input
stringlengths
1
130k
ባን ጊ ሙን ግልፅ እንዳደረጉትም አሁንም የሴቶችን መብት ከማስከበር አኳያ የተሠሩ ሥራዎች ቢኖሩም የሚቀሩት በርካታ ናቸዉ።
ከምንም በላይ የሰዎች አመለካከት መሠረታዊ ለዉጥ እንደሚያሻዉም ዋና ፀሐፊዉ ሳያስቡ አላለፉም።
በወቅቱም መንግሥታት የሴቶች መብት እንዲከበር የሚደነግገዉን ሕግ ተስማምተዉበት ተቀብለዋል።
ለዚህም ዓለም ይህን በይደር ያስቀመጠዉን የቤት ሥራ ትርጉም ባለዉ መልኩ እንዲያጠናቅቅ አሳስበዋል።
ዕለቱን አስመልክቶ የወጣ አንድ ጥናት የቤጂንጉን ዉል ከፈረሙት ሃገራት ቱ በሕገ መንግሥታቸዉ ማካተታቸዉን ያመለክታል።
ሕጉን በሕግነት መቀበሉ ብቻ በቂ አይደለምና አሁንም እዉን አድርጉት የሚል ጥሪ ነዉ የቀረበላቸዉ።
ሕጉን ከተቀበሉ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ለተግባራዊነቱ ምን ያህል ተሳክቶላታል
የኢትዮጵያ ሴት ማኅበራት ጥምረት ሥራ አስኪያጅ ወ ሮ ሳባ ገብረ መድህን ያስረዳሉ።
ቦኮሃራም በሕዝብ ላይ በሚፈፅመዉ አሳዛኝ ድርጊት ወጣት ልጃገረዶችን ከትምህርት ቤት ማገት መንደሮችን ማቃጠል ማኅበረሰቡን ሁሉ ማሸበር እና መግደል በጣም ተጨንቀናል።
በአንድ አካባቢ የነበረዉ ቡድን አሁን ወደምዕራብ አፍሪቃና ማዕከላዊ አፍሪቃ ሲስፋፋ እያየን ነዉ።
በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ነዉ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ንኮሳንዛና ድላሚኒ ዙማ የጉባኤዉን ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ በዚህ መልኩ ግልፅ ያደረጉት።
የአፍሪቃ ኅብረት ሰሜን ናይጀሪያ ዉስጥ በሚንቀሳቀሰዉ ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን ቦኮሃራም ላይ ወታደራዊ ርምጃ ለመዉሰድ አልሟል።
ይህም ባለፈዉ መስከረም ወር ናይሮቢ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ፅንፈኛ እስላማዊ የሽብር ድርጅቶችን ለመዋጋት ልዩ ስለበጀት የተነጋገሩበት ዝግጅት አካል ነዉ።
እንዲህ ያለዉ ዘመቻ ሲታሰብ የናይጀሪያን ፍላጎት ማካተት እንዳለበት የፀጥታ ጥናት ተቋም የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ሰሎምን ደርሶ ያሳስባሉ።
ናይጀሪያ እንዲህ ያለ ወታደራዊ ዘመቻ በግዛቷ እንደማትፈልግና ቦኮሃራምን ራሷ እንደምትቋቋም ገልጻለች።
እንዲህ ያለዉ የፖለቲካዊ መዕክት ነዉ በተደጋጋሚ ከናይጀሪያ ሲነገር የተደመጠዉ።
ስለዚህ ናይጀሪያ የዓለም አቀፍ ወታደራዊ ኃይልም ሆነ የፈረንሳይን ጦር ግዛቷ ዉስጥ እንዲዘምት ትፈቅዳለች ብዬ አልገምትም።
ለዓመታት የተነገረለት እንዲህ ባለዉ ወቅት ፈጥኖ የሚሠማራ የአፍሪቃ ተጠባባቂ ኃይል በምህፃሩ ን የመገንባቱ ነገር እስካሁን እዉን አልሆነም።
የተስፋፋዉ የቦኮሃራም ጥቃት የተናጠል ግብረ ሐይል መመሥረት አጠቃላዩ ትልቅ ሐይል ጋር ሊቀናጅ አይችልም።
ይልቁንም የሚያስፈልገዉ ፈጥኖ እርምጃ መዉስድ የሚችልበትን ሥልት መፈለግ ነዉ።
የአፍሪቃ ኅብረት በሰላምና ፀጥታዉ ምክር ቤቱ ሥር ይህን ሐይል ማቋቋምና ማዝመቱ ይሳካል ወይ የሚለዉን መገመት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
ሌላዉ ኅብረቱ በዚህ ጉባኤዉ የሚመለከተዉ በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል የቀጠለዉን ግጭትና ዉዝግብ ነዉ።
በሌላ በኩል ያለዉ መልካን ዜና የአፍሪቃ የኤኮኖሚ ኮሚሽን በኤቦላ ወረርሽኝ በአህጉሪቱ ኤኮኖሚ ላይ ያደረሰዉ ተፅዕኖ መጠነኛ መሆኑ መገለፁ ነዉ።
ድርድር ጦርነት ጦርነት ድርድር ሶሪያ አረብ የቋንቋ ባሕል እምነቱን አንድነት ደፍልቆ መጠፋፊያዉ ካደረገዉ ዘመናት አስቆጥሯል።
የሥልክና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሮሮ ካገልግሎት መስጪያ ዉጪ የደወሉት ቁጥር ከአግልግሎት መስጪያ ክልል ዉጪ ነዉ።
ያንኑ ቁጥር ደግመዉ ይሞክሩ መጀመሪያ ከሰሙት የተለየ መልዕክት ይሰማሉ እዚያዉ ኢትዮጵያ፥
የጦር ወንጀል በየመን ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመካከላቸው በሚመርጧቸው አባላት እንዲመራ የተስማሙበት ድርድር እና ፋይዳው የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው።
አውሮጳ ጀርመን የሽታይንማየር የአፍሪቃ ህብረት ጉብኝት የህብረቱ ቃል አቀባይ ለ እንደተናገሩት ሽታይንማየር የጀርመንን እና የአፍሪቃ ህብረትን ትብብር የማሳደግ ፍላጎት አላቸው።
የጀርመን መንግሥት በአፍሪቃ ህብረት አማካይነት የአባል ሀገራት ልማትን ሊያፋጥኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እየሰራ መሆኑንም ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል።
የሽታይንማየር የአፍሪቃ ህብረት ጉብኝት የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በኢትዮጵያ ያደረጉትን የ ቀናት ጉብኝታቸውን ዛሬ አጠናቀው ወደ ጀርመን እየተመለሱ ነው።
ፕሬዝዳንቱ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ከአዲስ አበባ ለመነሳት ቢያቅዱም አውሮፕላናቸው ባጋጠው የቴክኒክ ችግር ምክንያት ጉዞአቸው እንዲዘገይ መደረጉ ተዘግቧል።
ሽታይንማየር ዛሬ ጠዋት በአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን በመገኘት ከህብረቱ ባለሥልጣናት እና ሠራተኞች ጋር የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል።
የህብረቱ ቃል አቀባይ ለ እንደተናገሩት ሽታይንማየር የጀርመንን እና የአፍሪቃ ህብረትን ትብብር የማሳደግ ፍላጎት አላቸው።
ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
የኢትዮ ኤርትራ ጣጣ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የአውሮፓ ህብረትና ስደተኞች መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ኢትዮጵያ ጠሪያቸው ግልጽ ያልሆነው የኦሮሚያ ሰልፎች ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄደዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግስት የክልሉ ነዋሪዎች በሰልፎቹ ላይ ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡
የሚለው እያነጋገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ዛሬም በሱልልታ ተመሳሳይ ተቃውሞ ተካሂዷል፡፡
በሱሉልታ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል በአዲስ አበባ አቅራቢያ የምትገኘው ሱሉልታ ከተማ ሳምንታዊ የገበያ ቀኗ ሀሙስ ነው፡፡
በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ እና ቅዳሜ ደግሞ አነስ ያሉ ገበያዎችን ታስተናግዳለች፡፡
ሱቆቿ ተዘግተው የታክሲ አገልግሎት ቆሞ በከተማዋ ዋና አውራ ጎዳና ለሰዓታት የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ትንፋሿን ሰብስባ ስትከታተል ነበር፡፡
ሁኔታው ያስፈራቸው ዕለታዊ ክንውናቸውን ትተው በመኖሪያቸው ሁነው ተቃውሞውን ይከታተሉ እንደነበር ይናገራሉ፡፡
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሱሉልታ ነዋሪ ዛሬ ረፋዱን በከተማይቱ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ይገልጹታል፡፡
ምን እንደሚሉ አላውቅም ኮኮብ የሌለበት ባንዲራ ይዘው ነው የወጡት ይላሉ፡፡
እኚህ ነዋሪ ሰልፈኞቹ ሱቅ ሲያዘጉ መመልከታቸውን እና የታክሲ አገልግሎትም ተቃውሞውን ተከትሎ በከተማይቱ ማቋረጡን ያስረዳሉ፡፡
ተቃውሞ እንደሚካሄድ ቀድመው የሰሙት ነገር እንዳልነበር የሚናገሩት ነዋሪው በሰልፉ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የነበራቸውን ጉዞ ሰርዝው ወደቤታቸው ለመመለስ መገደዳቸውን ይናገራሉ፡፡
ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎችም ሰልፍ እንደሚካሄድ መረጃው እንዳልነበራቸው ገልጸውልናል፡፡
በጠዋት ወደ ገበያ መውጣታቸውን የሚናገሩ አንዲት የከተማዋ ነዋሪ ተቃውሞው የጀመረው በጋሪ ነጂዎች እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡
ጋሪ ነጂዎቹ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ወደ ካጂማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሄዱ በኋላ ተማሪዎች እንደተቀሏቀሏቸው ያብራራሉ፡፡
ከዚያ በኋላ የሰልፈኞቹ ቁጥር እያደገ የከተማው ሌላ ነዋሪም አብሯቸው መቃወም እንደቀጠለ ይናገራሉ፡፡
ሰላማዊ ነበር ባሉት በዚህ ተቃውሞ ፖሊሶች ሰልፈኞች ከመጠበቅ ውጭ ምንም ዓይነት እርምጃ አልወሰዱም ይላሉ፡፡
ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ የከተማዋ ነዋሪም ተመሳሳይ ገለጻ አላቸው፡፡
ሰልፉ ከሶስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ስምንት ሰዓት ድረስ መቆየቱን ይናገራሉ፡፡
እጃቸውን ከጭንቅላታቸው በላይ በማጣመር ተቃውሟቸውን ሲገልጹ የነበሩ ሰልፈኞች ያሰሟቸው የነበሩትን መፈክሮች ይዘረዝራሉ፡፡
አገዛዙ በቃን የታሰሩት ይፈቱልን ነጻነታችን ይከበርልን አይነት ነው የተላለፈው መልዕክት፡፡
በዚሁ አጋጣሚ ከሶማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የብሩን በመጠን ባላውቅም ብዙ ብር እርዳታ ተሰብስቧል፡፡
በሰልፉ ላይ ለኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ለክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ድጋፎች ሲደመጡ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆችን አልረዳም በሚልም የፌደራል መንግስት ላይ ወቀሳ መሰንዘሩን ጠቁመዋል፡፡
በሰልፉ ላይ ድጋፍ እና ተቃውሞ ቢስተናገድም ሰልፉን ማን እንደጠራው እንደማይታወቅ ይናገራሉ፡፡
እንደውም ከትላንት ጀምሮ አትውጡ ማንም አልጠራችሁም እየተባለ ነው የወጡት፡፡
ብዙ ሰው ነው የወጣው ይላሉ የሰልፉን ተሳታፊ ብዛት ሲያስረዱ፡፡
ሱልልታ ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ወደ ተረጋጋ ሁኔታ መመለሷን ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
በኦሮሚያ አሁን በተከታታይ እየተካሄዱ ላሉ ተቃውሞች መነሻ በነበረችው አምቦም ባለፈው ረቡዕ የሆነው ተመሳሳዩ ነበር፡፡
በሰላም የተጠናቀቀው ይህ ሰልፍ ዱብ እዳ እንደነበር ስሙን መጥቀስ ያልፈለገ አንድ የአምቦ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል፡፡
እንደ አምቦ ሁሉ በዚያው ቀን ጥቅምት ቀን ዓ ም ሻሸመኔ እና ዶዶላ ላይም ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡
ለእንዲህ አይነት ሰልፎች ድጋፍ በመስጠት የሚታወቁ መቀመጫቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ተሟጋቾች እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎችን ድጋፍ ነፍገዋል፡፡
በኖርዌይ የሚኖረው ግርማ ጉተማ ከኦሮሞ መብት ተከራካሪዎች አንዱ ነው፡፡
የአሁኖቹ ግን የተቀናጁ አይደሉም ሁለተኛ ደግሞ ሻሸመኔ ላይ የተከሰተው አሁን በጣም አሳዛኝ ነገር ነው፡፡
ሻሸመኔ ላይ ሰልፈኛውን እየመሩ ወደ ወታደር ካምፕ ላይ የሚወስዱ ሰዎች ነበሩ፡፡
ያንን ከሰማን ካጣራን በኋላ ነው በነገርህ ላይ እንዲህ እንደድሮው ለመብት ጥየቃ እንዳልሆነ እና የሆነ አካል እንደጠለፈው ዓይነት መረጃ የደረሰን፡፡
እና የእኛን ቄሮዎች በፊት ሪፖርት የሚያደርጉልንን የተወሰኑትን ጠልፈውብን ነበር፡፡
ሰዎቹ መረጃ ይሰጡናል ማለት ነው ከዚያ በግልጽ በመላው ኦሮሚያ ይካሄዳል ተብሎ ነበር የምንጀምር የነበረው፡፡
ስናየው ነገሩ ጥሩ እንዳልሆነ እና ወጣቱ ከእንደዚህ አይነት ነገር እንዲቆጠብ ነግረናል ፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን የኦሮሚያ መንግስት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡
ማህበራዊ ድረ ገጾች እና ሀሳብን በነጻ መግለፅ ማህበራዊ ድረ ገጾች ሰዎች የግል ሀሳባቸውን በነጻ እንዲገልጹ እንዲወያዩ እና እንዲከራከሩ እድል ፈጥረዋል።
የተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች ከሌሎች ሰዎች ጋር በዓለም ዙሪያ ሀሳብን ለመለዋወጥ ከፍተኛ እድል ፈጥረዋል።
አዳዲስ መረጃዎችን በጥቂት ሰከንድ ውስጥ ማግኘት እና የግል ሀሳብን ለሌሎች ማካፈል ይቻላል።
መረጃ ሰጪ እና አስተማሪ መልዕክቶች የሚያስተላልፉ እንዳሉ ሁሉ የዛኑ ያህል ህዝብን የሚያደናግሩ እና የሚያሳስቱ የጥላቻ አስተሳሰቦችን የሚያሰራጩ መልዕክቶችንም የሚፅፉ አሉ።
በተለይ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መረጃዎችን በተደራጀ መልኩ መልሰው ለኢትዮጵያውያን ከሚያቀርቡ ድረ ገዶች አንዱ ድሬ ቱዩብ ነው።
ድሬ ቲዮብ የፌስ ቡክ ገፁ ላይ ብቻ ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮች አሉት።
የድሬ ቲዮብ መስራች እና ባለቤት ቢኒያም ነገሱ የኢትዮጵያውያንን ማህበራዊ ድረ ገጽ አጠቃቀም ለማጤን በቂ እድል አግኝቷል።
ዶይቸ ቬለም በተለየያዩ ቋንቋዎች ባሰናዳቸው የፌስ ቡክ ገጹቹ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎቹ ያቀርባል ያወያያልም።
ባልደረባዬ እሸቴ በቀለ የገጹን ተጠቃሚዎች እያወያየ አስተያየታቸውንም ሰብሰብ አድርጎ ያቀርባል።
እሱስ የኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ድረ ገፅ አጠቃቀምን በተለይ የዶይቸ ቬለ ገፅን ተጠቃሚዎች እንዴት ይገልጸዋል
ኢትዮጵያ የሐዋሳ የዛሬ ውሎ ግጭትም እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
የሃዋሳ የዛሬ ውሎ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ርዕሰ ከተማ ሃዋሳ ዛሬ ውጥረት ሰፍኖ ነው የዋለው።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነገረ በኋላ በነቀምቴ እና በደምቢዶሎ ስለነበረው ተቃውሞ እና የጸጥታ ኃይላት ርምጃም አስተያየቶችን አሰባስበናል።
የምክር ቤት አባላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዳያጸድቊ ስለነበረው ውትወታም የተጻፉትን እናካትታለን።
ዋካንዳ ሰሞኑን በዓለም ዙሪያ የበርካቶች መነጋገሪያ የኾነው ብላክ ፓንተር የተሰኘው የሆሊውድ ፊልም ታሪክ የሚፈጸምባት ከተማ ናት።
ከዋካንዳ በተለየ መልኩ ግን ኢትዮጵያ ነጻነቷን ጠብቃ የቆየችው በአስማታዊ ንጥረ ነገር ሳይኾን በጀግኖች ተጋድሎ ነው ይላል ጽሑፉ።
ኢትዮጵያ በቀድሞ አጠራሯ አቢሲኒያ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ለአውሮጳውያን ምሥጢር የነበረች መኾኗ ከዋካንዳ ጋር በመጠኑ ያመሳስላታል ሲልም አክሏል።
በ ብላክ ፓንተር ፊልም ላይ አብይ ገጸ ባሕሪው ንጉሥ ቲ ቻላ ከንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምንሊክ ጋር እንደሚመሳሰል ደ ብርሀን ገልጧል።
ዳግማዊ ዓጼ ምንሊክም የ ዓመት ልጅ ሳሉ በንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ተጠልፈው መወሰዳቸው በአድዋ ድልም ለአፍሪቃውያን ኩራት መኾናቸውን በማነጻጸር ያቀርባል።
ደ ብርሀን ከጽሑፉ ጋር አያይዞ ያቀረባቸው የሌሎች ሰዎች የትዊተር መልእክቶችም ተመሳስሎውን የሚያጠናክሩ ናቸው።
ኤም ኤንድ ጂ ፍራይዴይ የተባለው የትዊተር ገጽ፦ የዋካንዳ ታሪክ ሊነጻጸር የሚችለው ከኢትዮጵያ ጋር ብቻ ነው ብሏል።
እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር አፈር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ
እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ አማኑኤል ተስፋዬ በትዊተር ያሰፈረው ከታሪካዊ ተውኔት የተቀነጨበ ጽሑፍ ነው።
ሔዋን ዘ ስምዖን፦ አድዋ የአሜሪካ ድል ቢኾን ኖሮ በሺህ የሚቆጠሩ የተለያዩ አይነት ፊልሞች ይሠሩ እንደነበር ትዊትር ገጽ ላይ ጠቅሳለች።