query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
1
300
passage
stringlengths
78
13.7k
category
stringclasses
7 values
link
stringlengths
28
740
⌀
source_dataset
stringclasses
3 values
a383d2e42cf88b2b831a5e666176ea44
b94a4e60789a475fa38cfc77457f07e6
የዘንድሮ ዓመት የተመዘገበው የሙቀት መጠን እጅግ ከፍተኛው ነው ተባለ
በዘንድሮው አመት የተመዘገበው የሙቀት መጠን እስካሁን ከተመዘገበው እጅግ ከፍተኛው  ነው ተባለ፡፡አለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ እኤአ በ2017 ዓመት የተመዘገበው ሙቀት ክብሮሰን መሆኑን ገልጿል፡፡ ድርጅቱ በዓመቱ የኢል ሊኖ ክስተት ጎልቶ ባይታይም  የዓለም ሙቀት አይሏል ብሏል፡፡የሳይንስ ሊቃውንት የሰው ልጅ እለት ተዕለት እንቅስቃሴ የአለም አየር ንብረት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑን በተጋጋሚ ያወሳሉ፡፡ በዚህ ዓመት የታዩት ያልተለመዱ የአየር ሁኔታ ክስተቶችም  መንሴያቸው የሰው ልጅ ተፅዕኖ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡በተባበሩት መንግስታት የዘንድሮው ዓመት የአየር ንብረት ምክክር የዓለም አቀፍ ሜትሮሎጂ ድርጅት ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡    በአከባቢ አየር ውስጥ ያለው የግሪን ሃውስ ጋዝ ልቀት መጨመር በአየር ውስጥ ከፍተኛ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ተከማችቶ ለሙቀት መጨመር መንስኤ መሆኑን ባደርገው ጥናት አመላክቷል፡፡        የአለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ያከናወነው ጥናት እንደሚያሳየውም የምድራችን ሙቀት በአሁኑ ሰዓት ከ1ነጥብ 3 በመቶ በላይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡በጥናቱ መሠረትም ከ 1950 ወዲህ አማካይ የሙቀት መጠን ጨምሮ ታይቷል፡፡ ውጤቱ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከ 1 ነጥብ 5 በላይ መድረሱን ተከትሎ በደሴቶች አካባቢ አደጋዉ ሊካፋ ይችላልና ተገቢ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ጥናቱ አሳስቧል፡፡የጥናቱ ዝርዝር እንደሚያሳየው የ2017 ሙቀት ከ 1983 አስከ 2010 በ አማካይ በ 0ነጥብ 47 በመቶ  ጨምሯል፡፡  ከ2016 ኤል ሊኖ ከተካሰተበት አንፃር ሲታይ ግን 0ነጥብ 56 አማካይ ቀንሶ ታይቷል፡፡አለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ተቋም የዘንድሮው አመት በ2015 ከተመዘገበው ሙቀት ሁለተኛው አልያም ሶስተኛው ሊሆን እንደሚችል አስቀምጧል፡፡ያለፉት ሶስት አመታት በተመዘገባበችው የሙቀት መጠን ቀዳሚውን ሶስት ደረጃ የሚይዙ ናቸው ሲሉ የተቋሙ ዋና ፀሓፊ ፔትሪስ ታላስ ይናገራሉ ፡፡እስከ 50 ሴልሸስ እጅግ አዳጋች የሆነ የአየር ንብርት በኤስያ መከሰቱ በዚህ ዓመት ተመዝግቧል፡፡ ታይቶ የማይታወቅ የሀሪኬን፤የጉዳት መጠኑ እጅግ የሰፋ ጎርፍ ብሎም በካሪቢያን እና በአትላንቲክ በተከታታይ የተከሰቱ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ተከስቷል፡፡አደጋው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን የጎዳ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ድርቅ ብሎም ጎርፍ በአፍሪካ ተከስቶ ነበር ሲሉም ፀሀፊው አክለዋል፡፡የሳይንስ ሊቃውንት እኤአ በ2017 የተከሰተውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን አስመልክቶ ተጨባጭ ጥናት ማድረግ አለባቸው ሲሉም ምክራቸውን ያክላሉ፡፡እየጨመረ የመጣው ያለም ሙቀት የባህር ማዕበል እንዲከሰትና ለጎርፍ መጥለቅለቅ መንስኤ  ሊሆን እንደሚችል የዘገባዉ ምንጭ ቢቢሲ አስነብቧል፡፡በተጨማሪም በሴራ ሊዮን፤ በኔፓል፤በሕንድ፤ በባንግላዴሽ እና በፔሩ መካከል  በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ውድመት አጋጥሞ  ነበር፡፡በተቃራኒው ድርቅ እና ሙቀት በአብዛኛዎቹ  የአፍሪካ እና የደቡብ አሜሪካ አካባቢዎች ተፅእኖ አሳርፏል፡፡ በሶማሊያ ከግማሽ በላይ የሚሆን እርሻ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በሀገሪቱ ድርቅ ባሳደረው ተፅዕኖ ከብቶች ከ 40-60 በመቶ  እንዲቀንስ ምክኒያት ሆኗል፡፡በጥቅሉም በምስራቅ አፍሪካ ከ 11 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ጠምግብ እጥረት ተዳርገዋል፡፡ እንደ የእንግሊዙ ሬዲንግ ዩነቨርሲቲ የአየር ንብረት ሳይንስ ፕሮፌሰር ሪቻርድ አላን 2017 በአየር ንብርት ለዉጥ አስከፊ ክስተቶች አልፈዉበታል፤ በሰበአዊ ሂዎት ላይ የደረሰዉ ጉዳትም በአጅጉ  ጨምሯል፡፡የምድር ሙቀት መጠን  በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ  በፓሪስ የአየር  ስምምነት ሰነድ ባስቀመጠዉ የጋዝ ልቀት መስፈርት መመራት የግድ ይላል፡፡ ሲሉም ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብር ምክክር ጉዳዩን ትኩረት የሰጠዉ ሲሆን በፓሪስ ስምምነት አላማ መመራት ካልተቻለ የአለም ዜጎች ፈታኝ እጣፈንታ የጠብቃቸዋል ያሉት የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ዋና ፀሃፊ ፓትሪሺያ ኢስፓኖሳ ናቸዉ፡፡ 
ሀገር አቀፍ ዜና
https://waltainfo.com/am/34058/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
28cdc17f3463dcf31f1f326d110e9e65
2df90447cd25c44abd0fe887f7aed653
አሜሪካ፡ በዓመት 125 ሚሊዮን ዶላር የተከፈላቸው የአፕል ሥራ አስፈፃሚ ቲም ኩክ ቢሊየነር ሆኑ
847 ሺህ 969 የኩባንያ አክሲዮኖች ባለቤት የሆኑት ኩክ ባለፈው ዓመት ብቻ 125 ሚሊዮን ዶላር [ወደ ብር ስናመጣው ወደ 4.4 ቢሊዮን ገደማ] ደመወዝ ተከፍሏቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን እየሾሩ ላሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ባለቤቶች ፍርቱና ሆኗል። ይህ የሆነው ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት መዋል መጀመራቸውና የሚፈልጉት ምርትና አገልግሎት በበይነ መረብ አማካይነት ማሰስ መጀመራቸው ነው። ባለፈው ሳምንት የፌስቡክ ባለቤት የሆነው ማርክ ዛከርበርግ የግል ሃብቱ ከ100 ቢሊዮን ዶላር በላይ መግባቱ ተሰምቶ ነበር። የዛከርበርግ ፌስቡክ ብቻ ሳይሆን አፕል፣ አማዞንና ማይክሮሶፍት ከወረርሽኙ ካተረፉ መካከል ናቸው። በዋናነት በአሜሪካ ገበያ ተፈላጊ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን የሚያመርተው አፕል 2 ትሪሊየን ዋጋ የሚያወጣ የመጀመሪያ የዓለማችን ኩባንያ ሊሆን ተቃርቧል። ከሁለት ዓመታት በፊት 1 ትሪሊየን ዋጋ ያለው የመጀመሪያው የዓለማችን ኩባንያ መሆን መቻሉ አይዘነጋም። ቲም ኩክ የአፕል ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት የስቲቭ ጆብስን [የኩባንያው መስራች] ሞት ተከትሎ ከ9 ዓመታት በፊት ነበር። ሰውዬው ሃብታቸው ቢሊዮን የደረሰው ከአክሲዮን ከሚያገኙት ገቢና ድርጅቱ ከሚከፍላቸው ደመወዝ ነው። በጎርጎሳውያኑ 2015 አብዛኛውን ገንዘባቸውን ለእርዳታ ድርጅቶች እንደሚያበረክቱ ቃል የገቡት ቲም ቃላቸውን ሳያጥፉ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ይለግሳሉ። የፌስቡኩ ዛከርበርግም እንዲሁም ሚሊዮን ዶላሮችን ዝቄ ለእርዳታ ድርጅቶች እሰጣለሁ ሲል ቃል መግባቱ አይዘነጋም። የፌስቡክ ፈጣሪው ዛከርበርግ፣ የአማዞን ባለቤት ጄፌ ቤዞስና የቴስላ መሥራች ኢላን ማስክ የግል ሃብታቸው በየቀኑ የሚያድገው በኩባንያዎች ውስጥ ባላቸው ትልቅ የአክሲዮን ድርሻ አማካይነት ነው። ምንም እንኳ አፕል እንደፈጠረው ተንቀሳቃሽ ስልክ ያለ ገበያውን ያመሰ አዲስ ምርት ባይኖረውም ኩባንያው አሁንም ጥንካሬውን እያሳየ ነው። ቲም ኩክ ኩባንያውን በኃላፊነት ከተረከቡት በኋላ የተለያየ ዓይነት የአይፎርን ምርቶች ለገበያ አቅርበዋል። አፕል ዎች የተሰኘ የተንቀሳቃሽ ስልክ ባህሪ ያለው የእጅ ሰዓትም ለገበያ አቅርበዋል። ከሌሎቹ ጉምቱ ባለሃብቶች ሲነፃፀር የቲም ኩክ ሃብት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በካሊፎርኒያ የግብር ሕግ መሠረት ቲም ኩክ 50 በመቶ ግብር እንዲከፍሉ ሊገደዱ ይችላሉ።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
10ff952ae9503edcfd250e4cae8cd8b4
c81f7dc31fcc62a51bd820b7f777b4ac
የህንድና የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ግንኙነት
የአሜሪካው ከፍተኛ ዲፕሎማት፣ ከህንዱ አቻቸው ኤስ ጃይ ሻን ካር እና ከህንዱ ጠ/ር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ዛሬ ረቡዕ በተገናኙበት ወቅት ነው ይህን ያስታወቁት።ጠ/ሚኒስትር ሞዲ ድጋሜ ከተመረጡ ወዲህ፣ የሁለቱ ሀገሮች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሲገናኙ ይሄ የመጀመሪያ መሆኑ ነው።
ዓለም አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/us-and-india-6-26-2019/4974765.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
acf579f04dafa207f1603b7813918884
eaa44ee855fed5f21388bac4387eac12
በሃማሬሳ የተፈናቃዮች ካምፕ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል
በምስራቅ ሀራርጌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሃማሬሳ የተፈናቃዮች ካምፕ አካባቢ እሁድ ከሰዓት በተፈጠረው  ግጭት የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የምስራቅ ሀራርጌ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ፡፡እንደ አስተዳዳሪው አቶ ጀማል መሃመድ ገለጻ በግጭቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ቆስለዋል፡፡      ግጭቱ የተነሳው ማንነታቸው ባልታወቀና እህል ጭነው ወደ ሀረር ሲሄዱ በነበሩ የጭነት ተሸከርካሪዎች ውስጥ በነበሩ ሰዎች ሲሆን መንስኤው እስካሁን በውል አለመታወቁ ነው የተዘገበው፡፡አከባቢው ባሁን ሰዓት የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ መሆኑን እና የችግሩ መንስኤ ተለይቶ ጥፋተኞችን ለህግ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ  አቶ ጀማል  ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉ  የስልክ ቆይታ ገልጸዋል፡፡
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/29635/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
6346fec0df0f255dffc1bc3209243fff
f726a9ead4656b3fe10968a7c216f3b0
አሰራሩ ለቱሪዝም ዘርፍ መቀጨጭ  ማነቆ እንደሆነ ተገለጸ
አዲስ አበባ፡- በአገሪቱ እየተስተዋለ ለሚገኘው ዝቅተኛ የቱሪዝም እንቅስቃሴ እስከዛሬ የነበረው የአሰራር ጉድለት ምክንያት እንደሆነ ቱሪዝም ኢትዮጵያ ተገለጸ ።ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከአስጎብኚ ድርጅቶች ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ እንደተገለጸው፤ በአገሪቱ ባለው የአሰራር ክፍተት ምክንያት መንግሥት ከአስጎብኚ ድርጅቶች ጋር የነበረው ትብብር መልካም አለመሆን የቱሪዝም ዘርፉ ተጎድቷል፡፡ የሀገሪቱ ቱሪዝምን በተፈለገው እርምጃ እንዳያድግ  እና ኢትዮጵያም ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ እንዳትሆን ማነቆ ሆኖ ዘርፉን አቀጭጮታል።የፓራዳይዝ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት ኃላፊ አቶ ፍጹም ገዛኸኝ እንደገለጹት፤ ለቱሪዝም ዕድገት በዘርፉ የሚገኙ የግል ድርጅቶች ተሳትፎ የላቀ ቢሆንም መንግሥት የሚጠበቅበትን ድርሻ እየተወጣ አይደለም። የሀገሪቱ የቱሪዝም ድርጅት ሲቋቋምም የግሉን ዘርፍ የማሳተፍ ዓላማ ይዞ ቢሆንም፤ ይህ ግን በተግባር አልታየም። ይልቁንም መንግሥት የግሉን ዘርፍ ያገለለ ሥራ ሲያከናውን ቆይቷል፤ በሚያወጣቸው ዕቅዶችና በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይም ተሳታፊ ባለማድረጉ ተቋማቱ የአብሮነቱን መንፈስ ተነፍገዋል።መንግሥት በተፈለገው ደረጃ የግል ዘርፉን አጣምሮ ባለመጓዙ ኢትዮጵያ ከዓለም የቱሪዝም ካርታ እንድትነጠልና በአሁኑ ጊዜም በተለያዩ የዓለም አቀፍ ንግድ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ እንዳይኖራት ምክንያት ሆኗል ያሉት አቶ ፍጹም፤ በካርታው ዳግመኛ ለመካተትም ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍል ገልጸዋል።በምክክር መድረኩ ላይ እንደተገለጸው ቱሪዝም ኢትዮጵያ በሚል ስያሜ የተዋቀረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት በተቋቋመበት የቱሪዝም አዋጅና ሥልጣን መሰረት ባለመሥራቱ የየዘርፉን እንቅስቃሴ በእጅጉ ሲጎዳው እንደቆየ ተጠቅሷል።ከተቋሙ ባለሙያዎች የዕውቀት ዝግጁነት ጀምሮ የቁሳቁስና የሰው ኃይል አቅርቦት ችግር እንዳለበት የጠቀሱት የሰንራይዝ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት አቶ ያዕቆብ መላኩ በበኩላቸው፤ ለቦታው የሚመጥን ባለሙያ በመመደብ የተዳከመውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ማነቃቃት የግድ እንደሚል ተናግረዋል።የተጠቀሱት ክፍተቶች መኖራቸውን በማመን በመድረኩ ለተነሱ ቅሬታዎች ምላሽ የሰጡት የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሌንሳ መኮንን፤ በዘርፉ በየጊዜው የሚቀያየረው አመራር ለችግሩ መስፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። እስከዛሬ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል የነበረውን ክፍተት በማጥበብ በጋራ ለመሥራትና ቁልፍ ችግሮችን ለመፍታት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ ለዚህ ስኬትም «ሁላችንም በጋራ እንተባበር » ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።በቱሪዝም ኢትዮጵያ የዕለቱ መድረክ አስተባባሪ አቶ ወልደ ገብርኤል በርሄ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በቱሪዝሙ ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስትመዝን ከ138 ሀገራት መካከል 118ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተናግረዋል። በተመሳሳይ ሁኔታም በቱሪዝም ደህንነት፣ በንጽህና አጠባበቅ፣ በትራንስፖርት አቅርቦትና ምቹነት፤ በሌሎችም መስፈርቶች በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠች ተናግረዋል።አስተባባሪው በመድረኩ ላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ ሌሎችም ችግሮች ለቱሪዝም አለማደግ እንቅፋት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በዚህ ዓመት በተቋሙ ዘርፉን ለማሻሻል የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎች እንደሚከናወኑ በመግለጽም፤ ከነዚህ መካከልም ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ የቱሪስት መመዝገቢያ ሳተላይት አካውንት ለመጀመር  በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።ቱሪዝም ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሦስት ቀናት በተመሳሳይ ከሌሎች  ባለድርሻ አካላት ጋር  የምክክር መድረክ እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 24/20111በመልካምስራ አፈወርቅ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=2389
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
89583676007a0ec80345df3ce29a1a9a
567fb87a11ad497dabf32d1a1df675cc
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጠራው ልዩ ስብሰባዉ የቀድሞ የክልሉ ሰንደቅ አላማ ተመልሶ የክልሉ መለያ ሆኖ እንዲያገለግል ወሰነ።
የሶማሌ ክልል የቀድሞው ሰንደቅ አላማ ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ\nከዓመታት በፊት ለውጥ ተደርጎበት የነበረው በከፊል የሶማሊያ የሰንደቅ ዓላማ ሰማያዊ ቀለምና ነጭ ኮከብ ያለው ሰንደቅ ተመልሶ እንዲያገልግል ተወስኗል። ቀደም ሲል የነበረው ሰንደቅ አላማ በከፊል ቢጫ ቀለምና የግመል ምስል ይዞ ቆይቶ ነበር። በቅርቡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ ሙስጠፋ ዑመር በፌስቡክ ገጻቸው በክልሉ ሰንደቅ አላማ ላይ ለውጥ መደረጉን በተመለከተ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ "በሶማሌነታችንና በኢትዮጵያዊነታችን መሀከል ተቃርኖ የለም" ሲሉ አስፍረዋል። • አብዲ ሞሃመድ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፈፈ • ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ የቀድሞው ሰንደቅ አላማ ተመልሶ ሥራ ላይ መዋል መጀመሩን በተመለከተም "የሶማሌ ክልል ህዝቦች ነን፤ ከፊትም ከኋላም ቅጥያ የለም፤ የቀደመው ሰንደቅ አላማ ተመልሷል" በማለት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በገፃቸው ላይ ገልፀዋል። የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደድር አቶ አብዲ ሙሀመድ ዑመር ከስልጣን ከተነሱ በኋላ የተተኩት አቶ ሙስጠፋ ዑመር፤ "የሶማሌነት መገለጫችንን በኩራት ስንጠብቅ ብሔራዊ ግዴታችንንም ባለመዘንጋት ነው" ብለዋል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት በዛሬው ልዩ ስብሰባው አዲስ አፈ-ጉባኤ ለምክር ቤቱ የሰየመ ሲሆን ለዳኞችም ሹመት ሰጥቷል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
3c0bca9f974e16007ac0e943a32c6a5d
fc7a9a59bca8f83c1a9ebac99886ead7
በኢትዮጵያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ሊከሰት እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።
ኢትዮጵያን የቢጫ ወባ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋት የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ\nድርጅቱ እንዳለው በመጋቢት ወር በበሽታው ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች ቁጥር ሦስት እንደነበረ አመልክቶ ባለንበት የሚያዝያ ወር ግን የተጠርጣሪዎችቹ አሃዙ ወደ 85 ከፍ ማለቱን ገልጿል። በሽታው አለባቸው ተብለው ከተጠረጠሩት ሰዎች መካከልም ስምንቱ በምርመራ በሽታው እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል። የቢጫ ወባ ክትባት ተመልሶ እንዲጀመር መደረጉን ያመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት፤ ከሚኖሩበት አካባቢ እርቀው የመሄድ የጉዞ ታሪክ በሌላቸው ሰዎች ላይ መታየቱ እንዳሳሰበው አመልክቷል። "በአገር ደረጃ ያለው የበሽታው ስጋት በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተደረሰበት" መሆኑን ድርጅቱ ጠቅሶ፤ በተለይ በደቡብ ክልል ውስጥ በሚገኘው የጉራጌ ዞን ገጠራማ አካባቢዎች ውስጥ የቢጫ ወባ በሽታው የመስፋፋት መጠን ፈጣን መሆኑን ተገልጿል። አክሎም "በሕዝብ ውስጥ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ዕድል ባልተፈጠረበት ሁኔታ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች መገኘታቸው በጣም አሳሳቢ ነው" ሲል ድርጅቱ ስጋቱን ገልጿል። በኢትዮጵያ ለቢጫ ወባ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በተለይ ትኩረት በማድረግ የበሽታው መከላከያ ክትባት ለሰዎች ሲሰጥ ቆይቷል። በዓለም ዙሪያ የኮሮናቫይረስ ዋነኛ የጤና ችግር በሆነበትና ትኩረት ሁሉ ወደዚህ ወረርሽኝ በዞረበት በዚህ ጊዜ ተጨማሪ በሽታዎች የሚከሰቱ ከሆነ የሚያስከትሉት ጉዳት የከፋ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
7497cffe11d4f8acfdd1eba9f16273bf
72faff11b9ce14d94e7ca2a3d8bb7aa7
ቻይና እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አመኔታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው ተገለጸ
በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን ፖለቲካዊ አመኔታ ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ተናገሩ። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ከቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ይ ጋር የተወያዩ ሙላቱ ኹለቱ አገራት የጋራ ጥቅማቸውን ከማስጠበቅ ባለፈ ያላቸውን የፖለቲካ አመኔታም ማሳደግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በበኩላቸው ቻይናዊያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ እንደሚያበረታቱ እና ቻይናም ቀጠናዊ እና ሉላዊ ችግሮችን ለመፍታት እንደምትተጋ አስታውቀዋል። አያይዘውም ቻይና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና በታላላቅ ግንባታዎች ለላይ ከመሳተፍ ባሻገር ታዳጊ አገራትን ጥቅመም ለማስጠበቅም እንደምትሰራ ተናግረዋል።ሙላቱ ተሾመ  በጉብኝታቸው ወቅትም የኹለቱነን አገራት አጋርነት እና ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚጠናከር ተስፋ ስለመጣላቸው ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://addismaleda.com/archives/7694
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
4c389a6acaa4000d41f1b45e8a34dcb0
739dbe7974ae9478ee375438b84b2aed
በግልና በመንግሥት ተቋማት ትብብር የሚሰጡ የትምህርት ፕሮራሞች ዕገዳ ጥያቄ አስነሳ
የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከግል ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰጡትን የድኅረ ምረቃ መርሐ ግብር እንዲያቋርጡ ያሳለፈው ውሳኔ ጥያቄ አስነሳ፡፡ ኤጀንሲው ከግል ኮሌጆች ጋር በትብብር የሚሰጡትን የድኅረ ምረቃ መርሐ ግብር እንዲያቋርጡ ደብዳቤ የጻፈባቸው ኤቢኤች ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር ለተባበረው ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ከዮም ኮሌጅ ጋር ለሚሠራው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ከናሽናል ኮሌጅ ለተጣመረው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲና ከአዲስ ኮንቲኔንታል የጤና ኢንስቲትዩት ጋር ይሠራ ለነበረው ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ታውቋል፡፡ በጤና አጠባበቅ የትምህርት መስክ በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም፣ በጤና መኮንንነት የትምህርት መስክ ደግሞ በቅድመ ምረቃ መርሐ ግብር የሚያስተምረው አዲስ ኮንቲኔንታል የጤና አጠባበቅ ኢንስቲትዩት ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመሥራት የጀመረውን ፕሮግራም አቋርጦ ሳለ፣ እንደ አዲስ ደብዳቤ መጻፉ ግርታ እንደፈጠረባቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው ኃላፊ ገልጸዋል፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ፣ ማንኛውም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የሚሰጠውን የትብብር የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲያቋርጥ ያሳለፈውን የመጨረሻ ማሳሰቢያ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀበለውም አሳውቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ኤቢኤች ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በትብብር የሚሰጣቸውን የትምህርት ፕሮግራሞቹን የመገደብ ሥልጣን ኤጀንሲው እንደሌለው አስታውቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከተቋሙ ጋር በትብብር የሚሰጠው የትምህርት ፕሮግራም፣ የከፍተኛ ትምህርትና የዩኒቨርሲቲው መቋቋሚያ አዋጆች በሚፈቅዱለት አግባብ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከግል ተቋማት ጋር በትብብር እንድሠራ ይፈቀድልኛል ያለውን የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 (ማንኛውም ተቋም ተገቢና ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ሆኖ ሲያገኘው የድጋፍ ሰጪ አገልግሎቶችን በሌሎች አገልግሎት አቅራቢዎች እንዲሰጥ ሊያደርግ ይችላል) ሥር የሰፈረውን ድንጋጌ በመጥቀስ፣ የትምህርት ፕሮግራሞቹን እየሰጠ የሚገኘው ሕጉ በሚፈቅድለት አግባብ መሆኑን ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. አዲስ አበባ በሚገኘው ካምፓሱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል፡፡ዩኒቨርሲቲው በ2000 ዓ.ም. ከተቋቋመው ኤቢኤች አማካሪ ድርጅት ጋር ያለው አሠራርም ሕጋዊ መስመሩን የተከተለ መሆኑን በዕለቱ አሳውቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ መዘምር ሰይፉ እንዳሉት፣ ዩኒቨርሲቲው በሚሰጣቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ኤቢኤች የማማከርና የሎጂስቲክስ ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት ብቻ ነው ያለው፡፡ የተማሪዎች ምልመላ፣ ምዝገባና ሌሎችም የአካዴሚክ ጉዳዮችን የሚመለከተው ፕሮግራሙን በበላይነት የሚመራው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ዩኒቨርሲቲው ሚኒስቴሩ ያስተላለፈውን ማሳሰቢያ የሚቃረን፣ ዜጎችን የሚያሳስት፣ ሕጋዊ ላልሆነ ሥልጠና ገንዘባቸውና ጊዜያቸውን እንዲያጠፉ የሚያደርግ ማስታወቂያ በብሥራት ኤፍኤም 101.1 ሬዲዮ መልቀቁንና እንዲቋረጥ ማድረጉን ኤጀንሲው በፌስቡክ ገጹ ላይ አስነብቧል፡፡ ዜጎችን ለማሳሳት የሚለው አገላለጽ ግን የአንጋፋውን ዩኒቨርሲቲ ስም የሚያጠለሽ በመሆኑ፣ ኤጀንሲው ዩኒቨርሲቲውን በግልጽ ይቅርታ እንዲጠይቅ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ኤጀንሲውን በሕግ ለመጠየቅ እንደሚገደድ አቶ መዘምር ገልጸዋል፡፡ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኤጀንሲው ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮችን ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ፣ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከግል ተቋማት ጋር የትብብር ሥልጠና መስጠት እንደማይችሉ፣ የጀመሩትንም እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ የተሰጣቸው በ2006 ዓ.ም. እንደነበር፣ ነገር ግን ተግባራዊ ሳይደረግ እንደቆየ ገልጸዋል፡፡ዩኒቨርሲቲዎቹ ከግል ተቋማት ጋር አብረው መሥራት እንደሚችሉ በሕግ የተቀመጠ ነገር ቢኖርም፣ የተለያዩ የአሠራር ክፍተቶች በመታየታቸው የትብብር ሥራቸውን እንዲያቆሙ ተጠይቀዋል ብለዋል፡፡ ከታዩ የአሠራር ችግሮች መካከል ዩኒቨርሲቲዎች ዋነኛ ተልዕኳቸውን ወደ ጎን ብለው በትብብር የትምህርት ፕሮራሞች የሚያገኟቸውን የውስጥ ገቢዎች ማሳደድ፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብን እንደ ግል ተቋም ዝቅ የማድረግ ነገር መታየቱን ገልጸው፣ ‹‹በኤጀንሲው እንደ መንግሥት ተቋም ይመዘገቡና ተማሪዎችን ለመቀበል ሲሆን ግን እንደ ግል የትምህርት ተቋም የመቁረጫ ነጥብ ዝቅ አድርገው ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ ማስታወቂያ ሲያስነግሩም እንደ ግል ተቋም በማስመሰል እንደሆነ፣ ይህም በአዋጅ የተቀመጠላቸውን ግዴታ የሚፃረር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ በበኩላቸው በኤቢኤች ካምፓስ የሚሰጠው የትምህርት ፕሮግራም 99 በመቶ የድኅረ ምረቃ መሆኑን፣ ለዚህም የመቁረጫ ነጥብ እንደማያስፈልግ፣ ተወዳድረው ያለፉትን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች እንደሚቀበልና ከዚህ ዓመት ጀምሮ ግን የሕክምና ትምህርት በቅድመ መርሐ ግብር ማስተማር መጀመሩን፣ ከ460 ነጥብ ጀምሮ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ተፈትነው መግባታቸውን በማስረዳት በትብብር የሚሰጠው የትምህርት ፕሮግራም አንድም የጥራት ችግር እንደሌለበት ተናግረዋል፡፡ የትምህርት ጥራት አለበት የሚባለውም አንድም የኤጀንሲው አካል ወደ ካምፓሱ ሄዶ አስፈላጊውን የፍተሻ ተግባር ሳያከናውን እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር የሚሰጠው ፕሮግራም በአሁኑ ወቅት ከ1,000 በላይ ተማሪዎች እንዳሉት፣ ማስጠንቀቂያውንም እንደማይቀበሉና ፕሮግራሞቹም እንደማይቋረጡ የኤቢኤች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርቆስ ፈለቀ (ዶ/ር) አሳውቀዋል፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.ethiopianreporter.com/article/16508
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
e8924b84ddf05fdeb09d864f3d28d6d6
89f708afc8919fd0ecb53ceac7bac95b
ሪፖርት | ወላይታ ድቻ እና መከላከያ አቻ ተለያይተዋል
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን መርሃ ግብር ሶዶ ላይ መከላከያን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በሜዳው ለአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች የነበረውን የበላይነት ከጦሩ ጋር ነጥብ በመጋራት ደምድሞታል፡፡ ጨዋታው በአፍሪካ መድረክ እና በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተከታታይ ድሎችን እያስመዘገበ የሚገኘው እና በሜዳው በሊጉ ለሚገኙ ቡድኖች ፈታኝ በመሆን በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ ላይ ከፍ በማለት ላይ ይገኝ የነበረው ወላይታ ድቻን እና ከአስልጣኝ ሥዩም ከበደ መምጣት በኃላ ወደ ድል እየተመለሰ እና ከውራጅ ቀጠና ራሱን ለማራቅ እየጣረ የሚገኘው መከላከያን በማገናኘቱ ተጠባቂ እንዲሆን አስችሎታል።እንደወትሮው ሁሉ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በሶዶ ስታድየም አከባቢ ከተለያዩ ወረዳዎች እና አጎራባች ከተሞች ቡድኑን ለመደገፍ በነቂስ የሚተመው የወላይታ ድቻ ደጋፊ ዛሬም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ወደ ሜዳ ለመግባት ጥረት ሲያደርግ ታይቷል። ጨዋታው እነደከዚህ ቀደሙ የዕረፍት ቀናት ላይ አለመደርጉ የደጋፊውን ቁጥር በመጠኑም ቢሆን የቀነሰው ቢመስልም የማታ ማታ ግን ስታዲየሙ ከአፍ እስከ ገደፍ መሙላቱ አልቀረም። ቡድኖቹ ወደ ሜዳ ሲገቡም የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ማህበር ያዘጋጀው የእንኳን ደህና መጣችሁ ባነር ለእንግዳው ቡድን ቀርቦ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ተዘምሮ ጨዋታው ተጀምሯል።ወላይታ ድቻ ባሳለፍነው እሁድ የሊጉን መሪ ደደቢትን 1-0 ካሸነፈበት 4-1-4-1 አሰላለፍ ውስጥ በጉዳት ባጣው ጸጋዬ ባልቻ ምትክ ያሬደ ዳዊትን ወደ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ሲያስገባ  መከላከያ ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያሸነፈበትን የ4-4-2 አሰላለፍ ሳይቀይር ከስብስቡ ውስጥ የተሸ ግዛውን በቴድሮስ ታፈሰ በመተካት ጨዋታውን ጀምሯል።በጨዋታው በመጀመሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ያልተረጋጋ የኳስ እንቅስቃሴ ያሳዩ ሲሆን ወላይታ ድቻ ረጃጅም ኳሶችን ወደ መከላከያ የግብ ክልል ለመጣል ሲሞክር በአንጻሩ መከላከያዎች ኳስን መስርተው ለመጫወት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። ባለሜዳዎቹ ድቻዎች የሰሞኑ ጠንካራ አቋማቸው ተዳክሞ በታየበት በዚህ ክፍለ ጊዜ ኳስን ተቆጣጥረው ለመጫወት በሚሞክሩበት አጋጣሚ ቶሎ ቶሎ ሲቆራረጥባቸው እና በመከላከያ የመሃል ሜዳ የበላይነት ሲወሰድባቸው ታይቷል። ዳዊት እስቲፋኖስ ፣ አማኑኤል ተሸመ ፣ ሳሙኤል ታዬ እና በጨዋታው ድንቅ የነበረው ቴድሮስ ታፈሰ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ድቻዎች ከዚህ ቀደም በመስመር የሚሰነዝሩት ጥቃት ሲገታባቸው እና ብቸኛው የፊት አጥቂ ጃኮ አራፋትን ግልጋሎት በሚገባ ማግኘት ሲሳናቸውም ታይተዋል።መከላከያዎች በሁለቱ አጥቂዎቻቸው ሳሙኤል ሳሊሶ እና ምንይሉ ወንድሙ አማካኝነት ጥቃት ለመሰንዘር ቢሞክሩም በተደጋጋሚ በድቻ የተከላካይ ክፍል ጥረት በተለይም በውበሸት አለማየሁ ኳስ የማጨናገፍ ክህሎት ድቻዎች ተጠቃሚ ሆነዋል። የጦሩ ተሰላፊዎች የመሀል ሜዳ ብልጫቸውን በመጠቀም አንድም የጠራ የጎል እድል ማግኘት ባይችሉም በ40ኛው ደቂቃ ላይ ከግራ የሜዳው ጫፍ በኩል ሳሙኤል ሳሊሶ ለምንይሉ ወንድሙ የላካት ኳስ የድቻ ተከላካዮች ለመመስ ጥረት በሚደረጉበት ወቅት ኳስ በእጅ ተነክቷል በማለት ጥያቄ ቢያቀርቡም የእለቱ ረዳት ዳኛ ጨዋታው እንዲቀጥል አድረገዋል፡፡ በዚህ ክፍለ ጊዜ በሁለቱም ቡድኖች አንድም ቀጥተኛ የሆነ ሙከራ ሳይደረግ ተጨዋቾቹ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡በሁለተኛው አጋማሽ መከላከያዎች 4-4-2 ነበረውን አስላለፋቸውን በይበልጥ ለማጥቃት በሚመስል መልኩ ወደ 4-3-3 ሲቀይሩ በመጀመሪያው አጋማሽ ከአራቱ አማካዮች ተርታ የነበረውን ሳሙኤል ታዬን ወደ ቀኝ መስመር በማውጣት መሃል ላይ በቀሪዎቹ ሶስት አማካዮች ኳስን በሚገባ ለመቆጣጠር ሲሞክሩ ተስተውለዋል። በአንጻሩ ድቻዎች በጨዋታ መሀከል የአምረላ ደልታታን እና ያሬድ ዳዊትን ቦታ ከመቀያየር ውጪ ምንም አይነት ለውጥ ሳያደርጉ ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡ መከላከያዎች ይህ ቅርጽ ከመጀመርያው አጋማሽ ይልቅ የጎል ዕድሎችን ሲፈጥርላቸውም ነበር። በተለይም በ47ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ታዬ ከቀኝ መስመር ያሻገራት ኳስ ዳዊት እስጢፋኖስ በግንባሩ አግኝቷት ወደ ውጪ የላካት በእለቱ የታየች የመጀመርያ የጎል አጋጣሚ ስትሆን ድቻዎች በረጃጅም ኳሶች ወደ መከላከያ የግብ ክልል በተደጋጋሚ ለመግባት ቢሞክሩም ጃኮ አራፋትን በሚገባ በተቆጣጠሩት አወል አበደላ እና ምንተስኖት ከበደ የሚመራው የመከላከያ ተከላካይ ክፍል ምንም አስደጋጭ ሙከራ ማድርግ እንዳይችሉ አስገድዷቸዋል።የመከላከያ ተጭኖ የመጫወት ሂደቱ ቀጥሎ በ65ኛው ደቂቃ ላይ ምናልባትም 3 ነጥብ ማግኘት ሚያስችላቸውን ሙከራ በቀኝ መስመር ድንቅ ከነበረው ቴዎድሮስ ተፈሰ እና ዳዊት አስቲፋኖስ ጋር በመሆን ስብሮ የገባው ሳሙኤል ታዬ ጎል ውስጥ ለሚገኘው ምንይሉ ወንድሙ በአግባቡ አድርሶት መንይሉ በግንባሩ ሞክሮት አገባ ሲባል ወንደወሰን ገረመው በድንቅ ሁኔታ አውጥቶበታል። ድቻዎች በዚህ ክፈለ ጊዜ ወስጥ አምረላ ደልታታን በ ዮናታን ከበደ ፣ እሸቱ መናን በዘላለም እያሱ ቀይረው ቢያስገቡም በ71ኛው ደቂቃ ከማዕዘን የተመታውን ኳስ አብዱለስምድ አሊ በግንባሩ ሞክሮ ውደ ውጪ ከወጣችበት ኳስ ውጪ ይህ ነው የሚባል የግብ ዕድል መፍጠር አልቻሉም፡፡መከላከያዎች ያሳኩትን የበላይነት ወደ ጎል ለመቀየር በማሰብ ማራኪ ወርቁን በሳሙኤል ታዬ ቀይረው በማስገባት አና በቴውድሮስ ተፈስ አማካይነት ተጭነው በመጫወት 87ኛው ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የመጣውን ኳስ ተቀይሮ የገባው ማራኪ ወርቁ በግነባሩ ሞክሮ የድቻ ተከላካይ ክፍል እንደምንም ከግብ ክልል ስር አርቀውበታል። ጨዋታው በዚህ መልኩ ምንም ግብ ሳያስተናግድ ለወላይታ ድቻ ከተከታታይ ድል በኃላ ነጥብ የጣለበት ወደ መነቃቃት እየገባ የሚገኘው የስዩም ከበደው መከላከያ ደግሞ ወሳኟን ነጥብ ይዞ የተመለስበት ሆኖ ተገባዷል። የአሰልጣኞች አስተያየት ዘነበ ፍስሀ – ወላይታ ድቻ“ጨዋታችን ዛሬ በፍፁም ልክ አልነበረም። ተጫዋቾቼ የተነጋገርንውን ሁሉ ዛሬ አልተገበሩም። በአጠቃላይ ጥሩ አደለንም፤ በቀጣይ እንድንዘጋጅ ብዙ ነገር ያመላከተን ጨዋታ ነበር። በተለይም መሐል ሜዳ ላይ ፍጹም የበላይነት ተውስዶብናል። ”ስዩም ከበደ – መከላከያ“ጨዋታው ጥሩ ነው ማለት ይቻላል። ነገር ግን ሜዳው እንድትጫወት የሚፈቅድ አይደልም ፤ እንድትጫወት ቀርቶ ኳስ ለመቆጣጠር ያስቸግራል፤ እንደኔ የሚታየኝ ወላይታ ድቻ ለወደፊቱም ራሱ የሜዳ አድቫንቴጁን ያጣል ብዬ አስባለው፤ በተረፈ እኛ የምንፈልገውን አግኝተናል። ከሜዳችን ውጪ ጥሩ ውጤት አግኝተናል ፤ ከነሱ በተሻለ መልኩ የጎል እድል አግኝተን ነበር። ብንጠቀመው ኖሮ ለሚቀጥለው ጨዋታ በራስ መተማመን የሚሰጠን ድል እናስመዘግብ ነበር። “
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/35274
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
818567a19e20a7f95a6d8d8ff704de1d
c4c288d478ccce296b87ec8159dfebf3
ኮሮናቫይረስ፡ የአፍሪካ አየር መንገዶች በዚህ ዓመት ብቻ 2 ቢሊዮን ዶላር ይከስራሉ
በዚህም ሳቢያ የአፍሪካ አየር መንገዶች ባለፈው ታኅሳስ ወር ከተገመተው 200 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ባሻገር በአጠቃላይ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ እንምደሚያጡ ተነግሯል። በዓለም ደረጃ የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ 84 ቢሊዮን ዶላር ይከስራል ተብሎ ተገምቷል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አገራት ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ በሆነው በአየር ትራንስፖርት እገዳ ምክንያት ዘርፉ ክፉኛ ተዳክሟል። በተጨማሪም በአፍሪካ ውስጥ በአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ የሦስት ሚሊየን ሰዎች የሥራ ዕድልም ስጋት ውስጥ መውደቁም ተነግሯል። አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ አየር መንገዶች ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ተጨማሪ አውሮፕላን ለመግዛት በሂደት ላይ የነበሩ ሲሆን፤ አሁን ግን ግዢዎችን የመሰረዝና የማዘግየት ውሳኔያቸውን እያስታወቁ ነው። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ኤርባስ የተባለው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ አንዳንድ አየር መንገዶች አዘዋቸው በሂደት ላይ በነበሩ አውሮፕላኖች ምክንያት ክስ እንደሚመሰረት አስታውቋል። በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ ብዛት ያለው አውሮፕላን ከኤርባስ አዞ የነበረው አዲሱ የናይጄሪያ አየር መንገድ ግሪን አፍሪካ ኤር የተባለው ሲሆን 50 ኤ220 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ነገር ግን በወረርሽኙ በተፈጠረው ችግር ምክንያት በተፈጠረ የገንዘብ ችግር ምክንያት እየተንገዳገደ ያለው አየር መንገዱ እንኳን አዲሶቹን አውሮፕላኖች ለቀበል ይቅርና በሥራው ላይ ለመቆየት ሲል የተወሰነ ንብረቱን በመሸጥ ላይ ይገኛል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
f53d309c44080f57e2c665a5b61def55
549407ad91a6c1c44421fd47e6b8929b
የአገር አቀፍ የማዳበሪያ ግዥ መዘግየት ሥጋት ፈጠረ
የአገር አቀፍ የማዳበሪያ ግዥ ከአንድ ወር በላይ በመዘግየቱና የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት በጨረታው ሒደት ላይ ውሳኔ ባለመስጠታቸው፣ በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ መዘግየት እንዳይከሰት ሥጋት ተፈጠረ፡፡መስከረም 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የግብርና ሥራ ኮርፖሬሽን በተከፈተ ዓለም አቀፍ የማዳበሪያ ግዥ ጨረታ ስድስት ዓለም አቀፍ የማዳበሪያ አቅራቢ ኩባንያዎች ተሳትፈው ነበር፡፡ ኮርፖሬሽኑ 1.25 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የተለያዩ ማዳበሪያዎች ለመግዛት ባወጣው በዚህ ጨረታ፣ ከስድስቱ አቅራቢዎች ውስጥ ኦሲፒና አግሪ ኮሞዲቲ የሚባሉ ሁለት ኩባንያዎች በአጠቃላይ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ አነስተኛ የመጫረቻ ዋጋ አቅርበው ነበር፡፡በዚህም መሠረት ኦሲፒ 625 ሺሕ ሜትሪክ ቶን መጠን ላላቸው የተለያዩ ዓይነት ማዳበሪያዎች 240 ሚሊዮን ዶላር አነስተኛ ዋጋ ሲያቀርብ፣ ቀሪውን ደግሞ አግሪ ኮሞዲቲ የተባለው ኩባንያ 180 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡በጨረታው የተወዳደሩት ስድስቱም አቅራቢዎች ያስገቡትን የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነዶችን ሲገመግም የነበረው የኮርፖሬሽኑ የጨረታ ቡድን፣ በመጨረሻ ውሳኔው አቅራቢ ኩባንያዎችን መርጦ እንደነበር የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡የተመረጡት ኩባንያዎች የብቃት ማረጋገጫ ቦንድ ከፍተው ማዳበሪያውን ለማቅረብ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም፣ የጨረታው ሒደት መቀጠል ሳይችል ቀርቷል፡፡ ኮርፖሬሽኑም በቅርቡ ከሥልጣናቸው በተነሱት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ይመራ ለነበረው የግብርናና የእንስሳት ሀብት ሚኒስቴር በጨረታው ላይ ውሳኔ እንዲሰጥበትና የግዥው ሒደት በአፋጣኝ እንዲጀመር ቢጠይቅም፣ እስካሁን ምንም ዓይነት ውሳኔ አለመሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም የጨረታ ሒደቱን በተመለከተ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በአስቸኳይ እንዲያስወስን ቢጠበቅም፣ ይኼን ማድረግ እንዳልቻለ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ኮርፖሬሽኑ የጨረታውን ሒደት በሳምንት ውስጥ አጠናቆ የነበረ ቢሆንም፣ በተፈጠረው የውሳኔ ክፍተት ምክንያት ለበልግ ወቅትና ለቀጣይ የምርት ወራት ቀድሞ ተገዝቶ ወደ አገር ውስጥ መግባት የነበረበት ማዳበሪያ ግዥ ዘግይቷል፡፡እስካሁን ለማዳበሪያ ግዥው የተመረጡ ኩባንያዎች ማቅረብ መጀመር ነበረባቸው ሲሉ የተናገሩ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ የመንግሥት ኃላፊ፣ የውሳኔው መዘግየት ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ይዞ ሊመጣ ይችላል ሲሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡አንደኛ ጨረታው ሲከፈት አቅራቢዎቹ የሰጡት ዋጋ ማብቂያው ላይ ሊደርስና በዓለም አቀፍ የማዳበሪያ ዋጋ ጭማሪ ሊያሳይ ስለሚችል፣ በዚህ ሳቢያ አቅራቢዎቹ የዋጋ ማስተካከያ ሊጠይቁ ይችላሉ ሲሉ ኃላፊው ሥጋታቸውን ተናግረዋል፡፡‹‹ይህ ደግሞ መንግሥትን ተጨማሪ ወጪ ሊያስወጣው ይችላል፤›› ሲሉ ኃላፊው አክለዋል፡፡በዋናነት የግዥው መዘግየት ከየካቲት ወር ጀምሮ አገር ውስጥ ገብቶ ለአርሶ አደሮች መከፋፈል ያለበትን ማዳበሪያ በማስተጓጎል፣ በእርሻ ሥራው ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ አይቀርም ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡በተለይም ደግሞ ለበልግ ወቅት ለገበሬው መከፋፈል ያለበት የማዳበሪያ ሥርጭት እንዳይዘገይ ሥጋት ተፈጥሯል፡፡
ቢዝነስ
https://www.ethiopianreporter.com/article/13694
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
116c4e3d4058139147339d0a85ee9711
4041a156b68a81e99d5288fa70045c16
የቅማንት ኮሚቴ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ ነኝ አለ
ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. የአማራ ክልልና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከማዕከላዊና ከምዕራብ ጎንደር ዞኖች የተውጣጡ የአማራና የቅማንት ተወላጆች በጭልጋ ወረዳ ባደረጉት ውይይት፣ የቅማንት ማንነትና ራስ አስተዳደር ይከበርልኝ ኮሚቴ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የአማራ ክልል መገናኛ ብዙኃን ድርጅት እንደዘገበው፣ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ውይይት፣ የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ ማሞ የቅማንት ኮሚቴ ያቀረበው ጥያቄ ለሁለቱ ማኅበረሰቦች ግጭት መንስዔ መሆን ስለማይገባው ለድርድር ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡ ሰላም በፍፁም ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥለት እንደማይገባም አስረድተዋል፡፡‹‹በግጭት ምክንያት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት መቆም አለበት፡፡ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እስኪፈታም በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር ከሚፈልጉ ማንኛውም አካላት ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነን፤›› ብለው፣ ሁለቱ ወንድማማች ማኅበረሰቦች በምንም ዓይነት ሁኔታ መጋጨት አይገባቸውም ሲሉ አክለዋል።የክልሉ መንግሥት ቀደም ሲል ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ መግለጫ ማውጣቱ፣ እንዲሁም የሕዝብ ጥያቄ በሕዝብ ይሁንታ መፈታት አለበት የሚሉ ሐሳቦች ኮሚቴው ተቀብሎት እንደነበር በማስታወስ፣ ‹‹እኛና እናንተ ሳንባባል በሕዝብና በመንግሥት መካከል ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ውይይት መጀመሩ አስፈላጊ ስለሆነ፣ ኮሚቴው የቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ለውይይትም ዝግጁ ነው፤›› ብለዋል።ነገር ግን በውይይቱ ወቅት የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ እናራምዳለን የሚሉ ሁለት ኮሚቴዎች መኖራቸውን፣ እነሱም በሕዝቡ መካከል ልዩነት እየፈጠሩ በመሆናቸው ለሰላማዊ ውይይት እንቅፋት አይሆንም ወይ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ፍቃዱ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹የቅማንት ኮሚቴ ነን የሚሉት በሥነ ምግባር ችግር ያሰናበትናቸው ግለሰቦች ናቸው። በሰላማዊ ሒደቱ ላይ እንቅፋት ሊፈጥሩ አይችሉም፡፡ አንድ ሕጋዊ ኮሚቴ ነው ያለው። እሱም እኔ በሰብሳቢነት የምመራው ነው። ሕዝቡም ዕውቅና ሰጥቶት ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል፤›› ሲሉ አስረድተዋል።በውይይቱ ወቅት የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ባደረጉት ንግግር፣ የአማራና የቅማንት ማኅበረሰቦች ቤተሰብ እንደሆኑና በቤተሰብ መካከል የተፈጠረ ችግር በቤተሰቡ ካልፈታ በቀር ማንም ሊፈታው አይችልም ብለዋል።በግጭት ማንም አሸናፊ መሆን እንደማይችልና ያለፈው ላይመለስ ለዛሬና ለነገ ሰላም ሁሉም የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸው፣ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሰላማዊ ውይይቶች በተለየ ይኼኛው ወደ ሰላም ሊያደርስ ያስችላል ተብሎ የታሰበ የመጀመሪያ ዙር ውይይት እንደሆነ አስረድተዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ሰላማዊ ውይይቱ ፍሬያማ እንዲሆን ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጡ ምሥጉንና ሚዛናዊ የአገር ሽማግሌዎች የተለያዩ ሥራዎችን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ማስታወሳቸው ተገልጿል። የተጀመረው ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የታሰሩ ሰዎች በምሕረት አዋጁ እንዲለቀቁ፣ እንዲሁም የተፈናቀሉ ወገኖች ዘላቂ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።በአማራና በቅማንት ማኅበረሰቦች መካከል በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ ግጭቶች በርካቶች መገደላቸውና መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በቅርቡ አውጥቶት በነበረው መግለጫ ከግጭቶቹ በስተጀርባ ሦስተኛ ወገን እንዳለ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
ፖለቲካ
https://www.ethiopianreporter.com/article/17213
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
6db31166cf3d45413e7108e80a88ba86
f65ae02a623ee9a92f6d69ed1a22c7d4
ሮበርት ሙጋቤ እና አራፕ ሞይ: አንጋፋዎቹ የአፍሪካ መሪዎች ሲታወሱ
እኚህ በአፍሪካ ታሪክ ትልቅ ቦታ ያላቸው መሪዎች በጸረ ቅኝ ግዛት ፖለቲካ ተሳታፊ ነበሩ፤ ሙጋቤ የትጥቅ ትግል ቢያደርጉም ሞይ ግን ጠመንጃ አላነሱም። ሁለቱም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር የነበሩ አገራትን የመሩ ሲሆን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ከነጭ ሰፋሪዎች ጋር ሲታገሉ ቆይተዋል። የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤጥም ሁለቱን መሪዎች ታደንቃቸው እንደነበር ይገለጻል። ኬንያንም ሆነ ዚምባብዌን በአካል ሄደውም ጎብኝተው ነበር። • የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ማን ነበሩ? • የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ አረፉ ሞይና ሙጋቤ ከገጠሪቱ የአገራቸው ክፍል ያደጉና ከብት በመጠበቅ ልጅነታቸውን ያሳለፉ መሆናቸው ከሚያመሳስሏቸው ነገሮች መካከል ይጠቀሳሉ። ለመሆኑ እነዚህን መሪዎች የሚያመሳስሏለቸው ሌሎች ነገሮች ይኖሩ ይሆን? የክርስትና ተጽዕኖ ሁለቱም መሪዎች ያለ አባት ሲሆን ያደጉት በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተት በሚሽነሪዎች ለመሙላት ጥረዋል። ሞይ መንፈሳዊ መጠለያ ፍለጋ በአንድ የፕሮቴስታንት ሚሽነሪ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በዛውም ነው የክርስትና ስማቸው ዳንኤልን ያገኙት። ሙጋቤ ደግሞ በነጮች ቁጥጥር ስር በነበረ የካቶሊክ ሚሽነሪ ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን ጀሮም ኦሂያ የተባሉ የሃይማኖት አባት ጋርም ጠበቅ ያለ ግንኙነት እንደነበራቸው ይታወቃል። ሁለቱም መሪዎች በመጀመሪያ የተሰማሩበት የስራ ዘርፍ መምህርነት ሲሆን የተሳካላቸው መምህራን ነበሩ። በፖሊሲዎቻቸውም ቢሆን ትምህርት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጡ ነበር። ሞይ በኬንያ ከሚታወቁበት ነገር አንዱ በትምሀርት ቤት ያስጀመሩት ነጻ የወተት አቅርቦት ሲሆን ሙጋቤ ደግሞ ለሁሉም ዜጎች ትምህርት ነጻ እንዲሆን በማድረግ ሃገሪቱ ያላትን የተማረ የሰው ኃይል ቁጥር ከፍ ማድረግ ችለዋል።። ፖለቲካዊ ጭቆና ሞይ በተለይም ደግሞ በጎርጎሳውያኑ ከ1982ቱ መፈንቅለ መንግስት በኋላ ተቃዋሚዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃን ወስደዋል። በጊዜውም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል፤ እንግልትና ስቃይ ተፈፅሞባቸዋል። በዛውም ሙሉ በሙሉ ስልጣን በእጃቸው እንዲሆን አድርገዋል። ሙጋቤም ቢሆን ተቃዋሚዎች ላይ ፈርጠም ያለ ክንዳቸውን በማሳረፍ ይታወቃሉ። ዚምባብዌያውያን ያለምንም ምክንያት ይታሰሩና ይሰቃዩ ነበር። ሙጋቤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተቺዎቻቸውን ዝም ለማሰኘት በርካታ እርምጃዎችን ወስደዋል። ልክ እንደ ሞይ ሁሉ ሙጋቤም ከታዋቂ ፖለቲከኞች ሞት ጋር ስማቸው አብሮ ይነሳል። ሙጋቤ በሌላም አንድ አሰቃቂ ነገር ይወነጀላሉ። 'ጉኩራሁንዲ' ተብሎ የሚጠራውና የንዴቤሌ ቋንቋ ተናጋሪዎችን የማጥፋት ዘመቻ አቀነባብረዋልም ይባላል። ዚምባብዌ ነጻነቷን ካገኘች ጥቂት ዓመታት በኋላ በተደረገው ይህ ዘመቻ የንዴቤሌ ቋንቋ ተናጋሪዎች ተገድለው በማእድን ማውጫ ጉድጓዶች ውስጥ ተቀብረዋል። • ለዘመናት በስልጣን ላይ ያሉት ስድስቱ መሪዎች • ኦማር አል-በሽር: ከየት ወደየት? ኬንያ ከእንግሊዝ ነጻነቷን ማግኘት ተከትሎ በሺዎች ሄክታር የሚቆጠር መሬት በመንግሥት እጅ ገብቶ ነበር።ፕሬዝደንት ጆሞ ኬንያታም ይሁን ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ መሬቱን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለህዝቡ ለማከፋፈል ፍላጎቱ አልነበራቸውም። እንደውም በኬንያ እጅግ ሰፋፊና በርካታ መዋእለ ነዋዮች የፈሰሱባቸው መሬቶች የባለስልጣናት ንብረት ናቸው። በሌላ በኩል ሙጋቤ ግን በነጭ ዚምባብዌያውያን ገበሬዎች ተይዘው የነበሩ መሬቶችን በመንጠቅ ለሀገሬው ዜጋ ለማከፋፈል ጥረት አድርገዋል። ነገር ግን በዚሁ ምክንያት የእርሻ ስራዎች በመስተጓጎላቸው አገሪቱ የምግብ እጥረትና ኢኮኖሚ መላሸቅ አጋጥሟት ነበር። ሙጋቤ...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
94af3956578aa48d37a22e1780533ab6
b3e686ae52ff4f90afe545ec27fa1d1d
በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ15 ሺህ በለጠ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ አህጉር በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ15 ሺህ መብለጡ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሚሊየን 900 ሺህ መብለጡን የሚያሳየው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፤ ከእነዚህም ውስጥ 15 ሺህ 346 በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ናቸው።በዓለም አቀፍ ደረጃ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ119 ሺህ ሲበልጥ፤ በአፍሪካም በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ830 ተሻግሯል።በአፍርካ ከ2 ሺህ 940 በላይ ሰዎች ደግሞ ከወረርሽኙ ማገገማቸውንም ነው የዩኒቨርሲቲው መረጃ የሚያመላክት ሲሆን፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ450 ሺህ በላይ ሰዎች አገግመዋል።ከአፍሪካ አህጉር 2 ሺህ 272 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የያዘችው ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን፤ በሀገሪቱ በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ውስጥ የ27 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 410 ሰዎች ማገገማቸውም ነው የተገለፀው።ግብፅበ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት 2 ሺህ 190 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ ከእነዚህም 589 ሲያገግሙ፤ 164 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።በአልጄሪያም 1 ሺህ 983 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ 313 ሰዎች ህይወታቸው አልፎ፤ 601 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመጣ ኬንያ 208 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ያስታወቀች ሲሆን፥ ከእነዚህም 40 ሰዎች ሲያገድሙ፤ 9 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።በጂቡቲ 298 ሰዎች፣ በኤርትራ 34 ሰዎች፣ በሶማሊያ 60 ሰዎች፣ ሱዳን 29 ሰዎች እንዲሁም ደቡብ ሱዳን 4 በቫይረሱ መያዛቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።በኢትዮጵያም እስከ ትናንትናው እለት ባለው መረጃ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 74 የደረሰ ሲሆን፥ ከእነዚህም 14 ሲያገግሙ፤ 3 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%89%a0%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8b%ab%e1%8b%99-%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%89%81-2/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
0a3786b39a4b807301295e5e9670c05e
5fd4f2dc245ec82e3c7998dcd74cdc2f
የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ፓርቲዎች በቅርበት አብረው እንዲሠሩ ለማስቻል ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው-ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረጉ ውይይቶች ፓርቲዎች በቅርበት አብረው እንዲሠሩ ለማስቻል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት የምክክር መድረክ አካሂደዋል።በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተሳታፊነት ተገኝተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ውይይቱን አስመልክቶ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ዛሬ በመቀጠሉ ደስ ብሎኛል” ብለዋል።እነዚህ ውይይቶች የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅርበት አብረው እንዲሠሩ፣ ለወቅታዊ ጉዳዮች የጋራ መፍትሔ እንዲያበጁ፣ እንዲሁም ለሀገራችን እና ለሕዝባችን የሚጠቅም የዕድገት እና የብልጽግና የጋራ ራእይን እንዲያዘጋጁ  ለማስቻል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል።በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው የምክክር መድረክ ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊነት በኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አደረጃጀት ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫና የማያግባቡን ታላላቅ አጀንዳዎች በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች የተወያዩት።ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊነት በኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ፖለቲካ አደረጃጀት ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው በሚሉት አጀንዳዎች ላይ የመወያያ ጽሁፎች ቀርበዋል።ፓርቲዎቹ ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊነት በኢትዮጵያ በሚል ባደረጉት ውይይት ወደ ኋላ በመመለስ ከህገ መንግስት በፊት ኢትዮጵያ ትተዳደርበት የነበረው ፍትሐ ነገስትን አንስተው መክረዋል።እንዲሁም በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን ከፍትሐ ነገስት ወደ ህገመንግስት ሽግግር የተደረገበት ጊዜና የህገመንግስቱ ደካማና ጠንካራ ጎኖች በውይይቱ ተነስተዋል።በ1983 ዓ.ም የተደረገውን የመንግስት ለውጥ ተከትሎ የመጣው ህገ መንግስትም ምን ዓይነት ጠንካራ ጎኖች ነበሩት በሚለው ላይ ትኩረት ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።በዚህም ህገ መንግስቱ ለብሄር ብሄረሰቦች ዕውቅና መስጠቱ፣ የስልጣን ገደብ ማበጀቱ እና ሌሎችም ተነስተውበታል።ከዚህ ባለፈም ወደ ተግባር የመውረድ ችግር ነበረበት በሚል የነበረበት ውስንነት በውይይቱ ወቅት ተጠቅሷል።እንዲሁም ነጻ የዴሞክራሲ ተቋማት ላይ ጣልቃ መግባት ከሚጠቀሱ ውስንነቶች መካከል መሆናቸውም ነው በመድረኩ የተነሳው።በጥቅሉ ከ1931 እስከ 1983 ዓ.ም የነበሩት ህገ መንግስቶች የራሳቸው የሆነ መልካምና ውስንነቶች ነበሩባቸው ተብሏል።እንደ ፍትሐ ነገስት፣ የገዳ ስርዓት እንዲሁም ሌሎች የሚጠቀሙባቸው ባህላዊ ስርዓቶች ያለማካተታቸው እንደችግር ተነስቷል።የግለሰብ መብትን መሰረት ያለማድረጋቸው፣ የቅቡልነት ችግር፣ ህገ መንግስቱን በማፀደቁ ሂደት የነበረው የአሳታፊነት ጉድለት እንደ ችግር ተጠቅሰዋል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8d%93%e1%88%ad%e1%89%b2%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8c%88%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%8c%89%e1%8b%b3%e1%8b%ae%e1%89%bd-%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%8a%a8%e1%88%a9/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
b8b2f9840a11b1799bb7377779a07066
24bf591ba7c222068a91c2f583424960
ለእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት የሚውሉ 122 ተሽከርካሪዎች በድጋፍ ተገኙ
አዲስ አበባ፡- የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የተለየዩ ክልሎች ተግባራዊ እየተደረገ ላለው የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ፕሮጀክት የሚውሉ 122 ተሽከርካሪዎችን በድጋፍ ሰጠ፡፡ የእንስሳትና የአሳ ሃብት ልማት ፕሮጀክት ብሄራዊ አስተባባሪ ዶክተር ቶማስ ቸርነት በግብርና ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ የተሽከርካሪ ርክክቡ በተካሄደበት ወቅት እንደገለፁት፤ ተሽከርካሪዎቹ በዋናነት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሚደረግባቸው ስድስት ክልሎችና ሰባት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤቶች ይከፋፈላሉ፡፡ ይህም ከዚህ ቀደም ተደራሽ ያልነበሩ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡ ለተሽከርካሪዎቹ ግዥ 101 ሚሊዮን ብር በላይ በአለም ባንክ ወጪ መደረጉን የገለፁት ዶክተር ቶማስ፤ የተሽከርካሪዎቹ ድጋፍ በተለይም በደጋና በወይና ደጋ አካባቢዎች ለተደራሽነት አዳጋች በሆኑ ቦታዎች ላይ ሰፍረው የሚገኙ አርሶአደሮችንና አርብቶአደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ይህም ከዚህ ቀደም ፕሮጀክቱን ለመተግበር የሚወስደውን ጊዜና ጉልበት የሚቀንስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ እንደ ዶክተር ቶማስ ማብራሪያ፤ የእንስሳትና የአሳ ሃብት ልማት ፕሮጀክቱ እየተተገበረ የሚገኘው በስድስት ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 58 ወረዳዎች እና 1ሺ755 ቀበሌዎች ውስጥ ሲሆን 8 ነጥብ 8 ሚሊዮን አርሶ አደሮችንንና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ በዋናነትም የስጋ፥ ወተት፥ አሳና ዶሮ ሃብት ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችሉ አሰራሮችን፥ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው ስድስት ዓመታት ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ የሆኑ አርሶአደሮችንና አርብቶአደሮችን የአመጋገብ ስርዓት ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን አስተባባሪው ገልፀው፤ ከዚሁ ጎን ለጎንም ለበርካታ ሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጠርም አስገንዝበዋል:: ይህም የገቢ አቅማቸውን ከማሳደግ ባሻገር በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ በ50 ዓመታት ውስጥ የሚከፈል 176 ሚሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ በብድር መገኘቱን የገለፁት ዶክተር ቶማስ፤ በኢትዮጵያ መንግስትም 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር መበጀቱን ጠቁመዋል:: በተጨማሪም ተጠቃሚዎች በጉልበታቸው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የሚያደርጉበት ፕሮጀክት በመሆኑ የባለቤትነት ስሜት እንዲኖራቸው የሚያደርግ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሀሰን በበኩላቸው፤ በድጋፍ የተገኙት ተሽከርካሪዎች ዘመናዊና የፍጥነት መቆጣጠሪያ ጂፒኤስ የተገጠመላቸው በመሆኑ ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እንዲተገበርና ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው አስገንዝበዋል፡፡ በተለይም ከዚህ ቀደም በተሽከርካሪ እጥረት ምክንያት በእንስሳት ጤና ላይ ይደርስ የነበረውን ጉዳት ለመቀነስ የላቀ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ አዲስ ዘመን ቅዳሜ ታህሳስ 4/2012 ማህሌት አብዱል
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=24147
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
3aad19d396298f2e35148154c4700bb8
ef0dee01f04a59f6060075f0030e5219
ህግ አስፈጻሚ
ህግ በጥቅል ትርጉሙ የደንቦችና የመመርያዎች አተገባበር ስርዓት ሲሆን ÷በህብረተሰቡ እንዲሁም በመንግሥት የሚወጡ ደንቦችና መመርያዎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ የሚያስገድድ ስርዓት ነው ። የህግ ትክክለኛ ብያኔ ለዘመናት ያከራከረ ጉዳይ ሲሆን ÷ የተለያዩ የአስተሳሰ ጎራዎች ÷ "ሳይንሳዊና ጥበባዊ የፍትህ አሰጣጥ ነው" ብለው ይጠሩታል ። ለምሳሌ መብራት ሐይል ፖለቲካ ሕግከ ስነ ዜጋ መጸሐነ ረ.ሞ.አ
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
21b3e55173ca6f655334c3c4533bbda8
94e540e5674d0b7800bf19b3d0d4b29d
ኡጋንዳ ከ1ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን መቀበሏን ገለጸች
ኡጋንዳ ባለፉት 12 ወራት ብቻ  የተቀበለቻቸው ስደተኞች ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ መድረሳቸው ተመልክቷል ፡፡ይህም ቀደም ሲል ከመላው ዓለም ስደተኞችን በከፍተኛ ቁጥር ሲቀበሉ ለነበሩት የአውሮፓ ሀገራት እፎይታን ፈጥሯል እየተባለ ነው፡፡ከአንድ ዓመት በፊት ግሪክና ቱርክ ነበሩ በርካታ ስደተኞን በመቀበል በዓለም ከሚገኙ ሀገራት ጫና   የስደተኞች ጎርፍ በርትቶባቸው  የነበረው፡፡በዚህም ምክንያት የታዋቂ ጋዜጦች የፊት ገፅ ማድመቂያ ፤ የበርካታ መገናኛ ብዙሃንም ርዕስ የነበረው እንደነ ግሪክና ቱርክ ያሉት ሀገራት ይህን ያህል ስደተኞችን ተቀብለው እያስተናገዱ ይገኛሉ የሚለው ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡በሚሊየን የሚቆጠሩ ስደተኞች ሶሪያን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ በእርስ በእርስ ጦርነት እየታመሱ ከሚገኙ ሀገራት ስደተኞች ወደ አውሮፓ ሲፈልሱ መቆየታቸውም የቅርብ ጊዜ የሚታወስ  ነው፡፡ስደተኞችን በመቀበል ረገድ እያከናወነች ያለችውና ለዚህ ስራዋ ግን ብዙም ዕውቅና ያልተቸራት ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኡጋንዳ በታሪኳ ደርሳበት የማታውቀውን የስደተኞች ቁጥር ለማስተናገድ ተገዳለች ይላል የኤቢሲ ኒውስ ዘገባ፡፡ባለፉት 12 ወራት ብቻ ሀገሪቱ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ስደተኞችን ተቀብላ ለማስተናገድ ተገዳለች፡፡ይህ ማለት በተጠቀሰው ዓመት ግሪክም ሆነ ቱርክ ብሎም የትኛውም ሀገር ይህን ያህል ቁጥር ያለው ስደተኛን በአንድ ዓመት ውስጥ  አላስተናገደም ማለት ነው፡፡ጦርነት ፣ ድርቅና ግጭትን በመሸሽ በየቀኑ ከ2 ሺህ በላይ ዜጎች ደቡብ ሱዳንን ከመሳሰሉ ጎረቤት ሀገራት ድንበር አቋርጠው የኡጋንዳን  ይገባሉ ።በተለይም በእርስ በእርስ ግጭት ስትታመስ በቆየችው ደቡብ ሱዳን  የዕለት የምግብ እርዳታ የሚያሻቸው ሰዎች ቁጥር ከ6 ሚሊየን ማሻቀቡ ነው የተነገረው፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት እንደሚጠቁመው በደቡብ ሱዳን ከ276 ሺህ በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጠ ነው፡፡በደቡብ ሱዳን ከ5 ሺህ ሰዎች አንዱ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ሳቢያ በየቀኑ የሚሞት ሲሆን÷ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ 30 በመቶ የሚሆነውም ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጠ ነው፡፡ይህን ተከትሎ ከደቡብ ሱዳንየሚመጡ ስደተኞች ቁጥር ከማሻቀቡ የተነሳ ቀደም ሲል በዓለም ካርታ ላይ ከነጥብ ብዙም ያልዘለለ ስፍራን የያዘውና በኡጋንዳ ሰሜናዊ ግዛት የሚገኘው የፓላብክ መንደር አሁን ላይ ከ170 ሺህ በላይ ስደተኞች መጠለያ ለመሆን ተገድዷል፡፡ሌላውና ቀደም ሲል በስደተኞች በመጣበቡ ምክንያት ተዘግቶ የቆየው ቢዲ ቢዲ የተሰኘው መንደርም መጠጊያ ያጡ ከ250 ሺህ ስደተኞችን በእቅፉ ይዞ ይገኛል፡፡የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኡጋንዳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞች በማስተናገድ አርአያነት ያለው ተግባር እያከናወነች መሆኗን ጠቅሰው፣አለምአቀፉ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለስደተኞች እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡የኡጋንዳ መንግስት በበኩሉ ሀገሪቱ ለምታከናውነው የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴዎች ከ8 ቢሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡ስደተኞችን  በመቀበልና በማስተናገድ  ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ተጠቃሽ ሀጋራት ናቸው፡፡ 
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/32998/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
ed4663d5ceb3a6a2847edfee3dc2fb05
78b30c57700d47107905a18706f3f1e1
የዘር ጥላቻን የሚያራግቡ የፌስቡክ ጓደኞቻችንን ምን እናድርጋቸው?
ቼሪ ዊልሰን ይህን ሰው እንምከረው ወይስ "እንቦልከው"? እኔን አሁን መከራ እያበላኝ ያለ አንድ አብሮ አደጌ አለ። የፌስ ቡክ ጓደኛዬ ነው። በዘር ጥላቻ የተለከፈ ነው። የእርሱን የፌስቡክ ሰሌዳ ጭራሽ ባላየው ደስ ይለኛል። ቶሎ ቶሎ ገረፍ አድርጌ ለማለፍ እሞክራለሁ። ይህ ሰው አሁን የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ ዘረኝነቱ ብሶበታል። ብዙ ሰዎች ስለእርሱ ስነግራቸው "አንቺ ደግሞ ቀለል አድርጊው እስኪ፤ አታካብጂ" ይሉኛል። ለምን ቀላል ነገር አድርገው እንደሚያስቡት አይገባኝም። ለእኔ እጅግ ዘረኛ አስተያየቶችን ከፌስቡክ ጓደኞቼ ሰሌዳ ላይ ስመለከት የሆነ የማቅለሽለሽ ስሜት አለው። ከፌስቡክ ውጪም እንዲሁ ነው። ሰዎች በተለያየ መንገድ ነው ዘረኝነታቸውን የሚያንጸባርቁት፤ አውቀውም ሆነ ሳያውቁት። ለምሳሌ እዚህ እንግሊዝ ውስጥ ብዙ ሰዎችን ስተዋወቅ "የእኔ ቆንጆ ከየት ነሽ?" ይሉኛል፤ ልክ እንደ ብርቅዬ እንሰሳ እየተመለከቱኝ። "ከዚሁ ከእንግሊዝ" እላቸዋለሁ። "ማለቴ የምር ከየት ነሽ. . . ?" ይሉኛል። በሌላ ቋንቋ (የቆዳ ቀለምሽን አይተሽዋል? ፈረንጅ አይደለሽም እኮ፤ ይህ የፈረንጅ አገር ነው።) እያሉኝ ነው። ይህ ዓይነቱ አስተያየት እኔና እህቴ ድሮ ወደ አንደንዳንድ የለንደን ቡና ቤቶች መሄድ ለምን እንፈራ እንደነበር ያስታውሰኛል። ቡና ቤቶቹ ውስጥ ለመስተናገድ ስንገባ "የእኛ ደንበኞች እኮ በብዛት የአውሮፓ ጎብኚዎች ናቸው" ይሉናል። ምን ማለታቸው ነው? (ጥቁሮች እባካችሁ አትምጡብን እያሉን ነው) ሌላው ግርም የሚሉኝ ጸጉሬን የሚነካኩ ሰዎች ናቸው። እኔምለው? የሆነች የቤት ውስጥ ድመት ነው እንዴ የምመስላቸው? ዘረኝነት አንድን ጥቁር "አንተ ኔግሮ!" ብሎ መጥራት ብቻ የሚመስላቸው አሉ። ዘረኝነት እጅግ ውስብስብና ጥልቅ ጉዳይ መሆኑን ለምን አይረዱም? አሁን እዚህ ፌስቡኬ ላይ እየመጣ ዘረኛ አስተያየት የሚሰጠውን ጓደኛዬን ምን እንደማደርገው ግራ ገብቶኛል። ለእርሱ ዝቃጭ አስተያየት መልስ መስጠት በራሱ ጉልበትን መጨረስ ሆኖ ይሰማኛል። ግን ደግሞ እንዲህ ሲንዘባዘብ ዝም ማለትም አግባብ መስሎ አልተሰማኝም። ዝም ሲባል ትክክል የሆነ ቢመስለውስ? በመጨረሻ አንድ ነገር ለማድረግ ወሰንኩ። ከዚያ በፊት ግን አሁን የምፈልገው "አንፍሬንድ" የሚለውን ቁልፍ ልጫን ነው ወይስ ምላሽ ልስጠው? በሚል ከእራሴ ጋር ተሟገትኩ። የማኅበራዊ ሥነልቦና አዋቂ ዶክተር ኬዎን ዌስት እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎች ግለሰቡ ምን ማሳካት ነው የፈለገው በሚለው ላይ የሚወሰኑ ነው የሚሆነው ይላል ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ምክሩን ሲለግስ። "ጤናሽን መጠበቅ ከፈለግሽ ለእንዲህ ዓይነት የፌስቡክ ጓደኞችሽ ባትመልሺ ይመረጣል። ለእነርሱ ምላሽ ብትሰጪ ጨጓራሽን ይበልጥ ይልጡታል።" ". . .ነገር ግን ዓላማሽ ነገሮችን ቀስበቀስ እንዲረዱና ባንቺ ጫማ ውስጥ ሆነው ሁኔታዎችን እንዲያገናዝቡ ከሆነ፤ መልስ መስጠቱ ክፋት የለውም።" ". . . እርግጥ ነው እንደነዚህ ዓይነት ዘረኞች ባንቺ አስተያየት ዘረኝነታቸውን እርግፍ አድርገው ይተዋሉ ማለት አይደለም። ነገር ግን መባል ያለበትንና መባል የሌለበትን ነገር እያወቁ እንዲመጡ ምክንያት ትሆኛቸዋለሽ።" ይህ የዶክተር ኬዎን ምክር ልክ ሊሆን ይችላል። እኔ ፌስቡክ ላይ አስተያየት ስሰጥ ሁልጊዜም "ጀመረሽ ደግሞ ይቺን የዘር ጨዋታ ልታመጫት ነው?" ይሉኛል። ሌሎች ጓደኞቼን በነገሩ እንዲያማክሩኝ ጠየቅኳቸው። "ኧረ ለመሆኑ ምንድነው የምታደርጉት? ዘረኛ ሰው ፌስቡክ ላይ ሲገጥማችሁ? አልኳቸው።" አንዷ ጓደኛዬ አሊሻ ስታንዲንግ 27 ዓመቷ ነው። አሊሻ "ለዘረኛ አስተያየቶች ምላሽ መስጠት ጀመሬ ነበር። የሚገርምሽ እየባሰባቸው ሄደ" አለችኝ።...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
010e6512a61916b157d259752081f912
4af8fac2c5614ccdaf47c41c8db12e66
የሱዳን አብዮት የፈነዳበት ሁለተኛ ዓመቱ እየታሰበ ነው
በዳቦ ዋጋ መናር ምክንያት ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን እንዲነሱ ያደረገው የሱዳን አብዮት ሁለተኛ ዓመቱ በተለያዩ ስሜቶች እየታሰበ ነው፡፡ ከዛሬ ሁለት ዓመት ወዲህ ፕሬዝዳንት አልበሽርን በመጣል አዲስ የሽግግር መንግስት የተቋቋመ ሲሆን ወታደሩንና ሲቪሉን የሚወክሉ መሪዎች ሀገሪቱን እያስተዳደሩ ነው፡፡ ዛሬ ካርቱምን ጨምሮ በሱዳን የተለያዩ ከተሞች በተካሔዱ ሰልፎች በአንድ ወገን አብዮቱን የሚደግፉ አካላት በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎችም ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ አብዮቱን በመደገፍ ሰልፍ የወጡ ሰልፈኞች የአብዮቱ ዓላማ ግን መስመሩን መሳቱን በመጥቀስ ቁጣቸውን አሰምተዋል፡፡ የኑሮ ውድነት እና የኢኮኖሚ ቀውስን በመቃወም ከሁለት ዓመት በፊት አብዮት ቢፈነዳም እነዚህን ችግሮች ከመቅረፍ አንጻር አብዮቱ ምንም አልፈየደም በሚል የተቃውሞ ድምጾች ተስተጋብተዋል፡፡ በሱዳን ያለው የኑሮ ውድነት ፣ ከፍተኛ የዳቦ እጥረት እና የሀገሪሩ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ ከአብዮቱ በተቃራኒ በመቆም የፕሬዝዳንት አልበሽርን መንግሥት በመደገፍ አደባባይ የወጡም አሉ፡፡ እነዚህ አካላት የአልበሽር ስርዓት እንዲመለስ የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ያም ሆነ ይህ ታዲያ የሀገሪቱ ሉኣላዊየሽግግር መንግስት ሊቀ መንበር በአብዮቱ 2ኛ ዓመት ላይ ትኩረት ያደረጉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ እና የሉኣላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን ፣የአልበሽር አገዛዝ የተወገደበትን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ሰራዊቱ በአብዮቱ የተገኙ ውጤቶችን እንደሚያስጠብቅ ፡፡ አል ቡርሃን በይፋዊው የትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ሱዳናውያንን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ሱዳናውያን ለመንግሥት ለውጥ ያበቃቸውን ተቃውሞ የጀመሩት በሰሜን ሱዳን በአትባራ ከተማ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 19 ቀን 2018 ነበር፡፡ በወቅቱ የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ ወደ ሌሎች ከተሞች በፍጥነት የተስፋፋ ሲሆን መነሻውም የዳቦ ዋጋ መናር ነበር፡፡ ዛሬ በአብዮቱ ሁለተኛ ዓመትም ብዙም የለውጥ ፍሬ ያላዩት ሱዳናውያን በተለያዩ ስሜቶች አደባባይ ወጥተዋል፡፡
ፖለቲካ
https://am.al-ain.com/article/today-two-types-of-demonstrations-took-place-in-various-cities-of-sudan
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
9ad4e531191684f8216c0dc2bbe14dbb
b5dc84ad9ff571a8d44e2383b477df28
ምርጫውን ሰላማዊ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡- ጠ/ሚ ኃይለማርያም
– ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያ ደሳለኝ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ማብራሪያ ሲሰጡ የ2007 ዓ.ም ሐገራዊ ምርጫ ሰለማዊ ማድረግ የሚችለው ህዝቡ ነው ብለዋል።ለዚህም ህዝቡ ከቅድመ ምርጫ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ በነቂስ ወጥቶ ተሳታፊ እንዲሆን መንገስት የበኩሉን ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።መንግስት ምርጫውን ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ነጻ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው።ተወዳዳሪ ፓርቲዎችም በምርጫ ሥነ- ምግባር ህጉ መሰረት በመንቀሳቀስ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው ብለዋል አቶ ኃይለማርያም።በፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ላይ በጋራ ሥራዎች እየተሰሩ ሲሆን የምክር ቤቱ አባል ያልሆኑ ፓርቲዎች ህጉን ተከትለው በመስራት ምርጫውን እንከን የለሽ ማድረግ ይገባቸል ብለዋል።ከዚህ ውጭ ምርጫውን ለመበጥበጥ የሚነሱ ኃይሎች የሚኖሩ ከሆነ ግን መንግስት ህግ የማስከበር ኃላፊነቱን ይሰራል ነው ያሉት።የ2007 ዓ.ም ሐገራዊ ምርጫን እንከን የለሽ ለማድረግ ህዝቡ፣ የምርጫ ቦርድ፣ ፓርቲዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የድርሻቸውን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።አቶ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ እና ግብጽ የሁለትዮሽ ግንኙነት ኢትዮጵያ እስከአሁን የያዘችውን አቋም ይዛ እንደምትቀጥል ነው ለምክር ቤቱ የገለጹት።በግብጽ አዲስ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነትን ለመመስራት መፈለጋቸው ጥሩ እንደሆነ ተናግረዋል።ይህም ለሁለቱ ሐገራት የእረስ በእርስ የተጠናከረ ግንኙነት ወሳኝ መሆኑን ጠቁሟል አቶ ኃይለማርያ ደሳለኝ።በቅርቡም የሁለቱ ሐገራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች በኢኳቶሪያል ጊኒ ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ይታወሳል። (ኢሬቴድ)
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/25011/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1b99e01303ca04c9badaf4ae03111671
6e35f03e1c916b8108b654756c727e26
የሰላም ሚኒስትሯ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ሌተናል ጄነራል ሼክ ሳይፍ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያዩ።በውይይታቸው ወቅት ሁለቱ ሃገራት ባላቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ መክረዋል።በተለይም በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊሲ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል።በምክክራቸው ላይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል ፖሊስ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።በተያያዘም የሰላም ሚኒስትሯ ከአቡ ዳቢ ለልማት ፈንድ ጄኔራል ዳይሬክተር ሞሃመድ ሳይፍ አል ሱዌይዲ ጋር ውይይት አድርገዋል።በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶችን መደገፍ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን መለየት በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።የሰላም ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር የልማት ፈንዱ እና የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።አያይዘውም የልማት ፈንዱ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ዘርፎች ለሚያደርገው ድጋፍ ያላቸውን አድናቆትም ገልጸዋል።ጄኔራል ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ፈንዱ በታዳጊ ሃገራት በተለይም በአፍሪካ የሚያደርገውን የልማት እንቅስቃሴ የማስፋት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።አያይዘውም የልማት ፈንዱ በአፍሪካ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የመንግስታቱን ድርጅት ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት የሚደረገውን ጥረት በሚደግፍ መልኩ ውጤት እያመጡ መሆኑን አስረድተዋል።ጉብኝቱም በኢትዮጵያ መንግስትና በልማት ፈንዱ መካከል የልማት ፕሮጀክቶችን መደገፍና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት በሚቻልበት አግባብ ላይ ተባብረው መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር የሚያስችል እድል ይፈጥራልም ነው ያሉት።የአቡ ዳቢ ለልማት ፈንድ ከፈረንጆቹ 2012 ጀምሮ በኢትዮጵያ ከ32 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በላይ ለሚያወጡ ፕሮጀክቶች ድጋፍ አድርጓል።መረጃው የኢሚሬትስ የዜና አገልግሎት ነው  
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%8b%e1%88%9d-%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%af-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%89%a3%e1%89%a0%e1%88%a9%e1%89%b5-%e1%8b%93%e1%88%a8%e1%89%a5-%e1%8a%a2%e1%88%9a%e1%88%ac/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
47f3f7049f5e1a0a7b316b5b8aa05f54
138492cca336a0f6dc2592bcfda8ecb7
ተስፋዬ በቀለ የአዳማ 10ኛው አዲስ ፈራሚ ሆኗል
አዳማ ከነማ የዝውውር መስኮቱ ዋና ተዋናይ መሆኑን ቀጥሏል፡፡ በርካታ ተጫዋቾችን ያስፈረመው አዳማ ከነማ ከመከላከያ ጋር ውሉ የተጠናቆ የተለያየው ተስፋዬ በቀለን አስፈርሟል፡፡ጠንካራው ሁለገብ ተከላካይ ከመከላከያ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየ ሲሆን በቡና እና መከላከያ አብሮት የተጫወተው ሲሳይ ደምሴን ተከትሎ ድሬዳዋ ከነማን ይቀላቀላል ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ራሱን በአዲስ መልክ እየገነባ ወደሚገኘው አዳማ ከነማ አምርቷል፡፡ከሴካፋ ውድድር በጊዜ የተሰናበተው አዳማ ከነማ በዘንድሮው ክረምት 9 ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ‹‹ጃምቦ›› 10ኛው ፈራሚ በመሆን ቡድኑን ተቀላቅሏል፡፡የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቡድን የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በአዳማ ከተማ ከትላንት በስቲያ የጀመረ ሲሆን ቡድኑ ለቀጣዩ አመት አዲስ መልክ ይዞ እንደሚቀርብ አሰልጣኝ አሸናፊ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡‹‹ ቡድኔን በአዲስ መልክ እየገነባሁት ነው፡፡ እስካሁን 10 ተጫዋቾችን የለቀቅን ሲሆን በምትኩም ሌሎች 10 አዳዲስ ተጫዋቾችን አምጥተን የቅድመ ውድድር ዝግጅታችንን ጀምረናል፡፡ የሰበታው ኤርሚያስ ፍስሃን ለማስፈረም ብንፈልግም ቀሪ አንድ አመት ኮንትራት ያለው በመሆኑ የክለቡን ፍቃደኝነት እየጠበቅን ነው፡፡ ›› ብለዋል፡፡አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ በድሬዳዋ ተገኝተው የብሄራዊ ሊጉን የማጠቃለያ ውድድር የተመለከቱ ቢሆንም ምንም ተጫዋች እንዳላስፈረሙ ታውቋል፡፡
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/3774
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
ad10b3da15fc6fa6553cde4f1da22374
8ae6b2ccb21de8c35d94226523bba21b
በሊጉ መርሃ ግብር ፋሲሎች ወደ ዋንጫው ሲጠጉ፤ ሲዳማዎች ሩጫቸውን አቀዝቅዘዋል
 እንደ ባለፈው ዓመት ሁሉ ዘንድሮም ሻምፒዮን የሚሆነውን ክለብ ቀደም ብሎ ማሳወቅ ያልቻለው የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቋጫውን ሊያገኝ ሶስት ጨዋታዎች ብቻ ቀርተውታል።የሊጉ 27ኛው ሳምንት መርሀ ግብርም በሳምንቱ የእረፍት ቀናት በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሲካሄድም በተለይ ለዋንጫው የተሻለ እድል አላቸው የተባለላቸው ክለቦች ብርቱ ትንቅንቅ አድርገዋል።ያልተጠበቁ ውጤቶቹም የዋንጫ ትንቅንቅ ይበልጥ እንዲፋፋም አድርገውታል።በ27ኛው ሳምንት መርሀ ግብር ቅዳሜ ግንቦት 24 የተካሄደውና መከላከያን ከሲዳማ ቡና ያገናኘው ጨዋታም ያልተጠበቀ ውጤት የተመዘገበበት ሆኗል።በ24ተኛው ሳምንት መሪው መቀሌን ማሸነፍ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች፤ በ25ተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡናን በሜዳና በደጋፊው ፊት 2ለ0 እንዲሁም ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ደርቢ ደቡብ ፖሊስን አራት ለሁለት ማሸነፋቸው ይታወሳል።ካለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሁሉንም ማሸነፍ የቻሉት ሲዳማዎች፤ አንደኛና ሁለተኛ ከተቀመጡት ፋሲልና መቀሌ እኩል 49 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ ብቻ ተቀድመው ሶስተኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ የዋንጫ ጉዞአቸውን በእጅጉ ማሳመራቸውም አይዘነጋም።ከወቅታዊ የመከላከያ አቅምና አቋም አንፃር ጨዋታው ለሲዳማዎች ፈታኝ እንደማይሆን ቢገመትም፤ ሜዳ ላይ የሆነው ግን የተገላቢጦሽ ነው። ባለሜዳዎቹ ሲዳማ ላይ አራት ግቦችን ሲያስቆጥሩ አንድ ግብ ብቻ ተቆጥሮባቸዋል።ጨዋታውን አሸንፈው ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ለ24 ሰዓት ሊጉን በቀዳሚነት መምራት የሚያስችላቸውን አጋጣሚ አሳልፈው የሰጡት ሲዳማዎች፤ያጧቸው ሶስት እጅ ወሳኝ ነጥቦች በዋንጫ ትንቅንቅ ላይ ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ታምኖበታል። ሲዳማዎች በቀጣይ በዋንጫ ትንቅንቅ ሻምፒዮን ለመሆን የግድ ቀሪ ጨዋታዎችን ሙሉ ለሙሉ ማሸነፍና የየተከታዮቻቸውን መሸነፍ መጠበቅ ግድ የሚላቸው ሆኗል። ሲዳማዎች በአጠቃይ ድሬዳዋና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና ደደቢትን የሚፋለሙ ይሆናል።በጨዋታው ወቅታዊ አቋም እያደር መዋዠቅና በውጤት ቀውስ የመውረድ አደጋ እንደተጋረጠበት መከላከያ በ26ተኛ ሳምንት መርሃ ግብር በስሁል ሽረ ከደረሰበት ሽንፈት አገግሞ ሲዳማ ላይ ያስመዘገበው ውጤትም ከወራጅ ቀጣናው እንዲወጣ አስችሎታል።ጦሩ በደረጃ ሰንጠረዝ፤ በ29 ነጥብ 13ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ተሸናፊው ሲዳማ ቡና በአንፃሩ በ49 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃው ላይ ተቀምጧል።በአማራ ደርቢ ፋሲል ከነማን ከባህር ዳር ከተማ አገናኝቷል።ባለሜዳዎቹ ፋሲሎች፤ በ25ተኛ ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር የአምናውን የሊጉ ሻምፒዮን ጅማ አባጅፋርን 6 ለ1 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ሲረከቡም በ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ወደ ሶዶ አቅንተው በወላይታ ዲቻ ያልተጠበቀ የ2ለ1 ሽንፈትን ማስተናገዳቸው ይታወሳል።በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ክለቦች ፍልሚያም፤ ለዋንጫ እንደሚፋለም ክለብ ድንቅና ወጥ አቋም ያሳዩት ፋሲሎች አራት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል።ከውጤቱ ባገኙት ውድ ሶስት ነጥብ የሊጉ መሪነታቸውን አስጥብቀዋል። የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውሰድ በመንደርደር ላይ ያሉት አፄዎቹ፤ይህን ታሪክ ለመስራት ደግሞ ከፊታቸው ከቅዱስ ጊዮርጊስ፤አዳማና ስሁል ሽረ ጋር ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቃቸዋል።የጨዋታውን ተሸናፊ ባህር ዳርቻዎች በአንፃሩ በመጀመሪያው የሊጉ መርሃ ግብር ድንቅ ብቃት ማሳየት ቢችሉም፤በሁለተኛው የሊጉ መርሃ ግብር መዳከማቸውን የሚያስመሰክር ውጤትን አስመልክተዋል።የጣና ሞገዶቹን ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች ስንመለከት እንኳን በ25ተኛ ሳምንት በሊጉ የደረጃ ግርጌ ላይ በሚገኘው ደደቢት የ 5 ለ2 ያልተጠበቀ ሽንፈት ሲደርስባቸው ከወልዋሎጋር ነጥብ ተጋርተዋል።በየደረጃው ሰንጠረዥም በ37ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።ሌላኛው ተጠባቂ የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡናን ከመቀሌ 70 እንደርታ አገናኝቷል። ይሁንና የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከጸጥታ ጋር በተገናኘ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተደርጓል። ጨዋታው ባለመካሄዱ መቀሌ በ49 ነጥብ በነበረበት ሁለተኛነት ሲቀጥል፤ ኢትዮጵያ ቡና በ34ነጥብ አስራ አንደኛ ደረጃን ይዟል። በ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም ወደ ጅማ አቅንተው፤2ለ 2 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው የተመለሱት መቀሌዎች፤የፋሲል መሸነፍ መሪ ለመሆን የሚያግዛቸው ቢሆንም ከጨዋታው አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘታቸውን ተከትሎም በግብ ክፍያ ተበልጠው በነበሩበት የሁለተኝነት ደረጃ ለመቀጠል መገደዳቸው ይታወሳል።በተለይ በሁለተኛ የሊጉ መርሃ ግብር በሌሎች ውጤት ላይ ሳይመሰረት ሻምፒዮን ሊያደርጉት የሚችሉ ወሳኝ ጨዋታዎች ላይ ነጥብ የጣለው መቀሌ፤ የሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውሰድ ከፊቱ፤ከድሬዳዋ ከነማ፣ ደቡብ ፖሊስ፣ መከላከያ ጋር የሚያደርገውን ፍልሚያ ማሸነፍ የግድ ይለዋል።ይህም በመሪው ፋሲል ነጥብ ማጣት ላይ ተጨማሪ መሰረቱን የሚያደርግ ይሆናል።ሌላኛው መርሃ ግብር ደደቢትን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሲያገናኝ ጨዋታው በፈረሰኞቹ የሶስት ለሁለት አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል።በ23ተኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብርም በሸገር ደርቢ ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም በ24ተኛው ሳምንት ከደቡብ ፖሊስ እንዲሁም በቀጣይ ከመከላከያ ጋር ነጥብ የተጋሩት ፈረሰኞቹ፤በ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም በሜዳና ደጋፊያቸው ፊት ድሬዳዋን አስተናግደው 2ለ0 ማሸነፋቸው ይታወሳል።ደደቢቶች በአንፃሩ በ25ተኛው ሳምንት መቀሌ ላይ በትግራይ ስታዲየም ባህር ዳርን ሳይጠበቁ 5ለ2 ቢያሸንፉም 26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም በአዳማ ከተማ አራት ለባዶ ተሸንፈው በቀጣዩ ዓመት የሊጉ ተፋላሚ እንደማይሆኑ ማረጋገጣቸው ይታወሳል።የጨዋታው አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአሁኑ ወቅት ከመሪው ፋሲል በስድስት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ46 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።።በ27ኛው ሳምንት መርሀ ግብር የተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ወላይታ ዲቻን ከጂማ አባጅፋር ያገናኘው ነው። ባሳልፈነው ሳምንት የሊጉን መሪ ፋሲል ሁለት ለአንድ ያሸነፉት ዲቻዎች፤ በዚህ ሳምንት ደግሞ የአምናውን የሊጉን ሻምፒዮንበፎርፌ ማሸነፍ ችለዋል፡፡ የወራጅ ስጋት ተጋርጦባቸው የነበሩት ዲቻዎች በሊጉ ሁለተኛ አጋማሽ ባሳዩት ድንቅ አቋም በፍጥነት ከወራጅ ቀጣና ስጋት መላቀቅ ችለዋል።በአሁኑ ወቅትም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ነጥባቸውን ወደ 34 ከፍ በማድረግ በደረጃ ሰንጠረዡ 12ተኛ ላይ ተቀምጠዋል።የአምናው ሻምፒዮና ጅማ አባጅፋር በአንፃሩ በ40 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዪኒቨርሲቲን ከአዳማ ከተማ አገናኝቷል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታም በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል።26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም በሜዳውና በደጋፊው ፊት ደደቢትን አስተናግዶ 4ለ0 ማሸነፋቸው ተከትሎ፤ ከወራጅ ቀጣናው ስጋት መለቀቁ አይዘነጋም።ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በአንፃሩ፤ባሳልፈነው ሳምንት ወደ ባህር ዳር አቅነተው ካለምንም ግብ ነጥብ ተጋርተው መመለሳቸው ይታወሳል።በደረጃ ሰንጠረዙ አዳማ በ34 ነጥብ አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ከቢጫ ሰርጓጆቹ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በአንፃሩ፤በ37 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ደቡብ ፖሊስ ከሃዋሳ ከተማ አገናኝቷል።በደቡብ ደርቢ በሁለቱ  ክለቦች መካከል የተካሄደው ጨዋታም በባለሜዳው ሶስት ለሁለት አሸናፊነት ተጠናቋል።በ25ተኛው ሳምንት መርሃ ግብር መቀሌን 1ለ0 ያሸነፉት ሃዋሳዎች፣ 26ኛ ሳምንት መርሃ ግብርም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ካለምንም ግብ ነጥብ መጋረታቸው ይታወሳል።በ26ስተኛ ሳምንት በሲዳማ ቡና የተሸነፉት ደቡብ ፖሊሶች በአንፃሩ በዚህ ሳምንት ሃዋሳ ምርታታቸውን ተከትሎ ከሊጉ ወራጅ ቀጣና ለማውጣት የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ ውጤት አግኝተዋል።ደቡብ ፖሊሶች አሁን ላይ በ28 ነጥብ በሊጉ 14 ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፤ ሃዋሳዎች በአንፃሩ በ38 ነጥብ 8ተኛ ደረጃ ይዘዋል።ድሬዳዋን ከስሁል ሽረ ያገናኘውም ሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር ነው። የሁለቱ ከለቦች ጨዋታም በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል።በሊጉ ሁለተኛ ዙር ድንቅ አቋምና ውጤት በማሳየት ደረጃቸውን በእጅጉ በማሻሻል ከወራጅ ቀጣናው ክለቦች ተርታ ስማቸውን ለማስወጣት እየጣሩ የሚገኙት ስሑል ሽረዎች፤በ26ተኛ ሳምንት መርሃ ግብር መከላከያን አስተናግደው 2ለ1 ማሸነፋቸው ይታወሳል።ብርቱካናማዎቹ ድሬዳዋዎች በአንፃሩ፤በ26ተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ለባዶ መሸነፋቸው ይታወሳል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ከወራጅ ቀጣናው የሚላቀቁበትን እድል ማግኘት ያልቻሉት ስሁሎች፤ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዝ በ27 ነጥብ 15ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ድሬዳዋዎች በአንፃሩ፤ በ35 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘዋል።የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ፋሲል ከነማ ሃምሳ ሁለት ነጥቦች በመሰብሰብ በቀዳሚነት ይመራል።መቀሌ ሰባ እንደርታና ሲዳማ ቡናም በተመሳሳይ አርባ ዘጠኝ ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበልጠው ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል።የሊጉን ወራጅ ቀጣና ስንመለከት፤ደቡብ ፖሊስ በሃያ ስምንት ነጥቦች አስራ አራተኛ፤ስሁል ሽረ በሃያ ሰባት ነጥቦች አስራ አምስተኛ እንዲሁም ደደቢት በአስር ሶስት ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል።የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ፉክክር የመቀሌው አማኑኤል ገብረሚካኤልና የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ በአስራ አምስት ግቦች አንደኛ ሁለተኛ ሲሆኑ የፋሲሉ ሙጂብ ቃሲም በአስራ አራት ግቦች ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።አዲስ ዘመን ግንቦት 27/2011 
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=11976
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
5033f3b04ead4b62a752c12c94fc5e9b
7688c5e7bd9fd27bf2067885dc8b16a1
የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 93ኛው መደበኛ ስብሰባ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 93ናው መደበኛ ስብሰባ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8a%92%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%ae%e1%89%bd-%e1%88%9d-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8b%9b%e1%88%ac%e1%8b%8d-%e1%8a%a5%e1%88%88%e1%89%b5-%e1%89%a3%e1%8a%ab%e1%88%84%e1%8b%b0/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
92181a266580c390d7aedcae87c0eba3
9a381a68233ae9e901b6ef7577034b36
በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው ኮትዲቯር ኒጀርን አሸንፋለች
ኒጀር፣ ኮትዲቯር፣ ኢትዮጵያ እና ማዳጋስካር በሚገኙበት ምድብ በተደረገ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኮትዲቯር ኒጀርን በሜዳዋ አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ደግሞ ጉዞዋን በሽንፈት ጀምራለች።በኢብራሂም ካማራ የሚሰለጥኑት ዝሆኖቹ በትላንቱን ጨዋታ ከተጋጣሚያቸው በተሻለ መንቀሳቀሳቸው ታይቷል። በተለይ አሰልጣኙ በአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ልምድ ያላቸው ተጨዋቾችን በመጠቀም ጨዋታውን እንዳከናወኑ ተስተውሏል። ኢብራሂም ካማራ ከተጠቀሟቸው የመጀመርያ 11 ውስጥ የቶተንሃሙ ሰርጂ ኦሪየር፣ የአርሰናሉ ኒኮላ ፔፔ፣ የቱሉዙ ማክስ አልን ግራድ እና የኤሲ ሚላኑ ፍራን ኬሲ ተጠቃሽ ናቸው።በጨዋታው ጥሩ ጥሩ የግብ እድሎችን ሲፈጥሩ የነበሩት ዝሆኖቹ በ68ኛው ደቂቃ በፍራንክ ኬሲ አማካኝነት ባስቆጠሩት የፍፁም ቅጣት ምት ኒጀርን ረተዋል። ቡድኑ ካስቆጠረው የ68ኛ ደቂቃ የፍፁም ቅጣት ምት ውጪ በ23ኛው ደቂቃ ሌላ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝቶ የቱሉዙ የመስመር አጥቂ ማክስ አለን ግራድ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።ውጤቱን ተከትሎ ኮትዲቯር ኢትዮጵያን 1-0 ያሸነፈችውን ማዳካስካር በአልፋ ቤት በልጣ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።ዋሊያዎቹ የማጣርያ ጉዟቸውን በሽንፈት ጀምረዋልበማሀማኒሳ ሙኒሲፓል ስታዲየም የተደረገው የማዳጋስካር እና ኢትዮጵያ ጨዋታ በጋባዦቹ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ የነበረችው ማዳጋስካርን ብቸኛ ጎል በ18ኛው ደቂቃ ራያን ራቬልሰን ከማዕዘን ከተሻማ ኳስ አስቆጥሯል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ በአንፃራዊነት ጥሩ የተንቀሳቀሰ ሲሆን የተሻሉ የጎል እድሎችን ቢፈጥርም ጎል ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል።ዝሆኖቹ ሰኞ ባህር ዳር ይገባሉኮትዲቫሮች ማክሰኞ የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ከኢትዮጵያ ጋር ለማከናወን ሰኞ ከሰዓት ባህር ዳር እንደሚገቡ ታውቋል። የዝሆኖቹ 2 አስተባባሪዎች ከትላንት በስትያ ባህር ዳር ገብተዋል። አስተባባሪዎቹ የመጡት ለቡድኑ የተመቸ ማረፊያ ለማመቻቸት እና የብ/ቡድኑን እለታዊ የምግብ ሜኑ ለሚያርፉበት ዊን ሆቴል ለማሳወቅ ነው ተብሏል፡፡በቻርተር አውሮፕላን ሰኞ እንደሚመጡ የሚጠበቁት ዝሆኖቹ በእለቱ በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስቴዲየም ልምምድ እንደሚሰሩ ይጠበቃል። ጨዋታውንም ማክሰኞ 10 ሰዓት ካከናወኑ በኋላ ምሽቱን ከኢትዮጵያ ለመውጣት እንዳቀዱ ሰምተናል።ዊልፍሬድ ዛሀ በኢትዮጵያው ጨዋታ ዝርዝር ውስጥ ይገኛልሶከር ኢትዮጵያ ቡድኑ ከሚያርፍበት ዊን ሆቴል እንዳገኘው መረጃ ከሆነ አስተባባሪዎቹ ለሆቴሉ በሰጡት የቡድን ዝርዝር ውስጥ የክሪስታል ፓላሱ የመስመር ተጨዋች ዊልፍሬድ ዘሃ እንደሚገኝ ተረጋግጧል። ነገር ግን ተጨዋቹ ትላንት ቡድኑ ኒጀርን በገጠመው ስብስብ ሳይካተት ቀርቷል።የደረጃ ሠንጠረዥ
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/51857
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
e24610446cbd874961b56a2f665f09fd
9c72e69b114497738588346386df6916
በቤኒሻንጉል ጉምዝና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች የፀጥታ ችግር የሚፈታ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ
በቤንሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎችን የጸጥታ ችግር የሚፈታ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ፡፡የኮማንድ ፖስቱ አባል አቶ ሰይፈዲን ሐሩን ለኢዜአ እንዳስታወቁት ኮማንድ ፖስቱ የፌደራልና የሁለቱ ክልሎች መንግሥታት፣ የአገር መከላከያ ሠራዊትና ፌዴራል ፖሊስን ያቀፈ ነው፡፡ኮማንድ ፖስቱ የተቋቋመው በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች የመሸገውን የታጠቀ ኃይል በመቆጣጠር የኅብረተሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡  መቀመጫውን በአሶሳ ከተማ  የሚያደርገው ኮማንድ ፖስቱ፣ ከሱዳን የጸጥታ ኃይሎች ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ አቶ ሰይፈዲን ገልጸዋል፡፡                              በቤኒሻንጉልና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች ባለፉት ሦስት ወራት በተከሰተ የጸጥታ ችግር ከ100 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡(ኢዜአ)
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/30720/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
ee99f6155a6405ea56b31f57a71fedaa
577153d18e9dd98f5010f3ebd61f9779
ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ወጪ ሆኗል የተባለ 53 ቢሊዮን ብር ሳይወራረድ ቀረ
ይህን ያለው ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና ለባለ እድለኞች ተላልፈው የሚሰጡበትን ውስብስብ ጉዳዮች እንዲያጠና የተጠየቀው ቡድን ነው። ይህን ጥናት ያካሄደው ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ሲሆን፤ የጥናት ቡድኑን ሲመሩ የቆዩት ቱሉ ቶላ (ዶ/ር) ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና መኖሪያ ቤቶቹ ተላልፈው የሚሰጡበትን ውስብስብ ችግር ለማጥናት ከአራት ወራት በላይ መፍጀቱን ይናገራሉ። በጥናት ውጤቱም መሠረት ለጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ወጪ ሆኗል የተባለ 53 ቢሊዮን ብር አለመወራረዱን፣ አልያም ለወጪው ሰነድ አለመገኘቱን ቱሉ ቶላ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተመሳሳይ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ21ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን በጥናት መረጋገጡን አስታውቆ ነበር። ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ 13 ሚሊየን 389 ሺህ 955 ካሬ ወይም 1 ሺህ 338 ሄክታር መሬት በሕገ-ወጥ መያዙን አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም 322 ግንባታቸው ያለቀና ያላለቀ ህንፃዎች ባለቤት አልባ ሆነው መገኘታቸውን እና 14,641 መኖርያና ለንግድ የተከራዩ የቀበሌ ቤቶችን ያለ አግባብና በሕገ-ወጥ ይዞታነት የሚገኙ መሆኑን አስታውቀዋል። ቱሉ ቶላ (ዶ/ር) መንግሥት ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር ተያይዞ ያለውን ውስብስብ ችግር ለመለየት በገለልተኛ አካል ጥናት እንዲካሄድ ሲወስን ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መመረጡን ይናገራሉ። በጥናቱ ላይ 7 የዩኒቨርሲቲው መምህራንን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ3ሺህ 500 ሰዎች በላይ በጥናቱ ላይ መስራታቸውንም ጠቅሰዋል። ጥናቱ ምን አመላከተ? ከአራት ወራት በላይ የፈጀው ጥናት ከ1996/97 ጀምሮ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ተመልክቷል። በከተማዋ የሚገኘው እያንዳንዱ የጋራ መኖሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ኮርፖሬሽን፣ የባንክ እና የባለቤትነት ሰነድ ጋር የማነጻጸር ሥራ መሰራቱን ይናገራሉ። ይህ የአጥኚ ቡድን በከተማዋ የተገነቡት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና ለተጠቃሚዎች ተላልፈው ከሚሰጡበት ሂደት በተጨማሪ ለግንባታ የተደረገውን ወጪ እና በመሬት ላይ ያለውን የግንባታ ሂደት ደረጃ መርምሯል። "ባካሄድነው ጥናት እንዳረጋገጥነው ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ወጪ ተደርጓል የተባለ 53 ቢሊዮን ብር ለምን ወጪ እንደተደረገ የሚያሳይ ሰነድ ለም። የፌደራል ኦዲተሮችም ሰነድ አጥተው ኦዲት ሊደረግ አይችለም ብለው ትተውታል። ታስቦበት ማረጋገጫ እንዲጠፋ ተደርጓል" ይላሉ ቱሉ (ዶ/ር)። እንደ የጥናት ቡድኑ መሪ ከሆነ እያንዳንዳቸው እስከ 30 ቤቶችን ሊይዙ የሚችሉ 28 ሕንጻዎች (ብሎኮች) ሳይገነቡ ቀርተዋል። "እነዚህ ያልተገነቡ ሕንጻዎች ለመገንባት ከተቋራጮች ጋር ስምምነት ተደርሶ ነበር። እነዚህ ቤቶች ለምን ሳይገነቡ እንደቀሩ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ወይም የኮርፖሬሽኑ ቦርድ የያዘው ቃለ ጉባኤ የለም። ክፍያ መፈጸሙን ወይም አለመፈጸሙን የሚያሳይ ሰነድ ጠፍቷል። ይህ የሚያመላክተው ክፍያ ሳይፈጸም እንደማይቀር ነው።" ይላሉ። ቱሉ (ዶ/ር)፤ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች 99 ሕንጻዎች ጠፍተዋል ተብሎ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መገለጹን አስታውሰው፤ ይህን በተመለከተ የፌደራል ኦዲተሮች ከ2008 ጀምሮ የኦዲት ሥራ ሲሰሩ ቢቆዩም የተገኘ ውጤት አለመኖሩን በጥናታችን አረጋግጠናል ይላሉ። ወጪ ተደርጎ ሰነድ አልተገኘለትም የተባለው 53 ቢሊዮን ብር ግንባታቸው እንዲፈጸሙ ከስምምነት የተደረሰባቸው ይሁን እንጂ በተጨባጭ መሬት ላይ ግንባታቸው ያልተፈጸሙ ቤቶች ድምር ሊሆን እንደሚችል ይገልጻሉ።...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
b96954c708f2793e1190b07c30f10fa2
9138c75efe217271fb8fbdc2c120a213
ስቶኮልም
ስቶኮልም (እስቶኮልም) የስዊድን ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 1,622,300 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,251,900 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። የስዊድን ከተሞች ዋና ከተሞች
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
d7965871429412480d4e9fa292ab3aad
50d83be0621dce84ddfa4280f6262ff2
የጆ ባይደን የምረጡኝ ቅስቀሳ - ፍሎሪዳ
የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚደንታዊ ዕጩ ጆ ባይደን ሁለቱም ፓርቲዎች ተቀራራቢ የህዝብ ድጋፍ ያላቸው በሆኑ፤ ለማሸነፍ ቁልፍ ናቸው ከሚባሉት ግዛቶች አንዷ በሆነችው ፍሎሪዳ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ቆይተዋል።ከኮቪድ-19 ህመማቸው በማገገም ላይ የሚገኙት ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በበኩላቸው ፈጥኜ ወደ ምርጫ ዘመቻ እመለሳለሁ ብለዋል። ኤሊዛቤት ሊ ያጠናቀረችውን ዘገባ ይዘናል።
ዓለም አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/us-vores-wrap-10-7-2020/5612851.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
92c170644663e306d17cdc6428da7728
6e27618df511eea6c5b17bf71d9ea0f8
ሽክርክርና ዘንግ
ሽክርክር እና ምሰሶ ከስድስቱ ቀላል ማሽን አንዱ ነው። ቀላል ሽክርክር እና ምሰሶ አንድ ሽክርክርና ከርሱ ጋር በጥብቅ የተገናኘ ምሰሶ ይኖረዋል። በዚህ ሁኔታ ትልቁን ሽክርክር በመጠቀም ከፍተኛ ቶርክ ወይም ጉልበት በትንሽየ ጉልበት መፍጠር ስንችል (ይሄ እንግዲህ ውሃ ለመቅዳትና ከባድ ነገሮችን ለማንቀሳቀስ ይጠቅመናል)፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ምሶሶውን በመጠቀም በአንስተኛ እንቅስቃሴ (ከፍተና ጉልበት)፣ ብዙ እንቅስቃሴን ከትልቁ ሽክርክር እናገኛለን (ምሳሌ፡ የብስክሌት ፔዳል)። ስሌዚህ እንደምናዞረው ሽክርክር፣ አንድ ጊዜ ፍጥነትን ለማብዛት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጉልበትን ለማብዛት ይጠቅመናል ማለት ነው። ሁለቱን በአንድ ላይ ማድረግ ግን በተፈጥሮ ህግ ክልክል ነው። ማሽን ሥነ-ተፈጥሮ
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
d86df8722b9a3e09b84bd45a2a4f29dd
d8fac16448538fa86efbb001bbf14a8f
የህክምና ባለሙያው ከተለመደው ሚና ውጪ..
ትናንት ጅማሮውን ባደረገው የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለወትሮው ከተለመደው ውጪ የህክምና ባለሙያውን በሌላ ሚና መመልከት ችለናል።በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከፋሲል ከነማ ያደረጉት የሊጉ የመጀመርያ ጨዋታቸውን ያለ ጎል በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል። ታዲያ በጨዋታው እንቅስቃሴ ላይ የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች ጉዳት አስተናግደው የህክምና ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ወቅት አንድ ትኩረት የሚስብ ነገር ተደጋግሞ መመልከት ችለን ነበር።አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ የህክምናው ባለሙያው ሽመልስን ከተለመደው ሙያዊ አገልግሎቱ ውጭ በቅርብ ርቀት ተጫዋቾችን አግኝተው ማረም ያልቻሉትን ነገር በህክምና ባለሙያው በኩል መልዕክት ሲያስተላልፉ ተመልክተናል።ይህ እምብዛም በሊጋችን በግልፅ ያልተለመደው ተግባር እንዴት እየሰሩበት እንደሆነ አሰልጣኝ ሥዩም ከበደን አናግረናቸው ይሄን ብለውናል።” የህክምና ባለሙያ በአንድ ክለብ ውስጥ የቴክኒክ ክፍሉ አባል ነው። ስለ ተጫዋቾች አሰላለፍ ስታወጣ እና ሌሎች ነገሮችን ማድረግ ስትፈልግ ከህክምና ባለሙያው ጋር አስቀድመህ ትነጋገራለህ። ለምሳሌ ትናንት ሱራፌል ህመም ስለነበረው እረፍት ላይ ነበር ማሳረፍ ፈልጌ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ተጫዋቾች ህመም እየተሰማቸው ቡድኑን ለማገልገል ሲሉ ሜዳ ላይ መቆየት ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ ቡድኑ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አለው። በዚህ ሰዓት ነው የህክምና ባለሙያው ሽመልስን ‘ስትሄድ ህመሙ ከከፋበት ተቀይሮ እንዲወጣ በግልፅ ንገረው’ በማለት የላኩት። በተጨማሪ ሜዳው ውስጥ ተጫዋቾችህ አለመረጋጋት ፣ አለመናበብ እና ስሜታዊ ሲሆኑ የጨዋታው እንቅስቃሴ በጉዳት ምክንያት ሲቋረጥ ተጫዋቾቹን ወደ እኔ ጠርቼ እስካናግር ድረስ በሆነ አጋጣሚ የጨዋታው እንቅስቃሴ ቢጀምር ማስተላለፍ የምፈልገውን መልክት ሳላደርስ ልቀር በመሆኑ የህክምናው ባለሙያ የእያንዳንዱን ተጫዋች ስብዕና ባህሪ በቅርብ ርቀት የሚረዳ በመሆኑ ከህክምናው ባሻገር እግረ መንገዱን የምትፈልገው መልዕክት ሜዳ ውስጥ ነግሮልህ ይወጣል።“ይህ የመልክት ማስለተላለፍ መንገድ ድሮም ቅዱስ ጊዮርጊስ እያለው (ነፍሱን ይማረውና) ዘላለም አዱኛ ያደርግልኝ ነበር። እንዲያውም በጣም ከመልመዱ የተነሳ እንዳዴ ‘ኮች የምነግርልህ ነገር አለ?’ ይለኝ ነበር። ምክንያቱም ሜዳ ውስጥ ከእኛ በተሻለ ለተጫዋቾቹ ቅርብ ናቸው። ስለዚህ ይህን መጠቀምህ ሥራህን ስለሚያቀልልህ ከዛ አኳያ ነው ይህን መንገድ በተደጋጋሚ እከተል የነበረው።”
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/52291
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
a652f0146025ad8065eb4d6835b2f579
361a1da5e982fd022acd473edae92368
የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ተገለፀ
ሙከራ ላይ ያሉ በርካታ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን በክትባቶቹ ሥራ አመራር ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናት ገለፁ።የእንግሊዝ እና የስዊድን የመድሃኒት ኩባኒያው አስትራዜኔካ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚከናወነው የክትባቱ የመጨረሻ ሙከራ ከተለያዩ ዘሮች ብሄሮችና መልክዓ ምድራዊ አካባቢዎች በተውጣጡ ሰላሳ ሺህ አዋቂዎች በማሳተፍ እንደሚጠናቀቅ አመልክቷል።የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የጤና ተቋማት ኤንአይኤች ተሰርቶ ሞደርና በተባለው ኩባኒያ ተመርቶ የሚወጣው ክትባትም ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብዙ ሺህዎች የተቆጠሩ ሰዎች በማሳተፍ ሙከራ ላይ ውሏል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/covid-vaccine-9-2-2020/5568071.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
19f137b9160c5d78e359d2685a36b7ab
9c5da34849718ef36ed2a4b368e5fc7b
የኢትዮጵያ-ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ አዳማ ላይ ሊገነባ ነው 
የኢትዮጵያ-ሁናን ሶስተኛው ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ፓርክ ከ250 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ አዳማ ላይ ሊገነባ ነው።የኢንዱስትሪ ፓርኩ የቻይናዋ ሁናን ግዛት ባለሃብቶች ማሽነሪዎች፣ የግንባታና የግብርና መሳሪያዎች የሚያመርቱበት ነው።የኢትዮጵያና ቻይና የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ዛሬ ሲካሄድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶክተር አርከበ ዕቁባይና የሁናን ግዛት ምክትል አስተዳዳሪ ሚስተር ሂ ባኦዢያንግ በፓርኩ ግንባታ ስምምነት ስነድ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።ሌሎች ሶስት ስምምነቶችም በኢትዮጵያ መንግስትና በሁናን ግዛት የስራ ኃላፊዎች ተፈርመዋል።የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የቻይና ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸው ለአገሪቷ ኢንዱስትሪና ለፓርኮች እድገት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ይላሉ።የመንግስት አቅጣጫ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ፓርኮችን መገንባት መሆኑን ጠቁመው በአዳማ የሚገነባው ሶስተኛው ምዕራፍ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተለያዩ ማሽነሪዎች የግብርናና የግንባታ መሳሪያዎች አምራቾች የሚሰማሩበት መሆኑን አክለዋል።በሃዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማሲ ዘርፍ የሚሰማሩ ኩባንያዎች የሚሳተፉ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።የተፈረመው ስምምነት የሁለቱን አገሮች የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር እንዲሁም የሁለትዮሽ ግንኙነት ያሳድጋል ተብሏል።የሁናን ምክትል አስተዳዳሪ ሚስተር ሂ ባኦዢያንግ ግዛቷ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ የልማትና ኢንቨስትመንት መስኮች የመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።ስምምነቱ የግዛቷ ባለሃብቶች የኢትዮጵያን መንግስት ድጋፍና ማበረታቻ ተጠቅመው በኢንዱስትሪ፣ በግብርናና ሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሲሳይ ገመቹ በአዳማ የሚገነባው "ኢትዮጵያ-ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ" ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር እንደሚከወን ጠቁመዋል።ግንባታው በ122 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ከ12 እስከ 18 ወራት በሚፈጅ ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ 365 ሄክታር የሚሸፍን ሲሆን በመጀመሪያው ምዕራፍ የአልባሳት፣ በሁለተኛው የጨርቃጨርቅና የሁናን ግዛት ድርጅቶች የሚሳተፉበት ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ የተለያዩ ማምረቻ፣ መገልገያ፣ የግብርናና የግንባታ መሳሪያዎች ይመረቱበታል-(ኢዜአ) ።
ቢዝነስ
https://waltainfo.com/am/23082/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
fc4f8a3ae933277cac90bd33730d2df4
94f00e65714d0c22a6d9369dfb8941ec
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ በአፍሪካ ኢኮኖሚያ ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቀነስ የሚያስችል የድጋፍ ምክረ ሀሳብ ለቡድን 20 አባል ሀገራት አቀረበች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ 19) ለመከላከል እና በአፍሪካ የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ የሚያስችል ባለ ሶስት ነጥብ የድጋፍ ምክረ ሀሳብ ለቡድን 20 አባል ሀገራት አቀረበች።የኮሮናቫይረስ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ያለው ምክረ ሀሳቡ፥ በተለይም በዓለም ደረጃ የወጪ ንግድ መጠን መቀነስ፣ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች መንገራገጭ እና የጉዞ እና የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ክፉኛ መጎዳት እንዲሁም ከኢትዮጵያ አንፃር ከሀገሪቱ የአገልግሎት ወጪ ንግድ ውስጥ ሁለት ሶስተኛውን ገቢ የሚያመጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያጋጠመው የበረራ ኢንዱስትሪ መቀዛቀዝ በኢኮኖሚዋ ላይ ስጋትን ደቅኗል ብሏል።አሁን በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነው የኢኮኖሚ ስጋት ሀገራት በግላቸው በሚወስዱት እርምጃ እና በፖሊሲ ብቻ የሚቀረፍ አይደለም ያለው የኢትዮጵያ ምክረ ሀሳብ፥ ይህንን ለመቋቋምም የተቀናጀ ዓለም አቀፋዊ ምላሽ ያስፈልጋል ብሏል።ኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሚመጣውን ጫና ለመቀነስ ከአጋር ሀገራት ጋር እየሰራች መሆኑን ያመላከተው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ፥ ኢትዮጵያ የቡድን 20 አባል ሀገራት በቀጣይ በሚያደርጉት ልዩ ስብሰባቸው ከግምት ውስጥ ቢያስገቧቸው ያለችውን ባለ ሶስት ነጥብ ምክረ ሀሳብ ማቅረቧንም ገልጿል።ከእነዚህም አንደኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የኮቪድ-19 የአስቸኳይ ጊዜ የፋይናንስ ድጋፍ ማዕቀፍ ሲሆን፥ በዚህም 150 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ እና የገንዘብ ድጋፉም የውጭ ምንዛሬ አቅምን እና የሴፍቲ ኔት መርሃ ግብሮችን ለማጠናከር የሚውል መሆኑ ተገልጿል።ሌላኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የአስቸኳይ ጊዜ የጤና ማዕቀፍ ሲሆን፥ በዚህም ለዓለም ጤና ድርጅት የሚደረገውን ድጋፍ በማጠናከር ድርጅቱ በአፍሪካ የሚያደርገውን ድጋፍ ማሳደግ፤ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል /ሲዲሲ/ እንዲሁም ለኤድስ፣ ወባ እና ቲቢ መከላከያ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ድጋፎችን ማጠናከር የሚለውም በምክረ ሀሳቡ ተካቷል።ሶስተኛው በኢትዮጵያ የቀረበው ምክረ ሀሳብ በአፍሪካ ሀገራት ላይ ያሉ እዳዎች እንዲሰረዙ እና የብድር መመለሻ ጊዜዎች እንዲራዘሙ የሚጠይቅ ሲሆን፥ በዚህም ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ላይ ያሉ የብድር ወለዶች እንዲሰረዙ እንዲሁም፤ የመክፈያ ጊዜያቸው የተቃረቡ ብድሮች ደግሞ ቢያንስ ለ10 ዓመታት ቢራዘሙ በሚል ጠይቃለች። በሙለታ መንገሻ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8d%8d%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%8a%a2%e1%8a%ae%e1%8a%96/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
dd87183cfa155798b7dce2bc8d8bcbc6
4ddd1b57967b937161c3ed302f919fd0
በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ለገበያ ቀረቡ
በደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ማንሳት ስራ ላይ ተሰማርቶ የቆየው ሮዝ ቢዝነስ ግሩፕ በሀገር ውስጥ ያመረታቸውን ባለ ሶስት እግር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለገበያ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው የጃፓን ቴክኖሎጂን የታጠቁ፣ ባትሪያቸውን በኤሌክትሪክ በመሙላት ብቻ የሚጓጓዙ፣ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ደብረ ዘይት አካባቢ በገነባው ፋብሪካው ማምረቱን የኩባንያው ባለቤት አቶ ሮቤል እስጢፋኖስ አስታውቀዋል፡፡ ፋብሪካውን ከአንድ ዓመት በፊት መገንባት እንደጀመሩ የጠቆሙት አቶ ሮቤል፤በአሁኑ ወቅት በአንድ ሰዓት አንድ የኤሌክትሪክ ባለ ሶስት እግር መኪና ማምረት እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ ለ4 ሰዓት በተሞላ ባትሪ መቶ ኪሎ ሜትር ድረስ መንዳት ያስችላል ያሉት ባለቤቱ፤ ኤሌክትሪክ ለመሙላትም 7 ብር ብቻ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል፡፡ ተሽከርካሪው በዋናነት ከከተማ ውጪ ላሉ አካባቢዎች የሚያገለግል ሲሆን ለሰፋፊ ግቢ የውስጥ ለውስጥ እንቅስቃሴ፣ ለሽርሽር እንዲሁም ለተለያየ ዓይነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል ነው ተብሏል፡፡ ሹፌሩን ጨምሮም 7 ሰዎች የመያዝ አቅም አለው፡፡ኩባንያው ተሽከርካሪውን ከኢትዮጵያ አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ገበያ ለማቅረብ ማቀዱንም ባለቤቱ ባለፈው ሰኞ፣ በተሽከርካሪው የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ተናግረዋል፡፡ የኩባንያው መነሻ ካፒታል 24.9 ሚሊዮን ብር መሆኑንና ለ105 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩን የጠቀሱት አቶ ሮቤል፤የተሽከርካሪውን ዋጋ በተመለከተ ገዥዎች ሲመጡ ብቻ ቢያውቁት ይሻላል በሚል ከመግለፅ ተቆጥበዋል፡፡   
ቢዝነስ
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=20329:%E1%89%A0%E1%8A%A4%E1%88%8C%E1%8A%AD%E1%89%B5%E1%88%AA%E1%8A%AD-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%B0%E1%88%A9-%E1%89%B0%E1%88%BD%E1%8A%A8%E1%88%AD%E1%8A%AB%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%88%88%E1%8C%88%E1%89%A0%E1%8B%AB-%E1%89%80%E1%88%A8%E1%89%A1&Itemid=240
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1543c8722f4907be55c94624fe307020
de5302b1d3d0410337cfa4fa85d26397
መተከል ዞን ውስጥ ሰዎች ተገደሉ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በማቆያ ውስጥ ያሉ የአራት አባላቱን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።በመተከል ዞን ውስጥ በሲቪሎች ላይ እየተፈፀመ ባለ ጥቃት ዛሬ ማለዳ ላይም ድባጤ ወረዳ ዚጊ ቀበሌ ውስጥ ሁለት ሰዎች ተገለዋል፤ አንድ ሰው ቆስሏል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ግብረኃይል የመተከል ዞንን ፀጥታ የማስከበር እንቅስቃሴ መጀመሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/benshangul-gumz-new-attacks-12-29-2020/5717507.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
f963b3f13227e329fbd6d6f579110577
0c720095e89a2f856090dc8efdf112d3
ቻን 2020 | ካፍ የኢትዮጵያ ጉብኝቱን ትላንት አጠናቀቀ
በ2020 የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) አስተናጋጅ የሆነችው ኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት በካፍ ከፍተኛ ባለሙያዎች የስታዲየምቿ ዝግጅት ተገምግሟል።ይህን ውድድር ያስተናግዳሉ ተብለው የተለዩትና ሙሉ ለሙሉ ተገንብተው መጠናቀቅ ያልቻሉት የሀዋሳ፣ መቐለ፣ ባህርዳር እና የአደይ አበባ ስታዲየሞችን ባሳለፍነው ዓመት ከካፍ በተላኩ ባለሙያዎች አማካኝነት በመዟዟር የተጎበኙ ሲሆን በዚህ ሳምንትም የመጨረሻው የግምገማ ምዕራፍ ተካሂዷል። የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት ሊሆድጋር ቴንጋ እና ሞሰስ ማጎጎ፣ የካፍ የክለቦች ፍቃድ ሰጪ ኃላፊ አህመድ ሀራዝ እና ሁለት የሚዲያ ባለሙያዎች ሐሙስ ወደ አዲስ አበባ ከገቡ በኃላ ዓርብ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉብኝታቸውን በማድረግ ነበር የግምገማ ጅማሮ ያደረጉት።በመቀጠል ቅዳሜ ወደ መቐለ በማምራት የትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየምን በመጎብኘት ግምገማ አድርገዋል። የመጫወቻ ሜዳውን እንዲሁም በስታዲየሙ ቅጥር ጊቢ የተሰራውን የመለማመጃ ሜዳ እና የመቐለ ዩኒቨርሲቲን ስታድየም የጎበኙ ሲሆን በተለይ የዓለም አቀፉን ስታድየም ውስጣዊ እና ውጫዊ አካል በመጎብኘት በሀዋሳ ስታዲየም የተገጠመው መብራት በመቐለ አለመከናወኑን እንደ ጉድለት ማንሳታቸው ታውቋል።ዕሁድ የሶስተኛ ጉብኝታቸው መዳረሻን ባህር ዳር በማድረግ ዓለም አቀፍ ስታድየም፣ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ (ፔዳ ጊቢ)፣ የአፄ ቴዎድሮስ ስታድየም ከመለማመጃ ሜዳው ጋር ተመልክተዋል። ትላንት ከሰዓት ደግሞ በግንባታ ላይ የሚገኘው የአደይ አበባ ስታዲየምን ከተመለከቱ በኋላ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ አስመልክቶ ጥያቄ አቅርበዋል። ለልምምድ ያገለግላሉ የተባሉትን በወጣቶች አካዳሚ ያሉ ሁለት የመለማመጃ ስፍራን ጨምሮ አንጋፋውን የአዲስ አበባ ስታዲየም የተመለከቱ ሲሆን አንድ የመለማመጃ ሜዳ ግን በቶሎ መሰራት እንዳለበት ለፌዴሬሽኑ ማሳሰባቸው ተነግሯል፡፡ ያለፍትን አምስት ቀናት የቻን 2020 የዝግጅት ግምገማን በማጠናቀቅም ትላንት ምሽት የተመለሱ ሲሆን ልዑኩ በቀጣይ ሳምንት የግምገማውን ውጤት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን እና ለሀገሪቱ መንግስት እንደሚልክ ተሰምቷል።ረጅም የግንባታ ዓመታት የወሰዱት እና እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ያልተጠናቀቁ በርካታ ስታድየሞች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የቻን ውድድርን ለማካሄድ ከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ በቀረበት በዚህ ወቅት ከሚመለከታቸው አካላት ስለ መስተንግዶው ቅድመ ዝግጅት እና እስካሁን እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ይፋዊ መረጃ እየተሰጠ የማይገኝ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ መሟላት ከሚገባቸው በርካታ ጉዳዮች አንዱ የሆነው የስታድየም ቅድመ ሁኔታዎች (ደረጃውን የጠበቀ የመጫወቻ ሳር፣ የተጠባባቂ ተጫዋቾች እና የቡድን አመራሮች መቀመጫ፣ ፓውዛ፣ በስታድየሙ የተለያዩ ክፍሎች የሚገጠሙ የኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎች፣ በቂ የመልበሻ ክፍል፣ የሚዲያዎች እና የጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል፣ በቂ መፀዳጃ ክፍሎች፣ በአንድ ከተማ እስከ አራት የልምምድ ሜዳ) እና የመሳሰሉትን በቀሪዎቹ ወራት የማሟላት ኃላፊነት ይጠበቅባታል።
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/45596
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
4801fc349ef10630f9b5f16963b2b5f5
7c84ac503336f93af8e8b10eea9d4592
አፍሪካውያን በዶፒንግ ስጋት ከዓለም ቀዳሚ ናቸው
ጎረቤታሞቹ የምስራቅ አፍሪካ የረጅም ርቀት ፈርጦች ኬንያና ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ያላቸውን መልካም ስም ያህል በስፖርቱ ትልቅ አደጋ እያንዣበበባቸው ይገኛል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአትሌቲክሱ አበረታች መድሃኒት ወይም ንጥረ ነገሮች ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ ሩሲያንን የመሳሰሉ ታላላቅ አገራት ከታላላቅ ውድድሮች እስከመታገድ ደርሰዋል። እነዚህ አገራት አትሌቶቻቸው በብዛት አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆነው ከመገኘታቸው ጋር ተያይዞ በመንግስት ጭምር ይደገፋሉ በሚል ከውድድሮች መታገዳቸው ይታወቃል። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ኤጀንሲ እነ ሩሲያን በቀጣበት ወቅት ኢትዮጵያና ኬንያ አደጋው በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሰጋቸው በማሳወቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክረሃሳብ ሰጥቷቸው ነበር። ሁለቱ አገራት በተለይም ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥታ በመስራት አበረታች ውጤት ማስመዝገቧም በኤጀንሲው ጭምር ተመስክሮላታል። ያም ሆኖ ስጋቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀርፏል ለማለት አይቻልም። ባለፈው ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያና ኬንያን በአበረታች መድሃኒት(ዶፒንግ) ምክንያት ስጋት ካለባቸው አገራት ቀዳሚውን ደረጃ እንደሚይዙ ማሳወቁ ይታወሳል። ዘንድሮም ሁለቱ አገራት በአበረታች መድሃኒት ስጋት ቁንጮውን ደረጃ መያዛቸው እንደማይቀር እየወጡ ያሉ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ለዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ አምስት የአፍሪካ አገራት አትሌቶች አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆነው መገኘታቸው ማሳያ ተደርጓል። ቤላሩስና ዩክሬን ሁለቱን የአፍሪካ አገራት ተከትሎ ስማቸው ከቁንጮዎቹ ተርታ ተፅፏል። የአስራ ስምንት ዓመቷ ኬንያዊት አትሌት አንጌላ ሙንጉቲ ከቀናት በፊት አበረታች መድሃኒት ተጠቅማ በመገኘቷ እገዳ ተጥሎባታል። በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የስምንት መቶ ሜትር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነችው ይህች አትሌት በዚህ ወንጀል የተያዘች አርባ አራተኛዋ ኬንያዊት አትሌት ሆናለች። አትሌቷ ባለፈው ዓመት አርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የወጣቶች ኦሊምፒክም በስምንት መቶ ሜትር አገሯን ወክላ መወዳደር ችላለች። የዓለም አቀፉ ፀረ አበረታች መድሃኒት አዋጅ የትኛውም አትሌት በውስጡ ለተገኘ አበረቻች ንጥረ ነገር ሃላፊነቱን ይወሳዳል። ይህችም አትሌት ኖራንድሮስቴሮን የተባለ አበረታች ንጥረነገር ተጠቅማ መገኘቷ ተረጋግጣል። ሙንጉቲ በስምንት መቶ ሜትር 2፡06፡21 የሆነ የራሷ ፈጣን ሰዓት ያላት ሲሆን ባለፈው ዓመት በኬንያ ከሃያ ዓመት ቻምፒዮና ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች። ፊሊፕ ሳንጋ ኪሙታይ የተባለው የሰላሳ ስድስት ዓመት ኬንያዊ አትሌት ቴስቴስትሮን የተባለ አበረታች ንጥረነገር ተጠቅሞ የተገኘ አርባ ሦስተኛው ኬንያዊ አትሌት ነው። የዚህ አትሌት ምርመራ በሂደት ላይ ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ከስፖርቱ ለአራት ዓመታት ሊታገድ እንደሚችል ታውቋል። ኪሙታይ በማራቶን 2፡06፡07 ሰዓት ያለው ሲሆን እኤአ 2011 ላይ በፍራንክፈርት ማራቶን ያስመዘገበው ይህ ሰዓት በውድድር ዓመቱ አስራ ሦስተኛው ፈጣን አትሌት አድርጎት ነበር። ይህ አትሌት ባለፈው ዓመት በጎልድ ኮስት ማራቶን አምስተኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ 2፡11፡44 ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል። በሆንግኮንግ ማራቶንም አስረኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡15፡31 ሰዓት ተመዝግቦለታል። በዚህ ወር በአበረታች መድሃኒት ተጠቃሚነት ቅጣት የተላለፈበት ወይንም የተገኘበት አርባ ሁለተኛው ኬንያዊ አትሌት ቪንሰንት ኪፕሴጊች ነው። ይህ የሰላሳ ዓመት አትሌት ቀደም ሲል የተጠቀሰው ኬንያዊ አትሌት ኪሙታይ በጎልድ ኮስት ማራቶን አምስተኛ ሲያጠናቅቅ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል። 2፡09፡59 የሆነ የራሱ ፈጣን ሰዓትም አለው። ሚያዝያ ወር ላይም በቬና ማራቶን ሰባተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ 2፡10፡02 አስመዝግቧል። በተመሳሳይ ከዓመት በፊት በሆኖሉሉ ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ጨርሷል። ኢትዮጵውያን አትሌቶች በተለይም በግል ውድድሮች ብቻ የሚታወቁት አልፎ አልፎ በአበረታች መድሃኒት ሲቀጡ ይታያል። ይሁን እንጂ አገርን ወክለው በሚወዳደሩ አትሌቶች ይህ ቅሌት አይታይም ማለት ይቻላል። ባለፈው ክረምት በሞሮኮ ራባት በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን ወክሎ በአስር ሺ ሜትር ወርቅ ማጥለቅ የቻለው ብርሃኑ ፀጉ ኢፒኦ የተባለ ንጥረ ነገር ተገኝቶበት ላልተወሰነ ጊዜ ከስፖርቱ ታግዷል። ይህ የሃያ ዓመት አትሌት ባለፈው ወር በኮፐንሃገን ግማሽ ማራቶን ላይ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ብርሃኑ ሔንግሎ በተካሄደው የዓለም ቻምፒዮና የኢትዮጵያውያን ማጣሪያ ውድድር ላይ 10ሺ ሜትሩን 27፡00፡73 በሆነ ሰዓት ማጠናቀቅ ችሏል። ብርሃኑ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ኤርትራዊው አሮን ክፍሌና ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ጀማል ይመር ተከትለውት መግባታቸው ይታወሳል። ብርሃኑ የወርቅ ሜዳሊያውን ተነጥቆ ለኤርትራዊው አትሌት፣ የብር ሜዳሊያው ደግሞ ለጀማል ይመር የሚሰጥ ሲሆን አራተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ኬንያዊው ኤድዊን ሦይ የነሐስ ሜዳሊያ ሊያገኝ እንደሚችል መረጃዎች እየወጡ ነው። በአዲስ አበባ አበረታች መድሃኒቶች በስቴድየም አካባቢ ካለ ሃኪም ማዘዣ ጭምር እንደሚሸጡ የእንግሊዝ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ተከትሎ የዓለም አትሌቲክስ ኢትዮጵያን ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች መድሃኒቶች ፅሕፈት ቤትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለአትሌቶች የተለያዩ ትምህርቶችን እየሰጡ ይገኛሉ። በቅርብ ወራት አበረታች መድሃኒት ተጠቃሚ ሆኖ በመገኘት ስማቸው ከተዘረዘሩ አፍሪካውያን መካከል ሞሮኳዊው ሙስጠፋ ኤል አዚዝ አንዱ ነው። ይህ አትሌት ለአራት ዓመታት ከስፖርቱ እንዲርቅ ቅጣት የተጣለበት ሲሆን 2014 የአፍሪካ ቻምፒዮና ላይ በአስር ሺ ሜትር የብር ሜዳሊያ በማጥለቁ ይታወቃል። ይህ የሰላሳ ሦስት ዓመት አትሌት ባለፈው ሰኔ ክሮሽያ ውስጥ በተካሄደ የጎዳና ላይ ውድድር አበረታች ንጥረነገር ተጠቅሞ በመገኘቱ እገዳው እንደተላለፈበት ተነግሯል። ሞሮኮ በአበረታች መድሃኒት አደጋ ውስጥ ከሚገኙ አገራት መካከል ትጠቀሳለች። ይሁን እንጂ በዚህ አደጋ እጅግ ችግር ውስጥ ካሉ አገራት ተርታ በ2017 የወጣች ቢሆንም አሁን ተመልሳ ገብታበታለች።አዲስ ዘመን ጥቅምት 17/2012 ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=21537
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
ac528c545f42a70217e3a1ab3db5edb9
e8b0d6949be4e3b6e0efa49ddd171335
"የእንግሊዙ ተቋም በኬንያ ዳግመ ምርጫ ጣልቃ ገብቷል"
ናሽናል ሱፐር አላያንስ (ናሳ) የተሰኘው የኬንያ ዋነኛ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ባለሥልጣን የሆኑት ኖርማን ማጋያ የተሰኙ ግለሰብ ለቢቢሲ አንደተናገሩት ገዢው ፓርቲና አማካሪው ተቋም የህዝብን ድምፅ በመስረቅ ወንጀል ሊከሰሱ ይገባል። የአማካሪ ተቋሙ ኃላፊዎች በኬንያ ምርጫ የነበራቸውን ሚና በኩራት ሲያወሩ ሳያስቡት በካሜራ እይታ ወስጥ ከገቡ በኋላ ነው ሁኔታው ቀልብ መግዛት የጀመረው። ተቋሙ በሂደቱ ውስት እጄ የለበትም ሲል ማስተባበሉ አልቀረም። ገዢው ጁቢሊ ፓርቲ ሁኔታውን ያጣጣለው ሲሆን አማካሪ ድርጅቱ ለማስታወቂያ ሥራ የተቀጠረ እንጂ ለሌላ ጉዳይ የመጣ አይደለም ብሏል። የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዳቪድ ሙራቴ ለሮይተርስ ዜና ወኪል ሲናገሩ "ድርጅቱ የፓርቲያችንን አርማ ማስታወቂያ ለመስራት የመጣ እንጂ ህግ ወጥ ተግባር ሊፈፅም የተቀጠረ አይደለም" ብለዋል። ተቋሙ በመገናኛ ብዙሃን ዓይን ውስጥ መግባት የጀመረው የአሜሪካው ፕሬዙደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደስልጣን እንዲመጡ አግዟል የሚል ወሬ መስፋፋት ከጀመረ ወዲህ ነበር። ከፌስቡክ ላይ የሰዎችን ግላዊ መረጃ ያለፈቃዳቸው ወስዷል በሚልም እየተከሰሰ ይገኛል። አከራካሪ ጉዳዮች ያልተለዩት የኬንያ ምርጫ በወርሃ ሰኔ ከተካሄድ በኋላ ኡሁሩ ማሸነፋቸው ተነግሮ ነበር። ነገር ግን ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት ተቃዋሚው ኦዲንጋ ተሳክቶላቸው ምርጫው በፍርድ ቤት ውድቅ ሆኖ ድጋሚ እንዲካሄድ ተወሰነ። በዳግመ-ምርጫው ወቅት ሁኔታዎች አሁንም ፍትሃዊ አይደሉም ያሉት ኦዲንጋ ምርጫውን አቋርጠው ወጡ፤ ኡሁሩም ድጋሚ አሸነፉ። በቅርቡ ግን የማይታሰብ የሚመስለው ሆነ። ኦዲንጋ እና መሪው ኡሁሩ ተቃቅፈው ታዩ። ልዩነቶቻችንን ለመፍታት ጠንክረን እነሠራለን ሲሉም ተደመጡ። ምንም እንኳ አሁን ላይ በሁለቱ ግለሰቦች መካከል ያለው ግንኙነት መልካም ቢመስልም የናሳው ማጋያ መሰል ማጭበርበሮች ለኬንያ ዴሞክራሲ ዕድገት ፀር ናቸው በማለት ነው እየከሰሱ ያሉት።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
1ee10ccab46c445d227c35add3274762
932921328f09a867725d324b1ee9525b
በጃፓን የእንክብካቤ ማዕከል በጎርፍ ተጥለቅልቆ 14 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ
ከሟቾቹ 14ቱ የተገኙት በጎርፍ በተጥለቀለቀ አንድ የእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ነው። የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል። ኩማሞቶ እና ካጎሺማ በአደጋው ክፉኛ የተጠቁ ግዛቶች ናቸው። የኩማሞቶ ገዢ ኢኮ ካባሺማ በእንክብካቤ ማዕከላት የነበሩት ተጎጂዎች ከልብ ህመም ጋር በተያያዘ መሞታቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ የጤና ባለሙያዎች የሞት ምስክር ወረቀት አለመስጠታቸውም ተገልጿል። አደጋውን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፤ ቤቶችና መኪኖች በጎርፍ ተውጠው ከሚያሳይ ፎቶ ጋር በኩማ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ በጎርፍ ሲወሰድ ያሳያሉ። ባለሥልጣናትም ከ200 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ያዘዙ ሲሆን፤ የነፍስ አድን ሰራተኞችን ለማገዝም 10 ሺህ ወታደሮችን ወደ ሥፍራው ልከዋል። ይሄው እየጣለ ያለው ዝናብ ዛሬም እንደሚቀጥል ትንበያ ተቀምጧል። ጠቅላይ ሚኒስተር ሽንዞ አቤ በበኩላቸው ሰዎች በተጠንቀቅ እንዲጠባበቁ አሳስበዋል። የጃፓን የሚትዮሮሎጂ ኤጀንሲ በአካባቢው እንደዚህ ዓይነት ዝናብ ከዚህ በፊት አጋጥሞ እንደማያውቅ ተናግረዋል። በተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ የሚገኙ አንድ ሴት ዝናብ ይህን ያህል ኃይለኛ ሊሆን ይችላል ብለው በእውናቸውም በህልማቸውም አስበው እንደማያውቁ ተናግረዋል። ሌላኛዋም በበኩላቸው በአቅራቢ ያለው ወንዝ እየነጎደ ሲወርድ ምን ያህል አደገኛ እንደነበር መረዳታቸውን ገልፀዋል። የጃፓን ብሔራዊ መገናኛ ብዙሃን (ኤንኤችኬ) ታኪኖ አካባቢ ስምንት ቤቶች በጎርፍ እንደተወሰዱ የሚያስረዱ ዘገባዎች መኖራቸውን ገልጿል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
8e7f3fc88510a7d47ba33580c1f85a64
1ea5abe2726d602873e9444ea9142e8d
የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ሲወጡ ሌላ ክስ የተመሠረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በዋስ ተለቀቁ
የአይኤስ አሸባሪ ቡድን ሊቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው አሰቃቂ ግድያ ምክንያት መንግሥት በጠራው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ረብሻ በመፍጠር ተከሰው የተፈረደባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ሲወጡ ከማረሚያ ቤት በራፍ ላይ ተይዘው ከተመሠረተባቸው ክስ በዋስ እንዲለቀቁ ብይን ተሰጠ፡፡የፓርቲው አባላት ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. እያንዳንዳቸው በ5,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቄራ ምድብ ችሎት ብይን የሰጠው በወይንሸት ሞላ፣ በኤርሚያስ ፀጋዬ፣ በዳንኤል ተስፋዬና በቤተልሔም አካለ ወርቅ ላይ ነው፡፡በተከሳሾቹ ላይ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ተሰጥቶ የነበረው፣ ሰላማዊ ሠልፉን በማወክ የተለያዩ ስድቦችን መንግሥትንና ዜጎችን በመሳደብ፣ ሥርዓቱን በማንጓጠጥና በፖሊስ አባላት ላይ ድንጋይ በመወርወር ወንጀል ተከሰው ነው፡፡ፍርደኞቹ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፍርድ በቀረቡበት ዕለት ሁለት ወር ከአንድ ቀን በእስር መቆየታቸው በመረጋገጡ፣ በዕለቱ ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ፖሊስ ሌላ ወንጀል መፈጸማቸውን በመግለጽ፣ ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእስር ተፈትተው ወደ ቤታቸው ለማምራት ማረሚያ ቤት ደጃፍ ላይ ሲደርሱ ተይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ፖሊስ ለፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ፣ ተከሳሾቹ ቀደም ብሎ በተከሰሱበት ወንጀል ላይ በምስክርነት ያቀረባቸውን ማስፈራራታቸውንና መዛታቸውን በመግለጽ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ክሱን ተቀብሎ ለሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. መዛታቸውን የሚያስረዱለትን ምስክሮቹን እንዲያቀርብ ቀጠሮ የሰጠ ቢሆንም፣ ፖሊስ ምስክሮቹን በተለያዩ ምክንያቶች ሊያቀርብ አለመቻሉን ገልጾ፣ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል፡፡ተከሳሾቹ ግን ፖሊስ ምስክሮቹን በተሰጠው ቀጠሮ ቀን ማቅረብ እንደነበረበት ገልጸው፣ ፍርድ ቤቱ ዋስትና እንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ጥያቄውን ተቀብሎ እያንዳንዳቸው በ5,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል፡፡ በሌላ በኩል ተከሳሾቹ ቀደም ብሎ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ሁለት ወራት ተፈርዶባቸው በነበረውና እስራቸውን ጨርሰው በወጡበት ክስ፣ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ እንዳለባቸውና ሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተጠቁሟል፡፡
ፖለቲካ
https://www.ethiopianreporter.com/article/7799
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
c9d156cfbb2b2d2ba9ee564bc21f0b64
a5f1c2fedcddba3b569783681b271794
ግበጽ እና ኦስትሪያ በትምህርትና በሳይንስ ዘርፍ የአምስት አመት የፕሮቶኮል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ግበጽ እና ኦስትሪያ በትምህርትና በሳይንስ ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያሰችላቸውን የአምስት ዓመት የፕሮቶኮል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ትኩረቱን በአዳዲስ ግኝቶችና ቴክኖሎጂዎች ላይ አድርጎ በኦስትሪያ ቪየና በተካሄደውየ አፍሪካና አውሮፓ ህብረት ፎረምላ ይተሳታፊ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡በዚህ ወቅትም ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ክሩዝ ጋር በአለም አቀፋዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ከማድረጋቸው ባሻገር የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ማካሄዳቸው ይታወቃል፡፡አልሲሲ በኦስትሪያቬና በነበራቸው ቆይታ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አሌግዛንደር ዳንደርቤልናንድ ጋር ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂደዋል፡፡ሀገራቸውም በኢኮኖሚው መስክ ከኦስትሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ጠቅሰዋል ። (ምንጭ:  ኢጂፕት ኢንዲፔንደንት ) 
ሀገር አቀፍ ዜና
https://waltainfo.com/am/33418/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
6821981f505265928ebc0315a8a10bf0
c100d6fe88b1cd7807809c1b854f4aca
ጀጎል ግንብ
የጀጎል ግንብ በ1551-1552 በንጉስ/አሚር ኑር ቢን ሙጃሂድ እንደተገነባ የታሪክ መዛግብት ያመላክታሉ። ይህ ግንብ ከምድር ከ4-5 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን ወርዱ ደግሞ ከ50-75 ሴንቲሜትር ይሰፋል። አጠቃላይ ስፋቱ 48 ሄክታር ነው። የግምቡ መፈጠር ዐቢይ ምክንያትም ሐረሪዎችን ከዘመኑ ወራሪዎች /ጦረኞች/ ለመታደግ ተብሎ እንደ ተሰራ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። ግንቡ አምስት በሮች ያሉት ሲሆን ውሃ ያለበትን አቅጣጫም ለማመልከት የተሰሩ ናቸው። የጀጎል አምስቱ ጥንታዊ ዋና ዋና በሮች:- በሐረሪ 1, አስማጂን በሪ 2, በድሪ በሪ 3, ሱጉድአጥ በሪ 4, አርጎባ በሪ 5, አሱሚይ በሪ በአማርኛ 1, ሸዋ በር 2, ቡዳ በር 3, ሰንጋ በር 4, ኤረር በር 5, ፈላና በር በሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰራው ዱክ በር ወይም መስፍን በር : አሁን ብዙዎቹ የሚጠሩት ሐረር በር ከጥንታዊዎቹ ጋር የማይገናኝ ነው። ብዙ ሰዎች የጥንቱን አምስት በሮች ጥሩ ሲባሉ፣ የሐረር በርንም ያካትታሉ። ባይሆን ስድስተኛው ብለን፣ በቅርቡ የተሰራ ብለን ልንጠራው እንችላለን። ሐረር
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
503d493de32d24823fd66f0c657a1416
280c0e2bb4209b731071f4760973fb3b
ጋዳፊ ከስልጣን እንዲወርዱ ሲደረግ በነበረ ግድያ የተሳተፉ 45 ሰዎች ላይ ሞት ተፈረደ
የሊቢያ አማፂያን በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን (ኔቶ) ታግዘው የጋዳፊን መንግሥት ከስልጣን ወርውረው ትሪፖሊን የተቆጣጠሩት ከ7 ዓመታት በፊት ነበር። የሊቢያ ፍትህ ሚኒስቴር እንዳለው 45ቱ ሚሊሻዎች የጋዳፊ መንግሥትን ለመጣል ብረት ያነገቡ አማጺያን ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካቶችን በመግደላቸው ነው የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው። ኤኤፍፒ እንደዘገበው ከጋዳፊ የስልጣን ዘመን በኋላ 45 ሰዎች ላይ በተመሳሳይ ጊዜ የሞት ፍርድ ሲተላለፍ ይህ ትልቁ ቁጥር ነው። • መንግሥትና ኦብነግ የጀመሩት ጉዞ የት ያደርሳል? • የመገንጠል መብት ለማን? መቼ? • የ"ይቻላል" መንፈስ የሰፈነበት የአዲስ አበባው ቴድኤክስ የንግግር መድረክ በሊቢያ ከተቀሰቀሰው ህዝባዊው አመጽ በኋላ አገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት ርቋት ቆይታለች። 45 ሰዎች ላይ ከተላለፈው የሞት ፍርድ በተጨማሪ 54 ሰዎች ላይ የአምስት ዓመት የእስር ፍርድ ተላልፏል። ሰይፍ አል-ኢስላም ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ወደ ፖለቲካው ዓለም ለመመለስ እየሰበ እንደሆነ ተናግሮ ነበር። የጋዳፊ ልጅ የሆነው ሰይፍ አል-ኢስላምን ጨምሮ በጋዳፊ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የነበሩት ላይ የሞት ፍርድ ተላልፎ ነበር። በሊቢያ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ፍርደኞች አብዛኛውን ጊዜ ፍርዱ ተፈጻሚ ሳይሆንባቸው እድሜ ልክ በእስር እንዲያሳልፉ ይደረጋል። ይሁን እንጂ ሰይፍ አል-ኢስላም ከአንድ ዓመት በፊት ከእስር ተለቋል። ሰይፍ አል-ኢስላም ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ከሬውተርስ ጋር ነበረው ቆይታ ወደ ፖለቲካው ዓለም ለመመለስ እየሰበ እንደሆነ ተናግሮ ነበር።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
7e227bc8100558aa690dd0da915941ba
599d9148edadb50c6b3b249698389b0a
ደቡብ ፖሊስ ተመስገን ዳናን በይፋ አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
በዐምናው የውድድር ዘመን ከፕሪምየር ሊጉ የወረደው እና የፎርማት ለውጡን ተከትሎ በድጋሚ ወደ ሊጉ የተመለሰው ደቡብ ፖሊስ ተመስገን ዳናን በይፋ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን ዛሬ በክለቡ ፅህፈት ቤት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የክለቡ አዲስ ተሿሚ ፕሬዝዳንት አቶ ታሪኩ ኡጋሞ፣ የክለቡ ሥራ-አስኪያጅ ኮማንደር ግርማ ዳባ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ ኢንስፔክተር እታገኝ ዜና እንዲሁም አዲሱ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና እና ሌሎች የክለቡ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።ረጅም ዓመታትን የክለቡ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲመሩ የነበሩት ኮማንደር ዳንኤል ገዛኸኝ በጡረታ መሰናበትን ተከትሎ የደቡብ ፖሊስ ፕሬዝዳንት በመሆን የተሾሙት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ ታሪኩ ኡጋሞ ስለ አዲሱ አሰልጣኝ ሹመት በተመለከተ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግራቸው ነበር ፕሮግራሙ የጀመረው። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው “በዋናነት አሰልጣኙ በታዳጊዎች የሚያምን በመሆኑና ይህንንም በቁርጠኝነት ተግባራዊ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ወጣት አሰልጣኝ በመሆኑ ልንመርጠው ችለናል። ከውጤታማነትም አንፃር ክለቡን ወደ አንድ ምዕራፍ ከፍ ያደርጋል የሚል እምነት ስላለን ነው እሱን የመረጥነው። ብለዋል።በመቀጠል የክለቡ ሥራ-አስኪያጅ ኮማንደር ግርማ ዳባ ባደረጉት ንግግር “ይህ ክለብ እጅግ በርካታ ስፖርቶኞችን እና አሰልጣኞችን ማፍራት ችሏል፡፡ የበርካታ ታዳጊ ልጆችም ማፍለቂያ ነው። ሠራዊታችን ከሚሰራው የፀጥታ ስራ ባለፈ እንደዚህ ወጣቱን የሚደግፍ እና ሠራዊቱንም ከህዝቡ የሚያገናኝ ሲሆን ከአገናኝ ድልድዮቹ መካከል ደግሞ ስፖርቱ አንዱ ነው። ክለባችን በእግር ኳሱም ብቻ ሳይሆን በሌሎች የክለቡ በያዛቸው የስፖርት ዓይነቶች በተለይ በአትሌቲክሱ ውጤታማ ስፖርተኞችን ለኢትዮጵያ አበርክቷል። እግር ኳስ ክለቡን ወደቀደመው ማንነቱ ለመመለስ እና ለእኛም ሆነ ለሠራዊቱ ትልቅ ደስታን ለመፍጠር ተዘጋጅተናል። ለ2012 የውድድር ዓመት ክለቡ የተሻለ እና ውጤታማ የሆነ ውጤት የሚያስመዘግብበት መንገድ ለመክፈት ተግተን በመስራት ለክለባችንም ሆነ ለሀገር ጥሩ ተጫዋቾችን እናወጣለን።” ብለዋል።በመቀጠል የክለቡ የቦርድ አባል እና የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር እታገኝ ዜና በበኩሏ “ተመስገን ዳናን ስንመርጥ ደስ ብሎን ነው። እንደ ክለብ ታዳጊዎች ላይ ለመስራት ፍላጎት ስላለን እና ክለቡን በሚገባ ስለሚያውቅ ወደተሻለ ተፎካካሪነት ያመጣናል ብለን እናምናለን። ላሰብነው ዕቅድ እሱን አሰልጣኝ በማድረጋችን ዕድለኛ ነን” በማለት ሀሳቧን ገልጻለች፡፡አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ በመሆን በይፋ የተሾመው ተመስገን ዳና በበኩሉ “ደቡብ ፖሊስ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ብዙ አበርክቷል። እግርኳሱን ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ስፖርት ትልቅ ደረጃ ለማድረስ እየሰራ ያለ ነው። ይሄ ቡድን ወጣቶች ላይ የሚሰራ በመሆኑ ሌሎች ክለቦች ላይ የመስራት ዕድል እያለኝ ነው ደቡብ ፖሊስን የመረጥኩት። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ ተፎካካሪ ለማድረግ ነው ዕቅዴ። ክለቡን የማሰልጠን ዕድልን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ። በ2012 ደቡብ ፖሊስ ከዚህ ቀደም ያላሳካቸውን ስኬቶች አሳካለው የሚል ትልቅ እምነት አለኝ። ” ብሏል።በመቀጠል በስፍራው ከተገኙ ጋዜጠኞች ጥያቄ ከተነሳ በኋላ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡አሰልጣኝ ተመስገን ዳናለፕሪምየር ሊጉ አዲስ መሆኑ“በእርግጥ ለፕሪምየር ሊጉ አዲስ አሰልጣኝ ነኝ። አዲስ ነኝ ማለት ግን ለእግር ኳሱ አዲስ ነኝ ማለት አይደለም። በደንብ አድርጌ የኢትዮጵያን እግር ኳስ አውቀዋለሁ። ለ20 ዓመታት ተመልክቼዋለሁ፤ ለአንድ ዓመት ደግሞ ውስጡ ገብቼ ሰርቼበታለሁ። ከዛ ውጪ ስልጠናው ለኔ አዲስ አይደለም። ውድድሩም ለኔ አዲስ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። ወጣት አሰልጣኝ እንደመሆኔ ከወጣቶች ጋር ተባብሮ በመስራት ቡድኑን ወደተሻለ ደረጃ ማምጣት ይቻላል የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ ስጋት ይኖራል ብዬ አላምንም”አቶ ታሪኩ ኡጋሞክለቡ ከዐምናው ምን ተምሯል? ወደ ፕሪምየር ሊግ እንደመመለሱ ከአሁኑ ምን ታስቧል?“ዐምና በነበረው ሂደት ደቡብ ፖሊስ ዝቅተኛ ውጤት ነበረው። አሁን ግን የነበሩትን ስህተቶች በማረም ጠንከር ያለ ተወዳዳሪ ለመሆን እንሰራለን። ባለኝ መጠነኛ ልምድ እንዳየሁት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብዙም የተራራቀ አይደለም፤ የተቀራረበ ነው። በጥቃቅን ስህተቶች አንዱ ክለብ ይሸነፋል አንዱ ደግሞ ያሸንፋል። እውነት ነው እኛጋ ትናንሽ ስህተቶች ነበሩ፤ እነሱን አሁን በሚገባ እንቀርፋለን። አሰልጣኙም በዚህ በኩል ዝግጅት እያደረገ ነው። ካለፈው ዓመት ተምረን ጥሩ ቡድን ለመገንባት በዝግጅት ላይ ነን።” በስፖርታዊ ጨዋነት ላይም የክለቡ ተጫዋቾችም ሆኑ መላው የክለቡ ቤተሰብን ለማስተማር ተዘጋጅተናል። ፌዴሬሽኑ ያወጣውን የደመወዝ ጣሪያ ስርዓት ተከትለን አዝናኝ እና ማራኪ እግር ኳስን የሚያሳይ እንዲሁም ወጣቶችን የሚያበቃ ቡድን ለመገንባት ቆርጠን ተነስተናል።”የክለቡ ስራአስኪያጅ በመጨረሻ ንግግራቸው ለአሰልጣኙ ሙሉውን ኃላፊነት እና ነፃነት የሰጡ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በአሰልጣኙም ምርጫ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት የማዋቀር መብት መሰጠቱን ገልፀዋል።
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/50641
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
146aa0c5336e79aa5f22ae5f18eae011
35487685e6ed464a6985309c6ffb4dc6
አቶ ቃሲም ፊጤ በነፃ ተሰናበቱ
የፌደራሉ ከፍተኛ  ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር  የመሬት አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ ባለስልጣን የቀድሞ ስራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም ፊጤ ተከሰው የነበረበትን የሙስና ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ  እንዲሰናበቱ ወሰነ። ተከሳሾቹ አቶ ቃሲም ፊጤን ጨምሮ  የሊዝ አሰባሰብ ክትትል ባለሙያ አቶ ገብረየስ ኪዳኔ፣ የመሬት አቅርቦት አፈፃፀም ንዑስ የስራ ሂደት መሪ በቀለ ገብሬ እና በአስተዳደሩ የፍትህ ቢሮ የምርመራና ክስ ኤክስፐርቱ ተስፋዬ ዘመድኩን ናቸው።የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ ተከሳሾች በህገ ወጥ መንገድ በመመሳጠር የተሰጣቸውን ስልጣንና  ሃላፊነት በግልፅ ተግባር ያላአግባብ በግድፈት በመገልገል፣ ለሌላ ሰው ህገ ወጥ የሆነ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ  የሙስና ወንጀል ነበር ክስ መስርቶባቸው የነበረው።ኢንጂነር ግርማ አፈወርቅ የሚባሉ ግለሰብ በቦሌ ክፈለ ከተማ ወረዳ 3 ክልል የተሰጣቸውን 500 ካሬ ሜትር ቦታ ያለአግባብ ለሌላ አልሚ ተመሳጥረው ባልተገባ መንገድ እንዲተላለፍ አድርገዋል የሚል ነበር ጥቅል ክሱ።የክሱ ሂደት እስከዛሬ ሲካሄድ ቆይቶ፥ ቀድም ብሎ አቃቤ ህግ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ክሱን ያስረዳልኛል ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቀረቧል።ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ይከላከሉ ወይም አይከላከሉ የሚለውን ለመበየን ዛሬ ይዞ በነበረው ቀጠሮ አቃቤ ህግ ክሱን በማስረጃ ማስረዳት ባለመቻሉ፥  አቶ ቃሲም ፊጤን ፣ አቶ ገብረየስ ኪዳኔንና በቀለ ገብሬን ክሱን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ይሰናበቱ ብሏል።ሌላው በክስ መዝገቡ የተካተቱት የአስተዳደሩ ፍትህ ቢሮ የምርመራ ክስ ኤክስፐርቱ አቶ ተስፋዬ ዘመድኩን የተመሰረተባቸው የሙስና ክስ የመንግስትን ስራ በማይመች አኳኋን መምራት በሚል በሌላ አንቀፅ ተሻሽሏል።ይህ ክስ ደግሞ የዋስትና መብት የሚከለክል ባለሙሆኑ 5 ሺህ ብር በዋስትና አስይዘው መፈታት እንዲችሉ በማለት እንዲከላከሉ ቀጠሮ ቢይዝም፥ ተከሳሹ አቶ ተስፋዬ ዘመድኩን የማቀርበው የመከላከያ ማስረጃ የለኝም፤ ቅጣት ይሰጠኝ በማለቱ ችሎቱ ለዛሬ ሳምንት ቀጠሮ ይዟል። (ኤፍ.ቢ.ሲ.)
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/24947/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
4d644980f979e6ca708710dd7d509596
2d53fae516cd14dffce09c3951da2f7e
አየር መንገዱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 130 ተማሪዎች አስመረቀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 130 ተማሪዎች አስመረቀ።ተመራቂዎቹ  በአብራሪነት ፣ በበረራ አስተናጋጅነት ፣ በአቪዬሽን ቴክኒሻን ፣ በማርኬቲንግ የሙያ መስኮች  የሰለጠኑ ናቸው።የአየር መንገዱ የአቪዬሽን አካዳሚ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል አሰፋ እንዳሉት ተቋሙ ለአፍሪካ ብሎም ለመላው አለም ብቃትና ጥራት ያላቸው የአቪዬሽን ባለሞያዎችን እያፈራ ይገኛል።ተመራቂዎች በሰለጠኑባቸዉ የሙያ መስኮች አየር መንገዱን በብቃት በማገልገል አገራዊ ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ አቶ ሳሙኤል ጥሪ አቅርበዋል።በበረራ መስተንግዶ ከተመረቁት ሰልጣኞቹ መካከል 19 ያህሉ ከቶጎ፣ ከአይቮሪኮስት፣ ከናይጄሪያ፣ ከጋናና፣ከጊኒ የመጡ ዜጎች ናቸው። በአብራሪነት ደግሞ 1 የስዋዚላንድ ዜጋ ተመርቋል።ለተመራቂ የበረራ ክንፍ፣ሪባንና ዲፕሎማ የሰጡት የአየር መንገዱ ቺፍ የኦፕሬቲንግ ኦፊሰር አቶ መስፍን ጣሰው ናቸው።
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/28572/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
f24fd9a15c2108562015f830849270fe
e93c3e1f8e248f6e87cfab37399b5fcc
የከፍተኛ ሊግ የሳምንቱ ጨዋታዎች እና አጫጭር መረጃዎች
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዚህ ሳምንት በርካታ ጨዋታዎች ተከናውነዋል። ከጨዋታዎቹ ጋር አያይዘን አዳዲስ መረጃዎችን እንዲህ አጠናቅረናል።የምድብ ሀ ጨዋታዎችበምድብ ሀ 25ኛ ሳምንት ባህርዳር እና ሽረ ድል አስመዝግበዋል። የምድብ ሀ አናት ላይ የተቀመጠው ባህር ዳር ከተማ በባህርዳር ደርቢ አውስኮድን ገጥሞ ከመመራት በመነሳት 3-1 አሸንፏል። ሙሉቀን ታሪኩ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር በሁለተኛው ዙር የተነቃቃው ፍቃዱ ወርቁ ቀሪውን ጎል አስቆጥሯል። ምድቡን ባህርዳር በ57 ነጥብ ከተከታዩ ሽረ በ10 ነጥቦች ርቆ ምድቡን እየመራ ይገኛል።ከነቀምት ጋር ጨዋታውን በአዲስ አበባ ያደረገው ሽረ እንዳሥላሴ ልደቱ ለማ በ18ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል 1-0 በማሸነፍ ሁለተኛ ደረጃውን አጠናክሯል። አዲስ አበባን ከወሎ ኮምበልቻ ያገናኘው ጨዋታ ያለግብ ሲጠናቀቅ በተመሳሳይ ሰበታ ከ ለገጣፎ እና ኢኮስኮ ከ ቡራዩ ያለምንም ጎል የተጠናቀቁ ጨዋታዎች ናቸው። ኢትዮጽያ መድን በጌትነት ተስፋዬ ሁለት ግቦች እንዲሁም በሀብታሙ መንገሻ ግቦች ታግዞ ደሴ ከተማን  3-2 ሲያሸንፍ የካ ክፍለከተማ ሱልልታ ከተማን 1-0 በማሸነፍ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ከወራጅ ቀጠናው መውጣት ችሏል። አአ ከተማ ፎርፌ ተወስኖበታልአዲስ አበባ ከ ፌደራል ፖሊስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ የተጫዋች ተገቢነት ክስ አስመዝግቦ የነበረው ፌዴራል ፖሊስ የፎርፌ ውሳኔ እንዳገኙ ታውቋል። የክለቡ የቡድን መሪ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ክሱ ውሳኔ ያገኘ መሆኑን ገልፀው 3 ነጥብ እና 3 ንፁህ ጎል ለፌደራል ፖሊስ ተወስኗል። ይህን ጨዋታ አአ ከተማ 5-0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።ከውሳኔው በኋላ ሰንጠረዡ ይህን ይመስላል:-የምድብ ለ ጨዋታዎች  በ23ኛ ሳምንት የምድብ ለ ተስተካካይ ጨዋታ ሀምበሪቾን የገጠመው ሀላባ ከተማ 3-0 አሸንፏል። ከጨዋታው መጀመር አስቀድሞ የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች በሀላባ ስታድየም ዙርያ የችግኝ ተከላ ሲያከናውኑ በሜዳ ላይም ጨዋታው ከመጀመሩ ቀደም ብሉ የሁለቱ ቡድኖች ተጫዋቾች አንድ ላይ በመሆን ለደጋፊዎች ሰላምታን ሰጥተዋል።ብዙም ሳቢ ባልነበረው ጨዋታ በመጀመርያዎቹ 15 ደቂቃዎች ሀላባ ከተማዎች ኳስ ይዞ ተጭኖ በመጫወቱ ረገድ የተሻሉ ነበሩ። በ3ኛው ደቂቃ ስንታየሁ መንግስቱ ከፉአድ አቢኖ መሀል ለመሀል የተሻገረለትን ኳስ ሳይጠቀምበት የቀረበት እንዲሁም በተመሳሳይ በ5ኛው እና በ11ኛ ደቂቃ ላይ ተመሳሳይ ለግብ የቀረቡ የግብ ማግባት አጋጣሚዎች ናቸው። ፍጹም ደስ ይበለው ከሰዒድ ግርማ የተቀበለውን ኳስ አክርሮ የመታትና በሀላባው ግብ ጠባቂ ሶፍያን ኑረዲን የመከነችው ኳስ በሀምበርቾዎች በኩል ለግብ የቀረበች ሙከራ ነበረች። በ13ኛው ደቂቃ ከግቡ በግምት ከ25 ሜትር አካባቢ የተሰጠውን ቅጣት ምት አብነት ወደግብነት ቀይሮ ሀላባን መሪ ሲያደርግ በ19ኛው ደቂቃ ስንታየው መንግስቱ ከማዕዘን የተሻማ ኳስ ወደግብነት በመቀየር የሀላባን መሪነት ወደ 2 ከፍ ማድረግ ችሏል። ከግቦቹ መቆጠር በኋላ የመጀመርያው አጋማሽ እስኪጠናቀቅ ለተመልካች አሰልቺ የሆነ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን ሀምበርቾዎች ወደ ግብ በመድረሱ ረገድ የተሻሉ ቢሆኑም ግብ ሳያስቆጥሩ የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል።ሽኩቻ እና ኃይል በተቀላቀለበት አጨዋወት የታጀበው የሁለተኛው አጋማሽ ሀምበርቾዎች ሰኢድ ግርማን በመቀየር የአጥቂ ቁጥራቸውን ጨምረው ቢጫወቱም 75 ደቂቃዎች እስኪቆጠሩ ድረስ እምብዛም የግብ ሙከራ አልታየም። በሀላባዎች በኩል በ75ኛው ደቂቃ ስንታየውን ቀይሮ የገባው ሆጴ የቡድኑን የማጥቃት እንቅስቃሴ ዳግም የመለሰ ሆኖ በተደጋጋሚ ጫና ፈጥሮ መጫወት ችለው መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨማሪው ደቂቃ ላይ አቦነህ ገነቱ ከፉአድ አቢኖ የተሻገረለትን ኳስ በአግባቡ ወደ ግብነት በመቀየር ጨዋታው በሀላባ ከተማ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል። ሀላባዎች በቀጣይ የ24ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታቸውን ከመቂ ከተማ ጋር ሐምሌ 17 ላይ ያደርጋሉ።የምድቡ 25ኛ ሳምንት ዛሬ ሲጀመር ናሽናል ሴሜንት በፋሚ እስክንድር ጎል መቂ ከተማን 1-0 አሸንፏል። ነገ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ቤንች ማጂ ከ ሀዲያ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ ከተማ ከ ሻሸመኔ ከተማ፣ ድሬዳዋ ፖሊስ ከ ቡታጅራ ከተማ፣ ስልጤ ወራቤ ከ ከተማ በተመሳመይ 04:00 የሚጫወቱ ይሆናል።የዲላ ከተማ ተጫዋቾች ቅሬታቸውን አሳምተዋል(በቴዎድሮስ ታከለ)ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደረግ እየተፎካከረ የሚገኘው ዲላ ከተማ ያለፉትን ሶስት ወራት ለተጫዋቾቹ የደመወዝ ክፍያ እና ጥቅማጥቅም እንዳላገኙ የቡድኑ ተጫዋቾች ለሶከር ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የዲላ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ እና የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ተስፋዬ ለሶከር ኢትዮጵያ ይህን ብለዋል፡፡ ” የተባለው እና ተጨዋቾቹ ያነሱት ቅሬታ ተገቢ ነው። የቡድኑ የፋይናንስ ችግር በአካባቢው በተፈጠረው ያለመረጋገት የተፈጠረ ችግር ነው። የፋይናንስ ችግሩን በሂደት ለመፍታት የሚቻለንን ጥረት እያደረግን ነው። ከመንግሥት ድጎማ የሚገኝ በመሆኑ በትዕግስት መጠበቁ ግድ ይላል።” ሲሉ ገልፀዋል። በዚህ ረገድ የክለቡ ውጤታማነት ላይ ተፅኖ አያመጣም ብለን ላነሳነው ጥያቄ ስራ አስኪያጁ ሲመልሱ “ምንም አይነት ተፅዕኖ ያመጣል ብለን አናስብም። አስቀድመን ለአሰልጣኙ ጉዳዩን ገልፀን ተጫዋቾቹ ክለቡን እያገለገሉ ክፍያውን እንፈፅማለን ተባብለናል። ይህን የደመወዝም ሆነ የኢንሴንቭ ችግራችንን ፈትተን በዚህ ወር በሙሉ ክፍያቸውን ለማጠናቀቅ ከሚመለከተው ጋር ተቀራርበን እየሰራን ነው። በሂደትም ይህ ችግር ዳግም እንዳይከሰት ጥንቃቄ ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን።” ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተውናል፡፡
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/38556
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
77360e818966c3d3e3723bde68764f50
4c65159d32dce9d0f71b9b151e950dfd
በአፍሪካ ሕብረት ለሚመራው ድርድር አሜሪካ ድጋፍ አደርጋለሁ አለች
አምባሳደሩ ይህን ስለማለታቸው የተሰማው ዛሬ ከውሃ፣ ኢነርጂ እና መስኖ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው። በቀጠናው በሚገኙ አገራት ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት አምባሳደር ፌልትማን ዛሬ ከኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቦ ነበር። ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ከአምባሳደር ፌልትማን ጋር መወያየታቸውን በትዊተር ገጻቸው ላይ ገልጸው፤ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ደረጃን በተመለከተ እና በአፍሪካ ሕብረት ስለሚመራው የድርድር ሂደት ዙሪያ ግልጽ ውይይት ማድረጋቸውን አስፍረዋል። አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን አገራቸው አድልዎ የሌለበት ድጋፍ እንደምታደርግ እና ሦስቱ አገራት በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት እንዲደርሱ ቁርጠኛ መሆኗን መናገራቸውን ገልጸዋል። የአባይ ወንዝ ለኢትዮጵያ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እና ወደፊት በድርድሩ እንዴት ከስምምነት መድረስ እንደሚቻል ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል። አምባሳደር ፌልትማን በተለያዩ በቀጠናው በሚገኙ አገራት ከሚያደርጉት ኦፌሴላዊ ጉብኝት በተጨማሪ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቢሮዎች፣ የአፍሪካ ህብረት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ከፖለቲካ አመራሮችና ከሰብአዊ እርዳታ ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ልዩ መልዕክተኛው በአፍሪካ ሃገራት ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ሃገራቸው በአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ፣ የጸጥታና ሰብአዊ ችግሮች በዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲፈቱ ያላትን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥና በቀጠናው ያላትን የፖሊሲ ትብብር ለማጠናከር ነው ተብሏል። አምባሳደር ፌልትማን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው በፕሬዝደንት ጆ ባይደን በቅርቡ መሾማቸው ይታወሳል። ልዩ መልዕክተኛ አዲስ አበባ ከመግባታቸው በፊት በግብጽ፣ ሱዳን እና ኤርትራ ተገኝተው ከየአገራቱ መሪዎች ጋር መወያየታቸው አይዘነጋም። አምባሳደር ፌልትማን ለሁለት ቀናት ሱዳን ከቆዩ ወደ አስመራ አቅንተው ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ረዘም ላለ ሰዓት መወያየታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀው ነበር። አራት ሰዓት በቆየው ውይይት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ኤርትራ ከአሜሪካ ጋር አብራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል ሲሉ የማስታወቂያ ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። አምባሳደሩ ከዚህ በተጨማሪ ወደ ግብጽ አምርተው ከፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ፣ ከውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ሳሚህ ሽኩሪ እና ከሃገሪቱ የውሃ ሚንስትር ጋር ስለመገናኘታቸው ተዘግቧል። በውይይታቸው ወቅት አል-ሲሲ ግብጽ ከአባይ ውሃ የምታገኘው ድርሻ መቀነስን አትታገስም በማለት ስለመናገራቸው ዋሽግተን ፖስት ዘግቧል። አምባሳደር ፌልትማን ከግብጽ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ የጆ ባይደን አስተዳደር በቀጠናው ላሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት ትኩረት ያደርጋል ሰለማለታቸው ዋሽንግተን ፖስት ምንጮቹን ጠቅሶ ጨምሮ ዘግቧል። ጄፍሪ ፌልትማን ፌልትማን ማን ናቸው? ጄፍሪ ፌልትማን በሹመታቸው ወቅት በተለይ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ስላሉ ሁኔታዎች የተለየ ትኩረት እንደሚሰጡ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አስታውቆ ነበር። ፌልትማን በድርድርና የሽምግልና ጉዳዮች ላይ ጥናትን በማካሄድና በአደራዳሪነትም ከፍ ያለ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል። ፌልትማን በፖለቲካዊና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀድሞውንና የአሁኑን ዋና ጸሐፊዎች ባን ኪሙን እና አንቶኒዮ ጉቱሬዝን ያማከሩ ሲሆን፤ ለጸጥታው ምክር ቤት በሠላምና በደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያዎችን በመስጠት ይታወቃሉ። በተባበሩት መንግሥታት ቆይታቸው...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
816938adef14e72307ba0b799522595f
a381063910b1cd31a1f2dbbb5ad38283
በሁለተኛው ምዕራፍ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር 32 ኪሎ ሜትር መስመር ታቅዷል
በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሁለተኛ ምዕራፍ ፕሮጀክትቶች ይፋ ሆኑ፡፡ ለሁለተኛው ምዕራፍ 32 ኪሎ ሜትር መስመር ዕቅድ ተይዟል፡፡ጥናታቸው እየተጠናቀቁ የሚገኙት መስመሮች ከመገናኛ-በኢምፔሪያል ሆቴል በኩል ቦሌ ኤርፖርት፣ በመቀጠልም ወደ ሳሪስ፣ ከሳሪስ በጎፋአድርጎ ለቡ ብሔራዊ የባቡር ጣቢያውን እንደሚቀላቀል፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታቸው በትሩ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ሌላኛው በሁለተኛው ምዕራፍ የሚካተተው መስመር ደግሞ ከጊዮርጊስ ምንሊክ አደባባይ በቸርችል ጎዳና ወደ ሜክሲኮ አድርጎ፣ በአፍሪካ ኅብረት ለቡ ብሔራዊ የባቡር ጣቢያ የሚገባ መሆኑን ዶ/ር ጌታቸው ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ምዕራፎች ደግሞ ከአያት ወደ ለገጣፎ፣ ከጦር ኃይሎች ቡራዩ፣ ከጊዮርጊስ ወደ ሽሮሜዳ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡በአጠቃላይ በተለያዩ አምስት ምዕራፎች አዲስ አበባ ውስጥ የባቡር ኔትወርክ ለመፍጠር መታቀዱን፣ ዓላማውም አንድ የባቡር መስመር ውስጥ የገባ ተሳፋሪ የፈለገበት ቦታ በባቡር ማድረስ መሆኑን ዶ/ር ጌታቸው ገልጸዋል፡፡የባቡር መስመር መዘርጋትና ትራንስፖርቱን ማስፋፋት የመንደላቀቅ ጉዳይ ሳይሆን፣ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑን መንግሥትም ጭምር እንዳመነበት ጠቁመዋል፡፡ባለፈው ሳምንት እሑድ መስከረም 9 ቀን 2008 ዓ.ም. በከፊል ሥራ የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በየቀኑ እየሰጠ በሚገኘው የትራንስፖርት አገልግሎት፣ በቀን እስከ መቶ አርባ ሺሕ ተሳፋሪዎችን እያጓጓዘ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡በዚሁ የትራንስፖርት አገልግሎት በየቀኑ በአማካይ እስከ ሁለት መቶ ሺሕ ብር እየሠራ መሆኑንም ዶ/ር ጌታቸው ገልጸዋል፡፡ ይህ ገቢና የማመላለስ አቅም በ12 ባቡሮች ብቻ በሚደረግ ምልልስ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ሙሉ በሙሉ በሁለቱም መስመር አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ በዓመት እስከ 48 ሜጋ ዋት እንደሚፈጅ የቀላል ባቡሩ ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ቦጋለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡በቃሊቲ የሥምሪት ማዕከል ውስጥ ኢትዮጵያውያንና ቻይናውያን ባለሙያዎች የባቡሩን እንቅስቃሴ በቪዲዮ ምሠልና በሲግናል ሲከታተሉ ሪፖርተር ለማስተዋል ችሏል፡፡ በዚህ ማዕከል የባቡሩ መስመር ውስጥ የሚገቡ ሌሎች ተሽከርካሪዎች ወይም እንስሳትና እግረኞች ቢኖሩ ቀድመው ለባቡሩ ሾፌር (ትሬይን ማስተር) ማሳወቅ እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በየጣቢያው ያለውን የተሳፋሪ መጠን በመመልከት የባቡር ሥርጭቱን መጨመር መቀነስ እንደሚያስችላቸው ለመገንዘብ ተችሏል፡፡የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላትም በዚሁ የሥምሪት ማዕከል ባልደረቦች ሲሆኑ፣ የእነሱ የሥራ ድርሻ ደግሞ የተለያዩ ወንጀሎችንና ዝርፊያዎችን መከታተል ነው፡፡በእያንዳንዱ ጣቢያ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ በሚመለከት የተመለከቱትን ወንጀል፣ ማጭበርበርና የመሳሰሉትን በአካባቢው ላለ የፖሊስ ባልደረባ የመጠቆም ኃላፊነት አለባቸው፡፡
ቢዝነስ
https://www.ethiopianreporter.com/article/8871
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
8dfa3646ec102b51d120460422ee517b
c8d73fdc7a4b596646b650167c21ed83
ጉምሩክ በ9 አገልግሎት አሰጣጥ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ
የጉምሩክ ኮሚሽን ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የተንዛዙና ጊዜ ይወስዱ የነበሩ 9 ጉዳዮችን በመለየት ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ በጊዜ አጠቃቀምና በወጪ ላይ ውጤት ያመጣሉ ያላቸውን ማሻሻዮቹን ይፋ አድርጓል፡፡በተደረጉት የአሰራር ማሻሻያዎችም እስክ 48 ሰዓታት ጊዜን እና 3 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጪ መቀነስ የሚያስችሉ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡የአሰራር ማሻሻያው የተደረገው ዕቃ ሳይደርስ የዕቃ አወጣጥ ስርዓት መፈፀም፣ ዕቃዎች ከደረቅ ወደብ በባንክ ጋራንቲ ማስተናገድ፣ ለገቢና ወጪ ዕቃዎች የሚጠየቁ ሰነዶች መቀነስ፣ የአስገዳጅ ታሪፍ መረጃ አሰጣጥ፣ ቀለል ያለ የጉምሩክ ስነስርዓት አፈፃፀም፣ አዲሱ የኢትዮጵያ የጉምሩክ ስር አመራር ስርዓት፣ በወጪ እና ገቢ ዕቃዎች ላይ የስጋት ስራ አመራር ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ እና ወጥነት ያለው የዕቃዎች ዋጋ መግለጫ ደረሰኝ ተግባራዊ ማድረግ በሚሉ 9 ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ምንጭ፡-የገቢዎች ሚንስቴር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=5715
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
3f7cac527341ad54171a362d38e9e4e8
795c479a27c13518849d507114346733
የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ለተንበረከኩላቸው አዛውንት ግራጫ ፖስታ ሲያድሉ የሚታይበት ተንቀሳቃሽ ምስል መነጋገሪያ ሆኗል።
ኡጋንዳውያን ለፕሬዝደንት ሙሴቪኒ ሲንበረከኩ የሚያሳየው ምስል አነጋጋሪ ሆኗል\nሙሴቪኒ ለአምስት ቀናት ጫካ ውስጥ ነው የምኖረው ብለው ዱር ከከተሙ ሶስት ቀናት ሆኗቸዋል። በዚህ የጫካ ኑሯቸው አብሯቸው የተሳተፈ አንድ ግለሰብ ነው ሙሴቪኒ በእንብርክክ ላሉ አዛውንቶች ግራጫ ፖስታ ሲያድሉ ቪድዮ ቀርፆ ማሕበራዊ ድር-አምባዎች ላይ የለቀቀው። ፕሬዝደንቱ ወደ ጫካ መመለስ ያስፈለጋቸው ሥልጣን ከመያዛቸው በፊት በታጣቂነት ዘመናቸው ያለፉበትን ለማስታወስ ነው ተብሏል። ሙሴቪኒ እና አጋሮቻቸው በ1978 ዓ.ም. ነው የኢዲ አሚን ዳዳን መንግሥት ገልብጠው ሥልጣን የያዙት። ከሰሞኑ በተለቀቀው ቪዲዮ ላይ ነዋሪዎች ዝማሬ እያሰሙ፤ ሙሴቪኒ ደግሞ ወንበር ላይ ተቀምጠው በእንብርክካቸው ወደ እሳቸው ለሚጠጉ አዛውንቶች በእርዳታ መልክ ግራጫ ፖስታ ሲያድሉ ይታያሉ። ሙሴቪኒ በግራጫ ፖስታ ውስጥ ገንዘብ እያደሉ እንደሆነ ተገምቷል እንደ ግሪጎሪ አቆጣጠር በ2021 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሙሴቪኒን ይገዳደራሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተቀናቃኞች መካከል የሆኑት ኪዛ ቤስጊዬ ድርጊቱ አረጋውያንን የሚያሸማቅቅ ነው ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከተለቀቀ በኋላ በርካታ ኡጋንዳውያን ድርጊቱን አውግዘውታል። አንዳንዶች ፕሬዝደንቱ ይህን የሚያደርጉት በሚቀጥለው ምርጭ ሕዝቡ እንዲመርጣቸው በማሰብ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ሙሴቪኒ ስለ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ምንም ያሉት ነገር የለም። ይልቁንስ በጫካ ጉዟቸው አብረዋቸው የተሳተፉትን ምስጋና እንካኝ ብለዋል። ፕሬዝደንቱ ታጣቂ በነበሩ ጊዜ ከያኔው የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ኦቦቴ ጦር ጋር የተዋጉበትን ቦታ ጎብኝተው በሚቀጥሉት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ መናገሻቸው ካምፓላ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
040b4c81372aafa08e1cc5bd88bed5eb
faf2186f6003c7aaa54ff37992746ac8
አዊ
ቋንቋ አዊ (ጎጃም አገው ምድር) አካባቢ አገውኛ (አዊኛ) ቋንቋ ይነገራል ። ሕዝብ ቁጥር 5000,000 ሚሊዮን እና ከዛ በለይ መልክዓ ምድር አዊ ዞን በቀድሞ አጠራሩ ጎጃም አገው ምድር በመኻል ጎጃም ይገኛል። አዊ ዞን በስተ ደቡብ እና ምስራቅ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ በሰተ ምዕራብ ቤንሻሻንጉል ጉምዝ ክልል እና በስተ ሰሰሜን ሰሜን ጎንደር ያዋስኑታል። በ16ወረዳወች የተዋቀረ ነው።ኮሶበር (እንጅባራ) በባንጃ ወረዳ የሚገኝ ከተማ ሲኾን የአገው አዊ ዞን አስተዳደር ማእከል ነው። የአዊ አገወች ከ12-15ኛው ክፍለ ዘመን ከዋግ ወደ ጎጃም እንደመጡ ይነገራል። ታሪክ ታዋቂ ሰዎች አዊ የኢትዮጵያ ብሔር ነው። የኢትዮጵያ ብሔሮች
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
1b73a24a8973e0523bb9aafb035a3180
4fc5bcc92951ba74be52e3867274b058
 የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ለመምከር ሱዳን እና ግብፅን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቴቨን ሙንሽን የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ለመምከር ሱዳን እና ግብፅን እየጎበኙ ይገኛሉ።በትናንትናው ዕለትም ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጋር የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሚኒስትሩ ከህዳሴ ግድብ ጋር ተይይዞ ሀገራቱ ያሏቸውን ልዩነቶች በፍትሃዊነት እንዲፈቱ ማሳሰባቸውን በካይሮ የአሜሪካ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ እና የግምጃ ቤት ሃላፊው በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ነው የተነገረው።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቴቨን ሙንሽን በሱዳን በዛሬው ዕለት ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን በተመሳሳይ በተለያዩ ጉዳዮች ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቴቨን ሙንሽን  በኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል በአሜሪካ ታዛቢነት የተካሄደውን እና ኢትዮጵያ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነትን የተቃወመችበትን ውይይት ሲመሩ የነበሩ መሆናቸው የሚታወስ ነው።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%9c%e1%88%aa%e1%8a%ab-%e1%8c%8d%e1%88%9d%e1%8c%83-%e1%89%a4%e1%89%b5-%e1%88%83%e1%88%8b%e1%8d%8a-%e1%8b%a8%e1%88%85%e1%8b%b3%e1%88%b4-%e1%8c%8d%e1%8b%b5%e1%89%a5%e1%8a%95/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
ea7a9237f353acb8744d0a34ff8dc38a
e4d96ab64cd0fedf90cd57f69999319c
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ኪብር ጋር ተወያዩ
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ኪብር ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።በውይይቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ኪብር በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እና የሃገር ግንባታ ጉዞን እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።በቀጣይ የሁለቱ ሀገራት ትብብርና ቅንጅት የበለጠ ተጠናክሮ ለቀጠናው ሃገራት ሰላምና ዕድገት እንደሚሰሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ኪብር ተናግረዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በበኩላቸው የሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ታሪካዊ ከፍታውን ጠብቆ ለማጠናከር የኢትዮጵያን ዝግጁነት አንስተዋል።በተለይ በቆዬው የህዝብ ለህዝብ ታሪካዊ መተሳሰር እና መተሳሰብ በንግድና ኢኮኖሚ የበለጠ እየዳበረ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትንቀሳቀስ አረጋግጠዋል። (ምንጭ፡-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት)
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/30725/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
0260cb8378eeebd607cec5b35e1b4fdb
ad8cbcafb436fd69962475556817859e
በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ቀጣይ ውይይት በሱዳን ይካሔዳል
በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሰሞኑን በግብፅ ካይሮ ሲመክሩ የነበሩት ሦስቱ የናይል ተፋሰስ አገራት ቀጣይ ውይይታቸውን በሱዳን ካርቱም እንዲሆን ወስነዋል። የሦስትዮሽ ውይይቱ የቴክኒክ ጉዳዮችን ያልተነሱበት እንደነበርና ኢትዮጵያ በግብፅና በሱዳን በቀረቡ ሀሳቦች ላይ ለመወያየት ፈቃደኛ ባለመሆኗ እንደሆነ ምንጮች አስታውቀዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም አስቸኳይ የሦስትዮሽ ስብሰባው በሱዳን እንዲካሔድ እንዲወሰን ምክንያት ሆኗል።በቀጣይ በሚካሔደው የሱዳኑ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በሚገባ እንድትሳተፍና በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ተደርሶ በ2007 በሱዳን ካርቱም የተገባው ስምምነት እንድታከብር ጥሪ ቀርቧል።በተያዘው ወር መጨረሻ ቀናት በሱዳን ካርቱም ይካሔዳል ተብሎ የሚጠበቀው የሦስቱ አገራት ውይይት በርካታ አዳዲስ ውሳኔዎችና በግድቡ የቴክኒክ ጉዳይ ላይም ሰፋ ያሉ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉት ገለልተኛ የሳይንቲስቶች ቡድንም በቀጣይ የሦስቱ አገራት የውሃ እና መስኖ ሚንስትሮች ጉባኤ እንደሚኖርም አስታውቀዋል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://addismaleda.com/archives/6676
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
933dccc909c486330b3307309c0b2445
24f038abca89c7cad0103d11372b2624
አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ
ሦስተኛው የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ውጤት ይፋ በሆነበት ወቅት ከተለያዩ አካላት ነቀፌታዎችን ማስተናገዱ ይታወሳል። በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ እና የአማራ ክልል ሕዝቦች ቁጥሮች ጋር በተያያዘ የቆጥራውን ውጤት የመጠምዘዝ ሥራ ተከውኗል ሲሉ የሚያጣጥሉት አሉ። አራተኛው ቆጠራ የሚከናወነው ከፍ ባለ ጉጉት ከሚጠበቀው ከቀጣዩ ምርጫ አንድ ዓመት በፊት እንዲሁም በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ራስን የማስተዳደር ጥያቄዎች በተበራከቱበት ወቅት ነው። ቆጣሪዎች የሚመለመሉት ደግሞ በየአካባቢው ባለስልጣናት ነው። • በአንድ ቦታ የተሰበሰቡ ሰዎችን ቁጥር እንዴት ማወቅ ይቻላል? የሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ እና የብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቢራቱ ይገዙ ቆጠራው ፖለቲካዊ ግብ ባይኖረውም፤ ለፖለቲካ ውሳኔዎች እና ፍላጎቶች ግብዓት መሆኑ ስለማይቀር የሚሰበሰበውን መረጃ ለራስ ፍላጎት እንደሚመች አድርጎ የመነካካት ዝንባሌ አንዱ ስጋታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ይህን ለመቆጣጠር በዚህ ቆጠራ ላይ ተግባራዊ የሚደረጉ በቴክኖሎጂ የታገዙ አሠራሮች አንድ መላ እንደሚሆኑ ይናገራሉ። ለቆጣሪዎቻቸው ይህን የሚመለከት ስልጠና እንደሚሰጡ፤ ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸውም አስረግጠው እንደሚያሳውቋቸውም አቶ ቢራቱ አክለው ያስረዳሉ። ከሚጠበቀው በተለየ የተጋነነ ለውጥ ካለ "በወረዳና በቀበሌ ያሉ የመስክ ታዛቢዎችን ለምን እንዲህ ያለ ልዩነት እንደመጣ ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፤ በጣም የተለየ ከሆነ ደግሞ ገለልተኛ ታዛቢ እንዲላክ ይደረጋል" ብለዋል። በምርጫ መጠይቅ ከሚሞሉ መረጃዎች አንደኛው የተቆጣሪዎቹ ብሔር ሲሆን፤ ድብልቅ የብሔር ማንነቶች ያሏቸው ተቆጣሪዎች አንደኛውን የመምረጥ ግዴታ እንደሌለባቸው የሚያስረዱት አቶ ቢራቱ "ብሔርን፣ ኃይማኖትን በተመለከተ መልስ ሰጭው የሰጠው ብቻ ነው የሚሞላው" ይላሉ። መረጃውን የሚሞላው ሰው በዚህ ጉዳይ ላይ የራሱን ብያኔ የመስጠት ስልጣን የለውም። ድብልቅ የብሔር ማንነት ያላቸውም ሆነ፤ የብሔር ማንነታቸውን መግለፅ የማይፈልጉ ሰዎች ይህንኑ ለቆጣሪያቸው ቢናገሩ፤ ቆጣሪያቸው የሚሞላው ወይንም የምትሞላው ኮድ አለ ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል። 2. ለሕዝብ እና ቤት ቆጥራው ምን ያህል ዝግጅት ተደርጓል? ኢትዮጵያ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራውን ለመጀመሪያ ጊዜ በዲጂታል መሣሪያዎች የምታከናውን ሲሆን ለዚሁ ተግባር ያገለግላሉ የተባሉ 180 ሺህ ታብሌቶች ከአንድ ዓመት በፊት ተገዝተዋል። ታብሌቶቹ ከኃይል መቆራረጥ ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይገጥማቸው ታስቦም በመጠባበቂያነት የሚያገለግሉ 126 ሺህ ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከማቻዎች (ፓወር ባንኮች) እንዲሁም 30 ሺህ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ የባትሪ አቅም መሙያዎች (ቻርጀሮች) ግዥ ተፈፅሟል። አቶ ቢራቱ ይገዙ ቆጠራውን በዲጂታል መሣርያዎች ማድረጉ "ለጥራት ቁጥጥርም፣ ለክትትልም፣ በጊዜ ለማድረስም፣ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍም" የተሻለ አማራጭ እንደሚሆን ታምኖበት የተወሰነ ነው ይላሉ። • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ሌላኛው የተከናወነው ሥራ የቆጠራ ክልል ማዘጋጀት ሲሆን እርሱም ሁለት ዓመታትን ወስዷል እንደ አቶ ቢራቱ ገለፃ። በዚህም መሠረት በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ቀበሌዎች በቆጠራ ክልልነት ተሸንሽነዋል። በገጠር ቤቶች ዘርዘር ብለው እንደመገኘታቸው ከአንድ መቶ እስከ አንድ መቶ ሃምሳ ቤተሰቦች በአንድ የቆጠራ ክልል የተጠቀለሉ ሲሆን በከተማ ደግሞ የቤቶቹ ቁጥር ከአንድ መቶ ሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ከፍ ይላል። የቆጠራ ክልሎቹ መገኛ በዓለም አቀፍ የአቀማመጥ ሥርዓት (ጂፒኤስ) ነጥባቸው ተወስዷል። እያንዳንዱ ቆጣሪ ከተሰጠው የቆጠራ ክልል ውጭ ቢንቀሳቀስ ዲጂታል መሣርያው...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
0ffbec51e40cf7b7f567e2d428f4404c
376a275dc66bad56b04259c005d30ee1
በአሜሪካ 129 የህንድ ተማሪዎች መታሰራቸዉን ተከትሎ ደልሒ በሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ ተቃዉሞ ተካሔደ።
በአሜሪካ ሀሰተኛ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች መታሰር በሕንድ ቁጣን ቀሰቀሰ\nባለፈዉ ረቡዕ የአሜሪካ መንግስት ህጋዊ ካልሆነ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ አገኘኋቸዉ ያላቸዉን 129 ሕንዳዉያን ተማሪዎችን አስሯል። ሚቺጋን ግዛት የሚገኘዉ ፋርሚንግተን የተባለዉ ዩኒቨርሲቲ የሀገር ዉስጥ የደህንነት መስሪያ ቤት ዉክልና አለኝ በማለት በህገወጥ መልኩ ወደ አሜሪካ የገቡ ተማሪዎችን ሲመዘግብ መቆየቱን መንግስት ደርሸበታለሁ ብሏል። •"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ •ሴት እስረኞችና የማዕከላዊ ምርመራ በተለይ ተማሪዎቹ በአሜሪካ እንዲቆዩ "ለመኖር መክፈል" በሚል እሳቤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን 8500 እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን 11000 ዶላር አመታዊ ክፍያ ያስከፍል ነበር። የሀሰት ዩኒቨርሲቲዉ በህገወጥ መልኩ ከተለያዩ ሀገራት ወደ አሜሪካ የገቡ ዜጎችን ታላሚ አድርጎ በጎርጎሳያውያኑ 2015 የተቋቋመ ነዉ። እናም ባለፈዉ ረቡዕ የአሜሪካ መንግስት ከዚሁ የሀሰት ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ አገኘኋቸዉ ያላቸዉን 129 ሕንዳዉያንን ጨምሮ 130 ተማሪዎችን አስሯል። •"ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች ተማሪዎቹን ለማስፈታት ቅዳሜ ህንድ ደልሂ በሚገኘዉ የአሜሪካ ኤምባሲ በመሰባሰብ ህንዳዉያን ተቃዉሟቸዉን አሰምተዋል። ኤምባሲዉ በበኩሉ የተካሄደዉን የተቃዉሞ ሰልፍ እዉቅና ቢሰጥም ስለጉዳዩ ግን ያለዉ ነገር የለም። የህንድ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰልፉ የታሳሪዎቹን ደህንነት እና አማካሪ የማግኘት መብታቸዉን ለማስከበር ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልጿል። ራሱን እንደህጋዊ ተቋም በተለያዩ አማራጮች የሚያስተዋዉቀዉ ፋርሚንግተን ዩኒቨርሲቲ በድረ ገፁ ተማሪዎች ክፍል ዉስጥ ሲማሩ ፤ ቤተመጽሃፍት ሲያነቡ እና በሳራማ ግቢ ሲዝናኑ በፎቶ ያሳያል። ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚያስተዋዉቅበትም የሀሰት የፌስቡክ ገጽ አለዉ። ነገር ግን ባለፈዉ ሳምንት ከፍርድ ቤት የወጣ መረጃ እንደሚያሳዉ የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኞች የኢምግሬሽንና የጉምሩክ ሰራተኞች እንጂ መደበኛ ሰራተኞች እንዳልሆኑ አረጋግጧል። መንግሥትም ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲዉ ህጋዊ አለመሆኑን እያወቁ የተመዘገቡ በመሆናቸዉ በህግ እንዲጠየቁ አደርጋለሁ ብሏል። የህንድ መንግሥት ግን ዜጎቼ በፍጹም ይህን አያደርጉም በወንበዴዎች ተታልለዉ በመሆኑ ምህረት ሊደረግላቸዉ ይገባል በማለት ተማጽኗል። በተለይ ተማሪዎቹ ያሉበት ሁኔታ እንዲገለጽ፤ ቀድመዉ ከእስር እንዲለቀቁ እና ከአሜሪካ እንዳይባረሩ የአሜሪካን መንግሥት መጠየቁን የህንድ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስታዉቋል። ከተማሪዎች በተጨማሪ 8 ሰዎች ስደተኞችን ለትርፍ በመጠቀም እና በቪዛ ማጭበርበር ወንጀል ተከሰዋል። እነዚህ ግለሰቦች በተለይ ተማሪዎችን በመመልመልና በማግባባት ከፍተኛ ሚና ነበራቸዉ ተብሏል። በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት በስደተኞች ጉዳይ ጥብቅ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። በተመሳሳይ ከሶስት አመት በፊት ስደተኞችን መሰረት ያደረገ የሃሰት ዩኒቨርስቲ በመገኘቱ ብዙዎቹ ከቻይና እና ከህንድ የሆኑ 21 ሰዎች በሰሜን ኒዉ ጀርሲ ታስረዉ ነበር። ባለፉት ሁለት የትራምፕ የአስተዳደር አመታት ደግሞ የብዙዎቹ ሰነድ አልባ እና ቪዛ ጠባቂዎች ጉዳይ እንዲዘጋ ተደርጓል። በዚህ ሂደትም በርካታ የስራ ቦታዎች የእስረኞች መገኛ ሆነዉ ቆይተዋል። በሁለቱ የትራምፕ አመታት ብቻ የኢምግሬሽንና የጉምሩክ መስሪያ ቤት ኦሃዮ ዉስጥ ከሚገኝ አንድ የስጋ አቃራቢ ድርጅት 146 ሰዎችን እና ቴክሳስ ዉስጥ ከሚገኝ ሌላ ፋብሪካ ዉስጥ ደግሞ 150 ስደተኞችን በዚሁ ምክንያት አስሯል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
17e3999fabd9da64d5a8ffd4be328269
2f8dc461163df8d8561219d04b815bd3
በኢትዮጵያ በፖሊሲና የህግ አተገባበር ክፍተት የዜጎች የሥራ ላይ አደጋ አሳሳቢ ሆኗል-ሚኒስትሩ  
 ረቂቅ አዋጁ በቅርቡ ከጸደቀ በኋላ ሁሉም አሰሪ ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉት የሚያስገድድ ህግም አብሮት ይወጣል ነው የተባለው። ሚኒስቴሩ የሥራ ላይ አዋጁን ተግባራዊ በማያደርጉ ተቋማትና አሰሪና ሰራተኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምርም አስታውቋል። ሚኒሰቴሩ "የሙያ ደህንነትና ጤንነት መረጃዎችን የመሰብሰብ የማደራጀትና በግብዓትነት የመጠቀም አቅም ማሳደግ ለ8ኛው የዘላቂ ልማት ግቦች አፈፃፀም አጋዥ እርምጃ" በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም አቀፍ የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ቀንን ትናንት ከባለድርሻ አካላት ጋር አክብሯል።   የሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኢታ ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የሥራ ላይ አደጋ በዓለም ሆነ በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል። በኢትዮጵያ በተለይም በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚደርሰው አደጋ ከሁሉም የሥራ ዘርፍ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ወይዘሮ ወርቅነሽ ገለጻ አሰሪ ተቋማት ላይ የሚታየው የፖሊሲና የህግ አተገባበር ክፍተቶች፣ ለሰራተኞቻቸው በቂ ሥልጠናዎችን አለመስጠትና ለችግሩ ትኩረት አለመስጠት በዋናነት የሚጠቀሱ ችግሮች ናቸው።  ሚኒስቴሩ አደጋውን ለመከላከል አዲስ የፖሊሲና ስትራቴጂዎች ረቂቅ አዘጋጅቶ በቅርቡ ሥራ ላይ ያውላል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በበኩላቸው በአብዛኛው ተቅጠረው የሚሰሩ ሰራተኞች የሥራ ዋስትና የተረጋገጠ አይደለም ብለዋል። "በዚህ ዓመት ከኮንስትራክሽን ግንባታዎች ላይ በመውደቅ፣ በመሠረት ቁፋሮ ወቅት በአፈር መደርመስና በኤሌክትሪከ አደጋዎች እንዲሁም በማሽን በመቆረጥ በሰራተኞች ላይ በርካታ አደጋዎች ደርሷል" ነው ያሉት። አሰሪ ተቋማትም ለሰራተኞቻቸው ምቹና የተረጋጋ የሥራ ቦታን መፍጠር እንደሚገባም አሳስበዋል። በአገሪቱ የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን መስፋፋትን ተከትሎ ለሰራተኛው ምቹ የሥራ ቦታን በመፍጠርና ሥልጠናዎችን በመስጠት በሥራ ላይ የሚደርሰውን አደጋ መቀነስ ይገባል ብለዋል። የሙያ ደኅንነትና ጤንነትን የተስተካከለ እንዲሆን በማድረግም ዘላቂ የልማት ግቦችን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። ሰራተኞችም በሚችሉት መጠን ራሳቸው ከአደጋ መከላከል እንደሚገባ ጠቁመዋል። ዓለም አቀፍ የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ14ኛ ጊዜ ተከብሯል(ኢዜአ) ። 
ሀገር አቀፍ ዜና
https://waltainfo.com/am/31635/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
cb886f1e1f465e38ca1e235f329f6598
294df56b9dc8b79e34f46deee4b83504
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ  ጉባኤውን  ማከናወን ጀመረ  ።የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት ለአራት ቀናት የሚቆየውን ጉባኤ በዛሬው ዕለት የጀመረ ሲሆን የ2010 ዓም የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጻም ዝርዝር ሪፖርት በማዳመጥ ስብሰባውን ጀምሯል ።የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የዘጠኝ ወራት ሪፖርትን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት በዘጠኝ ወራት ውስጥ አበረታች ለውጦች መመዝገባቸውን ጠቅሰው በተለያዩ ጊዚያት ሲንከባለሉ የቆዩ ተግባራትን በተሻለ ደረጃ ለማከናወን በበጀት ዓመቱ ቀሪ ጊዚያት ርብርብ ይደረጋል ።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጥልቅ ተሓድሶን መሠረት በማድረግ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በስኬት እንዲካሄዱ የማድረግ ሥራም ባለፉት ዘጠኝ ወራት መካሄዳቸውን አቶ ድሪባ አመልክተዋል ።በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍም በተከናወኑ የተለያዩ ሥራዎችም ከባለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ጊዚያት ከነበረው በተሻለ ውጤት መመዝገቡን  አቶ ድሪባ በሪፖርታቸው ጠቁመዋል ።በአዲስ አበባ ከተማ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ለተሰማሩ ዜጎችም  በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 7ሺህ ያህል  ሼዶች  ለዘርፉ አንቀሳቃሾች  ተከፋፈልዋል ብለዋል ከንቲባው ።በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪን የቤት ችግር ለመቅርፍም የጋራ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ሥራዎችን በማፋጠን  በአፋጣኝ ለህብረተሰቡ እንዲተላላፉ  ከፍተኛ ጥረቶች የሚካሄዱ መሆኑን  ከንቲባ ድሪባ ኩማ ተናግረዋል ።በመጨረሻም በአዲስ አበባ ከተማ የማህበራዊ አገልግሎት ችግሮችን  ለመፍታት  የተጠናከረ  ሥራ  ማከናወን አስፈላጊ መሆኑም በጉባኤው  ተነስቷል ።                          
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/29814/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
5be33536255b37654ab03e320285c872
8600279547a8da6337e78779ad815c22
ታሪካዊው የፍቅር ፊልም በዘረኝነት ምክንያት ታገደ
ከሰሞኑ ውሳኔውን ያሳወቀው ፊልም በድረገፅ የሚያሳየው ኤችቢኦ ማክስ ፊልሙ ከስምንት አስርት አመታት በፊት የተሰራ ከመሆኑ አንፃር ጊዜውን ቢያሳይም"ዘረኝነት የሚንፀባረቅበት ነው። በወቅቱም ስህተት ነበር አሁንም ስህተት ነው ብሏል። ድርጅቱ አክሎ እንዳስታወቀው ፊልሙ እንዲሁ ከድረገፁ ላይ ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ያለውን ታሪካዊ ዳራ የሚያሳይ ውይይት ተጨምሮበት እንደሚመለስ የገለፀ ሲሆን፤ ጊዜው መቼ እንደሆነ አልተጠቀሰም። መቼቱን የአሜሪካን የእርስ በርስ ጦርነት ያደረገው ይህ ፊልም ባርነትን የቀረፀበት መልኩ ከፍተኛ ትችቶችንና ውግዘቶችን ሲያስተናግድም ነበር። በማርጋሬት ሚቸል መፅሃፍ መነሻውን ያደረገው ይህ ፊልም ባርነት ከተወገደ በኋላ ጥቁር አሜሪካውያን በባርነት ዘመናቸው ህይወታቸው ሙሉ እንደነበርና ለቀድሞ ባለቤቶቻቸውም ታማኝ በመሆን በባርነት መቀጠል የሚፈልጉ ጥቁር አሜሪካውያን ህይወት ተንፀባርቆበታል። ፊልሙ ከፍተኛ ዝናን ከማትረፍ በተጨማሪም በፊልም ሽልማቶች ታላቅ የሚባለውን አስር የኦስካር ሽልማቶችን ማሸነፍ ችሏል። በፊልሙ ላይ የቤት ሰራተኛነትን ገፀ ባህርይ ተላብሳ የተጫወተችው ጥቁር አሜሪካዊቷ ሃቲ ማክ ዳንኤል በረዳት ተዋናይነት ያሸነፈች ሲሆን፤ የኦስካር ሽልማትን ለመቀበልም የመጀመሪያዋ ጥቁር ናት። ከሰሞኑም ታዋቂው ፀሃፊ ጆን ራይድሊ ፊልሙን አስመልክቶ ሎስ አንጀለስ ታይምስ በፃፈው ፅሁፍ " የባርነት ጊዜን ከፍ በማድረግ፤ ጥቁሮች ሲጨቆኑበትና ሲሰቃዩበት የነበረውንም ጊዜ ሌላ መልክ ለመስጠት ይሞክራል" የ'ትዌልቭ ይርስ ኦፍ ኤ ስሌቭ' ፀሃፊ አክሎም " በሆሊውድ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው ተዋናዮች የተሰባሰቡበት ፊልም ቢሆንም ባርነት ጥሩ እንደነበርና ለጥቁሮችም ጥሩ ወቅት እንደነበር ለመስበክ ይሞክራል። ይህ ግን ትክክል አይደለም" ብሏል። ኤችቢኦ ማክስ ባወጣው መግለጫ "ፊልሙ ዘረኝነትን በሚያንፀባርቅ መልኩ እንዲሁ እንዲታይና ያለ መግለጫና ውግዘት መተው ሃላፊነት የጎደለው ነው" ብሏል። ድርጅቱ አክሎም ፊልሙ ሲመለስ ብዙ እንደማይቀየር አመላክቷል። ከኤችቢኦ ማክስ በተጨማሪ ዲዝኒ በበኩሉ በጎርጎሳውያኑ 1941 የተሰራው የአኒሜሽን ፊልም ደምቦን ጨምሮ የቀድሞ ፊልሞቹ "ባህልን ዝቅ የሚያደርጉ ይዘቶች" ሊኖራቸው እንደሚችሉ አስጠንቅቋል። ከሰሞኑ ከፀረ ዘረኝነትና የፖሊስ ጭካኔ ጋር የተያያዙ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ፊልሙን ለማስወገድ የደረሰው ኤች ቢኦ ማክስ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ድረገፆች ፊልሞቻቸውን እየገመገሙ ነው። 'ሊትል ብሪቴይን' የተሰኘው ፊልም ከኔት ፍሊክስ፣ ብሪት ቦክስና ቢቢሲ አይ ፕሌየር እንዲወገድ ተደርጓል። ፊልሙ ዘረኝነት የሚንፀባረቅበትና አንዲት ነጭ ሴት ጥቁር ቀለም ተቀብታ በጥቁር ባህልና ማንነት ላይ ስትዘባበት ያሳያል ተብሏል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
c3eaa69ca9cc27cdff2ffe431a743b4a
419b529ece843b3a9c456bf89f484219
የሩዋንዳ መንግሥት አገሩ የሚገኙ የቡሩንዶ ስደተኞችን ወደ ሌላ ስርፋ እንደሚያዛውር አስታወቀ
የሩዋንዳ መንግሥት አገሩ ውስጥ የሚገኙ የቡሩንዶ ስደተኞችን ወደ ሌላ ስርፋ እንደሚያዛውር አስታወቀ፤ ምክንያት፣ "የሩዋንዳ ባለሥልጣናት የቡሩንዲ ስደተኞችን በቡሩንዲ ፕሬዚደንት ላይ ያሳምጻሉ" በማለት የዩናይትስ ስቴትስ ዲፕሎማቶች በመናገራቸው።ሩዋንዳ ዛሬ ዐርብ ይህን ባስታወቀቸት ወቅት፣ "አገራቸው ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ነውጥ በመሸሽ ወደ ሩዋንዳ የመጡ የቡሩንዲ ስደተኞችን በወጉ ለማስተናገድ፣ የቡሩንዲ መንግሥት ከዓለአቀፍ ማኅበረሰብ ሸሪኮቹ ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃደኛ" መሆኑን ገልጻለች።የስደተኞችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነቷን በውል እንደምትገነዘብ ሩዋንዳ በዛሬው መግለጫዋ ጠቅሳ፣ እነዚህን ስደተኞች ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ወገን እስካሁን አለመቅረቡንም አልሸሸገችም።
ዓለም አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/rwanda-to-relocate-burundian-refugees/3188706.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1062bbe88113e41a19ee76ce3df6ec27
1db7d6c591d52454e3be6f72a5f5eec0
ግሬታ፡ የአየር ንብረት ለውጥ እንደ ኮሮናቫይረስ ሊያሳስበን ይገባል
ስዊድናዊቷ የመብት ተሟጋች ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተገቢው ትኩረት ሊቸረው ይገባል ብላለች። ማኅብረሰቡ የአየር ንብረት ለውጥን እንዲሁም ጥቁሮች ላይ የሚደርሰውን ኢ-ፍትሐዊነት አይቶ እንዳላየ የሚያልፍበት ጊዜ እንዳለፈ ታምናለች። ታዳጊዋ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ በመጣሉ፤ ቤቷ ሆና ለማሰላሰል ጊዜ እንዳገኘች ትናገራለች። ግሬታ በ16 ዓመቷ ትምህርት አቋርጣ ነበር ወደ አየር ንብረት ለውጥ ንቅናቄ የገባችው። መስከረም ላይ የተባበሩት መንግሥታት በኒው ዮርክ ባዘጋጀው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ላይ ለመታደም ግሬታ አትላንቲክን በመርከብ ማቋረጧ ይታወሳል። የተለያዩ አገራት መሪዎች አብረዋት ፎቶ ሲነሱ ነበር። የጀርመኗ መራሔተ መንግሥት አንግላ መርከል፤ አብረው የተነሱትን ፎቶ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መለጠፍ ይችሉ እንደሆነ ጠይቀዋት እንደነበርም ታስታውሳለች። ግሬታ የዓለም ኃያላን አገራት ተግባር ብዙም አይዋጥላትም። “የነሱ ትውልድ በቀጣይ የሚመጡ ትውልዶችን ተስፋ በማጨለሙ ጥፋተኛነት እየተሰማቸው ይሆናል” ትላለች። ታዳጊዋ በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ ያደረገችውን ንግግር ብዙዎች ያስታውሱታል። መሪዎቹን “በባዶ ቃላችሁ ልጅነቴን ሰረቃችሁኝ፤ ህልሜን ገደላችሁት” ስትል ነበር የወቀሰቻቸው። “ሰዎች እየሞቱ ነው። እናንተ ግን ስለ ገንዘብና ዘላቂ የምጣኔ ኃብት እድገት ታወራላችሁ። እንዴት እንዲህ ታደርጋላችሁ?” ስትል መሪዎቹን ኮንናለች። የዛን ጉባኤ ያህል ተደማጭነት የምታገኝበት መድረክ እንደማታገኝ በማሰብ የተሰማትን ሁሉ ለመናገር መወሰኗን ለቢቢሲ ተናግራለች። ከጉባኤው ወጥታ ወዳረፈበችበት ሆቴል ስትሄድ ሰዎች ንግግሯን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ሲያደምጡ ብታይም ብዙም ደስተኛ አላደረጋትም። አሁንም ለአየር ንብረት ለውጥ መሰጠት ያለበት ትኩረት ያህል እንዳልተቸረውም ትናገራለች። “ሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ራሱ ስለ አየር ንብረት የሚያውቁት በጣም ትንሽ ነው። እውቀታቸው ከምታስቡት በላይ በጣም ውስን ነው” ትላለች። የካርበን ልቀትን መቀነስ የሚቻለው አኗኗራችን በመለወጥ እንደሆነ ታስረዳለች። ሆኖም ግን መሪዎች ልቀትን ለመቀነስ እንዳልቆረጡ ታክላለች። “ልቀትን ከመቀነስ ይልቅ ሪፖርት ማድረግ አቁመው ወደ ሌላ ቦታ ያዛውራሉ።” ዩናይትድ ኪንግደም፣ ስዊድን እና ሌሎች አገሮች የባህርና የአየር ጉዞ የሚያስከትለውን ልቀት እንዲሁም በሌሎች አገሮች በከፈቷቸው ፋብሪካዎች ያለውን ልቀትም እንደማይመዘግቡ ትናገራለች። “አረንጓዴ፣ ዘላቂነት፣ ለአካባቢ ተስማሚ፣ ዜሮ ልቀት የሚሉት ቃላት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ነገር ግን ትርጉማቸውን አጥተዋል።” ግሬታ እንደምትለው፤ ዓለም ከኮሮናቫይረስ መማር ያለበት በአደጋ ጊዜ መተባበር እንደሚያዋጣ ነው። ፓለቲከኞች ሳይንቲስቶችን መስማትም አለባቸው። በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ስለሚሞቱ ሰዎች ለማውራት መንገድ እንደሚከፈት ታዳጊዋ ተስፋ ታደርጋለች። ሆኖም ግን የሙቀት መጨመርን መቆጣጠር ይቻል ይሆን? የሚለው ላይ ጥያቄ አላት። “አገራት ቃል በገቡት መሠረት የካርን ልቀትን ቢቀንሱ እንኳን የዓለም ሙቀት ከ3 እስከ 4 ዲግሪ መጨመሩ አይቀርም። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውሱ አሁን ባለው የፖለቲካና ምጣኔ ኃብት አካሄድ አይገታም።” የመብት ተሟጋቿ በኃብት የናጠጠችው አሜሪካ ውስጥ ባየችው የካርበን ልቀት የበዛበት አኗኗር ደንግጣለች። የንፋስና የፀሐይ ኃይል የሚጠቀሙ መሣሪያዎች ጥቂት ናቸው። በቅርቡ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ መገደሉን ተከትሎ የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ተስፋ ሰጥቷታል። “ሰዎች ድምጻቸውን እያሰሙ ነው። ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉም አይተዋል” ትላለች። ያየችው ነገር ተስፋ...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
eb303e3babc220264186ff5ee15ed430
25a956093105b40fe359426aeb7fc977
ሰመራ የፌዴሬሽኑ ምርጫን ለማስተናገድ ዝግጅቷን ማጠናቀቋ ተገለፀ
የሰው ሰር መገኛ ምድር አፋር የፊታችን እሁድ በሚደረገው የፌዴሬሽን ምርጫ እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጅቷን ማጠናቀቋን አዘጋጅ ኮሚቴው አሳወቀ።የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን ለቀጣዩ አራት አመታት የሚመሩት ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈፃሚ አባላትን ለመምረጥ ከመስከረም 30 ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይደረግ ቆይቶ በእግርኳሱ የበላይ አካል ፊፋ አስገዳጅ ውሳኔ መሰረት የፊታችን እሁድ ግንቦት 26 በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሊደረግ የመጨረሻ ቀጠሮ ተይዞለታል።ሰመራ ከአንዴም ሁለቴ ምርጫውን ለማካሄድ በተሰጣት እድል መሰረት ለሆቴል እና ለመስተንግዶ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት  እንግዶቿን ለመቀበል እየተጠባበቀች ባለችበት ወቅት ምርጫው በመራዘሙ ከፍተኛ ኪሳራ እንዳስተናገዱ የሚገልፁት የአዘጋጅ ኮሚቴ አባላት በአሁኑ የመጨረሻ የምርጫ ቀጠሮ የፊታችን እሁድ ግንቦት 26 ሰመራ ላይ የሚደረገውን ምርጫ በጥሩ ሁኔታ ለማካሄድ እንደተዘጋጁ ገልፀዋል።” ምንም እንኳ ወቅቱ ለክልሉ ህዝብ የረመዳን ፆም ወር መሆኑ አስቸጋሪና አድካሚ ቢያደርግም የሚመጡት የስብሰባ ተሳታፊዎችን በሙሉ በጥሩ እንግዳ ተቀባይነት ባህል ተቀብሎ ለመሸኘት በሆቴል፣ በመስተንግዶ፣ በትራንስፖርት እና በሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሁሉ የክልሉ አስተዳደር እና ህዝብ ዝግጅታቸንን አጠናቀን እንግዶቻችንን ለመቀበል እየጠበቅን እንገኛለን።”  በማለት የአዘጋጅ ኮሚቴው አባል የአፋር ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ መሀመድ ያዮ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/36714
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
eb3c94cc0b1439b139979a5bccc26dd8
65ec21d227476a3d193000029eb5ac34
የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የ6 ወራት አፈጻጸሙን ገመገመ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የስድስት ወራት አፈጻጸም 51 በመቶ መሆኑን ተገለጿል፡፡ኮርፖሬሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ጉባዔ በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡በጉባዔው ኮርፖሬሽኑ  ባለፉት 6 ወራት ያስመዘገባቸው ስኬቶችና ተግዳሮቶች የተለዩ ሲሆን ቀጣይ አቅጣጫም ተቀምጧል፡፡የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሃይለመስቀል ተፈራ በጉባዔው ላይ እንደገለጹት ካለፉት ጊዜያት ሲንከባለሉ የመጡ ስራዎችን በማጠናቀቅ በኩል ባለፉት 6 ወራት የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡ለእቅድ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆን የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም የገንዘብ አጠቃቀም ችግር ግን ዋነኛው መሆኑን አቶ ሃይለመስቀል አስረድተዋል፡፡በተጨማሪም የፕሮጀክቶች አፈጻጸም መጓተት፣ ገንዘብ በአግባቡ አለመሰብሰብ፣ የመሃንዲሶች አቅም ውስንነት እና ሌሎችም ምክንያቶች እንደሚጠቀሱ ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡በተለይ ደግሞ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳጋጠመም ተገልጿል፡፡እነዚህ ማነቆዎች ወደ ቀጣይ ጊዜያት እንዳይንከባለሉ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ አቶ ሃይለመስቀል ተናግረዋል፡፡
ቢዝነስ
https://waltainfo.com/am/23725/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
af7c17d2e704b891aa16546aaef6fa0d
80dc91839eb939bcd727afcf82f83de7
ከ700 በላይ የሚሆኑ የስልጤ ዞን አመራሮች የአንድነት ፓርክን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ700 በላይ የሚሆኑ የስልጤ ዞን አመራሮች በዛሬው ዕለት የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።ጉብኝቱ የኢትዮጵያን ቀደምት እና አሁናዊ የታሪክ እሴቶች ለመመልከት ያስቻላቸው መሆኑን አመራሮቹ ተናግረዋል፡ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይት ያደረጉት አመራሮች እንደገለጹት፥ የአንድነት ፓርክ በቅብብሎሽ የመጣውን የኢትዮጵያ ቀደምት ገናናነት የሚያሳይ ነው።ይህም የህዝቦችን አንድነት እና ሁለንተናዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ነው የገለጹት።ፓርኩ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና ማማ ለመውጣት የምታደርገውን ተግባር የሚያሳይ ሆኖ እንዳገኙትም ተናግረዋል።ካለፉ ታሪኮች በመማር እና ጥሩውን እንደ ተሞክሮ በመውሰድ ወደፊት መሻገር አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።በመለሰ ምትኩ
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8a%a8700-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%88%86%e1%8a%91-%e1%8b%a8%e1%88%b5%e1%88%8d%e1%8c%a4-%e1%8b%9e%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%88%ab%e1%88%ae%e1%89%bd-%e1%8b%a8%e1%8a%a0/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
e721d3f6d065b5a93051edcbd2632670
f939fab159ab13f906567c32e01f099a
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መግለጫ
ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ የተሰኙ ድርጅቶች በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጠየቀ። ለአለፉት ዓመታት በኃይል በህወሓት ተወስደዋል ያላቸው የአማራ መሬቶች ወደነበሩበት እንዲመለሱም ጥሪ አቅርቧል።ሀገር አቀፍ ምርጫ መካሄድ ያለበት በአለው ህገ መንግሥት ላይ ህዝበ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ነው ብለዋል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/balderas-election-12-9-2020/5693448.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1a91abf7a2678e46929b47bf81043a8b
65e2734664487fd502042141e07ef202
አኖ ዶሚኒ
አኖ ዶሚኒ ከክርስቶስ ልደት በኋላ የነበረ የዘመን አቆጣጠር መለኪያ ሲሆን ብዙ የዘመን መቁጠርያ መሳሪያዎችን በውስጡ ያቅፋል ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ የኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ፣የግሪጎሪያውያን ቀን መቁጠርያ፣የሂጅራ ቀን መቁጠሪያ ይጠቀሳሉ።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
e01bbdb467b88c9b94d0e83153f13f5a
fb0c91add5e3df0b1de5fb212c084faf
የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 2-1 ሀድያ ሆሳዕና
መቐለ 70 እንደርታ በመጀመርያው የሊጉ መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕናን 2-1 ካሸነፈበት ጨዋታ በኃላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።“ካለብን የተጫዋቾች አማራጭ ችግር አንፃር ውጤቱ ጥሩ ነው” ገ/መድህን ኃይሌስለ ጨዋታው የመጀመርያ ጨዋታ እንደመሆኑ ውጤቱን እንፈልገው ነበር። ጨዋታው በዝግ መሆኑ አስቸጋሪ ነበር፤ ከዛ በተጨማሪ የአማራጭ እጥረት ነበረን። ካለብን የተጫዋቾች አማራጭ ችግር አንፃር የመጣው ውጤት ጥሩ ነው። በቀጣይ በቅጣት ያላሰለፍናቸው ተጫዋቾች ይመለሳሉ። በህመም ካጣናቸውም መሻሻል የሚያሳዩ ከሆኑ ወደ ቡድናችም እንቀላቅላለን። በአጠቃላይ ስናየው ግን እንደ ጅማሮ ጥሩ ጅማሮ ነው።ጨዋታው በዝግ መሆኑ ስለፈጠረው ተፅዕኖ እና ከደጋፊ ጋር ከሚደረግ ጨዋታ ጋር ስላለው ልዩነትአንደኛ ልዩነቱ ዳኝነት ላይ ነው። ደጋፊ ካለ ውሳኔዎች አወሳሰን ላይ ጥንቃቄ ይኖራል። ሌላው ደጋፊው የሚሰጥህ ሞራል መነሳሳት ይፈጥራል። በዚ ላይ ደግሞ ደጋፊያችን ትልቅ ሚና ስላለው ጨዋታው በዚህ መጠናቀቁ ጥሩ ነው።“ውጤቱ አይገባንም፤ መቀበል ስላለብን ግን ተቀብለናል” የሆሳዕና ምክትል አሰልጣኝ ኢዘዲን ዐብደላስለ ጨዋታው ጨዋታው ጥሩ ነበር። በሁለቱም ቡድኖች በኩል የታየው የመሸናነፍ ስሜት ጥሩ ነበር። ያለንን አቅም አውጥተን ለመጠቀም ሞክረናል። ውጤቱ አይገባንም። መቀበል ስላለብን ግን ተቀብለናል።ስለ ቡድናቸውለሊጉ አዲስ ነን። ግን እንደ አዲስ አደለም እየተጫወትን ያለነው። ራዕያችን ረዥም ነው። ባሉን ክፍተቶች ሰርተን ተፎካካሪ ለመሆን ነው እየሰራን ያለነው።
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/52266
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
3bc0af03602b002b490794d5c449b1ef
d5c6496263acaa44763a9c03498c8552
ኬንያውያን የመንግስት ሰራተኞች የአገራቸውን ልብስ እንዲለብሱ ተገደዱ
የኬንያ መንግስት፤ የመንግስት ሰራተኞች በሳምንት አንድ ቀንና በህዝባዊ በዓላት በአገር ውስጥ የተመረቱ ልብሶችን ብቻ እንዲለብሱ መመሪያ ማስተላለፉን ኦል አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡የአገሪቱ መንግስት አገር በቀል ኢንዱስትሪዎችን የማበረታታት ዓላማ ያለው ነው የተባለውን ይህንን መመሪያ ለሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማሰራጨቱን የጠቆመው ዘገባው፤ መመሪያውን ባላከበሩ የመንግስት ሰራተኞች ላይ ምን አይነት እርምጃ ይወሰዳል የሚለው በግልጽ አለመታወቁን አመልክቷል፡፡የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ባለፈው እሁድ በተከበረው የብሔራዊ ጀግኖች በዓል ላይ በአገር ውስጥ የተሰሩ አልባሳትን በመልበስ ለዜጎች ምሳሌ ሆነው ለመታየት መሞከራቸውንም ዘገባው አስታውሷል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=24429:%E1%8A%AC%E1%8A%95%E1%8B%AB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%88%B0%E1%88%AB%E1%89%B0%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8C%88%E1%88%AB%E1%89%B8%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%88%8D%E1%89%A5%E1%88%B5-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%88%88%E1%89%A5%E1%88%B1-%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%8B%B0%E1%8B%B1&Itemid=212
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
7d27936867c218417a15f73062c0c68c
fc5e0aebfd547e5f840d08443c538fe6
የዩክሬን አውሮፕላን በኢራን ሚሳይል ተመትቷል
ከሰሞኑ አሜሪካና ኢራን የጀመሩትና ያባባሱት እሰጥ አገባ ተጋግሎ መሰንበቱ የሚታወቅ ሲሆን ዋሽንግተን ከቴህራን ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነኝ በማለቷ ውጥረቱ የረገበ መስሎ ነበር፡፡ በዚህ መሰረትም በፐርሽያ አካባቢ ያለው ችግር መፍትሄ የተገኘለት የበረደም መስሎ ነበር የሚሉ ጸሃፊዎች ነበሩ፡፡ ባሳለፍነው ረቡዕ ንብረትነቱ የቱርክ የሆነ አውሮፕላን ከኢራኗ መዲና ቴህራን ተነስቶ ሲበር መከሰከሱ ይታወሳል በዚህ አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ 176 ሰዎች ሞተዋል፡፡ ከሰሞኑ የዚህ አውሮፕላን መከሰከስ መንስኤን ለማወቅ ዓለም የጓጓ ሲሆን አንዳንድ የምዕራብ አገሮች አውሮፕላኑ በኢራን ሳይመታ አልቀረም ሲሉ ሰንብተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ብሪታኒያ ዩክሬን እና ኢራቅ መንግሥታት አውሮፕላኑ በስህተት በሩሲያ ሰራሽ ሚሳኤል ተመትቶ ስለመውደቁ መረጃው አለን ማለታቸው ይታወሳል። ይሁንና የኢራን ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ኃላፊ አሊ አቤደዛዱህ አውሮፕላኑ በምዕራብ አቅጣጫ ከአውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ መብረር ከጀመረ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ወደ ቀኝ ዞሮ ተመልሶ ለማረፍ እየመጣ ሳለ ነው የተከሰከሰው በማለት ማስተባበያ ሰጥተው ነበር። ሌሎች የኢራን ሹሞች በበኩላቸው አውሮፕላኑ በኢራን ተመቶ ወድቋል የሚሉ አካላት ከነማስረጃቸው ይምጡ የሚል ክርክር ሲያነሱ ቆይተዋል፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጨምረውም የዓይን እማኞች አውሮፕላኑ አየር ላይ ሳለ በእሳት ተያይዞ ማየታቸውን ገልጸው ነበር፡፡  የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ፣ ትናንት አውሮፕላኑ ከምድር ወደ ሰማይ ተወንጫፊ በሆነ ሚሳኤል ተመትቶ ስለመጣሉ ብዙ የደህንነት መረጃዎች ደርሰውኛል ማለታቸው ሁኔታውን ሌላ አቅጣጫ አስያዘው።ካናዳውያን ጥያቄዎች አሏቸው ለጥያቄዎቻቸውም ምላሽ ማግኘት አለባቸው በማለት በአደጋው ዙሪያ ዝርዝር ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል። በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍረው ከነበሩት 176 ሰዎች መካከል 63ቱ ካናዳውያን ሲሆኑ፣ ከዩክሬኗ ኪዬቭ ወደ ቶሮንቶ ካናዳ የሚያቀኑ ነበሩ። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከትናንት በስቲያ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ከዚህ አውሮፕላን ጋር በተገናኘ ጥርጣሬ አለኝ። የሆነ አካል ስህተት ሳይሰራ አይቀርም ከማለት ውጪ ዝርዝር ነገር መናገርን አልፈቀዱም ነበር ። የዩናይት ኪንግደም ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰንም፣ ሀገራቸው ከካናዳ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሀገራት ጋር በትብብር እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ዛሬ ጠዋት ላይ ኢራን ንብረትነቱ የዩክሬን የሆነውን አውሮፕላን መትቼ ጥዬዋለሁ ስትል ለዓለም አስታወቀች፡፡ ይህንን ያደረገችው ደግሞ በስህተት ስለመሆኑ ነው ይፋ ያሳወቀችው፡፡ ይህ ጉዳይ ከሰሞኑ የአሜሪካና ኢራን ውዝግብ ጋር እንደሚገናኝ በርካቶች እየገመቱ ነው፡፡ ኢራን በአሜሪካ የተገደሉባት የኢራን ጄነራል ጉዳይ ስላበሳጫት ይህንን እርምጃ ወስዳለች የሚሉ መገናኛ ብዙሃና አሉ፡፡ ኢራን በበኩሏ ይህ የሆነው ታስቦበት አይደለም ብላለች፡፡ ሰሞኑን በአሜሪካና ኢራን የተጀመረው የተካረረ እሰጥ አገባ ወደ ድርድርና ንግግር ይመለሳል የሚል ተስፋ የነበረ ቢሆንም የአውሮፕላኑ ግን ነገሩን እንዳያባብሰው ተሰግቷል፡፡  የኢራን ጦር ባወጣው መግለጫ የዩክሬኑ የመንገደኞች አውሮፕላን ሆነ ተብሎ ሳይሆን በስህተት ተመቷል ይላል፡፡ የጦሩ መግለጫ አውሮፕላኑ በኢራን አብዮታዊ ጥበቃ አቅራቢያ በሚገኙ የደህንነት ቦታዎች እየበረረ ሳለ በስህተት ተመትቶ ነው የተጣለው የሚል ሃሳብ አለው፡፡ በዚህም መሰረት የመንገደኞች አውሮፕላኑ ተመቶ ለመውደቁ ኃላፊነት የሚወስዱት አካላት ተጠያቂ ይሆናሉ ብሏል መግለጫው፡፡ ከጄነራል ኡስማን ሱሌይማኒ መገደል በኋላ ኢራን የአጸፋ ምላሽ አሰጣለሁ ማለቷና በኢራቅ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት መሰንዘሯ የሚታወስ ሲሆን አውሮፕላኑንም መትታ የጣለችውም በተመሳሳይ ቀን ነው፡፡ ለበርካታ ንጹሃን ዜጎች ሞት ምክንያት የሆነው ይህ ሁሉ እሰጣ ገባ የጀመረው አሜሪካ በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ ጄነራል ቃሲም ሱሌይማኒን ከገደለች በኋላ ነው። ዶናልድ ትራምፕ፣ ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒን አሸባሪ ይበሉት እንጂ በኢራናውያን ዘንድ እንደ ጀግና ነበር የሚቆጠሩት። የጄነራል ቃሲም መገደል የዩክሬን አውሮፕላን መከስከስ ቀጣናውን ወደለየለት የግጭትና የትርምስ ቦታ እንዳያመራው ተሰግቷል፡፡ ምንጭ፡- ሲኤንኤን
ፖለቲካ
https://am.al-ain.com/article/iran-said-it-shot-down-ukrain-s-plane
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
26609dea181b18608382f8799e63ee5a
14a4bb7b7f1b430d9c0164172f05c326
ሹመት በነጻ ገበያው…
አዲሱ ገረመውበቅርብም፣ በሩቅም (እነ ዲያስፖራ) ያላችሁ ወዳጆቼ እንዴት ሰነበታችሁ? ሠላም ነው! ሰበር ዜናው፣ ማለቴ ቅዝቃዜው እንዴት ይዟችኋል? የሚመች ነገር ቢኖርም ባይኖርም ይመቻችሁ! ስሙኝማ ይልቅ የሙያ ቅጥር የሚባለው ገበያው ሲቀዘቅዝ ለአቅመ ሹመት የደረሱት ገበያውን እየተቆጣጠሩት ነው አሉ። እውነት ይሆን እንዴ?ለነገሩ በዘመነ ኢህአዴግ ገበያው ይሄው ሆኖ ነው የቆየው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተማረ ሰው እየተረሳ ነው፤ የሚሾመው ሌላ ሌላው ነው ሲባሉ ምን ብለው ነበር የመለሱት። የኢህአዴግን አላማ/አብዮታዊ ዴሞክራሲን ማለታቸው መሰለኝ/ እስከ አሳካ ድረስ የፈለገንን እንሾማለን ምን ትሆኑ አይነት ነገር ተናግረው ነበር።በዚህ አያያዝ እድገታችን ወደ ሦስት አሀዝ/ዲጂት/ ሊያሻቅብ ይችላል የሚል መላ ምት (መላ ለምን ይመታል ግን) ብናስቀምጥስ? “ወይ ጣሊያን!” አለች ምዕራብ ጀርመን! እንዲህ እንዲህ እያልን እንተንፍስ እንጂ። አንዱ ወዳጄ የሰሞኑን የአሜሪካውን አመጽና ሰልፍ አይቶ፣ እኛና አሜሪካ አንድ ነን፤ ሁለታችንም ዴሞክራት፤ ሁለታችንም ጋር የኑሮ ውድነት አለ፤ ሁለታችንም ጥጋብ አንወድም፤ ልዩነቱ እነሱ ተቸገርን ብለው በበላ አፋቸው በአደባባይ ሲጮሁ እኛ በአደባባይ ቀርቶ በባዶ ሆዳችን ተቸገርን ብለን ማሰብ አንችልም፤ አለኝ።እኔ ግን ተቃውሞዬን ገለጽኩለት። እኛ አገር አሁን ላይ እንኳን ጮሆ መናገር፣ ጮክ ብሎ መፃፍም ይቻላል አልኩታ። ለዚህ አይደል ታዲያ እኔስ ዳርዳር ማለቴ። እናላችሁ አገራችን በሹመት እምርታ አሳይታለች። ለዚህም በሹመት ቦታ መሙላት ምክንያት የባለሙያው መድረሻ ማጣትና እንግልት ምስክር ነው። ወዳጄ በቅርቡ ሥራ ስቀጠር በመጀመሪያው ወር ደመወዜ ማኪያቶ እጋብዛሃለሁ ያልከኝን አስታወስክ? ለካ እያሽሟጠጥክ ኖሯል? ግድ የለም ሹም ስትሆን ጋብዘኝ። ቅጥሩማ በየት በኩል። የስላቅ ሰፈሩ ወዳጄ የተጠበብክባት የማኪያቶ ግብዣ ስላቅ ግን ታስገርመኛለች እኮ። ሥራ ልትቀጠር ሄደህ ሹመት በሩን ዘጋብህ አይደል? እንግዲህ እኔ አልፈርድልህ፤ እርሱ አንድዬ ይመልከትህ እንጂ። ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው አንድ የመንግስት ተቋም ሰሞኑን ሽርጉድ በዝቶበታል። ሹመት የሚያገኙ አዳዲስ ሰዎች መኖራቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ከአመራር ተርታ የሚመድቡት ሲዶልቱ ነው የሚውሉት። ወሬው ሁሉ “እከሌ የት ቦታ ሊመደብ ይችላል?፤ እነ እከሌ እንኳን እነ እከሌ እያሉላቸው ምንም አይሆኑም” የሚል ሆኗል። ለዛሬው ይህችን አጭር መጣጥፍ ለመጻፍ መነሻ የሆነኝም ይኸው ነው። ሹመት በነፃ ገበያ ቢወዳደር ቅጥር ከሚያወጣው ዋጋ ያንስ ነበር። አንዳንዴ ተሿሚዎች ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ከባለሙያዎች ጋር ለሥራ ቢወዳደሩ ሌላኛው ችግር በደንብ ይገባቸው ነበር እላለሁ። ተሿሚ ደመወዙ ስንት እንደሆነ የሚያውቀው በዓመት አስልቶ እንጂ በወር ባንክ ቤት ተሰልፎ አይደለም። የወንበር ከሚለው ጀምሮ የነዳጅ፣ የቤት፣ የስልክ፣ የጉዞ፣ የማትግያ ወዘተ ተብለው በተሿሚዎች ቋንቋ ብቻ የሚታወቁ ጥቅማ ጥቅሞች አስክረውት በየት በኩል ደመወዙን ይቁጠር። በዚህ ላይ በትንሽ በትልቁ ከከተማ የሚያስወጣ ስብሰባና የመሳሰለው አለ፤ አበል የሚታጨድበት። ከእርሱ እኩል ተምረው እኩል የስራ ልምድ ኖሯቸው እንደውም በልጠው የሚገኙ ሰዎች ደግሞ ይህ ሁሉ ለእነርሱ ህልም ነው።ምን ህልም ብቻ ቅዥትም ነው። በነገራችን ላይ ሹመት የሚሰጠው፤ በዋነኛነት ለትልልቆቹ አመራሮች ባለው ቀረቤታ ላይ ተመስርቶ ነው። ትልልቆቹ አመራሮች ከወደዱህ፤ አንተ ብትማር፤ በፖለቲካ ብትበስል ባትበስል፤ ችግር የለውም። ካንተ የሚጠበቀው ትልቁ መስፈርት የነሱ አሸርጋጅ መሆን ነው። በዚህ መልኩ፤ እጅግ ብዙ አመራር ወደ ስልጣን መጥቷል። ወደ ስልጣን የመጣ አሸርጋጅ ከብሯል። የቪላና ፎቅ ቤት ባለቤት ሆኗል። ቪ ኤይት መኪናን ሲያሻው በሾፌር አሊያም በራሱ እጅ እንደልቡ አሽከርከሯል። አሁን እንዲህ አይነት ሰዎች፤ የህዝብን አጀንዳ ወደ ጎን ትተው፤ ቀን ከሌት ስለ ራሳቸው ጉዳይ ቢጨነቁ ምኑ ይገርማል? ለዚህ እኮ ነው ሹመት ቅጥ ይኑረው የምለው። እንደዚህ አይነት ሰዎች፤ በሆነ አጋጣሚ እንኳን ከሀላፊነት ቢነሱ፤ ምርጥ የተባለ ቦታ ተፈልጎላቸው ይመደባሉ፤ ይህ ምርጥ ቦታ ከጠፋም፤ በህግ ያልታወቀ / በመስሪያ ቤቱ መዋቅር የስራ መደብ የሌለ/ የስራ መደብ ይፈጠርላቸዋል፤ በዚህም መሰረት ተዘፍዝፈውበት ከከረሙት ስልጣን በሆነ አጋጣሚ ቢነሱ እንኳን፤ ሰናይ ኑሯቸውን እንዲገፉ ይደረጋል። ይሄ አሰራር በተለይም ለእነዚያ 27 ዓመታት ሲተገበር የኖረ ነው። ይሄን ሁሉ የተበላሸ አካሄድ ደግሞ፤ ህዝብ አንጀቱ እያረረ በአንክሮ ሲከታተልና ሲታዘበው ከርሟል። በአሁኑ ወቅት ለህዝባችን የሚያስፈልገው የሿሚ አገልጋይ ሳይሆን በውድድር ወደ ሥልጣን የሚመጣ አገልጋይ ነው።በሹመት ርዕዮተ ዓለም የበላይነት እሳቤ የቱንም ያህል የተማርክ ብትሆን፤ በአመራርና በፖለቲካው ብትበስል፤ እውነት ብትናገር ወዘተ. አንተ ለታላላቆቹ አመራሮች፤ እስካልተመቸሃቸው ድረስ ዋጋ ቢስ ነህ። ስለሆነም ሰበብ ተፈልጎልህ ከሥራ እንድትሰናበት ሁሉ ልትደረግ ትችላለህ። ያኔ ልክ ለእነሱ አሸርጋጆች እንደሚደረገው ሁሉ፤ ላንተ ጥሩ ቦታ ተፈልጎልህ የምትመደብ እንዳይመስልህ፤ ይልቁንስ ለሲቪል ሰርቪስ ቢሮ፤ በሚመጥነው ቦታ መድቡት ተብሎ ደብዳቤ ይጻፍልሀል። ሂድ አትበለው እንዲሄድ አርገው አይነት ስራም ይፈጥርልሃል። የሲቪል ሰርቪስ አመራርም፤ ቀድሞ ስለሚነገረው፤ ከወደደህ፤ እንደ ምንም ቦታ ፈላልጎ፤ በሚመጥንህ ይመድብሀል፤ ከደበርከው ደግሞ፤ ቦታው ስለሌለኝ፤ አንድ ደረጃ ዝቅ ብለህ ተመደብ ይልሀል፤ አንተም ደሀ ነህና እየቆዘምክ ትቀበላታለህ። ይህ ብዙዎች የተማሩ ሰዎች የገጠማቸው እጣ ፈንታ ነው። ይሄንን ኢ-ፍትሀዊ አሰራርም እስከመቼ በትዝብት እንመልከተው?ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲዎች ብቃትን ሳይሆን ፖለቲካዊና ዘውጋዊ ማንነትን ባማከለ መልኩ በተሾሙ የገዥው ፓርቲ እንደራሴዎች እንዲመሩ ተፈርዶባቸው ነበር። የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሾሙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። አሁን ላይ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት በተቋሙ ተልእኮና በዓለም አቀፍ መልካም ልምድ መሰረት፣ አካዳሚያዊ ነጻነት እንዲኖረው ተደርጎ ከሹመት ተኮር ይልቅ ውድድር ተኮር ሆኖ ተሻሽሏል። ይህ መልካም ጅማሮ በሌሎች የመንግስት ተቋማት ላይም ሊተገበር ይገባል። ይህ የዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ እየተቀመረ ወደ ሌሎች ተቋማት መውረድ ይኖርበታል። ምህንድስናን የተማረ ሰው በውድድር ቢመራ መንገዶቻችን ባልጎረበጡን፤ ፖለቲካው በዘርፉ ትምህርት ባለው ቢመራ ኖሮ አገራችን በፖለቲካዊ ቀውስ አትናጥም ነበር። የኢኮኖሚውን ጉዳይ የሚመራ ባለሥልጣን በዘርፉ ተምሮና ተወዳድሮ ቢመራ የእድገት ዲጂቱም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ይሆን ነበር። ሹመት የሚለው አሰራር ጎርበጥ ያደርጋል። እንደ ማህበረሰብ የሞራል ልዕልና ሰርቶ ጥሮ ግሮ በማግኘት የሚያምን ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል።ፖለቲካውን ማሳለጥ ከቻለ ከየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል አምጥተን እንሾማለን የሚለው ኢህአዴጋዊ መርህ አላረመደምና ቀስ በቀስ ልክ እንደ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶቹ ስልጣን በውድድር የሚያዝበት ወቅት እንዲመጣ እንፈልጋለን። 
መዝናኛ
https://www.press.et/Ama/?p=39343
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
796a4e7dfc8ea2fc893dfa881e151eff
941a5d855706625e336702c2068931ff
“ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት ከ12 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሆኗል” አቶ አለማዮሁ ተገኑ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2005 (ዋኢማ) – ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረጉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስትሩ አቶ አለማዮሁ ተገኑ በተለይ ለዋልታ እንደገለጹት በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ 16 ሚሊዮን ህዝብ  ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ እንደነበር አስታውሰው ቀሪው 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ በቀጣይ ተጠቃሚ  ይሆናል ብለዋል።በአገሪቱ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለማዳረስ የህዝብና የአመራር ንቅናቄ በመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ እስካሁን ባለው ጊዜ ሽፋኑ 61 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱን  አስታውቀዋል።ሚኒስትሩ አያይዘውም  በገጠር 93 ሺሕ  በከተማ  ደግሞ 1 ሺሕ 5 መቶ የውሃ ተቋማት ቆጠራና የሚገኙበትን ደረጃ የመለየት ስራ እንደተከናወነ ተናግረዋል።  አቶ አለማዮሁ አያይዘውም የአገሪቱ የመስኖ ስራ የሚከናወነው በፌዴራል መንግስት፣ በክልሎች፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና  በግል ባለሃብቶች እንደሆነ ጠቁመው በጥናትና በቅድመ ዝግጅት ደረጃ በሁሉም ወገኖች መጠናቀቁን ገልጸዋል።የመስኖ ስራ ሰፊና ከባድ አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ አገሪቱ ካላት  የመስኖ ሃብት አንጻር  ብዙ እንደሚቀር አቶ አለማዮሁ ተናግረዋል።አገሪቱ ካላት 1 መቶ 22 ቢሊየን ሜትር ክዩቢክ ውሃ እስካሁን ድረስ የተጠቀመችው  7 በመቶ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የመስኖ ስራ ከነበረበት 2 ነጥብ 5 ወደ 15 በመቶ ለማሳደግ እቅድ ተይዞ  7 በመቶ መፈጸሙን የጠቆሙት  ሚኒስትሩ  በቀሪው ጊዜ እቅዱን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/24650/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
7d6836e6e52cb523509d781374bd7141
a1da5e853e7233e6aa3a44da3330349f
ቻይና አዲሱ ህግ ሀገር ክህደትንና ሽብርተኝነትን ለመከላል ያለመ ነው ብላለች
ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ ባወጣችው አዲስ ህግ ምክንያት ከአውሮፓ ህብረት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብታለች ቤጅንግ የሆንግ ኮንግን ጉዳይ የተመለከተ አዲስ ያዘጋጀችው የጸጥታ ሕግ በአሜሪካና በአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟታል፡፡  “በአንድ ሀገር ሁለት ሥርዓት” ውስጥ ያለችው ሆንግ ኮንግ ከሌሎች የቻይና ግዛቶች የተለየ ነጻነትና አስተዳደር ያላት ሆንግ ኮንግ ከቤጅንግ የወጣላት አዲስ ሕግ ግን ይህንን ነጻነቷን ሊጋፋ ይችላል እየተባለ ነው፡፡ ግዛቲቱ በርካት የጸጥታ ችግሮች ሲስተዋሉባት እንደነበር የገለጸችው ቤጄንግ ለግዛቲቱ አዲስ የጸጥታ ሕግ ማውጣቷ ይታወሳል፡፡ ሕጉ ሆንግ ኮንግን ከቻይና ስለመገንጠል፣ ሀገር ክህደትንና ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለማውገዝ ያለመ ቢሆንም አሜሪካና አውሮፓ ግን ሆንግ ኮንግን ለማፈን ነው በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ፡፡ ቻይና ሕጉ በሆንግ ኮንግ ጉዳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመመከት እንደሚያግዛት በማመን በግንቦት በምክር ቤቷ አጽድቃለች፡፡የንብረት፣የኮንትራት፣የግለሰብ መብቶችን፣ጋብቻና ቤተሰብ፣ውርስና የፍትሐ ብሔር ተጠያቂነትን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የያዘው ይህ አዲስ ሕግ ታዲያ ቻይናን ማዕቀብ እንዲጣልባት አድርጓል ነው የተባለው፡፡ የአውሮፓ ሕብረት በዚሁ ቻይና ባወጣችው ሕግ ዙሪያ በቤጅንግ ላይ ማዕቀብ መጣሉን ወል ስትሬት ጆርናል አስነብቧል፡፡ በዚህም መሰረት የአውሮፓ ሕብረት የሆንግ ኮንግ የጸጥታ ሕግ ቻይና እንድትገነባ የሚያስችሉ የቴክኖሎጅ ቁሳቁሶችን ወደ ቻይና ላለመላክ መወሰኑን አስታውቋል፡፡ በአውሮፓ ሕብረት የሚገኘው የቻይና ተልዕኮም በሕብረቱ ድርጊት ማዘኑን የቻይናው ግሎባል ቴሌቪዥን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ሕብረቱ በቻይና የውስጥ ጉዳይ ላይ መግባት እንደሌለበት የገለጸው የቻይናው ተልዕኮ በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት የሚችሉት ቻይናውያን በተለይም የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች መሆናቸውንም ነው የገለጸው፡፡ ቻይና በሆንግ ኮንግ ተግባራዊ የሚደረገው ብሔራዊ የጸጥታ ሕግ ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ እንዳገዛቸው ስለመግለጻቸው አስታውቃለች፡፡ይሁንና አውሮፓ ሕብረት በቤጅንግ ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቋል፡፡ ቻይና በዚህች ልዩ ግዛት ላይ የጣለችው ማዕቀብ አውሮፓና አሜሪካን በተለየ መልኩ ለምን አሳሰባቸው የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ከብራሰልስና ከዋሸንግተን በተጨማሪም አምንስቲ ኢንተርናሽናልም ጉዳዩ የሰው ልጆችን የሰብዓዊ መብት የሚጋፋ ነው እያሉ ነው፡፡ አሜሪካ ቀደም ብላ ከቻይና ጋር የገባችውን የንግድ እሰጥ አገባ በሆንግ ኮንግ በኩል ለማቀጣጠል በማሰብ ሕጉን መቃመው ከተሰማ ቆይቷል፡፡ አሜሪካ ይህንን ጉዳይ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ለማሳወቅ እሰራለሁ ብትልም ሩሲያ ግን ጉዳዩ የቻይና የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ ሌላ የውጭ አካል በጉዳዩ ዙሪያ አይመለከተውም ማለቷ ይታወሳል፡፡ አውሮፓ ሕብረት መሪዎችም በሆንክ ኮንግ ጉዳይ እጅግ እያሰብን ነው ብለዋል፡፡ ይሁንና የሕብረቱ አመራሮች አዲሱ የጸጥታ ሕግ በጣም ያሳስበናል ከማለት ባለፈ ለምን እንዳሳሰባቸው ያነሱት ምክንያት የለም፡፡
ፖለቲካ
https://am.al-ain.com/article/china-eu-at-odds-with-new-chinese-s-hong-kong-law
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1ed905b8a332aff648dcd8afffc225de
4c43af1d574c032cbe32597cece18745
ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ያስገባቻቸውን ወታደሮቿን ለማስወጣት ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።
ኢትዮ-ኤርትራ፡ ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት ተስማማች\nፕሬዝደንት ኢሳያስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ሲሸኙ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ፣ አርብ ጠዋት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሐሙስ ዕለት አሥመራ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባደረጉት ውይይት ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማማታለች። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የድንበር አካባቢዎቹን ተረክቦ ጥበቃውን ወዲያውኑ እንደሚጀምር ሁለቱ መሪዎች ከስምምነት ደርሰዋል። በሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ተፈጽሞ ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ የህወሓት ኃይሎች ወደ አሥመራ ሮኬቶችን መተኮሳቸው የኤርትራ መንግሥት ተጨማሪ ጥቃቶችን ለማስቆምና ብሔራዊ ደኅንነቱን ለማስከበር ድንበር መሻገሩ ተገልጿል። የኤርትራ ሠራዊት ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት በግጭቱ ውስጥ እየተሳተፈ እንደሆነ የተለያዩ ሪፖርቶች ቢገልጹም እስካሁን ድረስ ከኤርትራ መንግሥት በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም። መግለጫው በተጨማሪም ሁለቱ አገራት በመተማመንና በመልካም ጉርብትና ላይ በተመሰረተ መንፈስ የጀመሩትን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ምጣኔ ሃብታዊ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ ባለው ሕዝብና ከድንበር ባሻገር ኤርትራ ውስጥ በሚገኘው ሕዝብ መካከል መተማመንን መሰረተ ባደረገው መልኩ ግንኙነቱ እንዲሻሻሻል ማድረግ አስፈላጊ ነው ብሏል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በኤርትራ ያደረጉት ጉብኝት መጠናቀቅን በማስመለክት የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚንስቴር መግለጫ አውጥቷል። ሚንስቴሩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሥመራ ቆይታ ወቅት መሪዎቹ በአገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይና በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ባለፉት 5 ወራት "የተሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎችን በጥልቀት ገምግመዋል" ብሏል። በቀጣይነትም ሁለቱ መሪዎች አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው ለመመክር መስማማታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትግራይ ከተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ጋር ተያይዞ የኤርትራ መንግሥትና ሕዝብ ሠራዊታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በገባበት ጊዜ ላደረገለት ድጋፍ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ ሲያመሰግኑ ቆይተዋል። ማክሰኞ ዕለት ከአገሪቱ ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስና ማብራሪያ ወቅት ይህንኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ጥቅምት መጨረሻ ላይ የህወሓት ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዙ በኋላ የኤርትራ ሠራዊት በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ እንደሆነ በተለያዩ ወገኖች ሲገለጽ ቆይቷል። ነገር ግን ሁለቱ አገራት የኤርትራን ሚና ሲያስተባብሉ ቆይተው ከቀናት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በድንበር አካባቢ ባሉ ቦታዎች ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ሠራዊት ከጀርባው ጥቃት እየተፈጸመበት የድንበር አካባቢውን መጠበቅ አስቸጋሪ ስለሆነበት የኤርትራ ጦር ድንበር አልፎ መግባቱን በማብራሪያቸው ላይ ተናግረዋል። አክለውም ሠራዊቱ የህወሓት ኃይሎችን ለመዋጋት ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች በመንቀሳቀሱ ክፍተት እንደተፈጠረና የኤርትራ መንግሥትም በዚህ ክፍተት ጥቃት እንዳይፈጸምበት በመስጋቱ ወደ ስፍራዎቹ መግባቱን ገልጸዋል። ቢሆንም ግን የኢትዮጵያ ሠራዊት ሌላውን ተልዕኮ ሲያጠናቅቅና አካባቢዎቹን መቆጣጠር ሲችል የኤርትራ ኃይሎች ከስፍራው እንደሚወጡ ተናግረው ነበር። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾችና ድርጅቶች በተደጋጋሚ ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ የኤርትራ...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
be01b268aba4b4ca53ab15f0f60b5291
ba26c875f18e57d8b8fe13c647ff50f0
ቱርክ የሳዑዲ አረቢያው ጋዜጠኛ ግድያን መረጃ ይፋ አደረገች
ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ አራቢያ ቆንስላ ውስጥ እንደተገደለ የታመነው ካሾግጂ ወደ ቅጥር ግቢው እንደገባ ነበር የታነቀው ስትል ቱርክ መግለጫ ሰጥታለች። ለሳምንታት የዓለም መገናኛ ብዙሃን ወሬ ማሟሻ ሆኖ የሰነበተው የካሾግጂ ግድያ ጉዳይ ቱርክ መረጃ እስክታወጣ ድረስ በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። • በመጨረሻም ጀማል ኻሾግጂ መገደሉን ሳዑዲ አመነች ምንም እንኳ ቱርክ ለመረጃዋ ማስረጃ ማቅረብ ግድ ቢላትም «በታቀደው መሠረት ካሾግጂ ልክ ወደ ቆንፅላው ቅጥር ግቢ ሲገባ በገዳዮች ታንቆ ነው የተገደለው» ስትል አትታለች። ከዚያም ይላል መረጃው ሲቀጥል «ከዚያም የጋዜጠኛው በድን አካል ተቆራርጦ እንዲጠፋ ተደርጓል። ይሁ ሁሉ የተከናወነው ቀድሞ በተፃፈ ስክሪፕት መሠረት ነው።» የቱርኩ ዋና አቃቤ ሕግ ኢርፋን ፊዳን ከሳዑዲ አቻቸው ጋር የነበራቸው ውይይት ውጤት አልባ እንደበረ ተነግሯል፤ ምንም እንኳ ሳዑዲ ስለጉዳዩ ሹክ ያለችው አንድም ነገር የለም። • ሳዑዲ ለሮቦት ዜግነት ሰጠች መኖሪያውን አሜሪካ በማድረግ ለዋሽንግተን ፖስት ይፅፍ የነበረው ሳዑዲ አረቢያዊው ካሾግጂ የንጉስ ሞሓመድ ቢን ሰልማን ቀንደኛ ተቺ እንደነበር ይነግርለታል። ምንም እንኳ የሰውዬው ሬሳ የት ይግባ የት ባይታወቅም ቱርክ፣ ሳዑዲ እንዲሁም አሜሪካ ካሾግጂ የሳዑዲ ቆንፅላ ፅ/ቤት ውስጥ እንደተገደለ እሙን ነው ብለዋል። በአሟሟቱ ላይ ግን የተለያየ መረጃ የምትሰጠውን ሳዑዲን ጨምሮ ሶስቱም ሃገራት ሰምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም። ቱርክ መገናኛ ብዙሃን በካሾግጂ ጉዳይ ከታማኝ ምንⶐች ያገኘናቸው ያሏቸውን ዝርዘር መረጃዎች ከማውጣት አልቦዘኑም። • የሳዑዲው ጋዜጠኛ ለመገደሉ ቱርክ አሳማኝ ማስረጃ እንድታቀርብ አሜሪካ ጠየቀች
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
68addb4959984f8deac65e15060af653
4a1d3eaedc26f6cccb0a803d6fc9b1a3
ሐረር ከተማ በፈረቃ ውሃ ማግኘት ጀምራለች
ባለፈው ሳምንት ሐረር ከተማ ያሉ ሰፈሮች እስከ ዘጠኝ ወር ድረስ ውሃ ሳያገኙ እንደቆዩ መዘገባችን ይታወሳል፤ የሐረር ከተማ ሰዎችም የድረሱልን ጥሪ አቅርበው ነበር። የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የከተማዋ አንድ ሦስተኛ ክፍል የቧንቧ ውሃ ማግኘት ጀምሯል። «የችግሩ ዋነኛ ምንጭ የነበረው የዓለማያ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት ከኦሮሚያ መስተዳድር እና ከዓለማያ እና አወዳይ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ጣቢያው አገልግሎት መስጠት እንዲቀጥል ተደርጓል» ይላሉ ባለስልጣኑ። • በዝምታ የምትጠማ ከተማ -ሐረር አክለውም «ከዓለማያ የሚመጣውን ውሃ ከድሬዳዋ ከሚመጣው ጋር በማጣመር ቢያንስ የከተማዋን አንድ ሦስተኛ ክፍል በማዳረስ ለማረጋጋት እየጣርን ነው» ብለዋል አቶ ተወለዳ። በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ደግሞ ሌሎች ውሃ ያልደረሳቸውን ቦታዎች በፈረቃ የማዳረስ ዕቅድ እንዳላቸው ባለሥልጣኑ አሳውቀዋል። የኤረር የውሃ መስመር ችግር እስካሁን እንዳልተፈታ የጠቆሙት አቶ ተወለዳ በሚቀጥሉት ሁለት ሦስት ቀናት ችግሩ እንደሚቀረፍ እምነት አላቸው። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ያሰቡት ነገር እንዳለ የተጠየቁት ሥራ አስኪያጁ «ሌሎች ውሃ አመንጪ ጉድጓዶች ቆፍረን መስመር ለመዘርጋት ዝግጅት ላይ ነን» ብለው፤ ወደ ሐረር ከተማ ውሃ የሚያሰራጩ መስመሮችን በማብዛት ሥራ መጠመዳቸውን ጠቁመዋል። • መስመር ያልያዘው የኢትዮ-ኤርትራ የንግድ ግንኙነት አክለውም «ለሚቀጥሉት አምስትና አስር ዓመታት ከተማዋ ምን ያህል ውሃ ያስፈልጋታል የሚል ጥናት ልናካሂድም ነው» ብለዋል። አቶ ዳንኤል በርሄ በሐረር ከተማ የሆቴል ባለቤት ናቸው። ላለፈው አንድ ወር በሳምንት ከግለሰብ ከቦቴ ውሀ በ2000 ብር እንደገዙ ያስታውሳሉ። አሁን ግን ውሃ መጥቶ «ትልልቅ ማጠራቀሚያቸውንም ባሊውንም ሞልተናል» ይላሉ፤ ሌሎች ከእርሳቸው ሰፈር በከፋ ለአራት ወራት ያክል ውሃ ያላገኙ ሥፍራዎች እንዳሉ በመጠቆም። ችግሩ ፀንቶባቸው የቆዩ ቦታዎች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የውሃ አቅርቦት እንዲኖራቸው መደረጉን ባለሥልጣኑ አክለው ነግረውናል። «ቅድሚያ የሰጠናቸው ለረዥም ወራት ውሃ የሚባል ያላገኙ አካባቢዎችን ነው፤ ለምሳሌ በተለምዶ ጊዮርጊስ ጋራ እና ከራስ ሆቴል በላይ ያሉ አካባቢዎችን ነው። ከራስ ሆቴል በታች ያሉትም ቢበዛ በአራት ቀናት ውስጥ ውሃ እንደሚያገኙ እምነቴ ነው» ብለዋል አቶ ተወለዳ። ባለስልጣኑ አክለውም «10 ሚሊዮን ብር ካልተሰጠን የዓለማያ ውሃ ጣቢያ አግልግሎት እንዲሰጥ አንፈቅድም ያሉ ሰዎችን አደብ በማስያዝ የኦሮሚያ ክልል አስተዋፅኦ አበርክቷል» ይላሉ። የሐረር ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ችግራቸውን ለማስታገስ የታሸገ ውሃ በመግዛት ለተጨማሪ ወጪ መዳረጋቸውን ገልፀውልን እንደነበር አይዘነጋም። ውሃ ሲጠፋ 55 ኪሎ ሜትር ድረስ ተጉዘው የሚቀዱ እንዳሉ እና ይህንን ማድረግ የሚችሉት መኪና ያላቸው እንደሆኑም የችግሩን ግዝፈት እንደሚያሳይ ተነግሮ ነበር። • በአላማጣ ግጭት ቢያንስ 5 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
8b7e5e4a06c39e8d7900db6b35d0329c
53b4d71d0f5533ca3138b22f07853ff0
ዛሬም ድረስ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ከሌለባቸው እኩል ተምረው የሚያድጉ፣ ሠርተው የሚቀየሩ የማይመስላቸው አይታጡም። ከዚህ የማህበረሰብ ጎምቱ አመለካከት ጋር ታግለው፣ የእለት ኑሯቸውን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ለሌላው አርአያ የሆኑ በርካታ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎችም አሉ።
#3 እሷ ማናት?፡ ማየትና መስማት የተሳናት የመብት ተሟጋችና የሕግ ባለሞያዋ ሃበን ግርማ\n"አታድግም፣ መማር፣ መስራት አትችልም፤ አታገባም የሚሉኝ ብዙ ሰዎች ነበሩ" ከሩቅ ዘመን ሔለን ኬለርን ብንጠቅስ ከቅርብ ደግሞ ሊ ሪድሊይ እማኛችን ነው። የኛዋን የትነበርሽ ንጉሤንም ሳንረሳ ማለት ነው። 'ሎስት ቮይስ' በሚል የሚታውቀው እንግሊዛዊው ሊ ሪድሊይ ለ39 ዓመታት ድምፅ ያልነበረው ኮሜዲያን ነው። ሰዎች ለአካል ጉዳት ያላቸውን አመለካከትና አገላለፅ ለማረም ሊ፣ እ.ኤ.አ በ2018 በተካሄደው ታዋቂው ልዩ የክህሎት ውድድር 'ብሪቴይን ጋት-ታለንት' ላይ የራሱ አካላዊ ጉዳትን እያነሳ በመቀለድ አሸንፏል። • የኢትዩጵያውያን አካል ጉዳተኞች ፈተናዎች ምን ድረስ? • ኢትዮጵያዊው የ100 ሜትር ክብረወሰን ባለቤት ይህ መናገር የማይችለው፣ ነገር ግን በሳቅ ጎርፍ የሚያጥለቀልቀው ኮሜዲያን፣ በጋዜጠኝነት ሁለት ዲግሪ ሲኖረው ለቢቢሲ እና ለሌሎች የሃገሪቷ ጋዜጦች በመሥራትም በርካታ ሽልማቶች የተጎናፀፈ ነው። ለዛሬው የእሷ ማናት ዝግጅታችን የመረጥናት ሐበንም አካል ጉዳት ሞራሏን ሳይበግረው፣ ለራሷም ለሌሎችም አርዓያ መሆን የቻለች ግለሰብ ናት። ሌላኛዋ ሄለን ኬለር ስወለድ ጀምሮ የመስማትም ሆነ የማየትም ችግር አብሮኝ ነበር የተወለደው። ለሆነ ነገር 'ገደብ' በማስቀመጥ አላምንም፤ 31 ዓመቴ ነው። ሐበን ግርማ እባላለሁ። ሁሌም አካላዊ ጉዳት ያላቸው ሰዎች መሥራት የሚችሉት ነገር የተገደበ ነው የሚሉ አስተሳሰቦችን ስታገል ኖሬያለሁ፤ አሁንም በዚሁ የትግል ሜዳ ውስጥ ነኝ። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪዬን አግኝቻለሁ። በዚህም በዩኒቨርስቲው ታሪክ የመጀመሪያዋ ማየትና መስማት የተሳናት የሕግ ምሩቅ ሆኛለሁ። በ2019 ደግሞ ''The Deaf blind Woman who Conquered Harvard Law'' የሚል መጽሐፍ ለንባብ አብቅቻለሁ። ይህን መጽሀፍ በስሜ የተሰየመ ሲሆን፣ የህይወት ተሞኩሮዬን፤ ውጣ ውረዴንና ስኬቴን ያሰፈርኩበት ነው። • በእራስ ውስጥ ሌሎችን ማየት በመላው ዓለም እየዞርኩ 'የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች፣ እኩል ተደራሽና ተጠቃሚ መሆን አለባቸው' የሚል ዘመቻ የማደርግ ሲሆን፣ ለዚህ የአካል ጉዳተኞች መብት እንዲከበር ለማደርገው ጥረት ዓለማችን መሪዎችና የተለያዩ አካሎች የማበረታቻ ቃላቸውን፣ እውቅናና አድናቆታቸውን ሰጥተውኝ ያውቃሉ። ከእነዚህም መካከል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የነበሩት ባራክ ኦባማና ቢል ክሊንተን፣ የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ይገኙበታል። ተወልጄ ያደግኩት በኦክላንድ ካሊፎርኒያ ነው። እናትና አባቴ ግን ከኤርትራ እና ከኢትዮጵያ ናቸው። መጀመሪያ ላይ በትንሹም ቢሆን ማየትና መስማት እችል ነበር፤ በኋላ ላይ ግን ዓይኖቼም ሆኑ ጆሮዎቼ የማየትና የመስማት አቅማቸው እየደከመ በመምጣቱ በመሳሪያ በመታገዝ ወደ መግባባት ተሸጋግሬያለሁ። አሁን ድምጽ ቀድቶ በሚይዝ መሣሪያ በመናገር ከሰዎች ጋር እግባባለሁ። የፈለግኩትን ማይል ብጓዝ የማይለየኝ ማይሎ ነው፤ ማይሎ ውሻዬ ነው፤ የቀኝ እጄ! "ዓለምን እዞራለሁ። ማይሎ የሚባል የሦስት ዓመት ዕድሜ ያለው የ'ጀርመን ሼፐርድ' ዝርያ ያለው ውሻዬ፣ እኔን መንገድ መምራት የሚያስችለው የሁለት ዓመት ትምህርት ተሰጥቶታል። አሁን ሁሉንም ነገር ማየት የሚችል ውሻ አለኝ። ደረጃዎች ላይ መቆም፣ አስቸጋሪ ቦታዎችን መለየት፣ መሻገሪያ መንገድ ስንደርስ መቆም እና ሌሎችንም ክህሎቶች ተምሯል። ሁለታችን አብረን እንጓዛለን፤ በአውሮፕላን ይሁን በእግር ጉዟችን አንድ ላይ ነው። ማይሎ ድንቅ የመንገድ መሪ ነው።" • ዐይነ ስውሩ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ሕንፃ ከሰባተኛ ፎቅ የአሳንሰር ጉድጓድ ውስጥ...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
95594992b6068bbf0102f23a8d1317f5
5ba3366480695e0b9891fc2db2461c7e
ባይደን በመጀመሪያ ቀናቸው አወዛጋቢ የተባለውን የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት ይሰርዛሉ ተባለ
የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው ፕሮጀክት አልሞ የነበረው የካናዳዊቷን ግዛት አልበርታንና የአሜሪካን ኔብራስካን ግዛትን የሚሸፍን 1 ሺህ 900 ኪሎሜትር እርዝማኔ እንዲኖረው ታቅዶ ነበር። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች እንዲሁም ቀደምት አሜሪካውያን ይህ ፕሮጀክት እውን እንዳይሆን ለአስር አመታት ያህል ታግለዋል። ፕሮጀክቱ በነበረበትም ጫና በተወሰነ መልኩ ስራዎች ተቋርጠው የነበረ ቢሆንም ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት አመታት በፊት እንዲጀመር አድርገውታል። ከትራምፕ በፊት በስልጣን ላይ የነበሩት ባራክ ኦባማ የማስተላላፊያ ቧንቧ ግንባታ ስራ እንዲቋረጥ የሚያዘውን ህግ በከፍተኛ ድምፅ እንዲፀድቅ ቢያደርጉም ትራምፕ ያንን ውሳኔ ቀልብሰውታል። የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሪጀክቱ 8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያስወጣልም ተብሎ ነበር። ባይደን ምን ሊሰሩ አቅደዋል? ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ቢሮ የተገኘ ደብዳቤ አይነተናል ያሉት የካናዳና አሜሪካ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ጆ ባይደን በበዓለ ሲመታቸው ቀን የኪስቶን ኤክስኤል ነዳጅ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት ፈቃድን ለመሰረዝ ፍፁማዊ ስልጣናቸውን እንደሚጠቀሙ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የካርበን ልቀትን ለመቀነስና ለመቆጣጠር የተፈረመውን አለም አቀፉን የፓሪስ ስምምነት አገራቸው እንድትመለስ ያደርጓታል። ትራምፕ ከአለም አቀፉ የፓሪስ ስምምነት አገራቸውን ያስወጧት በያዝነው አመት ህዳር ወር ላይ ነበር። ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአየር ንብረት ለውጥን መታገል አስተዳደራቸው የሚያስቀድመው ዋነኛ ተግባር ነው በማለትም አስምረዋል ። ከነዳጁ ማስተላለፊያ ቧንቧ ጋር በተያያዘም የአልበርታው መሪ ጃሰን ኬኒ የጆ ባይደን እቅድ ከፍተኛ ስጋት እንዳጨረባቸው ገልፀው የቧንቧ ዝርጋታው ፕሮጀክት የሚታጠፍ ከሆነ መንግሥታቸው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስበዋል። የኪስቶን ኤክስኤል የነዳጅ ቧንቧ 830 ሺህ በርሜል ያልተጣራ የነዳጅ ድፍድፍ ከአልበርታ ወደ ኔብራስካ እንዲያስተላልፍ ታቅዶ ነበር። ኔብራስካም ከደረሰም በኋላ እዚያው ያለው የማስተላለፊያ ቧንቧ ጋር በማገናኘት ሜክሲኮ ገልፍ ወዳለው ማጣሪያ ቦታም ይወሰዳል። የአልበርታ ነዳጅ ከአሸዋ፣ ውሃ፣ ሸክላ ጋር የተቀላቀለ በይዘቱም ወፈር ያለ ሲሆን፤ ነዳጁንም ለማጣራት ከፍተኛ የሆነ ኃይል ጉልበትና ወጪውም ጣራ የነካ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም የተነሳ እንደ ግሪን ፒስ ያሉ የአካባቢ መብት ጥበቃ ተሟጋቾች ከዚህ ነዳጅ የሚለቀቀው ጋዝ በተለምዶ ከሚታወቀው 30 በመቶ ጭማሬ አለው ይላሉ። ነገር ግን የካናዳ መንግሥት በበኩሉ ከባቢን በማይጎዳና ኃይልንም በማይጨርስ መልኩ ማጣራት የሚያስችል ቴክኖሎጂ አለ በማለት ይከራከራል። ቀደምት የአሜሪካ ህዝቦች በበኩላቸው የአልበርታን አካባቢ እንዲሁም የፌደራል መንግሥቱን ድፍድፍ ነዳጅ ለማውጣት በሚል ለ15 አመታት ላደረሱት ጉዳት ከሰዋል። ሰርተው የሚበሉበትንና መሬታቸውን ያለነሱ ፈቃድ ለከፍተኛ ጉዳት ዳርጎታልም በማለት ይከሳሉ።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
b9c3647fc7e83402cc75ae2c86b3055e
91230709a3798dac8d4a2d7c88e0f36c
የአሜሪካ ድምጽ 75ኛ ዓመቱን ሲያከብር፤ ቀጣይ ዓመታቱስ ምን ይመስላሉ?
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ስርጭት የጀመረበትን 75ኛ ዓመት፣ ዛሬ እአአ የካቲት 1 ቀን እያከበረ ነው። የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዳይሬክተር አማንዳ ቤኔትን የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ቃለመጠይቅ አድርጎላቸው ነበር፡፡"የአሜሪካ ድምጽ 75ኛ ዓመቱን ሲያከብር፤ የተቋቋመብትን ዓላማ ለማሳካት በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች መረጃ ማሰራጨቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመግለጽ እወዳለሁ። እውነተኛ፣ ተዓማኒ፣ ገለልተኛና የማይወግን የዜናና መረጃ ላለፉት 75ዓመታት እንዳሰራጨን ሁሉ ለቀጣይ 75 ዓመታት የምናደርገውም ይሄንኑ ነው። በግሌ እዚህ የአሜሪካ ድምጽ አካል ሆኜ፣ ከእናንተና ከሌላው ዓለም ጋር ስነጋገር፤ በቅድሚያ ለምን ጋዜጠኛ ለመሆን እንደወሰንኩ ያስታውሰኛል። የተጣለብንን ሃላፊነት ለመወጣት እኔም፤ እዚህ አብረውን የሚሰሩ ባልደረቦቼም ዝግጁ ናቸው። 75ኛ ዓመታችንን ስናከብር፤ ለቀጣይ 75 ዓመታት እንድትከታተሉን እየጋበዝኩ ነው።"አማንዳ ቤኔት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ዳይሬክተርለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይልና ቪድዮ ይመልከቱ።
ዓለም አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/voa-celebrates-75-years-voa-director-amanda-bennet-2-1-2017/3702118.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
cdddbba8c3c3b9b29263102b573a5c13
e17c338d6868883367d6637857acf47a
ደቡብ ካስቴል ዋንጫ ነገ ይጠናቀቃል
ትላንት በተካሄዱት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች አርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን በመለያ ምቶች በመርታት ለፍፃሜ መብቃት ችለዋል፡፡አርባምንጭ በተጋባዝነት ውድድሩ ላይ እየተካፈለ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ጋር መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ 1-1 አጠናቆ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች አርባምንጭ 5-4 ማሸነፍ ችሏል፡፡ በተመሳሳይ ሲዳማ ቡና ከሌላው ተጋባዥ ቡድን ድሬዳዋ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 አጠናቆ በመለያ ምቶች 9-8 ማሸነፍ ችሏል፡፡በክረምቱ አርባምንጭ ከተማን ለቀው ሲዳማ ቡናን የተቀላቀሉት ትርታዬ ደመቀ እና አበበ ጥላሁን በፍፀሜው የቀድሞ ክለባቸውን በተቃራኒው የሚገጥሙ ይሆናል፡፡ከፍጸሜው ጨዋታ በፊት 07፡00 ኢትዮጵያ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ለ3ኛ ደረጃ ይፋለማሉ፡፡ በከፍተኛ ድምቀት ሲካሄድ የቆየው ውድድሩ ከፍተኛ ተመልካች ያገኘ ሲሆን ከፍተኛ ገቢ እንደተገኘበትም ታውቋል፡፡
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/17006
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
e52232255d90c87dc84e2c749650baed
c7450fe1dd9c3c9320166e2d7d344aec
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ከኃላፊነታቸው ለቀቁ
የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን በተሾሙት አቶ ፍፁም አረጋ ምትክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን በሚያዝያ 2010 ዓ.ም. ተሹመው የነበሩት በላቸው መኩሪያ (ዶ/ር)፣ ከማክሰኞ መስከረም 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ  ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ፡፡ከሚሽነሩ በኃላፊነት የቆዩት ለአምስት ወራት ነው፡፡ ከኃፊነታቸው ለመልቀቃቸው ይኼ ነው የተባለ ምክንያት ባይሰጥም፣ በገዛ ፍላጎታቸው መልቀቃቸውን ግን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡በላቸው (ዶ/ር) ኮሚሽነር ሆነው እንዲያገለግሉ ሾመዋቸው የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ የኮሚሽነርነት ኃላፊነቱን ይዘው እንዲሠሩ ከመሾማቸው ቀደም ብሎ በምክትል ኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ ነበር፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የካቢኔ ሹም ሽር ወደ ኃላፊነት ከመጡት ተሿሚዎች የፓርቲ አባላት ካልሆኑት አንዱ የነበሩትን በላቸው (ዶ/ር)፣ ከአራቱ ምክትል ኮሚሽነሮች መካከል በአንደኛው አቶ ተካ ገብረየሱስ በተጠባባቂነት መተካታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡   
ፖለቲካ
https://www.ethiopianreporter.com/article/12995
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
31eb5aa169841b4daddd115a2adf4059
ef0c79d07ad832b7821dcbc1af1de78e
የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ከየካቲት 9 እስከ 11/2012 ዓ.ም ድረስ ያደረገውን አስቸኳይ ስብሰባ ተከትሎ ዛሬ ከሰዓት ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ አባላት ክህነታቸው ተይዟል ሲል ቅዱስ ሲኖዶሱ አወጀ\nየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሲኖዶሱን መግለጫ በጽሁፍ ያቀረቡት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ በሚከተሉት ላይ የቅዱስ ሲኖዶሱን አቋም አሳውቀዋል። የኦሮሚያ ቤተ-ክህነት አደረጃ ኮሚቴን በተመለከተ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደረጃ ኮሚቴን በማለት የኦሮሚያ ቤተ-ክህነትን ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት ሕገ-ወጥ እና ከቤተ ክርስቲያ እውቅና ውጪ የሚከናወን መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶሱ አስታውቋል። "ከቤተ-ክርስቲያኒቱ ሕግ እና ደንብ ውጪ በመነሳሳት የኦሮሚያ ቤተ-ክህነት እናቋቁማለን በማለት በሕገ-ወጥ መንገድ በቅዱስ ሲኖዶስ ተባርኮ ጽላት ተሰጥቶናል በሚል ቤተ ክርስቲያን አቋቁመናል የሚሉት፤ ቤተ-ክርስቲያኒቷ በማታውቀው መንገድ በአመጽ በመነሳሳት መዕመናንን ግራ እያጋቡ እና እያሳሳቱ ከቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ውጪ የክህደት ትምህርት ማስተማራቸው በመረጃ ተደግፎ ለቅዱስ ሲኖዶስ መቅረቡን ተከትሎ ከድርጊታቸው ተቆጥበው በንስሐ እስኪመለሱ ድረስ ከየካቲት 11/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰጣቸው ክህነት ተይዟል" ብሏል። ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች በቤተ ክርስቲያን ስም ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል ሲል ሲኖዶሱ መግለጫ አውጥቷል። "ግለሰቦቹ ከጥፋት ድርጊታቸው ተጸጽተው ለመመለስ ከፈቀዱ ጉዳያቸው በድጋሚ ሊታይ ይችላል" ብሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ ለግለሰቦቹ ከቤተ ክርስቲያኒቷ የተሰጣቸው ጽላት አለመኖሩን አስታውሶ ምዕመናኑም "ከእንዲህ አይነት ተሳስተው ከሚያሳስቱ ግለሰቦች እራሳቸውን፣ ኃይማኖታቸውን እና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትን ከምን ጊዜ በላይ እንዲጠብቁ ጉባኤው ያሳስባል።" ከአምልኮ ቦታ ጋር በተያያዘ ስለተፈጠረው ግጭት በአዲስ አበባ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአምልኮ ቦታ ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ በነበረው ክስተት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል። ቅዱስ ሲኖዶሱም "ጭካኔ ለተሞላበት ድርጊት" የፈጸሙ አካላት ላይ መንግሥት ጥብቅ ምርመራ በማድረግ ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡና ውጤቱ ለምዕመናኖቻችን በሚዲያ እንዲገለጽ እንጠይቃለን ብሏል ሲኖዶሲ። ከዚህ በተጨማሪም ቅዱስ ሲኖዶሱ ለግጭቱ ምክንያት የሆነው ቦታ ከአራት ዓመታት በፊት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኗ ለአከባቢው ነዋሪዎች ማምለኪያነት እንዲውል በተደጋጋሚ ለመንግሥትን ጥያቄ ስታቀርብ መቆየቷን አስታውሷል። ሲኖዶሱ መሬቱ ለቤተ ክርስቲያን ግንባታ እንዲሰጥ ጥያቄውን አቅርቧል። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ካህናት እና ወጣቶች በእሥራ ላይ እንደሚገኙ ያስታወሰው ቅዱስ ሲኖዶሱ፤ "እስር ላይ የሚገኙት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን" ብሏል። መገናኛ ብዙሃንን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶሱ ኦኤምኤን፣ ኦቢኤስ እና ኤልቲቪ የቤተ ክርስቲያኗን ክብር እና ልዕልናዋን የሚነካ መረጃ እያሰራጩ ነው ብሏል። የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ የጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ከመገናኛ ብዙሃን ደንብ እና ሕግ አኳያ በሕግ እንዲየቁና ከእንዲህ አይነቱ ሕገ-ወጥ ተግባር እንዲታቀቡ እንጠይቃለን ብሏል ቅዱስ ሲኖዶሱ። የአረብ ኤሜሬቶች የቤተ-ክርስቲያን ግንባታ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበርካታ ዓመታት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት ቦታ እንዲሰጠው በተደጋጋሚ ለሚመለከተወ አካል ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሰው፤ በቅርቡ የቤተ ክርስቲያኗ ጥያቄ ምላሽ ማግኙትን አስታውቀዋል። የቤተ ክርስቲያኗ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጠቅላይ ሚንስር ዐብይ አህመድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
e60ebc538d50109113746d0b90061eab
f4ffa616520918776c703587776bc3de
ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ወላይታ ድቻ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ከነገ ጨዋታዎች መካከል በዛሬ ቅድመ ዳሰሳችን የምንመለከተው ጨዋታ ድቻ እና ጊዮርጊስ የሚገናኙበትን ይሆናል።ከአሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ ጋር የተለያየው ወላይታ ድቻ ነገ በሶዶ ስታድየም 09፡00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስተናግዳል። አዲስ አባባ ላይ በተስተካካይ ጨዋታ በሲዳማ ቡና የተረታው ወላይታ ድቻ ከወራጅ ቀጠናው በአንድ ነጥብ ብቻ ከፍ ብሎ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የመጀመሪያውን ዙር በወራጅ ቀጠና ውስጥ ላለመጨረስም ወሳኝ በሆነው በዚህ ጨዋታ የዋና አሰልጣኙን ስንብት ተከትሎ በምክትል አሰልጣኙ ደለለኝ ደቻሳ እየተመራ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል። አምስት ድሎችን በመደዳ አስመዝግቦ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ የጀመረውን ግስጋሴ ጋብ የሚያደርጉ ሁለት የአቻ ውጤቶች ገጥመውታል። ተስተካካይ ጨዋታዎቹን በመጨረሱም በተከታዮቹ መቐለ እና ሲዳማ መሪነቱን ላለመነጠቅ ማድረግ የሚችለው ነገር ከሶዶ በድል ተመልሶ የነሱን ጨዋታዎች መጠበቅ ብቻ ይሆናል።ወላይታ ድቻ የበረከት ወልዴን አገልግሎት ከ5 ቢጫ ካርድ ቅጣት በኋላ የሚያገኝ ሲሆን ፍፁም ተፈሪ ፣ አንዱዓለም ንጉሴ ፣ እዮብ አለማየሁ ፣ ውብሸት ክፍሌ እና ግብ ጠባቂው ታሪክ ጌትነት ግን ከጉዳታቸው አላገገሙም። አብዱልከሪም መሀመድ ከጉዳት በተመለሰለት ቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ደግሞ መሀሪ መና ፣ ሳላዲን በርጌቾ  እና ጌታነህ ከበደ ጉዳት ላይ የሚገኙ ሲሆን መጠነኛ ጉዳት ያለባቸው ምንተስኖት አዳነ እና አቡበከር ሳኒ ግን ከቡድኑ ጋር ተጉዘዋል። የእርስ በርስ ግንኙነት እና እውነታዎች– ቡድኖቹ እስካሁን 10 ጊዜ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ ግማሹን በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆን ወላይታ ድቻ የአምናውን ድሉን ጨምሮ ሁለት ጊዜ አሸንፏል። በቀሪዎቹ 3 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ፈረሰኞቹ 17 ሲያስቆጥሩ የጦና ንቦቹ ደግሞ 6 ግቦች አሏቸው።– በወላይታ ድቻ ሜዳ በተደረጉ አምስት ጨዋታዎች ውስጥ ሦስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ ሁለቱም አንድ አንድ ጊዜ ድል አድርገዋል።– ወላይታ ድቻ በአዲስ አበባ ስታድየም ከሲዳማ ያደረገውን ጨዋታ ሳይጨምር ሽንፈት ባላስተናገደበት የሶዶ ስታድየም አምስት ጨዋታዎችን ሲያከናውን ሁለቱን በማሸነፍ ቢጀምርም ከመጨረሻዎቹ ሦስት ተጋጣሚዎቹ ጋር 1-1 ነበር የተለያየው።– ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጪ ስድስት ጨዋታዎችን ሲያደርግ ሦስት የ1-0 ድሎች አስመዝግቦ ሁለት ጊዜ ደግሞ ያለግብ በተጠናቀቁ ጨዋታዎች ሲመለስ አንድ ሽንፈት አስተናግዷል።                 ዳኛ– እስካሁን ከመራቸው ሦስት ጨዋታዎች መካከል በሁለቱ እነዚህን ተጋጣሚዎች የመዳኘት አጋጣሚ የነበረው ዮናስ ካሳሁን እርስ በርስ የሚገናኙበትን ይህን ጨዋታዎች ይመራል። ዮናስ በሦስቱ ጨዋታዎች ዘጠኝ የማስጠንቂያ ካርዶችን መዟል።ግምታዊ አሰላለፍወላይታ ድቻ (4-1-3-2)መኳንንት አሸናፊእሸቱ መና – ተክሉ ታፈሰ – ውብሸት ዓለማየሁ –  ኄኖክ አርፌጮበረከት ወልዴ – ኃይማኖት ወርቁቸርነት ጉግሳ – አብዱልሰመድ ዓሊ  – ሳምሶን ቆልቻባዬ ገዛኸኝ          ቅዱስ ጊዮርጊስ (3-5-2)ፓትሪክ ማታሲአስቻለው ታመነ  – ፍሬዘር ካሳ – ፍሪምፖንግ ሜንሱ በኃይሉ አሰፋ – ሙሉዓለም መስፍን – ናትናኤል ዘለቀ – ኄኖክ አዱኛታደለ መንገሻሳላሀዲን ሰዒድ – አቤል ያለው
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/44620
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
e7070fb40289e349e20d987cb7f14d1f
43fba865a15f660b471354e7e67506da
Metshafe henok
መጽሐፈ ሄኖክ ከክርስቶስ ልደት በፊት የአዳም ፯ኛ ትውልድ በሆነው ቅዱስ ሄኖክ ዕጅ የተጻፈ የሚስጥር እና ራዕይ መጽሐፍ ሲሆን ከዚያም ለልጅ ልጁ ኖኅ በማስተላለፍ ተሠወረ። ከዚያም ምድር በጥፋት ውኃ ስትጠፋ የአያቱን መጽሐፍ ይዞ ወደ መርከቢቱ በመግባት ይህ ቅዱስ መጽሐፍ ሊተርፍ ችሎ
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
5566f0d6cfc0deb10d73a545f28638cf
31c424ef7573cb983dc4a6c2ca026de0
የትግራይ ህዝብ ጸረ-ሰላም ኃይሎች የሚሸርቡትን ሴራ ለማክሸፍ ይታገላል -የህወሓት መግለጫ
ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ጸረ ሰላም ሃይሎች የሚሸርቡትን ሴራ ለማክሸፍ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ አስገነዘበ ፡፡በየዓመቱ ሰኔ 15 በትግራይ ክልል የሚከበረውን የሰማእታት ቀን ምክንያት በማድረግ ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ፀንቶ የኖረውን የአንድነትና የመቻቻል እሴት ለማደፍረስና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ጸረ ሰላም ኃይሎች የሚሸርቡትን ሴራ ለመመከት የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር በጋራ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ከሌሎች ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በመሆን  በትምክትና ጠባብነት አመለካከት ኃይሎችን በመታገል የአገሪቱን ህዳሴ ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትጋት እንደሚሰራ አስገንዝቧል።የህዳሴውን ጉዞ ለማደናቀፍ የሚሯሯጡ ጸረ ሰላም ኃይሎችን ለመመከትም ዛሬም እንደትናንቱ በንቃትና በብቃት እንደሚታገሉ መግለጫው አረጋግጧል ፡፡የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ባሳለፈው መራራ ትግል አሁን ለተገኘው ሰላም፣ ልማትና ዲሞክራዊ ስርዓት ግንባታ የከባድ መስዋእትነትና የአካል መጉደል፣ ስቃይና እንግልት እንደደረሰበት መግለጫው ጠቅሷል  ።ሀገሪቱ ካለችበት የድህነት አረቋ እንድትወጣ ሰማዕታት ትተውት የሄዱትን አደራ ማሳካት እንደሚገባም ነው የገለጸው ።በየጊዜው እየተፈጠሩ ያሉትን ተጨማሪ የህዝብ ፍላጎቶችን ለመመለስ አሁንም በጠራው የትግል መስመር ህወሓት ትግሉን የሚያጠናክርበት አጋጣሚ  መሆኑንም አንስቷል ።የሰማዕታት ቀን ሲዘከርም የትግራይ ህዝብ በከፈለው መስዋዕትነት የተገኙ ዓበይት ድሎችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዳግም ቃሉን በማደስ እንደሚሆን ነው ያስታወቀው ፡፡በአገሪቱ አሁን ለተረጋገጠው ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵዊያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን ከፍተኛ የህይወት መስዋእትነት መክፈሉን በማስታወስ ።በዓሉ የሚከበረውም ሰኔ 15/980 ዓመተ ምህረት ፋሽሽታዊው ደርግ በተዋጊ ጄቶች በገበያ በተሰበሰቡ 2 ሺህ 500 ንጹሃን በጅምላ የጨፈጨፈበት የሓውዜን ሰማእታት ሲዘከር ፍጹም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ጀግንነት የተሞላበት የትጥቅ ትግል መካሄዱን ለማስታወስ መሆኑን ገልጿል ።
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/29200/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
a9b35d60776e8ffebfdbb1b0b38d1c19
5ed1adec92cbfc71a6cd62b12f969e9f
ማባዛት
ማባዛት ማለት ከመደመር፣ መቀነስ፣ ማካፈል ጋር እንደ አራቱ መሰረታዊ የቁጥር ሂሳብ ስሌቶች የሚታይ ነው። ስራውም አንድን ቁጥር በሌላ ቁጥር ማብዛት ነው። የጥንቱ የኢትዮጵያውያን ዘዴ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲሰራበት የነበረው የማባዛት ዘዴ በምሳሌ እንሆ። 12ን በ13 ለማባዛተ ከፈለግን እንዲህ እናረጋለን፡- 12*13 አንደኛውን ቁጥር በ2 ካበዙ በኋላ ሌላኛውን ደግሞ በ2 ያካፍላሉ፣ ተካፍሎ የቀረውን ይተውታል ከዚያ በቀኝ በኩል በሚገኙት የማይካፈሉ (odd) ቁጥሮች ትይዩ ያሉትን የግራ ቁጥሮች ይደምራሉ። በምሳሌያችን ላይ እንደሚታየው 13፣ 3 እና 1 በቀኝ የማይካፈሉ ቁጥሮች ሲሆኑ፣ በነሱ ትይዩ ያሉትን ስንደምር 12+48+96= 156 ይህ ዘዴ ለኮምፒውተር ስራ አገልግሎት በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይቻላል ምክንያቱም ከባይናሪ የቁጥር ስርዓት ጋር ተዛማጅነት ስላለው። ሥነ ቁጥር
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
f6511d76b02e901804596169e7dcc89b
b1081c38c755c9c6137ed675d8b2a725
የገዳ ስርዓት – የኦሮሞ ሕዝብ የትልቅነቱ ምልክትም ሀብትም
አስቴር ኤልያስ ስፍራው በተለያዩ የሴቶችና የወንዶች አልባሳት ደምቋል::በአልባሳቱ ላይ ገኖ የሚታየው ነጭ ቀለም በመሆኑም አስተውሎ ለተመለከተው ዙሪያ ገባውን የፈካ ማሽላ አስመስሎታል::በተለያዩ ድንኳኖች ውስጥ ደግሞ የጉጂ የባህል ምግቦች እንዲሁም የተለያዩ ጌጣጌጦችና አልባሳት ለእይታ ቀርበዋል::በዚሁ ስፍራ አምስት የጎጆ ቤቶች በመደዳ ተሰድረው ይታያሉ::ስፍራው በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ የጉጂ ኦሮሞ የባህል ስርዓት የሚካሄድበት ቦሌ ሀገላ ነው ::በዕለቱ የገዳ ስርዓቱን ደረጃ የሚያሳይ ትርዒት በስፍራው የተካሄደ ነው ፣ እነዚህም ደበሌ፣ ቀሬ፣ ኩሳ፣ ራባ፣ ዶሪ፣ ገዳ፣ ባቱ እና ዩባ የተባሉት ናቸው ትርዒቱን ያቀረቡት::በዕለቱ መርሐግብሩን በንግግር የከፈቱት የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፈርያት መሀመድ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ የብዙ ባህል ባለቤት ናት::የኦሮሞ ህዝብ ደግሞ ከትውልድ ወደትውልድ ሲያስተላልፍ የመጣው የገዳ ስርዓት አንዱ ነው ፣ ይህም የገዳ ስርዓት እንደ እሬቻ፣ ስንቄ፣ ሞጋሳና ሌሎችንም በርካታ እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው::እነዚህም እሴቶች ለኦሮሞ ብሎም ለአገሪቱ ሕዝቦች ወንድማማችነት እንዲጠናከር የሚያግዙ ናቸው ::የገዳ እሴቶች ውበታቸውንም ጥንካሬያቸውንም ጠብቀው ከትውልድ ወደትውልድ እንዲተላለፉ የሁሉም ድርሻ ነው የሚሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ሚኒስትር መሥሪያ ቤታቸው ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን በቅንጅት እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት::የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው፤ የገዳ ስርዓት ለኦሮሞ ሕዝብ ሀብቱም ምልክቱም መሆኑን ይናገራሉ::ኦሮሞ በዚህ ሥርዓት ሲተዳደር እንደነበር ሁሉ ዛሬም በመተዳደር ላይ እንደሚገኝም ጠቅሰው፤ በዚህ ሥርዓት ውስጥ መብት እንዳለ ሁሉ ግዴታ መኖሩን ያመለክታሉ::በተለይም ደግሞ ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግርን አጥብቆ ስለሚከተል በዚህም ዓለም እንደሚያውቀው ነው የተናገሩት::እርሳቸው እንዳሉት፤ ይህ ስርዓት ቀደም ሲል በተወሰነ ደረጃ ተዳክሞ ነበር::ይሁንና በተሰሩ ጠንካራ ስራዎች አማካይነት በዩኔስኮ ከመመዝገቡም በተጨማሪ በክልል ደረጃ ከአንድ እስከ ስምንተኛ ክፍል ትምህርት የሚሰጥ ሲሆን፣ በዩኒቨርሲቲ ደረጃም እስከ ሶስተኛ ዲግሪ እየተሰጠ መገኘቱ ይበል የሚያሰኝ ጉዳይ ሆኗል::በመሆኑም ኦሮሞ አሊያም ኢትዮጵያ ብቻ የሚኮራበት ሳይሆን አህጉሪቱ አፍሪካ እንዲሁ የምትኮራበት ስርዓት ነው::የምዕራብ ጉጂ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ከድር ኤሌሞ በበኩላቸው፤ የሕዝቦችን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር ባህልን ማክበር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ የገዳ ስርዓት ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ የሚተዳደርበት የዴሞክራሲ መሰረት የሆነ በመሆኑ ሊከበርም ከትውልድ ወደትውልድ ለማሸጋገር በሚደረገው ሂደት መተባበርም ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል::የዴሞክራሲ መሰረት የሆነውን የገዳ ስርዓት ማጠናከር የሕዝብን አንድነት ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል::በዕለቱ ያነጋገርናቸው ወጣት ነጌቱ ደስታ እና ወጣት ሌሎ ሂርባዬ በየበኩላቸው፤ የገዳ ስርዓትን ለማስቀጠል በመጀመሪያ ግንዛቤን ከፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የተናገሩት::በተለይ የዴሞክራሲ መሰረት ነው የተባለውና በተግባሩም እየታየ የሚገኘው ይኸው ስርዓት በዩኔስኮ መመዝገቡ ብቻ በራሱ የዴሞክራሲን ስርዓት እንደማያስቀጠል ጠቅሰው፤ ስርዓቱን በማስቀጠል ረገድ ከወጣቱ ብዙ እንደሚጠበቅ ነው ያመለከቱት::የገዳ ስርዓት መለያ ምልክታቸው እንደሆነም ይናገራሉ::የገዳ ስርዓት አንደኛውን ትውልድ ከሌላኛው ትውልድ የሚያያዝ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ ሌላኛዎቹ ወጣቶች ጫልቱ ደስታ እና ገመዴ ገናሌ ናቸው::ወጣቶቹ የገዳ ሥርዓት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ መሰጠት መጀመሩ ለቅብብሎሽ ትልቁን ሚና የሚጫወት ስለመሆኑም ጠቅሰዋል::እነርሱ የተማሩት ከቤተሰቦቻቸው እንደመሆኑ እነሱም በቀጣይ ለትውልድ ለማስተላለፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ይናገራሉ:: ከትናንት በስቲያ የገዳ ስርዓት ለዓለም ቅርስነት የተመዘገበበትን 4ኛ ዓመት የመታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የገዳ ፓናል ውይይት በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በትናትናው ዕለት ደግሞ የጉጂ ባህልን የሚያመለክቱ የተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂደዋል::ወጣቶች የገዳ ስርዓት የኦሮሞ ሕዝብ ሀብትም ምልክትም ነው የሚሉት::
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=39254
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
6ddde9846e3685d4eac358faf8719055
0e45a26ea6f2ded6389d68f7134bd6be
የአሜሪካ ሴኔት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ሁኔታ በማስመልከት የውሳኔ ሐሳብ ማሳለፉ ተገለጸ።
የአሜሪካ ሴኔት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሐሳብ አሳለፈ\nበትግራይ ክልል ባለው ግጭት ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ህወሓት እና ሌሎች የግጭቱ ተሳታፊዎች ግጭቱን እንዲያቆሙ፣ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዲፈቀድ ጠይቋል። እንዲሁም ግጭቱን ተከትሎ ተዓማኒ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል እንዲመረመር ትብብር ያድርጉ ሲል ሴኔቱ የውሳኔ ሐሳብ አስተላልፏል። የውሳኔ ሃሳቡ ለሴኔቱ የቀረበው መቼ ነበር? ይህን የውሳኔ ሐሳብ ለሴኔቱ ያቀረቡት የሜሪላንድ ግዛት ዲሞክራቱ ሴናተር ቤንጃሚን ኤል ካርዲን ናቸው። ሴናተሩ እስካሁን ቢያንስ የ13 ሴናተሮችን ድጋፍ በማግኘት ምክረ ሐሳቡ ለሴኔቱ የቀረበው እአአ መጋቢት 9/2021 ነበር። ቀደም ሲል ቀርቦ በነበረው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። ሴኔቱ ምን አለ? ሴኔቱ በመግቢያው ላይ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ወዳጅነት ዘመናትን የተሻገር መሆኑን አትቷል። ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት አገር መሆኑን አስታውሶ፤ በፌደራሉ መንግሥት እና በህወሓት መካከል ግጭቱ እንዴት እንደተጀመረ ያስረዳል። ከግጭቱ መከሰት በኋላ የፌደራሉ መንግሥት የውጭ አካላት የተደራደሩን ጥያቄ አልቀበለውም ማለቱን አስታውሶ ግጭት ተከትሎ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸውን፣ ብዙ መልክ ያላቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በበርካታ አካላት ሪፖርት ስለመደረጋቸው በዝርዝር አትቷል። የሴኔቱ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይላል? ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ሐሳብ ላይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 10 ነጥቦችን ዝርዝሯል። በመጀሪያ ሴኔቱ በትግራይ ክልል ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል። በንሑሃን ዜጎች ላይ የሚደርስ ጥቃት በጽኑ ይወገዛል ብሏል። በሴኔቱ የውሳኔ ሃሳብ ላይ የቀረበው ሦስተኛው ሃሳብ ደግሞ፤ የኤርትራ ጦር በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ እንዲያስወጣ ይጠይቃል። ጨምሮም በትግራይም ሆነ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል በኤርትራ ሠራዊትም ሆነ በየትኛውም አካል የተፈጸሙ ማናቸውም አይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች፣ የመድፈር ወንጀሎች በጽኑ ይወገዛሉ ብሏል። ሴኔቱ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የፖለቲካ ውጥረቱ ወደ ወታደራዊ ግጭት መግባቱን ተቀባይነት የለውም ብሏል። በመላው ትግራይ የኤሌክትሪክ፣ የባንክ፣ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በአፋጣኝ እና ሙሉ በሙሉ መመለስ አለባቸው ብሏል። ሴኔቱ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ይጠበቅበታል ያለውን ሦስት ነጥቦች ዘርዝሯል። እነዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አንቶኒ ብሊንክ እና ለዓለም የምግብ ፕሮግራም ቃል በገባው መሠረት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማሻሻል ተጨባጭ እርምጃዎችን ይውሰድ ብሏል። የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙትን ተጠያቂ ማድረግ ይኖርበታልም ብሏል። በቁጥጥር ሥር የሚውሉ የህወሓት አባላትን በተመለከተም የኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፍ ሕጎች መከበር አለባቸው ብሏል ሴኔቱ። የኤርትራ ጦር በአስቸኳይ እና ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ እንዲወጣት የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲጠይቅ ሴኔቱ ጠይቋል። በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ደጋፊዎች፣ ማኅበራዊ አንቂዎች እንዲሁም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ተጠቅምው የታሰሩ ጋዜጠኞች በብሔራቸው፣ በሚያራምዱት ርዕዮተ ዓለም እና የፖለቲካ ወገንተኝነታቸው ሳይለዩ ከእስር ይለቀቁ ጠይቋል። በመላው አገሪቱ ተዓማኒነት ያለው እና ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ ብሔራዊ ውይይት እንዲካሄድም ጠይቋል። ሴኔቱ በተጨማሪም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ ግጭት እንዲያቆሙ፣ ያሉ ልዩነቶችን ለመፍታት የፖለቲካ መፍትሄ እንዲሰጥ፣ በዓለም አቀፍ ሕግጋቶች እንዲገዙ፣ በንሑሃን ዜጎች...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
a33bccbef110e2669b01767aed393f50
3067a1c7ecf435231540cdaf94d85b3e
የቀድሞ የማሌዢያ ቀዳማዊት እመቤት 17 ክሶች ተመሰረቱባቸው
 ባለቤታቸው ጠ/ሚ ናጂብ ራዛቅ የተመሰረቱባቸው ክሶች 25 ደርሰዋል    በስልጣን ዘመናቸው ፈጽመዋቸዋል በተባሉ የገንዘብ ማጭበርበርና በስልጣን የመባለግ ወንጀሎች 25 ክሶች የተመሰረቱባቸው የቀድሞው የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ራዛቅ ባለቤት ቀዳማዊት እመቤት ሮሳማህ ማንሶር፣ 17 የታክስና ገንዘብ ማጭበርበር ክሶች ተመስርቶባቸዋል፡፡የቅንጦት ኑሮን በመውደድና በሚሊዮን ዶላሮችን እያወጡ በውድ ጌጣጌጥ በማሸብረቅ የሚታወቁት የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሮሳማህ ማንሶር፣ ረቡዕ በአገሪቱ የጸረ ሙስና ተቋም ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ከትናንት በስቲያ በኳላላምፑር ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡የ66 አመቷ ሮሳማህ ማንሶር ፍርድ ቤት ቀርበው በሰጡት ምላሽ፣የተከሰሱባቸውን ሁሉንም የወንጀል ድርጊቶች አለመፈጸማቸውን ገልጸው፣ ክሶቹን መቃወማቸውንና የዋስ መብታቸው እንዲከበርላቸው መጠየቃቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ ፍርድ ቤቱም በግማሽ ሚሊዮን ዶላር  ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ መፍቀዱን አመልክቷል፡፡በብዙ ሚሊዮን ዶላሮች የሙስና ቅሌት 21 የወንጀል ክሶች ተመስርቶባቸው የነበሩት የቀድሞው የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ራዛቅ፤ ባለፈው ሳምንት 556 ሚሊዮን ዶላር የህዝብ ገንዘብ ያለ አግባብ ወደ ግል ካዝናቸው ከማስገባታቸውና በስልጣን ከመባለጋቸው ጋር በተያያዘ፣ አራት አዳዲስ ክሶች እንደተመሰረቱባቸው  ተዘግቧል፡፡  
ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=22496:%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%B5%E1%88%9E-%E1%8B%A8%E1%88%9B%E1%88%8C%E1%8B%A2%E1%8B%AB-%E1%89%80%E1%8B%B3%E1%88%9B%E1%8B%8A%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%88%98%E1%89%A4%E1%89%B5-17-%E1%8A%AD%E1%88%B6%E1%89%BD-%E1%89%B0%E1%88%98%E1%88%B0%E1%88%A8%E1%89%B1%E1%89%A3%E1%89%B8%E1%8B%8D&Itemid=212
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
8f9e7b7b706fcfadfc0c207312c3b401
bc0a72743cc69c1af967aded83939481
ባሕር ዳር ግንቦት ሃያ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ
የባሕር-ዳር ግንቦት ሃያ ዓለም አቀፍ ጥያራ ጣቢያ ከባህር ዳር ከተማ በስተ ምዕራብ ስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት፣ በ፩ሺ፰መቶ፳፩ ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ የአየር ጣቢያ ነው። ጥያራ ጣቢያው አንድ አስፋልት የለበሰ የሦስት ሺ ሜትር ርዝመት በአርባ አምስት ሜትር ስፋት ያለው የኮንክሪት ማኮብኮቢያ ያለው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ እንደ ቦይንግ 757 የመሳሰሉ ሦስት የጭነትና አራት ቦምባርዲዬር የመንገደኛ ጥያራዎችን ለማቆም የሚያስችል ሥፍራ አለው። ጥያራ ጣቢያው ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉት እንደ ጉምሩክ፣ ኢሚግሬሽን፣ የደህንነት ተቋማትና ኳራንቲን የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶችን ያሟላ ነው። የባሕር-ዳር ግንቦት ሃያ ዓለም አቀፍ ጥያራ ጣቢያ በሳምንት በአማካይ ሃያ አንድ በረራዎችን በማስተናገድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአካባቢው እያደገ ለመጣው የአበባ፣ ፍራፍሬና አትክልት ምርቶች ማቆያ የሚሆንና 150 ቶን የማከማቸት አቅም ያለው የቀዝቃዛ መጋዘንም ከ50 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ገንብቶ አጠናቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሕር-ዳርን እና መቀሌን ከካርቱም ጋር ለማገናኘት የተጀመረው አዲሱ ዓለም አቀፍ በረራ የሁለቱን አገራት የንግድ፣ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ ለማሸጋገር የላቀ ሚና እንደሚኖረው ሲገመት፤ የበረራ መስመሩ በሳምንት ለሦሰት ቀናት የሚከናወን ሲሆን ሰሜን ሱዳንን ከሰሜን የአገራችን ክፍል በቀጥታ የሚያገናኝ ነው። ምንጮች http://www.ethiopianairports.com/BahirDarAirPort.aspx ባሕር ዳር የኢትዮጵያ አየር ማረፊያዎች
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
d71dcb31d1ca5f8f779953afeed000d3
adf53fd57a79d2285842f6a176c87b1e
ዓለማችን በ2017 በግጭቶች ሳቢያ 14.8 ትሪሊዮን ዶላር አጥታለች
 በጦር ሜዳ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ10 ዓመታት በ246 በመቶ ጨምሯል የዓለማችን ሰላም ባለፉት አስር ዓመታት እያሽቆለቆለ መምጣቱንና ባለፈው የፈረንጆች አመት 2017 ብቻ የአለማችን አገራት በግጭቶች ሳቢያ በድምሩ 14.8 ትሪሊዮን ዶላር ማጣታቸውን አይኢፒ የተባለው የጥናት ተቋም አመለከተ፡፡ኢንስቲቲዩት ፎር ኢኮኖሚክስ ኤንድ ፒስ የተባለው የጥናት ተቋም፣ ባለፈው ረቡዕ ለ12ኛ ጊዜ ይፋ ያደረገው አለማቀፍ የሰላም ሁኔታ አመላካች ሪፖርት እንደሚለው፤ በአለማችን በጦር ሜዳዎች ላይ ለህልፈተ ህይወት የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር ባለፉት አስር አመታት በ246 በመቶ ያደገ ሲሆን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአንጻሩ በ203 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ባለፈው የፈረንጆች አመት 2017 በአለማችን 92 አገራት፣ የሰላም ሁኔታ ላይ ማሽቆልቆል የታየ ሲሆን ሶርያ፣ አፍጋኒስታንና ደቡብ ሱዳን በከፍተኛ ሁኔታ ሰላም የራቃቸው አገራት ናቸው ተብሏል፡፡በአመቱ የ71 የአለማችን አገራት ሰላም መሻሻል ታይቶበታል ያለው የተቋሙ ሪፖርት፤ በ2017 የፈረንጆች አመት 104 የአለማችን አገራት፣ የመከላከያ ወጪያቸውን ከኢኮኖሚ ወጪዎች ያነሰ ማድረጋቸውንና 115 አገራት ደግሞ ወታደራዊ የሰው ሃይላቸውን መቀነሳቸው  በመልካም ተሞክሮነት ጠቅሶታል፡፡በአለማችን በአመቱ ከፍተኛውን ሰላም ያስተናገዱት የአለማችን አገራት፤ አይስላንድ፣ ኦስትሪያና ፖርቹጋል መሆናቸውን የጠቆመው ተቋሙ፤ በአፍሪካ ሰላማቸውን በጥሩ ሁኔታ ያሻሻሉ አገራት፤ ጋምቢያ፣ ላይቤሪያና ብሩንዲ መሆናቸውንም አክሎ ገልጧል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=21943:%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9B%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%89%A02017-%E1%89%A0%E1%8C%8D%E1%8C%AD%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%88%B3%E1%89%A2%E1%8B%AB-148-%E1%89%B5%E1%88%AA%E1%88%8A%E1%8B%AE%E1%8A%95-%E1%8B%B6%E1%88%8B%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%8C%A5%E1%89%B3%E1%88%88%E1%89%BD&Itemid=212
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
5fe6fb1b16ebb213fffa9ffb434754e3
71ae6a3bf08411890767101849fdbfbd
ኢትዮጵያ ከ 2 ወራት በኋላ የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) ጉባዔንም ታስተናግዳለች
የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) እ.ኤ.አ. በ 2022 ሌሴቶ እንድታስተናግድ ተወስኖ የነበረውን አራተኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ውድድር ከሀገሪቱ ነጥቆ ወደ ኢትዮጵያ አዛውሯል፡፡ ሌሴቶ ለውድድሩ በቂ ዝግጅት እያደረገች ባለመሆኑ ውድድሩ ከማሴሩ ወደ አዲስ አበባ መዛወሩን ማህበሩ ስለማሳወቁ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ብሔራዊ ዝግጅት አባል አራያት ራያ ለአል ዐይን እንዳረጋገጡት ኢትዮጵያ ውድድሩን እንድታስተናግድ የተመረጠች ሲሆን ከአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ጋር በወጪ መጋራት እና መሰል ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ “የ 2022 የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች ለኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ ተሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ ለማስተናገድ ቁርጠኛ ነው” ሲል አኖካ በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡ ውድድሩን እንድታስተናግድ በ2018 ዕድሉ ተሰጥቷት የነበረችው ሌሴቶ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ላለፉት 2 ዓመታት ምንም ዝግጅት ሳታደርግ ስለመቆየቷ ነው ማኅበሩ የገለጸው፡፡ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚካሔደውን 4ኛውን የወጣቶች ውድድር የተነጠቀችው ሌሴቶ በምትኩ በቂ ዝግጅት በማድረግ ከአራት ዓመታት በኋላ በ2026 የሚካሔደውን 5ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች እንድታስተናግድ ተወስኗል፡፡ የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎች የመላው አፍሪካ ጨዋታዎችን በመተካት በየአራት ዓመቱ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች የሚካሔድ ውድድር ሲሆን ከዚህ ቀደም የተካሔዱትን 3 ውድድሮች ሞሮካ ፣ ቦትስዋና እና አልጄሪያ በቅደም ተከተል አስተናግደዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከሁለት ወራት በኋላ በአውሮፓውያኑ ታህሳስ 6 የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ጉባዔን እንደምታስተናግድም ከአል ዐይን ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ብሔራዊ ዝግጅት አባል አራያት ራያ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡
ስፖርት
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-replaces-losotho-to-host-4th-african-youth-games
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
b6d668d1e64402b75ff394700646e17a
beb9ad6f9e4ab182d87f5fad0feeef67
ወላይታ ድቻ የቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮን ሆነ
በተለያዩ ከተሞች ሲካሄድ የቆየው የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቮሊቦል የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ቻምፒዮን ሆኖ አጠናቋል። ወላይታ ድቻ በአጠቃላይ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮች 35 ነጥብ በመሰብሰብ ቻምፒዮን እንደሆነ የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ያደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡ ወላይታ ድቻን ተከትሎ የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 34 ነጥብ በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ሰላሳ ነጥቦችን መሰብሰብ የቻለው ሙገር ሲሚንቶ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል፡፡ ፕሪሚየር ሊጉ መጠናቀቁን ተከትሎ በተለያዩ ዘርፎች በውድድር ዓመቱ ኮከብ የሆኑ ቡድኖችና ተጫዋቾች እንዲሁም አሰልጣኞች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በዚህም መሰረት የዓመቱ ኮከብ አሰልጣኝ በመሆን ተፈራ በላቸው ከመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተሸላሚ ሲሆኑ፣ የዓመቱ ምስጉን ዳኛ ተስፋዬ ስለሺ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ የዓመቱ ኮከብ ቡድን መሪ አየለ ድራሞ ከ ወላይታ ድቻ፣ የዓመቱ ኮከብ ሴተራ አሸናፊ ደምሴ ከ ወላይታ ድቻ፣ የዓመቱ ኮከብ ሊብሮ ኃ/ሚካኤል ተስፋዮሐንስ ከ ወላይታ ድቻ፣ የዓመቱ ኮከብ ስፓይከር እስጢፋኖስ ዳልጋ ከመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣ የዓመቱ ኮከብ ሁለገብ ተጫዋች ሰለሞን ፍቃዱ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ መዳ ወለቡ ዩኒቨርሲቲ፣ የዓመቱ የልዩ ዋንጫ ተሸላሚ ሐበሻ ሲሚንቶ በመሆን ፕሪሚየር ሊጉ ተጠናቋል፡፡አዲስ ዘመን ሰኔ 13/2011ቦጋለ አበበ
ስፖርት
https://www.press.et/Ama/?p=12842
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1ca14bd9543dbc3111c1a70a018c8283
acc6cdb8941c46fc5613ee597dfba244
የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር
የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር (ሞታክ) በኢትዮጵያ መንግስት ስር ያለ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ነው። ዋና ፅሕፈት ቤቱ አዲስ አበባ ይገኛል። የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር ከ2003 ጀምሮ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሆኖ የተዋቀረ ሲሆን የመገናኛው ዘርፍ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስም ተዋቅሯል። የውጭ ንባብ (አማርኛ)የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር (Archive) የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር (Archive) የመገናኛ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት ሚኒስቴሮች የትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መገናኛ ሚኒስቴሮች
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
41dcd42270766b96c4676e2a7f02dfa6
d01dd6a1286d2090ee008a1770f60657
ኤፕሪል
ኤፕሪል (እንግሊዝኛ: April) በጎርጎርያን ካሌንዳር ውስጥ አራተኛው ወር ነው። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ይህ ወር የመጋቢት መጨረቫና የሚያዝያ መጀመርያ ነው። የጎርጎርያን ወሮች
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
833492159354c4f7e62be6062bf79106
aa4fab607011eb4637656065e4c45b48
የኢንዱስትሪ ግብርና እና የተፈጥሮ ሃብት ውጤቶች አውደ ርዕይ በጅግጅጋ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የኢንዱስትሪ ግብርና እና የተፈጥሮ ሃብት ውጤቶች አውደ ርዕይ ተከፈተ፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8a%95%e1%8b%b1%e1%88%b5%e1%89%b5%e1%88%aa-%e1%8c%8d%e1%89%a5%e1%88%ad%e1%8a%93-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8d%88%e1%8c%a5%e1%88%ae-%e1%88%83%e1%89%a5%e1%89%b5/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
130272319f29bdb52fe225de6707d4c8
0ca4b509dc2b3b5f6ad842ad7f030782
በአቶ ይልቃል የሚመራው የሰማያዊ ፓርቲ ቡድን ኢሕአዴግ ከጠራው የፓርቲዎች ውይይት እንዲወጣ ተደረገ
ኢሕአዴግ ለቅድመ ውይይት ከጠራቸው 22 ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል በአቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) የሚመራው የሰማያዊ ፓርቲ ቡድን የተገኘ ቢሆንም፣ በውይይቱ ላይ መሳተፍ የቻለው እስከ ሻይ ዕረፍት ድረስ ብቻ መሆኑን አስታወቀ፡፡ከመስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ወዲህ የሰማያዊ ፓርቲ ትክክለኛ መሪ ማን እንደሆነ በትክክል ማወቅ አልተቻለም፡፡ ማለትም የተወሰኑ አባላት የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ መሆናቸውን ሲገልጹ፣ ሌሎች ደግሞ አቶ ይልቃል ጌትነት መሆናቸውን እየገለጹ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ግን ለቅድመ ውይይት ባለቀ ሰዓትም ቢሆን እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበላቸው ለእነ አቶ ይልቃል መሆኑን፣ በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ እስከ ሻይ እረፍት ድረስ መሳተፋቸውን የገለጹት የፓርቲው ምክር ቤት አባላት አቶ ስለሺ ፈይሳና አቶ ይድነቃቸው አዲስ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ እነሱን ጨምሮ በውይይቱ ላይ 22 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተገኝተዋል፡፡ነገር ግን ለሻይ እረፍት ወጥተው ሲመለሱ፣ እነ አቶ ስለሺ በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ መጠራታቸውን፣ አቶ ሽፈራው ጠርተዋቸው ሕጋዊ የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ማን እንደሆነ ሲጠይቋቸው፣ እነሱ የሚያውቁትና በምርጫ ቦርድም የሚታወቁት አቶ ይልቃል ጌትነት መሆናቸውን እንደገለጹላቸው ተወካዮቹ መግለጻቸውን አስረድተዋል፡፡ ነገር ግን ሰማያዊ ፓርቲ በመደበኛ ጉባዔ የተመረጠ መሪ እንዳለው አቤቱታ ቀርቦላቸው፣ ከምርጫ ቦርድ ሲያረጋግጡ ትክክል መሆኑን ስለተረዱ ከሻይ ዕረፍት በኋላ መሳተፍ እንደማይችሉ ተገልጾላቸው መመለሳቸውን አስረድተዋል፡፡በዚህም የሚመለከተው አካል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እያለ ኢሕአዴግ የሚፈልገውንና የሚስማማውን የፓርቲ መሪ እሱ የሚወስን መሆኑንና ይኼ ደግሞ በእነሱ የተጀመረ ባለመሆኑ ብዙም እንዳልገረማቸው ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ድርጊቱ እንደ አገር ተገቢ አለመሆኑንና ሕግ ሊከበር እንደሚገባም አክለዋል፡፡በሌላ በኩል በውይይቱ ላይ መሳተፋቸውን የገለጹትና ስለሰማያዊ ፓርቲ ማብራሪያና አቋማቸውን መግለጻቸውን የተናገሩት ሌላው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አገርና ሕዝብን የማረጋጋት ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጠው ጥሪ ማቅረባቸውን ለሪፖርተር ተልጸዋል፡፡ በአቶ የሺዋስና በአቶ ይልቃል መካከል ያለውን ‹‹እኔ ነኝ ሊቀመንበር›› ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ምርጫ ቦርድ እያጠናው መሆኑን ገልጿል፡፡ኢሕአዴግ ጥር 10 ቀን 2009 ዓ.ም. በጠራው ቅድመ ውይይት ላይ የተገኙት 22 ፓርቲዎች፣ የየራሳቸውን ምክረ ሐሳብ (ፕሮፖዛል) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማስገባት መስማማታቸው ታውቋል፡፡ አራት የተስማሙባቸው ነጥቦችም ቀጥሎ የሚደረጉ ውይይቶችና ክርክሮች በማን እንደሚመሩ፣ በውይይቱ ላይ እነማን በታዛቢነት እንደሚሳተፉ፣ ውይይቱ ምን ዓይነት የአካሄድ፣ የአጀንዳና የንግግር ሥርዓት እንደሚኖረውና ከውይይትና ከድርድር በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫዎች እንዴት እንደሚሰጡ የሚገልጹ መሆኑም ታውቋል፡፡      
ፖለቲካ
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%89%B6-%E1%8B%AD%E1%88%8D%E1%89%83%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%98%E1%88%AB%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%8B%AB%E1%8B%8A-%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%89%B2-%E1%89%A1%E1%8B%B5%E1%8A%95-%E1%8A%A2%E1%88%95%E1%8A%A0%E1%8B%B4%E1%8C%8D-%E1%8A%A8%E1%8C%A0%E1%88%AB%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%89%B2%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%8B%8D%E1%8B%AD%E1%8B%AD%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%8B%88%E1%8C%A3-%E1%89%B0%E1%8B%B0%E1%88%A8%E1%8C%88
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification