query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
2
182
passage
stringlengths
137
1.88k
label
int64
0
1
82d7bac7f114103b3f9b4dd4c4a82122
880d4ae4dbffb667b8e6cec56cf3b085
ደቡብ ሱዳን በሌሎች ሃገራት የሚገኙ 39 ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ደቡብ ሱዳን በየትኛውም መንገድ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ተግባር መፈፀም እንደማትችል በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒፒያ ሞርጋን ገለፁ።አምባሳደር ጀምስ ፒፒያ ሞርጋን ደቡብ ሱዳን ከሰሞኑ ለግብጽ የጦር ሰፈር እንድትገነባ ፈቃድ ሰጥታለች በሚል የሚናፈሰው መረጃ ዙሪያ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።አምባሳደሩ በመግለጫቸውም ከሰሞኑ ደቡብ ሱዳን ለግብፅ በፓካግ የጦር ሰፈር እንድትገነባ መሬት ሰጥታለች የተባለው ፍፁም ሀሰት እንደሆነ ገልፀዋል።መረጃውን የሚያሰራጩ ቡድኖች የሁለቱን ሀገራት ትብብር የማጠልሸት ፍላጎት ያላቸው ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።ደቡብ ሱዳን ችግር ለይ በወደቀችበት ጊዜ ሁሉ ኢትዮጵያ ከጎና አለች ያሉት አምባሳደሩ፥ ይህንን ውለታ ደቡብ ሱዳናውያን መቼም አይዘነጉትም ብለዋል።ኢትዮጵያ ችግሮችን በውይይት እንደምትፈታ እምነት አንዳላቸውም አምባሳደር ጀምስ ፒፒያ ሞርጋን ገልፀዋል።በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ግን ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትሰለፍ አረጋግጠዋል።ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያሰበ ሀይል በደቡብ ሱዳን በኩል ሊመጣ ቢያስብ እንኳ ቀድሞ የሚጋፈጠው ደቡብ ሱዳናውያንን ነው ሲሉም ተናግረዋል።ደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያ በራሷ ግዛት የራሷን ተፈጥሯዊ ሀብት የመጠቀም መብቷን ሙሉ በሙሉ እንደምታከብምርም አምባሳደሩ ገልፀዋል።የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር መስሪያ ቤት በትናንት ባወጣው መግለጫ ጁባ ግብፅ በፓጋክ አካባቢ የጦር ሰፈር ትገነባ ዘንድ ይሁንታ ሰጥታለች በሚል እየተናፈሰ ያለው ወሬ ከእውነት የራቀ እና መሰረተ ቢስ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።በአላዛር ታደለ#FBCየዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
0
2579d0aaabf3899135c8d0816e0bcfa7
2fcdd04b755794338cb57ca1c347ed74
ዩ.ኤስ.ኤይድ በአፋር ክልል በጎርፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ650 ሺህ ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ)ኢትዮጵያ የጀመረችውን የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታን በገንዘብ እንደሚደግፍ አስታወቀ።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሲያን ጆንስን ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።በዚሁ ወቅትም የዩ.ኤስ.ኤይድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሲያን ጆንስን፥ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።በኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት፣ ግብርናን በቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ ታዳሽ ሃይልን ለማህበረሰቡ ለማዳረስ፣ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍም አስታውቀዋል።በተለይ የሴቶችን ጫና በሚያቃልሉ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታ ላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሲያን ጆንስ ተናግረዋል፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማ በከር ሴቶች ስራ እና ሃብት በመፍጠር በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የራሳቸውን ድርሻ እንዲጫወቱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።ለዚህ ስኬትም የዩ ኤስ ኤይድ ድጋፍ አስተዋፅኦው የጎላ መሆኑን ማብራራታቸውንም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
0
e4f1b8048be359bf315a5a21dfbe54aa
d98591e23368b08535cc4de228678ccd
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሾኽሪያ እና ከደህንነት ዳይሬክተሩ አባስ ከማል ጋር ተገናኝተው ተወያዩ፡፡ውይይቱን ያካሄዱት አዲስ አበባ ሲሆን፥ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ስብሰባ ጎንለጎን ነው ተብሏል፡፡ዶክተር አብይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክሩ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት አብድልፈታህ ኤልሲሲ ለዶክተር አብይ አህመድ ግብጽን እንዲጎበኙ ግብዣ እንዳቀረቡላቸውም አስታውቀዋል፡፡ (ኤፍቢሲ)
0
4376e213afd4f5de51963aa38102acaf
3bdc007b8914bea070e30251c39fb1e4
በአፍሪካ ከሣሃራ በታች በሚገኙ ሃገሮች እየተስፋፋ የመጣውን ፀረ ሰብል ተምች ለመዋጋት
በአማራ ክልል በ161 ወረዳዎች የወባ በሽታ መከስቱ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እንዳይፈጥር ተሰግቷል። ክልሉ እንዳስታወቀው ከበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ሀምሌ ወር እስካሁን ድረስ 400ሺህ ሰው በወባ በሽታ ተጠቅቷል።በተለይ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የክረምቱን መግባት ተከትሎ ወረርሽኙ እየተስፋፋ እንደሚገኝም ተመልክቷል።
0
ff936d4a14abd552fb410cd0bf48510c
ff936d4a14abd552fb410cd0bf48510c
በፓሪስ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ ተገድሏል
ዛሬ ፓሪስ ውስጥ፥ ጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን በቻርሊ ሄብዶ (Charlie Hebdo) መጽሔት ማደራጃ ቢሮ ላይ ያደረሰው ጥቃት የመጀመሪያ ዓመት በሚታሰብበት እለት፥ አንድ በፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ ተገድሏል።አንድ የፈረንሳይ ሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ባለሥልጣን ስለዚሁ ሲናገሩ፥ ስለት የያዘው ግለሰብ፥ ወደ ፖሊስ ጣቢያው በቀረበበት ወቅት ፈንጅ የታጠቀ ይመስል ነበር ብለዋል።ግለሰቡ በፖሊስ ተተኩሶበት ከመሞቱ በፊት፥ “አላሁ አክበር” ወይም “እግዚአብሔር ታላቅ ነው” እያለ ሳይጮህ አልቀረም ሲሉም የሃገር አስተዳደር ሚኒስቴሩ ባለሥልጣን አስረድተዋል።ድንገቱ እየተጣራ መሆኑም ተዘግቧል።በሌላ ዜና፥ የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ፍራንሷ ሆላንድ (Francois Hollande) የሄብዶ (Hebdo) ቢሮ በተጠቃበት ወቅት፥ የዜጎችን ሕይወት ሲከላከሉ የሞቱት ሦስት ፖሊሶች በታሰቡበት ሥነ-ሥርሣት ላይ፥ ለታጣቂ የፖሊስ መኮንኖች አዲስ የፀጥታ ጥበቃ መመሪያ አስተዋውቀዋል።ፖሊሶች ከሥራ ውጪም ትጥቃቸውን መያዝ ይችላሉ፥ 5 ሺህ ተጨማሪ ፖሊሶችም ይመደባሉ ብለዋል።ባሁኑ ወቅት በየትምህርት ቤቱ ደጃፍ፥ በአውሮፕላን ማረፊያዎችና በሌሎች ሕዝብ በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች፥ የሽብር ጥቃቶችን ለመከላከል የተመደቡትን የፀጥታ ጠባቂዎች አመስግነዋል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።
1
e1abc866a1a9119fbba3c70058b756be
9fb3d5715036465716de22388095592c
የመንግሥት ሹማምንትን ጨምሮ ከ130 በላይ የሙስና ተጠርጣሪዎች ታሰሩ
50 ሺህ ሰዎች በመፈንቅለ መንግስቱ ተጠርጥረው ፓስፖርታቸውን ተነጥቀዋል በቅርቡ ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ በዜጎቹ ላይ መረር ያለ እርምጃ መውሰዱን የቀጠለው የቱርክ መንግስት፣ያሰራቸው ሰዎች ቁጥር ከ26 ሺህ በላይ መድረሱን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘገበ፡፡የአገሪቱን የፍትህ ሚኒስትር በኪር ቦዝዳግን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፤ ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራው ጋር በተያያዘ 16 ሺህ ሰዎች በመደበኛ ሁኔታ ታስረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ሲሆን ሌሎች 6 ሺህ ታሳሪዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በሂደት ላይ ይገኛሉ፤8 ሺህ ያህል ታሳሪዎች ደግሞ ከእስር ቢፈቱም ምርመራ እየተደረገባቸው ነው፡፡ ሚኒስትሩ የቀሪዎቹን 4 ሺህ ያህል እስረኞች ጉዳይ በተመለከተ ያሉት ነገር እንደሌለ የጠቆመው ዘገባው፤ከመፈንቅለ መንግስቱ ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው ከታሰሩት 26 ሺህ ያህል ሰዎች መካከል ወታደሮች፣ ፖሊሶች፣ የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች ግለሰቦች እንደሚገኙበትና በሺዎች የሚቆጠሩትም ከስራቸው መባረራቸውን አመልክቷል፡፡ የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን መንግስት ከመፈንቅለ መንግስቱ ጋር በተያያዘ እየወሰደ ባለው እጅግ ከረር ያለ እርምጃ፣ ከ50 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ፓስፖርቶች መሰረዛቸውን፣ ጋዜጠኞችና ምሁራን መታሰራቸውን፣ ከ130 በላይ መገናኛ ብዙኃን መዘጋታቸውንም ዘገባው ገልጧል፡፡በቅርቡ በአገሪቱ መንግስት ላይ በተቃጣው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ፣ ከ246 በላይ ሰዎች ለሞት መዳረጋቸውንና ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑትም የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ዘገባው አስታውሷል፡፡
0
9dc7b0c2884605046e82109fed648657
9dc7b0c2884605046e82109fed648657
በዞን ዘጠኝ ተከሣሾች ላይ ዶሴ የአቃቤ ሕግ ምስክር ተሰማ
በነሶሊያና ሺመልስ የክስ መዝገብ በተከሰሱት ጋዜጠኛችና የኢንተርኔት አምደኞች ላይ አቃቤ ሕግ ከቆጠራቸው ምስክሮች ዛሬ ተሰሙ፡፡ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ተከሳሾቹ የአቶ ሌንጮ ለታን የፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ በኮምፕዩተሮቻቸው ውስጥ እንደተገኙ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ሌሎች ደግሞ ተከሣሾቹ ቢሮም ሆነ መኖሪያ ቤት ከገበያ ላይ የሚገዙ መፅሔቶችና ጋዜጦችን እንደተመለከቱ ለፍርድ ቤት ገልፀዋል፡፡ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን የችሎት ዘገባ ያዳምጡ፡፡
1
b1424d25a5227a594042e0ff2201ed2d
b1424d25a5227a594042e0ff2201ed2d
ህዝቡ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መንግስት በጋራ ቆመን ጠላቶቻችን የምናሸንፍበት ጊዜ ላይ ነን – የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝቡ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መንግስት በጋራ ቆመን ጠላቶቻችን የምናሸንፍበት ጊዜ ላይ ነን አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር::የአማራ ምሁራን መማክርት ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡በጉባኤው ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የአማራ ህዝብ ጠላቶች ስንጥቅ እየፈለጉ በጋራ እንዳንቆም እየሰሩብን ነው ብለዋል፡፡ጠላቶቻችን በጎጥና በመንደር እየከፋፈሉ መከራችንን ለማብዛት ይፈልጋሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ ህዝቡ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና መንግስት በጋራ ቁመን ጠላቶቻችን የምናሸንፍበት ጊዜ ላይ ነንም ብለዋል፡፡በመካከላችን ያለው የፖለቲካ አመላካከትና ርዕዮት አለም ሳይገድበን በህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎችና በጋራ እየተፈተንባቸው ባሉ አጀንዳዎች ላይ መግባባት አለብን ጊዜውም አሁን ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡“ላንጨርስ አልጀመርንም የጀመርነውን በድል እንጨርሳለን” ምሁራን ከዳር ተመልካችነት ወጥተውና ከአስፈጻሚው አካል ጋር መገፋፋቱን ትተው የህዝቡን ችግሮች ከነመፍትሄዎቻቸው በጥናት ሰንደው በማቅረብ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ርእሰ መስተዳደሩ አሳስበዋል፡፡የመማክርቱ ሰብሳቢ ገበያው ጥሩነህ (ዶ.ር) የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ለህዝብና ሀገር የሚጠበቅበትን ለመወጣት እየሰራ ያለ ተቋም ነው ብለዋል፡፡ለስራዎቹ ስኬታማነትም የመንግስት አስፈጻሚ አካላትና ምሁራን በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡መማክርቱ ለህዝቡ የሚበጁ ሀሳቦችን በማደራጀት ለተግባራዊነታቸው እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ አብመድ ዘግቧል፡፡
1
d87053cb6afc68780cd8525a4e464804
75b2596044991818c70985b0be18a3a2
የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላትና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት አረጋገጡ
የሕወሓት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ለአገር መከላከያ ሠራዊት እጃቸውን መስጠታቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡የመረጃ ማጣሪያው ማክሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ ወ/ሮ ኬሪያ ለመንግሥት እጃቸውን መስጠታቸውን አረጋግጧል፡፡በፌዴራል መንግሥት እጃቸውን እንዲሰጡ ለሁለት ጊዜ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠባቸው የሕወሓት አመራሮች አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ኬሪያ፣ እጃቸውን መስጠታቸው ከመረጋገጡ ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰጠም፡፡ወ/ሮ ኬሪያ ከወራት በፊት በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ምርጫ ባለመደረጉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሥራ ዘመን ለማራዘም፣ በሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ አማካይነት የቀረበውን ምክረ ሐሳብ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውይይት ሲጠራ፣ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በመሄድ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኞ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ተፈላጊዎቹ የሕወሓት አመራሮች ወደ አገረ ሰላም መሸሻቸውን ገልጸው፣ ቀንም ሆነ ሌሊት በመንግሥት ዕይታ ሥር መሆናቸውን አስታውቀው ነበር፡፡
0
02791bd4b7ad9a23ac8eda6d037da2fe
32a2576ca769b9d93955e8c9eb9261f6
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 164 ሺህ በላይ ደርሷል
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰወች ቁጥር ከ6 ሚሊየን መሻገሩ ተሰምቷል። በአለም በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ ተጽዕኖ ውስጥ ከገቡ አገራት ቀዳሚ ሆና ረዘም ላለ ጊዜ የቆየችው አሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰወች ቁጥር ከ6 ሚሊየን በላይ ሆኗል፡፡ይህም ማለት በአለም በአጠቃላይ በኮሮና ከተያዙ ሰወች ውስጥ ሩብ ያክሉ በአሜሪካ ይገኛሉ።በቻይና ውሃን ግዛት ከስምንት ወራት በፊት የተከሰተው ወረርሽኙ አሜሪካን ተጽዕኖ ውስጥ ከከተታት ሰነባብቷል።በትራምፕ አስተዳደር የቀረበው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መቀነስ ሃሳብ የህክምና ባለሙያወች እና በ33 የአሜሪካ ግዛቶች ተቃውሞ ገጥሞታል።ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ለኮሮና የሚመረመሩ ሰወች ቁጥር መቀነሱም ተነግሯል።ምንጭ፦ ሲጂቲኤን
0
aea78caedaa282b2135d1e4de41fc42e
5eded8b6bc7fe79c514461b18bace512
አራት ተጫዋቾች ድጋፍ አድርገዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ከተከፈተ አንድ ወር ቢያስቆጥርም ክለቦች እምብዛም በዝውውር ላይ እየተሳተፉ አይገኙም። ዓመቱን በ5ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው አዳማ ከተማ ከሌሎች ክለቦች በተሻለ ሁኔታ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያለ ክለብ ሲሆን አራት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል። ሳራ ነብሶ አዳማ ከተማ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች አንዷ ናት። የአጥቂ መስመር ተጫዋቿ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በጌዴኦ ዲላ 10 ጎሎችን አስቆጥራ ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ የቻለች ተጫዋች ናት። በመከላከያ ያለፉት አራት የውድድር ዓመታት የተመለከትናት አክበረት ገብረፃዲቅ ሌላዋ የአዳማ ከተማ ፈራሚ ስትሆን የሲዳማ ቡና አምበል የነበረችው ነፃነት ብርሀኑ እና የድሬዳዋ ከተማዋ ተከላካይ ትዕግስት ንጉሴ አዳማ ከተማን ተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው።ክለቡ በዝውውር መስኮቱ ተጨማሪ ተጫዋቾች ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የደደቢቶቹ አልፊያ ጃርሶ እና እፀገነት ብዙነህን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተነግሯል።
0
68a75eb54e4fde1213d43b717d07d629
f05c8f769bd3a218077e1aca3c0ae187
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሀገሪቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በኮሮና ቫይረስ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የ444 የስልክ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ ይፋ አደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የገንዘብና ቁሳቁስ አቅርቦት ማሰባሰቢያ ብሄራዊ የድጋፍ ሰብሳቢ ኮሚቴ አቋቁመዋል። በዚህ መሰረት ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎችን ማሳተፍ የሚያስችል የገቢ ማሰባቢያውን ይፋ ማድረጉን አስታውቋል። በመሆኑም ፡ ለ1 ብር A ለ5 ብር B ለ10 ብር C ለ25 ብር Dለ50 ብር E ለ100 ብር F ለ300 ብር G ለ500 ብር H ለ1000 ብር J ወደ 444 በመላክ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል አስታውቋል። ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!https://t.me/fanatelevision
0
761f2240c0afa1fd907d123f69a88bf3
761f2240c0afa1fd907d123f69a88bf3
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለግድቡ ግንባታ ድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፡- ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሮማን ገብረሥላሴ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በግድቡ ግንባታ በሚኖራቸው ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት ትናንት ሲካሄድ የሕዳሴው ግድብ የመላ ኢትዮጵያውያን የጋራ ፕሮጀክት በመሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባላቸው እውቀትና ገንዘብ አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው በግድቡ ግንባታ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያሉ ፖለቲካዊ ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው የዓባይን ጉዳይ የአገርና የልማት አጀንዳ አድርጎ መያዝና ሕዝባዊ ንቅናቄ መፍጠር እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ እንደርሳቸው ገለፃ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ኢትዮጵያ ግድቡን ለጋራ ተጠቃሚነት እየገነባች እንደሆነና የግድቡ ግንባታም ሌሎች አገራትን እንደማይጎዳ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የግድቡን ግንባታ በልዩ ልዩ መልኮች ሲደግፉ እንደነበር አስታውሰው፣ ወደፊትም ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡ በ2012 ዓ.ም እስካሁን ድረስ ለግድቡ ግንባታ 168 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማሰባሰብ እንደተቻለም ወይዘሮ ሮማን ጠቁመዋል፡፡ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ዶክተር አረጋዊ በርሔ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለግድቡ ግንባታ እስካሁን ያበረከቱት አስተዋፅዖ በሚፈለገው ልክ ነው ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ደጋፊዎቻቸውን በማንቀሳቀስ ለግድቡ ግንባታ ትልቅ አስተዋፅዖ ማበርከት እንሚችሉ ገልጸው፣ ከዚህ በኋላ ፓርቲዎቹ በተደራጀ መንገድ ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ግድቡን በተመለከተ የሚደረጉ ድርድሮች ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲካሄዱም አሳስበዋል፡፡ ግንባታው በ2003 ዓ.ም የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ግንባታው 70 ነጥብ አምስት በመቶ ደርሷል፡፡አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2012 አንተነህ ቸሬ
1
b770542a5c1276c5ec1f8d1e849884f5
8dec94bb15db7da62d6d1a49fcd015a0
ሀዋሳ ከተማ ከ ሱዳን ከ23 አመት ጋር ዛሬ ይጫወታል
አንጋፋው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ከአዳማ ከተማ ጋር በስምምነት በመለያየት በአንድ አመት ኮንትራት ኢትዮ ኤሌክትሪክን ተቀላቅሏል።በ2007 ክረምት ሀዋሳ ከተማን ለቆ ሁለት አመት ከግማሽ የውድድር ዘመን ያሳለፈበት አዳማ ከተማን የተቀላቀለው ታፈሰ ተስፋዬ በአዳማ የመጀመርያ አመት ቆይታው በ15 ጎሎች የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ቢያጠናቅቅም አምና እና ዘንድሮ በጉዳት ፣ እድሜ እና በቦታው ባለው ከፍተኛ ፉክክር ምክንያት እምብዛም የመሰለፍ እድል ማግኘት አለመቻሉን ተከትሎ ከቀናት በፊት ከክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየት ወደ አሳዳጊ ክለቡ ከረጅም አመት በኋላ የሚመልሰውን ዝውውር ፈፅሟል። በዛሬው እለት ከቡድኑ ጋር ልምምድ መስራቱም ታውቋል።5 ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ በማጠናቀቅ ብቸኛ የሆነው ታፈሰ ተስፋዬ በ1994 ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋናው ቡድን ያደገ ሲሆን በ1997 ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ እስከ 2002 ቆይቷል። ከየመን የአንድ አመት ቆይታ በኋላም በቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ አሳልፏል።
0
97457abe944c66aa8d0f9905e1372d00
917ebd683c405cb1a9414fada048e911
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፖሊስ ጣቢያ የተጠርጣሪ ማቆያዎችን ለማሻሻልና አዲስ ለመገንባት የሚያስችል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 1፤2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከሃገር የሸሹና በሃገር ውስጥ የተደበቁ በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ መዘጋጀቱን ገለፀ።ተቋሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሳወቀው በዋናነት በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ የሚያስችል የጥቆማ መቀበያ ስርአት እየዘረጋ ነው፡፡ይህ እየተዘረጋ ያለው የጥቆማ መቀበያ ሰርአት በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን በማጣራት ማስመለስ የሚያስችል ነው።ተቋሙ በአሁን ወቅት በኢሜይል እና በነጻ የስልክ ጥሪ ጥቆማ መቀበል የሚያስችለውን አሰራር መዘርጋቱን አሳውቋል፡፡ይህም በህገወጥ መንገድ በግለሰብ የተያዙ የህዝብ ሃብትን በሚሰጥ በወንጀል የተገኙ ሃበቶችን አጣርቶ ለማስመለስ ያሰችላል ተብሏል።በታሪክ አዱኛከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
3d5f597f2f49682679832a7ac15d482f
3d5f597f2f49682679832a7ac15d482f
የሀገሪቱ ሕዳሴ በትምክህተኞች እንዳይደናቀፍ በትኩረት ይሰራል -የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
የሀገሪቱ ሕዳሴ በጠባብና ትምክህተኛ አመለካከት እንዳይደናቀፍ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑንን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስገነዘቡ ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህርዳር ከተማ በተከበረው 2ኛው የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ቀን በዓል ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው እንዳስታወቁት፤ ባለፈው ሩብ ምዕተ ዓመት በህዝብና በመንግስት ትብብር በተከናወነው ጠንካራ ስራና በተመዘገበው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ ድህነትን በግማሽ መቀነስ ተችሏል ፡፡ኢትዮጵያ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግብ ካሳኩ ሀገራት መካከል መመደብ መቻሏንና በ2017 መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመሰለፍ ርብርብ እያደረገች መሆኗን ጠቅሰዋል ፡፡ይህ የዕድገት ግስጋሴ በጠባቦችና ትምክህተኞች እንዳይደናቀፍ መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል ፡፡በመልካም አስተዳደር፣ በጠባብነትና በትምክህት ችግር ምክንያት በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የታዩትን ችግሮችን በማስታመም እስካሁን መፍታት አለመቻል “አሳፋሪ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየአካባቢው እየተነሱ ያሉ ግጭቶች አመራሩ በጠባብና ትምክህተኛ አመለካከት ስር በመውደቁ የተፈጠረ ችግር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡በተለይም በጸገዴ መሬት አሳቦ የተፈጠረው ችግርም የትግራይና የአማራ ክልል መንግስታት አመራሮች ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው ለመፍታት በጋራ ባለመንቅሳቀሳቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡መንግስት በችግር የተፈተነ በሳል ልምድ ያለው በመሆኑ አደጋዎችን በመለየት ለመፍታት በትጋት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል ፡፡ከዚህ አንጻር በአሁኑ ወቅት ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ ችግሩን ለመፍታት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ፤በቅርቡም ችግሩ በዘላቂነት እልባት እንደሚያገኝ እምነታቸው ገልጸዋል፡፡የፖለቲካ ኢኮኖሚው እስኪዳብር ድረስ እንደዚህ አይነት ችግሮች የሚጠበቁ ቢሆንም የጠባነትና የትምክህተኝነት ችግር ከወዲሁ መቅረፍ ካልተቻለ ግን በሀገሪቱ ላይ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ነው ያስጠነቀቁት ፡፡"የኢትዮጵያ ህዳሴ በሀገር ልጆች" በሚል መሪ ሃሳብ በባህርዳር ከተማ በተከበረው 2ኛው የዲያስፖራ ቀን በዓል ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 2 ሺ 700 ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ሆነዋል።ሶስተኛው የዲያስፖራ ቀን በዓል በቀጣዩ ዓመት በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ ከተማ በሐዋሳ እንዲከበር መወሰኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ፡፡
1
bf0aef3d26281c1d71fc5d26cf059587
832b3fab0a0db1d1e17d95b506ca383f
ኬንያ የሳይበር በኢንተርኔት የሚፈፀሙ ወንጀሎችን የሚቆጣጠር ሕግ በሥራ ላይ አዋለች
ቅዳሜ ታኅሳስ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ከሰንሻይን ኮንስትራክሽን ሕንፃ ላይ የወደቀ ሠራተኛ መሞቱ የግንባታ ደኅንነት ጥያቄዎችን በድጋሚ ቀሰቀሰ፡፡ አደጋው የደረሰው መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገነባ ትልቅ ሕንፃ ላይ ሲሆን፣ ሃያት ዲጀንሲ ሆቴል ከሚገነባበት አጠገብ መሆኑን ሪፖርተር በሥፍራው ተገኝቶ ታዝቧል፡፡መለሰ አበራ የተባለ የ34 ዓመት ሠራተኛ በሕንፃው ላይ በሥራ ላይ በነበረበት ወቅት ወድቆ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ይህ በከተማይቱ ለግንባታ ደኅንነት የሚሰጠውን ትኩረት አናሳነት ያሳያል የሚሉ ተቃውሞዎች እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል፡፡ በቅርቡ ልጅ እንደተወለደ የተነገረው መለሰ ከሕንፃው እንደወደቀ ሕይወቱ አልፏል፡፡በኢትዮጵያ የግንባታ ደኅንነት ሕግ ወጥቶ ተግባራዊ የተደረገ ቢሆንም፣ በተለይ በአዲስ አበባ የዚህን ሕግ ድንጋጌዎች ባለመከተልና የመንግሥት ቁጥጥር አናሳ በመሆኑ ተደጋጋሚ አደጋዎች ይደርሳሉ፡፡
0
929ee033adbf6a5e85f6260a02824b54
5af75f2051a1189068494516fc4df2da
ኮሚሽኑ በአማራ ክልል የሙስና ወንጀል የፈጸሙ 211 ግለሰቦች መቀጣታቸውን አስታወቀ
በተለያየ የሙስና ወንጀል ተግባር ተጠርጥረው የታሰሩና ክስ ተመሥርቶባቸው የሚገኙ 152 ግለሰቦች፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የአቤቱታ ደብዳቤ ጻፉ፡፡ተከሳሾቹ በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዘርፍ በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር በኩል እንዲደርስላቸው፣ ሰባት ገጽ አቤቱታ መጻፋቸውን ሪፖርተር ከምንጮች አረጋግጧል፡፡ ነገር ግን የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አቤቱታውን በቀጥታ ለማድረስ ኃላፊነት ስለሌለው፣ በተከሳሾች ደብዳቤ ላይ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የፍትሕ ዳይሬክቶሬት መሆኑን በመጠቆም፣ ውሳኔ እንዲሰጥበት በዋና ሱፐር ኢንቴንደንት ጥላሁን አያሌው ፊርማ ሸኚ ደብዳቤ መላኩንም ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡በአቤቱታው የተካተቱት 152 ተከሳሾች አብዛኛዎቹ በ2009 ዓ.ም. በተለያዩ የሙስና ተግባራት ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ከፍተኛ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችና ሌሎችም ተከሳሾች ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ምንጮች ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ በአገሪቱ በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ተነስቶ በነበረው ተቃውሞና ግጭት ምክንያት የነበረውን የፖለቲካ አለመረጋጋት አቅጣጫ ለማስለወጥ፣ በእነሱ ላይ ተገቢ ያልሆነና ባልፈጸሙት ድርጊት ለእስርና ለክስ መዳረጋቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው ማሳወቃቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም የነበረውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትና እነሱም የፈጸሙት የሙስና የወንጀል ድርጊት እንደሌለ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ከእስር እንዲፈቱ መጠየቃቸው ታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አገሪቱ የጀመረችው የሰላም፣ የልማትና የዕድገት ጉዞ አጋር ለመሆን፣ ለአገራቸውና ለሕዝባቸው ባላቸው ዕውቀትና ችሎታ እንዲያገለግሉ እንዲታደጓቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩን መጠየቃቸውንም የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የተከሳሾቹ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መድረስ አለመድረሱን ሪፖርተር ለማረጋገጥ ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
0
8dca8168dc969fb980cde9319aa3f1dc
8dca8168dc969fb980cde9319aa3f1dc
ኤለን መስክ የምድራችን ቀዳሚ ሀብታሙ ሰው ሆነ
የቴስላ ኤሌክትሪክ መኪና እና የስፔስ ኤክስ የሕዋ ታክሲ ፈጣሪና ባለቤት ኤለን መስክ ባልተጠበቀ ፍጥነት የየዓለም ሀብታሙ ሰው ሆኗል።መስክ በድንገት 1ኛ የዓለም ሀብታም ሊሆን የቻለው የቴስላ የአክስዮን ዋጋ ማክሰኞ ዕለት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ሀብቱ ወደ 185 ቢሊዮን ዶላር በመመንደጉ ነው።ከፈረንጆቹ 2017 ዓ/ም ጀምሮ የዓለም ቢሊዮነሮች ዝርዝርን ከላይ ሆኖ ሲመራ የነበረው የአማዞኑ ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ነበር።የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ ቴስላ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአክስዮን መጠኑ በማይታመን ደረጃ እየጨመረ መጥቶ ትናንት ረቡዕ 700 ቢሊዯን ዶላር እንደደረሰ ቢቢሲ ዘግቧል።የኤለን መስክ ቴስላ የአክስዮን ፍላጎት ለመጨመሩ በርካታ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። ከነዚህ አንዱ መጪው ዘመን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ብዙ አገራት ፖሊሲያቸው ለኤሌክትሪክ መኪና የሚስማማ መሆኑ አይቀሬ እንደሆነ በመታመኑ ነው።
1
9d25086b74f7cc09c67f225c031cf6b6
6367b65d7dd85bcdf5dfced58a8a561f
የበረሃ አንበጣ መንጋውን ለመከላከል በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት እንዲደረግ አርሶ አደሮች ጠየቁ፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 27/2012 ዓ.ም (አብመድ) የበርሃ አንበጣ መንጋ መፈልፈያ ምቹ ናቸው ተብለው በሚገመቱ ቦታዎች ላይ በተካሄደ የአሰሳ ሥራ እንቁላል እየተፈለፈለ መገኘቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡ በተያዘው የመኸር ወቅት ከኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት በተጨማሪ የበረሃ አንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ለግብርናው ከፍተኛ ስጋት መሆኑን የቢሮው ኃላፊ መለስ መኮንን (ዶክተር) ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
0
b4aeaff3e9e826632985bd1fdf11f7f9
01046cd8c2ed64721b85bf17c418b747
በቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሴቶች ተሳትፎ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ፡፡
ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ እንዲራዘም በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰነዘሩ ጥያቄዎች ህዝብን የሚያደናግር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓቲዎችና ሲቪክ ማኅበራት ጋር በቀጣዩ ምርጫ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡የመንግሥት መገናና ብዙኃን ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ የሚል መሪ ሃሳብ ሰንቆ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተደርጓል ባሉት ውይይት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማኅበራት ተሳትፈዋል፡፡የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በይፋዊ ገጹ እንዳስታወቀው የውይይቱ ተሳታፊዎች ካነሷቸው ነጥቦች ውስጥ መሰረታዊ ነገሮች ሳይሟሉ ምርጫውን ለማካሄድ መጣደፍ ተገቢ አይደለም የሚለው ይገኝበታል፡፡
0
6f504bf65c8a67fbda9387c66bccd3ee
32c2fd3a219635a3a4933cb48c433b56
የአሜሪካ ምክር ቤት የትራምፕን በኢራን ላይ ጦር የማዝመት ስልጣን ገደበ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የተገባውን የኒኩሌር መርኃግብር ውል እንደማያድሱ አስታወቁ።ቴህራን በስምምነቱ መሠረት ልትፈፅም የሚገቧቸውን ግዴታዎቿን እየተወጣች ስለመሆኑ ትረምፕ ይንፈጉ እንጂ ውሉን ሙሉ በሙሉ አልሠረዙትም።በኢራን ላይ አዲስና የጠበቀ አካሄድ እንዲወሰድ ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ባደረጉት ንግግር አሳስበዋል።“ፍፃሜው የባሰ ሁከት መፍጠር፣ የባሰ ሽብርና የኢራን የኒኩሌር ጦር መሣሪያ ባለቤትነት የባሰ ሥጋት ወደሚሆንበት መጨረሻ እንደሚወስድ ቀድሞ መተንበይ የሚቻልበት ስምምነት እንዲቀጥል የሚያደርግ ማረጋገጫ ከእንግዲህ አልሰጥም” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።አዲሱ ስልት “የኢራንን መረጋጋት እንዳይኖር የሚያደርግ እንቅስቃሴና በአካባቢው የእጅ አዙር የሽብር ቡድኖችን የመደገፍ አካሄድ” ለመቀልበስ ከዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች ጋር መተባበርን የሚያካትት ነው ብለዋል ሚስተር ትረምፕ።በተጨማሪም ኢራን ለሽብር ፈጠራ ጉዳይ ትሰጠዋለች ያሉትን የገንዘብ ድጋፍ ለመቆጣጠር እና የመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢን ሥጋት ላይ የሚጥል የጦር መሣሪያዎች ግንባታዋን ለማስቆም ተጨማሪ ማዕቀቦችን መጣል እንደሚያስልግ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።ከኢራን የዛሬ ሁለት ዓመት ስምምነት ላይ የደረሱትና ውልም የፈረሙት አምስቱ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ አባላትና ጀርመን የነበሩ ሲሆን የዛሬው የፕሬዚዳንት ትረምፕ አቋም ለጊዜው ውሉን ሙሉ በሙሉ የሚሠርዝ ሳይሆን የተወካዮች ምክር ቤቱ ኢራን በውሉ መሠረት ተነስተውላት የነበሩ ማዕቀቦችን መልሶ እንዲጥል የስድሣ ቀናት ጊዜ የሚሰጥ ነው።
0
24833b29ac2bba91f06db67c2312f804
116c03def119c33a485708d9c9814e92
ሃያ ሰባት ዓመት በስደት
የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ባለፉት ሁለት ቀናት የመታው እጅግ የከበደ ዝናብ ያስከተለው የሃሩር አውራጃ ማዕበልና ውሽንፍር ለሰላሣ ሰው ሞት ምክንያት ሆኗል።ቅዳሜና ዕሁድ የጣለው “ሳይክሎን ሳጋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው የውቅያኖስ ማዕበል ኃይል በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢዎች ላይ እስከአሁን ከተመዘገቡት ሁሉ እጅግ የበረታው እንደሆነ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።በተለይ የሶማሊያን ዋና ከተማ ሞቃዲሾን የመታው ማዕበልና የወረደው ዶፍ ዝናብ ስድስት ሰው መግደሉን፤ ከሦስት መቶ በላይ ቤቶችን ማጥለቅለቁን የከተማዪቱ ከንቲባ አብዲራህማን ኦስማን ለቪኦኤ ገልፀዋል።በስተሰሜን ባለችው ተገንጣይዋ ሶማሊላንድ አውዳል፤ ሳህልና ሳላል አካባቢዎች ላይ ደግሞ ቢያንስ ሃያ አምስት ሰው መሞቱን ባለሥልጣናቷ የተናገሩ ሲሆን ከሰለባዎቹ አብዛኞቹ የሞቱት በደራሽ ጎርፍ ተወስደው መሆኑን የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች አመልክተዋል።ሌሎች ሃያ ሰባት ሰዎች የደረሱበት እስከአሁን እንደማይታወቅና 12 ሰዎች መጎዳታቸውን የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ፅሕፈት ቤት አስታውቋል።በከባዱ ዝናብ ወደ ስድስት መቶ ሰባ ሺህ የሚደርስ ሰው መጎዳቱን፣ እጅግ የሰፉ ማሳዎች ላይ ያለ ሰብል መውደሙንና ከሶማሊላንድ የእንሥሳት ሃብት ሰማንያ ከመቶ ያህል መውደሙንም የፕሬዚዳንቱ ፅሕፈት ቤት መግለጫ አስታውቆ ለግዛቲቱ ዓለምአቀፍ እርዳታ እንዲደርስ ተማፅኗል።ጂቡቲ ውስጥ ሁለት ሰዎች በከባድ ዝናብ ምክንያት መሞታቸውን፣ ሃያ ሺህ ሰው በዶፍና በጎርፉ መጎዳቱን፣ ሶማሊላንድ ውስጥ አሥር ሺህ ሰው መፈናቀሉን፣ ፑንትላንድ ውስጥም ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የመኖሪያ ቤቶችና አሣ ማስገሪያ ጀልባዎች መውደማቸውን የኖርዌይ የስደተኞች ጉዳዮች ምክር ቤት የሚባለው ግብረሰናይ ድርጅት አስታውቋል።
0
d6da73ec9833f842731b44d1e34638ba
c7cd45964b614aee75a37dc1cc76de08
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክና ብርሃን ኢንሹራንስ ኩባንያ በ10.1 ሚሊዮን ብር ዕዳ ተከሰሱ
ኮይሻ ወንጪና ጎራጎራን የቱሪስት መዳረሻ አድርጎ ለማልማት የተዘረጋውን የገበታ ለሃገር ፕሮጀክት በመደገፍ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች 283 ሺህ 328 ዶላር ማዋጣታቸውንና በሃገር ውስጥ ያሉ ተቋማትም ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ጠ/ሚኒስትሩ ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡ “ዜጎች ለገበታ ለሃገር እያደረጉ ያሉት ድጋፍ አስደናቂ ነው” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ የዲስፖራው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን ለጥሪው ምላሽ ከሰጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል አስር ዲያስፖራዎች በዕጣ ተመርጠው በህዳር አጋማሽ በሚካሄደው የገበታ ለሃገር እራት ላይ ሙሉ ወጪያቸውን ተችሎ ይጋበዛሉ ብለዋል።ለፕሮጀክቱ እየተሰበሰበ ያለው ገንዘብ በእቅዱ መሰረት እየተካሄደ ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፤ የታቀደውን ሶስት ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ የሚያሳካ መሆኑንን ማረጋገጣቸውንም አስታውቀዋል። የገንዘብ ማሰባሰብ ስራውን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከአንድ ወር በኋላ በደማቅ ስነ ስርአት እያንዳንዱ ሰው 5 ሚሊዮን ብር ከፍሎ የሚታደምበት ገበታ ለሃገር የእራት ፕሮግራም መዘጋጀቱንም ጠ/ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።ለገበታ ለሃገር ፕሮጀክት ድጋፍ ካደረጉ ተቋማት መካከል አዋሽ ባንክ 30 ሚሊዮን ብር፣ ኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ 5 ሚሊዮን ብር፣ አስመራ ሆሊዲንግ ሊትድ 10 ሚሊዮን ብር፣ ደቡብ ግሎባል ባንክ 5 ሚሊዮን ብር፣ ንብ ኢንተርናሽናል፣ባንክ 10 ሚሊዮን ብር፣ ፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራርና ሰራተኛ 10 ሚሊዮን ብር፣ ዳሽን ባንክ 30 ሚሊዮን ብር፣ ብርሀን ባንክ 20 ሚሊዮን ብር፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 10 ሚሊዮን ብር፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ 10 ሚሊዮን ብር ፣ አቢሲኒያ ባንክ 20 ሚሊዮን ብር ፣ዘመን ባንክ 10 ሚሊዮን ብር፣ ቡና ኢንተርናሸናል ባንክ 10 ሚሊዮን፣ ብር አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም 5 ሚሊዮን ብር፣ ሁርስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ አ.ማ 5 ሚሊዮን ብር፣ አባይ ባንክ 10 ሚሊዮን ብር ፣ የኢትዮጵያ ጠለፋ መድህን አ.ማ 5 ሚሊዮን ብር፣ ወጋገን ባንክ 10 ሚሊዮን ብር በማዋጣት ይጠቀሳሉ።
0
4c6a7758af77deb7906c4d30408eebb7
c189de82d099b47ffcab1688de3c0c9f
አየር መንገዱ በሶስት የቻይና ከተሞች አዲስ በረራ ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢሚሬትስ አየር መንገድ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ሁሉንም የመንገደኞች በረራ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠ።የኢሚሬትስ አየር መንገድ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፥ በሁሉም የዓለም አቀፍ መዳረሻዎች የሚያደርጋቸው የመንገደኞች በረራዎች ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ይቆማሉ ብሏል።የመንገደኞች በረራዎች ቢቋረጡም ሁሉም የጭነት (ካርጎ) በረራዎች ግን እንደሚቀጥሉ ነው አየር መንገዱ በመግለጫው ያስታወቀው።በበረራዎች መቋረጥ ለሚፈጠረው መስተጓጎል ደንበኞቹን ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ፤ በመንገደኞች ላይ የሚፈጠሩ ጫናዎችን ለመቀነስ እንደሚሰራም ነው የገለፀው።በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሁሉም የኢሚሬትስ ግሩፕ ሰራተኞች ከስራቸው እንደማይፈናቀሉም ነው ያስታወቀው።የአየር መንገዶች እና የጉዞ ኢንዱስትሪ በተለያየ ጊዜ ችግሮች ያጋጥሙታል ያለው ኢሚሬትስ አየር መንገድ፤ በመንገዶኞቹ ድጋፍ ሁሉንም ይታለፋል ብሏል።አሁን ላይ ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዘው ያሉ ጉዳዮችን በቅርበት እንደሚከታተል የገለፀው አየር መንገዱ፤ ሁኔታዎች በሚፈቅዱት ፍጥነት ወደ ስራ እንደሚመለስም አስታውቋል።
0
9c05867903bef792327b2cc2acdb5697
b8005a6bf07bb764f46465bfa9474cd3
ጅማ አባ ጅፋር ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል
ከፕሪምየር ሊጉ ከመውረድ በመጨረሻው ጨዋታ የተረፈው ወላይታ ድቻ የ3 ተጫዋቾችን ፊርማ እንዳጠናቀቀ አስታውቋል።የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሁሊሶ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ሳምሶን ቆልቻ፣ ታሪክ ጌትነት እና ኄኖክ ኢሳይያስ ለክለቡ ፈርመዋል።ሳምሶን ቆልቻ በ2006 ወላይታ ድቻ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ካስቻሉ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀስ ሲሆን አንድ የውድድር ዓመትም ከክለቡ ጋር በሊጉ ማሳለፍ ችሎ ነበር። በ2008 በደሴ ከተማ፣ በ2009 በሀዲያ ሆሳዕና እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በቻምፒዮኑ ጅማ አባ ጅፋር አሳልፎ ወደ ቀድሞ ክለቡ በመመለስ በ2 ዓመት ኮንትራት ተቀላቅሏል።ኄኖክ ኢሳይያስ በአንድ ዓመት ኮንትራት ድቻን ተቀላቅሏል። የቀድሞው የደደቢት አማካይ ባለፈው የውድድር ዓመት መጀመርያ ወደ ሽረ እንዳሥላሴ ካመራ በኋላ በግማሽ ዓመት ወደ ጅማ አባ ቡና አቅንቶ ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ የተጠናቀቀውን ዓመት በሌላው የጅማ ክለብ ጅማ አባ ጅፋር አሳልፏል። በተለያዩ ሚናዎች የሚጫወተው ኄኖክ ለአሰልጣኝ ዘነበ ፍስሀ አማራጮች እንደሚፈጥር ይጠበቃል።ሌላው ለቡድኑ የፈረመው ግብ ጠባቂው ታሪክ ጌትነት ነው። ታሪክ በ2004 ወደ ዋናው ቡድን ካደገ ወዲህ የተጫዋችነት ዘመኑን በደደቢት ያሳለፈ ሲሆን ለብሔራዊ ቡድንም በተደጋጋሚ የመጠራት እድል አግኝቷል። ግብ ጠባቂው በድቻ የአንድ ዓመት ኮንትራት ተፈራርሟል።ክለቡ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ ኮንትራታቸው የተገባደዱ 5 ተጫዋቾችንም ውል አድሷል። አብዱልሰመድ ዓሊ፣ ያሬድ ዳዊት፣ ሙባረክ ሽኩር፣ ጸጋዬ ብርሀኑ እና ውብሸት ዓለማየሁ ውላቸው የታደሰላቸው ተጫዋቾች ናቸው።የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ባለፈው ዓመት የተከሰቱ የዝውውር ስህተቶችን ላለመድገም ተጠንቅቀው በዝውውር መስኮቱ እንደሚሳተፉና ተጨማሪ ተጫዋቾችን በቀጣይ ጊዜያት ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀሱ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
0
0c2798bdf9f5c4a62e5b1140bb16fe1e
e91a5a4f5b787adcb345e62966267b4f
የኢትዮጵያንና የጀርመን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት በሁርሶ ኮንቲጀት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት እና ጎንደር ከተማ መካከል ያለውን የንግድ፣ባህል እና ፖለቲካ ግንኙት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ተገለጸ።በገዳሪፍ ዋና አስተዳዳሪ ሜጀር ጀኔራል ነስረዲን አብዲ የተመራ ልዑክ በትናንትናው ዕለት ጎንደር ከተማ መግባቱ ይታወቃል።የልዑካን ቡድኑ በዛሬው ዕለት ከጎንደር ከተማ አመራሮች ጋር በሱዳን የገዳሪፍ ግዛትና በጎንደር ከተማ መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይቷል፡፡የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ማስተዋል ስዩም፥የኢትዮጵያና ሱዳን ህዝቦች ለረጅም ዓመታት በአንድነት፣በወንድማማችነት እና በመተሳሰብ የኖሩ መሆናቸውን አውስተዋል።በሀገራቱ መካከል ያለውን ማህበራዊ ፣ፖለቲከዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።በገዳሪፍ ግዛት እና በጎንደር ከተማ መካከል የሚፈጠረው የባህልና የንግድ ግንኙነትም ለጎንደርና ለገዳሪፍ ግዛት ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል።ግንኙነቱን ለማሳደግም የገዳሪፍ ግዛት ነጋዴዎች የሚሳተፉበት የንግድ ባዛር በጎንደር ከተማ የሚዘጋጅ መሆኑን ምክትል ከንቲባው ጠቁመዋል።የጎንደር ከተማ ልዑካን ቡድኑም ወደ ግዛቷ በማቅናት የተለያዩ ተሞክሮዎችን እንደሚቀስም መናገራቸውን ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።የገዳሪፍ ግዛት ዋና አስተዳዳሪ ሜጀር ጀኔራል ነስረዲን አብዱል ከሪም በበኩላቸው፥በሱዳንና ኢትዮጵያ መተማ የሚባል የቦታ ስያሜ መኖሩን በመጥቀስ ይህም ሁለቱ ሀገራት ተመሳሳይ ባህል ያላቸው መሆኑን ያሳያል ብለዋል።ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ሀገሬ ውስጥ ያለሁ ያህል ይሰማኛል ያሉት አስተዳዳሪው፥የልዑካን ቡደኑ ጉብኝት በገዳራፍ ግዛትና በአማራ ክልል መካካል ያለውን ግንኙት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።ልኡካኑ በገዳራፍ ግዛት እና በአማራ ክልል መካከል ያለውን የሰላም፣ልማትና ፖለቲካ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ በቅንጅ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
0
e8c2fab45ffe7e3af543dd2aaa2bf87a
e8c2fab45ffe7e3af543dd2aaa2bf87a
ኮርፖሬቱ የትራፊክ አደጋ ግንዛቤ የማስጨበጫ ሥራዎችን ለማከናወን ተስማማ
ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት በአገሪቱ የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ለማከናወን ከፌደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር ተስማማ ። የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ነው የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ከዋልታ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባባር ከትራፊክ አደጋዎችጋር የተያያዙ የሚዲያ ውጤቶችን ለማቅረብ የስምምነት ፊርማ የፈጸመው።የኮርፖሬቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተተካ በቀለ በዚሁ ጊዜ እንገለጹት፤ ለአገሪቱ የጎላ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ ዜጎች በየዕለቱ እየተጠፋ ያለው ህይወት ለመታደግና አደጋውን ለመቀነስ ስምምነቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ፡፡በስምምነቱ መሰረት ዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት በእግረኞችና በአሽከሪካሪዎች ምክንያት በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ለህብረተሰቡ ያቀርባል ። ባለፈው ዓመት ብቻ በመላ አገሪቱ ከ4ሺህ 300 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን በትራፊክ አደጋ ምክንያት ያጡ ሲሆን ከ14ሺህ የሚበልጡ ዜጎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ።በበጀት ዓመቱ በትራፊክ አደጋው ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል በአደጋ ምክንያትም በህብረተሰቡ ላይ ቀላል የማይባል ማህበራዊ ቀውስ ደርሷል ።በኢትዮጵያ ለትራፊክ አደጋ መጨመር የእግረኛውና አሽከርካሪው የግንዛቤ እጥረትና የጥንቃቄ ጉድለት ዋነኛ መንስኤ እንደሆነ ይነገራል ።
1
932b4bfb0267f5a6f2f2c2912bbaaf98
694f72aac1cbd8376e3997b9c7f57484
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከሩብ ሚሊየን አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሚሊየን ሳይበልጥ እንዳልቀረ ተነገረ፡፡የሃገሪቱ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ከሆነ በአሜሪካ ቢያንስ 20 ሚሊየን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳይያዙ አልቀረም፡፡እንደማዕከሉ ገለጻ ትክክለኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አሁን ከተነገረው በ10 እጥፍ ከፍ ሊል ይችላል፡፡ይህ መረጃ የወጣው ቴክሳስ የእንቅስቃሴ ገደብ መላላቱን ለጊዜው እንዲቆይ ከወሰነች በኋላ ነው፡፡በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ነጥብ 4 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን 122 ሺህ 370 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ምንጭ፡-ቢቢሲ የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
0
65472a26c48bba6d3c8da832bb4acc61
023820fcfeaa4e905ca51666c360fa2b
ወልቂጤ ሁለት ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል
አንዱልራህማን ሙባረክ ወደ ወልቂጤ ከተማ ለማምራት ተስማማ።ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ ፋሲል ከነማ ከተቀላቀለ በኃላ በ2008 ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲገባ እና በሊጉ የተረጋጋ ዓመት እንዲያሳልፍ ጉልህ ድርሻ ካደረጉት ተጫዋቾች በግንባር ቀደም የሚጠቀሰው ይህ ፈጣን የመስመር ተጫዋች ባለፈው ዓመትም በተወሰኑ ጨዋታዎች ቡድኑ ማገልገሉ ይታወሳል። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶት የዋልያዎቹ ማልያ የለበሰው አብዱልራህማን ዛሬ ጠዋት ስምምነት የፈፀመ ሲሆን የአጥቂ አማራጮቹን ለማስፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ለሚገኘው ወልቂጤ ጥሩ ግልጋሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
0
345d94e873f1cbeda3e6c7a14fe610c8
19cc457b614eb2605eac9972841f6aa2
የኮሮና ቫይረስ 47 ሚሊየን የሚሆኑ ሴቶችን ወደ ድህነት ሊያስገባ ይችላል- ተመድ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 05/2012 ዓ.ም (አብመድ) በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አፍሪካ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ በከፋ በኮሮና ቫይረስ ልትጠቃ እንደምትችል አስጠንቅቋል፡፡በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ እንዳስታወቀው አፍሪካ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ለኮሮና ቫይረስ ተገቢውን የመከላከል እና የመቆጣጠር ሥራ ካልሠራች ለቫይረሱ ሁነኛ መፍትሄ እስከሚገኝለት ድረስ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙባት ይችላሉ፡፡በቀጣዮቹ ከሦስት እስከ ስድስት ወራት ብቻ ደግሞ በአህጉሩ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እስከ 10 ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ ሕይወታቸውን የሚያጡትም 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ነው ያስጠነቀቀው፡፡በሌላ በኩል በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከ5 እስከ 29 ሚሊየን ሰዎች ለከፋ ድህነት ሊዳረጉ እንደሚችሉም ኮሚሽኑ አስጠንቅቋል፡፡ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚችል የጤና እና የማኅበራዊ ደኅንነት ትስስርን ለመፍጠር ደግሞ ከ100 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ብሏል ኮሚሽኑ፡፡ የህክምና ቁሳቁስ ተደራሽ ለማድረግ ብቻ ደግሞ እስከ 44 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያስፈልጋል ነው ያለው፡፡
0
edd9be4f372713acc049f29b3718ee2b
b81942ef96d5b2770e706ae07f0965aa
በበጀት አመቱ 343 ሺህ ከረጢት ደም ለመሰብሰብ ታቅዷል
የአገሪቱ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም ለዜጎች ሰፊ የሥራ እድልን በመፍጠር እየተመዘበ ያለውን አገራዊ የምጣኔ ሃብት ዕድገት ቀጣይነት በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ በ2010 በጀት አመት ኢንቨስትመንት ለአገራዊ ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚኖረውን ድርሻ እንዲጎለብት ለማድረግ የሚያስችል አመርቂ ተግባር ማከናወኑም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡የሃገሪቱን የኢንቨስትመንት ዕድሎች በሚያስተዋውቁ ዓለም ዓቀፍ ፎረሞችና የንግድ ትርዒቶች ላይ በመሳተፍ በሃገሪቱ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና ምቹ ሁኔታዎች የማስተዋወቅ ስራ መሰራቱም ተጠቁሟል፡፡በበጀት ዓመቱ ሃገሪቱ ከ3 ነጥብ 7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ ችላለች፡፡ኢንቨስትመንትን ከመሳብ እንዲሁም የሃገርና የውጭ ባለሃብቶችን ከመደገፍ ባሻገር የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመንግስትም ሆነ በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በማስፋፋት አመርቂ ተግባር ተከናውኗል፡፡ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች የተሰሩ ከመሆኑም በላይ ኮሚሽኑ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ወደ ሃገሪቱ ገብተው ስራ ለጀመሩ ባለሃብቶችም የተለያዩ ድጋፎች አድርጓል፡፡በበጀት አመቱ በኢንቨስትመንት ምንጭነት ተቀዳሚ የሆኑ አገራትና ባለሃብቶች የተለዩ ሲሆን በቀዳሚነት ቻይና በሁለተኝነት የህንድና ቱርክ ባለሃብቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡በበጀት አመቱ 5 ነጥብ07 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ተሳትፎ ለማድረግ ያሰቡ 275 የውጭ ባለሃብቶችና ኩባንያዎችም የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥተዋል፡፡እንዲሁም የኢንቨስትመንት ማበረታቻ በዋና መስሪያ ቤትና በየፓርኮች መፍቀድን በተመለከተ በበጀት አመቱ 49 ቢሊዮን ብር ግምት የኢንቮይስ ዋጋ ላላቸው 8 ሺህ 36 የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ማበረታቻ ጥያቄዎች ፈቃድ ለመስጠት ተችሏል፡፡ካፒታላቸው 16 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሆኑ 198 ፕሮጄክቶችን ወደ ማምረት ወይም አገልግሎት መስጠት የተሸጋገሩ ሲሆን ከ57 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 252 ፕሮጄክቶች ወደ ትግበራ ተሸጋግረዋል፡፡ሃገሪቱ ኢንቨስትመንትን በመሳና በማስተዋወቅ እንዲሁም ውጤታማ የፖሊሲና የአሠራር ማሻሻያዎችን በመተግበር ላስመዘገበችው ላቅ ያለ የኢንቨስትመንት ፍሰት የዓለም ባንክ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የAIM 2018 ሶስት ሽልማቶች ባለቤት መሆኗም በመግለጫው ተካቷል ፡፡
0
e8bb22dfbb18690c2e86b53c7b57b289
e8bb22dfbb18690c2e86b53c7b57b289
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ተደረገ
አዲስ አበባ፦ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባሉ አንዳንድ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን የጤና ሚኒስትር አስታወቀ ። ሚኒስቴሩ ጥናንት ይፋ እንዳደረገው ፣በማሻሻያው መሠረት በማንኛውም ምክንያት በቤትም ሆነ በጤና ተቋማት ውስጥ ለሞት የሚዳረጉ ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በቤተሰብ የቀብር ሥነ-ሥርዓት የሚፈጸም ይሆናል። ከማንኛውም ሞት በኋላ የኮቪድ 19 ምርመራ ናሙና የሚወሰድ መሆኑን አመልክቶ ፣ የምርመራ ውጤቱ ሳይጠበቅ አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ ቤተሰብ ባዘጋጀው ቦታ ከዚህ ቀደም በተቀመጠው መሠረት 50 ሰዎች ብቻ ተገኝተው የቀብር ሥርዓቱን የሚያካሂዱ ይሆናል። ምንም ዓይነት ምልክት የሌላቸው ወይንም ቀላል ምልክት የሚያሳዩ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች የሚያገለግሏቸው የቤተሰብ አባላት እና የራሳቸው ፍላጎት ከግምት በማስገባት የአኗኗር ሁኔታቸው በተቀመጠው መመሪያ መሠረት አግባብ ከሆነ በቤታቸው እንዲቆዩ የሚደረግ እንደሚሆን አስታውቋል ። በቤት ለመቆየት የማይችሉ ከሆነ ከጤና ተቋማት ውጪ በተዘጋጁ ለይቶ ማቆያዎች እስኪያገግሙ እንዲቆዩ እንደሚደረግም አመልክቷል ። ከውጭ የሚገቡ ሰዎች ወደ ሀገር ውስጥ በገቡበት ሰዓት ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ ከመጡበት ሀገር ተመርምረው ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ይዘው ከመጡ ናሙና ተወስዶ በቤታቸው 14 ቀናት እንዲቆዩ እንደሚደረግ ገልጿል ። በሌላ በኩል ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ሪፖርተ ይዘው ለማይመጡ መንገደኞች ለሰባት ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ የሚደረግ ሲሆን ተመርምረው ነጻ ከሆኑ ቀሪውን ሰባት ቀን በቤታቸው መቆየቴ እንደሚችሉ አስታውቋል ።ዝርዝር መመሪያው በቅርቡ እንደሚወጣም አመልክቷል ። አዲስ ዘመን ሰኔ 15/2012 በጋዜጣው ሪፖርተር
1
5e4f684468a68b4741f050eb9d4462f5
48b4b155cbea112b3c3083e5dae69fc0
የጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ የግድያ ምርመራ ባፋጣኝ መጠናቀቅ አለበት ሲሉ ኤርዶዋን አሳሰቡ
ፓምፔዮ በሀንገሪ መዲና ቡዳፔስት ባለው የአሜሪካ ኤምባሲ ሆነው ሲናገሩ ዩናይትድ ስቴትስ አሳዛኙ የዣማል ኻሾግዢን በሚመልከት ምርመራ ማካሄዱን በመቀጠል “ተጨማሪ እርምጃ መውሰዱን ትቀጥላለች ብለዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ባለፈው ጥቅምት ወር ኢስታንቡል በሚገኘው የሳውዲ አረብያ ኤምባሲ ውስጥ ለተፈፀመው ግድያ ተጠያቂ ማነው? ለሚለው ምላሽ ለማግኘት የሰጠው የጊዜ ገደብ ግን ባለፈው አርብ አልፏል።
0
07ed9d161a567a6ab96b7c8d2d3e249f
5d7a0c38da218e7bff7f529ca5894027
የቱሪዝምና የግንባታው ክፍለ ኢኮኖሚ ለኬንያ ፈጣን ዕድገት ቁልፍ ሚና መጫወታቸው ተነገረ
የኢፌዲሪ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ64ኛው መደበኛ ስብሰባ የመካከለኛ ዘመን ፥ ከ2007 እስከ 2011 ዓመት የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ አፀደቀ፡፡የመጀመሪያው የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንሰፎርሜሽን እቅድ ትግበራ ፥ በሚቀጥለው 2007 በጀት ዓመት እንደሚጠናቀቅና በዕቅድ ዘመኑ የተያዙ ግቦችም በተጀመረው መልኩ በቀጣይ ዓመት ተግባራዊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ምክር ቤቱ የተጀመረው የህዳሴ ጉዞ ቀጣይ እንደሚሆንና በቀጣዮቹ ዓመታት የመንግስት የገቢ አሰባሰብ እየተሻሻለ እንደሚሄድ ታሳቢ በማድረግ በመንግስት በጀት ተግባራዊ የሚደረጉ ዕቅዶች ላይ ተወያይቷል።ከዚህ በተጨማሪም በ2007 በጀት ዓመት ዝርዝር በጀት ዝግጅትና አምስት ዓመት ድረስ በሚዘልቀው የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ የገቢ ትንበያ እና የወጪ ታሳቢዎችን በማየትም ውይይት አካሂዷል፡፡የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ዝግጅቱ የተለያዩ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ሁኔታዎችንም ታሳቢ አድርጓል። ባለፉት ሶስት የዕድገትና የትራንስፎርሚሽን ዕቅድ የትግበራ ዓመታት ከፍተኛና ፈጣን ዓመታዊ ዕድገት መመዝገቡ፤ በቀሩት የእቅዱ ጊዜያትም ዕድገቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ግቦቹን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ እንደሚደረግ ይጠበቃል።በተያያዘ የዋጋ ዕድገት በዕቅዱ በተቀመጠው ግብ መሠረት በማዕቀፉ ዘመናት ከ10 በመቶ በታች እንደሚሆን፣ ከ2007 እስከ 2011 አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት በጊዜው የገበያ ዋጋ ዕድገት በአማካይ 17 ነጥብ 1 በመቶ እንደሚሆንና የተረጋጋ የብር የውጭ ምንዛሬ ምጣኔ እንደሚኖረው ካለው ትንበያ ታሳቢ ተደርጓል፡፡በአጠቃላይ እነዚህን ታሳቢዎች በመውሰድ ባለው ከ2007 እስከ 2011 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ አመልካቾች ትንበያ መሠረት፥ ሀገራችን በአማካይ ባለ ሁለት አሃዝ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት ማስመዝገብ እንደምትችል ተቀምጧል፡፡የሚኒስትሮች ምክር ቤትም በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍን ተቀብሎ አፅድቋል፡፡በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለግብርና ስራው ዘመናዊነት የሚውል ከፖላንድ መንግስት የተገኘውን የ50 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የብድር ስምምነት ተወያይቶ በማፅደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ ምንጭ፤- ኤፍቢሲ
0
e34148a7859ebd5a1bbdc96658825dd4
246c84635dcef16473069306671deec0
ጅማ አባ ጅፋር አዲስ ዋና አሰልጣኝ ቀጠረ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች በነገው እለት እንደሚከናወኑ ሲጠበቁ የ2010 የፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኑ ጅማ አባ ጅፋር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሊያደረግ የተያዘለትን መርሐ ግብር እንደማያከናውን ክለቡ አረጋግጧል። የጅማ አባ ጅፋር ስራ አስኪያጅ አቶ እስከዳር ዳምጠው ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት የ2010 ኢትዮጵያ ዋንጫን በ2011 ማከናወን በክለቡ እቅድ ውስጥ እንደሌለ እና የውድድር ዘመኑ ዝግጅት አካል እንዳልሆነ ገልፀው የነገውን ጨዋታ እንደማያከናውኑ ተናግረዋል። ጅማ አባ ጅፋር ውሳኔውን ተከትሎ በ2010 የኢትዮጵያ ዋንጫ አንድም ጨዋታ ያልተጫወተ ክለብ ሆኗል። በመጀመርያው ዙር ደደቢት ራሱን በማግለሉ በፎርፌ ወደ ቀጣይ ዙር ሲያልፍ በሩብ ፍፃሜው ኤሌክትሪክ ሜዳ ላይ ባለመገኘቱ በተመሳሳይ በፎርፌ ለግማሽ ፍፃሜ ማለፉ የሚታወስ ነው። ከክለቡ ጋር በተያያዘ ዜና አወት ገብረሚካኤል እና ዲዲዬ ለብሪን ለማስፈረም መቃረቡ ታውቋል። ተጫዋቾቹ ከኤሌክትሪክ መልቀቂያቸውን ከወሰዱ ዛሬ ሊፈርሙ ይችላሉም ተብሏል። እንደ ስራ አስኪያጁ አቶ እስከዳር ገለፃ ከሆነ ደግሞ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር የተለያየው ያሬድ ዘውድነህን ጨምሮ ስምንት ተጫዋቾች (ስድስቱ ከውጪ) በሙከራ ጊዜ ላይ ሲሆኑ ከሁለት እስከ ሶስት ተጫዋቾች ሊፈርሙ ይችላሉ።
0
e774a97b2a51abdad461b3d1c86f9403
b4fa808b72a911feb43bdd9ccc655a5b
መምህራንን የቤት ባለቤት ለማድረግ ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሚቴው ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የተጀመረው የንግድ ስራ ቅልጥፍና ማሻሻያ እንዲሳካ ተቋማት ግልፅ የመረጃ ልውውጥና መናብበ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገለጸ። አገልግሎት ፈላጊዎች፣ ነጋዴዎችና አልሚዎች ባሉበት ቦታ ሆነው አልያም በአንድ መስኮት የተቀላጠፈ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑም ነው የተነገረው። የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የስራ ምቹነትና ቅልጥፍናን ለመፍጠር ተቋማት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። የብሄራዊ ኮሚቴው አካል የሆነው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የንግድ ስራ ለመጀመር የሚያስችል መረጃዎችን የያዘ የንግድ መረጃ አቀባይ (business portal) business.gov.et አልምቶ ይፋ ማድረጉን ገልጿል። መረጃ አቀባዩ ወደ ንግድ ስርዓቱ ውስጥ ለመግባት የሚፈልጉ ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው የተሟላ መረጃ ለማግኘት የሚያስችላቸው ነው። ንግድ ለመጀመርና ፍቃድ ለማውጣት የሚወስደው ጊዜ፣ የሚፈጀው ገንዘብ፣ መሟላት ያላባቸው መረጃዎች እና የመሳሰሉትንም የያዘ ነው። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አሀመዲን መሀመድ የንግድ ማኅበረሰቡና የመንግስት ሰራተኛ እውነተኛ የመረጃ መለዋወጫ እንዲኖረው እየተሰራ ነው ብለዋል።ባለፈው አመት በወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ በንግድ ስራ ቅልጥፍና ከዓለም ሀገራት 159ኛ ደረጃ ላይ ስትሆን በሚቀጥሉት አመታት ይህንን ደረጃ መቶዎቹ ዝርዝር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
ed9d3fdf5da48309bc434d48c0625ce1
ed9d3fdf5da48309bc434d48c0625ce1
የሀገር ግንባታ ሂደት የማያልቅ ከትውልድ ትውልድ በቅብብሎሽ የሚሰራ ነው – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት ላለፉት ሶስት ቀናት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት እና የሰላም ፎረም ተወካዮች የተካሄደው የስልጠናና የምክክር መድረክ ተጠናቋል።በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተገኝተው ለተማሪዎች የህይወት ልምዳቸውንና መልዕክት አስተላልፈዋል።ሚኒስትሯ በወቅቱም ሀገር በዜጎች ልቦና ውስጥ ነው የምትሰራው፣ የሀገር ግንባታ ሂደት የማያልቅ ከትውልድ ትውልድ በቅብብሎሽ የሚሰራ ነው ብለዋል።ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት ጅረት የሚፈስባቸው ቦታዎች ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ÷ ተማሪዎች ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ቆም ብለው በውይይትና በድርድር የመፍታት ባህልን ማሳደግ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።ሰው መርጦ ባልተወለደበት ብሔርና ማንነት ሊጣላና ሊባላ አይገባም ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪሃት÷ የችግሮች መነሻ አለመተዋወቅ በመሆኑ ተማሪዎች እርስ በርሳቸው ሊተዋወቁ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡የሰላም ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ወጣቶችንና ተማሪዎችን በቅርበት የሚያገኝበትን መንገድ እያመቻቸ እና በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ከሚኒስቴሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
1
6cce9abb9a740ced9bb7d62ed90cb49c
cca184e6d38a4d461b0f672ee8729693
አቶ ወርቁ አይተነው ለመከላከያ ሰራዊት እና ለአማራ ልዩ ሀይል 100 ሰንጋዎችንና 200 ኩንታል ፉርኖ ዱቄት ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዝቡ ለመከላከያ ሰራዊት አያደረገ ያለው ድጋፍ ለሀገሩና ለሰራዊቱ ያለውን ክብርና ፍቅር የሚያሳይ መሆኑን የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ ገለፁ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሚንስተር ዶክተር ቀናዓ ያደታ፣ የጅማ ዞን እና የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያበረከቱትን ድጋፍ ተረክበዋል።በስነ ስርዓቱ ላይም የሰላም ሚኒስትር ደኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው እና የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማን ጨምሮ ሌሎችን የፌደራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።የጅማ ዞን ነዋሪዎች ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ክህደት በማውገዝ ለመከላከያ ስራዊት 515 ሰንጋዎችን፣ 414 በግና 300 ኪሎ ግራም ማር በአጠቃላይ 15 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አድርጓል።በተመሳሳይ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ለኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በገንዘብና በአይነት ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል።የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ያደረጉት ለዞኑና ለከተማው ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።የሀገርን ዳር ድንበር እና ሰላም ለመጠበቅ ዘብ በቆሙት የሰሜን እዝ አባላት ላይ በባንዳው ህወሃት የተፈፀመው ክህደት አሳፋሪ ነው ብለዋል።ሰራዊቱ የሚገጥሙትን ፈተናዎች በቁርጠኝነት በማለፍ ድል እያስመዘገበ መሆኑንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።የኢትዮጵያ ህዝቦች ለመከላከያ ሰራዊት አያደረጉ ያለው ድጋፍ ለሀገራቸውና ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብርና ፍቅር የሚያሳይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም አለኝታነታቸውን ላረጋገጡት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርቧል።በሙክታር ጠሃ
0
d78076f7bdd369a78062676f6a97e3d4
d78076f7bdd369a78062676f6a97e3d4
የመቐለ፣ ሽሬ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለበረራ ዝግ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ
አዲስ አባበ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቐለ፣ ሽሬ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ::የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዛሬ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የመቐለ፣ ሽሬ፣ አክሱም አና ሁመራ ኤርፖርቶች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት ዝግ መሆናቸውን አስታወቀ።ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በተመሳሳይ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት (ኤርሜንስ) በተገቢው የመገናኛ ዘዴ (ኖታም) አንዲያውቁት መደረጉንም አስታውቋል።
1
12c749f38ef23b9c3eccfd66ba8aeb09
5ebafe6b71de0b45c44f7cfb1928bd44
” ይህ መሆኑ ደስ ብሎኛል ” ኤርሚያስ ኃይሉ (ጅማ አባ ጅፋር)
የፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኑ ጅማ አባጅፋር ዐወት ገብረሚካኤል እና ከድር ሳሊህን ሲያስፈርም ዲዲዬ ለብሪን በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚያስፈርም ይጠበቃል። ዐወት ገ/ሚካኤል ከ2004 ጀምሮ ከተጫወተበት አሳዳጊ ክለቡ ኤሌክትሪክ ጋር የነበረውን የአንድ ዓመት ኮንትራት የውል ማፍረሻ በመክፈል መልቀቂያውን የወሰደ ሲሆን የምዕራብ ኢትዮጵያውን ክለበ በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሏል። ባህር ዳር ከተማን ለመቀላቀል ተቃርቦ የነበረው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዐወት በጅማ አምና መልካም ጊዜ ያሳለፈውና ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያመራው ኄኖክ አዱኛን ክፍተት እንደሚሸፍን ታምኖበታል።ከድር ሳሊህ ሌላው የጅማ አባ ጅፋር ፈራሚ ነው። የመስመር አጥቂው አምና በወልዋሎ እንደክለቡ ሁሉ ድንቅ አጀማመር ቢያደርግም ቀስ በቀስ ተቀዛቅዞ ታይቷል። ከወልዋሎ ጋር የአንድ ዓመት ውል የነበረው የቀድሞው የአውስኮድ አጥቂ በውሉ ዙርያ ከወልዋሎ ጋር የነበረውን አለመግባባት መፍታቱን ተከትሎ ወደ ጅማ አባጅፋር በአንድ ዓመት ውል አምርቷል።ክለቡ በቀጣይ ቀናት በይፋ እንደሚያስፈርመው የሚጠበቀው አይቮሪኮስታዊው ዲዲዬ ለብሪ ነው። የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ እንደ ዐወት ሁሉ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢኖረውም ለኤሌክትሪክ የውል ማፍረሻ ለመክፈል ከስምምነት በመደረሱ ወደ ሀገር ቤት እንደመጣ የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች መሆኑ ይረጋገጣል።(ፎቶ ማስተካከያ – ከላይ በቀኝ በኩል የነበረው ፎቶ የከድር ሳይሆን የሌላ ተጫዋች የነበረ ሲሆን በኤዲት ተስተካክሏል)
0
36d27233bfbb5cad0b906ca3339d5d70
9707da2fe2e65e6a82d782abf064fc1e
በትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራው ልዑክ ከሱዳን የመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚንስትር ጋር ተወያየ
በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ በማለዳው ወደ ጅቡቲ አቅንቷል።ልዑኩ ወደ ጅቡቲ ያቀናው በጅቡቲ የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ ህልፈተ-ህይወትን ተከትሎ በቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው ተብሏል።ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ ጅቡቲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደደረሱ በአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አብዱልቃድር አህመድ ካሚል አቀባበል ተደርጎላቸዋል።በጅቡቲ የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ በሁለቱ አገራት መካከል የተጠናከረ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ ልማት እና ሰላም እንዲዳብር በሰጡት ታሪካዊ አመራር ይታወቃሉ።የታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ የኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ መሆናቸውም በስፋት ይነገርላቸዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ በታጁር ሱልጣን አብዱልቃድር ሁመድ ህልፈተ-ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በኢፌዴሪ መንግሥት ስም አስተላልፈዋል። መረጃው የምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ነው፡፡
0
a9fa58f78b954d0f6f809a3e9b003724
a9fa58f78b954d0f6f809a3e9b003724
የፕሪምየር ሊጉ የብሮድካስት ክፍፍል እንዴት እንደሚሆን ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከቴሌቭዥን፣ ሬድዮ እና ከሊጉ ሥያሜ የሚገኘውን ገንዘብ እንዴት እንደሚያከፋፍል ገለፃ አደገ።አክሲዮን ማኅበሩ በአሁኑ ሰዓት እየሰጠው ባለው መግለጫ ላይ በአንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ የተነሱ ጉዳዮችን ለጋዜጠኞች ገለፃ እያደረገ ይገኛል። ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ማኅበሩ ከሊጉን ስያሜ፣ ቴሌቭዥን እና ሬዲዮ መብት የሚገኘውን ገቢ ለክለቦች እንዴት እንደሚከፋፈል እና ጉባኤው ተወያይቶ ውሳኔዎች የተወሰኑባቸውን መለኪያዎች ይፋ አድርጓል።ማኅበሩ በሪፖርተር ጋዜጣ ባወጣው ጨረታ መሰረት የተባሉት ነገሮች ገቢ የሚያመጡ ከሆነ በሚከተሉት መለኪያዎች ክፍፍሎች ይፈፀማሉ።1- አስራ ስድስቱም የሊጉ ክለቦች ከሚገኘው ገቢ 50% የሚሆነውን ይከፋፈላሉ። ምክንያቱም የአክሲዮን ማኅበሩ አባል ስለሆኑ።2- ከሚገኘው ገቢ 15% የሚሆነው ለሊግ ካምፓኒው እንዲተው ይደረግና ቀሪው ድርሻ ክለቦቹ ባገኙት ደረጃ መሰረት እንዲሰጣቸው ይደረጋል።3- የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ መብቱን የሚገዛው ተቋም በሚመርጣቸው እና አንድ ክለብ በዓመቱ የተላለፉለትን ጨዋታዎች ታሳቢ ተደርጎ ይሰጣል።ከሥያሜው መብት የሚገኘውን ገቢ ለውድድር አሸናፊዎች እና ኮከቦች የሚሰጠውን ሽልማት እንዲሸፍን ይደረጋል። በዚህም የሉጉ አሸናፊ ክለብን ጨምሮ የሊጉ ኮከቦች ከዚህ ቀደም ከሚያገኙት የሽልማት ገንዘብ የተሻለ እንዲያገኙ ይደረጋል።የአክሲዮን ማኅበሩ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ”የስያሜ መብቱን ለመግዛት የሚመጣው ተቋም የክለቦችን ስፖንሰር የሚጨቁን (የሚመሳሰል) ከሆነ ስፖንሰር ሺፑን አንቀበልም” ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ሊጉ ከተቋረጠ በኋላ የማኅበሩ የቦርድ አመራቶች ትላልቅ የሃገራችን ተቋማት ጋር ሄደው የሊጉን ስያሜ እንዲገዙ እንደጠየቁ ነገርግን እስካሁን ምላሽ እንዳላገኙ ጠቁመዋል።
1
d926d7d825c621500bc07d3ffbc6a5a1
ba83ad87db6ecd32c5a7deecf31463c1
ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ
አቃቂ ቃሊቲ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ ሁለት ታዳጊዎቸችን አሳድጓል፡፡አሰልጣኝ ብዙዓየው ዋዳን ከቀጠሩ በኃላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ከቀናት በፊት አስፈርመው ከነባሮቹ ጋር አዋህደው ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የገቡት የአቃቂ ቃሊቲዎች ተጨማሪ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ ሔለን ሙሉጌታ (ግብ ጠባቂ ከፋሲል ከነማ)፣ ያብስራ ይታይህ (አጥቂ ከፋሲል ከነማ)፣ የትምወርቅ አሸናፊ (አጥቂ ከአርባምንጭ) አዳዲስ ፈራሚዎቹ ሲሆኑ ሩት ሚልዮን (ተከላካይ) እና ፍሬህይወት ኩማ (አማካይ) ከታዳጊ ቡድን ያደጉ ተጫዋቾች ሲሆን አጥቂዋ ሔለን መሰለ ደግሞ ውሏ መራዘሙን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ይጠቁማል፡፡
0
a67cc473c45b8aa3b01b06306c38280f
a67cc473c45b8aa3b01b06306c38280f
ሉሲ | ሰላም ዘርዓይ 11 ተጫዋቾችን ቀነሰች
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰላም ዘርዓይ ለ2019 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ከመረጠቻቸው 36 ተጫዋቾች መካከል 11 ተጫዋቾችን በመቀነስ የመጨረሻዎቹ 25 ተጫዋቾችን አሳውቃለች።ሉሲዎቹ ከሊቢያ ጋር ለሚያደርጉት የመጀመርያ ዙር የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ተጠርተው ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል ገነት አክሊሉ ፣ ሽብሬ ካንቦ ፣ እፀገነት ብዙነህ ፣ ፅዮን እስጢፋኖስ ፣ መዲና ጀማል ፣ አለምነሽ ገረመው ፣ ሜላት ደመቀ ፣ ልደት ቶላ ፣ ቤቴልሄም ሰማን ፣ ፎዝያ መሐመድ እና ትዝታ ፈጠነ የተቀነሱ ተጫዋቾች ናቸው።የመጨረሻ 25 ተጫዋቾች ዝርዝርግብ ጠባቂዎችማርታ በቀለ (መከላከያ) ፣ አባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ትዕግስት አበራ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)ተከላካዮች መሠሉ አበራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ፀጋነሽ ተሾመ (ድሬዳዋ ከተማ) ፣ ዘለቃ አሰደፋ (ደደቢት) ፣ ብዙአየሁ ታደሰ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ቤተልሄም ከፍያለው (ኤሌክትሪክ) ፣ መስከረም ካንኮ (ደደቢት) ፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ገነሜ ወርቁ (ጌዴኦ ዲላ)አማካዮችሠናይት ቦጋለ (ደደቢት) ፣ አረጋሽ ልኬሳ (አካዳሚ) ፣ ዙሌይካ ጁሀድ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ቤዛዊት ተስፋዬ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ህይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ እመቤት አዲሱ (መከላከያ) ፣ ብሩክታዊት ግርማ (ደደቢት)አጥቂዎችምርቃት ፈለቀ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ ሎዛ አበራ (ደደቢት) ፣ ትዕግስት ዘውዴ (ደደቢት) ፣ ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ) ፣ ረሂማ ዘርጋ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሰርካዲስ ጉታ (አዳማ ከተማ) ፣ ሲሳይ ገብረወልድ (አካዳሚ)ሉሲዎቹ ዝግጅታቸውን ከየካቲት 27 ጀምሮ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታቸውን ከሊቢያ ጋር ከሜዳቸው ውጪ ከመጋቢት 22 እስከ 24 ባሉት ቀናት ያደርጋሉ። የመልሱን ጨዋታ አአ ላይ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሲያደርጉ ይህን ዙር ካለፉም በቀጣይ የማጣርያ ዙር የሴኔጋል እና አልጄርያ አሸናፊን የሚገጥሙ ይሆናል።
1
2b77b50f966d2735a0f21a42d9a8b57a
8ede48a7fffb9071b96e422c3c4236cd
የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገለፀ
አዲስ አበባ፡- የአገር ውስጥ የባህል አልባሳት አምራቾች ከውጭ በሚመጡ ምርቶች ምክንያት ገበያቸው እየተዳከመ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡ የባህል አልባሳት ዲዛይን ባለቤትነት ጥበቃ አለመኖሩ ችግሩን እያባባሰ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የእደ ጥበባት ማበልፀጊያ የገበያ ልማት ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ አስናቀ ትናንት በኢትዮጵያ የባህል ጥበብ አልባሳት ተወዳዳሪነት ላይ ያተኮረ ውይይት ሲካሄድ እንዳሉት፤ የአገር ውስጥ የባህል አልባሳት አምራቾች የሚያመርቱት ምርት ከውጭ ተሰርቶ ከሚመጣው የባህል ልብስ ጋር ተወዳዳሪ መሆን አልቻለም፡፡ ለዚህ ደግሞ የአገር ውስጥ አምራቾች የሚሸጡበት ዋጋ መጨመርና የጥሬ እቃ እጥረት ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው፡፡እንደ አቶ ነጋሽ ገለፃ፤ የአገር ውስጥ የባህል አልባሳት አምራቾች ምርቶቻቸውን በብዛት አለማምረታቸውና በውድ ዋጋ መሸጣቸው ተጠቃሚው የቻይና ምርት የሆነውን ሽፎን እንዲገዙ አድርጓቸዋል፡፡ የባህል አልባሳት ላይ የሚሰሩት ዲዛይኖች ተመሳሳይ መሆንና በቴክኖሎጂ የተደገፉ አለመሆናቸውም በገበያው ላይ ተፈላጊነታቸውን ቀንሶታል፡፡‹‹የባህል አልባሳትን ለማምረት ከጥጥ በስተቀር ሁሉም ጥሬ እቃ የሚገባው ከውጭ አገር ነው›› የሚሉት አቶ ነጋሽ፤ ሸማኔው ድርና ማግ ለማግኘት መቸገሩ፣ የምርት ጥራት የሚያረጋግጥ ባለሙያ አለመኖር እንዲሁም አልባሳቱን ከበዓላት ውጭ እንዲለበሱ አድርጎ አለመስራት የባህል አልባሳት አምራቾች ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ማድረጉን አመልክተዋል፡፡በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት የእሴት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ወርቁ በበኩላቸው፤ በአገር ውስጥ የሚመረቱ የባህል አልባሳት ዲዛይን ጥበቃ እየተደረገለት አለመሆኑን ፤ የአልባሳቱ ዲዛይን ተመሳሳይነትና ባለቤት አልባ በመሆኑ ጥበቃ ለማድረግ አስቸጋሪ ማድረጉን እንዲሁም የባህል አልባሳትን በአዕምሯዊ ንብረትነት ጥበቃ ለማስመዝገብ ህጋዊ ማዕቀፍ አለመኖሩን አስረድተዋል፡፡ የባህል አልባሳት ዲዛይኖችን ለመጠበቅና እውቅና ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለባህል ልብሶች ዲዛይን የወል የንግድ ስሞችን ለመስጠትና ከውጭ የሚገቡትን ምርቶች ለመቆጣጠር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡አዲስ ዘመን ህዳር 3/2012መርድ ክፍሉ
0
a6fb0bf42011785b89fc742b78f19168
f1996e908ae5ba1d5897c6accbb9c0a0
የሩሲያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ፑቲን ያቀረቡትን የማሻሻያ እቅድ አፀደቀ
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ጽንስ ማቋረጥ በህግ የተፈቀደ ሲሆን ሴቶች ድርጊቱን እንዳይፈጽሙ ለመከላከል የራሳቸውን የቁጥጥር ህጎች ያወጡ አንዳንድ ክፍላተ ሀገር አሉ። የትናንቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለጽንስ ማቋረጥ መብት ተሟጓቾች አስደስቷዋል ።አምስት ለሶስት በሆነ የድምጽ ብልጫ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ይህ ውሳኔ በሩብ ምዕተ ዓመት ውስጥ ከሰጣቸው የጽንስ ማቋረጥ መብት ብይኖች ከፍተኛው መሆኑ ተመልክቷዋል።ፍርድ ቤቱ በዚህ ብይኑ የቴክሳስ ክፍለ ሀገር ክሊኒኮች የክፈለ ሀገርዋ ወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች ዓላማ ክሊኒኮቻችንን ለማዘጋት ነው ሲሉ ያቀረቡትን ሙግት ተቀብለዋል። የጽንስ ማስገወድ መብት ደጋፊዎች ትናንት ዋሽንግተን ዲስ ውስጥ ተሰባስበው ደስታቸውን ገልጸዋል።የደቡብ ምስራቅዋ ክፍለ ሀገር ቴክሳስ የጽንስ ማቋረጥ ኣገልግሎትየ የሚሰጡ ክሊኒኮች በአቅራቢያቸው ባለ ሆስፒታል ታካሚዎቻቸውን አስገብተው ለማከም የሚያስችል ውል ሊኖራቸው ይገባል። በሆስፒታል ደረጃ የሚሰራባቸው በውድ ዋጋ የሚገዙ መሳሪያዎች እንዲኖራቸው ያስገድዳል። ፍርድ ቤቱ ህገ መንግስቱን በሚጻረር መንገድ የሴቶችን መብት የሚጥስና በህክምናም ኣላስፈላጊ ነው በማለት በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጎታል። የቴክሳስ አገረ ገዢ ዳን ፓትሪክ ውንጀላውን ኣይቀበሉም።እንደያውም የኛ ሕጎች ዓላማቸው የሴቶችን ጤና ለመጠበቅ ነው በማለት ይከራከራሉ። ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የትናንቱን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሴቶችን የስነ ተዋልዶ መብት ላይ የተደነቀረ ከህገ መንግስት ውጭ የሆነ እንቅፋት የሚያስወግድ ውሳኔ ነው በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
0
a5d648eca1082f57a444e0995bf99173
8f03569044addc2fb4a24a28547589fd
በጎንደር የጥምቀት በዓል ላይ ለታዳሚዎች የተዘጋጀ ርብራብ ተደርምሶ ከ100 በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል በጎንደር የሚታደሙ ሰዎች ለበዓሉ በሰላም መከበር የበከሉላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጠየቀ።ከተለያዩ የአለም ሀገራት የመጡ እጅግ በርካታ ጎብኝዎች በሚታደሙበትና በዩኒስኮ ” በማይዳሰስ የሠው ልጆች ባህላዊ ቅርስነት የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።በመሆኑም ለደስታ በሚል ምክንያት ሮኬትም ሆነ ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ እንደሆነ ተገልጿል።እንዲሁም የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ ከመንግስት የጸጥታ አካል ውጭ በከተማዋ የጦር መሳሪያ ይዞ መዘዋወር የተከለከለ መሆኑን ከከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።ህብረተሰቡ ለእንግዶች የህዝቡን ባህል ፣ ወግ ፣ ትውፊት ፣ ደግነትና በጎ ገፅታዎችን በማስተዋወቅ የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ጥሪ አቅርቧል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
491a16f853d602acbc4a9365a184cabe
793b87e3ebfe3755d27b76fcf3133839
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 290 ተማሪዎችን አስመረቀ
ዩኒቨርሲቲዎች ሀገሪቱ የምትፈልገውን የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት በልማቱ ዘርፍ የምታሳየው ለውጥ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን እያበረከቱ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ገለጹ፡፡ አድማስ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት በስቲያ የዕለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በተገኙበት በተለያዩ የትምህርት መርሀ ግብሮች ያስተማራቸውን 7ሺ ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ ፕሮፌሰር ጣሰው በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ባለፉት 28 ዓመታት ወደ 50 የሚጠጉ የመንግሥትና ከ170 በላይ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተከፍተው ሀገሪቱ የምትፈ ልገውን የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት በልማቱ ዘርፍ የምታሳየውን ለውጥ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡ ፕሮፌሰር ጣሰው፣ መንግስት ባመቻቸው ዕድል ተጠቅመው በግሉ ሴክተር ከተሰማሩ በርካታ ተቋማት በተለይ ደግሞ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካሉት 4ቱ የግል ተቋማት አንዱና አንጋፋው አድማስ ዩኒቨርሲቲ እንደሆነ አስረድተ ዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው እስካሁንም ያስመዘገበውን አመርቂ ውጤትና የገነባውን መልካም ስም በማስጠበቅ ለጥራት፣ ለማህበራዊ አገልግሎትና ለጥናትና ምርምር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሞላ ፀጋዬ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የሀገሪቱን ሕዝብ በማገልገል፣ በመደገፍና በማልማት ከዚህን ቀደም ሲያደርገው የነበረውን እንቅስቃሴ አሁንም እያጠናከረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የማህበረሰብ አገልግሎት ስትራቴጂ ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝም አስረድተው፤ በዚህ መሰረት የተለያዩ የህብረተሰቡን ችግር የሚዳስሱ ጥናቶችን በማካሄድ የተለያየ የነፃ ስልጠናዎችንና ድጋፎችን መስጠቱንም አስረድተዋል፡፡ በዕለቱ የማዕረግ ተሸላሚ በመሆን ዋንጫ የተሸለመችው የአካውንቲንግና ፋይናንስ ክፍል ትምህርት ተማሪ ሩታ አካለወልድ እንደተና ገረችው፤ ለዚህ ውጤት የበቃችው ጠንክራ በመማሯ ነው፡፡ በተማረችው የትምህርት መስክ ለሀገሯና ለወገኗ በታማኝነት ማገልገል ትፈልጋ ለች፡፡ ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ሰባት ሺ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መርሐ ግብሮች ያስመረቀ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በዲግሪና በቴክኒክና ሙያ በመደበኛና በርቀት ትምህርት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በሶማሌ ላንድና በፑትላንድ ከ30 ሺ በላይ ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ ይገ ኛል፡፡ ላለፉት 20 ዓመታትም በመደበኛና በርቀት ትምህርት በዲግሪ፣በዲፕሎማና በሰርተፍኬት ከ70 ሺ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ይታወ ሳል፡፡አዲስ ዘመን ሀምሌ 16/2011
0
f38b0c8541b200b4d4e98d76f200e18d
f38b0c8541b200b4d4e98d76f200e18d
የኮቪድ ክትባት
እንግሊዝ አሜሪካዊው የመድኃኒት ምርምርና አምራች ኩባንያ ፋይዘር የሠራው ክትባት ለአጣዳፊ ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውል ፈቀደች።የሃገሪቱ የመድኃኒቶችና የጤና ጥበቃ ምርቶች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ከጀርመኑ ባዮንቴክ ጋር በመተባበር እየሠራ ያለው የፋይዘርን ክትባት አገልግሎች እንዲውል ዛሬ ፍቃድ መስጠቱ የኮሮናቫይረስ መከላከያ መድኃኒትን በመጠቀም እንግሊዝን ከምዕራቡ ዓለም የመጀመሪያ ያደርጋታል።ክትባቱ በሚቀጥለው ሣምንት መሰጠት የሚጀምር ሲሆን የብሄራዊው የጤና አገልግሎች ባልደረቦች እንዲሁም የአረጋዊያን መጦርያ ቤቶች ነዋሪዎችና ሠራተኞች የመጀመሪያዎቹ ተከታቢዎች እንደሚሆኑ ታውቋል።በዓለም ዙሪያ ወደ 64 ሚሊየን የሚሆን ሰው ለኮሮናቫይረስ መጋለጡንና ወደ አንድ ሚሊየን ተኩል የሚጠጋ ቁጥር ያለው ሰው በኮቪድ 19 መሞቱን በየዕለቱ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያሳያሉ።
1
73f039355e9b90c22085a3f4c846cbb0
73f039355e9b90c22085a3f4c846cbb0
በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ከሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት እና የሽግግር ወታደራዊ ም/ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሌ/ጄ መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራው ልዑክ ከሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት እና የሽግግር ወታደራዊ ም/ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሌተናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ጋር ተወያየ።በሱዳን ካርቱም በተካሄደው ሁለተኛው የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ጉዳዮች የከፍተኛ አመራር የፖለቲካ ውይይት ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ከሱዳን ሉዐላዊ ም/ቤት እና የሽግግር ወታደራዊ ም/ቤት ምክትል ሊቀ መንበር ሌተናንት ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ጋር ተወያይቷል።ልዑኩን የመሩት አቶ ደመቀ መኮንን ሲሆኑ በውይይቱም የሁለቱን ሀገራት ትብብርና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ርዕሶች ላይ መክረዋል።በተጨማሪም ወቅታዊ የሁለቱ ሀገራት ጉዳዮች እና አከባቢያው ሰላም ላይ ተወያይተዋል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
1
186e81d9a270bf2571ccd48b08fdcaae
186e81d9a270bf2571ccd48b08fdcaae
ሙላለም ጥላሁን የት ይገኛል ?
በአዲሱ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በእግርኳሱ ብቅ ካሉ ጥሩ አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ሙሉዓለም ጥላሁን የት ይገኛል ?ቀልድ አዋቂ ነው ይሉታል። ትውልድና ዕድገቱ አዲስ አበባ መርካቶ በልዩ ስሙ ጭድ ተራ በሚባል አካባቢ ነው። በሰፈር የጀመረው የእግርኳስ ህይወቱ ለአዲስ አበባ ከ15 እና ከ17 ዓመት በታች ምርጥ ቡድን ውስጥ ተመርጦ ባሳየው ድንቅ ብቃቱ በአሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ (ድሬ) አማካኝነት ዘጠናዎቹ መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ መድንን ተቀላቅሎ መጫወት ችሏል። በመድን ካሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በኋላ ድንቅ የውድድር ጊዜ ወደሳለፈበት ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ በተለይ በ2003 ኢትዮጵያ ቡና ፕሪምየር ሊጉ በአዲስ መልክ ከተጀመረ ወዲህ የመጀመርያውን ዋንጫ ሲያነሳ ትልቁን ሚና ከተወጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነበር። በኋላም በመከላከያ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ክለቦች እስከ 2010 ድረስ መጫወት ችሏል። ያለፉት 18 ወራትን ከሜዳ የራቀው ይህ አጥቂ እግርኳስ አቆምክ? ወይስ በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለህ? ስንል ጠይቀነው ተከታዩን ምላሽ ሰጥቶናል።“እግርኳስን አላቆምኩም። ለማቆምም ጊዜው አይደለም። የመጫወት አቅሙ አለኝ የ። እድሜም ገና ነው። አሁን የምገኘው ከባለቤቴ እና ከልጆቼ ጋር ጀርመን ሀገር ነው። ከሜዳ የራቅኹባቸው የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም በቀጣይ ነገሮች ሲስተካከሉ ወደ እግርኳሱ በቅርቡ እመለሳለው። ጎን ለጎን ከጀርመን ሀገር የተለያዩ ትጥቆችን በማምጣት በሀገሬ የንግድ ሱቅ በመክፈት እየተንቀሳቀስኩ እገኛለው።” ብሏል።ሶከር ኢትዮዽያ ከሙሉዓለም ጥላሁን ጋር አጠቃለይ የእግርኳስ ህይወቱ ዙርያ ሰፊ ቃለ መጠይቅ ያደረገች መሆኗን እየገለፅን በቅርቡ ለንባብ የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንጠቁማለን።
1
b1fea685c561fb5e7c6fcbcba74135ed
a2b8a155131560d17c782746d798e993
ኢትዮጵያ አዲስ የኢንቨስትመንት ህግ ማውጣት ለምን አስፈለጋት?
ከዚህ ቀደም ከተለመደው የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት በተለየ መልኩ ይከናውናል የተባለለት መርሐ-ግብር በቴሌቪዢን እንደሚተላለፍ ተገለፀ።የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አ/ማ ባስቀመጠው የውድድር ፕሮቶኮል መሠረት ለክለቦች ቅድሚያ ትዕዛዝን ካስተላለፈ በኃላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታኅሣሥ 3 እንደሚጀመር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ዘንድሮ ሊጉ ካለፉት ዓመታት በተለየ ተመልካች በማይገኝበት እና በቀጣዩ ሳምንት ይፋ በሚደረጉ በተመረጡ ሜዳዎች ላይ ብቻ ይደረጋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭትን የሚያገኘው ሊጉ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የሚከናወነው የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ቀኑ በይፋ ባይገለፅም ምናልባትም ከሁለት ሳምንታት በኃላ በቀጥታ ስርጭት ዓለምአቀፉዊ ይዘት ባለው መልኩ ለማስተላለፍ መዘጋጀታቸውን አቶ ክፍሌ ሰይፈ የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡“ፕሮግራሙን በጥሩ ሁኔታ ለማድረግ እያሰብን ነው፤ በቀጥታ ስርጭት ስለሚተላለፍ በጥሩ ሁኔታ ለማከናወን ጥረትም እያደረግን ነው፡፡ ከዚህ በፊት ከነበሩት እጅግ የተሻለ የዕጣ አወጣጥ ፕሮግራም ይኖረናል፡፡ ዲ ኤስ ቲቪን አናግረን ዕጣ ማውጫውን ቀንም ወስነን ነበር። ሆኖም እነሱን እየጠበቅን ስለነበር ለጊዜው አራዝመነዋል፡፡ በዚህም አዲስ መርሐ-ግብር አወጣጥን ትመለከታላችሁ። ከዚህ ቀደም የነበረው አወጣጥ 16ቱ ክለቦች ይመጣሉ፤ አንደኛ ሁለተኛ እየተባለ ይወጣል፡፡ አሁን ግን ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ዕጣ ማውጣትን ነው የምናደርገው። ለዚህም የተሻለ ቦታ እያዘጋጀን ነው፤ በቅርቡ እናከናውነዋለን።” ሲሉ ሥራ አስኪያጁ ገልፀውልናል፡፡
0
c22562d3ede168cbc0134a20f475e7f2
8459c7ab20e4d363c3e9913e18ba2e86
የኬንያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እየመከሩ ነው
በአገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የተማሪዎችን ቅበላን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመዋል። ተማሪዎችን ላልተወሰነ ጊዜ እንደማይቀበሉ ካስታወቁት ዩኒቨርስቲዎች መካከል አምቦ፣ ባህር ዳር ፣ ደብረ ማርቆስና ወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች ተጠቃሽ ናቸው። ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ባወጣው አስቸኳይ ማስታወቂያ ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 27 እና 28 2013 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲገቡ ጥሪ ማስተላለፉን አስታውሶ፤ "አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ጥሪ አድርገንላችሁ የነበራችሁ የዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች ወደፊት በአዲስ ማስታወቂያ ጥሪ እስከምናስተላልፍ ድረስ ባለችሁበት እንድትቆዩ እናሳስባን" ብሏል። አምቦ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ ጥቅምት 25 እና 26 2013 ዓ.ም ተጠርተው የነበሩ ተማሪዎች "አሁን በተፈጠረው አሁናዊ ሁኔታ የትራንስፖርት ችግር መፈጠሩን ተረድተናል። በመሆኑም በያላችሁበት ቆዩ" ብሏል። ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲው መድረስ ከቻሉ ግን ተማሪዎችን እንደሚቀበል በተጨማሪ ገልጿል።ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 30/ 2013 ዓ.ም ተማሪዎችን የመቀበል ጥሪ አስተላልፎ እንደነበረ አስታውሶ፤ "የምዝገባ ፕሮግራሙ የተለወጠ እና ላልተወሰነ ግዜ የተራዘመ መሆኑን አስታውቋል። ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲም "ተመራቂ ተማሪዎች አሁን ካለው ሀገራዊ ሁኔታ አንፃር ለደህንነታችሁ ባላችሁበት እንድትቆዩ" ሲል አሳስቧል።የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ ተገትቷል ተብሏል።ሚኒስቴሩ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባስተላለፈው መልዕክት በተመደቡበት ያሉ ተማሪዎች በግቢያቸው እንዲቆዩ እና በየግቢያቸው የሚሰጧቸውን ማሳሰቢያዎችም እየተከታተሉ እንድትንቀሳቀሱ ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ የተለየ ጉዳይ ሲያጋጥምም ለተቋሞቻቸው ሃላፊዎች እንድትሳውቁም በማለት መግለጫው አስፍሯል።ከአካባቢያቸው ያልተነሱ ተማሪዎች በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ በያሉበት እንዲቆዩም አሳስቦናል።
0
cb44ab8d34b416de08256f6bbbf4c5ee
bee44cd8ee851821dea4b9ab4001364d
ኮፓ አሜሪካ ዛሬ ማታ ዩናይትድ ስቴትስና ኮሎምቢያ ካሊፎርንያ ውስጥ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል
ዋይት ኃውስ በሰጠው መግለጫ፤ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዚህ ሳምንት ማብቂያ ገደማ ወደ ላቲን አሜሪካ ሊያደርጉ ያቀዱትን ጉዞ መሰረዛቸውን አመልክቶ፤ ሦርያን በተመለከተ የዩናይትድ ስቴትስን ምላሽ ለመከታተል መሆኑንም አስታውቋል።ለፕሬዚዳንት ትረምፕ ቀደም ሲል የተያዘው ዕቅድ በሊማ፣ ፔሩ በሚካሄደው 8ኛ የአሜሪካ ጉባዔ ላይ መካፈልና ወደ ቦጎታ፣ ኮሎምቢያ መጓዝ እንደነበርም ተገልጧል።በፕሬዚፋንት ትረምፕ ጥያቄ መሠረትም፣ ምክትል ፕሬዚደንቱ የላቲን አሜሪካውን ጉዞ እንደሚያደርጉ ተገልጧል።ፒሩ ውስጥ የሚካሄደው ጉባዔ የሚጀምረው የፊታችን አርብ መሆኑም ታውቋል።ፕሬዚዳንት ትረምፕ፤ ሦርያ በሽምቅ ተዋጊዎች ይዞታ ሥር በሆነው ምሥራቃዊ ጉታ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ ላደረሰችውና 40 ሰዎች ለሞቱበት የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቃት፣ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል።
0
40475206f9456329fcbf881d7bd176b8
f0f2d0d99e155bdc4873b199328ca869
የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የበጎ ፈቃድ ባለሙያዎች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ።አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚገኘውን እና በሃገር ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠሪያና የመረጃ ማዕከል ጎብኝተዋል።በተጨማሪም በኢንስቲትዩቱ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የስልጠና እና መሰል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።በጉብኝቱ ወቅት የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።በለይኩን አለም ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision
0
67c79c1beef30824adb143a0a63775d1
3b81cdcd454078cd70881ff1f8c188fa
የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት ከ35ዓመት አገልግሎት በኋላ ሥልጣን ለቀቁ
የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለእንግሊዝ ኤምባሲ ኦፊሴላዊ ደብዳቤ ስለመላክ አለመላኩ ለጊዜው አይታወቅም። ፕሬዚዳንት ትረምፕ ባወጡት የትዊተር መልዕክት ግን ዲፕሎማት ኪም ዳሮችን እንደማያውቋቸው፣ ዲፕሎማቱ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተወደዱ ወይም በመልካም የሚታዩ ሰው አለመሆናቸውን ገልፀዋል።እንግሊዛዊያኑ ግን አምባሳደር ዳሮች ወደ ሃገራቸው የሰደዱትን ዲፕሎማሲያዊ ጦማር አስሻልኮ ያወጣው ማን እንደሆነ ለማወቅ እየማሰኑ ናቸው።“ነገሩ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ማግኘት አለብን” ያሉት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀረሚ ኸንት መልዕክቱ የትና እንዴት እንደሾለከ ያወቁ ጊዜ ግን መዘዙ ብርቱ እንደሚሆን አስገንዝበዋል።ዋሺንግተን የሚገኙት የእንግሊዝ የንግድ ሚኒስትር ሊያም ፎክስም በጉብኝታቸው ወቅት ከፕሬዚዳንቱ ልጅና አማካሪ ኢቫንካ ትረምፕ ጋር ሲገናኙ “ይቅርታ” እንደሚሉ ተናግረዋል።የአምባሳደሩ መልዕክት የታሰበው ለእንግሊዝ ከፍተኛ ሚኒስትሮችና የመንግሥት ሠራተኞች በመሆኑ “ሹክ” ባዩም እዚያው የሎንዶን ፖለቲከኞችና ባለሥልጣናት መካከል ያለ እንጂ ከውጭ መግሥት የሚጠረጠር አለመሆኑን ባለሥልጣናቱ ያምናሉ።
0
f09cfe317fc45b85aa7f17ee497edeb8
a726dbd3775fb20043e752d6e4631340
” ኳሱን ልወረውር ስል ከጓንቴ ጋር ተጣበቀ… ” ዘውዱ መስፍን
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 17/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኦሮሚያ ክልል እና በሌሎችም አካባቢዎች ከሰሞኑ የተከሰተውን ሁከትና ግርግር ለማረጋጋት እየሠሩ መሆኑን የደቡብ እና የምሥራቅ ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች አስታውቀዋል፡፡በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ሙዘይ መኮነን ለአብመድ እንደተናገሩት በባሌ ሮቤ፣ ዶዶላ፣ አዳማ እና ሌሎችም አካባቢዎች ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቅንጅት እየሠሩ በመሆናቸው አንጻራዊ ሠላም እየታዬ ነው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ከትናንት ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ግጭት እንዳልተከሰተም ነው ጄኔራል ሙዘይ ያስረዱት፡፡ሠራዊቱ እያደረገ ባለው ጥረትም በዶዶላ ከተማ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው ያሉትን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረሰብ ክፍሎች ሕጋዊ ከለላ እንዲገኙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ይህንኑ ሐሳብ በችግሩ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችም ለአብመድ አረጋግጠዋል፡፡ ስጋት ይታይባቸዋል በሚባሉ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት እንዳይከሰትም የቅድመ መከላከል ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል ጄኔራሉ፡፡የምሥራቅ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዘውዱ በላይ ደግሞ በሀረር፣ ድሬዳዋ እና አሰበ ተፈሪ ከተሞች ኅብረተሰቡን እያረጋጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው ሠላማዊ እንቅስቃሴዎች እየታዩ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮችንም ከኅብረተሰቡ ጋር በውይይት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው›› ብለዋል ጄኔራል ዘውዱ፡፡ እየታዬ ያለው አንፃራዊ ሠላም እንዲደናቀፍ የሚሠሩ ግለሰቦች እንዳሉ ማረጋገጣቸውንም ለአብመድ ጠቁመዋል፡፡ግለሰቦቹ ሠራዊቱን ከሕዝቡ ለመነጠል እየተጠቀሙበት የሚገኘውን አደናጋሪ ሐሳብ ኅብረተሰቡ ውድቅ በማድረግ ከሠራዊቱ ጎን መቆም እንደሚጠበቅበትም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ዘጋቢ፡- ኃይሉ ማሞ
0
7f956751e8b92ff9ce3a9dc42efffaf2
7f956751e8b92ff9ce3a9dc42efffaf2
ሀዋሳ ከተማ ተከላካይ አስፈረመ
ምኞት ደበበ ሀዋሳ ከተማን ተቀላቀለ፡፡የቀድሞው የደደቢት ተጫዋች ያለፉት አራት ዓመታትን በአዳማ ከተማ በመጫወት ድንቅ ጊዜያትን ያሳለፈ ሲሆን ከወራት በፊት ውሉ ከአዳማ ጋር በመጠናቀቁ የቀድሞው አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለን ጥሪ ተከትሎ ለሀዲያ ሆሳዕና በነሀሴ ወር አጋማሽ ቅድመ ስምምነት ፈፅሞ የነበረ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ግን ለሀዋሳ ከተማ ፊርማውን አኑሯል፡፡ምኞት ከዝውውሩ በኋላ “ጥሩ ስሜት ነው የተሰማኝ። ከሀዋሳ ጋር ጥሩ ጊዜ እንደማሳልፍ ተስፋ አደርጋለሁ። ከአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ጋርም ለመስራት በመምጣቴ እጅግ ደስታን ፈጥሮልኛል።” በማለት ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡
1
df87aff697d7e91649fb27d3708dad84
df87aff697d7e91649fb27d3708dad84
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሁመራ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጣረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የህውሓት ቡድን ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን የሁመራ አውሮፕላን ማረፊያን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። በስሜን እዝ የ5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉ አለም አድማሱ፥ መከላከያ ሃይሉ የተፈፀመበትን ታሪካዊ ክህደት እና ጥቃት አክሽፎ ሁሉን አቀፍ ጥቃት እያካሄደ ነው ብለዋል። ህግ የማስከበር ኦፕሬሽኑን በድል እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በምእራብ ትግራይ በኩል ህግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ ያለው የኢፌዴሪ መከላከያ ሃይል እስካሁን የህወሓት ታጣቂ ቡድን ስፍሮባቸው የነበሩ ከተሞችን ሙሉ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥራል። በርካታ ህውሓት ያደራጃቸው የልዩ ኃይል፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። በዚህም የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት እስካሁን ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ መቆጣጠሩ ይታወቃል።
1
3415f2429abfc589215e7aba79f3168c
af72a2fa3e906f850e161a74c75fcf4b
በደቡብ ሱዳን በተቀሰቀሰ ውጊያና የምግብ ዕጥረት ብዙ ሺህ ህዝብ ወደ አጎራባች ሃገሮች እየተሰደደ ነው
በደቡባዊ አፍሪካ በ45 ሚልዮን የሚገመቱ ሰዎች፣ የምግብ ዋስትና እንደማያገኙ፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ጠቁሟል። በቂና አቅማቸውን የሚመጥን ተመጣጣኝ ምግብ የማያገኙት ሰዎች ብዛት፣ ካለፈው አመት በ10 ከመቶ ከፍ ማለቱን፣ የምግብ ፕሮግራሙ አክሏል።ለምግብ ዋስትናው እጦት ዋና ምክንያት የሆኑት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ክስተት፣ ከአየር ንብራት ለውጥና የበርካታ ሃገሮች ኢኮኖሚ በመንገዳገድ ላይ የሚገኝ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ ነው ተብሏል።ከሁሉም የተጎዳችው ግን ዚምባብዌ መሆንዋ ታውቋል። በሀገሪቱ የምግብ ዋስትና እጦት የገጠማቸው ሰዎች፣ እስከ ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ፣ 8.6 ሚልዮን ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። የደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ ለሚያደርሰው ጉዳት ተጋላጭ መሆኑን፣ በደቡባዊ አፍሪካ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ሎላ ካስትሮ ተናግረዋል።
0
a97cd89b654b3939c4bb487cf4167d60
5f2943e823531949ffdd3ecd5dae8515
ባለፉት 24 ሰዓታት ለ912 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 7 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ5 ሺህ 324 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 474 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 99 ሺህ 675 ደርሷል።በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰኣት 818 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ በአጠቃላይም 59 ሺህ 766 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 523 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺህ 384 ሰዎች መካከል 316 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 526 ሺህ 221 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።
0
df44044631f5b3e115c2e4df3da0ba45
7f08503a07bd9693016d32e0bd51339a
ጠ/ሚ ሼንዞ አቤ በጤና ምክንያት ከሥልጣን እንደሚሰናበቱ አስታወቁ
በአፍሪካ የጤና ዘርፍ ላይ በሚመክረው ‹‹የአፍሪካ ቢዝነስ ሔልዝ ፎረም 2019›› በአኅጉሪቱ በየዓመቱ የ66 ቢሊዮን ዶላር ለጤና አገልግሎት የሚያስፈልግ የበጀት ጉድለት እንደሚታይ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ቬራ ሶንግዌ (ዶ/ር) አስታወቁ። በአፍሪካ በግሉና በመንግሥት አጋርነት በኩል እስከ 450 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያስገኙ ዕድሎች እንዳሉም አስታውቀዋል። በኢትዮጵያም የዚህ ዓይነቱ አጋርነት ላይ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ዝግጅት እየተደረገበት እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ያለውና በኢኖቬሽን የታገዘ የጤና ምርመራ አገልግሎት በጥቁር አንበሳና በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታሎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ከአምስት ዓመት በታች የሕፃናት ሞትን በሁለት ሦስተኛ መጠን በመቀነስ ግቡን ከሦስት ዓመታት ቀድማ ማሳካቷን፣ በጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች አማካይነትም የጤና አገልግሎቶችን ለ70 በመቶው ሕዝብ ማዳረስ ስለመቻሏ በማውሳት፣ ‹‹ጤና ይስጥልኝ›› በማለትና ለታዳሚያኑ በማብራራት የጀመሩትን ንግግር በጤና ይስጥልኝ ዘግተዋል። የጅቡቲና የቦትስዋና ፕሬዚዳንቶች፣ የግብፅና የኬንያ ጤና ሚኒስትሮችም ስለየአገሮቻቸው ጤና ዘርፍ ተናግረዋል። የአሊኮ ዳንጎቴ ልጅ ሐሊማ ዳንጎቴም የአባቷ ፋውንዴሽን ስለሚያከናውናቸው እንቅስቃሴዎች ገልጸዋል።
0
efb476735e73c455ae22861ca6a7b1be
aeb5e76f699b9b76827ffd115ebe8f02
“ወንጀል ያልሰራ ሰው ነጻነት ይኑረው በሉ እንጅ የኔ ወገን አትበሉ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀደምት አርበኞች እግር እንደ መተካታችን እኛ የዚህ ትውልድ አባላትም የአንድነት፣ የሰላምና የብልጽግና ፋና ወጊዎች ነን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ 79ኛው ዓመት የኢትዮጵያዊያን አርበኞች የድል በዓል አስመልክተው በፌስቡክ ገፃቸው መልእክት አስተላልፈዋል።የመልእክታቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ከዘመኑ ቀድሞ ነግቶ የጨለመ፤ ጀግና ወድቋል ከፊት እኛን እያለመ ስለኛ እያሰበ።ከሁሉም ነገር በላይ ሀገርና ሕዝብ አስቀድመው ለነጻነታችን ዋጋ የከፈሉትን አባት እና እናት ዐርበኞች ዛሬ እንዘክራለን።ስለ ሀገራቸው እና ስለ ሕዝባቸው ሲሉ ተዋግተዋል። ለኢትዮጵያ የነበራቸው አቻ የለሽ ፍቅር በደም እና በሕይወት መሥዋዕትነት ተገልጧል። ይህንን ያደረጉት እንዲያው ለዝና ሳይሆን በአንድነት ለምትቆም ሉዓላዊት ሀገር ነው።በቀደምት አርበኞች እግር እንደ መተካታችን፣ እኛ የዚህ ትውልድ አባላትም የአንድነት፣ የሰላም እና የብልጽግና ፋና ወጊዎች ነን። እናቶቻችን እና አባቶቻችን የወሰኑት ታሪካዊ ውሳኔ ነጻነት፣ ሀገርና ሉዓላዊ ሕዝብ ከምንም በላይ መሆናቸውን አሳይቶናል።ከታሪካችን በመማር ተስፋ መቁረጥን ሳይሆን ዕድገትን፣ ጥላቻን ሳይሆን ፍቅርን፣ኪሣራን ሳይሆን ትርፍን፣ ቀውስን ሳይሆን ብልጽግናን እናያለን፡ክብር ለአርበኞቻችን!
0
143dbc059c01e837b906369267aee07c
7aba32223b4401931ac1fc4dbe9cb23b
የዘንድሮ ኢሬቻ በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
በዘንድሮው ዓመት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ካለፈው ዓመት በተለየ መልኩ ለማክበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ አግማስ በበዓሉ ወቅት የሚገኘው ታዳሚ መርኃግብሩን እንዲከታተል ቦታ ከማዘጋጀት ጀምሮ ሌሎች የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡በዓሉ በሚከበርበት ወቅት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል የጤና ሚኒስቴር ያወጣቸውን መመሪያዎች ለመተግበር እንዲያስችል ኮሚቴ መዋቀሩን የገለፁት ምክትል ከንቲባው፣ የታዳሚው ደህንነት እንዲረጋገጥ በፀጥታ ሁኔታው ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡በዓሉን ለመታደም የሚመጡ እንግዶች በሚያርፉበት አካባቢ የጥንቃቄ ስራ በመስራት ከበዓሉ ጎን ለጎን ታዳሚው ራሱን በመጠበቅ በዓሉን እንዲያከብር ዝግጅት ከመደረጉ በተጨማሪ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ ተሾመ ገልጸዋል፡፡በኢትዮጵያ በድምቀት ከሚከበሩ የኃይማኖት ክብረ በዓላት መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ሲሆን፣ በበዓል አከባበሩ ውስጥ የተለያዩ ባህላዊ እሴቶች ይተዋወቁበታል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ሀገሪቱ በዓሉን በምታከብርበት ወቅት ከሀገር ውስጥ እና ከአለም አቀፍ ጎብኝዎች የምታገኘው ገቢ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው፡፡(በሱራፌል መንግስቴ)
0
9fe2a8504ac1acf0f1f0c41891280b29
5adb817ef628035bd33306ed53b7eaf5
በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ተሽከርካሪዎች 85 በመቶ የሚሆኑት የመድን ዋስትና እንዲኖራቸው ታቅዷል
ዶ/ር አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመመረጣቸው 84 በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያውያን ደስተኞች መሆናቸውን የጠቆመው አንድ ጥናት፤ 88 በመቶው ዶ/ር አብይ ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል፡፡ጥናቱን ያካሄደው በማናጅመንትና የማህበራዊ ጥናትና ምርምሮች አማካሪነት የሚሠራው “ዋስ ኢንተርናሽናል” ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ፤ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በዶ/ር አብይ አህመድ መመረጥ ደስተኛ መሆኑንና ለውጥ ያመጣሉ ብሎ እንደሚያምን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ጥናቱ በአዳማ፣ አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ድሬደዋ፣ ሃዋሳ፣ ጅግጅጋ፣ መቀሌ፣ ደሴ፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ነቀምትና ደብረ ብርሃን ከተሞች ላይ የተካሄደ ሲሆን በጥናቱ ላይ በአጠቃላይ 1505 ሠዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡ዶ/ር አብይ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመመረጣቸው 94 በመቶ የአዳማ ነዋሪዎች ደስተኛ መሆናቸውን ሲገልፁ፤ ከባህርዳርና ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች 84 በመቶ ያህሉ ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል ይላል - ጥናቱ፡፡ 91 በመቶ የሚሆኑት የመቀሌ፣ 82 በመቶ የነቀምት፣ 89 በመቶ የጅማ፣ 84 በመቶ የጅግጅጋ፣ 88 በመቶ የሃዋሳ 76 በመቶ የጎንደር እንዲሁም 70 በመቶ የድሬደዋ ነዋሪዎች በዶ/ር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መመረጥ ደስታ እንደተሠማቸው ጥናቱ ጠቁመዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ 88 በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያውያን ጠ/ሚኒስትሩ ለውጥ ያመጣሉ ብለው እንደሚያምኑ ተጠቁሟል፡፡ 97 በመቶ የአዳማ፣ 87 በመቶ የአዲስ አበባ፣ 88 በመቶ የባህር ዳር፣ 88 በመቶ የደሴ፣ 90 በመቶ የደብረብርሃን፣ 85 በመቶ የጎንደር፣ 96 በመቶ የጅግጅጋ፣ 90 በመቶ የሃዋሳ፣ 92 በመቶ የጅማ፣ 94 በመቶ የመቀሌ እንዲሁም 91 በመቶ የነቀምት ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአመራር ጊዜያቸው ከፍተኛ ለውጥ ያመጣሉ ብለው የሚያምኑ ሲሆን ከድሬደዋ ነዋሪዎች 71 በመቶ ያህሉ ለውጥ እንደሚያመጡ ያምናሉ ብሏል- “የዋስ ኢንተርናሽናል” ጥናት፡፡ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በ4 እጅ በዶ/ር አብይ የለውጥ ተስፋ የሰነቁ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጠ/ሚኒስትሩ በእጅጉ ተስፋ አድርገዋል ይላል- የጥናት ሪፖርቱ።
0
fb09d8220eeb8c01a6b0a125104379cc
3859406375e4dfd0bc31e28700ef0e8f
ድምፃዊ ጊታሪስትና መምህር መስፍን አበበ (1944 - 2008)
ከቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ ባለሥልጣናትና ነጋዴዎች ስም ዝርዝርማክሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. መንግሥት እምነት በማጉደልና ሥልጣንን ያላግባብ በመገልገል በአገር ላይ ከ1.15 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ያላቸው ተጠርጣሪዎች ስም ዝርዝር ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣንኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌኢንጂነር ዋሲሁንኢንጂነር አህመዲንሚስተር ሚናሽ ሌቪ (ትህዳር ኮንስትራክሽን ኩባንያ)(ከ198 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንአቶ አብዶ መሐመድአቶ በቀለ ንጉሤአቶ ገላና ቦሪአቶ የኔነህ አሰፋአቶ በቀለ ባልቻአቶ ገብረ አናንያ ፃዲቅ(ከ646 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)መተሐራ ስኳር ፋብሪካአቶ እንዳልካቸው ግርማወ/ሮ ሰናይት ወርቁአቶ አየነው አሰፋአቶ በለጠ ዘለለው(ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴርአቶ ሙሳ መሐመድአቶ መስፍን ወርቅነህአቶ ዋሲሁን አባተአቶ ሥዩም ጎበናአቶ ታምራት አማረአቶ አክሎግ ደምሴአቶ ጌታቸው ነገራዶ/ር ወርቁ አብነት (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)አቶ ታመነ ደባልቄ (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)አቶ ዮናስ መርአዊ (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)(2.2 ሚሊዮን ዶላር ወይም 51.2 ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ)ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካአቶ አበበ ተስፋዬአቶ ቢልልኝ ጣሰው(ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)አቶ አበበ ተስፋዬአቶ የማነ ግርማይ (ጂዋይቢ ኮንስትራክሽን ኩባንያ)አቶ ዳንኤል አበበ(ከ20 ሚሊዮን በላይ ጉዳት በማድረስ)አቶ ፈለቀ ታደሰአቶ ኤፍሬም ታደሰ(ከ10 ሚሊዮን በላይ ጉዳት በማድረስ)ኦሞ ኩራዝ ስኳር ቁጥር ፋብሪካአቶ መስፍን መልካሙአቶ ሰለሞን ከበደሚስተር ሊዮ (የቻይና ጁጂአይሺኢ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ)አቶ ፀጋዬ ገብረ እግዚአብሔር ብርሃነወ/ሮ ሳሌም ከበደ(ከ184 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)
0
3a227fc21f82fb5833295a3e4b57d8dd
ed665b50b9d2963e043df6b6f04065a0
ፌደራሊዝም ግጭቶችን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት አስተማማኝ ነው – ሚኒስትር ከበደ ጫኔ
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 05/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሰባት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዩኒቨርሲቲዎችና አንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከሰተዉ የፀጥታ ችግር በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና ግጭቱ እንዲቆም በጋራ እንደሚሠሩ አስታወቁ፡፡ ፓርቲዎቹም የአማራ ዴሞክረታሲያዊ ፖርቲ (አዴፓ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ)፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ (አብፓ)፣ የአማራ ማኅበራዊ ራዕይ ግንባር (አማራ) ናቸው፡፡የሁለቱ ክልል ሕዝቦች ለውጥ ለማምጣት በአንድነት የታገሉ እና ሊነጣጠል የማይበማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች መፈጸም ጉዳቱ የጋራ በመሆኑ መንግሥትና ሁሉም ኅብረተሰብ ለማስቆም እንዲረባረብም ተጠይቋል፡፡ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዳሉትም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ያለዉን አስተሳሰብ ለማቀራረብና ሕዝብ በእኩል ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ለማመቻቸት ሁሉም ኃላፊነት እንዳለበት አስታዉሰዋል፡፡
0
91e5afe49607e233a920abd5f66aadb4
3e790c9d3843aa2039ae0d45f6bb54ee
ኢስቶኒያ ቆሻሻ ከውጭ አገራት እየገዛች ነው
ሕንድ ሩሲያ ሠራሽ የአየር መከላከያ ሥርዓት መግዛቷ እንዳሳሰባት ፓኪስታን አስታወቀች። ሕንድ ከሩሲያ ላይ ኤስ - 400 ትረምፍ መከላከያዎችን በመያዟ ምክንያት ስላደረባት ሥጋት ኢስላማባድም ተመጣጣኝ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።ሩስያና ሕንድ በቅርቡ የተፈራረሙት የ5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የተምዘግዛጊ ሚሣይል መከላከያ ሥርዓት እጅግ የረቀቀ እንደሆነ ባለሙያዎች ተናግረዋል።ሕንድ የአየር ክልሏን ከቻይናና ከፓኪስታን ጥቃት ለመከላከል ስትል እየገዛች ያለችው የከፍተኛ ሥፍራዎች መሣሪያ እንደሆነ ኒው ዴልሂ አስታውቃለች።አድራጎቱ ደቡብ እሥያን ወደ አዲስ የጦር መሣሪያ እሽቅድምድም ሊወስድ የሚችልና አካባቢውን ወዳለመረጋጋት የሚወስድ ነው ሲል የፓኪስታን መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል። ሩሲያ ሠራሽ የሆነው የመከላከያ ሥርዓት ከማንኛውም የአየር ጥቃት መጠበቅና ከሰላሣ ኪሎ ሜትር ከፍታ እስከ 4መቶ ኪሜ ሊወነጨፉ የሚችሉ ሚሣይሎችን ማቆም የሚችል የተራቀቀ ቴክኖሎጂ እንደሆነ ታውቋል።
0
004e8eed21f41bce31e122f2d9441983
b634de1874b624c3e8a6ae6ac9dd5386
በስፖርት አመራርነት የሚታወቁት አቶ ያሚ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የቀድሞው የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ዚን ኢል አብዲን ቢን አሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡የቀድሞው ፕሬዚዳንት በ83 ዓመታቸው በስደት እየኖሩ ባሉበት ሳዑዲ አረቢያ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡ቱኒዚያን ለ23 ዓመታት የመሩት ቢን አሊ ሀገሪቱ እንድትረጋጋ እና እንድትበለጽግ አድርገዋል ተብለው በብዙዎች ይነገርላቸዋል፡፡በአውሮፓውያኑ 2011 በሀገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ አመፅ በአረብ ሀገራት ሁሉ ተቀጣጥሎ ለእርሳቸውና ለሌሎች የአረብ ሀገራት ባለስልጣናት የስልጣን ማክተሚያ ምክንያት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡የቢን አሊ የቀብር ስነስርዓት በሳዑዲ አረቢያ እንደሚፈፀም ጠበቃቸው ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግሯል፡፡
0
379d15b51216ba5042e0c54ec3f06f1c
85f6290f4fca8dc8fa3ea8e782b713d0
የአቶ ገብሩ አሥራት የኢትዮጵያ ግምገማ
አቶ ገብረእግዚአብሔር ታደለ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ኢዴፓ የመቀሌ - ትግራይ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ናቸው።ከዘጋቢአችን ግርማይ ገብሩ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በክልሉ ለሕዝብ የፓርቲአቸውን ፕሮግራም ለማስተዋወቅ ያደረጉት ጥረት አጥጋቢ እንዳልነበረ ገልፀዋል። ምክንያቱንም ሲያስረዱ በእርሣቸውና አባሎቻቸው ላይ ከመንግሥት ካድሬዎች ዛቻና ወከባ እንደደረሰ አስረድተዋል።የተቃዋሚው ኢዴፓ አባል ሰለሆኑም በቤተሰባቸው ላይ ማግለልና ወከባ እንደሚደርስ ገልፀው ለምሳሌ የአባታቸው የእህት ልጅ ሲሞቱ በቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ወቅት ባህሉ እንደሚፈቅደው አባታቸው የሚደግፋቸው እንዳጡ ገልፀዋል።የመቀሌው የኢዴፓ መሪ ለግርማይ ገብሩ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ያድምጡ።
0
519c7dd5f7c1968b4f525e9a1a35ff0b
519c7dd5f7c1968b4f525e9a1a35ff0b
ኪም ጆንግ ኡን በደቡብ ኮሪያ ላይ ሊወስዱት የነበረውን ወታደራዊ እርምጃ አገዱ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰሜን ኮሪያ በጎረቤት ደቡብ ኮሪያ ላይ ልትወስድ የነበረውን ወታደራዊ እርምጃ ማገዷን አስታወቀች።የገዥው ፓርቲ ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን በቪዲዮ ኮንፈረስ የታገዘ ውይይት ካደረገ በኋላ ፒዮንግያንግ አስባው የነበረውን ወታደራዊ እርምጃ ማቋረጧን አስታውቋል።በቅርብ ሳምንታት ሁለቱ ሃገራት በሚዋሰኑት ድንበር ፀረ ሰሜን ኮሪያ ይዘት ያላቸው ፅሁፎች በስፋት ሲሰራጩ ነበር።ፒዮንግያንግም ድርጊቱ ሃገራቱ የገቡትን ስምምነት የጣሰና ብሄራዊ ክብርን የሚነካ ነው በማለት ኮንናዋለች።ለደቡብ ኮሪያዎች ምላሽ ለመስጠትም በድንበር አካባቢ ፀረ ደቡብ ኮሪያ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች የሚያስተላልፉ የድምጽ ማጉያዎችን ተክላም ቆይታለች።ይህን ተከትሎም ሁለቱ ሃገራት ከረር ያለ ፍጥጫ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል።በተጨማሪም ፒዮንግያንግ በደቡብ ኮሪያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል እቅዷን ነድፋ ስትንቀሳቀስ መቆየቷን መረጃዎች ያመላክታሉ።አሁን ላይም ማዕከላዊ ኮሚሽኑ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከእርምጃ መታቀቡን ገልጿል።ከዚህ ባለፈም በድንበር አቅራቢያ የተተከሉ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ድምጽ ማጉያዎችን ለማንሳት ተስማምታለች።ምንጭ፡- አልጀዚራ
1
c735b986c9cc595f3856edd108bf982e
174e16e1aa1ece430cc338ceebc5f2bc
ባለሥልጣኑ 100 ጥንታዊ የብራና መጻሃፍትን ለብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሓፍት ኤጀንሲ አስረከበ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና መጽሐፍት ኤጀንሲ በለይቶ ማቆያ ለሚገኙ ሰዎች የሚሆኑ 6 ሺህ መጽሐፍትን ለጤና ሚኒስቴር ዛሬ ለገሰ።መጽሐፍቱ በተለያዩ ዘውጎች የተጻፉ ሲሆኑ፥ ወደ ለይቶ ማቆያ የሚገቡ ሰዎች በቆይታቸው ወቅት ራሳቸውን በንባብ ለማበልጸግ እንደሚያስችሏቸው ተገልጿል።መጽሐፍቱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ለጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ አስረክበዋል።ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ወቅት ዜጎች ይህን አስቸጋሪ ወቅት በንባብ እንዲያሳልፉ ኤጄንሲው የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፥ የዛሬው ልገሳ አንደኛው መሆኑን አንስተዋል።ወደ ለይቶ ማቆያ የሚገቡ ሰዎች ሃሳባቸው በተለያዩ ጉዳዮች እንዳይወሰድና ለጭንቀት እንዳይዳረጉ መጽሐፍቱ ሚና እንዳላቸው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፥ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ለይቶ ማቆያዎች እንደሚያገለግሉም ገልጸዋል።በቀጣይ ለክልሎች ተመሳሳይ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አውስተው፥ መጽሐፍቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በግለሰብ ደረጃ የሚሰጡ እንጂ በውሰት እንደማይሰጡም አስረድተዋል።ግለሰቦቹ በለይቶ ማቆያዎች የነበራቸውን ቆይታ ሲያጠናቅቁ ወደየቤታቸው ይዘዋቸው እንደሚሄዱ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።ወይዘሮ ሳህረላ በበኩላቸው በቅርቡ ወደ ለይቶ ማቆያ የገባች አንዲት ኢትዮጵያዊት በተፈጠረባት ጭንቀት ምክንያት ሕይወቷን ማጥፋቷን አስታውሰው፥ መጽሐፍቱ መሰል ችግሮችን በመፍታት ረገድ ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።ለይቶ ማቆያዎች የንባብ ባህል እንዲዳብር እገዛ እንደሚያደርጉ ጠቁመው ኤጀንሲው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።#FBCየዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
0
a17e23223dbb5b8794785d75794bf676
476d72974781f1a709b3c8f27251775b
ኢትዮጵያ ከደቡብ ኮሪያ እድገት ብዙ መማር እንደምትችል አፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ገለፁ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “የልማት አርበኞች” በሚል ርእስ በአቶ አባዱላ ገመዳ የተፃፈው መጽሃፍ በዛሬው እለት ተመረቀ።መፅሃፉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል መንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው እለት ተመርቋል።“የልማት አርበኞች” የሚል ርእስ ያለው መፅሃፉ አቶ አባዱላ ገመዳ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግት ርእሰ መስተዳድር በነበሩበት ወቅት በክልሉ በተሰሩ የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑም ተነግሯል።በተመሳሳይ በመፅሃፍ ምርቃቱ ወቅት በክልሉ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።በዚህም ባለፉት ዓመታት በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ልምድ እና እስካሁኑ ጊዜ ያለው የልማት እንቅስቃሴ በመድረኩ ላይ ቀርቧል።
0
ae0c284240738d2e1f120419cb4b2c3a
b88e02801a565f3ccf3b1f124acc4fc1
የፋይናንስ ዘርፉን ለዳያስፖራዎች ክፍት የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ከፀደቀ በኋላ 42 የፌዴራል ፀረ ሙስናና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ዓቃቢያነ ሕግ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሲመደቡ፣ ሃያ ስምንቱ ሳይመደቡ መቅረታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡እንደ ምንጮች ገለጻ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተመድበው ከነበሩት ሁለቱ እንደገና ወደ ፌዴራል ፀረ ሙስናና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ተመልሰዋል፡፡በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ መሠረት የፀረ ሙስና የዓቃቤ ሕግ ሥራ ኮሚሽን ሥነ ምግባር ላይ እንዲያተኩርና ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንዲሄድ ተደርጓል፡፡ ፀረ ሙስና ኮሚሽንም ከመጪው አዲስ ዓመት ጀምሮ የረዥምና የአጭር ጊዜ ዕቅድና አሠራሮቹን መከለሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተመደቡት ዓቃቢያነ ሕግ ምናልባትም ሌሎች የሕግ ባለሙያዎች በሚሠሩባቸው ዘርፎች ተመድበው በኮሚሽኑ እንዲቀሩ ሊደረግ እንደሚችል የሚገልጹት ምንጮች፣ ዓቃቤያኑ ሕጉ ያለመመደባቸው ምክንያቱ አለመታወቁን ይጠቁማሉ፡፡ፍትሕ ሚኒስቴርን የሚያፈርሰውና በምትኩ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንዲቋቋም የሚያስችለው ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ የቀረበው መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ነበር፡፡ የረቂቅ አዋጁ አባሪ የሕግ ማስከበር ተግባር በዓቃቤ ሕግ የሚከናወን መሆኑን፣ ይህ የዓቃቤ ሕግነት ሥራ ግን ተበታትኖ በተለያዩ ተቋማት እየተሠራ እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡ ከተቋማቱም ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ እንዲሁም የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን እንደሚጠቀሱ፣ ይህ ደግሞ ወጥነት እንደሚጎለው ይጠቁማል፡፡ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሕግ ጉዳዮች የፌዴራል መንግሥት ዋና አማካሪና ተወካይ ሆኖ እንደሚሠራ የሚገልጸው ረቂቅ የማቋቋሚያ አዋጁን የሕግ፣ የፍትሕና የአስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ ከሰማ በኋላ ሚያዝያ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ፓርላማው አፅድቆቷል፡፡
0
1fcacdbca467705a98a93b488909b987
b4da0717540e04ded505ce5b0b9694dd
በ2010 በጀት ዓመት ኦዲት 129 የኦዲት ግኝት መታየቱ ተገለጸ
ለመጀመርያ ጊዜ በተሟላ ደረጃ መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎችን ኦዲት በማድረግ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኦዲት አድማሱን በማስፋት በባለ ኮከብ ሆቴሎችና በኢንዱስትሪዎች ላይ ቆጠራ ሊያካሂድ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1995 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ኅዳር 2004 ዓ.ም. የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው እስኪወጣበት ጊዜ ድረስ፣ ላለፉት 15 ዓመታት በኢንዱስትሪ ዞኖችና በተናጠል ለሚካሄዱ ፋብሪካዎች በርካታ ቦታዎችን ሰጥቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለበርካታ ሆቴሎች ግንባታ የሚሆን ሰፋፊ ቦታዎችንም እንዲሁ አቅርቧል፡፡ነገር ግን አስተዳደሩ በሰጣቸው ቦታዎች ላይ ስለተከናወነው ልማትም ሆነ፣ የተከናወኑት ግንባታዎች በውላቸው መሠረት ስለመካሄዳቸው በትክክል የተጠናቀረ መረጃ እንደሌለ ይገልጻል፡፡በከተማው ውስጥ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችንና ባለ ኮከብ ሆቴሎችን ቁጥር ለማወቅ፣ በአግባቡ ሥራዎችን ባላካሄዱት ላይ ደግሞ የማስተካከያ ዕርምጃ ለመውሰድ ኦዲት እንደሚከናወን ለማወቅ ተችሏል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር፣ ‹‹እስካሁን ግንባታ ሳይካሄድባቸው ለዓመታት ታጥረው የቆዩ ከአራት ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ ቦታ መልሰን ወስደናል፤›› ብለዋል፡፡‹‹‹ይህ ትልቅ ሥራ ነው፤›› በማለት ምክትል ከንቲባው ገልጸው፣ በቀጣይ ደግሞ በሆቴሎች፣ በኢንዱስትሪዎች፣ በድንጋይ ማምረቻ ካባዎች፣ እንዲሁም በመኖሪያ ቤቶች ላይ ኦዲት ተካሂዶ ዕርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሥራው ውስብስብ በመሆኑ የሚካሄደው ኦዲት አንዴ ብቻ ሳይሆን ሦስት፣ አራት ጊዜ ይታያል፡፡ ካስፈለገም የማረጋገጡን ሥራ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሊያከናውን ይችላል፤›› በማለት ምክትል ከንቲባው አስረድተዋል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ሆቴሎች፣ ለድንጋይ ማውጪያ የተሰጡ ቦታዎች ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ በትክክል አይታወቅም፡፡ ለእነዚህ ዘርፎች የቀረበው ቦታ ለታለመለት ዓላማ በትክክል ስለመዋሉ፣ ከዘርፉ የሚመነጨው ኢኮኖሚም ሆነ የተፈጠረው የሥራ ዕድል ሽፋን እምብዛም አይታወቅም፡፡ይህንን ሥራ በተሻለ ደረጃ ለመሥራት የከተማው ኢንዱስትሪ ቢሮ ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመሥራትም መስማማታቸው ታውቋል፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የቢዝነስ ስታትስቲክስ ዳይሬክተር አቶ ዘለዓለም ኃይለ ጊዮርጊስ፣ በሆቴሎችና በኢንዱስትሪዎች ላይ ቆጠራውን ለማካሄድ ሙሉ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸው፣ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
0
e84222a790df9b152478916801bc61e8
e84222a790df9b152478916801bc61e8
በከተማዋ የቱሪስት ፍሰትን ለመጨመር የሚያግዝ መመሪያ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ:- የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ንግድ ዘርፍ ማህበር በአዲስ መልክ ለሦስተኛ ዙር ያሳተመውን የሆቴልና ከተማ መመሪያ ይፋ አደረገ።መመሪያው በአዲስ አበባ ከተማ የቱሪስት ፍሰትን ለመጨመር እንዲሁም የማህበረሰቡንና የሀገርን ገቢ ከፍ ለማድረግ የሚጠቅም መሆኑ ተገለጸ።የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም ብስራት ማህበሩ ያሳተመውን የሆቴልና ከተማ መመሪያ አስመልክተው ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣መምሪያው 120 ባህላዊና ዓለም አቀፍ ሆቴሎችን ጨምሮ በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ከነስማቸው በዝርዝር የያዘና ስለሚሰጡት አገልግሎት የተሟላ መረጃ ያለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ሥራ አስኪያጁ እንዳብራሩት፤ይህ ሦስተኛው የአዲስ አበባ ከተማና ሆቴሎች ቱሪስት መመሪያ ባለፉት ጊዜያቶች ካዘጋጇቸው በብዙ መልኩ የተሻሉና የቱሪስት ፍሰቱንም የሚጨምር ሲሆን፣ ጎብኚዎች በከተማዋ የሚኖራቸው ቆይታ እንዲጨምር ያስችላል፡፡በተጨማሪም በከተማዋ የኮንፈረንስ ቱሪዝም እንዲያድግ የተለያዩ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም የሚሆኑ ሀብቶች በማስተዋወቅ ትልቅ ሚና ይጫወታል።መመሪያው በድረ-ገጽ ለሁሉም ተደራሽና ከዚህ ቀደም ከነበረው በአጠቃቀም የተለየ መሆኑም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡የከተማ መመሪያ በየዓመቱ እንደሚዘጋጅና ከዓመት ዓመት ደረጃውን በጠበቀና ጥናቶችን በማካተት እየተሻሻለ የሚቀርብ እንዲሁም የቱሪስት ፍሰቱ በሀገሪቱ እንዲጨምር አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑም ተገልጿል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 12/2011በሰሎሞን በየነ
1
d20f6b062d03634144c050c0641d3ac1
812189f301ee7e1415faa4f9f17d8919
አገር በቀሉ ኩባንያ የአሉሙኒየም ማዕድን ፍለጋ ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 07/2005 (ዋኢማ) – ከ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባውና በዓመት 24 ሺህ ኪሎሜትር የኦፕቲክ ፋይበር ኬብል የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ በመጪው መስከረም /2006 ዓ/ም ምርት ይጀምራል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በሰበታና አለምገና ከተሞች የሚገኙ የልዩ ልዩ ኬብል ማምረቻ ፋብሪካ/BMET/፣ አይካአዲስና ሳይገንዲማ የጨርቃጨርቅና አልባሳ ፋብሪካዎች ጉብኝት ሲያደርጉ እንዳሉት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በመሳብ እየተስፋፋ ያለው የውጭ ገበያን መሰረት ያደረገው ኢንዱስትሪ ይበልጥ እንዲጠናከር ፋብሪካዎቹ የማስፋፍያ ስራ እንዲሰሩና ባለሃብቶቹም ሌሎች የውጭ ኩባንያዎችም ወደ ሀገሪቱ እንዲመጡ ግፊት እንዲደርጉ ጠይቀዋል፡፡ለዚህም መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ለፋብሪካዎቹ ሀላፊዎች አረጋግጠዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፡፡በዚህ መሰረትም በአለምገና ከተማ የሚገኘው የአይካዲስ ኩባንያ ፕሬዝደንት ዮሱፍ አይደኒስ ሌሎች የቱርክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ እንዲከፍቱ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡ #እኔ 20 የጨርቃመርቅ ኩባንያዎች ከቱርክ መጥተው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሰሩ ለማድረግ አስቤያለው፡፡ይህንን ነው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የተነጋገርነው፡፡ እነዚህ 20 ኩባንያዎች ለተጨማሪ 60 ሺህ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራሉ፡፡ይህም የጨርቃጨርቅ ምርትን ወደ ውጭ በመላክ በዘመት 2ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያስገኝል፡፡ከሰባት አመት በፊት ግንባታውን የተጀመረው የአይካ አዲስ ኩባንያ አሁን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ገብቷል፡፡ 7 ሺህ 500 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውን የስራ እድል ፈጥሯል፡፡
0
40990f095a3614de6beb619d90efd193
40990f095a3614de6beb619d90efd193
ለአበርክቷቸው ዘወትር ሲያመሰግኗቸው የሚደመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ኢንጂነር ስመኘውን እንደ ብሄራዊ ጀግና ይጠቅሷቸዋል
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት በተያዘለት ዕቅድ መሰረት በመፈጸሙ ከፍ ያለ ደስታ እንደተሰማው የቀድሞው የግድቡ የግንባታ ፕሮጄክት ዋና ስራ አስኪያጅ የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ልጅ ተናገረ፡፡ የሙሌቱን መጠናቀቅ ዜና ከአያቱ መስማቱን ለአል ዐይን አማርኛ የተናገረው በዕምነት ስመኘው በቀለ መላ የቤተሰቡ አባላት በተሰማው ብስራት መደሰታቸውን ገልጿል፡፡ ቤተሰቡ የተሰማውን ደስታ ለማጋራት ወዲያውኑ ለውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ለዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ስልክ መደወሉን የተናገረም ሲሆን ሚኒስትሩ “አይዟችሁ የጀግና ልጆች ናችሁ” እንዳሉዋቸውም ነው የገለጸው፡፡ በዕምነት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶፍትዌር ምህንድስና የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነው፡፡ ኢንጂነር ስመኘው ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ እየገነባቸው ያለውን ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነት የመሩ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ህይወታቸው እስካለፈበት እስከ ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ድረስም ግንባታውን በስራ አስኪያጅነት መርተዋል፡፡ ኢንጂነሩ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅነታቸው አስቀድሞም በግልገል ጊቤ ቁጥር 2 የኃይል ማመንጫ ግድብ የግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነት አገልግለዋል፡፡ ለአበርክቷቸው ዘወትር ሲያመሰግኗቸው የሚደመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደ ብሄራዊ ጀግና ሲጠቅሷቸው መመልከትም የተለመደ ነው፡፡ የኢንጂነሩ 2ኛ የሙት ዓመት ሊሞላ የቀናት ዕድሜ ብቻ ይቀረዋል፡፡
1
1e70bef86b71d369cc81012a6484ca34
98ff7f9a41791d1fa6cdfebd6a1d18fb
ኢህአፓ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው
ለሁለት የተከፈሉት የአንድነት አባላት እሁድ በየፊናቸው ጠቅላላ ጉባዔ ሲያካሂዱ በተመሳሳይ መኢአድም ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል።በሁለት ጎራ የተከፈሉ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት በሁለት የተለየዩ መድረኮች እሁድ መሪዎቻቸውንም መርጠዋል።አቶ በላይ ፍቃዱ የሚመሩት የአንድነት ፓርቲ 205 ጠቅላላ የጉባዔ አባላት ተገኝተውበታል ባለውና በአንድነት ፅህፈት ቤት በተካሄደው ስብሰባ በሚስጥር ድምጽ አሰጣጥ ሂደት አቶ በላይን በድጋሚ በአብላጫ ድምጽ ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።ሌላኛው የአንድነት ፓርቲ ስብስብ ደግሞ በዲአፍሪክ ሆቴል በጠራው ጉባኤ 150 አባላት በጉባዔው የተገኙ ሲሆን፥ አቶ ትእግስቱ አዎሎን ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።የምስራቅ ቀጠና ሃላፊ እና የብሄራዊ ምክር ቤቱ አባል አቶ አየለ ስሜነህ ሊቀመንበር የመረጥነው በፓርቲው የ2004 መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ነው ብለዋል።በሌላ በኩል በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው መኢአድ ዛሬ ጠቅላላ ጉባኤውን በፅህፈት ቤቱ አካሂዷል።ድርጅቱ አቶ ማሙሸትን ፕሬዝዳንት አድርጎ ሲመርጥ ሌሎች የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትና የምክር ቤት አባላትንም ምርጫ አካሂዷል።ህጋዊ የድርጅቱ ፕሬዝዳንት እኔ ነኝ የሚሉት አቶ አበባው መሃሪ ደግሞ የተጠራው ጠቅላላ ጉባዔ ተቀባይነት የሌለው ህገ ወጥ ነው ብለዋል።አቶ ማሙሸት አማረ፥ እነ አቶ አበባው መሃሪ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፈንላቸዋል ቢሉም ፋና ብሮድስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው አቶ አበባው ግን በጉባዔው ላይ እንድንገኝ የተላለፈ ጥሪ የለም፣ የጥሪው አካሄድም ትክክለኛውን አሰራር ያልተከተለ ነው ብለዋል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)
0
147f864e63bdbf4893970fffd49ab611
147f864e63bdbf4893970fffd49ab611
በቅርቡ በጓንዙ በሚኖሩ አፍሪካውያን በአከራዮቻቸው ከሚኖሩበት ቤት እንዲወጡ እየተደረጉ ነው የሚል ቅሬታ እየተሰማ ነው
በቻይና የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች በቻይና ጓንዙ ግዛት በሚገኙ አፍሪካውያን ላይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ መገለል እየደረሰባቸው ነው በማለት ለቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቅሬታ ማስገባታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በተናጠል ጭምር ቻይና በተለይ በደቡባዊቷ ከተማ ጓንዙ በአፍሪካውያን ላይ የሚደርሰውን ማግለልና መተንኮስ በሚመለከት መልስ እንድትሰጣቸው ይፈልጋሉ፡፡ ኮሮና ቫይረስ አሁን ከ200 በላይ ሀገራት ተከስቶ የሁሉም ስጋት ከመሆኑ በፊት ባለፈው ታህሳስ ወር ነበር በቻይናዋ ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው፡፡ ቻይና ኮሮና ቫይረስ የተቀሰቀሰበትን ውሀን ከተማ በቁጥጥር ስር ከደረገች በኋላ ዋነኛው ስጋቷ ከውጭ የሚመጣው በመሆኑ ምክንያት ከውጭ ወደ ሀገሪቱ በሚገቡ የውጭ ዜጎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገች ነው፡፡ ቻይና ምንም አይነት ማግለል እያደረገች እንዳልሆነ አስታውቃለች፡፡ በቅርቡ በጓንዙ የሚኖሩ አፍሪካውያን በአከራዮቻቸው ከሚኖሩበት ቤት እንዲወጡና የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በርካታ ጊዜ ቢደረግላቸውም ውጤቱም አይሰጣቸውም፤ በአደባባይ እየተንጓጠጡና እየተገለሉ ይገኛሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ቅሬታ በማህበራዊ ሚዲያ እንደሚነገር ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የአፍሪካ አምባሳደሮች ይህ አይነት መድሎና ማግለል ቫይረሱ በአፍሪካውያን እየተሰራጨ ነው የሚል ውሸት አንደምታ ይፈጥራል፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛኦ ሊጂያን በበኩላቸው የጓንዙ ባለስልጣናት ለአፍሪካ ትልቅ ትኩረት ይሠጣሉ፤ ስለሆነም የአፍሪካ ሀገራት ያነሱትን ቅሬታ በፍጥነት እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡ ነገርግን ቃል አቀባዩ ዛኦ በአፍሪካውያን ላይ እየደረሰ ነው ስለሚባው ማግለል ያሉት ነገር የለም፡፡
1
797a05ebb77c5aa7f241d1c12c4f8c34
e2ebf40bc672551726e62665ff078b79
ሳላዲን ቋሚ ሆኖ በተጫወተበት ጨዋታ ኤምሲ አልጀር ሲያሸንፍ የጌታነህ አማተክስ አቻ ወጥቷል
የኢትዮጵያዊው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወኪል የሆኑት ግብፃዊው አብዱልራህማን መግዲ ሳላዲን ወደ አልጄሪያው ክለብ ኤምሲ አልጀርስ ሊያቀና ነው የሚሉትን ዜናዎች ከእውነት የራቀ በማለት አጣጥለዋል፡፡ አብዱልራህማን መግዲ ስለተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት “ሳላ ወደ አልጄሪያ እየሄደ አይደለም፡፡ በአሁን ሰዓት ስለዝውውሩ ማውራት አልችልም፡፡ ስለዝውውሩ የተነሳው ዘገባ ከእውነት የራቀ ነው፡፡” ብለዋል፡፡በግብፁ አል አሃሊ ኑሮ የከበደው የሚመስለው ሳላዲን ክለቡ በመጪው የዝውውር መስኮት ሊለቀው እንደሚችል ከግብፅ የሚመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የምዕተ ዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ ክለብ አል አሃሊ ባሳለፍነው ሳምንት ጋናዊውን የቀድሞ የኢስማኤሊ አጥቂ ጆን አንትዊን ከሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ሻባብ በ1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማስፈረሙ የሳላዲንን በክለቡ የሚኖረውን ቆይታ አጣራጣሪ አድርጓታል፡፡ ስለጉዳዩ አብዱልራህማ መግዲ “ስለአል አሃሊ የወደፊት ቆይታው አሁን ላይ መናገር ያስቸግራል፡፡” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አብዱልራህማን መግዲ የኢትዮጵያዊያኖቹ ሳላዲን ሰዒድ እና ሽመልስ በቀለ ወኪል ናቸው፡፡ ሳላዲን ሰዒድ ለአል አሃሊ 4 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡
0
d423396e3e7bf9c529f80666a296c4c8
d423396e3e7bf9c529f80666a296c4c8
አየር ሀይሉ ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን የተመረጡ ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ አድርጓል-ሜ/ጄ ይልማ
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል።በመግለጫቸው አየር ሀይሉ ለጁንታው እስትንፋስ የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ምርጥ ኢላማዎችን ያለምንም ከልካይ ጀቶች አውድመዋቸዋል ብለዋል።ፓይለቶች የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው በሚሄዱበት ወቅት ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ እንደሚገኙም መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ጁንታው እንመታለን የሚለው ፣ እድሜውን ሲዋሽ ስለኖረና እየዋሸ ስለሚቀበር ባህሪው ነው ያሉት ሜጀር ጄኔራል ይልማ ፤ አሁንም ቡድኑ ለህግ እስኪቀርብ ድረስ አየሩ ሀይሉ ጥቃቱን እንደሚቀጥል ገልፀዋል።የተመረጡ
1
2e4d8b79547cd717750443710c0540b9
58d3a4976a1e5b99d382290a71ebd7c5
የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ስነ- አዕምሮ ህክምና ክፍል ለኮቪድ-19 ህሙማን አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የኩላሊት ህመምተኞችን ከኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከ5 ሺህ በላይ ታክሲዎች ለህመምተኞቹ ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገለፀ።የነጻ የትራስፖርት አገልግሎቱን መስጠት የጀመሩትም ዘሉሲ ሜትር ታክሲና ሰማያዊ በነጭ ታክሲዎች ማህበር አባላት ናቸው።ዘሉሲ ሜትር ታክሲና ሰማያዊ በነጭ ታክሲዎች ማህበር አባላት ለኩላሊት ህመምተኞች ነጻ የትራስፖርት አገልግሎት ያመቻቹት ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስና ያለባቸውን የወጪ ጫና ለማቃለል ታሰቦ እንደሆነ ተገልጿል።የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ እስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ህመምተኞች ከሌሎች ግለሰቦች ጋር በህዝብ ትራስፖርት ቢጠቀሙ ለቫይሰሩ የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ታክሲዎች ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል።ምንጭ፡- ኢዜአ
0
ff93012a1cfd384ab9921c9feac942f7
ff93012a1cfd384ab9921c9feac942f7
በህግ ማስከበሩ ዙሪያ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስረዳት በኩል የተሳካ የዲፕሎማሲ ስራ ተሰርቷል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረው ህግ የማስከበር እና የህልውና ዘመቻ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስረዳት በኩል የተሳካ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱን አስታወቀ፡፡የሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደተናገሩት ህግን የማስከበር እርምጃው ዋና ዓላማዎችና ተያያዥ ጉዳዮች በማስረዳት በኩል የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡በተለይም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው የልዑካን ቡድን በአፍሪካ እና በአውሮፓ ያደረጋቸው የዲፕሎማሲ ስራዎች የተሳኩ እንደነበሩ ነው የገለጹት አምባሳደሩ፡፡አምባሳደሩ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በኩልም በተለያዩ ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን በተመለከተም ወደ ሀገር ውስጥ ለመመለስ የተፈናቃዮች ቁጥር፣ ማንነት፣ የት እንደሚገኙ እና መሰል መረጃዎችን ለማጣራት ከሱዳን ኤምባሲ ጋራ በጋራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በለይኩን አለም ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
1
6d969aaa30a439d4239e425f85c786d1
5ed42aa5babcfd7e4f732a8aea680d6c
ዓመቱ በዲፕሎማሲው መስክ ታሪካዊ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው
ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ። የጽህፈት ቤቱ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም እንደተናገሩት፤በ2010 ዓ.ም እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ ለግድቡ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዷል። ባለፉት ስድስት ወራት ከቦንድ ሽያጭ፣እየተዘዋወረ ካለው የህዳሴ ግድብ ዋንጫ፣ ከግድቡ ችቦ ከመሳሰሉ የንቅናቄ መርሃ ግብሮች ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አብራርተዋል። ቃል የገቡ ባለሃብቶች ቃላቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ በየተሰማሩበት የሥራ መስክ የማወያየት ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸው ከየካቲት 20 በኋላ ግድቡን እንዲጎበኙ ይደረጋል ብለዋል። እንደ አቶ ኃይሉ ገለጻ የግድቡ ግንበታ የተጀመረበትን ሰባተኛ ዓመት አስመልክቶ በሚካሄዱ የህዝባዊ ንቅናቄ ሥራዎች ቀሪውን ገቢ ለመሰብሰብ ይሰራል።የግድቡ ችቦ በአገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች በማዘዋወር ገቢ የመሰብሰብ እንቅስቃሴ መጀመሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ የሙዚቃ ኮንሰርት፣ሙዚቃዊ ድራማ፣ የሥነ ጹሁፍ ምሽቶች፣የፎቶ አውደ ርዕይ እንዲሁም መኪናዎች ላይ የህዳሴ ግድብ ቦሎ እንዲለጠፍ ማድረግ ከሚሰሩ ሥራዎች መካከል መሆኑን ጠቅሰዋል። የቦንድ ሳምንት መርሃ ግብርና በ100 ከተሞች ከ500 ሺህ በላይ ሯጮችን የሚያሳትፍ ሩጫ በማዘጋጀት ተጨማሪ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ነው የተናገሩት፡፡እስካሁንም ከቦንድ ሽያጭ፣ ከስጦታ፣ ከ8100፣ከወረቀት ሎቶሪ፣ ከቲሸርት ሽያጭና ከመሳሰሉ መርሃ ግብሮች ከ10 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።(ኢዜአ)
0
037044d24dc5fd25c22ab290358c0ac9
037044d24dc5fd25c22ab290358c0ac9
ብአዴን አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አገደ
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አግዳዋል።ማዕከላዊ ኮሚቴው ሁለቱን ነባር አመራሮች ያገደው መስከረም ወር እስከሚካሄደው ጉባዔ ድረስ ነው።አመራሮቹ የታገዱት ጥረት ኮርፖሬት ውስጥ በፈፀሙት ችግር ነው ተብሏል።ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት ያደረገውን ስብሰባ ያጠናቀቀ ሲሆን መግለጫውን እንደሚያወጣም ይጠበቃል።
1
aef4d0a2d124e72dc425eb59fcce04ea
67bb1f72eac74f30327e47eb52b0ef4d
አርሶ አደሩን ወደ ዘመናዊ የአመራረት ዘዴ ለማሸጋገር ምሁራን በዕውቀታቸው መደገፍ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 28/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ እየተከናወነ ያለውን ውጤታማ የጠረጴዛ እርከን የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሠራ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ ተናገሩ።ርእሰ መስተዳድሩ በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የተፋሰስ ልማትን ጎብኝተዋል።በልዩ ወረዳው 22 የተፋሰስ ልማቶች ተለይተው በጠረጴዛ እርከን አቮካዶ፣ ማንጎና ሀብሀብ የመሳሰሉ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት እየተከናወነ መሆኑንም ነው የገለጹት።አርሶ አደር አህመድ ሰይድ በብሔረሰብ ልዩ ወረዳው 01ቀበሌ በተከናወነው የጠረጴዛ እርከን የተፋሰስ ልማት አትክልትና ፍራፍሬ እያለሙ ተጠቃሚ እየሆኑ ካሉ አርሶ አደሮች መካከል አንዱ ናቸው። እርሳቸው እንዳሉት የተፋሰስ ልማት ተግባራዊ ከሆነ ወዲህ ወጣቶች ወደ ስደት ከመሄድ ተቆጥበው እየተደራጁ በአካባቢ ጸጋ እየተጠቀሙ መሆኑን ነግረውናል።የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ታደሰ ግርማ እንዳሉት የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳን ጨምሮ በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች የተፈጥሮ ሀብት ልማትን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል የተከናወነው ተግባር አበረታች ውጤት አስመዝግቧል።በተያዘው ዓመትም ከ16 ሺህ በላይ ወጣቶችን በግብርና ልማት ዘርፍ ለመፍጠር ታልሞ እየተሠራ መሆኑንም ነው የገለጹት።የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ በበኩላቸው በአርጎባ ማኅበረሰብ እየተከናወነ ያለው የጠረጴዛ እርከን የተፋሰስ ልማት ሥራ ለሌሎች የክልሉ አካባቢዎች በአርአያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል። ይህን መልካም ተሞክሮ በማስፋት የክልሉን አርሶ አደር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሠራም ነው ያረጋገጡት።የተፈጥሮ ሀብት የተፋሰስ ልማት ሥራውን ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በማስተሳሰር የገጠር ወጣቶች ሀብት እንዲያፈሩም በቅንጅት ይሠራል ብለዋል።
0
b2f054e2451245cb9aecc673120f9aa4
212a1bcb8783271df5ae8e892aa4d87b
የአቶ ልደቱ አያሌው ከእሥር በዋስ የመፈታት ጉዳይ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገመንግስቱን ለመናድ በማሰብ የተለያዩ ህገመንግስቱን የሚቃረኑ የሽግግር ሰነዶችን በማዘጋጀት ወንጀል ክስን በችሎት ለማንበብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።አቶ ልደቱ ዛሬ ረፋድ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።አቶ ልደቱ በተከሰሱበት በ1996 የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 238 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 256 በመተላለፍ ህገመንግስቱን ለመናድ በማሰብ የተለያዩ ህገመንግስቱን የሚቃረኑ የሽግግር ሰነዶችን በማዘጋጀት ወንጀል ክስን በችሎት ለማንበብ ነበር ለዛሬ ቀጠሮ የተሰጠው።ይሁንና አቶ ልደቱ ዛሬ ጠበቆቼ ባለመገኘታቸው ጠበቆቼ ባሉበት ተማክሬ ይነበብልኝ ማለታቸውን ተከትሎ ክሱን በችሎት በንባብ ለማሰማት ለፊታችን አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ልደቱ አያሌው ከዚህ በፊት በተከሰሱበት ህገ ወጥ ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ይታወሳል።ባሳለፍነው ሃሙስ ህገመንግስቱን ለመናድ በማሰብ የተለያዩ ህገመንግስቱን የሚቃረኑ የሽግግር ሰነዶችን በማዘጋጀት ወንጀል ክስ መመስረቱን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡በታሪክ አዱኛ
0
738b8a6236162f445eb09b653fb06693
9ae8adec76701003b99f3996c402c94c
ጥንዶቹ ዘንድሮም የአለማችን ድንቅ ሰዎች ተብለው ተመርጠዋል
የኢፌዲሪ ኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽእኖ ፈጣሪ ከተባሉ አንድ መቶ ግለሰቦች መካከል አንዱ ሆነው ተመረጡ። ኢንጅነሩ በመንግስት የዲጂታል አሰራር ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ በሚል እንደተመረጡ ታውቋል።ተጽእኖ ፈጣሪ ተብለው ለመመረጥ አምስት መቶ ሰዎች የተወዳደሩ ሲሆን አንድ መቶ ተወዳዳሪዎች ተመርጠዋል ከዚህም ውስጥ ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በመንግስት ኃላፊዎች ዘርፍ እንደተመረጡ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር አስታውቋል። በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ የተካሔደውን የችግኝ ተከላ በቴክኖሎጂ ተደግፎ እንዲቆጠር በማድረግና ኢትዮጵያ በዐስር ዓመታት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እንደትሰለፍ በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያደረጉ የሚገኘው እንቅስቃሴ ለመመረጣቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።በዚህ ውድድር በመንግስት ኃላፊዎች ዘርፍ ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የሎስ አንጀለስ ከንቲባ ኤሪክ ጋርሲቲ፤ የካናዳ የዲጂታል ገቨርንመንት ሚኒስትር ጆይሲ ሙራይ ቀዳሚውን ስፍራ እንደያዙ ተገልጿል፡፡
0
2ec376c12bd9e887ec51041e34467fed
d602d48df2b5d67cc6c5dd4970263668
የመለስ መታሰቢያ የቴክኖሊጂና የምርምር ማእከል ሊገነባ ነው
አዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ በስፋት እየተሰራ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ስራን እንደሚያደንቁ የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን የቦርድ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ገለጹ፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሰባተኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ በጉለሌ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ፓርክ ትናንት ሲከበር ወይዘሮ አዜብ እንዳሉት፤ አሁን በሀገሪቱ በስፋት እየተሰራ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ስራ የሚደነቅ ነው፡፡ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ወቅት ለአረንጓዴ ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውንና በርካታ ስራዎች መስራታቸውንም ተናግረዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃም ዕቅድ ተይዞበት መሰራቱንና በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችም መተከላቸውን አስታውሰዋል፡፡ ባለፉት ሰባት አመታት መለስ ፋውንዴሽን በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ያሉት ወይዘሮ አዜብ፤ ከወዳጅ ሀገራት፣ ከሀገር ውስጥና ከተለያዩ ክልሎች በተውጣጣ ገንዘብ በአቶ መለስ ስም የህዝብ መናፈሻ ፓርክ እየተሰራ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡ ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሲገባም ለሀገርና ለወገን እንደሚጠቅም አስረድተዋል፡፡በፓርኩ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የግንባታ ዲዛይኖች ከባድና ያልተለመዱ በመሆናቸው በጣም ረዥም ጊዜን እንደፈጁም ወይዘሮ አዜብ ተናግረዋል፡፡ ግብአቶቹም ከሁሉም ክልሎች የመጡ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡እንደ ወይዘሮ አዜብ ገለፃ፤ በፓርኩ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የአቶ መለስ ስራዎች ማንፀባረቂያ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው፡፡አሁን የፓርኩ ማጠቃለያ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው፤ በ2012 ዓ.ም አጋማሽ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ባለፉት ሰባት አመታት አቶ መለስ በህይወት እያሉ ያጠኗቸው፣ የፃፏቸው ፅሁፎች፣ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ መድረኮች ላይ ያደረጓቸው ንግግሮች እና ማስታወሻዎችን በማሰባሰብና ለመጪው ትውልድ በሚጠቅም መልኩ ዲጂታላይዝድ በማድረግ ወደ መለስ ፋውንዴሽን የማስገባት ስራም መሰራቱን ወይዘሮ አዜብ ተናግረዋል፡፡ በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ በፓርኩ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ የግንባታ ስራዎች የተጎበኙ ሲሆን፤ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በፋውንዴሽኑ ድጋፍ ለአንድ ወር የክረምት ወቅት ስልጠና ሊወስዱ የመጡ ተማሪዎች እና የአቶ መለስ የቀድሞ የስራ ባልደረቦች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርም በፓርኩ ቅጥር ግቢ ተካሂዷል፡፡አዲስ ዘመን ነሀሴ 15/2011ሐይማኖት ከበደ
0
781ffa07980ccd5721a20673650b8e5a
781ffa07980ccd5721a20673650b8e5a
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ብራዚል አዲስ በረራ ዛሬ ጀመረ
– የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት ወደ ደቡብ አሜሪካ ብራዚል አዲስ በረራ ጀመረ። በአፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ በብራዚል በሚገኙት ሪዮ ዲ ጄኒሮና ሳኦ ፓውሎ ከተሞች አዲስ በረራ መጀመሩን አበስሯል። ድርጅቱ ዛሬ እንዳስታወቀው የደቡብ አሜሪካው አዲስ የበረራ መስመር መከፈት አየር መንገዱ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን አህጉራት ቁጥር አምስት ያደርሰዋል። ወደ ሳኦ ፓውሎና ሪዮ ዲ ጄኒሮ የሚደረጉት በረራዎች ሙሉ በሙሉ በአዲሱና ዘመናዊው ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች አማካኝነት የሚከናወን መሆኑንም አየር መንገዱ ገልጿል። ወደ ብራዚል የሚደርገው በረራም የቶጎን መዲና ሎሜን ማእከል ያደረገ ሲሆን በረራው በሳምንት ለሦስት ቀናት የሚከናወን መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል። ወደ ሁለቱ ከተሞች የተጀመረው በረራ የድርጅቱን ዓለም አቀፍ የመዳረሻ ከተሞች ቁጥር 75 ያደርሰዋል። አዲሱ በረራ ምዕራብ አፍሪካን ከብራዚል የሚያገናኝ ብቸኛ መስመር መሆኑን የገለጸው አየር መንገዱ ብራዚል በዓለም ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ አገራት መካከል አንዷና የዓለማችን አምስተኛው ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት መሆኗንም ጠቁሟል። የአየር መንገዱ መዳረሻ ከሆኑት ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው ሳኦ ፓውሎ የብራዚል ትልቋ ከተማና በደቡብ ንፍቀ ክብብ ከሚገኙ የዓለማችን ከተሞችም በስፋቷ ተወዳዳሪ የላትም። ከተማዋ የብራዚል የፋይናንስ ማእከልና የበርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መቀመጫ እንደሆነችም አየር መንገዱ አመልክቷል።ሪዮ ዲ ጄኒሮም የአገሪቱ ሁለተኛ ታላቅ ከተማና በደቡብ ንፍቀ ክበብ በበርካታ ቱሪስቶች ዘንድ የምትጎበኝ ቀዳሚ ከተማ ናት። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ድርጅቱ የበረራ አድማሱን ወደ ደቡብ አሜሪካ ማስፋቱ ለመንገደኞችና ለንግዱ ማኅበረሰብ ተጨማሪ ዕድል የሚፈጥር መልካም አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመዋል።
1
6dc7cab810df71a5197bbc34531b270f
6dc7cab810df71a5197bbc34531b270f
በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ያለውን ሠላም ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሠሩ የሃገራቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ ገለጸ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ያለውን ሠላም ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሠሩ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ ገለጸ፡፡የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ በድንበር አካባቢ ሠላምን ለማረጋገጥ በሚቻልበት አግባብ በባሕር ዳር ከተማ ምክክር እያካሄደ ነው፡፡የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ፅሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እርዚቅ ኢሳ አትዮጵያና ሱዳን በባህል፣ በኢኮኖሚ በከፊልም በቋንቋና በሃይማኖት እንደሚቀራረቡ ተናግረዋል፡፡ሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር ለመከላከል የሚረዳ የተሳካ ውይይት እንደሚያደርጉም ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡ በቅርቡ የሱዳን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተሳካ ጉብኝት ማድረጋቸው ሀገራቱ ግንኙነታቸውን በኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር እየሄዱበት ያለውን ርቀት ማሳያ ነው ብለውታል፡፡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ መሪ ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉዓለም ዓድማሱ እና የሱዳኑ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ መሪ ሜጀር ጄኔራል ሷልህ አብደላ ኢሳቅ በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ ያለውን ሰላም ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሠሩ አስታውቀዋል፡፡በቆይታቸውም በሀገራቱ ድንበር አካባቢ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የተሳካ ውይይት በማድረግ በትብብር እንደሚሠሩ መግለጻቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡
1
fe7851b205d59d1c859c07d9c91a4a8f
0e8790d22b3c7f04bee45a82f53ca79a
ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከአንድ ቢሊዮን 300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
ዋቅሹም ፍቃዱ አዲስ አበባ፡- የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና የኢትዮጵያ ወደ ዉጭ አፍሪካ የምትልካቸውን ምርቶች በመጨምር የአገሪቱን ጠቅላላ የአገር ዉስጥ ገቢም በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከፍ እንደሚያደርግ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የመንግሥት ገቢም በትንሽ እንደሚቀንስ አመለከተ። የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቬራ ሶንጌ በተለይ ለሄራልድ ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፣ ኢትዮጵያ በጨርቃ ጨርቅ፣ በተለያዩ ምግቦችና በቀላል ማኑፋክቸሪግ ትልቅ ገቢ እንደሚታገኝና ወደ አፍሪካየምትልካቸዉ ምርቶችም ከ23 እስከ 26 በመቶ በማሳደግ አጠቃላይ የአገር ዉስጥ ገቢዋን በ 0.07 እንዲያድግና የመንግሥት ገቢም በ0.7 በመቶ በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ እንደ ዋና ፀሐፊዋ ገለጻ፣ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ከዉጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ ተወዳዳሪና ተመጣጣኝ ለመሆን ቢያንስ በ2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መቀነስ ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም አገሪቱ የምርት ጥራት በማሻሻል በዓመት 239 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ትርፍ ታገኛለች። በተጨማሪም ምሥራቅ አፍሪካ ለንግድ መሰረተ ልማቶች ኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ የመሥራቅ አፍሪካ የንግድ ምልክት ፕሮግራም የሚባለዉ ድርጅት 800 የአሜሪካ ዶላር ፈሰስ ማድረጉን አስታውቀዋል። የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በ38 አገሮች ጋር የንግድ ቀጣናዉን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን አመልክተው ፣ ከእነዚህም ውስጥ 11 አገራት ወደ ትግበራ ገብተዋል ብለዋል። የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ስትራቴጂዉን በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነቱን ወደ አማርኛ በመተርጎም ዉይይት መደረጉንም ገልጸዋል። እንደ ኮሚሽኑ ትንበያ አፍሪካ የቀጣናዉን ስትራቴጂ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ካደረገች እ.ኤ አ. በ2040 ዓመታዊ አጠቃላይ ምርቷ ከ28 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወደ 44 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። በተመሳሳይ መልኩ አፍሪካ ወደ ዉጭ የምትልከዉ ምርት ከ40 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወደ 56 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያድግም ይገመታል። በዚህም በምሥራቅ አፍሪካ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጠራል ብለዋል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 23/2013
0
d2f592a6a6cf2759192ddc9161466021
22a1e6e732310999680683a389a7c005
ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያስተሳስረው የሀዋሳ ሞያሌ መንገድና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት ዛሬ ይመረቃል
አቶ ዳጂ ጃራ ኩምቢ በተባሉ ባለሀብት በአዳማ ከተማ ወንጂ መታጠፊያ ላይ የተሰራውና 55 ዘመናዊ የመኝታ ክፍሎች ያሉት ደንበል ቪው ኢንተርናሽናል ሆቴል ዛሬ ይመረቃል፡፡ ሆቴሉ ሁሉም ነገር የተሟሉለት ሱትስ፣ 2 ደሉክስ ቲውን፣ 21 ደሉክስ ስታንዳርድ፣ 13 ሲንግል ስታንዳርድና 12 ሲንግል ክፍሎች ሲኖሩት፣ ከ30 እስከ 300 ሰዎች ማስተናገድ የሚችሉ 4 አዳራሾች አሉት፡፡ ክፍሎቹ፣ ቲቪ፣ ስልክ፣ ጠረጴዛና ወንበር፣ ሶፋ፣ ሻወር፣ ነፃ ዋይፋይ … ያሉት ሲሆን እንግዶችን የሚያረካ አገልግሎትና መስተንግዶ ለመስጠት እየተጠባበቀ ነው ተብሏል፡፡
0
4c6222fa404394d727e43b5354b68139
278a1e2e47c9d9e011548199b4bb7d95
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖች ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፊንላንዱ ፕሬዚደንት ሳውሊ ኒሲቶ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡ፕሬዚደንቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸውላቸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ሽልማቱ 10 በመቶ እውቅና፣ 90 በመቶ ደግሞ ለሰላም በርትተው እንዲሠሩ አደራም ጭምር እንደ ሆነ ጠቁመው ለውጡ ያስገኛቸውን ዋና ዋና ስኬቶች እንዲሁም የፊንላንድ መንግሥት ድጋፍ ሊያደርግባቸው የሚችልባቸውን የልማት አቅጣጫዎች አመላክተዋል።ሁለቱ መሪዎች የጋራ ጥቅምን እውን በሚያደርግ መልኩ የአፍሪካና የአውሮፓን ግንኙነት በማጠናከር ሂደት ላይ መምከራውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
0
bda81fdb390d0baa781a9e5ff8ed13e8
7b6214392cf5620c5965d13e97a65533
የደረሱ ሰብሎች በዝናብ ጉዳት ሳይደርስባቸው ቀድሞ መሰብሰብ እንደሚገባ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አሳሰበ፡፡
ችግኞችን ከመትከል ባሻገር መንከባከብ እና ማፅደቅ፣ ነባር ደኖችንም መጠበቅ እንደሚገባ የዘርፉ ተመራማሪ ጠቁመዋል፡፡የደን ሽፋኑን ለማሳደግ በኢትዮጵያ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች ይተከላሉ፡፡ አማራ ክልልም በየዓመቱ በሥፋት የችግኝ ተከላ ከሚካሄድባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ይጠቀሳል፡፡ በያዝነው ዓመትም 1 ነጥብ 75 ቢሊዮን ችግኝ በ187 ሺህ 492 ሄክታር መሬት ላይ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ለተከላ ከተዘጋጁት መካከል 82 ሺህ 864 ያህሉ ለጥምር ደን ልማት የሚውል ናቸው፡፡ ቀሪው ደግሞ ለደን አገልግሎት እንደሚሆን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አንተነህ ሰውአገኝ ለአብመድ ገልጸዋል፡፡ለመሆኑ የነበረውን የደን ብዝኃ ሕይወት ለመመለስ እየተደረገ ያለው ጥረት እንዴት ይታያል? አብመድ ከደንና ብዝኃ ሕይወት ተመራማሪና የአመልድ ዋና ዳይሬክተር ዓለማየሁ ዋሴ (ዶክተር) ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡ እንደ ዶክተር ዓለማየሁ ማብራሪያ ደንና የውኃ አካላት የብዝኃ ሕይወት መገኛ ናቸው፡፡ ከመሬት በላይ ያሉ በራሪ፣ ተሳቢና ተራማጅ እንስሳት እንዲሁም በመሬት ውስጥ ያሉ በዐይን የማይታዩ ፍጡራን የመኖር ኅልውና የተመሠረተውም በብዝኃ ሕይወት ደኅንነት ላይ ነው፡፡ ይህንን ለመጠበቅ በመንግሥት በኩል ያለው ፍላጎትና ተነሳሽነት መልካም እንደሆነ ዶክተር ዓለማየሁ ተናግረዋል፡፡ እየባከነ ባለው ጉልበትና ገንዘብ ልክ ግን ውጤት እየመጣ አለመሆኑን ነው ያስረዱት፡፡ እንደ ተመራማሪው ማብራሪያ የችግሩ ዋነኛ መንስኤ ደግሞ የደን ሽፋኑን በተመለከተ በትክክል የተቀመጠ ግብ አለመኖሩ ነው፡፡ ‘‘ገንዘብ ወጥቶባቸው በየዓመቱ የሚፈሉ ችግኞችን ማን? እንዴት ባለ መሬት? ለምን ዓላማ ይተክላቸዋል? እንዴትስ ይንከባከባቸዋል? የሚለውን መለየት ላይም ችግር መኖሩን ጠቁመዋል፡፡
0
9c23ae8e826a610626d6da993df6f526
40b5004d1b1b0bef80f97e61061a38fa
የሳይበር ደኅንነት ግንዛቤ ማስበጫ ሳምንት ሊከበር ነው
የቀጣይ አራት ዓመታት እቅዳቸውን ለመንደፍ እየሞከሩ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች ዓለም አሁን ከገጠማት ይበልጥ ውስብስብ ትርምስ ጋር ይጋፈጣሉ።ዛሬ በዓለማችን ምዕራብ መራሹ ዓለምቀፍ ሥርዓት መዳከም ፈጣን የቴክኖሎጂ ለውጥ እየተካሄደ መሆኑና አስተማማኝነት የሌለው የፕሮዤዎች ማስፈፀሚያ ገንዘብ የማግኘት ዕጥረት የፈጠረው ችግር ሁኔታዎችን ይበልጥ አወሳስቧል ይላሉ - የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት መሥሪያ ቤቶች።ትላንት ይፋ በተደረገው ብሄራዊ የዩናይትድ ስቴትስ ደኅንነት የቀረበው ትልም ዝርዝር ይዟል።ትልሙ “ከቀደመው ስትራቴጂ አስፈላጊ ሲሉ የገለፁት መሻሻል የታየበትና አስተማማኝ ባልሆነ ጊዜ የአሜሪካውያን ደኅንነት የተጠበቀ እንደሚሆን ዳግም ለማረጋገጥ የታለመ ነው” ብለዋል ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ።በሃገር ውስጥ እና በዓለምቀፍ ደረጃ ብርቱ ፈተናዎችን እንጋፈጣለን ያለው የዩናይትድ ስቴትስ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶቹ ያቀረቡት ጥናት - አሁን ያለውን ማዕበልና ውስብስብ የዓለም ሁኔታ በጥንቃቄ ለማለፍ ነገሮችን ከቀድሞው በተለየ መልክ መሥራት ይጠበቅብናል ሲል አስገንዝቧል።
0
0f67a3cadfd318231b50d699bb4c371a
1e9d539ea96d313a326f711c545efa45
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በትግራይ ክልል በርካታ የጦር መሳሪያዎች መያዙን አስታወቀ
አዲስአ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ብሬል መትረየስን ጨምሮ 153 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከ17 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችና ሌሎች ለወንጀል ተግባር የተዘጋጁ ቁሳቁሶች ጋር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የአካባቢ ሰላም ማስከበር ምክትል ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር ተሬሳ ዴሬሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጦር መሳሪያዎቹና ሌሎች ህገ ወጥ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በዞኑ 13 ወረዳዎችና ሶስት የከተማ አስተዳድሮች ውስጥ ነው።ባለፉት 20 ቀናት በተደረገ ድንገተኛ የጎዳናና የቤት ለቤት ፍተሻ ከተያዙት መሳሪያዎች መካከል ሰባት ብሬን መትረየስ፣ 19 ክላሽንኮቭ እና 127 ሽጉጦች ይገኙበታል።እንዲሁም 17 ሺህ 451 ተተኳሽ ጥይቶች፣ አራት ቦንቦች የተለያዩ የሬዲዮ መገናኛዎችና የጦር ሜዳ መነፅሮች መገኘታቸውንም አስረድተዋል።ከእነዚህ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 56 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ተሬሳ ገልጸዋል።ባለፉት ሶስት ወራት 48 ተጠርጣሪዎች ላይ በህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በፍርድ ቤት ተከሰው እስከ 11 ዓመት በሚደርስ እስራትና እስከ 50 ሺህ ብር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑንም አውስተዋል።“ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው” ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ፤ እነዚህን መሳሪያዎች ለመያዝ ህዝቡ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ ይጎብኙ፤ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን ይወዳጁንዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
49dd7b1dac4a5b8e10abe1661efa3dde
49dd7b1dac4a5b8e10abe1661efa3dde
እስራኤል ሌሊቱን በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብድባ አካሄደች
እስራኤል ሌሊቱን በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብድባ አካሂዳለች። የፍልስጤማዊያን ታጣቂዎች በበኩላቸው ወደእስራኤል ግዛቶች ሮኬት ተኩሰዋል።በሁኔታው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመካከለኛው ምሥራቅ ልዩ ልዑክ ስጋታቸውን ገልፀዋል።የተመድ የመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ሂደት አስተባባሪ ኒኮላይ ምሊዴኖቭ አሁን እየተጋጋለ ያለውን ሁኔታ መቆጣጠር ካልተቻለ አጠቃላዩን ህዝብ ለከባድ ጉዳት የሚያጋልጥ ደረጃ ላይ ሊደረስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
1