረገው ጥረት አርሶ አደሮች የሚቀርበው የብድር አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በዘርፉ የሚሰሩት የመንግስታቱ ድርጅት ተቋማት ገለፁ፡፡ የገንዘብ አቅርቦት ለልማት በተሰኘው መርሃ ግብር የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ልዩ መልእክተኛ  የኔዘርላንድ ንግስት ማክሲማ ፣የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፣የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት እና የዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ ተወካዩች በሃዋሳ አካባቢ እየተካሄደ ያለውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ስራዎች ላይ መጐብኘታቸውን አመልክተዋል፡፡ ተወካዮቹ በጉብኝታቸው በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን መረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡ የተቋማቱ ተወካዮችና የኔዘርላንድ ንግስት ማክሲማ እንደገለፁት የገንዘብ አቅርቦት ለሚያስፈልጋቸው በአንስተኛ ማሳ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች አገልግሎቱን በማስፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ አቅርቦቱ እንዲሰፋ የመንግስትና የግል ተቋማት በጋራ መስራት እንደሚያሻም ጠቁመዋል፡፡ለዚህም የሚቻለውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል ሲል የኢሬቴድ ዘገባ ያስረዳል፡፡  ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
322
ኢንስቲትዩቱ ከ 63 ሺ በላይ አርሶ አደሮችን የቴክኖሊጂ ተጠቃሚ ማድረጉን ገለጸ, .._2014. 0 260 195 ; 5; አዲስ አበባ ሚያዚያ 182006 (ዋኢማ) – በያዝነው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ዘጠኝ ወራት ከ63 ሺሕ 756 አርሶ አደሮችን የቴክኖሎጂ ቅድሚያ ማስፋፊያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረጉን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ገለጸ ። በኢንስቲትዩቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሮክቶሪየት ዳይሬክተር አቶ ደረሰ ተሾመ ለዋልታ እንደገለጹት በዘጠኝ ወሩ 57 ሺ232 አርሶ አደሮችን የተሻሻሉ የሰብልና የእንስሳት ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እንደነበር ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ ከአገሪቱ ስነ ምህዳሮች ጋር ተስማሚ የሆኑትንና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ 24 የሰብልና የእንስሳት ዝርያዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገብቷል ያሉት አቶ ደረሰ  በ17 የምርምር ማዕከላት  የማላመድ ሥራው እየተከናወነ ነው ብለዋል ። በአገሪቱ የተለያዩ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም  የማስፋፋት  ሥራ እየተከናወነ ነው ያሉት አቶ ደረሰ ባለፉት  ዘጠኝ ወራት  9 ሺሕ 475 አርሶ አደሮች ፤አርብቶአደሮች ፤ ከፊል  አርብቶ አደሮችና የልማት ሠራተኞች ሥልጠና ወስደዋል ብለዋል። ኢንስቲትዩቱ በሃገሪቱ ምርጥ ዝርያዎች ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ጥረት እንደሚያደርግ ገልጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት 17 ሺሕ ኩንታል ምርጥ የሰብልና የእንስሳት ዝርያዎች   ለክልሎች ተሠራጭተዋል ብለዋል ። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር   17  የግብርና ምርምር ማዕከላት ያሉት ሲሆን 835 ተመራማሪዎችና  1ሺሕ 234  የምርምር ቴክኒክ  ረዳቶች መኖራቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን  ማዕከል  ዘግቧል ። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
323
በትግራይ አንድ ሚሊየን የደሮ ጫጩቶች ለአርሶ አደሩ እየተከፋፈሉ ነው, - ; .._2014. 0 259 169 ; 5; አዲስ አበባ ፤ ህዳር 1 2007 (ዋኢማ) - በትግራይ ክልል አንድ ሚሊየን የዶሮ ጫጩቶች ለአርሶ አደሩ እየተከፋፈሉ መሆናቸውን የክልሉ እርሻና ገጠር ልማት ቢሮ አስታወቀ። - ; በክልሉ በሚገኙ ገጠር ወረዳዎች በተያዘው በጀት ዓመት ለ20ሺ አርሶ አደሮች ለማከፋፈል ከታቀደው አንድ ሚሊየን የዶሮ ጫጩቶች ውስጥ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ218 ሺ በላይ ጫጩቶች ለ4ሺ 360 ተጠቃሚዎች ተከፋፍሏል። - ; በሩብ የበጀት ዓመቱ የተሰራጩት ጫጩቶች ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ54ሺ ጫጩቶች በላይ ብልጫ እንዳለው የቢሮው እንስሳት ቀለብ ባለሙያ አቶ ጌታቸው ተክለሃይማኖት ገልጸዋል። - ; ለቁጥሩ መጨመር ለአርሶ አደሩ በልማት ቡድን በኩል ንቀናቄ በመፈጠሩ ፣ተጠቃሚውም በአጭር ጊዜ ከችግር የሚያላቅቅ ስራ መሆኑን በመገንዘባቸው መሆኑን አብራርተዋል። - ; ለተቃሚ አርሶ አደሮችም የዶሮ አረባበና አያያዝ በእርሻ ባሙያዎች አስፈላጊው ስልጠና መሰጠቱንም አቶ ጌታቸው ጠቅሰዋል ። - ; ዓምና ለአንድ ሰው 30 የዶሮ ጫጩቶች መሰጠቱን የጠቆሙት ባለሙያው አሁን ግን ከዘርፉ የሚገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላቅ ያለ መሆኑን በመገንዘብ ለአንድ ሰው 50 ጫጩቶች እየተከፋፈሉ መሆኑን አስረድተዋል ። - ; በተለይም በክልሉ ያሉት ሴቶችና ወጣቶች በምግብ ራሳቸውን በመቻል ካለባቸው ድህነት ለማላቀቅና ወደ ተሻለ ኑሮ ለማሸጋገር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ ጌታቸው ገልጸዋል። - ; በመቀሌ ከተማ የሚገኘው የዶሮ እርባታ ተቋም በቂ ጫጩቶች የማቅረብ ዓቅም አለው ያሉት አቶ ጌታቸው፤ በወረዳዎችም የሚገኙ አንዳንድ ወጣቶች ጫጩቶችን በብዛት  ለአርሶ አደሩ እያቀረቡ መሆናቸውን ጠቁመዋል  ። - ; ባለፈው በጀት ዓመት 647ሺ 754 ጫጩቶች ለ56ሺ 360 ተጠቃሚ አርሶ አደሮች መከፋፈሉን ባለሙያው ጠቅሶ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
324
በክልሉ 30 ሺ የሚሆኑ ሞዴል አርሶ አደሮች የግብርና ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ , - ; .._2014_30. 0 258 146 ; 5; አዲስ አበባ ፤ ታህሳስ 21 2007 (ዋኢማ) - በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ 30ሺ ሞዴል አርሶ አደሮች በተለያዩ ሥፍራዎች በሚገኙ የአርሶአደሮች የማሠልጠኛ ማዕከላት ሰርቶ ማሣያዎችን በመጠቀም ውጤታማ ሥራዎችን በማከናወን ተጠቃሚ እየሆኑ ነው። - ; በክልሉ የግብርና ቢሮ የኤክስቴንሽን ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አብርሃም ሙጩ ለዋልታ እንደገለጹት ሞዴል አርሶአደሮቹ በአቅራቢያቸው ከሚገኙት ማሠልጠኛ ማዕከላቱ የሚወጡትን የተለያዩ የግብርና ምርምር ውጤቶችን በሰርቶ ማሳያቸው ተግባራዊ በማድረግ በኑሯቸው ላይ ትልቀ ለውጥ እያመጡ ነው ። - ; የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ የሰብልና የእንስሳት ዝርያዎች ማስፋፊያ ሥራዎች እየተጠናከሩ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አብርሃም በክልሉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የክልሉ አርሶ አደሮችን ከሞዴል አርሶአደሮቹ ምርጥ ተሞክሮውን እንዲቀስሙ ተደርጓል ብለዋል ። - ; በክልሉ 2ሺ600 በሚሆኑ ሠርቶ ማሳያዎች በስነ አዝርዕት፤ በእንስሳት እርባታና በተለያዩ የግብርና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ያብራሩት አቶ አብረሃም አርሶ አደሩ በቀላሉ ቴክኖሎጂዎችን እየተላመዳቸው ይገኛል ብለዋል። - ; በሲሪንቃና በደብረ ብርሃን  የግብርና ምርምር ማዕከላት የተሠራጩት የዳልፐርና ያዋሲ የተባሉ የተሻሻሉ የበግ ዝርያዎች በሶስት ወር ውስጥ ደልበው ለእርድ የሚደርሱ በመሆናቸው  የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት  እያሳደጉ ይገኛል ብለዋል ። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
325
በ7ኛው የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ፌስቲቫል 920 ግለሰቦች ይሸለማሉ, .._2015. 0 263 198 ; 5; አዲስ አበባ ፤ የካቲት 19 2007 (ዋኢማ) - ከካቲት 20 እስከ 22 በደቡብ ክልል ሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው 7ኛው አገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ፌስቲቫል ላይ 920 ለሚሆኑ ሞዴል አርሶአደሮች ፣ አርብቶ አደሮችና ድጋፍ ሠጪ አካላት የዕውቅና ሽልማት እንደሚሠጥ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አስራት ተክለፃዲቅ ለዋልታ እንደገለጹት ሽልማቱ የሚሰጠው በልማት ቡድን ተደራጁና የተለያዩ የግብርና ግብዓቶችን፣ ቴክኖሎጂዎችንና አሠራሮችን ተግባራዊ አድርገው ውጤት ያመጡ የአንድ ለአምስት አደረጃጀቶች ናቸው። በአጠቃላይ ከ1ነጥብ5 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት ያፈሩ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በሽልማቱ እንደሚካተቱ የጠቆሙት አቶ አሥራት ከተሸላሚዎቹ ውስጥ 30 በመቶ ሴቶች 20 በመቶ ደግሞ ወጣቶች እንደሚሆኑ ተናግረዋል። የሽልማቱ ዓለማ በአገር አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ አርሶ አደሮችን እውቅና በመስጠት ወደ ባለሃብትነትና ወደ ኢንዱስትሪ ልማት እንዲሸጋገሩ እንዲሁም የግብርና ዘረፉ እንዲያድግ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው። የአገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ፌስቲቫል በ1999 ዓም የተጀመረ ሲሆን እስካሁን 4ሺ 510 አርሶ አደሮች ፤ አርብቶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች እውቅና እና ሽልማት ማግኘታቸው ታውቋል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
326
የአርሶ አደሩ ውጤታማነት የግብርናው ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው, - ; .._2015. 0 187 196 ; 5; አዲስ አባባ የካቲት 242007 (ዋኢማ) - አርሶ አደሩ እያከናወነ ያለው ውጤታማ ተግባር የግብርናው ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡ - ; ሰባተኛው አገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን እምርታዊ ለውጥ በምርታማነትና በአመራረት ዘይቤ በሚል መሪ ቃል በሃዋሳ ከተማ ተከብሯል። - ; በበዓሉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመከተል አርሶ አደሩ ገበያ ተኮር ምርት አያመረተ ተጠቃሚነቱን ማሳደግ ችሏል፡፡ - ; አርሶ አደር መሆንና በግብርና ሙያ መሰማራት ኋላቀርነት ተደርጎ ከሚታይበት የአስተሳሰብ ድህነት በመላቀቅ ፋና ወጊ መሆናችሁና ለበርካቶች መለወጥና ማደግ ምክንያት የሆናችሁት በግል ጥረታችሁና በልማታዊ መንግስታችን ድጋፍ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ - ; በርካታ አርሶ አደሮች ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮ በመላቀቅ ዛሬ ለአለም ገበያ ተፈላጊ የሆነ ምርት ማምረት ስራ ውስጥ መግባታቸው በግብርናው መስክ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ትክክለኛና ፈር ቀዳጅ ጉዞ መጀመራቸውን እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ - ; የሀገሪቱ የግብርና ስራ ውጤታማ መሆን የቻለው የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን መቀበልና መተግበር በመቻላቸው መሆኑንና ይህ ተጠናክሮ  እስከቀጠለ ድረስ ዘርፉን ሌሎች ከደረሰሰቡት ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ - ; በአለም አቀፍ ደረጃ የስንዴ ምርታማነት በሄክታር 180 ኩንታል መድረሱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በሞዴል አርሶ አደሮች በአማካይ 60 ኩንታል መሆኑ ሲታሰብ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ በአርሲ ዞን ሲሬ ወረዳ ሞዴል አርሶ አደር የሆኑት በሄክታር 120 ኩንታል ላይ ለመድረስ በትጋት መስራት እንዳለባቸው አቶ ኃይለማርያም አሳስበዋል፡፡ - ; የግብርና ምርታመነት የሚያኮራ ደረጃ ላይ አልደረስንም፤ በበሌሎች ሰብሎችና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍም ቢሆን መድረስ ከሚገባን አንጻር ብዙ ይቀረናል ብለዋል፡፡ - ; እንደ ኢዜአ ዘገባ ለዚህም ምክንያቱ ሞዴል አርሶ አደሮች ከደረሱበት ደረጃ አብዛኛው አርሶ አደር ያልደረሰ መሆኑን በመረዳት በቀጣይ ጥቂት አመታት ሞዴል አርሶ አደሮች ደረጃ ለማድረስ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ - ; ሞዴል አርሶ አደሮቹ በሚያከናወኑት የግብርና ልማት ስራ ሌሎችን ለማብቃት ተግተው እንዲሰሩና ይህን ተግባር ለማገዝ መንግስት ምንጊዜም ከጎናቸው እንደሚቆም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ - ; በተጨማሪም የግብርና ምርቶችን በማቀነባበር፤ የአርሶ አደሩን ምርት በመረከብና አርሶ አደሮችን በማስተባበርና በማደራጀት የተሻለ የገበያ ስርዓት በመዘርጋት ረገድ የህብረት ስራ ማህበራት የሚያከናውኑት ተግባር ከፍተኛ በመሆኑ ማህበራቱን የማጠናከር ስራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ - ; የግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው ያለፉት ዓመታት የአርሶ አደሮች የሽልማት ስነስርዓት በአርሶ አደሮች መካከል ጠንካራ የውድድር መንፈስና መነሳሳት እንዲፈጠርና የበለጠ ተግተው በመስራት የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስችላል ብለዋል፡፡ - ; በርካታ አርሶ አደሮች ራስን ከመቻል ባለፈ ወደ ባለሀብትነት ጎራ እንዲቀላቀሉና ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ እሴት ወደሚጨምሩ ስራዎች በመሸጋገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ ሚናም አሻራቸውን ማሳረፍ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ - ; በዓሉ መከበር ከጀመረ ወዲህ የውጤታማ ሞዴል አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቁጥር እያደገ በመምጣቱ የዛሬ ተሸላሚዎች 920 መድረሱን ገልፀዋል፡፡ - ; በዘንድሮው ሽልማት በልማት ቡድን ተደራጅተው የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና የተሻሻሉ አሰራሮችን በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ በመተግበር ውጤት ያመጡ የልማት ቡድኖችና አንድ ለአምስት ትስስሮች መካተታቸውን አቶ ተፈራ አስረድተዋል፡፡ - ; ከሞዴል ተሸላሚ አርሶ አደሮች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ስሬ ወረዳ የመጡት አርሶ አደር አበበ ትርፌ እንዳሉት በስንዴ ልማት መስክ ለተወሰኑ አመታት ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በገበያ ተፈላጊ ወደሆነው የሽንኩርት ልማት በመሰማራት በሄክታር ከ300 ኩንታል በላይ እያመረቱ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ካፒታላቸውን ወደ 20 ሚሊዮን ብር ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ - ; መንግስት በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ በሰሩት ስራ ከግብርና ስራቸው በተጨማሪ በሆቴል ስራ በመሰማራት በሲሬ ከተማ ባለሁለት ፎቅ ህንጻ በመገንባት እየሰሩ አንደሚገኙና በቀጣይ የግብርና ስራቸውን በማጠናከር የበለጠ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ ባከናወኑት ውጤታማ ስራ አሁን ወደ ባለሀብትነት ደረጃ አድገው እውቅና ማግኘታቸው እንዳኮራቸው ተናግረዋል፡፡ - ; ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ማኦ ኮሞ ወረዳ የመጡትና ወደ ባለሀብትነት ደረጃ አድገው በበዓሉ ላይ እውቅና የተሰጣቸው አርሶ አደር ጅብሪል ኢሳ በበኩላቸው በቡና፣ በማሽላና ሌሎች የአገዳና ቅባት ሰብሎች ልማት ተሰማርተው ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ - ; የግብርና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክር በመቀበልና ባለፉት አመታት የተከናወኑ በዓላት በአርሶ አደሩ መካከል የልማት ፉክክር በማምጣቱና እሳቸውም የበለጠ በመስራታቸው ሀብታቸውን ማሳደግና ሌሎችንም ወደ ባለሀብትነት ደረጃ እንዲያድጉ ማብቃት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ - ; በሰባተኛው አገርዓቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን ላይ 920 አርሶ አሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ ባለሀብቶችና ሌሎች አጋዥ አካላት ተሸልመዋል፡፡ - ; ሽልማትና እውቅና ከተሰጣቸው መካከል 580 አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ሲሆኑ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ወጣቶች ናቸው፡፡ - ; የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ስድስት የአርሶ አደሮች ቀን 5 ሺህ 430 አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ - ; የአርሶ አደሩ ውጤታማነት የግብርናው ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው አዲስ አባባ የካቲት 242007 (ዋኢማ) -  አርሶ አደሩ እያከናወነ ያለው ውጤታማ ተግባር የግብርናው ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡ - ; ሰባተኛው አገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን እምርታዊ ለውጥ በምርታማነትና በአመራረት ዘይቤ በሚል መሪ ቃል በሃዋሳ ከተማ ተከብሯል። - ; በበዓሉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመከተል አርሶ አደሩ ገበያ ተኮር ምርት አያመረተ ተጠቃሚነቱን ማሳደግ ችሏል፡፡ - ; አርሶ አደር መሆንና በግብርና ሙያ መሰማራት ኋላቀርነት ተደርጎ ከሚታይበት የአስተሳሰብ ድህነት በመላቀቅ ፋና ወጊ መሆናችሁና ለበርካቶች መለወጥና ማደግ ምክንያት የሆናችሁት በግል ጥረታችሁና በልማታዊ መንግስታችን ድጋፍ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ - ; በርካታ አርሶ አደሮች ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮ በመላቀቅ ዛሬ ለአለም ገበያ ተፈላጊ የሆነ ምርት ማምረት ስራ ውስጥ መግባታቸው በግብርናው መስክ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ትክክለኛና ፈር ቀዳጅ ጉዞ መጀመራቸውን እንደሚያሳይ ገልጸዋል፡፡ - ; የሀገሪቱ የግብርና ስራ ውጤታማ መሆን የቻለው የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን መቀበልና መተግበር በመቻላቸው መሆኑንና ይህ ተጠናክሮ  እስከቀጠለ ድረስ ዘርፉን ሌሎች ከደረሰሰቡት ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ - ; በአለም አቀፍ ደረጃ የስንዴ ምርታማነት በሄክታር 180 ኩንታል መድረሱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በሞዴል አርሶ አደሮች በአማካይ 60 ኩንታል መሆኑ ሲታሰብ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ በአርሲ ዞን ሲሬ ወረዳ ሞዴል አርሶ አደር የሆኑት በሄክታር 120 ኩንታል ላይ ለመድረስ በትጋት መስራት እንዳለባቸው አቶ ኃይለማርያም አሳስበዋል፡፡ - ; የግብርና ምርታመነት የሚያኮራ ደረጃ ላይ አልደረስንም፤ በበሌሎች ሰብሎችና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍም ቢሆን መድረስ ከሚገባን አንጻር ብዙ ይቀረናል ብለዋል፡፡ - ; እንደ ኢዜአ ዘገባ ለዚህም ምክንያቱ ሞዴል አርሶ አደሮች ከደረሱበት ደረጃ አብዛኛው አርሶ አደር ያልደረሰ መሆኑን በመረዳት በቀጣይ ጥቂት አመታት ሞዴል አርሶ አደሮች ደረጃ ለማድረስ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ - ; ሞዴል አርሶ አደሮቹ በሚያከናወኑት የግብርና ልማት ስራ ሌሎችን ለማብቃት ተግተው እንዲሰሩና ይህን ተግባር ለማገዝ መንግስት ምንጊዜም ከጎናቸው እንደሚቆም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ - ; በተጨማሪም የግብርና ምርቶችን በማቀነባበር፤ የአርሶ አደሩን ምርት በመረከብና አርሶ አደሮችን በማስተባበርና በማደራጀት የተሻለ የገበያ ስርዓት በመዘርጋት ረገድ የህብረት ስራ ማህበራት የሚያከናውኑት ተግባር ከፍተኛ በመሆኑ ማህበራቱን የማጠናከር ስራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ - ; የግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው ያለፉት ዓመታት የአርሶ አደሮች የሽልማት ስነስርዓት በአርሶ አደሮች መካከል ጠንካራ የውድድር መንፈስና መነሳሳት እንዲፈጠርና የበለጠ ተግተው በመስራት የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስችላል ብለዋል፡፡ - ; በርካታ አርሶ አደሮች ራስን ከመቻል ባለፈ ወደ ባለሀብትነት ጎራ እንዲቀላቀሉና ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ እሴት ወደሚጨምሩ ስራዎች በመሸጋገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ ሚናም አሻራቸውን ማሳረፍ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ - ; በዓሉ መከበር ከጀመረ ወዲህ የውጤታማ ሞዴል አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቁጥር እያደገ በመምጣቱ የዛሬ ተሸላሚዎች 920 መድረሱን ገልፀዋል፡፡ - ; በዘንድሮው ሽልማት በልማት ቡድን ተደራጅተው የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና የተሻሻሉ አሰራሮችን በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ በመተግበር ውጤት ያመጡ የልማት ቡድኖችና አንድ ለአምስት ትስስሮች መካተታቸውን አቶ ተፈራ አስረድተዋል፡፡ - ; ከሞዴል ተሸላሚ አርሶ አደሮች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ስሬ ወረዳ የመጡት አርሶ አደር አበበ ትርፌ እንዳሉት በስንዴ ልማት መስክ ለተወሰኑ አመታት ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ በገበያ ተፈላጊ ወደሆነው የሽንኩርት ልማት በመሰማራት በሄክታር ከ300 ኩንታል በላይ እያመረቱ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ካፒታላቸውን ወደ 20 ሚሊዮን ብር ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ - ; መንግስት በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በመታገዝ በሰሩት ስራ ከግብርና ስራቸው በተጨማሪ በሆቴል ስራ በመሰማራት በሲሬ ከተማ ባለሁለት ፎቅ ህንጻ በመገንባት እየሰሩ አንደሚገኙና በቀጣይ የግብርና ስራቸውን በማጠናከር የበለጠ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ ባከናወኑት ውጤታማ ስራ አሁን ወደ ባለሀብትነት ደረጃ አድገው እውቅና ማግኘታቸው እንዳኮራቸው ተናግረዋል፡፡ - ; ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ማኦ ኮሞ ወረዳ የመጡትና ወደ ባለሀብትነት ደረጃ አድገው በበዓሉ ላይ እውቅና የተሰጣቸው አርሶ አደር ጅብሪል ኢሳ በበኩላቸው በቡና፣ በማሽላና ሌሎች የአገዳና ቅባት ሰብሎች ልማት ተሰማርተው ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ - ; የግብርና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክር በመቀበልና ባለፉት አመታት የተከናወኑ በዓላት በአርሶ አደሩ መካከል የልማት ፉክክር በማምጣቱና እሳቸውም የበለጠ በመስራታቸው ሀብታቸውን ማሳደግና ሌሎችንም ወደ ባለሀብትነት ደረጃ እንዲያድጉ ማብቃት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ - ; በሰባተኛው አገርዓቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ቀን ላይ 920 አርሶ አሮች፣ ከፊል አርብቶ አደሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች፣ ባለሀብቶችና ሌሎች አጋዥ አካላት ተሸልመዋል፡፡ - ; ሽልማትና እውቅና ከተሰጣቸው መካከል 580 አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ሲሆኑ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ወጣቶች ናቸው፡፡ - ; የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ስድስት የአርሶ አደሮች ቀን 5 ሺህ 430 አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
327
የአርሶ አደሩን ምርት በአለምና በአገሪቱ ገበያ ለማሰራጨት መሰረተ ልማት ወሳኝ ነው, - 12.1599998474121; - 1.3; .._2015. 0 260 195 ; 5; አዲስ አበባ፤ ግንቦት 62007 (ዋኢማ) - በአገሪቱ አርሶ አደሮች ላይ የተመሰረተዉ የግብርና ምርት እየጨመረ በመምጣቱ በአለምና በአገሪቱ ገበያ ተሰራጭቶ የግብይት ስርአቱ ቀልጣፋ ሆኖ እንዲቀጥል መሰረተ ልማት መገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም በምእራብ ሸዋ ዞን በአምቦ ከተማ ከአዲስ አበባ አምቦ፣ኢጃጂ፣በደሌ የባቡር መስመር ግንባታን ለማስጀመር የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡የመሰረተ ድንጋዩን ካኖሩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ እንዳስታወቁት በመጀመሪያዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ወቅት ስንረባረብ የቆየነው የልማት ሁሉ መሰረት በሆነዉ የግብርና ልማት ላይ ነበር፡፡በአርሶ አደሩ የተመሰረተዉ ዋንኛዉ የግብርና ምርት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን ገልጸው ምርቱን በአለምና በአገር ገበያ ተሰራጭቶ የግብይት ስርአቱ ቀልጣፋ ሆኖ እንዲቀጥል ካስፈለገ መሰረተ ልማት መገንባት ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል። የምእራብ ሸዋ ዞን ሰፋፊ የቴክኖሎጂ አማራጭ በመጠቀም የግብርና ምርት የሚመረትበት አካባቢ በመሆኑ ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ የባቡር መሰረተ ልማት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት መሰረተ ልማቱ በዚያው እንዲያልፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡በአምቦ ከተማ በሚቀጥሉት አምስት አመታት የባቡር መስመር ዝርጋታዉ ሲጠናቀቅ አካባቢዉ የኢንዱስትሪ ማእከል እንደሚሆን እምነታችን የጸና ነዉ ብለዋል፡፡ልማታዊና ዴሞኪራሲያዊ መስመር የያዘዉን ኦህዴድኢሀአዴግን በመምረጥ ድህነትን በአንድ ላይ ታግለን ማሸነፍ ይኖርብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ጥሪ አቅርበው ይህን የምናደርገዉ በምርጫ ለማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ ግንባታ ካልተፋጠነ እድገታችን ቀጣይነት የማይኖረዉ መሆኑን ለማስገንዘብ ነዉ ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኢንጂነር ጌታቸዉ በትሩ እንደገለጹት በአምቦ ከተማ የመሰረተ ድንጋይ የሚቀመጥለት የባቡር መስመር ፕሮጀክት መንግስት በአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዉስጥ ሊያስገነባቸዉ ካቀዳቸዉ የባቡር ፕሮጀክቶች አንዱ ነው። ስራዉ በቅርቡ የሚጀመረዉና 491 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባቡር መስመር የምእራቡን የአገሪቱ ክፍል ከሌሎች አካባቢዎች የሚያገናኝ ከመሆኑም ሌላ ከደቡብ ሱዳንና ከሌሎችም የአፍሪካ ሀገራት ጋር የሚገናኝ ነዉ ብለዋል፡፡በአገሪቱ እየተገነቡ ያሉና ወደፊትም የሚገነቡ የባቡር መስመሮች ለህዝቦች የኢኮኖሚ፣የፖለቲካና ማህበራዊ ትስስር ጉልህ አስተዋጽኦ ከማድረግ ባሻገር ከጎረቤት አገራት ጋር ያሉንን ግንኙነቶች እንደሚያጠናክረው አስታውቀዋል። የባቡር መስመሩ መገንባት ለአካባቢዉ ህብረተሰብ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ የዜጎችን የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሰረተ ልማት መሆኑን ተናግረዋል፡፡የዚህ ግዙፍ መሰረተ ልማት ግንባታ እዉን ሊሆን የሚችለዉ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት አካላትና የህብረተሰቡ ድጋፍ  ሲኖር በመሆኑ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለግንባታዉ መሳካት የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡የትራንስፖርት ሚኒስትር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ እንዳሉት ከአዋሽ ወልዲያ ፣ከወልዲያ መቀሌ ከአዲስ አበባ አምቦ ኢጃጂ፣በደሌና ጅማ የሚዘረጋዉ የባቡር መስመር ወደ ጎረቤት ሱዳን የሚቀጥል ነው። ይህም በሀገር ዉስጥ የሚመረተው ምርት ወደ ዉጭ በፍጥነት በማጓጓዝ የወጪና ገቢ ንግዱን ለማቀላጠፍ ከመርዳቱም ሌላ የአገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ትስስርና የህዝቦችን አንድነት ያጠናክራል ብለዋል፡፡የባቡር መስመር ዝርጋታዉ የአገሪቱን የልማት ማእከል የሚያስተሳስርና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስታውቀዋል፡፡ግዙፉ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለታሰበለት አላማ እንዲዉል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ አሳስበዋል። አንዳንድ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች የዘመናት ጥያቄአቸዉ መልስ በማግኝቱ በመደሰት እንደከዚህ በፊቱ ከመንግስት ጎን በመቆም የተጀመረዉን ልማት ለማፋጠን መነሳሳታቸዉን አረጋግጠዋል፡፡አገሪቱ በመጀመሪያው የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት አጠናቃ ለአገልግሎት ለማብቃት በሙከራ ወቅት ላይ ነች። ከአዲስ አበባ-ሞጆ-አዋሽ-ድሬዳዋ-ደዋሌ የሚያመራውና ከጅቡቲ የሚያገናኘው የባቡር መሥመር ሥራም በአሁኑ ወቅት 80 መቶ ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል። እንዲሁም ቀደም ሲል በተመሳሳይ ሁኔታ የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለት የመቀሌ-ወልዲያ-ሐራ ገበያ- ሰመራ -አሳይታ የባቡር መሥመር   ስራ በመጀመር ላይ መሆኑም ተገልጿል። አገሪቱ በአጠቃላይ ከአምስት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸውና በስምንት አቅጣጫ የባቡር መስመር ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል። እንደ ኢዜአ ዘገባ በአምቦ ከተማ በተካሄደው የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ ስርአት ላይ ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናት፣የአካባቢዉ ነዋሪዎች፣የእምነት አባቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
328
በቀጣይ 5 ዓመታት በአርሶ አደር ደረጃ የሰብል ምርትን ከ270 ወደ 406 ሚልዮን ኩንታል ለማሳደግ ታቅዷል - , - ; .._2015_3. 0 264 198 ; 5; አዲስ አበባ፣ ሰኔ 262007(ዋኢማ)-ቀጣዩ የትራንስፎርሜሽንና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ዘመን በአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ላይ የተመሠረተ የግብርና ልማት ማፋጠን ላይ ትኩረትን ያደረገ ነው። - ; በተጨማሪም የተማሩ ወጣቶችን በማደራጀት በግብርና ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ በማድረግ፣ አገራዊ እና የተመረጡ የውጭ የግል ባለሃብቶች እንደየችሎታቸው በከፍተኛ ደረጃ እንዲሳተፉ በማድረግ በሰብል፣ በአበባ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፎች ትራንስፎርሜሽን ለማምጣትም ታቅዷል፡፡ የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሩ ግብርና አሁንም ዋናው የግብርና ዕድገት መሠረት ሆኖ እንዲቀጥልና የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሩ ግብርና ፈጣን እድገት እንዲያረጋግጥ የማስፋት ስትራቴጂውን አሟልቶ መተግበር፣ የልማት ቀጠናዎችን - ; መሠረት ያደረገ የግብርና ልማት መከተል እና ሌሎች በግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ ችግሮችን መፍታት ትኩረት የሚሰጣቸዉ ይሆናል፡፡ - ; በተመሳሳይ የግል ባለሀብቱ በግብርና ልማት ላይ የሚኖረው ድርሻ ከፍ እንዲል በማድረግ ሀገሪቱ ለያዘችው ልማትና ከድህነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት እንዲያግዝ ትኩረት ተሰጥቶ ይሠራል፡፡ - ; የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን በማጎልበት አስተማማኝ የግብርና ልማት ለማረጋገጥ እንዲቻል የግብርና ልማት ዕቅዶች በይዘትም በትግበራም ከአርንጓዴ ልማት ራዕይ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ማስቻል ከዚሁ ጋር የመስኖ ልማትን ማስፋፋት ሌሎች የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡ - ; የአርሶ አደሩን ገቢ በፍጥነት ለማሳደግ አርሶ አደሩ የላቀ ዋጋ ወዳላቸው ምርቶች ማምረት እንዲሸጋገር ማድረግና የግብርና ግብይትን በተቀላጠፈ አካሄድ ተግባራዊ ማድረግ፣ በገጠር ፈጣን ዕድገት የሚፈጥረውን ዕድል በመጠቀም የወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሌሎች ትኩረት የሚሰጣቸዉ መሆኑም በእቅዱ ተካቷል። - ; በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የአርሶ-አደርና የአርብቶ-አደር ምርታማነትን ለማሳደግና የምርት ጥራት ለማረጋገጥ የተጀመርው ሥራ በዘርፉ ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጣ ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑ ተገልጿል። - ; በዚህም ከአነስተኛ አርሶ-አደር ማሳ በመኸር ወቅት የሚገኘው የሰብል ምርት በ2007 ከነበረበት 270 ሚልዮን ኩንታል ወደ 406 ሚልዮን ኩንታል ለማሳደግ ታቅዷል፡፡ - ; የአገዳ ሰብል ምርታማነትን በ2007 ከነበረበት 28.5 ኩንታል በሄክታር በ2012 ወደ 41.9 ኩንታል በሄክታር በማሳደግ አጠቃላይ ዓመታዊ ምርቱንም በ2007 ከነበረበት 115 ሚሊዮን ኩንታል በ2012 ወደ 171.78 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ፣ - ; የብርዕ ሰብል ምርታማነትን በ2007 ከነበረበት 19.5 ኩንታል በሄክታር በ2012 ወደ 30.8 ኩንታል በሄክታር በማሳደግ አጠቃላይ ዓመታዊ ምርቱን በ2007 ከነበረበት 123 ሚሊዮን ኩንታል በ2012 ወደ 184.22 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ፣ - ; በጥራጥሬ ሰብል ምርታማነት በ2007 ከነበረበት 16.4 ኩንታል በሄክታር በ2012 ወደ 24 ኩንታል በሄክታር በማሳደግ አጠቃላይ ዓመታዊ ምርቱን በ2007 ከነበረበት 24.4 ሚለዮን ኩንታል በ2012 ወደ 38.75 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ፣ - ; የቅባት ሰብል ምርታማነት በ2007 ከነበረበት 8.99 ኩንታል በሄክታር በ2012 ወደ 12.7 ኩንታል በሄክታር በማሳደግ አጠቃላይ ዓመታዊ ምርቱን በ2007 ከነበረበት 7.9 ሚለዮን ኩንታል በ2012 ወደ 11.5 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ፣ - ; የቡና ምርታማነትና ምርት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በ2007   ከተመዘገበው 7.04 ኩንታል በሄክታር በ2012 መጨረሻ ላይ ወደ 10.83 ኩንታል በሄክታር በማሳደግ የቡና ምርት በ2007 በጀት ዓመት ከተደረሰበት 548.2 ሺህ ቶን በ2012 መጨረሻ ወደ 1102.62 ሺህ ቶን ለማሳደግ ግብ ተቀምጧል፡፡ - ; በአርሶአደር አቅም የሚሠራው የመስኖ ልማት በማጠናከር በትራንስፎርሜሽንና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ዘመን ከ4 ሚልዮን ሄክታር በላይ መሬት እንዲለማ ለማደረግም ታቅዷል፡፡ - ; በተጓዳኝ በክልልና በፌዴራል መንግሥት ደረጃ የሚሠሩ አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ልማትና ግድብ ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑም ተገልጿል። - ; በተግባር ተፈትሸው ውጤት ያመጡ ቴክኖሎጂዎች ለሁሉም ለማዳረስና ሁሉም እንዲያከናውኗቸው ለማድረግ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በተከታታይ ተፈትሸው እንዲቀርቡ እንዲሁም የግብርና ምርምር ተቋሞቻችንና የግብርና ኤክስቴንሽን ተቋሞቻችን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ እንዲሸጋገሩ ማድረግ የትራንስፎርሜሽንና ዘላቂ ልማት ዕቅዳችን የግብርና ልማት ግቦች ይሆናሉ፡፡ - ; በሦስተኛ ደረጃ  በአርሶ-አደሩና በአርብቶአደሩ ዘንድ እመርታ ማምጣት ያለብን በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ሲሆን፥ በመጀመሪያው የዕቅድ ዘመን የመጨረሻዎቹ ዓመታት አካባቢ በዳልጋ ከብቶችና ዶሮ ዝርያ ማሻሻል ረገድ መጠነኛ ለውጥ የመጣ ቢሆንም አመርቂ አለመሆኑ ታይቷል፡፡ - ; እስከአሁን ያሉንን ምርጥ ተሞክሮዎች በማስፋት በቀጣዩ የትራንስፎርሜሽንና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ዘመን ትራንስፎርሜሽን ማምጣት የሚያስፈልግ ሲሆን፥ ይህንንም ለማድረግ የእንስሳት ሃብት ልማት ሥራው የሚካሄድበትን የልማት ቀጠና በአግባቡ ይለያል ። - ; እዚህ ላይ በአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢዎች የአካባቢ ዝሪያ መርጦ የማዳቀል ወይም የማራባት ሥራ እንዲሁም በግል ባለሃብቶች የሚሠሩ ዘመናዊ የእርባታ ማዕከላት (ራንቾች) እንዲስፋፉ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል፤ ከዚህ አኳያ ከመሬት አቅርቦት ጀምሮ ሁሉአቀፍ ድጋፍ ማድረግ ዋናው የትኩረት አቅጣጫም ይሆናል፡፡ - ; ከላይ የተጠቀሱትን የግብርና ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ የመጨመር ጉዳይ የግብርና ምርቶች ግብይትን ዘመናዊ ከማድረግ ውጭ ሊሳካ እንደማይችል ግንዛቤ ተወስዷል። - ; በመጀመሪያ የዕድገትና ትራንስፎርመሽን ዕቅድ ዘመን የግብርና ግብይትን ለማሻሻል የተደረገው  ጥረት መሻሻል ያሳየ ቢሆንም መሠረታዊ ለውጥ አላመጣም ፤ ከዚህ አኳያ የግብርና ግብይት ሥርዓቱን ቀልጠፋና ውጤታማ ለማድረግ መሥራት ላይ ትኩረት ይደረጋል። - ; ከግብይት ባልተናነሰ ሁኔታ ከፍ ሲል የተጠቀሱት የግብርና ልማት ሥራዎች በተለይም እስከአሁን በውጤታማነቱ ብዙ ልምድ በሌለን በአትክልትና ፍራፍሬ እና በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ከፍተኛ የግብዓት አቅርቦት ችግር እንደሚከሰት ይጠበቃል። - ; የግብርና ምርታማነትን ከመጨመር አኳያ የራሱ አስተዋፅዖ የሚያበረክተው የግብርና ሜካናይናዜሽን ግብዓቶች በተደራጀ መንገድ እንዲቀርቡ ይደረጋል፤ በተመሳሳይም የግብኣት አቅርቦት አቅም በሁለንታዊ መልኩ በፌዴራልና በክልሎች ደረጃ እንዲጠናከር ይሰራል፡፡ - ; የተማሩ  ወጣቶችና  የግል  ባለሃብቶች  የግብርና  ልማት  ሥራ፦ - ; የተማሩ ወጣቶች በተደራጀ መንገድ በግብርና ልማት ሥራ እንዲሳተፉ የተቀናጀ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ የሚሰጥ ነው የሚሆነው። - ; በተለይ ለኤክስፖርት ገበያና ለአግሮ ፕሮስሲንግ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማምረት ለይ ትኩረት በመቸር፥ ከዩኒቨርስቲና ከኮሌጅ የተመረቁ ወጣቶች ለኢንተርፕራይዝ ልማት የሚያስፈልጉትን ሙያዎች አጣምረው እንዲይዙ  በወጣቶቹ ፍላጐት ላይ በመመስረት እንዲደራጁ  ድጋፍ ይሰጣል። - ; ሀገራችን ካላት ዕምቅ ለግብርና ምቹ የሆነ መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ሁኔታ ጋር የሚመጣጠን የግል ባለሃብቱ የግብርና ኢንቨስትመንትና ልማት ግን እስከአሁን አልተረጋገጠም፡፡ ስለሆነም ከ3 ሚሊዮን ሄክታር ያላነሰ ምቹ መሬት ውስጥ ከ100 ሄክታር እስከ 5 ሺህ ሄክታር መሬት የያዙ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች ወይም አነስተኛና መካከለኛ ባለሃብቶች የያዙትን መሬት በአግባቡ እንዲያለሙት የተቀናጀ ድጋፍ ይደረግላቸውል፡፡ - ; በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ ልማት ውስጥ በአዲስ መልክ ለሚገቡትም ክልሎች መሬት አዘጋጅተው ከተቀናጀ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ጋር እንዲያቀርቡ የሚደረግ ነው የሚሆነው። - ; በተመሳሳይ አነስተኛና መካከለኛ ባለሃብቶች ከተማሩ ወጣት የግብርና ኢንቨሰተሮችና ከከፍተኛ ባለሃብቶች ጋር የሚቀናጁበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ - ; በአጠቃላይ ግብርና በተለይም ለሴቶችና ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ተኪ የለሽ ሚናውን እንዲጫወት ይደረጋል፡፡ - ; በዚህ መሠረት ግብርና በመሰረታዊ አማራጭ ቢያንስ በየዓመቱ የ8 በመቶ ዕድገት እንዲቀጥል ከተቻለም በእጥፍ እንዲያድግና የግብርና ዕድገት የኢኮኖሚ ዕድገታችን ዋነኛ ምንጭ ሆኖ በማገልገል፣ የምግብ ዋስትናችንን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ፣ የዋጋ ግፊትን ለመቋቋም፣ የአግሮ-ፕሮስሲንግ ኢንዱስትሪዎች የጥሬ ዕቃ ፍላጐት ለማሟላትና የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) ገበያ በማሳደግ የክፍያ ሚዛኑን እንዲያጠብ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል። - ; በተመሳሳይ የሰብልና የእንስሳት ምርታማትን ለማሻሻል የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በግብዓት አቅርቦትና አጠቃቀም፣ በግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ የህብረት ሥራ ማህበራትን በማጠናከር፣ የግብርና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ዙሪያም  የቅርብ ክትትልና አስፈላጊ ድጋፎች ይደረጋሉ፡፡(ኤፍ.ቢ.ሲ)),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
329
በስኳር አገዳ ምርት የተሰማሩ አርሶ አደሮች ኑሮ እየተሻሻለ መሆኑን ገለጹ, - ; .._2015_3. 0 259 195 ; 5; አዲስ አበባ፤ሐምሌ 272007(ዋኢማ)- በወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አከባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች የስኳር አገዳ ምርት በማቅረብ ኑሮአቸው እተሻሻለ መምጣቱን ገለጹ። - ; ፋብሪካው ከሚጠቀመው ከ12 ሺ በላይ ሄክታር መሬት ስኳር አገዳ 7 ሺ ሄክታሩ በአካባቢው አርሶ አደሮች የተሸፈነ ነው። - ; በአዳማ ወረዳ በአዱላላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ በለጡ ቱሎማ፣አቶ አዲሱ አባተ እና አቶ ሃይሉ ተሊላ ለዋልታ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም እያንዳንዳቸው ባላቸው ሁለት  ሄክታር መሬት ላይ በዓመት አንዴ ዝናብ ጠብቀው የሚያመርቱት አሁን በዓመት ሦስት ጊዜ እንደሚያመርቱ ገልጸዋል። - ; የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአካባቢው ለሚኖሩ አርሶ አደሮች ከ14 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የአዋሽ ወንዝን  በመጥለፍ  ወደ ማሳዎቻቸው እንዲዳረስ  የተደረገ ሲሆን  በመስኖ ከሚያለሙት የአገዳ ምርት  በየዓመቱ  ከ 30ሺ እስከ 60ሺ ገቢ እንደሚያገኙ አስረድተዋል።                            አርሶ አደሮቹ ከሚያገኙት ገቢም በእንስሳት ማድለብና በሸቀጣሸቀጥ ንግድ በመሠማራት በምግብ ራሳቸውን ከመቻላቸው አልፎ ድህነትን በማስወገድ በቀጣይ የተሻለ ዘመናዊ ኑሮ ለመምራት አቅደው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን አመልክተዋል። - ; በፋብሪካው ዙሪያ የሚገኙ ከ30ሺ በላይ አርሶ አደሮች በማህበር በመደራጀት የስኳር አገዳ ምርት አቅርቦት ለማስፋፋት ፋብሪካው እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ የሚያበረታታ መሆኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን  ማዕከል ዘግቧል ። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
330
 አርሶ አደሩ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ያሳየውን ህዝባዊ ንቅናቄ በሰብል ልማቱም በመድገም እንዲረባረብ ጥሪ ቀረበ, -  ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን በሰሜን ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ በአርሶ አደሩ ተሳትፎ የተከናወነውን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ጎብኝተዋልØ በዘንድሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ከ300 ሺህ ሄክታር በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች የእርከንና ክትር ስራዎች አከናውነዋልØ በተዘጋጀው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይም የድምጽ ማጉያ፣ የሞባይል ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ዲጂታል የፎቶ ካሜራና የህዳሴው አረንጓዴ ዋንጫ ከክቡር ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን ለአሸናፊዎች ተበርክቷል። አርሶ አደሩ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ያሳየውን ግንባር ቀደም ህዝባዊ ንቅናቄ በሰብል ልማቱም በመድገም እንዲረባረብ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አሳሰቡ። በሰሜን ጎንደር በበጋ ወራት ሲካሄድ የቆየውን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የተፈጥሮ ሀብት ልማት የማጠናቀቂያ ፌስቲቫል ትናንት በደማቅ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን በዞኑ ምዕራብ በለሳ ወረዳ በአርሶ አደሩ ተሳትፎ የተከናወነውን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ትናንት በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት አርሶአደሩ ለተፈጥሮ ሀብት ሰራው የሰጠው ልዩ ትኩረትና ያበረከተው አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው። መንግስት በዘንድሮ ዓመት ባስቀመጠው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ አቅጣጫ መሰረት በአማራ ክልል በአርሶአደሩ ግንባር ቀደም ተሳትፎ የተከናወኑት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎች በጥራትም ሆነ ዕቅዱን በማሳካት ረገድ አበረታች ናቸው። በተለይም የሴት አርሶ አደሮች ተሳትፎ ለእቅዱ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም በላይ ከወንዶች እኩል ተሳታፊ በመሆን ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ግምትና ቦታ የሚሰጠው ነው ብለዋል። አርሶ አደሩ በተፈጥሮ ሀብት ልማቱ ያሳየውን የነቃ ተሳትፎ በመጪው ክረምትም በሰብል ልማቱ በመረባረብ እርሻን በወቅቱ ደጋግሞ በማረስ፣ በመዝራትና በማረም እንዲሁም የምርት ማሳደጊያ ግብአቶችን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀመጠውን ግብ ማሳካት እንደሚጠበቅበትም ገልጸዋል። ለተፈጥሮ ሀብት ልማት ሰራው ዕቅድ መሳካት አስተዋጽኦ ያደረገውን የልማት ቡድን አደረጃጀት ወደፊትም በተጠናከረ መንገድ በመተግበር በአርሶ አደሩ ዘንድ የተፈጠረውን የልማት ተሳትፎ ግለት ወደፊት ማስቀጠል እንደሚገባ ሚኒሰትሩ አሳስበዋል። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው የሰሜን ጎንደር ዞን በዚህ ዓመት ያከናወናቸው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሰራዎች ወደፊትም ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል። የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሰራዎቹ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምም ሆነ ምርታማነትን ለማሳደግ አስተዋጽዖቸው የላቀ በመሆኑ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታትም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛት አብዩ የዞኑን የዘንድሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉንና በዕቅዱ መሰረትም ከ300 ሺህ ሄክታር በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች የእርከንና ክትር ስራዎች ማከናወናቸውን ተናግረዋል። በምዕራብ በለሳ ወረዳ በአሳ ወጋሪ ቀበሌ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራው ከተሳተፉ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ጌታነህ አስማረ በጉብኝቱ ወቅት በሰጠው አስተያየት የተጎዳውን የተፈጥሮ ሀብትን ወደ ነበረበት ለመመለስ አርሶ አደሩ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል። በፌስቲቫሉ ማጠናቀቂያ በተዘጋጀው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይም የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 69 ቀበሌዎችና የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች የድምጽ ማጉያና የሞባይል ስልክ እንዲሁም አራተኛና አምስተኛ ለወጡ ወረዳዎች ደግሞ ዲጂታል የፎቶ ካሜራ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በልማት ሰራው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ወረዳዎችም የኮምፒውተር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በተለይም በዓመቱ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ አንደኛ የወጣው የላይ አርማጭሆ ወረዳ የተዘጋጀለትን የህዳሴው አረንጓዴ ዋንጫ ከክቡር ሚኒስትሩ ከአቶ በረከት ስምኦን እጅ ተቀብሏል። በማጠናቀቂያ ፌስቲቫሉና በተፈጥሮ ሀብት ልማት ሰራው ጉብኝት ላይ ከክልሉ የተለያዩ ዞኖች የተጋበዙ የግብርና ባለሙያዎችና አመራሮች እንዲሁም የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተካፋይ ሲሆኑ ለዝግጅቱ መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም የተሳትፎ ምስክር ወረቀት መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
331
ለትራንስፎርሜሽን እቅዱ መሳካት የአርሶ አደሩን አቅም ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ, - ; .._2013. 0 260 196 ; 5; አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 122005 (ዋኢማ)- አገሪቱ ለተያያዘችው የትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬታማነት የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር በዘላቂነት ማስወገድ ይገባል ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አስገነዘቡ። ሚኒስትሩ አቶ ሙክታር ከድር በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ለሞዴል አርሶ አደሮች የተዘጋጀውን የግንዛቤ መስጨበጫ ልጠና ለመመልከትና የሥራ መመሪያ ለመስጠት ትናንት በዲገሉጢጆና ጢዮ ወረዳዎች ጉብኝት አድርገዋል። በአርሶ አደሩ ዘንድ የሚታየውን ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ በአግባቡ አለመጠቀም ችግር በዘላቂነት በማስወገድ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተያዘውን ምርትና ምርታማነት በእጥፍ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና የሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ሙክታር ከድር ገልጸዋል። ሀገሪቱ በተያያዘችው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የግብርናን ምርትና ምርታማነት ከዕጥፍ በላይ ለማሳደግ በየደረጃው ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እቅዱን ለማሳካት ለአርሶ አደሩ ፣ለግብርና ባለሙያዎች ፣ለልማት ጣቢያ ሠራተኞችና አመራር አካላት ሥልጠና ከመሰጠቱም ሌላ ከዚህ ቀደም ከተሰራጨው በተጨማሪ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦት መከናወኑን አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ በየደረጃው የሚገኙ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ በአግባቡ ያለመጠቀምና አቅማቸውን አሟጠው ሥራ ላይ ያለማዋል ሁኔታ አጋጥሟል ብለዋል። በቅርቡ የተካሄደው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ ችግሩን ለማስወገድ በተለይ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ሞዴል አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በስፋት የማሠልጠን ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መወሰኑን አስገንዝበዋል። አርሶ አደሩን ሕይወት መለወጥ የሚችሉና የግብርናውን ዘርፍ ዕድገት የሚያረጋግጡ በቂ ቴክኖሎጂ መኖራቸውን ገልጸው የአምራቹን ሐይል ከምንግዜውም በበለጠ ቴክኖሎጂውን የመጠቀም ልምድ በማሳደግ በዘርፉ የተቀመጠውን ግብ ለማሳከት ትኩረት መሰጠቱን አብራርተዋል። እስካሁን በተከናወኑ የግብርናን ምርትና ምርታማነት ማሳደግና ገበያ ተኮር በማድረግና እንዲሁም በመደበኛና በአነስተኛ መስኖ፣ በውሃ ማቀብ ፣በተፋሰስ ልማትና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብድቃድር ሁሴን በበኩላቸው የምርጥ ዘርና ማዳበሪያ አጠቃቀምን በጥራት በማከናወን የዞኑን ዓመታዊ የግብርና ዕድገት ከ18 ሚሊዮን ወደ 25 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል። የዲገሉጢጆና የጢዮ ወረዳ አርሶ አደሮች በመንግስት የሚቀርብላቸውን የግብርና ቴክኖሎጂ በግንዛቤ ማነስ በሙሉ ፍቃደኝነትና ፍላጎት ሥራ ላይ ባለማዋላቸው ምርታቸው መቀነሱን ገልጸው በቀጠይ ቴክኖሎጂውን በአግባቡ በመጠቀም ምርታቸውን ለማሳደግ መነሳሳታቸውን ተናግረዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ በአርሲ ዞን በ20045 የምርት ዘመን ከ652 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 19 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ተቅዶ 18 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ),

332
አርሶ አደሩ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ያሳየውን ህዝባዊ ንቅናቄ በሰብል ልማቱም በመድገም እንዲረባረብ ጥሪ ቀረበ, .._2012_. 0 254 190 ; 5; አዲስ አበባ፤ 242004 (ዋኢማ) -  ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን በሰሜን ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ በአርሶ አደሩ ተሳትፎ የተከናወነውን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ጎብኝተዋልØ በዘንድሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ከ300 ሺህ ሄክታር በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች የእርከንና ክትር ስራዎች አከናውነዋልØ በተዘጋጀው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይም የድምጽ ማጉያ፣ የሞባይል ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ዲጂታል የፎቶ ካሜራና የህዳሴው አረንጓዴ ዋንጫ ከክቡር ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን ለአሸናፊዎች ተበርክቷል። አርሶ አደሩ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ያሳየውን ግንባር ቀደም ህዝባዊ ንቅናቄ በሰብል ልማቱም በመድገም እንዲረባረብ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አሳሰቡ። በሰሜን ጎንደር በበጋ ወራት ሲካሄድ የቆየውን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የተፈጥሮ ሀብት ልማት የማጠናቀቂያ ፌስቲቫል ትናንት በደማቅ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን በዞኑ ምዕራብ በለሳ ወረዳ በአርሶ አደሩ ተሳትፎ የተከናወነውን የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ ትናንት በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት አርሶአደሩ ለተፈጥሮ ሀብት ሰራው የሰጠው ልዩ ትኩረትና ያበረከተው አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው። መንግስት በዘንድሮ ዓመት ባስቀመጠው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ አቅጣጫ መሰረት በአማራ ክልል በአርሶአደሩ ግንባር ቀደም ተሳትፎ የተከናወኑት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎች በጥራትም ሆነ ዕቅዱን በማሳካት ረገድ አበረታች ናቸው። በተለይም የሴት አርሶ አደሮች ተሳትፎ ለእቅዱ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም በላይ ከወንዶች እኩል ተሳታፊ በመሆን ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ግምትና ቦታ የሚሰጠው ነው ብለዋል። አርሶ አደሩ በተፈጥሮ ሀብት ልማቱ ያሳየውን የነቃ ተሳትፎ በመጪው ክረምትም በሰብል ልማቱ በመረባረብ እርሻን በወቅቱ ደጋግሞ በማረስ፣ በመዝራትና በማረም እንዲሁም የምርት ማሳደጊያ ግብአቶችን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ የተቀመጠውን ግብ ማሳካት እንደሚጠበቅበትም ገልጸዋል። ለተፈጥሮ ሀብት ልማት ሰራው ዕቅድ መሳካት አስተዋጽኦ ያደረገውን የልማት ቡድን አደረጃጀት ወደፊትም በተጠናከረ መንገድ በመተግበር በአርሶ አደሩ ዘንድ የተፈጠረውን የልማት ተሳትፎ ግለት ወደፊት ማስቀጠል እንደሚገባ ሚኒሰትሩ አሳስበዋል። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው የሰሜን ጎንደር ዞን በዚህ ዓመት ያከናወናቸው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሰራዎች ወደፊትም ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል። የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሰራዎቹ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምም ሆነ ምርታማነትን ለማሳደግ አስተዋጽዖቸው የላቀ በመሆኑ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታትም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግዛት አብዩ የዞኑን የዘንድሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉንና በዕቅዱ መሰረትም ከ300 ሺህ ሄክታር በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች የእርከንና ክትር ስራዎች ማከናወናቸውን ተናግረዋል። በምዕራብ በለሳ ወረዳ በአሳ ወጋሪ ቀበሌ በተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራው ከተሳተፉ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ጌታነህ አስማረ በጉብኝቱ ወቅት በሰጠው አስተያየት የተጎዳውን የተፈጥሮ ሀብትን ወደ ነበረበት ለመመለስ አርሶ አደሩ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል። በፌስቲቫሉ ማጠናቀቂያ በተዘጋጀው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይም የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 69 ቀበሌዎችና የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች የድምጽ ማጉያና የሞባይል ስልክ እንዲሁም አራተኛና አምስተኛ ለወጡ ወረዳዎች ደግሞ ዲጂታል የፎቶ ካሜራ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በልማት ሰራው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ወረዳዎችም የኮምፒውተር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በተለይም በዓመቱ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራ አንደኛ የወጣው የላይ አርማጭሆ ወረዳ የተዘጋጀለትን የህዳሴው አረንጓዴ ዋንጫ ከክቡር ሚኒስትሩ ከአቶ በረከት ስምኦን እጅ ተቀብሏል። በማጠናቀቂያ ፌስቲቫሉና በተፈጥሮ ሀብት ልማት ሰራው ጉብኝት ላይ ከክልሉ የተለያዩ ዞኖች የተጋበዙ የግብርና ባለሙያዎችና አመራሮች እንዲሁም የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተካፋይ ሲሆኑ ለዝግጅቱ መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም የተሳትፎ ምስክር ወረቀት መሰጠቱን ኢዜአ ዘግቧል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
333
 አርሶ አደሮቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ምርት እንዲጨምር ማድረጋቸው አበረታች ነው - በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመጠቀም ምርት እንዲጨምር ያደረጉት ጥረት አበረታች መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዞኑ የሰብል ልማት ዓመታዊ በዓል አከባበር ፕሮግራም ላይ በመገኘት እንደገለጹት፣ በዞኑ በየደረጃው ያሉ አመራር አባላት፣ ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች በጋራ መንቀሳቀስ በመቻላቸው በሁሉም የልማት መስክ አበረታች ውጤት መመዝገብ ችሏል፡፡ በተለይ የዞኑ አብዛኛው አርሶ አደር ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ አዳዲስ አሰራሮችን ፈጥኖ መቀበል በመቻሉ የግብርናውን ምርት ማሳደግ ተችሏል። የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጤታማ አርሶ አደሮችን ተሞክሮዎችን ለማስፋትና ለሁሉም አርሶ አደሮች ለማዳረስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠንክሮ መስራት ወሳኝ ሆኗል። በዞኑ በጣም ጥቂት የነበሩትን የአርሶ አደሮች የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላት በሁሉም ቀበሌ በማቋቋምና ውስጣዊ አደረጃጀታቸው እንዲሟላ ማድረግ በመቻላቸው የአርሶ አደሩ ህይወት ለመወጥ ችሏል። እንዲሁም የግብርና ምርምር ውጤቶችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ ረገድ የተደረገው ድጋፍ ምርታማነት በመጨመር የሚያበረታታ ለውጥ መታየቱን አቶ ደመቀ አስረድተዋል። በተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ የተጀመሩ የልማት ጥረቶችን በዚህ ዓመትም አጠናክሮ በማስቀጠል የትራንፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል። የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው በዞኑ ለግብርና ልማት የሚያስፈልጉ ተቋማት ባለሙያዎችና ግብአቶችን አጣምሮ መጠቀም በመቻሉ የዞኑ ምርት ውጤት እያደገ መጥቷል፡፡ እንደ አዲስ ዘመን ዘገባ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቴ አሰፋ እንደገለጹት አርሶ አደሩ፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በቅድሚያ ችግሮችን ለይቶ መፍትሄ በማስቀመጡና ከአርሶ አደሩ ጋር መግባባት በመፈጠሩ ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል፡፡),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
334
762 አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ተሸለሙ, - ; .._2013. 0 260 196 ; 5; አዲስ አበባ፤ የካቲት 252005 (ዋኢማ) - በ6ኛዉ ሀገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች በዓል ላይ 762 አርዓያ የሆኑ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ዛሬ የካቲት 242005 ተሸልመዋል “የታላቁ መሪ የክቡር አቶ መለስ ዜናዊን የግብርና ራዕይ ለማሳካት በላቀ ፅናትና ቁርጠኝነት እንሰራለን” በሚል መሪ ቃል በተከበረዉ በዓል ላይ ከተሸለሙት ዉስጥ 30 በመቶ ያክሉ ሴቶች ሲሆኑ 20 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ወጣቶች ናቸዉ ዘንድሮ ከተሸለሙት ዉስጥ 70 ከመቶ ያክሉ አዲስ ተሸላሚዎች ናቸዉ አርሶ አደሮቹና ከፊል አርብቶ አደሮቹ ለሽልማት የበቁት የተሻሻሉ የግብርና ግብዓቶችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነታቸዉን በማሳደጋቸዉ ነዉ ተሸላሚዎቹ በተፋሰስ ስራና በመስኖ ልማት እንደዚሁም በሌሎች የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም የሆኑ ናቸዉ ተሞክሯቸዉን ለሌሎች በማካፈልና መሰሎችን በማፍራትም ዉጤታማ እንደሆኑ በስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል በበዓሉ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በግብርናዉ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል በላቀ ፅናት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል በዓሉን ስናከብርም በግብርና ምርታማነታችን ላይ እመርታ ለማምጣት ቃል በመግባት ሊሆን ይገባል ብለዋል የግብርና ሚንስትሩ አቶ ተፈራ ደርበዉ ደግሞ በአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች መካከል የተሻለ የዉድድር መንፈስ በመፍጠርና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ማሳካት ቁልፍ ተግባራችን ነዉ ብለዋል የበዓሉ አዘጋጅ የሆነዉ የአማራ ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አያሌዉ ጎበዜ በበኩላቸዉ በግብርናዉ ዘርፍ ዉጤት ያመጣንዉ አመራሮች፤ ባለሙያዎች፤ አርሶ አደሮች፤ ከፊል አርብቶ አደሮችና ባለሃብቶች ባደረጉት የተቀናጀ ርብርብ ነዉ ብለዋል ስለሆነም ለእነዚህ አካላት እዉቅና መስጠት ለቀጣይ ስኬታችን መሰረት ይሆናል ነዉ ያሉት ኢዜአ እንደ ዘገበው አርሶ አደሮቹና ከፊል አርብቶ አደሮቹ ከሜዳሊያ ባሻገር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድም ተሸልመዋል ከ1999 ጀምሮ እየተካሄደ ባለዉ ሀገር አቀፍ የአርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች በዓል እስካሁን 3709 አርሶ አደሮች፤ ከፊል አርብቶ አደሮች፤ አጋር አካላትና ድርጅቶች ተሸልመዋል),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
335
በአነስተኛ የእርሻ ማሳ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ምርት ማሰደግ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ, - ; .._2012. 0 260 195 ; 5; አዲስአበባ ጥቅምት28 2005 (ዋኢማ) ¬ በአነስተኛ የእርሻ ማሳ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው  ግብርና ሚኒስትር አስታወቀ። - ; ሚኒስትር ዲኤታ  አቶ ወንዲራድ   ማንደፍሮ  በአዲስ አበባ  በተካሄደው የግብርና እሴት ሰንሰለት  አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር በአነስተኛ የእርሻ መሬት የሚተዳደሩ አርሶ አደሮች የምርት  አቅም  ማሳደግ ለአገሪቱ አጣቃላይ ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ   ነው ፡፡ - ; በአፍሪካ   የግብርና  ውጤቶች   የወጪ  ንግድና ፍጆታ  ከጊዜ  ወደ  ጊዜ  እየጨመረ  መምጣቱን  የገለጹት  አቶ ወንዲራድ    በአነስተኛ  ደረጃ  የሚገኙ   ገበሬዎችን  ምርታማነት   በመጨመር  የአፍሪካን  ገበያ ፍላጎት    በሟሟላት  አጠቃላይ  ኢኮኖሚውን   መደገፍ  እንደሚቻል   ገልጸዋል፡፡ - ; ኢትዮጵያ ለተከታታይ 9 አመታት በግብርናምርታማነት የ8 በመቶ እድገት ማስመዝገቧን   በምሳሌነት  ያስቀመጡት  ሚኒስትር ዲኤታው    ለዘርፉ   እድገት   መንግሥት    በአነስተኛ ደረጃ  ለሚገኙ    ገበሬዎች   የቴክኒክ  ድጋፍ በመስጠትና   የግብርና   ግብአቶችን  በማቅረብ   እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ - ; በግብርናና  የገጠር ልማት  ኮርፖሬሽን  የቴክኒካል ማዕከል  ዳይሬክተር  አቶ ሚካኤል   ሃይሉ  በበኩላቸው ኮንፍረንሱ በአይነቱ  ለመጀመሪያ  ጊዜ  የተካሄደ መሆኑንና የሚመለከታቸውን ሁሉንም ዘርፎች በማሳተፍ  በአነስተኛ ደረጃ   አምራች የሆኑ   ገበሬዎችን   የግብርና  እሴት  ሰንሰለት  ለማጠናከር  ይረዳል  ብለዋል ፡፡ - ; ከ  ህዳር 6  እስከ 9  ቀን 2005 ዓም ድረስ  እየተካሄደ  ባለው   ኮንፈረንስ   ከ70  ሃገራት   የተውጣጡ   5 መቶ   ያህል   ሰዎች  በመሳተፍ ላይ  ይገኛሉ ፡፡),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
336
አንድ ሺ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ወንዞች ተለፋ ተካሄደ ። በሰሜን ወሎ ዞን በሁለት ወረዳዎች በ2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ወጪ በህዝብ ተሳትፎ የወንዞች ተለፋ በመካሄዱ ከአንድ ሺ የሚበልጡ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ኢንደሚሆኑ የሉተራን አለም ፌዴራሽን የአፈርና ውሃ ኢቀባ ፕሮጀክት የዞኑ ቅርንጫፍ ስህፈት ቤት ገለጸ ። በቆቦና ሀብሩ ወረዳዎች የሆርማትና መገናኛ ወንዞች ተለፋ ስራ ተካሂዶ በተያዘው ወር መጀመሪያ ላይ የተጠናቀቀው ከ24 ሺ በላይ አርሶ አደሮች በምግብ ለስራ ፕሮግራም በመሳተፋቸው መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ቴክኒክ ሃላፊ አቶ ሞገስ መንግስቱ ገልጸዋል ። የወንዞች ተለፋው በአመት ሁለት ጊዜ 302 ሄክታር የማልማት አቅም ኢንዳለው የገለጹት ሃላፊው በአሁኑ ወቅት ስራ ላይ መዋል ኢንደሚችሉ ተናግረዋል ። በቆቦ ወረዳ የሆርማት አካባቢና በሀብሩ ወረዳ የመገናኛ ቀበሌ አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት ወንዞችን ለመስኖ ኢርሻ ለማዋል ከሰው ጉልበት አቅም በላይና ለአጠቃቀም በማስቸገራቸው ሳይጠቀሙ መቆየታቸውን አስታውሰው ፤ ወንዞቹ ተጠልፈው በእርሻቸው ላይ ውሃ ኢንዲፈስ በመደረጉ ዘንድሮ የተሻለ ምርት ኢንደሚያገኙ ያላቸውን ኢምነት ገልጸዋል ።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
337
ለትራንስፎርሜሽን እቅዱ መሳካት የአርሶ አደሩን አቅም ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ, - ; .._2013. 0 260 196 ; 5; አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 122005 (ዋኢማ)- አገሪቱ ለተያያዘችው የትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬታማነት የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር በዘላቂነት ማስወገድ ይገባል ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አስገነዘቡ። ሚኒስትሩ አቶ ሙክታር ከድር በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ለሞዴል አርሶ አደሮች የተዘጋጀውን የግንዛቤ መስጨበጫ ልጠና ለመመልከትና የሥራ መመሪያ ለመስጠት ትናንት በዲገሉጢጆና ጢዮ ወረዳዎች ጉብኝት አድርገዋል። በአርሶ አደሩ ዘንድ የሚታየውን ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ በአግባቡ አለመጠቀም ችግር በዘላቂነት በማስወገድ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተያዘውን ምርትና ምርታማነት በእጥፍ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና የሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ሙክታር ከድር ገልጸዋል። ሀገሪቱ በተያያዘችው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የግብርናን ምርትና ምርታማነት ከዕጥፍ በላይ ለማሳደግ በየደረጃው ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል እቅዱን ለማሳካት ለአርሶ አደሩ ፣ለግብርና ባለሙያዎች ፣ለልማት ጣቢያ ሠራተኞችና አመራር አካላት ሥልጠና ከመሰጠቱም ሌላ ከዚህ ቀደም ከተሰራጨው በተጨማሪ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የማዳበሪያና የምርጥ ዘር አቅርቦት መከናወኑን አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ በየደረጃው የሚገኙ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ በአግባቡ ያለመጠቀምና አቅማቸውን አሟጠው ሥራ ላይ ያለማዋል ሁኔታ አጋጥሟል ብለዋል። በቅርቡ የተካሄደው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ ችግሩን ለማስወገድ በተለይ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ሞዴል አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በስፋት የማሠልጠን ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መወሰኑን አስገንዝበዋል። አርሶ አደሩን ሕይወት መለወጥ የሚችሉና የግብርናውን ዘርፍ ዕድገት የሚያረጋግጡ በቂ ቴክኖሎጂ መኖራቸውን ገልጸው የአምራቹን ሐይል ከምንግዜውም በበለጠ ቴክኖሎጂውን የመጠቀም ልምድ በማሳደግ በዘርፉ የተቀመጠውን ግብ ለማሳከት ትኩረት መሰጠቱን አብራርተዋል። እስካሁን በተከናወኑ የግብርናን ምርትና ምርታማነት ማሳደግና ገበያ ተኮር በማድረግና እንዲሁም በመደበኛና በአነስተኛ መስኖ፣ በውሃ ማቀብ ፣በተፋሰስ ልማትና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል። የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብድቃድር ሁሴን በበኩላቸው የምርጥ ዘርና ማዳበሪያ አጠቃቀምን በጥራት በማከናወን የዞኑን ዓመታዊ የግብርና ዕድገት ከ18 ሚሊዮን ወደ 25 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል። የዲገሉጢጆና የጢዮ ወረዳ አርሶ አደሮች በመንግስት የሚቀርብላቸውን የግብርና ቴክኖሎጂ በግንዛቤ ማነስ በሙሉ ፍቃደኝነትና ፍላጎት ሥራ ላይ ባለማዋላቸው ምርታቸው መቀነሱን ገልጸው በቀጠይ ቴክኖሎጂውን በአግባቡ በመጠቀም ምርታቸውን ለማሳደግ መነሳሳታቸውን ተናግረዋል። እንደ ኢዜአ ዘገባ በአርሲ ዞን በ20045 የምርት ዘመን ከ652 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 19 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ተቅዶ 18 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
338
 አርሶ አደሮቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ምርት እንዲጨምር ማድረጋቸው አበረታች ነው - ምጠሚኒስትር ደመቀ መኮንን, - ; .._2012_. 0 260 197 ; 5; አዲስ አበባ፤ ህዳር 42005 (ዋኢማ) - በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ አሰራሮችን በመጠቀም ምርት እንዲጨምር ያደረጉት ጥረት አበረታች መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዞኑ የሰብል ልማት ዓመታዊ በዓል አከባበር ፕሮግራም ላይ በመገኘት እንደገለጹት፣ በዞኑ በየደረጃው ያሉ አመራር አባላት፣ ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች በጋራ መንቀሳቀስ በመቻላቸው በሁሉም የልማት መስክ አበረታች ውጤት መመዝገብ ችሏል፡፡ በተለይ የዞኑ አብዛኛው አርሶ አደር ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና የተሻሻሉ አዳዲስ አሰራሮችን ፈጥኖ መቀበል በመቻሉ የግብርናውን ምርት ማሳደግ ተችሏል። የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጤታማ አርሶ አደሮችን ተሞክሮዎችን ለማስፋትና ለሁሉም አርሶ አደሮች ለማዳረስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጠንክሮ መስራት ወሳኝ ሆኗል። በዞኑ በጣም ጥቂት የነበሩትን የአርሶ አደሮች የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላት በሁሉም ቀበሌ በማቋቋምና ውስጣዊ አደረጃጀታቸው እንዲሟላ ማድረግ በመቻላቸው የአርሶ አደሩ ህይወት ለመወጥ ችሏል። እንዲሁም የግብርና ምርምር ውጤቶችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ ረገድ የተደረገው ድጋፍ ምርታማነት በመጨመር የሚያበረታታ ለውጥ መታየቱን አቶ ደመቀ አስረድተዋል። በተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ የተጀመሩ የልማት ጥረቶችን በዚህ ዓመትም አጠናክሮ በማስቀጠል የትራንፎርሜሽን እቅዱን ለማሳካት ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል። የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው በዞኑ ለግብርና ልማት የሚያስፈልጉ ተቋማት ባለሙያዎችና ግብአቶችን አጣምሮ መጠቀም በመቻሉ የዞኑ ምርት ውጤት እያደገ መጥቷል፡፡ እንደ አዲስ ዘመን ዘገባ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቴ አሰፋ እንደገለጹት አርሶ አደሩ፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በቅድሚያ ችግሮችን ለይቶ መፍትሄ በማስቀመጡና ከአርሶ አደሩ ጋር መግባባት በመፈጠሩ ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል፡፡),
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
339
ለገጠሩ ልማት ተግባራዊነት የአርሶአደሩን ቤተሰብ ቴንነት መጠበቅ ወሳኝ እንደሆነ ተጠቆመ ። ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን የልማት እድገት ለማስመዝገብና ድሀነትን ለማጥፋት የአርሶአደሩና ቤተሰቡን ቴንነት መጠበቅ ዋነኛ ተግባር ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት የአማራ ክልል ቴና ትበቃ ቢሮ አመለከተ ። በባህርዳር ከተማ ቤተሰብ መምሪያ አዳራሽ ዛሬ በተጀመረው የተቀናጀ የህጻናት ህክምና እንክብካቤ አውደ ጥናት ላይ የቢሮው ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ሃይሉ እንዳሉት ገጠርና ግብርናን ማእከል አድርጎ መንግስት የነደፈውን ፖሊሲና ስትራቴጂ በስራ ለመተርጎምና የአርሶአደሩን የማምረት አቅም ለማጎልበት ቴንነቱን መጠበቅ ወሳኝነት አለው ። በተለይም ህጻናት የነገ አርሶአደሮችና የሀገር ተረካቢዎች ከመሆናቸው አንጻር ለህጻናት የጤና አገልግሎትና ፍላጎት ልዩ ትኩረትና ቅድሚያ መሰጠት እንዳለበት ሃላፊው አስገንዝበዋል ። በቅርቡ የአለም ቴና ትበቃ ድርጅት ያወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው በሀገራችን በህይወት ከሚወለዱት 1ሺ ህጻናት መካከል 166ቱ እድሜያቸው አምስት አመት ሳይሞላ ለህልፈተህይወት እንደሚዳርጉ ያመለከቱት ሃላፊው ፤ ለህጻናቱ ሞት ምክንያት ከሆኑት የጤና ችግሮች ውስጥ የሳንባ ምች ፣ ተቅማጥ ፣ የምግብ እጥረት ፣ ኩፍኝና የወባ በሽታዎች እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል ። በሽታዎችን ለመከላከል የጤና ፕሮግራሞችና ስልቶች ተግባራዊ ሲደረጉ የቆዩ ቢሆንም ፤ የተቀናጁ ባለመሆናቸው የተፈለገውን ያህል ውጤት እንዳላስገኙ ተናግረዋል ። በስትራቴጂው መሰረት በክልሉ በተቀናጀ መልክ የህጻናትን በሽታ ለመከላከል በናሙናነት ከተመረጡት የባህርዳር ፣ ሰሜን ጎንደር ፣ ደቡብና ሰሜን ወሎ ዞኖች ለተውጣጡ ቴና ባለሙያዎች ካለፈው አመት ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ዙር ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል ። ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚሁ አውደጥናት ላይ በሀገራቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የህጻናት በሽታ መከላከልና እንክብካቤ ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ተሾመ ደስታ በበኩላቸው ለፕሮግራሙ መሳካት በፌዴራል መንግስት ደረጃ በተሰጠው ትኩረት የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግና የመድሃኒት አቅርቦትን ለማጠናከር መድሃኒትቤቶችን ለመክፈት ትናቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል ። በአውደጥናቱ ላይ ከመንግስት ሴክተር መስሪያቤቶች ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ፣ ከሃይማኖት ተቋማትና ከዞን የጤና ተቋማት የተውጣጡ 50 ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል ።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
340
 በሱማሌ ክልል አርብቶ አደሮችን ለልማት አመቺ በሆነ አካባቢ ለማስፈር የተካሄደው ጥናት ተጠናቀቀቭ ። በሱማሌ ክልል ለአርብቶ አደር አካባቢዎች የተዘጋጀውን የልማትና ሰፈራ ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን ጥናት ማጠናቀቁን የክልሉ ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አስታወቀ ። የቢሮው ሃላፊ አቶ በሽር ሰኢድ ትናንት እንደገለጹት ቢሮው ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስተር ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ጥናቱን ያካሄደው በእርሻና ከብት እርባታ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሚበዙባቸው ጅጅጋና ጎዴ ዞኖች በተመረጡ ሁለት ወረዳዎች ነው ። በጥናቱ የጎሳ መሪዎች ፣ የእርሻና አርብቶ አደሩ ሀብረተሰብና የመንግስት ሰራተኞች አስተያየት ያካተተ መረጃ የተሰበሰበ ሲሆን ፤ ሀብረተሰቡን በፍላጎቱ ለማስፈር በሚደረገው ጥረት የትምህርት ፣ የጤናና የመስኖ ልማት በተጓዳኝነት የሚስፋፉበት ሁኔታ መመቻቸት እንዳለበት ተጠቁሟል ። በመሆኑም አርብቶ አደሩ ሀብረተሰብ በአንድ ቦታ ተረጋግቶ እንዲሰፍር ለማስቻል ለከብቶቹ ውሃ ፣ የግጦሽ መኖና ህክምና ፤ ለራሱ ደግሞ የሰብል ልማትና የአዳሪ ትምህርት ቤት አገልግሎት የሚያገኝበት አቅጣጫ መቀየሱን ተናግረዋል ። እንዲሁም ሰፋፊ ወንዞች ባሉባቸው አካባቢዎች የመስኖ ልማት የሚስፋፋበትና በአማካይ ስፍራዎችም የተመቻቸ የእንስሳት ገበያ የሚፈጠርበት ሁኔታ መጠቆሙን አስረድተዋል ። የሰፈራ ፕሮግራሙ ጥናት ለፌዴራል መንግስት ቀርቦ በተያዘው አመት ወደ ተግባር ለማሸጋገር ተገቢ ትኩረት ተሰጥቶት ዝግጅት በመካሄድ ላይ እንደሆነም ሃላፊው መግለጻቸውን ዋልታ ኢንፎሜሽን ማእከል ዘግባል ።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
341
 በመሬት መንሸራተት የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች በቋሚነት የሚሰፍሩበት ቦታ ባለማግኘታቸው ተቸግረዋል ። በደቡብ ወሎ ዞን ሳይንት ወረዳ ባለፈው አመት በመሬት መንሸራተር ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከሁለት ሺ የሚበልጡ አርሶ አደሮች በቋሚነት የሚሰፍሩበት ቦታ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን አመለከቱ ። በወረዳው ርእሰ ከተማ አጅባር አካባቢ የሰፈሩ አርሶ አደሮቹ ሰሞኑን ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል እንደገለጹት ባለፈው አመት ህዳር ከቀያቸው ከተፈናቀሉ ወዲህ ለዘለቄታው የሚሰፍሩበት ሁኔታ ባለመመቻቸቱ የእርሻ መሬትና ለከብቶቻቸው መዋያ ቦታ አላገኙም ። የወረዳው ምክር ቤት ዋና አስተዳዳሪ አቶ በድሉ አሰፋ ተጠይቀው በጭቅማ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች የእለት እርዳታ ከማግኘት ውጪ በዘለቄታ የሚሰፍሩበት ቦታ እንዲመቻችላቸው በተደጋጋሚ የዞኑን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት መምሪያ ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተገኘ ተናግረዋል ። የዞኑ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት መምሪያ የኦፕሬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ ሁሴን ረታ ከክልል የተውጣጣ አንድ የባለሙያ ቡድን ወደ አካባቢው ተጉዞ አደጋውን መመልከቱን ገልጸው ፤ ለዘለቄታው የሚስፍሩበትን ሁኔታ ለማመቻቸትም ከክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑን አስታውቀዋል ። የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቻላቸው ታረቀኝ በበኩላቸው በመሬት መንሸራተት የተፈናቀሉ ወገኖች በደቡብ ወሎ ዞን ሳይንት ወረዳ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳም ስለሚገኙ ሁሉም በፈቃደኝነት የሚሰፍሩበት መርሀ ግብር እየተነደፈ ነው ብለዋል ። ፕሮግራሙ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ተፈናቃዮቹ በያሉበት መጠለያ ጣቢያ የምግብ ፣ የአልባሳት ፣ የህክምናና ሌሎች አገልግሎቶች በመንግስትና በለጋሽ ድርጅቶች እየተሰጧቸው መሆኑን ገልጸዋል ።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
342
ኣርሶ አደሮች ገበያ ተኮር የእርሻ ዘዴን እንዲከተሉ ስልጠና እየተሰጠ ነው ። በሃገሪቱ ያሉ አርሶ አደሮች ገበያ ተኮር የእርሻ ዘዴን እንዲከተሉ እና ወጪያቸውን ከገቢያቸው ጋር ማጣጣም እንዲችሉ የሚረዳ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተካሄደ ነው ። ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የግብርና አክስቴንሽን የአሰልጣኞች ስልጠና በግብርና ሚኒስቴር የኤክስቴንሽን መምሪያ ከፍተኛ አክስፐርት አቶ ሳሙኤል አብዮ ዛሬ እንደገለጹት ስልጠናው ያስፈለገው አርሶ አደሮች የተወኑ የሰብል አይነቶችን በየአመቱ ማምረታቸውንና ወጪያቸውን ከገቢ ጋር አለማጣጣማቸው በኑሮአቸውና በአገሪቱ እኮኖሚ ላይ ችግር በማስከተሉ ነው ። ከዚህ አንጻር አርሶ አደሮች ለእርሻ የሚያወጡትን ጉልበትና ጊዜ በገንዘብ ከማስላት ጀምሮ የምርት ግባቶችን በውጪ በመመዝገብ ከሚያገኙት የምርት ገቢ ጋር በማነጻጸርና የተሻሻሉ የእርሻ ዘዴዎችን በመጠቀም ኑሮአቸውን እንዲለውጡ ለማድረግ መታቀዱን አክስፐርቱ ተናግረዋል ። የግብርና ሚኒስቴር ከብሄራዊ ማዳበሪያ አጀንሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይኸው የአሰልጣኞች ስልጠና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከኦሮሚያ ፣ ደቡብ ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ እና ከአዲስ አበባ ግብርና ቢሮዎች የተውጣጡ የኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ። በስልጠናው የመስኖ ውሃ ልማት እና አጠቃቀም ፣ የኤክስቴንሽን ማእቀፍ ስራዎች እቅድና ግምገማ ፣ ዘመናዊ የቤት እንስሳት አረባብና የጸረ-ሰብል ተባዮች ቁጥጥር ዘዴዎች ቸምሮ 10 ያህል ትናታዊ እሁፎች እንደሚቀርቡ የገለጹት አቶ ሳሙኤል ፤ ስልጠናው በቀጣይ በየክልሎቹ ከባለሙያ እስከ አርሶ አደሩ በየደረጃው እንደሚቀጥል ማሳወቃቸውን ዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል ።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
343
”አርሶ አደሩ በተፈጥሮ ሀብት ሥራና አጠባበቅ ላይ እንዲያተኩር ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል”- ም/ጠ/ሚኒስትር ደመቀ 90 Share ደብረብርሃን የካቲት 17/2011 ለአርሶ አደሩ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ማረጋገጫ ዘመናዊ ካርታና ደብተር ከመስጠት ባሻገር በተፈጥሮ ሀብት ሥራና አጠባበቅ እንዲያተኩር ድጋፍ እንዲደረግለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ አሳሰቡ። በአማራ ክልል ለሰሜን ሸዋ ዞን አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለአርሶ አደሩ ተሰጥቷል። ሁለተኛ ደረጃ ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማለት በዘመናዊ ካርታ የተደገፈ ሆኖ አዋሳኞችን ያሳያል። አርሶ አደሩ የመሬቱን ካርታ አስይዞ ከገንዘብ አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ በመውሰድ ኑሮውን የሚያሻሽልበት፣ ሊያከራይ፣ ለልጆቹም ሊያወርስበት ይችላል፡፡ የመጀመሪያው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አርሶ አደሩ የመሬቱን መጠን ለይቶ የማያውቅበትና ለብድር የማይጠቀምበት ነበር፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደብረ ብርሃን ከተማ ካርታና ደብተሩንለአርሶ አደሮች ሲሰጡ እንዳስገነዘቡት አመራሩ የአርሶ አደሩን በመሬቱ የመጠቀም መብቱን ከማረጋገጥ በላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራውን ማገዝ ይገባዋል። በዘመናዊ መንገድ የተካሄደው የመሬት ልኬት በዘርፉ የሚነሱትን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንደሚፈታም እምነታቸውን ገልጸዋል። የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የግብአት አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደሚበጅ አቶ ደመቀ አመልክተዋል። የአማራ ክልል ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋ አራጌ በክልሉ 70 ወረዳዎች በካርታ የተደገፈ የሁለተኛ ደረጃ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ካርታ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። እስካሁንም በ23ወረዳዎች ለሚኖሩ ሦስት ሚሊዮን አርሶ አደሮች ካርታና ደብተሩ መሰጠቱን ተናግረዋል። በዚህም መሬታቸውን በአግባቡ ለመንከባከብ እንደሚያስችልና ከአበዳሪ ተቋማት ገንዘብ ወስደው ለመሥራት ያስችላቸዋል ብለዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድም አገኘሁ በዞኑ 264ሺህ አርሶ አደሮች የምስክር ወረቀቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በመጀመሪያ ደረጃ ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰጣጥ ላይ ባጋጠሙ ተግዳሮቶች በተጭበረበረ ማስረጃ መብታቸውን የተነጠቁ ከ93 በላይ ሰዎች መሬታቸው እንደተመለሰላቸውም ገልጸዋል። ከእንሳሮ ወረዳ ወቀሎ አንፆኪያ ቀበሌው አርሶ አደር ፍቅረ ማሪያም ሳህለ ለሁለት ሄክታር መሬት የተዘጋጀውን ደብተርና ካርታ መቀበላቸውንና ይህም በመሬታቸው ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል። በዚህም ከግብርና ሥራቸው በተጓዳኝ በንግድ ሥራ ለመሳተፍ ብድር ለማግኘት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል። የቀወት ወረዳ አርሶ አደር ጌጤነሽ ጎርፉ በበኩላቸው ደብተሩና ካርታው የገጠር ሴቶች መሬታቸውን በጉልበተኞች ይነጠቁ የነበረውን ሁኔታ እንደሚፈታ አመልክተዋል።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
344
የኦሮሚያ ክልል ለ717 ውጤታማ አርሶ አደሮች እውቅናና ሽልማት አበረከተ Sun, Feb 24, 2019ዋልታ የሀገር ዉስጥ ዜና የኦሮሚያ ክልል የውጤታማ አርሶ አደሮች እውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብር ተካሂዷል። የሽልማት እና የውቅና ስነ ስርዓቱም “በሺውዎች የሚቆጠሩ የልማት አርበኞችን በማበረታታት በሚሊየን የሚቆጠሩ የልማት አርበኞችን እናፍራ” በሚል መሪ ቃል ነው ለ12ኛ ጊዜ የተካሄደው። በአዳማ ገልመ አባ ገዳ አደራሽ በተካሄደው የሽልማት መርሃ ግብር ላይም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ እና የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴንን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይም የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ባስተላለፉት መልእክት፥ በዛሬው እለት ውጤታማ በመሆን ለምሽማት ለበቁ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ተሸላሚ አርሶ አደሮች በሚሊየን ከሚቆጠር አርሶ አደር ውስጥ ውጤታማ በመሆን መሸለማቸው በርትቶ ከተሰራ መለወጥ እና ማደግ እንደሚቻል ያሳያችሁ ናቸሁ ብለዋል። አርሶ አደሮቹ ከዛሬው ሽልማት በዘለለም ከጀርባ እየመጣ ላለው ወጣቱ ትውልድ በግብርናው ዘርፍ በርትቶ ከተሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ማስተማሪያ ናችሁ ሲሉም ተናግረዋል። ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ አክለውም፥ ሀገርን ማሳደግ ከፈለገን ግብርናውን ማዘመን የግድ ይለናል ብለዋል። በአንድ በኩል ሀገር አድጋለች እያልን አሁንም ግን አርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ ብችግር ውስጥ ነው፤ ሀገሪቱን ለስንዴ ግዢ በሚሊየን የሞቆጠር ገንዘብ እያወጣች ነው ያሉ ሲሆን፥ ህዝቡን ከችግር ማላቀቅ ስንችል ሙሉ ለውጥ ይመጣል ሲሉም ተናግረዋል። አርሶ አደሮቻችንን ከችግር ማላቀቅ እና ህይወቱን መለወጥ አለብን ያሉት አቶ ለማ፥ ለዚህ ደግሞ ባለን አቅም በሙሉ መስራት አለብን ብለዋል። ኦሮሚያ ክልል በቂ መሬት እና የሰው ሀይል አለው፤ ይህንንም የኦሮሞ አርሶ አደር አበግባቡ እንዲጠቀም በማድረግ እንዲለወጥ ማድረግ አለብን ሲሉም ተናግረዋል። የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትልቁ ትኩረቱ ግብርና ነው ያሉት አቶ ለማ፥ ከዚህ በፊት ግብርናውን ለማዘመን በመንግስት በኩል የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። የኦሮሚያ ክልል የግብርና እና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ በበኩላቸው፥ ሽልማት የተበረከተላቸው ውጤታማ አርሶ አደሮች በምርት ዘመኑ የግብርና ፓኬጆችን በሙሉ በመጠቀም የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው ብለዋል። በዛሬው እለት ከተሸለሙት አዳዲስ ውጤታማ አርሶ አደሮች ይገኙበታል የተባለ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ ከ130 ሺህ እስከ 10 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ያስመዘገቡ ሴት ውጤታማ አርሶ አደሮች ይገኙበታል ብለዋል። በተጨማሪም ከ500 ሺህ እስከ 21 ሚሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ወጣት አርሶ አደሮች እና ከ300 ሺህ ብር እስከ 37 ሚለየን ብር ያስመዘገቡ 211 አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች እንደሚገኙበትም ገልፀዋል። እውቅና እና ሽልማት ከተበረከተላቸው 717 ውጤታማ አርሶ አደሮች ውስጥም 50ዎቹ ከአርሶ አደርነት ወደ ኢንቨስተርነት የተሸጋገሩ መሆናቸውም ተነግሯል።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
345
በኦሮሚያ ክልል ከ70 በላይ አርሶ አደሮች የብሔር ጥቃት ደርሶባቸዋል” ሰመጉ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ከ70 በላይ አማርኛ ተናጋሪ ገበሬዎች፣ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀላቸውን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) በሪፖርቱ አመለከተ፡፡ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱንም አረጋግጫለሁ፤ ብሏል፡፡ ሰመጉ ጉዳዩን ሲመረምር መክረሙን ጠቁሞ፣ “ብሔር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት በአስቸኳይ ይቁም” በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው 136ኛ ሪፖርቱ የወረዳው የጸጥታ ሓላፊዎችና ባለሥልጣናት የብሔር ግጭቱን መቀስቀሳቸውን አስታውቋል፡፡ እንደ ሪፖርቱ፣ የወረዳው ባለስልጣናትና የፀጥታ ኃላፊዎች አርሶ አደሮቹን፣ “እናንተ የዚህ የአካባቢው ተወላጅ ሳትሆኑ ሀብት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጆች ግን ከእናንተ ያነሰ ገቢ ነው ያላቸው፤ … ይህን ገቢ ያገኛችሁት በኛ መሬት ነው፤ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ፤” በማለት በተለያዩ ጊዜያት ንብረታቸውን በመንጠቅና ለእስራት በመዳረግ እንግልት ሲፈፅሙባቸው ቆይተዋል፡፡ በተለይ መጋቢት 27 ቀን 2007 ዓ.ም አንድ የአካባቢው ተወላጅ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ የወረዳው የፀጥታ ኃላፊ “ግድያው የተፈፀመው በአማራ ብሄር ተወላጆች ነው” በማለታቸው ግጭት ተቀስቅሶ፤ ሚያዚያ 9 ቀን 2007 ዓ.ም 85 አርሶ አደሮች ለእስራት መዳረጋቸውን፣ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ መደረጉን እንዲሁም የታሠሩትን የነዳጅ በሚል 300 ብር ከእያንዳንዳቸው በመቀበል እንደተለቀቁ ሰመጉ አጣርቻለሁ፤ ብሏል፡፡ በግጭቱ የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ 10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ 99 የሳር ክዳን ቤቶችና 25 የቆርቆሮ ቤቶች በእሳት ተቃጥለው መውደማቸውን የዘረዘረው ሰመጉ፤ መኖሪያ ቤታቸው ለተቃጠለበቸውና በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው ለሚገኙ ዜጐች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡ መንግሥትም ለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የተጠናና የማያዳግም የመፍትሔ ርምጃ ከሕዝብ ጋር በመመካከር እንዲወሰድ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አመልክቷል፡፡
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
346
 ቀደም ሲል ባከናወኗቸው የተፋሰስ ልማት ሥራዎች የግብርና ምርታማነታቸው እያደገ በመምጣቱ ዘንድሮም ልማቱን አጠናክረው መቀጠላቸውን የወላይታ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ፡፡ በዞኑ በዘንድሮው የተቀናጀ አፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ንቅናቄ ከ88 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የማልማት ሥራ ተጀምሯል። በሶዶ ዙሪያ ወረዳ የጉርሞ ኮይሻ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ወልደሚካኤል ሞታ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በአካባቢያቸው የነበረው "ሎንቄ" የተባለ ምንጭ በመድረቁ ለከብቶቻቸው የሚሆን የግጦሽ ሳር አጥተው ሲቸገሩ እንደነበር አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅት ምንጩ መልሶ እያገገመ መሆኑን የገለጹት አርሶአደሩ ተዳፋታማ በሆነ አካባቢ ጠረጴዛማ እርከን በመስራት መሬታቸው ምርት መስጠት በመጀመሩ ልማቱን አጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል። በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የሚኖሩት አርሶ አደር መስቀሌ ሄባና በበኩላቸው በአካባቢያቸው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ በተጠናከረ መልኩ መስራት ከተጀመረ ወዲህ ደኑ መልሶ እያገገመና መሬታቸውም ለምነቱ እየጨመረ በመምጣቱ የግብርና ምርትና ምርታማነታቸው እያደገ መጥቷል፡፡ የደረቁ ምንጮች መልሰው ውሃ መስጠት በመጀመራቸው አማራጭ የግብርና ሥራዎች ላይ በተለይ በአነስተኛ መስኖና እንስሳትን በማድለብ ሥራ በመሳተፍ ገቢያቸው መጨመሩን ተናግረዋል፡፡ የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳሌ በበኩላቸው እንዳሉት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራው በስፋት ከመከናወኑ በፊት ይከሰት የነበረው የአፈር መሸርሸር የግብርና ምርታማነት እንዲቀንስ አድርጎ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደርቀው የነበሩ ምንጮች ከማገገማቸው በተጨማሪ የከርሰ ምድር ውሃ በቅርበት ማግኘት በመቻሉ አርሶአደሮች የመስኖ ልማት ላይ ተሳትፈው ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ የተደራጀ የአፍርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ንቅናቄ በየዓመቱ ከመስራት ባሻገር የተሰሩትን በመንከባከብና በመጠበቅ ዘላቂ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ በ342 ንዑስ ተፋሰሶች በሚገኝ ከ88 ሺህ 316 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የሚከናወን መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራው ከተጀመረ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ከ319 ሄክታር በላይ መሬት መልማቱ ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
347
በጌዴኦ ዞን 164 ቡና አልሚ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በራሳቸው ለገበያ ለማቅረብ ፈቃድ አገኙ በጌዴኦ ዞን 164 ቡና አልሚ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በራሳቸው ለገበያ ለማቅረብ ፈቃድ አገኙ ዲላ መጋቢት 5/2010 በጌዴኦ ዞን 164 ቡና አልሚ አርሶ አደሮች ምርታቸውን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ፍቃድ መውሰዳቸውን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ገለፀ ፡፡ የመምሪያው ምክትልና የቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ ተፈራ ለኢዜአ እንደገለፁት፣ የቡና አልሚ አርሶ አደሮች ፈቃድ የወሰዱት በተያዘው የምርት ዘመን ወደሥራ ለመግባት ነው። አርሶ አደሮቹ ፍቃድ የተሰጣቸው በ2009 ዓ.ም መንግስት አዲስ ባወጣው የቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥር አዋጅ መሰረት ነው፡፡ በአዋጁ ሁለት ሄክታርና ከዚያ በላይ በሆነ መሬት ላይ ቡና የሚያለሙ አርሶ አደሮች ምርታቸውን ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል፡፡ አዋጁን መሠረት በማድረግ መስፈርቱን የሚያሟሉ ቡና አልሚ አርሶ አደሮችን ማሣ ይዘት የመገምገምና በዘመናዊ የልኬት መሳሪያ ስፋቱን የማረጋገጥ ተግባራት መከናወኑን አቶ አድማሱ ገልጸዋል፡፡ በዚህ መሰረትም 164 አርሶ አደሮች መስፈርቱን በማሟላታቸው ያመረቱትን ምርት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ፍቃድ አግኝተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 50 የሚሆኑት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የገበያ ትስስር እንደተፈጠረላቸው የገለጹት አቶ አድማሱ፣ ገበያ የማፈላለጉ ሥራ በአርሶ አደሮቹ የግል ጥረትና በመንግስት ድጋፍ የሚከናወን መሆኑን አመልክተዋል፡፡ እንደኃላፊው ገለጻ፣ አርሶ አደሮቹ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ምርታቸውን በቀጥታ ማቅረብ መቻላቸው ከነበረው አሰራር የተሻለ ገቢ በማገኘት የላቀ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል፡፡ " የፍቃድ አሰጣጥ ሂደቱ ከቡና ማሳ አያያዝ ግምገማ የሚጀምር በመሆኑ አሰራሩ ምርጥ ተሞክሮን ወደሌሎች አርሶ አደሮች ለማስፋት እንደሚጠቅምና የቡና ምርታማነትና ጥራትን ለማሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ አለው" ብለዋል ፡፡ የዕድሉ ተጠቃሚ ከሆኑ አርሶ አደሮች መካከል በጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ የሚኖሩት ሴት አርሶ አደር ፅጌ ጂግሶ በዘጠኝ ሄክታር መሬት ላይ ቡና እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሯ እንደተናገሩት መሬታቸው ከተለካና የማሳቸው አያያዝ እንዲሁም የምርት ጥራት አጠባበቃቸው በባለሙያዎች ከተገመገመ በኋላ ነው ፍቃድ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ "ምርታችን ከጊዜ ወደጊዜ ዋጋ እያገኘ መምጣቱ ምርታማነትን ለማሻሻል የበለጠ እንድንሰራ አድርጎናል" ብለዋል ፡፡ ከቡና ምርታቸው በዓመት እስከ ሁለት መቶ ሺህ ብር የሚያገኙት አርሶ አደሯ ዘንድሮ ጥራት ያለው ቡና አምርተው ያለደላላ በራሳቸው ስለሚሸጡ ከዚህ የተሻለ ገቢ አገኛለሁ ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል ፡፡ በቡና የተሸፈነ ስድስት ሄክታር መሬት እንዳላቸው የገለጹት ደግሞ የወናጎ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ዘለሉ አራርሶ ናቸው፡፡ ለቡና ተክላቸው የተፈጥሮ ማዳበሪያ በመጠቀምና አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ ጥራት ያለው ቡና ሊያመርቱ መቻላቸውን ተናግረዋል ፡፡ በምርት ዘመኑ ያመረቱትን ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆናቸውንም አክለው ገልፀዋል ፡፡ ፍቃድ ያገኙት እነዚህ 164 ቡና አልሚ አርሶ አደሮች በያዝነው ምርት ዘመን ከአራት ሺህ 612 ቶን በላይ የቡና ምርት መሰብሰባቸውን ከዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት መምሪያ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
348
በደቡብ ጎንደር ዞን በቢራ ገብስ ልማት የተሳተፉ አርሶ አደሮች የተሻለ ገቢ እያገኙ ነው በደቡብ ጎንደር ዞን በቢራ ገብስ ልማትና ዘር ብዜት ሥራ መሳተፍ የጀመሩ አርሶ አደሮች የተሻለ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ተናገሩ። የጎንደር ብቅል ፋብሪካም በተያዘው በጀት ዓመት እስካሁን ድረስ 70 ሺህ ኩንታል የብቅል ገብስ ከአርሶ አደሮች መረከቡን ገልጿል። በዞኑ እስቴ ወረዳ የዱርጌ ማሽንት ቀበሌ አርሶ አደር ብርሃን ይመር ትላንት ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በቢራ ገብስ ልማት መሳተፍ ከጀመሩ ስድስት ዓመት ሆኗቸዋል። ባለፈው ዓመት ከአራት ሄክታር በላይ መሬት አልምተው ያገኙትን 94 ኩንታል የቢራ ገብስ ለጎንደር ብቅል ፋብሪካ በማስረከብ ከ104 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። በ2009/2010 የምርት ዘመን መሬቱን ለማፈራረቅ በሚል ድንች ቢያለሙም ገቢያቸው ከቢራ ገብሱ አንጻር አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል። "ዘንድሮ ከድንቹ ጎን ለጎን ከግማሽ ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ አልምቼ ከሰበሰብኩት 15 ኩንታል የቢራ ገብስ 17 ሺህ 850 ብር ገቢ በማግኘት ተጠቃሚ ሆኛለሁ" ብለዋል። በምርት ዘመኑ ከቢራ ገብስ ዘር ብዜትና ልማት ያገኙትን 22 ኩንታል ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝና ለጎንደር ብቅል ፋብሪካ ማስረከባቸውን የገለጹት ደግሞ የላይ ጋይንት ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አለምነው ውቤ ናቸው። ከዚህም 28 ሺህ ብር ገቢ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። እንደ አርሶ አደር አለምነው ገለጻ፣ በቢራ ገብስ ልማትና ዘር ብዜት ሥራ መሳተፍ ከጀመሩ ካለፉት ሰባት ዓመታት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከገቢያቸው ከ115 ሺህ ብር በላይ በባንክ መቆጠብ ችለዋል። የቢራ ገብስ ልማት አዋጭ በመሆኑ በመጪው የመኽር ወቅት አብዛኛው መሬታቸውን በቢራ ገብስ ሸፍነው በማልማት የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን ከወዲሁ ተዘጋጅተዋል። የጎንደር ብቅል ፋብሪካ የቢራ ገብስ ምርትና አገልግሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ አደባባይ ፀጋው በበኩላቸው፣ ፋብሪካው በዚህ ዓመት 230 ሺህ ኩንታል የቢራ ገብስ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል። "በምርት ዘመኑ ከመኽርና በመስኖ ከለማው 90 ሺህ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ የብቅል ገብስ ከአርሶ አደሮች ኩንታሉን በአንድ ሺህ 190 ብር ለመግዛት አቅዶ እስካሁን የ70 ሺህ ኩንታል ግዥ ፈፅሟል" ብለዋል። " ፋብሪካው በዕቅድ የያዘውን የቢራ ገብስ ከአርሶ አደሩ ሙሉ በሙሉ ሲያሰባስብ ከውጭ ለቢራ ገብስ ግዥ ሊያወጣ የሚችለውን አምስት ሚሊዮን ዶላር " የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንደሚችልም አስረድተዋል። በቀጣይም አርሶ አደሮች የውጭ ምንዛሬን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ጥራቱን የጠበቀ የብቅል ገብስ በጥራትና በብዛት አምርተው በተሻለ ዋጋ ለፋብሪካው በማስረከብ ተጠቃሚ ለመሆን በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። እንደ አቶ አደባባይ ገለጻ፣ ፋብሪካው ባለፈው ዓመት ከአምራች አርሶ አደሮች 85 ሺህ ኩንታል የጥራት ደረጃው የተረጋገጠለት የብቅል ገብስ ከአርሶ አደሮች ተረክቦ ጥቅም ላይ አውሏል። ከአማራ ከልል ግብርና ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በ2009/2010 የምርት ዘመን በክልሉ በቢራ ገብስ ከለማው 15 ሺህ 273 ሄክታር መሬት ከ290 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
349
አርሶ አደሩን የአዲሱ የግብርና ዕድገት ፓኬጅና ስትራቴጅ ግኝቶች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው አርሶ አደሩ የአዲሱ የግብርና ዕድገት ፓኬጅና ስትራቴጅ ግኝቶች ተጠቃሚ እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በአዲሱ የግብርና አሰራር ፓኬጅና ስትራቴጅ የአርሶ አደሩን የመካናይዜሸን መሳሪያ አጠቃቀም በእርሻ 60 በመቶ በአጨዳ ደግሞ 50 በመቶ ለማድረስ ግብ ተጥሏል። ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ተስፋዬ መንግስቴ እንደገለፁት የግብርና ምርቶች በዓለም ገበያ ያላቸው ተወዳዳሪነት እንዲጨምር በማድረግ ረገድ በየደረጃው የሚገኝ የግብርና ልማት ባለሙያ ኃላፊነት ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም አርሶ አደሩ ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ አዲስ የአስራርና የቴክኖሎጅ ግኝቶችን እንዲጠቀም ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ሙሉ በሙሉ በሚቻል መልኩ በበሬ ጉልበት ላይ የተመሰረተውን የአስተራረስ ዜይቤ በመለወጥ አርሶ አደሩን የግብርና መካናይዜሸን አገልግሎትን በስፋት እንዲጠቀም ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። በአዲሱ የግብርና ዕድገት ፓኬጅና ስትራቴጅ ዙሪያ ለዘርፋ ባለሙያዎች የተዘጋጀ የአምስት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዳማ ከተማ ተካሄዷል፡፡ እንዲሁም አርሶ አደሩ ጥራትና ተወዳዳሪ የሆነ ምርት እንዲያመርት በማድረግ በቀጣይ ዓመት ከዘርፋ 4 ነጥብ 5 ቢሊዩን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል። አግሮ ኢንዱስትሪዎችን በቋሚነት ጥሬ እቃ በመመገብ ከውጪ የሚገቡ የግብርና ጥሬ እቃዎችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ግብ መያዙንም ተናግረዋል፡፡ በሀገሪቱ አሁን በግንባታ ላይ የሚገኙ አራት የተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቻ ከ80 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ጥሬ እቃ የሚፈልጉ በመሆኑ ለዚህ ምላሸ የሚሰጥ ግብርና መገንባት እንደሚገባ አመልከተዋል። ''አዲሱ ፓኬጅ መሰረት ያደረገው ከ2007 ዓ.ም ወዲህ በምርምር የወጡ የአስራርና የቴክኖሎጅ ግኝቶችን ነው'' ያሉት ደግሞ በሚኒስቴሩ የግብርና ኤክስቴሸን ዳይሬክቶሬት ጀኔራል አቶ ወንደለ ሀብታሙ ናቸው። የአፈር አሲዳማነትን መቀነስ፣ የኮትቻ አፈር ምርታማነትን ማሳደግ ፣ የእርሻ ማሳን አፈራርቆ መዝራት ፣ ባለሙያዎችና የአርሶ አደሩ የአቅምና የአመለካከተ ክፍተት ሙሉ በሙሉ የሚቀረፍበት መሆኑንም ገልጠዋል። የስልጠናው ዓላማ ለፓኬጁ ውጤታማነት የግብርና ሴክተር አመራሮች፣ የዘርፋ ተመራማሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ የልማት ጣቢያ ስራተኞችና አርሶ አደሩ በአተገባበሩ ዙሪያ ተገቢውን እውቀትና ግንዛቤ እንዲጨብጡና ለተፈፃሚነቱ እንዲረባረቡ ለማድረግ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ የስሪንቃ ግብርና ምርምር የማሽላ ተመራማሪ ዶክተር ሰለሞን አሰፋ በበኩላቸው የግብርና አሰራሩን ሙሉ በሙሉ መለወጥ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ''ዘርፋን በይዘት ፣ በአይነትና ወደ አዲስ የአስራርና ቴክኖሎጅ ግልጋሎት ማሸጋገር ይጠበቅብናል'' ብለዋል። ዛሬ በተጠናቀቀው ስልጠና ላይ ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብና ትግራይ ክልሎች የተውጣጡ 300 የሚሆኑ የዘርፋ አመራሮች ፣ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
350
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ለ150 ሺህ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጠ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለ150 ሺህ አርሶ አደሮች የገጠር መሬት የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ መሰጠቱን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ዘካርያስ ሽፈራው ለኢዜአ እንደገለፁት ካርታው የተሰጣቸው ነዋሪዎች በስድስት ወረዳዎች ከሚገኙ 760 ሺህ አርሶ አደሮች መካከል ናቸው ። እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ለ610 ሺህ አርሶ አደሮች ካርታውን ለመስጠት የአየር ፕላን ማንሳትና ተዛማጅ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል። በወረዳዎቹ ከግማሽ ሚሊዮን ሄክታር በላይ የገጠር መሬት ተለክቶ ለአርሶ አደሩ በነፍስ ወከፍ በማከፋፈል የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እየተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል። "ካርታውን መስጠት ያስፈለገው በገጠር የመሬት አጠቃቀምን ፍትሀታዊነትን ለማስፈንና በዘርፉ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ነው" ብለዋል ። በተጨማሪም አርሶ አደሩ መሬትን በባለቤትነት ስሜት በመጠበቅና በማልማት ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥና ከእርሻ ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለማስቀረት መሆኑን ገልፀዋል። አለአግባብ የተወረረ የህዝብና የመንግስት መሬት በማስመለስ ሀብቱ በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል ማስቻል ሌላው ካርታውን መስጠት ያስፈለገበት ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል። የይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ከተሰጣቸው አርሶ አደሮች መካከል በታህታይ ቆራሮ ወረዳ የሚኖሩት አቶ መብራህቶም ገብሩ በሰጡት አስተያየት “ከወሰን ችግር የፀዳ የእርሻ መሬት ይዞታ ማረጋገጫ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል። አርሶ አደር ተመስገን በላይ በበኩላቸው የተሰጣቸው ካርታ የሚጠቀሙበትን የእርሻ መሬት ከመቼውም በላይ ባለቤትነት ስሜት ይዘው ለመጠበቅና ለመንከባከብ የተሻለ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል ። “የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታው የእርሻ መሬቴን ከህገወጥ ወራሪዎች ታድጎልኛል " ያሉት ደግሞ ሌላው የወረዳው ነዋሪ አርሶ አደር በሪሃ ንጉሰ ናቸው።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
351
በምእራብ ሸዋ ዞን ከ40 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጠ በምእራብ ሸዋ ዞን ከ40 ሺህ 700 ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መሰጠቱን የዞኑ የመሬትና አካባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሮባ ቱርጩ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት በዞኑ ስምንት ወረዳዎች የሚገኙ አርሶ አደሮችን ይዞታ በዘመናዊ መንገድ በመለካት ካርታ የማዘጋጀት ስራ እየተከናወነ ነው፡፡ እስካሁንም 88 ሺህ 800 በላይ ካርታ ተዘጋጅቶ 40 ሺህ 767 የሚሆነው በባለይዞታዎች አጅ የገባ ሲሆን ቀሪው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2010 ድረስ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው አሰራር ግምታዊ ስለነበር ባለሃብቶች ከተፈቀደላቸው ይዞታ በላይ መሬት እንዲይዙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ይህም በአርሶ አደሮችና በባለሃብቶች መካከል ግጭት ሲፈጠር መቆየቱን ገልጸው ፅህፈት ቤቱ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ከተሃድሶ በኋላ ይዞታን የመለከት ስራ መጀመሩ ተናግረዋል። መሬቱን በዘመናዊ መንገድ መለካቱ በአርሶ አደሮች እርስ በርስና በባለሃብቶች መካከል ይፈጠር የነበረውን አለመግባባት ከመቅረፍ ባሻገር በገጠር መሬት ላይ ይከሰት የነበረው ኪራይ ሰብሳቢነት ለመቅረፈ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡ ይዞታን የመለካትና ካርታ የማዘጋጀ ስራው አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በቶኬ ኩታዬ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ሞቲ ተስፋዬ በሰጡት አስተያየት ይዞታቸው በዘመናዊ መንገድ ተለክቶ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በማግኘታቸው ለበለጠ ልማት እንዳነሳሳቸው ገልፀዋል፡፡ ባለፉት አመታት የይዞታ ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ይዞታቸው በድንበርተኞች እየተገፉ ለእንግልት ተዳርገው እንደነበር ያስታወሱት ደግሞ የደንዲ ወረዳ አርሶ አደር ጫልቺሳ ደበላ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይዞታቸው በዘመናዊ መንገድ ተለክቶ ካርታ በመውሰዳቸው ያለምን ችግር ልማቱን ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
352
የአጋርፋ ወረዳ አርሶ አደሮች ለበልጉ እርሻ ያዘጋጁትን ማሳ በተለያዩ የሰብል ዘሮች እያለሙ ነው የአጋርፋ ወረዳ አርሶ አደሮች ለበልጉ እርሻ ያዘጋጁትን ማሳ በተለያዩ የሰብል ዘሮች እያለሙ ነው ጎባ መጋቢት 12/2010 የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችንና ግብዓት በመጠቀም ለበልጉ እርሻ ያዘጋጁትን ማሳ በተለያዩ የሰብል ዘሮች ማልማት መጀመራቸውን በባሌ ዞን የአጋርፋ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ፡፡ በተያዘው የበልግ ወቅት ከ299 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል ዘሮች የመሸፈኑ ሥራ መጀመሩን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በአጋርፋ ወረዳ አሚኛ - ሀሮ ቀበሌ አርሶ አደር ሱፊያን አህመድ እንዳሉት በበልጉ ወቅት ሁለት ሄክታር ማሳቸውን አራት ጊዜ ደጋግመው በማረስ አለስልሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል፡፡ ለበልጉ እርሻ የሚሆን ማዳበሪያ በወቅቱ ስለደረሳቸው በአሁኑ ወቅት በአካባቢው እየጣለ ያለውን ዝናብ በመጠቀም ዘር መዝራታቸውን ነው የገለጹት፡፡ ሌላው የቀበሌው አርሶ አደር ኡስማን ከድር በበኩላቸው " ከኦሮሚያ ምርጥ ዘር የባሌ ቅርንጫፍ በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኙሁትን ምርጥ ዘር ስንዴ በመጠቀም አንድ ተኩል ሄክታር ማሳዬን አልምቺያለሁ " ብለዋል፡፡ የበልጉ ዝናብ አጀማመሩም ሆነ ስርጪቱ የተስተካከለና ወቅቱን የጠበቀ በመሆኑ አዝመራቸውን ባቀዱት መሰረት በመከናወን ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ አንድ ሄክታር መሬታቸውን ደጋግመው በማረስ በገብስ ዘር መሸፈናቸውን የገለጹት ደግሞ በወረዳው የሀምቤንቱ ቀበሌ አርሶ አደር ሀሰን ሙክታር ናቸው። ባለፈው ዓመት በበልግ ወቅት ይህን መሬታቸውን ደጋግመው አርሰው ስንዴ በማልማት ከ60 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘታቸውን አስታውሰዋል፡፡ ዘንድሮ በመስመር የመዝራት ቴክኖሎጂን ጨምሮ ምርጥ ዘርና ማደባሪያ በአግባቡ በመጠቀማቸው የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሰሩ መሆናቸውን አርሶአደሩ ተናግረዋል። በዞኑ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የሰብል ልማት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አለምእሸት አለመያሁ በበኩላቸው በዞኑ በ2010/2011 የበልግ ወቅት ከ299 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል ዘሮች የመሸፈን ሥራ ተጀምሯል ። በእስካሁኑ እንቅስቃሴ 200 ሄክታር የሚሆን መሬት በተለያዩ የሰብል ዘሮች መሸፈኑንም ነው የገለጹት፡፡ "በበልጉ ወቅት በልማቱ የሚሳተፉ 206 ሺህ አርሶና አርብቶ አደሮች ደጋግመው ያረሱትን መሬታቸውን ከመጋቢት መጀመሪያ ጀምሮ እየጣላ ያለውን ዝናብ በመጠቀም በገብስ፣ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ማሾና ሌሎች የጥራጥሬ ሰብሎች እያለሙ ናቸው " ብለዋል፡፡ በምርት ወቅቱ ታርሶ በዘር ከሚሸፈነው መሬት 5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም አስታውቀዋል። አስተባባሪው እንዳሉት የበልጉን የእርሻ ወቅት ውጤታማ ለማድረግ ከ126 ሺህ 453 ኩንታል በላይ የተለያየ አይነት ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ ቀርቧል። ከቀረበው የማዳበሪያ ግብዓት መካከል ከ20 ሺህ ኩንታል የሚበልጠው ተሰራጭቶ አርሶ አደሩ እጅ መድረሱን ጠቁመው፣ ቀሪውን ግብዓት የማሰራጨቱ ስራ መቀጠሉን ተናግረዋል ፡፡ በባሌ ዞን ባለፈው ዓመት የበልግ ወቅት ከለማው መሬት 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገኝቶ እንደነበር ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
353
የአርሶ አደሩን የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለማስፋፋት የሚያስችል መርሀ ግብር ተግባራዊ ይደረጋል የአርሶ አደሩን የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለማስፋፋት የሚያስችል መርሀ ግብር ተግባራዊ ይደረጋል አዳማ መጋቢት 11/2010 የአርሶ አደሩን የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል መርሀ ግብር ለመተግበር ዝግጅት መደረጉን የግብርና ትራንስፎርሜሸን ኤጀንሲ አስታወቀ። ተግባራዊ የሚሆነው "የተፋጠነ የሙሉ ፓኬጅ ማስፋፋት መርሀ ግብር" ዋና አላማ የአርሶ አደሩን የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ወጥነት ችግር በመፍታትና በማስፋፋት ምርታማነትን ማሳደግ ነው። በኤጀንሲው የገበያ ተኮር ሰብሎች ኩታ ገጠም ልማት ዳይሬክተር ዶክተር ተሾመ ዋለ ለኢዜአ እንደገለጹት በአርሶ አደሩ ደረጃ የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች፣ ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ በመጠቀም ምርታማነትን የማሳደግ ተሞክሮ በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ማረጋገጥ የመርሀ ግብሩ የትኩረት አቅጣጫ ነው ። በተጨማሪም የተሻሻሉ የግብርና መሳሪያዎችን በመጠቀም በኩታ ገጠም ማሳ ላይ ለግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ግብአት የሚሆኑ ሰብሎችን በማምረት የአቅርቦት ፍላጎቱን ማሟላት ሌላው በመርሀ ግብሩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ተናግረዋል ። በምርምር የሚገኙ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ጨምሮ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን አቅርቦት የማስፋፋትና የማሻሻል ስራ በመርሀ ግበሩ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል ። "መርሀ ግበሩ በ2010/11 ምርት ዘመን መኸር ወቅት ዋና ዋና ሰብል በሚለማባቸው አራት ክልሎች 162 ወረዳዎችና በ2ሺህ 690 ቀበሌዎች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ይሆናል " ብለዋል ። በሙከራ መርሀ ግብሩ ከ600ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በምርት ወቅቱ በማሳተፍ ከ320ሺህ ሄክታር በላይ ኩታ ገጠም ማሳ ለማልማት መታቀዱን አመላክተዋል። በሙከራ ደረጃ ጥራጥሬና ቅመማ ቅመምን ጨምሮ ሰባት ዋና ዋና ሰብሎች በማልማት ከ14 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት በእቅድ መያዙንም ገልፀዋል ። በአርሶ አደሩ ደረጃ በዋና ዋና ሰብሎች በሄክታር በአማካኝ እየተገኘ ያለውን 23 ኩንታል ምርት ወደ 38 ኩንታል ለማሳደግ ግብ መጣሉን አመላክተዋል። የሙከራ መርሀ ግበሩን በመኸር ወቅት ተግባራዊ ለማድረግ በዞንና በወረዳ ደረጃ ለአርሶ አደሩ በቅረበት ድጋፍ የሚያደረጉ የግብርና ባለሙያዎችን በአቅም ፣ አመለካከትና በተግባር የማዘጋጀት ሥራ መጠናቀቁን ዶክተር ተሾመ ተናግረዋል ። "በሀገሪቱ በየዓመቱ ከሚለማው 12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ 62 በመቶ ማዳበሪያ በመጠቀም በዘር ይሸፈናል"። እንዲሁም የምርጥ ዘር አጠቃቀም 12 በመቶና የተሻሻሉ የግብርና መሳሪያዎች አጠቃቀም ደግሞ 6 በመቶ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በመርሀ ግብሩ አሁን ያለውን የምርጥ ዘርና የተሻሻሉ የግብርና መሳሪያዎች የመጠቀም ደረጃ ለማሻሻል ይሰራል ብለዋል። የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ለማ በበኩላቸው ሚኒስትቴር መስሪያ ቤቱ ለመርሀ ግብሩ ወጤታማነት ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ ከክልሎች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በአቅም ግንባታ፣ በግብዓት አቅርቦትና በፓኬጅ አተገባበር ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። "እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው መርሀ ግብር አሁን ካለው ከ16 ሚሊዮን ሙሉ ፓኬጅ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ውስጥ አብዛኛዎቹ በገበያ ተኮር ሰብሎች ልማት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አመላክተዋል። በኦሮሚያ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ የግብዓት አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ አበራ በየነ በሰጡት አስተያየት ፓኬጅ አርሶ አደሩ በገበያ ተኮር ሰብሎች በማልማት ገቢውን እንዲያሳድግ እድል የሚፈጥርለት መሆኑን ገልጸዋል ። በክልል ደረጃ መርሀ ግብሩን ተግባራዊ ለማድረግ ከዚህ ቀደም ለዞንና ወረዳ የግብርና ባለሙያዎች የመጀመሪያ ዙር ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል ።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
354
አርሶ አደሩ የግብርና መካናይዜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኝ እየተሰራ ነው አርሶ አደሩ የግብርና መካናይዜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኝ እየተሰራ ነው አዳማ የካቲት 20/2010 አርሶ አደሩ የግብርና መካናይዜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎትን በቅርበት እንዲያገኝ በጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ወጣቶች በዘርፉ እንዲሳተፉ በመደረግ ላይ መሆኑን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስቴር ገለጸ። አምስት የወጣቶች ጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ እንተርፕራይዞች ከሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የግብርና መካናይዜሽን መሳሪያዎች ተበርክቶላቸዋል። ለወጣቶቹ ከተሰጡት መሳሪያዎች መካከል ከጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ደርጀት በተገኘ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ የተገዙት አምስት የእርሻ ትራክተሮች ይገኙበታል። የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ መንግስቴ በትራክተሮቹ ርክክብ ወቅት እንዳሉት ማሳሪያዎቹን አርሶ አደሩ የግብርና መካናይዜሽን አገልግሎቱን ከተደራጁ ወጣቶች በስፋትና በቅርበት እንዲያገኝ ለማስቻል ነው። ወጣቶቹ በአርሲ ዞን በምርታማነታቸው በሚታወቁ አምስት ወረዳዎች በግብርና መካናይዜሽን ኦፕሬተርነት ተደራጅተው ተገቢውን ሙያዊ ዕውቀት በማግኘት ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን አመልክተዋል። በተጨማሪም ወጣቶቹ በቀጣይ የማሽነሪ ሊዝ አገልግሎት፣ የብድር፣ የክህሎትና የሙያ ስልጠና ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አቶ ተስፋዬ አመልክተዋል። በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን አርሶ አደሮች የእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በሚንስቴሩ የግብርና መካናይዜሽን ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ሀብቴ ናቸው። በእዚህም በ2012 ዓ.ም 60 በመቶ የሚሆነው አርሶ አደር በአጨዳ ወቅት የኮምፓይነር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ግብ ተይዞ እየተሰራ ነው። የግብርና መካናይዜሽን ልማት ከነበረበት 3 በመቶ ወደ 15 በመቶ ማደጉን ጠቅሰው፣ በቀጣይ ዘርፉን ለማዘመንና ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሰለጠነውን የሰው ኃይል በማህበር በማደራጀት በስፋት ለማሳተፍ ስትራቴጅ ተነድፎ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል። ሀገሪቷ ከደረሰችበት ልማትና ዕድገት አኳያ ከ2 ሺህ 500 በላይ ትራክተሮችና ኮምባይነሮች እንደሚያስፈልጉም ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም በሀገሪቷ 1 ሺህ 50 ኮምባይነሮችና 750 ትራክተሮች የግብርና መካናይዜሽን አገልግሎት በመስጣት ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል። የአርሲ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መላኩ ታምሩ በበኩላቸው በዘንድሮ ዓመት በዞኑ 56 የእርሻ ትራክተሮች በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች መሰጠቱን ገልጸዋል። ወጣቶቹ ከዞኑ መስተዳደር የተሰጣቸውን ከ3 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በትራክተር ታግዘው እያለሙ ከመሆን ባለፈ ለአካባቢው አርሶ አደሮች የኪራይ አገልግሎት በመስጠት አማራጭ ገቢ እየፈጠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። በማህበር ተደራጅተው በዘርፉ ከተሰማሩት ወጣቶች መካከል ወጣት በፍቀደ ኃይለገብርኤል ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ በእጽዋት ሳይንስ ተመርቆ ከአንድ ዓመት በላይ ሥራ ሲፈልግ እንደነበር አስታውሷል። መንግስት ባመቻቸው የሥራ ዕድል 11 ሆነው የግብርና መካናይዜሽን መሳሪያ አገልግሎት ለአርሶ አደሩ ለመስጠት መደራጀታቸውን ገልጿል። በአሁኑ ወቅት ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስቴር አንድ የእርሻ ትራክተር ማግኘታቸውንና በቀጣይ ለአርሶ አደሩ አገልግሎቱን በኪራይ ለመስጠትና ለመለወጥ እንደሚሰሩ አመልክቷል።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
355
በጌዴኦ ዞን 12 ሺህ 475 መሬት የሌላቸውን አርሶ አደሮች በገቢ ማስገኛ የሥራ መስኮች ሊሰማሩ ነው በጌዴኦ ዞን 12 ሺህ 475 መሬት የሌላቸው የቤተሰብ መሪ አርሶ አደሮችን ከእርሻ ውጭ ባሉ የገቢ ማስገኛ የሥራ ዘርፎች ለማሰማራት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። አርሶ አደሮቹን በሥራ መሰኮች ለማሰማራት በተዘጋጀ ፓኬጅ ትግበራ ላይ ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር አካላት መድረክ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው። የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በዞኑ ከቤት መስሪያ ውጭ ለእርሻ የሚሆን መሬት የሌላቸው 12 ሺህ 475 አርሶ አደሮች ናቸው። የቤተሰብ መሪ አርሶ አደሮችን ከእርሻ ውጭ በሆኑ የገቢ ማስገኛ የሥራ መስኮች ለማሰማራት የተዘጋጀ ፓኬጅ ወደ ትግበራ እየተገባ ነው ። በተጨማሪም ከ ግማሽ ሄክታር በታች የእርሻ መሬት ያላቸው 48 ሺህ 675 የቤተሰብ መሪ አርሶ አደሮችም በፓኬጁ ታቅፈው በገቢ ማስገኛ ስራዎች እንደሚሰማሩ ተናግረዋል ። ፓኬጁን ከኪራይ ሰብሳቢነትና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫና የስልጠና መድረክ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል ። ፓኬጁን ተግባራዊ ለማድረግ ከ175 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የሚጠይቅ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው፣ ከሥልጠናና ሥራ ማስኬጃ በስተቀር ወጭው በክልሉ መንግስት የሚመደብ መሆኑን አስታውቀዋል ።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
356
የባሌ ዞን አርሶ አደሮች ምርታማነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናገሩ የባሌ ዞን አርሶ አደሮች በተሻሻለ የግብርና አሰራር ላይ ከግብርና ማሰልጠኛ ተቋማት ያገኙትን ተሞክሮ ተግባራዊ በማድረጋቸው ምርትና ምርታማነታቸውን እያሳደገው መሆኑን ተናገሩ። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ አርሶ አደሮቹ እንደገለጹት በአካባቢያቸው የሚገኙ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ተቋማት በተሻሻሉ የግብርና አሰራሮች ላይ የሚያገኙትን ተሞክሮ ተግባራዊ በማድረጋቸው ምርታቸው በእጥፍ ጨምሯል። በሲናና ወረዳ ወልተኢ ወቾ ቀበሌ አርሶ አደር አደም ማህሙድ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ከአካባቢያቸው ሞዴል አርሶ አደሮች ምርጥ ተሞክሮ መውሰዳቸውን ተናግረዋል። በባለሙያዎች በተደረገላቸው ድጋፍ በመስመር የመዝራት ቴክኖሎጂን ጨምሮ ሌሎች የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን የመጠቀም ልምዳቸው በየጊዜው እየዳበረ መምጣቱንም ገልጸዋል፡፡ በእዚህም ቀደም ሲል በዘልማድ ከሚያለሙት የስንዴ ሰብል የሚያገኙት ምርት በሄክታር ከ15 ወደ 65 ኩንታል ከፍ ማለቱን በማሳያነት ጠቅሰዋል ፡፡ አርሶ አደር መሐመድ በያን በበኩላቸው በአካባቢያቸው የሚገኙ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ከምርምር ማዕከላት ከሚያገኙት የተለያዩ የሰብል ዝርያዎች መካከል ከስነ- ምህዳሩ ጋር ተስማሚ የሆኑትን በመምረጥና የመስመር አዘራሩን በተግባር በማሳየት ተጠቃሚ እያደረጓቸው መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ እንደ አርሶ አደሩ ገለጻ፣ ከማሰልጠኛ ተቋማቱ በሚያገኙት ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ወደ ተግባር ከገቡ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በሄክታር የሚያገኙት ምርት ከ30 ወደ 70 ኩንታል አድጓል። በአሁኑ ወቅት ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግ በመቻላቸው ቤታቸውን ከሳር ክዳን ወደ ቆርቆሮ ቤት ከመቀየር ባለፈ በባንክ ገንዘብ መቆጠብ መጀመራቸውን ገልጸዋል። በግብርና ሥራ የቆየ ልምድ ቢኖራቸውም የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ባህል እንዳልነበር የገለጹት ደግሞ የሮቤ አካባቢ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ኡመር በከር ናቸው ። በዘልማዳዊ የአስተራረስ ዘዴ ሲያለሙት የነበረው ሰብል ከምግብ ፍጆታ የሚተርፍ እንዳልነበረም አስታውሰዋል። በቀበሌያቸው በሚገኘው የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ተቋም በግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ያገኙት ትምህርትና የአርሶ አደሮች የመስክ ቀን ተሞክሮ ምርትና ምርታማነታቸውን እያሳደገው መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የሰብል ልማት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አለምእሸት አለማየሁ እንዳሉት፣ በዞኑ የሚገኙ 96 የገበሬዎች ማሰልጠኛ ተቋማት የአርሶ አደሮችን የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲያሳድጉ በትኩረት እየተሰራ ነው ፡፡ በዞኑ ባለፈው የመኸር አርሻ በስንዴ ከለማው ከ200 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ሙሉ የግብርና ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረግ የለማ መሆኑንና በልማቱም ከ100 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ጠቁመዋል፡፡ ባለሙያው እንዳሉት አርሶ አደሩ ከግብርና ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር ያለው ቁርኝት እያደገ በመምጣቱ በዚያው ልክ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ባህሉ ጨምሯል። በተለይ ባለፈው የመኽር እርሻ አርሶ አደሮች የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችና ግብአቶችን የመጠቀም ልምዳቸው ከሌላው ጊዜ ከፍ ብሎ መታየቱን ጠቁመዋል። በእዚህም በአሁኑ ወቅት ከ30 በመቶ በላይ የምርት ጭማሪ ሊገኝ እንደሚችል በቅድመ ምርት ግምገማ መረጋገጡን ነው ያስረዱት። በባሌ ዞን በ2009/10 የመኽር እርሻ በዘር ከተሸፈነው ከ373 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከ10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁንም 85 በመቶ የሚሆነው ምርት መሰብሰቡን ከዞኑ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
357
የኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሮች ማህበር የክልሉ አርሶ አደሮች ምርታማነትን አሳድገው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከልማት ኃይሎች ጋር ተባብሮ በመሰራት መሆኑን አስታወቀ፡፡ የማህበሩ ለቀመንበር አቶ አማን ገመዳ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የክልሉ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና መሳሪያዎችን ተጠቅመው ምርታማነትን እንዲያሳድጉ ማህበሩ ከሚመለከታቸው አካላትና ከልማት ኃይሎች ጋር ተባብሮ እየሰራ ነው፡፡ ማህበሩ የአርሶ አደሮቹን ምርታማነት ለማሳደግ አብሮ ከሚሰራ የልማት ኃይሎች መካከል የህብረት ስራ ማህበራት፣ የምርት ማሳደጊያ አቅራቢ ድርጅቶችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይገኙባቸዋል፡፡ የምርት ማሳደጊያ ግበዓቶችንና ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን አርሶ አደሩ በአቅራቢያው አግኝቶ ያባክን የነበረውን ጊዜና ጉልበት በግብርና ስራው ላይ እንዲያውል ማህበሩ ከልማት ኃይሎቹ ጋር በትጋት ተባብሮ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አርሶ አደሩ የመሬቱን ለምነት ጠብቆና የአካባቢውን የተፈጥሮ ሀብት ተንከባክቦ ለምርታማነት እንዲሰራ ከፍተኛ ሚና ያለውን የመሬት ባለቤትና ማረጋገጫ ደብተር እንዲያገኝ ከሚመለከታቸው አስፈፃሚ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ከክልሉ በታታሪነታቸው የተመረጡ አርሶ አደሮች በብሔራዊ ደረጃ መሸለማቸው ሌሎች አርሶ አደሮች ለልማት እንዲነሳሱ ማድረጉን ሊቀመንበሩ ገልፀው የተገኘው ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረውም ማህበሩ የሚጠበቅበትን ሁሉ ያደርጋል ብለዋል፡፡ በ1997 ተየቋቋመው የኦሮሚያ አርሶ አደሮች ማህበር በአሁኑ ወቅት 600ሺህ አባላት እንዳሉት ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል፡፡
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
358
በቤንች ማጂ ዞን በያዝነው ዓመት ከ3ሺሀ 800 በላይ አባወራ አርሶ አደሮችን ለማስፈር መታቀዱን የዞኑ ምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ዴስክ አስታወቀ፡፡ የዴስኩ ኀላፊ አቶ መስፍን ግዛው ትላንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት በደቡብ ክልል ከሚገኙና በድርቅ ከተጎዱ የተለያዩ አካባቢዎች በፈቃደኝነት የሚነሱት እነዚሁ አርሶ አደሮች የሚሰፍሩት በዞኑ በሚገኘው የጉራፈርዳ ወረዳ ነው፡፡ ሰፋሪዎቹ በምግብ ሰብል ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ የእርሻ በሬ፣ የግብርና ቁሳቁስና የተለያዩ የምርት ግብዓቶች በነፃ እንደሚሰጧቸውም አስረድተዋል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከሲዳማ፣ ጌድኦና ጉራጌ ዞኖች በፈቃደኝነት የተነሱ ከ1ሺህ 500 በላይ አባወራ አርሶአደሮች በዞኑ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡ ለእነዚህ ሰፋሪዎች በነፍስ ወከፍ ሁለት ሄክታር የእርሻ መሬት፣ 1 ሺሀ ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት መስሪያና የጓሮ አትክልት ማልሚያ ቦታ፣ የእርሻ በሬና የተለያዩ ቁሳቁስ የተሰጣቸው በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ በምግብ ሰብል ምርት ራሳቸውን ለመቻል መብቃቸውን አቶ መስፍን ጨምረው ገልጠዋል፡፡
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
359
 አርሶ አደሩ ሦስት የተሻሻሉ የጤፍ ዝርያዎችን አገኙ ናዝሬት(ኢዜአ)፦ ምሥራቅ ሸዋ ውስጥ በሶስት ወረዳ አንድ አርሶ አደር በጤፍ ሰብል ላይ ለ11 ዓመታት ባካሔዱት የዘር መረጣ የተሻለ ምርት የሚሰጡ ሶስት የጤፍ ዝርያዎች ማግኘታቸውን ገለጡ። አርሶ አደሩ ያገኙአቸው የጤፍ ዝርያዎች በምርምር ከተገኙት ምርጥ ዘሮች እንደማያንሱ ባለሙያዎች አረጋገጡ። በኤክስቴንሽን አገልግሎት የታቀፉ አርሶ አደሮችን እንቅስቃሴ ለመገምገም በተዘጋጀው ዓመታዊ የሰብል በዓል ላይ የጤፍ ዝርያዎቹን ያገኙት የወለንጪቲ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አቶ ሲሳይ ተክለ ሥላሴ እንደገለጡት ዝርያዎቹ በአጭር ጊዜ የመድረስና ድርቅን የመቋቋም አቅም አላቸው። ከ1979 ጀምሮ የተለያዩ የጤፍ ዘሮችን ሲመርጡ መቆየታቸውንና ዝርያዎቹን የማሰባሰብን ሥታ በ1982 ማጠናቀቃቸውን እኚሁ አርሶ አደር አመልክተዋል። ለሁለት ዓመታት ባካሄዱት ሙከራ ሶስቱ የጤፍ ዝርያዎች በሄክታር ከ20 ኩንታል በላይ ምርት ማስገኘታቸውን አቶ ሲሳይ ገልጠው ያባዙትን ምርጥ ዘር ለሌሎች 10 አርሶ አደሮች ሰጥተው የተዘራው ጤፍም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል። እነዚሁ የጤፍ ዝርያዎች ከአዋሽ መልከሳ የእርሻ ምርምር ማእከል ከተገኙት ሶስት የጤፍ ዝርያዎች ተመሳሳይ ምርት እንደሚሰጡ በሙከራ ማረጋገጣቸውን አርሶ አደሩ ገልጠዋል። አቶ ሲሳይ በጥረታቸው ያገኙአቸውን ሶስት የጤፍ ዘሮች ፍፁም ኢያሱና ቅድስት በተባሉት ልጆቻቸው ስም መሰየማቸውንና ስያሜውም በምርምር ማእከሉ እውቅና አግኝቶ አርሶ አደሮች እየተጠቀሙበት መሆኑን አስታውቀዋል። ከጤፍ ዝርያዎቹ መካከል ፍጹም የተሰኘውን በመኸር ወቅት በሶስት ነጥብ አምስት ሔክታር መሬት ላይ መዝራታቸውንና ይኸው ዘር በ30 ቀናት ውስጥ እንደሚያዘረዝር አስረድተዋል። የጤፍ ዝርያዎቹ ከአለማያ ግብርና ዩኒቨርስቲ ለጉብኝት በመጡ ባለሙያዎች አድናቆት ማትረፋቸውን አቶ ሲሳይ ተናግረዋል። ባለፉት ሶስት ዓመታት ደግሞ በኤክስቴንሽን አገልግሎት ታቅፈው ከባለሙያዎች በተደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምርት አግኝተው ሁለት ጥማድ በሬ መግዛታቸውንና የቆርቆሮ ክዳን ቤት መሥራታቸውን አቶ ሲሳይ አመልክተዋል። የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታቸው በየነ በዚሁ የሰብል ግምገማ በዓል ላይ እንደገለጡት አርሶ አደሩ በግል ጥረታቸውን የጤፍ ዝርያዎቹን በማግኘት ከምርምር ማእከላት የማያንስ ውጤት ማስመዘገባቸውን አስታውቀዋል። በአዋሽ መልካሳ የምርምር ማእከል የብሔራዊ ግብርና መካናይዜሽን ምርምር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መለሰ ተመስገን በበኩላቸው ከምርምር ማእከሉ በተደረገላቸው እገዛ አርሶ አደሩ ያገኙአቸው ሶስቱ የጤፍ ዝርያዎች በማሳ ላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጠዋል።
[ 103 ]
[ "አርሶ አደሮች" ]
[ "በአርሶ አደሮች ላይ ስለተከናወኑ መርሃ ግብሮች የሚያትሰቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአርሶ አደሮች የስር ባህልና የኑሮ ሁኔታ, ስለሚሰሩአቸው ስራወች, ስለሚያመርቱዋቸው ምርቶቸ, ምርታማነት ለማሻሻል ሰለተደረጉ የስራ ክንውኖች የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ አርብቶ አደሮች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
360
የአለም የደም ለጋሾች ቀን ለ9ኛ ጊዜ ተከበረ, .._2012___. 0 300 226 ; 5; አዲስ አበባ ሐምሌ 232004ዋኢማ - የበጎ ፍቃድ ደም ልገሳ በወሊድና በአደጋ ወቅት ለሚያጋጥም የሞት አደጋ መቀነስ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተባለ፡፡ እያንዳንዱ ደም ለጋሽ ጀግና ነው በሚል መሪ ቃል ዛሬ የአለም የደም ለጋሾች ቀን ለ9ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል፡፡ በበአሉ ላይ በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመድ ኢማኖ የደም መስጫ ማእከላትን የማስፋፋቱ ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሚገኝ የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው፡፡ ደም በመለገስ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦችም የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል። ),
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
361

362
ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች 52ሺ የደም ከረጢት ደም ተሰበሰበ , - ; .._2012_. 0 253 197 ; 5; አዲስ አበባ ነሐሴ 22004ዋኢማ - ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች 52ሺ የደም ከረጢት በመሰብሰብ ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ማከፋፈሉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የቢሔራዊ የደም ባንክ ዳይሬክተር ዶክተር ግሩም ተስፋዬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ከተሰበሰበ ደም 99 ነጥብ 4 በመቶ ለተጠቃሚው ተሰጥቷል። በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከበጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች ለመሰብሰብ የታቀደው 79ሺ ከረጢት ደም እንደነበረ ገልፀው፤ የተሰበሰበው ግን 52ሺ ኪረጢት መሆኑን ተናግረዋል። በአገሪቱ የሆስፒታሎችና የጤና ጣቢያዎች ቁጥር እየተበራከተና የጤና አገልግሎት ሽፋኑ እየተስፋፋ መምጣቱን የተናገሩት ዶክተር ግሩም  ከመስፋፋቱ ጋር ተያይዞ ደም ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ይናገራሉ። እየጨመረ የመጣውን የደም ፍላጎት ለማሟላት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየክልል ዋና ከተሞች አንድ አንድ የደም ባንክ ማዕከል እንዲኖር የተደረገ ሲሆን፤ በሰፋፊ ክልሎች ደግሞ ከአንድ በላይ የደም ባንክ ማዕከል እንዲኖር ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል። ይህም አሁን ያለውን 12 የደም ባንኮች ቁጥርን በማሳደግ ወደ 26 ያደርሰዋል ብለዋል። በደም ባንኩ ውስጥ በቂ ደም ባለመኖሩ አንዳንድ ችግሮች እንዳሉ የተናገሩት ዶክተር ግሩም በጣም የተቸገረ ድንገተኛ ታማሚ ሲኖር ሆስፒታሎች ችግሩን ስለሚያውቁ በቀጥታ ወደ ደም ባንኩ ይደውላሉ እኛም የሰው ነፍስ ለማትረፍ እንሰራለን ብለዋል። በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች በብዛት መኖራቸው የበርካታ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ እንደሚያስችል የተናገሩት ዶክተር ግሩም ደም በፍቃደኝነት የመለገስ ባህልን ሁሉም ህብረተሰብ ሊለምደው ይገባዋል ብለዋል።     የደም ባንክ ማዕከል በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስር በመሆን ላለፉት 42 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል። ),
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
363
የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር እያደገ መሆኑ ተጠቆመ ። በኢትዮጵያ የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር እያደገ መምጣቱን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሀበር አስታወቀ ። በማሀበሩ የደም ለጋሾች ማስተባበሪያ ሃላፊ አቶ ዝናቡ ከበደ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንደገለጹት ከሶስት አመታት በፊት የደም ባንኩ ከሚሰበስበው ደም 18 በመቶ የነበረው የበጎ ፈቃደኞች ሽፋን ባለፈው አመት ወደ 41 ነጥብ 3 በመቶ አድጓል ። በተለይም በግለሰብና ቤተሰብ ደረጃ የመደበኛ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር እያደገ መምጣቱን የጠቆሙት ሃላፊው ፤ በአመት እስከ 107 ጊዜ ያህል ደም የሚለግሱ መደበኛ ለጋሾች መኖራቸውን ጠቁመዋል ። ከመደበኛ ደም ለጋሾች በተጨማሪ በትምህርት ቤቶች ፣ በማሰልጠኛ ተቋማትና ገዳማት በየአመቱ በበጎ ፈቃደኝነት የሚለግሱ ዜጎች መኖራቸውን አቶ ዝናቡ አመልክተው ፤ ይህም ሀብረተሰቡ በበጎ ፈቃደኝነት ደም በመለገስ የብዙዎችን ህይወት ማዳን እንደሚችል ግንዛቤው እየዳበረ መምጣቱን ያሳያል ብለዋል ። በተለይም የበጎ ፈቃደኞች መበራከት ከህሙማን ቤተሰብ ለጋሾች የሚወሰደውን ደም ለመቀነስ ከማስቻሉም በላይ ወደፊት ለህሙማን በነጻ የሚታደል ደም በበቂ ሁኔታ ለማከማቸት እንደሚያስችል ጠቁመዋል ። ይሁን እንጂ የበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች ቁጥር እድገት እያሳየ ቢሆንም ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑን ተቅሰዋል ። የደም ባንኩም ቢሆን ስለበጎ ፈቃደኝነት ደም ልገሳ ሀብረተሰቡን በማስተማርም ሆነ በመቀስቀስ ረገድ እስካሁን አጥጋቢ እንቅስቃሴ አለማድረጉንና በቀጣይ የሚያተኩርበት ተግባር መሆኑን የማስተባበሪያ ሃላፊው ገልጸዋል ። ሆኖም የደም ባንኩም የደም ለጋሾችን ቁጥር ከማሳደግ ጎን ለጎን በደም ምርመራውም ሆነ አገልግሎቱን በማዳረሱ ረገድ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ፤ ከዚህ አኳያ አገልግሎቱን ለማስፋት አሁን ካሉት ዘጠኝ ቅርንጫፎች በተጨማሪ ሌሎች ማእከላትን በተለያዩ ክልሎች ለመክፈት ጥናት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል ። በደም ባንኩ የሚከናወኑ የደም ምርመራዎች አስተማማኝ ከመሆናቸውም በተጨማሪ የማንኛውም ደም ለጋሽ ሚስጥር የሚጠብቅ በመሆኑ ሀብረተሰቡ በጎ ፈቃደኝነቱን ደም እንዲለግስ ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል ።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
364
የመዲናዋ ስራ አስፈጻሚ አካላት ደም በመለገስ አርአያ እንዲሆኑ ጥሪ ቀረበ አዲስ አበባ የካቲት 5/2011 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ስራ አስፈጻሚ አካላት ደም በመለገስ የአርአያነት ተግባር እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀረበ። ከመቶ በላይ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት በጥር ወር በተለያዩ ተግባራት የተከበረውን የጤናማ እናትነት ወር በማስመልከት ዛሬ በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ተገኝተው ደም ለግሰዋል። የምክር ቤቱ አባላት በቀጣይም ደም ልገሳን የዘመቻ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባራቸው በማድረግ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማነቃቃት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ደም መለገስ ከእለት ተእለት ተግባራት አንዱ እንዲሆን ለማስቻል ምክር ቤቱ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል። የከተማዋ ምክር ቤት አባላት በየሶስት ወሩ የደም ልገሳ ንቅናቄ በማድረግ ጤናማ ሰው በዓመት ሶስት ጊዜ ደም በመለገስ የዜጎችን ህይወት መታደግ እንደሚችል ‘ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል’ ብለዋል። የጤናማ እናትነት ወርን አስመልክቶ የተካሄደው የደም ልገሳ ቀጣይነት እንዲኖረውና ህብረተሰቡም እንዲተገብረው ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኙ በጎ ፈቃደኞችና ጽህፈት ቤቶች ጋር ዓመቱን ሙሉ እንዲከናወን ይደረጋል ነው ያሉት። የምክር ቤቱ የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሂሩት አጽብሃ ባለፈው ጥር የጤናማ እናትነት ወር የተለያዩ ተግባራት ቢከበርም ደም ልገሳ በየወቅቱ እንዲከናወን ንቅናቄ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ አባላት በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት በተለይም በደም ልገሳ ፈር ቀዳጅ በመሆን ለህብረተሰቡ ምሳሌ መሆን እንደሚችሉም አመልክተዋል። በተጨማሪም የከተማዋ ስራ አስፈጻሚ አካላት ከተጣለባቸው ሃላፊነት ጎን ለጎን በስራቸው ከሚገኙ ሰራተኞች ጋር በመሆን የደም ልገሳን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል። የምክር ቤቱ አባላት የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ደም በመለገሳቸው መደሰታቸውንና ይህን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል። ወይዘሮ አበባ ደሴ እና አቶ ደረጀ አበራ እናቶች በደም መፍሰስ ሳቢያ እንዳይሞቱ ደም በመለገስ ባደረጉት አስተዋጽኦ የህሊና እርካታ እንዳገኙ ገልጸዋል። የህክምና ምርመራ አድርጎ ደም መለገስ እንደሚቻል የተረዳ ማንኛውም ሰው የዜጎችን ህይወት መታደግ እንደሚችልና ደም መለገስ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያስከትልም ግንዛቤ ማግኘታቸውንም አክለዋል። የደም ልገሳ ተግባር ወደ ማህበረሰቡ እንዲሰርጽ በማድረግ የህብረተሰቡ የበጎ ፈቃደኝነት ተሳትፎ እንዲጎለብት የበኩላቸውን እንደሚወጡ የተናገሩት ደግሞ የምክር ቤቱ አባል አቶ ብዙአየሁ ገዛኸኝ ናቸው።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
365
የደም መለገስ ባህል ህብረተሰቡ እንዲያዳብር ጥሪ ቀረበ ጋምቤላ ጥር 21/2011 ኅብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን እንዲያጎለብት የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጠየቁ። ”በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት በጋራ እንከላከል!’‘ በሚል መሪ ቃል ትናንት በጋምቤላ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። ምከትል ርዕሰ መሰተዳድሩ አቶ ተንኳይ ጆክ በዚሁ ወቅት የእናቶችን የጤና አገልገሎት በማሻሻል ውጤታማ ተግባራት ቢከናወኑም፤ከወሊድ ጋር በተያያዘ በሚከሰተው የደም መፍሰስ ችግር እናቶች ተጎጂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በደም መፍሰስ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችን ሞት ለመቀነስ ደም የመለገስ ባህል እንዲጠናከር ጠይቀዋል። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኡማን አሙሉ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የምዕተ ዓመቱ የጤና ልማት መርሃ ግብር የእናቶችን የጤና አገልገሎት በማሻሻል ረገድ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የእናቶች የጤና አገልገሎት በተፈለገው ደረጃ አለመሟላቱን ጠቁመዋል። የእናቶች ሞት ከቤተሰብ አልፎ በኅብረተሰቡና በአገር ላይ የሚያስከትለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የከፋ ነው ያሉት ኃላፊው፡ ለእናቶች ጤና መሻሻል የአመራሩና የህዝቡ አጋርነት እንዲጠናከር ጠይቀዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ዶክተር ሎው ኡቡፕ በሰጡት አስተያየት ለእናቶች ጤና አገልግሎት የተመደቡ አምቡላንሶችን ለታለመላቸው ዓለማ በማዋል ረገድ የሚታዩ ችግሮች መታረም አለባቸው ብለዋል። በደም መፍሰስ ምክንያት የሚገጥመውን ችግር ለማቃለል ወደ መቱ ሆስፒታል የሚላኩ እናቶች ለእንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። የእናቶችን የጤና አገልገሎት ለማሻሸል በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። በወሊድና በቅድመ ወሊድ ወቅት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማቱ የሚሄዱ እናቶች በአግባቡ እንደማይስተናገዱ የገለጹት ሌላዋ የውይይቱ ተሳታፊ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ ናቸው። በባለሙያዎች ስነ ምግባር ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር መጠናከር እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዋ ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልል፣የዞን፣የወረዳ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ባለድርሻ አካላት ደም ለግሰዋል። በኢትዮጵያ የጥር ወር የጤናማ እናትነት ወር በሚል በተለይ ለወላዶች ጤና ትኩረት ይሰጥበታል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
366
ህብረተሰቡ ደም በመለገስ ያሳየው ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሀዋሳ ደም ባንክ ጠየቀ 252 Share ሀዋሳ ጥቅምት 18/2012 ኢዜአ ህብረተሰቡ ደም በመለገስ የእናቶችና ህጻናትን ሞት ለመከላከል ያሳየውን መልካም ተነሳሽነት አጠናክሮ እንዲቀጥልበት የሀዋሳ ደም ባንክ ጥሪ አቀረበ ። ባንኩ ከእቅዱ በላይ ደም የሰበሰበ ሲሆን የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ የሀዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ሰራተኞች በደም ልገሳው ተሳትፈዋል ። የኢንድስትሪያል ፓርኩ ሰራተኞች ባካሄዱት የደም ልገሳ ስነስርዓት ላይ የሀዋሳ ደም ባንክ እንደገለፀው ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስ ህብረተሰቡ የሚለግሰው ደም ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ነው። በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የሀዋሳ ደም ባንክ የደም ለጋሾች መልማይ ኦፊሰር አቶ ማቲያስ አንጅሎ እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘመቻ ደም የመለገስ ቀንን ምክንያት በማድረግ ጥቅምት 15 በተካሄደው ዘመቻ 638 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 740 ዩኒት መሰብሰብ ተችሏል። የደም ልገሳ ቀን ከመድረሱ አንድ ሳምንት አስቀድሞ የምዝገባና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች መሰራታቸውን የጠቆሙት አቶ ማቲያስ ከአራት ሺህ በላይ ደም ለጋሾች በቋሚነት ለመለገስ ምዝገባ እንዳደረጉ ገልጸዋል። ሁሉጊዜ በዘመቻ ማስኬድ አይቻልም ያሉት ኦፊሰሩ “ህብረተሰቡ የደም ልገሳን ባህሉ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል ። አሁን የተመዘገቡት ሰዎች በዓመት ቢያንስ አራት ጊዜ በመስጠት ቋሚ ደም ለጋሽ ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ። ከኢንዱስትሪያል ፓርኩ ደም ለጋሾች መካከል ወይዘሪት አብነት አርጋው በሰጠችው አስተያየት በርካታ ቁጥር ያላቸው እናቶች በወሊድ ወቅት በሚያጋጥማቸው የደም መፍሰስ አደጋ ህይወታቸው እንዳያልፍና እኔም በሴትነቴ ነገ ደም ሊያስፈልገኝ እንደሚችል በማሰብ ጭምር ደም እየለገስኩ ነው ብላለች። የዛሬውን ጨምሮ ለሶስተኛ ጊዜ ደም መስጠቷን የተናገረችው ወይዘሪት አብነት “ደም በመስጠቴ እኔ በጣም ደስ ብሎኛል ” በማለት ሌሎችም አርአያነቷን እንዲከተሉ መክራለች ። ሌላው ደም ለጋሽ አቶ ናትናኤል ሰብል በበኩሉላቸው በማንኛው ሰዓት ደም በመለገስ የእናቶችና ህጻናት እንዲሁም በተለያዩ አደጋዎች በሚያጋጥም የደም መፍሰስ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን ሞት ለመታደግ የበኩሌን ደርሻ እያበረከትኩኝ እገኛለሁ ብለዋል ። ደም ሲለግሱ የአሁኑ ለሰባተኛ ጊዜ መሆኑን ገልፀው በሚሰጡት ደም የወገናቸውን ህይወት የሚታደግ በመሆኑ ደስተኛነት እንደሚሰማቸው አስረድተዋል ። ለሶስተኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውንና ባደረጉት የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሌሎች ህይወት ለማዳን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ኤልያስ ሽታ ናቸው፡፡ “በኔ ደም ሰው መጠቀም ከቻለ እኔ ደሞ መስጠት ከቻልኩ ምንም ችግር የለውም ። ምክንያቱም በምጠጣው ውሀ የሚመለስ ስለሆነ ሁላችንም እንለግስ ” ብለዋል። የኢንደስትሪያል ፓርኩ ባለሀብቶች ማህበር አስተባበሪ ወይዘሪት ትርሲት እንድሪያስ እንዳሉት በዛሬው የደም ልገሳ ስነስርዓት በኢንደስትሪያል ፓርኩ የሚገኙ ባለሀብቶችና የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች የደም ልገሳ ያደርጋሉ። በነገው ዕለትም ሌሎች የፓርኩ ሰራተኞች ልገሳ እንደሚያደርጉና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቶ ሁሉም ፈቃደኞች መሆናቸውን ተናግረዋል። የፓርኩ የአስተዳደር ሰራተኞች በአብዛኛው በቋሚነት ደም ለመለገስ መስማማታቸውንም ጠቁመዋል። “በሀገር አቀፍ ደረጃ በታወጀው መሰረት እኛም የበኩላችንን ለማድረግ ስምምነት ላይ በመድረሳችን ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ እየተሳተፈ ይገኛል” ብለዋል። በደም ልገሳው ላይ በፓርኩ የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች ጭምር ተሳታፊ ሆነዋል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
367
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የደም ልገሳን ባሕል አድርጎ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር፡ ሕዳር 28/2012ዓ.ም (አብመድ) የኢዜማ የባሕር ዳር ከተማ ምርጫ ወረዳ ‹‹ደም ለማኅበራዊ ፍትሕ ሲውል›› በሚል መሪ ሐሳብ በጽሕፈት ቤቱ ግቢ ውስጥ ዛሬ የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሂዷል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት ደም የለገሱት የፓርቲው የባሕር ዳር ከተማ ምርጫ ወረዳ ምክትል ሊቀ መንበር ታያቸው ንጉሤ እንደተናገሩት የደም ልገሳ መርሀ ግብሩ ደም የሚያስፈልጋቸውንና ሕክምና ላይ ያሉ ወገኖችን በደም እጥረት እንዳይቸገሩ ማገዝን ዋና ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ የፓርቲው መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች ጥሪውን ተቀብለው በጽሕፈት ቤቱ በመገኘት በደም እጦት ለሚጎዱ ዜጎች በሙሉ ፍቃደኝነት ደም ለግሰዋል፤ ለሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም ጭምር አርዓያ መሆናቸው የሚበረታታ ተግባር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በደም ልገሳ መርሀ ግብሩ ከተሳተፉት የፓርቲው ወጣት አባላት መካካል አቶ መንግሥቱ አማረ እና ወይዘሮ መልካም ተበጀ እንደተናገሩት ደግሞ ከፖለቲካ ተሳትፎቸው ባሻገር በማኅበራዊና ሰብዓዊ ተግባራት በመሳተፋቸው ተደስተዋል፡፡ ‹‹ደም ዘር የለውም›› ያሉት አስተያዬት ሰጭዎቹ ደም ሕይወትን ለማትረፍ እንጅ ለብሔር የሚሰጥ ባለመሆኑ በጎ ተግባሩን እንደ ባሕል በመያዝ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ ደም ባንክ ቡድን አስተባባሪ አጸደ ማኅቶት ደግሞ የኢዜማ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች ደም በመለገስ የዜግነት ኃላፊነታቸውን በመወጣታቸው አመስግነዋል፡፡ በተመሳሳይም በአማራ ክልል ከሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አዴፓ እና አብን በደም ልግሳ መሳተፋቸውን አስታውሰዋል፡፡ የደም ልገሳ መርሀ ግብሩ በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ እየተካሄደ በመሆኑ በዚህ ወቅት ምንም ዓይነት የደም እጥረት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ ደም ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት 12 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፤ ባለፉት አራት ወራት ብቻ መሰብሰብ ከነበረበት 4ሺህ ዩኒት ደም በላይ 8 ሺህ 300 ዩኒት ሰብስቧል፡፡ አፈፃፀሙም በኢትዮጵያ ከሚገኙ 42 የደም ባንኮች ጋር ሲነፃፀር አንደኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑንም ከባሕር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) በኢትዮጵያ የእያንዳንዱ ዜጋ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ማኅበራዊ ፍትሕ የሰፈነባት፣ በዜጎች ጽኑ የአንድነት ማዕቀፍ፣ የተለያዩ ባሕሎች፣ ቋንቋዎችና እምነቶች ሳይበላለጡ በነፃነት የሚስተናገዱባት፣ ሠላምና መረጋጋት የተረጋገጠባት፣ በላቀ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሁለንተናዊ ዕድገትና ብለጽግና የተጎናጸፈች፣ ሁሉም ዜጎች የሚኮሩባት ታላቅና ገናና ሀገር ሆና የማየት ራዕይን ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አቶ ታያቸው ገልፀዋል፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
368
ደም በመለገስ ህይወት በመታደጋቸው መደሰታቸውን ለጋሾች ገለጹ 309 Share ባህርዳር/ ሰመራ ኢዜአ ጥቅምት 15/2012፡- ደም በመለገስ ህይወታቸውን ሊያጡ የነበሩ ወገኖችን መታደጋቸው እንዳስደሰታቸውና ባህልም ሆኖ እንዲቀጥል ፍላጎታቸው መሆኑን በባህርዳርና ሎጊያ ከተሞች የሚኖሩ ለጋሾች ገለጹ። “ህይወትን ለህይወት ደም በመለገስ ህይወት ያድኑ ” በሚል የደም ልገሳ መርሃ ግብር በባህርዳር እና ሰመራ- ሎጊያ ከተሞች እየተካሄደ ነው። በባህርዳር የዳግማዊ ምኒሊክ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ወጣት ግርማ ጌቴ በሰጠው አስተያየት ዛሬ የለገሰው ደም ለሁለተኛ ጊዜው እንደሆነ ተናግሯል። ደም ለመለገስ ያነሳሳውም ቤተሰብ ታሞበት ሆስፒታል በነበረበት ወቅት በመኪና አደጋ የተጎዳ ሰው መጥቶ ደም እንደሚያስፈልገው ሰጠየቅ በፈቃደኝነት ሰጥቶ ህይወቱን ማትረፍ በመቻሉ እንደሆነ ገልጿል። “የሰጠሁት ደም ህይወቱን ሊያጣ የነበረን ሰው ማትረፍ ከቻልኩ በየሶስት ወሩ አንድ ዩኒት ደም በመለገስ ብዙ የተቸገሩ ህመምተኞችን ለማዳን በመወሰኔ ዛሬ ለመስጠት በቅቻለሁ” ብሏል። ሌላኛው የከባድ ተሽከርካሪ ሾፌር አቶ ጥበቡ ተገኝ በበኩላቸው ደም ለመለገስ የነበረው ፍላጎተ ከስራው ባህሪ አኳያ ሳይሳካለት ቢቆይም ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በመለገሳቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል። በወሊድና በትራፊክ አደጋ በርካታ ሰዎች በሚያጋጥማቸው የደም መፍሰስ ህይወታቸውን ሲያጡ ስለሚመለከቱ ደም ለመለገስ እንደተነሳሱ ገልጸዋል። “በምለግሰው ደም ልትቆረጥ የደረሰችን እስትንፋስ ዳግም እንድትቀጥል ከማድረግ የበለጠ የሚያስደስተኝ ነገር የለም “ያለችው ደግሞ የመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፌቨን ተሾመ ናት። ሌሎች ጓደኞቿ እንዲለግሱም እንደምትመክርና ዛሬ ለሶስተኛ ጊዜ መለገሳን ገልጻ በቀጣይም በየሶስት ወሩ ሳታቋርጥ እንደምትሰጥ ተናግራለች። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የደም ባንክ አስተባባሪ አቶ አንዳርጌ አጥናፉ በበኩላቸው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ዛሬ ባህርዳርን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ መርሃ ግብርም 3ሺህ 448 ዩኒት ደም ለመሰብሳብ ታቅዷል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል ሎግያ ከተማ በደም ልገሳ መረሃ ግብር ከተሳተፉት መካከል አቶ አሊ ሁሴን እንዳሉት የዛሬን ጨምሮ ደም ለሰባት ጊዜ ለግሰዋል። ህብረተሰቡ ደም በመለገስ የራሱን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር ኝ በደም እጦት ምክንያት የሚሰቃዩ ወገኖቹን መርዳትን ባህሉ አድርጎ ቢቀጥል ፍላጎታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው በዚሁ ከተማ ደም ሲለግሱ የነበሩት አቶ ኢብራሂም አደም በበኩላቸው በተሰማሩበት የህክምና ሙያ ብዙ ጊዜ ሰዎች በደም እጦት ምክንያት እንደሚቸገሩ ገልጿል። በዚህም ዛሬን ጨምሮ ለዘጠነኛ ጊዜ ደም መለገሱን ገልጾ በህብረተሰቡ ዉስጥ ስለደም መስጠት ያለዉን አመለካከት ለመቀየር ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መጠናከር እንዳላበት አመልክቷል። የሰመራ ደም ባንክ ኃላፊ አቶ አወል በአካባቢው ህብረተሰብ ደም የመለገስ ባህሉ ቢሻሻልም ከሚፈለገው ደረጃ ላይ ለማድረስ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እንደሚካሄድ ተናግረዋል። የአፋር ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፈረጅ ረቢሳ እንዳሉት ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ባሉት የደም ባንኮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ደም በመሰብሰብ በአቅራቢዉ ለሚገኙ ሆስፒታሎች የማቅረብ አገልግሎት እየተሰጠ ነው። በክልሉ የሀገር-አቀፉ ንቅናቄ አካል በሆነው የዛሬው ፕሮግራም 290 ዩኒት ደም በአዋሽ ሰባት ኪሎና በሰመራ-ሎግያ ከተሞች ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
369
በአንድ ቀን 10 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑን ብሔራዊ የደም ባንክ ገለጸ 277 Share ኢዜአ ጥቅምት 15/2012ዓ/ም ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ 10 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑን ብሔራዊ የደም ባንክ አስታወቀ። “ደም እንለግስ ህይወት እናድን” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ከ10 ሺህ በላይ ዩኒት ደም የመሰብሳብ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአገሪቷ ያሉ 43 ቅርጫፎችን በማሳተፍ 10 ሺህ ዩኒት ደም ከደም ለጋሾች የመሰብሰብ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የደም ባንኩ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ያረጋል ባንቴ ተናግረዋል። በዓመት እየተሰበሰበ ያለው 223 ሺህ ዩኒት ደም ሲሆን ለአገሪቷ የሚያስፈልገው ግን አንድ ሚሊዮን ዩኒት ደም መሆኑንም ገልጸዋል። ከአንድ ሰው የሚሰበሰበው ደም ለ42 ቀናት ብቻ የሚቆይ ሲሆን አንድ ሰው ደም ለገሰም አልገሰም አንድ የደም ሴል መቆየት የሚችለው ከ3 እስከ 4 ወራት ብቻ በመሆኑ ሰዎች ለወገናቸው ደም መለገስ ይገባቸዋል ብለዋል። ደም የሚለግሱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም አሁን ብዙ ስራዎች የሚቀሩ መሆኑን ጠቅሰው በትምህርት ቤቶች፣ በሚዲያና በሌሎች ዘዴዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ጠቁመዋል። ዛሬ ለመሰብሰብ የታቀደው 10 ሺህ ዩኒት ደም መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ በስፋት ለመሰብሰብ ይሰራል ያሉት ዳይረክተሩ፤ አሁን በወር ከ18 ሺህ ዩኒት ደም በላይ ያስፈልጋልም ብለዋል። የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ በበኩላቸው የደም ለጋሾችን መረጃ ኮምፒውተራይዝድ ለማድርግ የሚያስችል አሰራር ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት ላይ ይውላልም ብለዋል። በዚህም ደም ለጋሾች በየሶስት ወሩ ደም መስጠት የሚያስችላቸውን መረጃ በአጭር መልክት ለመሳወቅ የሚያስችል አሰራር ከቴሌ ጋር በመሆን የተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። ከዚህም በተጨማሪ የደም ለጋሹ ደም አገልግሎት ላይ ሲውል የምስጋና መልዕክት ይላክለታል ብለዋል። መሰረታዊ የደም ልገሳ ባህል በአገራችን ባለመዳበሩ አብዛኛው ጊዜ የደም እጥረት ይከሰታል፣ የአገሪቷ ዜጎችም ደም በመለገስ ደም የሚፈልጉ ወገኖቻችንን ህይወት መታደግ አለባቸው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። ደም በመለገስ ላይ የነበሩ ሰዎች በሰጡት አስተያየትም ህይወት ለማዳን ደም በመስጠታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሰው ለሌላው ሰው ደም በመስጠትም የዜጎቹን ህይወት ማዳን አለበት ብለዋል። ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል አቶ ዘውድነህ አብዲ እንዳሉት ደም ሲሰጡ የመጀመሪያቸው ሆኖ ከእሳቸው በሚሰወድ ደም ሌላውን ማዳን በጣም የሚያስደስታቸው መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ደም መስጠት እንደሚፈልጉና ደም በመስጠት በደም እጥረት የሚሞቱትን ሰዎች ለማደን ሁሉም ደም መስጠት እንዳለበት ተናግረዋል። ደም መለገስ ለሌሎች ጥቅም ብቻ ሳይሆን የራስንም የደም አይነት ለማወቅና ያሉበትን የጤንነት ደረጃም ለማወቅ ይረዳልም ብለዋል። ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ አያት ኑር በበኩላቸው ለ6ኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውን ጠቅሰው በየጊዜው ደም መስጠት በመቻላቸውና በሰጡት ደምም ሰውን ከማዳን በላይ የሚያስደስት አለመኖሩን ገልጸዋል። ቤተሰቦቿም ደም የመለገስ ባህል ያላቸው መሆኑን ጠቁመው “ሁላችንም ደም የመለገስ ባህል ልናደርግ ይገባልም” ብለዋል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
370
ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት 106 ሺህ ከረጢት ደም ሰበሰበ 860 Share አዲስአበባ የካቲት 6/2011 ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት በአገር አቀፍ ደረጃ 106 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች መሰብሰቡን አስታወቀ። በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 38 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች በማግኘት የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካት ችሏል። የዕቅድ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11 ሺህ ከረጢት ደም ብልጫ አለው። የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ሄለን ኃይሉ እንዳሉት የኀብረተሰቡ በፈቃደኝነት ደም የመለገስ ልምድ እያደገ በመምጣቱ በግማሽ ዓመት 90 በመቶ የዕቅድ አፈጻጸም ማሳካት ተችሏል። በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፈቃደኝነት የደም ልገሳ ካደረጉ በኋላ የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች ቁጥር እንደጨመረም ገልጸዋል። አንድ ሰው የሚለግሰው ደም የሦስት ሰዎችን ህይወት ማዳን እንደሚቻል የገለጹት ዶክተር ሄለን ኀብረተሰቡ ደም መለገስን ባህል ሊያደርገው ይገባልም ነው ያሉት። እንደ ዶክተር ሄለን ገለጻ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 65 ዓመት ድረስ ያሉ ሰዎች ደም ቢለግሱ የዜጎችን ህይወት ከመታደግ ባሻገር ለራሳቸውም ጤንነት ጠቃሚ ነው። አንድ ሰው ደም በሚለግስበት ወቅት አሮጌው የደም ህዋስ በአዲስ የሚተካ በመሆኑ ከደም ጋር በተያያዘ ከሚፈጠር ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት መዳን እንደሚቻልም አስረድተዋል። ጄ ኤሰ አይ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በአጋርነት መስራት የጀመረበትን 25ኛ ዓመት ዛሬ ደም በመለገስ አክብሯል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
371
የጀመርነውን የደም ልገሳ አጠናክረን እንቀጥላለን ….በጋምቤላ ደም ለጋሾች 55 Share ጋምቤላ ጥር 22/2011 በጋምቤላ ክልል በደም እጦት ምክንያት የሚሞቱ ዜጎችን ለመታደግ የጀመሩትን የደም ልገሳ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ደም ሲለግሱ የተገኙ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ፡፡ የክልሉ ደም ባንክ በበኩሉ የለጋሾችን ቁጥር በማሳደግ የደም አቅርቦት እጥረትን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጿል፡፡ የጤናማ እናትነትን ወር አስመልክተው ደም ሲለግሱ የነበሩ አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች እንዳሉት በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰተውን የሰው ሞት ለመታደግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡ ደም ሲለግሱ ካገኘናቸው ነዋሪዎች መካከል ፓስተር መኮንን እንኮሳ እንዳሉት በተለያዩ ምክንያቶች ለተጎዱ ዜጎች ደም መስጠት በሃይማኖታዊ አስተምህሮም ቢሆን የሚደገፍ በመሆኑ ደምል ለመለገስ መምጣታቸውን ገልጸዋል። የጀመሩትን የደም ልገሳ ወደፊትም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው በደም እጦት ምክንያት በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ሞት ለመታደግ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክተዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኩዊች ዊው በሰጡት አስተያየት በክልሉ በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰተውን ሞት ለመከላከል ደም በመለገሳቸው የድርሻቸውን በመወጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በክልሉ የሚገኙ የአመራር አካላት ህብረተሰቡን ከማወያየት ባለፈ ደም በመለገስ ለሌሎች ምሳሌ ለመሆን መስራት አለብን ብለዋል። የኑዌር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሉዋል ዶስ በበኩላቸው በዞኑ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የሚደርስባቸው ዜጎች በደም እጥረት ምክንያት ለሞት የሚጋለጡበት ሁኔታ መኖሩን ጠቅሰው ይህንን ለመታደግ የሚለግሱትን ደም በማጠናከር የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። ራሳቸው ደም ከመለገስ ባለፈ ሌሎች እንዲለግሱ ግንዛቤ ለማሳደግና ለማስተማር ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ደም መለገስ የሌሎችን ሕይወት ከመታደግ ባለፈ ለራስ ጤንነት አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ከፑኝዶ ሆስፒታል የመጡት ዶክተር አብዱር አዛክ ናቸው፡፡ ለ12ኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውን የተናገሩት ዶክተሩ በእዚህም ምንም የጤና ችግር እንዳልገጠማቸውና ደም መለገስ ለታማሚውም ጭምር ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም የጀመሩትን የደም ልገሳ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የገለጹት። የጋምቤላ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜድካል ዳይሬክተር ተወካይ ዶክተር ኡማን ኡጉድ በበኩላቸው በሆስፒታሉ ያለው የደም አቅርቦት ቀደም ሲል ከነበረው እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም የሆስፒታሉን የደም ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማሟላት ከክልሉ ደም ባንክ ጋር ያላቸውን ቅንጅታዊ ሥራ በማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ደም ባንክ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኡጁሉ ኡጋላ በበኩላቸው በደም እጦት ምክንያት የሚከሰተውን የዜጎች ሞት ለመታደግ ዘንድሮ 1ሺህ 500 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ቢታቀድም እስካሁን ማሳካት የተቻለው 350 ዩኒት ደም ብቻ ነው። በክልሉ ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር በእቅዱ መሰረት ደም ለመሰብሰብ እንቅፋት መሆኑንም ገልጸው፣ የተሰበሰበው ደም ለጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል መላኩን አስረድተዋል። የደም ለጋሾችን ቁጥር ለማሳደግ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በመስራት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ የሚሰበሰበውን የደም መጠን ለማሳደግ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ህዝባዊ መድረኮች ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሰራቱን ገልጸው፣ በቀጣይ በጋምቤላ ጠቅላላ ሆስፒታል በተለያዩ መድረኮች ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ እንደሚጠናከር ገልጸዋል። ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራረን በማስፋት የሆስፒታሉን የደም ፋላጎት ለማሟላት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
372
የደም መለገስ ባህል ህብረተሰቡ እንዲያዳብር ጥሪ ቀረበ 72 Share ጋምቤላ ጥር 21/2011 ኅብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን እንዲያጎለብት የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጠየቁ። ”በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት በጋራ እንከላከል!’‘ በሚል መሪ ቃል ትናንት በጋምቤላ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። ምከትል ርዕሰ መሰተዳድሩ አቶ ተንኳይ ጆክ በዚሁ ወቅት የእናቶችን የጤና አገልገሎት በማሻሻል ውጤታማ ተግባራት ቢከናወኑም፤ከወሊድ ጋር በተያያዘ በሚከሰተው የደም መፍሰስ ችግር እናቶች ተጎጂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በደም መፍሰስ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችን ሞት ለመቀነስ ደም የመለገስ ባህል እንዲጠናከር ጠይቀዋል። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኡማን አሙሉ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የምዕተ ዓመቱ የጤና ልማት መርሃ ግብር የእናቶችን የጤና አገልገሎት በማሻሻል ረገድ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የእናቶች የጤና አገልገሎት በተፈለገው ደረጃ አለመሟላቱን ጠቁመዋል። የእናቶች ሞት ከቤተሰብ አልፎ በኅብረተሰቡና በአገር ላይ የሚያስከትለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የከፋ ነው ያሉት ኃላፊው፡ ለእናቶች ጤና መሻሻል የአመራሩና የህዝቡ አጋርነት እንዲጠናከር ጠይቀዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ዶክተር ሎው ኡቡፕ በሰጡት አስተያየት ለእናቶች ጤና አገልግሎት የተመደቡ አምቡላንሶችን ለታለመላቸው ዓለማ በማዋል ረገድ የሚታዩ ችግሮች መታረም አለባቸው ብለዋል። በደም መፍሰስ ምክንያት የሚገጥመውን ችግር ለማቃለል ወደ መቱ ሆስፒታል የሚላኩ እናቶች ለእንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። የእናቶችን የጤና አገልገሎት ለማሻሸል በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። በወሊድና በቅድመ ወሊድ ወቅት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማቱ የሚሄዱ እናቶች በአግባቡ እንደማይስተናገዱ የገለጹት ሌላዋ የውይይቱ ተሳታፊ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ ናቸው። በባለሙያዎች ስነ ምግባር ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር መጠናከር እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዋ ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልል፣የዞን፣የወረዳ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ባለድርሻ አካላት ደም ለግሰዋል። በኢትዮጵያ የጥር ወር የጤናማ እናትነት ወር በሚል በተለይ ለወላዶች ጤና ትኩረት ይሰጥበታል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
373
በ6 ወራት ውስጥ ከ106 ሺህ ዩኒት በላይ ደም መሰብሰቡን የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ Thu, Jan 24, 2019ዋልታ ጤና ባለፉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ከ106 ሺህ በላይ ዩኒት ደም በአገር አቀፍ ደረጃ መሰብስቡን የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ የደም ባንክ አገልግሎቱ በየወቅቱ የሚገጥመውን የደም እጥረት መፍታት የሚያስችሉና በደም ልገሳ ማዕከላትና በደም መለገሻ ተሽከርካሪዎች የታገዘ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የደም ልገሳ ከተጀመረበት ከ1962 ዓ.ም ጀምሮ በሰብዓዊነት የሌሎችን ህይወት ለመታደግ የደም ልገሳን በቋሚነት የሚያደርጉ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ደም የማይለግሱ ሰዎች ቁጥርም ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡ በዚህም አሁን ላይ እየተሰጠ ያለው የደም መጠን ከአገልግሎት ፈላጊዎች ቁጥር አንጻር ሲታይ አነስተኛ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ደም መለገስ የሚሹ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ገልጿል፡፡ የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ዋና ዳሬክተር ዶክተር ሄለና ኃይሉ በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ጊዜ ወስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ106 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ተሰብስቧል ብለዋል። እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ በጥር ወር በመንግስትና በግል ተቋማት የሚገኙ ስራተኞች በፍቃደኝነት የደም ልገሳ እያደረጉ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ በበጎ ፍቃደኝነት ደም ለመለገስ የሚመጡ ስዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ ህብረተሰቡ ደም በመለገስ የሰዎችን ህይወት እንዲታደግም ጥሪ አቅርበዋል፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
374
ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ የደም ልገሳን ባህል ማድረግ ያስፈልጋል– የጤና ሚኒስቴር 84 Share አዲስ አበባ ጥር 13/2011 ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ የደም ልገሳን ባህል ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ”በደም መፍሰስ የሚደርሰውን የእናቶች ሞት በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ሃሳብ ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረው የእናቶች ወር በተለያየ መልኩ እየተከበረ ነው። የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች ወሩን በማስመልከት ዛሬ የደም ልገሳ አድርገዋል። ከሰራተኞች ጋር በመገኘት ደም የለገሱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰሃርላ አብዱላሂ እንደገለጹት፤ በደም እጦት ምክንያት ብዙ ወላድ እናቶች ህይወታቸውን ያጣሉ። የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ህብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታዋ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች አረአያ እንዲሆኑ በዘመቻ የደም መለገሳቸውን ተናግረዋል። በደም ልገሳው የተሳተፉት የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው፤ የእናቶችንና የህጻናትን ህይወት ለመታደግ እንዲሁም ሞት ለመቀነስ የደም ልገሳ እየተደረገ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ይገልጻሉ። በመሆኑም የበጎ ፍቃድ ደም ለጋሽ ቁጥር እየጨመረ እንዲሄድና የደም አቅርቦት ችግር እንዳይኖር ክልሎችና ሆስፒታሎች በተቀናጀ መልኩ ተቀራርበውና ህብረተሰቡን አስተባብረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ የሚሰማኝ ደስታ ብዙ ነው ደሙም የሚተካ ነው ወሩም የእናትነት ስለሆነም እናቶች ወይ ደም በመፍሰስ ምክንያት ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ እነዛን እናቶች ለመታደግ በጣም ደስታ ነው የሚሰማኝ ደም በመለገስ በኩል ትንሽ ግንዛቤው እየተስተካከለ መጥቷል በተለየ የእናቶችንና የህጻናትን ህይወት ለመታደግ፤ ሞት ለመቀነስ ደም በመለገስ በየወቅቱ የተለያዩ ስራዎች አየተሰሩ ነው ማለት ይቻላል ግን እንዳጠቃላይ ስናይ በቂ አይደለም ደም በፈቃደኝነት መለገስ አለበት ብለዋል፡፡ የሚኒስቴሩ የበጎ አድራጎት ማህበር አስተባባሪ አቶ ያዕቆብ ወንዲይራድ ደም ልገሳ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል የሚሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጀምሮ ሁሉም በየደረጃው በዓመት ውስጥ ሶስትና አራት ጊዜ ደም እንዲለግሱ ለማድረግ ሚኒስቴሩ እንደሚሰራ ገልጸው እናቶችን ከአደጋ የመጠበቅ ሃላፊነት የሁሉም እንደሆነ ተናግረዋል። ደም በመለገሳቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት የሚኒስቴሩ የሪፎርምና መልካም አስተዳዳር ዳሬክተር አቶ አሰፋ አይዴ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አካባቢዎች የደም እጥረት በመኖሩ በበጎ ፈቃደኝነት ደም የመለገስ ባህሉን ለማሳደግ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በቤት ውስጥ የሚወልዱና በተለያዩ የመዘግየት ምክንያቶች ወደ ጤና ተቋም የማይሄዱ እናቶች ቁጥር 72 በመቶ የሚደርስ ሲሆን በየዓመቱ ከ100ሺ እናቶች መካከል 412 የሚሆኑት የወለዷቸውን ልጆች ሳያዩ እንደሚያሸልቡ ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
375
በፍቼ ከተማ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና የሕክምና ባለሙያዎች ደም ለገሱ 541 Share ፍቼ ጥቅምት 17/2011 በፍቼ ከተማ 210 በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና የሕክምና ባለሙያዎች ለፍቼ ከተማ ሪፈራል ሆስፒታል ደም ለገሱ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አውራሪስ ታዬ እንደገለጹት “ጤናማ ደም ከጤናማ ሰው ይገኛል” በሚል መርህ በሆስፒታሉ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተዘጋጅቷል። በመርሀ ግብሩም 21ዐ የከተማዋ ወጣቶች፣ ሴቶችና የሆስፒታሉ ማህብረሰብ ደም በመለገስ ተሳትፈዋል። ከደም ለጋሾቹ የተገኘው ደም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የጤና ጉዳት ለደረሰባቸው እናቶችና ሌሎች ወገኖች እንደሚውልም ጠቁመዋል። በከተማዋ ወጣቶችና በሆስፒታሉ ሠራተኞች የተጀመረው የደም ልገሳ በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሆስፒታሉ የቅስቀሳና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ደም ከለገሱ ወጣቶች መካከል ከአስር ጊዜ በላይ ደም የለገሱ እንደሚገኙበት አመልክተው ደም መለገስ ለጤናማ ሰው ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለውና የሌሎችን ሕይወት በማትረፍ ውስጣዊ እርካታ እንደሚያስገኝ ገልጸዋል፡፡ በደም ልገሳው ከተሳተፉት መካከል ወጣት ፍሬሕይወት ግዛው በበኩሏ በደም እጥረት እየተቸገሩ ያሉ ወገኖችን ሕይወት ለመታደግ ተነሳስታ ደም መለገሷን ትናገራለች። የፍቼ ከተማ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት አሸብር ኦልጂራ በበኩሉ የደም ለጋሾች ማህበር ለመመስረትና የተጐዱ ወገኖችን በልዩ ሁኔታ ለመርዳት የሚያስችል ኮሚቴ አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጾ የደም ልገሳውም የእዚሁ አካል መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለአምስት ቀናት የተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ትናንት ሲጠናቀቅ ለተሳታፊዎቹ በመጀመሪያ የሕክምና እርዳታና በተላላፊ በሽታዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
376
ዜጎች ደም በመለገስ ችግር ወስጥ የወደቁ ወገኖችን ሕይወት እንዲያተርፉ ሚኒስትሩ ጠየቁ 830 Share መቀሌ ጥቅምት 15/2011 ዜጎች ደም በመለገስ ችግር ወስጥ የወደቁ ወገኖችን ሕይወት እንዲያተርፉ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አሚን ዛሬ ጠየቁ። ሚኒስትሩ በመቀሌ ከተማ ደም ለግሰዋል። ዶክተር አሚር በከተማው እየተካሄደ ካለው 20ኛው አገር አቀፍ የጤና ልማት ጉባዔ በተጓዳኝ ደም ለግሰዋል፡፡ በዚሁ ወቅት እንዳስገነዘቡት ዜጎች በደም እጥረት የሚቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት ደም ልገሳ መለገስ ይጠበቅባቸዋል። በርካታ ዜጎች በደም እጥረት ምክንያት የቀዶ ጥገና ህክምና እንዲራዘም ከማድረግ ባለፈ ውድ ህይወታቸውን እያጡ ያሉት ማጣታቸውንመር አስረድተዋል፡፡ በአገሪቱ ደም ልገሳ ባህል እንዲሆን በየደረጃው የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የማያቋርጥ ቅስቀሳና የግንዛቤ ማሳደጊያ ትምህርት መስጠት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ዶክተር አሚር። በኢትዮጵያ ለ70 ጊዜ ደም በመለገስ የሚታወቁትና የብሄራዊ ደም ባንክ የቅስቀሳ ክፍል አባል ሲስተር አሰጋች ጎሳ ሰብዓዊነት ከሚገለፅባቸው በጎ ተግባራት መካከል አንዱና ዋናው ደም ለተቸገረ ዜጋ መስጠት መሆኑን ገልጸዋል። ”ለእያንዳንዱ ዜጋ ደም መለገስ አንድ ጠብታ ነው።የደም እጥረት ላጋጠመው ግን ዘለዓለማዊ ህይወት ማስቀጠል መሆኑ ሳንዘነጋ ደም መለገስ ይገባናል” ብለዋል። ለጉባዔው ከአዲስ አበባ የመጡት ወይዘሮ ሙሉ ወንድራድ ለ49ኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውን ይናገራሉ። ”በትክክል ለሚገነዘበው ሰው ደም መስጠት ጤና ነው።ደም መስጠት የህሊና እርካታ ነው።ስለዚህ በየአካባቢው በሚገኙ የደም ባንኮች በመሄድ ደም መስጠት አለብን” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የመቀሌ የደም ባንክ ማዕከል ባለሙያ አቶ መኮንን አስፍሃ የጉባዔው ተሳታፊዎች እስከ እኩለ ቀን ድረስ ሚኒስትሩን ጨምሮ 26 የሚሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና ባለሙያዎች ደም መለገሳቸውን አስታውቀዋል። ማእከሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከ13ሺህ የደም ከረጢት በላይ ለመሰብሰብ እቅድ የያዘ ሲሆን፣እስካሁን ከሁለት ሺህ በላይ የደም ከረጢት መሰብሰቡን ገልጸዋል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
377
በትግራይ ክልል የበጎ ፍቃድ ደም ልገሳ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ 1484 Share መቀሌ ሀምሌ 8/2010 በትግራይ ክልል በደም እጦት ምክንያት ለሞት አደጋ የሚጋለጡ ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ሕብረተሰቡ የጀመረውን የበጎ ፍቃድ ደም ልገሳ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ። በክልሉ የመቀሌ የደም ባንክ ማስተባበሪያ ማዕከል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሊሰበሰብ ካቀደው 11 ሺህ የደም ከረጢት ውስጥ መሰብሰብ የቻለው 9 ሺህ 400 ኪረጢት ብቻ መሆኑ ተመልክቷል። የደም ባንኩ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ ፍሰሃ ብርሃነ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት በተጠናቀቀው የ2010 በጀት ዓመት ማስተባበሪያው ከተለያዩ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች 11ሺህ ከረጢት ደም ለመሰብሰብ ካቀደው በ1 ሺህ 600 የደም ከረጢት ያነሰ ደም መሰብሰቡን ተናግረዋል። “በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ ደም ለጋሾች ከተሰበሰበው ደም ውስጥ 8 ሺህ ኪረጢት ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖችን በመስጠት ሕይወታቸውን መታደግ ተችሏል” ብለዋል። የመቀሌ የደም ባንክ ማስተባበሪያ 28 ወረዳዎችና 24 ሆስፒታሎችን እንደሚፈሽን የገለጹት ዳይሬክተሩ ለሕሙማን የሚለገሰው የደም መጠን ከፍላጎት ጋር ሲነጻጸር ብዙ እንደሚለያይ ተናግረዋል። ሕብረተሰቡ ደም መለገስ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለውና ደም መለገስ የበርካታ ወገኖችን ሕይወት ከሞት እንደሚታደግ አውቆ የጀመረውን የደም ልገሳ አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ፍስሃ ጥሪ አቅርበዋል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
378
‹‹ደም ያስተሳስረናል፤ አባቶች ሀገር ያቆዩን ደም አፍስሰው አጥንት ከስክሰው ነው፡፡ እኛም ደም በመለገስ ወገናችንን እንታደግ፡፡›› የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 06/2011ዓ.ም (አብመድ) ‹‹ደም ያስተሳስረናል፤ ደም በመለገስ የወገናችን ሕይወት እናትርፍ›› በሚል መሪ ሐሳብ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከባሕር ዳር የደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ሥነ-ሥርዓት እያከናወነ ነው፡፡ የአብን ከፍተኛ አመራሮች እና ደጋፊዎቻቸው በባሕር ዳር ከተማ ደም እየለገሱ ነው፡፡ በደም ልገሰው ከተገኙ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች መካከል ወጣት ሱራፌል ቢኒያም ‹‹ደም መለገስ ክቡር ሕይወት ማትረፍ በመሆኑ ያስደስታል፡፡ እኔ ጤነኛ ሆኜ ለሌሎች ጤና እና ሕይወት መስጠት ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ ወደፊትም ደም በመለገስ ወገኔን እታደጋለሁ›› ብሏል፡፡ ሌላኛው ደም ለጋሽ ሙሐመድ አልናስር ደም በመለገሱ ደስተኛ እንደሆነ ገልጾ ወደፊትም በየሦስት ወር ልዩነት ደም እንደሚለግስ ተናግሯል፡፡ ወጣቱ ደም በመለገስ እናቶችን እና ሕጻናትን ከሞት እንዲታደግም ጥሪ አቅርቧል፡፡ በደም ልገሳ ሥነ ሥርዓቱ የንቅናቄው ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔን ጨምሮ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ሌሎችም የንቅናቄው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ደም ለግሰዋል፡፡ በደም ልገሳው ወቅት የአብን ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ‹‹አብን ሕዝባችን ከፖለቲካ ውጭ በሚፈልገው ማንኛውም ማኅበራዊ ጉዳይ ላይ በመሳተፍ ኃላፊነታችን ለመወጣት ነው፤ ደም በመለገስ ተግባር የተሰማራነው›› ብለዋል፡፡ ከዚህ ከደም የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ እና የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የልደት በዓልን ምክንያት በመድረግ የደም ልገሳ ሥነ-ሥርዓት ላይ ደም እንደለገሱ ያስታወሱት ዶክተር ደሳለኝ ‹‹ወደፊትም ንቅናቄው ከደጋፊዎቹ ጋር ደም በመለገስ በበጎ ተግባሩ ይቀጥላል›› ነው ያሉት፡፡ ደም መለገስ የሰብዓዊነት ጉዳይ መሆኑን ያስታወቁት ዶክተር ደሳለኝ ሁሉም ሰው ደም በመለገስ የወገኑን ሕይወት መታደግ እንደሚገባውም ጥሪ አስተላፈዋል፡፡ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ደግሞ ‹‹ደም ስንለግስ ሕይወት እያተረፍን ነው፡፡ እኔ ደም በመለገሴ አንዲት ነብስ እንዳተረፍኩ ይሰማኛል፡፡ ደም በመለገስ ሕይወት ማትረፍ ይቻላል እንጂ በራስ ላይ ችግር አያመጣም፡፡ በመሆኑም ሁሉም ዜጋ ደም በመለገስ የወገኑን ክቡር ሕይወት ማትረፍ መቻል አለበት፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹አባቶች ሀገር ያቆዩን ደም አፍስሰው አጥንት ከስክሰው ነው፡፡ እኛም ደም በመለገስ ወገናችንን እንታደግ›› ሲሉም አቶ ክርስቲያን ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ደም ለመለገስ ብሔር፣ ሃይማኖት … የሚባሉ ፍረጃዎች እንደማያስፈልጉ ያስረዱት አቶ ክርስቲያን ደም ለመለገስ ሰብዓዊነት በቂ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ ‹‹ደም መለገስ በሰውም በፈጣሪም ዘንድ ጥሩ ተግባር በመሆኑ ደም በመለገስ የወገናችንን ሕይወት እንታደግ›› ሲሉ ነው ጥሪ ያስተላለፈው፡፡ የባሕር ዳር ከተማ የደም ባንክ አገልግሎት ኃለፊና የማኅበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት ምክሩ ሽፈራው ‹‹ከተማውም ሆነ ክልሉ አስፈላጊው የደም አቅርቦት የላቸውም›› ብለዋል፡፡ ለአማራ ክልል በዓመት 200 ሺህ የደም ከረጢት እንደሚያስፈልገው የገለጹት ኃላፊው አሁን ላይ ያለው 35 ሺህ ከረጢት ብቻ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ የሚለገሰው ደም የሚሰጠው አገልግሎት በርካታ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው ‹‹የቀይ የደም ሕዋስ እጥረት ላለባቸው፣ የኩላሊት እጥበት ለሚያስፈልጋቸው፣ ለወላድ እናቶች፣ ለድንገተኛ አደጋ በተለይም ለመኪና አደጋ እና ቀዶ ጥገና ለሚያደርጉ ዜጎች ይውላል›› ነው ያሉት፡፡ ደም ከሌለ ቀዶ ጥገና እንደሚዘገይ፤ ሕሙማንም መዳን በሚገባቸው ጊዜ ሳይድኑ እንደሚቀሩ አስድተዋል፡፡ አሁን ባለው አገልግሎት ለእናቶች ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሠሩ የተናገሩት ኃላፊው ካለው ደም 25 በመቶ ለእናቶች፣ 25 በመቶው የቀይ ደም ሕዋስ እጥረት ላለባቸው፣17 በመቶ ለመኪና አደጋ ተጎጂዎች፣19 በመቶ ለአጠቃላይ ቀዶ ሕክምና እና የቀረው ለሌሎች የሕክምና አግልግሎቶች እንደሚውልም ኃለፊው አስታውቀዋል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከባሕር ዳር ከተማ የደም ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባር ባዘጋጀው የደም ልገሳ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ሚያዚያ 6 ቀን 2011ዓ.ም ከጧት ጀምሮ እስከ ምሽት 12 ሰዓት ይዘልቃል፡፡ ከበጎ ፈቃደኞችም ከ400 እስከ 600 የደም ከረጢት ደም እንደሚገኝ ይጠበቃል፡፡ የታቀደው የደም ቁጥር ከተገኘም በባሕር ዳር ከተማ የደም ባንክ ስር ለሚተዳደሩ እስከ ቻግኒ ለሚደርሱ በርካታ ሆስፒታሎች ለ15 ቀን አገልግሎት እንደሚሆንም ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
379
የትዴፓ አመራርና አባላት የህወሓት 45ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ደም ለገሱ Wed, Feb 19, 2020ዋልታ የሀገር ዉስጥ ዜና የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ትዴፓ) ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ትግል የጀመረበትን 45ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አመራርና አባላቱ ደም ለገሱ። የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ደም ባንክ ተገኝተው ደም ለግሰዋል። የፓርቲው አመራርና አባላት ደም የለገሱት "ለአንድነት፣ ፍትህና እኩልነት ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉ ታጋዮችን" ለማሰብ መሆኑ ታውቋል። አጋጣሚውን በመጠቀም ወላድ እናቶችና አደጋ የደረሰባቸው ዜጎች በሚለገስላቸው ደም ህይወታቸው እንዲተርፍ የራሳቸውን አስተዋፆ ለማድረግ መሆኑንም ዶክተር አረጋዊ ተናግረዋል። "እለቱን በተለየ ፌሽታና ጭፈራ ማክበሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል" ያሉት ዶክተር አረጋዊ "በጎ ተግባር በመፈፀም ማክበሩ ከውስጣዊ እርካታ ባሻገር ለወገን አለኝታነትን ማሳያ ነው" ብለዋል፡፡ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚና ዋና ጸሐፊ አቶ ጊዶና መድህን በበኩላቸው መሪዎቻችን ከ45 ዓመታት በፊት ለሰላም፣ ለዴሞክራሲና ለልማት የከፈሉትን መስዋእትነት ለማስታወስና ደም ለሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች አጋርነትን ለማሳየት የደም ልገሳው መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡ "ደም አናፈስም ደም እንሰጣለን" በሚል አላማ መንቀሳቀሳቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ፓርቲው ከትግራይም ሆነ አጠቃላይ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን የተሰለፈ መሆኑን ለማሳየትም የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተደረገው የደም ልገሳ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከ30 በላይ አባላቱ የተሳተፉ ሲሆን ሌሎች አባላትና ደጋፊዎቻቸውም በያሉበት ተመሳሳይ ተግባር መፈፀማቸው ታውቋል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
380
በጎ ፈቃደኛ የለገሱት ደም ሕይወታችንን ታድጎልናል”-የባህር ዳር ወላድ እናቶች ባህር ዳር የካቲት 1/2011 በጎ ፈቃደኛ የለገሱት ደም ህይወታቸውን እንደታደገላቸው በባህርዳር ከተማ ፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና የሚከታተሉ ወላድ እናቶች ተናገሩ። በአማራ ክልል በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት ከበጎ ፈቃደኞች ከ22 ሺህ 500 በላይ ዩኒት ደም ተሰብስቧል። በሆስፒታሉ ሕክምናቸውን በመከታተል የሚገኙ እናቶች ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በበጎ ፈቃደኞች የተለገሰው ደም ተጋርጦባቸው ከቆየው አደጋ በማውጣት ሕይወታቸውን አትርፎላቸዋል። በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ሕይወትን ለመታደግ የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። ከምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ የመጡት ወይዘሮ ጥሩ አበጀ በወሊድ ምክንያት አጋጥሟቸው በነበረ የደም መፍሰስ ለአደጋ ተጋልጠው እንደነበር አስታውሰው፣በጎ ፈቃደኞች በለገሷቸው ደም ከሕመማቸው እንዳገገሙ ተናግረዋል። ከምስራቅ ጎጃም ዞን የቢቸና ወረዳ ወይዘሮ አሞኘች ሀብቴ በበኩላቸው አጋጥሟቸው በነበረው የደም እጥረት ተቸግረው እንደነበርና በተሰጣቸው አምስት ዩኒት ደም ሕይወታቸውን መትረፉን ገልጸዋል። “በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች የለገሱትን ደም ባላገኝ ኖሮ፤ አሁን በሕይወት አልገኝም ነበር” ብለዋል። በፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አዋላጅ ነርስ ጌታነህ አጥናፉ በሆስፒታሉ በደም እጥረት ምክንያት የወላድ እናቶችና ህፃናት ሕይወት ያልፍ እንደነበር አስታውሰው፣በአሁኑ ወቅት የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር በመጨመሩ ችግሩ መወገዱን ተናግረዋል። ኑሮውን በደብረ ማርቆስ ከተማ ያደረገውና የቴክኒክና ሙያ ተማሪው ነቢዩ ዳንኤል ደም መለገስ ከጀመረ ሶስት ዓመታት እንዳስቆጠረ ተናግሯል። ለዘጠኝ ጊዜ ደም መለገሱን ያስረዳው ወጣቱ ሌሎችም ደም በመለገስ በአደጋና በወሊድ ወቅት ደም የሚፈሳቸውን ወገኖች ሕይወት እንዲታደጉ ጠይቋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪው መጋቤ ኩራልኝ ሞገስ በበኩላቸው “በምለግሰው ደም ክቡር የሆነውን የሰው ህይወት ከማትረፍ የበለጠ የሚያስደስተኝ ነገር የለም” ብሏል። የቅርብ ጓደኛቸው ባለቤት ታመው በሰጡት ደም ህይወታቸው መትረፉን የገለጹት አስተያየት ሰጪው፣ እስካሁን ለ20 ጊዜ ደም መለገሳቸውን ተናግረዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የደም ባንክ አስተባባሪ አቶ አንዳርጌ አጥናፉ በተጠናቀቀው ግማሽ በጀት ዓመት ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ከ22 ሺህ 500 በላይ ዩኒት ደም መሰብሰቡን አስታውቀዋል። ከተሰበሰበው ደም ውስጥ 21 ሺህ 132 ዩኒት ደም ለመንግሥትና ለግል ጤና ተቋማት ተሰራጭቶ ጥቅም ላይ መዋሉን አስረድተዋል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጥቅም ላይ ከዋለው ደም ጋር ሲነፃፀር በ2 ሺህ 618 ዩኒት ደም ብልጫ እንዳለው አመልክተዋል። የተሰበሰበው ደም በወሊድ ምክንያት ደም ለፈሰሳቸው እናቶች፣ የመኪና አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖችና ሌሎች የደም እጥረት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ጥቅም ውሏል ብለዋል። የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር መጨመር ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ እንዳስቻለ አስተባባሪው አስረድተዋል። ከለጋሾች የሚሰበሰበው ደህንነቱ የተጠበቀ ደም ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ዘጠኝ የደም ባንኮች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
381
ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት 106 ሺህ ከረጢት ደም መሰብሰቡን አስታወቀ Thu, Feb 14, 2019ዋልታ ጤና ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት በአገር አቀፍ ደረጃ 106 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች መሰብሰቡን አስታወቀ። በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 38 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች በማግኘት የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካት ችሏል። የዕቅድ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11 ሺህ ከረጢት ደም ብልጫ አለው ተብሏል። የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ሄለን ኃይሉ እንዳሉት የኀብረተሰቡ በፈቃደኝነት ደም የመለገስ ልምድ እያደገ በመምጣቱ በግማሽ ዓመት 90 በመቶ የዕቅድ አፈጻጸም ማሳካት ተችሏል። በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፈቃደኝነት የደም ልገሳ ካደረጉ በኋላ የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች ቁጥር እንደጨመረም ገልጸዋል። አንድ ሰው የሚለግሰው ደም የሦስት ሰዎችን ህይወት ማዳን እንደሚቻል የገለጹት ዶክተር ሄለን ኀብረተሰቡ ደም መለገስን ባህል ሊያደርገው ይገባልም ነው ያሉት። እንደ ዶክተር ሄለን ገለጻ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 65 ዓመት ድረስ ያሉ ሰዎች ደም ቢለግሱ የዜጎችን ህይወት ከመታደግ ባሻገር ለራሳቸውም ጤንነት ጠቃሚ ነው። አንድ ሰው ደም በሚለግስበት ወቅት አሮጌው የደም ህዋስ በአዲስ የሚተካ በመሆኑ ከደም ጋር በተያያዘ ከሚፈጠር ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት መዳን እንደሚቻልም አስረድተዋል። ጄ ኤስ አይ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በአጋርነት መስራት የጀመረበትን 25ኛ ዓመትም ደም በመለገስ አክብሯል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
382
የደም ልገሳን ባሕል ለማድረግ ከዘመቻ ሥራ መውጣት እንደሚገባ አቶ ዮሐንስ ቧያለው አሳሰቡ፡፡ ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 15/2012 ዓ.ም (አብመድ) ደም በመለገስ በደም መፍሰስ ችግር ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችን መታደግ እንደሚገባ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ምክትል ሊቀ መንበርና የማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው አሳሰቡ፡፡ አንድ ሰው ካለው አጠቃላይ ደም እስከ 10 በመቶ ቢለግስ በጤናው ላይ ችግር እንደማያስከትልበት ደግሞ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ የአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር እና የማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው እንደተናገሩት ደም በመለገስ በተለያዩ አደጋዎች ደም በመፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን መታደግ ይገባል፡፡ ‹‹በግንዛቤ እጥረት ችግር ካልሆነ በስተቀር ማኅበረሰቡ ሁሉን ነገሩን የሚሰስት አይደለም›› ያሉት አቶ ዮሐንስ በደም ልገሳ የሚታየውን የግንዛቤ ችግር ለመቅረፍም ከጤና ተቋማት ባለፈ በማንኛውም ቦታ በኃላፊነት የሚገኝ ሁሉ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የግንዛቤ ችግሩን ለመቀረፍ ተከታታይነት ያለው ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግም ነው አቶ ዮሐንስ ቧያለው ያስገነዘቡት፡፡ ‹‹የደም ልገሳን ባሕል ለማድረግ ከዘመቻ ሥራ ወጥቶ በመደበኛነት በትኩረት መሠራት አለበት›› ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡ የደም ልገሳን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ከሌሎች ተግባራት ጋር በመደበኛነት አቀኛጅቶ መሥራት እንዳለበትም ነው አቶ ዮሐንስ ያሳሰቡት፡፡ በክልሉ በደም ባንክ ማዕከላት እና በዘመቻ ደም እንደሚሰበሰብ የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል፡፡ በቢሮው የድንገተኛ የፅኑ ሕሙማን እና የደም ባንክ አገልግሎት ኬዝቲም አስተባባሪ አቶ አንዳርጌ አጥናፍ እንደተናገሩት ፈቃደኛ ደም ለጋሾች በየሦስት ወሩ በደም ባንኮች እንዲለግሱ ቢፈለግም በማዕከላቱ የሚሰበሰበው ደም 10 ከመቶ አይሞላም፡፡ የማኅበረሰቡ ግንዛቤ ውስን በመሆኑ 90 በመቶ የሚሆነው ደም የሚሰበሰበው በዘመቻ መሆኑንም ነው አስተባባሪው የገለጹት፡፡ ‹‹ደም ከበጎ ፈቃደኞች በአራቱ ደም ተህዋስያን አማካኝነት ከሚተላለፉ በሽታዎች ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ተረጋግጦ ይሰበሰባል፡፡ የተሰበሰበውም ያለምንም ብክነት ለሕይወት አድን ተግባር ይውላል›› ብለዋል አቶ አንዳርጌ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት መስፈርትን ጠቅሰው እንዳብራሩትም በአንድ ሀገር ወይም ክልል ከሚኖረው ሕዝብ ከ1 እስከ 3 በመቶ የሚሆው ደም መለገስ ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም መሠረት ከአማራ ክልል ሕዝብ ከ200 ሺህ አስከ 600 ሺህ ዩኒት ደም መሰብሰብ እንደሚቻል አመልክተዋል፡፡ ይሆን እንጅ የማኅበረሰቡ የደም ልገሳ ባሕል ዝቅተኛ በመሆኑ በሩብ ዓመቱ በክልሉ 10 ሺህ 509 ዩኒት ደም ብቻ ነው መሰብሰብ የተቻለው፡፡ ማንኛውም ጤነኛ የሆነ በጎ ፈቃደኛ ሰው ካለው አጠቃላይ ደም እስከ 10 በመቶ ቢለግስ በጤናው ላይ የሚያመጣበት ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለም ነው አቶ አንዳርጌ የተናገሩት፡፡ በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት የደም ፍላጎታቸውን በአራቱ የደም ዓይነቶች በየጉድኝታቸው (በየክላስተራቸው) ለሚገኙ 10 የደም ባንኮች እንደሚያቀርቡና የተሰበሰበው ደም በፍትሐዊነት እንደሚሠራጭም አቶ አንዳርጌ አመልክተዋል፡፡ በክልሉ በመኪና አደጋ፣ በወሊድ፣ በኩላሊት እጥበት፣ በካንሰር፣ በቀዶ ጥገና፣ በደም ማነስ እና በመሳሰሉት በሽታዎች ምክንያት ደም የሚፈሳቸውን ወገኖች ሕይወት ለመታደግ ማኅበረሰቡ ደም መለገስ እንዳለበትም አቶ አንዳርጌ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ‹‹ሕይወት ለሕይወት፤ ደም ለግሰን ሕይወት እናድን›› በሚል መሪ ሐሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር ከ10 ሺህ ዩኒት በላይ ደም፣ በአማራ ክልል ደግሞ 3 ሺህ 748 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
383
በለገሱት ደም በትንሹ የ86 ሰዎችን ህይወት ያተረፉት ጀግና ማን ናቸው? ‹‹ደም ለግሰን በደም መፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን መታደግ ትልቅ የሰብዓዊነት ጥግ ነው፡፡›› ለ86ኛ ጊዜ ደም የሚለግሱት ግለሰብ ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 15/2012 ዓ.ም (አብመድ) ነዋሪነታቸው በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ነው፡፡ የሚተዳደሩት ደግሞ በግል ሥራ ነው፡፡ ከ26 ዓመት በፊት ነበር ደም መለገስ የጀመሩት፡፡ አሁን ላይ ደግሞ በኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ደም ለጋሾች ማኅበር መሥራች እና የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ናቸው፤ አቶ ሙሉጌታ ይርጋ፡፡ አቶ ሙሉጌታ ደም መለገስ የጀመሩት በ1985 ዓ.ም ነው፤ ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ ቀንም ለ86ኛ ጊዜ ደም እንደሚለግሱ ነግረውናል፡፡ አቶ ሙሉጌታ ደም ለመለገስ መነሻ የሆናቸው አንድ ግለሰብ በክረምት ወራት የውኃ ማፋሰሻ ቱቦ ውስጥ ወድቆ ጉዳት ደርሶበት በማየታቸውና ግለሰቡን ለመታደግ ከቤታቸው ደርሰው ሲመለሱ ሕይወቱ አልፎ ማግኘታቸው ነው፡፡ የግለሰቡን ሕይወት ማትረፍ ባለመቻላቸውም ‹‹በራሴ እጅ እንደጠፋች አድርጌ ነው የማየው›› ብለዋል በፀፀት ስለሁኔታው ሲናገሩ፡፡ በወቅቱ ደሴ ላይ ቀይ መስቀል ስለነበር በራሳቸው ተነሳሽነት ከኮምቦልቻ ደሴ 23 ኪሎ ሜትር በመመላለስ ደም መለገስ እንጀመሩ ነው አቶ ሙሉጌታ የተናገሩት፡፡ ደም በመለገሳቸውም የደረሰባቸው ችግር እንደሌለ አመልክተዋል፡፡ ‹‹በሚሊዮን የሚቆጠሩ የደም ሕዋሳት ይሞታሉ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ይተካሉ፡፡ የደም ሕዋሳት ያለምንም ጥቅም ከሚሞቱ ደም ለግሰን በደም መፍሰስ ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን መታደግ ትልቅ የሰብዓዊነት ጥግ ነው›› ብለዋል አቶ ሙሉጌታ፡፡ በተከታታይ ደም በመለገስ በክልሉም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወዳደራቸው አልተገኘም፡፡ ደም ሲለግሱ ከቤተሰቦቻቸው ተቃውሞ ይደርስባቸው እንደነበርም ነው አቶ ሙሉጌታ ለአብመድ የገለጹት፡፡ ይሁን እንጅ ደም መለገስ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያስከትልና ይልቁንም ለጤና ጠቀሜታ እንዳለው በሂደት በመረዳታቸው አንደኛዋ እህታቸው ለ11ኛ ጊዜ ደም የለገሰች መሆኑንና ሌሎች ቤተሰቦቻቸውም እየለገሱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የምለግሰው ደም ነው፤ እንደ ደም ሲለገስ ጉዳት የማያስከትልና የሌላውን ሕይወት መታደግ የሚችል ከደም በላይ ሌላ ስጦታ ቢኖርም መለገስ እችል ነበር›› ብለዋል አቶ ሙሉጌታ፡፡ አቶ ሙሉጌታ ደም ከመለገስ ባለፈ በ2007 ዓ.ም ከክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ፈቃድ ወስደው የኮምቦልቻ ደም ለጋሾች ማኅበርን መስርተዋል፡፡ ማኅበሩ አሁን ላይ 530 የደም ለጋሽ አባላት እንዳሉት አስታውቀዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ማኅበሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተመሥርቷል፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
384
”በጎ ፈቃደኛ የለገሱት ደም ሕይወታችንን ታድጎልናል”-የባህር ዳር ወላድ እናቶች 855 Share ባህር ዳር የካቲት 1/2011 በጎ ፈቃደኛ የለገሱት ደም ህይወታቸውን እንደታደገላቸው በባህርዳር ከተማ ፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ሕክምና የሚከታተሉ ወላድ እናቶች ተናገሩ። በአማራ ክልል በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት ከበጎ ፈቃደኞች ከ22 ሺህ 500 በላይ ዩኒት ደም ተሰብስቧል። በሆስፒታሉ ሕክምናቸውን በመከታተል የሚገኙ እናቶች ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በበጎ ፈቃደኞች የተለገሰው ደም ተጋርጦባቸው ከቆየው አደጋ በማውጣት ሕይወታቸውን አትርፎላቸዋል። በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ሕይወትን ለመታደግ የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። ከምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ የመጡት ወይዘሮ ጥሩ አበጀ በወሊድ ምክንያት አጋጥሟቸው በነበረ የደም መፍሰስ ለአደጋ ተጋልጠው እንደነበር አስታውሰው፣በጎ ፈቃደኞች በለገሷቸው ደም ከሕመማቸው እንዳገገሙ ተናግረዋል። ከምስራቅ ጎጃም ዞን የቢቸና ወረዳ ወይዘሮ አሞኘች ሀብቴ በበኩላቸው አጋጥሟቸው በነበረው የደም እጥረት ተቸግረው እንደነበርና በተሰጣቸው አምስት ዩኒት ደም ሕይወታቸውን መትረፉን ገልጸዋል። “በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች የለገሱትን ደም ባላገኝ ኖሮ፤ አሁን በሕይወት አልገኝም ነበር” ብለዋል። በፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል አዋላጅ ነርስ ጌታነህ አጥናፉ በሆስፒታሉ በደም እጥረት ምክንያት የወላድ እናቶችና ህፃናት ሕይወት ያልፍ እንደነበር አስታውሰው፣በአሁኑ ወቅት የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር በመጨመሩ ችግሩ መወገዱን ተናግረዋል። ኑሮውን በደብረ ማርቆስ ከተማ ያደረገውና የቴክኒክና ሙያ ተማሪው ነቢዩ ዳንኤል ደም መለገስ ከጀመረ ሶስት ዓመታት እንዳስቆጠረ ተናግሯል። ለዘጠኝ ጊዜ ደም መለገሱን ያስረዳው ወጣቱ ሌሎችም ደም በመለገስ በአደጋና በወሊድ ወቅት ደም የሚፈሳቸውን ወገኖች ሕይወት እንዲታደጉ ጠይቋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪው መጋቤ ኩራልኝ ሞገስ በበኩላቸው “በምለግሰው ደም ክቡር የሆነውን የሰው ህይወት ከማትረፍ የበለጠ የሚያስደስተኝ ነገር የለም” ብሏል። የቅርብ ጓደኛቸው ባለቤት ታመው በሰጡት ደም ህይወታቸው መትረፉን የገለጹት አስተያየት ሰጪው፣ እስካሁን ለ20 ጊዜ ደም መለገሳቸውን ተናግረዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የደም ባንክ አስተባባሪ አቶ አንዳርጌ አጥናፉ በተጠናቀቀው ግማሽ በጀት ዓመት ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ከ22 ሺህ 500 በላይ ዩኒት ደም መሰብሰቡን አስታውቀዋል። ከተሰበሰበው ደም ውስጥ 21 ሺህ 132 ዩኒት ደም ለመንግሥትና ለግል ጤና ተቋማት ተሰራጭቶ ጥቅም ላይ መዋሉን አስረድተዋል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጥቅም ላይ ከዋለው ደም ጋር ሲነፃፀር በ2 ሺህ 618 ዩኒት ደም ብልጫ እንዳለው አመልክተዋል። የተሰበሰበው ደም በወሊድ ምክንያት ደም ለፈሰሳቸው እናቶች፣ የመኪና አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖችና ሌሎች የደም እጥረት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ጥቅም ውሏል ብለዋል። የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር መጨመር ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ እንዳስቻለ አስተባባሪው አስረድተዋል። ከለጋሾች የሚሰበሰበው ደህንነቱ የተጠበቀ ደም ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ዘጠኝ የደም ባንኮች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
385
የደም መለገስ ባህል ህብረተሰቡ እንዲያዳብር ጥሪ ቀረበ 959 Share ጋምቤላ ጥር 21/2011 ኅብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን እንዲያጎለብት የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጠየቁ። ”በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት በጋራ እንከላከል!’‘ በሚል መሪ ቃል ትናንት በጋምቤላ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። ምከትል ርዕሰ መሰተዳድሩ አቶ ተንኳይ ጆክ በዚሁ ወቅት የእናቶችን የጤና አገልገሎት በማሻሻል ውጤታማ ተግባራት ቢከናወኑም፤ከወሊድ ጋር በተያያዘ በሚከሰተው የደም መፍሰስ ችግር እናቶች ተጎጂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በደም መፍሰስ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችን ሞት ለመቀነስ ደም የመለገስ ባህል እንዲጠናከር ጠይቀዋል። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኡማን አሙሉ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የምዕተ ዓመቱ የጤና ልማት መርሃ ግብር የእናቶችን የጤና አገልገሎት በማሻሻል ረገድ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የእናቶች የጤና አገልገሎት በተፈለገው ደረጃ አለመሟላቱን ጠቁመዋል። የእናቶች ሞት ከቤተሰብ አልፎ በኅብረተሰቡና በአገር ላይ የሚያስከትለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የከፋ ነው ያሉት ኃላፊው፡ ለእናቶች ጤና መሻሻል የአመራሩና የህዝቡ አጋርነት እንዲጠናከር ጠይቀዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ዶክተር ሎው ኡቡፕ በሰጡት አስተያየት ለእናቶች ጤና አገልግሎት የተመደቡ አምቡላንሶችን ለታለመላቸው ዓለማ በማዋል ረገድ የሚታዩ ችግሮች መታረም አለባቸው ብለዋል። በደም መፍሰስ ምክንያት የሚገጥመውን ችግር ለማቃለል ወደ መቱ ሆስፒታል የሚላኩ እናቶች ለእንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። የእናቶችን የጤና አገልገሎት ለማሻሸል በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። በወሊድና በቅድመ ወሊድ ወቅት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማቱ የሚሄዱ እናቶች በአግባቡ እንደማይስተናገዱ የገለጹት ሌላዋ የውይይቱ ተሳታፊ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ ናቸው። በባለሙያዎች ስነ ምግባር ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር መጠናከር እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዋ ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልል፣የዞን፣የወረዳ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ባለድርሻ አካላት ደም ለግሰዋል። በኢትዮጵያ የጥር ወር የጤናማ እናትነት ወር በሚል በተለይ ለወላዶች ጤና ትኩረት ይሰጥበታል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
386
የደም እጥረቱ አሁንም አሳሳቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም (አብመድ) ሰራተኞቹ ደም ለግሰዋል፤ ተግባሩን በቋሚነት እንደሚያስቀጥሉም አስታውቀዋል፡፡ የአማራ ክልል ሴቶች፣ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የ2011 የበጀት ዓመት የተግባር አፈፃፀምን ምክንያት በማድረግም ዛሬ ነሐሴ 27/2011 ዓ.ም የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡ በደም እጦት የሚሞቱ እናቶችን ህይዎት ለመታደግ ደም በቋሚነት የሚለገስበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራም ቢሮው አስታውቋል፡፡ በመርሀ ግብሩ የቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ አስናቁ ድረስ ደም ለግሰዋል፡፡ መስሪያ ቤቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ሲያስተባብር መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡ ደም ልገሳውም አንድም እናት በደም እጦት እንዳትሞት ከመደበኛ እቅድ ጋር ተይዞ እንደሚሰራ ነው ቢሮ ኃላፊዋ የተናገሩት፡፡ ቢሮው የደም ባንክ ማኅበር አባል በመሆኑ በቋሚነት የመለገስ ተግባር እንደሚያከናውንም ነው የተገለጸው፡፡ የባሕር ዳር በጎ ፈቃደኛ ደም ባንክ አስተባበሪ አቶ መላኩ ውዴ ለአብመድ እንደተናገሩት በክልሉ ቋሚ ደም ለጋሽ ባለመኖሩ እናቶች በደም እጥረት ምክንያት እየሞቱ ነው፡፡ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 65 ዓመት የሆኑ እና ከ45 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝኑ ጤነኛ ሰዎች በየሦስት ወራት ደም መለገስ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም በበጎ አድራጎት ተግባሩ በቋሚነት በመሳተፍ የእናቶችን ህይዎት ማትረፍ እንደሚገባም ነው አቶ መላኩ ያሳሰቡት፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
387
የደብረ ማርቆስ ከተማ ደም ለጋሾች ከጤና ባለሙያዎች ቁጥር በላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 15/2012 ዓ.ም (አብመድ) የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች 10 ሺህ ዩኒት ደም በአንድ ጀምበር መርሀ ግብር እንዲሳካ በብዛት ደም እየለገሱ ነው። በከተማዋ በአንድ ሰዓት ብቻ ከ70 በላይ በጎ ፈቃደኞች ደም ለግሰዋል። ‹‹ደም የሚቀበለው ባለሙያና ሊለግስ የወጣው ሕዝብ ባለመጣጣሙ ብዙ ለመቆም ተገድደናል›› ብለዋል የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾቹ በሰጡት አስተያዬት፡፡ የደብረ ማርቆስ ደም ባንክ አገልግሎት ከራሱ ባለሙያዎች በተጨማሪ ከደብረ ማርቆስ ራፈራል ሆስፒታልና ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የጤና ባለሙያዎችን ጠይቆ ተጨማሪ ባለሙያዎችን ማሰማራቱን ደግሞ የደም ባንክ አገልግሎት ኃላፊዉ አቶ ከፋለ ገበየሁ ተናግረዋል። የደብረ ማርቆስ ደም ባንክ አገልግሎት በመርሀ ግብሩ ከ2 ሺህ 90 በጎ ፈቃደኞች 250 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዷል። በደም ልገሳ መርሀ ግብሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ተማሪዎች፣ ነጋዴዎችና ሌሎም የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
388
ዛሬ የደም ልገሳ ቀን ነው፤ በዕለቱም የብሔራዊ የደም ባንክ ሕንጻ ተመርቋል፡፡ ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 15/2012 ዓ.ም (አብመድ) የደሴ ከተማ ወጣቶች፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንዲሁም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የደም ልገሳ ቀንን ምክንያት በማድረግ ደም በመለገስ ላይ ናቸው፡፡ በደሴ ከተማ አስተዳደር በአንድ ጀምበር ብቻ 650 ዩኒት ደም ከበጎ ፈቃደኞች እንደሚሰበሰብ ተገምቷል፡፡ የደሴ ደም ባንክ አገልግሎት ደሙን ለመሰብሰብ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ እና ኮምቦልቻ ግቢዎች እንዲሁም በደም ባንኩ ግቢ ውስጥ ነው:: የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በማኅበራዊ ገጻቸው እንዳስታወቁት ደግሞ የብሔራዊ ደም ባንክ ያስገነባው ሕንጻ አዲስ አበባ ላይ ተመርቋል፡፡ ሕንጻውን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ እና በአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ሚሽን ዳይሬክተር ሲን ጆንስ መርቀውታል፡፡ ከምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ጎን ለጎንም የደም ልገሳ መርሀ ገብር እየተካሄደ ነው፡፡ ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 10 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ ያለበት የደም ልገሳ ቀን ነው፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
389
የደም መለገስ ባህል ህብረተሰቡ እንዲያዳብር ጥሪ ቀረበ 149 Share ጋምቤላ ጥር 21/2011 ኅብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን እንዲያጎለብት የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጠየቁ። ”በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት በጋራ እንከላከል!’‘ በሚል መሪ ቃል ትናንት በጋምቤላ ከተማ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። ምከትል ርዕሰ መሰተዳድሩ አቶ ተንኳይ ጆክ በዚሁ ወቅት የእናቶችን የጤና አገልገሎት በማሻሻል ውጤታማ ተግባራት ቢከናወኑም፤ከወሊድ ጋር በተያያዘ በሚከሰተው የደም መፍሰስ ችግር እናቶች ተጎጂ መሆናቸውን ተናግረዋል። በደም መፍሰስ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችን ሞት ለመቀነስ ደም የመለገስ ባህል እንዲጠናከር ጠይቀዋል። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኡማን አሙሉ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የምዕተ ዓመቱ የጤና ልማት መርሃ ግብር የእናቶችን የጤና አገልገሎት በማሻሻል ረገድ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የእናቶች የጤና አገልገሎት በተፈለገው ደረጃ አለመሟላቱን ጠቁመዋል። የእናቶች ሞት ከቤተሰብ አልፎ በኅብረተሰቡና በአገር ላይ የሚያስከትለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የከፋ ነው ያሉት ኃላፊው፡ ለእናቶች ጤና መሻሻል የአመራሩና የህዝቡ አጋርነት እንዲጠናከር ጠይቀዋል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ዶክተር ሎው ኡቡፕ በሰጡት አስተያየት ለእናቶች ጤና አገልግሎት የተመደቡ አምቡላንሶችን ለታለመላቸው ዓለማ በማዋል ረገድ የሚታዩ ችግሮች መታረም አለባቸው ብለዋል። በደም መፍሰስ ምክንያት የሚገጥመውን ችግር ለማቃለል ወደ መቱ ሆስፒታል የሚላኩ እናቶች ለእንግልት እየተዳረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። የእናቶችን የጤና አገልገሎት ለማሻሸል በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። በወሊድና በቅድመ ወሊድ ወቅት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማቱ የሚሄዱ እናቶች በአግባቡ እንደማይስተናገዱ የገለጹት ሌላዋ የውይይቱ ተሳታፊ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ ናቸው። በባለሙያዎች ስነ ምግባር ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር መጠናከር እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዋ ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልል፣የዞን፣የወረዳ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና ባለድርሻ አካላት ደም ለግሰዋል። በኢትዮጵያ የጥር ወር የጤናማ እናትነት ወር በሚል በተለይ ለወላዶች ጤና ትኩረት ይሰጥበታል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
390
የገንዳ ውሃ ከተማ በጎ ፍቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎች 1ሺህ ዩኒት ደም ለገሱ በምእራብ ጎንደር የገንዳ ውሃ ከተማ በጎ ፍቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎች 1ሺህ ዩኒት ደም መለገሳቸውን የከተማው የደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ። የከተማው ደም ባንክ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ወንድሙ አሰፋ ለኢዜአ እንደገለፁት ደም የለገሱት የመንግስት ሰራተኞች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የከተማው ነዋሪዎች ናቸው ። ከበጎ ፍቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎቹ ደሙ የተሰበሰበው ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ ነው ። የደም ባንኩ በግንቦት 3 ቀን 2009 ዓ.ም መቋቋሙን የገለፁት አስተባባሪው ለመጀመሪያ ጊዜ ደም መሰብሰቡን ተናግረዋል ። የተሰበሰበው ደም በመተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተሰጥቶ እጥረት ላጋጠማቸው ህሙማን ጥቅም ላይ መዋሉን ተናግረዋል ። "የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የበጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾችን ቁጥር ለማሳደግ ይሰራል " ብለዋል ። በመተማ ሆስፒታል ባለሙያ የሆኑት ሲስተር አይናዲስ መላኩ በበኩላቸው ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም የደም እጥረት ሲያጋጥመው ከጎንደር ደም ባንክ አገልግሎት ያስመጣ እንደነበር አስታውሰዋል ። አሁን ላይ በአቅራቢያው የደም ባንክ አገልግሎት በመቋቋሙ የሚፈለገውን ደም ለህሙማን ፈጥኖ ማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል ። በሆስፒታሉ ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን መካከል አቶ አዲሱ ተስፋሁን "በአባላዛር በሽታ ተይዥ በሆስፒታሉ በመተኛቴ በተሰጠኝ ደም ከህመሜ አገግሜአለሁ" ብለዋል ። የመተማ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ከበሩ አዳነ በበኩላቸው ዘንድሮ ለስድሰተኛ ጊዜ ደም በመለገሳቸው የመንፈስ እርካታ የፈጠረላቸው መሆኑን አስታውቀዋል ።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
391
የመቀሌ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር ደም ለገሱ የመቀሌ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር አባላት የጀመሩትን ደም የመለገስ ተግባር በየሦስት ወሩ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ። ማህበሩ ከመቀሌ ከተማ የደም ባንክ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ላይ ከ400 በላይ ወጣቶች ደም ለግሰዋል። ደም ከለገሱ ወጣቶች መካከል ከመቀሌ ከተማ የቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ወጣት ግርማይ ግደይ እንዳለው ደም በመለገስ ከዚህ ቀደም ለወገኖቹ ድጋፍ ለማድረግ የነበረውን ምኞት ማሳካቱን ተናግሯል የሚሰበሰበው ደም በተለይ የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመታደግ ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ በቀጣይ በየሦስት ወሩ ደም ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። በመቀሌ ከተማ "ሮማናት አደባባይ" በተዘጋጀው የደም ማሰባሰብ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ደም የለገሰውና በዓይደር ክፍለከተማ የሚኖረው ወጣት ሐጎስ ብርሃነ በበኩሉ፣ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ በፈቃደኝነት ደም መለገሱን ተናግሯል። "አሁንም ለሦስተኛ ጊዜ በክለቡ ስም ደም ለግሼ ወገኖቼን በመታደጌ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል" ብሏል። "የመቀሌ እግር ኳስ ክለብን ከመደገፍ በላይ ወገንን መታደግ ይበለጥ ክብር እንዲሰማኝ ስለሚያደርግ ደሜን ለግሺያለሁ" ያለው ደግሞ ከሐድነት ክፍለ ከተማ የመጣው ገብሩሽ ኪሮስ ነው። በማህበሩ ቀስቃሽነት የጀመረውን ደም የመስጠት ተግባር በቀጣይም አጠናክሮ በማስቀጠል ደም የሚያስፈልጋቸውን ወጎኖች ከሞት እንደሚታደግ አስታውቋል። የመቀሌ እግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ሊቀመንበር መምህር አታክልቲ ኃይለስላሴ በበኩላቸው እንዳሉት፣ ለአንድ ቀን በተዘጋጀው የደም ማሰባሰብ መርሃ ግብር ላይ አንድ ሺህ የክለቡ ደጋፊዎች ደም እንዲለግሱ ቢታቀድም ከዕቅድ በታች መሰብሰቡን ተናግረዋል። የቅድመ ዝግጅት ማነስ እንዲሁም የከተማው ደም ባንክ የጤና ባለሙያዎችና መሳሪያዎችን በብዛት አለማቅረብ ለዕቅዱ አለመሳካት ዋነኛ ምክንያት መሆኑንም አመልክተዋል። ብዛት ያላቸው የከተማው ወጣቶች ደም ለመለገስ ቢመጡም በሚያስተናግዱ ባለሙያዎች እጥረት በርካታ ወጣቶች ደም ሳይለግሱ መመለሳቸውን ተናግረዋል። "ወጣቶቹ የሚቆዩበት ማረፊያ ቦታ አለመዘጋጀቱ ሌላው ምክንያት ነበር" ያሉት ሊቀመንበሩ፣ የታዩትን ችግሮች በቀጣይ በማስተካከል የተሻለ ስራ ለመስራት ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። በመቀሌ ደም ባንክ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ገብረገርግስ በዛብህ በበኩላቸው፣ የደም ባንኩ ካለው ንብረትና የሰው ኃይል በተጨማሪ ከአክሱምና ከመከላከያ ሆስፒታል ተጨማሪ አልጋዎች እንዲቀርቡ ማድረጉን ተናግረዋል። አራት የደም መስጫ ቦታዎች እንዲዘጋጁ ቢደረግም በተወሰኑ የደም መስጫ ቦታዎች ላይ ለተወሰኑ ሰዓታት ደም ለጋሾች በብዛት መምጣታቸው ክፍተት እንዲፈጠር ማድሩን ጠቁመዋል። በመቀሌ ደም ባንክ የደም ለጋሾች አስተባባሪ ወይዝሮ ትንስኡ ግደይ በበኩላቸው፣ በከተማው ህብረተሰቡ ስለ ደም ልገሳ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
392
በባሌ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ4 ሺህ 815 ዩኒት በላይ ደም ከበጎ ፍቃደኞች በልገሳ መገኘቱን የጎባ ደም ባንክ አገልግሎት ገለጸ። በጎ ፍቃደኞቹ በሚሰጡት ደም ሕይወታቸው መትረፉን በጎባ ሪፈራል ሆስፒታል የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ተናግረዋል የጎባ ደም ባንክ ኃላፊ አቶ ሴይፉዲን መሐመድ ለኢዜአ እንደገለጹት ከበጎ ፍቃደኞች የተሰበሰበው ደም በበጀት ዓመቱ ለመሰባሰብ በዕቅድ ከተያዘው 5ሺህ ዩኒት ደም ውስጥ ነው፡፡ ደም የለገሱት በዋናናት የሁለተኛ ደረጃና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እንዲሁም የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት ሠራተኞች ናቸው ብለዋል ፡፡ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበው ደም በባሌ ዞን የሚገኙ ሆስፒታሎችን ጨምሮ ለምዕራብ አርሲ፣ ቦረና፣ ጉጂና ሶማሌ ክልል ሊበን ዞን ለሚገኙ 20 ሆስፒታሎች መሰራጨቱን አቶ ሴይፉዲን ጠቁመዋል። የተሰበሰበው ደም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ዩኒት ብልጫ እንዳለው የገለጹት ኃላፊው፣ ለእዚህም የሕብረተሰቡ ደም የመለገስ በህል እየዳበረ መምጣት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል። በጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ሁለተኛ ልጃቸውን የተገላገሉት ወይዘሮ መሰረት በላቸው በሰጡት አስተያየት የደም እጥረት አጋጥሟቸው ከጎባ ደም ባንክ ባገኙት የደም አገልግሎት ሕይወታቸው ሊተርፍ መቻሉን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ደም በመለገስ እሳቸውን ጨምሮ የብዙ አናቶችን ሕይወት ለታደጉ በጎ ፍቃደኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ከጊኒር ወረዳ ወደ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ለተሻለ ሕክምና የመጡት አቶ አበራ ከተማ በበኩላቸው "የደም እጥረት አጋጥሞኝ ከደም ባንኩ ባገኘሁት ነፃ የደም አገልግሎት ሕይወቴ ተርፏል" ብለዋል፡፡ በጎባ ከተማ በፈቃደኝነት ደም ከሚለግሱ ወጣቶች መካከል አቤል ግርማ በሰጠው አስተያየት እናቶች በወሊድ ጊዜ በደም መፍሰስ ምክንያት ከሚደርስባቸው አደጋ ለመታደግ በሚል ለአምስተኛ ጊዜ በፈቃደኝነት ደም መለገሱን ተናግሯል፡፡ በደም እጦት ምክንያት የበርካቶች ሕይወት ሲያልፍ መመልከታቸው ደም በየጊዜው ለመለገስ እንዳነሳሳቸው የገለጹት ደግሞ በከተማው የምስራቅ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሴይፉ ጉርሙ ናቸው፡፡ ደም መለገስ በጤና ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያስከትል በመገንዘባቸው ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል፡፡ የጎባ ደም ባንክ 134 ቋሚና ከአራት ሺህ 800 በላይ ቋሚ ያልሆኑ በጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች እንዳሉት ከደም ባንኩ የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
393
በፍቼ ከተማ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና የሕክምና ባለሙያዎች ደም ለገሱ 526 Share ፍቼ ጥቅምት 17/2011 በፍቼ ከተማ 210 በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና የሕክምና ባለሙያዎች ለፍቼ ከተማ ሪፈራል ሆስፒታል ደም ለገሱ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አውራሪስ ታዬ እንደገለጹት “ጤናማ ደም ከጤናማ ሰው ይገኛል” በሚል መርህ በሆስፒታሉ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ተዘጋጅቷል። በመርሀ ግብሩም 21ዐ የከተማዋ ወጣቶች፣ ሴቶችና የሆስፒታሉ ማህብረሰብ ደም በመለገስ ተሳትፈዋል። ከደም ለጋሾቹ የተገኘው ደም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የጤና ጉዳት ለደረሰባቸው እናቶችና ሌሎች ወገኖች እንደሚውልም ጠቁመዋል። በከተማዋ ወጣቶችና በሆስፒታሉ ሠራተኞች የተጀመረው የደም ልገሳ በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሆስፒታሉ የቅስቀሳና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ደም ከለገሱ ወጣቶች መካከል ከአስር ጊዜ በላይ ደም የለገሱ እንደሚገኙበት አመልክተው ደም መለገስ ለጤናማ ሰው ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለውና የሌሎችን ሕይወት በማትረፍ ውስጣዊ እርካታ እንደሚያስገኝ ገልጸዋል፡፡ በደም ልገሳው ከተሳተፉት መካከል ወጣት ፍሬሕይወት ግዛው በበኩሏ በደም እጥረት እየተቸገሩ ያሉ ወገኖችን ሕይወት ለመታደግ ተነሳስታ ደም መለገሷን ትናገራለች። የፍቼ ከተማ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት አሸብር ኦልጂራ በበኩሉ የደም ለጋሾች ማህበር ለመመስረትና የተጐዱ ወገኖችን በልዩ ሁኔታ ለመርዳት የሚያስችል ኮሚቴ አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጾ የደም ልገሳውም የእዚሁ አካል መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለአምስት ቀናት የተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር ትናንት ሲጠናቀቅ ለተሳታፊዎቹ በመጀመሪያ የሕክምና እርዳታና በተላላፊ በሽታዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
394
የደም የማሰባሰብ ስራ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ 138 Share ሚያዝያ 7/2011 አማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርና ሰሜን ሸዋ ዞኖች በተከሰተው የጸጥታ ችግር ለተጎዱ ሰዎች በኮምቦልቻ ከተማ ደም እየተሰባሰበ ነው፡፡ በዞኖቹ በተፈጠረው ችግር በራሳቸው ተነሳሽነት ደም እያሰባሰቡ ያሉት ወጣቶች መሆናቸውን የደሴ ደም ባንክ አገልግሎት ባለሙያ አቶ ኪዳነማሪያም ወርቁ ለኢዜአ አስታውቀዋል፡፡ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ልገሳ መርሐ ግብር ከበጎ ፈቃደኞች እስካሁን 5 ሺህ ዩኒት ደም ለተጠቃሚዎች ተሰጥቷል፡፡ በቆይታውም 10 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱን አስረድተዋል። ወጣቶቹ ኅብረተሰቡን በማስተባበር በደም እጦት የሚሞቱ ሰዎችን ለመታደግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ደም ለጋሾች ማህበር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ ይርጋ ማህበሩ ወጣቶችን በማስተባበር የደም ልገሳውን በማስተባበርና በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በግላርቸው ለ84 ጊዜ ደም መለገሳቸውን የተናገሩት አቶ ሙሉጌታ፣ በዚህም ውስጣዊ እርካታ ይሰማኛል ብለዋል፡፡ በከተማው የ01 ቀበሌ ነዋሪ ወጣት ሙሐመድ ዓሊ በበኩሉ በደም እጦት የሚሞቱ እናቶችና ህጻናትን ለመታደግ የማህበሩ አባል በመሆን ለሦስተኛ ጊዜ ደም መለገሱን ተናግሯል፡፡ በመርሐ ግብሩ ደም ልገሳ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ተማሪዎችና ማህበረሰቡ እየተሳተፉ ነው፡፡
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
395
ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ የደም ልገሳን ባህል ማድረግ ያስፈልጋል– የጤና ሚኒስቴር 1145 Share አዲስ አበባ ጥር 13/2011 ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ የደም ልገሳን ባህል ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ”በደም መፍሰስ የሚደርሰውን የእናቶች ሞት በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ሃሳብ ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረው የእናቶች ወር በተለያየ መልኩ እየተከበረ ነው። የጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች ወሩን በማስመልከት ዛሬ የደም ልገሳ አድርገዋል። ከሰራተኞች ጋር በመገኘት ደም የለገሱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰሃርላ አብዱላሂ እንደገለጹት፤ በደም እጦት ምክንያት ብዙ ወላድ እናቶች ህይወታቸውን ያጣሉ። የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ህብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህሉን ለማሳደግ እየተሰራ እንደሆነ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታዋ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች አረአያ እንዲሆኑ በዘመቻ የደም መለገሳቸውን ተናግረዋል። በደም ልገሳው የተሳተፉት የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው፤ የእናቶችንና የህጻናትን ህይወት ለመታደግ እንዲሁም ሞት ለመቀነስ የደም ልገሳ እየተደረገ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ይገልጻሉ። በመሆኑም የበጎ ፍቃድ ደም ለጋሽ ቁጥር እየጨመረ እንዲሄድና የደም አቅርቦት ችግር እንዳይኖር ክልሎችና ሆስፒታሎች በተቀናጀ መልኩ ተቀራርበውና ህብረተሰቡን አስተባብረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ የሚሰማኝ ደስታ ብዙ ነው ደሙም የሚተካ ነው ወሩም የእናትነት ስለሆነም እናቶች ወይ ደም በመፍሰስ ምክንያት ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ እነዛን እናቶች ለመታደግ በጣም ደስታ ነው የሚሰማኝ ደም በመለገስ በኩል ትንሽ ግንዛቤው እየተስተካከለ መጥቷል በተለየ የእናቶችንና የህጻናትን ህይወት ለመታደግ፤ ሞት ለመቀነስ ደም በመለገስ በየወቅቱ የተለያዩ ስራዎች አየተሰሩ ነው ማለት ይቻላል ግን እንዳጠቃላይ ስናይ በቂ አይደለም ደም በፈቃደኝነት መለገስ አለበት ብለዋል፡፡ የሚኒስቴሩ የበጎ አድራጎት ማህበር አስተባባሪ አቶ ያዕቆብ ወንዲይራድ ደም ልገሳ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማስቻል የሚሰራ መሆኑን አመልክተዋል። ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጀምሮ ሁሉም በየደረጃው በዓመት ውስጥ ሶስትና አራት ጊዜ ደም እንዲለግሱ ለማድረግ ሚኒስቴሩ እንደሚሰራ ገልጸው እናቶችን ከአደጋ የመጠበቅ ሃላፊነት የሁሉም እንደሆነ ተናግረዋል። ደም በመለገሳቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹት የሚኒስቴሩ የሪፎርምና መልካም አስተዳዳር ዳሬክተር አቶ አሰፋ አይዴ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አካባቢዎች የደም እጥረት በመኖሩ በበጎ ፈቃደኝነት ደም የመለገስ ባህሉን ለማሳደግ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በቤት ውስጥ የሚወልዱና በተለያዩ የመዘግየት ምክንያቶች ወደ ጤና ተቋም የማይሄዱ እናቶች ቁጥር 72 በመቶ የሚደርስ ሲሆን በየዓመቱ ከ100ሺ እናቶች መካከል 412 የሚሆኑት የወለዷቸውን ልጆች ሳያዩ እንደሚያሸልቡ ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
[ 104 ]
[ "ደም ልገሳ" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ደም ልገሳና ጥቅም, ስለ ለጋሾች, ስለ ደም ባንክ የሚጠቅሱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ቀይ መስቀል,ስለ ቀይ እና ነጭ የደም ሴሎች የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
396
በክልሉ ሜጢ ከተማ የመጀመሪያ የሆነ የተሽከርካሪዎች መናኸሪያ ግንባታ ተጠናቀቀ, በጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን ዋና ከተማ ሜጢ  የመጀመሪያ የሆነ የተሽከርካሪዎች መናኸሪያ ግንባታ ተጠናቆ በቅርቡ ለአገልግሎት መብቃቱን የከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ።    የማዘጋጃ ቤቱ ምክትል ሹም አቶ ሞገስ ተፈራ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤ ግንባታው የተጠናቀቀው የተሽከርካሪዎች መናኸሪያው ከ317 ሺ ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል። የመናኸሪያው መገንባት በከተማው ያለውን የትራንስፖርት ችግር የሚያቃልል ከመሆኑም በላይ ባለንብረቶችና ተጓዦች ደህንነታቸውን እንዲጠበቅ የሚያስችል መሆኑን ገልፀው፤ በአካባቢው ያለው የንግድ እንቅስቃሴ እንዲጠናከርም ያስችላል ብለዋል። በከተማው የተፋሰስ ስራዎችን ለማከናወን ማዘጋጃ ቤቱ 600ሺ ብር የመደበ ሲሆን፤ ህብረተሰቡም የግንባታው ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን አቶ ሞገስ ገልፀዋል። በከተማዋ የ01ና 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አወል ጀማልና አቶ እንዷለም አባትነትህ በሰጡት አስተያየት የሚኖሩበት ከተማ የዞኑ ዋና ከተማ እንደመሆኗ እስካሁን ምንም ዓይነት የጠጠር መንገድ ባለመገንባቱ ቅሬታ ቢሰማቸውም ለጠጠር መንገድ ግንባታው በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸውና በጉልበታቸው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ),
[ 105 ]
[ "የመናኸርያ ግንባታ" ]
[ "የመናኸርያ ግንባታ ስለተደረገባቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት ፡፡" ]
[ "ስለ አዳዲስ መናኸርያ ግንባታወችና ስለተመደበላቸው በጀት, ስለ ተበላሹ መናኅሪያወች ጥገና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ መንገድና ስለቤት ግንባታ, ስለ አወቶቢስ የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
397
የሸጎሌ የአውቶብስ ዴፖ ተመረቀ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመደበለት 555 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የሸጎሌ የአውቶብስ ዴፖ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡ ዴፖው የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ኢንጂነር ሰለሞን ኪዳኔ እንዲሁም ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው፡፡ የአውቶቢስ ማቆሚያ ዴፖው የራሱ ገራዥ ፣ መኪና ማጠቢያ ፣ ነዳጅ ማዲያ በውስጡ ያካተተ ሲሆን በተገነባለት ህንጻ ውስጥ የንግድ ማዕከላት ፣ የመዝናኛ ቦታዎችና አረንጓዴ ሥፍራዎች ተካተዋል፡፡ ዴፖው ከቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ ንግስት ጀምሮ በእንጨትና ቆርቆሮ ተሰርቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን አሁን በዘመናዊ መልክ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡ ዴፖው አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ከአውቶብስ ደህንነት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን እንደሚፈታ እና ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችልም ነው በምረቃው ወቅት የተገለፀው፡፡ ለተሸከርካሪ እጥበት የሚውለው ውሃ ከከርሰ ምድር የተገኘ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ 212 አውቶብሶችን በአንድ ጊዜ ለማቆም እንደሚያስችል የተነገረው ዴፖው፤ 52 ሺህ ካሬ ሜትር ስፍራ ላይ ያረፈ ነው፡፡
[ 105 ]
[ "የመናኸርያ ግንባታ" ]
[ "የመናኸርያ ግንባታ ስለተደረገባቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት ፡፡" ]
[ "ስለ አዳዲስ መናኸርያ ግንባታወችና ስለተመደበላቸው በጀት, ስለ ተበላሹ መናኅሪያወች ጥገና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ መንገድና ስለቤት ግንባታ, ስለ አወቶቢስ የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
398
የራሱ መናኽሪያ ያልነበረው የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አዲስ መናኽሪያ ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ፡፡ ባሕር ዳር፡ጥር 26/2011 ዓ.ም(አብመድ) ለዘመናት የነበረውን የትራንስፖርት መናኽሪያ ለማህበር አሳልፎ በመስጠቱ የራሱ መናህሪያ ያልነበረው የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አዲስ መናኽሪያ ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል፡፡ የመሰረት ድንጋዩን የሰሜን ሽዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድምአገኝ አስቀምጠዋል፡፡ መናህሪያው 14 ሺህ ካሬ ላይ የሚያርፍ ይሆናል፡፡ መናኽሪያው መካከለኛ ደረጃ ያለው ሆኖ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችም ይኖሩታል፡፡ የግንባታው ወጭ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በመናኽሪያው የውስጥ ገቢ የሚሽፈን ነው፡፡ ግንባታው በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅም ለማወቅ ተችሏል፡፡
[ 105 ]
[ "የመናኸርያ ግንባታ" ]
[ "የመናኸርያ ግንባታ ስለተደረገባቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት ፡፡" ]
[ "ስለ አዳዲስ መናኸርያ ግንባታወችና ስለተመደበላቸው በጀት, ስለ ተበላሹ መናኅሪያወች ጥገና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ መንገድና ስለቤት ግንባታ, ስለ አወቶቢስ የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
399
በጅማ የነባሩ መናኽርያ አገልግሎት በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተዛወረ 348 Share ኢዜአ /ጥቅምት 29 / 2012 በጅማ ከተማ በነባሩ መናኽሪያ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች አካባቢዎች መዛወሩን የከተማው የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ የባለስልጠኑ ኃላፊ አቶ ረሻድ አባሚልኪ ለኢዜአ እንደገለጹት በመናኽርያው ይሰጥ የነበረው አገልገሎት ከትላንት ጀምሮ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲዛወር ተደርጓል። “የነባሩ መናኽሪያ በማስፋፊያ ግንባታ ላይ በመሆኑና በተለዋጭነት በመሰራት ላይ የሚገኘው የቴክኒክ ሜዳን ባለው ዝናባማ የአየር ጸባይ ወደ ስራ ማስገባት ባለመቻሉ አገልግሎቱ ወደሌሎች አካባቢዎች እንዲዛወር ተደርጓል ” ብለዋል ። በነባሩ መናኽሪያ ይሰጡ የነበሩ አገልገሎቶች መካከል የሀገር አቋራጭ አውቶቢሶች መሳፊሪያ ወደ ከተማው የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ፣ የአጋሮ መስመር ጉዞ ስታዲዬም አጠገብ፣ የሰቃ መስመር ጉዞ ረሃ ሆቴል አጠገብ መዛወራቸውን አስታውቀዋል። የሰርቦ መስመር ጉዞ አበጋዝ ሁቴል አጠገብ፣ የወልቂጤ መስመር ጉዞ በሬለምኔ ምግብ ቤት አጠገብ፣ የዴዶና ጭዳ መስመር ጉዞ ሳዳት ዳቦ ቤት አጠገብ ተደርጓል። የከተማው ስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ መናኽሪያ ሆነ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለ መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ህብረተሰቡ በመገንዘብ አገለግሎቱ ወደ ነባሩ መናኽርያ እስኪመለስ በጊዜያዊነት በተዘጋጁ ስፍራዎች በትዕግስት እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፈዋል ። የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መኪዩ መሐመድ ህብረተሰቡ የነባሩ መናኽርያ ግንባታ እሰኪጠናቀቅ አገልገሎቱን በጊዜታዊ የስምሪት ስፍራዎች በመጠቀም ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። Related Posts:
[ 105 ]
[ "የመናኸርያ ግንባታ" ]
[ "የመናኸርያ ግንባታ ስለተደረገባቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት ፡፡" ]
[ "ስለ አዳዲስ መናኸርያ ግንባታወችና ስለተመደበላቸው በጀት, ስለ ተበላሹ መናኅሪያወች ጥገና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ መንገድና ስለቤት ግንባታ, ስለ አወቶቢስ የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
400
በሮቤ በ187 ሚሊዮን ብር አውቶብስ መናኸሪያ ሊገነባ ነው 254 Share ጎባ ሚያዝያ 11/ 2011 የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን በማስፋፋት አገልግሎቱን ቀልጠፋ ለማድግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ገለጸ፡፡ በባሌ ሮቤ ከተማ ከ187 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ለሚገነባው አዲስ ዘመናዊ መናኸሪያ የመሰረት ድንጋይ ዛሬ ተቀምጧል፡፡ የመሰረት ድንጋዩን ያኖሩት የክልሉ የትራንስፖርት ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ አህመድ አባጊሳ እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት የትራንስፖርት አገልግሎትን ቀልጠፋ ለማድረግ በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ አትኩሮ እየሰራ ነው፡፡ መናኸሪያውን በተሻለ መንገድ አገልግሎት እንዲሰጥ በኮንክሪት አስፋልት ደረጃ እንደሚገነባ የተናገሩት ምክትል ዳይሬክተሩ ለተለያዩ የቢሮና ተያያዥ አገልግሎቶች የሚውል ባለ ሁለትደረጃ ፎቅ ሕንጻን ያከተታ መሆኑንም ገልጿል፡፡ ሶስት ሄክታር በሚጠጋ መሬት ላይ የሚሰራው ዘመናዊ መናኸሪያው በቀን ከ1ሺህ 200የሚበልጡ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ተናግረዋል፡፡ አዲስ የሚገነባው መናኸሪያ የትራስንፖርት አገልግሎትን ከማሳለጡም በላይ የአካባቢውንየቱሪዝም ፍሰት በማሳደግ ረገድ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የክልሉ መንግስት በመደበው በጀት የሚሰራው ይህ መናኸሪያ ሶስት ሔክታር በሚጠጋ መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን በ540 ቀናት ውስጥ እንዲጠናቀቅም ታስቧል። የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ብርሃኑ ዳዲ በበኩላቸው እንደገለጹት በከተማው የሚገኘውነባሩ መናኸሪያ ለበርካታ ጊዜያት ከፍተኛ የህዝብ ቅሬታ ሲነሳበት መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡ አዲሱ መነሃሪያ ለህዝብ ምላሽ ከመስጠትና የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ከመቅረፍምበተጓዳኝ የነዋሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ የነቃቃል የሚል እምነት እንዳለቸው ገልጸው ፕሮጄክቱበወቅቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የሚፈለግባቸውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉተናግረዋል፡፡ ከከተማዋ ነዋሪዎቹ መካከል አቶ አህመድ አማን በሰጡት አስተያየት ግንባታው የሚበረታታመሆኑን ገልጸው የአካባቢውን ህዝብ ቅሬታ ለመፍታት ታስቦ የሚቀመጥ የመሰረት ድንጋይ በወቅቱ ግንባታው ሊከናወን ይገባል። ከከተማዋ አሽከርካሪዎች መካከል አቶ አሸናፊ መንግስቱ በበኩላቸው ነባሩ መናኸሪያከሚያስተነግደው የተሽከርካሪ ብዛትና ከሰጠው ረጅም አገልግሎት የተነሳ በበጋ አቧራና በክረምት ደግሞ ውሃ እየሞላ ተገልጋዮችን ሲያንገላታ መቆየቱን ተናግረዋል። አዲሱ መናኽሪያ በአስፋልት ኮንክሪት የሚገነባ መሆኑ የተቀላጠፈ የትራንስፖርት አገልግሎት ለተጠቃሚው ከመስጠት በተጓዳኝ ለእቃ መለዋዋጫ በየጊዜው ያወጡ የነበረውን ወጪእንደሚያስቀርላቸውም ገልጸዋል። ባለሥልጣኑ የሚሰጠውን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማቀላጠፍ የባሌ ሮቤን ጨምሮ በአምስትየክልሉ ከተሞች ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ አዳዲስ ዘመናዊ መናኸያዎችን ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑንን ከክልሉ ትራንስፖርት ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።