doc_no
int64
1
12.6k
doc_text
stringlengths
81
395k
relevant_topic_nos
sequencelengths
0
1
relevant_topic_titles
sequencelengths
0
1
relevant_topic_descriptions
sequencelengths
0
1
relevant_topic_narratives
sequencelengths
0
1
601
የጥላቻ ንግግር መከላከያ ረቂቅ አዋጁ በደንብ ታጥቦ መተኮስ አለበት December 4, 201998 Share «ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው» እንደምን ሰነበታችሁ! እንኳን በጤና ተገናኘን! “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” የሚሉት አባባል አለ። የቀደሙቱ አባት እናቶቻችን ይህንን አባባል ሲናገሩ ያለምክንያት አልነበረም። ጦርነት ሕዝብ አስጨራሽ፣ አገር አፍራሽ ስለሆነ፤ ከጦርነት በሚብስ ሁኔታ ደግሞ ወሬ አስከፊ ውጤት ስለሚያስከትል ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በምድረ-ኢትዮጵያ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። በርካቶች በብሔራቸው ተለይተው ግፍ ተፈጽሞባቸዋል። ንብረታቸው ወድሟል፤ ተዘርፏልም። አብያተ-ክርስቲያናት እና መስኪዶች ተቃጥለዋል። የአገልጋዮችና የምዕመናን ደም ፈሷል። ይህ ሁሉ የሆነው በጦርነት አልነበረም፤ በወሬ እንጂ። በማህበራዊ የትስስር ገጾችና በሚዲያዎች አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ፣ ብሄርን፣ ሃይማኖትን ወይም የፖለቲካ አስተሳሰብን መሰረት ያደረጉ ወሬዎች በመሰራጨታቸው አገሪቱ ለዚህ ሁሉ ችግር ተጋልጣለች። ከዚህ ሁሉ በኋላ “የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ” በሚል ረቂቅ ሕግ ተዘጋጅቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰሞኑ ቀርቧል። የጥላቻ ንግግር ሕግ ወሰን እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሚዛናዊነት የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ራሱን የቻለ ሕግ መውጣቱን ተከትሎ አንዳንዶች መንግስት የተቺዎቹን አፍ ለማዘጋት የሚያወጣው በመሆኑ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ይናገራሉ። ገሚሶቹ ደግሞ የሕጉን መውጣት በመርህ ደረጃ ቢደግፉም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋ ይሰጋሉ። ያም ሆነ ይህ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ፣ ከሌሎች አገራት ተሞክሮና ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሥምምነቶች አንጻር ሲታይ የሕጉ አስፈላጊነት ክርክር አይነሳበትም። አገራችን በወሬ ልትፈታ ስጋት ውስጥ ወድቃለች። በናዚ የአይሁዶች ጭፍጨፋና የርዋንዳው የዘር ፍጅት፤ በአሁኑ ወቅትም በማይንማር የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ወደ ባንግላዴሽ መሰደድ ለእኛም የማንቂያ ደወል ነው። ኢትዮጵያ የፈረመችውና እኤአ በ1965 ዓ.ም. የወጣው ሁሉንም ዓይነት የዘር ልዩነቶችን ለማስወገድ የተደረገው ዓለም አቀፍ ሥምምነት አገሮች ብሔራዊ የበላይነትን የሚሰብኩ ወይም የዘር ጥላቻንና ልዩነትን የሚያራምዱ ተቋማትንና ንግግሮችን ለማስወገድ ሕግ ማውጣት እንዳለባቸው ያስገነዝባል። እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኢጣሊያ፣ ዴንማርክና ሌሎችም የአውሮፓ አገራት ከናዚ መንኮታኮት ማግስት የጸረ-ጥላቻ ንግግር ሕግ አውጥተዋል። ከዚህ መነሻ ታዲያ በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ለመከላከል ሕግ መውጣቱ ካሳለፍነው ችግር አንጻር ሲታይ ዘግይቷል ከሚባል ውጭ አስፈላጊነቱ ላይ ጥርጣሬ አይኖርም። ይልቁንም ሕጉ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን የሚጋፋ እንዳይሆን ነው ጥንቃቄ የሚያስፈልገው። እርግጥ ነው ሃሳብን በነጻነት መግለጽ መሰረታዊ ከሚባሉት መብቶች ውስጥ አንዱ ነው። ይሁንና የሕዝብንና የአገርን ደህንነት አደጋ ላይ እስከሚጥል ድረስ ተለጥጦ የሚተገበር ሳይሆን ልጓም የሚበጅለት መብት ነው። ረቂቅ አዋጁ ባለፈው ሳምንት ለፓርላማ ሲቀርብ “ሀሳብን በነፃነት በመግለፅ ሽፋን የሚከሰቱ ጥላቻን፣ ማግለልን፣ ግጭትን፣ ጥቃትንና መሰል በግለሰቦችና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነትን የሚያሳሱና የሚጎዱ ንግግሮችንና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በህግ መከላከል ያስፈልጋል” በሚል ከአስፈጻሚው የቀረበው ማብራሪያም መነሻው ይኸው ነው። እናም የጥላቻ ንግግር መከላከያ ሕጉ ወሰንና የያዛቸው ድንጋጌዎች ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር ሚዛናቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው። ከሁሉም በላይ ሕጉ ግልጽ መሆን አለበት። ለዴሞክራሲ መሰረት የሆነውን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን በማይጋፋ መልኩ በጠባቡ የሚተረጎምና ለመንግስት አካላት የተለጠጠ ሥልጣን የማይሰጥ መሆን አለበት። ስለዚህ በመብቱ ላይ የሚጣል ገደብ ተመጣጣኝ ከሆነና በጥንቃቄ ተግባራዊ የሚደረግ እስከሆነ ድረስ ሕጉ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተቀባይነት ያለው ነው። በእነዚህ መሰረታዊ ሃሳቦች መነጽርነት ታዲያ ረቂቅ አዋጁን እንደሚከተለው እንቃኘው። የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ በአዋጁ መሰረት የጥላቻ ንግግር ማለት በአንድ ሰው (የተወሰነ ቡድን) ላይ ያነጣጠረ፣ ብሄርን፣ ብሄረሰብንና ህዝብን፣ ሃይማኖትን፣ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ጥላቻን፣ መድሎን ወይም ጥቃትን የሚያበረታታ ንግግር ነው። ሃሰተኛ መረጃ የሚባለው ደግሞ ውሸት የሆነና የመረጃውን ውሸት መሆን በሚያውቅ ወይም መረጃውን የሚያሰራጨው ሰው ካለበት አጠቃላይ ሁኔታ አንጻር የመረጃውን ሃሰተኝነት ሊያውቅ ይገባ ነበር የሚያስብል በቂ ምክንያት እያለ የሚሰራጭ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ከፍ ያለ ንግግር ነው። በዚሁ መነሻ የጥላቻ ንግግርን ወይም ሃሰተኛ መረጃን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚድያ በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪድዮ ማሰራጨት ወንጀል ነው። ሕጉ ሃሰተኛ መረጃን ሲተረጉም “… ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ከፍ ያለ ንግግር ነው” የሚል አገላለጽ መጠቀሙ ግልጽነት ስለሚጎድለውና ለትርጉም ስለሚጋለጥ “… ጥቃት እንዲደርስ የሚያደርግ ንግግር ነው” በሚል መስተካከል ይኖርበታል። ከዚህ ሌላ በግለሰብ ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግርን ማሰራጨት የተከለከለ ቢሆንም ግለሰብን የተመለከተ ሃሰተኛ መረጃን ማሰራጨት ስለመከልከሉ አዋጁ በግልጽ አያሳይም። ያም ሆኖ አንቀጽ 7(5) “…ሃሰተኛ መረጃ በመሰራጨቱ ምክንያት በግለሰብ (በቡድን) ላይ ጥቃት የተፈጸመ ወይም…” በሚል የተገለጸው ድንጋጌ ግለሰብን የተመለከተ መረጃን ማሰራጨትም በሕጉ ሊከለከል እንደሚገባ አመላካች በመሆኑ ይኸው በግልጽ መቀመጥ ይኖርበታል። የአንቀጽ 6 እና የሕጉ ዓላማ ተቃርኖ ረቂቅ አዋጁ የጥላቻ ንግግርን ወይም ሃሰተኛ መረጃን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨትን በመከልከል ወንጀል አድርጓቸዋል። አንቀጽ 6 ደግሞ አንድ ንግግር እንደ ጥላቻ ንግግር ወይም እንደ ሃሰት መረጃ ተወስዶ ለማሰራጨት የማይከለከልባቸውን ልዩ ሁኔታዎች አስቀምጧል። እነዚህም ንግግሩ (መረጃው) የትምህርታዊ ወይም ሳይንሳዊ ምርምር አካል፤ የዜና ዘገባ፣ የትንታኔ ወይም የፖለቲካ ትችት አካል፤ የኪነጥበብ፣ የትወና ወይም መሰል የስነጥበብ ውጤት እንዲሁም የሃይማኖታዊ አስተምህሮ አካል እንደሆነ ነው። መንግስት ለዚህ ያቀረበው ምክንያት “ህጉ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ ሊኖረው የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቀነስ ነው” የሚል ነው። ይሁንና የሕጉ ዓላማ የጥላቻ ንግግርንና የሃሰት መረጃዎችን መከልከል እስከሆነ ድረስ ሊተኮርበት የሚገባው ጉዳይ የንግግሩ ወይም የመረጃው ይዘት የጥላቻ ወይም የሃሰት መሆን/ያለመሆኑ ነው። ስለዚህ በየትኛውም መልኩ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግርም ሆነ የሃሰት መረጃ በሕጉ የሚያስቀጣ መሆን አለበት። ይህ መሆኑ ደግሞ የዜጎችን መብት የሚገድብ ሳይሆን በማንኛውም መንገድ ሃሳባቸውን በነጻነት ሲገልጹ ከጥላቻ ንግግርና ከሃሰት መረጃ እንዲቆጠቡ ያደርጋቸዋል። የብሮድካስትና የማህበራዊ ሚዲያዎች መደበላለቅ የአዋጁ መሰረተ ሃሳብ የጥላቻ ንግግርን ወይም ሃሰተኛ መረጃን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚድያ ማሰራጨትን መከልከል ነው። ይሁንና የብሮድካስትና የማህበራዊ ሚዲያዎች በየራሳቸው ያላቸውን ልዩና ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ አይመስልም። የብሮድካስት ሚዲያዎች (በአዋጅ ቁጥር 590/2000 መሰረት መገናኛ ብዙሃን በሚል የሚጠሩትን የህትመት ሚዲያዎችን ጨምሮ) ስለአመዘጋገባቸው፣ ሥለአሰራራቸው፣ ሥለ አደረጃጀታቸውና ስለኤዲቶሪያል ጉዳዮቻቸው በሕግ በተቀመጠ ሥርዓት የሚመሩ ናቸው። በአንጻሩ በአብዛኛው ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚባሉት ተቀማጭነታቸውን በውጭ አገራት ያደረጉና ከአገራችን የሕግ የግዛት ወሰን ውጭ ናቸው። የማህበራዊ ሚዲያ የሕግ ማዕቀፍም የለንም። በመሆኑም በእነዚህ በሁለቱ የሚዲያ ዘውጎች የሚሰራጩ መረጃዎችን ለመቆጣጠር ተመሳሳይ የሕግ ማዕቀፍ መቅረጽ ለአፈጻጸም አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርም። ከዚህ በተጨማሪ ረቂቅ ሕጉ የጥላቻ ንግግርን ወይም ሃሰተኛ መረጃን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨትን የሚከለክል ሆኖ ሳለ “የአገልግሎት ሰጪዎች ግዴታ” በሚል ባስቀመጠው ድንጋጌ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ግዴታን በመጣል የብሮድካስትና የሕትመት ሚዲያዎችን ከግዴታ ውጭ አድርጓቸዋል። በማህበራዊ ሚዲያዎቹ ላይ ብቻ የተጣለው ይህ ግዴታ በይዘቱም ሆነ ከአፈጻጸም አንጻር ሲታይ መሰረታዊ ሕጸጾች አሉበት። በይዘት ረገድ ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠርና ለመግታት ጥረት ማድረግ እንዳለበት መደንገጉ በራሱ “ምን ዓይነት ጥረት?” ኢትዮጵያ ውስጥ ሕጋዊ ሰውነት ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስ የማህበራዊ ሚዲያ ድርጅትስ አለ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን ስለሚያስነሳ ግልጽነት ይጎድለዋል። በተጨማሪም “ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የጥላቻ ንግግርን ወይም የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ ጥቆማ ሲደርሰው በፍጥነት ይህን መሰል መልዕክቶችን ወይም ንግግሮችን ከአገልግሎት አውታሩ ሊያስወግድ ይገባል” ይላል። ይህ በእርግጥም የመፈጸሙ ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባ ድንጋጌ ነው። “በፍጥነት” የሚለው ለትርጉም የተጋለጠ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሕጉ ውስጥ ማህበራዊ ሚዲያዎችን ሕጋዊ ሰውነት እንዳለው አካል የሚመለከት፤ መስራቾቻቸውን ወይም ባለቤትና የተለያዩ የስራ ኃላፊዎቻቸውንም የተመለከተ ድንጋጌ የለም። “በፍጥነት” መረጃው ስለመጥፋቱ የሚከታተል አካልስ ማን ነው? “በፍጥነት” በማያስወግድ ማህበራዊ ሚዲያ ላይስ ምን ዓይነት ርምጃ ይወሰዳል? ጥቆማውስ ከማን ነው መቅረብ ያለበት? የሚሉት መሰረታዊ ጥያቄዎችም በሕጉ ምላሽ የላቸውም። በጣም የሚያስገርመው ድንጋጌ ደግሞ ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ግዴታውን ለመወጣት የሚያስችለው አሰራርና ፖሊሲ ሊኖረው እንደሚገባ የሚደነግገው ነው። በዚህ ሳይበቃ ሕጉ አሰራርና ፖሊሲ ባልዘረጉት ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እየተከታተለ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ሪፖርት እንደሚያዘጋጅ ይገልጻል። ባለኝ መረጃ እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ “የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ድርጅት” የሚል ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች ስለመኖራቸው እርግጠኛ አይደለሁም። ነገር ግን የምንጠቀማቸው አብዛኞቹ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተቀማጭነታቸውን በውጭ አገራት ያደረጉና ከአገራችን የሕግ የግዛት ወሰን ውጭ ስለመሆናቸው እርግጠኛ ነኝ። ነባራዊው እውነታ ይህ ሆኖ ሳለ ሕጉ እንዲህ ያለ ድንጋጌ መያዙ አስገራሚ ሆኗል። ሌላው ሳይጠቀስ ሊታለፍ የማይገባው ጉዳይ አዋጁ የብሮድካስት ባለስልጣንና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሃሰት መረጃ ስርጭትና ጉዳትን ለመከላከል የሚረዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮችን የማዘጋጀት ኃላፊነት የጣለባቸው መሆኑ ነው። በተቋማት ላይ የኃላፊነት መደራረብን የሚያመጣ ከመሆኑም በላይ የሀብትና የሰው ኃይል ብክነትን የሚያስከትል ብሎም ለተጠያቂነት አሰራር እንቅፋት እንደሚሆን ግልጽ ነው። የወንጀል ድንጋጌዎቹ ሕጸጾች በአገራችን ከባድ አደጋን ጋርጧል የተባለውን ችግር ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቀረጸው ይህ አዋጅ አስር አንቀጾች ብቻ ናቸው ያሉት። ከእነዚህ ውስጥ የወንጀል ተጠያቂነትን የደነገገው አንቀጽ 7 መሰረታዊ የሚባሉ ሕጸጾች አሉበት። የመጀመሪያው ለየድርጊቶቹ የተቀመጡት ቅጣቶች አነስተኛ መሆናቸው ነው። እርግጥ ነው የወንጀል ቅጣት ተቀዳሚ አላማው ፈጻሚውንና ማህበረሰቡን ማስተማር ቢሆንም ቅሉ፤ ከድርጊቶቹ አደገኛነት አንጻር በአጥፊዎች ላይ ተመጣጣኝ ቅጣት ሊጣል ይገባል። በመሆኑም በወንጀል ሕጉና በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ በሌሎች የማነሳሳት አድራጎቶች ላይ ከሚጣለው ቅጣት ያልተናነሰ፤ እንዲያውም ከፍ ያለ ቅጣት ሊቀመጥ ይገባል። ሌላው ጉዳይ የወንጀል ተጠያቂነቶቹ የሚያጠነጥኑት የጥላቻ ንግግሩን ማድረግ ወይም የሃሰት መረጃውን ማሰራጨት ላይ ሲሆን፤ የሚቀጡትም እነዚህን ድርጊቶች የፈጸሙትን ሰዎች ነው። ከዚህ ውጭ ግን ኮሜንት፣ ሼር፣ ላይክ፣ ሪትዊትና መሰል የስርጭት ተሳትፎዎችን በተመለከተ ሕጉ ምንም የሚገልጸው ነገር የለም። የአዋጁ አንቀጽ 7(4) የጥላቻ ንግግሩ ወይም ሃሰተኛ መረጃው የተሰራጨው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከሆነ ቅጣቱን በማክበድ አስቀምጧል። ይሁንና ይህ “ከ5ሺ በላይ ተከታይ” የሚለው መለኪያ በሕጉ የተቀመጠበት አመክንዮ ግልጽ አይደለም። ይሁንና በርካታ ተከታዮች ባሉት ማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ የጥላቻ ንግግር ወይም ሃሰተኛ መረጃ ለበርካቶች ስለሚደርስ ከባድነቱን ለማመልከት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ያም ሆነ ይህ ግን የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ወይም ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑ ከግምት ውስጥ እንዲገባ ባልተደረገበት ሁኔታ 5ሺ ተከታዮች ባሉት ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ የተሰራጨን መረጃ 4999 ተከታዮች ካሉት ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ለይቶ በማክበድ ቅጣት ማስቀመጥ በዘፈቀደ የተገመደለ እንጂ ቅቡልነት ባለው አመክንዮ የተቀረጸ አይመስልም። ይህ ብቻ ሳይሆን በርካታ ተከታይ ያላቸው ገጾች ባለቤት የሆኑ ተጠቃሚዎችስ በተከታዮቻቸው ወይም በሃሰተኛ ስም የጥላቻ ንግግር ወይም ሃሰተኛ መረጃ በገጻቸው ላይ ቢሰራጭ የሚኖርባቸው ተጠያቂነት ምንድን ነው የሚለውን ሕጉ በዝምታ አልፎታል። ከወንጀል ተጠያቂነት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ቁልፍ ጉዳይ የወንጀል አድራጊዎቹን የመለየት ፈተና ነው። በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችና የሃሰት መረጃዎች የሚፈበረኩት በሃሰተኛ ስሞች ወይም ማንነታቸው ባልተለዩ ተዋንያን ነው። ይህ ሁኔታ ደግሞ ወንጀል ፈጻሚዎቹን በትክክል ለይቶ ለሕግ እንዳይቀርቡ እንቅፋት ነው። ከዚህ መነሻ ታዲያ ረቂቅ አዋጁ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የማስረጃ አሰባሰብም ሆነ የሥነ-ሥርዓት ማዕቀፍ አልዘረጋም። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የጥላቻ ንግግሩን “ወዲያውኑ” እንዲያስወግዱ ግዴታ ሲያስቀምጥ የወንጀሉ ማስረጃ እየጠፋ መሆኑንም የዘነጋው ይመስላል። አዋጁ በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጁና በማቋቋሚያ አዋጁ ውስጥ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተለይም የኦንላይን መረጃ ሥርጭቶችን በተመለከተ ቀጥተኛ ኃላፊነት ሊሰጠው የሚገባውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ገሸሽ ማድረጉ ደግሞ የሕጉን ተፈጻሚነት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል። የአዋጁ አንቀጽ 7(7) የተከለከሉት ተግባራት የተፈጸሙት በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ከሆነ የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ይገልጻል። ከጅምሩ ይህ ድንጋጌ ወንጀሉ የተፈጸመው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚድያ ገጽ ከሆነ ወይም በብሮድካስት አገልግሎት ወይም በየጊዜው በሚወጣ የህትመት ውጤት ከሆነ ቅጣቱን ከሚያከብደው ከአንቀጽ 7(4) ጋር ሲነጻጸር ድግግሞሽ ነው። ያም ሆኖ ወደ ወንጀል ሕጉ መምራቱ በራሱ ችግር አለበት። ምክንያቱም በወንጀል ሕጉ ከአንቀጽ 42 እስከ 47 ያሉት በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት በሚደረጉ ወንጀሎች ተካፋይ መሆንን የሚመለከቱ የመርህ ድንጋጌዎች እንጂ ዝርዝር የወንጀል አንቀጾች አይደሉም። በመሆኑም በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ የተቋሙን ሕጋዊ ሰውነት ጨምሮ የተለያየ ድርሻ ያላቸው አካላት (ዋና አዘጋጅ፣ ሪፖርተር፣ ብሮድካስተር፣ አሳታሚ፣ አታሚ፣ አከፋፋይ ወዘተ) በመኖራቸው የትኛው አካል የትኛውን የአዋጁን ድርጊት ሲፈጽም ምን ዓይነት የወንጀል ተጠያቂነት አለበት የሚለውን ሕጉ በግልጽ ማሳየት አለበት። የወንጀል ተጠያቂነትን በሚደነግገው የአዋጁ አንቀጽ ውስጥ ያልተካተቱ ነገር ግን መካተት ያለባቸው ጉዳዮች ከሚባሉት ውስጥ የጥላቻ ንግግሩን ወይም የሃሰት መረጃውን ያሰራጨው የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ በሚሆንበት ጊዜ ቅጣቱ ከብዶ እንዲጣል የሚያደርግ ድንጋጌ አንዱ ነው። በተጨማሪም የመገናኛ ብዙሃን ለሚፈጽሙት ወንጀል ማረሚያ የማውጣት፣ ተጎጂዎች ካሉ ሃሳባቸውን ያለክፍያ እንዲያቀርቡ የማድረግና እና ሌሎች ግዴታዎችም በተጨማሪነት ሊጣልባቸው ይገባል። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ሌሎች ወንጀል ደንጋጊ አዋጆች እንደሚያደርጉት የወንጀል ክሶቹ የሚቀርቡበትንና የመዳኘት ሥልጣን ያለውን ፍርድ ቤት ሕጉ ሊያመለክት ይገባል።
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
602
ለጥላቻ ንግግር” ሕግ ያስፈልጋል? Written by (ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል) font size decrease font size increase font size Print Email Rate this item1 2 3 4 5 (3 votes) ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ወንድሜ አቶ ሙሼ ሰሙ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የሚያዝያ 5 ቀን 2011 ዓ.ም እትም ላይ “ስለ ሕግ ሳይሆን ስለ ሪፐብሊኩ አምላክ” በሚል ርእስ የጻፈው መጣጥፍ ነው:: (ሙሼን “አንተ” ያልኩት ባለን የ30 ዓመታት ጓደኝነትና ቀረቤታ ምክንያት ነው) የአቶ ሙሼ ጽሁፍ ትኩረት ያደረገው “… አማራጭ ማህበራዊ መድረክ መሆን የሚገባው ፌስቡክ ሜይን ስትሪም ሚዲያ ወደመሆን እየተንደረደረ ነው:: ይህም ሊሆን የቻለው በዋናነት በመንግሥት በኩል ያለው የመረጃ አቅርቦት ክፍትትና መረጃን በሞኖፖል በሚያገኙ የፌስቡክ አጋፋሪዎች ምክንያት ነው፡፡ እነዚህ የፌስቡክ አርበኞች ተገቢ ባልሆነ መንገድ ያገኙትን መንግስታዊ፣ ሀገራዊ፣ ድርጅታዊ፣ ማህበረሰባዊና ግለሰባዊ ሚስጥር ኃላፊነት በማይሰማው መንገድ ፌስቡክ ላይ በመዘክዘክ አደጋ እየፈጠሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በሀገራዊ ሚስጥርና በሕዝብ መረጃ የማግኘት መብት መካከል ያለው ቀይ መስመር ተጥሷል፡፡ … ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የመንግስት ባለስልጣናት ቃለ መሃላ ከፈጸሙባቸው ጉዳዮች አንዱ የሪፐብሊኩን ሚስጥር መጠበቅ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት ሲካሄድ የነበረውን ትግል ለማገዝ የተከፈቱ ኢ-መደበኛ የመረጃ በሮች መዘጋት አለባቸው፡፡ መረጃ ለሁሉም ዜጋ በመደበኛ ተቋም አማካይነት ሊሰራጭ ይገባል፡፡ … ማንም አክቲቪስት፣ ማንም ውስጥ አዋቂ ነኝ ባይ ማወቅ ከሚገባው በላይ መረጃ ሊኖረው አይገባም” በሚሉት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ የጥላቻ ንግግርን ለማስቆም በሚል ሰበብ እየተረቀቀ ያለውን ሕግ በተመለከተም “የፌስቡክ ችግር ምንጊዜም ወቅታዊ ስለሆነ የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት ብቻ የሚፈታ አይደለም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሕግ ጊዜያዊ ችግር ከመቅረፍ ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡ እንዲህ ዓይነት ህግ እንዲያውም ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን የማፈን ውጤት ሊያመጣ ይችላል” የሚል ስጋት እንዳለው ይገልጻል ሙሼ፡፡ እነዚህን የሙሼን ሃሳቦች እኔም እጋራቸዋለሁ:: በተለይም “እንዲህ ዓይነት ህግ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን የማፈን ውጤት ሊያመጣ ይችላል” የምትለዋን ሃሳብ በመያዝ ነው የጽሁፌን ርእስ “የጥላቻ ንግግር ሕግ ያስፈልጋል?” የሚል እንዲሆን ያደረግኩት፡፡ ትኩረቴም በዚሁ ዙሪያ ይሆናል፡፡ በዚህ ጽሁፍ በቅድሚያ በእንግሊዝኛ “Hate speech” የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ትርጉም እናያለን፡፡ የጽንሰ ሃሳቡን ትርጉም ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገሮች ያለውን ተሞክሮ አለፍ አለፍ ብለን ለመጠቃቀስ እሞክራለሁ፡፡ በመጨረሻም በእኛስ ሀገር ምን ቢደረግ ይሻላል? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት ምክረ-ሃሳብ ለማቅረብ ይሞከራል፡፡ “Hate Speech” - የፅንሰ ሃሳቡ ምንነት የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ከሚነሱት አከራካሪ ጉዳዮች አንደኛው “የጽንሰ ሃሳቡ ትርጉም ምንድነው?” የሚል ነው፡፡ በርግጥ በዚህ ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ ወጥነት ያለው፣ ሁሉም ሀገሮች የሚስማሙበት ትርጉም ለማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በየሀገሩ በርካታ ክርክሮች ይደረጋሉ፡፡ የክርክሮቹ መነሻ የጥላቻ ንግግር በሚለው ጽንሰ ሀሳብ ውስጥ ምን ምን ነገሮች ይካተቱ የሚለው ነው፡፡ በእንግሊዝኛ “Hate Speech” የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ወደ አማርኛ ሲመለስ “የጥላቻ ንግግር፣ ክፉ ቃል፣ መጥፎ ንግግር” የሚል ቀለል ያለ ቀጥተኛ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን፡፡ “የጥላቻ ንግግር ማለት በግለሰብ ወይም በቡድን፣ በብሔር፣ በዘር፣ በሃይማኖት ወዘተ. ላይ በማነጣጠር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያስቆጣ ቃልን መወርወር ማለት ነው” የሚል ትርጉምም በአንዳንድ ሰነዶች ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የቀረቡት ሃሳቦች እነዚህን ትርጉሞች መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡ በሌሎች ሀገሮች ያለ ተሞክሮ የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ህግ ማውጣት ያስፈልጋል ወይም አያስፈልግም? የሚል ውዝግብ እንደቀጠለ ቢሆንም፤ የተለያዩ ሀገሮች መንግስታት ጉዳዩን ካሉበት ማህበረሰብ ችግርና ፍላጎት በመነሳት ውሳኔ ያሳለፉበት ሁኔታ ይታያል፡፡ አንዳንድ ሀገሮች የጥላቻ ንግግር ማድረግ ወንጀል ነው በሚል መንፈስ በወንጀለኛ መቅጫ ህጎቻቸው በተደነገገው መሰረት ውሳኔ እንዲያገኝ ማድረግን መምረጣቸው ይስተዋላል፡፡ ሌሎች ሀገሮች ደግሞ የተለየ ህግ በማውጣት ውሳኔ መስጠታቸው ይታያል፡፡ በዚሁ መሰረት አንዳንድ ሀገሮች ያወጧቸውን ድንጋጌዎች አለፍ አለፍ ብለን እንመልከት፡፡ በመሰረቱ ክፉ ቃል መናገርን በየትም ሀገር ያለ ማህበረሰብ አይወደውም፡፡ እናም የጥላቻ ንግግር በማህበረሰብ የተጠላና የተወገዘ ችግር ነው፡፡ አንዳንድ ሀገሮች ይህንን ችግር ለመቅረፍ መጥፎ ንግግር የሚዳኝበት ህግ አውጥተዋል፡፡ ይህንን ህግ ካወጡ ሀገሮች ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው:: ከአውሮፓ ሀገራት እንጀምር፡፡ በፊንላንድ “የጥላቻ ንግግር” በሚለው ፅንሰ ሃሳብ ትርጉም ዙሪያ ሰፊ ውዝግብ አለ፡፡ በአንድ በኩል፤ “የጥላቻ ንግግር ማለት ዘረኛ ቅስቀሳ ማድረግ ማለት ነው የምንል ከሆነ ይህንን በተመለከተ በፊንላንድ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ውስጥ የተካተተ ህግ አለ:: እናም ለብቻው ህግ ማውጣት አያስፈልግም” የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤ “የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ህግ አወጣለሁ ማለት የማይፈለጉ ትችቶና አስተያየቶች እንዳይቀርቡ ዝም ማሰኘት ነው፡፡ ውይይትንም ይገታል፡፡ እናም የጥላቻ ንግግር ማለት ምን ማለት ነው በሚለው ትርጉም ዙሪያ ስምምነት ሳይፈጠር ስለ ‘የጥላቻ ንግግር’ ህግ ማውራት አስቸጋሪ ነው” ይላሉ፡፡ በጽንሰ ሃሳቡ ትርጉም ዙሪያ በፊንላንድ የፓርላማ አባላት መካከልም ስምምነት የለም፡፡ ዘርን፣ የቆዳ ቀለምን፣ ዜግነትን፣ አካላዊ ገጽታን፣ ፆታን፣… መሰረት ያደረገ ስም ማጥፋት፣ ስድብ፣ ጥላቻ፣ ማግለል፣… የመሳሰሉ ወንጀሎችን በተመለከተ በፈረንሳይ የወንጀለኛ መቅጫ እና የፕሬስ ህግ ውስጥ ድንጋጌ ተቀምጧል፡፡ እነዚህ ወንጀሎች ከዘር ማጥፋት ጋር የተያያዙ መሆናቸውም በህጉ ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ፈረንሳይ የተለየ “የጥላቻ ንግግር” ህግ የላትም፡፡ የጥላቻ ቅስቀሳ ማድረግ፣ ስድብ፣ ስም ማጥፋት ወዘተ. በጀርመን የወንጀል ህግ መሰረት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት የሚያስከትል ወንጀል ነው፡፡ አንድ የጀርመን ዜጋ ከጀርመን ሀገር ውጪ ሆኖ “የጥላቻ ንግግር” ቢያደርግ እንኳ በዚህ ህግ መሰረት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡ አይስ ላንድ በምትባል ሀገር በአደባባይ መሳደብ፣ መዝለፍ፣ ስም ማጥፋት፣… ለሁለት ዓመት የእስር ቅጣት ይዳርጋል:: “የጥላቻ ንግግር አሜሪካንን እየመረዛት ነው፣ ይህንን ጥፋት በህግ ድንጋጌ ማቀብ ግን ችግሩን አይፈታውም” ይላሉ የአሜሪካ ሊቃውንት፡፡ በዚህም ምክንያት አሜሪካ በህገ መንግስቷ እውቅና የተሰጠውን ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን ምክንያት በማድረግ የጥላቻ ንግግርን የሚያቅብ የተለየ ህግ አላወጣችም፡፡ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በህንድ ህገ መንግስት በአንቀጽ 19 (1) መሰረት እውቅና የተሰጠው መብት ነው፡፡ በዚሁ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ደግሞ “ስም ማጥፋትን” በተመለከተ ሃሳብን በነፃነት በመግለጽ መብት ላይ “ምክንያታዊ ገደብ” ሊደነገግ እንደሚችል ተቀምጧል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአየር ላንድ ህገ መንግስት ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ተደንግጓል፡፡ ይሁን እንጂ በመገናኛ ብዙሃንም ይሁን በአደባባይ በሚደረግ የጥላቻ ንግግር ላይ ይህ መብት ሊገደብ እንደሚችል እ.ኤ.አ በ1989 በወጣ ህግ ተደንግጓል፡፡ የቤልጅየም ህገ መንግስትም ዘረኝነትንና ጥላቻን በህገ ወጥነት ይፈርጃል፡፡ በእንግሊዝ የጥላቻ ንግግርን ወንጀል የሚያደርጉ የተለያዩ ድንጋጌዎች ወጥተዋል:: ተመሳሳይ የህግ ድንጋጌዎች በሰርቢያ፣ በፖላንድ፣ በሩሲያ፣ በሩማንያ፣ በሲንጋፖር፣ በደበብ አፍሪካ፣ በአውስትራሊያ፣ በብራዚል፣ በካናዳ፣ በዩክሬን፣ በቺሊ፣ በክሮኤሽያ፣ በዴንማርክ፣ በስዊድን ህገ መንግስትና ሌሎች ህጎች ውስጥ የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ተቀምጠዋል፡፡ እንደ ፌስቡክ፣ ጉግል፣ ማይክሮ ሶፍት እና ትዊተር ያሉ ማህበራዊ የግንኙነት አውታሮችን የሚመሩ የኢንተርኔት ባለቤቶች በጥላቻ ንግግር ዙሪያ የሚያራምዷቸው አቋሞች አሏቸው፡፡ እነዚህ ተቋማት የአውሮፓ ህብረትን የስነ-ምግባር ህግ ድንጋጌዎች በጋራ በመቀበል “ፖስት የተደረጉ የጥላቻ ንግግሮችን” በ24 ሰዓት ለማስወገድ ተስማምተዋል፡፡ ምክረ-ሃሳብ - በእኛስ ሀገር ምን ቢደረግ ይሻላል? ወደ እኛ ሀገር እንምጣ፡፡ አቶ ሙሼ ሰሙ ባለፈው ሳምንት ጽሁፉ እንዳመላከተው በየእለቱ እየተፈበረከ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቅን የጥላቻ ንግግር ማቀቢያ ህግ በመደንገግ ማስቆም ይቻላል? የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ህግ ማውጣትስ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚለው ጥያቄ በአግባቡ መፈተሽ ይገባዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በአሜሪካ አንድን ግለሰብ ወይም ቡድን መጥላት ወንጀል አይደለም፡፡ በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር ማድረግም ወንጀል አይደለም፡፡ የጥላቻ ንግግር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ብያኔው በህግ ካልተቀመጠ በስተቀር የጥላቻ ንግግርን ከትችት፣ የጥላቻ ንግግርን አስተያየት ከመስጠት ለይቶ ማወቅ አስቸጋሪ ነው - በአሜሪካ፡፡ በእኛም ሀገር ይህ ሁኔታ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በመሆኑም ይህንን ህግ ከማውጣታችን በፊት ሁለት ነገሮች ቢታዩ ጠቃሚ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ አንደኛ፤ ሃሳብን በነፃነት በመግለጽ መብትና በጥላቻ ንግግር መካከል ያለው ዳር ድንበር ምንድነው? ሃሳብን በነፃነት መግለጽ ማለት የጥላቻ ንግግር ማድረግን ይጨምራል? ሁለተኛ፤ አዲስ ህግ ከማውጣት ይልቅ እንደ ወንጀል የጥላቻ ንግግር በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ምላሽ ሊያገኝ አይችልም ወይ? እዚህ ላይ “ለመሆኑ የአንተ አቋም ምንድነው?” የሚል የግልጽነት ጥያቄ ሊቀርብ እንደሚችል አስባለሁ፡፡ የህግ ባለሙያ ባልሆንም የሀገራችን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አፍ እላፊ፣ ስድብ፣ ዘለፋ፣ ስም ማጥፋት፣… የመሳሰሉ መለስተኛ ወንጀሎች ሲፈጸሙ አጥፊዎች የሚቀጡበት ድንጋጌ እንዳለው ሰምቻለሁ፡፡ በሌላ በኩል፤ እንደ ፌስቡክ ባሉ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ከአፍ እላፊና ከተራ ስድብ የዘለሉ፣ መረን የለቀቁ የጥላቻ ንግግሮችና የበሬ ወለደ ውንጀላዎችና ፍረጃዎች በስፋት እንደሚሰራጩም አስተውያለሁ፡፡ ግን ይህ ሁኔታ በህግ ድንጋጌ ሊቆም ይችላል? አይመስለኝም! እናም በኔ እይታ መፍትሄው ህግ ማውጣት ሳይሆን በማስተማር የህብረተሰቡን አመለካከት መለወጥ፣ መብትና ግዴታውን የተገነዘበ፣ ወንጀልን የሚጸየፍ ዜጋ ለማፍራት መጣር ነው፡፡
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
603
የጥላቻ ንግግር ህጉና ህገ-መንግስቱ! | (በአፊላስ አእላፍ) ለጥቅል ግንዛቤ ይረዳን ዘንድ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል በወጣውና በቅርቡ በሚንስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በተላከው ረቂቅ አዋጅ ክፍል አንድ ላይ፡- << “የጥላቻ ንግግር” ማለት የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ዉጪያዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ ፣ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳስስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈጸም፤ ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ንግግር ነው።›› የሚል የትርጉም ብይን ይሰጣል፡፡ እንዲሁም በረቂቅ አዋጁ ‹‹ “ሃስተኛ መረጃ” ማለት የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት የሆነና ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልጽ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ ንግግር ነው።›› የሚል ፍቺ ይሰጠዋል፡፡ የረቂቅ አዋጁን አላማዎች በተመለከተም ፤ ሰዎች ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ተግባራዊ ሲያደርጉ ሰብዓዊ ክብርን፣ የሌሎችን ደህነነትና ሰላም አደጋ ላይ ከሚጥል ንግግር እንዲቆጠቡ ለማስቻል፤ በማህበረሰቡ ውስጥ እኩልነት እንዲሰፍን፣ መከባበር እንዲኖርና መግባባትና ዲሞክራሲያዊ ስርዐት እንዲጎለብት ለማድረግና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት አደጋ የሆኑ የጥላቻ አመለካከትና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን መስፋፋትን እና ተያያዥ ወንጀሎችን መከላከል እና መቀነስ እንደሆነም ተብራርቷል። እንግዲህ የጥላቻ ንግግር ተግባራት በምን ይገለጻሉ? የሚል መጠይቅ ከተነሳም ረቂቅ አዋጁ ‹‹ ሆነ ብሎ የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ዉጪያዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ ፣ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳስስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈጸም፤ ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል መልእክቶችን መናገር፤ ፅሁፍ መፃፍ፤ የኪነጥበብ እና እደ-ጥበብ ውጤት መስራት፤ የድምጽ ቅጂ ወይም ቪድዮ ማተም፤ ማሳተም ወይም ማሰራጨት፤ መልእክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት፤ ወይም በሌሎች ማናቸዉም መገናኛ መንገዶች ለህዝብ መልእክቱ እንዲደርስ ማድረግ ክልክል “መሆናቸውን በአጽንኦት ይደነግጋል፡፡ የሃሰት መረጃንም በተመለከተ ‹‹ የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው፣ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልጽ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ መረጃን ሆነ ብሎ በማንኛውም መንገድ ማሰራጨትና ለህዝብ እንዲደርስ ማድረግ የተከለከለ ነው። ›› ይላል፡፡ ረቂቅ አዋጁ አንድ ንግግር እንደ ጥላቻ ንግግር ተወስዶ በወንጀል የማያስጠይቅበትን ልዩ ሁኔታም ሲያብራራ፡- ድርጊቱ ለትምህርታዊ ወይም ሳይንሳዊ ምርምር የተደረገ እንደሆነ፤ የሚዛናዊ እና ትክክለኛ ዘገባ፤ በዲሞክራሲያዊ ስርዐት ውስጥ ተቀባይነት ያለው ትችትና የፖለቲካ ንግግር፤ የማስታወቂያ ወይም ማስጠንቀቂያ አካል እንደሆነ፤ በቅን ልቦና የሚደረጉ ሃይማኖታዊ አስተምሮት ወይም አተረጓጎም ከሆነ፤ ንግግሩ የጥሬ ሃቅ ዘገባ ወይም ዜና ከመሆን ይልቅ ወደ ፖለቲካ አስተያየትና ትችትነት ያጋደለ ከሆነ፣ ንግግሩ ቀልድ፣ ስላቅ ወይም ልብወለድ መሆኑ ግልጽ ከሆነ፣ንግግሩን ያደረገው ሰው የመረጃውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ በሱ ሁኔታ ካለ ሰው የሚጠበቀውን ምክንያታዊ ጥረት ያደረገ እንደሆነ እንደ ጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ ተወስዶ በወንጀል እንደማያስጠይቀው በግልጽ ያብራራል። እንዲሁም በረቂቅ አዋጁ ማንኛውም ግለሰብ፤ የሚዲያ ተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች በአዋጁ የተከለከሉ ተግባራትን የፈጸሙ እንደሆነ፤ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስምሮበታል፡፡ እንግዲህ የኛን የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በግርድፉ ካየን ዘንዳ እስቲ ደግሞ አቶ ውብሸት ሙላት ‹‹ መጥላት ላለብን የጥላቻ ንግግር የተጨማሪ ሕግ አስፈላጊነት›› በሚለው መጣጥፋቸው በወፍ በረር የሌሎች ሀገራትን ህግጋትና አካሄድ ያስቃኙናል፡፡ ‹‹ስለጥላቻ ንግግር የአሜሪካ መንገድ፡- አሜሪካ ትልቅ ቦታ የምትሰጠው እሴት ቢኖር ነፃነት ነው፡፡ ነፃ ንግግር ደግሞ አንድም የሰው ልጅ ህልውና አካል ሲሆን፣ በሌላ መልኩ ደግሞ ነፃነትና ዴሞክራሲ፤ ያለ ነፃ ንግግር ምንጊዜም ጎደሎ እንደሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም የአሜሪካ መርህ ነፃነትን ራሱን የሚያጠፋ እስካልሆነ ድረስ፤ ንግግር ላይ ገደብ አይኖርም፡፡ በተለይም ደግሞ የንግግሩ ይዘት፤ ጥላቻን ያዘለ ነው በሚል ሰበብ ብቻ ክልከላ የለም፡፡ ገደብ የሚደረገው፤ ንግግሩ የሚደረገበትን ዐውድ በማየት ይሆናል፡፡ የተደረገው ንግግር የኃይል ድርጊት ላይ የተመሠረተ ሕገወጥ ድርጊት ለማስነሳት ቅርብ ከሆነ፤ ሊገደብ ይችላል ፡፡ ካልሆነ ንግግርን መልሶ በንግግር በመጋፈጥ እንጂ፤ በመገደብና በማፈን ዴሞክራሲ አይሰፍንም የሚል ነው የአሜሪካ አካሄድ፡፡ የብዙኃኑ መንገድ፡- በርካታ አገሮች ከአሜሪካ የተለየ መንገድ ነው የሚከተሉት፡፡ አገሮች ለተለያየ እሴት ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ የእሴቶቻቸው መነሻ ደግሞ የራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡ ለአንዳንዶች እኩልት፤ ለሌሎች ሰብዓዊ ክብር ወይንም ተከባብሮና ተፈቃቅዶ መኖር አሊያም የእነዚህ ቅይጥ ሊሆን ይችላል፡፡ እኩልነትን የሚያስቀድሙት፤ አንድን ግለሰብ ከሌላ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ ስለግለሰቡ ነጠላ ሕይወት ወይንም ምርጫ ሳይሆን ከሌሎች ጋር የሚኖረው መስተጋብር ነው ዋና ማጠንጠኛቸው፡፡ ሰብዓዊ ክብርን የሚመርጡ ደግሞ፤ ማንም ሰው የሌላውን ስም ሳያጎድፍ፣ ሳያንኳስስ፣ ሳያጣጥል፣ ወዘተ. እንዲኖርና መከባበር እንዲሰፍን ይመርጣሉ፡፡ በቡድኖች መካከል ተከባብሮና ተፈቃቅዶ መኖርን የሚመርጡም አሉ፡፡ ስለሆነም ሰብዓዊ ክብርን የሚነካ፣ ተቻችሎና ተፈቃቅዶ የሚኖርን ማኅበረሰብ እንዳይኖር እንከን የሚሆን፣ በማኅበረሰብ መከካል ያለው የባህል ሥሪት አንዱ ከአንዱ የሚበልጥ እንደሆነ የሚሰብክ ንግግር እንዲኖር አይፈቀድም ወይንም አይበረታታም፡፡ የኢትዮጵያንም ሕገ መንግሥት ስናጤነው፤ ትልቁ እሴቱ የግለሰቦች ነፃነት ላይ የተመረኮዘ ሳይሆን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እኩልነት፤ ተከባብሮና ተፈቃቅዶ መኖርን የመረጠ ስለሆነ፤ ነፃ ንግግር ወይንም ሐሳብን በነፃነት መግለጽና ለእነዚህ እሴቶች ተገዥ መሆን ግድ ነው፡፡ ኢትዮጵያም በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች መ/ቤት ታጸድቀዋለች ተብሎ የሚጠበቀው ሕግም የሚጸድቅ ከሆነ ከወዲሁ ትርፍና ኪሳራዎቹን ለመለየት በሁለት ጎራ የሚነሱት መከራከሪያዎችን በጥቂቱ እናንሳ፡፡ ንግግር፣ የጥላቻም ቢሆን ወንጀል መሆን የለበትም ባዮች፡- የመጀመሪያው መከራከሪያቸው ንግግርን ወንጀል በማድረግ ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ፣ ጥላቻ ባለው ንግግር የሚፈጠረውን ጉዳት መታገስ የሚያስገኘው ይበልጣል የሚል ነው፡፡ ንግግርን ማፈን በርካታ መብቶችን እንዲጣበቡ ያደርጋል፣ በርም ይከፍታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም መጥፎ ሐሳብ የሚጠፋውና ማምከኛ ሊሆን የሚችል ተቃራኒ ሐሳብ በማቅረብ እንጂ፤ ንግግሩን በመከልከል አይደለም፤ መንግሥትም የምንናገረውን ነገር ይዘቱን ሊመርጥልን አይገባም፤ ግለሰቦችም ክፉን ከበጎ ለይቶ የማወቅ አቅምም ችሎታም ስላላቸው፤ ይኼንኑ ነፃነታቸውን ማክበር ተገቢ ነው፡፡ ሕግም ቢሆን ክፉ የማሰብንና የመናገርን ባሕርይን ሊቀይር አይችልም፤ ስለሆነም ወንጀል ማድረጉ ፋይዳ ቢስ ነው ይላሉ፡፡ የጥላቻ ንግግር ይከልከል የሚሉት መከራከሪያዎች፡- ጥላቻን ያዘለ ንግግር በብዙ ምክንያት ጠቃሚ አይደለም፣ አስጸያፊ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህ ከሚያቀርቡት ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የንግግሩ ሰለባ የሚሆኑትን የአንድ ቡድን አባላት እንደ ጠላት እንዲቆጠሩ ያደርጋል፤ ለብዙ ነገሮች ተጠርጣሪዎች እንዲሆኑ ያመቻቻል፡፡ ሌላው መከራከሪያ ደግሞ ሌሎች የማኅበረሰብ አባላት በእኩልነት አይታዩም፡፡ ለምሳሌ እንደ ተገንጣይ የሚሳሉ ከሆነ የመገንጠል ፍላጎት ከሌላቸው ጋር እኩል ተደርገው አይታዩም፡፡ ከዚህ ሌላ ደግሞ፣ በማኅበራዊ አቋማቸው ዝቅ ተደርገው እንዲታዩ ያደርጋል፡፡ ከሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር የተረጋጋና ቅንነት የተሞላበት ግንኙነት እንዳይኖር እንቅፋት ይፈጥራል፡፡ በግለሰቦችና በቡድኖች መካከልም ጥርጣሬና ውጥረት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡ አንዱ የሃይማኖት ተከታይ ወይንም የብሔር አባላት የበለጠ ለአገር አሳቢ፤ ሌላውን ጠላት አድርጎ የመሳል አዝማሚያን ይፈጥራል፡፡ ችሎታቸውንና አቅማቸውን በተገቢው ሁኔታ እንዳይጠቀሙ ያደርጋል፤ የተወሰኑ ሰዎችን ባሕርይ ለጠቅላላው የማሳደግ አዝማሚያን ስለሚያበረታታ፤ የቡድኑን አባላት በሙሉ ተጠቂና ሰለባ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ጥላቻ አዘል ንግግር መከልከል አለበት ይላሉ፡፡›› መልካም ወደ ማጠቃለያው ስንመጣ የንግግር ነፃነትን አስመልክቶ ህገ-መንግስታችን ገደብ ሰጥቶታል ወይ የሚል መጠይቅ መንሳቱ ተገቢ ይሆናል፡፡ በሕገ መንግሥታችን አንቀጽ 29(6) ላይ በማያሻማና በግልጽ ቋንቋ እንደተገለጸው፤ ሐሳብን በፕሬስና በማናቸውም መገናኛ ብዙኃን ማንኛውም ሰው ሲገልጽ፤ የሐሳቡ ይዘት ምንም ይሁን ምን፣ ሐሳቡ በመገለጹ የሚያስከትለው ውጤት ምንም ይሁን ምን፣ መከልከል አይቻልም፡፡ በመሆኑም ይዘቱን መሠረት በማድረግ ሐሳብን የመግለጽ ክልከላ አይኖርም ማለት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አንድ ጽሑፍ ታትሞ በመውጣቱ፤ የመንግሥትን ተአማኒነት ያሳጣል በማለት መከልከል አይቻልም፡፡ ጠንከር ስናደርገው ደግሞ፤ አንድ ጽሑፍ መውጣቱ፤ አንድን ብሔር ከሌላው ጋር ሊያጋጭ ይችላል በሚል ምክንያት ክልከላ አይኖርም፡፡ የሚከለክል ሕግም ማውጣትም አይቻልም፡፡ ይህ ደግሞ የሚያስከትለውን ውጤት በማሰብ ብቻ መገደብ አይቻልም ማለት ነው፡፡ በሕግ የሚገደብባቸው ምክንያቶች ‘የወጣቶችን ደኅንነት የሚያናጉ፣ የግለሰብን መብት የሚጥሱና ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ፤ የአደባባይ መግለጫዎችን ማድረግ፣ የጦርነት ቅስቀሳ ማድረግ’ ብቻ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ከአራቱ ውጪ፤ በሌሎች ምክንያት ፈጽሞ የሐሳብን ነፃነትን፤ በማናቸውም የፕሬስ ውጤቶችም ይሁን በኤሌክትሮኒክስ መንገድ እንዳይገለጹ መከልከል ወይንም ወንጀል ማድረግ ፈጽሞ ሕገ -መንግሥቱን መጣስ ነው፡፡ ከላይ የተገለጹትን ግቦች ለማሳካት ሲባል ብቻ ነው የንግግር ነፃነትን መገደብ የሚቻለው፡፡ ባጭሩ የጥላቻ ያዘሉ ንግግሮችን ለመገደብ መነሻዎቹ እነዚህ ብቻ መሆን አለባቸው፡፡ ባጠቃላይ በዚህ ጽሁፍ ለማሳየት የተሞከረው በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ‹‹የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን መከላከል›› ረቂቅ አዋጅ ከሌሎች ሀገራት ተመክሮና ከህገ-መንግስታችን አንጻር ያለውን አዎንታዊና አሉታዊ መስተጋብር ለማሳየት ነውና አንባቢው የራሱን ሃሳብና አተያይ ያክልበት ዘንድ በመሻት ነው፡፡
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
604
ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በተመለከተ የቀረበ አዋጅን አፀደቀ Published: 86 days ago የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን አፀደቀ። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በዛሬው እለት አካሄደ። ምክር ቤቱ በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል። አዋጁ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ስምሪት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብዓዊ ክብር እና ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ በተለይም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በህብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለሀገርም ስጋት እየደቀኑ በመሆናቸው እንዲሁም እነዚህን ችግሮች አሁን ባሉት ህጎች መፍታት የማይቻል በመሆኑ መዘጋጀቱ ተገልጿል። የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ዴሞክራሲያዊ ውይይት እና ክርክር ለማድረግ እንቅፋት በመሆኑ ከብሄር እና ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ የጥላቻ ንግግር እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨትን እንዲሁም ዘርን፣ ጾታን እና አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ተገልጿል። እንዲሁም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን በህግ መከልከል አስፈላጊ በመሆኑ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱም ተነግሯል። የምክር ቤቱ አባላትም በአዋጁ ላይ ያላቸውን ሃሳብ እና አስተያየት የገለጹ ሲሆን፥ ለአብነትም ይህ አዋጅ የዜጎችን ሃሳብ በነጻነት የመግለጽ መብት የሚጋፋ እንደሆነ ያነሱ ሲሆን፥ የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቶበታል። በዚህም አዋጁ በህገ-መንግስቱ ላይ ከተቀመጠው የመናገር መብት ጋር እንደማይቃረን፣ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 29 (6) እና (7) ከተቀመጡት ገደቦች ውስጥም አንዱ ምክንያት ሰብአዊ ክብርን መጠበቅ ሲሆን፥ የጥላቻ ንግግር ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ዋነኛው በመሆኑ ከተቀመጠው ገደብ ጋር የሚገናኝ መሆኑ ምላሽ ተሰጥቶበታል። ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በ23 ተቃውሞ እና በ2 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
605
የጥላቻ ንግግር አገር እንዳይበትን ፖለቲከኞች ተወያይተው የፖለቲካ መፍትሄ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ተባለ June 29, 2019 behabtu Share on FacebookShare on Twitter ሰኔ 22/2011 የጥላቻ ንግግርና ጽንፈኝነት ኢትዮጵያን ወደ ትርምስ እንዳይከት የፓለቲካ ልሂቃን በሰከነ መንፈስ በመወያየት የሚያግባባ መፍትሔ ማምጣት እንደሚገባቸው ምሁራን አሳሰቡ። የኢዜአ ሰሞኑን በአማራ ክልልና በአዲስ አበባ ተፈጽመው በነበሩ የከፍተኛ አመራሮች ግድያን የአገሪቱን የፖለቲካ አቅጣጫ ወዴት ይወስደዋል? በየማኅበራዊ ሚዲያውና በተለመደው ሚዲያ ከየአቅጣጫው የሚሰነዘሩ የጥላቻ ንግግሮች ምን እያስከተሉ ነው? በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከምሁራን ጋር ውይይት አድርጓል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ፤ ”የጥላቻ ንግግር የአገራችን ፖለቲካ ወዴት ያመራዋል የሚለውን ጥያቄ ከመመለሴ በፊት ሰሞኑን በአገራችን የፖለቲካ መሪዎች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት አንድምታን ከመናገር እጀምራለሁ” ይላሉ። ድርጊቱ ኢትዮጵያዊ አንድነትንና ማዕከላዊነትን በመጻረር የተፈጸመ እንደሆነ በመግለጽ አውግዘውታል። ያስከተለው በአንድ በኩል መንግሥት በሚከተለው አዲስ የፖለቲካ አካሄድ የተዳከመ በመምሰሉና የለውጥ ሃይል ሆነው እየሠሩ የነበሩ የጥቃቱ ሰለባ በሆኑት አመራሮች የተነዛው የጥላቻ ዘመቻ ውጤት ነው ይላሉ የፍልስፍና መምህሩ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ። ”ኢትዮዽያ ክልል ብቻ አይደለችም መንግሥትም” አላት የሚሉት ዶክተር ዳኛቸው፤ በተለይ በትግራይ፣ በአማራና ኦሮሚያ አካባቢ በልዩ ሃይል ስም የሚታየው የጸጥታ ሃይል አሰላለፍ የፌዴራል መንግስቱን እይተፈታተነ በመሆኑ በሕግ አግባብ መስተካከል አለበት ይላሉ። በአንድ ሀገር ውስጥ ልዩነት ሊኖር ይችላል ልዩነቱ ግን በመሳሪያ ሳይሆን በውይይትና በክርክር እንዲሁም በመደማመጥ ሊፈታ ይገባል እንጂ የከፋው ሁሉ ነፍጥ እያነሳ እልቂት መፍጠር አይገባም የሚሉት የፍልስፍና መምህሩ፤ አዲሱ የለውጥ ሃይል የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋቱ ሃሳብ ያለ ገደብ ሲገለጽ እየተመለከትን ነው በማለት ያስረዳሉ። ”የኢትዮዽያ ሕዝብ ማከላዊነትን ይፈልጋል ጽንፈኝነትን አይወድም” የሚሉት ዶክተር ዳኛቸው ”የፖለቲካ ውይይት ባለመኖሩ ሁሉም የኔነውና እኔነኝ ልክ የሚል ትርክት በማብዛቱ ጽንፈኝነት ነግሷል” ሲሉ አስረድተዋል። ፖለቲከኛውና የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የኢትዮዽያ ፖለቲካ በህመም ላይ በመሆኑ የፖለቲካ መፍትሔ ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል። አሁን በአገሪቱ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰጥቶ መቀበልና በጋራ መግባባት ላይ የተመሰረተ አንድ ሁለት ተብሎ ሊቆጠር የሚችል መግባቢያ ባለመኖሩ ዋልታ ረገጥ በሆኑ ትርክቶች የተሞሉ ናቸው የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ ፤ የአገሪቱን የፖለቲካ ህመም የሚፈውስና ሁሉን አቀፍ ስምምነት መቀመጥ ይኖርበታል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽንት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ዘነበ በየነ የኅብረተሰቡን ማስተዋልና ጥበብ ባይኖር ኖሮ በማህበራዊና በመደበኛው ሚዲያ የሚሰራጨው የጥላቻ ንግግር አገሪቱን ይበትናት እንደነበር ገልጸዋል። በመሆኑም የጥላቻ ንግግርን ከመከላከል ጎን ለጎን የህብረተሰቡን አብሮ የመኖር እሴት በመጠበቅና በማጥናት ይበልጥ ማዳበር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
606
1 አዋጅ ቁጥር…/2012 የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ሆን ተብሎ የሚሰራጩ የጥላቻና ሃሰተኛ ንግግሮችን በሕግ መከልከልና መቆጣጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኝቱ፤ የጥላቻ ንግግርና የሃስተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ስምረት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለሃገራዊ አንድነት፣ ለሰብአዊ ክብር፣ ለብዝሃነትና ለእኩልነት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ፤ መሰረታዊ መብቶች ላይ የሚጣሉ ገደቦች በሕግ የተደነገጉ፣ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውን አላማ ለማሳካት አስፈላጊ የሆኑ፣ተመጣጣኝና በጠባቡ የተበጁ መሆን እንዳለባቸው በመገንዘብ፤ በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት እንቀፅ 55(1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ 1. አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “የጥላቻ ንግግርን እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር …/2012” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። 2. ትርጉም የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካለሆነ በቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡- 1/ “ንግግር” ማለት በቃል፣ በጽሑፍ፣ በምሥልና ሥዕል፣ በቅርጻ ቅርጽ እና በሌሎች ተመሳሳይ መንገዶች መልእክትን የማሰራጨት ተግባር ነዉ፡፡ 2 2/ “የጥላቻ ንግግር” ማለት በአንድ ሰዉ ወይም የተወሰነ ቡድን ላይ ያነጣጠረ፣ ብሄርን፡ብሄረሰብንና ህዝብን፣ ሀይማኖትን፤ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ጥላቻን፣ መድሎን ወይም ጥቃትን የሚያበረታታ ንግግር ነው። 3/ “ሃስተኛ መረጃ” ውሸት የሆነና የመረጃውን ውሸት መሆኑን በሚያውቅ፣ ወይም መረጃውን የሚያሰራጨው ሰው ካለበት አጠቃላይ ሁኔታ አንጻር የመረጃውን ሃሰተኝነት ሊያውቅ ይገባ ነበር የሚያስብል በቂ ምክንያት እያለ የሚሰራጭ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ከፍ ያለ ንግግር ነው። 4/ "ብሮድካስት ማድረግ” ማለት በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዥን ሥርጭት ማድረግ ነዉ፡ ፡ 5/ "ማህበራዊ ሚዲያ" ማለት ሰዎች መልዕክት ለመለዋወጥ ፤ ትስስር ለማዳበር፤ ሀሳብ ለመጋራት የሚጠቀሙበት በኢንተርኔት አማካኝነት በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች መረጃ የሚደርስበት፣ ወይም ማህበራዊ መስተጋብር የሚስተናገድበት መንገድ ነዉ፡፡ 6/ “የህትመት ሚድያ” ማለት ለህዝብ ስርጭትየተዘጋጀ ማንኛውም የህትመት ወጤት ነው። 7/ "ሰዉ" ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ ሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው። 8/ ማንኛዉም በወንድ ጾታ የተገለጸ ለሴት ጾታ ያገለግላል፡፡ 3. አላማ የአዋጁ አላማዎች: 1/ ሰዎች ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ሲጠቀሙ ግጭት ወይም ሁከትን የሚቀሰቅስ ወይም ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ በግለሰብ ወይም በተለየ ቡድን ላይ ጥላቻ ወይም መድልዎ የሚያስፋፋ ንግግር ከማድረግ እንዲቆጠቡ ማድረግ፤ 2/ መቻቻልን፣ የዜጎች ውይይትና ምክክርን፣ መከባበርና መግባባትን ማበረታታትና ዲሞክራሲያዊ ስርዐትን ማጎልበት፤ 3 3/ የጥላቻ ንግግርን፣ የሃሰተኛ መረጃና ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች የውሸትና አሳሳች መረጃዎችን ስርጭትና መበራከትን ለመቆጣጠርና መግታት ነው። 4. የጥላቻ ንግግር ስለመከልከሉ የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚድያ በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪድዮ ማሰራጨት የተከለከለ ነው፡፡ 5. የሃሰት መረጃን ማሰራጨት ስለመከልከሉ የሃሰት መረጃን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚድያ በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪድዮ ማሰራጨት የተከለከለ ነው፡፡ 6. ልዩ ሁኔታ 1/ የዚህ አዋጅ አንቀፅ 4 እና 5 እንደተጠበቁ ሆኖ አንድ ንግግር እንደ ጥላቻ ንግግር ወይም እንደ ሃሰት መረጃ ተወስዶ ማሰራጨት የማይከለከለው፡- ሀ) የትምህርታዊ ወይም ሳይንሳዊ ምርምር አካል እንደሆነ፤ ለ) የዜና ዘገባ፤ ትንታኔ ወይም የፖለቲካ ትችት አካል እንደሆነ፤ ሐ) የኪነጥበበ ፣ ትወና ወይም መሰል የስነጥበበ ውጤት ከሆነ፣ መ) የሃይማኖታ አስተምህሮት አካል እንደሆነ ነው። 2/ የዚህ አዋጅ አንቀፅ 5 እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ንግግር እንደ ሃሰተኛ መረጃ ተወስዶ የማይከለከለው ንግግሩን ያሰራጨው ወይም ያደረገው ሰው የመረጃውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ በሱ ሁኔታ ካለ ሰው የሚጠበቀውን ምክንያታዊ ጥረት ያደረገ እንደሆነ ወይም ንግግሩ የጥሬ ሃቅ ዘገባ ወይም ዜና ከመሆን ይልቅ ወደ ፖለቲካ አስተያየትና ትችትነት ያጋደለ ከሆነ ነው። 7. የወንጀል ተጠያቂነት 1/ ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀፅ 4 መሰረት የተከለከለዉን የጥላቻ ንግግር ያደረገ እንደሆነ እስከ ሶስት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከብር 100,000 ያልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፡፡ 2/ በጥላቻ ንግግሩ ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ አምስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ይሆናል። 4 3/ ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀፅ 5 መሰረት ክልከላ የተደረገበትን ተግባር የፈጸመ እንደሆነ እስከ አንድ አመት በሚደርስ በቀላል እስራት ወይም ከብር 50,000 ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፡፡ 4/ የጥላቻ ንግግር ወይም የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ወንጀሉ የተፈጸመው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚድያ ገጽ ከሆነ ወይም በብሮድካስት አገልግሎት ወይም በየጊዜው በሚወጣ የህትመት ውጤት ከሆነ ቅጣቱ አስከ ሶስት አመት የሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከብር 100,000 ያልበለጠ መቀጮ ይሆናል፡፡ 5/ ሃሰተኛ መረጃ በመሰራጨቱ ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ ወይም የተሞከረ ከሆነ፣ ሁከት ውይም ግጭት የተከሰተ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይሆናል። 6/ በጥላቻ ንግግር ውይም በሃሰተኛ መረጃ ወንጀል መፈጸም ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት ያልተፈጸመ ወይም ያልተሞከረ ከሆነ፣ ሁከት ውይም ግጭት ያልተከሰተ እንደሆነ እና ጥፋተኛዉን ለማረም የተሻለ ነው ብሎ ሲያምን ፍርድ ቤቱ በእስራት ምትክ የግዴታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራን በአማራጭ ቅጣትነት ሊወስን ይችላል። 7/ በዚህ አዋጅ የተከለከሉት ተግባራት የተፈጸሙት በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት ከሆነ በወንጀል ሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተካተቱት በመገናኛ ብዙሃን አማካይነት የሚደረጉ ወንጀሎችን የተመለከቱ ድንጋጌዎች( አንቀጽ 42-47) ተግባራዊ ይሆናሉ። 8. የተቋማትና የአገልግሎት ሰጪዎች ሀላፊነት 1/ ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመቆጣጠርና ለመግታት ጥረት ማድረግ አለበት። 2/ ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት የጥላቻ ንግግርን ወይም የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን የተመለከተ ጥቆማ ሲደርሰው በፍጥነት ይህን መሰል መልዕክቶችን ወይም ንግግሮችን ከአግልግሎት አውታሩ ሊያስወግድ ይገባል። 5 3/ ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ(1) ና (2) የተንደነገገውን ግዴታውን ለመወጣት የሚያስችለው አሰራርና ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል። 4/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1-3) የተደነገገውን ግዴታ አለመወጣት ሊያስከትል የሚችለው የፍትሃ ብሄር ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በዚህ አንቀጽ የተቀመጠውን ግዴታቸውን ባግባቡ መወጣታቸውን እየተከታተለ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ረፖርት ያዘጋጃል። 5/ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የሃሰት መረጃ ስርጭትና ጉዳትን ለመከላከል የሚረዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት ተግባራዊ ያደርጋል። 6/ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል የሚረዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት ተግባራዊ ያደርጋል። 7/ የተቋማትና የአገልግሎት ሰጪዎች ሀላፊነትን ዝርዝር የሚደነግግ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊወጣ ይችላል። 9. ስለተሻሩ ህጎች የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ የወንጀል ህግ አንቀጽ 486 በዚህ አዋጅ ተሽሯል። 10.አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ አዲስ አበባ-----ቀን----2012 ዓ/ም ሳህለወርቅ ዘዉዴ የኢፌድሪ ፕሬዚደንት
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
607
በኢትዮጵያ ለሰዎች መገደል ምክንያት የሆነውን የጥላቻ ንግግር፣ ህግ ይገድበው ይሆን? 12 ኤፕረል 2019 ይህንን ለሰው አጋራ Facebook ይህንን ለሰው አጋራ Messenger ይህንን ለሰው አጋራ Twitter ይህንን ለሰው አጋራ ኢሜይል ያጋሩ መሀመድ አደሞ፣ አብዱ አሊ ሂጂራና ዝናቡ ቱኒ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በማህበረሰቡ ዘንድ መጠራጠርና ፍራቻ ነግሶ የሰው ልጅ በአደባባይ የተሰቀለበት፣ ለምርምር የወጡ የዩኒቨርስቲ ምሁራን ተወግረው የተገደሉበትና እንዲሁም ሌሎች ለመስማት የሚሰቀጥጡ ዜናዎች የተሰሙበትና በአገሪቱም ላይ ጠባሳን ትቶ አልፏል። በተለያዩ በይነ መረቦችና ማህበራዊ ገፆችም ላይ የተለያዩ ማህበረሰቦችን ለጥቃት የሚያነሳሱ፣ የግድያንና የመፈናቀልን የሚቀሰቅሱ መልዕክቶች በተለያዩ ጊዜያት ይስተዋላሉ። በዚህ ደግሞ ተራ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ማህበረሰቡን የሚመሩ የመብት አራማጆች ማህበረሰቡን እርስ በርስ በማጋጨት በመወቀስ ላይ ናቸው። •መከፋፈል ያጠላበት ጉዞ አድዋ •"የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ" መሐመድ አደሞ የአንዳንድ የመንግሥት ኅላፊዎችም ንግግር ከአውድ ውጭ እየተወሰደ በተፈጠረው መከፋፈል ላይ ቤንዚን በእሳት ላይ እንደ ማርከፍከፍ ሆኖ ለአንዳንድ ጥላቻዎችና መፈራቀቆች መቀጣጠል ምክንያት ሆኗል። ለተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መልሶች በሙሉ ጥላቻንና ጥቃትን ምላሽ ያደረጉና ሃይ ባይ ያጡ መልዕክቶች ለፖለቲካዊ ቀውስ ምክንያት እንዳይሆኑ ያሰጋል። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ግድያ፣ ጦርነት፣ ዘር ማጥፋት እንደተለመደ ነገር ተደርጎ መቀስቀሱ ቀጥሏል። በዚህም ምክንያት ሀገሪቷ ውስጥ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ተፈናቅለዋል፤ በርካቶች ለሞት ሲዳረጉ እንዲሁም ለብዙዎች በስጋት ውስጥ ለመኖር ምክንያት ሆኗል። • ብሔርን ከመታወቂያ ላይ ማስፋቅ. . . የተለያዩ ሰብአዊ መብት ድርጅቶችና እንዲሁም የጠቅላይ አቃቤ ህግ ጥናት እንደሚያሳየው ለዚህ ሁሉ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የጥላቻ ንግግር እንደሆነ ያሳያል። ይሄንንም በጄ ለማለት ከሰሞኑ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ረቂቅ አዋጅ ወጥቷል። ረቂቅ ህጉ ምን ይዟል? ረቂቅ አዋጁ የጥላቻ ንግግር ትርጉም ብሎ ሲያስቀምጥ "ሆን ብሎ የሌላ ግለሰብን፣ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሔርን፣ ሃይማኖትን፣ ቀለምን፣ ፆታን አካል ጉዳኝነትን ዜግነትን፣ ስደተኝነትን፣ ቋንቋን፣ ውጫዊ ገፅታን መሰረት በማድረግ ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል የሚያንኳስስ፣ የሚያስፈራራ፣ መድልዎ እንዲፈፀም፣ ወይም ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል መልዕክቶችን በመናገር፣ ፅሁፍ በመፃፍ፤ በኪነ ጥበብ እና እደ ጥበብ፣ የድምፅ ቅጂ ወይም ቪዲዮ፣ መልእክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨትን ይመለከታል።" ከዚህም በተጨማሪ ረቂቅ ሕጉ የሐሰት መረጃን በተመለከተም "የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው፤ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልፅ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ መረጃን ሆን ብሎ በማንኛውም መንገድ ማሰራጨትና ለህዝብ እንዲደርስ ማድረግ" እንደሆነ አስቀምጧል ። እነዚህን ድርጊቶች የፈጸመ ሰው በህጉ በተቀመጠው አግባብ መሰረትም በእስራትና በገንዘብ መዋጮ እንደሚቀጣ አስቀምጧል። ምንም እንኳን የጥላቻ ንግግር አደገኛነት ሳይታለም የተፈታ ነው ቢባልም መፍትሄው አዲስ ህግ ማውጣት ነው ወይ? ለሚለው ብዙዎች የራሳቸውን ጥርጣሬ ያስቀምጣሉ። አዲስ ህግ ያስፈልግ ይሆን? በተለይም ህግ አውጪውና፣ ህግ አስፈፃሚው ወይም የፍትህ ሰጪ መዋቅሮች ነፃ ባልሆኑበት መንገድ እንዲህ አይነት አዲስ ህግ ማስተዋወቅ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚበልጥ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነትን የሚመለከተውን አንቀፅ 19ን ከመፈረም በተጨማሪ ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብትን አስመልክቶ አንቀፅ 29 በሕገ መንግሥቱ ተካቷል። እንደ አንቀፅ 29 ከሆነ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በፅሁፍ ወይም በህትመት፤ በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ሀሳብ የመሰብሰብ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን የሚያካትት ነው። በዚሁ አንቀፅ ላይ ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ ቅስቀሳዎችን እንዲሁም ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትም አንዱን ከአንዱ በማጋጨት ሌሎችንም ሰዎች አደጋ ላይ የሚጥል ሆኖ ከተገኘ በህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል በግልፅ አስቀምጧል። •"ምርኩዜን ነው ያጣሁት" የካፒቴን ያሬድ አባት ይሄን ህግ ማስከበር እንዲሁም ማሻሻል እየተቻለ ለምን አዲስ ህግ ማውጣት አስፈለገ? የህግ ባለሙያውና ጋዜጠኛ አቶ አብዱ አሊ ሒጂራ ጥያቄ ነው። "አንቀፅ 29 የጥላቻ ንግግር ባይለውም ፕሮፓጋንዳን ሰውን ማንኳሰስን፤ ለዘር ማጥፋት የሚያነሳሳን 'በለው በለኝና ላሳጣው መድረሻ' የሚልን ነገር አልታገስም ይላል። የህጎቹ መሰረት የተደላደለ ቢሆንና ያሉትን ህጎች ህይወት የሚሰጥ ፍርድ ቤት ቢኖረን እንኳን ለራሳችን ለሌላ በተረፍን ነበር" ይላሉ። የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ በበኩላቸው ይህ ህግ የተረቀቀው በዘፈቀደ ሳይሆን አገሪቷ ያለችበትን ውጥንቅጥ ምክንያት መሰረት በማድረግ ጥልቅ ጥናት ከተደረገ በኋላ ነው ይላሉ። የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት ጠንቅ ነው የሚሉት አቶ ዝናቡ "የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን ተከትሎ በርካታ የሃገራችን ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው፤ በርካታ ንብረት ወድሟል፤ ህይወትም ጠፍቷል። ይሄ መከላከልም ይጠይቃል" ይላሉ። ከዚህም በመነሳት ከዚህ በፊት የነበሩት ህጎች የወንጀል ጉዳይን የሚያመላክቱ ስላልነበሩ የዚህን ረቂቅ ህግ አስፈላጊነት አበክረው ይናገራሉ። ለሰዎች መገደል ምክንያት የሆነውን የጥላቻ ንግግር ህግ ይገድበው ይሆን?Image copyrightGETTY IMAGES አቶ አብዱ በዚህ አይስማሙም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ህግ በቂ ነው ባይ ናቸው። "ካወቅንበት አሁን ያለው ህግ ይበቃናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር አዲስ መፍትሄ ማምጣት አያስፈልገንም" በማለት። ረቂቁ ሕጉ ነፃነትን ይገድብ ይሆን? ምንም እንኳን በሀገሪቱ የሰፈነውን የጥላቻ ንግግር አስፈሪነት አቶ አብዱ ባይክዱትም ይሄንን የሚከላከል ሕግ ለማውጣት በምታደርጋቸው ጥረቶች ኢትዮጵያ በዘርፉ የተሳካላት ሆና እንደማታውቅ አጥብቀው ይከራከራሉ። እንደ ምሳሌነትም የሚያነሱትም ብዙዎችን ለእስር የዳረገውና፤ ብዙ ጋዜጠኞችንም የመናገርም ሆነ የመፃፍ ነፃነታቸውን ሸብቦ ያሸማቀቀውን የፀረ ሽብር ህጉን ነው። "የፀረ ሽብር ህጉ ቦርቃቃ ነው፤ ለትርጉም የሚመች ነው" የሚሉት አቶ አብዱ የጥላቻ ንግግሩም ለትርጉም ክፍት የሆነና አደገኛም እንደሆነ ይገልጻሉ። "የፈለገው ፖሊስ ወይም አቃቤ ህግ ጋዜጣ አንስቶ ይሄማ የጥላቻ ንግግር ነው ቢል ፍርድ ቤት 'እልል' ብሎ የሚቀበልበት ሁኔታ ነው ያለው" ይላሉ። በተለይም የፀረ ሽብር ሕጉ ፕሬሱን የማጥቂያ መንገድ አድርገው የሚወስዱት ባለሙያዎችም የፀረ ሽብር ሕግ ከመውጣቱ በፊት አሸባሪነትን የሚከላከል ሕግ ቢኖርም አጠቃላይ ሂደቱ ሚዲያን ዝም የማሰኘት ነበር ባይ ናቸው። "ሽብር ማለት እኔን የጠላ ሁሉ አሸባሪ ነው የሚል ትርጉም ተሰጥቶት፤ አንድ ቦታ ላይ ያለ ሰው ድንገት ሊቆጣ ይችል ይሆናል፤ ሌላው ሰው እንዲህ ይተረጉምብኝ ይሆን እንዴ? ብሎ እስከመሸማቀቅ በሚል ነፃነትን የገደበ፤ ፕሬሱንም ያሸማቀቀ ነው" ይላሉ የሕግ ባለሙያው አብዱ። የጥላቻ ንግግር ህግ ወጣም አልወጣም ማንኛውም የንግግር ነፃነት ገደብ እንዳለው የሚናገሩት አቶ አብዱ ከኢትዮጵያ ልምድ በመነሳትም "ገደብ ይጣልበታል ሲባል ገደቡ ገደብ የሌለው ይመስላቸዋል" ይላሉ። ለአቶ አብዱ ዋነኛው አስጊ ነገር የንግግር ነፃነትን የሚገድብ መሆኑ ነው። የንግግር ነፃነት የተፈጠረው ሰውን ለማወደስ ብቻ ሳይሆን ለማስቀየምም ወይም ለማስደንገጥ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አብዱ ኢትዮጵያ በጣሊያን በተወረረችበት ጊዜም ሞሶሎኒ ለዘላለም ይኑር፤ ጣልያን ጥሩ ናት የሚሉ ንግግሮች እንደነበሩ ያወሳሉ። "ሞሶሎኒ ለዘላለም መኖር የለበትም፤ ሞሶሎኒ ፋሽስት ነው ለማለት ነው የንግግር ነፃነት የሚገባው። የንግግር ነፃነት ሰው ሊያስቀይም ይችላል ይህ ግን አደጋ እንዳያስከትል ይሄንን ከህግ ይልቅ በወግ በባህል ነው ልንገነባው የምንችለው" ይላሉ። አቶ ዝናቡ በበኩላቸው የተወሰኑ ግለሰቦችንም ሆነ የተወሰነ ህብረተሰብን ክፍል ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ለመገደብ ታስቦ የተዘጋጀ ምንም መነሻ መሰረት የሌለውና ከፀረ ሽብር ሕጉ ጋር በምንም እንደማይገናኝ ይናገራሉ። "ይህ ረቂቅ ህግ ዜጎች ሰብአዊ ክብራቸው እንዲጠበቅ የዜጎች አብሮ በመኖር፣ በእኩልነት፣ በአንድነት፣ በሰላማቸው ላይ አደጋ እያመጣ ያለውን ነገር እንዲጠብቅ የሚያስችል አቅም ያለው ነውም" ይላሉ። አቶ አብዱ ግን በተለይም የሕግ አውጭ፣ ተርጓሚውና አስፈፃሚዎች ነፃ ባልሆኑበትና "ለይተው የማያውቁትን ሕግ ማስታጠቅ ማለት ትክክል አይደለም፤ ሕግ የሚያወጡ አካሎቻችን ሁሉ አንካሶች ናቸው። ህግ የማውጣትም፤ ህግ የማስፈፀምም ህመምተኞች ነን፤ መጀመሪያ ከእሱ መፅዳት ያስፈልጋል" ብለዋል። የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት የተለያዩ ግብአቶችን በመሰብሰብ ላይ እንደሆኑ የሚናገሩት አቶ ዝናቡ በሰከነ መልኩ በደንብ ግብአት ተወስዶ እንደሚፀድቅ ይናገራሉ። የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ጠንቅ እንደሆነ በመረዳትም የሌሎች ሃገራትን መነሻ አድርገው ሕጉ እንደተረቀቀ አቶ ዝናቡ ይናገራሉ። ምንም እንኳን የረቂቅ ህጉ መነሻ የተወሰደው ከተለያዩ ሃገራት ስለሆነ ጥሩ ነው የሚል መከራከሪያ ቢያቀርቡም አቶ አብዱ በበኩላቸው "አፋኝ ተብሎ የሚጠራውም የፀረ ሽብር ሕጉም የተወሰደው ከእንግሊዝ ነው" ይላሉ። መፍትሄ ለአቶ አብዱ ከህግ በላይ ዋነኛው መፍትሄ ንግግር ነው ይላሉ። "ጋዜጠኞችና የመብት አራማጆች ነፃነቱ የሚጠይቀውን ኅላፊነትና ጨዋነት ሊኖራቸው ይገባል። ዝም ተብሎ አፍ ያመጣው ነገር ሁሉ አይነገርም። ስንናገር የምንናገረው ነገር ምን ተጨማሪ እሴት አለው መባል አለበት ይላሉ። በከፍተኛ ሁኔታ ማህበረሰብ በተፈራቀቀበት ሁኔታ ዋነኛው ነገር ህዝብን ማቀራረብ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ አብዱ መከባበርና መቻቻል ባህል ከሆነ በኋላ ሕግ ማውጣት እንደማያስፈልግም አፅንኦት ሰጥተው ይሞግታሉ። •ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰዎች ምን ይጠብቃሉ? "ጨዋነት የሚፈጠረው ህግ በማውጣት አይደለም። ማክበር፣ መከባበርና መቻቻል ባህል ከሆነ በኋላ ሕግ ማውጣት አያስፈልግም። ወደ ህግ የሚኬደው እኮ ሌሎች ማህበራዊ ተቋማት ሲከሽፉ ነው" ብለዋል። አቶ ዝናቡ በበኩላቸው የጥላቻ ንግግርንም ሆነ ሐሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት በህግ ብቻ የሚገታ ሳይሆን ህዝቡ ያሉትን መልካም የጋራ እሴቶች ማዳበርና ከዚህ ባሻገር ሲሆን የህግ ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባ ይናገራሉ። የኦፕራይድ መስራች፤ የቀድሞ የአሜሪካ አልጀዚራ ኤዲተር መሐመድ አደሞ በበኩሉ ዲሞክራሲ ሂደት እንደመሆኑ መጠን ሁሉ ነገር በአንድ ምሽት እንደማይመጣ ይናገራል። ያለውን የዲሞክራሲ ሂደት ለማስቀጠል የጥላቻ ንግግር ሕግ ሊበጅለት እንደሚገባ የሚያስረዳው አቶ መሐመድ ሁሉን የሚያስማማና ሁሉም የእኔ ነው የሚለውና ተቀባይነት ያለው ህግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን ያሰምርበታል። "ሁሉንም ነገር ለመንግሥት መተው ግን ተገቢ አይደለም። መንግሥት ሁሉን አካታቶ፣ ረቂቁ ላይም የሲቪል ማህበራቱ፣ ጦማርያን፣ ጋዜጠኞችና የሕግ ባለሙያዎች ቢወያዩ፤ መንግሥት እንደመጨቆኛ መሳሪያ እንዳይጠቀምበት መከታተል ያስፈልጋል" ይላል። ይህም ሁኔታ ሕጉን የመንግሥት ብቻ ነው ብሎ ከመግፋት እንደሚታደገውና የሁላችንም ነው የሚል ስሜት እንዲኖረው እንደሚያደርግ ይናገራል።
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
608
የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ Anonymous የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ 12/30/19 9:46 AM የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅአጭር ማብራርያ 1. መግቢያ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት ዕውቅና ከተሰጣቸው መብቶች አንዱ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ነው፡፡ ይህ መብት በሕገ-መንግስቱ ብቻ ሣይሆን ሕገ-መንግስቱን ለመተርጐም እንደ አጋዥ ተደርገው በሚቆጠሩና የሃገራችን የሕግ ስርዓት አካል በሆኑት አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶችም የተካተተ ነው፡፡ ሕገ-መንግስቱንና እነዚህን አለም አቀፍ ስምምነቶች ስንመለከት፣ እንዲሁም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በማክበር ረገድ ጥሩ ሥም ያላቸውን ሃገራት ልምድም ስንመለከት ይህ መብት ፍፁም የሆነ መብት ሣይሆን፣ ገደብ ሊጣልበት የሚችል መብት መሆኑን እንረዳለን፡፡ በመብቱ ላይ የሚጣለውን ገደብ ዓላማ፣የገደቡን አስፈላጊነትና ተመጣጣኝነትን በጥንቃቄ መርምሮና አመዛዝኖ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ በሕግ ገደብ ማስቀመጥ በዲሞክራሲያዊ ሃገራት ተቀባይነት ያለውና የተለመደ አሰራር ነው፡፡ በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን የማጠናከር እንቅስቃሴም ከዚህ ልምድና አሰራር ውጪ ሊሆን አይችልም፡፡ በተለይም አሁን ካለው ፓለቲካዊ ነፃነት ጋር እየተበራከተ የመጣው የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ ንግግር ሥርጭት መፍትሔ ካልተበጀለት ለሃገራዊ ሠላምና ደህንነት እንዲሁም ለለውጥ እንቅስቃሴው ዘላቂነት ትልቅ አደጋ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የጥላቻ ንግግር ተስፋፍቶ በጠረገው መንገድ እ.ኤ.አ በ1994 በሩዋንዳ፣ እንዲሁም በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በጀርመንና በመላው አውሮፖ የደረሰው የከፋ እልቂት ተጠቃሽና ትምህርት ሊወሰድባቸው የሚገቡ ክስተቶች ናቸው፡፡ ይህን መሰል ጥፋት እንዳይደርስ የጥላቻ ንግግርን መከልከልና በወንጀልነት መደንገግ አስፈላጊ ነው፡፡ የአለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ወይም ICCPR አንቀጽ 19(3) ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት ከኃላፊነት ጋር እንደሚመጣና አስፈላጊ የሆኑ ገደቦች፣ በተለይም የሌሎችን መብት፣ ብሔራዊ ደህንነትና ሠላምን ለመጠበቅ ሲባል በሕግ ሊደነገጉ እንደሚችሉ በግልፅ ያስቀምጣል፡፡ የዚሁ ስምምነት አንቀጽ 20 ከዚህም በማለፍ በሃገራት ላይ በብሄር፣ በዘር ወይም በሃይማኖት ላይ በመመስረት ጥላቻን፣ ጥቃትና መድልኦን የሚያራግቡ ንግግሮችን በሕግ እንዲከለከሉ ግዴታ ይጥላል፡፡ከላይ ከተጠቀሱት እውነታዎች በመነሳት የጥላቻ ንግግርን በግልፅና በቀጥታ የሚከለክል ሕግ አስፈላጊነት ግልፅ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ሆን ተብሎ የሚደረግ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ነው፡፡ በተለይም የማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋትንና ከዚህ ጋር የተገናኙ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን በመጠቀም ሃሰተኛ የሆኑና ሆን ተብሎ የተዛቡ መረጃዎችን ማሠራጨት በተለያዩ ሃገራት የፖለቲካ ቀውስ ከማስከተል አልፎ ለግጭትና ጉዳት መንስኤ ሆኗል፡፡ ይህ ችግር ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እድገት ጋር እየተስፋፋ የመጣና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ የተለያዩ ሃገራት ችግሩን ለመቅረፍ ሕጐችን በማውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ሃገራት መካከል ፈረንሣይ፣ጀርመንና ኬንያ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዓለማችን ትልቋ ዲሞክራሲ በሆነችው ህንድም የሃሰት መረጃ ስርጭት ያስከተለውን ጦስ ለመከላከል የሕግ ማሻሻያ ለማድረግ ሂደቱ የተጀመረ ሲሆን፣ የችግሩ አስከፊነት በተለያዩ ጊዜያት የኢንተርኔት አገልግሎት እስከመዝጋት ድረስ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ አስገዳጅ ሆኗል፡፡ በሃገራችን ኢትዮጵያም በቅርቡ በሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የተነሣ የተቀሰቀሱ ግጭቶችንና ጥቃቶች የሰው ህይወት እንዲጠፋና ሌላም ጉዳት እንዲደርስ መንስዔ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ሆኖም ይህንን ጉዳይ በቀጥታና በበቂ ሁኔታ ሊሸፍን የሚችል ሕግ አለመኖሩ የፈጠረው ክፍተት ችግሩ እንዲባባስና ከፍተኛ ሃገራዊ ጉዳት እንዲደርስ እድል ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ ይህን ክፍተት የሚሞላና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ፈፅሞ አግባብነት በሌለውና ከመብቱ መነሻና ዓላማ በተቃረነ መንገድ በመጠቀም በሃገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መከላከል ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ልብ ሊባል የሚገባው የጥላቻ ንግግርንና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት ሕግ የሚወጣው መሠረታዊ የሆኑ የዜጐችን መብቶች፣ የሃገርና የህዝብ ደህንነትን፣ ሠላምን ለመጠበቅ፣ዲሞክራሲንና ነፃነትን ከጥላቻና ከሃሰት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ መነሻ ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የሚጣል ገደብ፣ ተመጣጣኝና በጥንቃቄ ተግባራዊ የሚደረግ እስከሆነ ድረስ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ 2. ረቂቅ አዋጁ በሚዘጋጅበት ጊዜ የነበረው ሂደት ረቂቁን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ከላክነው በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቢት ቤት በሰጠው አቅጣጫ መሰረት በረቂቁ ላይ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሳተፉ ጥሪ በማድረግ በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እንዲገኙ በማድረግ ውይይት ተደርጓል፡፡ ከዚህ በፊት በላክነው ረቂቅ አዋጅ ላይም የተለያዩ የወይይት መደረኮችን በማዘጋጀት፣ እንዲሁም ረቂቁን በጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋዊ የማህበራዊ ገጽ በመልቀቀና በጹሁፍ አሰተያየት የሚሰበሰብበትን መንገድ በማመቻቸ፣ ረቂቁን ለማሻሻል የሚረዳ ግብዐት ለማሰባሰብ ተችሎዋል። ይተዘጋጁት የውይይይት መደርኮች ያተኮሩት በዘርፉ ላይ ምርምር ያደረጉ ምሁራን፣ ከጋዜጠኞች፣ ከሲቪል ማበረሰብና ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ነው። ገጽ ለገጽ ከተካሄዱ የውይይት መደረኮች በተጨማሪ በጽሁፍም የተሰጡ አስተያየቶች ነበሩ። በነዚህ መንገዶች የተገኙ አስተያየቶች የተለያዩ ሲሆኑ በቅድሚያ አሰተያየትቶቹ ያተኮሩት በህጉ አስፈላጊነት ላይ ነበር። አንዳንዶች ይህን አይነት ህግ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፣ መንግስት የሚተቹትን ለማሸማቀቅ ሊጠቀመው ይችላል በማለት የተከራከሩ ሲሆን ባንጻሩ ህጉ ያስፈልጋል፣ ከዚህም ቀደም ብሎ መውጣት ነበረበት ብለው አስተያየት የሰጡም አሉ። በተለይም እንዲህ ያለ ህግ ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር ባለው ግንኙነት ዙርያ ሰፊ ክርክርና ውይይት ተካሄዶዋል። በማስከተልም በረቂቁ ይዘት ላይ በተለይም የተከለከሉ ተግባራት ብያኔ፣ የቅጣት መጠንን በተመለከተ፣ እንዲሁም የተከለከሉ አይነት ንግግሮችን ለማሰራጨት በማሰብ መያዝን አስመልክቶ በተደጋጋሚ የተሰጡ አስተያየቶች የተስተናገዱ ሲሆን እነዚህንም አስተያየቶች እንደያግባብነታቸው በማካተት፣ ረቂቂን ለማሻሻል ጥረት ተደርጓል። 3. የረቂቅ አዋጁ ዝርዝር ይዘት ሀ/ አጠቃላይ ስለ ጠቅላላ ድንጋጌዎች የሚያትተዉ የአዋጁ ክፍል አንድ ሶስት አንቀጾችን የያዘ ሲሆን አንቀጽ አንድ የአዋጁን አጭር ርእስ ወይም ስያሜዉን የሚያስረዳ ነዉ፡፡ አንቀጽ ሁለት ደግሞ በአዋጁ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉና ለዚህ አዋጅ አጠቃቀም ትርጉም ያስፈልጋቸዋል የተባሉ ቃላቶችን እና ሀረጎችን ትርጓሜ ያስቀምጣል፡፡ በአንቀጽ ሶስት ላይ የተገለጸዉ የአዋጁ ዓላማ ሲሆን አዋጁን ማዉጣት ያስፈለገዉ በሶስት አላማዎች እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ እነዚህም አንደኛ ሰዎች ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ሲጠቀሙ ግጭት ወይም ሁከትን የሚቀሰቅስ ወይም ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ በግለሰብ ወይም በተለየ ቡድን ላይ ጥላቻ ወይም መድልዎ የሚያስፋፋ ንግግር ከማድረግ እንዲቆጠቡ ማድረግ፤ ሁለተኛ መቻቻልን፣ የዜጎች ውይይትና ምክክርን፣ መከባበርና መግባባትን ማበረታታትና ዲሞክራሲያዊ ስርዐትን ማጎልበት በሶስተኛነት የጥላቻ ንግግርን፣ የሃሰተኛ መረጃና ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች የውሸትና አሳሳች መረጃዎችን ስርጭትና መበራከትን ለመቆጣጠርና ለመግታት መሆናቸው ተገልጾዋል። በአጭሩ፣ እነዚህን አላማዎች ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስችሉ እና አሁን እየታዩ ያሉ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያስከትሉትን አደጋዎች በሚፈለገዉ ደረጃ ለመዋጋት የሚያስችሉ ነባር ህጎች ባለመኖራቸዉ ይህንን አዋጅ ማዉጣት አስፈልጓል፡፡ ለ/ የተከለከሉ ተግባራት በአዋጁ ክፍል ሁለት የተከለከሉ ተግባራት በሚለዉ ርእስ ስር የጥላቻ ንግግር መከልከል ፤ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መከልከል እንዲሁም በልዩ ሁኔታ የሚታዩ ድርጊቶች ተዘርዝረዉ ተቀምጠዋል፡፡ በአንቀጽ 4 የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚድያ በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪድዮ ማሰራጨት የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ በአንቀጽ 2(2) መሰረት የጥላቻ ንግግር ማለት በአንድ ሰዉ ወይም የተወሰነ ቡድን ላይ ያነጣጠረ፣ ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ዘርን፣ ጾታን ወይም አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ ጥላቻን፣ መድሎን ወይም ጥቃትን የሚያበረታታ ንግግር ነው።በአንቀጽ 5 የሃሰት መረጃን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚድያ በጽሁፍ፣ በምስል፣ በድምጽ ወይም በቪድዮ ማሰራጨት የተከለከለ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ በዚህ አንቀጽ መሰረት አንድ መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ብቻ በወንጀል የሚያስጠይቀው መቼ እንደሆነ ለመረዳት በአንቀጽ 2(3) የተቀመጠውን የሃሰተኛ መረጃ ትርጉም በሚገባ ማጤን ያስፈልጋል፡፡ በአንቀጽ 2(3) መሰረት“ሃስተኛ መረጃ” ውሸት የሆነና የመረጃውን ውሸት መሆኑን በሚያውቅ፣ ወይም መረጃውን የሚያሰራጨው ሰው ካለበት አጠቃላይ ሁኔታ አንጻር የመረጃውን ሃሰተኝነት ሊያውቅ ይገባ ነበር የሚያስብል በቂ ምክንያት እያለ የሚሰራጭ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ከፍ ያለ ንግግር ነው። የአዋጁ አንቀጽ 6 የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት የተከለከለ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በልዩ ሁኔታ የሚታዩ ነጥቦችን የሚዘረዝር ሲሆን በንኡስ አንቀፅ 1 ስር አንድ ንግግር እንደ ጥላቻ ንግግር ወይም እንደ ሃሰት መረጃ ተወስዶ ማሰራጨት የማይከለከለው መረጃው የትምህርታዊ ወይም ሳይንሳዊ ምርምር አካል ፤የዜና ዘገባ፤ ትንታኔ ወይም የፖለቲካ ትችት አካል ፤ የኪነጥበበ ፣ ትወና ወይም መሰል የስነጥበበ ውጤት፣ ወይም የሃይማኖታ አስተምህሮት አካል እንደሆነ ተገልጾዋል፡፡ ስለሆነም ከእነዚህ ከተገለጹት መንገዶች ለአንደኛዉ አላማ የሚደረግ ንግግር እንደ የጥላቻ ንግግር ወይም እንደ ሃስተኛ መረጃ ተወስዶ የሚከለከልና የሚያስቀጣ አይሆንም፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 2 ስር የተደነገገዉ ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨትን በተመለከተ በልዩ ሁኔታ የሚታይ ሀሳብን ነዉ፡፡ ይኸዉም አንድ ንግግር እንደ ሃሰተኛ መረጃ ተወስዶ የማይከለከለው ንግግሩን ያሰራጨው ወይም ያደረገው ሰው የመረጃውን እውነተኛነት ለማረጋገጥ በሱ ሁኔታ ካለ ሰው የሚጠበቀውን ምክንያታዊ ጥረት ያደረገ እንደሆነ ወይም ወይም ንግግሩ የጥሬ ሃቅ ዘገባ ወይም ዜና ከመሆን ይልቅ ወደ ፖለቲካ አስተያየትና ትችትነት ያጋደለ መሆኑ ተገልጾዋል። ይህን አይነት ልዩ ሁኒታዎች መደንገግ የሚያስፈልገው ህጉ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ ሊኖረው የሚችለውን አሉታዊ ተጽንዖ ለመቀነስ ነው። ሐ/ የወንጀል ተጠያቂነት፣ የተቋማትና የአገልግሎት ሰጪዎች ሀላፊነት የአዋጁ ክፍል ሶስት የሚያስቀምጠዉ በአንቀጽ 4 እና 5 ላይ የተደነገጉት የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ወንጀሎች የሚያስቀጡትን ቅጣት፤ የተቋማት እና የአገልግሎት ሰጪዎች ሀላፊነት፤ ስለ ተሻሩ ህጎች እና አዋጁ የሚጸናበት ግዜን ይደነግጋል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 7 ስር የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ወንጀሎች የሚያስቀጡትን ቅጣቶች ይደነግጋል፡፡ የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ በንኡስ ቁጥር 1 ላይ የተቀመጠዉ በአዋጁ አንቀጽ 4 የተመለከቱትን ወንጀሎች መፈጸም እስከ ሶስት አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከመቶ ሺህ ብር ያልበለጠ መቀጮ እደሚያስቀጣ፤ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 4 የተከለከሉት ተግባራት በመፈጸማቸው የተነሳ በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ ወይም የተሞከረ ከሆነ በአንቀጹ የተከለከሉትን ተግባራት የፈጸመ ሰው እንደነገሩ ሁኔታ እስከ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ በሌላ በኩል የሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨትን በተመለከተ ማንም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀፅ 5 የተመለከትውን የተከለከለ ተግባር የፈጸመ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ እስከ አንድ አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከሀምሳ ሺህ ብር ያልበለጠ መቀጮ እንደሚቀጣ፤ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 5 የተመለከተውን የተከለከለ ተግባር የፈጸመው ሰው ድርጊቱን የፈጸመው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚድያ ገጽ ከሆነ ወይም በብሮድካስት አገልግሎት ወይም በየጊዜው በሚወጣ የህትመት ውጤት ከሆነ ሶስት አመት በሚደርስ በቀላል እስራት ወይም ከብር100,000 ያልበለጠ መቀጮ እንደሚቀጣ፤ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 5 የተከለከለው ተግባር በመፈጸሙ በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ ወይም የተሞከረ ከሆነ፣ ሁከት ወይም ግጭት የተከሰተ እንደሆነ የአንቀጽ 5 ድርጊትን የፈጸመ ሰው እንደነገሩ ሁኔታ እስከ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፍርድ ቤት በዚህ አዋጅ የወንጀል ተጠያቂ የሆነ ሰውን ለማረም የተሻለ ነው ብሎ ሲያምንና የተከለከለው ተግባር በመፈጸሙ በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት ያልተፈጸመ ወይም ያልተሞከረ ከሆነ፣ ሁከት ወይም ግጭት ያልተከሰተ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ በእስራት ምትክ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራን በአማራጭ ቅጣትነት ሊወስን እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ በአንቀጹ የተቀመጡትን ቅጣቶች በዚህ መጠን ማስቀመጥ ያስፈለገበት በተጠቀሱት ወንጀሎች የሚሳተፉ አካላትን ለማስተማር በቂ እና ተመጣጣኝ ናቸዉ የሚል እሳቤ በመያዝ ሲሆን ወንጀሉን ቅጣት በማግዘፍ ብቻ ከማስወገድ ይልቅ ትምህርት እና ስልጠና በመስጠት የሚቀንስ ብሎም የሚወገድበት አግባብ በሂደት መቀየስ አስፈላጊነትን ታሳቢ በማድረግ ነዉ፡፡ መ/ ተቋማት እና አገልገልግሎት ሰጪዎች ሀላፊነት በአዋጁ አንቀጽ 8 ስር ተቋማት እና አገልግሎት ሰጪዎች የሚኖራቸዉን ሀላፊነት የሚደነግግ ሲሆን ማንኛዉም ማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በአንቀጽ 4 እና በአንቀጽ 5 ስር የተከለከሉ ንግግሮች እንዳይተላለፉ ወይም እንዳይሰራጩ የመቆጣጠር እና የመግታት የተከለከሉ ንግግሮችን በተመለከተ ጥቆማ ሲደርሰዉ እና ጥቆማዉ አሳማኝ ሲሆን ንግግሩን በአፋጣኝ የማስወገድ ወይም ከስርጭት የማዉጣት ግዴታ እንዳለበት፤ ማንኛዉም የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት በንኡስ ቁጥር 1 እና 2 የተደነገገዉን ግዴታ ለመወጣት የሚያስችለዉ አሰራር እና ፖሊሲ ሊኖረዉ እንደሚገባ፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በአዋጁ የተደነገገውን ግዴታቸውን ባግባቡ እንዲወጡ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ እና የሃሰት መረጃ ስርጭትና ጉዳትን ለመከላከል የሚረዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብሮችን በማዘጋጀት ተግባራዊ እንደሚያደርግ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል የሚረዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብሮችን በማዘጋጀት ተግባራዊ እንደሚያደርግ እና የተቋማትና የአገልግሎት ሰጪዎች ሀላፊነትን ዝርዝር የሚደነግግ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊወጣ እንደሚችል ተደንግጓል። ከዚህም በተጨማሪ በአዋጁ የተደነገገውን ግዴታ አለመወጣት ሊያስከትል የሚችለው የፍትሃ ብሄር ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በአዋጁ የተቀመጠውን ግዴታቸውን ባግባቡ መወጣታቸውን እየተከታተለ በአመት ሁለት ጊዜ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ረፖርት እንደሚያዘጋጅ ተግልጾዋል። የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ላይ የተጣለው ግዴታ በቅጣትና በወንጀል ተጠያቂነት ላይ ያተኮረ ሳይሆን፣ እነዚህ ተቋማት ሃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንዲንቀሳቀሱ የሞራል ተጽኖ ለማሳረፍ እና ከዛም አልፎ ለሚኖርባቸው የፍትሃ ብሄር ተጠያቂነት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የታሰበ ነው። ሠ/ስለ ተሻሩ ህጎች እና አዋጁ የሚጸናበት ግዜ በመጨረሻም አዋጁ በአንቀጽ 9 ላይ የወንጀል ህግ አንቀጽ 486 የተሻረ መሆኑን እንዲሁም በአንቀጽ 10 ላይ አዋጁ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተቀምጧል፡፡ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 486 መሻር አስፈላጊ የሚደርጉ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። በቅድሚያ ይህ አንቀጽ መንግስትና ባለስጣኖችን ከሓሰት ወሬና ሃሜታዎች የሚጠብቅ አንቀጽ ነው። ይህን አይነት ጥበቃ ለባለሰልጣናት ማድረግ በተለይም በዲሞክራሲያዊ አውድ ተቀባይነት የለውም። በዲሞክራሲያዊ ስርዐት ባለስልጣናትና መንግስት ከሌሎች ዜጎች በተለየ ሁኔታ ክሓሰት ወሬና ከጥርጣሬ ወይም ከሃሜታ ጥበቃ አይደረግላቸውም። ባለስልጣናትና መንግስት ከተራ ዜጋ በተሻለ መልኩ የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና የተወራባቸውን የማስተባበል እድልና አቅም አላችው ተብሎ ይገመታል። በተጨማሪም የመንግስት ሃላፊነትን የያዘ ሰው ክሃላፊነቱ ጋር ምክንያታዊ የሆኑም ሆነ ያልሆኑ፣ በሃቅ ላይ የተመሰረቱም ሆነ ከሃቅ የራቁ ትችቶች ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ እያወቀ ሃላፊነቱን ተረክቦዋል ተብሎ ይታሰባል። የተጋነኑና በእውነታ ላይ ያልተመሰረቱ ትችቶችን ማድረግ ወንጀል ሆኖ ቢያስጠይቅና ቢያስቀጣ የፖለቲካ ትችትና ክርክር ላይ እጅግ ከባድ ጥላ ስለሚያጠላ በዲሞክራሲያዊ አውድና ስርዐት ይህን አይነት ንግግሮች ወንጀል ሊደረጉ አይገባም። በተጨማሪም አንቀጽ 486 በበቂ ሁኔታ ዝርዝር ሆኖ የሃሰትት መረጃና የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል የሚያስችል ስላልሆነ በዚህ አዋጅ መተካቱ የተሻለ አማራጭ ነው። 4. ማጠቃለያ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሰዎች መሰረታዊ መብት ከሚባሉት ዉስጥ የሚጠቀስ ሲሆን ይህ መብት ምንም እንኳን መሰረታዊነቱ የሚጠያይቅ ባይሆንም በህግ ክልከላ ከሚቀመጥባቸዉ መብቶች ዉስጥም የሚመደብ ነዉ፡፡ ማለትም ሀሳብን በነፃነት በመግለፅ ሽፋን የሚከሰቱ ጥላቻን፣ ማግለልን፣ ግጭት፤ ጥቃትን እና መሰል በግለሰቦች እና እንደ አጠቃላይ በመሀበረሰቡ መካካል ያለ መልካም ግንኙነትን የሚያሳሱ እና የሚጎዱ ንግግሮችን እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በህግ መከላከል ያስፈልጋል፡፡ በተለይም በአሁን ወቅት በሀገራችን በህብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በእነዚህ ጥላቻ ንግግሮች እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩ እና ለሀገርም ስጋት የደቀኑ በመሆናቸዉ እንዲሁም እነዚህን ችግሮች አሁን ባሉት ህጎች መፍታት የማይቻል በመሆኑ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የሚቆጣጠር አዋጅ አርቅቀን ከዚህ ማብራርያ ጋር የላክን መሆኑን እንገልጻለን።
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
609
የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ቁጥጥር አዋጅ ፀደቀ የኢትጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ 5 ስብሰባ ሲያነጋግር የቆየውን የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን የተመለከተውን ረቂቂ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ። አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:33 ረቂቂ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል የኢትጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ 5 ስብሰባ ሲያነጋግር የቆየውን የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን የተመለከተውን ረቂቂ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ። በንግግር ነጻነት ላይ ተጽእኖን ሊያሳድር ይችላል ተብሎ በተለያዩ ወገኖች ትችት ሲቀርብበት የነበረው ይህ ረቂቅ ሕግ፤ ከምክር ቤቱ አባላት 23 የተቃውሞ ድምጽ ገጥሞታል። 2 ድምጸ ተዐቅቦም ተመዝግቧል። በምክር ቤቱ እንደተጠቀሰው በረቂቅ ሕጉ ላይ አንዳንድ ክለሳዎች መደረጋቸውም ተገልጿል። ቢሆንም ግን አሁንም አንዳንድ ግልጽነት የሚጎላቸው ሐሳቦች እንዳሉትም ተነስቶ ነበር ተብሎአል። የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁን በአብላጫ ድምጽ አጽድቆአል። ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ልዝርዝር ምርመራ ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ መርቶታል። ይህ ሕግ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ የፈጠረው ስጋትን ምን ይሆን? የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት አዋጅ መጽደቅን ተከትሎ በኢትዮጵያ የመብቶችና ዴሞክራሲ ብልጽግና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር በፈቃዱ ኃይሉን ጠይቀነዋል። የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
610
የጥላቻ ንግግር ከትችት እንዴት ይለያል? በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ያለው የጥላቻ ንግግር እና የሀሰት ወሬን አስመልክቶ ሀገሪቱ የፀረ ጥላቻ ንግግር ህግ አርቅቃለች። ባለፈው ሳምንት ይፋ የሆነው ረቂቅ ከፀደቀ ህጉ በነፃነት የመናገር መብታችንን ሊነፍግ ይችላል የሚሉ አንዳንድ ወጣቶች ስጋታቸውን አካፍለውናል። በርግጥ ስጋታቸው ከፀረ ጥላቻ ህግ ጋር ይገናኛል? ወይስ ህጉን አልተረዱትም? This video file cannot be played. (Error Code: 102630) አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:16 የፀረ ጥላቻ ንግግር ረቂቅ ህጉ ፀድቆ ተግባራዊ እስከሚሆን ረዥም ሂደት አለው።ረቂቁ ላይ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ይቀርባል። ይህም ምክር ቤት ካጸደቀው ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይተላለፋል። ከዛ በኋላ ነው ፀድቆ ተግባራዊ መሆን የሚችለው። በአሁኑ ወቅት በተለይ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በብሔር ላይ የተመረኮዙ የጥላቻ መልዕክቶች መነበባቸው ቀጥሏል። ከዛም አልፎ ምስሎችን በመቀያየር የተሳሳተ መረጃዎች ይሰራጫሉ። አብዮት ግን ስለ ጥላቻ ንግግር ረቂቅ ህጉ ብዙ መረጃ ባይኖረውም በደፈናው ይቃወመዋል። « የግድ ቃላትን መምረጥ ያስፈልጋል። መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ያኔ ደግሞ ላለመናገር ወደመፈለግ ያመራል» ይላል። የፀረ ጥላቻ ንግግር ህግ የመናገር መብትን እንዳልገደበ የሌሎች ህጉን ተግባራዊ ያደረጉ ሀገሮች ተሞክሮ ያመላክታል። ይልቁንስ ሰዎች የሚያሰራጭቱን መልዕክት ሁለት ጊዜ እንዲያጤኑት ነው ያበረታታው። የጥላቻ ቃል ምንድን ነው? እዚህ ጀርመን ከጥላቻ ንግግር ጋር በተያያዘ የተሰጡ ፍርዶችን በምሳሌነት እንጥቀስ፣ አንድ የ 28 ዓመት ጀርመናዊ መራሄ መንግሥት ሜርክል « በአደባባይ በድንጋይ መደብደብ አለባቸው » የሚል መልዕክት በማህበራዊ መገናኛ በማሰራጨቱ 2000 ዩሮ እንዲቀጣ ተፈርዶበታል። መልዕክቱ ሌሎችን ለአመፅ ይጠራል በሚል ነው። አንድ የ 34 ዓመት በርሊናዊ ደግሞ የጥላቻ ንግግሩን በማን ላይ እንደነበር ግልፅ ሳያደርግ በጥቅሉ « የጋዝ ክፍሎች መከፈት አለባቸው» በማለቱ 4800 ዩሮ ተቀጥቷል። በእነዚህ ክፍሎች በናዚ አገዛዝ ጊዜ የብዙ አይሁዳውያን ህይወት በጋዝ ታፍነው የተገደሉበት በመሆኑ ነው። Symbolbild Laptop & Internet (picture-alliance/dpa/empics/D. Lipinski) ሌላው ደግሞ ሶስት ዓመት ከአራት ወር እስራት የተፈረደበት የአልቃይዳ ቡድን የሰዎችን ሲገድል የሚያሳይ ቪዲዮ ሌሎች እንዲያዩት በማሰራጨቱ ወይም በግል ገፁ ላይ ሼር በማድረጉ ነው። አንድን ፖለቲከኛ «ህፃናት ደፍሯል» ሲል የሀሰት ወሬ ያሰራጨ ጎልማሳ ደግሞ በስም ማጥፋት ወንጀል 1 ዓመት ከ 9 ወር እስራት ተፈርዶበታል። ወደ አልጸደቀው የኢትዮጵያ የፀረ ጥላቻ ህግ ረቂቅ እንመለስ፤ እዛ ላይ ሶስት አይነት ቅጣቶች ተቀምጠዋል።ቅጣቱ እንደ ጥፋቱ ክብደት ይለያያል። የፌደራል ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ለDW እንደገለፁት ቅጣቱ የማህበረሰብ አገልግሎች ከማበርከት እስከ ገንዘብ እና እስራት ቅጣት ሊደርስ ይችላል። ይህም ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ነው። የረቂቅ ህጉን የተከታተለው ወጣት ቅጣቱ ከፍ ማለት እና ህጉም በፍጥነት ተግባራዊ ቢሆን ይመርጣል። « ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ይሄ ትንሽ ነው ባይ ነኝ። ህጉ ቢሆር ደስተኛ ነኝ። መንግስት ይህንን በፍችነት ቢያደርገው እና ሀገሪቱን ማረጋጋት ቢቻል ጥሩ ነው ይላል። እዮብም የውሹት ና የጥላቻ ንግግርን የሚያስተላልፉትን ማስቆሙ ጥሩ ነው ይላል። እንደ እሱ ከሆነ ግን ለዚህ የግድ ህግ መውጣት የለበትም። « ውሸትን ለማጥፋት አስር ጊዜ ህግ ማውጣት ሳይሆን መንግሥት እውነትን እና ፈጣን ርምጃ ሲዘረጋ ነው። ችግር ሲደርስም ቶሎ አለሁ ሲል ነው።» እዮብ የማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን አጠቃቀሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደተቀየረ እና ስሜታዊ እየሆነ መምጣቱንም ነግሮናል። « ሰው ነኝ እና የሆነ የሚያናድድ ነገር ስሰማ ለዛ ምላሽ እሰጣለሁ። አንዳንዴ ከተናገርኩት በኋላ ይጸፅተኛል።» Infografik Percentage of social media hate speech deleted after user reports ወጣት አህመድ ሀገሪቱ ያለችበት ቀውስ ነው ለጥላቻና ለሀሰት ወሬዎች ምክንያት የሆኑት ይላል። መረጃዎቹን የሚያገኘው ከመገናኛ ብዙኃን ይሁን ከግለሰቦች ሳይገልፅ የሚያነባቸው ብዙው መረጃዎች ግን ትክክል ናቸው ይላል። « በርግጥ የተጋነነ ቢሆንም እውነታ አላቸው።» ይላል። አብዛኛውን ጊዜ የጥላቻ ንግግሮች ወይም የሀሰት መረጃዎች ተስፋፍተው የሚታዩት ወይም የሚነበበቡት እንደ ፌስቡክ ባሉ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ነው። ከመልዕክቱ በስተጀርባ ያለው ሰው የግድ ግልፅ አይደለም። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን የኢንተርኔት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ሰዎች ማንነታቸው እንዳይታወቅ አድርገው ስለሆነ ወንጀል የሚሰሩት የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩትን ሰዎች ለይቶ ማግኘትን የስራው ሂደት አድርገው ይመለከቱታል። ወንጀሉን የሰራውን መርምሮ ማግኘት እና ማጣራት ደግሞ የፖሊስ ስራ ስለሆነ በተመሳሳይ አግባብ እንደሚስተናገድ ገልፀውልናል። ግለሰቦቹ ከሀገር ውጪ ከሆነስ የሚገኙት? ዶክተር ጌዲዮን ቃል በቃል ያሉን እንደሚከተለው ይነበባል።« ከተለያዩ ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት በህግ ጉዳዮች ላይ ትብብር የማድረግ ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያየ ጊዜ ተፈራርሟል። እየተፈራረመም ይሄዳል። በተለይ የሰብዓዊ መብት አያያዛችን እየተሻሻለ በሄደ ቁጥር ፣ ተቋሞቻችን እና ህጎቻችን ላይ የምናደርገው ማሻሻያ ፍሬ እያፈራ በሄደ ቁጥር ብዙ ሀገሮች አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ ይሆናሉ። » ይላሉ የህጉ ባለሙያ። የፀረ ጥላቻ ንግግር ህጉ ተግባራዊ እስኪሆን መጣቶች እንዴት መረጃ መሰብሰብ ይጠበቅባቸዋል? ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ «ህጉ ሳይወጣም ሆነ ከወጣም በኋላ ከዜጎች የሚጠበቀው የሚያሰራጩትን፣ የሚያነቡትን የሚቀበሉትን ማንኛውንም መረጃ እና ዜና ከተአማኒ ምንጭ ነው የመጣው አይደለም ፤ መረጃውን እያሰራጨ ያለው ሰው ማነው ብለው ማጤን ይገባቸዋል።» ብለዋል።
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
611
 የጥላቻ ንግግር ህግ አዋጅና እድምታዎቹ መግቢያ የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ያለዉን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለዉን የጥላቻ ህግ ረቂቅ አዋጅ ይፋ በማድረግ ህጉን በማፅደቅ ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። አገሪቱ ዉስጥ ያለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24 2010 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ አግሪቱ በከፍተኛ የፖለቲካ ለዉጥና ነዉጥ ዉስጥ ትገኛለች። ለዉጡን ተከትሎ የመጣዉ የፖለቲካ ምህዳሩ መከፈት ግለሰቦች፥ የብሄር ድርጅቶችና ሚድያዎች ሃሳባቸዉን በአንፃራዊ ነፃነት የሚገልፁበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። የአገሪቱ የፖለቲካ አወቃቀር ብሄርን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የፖለቲካ ምህዳሩ መከፈት ተከትሎ ብሄር ተኮር የፖለቲካ ሃይሎች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክረዉ በመዉጣታቸዉ የብሄር ግጭት፥ መፈናቀል፥ ዝርፊያና አለመረጋጋት በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቷል።1 በቅርቡ በአማራና በደቡብ ክልሎች የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ መንግስት የሃይል እርምጃ በመዉሰድ ብዙዎች ለእስር ተዳርገዋል። 2 መንግስት ከፍተኛ ተቃዉሞ የቀረበበትን የ ፀረ ሽብርተኝነት ህጉን በመጠቀም የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ ክስ ማቅረቡ ለዉጡ እየተቀለበሰ ነዉ የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። አገሪቱ ዉስጥ ካለዉ ዘርን መሰረት ባደረገዉ የፖለቲካ ስርአት ምክንያት የዘር መከፋፈልና ጥላቻ እየተስፋፋ በመምጣቱ የጥላቻ ህግን ማዉጣት በመርህ ደርጃ አስፈላጊ ቢሆንም የህጉ መዉጣት የሚያስከትለዉን ችግር ማንሳት አስፈላጊ ነዉ። ይህ ፅሁፍ የጥላቻ ህግ ታሪካዊ አመጣጥ ፥ አለም አቀፍ ልምዶችና በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ባለዉን ህገ መንግስታዊ ስርአትና ፖለቲካዊ ሁኔታ አንፃር በመዳሰስ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመጠቆም ይሞክራል። 1. የጥላቻ ህግ ታሪካዊ አመጣጥና አለም አቀፍ ልምዶች የጥላቻ ህግ ታሪካዊ አመጣጥ ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ ጋር በቅርብ የተቆራኘ ነዉ። ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በጥንታዊ አቴንስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በስድስተኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ትኩረት ያገኘ መሰረታዊ መብት ነዉ። ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን በነበረዉ የእንግሊዝ የመብት ትግል እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ1789 ዓም በፈረንሳይ አብዮት ወቅት የወጣዉ የሰዉ ልጆች መብት ድንጋጌ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ትልቅ ዋስትና ሊኖረዉ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አፅኖት አድርጎበታል። እ.ኤ.አ. በ 1789 ዓም የወጣዉ የአሜሪካ ህገ መንግስት የመጀመርያዉ ማሻሻያ ( First Amendment) 1 Ethiopia: 3 million internally displaced in escalating humanitarian crisis, https://www.euronews.com/2019/01/31/ethiopia-3-million-internally-displaced-in-escalating-humanitarian-crisis 2 In era of reform, Ethiopia still reverts to old tactics to censor press, https://cpj.org/blog/2019/07/ethiopia-coup- internet-censored-blocked-jailed-journalists.php የአሜሪካ ም/ቤት ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን የሚገድብ ምንም አይነት ህግ ማዉጣት እንደማይችል በመደንገግ የንግግር ነፃነት በአሜሪካ ማህበረሰብና በአለም አቀፍ ደረጃ ገደብ እንዳይደረግበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲኖረዉ አድርጓል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.ኤ.አ. 1945 ዓም ከተመሰረተበት ወቅት ጀምሮ ትኩረት ያገኘዉ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መብት በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል። እ.ኤ.አ. በ 1948 ዓም የወጣዉ አለም አቀፉ የሰብአዊ መበት ድንጋጌ ( Universal Declaration of Human Rights) በአንቀፅ 19 ላይ እንዳስቀመጠዉ ማንኛዉ ሰው ሃሳቡን በነፃነት የመግለፅና የማሰራጨት ያለገደብ መብት እንዳለዉ አረጋግጧል። እንዲሁም እኤአ በ 1966 ዓም የወጣዉ አለም አቀፉ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ድንጋጌ ( International Covenenat on Civil and Poltical Rights) አንቀፅ 19 ላይ የተቀመጠዉ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አሁን በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ላጋኘዉ ህሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንቅስቃሴ መሰረት ጥሎአል። የቀዝቃዛዉን ጦርነት ማብቃት ተከትሎ በጭቆና ስር የነበሩት ታዳጊ አገሮችም ሳይቀሩ ሀሳብን በነፃነት መብትን እውቅና የሚሰጥ የህገ መንግስትና የፖለቲካ ስርአት ደንግገዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከሰቱ አለም አቀፍ ሁኔታዎች የጥላቻ ንግግር እንዲስፋፉ ምክንያት እንደሆኑ ይታመናል። ሉላዊነት ( globalaization) በአሜሪካና አዉሮፓ በሃብታምና ድሃዎች መካከል የፈጠረዉ ልዩነትና ስደተኞች ያለ ገደብ ድንበር አቋርጠዉ መግባታቸዉ በስደተኞች ላይ ጥላቻን መሰረት ያደረጉ ወንጀሎች እንዲስፋፉና ቀኝ አክራሪ ብሄርተኛ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ስልጣን እንዲይዙ ምክንያት ሆንዋል። ከዚህም በተጨማሪ በድህረ ገፆችና ማህበራዊ ሚድያዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችና ሀሰተኛ ወሬዎች ( fake news) በከፍተና ደረጃ በመጨመሩ መንግስታት ይህንን አካሄድ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ሙከራ እያደረጉ ነዉ። ከቅርብ አመታት ወዲህ የመገናኛ ብዙሃን ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ ምክንያት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በከፍተኛ ደረጃ እድገት አሳይቷል። በተለይም ደግሞ በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ እድገት ምክንያት የመረጃ አቅርቦትና ስርጭትን ታላቅ እምርታ የታየበት ሲሆን ማህበራዊ ሚዲያዉ መደበኛ የመገናኛ ብዙሃንን በመተካት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነትን አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ቀይሮታል። አለማችንን ያስተሳሰረዉ የቴኖሎጂ እድገት ግን የራሱን ችግሮች ይዞ ብቅ ብሎአል። የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የሚፈፀሙ የሽብርና የጥላቻ ንግግሮች የፈጠሩት ተፅእኖ ቴክኖሎጂዉን ለመቆጣጠር አቅም የሌላቸዉን ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ የበለፀጉትንም አገራት ስጋት ላይ ጥሎአል። ይህ ችግር በተለይ በታዳጊ አገሮች ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ይገኛል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ለዘመናት በጭቆና ዉስጥ ያሉ አገሮች ማህበራዊ ሚድያዉ ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ ተደርጎ ስለሚቆጠር የራሱ በጎ ቢኖረዉም የጥላቻና ሃሰተና ወሬዎች በማሰራጨትና ከፈተኛ ችግር ይፈጥራል። በአደጉትም ሆነ በታዳጊ አገሮች በማህበራዊ የትስስር መድረኮች የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮች ስደተኞችንና በቀለም ወይም በዘር ከህብረተሰቡ ለየት ያሉ ግለሰቦች ለጥቃት እንዲጋለጡ ማድረጉን ጥናቶች አረጋግጠዋል።3 በተለይ በአዉሮፓና አሜሪካ ቀኝ ዘመም የፖለቲካ መሪዎች ወደ ስልጣን መምጣት ብሄረኝነትንና ዘረኝነትን አልፈዉታል የሚባሉትንም ዴሞክራሲያዊ ስርአት የገነቡትን አገሮችንም 3 Hate Speech on Social Media: Global Comparisons, https://www.cfr.org/backgrounder/hate-speech-social- media-global-comparisons የጥላቻ ንግግር እየናጣቸዉ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ በአወጣዉ መግለጫ ፀትላቻ ንግግሮች በለም ዙርያ በከፍተኛ ደረጃ እያደጉ መምጣታቸዉን በመግለፅ ይህን ለመቋቋም የሚያስችል የድርጊት መርሃ ግብር ቀይሷል።4 ምንም እንኳን የጥላቻ ንግግር በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እያገኘ ቢመጣም የጥላቻ ንግግር ምን ማለት እንደሆነ የሚያስረዳ አለም አቀፍ ስምምነት ግን የለም። የአዉሮፓ ም/ቤት ያወጣዉ አንድ ሰነድ የጥላቻ ንግግርን ማንኛዉም ዘርን ፥ የዉጭ አገር ዜጎችን፥ አይሁዳውያንን አስመልክቶ የሚያሰራጭ፥ የሚያነሳሳና የሚያስፋፋ ማንኛዉም ሃሳብን የመግለፅ መንገድ በተለይም ህዳጣንንና ስደተኞችን የሚያገል ፅንፈኛ ብሄርተኝነት፥ አድልዎና ጥላቻ የሚያካትት መሆኑን ይገልፃል።5 አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች የጥላቻ ንግግር ምን እንደሆነ ግልፅ ትርጉም ባይሰጡም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የጥላቻ ንግግሮች ለመቆጣጠር ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል ይደነግጋሉ። እ. ኤ. አ. በ1966 ዓም የወጣዉ አለም አቀፉ የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች ስምምነት ሃሳብን በመነፃነት የመግለፅ መብትን መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች አካል አድርጎ ቢቀበለዉም ማንኛዉም የብሄርን፥ የዘርና የሃይማኖት ጥላቻ የሚያስፋፋ ንግግር መድልዎን፥ ጥላቻንና ጥቃትን የሚያነሳሳ ስለሆነ በህግ እንደሚከለከል ይደነግጋል።6 እ.ኤ.አ. በ 1965 የወጣዉ አለም አቀፉ የፀረ መድልዎ ስምምነት ማንኛዉንም የዘር የበላይነትን፥ ጥላቻንና የዘር መድልዎን ወይም ጥቃት እንዲደርስ የሚገፋፉ ማንኛዉንም ግግሮችን ማሳራጨት በወንጀል እንዲቀጡ አባል አገራትን ያሳስባል ። 7 የዴሞክራሲያ ስርአት አገሮች የጥላቻ ህግን የሚያስተናግዱበት መንገድ ይለያያል። በተለይም የዴሞክራሲያዊ ስርአት በሚከተሉት አሜሪካንና አዉሮፓ አገሮች የጥላቻ ህግን አስመልክቶ ያላቸዉ ልምድ በእጅጉ ይለያያል። በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ወቅት ናዚ ጀርመን በአይሁዳዉያን ላይ በፈፀመዉ ጥላቻን መሰረት ያደርገ ዘር ማጥፋት ወንጀል ምክንያት በአዉሮፓ የንግግር ነፃነትን የሚገድብ ጠንከር ያሉ የጥላቻ ህጎች ወጥተዋል። ዴንማርክ፥ ፈረንሳይ፥ ኔዘርላንድና እንግሊዝን በመሳሰሉት አገሮችም ማንኛዉም ዘርን፥ ሃይማኖትንና ፆታን መሰረት ያደርገ የጥላቻ ንግግርም ሆነ ስድብ የተከለከለ ነዉ። በአዉሮፓ ዉስጥ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እዉቅና ያለዉ ቢሆንም በርካታ ገደቦች ይጣሉበታል። ከጦርነቱ ማብቃት በሁዋላ የአዉሮፓ አገሮች የተስማሙበትና እ.ኤ.አ. በ1950 ዓም በአዉሮፓ ም/ቤት የፀደቀዉ የአዉሮፓ የሰብአዊ መብት ስምምነት 4 UN Warns of Global “ Groundswell” Hate Speech, https://www.cbsnews.com/news/un-secretary-general-antonio- guterres-warns-of-global-groundswell-of-hate-speech/ 5 Recommendation (97)20 of the Council of Europe, 30 October 1997 - “the term ‘hate speech’ shall be understood as covering all forms of expression which spread, incite, promote or justify racial hatred, xenophobia, anti-Semitism or other forms of hatred based on intolerance, including: intolerance expressed by aggressive nationalism and ethnocentrism, discrimination and hostility against minorities, migrants and people of immigrant origin”. 6 Article 20 (2) of the International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR) states: Any advocacy of national, racial or religious hatred that constitutes incitement to discrimination, hostility or violence shall be prohibited by law. 7 Article 4, International Convention on the Elimination of Racial Discrimination, 1965 States “shall declare an offence punishable by law all dissemination of ideas based on racial superiority or hatred, incitement to racial discrimination, as well as all acts of violence or incitement to such acts against any race or group of persons of another colour or ethnic origin, and also the provision of any assistance to racist activities, including the financing thereof” ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን እውቅና ቢሰጥም ገደብ ሊጣልባቸዉ የሚቻልበትን ምክንያቶች ይዘረዝራል። 8 በዚህም መሰረት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የዴሞክራሲ ስርአት ለመገንባት፥ ለብሄራዊ ደህንነት፥ የሃገር አንድነትና የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ፥ ሁከትን ወይም ወጀልን ለመከላከል፥ የህዝብን ጤና ወይም ግብረገብነትን ፥ የሌሎች ሰዎችን ክብርና ደህንነት ለመጠበቅ በህግ ገደብ ሊጣልበት ይችላል። 9 ይህንንም ድንጋጌ መሰረት በማድረግ በርካታ የአዉሮፓ አገሮች የጥላቻ ህግን የሚቆጣጠር ህጎችን አዉጥተዋል። ሌሎች የአዉሮፓ አቀፍ ተቋማትም የጥላቻ ህግን በማስመልከት በርካታ ህግጋትን ደንግገዋል። የአዉሮፓ ም/ቤት የሚኒስትሮች ኮሚቴ ያወጣዉ የጥላቻ ንግግር ትርጉም ሰፋ ያለ ዝርዝር ያለው ነዉ። ኮሚቴዉ የጥላቻ ንግግርን ማንኛዉም የዘር ፥ የዉጭ ዜጎችን፥ ፀረ ሴማዊነት ጥላቻን የሚያንሳሳ፥ የሚያሰራጭና የሚያስፋፋ ንግግር ወይም መቻቻልን የሚፃረር ፅንፈኛ የሆነ ብሄርተኝነት እንዲሁም የህዳጣንንና ስደተኞችን መድልዎና ጠላትነት የሚያስፋፋ ንግግርን ያጠቃልላል። 10 የአዉሮፓ ፀረ ዘረኝነት ኮሚሽን ምክረ ሃሳብም የጥላቻ ንግግርን ምንነት በእጅጉ በመለጠጥ ማንኛዉንም ግለሰብ ወይም ቡድን ዘር፥ ፆታ፥ ሃይማኖት፥ ቋንቋ፥ ወይም ሌላ መለያ መሰረት በማድረግ የሚደረግ ስድብ፥ ማንቋሸሽና አሉታዊ ንግግር ሁሉ የጥላቻ ንግግር ተደርጎ እንደሚቆጠር ይገልፃል። 11 የአዉሮፓ ህብረት ምክረ ሃሳብ የዘር ፍጅት መካሄዱን መካድ ፥ ማጣጣል ወይም መደገፍን አባል ሃገራት እንደ ጥላቻ ንግግር በመቁጠር በወጀለኛ ህጋቸው ዉስጥ እንዲያካትቱ ያሳስባል።12 8 “Everyone has the right to freedom of expression. This right shall include freedom to hold opinions and to receive and impart information and ideas without interference by public authority and regardless of frontiers. This Article shall not prevent States from requiring the licensing of broadcasting, television or cinema enterprises,” Art 10(1) European Convention on Human Rights, 1950. 9 “The exercise of these freedoms, since it carries with it duties and responsibilities, may be subject to such formalities, conditions, restrictions or penalties as are prescribed by law and are necessary in a democratic society, in the interests of national security, territorial integrity or public safety, for the prevention of disorder or crime, for the protection of health or morals, for the protection of the reputation or rights of others, for preventing the disclosure of information received in condence, or for maintaining the authority and impartiality of the judiciary,”Art 10(2), ECHR. 10 Committee of Ministers of the Council of Europe Recommendation No R 97(20) 30.10.1997 on “hate speech” “All forms of expression which spread, incite, promote or justify racial hatred, xenophobia, antisemitism or other forms of hatred based on intolerance, including: intolerance expressed by aggressive nationalism and ethnocentrism, discrimination and hostility against minorities, migrants and people of immigrant origin” 11 European Commission against Racism and Intolerance (ECRI), General Policy Recommendation No 15 on ”hate speech” 8.12.2016 “the use of one or more particular forms of expression – namely, the advocacy, promotion or incitement of the denigration, hatred or vilification of a person or group of persons, as well any harassment, insult, negative stereotyping, stigmatization or threat of such person or persons and any justification of all these forms of expression – that is based on a non- exhaustive list of personal characteristics or status that includes “race”, colour, language, religion or belief, nationality or national or ethnic origin, as well as descent, age, disability, sex, gender, gender identity and sexual orientation” 12 Council framework decision on “combating certain forms and expressions of racism and xenophobia by means of criminal law” 2008/913/JHA, 28.11.2008 በአንዳንድ የአዉሮፓ አገሮችን ያለዉን የጥላቻ ህግ መዳሰሱ በአዉሮፓ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ ለመረዳት ያስችላል። ጀርመን በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ከደረሰባት ከፍተኛ ዉድቀት የተነሳ ጠንካራ የሚባል የጥላቻ ህግ አውጥታለች። በጀርመን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ማንኛዉም ሰዉ የህዝብን ሰላም ለማወክ አንድን የብሄር፥ ዘር፥ ሃይማኖት ማህበረሰብ ወይም ግለሰቦችን ያላቸዉን ሃይማኖት ወይም ዘር መሰረት በማድረግ የጥላቻ ቅስቀሳ ያደረገ ወይም እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎችን ክብር የሚነካ ስድብና ማዋረድ ያደረገ ከሶስት ወር እስከ አምስት አመት እስራት ያስቀጣል።13 ጀርመን ዉስጥ የናዚን ምልክት ማሳየት ወይም በአይሁዳዉያን ላይ የደረሰዉን የዘር እልቂት መካድም እንደ ጥላቻ ወንጀል በመቆጠር ያስቀጣል። ከዚህ ባለፈ ጀርመን በቅርቡ ያወጣችዉ በኢንተርነኔት የሚተላለፉ የጥላቻ ወይም ህገወጥ መልእክቶችን የሚቆጣጠር አዋጅ የማህበራዊ የትስስር መረብ ባላቤቶች ህገወጥ የሆኑ መልእክቶችን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ካላነሱ ድርጅቶች በሚልዮን ዶላር የሚቆጠር ቅጣት እንዲጣልባቸዉ ያዝዛል።14 የጀርመን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ የጥላቻን ህግ ከመከልከል ባለፈ ‘ኢ ህገ መንግስታዊ’ የፖለቲካ ድርጅቶችን አርማዎችና ምልክቶች በአደባባይ መያዝን ህገ ወጥ በማድረግ በተለይ የናዚ ፓርቲ መለያዎች ለምርምርና ትምህርታዊ አላማዎች ዉጪ በማንኛዉም መልኩ መጠቀም የተከለከለ የጥላቻ ንግግር አካል አድርጎ ያስቀምጠዋል። ፊንላንድም ማንኛዉም ዘርንና ሃይማኖትን መሰረት አድርገው የሚነዙ የጥላቻ ቅስቅሳዎችን በህግ ከልክላለች። 15 በተለይም የጥላቻ ንግግሩ የዘር ፍጅት እንዲከሰት የሚቀሰቅስ ከሆነ ከበድ ያለ ቅጣትን ያስከትላል።16 እንግሊዝም በተመሳሳይ 13 Incitement of the People (Volksverhetzung) is defined by § 130 (Incitement to hatred) Section 1 of the Criminal Code፡ Whosoever, in a manner capable of disturbing the public peace: 1. incites hatred against a national, racial, religious group or a group defined by their ethnic origins, against segments of the population or individuals because of their belonging to one of the aforementioned groups or segments of the population or calls for violent or arbitrary measures against them; or 2. assaults the human dignity of others by insulting, maliciously maligning an aforementioned group, segments of the population or individuals because of their belonging to one of the aforementioned groups or segments of the population, or defaming segments of the population, shall be liable to imprisonment from three months to five years. 14 Germany’s NetzDG and the Threat to Online Free Speechhttps://law.yale.edu/mfia/case-disclosed/germanys- netzdg-and-threat-online-free-speech 15 Section 10 - Ethnic agitation (511/2011) A person who makes available to the public or otherwise spreads among the public or keeps available for the public information, an expression of opinion or another message where a certain group is threatened, defamed or insulted on the basis of its race, skin colour, birth status, national or ethnic origin, religion or belief, sexual orientation or disability or a comparable basis, shall be sentenced for ethnic agitation to a fine or to imprisonment for at most two years. 16 Section 10(a) – Aggravated ethnic agitation (511/2011) If the ethnic agitation involves incitement or enticement (1) to genocide or the preparation of genocide, a crime against humanity, an aggravated crime against humanity, a war crime, an aggravated war crime, murder, or manslaughter committed for terrorist intent, or (2) to serious violence other than what is referred to in paragraph 1 so that the act clearly endangers public order and safety, and the ethnic agitation also when assessed as a whole is aggravated, the offender shall be sentenced for aggravated ethnic agitation to imprisonment for at least four months and at most four years.[1] ማንኛዉም ሰዉ ጥላቻን መሰረት ያደረገ የፅሁፍም ሆነ ሌላ አይነት ምልክት በመጠቀም የዘር ጥላቻን ለመቀሰቀሰ የሞከረ ከባድ የእስር ጥቃት ያስከትላል።17 በሁሉም የአዉሮፓ አገሮች የጥላቻ ንግግርን የሚቆጣጠሩ ህግጋት ተግባራዊ ተደርገዋል። ከአዉሮፓ በተቃራኒዉ በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ አካል ተደርጎ ስለሚቆጠር ንግግሩ ብቻዉን አያስቀጣም። በአሜሪካ ዉስጥ ያለዉን ሰፊ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የመጀመርያዉ የህገ መንግስት ማሻሻያ ተብሎ በሚታወቀዉ ህግ ዋስትና ያገኘ ነዉ። በዚህ ህግ መሰረት የአሜሪካ ኮንግረስ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን፥ የመሰብስብንና የእምነት ነፃነትን የሚገድብ ምንም አይነት ህግ ማዉጣት አይችልም።18 የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት የጥላቻን ንግግሮችን አስመልክቶ የተለያዩ ዉሳኔዎች የሰጠ ቢሆንም የጥላቻ ህግን እንደ ወንጀል ቆጥሮአቸዉ አያዉቅም። ፍ/ቤቱ እ.ኤ.አ. በ 1969 ዓም በሰጠዉ ዉሳኔ መንግስት የጥላቻ ንግግሩ ረብሻን የመቀስቀስ እድሉ የማይቀር ከሆነ ብቻ መንግስት እንዲህ አይነቱ ንግግር ገደብ ሊጥልበት እንደሚችል ይፈቅዳል።19 ከዚህ ዉጭ ግን አንድ ንግግር የዘር ጥላቻን የሚመመለከት ነው በሚል ብቻ በህግ አያስጠይቅም። የጥላቻ ንግግር ገደብ እንዲዲደረግበት የሚጠይቁ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም እስከ አሁን የጥላቻ ንግግርን የሚፈቅደዉ ህግ አልተሻሻለም። አሜሪካ ህገ መንግስት ሃሳብን በነፃነት መግለፅ ያለ ገደብ የተጠበቀ በመሆኑ ከጥላቻ ንግግር ( hate speech) ይልቅ የጥላቻ ወንጀል ( hate crime) በህግ ከባድ ቅጣት ያስከትላል። ማንኛዉም የዘር ጥላቻን መሰረት አድርጎ በንብረት ወይም በሰዉ ላይ የሚፈፀም የጥላቻ ወንጀል ተደርጎ ይቆጠራል። 20 በአሜሪካን ህግ አንድ ሰዉ በዘር ወይም ሃይማኖታዊ ጥላቻ ላይ ተመስርቶ የሚፈፅመዉ ማንኛዉም ጥቃት ከፍተኛ የሆነ የወንጀል ተጠያቂነት ያመጣል። የሜሪካን ህግ ከፍተኛ ትኩረት የሚያደርገዉ ከጥላቻ ንግግር ይልቅ የጥላቻ ወንጀሎች በጥብቅ መከታተል ላይ ነዉ ። 2. ዘር ተኮር ፖለቲካና የጥላቻ ንግግር በአለማችን ያሉት ዴሞክራሲያዊ አገሮች መሰረት የሆነዉ ሌብራል አስተሳሰብ ዜጎች ያላቸዉን የሃይማኖትና የዘዉግ ማንነት ወደ ጎን በመተዉ ዜጎች በሰዉነትወይም ዜግነት እኩል መብት እንዲኖራቸዉ በማድረግ ከጎሳና ሀይማኖት ልዩነት ምክንያት ሊፈጠር የሚችለዉን ግጭት በማስወገድ የተረጋጋና የበለፀገ ማህበረሰብ እንዲፈጠር አስችሎአል። አዉሮፓውያን ለረጅም 17 Public Order Act 1986 prohibits, by its Part 3 A person who uses threatening, abusive or insulting words or behaviour, or displays any written material which is threatening, abusive or insulting, is guilty of an offence if— (a) he intends thereby to stir up racial hatred, or (b) having regard to all the circumstances racial hatred is likely to be stirred up thereby. Offences under Part 3 carry a maximum sentence of seven years imprisonment or a fine or both. 18 Amendment I፡ Congress shall make no law respecting an establishment of religion, or prohibiting the free exercise thereof; or abridging the freedom of speech, or of the press; or the right of the people peaceably to assemble, and to petition the government for a redress of grievances. 19 Brandenburg v. Ohio, 395 U.S. 444 (1969) 20 The FBI has defined a hate crime as a “criminal offense against a person or property motivated in whole or in part by an offender’s bias against a race, religion, disability, sexual orientation, ethnicity, gender, or gender identity.” ዘመናት በሃይማኖትና ቋንቋ ልዩነት እርስ በርስ በጦርነት ሲታመሱ ከኖሩ በሁዋላ በመጨረሻዉ ብቸኛ መፍትሄ አድርገዉ የወሰዱት ሃይማኖትንና ብሄርን ከፖለቲካ ሂደቱ በማስወጣት በሲቪል ብሄርተኝነት (civic nationalism) ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስርአት ማካሄድ ነው። በተቃራኒው ከሊብራል ፖለቲካዊ እሳቤ ያፈነገጠዉ ፋሽዝም በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ወቅት የፈጠረው እልቂት፤ አክራሪ ብሄርተኝነት የሚወልደዉ ጥላቻ ምን ያህል ጥፋት እንደሚያደርስ በመረዳት መረዳት ይቻላል። በታዳጊ አገሮች ያለዉ ሁኔታ ከአውሮፓ በእጅጉ የተለየ ነዉ። ቅኝ ገዥዎች በአፍሪካ ዉስጥ ያላቸዉን ስልጣን ለማስጠበቅ ህዝቡን እርስ በርስ በጎሳ እንዲከፋፈል በማድረግ ፖለቲካዊ ትርጉም ያልነበራቸዉን የቋንቋ ልዩነቶች በማራገብ ህዝቡን የጎሪጥ እንዲተያይ በማድረግ ያልተቋረጠ ግጭት እንዲፈጠር አድርገዋል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ቤልጅየም በሩዋንዳ የፈፀመችው የዘር መከፋፈል ነዉ። አንድ ቋንቋ የሚናገሩትን የሁቱና የቱትሲ ጎሳዎች አንዱን የበላይና ሌላዉን የበታች አድርጎ በማቅረብ እርስ በርስ እንዲቃቃሩ በማድረግ በመጨረሻ ለተፈፀመዉ የሩዋንዳ ዘር ማጥፈት ወንጀል ምክንያት ሆነዋል። በ 1994 ዓም በሩዋንዳ ከተፈፀመዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል በሁዋላ ሩዋንዳ ዉስጥ ማንም ሰዉ ሌላዉን ጎሳህ ምንድን ነዉ ብሎ እንዳይጠይቀዉ በመከልከሉ አገሪቱ ብሄርን መሰረት ካደረገ ጥላቻና ግጭት ነፃ ሆናለች። በሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ቅኝ ገዥዎች ያመጡትን የዘር መከፋፋል በማስወገድ ማንኛዉም የዘር ጥላቻን መሰረት አድርጎ በንብረት ወይም በሰዉ ላይ የሚፈፀም የጥላቻ ወንጀል ተደርጎ ይቆጠራል። 21 የብሄር ፖለቲካ የሚያመጣዉን ጠንቅ በመረዳት ብዙዎች የአፍሪካ አገሮች በህገ መንግስታቸዉ በዘር ወይም በሃይማኖት ላይ የተመሰረት የፖለቲካ አደረጃጀትንም ከልክለዋል። 3. የብሄር ፖለቲካ የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ ጥንታዊ ሃገረ መንግስት የነበራትና ብቸኛዋ በአዉሮፓዉያን ቅኝ ያልተገዛችዉ ኢትዮጵያ ደግሞ በተቃራኒዉን ዘርን መሰረት ባደረገ ፖለቲካ ተጠላልፋ ህልዉናዋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። በሰኔ 2019 የወጣዉ የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜታ እንደዝገበዉ ኢትዮጵያ በአገሪቱ በተፈጠረዉ ዘርን ማዕከል ባደረገ ጥቃት ወደ ሶስት ሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸዉ እንደተፈናቀሉ ገልጿል። ይህም ሁኔታ አገሪቱን በተፈናቃዮች ቁጥር በአለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን አድርጓታል። የዚህ መፈናቃልና ስደት ብቸናው ምክንያት አገሪቱ ለአለፉት 28 አመታት ተግባራዊ ያዳረገችዉ ዘርን መሰረት ያደረገዉ የፖለቲካ ስርአት መሆኑ ግልፅ ነዉ። በተማሪዎንች እንቅሳቅሴ በ 1960ዎቹ ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ብቅ ያለዉ የብሄር ፖለቲካ ከጅምሩም በጥላቻ የተወለደ ነዉ። ማርክሲዝምንም ሆነ የአገሪቱን ታሪክ ያልተገነዘቡት የዩንቨርስቲ ተማሪዎች የኢትዮጵያ ችግር ‘የብሄር ጭቆና ነዉ’ በሚል በወስዱት አቋም ባለፉት 50 አመታት የአገሪቱን ፖአቲካ ትርምስ ዉስጥ ከቷታል ። በተለይ ህወሃት፥ ሻእብያና ኦነግን የመሳሰሉት የብሄር ድርጅቶች ‘አማራ ጨቁኖናል’ በሚል ተንሳስተዉ ተከታዮቻቸዉ ፀረ አማራ አስተሳሰብ እብዲኖራቸው በማድረግ አማራዉ ማህበረሰብ በሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደ ጠላት እንዲያታይ አድርገዉታል። በተለይም ህወሃት በ1968 21 The FBI has defined a hate crime as a “criminal offense against a person or property motivated in whole or in part by an offender’s bias against a race, religion, disability, sexual orientation, ethnicity, gender, or gender identity.” ዓም ባወጣዉ የፖለቲካ ፕሮግራም አማራዉ የትግራይ ጠላት እንደሆነ በማስቀመጥ የትጥቅ ትግል አድርጎ የፖለቲካ ስልጣን በመያዝ የጥላቻ ፕሮግራሙን ወድ ተግባር የሚቀይርበት እድል አግኝቶ አማራዉ በገዛ አገሩ እንደ ጠላት የሚታይበት ስርአት ላለፉት 28 አመታት ተግባራዊ ተደርጓል። ይህ ስርአት በ 1983 ዓም ከተደረገዉ ህወሃት መራሹ የሽግግር ሂደት ጀምሮ አማራዉን ያገለለና አማራን እንደ ጠላት የሚቆጠር ሀገ መንግስት ቀራጾ የህዋሀትን ማኒፌስቶ ተግባራዊ አድርጓል። ህውሃት በጠራዉና በሰኔ 1983 ዓም በተካሄደው የሽግግር መንግስት ጉባኤ ሁሉም ብሄረሰቦች ከሞላጎደል ሲወከሉ አማራዉ ግን ሆነ ተብሎ እንዲገለል ተደርጓል። ሀወሃት ህገ መንግስት ወደ ማርቀቅና ማፅደቅ ሂደት ሲገባም አጠቃላይ ውይይቱና ቅኝቱ አማራውን በማግለልና በአማራ ጥላቻ ላይ ያተኮረ ነበር። የህገ መንግስቱ መግቢያ እንደሚስረዳዉ የህገ መንግስቱና የፌዴራል ስርአቱ ዋና ግብ ‘በታሪካችን የወረስነዉን የተዛባ ግንኙነት በማረም’ ላይ ያተኮረ ነዉ በሚል አማራዉ በቀደመዉ ዘምን የተለየ ጥቅም እንደነበረዉ በማስመሰል የተቀመጠው መርህ ህገ መንግስታዊ ስርአቱ አንድን ብሄር ለማትቃት የተዘጋጀ ሰነድ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ። ህገ መንግስቱ ከመውጣቱ በፊት የህዋሀት ማኒፌስቶን መሰረት በማድረግ አማራን ሊጎዳ በሚችል መልኩ አገሪቱ በዘር እንድትሸነሸን ከመደርጉም በላይ በህገ መንግስት የዘር ፓለቲካን በመፍቀድ አሁን ላለልበት መስቀለኛ መንገድ ዳርጎናል። በተለይ በመላ የአገሪቱ ክፍሎች ተበትኖ የሚኖረዉን የአማራ ማህበረሰብ በሚጎዳ መልኩ የተካለለው የክልሎች ድንበር አማራዉ በገዛ አገሩ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ እንዲኖር አድርጎታል። ክልሎቹ ሲካለሉ አማራው ወኪል ስላልነበረዉና ህወሃት አማራዉን ለመበቀል በውሰደው እርምጃ በአማራ እርስትነት የሚታወቁት አካባቢዎች እንዲውሰዱበት ተድርጓል። ባለፉት 28 አመታት አማራዉ ከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እንዲባረርና እንዲሰደድ ተደርጓል። ህወሃት አማራዉን ከፖለቲካና ኤኮኖሚያዊ መዋቅሮች በማባረር የበይ ተመልካች አድርጎታል። የአማራ ክልል ተብሎ በተዋቀረዉ አካባቢ የልማት ስራዎች እንዳይሰሩ በማድረግ ህቡን የማቆርቆዝ ስራዎች ተሰርተዋል። የማራዉን ሃብት ህውሃት ያለከልካይ በመዝረፍ የትግራይ ክልልን ለማልማት ተጠቅሞበታል። ህውሃት ፖአቲካዉን፥ ደህንነትና መከከላከያዉን በመቆጣተር የአንድን ዘር የበላይነት ለማረጋገጥ ከፍተና ጥረት አድርጓል። እንዲህ ስር የሰደደ መዋቅራዊ ችግር ባላበት አገር የጥላቻ ህግ ማዉጣት ያለዉን ችግር ምን ያህል ሊቀርፈዉ ይችላል የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ጥላቻና ግጭት ለማስወገድ የመጀመርያዉና ዋናው ህገ መንግስታዊ ስርአቱ ዘርን መሰረት አድርጎ የተዋቀረዉን በሌላ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መተካት ነዉ። የስርአቱ መሰረታዊ መዋቅር እስካልተስተካከለ ድረስ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጣለ ያለዉ ጥላቻና ግጭት የጥላቻን ህግ በማዉጣት አይፈታም ። ስለዚህ መንግስት ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባዉ ይህ አንድን ብሄር በጠላትነት በመፈረጅ የተቋቋመዉን ህገ መንግስት ማሻሻልና የዜጎች መብት በእኩልነት የሚያስተናግድ የፖለቲካ ስርአት መፈጠር ላይ ነዉ። 4. የጥላቻ ንግግር ህግ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የሚያመታዉ ተፅዕኖ ተግባራዊ እንዲሆን የታሰበዉ የጥላቻ ህግ በአገሪቱ ያለዉን ዉሱን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መብት የበለጠ ሊያዳክመዉ እንደሚችል ስጋት አለ ። በ1987 ዓም ባወጣዉ ህገ መንግስት በአንቀፅ 29 ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የተረጋጋጠ ቢሆንም ላለፉት 28 እንደታየዉ ሃሳብን የመግለፅ መብት ሙሉ በሙሉ ተገድቦ ቆይቷል። ህወሃት ስልጣን እንደያዘ በርካታ ጋዜጦችና መፅሄቶች በብዛት ይታታሙ ነበር። ነገር ግን መንግስት በህገ መንግስቱ ያስቀመጠዉን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነት ወድ ጎን በመተዉ በትቂት አመታት ዉስጥ ሁሉንም የግል ጋዜጦች በመዝጋት በመንግስት ሚድያዎች ብቻ ፕሮፓጋንዳ እንዲያስተላልፉ ይደረግ ነበር ። በተለይም የ1997 ምርጫ ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩ ሙሉ በሙሉ በመዘጋቱ ዜጎች ሃሳባቸዉን መግለፅ አይደለም አገዛዙን ያልደገፉ ዜጎች ሰርቶ የመኖር መብታቸዉን ሳይቀር አደጋ ዉስጥ ወድቆ ነበር። 22 መንግስት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለመገደብ በርካታ አፋኝ ህጎችን አዉጥቶ ተግባራዊ አድርጓል። ከነዚህ አፋኝ ህጎች ዋና ዋናዎቹ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህግ፥ የፕሬስና የመረጃ ነፃነት መብትና የፀረ ሽብር ህግ ዋና ዋናዎቹ ናችዉ። በተለይም በ 2001 ዓም የወጣዉ የፀረ ሽብር ህግ ሃሳብን የመግለፅ መብትን ሙሉ በሙሉ በመገደብ የፖለቲካ ምህዳሩና ኢኮኖሚዉ ሙሉ በሙሉ በአገዛዙ ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ ተደረገ። የሽብርተኝነትን ትርጉም አለአግባብ በመለጠጥ ህጋዊ የፖለቲካ ተቃዉሞንና ሃሳብን በነፃነት መግለፅን እንደ ሽብርተኛ በመቁጠር በርካታ የፖለቲካ መሪዎችና አባላት፥ ጋዜጠኞችና የመብት ታጋዮች ወህኒ እንዲወርዱ ተደርጓል። 23 ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ይህንን የፀረ ሽብር ህግ ለማሻሻል ሂደቶች ተጀምረዋል ቢባልም ሰኔ 15, 2011 ዓም የተከሰተዉን ግድያ ተከትሎ በርካታ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች፥ ጋዜጦችና የፖለቲካ ፓርቲዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በተወገዘዉ የፀረ ሽብር ህግ ክስ ቀርቦባቸዋል። ይህ አካሄድ ስርአቱን ለ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ያለዉን ቁርጠኝነት ጥያቄ ዉስጥ አስገብቶታል። 24 መንግስት ለስልጣኑ ያሰጉኛል ያላቸዉን የፖለቲካ ቡድኖች ለማጥቃት የፀረ ሽብር ህጉንና ሌሎች መደበኛ ህጎችን የሚጠቀም አገዛዝ ሊወጣ የታሰብዉን የጥላቻ ህግ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ሊጠቀምበት እንደሚችል ያሳያል። በተለይም ስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ሁሉንም የተቃዋሚ ሃይሎች በእኩል ዓይን እንደማይመለከት የሚያሳዩ ሁኔታዎች እየተበራከቱ መምጣታቸዉ የጥላቻ ህጉን የተወሰኑ የፖለቲካ ሃይሎችን ለይቶ ለማጥቃት እንደሚያዉለዉ አመላካች ነዉ። ይህንን ጥርጣሬ የሚያጠናክረዉ ባለፈዉ አንድ አመት የተካሄደዉ የፖለቲካ ለዉጥ አቅጣጫ የሌለዉ፥ ተቋዋማዊ ለዉጡ አስተማማኝ ያልሆነና የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች በተረኝነት ስም ፈላጭ ቆራጭ የሆኑበት ስርአት እየተፈጠረ መሆኑ ነዉ። 22 https://freedomhouse.org/report/countries-crossroads/2007/ethiopia 23 Ethiopia: Stop Using Anti-Terror Law to Stifle Peaceful Dissent,https://www.hrw.org/news/2011/11/21/ethiopia- stop-using-anti-terror-law-stifle-peaceful-dissent 24 Ethiopia Is at a ‘Very Critical Juncture’https://foreignpolicy.com/2019/06/24/ethiopia-is-at-a-very-critical-juncture-abiy-bahir- dar/ ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያዊነትንና አንድነትን ቢሰብኩም ዋና ዋና የስልጣን ቦታዎች በአንድ አካባቢ ሰዎች እየተያዘ እንደሆን በመታየቱ የህዝብ ቅቡልነታቸዉን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ አድርጓል ። አሁንም ስልታዊ በሆነ ሁኔታ ዋና ዋና የፍትህ ተቋማት በኦዴፓ ሰዎችና የዶ/ር አብይ የቅርብ ወዳጆች የተያዙ መሆናቸዉ የጥላቻ ህጉን በመጠምዘዝ ለፈለጉት አላማ ሊያዉሉት የሚችሉበት እድል ከፍተኛ ነዉ። ከዚህም በተጨማሪ የህወሃት ስርአት የሚመራባቸዉ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችና አደረጃጀቶች አሁንም ስራ ላይ ባሉበት ሁኔታ የጥላቻ ህጉ ቀደም ሲል የፀረ ሽብር ህጉ በመንግስት ላይ የሚደረጉትን ተቃዉሞዎች ለማዳፈን ጥቅም ላይ እንደዋለ አሁንም ለተመሳሳይ አላማ የማይዉልበት ምክንያት አይኖርም። ህወሃት ያቋቋማቸዉ ህገ መንግስታ ተቋማት ባልተለወጡበት ሁኔታና ተቃዋሚ ሃይሎችን ለማጥቃት ስራ ላይ እየዋሉ መሆኑ ሲታይ የጥላቻ ህጉን ተግባራዊ ማድረግ በተለየ መልኩ ስርአቱን የሚቃወሙ ሃይሎችን ለማጥቃት ስራ ላይ እንደሚዉል እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ስለዚህ ይህ ህገ መንግስትና ጨቋኝ ተቋማት በተገቢዉ መልኩ ተሻሽለዉ በገለልተኛ ተቋማት ሳይተኩ ይህንን የጥላቻ ንግግር ህግ ተግባራዊ ማድረግ ላለፉት 28 አመታት የቀጠለዉን ፀረ ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ በአዲስ መልኩ ለማክናወን የታሰብ አዲስ እቅድ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። 5. ረቂቅ የጥላቻ ንግግር ህጉ ያሉበት ክፍተቶች በጠቅላይ አቃቢ ህጉ አማካኝነት የተሰራጨዉ ረቂቅ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣ አዋጅ ህጉን ለማወጅ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዳ የጥላቻ ንግግርና የሃስተኛ መረጃ ስርጭት የሚያስከትሉት ግጭትና ጉዳት ለእኩልነት፣ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ለሕዝቦች አንድነት ትልቅ ጠንቅ በመሆኑ ይህንን ለማስቆም አላማ ያደረገ መሆኑን ያትታል። በረቂቅ ህጉ ላይ እንደተገለፀዉ የጥላቻ ንግግር ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ምንም አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን የጥላቻ ንግግርን ለመቆጣጠር የተለየ ህግ ማዉጣት ያስፈልጋል ወይ የሚለዉ አንዱ ጥያቄ ነዉ። በኢትዮጵያ ህግ ዘርን፥ ሃይማኖትንና የፖለቲካ አመለካከት መሰረት ያደረገ ጥላቻ በወንጀል ህጉ የተከለከለ ነዉ።25 ህዝብን በማንኛዉም መንገድ ወደ ግጭት የሚመሩ ንግግሮችና ድርጊቶች በኢትዮጵያ ህግና ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸዉ አለም አቀፍ ስምምነቶች የተከለከሉ ድርጊቶች ናችዉ።26 ምንም እንኳን በማህበራዊ የትስስር መድረኮች የሚተላለፉትን የጥላቻ ንግግሮች ለመቆጣጠር ራሱን የቻለ ህግ ማስፈለጉ ቢታወቅም መንግስት የጥላቻ ንግግርን መቆጣጠር ከፈለገ በስራ ላይ ያሉትን ህጎች ተጠቅሞ ህግና ስርአትን በማስከበር ረገድ ብዙ እርቀት መሄድ ይችል ነበር። ያሉትን የህግ ድንጋጌዎች ተጠቅሞ የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ጥረት 25 የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 29(6) ፥ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 486 26 Article 20 (2) of the International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR) states: Any advocacy of national, racial or religious hatred that constitutes incitement to discrimination, hostility or violence shall be prohibited by law. Article 4, International Convention on the Elimination of Racial Discrimination, 1965 States “shall declare an offence punishable by law all dissemination of ideas based on racial superiority or hatred, incitement to racial discrimination, as well as all acts of violence or incitement to such acts against any race or group of persons of another colour or ethnic origin, and also the provision of any assistance to racist activities, including the financing thereof” በማድረግ ተቋማትን ማጠናከርና አቅሙን መፈተሽ ሲገባዉ በቀጥታ አዲስ ህግ ወደ ማርቀቅ መሄዱ ምን ያህል ዉጤታማ ሊሆን ይእላል የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ሌላዉ ስጋት በረቂቅ ህጉ ዉስጥ የሚታዩት ክፍተቶች ናቸዉ። ረቂቅ ህጉ የጥላቻ ንግግርን ሲተረጉመዉ የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ዉጪያዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ ፣ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳሰስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈጸም፤ ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ንግግር ነው በማለት ይገልፀዋል።27 ይህ አገላለፅ እጅግ ለትርጉም የተጋለጠና ቀደም ሲል የፀረ ሽብር ህጉን በመጠምዘዝ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ መብትን ለመደፍጠጥ በቀላሉ ጥቅም ላይ መዋል የሚችልበትን እድል ሊፈጥር ይችላል። በአዋጁ’ እኩይ አድርጎ ማቅረብ፥ ማንኳሰስ’ ማለት ምን ማለት ነዉ? መንግስታዊ ስርአቱ ዘርን መሰረት አድርጎ በተዋቀረበት አገር አንዱ ብሄርን ማንኳሰስ ብርቅ ነው ወይ? አማራዉ 28 አመታት ሙሉ በመንግስት ደረጃ ነፍጠኛና ትምክህተኛ እየተባለ ሲንኳሰስ አልነበረም ወይ? አሁንስ እየተንኳሰሰ አይደለም ወይ? ይህን ስርአት እንዲቀትል እየፈለጉ ብሄርን የሚያንንኳስስ ንግግር እንዴት ህገ ወጥ ማድረግ ይቻላል? አንድን ግለሰብ ወይም ቡድን ’ እኩይ አድርጎ ማቅረብ፥ ወይም ማንኳሰስ’ ትችት ከማቅረብ በምን ይለያል? ማነዉ አንድን ድርጊት ’ እኩይ አድርጎ ማቅረብ ወይም ማንኳሰስ’ ነዉ ብሎ ብይን የሚሰጠዉ? ይህንን ስራ በብቃትና በገለልተኛነት ሊወስን የሚችል ፖሊስ፥ አቃቢ ህግ ወይም ፍርድ ቤት አለ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሳል። እንደተለመደዉ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት መሪዎች ይህንን ህግ አምርረዉ የሚተቹዋቸውን ተቃዋሚዎች ለመምታት ሊጠቀሙበት የመቻላቸዉ እድል ከፍተኛ ነዉ። በረቂቅ አዋጁ አንቀፅ 4 እና 5 የጥላቻ ንግግርንና የሃሳት መረጃን አስመልክቶ የተገለፀዉ የበለጠ ስጋትን የሚጭር ነዉ። አንቀፅ 4 የጥላቻ ንግግርን አስመልክቶ ሲያስቀምጥ ‘ሆነ ብሎ የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ዉጪያዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ ፣ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳስስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈጸም፤ ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል መልእክቶችን በመናገር፤ ፅሁፍ በመፃፍ፤ ምስል፤ ስእል፤ የኪነጥበብ እና እደ ጥበብ ውጤት፤ የድምጽ ቅጂ ወይም ቪድዮ በማተም፤ በማሳተም ወይም በማሰራጨት፤ መልእክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት፤ ወይም በሌሎች ማናቸዉም መገናኛ መንገዶች ለህዝብ መልእክቱ እንዲደርስ ማድረግ ክልክል ነው ’ ይላል። ከፍ ሲል እንደተገለፀዉ ይህም ክፍል እጅግ ሰፊና ለትርጉም በቃላሉ የተጋልጡ አባባሎችን የያዘ ነዉ። ብሄርን ፥ ሃይማኖትን፥ ፆታን፥ ቋንቋን መሰረት በማድረግ የሚቀርቡ ትችቶችን በቀላሉ በዚህ አንቀፅ መሰረት የጥላቻ ንግግሮች ናቸዉ በሚል ክስ ለማቅረብ ያስችላል። በተለይ ሁሉም ወገን በብሄር ተደራጅቶ ዳርና ዳር ቆሞ በሚሰዳደብበትና አገሪቱን ለሚንጣት የጎሳ ፖለቲካ ፖለቲካዊ መፍትሄ ባልተቀመጠበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ህግን በማዉጣት የጥላቻ ንግግር እቆጣጠራለሁ 27 በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣ አዋጅ፥ አንቀፅ 2(2) ማለት የማይቻልና ይልቁንም በቀላሉ መንግስትን የሚቃወሙትን ለማጥቃት ስራ ላይ ሊዉል የሚችል አንቀፅ ነዉ። በተለይም ይህ አንቀፅ በማህበራዊ ሚድያ የሚደረጉትን የሃሳብ ልዉዉጦች ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ ግልፅ ነዉ። አዋጁ በአንቀፅ 5 የሚደነግገዉ የሃሰተኛ መረጃ አንቀፅም ሃሳብን የመግለፅ መብትን የሚገድብ ነዉ። ይህ አንቀፅ ‘የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው፣ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልጽ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ መረጃን ሆነ ብሎ በማንኛውም መንገድ ማሰራጨትና ለህዝብ እንዲደርስ ማድረግ የተከለከለ ነው’ ይላል ። መረጃ በፈጠን መንገድ በሚተላልፍበት በዚህ ዘመን አንድ ሰዉ የሚያሰራጨዉ መረጃ እዉነት አለዉ ብሎ ያመነበት ከሆነ ከማሰራጨት ሊገደብ አይገባም። ይህንን ሁኔታ ለመቆጣጠርም እጅግ አዳጋችም ነዉ። ማህበራዊ ሚድያዉ በአለም አቀፍ ደረጃ የሃሰት መረጃን በማሰራጨት የሚነቀፍ መሆኑ ቢታወቅም ችግሩ ግን የሚቀረፈዉ ግልፅ እና ተጠይቂነት ያለው የመንግስት አሰራርና ተቋማት በመገንባት ነዉ። የመንግስት አካላት ተጠያቂነት ሳይኖራቸዉና ራሱ መንግስት የሃሰት መረጃን በሚያሳራጭበት አገር ህዝብን ለማፈን የሚደረግ እንቅስቃሴ በቋፍ ያለዉን የአገሪቱን ሁኔታ የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል ። የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት የሆነዉ የሂማን ራይትስ ዋች ( Human Rights Watch) በቅርቡ ለቂቅ የጥላቻ ንግግር ህጉን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ እንደገልችፀዉ ሊወጣ የታሰበው ህግ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ሊጎዳ እንደሚችልና የጥላቻ ንግግር ለመቆጣጠር የተሻለዉ አካሄድ ህዝብን ማስተማርና መንግስት ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ሲያዳብር መሆኑን አስገንዝቧል። ማጠቃለያ የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ ዉስጥ ባለዉ የፖለቲካ ሁኔታ የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና ከፈተኛ ችግር እየፈጠረ ይገኛል። ከዚህ አንፃር መንግስት በስራ ላይ ያሉትንም ሆነ አዳዲስ ህጎችን በማዉጣት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ቢያደርግ ክፋት የለዉም። ነገር ግን በአገራችን ሁኔታ የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል ምን አይነት መፍትሄ ያስፈልጋል የሚለዉ ትልቅ ትኩረት የሚጠይቅ ጉዳይ ነዉ። በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ባወጣዉ የድርጊት መርሃ ግብር መሰረታዊ መፍትሄዎችን ያስቀምጣል። 29 የመንግስታቱ ድርጅት የድርጊት መርሃ ግብር የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ትልቅ ትኩረት የሰጠዉ የጥላቻ ንግግር ዋናዉ መነሻ ምክንያትና የሚያባብሱትን ሁኔታዎችን መለየት ነዉ። ይህን ሁኔታ በአገራችን ሁኔታ ስናየዉ አሁን በከፈተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ላለዉ የጥላቻ ንግግር ስር መሰረቱ አገሪቱ ባልፉት 28 አመታት የተከተለችዉ ጎሳን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ስርአት መሁኑን ብዙዎች ይስማሙበታል። ይህ ስርአት የብሄር መብቶችን ለማከበር ነዉ የሚል ትርጉም ቢሰጠዉም መነሻዉና መድረሻዉ ግን ጥላቻ ነዉ። ይህንን ህገ መንግስት ተሸክመን የጥላቻ ንግግርን ዋጅ በማዉጣት እናሶግደዋለ ማለት የዋህነት ነዉ። ስለዚህ የመንግስት ትልቁ ትኩረት ሊሆን የሚገባዉ ይህን ጥላቻን የሚፈለፍል ስርአት ዜጎች በእኩልነት በሚኖሩበት ስርአት መቀየር ካልተቻለ ጥላቻ የማህበረሰቡ ጠንቅ ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር ነገር ነዉ። የመንግስታቱ ድርጅት የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ሌላዉ ትኩረት ያደረገባቸዉ ጉዳዮች የጥላቻ ንግግር ሰለባዎችን መርዳት፥ የጥላቻ ንግግር የሚያራምዱትን እንዲቀራረቡ ማድረግ፥ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማስተማርና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አሳታፊ አሰራር ማስፈን ናቸዉ። ከዚህ ዝርዝር የጥላቻ ህግን መጠቀም የመጨረሻው አማራጭ እንደሆነ እንረዳለን። አገራችንን ከጥላቻና መለያየት ለማዳን ዋናዉ መንገድ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መፍትሄዎች ላይ ማተኮር ነዉ። ብሄራዊ እርቅና መግባባት፥ ህብረተሰቡም ማስተማር፥ መንግስታዊ ተቋማት ከአድልዎ ነፃ ማደረግ፥ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት ስርአት መገንባት የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል። የጣላቻ ንግግር ህግ ማዉጣት በራሱ ችግር ባይሆንም ውስብስብ ከሆነው የአገራችን ሁኔታ አንፃር ይህን ህግ ተግባራዊ በማድረግ ችግሩን ለመፍታት መሞከር ትልቅ ችግር ሊፈጥር ስለሚችል ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
612
መጥላት ላለብን የጥላቻ ንግግር የተጨማሪ ሕግ አስፈላጊነት Print Email ኢትዮጵያውን የሚሳተፉባቸውን የማኅበራዊ ሚዲያዎች ለሚጠቀምና ሌሎች ተጠቃሚዎች የሚጽፏቸውን ወይንም የሚጭኗቸውን ጽሑፎች፣ ምሥሎችና ድምፆች ለሚከታተል ሰው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድ ግልጽ የሆነ አዝማሚያ እያደገ መምጣቱን ያስተውላል፡፡ ይኼውም ጥላቻን ያዘሉ ንግግሮች መበራከታቸውን ነው፡፡ የጥላቻ ንግግር እጅግ ብዙ የሆኑ በጎ እሴቶችን የመናጃ መንደርደሪያ ነው፡፡ የጥላቻ ንግግር ጥላቻ ላይ የተመሠረቱ ወንጀሎችን መጥሪያ ነው፡፡ የጥላቻ ንግግር አድልኦና መገለልን ያመጣል፡፡ የጥላቻ ንግግር የአንድን ብሔር አባላት፣ የሃይማኖት ተከታዮች፣ ስደተኞችንና ሌሎች ቡድኖችን እንበለ ምክንያት በጭፍኑ እንዲጠሉ መንገድ ያለሰልሳል፡፡ የከፋው ደግሞ የዘር ማጥፋትን ወይንም ቡድን ጠረጋን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በበርካታ አገሮችም ተከስቶ ነበር፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አይሁዶችን የጀርመን ናዚዎች ከማጥፋታቸው በፊት በርካታ አይሁዶች በጀርመንና ሌሎች አገሮች በተሻለ የኑሮ ደረጃ ይመሩ ስለነበር እንደ ባለጠጋ ጥገኛ ተሕዋስያን (Wealthy parasite) ተደርገው ተስለዋል፡፡ ጀርመኖች ደግሞ ከሌሎች የላቁ እንደሆኑ ራሳቸውን ቆጥረዋል፡፡ ሁቱዎች በረሮ እንጂ ቱትሲዎች ብሎ መጥራት አቁመው ነበር፡፡ ይህ እንግዲህ ጥላቻው በሕዝብ ደረጃ ከፍ ባለበት ወቅት ነው፡፡ አጠራሩንም አንዱ ቡድን በጅምላ የሌላውን ተቀብሎ አጽድቆታል ማለት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱን ፍረጃም ይሁን ስያሜ መነሻው እውነት እንዲሆን አይጠበቅም፡፡ ሕዝቡም ሲጋራው በምክንያታዊነት አስቦና አሰላስሎ አይደለም፡፡ ምክንያታዊነት የግለሰብ ባህርይ እንጂ የሕዝብ አይደለችም፡፡ ቡድንን ጅምላዊነት ያጠቃዋል፡፡ እንደ ግለሰብ ሲታሰብ ወለፈንድና ሐሰት መሆኑን የምንረዳውን ነገር ከቡድናችን ጋር ስንቀላቀል ግን እንተወዋለን፡፡ የጥላቻ ንግግርም ቡድናዊ ቅርጽ ለመያዝ በእጅጉ የተጋለጠ ነው፡፡ ታሪክም ያሳየን ይኼንኑ ነው፡፡ በርካታ አገሮች ከራሳቸውም ገጠመኝም ይሁን ከሌሎች የታሪክ ጠባሳ በመማር የጥላቻ ንግግሮችን የሚከለክሉ ሕግጋት አውጥተዋል፤ ተግባራዊ ለማድረግም ተቋማትን አደራጅተዋል፡፡ የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራትም የጥላቻ ንግግር ምንነቱን፣ ይዘቱን፣ መንስዔውን፣ መዘዙንና ሌሎችም ጭብጦች ላይ በመመርኮዝ ጥናት ያጠናሉ፤ የፍትሕ ተቋማትን ያሠለጥናሉ፤ ሕዝብን የማንቃት ሥራ ይፈጽማሉ፡፡ ብሎም ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ለመገንባት አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ በዚህ መንገድ ብዙ ማኅበረሰቦች በሠላምና በመቻቻል እንዲኖሩ እያደረጉ ነው፡፡ ይህ ጽሑፍ የጥላቻ ንግግርን ምንነትና ከሌሎች ንግግሮች የሚለይበትን መንገዶች ይገልጻል፡፡ የኢትዮጵያን የሕግ ሁኔታ በመቃኘት የተጨማሪ ሕግ ወይንም ሥርዓት አስፈላጊነቱን በአንድ በኩል ከሕገ መንግሥቱ ጋር ለማጣጣም አስቸጋሪነቱን በሌላ በኩል ያሳያል፡፡ ይህን ለማድረግም ደግሞ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎች በመቃኘት እንዲሁም ከሌሎች አገሮች ሕግና አሠራር ጋር በማነፃፀር ያሉትን ክፍተቶች በመጠቆም ምን መደረግ እንዳለበት ጥቆማ ያቀርባል፡፡ የጥላቻ ንግግር ምንነትና መለያዎቹ የጥላቻ ንግግርን ምንነት በተመለከት ቁርጥ ያለና ወጥ ብያኔ የለም፡፡ ይሁን እንጂ በርካታ ብያኔዎች የሚጋሯቸው ነጥቦች አሉ፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የዘር ጥላቻን፣ የሌላ አገር ዜጋን ወይንም ስደተኛን በጭፍኑ መጥላትን፣ ፀረ ሴማዊነትን፣ ትዕግሥት አልባና አግላይ የሆነ ብሔርተኝነትን፣ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ብሔረሰቦችን ሰበብ እየፈለጉ መገለል እንዲደርስባቸው የሚሰብኩ፣ የሚያሠራጩ፣ የሚያነሳሱ፣ የሚያበረታቱና ትክክል እንደሆኑ ለማስረዳት የሚደረጉ ጥረቶች የያዙ ቃላዊ ገለጻዎች፣ ጽሑፎች፣ ምሥሎችና ሥዕሎች፣ ቅርጻ ቅርጾች በሙሉ የጥላቻ ንግግር ይሰኛል፡፡ ስለሆነም ንግግር (Speech) የሚለው ቃል ድምፅን ብቻ የሚያመለክት አይደለም፡፡ በዚህ ጽሑፍም ውስጥ የጥላቻ ንግግር ሲባል ድምፅን፣ ጽሑፍን፣ ምሥልን፣ ቅርፃ ቅርፅን፣ የድምፅና ምሥል ቅንብሮች፣ ካርቱኖችን ያካትታል፡፡ የጥላቻ ንግግር አድራጊው የተለያዩ ቡድኖችን ባላቸው ማኅበራዊ መሠረትና አቋም ወይንም ርዕዮተ ዓለምም ላይ በመመርኮዝ እነዚህ ቡድኖችን በጥቅል ወይንም በተናጠል አባሎቻቸውን መገለልና መድልኦ እንዲደርስባቸው ማድረግ ነው፡፡ እንደ አይሁዶች፣ ቱትሲዎች፣ ጂፕሲዎች፣ የአውስትራሊያ ነባር ሕዝቦች ብሔርን መሠረት ሊያደርግ ይችላል፡፡ በበርካታ አውሮፓና ሌሎች አገሮችም እንደሚፈጸመው ሃይማኖታዊ መነሻ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ቀለም ላይ የተመሠረት ጥቁሮች ላይ እንደደረሰው ሊሆን ይችላል፡፡ የጥላቻ ንግግር ውጤቱ ከማኅበራዊ ተቋማት ኢኮኖሚያዊ መስክ እንዲገለሉ ወይንም እንዳይሳተፉ ማድረግ ሲከፋው እንዲገደሉ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በአጭሩ ዘርን፣ ብሔርን፣ ሃይማኖትና እንደ ስደተኛነት ያሉ ማኅበራዊ መሠረቶችን ምርኩዝ አድርጎ የሚፈጸሙ ንግግሮች ከጥላቻ እስካልጸዱ ድረስ ወይንም ጥላቻ ካዘሉ የጥላቻ ንግግር ይባላሉ፡፡ ሕግም ሲወጣ ይኼንኑ ለመከልከል ነው፡፡ ተናጋሪውንም፣ ጥላቻን ያዘለ ንግግር ካደረገ የወንጀል ኃላፊነት እንዲኖርበት ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ የጥላቻ ንግግርን በቀላሉ መለየት አዳጋች ነው፡፡ አዳጋችነቱ የንግግሩ ሰለባ ለሆነው አይደለም፤ ለሌላ ወገን እንጂ በማር የተለወሰ ንግግር ሆነው የሚቀርቡ አሉ፡፡ ለምሳሌ፣ ቅኔያዊ ንግግሮች ይሆኑና ስናነባቸው ወይንም ስንሰማቸው ወይንም ስናያቸው በአንዴ የማናስተውላቸው አሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹን፣ ከአውሮፓዊው የሕግ አተረጓጎም ልማድ የሚያሳየን በዚህ መጠን የንግግር ነፃነት መገደብ ተገቢ አይደለም በሚል ምክንያት የሚያስቀጡ አለመሆናቸውን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጥላቻ የሌላቸው መሆናቸውን አያሳይም፡፡ ስለጥላቻ ንግግር የአሜሪካ መንገድ አሜሪካ ትልቅ ቦታ የምትሰጠው እሴት ቢኖር ነፃነት (Liberty) ነው፡፡ ነፃ ንግግር ደግሞ አንድም የሰው ልጅ ህልውና አካል ሲሆን፣ በሌላ መልኩ ደግሞ ነፃነትና ዴሞክራሲ ያለ ነፃ ንግግር ምንጊዜም ጎደሎ እንደሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም የአሜሪካ መርህ ነፃነትን ራሱን የሚያጠፋ እስካልሆነ ድረስ ንግግር ላይ ገደብ አይኖርም፡፡ በተለይም ደግሞ የንግግሩ ይዘት ጥላቻን ያዘለ ነው በሚል ሰበብ ብቻ ክልከላ የለም፡፡ ገደብ የሚደረገው ንግግሩ የሚደረገበትን ዐውድ በማየት ይሆናል፡፡ የተደረገው ንግግር የኃይል ድርጊት ላይ የተመሠረተ ሕገወጥ ድርጊት ለማስነሳት ቅርብ ከሆነ ሊገደብ ይችላል፡፡ ካልሆነ ንግግርን መልሶ በንግግር በመጋፈጥ እንጂ በመገደብና በማፈን ዴሞክራሲ አይሰፍንም የሚል ነው የአሜሪካ አካሄድ፡፡ የብዙኃኑ መንገድ በርካታ አገሮች ከአሜሪካ የተለየ መንገድ ነው የሚከተሉት አገሮች ለተለያየ እሴት ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ የእሴቶቻቸው መነሻ ደግሞ የራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡ ለአንዳንዶች እኩልት፣ ለሌሎች ሰብዓዊ ክብር ወይንም ተከባብሮና ተፈቃቅዶ መኖር ወይንም የእነዚህ ቅይጥ ሊሆን ይችላል፡፡ እኩልነትን የሚያስቀድሙት አንድን ግለሰብ ከሌላ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ ስለግለሰቡ ነጠላ ሕይወት ወይንም ምርጫ ሳይሆን ከሌሎች ጋር የሚኖረው መስተጋብር ነው ዋና ማጠንጠኛቸው፡፡ ሰብዓዊ ክብርን የሚመርጡ ደግሞ ማንም ሰው የሌላውን ስም ሳያጎድፍ፣ ሳያንኳስስ፣ ሳያጣጥል፣ ሳያገልል ወዘተ. እንዲኖርና መከባበር እንዲሰፍን ይመርጣሉ፡፡ በቡድኖች መካከል ተከባብሮና ተፈቃቅዶ መኖርን የሚመርጡም አሉ፡፡ ለእነዚህ እሴቶች ከፍተኛ ቦታ ለሚሰጡ አገሮች ነፃ ንግግር ለእነዚህ እሴቶች ማጎልመሻ እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም ሰብዓዊ ክብርን የሚነካ፣ ተቻችሎና ተፈቃቅዶ የሚኖርን ማኅበረሰብ እንዳይኖር እንከን የሚሆን፣ በማኅበረሰብ መከካል ያለው የባህል ሥሪት አንዱ ከአንዱ የሚበልጥ እንደሆነ የሚሰብክ ንግግር እንዲኖር አይፈቀድም ወይንም አይበረታታም፡፡ የኢትዮጵያንም ሕገ መንግሥት ስናጤነው ትልቁ እሴቱ የግለሰቦች ነፃነት ላይ የተመረኮዘና ግለሰብ ዜጎችን ነፃነት ሳይሆን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እኩልነትና ተከባብሮና ተፈቃቅዶ መኖርን የመረጠ ስለሆነ ነፃ ንግግር ወይንም ሐሳብን በነፃነት መግለጽ ለእነዚህ እሴቶች ተገዥ መሆኗ ግድ ነው፡፡ የአውሮፓውያኑም መንገድ ይኼው ነው፡፡ ከአሜሪካን ውጭ ያሉት አገሮች በሙሉ የጥላቻ ንግግርን ወንጀል አድርገዋል ማለት አይደለም፤ ያደረጉትም ቢሆኑ ተመሳሳይ ይዘት የላቸውም፡፡ ወንጀል ያደረጉበት ነባራዊ ምክንያትም ይለያያል፡፡ ወንጀል እንዲሆን በተለያዩ ምሁራንም የሚቀርበው ክርክር እንዲሁ ወጥ አይደለም፡፡ ወንጀል የሆነባቸውም አገሮችም ሕጎቻቸውን እንዲሰረዙ የሚቀርብ ክርክርና ውትወታ አለ፡፡ ኢትዮጵያም ወደፊት ይኼንን የሚመለከት ሕግ የምታወጣ ከሆነ ትርፍና ኪሳራዎቹን ለመለየት በሁለቱም ጎራ ከሚነሱት መከራከሪያዎች የተወሰኑትን ብቻ አቀርባለሁ፡፡ ንግግር፣ የጥላቻም ቢሆን ወንጀል መሆን የለበትም ባዮች የመጀመሪያው መከራከሪያቸው ንግግርን ወንጀል በማድረግ ከሚገኘው ጥቅም ይልቅ፣ ጥላቻ ባለው ንግግር የሚፈጠረውን ጉዳት መታገስ የሚያስገኘው ይበልጣል የሚል ነው፡፡ ንግግርን ማፈን በርካታ መብቶችን እንዲጣበቡ ያደርጋል፣ በርም ይከፍታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም መጥፎ ሐሳብ የሚጠፋውና ማምከኛ ሊሆን የሚችል ተቃራኒ ሐሳብ በማቅረብ እንጂ ንግግሩን በመከልከል አይደለም፤ መንግሥትም የምንናገረውን ነገር ይዘቱን ሊመርጥልን አይገባም፤ ግለሰቦችም ክፉን ከበጎ ለይቶ የማወቅ አቅምም ችሎታም ስላላቸው ይኼንኑ ነፃነታቸውን ማክበር ተገቢ ነው፡፡ ሕግም ቢሆን ክፉ የማሰብንና የመናገርን ባሕርይን ሊቀይር አይችልም፤ ስለሆነም ወንጀል ማድረጉ ፋይዳ ቢስ ነው ይላሉ፡፡ የጥላቻ ንግግር ይከልከል የሚሉት መከራከሪያዎች ጥላቻን ያዘለ ንግግር በብዙ ምክንያት ጠቃሚ አይደለም፣ አስጸያፊ ነው ይላሉ፡፡ ለዚህ ከሚያቀርቡት ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የንግግሩ ሰለባ የሚሆኑትን የአንድ ቡድን አባላት እንደ ጠላት እንዲቆጠሩ ያደርጋል፤ ለብዙ ነገሮች ተጠርጣሪዎች እንዲሆኑ ያመቻቻል፡፡ ሌላው መከራከሪያ ደግሞ ከሌሎች የማኅበረሰብ አባላት በእኩልነት አይታዩም፡፡ ለምሳሌ እንደ ተገንጣይ የሚሳሉ ከሆነ የመገንጠል ፍላጎት ከሌላቸው ጋር እኩል ተደርገው አይታዩም፡፡ ከዚህ ሌላ ደግሞ፣ በማኅበራዊ አቋማቸው ዝቅ ተደርገው እንዲታዩ ያደርጋል፡፡ ከሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር የተረጋጋና ቅንነት የተሞላበት ግንኙነት እንዳይኖር እንቅፋት ይፈጥራል፡፡ በግለሰቦችና በቡድኖች መካከልም ጥርጣሬና ውጥረት እንዲሰፍን ያደርጋል፡፡ አንዱ የሃይማኖት ተከታይ ወይንም የብሔር አባላት የበለጠ ለአገር አሳቢ ሌላውን ጠላት አድርጎ የመሳል አዝማሚያን ይፈጥራል፡፡ ችሎታቸውንና አቅማቸውን በተገቢው ሁኔታ እንዳይጠቀሙ ያደርጋል፤ የተወሰኑ ሰዎችን ባሕርይ ለጠቅላላው የማሳደግ አዝማሚያን ስለሚያበረታታ የቡድኑን አባላት በሙሉ ተጠቂና ሰለባ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ጥላቻ አዘል ንግግር መከልከል አለበት ይላሉ፡፡ የንግግር ነፃነት የሚገደብባቸው ምክንያቶች በሕገ መንግሥታችን አንቀጽ 29(6) ላይ በማያሻማና በግልጽ ቋንቋ እንደተገለጸው ሐሳብን በፕሬስና በማናቸውም መገናኛ ብዙኃን ማንኛውም ሰው ሲገልጽ የሐሳቡ ይዘት ምንም ይሁን ምን፣ ሐሳቡ በመገለጹ የሚያስከትለው ውጤት ምንም ይሁን ምን፣ መከልከል አይቻልም፡፡ ከዚህ የምንረዳው አንዱ ነጥብ አንድን ቡድን (ምሳሌ ብሔር) ባህል የሚተች ይዘት ያለው ጽሑፍ ማተም ወይንም ማሠራጨት አይቻልም የሚል ሕግ ሊኖር አይችልም፡፡ በመሆኑም ይዘቱን መሠረት በማድረግ ሐሳብን የመግለጽ ክልከላ አይኖርም ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አንድ ጽሑፍ ታትሞ በመውጣቱ የመንግሥትን ተአማኒነት ያሳጣል በማለት መከልከል አይቻልም፡፡ ጠንከር ስናደርገው ደግሞ አንድ ጽሑፍ መውጣቱ አንድን ብሔር ከሌላው ጋር ሊያጋጭ ይችላል በሚል ምክንያት ክልከላ አይኖርም፡፡ የሚከለክል ሕግም ማውጣትም አይቻልም፡፡ ይህ ደግሞ የሚያስከትለውን ውጤት በማሰብ ብቻ መገደብ አይቻልም ማለት ነው፡፡ ወንጀል ማድረግማ ፈጽሞ አይታሰብም፡፡ በሕግ የሚገደብባቸው ምክንያቶች ‘የወጣቶችን ደኅንነት የሚያናጉ፣ የግለሰብን መብት የሚጥሱና ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎችን ማድረግ፣ የጦርነት ቅስቀሳ ማድረግ’ ብቻ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ከአራቱ ውጪ በሌሎች ምክንያት ፈጽሞ ሐሳብን በነፃነት በማናቸውም የፕሬስ ውጤቶችም ይሁን በኤሌክትሮኒክ መንገድ እንዳይገለጹ መከልከል ወይንም ወንጀል ማድረግ ፈጽሞ ሕገ መንግሥቱን መጣስ ነው፡፡ ከላይ ተገለጹትን ግቦች ለማሳካት ሲባል ብቻ ነው የንግግርን ነፃነት መገደብ የሚቻለው፡፡ ጥላቻ ያዘሉ ንግግሮችን ለመገደብ መነሻዎቹ እነዚህ ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር ሕጉ ቢወጣ፣ ሕገ መንግሥታዊ ይሆን ዘንድ ንግግሮቹ የጦር ፕሮፓጋንዳ፣ የወጣቶችን አስተዳደግ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ከሆነ፣ ወይንም የግለሰብን መብት ወይንም ክብርና ሰብዓዊ ክብር የሚቃረኑ ንግግሮችን ብቻ ነው በጥላቻ ንግግርነት ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉት፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሕገ መንግሥታዊ ለማድረግ የሚቻለው በአንዱ ብቻ ነው፡፡ የአንድን ግለሰብ ብሔሩን፣ ሃይማኖቱን፣ ዘሩን ወይንም ሌላ ማኅበራዊ መገለጫን መሠረት አድርጎ የሰውን ክብር (Individual Honour) ወይንም ሰብዓዊ ክብርን (Human Dignity) የሚጻረሩ ንግግሮችን አስቀድሞ ሕግ በማውጣት መገደብ ይቻላል፡፡ ከሕገ መንግሥቱ በመነሳት በሥራ ላይ ያሉትን ሌሎች ሕጎችን እንቃኝ፡፡ ሃይማኖትን፣ ፖለቲካን፣ ዘርን (ብሔርን አይልም) መሠረት ያደረገ በሐሰት የሚያነሳሳ፣ የሚያጥላላ፣ የሚስፋፋ ማናቸውም ድርጊት ወንጀል እንደሆነ በወንጀል ሕጉ በግልጽ አለ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድ ሃይማኖት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ጸያፍና የአማኙን ስሜት የሚነካ ድርጊት የፈጸመ ሰው በደንብ መተላለፍ ሊቀጣ የሚቻልበት ሕግ አለ፡፡ ሕዝብን በተለያዬ መንገድ ወደ ግጭትና አመጽ የሚመሩ ንግግሮችን ማድረግ ወንጀል እንደሆነ በመደበኛው የወንጀል ሕግም ይሁን የኮምፒውተር ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ላይ አሉ፡፡ እንዲሁም በርካታ ሕጎች ብሔርን፣ ዘርን፣ ሃይማኖትን፣ ጾታን፣ የፖለቲካ አቋምን መሠረት አድርጎ አድልኦ መፈጸም እንደማይቻል ተደንግጓል፡፡ ይህ እንግዲህ በተወሰነ መልኩ የጥላቻ ንግግርን ወንጀል መሆናቸውንና በሌሎች አስተዳደራዊም ይሁን ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔርን ወይንም ሃይማኖትን መሠረት አድርጎ በሚኖር ያልተገለጠ ውስጣዊ ጥላቻ ቢኖር እንኳን አድልኦ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ዓለም አቀፍ ሰነዶችን ኢትዮጵያ ስላጸደቀች እነዚህ ስምምነቶችም የዘር፣ የብሔር፣ የሃይማኖትና ሌሎች ነገሮችን ታሳቢ ያደረገ ማዳላት ስለሚከለክሉ ያው የአገራችን ሕጎች ናቸውና እነሱም አሉን፡፡ ነገር ግን ክልከላው የወንጀል ስላልሆነ በወንጀል አያስቀጡም፡፡ በመሆኑም እነዚህ አገራዊም ይሁኑ ዓለም አቀፋዊ ሕጎች የንግግር ነፃነት ወይንም መብት ፍጹማዊ ስላልሆነ በምን ሁኔታ እንደሚገደቡ፣ ከገደቡ ሲታለፍም ሊያስቀጡ መቻላቸውንም ነው ለመግለጽ የተሞከረው፡፡ ሕገ መንግሥቱን የሚገዳደሩ ሕጎች ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕገ መንግሥቱ ከጸደቀ ወዲህ ከላይ ከገለጽናቸው መሥፈርቶች ጋር የማይሄዱ በርካታ ድርጊቶች ወንጀል ሆነዋል፡፡ ለምሳሌ የመንግሥትን ስም ማጥፋት፣ መንግሥትን መስደብ፣ አገራዊ ዓርማንና ባንዲራን መስደብ፣ ሌሎች አገሮችን፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትን፣ ዓርማዎቻቸውንና ባንዲራዎቻቸውን መስደብና ስም ማጥፋትና የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች ለጠላት አገር አሳልፎ መስጠት ወዘተ፡፡ በዓለም ላይ በሕገ መንግሥቷ የአገር ደኅንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መረጃም ቢሆን እንኳን ያልከለከለች ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ይሁን እንጂ ሕገ መንግሥቱ ላይ ከሰፈረው በእጅጉ በራቀና በተቃረነ ሁኔታ ባንዲራን መስደብ፣ የመንግሥት ስም ማጥፋት የመሳሰሉትን ወንጀል ሆነዋል፡፡ በየትኛውም አገር ደግሞ የአገሮችን የደኅንነት ሁኔታ አደጋ ላይ የሚጥል መረጃን ለጠላት መንገርን ወይንም መግለጽን መከልከል ሕገ መንግሥታዊ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ሕገ መንግሥታችን ከየትኛውም ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ሰነድ ይሻላል፡፡ የብዙዎቹ መለኪያዎች በሕግ መደንገግና ለዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ አስፈላጊ መሆን ሲሆኑ የሁለተኛውን መሥፈርት አስፈላጊነቱን የመወሰን በአብዛኛው የተተወው ለሚመለከታቸው አገሮች ነው፡፡ እነዚህ መሥፈርቶች፣ እንደፈለጉ ለመፈንጠዝ የተመቹ ሲሆኑ በተቃራኒው የእኛ ሕገ መንግሥት የመረጣቸው ደግሞ ጥብቅ እንዲሁም ለመለካት የማያስቸግሩ መሥፈርቶችን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከላይ እንዳየነው መንግሥት አሁን ባለው አሠራር ከቀጠለ የጥላቻ ንግግርን በተለይ ብሔርን ከብሔር፣ አንድ የሃይማኖት ተከታይን ከሌላው ለማጋጨት የሚያነሳሱ፣ ወይንም ጥላቻን በቡድኑ ላይ የሚነዙ ንግግሮች መከልከል አይሳነውም፡፡ ብዙ ያልተሳኑትን ሕጎች ዓይተናል፡፡ የተጨማሪ ሕግ ወይንም ሥርዓት አስፈላጊነት ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት ስለሰብዓዊ መብት አፈጻጸሟ ሪፖርት ስታቀርብ በተሰጣት ግበረ መልስ ውስጥ የጥላቻ ንግግርን ወንጀል ማድረግ አንዱ ነበር፡፡ በበጎም ተቀብላው ነበር፤ ምንም እንኳን ሕግ ማውጣቱ ላይ እመርታ ባታሳይም፡፡ ስለምን ሕግ ያስፈልገናል ብንል በርካታ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ የጉዳዩ አሳሳቢነትም መንግሥትም የተረዳው ይመስላል፡፡ በቴሌቪዥን የተለያዩ ፕሮግራሞች ሲቀርቡ ተመልክተናል፡፡ በተለይ ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያ ስለሚተላለፉና ስለሚሠራጩ የጥላቻ ንግግሮች፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ከሚያስፋፉት ውስጥ አንደኛው መንግሥት ራሱ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ አንዱን የመንግሥት አድራጎት ብቻ እንመልከት፡፡ እሱም መንግሥታዊ ፍረጃን ይመለከታል፡፡ እርግጥ ነው የአገራችን መለያ ከሆነ ቆይቷል፡፡ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የዓረብ ቅጥረኞች፣ በደርግ ገንጣይ፣ አስገንጣይና ወንበዴዎች፣ በኢሕአዴግ ደግሞ ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛና ጠባብ የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማው አሁን ያለው የአገራችንን ሁኔታ ስለሆነ ጠባብ፣ ትምክህተኛና ነፍጠኛ የሚሉትን ቃላት ብቻ እንደ ምሳሌ ይወስዳል፡፡ ስለሆነም እነዚህ ስያሜዎች ከጥላቻ ንግግር አንፃር በአጭሩ ለማየት ይሞክራል፡፡ የሁለቱን ትርጉም ኢሕአዴግ ካወጣቸው ሰነዶች በመነሳት እናስቀምቸጣው፡፡ ጠባብ ብሔርተኝነት ወይንም ጠባቦች የሚባሉት ሌሎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችን በጭፍን በጠላትነት የሚያዩ ሲሆኑ፣ አብሮ የመኖር ጥያቄን ፈጽሞ የማስተናገድ ፍላጎት ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡ ትምክህተኛ ብሔርተኝነት ወይንም ትምክህተኞች የሚባሉት አመክንዮታዊነት በጎደለውና ከልክ ባለፈ ሁኔታ የራስን ብሔር፣ ቋንቋና ባህል ከሁሉም በላይ ልዕልና እንዳለው የሚያምን፣ ከዚህ ባለፈም ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች የራሳቸውን ማንነት በመካድና በመተው ትምክህተኛውን ብሔር የበላይ ነው ብለው እንዲያምኑና ያንን ማንነት እንዲላበሱ የሚፈልግ የብሔርተኝነት ዘውግ ነው፡፡ ከእነዚህ የብሔርተኝነት ዓይነቶች ኢሕአዴግ የሚዋጋቸው እንደሆኑ ይገልጻል፡፡ በዋናነት እነዚህ የብሔርተኝነት ዓይነቶች ለሁለት የብሔር የተሰጡ ስያሜዎች እንደ ይታወቃል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ተበደለ የሚሉትን ጠባብ፣ የአማራ ሕዝብ በዚህ በዚህ ቦታ ችግር እየደረሰበት ነው የሚሉትን ትምክህተኛ እያሉ መፈረጅ የዕለት ተዕለት ሥራ ሆኗል፡፡ እንዲህ ዓይነት የመፈራረጃ ሐሳቦች ግልጽና የማያወላዱ መለያ ባሕርያት ስለሌላቸው ከመሬት ተነሥቶ ለመኮነንና ለመውቀስ ቀላል ናቸው፡፡ እነዚህ ፍረጃዎች፣ ሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ መሆናቸው የሚወላዳ አይደለም፡፡ የሰፊነት ወይንም መለኪያ በሌለበት የብሔሩን መብት የጠየቀን ኦሮሞ ሁሉ ጠባብ ማለት ዞሮ ዞሮ ኦሮሞ ስለሆነ የሚመጣ ንግግር ነው፡፡ የተለያዩ ዜግነትን መሠረት ያደረጉ መብቶች የሚጠይቅን አማራ ሁሉ ትምክህተኛ ማለት አማራ ከመሆኑ የሚመነጭ ነው፡፡ ስለሆነም ጥላቻን የሚሳድግና የሚበረታታ ነው፡፡ ይህ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ደግሞ ኦሮሞን በአማራ ዘንድ እንዴት እንዲሳል እንደተደረገ ማወቅ ይበቃል፡፡ አማራም በኦሮሞ ዘንድ እንዲሳል የተደረገውም ተመሳሳይ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን አካሄድ ለማስቀረት እነዚህን ወደ ብሔር ያጋደሉ ፍረጃዎችን እንደ ጥላቻ ንግግር በመውሰድ ወንጀል ብናደርጋቸው የተሻለ ይሆናል፡፡ ዋነኛው የጥላቻ ንግግር ፈጻሚ መንግሥት ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ምናልባት የጥላቻ ንግግርን ወንጀል እንዲደረግ አስተያየት የሰጡት አገሮች ምንን መሠረት አድርገው እንደሆነ ባይታወቅም ቅሉ ጠባቦች፣ ትምክህተኞችና ነፍጠኞች እያሉ የሰብዓዊ ክብርን የሚነካና የሚያሸማቅቅ ነው፡፡ ከላይ የጥላቻ ንግግር ወንጀል እንዲሆን ከሚሟገቱት ምሁራን ክርክሮች ጋር ስናስተያያቸው ተመሳሳይ ውጤት ማምጣቸው አይቀሬ ነው፡፡ የመንግሥት እንዲህ ዓይነት ንግግሮችን መጠቀሙን መተው የጥላቻ ንግግር ወንጀል በማደረግ የሚገኘውን ግብ ለማሳካት ይረዳል፡፡ ብሎም ሌሎች ግለሰቦችምና ብሔሮች የሚኖራቸውን ግንኙነት የተሻለ ያደርጋል፡፡ በሕገ መንግሥቱ መግቢያ ላይ የተጻፈውን አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባት ይረዳል፡፡ በተጨማሪም የጥላቻ ንግግር ወንጀል ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እስካሁን እንደታየው መንግሥት የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ለማፈን ከሆነ ግን የበለጠ ቅራኔ ከመፍጠር የሚዘል ፋይዳ አይኖረውም፡፡ የንግግር ነፃነት ላይ ገድብ የሚጣለው ለዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ግንባታ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ደግሞ መቻቻልና ብዙኃነት ከመለያ ባህርያቱ መካከል ናቸው፡፡ መቻቻልን የሚያጠፋና ብዙኃነትን የሚቃረንን ንግግር ደግሞ ለዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ግንባታ ጠንቅ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ንግግሮችን መታገስ ደግሞ ውሎ አድሮ ራሱን ዴሞክራሲን ያጠፋል፡፡ ስለሆነም ዴሞክራሲን ራሱን ከጥፋት ለመታደግ የዴሞክራሲ መገለጫ የሆነው የንግግር ነፃነት ላይ ገደብ እንዲኖር ግድ ይላል ማለት ነው፡፡ ለዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ግንባታ የሚያስፈልጉ ነገሮች ደግሞ ከአገር አገር ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ ፈረንሳይና ቱርክ ሃይማኖታዊ የሆኑ ጉዳዮች ወደ መንግሥታዊ ተቋማት ብቅ ማለትን ለዴሞክራሲ እንደ ጠንቅ ያዩታል፡፡ ጀርመን የናዚና የፋሽስት አዝማሚያ፣ በስፔን ደግሞ መገንጠልን የሚያነሳሳ ወይም የሚደግፍ፣ በእስራኤል የአገሪቱን መኖር የማይቀበል ወዘተ. ለዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ፀር እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ ይሁንና እነዚህን ጉዳዮች አስቀድሞ በሕግ ማሳወቅን ይጠይቃል፡፡ ለማጠቃለል አገራዊ አንድነት ለማጠናከር በተለይ ብሔር ላይ የተመሠረቱ የጥላቻ ንግግሮችን ወንጀል ቢሆኑ ይጠቅማል፡፡ ከሌሎች አገሮች ልምድ ስናስተያየው በቂ ሕግ የለንም፡፡ መንግሥትም እንዲሁ ለጥላቻ ንግግር መሪነቱን ባይዝ ጥሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉንም የጥላቻ ንግግሮች በፍርድ ቤት ብቻ እንዲታዩ ማድረግ የበለጠ የብሔርና የሃይማኖት ብጥብጥ ሊያስነሳ ስለሚችል በርካታ አገሮች እንደሚያደርጉት ንግግሮቹ የተላለፉበትን ሚዲያ መነሻ በማድረግ ቅድሚያ በእርቅና በሽምግልና ሊያልቁ የሚችሉበትን ዘዴ መሻት ነው፡፡ አዲሱ ዘመን የጥላቻ ንግግር የሚቀርበት ይሁንልን፡፡
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
613
ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በተመለከተ የቀረበ አዋጅን አፀደቀ On Feb 13, 2020 977 አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን አፀደቀ። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በዛሬው እለት አካሄደ። ምክር ቤቱ በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተመልክቷል። አዋጁ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ለማህበራዊ ስምሪት፣ ለፖለቲካ መረጋጋት፣ ለሀገራዊ አንድነት፣ ለሰብዓዊ ክብር እና ለብዝሃነት ጠንቅ መሆኑን በመገንዘብ በተለይም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በህብረተሰቡ መካከል ያሉ መልካም እሴቶች በጥላቻ ንግግሮችና በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ እየተሸረሸሩና ለሀገርም ስጋት እየደቀኑ በመሆናቸው እንዲሁም እነዚህን ችግሮች አሁን ባሉት ህጎች መፍታት የማይቻል በመሆኑ መዘጋጀቱ ተገልጿል። የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ዴሞክራሲያዊ ውይይት እና ክርክር ለማድረግ እንቅፋት በመሆኑ ከብሄር እና ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ የጥላቻ ንግግር እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨትን እንዲሁም ዘርን፣ ጾታን እና አካል ጉዳተኝነትን መሰረት በማድረግ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች እና ሃሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ተገልጿል። እንዲሁም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን በህግ መከልከል አስፈላጊ በመሆኑ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱም ተነግሯል። የምክር ቤቱ አባላትም በአዋጁ ላይ ያላቸውን ሃሳብ እና አስተያየት የገለጹ ሲሆን፥ ለአብነትም ይህ አዋጅ የዜጎችን ሃሳብ በነጻነት የመግለጽ መብት የሚጋፋ እንደሆነ ያነሱ ሲሆን፥ የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥቶበታል። በዚህም አዋጁ በህገ-መንግስቱ ላይ ከተቀመጠው የመናገር መብት ጋር እንደማይቃረን፣ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 29 (6) እና (7) ከተቀመጡት ገደቦች ውስጥም አንዱ ምክንያት ሰብአዊ ክብርን መጠበቅ ሲሆን፥ የጥላቻ ንግግር ሰብአዊ ክብርን የሚነካ ዋነኛው በመሆኑ ከተቀመጠው ገደብ ጋር የሚገናኝ መሆኑ ምላሽ ተሰጥቶበታል። ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ አዋጅን በ23 ተቃውሞ እና በ2 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
[ 111 ]
[ "የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት" ]
[ "ስለጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ አይነቶች፣ የሚያሰከትሉት ጉዳት እና መከላከያ መንገዶች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡" ]
614
ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የተውጣጣ የሕክምና ቡድን የዓይን ሞራ ሕክምና በወረታ እና አዲስ ዘመን እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 08/2012ዓ.ም (አብመድ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በወረዳው እና አካባቢው ያሉ የኅብረተሰብ ክፈሎች የዓይን ሞራ የጤና ችግርን ለመቅረፍ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዓይን ሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የወረታ ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ካሳነሽ አባተ ገልጸዋል፡፡ ሕክምናው የሚሰጠው በወረታ በሚገኙ ሁሉም የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እና በአዲስ ዘመን ከተማ በመንቀሳቀስ ነው፤ ችግሩ ከበድ ያለባቸው ሰዎች ደግሞ በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ቀዶ ጥገና እየተሠራላቸው መሆኑን ነው ኃላፊዋ የተናገሩት፡፡ የሕክምና ቡድኑ 20 አባላትን ያቀፈ ነው፡፡ ከሕክምና ቡድኑ አባል ያነጋገርናቸው ‹ኦፕቶሜትሪስት› ነቢያት ፈለቀ ሕክምናው የዓይን ሞራ ቀዶ ጥገና፣ የዓይን ግፊት ግላኮማና ተያያዥ የዓይን ችግሮች ባሉባቸው አካባቢዎች ጥናት ተደርጎ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኦፕቶሜትሪስት ነቢያት እንደገለጹት የሕክምና ቡድኑ ከ4 ሺህ በላይ የዓይን ጤና ችግር ላለባቸው የኅበረተስብ ክፍሎች ሕክምና ለመስጠት ታሳቢ አድርጎ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው፡፡ ቡድኑ ሕክምናውን እስከ ታኅሳስ 11/2012 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ በመሆኑ ማኅበረሰቡ አስፈላጊውን ሕክምና እንዲያደርግም ባለሙያው አሳስበዋል፡፡ የዓይን ሞራ ሕክምና ካገኙ ሰዎች መካከል አቶ ፍሬው አሻግሬ እና ወይዘሮ እንግዳይቱ መንግሥቱ እንደተናሩት በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ለመሥራት ተቸግረው፣ በሌሎች ሰዎች ላይ ጥገኛ ሆነው ቆይዋል፡፡ ሕክምናውን ካገኙ በኋላ የዓይን ብርሃናቸው መመለሱንም ተናግረዋል፡፡ ከሌሎች ሰዎች ከነበራቸው ጥገኝነት ወጥተው ራሳቸውን ችለው ቤተሰባቸውን መርዳት የሚያስችላቸው በመሆኑም መደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
615
ከ800 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የዓይን የሞራ ግርዶሽ ሕክምና በነፃ ሊሰጥ ነው፡፡ ባሕር ዳር፡ የካቲት 14/2012 ዓ.ም (አብመድ) የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ‹ዳይሬክት ኤድ› ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የበጎ አግልግሎት ከ800 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነፃ የዓይን የሞራ ግርዶሽ ሕክምና አግልግሎት እንዲያገኙ ሊያደርግ ነው፡፡ የእንጅባራ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ሀብታሙ ምሕረት ለአብመድ እንደተናገሩት ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና አግልግሎት የሚሰጣቸውን ዜጎች ከየካቲት 16 እስከ 22/212 ዓ.ም የልየታ ሥራ ይካሄዳል፡፡ ልየታው በባለሙያ እና በመሣሪያ በመታገዝ የሚሠራ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ ነፃ የዓይን የሞራ ግርዶሽ ሕክምና ለመስጠት የሚያስችሉ አራት የቀዶ ሕክምና ክፍሎችና ባለሙያዎችም ሙሉ ዝግጅት ማድረጋቸውን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ በዓይን ሞራ ግርዶሾ ምክንያት ማየት የማይችሉ 800 ሰዎች አልግሎቱን እንደሚያገኙ የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ የልየታ ሥራው እንደተጠናቀቀ የሕክምና አግልግሎቱ ይሰጣል ብለዋል፡፡ በሆስፒታሉ በዓይን ሕክምና ዘርፍ ረዥም ልምድ ያላቸው ሐኪሞች ተገኝተው አገልግሎት ስለሚሰጡ ዜጎች በእንጅባራ ሆስፒታል የነፃ ሕክምና አገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
616
በደባርቅ ሆስፒታል በአይን ሞራ ግርዶሽ ሳ ቢያ ማየት ለተሳናቸው ሰዎች የቀዶ ሕክምና እየተደረገ መሆኑን የሆስፒታሉ ሜዲካል ድሬክተር ትናንተ አስታወቁ፡፡ በላይንስ ክለብ ድጋፍ በነጻ የሚሰጠውን ይህንኑ ሕክምና የሚያካሂደው 15 አባላት ያሉት የሕከምና ቡድን መሆኑን ሜዲካል ድሬክተሩ አቶ ሞላ ታየ አመልከተዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆየውን ሕክምና የሚሰጡት እነዚሁ አባላት አዲስ አበባ፣ ባሕር ዳርና ጎንደር ከሚገኙ የመንግስት ሆስፒታሎች የተውጣጡ የአይን ሕክምና ስፔሻሊስቶችና የጤና ባለሞያዎች መሆናቸውንመ ገልጠዋል፡፡ ከቀዶ ሕክምናው በተጨማሪ የአይን መድሃኒትና መነጽር በነጻ በላንይንስ ክለብ አማካይነት እንደሚሰጥ ጠቁመው፣ሕክምናውን ለማግኘት እስካሁን ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡ ባለሞያዎቹ በየቀኑ ከ110 እስከ 120 ለሚደርሱ ሰዎች የአይን ቀዶ ሕክምና እየሰጡ መሆኑንም አቶ ሞላ አመልክተዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
617
የአይን ሞራ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው የጉራጌ ዞን ችሃ ወረዳ 251 ነዋሪዎች ማየት መቻላቸውን የእንድብር ጤና ጣቢያ አስታወቀ፡፡ የጤና ጣቢያው ባለሙያ ሲስተር አማረች ፊጣ ትናንት ለኢትዮጰያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ኦርቢስ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት በአካባቢው ያለውን የአይን ሞራ ችግር በማጥናት በሰጠው የቀዶ ጥገና አገልግሎት ከወረዳው የተለያዩ አከባቢዎች የመጡ 251 ሰዎች ከሕክምናው በኋላ ማየት ችለዋል፡፡ ድርጅቱ ከምስከረም 25 እስከ ጥቅምት 20 ቀን በሰጠው በዚሁ አገልግሎት ከተመረመሩት 750 ሰዎች የማየት ችግር የነበረባቸውን በመምረጥ ችግራቸውን ማቃለል መቻሉንም ባለሙያዋ አስረድተዋል፡፡ በአካባቢው ያለው የዓይን ማዝ በሽታ የሚያስከትለውን አይነስውርነት ለመከላከልም ድርጅቱ የተለያዩ መድሃኒቶችና መነፅር ለነዋሪዎች እያደለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
618
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሁለት ወረዳዎች ሰሞኑን በተካሄደው የዓይን ሕክምና ከ1ሺህ 500 በላይ ሰዎች ማየት መቻላቸውን በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚገኘው የምድረ ገነት ሆስፒታል አስታወቀ፡፡ የሆስፒታሉ የዓይን ህክምና ክፍል ኃላፊ ሲስተር ፌቨን ስብአተለአብ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት በመደባይ ዛናና ላዕላይ አዲያቦ ወረዳዎች የሚገኙት እነዚህ ወገኖች ማየት የቻሉት ሰሞኑን በተደረገ ህክምና ነው፡፡ በህክምናው ከተፈወሱት መካከል 500ዎቹ በዓይን ሞራ ግርዶሽ ከ480 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በትራኮማ በሽታ ሲሰቃዩ የቆዩ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡ በ92 ቀበሌዎች በተካሄደው የህክምና ዘመቻ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ከ780 በላይ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን የተናገሩት ኀላፊዋ ህጻናትና ሽማግሌዎች እንደሚገኙባቸውም አመልክተዋል፡፡ ከህክምናው በተጓዳኝ ለ54ሺህ ህዝብ የዓይን በሽታ መንስኤዎችንና መከላከያ መንገዶችን በሚመለከት ትምህርት መሰጠቱን ኃላፊዋ ጨምረው ገልጠዋል፡፡ ህክምናውን ካገኙት ወገኖች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ከ5 እስከ 10 ዓመታት ማየት ተስኗቸው የቆዩ ቢሆንም በሆስፒታሉ ባለሙያዎች አማካኝነት በተደረገላቸው ህክምና ማየት በመቻላቸው መደሰታቸውን አስታውቀዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
619
ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ለ218 ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ በቀዶ ህክምና በማስወገድ ማየት እንዲችሉ ማድረጉን በድርጅቱ የጋሞ ጎፋ ቅርንጫፍ ፕሮጀክት ተቆጣጣሪ ገለፁ፡፡ የፕሮጀክት ተቆጣጣሪው ዶክተር አለማየሁ ሲሳይ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ድርጅቱ ከአርባ ምንጭ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ህክምናውን የሰጠው ከሐምሌ ወር 1998 እስከ መስከረም ወር 1999 መጨረሻ ድረስ ነው፡፡ ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው ሰዎች ከጋሞ ጎፋ፣ ከደቡብ ኦሞ ዞኖች፣ ከኮንሶና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ መሆናቸውን የገለጹት ተቆጣጣሪው ፣ሕክምናው የተሰጠው በነጻ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ድርጅቱ ባለፈው አመት ከ1 ሺህ 100 ለሚበልጡ ነርሶች፣ የቀበሌ ጤና ተጠሪዎች፣ የሴቶች ማህበራት ሃላፊዎችና የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ስለዓይን ጤና አጠባበቅ በማሰልጠን ለሕብረተሰቡ ትምህርት እንዲሰጡ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡ ለቀጣዮቹ ሶስት ወራትም በአርባ ምንጭ ሆስፒታልና በሳውላ ጤና ጣቢያ ለ250 ሰዎች አገልግሎቱን በነፃ ለመስጠት ማቀዱን አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ1 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በነፃ መስጠቱንም አብራርተዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
620
በባሌ ዞን 23 የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ ነጻ የዓይን ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው 485 Share ጎባ ታህሳስ 9/2011 በባሌ ዞን 23 የጤና ተቋማት የትራኮማ በሽታና የአይን ቆብ ችግር ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ የህክምና አገልግሎት በዘመቻ እየተሰጠ ነው፡፡ የዞኑ የጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት እንዳመለከተው በ2005 ዓ.ም በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ከአጠቃላይ የባሌ ህዝብ መካከል 49 በመቶ የሚሆነው ለትራኮማ በሽታ ተጋላጭ ሲሆን የህክምና አገልግሎቱም ይህንን ለመከላከል ነው፡፡ የትራኮማ በሽታ መድኃኒት እድላን ጨምሮ የህክምና አገልግሎቱ እየተሰጠ ያለው በዞኑ 18 የገጠር ወረዳዎች ውስጥ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ተወካይ አቶ እሸቱ ቶሎሳ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ በትራኮማ በሽታና የአይን ቆብ ህክምና አገልግሎቱ እየተሰጠ ያለው ከታህሳስ 6/2011 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት በዞኑ በሚገኙ አምስት ሆስፒታሎችና 18 ጤና ጣቢያዎች ውስጥ አስቀድመው በዘርፉ በሰለጠኑ ባለሙያዎች ነው፡፡ ባለሙያዎቹ በቡድን ሆነው የተሰማሩ ከ1ሺህ በላይ አባላት ናቸው፡፡ እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴም ከ327ሺህ 900 የሚበልጡ ሰዎች የትራኮማ በሽታ ህክምና አገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ እሸቱ ከነዚህም 6ሺህ የሚሆኑት የአይን ቆብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን አስረድተዋል፡፡ የትራኮማ በሽታ በህክምና የሚዳን ቢሆንም ከዕድሜ መግፋት፣ ከግልና ከአካባቢ ንጽህና ጉድለት የሚመጣ የጤና ችግር በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከህክምናው በተጓዳኝ የግንዛቤው የማሳደግ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ለማህበረሰቡ በነፃ የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት በግል የጤና ተቋማት ቢሰጥ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚጠይቅ ተወካዩ ጠቁመው ህብረተሰቡም በዚህ አጋጣሚ በህክምናው በአግባቡ መጠቀም እንዳለበትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል በአጋርፋ ወረዳ የኢላኒ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አብዱረህማን ሰኢድ በሰጡት አስተያየት በተደረገላቸው ቀዶ ህክምና የዓይን ብርሃናቸውን መመለሱን ተናግረዋል፡፡ “ዓይኔን ታክሜ ለውጥ በማየቴ ሌሎችንም የአካባቢዬ ሰዎችን በማስተባበር እንዲታከሙ ለማድረግ የድርሻዬን እወጣለሁ” ብለዋል፡፡ በወረዳው የአምቤንቱ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ በድሪያ ሹክሪ በበኩላቸው የዓይናቸው ጸጉር ወደ ውስጥ በመቀልበሱ በአግባቡ ማየት ሳይችሉና ለመስራትም ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በግላቸው ለመታከም የገንዘብ ችግር እንደነበረባቸው ጠቅሰው አሁን በነፃ በተሰጣቸው ህክምና የዓይን ብርሃናቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። የህክምና አገልግሎቱ የሚሰጠው የፌዴራልና የክልሉ ጤና ጥበቃ መስሪያ ቤቶች ከውጪ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር መሆኑም ተመልክቷል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
621
በተሰጠን ነጻ የዓይን ሕክምና ብርሃናችን ተመልሷል….በአፋር ክልል የዓይን ሕሙማን ታካሚዎች 844 Share ሰመራ ህዳር 1/2011 በዱብቲ ሆስፒታሉ ባገኙት ነጻ የዓይን ሕክምና የዓይን ብርሃናቸው መመለሱን ከተለያዩ የአፋር ወረዳዎች የመጡ ታካሚዎች ገለጹ። ለተከታታይ ስድስት ቀናት ለህሙማኑ ነጻ የሕክምና አገልግሎት የሰጠው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የዓይን ሕክምና ቡድን በበኩሉ በአገልግሎት ከ2ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውቋል። ከተላላክ ወረዳ የመጡት ወይዘሮ ሳልሃ መሃመድ እንደተናገሩት ከሦስት ዓመት በፊት አንድ ዓይናቸው በዓይን ሞራ እንደተሸፈነና በነበረባቸው የገንዘብ እጥረት ሕክምና ሳያገኙ መቆየታቸውን ተናግረዋል። በዚህም እንደልባቸው ተንቀሳቅሰው ለመስራት ከመቸገራቸውም በላይ በተለይ ማታ ማታ ያለሰዎች እርዳታ ምንም አይነት ሥራ ተግባር ማከናወን ተስኗቸው አነደነበር ገልጸዋል። የሕከምና ቡድኑ በዱብቲ ሆስፒታል ባከናወነላቸው የዓይን ሞራ ገፈፋ ቀዶ ሕክምና ዓይናቸው ማየት መቻሉንና በእዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከአይሳኢታ ወረዳ የመጡት ወይዘሮ አይሻ ከሎይታ በበኩላቸው ከሦስት ዓመት በፊት የጀመራቸው የዓይን ሕመሙ ከቀርቡ ግዜ ወዲህ እየባሰባቸው መምጣቱን አስታውሰዋል። በእዚህም ብዙ ገንዘብ አውጥተው ወደ መቀሌ ከተማ በመሄድ ለመታከም ቢሞክሩም ለህክምና አገልግሎቱ ረጅም ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። “በአሁኑ ወቅት ባገኘሁት ነጻ የህክምና የአይን ብርሃኔ በመመለሱ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፤ የመኖር ተስፋዬም እየለመለመ ነው” ብለዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በአንድ ዓይናቸው ላይ በተፈጠረ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት የመንግስት የሥራ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት ሲቸገሩ እንደነበር የገለጹት ደግሞ ከዱብቲ ወረዳ የመጡት አቶ ሰኢድ አህመድ ናቸው። “ወደሌሎች አካባቢዎች ሄጄ ህክምና ለማግኘት ብፈልግም ከአቅም ማነስ የተነሳ ሳይሳካልኝ በመቆየቱ በህመሙ ስሰቃይ ቆይቺያለሁ ብለዋል። በነጻ በተሰጣቸው የዓይን ቀዶ ሕክምና አገልግሎት የዓይናቸው ጤና መመለሱን በቀጣይ የሥራ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር እንደሚችሉ ተናግረዋል። በዱብቲ ሆስፒታል ነጻ የሕክምና አገልግሎቱን የሰጠው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የዓይን ሕክምና ቡድን መሪ ዶክተር ግሩም ወልደገብሬል በበኩላቸው ከዱብቲ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከጥቅምት 25 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለ6 ተከታታይ ቀናት ለሕብረተሰቡ ነጻ የዓይን ህክምና መስጠታቸውን ተናግረዋል። በዚህም አስከ 2ሺህ ለሚደርሱ የአካባቢው ነዋሪዎች የዓይን ሞራ ገፈፋ፣ እንደ አስፈላጊነቱ አጋዥ መነጽርና ተያያዥ የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጋቸውን አመልክተዋል። በቀጣይም የሕከምና ቡድኑ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ተመሳሳይ የህክምና አገልግሎቶችን ለመስጠት ማቀዱን ዶክተር ግሩም ተናግረዋል።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
622
እይታቸው እስከ 10 አመታት ጠፍቶ የነበሩ ዜጎች በቀዶ ህክምና የዓይን ብርሃናቸው ተመለሰ 1044 Share ደብረ ማርቆስ ጥቅምት 17/2011 እስከ አስር አመታት በሞራ ግርዶሽ ምክንያት ማየት ተስኗቸው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተደረገላቸው ቀዶ ህክምና የዓይን ብርሃናቸው ተመለሰ፡፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል በተደረገላቸው የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እይታቸው መመለሱን ነው ተጠቃሚዎች የተናገሩት፡፡ የእናርጅና እናውጋ ወረዳ ነዋሪ አቶ ንጉሴ አካሌ ከ10 ዓመታት በፊት የዓይን ብርሃናቸውን አጥተው በመሪ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩበት ሁኔታ ወጥተው በሆስፒታሉ ሰሞኑን በተደረገላቸው ህክምና ሙሉ በሙሉ ለማየት በቅቻለሁ ብለዋል። የስናን ወረዳ ነዋሪው አቶ ፋሌ አላምሬ እንዳሉት ለ4 ዓመታት ያህል ማየት ከልክሏቸው ቤት ውለው እንደነበር ያስታውሳሉ። እንቅስቃሴ ሳደርግ ጉድጓድ ውስጥ እየገባሁ ጉዳት ይደርስብኝ ነበርም በማለትም የዓይን በርሃናቸውን በማጣት የገጠማቸውን ያወሳሉ። በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ህክምና “የዓይን ብርሃኔን በማግኘቴ ዳግም የተወለድኩ ያህል ደሰማኛል” ብለዋል። ከአዊ ብሔረሰብ ዞን የእንጅባራ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ያለምዘውድ መኩሪያ በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ህክምና ከ3 ዓመታት በፊት አጥተውት የነበረውን የዓይን ብርሃናቸውን መልሰው ማግኘታቸውን ይናገራሉ። በሆስፒታሉ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሰርጅን ወይዘሮ መቅደስ ዳኜ እንዳሉት ዳይሬክት ኤድ ከተባለ ድርጅት ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የዓይን ግርዶሽ ችግር ላለባቸው ሰዎች የህክምና አገልግሎት ከጥቅምት 12-19/ 2011 በመስጠት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በዚህም ሆስፒታሉ ኤድ ከተባለ መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ለ700 ሰዎች ህክምናውን የሰጠው። ህክምናው በመደበኛው ህክምና አሰጣጥ ረጅም ጊዜ የሚወስደውን አገልግሎት በተደራጀ አግባብ በአጭር ጊዜ በርካቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዓላማ እንዳለውም አብራርተዋል። በተጓዳኝም በትራኮማ ምክንያት እይታቸውን ላጡ ከ100 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች የዓይን ቆዳ መገልበጥ ህክምና እንደተደረገላቸው ወይዘሮ መቅደስ አስረድተዋል። በኢትዮጵያውያ የማየት ችግር ካለባቸው 1ነጥብ5 ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 600 ሺህ የሚሆኑት የዓይን ብርሃናቸውን ያጡት በዓይን ሞራ ግርዶሽ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
623
የአይን ሞራ ግርዶሽ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የማየት ችግር መንስዔ ሆኗል፡ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 872 Share አዲስ አበባ መስከረም 25/2011 የአይን ሞራ ግርዶሽ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የማየት ችግር መንስዔ እንደሆነ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አመለከተ። የማየት ችግር ካለባቸው 1ነጥብ5 ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 600 ሺህ የሚሆኑት የዓይን ብርሃናቸውን ያጡት በዓይን ሞራ ግርዶሽ እንደሆነም ተጠቁሟል። በዋናነት ለዓይን ስውርነት እያጋለጡ ያሉ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ተግባር በሚኒስቴሩ በኩል እየተከናወነ እንደሆነ ተገልጿል። ”በተለይም የትራኮማና የዓይን ሞራ ግርዶሽ በሽታዎችን ለመከላከል ከጤና ኤክስቴንሽን ጀምሮ እስከ ሚኒስቴሩ ድረስ የተቀናጀ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል” ተብሏል። በሚኒስቴሩ የሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ዳንኤል ገብረሚካኤል ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአይን ሞራ ግርዶሽና የትራኮማ በሽታ የያዛቸው ሰዎች ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ካልተቻለ የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ። ”በአሁኑ ወቅት በዓይን ሞራ ግርዶሽ ከ600 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በሽታው እንዳጋጠማቸው ይታወቃል” ያሉት ጀኔራል ዳይሬክተሩ ፈጣን በሆነ ሁኔታ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል ልዩ ስትራቲጂክ እቅድ ወጥቶ ክልሎችና የሚመለከታቸው አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ጋር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የትራኮማ ተጠቂዎችም በብዛት እንዳሉ ገልጸው፤ ችግሮቹን ከሚያባብሱት ነገሮች መካከል በዘርፉ የሰለጠነ በቂ የሰው ሃይል አለመኖሩ በመሆኑ የሰው ሃይል ለማልማት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል። ”በኢትዮጵያ 10 የዓይን ስፒሻሊስት ሃኪሞች ብቻ ይገኛሉ” ያሉት ዶክተር ዳንኤል ሃኪሞቹ የሚገኙት በከተሞች ላይ በመሆኑና አገልግሎቱን በብዛት የሚፈልጉት ገጠር ላይ የሚገኙት የህብረተሱ ክፍሎች በመሆናቸው ችግሩን ማባባሱን ገልጸዋል። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም የዓይን በሽታ ትኩረት የሚሻ መሆኑን በመገንዘብ ችግሩን ቀድሞ ለመከላከል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ውስጥ በማካተት እስከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል እየተሰራበት መሆኑንም ዶክተር ዳንኤል ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ለምለም አየለ በበኩላቸው ከ12 ዓመታት በፊት የተካሄደ ጥናትን አስታውሰው በወቅቱ በኢትዮጵያ ከ300 ሺህ በላይ ዜጎች የዓይን ብሌን ጠባሳ ችግር ተጠቂ መሆናቸው መታወቁን ገልጸዋል። ከችግሩ ስፋት አንጻር ሰፊ የሆነ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበው የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግና የዓይን ብሌን ለጋሾችን በማበራከት ችግሩን ለመቀነስ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የዓይን ባንኩ ከአጋር ድርጅቶቹ ጋር እየሰራ ሲሆን አሁን ባለው የዓይን ብሌን ንቅለተከላ ፍላጎት አንጻር በቂ የሆነ የአገልግሎት ሽፋን አለመኖሩን ገልጸዋል።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
624
ለዓይን ሞራ ግርዶሽ ተጠቂዎች ወቅቱን የጠበቀ ህክምና መስጠት አልተቻለም-የአማራ ክልል ጤና ቢሮ 124 Share ሚያዝያ 28/2011 ለዓይን ሞራ ግርዶሽ ተጠቂዎች ወቅቱን የጠበቀ ህክምና መስጠት እንዳልቻለ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ህክምናውን ያገኙ ሰዎች ቁጥር ከ3ሺህ አይበልጥም። በቢሮው ትኩረት የሚሹ በሽታዎች ባለሙያ አቶ መልካሙ በየነ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ምክንያት ለዝቅተኛ የዕይታ ችግር ተጋልጠዋል። “በዘርፉ የባለሙያዎች እጥረትና ህክምናውን የሚሰጥባቸው ጤና ተቋማት ውስን መሆን ለተጠቂዎች ወቅቱን የጠበቀ ህክምና እንዳይሰጥ አድርጓል” ብለዋል። በክልሉ ከሚገኙ ከ67 በላይ ሆስፒታሎች ውስጥ የዓይን ቆብ ቀዶ ህክምና የሚሰጡት ሰባት ብቻ መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል። በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆናቸው ህክምናውን ተደራሽ ማድረግ አንዳልተቻለም ገልጸዋል። አንድ ሆስፒታል በዓመት ለ2ሺህ ሰዎች ህክምና እንዲያደርግ ቢታቀድም፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሆስፒታሎቹ በመደበኛና በዘመቻ ህክምናው የተሰጣቸው ሰዎች ከ3ሺህ እንደማይበልጡ ተናግረዋል። የዓይን ሞራ ግርዶሽ በእድሜ መግፋት የሚከሰትና በወቅቱ ታክሞ ከመዳን ውጭ የማይከላከሉት መሆኑን የገለጹት ባለሙያው፣ “በክልሉ በወቅቱ ህክምና ማግኘት ያልቻሉ 300ሺህ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የዓይን ብርሃናቸውን እንዳጡ ከሶስት ዓመት በፊት በተካሄደ ጥናት ተረጋግጧል” ብለዋል። እንደ ባለሙያው ገለጻ እስከ 2014 ድረስ በሁሉም ሆስፒታሎች የቀዶ ጥገና ህክምናውን በመስጠትና የባለሙያዎች ቁጥር በማሳደግ ህክምናውን ተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው። የባህርዳር ፈለገ-ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ከአሜሪካው “ሄልሚን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ፕሮጀክት “ ጋር በመተባበር ሰሞኑን ለ400 ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሰጥቷል። የሄልሚን የዐይን ሞራ ግርዶሽ ፕሮጀክት” ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ማት ኦሊቫ በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት የሚከሰት ዓይነ-ስውርነት ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ እንደሚከሰት ገልጸዋል። የዐይን ሞራ ግርዶሽ ለዓይነ ስውርነት ከሚዳርጉ በሽታዎች መካከል በዋነኝነት የሚጠቀስ ቢሆንም፤ በቀላሉ የቀዶ ጥገና ህክምና በማድረግ የዓይን ብርሃንን ወደ ነበረበት መመለስ እንደሚቻል ገልጸዋል። በፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል በቁ የዓይን ህክምና ባለሙያዎች ስላሉ ህክምናውን ለማገኘት ወደ ባህርዳር የሚመጡ ሰዎች በርካታ መሆናቸውን የገለጹት ሜዲካል ዳይሬክተሩ፣”ባለሙያዎችን በማብዛት ኅብረተሰቡን ከጉዳት መታደግ ይገባል” ብለዋል። የፈለገ-ሕይወት ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ህይወት ደግነህ በበኩላቸው በክልሉ የዓይን ህክምና ተቋማት ውስንነት ቢኖርም፤ኅብረተሰቡ አገልግሎቱን ወደሚሰጡ ተቋማት በመሄድ ራሱን ከጉዳት ሊታደግ እንደሚገባ መክረዋል ። “ኅብረተሰቡ የዓይኑ የማየት አቅም እየቀነሰ ሲመጣ፣ በተለይ ቀለሞችን ከርቀት የመለየት ችግር ሲገጥመውና ጭጋግ ሲያለብሰው ቶሎ ወደ ህክምና ተቋማት መሄድ ይጠበቅበታል” ሲሉም መክረዋል። አርሶ አደር ገነት ብርሃኑ የ25 ዓመት ወጣት ናቸው። ከአንድ ዓመት በፊት የሁለቱም ዓይኖቻቸው የማየት አቅም አጥቶ ከወራት ወዲህ ሙሉ በሙሉ ማለት ማቆማቸውን ተናግረዋል ። በተደረገላቸው ህክምና ማየት በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልጸው፣ ‘ሌሎች ተጠቂዎች ወደ ህክምናውን እንዲያደርጉ ምክራቸውን ለግሰዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት የዓይናቸውን ብርሃን እንዳጡ የገለጹት እማሆይ ለምለም ዓለማየሁ በበኩላቸው በተደረገላቸው ህክምና ማየት ችያለሁ ብለዋል።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
625
የዱብቲ ሆስፒታል 300 ለሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ሰጠ 253 Share ሰመራ ጥር 17/2011 የዱብቲ ሆስፒታል 300 ለሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና መስጠቱን አስታወቀ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ ዩሱፍ ለኢዜአ እንደገለጹት ከጥር 11/2011ዓ.ም. ጀምሮ ለአምስት ቀናት በቆየው የነጻ-የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የተሰጣቸው ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለመጡ ነዋሪዎች ነው። የነጻ ህክምናው የተሰጠው ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ የዓይን ህክምና ክፍል ጋር በመተባባር መሆኑን አመልክተዋል፡፡ አቅመ ደካሞችና ህጻናትን ጭምር የነጻ ህክምናው ተጠቃሚ በመሆን የዓይን ብርሃናቸው እንዲመለስ ማድረጉን ዶክተር መሐመድ ተናግረዋል፡፡ ይህም ህብረተሰቡ የህክምናው እድሉን ለማግኘት ወደ አጎራባች ክልሎች በመሄድ ይደርስበት የነበረውን ወጪና እንግልት ማስቀረቱን ገልጸዋል። ህክምናው ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ረዘም ያለ ጊዜ ተወስዶ የተሰጠ በመሆኑ ታካሚዎቹ በአገልግሎቱ እርካታ እንዲያገኙ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁሟል። ህክምናው ለሆስፒታሉ የዓይን ህክምና አገልግሎት ክፍል ባለሙያዎችም የተሻለ ልምድና የእውቀት ሸግግር ዕድል የፈጠረ እንደነበር አስታውቀዋል። ከአይሳኢታ ወረዳ የመጡት ወይዘሮ ኤይሻ አብደላ ህክምናውን በአቅራቢያ ማግኘት ባለመቻላቸው ሲቸገሩ መቆየታቸውን አስታውሰው በሆስፒታሉ ባገኙት ነጻ የህክምና እይታቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ተናግረዋል። ከደዌ ወረዳ የመጡት ወይዘሮ ፋጡማ መሐመድ በበኩላቸው በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ማየት ተስኗቸው መቆየቱን ገልጸው በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ህክምና ማየት እንደቻሉ ገልጸዋል። ማየት መቻላቸው ቤተሰባቸውን የመንከባከብ ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለመዋጣትም ሆነ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። የዱብቲ ሆስፒታል ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር የአሁኖቹ ጨምሮ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ1ሺ ለሚበልጡ ሰዎች የነጻ የዓይን ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጿል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
626
ሆስፒታሉ ለ400 ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አደረገ 95 Share አምቦ ግንቦት 2 ቀን 2011 የአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በዓይን ሞራ ግርዶሽ ለተጠቁ 400 ሰዎች ነፃ የቀዶ ጥገና ህክምና መስጠቱን አስታወቀ። በተደረገላቸው ህክምና የዓይን ብርሀናቸው መመለሱን ታካሚዎች ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ስራ አስኪጅ አቶ ደበበ ፈጠነ ለኢዜአ እንደገለፁት የቀዶ ህክምናው የተሰጠው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍልና ሂማሊያን ካታራክት ፕሮጄክት በተሰኘ አለም አቀፍ ድርጅት የገንዘብና የባለሙያ ትብብር ነው። ሕክምናው ከምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ፣ ጅባት፣ ደንዲ፣ ድሬ ኢንጪኒ፣ ቶኬ ኩታዬና አምቦ ወራዳዎች ለተውጣጡና ከፍለው መታከም ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መሰጠቱን ተናግረዋል። የሂማሊያን ካታራክት ፕሮጄክት አስተባባሪ አቶ አሳሳኽኝ ንጉሴ” ከፍለው መታከም የማይችሉ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ተጠቂዎችን ከዓይነ ስውርነት ለመታደግ ህክምናው ተሰጥቷል” ብለዋል ። የኖኖ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ አቦነሽ መንግስቱ የአንድ ዓይናቸውን ብርሃን ካጡ ሶስት ዓመት እንደሆናቸው አስታውሰዋል። ሁለተኛው አይናቸውም ካለፈው ዓመት ጀምሮ እይታው እየቀነሰ በመምጣቱ በሰዎች እርዳታ ይንቀሳቀሱ እንደነበር ተናግረዋል። “አምቦ ሆስፒታል መጥቼ በተደረገልኝ ህክምና የሁለቱም ዓይኖቼ ብርሀን በመመለሱ ተደስቻለሁ” ሲሉ ተናግረዋል። በአምቦ ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪ ወይዘሮ ብርሃኔ ሰለሞን “አንድ ዓይኔ ማየት ካቆመ ሁለት ዓመት ሆኖታል” ብለዋል። ከፍለው መታከም ባለመቻላቸው ሲቸገሩ መቆየታቸውን ያስታወሱት ታማሚዋ፣”በሆስፒታሉ መጥቼ ዛሬ ህክምናውን በማግኘቴ ያጣሁትን የዓይኔን ብርሃን መልሼ አግኝቻለሁ” ብለዋል፡፡ ከጅባት ወረዳ ነዋሪው አቶ አበበ መኮንን በበኩላቸው በህክምናው ዕይታቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ህክምናውን ላደረጉላቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
627
ቤተ ቤተክርስቲያኗ ለምዕራብ ኢትዮጵያ ነዋሪዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና እየሰጠች ነው 111 Share ነቀምቴ ሚያዝያ 1/2011 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለምዕራብ ኢትዮጵያ ነዋሪዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና እየሰጠች ነው። የቤተ ቤተክርስቲያኗ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ማዕከል ሲኖዶስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ቄስ ተሰማ ኤጀታ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ለ10 ቀናት የሚቆየው አገልግሎት እየተሰጠ ያለው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ወገኖችን ለመርዳት ነው። በነቀምቴ የዓይን ሕክምና ክሊኒክ በሚሰጠው አገልግሎት አንድ ሺህ ሰዎች ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑና ከነዚህም 400 የሚሆኑት የዓይን ሞራ ቀዶ ጥገና እንደሚከናወንላቸው አስታውቀዋል። በዚህም ከመለስተኛ እስከ ከፍተኛ የዓይን ሞራ ቀዶ ጥገና የሚደረግ ሲሆን፣ ለግላኮማ በሽተኞች ነፃ የመድኃኒትና የሕክምና አገልግሎት ያገኛሉ። አገልግሎቱ በስድስት የውጭና የአገር ውስጥ ሐኪሞች እንደሚሰጥ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። ቤተ ክርስቲያኗ በምዕራብ ኦሮሚያ በተቋቋሙ ሰባት ማዕከላት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕዝብን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራች መሆኗንም አመልክተዋል። ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መካከል በጅማ ዞን የሊሙ ሰቃ ወረዳ የማነሳ ኤጀርሳ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ደጀነ ስርና በሰጡት አስተያየት በአገልግሎቱ የተፈወሱ ሰዎችን አይተው በመጡበት አገልግሎት ረክቻለሁ ብለዋል። አገልግሎቱ ከሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት የተሻለ መሆኑን የገለጹት አስተያየት ሰጪው፣ የታዘዛላቸው መነጽር ዋጋም ተመጣጣኝ ሆኖ እንዳገኙት ተናግረዋል። የነቀምቴ ከተማ ነዋሪው አቶ ወጋሪ ቀልበሳ በሰጡት አስተያየት ቤተክርስቲያኗ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ዕውቀትና ልምድ ባላቸው ሐኪሞች በምትሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ተራ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ገልጸዋል። አገልግሎቱ እስከ ሚያዝያ 9/2011 ይሰጣል። ቤተክርስቲያኗ በጤና፣በድህነት ቅነሳ፣ሴቶችን በማብቃትና የአየር ንብረት ለውጥ በመከላከል መስኮች እየሰራች መሆኗንም ገልጻለች።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
628
በአሜሪካን ሀገር ኮሎራዶ የሚገኝ የዓይን ህክምና ፕሮጀክት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በእብናት ወረዳ የዓይን ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ ባሕር ዳር፡ጥር 23/2011 ዓ.ም(አብመድ) የህክምና አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እየተሰጠ ያለው፡፡‹‹ ላይዮንስ ክለብ ኦፍ ኮሎራዶ›› የተሰኘው የዓይን ህክምና ፕሮጀክት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሱዚ ሶሪዮ ኪንስኪ እንደነገሩን ከ4 ሺህ በላይ ህሙማንን ለመርዳት አስበው ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፡፡ ‹‹ዓላማችን ማህበረሰቡ የተሻለ እይታ እንዲኖረው ማስቻል ነው››ያሉት ፕሬዝዳንቷ በዓለም ላይ የዚህ አይነት ህክምና የሚያስፈልጓቸው በርካታ ማህበረሰቦች ናቸው፤ ወደ ኢትዮጵያም የመጣነው በሀገሪቱ በእይታ ችግር የሚሰቃዩ ሰዎችን ለመርዳት ነው ብለዋል፡፡ የህክምና ቡድኑ ለታካሚዎች ምርመራ በማድረግ እንደየ ህሙማን እይታ መጠን ህክምናውን ይሰጣል፡፡ መነጽሮቹ ከለጋሽ አካላት በፕሮጀክት የተሰበሰቡ ሲሆኑ ጥራታቸውን ጠብቀው ለተገልጋዮች እንዲደርሱ በጥንቃቄ መሰራታቸውንም የፕሮጀክቱ ፕሬዝዳንት ነግረውናል፡፡ ሌሎች ህክምናዎችን ለማድረግ ከፍተኛ በጀት ይጠይቀናል፤ በመሆኑም የሀገር ውስጥ ዶክተሮች እኛ የምንሰጣቸውን መረጃ ይዘው ለታካሚዎች የህክምና ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው እንመክራለን ብለዋል፡፡ተጨማሪ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማንም ወደ ጤና ተቋም ሄደው እንዲታከሙ መክረዋል፡፡ ወይዘሮ ሱዚ ‹‹የምናደርገው ድጋፍ በቂ እይደለም፤ ነገር ግን ያለንን ድጋፍ አድርገን ቀጣይ ተመልሰን በስፋት ለመስራት የቤት ስራ ይዘን እንሄዳለን›› ብለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስራቸውን በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ የጀመሩት የህክምና ቡድኖቹ ወደ ጎንደር፣አክሱም፣ላል ይበላ እንዲሁም ወደ ደቡብ ክልል እና ሌሎች ቦታዎችም ተጉዘው ለመስራት እቅድ ይዘዋል፡፡ የእይታ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ መንግስት እና ሌሎች ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ሊሰሩ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቷ በሰጡት አስተያየት ህዝቡ ህክምና ለማግኘት ያለው ፍላጎት እጅግ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡ ለመታከም ካላቸው ፍላጎት አንጻር ስርዓት አስይዘን ለመስራት ተቸግረናል ያሉት ወይዘሮ ሱዛን መንግስት ከጎናቸው ሆኖ እንዲረዳቸው ጠይቀዋል፡፡ የህክምና ቡድኑ በሚሰጠው አገልግሎት መንግስትን እያገዘው ነው፡፡ ታካሚዎችን ከመለየት ጀምሮ ህክምና ቦታ እስኪመጡ ድጋፍ አድርገናል፤ በህክምና ሂደቱም ቀጥታ ተሳትፎ እያደረግን ነው ያሉት የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ.ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ደሳለኝ መንበር ናቸው፡፡ የህክምና አገልግሎት ያገኙ አስተያየት ሰጪዎችም በአገልግሎቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ዋጋው አንዳርጌ አይናቸውን ጋርዷቸው እንደልባቸው ማየት አይችሉም፡፡ ጤና ጣቢያ ሄደው ሲመረመሩም የአይን ሞራ ግርዶሽ እንዳለባቸው እና ለጋ በመሆኑ ቶሎ እንደማይሰራላቸው ተነግረው ነበር፡፡ አሁን ተገቢው ምርመራ ተደርጎላቸው መነጽር መሰጠታቸው ወደፊት እንደልባቸው ማየት እንደሚያስችላቸው ተስፋ አድርገዋል፡፡ ተማሪ ፋሲካው መንግስቱ ደግሞ የአጭር እይታ ችግር ተጠቂ በመሆኑ ጽሁፍ እንደልቡ ማንበብ እንደማይችል ገልጾልናል፡፡ ይሁን እንጂ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ወደ ጤና ተቋም ሄዶ መታከም አልቻለም፡፡ ዛሬ በተደረገለት ህክምና ወረቀት ላይ ለማንበብ ሞክሮ በተሻለ መልኩ ማንበብ ችሏል፡፡ ሁለቱን ለአብነት አነሳን እንጂ እገዛ የተደረገላቸው ሰዎች ሲደሰቱ ተመልክተናል፡፡ ፕሮጀክቱ በእንግሊዝ እና በአሜሪካ ለሚገኙ ስደተኞች የአይን ህክምና እገዛ አድርጓል፡፡ በሴኔጋል፣በሞንጎሊያ፣በሜክሲኮ፣በኢኳዶር እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የህክምና እርዳታ ሰጥቷል፡፡ ኤስያን ጨምሮ በሌሎች አህጉራት በመዘዋወር ህክምናውን ሰጥተዋል፡፡ እኛም እንደተመለከትነው የህክምና ቡድኑ ከተማሪ እስከ አዛውንት አገልግሎቱን ሲሰጡ ተመልክተናል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
629
ፋውንዴሽኑ 700 ለሚሆኑ ዜጎች ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሰጠ አክሱም ህዳር 5/2011 አልባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከአክሱም ቅድስተ ማርያም ሆስፒታል ጋር በመተባበር 700 ለሚሆኑ ዜጎች ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ሰጠ፡፡ ህክምናውን የተሰጠው በቅስት ማሪያም ሆስፒታሉ ውስጥ ለሶስት ቀናት በቆየ ዘመቻ ነው፡፡ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ገብረሚካኤል ወልደገብሪኤል እንደተናገሩት የፋውንዴሽኑ ሀኪሞች ከሰባት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የአይን በሽታ ምርመራ አድርገዋል፡፡ ከእነዚሁ ውስጥ 700 ሰዎች የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ የተለያየ መድሀኒት በነጻ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ የአይን በሽታ ለመከላከል በገጠር አካባቢ የግልና አከባቢ ንጽህና አጠባበቅ ለማጠናከር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡ በቀጠይም ሆስፒታሉ ከኲሓ ሆስፒታል ፣ከትግራይ ጤና ቢሮና እና ሂዩማሊያን ካታራክት ከተባለ በጎ አድራጊ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከህዳር 22/2011ዓ.ም ጀምሮ ነጻ አይን ህክምና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡ በሆስፒታሉ የአይን ህክምና ባለሙያ ዶክተር ሓጎስ በየነ በበኩላቸው የአይን ሞራ በሽታ ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣ እና ለአይነ ስውርነት የሚዳርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሽታው በቀዶ ህከምና የሚድን በመሆኑ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ ተጨማሪ ስራዎች እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡ ሁለቱም አይናቸው ለዓመታት ማየት ተስኗቸው ከስራ ተገልለው እንደቆዩ የተናገሩት ደግሞ የአይን ሞራ ግርዶች ቀዶ ህክምና የተደረገላቸው የአድዋ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ ክርስቱ ሀፍቱ ናቸው፡፡ በአቅም ማነስ ምክንያት ሳይታከሙ እንደቆዩ ተናግረው አሁን በተደረገላቸው ህክምና ብርሀናቸው መመለሱን ገልጸዋል፡፡ ከላዕላይ ማይጨው ወረዳ የሓጸቦ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ገብረእግዚአብሔር አስረሱ በበኩላቸው በበሽታው ላለፉት ስድስት ዓመታት ማየት ተስኗቸው እንደቆዩ ተናግረው አሁን በተደረገላቸው ህክምና በመደናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ ፋውንዴሽኑ በአክሱም ከተማ ነጻ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ሲሰጥ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
630
በሰባት ቀናት ብቻ የ840 ሰዎችን የዓይን ብርሃን መመለስ እንደተቻለ ተገለጸ፡፡ ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 30/2011 ዓ.ም(አብመድ) ለ 25ኛ ጊዜ በተደረገ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ከ16 ሺህ በላይ ሰዎች ማየት እንደቻሉ ተገልጿል፡፡ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና እየተሰጠ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ዓይነ ስውራን እንደሚኖሩ በዘርፉ ላይ የተሰራ ጥናት ያመላክታል፡፡ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ የእይታ ደረጃቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ነው ጥናቱ የሚያሳየው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ታክሞ መዳን በሚችል የዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት በሚፈጠር ዓይነ ስውርነት ብርሃናቸውን ያጡ ናቸው፡፡ ችግሩን ለመቀነስ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና እየተሰጠ ነው፡፡ ህክምናውን እየሰጠ የሚገኘው “ዳይሬክት ኤይድ” የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት አስተባባሪ ጌትነት ንጉሴ (ዶክተር) እንደገለጹት ለ25ኛ ጊዜ በተደረገ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ከ16 ሺህ በላይ ዜጎች ማየት ችለዋል፡፡ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በአይን ሞራ ግርዶሽ የዓይን ብርሃናቸውን ያጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከነሐሴ 24 እስከ 30/2011 ዓ.ም በሚቆይ የነጻ የዓይን ቀዶ ህክምና ተጠቃሚ እየሆኑ ነው፡፡ በዞኑ ለ800 ሰወች አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እስከ ዛሬ (ነሐሴ 30) ድረስ ብቻ 840 ሰወች አገልግሎቱን ማግኘታቸውን የወልዲያ ጠቅላላ ሆስፒታል ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ በላይ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ ከራያ ቆቦ ወራዳ ወደ ወልዲያ መጥተው ህክምና ያገኙት ወይዘሮ ዓይናዲስ ወልዴ የዓይን ብርሃናቸውን ካጡ ከሰባት ወራት በላይ ተቆጥሯል፡፡ በተደረገላቸውን ህክምና የዓይን ብርሃናቸውን አግኝተው በድጋሜ ማየት ከጀመሩ ዛሬ ሦስተኛ ቀናቸው እንደሆነ ነግረውናል፡፡ ከግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ የመጡት አቶ ፈቃዴ ደረበ ደግሞ የዓይን ብርሃናቸውን ካጡ ከሁለት ዓመታት በኋላ ሰሞኑን በተደረገላቸው ቀዶ ህክምና ማየት ችለዋል፡፡ ብርሀናቸውን ድጋሜ በማግኘታቸው ደስታቸውን የገለጹት ታካሚዎቹ ተመሳሳይ ችግር ላለባቸው ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎቱ ቢሰጥ መልካም እንደሆነ አስተያዬት ሰጥተዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ጠዋትና ማታ ፊቱን በንጹና ውሃ እና በሳሙና በመታጠብ የዓይን ጤንነቱን መጠበቅና ችግር ሲያጋጥም ደግሞ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በመታከም የዓይን ብርሃኑን ሊጠብቅ እንደሚገባ ዶክተር ጌትነት መክረዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
631
የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና እየሰጠ ነው Fri, Nov 08, 2019በአድማሱ አራጋው ጤና የአማራ ክልል ቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ። በነጻ ሕክምናው 1ሺህ 500 የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የገለጹት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተበጀ፤ ከደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ከኦሮሚያ ብሔረሰብ አስተዳደር እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የሚመጡ ሕሙማን ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል። በዚህም ቀደም ሲል በባለሙያ ተለይተው ሕክምናውን ሲጠባበቁ የነበሩና በዕድሜ መግፋት፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ማየት የተሳናቸው ሰዎች ሕክምናውን እንደሚያገኙ ገልጸዋል፡፡ አቶ ሲሳይ እንዳሉት ሕክምናው እየተሰጠ ያለው ከውጭ ሃገር በመጡና ከአገር ውስጥ በተውጣጡ 13 ከፍተኛ የዓይን ሕክም ባለሙያዎች በጋራ ሆነው ነው። ላለፉት ሁለት ቀናት በተሰጠው ስልጠናም የዓይን ብሌናቸው በሞራ ተሽፍኖ የነበረ 516 ሰዎች የዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምና ተሰጥቷቸው መዳናቸውን ተናግረዋል። የዓይን ሞራ ሕክምና የሚደረግላቸው ሕሙማን ከሕክምናው በተጨማሪ በሆስፒታሉ በሚቆዩበት ጊዜ የምግብና የመኝታ እንዲሁም የትራንስፖርት ሙሉ ወጪ እንደሚሸፈንላቸው አመልክተዋል። ሁሉም የዓይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸው ወገኖች በነጻ ህክምናው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባለድርሻ አካላት ቅስቀሳ በማድረግ ዓይነ ስውርነትን በጋራ እንዲከላከሉም አቶ ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የነጻ ሕክምናው ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል በመቅደላ ወረዳ ቀበሌ 30 የሚኖሩት አቶ መሃመድ ሰይፉ እንዳሉት ሁለት ዓይኖቻቸው ማየት ተስኗቸው በቤት ውስጥ መዋል ከጀመሩ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአካባቢው በሚገኙ የጤና ተቋማት ሕክምና ቢያደርጉም መፍትሄ ማጣታቸውን አስታውሰው ወደደሴና አዲስ አበባ ከተማ ሂደው ለመታከም አቅም ስለሌላቸው ህመማቸውን ተቀብለው መኖራቸውን አስታውሰዋል። “በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል በመጀመሪያው ቀን በተደረገልሽ ነጻ የዓይን ቀዶ ሕክም የዓይኖቼ ብርሃን በመመለሳቸው ተደስቺያለሁ” ብለዋል፡፡ በእርጅና ምክንያት ማየት ከተሳናቸው ስምንት ዓመታት እንዳስቆጠሩ የገለጹት ደግሞ በአንባሰል ወረዳ የቀበሌ 05 ነዋሪ ወይዘሮ ሀድያ ዳውድ ናቸው። በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ለሁለቱም ዓይኖቻቸው በተደረገላቸው ሕክምና ብርሃናቸው መመለሱን ጠቁመው ለተደረገላቸው ድጋፍና መልካም መስተንግዶም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ሆስፒታሉ ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምናውን ከጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ ሲሆን ህክምናውም ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይም ታውቋል። ሆስፒታሉ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሕሙማን በተለያዩ ጊዜያት ህክምናውን በመስጠት የዓይን ብርሃናቸው እንዲመለስ ማድረጉ ተገልጿል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
632
በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ1 ሺህ 100 ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ተሰጠ 3726 Share አርባ ምንጭ ሚያዝያ 25/2010 “ሂማሊያን ካትራክት” የተሰኘ የአሜሪካን ግብረ ሰናይ ፕሮጀክት ላለፉት ሰባት ቀናት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ1 ሺህ 100 ሰዎች የነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምናና የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መካከል አቶ ኑሩ ኢብራሂም በሰጡት አስተያየት በዓይን ብሌን ጠባሳ ችግር ምክንያት ከልጅነታቸው ጀምሮ ህመም ሲሰማቸው መቆየቱንና ከ3 ዓመት ወዲህ ሙሉ በሙሉ ማየት እንደተሳናቸው ተናግረዋል ፡፡ በሆስፒታሉ ከአሜሪካን በመጡ የዓይን ህክምና ባለሙያዎች በተደረገላቸው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና ዳግም ማየት መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡ ”ብርሃኔ ዳግም በመመለሱና ሠርቼ ቤተሰቤን ለማስተዳደር በመብቃቴ ደስታዬ ወደር የለውም” ሲሉም ገልጸዋል ፡፡ በተመሳሳይ ከያቤሎ የ2 ዓመት ልጃቸውን ያሳከሙት አቶ ቦሩ ጃሮ በበኩላቸው ልጃቸው ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ ማየት እንደማይችል ተናግረዋል ፡፡ በተደረገው ነፃ ህክምና ልጃቸው ማየት በመቻሉ ደስታቸው ወደር እንደሌለው ጠቅሰዋል፡፡ ”ገና ህፃን እያለሁ በአግባቡ ማየት ባለመቻሌ ምክንያት ወላጆቼ በባህላዊ መንገድ ያደረጉልኝን እገዛ ተከትሎ ሙሉ በሙሉ ማየት ተስኖኝ ነበር” ያለችው በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ የ20 ዓመት ወጣት ትዕግስት በቀለ ናት ፡፡ ”በተደረገልኝ ህክምና አሁን ሰዎችንና አከባቢዬን ለማየት በመታደሌ ዳግም የተወለድኩ ያህል ተሰምቶኛል” ብላለች፡፡ በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓይን ክፍል ኃላፊና ስፔሻሊስት ዶክተር ዳዊት ግዴይ “ሂማሊያን ካታራክት” የተሰኘ ግብረ -ሰናይ ድርጅት ባደረገው ነፃ የዓይን ህክምና 1ሺህ 100 ወገኖች ብርሃናቸውን መመለስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ የዓይን ብሌን ጠባሳ ችግር ያለባቸው በመሆኑ የብሌን ንቅለ ተከላ ተካሄዶላቸዋል፡፡ በሆስፒታሉ የ”ሂማሊያን ካትራክት ፕሮጀክት“ አስተባባሪ አቶ ደመቀ ደበበ በበኩላቸው በኢኮኖሚም ሆነ በባለሙያ ችግር በርካታ ዜጎች መዳን እየቻሉ የዓይን ብርሃናቸውን እንደሚያጡ ጠቅሰዋል፡፡ በሆስፒታሉ የተደረገው ነፃ ህክምና 10 ሚሊዮን ብር እንደሚገመትና ውጤታማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
633
የዱብቲ ሆስፒታል 300 ለሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ሰጠ 278 Share ሰመራ ጥር 17/2011 የዱብቲ ሆስፒታል 300 ለሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና መስጠቱን አስታወቀ። የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ ዩሱፍ ለኢዜአ እንደገለጹት ከጥር 11/2011ዓ.ም. ጀምሮ ለአምስት ቀናት በቆየው የነጻ-የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የተሰጣቸው ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለመጡ ነዋሪዎች ነው። የነጻ ህክምናው የተሰጠው ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ የዓይን ህክምና ክፍል ጋር በመተባባር መሆኑን አመልክተዋል፡፡ አቅመ ደካሞችና ህጻናትን ጭምር የነጻ ህክምናው ተጠቃሚ በመሆን የዓይን ብርሃናቸው እንዲመለስ ማድረጉን ዶክተር መሐመድ ተናግረዋል፡፡ ይህም ህብረተሰቡ የህክምናው እድሉን ለማግኘት ወደ አጎራባች ክልሎች በመሄድ ይደርስበት የነበረውን ወጪና እንግልት ማስቀረቱን ገልጸዋል። ህክምናው ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ረዘም ያለ ጊዜ ተወስዶ የተሰጠ በመሆኑ ታካሚዎቹ በአገልግሎቱ እርካታ እንዲያገኙ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁሟል። ህክምናው ለሆስፒታሉ የዓይን ህክምና አገልግሎት ክፍል ባለሙያዎችም የተሻለ ልምድና የእውቀት ሸግግር ዕድል የፈጠረ እንደነበር አስታውቀዋል። ከአይሳኢታ ወረዳ የመጡት ወይዘሮ ኤይሻ አብደላ ህክምናውን በአቅራቢያ ማግኘት ባለመቻላቸው ሲቸገሩ መቆየታቸውን አስታውሰው በሆስፒታሉ ባገኙት ነጻ የህክምና እይታቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ተናግረዋል። ከደዌ ወረዳ የመጡት ወይዘሮ ፋጡማ መሐመድ በበኩላቸው በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ማየት ተስኗቸው መቆየቱን ገልጸው በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ህክምና ማየት እንደቻሉ ገልጸዋል። ማየት መቻላቸው ቤተሰባቸውን የመንከባከብ ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለመዋጣትም ሆነ ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። የዱብቲ ሆስፒታል ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር የአሁኖቹ ጨምሮ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ1ሺ ለሚበልጡ ሰዎች የነጻ የዓይን ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጿል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
634
ሆስፒታሉ ለ400 ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አደረገ 128 Share አምቦ ግንቦት 2 ቀን 2011 የአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በዓይን ሞራ ግርዶሽ ለተጠቁ 400 ሰዎች ነፃ የቀዶ ጥገና ህክምና መስጠቱን አስታወቀ። በተደረገላቸው ህክምና የዓይን ብርሀናቸው መመለሱን ታካሚዎች ገልጸዋል። የሆስፒታሉ ስራ አስኪጅ አቶ ደበበ ፈጠነ ለኢዜአ እንደገለፁት የቀዶ ህክምናው የተሰጠው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍልና ሂማሊያን ካታራክት ፕሮጄክት በተሰኘ አለም አቀፍ ድርጅት የገንዘብና የባለሙያ ትብብር ነው። ሕክምናው ከምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ፣ ጅባት፣ ደንዲ፣ ድሬ ኢንጪኒ፣ ቶኬ ኩታዬና አምቦ ወራዳዎች ለተውጣጡና ከፍለው መታከም ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መሰጠቱን ተናግረዋል። የሂማሊያን ካታራክት ፕሮጄክት አስተባባሪ አቶ አሳሳኽኝ ንጉሴ” ከፍለው መታከም የማይችሉ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ተጠቂዎችን ከዓይነ ስውርነት ለመታደግ ህክምናው ተሰጥቷል” ብለዋል ። የኖኖ ወረዳ ነዋሪ ወይዘሮ አቦነሽ መንግስቱ የአንድ ዓይናቸውን ብርሃን ካጡ ሶስት ዓመት እንደሆናቸው አስታውሰዋል። ሁለተኛው አይናቸውም ካለፈው ዓመት ጀምሮ እይታው እየቀነሰ በመምጣቱ በሰዎች እርዳታ ይንቀሳቀሱ እንደነበር ተናግረዋል። “አምቦ ሆስፒታል መጥቼ በተደረገልኝ ህክምና የሁለቱም ዓይኖቼ ብርሀን በመመለሱ ተደስቻለሁ” ሲሉ ተናግረዋል። በአምቦ ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪ ወይዘሮ ብርሃኔ ሰለሞን “አንድ ዓይኔ ማየት ካቆመ ሁለት ዓመት ሆኖታል” ብለዋል። ከፍለው መታከም ባለመቻላቸው ሲቸገሩ መቆየታቸውን ያስታወሱት ታማሚዋ፣”በሆስፒታሉ መጥቼ ዛሬ ህክምናውን በማግኘቴ ያጣሁትን የዓይኔን ብርሃን መልሼ አግኝቻለሁ” ብለዋል፡፡ ከጅባት ወረዳ ነዋሪው አቶ አበበ መኮንን በበኩላቸው በህክምናው ዕይታቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ህክምናውን ላደረጉላቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
635
በሰሜን ሸዋ ዞን ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በዘመቻ እየተካሄደ ነው 1753 Share ደብረብርሃን ህዳር 11/2011 በሰሜን ሸዋ ከ14 ሺህ በላይ ለሚበልጡ ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን የዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ። ህክምናው እየተሰጠ ያለው የዓይን በሽታ ችግር እንዳለባቸው በጥናት ለተለዩ ሰዎች ነው፡፡ በካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ለአንድ ወር ያህል በሚሰጠው የነጻ ህክምናው 41 ባለሙያዎች ሰልጥነው መሰማራታቸውን በመምሪያው የዓይነስውርነት መከላከል ኦፊሰር ወይዘሮ አበባ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ እስካሁን በተሰጠው የነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና 530 ሰዎች ተጠቃሚ ማደረግ እንደተቻለ አመልክተዋል። ሞጃና ወደራ፣ ሀገረማሪያም፣ ሲያደብርና ዋዩ፣ አንጾኪያ ገምዛ፣ ኤፍራታ ግድም፣ እንሳሮ፣ ቀወትና ጣርማ በር ወረዳዎች ህክምናው የሚሰጥባው ናቸው፡፡ የሚሰጠውን ነጻ የዓይን ህክምና ማህበረሰቡ በመጠቀም ከበሸታው ተፈውሶ ዓይነ ስውርነትን መከላከል እንደሚነርበትም ኦፊሰሯ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ሰሜን ሸዋ ዞን የትራኮማ ማጥፋት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ መሃመድሳኒ ሀሰን በበኩላቸው የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለሚያፈልጋቸው 14 ሺህ ሰዎች የሚሆን 15 ሚሊዮን 300ሺህ ብር በጀት ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በተጓዳኝም ጥናት በማድረግ ተጨማሪ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንደሚሰጥ አመልክተው በትራኮማና በዓይነ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ጉድለት ሳቢያ የዜጎችን ዓይን ከጉዳት ለመታደግ በትኩረት እንደሚሰሩም አስረድተዋል፡፡ በሞጃና ወደራ ወረዳ የዙብአምባ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ገደለ ማሞ በተደረገላቸዉ ቀዶ ህክምና የዓይን ብርሃናቸውን መልሰው እንዳገኙ ተናግረዋል፡፡ በተደረገላቸው ህክምናም ቀደም ሲል በዓይን ህመም ይሳቃዩ የነበረው አሁን መዳናቸውንና ያለችገር ማየት እንደቻሉ ገልጸዋል። ” ባለፈው ዓመትም አንድ ዓይኔን ታክሜ ለውጥ በማየቴ ሌሎችንም በማስተባበር እንዲታከሙ ለማድረግ የደርሻዬን እወጣለሁ “ብለዋል፡፡ ሌላዋ የፊላገነት ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ንጋት አደናግር በበኩላቸው የዓይናቸው ጸጉር በመቀልበሱ ማየት ሳይችሉና ለመስራትም ይቸገሩ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ በግላቸው ለመታከምም የገንዘብ ችግር እንደነበረባቸው ጠቅሰው አሁን በነፃ በተሰጣቸው ህክምና የዓይን ብርሃናቸውን መልሰው ማግኘታቸው መደሰታቸውን አስረድተዋል። በዞኑ ከሁለት ዓመት በፊት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከ29 ሺህ በላይ ሰዎች የበሽታው ተጠቂ እንደነበሩም ተመልክቷል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
636
በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ1 ሺህ 100 ሰዎች የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ተሰጠ 3726 Share አርባ ምንጭ ሚያዝያ 25/2010 “ሂማሊያን ካትራክት” የተሰኘ የአሜሪካን ግብረ ሰናይ ፕሮጀክት ላለፉት ሰባት ቀናት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ1 ሺህ 100 ሰዎች የነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምናና የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ ከአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መካከል አቶ ኑሩ ኢብራሂም በሰጡት አስተያየት በዓይን ብሌን ጠባሳ ችግር ምክንያት ከልጅነታቸው ጀምሮ ህመም ሲሰማቸው መቆየቱንና ከ3 ዓመት ወዲህ ሙሉ በሙሉ ማየት እንደተሳናቸው ተናግረዋል ፡፡ በሆስፒታሉ ከአሜሪካን በመጡ የዓይን ህክምና ባለሙያዎች በተደረገላቸው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና ዳግም ማየት መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡ ”ብርሃኔ ዳግም በመመለሱና ሠርቼ ቤተሰቤን ለማስተዳደር በመብቃቴ ደስታዬ ወደር የለውም” ሲሉም ገልጸዋል ፡፡ በተመሳሳይ ከያቤሎ የ2 ዓመት ልጃቸውን ያሳከሙት አቶ ቦሩ ጃሮ በበኩላቸው ልጃቸው ከተወለደ ጊዜ ጀምሮ ማየት እንደማይችል ተናግረዋል ፡፡ በተደረገው ነፃ ህክምና ልጃቸው ማየት በመቻሉ ደስታቸው ወደር እንደሌለው ጠቅሰዋል፡፡ ”ገና ህፃን እያለሁ በአግባቡ ማየት ባለመቻሌ ምክንያት ወላጆቼ በባህላዊ መንገድ ያደረጉልኝን እገዛ ተከትሎ ሙሉ በሙሉ ማየት ተስኖኝ ነበር” ያለችው በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ የ20 ዓመት ወጣት ትዕግስት በቀለ ናት ፡፡ ”በተደረገልኝ ህክምና አሁን ሰዎችንና አከባቢዬን ለማየት በመታደሌ ዳግም የተወለድኩ ያህል ተሰምቶኛል” ብላለች፡፡ በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓይን ክፍል ኃላፊና ስፔሻሊስት ዶክተር ዳዊት ግዴይ “ሂማሊያን ካታራክት” የተሰኘ ግብረ -ሰናይ ድርጅት ባደረገው ነፃ የዓይን ህክምና 1ሺህ 100 ወገኖች ብርሃናቸውን መመለስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ የዓይን ብሌን ጠባሳ ችግር ያለባቸው በመሆኑ የብሌን ንቅለ ተከላ ተካሄዶላቸዋል፡፡ በሆስፒታሉ የ”ሂማሊያን ካትራክት ፕሮጀክት“ አስተባባሪ አቶ ደመቀ ደበበ በበኩላቸው በኢኮኖሚም ሆነ በባለሙያ ችግር በርካታ ዜጎች መዳን እየቻሉ የዓይን ብርሃናቸውን እንደሚያጡ ጠቅሰዋል፡፡ በሆስፒታሉ የተደረገው ነፃ ህክምና 10 ሚሊዮን ብር እንደሚገመትና ውጤታማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
637
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው 197 Share ሆሳዕና የካቲት 14/2011 በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የንግሥት ኢሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ሆስፒታል ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው። ታካሚዎች በተደረገላቸው ሕክምና ብርሃናቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከሐዲያ ዞን ግምቢቹ ከተማ የመጡት አቶ ታደሰ ሀባሞ ዓይኖቻቸው ከአንድ ዓመት በፊት ማየት አቁመው እንደነበር ይናገራሉ፡፡ በሆስፒታሉ በተደረገላቸው ሕክምና ብርሃናቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከዞኑ ሌሞ ወረዳ የመጡት አቶ ጴጥሮስ ሚሺሶ ለሁለት ዓመታት የቀኝ ዓይናቸው የማየት ችግር ገጥሞት እንደነበር አመልክተው፣ሕክምናው እይታቸውን መልሶ ለማግኘት እንዳስቻላቸው አመልክተዋል። ሕክምናውን ”በገንዘብ የማይገኝና እንክብካቤውም ሕመሜን ያስረሳ” ብለውታል፡፡ የሆስፒታሉ ክሊኒካል ዋና አስተባባሪ ዶክተር ጳውሎስ አሼቦ ሕክምናውን ከሁለት መንግሥታዊ ድርጅቶች ፕሮጀክቶች ጋር በመተባበር አገልግሎቱን መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ አገልግሎቱ ለችግሩ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት መከናወኑንም ገልጸዋል፡፡ የዊማ ኢንተርናሽናል ፕሮጀክት የአገር ውስጥ ተጠሪ አቶ ቴዌድሮስ በላቸው ፕሮጀክቱ የዓይን ሞራ ግርዶሽን የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል እገዛ እያደረገ ነው። በዚህም ለታካሚዎች የሕክምና፣የምግብና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
638
እይታችን በመመለሱ ተደስተናል- የአይን ሞራ ግርዶሽ ታካሚዎች 489 Share ደሴ ጥቅምት 22/2011 በደሴ ከተማ በሚገኘው የቦሩ ሜዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተደረገላቸው የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እስከ 10 ዓመት ብርሃናቸውን አጥተው የነበሩ ግለሰቦች እይታቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ገለጹ፡፡ ሆስፒታሉ ለ700 ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶች ቀዶ ህክምና መደረጉን አስታወቀ። የህክምናው አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለኢዜአ እንደገለጹት ለዓመታት ብርሃናቸውን አጥተው የነበሩ ቢሆንም በተደረገላቸው የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የአይን ብርሃናቸው ተመልሶላቸዋል፡፡ ከህክምናው አገልግሎት ተጠቃሚዎች መካከል አንዱ የሆኑትና ከአልብኮ ወረዳ ጀማ ንጉሥ አካባቢ የመጡት አቶ ሃሰን ሰይድ በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት ከአስር ዓመታት በላይ ዓይናቸው ሙሉ በሙሉ እይታ ጋርዷቸው ማየት ተስኗቸው መቆየቱን አስታውሰዋል። በዚህም የተነሳ ሰርተው መብላት ባለመቻላቸው እርሳቸውም ሆነ ቤተሰቦቻቸው ጥገኛ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በተደረገላቸው የዓይን ሞራ ግርዶች ቀዶ ህክምና ለዓመታት ከቆዩበት የጨለማ ህይወት በመውጣት የፀሐይን ብርሃንና ቤተሰቦቻቸውን ማየት እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ ከወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ አካባቢ የመጡት አቶ ይመር አሊ በበኩላቸው ለአምስት ዓመታት ያህል በዓይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት የአይን ብርሃናቸውን አጥተውና ከስራ ተግልለው ቤት ውስጥ መቀመጣቸውን ተናግረዋል፡፡ ስራ አለመስራታቸው በጤናቸው ላይ ተጽእኖ አሳድሮ እንደነበር የተናገሩት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የዓይን ብርሃናቸው በመመለሱ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ የኤች ሲ ፒ ካንትሪ ዳይሬክተርና በቀዶ ህክምናው ከተሰማሩት ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶክተር ማት ኦሊቫ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ካላት አጠቃላይ ህዝብ ውስጥ 2 በመቶ የሚገመቱት ዓይነ ስውር መሆናቸውን ጠቁመዋል። አብዛኛው የአይን ሞራ ግርዶሽ በቀዶ ህክምና ሊድን የሚችል ቢሆንም በግንዛቤ እጥረትና በህክምና አቅርቦት እጥረት ታክመው መዳን አልቻሉም፡፡ የቀዶ ህክምናው የዓይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን ሰዎች መፈወስ ብቻ ሳይሆን በሽታው በቀላል ህክምና ሊድን ስለሚችል ችግሩ ያለባቸው ሰዎች ወደ ጤና ህክምና በመምጣት አገልግሎቱን እንዲያገኙ ግንዛቤ መፍጠርንም ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ድርጅታቸው ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር በተያዘው ዓመት ቦሩ ሜዳ ሆስፒታልን ጨምሮ በአገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ የህክምና ተቋማት ለ25 ሺህ ሰዎች የቀዶ ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡ የቦሩ ሜዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር እጸገነት አረጋ አገልግሎቱን ለመስጠት ታካሚዎችን የመለየት ስራ መካሄዱን ጠቁመው የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ወደ ሆስፒታሉ ሲመጡ የተሸከርካሪ፣ የምግብና የመጠለያ አገልግሎት እንደተዘጋጀላቸው አብራርተዋል፡፡ ባለፉት አራት ቀናት በተካሄደ የአይን ሞራ ግርዶች ነጻ ህክምና 700 ሰዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ታካሚዎቹ ከደቡብ ወሎ፣ ከኦሮሞ ብሔረሰብና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የመጡ ሲሆን ከአሜሪካ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከባህርዳርና ከወልዲያ ጤና ተቋማት የመጡ የህክምና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ህክምና ክፍል የመጨረሻ ዓመት ተማሪ የሆነችው ቤተልሄም ስለሽ በቀዶ ህክምና ዘመቻው ተሳታፊ በመሆኗ የተሻለ ልምድ እንድትቀስም እንዳስቻላት ተናግራለች፡፡ ዘመቻው ኢትዮጵያዊያን ሀኪሞች በህክምና ሊድን የሚችለውን የዓይነ ስውርነት ችግር መከላከል የሚያስችል እውቀትና ክህሎት እንዳላቸው የተገነዘበችበት አጋጣሚ እንደሆነም ገልጻለች፡፡ ወደፊት ተመርቃ ወደ ስራ ዓለም ስትሰማራም የዓይነስውርነት ችግርን ለመፍታት በህክምናና በምርምር ተሳትፎ እንደምታደርግ አረጋግጣለች፡፡ ከጥቅምት 19 እስከ 25/2011 ዓ.ም በሚቆየው የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ከ1ሺህ 400 በላይ ለሚሆኑ ታካሚዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
639
የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና እየሰጠ ነው Fri, Nov 08, 2019በአድማሱ አራጋው ጤና የአማራ ክልል ቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ። በነጻ ሕክምናው 1ሺህ 500 የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የገለጹት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተበጀ፤ ከደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ከኦሮሚያ ብሔረሰብ አስተዳደር እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የሚመጡ ሕሙማን ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል። በዚህም ቀደም ሲል በባለሙያ ተለይተው ሕክምናውን ሲጠባበቁ የነበሩና በዕድሜ መግፋት፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ማየት የተሳናቸው ሰዎች ሕክምናውን እንደሚያገኙ ገልጸዋል፡፡ አቶ ሲሳይ እንዳሉት ሕክምናው እየተሰጠ ያለው ከውጭ ሃገር በመጡና ከአገር ውስጥ በተውጣጡ 13 ከፍተኛ የዓይን ሕክም ባለሙያዎች በጋራ ሆነው ነው። ላለፉት ሁለት ቀናት በተሰጠው ስልጠናም የዓይን ብሌናቸው በሞራ ተሽፍኖ የነበረ 516 ሰዎች የዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምና ተሰጥቷቸው መዳናቸውን ተናግረዋል። የዓይን ሞራ ሕክምና የሚደረግላቸው ሕሙማን ከሕክምናው በተጨማሪ በሆስፒታሉ በሚቆዩበት ጊዜ የምግብና የመኝታ እንዲሁም የትራንስፖርት ሙሉ ወጪ እንደሚሸፈንላቸው አመልክተዋል። ሁሉም የዓይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸው ወገኖች በነጻ ህክምናው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባለድርሻ አካላት ቅስቀሳ በማድረግ ዓይነ ስውርነትን በጋራ እንዲከላከሉም አቶ ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የነጻ ሕክምናው ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል በመቅደላ ወረዳ ቀበሌ 30 የሚኖሩት አቶ መሃመድ ሰይፉ እንዳሉት ሁለት ዓይኖቻቸው ማየት ተስኗቸው በቤት ውስጥ መዋል ከጀመሩ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአካባቢው በሚገኙ የጤና ተቋማት ሕክምና ቢያደርጉም መፍትሄ ማጣታቸውን አስታውሰው ወደደሴና አዲስ አበባ ከተማ ሂደው ለመታከም አቅም ስለሌላቸው ህመማቸውን ተቀብለው መኖራቸውን አስታውሰዋል። “በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል በመጀመሪያው ቀን በተደረገልሽ ነጻ የዓይን ቀዶ ሕክም የዓይኖቼ ብርሃን በመመለሳቸው ተደስቺያለሁ” ብለዋል፡፡ በእርጅና ምክንያት ማየት ከተሳናቸው ስምንት ዓመታት እንዳስቆጠሩ የገለጹት ደግሞ በአንባሰል ወረዳ የቀበሌ 05 ነዋሪ ወይዘሮ ሀድያ ዳውድ ናቸው። በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ለሁለቱም ዓይኖቻቸው በተደረገላቸው ሕክምና ብርሃናቸው መመለሱን ጠቁመው ለተደረገላቸው ድጋፍና መልካም መስተንግዶም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ሆስፒታሉ ነጻ የዓይን ሞራ ቀዶ ሕክምናውን ከጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ ሲሆን ህክምናውም ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይም ታውቋል። ሆስፒታሉ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሕሙማን በተለያዩ ጊዜያት ህክምናውን በመስጠት የዓይን ብርሃናቸው እንዲመለስ ማድረጉ ተገልጿል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
[ 112 ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታና ህክምና የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽታ, የአይን ሞራ ግርዶሽ በሽተኞች ስለተደረገላቸው ህክምና የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚወች ናቸው፡፡ ስለ ሌላ አይን በሽታ የሚገልጹ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
640
ነሐሴ ፱ ነሐሴ ፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፱ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፯ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፮ ቀናት ይቀራሉ። ነሐሴ ፩ ነሐሴ ፩ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፩ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፴፭ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፴፬ ዕለታት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
641
ሐምሌ ፳ ሐምሌ ፳ ሐምሌ ፳ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፳ ኛው እና የክረምት ወቅት ፳፭ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፵፮ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፵፭ ዕለታት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
642
ሰኔ ፳፰ ሰኔ ፳፰ ሰኔ ፳፰ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፺፰ኛው እና የክረምት ወቅት ፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፷፰ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፷፯፭ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
643
የካቲት ፲፱ የካቲት ፲፱ የካቲት ፲፱፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፷፱ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፶፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፺፯ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፺፮ ቀናት ይቀራሉ። ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ዕለተ ሞት ዋቢ ምንጮች የካቲት ፳፫ የካቲት ፳፫ የካቲት ፳፫፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፸፫ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፶፰ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፺፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፺፪ ቀናት ይቀራሉ። ይሄ ዕለት በኢትዮጵያ የአድዋ ጦርነት የድል በዓል መታሰቢያ ነው።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
644
ሰኔ ፳፱ ሰኔ ፳፱ ሰኔ ፳፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፺፱ ነኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፷፯ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፷፮ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
645
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ (እንዲሁም በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት (ስድስት በአራት ዓመት) ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ (ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው) እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ። የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ 'አኖ ዶሚኒ' በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1 ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በ"ትስብዕት ዘመን" 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517 ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር ("አኖ ዶሚኒ") አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የ"አኖ ዶሚኒ" አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በ"አኖ ዶሚኒ" 9 እ.ኤ.አ. ሆነ። የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም። በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ (Dionysius Exiguus) የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም። ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ (Anno Domini ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1 ፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር ያሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቈጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 X 28) ተደጋጋሚ ናቸው። የወራት አቆጣጠር የተወረሰ ከቅብጢ ዘመን አቆጣጠር፣ ይህም የወጣ ከጥንታዊ ግብጽ ዘመን አቆጣጠር ነው። ሆኖም የወሮች ስሞች በግዕዝ ተለውጠዋል።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
646
መስከረም ፪ መስከረም 2 ቀን: ብሄራዊ ቀን በኬፕ ቨርድ... መስከረም ፪ መስከረም ፫ መስከረም ፫ ቀን በየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫ኛ እና የክረምት ወቅት ፸፫ኛ ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፷፫፤ በ[ዘመነ ዮሐንስ]]፤ ዘመነ ማርቆስ እና በዘመነ ማቴዎስ ደግሞ ፫፻፷፪ ቀናት ይቀራሉ። መስከረም ፬ መስከረም ፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፬ኛው እና የክረምት ፸፬ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፷፪ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፷፩ ዕለታት ይቀራሉ። ጳጉሜ ፭ ጳጉሜ ፭ ቀን: ብሄራዊ ቀን በጂብራልታር... ጳጉሜ ፬ ጳጉሜ ፬ ቀን: ሬፑብሊክ ቀን በስሜን ኮርያ፣ ነጻነት ቀን በታጂኪስታን፣ ብሄራዊ ቀን በቡልጋርያ... ታሪካዊ ማስታወሻዎች. =ዋቢ ምንጮች= ጳጉሜ ፫ ጳጉሜ ፫ ቀን: ብሄራዊ በአል በአንዶራ... ጳጉሜ ፪ ጳጉሜ ፪ ቀን: ነጻነት ቀን በብራዚል፣ የድል ቀን በሞዛምቢክ... ጳጉሜ ፩ ጳጉሜ ፩ ቀን: ነጻነት ቀን በስዋዚላንድ፣ አንድነት ቀን በቡልጋሪያ... ነሐሴ ፴ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፷ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፮ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ማቴዎስ እና ማርቆስ ደግሞ ፭ ዕለታት ይቀራሉ። ነሐሴ ፳፱ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፱ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፯ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ማቴዎስ እና ማርቆስ ደግሞ ፮ ዕለታት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
647
ሚያዝያ ፯ ሚያዝያ ፯ ሚያዝያ ፯፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፯ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፲፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፵፱ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፵፰ ቀናት ይቀራሉ። ሚያዝያ ፰ ሚያዝያ ፰፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፰ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፲፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፵፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፵፯ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
648
የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓውያን ጋር ያለው ልዩነት መንስኤ እና ትክክለኛ መሰረቱ (ልዩ ጥንቅር ጉዳያች ጡመራ GUDAYACHN BLOG) የዘመን መስፈሪያዎች እግዚአብሔር «ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ፣ ለዕለታት፣ ለዘመናትና ለዓመታት ምልክት ይሆኑ ዘንድ» / ዘፍ.1. 14- 15/ የፈጠራቸውን የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴ መሠረት ያደረጉት መስፈሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህም፤ ሀ. ዕለት- አንድ ዕለት አንድ ቀንን /የብርሃን ክፍለ ጊዜን / እና አንድ ሌሊትን /የጨለማ ክፍለ ጊዜን/ ያካተተ ፀሐይ አንድ ጊዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን አንድ ዕለት ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ የምትሸከረከርበት ጊዜ ነው፡፡ ለ. ውርኅ- ወርኅ ማለት በግእዝ ጨረቃ ማለት ነው፡፡ አንድ ወርኅ የሚባለው ጊዜ ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን / በጥንቱም ጨምሮ/ ይህ ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዙራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ወር ሃያ ዘጠኝ ተኩል ዕለታትን ይፈጃል፡፡ ሐ. ዓመት- አንድ ዓመት ማለት መሬት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ ይህም 365 ከ1/4 / ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከሩብ/ ዕለታት ይፈጃል፡፡ይህ ከመታወቁ በፊትም ግን የዓመት ጽንሰ ሓሳብ ነበር፡፡ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ የፅንሰ ሐሳቡን አመጣጥ እንዲህ ያስረዳሉ፡፡ ሰዎች ርዝመታቸው እኩል የሆኑ ሁለት ሻማዎችን ሠሩና ልክ ፀሐይ ስትወጣ /ቀኑ ሲያልቅና ሌሊቱ ሲጀምር/ አንዱን ሻማ አበሩት፡፡ልክ ፀሐይ ስትወጣ እሱን አጠፋና ሌላውን / ሁለተኛውን/ ሻማ አበሩት፤ ጧት ፀሐይ እንደገና ስትወጣ / ሌሊቱ አልቆ ሌላ ቀን ሲጀምር/ ሻማውን አጠፉት፡፡ አሁን እንግዲህ ከየሻማዎቹ /ከሁለቱ ሻማዎች/ ምን ያህል እንደተቃጠለላቸው ሲያስተያዩት ከሁለቱ ሻማዎች የተቃጠለው እኩል አለመሆኑን ተመለከቱ በዚህም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ እኩል አለመሆኑን ተረዱ፡፡ ቀደም ብለውም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ በተለያዩ ወቅቶች የተለያየ መሆኑን ልብ ብለው ነበርና ይህንን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ በቀኑና በሌሊቱ ርዘማኔ / በሚቃጠለው የሻማዎቹ መጠን/ መካከል ያለው ልዩነት ከወቅት ወቅት የተለያየ እንደሆነ ተመለከቱ ይህን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ ግን በየ182 /ተኩል/ ዕለቱ ቀኑና ሌሊቱ እኩል የሚሆኑባቸው ሁለት ዕለታት በዓመት ውስጥ እንዳሉ ተገነዘቡ፡፡ እነዚህ ዕለታት አንዱ የሙቀት ወራት ከመጀመሩ በፊት የሌላው ደግሞ የቅዝቃዜው ወራት ከመጀመሩ በፊት የሚመጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት አንድ ጊዜ እኩል ሁኖ ደግሞ በዚያው ወቅት እኩል እስከሚሆን ድረስ ያለውን ጊዜ ማለትም / 182 ተኩል + 182 = 365/ ዕለት አንድ ዓመት አሉት፡፡ አሁን ባለን ግንዛቤ ምድር በራሷ ዛቢያ እንደተሽከረከረች በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች፡፡ ምድር በፀሐይ ዙሪያ የምትዞረው ወደ ጎን 23 ተኩል ዲግሪ ያህል አጋድላ ነው፡፡ ይህ የቀንና የሌሊት ርዝመት መለያየትም የሚከሰተው በዚህ ማጋደል ምክንያት ነው፡፡ እንግዲህ በአጠቃላይ ዋናዎቹ የጊዜ / የዘመን/ መስፊሪያዎች ዕለት፣ ወር እና ዓመት ናቸው፡፡ ሦስትቱም ተመላላሽ ክስተቶችን / ለምሳሌ የፀሐይን መውጣት/ መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚሀ ተመላላሽ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪከሰቱ የሚፈጁት ዘመን ወይም ጊዜ ዓውድ ይባላል፡፡ ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ እንደ ቀለበት ዙሮ የሚገጥም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዓውድ ማለት ክስተቶቹ አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪመጡ ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከላይ ያየናቸው ሦስት መስፈሪያዎች / ዕለት፣ ወርኀ፣ ዓመት/ ዓዕዋዳት / ዓውዶች/ የሚወጡበት ጊዜ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ወርኀ፣ ዓውደ ዓመት ይባላሉ፡፡ መጀመሪያ ላይ ሰዎች እነዚህን ሦስቱን መስፈሪያዎች /ዓዕዋዳት/ /በተለይም ቀንና እና ወርን/ ለየብቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡ ከዚህን ያህል ቀን፣ ከዚህን ያህል ወር በኋላ /በፊት/ እያሉ ጊዜን ይለኩ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስቱን በቅንብር /በቅንጅት/ ለመጠቀም ሲፈለግ ግን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አንድ ወር 29 ከግማሽ ቀን ነው፡፡ እንዲሁ እንዳለ ለመቁጠር ቢፈለግ የመጀመሪያው ወር ጠዋት ላይ ቢጀመር ሁለተኛው ወር ምሽት ላይ ይጀምራል፣ ሦስተኛው ደግሞ ድጋሚ ጠዋት ላይ ይጀምራል፤ ይህን ለመቅረፍ ወሩን ሙሉ ሰላሳ ቀን ቢያደርጉት ከትክክለኛው ወር /የጨረቃ ዐውድ/ ግማሽ ቀን ይተርፋል፤ 29 ቀን ብቻ ቢያደርጉት ደግሞ ግማሸ ቀን ይጎድላል፡፡ አንድ ዓመት 365 ከሩብ ዕለታት አሉት፡፡ ዓመትን በወራት ለመቁጠር ቢፈለግ፤ ዓመቱን 12 ወር ቢያደርጉት የዓመቱ /የዕለታት ቁጥር /29.5X12=354/ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም ከትክክለኛው ዓመት /365-354=11/ ዕለታት ያህል ያንሳል፡፡ 13 ወር ቢያደርጉት ዓመቱ /365X13=385.5/ ቀናት ይሆናል ይህም ከትክክለኛው ዓመት /383.5-365=19/ ቀናት ያህል ይበልጣል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መስፈሪያዎች በቅንጅት ለመጠቀም ይህንን አለመጣጣም የሚፈታ ቀመር /የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት/ ያስፈልጋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የዘመን አቆጣጠሮች ተዘጋጅተዋል፡፡ የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 29 እና 30 ዕለታት ያሏቸው 12 ወራት አሏቸው፤ ተ.ቁ የአይሁድ ወራት የዕለታት ብዛት ወራቱ በእኛ 1 ኒሳን 30 መጋቢት/ ሚያዝያ 2 ኢያር 29 ሚያዝያ/ ግንቦት 3 ሲዋን 30 ግንቦት/ ሰኔ 4 ታሙዝ 29 ሰኔ/ ሐምሌ 5 አቭ 30 ሐምሌ/ ነሐሴ 6 አሉል 29 ነሐሴ/ መስከረም 7 ኤታኒም 30 መስከረም/ ጥቅምት 8 ቡል 29/30 ጥቀምት/ ኅዳር 9 ከሴሉ 30/29 ኅዳር/ ታህሳስ 10 ጤቤት 29 ታህሳስ/ ጥር 11 ሳባጥ 30 ጥር/ የካቲት 12 አዳር 1 29 የካቲት/ መጋቢት እነዚህ የዓመቱ 12 ወራት በአጠቃላይ 354 ያህል ብቻ ዕለታት ይኖሯቸዋል፡፡ ይህም በትክክለኛው ዓመት በ11 ዕለታት ያህል ቢያንስም አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ልዩነቱ በሁለት ዓመታት 22 ዕለታት፣ በሦስት ዓመት ደግሞ 33 ዕለታት ያህል ይሆናል፡፡ ስለዚህ በየሦስት ዓመቱ ከአስራ ሁለተኛው ወር ጳጉሜን በፊት አንድ ሌላ ወር ይጨምሩና ጨምረው የዓመቱን የወራት ቁጥር ዐሥራ ሦስት ያደርጉና ልዩነቱን ያስተካክሉታል፡፡ የኢትዮጵያውያንና የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የጥንት ግብጻውያን /ዛሬም ድረስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት በሀገር ደረጃ የምትጠቀም ኢትዮጵያ ብቻ ነች/ የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለታችንም እኩል ሰላሳ ቀናት ያሏቸው 12 ወራት አሉን፡፡ እነዚህ 12 ወራት / 12X30=360/ ቀናት አሏቸው እነዚህ ቀናት በትክክለኛው ዓመት በ/365.25-360=5.25/ ቀናት ያንሳሉ፡፡ ይህንንም 5 ቀናት / በ4 ዓመት አንድ ጊዜ 6 ቀናት/ ያሏትን 13ኛ ወር በመጨመር ያስተካክሉታል፡፡የኢትዮጵያውያን እና የግብጻውያን ወሮች ስም እንደሚከተለው ነው፡፡ ተ.ቁ የግብጽ ወሮች የኢትዮጵያ ወሮች 1 ቱት/ዩት መስከረም 2 ባባ/ፓከር ጥቅምት 3 ሀቱር ኅዳር 4 ኪሃክ/ከያክ ታኅሣሥ 5 ጡባ/ቶቢር ጥር 6 አምሺር/ሜሺር የካቲት 7 በረምሃት መጋቢት 8 በርሙዳ ሚያዝያ 9 በሸንስ ግንቦት 10 ቦኩሩ ሰኔ 11 አቢብ ሐምሌ 12 መስሪ ነሐሴ 13 ኒሳ/አፓጎሜኔ ጳጉሜን /ባሕረ ሐሳብ፣ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ፣ገጽ.65/ የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር ኢትዮጵያዊ ነው ከሌላ የተቀዳ አይደለም የኢትዮጵያ እምነታዊ ባህል የሚወረሰው በሦስት ዐይነት ጠባይ ነው። አንዱ ሕገ ልቡና ይባላል። ከመጽሐፍ በፊት የነበረ ነው። ከአበው ቃል በቃል የተወረሰ ነው። ሁለተኛው በሕገ ኦሪት ከኦሪት የተቀዳ ነው። ሦስተኛው በሕገ ወንጌል ከወንጌል የተማርነው ነው። እና በሦስት ዐይነት ጠባይ የሚመራ ነው። በዚህ ዐይነት ከወረስናቸው በዓላት ማለት በሦስቱም ጠባያት ከወረስናቸው በዓላት የየራሳቸው መልክ ያላቸው አሉ። ለምሳሌ ልደት፥ ጥምቀት፥ ዕርገት፥ ደብረ ታቦር እነዚህን የመሳሰሉት ከወንጌል የተማርናቸው ናቸው፤ በብሉይ የሉም። ፋሲካ፥ በዓለ ጰራቅሊጦስ ደግሞ ከኦሪት የተማርናቸው ናቸው። የዘመን መለወጫ በዓል ግን ከሕገ ልቡና ቃል በቃል ተምረን፥ በኦሪት የመጽሐፍ መሠረት አግኝተንለት በወንጌልም አጽንተን ይዘነው የኖርነው ሦስት የሥራ ዘመን ክፍል የተላለፈና እዚህ የደረሰ ነው። እኛ የዘመን መለወጫ ብለን በሀገራችን ባህል የምናከብረው ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር የተገኘበት፥ ብርሃን፥ ጊዜ፥ ዕለት፥ ሰዓት የተፈጠሩበት፤ ለብርሃን፥ ለጊዜ፥ ለዕለት፥ ለወር ለዓመት ጥንት መሠረት የሆነ ቀን ነው። ይህንን ሁሉ በማስገኘት እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት፥ ዓለምን በመፍጠር ከሃሊነቱን ያረጋገጠበት ቀን ነው ብለን ነው የምናከብረው። ስለዚህም ጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዕለት፥ ጥንተ ጊዜ፥ ጥንተ ፍጥረት ርእሰ ዐውደ ዓመት ብለን ነው የምናከብረው። በዚህ ስያሜ በዓሉ ርእሰ ዐውደ ዓመት፥ ቅዱስ ዮሐንስ፥ የዘመን መለወጫ ብለን እናከብረዋለን። ቅዱስ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ በዓል ሌላው ስሙ ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል። ቅዱስ ዮሐንስ የሚባልበትም ሁለት ጠባይ አለው። አንዱ፤ መጥምቁ ዮሐንስ በሄሮድስ አንቲጳስ ጊዜ ከጳጉሜን ፩ ቀን ጀምሮ ታስሮ ሰንብቶ በመስከረም ፩ ቀን ዐሳብ ስለ ተቆረጠበትና በመስከረም ፪ ቀን እንዲሞት ውሳኔ ስለ ተሰጠበት አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ስለ ሞተ ሊቃውንት ይህንን በዓል እሱ ራሱ ለኦሪትና ለወንጌል መገናኛ መምህር ስለ ነበረ ይህም በዓል ላለፈው ዘመን መሸኛ፥ ለሚመጣው ዘመን መቀበያ እንዲሆን ብለው በመስከረም ፩ ቀን እንዲከበር ስላደረጉ በሱ ስም ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል። በሁለተኛው ግን ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ ወንጌላዊ ዮሐንስ የተሰየመበት ስለ ሆነ በአቆጣጠርም ተራ ወደ ኋላ ተመልሶ ቢቈጠር ዓለም የተፈጠረበት ዘመን በዘመነ ዮሐንስ እንዳጋጣሚ ሆኖ ስለሚገኝ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ ይጠራል። ዕንቍጣጣሽ በዚያም ጊዜ የነበሩ ኖኅና ልጆቹ ሰማዩ በደመና በመክበዱ ምክንያት ማየ አይኅ እንደገና ይመጣ ይሆን፥ የጥፋት ውሃ እንደገና ይዘንም ይሆን እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ስላዩ፥ ምድር በአበባ አሸብርቃ ስለ ተገለጠችና በዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት፥ የቃል ኪዳኑን መጽናት ስለ ተረዱ ይህንን በዓል ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ያው ጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዓመት፥ ጥንተ ዕለት አድርገው አክብረውታል። ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፥ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕት ይሠዉነት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር ገጸ በረከት አቅርበው ከዚያ በኋላ ግን እርስ በርሳቸው የአበባ ስጦታ በመለዋወጥ አክብረውታል። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል እውነት የመልካም ሞኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር። ዕንቍጣጣሽ ማለትንም ብዙ ታሪክ ጸሓፊዎች በልዩ ልዩ መልክ ተርጕመውታል። እንዲያውም ንጉሡ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የዕንቍ ቀለበት ሰጥቷት ነበርና «ዕንቍ ለጣትሽ» ማለት ነው ብለው የጻፉ ብዙ ሰዎችም አሉ፤ የሚናገሩም አሉ። ነገሩ ግን እንዲህ አይደለም። ዕንቍጣጣሽ ማለት ተንቈጠቈጠ፥ አንቈጠቈጠ ከሚለው ቃል ተወስዶ ምድር በአበባ አጌጠች፥ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ እንደ ማለት ሰማይን በከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው እንጂ ስለ ሳባ ንግሥት የተሰጠ አይደለም። ሁለተኛም አባቶቻችን ኢትዮጵያን በሙሉ ሀብት ተረክበዋት ነበርና፤ «ዕንቍ ዕጣ ወጣሽ፤» ሲሉ ወደ አገራቸው ሲገቡ ለአገራቸው መታሰቢያ አድርገው የተጠቀሙበት ቃል ነው ይባላል። በመሠረቱ ግን ያ የጥፋት ውሃ ቀርቶ ምድር ጸንታ፥ አበባ ቋጥራ፥ ፍሬ ለመስጠት ተዘጋጅታ መገኘቷን የሚያበሥር ቃል ነው። መስከረም መስከረም የሚባለው ወርም ኖኅ በመርከብ ውሥጥ በነበረ ጊዜ እንደ ዕብራውያን አቈጣጠር ሰባተኛ በሆነው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ መርከቢቱ አራራት ከሚባለው ተራራ ላይ ዐርፋ ምድር ጨብጣለች። በግእዝ ቋንቋ መርከብ መስቀር ይባላል። ከዘመን ብዛት በኋላ «ቀ» ወደ «ከ» ተለውጦ መስከረም ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፥ መርከብም ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የወሩ ስያሜ ነው። ርእሰ ዐውደ ዓመት የምንለው፤ ዐውድ ማለት በግእዙ ቋንቋ ዙሪያ፥ ክብ የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ ቀኖች መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉት ሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታት ኀምሳ ሁለት ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል። ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፥ የደቂቃ፥ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስተኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ይህቺ ቀን እንግዲህ ዙሪያ፥ ክብ መግጠሚያ ናት ማለት ነው። በዚህች ቀን አማካይነት ወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ እንተላለፋለን። ይህቺ ቀን ዕለት አዕዋዲት፥ ዕለተ ምርያ የመዘዋወሪያ ቀን ወይም የመጨረሻ ቀን ተብላ ትጠራለች። በአራት ዓመት ደግሞ ከዚህች መሳሳብ የምትገኝ አንዲት ቀን ትመጣለች። ሦስት መቶ ስድሳ ስድስተኛ። ይህቺ ቀን ዕለተ ሰግር ትባላለች። መረማመጃ ማለት ነው። አንድ ቀን ታስተላልፋለች። እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች ተከትሎ የሚመጣው ቀን የዘመን መጀመሪያ፥ የዘመን ክብ መነሻና መድረሻ ተብሎ ርእሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ በግእዙ ይጠራል። እነዚህ ቀኖች በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ተጠቃለው አንድ ጊዜ የሚገኙ ናቸው። የኢትዮጵያ ቍጥር መሠረቱ የመፅሐፍ ቅዱስ አካል የሆነው መጽሐፈ ሔኖክ ነው። መጽሐፈ ሔኖክ በ፲፱፥ ፳፥ ፳፩ እና ፳፪ ምዕራፎች የሚሰጠን የፀሐይን፥ የጨረቃን ጉዞ መነሻ አድርጎ የወሮችን፥ የዕለታትን፥ የዓመታትን መነሻ፥ መድረሻ፥ መዘዋወሪያ ብተታቸውን፥ ጥንታቸውን ነው የሚያሳየው። ስለዚህም በሔኖክ ቍጥር የወር ቀኖች ቍጥር ሠላሳ ናቸው። በሦስት በሦስት ወር ግን አንድ ቀን ትከተላቸዋለች። እና ዓመቱ ለአራት ይከፈላል። በዘጠና አንድ በዘጠና አንድ ቀን። ጠቅላላው ይሄ ድምር ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት ቀን ይመጣል። ይህ ካለቀ በኋላ አንዲት ቀን ለዘመን ማገጣጠሚያ ዕለተ ምርያ የምትባለው ትመጣለች። እንግዲህ በኢትዮጵያውያን ቍጥር ወሩ ከሠላሳ አያንስም፤ ከሠላሳ አይተርፍም። ለዓመቱም ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ቀን መደበኛው አቆጣጠር ነው ማለት ነው። ይህ ነገር በአውሮፓውያን ቍጥርም አለ። ግን እነሱ ከዓመት ወሮች ሰባቱን ሠላሳ አንድ ሠላሳ አንድ አድርገው አራቱን ደግሞ ሠላሳ ሠላሳ አድርገው አንዷን ወር ሦስቱን ዓመት ሃያ ስምንት፥ በአራተኛው ዓመት ሃያ ዘጠኝአድርገው ያጣጧታል። እንግዲህ የአቀማመጡ ለውጥ ካልሆነ በስተቀር በቍጥር አካሄድ ዞሮ ዞሮ የዓመት ቀኖች ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ወይም ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት በመሆን አንድ ሆነዋል ማለት ነው። ልዩነቱ ግን የአቀማመጥ ለውጥ ነው። በኢትዮጵያ አቈጣጠር ግን ጠቅላላውን ፲፪ ወሮች መደባቸው ሠላሳ ብቻ ነው። እነዚያ በሔኖክ መጽሐፍ በጣልቃ ገብነት የነበሩት አራት ቀኖች ተጠቅለው ጳጉሜን በሚባል በዓመቱ መጨረሻ ላይ ተገኝተዋል። ዐምስተኛዪቱ ቀንም ከእነሱ ጋር ተገኝታለች። ይህም ለቍጥር ተራ ቅምር መቅናት የተደረገ እንጂ ቀኑን የሚለውጥ ምንም ነገር የለበትም። እና ከእነዚህ ቀኖች በኋላ የምናገኘው ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመት ይባላል። ይህንን በዓል ከአዳም ጀምሮ እስከ ኖኅ ድረስ የነበሩ ዐሥሩም አበው በዐሥሩ ትውልድ እስከ ማየ አይኅ ድረስ ሲያከብሩት እንደ ቆዩና ኋላም የኖኅ ልጆች ከአባታቸው ተቀብለው ሲያከብሩት እንደ ነበረ ኩፋሌ የተባለው መጽሐፍ በምዕራፍ ፯ ያስረዳናል። እንግዲህ ኢትዮጵያ ይህንን ቀን የወረሰችው ከአበው ነው የምንለው በዚህ ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከሌሎቹ የሚለይባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች እና ከኢትዮጵያውያን እና አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ትክክለኛው የቱ ነው? ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ የዘመን አቆጣጠር መለያየትን መነሻ እንዲህ በማለት ያብራራሉ፤ «ክብ የሆነ ነገር ሲከብ ከየትኛውም ቦታ መጀመር ይቻላል፤ የዘመን አቆጣጠር /ዓውደ ዓመትም/ ይኸው ነው፡፡ ዋናው ነገር አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ ነው፤ የዘመን አቆጣጠሮቹም ልዩነት መንስኤው ይኸው ነው» ይላሉ፡፡ ባሕረ ሐሳብ፣ ጌታቸው ኃይሌ፣ ገጽ.65/ ለምሳሌነትም ሮማውያን የሮም ከተማ የተቆረቆረችበትን ጊዜ መነሻ ማድረጋቸውን/ በኋላም ታላቁ እስክንድር የነገሠበት ዘመን የዘመን ቆጠራ መነሻ ሆነው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ መሐመድና ተከታዮች ከመካ ወደ መዲና ያደረጉትን ስደት መነሻ የሚያደርገው ኢስላማዊ የዘመን አቆጣጠርም ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡ የአይሁድን አቆጣጠር ትተን ከላይ ያየናቸው ሁለቱ የዘመን አቆጣጠሮች /የምዕራባውያኑ የጁልየስ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርና የኢትዮጵያና የግብጽ አቆጣጠር/ ሁለቱም ዘመንን የሚቆጥሩት ከክርስቶስ ልደት መነሻ አድርገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ ዛሬ 2008 ዓ.ም ነው ስንል እነርሱ ደግሞ 2015 ዓ.ም ነው ይላሉ፡፡ በመካከሉ የ7 ዓመታት ልዩነት አለ፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ትክክለኛው የትኛው ነው? የሚለው ነው፡፡ ጉዳዩ መጻሕፍትን ሊያጽፍ የሚችልና በእርግጥም የተጻፉበት ቢሆንም ለማሳያ ያክል ሁለት ነገሮች እንመልከት፤ 1. አሁን ባለው የምዕራባውያን አቆጣጠር ከሄድን ሄሮድስ የሞተው 4 ዓመት ቅ.ል.ክ (ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ነው፡፡ ሄሮድስ የሞተው ጌታ ተወልዶ በስደት ሦስት ዓመት ያህል በግብጽ ከቆየ በኋላ ነው፡፡ ይህ ማለት በእርሱ አቆጣጠር ጌታ የተወለደው በ7 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ጌታ በትክክል በተወለደበት በአንድ ዓ.ም እነርሱ ጌታ ሰባት ዓመት ሆኖታል ይላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት አሁን ካላቸው ቁጥር ላይ ሰባት ዓመት መቀነስ አለባቸው፡፡ 2. ፍላቪየስ ጆሴፈስ የተባለው የአይሁድን ታሪክ የጻፈው ሊቅ እንደመሰከረው ጌታ የተወለደበት ዓመት ነው ተብሎ በወንጌል ላይ የተጻፈው የቆጠራ ዓመት /ሕዝቡ ሁሉ የተቆጠረበትን ዘመን /ሉቃ.2.1/ በጎርጎሪያን ዘመን አቆጣጠር «7 ዓመተ እግዚአ /A.D/ ላይ ነው፡፡» በማለት መረጃ ትቶልናል ይህ ማለት ደግሞ ከምዕራባውያኑ ዘመን አቆጣጠር ላይ 7 ዓመቶች የግድ መቀነስ አለበት ማለት ነው፡፡ ያ ሲደረግ ደግሞ የኛን ዘመን አቆጣጠር ያመጣል፡፡ የዘመን መለወጫ ቀን ልዩነት ሁለተኛው ጉዳይ የዘመን መለወጫ ወርና ዕለት ልዩነት ነው፡፡ እኛ መስከረም 1 አዲስ ዓመት ስንጀምር እነርሱ በ January 1 / በእኛ ታኅሣሥ 23/ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ከየት የመጣ ልዩነት ነው? የእኛ እና የግብጻውያን አቆጣጠር እዚህ ጉዳይ ላይ ከአይሁድ አቆጣጠር ጋር ይስማማል፡፡ በአይሁድ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ኒሳን የሚባለው /በእኛ መጋቢት/ ሚያዝያ/ ነው፡፡ «ይህ ወር የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፣ በዚህም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የአንድ ዓመት ተባዕት ላይ ወስደው ይረዱ፡፡ . . .»/ዘፀ.12.1-14/ ተብሎ የተሰጣቸውን የፋሲካ በዓል የሚያከብሩት በዚህ ወር ነው፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ የዓመት በዓል አድርገው የሚያከብሩት «የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁናችሁ፡፡ በዚሁ በመለከት ድምጽ የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ መስዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑበት» /ዘሌ.13.23-25/ ተብሎ የተሰጣቸው የሮሽ ሆሻና፣/የመለከት በዓል ወይም በዓለ መጥቅዕ/ ተብሎ የሚጠራው በዓል ነው፡፡ ይህም ማለት አዲስ ዓመት የሚያከብሩት በሰባተኛው ወር በኢታኒም ወር /በእኛ መስከረም ጥቅምት/ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችንም ትምህርት ዓለም የተፈጠረው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ መስከረም ደግሞ ከመጋቢት ጀምሮ ሲቆጠር ሰባተኛው ወር ነው፡፡ ይህም ከአይሁድ ዘመን አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አይሁድስ ቢሆኑ የመጀመሪያው ወር እያለ አዲስ ዓመትን ለምን በሰባተኛው ወር ያከብራሉ ለሚለው ጥያቄ ሁለት ዓይነት ምላሾች /ምክንያቶች/ ይሰጣሉ፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት «ሰባተኛው ወር ኖኅ ከመርከብ የወጣበት ወር በመሆኑ ይህ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ተደርጎ መከበር በመጀመሩ ነው» የሚል ነው፡፡ በዘመን መለወጫ ዕለት ልጃገረዶች አበባ እና ለምለም ሣር መያዛቸው ርግቢቱ ለኖኅ ካመጣችው ለምለም ወይራ /ቄጠማ/ ጋር ተያይዞ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ መስከረም የቀንና የዕለቱ ርዝመት እኩል የሚሆኑበት ወር በመሆኑ ነው የሚል ነው፡፡ የመስከረም 1 ቀን ስንክሳር «የተባረከ የመስከረም ወር የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው፤ የቀኑ ሰዓትም ከሌሊቱ ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው» ይላል፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባው ሌላው ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ትምህርት እመቤታችን ጌታን የጸነሰችው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ጳዉሎስ ፣የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ተወለደ» /ገላ.4.4/ እንዳለው የ5500 ዘመኑ ፍጻሜ /ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ/ ነው፡፡ ጽንሰትን መጋቢት 29 ካልን በኋላ ልደትን ታህሣሥ 29 ቀን እናከብራለን፡፡ ከመጋቢት 29 እስከ ታህሣሥ 29 ድረስ 9 ወር ከ5 ቀን ነው፡፡ /ጳጉሜን ጨምሮ/፡፡ ጳጉሜ 6 በምትሆንበት ጊዜ ደግሞ ታህሣሥ 28 ቀን ልደት ስለሚከበር አሁንም በመሐሉ ያለው ጊዜ 9 ወር ከአምስት ቀን ይሆናል፡፡ ማጠቃለያ በመጨረሻም የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ፍፁም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሚቆጥር መሆኑን እንጂ እንደ ዘመኑ ነገስታት ፍላጎት በታሪክ ክስተትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ከተረዳን ይህንን ሃሳባችንን የሚያጠናክርልን የሳምንታንት እና የወራት ስያሜዎቻችንን እንዲሁም የልሎቹ የቀን አቆጣጠር ምንጭን ከ እዚህ በታች ባሉት ሰንጠረዦች እንመልከት።ለምሳሌ እነኚህ የሳምንታንት ልዩነቶች አውሮፓውያን ከጥንት ከነበረ አምልኮት ጋር የትዛመደ ሲሆን የእኛ ግን እግዚአብሔር አለምን መፍጠር ከጀመረ የመጀመርያ ቀን ስንል እሁድ ማለታችንን ሁለተኛ ቀን ስንል ሰኑይ (ሰኞ) ማለታችንን ወዘተ እንረዳለን። ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም አሮጌው ዘመን 2007 ዓም ተጠናቆ አዲሱን 2008 ዓም ልንቀበል ሰዓታት ቀርተውናል። የሮማ ካቶሊክ ፓፓ ቤኔዲክት 16ኛ ''የናዝሬቱ እየሱስ'' በተሰኘ መፅሐፋቸው አሁን አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት የክርስቶስ የልደት ዘመን ትክክለኛ እንዳልሆነ ሲገልጡ እንዲህ ብለዋል-“The calculation of the beginning of our calendar—based on the birth of Jesus—was made by Dionysius Exiguus, who made a mistake in his calculations by several years,” ''ከጅምሩ የቀን አቆጣጠራችን ክርስቶስን ተወለደ ያለበት ዘመን መሰረት (በእክስጉሥ የተቀመረው) የብዙ አመታት የስሌት ስህተት አለው'' ብለዋል። (http://www.charismanews.com/world/34714-pope-says-jesus-birth-date-is-wrong) ይህ ከአንድሚልዮን ኮፒ በላይ እንደተሸጠ የተነገረው መፅሐፍ ላይ ፓፓው ይህንን ይበሉ እንጂ ስህተቱን ለማረም እና ወደ ትክክለኛው ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለመምጣት የደፈረ እስካሁን አልታየም።ወደፊት ግን ይጠበቃል። ጉዳያችን ይህ ፅሁፍ በእዚሁ ጡመራ በጳጉሜን 2/2006 ዓም ወጥቶ ነበር። አስፈላጊነቱን በማሰብ ዛሬ ጳጉሜን 5/2007 ዓም እንደገና ወጥቷል።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
649
የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓውያን ጋር ያለው ልዩነት መንስኤ እና ትክክለኛ መሰረቱ ልዩ ጥንቅር ጉዳያች ጡመራ የዘመን መስፈሪያዎች እግዚአብሔር “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ፣ ለዕለታት፣ ለዘመናትና ለዓመታት ምልክት ይሆኑ ዘንድ» / ዘፍ.1. 14- 15/ የፈጠራቸውን የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴ መሠረት ያደረጉት መስፈሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህም፤ ሀ. ዕለት– አንድ ዕለት አንድ ቀንን /የብርሃን ክፍለ ጊዜን / እና አንድ ሌሊትን /የጨለማ ክፍለ ጊዜን/ ያካተተ ፀሐይ አንድ ጊዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን አንድ ዕለት ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ የምትሸከረከርበት ጊዜ ነው፡፡ ለ. ውርኅ– ወርኅ ማለት በግእዝ ጨረቃ ማለት ነው፡፡ አንድ ወርኅ የሚባለው ጊዜ ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን / በጥንቱም ጨምሮ/ ይህ ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዙራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ወር ሃያ ዘጠኝ ተኩል ዕለታትን ይፈጃል፡፡ ሐ. ዓመት– አንድ ዓመት ማለት መሬት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ ይህም 365 ከ1/4 / ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከሩብ/ ዕለታት ይፈጃል፡፡ይህ ከመታወቁ በፊትም ግን የዓመት ጽንሰ ሓሳብ ነበር፡፡ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ የፅንሰ ሐሳቡን አመጣጥ እንዲህ ያስረዳሉ፡፡ ሰዎች ርዝመታቸው እኩል የሆኑ ሁለት ሻማዎችን ሠሩና ልክ ፀሐይ ስትወጣ /ቀኑ ሲያልቅና ሌሊቱ ሲጀምር/ አንዱን ሻማ አበሩት፡፡ልክ ፀሐይ ስትወጣ እሱን አጠፋና ሌላውን / ሁለተኛውን/ ሻማ አበሩት፤ ጧት ፀሐይ እንደገና ስትወጣ / ሌሊቱ አልቆ ሌላ ቀን ሲጀምር/ ሻማውን አጠፉት፡፡ አሁን እንግዲህ ከየሻማዎቹ /ከሁለቱ ሻማዎች/ ምን ያህል እንደተቃጠለላቸው ሲያስተያዩት ከሁለቱ ሻማዎች የተቃጠለው እኩል አለመሆኑን ተመለከቱ በዚህም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ እኩል አለመሆኑን ተረዱ፡፡ ቀደም ብለውም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ በተለያዩ ወቅቶች የተለያየ መሆኑን ልብ ብለው ነበርና ይህንን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ በቀኑና በሌሊቱ ርዘማኔ / በሚቃጠለው የሻማዎቹ መጠን/ መካከል ያለው ልዩነት ከወቅት ወቅት የተለያየ እንደሆነ ተመለከቱ ይህን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ ግን በየ182 /ተኩል/ ዕለቱ ቀኑና ሌሊቱ እኩል የሚሆኑባቸው ሁለት ዕለታት በዓመት ውስጥ እንዳሉ ተገነዘቡ፡፡ እነዚህ ዕለታት አንዱ የሙቀት ወራት ከመጀመሩ በፊት የሌላው ደግሞ የቅዝቃዜው ወራት ከመጀመሩ በፊት የሚመጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት አንድ ጊዜ እኩል ሁኖ ደግሞ በዚያው ወቅት እኩል እስከሚሆን ድረስ ያለውን ጊዜ ማለትም / 182 ተኩል + 182 = 365/ ዕለት አንድ ዓመት አሉት፡፡ አሁን ባለን ግንዛቤ ምድር በራሷ ዛቢያ እንደተሽከረከረች በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች፡፡ ምድር በፀሐይ ዙሪያ የምትዞረው ወደ ጎን 23 ተኩል ዲግሪ ያህል አጋድላ ነው፡፡ ይህ የቀንና የሌሊት ርዝመት መለያየትም የሚከሰተው በዚህ ማጋደል ምክንያት ነው፡፡ እንግዲህ በአጠቃላይ ዋናዎቹ የጊዜ / የዘመን/ መስፊሪያዎች ዕለት፣ ወር እና ዓመት ናቸው፡፡ ሦስትቱም ተመላላሽ ክስተቶችን / ለምሳሌ የፀሐይን መውጣት/ መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚሀ ተመላላሽ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪከሰቱ የሚፈጁት ዘመን ወይም ጊዜ ዓውድ ይባላል፡፡ ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ እንደ ቀለበት ዙሮ የሚገጥም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዓውድ ማለት ክስተቶቹ አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪመጡ ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከላይ ያየናቸው ሦስት መስፈሪያዎች / ዕለት፣ ወርኀ፣ ዓመት/ ዓዕዋዳት / ዓውዶች/ የሚወጡበት ጊዜ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ወርኀ፣ ዓውደ ዓመት ይባላሉ፡፡ መጀመሪያ ላይ ሰዎች እነዚህን ሦስቱን መስፈሪያዎች /ዓዕዋዳት/ /በተለይም ቀንና እና ወርን/ ለየብቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡ ከዚህን ያህል ቀን፣ ከዚህን ያህል ወር በኋላ /በፊት/ እያሉ ጊዜን ይለኩ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስቱን በቅንብር /በቅንጅት/ ለመጠቀም ሲፈለግ ግን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አንድ ወር 29 ከግማሽ ቀን ነው፡፡ እንዲሁ እንዳለ ለመቁጠር ቢፈለግ የመጀመሪያው ወር ጠዋት ላይ ቢጀመር ሁለተኛው ወር ምሽት ላይ ይጀምራል፣ ሦስተኛው ደግሞ ድጋሚ ጠዋት ላይ ይጀምራል፤ ይህን ለመቅረፍ ወሩን ሙሉ ሰላሳ ቀን ቢያደርጉት ከትክክለኛው ወር /የጨረቃ ዐውድ/ ግማሽ ቀን ይተርፋል፤ 29 ቀን ብቻ ቢያደርጉት ደግሞ ግማሸ ቀን ይጎድላል፡፡ አንድ ዓመት 365 ከሩብ ዕለታት አሉት፡፡ ዓመትን በወራት ለመቁጠር ቢፈለግ፤ ዓመቱን 12 ወር ቢያደርጉት የዓመቱ /የዕለታት ቁጥር /29.5X12=354/ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም ከትክክለኛው ዓመት /365-354=11/ ዕለታት ያህል ያንሳል፡፡ 13 ወር ቢያደርጉት ዓመቱ /365X13=385.5/ ቀናት ይሆናል ይህም ከትክክለኛው ዓመት /383.5-365=19/ ቀናት ያህል ይበልጣል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መስፈሪያዎች በቅንጅት ለመጠቀም ይህንን አለመጣጣም የሚፈታ ቀመር /የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት/ ያስፈልጋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የዘመን አቆጣጠሮች ተዘጋጅተዋል፡፡ የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 29 እና 30 ዕለታት ያሏቸው 12 ወራት አሏቸው፤ ተ.ቁ የአይሁድ ወራት የዕለታት ብዛት ወራቱ በእኛ 1 ኒሳን 30 መጋቢት/ ሚያዝያ 2 ኢያር 29 ሚያዝያ/ ግንቦት 3 ሲዋን 30 ግንቦት/ ሰኔ 4 ታሙዝ 29 ሰኔ/ ሐምሌ 5 አቭ 30 ሐምሌ/ ነሐሴ 6 አሉል 29 ነሐሴ/ መስከረም 7 ኤታኒም 30 መስከረም/ ጥቅምት 8 ቡል 29/30 ጥቀምት/ ኅዳር 9 ከሴሉ 30/29 ኅዳር/ ታህሳስ 10 ጤቤት 29 ታህሳስ/ ጥር 11 ሳባጥ 30 ጥር/ የካቲት 12 አዳር 1 29 የካቲት/ መጋቢት እነዚህ የዓመቱ 12 ወራት በአጠቃላይ 354 ያህል ብቻ ዕለታት ይኖሯቸዋል፡፡ ይህም በትክክለኛው ዓመት በ11 ዕለታት ያህል ቢያንስም አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ልዩነቱ በሁለት ዓመታት 22 ዕለታት፣ በሦስት ዓመት ደግሞ 33 ዕለታት ያህል ይሆናል፡፡ ስለዚህ በየሦስት ዓመቱ ከአስራ ሁለተኛው ወር ጳጉሜን በፊት አንድ ሌላ ወር ይጨምሩና ጨምረው የዓመቱን የወራት ቁጥር ዐሥራ ሦስት ያደርጉና ልዩነቱን ያስተካክሉታል፡፡ የኢትዮጵያውያንና የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የጥንት ግብጻውያን /ዛሬም ድረስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት በሀገር ደረጃ የምትጠቀም ኢትዮጵያ ብቻ ነች/ የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለታችንም እኩል ሰላሳ ቀናት ያሏቸው 12 ወራት አሉን፡፡ እነዚህ 12 ወራት / 12X30=360/ ቀናት አሏቸው እነዚህ ቀናት በትክክለኛው ዓመት በ/365.25-360=5.25/ ቀናት ያንሳሉ፡፡ ይህንንም 5 ቀናት / በ4 ዓመት አንድ ጊዜ 6 ቀናት/ ያሏትን 13ኛ ወር በመጨመር ያስተካክሉታል፡፡ የኢትዮጵያውያን እና የግብጻውያን ወሮች ስም እንደሚከተለው ነው፡፡ ተ.ቁ የግብጽ ወሮች የኢትዮጵያ ወሮች 1 ቱት/ዩት መስከረም 2 ባባ/ፓከር ጥቅምት 3 ሀቱር ኅዳር 4 ኪሃክ/ከያክ ታኅሣሥ 5 ጡባ/ቶቢር ጥር 6 አምሺር/ሜሺር የካቲት 7 በረምሃት መጋቢት 8 በርሙዳ ሚያዝያ 9 በሸንስ ግንቦት 10 ቦኩሩ ሰኔ 11 አቢብ ሐምሌ 12 መስሪ ነሐሴ 13 ኒሳ/አፓጎሜኔ ጳጉሜን /ባሕረ ሐሳብ፣ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ፣ገጽ.65/ የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር ኢትዮጵያዊ ነው ከሌላ የተቀዳ አይደለም የኢትዮጵያ እምነታዊ ባህል የሚወረሰው በሦስት ዐይነት ጠባይ ነው። አንዱ ሕገ ልቡና ይባላል። ከመጽሐፍ በፊት የነበረ ነው። ከአበውቃል በቃል የተወረሰ ነው። ሁለተኛው በሕገ ኦሪት ከኦሪት የተቀዳ ነው። ሦስተኛው በሕገ ወንጌል ከወንጌል የተማርነው ነው። እናበሦስት ዐይነት ጠባይ የሚመራ ነው። በዚህ ዐይነት ከወረስናቸው በዓላት ማለት በሦስቱም ጠባያት ከወረስናቸው በዓላት የየራሳቸውመልክ ያላቸው አሉ። ለምሳሌ ልደት፥ ጥምቀት፥ ዕርገት፥ ደብረ ታቦር እነዚህን የመሳሰሉት ከወንጌል የተማርናቸው ናቸው፤ በብሉይየሉም። ፋሲካ፥ በዓለ ጰራቅሊጦስ ደግሞ ከኦሪት የተማርናቸው ናቸው። የዘመን መለወጫ በዓል ግን ከሕገ ልቡና ቃል በቃል ተምረን፥በኦሪት የመጽሐፍ መሠረት አግኝተንለት በወንጌልም አጽንተን ይዘነው የኖርነው ሦስት የሥራ ዘመን ክፍል የተላለፈና እዚህ የደረሰ ነው።እኛ የዘመን መለወጫ ብለን በሀገራችን ባህል የምናከብረው ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር የተገኘበት፥ ብርሃን፥ ጊዜ፥ ዕለት፥ ሰዓትየተፈጠሩበት፤ ለብርሃን፥ ለጊዜ፥ ለዕለት፥ ለወር ለዓመት ጥንት መሠረት የሆነ ቀን ነው። ይህንን ሁሉ በማስገኘት እግዚአብሔር ራሱንየገለጠበት፥ ዓለምን በመፍጠር ከሃሊነቱን ያረጋገጠበት ቀን ነው ብለን ነው የምናከብረው። ስለዚህም ጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዕለት፥ ጥንተጊዜ፥ ጥንተ ፍጥረት ርእሰ ዐውደ ዓመት ብለን ነው የምናከብረው። በዚህ ስያሜ በዓሉ ርእሰ ዐውደ ዓመት፥ ቅዱስ ዮሐንስ፥ የዘመንመለወጫ ብለን እናከብረዋለን። ቅዱስ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ በዓል ሌላው ስሙ ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል። ቅዱስ ዮሐንስ የሚባልበትም ሁለት ጠባይ አለው። አንዱ፤መጥምቁ ዮሐንስ በሄሮድስ አንቲጳስ ጊዜ ከጳጉሜን ፩ ቀን ጀምሮ ታስሮ ሰንብቶ በመስከረም ፩ ቀን ዐሳብ ስለ ተቆረጠበትና በመስከረም፪ ቀን እንዲሞት ውሳኔ ስለ ተሰጠበት አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ስለ ሞተ ሊቃውንት ይህንን በዓል እሱ ራሱ ለኦሪትና ለወንጌል መገናኛመምህር ስለ ነበረ ይህም በዓል ላለፈው ዘመን መሸኛ፥ ለሚመጣው ዘመን መቀበያ እንዲሆን ብለው በመስከረም ፩ ቀን እንዲከበርስላደረጉ በሱ ስም ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል። በሁለተኛው ግን ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ ወንጌላዊ ዮሐንስ የተሰየመበት ስለሆነ በአቆጣጠርም ተራ ወደ ኋላ ተመልሶ ቢቈጠር ዓለም የተፈጠረበት ዘመን በዘመነ ዮሐንስ እንዳጋጣሚ ሆኖ ስለሚገኝ ቅዱስ ዮሐንስተብሎ ይጠራል። ዕንቍጣጣሽ በዚያም ጊዜ የነበሩ ኖኅና ልጆቹ ሰማዩ በደመና በመክበዱ ምክንያት ማየ አይኅ እንደገና ይመጣ ይሆን፥ የጥፋት ውሃ እንደገና ይዘንምይሆን እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ስላዩ፥ ምድር በአበባ አሸብርቃ ስለ ተገለጠችናበዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት፥ የቃል ኪዳኑን መጽናት ስለ ተረዱ ይህንን በዓል ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ያው ጥንተብርሃን፥ ጥንተ ዓመት፥ ጥንተ ዕለት አድርገው አክብረውታል። ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፥ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕትይሠዉነት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር ገጸ በረከት አቅርበው ከዚያ በኋላ ግን እርስ በርሳቸው የአበባ ስጦታ በመለዋወጥአክብረውታል። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል እውነት የመልካም ሞኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር። ዕንቍጣጣሽ ማለትንምብዙ ታሪክ ጸሓፊዎች በልዩ ልዩ መልክ ተርጕመውታል። እንዲያውም ንጉሡ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የዕንቍ ቀለበት ሰጥቷት ነበርና“ዕንቍ ለጣትሽ» ማለት ነው ብለው የጻፉ ብዙ ሰዎችም አሉ፤ የሚናገሩም አሉ። ነገሩ ግን እንዲህ አይደለም። ዕንቍጣጣሽ ማለትተንቈጠቈጠ፥ አንቈጠቈጠ ከሚለው ቃል ተወስዶ ምድር በአበባ አጌጠች፥ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ እንደ ማለት ሰማይንበከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው እንጂ ስለ ሳባ ንግሥት የተሰጠ አይደለም።ሁለተኛም አባቶቻችን ኢትዮጵያን በሙሉ ሀብት ተረክበዋት ነበርና፤ “ዕንቍ ዕጣ ወጣሽ፤» ሲሉ ወደ አገራቸው ሲገቡ ለአገራቸውመታሰቢያ አድርገው የተጠቀሙበት ቃል ነው ይባላል። በመሠረቱ ግን ያ የጥፋት ውሃ ቀርቶ ምድር ጸንታ፥ አበባ ቋጥራ፥ ፍሬለመስጠት ተዘጋጅታ መገኘቷን የሚያበሥር ቃል ነው። መስከረም መስከረም የሚባለው ወርም ኖኅ በመርከብ ውሥጥ በነበረ ጊዜ እንደ ዕብራውያን አቈጣጠር ሰባተኛ በሆነው በመስከረም ወርመጀመሪያ ላይ መርከቢቱ አራራት ከሚባለው ተራራ ላይ ዐርፋ ምድር ጨብጣለች። በግእዝ ቋንቋ መርከብ መስቀር ይባላል። ከዘመንብዛት በኋላ “ቀ» ወደ “ከ» ተለውጦ መስከረም ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፥ መርከብም ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የወሩስያሜ ነው። ርእሰ ዐውደ ዓመት የምንለው፤ ዐውድ ማለት በግእዙ ቋንቋ ዙሪያ፥ ክብ የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ ቀኖች መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉትሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታትኀምሳ ሁለት ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል። ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፥ የደቂቃ፥ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ ሦስት መቶ ስድሳዐምስተኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ይህቺ ቀን እንግዲህ ዙሪያ፥ ክብ መግጠሚያ ናት ማለት ነው። በዚህች ቀን አማካይነትወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ እንተላለፋለን። ይህቺ ቀን ዕለት አዕዋዲት፥ ዕለተ ምርያ የመዘዋወሪያ ቀን ወይም የመጨረሻ ቀን ተብላትጠራለች። በአራት ዓመት ደግሞ ከዚህች መሳሳብ የምትገኝ አንዲት ቀን ትመጣለች። ሦስት መቶ ስድሳ ስድስተኛ። ይህቺ ቀን ዕለተሰግር ትባላለች። መረማመጃ ማለት ነው። አንድ ቀን ታስተላልፋለች። እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች ተከትሎ የሚመጣው ቀንየዘመን መጀመሪያ፥ የዘመን ክብ መነሻና መድረሻ ተብሎ ርእሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ በግእዙ ይጠራል። እነዚህ ቀኖች በኢትዮጵያውያንአቆጣጠር ተጠቃለው አንድ ጊዜ የሚገኙ ናቸው። የኢትዮጵያ ቍጥር መሠረቱ የመፅሐፍ ቅዱስ አካል የሆነው መጽሐፈ ሔኖክ ነው። መጽሐፈ ሔኖክ በ፲፱፥ ፳፥ ፳፩ እና ፳፪ ምዕራፎችየሚሰጠን የፀሐይን፥ የጨረቃን ጉዞ መነሻ አድርጎ የወሮችን፥ የዕለታትን፥ የዓመታትን መነሻ፥ መድረሻ፥ መዘዋወሪያ ብተታቸውን፥ጥንታቸውን ነው የሚያሳየው። ስለዚህም በሔኖክ ቍጥር የወር ቀኖች ቍጥር ሠላሳ ናቸው። በሦስት በሦስት ወር ግን አንድ ቀንትከተላቸዋለች። እና ዓመቱ ለአራት ይከፈላል። በዘጠና አንድ በዘጠና አንድ ቀን። ጠቅላላው ይሄ ድምር ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት ቀንይመጣል። ይህ ካለቀ በኋላ አንዲት ቀን ለዘመን ማገጣጠሚያ ዕለተ ምርያ የምትባለው ትመጣለች። እንግዲህ በኢትዮጵያውያን ቍጥርወሩ ከሠላሳ አያንስም፤ ከሠላሳ አይተርፍም። ለዓመቱም ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ቀን መደበኛው አቆጣጠር ነው ማለት ነው። ይህ ነገርበአውሮፓውያን ቍጥርም አለ። ግን እነሱ ከዓመት ወሮች ሰባቱን ሠላሳ አንድ ሠላሳ አንድ አድርገው አራቱን ደግሞ ሠላሳ ሠላሳአድርገው አንዷን ወር ሦስቱን ዓመት ሃያ ስምንት፥ በአራተኛው ዓመት ሃያ ዘጠኝአድርገው ያጣጧታል። እንግዲህ የአቀማመጡ ለውጥ ካልሆነ በስተቀር በቍጥር አካሄድ ዞሮ ዞሮ የዓመት ቀኖች ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ወይም ሦስት መቶስድሳ ስድስት በመሆን አንድ ሆነዋል ማለት ነው። ልዩነቱ ግን የአቀማመጥ ለውጥ ነው። በኢትዮጵያ አቈጣጠር ግን ጠቅላላውን ፲፪ወሮች መደባቸው ሠላሳ ብቻ ነው። እነዚያ በሔኖክ መጽሐፍ በጣልቃ ገብነት የነበሩት አራት ቀኖች ተጠቅለው ጳጉሜን በሚባልበዓመቱ መጨረሻ ላይ ተገኝተዋል። ዐምስተኛዪቱ ቀንም ከእነሱ ጋር ተገኝታለች። ይህም ለቍጥር ተራ ቅምር መቅናት የተደረገ እንጂቀኑን የሚለውጥ ምንም ነገር የለበትም። እና ከእነዚህ ቀኖች በኋላ የምናገኘው ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመት ይባላል። ይህንን በዓል ከአዳምጀምሮ እስከ ኖኅ ድረስ የነበሩ ዐሥሩም አበው በዐሥሩ ትውልድ እስከ ማየ አይኅ ድረስ ሲያከብሩት እንደ ቆዩና ኋላም የኖኅ ልጆችከአባታቸው ተቀብለው ሲያከብሩት እንደ ነበረ ኩፋሌ የተባለው መጽሐፍ በምዕራፍ ፯ ያስረዳናል። እንግዲህ ኢትዮጵያ ይህንን ቀንየወረሰችው ከአበው ነው የምንለው በዚህ ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከሌሎቹ የሚለይባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች እናከኢትዮጵያውያን እና አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ትክክለኛው የቱ ነው? ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ የዘመን አቆጣጠር መለያየትን መነሻ እንዲህ በማለት ያብራራሉ፤ “ክብ የሆነ ነገር ሲከብ ከየትኛውም ቦታ መጀመር ይቻላል፤ የዘመን አቆጣጠር /ዓውደ ዓመትም/ ይኸው ነው፡፡ ዋናው ነገር አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ ነው፤ የዘመን አቆጣጠሮቹም ልዩነት መንስኤው ይኸው ነው» ይላሉ፡፡ ባሕረ ሐሳብ፣ ጌታቸው ኃይሌ፣ ገጽ.65/ ለምሳሌነትም ሮማውያን የሮም ከተማ የተቆረቆረችበትን ጊዜ መነሻ ማድረጋቸውን/ በኋላም ታላቁ እስክንድር የነገሠበት ዘመን የዘመን ቆጠራ መነሻ ሆነው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ መሐመድና ተከታዮች ከመካ ወደ መዲና ያደረጉትን ስደት መነሻ የሚያደርገው ኢስላማዊ የዘመን አቆጣጠርም ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡ የአይሁድን አቆጣጠር ትተን ከላይ ያየናቸው ሁለቱ የዘመን አቆጣጠሮች /የምዕራባውያኑ የጁልየስ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርና የኢትዮጵያና የግብጽ አቆጣጠር/ ሁለቱም ዘመንን የሚቆጥሩት ከክርስቶስ ልደት መነሻ አድርገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ ዛሬ 2008 ዓ.ም ነው ስንል እነርሱ ደግሞ 2015 ዓ.ም ነው ይላሉ፡፡ በመካከሉ የ7 ዓመታት ልዩነት አለ፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ትክክለኛው የትኛው ነው? የሚለው ነው፡፡ ጉዳዩ መጻሕፍትን ሊያጽፍ የሚችልና በእርግጥም የተጻፉበት ቢሆንም ለማሳያ ያክል ሁለት ነገሮች እንመልከት፤ 1. አሁን ባለው የምዕራባውያን አቆጣጠር ከሄድን ሄሮድስ የሞተው 4 ዓመት ቅ.ል.ክ (ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ነው፡፡ ሄሮድስ የሞተው ጌታ ተወልዶ በስደት ሦስት ዓመት ያህል በግብጽ ከቆየ በኋላ ነው፡፡ ይህ ማለት በእርሱ አቆጣጠር ጌታ የተወለደው በ7 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ጌታ በትክክል በተወለደበት በአንድ ዓ.ም እነርሱ ጌታ ሰባት ዓመት ሆኖታል ይላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት አሁን ካላቸው ቁጥር ላይ ሰባት ዓመት መቀነስ አለባቸው፡፡ 2. ፍላቪየስ ጆሴፈስ የተባለው የአይሁድን ታሪክ የጻፈው ሊቅ እንደመሰከረው ጌታ የተወለደበት ዓመት ነው ተብሎ በወንጌል ላይ የተጻፈው የቆጠራ ዓመት /ሕዝቡ ሁሉ የተቆጠረበትን ዘመን /ሉቃ.2.1/ በጎርጎሪያን ዘመን አቆጣጠር “7 ዓመተ እግዚአ /A.D/ ላይ ነው፡፡» በማለት መረጃ ትቶልናል ይህ ማለት ደግሞ ከምዕራባውያኑ ዘመን አቆጣጠር ላይ 7 ዓመቶች የግድ መቀነስ አለበት ማለት ነው፡፡ ያ ሲደረግ ደግሞ የኛን ዘመን አቆጣጠር ያመጣል፡፡ የዘመን መለወጫ ቀን ልዩነት ሁለተኛው ጉዳይ የዘመን መለወጫ ወርና ዕለት ልዩነት ነው፡፡ እኛ መስከረም 1 አዲስ ዓመት ስንጀምር እነርሱ በ January 1 / በእኛ ታኅሣሥ 23/ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ከየት የመጣ ልዩነት ነው? የእኛ እና የግብጻውያን አቆጣጠር እዚህ ጉዳይ ላይ ከአይሁድ አቆጣጠር ጋር ይስማማል፡፡ በአይሁድ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ኒሳን የሚባለው /በእኛ መጋቢት/ ሚያዝያ/ ነው፡፡ “ይህ ወር የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፣ በዚህም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የአንድ ዓመት ተባዕት ላይ ወስደው ይረዱ፡፡ . . .»/ዘፀ.12.1-14/ ተብሎ የተሰጣቸውን የፋሲካ በዓል የሚያከብሩት በዚህ ወር ነው፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ የዓመት በዓል አድርገው የሚያከብሩት “የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁናችሁ፡፡ በዚሁ በመለከት ድምጽ የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ መስዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑበት» /ዘሌ.13.23-25/ ተብሎ የተሰጣቸው የሮሽ ሆሻና፣/የመለከት በዓል ወይም በዓለ መጥቅዕ/ ተብሎ የሚጠራው በዓል ነው፡፡ ይህም ማለት አዲስ ዓመት የሚያከብሩት በሰባተኛው ወር በኢታኒም ወር /በእኛ መስከረም ጥቅምት/ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችንም ትምህርት ዓለም የተፈጠረው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ መስከረም ደግሞ ከመጋቢት ጀምሮ ሲቆጠር ሰባተኛው ወር ነው፡፡ ይህም ከአይሁድ ዘመን አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አይሁድስ ቢሆኑ የመጀመሪያው ወር እያለ አዲስ ዓመትን ለምን በሰባተኛው ወር ያከብራሉ ለሚለው ጥያቄ ሁለት ዓይነት ምላሾች /ምክንያቶች/ ይሰጣሉ፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት “ሰባተኛው ወር ኖኅ ከመርከብ የወጣበት ወር በመሆኑ ይህ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ተደርጎ መከበር በመጀመሩ ነው» የሚል ነው፡፡ በዘመን መለወጫ ዕለት ልጃገረዶች አበባ እና ለምለም ሣር መያዛቸው ርግቢቱ ለኖኅ ካመጣችው ለምለም ወይራ /ቄጠማ/ ጋር ተያይዞ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ መስከረም የቀንና የዕለቱ ርዝመት እኩል የሚሆኑበት ወር በመሆኑ ነው የሚል ነው፡፡ የመስከረም 1 ቀን ስንክሳር “የተባረከ የመስከረም ወር የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው፤ የቀኑ ሰዓትም ከሌሊቱ ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው» ይላል፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባው ሌላው ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ትምህርት እመቤታችን ጌታን የጸነሰችው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ጳዉሎስ ፣የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ተወለደ» /ገላ.4.4/ እንዳለው የ5500 ዘመኑ ፍጻሜ /ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ/ ነው፡፡ ጽንሰትን መጋቢት 29 ካልን በኋላ ልደትን ታህሣሥ 29 ቀን እናከብራለን፡፡ ከመጋቢት 29 እስከ ታህሣሥ 29 ድረስ 9 ወር ከ5 ቀን ነው፡፡ /ጳጉሜን ጨምሮ/፡፡ ጳጉሜ 6 በምትሆንበት ጊዜ ደግሞ ታህሣሥ 28 ቀን ልደት ስለሚከበር አሁንም በመሐሉ ያለው ጊዜ 9 ወር ከአምስት ቀን ይሆናል፡፡ ማጠቃለያ በመጨረሻም የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ፍፁም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሚቆጥር መሆኑን እንጂ እንደ ዘመኑ ነገስታት ፍላጎት በታሪክ ክስተትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ከተረዳን ይህንን ሃሳባችንን የሚያጠናክርልን የሳምንታንት እና የወራት ስያሜዎቻችንን እንዲሁም የልሎቹ የቀን አቆጣጠር ምንጭን ከ እዚህ በታች ባሉት ሰንጠረዦች እንመልከት።ለምሳሌ እነኚህ የሳምንታንት ልዩነቶች አውሮፓውያን ከጥንት ከነበረ አምልኮት ጋር የትዛመደ ሲሆን የእኛ ግን እግዚአብሔር አለምን መፍጠር ከጀመረ የመጀመርያ ቀን ስንል እሁድ ማለታችንን ሁለተኛ ቀን ስንል ሰኑይ (ሰኞ) ማለታችንን ወዘተ እንረዳለን። ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም አሮጌው ዘመን 2006 ዓም ተጠናቆ አዲሱን 2007 ዓም ልንቀበል ሰዓታት ቀርተውናል። የሮማ ካቶሊክ ፓፓ ቤኔዲክት 16ኛ ”የናዝሬቱ እየሱስ” በተሰኘ መፅሐፋቸው አሁን አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት የክርስቶስ የልደት ዘመን ትክክለኛ እንዳልሆነ ሲገልጡ እንዲህ ብለዋል-“The calculation of the beginning of our calendar—based on the birth of Jesus—was made by Dionysius Exiguus, who made a mistake in his calculations by several years,” ”ከጅምሩ የቀን አቆጣጠራችን ክርስቶስን ተወለደ ያለበት ዘመን መሰረት (በእክስጉሥ የተቀመረው) የብዙ አመታት የስሌት ስህተት አለው” ብለዋል። (http://www.charismanews.com/world/34714-pope-says-jesus-birth-date-is-wrong) ይህ ከአንድሚልዮን ኮፒ በላይ እንደተሸጠ የተነገረው መፅሐፍ ላይ ፓፓው ይህንን ይበሉ እንጂ ስህተቱን ለማረም እና ወደ ትክክለኛው ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለመምጣት የደፈረ እስካሁን አልታየም።ወደፊት ግን ይጠበቃል። ጉዳያችን ይህ ፅሁፍ በእዚሁ ጡመራ በጳጉሜ 2/2006 ዓም ወጥቶ ነበር። አስፈላጊነቱን በማሰብ ዛሬ ጳጉሜ 5/2007 ዓም እንደገና ወጥቷል። ፅሁፉ የተጠናቀረባቸው ምንጮች – 1/ መስከረም 2004 አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም 2/ አለቃ አያሌው ታምሩ ትምህርት http://www.aleqayalewtamiru.org/new_year_2003.html 3/ ማኅበረ ቅዱሳን ድህረገፅ http://www.eotc-mkidusan.org/site/-mainmenu-24/–mainmenu-26/30—- 4/ደጀ ሰላም መስከረም 11/ 2011 http://www.dejeselam.org/2011/09/blog-post_11.html#more 5/ማኅበረ ቅዱሳን 2000 ዓም አውደ ርዕይ Source:: gudayachn
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
650
ግንቦት ፫ ግንቦት ፫ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፪ ቀናት ይቀራሉ። ግንቦት ፬ ግንቦት ፬ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፬ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፩ ቀናት ይቀራሉ። ግንቦት ፮ ግንቦት ፮ ግንቦት ፮ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፵፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፱ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
651
ግንቦት ፱ ግንቦት ፱ ግንቦት ፱ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፱ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፵፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፲፯ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፮ ቀናት ይቀራሉ። ግንቦት ፲ ግንቦት ፲ ግንቦት ፲ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፶ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፵፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፲፮ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፭ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
652
መጋቢት ፴ መጋቢት ፴ መጋቢት ፴፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፮ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፭ ቀናት ይቀራሉ። =ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች= =ልደት= ሚያዝያ ፩ ሚያዝያ ፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፩ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፬ ቀናት ይቀራሉ። =ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ሚያዝያ ፪ ሚያዝያ ፪፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፪ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፬ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፫ ቀናት ይቀራሉ። =ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች= =ዕለተ ሞት ሚያዝያ ፫ ሚያዝያ ፫ ሚያዝያ ፫፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፪ ቀናት ይቀራሉ። =ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች= =ዕለተ ሞት ሚያዝያ ፬ ሚያዝያ ፬ ሚያዝያ ፬፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፬ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፩ ቀናት ይቀራሉ። =ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች። ሚያዝያ ፮ ሚያዝያ ፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፲፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፵፱ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
653
ሚያዝያ ፳፩ ሚያዝያ ፳፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፩ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፮ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፬ ቀናት ይቀራሉ። ሚያዝያ ፳፬ ሚያዝያ ፳፬፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፬ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፩ ቀናት ይቀራሉ። ሚያዝያ ፳፭ ሚያዝያ ፳፭፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፭ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፩ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴ ቀናት ይቀራሉ። ሚያዝያ ፳፮ ሚያዝያ ፳፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፱ ቀናት ይቀራሉ። ሚያዝያ ፳፰ ሚያዝያ ፳፰፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፰ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፯ ቀናት ይቀራሉ። ግንቦት ፪ ግንቦት ፪ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፪ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፬ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፫ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
654
ግንቦት ፲፪ ግንቦት ፲፪ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፶፪ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፵፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፲፬ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፫ ቀናት ይቀራሉ። < ግንቦት ፲፫ ግንቦት ፲፫ ግንቦት ፲፫ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፶፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፵፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፲፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፪ ቀናት ይቀራሉ። ግንቦት ፲፬ ግንቦት ፲፬ ግንቦት ፲፬ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፶፬ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፵፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፲፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፩ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
655
ሚያዝያ ፳፪ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፴፪ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፬ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፫ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
656
መስከረም ፩ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ የመጀመሪያው ዕለት ነው። በመሆኑም ቀኑ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በዓል ወይም ዕንቁጣጣሽ በመባል ይታወቃል። ታኅሣሥ ፳፪ ታኅሣሥ ፳፪ ታኅሣሥ ፳፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፲፪ተኛው እና የመፀው ወቅት ፹፯ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፶፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፶፫ ቀናት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
657
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ከየት ይጀምራል? የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚጀምረው ከፍጥረተ ዓለም፣ ከፍጥረተ ጸሐይ፣ ከፍጥረተ ጨረቃ ጋር የተያያዘ ሲሆን የሚጀምረውም ጥንት ከሚለው ነው። ጥንትነቱም ከእነዚሁ ከዓለም፣ ከጸሀይ ፣ ከጨረቃና ከዋክብት መፈጠር ጋር የተያያዘ ሲሆን በጸሐይ ሶስት ጥንታት አሉ። እነሱም፦- 1. ጥንተ ዕለት፦ ጥንተ ዕለት እሑድ ሲሆን በዚህ ቀን ዓለም ማለትም ሰማይና ምድር የተፈጠረበት ቀን ነው። 2. ጥንተ ቀመር፦ ይህ ዕለት ሠሉስ /ማክሰኞ/ ሲሆን በዚህ ቀን በዓለም ውስጥ የሚገኙ ፍጥረታት /ዕፅዋት፣ አዝርዕት፣ አታክልት/ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠሩበት ቀን ነው። 3. ጥንተ ዮን፦ ጥንተ ዮን ዕለተ ረቡዕ ሲሆን በዚህም የቀንና የሌሊት መክፈያ የሆኑት ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት የተፈጠሩበት ቀን ነው። ዮን ማለት ጸሐይ ማለት ነው። “ዮን ይዕቲ ስማ ለጸሐይ ሀገረ ጸሐይ ዮን ይዕቲ” እንዲል። እንግዲህ የኢትዮጵያ ዘመን መቆጠር የጀመረው ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ስለ ዘመን ቆጠራም ስንናገር “ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ” እንላለን። ስለዚህ ዘመን ቆጠራችን ከሥነ ፍጥረት ጋር የተያያዘ ነው።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
658
የኢትዮጵያን የምዕራባውያን ዘመን ለዩነት ከየት መጣ? በኢትዮጵያውያንና በአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር መካከል በርካታ መሠረታዊ የሚባሉ ልዩነቶች ይታያሉ፡፤ ለዚህም ይመስላል ብዙዎች ዘመን መለወጫ በመጣ ቁጥር ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ዕለተ ቀመርን ወይንም ዘመን መለወጫን የምናደርገው በመስከረም ሲሆን የአውሮፓውያን የዘመን መለወጫ ፤ ታህሳስ /December/ 29 ልደትን አክብረው ጥር /January/ 1ቀን ዘመን መለወጫቸው ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ዓመተ ምህረታችን 2005 ሲሆን የነሱ 2013/2014 ይሆናል፡፡ ይህም የሰባት ዓመት ከስምንት ወር ልዩነት ይኖረናል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ሁሉንም ወራት በሠላሳ ቀናት ከፍለን አስራ ሁለት ወር ከ 5 ቀን ጳጉሜ አድርገን ስንቆጥር ፤ አውሮፓውያን ግን 28፣ 30፣ 31 በማድረግ 365 ቀኑን አስራ ሁለት ወር ብቻ በማድረግ ይቆጥራሉ፡፡ ከላይ የተመለከትናቸው ዋና ዋና ልዩነቶች ሲሆኑ ከዚህ ቀጥለን እነዚህ ልዩነቶች ለምን እንደተፈጠሩ ባጭሩ እንመለከታልን፡፡ # የዘመን መለወጫ ልዩነት# ኢትዮጵያዊያን ዘመን የምንለውጠው መስከረም አንድ ቀን /ዕለተ ቀመር/ ነው፡፡ መስከረም የዘመን መለዋጫ የሆነበት ምክንያት፡- በዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱን እኩል የሚሆኑበት ነው፡፡ ቀኑ ሙሉ 12 ሰዓት ሌሊቱም ሙሉ 12 ሰዓት ይሆናል፡፡ አንድም ከጥንቱም ዘመን ሲቆጠር ዓለም በተፈጠረ በ5 ወር ከስድስት ቀን በመስከርም አንድ ቀን በዕለተ ሰሉስ ቁጥር/ቀመር ስለጀመረ በዕዚህ ዕለት ዘመንን እንለውጣለን፡፡ ሀገራችን ይህ በዓል ለመከበሩ የሚቀመጡ እውነታዎች ሲኖሩ ይኸውም በዚህ ወር ንግሥት ሳባ ኢየሩሳሌም ደርሳ የጠቢብ ሰሎሞንን ጥበብ አድንቃ ስትመለስ ዕንቍ ለጣትሽ ብሎው በርካታ የከበሩ ዕንቍ በስጦታ የተበረከተላት በዚህ ወር በመሆኑ የዘመን መለወጫ በመስከረም አንድም እናደርጋለን፡፡ በዚህም የተነሳ መስከረም አንድ ቀን እንቁጣጣሽ በመባል ይታወቃል፡፡ መሳ10÷1 በሌላ መልኩ ፀሓይ የ365 ቀናትና ጉዞዋን ፈፅማ አንድ ብላ የምትጀምረው በዚህ ወር ነው፡፡ አንድም፡- የክረምቱ /የጨለማው/ ወራት የሚያበቃበትና ወርሃ ጽጌ የሚጀምርበት ወር በመሆኑና አንድም፡- ኖህና ቤተሰቡ ከጥፋት ውኃ ድነው ምድር መድረቋን /አበባና ፍሬ መስጠቷን/ የተመለከተው በዚህ ወር ነበር፡፡ ዘፍ. 8÷8 በዓመቱም /ከ12 ወር በኋላ/ የዘመን መባቻ መጀመሪያ ወይም የዘመን መለወጫ አድርጎ አክብሯል፡፡ ኩፋሌ 24÷7 ‹‹በመጀመሪያ ወር መባቻ ለራሱ መርከብ ይሠራ ዘንድ ታዘዘ በእርሷም ምድር ደረቀች፡፡›› እንዲሁም እግዚአብሔር በዚህ ወር ለሙሴ የዘመን መለወጫ ይሆን ዘንድ አዞታል፡፡ ዘሌ 23÷53 እግዚአብሔር ለእስራኤል በአዘዘው ሥርዓት መሠረት ከግብፅ በወጡበት በሰባተኛው ወር የሚከበር በዓል ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ታሪክን እና መጽሐፍ ቅዱስን አብነት በማድረግ በመስከረም አንድ ቅን የዘመን መለወጫ በኣልን እናከብራለን፡፡ በክርስትናው ዘመን እስከ ዐሥራ አንደኛው ክ/ዘመን ድረስ ዓለም በአንድነት በዚህ ወር በመጀመሪያው ዕለት ያከብር ነበር፡፡ ነገር ግን ጎርጎርዮስ ሰባተኛ /1073-1035/ የዘመን መለወጫ ከልደት በዓል ጋር እንዲያያዝ በማለት ወደ ጥር አዞረው በዚሁ መሠረት የምዕራቡ ዓለም በጥር ወር ሲያከብር የምሥራቅ ግን እስካሁን መስከረምን አለቀቁም በዚህ ወር አዲስ ዓመታችን ከሚጀምሩ መካከል ግሪክ፣ ሩስያና ሮማንያ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ለኢትዮጵያና ለእስክንድሪያ ቤተ ክርስቲያንም ይኸው መስከረም ወር አዲስ ዓመታቸው መባቻ /መግቢያ/ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ቤተክርስቲያናችን ዕለቱን እስከዚህ ያደረስን በማለት እግዚአብሔርን የምታመሰግንበት የአጽዋማትና የበዓላትን /የዐዋድያቱን/ የምታውጅበት ፍሬ ምድርን ባረካ የአዲሱ ዓመት አገልግሎት አሐዱ ብላ የምትጀምርበት ታላቅ በዓል ነው፡፡ የሰባት ዓመት ከስምንት ወር ልዩነት ለምን ተገኘ? #የምዕራባውያኑ የጁልየስ# ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርና የኢትዮጵያና የግብጽ አቆጣጠር ሁለቱም ዘመንን የሚቆጥሩት ከክርስቶስ ልደት መነሻ አድርገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ ዛሬ 2008 ዓ.ም ነው ስንል እነርሱ ደግሞ 2015 ዓ.ም ነው ይላሉ፡፡ በመካከሉ የ7 ዓመታት ልዩነት አለ፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ትክክለኛው የትኛው ነው? የሚለው ነው፡፡ ጉዳዩ መጻሕፍትን ሊያጽፍ የሚችልና በእርግጥም የተጻፉበት ቢሆንም ለማሳያ ያክል ሁለት ነገሮች እንመልከት፤ይውጥላል........
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
659
የዘመን አቆጣጠር አመጣጥ Tuesday, September 2, 20142comments አዳም አትብላ የተባለውንየእግዚአብሔርን ትዕዛዝበመሻሩና በመብላቱ ምክንያትከገነት ከተባረረ በኋላየነበረው ጊዜ የስቃይ የመከራየኩነኔ ዘመን በመሆኑ እስከክርስቶስ ልደት ድረስ ዘመነኩነኔ ወይም ዘመነ ፍዳበመባል ይታወቃል::እግዚአብሔርም ለአዳምከልጅ ልጅህ ተወልጄአድንሃለሁ ብሎ በገባለት ቃልኪዳን መሠረት፤ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል የምሥራች አማካኝነት ከንጽሕት ቅድስትድንግል ማርያም ተወልዶ፤ ተገርፎ፤ ተሰቅሎ፤ ሞቶ፤ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎከተነሳ በኋላ አርጓል፤ እኛንም ልጆቹን ከእርሱ ጋር አስታረቀን፤ ለፍርድም እንደሚመጣእናምናለን፤ እስከ እዚህ ድረስ ያለው ዘመን ደግሞ ዘመነ ምሕረት ወይም ዓመተ ምሕረት(የምሕረት ዘመን) በመባል ይታወቃል:: የሁለቱ ድምር ደግሞ ዓመተ ዓለም በመባልይታወቃል:: በዚህ መሠረት ዘንድሮ 7506 ዓመተ ዓለም ሲሆን የ 2006 ዓመተ ምሕረትና የ5500 ዓመተ ፍዳ ወይምዓመተ ኩነኔ ድምር ነው:: አዳም ከገነት ያችን ዕፀ በለስ በልቶ ከተባረረ ወዲህ እግዚአብሔር አምላካችን ለአዳምተስፋ ሰጠው:: ተስፋውም ከአምስት ቀን ትኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁብሎ የገባለትን ቃል ኪዳን ከሰማ ወዲህ ቀን መቁጥር ወይም ማስላት ተጀመረ:: በናምሩድ ዘመን በሰናዖር የሰው ልጅ ቋንቋ ከተደበላለቀ በኋላ 5500 ዘመን መቁጠሩተዘነጋ:: ስለዚህ አንዳንዶች በጨረቃ እኩሎቹ በከዋክብት ሌሎቹ ደግሞ በፀሐይ ሲቆጥሩለዘመናት ያህል ኖረዋል:: እግዚአብሔር ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳንና ተስፋውን የሚጠባበቁ ካልሆነ በስተቀርየ 5500 ዘመን ማለትም የቀጠሮዋን ቀን የሚቆጥር፤ የሚያስብና የነብያትን ሱባኤየሚመረምር የሚያስተውል ሕዝብ ጠፋ:: ስለዚህ ፀሐይን የሚያመልክ በፀሐይሲቆጥር፤በጨረቃ የሚያመልክ ደግሞ በጨረቃ ሲቆጥር እንዲሁም በከዋክብት የሚያመልክደግሞ በከዋክብት ይቆጥሩ ጀመር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችን ፀሐይን፤ጨረቃን፤ከዋክብትን ለዘመን መቁጠሪያ አድርጎ ነበር ለሰው ልጅ የሰጠው ነገር ግን የሰውልጅ አማልክት አደረጉአቸው:: የዘመንን አቆጣጠር ማን ቀመረው? * 12ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲሜጥሮስ የዘመን አቆጣጠርን ቀመረው * ቅዱስ ዲሜጥሮስ የአጽዋማትንና የበዓላትን የሚወስን የቁጥር ሕግ ለማግኘት ተመኘበመልአኩም አሳሳቢነት ሱባኤ ገብቶ ያሰበውንና የተመኘውን እግዚአብሔር አምላክገለጸለት እነሱም * ሁልጊዜ ጾም ከሰኞ እንዲጀምር ወይም እንዳይወጣ ሥርዓትን ሰራላቸው በበዓላት ጊዜ * ደብረዘይት፤ ሆሳዕና፤ ትንሳኤ፤ ጰራቅሊጦስ ከዕሁድ እንዳይወጣ * ስቅለት ከአርብ እንዳይወጣ * ጾመ ድህነት ከረቡዕ እና አርብ እንዳይወጣ * ርክበ ካህናት ከረቡዕ እንዳይወጣ * ዕርገት ከሐሙስ እንዳይወጣ አደረገ * ከጾመ አርባ ጋር አያይዘው እንዲያከብሩ የሕማማትን ሳምንትና የትንሳኤን በዓል ሥርዓትሠራላቸው * የቀመር ሕግ አውጥቶ በዓመት ውስጥ ከወሰነላቸው ጊዜ ወደታች ወይም ወደላይእንዳይወጡ ባስቀመጠላቸው ቀመር እንዲጠቀሙ አደረገ የተለያዩ የዘመን አቆጣጠር * የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር * አይሁዳውያን አመታቸውን የሚጀምሩት ከክርስቶስ ልደስ በፊት ከ3761ዓመት ነው:: ምክንያቱም አይሁድ የክርስቶስን መወለድ ስላልተቀበሉና ገና ይወለዳል ብለው ስለሚያምኑ ብቻ ነው:: * የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር * እስክንድርያ የፈራክና ኮከብ ቆጠራ ማእከል ነበረች * ዓመታቸውን በጨረቃ ሲቆጥሩ ከቆዩ በሁዋላ በፀሐይ ቆጥራለች * በአንድ ወር ውስጥ ሠላሳ ቀናት ያላቸውን 12ቱን ወራት አምስት ቀን በመጨመር 365 ቀናት አንድ ዓመት መሆኑን ይናገራሉ * በ239 ቢሲ 1/4ኛ ቀን ጨመሩ ይህም እኛ አሁን የምንጠቀምበትነው * የዮልዮስ ቄሳር ዘመን አቆጣጠር * ዓመት ብለው የሚጠሩት አስሩን ወራት ነበር ወራቶቹም 304ቀናትን የያዙ ነበር * የሮምን ከተማ ከመሰረተው ንጉስ ቀጥሎ የነገሰው ንጉስ 304የነበሩትን ቀናት ጨምሮ 355 አድርጎታል * በ46 ቢሲ ዲሊየስ ቄሳር በነገሰ ወቅት የአሌክሳንደራውያን ዘመንአቆጣጠር ዓመት ቀናት አብነት በማድረግ 365 ቀናት አደረገው ነገርግን የጳጉሜን ቀናቶች በየወራቱ በትኖ አከፋፍሎ አስቀመጣቸው:: * ዲዮናስዮስ ኤክሲጅየስ የተባለው የሮም ሊቅ መነኩሴ በ532 ዓ.ምእንዲህ በማለት ስለ ቀናትና ዓመታት ተናገረ:: ክርስቶስ ተወልዶበታልየተባለውን ዘመን ወደ ሁዋላ ስምንት ዓመት ወስዶታል:: የዚህ ዘመንጭማሪም 256 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን አድርጎአል:: ይህምዘመን የዘመነ ዲዮቅልጥያኖስ መነሻ ሲሆን በሌላ በኩልም የዘመነሰማዕታት መጀመሪያ ነበር:: በዚህም 532 ዓ.ም ላይ ሆኖ ሳለ 276ይል የነበረውን አቆጣጠር 284 ብለው እንዲቆጥሩ አድርጎአልምአውጆአልም:: ከዚህ ዘመን ወዲህ የሰባትና ስምንት ዓመት ልዩነትእንዲፈጠር ዋና ምክንያት ሆኖአል ማለት ነው:: * ግሪጎሪ የሚባል የ13ኛው የሮም ፓፓ ከ46 ዓመተ ዓለም ጀምሮየነበረውን የዘመን አቆጣጠር 10 ቀናቶችን ጨምሮ ለውጥ በማድረጉምክንያት ግሪጎሪያን ዘመን አቆጣጠር ተባለ:: የግሪጎሪያን አቆጣጠርመነሻውም የዓመቱ ቀናት 365 ከ6 ሰዓት የነበረውን 365 ቀናት ከአምስት ሰዓት ከ 48 ደቂቃና 46 ሰከንድ አደረገው:: በዚህምያልተኖረባቸውን 10 ቀናት እ.ኤ.አ ከ325 ዓ.ም ጀምሮ በማስላትእንዲወገዱ አውጁአል:: በዚህም መሠረት መስከረም ላይ የአስር ቀናትልዩነት ተፈጠረ:: ለምሳሌ ግሪጎሪ ጥቅምት 5 ቀን 1575 ዓ.ም /በኢትዮጵያ አቆጣጠር የነበረውን/ ጥቅምት 15 ቀን 1575 ዓ.ምእንዲሆን አዋጅ አድርጎአል:: * መሰግላን/መጥዓውያን/ (ጠንቁአዮች ኮከብ ቆጣሪዎች) * በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ምድርግን ባዶ ነበረች አትታይምም ነበር የተዘጋጀችም አልነበረችምጨለማም በዉኃው ላይ ነበረ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይይፈስ ነበር:: እግዚአብሔርም "ብርሃን ይሁን አለ" ብርሃንም ሆነ::እግዚአብሔር አምላክም ብርሃኑን ቀን ጨለማውን ሌሊት ብሎጠራው:; እግዚአብሔርም አለ "በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በቀንናበሌሊትም ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ:: ለምልክቶች; ለዘመናት: ለእለታት; ለዓመታትም ይሁኑ:: በምድርላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ለማብራት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ:: እግዚአብሔር ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ: ትልቁ ብርሃን(ፀሐይ) ቀንን እንዲመግብ ትንሹ ብርሃንም (ጨረቃ) ከከዋክብት ጋርሌሊትን እንዲመግብ አደረገ በመዓልትም በሌሊትም እንዲለዩ ሆነ(ዘፍ 1- 1-14):: እግዚአብሔር አምላካችን ይህን ያደረገው ለእኛበምድር ለምንኖር ፍጥረቱ ሆኖ ሳለ በከዋክብት በጨረቃና በፀሐይዘመናትን; ዕለታትንና ዓመታትን በመቁጠር ፋንታ በከዋክብት;በጨረቃና በፀሐይ ዘመናትን ቆጥረው የፈጠራቸውን አምላክ ማምለክሲገባ እነዚህ መሰግላን ወይም መጥዓውያን ግን ያመልኩአቸዋል:: * ሰብአ ሰገልም ይህን የአቆጣጠር ዓይነት ተጠቅመውበታል * ሠራዕያነ ህግ * በዚህ ዓለም የምንኖር ፍጥረት የሰው ልጅንም ጨምሮ የሚኖረውለ7000 ዓመት ብቻ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው * የሚገርመው ግን በነሱ ህግ መሠረት ይህች ዓለም መጥፋትየነበረባት የዛሬ 504 ዓመት ነበር ምክንያቱም 5500 + 2004 = 7504 ይሆናል ማለት ነው:: በዚህ አጋጣሚ በመነሳት ብዙ ሰዎችበተለይ በኛ ሕብረተሰብ ዘንድ 8ኛው ሺህ የሚባለው አባባል የዚህተጽሕኖ ሳይሆን አይቀርም ብየ አምናለሁ:: * ፍሌካውያን * ከመሰግላን የተወሰነውን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ወስደውየጎደለውን በነገስታቱ አማካኝነት እያስወሰኑ የመጡ ናቸው * የሃያ አራት ሰዓት መነሻን እኩለ ቀንን ያደረጉ ናቸው የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር * የፀሐይና የጨረቃ ጥምር አቆጣጠር ትጠቀማለች * አንድ ዕለት የሚጀምረው ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ አስራ ሁለት ሰዓትነው:: የወሩ መጀመሪያ መስከረም እና የወሩ መጨረሻ ጳጉሜ ሲሆን የሳምንቱ መጀመሪያቀን ደግሞ እሁድ ነው:: * አንድ ዓመትም በውስጡ በ91 ቀናት የተከፋፈሉ አራት ክፍላተ ዘመናት አሉት እነሱምመፀው; ሐጋይ; ፀደይ እና ክረምት ናቸው:: *የሐሳበ ዘመኑ ትምህርት አቡሻህር ይባላል * በአቡሻህር መጽሐፍ መግቢያ ላይ እንደገለጸው ይህትምህርት በዮሐንስ አቡሻህር ስም እንደተሰየመ ይነግረናል * የአቡሻህር ስያሜዎችም * ባህረ ሐሳብ - ስፋቱን ስለሚገልጽ * ዘመነ ዓለም - የአዳምን ዘመን የሚቀምረውን ስለሚገልጽ * መርሐ ዕውር - አዋቂውም አላዋቂውም ስለሚጠቀምበት * የቁጥር ትምህርት - የዘመን አቆጣጠር ፈሊጥ ስለሚናገር * በ81 መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ መጽሐፈ ሄኖክ እና የተወሰኑ መጽሐፍቶችደግነታቸው ቢታወቅም የዘመን አቆጣጠርን ስለሚናገሩ በዘመኑ ግሪካውያን ምንም ክርስትናን ቢቀበሉም የቀድሞው የአያቶቻቸው የኮከብ ቆጠራና ሥነ ፈለክልምዳቸውም ስለነበር መጽሐፍቱን አልተቀበሉትም:: በአንዳንድ የክርስትና እምነት ተከታዮች እነዚህን አቡሻህር እና ሌሎች የቁጥር መጻሕፍት ከ 81 መጽሐፍቅዱስ ውስጥ ያልተካተቱበት ምክንያትም ለዚህ ነው::
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
660
የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር በዲያቆን ኃይለ ኢየሱስ ቢያ መስከረም ፮ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም የዘመን አቈጣጠር ዓመታትን፣ ወራትን፣ ሳምንታትን፣ ዕለታትን፣ ደቂቃን እና ድቁቅ ሰዓታትን በየሥፍራቸው (በየመጠናቸው) የሚገልጽ፤ የሚተነትን፤ የሚለካ የቤተ ክርስቲያን የቍጥር ትምህርት ነው፡፡ እነዚህ ዅሉ ተመርምረው፣ ተመዝነው፣ ተቈጥረው ሲያበቁ ምድብና ቀመር ተሰጥቷቸው የሚገኙበትን ውሳኔና ድንጋጌ የሚያሳውቅ የዘመን አቈጣጠር – ‹ሐሳበ ዘመን› ይባላል፡፡ ዓመታት፣ ወራት፣ ሳምንታት፣ ዕለታትና ሰዓታት የሚለኩት (የሚሠፈሩት፣ የሚቈጠሩት) በሰባቱ መሥፈሪያና በሰባቱ አዕዋዳት ነው፡፡ ሰባቱ መሥፈርታት የሚባሉትም፡- ሳድሲት፣ ኃምሲት፣ ራብዒት፣ ሣልሲት፣ ካልዒት፣ ኬክሮስ እና ዕለት ሲኾኑ ሰባቱ አዕዋዳት ደግሞ፡- ዐውደ ዕለት፣ ዐውደ ወርኅ፣ ዐውደ ዓመት፣ ዐውደ ፀሐይ፣ ዐውደ አበቅቴ፣ ዐውደ ማኅተም እና ዐውደ ቀመር ናቸው፡፡ ዐውደ ዕለት – ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ያሉት ሰባቱ ዕለታት ሲኾኑ፤ አውራኅን (ወራትን) ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡ ዐውደ ወርኅ – በፀሐይ ፴ ዕለታት፣ በጨረቃ ፳፱ ወይም ፴ ዕለታት ናቸው፤ ዓመታትን ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡ ዐውደ ዓመት – በፀሐይ ቀን አቈጣጠር ፫፻፷፭ ቀን ከ፲፭ ኬክሮስ፤ በጨረቃ አቈጣጠር ፫፻፶፬ ቀን ከ፳፪ ኬክሮስ ነው፡፡ እነዚህ ሦስቱ በዕለት፤ አራቱ ደግሞ በዓመት ይቈጠራሉ፡፡ ዘመናትን ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡ ዐውደ ፀሐይ – ፳፰ ዓመት ነው፤ በዚህ ዕለትና ወንጌላዊ ይገናኙበታል፡፡ ዐውደ አበቅቴ – ፲፱ ዓመት ነው፤ በዚህ ፀሐይና ጨረቃ ይገናኙበታል፡፡ ዐውደ ማኅተም – ፸፮ ዓመት ነው፤ በዚህ አበቅቴና ወንጌላዊ ይገናኙበታል፡፡ ዐውደ ቀመር – ፭፻፴፪ ዓመት ነው፤ በዚህ ዕለትና ወንጌላዊ፣ አበቅቴም ይገናኙበታል፡፡ የዘመናት (የጊዜያት) ክፍል እና መጠን አንድ ዓመት በፀሐይ ፫፻፷፭ ቀን ከ፲፭ ኬክሮስ፤ በጨረቃ ፫፻፶፬ ቀን ከ፳፪ ኬክሮስ ነው፡፡ አንድ ወር በፀሐይ ፴ ዕለታት አሉት፤ በጨረቃ ፳፱ ወይም ፴ ዕለታት አሉት፡፡ አንድ ዕለት ፳፬ ሰዓት፤ አንድ ቀን ፲፪ ሰዓት፤ አንድ ሰዓት ፷ ደቂቃ ነው፡፡ አንድ ደቂቃ ፷ ካልዒት፤ አንድ ካልዒት ፩ ቅጽበት ነው፡፡ ኬክሮስ ማለት የክፍለ ዕለት ሳምንት (የዕለት ፩/፷ ወይም ፩/፳፬ኛ ሰዓት) ነው፡፡ አንድ ዕለት ፳፬ ሰዓት ወይም ፷ ኬክሮስ ነው፡፡ ክፍላተ ዓመት (የዓመት ክፍሎች) የዓመት ክፍሎች፡- መጸው፣ በጋ፣ ፀደይ እና ክረምት ናቸው፡፡ ከመስከረም ፳፮ እስከ ታኅሣሥ ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ክፍለ ዓመት መጸው ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት ሌሊቱ ረጅም፣ ቀኑ አጭር ነው፡፡ ከታኅሣሥ ፳፮ እስከ መጋቢት ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ክፍለ ዓመት በጋ ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት እኩል ነው፡፡ ከመጋቢት ፳፮ እስከ ሰኔ ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ወቅት ፀደይ ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት ቀኑ ይረዝማል፤ ሌሊቱ ያጥራል፡፡ ከሰኔ ፳፮ እስከ መስከረም ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ክረምት ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት እኩል ነው፡፡ የዘመናት አከፋፈል በአራቱ ወንጌላውያን እና ዘመን የሚለወጥበት ሰዓት ማቴዎስ ዘመኑን ከምሽቱ ፩ ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከሌሊቱ ፮ ሰዓት ይፈጽማል፡፡ ማርቆስ ዘመኑን ከሌሊቱ ፯ ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከጠዋቱ ፲፪ ሰዓት ይፈጽማል፡፡ ሉቃስ ዘመኑን ከጠዋቱ ፩ ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከቀኑ ፮ ሰዓት (በቀትር) ይፈጽማል፡፡ ዮሐንስ ዘመኑን ከቀኑ ፯ ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከቀትር በኋላ ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት ይፈጽማል፡፡ የወራት፣ የሌሊትና የቀን ሥፍረ ሰዓት መስከረም – ሌሊቱ ፲፪፤ መዓልቱም (ቀኑ) ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ጥቅምት – ሌሊቱ ፲፫፤ መዓልቱ ፲፩ ሰዓት ነው፡፡ ኅዳር – ሌሊቱ ፲፬፤ መዓልቱ ፲ ሰዓት ነው፡፡ ታኅሣሥ – ሌሊቱ ፲፭፤ መዓልቱ ፱ ሰዓት ነው፡፡ ጥር – ሌሊቱ ፲፬፤ መዓልቱ ፲ ሰዓት ነው፡፡ የካቲት – ሌሊቱ ፲፫፤ መዓልቱ ፲፩ ሰዓት ነው፡፡ መጋቢት – ሌሊቱ ፲፪፤ መዓልቱ ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ሚያዝያ – ሌሊቱ ፲፩፤ መዓልቱ ፲፫ ሰዓት ነው፡፡ ግንቦት – ሌሊቱ ፲፤ መዓልቱ ፲፬ ሰዓት ነው፡፡ ሰኔ – ሌሊቱ ፲፱፤ መዓልቱ ፲፭ ሰዓት ነው፡፡ ሐምሌ – ሌሊቱ ፲፤ መዓልቱ ፲፬ ሰዓት ነው፡፡ ነሐሴ – ሌሊቱ ፲፩፤ መዓልቱ ፲፫ ሰዓት ነው፡፡ የበዓላት እና አጽዋማት ኢየዐርግ እና ኢይወርድ (ከፍታ እና ዝቅታ) ጾመ ነነዌ ከጥር ፲፯ ቀን በታች፤ ከየካቲት ፳፩ ቀን በላይ አይውልም፡፡ ዐቢይ ጾም ከየካቲት ፩ ቀን በታች፤ ከመጋቢት ፭ ቀን በላይ አይውልም፡፡ ደብረ ዘይት ከየካቲት ፳፰ ቀን በታች፤ ከሚያዝያ ፪ ቀን በላይ አይውልም፡፡ በዓለ ሆሣዕና ከመጋቢት ፲፱ ቀን በታች፤ ከሚያዝያ ፳፫ ቀን በላይ አይውልም፡፡ በዓለ ስቅለት ከመጋቢት ፳፬ ቀን በታች፤ ከሚያዝያ ፳፰ ቀን በላይ አይውልም፡፡ በዓለ ትንሣኤ ከመጋቢት ፳፮ ቀን በታች፤ ከሚያዝያ ፴ ቀን በላይ አይውልም፡፡ ርክበ ካህናት ከሚያዝያ ፳ ቀን በታች፤ ከግንቦት ፳፬ ቀን በላይ አይውልም፡፡ በዓለ ዕርገት ከግንቦት ፭ ቀን በታች፤ ከሰኔ ፲፱ ቀን በላይ አይውልም፡፡ ጾመ ሐዋርያት ከግንቦት ፲፮ ቀን በታች፤ ከሰኔ ፳ ቀን በላይ አይውልም፡፡ ጾመ ድኅነት ከግንቦት ፲፰ ቀን በታች፤ ከሰኔ ፳፪ ቀን በላይ አይውልም፡፡ የተውሳክ አወጣጥ ፩. የዕለት ተውሳክ የዕለት ተውሳክ በቅዳሜ ይጀምራል፡፡ የቅዳሜ ተውሳክ ፰፤ የእሑድ ተውሳክ ፯፤ የሰኞ ተውሳክ ፮፤ የማክሰኞ ተውሳክ ፭፤ የረቡዕ ተውሳክ ፬፤ የሐሙስ ተውሳክ ፫፤ የዓርብ ተውሳክ ፪ ነው፡፡ ፪. የአጽዋማትና የበዓላት ተውሳክ የነነዌ ተውሳክ አልቦ (ባዶ)፤ የዐቢይ ጾም ተውሳክ ፲፬፤ የደብረ ዘይት ተውሳክ ፩፤ የሆሣዕና ተውሳክ ፪፤ የስቅለት ተውሳክ ፯፤ የትንሣኤ ተውሳክ ፱፤ የርክበ ካህናት ተውሳክ ፫፤ የዕርገት ተውሳክ ፲፰፤ የጰራቅሊጦስ ፳፰፤ የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ ፳፱፤ የጾመ ድኅነት ተውሳክ ፩ ነው፡፡ በዓላት እና አጽዋማት የሚውሉባቸው ዕለታት ጾመ ነነዌ፣ ዐቢይ ጾም እና ጾመ ሐዋርያት – ሰኞ፡፡ ደብረ ዘይት፣ ሆሣዕና፣ ትንሣኤ እና ጰራቅሊጦስ – እሑድ፡፡ ስቅለት – ዓርብ፡፡ ርክበ ካህናት እና ጾመ ድኅነት – ረቡዕ፡፡ ዕርገት – ሐሙስ ቀን ይውላል፡፡ መጥቅዕ እና አበቅቴ መጥቅዕ እና አበቅቴ ከየት መጣ ቢሉ፣ የመጀመሪያው – የፀሐይና የጨረቃ ቀን አቈጣጠር ልዩነት ነው፡፡ አንድ ዓመት በፀሐይ ፫፻፷፭ ቀን ከ፲፭ ኬክሮስ፤ በጨረቃ ፫፻፶፬ ቀን ከ፳፪ ኬክሮስ ነው፡፡ የሁለቱ ልዩነት (፫፻፷፭ – ፫፻፶፬ = ፲፩) አበቅቴ ይባላል፡፡ ሁለተኛው – የቅዱስ ድሜጥሮስ ሱባዔ ውጤት ነው፡፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ በዓላትና አጽዋማት የሚውሉበት ቀን በጥንተ ዕለቱ እንዲውል ለማድረግ ይመኝ ነበርና ከሌሊቱ ፳፫ ሱባዔ፤ ከቀኑ ፯ ሱባዔ ገብቷል፡፡ ፳፫×፯ = ፻፷፩ ይኾናል፡፡ ፻፷፩ ለ፴ ሲካፈል ፭ ይደርስና ፲፩ ይተርፋል፤ ይህን ቀሪ አበቅቴ አለው፡፡ ፯ በሰባት ሲባዛ ፵፱ ይኾናል (፯×፯ = ፵፱)፡፡ ፵፱ ለ፴ ሲካፈል (፵፱÷፴) ፩ ደርሶ ፲፱ ይቀራል፤ ይህን ቀሪ መጥቅዕ አለው፡፡ ዓመተ ዓለምን፣ ወንጌላዊን፣ ዕለትን፣ ወንበርን፣ አበቅቴን፣ መጥቅዕን፣ መባጃ ሐመርን፣ አጽዋማትን እና በዓላትን ለይቶ ለማወቅ ሒሳባዊ ሰሌቱ እንዲሚከተለው ነው፤ ዓመተ ዓለምን ለማግኘት ስሌቱ ዓመተ ኵነኔ ሲደመር ዓመተ ምሕረት ሲኾን፣ ውጤቱ ዓመተ ዓለም ይባላል፡፡ ለምሳሌ ፶፭፻ + ፳፻፲ = ፸፭፻፲ (5500 + 2010 = 7510)፤ ፸፭፻፲ (7510) ዓመተ ዓለም ይባላል፡፡ ወንጌላዊን ለማግኘት ስሌቱ ዓመተ ዓለምን ለአራት ማካፈል ነው፡፡ ዓመተ ዓለሙ ለአራት ተካፍሎ ፩ ሲቀር ዘመኑ ማቴዎስ፤ ፪ ሲቀር ማርቆስ፤ ፫ ሲቀር ሉቃስ፤ ያለ ቀሪ ሲካፈል ዮሐንስ ይኾናል፡፡ ዕለቱን (ለምሳሌ መስከረም ፩ ቀንን) ለማግኘት ስሌቱ ዓመተ ዓለም ሲደመር መጠነ ራብዒት (ለአንድ ወንጌላዊ የደረሰው) ሲካፈል ለሰባት ነው፡፡ ዓመተ ዓለም እና መጠነ ራብዒት ተደምሮ ለሰባት ተካፍሎ ፩ ሲቀር ማክሰኞ፤ ፪ ሲቀር ረቡዕ፤ ፫ ሲቀር ሐሙስ፤ ፬ ሲቀር ዓርብ፤ ፭ ሲቀር ቅዳሜ፤ ፮ ሲቀር እሑድ፤ ያለ ቀሪ እኩል ሲካፈል ሰኞ ይኾናል፡፡ ተረፈ ዘመኑን (ወንበሩን) ለማግኘት ዓመተ ዓለም ለሰባት ተካፍሎ የሚገኘው ቀሪ ተረፈ ዘመን (ወንበር) ይባላል፡፡ ከቀሪው ላይ ስለ ተጀመረ ተቈጠረ፤ ስላልተፈጸመ ታተተ (ተቀነሰ) ብሎ አንድ መቀነስ ስሌቱ ሲኾን ቀሪው ወንበር ይባላል፡፡ አበቅቴን ለማግኘት ወንበር ሲባዛ በጥንተ አበቅቴ (፲፩) ሲካፈል ለ፴ ኾኖ ቀሪው አበቅቴ ይባላል፡፡ መጥቅዕን ለማግኘት ወንበር ሲባዛ በጥንተ መጥቅዕ (፲፱) ሲካፈል ለ፴ ኾኖ ቀሪው መጥቅዕ ይባላል፡፡ ከዚህ ላይ አዋጁን (መመሪያውን) እንመልከት፤ አዋጁም መጥቅዕ ከ፲፬ በላይ ከኾነ መጥቅዕ በመስከረም ይውላል፤ የመስከረም ማግስት (ሳኒታ) የካቲት ይኾናል፡፡ ፲፬ ራሱ መጥቅዕ መኾን አይችልም፡፡ መጥቅዕ ከ፲፬ በታች ከኾነ በጥቅምት ይውላል፤ የጥቅምት ማግስት (ሳኒታ) ጥር ነው፡፡ መጥቅዕ ሲደመር አበቅቴ ውጤቱ ዅልጊዜ ፴ ነው፡፡ መጥቅዕ አልቦ (ዜሮ) ሲኾን መስከረም ፴ የዋለበት የቀኑ ተውሳክ መባጃ ሐመር ይኾናል፡፡ መባጃ ሐመርን ለማግኘት የዕለት ተውሳክ ሲደመር መጥቅዕ ሲካፈል ለሠላሳ ነው (የዕለት ተውሳክ+መጥቅዕ÷፴ = መባጃ ሐመር)፡፡ ቍጥሩ ለሠላሳ መካፈል ካልቻለ እንዳለ ይወሰዳል፡፡ የአጽዋማት እና የበዓላት ተውሳክ አወጣጥ ጾምን ለማግኘት ስሌቱ መባጃ ሐመር ሲደመር የጾም ተውሳክ ሲካፈል ለሠላሳ ነው (መባጃ ሐመር+የጾም ተውሳክ÷፴ = ጾም)፡፡ ቍጥሩ ለሠላሳ መካፈል ካልቻለ እንዳለ ይወሰዳል፡፡ በዓላትን ለማግኘት ስሌቱ መባጃ ሐመር ሲደመር የበዓል ተውሳክ ሲካፈል ለሠላሳ ነው (መባጃ ሐመር+የበዓል ተውሳክ÷፴ = በዓል)፡፡ ቍጥሩ ለሠላሳ መካፈል ካልቻለ እንዳለ ይወሰዳል፡፡ በዚህ ሒሳብ መሠረት በየዓመቱ የሚመላለሱ በዓላት እና አጽዋማት የሚዉሉበትን ቀን ማወቅ ይቻላል፡፡
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
661
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር Jump to navigationJump to search የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ (እንዲሁም በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት (ስድስት በአራት ዓመት) ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ (ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው) እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ። የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ 'አኖ ዶሚኒ' በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1 ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በትስብዕት ዘመን 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517 ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር (አኖ ዶሚኒ) አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የአኖ ዶሚኒ አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በአኖ ዶሚኒ 9 እ.ኤ.አ. ሆነ። የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም። በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ (Dionysius Exiguus) የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም ይላሉ ዶክተር ኣበራ ሞላ። [1] [2] [3] ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ (Anno Domini ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1 ፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር ያሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቈጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 X 28) ተደጋጋሚ ናቸው። [1][4]
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
662
የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓውያን ጋር ያለው ልዩነት መንስኤ እና ትክክለኛ መሰረቱ Published Posted on September 12, 2015 by Teshome Woldeamanuel | By TZTA News የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓውያን ጋር ያለው ልዩነት መንስኤ እና ትክክለኛ መሰረቱ እና ትክክለኛ መሰረቱ September 9th, 2015 by Satenaw ልዩ ጥንቅር ጉዳያች ጡመራ የዘመን መስፈሪያዎች እግዚአብሔር “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ፣ ለዕለታት፣ ለዘመናትና ለዓመታት ምልክት ይሆኑ ዘንድ» / ዘፍ.1. 14- 15/ የፈጠራቸውን የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴ መሠረት ያደረጉት መስፈሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህም፤ ሀ. ዕለት– አንድ ዕለት አንድ ቀንን /የብርሃን ክፍለ ጊዜን / እና አንድ ሌሊትን /የጨለማ ክፍለ ጊዜን/ ያካተተ ፀሐይ አንድ ጊዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን አንድ ዕለት ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ የምትሸከረከርበት ጊዜ ነው፡፡ ለ. ውርኅ– ወርኅ ማለት በግእዝ ጨረቃ ማለት ነው፡፡ አንድ ወርኅ የሚባለው ጊዜ ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን / በጥንቱም ጨምሮ/ ይህ ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዙራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ወር ሃያ ዘጠኝ ተኩል ዕለታትን ይፈጃል፡፡ ሐ. ዓመት– አንድ ዓመት ማለት መሬት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ ይህም 365 ከ1/4 / ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከሩብ/ ዕለታት ይፈጃል፡፡ይህ ከመታወቁ በፊትም ግን የዓመት ጽንሰ ሓሳብ ነበር፡፡ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ የፅንሰ ሐሳቡን አመጣጥ እንዲህ ያስረዳሉ፡፡ ሰዎች ርዝመታቸው እኩል የሆኑ ሁለት ሻማዎችን ሠሩና ልክ ፀሐይ ስትወጣ /ቀኑ ሲያልቅና ሌሊቱ ሲጀምር/ አንዱን ሻማ አበሩት፡፡ልክ ፀሐይ ስትወጣ እሱን አጠፋና ሌላውን / ሁለተኛውን/ ሻማ አበሩት፤ ጧት ፀሐይ እንደገና ስትወጣ / ሌሊቱ አልቆ ሌላ ቀን ሲጀምር/ ሻማውን አጠፉት፡፡ አሁን እንግዲህ ከየሻማዎቹ /ከሁለቱ ሻማዎች/ ምን ያህል እንደተቃጠለላቸው ሲያስተያዩት ከሁለቱ ሻማዎች የተቃጠለው እኩል አለመሆኑን ተመለከቱ በዚህም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ እኩል አለመሆኑን ተረዱ፡፡ ቀደም ብለውም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ በተለያዩ ወቅቶች የተለያየ መሆኑን ልብ ብለው ነበርና ይህንን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ በቀኑና በሌሊቱ ርዘማኔ / በሚቃጠለው የሻማዎቹ መጠን/ መካከል ያለው ልዩነት ከወቅት ወቅት የተለያየ እንደሆነ ተመለከቱ ይህን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ ግን በየ182 /ተኩል/ ዕለቱ ቀኑና ሌሊቱ እኩል የሚሆኑባቸው ሁለት ዕለታት በዓመት ውስጥ እንዳሉ ተገነዘቡ፡፡ እነዚህ ዕለታት አንዱ የሙቀት ወራት ከመጀመሩ በፊት የሌላው ደግሞ የቅዝቃዜው ወራት ከመጀመሩ በፊት የሚመጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት አንድ ጊዜ እኩል ሁኖ ደግሞ በዚያው ወቅት እኩል እስከሚሆን ድረስ ያለውን ጊዜ ማለትም / 182 ተኩል + 182 = 365/ ዕለት አንድ ዓመት አሉት፡፡ አሁን ባለን ግንዛቤ ምድር በራሷ ዛቢያ እንደተሽከረከረች በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች፡፡ ምድር በፀሐይ ዙሪያ የምትዞረው ወደ ጎን 23 ተኩል ዲግሪ ያህል አጋድላ ነው፡፡ ይህ የቀንና የሌሊት ርዝመት መለያየትም የሚከሰተው በዚህ ማጋደል ምክንያት ነው፡፡ እንግዲህ በአጠቃላይ ዋናዎቹ የጊዜ / የዘመን/ መስፊሪያዎች ዕለት፣ ወር እና ዓመት ናቸው፡፡ ሦስትቱም ተመላላሽ ክስተቶችን / ለምሳሌ የፀሐይን መውጣት/ መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚሀ ተመላላሽ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪከሰቱ የሚፈጁት ዘመን ወይም ጊዜ ዓውድ ይባላል፡፡ ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ እንደ ቀለበት ዙሮ የሚገጥም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዓውድ ማለት ክስተቶቹ አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪመጡ ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከላይ ያየናቸው ሦስት መስፈሪያዎች / ዕለት፣ ወርኀ፣ ዓመት/ ዓዕዋዳት / ዓውዶች/ የሚወጡበት ጊዜ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ወርኀ፣ ዓውደ ዓመት ይባላሉ፡፡ መጀመሪያ ላይ ሰዎች እነዚህን ሦስቱን መስፈሪያዎች /ዓዕዋዳት/ /በተለይም ቀንና እና ወርን/ ለየብቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡ ከዚህን ያህል ቀን፣ ከዚህን ያህል ወር በኋላ /በፊት/ እያሉ ጊዜን ይለኩ ነበር፡፡ እነዚህ ሦስቱን በቅንብር /በቅንጅት/ ለመጠቀም ሲፈለግ ግን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አንድ ወር 29 ከግማሽ ቀን ነው፡፡ እንዲሁ እንዳለ ለመቁጠር ቢፈለግ የመጀመሪያው ወር ጠዋት ላይ ቢጀመር ሁለተኛው ወር ምሽት ላይ ይጀምራል፣ ሦስተኛው ደግሞ ድጋሚ ጠዋት ላይ ይጀምራል፤ ይህን ለመቅረፍ ወሩን ሙሉ ሰላሳ ቀን ቢያደርጉት ከትክክለኛው ወር /የጨረቃ ዐውድ/ ግማሽ ቀን ይተርፋል፤ 29 ቀን ብቻ ቢያደርጉት ደግሞ ግማሸ ቀን ይጎድላል፡፡ አንድ ዓመት 365 ከሩብ ዕለታት አሉት፡፡ ዓመትን በወራት ለመቁጠር ቢፈለግ፤ ዓመቱን 12 ወር ቢያደርጉት የዓመቱ /የዕለታት ቁጥር /29.5X12=354/ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም ከትክክለኛው ዓመት /365-354=11/ ዕለታት ያህል ያንሳል፡፡ 13 ወር ቢያደርጉት ዓመቱ /365X13=385.5/ ቀናት ይሆናል ይህም ከትክክለኛው ዓመት /383.5-365=19/ ቀናት ያህል ይበልጣል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መስፈሪያዎች በቅንጅት ለመጠቀም ይህንን አለመጣጣም የሚፈታ ቀመር /የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት/ ያስፈልጋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የዘመን አቆጣጠሮች ተዘጋጅተዋል፡፡ የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 29 እና 30 ዕለታት ያሏቸው 12 ወራት አሏቸው፤ ተ.ቁ የአይሁድ ወራት የዕለታት ብዛት ወራቱ በእኛ 1 ኒሳን 30 መጋቢት/ ሚያዝያ 2 ኢያር 29 ሚያዝያ/ ግንቦት 3 ሲዋን 30 ግንቦት/ ሰኔ 4 ታሙዝ 29 ሰኔ/ ሐምሌ 5 አቭ 30 ሐምሌ/ ነሐሴ 6 አሉል 29 ነሐሴ/ መስከረም 7 ኤታኒም 30 መስከረም/ ጥቅምት 8 ቡል 29/30 ጥቀምት/ ኅዳር 9 ከሴሉ 30/29 ኅዳር/ ታህሳስ 10 ጤቤት 29 ታህሳስ/ ጥር 11 ሳባጥ 30 ጥር/ የካቲት 12 አዳር 1 29 የካቲት/ መጋቢት እነዚህ የዓመቱ 12 ወራት በአጠቃላይ 354 ያህል ብቻ ዕለታት ይኖሯቸዋል፡፡ ይህም በትክክለኛው ዓመት በ11 ዕለታት ያህል ቢያንስም አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ልዩነቱ በሁለት ዓመታት 22 ዕለታት፣ በሦስት ዓመት ደግሞ 33 ዕለታት ያህል ይሆናል፡፡ ስለዚህ በየሦስት ዓመቱ ከአስራ ሁለተኛው ወር ጳጉሜን በፊት አንድ ሌላ ወር ይጨምሩና ጨምረው የዓመቱን የወራት ቁጥር ዐሥራ ሦስት ያደርጉና ልዩነቱን ያስተካክሉታል፡፡ የኢትዮጵያውያንና የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የጥንት ግብጻውያን /ዛሬም ድረስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት በሀገር ደረጃ የምትጠቀም ኢትዮጵያ ብቻ ነች/ የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለታችንም እኩል ሰላሳ ቀናት ያሏቸው 12 ወራት አሉን፡፡ እነዚህ 12 ወራት / 12X30=360/ ቀናት አሏቸው እነዚህ ቀናት በትክክለኛው ዓመት በ/365.25-360=5.25/ ቀናት ያንሳሉ፡፡ ይህንንም 5 ቀናት / በ4 ዓመት አንድ ጊዜ 6 ቀናት/ ያሏትን 13ኛ ወር በመጨመር ያስተካክሉታል፡፡ የኢትዮጵያውያን እና የግብጻውያን ወሮች ስም እንደሚከተለው ነው፡፡ ተ.ቁ የግብጽ ወሮች የኢትዮጵያ ወሮች 1 ቱት/ዩት መስከረም 2 ባባ/ፓከር ጥቅምት 3 ሀቱር ኅዳር 4 ኪሃክ/ከያክ ታኅሣሥ 5 ጡባ/ቶቢር ጥር 6 አምሺር/ሜሺር የካቲት 7 በረምሃት መጋቢት 8 በርሙዳ ሚያዝያ 9 በሸንስ ግንቦት 10 ቦኩሩ ሰኔ 11 አቢብ ሐምሌ 12 መስሪ ነሐሴ 13 ኒሳ/አፓጎሜኔ ጳጉሜን /ባሕረ ሐሳብ፣ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ፣ገጽ.65/ የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር ኢትዮጵያዊ ነው ከሌላ የተቀዳ አይደለም የኢትዮጵያ እምነታዊ ባህል የሚወረሰው በሦስት ዐይነት ጠባይ ነው። አንዱ ሕገ ልቡና ይባላል። ከመጽሐፍ በፊት የነበረ ነው። ከአበውቃል በቃል የተወረሰ ነው። ሁለተኛው በሕገ ኦሪት ከኦሪት የተቀዳ ነው። ሦስተኛው በሕገ ወንጌል ከወንጌል የተማርነው ነው። እናበሦስት ዐይነት ጠባይ የሚመራ ነው። በዚህ ዐይነት ከወረስናቸው በዓላት ማለት በሦስቱም ጠባያት ከወረስናቸው በዓላት የየራሳቸውመልክ ያላቸው አሉ። ለምሳሌ ልደት፥ ጥምቀት፥ ዕርገት፥ ደብረ ታቦር እነዚህን የመሳሰሉት ከወንጌል የተማርናቸው ናቸው፤ በብሉይየሉም። ፋሲካ፥ በዓለ ጰራቅሊጦስ ደግሞ ከኦሪት የተማርናቸው ናቸው። የዘመን መለወጫ በዓል ግን ከሕገ ልቡና ቃል በቃል ተምረን፥በኦሪት የመጽሐፍ መሠረት አግኝተንለት በወንጌልም አጽንተን ይዘነው የኖርነው ሦስት የሥራ ዘመን ክፍል የተላለፈና እዚህ የደረሰ ነው።እኛ የዘመን መለወጫ ብለን በሀገራችን ባህል የምናከብረው ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር የተገኘበት፥ ብርሃን፥ ጊዜ፥ ዕለት፥ ሰዓትየተፈጠሩበት፤ ለብርሃን፥ ለጊዜ፥ ለዕለት፥ ለወር ለዓመት ጥንት መሠረት የሆነ ቀን ነው። ይህንን ሁሉ በማስገኘት እግዚአብሔር ራሱንየገለጠበት፥ ዓለምን በመፍጠር ከሃሊነቱን ያረጋገጠበት ቀን ነው ብለን ነው የምናከብረው። ስለዚህም ጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዕለት፥ ጥንተጊዜ፥ ጥንተ ፍጥረት ርእሰ ዐውደ ዓመት ብለን ነው የምናከብረው። በዚህ ስያሜ በዓሉ ርእሰ ዐውደ ዓመት፥ ቅዱስ ዮሐንስ፥ የዘመንመለወጫ ብለን እናከብረዋለን። ቅዱስ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ በዓል ሌላው ስሙ ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል። ቅዱስ ዮሐንስ የሚባልበትም ሁለት ጠባይ አለው። አንዱ፤መጥምቁ ዮሐንስ በሄሮድስ አንቲጳስ ጊዜ ከጳጉሜን ፩ ቀን ጀምሮ ታስሮ ሰንብቶ በመስከረም ፩ ቀን ዐሳብ ስለ ተቆረጠበትና በመስከረም፪ ቀን እንዲሞት ውሳኔ ስለ ተሰጠበት አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ስለ ሞተ ሊቃውንት ይህንን በዓል እሱ ራሱ ለኦሪትና ለወንጌል መገናኛመምህር ስለ ነበረ ይህም በዓል ላለፈው ዘመን መሸኛ፥ ለሚመጣው ዘመን መቀበያ እንዲሆን ብለው በመስከረም ፩ ቀን እንዲከበርስላደረጉ በሱ ስም ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል። በሁለተኛው ግን ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ ወንጌላዊ ዮሐንስ የተሰየመበት ስለሆነ በአቆጣጠርም ተራ ወደ ኋላ ተመልሶ ቢቈጠር ዓለም የተፈጠረበት ዘመን በዘመነ ዮሐንስ እንዳጋጣሚ ሆኖ ስለሚገኝ ቅዱስ ዮሐንስተብሎ ይጠራል። ዕንቍጣጣሽ በዚያም ጊዜ የነበሩ ኖኅና ልጆቹ ሰማዩ በደመና በመክበዱ ምክንያት ማየ አይኅ እንደገና ይመጣ ይሆን፥ የጥፋት ውሃ እንደገና ይዘንምይሆን እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ስላዩ፥ ምድር በአበባ አሸብርቃ ስለ ተገለጠችናበዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት፥ የቃል ኪዳኑን መጽናት ስለ ተረዱ ይህንን በዓል ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ያው ጥንተብርሃን፥ ጥንተ ዓመት፥ ጥንተ ዕለት አድርገው አክብረውታል። ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፥ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕትይሠዉነት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር ገጸ በረከት አቅርበው ከዚያ በኋላ ግን እርስ በርሳቸው የአበባ ስጦታ በመለዋወጥአክብረውታል። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል እውነት የመልካም ሞኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር። ዕንቍጣጣሽ ማለትንምብዙ ታሪክ ጸሓፊዎች በልዩ ልዩ መልክ ተርጕመውታል። እንዲያውም ንጉሡ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የዕንቍ ቀለበት ሰጥቷት ነበርና“ዕንቍ ለጣትሽ» ማለት ነው ብለው የጻፉ ብዙ ሰዎችም አሉ፤ የሚናገሩም አሉ። ነገሩ ግን እንዲህ አይደለም። ዕንቍጣጣሽ ማለትተንቈጠቈጠ፥ አንቈጠቈጠ ከሚለው ቃል ተወስዶ ምድር በአበባ አጌጠች፥ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ እንደ ማለት ሰማይንበከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው እንጂ ስለ ሳባ ንግሥት የተሰጠ አይደለም።ሁለተኛም አባቶቻችን ኢትዮጵያን በሙሉ ሀብት ተረክበዋት ነበርና፤ “ዕንቍ ዕጣ ወጣሽ፤» ሲሉ ወደ አገራቸው ሲገቡ ለአገራቸውመታሰቢያ አድርገው የተጠቀሙበት ቃል ነው ይባላል። በመሠረቱ ግን ያ የጥፋት ውሃ ቀርቶ ምድር ጸንታ፥ አበባ ቋጥራ፥ ፍሬለመስጠት ተዘጋጅታ መገኘቷን የሚያበሥር ቃል ነው። መስከረም መስከረም የሚባለው ወርም ኖኅ በመርከብ ውሥጥ በነበረ ጊዜ እንደ ዕብራውያን አቈጣጠር ሰባተኛ በሆነው በመስከረም ወርመጀመሪያ ላይ መርከቢቱ አራራት ከሚባለው ተራራ ላይ ዐርፋ ምድር ጨብጣለች። በግእዝ ቋንቋ መርከብ መስቀር ይባላል። ከዘመንብዛት በኋላ “ቀ» ወደ “ከ» ተለውጦ መስከረም ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፥ መርከብም ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የወሩስያሜ ነው። ርእሰ ዐውደ ዓመት የምንለው፤ ዐውድ ማለት በግእዙ ቋንቋ ዙሪያ፥ ክብ የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ ቀኖች መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉትሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታትኀምሳ ሁለት ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል። ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፥ የደቂቃ፥ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ ሦስት መቶ ስድሳዐምስተኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ይህቺ ቀን እንግዲህ ዙሪያ፥ ክብ መግጠሚያ ናት ማለት ነው። በዚህች ቀን አማካይነትወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ እንተላለፋለን። ይህቺ ቀን ዕለት አዕዋዲት፥ ዕለተ ምርያ የመዘዋወሪያ ቀን ወይም የመጨረሻ ቀን ተብላትጠራለች። በአራት ዓመት ደግሞ ከዚህች መሳሳብ የምትገኝ አንዲት ቀን ትመጣለች። ሦስት መቶ ስድሳ ስድስተኛ። ይህቺ ቀን ዕለተሰግር ትባላለች። መረማመጃ ማለት ነው። አንድ ቀን ታስተላልፋለች። እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች ተከትሎ የሚመጣው ቀንየዘመን መጀመሪያ፥ የዘመን ክብ መነሻና መድረሻ ተብሎ ርእሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ በግእዙ ይጠራል። እነዚህ ቀኖች በኢትዮጵያውያንአቆጣጠር ተጠቃለው አንድ ጊዜ የሚገኙ ናቸው። የኢትዮጵያ ቍጥር መሠረቱ የመፅሐፍ ቅዱስ አካል የሆነው መጽሐፈ ሔኖክ ነው። መጽሐፈ ሔኖክ በ፲፱፥ ፳፥ ፳፩ እና ፳፪ ምዕራፎችየሚሰጠን የፀሐይን፥ የጨረቃን ጉዞ መነሻ አድርጎ የወሮችን፥ የዕለታትን፥ የዓመታትን መነሻ፥ መድረሻ፥ መዘዋወሪያ ብተታቸውን፥ጥንታቸውን ነው የሚያሳየው። ስለዚህም በሔኖክ ቍጥር የወር ቀኖች ቍጥር ሠላሳ ናቸው። በሦስት በሦስት ወር ግን አንድ ቀንትከተላቸዋለች። እና ዓመቱ ለአራት ይከፈላል። በዘጠና አንድ በዘጠና አንድ ቀን። ጠቅላላው ይሄ ድምር ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት ቀንይመጣል። ይህ ካለቀ በኋላ አንዲት ቀን ለዘመን ማገጣጠሚያ ዕለተ ምርያ የምትባለው ትመጣለች። እንግዲህ በኢትዮጵያውያን ቍጥርወሩ ከሠላሳ አያንስም፤ ከሠላሳ አይተርፍም። ለዓመቱም ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ቀን መደበኛው አቆጣጠር ነው ማለት ነው። ይህ ነገርበአውሮፓውያን ቍጥርም አለ። ግን እነሱ ከዓመት ወሮች ሰባቱን ሠላሳ አንድ ሠላሳ አንድ አድርገው አራቱን ደግሞ ሠላሳ ሠላሳአድርገው አንዷን ወር ሦስቱን ዓመት ሃያ ስምንት፥ በአራተኛው ዓመት ሃያ ዘጠኝአድርገው ያጣጧታል። እንግዲህ የአቀማመጡ ለውጥ ካልሆነ በስተቀር በቍጥር አካሄድ ዞሮ ዞሮ የዓመት ቀኖች ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ወይም ሦስት መቶስድሳ ስድስት በመሆን አንድ ሆነዋል ማለት ነው። ልዩነቱ ግን የአቀማመጥ ለውጥ ነው። በኢትዮጵያ አቈጣጠር ግን ጠቅላላውን ፲፪ወሮች መደባቸው ሠላሳ ብቻ ነው። እነዚያ በሔኖክ መጽሐፍ በጣልቃ ገብነት የነበሩት አራት ቀኖች ተጠቅለው ጳጉሜን በሚባልበዓመቱ መጨረሻ ላይ ተገኝተዋል። ዐምስተኛዪቱ ቀንም ከእነሱ ጋር ተገኝታለች። ይህም ለቍጥር ተራ ቅምር መቅናት የተደረገ እንጂቀኑን የሚለውጥ ምንም ነገር የለበትም። እና ከእነዚህ ቀኖች በኋላ የምናገኘው ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመት ይባላል። ይህንን በዓል ከአዳምጀምሮ እስከ ኖኅ ድረስ የነበሩ ዐሥሩም አበው በዐሥሩ ትውልድ እስከ ማየ አይኅ ድረስ ሲያከብሩት እንደ ቆዩና ኋላም የኖኅ ልጆችከአባታቸው ተቀብለው ሲያከብሩት እንደ ነበረ ኩፋሌ የተባለው መጽሐፍ በምዕራፍ ፯ ያስረዳናል። እንግዲህ ኢትዮጵያ ይህንን ቀንየወረሰችው ከአበው ነው የምንለው በዚህ ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከሌሎቹ የሚለይባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች እናከኢትዮጵያውያን እና አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ትክክለኛው የቱ ነው? ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ የዘመን አቆጣጠር መለያየትን መነሻ እንዲህ በማለት ያብራራሉ፤ “ክብ የሆነ ነገር ሲከብ ከየትኛውም ቦታ መጀመር ይቻላል፤ የዘመን አቆጣጠር /ዓውደ ዓመትም/ ይኸው ነው፡፡ ዋናው ነገር አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ ነው፤ የዘመን አቆጣጠሮቹም ልዩነት መንስኤው ይኸው ነው» ይላሉ፡፡ ባሕረ ሐሳብ፣ ጌታቸው ኃይሌ፣ ገጽ.65/ ለምሳሌነትም ሮማውያን የሮም ከተማ የተቆረቆረችበትን ጊዜ መነሻ ማድረጋቸውን/ በኋላም ታላቁ እስክንድር የነገሠበት ዘመን የዘመን ቆጠራ መነሻ ሆነው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ መሐመድና ተከታዮች ከመካ ወደ መዲና ያደረጉትን ስደት መነሻ የሚያደርገው ኢስላማዊ የዘመን አቆጣጠርም ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡ የአይሁድን አቆጣጠር ትተን ከላይ ያየናቸው ሁለቱ የዘመን አቆጣጠሮች /የምዕራባውያኑ የጁልየስ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርና የኢትዮጵያና የግብጽ አቆጣጠር/ ሁለቱም ዘመንን የሚቆጥሩት ከክርስቶስ ልደት መነሻ አድርገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ ዛሬ 2008 ዓ.ም ነው ስንል እነርሱ ደግሞ 2015 ዓ.ም ነው ይላሉ፡፡ በመካከሉ የ7 ዓመታት ልዩነት አለ፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ትክክለኛው የትኛው ነው? የሚለው ነው፡፡ ጉዳዩ መጻሕፍትን ሊያጽፍ የሚችልና በእርግጥም የተጻፉበት ቢሆንም ለማሳያ ያክል ሁለት ነገሮች እንመልከት፤ 1. አሁን ባለው የምዕራባውያን አቆጣጠር ከሄድን ሄሮድስ የሞተው 4 ዓመት ቅ.ል.ክ (ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ነው፡፡ ሄሮድስ የሞተው ጌታ ተወልዶ በስደት ሦስት ዓመት ያህል በግብጽ ከቆየ በኋላ ነው፡፡ ይህ ማለት በእርሱ አቆጣጠር ጌታ የተወለደው በ7 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ጌታ በትክክል በተወለደበት በአንድ ዓ.ም እነርሱ ጌታ ሰባት ዓመት ሆኖታል ይላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት አሁን ካላቸው ቁጥር ላይ ሰባት ዓመት መቀነስ አለባቸው፡፡ 2. ፍላቪየስ ጆሴፈስ የተባለው የአይሁድን ታሪክ የጻፈው ሊቅ እንደመሰከረው ጌታ የተወለደበት ዓመት ነው ተብሎ በወንጌል ላይ የተጻፈው የቆጠራ ዓመት /ሕዝቡ ሁሉ የተቆጠረበትን ዘመን /ሉቃ.2.1/ በጎርጎሪያን ዘመን አቆጣጠር “7 ዓመተ እግዚአ /A.D/ ላይ ነው፡፡» በማለት መረጃ ትቶልናል ይህ ማለት ደግሞ ከምዕራባውያኑ ዘመን አቆጣጠር ላይ 7 ዓመቶች የግድ መቀነስ አለበት ማለት ነው፡፡ ያ ሲደረግ ደግሞ የኛን ዘመን አቆጣጠር ያመጣል፡፡ የዘመን መለወጫ ቀን ልዩነት ሁለተኛው ጉዳይ የዘመን መለወጫ ወርና ዕለት ልዩነት ነው፡፡ እኛ መስከረም 1 አዲስ ዓመት ስንጀምር እነርሱ በ January 1 / በእኛ ታኅሣሥ 23/ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ከየት የመጣ ልዩነት ነው? የእኛ እና የግብጻውያን አቆጣጠር እዚህ ጉዳይ ላይ ከአይሁድ አቆጣጠር ጋር ይስማማል፡፡ በአይሁድ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ኒሳን የሚባለው /በእኛ መጋቢት/ ሚያዝያ/ ነው፡፡ “ይህ ወር የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፣ በዚህም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የአንድ ዓመት ተባዕት ላይ ወስደው ይረዱ፡፡ . . .»/ዘፀ.12.1-14/ ተብሎ የተሰጣቸውን የፋሲካ በዓል የሚያከብሩት በዚህ ወር ነው፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ የዓመት በዓል አድርገው የሚያከብሩት “የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁናችሁ፡፡ በዚሁ በመለከት ድምጽ የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ መስዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑበት» /ዘሌ.13.23-25/ ተብሎ የተሰጣቸው የሮሽ ሆሻና፣/የመለከት በዓል ወይም በዓለ መጥቅዕ/ ተብሎ የሚጠራው በዓል ነው፡፡ ይህም ማለት አዲስ ዓመት የሚያከብሩት በሰባተኛው ወር በኢታኒም ወር /በእኛ መስከረም ጥቅምት/ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችንም ትምህርት ዓለም የተፈጠረው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ መስከረም ደግሞ ከመጋቢት ጀምሮ ሲቆጠር ሰባተኛው ወር ነው፡፡ ይህም ከአይሁድ ዘመን አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አይሁድስ ቢሆኑ የመጀመሪያው ወር እያለ አዲስ ዓመትን ለምን በሰባተኛው ወር ያከብራሉ ለሚለው ጥያቄ ሁለት ዓይነት ምላሾች /ምክንያቶች/ ይሰጣሉ፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት “ሰባተኛው ወር ኖኅ ከመርከብ የወጣበት ወር በመሆኑ ይህ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ተደርጎ መከበር በመጀመሩ ነው» የሚል ነው፡፡ በዘመን መለወጫ ዕለት ልጃገረዶች አበባ እና ለምለም ሣር መያዛቸው ርግቢቱ ለኖኅ ካመጣችው ለምለም ወይራ /ቄጠማ/ ጋር ተያይዞ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ መስከረም የቀንና የዕለቱ ርዝመት እኩል የሚሆኑበት ወር በመሆኑ ነው የሚል ነው፡፡ የመስከረም 1 ቀን ስንክሳር “የተባረከ የመስከረም ወር የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው፤ የቀኑ ሰዓትም ከሌሊቱ ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው» ይላል፡፡ እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባው ሌላው ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ትምህርት እመቤታችን ጌታን የጸነሰችው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ጳዉሎስ ፣የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ተወለደ» /ገላ.4.4/ እንዳለው የ5500 ዘመኑ ፍጻሜ /ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ/ ነው፡፡ ጽንሰትን መጋቢት 29 ካልን በኋላ ልደትን ታህሣሥ 29 ቀን እናከብራለን፡፡ ከመጋቢት 29 እስከ ታህሣሥ 29 ድረስ 9 ወር ከ5 ቀን ነው፡፡ /ጳጉሜን ጨምሮ/፡፡ ጳጉሜ 6 በምትሆንበት ጊዜ ደግሞ ታህሣሥ 28 ቀን ልደት ስለሚከበር አሁንም በመሐሉ ያለው ጊዜ 9 ወር ከአምስት ቀን ይሆናል፡፡ ማጠቃለያ በመጨረሻም የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ፍፁም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሚቆጥር መሆኑን እንጂ እንደ ዘመኑ ነገስታት ፍላጎት በታሪክ ክስተትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ከተረዳን ይህንን ሃሳባችንን የሚያጠናክርልን የሳምንታንት እና የወራት ስያሜዎቻችንን እንዲሁም የልሎቹ የቀን አቆጣጠር ምንጭን ከ እዚህ በታች ባሉት ሰንጠረዦች እንመልከት።ለምሳሌ እነኚህ የሳምንታንት ልዩነቶች አውሮፓውያን ከጥንት ከነበረ አምልኮት ጋር የትዛመደ ሲሆን የእኛ ግን እግዚአብሔር አለምን መፍጠር ከጀመረ የመጀመርያ ቀን ስንል እሁድ ማለታችንን ሁለተኛ ቀን ስንል ሰኑይ (ሰኞ) ማለታችንን ወዘተ እንረዳለን። ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም አሮጌው ዘመን 2006 ዓም ተጠናቆ አዲሱን 2007 ዓም ልንቀበል ሰዓታት ቀርተውናል። የሮማ ካቶሊክ ፓፓ ቤኔዲክት 16ኛ ”የናዝሬቱ እየሱስ” በተሰኘ መፅሐፋቸው አሁን አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት የክርስቶስ የልደት ዘመን ትክክለኛ እንዳልሆነ ሲገልጡ እንዲህ ብለዋል-“The calculation of the beginning of our calendar—based on the birth of Jesus—was made by Dionysius Exiguus, who made a mistake in his calculations by several years,” ”ከጅምሩ የቀን አቆጣጠራችን ክርስቶስን ተወለደ ያለበት ዘመን መሰረት (በእክስጉሥ የተቀመረው) የብዙ አመታት የስሌት ስህተት አለው” ብለዋል። (http://www.charismanews.com/world/34714-pope-says-jesus-birth-date-is-wrong) ይህ ከአንድሚልዮን ኮፒ በላይ እንደተሸጠ የተነገረው መፅሐፍ ላይ ፓፓው ይህንን ይበሉ እንጂ ስህተቱን ለማረም እና ወደ ትክክለኛው ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለመምጣት የደፈረ እስካሁን አልታየም።ወደፊት ግን ይጠበቃል።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
663
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ (እንዲሁም በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11 ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት (ስድስት በአራት ዓመት) ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ (ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው) እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ። የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ 'አኖ ዶሚኒ' በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1 ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በትስብዕት ዘመን 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517 ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር (አኖ ዶሚኒ) አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የአኖ ዶሚኒ አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በአኖ ዶሚኒ 9 እ.ኤ.አ. ሆነ። የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም። በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ (Dionysius Exiguus) የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም ይላሉ ዶክተር ኣበራ ሞላ። [1] [2] [3] ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ (Anno Domini ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1 ፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር ያሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቈጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 X 28) ተደጋጋሚ ናቸው። [1][4] ወራት የወራት አቆጣጠር የተወረሰ ከቅብጢ ዘመን አቆጣጠር፣ ይህም የወጣ ከጥንታዊ ግብጽ ዘመን አቆጣጠር ነው። ሆኖም የወሮች ስሞች በግዕዝ ተለውጠዋል። አማርኛ ጎርጎርዮስ በሰግር ዓመት መስከረም ሰፕቴምበር 11 ሰፕቴምበር 12 ጥቅምት ኦክቶበር 11 ኦክቶበር 12 ኅዳር ኖቨምበር 10 ኖቨምበር 11 ታኅሣሥ ዲሰምበር 10 ዲሰምበር 11 ጥር ጃንዋሪ 9 ጃንዋሪ 10 የካቲት ፈብርዋሪ 8 ፈብርዋሪ 9 መጋቢት ማርች 10 ማርች 10 ሚያዝያ ኤፕሪል 9 ኤፕሪል 9 ግንቦት ሜይ 9 ሜይ 9 ሰኔ ጁን 8 ጁን 8 ሐምሌ ጁላይ 8 ጁላይ 8 ነሐሴ ኦገስት 7 ኦገስት 7 ጳጉሜ ሰፕቴምበር 6 ሰፕቴምበር 6 ዘመነ ማቴዎስ ዘመነ ማርቆስ ዘመነ ሉቃስ ዘመነ ዮሀንስ የውጭ መያያዣዎች ቀን መለወጫ ኣበራ ሞላ የኢትዮጵያ ዘመን ኣቈጣጠር An Open Letter to His Holiness Pope Benedict XVI በዶ/ር ኣበራ ሞላ ^ ኣበራ ሞላ 1656 1656 አመተ ምኅረት የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር አመት ነበር። በጎርጎርያን ካሌንዳር የ1663 እ.ኤ.አ. መጨረሻና የ1664 እ.ኤ.አ. መጀመርያ ይቆጠራል። በዚሁ ዓመት እንግሊዞች ኒው አምስተርዳም («አዲስ አምስተርዳም») አሜሪካዊ ቅኝ አገር ከሆላንድ ያዙትና ስሙን ወደ ኒው ዮርክ («አዲስ ዮርክ») ቀየሩት። ባህረ ሀሳብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውሃዶ ቤ/ክ በብችኝነት ከምትታወቅባቸው ኣንደ የራስዋ የሆነ የዘመን ኣቆጣጠር ወይም ባሕረ ሐሳብ መነርዋ ነው። ይህውም ከዓለም የተለየች እንድትሆን ኣስችሏታል። ይህም ባሕረ ሐሳብ ለድሜጥሮስ በገለጸለት መሰረት በየጊዜው በተነሱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቷዋል። በኣሁኑ ወቅት ዘመኑ የመረጃ ዘመን በመሆኑና ሊቃውንቱ ሳያልፉ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም መስራት ከሚኖርብን ኣያሌ መንፈሳውያን ስራዎች ውስጥ ባሕረ ሐስብ አንዱ ነው። ምክንያቱም የአሁኑ ትውልድ በቀላሉ ሊረዳው ባለመቻሉ ማወቅና መረዳት እየፈለገ ከቁጥሩ ስሌት ረቂቅነት ኣንፃር ብዙ ሲቸገር ይታያል። ስለሆነም በዚህና በተመሳሳይ ጽሁፎች የተቻለንን ለማሳወቅ እንሞክራለን። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ-አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች። የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ ፲፱፻፷፯ (1967) ዓ.ም.፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት (African Union) እና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ የእራሷ ጥንታዊ ፊደል ያላት ሀገርም ናት። ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። ሶፍ ዑመር ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ ዳሎል ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም ኦሮሞና አማራ በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የቡና ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና ማር አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች። ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትናን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሁለተኛው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ነው። የመጀመሪያው የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። ነጋሽ በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ ቤተ-እስራኤሎች በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት። ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የናይል(ኣባይ) ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ነገር ግን ቀስ በቀስ ሀገሩዋ እያገገመች ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ውስጥ በፍጥነት ከሚያድጉት አንዱ ነው። ኣበራ ሞላ ዶ/ር ኣበራ ሞላ (መጋቢት ፳፬ ቀን ፲፱፻፵ ዓ.ም.) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ መናገሻ ኣውራጃ፣ በረህ ወረዳ፣ ሰንዳፋ ከተማ የተወለዱ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ዶክተር ኣበራ ሞላ የታወቁባቸው ዋናዎቹ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው። የመድንን ማነስ በማስወገድ ከዓለም የእንስሳት ሓኪሞች ኣንዱ ታዋቂ ምሁር፣ የግዕዝ ፊደል በኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ውስጥ በኣለውም መጠቀም እንዲቻል የኣደረጉ ሰባት የዩናይትድ እስቴትስና ኢትዮጵያ ፓተንቶች ብቻቸውን የኣሏቸው የግኝት ሊቅና የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጣልያንን በማስፈራራት ወሳኙን እርምጃ የወሰዱ ኣርበኛ ናቸው። [1] [2] [3] [4] [5] [6] [7] [8] [9] [10] [11] [12] [13] ዶክተሩ የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ቀለሞችና የግዕዝ ኣሥር ቤት ኣኃዛዊ ቍጥሮች ፈጣሪም ናቸው። [14] [15] ዓክልበ. ዓክልበ. (ዓመቶች ከክርስቶስ ልደት በፊት) ወይም ክ.በ. (ከክርስቶስ በፊት) ወይም ቅ.ል.ክ. (ግዕዝ፣ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ማለት ከ1ኛው ዓመተ ምሕረት (ዓ.ም.) አስቀድሞ የነበሩት ዓመቶች የመቆጠሪያ ዘዴ ነው። 1 ዓ.ም. የዓመተ ምህረት መጀመርያ ዓመት እንዲሆን የወሰነው መኖኩሴ አኒያኖስ እስክንድራዊ ተባለ። የፈረንጅ አቆጣጠር ግን የአኒያኖስን ሳይሆን የሌላውን መነኮሴ የዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ቁጠራ በመከተሉ፣ ዓመቱ 1 እ.ኤ.አ. ከዚያው 8 ዓመታት በፊት (ወይም በ8 ዓክልበ.) ይጀመራል። የአሁኑ መምህራን ደግሞ ኢየሱስ የተወለደበት ዓመት 12 ዓክልበ. ግድም እንደ ሆነ የሚል ግምት አላቸው። በዚሁ አቆጣጠር ዘዴ ዓመቶቹ ወደፊት እየሄዱ ቁጥራቸው ይቀነሳል። ስለዚህ 3000 ዓክልበ. ከ2000 ዓክልበ. በፊት ሆነ፣ ይህም ከ1000 ዓክልበ. በፊት ነበር። አንዳንዴ ይህ የመቆጠር ዘዴ በስሕተት «ዓ.ዓ.» (ዓመተ ዓለም) ይባላል። በትክክል ዓመተ ዓለም (ሮማይስጥ፦ Anno Mundi) ግን ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ የሚቆጠር ዘዴ ስለሆነ፣ ዓመቶቹ ወደፊት እየሄዱ ቁጥራቸው ይበዛል። 1000 ዓ.ዓ. ከ2000 ዓ.ዓ. በፊት፣ 2000 ዓ.ዓ. ከ3000 ዓ.ዓ. በፊት ደረሰ ማለት ነው። ደግሞ ይዩ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዕንቁጣጣሽ ዘመነ ማቴዎስም፣ ዘመነ ማርቆስም፣ ዘመነ ሉቃስም ሆነ ዘመነ ዮሐንስ፤ በአራቱም ዘመናት አስቀድሞ ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ ይዘከራል፡፡ ዮሐንስ የስሙ ትርጉም «ጸጋ እግዚአብሔር» ማለት ነው፡፡ ዘመናት ዘመናትን እየወለዱ፣ ሰዓታት ደቂቃን ቅጽበትን /ሰኮንድን/ ሳይቀር እየሰፈሩ/እየቆጠሩ/ ዕለታት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን አሁን ላለንበት ዘመን ደርሰናል፡፡ ዓውደ ዓመት በግእዝ ሲሆን በአማርኛ የዘመን መለወጫ/ ቅዱስ ዮሐንስ፣ ዕንቁጣጣሽ እየተባለም ይጠራል፡፡ የቀን መቁጠሪያ የቀን መቁጠሪያ ወይም ካሌንዳር ማለት አንድ ድርጊት የተፈጸመበት ቀን፣ ወር ወይም አመት ወዘተ. በቅደም-ተከተል ለማወቅ የሚጠቀም ዘዴ ነው። እንዱሁም ወደፊት ለሚሆኑ ድርጊቶች ለመዘጋጀት ወይም ለማቀድ የሚጠቀም መሣርያ ነው። በታሪክ ላይ እንደ ባሕሎቹ ልዩነት ብዙ ልዩ ልዩ ዘዴዎችና ለውጦች ተፈጽመዋል። የዓመትና የወሮች አከፋፈል ባጠቃላይ በፀሐይ ወይንም በጨረቃ ረገዶች በጠፈር ውስጥ ከመሬት ላይ ሲታዩ በሚሉ አከፋፈሎች ነው። ፀሐይም በመሃሉ ቢታይ፣ መሬት በየወሩ 1/12ኛ ያሕል ምኋር ይጓዛል። በሰዓት መልክ ላይ እንደ መሠለ፣ ከ#1 እስከ #12 ክፍሎች በመሃሉ ዙሪያ ተካፍለዋል፤ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ምድሪቱ አንድ መላ ክብ ምኋር ታደርጋለች። ክረምትና በጋ፣ ሌሎችም ወራቶች ሁልጊዜ በአመቱ ውስጥ በተጠበቀው ጊዜ እንዲመጡ ያገለገለ መለኪያ ነው። የቀን፣ የሳምንትና የወር አከፋፈል ይሁንና የዓመታት አቆጣጠር ደግሞ በየባሕሉ ወይም በየዘዴው ይለያያል። ለምሳሌ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2010 ዓመተ ምኅረት ሲሆን፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ይህ በከፊል 2017 እ.ኤ.አ. እና 2018 እ.ኤ.አ. ነው። እስከ አሁን ድረስ በአለም ውስጥ በርካታ የጊዜ መቁጠሪያዎች ይገኛሉ፣ ለምሳለ፦ የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ጎርጎርያን ካሌንዳር የቻይና አመት መቁጠሪያ ጥቅምት ፬ ጥቅምት ፬ ቀን የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፴፬ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ ፍጻሜ ድረስ፤ በዘመነ ሉቃ ፫፻፴፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፩ ዕለታት ይቀራሉ።
[ 113 ]
[ "የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር" ]
[ "ስለኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የሚያትቱ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ስሌት, የበአላት ቀናት የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ሌሎች ሀገሮች የቀን አቆጣጠር የሚገልጹ ሰነዶች ጠቃሚወች አይደሉም፡፡" ]
664
የቱሉ ቦሎ ምጥን ማዳበሪያ ፋብሪካ ተመረቀ, .._2014. 0 261 196 ; 5; አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2006 (ዋኢማ) - የቱሉ ቦሎ ምጥን ማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተመረቀ። የፋብሪካው አጠቃላይ ግንባታ 31 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የፈጀ ሲሆን ፥ በዓመት 1 መቶ ሜትሪክ ቶን ምጥን ማዳበሪያ ያመርታል። ከዚህ ቀደም ከውጭ የሚመጣው ዳፕና ዩሪያ ማዳበሪያ የሚይዘው ንጥረ ነገር ውስን የነበረ ሲሆን ፥ የቱሉ ቦሎ ምጥን ማዳበሪያ ፋብሪካ የሚያመረተው ማዳበሪያ በውስጡ ከ10 በላይ ንጥረ ነገሮችን ያቀፈ በመሆኑ ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ያደረጋል ተብሏል። ለዚህም በ225 ወረዳዎች የአፈር ጥናት ምርምር ሲካሄድ መቆየቱም በምርቃቱ ወቅት ተገልጿል። በተያያዘ በትግራይ ፣ በአማራና በደቡብ ክልሎች ሶስት የምጥን ማዳበሪያ ፋብረካዎች ወደ ስራ በማስገባት ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል። (ኤፍ.ቢ.ሲ) ),
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
665
ክልሉ ለ200708 ዓ.ም የምርት ዘመን 3 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ እያሰራጨ ነው, - ; .._2015_3. 0 261 154 ; 5; አዲስ አበባ ፣ የካቲት 242007 (ዋኢማ) - በአማራ ክልል ለ200708 ዓ.ም የምርት ዘመን የሚያገልግል 3 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ማከፋፈል መጀመሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። - ; የቢሮው የሰብል ልማት ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ስራ ሂደት ባለቤት ዶክተር ሺመላሽ የሻነህ ለዋልታ እንደገለጹት ለአርሶ አደሩ እየተከፋፈለ ያለው ማደበሪያ ዩሪያና የሰልፈር ማዳበሪዎች ናቸው። - ; በዘንድሮው የምርት ዘመን ጥቅም ላይ ከሚውለው ማዳበሪ ውስጥ 1ነጥብ5 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ እንደሚሆን አስረድተዋል። - ; ከዚህ በፊት አርሶ አደሮች ይጠቀሙበት የነበረው ዳፕ ማዳበሪያ ምርትና ምርታማነት ላይ ያለው ውጤቱ አነስተኛ መሆኑ በጥናት በመረጋገጡ በዘንድሮው ዓመት ጥቅም ላይ እንዳማይውልና በሰልፈር ማዳበሪያ እንደሚተካ አስታውቀዋል። - ; ባለፈው ዓመት ለአርሶ አደሩ ከተሰራጨው ግማሽ ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ውስጥ ሰልፈር ያለበት ማዳበሪያ ጥቅም ላይ መዋሉንና ውጤታማ በመሆኑ በተጠቃሚው ዘንድ ተቀባይነቱ ከፍተኛ እንደሆነ ዶክተር ሺመላሽ አስረድተዋል። - ; ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ እንደየአከባቢው የመሬት የንጥረ ነገር ይዘት ፖታሽ ወይም ዚንክ ያለበት ማዳበሪያ የሚያስፈልጋቸው እየተለዩና እየተጠኑ ምርታማነትን ለማጎልበት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል። - ; በአመራ ክልል በ200708 ዓ.ም የምርት ዘመን ከ4 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በሰብል ለመሸፈንና የተሻለ ምርት ለማፈሰ ከወዲሁ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። - ; እንደ ዶክተር ሺመላሽ ገለጻ በሰብል ልማቱ ላይ 3 ነጥብ 6 ሚሊየን አርሶ አደሮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ዋልታ ኢንፈርሜሽን ማዕከል ዘግቧል። ),
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
666
ሚኒስቴሩ ከ20 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እያሰራጨ ነው, - ; .._2015 _22. 0 260 195 ; 5; አዲስ አበባ፤ሰኔ 132007(ዋኢማ) - በአገሪቱ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ባለፉት 6 ወራት ከ20 ሚሊየን ኩንታል በላይ የማዳበሪያና ምርጥ ዘር እያሠራጨ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ ። በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ተወካይ አቶ አስራት ገብረጻዲቅ እንደገለጹት ከዘንድሮ  የበጀት ዓመት አጋማሽ ጀምሮ 16 ሚሊየን 650 ሺ ኩንታል የኬሚካልና ማዳበሪያ ግብዓቶችን ለማቅረብ አቅደው ለአርሶ አደሩና፣ለከፊል አርብቶ አደሩ እየተሰራጨ ይገኛል ። የምርጥ ዘር አቅርቦትን በተመለከተ በዘንድሮ የግማሽ ዓመት 3ነጥብ6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ  ምርጥ ዘር በመላ አገሪቱ  ለሚገኙ አርብቶ አደሮች እየተከፋፈለ መሆኑን አቶ አስራት አክለው ገልጸዋል ።    በመላ አገሪቱ ማዳበሪያ የመጠቀም ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የገለጹት አቶ አስራት  ከ2002ዓም አንጻር ሲወዳደር በዘንድሮ የበጀት ዓመት  የማዳበሪያ ግብዓት መጠቀም  በ103  በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን  አስረድተዋል ። በአንድ ሄክታር መሬት ላይ ምን ያህል የተመጠነ የማዳበሪያ ግብዓት ጥቅም ላይ እንደሚውል አርሶአደሩን ለማስገንዘብ  ጥረቶች እየተደረጉ ነው ያሉት አቶ አሥራት በአገር ደረጃ በባለሙያ የሚክረ ሓሳብ አገልግሎት  ላይ እየተሠራ ነው ብለዋል ።      በመላ አገሪቱ በ20078 የምርት ዘመን ከ12 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች የመሸፈን  ስራው መጀመሩን ይታወቃል ። ),
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
667
ኩባንያው ዘንድሮ 10 ሺ ቶን ማዳበሪያ ያመርታል ። በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትና በአንድ ባለሀብት የተቋቋመው ብሄራዊ የማዳበሪያ ማምረቻ ኩባንያ በተያዘው አመት 10 ሺ ቶን ኦርጋኒክ ማዳበሪያ እንደሚያመርት ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ ። የግብርና ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር አቶ በላይ እጅጉ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንደገለጹት ኩባንያው ከአጥንት ፣ ቀንድ ፣ ሸኾና ፣ ደምና ፈርስ የሚያመርተው ማዳበሪያ በአመቱ ከውጪ ከሚገባው ኬሚካል ማዳበሪያ ጋር ሲነጻጸር በአነስተኛ ዋጋ ለአርሶ አደሮች ይቀርባል ። ኩባንያው በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር በአመት 50ሺ ቶን ማዳበሪያ እንደሚያመርት አቶ በላይ ተናግረዋል ። በሌላ በኩል ብሄራዊ የአፈር ምርምር ማእከል ለአገሪቱ የሚስማማና በዋጋ ዝቅተኛ የሆነ ማዳበሪያ በሚመረትበት ሁኔታ ላይ ምርምር እያደረገ መሆኑን ምክትል ሚኒስትሩ አመልክተዋል ። ከዚህ አኳያ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች በተለይ ስለ ኦርጋኒክ ማዳበሪያ አመራረት ፣ አያያዝ ፣ አጠቃቀምና ሙከራ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል ። በካሉብ - ኦጋዴን የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ እና ከሰል በመጠቀም ኬሚካል ማዳበሪያን ለማምረት የሚካሄደው ትናት ውጤት እያሳየ መሆኑንም አቶ በላይ ጨምረው ተናግረዋል ። በአገር ውስጥ የሚገኙ ጥሬ እቃዎችን በመጠቀም እትዮጵያ ውስጥ ኦርጋኒክና ኬሚካል ማዳበሪያን ማምረት በወቅቱ ለአርሶአደሮች ማዳበሪያ ለማቅረብ ከማስቻሉ ባሻገር የስራ እድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል ።
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
668
ግብረሃይሉ በስምንት ክፍሎች የተካተቱ ማዳበሪያ ሃሳቦች አዘጋጀ የድህነት ቅነሳ ስልት ሰነድን ለማዳበር ያግዛል ። መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የድህነት ቅነሳ ስልቱን ሰነድ ለማዳበር ያቋቋሙት ግብረሃይል በስምንት ዋናዋና ክፍሎች የተካተቱ የማዳበሪያ ሀሳቦች ማዘጋጀቱን አስታወቀ ። ግብረሃይሉ ዛሬ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንደገለጸው ግብረሃይሉ ያዘጋጀው የማዳበሪያ ሃሳብ በእርሻና የተፈጥሮ ሀብቶች ፣ በኤቻይቪአድስ ፣ በጤና ፣ በህጻናትና ወጣቶች ፣ በትምህርት ፣ በጾታ ፣ በከተሞች እድገት ፣ በአርብቶአደሩ ህይወት መሻሻልና በውሃ ሀብት ልማት ዙሪያ ያተኮረ ነው ። በተለይም የአር ሶአደሩን የካፒታል አቅም ከማሳደግ ፣ የማዳበሪያና የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነቱን ከማረጋገጥ ፣ ለምርቶቹ በቂ ገበያ የሚያገኝበትን ሁኔታ ከማመቻቸትና ስለተፈጥሮ ሀብት ትበቃና ስለተሻሻለ የመሬት አጠቃቀም ያለውን ግንዛቤ ከማጎልበት አኳያ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያቀርቧቸው ሀሳቦች ጉልህ ተቀሜታ ስላላቸው የማዳበሪያ ሀሳቦቹ ድርሻ ይኖራቸዋል ብሏል ። እንዲሁም አርሶአደሩ ወቅታዊ መረጃ የሚያገኝበትን ፣ የአነስተኛ የብድርና የተሻሉ መሰረተ ልማቶች ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችሉና በጥናት የተደገፉ ሀሳቦችን ለመንግስት እንደሚያቀርብ ግብረ-ሃይሉ አስረድቷል ። በተጨማሪም ወጣቶች የሙያ ስልጠናና የትምህርት እድል እንዲያገኙ በልማትና በማሀበራዊ እንቅስቃሴዎች የሴቶች ተሳትፎ እንዲጠናከር ፣ የድህነት ቅነሳ ስልቱ ከጸረኤድስ ዘመቻው ጋር እንዲተሳሰር ፣ የቤተሰብ ምጣኔና የጤና ትምህርት አንዲስፋፋና በኤቻይቪኤድስ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ልዩ እንክብካቤ አንዲያገኙ ከመንግስት ጋር ተባብሮ ለመስራት የሚያስችሉትን ሁኔታዎች ማመቻቸቱንም ግብረሃይሉ አስታውቋል ። አርብቶ አደሩም ችግሮቹን ለመፍታት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ፣ በሰነዱ ላይ የሚሰፍሩ ስልቶችና አቅጣጫዎች አርብቶአደሩን በእኩል ደረጃ ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ፣ ለአርብቶአደሩ የሚሰጠው እርዳታ ከአጠቃላይ የእድገት ፕሮግራሞች ጋር የተገናዘበ እንዲሆንና አርብቶአደሩ በቂ ገበያ እንዲያገኝ የሚያስችሉ አሰራሮች በሰነዱ ላይ መስፈራቸውን ግብረሃይሉ አመልክቷል ። የከተሞችን እድገት ለማፋጠንም አጠቃላይ የከተማ እድገት ፖሊሲው የመሬት አጠቃቀምን ፣ የአካባቢ ትበቃን ፣ የአመራርና የፋይናንስ አስተዳደርንና የአፈጻጸም ብቃትን በሚያሳድግ መልኩ የማሻሻያ ሃሳቦች ማዘጋጀቱን ግብረ-ሃይሉ አስታውቋል ።
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
669
በኢሉአባቦር ዞን ከ48ሺ ኩንታል ባላይ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶአደሩ እየተሰራጨ ነው የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌቱ ለገሰ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ለዘንድሮው የበልግ እና መኸር አዝመራ ጥቅም ላይ እንዲውል እየተሰራጨ ካለው ግብአት ውስጥ ከ42ሺ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ሲሆን ቀሪው ከ3ሺ 500 ኩንታል በላይ የበቆሎ ምርጥ ዘር ነው፡፡ ዘንድሮ ለአርሶአደሩ እየተሰራጨ ያለው ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ባለፈው የምርት ወቅት ከቀረበው ከ7ሺህ ኩንታል በላይ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በምርት ወቅቱ የአርሶአደሩን የግብአትና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አቅም በማሳደግ በሁሉም ሰብሎች የምርታማነት መጠኑን በ7 በመቶ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዘርፉ ለአርሶአደሩ ድጋፍ የሚያደርጉ ከ100 በላይ የግብርና ባለሙያዎች በተሟላ የግብርና ፓኬጅ አጠቃቀም ዙሪያ በክልል ደረጃ ስልጠና ወስደው ለአርሶአደሩ እገዛ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በአሌ ወረዳ አጋጊ በጨና ቀበሌ አርሶአደር ቢያ አጋ እንዳሉት በመስኖው ልማት ያገኙትን ገቢ ለግብአት ግዥ በማዋል ያላቸውን ሁለት ሄክታር ማሳ በበልግና መኸር አዝመራ ግብአት ተጠቅመው ለማልማት ተዘጋጅተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ግብአት በወቅቱ እንደማይቀርብላቸው ገልጸው ዘንድሮ አስቀድሞ በመድረሱ ልማቱን ወቅቱን ጠብቀው ለማከናወን እንዳገዛቸው ተናግረዋል፡፡ “ግብአት መጠቀም የሚያስገኘውን ውጤት በተግባር አይተናል በመሆኑም መንግስት ትኩረት ሰጥቶት በብዛት ሊያቀርብን ይገባል” ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ የወረዳው አርሶአደር ወርቅነሽ ዲማ ናቸው፡፡ በበልግ ወቅቱ በቆሎ በመኸር ደግሞ ጤፍ፣ ባቄላ እና አተር ለማልማት ከአንድ ሄክታር በላይ የሚሆን ማሳቸውን እያዘጋጁ እንደሆነም አርሶአደሯ ተናግረዋል፡፡ በዞኑ በዘንድሮው የበልግ አዝመራ ከ132ሺ በላይ አባወራ አርሶአደሮች በማሳተፍ ከ145ሺ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
670
ለመኸር እርሻ የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሆሮ ጉዱሩ ወረዳዎች እየደረሰ ነው የመኸር እርሻ በግብአትነት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ወረዳዎች እየደረሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን ደግሞ በመኸሩ ከ19 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የምግብ ሰብል ለማምረት ታቅዶ የእርሻ ስራ ተጀምሯል፡፡ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሕብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያና ማደራጃ ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ አቶ ባይሳ ኩምሣ እንዳሉት ባለፈው የመኸር ወቅት የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ባለመድረሱ በአርሶ አደሩ ስራ ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይደገም ዘንድሮ ከወዲሁ በመዘጋጀት እየተሰራ ነው፡፡ አሁን ላይ ዳፕ ማዳበሪያው ጨረታውን ባሸነፉ ባለሀብቶች አማካኝነት ከአዲስ አበባ ተጭኖ ወደ ሁሉም የዞኑ ወረዳዎች በማጓጓዝ እየደረሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስካሁንም ለምርት ወቅቱ ከሚያስፈልገው 195ሺህ 988 ኩንታል ዩሪያና ዳፕ ማዳበሪያ ውስጥ ከ118ሺህ900 ኩንታል በላይ ዳፕ ማዳበሪያ ዞኑ አርሶ አደሮች ለሚያከፋፍሉ ሶስት የገበሬዎች የሕብረት ሥራ ዩኒየኖች መድረሱን አቶ ባይሣ አመልክተዋል፡፡ ማደበሪያው ከደረሳቸው መካከል የጨፌ ቡሉቅ የገበሬዎች የሕብረት ሥራ ዩኒየን ምክትል ስራ አስኪጅ አቶ ታደሰ ጊቺሌ በበኩላቸው 18ሺህ 567 ኩንታል ማዳበሪያ ለአምስት ወረዳዎች ማከፋፋላቸውን ተናግረዋል፡፡ ጅማ ገነቲ፣ሆሮ ቡሉቅ፣ሆሮ ፣ አሙሩ እና ጃርደጋ ጃርቴ ማዳበሪያው የተከፋፈላቸው ወረዳዎች መሆናቸውን ጠቅሰው በአባል የህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሩ እንደሚደርስም አመልክተዋል፡፡ የሀራጉ የገበሬዎች የህብረት ሥራ ዩኒየን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ጫላ እንዳሉት የደረሳቸውን የአፈር ማዳበሪያ በስራቸው ለሚገኙ አምስት ወረዳዎች በመከፋፈል ላይ ናቸው፡፡ ምሥጋኑ ኤጀታ በዞኑ ጉድሩ ወረዳ የቱሉ ሀቢብ ቀበሌ አርሶ አደር ሲሆኑ በቆሎ ለመዝራት እርሻ መጀመራቸውና ሆኖም እስከ አሁን የዩሪያ ማዳበሪያ ባለመግባቱ የዘር ጊዜ ያልፍብናል ብለው መስጋታቸውን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡ በሀባቦ ጉዱሩ ወረዳ የእኒ አማ ቶለራ ቀበሌ አርሶ አደር እምሩ ኤጀታ በበኩላቸው ለበቆሎ ማሳቸው የሚያስፈልጋቸው ዩሪያ ማዳበሪያ እስካሁን በአካባቢያቸው አለመድረሱን ተናግረዋል፡፡ የሀራጉ የገበሬዎች የሕብት ሥራ ዩኒየን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ በበኩላቸው እስካሁን እየገባ ያለው ዳፕ ቢሆንም ለበቆሎ ሰብል የሚያስፈልገው ዩሪያ ማዳበሪያው የዘር ወቅት ከማለፉ በፊት እንዲመጣላቸው ለኦሮሚያ የሕብረት ሥራ ማስፋፊያና ማደራጃ ኤጀንሲ መጠየቃቸውን አስረድተዋል፡ የኦሮሚያ የሕብረት ሥራ ማስፋፊያና ማደራጃ ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደለ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ዩሪያ ማዳበሪያው ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚደርስ አስታውቀዋል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ ሸዋ ዞን በመጪው የመኸር ወቅት ከ19 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የምግብ ሰብል ለማምረት ታቅዶ የእርሻ ስራ መጀመሩን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በጽህፈት ቤቱ የአዝርት ባለሙያ አቶ ባይሳ ተረፈ ለኢዜአ እንደገለፁት በምርት ዘመኑ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ምርት ታርሶ በዘር ከሚሸፈነው 614ሺህ 967 ሄክታር መሬት ላይ ነው። በአሁን ወቅት አርሶ አደሩ የማሳ ዝግጅት እያካሄደ መሆኑን የገለፁት ባለሙያው ለወቅቱ የሚሆን ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እየቀረበ መሆኑን አመልክተዋል። በምዕራብ ሸዋ ዞነ በ2009/ 2010 የመኽር ወቅት ከለማው 612 ሺህ 630 ሄክታር መሬት 17 ሚሊዮን 183ሺህ ኩንታል ምርት መገኘቱ ይታወሳል
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
671
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች እየተሰራጨ ነው ደብረ ማርቆስ መጋቢት 18/2010 በምስራቅ ጎጃም ዞን ለቀጣዩ የመኸር ወቅት አገልግሎት የሚውል ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ቀርቦ ለአርሶ አደሮች እየተሰራጨ ነው፡፡ በዞኑ ግብርና መምሪያ የግብአት አቅርቦት የስራ ሂደት አስተባበሪ አቶ ሀይለየሱስ ዳምጤ ለኢዜአ እንደተናገሩት ማዳበሪያውን ከወዲሁ ማሰራጨት ያስፈለገው ባለፈው ዓመት በግብዓት አቅርቦት መዘግየት ምክንያት በአርሶ አደሮች ዘንድ ተከስቶ የነበረውን መጉላላት ለማስቀረት ነው። በምርት ዘመኑ ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን 300 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለመሰረታዊ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ደርሶ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ ነው፡፡ ቀሪውን ማዳበሪያም በወቅቱ ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። የዞኑ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያና ማደራጃ ተጠሪ ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ተዋበ ደምሴ በበኩላቸው ወቅቱን የጠበቀ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ በ192 መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት እንዲሰራጭ እየተደረገ ነው፡፡ የስናን ወረዳ የገዳማይት ቀበሌ አርሶ አደር ተመቸው ገድፍ እንዳሉት ባለፈው አመት የአፈር ማዳበሪያ እጥረት አጋጥሟቸው እንደነበር ገልፀዋል። በዚህም ተገቢውን ማዳበሪያ መጠቀም እንዳልቻሉ ጠቁመው በዚህ አመት ግን ማዳበሪያው ቀድሞ እየገባ በመሆኑ ያለፈው ችግር እንደማይደገም ተስፋ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የጎዛምን ወረዳ የአባሊባኖስ ቀበሌ አርሶ አደር መርሻ ገዳሙ እንዳሉት ባለፈው አመት የአፈር ማዳበሪያ እጥረት በማጋጠሙ ሁለት ኩንታል በሌላ አካባቢ ከሚኖሩ ዘመዶቻቸው ተበድረው መጠቀማቸውን አመልክተዋል። ማዳበሪያው በዚህ ወቅት መምጣቱ የእርሻና የዘር ስራቸውን ወቅቱን ጠብቀው ለማከናወን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡ በዞኑ በመጭው የመኸር ውቅት ከ650 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት ከ20 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
672
በኢሉአባቦር ዞን ከ48ሺ ኩንታል ባላይ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶአደሩ እየተሰራጨ ነው የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌቱ ለገሰ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ለዘንድሮው የበልግ እና መኸር አዝመራ ጥቅም ላይ እንዲውል እየተሰራጨ ካለው ግብአት ውስጥ ከ42ሺ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ሲሆን ቀሪው ከ3ሺ 500 ኩንታል በላይ የበቆሎ ምርጥ ዘር ነው፡፡ ዘንድሮ ለአርሶአደሩ እየተሰራጨ ያለው ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ባለፈው የምርት ወቅት ከቀረበው ከ7ሺህ ኩንታል በላይ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በምርት ወቅቱ የአርሶአደሩን የግብአትና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አቅም በማሳደግ በሁሉም ሰብሎች የምርታማነት መጠኑን በ7 በመቶ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዘርፉ ለአርሶአደሩ ድጋፍ የሚያደርጉ ከ100 በላይ የግብርና ባለሙያዎች በተሟላ የግብርና ፓኬጅ አጠቃቀም ዙሪያ በክልል ደረጃ ስልጠና ወስደው ለአርሶአደሩ እገዛ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በአሌ ወረዳ አጋጊ በጨና ቀበሌ አርሶአደር ቢያ አጋ እንዳሉት በመስኖው ልማት ያገኙትን ገቢ ለግብአት ግዥ በማዋል ያላቸውን ሁለት ሄክታር ማሳ በበልግና መኸር አዝመራ ግብአት ተጠቅመው ለማልማት ተዘጋጅተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ግብአት በወቅቱ እንደማይቀርብላቸው ገልጸው ዘንድሮ አስቀድሞ በመድረሱ ልማቱን ወቅቱን ጠብቀው ለማከናወን እንዳገዛቸው ተናግረዋል፡፡ “ግብአት መጠቀም የሚያስገኘውን ውጤት በተግባር አይተናል በመሆኑም መንግስት ትኩረት ሰጥቶት በብዛት ሊያቀርብን ይገባል” ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ የወረዳው አርሶአደር ወርቅነሽ ዲማ ናቸው፡፡ በበልግ ወቅቱ በቆሎ በመኸር ደግሞ ጤፍ፣ ባቄላ እና አተር ለማልማት ከአንድ ሄክታር በላይ የሚሆን ማሳቸውን እያዘጋጁ እንደሆነም አርሶአደሯ ተናግረዋል፡፡ በዞኑ በዘንድሮው የበልግ አዝመራ ከ132ሺ በላይ አባወራ አርሶአደሮች በማሳተፍ ከ145ሺ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
673
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከአምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመረ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ለመጪው የመኽር እርሻ ጥቅም ላይ የሚውል ከአምስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ እንስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ። በቢሮው በግዥ የሚቀርቡ የግብርና ግብዓቶች ክትትል ባለሙያ አቶ ይሁኔ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ ከሁለት ሚሊዮን 600 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል፡፡ ከዚህ ውስጥም 650 ሺህ ኩንታሉ ወደ ተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ተጓጉዞ ለ23 ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየኖች ተከፋፍሏል። ቀሪውን ማዳበሪያም እስከ መጪው ሚያዚያ ወር 2010 ዓ.ም በማጓጓዝ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ እንደሚቀርብ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ ማዳበሪያው በወቅቱ እንዲገባ እየተደረገ ያለው በቀጣይ በዘር ወቅት የሚስተዋለውን የግብዓት አቅርቦት መዘግየት ለመፍታት ታስቦ መሆኑን ጠቁመው፤ ማዳበሪያው እየቀረበ ያለውም የአርሶ አደሩን ፍላጎት መሰረት አድርጎ በተሰበሰበ መረጃ መሰረት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ለማዳበሪያ መግዥ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ መመደቡን ያመለከቱት አቶ ይሁኔ ለማቅረብ የታቀደው የማደበሪያ መጠንም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር በአንድ ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል። እንደ ባለሙያው ገለጻ በስርጭት ሂደቱም ቀድሞ የመኽር ሰብል ዘር በሚጀመርባቸው የክልሉ አካባቢዎች ፈጥኖ እንዲገባ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። 120 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ ማዳበሪያ ተጓጉዞ ወደ ዩኒየኑ መጋዘን መድረሱን የተናገሩት ደግሞ በባህርዳር የሚገኘው የመርከብ ዩኒየን የግብይት ክፍል ኃላፊ አቶ ተመስገን አበበ ናቸው። ቀድሞ የገባውን ማዳበሪያም በአርሶ አደሩ አቅራቢያ ወደ ሚገኙ 132 የህብረት ስራ ማህበራት እያጓጓዙ እንደሚገኝም ጠቅስዋል። አቶ ተመስገን እንዳሉት አሁን በተያዘው ፍጥነት ሁሉም ማዳበሪያ ተጠቃሎ ከገባ አርሶ አደሩ ይገጥመው የነበረው የግብዓት አቅርቦት ችግር ይፈታል፡፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኘው የሞጣ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ዘገየ አዳነ ከዚህ ቀደም ማዳበሪያ ተጓጉዞ ወደመጋዝናቸው የሚደርሰው በየካቲት ወር መጨረሻ እንደነበር ጠቁመዋል። ዘንድሮ መንግስት ትኩረት በመስጠቱ ከሶስት ቀን በፊት በዩኒየኑ መጋዘን ከ10 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ መራገፍ እንደጀመረ አመልክተው አቅርቦቱ ሳይቆራረጥ ከቀጠለ ችግሩ እንደሚፈታም ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ባለፈው ዓመት ከሶስት ሚሊዮን 900ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ቀርቦ ጥቅም ላይ እንደዋለም ተመልክቷል፡፡
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
674
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች እየተሰራጨ ነው በምስራቅ ጎጃም ዞን ለቀጣዩ የመኸር ወቅት አገልግሎት የሚውል ከ300 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ቀርቦ ለአርሶ አደሮች እየተሰራጨ ነው፡፡ በዞኑ ግብርና መምሪያ የግብአት አቅርቦት የስራ ሂደት አስተባበሪ አቶ ሀይለየሱስ ዳምጤ ለኢዜአ እንደተናገሩት ማዳበሪያውን ከወዲሁ ማሰራጨት ያስፈለገው ባለፈው ዓመት በግብዓት አቅርቦት መዘግየት ምክንያት በአርሶ አደሮች ዘንድ ተከስቶ የነበረውን መጉላላት ለማስቀረት ነው። በምርት ዘመኑ ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን 300 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለመሰረታዊ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ደርሶ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ ነው፡፡ ቀሪውን ማዳበሪያም በወቅቱ ለአርሶ አደሮች ለማሰራጨት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። የዞኑ ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያና ማደራጃ ተጠሪ ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ተዋበ ደምሴ በበኩላቸው ወቅቱን የጠበቀ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ በ192 መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት እንዲሰራጭ እየተደረገ ነው፡፡ የስናን ወረዳ የገዳማይት ቀበሌ አርሶ አደር ተመቸው ገድፍ እንዳሉት ባለፈው አመት የአፈር ማዳበሪያ እጥረት አጋጥሟቸው እንደነበር ገልፀዋል። በዚህም ተገቢውን ማዳበሪያ መጠቀም እንዳልቻሉ ጠቁመው በዚህ አመት ግን ማዳበሪያው ቀድሞ እየገባ በመሆኑ ያለፈው ችግር እንደማይደገም ተስፋ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የጎዛምን ወረዳ የአባሊባኖስ ቀበሌ አርሶ አደር መርሻ ገዳሙ እንዳሉት ባለፈው አመት የአፈር ማዳበሪያ እጥረት በማጋጠሙ ሁለት ኩንታል በሌላ አካባቢ ከሚኖሩ ዘመዶቻቸው ተበድረው መጠቀማቸውን አመልክተዋል። ማዳበሪያው በዚህ ወቅት መምጣቱ የእርሻና የዘር ስራቸውን ወቅቱን ጠብቀው ለማከናወን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡ በዞኑ በመጭው የመኸር ውቅት ከ650 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት ከ20 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
675
ለመኸር እርሻ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶአደሩ የማጓጓዝ ሥራ መጀመሩ ተገለጸ ኢኮኖሚ ለመጪው የመኸር እርሻ የሚሆን ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ የማጓጓዝ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የእርሻ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ መንግስቱ ለኢዜአ እንደገለጹት የግብርና ግብአትን ለአርሶአደሩ በወቅቱ ማድረስ በምርትና ምርታማነት ላይ ጠቀሜታ ስላለው ዘንድሮ በወቅቱ ለማድረስ እየተሰራ ነው። አምና በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ መንጠባጠብ እንደነበር አስታውሰው፣ ዘንድሮ የአርሶ አደሩን የግብዓት ፍላጎት ለማሟላትና ችግሩን ከወዲሁ ለመፍታት የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የማሰራጨት ሥራ በሙሉ አቅም እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። ለመጪው የመኸር እርሻ ከ15 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የማዳበሪያ ምርት ለአርሶ አደሮች እንደሚቀርብ ጠቁመው፣ ከዚህ ውስጥ ከቀዳሚው የምርት ዘመን የተረፈ 6 ሚሊዮን ኩንታል በዩኒየኖች መጋዘን እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዘንድሮ አዲስ ከሚቀርብ 9 ሚሊዮን ማዳበሪ ውስጥ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሚሆነው በአሁኑ ወቅት ወደ ዩኒየኖችና መሰረታዊ ማህበራት መከፋፈሉን አመልክተዋል። በቀጣይ ሁለት ወራት ቀሪውን 5 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ማዳበሪያ የማሰራጨት ሥራ አንደሚሰራ ገልጸው፣ ለማዳበሪያ ግዥ 600 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል። አርሶ አደሩ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ያለበትን ውስንነት ለመፍታት በወቅቱ የተሟላ የግብርና ግብአት ማቅረብ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲው የገበያ ተኮር ሰብሎች ኩታ ገጠም ልማት ዳይሬክተር ዶክተር ተሾመ ዋለ ናቸው ። "አርሶ አደሩ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በበቂ ሁኔታ እንዲያገኝ ከማድረግ ባሻገር በምርምር የተገኙ የአሰራርና የቴክኖሎጂ ግኝቶች አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ ይጠበቅብናል" ብለዋል ። በግብርና ኤክስቴንሽን ልማት ላይ በተደረገ ጥናት በየዓመቱ ከሚለማው ከ12 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ በማዳበሪያ የሚዘራው 62 በመቶ ሲሆን ምርጥ ዘር ተጠቅሞ የሚዘራ 26 በመቶ መሆኑንም ገልፀዋል። "በግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የሚስተዋለውን ይህን ክፍተት ለመሙላት በወቅቱ የተሟላ የግብርና ግብአት ማቅረብ አለብን" ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የማሳ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን የገለጹት የምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ባቱ ጋርማማ ቀበሌ አርሶ አደር ቃቻ ተሊላ በበኩላቸው የሚቀርብላቸውን ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። አምና ለአንድ ሄክታር መሬት ሁለት ኩንታል ማዳበሪያ መጠቀማቸውን የገለጹት አርሶአደሩ፣ በወቅቱ በማዳባሪያና ምርጥዘር አቅርቦት ላይ መንጠባጠቦች እንደነበሩ አስታውሰዋል። "በዘንድሮ ዓመት በአዳዲስ አሰራርና የቴክኖሎጂ ግኝቶች አጠቃቀም ላይ የሚሰጠው ስልጠና በተፋጠነ የማዳበሪያ ምርጥ ዘር አቅርቦት መደገፍ አለበት "ብለዋል። "በተደጋጋሚ ያረስኩትን መሬት በአሁኑ ወቅት በኩታ ገጠም በቆሎ ለመዝራት ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ገዝተን ዝናብ እየተጠባበቅን ነው" ያሉት ደግሞ በአዳማ ወረዳ የአዱላ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዳዲ በዳዳ ናቸው ።
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
676
ለአርሶ አደሮች የሚቀርበው ማዳበሪያ ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ በዓለም አቀፍ ገበያ ከዩሪያ በስተቀር በሌሎች የማዳበሪያ ዓይነቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ባይደረግም፣ ብር ከዶላር ጋር ያለው ምጣኔ በ15 በመቶ እንዲቀንሰ በመደረጉ ምክንያት ለአርሶ አደሮች በሚቀርበው ማዳበሪያ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡ ለ2010/2011 ምርት ዘመን መንግሥት ከአንድ ሚሊዮን ቶን በላይ አምስት ዓይነት ማዳበሪያዎችን ጨረታ አውጥቶ ግዥ ፈጽሟል፡፡ ማዳበሪያዎቹ ኤንፒኤስ፣ ኤንፒኤስ ቦሮን፣ ኤንፒኤስ ዚንክና ኤንፒኤስ ዚንክ ቦሮን ናቸው፡፡ አንዱ ደግሞ በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ዘንድ የሚታወቀው ዩሪያ ነው፡፡ የአራቱ ማዳበሪያዎች የዓለም አቀፍ ገበያ ዋጋ ከአምናው ምርት ዘመን ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም፣ በዩሪያ ማዳበሪያ ላይ ግን ጭማሪ ታይቷል፡፡ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የግብርና ግብዓቶች ግብይት ዳይሬክተር አቶ ሰይፉ አሰፋ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 550 ሺሕ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ ለመግዛት ዕቅድ ተይዞ ነበር፡፡ ነገር ግን በዓለም አቀፍ ገበያ የዋጋ ጭማሪ በመደረጉ፣ ሦስት ጊዜ ጨረታ ቢወጣም መግዛት አልተቻለም፡፡ ‹‹ዩሪያ ማዳበሪያ የግድ መግዛት ስለሚያስፈልግ አምራቾችን በቀጥታ በማግኘት 500 ሺሕ ቶን ተገዝቷል፤›› ሲሉ አቶ ሰይፉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት የአንድ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ ዋጋ 257 ዶላር ነበር፡፡ በዚህ ዓመት ግን የአንድ ቶን ዋጋ 320 ዶላር ሆኗል፡፡ ዩሪያ ማዳበሪያ ባለፈው ዓመት በኩንታል ከአንድ ሺሕ ብር በታች በሆነ ዋጋ ለአርሶ አደሩ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ብር ከዶላር ጋር ያለው ምጣኔ በ15 በመቶ እንዲቀንስ በመደረጉ ምክንያት የአንድ ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ የመሸጫ ዋጋ 1,150 ብር መግባቱ ተመልክቷል፡፡ የኤንፒኤስ ማዳበሪያ ዓይነቶችም እንዲሁ በዓለም ገበያ ላይ የዋጋ ጭማሪ ባይደረግባቸውም፣ የብር የመግዛት አቅም በመዳከሙ ምክንያት የመሸጫ ዋጋቸው ላይ ጭማሪ ተደርጓል፡፡ ባለፈው ዓመት የኤንፒኤስ ማዳበሪያ የአንድ ኩንታል ዋጋ ከአንድ ሺሕ ብር በታች ቢሆንም፣ ሩቅ በሚባለው ሁመራ 1,200 ብር ሲገባ ቅርብ በሚባለው አዳማ ደግሞ 1,050 ብር በኩንታል ተሸጧል፡፡ የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የማዳበሪያ ፍላጎት በዓይነትም በመጠንም ጨምሯል፡፡ በ2008/2009 ምርት ዘመን ስምንት ሚሊዮን ኩንታል የተጠቀመው የግብርና ዘርፍ፣ በ2009/2010 ዓ.ም. ምርት ዘመን ደግሞ 13 ሚሊዮን ኩንታል አስፈልጎታል፡፡ በቅርቡ ከሪፖርተር ጋር ቆይታ ያደረጉት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ባለፈው ምርት ዘመን 13 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለመግዛት 400 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተዳርጓል፡፡ በዚህ ዓመት የሚያስፈልገውን 15 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለመግዛት 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል ብለው ነበር፡፡
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
677
በምስራቅ ወለጋ ዞን የጊቤ ዴዴሳ ገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዬን ዘንድሮ ከ250ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ማሰራጨቱን አስታወቀ ። የዩኒዬኑ ስራ አስኪያጅ አቶ ግንባር ዋቅጋሪ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልገሎት እንደገለጡት 90 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለዉ ማዳበሪያ የተሰራጨዉ በምእራብ ኦሮሚያ ሰባት ዞኖች ለሚገኙ አርሶ አደሮች ነዉ ። ዩኒዬኑ ከዉጭ ያስገባዉን ማዳበሪያ ያሰራጨዉ ለምስራቅ ወለጋ፤ ለሆሮ ጉድሩ ወለጋ ፤ለምእራብ ወለጋ ፤ለቄለም ወለጋ ፤ለኢሉባቡር ፤ለጅማና ለምእራብ ሸዋ ዞኖች አርሶ አደሮች መሆኑን አስረድተዋል ።
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
678
የአፈር ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረቶችን ለመቅረፍ እየተሠራ እንደሆነ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ ባሕር ዳር፡ ግንቦት 23/2011ዓ.ም (አብመድ) ቢሮዉ ግብርናውን ለማዘመን እና ምርትን ለማሳደግ የብድር አገልግሎት የማመቻቸት እና ሞዴል አርሶ አደሮችን የማብዛት ተግባር ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግሥቴ የምርጥ ዘር እና የማዳበሪያ ፍላጎቶች እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2011ዓ.ም ድረስ ለአርሶ አደሮች ተሰራጭተው መጠናቀቅ ቢኖርባቸውም አለመሳካቱን አመልክተዋል፡፡ በየዓመቱ የምርጥ ዘር እና የማዳበሪያ አቅርቦት መጓተት ዋና ዋና ምክንያቶች ተብለው ከተጠቀሱ ውስጥ የጨረታ መዘግዬት፣ የግዥ መጓተት እና የትራንስፖርት ችግሮች መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ተስፋሁን የአፈር ማዳሪያ ባለፈው ዓመት እስከ ዚህ ወር ድረስ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል አስገብተው እንደነበረ አስታውሰው በዚህ ዓመት ግን 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ መሠራጨቱን ገልጸዋል፡፡ ካለፈዉ ዓመት የተሻለ አቅርቦት ቢኖርም ከዕቅዱም ሆነ ከፍላጎቱ አንፃር ግን ተመጣጣኝ እንዳልሆነም ምክትል ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡ አርሶ አደሩ ‹‹የአፈር ማዳበሪያ የለም›› በሚል እንዳይሸበር ያሳሰቡት ምክትል ኃላፊው በትራንስፖርት በኩል ያለው ችግር ከሰሞኑ እየተፈታ በመሆኑ በቀን እስከ 110 መኪና ተጭኖወደ ክልሉ እየገባ እንደሆነና አቅርቦቱ በዚህ መልኩ ከቀጠለም እጥረቱን ከሰኔ 15 እስከ 30 ሙሉ በሙሉ እንደሚፈታ አስታውቀዋል፡፡ የማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር እጥረቶችን ለመቅረፍ በወቅታዊነት እስከ ሰኔ አጋማሽ የሚዘሩ ሰብሎችን ለሚጠቀሙ አርሶ አደሮች ቅድሚያ እንዲሰጥም ከቀበሌ ባለሙያዎች ጋር የጋራ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ ምርጥ ዘር አቅርቦትን በተመለከተ ስንዴ ለአከፋፋይ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በመስጠታቸው ለሁሉም እንደሚደርስ ተናግረዋል፤ ጤፍ፣ በቆሎ ‹660› እና ‹661› የተሰኙ ዝርያዎች እና የቢራ ገብስ ላይ እጥረት እንደሌ አመልክተው የሚፈልግ ወረዳ ካለም ከዛሬ ጀምሮ ጠይው መውሰድ እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡ በቆሎ ‹540› ዝርያ እና ጥራጥሬ ላይ የተወሰኑ የምርጥ ዘር እጥረቶች እንዳሉ ያመላከቱት ኃላፊው የሚመለከተውን አካል ጠይቀው ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነም ነግረውናል፡፡ ሰሊጥ አምራች የጎንደር አካባቢዎች ላይም ብዙ ጊዜ የአከባቢ ሰሊጥ እንደሚፈልጉ የገለጹት አቶ ተስፋሁን የተሻሻሉ ዝርያዎችን ከፈለጉ ግን ከግብርና ቢሮም ሆነ ከምርምር ተቋማት ማግኘት እንደሚችሉ ነው ያስገነዘቡት፡፡ ‹‹የሰሊጥ ምርጥ ዘር የሌለ እንኳ ቢሆን እስከ ፌዴራልም ጠይቀን እናስመጣለን፤ ያለንን ግን ከዛሬ ጀምሮ የሚፈልጉትን መጠን ጠይቀው መውሰድ ይችላሉ” ብለዋል፡፡ ምክትል ኃላፊው እንዳሉት ግብርናውን ለማዘመን የግብርና ሜካናይዜሽን ሥራዎች ላይ ትኩረት የመስጠት ክፍተቶች አሉ፤ ትራክተር እና ኮምባይነር ለመግዛት የገንዘብ እጥረት ለአርሶ አደሩ ማነቆ ሁኗል፡፡ ችግሩን ለመፍታት አርሶ አደሮቹ በኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል እንዲገዙና በዘርፉ ባለሀብቶች እንዲሰማሩም ብድር ለማመቻቸት ከልማት ባንክ ጋር የተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ የሀገሪቱን የግብርና ዘርፍ በአፈር ማደበሪያ እና ምርጥ ዘር አቅርቦት ለማገዝና በወጥነት ግብዓት በመጠቀም ከ30 እስከ 50 በመቶ የምርት ዕድገት ስለሚያስገኝ ቀዳሚ ተግባር ተደርጎ መሠራት እንዳለበት አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡ በየዓመቱ ከጨረታ እስከ አርሶ አደሮች ድረስ ያለውን ሂደት አጠናቅቆ የግብዓት አቅርቦት እስከ ሚያዝያ 30 እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ጥረት መደረግ እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡ የኩታ ገጠም አስተራረስን 50 በመቶ ማድረስ እና ሁሉንም ‹ፓኬጆች የሚጠቀሙ ሞዴል አርሶ አደሮችን አሁን ካሉበት 29 በመቶ ከፍ ማድረግ የግድ መሆን እንዳለበትም ምክትል ኃላፊዉ አሳስበዋል፡፡
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
679
ፖሊተር የተሰኘ የአፈር ማዳበሪያ ስራ ላይ ሊውል ነው 116 Share አዲስ አበባ ጥር 6/2011 የግብርና ሚኒስቴር ለሁሉም የአፈርና የምርት አይነት ተስማሚ ነው የተባለ አዲስ የአፈር ማዳበሪያ ማስተዋወቅ ጀመረ። ‘ፖሊተር’ የተሰኘው ማዳበሪያው በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ወልመራ ወረዳ ለሙከራ ቀርቧል። ፖሊተር በተሰኘ የፈረንሳይ ኩባንያ የተመረተው ማዳበሪያ በአንድ ሄክታር መሬት ላይ 10 ኪሎ ግራም መጠቀም ያስችላል ተብሏል። አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ከዋለ ከሶስት እስከ አምስት ዓመት መሬቱ ያለ ተጨማሪ ማዳበሪያ ተመሳሳይ ምርት መስጠት እንደሚያስችልም ተነግሯል። ግብርና ሚኒስቴር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ወደ አገር ቤት የመጣው ማዳበሪያ ምርትና ምርታማነት ያሳድጋል፤ ለሁሉም የአፈር አይነት ተስማሚ በመሆኑም አሲዳማ መሬትን በኖራ ለማከም ይወጣ የነበረውን ወጪ ያስቀራል ነው የተባለው። ለሁለት ሰዓት በውሃ በመዘፍዘፍ ጥቅም ላይ የሚውለው ፖሊተር፤ ውሃ ውስጥ ሲዘፈዘፍ መጠኑ በ500 እጥፍ የሚጨምር ሲሆን ይህም ከሌሎች የማዳበሪያ አይነቶች የሚለይበት ነው። 700 ግራም ማዳበሪያ በ150 ሌትር ውሃ ውስጥ በመዘፍዘፍ ነው ጥቅም ላይ የሚውለው። በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የግብርና ሚኒስትሩ አማካሪ ዶክተር ኢያሱ አብርሃ እንዳሉት ማዳበሪያው ጥቅም ላይ ሲውል ለአጠቃቀም ምቹና በመጠንም አነስተኛ በመሆኑ ለማዳበሪያ ግዥና ማጓጓዣ ይወጣ የነበረውን ወጪ ይቀንሳል፤ በውሃ አጠር መሬት ላይም መጠቀም ይቻላል። ማዳበሪያው በተለያዩ ሂደቶች ተግባር ላይ ከዋለና ውጤታማነቱ ከተሞከረ በኋላ በ2012 ዓም በስፋት ለአርሶ አደሩ ይከፋፈል ብለዋል ዶክተር ኢያሱ። “የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ነው፤ ይህ አሁን የመጣው ለሙከራ ነው በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ይሞከራል፤ ውጤቱ ታይቶ እንዴት መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንወስናለን።” ብለዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እንዳሉት ደግሞ ግብርናን ለማዘመን በቴክኖሎጂ መደገፍ የሚያስችልና አገሪቱ የጀመረችውን ልማት የሚያጠናክር ነው። ሚኒስትሩ በቴክኖሎጂ ግብርናን ለማዘመን የያዘውን ስራ ያጠናከራል ሲሉም ተናግረዋል። ማዳበሪያው አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ ከሶስት እስከ አምስት ዓመት ያገለግላል፣ ኢሲድን ከአፈር ውስጥ ያጠፋል፣ የተመረዘውን አፈርም ያክማል ብለዋል። ከፖሊተር ኩባንያ የመጡት ሚስተር ክርስቲያን ናዳ በበኩላቸው ማዳበሪያው ውሃን ስለሚቆጥብ በደረቃማ አካባቢዎች ጥቅም ላይ እንደሚውልና ለሁሉም አይነት ምርትና አፈር መጠቀም ይቻላል ሲሉ አስተዋውቀዋል። ትናንት በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በወልመራ የተሞከረው የፖሊተር ማዳበሪያ በአውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካና በአፍሪካ የተለያዩ አገሮች ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑም ተገልጿል።
[ 114 ]
[ "የማዳበሪያ ስርጭት" ]
[ "ስለ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጪት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ስለ ማደበሪያ አቅርቦት, ማዳበሪያ ስለተሰረጨላቸው አካባቢወች የሚያትቱ ሰነዶች ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች ናቸው፡፡ ስለ ማዳበሪያ አዘገጃጀት የሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
680
የተቋማቱ መቋቋም ለሴቶች መብት መከበር ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተጠቆመ ። የሰባዊ መብት ኮሚሽንና የእንባ ተባቂ ተቋም እጩ አቅራቢ ኮሚቴዎች ስራ መጀመራቸው ለሴቶች መብት መከበር ጉልህ አስተዋእኦ እንደሚያደርግ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማሀበር አመለከተ ። የማሀበሩ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ ዛሬ ለዋልታ እንፎርሜሽን ማእከል እንደገለጹት ሀብረተሰቡ ለመብቶቹ መከበር አበክሮ እንደሚንቀሳቀስ ተቋማቱ ስለሚረዱ የኮሚቴዎቹ ስራ መጀመር አንድ እርምጃ ነው ። በተለይም አስተዳደራዊ በደሎችን ለማጋለጥ ፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ በደሎችን ለማስወገድና የዴሞክራሲያዊ ስራት ግንባታውን ለማፋጠን ተቋማቱ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርጉ ወይዘሮ መአዛ ተቁመዋል ። በአገሪቱ ለሰባዊ መብት መከበር የሚታገሉ የሲቪል ተቋማት ቁጥር እጅግ አናሳ መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ መአዛ መንግስት ለተቋማቱ መቋቋምና መጠናከር ከሰጠው ትኩረት አንጻር በቀጣይ ለሰባዊ መብት መከበር የሚንቀሳቀሱ ሲቪል ተቋማት እንደሚበራከቱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ። ከዚህ አኳያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማሀበር ከተቋማቱ ጋር ተባብሮ ለመስራት ከወዲሁ መዘጋጀቱን ፕሬዚዳንቷ ገልጸው ፤ ማሀበሩ በኢትዮጵያ ያለውን የሴቶች ሁኔታ አስመልክቶ የተደረጉ ትናቶችና ተያያዥ መረጃዎችን በመስጠት አስተዋእኦ እንደሚያደርግ አመልክተዋል ። በተለይ በህጻናትና ሴቶች ላይ የሚደርሱ በደሎችን በመጠቆምና ችግሮችን በማሳወቅ ማሀበሩ ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል ። ለሰባዊ መብት ኮሚሽንና ለእንባ ተባቂ ተቋም አባልነት እጩ አቅራቢ ኮሚቴዎች ሰሞኑን ስራ መጀመራቸውና በክቡር አፈ-ጉባኤ ዳዊት ዮሀንስ ሰብሳቢነት የጋራ ስብሰባ ማካሄዳቸው ይታወሳል ።
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
681
በአዲሱ ሚሌኒየም በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆምና የጾታ እኩልነትን ለማስፈን ሁሉም አካላት ድርሻቸውን እንዲወጡ የአማራ ክልል ሴቶች ጉዳይ ጽህፈትቤት ጥሪ ቀረበ። የባህርዳር ከተማ ሴቶች የሚሌኒዬሙን ግብ ለማሳካት በአንድነት እንነሳ በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። የአማራ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ወለላ መብራት በሰልፉ ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት ባለፉት 2 ሺህ ዓመታት የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑ ሴቶች የመብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸው ተጠቃሚ ሳይሆኑ ቆይተዋል። የጾታ አድሎ ጎልቶ የሚታይበት ባህላችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለሴቶች መብቶችና ጥቅሞች አለመከበር ዋና ዋና ምክንያቶች መሆናቸውን ገልጸው በባህል ተጽዕኖናና በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መስፋፋት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከልና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር የፌዴራል መንግስት ህጎችን ከማውጣት ጀምሮ የወሰዳቸው እርምጃዎች አበረታች ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል። በክልሉ የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ገልጠው አስገድዶ መድፈር፣ ያለዕድሜ ጋብቻና ሌሎችም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በወንጀል ህጉ እንዲካተቱ መደረጉ የመንግስት ጥረት ውጤቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
682
ሰሜን ጎንደር ውስጥ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 255 ሺህ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰለአዲሱ የሴቶች የለውጥና የዕድገት ፓኬጅ የግንዛቤ የማስጨበጥ ትምህርት መሰጠቱን የዞኑ ሴቶች ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ሃላፊ ወይዘሮ እንኳየሁሽ ሙሉ ከትናንት በስተያ እንዳስረዱት የሴቶችን የጾታ እኩልነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በዞኑ ወረዳዎች ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ እንዲሁም አዲሱን የሴቶች የልማትና የለውጥ ፓኬጅ የማስተዋወቅ ስራ መከናወኑንና የአቅም ግንባታ ስልጠናም በየደረጃው መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ ስልጠናው ስር የሰደደውን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማሰወገድ፣ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል ፣ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትን ለማስፋፋትና የቤተሰብ ህግን ለማስተዋወቅ የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም ሴቶች በየአካባቢያቸው በሚከናወኑ የልማት ስራዎች በመሳተፍ የልማት ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል እንደሆነ ገልጠዋል ፡፡ ለዘመናት ትኩረት ተነፍጓቸው የቆዩት ሴቶች በተነደፈው ፖሊሲ መሰረት በትምህርት ፣በጤናና በግብርናው ዘርፍ የጀመሩትን ጥረት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያሸጋግሩ የአመራር አባላት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሴቶችን ካለባቸው የኢኮኖሚ ጥገኝነት ለማላቀቅ ከተለያዩ አበዳሪ ድርጅቶች ከ23 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ለ4 ሺህ 600 ሴቶች ብድር በመስጠት በእንስሳት እርባትና ማድለብ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ በባልትና ውጤቶች፣ በሀር ምርትና በሌሎች የስራ መስኮች እንዲሰማሩ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዘጠኝ ዝናብ አጠር ወረዳዎች የሚገኙ 93 ሺህ ያሀል ሴቶች በሴፍቲኔት ፕሮግራም ተሳትፈው ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ስራ እንዲሰሩ ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን ወይዘሮ እንኳየሁሽ አስታውቀዋል፡፡
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
683
በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡ የሴቶችን መብት በተግባር ለማረጋገጥ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ መረባረብ እንደሚገባቸው የድሬዳዋ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትናንት ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብትና የሲቪክ ትምህርት ማሳደጊያ ማህበር በሴቶች የመማርና የተሳትፎ መብቶች ዙሪያ በድሬደዋ ከተማ ያዘጋጀው ዐውደ ጥናት ላይ የቢሮው ተወካይ ወይዘሮ ስንዱ ከበደ እንደገለጹት በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጡ መብቶችን ወደ ተግባር ለማሸጋገር ባለ ድርሻ አካላት ብዙ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የኅብረተሰቡ ግማሽ አካላት የሆኑት ሴቶች ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶቻቸው ተከብረው ከወንዶች እኩል ተሳታፊ የሚሆኑበት ሁኔታ በተግባር መረጋገጥ እንዳለበት አሳስበዋል ።
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
684
ጋዜጠኞች የሴቶችን ጥቅምና መብት ለማስጠበቅ የወጡ ሕጐችንና አፈጻጸማቸውን ተከታትለው ለሕዝብ የማሳወቅ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለሙያ ሴቶች ማህበር አሳሰበ ፡፡ ማህበሩ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በባሕር ዳር ከተማ ለጋዜጠኞች ያዘጋጀው ስልጠና ሲጠናቀቅ የማህበሩ የቦርድ አባል ወይዘሮ ሰሎሜ ደስታ እንደገለጹት የሴቶችን ሰብአዊ መብት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅም የሚያስጠብቁ በርካታ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በፌዴራልና በክልል መንግስታት ወጥተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በየጊዜው በሴቶች ላይ የሚፈጸሙት ያለእድሜ ጋብቻ፣ ጠለፋ፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ የስራ ጫናና ሌሎች ድርጊቶች ሕብረተሰቡ ስለህጐቹ ያለውን ዝቅተኛ ግንዛቤ እንደሚያመለክት ተናግረዋል፡፡ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ በደል ለማስቆም በየደረጃው ያሉ የፍትህና የአስተዳደር አካላት የሚሰጡት ሕጋዊ መፍትሄ በመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች መታገዝ እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡ በተለይ ጋዜጠኞች የሴቶችን መብት የሚያስጠብቁ ሕጐችን ለሕብረተሰቡ የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው የገለጹት ወይዘሮ ሰሎሜ፣ በሕጐቹ አፈጻጸም ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችንም ተከታትለው ለሕዝብ የመግለጽና ስህተቶች እንዲታረሙ አማራጭ የመጠቆም ሚናም መጫወት አለባቸው ብለዋል፡፡ የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሚያዘጋጇቸው የዜና ዘገባዎችና ፕሮግራሞች የሴቶችን ጉዳይ አካተው ለመስራት እንደሚጥሩ አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለሙያ ሴቶች ማህበር ባዘጋጀው በዚሁ ስልጠና ከአማራ ብዙሐን መገናኛ ኤጀንሲ፣ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅትና ከዋልታ ኢንፎርማሽን ማእከል የተውጣጡ ጋዜጠኞችና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ፡፡
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
685
በአዲሱ ሚሊኒየም ሴቶች በየመስኩ የመብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብትና የሲቪክ ትምህርት ማሳደጊያ ማህበር ሰሞኑን በደብረ ብርሀን ከተማ በሴቶች የትምህርት ተሳተፎ መብት ዙሪያ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ እንደገለጹት በሚሊኒየሙ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ተጽእኖዎችን ለማሰወገድ ጥረት ያደርጋሉ ፡፡ ሴቶች ከባህላዊ ጭቆና ለመላቀቅና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ለማሰከበር በተደራጀ መልክ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል ፡፡ ግርዛትና የመሳሰሉት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ሐይማኖታዊ መሰረት እንደሌላቸው የገለጹት እነዚሁ የህበረተሰብ ክፍሎች፣ በየአካባቢያቸው የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቀረት በሚደረገው ጥረት ተሳትፏቸውን አጠናከረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል ፡፡
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
686
በአዲሱ ሚሊኒየም ሴቶች በየመስኩ የመብታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብትና የሲቪክ ትምህርት ማሳደጊያ ማህበር ሰሞኑን በደብረ ብርሀን ከተማ በሴቶች የትምህርት ተሳተፎ መብት ዙሪያ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ እንደገለጹት በሚሊኒየሙ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ተጽእኖዎችን ለማሰወገድ ጥረት ያደርጋሉ ፡፡ ሴቶች ከባህላዊ ጭቆና ለመላቀቅና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ለማሰከበር በተደራጀ መልክ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል ፡፡ ግርዛትና የመሳሰሉት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ሐይማኖታዊ መሰረት እንደሌላቸው የገለጹት እነዚሁ የህበረተሰብ ክፍሎች፣ በየአካባቢያቸው የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቀረት በሚደረገው ጥረት ተሳትፏቸውን አጠናከረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል ፡፡
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
687
በመጪዎቹ አመታት የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥና ድህነትን ለማስወገድ ጥረት እንደሚደረግ የትግራይ ማእከላዊ ዞን የሴቶች ማህበር ሊቀ መንበር አስታወቁ፡፡ ሊቀ መንበሯ ወይዘሮ አልማዝ አለሙ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት በሚቀጥሉት አመታት የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዲወገዱ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የሚሊኒየሙን በአል ምክንያት በማድረግም 800 ለሚሆኑ ችግረኛ የማህበሩ አባላት 19 ሺህ ብር የሚጠጋ ድጋፍ በቅርቡ መደረጉን ገልጸው፣በማህበሩ አባላት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው ሴቶች በገቢ ማሰገኛ ስራ ተሰማርተው በምግብ እህል ራሳቸውን ለመቻል ጥረት እንደጀመሩም ገልጸዋል፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሴቶች ትምህርት ቤት እንዲገቡ በማበረታታትና በልማት ስራ በማሳተፍ ድህነትን ለማስወገድ አንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ብለዋል ፡፡ እንዲሁም በጤና ኤክስቴንሽን በመሳተፍ ላይ የሚገኙ 144 ሺህ ያህል የማህበሩ አባላት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የጽዳት ዘመቻ መጀመራቸውን አስረድተዋል፡፡ የዞኑ ሴቶች ማህበር አባላት የሚሊንየሙን በአል ምክንያት በማደረግ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ችግኞች መትከላቸውንና እንዲጸድቁ በዘላቂነት እንክብካቤ እያደረጉ መሆኑን ወይዘሮ አልማዝ ገልጸዋል፡፡
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
688
የሴቶች እኩልነት እና መብት ሴቶች ዛሬም በ21ኛውም ክፍለ ዘመን መብታቸውን ከወንዶች እኩል አይከበርም። እንብዛም በኃላፊነት ቦታ ላይ አይታዩም። ያሉት ደግሞ እኩልነታቸውን ለማስከበር ብዙ መታገል አለባቸው። በተለይ ከሌሎች ሃገራት ጋር ሲነፃፀር ሴቶች አፍሪቃ ውስጥ በፖለቲካውም መድረክ ላይ እጅግ ስፍራ የላቸውም። አልፎ አልፎ ግን መድረኩን የሚደፍሩ አሉ። አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:24 የሴቶች እኩልነት እና መብት የፆታን እኩልነት ከሚያስከብሩ የዓለማችን አምስት ቀደምት ሃገራት ተርታ አፍሪቃዊቷ ሀገር ሩዋንዳ አንዷ ናት። እንደ Global Gender Gap የ 2016 ዓ ም መዘርዝር ምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ከአይስላንድ፣ ፊንላንድ፣ ኖርዌይ እና ስዊዲን ቀጥላ በአምስተኛነት ደረጃ ትሰለፋለች። ከአፍሪቃም ለነጋዴ ሴቶች ምርጥ ከሚባሉ ቦታዎች አንዷ ናት። በመዲና ኪጋሊ ሴቶች 40 ከመቶውን የንግዱን ቦታ ተቆጣጥረው ይገኛሉ። ይህ ብቻ አይደለም። በሩዋንዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ሴቶች ከ 60 ከመቶው በላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ደግሞ በፆታው እኩልነት መዘርዝር መሠረት 109ኛ ተርታ ላይ ትገኛለች። በፖለቲካው ዓለም ደግሞ 23 ከመቶ ያህሉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተሳትፎ እንዳላቸው መዘርዝሩ ይጠቁማል። የ33 ዓመቷ ኬንያዊት ናሱላ ሌሱዳ የማህበረሰቧን ባህል እና ወግ ተጋፍጣ በኬንያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያዋ ሴት አባል ለመሆን በቅታለች። ሁሉም ነገር እንዴት እንደጀመረ ለዶይቸ ቬለ እንዲህ ስትል ነበር የገለፀችው « የፖለቲካ ሥራዬን የጀመርኩት የፕሬዲንት ኡሁሩ ኬንያታ የምረጡኝ ዘመቻ በሚካሄድበት ወቅት በ 2012 ዓም ነው። ለፓርቲው ካገለገልን በኋላ በተለይ የሴቶችን ፍላጎትን ለሴኔቱ እንዳቀርብ እጩ ሆኜ ተመረጥኩ። በዚህ አጋጣሚ ነው ወደ ፖለቲካው የገባሁት።» ፖለቲከኛ መሆን ናሱላ ሌሱዳ የምትመኘው ሥራ ነበር? ምክንያቱም ወደ ፖለቲካው ከመግባቷ በፊት ጋዜጠኛ ነበረች።« በፍፁም ማለቴ የጋዜጠኝነት ሙያዬን ማዳበር እፈልግ ነበር። እና ጋዜጠኛ ሆኜ ለብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያው የዜና ክፍል በምሠራበት ወቅት፤ የበለጠ የምረዳውን፣ መዘገብ ደስ እንደሚለኝ ይበልጥ አውቅ ጀመር። እና ብዙውን ግዜ ስለመጣሁበት የሳምቡሩ ማኅበረሰብ እንድዘግብ እታዘዝ ነበር። እና ሥራዬን በምሰራበት ወቅት በዚህ አካባቢ ብዙ ተስፋ የቆረጡ ሰዎችን እታዘብ ነበር። ልጆች ትምህርት ቤት አይሄዱም። ውኃ የለም። ረሃብ ፣ድርቅ የመሳሰሉትን። አዕምሮዬ ውስጥ የቀረው ግን በአካባቢው የነበረው ግጭት ነው። ሰዎች በዚህ አካባቢ የሚፈልጉትን ለማግኘት ይገዳደላሉ። መሣሪያ ስላለን ላሞቻችሁን መስረቅ እንችላለን በሚል አይነት። የዚህ ተጠቂዎች ደግሞ ሕፃናት፣ ሴቶች እና ወጣት ወንዶች ነበሩ። እና ከማኅብረሰቡ ጋር በነበረኝ ቅርበት ይህንን ነገር መቀየር አለብኝ ብዬ ወሰንኩ። እና በዚህ አጋጣሚ ነው የህዝብ ግንኙነት ሥራዬን ትቼ ከዚህ አካባቢ የሚመጡ ታሪኮችን መቀየር ከሚፈልጉት ጋር ለመቀላቀል የቻልኩት።» ለወንድም ይሁን ሴት ወደፖለቲካው ዓለም ለመግባት የራሱ የሆነ ሂደት አለው። ወጣቷ ናሱላ በአብዛኛው ወንድ ከሚወስንበት ማኅበረሰብ ነው የመጣችው። ይህንን ሁሉ እንቅፋት ለመሻገር ከባድ ነበር ትላለች። «ስላላገባሁ ልጃ ገረዷ ብለው ነበር የሚጠሩኝ። እኔ ግን ቢያንስ አንዲት እንኳን ተነስታ ፈተናውን የምትጋፈጥ ሴት መኖር አለባት ብዬ ወሰንኩ።» በፖለቲካ አባልነት ቀርቶ ለሴቶች በተቃውሞ ሰልፍ ላይ ለመገኘት እንኳን ተስፋ አስቆራጭ ነው የምትለው ኢትዮጵያዊት የ 32 ዓመቷ ጠይባ ናት። እሷ እንደምትለው የሴቶች እኩልነት ከትዳር አጋራቸው ጋር ባለ ፉክክር ያበቃል። « በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳትፌ ነበር ነገር ግን ለምን አርፋችሁ እቤታችሁ አትቀመጡም። ከምን ከማይመጥናችሁ ጉዳይ መግባት እያሉ ክብር የሚነካ ነገር ነበር የሚነግሩን።» ጠይባ በነበራት ተሞክሮ የተነሳ ሀሳቧን በአደባባይ ከመግለፅ ተቆጥባለች። የ26 ዓመቷ ኢየሩሳሌም ተስፋው ደግሞ በ 97 ዓም የነበራት ተሞክሮዋ ነው ወደ ፖለቲካው ዓለም ያስገባት። « ምንም በማናውቀው ነገር ነው በ14 ዓመታችን ወታደሮች ከትምህርት ቤት እየገሩፉ የወሰዱን። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ነው በዚህ መንግሥት ላይ ውስጤ ጥሩ ያልሆነ ነገር ቋጥሬ ወደዚህ የገባሁት።» Symbolbild Frauenrechte Anne-Sophie Brändlin (DW) ኢየሩሳሌም እስከ 2007 ዓም ድረስም የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆና ቆይታለች። ከዛ በኋላ ግን እሷ እንደምትለው ከዛ በላይ የሰላማዊ ትግል ይቻላል ብላ ስላላመነች፤ መንግሥት የአሸባሪ ቡድን ብሎ የፈረጀውን የግንቦት ሰባት ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ስትጓዝ እሷ እና ጓደኞቿ ድንበር ላይ ተይዘው ለእስር ተዳርገዋል። አራት ዓመት ከአምስት ወር ተፈርዶባት በአመክሮ ከ 3 ዓመት እስራት በኋላ ቅርብ ጊዜ ነው ኢየሩሳሌም ከወህኒ የወጣችው። ኢየሩሳሌም ከፖለቲካዊ ተሳትፎዋ ባሻገርስ ሴቶች በዕለት ከዕለት ኑሯቸው ፣ በሥራው ዓለም ምን ያህል ተቀባይነት አላቸው ትላለች? « በበፊቱ የተሻለ ነገር አለ።» ትላለች። ጠይባም ብትሆን በማኅበራዊ ኑሮ በኩል በሴቶች መብት ላይ የተሻሻለ ነገር አለ ብላ ታምናለች። ይሁንና በአመራር ቦታ ላይ ያሉ ሴቶች አሁንም ብዙ መታገል አለባቸው። የመጀመሪያ ደረጃ መምህር ሆኖ ሰሜን ወሎ ውስጥ ያገለገለው አበበ በላይ የፆታ እኩልነት መከበር በገጠሩ አካባቢ ገና ብዙ እንደሚቀረው ነው የታዘበው። «ምክንያቱም ራሳቸው ሴቶች የፆታ እኩልነትን አምነው አልተቀበሉትም። ሴት ልጅ በትዳር ትቆያለች ስትፋታ አንዲት ላም ከነበረቻት ያቺን ላም ነው ይዛ የምትሄደው» አበበ የፆታ እኩልነት ልዩነቱን የታዘበው የፍች መብትን በማስከበር ላይ ብቻ አልነበረም። « የቅጥር ማስታወቂያ ራሱ የሆነ ጫና አለው። ሴቶች ከወንዶች አያንሱም ከተባለ እኩል ተፈትነው እና ተወዳድረው መቀጠር ይኖርባቸዋል።» ይላል። አበበ ሴቶች በአንድ በኩል እኩለነታቸውን በመጀመሪያ አምነው መቀበል አለባቸው ከዛ ባሻገር ደግሞ በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ላይ እንደተሰራው ሰፊ ሥራ መሰራት አለበት ሲልም ይመክራል።
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
689
የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከህገ መንግስቱ አኳያ Tue, Nov 01, 2016ቶሎሳ ኡርጌሳ ሐተታ የኢፌዴሪ ህገ መንግስት ልዮ ትኩረት ከሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ሴቶች ቀዳሚዎቹ ናቸው። በህገ መንግስቱ “የሴቶች መብት” አንቀፅ 35 ስር በተዘረዘሩ በዘጠኝ ንዑሳን አንቀፆች አማካኝነት እነዚህ የሴቶች ልዩ ትኩረትና ተጠቃሚነት ተገልፀዋል። በተለይም በንዑስ አንቀፅ ሶስት ላይ፤ “ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው። በዚህ በኩል የሚወሰዱ እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግስትና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው” በሚል ሴቶች ቀደም ባሉት ጊዜያት በነበሩባቸው የተለያዩ ማህበራዊ መስተጋብሮች ሳቢያ በበታችነትነና በተጨቋኝነት መንፈስ ያሳልፉ የነበረው ሁኔታ በህገ መንግስቱ ፍፁም መሻሩና የቀረ መሆኑ ተመልክቷል። ይህ ብቻ አይደለም። በዚሁ አንቀዕ ንዑስ አንቀፅ ስድስትና ሰባት ላይ፤ ሴቶች በብሔራዊ ልማት ፖሊሲዎች ዕቅድና በፕሮጀክቶች ዕቅድና አፈፃፀም፣ በተለይም የሴቶችን ጥቅም በሚነኩ ፕሮጀክቶች ሃሳባቸውን በተሟላ ሁኔታ እንዲሰጡ የመጠየቅ እንዲሁም ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደር፣ የመቆጣጠር፣ የመጠቀምና የማስተላለፍ መብት ያላቸው መሆኑን፤ በተለይም መሬትን በመጠቀም፣ በማስተላለፍ በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት እንዳላቸው ብሎም ውርስን በሚመለከት በእኩልነት የመታየት መብት እንዳላቸው ተደንግጓል። ከሴቶች መብቶች ጋር በተያያዘ የተገለፁት ሌሎች አንቀፆችም ቢሆኑ፤ ሴቶች በህብረተሰቡ የህይወት መዘውር ውስጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በመሆናቸው በህግ የተደረገላቸውን ልዮ ትኩረትና ጥበቃ የሚተነትኑ ናቸው። ታዲያ እዚህ ላይ ‘ህገ መንግስቱ ለሴቶች ልዩ ትኩረትና ጥበቃ ካደረገላቸው ዘንዳ፣ ህገ መንግስቱን በስራ በመተርጎምና የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ምን ተከናውኗል?’ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል። እናም በዚህ ፅሑፌ ላይ ከህገ መንግስቱ አኳያ ሴቶች ምን ያህል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንደሆኑ እንዲሁም በዚህ ሂደት የተከሰቱትን ተግዳሮቶች ለማሳየት እሞክራለሁ። ይህም የኢፌዴሪ መንግስት ልዩ የትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች እያደረገ ያለውን ጥረትና የሚፈጠሩ ችግሮችን በምን መንገድ እየፈታ እንደመጣ ሁነኛ ማሳያ ይሆናል በዬ አስባለሁ። የኢፌዴሪ መንግስት ህገ መንግስቱን ተከትሎ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ፖሊሲዎች እና እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወቃል—በሽግግር መንግስቱ ቻርተርና ኋላ ላይም ህገ መንግሰቱ በስራ በዋለባቸው 22 ተከታታይ ዓመታት። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ ከተሳትፎ አኳያ የሴቶች አጀንዳዎች በሁሉም ዘርፎች እንዲካተቱና ተጠያቂነትን በሚያጎሉ መንገድ ክትትል የማድረግ አቅጣጫ ተቀምጦ ገቢራዊ ሆኗል። በመሆኑም ሴቶች በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በአደረጃጀታቸው የአባላት ብዛትና በአመራር ሰጪነት ብቃት እንዲሁም በፖለቲካው መስክ የሚያደርጉት ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው እንዲጠናከሩ የሚያደርጉ ስራዎች ዕውን ሆነዋል። የፖለቲካውን ዘርፍ ስንመለከት፤ በዘርፉ በፌዴራልና በክልል ደረጃ ውሳኔ ሰጪነታቸው ትልቅ እመርታን አስመዝግቧል። በዚህም በህግ አውጪው (በፓርላማ) ያላቸው ተሳትፎ በፌዴራል ደረጃ 38 ነጥብ ስምንት በመቶ፣ በክልል እስከ 48 በመቶ እንዲሁም በወረዳ ደረጃ እስከ 50 በመቶ ደርሷል። በህግ ተርጓሚው ውስጥም ተሳትፏቸው 20 ነጥብ ስድስት በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ በህግ አስፈፃሚው ውስጥ ደግሞ 13 ነጥብ 72 በመቶ ያህል የሚሆኑት በከፍተኛ አመራርነት፣ 34 ነጥብ 12 የሚሆኑት ደግሞ በመካከለኛ አመራርነት ተሳታፊ ሆነዋል። ከምጣኔ ሃብት ተሳትፎና ተጠቃሚነት አኳያም፤ በመንግስት ከፖሊሲ ጋር የተያያዙ እርምጃዎች በመወሰዳቸው ሴቶች በተለያዩ ሀገራዊ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊ መሆን ችለዋል። በዚህም አበረታች ሊባል የሚችል ውጤት ተመዝግቧል። በተለይም ሴቶች መሬት፣ ብድርና ቴክኖሎጂ የመሳሰሉ የኢኮኖሚ ሃብቶችን የመጠቀምና የመቆጣጠር መብት እንዲጐናፀፉ ተደርጓል—ባለፉት ዓመታት። በህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረውን የሴቶችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች የመሬት ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አግኝተዋል። በቤት ውስጥ ያለባቸውን የስራ ጫና ለመቀነስም ሶስት ነጥብ አራት ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶችን የአማራጭ ኢነርጂና የተለያዩ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህም የሴቶችን ጊዜና ጉልበት በመቆጠብና ያለ ብዙ ድካምና እንግልት ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስችሏቸዋል። በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በስልጠና፣ የብድር አገልግሎት በማመቻቸትና የቁጠባ ባህላቸውን የሚያበረታታ እንቅስቃሴም ተከናውኗል። በህገ መንግስቱ ጥበቃ ያገኙት እንደ ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደርና የመቆጣጠር መብታቸውም የመሬት ተጠቃሚነት የባለቤትነት መብታቸውን አረጋግጧል። ይህም የባለቤትነት ስሜቱን ይበልጥ በማረጋገጥ በተዘረጋው የኤክስቴንሽን አገልግሎት በሥልጠና፣ በቴክኖሎጂ አቅርቦት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የሴቶችን እኩል የመሬት ተጠቃሚነትን መብት ለማረጋገጥ የክልል መንግስታት የመሬት ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በአባወራዎችና በእማወራዎች ስም በጥምር የመመዝገብ እርምጃ በመውሰዳቸውም፤ ሁለት ሚሊዮን እማወራና ዘጠኝ ነጥብ 11 ሚሊዮን እማወራና አባወራ በጥምረት የመሬት ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል። በጥቃቅንና አነስተኛ የልማት ዘርፍ ውስጥም ቢሆን የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ ነው። በዚህም በስልጠና፣ በመስሪያና በመሸጫ ቦታ እንዲሁም በብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። በግንባታ፣ በንግድና በከተማ ግብርና በመደራጀትም ተጠቃሚነታቸውን ከፍ አድርገዋል። በከተማ በዝቅተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሴቶች የቤት ባለቤት የመሆን፣ ንብረት የማፍራት፣ የማስተዳደርና የመቆጣጠር ህገ መንግስታዊ መብታቸው ዕውንና ተፈፃሚ ሆኗል። በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፕሮግራም የሚሳተፉ ሴት አንቀሳቃሾች ብድር እንዲያገኙና የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ምቹ ሁኔታዎች የተፈጠሩ ሲሆን፤ ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ፣ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ፣ ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሸጋገሩበት አቅጣጫ ተቀምጦም ተግባራዊ እንዲሆን በመደረጉ በመስኩ ያላቸው ተጠቃሚነት ከፍተኛ ሊሆን ችሏል። በዚህ ረገድ ያገኘኋቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ መንግስት በጥቃቅንና አነስተኛ ልማት መስክ 50 በመቶ የሚሆነውን የሥራ ዕድል ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ እንዲሆን በከተማ ልማት ፓኬጅ ግብ ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል። በዚህ ግብ መነሻነትም በርካታ ሴቶች ተጠቃሚ መሆን የቻሉ ሲሆን፤ በመንግስት ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ ካለው የስራ ዕድል 40 በመቶ የሚሆነው በሴቶች እንዲሸፈን ተደርጓል። ባለፉት 22 ህገ መንግስታዊ ዓመታት ሴቶች በሀገሪቱ ውስጥ በተፈጠሩ የመሰረተ-ልማት አውታሮችም ተጠቃሚነታቸው እየጎላ መጥቷል። ለምሳሌ ያህል በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ንፁህ የመጠጥ ውሃ በገጠር 82 በመቶ፣ በከተማ 91 በመቶና በሀገር አቀፍ ደረጃ 84 በመቶ ሽፋን በመድረሱ፤ ውሃን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ የሴቶችን ህይወት ይበልጥ ቀላል እንዲሆን አድርጎታል። ይህም ሴቶች ረጅም ርቀት ተጉዘው የሚያባክነኑትን ጊዜና ጉልበት በመቀነስ በምርት ተግባር ላይ እንዲያውሉ አድርጓቸዋል። በመንገድ መሰረተ-ልማትም በአሁኑ ወቅት በመላው ሀገሪቱ የተዘረጋው ጠቅላላ የመንገድ ርዝመት 110 ሺህ 414 ኪሎ ሜትር በመድረሱና ወደ 76 በመቶ የሚጠጉ የሀገራችን የገጠር ቀበሌዎች ክረምት ከበጋ በሚያስኬዱ መንገዶች እንዲገናኙ በመደረጉ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽፋን ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት በማሳየቱ፤ በርካታ የገጠር ከተሞችንና ቀበሌዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ከመቻለሉም በላይ፤ የሴቶችን ተጠቃሚነት የጎላ እንዲሆን አድርጎታል። የአገልግሎቱ መስፋፋት ሴቶችን ወጪ፣ ጊዜና ማገዶ ቆጣቢ በሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲጠቀሙ አስችሏቸዋል። በማህበራዊ መስክም ሴቶች ተሳትፏቸውና ተጠቃሚነታቸው እየጎለበተ መጥቷል። በተለይ “ሴት ልጅ ወደ ማጀት” የሚለውን ጎታች የህብረተሰቡን ባህልና አመለካከት በመቀየር፣ የትምህርት ተሳትፏቸውን የሚገድቡ እንቅፋቶችን የማቃለልና የመደገፍ ተግባራት ገቢራዊ ሆነዋል። ባለፉት ስርዓቶች የነበረው የስርዓተ-ፆታ ልዩነትም እየጠበበ መጥቷል። በዚህም ሴቶች ተሳትፏቸው በሁለተኛ ደረጃ 41 ነጥብ ዘጠኝ በመቶ፣ በመሰናዶ 30 በመቶ፣ በቴክኒክና ሙያ 51 ነጥብ ሁለት በመቶ እንዲሁም በዩኒቨርስቲ 32 በመቶ ሊደርስ ችሏል። ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም እንዲገቡ እየተደረገ ያለው የልዩ ድጋፍ እርምጃም (Affirmative Action) ተሳትፏቸው እንዲያድግ ሚናው የላቀ ነው። ሴቶች በገንዘብ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡም፤ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ ስልጠና በመስጠትና ተጨማሪ የትምህርት ጊዜ በማመቻቸት ትምህርታቸውን በውጤታማነት እንዲፈፅሙ እየተደረገ ነው። እዚህ ላይ ሳይጠቀስ የማይታለፈው ጉዳይ ቢኖር፣ ሴቶች በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ያገኙት ከፍተኛ ተጠቃሚነነት ነው። በጤና የልማት ሰራዊት ምክንያት በበርካታ አካባቢዎች በተከናወኑ አመርቂ ስራዎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ሽፋኑ ወደ 98 በመቶ አድጓል—በ38 ሺህ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ርብርብ። በዚህም የቤተሰብ ምጣኔ ወደ 42 በመቶ ከፍ ብሏል። እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ አማካኝነት የሚያገኙት የወሊድ አገልግሎትም ወደ 60 ነጥብ ሰባት በመቶ ማደግ ችሏል። የድህረ-ወሊድ አገልግሎትም ወደ 90 በመቶ ከፍ ብሏል። የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤቶችም የእናቶች ሞት ምጣኔ በ1982 ዓ.ም በመቶ ሺህዎች ውስጥ 1400 የነበረውን ጥምረት ወደ ከመቶ ሺህ ውስጥ 420 ዝቅ እንዲል አድርጓል። ይህ የእናቶች ሞት ምጣኔ መቀነስ ትርጉም ያለው ብቻ ሳይሆን፤ በጤናው ዘርፍ ያለውን እመርታ በጉልህ በማሳየት በህይወት የመኖር (Life Expectancy) ሁኔታን በመጨመር ሀገራችን በመስኩ ያስመዘገበችውን ድል ከፍ አድርጎ የሚናገር ይመስለኛል። ታዲያ ከላይ የጠቀስኳቸው ህገ መንግስቱንና እርሱን ተከትለው በወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ፕሮግራሞች አማካኝነት የተከናወኑት እነዚህ ተግባራት ከሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት አኳያ ሲመዘኑ መልካም ሊባሉ የሚችሉ ቢሆንም፤ ምንም ዓይነት ችግሮች አልነበሩም ማለት አለመሆኑ ግን ግልፅ ይመስለኛል። እናም በየትኛውም የስራ መስክ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እንደማይሆነው ሁሉ፤ በዚህም ዘርፍ ተግዳሮቶች መኖራቸው አይቀርም። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ ለሴቶች የሚሰጠው የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ሽፋኑና ጥራቱ የሚፈለገውን ያህል ያለመሆን፣ የስራ ጫናን የሚያቃልሉና በፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በሚፈለገው ደረጃ አለመቅረባቸው፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የእማወራዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት የሚጋፉ ሁኔታዎች መኖራቸውና ለድሃ ሴቶች የሚሰጠው የብድር አገልግሎት አቅርቦት የሚፈለገውን ያህል አለመሆን በተግዳሮትነት የሚጠቀሱ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የሴት ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያላቸው ውጤት አጥጋቢ እንዲሁም ተቋማቱ በሚፈለገው መጠን ምቹ ያለመሆናቸውና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና የሃይል ጥቃቶች በትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ተደማሪ ችግሮች ናቸው። በእኔ እምነት በሚቀጥሉት ጊዜያት እነዚህን ተግዳሮቶች በመፍታት የሴቶችን ህገ መንግስታዊ መብቶችን ይበልጥ ማጠንከር የሚገባ ይመስለኛል። በአጠቃላይ በሽግግር መንግስቱም ይሁን በሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በሙሉ ፈቃዳቸው ዕውን ባደረጉት ህገ መንግስት አማካኝነት ሴቶች ሁሉን አቀፍ መብቶቻቸው ተጠብቆላቸዋል። በተግባርም ተሳትፏቸውንና ተጠቃሚነታቸውን አረጋግጦላቸዋል። በዚህም ጠንካራ ስራዎች ተከናውነዋል። ታዲያ ጠንካራዎቹን ይበልጥ በማጎልበትና የተጠቀሱትን ተግዳሮቶች በተገቢው ሁኔታ እንዲፈቱ ማድረግ የሚቻል ይመስለኛል። ያም ሆኖ የኢፌዴሪ መንግስት እንደ የወጣቶች የልማት ፓኬጅ ዓይነት አሰራሮች ውስጥ ሴቶችን በማሳተፍና ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመው ዕቅድን በመሳሰሉ መስኮችን በማጠናከር በመስኩ የሚታዩ ችግሮችን እንደሚፈታ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻል ይመስለኛል።
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
690
የሴቶች መብት በኢስላም ክፍል 3 06 JAN 16. በሌሎች አናቅጽ መልዕክት መሠረት ወንድ የሴት ወንድም ነው። ሴትም የወንድ እህት ናት። የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን አስመልክተው ሲናገሩ፡- ﺇﻧﻢﺍ 17. “ሴቶች የወንዶች እህቶች ናቸው።” (አህመድ፣ አቡዳዉሩ፣ ቲርሚዚና ዳረሚይ ዓኢሻን ዋቢ በማግረግ ዘግበውታል።) በመለኮታዊ ትእዛዙ፣ በአምልኮዎችና በሃይማኖታዊ አጀንዳዎች ሴት ልጅ ከወንድ እኩል መሆኗን ቁርኣን ሲያስተምር፡- 18. “ሙስሊም ወንዶችና ሙስሊም ሴቶች፣ አማኝ ወንዶችና አማኝ ሴቶች፣ ታዛዥ ወንዶችና ታዛዥ ሴቶች፣ እውነተኛ ወንዶችና እውነተኛ ሴቶች፣ ታጋሽ ወንዶችና ታጋሽ ሴቶች፣ አላህን ፈሪ ወንዶችና አላህን ፈሪ ሴቶች፣ መጽዋች ወንዶችና መጽዋች ሴቶች፣ ጿሚ ወንዶችና ጿሚ ሴቶች፣ ብልቶቻቸውን (ከዝሙት) ጠባቂ ወንዶችና ሴቶች፣ አላህን በብዛት የሚያወሱ ወንዶችና ሴቶች አላህ ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን አዘጋጅቶላቸዋል።” (አል-አሕዛብ 33፤ 35) በሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ኃላፊነቶች ቁርኣን ሁለቱንም ጾታዎች እኩል ያደርጋል። 19. “የወንድና የሴት አማኞች ከፊሉ የከፊሉ ረዳት ናቸው። በመልካም ያዛሉ። ከክፉ ይከለክላሉ። ሶላትንም ደንቡን አሟልተው ይሰግዳሉ። ዘካንም ይሰጣሉ። አላህንና መልዕክተኛውንም ይታዘዛሉ። ለእነርሱ አላህ ያዝንላቸዋል። አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና።” (አት-ተውባህ 9፤ 71) 20. በአደም ታሪክ ውስጥ መለኮታዊ ትእዛዝ የተላለፈላቸው ለርሱም ለባለቤቱም ነው፡- 21. “አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ ገነት ውስጥ ተቀመጥ። ከርሷም (ከመልካም ፍሬዎቿም) በፈለጋችሁበት ሥፍራና ጊዜ ያሻችሁትን ተመገቡ። ይህችን ዛፍ ግን አትቅረቡ፤ ከበዳዮች ትሆናላችሁና።” (አል- በቀራህ 2፤ 35) ይሁንና በዚህ ታሪክ ውስጥ- በቁርኣን ትረካ መሠረት- ኃጢአት የማሠራቱን “ተግባር” የፈፀመው ሰይጣን እንጅ ሐዋእ አይደለችም። 22. “ሰይጣንም ከርሷ (ከገነት) አስወገዳቸው። ከነበሩበት (በውስጧም ከነበረው የገነት ድሎትም) አወጣቸው።” (አል-በቀራህ 2፤ 36) ሐዋእ ፍሬዋን ብቻዋን አልበላችም። ጀማሪም አልነበረችም። ስህተቱ የሁለቱም ነበር። ፀፀቱና ንስሐቸውም እንዲሁ የሁለቱም ነበር። “ታችን ሆይ! ራሳችንን በድለናል። ካልማርከንና ካላዘንክልን ከከሣሪዎች እንሆናለን በማለት (ጌታቸውን) ተማፀኑ።” (አል-አዕራፍ 7፤ 23) እንዲያውም በአንዳንድ የቁርኣን አንቀጾች ኃጢአቱ በዋነኛነት የአደም መሆኑ ተገልጿል፡- “ከዚህ ቀደም ከአደም ቃልኪዳን ይዘናል። ግና ረሳው። ቁርጠኝነትንም አላገኘንበትም።” (ጧሃ 20፤ 115) “ግና ሰይጣን ጐተጐተው። አደም ሆይ! ዝንተዓለም መኖርና የማይወገድ ሥልጣን ማግኘት የምታስችልህን ዛፍ ላመላክትህን? አለው።” (ጧሃ 20፤ 120) “አደም (በዚህ አኳኋን) የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ። ስህተት ላይ ወደቀም።” (ጧሃ 20፤ 121) ንስሐውም እንዲሁ የርሱ ብቻ እንደሆነ ተደርጐ ቀርቧል፡- “ከዚያም ጌታው መረጠው። ንስሐውንም ተቀበለው። መቀናትንም ለገሰው።” (ጧሃ 20፤ 122) ከነዚህ አናቅጽ የምንረዳው የኃጢአቱ አነሳሽ እርሱ እንደነበር እና ሐዋእ ተከታይ ብቻ እንደነበረች ነው። ምንም ይሁን ምን የሐዋእ ኃጢአት በርሷ ብቻ ተወስኖ የሚቀር እንጅ ወደ እንስት ልጆቿ የሚተላለፍ አይደለም። የአንዷን ነፍስ ኃአጢት ሌላዋ አትሸከምምና። “ይህች ያለፈች ሕዝብ ናት። ለርሷም የሥራዋ አላት። ለናንተም የሥራችሁ አላችሁ። እነርሱ ይሠሩት በነበረው እናንተ አትጠየቁም።” (አል- በቀራህ 2፤ 134) ሁለቱም ፆታዎች በምንዳና ጀነትን በመጐናፀፍ እኩል መሆናቸውን ቁርኣን ሲያብራራ፡- “ጌታቸውም ልመናቸውን ተቀበለ። እኔ ከናንተ ውስጥ ሴትም ሆነ ወንድ የማንኛችሁንም (መልካም) ሥራ ከንቱ አላደርግም። ከፊላችሁ የከፊሉ አካል ነው (አለ)።” (ኣሊ ዒምራን 3፤ 195) መልካም ሥራ እንደማይጠፋ በግልፅ አስቀምጧል። የወንድም የሴትም መልካም ሥራ። ሁለቱም ፆታዎች አንድ ናቸው። ከአንድ ዓይነት አፈር ከተመሳሳይ ቁስ ተፈጠሩ። አላህ እንዲህ ብሏል፡- “ከሴትም ይሁን ከወንድ አማኝ ሆነው መልካም የሠሩትን ጥሩ ሕይወትን እናኖራቸዋለን። ምንዳቸውንም ከሠሯቸው መልካም ሥራዎች ይበልጥ መልካም በሆነው (መኖሪያ) እንመነዳቸዋለን።” (አን-ነሕል 16፤ 97) “ከሴትም ከወንድም አማኝ ሆነው መልካም ሥራዎችን የሚሠሩ በእርግጥም ገነትን ይገባሉ። ቅንጣት ያህልም በደል አይደርስባቸውም።” (አን- ኒሳእ 4፤ 124)
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
691
የሴት ልጅ መብት በእስልምና የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ ይህን ይጫኑ ①.☞ የ ሴቶች የማስተማር መብት በኢስላም ”ኣማኝ ወንዶችና ኣማኝ #ሴቶች ከፊሎቻቸው ለ ከፊሉ ረዳቶች ናቸው በመልካም ያዛሉ ከመጥፎ የከለክላሉ።” (ሱራ 9:71) ②.☞ ገነት(ጀነት) #በእናት እግር ስር ናት (ነቢዩ ሰዐወ)። እናት ለዚሁ ከባድ ውለታዋ ይመስላል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም ‘ ☞ጀነትን #በእናቶች እግር ስር ናትና ፈልጓት ’ በማለት አቅጣጫ ማመለከታቸው ። ከእናቶች እንዳንርቅ በክድሚያቸው እንድንበረታ ጓደኝነታቸውን እንድንፈልግና እንድናጠብቅ ማሳሰባቸው ። እናም ሴቶች የኸይር(የጥሩ) ነገሮች በር መክፈቻ ናቸው ማለት ነው። ③☞ ሴትን ልጅ የሚያልቅ ሰው የለም እርሱ የላቀና የተከበረ ሰው ቢሆን እንጂ ሴትን የሚያዋርድ ሰው የለም እርሱ የተዋረደ ሰው ቢሆን እንጂ ። ረሱል (ሰዐወ) ④☞‹‹ስለ ሚስቱ የተገደለ ሰው ሰማዕት (ሸሂድ) ነው፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1421/ አቡ ዳውድ 4772) ⑤☞ በአንድ ወቅት አንድ ሰው ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም ዘንድ መጣና ‘ ልወዳጀው ዘንድ ለመልካም ወዳጅነት እጅግ ተገቢው ሰው ማነው ?’ አላቸው ። እሳቸውም በመጀመሪያ እናትህ አሉት ። ሰውዬውም ‘ ቀጥሎስ ?’ አላቸው ። ነብዩም ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለምም በ2ኛም ‘ እናትህ ’ አሉት ። ሰውዬው አሁንም ‘ ቀጥሎስ ? ’ አላቸው ‘ በ3ኛ ደረጃም እናትህ ’ ሲሉ መለሱለት ረሱል(ሰዐወ) ። ሰውዬው አሁንም ‘ ቀጥሎስ ? ’ አላቸው ። እሳቸውም በመጨረሻ(በ4ኛው) ‘ አባትህን ’ አሉት ። ተመልከት እናት የወርቅ፣የብር፣የነሃስ መደሊያውን ስታጠልቅ አባት ግን የ4ኛ ደረጃ (የዲፕሎም) ተሸላሚ ነው። የመፅሃፍ ቅዱሱን ስለ ሴት ልጅ ለማንበብ☞ click☞ https://goo.gl/hwS9Gn መፅሀፍ ቅዱስ በፍፁም ስለ እናት አያወራም ስለ አባት ግን ጠቢብ ልጅ የአባቱን ምክር በማስተዋል ይሰማል ምሳሌ13:1ይገልፃል ⑥☞ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግን “ከአማኞች ኢማኑ (እምነቱ) የተሟላው ስነ ምግባሩ ያማረው ነው፡፡ ከናንተ በላጫቻችሁ #ለሴቶቻቸው በላጭ የሆኑት ናቸው” ብለው ነበር፡፡ [አስሶሒህ፡ 284] ⑦☞መልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “#በሴቶች ጉዳይ አደራችሁን” ብለው ነበር፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] ⑧☞ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዱንያ መጣቀሚያ ነች፡፡ ከመጣቀሚያዎቿ ሁሉ በላጩ ደግ (ሷሊህ) የሆነች #ሴት ናት” ፡፡ [ሙስሊም] ⑨☞ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “አንድ ሙእሚን ወንድ አንዷን ሙእሚናህ #ሴት (ሚስቱን) አይጥላ፡፡ ከሷ የሆነን ባህሪ ቢጠላ ሌላ የሚወደው አለውና፡፡” [ሙስሊም] ☞ #ባል የሌላት ሴት ምስኪን ደሀ ናት አሉ ረሱል (ሰ.አ.ወ) ለምን? ተብለው ሲጠየቁ ሚስት የባሏን ፊት በፈገግታ ስትመለከት ብቻ ቤተል ጣኢፍን የተመለከተች ያህል ነው። ደስታው ለባሏ መልካም የሆነች ሴት ከቤተሰቦቿ አርባ የሚሆኑ ለጀሀነም የተወሰኑ በሷ ምትክ ነጃ ይወጣሉ። (ረሱል ሰዐወ) ⑩☞ረሱል(ሰዐወ) ሊሞቱ ሲሉ ለሰሃቦቻቸው ሰብስበው ካደረጉት ከመጨረሻ ንግግራቸው ውስጥ አንዱ:- ☞ “#በሴቶቻችሁ ላይ አላህን ፍሩ (እንዳትበድሏቸው) #በሴቶቻችሁ መልካምን እንድትውሉ እመክራቹሀለው “። ⑪☞ውዱ ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ #ለሴቶች ከምትበሉት አብሏቸው፡፡ ከምትለብሱትም አልብሷቸው፡፡ አትምቷቸውም፡፡ አላህ አስቀያሚ ያድርግሽ እያላችሁም አትርገሟቸው” ብለዋል፡፡ [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1861] ⑫☞“ሁለት #ሚስት ኖሮት ወደ አንዷ ያጋደለ ሰው ነገ በቂያማ ቀን አንድ ጎኑ የወደቀ ሆኖ ይመጣል” ይላሉ፡፡ [ሶሒሑ መዋሪዱዝዞምኣን፡ 1089] ⑬☞ (ለእነሱም (#ለሴቶቹ) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ሃላፊነት) አምሳያ (ሐቅ በባሎቻቸው ላይ) አላቸው፡፡” [አልበቀራህ፡ 228] ⑭☞ (ሴቶችን በመልካም ተኗኗረዋቸው፡፡) [አንኒሳእ፡ 19] ⑮☞ “አዋጅ! ለናንተ #በሴቶቻችሁ ላይ ሐቅ አላችሁ፡፡ #ለሴቶቻችሁም በናንተ ላይ ሐቅ አላቸው፡፡” [ሶሒሑልጃሚዕ፡ 7880] ⑯☞“ለቤተሰብህም ባንተ ላይ ሐቅ አለ፡፡ እያንዳንዱን ባለ ሐቅ ሐቁን ስጥ!” [ቡኻሪ] click☞ https://goo.gl/hwS9Gn ⑰☞ድንገት በሴትና በወንድ መካከል ፀብ ቢፈጠር በመልካም ሁኔታ መለያየት እንዳለባቸው አላህ (ሱወ) እንዲህ ይነግረናል፡፡ ☞(በመልካም መያዝ፤ ካልሆነ በበጎ መለያየት) ፡፡ [አልበቀራህ፡ 229] ⑱☞ “ለሚስትህ ባንተ ላይ ሐቅ አለት፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም] ⑲☞ቡረይዳህ አባቱን ዋቢ አድርጎ ያስተላለፈው ነው በማለት አልበራዝ በዘገቡት ሀዲስ አንድ ሰው #እናቱን በጀርባው ተሸክሞ በከዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ያደርጋል ። ሰውየው ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም አገኛቸውና ‘ ውለታዬን መልሻለሁን ? ’ ሲል ጠየቃቸው ። እሳቸውም ‘ በፍፁም አልመለስክም ። ይህ ስራህ እሷ ላንተ ስትል የደነገጠችውን አንዲት ድንጋጤ እንኳን የሚመጥን አይደለም ። ’ አሉት ። ⑳☞ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከሙእሚኖች መካከል የተሟላው ሙእሚን በስነ ምግባሩ በላጭ የሆነው ነው፤ በላጮቻችሁ ለሚስቶቻቸው በስነ ምግባራቸው ጥሩዎቹ ናቸው፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1162) 21☞ ረሱል(ሶዐወ) አራት ነገሮች ደስታን የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል ። 1ኛ☞ጥሩ(ሷሊህ) #ሚስት 2ኛ☞ ሰፊ ቤት 3ኛ☞መልካም ጎረቤት 4ኛ☞ምቹ መጓጓዣ 22☞ ሴቶችን መንከባከብ ያላው ፋይዳ ዓኢሻ(ረዐ) እንዲህ ብለዋል:- << አንዲት ሁለት ሕፃናትን የያዘች ሴት ወደኔ መጣችና እንድረዳት ጠየቀችኝ። በወቅቱ ቤቴ ውስጥ የነበረው አንድ ፍሬ ቴምር ብቻ ስለ ነበር እሱን ሰጣዋት። ሴትየዋም ተቀብላኝ ቴምሩን ከፍላ ለሁለቱ ሴት ልጆቿ ሰጠቻቸው። ከተምሩ ለራሷ ምንም ነገር አልቀመሰችም። በኋላ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ቤት ሲመጡ ስለሴትየዋ ድርጊት ነገርኳቸው። እሳቸዉም:- ☞ “#በሴት ልጆች ምክንያት ፈተና ውስጥ የወደቀ ማንኛውም ሰው ለእነርሱ በሚያደርገው እንክብካቤ የተነሳ ከጀሃነም እሳት ይጠበቃል” አሉኝ። (ቡኻሪና ሙስሊም ቲርሙዚ) 23.☞ስለ ወር አበባ ደም(ሀይድ)በኢስላም አዒሻ ረ.ዐ እንዲህ አሉ:- የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ በወር አበባ ላይ እያለው በታፋዬ ላይ የሚደገፉና ቁርአን የሚቀሩ ነበር (ቡኻሪይ 301 ሙስሊም 8/297) ስለ ወር አበባ በክርስትና ሴት ጊዜውን እየጠበቀ የሚመጣው የደም መፍሰስ ቢኖርባት የወር አበባ እርኩሰት እስከ ሰባት ቀን ይቆያል በዚህ ጊዜ ማንም ሰው ቢነካት እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል የተጠቀመችበትን ማንኛውም ነገር የነካ ሰው ልብሱን ይጠብ ሰውነቱንም በውሀ ይታጠብ እስከ ማታ ድረስ ግን እርኩስ ይሆናል ዘሌላውያን15:19-22 የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ ይህን ይጫኑ☞click☞ https://goo.gl/hwS9Gn 24.☞በሙሰሊም #ሴት_ልጅ <“በእርግዝናና በወሊድ እሰከ ማጥባት ባለው ጊዜ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ጂሃድ(ታጋይ) ምንዳን ታገኛለች:: በዚሁ መካከል ሕይወቷ ቢያልፍ የሸሂድ (የሰማዕትትን) ምንዳ ታገኛለች” > (ጠበራኒ የዘገቡት) 25.☞ እንደዚሁ #ሴት ልጅ ከደረሰች ቦሃላ ስታገባ ባልዋ ግማሽ ኢማኑ(እምነቱ) እንዲሞላ ምክንያት ናት። 26.☞ ነብዩ መሐመድ(ሰዐወ) ስለ መልካም #ሚስት እንዲህ ብለዋል “አለም ለመኖር የሚያስፈልጉትን መጠቀሚያዎች አካታ የያዘች ስትሆን ከይዘቶቿ ሁሉ በላጩ ደግሞ ምግባረ በጎ (ጥሩ) #ሚስት ነች” (ሙስሊም ዘግበውታል) 27.☞ “ያን በርሱ (የጋራ መብቶቻችሁን) የምትጠያየቁበትን አላህ ፍሩ፤ ዝምድናንም (ከመቁረጥ ተጠንቀቁ)።” (አን-ኒሳእ 4፤1) የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ይህን አስመልክተው ሲናገሩ፡- በሌሎች አናቅጽ መልዕክት መሠረት ወንድ የሴት ወንድም ነው፡፡ ሴትም የወንድ እህት ናት፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ›አ›ወ) ሲናገሩ፡- ‹‹ ሴቶች የወንዶች እህቶች ናቸው፡፡››(አህመድ፤ አቡዳውድ፤ ቲርሚዚና ዳርማይ ዓኢሻን ዋቢ በማድረግ ዘግበውታል) 28.☞ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው።” በሁሉም ላይ። ፆታ አልተለየም(ወንድ እና ሴት)። 29.☞ ሴት ጥበቃና ከለላ ለጠየቃት የመስጠት መብትም አላት። ከለላዋም ይከበርላታል። ☞የአቡ ጧሊብ ልጅ ኡም ሃኒእ መካ በድል በተከፈተችበት ዕለት ከአጋሪዎች ለአንዱ ከለላ ሰጥታለች። በእርግጥ ወንድሟ ሊገድለው ፈለገ። ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰሰችው። “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እኔ ጥበቃና ከለላ የሰጠሁትን ሰው የእናቴ ልጅ ሊገድለው ያንገራግራል” አለቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም፡- “አንቺ ከለላ የሆንሽለትን ከለላ ሰጥተነዋል” አሏት። (ቡኻሪና ሙስሊም) 30.☞ የሰው ልጆች ሁሉ ቁንጮ የሆኑት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ለዑመር እንዲህ ብለውታል፡-‹‹አንድ ወንድ በዚህች ዓለም ውስጥ ከሚኖሩት ሃብቶች ሁሉ እጅግ ውድ የሆነው የትኛው እንደሆነ ታውቃለህን? ለወንድ ልጅ በዚህች ዓለም ውስጥ ውዷ ሃብቱ፤ ሲያያት የምታስደስተው፤ ሲያዛት የምትታዘዘው፤ ርቆ ሲሄድ ታማኝ ሆና የምትጠብቀውታማኝ ሚስት ናት፡፡››(አቡ ዳውድና ሐኪም) አንጸባራቂው ቁርአን ይህንን በማስመልከት እንዲህ ይላል፡- 31.☞ ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም ተጣማሪዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን ከሁለቱም በርካታ ወንዶችንና ሴቶች ያበዛውን ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ያን በርሱ (የጋራ መብቶቻችሁን)የምትጠያየቁበትን አላህን ፍሩ፤ ዝምድናንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡ ›› (ሱረቱ አል- ኒሳእ ምዕ.4 ቁ.1) አንድ ምሁር ይህን የቁርዐን ጥቅስ አስመልክቶ እንዳሰፈረው፡- ‹‹ እንደሚታመነው ሴት ስብአዊ ፍጡርነት በሁሉም አቅጣጫ እንዲህ በሚያስደንቅ አጭር አገላለጽ ጥልቀትና አዲስነት ባለው ጥበብ የተሞላበት የፈጣሪ ህግ ማሳመኛ በማኛውም ፅሁፍ በአሮጌውም በአዲሱም የለም፡፡››(El- khouly, Al Bahly, ‘min usus kadiyat Almar’ah’ (Al-wa’ay-Islam, ministry ok wakf, Kuwait, Vol.3, No.27, June 9,1965) p.17) ☞ሴት ልጅ ልክ እንደ ወንዱ በመንፈሳዊ ህይወት አላህ(ሱ.ወ) ዘንድ እኩል ናት። …….መንሳዊ ህይወትን በተመለከተ ሴቶችም በአላህ ዘንድ ከወንዶች ጋር እኩል ደረጃ እንደሚታዩ በተከበረው ቁርአን ውስጥ በማያሻማ ሁኔታ ተገልጿል አላህ (ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡- 32.☞‹‹ነፍስ ሁሉ በሰራችው ሥራ ተያዥ ናት›››(ሱረቱ አል-ሙደሲር 74፡38) ﻓَ33.☞ ‹‹ጌታቸውም ‹‹እኔ ከናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሰሪን ስራ አላጠፋም፤ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው በማለት ልመናቸውን ተቀበለ፡፡›› (ሱረቱ አል- ኢምራን 3፡195) 34.☞ ‹‹ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡›› (አል-ነህል 16፡97) 35.☞ ‹‹ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም፡፡›› (ሱረቱ አል-ኒሳእ 4፡124) 36.☞ ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡›› (ሱረቱ አል-ሁጁራት 40፡13) የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ ይህን ይጫኑ ☞ click☞ https://goo.gl/hwS9Gn ከላይ ያየናቸው የቁርአን አንቀጾች እንደሚያመለክቱት ሴት ልጅ ልክ እንደ ወንዱ በመንፈሳዊ ህይወት አላህ(ሱ.ወ) ዘንድ እኩል ናት ሴት ልጆችን በመንከባከባችን ከአላህ(ሱወ) የምናገኘው ትሩፋት ። 37.☞‹‹ማንኛውም ሴት ልጅ ያለው ሰው በህይወት እያለች ያልቀበራት ፤ ያላዋረዳት፤ በርሷም ላይ ወንድ ልጁን አብልጦ ያልተመለከተ አላህ ገነትን ይመነዳዋል፡፡›› (የኢብን ሐምበል የሀዲስ መፅሐፍ ቁ.1957) 38.☞‹‹ለአቅመ ሄዋን ብቁ እስኪሆኑ ድረስ ሁለት ሴት ልጆችን አንከባክቦ ያሳደገ እኔና እርሱ በፍርድ ቀን አንድ ላይ እንመጣለን። በማለት/ሁለት ጣቶቻቸውን በማገናኘት/ አረጋግጠዋል፡፡›› በተመሳሳይ ሁኔታም ሁለት እህቶቹን የሚል የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር። (በኢብኑ ሐምበል የሀዲስ መጽሀፍ ቁ.2104 ) 39.☞ኢብን ዐባስ እንዳተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሁለት ሴት ልጆች ኑረውት ለነርሱ የሚያደርገውን እንክብካቤ ያሳመረ፤ አንድም ሙስሊም የለም፤ ጀነት ያስገቡት ቢሆን እንጅ፡፡›› (ቡኻሪ፤ ኢብን አቢ ሸይባህ፤ አህመድና ኢብን ማጃህ) 40.☞‹‹ሦስት ሴት ልጆች ወይም ሦስት እህቶች አሊያም ሁለት ሴት ልጆች ወይም ሁለት እህቶች ያለው መልካም ከዋለላቸው ፤ በነርሱ ላይም ከታገሰ (በጽናት ካገለገላቸው) እና በነርሱም ላይ አላህን ከፈራ ጀነት (ገነት) በእርግጥ ይገባል፡፡›› (አቡዳውድ፤ ቲርሚዚ እና ኢብን ሂባን የዘገቡት) 41.☞እንዲሁም የአላህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ሴት ልጆቻችን ተንከባክቦና በመልካም ሥነ-ምግባር አንጾ ለሚያሳድግ ሰው ጀነትን ቃል ገብተውለታል፡፡ ጀነት ውስጥ ከርሳቸው ጎን እንደሚሆንም አበስረውታል፡፡ ቲርሚዚ ባሰፈሩት ሌላ ዘገባ ደግሞ፡- 42.☞ ‹‹ሁለት እንስቶችን የተንከባከበ፤ እኔና እርሱ ወደ ጀነት እንደዚህ ሆነን እንገባለን በማለት በአውራና በሌባ ጣቶቻቸው አመላከቱ፡፡›› ሌሎች የሀዲስ ዘገባዎች ደግሞ ለየትኛዋም ሴት ልጅ ቁጥሯ አንድም ይሁን ከዚያም በላይ መልካም የዋለ ሁሉ ይህን መለኮታዊ ሽልማት እንደሚያገኝ አስፍረዋል፡፡ 43.☞አቡ ሁረይራ(ረ.ዐ) ባስተላለፉት ዘገባ መልዕክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) ‹‹በስሩ የሚያስተዳድራቸው ሦስት ሴት ልጆች ኑረውት ክፉ ደጋቸውን ተጋርቶ ያሳደጋቸው፤ አላህ በነርሱ ሰበብና እዝነት ጀነት ያስገባዋል›› በማለት ተናገሩ፡፡ ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሁለት ቢሆኑስ? አላቸው አንድ ሰሃባ(የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረባ)፡፡ ‹‹ሁለትም ቢሆኑም›› አሉ፡፡ አንድ ሌላ ሰውም፡- ‹‹አንድ ብትሆንስ?›› አላቸው፡፡ ‹‹አንዲትም ብትሆን›› ሲሉ መለሱ፡፡›› ☞ነቢዩ (ሰዐወ) ከመምጣታቸው በፊት(በጃህሊያ ዘመን) ሴት ልጅ ስትወለድ ከነህይወቷ ትቀበር ነበር ። እዚህ ጋር ቆም ብለን አንድ ነገር ማስተዋል ግድ ይለናል፡- እንደሚታወቀው ዐረቦች ነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጠፍቶና ተረስቶ የነበረው የፈጣሪ ሃይማኖትን ኢስላምን ለማዳረስ ከመላካቸዉ በፊት ሴት ልጅ ስትወለድላቸው ይሸማቀቁ ነበር፡፡ ከዚያም ይባስ ብሎ ሴት ልጅ ስትወለድላቸው ከነህይወቷ እስከመቅበር ይደርሱ ነበር፡፡በቀድሞው አረቢያ ምድር ኑሮ ለሴቶች ምን እንደሚመስል በለንደኑ የቤክ ኮሌጅ መምህርት የሆነችው ኘሮፌሰር ከረን አርምስትሮንግ እንዲህ ትገልፃለች፡- ☞“የግድ ልናስታውስ የሚገባነ ሴት ልጅን ከነህይወት መቅበር ልማድ በነበረበት በምንም መልኩ መብት ባልነበራቸውና የበታች ፍጥረት እንደባሪያ ተደርገው በቀድሞው አረቢያ ሴቶች በሚታዩበት ጊዜ ሙሐመድ ለሴቶች የዋለው ውለታ ልዩ ነበር፡፡ በተለይ ህዝቡን ያስገረመው የድርሻቸውን መውረስና ምስክር መሆን ይችላሉ ማለቱ ነበር፡፡” (Karan Armstrong Mohammed, a biography of the prophet, p. 191) የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ ይህን ይጫኑ ☞ click☞ https://goo.gl/hwS9Gn በቀድሞ አረብያ የሴት ከነህይወቷ መቀበር እውነቷ አላህ(ሱ.ወ) አንጸባራቂ በሆነ ቃሉ ድርጊቱን በማውገዝ እንዲህ ይላል፡- 44.☞ ‹‹ከነሕይወቷ የተቀበረች ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤ በምን ወንጀሏ እንደተገደለች፤›› (ሱረቱ አል- ተክዊር 81፡7-8) 45.☞ በተጨማሪም አላህ (ሱ.ወ) አባቶች ሴት ልጆች በተወለዱላቸው ጊዜ ይሰማቸው የነበረውን ስሜት እንዲህ ገልጾታል፡- ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺑُﺸِّﺮَ ﺃَﺣَﺪُﻫُﻢ ﺑِﺎﻟْﺄُﻧﺜَﻰٰ ﻇَﻞَّ ﻭَﺟْﻬُﻪُ ﻣُﺴْﻮَﺩًّﺍ ﻭَﻫُﻮَ ﻛَﻈِ ‹‹በነርሱ መካከል አንዱ በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ ፊቱ በሐዘን ይጠቁራል፡፡ ቅስሙ ይሰበራል፡፡ በተነገረው ‹‹መርዶ›› ሰበብ ራሱን ከሰዎች ይደብቃል፡፡ የሚደርስበትን ውርደት ችሎና ተሸክሞ ይያዛት ወይስ አፈር ውስጥ ይቅበራት? አዋጅ ፍርዳቸው እጅግ ከፋ!›› (ሱረቱ አል-ነህል 16፡ 58-59) በነዚያ ልጆቻቸውን በሚገድሉ ጨካኝና አረመኔ ወላጆች ላይ ቁርአን ጠንካራ ውግዘት ሰንዝሯል ፡- 46.☞‹‹እነዚያ በቂልነትና በአላዋቂነት ልጆቻቸውን የገደሉ ›› (ሱረቱ አል-አንአም 6፡140) 47.☞‹‹ድህነት በመስጋት ልጆቻችሁን አትግደሉ፡፡ እኛ እናበላቸዋለን፡፡ እናተንም እንዲሁም:: እነርሱን መግደል በእውነቱ ታላቅ ኃጢአት ነው፡፡›› (ሱረቱ አል-ኢስራእ 17፡31) አንዳንድ ቀደምት ሕጎችና ልምዶች አባት ልጁን ሰፈልግ እንዲሸጥ መብት ይሰጡት ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ ምሳሌ የሐሙራቢ ሕግ አንድ ኣባት የሌላን ሰው ሴት ልጅ ከገደለ ለባለ ደሞቹ የራሱን ሴት ልጅ ይገድላት ወይም በሃብትነት ይጠቀምባት ዘንድ የመስጠት ደንብ ደንግገውለታል፡፡ ኢስላም ሲመጣ ሴት ልጅ እንደወንዱ ሁሉ የአላህ ስጦታ መሆኗን አወጀ፡፡ አላህ ለሚሻው የሚሰጣት ለሚሻው የሚነፍጋት ፀጋ መሆኗን ገለፀ፡፡ ይህንንም አስመልክቶ አላህ (ሱ.ወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል፡- 48.☞‹‹ የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል፡፡ ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም መካን ያደርጋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ(ያሻውን መፈፀም)የሚችልም (አምላክ) ነውና፡፡ ›› (ሱረቱ አል-ሹራ 49-50) በሚገርም ሁኔታ አንዳንድ እንስቶች ከወንዱ ይበልጥ ክብርና ዝና ያላቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ቁርአን በትረካዎቹ አስተምሯል፡፡ የመርየም- የኢምራን ልጅ ታሪክ እንደምሳሌ ይጠቀሳል፡፡ አላህ መረጣት፡፡ ንጽሕትና በፅዕት አደረጋት፡፡ ከዓለማት እንስቶችም አበለጣት፡፡ እናቷ እርሷን አርግዛ እያለ ፅንሷ ወንድ ቢሆን ትመኝ ነበር ፡፡ የቤተ-አምልኮ አገልጋይ እንዲሆን፤ ከደጋግ ሰዎች እንዲሆን ታልም ነበር፡፡ ይህንንም አስመልክቶ አላህ(ሱ.ወ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡- 49.☞‹‹የዒምራን ሚስት እንዲህ ባለች ጊዜ(የሆነውን አስታውስ)፡-‹‹ጌታዬ ሆይ! ከሆዴ ውስጥ የተሸከምኩት (ፅንስ) (ተግባሩ አንተን ብቻ ማገልገል) ይሆን ዘንድ ተሳልኩ፡፡ ይህንን ተቀበለኝ፡፡ አንተ ሰሚም ዐዋቂም ነህ፡፡›› በወለደቻት ጊዜ፡- ‹‹ጌታዬ ሆይ! የወለድኳት ሴት ልጅ ናት›› አለች፡፡(ይህን ተናገረች አልተናገረች ለውጥ የለውም፡፡) የወለደችው ምን እንደሆነ አላህ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ‹‹ሴት ልጅ እንደወንድ ልጅ አይደለችም፡፤ መርየም ብዬ ሰይሜያታለሁ፡፡ እርሷንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ›› (ስትል አከለች)፡፡ አላህ በመልካም አቀባበል ተቀበላት፡፡ መልካም አስተዳደግም አሳደጋት፡፡›› ( ሱረቱ አል-ኢምራን 3፡ 35-37) 50.☞ ‹‹ኢስላም ለአንዱ ፆታ ‹‹ወንድ›› ለሌላኛው ‹‹ሴት›› በሚለው መጠራታቸው መበላለጥን አያመለክቱም በማለት ያስተምራል፡፡ በሴት ጾታ መጠራት የበታችነትን አያመለክትም፡፡ የበታችነትን የሚያመለክት ቢሆን ኖሮ አላህ(ሱ.ወ) በቁርአን ጨረቃን በወንድ ጾታ ፀሐይን በሴት ጾታ ባልጠራ ነበር ። ምክኒያቱም ከጨረቃ ፀሐይ ትበልጣለችና፡፡ እንደዚሁም አላህ ሰማይን ፤ ዓለምን ፤ ነፍስ ምድርን እና ገነትን(ጀነትን)በሴት ጾታ ጠርቷቸዋልና፡፡ (የሴቶች መብትና እኩልነት ገጽ 38) ነብዩ ሙሐመድ(ሰ›ዐ.ወ) ያለ ጾታ ልዩነት ሁሉም ሰው እኩል መሆኑን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፡- 51.☞‹‹ሰዎች በሙሉ እንደ ማበጠሪያ ጥርስ እኩል ናቸው፡፡ ዐረብ የሆነው ዐረብ ካልሆነው(ዐጀም) በላይ ሊታይ የማይችልበት ነው፡፡ ነጩ የጥቁር የበላይ የሚሆንበት ወንዱ ከሴት የሚበልጥበት መንገድ የለም፡፡ በአላህ ዘንድ ይበልጥ የሚወደዱት (የተከበሩት) እሱን የሚፈሩት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡›› (ኢማሙ አህመድ የዘገቡት) ሴት ልጅ ጋብቻ እና ትዳር መረጣን በተመለከተ :- ይህን ይጫኑ☞ click☞ https://goo.gl/hwS9Gn እንደ ኢስላም አስተምሮ አባት ሴት ልጅን እርሷ ለማትፈልገውና ላልወደደችው ባል መዳር አይችልም ፡፡ በርሷ ጋብቻ ጉዳይ ሊያማክራት ግድ ይላል፡፡ ፈቃደኝነቷን ማረጋገጥ አለበት ፡፡ ከአሁን ቀደም የጋብቻን ህይወት የምታውቅ ከሆነች አዲሱን ጋብቻ በግልጽ ቋንቋ ማጽደቋ መረጋገጥ አለበት፡፡ ልጃገረድ ከሆነች ደግሞ ሐፍተት ስለሚይዛት ስምምነቷን በዝምታ መግለጽ ይኖርባታል፡፡ ዝምታዋ ከስምምነት ይቆጠራል ፡፡ ሴት ልጅ ጋብቻው አይሆንም ካለች ግን የማትፈልገውን እንድታገባ አባት ሊያስገድዳት ሥልጣን የለውም፡፡ 52.☞ቡኻሪና ሙሰሊም አቡ ሁረይራን በመጥቀስ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፡- ‹‹ሴት ልጅ ያለፈቃዷ ልትዳር አይገባም፡፡ ልጃገረድም ፈቃዷ መጠየቅ አለበት››አሉ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! (ልጃገረድ) መፍቀዷ በምን ይታወቃል?›› አሏቸው፡፡ ‹‹በዝምታዋ›› ሲሉ መለሱ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም) 53.☞ኢብን አባስ እንዳተላለፉት አንዲት ልጃገረድ ከነብዩ ዘንድ ቀረበች ፡፡ አባቷ ያለፍቃዷ ሊድራት መሆኑን ነገረቻቸው፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) የፍላጎቷን ትመርጥ ዘንድ ዕድል ሰጧት፡፡›› (አህመድ፤ አቡዳውድ፤ ኢብን ማጃህና ዳረል ቁጥን) 54.☞ቡኻሪና ሙስሊም ባሰፈሩት ሌላ ዘገባ እንደተመለከተው ዓኢሻ ነብዩን፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሴት ልጅ ለጋብቻ ፍቃዷ ሊጠየቅ ይገባልን? በማለት ጠየቀች፡፡ ‹‹አዎ›› አሏት፡፡ ልጃገረድ እኮ ፈቃድ ስትጠየቅ ሐፍረት ተስምቷት ዝም ልትል ትችላለች›› አለቻቸው፡፡ ‹‹ዝምታዋ የፈቃዷ መግለጫ ነው›› አሏት፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም የኢስላም ሊቃውንቶች ከዚህ ሐዲስ በመነሳት፡- ለልጃገረድ ዝምታዋ ፈቃዷ መሆኑን መንገር ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ 55.☞ኸንሳእ ቢንት ኀዳም አል-አንሷሪያ የተባለች ሴት እንዳስተላለፈችው አባቷ ለማትፈልገው ሰው ዳራት፡፡ አግብታ የፈታች ነበረች፡፡ ከነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ መጣችና ስሞታ አሰማች፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ጋቻውን ውድቅ አደረጉ፡፡ (ሁሉም የሐዲስ አውታች ዘግበውታል ሙስሊም ሲቀሩ) ልጃገረድን ለመዳር የርሷ ፍቃድ እና ስምምነት ማግኘት የግድ በመሆኑ ረገድ አባት ከሌሎች የተለየ መብት እንደሌለው እነኝህ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ ሙስሊም እና ሌሎች የሀዲስ ጠበብት ባሰፈሩት ዘገባ ዘንዲህ ተብሏል፡- 56.☞‹‹ልጃገረድ አባቷ ፍቃድ ሊጠይቃት ይገባል፡፡›› 57.☞ዓኢሻ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው፤ አንዲት ሴት ከርሷ ዘንድ መጣችና አባቷ ለወንድሙ ልጅ ሊድራት መሆኑን ገለጸች፡፡ ዓኢሻም ‹‹ነብዩ እስኪመጡ ድረስ ተቀመጭ›› አለቻት፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲመጡ የሆነውን ነገረቻቸው፡፡ ነብዩም ወደ አባቷ መልዕክት ልከው አስጠሩት፡፡ የመወሰን ስልጣኗን ለርሷ ሰጡ፡፡ ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የአባቴን ተግባር አጽድቄያለሁ፡፡ እንስት በጋብቻ ጉዳይ የፈቀደችውን የማግባት መብት እንዳላት ለማወቅ ብዬ ነው ክስ ያቀረብኩት›› አለች፡፡ (ነሳኢ ዘግበውታል) የሀዲሱ ግልጽ መልእክት የሚያሳየው እንስት- ልጅገረድም ትሁን ፈት- ፈቃዷ መጠየቁ የጋብቻ መስፈርት እንደሆነ ነው፡፡ አባቷ ወይም ሌላ ወኪሏ ያለፈቃዷ ጋብቻ እንዲፈጸም ካደረጓት የጋብቻው ውል ሕጋዊ ተቀባይነት የለውም፡፡ ከላይ ያየነው የኸንሳእ ቢንት ኸዳሚ ታሪክ ይህን ያመለክታል፡፡ 58.☞ልጃገረድን በተመለከተ ‹‹ምርጫው የሷ ነው ፡፡ ከፈለገች ጋብቻውን ትቀበላለች፡፡ ካልፈለገች ጋብቻውን ውድቅ የማድረግ መብት አላት፡፡ ፍቃደኛ ካልሆነች ጋብቻው ውድቅ ይደረጋል፡፡ አንድኛው የሀዲስ ዘገባ እንደሚያመለክተው›› (ነይሉል አውጧር 6፤254-256) ሌላው ከኢስላም ድንቅ አቋሞች አንዱ በሴት ልጅ የጋብቻ ጉዳይ እናቷን ማማከር ግድ መሆኑን ማስተማሩ ነው፡፡ ጋብቻን በሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ የጋራ ስምምነት ይፈጸም ዘንድ ይህንን ደንግጓል፡፡ ኢብነ ኡመር(ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- 59.☞‹‹ሴቶችን በእንስት ልጆቻቸው የጋብቻ ጉዳይ አማክሯቸው፡፡› (አህመድና አቡዳውድ) የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ ይህን ይጫኑ click☞ https://goo.gl/hwS9Gn ኢማም ሱለይማን አልኸጣቢ ‹‹ሙዓሊመ ሱነን›› በተባለ መጽሐፋቸው ይሀን ሐደስ ሲያብራሩ ያሰፈሩት ቃል- ጥበብና ትምህርት ያዘለ በመሆኑ ሊጠቀስ የሚገባ ነው፡፡ እንዲህ ብለዋል፡- 60.☞ከሴቶች መሰረታዊ መብቶች ውስጥ ፍቺ ይገኝበታል፡፡ ለዘላቂ ህይወት ሴት ከአንድ ወንድ ጋር በጋብቻ ስትጣመር እና ጋብቻው ሊሰምር ካልቻለ የመጨረሻው አማራጭ መፍታት እና ከሚሆናት ሌላ ወንድ ጋር ዳግም ጋብቻ መመስረት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ይህንን የማይቀበል ሲሆን ሴትም ብትፈታ የተሰጣትአማራጭ ሳታገባ መኖር ነው፡፡ ስለ ፍቺ በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ መልኩ ትእዛዝ ተላልፏል ፡- ‹‹ሚስትም ከባልዋ አትለያይ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፡፡››(1ኛ ቆሮንቶስ 7፡10-11 ) በኢስላም የሚደገፉት ፍቺዎች ሁሉም አይደሉም ፡፡ እንዳንዱን ፍች ኢስላም ይጠላዋል፡፡ ሌላኛውን ደግሞ እርም ያደርገዋል፡፡ ፍችን ኢስላም ኢንዲታነጽ የሚጓጓለትን ከታነፀም በኋላ እንዳይናጋ የሚንከባከበውና ቤተሰባዊ ሕይወት ማናድ ነውና፤ ያለጥንቃቄ በዘፈቀደ እንዲፈጸም አይሻም ፡፡ ለዚህም ነው በአቡዳውድ በተዘገበው በተከታዩ ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ያሉት፡- 61.☞‹‹ከአላህ ዘንድ የሚጠላ ሐላል ነገር ፍች ነው፡፡›› (አቡዳውድ) ይህ ከመሆኑ አኳያ ቁርአን በባልንና ሚስትን ማለያየትንና ማፈጀትን ከከሐዲያን ደጋሚዎች እኩይ አድራጎት መፈረጁ አያስገርምም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- 62.☞‹‹ከሁለቱም (ሰዎች) ባልንና ሚስትን የሚለያዩትን (የድግምት ዕውቀት) ይማራሉ፡፡›› (ሱረቱ አል-በቃራህ 2፡102) እንደዚሁም በሁለት ተጋቢዎች መካከል ጥልና አለመግባባት ሲነግስ፤ ለማስማማት የተደረጉ ጥሩቶች ሁሉ ሲከሽፉ፤ በዚህ ጊዜ ፍች ብቸኛ አማራጭ ይሆናል፡፡ መድኃኒቱ እርሱም ብቻ ነውና ቢመርም ይወስዳል፡፡ ‹‹ስመምምነት ከጠፋ መለያየት ደግ ነው›› ይበላል ፡፡ ታላቁ ቁርአን እንዲህ ይላል፡- 63.☞‹‹ከተለያዩም (ከተፋቱ) አላህ ለሁሉም ከሲሳዩ ይለግሳል፡፡ አላህ (ችሮታው) ሰፊ፤ ጥበበኛ ነውና፡፡››(ሱረቱ አል-ኒሳእ፤ 130) 64.☞ በሀዲስም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡- ‹‹አማኝ ወንድ አማኝን ሴት ሙሉ በሙሉ አይጥላ፡፡ አንድ ባህሪዋ ቢያስከፋው ሌላኛው ያስደስተዋል፡፡›› (አህመድና ሙስሊም ዘግበውታል) ሰውየው አስቦና ተጨንቆ ጉዳዩን በሚገባ አጥንቶና አጢኖ ሊታገሰው ካልቻለው የጋብቻ ህይወት ለመውጣት ብቸኛውና የተሻለው መንገድ ፍች መሆኑን ካመነበት በኃላ የሚፈጽመው ፍች ነው፡፡ ተከታዩ የኢብን ዐባስ ቃል ይህን ያመለክታል፡- 65.☞“ፍች ተቀባይነት የሚኖረው ታስቦበት ሲፈፀም ብቻ ነው፡፡” /ቡኸሪ/ የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ ይህን ይጫኑ☞ https://goo.gl/hwS9Gn ፍች ሴት ከባሏ የምታገኘውን ቀለብ አያሳጣትም፡፡ በ”ዒዳ” ወቅት ሊቀልባት ግድ ይላል፡፡ ባልም ከቤቷ ሊያስወጣት አይፈቀድለትም፡፡ ከርሱ ቀረብ ብላ እንደትቆይ ሸርዓው ያስገድደዋል፡፡ ይህ የሆነበት የፍቅር ስሜት ዳግም እንዲያንሰራራ፣ ጥልና ብዥታ ተገፎ ትዳርን የማደስ ሀሳብ ህያው እንዲሆን ዕድል ለመስጠት ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- 66.☞“አላህ ከዚህ /ፍች/ በኃላ አዲስ ሁኔታን /ዳግም የመጣመርን ጉጉት ይፈጥር እንደሆነ የምታውቀው ነገር የለምና፡፡” (ሱረቱ አል – ጦላቅ፡ 1) ፍች ወንዱ የሴቷን የጥሎሽ ገንዘብ /መህር/ እንዲያስቀር ወይም ያበረከተላትን ስጦታ እንዲያስመልስ ዕድል ወይም ፍቃድ የሚሰጥ አይደለም፡፡ አላህ(ሱ.ወ) ይህን አስመልክቶ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡- 67.☞“እናንተ ባሎች፣ ለሚስቶቻችሁ ከሰጣቸኃቸው ጥሎሽ /መህር/ ቅንጣት ልትቀበሉ አይፈቀድላችሁም፡፡” /አል – በቀራህ! 229/ ቁሳዊ ድጋፍ የማግኘት መብት አላት፡፡ የባልን አቅምና የህብረተሰቡን ተጨባጭ ባገናዘበ መልኩ፡፡ 68.☞“የተፈቱ ሴቶች በ”መዕሩፍ” /የባልን አቅም ግምት ውስጥ የከተተ/ የገንዘብ ድጐማ ተደንግጐላቸዋል፡፡ ይህ /ድጐማ/ አላህን በሚፈሩ ሰዎት ላይ በገዴታነት ፀና፡፡” /አል – በቀራህ፡ 241/ ይህ ቁሳዊ ድጋፍ ሁሉንም በፍች ከባላቸው የተለዩ ሴቶችን ያጠቃልላል፡፡ ድንጋግጌው ሴቷ በፍች የሚደርስባትን የቀልብ ስብራት ለመጠገን የታለመ ነው፡፡ 68.☞ ባልም የፈታትን ሚስቱን ስም ማጥፋት፣ እርሷንም ሆነ ቤተሰቧን ማወክ አይፈቀድለትም፡- “ከዚያ በኃላ /ባል ሚስቱን/ በመልካም ሁኔታ መያዝ ወይም በበጐ አኳኋን /ሳይበድላትና መብቷን ቅንጣት ሳይደፈር ማሰናበት ግድ ይሆንበታል፡፡” /አል – በቀራህ፡ 229/ 69.☞“በመካከላችሁ /ባለ ግንኙነት/ ችሮታን /ከግዴታ በላይ መስጠት፣ ለሌሎች ጥቅም ሲሉ የራስን ድርሻ መተውን/ አትዘንጉ፡፡” /አል – በቀራህ፡ 237/ #ሚስት #ባለሃብት ብትሆንም እንኳ፣ ባል ለሚስቱ የምግቧን፣ የመጠጧን፣ የልብሷንና የአስፈላጊ ጉዳዮች ወጪዋን የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡ እንዲሁም ለርሷ ተመጣጣኝ የሆነን መኖሪያ ወይም ማረፊያም ሊያዘጋጅላት ይገባል፡፡ የወጪ መጠን፡ ወጪ የሚለካ”ው እንደ ባልየው የገቢ መጠንና እንደየ አገሩ የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን፣ ማባከንም ሆነ መጨናነቅ የሌለበት ሊሆን ይገባል፡፡ 69.☞አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፤ በርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበት ሰው፣ አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድዳትም፡፡›› (አል ጠላቅ 7) #የባልና_የሚስት_መብቶች_በእስልምና አላህ (ሱ.ወ) በባልም በሚስትም ላይ ሊጠብቁት የሚገባ የሆነ መብት ሰጥቷቸዋል፡፡ እንዲሁም የጋብቻን ሕይወት የሚያሳምሩና የሚጠብቁ ነገሮችን በሙሉ እንዲፈፅሙ አነሳስቷል፡፡ እነኚህን ጉዳዮች የመጠበቅ ኃላፊነት በሁለቱም ወገን ላይ የተጣለ ነው፡፡ ባልም ሆነ ሚስት አንዳቸው ከሌላኛው የማይቻልን ነገር እንዲፈፅም መጠየቅ የለባቸውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- 70.☞ ‹‹ለነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኗኗር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው፡፡›› (አል በቀራ 228) የሕይወት ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው አና የተከበረው ቤተሰብ እንዲጸና ነገርን ማግራራትና ጉድለትን ማለፍ እንዲሁም መለገስ ያስፈልጋል፡፡ #የሚስት_መብቶች የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ click☞ https://goo.gl/hwS9Gn 1. ቀለብና መጠለያ አንድ ሰው በአካባቢው ተለምዶ መሰረት የባለቤቱንና የልጆቹን ወጪ የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡ #ሚስት #ባለሃብት ብትሆንም እንኳ፣ ባል ለሚስቱ የምግቧን፣ የመጠጧን፣ የልብሷንና የአስፈላጊ ጉዳዮች ወጪዋን የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡ እንዲሁም ለርሷ ተመጣጣኝ የሆነን መኖሪያ ወይም ማረፊያም ሊያዘጋጅላት ይገባል፡፡ የወጪ መጠን፡ ወጪ የሚለካ”ው እንደ ባልየው የገቢ መጠንና እንደየ አገሩ የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን፣ ማባከንም ሆነ መጨናነቅ የሌለበት ሊሆን ይገባል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፤ በርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበት ሰው፣ አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድዳትም፡፡›› (አል ጠላቅ 7) ይህን ወጪ ሲሸፍን መመጻደቅ፣ እንዲሁም በመጨናነቅ እሷንም ሆነ እራሱን ማዋረድ የለበትም፡፡ በኢስላም፣ በሚስትና በቤተሰብ ላይ የሚወጣ ወጪ ከባድ ምንዳን ያጎናጽፋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድ ሙስሊም ከአላህ እመነዳበታለሁ በሚል እሳቤ በሚስቱ ላይ ወጪ ሲያወጣ ለርሱ ምጽዋት ይሆንለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 5036 / ሙስሊም 1002) በሌላም ዘገባ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በርሷ ብትመነዳባት እንጂ አንተ የአላህን ፊት ከጃይ ሆነህ አንድም ወጪን አታወጣም፤ በሚስት አፍ ውስጥ የምታስቀምጣት ጉርሻ እንኳን ብትሆን፡፡›› (አል ቡኻሪ 56 /ሙስሊም 1628) ወጪ አልሰጥም ያለ ሰው፣ ወይም እየቻለ ማውጣት ካለበት የቀነሰ ሰው፣ በርግጥ ከባድ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ለአንድ ሰው ወንጀለኛነት፣ የሚያስተዳድረውን ሰው ማንገላታቱ ይበቃዋል፡፡›› (አቡ ዳውድ 1692) 2. መልካም አኗኗር ወይም ግንኙነት መልካም አኗኗር በሚለው የተፈለገው መልዕክት መልካም ስነ ምግባር የሚለው ነው፡፡ ልበ ለስላሳነት፤ ለብ ያለ ንግግርን መናገር፤ አንድም የሰው ልጅ ሊርቃቸው የማይችሉ ስህተቶችንና ድክመቶችን ችሎ ማለፍና የመሳሰሉትን ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፤ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ) ፤ አንዳችን ነገር ልትጠሉ፣ አላህም በርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡›› (አል ኒሳእ 19) ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከሙእሚኖች መካከል የተሟላው ሙእሚን በስነ ምግባሩ በላጭ የሆነው ነው፤ በላጮቻችሁ ለሚስቶቻቸው በስነ ምግባራቸው ጥሩዎቹ ናቸው፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1162) ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህም ብለዋል፡- ‹‹ከሙእሚኖች መካከል የተሟላው ሙእሚን በስነ ምግባሩ ጥሩውና ለሚስቱ ገራገር የሆነው ነው፡፡›› (አል ቲርሙዚ 2612 / አህመድ 24677) ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በላጫችሁ ለቤተቡ ጥሩዋችሁ ነው፤ እኔ ለቤተሰቤ ጥሩዋችሁ ነኝ፡፡›› (አልቲርሚዚ 3895) አንድ ሠሐቢይ፣ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ)፡- «አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ የአንዳችን ሚስት በሱ ላይ ያላት መብት ምንድን ነው?» በማለት ጠየቃቸው፤ እሳቸውም፡ ‹‹ስትበላ ልታበላት፤ ስትለብስም ልታለብሳት፤ ፊቷን ላትመታት፤ ላታዋርዳት፤ በቤትህ ውስጥ እንጂ ላታኮርፋት ነው፡፡›› አሉት፡፡ (አቡ ዳውድ 2142) 3. #መቻቻል የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ ይህን ይጫኑ click☞ https://goo.gl/hwS9Gn የሴቶች ተፈጥሯዊ ባህሪ ከወንዶች ጋር ይለያያል፤ በመሆኑም ይህን የሚለዩባቸውን ባህሪያት ወንዱ ሊላመደውና አቅልሎ ሊመለከተው ይገባል፡፡ የጋብቻን ሕይወት ከብዙ አቅጣጫ ለማየት ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ ማንም ከስህተት ነፃ አይደለም፤ እናም ስህተት ሲከሰት ትዕግስት ማድረግና ከስህተቱ ባሻገር ያሉትን መልካም ጎኖች መመልከት ያስፈልጋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ ባልንም ሚስትንም፣ አንዱ የሌላኛውን መልካም ወይም ጠንካራ ጎን እንዲመለከቱ ያሳስባል፡፡ እንዲህ ይላል፡- ‹‹በመካከላችሁም ችሮታን አትርሱ፡፡›› (አል በቀራ 237) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፣ ለሴቶች ልዩ ትኩረት እንዲሰጣቸውና ወንዶች በመልካም እንዲኗኗሯቸው አሳስበዋል፡፡ 4.#ክብርህና_ሞገስህ_ስለሆነች_ልትከላከላት_ይገባል ፡፡ አንድ ሰው ሲያገባ፣ ያገባት ሴት የእርሱ ክብሩ ነች፡፡ ስለሆነም ለሞት የሚዳርገው ቢሆንም እንኳን ይህን ክብሩን ሊከላከልና ሊሟገትለት ይገባል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ስለ ሚስቱ የተገደለ ሰው ሰማዕት ነው፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1421/ አቡ ዳውድ 4772) 5 #የሚስትን_ሚስጥር_አለማባከን አንድ ሙስሊም፣ የሚስቱን ልዩ ባህሪያትና፣ በርሱና በርሷ መካከል ስለ ተፈፀመ የአልጋ ላይ ሚስጥር ለሰዎች ሊያወራ አይፈቀድለትም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹የትንሳኤ(የቂያማ) ቀን ከሰዎች ሁሉ ከደረጃ በኩል የከፋ ሰው ማለት፣ እርሱ #ለሚስቱ ተገላልጦ፣ #ሚስቱም ለርሱ ከተገላለጠች በኋላ የሷን ሚስጥር አውጥቶ የሚበትን ሰው ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 1437) 6. #በሴት_ላይ_ድንበር_ማለፍ_አይፈቀድም። ኢስላም ለሚፈጠሩ ችግሮች በርካታ መፍትሄዎችን አስቀምጧል፡፡ ከነዚህም መካከል፡ ስህተቶች በመወያየት፣ በመመካከርና በተግሳጽ ሊታረሙ ይገባል፡፡ ከሦስት ቀናት ላልበለጠ ጊዜ አለማናገር ወይም ማኩረፍ ከዚያም ከቤት ሳይወጣ በመኝታና በግብረ ስጋ ግንኙነት ማኩረፍ ይፈቀድለታል፡፡ እመት ዓኢሻ እንዲህ ብለዋል፡- ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአላህ መንገድ ላይ ሲዋጉ ካልሆነ በስተቀር አንዲትንም ሴት ሆነ ባሪያ መራቅ አያውቁም፡፡ 7. #ማስተማርና_መምከር ሰውየው ሚስቱን በመልካም ሊያዛትና ከመጥፎ ሊከለክላት ይገባል፡፡ ወደ ጀነት ጸጋ የሚያዳርሳቸውን፣ ከእሳት ቅጣት የሚያርቃቸውን ነገሮች በማመቻቸትና በሱም ላይ በማበረታታት፣ እንዲሁም እርም ነገሮችን በመከልከልና እንዲጠሉ በማድረግ ልዩ ትኩረት መስጠት አለበት፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ሚስትም ባሏን በመምከር፣ ወደ መልካም ነገር በመገፋፋትና በመጠቆም፣ ልጆችን በጥሩ ስነ ምግባር ኮትኩቶ በማሳደግ ላይ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት ጠብቁ፡፡›› (አል ተህሪም 6) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሰውየው በሚስቱ ላይ ጠባቂ ነው፣ ስለጠበቀው ነገር ይጠየቃል፡፡›› (አል ቡኻሪ 2416 / ሙስሊም 1829) 8. #ሚስቱ_ያስገባችውን_ቃል_መጠበቅ ባል በጋብቻ ውል ላይ የተጠቀሱ ቅድመ መስፈርቶችን የመጠበቅና የመሙላት ግዴታ አለበት፡፡ ጋብቻው በሚፈፀምበት ጊዜ፣ ሚስት ለምሳሌ፣ ይዘቱ ለየት ያለ ቤትን ሊገዛላት ወይም ሊሰራላት ዓይነት የተፈቀዱ ነገሮችን እንዲፈፅምላት ቃል ካስገባችው፣ ቃሉን የመጠበቅና የመሙላት ግዴታ አለበት፡፡ ምክንያቱም የጋብቻ ውል ከቃልኪዳኖች ሁሉ ትልቁና ከባዱ በመሆኑ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከመስፈርቶች ሁሉ እጅግ በርሱ ልትሞሉ የሚገባው ብልትን የተፈቀደ ያደረጋችሁበት ቃል ኪዳን ወይም መስፈርት ነው፡፡›› (አል ቡኻሪ 4856 /ሙስሊም 1418) የሴት ልጅ መብት በክርስትና ለማንበብ
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
692
የሴቶችን መብት ማስከበር የሁሉም ሰዉ ኃላፊነትና ግዴታ ነው። በመጀመሪያ የጾታ እኩልነት ምን ማለት ነው? የጾታ እኩልነት ሴቶች እና ወንዶች አንድ አይነት መብት እና ግዴታ ያላቸው ሆነው ማንኛውም ሰው በህብረተሰብ ውስጥ አንድ አይነት እድል አላቸው ማለት ነው። የጾታ እኩልነት በቤተሰብ እና ህብረተሰብ ስለሚኖረው ፍትህ እና የኃላፊነት ክፍፍል ማለት ነው። ጾታ ያሉንን የግል ብልጫዎች እና እጥረቶች ከማየት የሚከለክለን ሲሆን ወደ አድሎ እና የታጠሩ የግለሰቦች እድሎች ሊያመራ ይችላል። ለማንኛውም የዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ታሪክን በጥሞና ለተመለከተ ቅን ሃሳቢ ዜጋ ባለፉት መቶ ዓመታት በዚህ በኩል የተደረጉት እንቅስቃሴዎች ለማህበራዊና ፖለቲካዊ ፍትህ መገኘት የተደረጉ ትግሎች መሆኑን ይገነዘባል። ይህ የሴቶች ቀን አንዳንዴም የእናቶች ቀን የሚል ስያሜን አግኝቶ ማርች 8 ቀን በየአመቱ በመላው ዓለም የሚከበረው፣ በመላ ዓለም ለሚገኙ ሴቶች ሁሉ የተሻለ የሥራና የኑሮ ሁናቴ፤ የመብት መከበር፤ …ወዘተ እንዲኖር ዓላማ ያደረገን ትግል ለማክበር የተወሰነ ቀን ሲሆን፤ የኦሮምያ ሴቶችም የፆታ አምሳያቸው ከሆኑት የዓለም ሴቶች አካል ናቸውና፤ የአንድነታቸውም መገለጫ ነውና አመቺ መስሎ በታያቸው ሁናቴ በየቦታው የሚያከብሩት መሆኑ ግልፅ ነው። እንዲሁም ይህ ቀን ሥርነቀል የሆነ ለውጥ ለማምጣት ሴቶች ያደረጉትን እንቅስቃሴና እንዲሁም ባሕልና ጥረታቸውን ለማስታወስና በተለይም ደግሞ ለዚሁ ዓላማ ሲሉ የተሰዉትን ጀግና ሴቶችንና ታሪካቸውን ለመዘከሪያ እያገለገለ የሚገኘውም መሰረቱ ይኸው ነው። ባለፉት አንድ መቶ አመታት ለጾታ እኩልነት፤ ለሴቶች ነፃነት መጎናፀፍና መብት መከበር ለተደረገውና አሁንም እየተደረገ ያለውን ትግል ለማስታወስ በያመቱ እንደሚከበር ማወቅ ያስፈልጋል። ታዲያ ዛሬ በኦሮሚያ አካባቢዎች በነዚህ መቶ አመታት በተወሰኑ የዓለም አካባቢዎች በትግል የተገኙ ድሎች ቢኖሩም አሁንም ገና ያልተሟሉ ቀጣይና ያላሰለሰ ትግልን የሚጠይቁ፤ የሴቶችንም በጋራ በአንድነት መቆምንና የወንዱንም ከፍተኛ አጋርነት የሚሹ በርካታ ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ጥያቄዎች እንዳሉ ግልፅ ነው።በኦሮሚያ በአብዛኛዉ ክፍል ደግሞ ባለንበት በ21ኛ ምዕተ ዓመት በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው በደልና ጭቆና፤ የከፋና ሀዘን የተሞላበት ከመሆኑም በላይ ኑሯቸው አሰቃቂና አስከፊ መሆኑ በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ማክበር ለእነዚህ ክፍሎች ጥብቅና መቆምን መግለፅና ሁኔታቸውን ለሰላምና ፍትህ ወዳድ ኃይሉ ማሳወቅን የሚያጠቃልል ነው። በተለይም በተለያዩ ሀገራት እንደሚታየው በስንት ትግልና ጥረት የተገኙ ድሎች ሁሌም ጥበቃና እንክብካቤ ካልተደረገላቸው እምነትና ባህልን ሽፋን (መሰረት) በማድረግ የሚቀለበሱ መሆናቸው ደግሞ የሚታይ ነው። ምስራቅ አውሮፓ ለዚህ መልካም ምሳሌ ነው። በሰሜን አፍሪካና በሌሎች አረብ ሀገራት አምባገነን አገዛዝንና መሪዎችን ለመጣል በተደረገው ትግል የሴቶች ተሳትፎና የከፈሉት መስዋዕት ከፍተኛ ቢሆንም የትግላቸውን ፍሬ ለመቋደስ የተቸገሩበት ምክንያት የዚሁ የቅልበሳ ነፀብራቅ በመሆኑ ነው። ሕዝባዊ ድርጅቶች የሚያከብሩት በመሆኑ ብቻ ሳይሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለጉዳዩ በሰጠው ትኩረት በ1977 ዓ.ም ባደረገው ጠቅላላ ስብሰባው በዓመት አንድ ቀን “የሴቶች መብትና የሰላም ቀን“ በተሰኘ መርሃ መፈክር ተከብሮ እንዲውል በመወሰኑም ጭምር ነው። ወደ እኛ ስንመጣ የዚህ ትውልድ ነፀብራቅ የሆነው ኦነግ ከተመሠረተበት ከዛሬ 40 አመት ጀምሮ እንቅስቃሴዎቹን ባካሄደባቸው አካባቢዎች ሁሉ ለሴቶች መጨቆን አስተዋጽዖ እያበረከቱ ያሉ ጎጂ ልማዶች፣ ወጎች፣ ባሕሎች፣ አመለካከቶች፤ አነጋገሮች፣… እንዲወገዱ በማስተማር ያደረጋቸው ሥራዎች በዚህ የተካፈለው ሕዝብ እራሱ ምስክር ነው። መብታቸውንም በማስከበር ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ተደራጅተው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ፤ በተለያዩ የድርጅቱ ተቋማት ውስጥም የአመራር ኃላፊነት ተረክበው ለሕብረተሰቡ ነፃነት መጎናፀፍና የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ያደረጋቸው ጥረቶችና ያስገኛቸው ውጤቶች ለሌሎች አርዓያ የሚሆኑ ከቶም ሊረሱ የማይችሉ የትግሉ ታሪክ ናቸው። የአሁኑ አምባገነን የወያኔ አገዛዝ ሕገ መንግሥታችን በሚሉት ሰነዳቸው ላይ ስለ ሴቶች መብትና ነፃነት የሚገልፁ አንቀጾችን ሸንቁረው መጠነ ሰፊ ፕሮፓጋንዳ ቢነዙም፤በባዕዳን ጥቂት እርጥባን እየተደገፉ እዚህም እዚያም ከሚንቀሳቀሱት ሕዝባዊ ድርጅቶች በስተቀር በሙሉ ልብ ኃላፊነትና ግዴታ ተሰምቷቸው በተጨባጭ የሴቶችን መብት ያስከበሩበት ሁኔታ የለም። የወያኔ አገዛዝ ነጋ ጠባ በየአደባባዩና በየመሥሪያ ቤቶች መፈክር በመስቀል የኦሮሞን ሕዝብን ከማስቸገርና ከማስጨነቅ በላይ ምንም እንዳልሄደ ድርጊቶቹ የሚያጋልጡት ናቸው። ለፆታ እኩልነት ተቆርቋሪ ነኝ እያለ ለጆሮ የሰለቸ ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም በአገዛዙ በኩል ለሴቶች የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ በመሆኑ ሴቶች ከወንዱ ጋር ሲነፃፀር በሁሉም መስክ ያላቸው ተሳትፎ እጅግ ወደኋላ የቀረ ነው። በመሆኑም ዛሬ ብዙሃን ሴቶች ከየመድረኩ ተገለውና ተጨቁነው መገኘታቸው (በወያኔ ፈቃድ አንዳንድ ሴቶች በሚኒስትርነትና በዳይሬክተርነት ማዕረግ መሾማቸው የፆታ እኩልነትን የሚገልጽ ባለመሆኑ) ፆታቸውን ተንተርሶ በገጠርም ሆነ በከተማ ኗሪ በሆኑ ሴቶች የሚደርሰው በደል መባባሱ፤የሚያረጋግጠው አንድ ነገር ቢኖር ይህንን ተጨባጭ ሁናቴ ነው። የኦሮሞ ሴቶችና በሁሉም የኦሮሞ ዜጋ ላይ ባጠቃላይ በሚፈፀመው የጋራ ጥቃት ባሻገር በሴትነታቸው ብቻ የሚደርስባቸውን ድርብ ጥቃት ጨርሶውኑ ለማስወገድ ቀርቶ በአግባቡ እንኳን ለመቀነስ አልተቻለም። አሁንም ድረስ በኦሮምያ የፆታ እኩልነት በተግባር በሚገባ አልተረጋገጠም። በጣም ጥቂት የሆኑ ሴቶች በራሳቸው ጥረት የሥራ እድል አግኝተው ለመቀጠር ቢችሉም ለተመሳሳይ ሥራ እኩል የደሞዝ ክፍያ አያገኙም። በትዳር የተጎዳኙ ሁለቱም የሥራ እድል አግኝተው የሚሰሩ ቢሆን እንኳ የቤተሰብ ኃላፊነቱ በሴቶች ትከሻ ላይ በመሆኑ ሕጻን ልጆቻቸውን ተንከባክቦ ከማሳደግ ጀምሮ አቅም ያነሳቸው፤ በእርጅናም ምክንያት ጉልበት እያጡ የሚሄዱ ወላጆቻቸውን ጭምር ማሰባሰብና መንከባከብ በዋናነት በሴቶቹ ትከሻ ላይ የወደቀ ነው። አበረታች እየተባሉ የመመፃደቂያ፣ የማደናገሪያ፣ የመደለያ መግለጫዎች በወያኔ አገዛዝ አሁንም ድረስ ቢዥጎደጎዱም የቤተሰብ ኃላፊነታቸው እየከበደ እንጂ እየቀለለ ሲሄድ አይታይም። ሴቶች ከቤት ውስጥ ጀምሮ በትምህርት ቤት፣ በሥራቦታ፣ በጓሮ እርሻ፡ … በሕብረተሰብ መካከል ለተለያዩ በደሎች የተጋለጡ ናቸው። በጋብቻ መልክ ቁርኝት ባለበትም ወንዶች የገቢ ምንጭ፣ የቤት የበላይና ውሳኔ ሰጪ መሆን በቀጣይነት ያለ በመሆኑ ሴቶች በዝቅተኝነት እንዲታዩ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል። በተለያዩ ጥናቶች እንደተረጋገጠው ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ለቤት ውስጥ የኃይል ጥቃት ሰለባዎች የሆኑበት፤ አካላዊ ደህንነታቸው ለተለያዩ አደጋዎችና በሽታዎች የተጋለጡበት፤በማህበራዊ ሕይወት ተሳትፎ ደረጃ፣ በኤኮኖሚ አቅም፣ በውሳኔ ስጪነት ሴቶች ዝቅ ተደረግው የሚታዩበት ሁናቴ ሰፍኖ ያለበት ነው። የትዳር ሕይወትን በአግባቡ ማጣጣም በጣም ከባድ በሚሆንበት ሁናቴ ደግሞ አብሮነቱ ትርጉም የሌለው እርካታም የማይገኝበት በመሆኑ የአካል፣ የመንፈስ፣ የሥነ አዕምሮና የሥነ ልቦና ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች በተለይ ባለፉት 20 አመታት የመለስ አገዛዝ ባሰፈነው የሞራል ድቀትና የሥነምግባር ብልሹነት የተነሳ ቁጥራቸው በሚያስገርምና በሚያስደንቅ ሁናቴ እየተበራከቱ መሆናቸው በጥናት የተደረሰበት ነው። ድብቅና ግልፅ ሴተኛ አዳሪነት በጣም እየተስፋፋ ነው። ይህ በራሱ አስከፊነቱ አልበቃ ብሎ በአገዛዙ አቀናባሪነትና ድጋፍ ሰጪነት በአረብ ሀገር ለዘመናዊ ባርነት እየተዳረጉ ያሉ ወጣት ሴቶቻችን ከድብደባ ጀምሮ ለተለያዩ ጥቃቶች እየተጋለጡ መገኘታቸው በተደጋጋሚ የተገለፀ ነው። ኦነግ ይህንን በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ድርብ ጭቆናና በደል አጥብቆ ይቃወማል፤ ያወግዛልም። ይህ ሥር የሰደድ ችግር ከጠቅላላው የሕብረተሰቡ ሁለንተናዊ ችግሮች ተለይቶ ለብቻው መፍትሄ እንደማያገኝ የኦነግ ፅኑ እምነቱ ነው። ስለዚህም መሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ ለማስገኘት ለዴሞክራሲና ለሰብዓዊ መብት መከበር የቆሙ የኦሮሞ ዜጎች ሁሉ ይህንን በሚገባ ተገንዝበው የወያኔን አገዛዝን ከሥልጣን ለማባረር ይቻል ዘንድ የጋራ የትግል ጥሪ በትግሉ ሜዳ እንዲመሠረት ደግሞ ደጋግሞ ያቀርብላቸዋል። የሴቶች ቀንን ስናከብረውና ሴት ጀግኖቻችንንም ስንዘክራቸው ባለፉት መቶ ዓመታት የትግል ሂደት ውስጥ ገና በአግባቡ መፍትሄ አላገኙምና ለስኬታማነታቸው ከሴት እናቶቻችን፣ እህቶቻችን፣ ልጆቻችን ጋር በመሆን በፅናት እንታገል በማለት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጥሪውን ያቀርባል። ሴቶችም ለመብታቸው እንዲታገሉ ነፃ ድርጅታቸውን እንዲያቋቁሙ፤ የተቋቋሙትም እንዲጠናከሩና እንዲተባበሩም ጭምር በሙሉ ልብ ልናበረታታ ልንረዳ ግድ ይላል። ይህንንም እንደግፍ ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የጠበቀ አደራውን ያስተላልፋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሴቶች ጥያቄ የትግላችን እእምብርት መሆኑን እያረጋገጠ፤ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር ማክበር ብቻ ሳይሆን የሚያስተላልፈው ልዩ መልዕክትም የኦሮሞ ሴቶችን መብት ለማስከበር አሁንም ከነፃነት ትግሉ ጋር በመቀላቀል የኦሮሞን ህዝብና የኦሮሞ ሴቶችን መብት አብረን ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር እንሰለፍ!!! የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለመላው የኦሮሞ ሴቶች ጥሪው መደራጀት፡ እየተደራጁም መተባበርና መታገል! – የወቅቱ መርሃ ግብር ነው በማለት ያስተላለፋል። ከአዊ ኦላኒ ከሰሳ
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
693
ሳዑዲ አረቢያ ሶስት የሴቶች መብት ተሟጋቾችን ለጊዜው ከእስር መፍታቷን ገልፃለች፡፡ አልጀዚራ የሃገሪቱን ዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘገበው ሳዑዲ አረቢያ እእረኞቹን ለጊዜው ብትለቅም ጉዳያቸውን ግን አሁንም እየመረመረች ነው፡፡ ከዓመታት በፊት ሳዑዲ አረቢያ ለሴቶች መብት መከበር ከማይመቹ የዓለም ሃገራት ተርታ ስሟ ተደጋግሞ ሲነሳ ቆይቷል፡፡ ተሸከርካሪዎችን ከማሽከርከር ጀምሮ ሌሎች የተለያዩ መብቶች ለወንዶች ብቻ በመፍቀድ ለሴቶች የተከለከሉ በርካታ ተግባራት እንዲስተካከሉ ከፈቀደች አንድ ዓመት እንኳን አልሞላትም፡፡ ምንም እንኳን ሃገሪቱ ቀድመው በሴቶች ላይ ተጥለው የነበሩ ስታዲየም እንዳይገቡ፣ ሲኒማ እንዳይመለከቱ እና እንዳያሽከረክሩ የሚከለክለውን ህግ ብታነሳም አሁንም ግን በርከት ያሉ መብቶችን ለሴቶች ከልክላለች፡፡ የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ መኪና መግዛት እና ፍች የመፈፀም መብት አሁንም ለሴቶች አልተሰጡም፡፡ በመሆኑም ሃገሪቱ የወንዶች ዓለም ተብላ እንድትጠራ አድርጓታል፡፡ ይህ የመብት ክልከላ ግን በበርካቶች ዘንድ ሰላማዊ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ሃገሪቱን ለቀው የወጡ ሴቶችም መመለስ እንደማይችሉ ቢመለሱም ግን ዘብጥያ እንደሚወርዱም ደጋግመው ይናገራሉ፡፡ እዚያው ሳኡዲ አረቢያ ሆነው ለሴቶች መብት ጥብቅና የቆሙ ዜጎች በሙሉ ዘብጥያ መውረዳቸው ደግሞ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ይነሳል፡፡ አልጀዚራ የሳዑዲ አረቢያ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ እንደዘገበው ለአለም አቀፍ ሪፖርተሮች እና ዲፕሎማቶች ዝግ በነበረው የሃገሪቱ ችሎት ላይ እስረኞቹን ለጊዜው ብትለቅም ጉዳያቸውን ግን አሁንም እየመረመረች ነው፡፡ ትናንት ለጊዜው ከእስር የተለቀቁት ሶስት የመብት ተሟጋቾች ስማቸው ይፋ ባይሆንም ጦማሪ ኢማን አል ናፍጃን፣ አዚዛ አል የሱፍ እና በኪንግ ሳኡዲ ዩኒቨርሲቲ መምህርት የነበሩት ሮቃይ አል ሞሃረብ ሳይሆኑ አይቀሩም ሲል አልጀዚራ ዘግቧል ፡፡ ቀረቤታ ያላቸው ግለሰብ ለአጃንስ ፍራንስ ፕረስ እንደገለፁት ከእስር የተፈቱት እንስት የመብት ተሟጋቾች በቀጣይ ወር ለፍርድ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
694
የሴቶች መብት ምን ያህል ይከበራል? « የሴቶች መብት ተብሎ ወረቀቱ ላይ የተፃፈዉ እዳለ ሆኖ፤ ከወንዱ እኩል ቡና ቤት ከመሄዱ፤ ለሊት ሲጨፍሩ ከማደሩ በዘለለ፤ በትክክል ሴት ልጅ የሚገባትን መብት አግኝታለች ተብዬ ብጠየቅ፤ የሚታየኝ ምንም ነገር የለም። ዛሬም ዩንቨርስቲ የሚገኙ ተማሪዎች ለአስተማሪዎቻቸዉ ራሳቸዉን ሸጠዉ ዉጤት የሚቀበሉ አሉ። This video file cannot be played. (Error Code: 102630) አውዲዮውን ያዳምጡ። 16:51 የሴቶች መብት ምን ያህል ይከበራል? በተለያየ ሞያ ዉስጥ ገብተዉ መዉጣት አቅቶአቸዉ፤ ለቀጠርዋቸዉ ሰዎች ወይም ደግሞ ለአሰልጠኑዋቸዉ ሰዎች ወይም አለቃዎቻቸዉ ለሆኑ ወንዶች ራሳቸዉን አስገዝተዉ የሚወጡ ሴቶችም አሉ። ታድያ እነዚህ ሴቶች መብታቸዉ ተከብሮላቸዋል?» ጋዜጠኛ የትነበርክ ታደለ። Mesob Traditioneller Esstisch Äthiopien በፍቅረኛሞች ዘንድ ታስቦ የዋለዉን «ቫለንታይን ዴይ » የፍቅረኛሞች ቀንን አስታከን ለጋዜጠኛ የትነበርክ ታደለ በኢትዮጵያ ስላለዉ የሴቶች መብት ጉዳይ ላቀረብንለት ጥያቄ ያካፈለን ኃሳብ ነበር። በምዕራባዉያኑ ዘንድ በቀይ ጽጌረዳና ልብስ ደምቆ የሚታሰበዉ ቀን በሃገራችን በተለይ በከተሜዉ ወጣቶች ዘንድ እየተዘወተረ መጥቶአል። በከተሞች አካባቢ ሽያጮችን ያካተተቱ እለቱን የሚዘክሩ ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች መካሄድ ጀምረዋል። በርግጥ የፍቅረኛሞች ቀን መታሰቡን የማይቃወሙ እንዳሉ ሁሉ ባህላችን ስላልሆነ እለቱ መዘከሩ አያስፈልግም የሚሉም አሉ። ይህ ቀን ምን ያህል እንደማፈቅር ለሰዉ እዩልኝ ለማለት ካልሆነ በስተቀር፤ እዉነተኛ ፍቅርን ከመግለፅ ጋር ምንም ግንኙነት የለዉም የሚሉ ኢትዮጵያዉያን ጥቂት አይደሉም። በዓለማችን የፍቅረኞችም ቀን ሆነ የሴቶች ቀን ብሎም የእናቶች ቀን፤ ይከበራል። ነገርን ነገር ያነሳል ነዉና በእለቱ ዝግጅታችን፤ በሀገራችን የሴቶች መብት ምን ያህል ይከበራል? ጎታች የሆነዉ ሴትን ልጅን ወደ ጓዳ የሚለዉ ልማድ ምን ያህል እያስቀረነዉ ነዉ? የእለቱ መሰናዶአችን ርዕስ አድርገን ይዘናል። ስለ ሴቶች መብት ሲጠቀስ በዋነኛነት የምናነሳው መሠረታዊ ስለሆነው የሰው ልጆች መብት ነዉ። ይህ ደግሞ ስለ እናቶቻችን፤ እህቶቻችን ሴት ልጆቻችንና ሴት አያቶቻችን፤ መብት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም መሠረታዊ በሆነው የሴቶች መብትና በሌሎች ሰዎች መብት መካከል የምንፈጥረው ምንም ዓይነት ድንበርም ሆነ መለያ ክልል ሊኖር አይችልም፡፡ የሴቶችን መብት በተመለከተ መንግሥት ብዙ ሥራ ቢያከናዉንም ሕግጋትን ቢያወጣም የሴት እኩልነትን ማኅበረሰቡ ተግባራዊ እስኪያደርገዉ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅበታል ሲሉ የገለፁልን በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉን ጥቃት ለደረሰባቸዉ ሴቶች ቤት ያቋቋሙት ወ/ሮ ማሪያ ሙኒር፤ «እንደ መንግሥት ሕግ ነዉ የሚወጣዉ፤ በሕገ-መንግሥቱ የወጣ ሕግ አለ። ግን ሕጉ መኖሩ የኅብረተሰቡን አስተሳሰብ ይቀይረዋል ማለት አይደለም። ሕጉ ለአጠፋ ሰዉ መቅጫ ወደ ሕግ ፊት ሲቀርብ መብት ማስከበርያ ነዉ የሚሆነዉ። ነገር ግን በባህል ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻችን ጋር ስናድግም ሆነ ልጆችን ስናሳድግ ቤተስብም ልጆችን ሲያሳድግ ወንድና ሴት ልጅ መካከል ልዮነት የሚፈጥረዉን ለሴት የሚሰጠዉ ቦታ ቀደም ሲል ጊዜ ጀምሮ ዝቅ ያለ ስለሆነ አሁን መሰራት ያለበት የሰዉን አዕምሮ በመቀየር ላይ ነዉ ብዙ መሰራት ያለበት። አሁንም የሚታየዉን ሁላችንም የምናዉቀዉ ነዉ። በየቦታዉ ለሴቶች የሚሰጠዉ ክብር አንዳንድ ቦታ ጥሩ ሲሆን፤ በብዛት የሚታየዉ ግን አሁንም እንዳልተቀየረ በጣም ዝቅተኛ የሆነ ክብር እንዳለ ነዉ። ተቀይሮአል ክብር እየተሰጠ ነዉ በሚባልበት ቦታም ቢሆን ለዉጡ ገና አዝጋሚ እንደሆነም ይታያል። ስለዚህም የሴት መብት ተከብሮአል ፤ ሴቶች ከወንዶች እኩል እየታዩ ያለበት ሁኔታ ነዉ ማለት አይቻልም።» Valentinstag in Deutschland በተለይ በምዕራቡ ዓለም የጎርጎረሳዉያኑ የካቲት ወር በገባ በሁለተኛዉ ሳምንት የሚከበረዉ ቫለንታይንስ ዴይ ማለት «የፍቅረኛሞች ቀን» ባሳለፍነዉ እሁድ ታስቦ ዉሎአል። በምንኖርበት የግሎባላይዜሽን ማለትም በአፅናፋዊዉ የኤኮኖሚ ትስስር ዘመን ዓለም ከሌላዉ ማኅበረሰብ የምንወስደዉን ተለምዶ ማየቱ እንደማይከፋ የሚገልፀዉ ጋዜጠኛ የትነበርክ ታደለ ቀኑ ይላል፤ « የኔ እይታ ብዙዉን ጊዜ ከባህል አንፃር ነዉ። ከራሳችን ባህል ጋር የሚጣጣም ነዉ፤ ወይስ አይደለም? ምን መዉሰድ አለብን፣ የትኛዉን ማስቀረት አለብን የሚለዉን እመለከታለሁ። የፍቅር ቀን « ቫለንታይንስ ዴ » የሚባለዉን ቃሉን ስንመለከት ማንም ሰዉ ሊያደርገዉ የሚገባ፤ ሰዎች ሁሉ እርስ በርሳቸዉ ፍቅራቸዉን እንዲገልፁ ቢሆን፤ ፍቅረኛ ለፍቅረኛዉ ቢያደርገዉ መልካም ነዉ። ግን ሌሎች አብረዉ ተያይዘዉ የሚመጡ ባህላዊ የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ ከራሳችን ነገር ጋር ማያያዝ ያለብን ይመስለኛል። » ቀኑ እንዳየነዉ ፍቅረኛ ለፍቅረኛዉ አበባ የሚሰጥበት ፍቅሩን የሚያሳይበት ሆኖዉ ነዉ? « በእዉነቱ አገላለፁ በጣም ጥሩ ነዉ፤ ግን ፤ አንደኛ ቀኑ ከንግድ ጋር የሚያያዝ ነዉ። ስለዚህ ቀን ምንነት የሚነገረዉ አብዛኛዉን ጊዜ ከአንድ ወገን ብቻ ነዉ። በዚህ ቀን ሰዎች አላስፈላጊ ወጭ እንዲያወጡ ይገደዳሉ። የሚሰሙት ማስታወቅያዎች ወጣቱን ባልሆነ መንገድ የሚያማልሉ ናቸዉ ። እንደሚታወቀዉ ወጣቱ ለእንደዚህ ዓይነት ነገሮች በቀላሉ የሚሰነፍ ነዉና ካሉብን ሃገራዊ በአላት ላይ ተጨማሪ አንድ ወጭ የሚያስወጣ በዓል እጨምራለን ማለት ነዉ። በዚህ ቀን የሚወጣዉ ወጭ ብዙ ነዉ። ፍቅረኛሞቹ የሚለብሱት ተመሳሳይ መሆን አለበት። ቀይ ኮፍያ፤ ቀይ ሸሚዝ ፤ቀይ ቀሚስ የመሳሰሉ ነገሮች ይኖራሉ። ስለዚህ ቀኑ እንደ በዓል ታስቦ፤ ሰዉ እቁብ ሊገባ፤ ሊበደር ነዉ ማለት ነዉ። ስለዚህም እኔ ይህ የፍቅረኛሞች ቀን ለአንድ ቀን ብቻ መሆን የለበትም ከሚሉት ወገን ነኝ። ፍቅር የሕይወታችን አንድ አካል ስለሆነ በየቀኑ ልንተሳሰብ፤ እናደርግ ካልን ደግሞ በራሳችን የራሳችን የምንለዉ ቀን ሊኖር ይገባል እንጂ፤ ይህ የፍቅር ቀን ተብሎ ተወስኖ፤ በዚህ ቀን አላደረክልኝም የሚል ወቀሳም ሊመጣብን ሁሉ ይችላል። ስለዚህ ሰዎች ቀኑን ሳይወስኑ ማታም ሆነ ጠዋት ነገም ሆነ ዛሬ ፍቅራቸዉን ሊገላለፁ ከፈለጉ አንድ የራሳቸዉ የተለየ ቀን ሊኖራቸዉ ይችላል። ከዝያ በተረፈ የግዴታ « ፊብርዋሪ 14 ነዉ» የሚለዉ ወደ አለመግባባት ሊያመጣ ይችላል የሚል ኃሳብ አለኝ» ይልቁንም የሴቶች መብት ቢከበር ለሴት የሚገባትን ክብር ብንሰጥ ያሉን በሴቶች መብት ጉዳይ ላይ የሚሰሩት ወ/ሮ ማሪያ ሙኒር፤ ሴትን ወደ ጓዳ የሚለዉን ልምዳችን ለማስቀረት መሥራት ይጠበቅብናል። « እኔ መቼም አስተዳደጋችን መሠለኝ። አስተዳደጋችን አሁንም ሆነ ቀደም ሲልም የነበረዉ፤ አባት ሚስቱን እንዴት ይይዛት እንደነበረ የሚያይ ልጅ፤ እሱም ራሱ ሚስቱን እንደዝያ ነዉ የሚይዘዉ። እቤት ዉስጥ አባት ሴት ልጁን በትክክል የማያይ ከሆነ ሴት ልጁም እንደ አልቃሻ የምትታይ ከሆነ፤ ወንዱ ልጅም ደብዳቢ፤ ጉልበተኛ ሆኖ በሚታይበት ኅብረተሰብ ዉስጥ ያንን ይዞ ነዉና የሚሄደዉ፤ ያንን አስተዳደግ ላይ መቀየር ካልቻልን፤ ከሕፃንነት መቀየር ካልቻልን ፤ ይህ ፀባይ እየቀጠለ ነዉ የሚሄደዉ። በሴቶች ጉዳይ ላይ ከ 20 ዓመታት በላይ ሰርቻለሁ። ቀደም ሲልም እንደምናየዉ ትንሽ የባል ለዉጦች ይታያሉ ፤ ይህ ለዉጥ ደግሞ በአዲሱ ትዉልድ ላይ እየታየ ነዉ ማለት እችላለሁ። እቤት ዉስጥ መረዳዳቱም ወጣት ባለትዳሮች ላይ ይታያል። ይህ ደግሞ ሁለቱ ሰርተዉ ስለሚገቡ ኑሮም ሊሆን ይችላል። ምናልባት በጣም በቁጥር በተወሰነ፤ ቤተሰብ አካባቢ ለዉጥ ይታያል። በጣም ዉስነነት አለዉ ቢሆንም ሊበረታታ የሚገባዉ ነዉ። ችግሩ ወንዶች ብቻ ላይ አይደለም የሚታየዉ። አሳዳጊዎቹ ሴቶችም ነን፤ እኛ ሴቶች ራሳችን ልጆቻችን ላይ ልዩነት ፈጥረን እናሳድጋለን። እናቶች ሴትዋ ልጃችን ከትምህርት ቤት ስትመጣ ቶሎ ብለን የምንሰጣት የማዕድ ቤት ሥራን ነዉ። ወንዱ ልጅን ደግሞ ወጥቶ ኳስ እንዲጫወት እንፈቅድለታለን። እናም ይህን አይነት ተፅኖ እንዲመጣ የምናደርገዉ እኛ ራሳችን አሳዳጊ እናቶችም ነን። ይህን ፀባይ ደግሞ እኛ እንዳደግንበት ከጥንት ይዘን እንደመጣነዉ መሆኑ ነዉ። ወንዶች እቤት ዉስጥ ሲሰሩ «ይሄማ ሴታ ሴት ነዉ» እያልን እንወርፋለን። Feuerholz zum Heizen Äthiopien እቤት ወስጥ አንድ ወንድ ልጅ እናቱን ሊጥ እያቦካ እንጀራ እየጋገረ፤ እንዲሁም ቡና እያፈላ ከአገዘ፤ እነዚህን ልጆች ጓደኞቻቸዉም ሆነ ሌላዉም ኅብረተሰብ ይሄማ ሴታ ሴት ነዉ፤ ማዕድ ቤት ሲሰራ ነዉ የሚዉለዉ ሲሉ ይናገራሉ፤ ይወርፋሉ፤ ያንጓጥጣሉ። ይህ የሚያሳየዉ በኅብረተሰቡ የአስተሳሰብ ለዉጥ አለመኖሩን ነዉ። አንዳንድ ሚስቶችም ቢሆኑ ባሎቻቸዉ ወደ ጓዳ ገባ ገባ ሲሉ «ይሄ እንደዉ ሴታ ሴት ማዕድ ቤት እየገባ» «እንደ ሴት ማዕድ ቤት እየገባ» የሚሉና ወንዶች ወደ ማዕድ ቤት ሲገባ የማይወዱ ሴቶች አሉ ሲሉ ተናግረዋል። ይልቁንም የሴቶች መብት ቢከበር ለሴት የሚገባትን ክብር ብንሰጥ ያሉን በሴቶች መብት ጉዳይ ላይ የሚሰሩት ወ/ሮ ማሪያ ሙኒር፤ ሴትን ወደ ጓዳ የሚለዉን ልምዳችን ለማስቀረት መሥራት ይጠበቅብናል። እና ይህ ማኅበረሰቡን መቀየር ሥራ ከራስ ቤት ይጀምራል ነዉ። በሌላ በኩል ማኅበረሰቡ ዉስጥ የሚታየዉን አንዳንድ ጎታች አስተሳሰብ ጥቂት ኢትዮጵያ ሚዲያዎችም በጣም በጥቂቱ ይንቀሳቀሳሉ ያሉት ወ/ሮ ማሪያ እንዲያም ሆኖ በሚዲያ የሚተላለፉት አንዳንድ ነገሮችም ሴትን አሳንሰዉ የሚያሳዩ ሆነዉ የሚታዩና የሚደመጡ መኖራቸዉን ሳይገልፁ አላለፉም። ጋዜጠኛ የትነበርክ ታደለም የወ/ሮ ሚርያምን ኃሳብ ይጋራል። የሴት ልጅ እኩልነት የሚለካዉ ለዉጭ ዓለም እራስዋን በምታሳይበት መንገድ ሳይሆን በሚሰጣት መልካም እድል ነዉ ሲል ተናግሮአል። ለእህት እናቶቻችን አያት አክስቶቻችን በአጠቃላይ ለሴቶች መብት መከበር በቅድምያ በትምህርቱ በሥራዉ እንዲሁም በመሪነት ደረጃ ለሴቶች እድልን በመክፈት፤ ሴቶችን የሚያሳንሱ ጎታች ልምዶችን ከማኅበረሰቡ መቅረፍ ይቻላል፤ ሚዲያዎችም ለዚህ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ በመሰናዶዉ ላይ ቃለ- ምልልስ የሰጡንን በማመስገን የእለቱን ዝግጅት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
695
እውነተኛ የሴቶች መብት አክባሪ በማርሊን አዳምሰን -ብዙ ጊዜ ኃይማኖቶች ስለሴቶች ባላቸው አመለካከት በሴት መብት ተከራካሪዎች ይነቀፋሉ። መሆንም አለበት። በመላው ዓለም የሴቶችን ክብረ የሚነኩ አያሌ ምሣሌዎችን ማግኘት ተችላላቸሁ። እነዚህ የሴት መብት አስከባሪ ድርጅቶች የማያውቁት ነገር ቢኖር ጌታ ኢየሱሰ ክርስቶስ ዕውነተኛ የሴቶች መብት አክባሪና አጋራቸው እንደሆነ ነው። ከ2000 ዓመታት በፊት በእሥራኤል ምድር እየሱስ በኖረበት ዘመን የኃይማኖት መሪዎች እግዚአብሔር ሆይ ሴት አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አመሰግንሃለሁ ይሉ ነበር። እየሱስ ግን ስለሴቶቸ ያለው አመለካከት በጊዜው በመካከለኛ ምሥራቅ ውስጥ ካለው አመለካከት እጅግ ፍጹም የተለየ ነበር። በዚያ ሴቶች የሚታዩት እንደ ሰው ሳይሆን ከአንድ ቁስ ተለይተው አይታዩም ነበር። ስለዚህም በማህበራዊ ጉዳይ ውስጥ ሚናቸው በብዙ የተገደበና አስፈላጊነታቸው ለባሎቻቸውና ለልጆቻቸው ብቻ ነበር። አንድ የአይሁድ ዕምነት መምህር በቤተ መቅደስ ውስጥ ኃይማኖታዊ ሥርዐቱን ሲፈጽም ምንም ቅር ሳይለው የተባረክከው አምላካችን ሆይ ሴት አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አመሰግንሃለሁ ብሎ ይጸልያል ። ሁሉም ሴቶች በማንኛውም በጉባኤ ከሚደረገው ኃይማኖታዊ ሥርዓት የተገለሉ ናቸው። የሙሴን ሕግ ቶራ የሚባለውን የአይሁድ ዕምነት ቅዱስ ዕምነት መጽሐፋቸውን በግላቸውመ ቢሆን እንኳ የተማሩት ጥቂት እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው። አንድ አይሁዳዊ ባል ሚስቱን ያለምንም ምክንያት ይፈታት ዘንድ ሕጉ ይፈቅድለት ነበር። ለምሳሌ እራት በጊዜ ካላዘጋጀች ለመፈታት በቂ ምክንያት ነበር፡፤ ሚስት ይህን እርምጃውን ለመቃወም የሚያስችላት ምንም መብት የላትም። በቀላሉ የፍችዋን ጽሕፈት አዘጋጅቶ መስጠትና ማባረር ብቻ ነው ከባልየው የሚጠበቀው። ይታያችሁ ይህ ሕግ ሴቶችን ምን ያህል አለኝታ እንዳሳጣቸውና ክፉኛ እንደጨከነባቸው፡፡ በአንጻሩ ሚስቶች ባሎቻቸውን በራሳቸው ፈቃድ መፍታት ፋጽሞ አይችሉም። በምንም ምክንያት። በተወሰኑ ዐረብ አገሮች ውስጥ ውስጥ አሁንም እንኳ በሴቶቸ ላይ ተግባራዊ እገዳ የሚያደርግ ሃይማኖትና ባህል አለ። ሴት ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ተሸፋፍና እንድትሄድ የሚያስገድድ ተግባራዊ የሚያደርጉ የዐረብ አገሮች ብዙ ናቸው። ሴት ብቻዋንም ሆነ ከጓደኛዋ ጋር ከቤት እንድትወጣ አይፈቀድላትም። ከወንድ ጋር እንጂ ብቻዋን በአደባባይ በሚከበር ክብረ በዐል ላይ እንድትገኝ ከቶም አይፈቀድላትም። በአንዳንድ የአረብ አገር ውስጥ ሴቶች መኪና እንዲነዱ አይፈቀድላቸውም። እንደዚሁም ባሎቻቸው ሊላ ሚስት ሲያገቡ ምንም የተቃውሞ ድምጽ እንዲያሰሙም አይፈቀድላቸውም። ኢየሱስ ክርስቶስ በአደባባይ ከሚያስተምራቸው ደቀመዛሙርቶቹ መካከል በርካታ ሴቶች ነበሩ። ሕዝቦች ሲሰበሰቡና ሲያስተምርም ወንዶችም ሴቶችም አንድ ላይ ተደባልቀው ያስተምራቸው ነበር። ሴቶችን ከወንዶች ሳይለይ ተዓምራትን በሕይወታችው ፈጽሟል። ፊሊፕ ያንሲ የተባለ አንድ ጸሐፊ ፡- « ለሴቶቸና ለተጨቆኑት ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የጊዜውን ሕግና ጥበብ እንዳልነበረ አድርጎ ገለባብጣታል። ጌታ ኢየሱስ በማህበረሰቡ ውስጥ ዋንኛና ተገቢ ነው ብለው የተቀበሉትን የአኗኗር ዘይቤ በተለይም የሴቶችን መብት በማክበርና በመጠበቅ እንዳሳየ በአራቱ ወንጌላት ውስጥ አንብቦ መረዳት ይቻላል ። » አለ። እጅግ ብዙ የሆኑ ሰዎች ኢየሱስን ተከተሉት። ገሚሱ ተዓምራት እንዲያደርግላቸው፤ ገሚሱ እንዲያስተምራቸው፤ ይከተሉት ነበር፤ ዝናው በጅማሬው ላይ በራሱ ላይ ችግር ፈጥሮበት ነበር። የሃይማኖት ባለሥልጣናት ይህ ሁኔታ አልተመቻቸውም ፤ ስለዚህ እርሱን በነገር ሊያጠምዱት ዕቅድ አወጡ። እነሱም ሆነ ሌሎችም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሚያስተምረው ስለፍቅር፣ ስለምህረትና ፣ስለርህራሄ ሰምተዋል። የሃይማኖት መሪዎቹ ይህንን ለማጥመጃ እንዲሆናቸው አድርገው ሊጠቀሙበት ፈለጉ። ከሃይማኖት ሕጎቻቸው ውስጥ በተለይም ሴቶችን አስመልክቶ እጅግ ከባዱ የሚባለውና በድንጋይ ተወግረው እንዲገደሉ የሚደነግገው ሕግ አንዲት ሱት በዝሙት ምክንያት ከተያዘች ነበር። ስለዚህ ሕዝቡን አስተባበሩና አንዲትን ሴት በዝሙት ይዘው ለመገደል አመቻችተው እሱንም ለማጥመድ አድርገው በጌታ ኢየሱስ ፊት አቀረቧት። ምናልባትም ይቺ ሴት ከአንድ ጓደኛቸው ጋ ይሆናል የያዝዋት፤ ከዚያም ለጌታ ኢየሱስ እንዲህ አሉት፡- መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ዮሐ 8፥3-4 አሁን ገና አገኘነው ብለው ነው ያሰቡት። መፈናፈኛ እንዳሳጡት አድርገው ነው የቆጠሩት። ምህረት ቢያደርግላት ዝሙትን እንደደገፈና የሙሴን ሕግ እንዳቃለለና የሙሴ ሕግ ጠላት እንደሆነ በቂ ማረጋገጫ አገኙ ማለት ነው። በአንጻሩ ሴቲቱን እንደ ሙሴ ሕግ ልክ እንዳሉት አንድትወገር ቢፈርድ፣ የሴቶችን መብት የማክበር ፋይዳው ምንም እንዳልሆነ ይታይና ስለምህረት ፣ ስለፍቅርና ስለቸርነት የሚያስተምረው ትምህርት እንደው ለማስተማር ብቻ እንጂ ሕይወት የለውም ማለት ነው ለማለት ተዘጋጅተዋል። ታዲያ ምን ሆነ መሰላችሁ! የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። ዮሐ 8፥6-7 ከዚህ በኋላ ማንም እዚያ ለመቂየት የደፈረ አልነበረም። ከታላቁ ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ሄደ። ኢየሱስና ሴቲቱ ብቻ ቀሩ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት። ዮሐ.8፥9-11 ምን ይደንቃል ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበትና በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሞተበት ጊዜ ወንዶቹ እግሬ አውጪኝ ብለው ሲሸሹ እስከ መስቀሉ ድረስ ከዛም አልፎ ነፍሱ እስክትወጣና እስከመቃብር ድረስ ሴቶች ተከትለው በመሄድ ፍቅራቸውን ቢገልጹልት ምን ይደንቃል? ኢየሱስን ሞትን ድል አድርጎ በተነሳ ጊዜ የርሱን ከሞት መነሳት ያበስሩ ዘንድ ሴቶችን ለዚህ ታላቅ የምሥራች ተናጋሪ አድርጎ በመምረጥ አከበራቸው። ሴቶች ለቁም ነገር በማይታሰብቡበት በሕግና በሃይማኖት ጭቆና ቀንበር ስር ባሉበት ማህበረሰብ ውስጥ ሴትን የአንድ ታላቅ ዕምነት ድንቅ የትንሣኤውን መረጃ ለማቀበል አፈቀላጤ አድርጎ መለየት ይህ ታላቅ ነገር ነው። ግን ለምን? የመጣው ለወንዶችም ለሴቶችም ኃጢዓት ሲል ለመሞት እንደሆነ በመጨረሻ አጠንክሮ በተጨባጭ ለማስቀመጥ ሊሆን ይችላል። ምናልባትም ሁለቱንም ወንዶችንም ሴቶችንም ሙሉ ይቅርታ እንዳደረገላቸውና ለሰላምና ለዘላለም ሕይወት እኩል ወራሽነት በዚህ መልክ ለማጽናት ፈልጎ ይሆናል። በተጨማሪም ይህንን ዕውነት በተጨባጭ ከሳምራዊቱ ሴት ጋር ባደረገው ጭውውት በሚገባ አሳይቷል። በትችትና በነቀፋ ከማህበረሰቡ መገለልና መድልዎ የደረሰባትን ምሥኪን ሴት ውሃ በምትቀዳበት ቦታ ጠብቋት አነጋገራት። አምስት ጊዜ አግብታ ፈታለች። ይታያቸሁ አምስት ወንዶት ተፈራርቀው ተጠቅመውባት እንደ ዕቃ በንቀት ጥለዋት ሄደዋል። ይህ ምን ስሜት ውስጥ እንደሚከት ማሰቡ ይከብዳል። ጌታ ኢየሱስ ግን ሊያናግራት ውሃ ወደ ምትቀዳበት ጉድጓድ ድረስ መጣና እንዲህ አላት « ። ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። ዮሐ 4፥13-14 የጌታ ኢየሱስ ፍላጎት ሁልጊዜም እንደዚህ ነው። የርሱን ሕይወት ለዘላለም እንድንለማመድ ነው የሚፈልገው።
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
696
የፆታ እኩልነት ጉዳይ በውለታ የተገኘ ሳይሆን በሰውነታችን የተገባን መብታችን ነው-ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ On Mar 8, 2019 591 አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ ለ43 ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የሴቶችን ቀንን ምክንያት በማድረግ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸው በአውሮፓውያኑ 1975 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓመቱን ለሴቶች ሲል አውጆ እንደነበረ አስታውሰዋል። በዚህ ሳያበቃም ከዚያ ዓመት በማስከተል ያሉትን አሥር አመታት የሴቶች ዐሥርት ዓመታት (Women’s Decade) ተብለው እንዲታሰቡ መወሰኑን ጠቅሰዋል፤ እነዚህ አመታት ዛሬ ላይ ለምናነሳቸው ታዋቂ የሴቶች መብት ማስከበሪያ የዓለም አቀፍ ሥምምነቶች መፈረም፥ መሠረታዊ የሆኑ የስርዐተ ፆታ ውይይቶች በአለም አቀፍ ደረጃ መጀመር እና የሴቶች ጉዳይ መታሰቢያ በዓላት መፈጠር ምክንያት ሆነው አልፈዋል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ። እኛ ኢትዮጵያውያንም ዛሬም አለም አቀፉን የሴቶች ቀን ዘንድሮ ለ43ኛ ጊዜ ስናከብር ባለፉት አራት አስርተ አመታት የሀገራችን ሴቶች ሕይወት ምን ያህል ተለውጧል? እኛስ የሚገባንን አድርገናልን? ብለን መጠየቅም ይገባናል ብለዋል። ይህን ጥያቄም በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በየእለቱ ልንጠይቅ፡ አጥጋቢ ያልሆኑ ምላሾችንም ልንሞግት ይገባናል ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ የፆታ እኩልነት ጉዳይ በውለታ የተገኘ ሳይሆን በሰውነታችን የተገባን መብታችን ነው ሲሉ ገልፀዋል። የመብት ጉዳይ ደግሞ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በየእለቱ በመቆጨት እና በሀላፊነት ስሜት ልናነሳውና ልንሰራበት የሚገባ ነው ብለዋል ባስተላለፉት መልዕክት። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን ውስጥ የሴቶችን ውክልና ለማረጋገጥ የሚወሰዱ ውሳኔዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፥ በፌደራል መንግስት ካቢኔ ውስጥ የሴቶች ድርሻ ሀምሳ በመቶ መሆኑ፡ ብቃት ያላቸው ባለሙያ ሴቶች በተለያዩ ቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ መሾማቸው መልካም ጅምር እና ለወጣት ሴቶች እና ወንዶች ተምሳሌት እንደሚሆንም ጠቅሰዋል፡፡ በእርግጥም በሴቶች ጉዳይ ላይ የተመዘገቡት ውጤቶች በቀላሉ የሚታዩ አይደሉም። ነገር ግን ይህ ጅምር “የሴቶች ጥያቄ ተመልሷል! የሚበቃቸውን አግኝተዋል!” የሚል ስሜት ሊፈጥርም ሆነ እጃችን ላይ ካለው ሥራ ሊያዘናጋን አይገባምም ነው ያሉት። ለዚህም የስርዐተ ፆታ ልዩነትን ለማጥፋት ከሰሀራ በታች ላሉ ሀገራት አሁን ባለው አያያዝ 135 አመት እንደሚፈጅ በተለያዩ መድረኮች መጠቀሱን አንስተዋል፤ በሀገራችን ደግሞ ያላቻ ጋብቻ የሴት ልጅ እና ግርዛት ዛሬም እንደሚካሄድ በመጥቀስ። ፕሬዚዳንቷ በመልዕክታቸው ከወንዶች ተማሪዎች በላቀ ቁጥር ሴት ልጆቻችን ከመጀመሪያ፥ ከሁለተኛ ደረጃ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን ትምህርታቸውን እንደሚያቋርጡ ጠቁመዋል። በአሁኑ ሰዓት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶች ውስጥ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ሴቶች 34 በመቶ፣ የሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር 17 መቶ እንዲሁም የዶክትሬት መርሀ ግብር ውስጥ ደግሞ 8 በመቶ ብቻ መሆናቸውን በመልዕክታቸው አስፍረዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ሴት ልጆች ትምህርታቸውን እየተከታተሉም የቤት ሥራ ጫናን ይሸከማሉ ለፆታዊ ጥቃትም ይጋለጣሉ። ይህን ተቋቁመው ያለፉት ደግሞ ብቃታቸውን ተማምኖ የሚቀጥር፥ ይገባታል ብሎ በስራ የሚያሳድግ እንዲሁም የእነሱን ማደግ እና መለወጥ ፈልጎ የሚሰራ ተቋም እና ማህበረሰብ ባለማግኘት እንደሚንገላቱም አውስተዋል። ከሁሉ በላይ ደግሞ በገጠሪቱ የሀገራችን ክፍል ያሉ እናቶች እና ህፃናት የድህነትን መራር ገፈት በዋናነት እየተቀበሉ እንደሚኖሩ አብራርተዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ችግሮች ተያያዥ እና ተመጋጋቢ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንቷ የሚያስተሳስራቸው ዋነኛው ሰበዝ ለሴቶች እንደማህበረሰብ የምንሰጠውን ቦታ የሚቀርፁ በዘመናት ውስጥ የደረጁ ጎታች አስተሳሰቦች መሆናቸውን ጠቁመዋል። እነዚህ ጎጂ ልማዶች እና አስተሳሰቦች የባህላችን እና እሴቶቻችን አንድ አካል ናቸው። ስለ ስርዐተ ፆታ እኩልነት ያለን አስተሳሰብ ካልተለወጠ፡ ሴቶችን እንደ ሙሉ ሰው እና አቻ ዜጋ እስካላየን ድረስ ትርጉም ያለው እና ዘላቂ ለውጥ ልናመጣ አንችልም ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ ወደፊት መራመድ ከፈለግን እንደ ማህበረሰብ በመጀመሪያ ደረጃ መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ እንዳለብን እና 51 በመቶ የሚሆነውን የህብረተሰባችንን ክፍል እየገፋን መሆኑን መገንዘብ ያሻል። የመፍትሄ ህሳቦቻችንም ይህንን ያገናዘቡ መሆን አለባቸው ነው ያሉት። በአመራር ቦታዎች ላይ በዘላቂነት በቂ ሴቶች እንዲኖሩ ተቋማቶቻችን በእኩልነት እንዲመሩ ከተፈለገ ሴት ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ መደገፍ እና በመንገዳቸው ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን ማስወገድ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ በፆታ የሚደረግ መድሎ እንዲወገድ ከተፈለገም እነዚህ ተግዳሮቶች ከየት ነው የሚመጡት፥ ህብረተሰቡስ ሴቶችን በዚህ መልኩ የሚፈርጀው ለምንድነው ብለን መጠየቅ አለብን ያሉ ሲሆን እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችን ስንጠይቅ ችግሩን ከስር መሰረቱ የመፍታት እድል ይጨምራል ብለዋል። ሰብዐዊነት ውስጣችን ሲገባ የሰብዐዊ መብት መረዳታችን ምሉዕ ሲሆን ማንም ወገን ሲገፋ እና ሲጠቃ አይተን ዝም ማለት አንችልም ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እንደሴቶች ደግሞ እህትማማችነት በመሀላችን ሲፀና እኩልነትን ለሁሉም እንሻለን፣ በአገኘነው አጋጣሚ ሁሉ፥ ለኛ የተከፈተውን በር ከኋላችን ለምትመጣው ክፍት አድርገን ይዘን አለሁልሽ እንላለን። እነዚህን ለማድረግ በአመት ውስጥ 365 ቀናት እንዳሉ ይህንምም መጠቀም እንደሚያስፈልግ በመግለፅ የዛሬው አይነት በዓላትም ማስታወሻ ይሆኑናል። ነገር ግን ከአራት አስርት አመታት በፊት የወቅቱን ሁኔታ ተገንዝበው ተጨማሪ ጊዜ አሳውጀው ብዙ ተግባራትን እንዳከናወኑት ሁሉ እኛም ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ የሴቶች ቀን በአመት አንዴ ብቻ ታስቦ በመዋል መታለፍ የለበትም። የስርዐተ ፆታ ጉዳይን ብሄራዊ አጀንዳ አድርገን ሰፋ ያለ ጊዜ ወስደን የኢትዮጵያውያን ሴቶች ወር (የሴቶች ወር) ብለን ብናከብር መልካም ይሆናል ብለዋል። ይህ ጊዜም በሀገር ደረጃ ህብረተሰባችንን፥ ባህላዊ እሴቶቻችንን እና ታሪካችንን እየፈተሽን የሚበጁንን እያፀናን እና እያከበርን እንድንቀጥል መሻሻል ያለባቸውን እየለየን እየለወጥን እንድንሄድ ተሰባስበን የምንመክርበት ይሆናል። እንዲሁም ለለየናቸው ችግሮች መፍትሔ የምንፈልግበት፣ ያሉንን ብርቱዎች የምናደንቅበት፣ እስካሁን ከሠራነው የምንማርበት ይሆናል። ይህን መርሀ ግብር የትኛው ወር ላይ ብናደርገው መልካም ነው የሚለውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተን የምናሳውቅ ይሆናል ሲሉ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ገልፀዋል። በመጨረሻም በዚህ ሰዓት ሀላፊነት ተሰምቷችሁ ባላቸው አቅም የሴቶችን ህይወት የተሻለ ለማድረግ፣ የሀገራችንን ተቋማት ፍትሀዊ እና አሳታፊ ለማድረግ ለሚተጉት ሁሉ ምስጋናዬ አቀርባለሁ ብለዋል። የማህበራዊ ለውጥ ሥራ ጊዜ የሚፈጅ እና ትእግስት የሚጠይቅ መሆኑን ተገንዝበን የወደፊቱን ተስፋ ሰንቀን እርስ በርስ እየተደጋገፍን እንድንሰራ ይሁን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸው በሀገራችን ዙርያ ያሉ ሴት ኢትዮጵያውያን በሙሉ ያለ ሥጋት ውለው የሚያድሩባት፣ በሴትነታቸውም በፍፁም አንሰው የማይታዩባትን ኢትዮጵያን ሴቶች እና ወንዶች በጋራ እንገንባ በማለት ጥሪ አቅርበዋል። የዛሬ አመት እስካሁን ከተመዘገበው የላቀ መልካም የእኩልነት እና ፍትህ ዜና የምንሰማበት፣ ብዙ ሴቶች በህዝብ ተወክለው ለምርጫ የሚወዳደሩበት እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶቻችን የተሻለ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የሚመረቁበት ይሁን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
697
ሴቶችን የተመለከቱ አለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ገጽታ በኢትዩጲያ በህግ ጥናት፣ ማርቀቅ እና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት የተዘጋ መግቢያ በሃገራችን ኢትዮጵያ ሴቶች ግማሽ ያህሉን የህብረተሰብ ክፍል ይወክላሉ፡፡ ሴቶች ሰው በመሆናቸው በአለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እንዲሁም ብሄራዊ ህጎች ላይ የተቀመጡ የሰብአዊ መብቶች እኩል ተጠቃሚ ናቸው፡፡ ይሁንና በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት እና አድሎአዊ አሰራር ዓለማቃፋዊ እውነታ ነው፡፡ በዓለማቀፍም ሆነ በሀገራቀፍ ደረጃ ሴቶች የሰብኣዊ መብቶች ባለቤት መሆን ቢችሉም መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ይህን አያሳይም፡፡ ሴቶች ለአድሎአዊ አሰራር እና ለተለያ ጥቃቶች ተጋልጠው ቆይተዋል፡፡ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶቻቸውን እና ነጻነቶቻቸውን ተነፍገው ቆይተዋል፡፡ ለምሳሌ ትምህርት የማግኘት መብት፣ የጤና መብት፣ አድሎአዊ እና አግላይ የሆኑ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች (የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ያለእድሜ ጋብቻ እና ግርዛት) የንብረት እና ሃብት የማፍራት መብቶቻቸውን ተነፍገው በመቆየታቸው በማህበረሰብ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ እንዲቀንስ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ሁኔታም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ታዳጊ ሀገራት የሴቶችን ሚና በተመለከተ ያለው ባህላዊ እና ልማዳዊ አስተሳሰብ የሴቶችን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሴቶች ለስነ-ልቦናዊ፣ አካላዊ እና ማህበራዊ ችግሮች ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡ ለችግሩ እልባት ለመስጠትም አህጉራዊ፣ አለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ከሁለተኛው የኣለም ጦርነት በኋላ የስርዓተ ጾታ ጉዳይ ትኩረት አግኝቶ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የተለያዩ አለማቀፍ የሰብኣዊ መብቶች ስምምነቶች፣ ጾታን መሰረት ያደረጉ ልዩነቶችን መፈጸም የተከለከለ መሆኑን በሰነዶቹ ውስጥ መካተት መቻሉ አንድ እርምጃ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ሆኖም የሚፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ የሴቶችን ሰብኣዊ መብቶች በተናጠል የሚመለከቱ ስምምነቶች በአለማቀፍ ደረጃ ተደርገዋል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችና ልዩነቶች ከማህበረሰቡ ባህላዊና ልማዳዊ አስተሳሰቦች ጋር ተቆራኝተው የሚገኙበት እና የወንዶች የበላይነት የሚንጸባረቅበት ሁኔታ ሰፊ ነው፡፡ ችግሩን ለማስወገድም በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ በሴቶች ላይ የሚደረገውን ማንኛውንም ልዩነት የሚከለክለውን ዓለማቀፍ ስምምነት ተቀብሎ ከማጽደቅ አንስቶ የሴቶችን የሰብኣዊ መብቶች በህገመንግሰቱ በማካተት እውቅናና ጥበቃ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ ጉዳዩን የሚመለከቱ ሀጎችን በማውጣት እና ቀድሞ የነበሩትንም በማሻሻል ረገድ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ ነገር ግን ከችግሮቹ ስፋት እና ጥልቀት አንጻር ችግሮቹ ሙሉ በሙሉ የተቀረፉ ባለመሆናቸው የተጀመሩት መልካም ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍም በሶስት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል የሴቶችን ሠብዓዊ መብቶች ለማስከበር በዓለማቀፍ ደረጃ የተደረጉ ስምምነቶችን የሚዳስስ ይሆናል፡፡ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ የሴቶችን ሰብአዊ መብቶች ለማስከበርና ለማረጋገጥ የአባል መንግስታት ግዴታዎችን ተከትሎ በኢትዩጲያ የተቀረጹ የህግ እና የፖሊሲ ማዕቀፎችን በአጭሩ የሚመለከት ነው፡፡ በመጨረሻም አለም አቀፍ ስምምነቶችን ከብሄራዊ ህጎች ጋር በማዋሃድ ያለው አፈጻጸምን በተመለከተ የሚታዩ የህግ እና የአተገባበር ክፍተቶች ምን እነደሆኑ የሚቀርብበት ነው፡፡ 1. የሴቶች ሰብኣዊ እና የእኩልነት መብቶች ከአለምአቀፍ እና አህጉራዊ ህግጋት አንጻር በዚህ ክፍል የሴቶች መብቶች ከተባበሩት መንግስታት ቻርተር፣ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ ከሲቪልና የፖሊቲካ መብቶች ስምምነት፣ ከዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊናባህላዊ መብቶች ስምምነት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የሴቶች የፖሊቲካ መብቶች ስምምነቶች እና ከዓለምአቀፍ ማንኛውንም ልዩነት ለማስዎገድ የተደረገ መግለጫና ስምምነት አንጻር ይዳሰሳል፡፡ 1.1 የሴቶች መብት ከተባበሩት መንግስታት ቻርተር እይታ የተባበሩት መንግስታት ቻርተር የሴቶችን የእኩልነት መብት መሰረታዊ መብት በማድረግ ያካተተ ሰነድ ነው፡፡ በቻርተሩ አንቀጽ 1 ላይ እንደተመለከተው የሰው ልጆች (ሴቶችን ጨምሮ) ማንኛውም አይነት ልዩነት ሳይደረግባቸው በእኩልነት የመኖር መብት አላቸው፡፡ ስለዚህ የሴቶች የእኩልነት መብት ሳይከበር የሴቶችን መብት እና የዓለምን ሰላም ማስጠበቅ የማይቻል መሆኑን ያመላከተ ሰነድ ነው ማለት ነው፡፡ 1.2 የሴቶች መብት በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ ምንም እንኳን መግለጫ ከመሆኑ አንጻር ህጋዊ አስገዳጅነት ያለው ባይሆንም በአሁኑ ጊዜ ልማዳዊ ህግ(customary law) እየሆነ በመምጣቱ ተቀባይነቱ እየጨመረ የመጣና ለሌሎች የሰብአዊ መብቶች እና ነጸነቶች መሰረት የሆነ ዓለም አቀፍ ህግ ነው፡፡ መግለጫው ሰዎች ሁሉ የማይገሰስ እኩል መብት እና ክብር ያላቸው ስለመሆኑ እና ይህም ለዓለም ሰላም መከበር እና ለሰው ልጆች መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች መረጋገጥ ሚና እንዳለው ደንግጓል፡፡ የሴቶች የእኩልነት መብትም በመግለጫው ተካትቷል፡፡ በመግለጫው አንቀጽ 16 ላይ እንደተመለከተው ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ ከትምህርት መብት አንጻርም መግለጫው በአንቀጽ 20 ላይ ሁሉም ሰው የትምህርት መብት (ት/ት የማግኘት (availability, acceptability, accessibility and adaptabilty)( Equal enjoyment of, and equal access to, educational opportunities and facilities) ያለው ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትም ለሁሉም በነጻ አሰገዳጅ በሆነ ሁኔታ (Compulsory and free primary education) እንዲዳረስ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ት/ትም ብቃትን መሰረት አድርጎ ለሁሉም መዳረስ ያለበት ስለመሆኑ (Generally available and accessible secondary education and equally accessible higher education) አስቀምጧል፡፡ የቴክኒክ እና ሙያ ት/ትም እንዲሁ፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን የአባል ሀገራት የት/ት ስርዓት የሰብኣዊ ልማትን እና የሰብአዊ መብቶችን መሰረት አድርጎ መቀረጽ ያለበት ስለመሆኑም ጭምር ይደነግጋል፡፡ ይህም ትምህርት ለሰብኣዊ መብት መከበር ካለው ፋይዳ በመነሳት ነው፡፡ በትምህርት መብት ላይ የሚደረግ ጾታን መሰረት ያደረገ ማንኛውም አይነት ልዩነትም የሰብአዊ መብት ጥሰት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም የሴቶች የስራ መብት በመግለጫው አንቀጽ 23 (1) የተደነገገ ሲሆን ከዚኅ አንጻርም ጾታን መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር መፈጸም ህገወጥ ተግባር ነው ሊባል ይችላል፡፡ ይህም በመሬት ላይ በግልጽ ያለና የሚታይ የቅጥር መድሎ (defacto discrimination) ወይም የህግ መሰረት ያለው አድሎ (dejure Discrimination) ሊሆን ይችላል፡፡ የመግለጫው አንቀጽ 23(2) ም ሴቶች ለተመሳሳይ ሙያ (ስራ) እኩል ክፍያ የማግኘት መብት ያላቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ይህም ቅድመ-ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ እና ድህረ-ወሊድ ያለውን የክፍያ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ የሴቶችን እኩል የፖሊቲካ ተሳትፎ በተመለከተም የመግለጫው አንቀጽ 21 ሴቶች እንደማንኛውም ሰው በመንግስት አስተዳደር፣ በፖሊቲካና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ በእኩልነት የመሳተፍ እና ውሳኔ የማሳለፍ መብት እነዲሁም በእኩልነት የመወከል መብት እንዳላቸው ያስቀምጣል፡፡ 1.3 የሴቶች የፖለቲካ መብት ስምምነት እ.ኤ.አ በ1952 ዓ.ም የሴቶች የፖሊቲካ መብቶች ስምምነት የተፈረመ ሲሆን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሴቶችን ለማሳተፍ ብዙ ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህ ስምምነት የሴቶችን የፖሊቲካ ተሳትፎ ለመጀመሪያ ጊዜ እውቅና የሰጠ ስምምነት ሲሆን ከወንዶች ጋር ያላቸውን እኩል የመምረጥ እና የመመረጥ እንዲሁም የመወከል እና የመወከል መብት ያረጋገጠ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህም ሴቶች የአለማችንን ወይም የሀገራችንን ህዝብ ግማሽ የሚወክሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን የሚሰጧቸው ውሳኔዎች በሌሎች ላይ ያለው ትርጉም ላቅ ያለ በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ 1.4 በቅጥርና በስራ ላይ የሚደረግ አድሎን ለመደንገግ የወጣ ስምምነት እ.ኤ.አ በ1958 ዓ.ም የተደረገው በስራ ቅጥርና በስራ የሚደረግ አድሏዊ ልዩነትን ለመደንገግ የተደረገ ስምምነት (Discrimination (Employment and Occupation) Convention) በስራ ቦታ የሚፈጸም ጾታን መሰረት ያደረገ አድሏዊ ልዩነትን አንደሚከተለው ተርጉሞታል፡ Any distinction, exclusion or preference based on designated criteria such as race, color, sex, religion, political opinion, national extraction, social origin or other designated criteria which have the effect of nullifying or impairing equality of opportunity or treatment in employment or occupation. ስራን በሚመለከት የሚደረገው ልዩነት ሁለት ዓይነት ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህም፡ 1. በተግባር ያለ (እውናዊ) ነገር ግን በህግ ያልተደገፈ (defacto employment discrimination) 2. ስርዓታዊ እና በህግ የሚደገፍ (systematic and/or dejure employment discrimination) ናቸው፡፡ በስራ ቅጥርና በስራ የሚደረግ አድሏዊ ልዩነትን ለመደንገግ የተደረገው አለማቀፍ ስምምነት አንቀጽ 5 በጾታቸው፣ በእድሜያቸው፣ በአካል ጉዳተኝነታቸው ወይም በቤተሰብ ኃለፊነታቸው ወይም በማኅበረሰባዊ ተቀባይነታቸው ምክንያት ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲባል የሚወሰዱ ልዩ እርምጃዎች አድሏዊ አይደሉም፡፡ ምክንያቱም ተንሰራፍቶ የነበረውን አድሎ ለማስተካከልና እድላቸውን ለማስፋት (corrective and promotional) የሚወሰዱ ከመሆናቸውም በላይ ጊዜያዊ ውጤት ያላቸው በመሆናቸው አዎንታዊ እርምጃዎች ናቸው፡፡ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅም በውድድር ጊዜ ሌሎች መመዘኛዎች እኩልና ተመሳሳይ በሆኑ ጊዜ ቅድሚያ ምርጫው ለሴቶች መሰጠት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ 1.5 የሴቶች መብት በአለም አቀፍ የሲቪል እና የፖሊቲካ መብቶች ስምምነት ይህ ዓለም አቀፍ ስምምነት ልክ እንደ ሰብአዊ መብቶች መግለጫ ሁሉ በስምምነቱ የተካተቱት የሲቪል እና የፖሊቲካ መብቶች በእኩልነት (ያለ እድሎኣዊ ልዩነት) ይከበሩላቸው ዘንድ አባል መንግስታት ተገቢ እርምጃዎችን (ህጋዊ፣ አስተዳደራዊ እና የፖሊሲ) እንዲወስዱ ያስገድዳል (አንቀጽ 3) ፡፡ በዚህም መሰረት የሴቶችን እና የወንዶችን እኩል ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በተጨማሪም የስምምነቱ አንቀጽ 23 ሴቶች በጋብቻ ውስጥ እኩል ግንኙነት ያላቸው ስለመሆኑ አስቀምጧል፡፡ የስምምነቱ አንቀጽ 17 የሰዎችን ግላዊ ነጻነት እና ሙሉ ስብእና በተመለከተ የደነገገ ሲሆን አንቀጽ 27 ደግሞ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እና በህግ ጥላ ስር እኩል መስተናገድ ያለበት ስለመሆኑ ይደነግጋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም የስምምነቱ ፈራሚ ብቻ ሳተሆን አፅዳቂም በመሆኗ አለም አቀፍ ግዴታ አለባት፡፡ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የባህል መብቶች ስምምነትም ተመሳሳይ ድንጋጌዎች ተካትተዋል፡፡ 1.6 በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ መግለጫ (1967) ምንም እንኳን ከዚህ በፊት የተደረጉ ስምምነቶች ቢኖሩም ተግባራዊ አፈጻጸማቸው ግን የሴቶችን ሁለንተናዊ መብቶች ለማሰከበር ባለመቻሉ ለዚህ መግለጫ መውጣት እንደቅርብ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የአባል መንግስታት የሪፖርት አቀራረብ ስርዓት በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆን እና ሰነዱ ህጋዊ አስገዳጅነት የሌለው መሆኑ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡ በመሆኑም አስገዳጅነት ያለውና የሴቶችን ሰብኣዊ መብቶች ያካተተ ስምምነት እንዲወጣ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህም የ1979ኙ (እ.ኤ.አ) በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ልዩነት ለማስወገድ የተደረገው ስምምነት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ህጋዊ አስገዳጅነት አይኑረው እንጅ በሴች ላይ የሚፈጠሙ ጥቃቶችን ለማስቆም በ1993 (እ.ኤ.አ) የተደረገ የተባበሩት መንግስታት መግለጫ (declaration) ወጥቷል፡፡ በዚህ መግለጫ መሰረትም በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች የሚባሉት በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ጨምሮ አካላዊ፣ ጾታዊ (ጾታዊ ጥቃት እና ትንኮሳ) እና ስነልቦናዊ ጥቃቶች (ለምሳሌ ማስፈራራት) የተካተቱ ሲሆን ነገር ግን የሴቶች ጥቃት በነዚህ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ በዚህ መግለጫ አንቀጽ 2 ላይ እንደተደነገገው በሴቶች ላይ የሚፈጠሙ የኃይል ተግባራት ከፈቃድ ውጭ መንካትን፣ በቤት ውስጥ በሴት ህጻናት ላይ የሚፈጸም የወሲብ ጥቃትን፣ ከጥሎሽጋር የተያያዙ የሃይል ጥቃቶችን፣ በትዳር ጓደኛ የሚፈጸም ተገዶ መደፈርን (marital rape)፣ የሴቶች ግርዛትና ሴቶችን የሚጎዱ ሌሎች ልመዳዳዊ ድርጊቶችን፣ ከትዳር ጓደኛ ውጭ የሚፈጸሙ የኃይል ተግባራትን እና ከብዝበዛ ጋር የተያያዙ የኃይል ተግባራትን የሚያካትት በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጸም አካላዊ፣ ወሲባዊ እና ስነ-ልቦናዊ የኃይል ድርጎቶችን፤ተገዶ መደፈርን፣ የወሲብ ትንኮሳን፣ በስራ ቦታ በት/ት ተቋማት እና በሌሎች ቦታዎች የሚፈጸም የወሲብ ጥቃትን፣ እንዲሁም በሴቶች መነገድን እና ተገዶ ሴተኛ አዳሪ መሆንን የሚየካትት በጠቅላላው በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጸሙ አካላዊ፣ ወሲባዊ እና ስነ-ልቦናዊ የኃይል ድርጊቶችን ያጠቃልላል፡፡ 1.7 በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት (CEDAW) ከሴቶች መብቶች ጋር በተገናኘ በዋነኛነት የሚጠቀሰው ዓለም አቀፍ ስምምነት እ.ኤ.አ በ 1979 ዓ.ም ፀድቆ እ.ኤ.አ 1981 ዓ.ም ተፈጻሚ የሆነው ስምምነት ሲሆን ቀደም ሲል በተለያዩ መግለጫዎች እና ስምምነቶች ተበታትነው ይገኙ የነበሩ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን የያዘ በመሆኑ ከሌሎቹ የተሻለ የተሟላ እና የተጠቃለለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ስምምነቱን ማውጣት ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደረግ አድሎኣዊ ልዩነትን በማስወገድ ሴቶች በሁሉም መስክ ከወንዶች እኩል በሀገራቸው ፖለቲካዊ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ባሕላዊ ጉዳዮች ለመሳተፍና አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን እምቅ ችሎታ እንዲያጎለብቱ፣ እናትነት እና ሴትነት ያለውን ማህበራዊ አስተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማስገባት የሰውን ልጅ ዘር በማብዛት ረገድ ያላቸውን ሚና ለአድሎኣዊ ልዩነት መሰረት መሆን እንደሌለበትና ለሴቶች ልዩ ጥበቃ እና እንክብካቤ ማድረግ በማስፈለጉ ነው፡፡ ይህ ስምምነት 30 አንቀጾችን የያዘ ሲሆን በይዘቱም ሁሉ አቀፍ፣ በአፈጻጸም ወሰኑ ሰፊ (አጠቃላይነት ያለው) እና ህጋዊ አስገዳጅነት ባህርይ ያለው ሲሆን ሶስት አይነት ድንጋጌዎችን የያዘ ነው፡፡ እነዚህም፡ 1. አድሎኣዊ ልነቶችን የሚከለክሉ ድንጋጌዎች (Non-Discriminatory Provisions) 2. የማስተካከያ እርምጃዎችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች (Corrective Provisions) እና 3. ጥበቃ የሚያደርጉ ድንጋጌዎች (Protective Provisions) የሚሉት ናቸው፡፡ ይህ ስምምነት ከሌሎች አለም አቀፍ ስምምነቶች ልዩ የሚያደርገው በጾታ ላይ የተመሰረተን አድሎኣዊ ልዩነት፣ ገደብ ወይም ማግለልን ብቻ በትረጉሙ ውስጥ ማካተቱ ነው፡፡ ስለዚህ በሌሎች ምክንያቶች ለምሳሌ በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በፖለቲካ አመለካከት የሚደረግ አድሎኣዊ ልዩነት፣ ገደብ ወይም ማግለል በትርጉሙ ውስጥ አልተካተተም ማለት ነው፡፡ የስምምነቱ አንቀጽ 1 ጾታን መሰረት አድርጎ የሚፈጸም ማንኛዉንም አይነት አድሏዊ ልዩነት የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህም ማለት በማወቅም ይሁን ባለማዎቅ ሴቶችን መጉዳት፣ የሴቶች መብቶች እና ነጻነቶች በህግ እና በማህበረሰቡ ዘንድ እወቅና እንዳያገኙ መከልከል ወይም መብቶቻቸውን እንዳይጠቀሙ መከልከል ጾታን መሰረት ያደረገ እስከሆነ ድረስ በትርጉሙ ውስጥ የሚካተት ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን ማንኛውም ልዩነት አድሏዊ ነው ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ በዚህ ትርጉም መሰረት ልዩነቱ ብቻ ሳይሆን ያሰከተለውም ውጤት (ጉዳት) አብሮ መታየት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ ልዩነቱ በማናቸውም ሁኔታ የእኩልነት መብት ላይ ጉዳት ካመጣ አድሎኣዊ ልዩነት ነው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም አዋጁ መደበኛ የእኩልነት መብትን (formal equality right) ብቻ ሳይሆን ሳብሰታነቲቭ እኩልነትን (substantive equality right) ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ የስምምነቱ አንቀጽ 1 በሴቶች ላይ የሚደረግ አድሏዊ ልዩነትን እንደሚከተለው ተርጉሞታል፡ “ በሴቶች ላይ የሚደረግ አድሏዊ ልዩነት ማለት ጾታን መሰረት በማድረግ ሴቶች አገቡም አላገቡ፤ ከወንዶች ጋር በእኩልነት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና ባህላዊ፤ በሲቪልና ሌሎች መስኮች የሰብኣዊ መብቶች እና ነጻነቶች ሙሉ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የሚያደርግ ማንኛውም ልዩነት፣ ማግለል ወይም ገደብ ማለት ነው” ይሁን እንጅ ስምምነቱ ስርዓተ-ጾታን መሰረት ያደረገ አድሏዊ አሰራርን በተመለከተ በትረጉሙ ውስጥ አላከተተም፡፡ ስርዓተ-ጾታን መሰረት ያደረገ ልነት ዋናው ምክንያት ደግሞ የሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል ሆኖ አለመታየት (power inequalities between women and men) መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ጾታን መሰረት ያደረገ አድሏዊ ልዩነት ስምምነትን ለመከታተል የተቋቋመው ኮሚሲዮን (CEDAW Monitoring Committee) በሰጠው አስተያየት (እ.ኤ.አ 1992) ጾታን መሰረት ያደረገ ልዩነት ክልከላ ስርዓተ-ጾታን መሰረት ያደረገ ልነት መሰረት በማድረግ የሚፈጸም አድሏዊ አሰራርን ጭምር ባካተተ መንገድ መተርጎም እንዳለበት አስቀምጧል፡፡ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ (ምንም እንኳን አስገዳጅነት ባይኖረውም) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ (DEVAW) ጾታዊ ጥቃትን ሰፊ እና አካታች በሆነ መንገድ እንደሚከተለው ገልጾታል፡ “Any act of gender-based violence that results in, or is likely to result in, physical, sexual, or psychological harm or suffering to women, including threats of such acts, coercion or arbitrary deprivation of liberty, whether occurring in public or private life. ይህ አገላለጽ ጾታዊ ጥቃት ከጾታ ባሻገር የስርዓተ ጾታ ልዩነትን መሰረት ያደረጉ አድሏዊ አሰራሮችን ከማካተቱም በላይ ወጤታቸውን እና በህዝባዊም ሆነ በግልህይወት የሚያገጥሙ መሆናቸውን ጭምር ያስቀምጣል፡፡ 1.8 የሴቶች መብቶች በአፍሪካ የሰዎች እና የህዝቦች ቻርተር ይህ ቻርተር ሴቶች ለአፍሪካ የነጻነት እና የእኩልነት ጥያቄ የነበራቸውን ድርሻ እውቅና የሰጠ የመጀመሪው አፍሪካዊ ሰነድ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ቻርተሩ በአንቀጽ 18 ስር እንደነገገው ሴቶች ከወንዶች እኩል ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን ቻርተሩ የሴቶችን ሁለንተናዊ እኩልነትና የሚስተዋለውን አድሏዊ ልዩነት ለማሰወገድ መወሰድ ስላለባቸው ልዩ እርምጃዎች በዝርዝር ያላስቀመጠ በመሆኑ በቻርተሩ ላይ ለተፈረመው ፕሮቶኮል (በአፍሪካ ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል) መነሻ ሆኗል፡፡ 1.9 የአፍሪካ ሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (እ.ኤ.አ 2003 ዓ.ም) ይህ ፕሮቶኮል በሴቶች ላይ የሚደረጉ አድሏዊ ልዩነቶችን ለማስወገድ የወጣው አለም አቀፍ ስምምነት ከያዛቸው ድንጋጌዎች ጋር ተመሳሳይ ድንጋጌዎችን የያዘ ሲሆን የአፍሪካን ሴቶች ነባራዊ ሁኔታ ማለትም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚደርስባቸውን በደልና የስርዓተ-ጾታ ችግሮች ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ኣለም አቀፉን ህግ በአፍሪካ ልዩ መነጽር የተመለከተ ህግ ነው ብሎ ማስቐመጥ ይቻላል፡፡ የአፍሪካ ሴቶች መብት ፕሮቶኮል ከቻርተሩ አንጻር ሲታይ የቤት ውስጥ ጥቃትን (አንቀጽ 4(2)) ፣ ከአንድ በላይ ጋብቻን (Polygamous Marriage) ና ኤች. አይ.ቪ ኤድስን (አንቀጽ 6(ሐ)) ፣ በህክምና የሚደረግ ጽንስ ማሰወረድን (አንቀጽ 14(1(ሠ) ፣ አንቀጽ 14(2(ከ)) እንዲሁም የስርዓተ-ጾታ እና የስነ-ተዋልዶ ጉዳዮችን ያካተተ የመጀመሪያው አስገዳጅነት ያለው አፍሪካዊ ስምምነት ነው፡፡ በጦርነት አካባቢ ያሉና የተሰደዱ ሴቶችን ለመጠበቅየሚያስችሉ ዝርዝር ድንጋጌዎችንም አካቷል (አንቀጽ 11፣ 4(2(ተ)) ፡፡ ፕሮቶኮሉ በአንቀጽ 1(በ) ላይ በሴቶች ላይ የሚደረገውን አድሏዊ ልዩነት በሚመለከት ግልጽና ዝርዝር በሆነ ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ጉዳት፣ የሴቶች ጾተዊ ጥቃት በዝርዝር ተካተውበታል፡፡ እንደ ሴት ልጅ ግርዛት የመሳሰሉ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ራሳቸውን ችለው የተከለከሉ (Specifikaly Prohibited) መሆናቸው በአንቀጽ 5 ላይ ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪም ፕሮተኮሉ በመግቢየው ላይ አወንተዊ የአፍሪካ እሴቶች የሚባሉትን ለምሳሌ እኩልነት፣ ስላም፣ ሰብአዊ ክብር፣ ነጻነት፣ ወንድማማችነት፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ መሰረታዊ መርሆዎች እንደሆኑ አስቀምጧል፡፡ ከአለም አቀፉ ስምምነት እና ከአፍሪካ የሰብአዊና የህዝቦች መብት ቻርተር ይልቅ ስለ ማህበራዊናኢኮኖሚያዊ መብቶች በዝርዝር ደንገጓል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሴቶች የምግብ ደህንነት እና በቂ መጠለያ የማግኘት መብቶች ይገኙበታል (አንቀጥ 12-16)፡፡ በጋብቻ ውስጥ ወይም ከጋብቻ ውጭ (በቤተሰብ ደረጃ) በሴቶች ላይ ስለሚደርስ ጾታዊ ጥቃትም (ለምሳሌ በትዳር ጓደኛ መደፈር) በብሔረዊ ህጎች መደንገግ እና መከልከል እንዳለባቸውም ከአንቀጥ ድንጋጌዎችን አስቀምጧል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ሴቶች ፕሮቶኮል የትዳር አጋርን በማጣት፣ በእድሜ መግፋት፣ በድህነት እና በአካል ጉዳተኝነት ምክንያት ሴቶች የሚደርስባቸውን ጉዳት ለማስቀረት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችንም አካትቷል (አንቀጽ 20-24) ፡፡ አድሏዊ ልዩነቶችን ለማሰወገድ የሚወሰዱ እርምጃዎችንም ከአለም አቀፉ ስምምነት ይልቅ በዝርዝር እና በግልጽ (አስፈላጊ በሚሆኑበት ቦታ ሁሉ) በፕሮቶኮሉ ውስጥ ተመልክተዋል፡፡ አባል መንግስታትም የሴቶችን ተግባራዊ አኩልነት (Defacto Equality) ለማረጋገጥ ከወንዶች ይልቅ ልዩ እርምጃዎች (ለምሳሌ የኮታ ስርዓት) መውሰድ እንዳለባቸው በአንቀጽ 2 ፣ 9 እና 12 ላይ ተመልክተዋል፡፡ ይሁን እንጅ የአፍሪካ ሴቶች ፕሮቶኮልም ቢሆን የራሱ ውስንነቶች አሉበት፡፡ ለምሳሌ ያህል ከስነተዋልዶ እና ከኤች.አይ.ቪ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሴቶች ከጋብቻ ወይም ጓደኝነት በፊት ስለወንድ አጋራቸው (Partner) የማዎቅ፣ የገጠር ሴቶች መብቶች ልዩ ጾታዊ እና ስርዓተ-ጾታ እንዲሁም የድህነት ሁኔታ በዝርዝር መካተት ይኖርባቸዋል፡፡ ስለ አባል መንግስታት የልዩነት ሀሳብም አላስቀመጠም፡፡ ይህም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ያላቸው መንግስታት ስምምነቱን በሚጎዳ መንገድ እንዲለዩ ሊያደርግ ይችላል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በግልጽ ሊካተቱ የሚገባቸው ሲሆን አጠቃላይ አፈጻጸሙ ግን ከሌሎች አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ህግጋት አንጻር መታየት ይኖርበታል፡፡ 1.10 ሌሎች አለማቀፋዊ፣ አህጉራዊ ስምምነቶች • የአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች ቻርተር፣ • አለማቀፍ የህጻናት መብት ስምምነት • በአፍሪካ የሰዎች እና ህዝቦች ቻርተር የሴቶች መብት ፕሮቶኮል፣ • የአፍሪካ ህጻናት መብት እና ደህንነት ቻርተር፣ • ዓለማቀፍ የሰራተኞች ድርጅት ስምምነት (ILO Convention) • ስለፈቃድ ጋብቻ፣ ዝቅተኛ የጋብቻ እድሜ እና ስለ ጋብቻ ዝምድና የተደረገ ኣለም አቀፍ ስምምነት፣ • የቤጅንግ ፕላትፎርም ፎር አክሽን ይገኙበታል፡፡ 2. የሴቶችን ሰብአዊ መብት በማስከበር የአባል መንግስታት ግዴታዎች እና በኢትዩጵያ የተወሰዱ የህግና የፖሊሲ እርምጃዎች 2.1 የአባል መንግስታት ግዴታዎች በማንኛውም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነት መሰረታዊ የመንግስታት ግዴታዎች ሶስት ናቸው፡፡ እነዚህም፡ 1. ሰብአዊ መብቶችን ማክበር 2. ሰብአዊ መብቶችን መጠበቅ ወይም ሌሎች እንዲያከብሩ ማድረግ 3. ሰብአዊ መብቶችን ማሟላት ናቸው፡፡ ሴቶችን በተመለከተ ካሉ የሰብአዊ መብት ሰነዶች ትልቁን ድርሻ የሚይዘው በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ልዩነት ለማስወገድ የተደረገው ስምምነት (CEDAW) በአባል ሃገራት ላይ የሴቶችን ሰብአዊ መብት ለማስከበረው የተለያ ግዴታዎችን ይጥላል፡፡ በስምምነቱ አንቀጽ 2 ላይ የስምምነቱ አባል መንግስታት መውሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች የተደነገገ ሲሆን ከነዚህም መካከል፡ 1. የሴቶችን እኩልነት በሚመለከት ፖሊሲዎችን ማውጣት፣ በብሄራዊ ህጎቻቸው ውስጥ ማካተት እና ነባር ህጎችን ማሻሻል፤ 2. ከህግና ከፖሊሲ እርምጃ ባለፈ ተግባራዊ አፈጻጸሙን መከታተል እና ድጋፍ ማድረግ፤ 3. ብቃት ያላቸውን የፍትህ አካላት በማቋቋም የህጎችን ተፈጻሚነት ማረጋገጥ፤ 4. ጾታዊ ጥቃትን በህዝባዊ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ሰው፣ ድርጅት ወይም የንግድ ስራ ተቋም እና በሴቶች የግል ሕይወት ጭምር ማስወገድ፤ 5. ልዩነት የሚያደርጉ ልማዶችን፣ ባህሎችን እና አመለካከቶችን (discriminatory customs and practices) ማስወገድ፤ ከነዚህ እርምጀዎች በተጨማሪ መንግስታት ልዩ ጊዜያዊ የድጋፍ እርምጃዎችን (Temporary special measures) መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነዚህ ልዩ የድጋፍ እርምጃዎች በጊዜያዊነት የሴቶችን አንጻራ ተጠቃሚነት፣ በሂደት (በረጅም ጊዜ) ደግሞ የሴቶችን ሁለንተናዊ እና ነባራዊ እኩልነት (substantive equality) ለማረጋገጥ የሚወሰዱ እርምጃዎች ናቸው፡፡ ልዩ የድጋፍ እርምጃዎችን በተመለከተ ማንኛውንም አድሏዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገው ስምምነት አንቀጽ 4 (1) እንደሚከተለው ይደነግጋል፡ “Adoption by states parties of temporary special measures aimed at accelerating de facto equality between men and women shall not be considered discrimination as defined in the present convention, but shall in no way entail, as a consequence, the maintenance of unequal or separate standards; these measures shall be discontinued when the objective of equality of opportunity and treatment have been achieved”. ከድንጋጌው መረዳት እንደሚቻለው ጊዜያዊና ልዩ የድጋፍ እርምጃዎች የሚወሰዱት በተግባር የሚታየውን አድሏዊ ልዩነት (defacto discrimination) ለማሰወገድ የሚደረገውን ጥረት ለማፋጠን እንጅ በወንዶች እና በሴቶች መካከል የተለያየ ደረጃ ለመፍጠር አለመሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ግዜያዊ ልዩ የድጋፍ እርምጃ የሚወሰደው በተጨባጭ ካለው አድሏዊ ልዩነት መነሻ በማድረግ ሊሆን ይገባል፡፡ የሚሰጠው ድጋፍ ጊዜያዊ እና ግቡ (substantive equality) እስኪሳካ ድረስ እንጅ ዘላቂ አይሆንም፡፡ ብዙ ጊዜ ልዩ እርምጃዎች አድሏዊ መስተንግዶን አንደማበረታታት (preferencial treatment) ሲወሰዱ እንመለከታለን፡፡ ነገር ግን የነዚህ ጊዜያዊ ልዩ የመፍትሔ እርምጃዎች ዓላማ እኩል የመጫወቻ ሜዳን በመፍጠር በአድሏዊ አሰራር እና ተገቢነት (preference and priviledge) ምክንያት ተዘብቶ የኖረውን የወንድ እና የሴት ግንኙነት ማስተካከል እና መዋቀራዊ እና ማህበራዊ ወይም ነባራዊ አድሏዊ ልዩነቶችን ማሰወገድ ነው፡፡ ይህንን የረዥም ጊዜ ግብ ለማሳካትም አስቻይ ሁኔታዎችን ተግባራዊ ማድረግ ተገቢነት ይኖረዋል፡፡ አስቻይ ሁኔታዎች የሚባሉትም የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልን፣ መዋቅራዊ የፖሊሲ እርምጃዎች እና ልዩነቱን ለማስቆም ወይም ለማስወገድ የሚወሰዱ ውጤታማ ተቋማዊ የመፍትሔ እርምጃዎች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ የስምምነቱ ፈራሚ ሀገራት (ኢትዮጵያን ጨምሮ) በተለያዩ መንገዶች የሚፈጸመውን አድሏዊ ልዩነት ለማሰወገድ ልዩ የድጋፍ እርምጃዎችን መወሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በስምምነቱ አንቀጽ 10 ላይ እንደተመለከተው መንግስታት በትምህርት ዘርፍ የሴቶችን እኩል ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተገቢ እርምጃዎችን ሁሉ (all appropriate measures) መውሰድ እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡ ጊዜያዊ እና ልዩ የድጋፍ እርምጃዎች ለምን ያስፈልጋሉ? ሀ. ልዩ ድጋፍ እንደ ፍትሐዊ የካሳ አፈጻጸም፡- የሴቶችን ያለፈ ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት የሴቶችን መጻዒ እድል መወሰንን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ ለ. ስርጭተዊ ፍትህ እና የሴቶች እኩል ተጠቃሚነት ግድ ስለሚል፡- ይህም ማለት ነባራዊ የተዛቡ ግንኙቶችን በማስተካከል በማንኛዉም የህይዎት ዘርፍ የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነት ማረጋገጥን መሰረት ያደረገ ወደፊት ተመል ካች አቀራረብ ነው፡፡ለምሳሌ ያህል በፖለቲካ ዉክልና ወይም በውሳኔ አሰጣጥ የሴቶችን የተሳተትፎ መጠን 30 ፐርሰንት ማድረስ የዚህ አንዱ መገለጫ ነው፡፡ ሐ. ልዩ ድጋፍ ለጠቅላላው ማኅበራዊ ተጠቃሚነት (social utility) ፡- የሴቶችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም በማሳደግና ማህበራዊ ለውጥን እና የልዩነትን የጋራ መስተጋብር በማበረታታት ብሎም በማፋጠን የጠቅላላውን ኅብረተሰብ ተጠቃሚት ማስጠበቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሴቶች ገቢ ሲጨምር የህጻናት ተጠቃሚነት ይጨምራል፡፡ መ. ሰብአዊ መብቶችን ተደራሽ ለማድረግ፡- የሴቶች የልዩ ድጋፍ ተጠቃሚ መሆን ሰብኣዊ መብቶቻቸውን እንዲጠይቁ እና እንዲያስከብሩ ይረዳቸዋል፡፡ ሰብአዊ መብቶችም በባህሪያቸው ተደጋጋፊ በመሆናቸው የአንዱ መብት መከበር ሌላውን ለማስከበር ይረዳል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሴቶች የኢኮኖሚ መብቶች መከበር የሲቪል እና የፖለቲካ እንዲሁም የስነ-ተዋልዶ መብቶቻቸውን በቀላሉ ለማስከበር ይጠቅማቸዋል፡፡ 2.2 በኢትዮጵያ የተወሰዱ የህግና የፖሊሲ እርምጃዎች የኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ከማቋቋም ጀምሮ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት መገለጫ(UDHR) ላይ በቀዳሚነት ከተሳተፉና ከፈረሙ ሃገራት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ስምምነት፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ መብቶች ስምምነት፣ በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ልዩነት ለማስወገድ የተደረገው ስምምነትን የፈረመች ሲሆን እ.ኤ.አ ሀምሌ 1980 ዓ.ም አለም አቀፉን በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሏዊ ልዩነት ለማስወገድ የወጣውን ስምምነት ከፈረመበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ከነዚህም ተግባራት አንዱ የሴቶች መብት በህገ መንግስቱና ሌሎች ዝርዝር ህጎች ውስጥ እንዲሁም በፖሊሲና ስትራቴጂ ሰነዶች ውስጥ ተካተው ይገኛሉ፡፤ ከነዚህም የህግና የፖሊሲ ማእቀፎች ውስጥ የሚከተሉት ዋንኞቹ ናቸው፡፡ • ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገመንግስት፣ • የመንግስት ሰራተኖች አዋጅ፣ • የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ (አ.ቁ 377/96) • የወንጀል ህግ • የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ • የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ፖሊሲ ይገኙበታል፡፡ 2.2.1 የሴቶች የመማር መብት በህገ መንግስቱ እና በሌሎች ፖሊሲ ማእቀፎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ከተወሰደ እርምጃዎች አንዱና ዋነኛው በትምህርት ዘርፍ የትወሰደው ልዩ የማበረታቻ እርምጃ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በዘርፉ ስር የሰደደና ጾታን መሰረት ያደረገ (deep gender based discrimination on education)፣ ስርዓታዊ (systematic) ና ከባህል ጋር የጠቆራኘ አድሏዊ ልዩነት ሰፍኖ በመቆየቱ ነው፡፡ ይህንን ክፍተት ለመሙላትና የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ መንግስት የሴቶችን ወደትምህርት ቤት መግባት እና ት/ት የማጠናቀቅ ምጣኔ በማሳደግ ላይ በማተኮር በሁሉም የት/ት ደረጃዎች ተሳተፏቸው እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ በከፍተኛ የት/ት ተቋማት የሴቶችን ድርሻ ከ30-50 በመቶ በማሳደግ እና ነጻ የት/ት እንዲያገኙ በማድረግ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ ነገር ግን የትምሕርት ጥራትን ከማሳደግ አኳያ ብዙ መሰራት እንዳለበት አመላካች ጥናቶች አሉ፡፡ በሌላ በኩል የት/ት ተደራሽነትን ከማሳደግ አንጻር በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን (መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ) በማስፋፋት እና የመገናኛ ብዙሃንን ብሎም ዘመናዊ ስነ-ኪንን (technology) በማሳደግ ሴቶች የሚደርስባቸውን መገለል፣ አድሎ እና ገደብ ለመቀነስ ጥረት ተደርጓል፡፡ ከልዩ የድጋፍ እርምጃዎች በተጓዳኝ በትምህርት ዘርፍ አድሏዊ ልዩነትን ለማሰወገድ የፖሊሲ እርምጃዎችም ተወስደዋል፡፡ ከነዚህም መካከል፡ የሴቶች ት/ት ልማት ፖሊሲ እና የማስፈጸሚያ ስልት፣ የስርዓተ-ጾታ ጉዳይን በት/ት ስርዓት ቀረጻ እና በልማት እነዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች የማካተት ስራ (gender mainstreaming)፣ የስርዓተ-ጾታ ስልጠናና ጥናቶችን ማካሔድ የትምህርት መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት የግብርና መር የልማት ፖሊሲ የስነ-ህዝብ ፖሊሲ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ የጤና ፖሊሲ የልማት እና የማህበራዊ ደህንነት ፖሊሲ የባህል ፖሊሲ የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲ የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ይህም ሃገሪቷ በ CEDAW ስምምነት አንቀጽ 10 ላይ የተጣለባትን ግዴታ እንድትወጣ ያስችላታል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህን የፖሊሲ እና የህግ ማዕቀፎች ለመከታተል እና ለመቆጣጠር በክልልና በፌደራል ደረጃ የተቋቋሙ አካላት (WAO, WADs) የተቀናጁ ካለመሆናቸውም በላይ የአቅም ውስንነት (በግብአትና በሰው ኃልአቅርበት) ይታይባቸዋል፡፡ 2.2.2 የሴቶች ቅጥር እና የክፍያ ሁኔታ በሴቶች ላይ የሚደረጉ አድሏዊ ልዩነቶችና ጾታዊ ጥቃቶች ዘርፈ ብዙና ውስብስብ ሲሆኑ (ያለ እድሜ ጋብቻ፣ የሴት ልጅ ግርዛት፣ አስገድዶ መድፈር፣ የቤት ውሰጥ ጥቃት፣ ጠለፋ፣ በሴቶች መነገድ፣ ህገወጥ ዝውውር፣ ንብረት መቀማት ወዘተ …) በሴቶች ቅጥር እና የደመወዝ አከፋፈል እንዲሁም በስራ ቦታ አካባቢ የሚደረግ ጾተዊ ጽቃት (ትንኮሳ) ና አድሏዊ ልዩነት አንዱ ነው፡፡ ጾታን መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ሊፈጸም ይችላል፡፡ ለምሳሌ በስራ ማስታዎቂያዎች ወይም ውድድሮች ላይ ጾታን በመወሰን የሚደረገው ገደብ በቀጥተኛ መንገድ የሚፈጸም ሲሆን ከውድድር (ፈተና) በኋላ በምልመላ ሂደት፣ ከወሊድ፣ እርግዝና እና ህክምና ጋር በተያያዘ ሴቶችን ለማግለል የሚፈጠሩ መስፈርቶች ደግሞ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ እነዚህ የማግለል እና የመገደብ እርምጃዎች በአብዛኛው በግል ድርጅቶች (ኢንዱስተሪዎች) የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው፡፡ ነገር ግን አድሏዊ የስራ ቅጥርን ማስወገድ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሴቶች ከወንዶች እኩል ተወደዳሪ እንዲሆኑ በትምህርት እና በስልጠና ማብቃት ተገቢ ነው፡፡ ሌላው በስራ ቅጥር እና የስራ ሁኔታ ከሚፈጸሙ የማግለል፣ የአድሎ እና መገደብ ችግሮች በተጨማሪ በስራ ቦታ የሚፈጸም ጾታዊ ትንኮሳ ሌላው የችግሩ ገጽታ ነው፡፡ ይህም በቃል፣ በአካለዊ እንቅስቃሴና በተግባር ወይም በሁሉም አይነት መንገዶች ሊፈጸም ይችላል፡፡ ይህም እንደማግባባት፣ ማነሳሳት፣ ማታለል እና ማስገደድ ወይም አካላዊ ጉዳት ማድረስ ወይም ዛቻ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት ምቹ ያልሆነ የስራ አካባቢ ይፈጠራል ወይም በሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሰረተና እኩል ያልሆነ ጾታዊ ግነኙነት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህንን ችግር በተመለከተ በሴቶች ላይ የሚደረገውን ማንኛውንም ልዩነት ለማሰወገድ የተደረገውን ስምምነት ለመከታተል የተቋቋመው ኮሚቴ በ1989 እና 1992 እ.ኤ.አ በሰጠው አስተያየት አባል መንግስታት ይህንን ተግባር ለማስወገድ ህግ ማውጣት እንዳለባቸው ቢያስቀምጥም በየሀገራቱ (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ካለው ስር የሰደደ የባህል እና ልማዳዊ አስተሳሰብ የተነሳ ተግባራዊ ካለመሆኑም የተነሳ አስተያየቱም በመደበኛው የስራ ቅጥር እና የስራ ቦታ የሚፈጸመውን ትንኮሳ ብቻ የሚመለከት በመሆኑ በቤት ውስጥ እና ከሀገራቸው ውጭ የሚኖሩትን እና ህጋዊ ያልሆኑትን የማያጠቃልል በመሆኑ አስተያየቱ ህጋዊ አስገዳጅነት የሌለው ከመሆኑ በተጨማሪ ችግሩ ሳይፈታ ቆይቷል፡፡ ይህ ችግር ውስን የስራ እድል ባለባቸው እና የመደራደር አቅም በሌላቸው ሴቶች ላይ በስፋት የሚሰተዋል ችግር ነው፡፡በተጨማሪም እንደ ሳውዲ አረቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በሚኖሩበት አካባቢ ስምምነቱን በሙሉ ያልተቀበሉ (Reserving States Parties) ስምምነቱ አስገዳጅ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን መብት ለማሰከበር የሁለትዮሽ ስምምነት ማድረግ ወይም የዲፕሎማሲ ስራውን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ የ1951ዱ የሴቶችን የስራ ክፍያ እኩልነት ለመደንገግ የወጣው አለም አቀፍ ስምምነት (አንቀጽ 1 እና 2) ለተመሳሳይ ስራ ተመሳሳይ ክፍያ መከፈል እንዳለበት ያስገድዳል፡፡ የአፍሪካ የሰዎች እና ህዝቦች ቻርተር እና ይህንን ተከትሎ የወጣው ፕሮቶኮልም (በተከታታይ አንቀጽ 15 እና አንቀጽ 13) ተመሳሳይ ድንጋጌዎች አሏቸው፡፡ ይሁን እንጅ ሀገራችን ኢትዮጵያ ይህንን ስምምነት አላጸደቀችም፡፡ ነገር ግን በህገመንነግሰቱ አንቀጽ 35 እና 41 ላይ እንደተደነገገው የሴቶች ሁለንተናዊ እኩልነት በህግ የተረጋገጠ በመሆኑ ብዙ ችግር የሚፈጥር አይሆንም፡፡ በአጠቃላይ የሴቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉት የሴቶች የስራ መብቶች የሚከተሉትን ያጠቃለሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ • የሥራ እድል የማግኘት መብት፣ • ከጾታቸው እና ከተፈጥሯቸው አንጻር ምቹ የስራ አካባቢ እና ሁኔታ፣ • የስራ ነጻነት እና ዋስትና የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህ መብቶች በህገ መንግስቱ አንቀጽ 35(8) እንዲሁም በኢትዮጵያ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ (አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 87) ላይ በግልጽ ተደንግጓል ፡፡ ይህም በ CEDAW ስምምነት አንቀጽ 11 የሴቶችን ቅጥርና የስራ ሁኔታ አስመልክቶ ኢትዩጲያ የተጣለባትን ግዴታ እንድትወጣ ያስችላታል፡፡ 2.2.3 የሴቶች የጤና እና የስነ-ተዋልዶ መብት ሌላው እውቅና የተሰጠው ጉዳይ ደግሞ የሴቶች የስነ ተዋልዶ ጤና ጉዳይ ነው፡፡ ይህ መብት ሴቶች በሰብኣዊነታቸው ብቻ ሳይሆን በሴትነታቸውም ጭምር የተጎናጸፉትን እንደ እንክብካቤ የማግኘት፣ የወሊድ ፈቃድ እና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ባለው ምክንያት ከሚፈጠሩ ውስብስብ የጤና ችግሮች የመጠበቅ መብቶችን ያጠቃልላል፡፡ በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 35(5) እና (9) የሴቶች የጤና እና ስነ ተዋልዶ መብት በግልጽ የተደነገገ ሲሆን ይህን ተከትሎም የጤና ፖሊሲ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ ላይ በጤና ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለመጠበቅ፣ በወሊድ ግዜ የሚከሰት የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ሰፊ ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በቤት ውስጥ እንዲሁም በማህበረሰብ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እንዲሁም የኢኮኖሚ ምርታማነታቸውን ለመጨመር የስነ ተዋልዶ ትምህርት እየተሰጣቸው በፍቃዳቸው የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይህም ኢትዪጲያ በ CEDAW ስምምነት አንቀጽ 13 ስር የሚጠበቅባትን የሴቶችን ከወንዶች እኩል የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት መብት ለመተግበር ያስችላታል፡፡ 2.2.4 የሴቶች የጋብቻና እና በትዳር የመኖር መብት የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት መግለጫ ሰነድ ጋብቻ በተጋቢዎች ነጻ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ በተመሳሳይም በ CEDAW ስምምነት አንቀጽ 16 ስር በጋብቻና ቤተሰባዊ ሁኔታን በተመለከተ ሴቶች ያለ አድሎ ከወንዶች እኩል የጋብቻና ትዳር ህይወታቸው ላይ የመወሰን መብት እንዳላቸው ተደንግጓል፡፤ ከይህም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 35 እንዲሁም በ1992ዓ.ም በተሸሻለው የቤተሰብ ህግ ላይ በግልጽ ተንጸባርቋል፡፡ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ላይ ጋብቻ መመስረቻ እድሜ ለሴትም ሆነ ለወንድ 18 አማት እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ ይህም የሴቶችን ያለ እነድሜ ጋብቻ ለማስቀረት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ላይ ጋብቻ ሁለቱም ጾታዎች በነጻና ሙሉ ፍቃድ የሚፈጽሙት ጥምረት መሆኑን፣ የሚኖሩበትን ስፍራ በጋራ እንደሚወስኑ እንዲሁም የጋራ ሃብታቸውን በጋራ እንደሚያስተዳድሩ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ይህ የሴቶች የጋብቻ መብትን በተመለከተ ኢትዩጲያ የፈረመቻቸውን ሆነ ያልፈረመቻቸው አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶችን ለመተግበር የያስችላታል፡፡ 3. የአለም አቀፍ እና ብሔራዊ ህግጋት ተግባራዊ አፈጻጸም፣ ችግሮች እና የመፍትሔ ሀሳቦች ሴቶችን የሚመለከቱ አለም አቀፍና ብሔራዊ ህጎችን በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የሕግ፣ የፖሊሲ እና ተግባራዊ እርምጃዎችን (Reactive Measures) የመውሰድ አለም አቀፍ ግዴታ አለበት፡፡ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ እንደሚያሳየው ህጉን በማስፈጸም ረገድ ከሚስተዋሉት ችግሮች በተጨማሪ የህግ ክፍተቶች ይስተዋላሉ፡፡ 1. የህግ ክፍተቶች (Legal Gaps)፡- ሐገራችን ኢትዮጵያ አለምአቀፍ ስምምነቶችን ተቀብላ ያጸደቀች ቢሆንም እነዚህ ህግጋት በተግባር ያላቸው ተጽእኖ (Concrete Application) ግን ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደረገውን ማንኛውንም ልዩነት ለማስወገድ የተደረገውን ስምምነት ጨምሮ ወደ ብሔራዊ ህግነት ስላልተቀየሩ (Transformation) እና እነዚህ አለም አቀፍ ስምምነቶች እና መግለጫዎች ወደ ሀገራዊ ህግነት ሳይቀየሩ በራሳቸው የማይፈጸሙ በመሆናቸው (Non self-executing) በመሆናቸው ነው፡፡ የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣን ለማውጣት የወጣው አዋጅ ቁጥር 3/1995 አንቀጽ 2(3) እንደሚደነግገው በነጋሪት ጋዜጣ ያልወጣ ማንኛውም ህግ እንደ ህግ ተቆጥሮ የሚተገበር አይሆንም፡፡ በሌላ በኩል እነዚህ አለም አቀፍ ስምምነቶች በተወካዮች ምክርቤት የሚጸድቁ በመሆናቸው በሀገር ውስጥ ያላቸው ቦታ ከህገመንግስቱ በታች እና ከአዋጆች ጋር እኩል ቦታ የሚኖራቸው በመሆኑ ተቃርኖ ወይም አለመጣጣም በተፈጠረ ጊዜ ሕገ መንግስቱ የበላይ ህግ በመሆኑ (አንቀጽ 9(1)) ምንም እንኳን ከህገመንግስቱ የተሻሉ ዝርዝርና ልዩ ህጎች ቢሆኑም ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡ በሌላ በኩል ግን እነዚህ አለም አቀፍ ስምምኖች ተጣጥመው መተርጎም ያለባቸው ስለመሆኑ እና እንደመተርጎሚያ መሳሪያ ማገልገል እንዳለባቸው እንዲሁም የፍትህ አካላት እነዚህን አለማቀፍ ስምምነቶች የማስፈጸም ህገመንግስታዊ ግዴታ ስላለባቸው እነዚህ አለም አቀፍ ህግጋት የቀዳሚነት ስፍራ ይኖራቸዋል የሚል ክርክር አለ፡፡ ይህ ክፍተት ኢትዩጲያ የፈረመቻቸውን አለም አቀፍ ሰነዶች በብሄራዊ ህጎች ውስጥ ያላቸውን ደረጃ እና ተፈጻሚነትነት ላይ ውስንነት ሚፈጥር በመሆኑ ሊታይ የሚገባው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ ህግጋት ካለመታተማቸውም ባሻገር ወደየስራ ቋንቋዎች ያልተተረጎሙ በመሆናቸው ሕብረተሰቡም ሆነ ህግ አስፈጻሚ አካላት በቀላሉ የሚያገኟቸው አይደሉም፡፡ በዚህ ረገድ ያለው መረጃ እና የግንዛቤ ደረጃ አነስተኛ በመሆኑ ችግሩን የጎላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ምክንያት ፍርድ ቤቶችም ሆኑ ሌሎች የፍትህ አካላት እነዚህን አለም አቀፍ ህግጋት ለውሳኔያቸው መነሻ ሲያደርጓቸው አይስተዋልም፡፡ ብሔራዊ ህግጋትን በሚመለከት ደግሞ በሀገራቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የሴቶች ህግ (Women’s Act) በላይ ያሉት ህግጋትም በቂ የሚባሉ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ አሁን ያለው የወንጀል ህግ ጾታዊ ጥቃትን በጠቅላላው የሚመለከት እንጅ ዝርዝር እና ፈርጀብዙ (ውስብስብ) የጾታዊ ጥቃት አይነቶችን (በትዳር ጓደኛ፣ ማሳደድን፣ የቤተሰብ ጾታዊ ጥቃት፣ አኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ስነልቦናዊና ስሜታዊ ጥቃት እና ትንኮሳን) በዝርዝር የሚደነግግ አይደለም፡፡ ይህም የህጉን የተፈጻሚነት ወሰን ያጠበዋል፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 564 የተደነገገው በትዳር ጓደኛ የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃትን የሚመለከት ሲሆን ከዚህ የዝምድና ደረጃ በዘለለ በሌሎች የቤተሰብ አባላት የሚፈጸመው ዘርፈ-ብዙ ጥቃት (family violence) ግን አከራካሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም ይኸው ድንጋጌ የሚያስከትለው ቅጣት በሌሎች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚደርሱትን ጥቃቶች በሚመለከት በተቀመጡት ድንጋጌዎች (አንቀጽ 555-560) መሰረት የሚወሰን በመሆኑ ቅጣቱ አነስተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም ድንጋጌው አካላዊ እና አዕምሯዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ከማለት ባለፈ ሌሎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሞራላዊ ጉዳት የሚያስከትሉትን ጥቃቶች ያላካተተ ይመስላል፡፡ እነዚህ አከራካሪና ለሰፊ የትርጉም ሽፋን የተጋለጡ ቢሆንም ተገቢውን ትንታኔ ተሰጥቷቸው አልተቀመጡም፡፡ በተጨማሪም የእነዚህ ነገሮች መነሻ፣ አጋላጭ ምክንያቶችና የችግሩ ስፋትን በሚመለከት የተደረጉ ሰፊ ጥናቶች የሉም፡፡ 2. የአፈጻጸም እና የአተረጓጎም ችግሮች፡- በፍትህ አካላት የሴቶችን መብቶች በማስከበር እና በመጠበቅ አንጻር የአቅም ውስንነት ችግሮች ማለትም በሴቶች አለም አቀፍ እንዲሁም ብሄራዊ ህግ ላይ የተሟላ ግንዛቤ ያለመኖር ፣ መብቶችን ለማስፈጸም የቁርጠኝነት ማነስ እንዲሁም በህበረተሰቤ የተዛባ አቸመለካከት የመወሰድ ችግሮች ይስተዋልባቸዋል፡፡ የህግ ባለሞያዎች ማለትም አቃቢያነ ህግ፣ ዳኞች እንዲሁም ጠበቆች ሴቶች በአለም አቀፍ እንዲሁም አህጉር አቀፍ ሰነዶች ላይ የተቀመጠላቸውን እና ኢትዩጲያ ያጸደቀቻቸውን የሰብአዊ መብት ሰነዶች ለይተው የማወቅ እንዲሁም መብቶቹን ጠቅሰው ሲከራከሩ ማየት አልተለመደም፡፡ በተመሳሳይ ዳኞች በፍርድ ውሳኔዎች ላይ የሴቶችን መብት ለማስከበር የወጡ አለም አቀፍ ስምምነቶች ከብሄራዊ ህጎች ጋር ተዋህደው እንዲሄዱ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ ሰፊ የህግ ትርጉም ሲያደርጉ አይስተዋልም፡፡ የአለም አቀፍ ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ ከሚጠቅሙ መንገዶች አንዱ ብሄራዊ ህጎች ከአለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር ተጣጥመው በሚሄዱበት መልኩ የህግ ትርጓሜ መስጠት አንዱ እንደመሆኑ ዳኞች የህግ አተረጓጎም ከአለም አቀፍ ስምምነቶች አንጻር መሆን ይኖርበታል፡፡ በሌላ በኩል የሴቶችና መብት ለማስከበርና ለመጠበቅ በአዋጅ ስልጣን የተሰጣቸው አካላት የሴቶች መብት የሰብአዊ መብት መሆኑን በማሳወቅ ሴቶችን የተመለከቱ መብቶችን በስፋት የማስተዋወቅ ተግባር ላይ ሰፊ እጥረቶች ይታያሉ፡፡ የሴቶችን መብት በማስከበርና በማስጠበቅ በኩል በሁሉም የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ባህላዊ መብቶች ዙሪያ ሁሉን አቀፍ መብቶችን የማስተዋወቅ ተግባራት የሚጠበቁ ቢሆንም በተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሴቶች መብት በአመታዊ ክብረ በአላት ላይ የአንድ ወቅት ጉዳይ አድርጎ ከማክበር ባለፈ የሴቶች መብትን በጥልቀት ተፈጻሚ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት አነስተኛ ናቸው፡፡በተመሳሳይም ምንም እንኴን ሴቶችን የተመለከቱ አለም አቀፍ ስምምነቶች የተለያዩ ቢሆኑም የሴቶች መብት ሲነሳ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን ብቻ መሰረት ያደረገ ብቻ የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ባለሙያዎች በህብረተሰቡ የሚታየው ጥልቅ ልማድ እና ጎጅ ባህል ሰለባ በመሆናቸው የአስተሳሰብ ችግሮች አሉባቸው፡፡የፍትህ አካላት የጾታዊ ጥቃት ጉዳዮችን በሚያስተናግዱበት ጊዜ የጉዳዮችን የሁኔታ ግምገማ (Situational Analysis) መሰረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምክንያቱም ጉዳዩ ከተጎጅዋ እድሜ፣ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ሁኔታ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሊያያዝ ስለሚችል ነው፡፡ ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች አስተማሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለጉዳዩ አግባብነት ያለውን አለም አቀፍ ወይም ብሔራዊ የህግ ድንጋጌ ከመጠቀም ጀምሮ ተጨማሪ እርምጃዎችን መውሰድ ውሳኔው አስተማሪ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን ጉዳዮች እንመልከት፡፡ በኦሮሚያ ክልል በአንዲት የ 13 ዓመት ታዳጊ ላይ በተፈጸመ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጉዳይ ደፈረ የተባለው ተከሳሽ እና ግብረ-አበሮቹ በዋስትና በመለቀቃቸው ተበዳይዋን ህጻን ለሁለተኛ ጊዜ ጠልፈው የደፈሯት ከመሆኑም በላይ ህጻኗ ጋብቻን አልቀበልም በማለቷ በቤተሰቦቿ ተደብድባለች፡፡ ጉዳዩ የቀረበለት የክልሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ይህንን ሁሉ የፈጸሙትን ዋና ወንጀል አድራጊና ግብረ አበሮቹን ከ8-10 ዓመት በሚደርስ የእስራት ቅጣት ብቻ ቀጥቶ ውሳኔ ቢሰጥም ጉዳዩ በይግባኝ ታይቶ ተበዳይ ለጋብቻውም ሆነ ለጾታዊ ግንኙነቱ ፈቃደኛ ነበረች በሚል ምክንያት በነጻ እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡ ለመሆኑ የ13 ዓመት ሕጻን ልጅ እንዴት ለዚህ ተግባር ፈቃደኛ ልትሆን ትችላለች? በዚህ ምክንያት ተጎጅዋ ህጻን ተከሳሾቹ ከእስር ቤት ወጥተው ጉዳት እንዳያደርሱባት ስትማጸን እንደነበር ጉዳዮን ሲከታተሉ የነበሩ ሁሉ የታዘቡት ጉዳይ ነው፡፡ በየደረጃው ያሉት ፍርድ ቤቶች አስተማሪ እርምጃ ካለመውሰዳቸውም በላይ ተበዳይ ምንም አይነት ካሳ አልተከፈላትም፡፡ በተከሳሾቹ ላይም ተጨማሪ የጥንቃቄ እርምጃ አልተወሰደም፡፡ ጉዳዩ የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም እ.ኤ.አ 2005 የተፈጸመ የሕግ ስህተት የለም በማለት አቤቱታውን ውድቅ በማድረጉ ከዚህ ጌዜ በኋላ ሌሌች የጠለፋ እና የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮች ተባብሰው ቀጥለው እንደነበር ከተለያዩ መዛግብት መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ጉዳይ በሴት የህግ ባለሙያ ሴቶች አማካኝነት አለም አቀፍ ተኩረት እንዲያገኝ በመደረጉ ስለታወቀ እንጅ እያንዳንዱን የፍርድ ቤት ጉዳዮች መፈተሽ ቢቻል ከዚህ የባሱ ችግሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ መረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ኢትዩጲያ በ CEDAW ስምምነት መሰረት ካላባት ግዴታዎች አንዱ የሴቶች መብትን በተመለከተ የተከናወኑ ተግባራትን ወቅታዊ ሪፖርት ማቅረብ ነው፡፡ ይህም ቢያንስ በየአራት አመቱ የሴቶችን መብት አፈጻጸም የተመለከተ ሃገራዊ ሪፖርት እንድታቀርብ የሚጠበቅ ቢሆንም ኢትዩጲያ የመጀመሪያውን፣ 2ኛ አንዲሁም 3ኛ ሪፖርት በጥምረት የላከቸው እ.ኤ.አ በ1993 ሲሆን ከዚያ ወዲህ የላከቸው ሪፖርት የለም፡፡ ይህም ችግር አለም አቀፍ ግዴታን እንዳለመፈጸም የሚታይ ብቻ ሳይሆን በሴቶች መብት ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትን የተጠቃለለ መረጃ እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ሴቶችን አስመልክቶ የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫን ለመለየት እንቅፋት ይፈጥራል፡፡ በአጠቃላይ ሃገራችን ኢትዩጲያ አብዛኛውን የሴቶች መብትን የተመለከቱ እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸው የሰብአዊ መብት ሰነዶች ፈረመች ሲሆን ለተግባራዊነታቸውም በዝርዘር ህጎች፣ ፖሊሲ እና ሰተራቴጅክ ሰነዶች ላይ አካታቸወዋለች፡፡ ይህም ሀገሪቷ ለተጣለባት አለም አቀፍ ግዴታዎች ማስፈጸም ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል ፡፡ ይሁንና አብዛኞቹ አለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ የሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ያላቸው ግንዛቤ በቂ ባለመሆኑ፣ አለም አቀፍ ሰነዶች በሃፈሪቱ ህጎች ውስጥ ያላቸው ደረጃ እንዲሁም ተፈጻሚነታቸው( status and justiciblity) ላይ ግልጽነት ባለመኖር፣ አለም አቀፍ ሰነዶች ወደ ሃገሪቱ የስራ ቋንቋዎች ተተርጉመው በበቂ ሁኔታ ባለመሰራጨታቸው እንዲሁም የህግ ባለሞያዎች አለም አቀፍ ሰነዶችን ከብሄራዊ ህጎች ጋር አዋህዶ የመተርጎም ልምድ ባለመኖሩ ተፈጻሚነታቸው ላይ ውስንነት ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም ኢትዪጲያ ሴቶችን የሰብአዊ መብት መማስከበር እንዲሁም በመጠበቅ ረገድ የሚጠበቅባትን ግዴታዎች ለመወጣት ከላይ የተነሱትን ክፍተቶች በዝርዘር በመመልከት መፍትሄ መስጠት ከሁሉም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ይጠበቃል፡፡
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
698
የሴቶች መብት ከነቢዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) መላክ በፊት የሴቶች መብት እና በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የነበራት ስፍራ በጣም የወረደ እና ይልቁንስ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ መብቶች እንኳን የማይሰጣት ምስኪን ፍጥረት ነበረች። በተለይም በአረቡ አለም። ሴት በመሆኗ ብቻ የመኖር መብት የተነፈገችበት ጊዜ ነበር። አንድ አባት ሴት ልጅ ስትወለድ ሀፍረትና ውርደት ነበር የሚሰማው፤ እናም ከዚህ ውርደት ጋር መኖር እንደሌለበት በማሰብ የተወለደችለትን ልጅ አይኗ እያየ ከነሕይወቷ ከሚረማመድበት ምድር ስር ይከታታል። በሌላ መልኩም ሴት ልጅን ሕይወት እንዳለው ፍጥረት ሳይሆን እንደ ዕቃ ነበር የሚመለከቷት፤ በጨዋታቸው ላይ እንደ ገንዘብ ሴት ልጅን ነበር አስይዘው ቁማር የሚጫወቱት። ከዚህ በበለጠ ደግሞ የሚገርመው ሴት ልጅ ሕይወት አላት ወይንስ የላትም የሚል ክርክር እና ውይይት የሚደረግባት ፍጥረት ሆና ቆይታ ነበር። ብቻ ብዙ ብዙ … የነቢዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) መላካቸው ግን እነዚህን ታሪኮች በሙሉ ቀያሪ ሆነ፤ የሴቶች ህይወት እንደገና አበበ። ሴት ልጅ እንደ ገንዘብ የምትወረስ ሳይሆን ወራሽነቷ ተረጋገጠ፣ ነገሩ ሴት ህይወት የላትም ሳይሆን የህብረተሰቡ ግማሽ አካል እንዲያውም ከዚያ በላይ መሆኗ ተረጋገጠ። ነገር ግን ይህን እና ሌሎችን መብቶች በማስተባበል የእስልምናን እውነታ ባለማወቅም ሆነ እያወቁ እስልምና ሴት ልጅን እንደሚበድል በተለያዩ ሚዲያዎችና የሀይማኖት ተከታዮች ይለፈፋል። እስቲ እስልምና ወይንስ ክርስትና የሴትን ልጅ መብት የሚያረጋግጠው … የሴቶች መብት እና ክብር በመፅሐፍ ቅዱስ(በጥቂቱ) ወደ ጢሞቲዎስ 2፡12 -14 ሴት ልጅ ወንድን ማስተማርም ሆነ በወንድ ላይ ምንም ስልጣን ሊኖራት አይችልም ይህ የሚሆነውም በመጀመሪያ የተፈጠረው አዳም በመሆኑ ነው። ወደ ቆሮንጦስ 11፡ 5 – 10 ሴት ልጅ ከወንድ ተገኘች እንጂ ወንድ ከሴት አልተገኘም፤ ሴት ለወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም። ኦሪት ዘዳግም 22፡28 ለሌላ የታጨችን ልጃገረድ ድንግልና የወሰደ ለአባቷ ሀምሳ ጥሬ ብር ዋጋ ይከፍላል እሷም ያለ ፍላጎቷ ሚስት ትሆናለች በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መፍታት አይችልም መፅሐፈ መሳፍንት 21፡20 ሴት ልጅን መጥለፍ እንደሚፈቀድ ይናገራል ኦሪት ዘሌዋዊያን 12፡2-8 – ሴት ልጅ ወንድ ልጅ ከወለደች ለ 7 ቀን ትረክሳለች – ሴት ልጅ ሴት ብትወልድ ለ 17 ቀን ትረክሳለች በመርከሷም ምክኒያት የሚቃጠል መስዋዕት ሆኖ የሚቀርብ አንድ ጠቦትና ለሀጢያት ስርየት መስዋዕት የሚሆን ዕርግብ ወይንም ዋኖስ ለእግዚአብሔር ቤት ካህን መስጠት አለባት ከነዚህ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በግልፅ የምንረዳው መፅሐፍ ቅዱስ (ክርስትና ለሴት ልጅ መብት የቆመ የሴት ተከራካሪ ሳይሆን ተፈጥሮአዊ መብቶቿን እንኳን እንዳልሆነ ነው።) የሴቶች መብት እና ስፍራ በኢስላም በኢስላማዊው የቤተሰብ መዋቅር ውስጥ ሚስት የቤቷ ንግስት ነች። ነቢዩ(ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል «ሚስት በባሏ ቤት ጠባቂ ነች እናም በቤተሰቡ ባህሪና ጉዳዮች ላይ ተጠያቂ ነች» ቡኻሪ የዘገቡት – ሴት ልጅ ከቤት ውጪ በሚከናወኑ ሃይማኖታዊ ግዴታዎች ነፃ ነች ቡኻሪ የዘገቡት – ሴት ልጅ ረጅም ጉዞ ለማድረግ ብትፈልግ ምንም አይነት ጥቃት እንዳይደርስባት ከቅርብ ቤተሰቧ ጋር (አባት፣ ወንድም፣ ባለቤት፣ አጎት፣ ልጅ) መሄድ ግዴታነቱን ኢስላም ደንግጓል። – ሴት ልጅ ያለምንም በቂ ምክኒያት ከቤት መውጣቷን ኢስላም አያበረታታም – ሴት ልጅ የትዳር አጋሯን የመምረጥ መብት አላት – ነቢዩ(ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል «አንዲት ሴት(አግብታ የምታውቅ) ከቤተሰቧ ይልቅ የራሷን እጣ የመወሰን መብት አላት አግብታ የማታውቅን ሴት ያለ ፍቃድ አታኑሯት» – ባሎቻቸው የሞቱባቸው የተፈቱ ሴቶች እና ጋብቻቸው በህግ ውድቅ የተደረገ ሴቶች አዲስ ትዳር የመመስረት ሙሉ በሙሉ መብት አላቸው። «ለእነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በእነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኑዋኑዋር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው፡፡» ሱረቱ አል በቀራህ 228 – ሴት ልጅ የመውረስ መብት አላት «ለወንዶች ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተዉት (ንብረት) ፋንታ (ድርሻ) አላቸው፡፡ ለሴቶችም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተዉት ከእርሱ ካነሰው ወይም ከበዛው ፋንታ አላቸው፡፡ የተወሰነ ድርሻ (ተደርጓል)፡፡» ሱረቱ አን ኒሳእ 7 – ሴት ልጅ በሰብአዊነቷ ከወንድ እኩል ነች፤ ወንድም ሆነ ሴት ምንዳቸውን የሚያገኙት በሰሩት ስራ ልክ ነው። «አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በእርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ፡፡ ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው፡፡ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፡፡ አላህንም ከችሮታው ለምኑት፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡» ሱረቱ አን ኒሳእ 32 «ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ መጽዋቾች ወንዶችና መጽዋቾች ሴቶችም፣ ጿሚዎች ወንዶችና ጿሚዎች ሴቶችም፣ (ካልተፈቀደ ሥራ) ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡» ሱረቱ አል-አሕዛብ 35 ሴት ልጅ ታላቅ ስጦታ ናት «አካለ መጠን ደርሰው ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ ሁለት ሴት ልጆችን ያሳደገ የፍርዱ ቀን ከኔ ጋር እኩል ይቆማል» ብለዋል ሁለት ጣቶቻቸውን አጠጋግተው በማሳየት ሴት ልጆች ብቻ ያሉት ሰው እርሱም በትክክል ካሳደጋቸው ከጀሃነም እሳት ሽፋን ይሆኑለታል። ከመልካም ሚስት የበለጠ ፀጋ በዚህ አለም አይገኝም (ኢብን ማጃህ) አንድ ሰው ወደ ነቢዩ መጥቶ እንዲህ በማለት ጠየቀ «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ይበልጥ እንክብካቤ ላደርግለት የሚገባኝ ሰው ማን ነው?» «እናትህ» አሉት «ከዚያስ» «እናትህ» አሉት «ከዚያስ» «እናትህ» አሉት «ከዚያስ» «አባትህ» አሉት። ወደ እናታችን በሶስት እጥፍ ስንቀርብ ወደ አባታችንአንድ ጊዜ ይሆናል ማለት ነው። ይህም እናት የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ድርሻ ሲኖራት አባት የሰርተፊኬት ድርሻ ያገኛል ማለት ነው። የሴቶችን መብትና ክብር በእስልምና በዚህች ፅሁፍ የምናጠቃልለው አይደለም። ከባህር የማንኪያ ያህል ነው። ከዚህ ጋር መረዳት ያለብን ነገር ከማንም እና ከምንም የበለጠ ለሴት ልጅ ክብርና መብት ተቆርቋሪ ከእስልምና ውጪ አልነበረም፤ የለም፤ አይኖርምም። በአለማዊ ጥቅማጥቅሞች እና በምዕራባዊያን propaganda በሚዲያን መሰረተ ቢስ አስተምህሮቶች ይህን የማንነት መገለጫ፤ የሕይወቷ መሰረት ፤ የስኬታማነቷ መንገድ የሆነውን ሃይማኖት ልትለቅ አይገባም
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
699
የሴቶች መብቶች መግለጫ (1791) የ የሴቶች መብቶች መግለጫ የተፃፈው በኦሊምፔ ዴ ጎuge በ 1791 ነበር ፡፡ ካቀረቧቸው ቅሬታዎች መካከል የ genderታ እኩልነት አለመኖር አብዮት አለመሳካት ነበር- “አንቺ ሴት ፣ ንቃት! በምክንያታዊነት ውስጥ ጽንሰ-ሀሳቡ በመላው አጽናፈ ሰማይ ውስጥ ይሰማል። መብቶችዎን ያግኙ! የተፈጥሮ ኃያል መንግሥት ከእንግዲህ በጭፍን ጥላቻ ፣ አክራሪነት ፣ አጉል እምነት እና ውሸቶች የተከበበ አይደለም ፡፡ የእውነት ነበልባል የሞኝነትንና የበዙን ደመና ሁሉ ዘረጋ። የታሰረ ሰው ሰንሰለቱን ለማፍረስ ኃይሉን ያበዛል እናም የእናንተን ዋጋ እንዲሰጥ ይፈልጋል ፡፡ ነፃ ከወጣ በኋላ ለባልንጀራው ኢፍትሐዊ ሆኗል ፡፡ ኦ ሴቶች ፣ ሴቶች! ዕውር መሆኔን መቼ ያቆማሉ? ከአብዮቱ ምን ጥቅም አግኝተዋል? ይበልጥ ጎልቶ የተሰማ ውርደት ፣ ይበልጥ ምልክት የተደረገበት ውርደት። በዘመናት ምግባረ ብልሹነት ገዝተውት የነበረው የሰዎችን ድክመት ብቻ ነበር ፡፡ በጥበብ ተፈጥሮአዊ ድንጋጌዎች ላይ በመመስረት የአባትነትዎን መልሰ-ምትክ… ከእንደዚህ ዓይነቱ መልካም ሥራ ምን ይፈራሉ? … ጊዜው ያለፈበት በፖለቲካ ልምምዶች ምክንያት የረጅም ጊዜ የዚያ የሞራል ህግ አውጭዎች የፈረንሳያ ሕግ አውጭዎቻችን አሁንም እርስዎን የሚናገሩ ናቸው? ሁሉም ነገር ፣ መልስ መስጠት ይጠበቅብዎታል ፡፡ በድክመታቸው ከቀጠሉ እና ከመሠረታዊ መርሆዎቻቸው ጋር የሚቃረኑ ከሆነ ፣ የጥሩነትን አስመስሎ ባዶ ምክንያቶች አስመስለው በድፍረት ይቃወሙ ፣ እርስዎን ከፍልስፍና ደረጃ በታች ያጣምሩ ፤ የባህሪይዎን ኃይል ሁሉ ያሰማሩ ፣ እናም በቅርብ ጊዜ እነዚህን ትዕቢተኞች ሰዎች በእግርዎ እንደ አገልጋይ አድርገው እንደማይወዱ ፣ ግን የታላቁን የልዑል ሀብት ማካፈል ይኮራሉ ፡፡ እንቅፋቶች ቢያጋጥሟችሁም ፣ እራሳችሁን ነፃ ለማውጣት በችሎታችሁ ውስጥ ነው ፡፡ እርስዎ የሚፈልጉት ብቻ ነው… የሴቶችን ነፍስ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ብልህነት ያልሆነ መንገድ አቀርባለሁ ፤ ከሰው ሥራዎች ሁሉ ጋር መቀላቀል ነው ፡፡ አንድ ሰው በዚህ መንገድ ሕገ-ወጥ ሆኖ ለመገኘቱ ከቀጠለ ሀብቱን በሴቶች ሳይሆን በሀብት ጥበብ ይናገር ፡፡ ጭፍን ጥላቻ ይወድቃል ፣ ሥነምግባር ይነጻል ፣ ተፈጥሮም ሁሉንም መብቶ regaን ታገኛለች። በዚህ ላይ የካህናትን ጋብቻ እና የንጉ kingን ዙፋን በዙፋኑ ላይ ማጎልበት ፣ እናም የፈረንሣይ መንግሥት ሊሳካለት አልቻለም ፡፡ ”
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]
700
የሴቶች መብት እና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና {PART-5} ……..በጥናት የተራጋገጡ የወንድ እና የሴት መጠነ ሰፊ ልዩነቶች፡- ሴቶችና ወንዶች ካሏቸው መጠነ ሰፊ ልዩነቶች ውስጥ ሜዲካል መጽሔት በሚያዚያ ወር በ1999 ዓ.ል ባወጣው እትሙ ያሰፈረውን በጥቂቱ እንመልከት፡-  የወንዶችና የሴቶች አካላዊ ልዩነት ፡- ወንድ ልጅ በሴት ልጅ ላይ በአማካይ 20 በመቶ እርከን አካላዊ ብልጫ አለው(በክብደት)፡፡ ይህ የሆነው ወንዶች በጡንቻ ክምችትና ውፋሬ ላቅ ያለ ተፈጥሮ ስላላቸው ነው፡፡ ሴቶች ግን በዛ ያለ ቅባት ክምችት አላቸው፡፡  ሴቶች እረጅም የሆነ እድሜ ይኖራሉ፡፡  ሴት ሰላማዊ ወንድ ወንጀል ወዳድ ነው፡፡  ሴቶች በቶሎ ያለቅሳሉ፡፡ በቶሎ ይስቃሉ፡፡  በሂሳብ አቀማመር ወንዶች ይሻላሉ፡፡  ሴቶች ዙሪያ ጥምጥም ወንዶች ግን በቀጥታ ያስባሉ፡፡  በገንዘብ አያያዝ ሴቶች የተሸሉ ናቸው፡፡  ስሜትን ለመቆጣጠር የሚያገለግለው የአንጎል ክፍል ወንዶች ላይ ያንሳል፡፡  ግራ እና ቀኝ ያሉት አንጎል ክፍሎች ሴቶች ላይ የተሸለ ትስስር አላቸው፡፡  የወንዶች አንጎል በመጠኑ ከሴቶች ይበልጣል፡፡  የሴቶች አንጎል ቀድሞ እድገቱን ይጨርሳል፡፡  ወንዶች የተሸለ እንቅፋቶችን የመጋፈጥ አዝማሚያ የሚጠይቁ ተደጋጋሚ ውድቀቶች ሲያጋጥሙ ሴቶች በፍጥነት ተስፋ የመቁረጥ አዝማሚያ ሲኖራቸው ወንዶች ግን ያለ ሽንፈት መጋፈጥ ይመርጣሉ፡፡  ወንዶች ከሴቷ ጋር በሚፈጽሙት ተራክቦ ወቅት በአንድ የዘር ፍሰት ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጉ የስፐርም ሰራዊቶችን ለፅንሰት ሲለቅ ሴቷ ግን ለዚህ ስኬታማነት አንድ እንቁላል ብቻ ነው የሚታዘጋጀው፡፡ ይሁንና ከ60 ሚሊዮን ስፐርሞች ውስጥ ከአንዲቷ የሴት እንቁላል ጋር የሚዋሃደው እንዱ ብቻ ሲሆን ሌሎቹ ስፐርሞች በማህጸን ውስጥ ይሞታሉ፡፡  የወንድ ዘር ከሴቷ ዘር ይልቅ ረጅም እድሜ ይኖረዋል፡፡  ሴት ለፅንስ የሚያበቃትን አንዲት እንቁላል በወር አባባ አጋማሽ ላይ ብቻ ስታመርት ወንዱ ግን በየቀኑ የስፐርም ዘር ያመርታል፡፡  ሴት ልጅ የዘር እንቁላል ታወድማለች፡፡አንዲት ሴት በእናቷ ማህጸን ውስጥ እያች ከ3-4 ሚሊዮን የሚሆኑ እንቁላሎች የሚኖሯት ይሁን እንጂ ስትወልድ ግን አንድ ሚሊዮን የሚሆኑት ብቻ አብረዋት ይወለዳሉ፡፡ ሌሎች ግን ይወድማሉ፡፡ ከ16-45 ዓመት አድሜ ዘመኗ በወር አንዴ እንቁላል እያፈለቀች ትቆይና የተቀሩት እንቁላሎቿ በመጨረሻ (በ50ዎች እድሜ) ወደ ዜሮ ይወርዳሉ፡፡ በዚህ ወቅት ሴቷ ታርጣለች፡፡ ወንድ ልጅ እንዲህ አይነት የዘር ማሽቆልቆል አይታይበትም፡፡  ሴቶች በደንብ ያርጣሉ፡፤ ወንዶች በመጠኑ ያርጣሉ፡፡  ሴቶች ልጆቻቸውን ማይቶኮንድሪያ ያወርሳሉ፡፤ ወንዶች ግን አያወርሱም ፡፡  ሴቶች ፍቅርን ያስቀድማሉ፡፡ ወንዶች ወሲብን ያስቀድማሉ፡፡  ሴቶች ትከሻ ሰፊ ወንድን ንዶች ደግሞ ዳሌ ሰፊ ሴትን ለፍቅር ይመርጣሉ፡፡(ዶ/ር አቡሽ አያሌው፤ ሜዲካል መጽሔት፤ ሚያዚያ 1999፤ ገጽ 18) እነዚህ ከሴትና ከወንድ መጠነ ሰፊ ልዩነቶች ውስጥ በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ እንዴት ታዲያ ወንድና ሴትን አንድ አድርገን ልንመለከታቸው ይቻለናል? ‹‹እኩልነት ማለት አንድ አይነት ማለት አይደለም›› የሴት እና የወንድ እኩልነት በመንፈሳዊ ህይወታቸው (እዚሁ ፔጅ ላይ የሴቶች መብትና እኩልነት part-2 የሚለው ላይ በሰፊው ተዳሷል እዛ ላይይመልከቱ)
[ 115 ]
[ "የሴቶች መብት" ]
[ "ስለሴቶች መብትና ተጠቃሚነት የሚገልጹ ሰነዶችን መለየት፡፡" ]
[ "ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች የሴቶች ህገመንግስታዊና ሰባዊ መብቶች ያስረዳሉ, ኢኮኖሚያዊ, ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ይገልጻሉ ፡፡ ስለሌላ ሴት ልጅ ጉዳይ ሚያትቱ ሰነዶች አይጠቅሙም፡፡" ]