id
stringlengths
4
5
url
stringlengths
31
525
title
stringlengths
1
65
text
stringlengths
9
241k
18028
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%8C%A3%E1%88%AA%20%E1%88%99%E1%88%AD%E1%8C%A5%20%E1%8C%AB%E1%88%AA
ተፈጣሪ ሙርጥ ጫሪ
ተፈጣሪ ሙርጥ ጫሪ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ተረትና ምሳሌ
46554
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%93%E1%88%BD%E1%89%AA%E1%88%8D%E1%8D%A3%20%E1%89%B4%E1%8A%90%E1%88%B2
ናሽቪል፣ ቴነሲ
ናሽቪል (እንግሊዝኛ፦ ) የቴነሲ አሜሪካ ከተማ ነው። በ1771 ዓ.ም. ተመሠረተ። የአሜሪካ ከተሞች
47635
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%8D%E1%88%BD%E1%8C%A3
ግሽጣ
ግሽጣ () የኢትዮጵያ ተክል ነው። የአምበሾክ ዘመድ ነው። የኢትዮጵያ እጽዋት
22811
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%A5%E1%8B%B5
ጥድ
ጥድ ወይም ጽድ () ኢትዮጵያና አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ የዛፍ ዝርያ ነው። የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር የተክሉ ጥቅም ጥድና ዝግባ በኢትዮጵያ ዋና የሳንቃ እንጨቶች ናቸው። ታናናሽ ቀንበጥ ጭራሮች ተደቅቀው ትልን ለማስወጣት ተጠቅመዋል። ቅጠሉም ተደቅቆ ለቁስል ይለጠፋል። የኢትዮጵያ እጽዋት
19604
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%89%BB%E1%8B%AD%E1%8A%93%20%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%88%AD%20%E1%8A%B3%E1%88%B5%20%E1%88%9B%E1%88%85%E1%89%A0%E1%88%AD
የቻይና እግር ኳስ ማህበር
የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ እግር ኳስ ማህበር ወይም የቻይና እግር ኳስ ማህበር የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1924 እ.ኤ.አ. በቤዪጂንግ የተመሠረተ ሲሆን የፊፋ አባል የሆነው በ1931 እ.ኤ.አ. ነው። ከየቻይና የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ እንደገና በ1955 እ.ኤ.አ. የተቋቋመ ሲሆን፣ በ1979 እ.ኤ.አ. እንደገና የፊፋ አባል ሆኗል።
21934
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%AD%E1%8B%88%E1%8B%B0%E1%8B%8B%E1%88%8D%20%E1%8A%AB%E1%88%89%20%E1%8B%AD%E1%88%98%E1%8A%AD%E1%88%A9%E1%8B%8B%E1%88%8D%20%E1%8B%AD%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%8B%B0%E1%8B%8B%E1%88%8D%20%E1%8A%AB%E1%88%89%20%E1%8B%AD%E1%88%98%E1%88%B5%E1%88%8F%E1%88%8D
ይወደዋል ካሉ ይመክሩዋል ይወልደዋል ካሉ ይመስሏል
ይወደዋል ካሉ ይመክሩዋል ይወልደዋል ካሉ ይመስሏል የአማርኛ ምሳሌ ነው። ይወደዋል ካሉ ይመክሩዋል ይወልደዋል ካሉ ይመስሏል የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
12852
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%81%E1%8C%A5%E1%88%AD
ቁጥር
ቁጥር ፦ ለመቁጠር ወይም ደግሞ ለመለካት የምንጠቀምበት የሂሳብ ቁስ ነው። ቁጥሮች ከዚህ ከሁለቱ ጥቅማቸው ውጭ በአሁኑ ጊዜ ለልዩ ልዩ ጥቅም ይውላሉ። ለምሳሌ፦ አንድን ነገር ለመለየት (ምሳሌ ስልክ ቁጥር)፣ ለመደርደር (ሲሪያል ቁጥር)፣ ኮድ ለማበጀት ( ቁጥር) ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው። አንድንድ ሂደቶች አንድ ወይም ሁለት ቁጥሮችን ወስደው ሌላ ቁጥርን ይሰጡናል። እኒህ ሂደቶች ኦፕሬሽን ይባላሉ። ለምሳሌ ቁጥር ሲስጠን ቀጣዩን ቁጥር የምናገኝ ከሆነ ይህ ሂደት ቀጣም በመባል ይታወቃል፣ የሚወስደውም ቁጥር ብዛት አንድ ብቻ ስለሆነ ዩናሪ ኦፐሬሽን ይባላል። እንደ መደመር፣ መቀነስና፣ ማባዛት፣ ማካፈል ያሉት ደግሞ ባይናሪ ኦፕሬሽን ይባላሉ። እንደዚህ ያሉትን የቁጥር ኦፕሬሽን የሚያጠናው የሂሳብ ክፍል ሥነ ቁጥር ወይም አርቲሜቲክ (በእንግሊዝኛ ) ይሰኛል። የቁጥሮችን ቁመና በግሩፕ፣ ቀለበት ና ሜዳ የሚያጠናው የሂሳብ ክፍል የነጠረ አልጀብራ ተብሎ ይታወቃል። የቁጥር ምልክቶች የሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥሮች ምልክቶች በዘመናዊ ቅርጾቻቸው በአውሮፓ ከ1550 ዓም ግድም ጀምሮ ነው። ከዚያ በፊት በነባሮች ቅርጾቻቸው በአውሮፓ ከ968 ዓም ጀምሮ ይታወቁ ነበር። እነርሱም ከአረብኛ ቁጥሮች ተወሰዱ። አረቦችም የሕንድ ቁጥሮች የበደሩ ከ768 ዓም ጀምሮ ነበር። የአረብ ሊቃውንት ከአውሮፓ ሊቃውንት በነዚህ ፪ መቶ አመታት በዜሮ ጥቅም ቅድምትነታቸው ምክንያት፣ በሥነ ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሳይንስ ዘርፎች ሥነ ቁጥሮች በመቀለላቸው በኩል፣ ለጊዜው የአረብ አለም ሊቃውንት በይበልጥ ለመግፋት ቻሉ። ሕንዶችም የዜሮ ጥቅም ያወቁት ቢያንስ ከ620 ዓም ጀምሮ ነበር። ለያንዳንዱ ሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥር ምልክት አደረጃጀት፣ በየአማርኛ ስሙ አንድ ሁለት ሦስት አራት አምስት ስድስት ሰባት ስምንት ዘጠኝ ይዩ። የግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች በቀጥታ ከግሪክ ፊደል ቁጥሮች ተበደሩ፤ እንዲሁ፦ ይህ የግሪኮች ዘዴ የተለማ ምናልባት 400 ዓክልበ. ግድም ሲሆን፣ ከዚያ ቀድሞ ሌላ የአቆጣጠር ዘዴ ለግሪኮቹ ነበራቸው። የግዕዝ ቁጥር ቅርጾች ከ500 ዓም ያህል ጀምሮ ናቸው (የአባ ገሪማ ብራናዎች)። በአውሮፓ ከሕንዳዊ-አረባዊ ቁጥሮች በፊት የነበረው ዘዴ ሮማዊ ቁጥሮች በአንዳንድ ቦታ እስካሁን ይገኛል። በዚህም፦ = ፩ ፣ = ፪ ፣ = ፫ = ፬ ፣ = ፭ ፣ = ፮ ፣ = ፯ ፣ = ፰ = ፱ ፣ = ፲ ፣ = 11 ወዘተ. = ፳ ፣ = ፴ = ፵ ፣ = ፶ ፣ = ፷ = ፺ ፣ = ፻ ፣ = ፪፻ ፣ = ፫፻ = ፬፻ ፣ = ፭፻ ፣ = ፮፻ ወዘተ. = ፱፻ ፣ = ፲፻ ፣ = ፲፩፻ እነዚህ ቅርጾች እንደ ላቲን አልፋቤት ፊደላት ለመምሰል የጀመሩ ከ1 ዓም አካባቢ ነው። ሆኖም በውነት ከጥንታዊ ኤትሩስክኛ ቁጥሮቹ ምልክቶች («𐌠, 𐌡, 𐌢, ⋔, , ⊕» ለ«») የተለሙ ናቸው። ከነዚህ ዘዴዎች በቀር በጣም ብዙ ሌሎች የአቆጣጠር ምልክቶች ዘዴዎች ከቦታ ወደ ቦታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለያዩ በሰው ልጆች ታሪክ ላይ ተገኝተዋል። ሥነ ቁጥር
15199
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%8B%E1%88%88%E1%8D%88%E1%8B%8D%20%E1%8A%AD%E1%88%A8%E1%88%9D%E1%89%B5%20%E1%8B%8D%E1%88%80%20%E1%88%9B%E1%89%86%E1%88%AD%20%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%89%BB%E1%88%8D%E1%88%9D
ላለፈው ክረምት ውሀ ማቆር አይቻልም
ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራም መደብ : ተረትና ምሳሌ
13751
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%88%8D%E1%8C%8B%20%E1%88%8B%E1%8B%AD%20%E1%8B%88%E1%8B%B5%E1%89%84%20%E1%8A%90%E1%8B%8D
ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው
ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው አለቃ አንድ ቀን መንገድ መሽቶባቸው አንዲት ሴትዮ ቤት እንድታሳድራቸው ለምነው ቤት ለእንግዳ ብላ አስገባቻቸው። አለቃ ያው እንደሚተረከው ቅንዝራም ቢጤ ናቸው። እራት በልተው ከጨረሱ በኋላ በሉ እኔ መደብ ላይ እርሶ መሬት ላይ ተኙ ብላቸው ተኙ። ከዚያ ጨለማን ተገን በማድረግ ሴትየዋ መደብ ላይ ዘፍ ብላው መዳሰስ ይጀምራሉ። ሴትየዋም በድንጋጤ ነቅታ እንዴ ምን እየሰሩ ነው ስትላቸው ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው አሏት። እንዴት መሬት ተኝተው ስትላቸው እኔንስ የገረመኝ እሱ አይደል አሏት ይባላል። የኢትዮጵያ ቀልዶች
11280
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%A8%E1%8A%95%E1%8C%93%E1%8B%B4%20%E1%8B%9B%E1%8C%8E%E1%88%8D%20%E1%8A%A0%E1%88%B3
አረንጓዴ ዛጎል አሳ
አረንጓዴ ዛጎል አሳ (ሮማይስጥ፦ ) 2 ክፍት-ክድን ባለ ዛጎል ውስጥ ከሚኖሩት አሶች አንድ ዝርያ ነው። ዝርያው የሚገኘው በኒው ዚላንድ ጠረፍ አጠገብ ነው። ለኒው ዚላንድ ምጣኔ ሀብት እርግጥኛ ሚና አለው። ይኸ የዛጎል አሣ ዝርያ በተለይ ለአንጓ ብግነት (ሪህና ቁርጥማት) የሚያስታግስ ልዩ መድኃኒት በውስጡ ይሠራል። በዚህ ምክንያት በኒው ዚላንድ የሚበሉት ማዖሪ ኗሪዎች ከአንጓ ብግነት እምባዛም አይቸገሩም፤ ከአሳው የወጣው መድኃኒት ደግሞ በሌላ አገር በሚኖሩት የቁርጥማትና የሪህ ህመምተኞች ይፈለጋል። ኒው ዚላንድ
21076
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%98%E1%8C%A3%E1%8B%8D%E1%8A%95%20%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%89%B3%E1%8B%8D%E1%89%85%20%E1%8B%AB%E1%88%88%E1%8D%88%E1%8B%8D%E1%8A%95%20%E1%8A%A5%E1%8B%88%E1%89%85
የሚመጣውን እንድታውቅ ያለፈውን እወቅ
የሚመጣውን እንድታውቅ ያለፈውን እወቅ የአማርኛ ምሳሌ ነው። የሚመጣውን እንድታውቅ ያለፈውን እወቅ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
17894
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%AB%E1%89%B2%E1%89%B5%20%E1%8D%AF
የካቲት ፯
የካቲት ፯፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፶፯ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፵፪ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፱ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፰ ቀናት ይቀራሉ። ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፶፩ ዓ/ም - በሰሜን ምዕራብ የአሜሪካ ኅብረት የምትገኘው የኦሪጎን ግዛት ፴፫ ኛዋ የኅብረቱ አባል ሆነች ፲፱፻፬ ዓ/ም - በደቡብ ምዕራብ የአሜሪካ ኅብረት የምትገኘው የአሪዞና ግዛት ፵፰ ኛዋ የኅብረቱ አባል ሆነች ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - ‘የዓለም አቀፍ የንግድ ሒሣብ መሣሪያዎች ድርጅት’ () ተመሠረተ። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም በዓለም የመጀመሪያው ሁለ-ገብ መቀምር () ወይም ኮምፕዩተር ይፋ ተደረገ። ፲፱፻፵፩ ዓ/ም በእስራኤል የሕዝብ ምክር ቤት ክኔሰት () ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰበሰበ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የመከላከያ ንዑስ ሸንጎ አባላት አዲስ አበባ ላይ ስብሰባቸውን ጀመሩ። ዕለተ ሞት ዋቢ ምንጮች
19571
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%90%E1%8C%88%E1%88%AD%20%E1%8A%A8%E1%88%B5%E1%88%A9%20%E1%8B%8D%E1%88%80%20%E1%8A%A8%E1%8C%A5%E1%88%A9
ነገር ከስሩ ውሀ ከጥሩ
ነገር ከስሩ ውሀ ከጥሩ የአማርኛ ምሳሌ ነው። መደብ : ተረትና ምሳሌ
49966
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%9D%E1%88%B3%E1%88%8C
ምሳሌ
ምሳሌ ማለት በአንድ ቋንቋ ወይም ባሕል ውስጥ የሚጠበቅ የጥበብ ቃል ወይም ዘይቤ ነው። ብዙ ምሳሌዎች ከቋንቋ ወደ ቋንቋ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ወይም ከሃይማኖቶች የሚተላለፉ ናቸው። ለምሳሌ በብሉይ ኪዳን መጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ያሉት የንጉሥ ሠለሞን ምሳሌዎች በበርካታ ክርስቲያን ባህሎች ታውቀዋል። እንዲሁም በተረፉት መጻሕፍት የተወሰዱ ምሳሌዎች አሉ። አማርኛ ምሳሌ የብዙ አማርኛ ምሳሌ ትርጉም በ[=704 አዲሱ የምሳሌያዊ አነጓገሮች] ይገኛል። እንግሊዝኛ ምሳሌ " (ቤንጃሚን ፍራንክሊን)፤ ቶሎ ለመኝታ፣ ቶለ ለመነሣት፣ ሰውን ጤንኛ፣ ባለጸጋና ጥበበኛ ያደርገዋል። ተረትና ምሳሌ
21221
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%9B%E1%8B%AD%E1%8C%A0%E1%88%A8%E1%8C%A5%E1%88%AD%20%E1%89%A4%E1%89%B1%E1%8A%95%20%E1%8A%A0%E1%8B%AB%E1%8C%A5%E1%88%AD
የማይጠረጥር ቤቱን አያጥር
የማይጠረጥር ቤቱን አያጥር የአማርኛ ምሳሌ ነው። የማይጠረጥር ቤቱን አያጥር የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
47269
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%AA%E1%89%BB%E1%88%AD%E1%8B%B5%20%E1%89%AB%E1%8C%8D%E1%8A%90%E1%88%AD
ሪቻርድ ቫግነር
ሪቻርድ ቫግነር (ጀርመንኛ፦ ) ከ1805 እስከ 1875 ዓም የኖረ የጀርመን ኦፔራ ደራሲ ነበር። የጀርመን ሰዎች
34195
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B3%E1%8A%85%E1%88%A3%E1%88%A5%20%E1%8D%B2%E1%8D%AE
ታኅሣሥ ፲፮
ታኅሣሥ ፲፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፮ተኛው እና የመፀው ወቅት ፹፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፷ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፶፱ ቀናት ይቀራሉ። ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከፈረንሳይ መንግሥት የተለገሡትን ሄሊኮፕተር ተረከቡ። ዕለተ ሞት ዋቢ ምንጮች
31667
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A6%E1%8A%95
ቦን
ቦን (ጀርመንኛ፦ የጀርመን ከተሞች
22922
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B3%E1%8A%85%E1%88%A3%E1%88%A5%20%E1%8D%B2%E1%8D%B1
ታኅሣሥ ፲፱
ታኅሣሥ ፲፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፱ነኛ እና የወርኀ መፀው ፹፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፶፯ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፶፮ ቀናት ይቀራሉ። ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፱፻፩ ዓ/ም - በሲሲሊ ደሴት፣ መሲና ከተማ አካባቢ የተነሣው የመሬት እንቅጥቅጥ ከ፸፭ሺህ በላይ የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ። ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማኅበር ሊቀ መንበር፣ ጥላሁን ግዛው በፖሊስ ተገደለ። ይህ ድርጊት በርዶ የነበረውን የተማሪዎች አመጽ እንደገና አፋፍሞታል። ፳፻፩ ዓ/ም - በሶማሊያ የሥልጣን ትግል ውጊያ የአገሪቱ ጊዜያዊ ፌዴራላዊ መንግሥት ሠራዊት እና አጋሮቻቸው የኢትዮጵያ ወራሪ ኃይል የሞቃዲሹን ከተማ በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ። ፳፻፫ ዓ/ም - በተለምዶ የአረብ መፀው () የተባለው ሕዝባዊ ፀረ-አምባ ገነን አብዮት በአልጄሪያም በዚህ ዕለት ተለኮሰ። ዕለተ ሞት ዋቢ ምንጮች
44208
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%B8%E1%88%8E%E1%89%B5
ጸሎት
ፀሎት ማለት የሰው ልጅ አምላኩን በተመስጦ የሚያመሰግንበት ሁኔታ ነው።
22247
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%85%E1%89%A5%20%E1%8A%AA%E1%89%A0%E1%88%8B%E1%88%85%20%E1%8C%85%E1%89%A5%20%E1%89%A0%E1%88%8D%E1%89%B0%E1%88%85%20%E1%89%B0%E1%89%80%E1%8B%B0%E1%88%B5
ጅብ ኪበላህ ጅብ በልተህ ተቀደስ
ጅብ ኪበላህ ጅብ በልተህ ተቀደስ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ጅብ ኪበላህ ጅብ በልተህ ተቀደስ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
2471
https://am.wikipedia.org/wiki/1994%20%E1%8A%A5.%E1%8A%A4.%E1%8A%A0.
1994 እ.ኤ.አ.
1994 እ.ኤ.ኣ. = 1986 አ.ም. 1994 እ.ኤ.ኣ. = 1987 አ.ም.
40609
https://am.wikipedia.org/wiki/18%20May
18 May
በጎርጎርያን ካሌንዳር የቀን ስም በእንግሊዝኛ ሲሆን ይህ ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር (ከ1892 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2091 ዓ.ም. ድረስ) ምንጊዜም ግንቦት 10 ቀን ማለት ነው። ከ1892 ዓ.ም. አስቀድሞ ወይም ከ2091 ዓ.ም. በኋላ ለሆኑት ዓመታት ግን በሌላ ቀን ላይ መሆኑን ይገንዘቡ። ለእነዚያ ዓመቶች ይህ የቀን መለወጫ መሣርያ ይረዳል። የፈረንጅ ቀኖች
17938
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B0%E1%8A%A9%E1%88%8B%20%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B0%20%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%89%A0%E1%88%B3%20%E1%8A%A5%E1%8C%AE%E1%88%85%20%E1%89%A5%E1%88%8B%20%E1%89%B0%E1%89%B0%E1%88%A8%E1%89%B0%E1%88%A8%E1%89%BD
ተኩላ እንደ አንበሳ እጮህ ብላ ተተረተረች
ተኩላ እንደ አንበሳ እጮህ ብላ ተተረተረች የአማርኛ ምሳሌ ነው። ተረትና ምሳሌ
21589
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%AB%E1%88%88%20%E1%8B%AD%E1%89%A0%E1%8B%9B%E1%88%8D%20%E1%8A%A0%E1%88%88%20%E1%8B%88%E1%8D%8D%E1%8C%AE
ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ
ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
17225
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A3%E1%88%88%E1%8D%88%20%E1%8A%AD%E1%88%A8%E1%88%9D%E1%89%B5%20%E1%89%A4%E1%89%B5%20%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%88%B0%E1%88%AB%E1%88%9D
ባለፈ ክረምት ቤት አይሰራም
ያለፈን ጊዜ መልሶ ማምጣት ስለማይቻል ወደፊት ተመልከት መደብ :ተረትና ምሳሌ
21437
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%8B%B0%E1%8B%B1%E1%89%B5%E1%8A%95%20%E1%88%B2%E1%8B%AB%E1%8C%A1%20%E1%8B%A8%E1%8C%A0%E1%88%89%E1%89%B5%E1%8A%95%20%E1%8B%AD%E1%89%80%E1%88%8B%E1%8B%8D%E1%8C%A1
የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ
የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ የአማርኛ ምሳሌ ነው። የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
34935
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%8C%8A%E1%8B%AB%E1%88%8C%E1%8B%8E%E1%88%B5
አይጊያሌዎስ
አይጊያሌዎስ በግሪክ አፈ ታሪካዊ ዜና መዋዕል ዘንድ የሲክዮን መንግሥት መሥራች ነበረ። አውሳብዮስ (317 ዓ.ም. ጽፎ) ካስቶርን (150 ዓክልበ. ግድም) ሲጠቅስ፣ የአይጊያሌዎስ ዘመን 52 ዓመታት ሲሆን በአሦር ንጉሥ ቤሉስ 15ኛው ዓመት ጀመረ፤ ይህም በግሪክ መጀመርያው መንግሥት (ምናልባት ከ2360-2308 ዓክልበ. ግድም) ነበር ይላል። ከዚህ በላይ ፔሎፖኔሶስ መጀመርያ በእርሱ ስም «አይጊያሌያ» ይባል ነበር፣ ተከታዩም ኤውሮፕስ ነበር ይለናል። ፓውሳንዮስ (107 ዓ.ም. ግድም) እንደ ጻፈ፣ «ሲክዮንያውያን፣ በዚሁ ጠረፍ ክፍል የቆሮንቶስ ሰዎች ጎረቤቶች፣ ስለ ራሳቸው አገር እንደሚሉ አይጊያሌዎስ መጀመርያው ኗሪ ነበረ፣ እስካሁን አይጊያሎስ የተባለው የፔሎፖኔሶስ አውራጃ እርሱ ስለነገሠበት ስለርሱ ተሰየመ፣ በሜዳውም ላይ አይጊያሌያ የተባለውን ከተማ መሰረተ። በተጨማሪ አይጊያሌዎስ ኤውሮፕስን ወለደ፣ ኤውሮፕስም ቴልቂንን ወለደ፣ ቴልቂንም አፒስን ወለደ።» ቢብሊዮጤኬ የተባለው መጽሐፍ (ከ150 ዓክልበ. በኋላ፣ በአፖሎዶሮስ ተጽፎ እንደተባለ) እንደ ጻፈ፣ «ኢናቆስ (የውቅያኖስና ጤቲስ ልጅ) እና ሜሊያ (የውቅያኖስ ልጅ) ወንድ ልጆች ፎሮኔዎስና አይጊያሌዎስ ነበሯቸው። አይጊያሌዎስ ያለ ልጅ አርፎ መላው አገር አይጊያሊያ ተባለ፤ ፎሮኔዎስም በኋላ ፔሎፖኔሶስ በተባለው አገር ሁሉ ነግሦ አፒስንና ኒዮቤን በሴት አድባሩ ቴሌዲኬ ወለዳቸው።» የሲክዮን ነገሥታት
2783
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8A%A8%E1%88%A8%E1%88%9D%20%E1%8D%B2%E1%8D%AC
መስከረም ፲፬
መስከረም ፲፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፲፬ኛው ዕለት እና የክረምት ፹፭ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፶፪ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፶፩ ዕለታት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፮፻፲፭ ዓ/ም - ነቢዩ መሐመድ ከመካ እስከ መዲና ያደረገውን የሱባዔ ጉዞ (ሂጅራ) ፈጸመ። ፲፱፻፷፩ ዓ/ም-ስዋዚላንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም -ጊኒ-ቢሳው ነጻነቷን ከፖርቱጋል ተቀዳጀች። ፲፱፻፷፱ ዓ/ም - በአፍሪቃ አኅጉር ደቡባዊ አካል፣ በ ኢያን ስሚዝ የሚመራው የሮዴዚያ (የአሁኗ ዚምባብዌ) የነጭ አስተዳደር መንግሥቱን ለበዢው የጥቁር ሕዝብ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማስረከብ ተስማማ። ዕለተ ሞት ዋቢ ምንጮች
10349
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8D%93%E1%8A%95%E1%8C%8B%E1%88%B2%E1%8A%93%E1%8A%95%E1%8A%9B
ፓንጋሲናንኛ
ፓንጋሲናንኛ በተለይ በፊሊፒንስ በ2 ሚልዮን ሰዎች ገዳማ የሚናገር ቋንቋ ነው። ዛሬ ቋንቋው የሚጻፍበት በላቲን ፊደል ነው። እስፓንያውያን ከደረሱ አስቀድሞ ግን የራሱ «ባይባዪን» ፊደል ነበረው። - ኢሳ - ዱዋ - ታሎ - አፓት - ሊማ - አነም - ፒቶ - ዋሎ - ሲያም - ሳንፕሎ አውስትሮኔዚያን ቋንቋዎች
20899
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%9D%E1%88%9D%20%E1%89%A5%E1%89%B5%E1%88%8D%20%E1%89%A3%E1%89%B5%E1%8A%A8%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%88%9D%20%E1%89%BD%E1%88%8B%20%E1%89%B5%E1%89%A3%E1%88%8D%E1%89%A0%E1%89%B3%E1%88%88%E1%88%85
ዝም ብትል ባትከበርም ችላ ትባልበታለህ
ዝም ብትል ባትከበርም ችላ ትባልበታለህ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ዝም ብትል ባትከበርም ችላ ትባልበታለህ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
22604
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8B%B6
ሰርዶ
ሰርዶ () ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ ሴልዶ ከፕላስቲክ የተሠራ ሣር ነው በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር የተክሉ ጥቅም የኢትዮጵያ እጽዋት
8764
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8A%A8%E1%88%A8%E1%88%9D%20%E1%8D%B2%E1%8D%AA
መስከረም ፲፪
መስከረም ፲፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፲፪ ኛው ዕለት እና የክረምት ፹፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፶፬ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፶፫ ዕለታት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. - የሙሶሊኒ አዲስ ፋሺስታዊ መንግሥት በአዶልፍ ሂትለር ግፊት እና ድጋፍ 'የጣልያን ሕብረተሰባዊ ሪፑብሊክ' በሚል ስም በሰሜን ጣልያን ጀመረ። ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. - ቀድሞ "የፈረንሣይ ሱዳን" የተባለው ቅኝ ግዛት የማሊ ሪፑብሊክ ተብሎ ነጻነቱን አወጀ። ዕለተ ሞት ዋቢ ምንጮች
22284
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%AB%E1%88%8D%E1%8B%B0%E1%8D%88%E1%88%A8%E1%88%B0%20%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%8C%A0%E1%88%AB%E1%88%9D
ካልደፈረሰ አይጠራም
ካልደፈረሰ አይጠራም የአማርኛ ምሳሌ ነው። ካልደፈረሰ አይጠራም የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
3406
https://am.wikipedia.org/wiki/1937
1937
1937 አመተ ምኅረት ነሐሴ 9 ቀን - ጃፓን እጁን ሰጥቶ 2ኛ አለማዊ ጦርነት ጨረሰና ኮርያ ከጃፓን ነጻ ወጣ። ፍራንክሊን ሮዘቨልት በአሜሪካ ምርጫ ለአራተኛ ዘመን ፕሬዚዳንት ተመረጡ። ሚያዝያ 22 ቀን - አዶልፍ ሂትለር ዮፍታሄ ንጉሴ
11865
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%85%E1%8B%B3%E1%88%AD%20%E1%8D%B2%E1%8D%A9
ኅዳር ፲፩
ኅዳር ፲፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፩ኛው እና የመፀው ወቅት ፵፮ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺፬ ቀናት ይቀራሉ። ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፱፻፲ ዓ/ም - ዩክራይን ሪፑብሊክ ሆነች። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - በጀርመን የናዚ ቡድን መሪዎች የነበሩ ሃያ ሰዎች በተከሰሱበት የጦርነት ወንጀሎች በኑረንበርግ ከተማ ወታደራዊ ችሎት ለፍርድ ቀረቡ። ፲፱፻፵ ዓ/ም - የብሪታንያ አልጋ ወራሽ ልዕልት ኤልሳቤጥ (የአሁኗ ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ) በለንደን ዌስትሚኒስተር አቤ ሌፍተናንት (አሁን ልዑል የኤዲንበራ ዱከ) ፊሊፕ ማውንትባተን አገባች። ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - የልደታን አየር ዠበብ ማረፊያ የተካው አዲሱ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ(የቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አውሮፕላን ማረፊያ) በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ። በዚሁ ዕለት ንጉሠ ነገሥቱ የዓመቱን የፓርላማ ጉባዔ ከፈቱ። በዚሁ ዕለት እና ሰዓት የየጠቅላይ ግዛቱ ገዢዎች በተገኙበት ሥርዓት የአስመራ፤ የድሬ ዳዋ እና የጅማ አየር ማረፊያ ጣቢያዎች ተመርቀዋል። ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በአስተዳደር ጥፋት እና በሙስና ወንጀል ተከሰው በልዩ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የቀረቡትን የቀድሞ ባለ-ሥልጣናት መመርመሪያ እንዲሆን የተዘጋጀው አዲስ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ አዋጅ ቁጥር ፰ ታውጆ ወጣ። ይህ ድንጋጌ ባ፲፱፻፵፱ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ ተጨማሪ ነው። ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ከወላይታ-ሶዶ ተነስቶ በምዕራብ ወለጋ ዞን ወደምትገኘው በጊ መንገደኞችን የጫነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዲ-ሲ ፫ () ለመነሳት ሲያኮበክብ ተከስክሶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በዚህ አደጋ ሦስቱ አብራሪዎቹ ሕይወታቸው አልፏል። ፲፱፻፹፰ ዓ/ም - የብሪታንያ አልጋ ወራሽ የልዑል ቻርልስ ሚስት ልዕልት ዳያና ስለጋብቻቸው መፍረስ እና እርሷም ከሌሎች ወንዶች ጋር ስለማመንዘሯ በቢ. ቢ. ሲ. ቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ አደረገች። ፲፱፻፲፰ ዓ/ም - በአሜሪካ የ፲፱፻፷፩ ዓ.ም. የፕሬዚደንትነት ምርጫ ተወዳዳሪ እና የሟቹ የፕሬዚደንት ጆን ፊትዝጄራልድ ኬኔዲ ታናሽ ወንድም ሮበርት ፍራንሲስ ኬኔዲ ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - ደራሲውና ጋዜጠኛው ጳውሎስ ኞኞ ቁልቢ አካባቢ ተወለደ። ዕለተ ሞት ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - እስፓኝን በአምባ ገነን ስርዐት ለሠላሳ ስድስት ዓመት የገዛው ጄኔራል ፍራንሲስኮ ፍራንኮአረፈ። ፳፻ ዓ/ም - በቀድሞዋ ሮዴዥያ (የዛሬይቱ ዚምባብዌ) ሕገ ወጥ ነጻነትን ያወጀው ኢያን ስሚዝ ዋቢ ምንጮች
12092
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%B0%E1%89%A1%E1%89%A5%20%E1%8A%A0%E1%88%9C%E1%88%AA%E1%8A%AB
ደቡብ አሜሪካ
ደቡብ አሜሪካ በአለም ካርታ ላይ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ምእራብ የሚገኝ አህጉር ነው። ደቡብ አሜሪካ
49293
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%80%E1%89%B5%20%E1%88%8A
ጀት ሊ
ጀት ሊ (1955 አም ተወለደ) ዝነኛ ቻይናዊ የኩንግ-ፉ ፊልም ተዋናይ ነው። አሁን በሲንጋፖር ይኖራልና ኡእሲንጋፖር ዜጋ ሆኗል። የቻይና ሰዎች
16319
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%8D%E1%89%A5%E1%8B%88%E1%88%88%E1%8B%B5%20%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AD%20%E1%8C%A6%E1%89%A2%E1%8B%AB
ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ
ጦቢያ ወይም ልብወለድ ታሪክ ጦቢያ በአፈወርቅ ገብረ እየሱስ በ፲፱፻ ዓ.ም. በሮማ የታተመ ሲሆን 90 ገጾች አሉት። በኢትዮጵያ የሥነ ፅሑፍ ታሪክ የመጀመሪያ ልብወለድ መፅሐፍ ለመሆኑ የሚነገርለት ይህ መጽሐፍ በወቅቱ ተነስቶ የነበረውን የአረማውያንንና የክርስቲያኖችን ጦርነት ይተርካል። ደራሲው በመፅሐፉ ውስጥ ስለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም ስለደግነትና ክፋት፣ ስለሀይማኖትና ፍቅር በሰፊው ያትታሉ። መፅሐፉ በተለይ የፍቅርን ሀያልነት ለማሳየትና የሀይማኖት ልዩነት ስላልበገረው ታላቅ ፍቅር በሰፊው ይተርካል። በተጨማሪም ደራሲው በጽሑፉ ውስጥ ሊያስተላልፉ የሞከሩት መልዕክት የሰው ልጅ በባዕድ አምልኮ ተሸብቦ ከመኖር ይልቅ ፈተናና ችግር ቢገጥሙት እንኳን ለእነዚህ ሳይበገር በአንድ አምላክ አምኖ ከጸና ድል ሊያደርግ እንደሚችል ነው። ጦቢያን ወደ እንግሊዝኛ ለመተርጎም ጥረቱ ተጀምሯል። ከዚህ በፊት የመጀመሪያውን የትግርኛ ልብወለድ መጽሐፍ ወደ እንግሊዝኛ የተረጎመው ግርማይ ነጋሽ በሚቀጥሉት ጊዚያት ጦቢያን ለመተርጎም ወደደቡብ አፍሪካ እንደሚያመራ አሳውቁአል። የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ
16697
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%85%E1%88%8D%E1%8B%8D%E1%8C%A5%20%E1%8A%A0%E1%88%B3%E1%88%B5%E1%89%A6%20%E1%8B%AD%E1%8C%A5%E1%88%8B%E1%88%8D%20%E1%8B%98%E1%88%98%E1%89%BB
ቅልውጥ አሳስቦ ይጥላል ዘመቻ
ቅልውጥ አሳስቦ ይጥላል ዘመቻ የአማርኛ ምሳሌ ነው። መደብ : ተረትና ምሳሌ
11511
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B4%E1%8B%8E%E1%89%A5%E1%88%B5%E1%89%B3
ቴዎብስታ
ቴዎብሰታ የቅዱስ ጊዮርጊስ እናት ናት። በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ልማድና ትምህርት ከፍልስጥኤም ነበረች፣ ልጇም ሲያድግ እርስዋና አባቱ የቀጴዶቅያ አለቃ አናስታስዮስ አርፈው ነበር። በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቶያን ልማድ ግን የወላጆቹ ስሞች ጌሮንቲዩስ እና ፖሊክሮኒያ ተባሉ።
40139
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%88%8B%E1%8A%A9%20%E1%8B%88%E1%88%A8%E1%8B%B0
መላኩ ወረደ
መላኩ ወረደ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከኣሉ ስምንት የተለያዩ የእጽዋት ክምችቶች ከኣሉበት ኣገሮች ኣንዷ ናት። ኢትዮጵያ ላይ በተደጋጋሚ በደረሰው ድርቅና ጠኔ የተነሳ የኣገርዋ የሰብል ዘሬች እንዳይጠፉ በመሰብሰብና እንዳስፈላጊነቱም መልሶ ለገበሬዎች በመስጠት ዶ/ር መላኩ ወረደ የሚደነቅ ሥራ ኣከናውነዋል። የሥራቸውም ውጤት ከኣፍሪቃ ተርፎ በዓለም ከኣሉት ኣስተማማኝ ክምችቶች ኣንዱ ሆኗል። ዶ/ር መላኩ በእርሻ ማልማት ላይ የብዙኅ ሕይወትን ለመጠበቅና ለማብዛት እንደሚቻል ያሳወቁ፣ ያረጋገጡ ፈር ቀዳጅ ተመራማሪ ስለመሆናቸውም ዓለም አቀፍ ዘገባዎች ይመሰክራሉ። ዶ/ር መላኩ ወረደ ይህ የእጽዋት ክምችት እንዳይጠፋ በኣለፉት ኣያሌ ዓመታት ትልቅ ኣስተዋጽዖ ኣድርገዋል። ለእዚህም ሥራቸው “ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ” ወይም “” የሚባል ሽልማት በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. ተሰጥቷቸዋል። ዋቢ ምንጮች 1989 “ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ” ኣበራ ሞላ፣ ስመ እጽዋት «ትልቁ ችግራችን በእጃችን ላይ ያለውን ሀብት በትክክል አናውቀውም» ዶ/ር መላኩ ወረደ የኢትዮጵያ ሰዎች ራይት ላይቭሊሁድ ኣዋርድ
12790
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%8C%E1%8C%A3%E1%8C%8C%E1%8C%A5
ጌጣጌጥ
ጌጣጌጦች ለተጨማሪ ውበት የሚለበሱ ወይም የሚደረጉ እንደ የአንገት ሐብል፣ የእጅ አምባር፣ የጣት ቀለበት እና የጆሮ ጌጥ የሉ እቃዎች ናቸው። የሠው ልጆች ለሺዎች አመታት ለመዋቢያነት ሲያመርቷቸው እና ሲጠቀምባቸው ቆይተዋል። እነዚህ መዋቢያዎች እንደየሀገሩ ባህል እና እምነት (የንጥረ-ነገሮች የመገኘት አቅም ጋር ተያይዞ) ከተለያዩ ነገሮች ሊሠራ ይችላል። ማንኛውም ጌጣጌጥ ከግል መዋቢያነት በተጨማሪ እንደ ሀብት መለኪያ ተደርጎ ሊወሰድም ይችላል። እንደ ቀበቶ እና ቦርሳ ያሉት ከጌጣጌጦች ጋር አይመደቡም።
19887
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B3%E1%88%AD%E1%89%84%20%E1%89%B0%E1%88%98%E1%88%AD%E1%89%84%20%E1%89%B3%E1%8C%A5%E1%89%A4%20%E1%89%B0%E1%88%88%E1%89%83%E1%88%8D%E1%89%84
ታርቄ ተመርቄ ታጥቤ ተለቃልቄ
ታርቄ ተመርቄ ታጥቤ ተለቃልቄ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ጥሩ ሆነለኝ መደብ :ተረትና ምሳሌ
16570
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%80%E1%8A%95%20%E1%8B%A8%E1%8C%8E%E1%8B%B0%E1%88%88%E1%89%A0%E1%89%B5%20%E1%8C%A0%E1%8C%88%E1%88%AB%20%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%8C%A5%20%E1%8B%AD%E1%89%A0%E1%88%8B%E1%8B%8B%E1%88%8D
ቀን የጎደለበት ጠገራ አይጥ ይበላዋል
ቀን የጎደለበት ጠገራ አይጥ ይበላዋል የአማርኛ ምሳሌ ነው። መደብ : ተረትና ምሳሌ
49048
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%99%E1%88%89%E1%8A%9B
ዙሉኛ
ዙሉኛ ( /ኢሲዙሉ) ከባንቱ ቋንቋዎች ቤተሠብ አንድ ነው። የሚነገርበት በተለይ በደቡብ አፍሪካ አገር ምሥራቅ ነው። ተናጋሪዎቹ 10 ሚልዮን ናቸው። ውሃ - /አማንዚ/ ደመና - /ኢፉ/ ማር - /ኡጁ/ አንበሳ - /ኢምቡቤ/ ላም - /ኢንኮሞ/ ቀንድ - /ኡጶንዶ/ ባንቱ ቋንቋዎች
8880
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%90%E1%88%9B%E1%8B%9A
ሐማዚ
ሐማዚ ምናልባት በ2420 ዓክልበ. ገዳማ የነበረ መንግሥት ሲሆን በምዕራብ ዛግሮስ ተራሮች ከኤላምና ከአሦር መካከል እንደተገኘ ይታሥባል። ሐማዚ ለሥነ-ቅርስ ጥናት መጀመርያ የታወቀው በዚህ ቦታ ላይ የኪሽ ንጉሥ ኡቱግ ወይም ኡሁብ ድል የሚመዝገብ በጥንታዊ ባለ-ማዕዘን (ኩኔይፎርም) ጽሕፈት የተጻፈ ጽላት ሲገኝ ነበር። ሌላ ጥንታዊ ጥቅስ ደግሞ ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ በተባለ አፈ ታሪክ ተገኝቷል። እዚህ ኡሩክና ኤሪዱ ግንቦች በተሠሩ ጊዜ ስለ ልሣናት መደባለቅ የተለያዩ አገራት ሲዘረዘሩ በመዝሙር ይጠቀሳል። በዚሁ ዝርዝር፣ ሐማዚ ብቻ «ባለ ብዙ ልሳናት» የሚል ስያሜ ይሠጣል። የሚከተለው ጽሑፍ ኤንመርካርና ኤንሱህከሽዳና እንደሚለው፣ ሐማዚ ከጠፋ በኋላ የሐማዚው ጠንቋይ ኡርጂሪኑና ወደ አራታ ፈልሶ፣ ከዚያ የአራታ ንጉሥ ኡሩክን ለማሸነፍ በኤንመርካር ላይ ልኮት አልተከናወነም። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር መሠረት የሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ ኪሽን ካሸነፈ በኋላ (2243 ዓክልበ. ግ.) በሱመር ላይ ላየኛነት ያዘ። እሱ ግን በተራው በ2215 ዓክልበ. ግ. በኡሩክ ንጉስ በኤንሻኩሻና ድል ሆነ። በኤብላ ከተማ በሶርያ በተገኘ የሸክላ ጽላት ላይ አንድ ዲፕሎማቲካዊ መልእክት ከኤብላ ንጉስ ኢርካብ-ዳሙ (2110 ዓክልበ. ግ.) ወደ ሐማዚ ንጉስ ዚዚ ከብዙ ዕንጨት ጋር ተላከ። እንደ ወንድም ሆኖ ሰላምታ ሰጥቶ በምላሽ ወታድር እንዲልክለት ይጠይቀዋል። በአዲስ ሱመራዊ ኡር መንግሥት ጊዜ በንጉስ አማር-ሲን ዘመን (1918-1909 ዓክልበ.) ሐማዚ ከጠቅላይ ግዛቶቹ አንድ ነበር። በዚህ ዘመን የአገረ ገዥ ስሞች ኡር-ኢሽኩር እና የናምሃኒ ልጅ ሉ-ናና ይታወቃሉ። የኡር መንግሥት ሊወድቅ ሲል (1879 ዓክልበ. ገዳማ) ጠቅላይ ግዛቱን የኢሲን አለቃ ኢሽቢ-ኤራ ወረረው። ታሪካዊ አገሮች የፋርስ ታሪክ የመስጴጦምያ ታሪክ
16040
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B1%20%E1%8A%95%E1%8B%8B%E1%8B%AD
መንግሥቱ ንዋይ
መንግሥቱ ንዋይ በ፲፱፻፰ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ አራዳ ጊዮርጊስ ገዳም ሠፈር አካባቢ ተወለዱ። አባታቸው ዓለቃ ንዋይ የደብሩ ዓለቃ ነበሩ። ትምሕርታቸውን በተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ተከታትለው አዲሱ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት ሲመሰረት ወደዚያ ተዛውሩ። የገነት ጦር ትምሕርት ቤት ሲከፈት ደግሞ፣ መንግሥቱ ንዋይ ተመልምለው ከገቡት ዕጩ መኮንኖች አንዱ ነበሩ። ሌሎች (በኋላ ጄነራሎች) እንደነ አቢይ አበበ፣ አሰፋ አያና፣ ኢሳያስ ገብረሥላሴና ከበደ ገብሬ በዚሁ ትምሕርት ቤት ከመንግሥቱ ጋር የነበሩ ዕጩ መኮንኖች ናቸው። መንግሥቱ ከዚያው የጦር ትምሕርት ቤት በመቶ አለቃ ማዕረግ ተመርቀው ሲወጡ ወዲያው የጠላት ኢጣልያ ጦር አገሪቱን ይወርና እሳቸው ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር ወደማይጨው ዘምተው ግዴታቸውን ተውጥተዋል። ጠላትም ድሉን ሲቀዳጅ እና ንጉሠ ነገሥቱ ሲሰደዱ መቶ አለቃ መንግሥቱ በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደሸሸበት ነቀምት ሄደው እዚያ “ጥቁር አንበሳ” የሚባለውን ማኅበር መሥራች አባል ናቸው። ከጥቂት ጊዜም በኋላ ከጓደኞቻቸው ጋር ወደጅቡቲ ተሰደዱ። በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ንጉሠ ነገሥቱ ተመልሰው ካርቱም ሲገቡ እነኚህን ስደተኛ መኮንኖች ከጅቡቲ ወደካርቱም እንዲመጡ ይደረግና መንግሥቱ ንዋይ ከነ ሙሉጌታ ቡሊ፣ ነገሠ ወልደሐና፣ ወልደማርያም ኃይሌ፣ ዘውዴ ገበሳ እና ታምራት ዘገየ ጋር ሆነው ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ተቀላቀሉ። ወዲያውም ከእሳቸው ጋር በ፲፱፻፴፫ ዓ/ም አብረው ወደኢትዮጵያ በድል ሲገቡ በክብር ዘበኛ ውስጥ በጄኔራል ሙሉጌታ ሥር ሻምበል ሆነው ቆዩ። በመስከረም ወር ፲፱፻፵፱ ዓ/ም ኮሎኔል መንግሥቱ ብርጋዴር ጄኔራል ተብለው የክብር ዘበኛ ጠቅላይ አዛዥነትን ተሾሙ። ተራማጅ እና የክብር ዘበኛን ሠራዊት በሰገላዊ ውትድርና ንቃተ ሕሊናውን ለማዳበር ብዙ የጣሩ መኮንን እንደነበሩ ተመስክሮላቸዋል።
51030
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%89%B1%E1%8A%92%E1%8B%9A%E1%8B%AB%20%E1%89%A5%E1%88%94%E1%88%AB%E1%8B%8A%20%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%88%AD%20%E1%8A%B3%E1%88%B5%20%E1%89%A1%E1%8B%B5%E1%8A%95
የቱኒዚያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን
የቱኒዚያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ቱንሲያን ወክሎ በእግር ኳስ ይወዳደራል። አስተዳዳሪው አካል የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው። ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች
20113
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B5%E1%8D%88%E1%8C%AD%20%E1%8B%A8%E1%8A%90%E1%89%A0%E1%88%A8%E1%89%BD%20%E1%88%9B%E1%8A%95%E1%8C%93%E1%88%88%E1%88%8D%20%E1%89%B0%E1%88%B3%E1%8A%93%E1%89%B5
ትፈጭ የነበረች ማንጓለል ተሳናት
ትፈጭ የነበረች ማንጓለል ተሳናት የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ
32745
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%96%E1%88%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%BD%20%E1%89%80%E1%8A%95%E1%89%A0%E1%88%AD
የኖርማኖች ቀንበር
«የኖርማኖች ቀንበር» በተለይ በ17ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ አገር ፖለቲካ አንዳንዴ የሚሰማ ዘይቤ ነው። በፑሪታን ዘመን በአንዳንድ ወገን (ለምሳሌ የቆፋሪዎቹ መስራች ጄራርድ ዊንስታንሊ) አስተሳሰብ፣ ከኖርማኖች ወረራ (1058 ዓ.ም.) አስቀድሞ እንግሊዞች (አንግሎ-ሳክሶኖች) ቀና፣ ጻድቅ፣ እና በእኩልነት የኖረ ነገድ ሆነው ነበር። ኖርማኖች ከፈረንሳይ ከወረሩ በኋላ ግን መንግሥቱን በመያዛቸው የአገሩ መኳንንት ሆኑ፣ ኗሪ እንግሊዞች ግን ተራ ሕዝቦች ሆነው በኖርማኖች ሥር («የኖርማኖች ቀንበር») ተጨቆኑ። በዚሁ ሃሣብ የእንግሊዝ ንጉሥና የእንግሊዝ መንግሥት የኖርማኖች ተከታዮች እንደ ሆኑ ይታዩ ነበር። የአውሮፓ ታሪክ
22226
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%85%E1%89%A5%20%E1%88%9D%E1%8A%95%20%E1%8B%AD%E1%88%98%E1%88%B5%E1%88%8B%E1%88%8D%20%E1%8A%A5%E1%8C%8D%E1%88%A9%20%E1%8B%AB%E1%8A%90%E1%8A%AD%E1%88%B3%E1%88%8D%20%E1%8A%A0%E1%8D%89%20%E1%8B%AD%E1%8A%90%E1%8A%AD%E1%88%B3%E1%88%8D
ጅብ ምን ይመስላል እግሩ ያነክሳል አፉ ይነክሳል
ጅብ ምን ይመስላል እግሩ ያነክሳል አፉ ይነክሳል የአማርኛ ምሳሌ ነው። ጅብ ምን ይመስላል እግሩ ያነክሳል አፉ ይነክሳል የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
22594
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%9B%E1%88%BD%E1%88%8B
ማሽላ
ማሽላ () ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ወገን ነው። የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ ዘንጋዳ () በዚህ ወገን አለ። በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር የተክሉ ጥቅም የኢትዮጵያ እጽዋት
47327
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%86%E1%8A%A9%E1%88%B3%E1%8B%AD
ሆኩሳይ
ካጹሺካ ሆኩሳይ (ጃፓንኛ፦ 1753-1841 ዓም) ዝነኛ የጃፓን ሰዓሊ ነበር። የጃፓን ሰዎች
12394
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%83%E1%8A%95%20%E1%8B%93%E1%88%98%E1%89%B5
የብርሃን ዓመት
የብርሃን አመት ብርሃን በሰከንድ እስከ 300,000 ኪ.ሜ. እየተጓዘ በአንድ አመት የሚጨርሰው ርቀት ነው። ብዙ ጊዜ ይህ ርቀት በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ በጠፈር ውስጥ ያሉ ርቀቶችን ለመለካት እንጠቀምበታለን። ሥነ ፈለክ
20902
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%9D%E1%88%9D%E1%89%B3%20%E1%88%88%E1%89%A0%E1%8C%8D%E1%88%9D%20%E1%8A%A0%E1%88%8D%E1%89%A0%E1%8C%83%E1%89%B5%20%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%88%AB%20%E1%88%81%E1%88%88%E1%89%B5%20%E1%88%86%E1%8A%93%20%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5%20%E1%8A%90%E1%89%A5%E1%88%AD%20%E1%8D%88%E1%8C%83%E1%89%B5
ዝምታ ለበግም አልበጃት አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት
ዝምታ ለበግም አልበጃት አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት የአማርኛ ምሳሌ ነው። ዝምታ ለበግም አልበጃት አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
20905
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%9D%E1%88%9D%E1%89%B3%20%E1%8B%88%E1%88%AD%E1%89%85%20%E1%8A%90%E1%8B%8D
ዝምታ ወርቅ ነው
ዝምታ ወርቅ ነው የአማርኛ ምሳሌ ነው። እንዲሁም የሚል ምሳሌ ደግሞ በቻይንኛና በአለም ዙሪያ ይገኛል። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
31891
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%8A%93%E1%8B%B3
ግራናዳ
ግራናዳ (እስፓንኛ፦ ) የእስፓንያ ከተማ ነው። የእስፓንያ ከተሞች
20229
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%95%E1%8C%89%E1%88%B1%20%E1%89%A2%E1%88%9E%E1%89%B1%20%E1%8A%A8%E1%88%9B%E1%8A%95%20%E1%8B%AD%E1%88%9F%E1%8C%88%E1%89%B1
ንጉሱ ቢሞቱ ከማን ይሟገቱ
ንጉሱ ቢሞቱ ከማን ይሟገቱ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ
20264
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A5%E1%89%B0%E1%8A%AB%E1%8A%A8%E1%88%8D%20%E1%89%B0%E1%8C%8D%E1%88%98%E1%88%8D
እተካከል ተግመል
እተካከል ተግመል የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ
30939
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A3%E1%89%A2%E1%88%8E%E1%8A%95
ባቢሎን
ባቢሎን (አካድኛ፦ ባቢሊ፣ ዕብራይስጥ፦ ባቤል) በመስጴጦምያ የነበረ ጥንታዊ ከተማ ነው። ስሙ በአካድኛ ከ/ባብ/ (በር) እና /ኢሊ/ (አማልክት) ወይም «የአማልክት በር» ማለት ነበር። በዕብራይስጥ ግን ስሙ «ደባልቋል» እንደ ማለት ይመስላል (ዘፍ. 11:9)። «ባቢሎን» የሚለው አጠራር እንደ ግሪክኛው ነው። መጀመርያው «ባቢሎን» የደቡብ ሱመር ከተማ የኤሪዱ መጠሪያ ስም እንደ ነበር ይመስላል። በሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ከማየ አይኅ ቀጥሎ ኤሪዱ የዓለሙ መጀመርያው ከተማ ሲሆን፣ ንጉሡ ኤንመርካር (2450 ዓክልበ. አካባቢ) ታላላቅ ዚጉራቶችን (የቤተ መቅደስ ግንቦች) በኤሪዱ እና በኦሬክ እንዳሠራ ይለናል። ይህም በሌሎች ልማዶች እንደሚተረክ የባቢሎንና የኦሬክ መሥራች ናምሩድ የባቢሎን ግንብን እንደ መሥራቱ ታሪክ ይመስላል። ከሱመር ጽላቶች እንደምናውቅ፣ የኤሪዱ ግንብ ከተተወ በኋላ፣ የሱመር ዋና ከተማ (ዋና ቤተ መቅደስ የተገኘበት) ወደ ኒፑር ተዛወረ። ከዚያ ዘመን በኋላ የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን (2070 ዓክልበ. ግድም) አዲስ የዋና መቅደስ ከተማ ወደ ስሜኑ ሠርቶ ማዕረጉን ከኒፑር አንዳዛወረ እናንብባለን። በአንዱ ዜና መዋዕል ዘንድ ሳርጎን «የባቢሎን ጒድጓድ አፈር ቆፍሮ አዲስ ባቢሎን በአካድ ፊት ሠራ»፣ በሌላም «ከጒድጓዱ አፈር ቆፍሮ በአካድ ፊት ከተማ ሠራ፣ ስሙንም 'ባቢሎን' አለው።» ከዚህ መረጃ ሳርጎን የኤሪዱን አፈር ወስዶ አዲሱን ባቢሎን በሥፍራው እንደመሠረተው መገመት እንችላለን። ሳርጎንም እንደ ፊተኛው ኤንመርካር «የአራት ሩቦች ንጉሥ» በመባሉ በሌሎች መንግሥታት ሁሉ በላይ ሆኖ በመላው ዓለም ላይ ይግባኝ ማለት እንደ መጣሉ ነበር። ሆኖም ይህ የኒፑር ቅድምትነት መተካቱ ለጊዜው በሱመራውያን መካከል ተቃውሞ ያገኝ ነበር። ከአካዳውያን፣ ጉታውያንና ሱመራውያን ገዥነት በኋላ፣ አሞራውያን የተባሉት ብሔር ወርሮ አያሌ ከተማ-ግዛቶች መሠረቱ። ከዚህም መካከል አንዱ ካዛሉ ሲሆን አሞራዊው አለቃ ሱሙ-አቡም በ1807 ዓክልበ. ግድም የባቢሎን ነጻነት ከካዛሉ አዋጀ፤ በዚያን ጊዜ እሱ የባቢሎን መጀመርያ ንጉሥ ሆነ። ከባቢሎን ነገሥታት ሃሙራቢ የሃሙራቢ ሕግ ፍትሕ ስለ መፍጠሩ በተለይ ይታወቃል። የባቢሎን መጀመርያ ውድቅት በ1507 ዓክልበ. (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) በኬጥያውያን ንጉሥ ፩ ሙርሲሊ እጅ ደረሰ። ከዚያ የኬጥያውያን ጓደኞች የነበሩት ካሣውያን ብሔር ባቢሎንን ገዛ፣ የከተማውም ስም በካሣኛ «ካራንዱኒያሽ» ተባለ። እነዚህ ካሣውያን እስከ 1163 ዓክልበ. ድረስ ባቢሎኒያን ገዙ። ለረጅም ዘመናት አሦር በስሜንና የባቢሎኒያ መንግሥት በደቡብ ለመስጴጦምያ ዋና ተወዳዳሪዎቹ ሆኑ። ከ919 ዓክልበ ጀምሮ አሦር ይበረታ ነበር፤ እስራኤልንና ግብጽን እስከሚያሸንፋቸው ድረስ። ከ634 ዓክልበ. በኋላ ግን አሦር ወድቆ ባቢሎኒያ በናቦፖላሣር ሥር እንደገና ነጻነት አገኘ። ልጁም 2 ናቡከደነጾር ከብሉይ ኪዳን እንደሚታወቅ፣ ኢየሩሳሌምን የይሁዳንም ሕዝብ የማረከው (የባቢሎን ምርኮ) ነቢዩም ዳንኤል የነበየለት ንጉሥ ነው፤ ዳንኤልም የናቡከደነጾር የምስል ሕልም አስተረጎመለት። ይህ የባቢሎኒያ መንግሥት በ547 ዓክልበ. ለፋርስ ንጉሥ ታላቁ ቂሮስ ወደቀ። በ283 ዓክልበ. በግሪኮች ዘመን (ከታላቁ እስክንድር በኋላ)፣ የባቢሎን ኗሪዎችና መቅደስ ወደ ሴሌውክያ በግድ ተዛወሩ። ከዚህ ጀምሮ ባቢሎን አነስተኛ ሥፍራ ሆነ። በኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች በቀድሞ ክርስቲያኖች መሃል፣ የአረመኔው የሮሜ መንግሥት በሥውር እንደ «ባቢሎን» እንደ ታወቀ ይታሥባል። በዚህ ዘመን ስለ ሮሜ መንግሥት በገሃድ ትዝብት ማድረስ እንደ ወንጀል ተቆጠረና። እንዲሁም «ባቢሎን» በዮሐንስ ራዕይ ይጠቀሳል። ዛሬውም በተገኘው በራስታፋራይ እንቅስቃሴ ደግሞ «ባቢሎን» ሲባል ከንጉሣቸው ያመጹትን መንግሥታትና ሥልጣናት ያመልክታል። ቂሮስ አይሁዶች ወደ ይሁዳ እንዲመለሱ ቢፈቅድም፣ ብዙ አይሁዶች በባቢሎን አካባቢ ቀሩ፣ እነኚህ ከ370-470 ዓም ያህል የባቢሎኒያ ተልሙድ የተባለውን እምነት ጽሑፍ ፈጠሩ። በ1975 ዓም የኢራቅ ገዢ ሳዳም ሁሠይን አዲስ ባቢሎን በፍርስራሹ ላይ ማገንባት ጀመረ። በ1996 ዓም ግን የአሜሪካ ሥራዊት በጦርነት አጠፉት። ደግሞ ይዩ የባቢሎን ነገሥታት ዝርዝር የመስጴጦምያ ታሪክ የቀድሞ ከተሞች
13292
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%89%85%E1%88%B0%E1%8D%8D%E1%89%B5%20%28%E1%88%8D%E1%89%A6%E1%88%88%E1%8B%B5%29
መቅሰፍት (ልቦለድ)
የተደረሰበት ጊዜ፡ በ እድገት በህብረት ዘመቻ እስከ ቀይ ሽብር በነበረው የማበራዊ ኑሮ ቀውስ ላይ ተመስርቶ ፣ ሁለት ፍቅረኞችን በወቅቱ በነበረው ቀውስ ውስጥ ለማለፍ የሚያድርጉትን ትግል የሚተርክ ባላ 510 ገጥ ልቦልድ ነው... መደብ : የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ
1988
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8C%A5%E1%8A%95%E1%89%B0%20%E1%8A%95%E1%8C%A5%E1%88%AD%20%E1%8C%A5%E1%8A%93%E1%89%B5
የጥንተ ንጥር ጥናት
ኬሚስትሪ ወይም የጥንተ-ንጥር ጥናት የቁሶችን አሰራር እና ጸባይ ያጠናል። የ«ኬሚስትሪ» ስም የሚመጣ ከእንግሊዝኛ ሲሆን እሱ የተወለደ ከ1700 ዓ.ም. አካባቢ በፊት «አልኬሚ» ከተባለ ሌላ ጥናት ነበር። ይህም አልኬሚ ዋና ዒላማ ብረት ወደ ወርቅ ለመቀየር ነበር። የማይቻል ምኞት እንደ ነበር የዛኔ ተገነዘበ። አልኬሚ የሠራ ሰው 'አልኬሚስት' ተባለ ወይም በአጭሩ 'ኬሚስት'። በኋላ ትውልድ የኬሚስት ሥራ 'ኬሚስትሪ' ተባለ። የ«አልኬሚ» ስም ደግሞ የወጣ ከዓረብኛ «አል-ኪሚያ» ( ወይም ) ማለት «የመቀየር ጥበብ» ሲሆን የዚህ ቃል መነሻ በእርግጠኝነት አይታወቅም። ወይም ከግሪክ «ቄሜያ» (, ቀላጭ ብረታብረት) ወይም ከግብጽ ዱሮ ስም «ከመት» («የከመት ጥበብ» ለማለት) ሊሆን ይችላል። እንዲሁም በእንግሊዝኛ ኬሚካል የሚለው ቃል ድምጽ ኃይል ከ«ኬሚስትሪ» ሲሆን፣ በዐማርኛ «ጥንተ ንጥር» መባሉ ከግዕዝ ነው። «ንጥር» ማለት የተነጠረ ወይም የተጠራ እንደ ንጥር ቅቤ ቢሆን ፅንሰ ሀሣቡ ከነጥሮን (ሶዲየም ከሰላ ወይም አምቦ አመድ) ጋር፣ በግሪክም /ኒትሮን/፣ ዓረብኛ /ናጥሩን/፣ ዕብራይስጥ /ኔቴር/፣ ግብጽኛ /ነቸሪት/ («የአምላክ») እንደ ተዛመደ ይታሥባል። የንጥረ ነገሮች ሰንጠረዥ ፔሪዮዳዊ ሢስተም'ክፍለ ጊዜአውዊ ስርአቱ' ባምርኛ የሚለውን´ ጴር ዮድ´ ተብሎ ማድመጽ ዪቻል ይሆን ? ግ እዝ የባህር ማዶን ቃል ውደራሱ ቛንቛ ማድመጽ ስፊ ልምምድ አለው፡ ሌሎች ቛንቋዎች ይህን ያደርጋሉ፡፡ የንጥረ ነገር ስሞች በአማርኛ፦ - ጥላት - ድኝ - ብረት - መዳብ - ብር ዚንቅ ዚንክ በንግሊዘኛው ሊድ በአማርኛው ቴሞን ውይም እርሳስ እንቆቅ--ብረት (ኮፐር) አሴቶ አቼቶ አሴቲን ባሩድ....ፈንጂ ማቴርያዉነት (ማቴርያል) መርዛሜነት.... የተፍጥሮ ዘረ መሰረት (ኤሌሜንት) ባህርይ - ቆርቆሮ - ኩል - ወርቅ - ባዜቃ - እርሳስ የጥንተ ንጥር ጥናት
49197
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%9B%E1%89%B4%E1%8B%8E%E1%88%B5%20%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%88%E1%88%BB
ማቴዎስ መንገሻ
ማቴዎስ መንገሻ በ1978 ሰኔ 23 እንደ ኢትዮጲያ አቆጣጠር በአዲስ አበባ ከተማ ከእናቱ ከወ/ሮ አዲስ በቀለ እና ከአባቱ መንገሻ መጃ ተወለደ ፡፡ እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢው በሚገኘው ብርሃንና ሰላም ና የካቲት 23 አንደኛ ደረጃዎች ከተማረ በኃላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በከፍተኛ 7 2ኛ ደረጃ ተከታትሏል በመቀጠልም ከአድማስ ኮሌጅ በአካውንቲንግ በዲግሪ ተመርቆ በግል ድርጅቶች ለአራት አመታት ተቀጥሮ ሲያገለግል ከቆየ በኋላ የራሱን የግል የልብስ መሸጫ ቡቲክ እና የሞባይል መሸጫና የጥገና ማእከል በወላይታ ሶዶ ከተማ በመክፈት ህብረተሰቡን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በ2009 ዓ.ም ደግሞ ከወይዘሪት ሠላም አሰፋ ጋር ጋብቻ የፈፀመ ሲሆን ሔማን ማቲዎስ ተብላ የምትጠራ የአንዲት ሴት ልጅ አባት በ2010 ዓ.ም ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ሰዎች
16362
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%BB%E1%88%9B%20%E1%88%AB%E1%88%B1%20%E1%8A%90%E1%8B%B6%20%E1%88%AB%E1%88%B1%20%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%80%E1%8A%95%20%E1%8B%AD%E1%88%B0%E1%8C%A3%E1%88%8D
ሻማ ራሱ ነዶ ራሱ ብርሀን ይሰጣል
ሻማ ራሱ ነዶ ራሱ ብርሀን ይሰጣል የአማርኛ ምሳሌ ነው። እራሱን ጎድቶ ሌላውን የሚጠቅም ሰው የሚያሳይ መደብ : ተረትና ምሳሌ
50989
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%93.%E1%88%9D.
ዓ.ም.
ዓመተ ምሕረት ከኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ አለም መምጣት ጋር ተያይዞ በአብዘኛው ክርስቲያናዊ ማሕበረሰብ ዘንድ ለዘመን መግለጫነት ወይም መጠሪያነት የሚሰጥ ስያሜ ነው። በመካከለኛው ዘመን ላቲንኛ ዐኖ ዶምኒ () ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ትርጓሜው ዘመነ ጌታ ወይም የጌታችን ዘመን የሚል ነው፤ ይህም የተወሰደው "ዐኒ ዶምኒ ኖስትሪ ጄሱ ክርስቲ" (በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን) ከተሰኘ ላቲን ኃይለ ቃል ነው። በኢትዮጵያም ለዚሁ በቀረበ መልኩ ዓመተ ምሕረት በመባል ተተርጉሟል። አንዳንድ ጊዜ ሰኩለር ለማድረግ ስፈልጉ የተለያዩ ፀሐፍት ከ፲፯ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ የጋራ ዘመን ወይም ኮሜን ኢራ(ሲ.ኢ) በማለት የመጻፍ የጀመሩ ቢሆንም እንደምክንያትነት የሚወሰደው ነገር የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት እንድሆነ ይታምናል።
11430
https://am.wikipedia.org/wiki/1986
1986
ጥቅምት 6 ቀን - ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር የሱዳን ፕሬዝዳንት ሆኑ። መጋቢት 28 ቀን - በሩዋንዳ በሁቱ እና በቱጺ ነገዶች መካከል የደረሰው ፍጅት ጀመረ።
12651
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B3%E1%89%B5%E1%8B%AB%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%88%83
ሳትያግራሃ
ሳትያግራሃ (ሳንስክሪት፦ ) ማለት ማህተማ ጋንዲ የጀመሩት የሰላማዊ መቃወም ዘዴ ነው። ጋንዲ በሕንድ ነጻነት እንቅስቃሴ እንዲሁም ከዚህ ቀድሞ በደቡብ አፍሪካ ትግል ይጠቀማቸው ነበር። ከዚህ በላይ የሳትያግራሃ ፍሬ ሂሳብ ለኔልሰን ማንዴላ፣ ለማርቲን ሉተር ኪንግና ለሌሎች ትግል መሪዎች ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል። ሳትያግራሃ የሚፈጽመው ሰው ሳትያግራሂ ይባላል። የሳትያግራሃ ትርጉም ሳትያግራሃ የሚለው ቃል ከሳንስክሪት ቃላት ሳትያ (ዕውነት) እና አግራሃ (ጽናት ወይም አጥብቆ መያዝ) ይመጣል። ለጋንዲ፣ ሳትያግራሃ ዝም ብሎ ከመቃወም በላይ ሲሆን ሰላማዊነታቸው ብርታታቸው ሆነ። እሳቸው እንዳሉት፣ ዕውነት ፍቅር ነው፣ ጽናትም ኃይል ነው፣ ስለዚህ የሳንስክሪት ስም ከእውነትና ከፍቅር (ወይም ሰላም) የተወለደው ሃይል መሆኑን ያሳያል አሉ። ሌላ የሰጡት ትርጉም «የፍቅር ሃይል» ወይም «የነፍስ ሃይል» ነበረ። የሳትያግራሃ ጽንሰ ሃሳብ ማሸነፍ ምንድነው አብዛኛው ጊዜ «ትግል» ማለት ባላንጣውን ማሸነፍ - ወይም ዓላማውን በመከልከል ወይም ባላንጣው የከለከለውም ዓላማ በመፈጸም - ይሆናል። በሳትያግራሃ ግን አላማው እንዲህ አይደለምን። በዚህ ፋንታ፣ ጋንዲ እንዳሉ፣ አላማው የበደለኛውን ዐእምሮ መቀይሩ ነው ኢንጂ ማስገደድ አይሆንም። እንግዲህ ማሸነፍ ወይም መከናወን ማለት ከባላንጣው ጋራ ተስማምቶ ምናልባት በደል መሆኑን ያልገነዘቡት እንደ ሆነ በደሉ በደንብ እንዲስተካከል ነው። ይህም ሊያልፍ እንዲመጣ፣ ባላንጣው ለትክክለኛው ፍች መሰናከል መሆኑን እንዲገነዝብ፣ አዕምሮው ሊለወጥ አለበት። የሳትያግራሂ ደንቦች ጋንዲ ሳትያግራህያን እነዚህን ደንቦች እንዲጠብቁ ጠየቁዋቸው፦ ሰላማዊነት ወይም ያለ ግፍ መታገል (አሂምሳ) ዕውነት፤ ይህም ማለት ቅንነት፣ ለዕውነቱም በሙሉ ለመኖርና ለመስማማት ነው። ቸዋነት (ብራህማቻርያ) — በወሲብ ረገድ ግብረ ገብ ማመልከት፣ እንዲሁም ስሜት ከመፈጸም ይልቅ ዕውነቱን በመከተል አትኩሮ ማሰብ ነው። ንብረት አለመያዝ (ነገር ግን ይህ ሃሳብ እና ድሃ መሆን አንድላይ አይደሉም) የሰውነት ሥራ ወይም የዳቦ ሥራ ሆዱን ማሠልጠን - ብዙ ጥሩ ያልሆነ ምግብ አለመብላት። ለሁሉ ሃይማኖቶች እኩል ክብር ማሳየት ቦይኮት መጠቀም (መሰናከል ከሆነ ድርጅት አለመግዛት ወይም በብር አለመደግፍ) ከዳሊት ነጻነት፣ ይህም ማለት ዝቅተኛ የማይነካ ሕዝብ ይኖራል ከሚለው አስተሳሰብ ነጻነት። ሌላ ጊዜ ጋንዲ ሰባት ቁም ነገር የሆኑት ደንቦች አወጡ። ሳትያግራሂው፦ በእግዚአብሔር ጽኑና ኗሪ እምነት መያዝ አለበት፤ በእውነትና በሰላማዊነት፤ ሰብአዊ ጸባይ በመሠረቱ ደግ እንደ ሆነ ማመን አለበት። ግብረገባዊ ሕይወት መኖር አለበት፤ ለመሞት ወይም ሁሉን ለማጣት ዝግጁ መሆን አለበት፤ 'ቃዲ' የተባለው ልብስ መልበስ አለበት፤ ከአረቄ መራቅ አለበት ጋንዲ የሚሰጡት ሌሎች ድንጋጌዎች ሁሉ መጠበቅ አለበት፤ በወህኒ ቢታሠር፣ ለወህኒ ቤት ደንቦች መገዛት አለበት፤ ነገር ግን ማንኛውም ደንብ በተለይ ክብሩን ለመጎዳት ከተደረገ መገዛት የለበትም።
50390
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%BB%E1%88%9D%E1%89%A0%E1%88%8D%20%E1%8A%A0%E1%8D%88%E1%8B%88%E1%88%AD%E1%89%85%20%E1%8B%AE%E1%88%90%E1%8A%95%E1%88%B5%20%E1%8C%88%E1%89%A5%E1%88%A8%20%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%9D
ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ ገብረ ማርያም
በአዲስ አበባ ከተማ በ፲፱፲፱ ዓ.ም. የተወለዱት ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ የቄስ ትምህርትን ከማይጨው ዘመቻ በፊት አጠናቅቀዋል፡፡ በጣሊያን የወረራ ወቅት በኢጣልያን ትምህርት ቤት ገብተው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በ፲፱፴፭ ዓ.ም. በጦር ሠራዊት ውስጥ ወታደርነት በመግባት ወታደራዊ ትምህርት ተምረዋል፡፡ ከዚያም በ፲፱፴፯ ዓ.ም. ሐምሌ 10 ቀን በክብር ዘበኛ መድፈኛ ክፍል የከፍተኛ ቴክኒክ ት/ቤት ገብተው የአምስት ዓመታት ኮርስ ተከታትለዋል፡፡ በመድፈኛ መኮንንነት ደረጃ ተመርቀዋል፡፡ እስከ ሻምበልነት ማዕረግ ደርሰው የነበሩት ሻምበል አፈወርቅ በ፲፱፶፫ ዓ.ም. የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ተካፋይ ሆነዋል በመባል ለሦስት ዓመታት በእስራትና በግዞት ቆይተዋል፡፡ ከ፲፱፶፮ ዓ.ም. ጀምሮ በሬዲዮ ጋዜጠኝነት አገልግለዋል፡፡ ሻምበል አፈወርቅ በ፲፱፶፯ ዓ.ም. ግጥሞች፣ ለዘፈን ለትካዜ፣ ለደስታ እና ልዩ ልዩ ታሪኮች በሚል የሥነ ግጥም መጽሐፍ፤ በ፲፱፶፯ ዓ.ም. ችግረኞች በሚል ርዕስ ከዓለም ታላላቅ ድርሰቶች ተጠቃሽ የሆነውን ልብወለድ መጽሐፍ ተርጉመው አሳትመዋል፡፡ የኔ ግጥሞች፣ የዓለም አስደናቂ ልዩ ልዩ ታሪኮች፣ ፍቅር በሰዎች ዘንድ፣ የሞራል ግዴታ ስሜታዊ ግጥሞችንም አሳትመው አልፈዋል፡፡ ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ ተጨማሪ እትመት ሀዘን እና ደስታ (ታላላቅ የአለም አጫጭር ታሪኮች ትርጉም)
20858
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%20%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%89%B0%E1%8A%A8%E1%88%88%20%E1%88%8D%E1%89%A5%20%E1%89%B0%E1%8A%A8%E1%8D%88%E1%88%88
ዘንግ ከተተከለ ልብ ተከፈለ
ዘንግ ከተተከለ ልብ ተከፈለ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ዘንግ ከተተከለ ልብ ተከፈለ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
21455
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8B%A8%E1%8C%81%20%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%89%B0%E1%88%AB%20%E1%89%85%E1%8A%94%20%E1%89%A2%E1%8B%AB%E1%88%8D%E1%89%85%E1%89%A0%E1%89%B5%20%E1%89%80%E1%88%A8%E1%88%AD%E1%89%B6%20%E1%8C%A8%E1%88%98%E1%88%A8%E1%89%A0%E1%89%B5
የየጁ ደብተራ ቅኔ ቢያልቅበት ቀረርቶ ጨመረበት
የየጁ ደብተራ ቅኔ ቢያልቅበት ቀረርቶ ጨመረበት የአማርኛ ምሳሌ ነው። የየጁ ደብተራ ቅኔ ቢያልቅበት ቀረርቶ ጨመረበት የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
20747
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%88%E1%8C%A1%20%E1%88%B3%E1%8B%AD%E1%8B%88%E1%8C%A0%E1%8B%88%E1%8C%A5%20%E1%8B%88%E1%88%B5%E1%8A%A8%E1%88%9D%E1%89%A2%E1%8B%AB%E1%8B%8D%20%E1%89%82%E1%8C%A5%E1%8C%A5
ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጥጥ
ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂብ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂብ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
22803
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%93%E1%88%B3
ጓሳ
ጓሳ ወይም በደኔ ወይም ጀሞ () ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ዛፍ ነው። የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ እስከ 10 ሜትር ድረስ የሚቆም ቀጭን ዛፍ ነው። ለቅርንጫፎቹ ረጅም፣ ቀጥ ያሉ ዐረንጓዴ እሾሆች በጥምዝምዝ አሉባቸው። ከእሾሆቹ መሠረት ጨለማ-አረንጓዴ ውሁድ ቅጠሎች ይበቅላሉ፣ ውሁዱም ቅጠል ከ፪ ቅጠሊቶች እየሆነ በቅርጽም ሆነ በስፋት ሊለያዩ ይችላሉ። ሽንሽን ግንዱ ግራጫማ-ቡኒ ሻካራ ልጥ አለው፤ ይህም በረገፈበት ቦታ ቢጫ-አረንጓዴ እራፊ ይኖረዋል። ህብረአበባው የጥቂት አበቦች ዘለላ ሲሆን አበቦቹም ወይም ዘንግ-አልባ ወይም በአጭር አገዳ ላይ የሚቀመጡ ናቸው። የአበባው እንቡጥ ሞላላ እና በጉርምስና ሥሥ ጽጉር ያለበት ነው። አበቦቹ አረንጓዴ-ቢጫ ቀለም፣ ፍናፍንታም ጾታ፣ አምስት ቅጠል በክቦሽ ምጥጥን ያላቸው ናቸው፤ የአበባ ቅጠሎች 8-14 ሚሊሜትር ባጋማሽ ናቸው። የኅብራበባ ስሪት ግራጫማ ቀለም፣ ለሥላሣ ጽጉር ያለው፣ ከ10 ሚሊሜትር ያልረዘመ ነው። ሞልሟላ ፍሬው በተለምዶ ከ4 ሴንቲ ሜትር ያልረዘመ ነው፣ ያልበሰለ ሲሆን አረንጓዴ ነው፣ ሲበሰልም ቡናማ ይሆናል፣ ከሽካሽ ቆዳው ዝልግልግ ቡናማ ልጥልጥ አለበት፣ ይህም ጽኑ ፍሬ ድንጋይ አለበት። አናጢ ጉንዳን ከአበባው ከሚንቆረቆር ወለላ ይመገባል። የጥቅል ጎመን ዛፍ ንጉሥ ብል () ኤጭ ዛፉን ርግፈ ቅጠል ያደርገዋል። በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር ዛፉ በአፍሪካ በኩል ይገኛል። የተክሉ ጥቅም ጓሳ በግብጽ ቢያንስ ለ4,000 ዓመታት ታርሷል። ከ2000 ዓክልብ. በመቃብሮቹ ውስጥ የፍሬው ድንጋይ እንደ ስለት እቃ ተገኝቷልና። ዘሩ ያለበት ብጫው ፍሬ መራራ ቢሆንም ሊበላ ይችላል። ዝሆን ቢያገኘው ይበላዋል። በተረፈ እንደ ረሃብ ምግብ ያገልግላል፤ ቅጠሉም አበባም በሰዎች ሊበሉ ይቻላል፤ ዘይታም ዘሩ መራራነቱ እንዲቀነስ ይፈላል፤ ከማሽላ ጋር ይበላል። በደረቅ ወራት ቢሆንም ፍሬውን ስለሚያስገኝ፣ ለበረሃ ምድሮች ዋጋ ያለው ዛፍ ይቆጠራል። ፍሬውም ለአረቄ ሊቦካ ይቻላል። እመጫቶች ፍሬውን በአጥሚት ይበሉታል፤ ዘይቱ ማጋቱን ያሻሽላል። ዘይቱ ደግሞ ለራስ ምታት ያሻሽላል። ዘይቱ ከወጣ በኋላ የተረፈው ዘር ቂጣ በአፍሪካ በተለምዶ ለመኖ ይጠቅማል። የጓሳ ዘር፣ ፍሬ፣ እና የልጥ ውጥ ቢልሃርዝያን ወዘተ. የሚፈጥሩትን ቀንድ አውጣዎችና ትሎች ይገድላል። የትል፣ የጉበት ወይም የጣፊያ ችግሮች እንዲህም ይታከማሉ። በምዕራብ አፍሪካ ባህላዊ መድሃኒት፣ የልጡ ውጥ ደግሞ ለፍላጻ መርዝ የሚሽር መድሃኒት የጠቅማል። ዛፉ ናይትሮጅን ቅንበራ ያደርጋል። ቡናማ-ቢጫው እንጨቱ እቃ ለመሥራት ይስማማል፤ ለማገዶ ብዙ ባለማጤሱ መልካም ነው፣ ለከሰልም ጥሩ ነው። ልጡም ጭረት ይሰጣል፣ የቅርንጫፎች ሙጫ ለማጣበቂያ ያገልግላል፤ ጽኑ ዘሮችም ለዶቃ ወይንም ለጌጥ ተጥቅመዋል። በአፍሪካ ሳህል የሚኖሩ ነገዶች እሾሁን በንቅሳት ይጠቅማሉ። የኢትዮጵያ እጽዋት
44485
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A1%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%AB%E1%88%AC%20%E1%8A%B8%E1%8A%95%E1%8C%80%E1%88%AD
ኡሰርካሬ ኸንጀር
ኡሰርካሬ ኸንጀር ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1774 እስከ 1766 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። ምናልባት የኹታዊሬ ወጋፍ ተከታይ ነበረ። በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ «ኡሰር<..>ሬ <...>ጀር» ይገኛል። በመምኅር ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ፣ «ኸንጀር» የሚለው ስያሜ ግብጽኛ ሳይሆን በአንዳንድ ሴማዊ ቋንቋዎች «እሪያ» ማለት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሴማዊው ፲፬ኛው ሥርወ መንግሥት በጌሤም እየገዛ ምናልባት የሴማውያን ተጽእኖ በጤቤስ መንግሥት ደግሞ በዚህ ሊታይ ይችላል። ኸንጀር በተለይ ስላሠራው «የኸንጀር ሀረም» ይታወቃል። በዚህ ሀረም በሁለት ድንጋዮች የኸንጀር ፩ኛው ዓመትና የ፭ኛው ዓመት ዘመነ መንግሥት ተመዘገበ። ስለዚህ ብዙ ሊቃውንት ከ፭ ዓመታት በላይ እንደ ገዛ አያምኑም። በዚህ ዘመን «ኦሩስ፣ አኸንኸሬስ፣ አኮሪስ፣ ኸንክሬስ፣ አኸሬስ» በግብጽ እንደ ገዙ በአንዳንድ ምንጭ ይገኛል። እነዚህ ስሞች ሆር አዊብሬ፣ ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው፣ ሰጀፋካሬ፣ ኸንጀር፣ እና ስመንኽካሬ ቢመስሉም፣ ከማኔጦን ጀምሮ ስሞቻቸው ከ፲፱ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ጋር እንደ ተዛቡ ይመስላል። «ኸንክሬስ» የ፰ ወይም ፲፪ ዓመታት ዘመን እንደ ነበረው ይባላል። በአንዳንድ የድሮ ምንጭ ደግሞ «ኸንክሬስ» በዘጸአት ዘመን የጠፋው ፈርዖን ሲባል ይህ ደግሞ እንደ ተዛበ ይመስላል። በኸንጀር ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትሩ («ጨቲ» የሚባለው ሹመት) አንኹ እንደ ነበር ይታወቃል። የአንኹ ቤተሠብ ኃይለኛ ሹሞች ነበሩ፣ አባቱ ዛሞንት በ3 አመነምሃት ዘመን ጨቲ ሲሆን የአንኹ ሁለት ወንድ ልጆች ረሠነብና ኢይመሩ በኋላ ጨቲዎች ሆኑ። ይህም አንኹ ደግሞ በኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ (1795-1791 ዓክልበ. ግ.) ጨቲ መሆኑ ታውቋል፤ ስለዚህ አንኹ ምናልባት ከኻአንኽሬና ከኸንጀር መካከል ለገዙት ፈርዖኖች ለሁላቸው እንደ ጨቲ ያገልግል ነበር። እንዲህ ከሆነ፣ በዚህ ዘመን ጨቲው እውነተኛው ባለሥልጣን ሲሆን ፈርዖኖች ግን ድካሞችና በቶሎ የሚተኩ እንደ ነበሩ ይመስላል። ዋቢ ምንጭ የሁለተኛው ጨለማ ዘመን ፈርዖኖች
53983
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A1%E1%88%B5%E1%88%83%E1%89%82
ቡስሃቂ
ቡስሃቂ የሚከተሉትን ሊያመለክት ይችላል: ቡዚድ ቡስሃቂ - የአልጄሪያ ፖለቲከኛ እና የንግድ ህብረት ባለሙያ። ሙስታፋ ይስሐቅ ቡስሃቂ - አልጄሪያዊ ሳይንቲስት. አብደኑር ቡስሃቂ - አልጄሪያዊ ፖለቲከኛ.
14762
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%88%E1%88%8B%E1%88%9D%20%E1%8A%A8%E1%8C%A5%E1%8C%83%E1%8B%8B%E1%8A%93%20%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%88%8B%E1%89%A2%E1%8B%8B%20%E1%88%9B%E1%8A%95%20%E1%8B%AD%E1%89%80%E1%88%AD%E1%89%A3%E1%89%B3%E1%88%8D
ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል
ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል የአማርኛ ምሳሌ ነው። ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል የአማርኛ ምሳሌ ነው። ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል የአማርኛ ምሳሌ ነው። ሁለቱም የእሷ ጥገኞች ናቸው። ምንጭ፦ አዲሱ የምሳሌያዊ አነጋገሮች መጽሐፍ ፣ ገጽ ፲፯ ተረትና ምሳሌ
44479
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%B0%E1%8C%80%E1%8D%8B%E1%8A%AB%E1%88%AC
ሰጀፋካሬ
ሰጀፋካሬ ካይ ፮ አመነምሃት ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1781 እስከ 1776 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የጀድኸፐረው ተከታይ ነበረ። ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ ይገኛል። እንዲሁም ከሥነ ቅርስ ረገድ ፈርዖንነቱ እርግጥኛ ነው። በመምኅር ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ፣ ተከታዩ ኹታዊሬ ወጋፍ ነበረ። ዋቢ ምንጭ የሁለተኛው ጨለማ ዘመን ፈርዖኖች
18678
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%B3%E1%88%BC%E1%88%8D%20%E1%88%83%E1%88%9C%E1%89%B5
ዳሼል ሃሜት
ዳሼል ሃሜት (እ.አ.አ. ከ1894-1961) ታዋቂ አሜሪካዊ ደራሲ ነው። በዋናነት እንግሊዝኛ: በተሰኘው ስራው ይታወቃል። ‎የአሜሪካዊ ደራሲያን ዝርዝር የአሜሪካ ጸሓፊዎች
48283
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%B2%E1%88%8D%E1%88%9B%20%E1%88%A9%E1%88%B0%E1%8D%8D
ዲልማ ሩሰፍ
ዲልማ ሩሰፍ (ፖርቱጊዝኛ፦ ) ከጥር 2003 እስከ ነሐሴ 2008 ዓም ድረስ የብራዚል ፕሬዚዳንት ነበረች። በ2008 ዓም በሙስና ሳቢያ ከማዕረጓ ተሻረች።
14909
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%88%E1%89%A4%E1%89%B5%20%E1%88%B3%E1%88%9B%20%E1%88%88%E1%8B%8D%E1%8C%AD%20%E1%89%84%E1%8C%A4%E1%88%9B
ለቤት ሳማ ለውጭ ቄጤማ
ለቤት ሳማ ለውጭ ቄጤማ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ሳማ የሚለባለብ አትክልት ነው። ቤት ውስጥ መግባት የለበትም። ቄጤማ ደግሞ ቤት ውስጥ የሚነጠፍ የሳር አይነት ነው። መደብ : ተረትና ምሳሌ
23271
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AD%20%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%A5%E1%89%B5%20%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%83%E1%8A%95%20%E1%88%9E%E1%8C%88%E1%88%B3
ታሪክ ወንግሥት ብርሃን ሞገሳ
ታሪክ ወንግሥት፡ ብርሃን፡ ሞገሳ ፣ ታሪክ፡ ዘንጉሠ፡ ነገሥት፡ አድያም፡ ሰገድ በዘመናቸው በነበረው ፀሐፊ በግዕዝ እንደተጻፈና በኢኛትሲዮ ግዊዲ በ1895 ፣ በጣሊያን አገር እንደታተመ ከጎን ቀርቧል። ይህ የንግሥት ምንትዋብና የልጇን ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱን ዜና ውሎ ይተርካል። በተጨማሪ የዓፄ ኢያሱን ልጅ የዓፄ ኢዮአስን ዜና መዋዕል በተከታዩ ገጽኦች አካቶ ይዟል። ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ የኢትዮጵያ ታሪክ የኢትዮጵያ ዜና መዋዕል
49998
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8C%8D%E1%8A%95%E1%89%A3%E1%89%B3%20%E1%88%9D%E1%88%85%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%88%B5%E1%8A%93
የግንባታ ምህንድስና
የግንባታ ምህንድስና የግንባታ ሂደትን የማቀድ፣ የማስፈጸም፣ ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝና የማቅረብ፣ እንዲሁም የግንባታ ቦታውን ለሚፈለገው የግንባታ አካል እንዲውል በግንባታው አካባቢ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃ መሟላቱን የማረጋገጥ፣ የግንባታ ቦታው ለግንባታ ስራ ደህንነትና ምቹነት ያለው መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም አግባብ የሆነ የግንባታ መሬት አጠቃቀምን የሚከታተልና የሚያስፈጽም የምህንድስና ዘርፍ ነው። የግንባታ ተቋራጮች በሌሎች የሲቪል ምህንድስና አገልግሎቶች ላይ ከተሰማሩ የአገልግሎት ተቋሞች አንጻር የተሰማሩበት መስክ ከፍተኛ የንግድ አደጋ ወይም መዋዠቅ ስለሚከሰትበት የግንባታ መሃንዲሶች አብዛኛውን ጊዜያቸውን ንግድን በተመለከቱ ጉዳዮች ለምሳሌ ያህል የግንባታ ውሉን በመገምገም እና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በማርቀቅ፣ የግንባታ ግብአቶችን አቅርቦት ፍሰት በመቆጣጠር፣ እንዲሁም የግንባታ እቃዎች የገበያ ዋጋ መረጃን በመሰብሰብ ላይ ያውላሉ። ግንባታ ምህንድስና
31629
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%B4%E1%8A%AA%E1%8A%AD%E1%88%B5%E1%8A%AA%E1%8B%AB%E1%8A%AD
ቴኪክስኪያክ
ሳንቲያጎ ቴኪክስኪያክ (እስፓንኛ፦ የሜክሲኮ ከተሞች
14781
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%88%E1%88%98%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%89%B5%20%E1%8B%AB%E1%8D%88%E1%88%A8%20%E1%88%88%E1%88%98%E1%89%A5%E1%88%8B%E1%89%B5%20%E1%8B%B0%E1%8D%88%E1%88%A8
ለመስራት ያፈረ ለመብላት ደፈረ
ለመስራት ያፈረ ለመብላት ደፈረ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ሰነፍ አይናውጣን ለመውቀስ የሚጠቅም መደብ : ተረትና ምሳሌ
10335
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%B0%E1%88%A8%E1%8C%80%20%E1%8A%A8%E1%89%A0%E1%8B%B0
ደረጀ ከበደ
ደረጀ ከበደ እውቅ የክርስቲያን ዘማሪ፡ የዘመራቸው መዝሙሮች አብዛኛዎቹ ከሕይወቱ ገጠመኝ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ልዩ ያረገዋል ደረጀ ከበደ የመጀመሪያ ቋንቋው አማርኛ ቢሆንም በኦሮምኛም ዘምሮአል ። ደረጀ በተለይ በውብ ድምጸ ቅላጤው ሲዘምር የሰሚውን ጆሮና ልብ ያነቃቃል። ዝማሬዎቹ የአብዛኞችን ህይወት ለውጠዋል፥ አፅናንተዋል፥ አንፀዋል የክህደት ትምህርቶችን ገስፀዋል በኢትዮጵያ የፕሮቴስታንት አማኞች ዘንድ በመንግስታት ለተጎዱ ህዝቦች መብት መቆም() መቃወም የሚያስገፋና መጥፎ ስሞችን የሚያሰጥ ሲሆን ዶ/ደረጀ ከበደ ግን በዝማሬዎቹም በዩትዩብ የምስል ቪዲዮ ኢሰብዐዊነትን ማጋለጡ ለየት ከማድረጉም በልይ ከብዙ ታዋቂ የፕሮቴስታንት አባቶች ጋርም ያመሳስለዋል። ዶ/ር ደረጀ ከበደ የመጀመሪያ ዲግሪውን በአግሮ ኢኮኖሚክስ - በክርስቲያን ትምርህት የማስተርስ ዲግሪ -በ አዲክሽን ስተዲስ የማስተርስ ዲግሪ እና በሄልዝ ሳይንስ በዶክትሬት ተመርቆ እየሠራ ይገኛል።
30844
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%8A%90%E1%8D%8D%20%E1%88%8D%E1%89%A1%20%E1%8B%93%E1%8B%AD%E1%8A%91%20%E1%8A%90%E1%8B%8D
የሰነፍ ልቡ ዓይኑ ነው
የሰነፍ ልቡ ዓይኑ ነው የአማርኛ ምሳሌ ነው። የሰነፍ ልቡ ዓይኑ ነው የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
49809
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%86%E1%8B%B0%E1%8A%96%E1%88%BE%E1%8A%92
ሆደኖሾኒ
ሆደኖሾኒ («የረዘመው ቤት ሕዝብ») ወይም በእንግሊዝኛ ኢሮኳ የተባለው ብሔር በአሁኑ አሜሪካና ካናዳ የተገኙ የጥንታዊ ኗሪዎች ትብብር ናቸው። ጥንታዊ ሕገ መንግሥታቸው ጋያነሸጎዋ ምናልባት በ1100 ዓም ግድም እንደ ተመሠረተ ተብሏል። እስከ 1714 ድረስ ሌላ ስማቸው «አምስቱ ብሔሮች» ከዚያ በኋላ «ስድስቱ ብሔሮች» ሆነ። የስሜን አሜሪካ ኗሪ ብሔሮች
22691
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A3%E1%88%9D%E1%89%A3%E1%88%A9%E1%8B%B5
ኣምባሩድ
ኣምባሩድ () ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው። የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር የተክሉ ጥቅም የኢትዮጵያ እጽዋት የኣውጥ ወገን
20396
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B3%E1%8B%A8%E1%8A%95%20%E1%8C%A4%E1%8D%8D%20%E1%8A%A0%E1%8C%8B%E1%8B%A8%E1%8A%95
እንዳየን ጤፍ አጋየን
እንዳየን ጤፍ አጋየን የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ
3603
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%89%A4%E1%88%8D%E1%88%9E%E1%8D%93%E1%8A%95
ቤልሞፓን
ቤልሞፓን የቤሊዝ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 12,300 ሆኖ ይገመታል። ከተማው ላይ ተቀምጦ ይገኛል። ከተማው መጀመርያ በ1958 ዓ.ም. ተሠርቶ፣ በ1962 ዓ.ም. የመንግሥት መቀመጫ ወደዚያ ከቤሊዝ ከተማ ተዛወረ። ዋና ከተሞች
10473
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%94%E1%88%8D%E1%88%B0%E1%8A%95%20%E1%88%9B%E1%8A%95%E1%8B%B4%E1%88%8B
ኔልሰን ማንዴላ
ኔልሰን ማንዴላ ዘረኛውን የደቡብ አፍሪካ መንግስት በመቃወማቸው ለ27 ዓመት እስር ቤት ማቀዋል። ከእስር ቤት እንደተለቀቁም የመጀመሪያዋ የነጻይቱ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ በቅተዋል። ማንዴላ 94 ዓመታቸውን በዛሬዋ ዕለት አከበሩ። የአፍሪካ መሪዎች ደቡብ አፍሪካ
20923
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%9D%E1%8A%93%E1%89%A5%E1%8A%93%20%E1%88%8D%E1%8C%85%20%E1%88%B2%E1%8C%A0%E1%88%89%E1%89%B5%20%E1%8B%AB%E1%8A%A8%E1%89%A5%E1%88%AD
ዝናብና ልጅ ሲጠሉት ያከብር
ዝናብና ልጅ ሲጠሉት ያከብር የአማርኛ ምሳሌ ነው። ዝናብና ልጅ ሲጠሉት ያከብር የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
22257
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%85%E1%89%A5%E1%8A%95%20%E1%88%B2%E1%8B%88%E1%8C%89%20%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%8B%AB%20%E1%8B%AD%E1%8C%A0%E1%8C%89
ጅብን ሲወጉ በአህያ ይጠጉ
ጅብን ሲወጉ በአህያ ይጠጉ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ጅብን ሲወጉ በአህያ ይጠጉ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
44516
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A1%E1%88%AD%E1%8B%B1%E1%8A%A9%E1%8C%8B
ኡርዱኩጋ
ኡርዱኩጋ ከ1744 እስከ 1741 ዓክልበ. ድረስ የኢሲን ንጉሥ ነበረ። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር መሠረት ለ4 አመት ብቻ ነገሠ። ከተገኙትም የአመት ስሞች የተነሣ ከ3 ወይም 4 አመት በላይ እንዳልነገሠ ይመስላል። ኡርዱኩጋ ኢተር-ፒሻን ተከተለው። ከእርሱ በኋላ ሱመርኛ ስም ያለው ንጉሥ በመስጴጦምያ አልነገሠም፤ በዚህ ወቅት ሱመርኛ መነጋገሪያ ከመሆን ቢጠፋም ተማሪዎች ግን ይማሩት ነበር። ከዘመኑ አንዳንድ ቅርስ ተገኝቷል። ከዚያ በኋላ ሲን-ማጊር ኡርዱኩጋን በኢሲን ተከተለው። የውጭ መያያዣ የኡርዱኩጋ ዓመት ስሞች የኢሲን ነገሥታት
16868
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%8A%E1%89%A8%E1%88%AD%E1%88%9E%E1%88%AA%E1%8B%A8%E1%88%9D
ሊቨርሞሪየም
ሊቨርሞሪየም በየንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥ ውስጥ ኬሚካዊ ውክሉ እና አቶማዊ ቁጥሩ 116 ለሆነ ሲንተቲክ በጣም ከባድ ንጥረ ነገር ነው። በ2004 ዓ.ም. ስሙ በይፋዊ ስምምነት ሊቨርሞሪየም ሆነ። ከዚያ በፊት ጊዜያዊ ስያሜው ዩኔንሄክሲየም () ሆኖ ነበር። የጥንተ፡ንጥር ጥናት (ኬሚስትሪ) ንጥረ ነገሮች
17982
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8C%A5%E1%88%AD%20%E1%8D%B2%E1%8D%B1
ጥር ፲፱
ጥር ፲፱፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፴፱ ነኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፳፬ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳፯ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፳፮ ቀናት ይቀራሉ። ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፸፱ ዓ/ም - ራስ ዐሉላ ለወረራ ድንበር ጥሶ የመጣውን የጣልያን ግንባር ቀደም ሠራዊት ዶጋሌ ላይ ገጥመውት ፭ መቶ ጣልያኖችን ፈጁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ መርድ አዝማች አስፋ ወሰን ሌሊቱን በደም ቋጠሮ ምት ታመው የእንግሊዝ የጦር አየር ዠበብ ለሕክምና በአስቸኳይ ወደእንግሊዝ አገር እንዲወስዳቸው ተለመነ። የጦር አየር ዠበብ በማግሥቱ ይዟቸው ወደሎንዶን በረረ። ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - በሶማሊያ ሞሀመድ ሲያድ ባሬ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ወረዱ። ፲፱፻፺፫ ዓ/ም ጉጅራት በሚባለው የሕንድ ግዛት የተከሰተው ዐቢይ የመሬት እንቅጥቅጥ እስከ ፳ሺህ ሰዎችን ሕይወታቸውን አጥፍቷል። ዕለተ ሞት ዋቢ ምንጮች
21231
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%88%9D%E1%88%8B%E1%88%B5%20%E1%8C%A6%E1%88%AD%20%E1%89%A2%E1%89%B3%E1%8A%A8%E1%88%9D%20%E1%8A%A0%E1%8B%AD%E1%8B%B5%E1%8A%95%E1%88%9D
የምላስ ጦር ቢታከም አይድንም
የምላስ ጦር ቢታከም አይድንም የአማርኛ ምሳሌ ነው። የምላስ ጦር ቢታከም አይድንም የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ ተረትና ምሳሌ
16979
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8D%8D%E1%8B%A8%E1%88%8D%20%E1%88%98%E1%8A%95%E1%89%B3%20%E1%89%B5%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%8B%B5%E1%8A%93%20%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B1%20%E1%88%88%E1%8B%88%E1%8A%93%E1%8D%8D%20%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B1%20%E1%88%88%E1%88%98%E1%8C%BD%E1%88%80%E1%8D%8D
ፍየል መንታ ትወልድና አንዱ ለወናፍ አንዱ ለመጽሀፍ
ፍየል መንታ ትወልድና አንዱ ለወናፍ አንዱ ለመጽሀፍ የአማርኛ ምሳሌ ነው። ፍየል መንታ ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ መደብ :ተረትና ምሳሌ
20411
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8C%80%E1%88%AB%20%E1%8B%A8%E1%88%88%E1%88%9D%20%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8C%82%20%E1%89%A0%E1%8B%88%E1%89%B0%E1%89%B5%20%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%8C%88%E1%88%85%20%E1%89%B5%E1%89%A0%E1%88%8B%20%E1%8A%90%E1%89%A0%E1%88%AD
እንጀራ የለም እንጂ በወተት አምገህ ትበላ ነበር
እንጀራ የለም እንጂ በወተት አምገህ ትበላ ነበር የአማርኛ ምሳሌ ነው። ያልተተረጎመ ምሳሌ
31656
https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%AB%E1%89%AC%E1%8A%93
ራቬና
ራቬና (ጣልያንኛ፦ ) የጣልያን ከተማ ነው። በአንድ አፈ ታሪክ ዘንድ ራቬና የተመሠረተው በያፌት ልጅ ቶቤል ነበረ። ቶቤል በመርከብ ደርሶ ሠርፈረኞችን በዚያ እንደ ተወ፣ ከዚያም የቶቤል ልጅ ሱብረስ ሌላ ከተማ በሚላኖ እንደ ሠራ በድሮ ጸሓፍት ተተርኳል። የጣልያን ከተሞች