input
stringlengths
1
130k
ሆኖም ኛ ዓመቱ ሊደፍን እጅግ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት በበረዶው ላይ በፍጥነት ይንሸራተትና የራስ ቅሉ ከድንጋይ ጋር ይላተማል።
ራሱ ላይ የደፋው መከላከያ ቆብ ተጠርምሶ የራስ ቅሉ በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል።
በፍጥነት ሀኪም ቤት ቢወሰድም አደጋው ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ አዕምሮው ውስጥም ጉዳት እንዳስከተለ ሐኪሞች በወቅቱ አስታውቀዋል።
ሹማኸር ለረዥም ጊዜያት ሐኪም ቤት ውስጥ ራሱን እንደሳተ ለመቆየት ተገዷል።
ሹማኸር ራሱን ማወቁ በሥራ አስኪያጁ በኩል ይፋ የሆነው አደጋ ከተከሰተ ከስድስት ወራት በኋላ ነበር።
ስዊትዘርላንድ ጔኔቫ ወሚገኘው ቤቱ ተዛውሮ የሕክምና ክትትል ከጀመረ ሦስት ወራት ተቆጥሯል።
ፈርናንዶ ቶሬዝ ከኹለት ቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ ከቸልሲ ወደ ጣሊያኑ ኤስ ሚላን በማቅናት በቋሚነት መጫወት እንደሚፈልግ ገልጦ ነበር።
ሆኖም ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ እንደሚያቀና ቡድኑ በድረ ገፁ ማረጋገጫ ሰጥቷል።
ዝውውሩ በውሰት ሲሆን ለአንድ ዓመት የሚቆይ መሆኑም ይፋ ሆኗል።
ቶሬዝ በ ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቸልሲ ከመዛወሩ በፊት ለሊቨርፑል ለ ዓመት ተሰልፎ ተጫውቷል።
ወደ ሊቨርፑል ከማቅናቱ በፊት ደግሞ የ ዓመት ልጅ ሳለ የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ ማሊያን ለብሶ ተጫውቷል።
በወቅቱ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ተሰልፎ በ ግጥሚያዎች ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሎ ነበር።
ፈርናንዶ ቶሬዝ የፊታችን ሰኞ የሐኪም ምርመራውን አጠናቆ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ልምምድ እንደሚጀምር ቡድኑ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ሊቨርፑል የዌስት ብሮሚቹ አጥቂ የ ዓመቱ ሣይዶ ቤራሂኖ ላይ ዓይኑን ጥሏል።
የዌስት ብሮሚቹ አጥቂ ከ ዓመት በታች የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ጊዜ ተሰልፎ ግቦችን ማስቆጠሩ ይታወቃል።
ሊቨርፑል ሣይዶን ለማስመጣት ሲሯሯጥ ቀደም ሲል ለቡድናችን ያስፈልገናል ያለለት የባየር ሙይንሽኑ የክንፍ ተጨዋች ዤርዳን ሻቃሪን ፈጣኖች ሊሞጨልፉት ነው።
የቀድሞው የሊቨርፑል አሠልጣኝ ዴቪድ ሞየስ በበኩላቸው አሁን ለሚያሠለጥኑት የስፔኑ ሪያል ሶሴዳድ ቡድን የሊቨርፑሉ ኤምሬ ካንን በውሰት ማምጣት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
የጣሊያኑ ሣምፕዶሪያ ቡድን የሊቨርፑሉ አጥቂ ማሪዮ ባሎቴሊን ከሰሞኑ መውሰድ እንደሚፈልግ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ከአራት ወራት በፊት በ ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ሊቨርፑል የመጣው ማሪዮ ባሎቴሊ በ ጨዋታዎች ኳስ ከመረብ ያሳረፈው ለኹለት ጊዜ ብቻ ነው።
ማሪዮ ባሎቴሊ ቸልሲ የክሮሺያው የፊት አጥቂ አንድሬ ክራማሪችን በሚቀጥለው ወር ወደ ቡድኑ ለማስመጣት ሚሊዮን ፓውንድ መመደቡ ተገልጧል።
የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን የአርሰናሉ አጥቂ ሉቃስ ፖዶሊስኪን ለመውሰድ መቃረቡ ተነግሯል።
ኢንተር ሚላኖች ከትናንት በስትያ ከአርሰናል ዋና ሰዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ጀርመናዊውን የአርሰናል አጥቂ ለመውሰድ ተቃርበናል ብለዋል።
አርሰናል በበኩሉ የዌስት ሐሙ ተከላካይ ዊንተን ራይድን ለማስመጣት ሚሊዮን ፓውንድ መመደቡ ታውቋል።
በ ነጥብ የአውሮጳ የዓመቱ ምርጥ ስፖርተኛ ተብሎ የተሸለመው በፎርሙላ አንድ የመኪና ሽቅድምድም ባለድሉ እንግሊዛዊው ሌዊስ ሐሚልተን ነው።
ሠርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ዝነኛ ኖቫክ ጆኮቪች ክሪስቲያኖ ሮናልዶን በልጦ በ ነጥብ ሦስተኛ ሆኗል።
ለሪያል ማድሪድ የሚጫወተው የፖርቹጊዙ አጥቂ ክሪስቲኖ ሮናልዶ ድምፅ ከሰጡት ጋዜጠኞች ያገኘው ነጥብ ሲሆን ደረጃው አራተኛ ነው።
ማሪዮ ሌሚና ከ ዓመት በታች የፈረንሣይ ቡድን ውስጥ ተሰልፎ የዓለም ዋንጫ መጨበጡ ይታወቃል።
ማሪዮ በፈረንሣይ ዋናው ቡድን ጥሪ ይደረግልኛል በሚል ተድፋ እየተጠባበቀ መሆኑም ታውቋል ።
የጋቦን ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዙሪያ ተሰልፈው የሚጫወቱ ድንቅ ተጨዋቾችን ማካተቱ ተገልጧል።
ከተጨዋቾቹ መኻከል የቦሩስያ ዶርትሙንዱ አጥቂ ፒየር ኤመሪክ የካርዲፉ ተከላካይ ብሩኖ ማንጋ እና የቻርልተን አትሌቲክ አጥቂ ፍሬድሪክ ቡሎት ይገኙበታል ተብሏል።
ምድቡ የአፍሪቃ ዋንጫ አስተናጋጇ ኢኳቶሪያል ጊኒ ቡርኪና ፋሶ እና ኮንጎ ይገኙበታል።
በሚል ጥያቄ ሲያስደምሙ ደግሞም ሲያስደንሱ የማታ የማታ ደግሞ በዚያዉ በዉብ የሙዚቃ ድግሳቸዉ ምዕራባዉያኑን ወደ ኢትዮጵያ ሲጋብዙ ሰንብተዋል።
አንጋፋዉ ከያኒ አየለ ማሞ በመድረክ ማንዶሊንን ከመጫወት የሙዚቃ ቡድኑን በድምፅ ከማጀብ ባሻገር በዉዝዋዜያቸዉ የእድምተኛዉን ቀልብ ስበዉ ነበር ያመሹት ።
በአሁኑ ሰዓት አኩስቲክ ጃዝ ባንድ ወደ አገር ቤት ተመልሶ የሙዚቃ ድግሱን ለማሳየት ወደ ቻይና ለመጓዝ ዝግጅት ላይ እንደሆነም ተነግሮአል።
በሙዚቃ ድግሱ ምሽት የተገኘዉ አብዛኛዉ ጀርመናዊ ታዳሚ ኢትዮጵያን በስራ ጉዳይ የሚያዉቅ አልያም ኢትዮጵያዊ ባልንጀራ ያለዉ በመሆኑ ነበር።
ለዶቼ ቬለ ራድዮ ጣብያም ትዉስታ የሚለዉን የሙዚቃ አልብሙን ለማስታወሻ ሰትዋል።
ችግሩ ያሳሰባቸዉ የተፈጥሮ ሐብት ተሟጋቾችና የሐይቁ ተጠቃሚዎች አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጠዉ በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ።
የየስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ልማት ፅሕፈት ቤት እና የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ለረጅም ጊዜዉ ጥያቄ መልስ ለመስጠት መዘጋጀታቸዉን ይናገራሉ።
የሀዋሣ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ተድላ ወ ሚካኤል ከሀዋሣ ሀይቅ ጋር ያላቸው ትውውቅ አራት አስር ዓመታትን ይሻገራል፡፡
በወቅቱ የሐይቁ ዳርቻ ጥቅጥቅ ባለደን የተሸፈነ በመሆኑ ሰዎች በቅርበት ካልተጠጉ በቀር እንዳአሁኑ ከርቀት ለማየት ይቸገሩ እንደነበርም ያስታውሳሉ፡፡
ይሁን እንጂ የሀይቁን ዙሪያ መለስ የከበበው ደን ለማገዶ መሬቱን ደግሞ ለእርሻ ሥራ በመዋሉ ዛሬ ላይ ያኔ የነበረውን ውበቱን ማጣቱን ይናገራሉ፡፡
ከስምጥ ሸለቆ ሀይቆች አንዱ የሆነው የሀዋሣ ሀይቅ ሕገ ወጥ የእርሻ ሥራዎች ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡
ሊቢያ የለዉጥ ጅምር አንደኛ አመት የያኔዉ እስረኛ ያሁኑ ሚንስትር፥
መታሰራቸዉን የሰማዉ አምስት መቶ ያሕል የቤንጋዚ ሕዝብ ፖሊስ ጣቢያዉን ከበቦ ይዘመር ፥
ግን ለአንድ ሐገር ሕዝባቸዉ የሚያልሙ የሚያደርጉት ያቃረናቸዉ የሥልጣን ሙያ ጠልቅ ልዩነት ያራራቃቸዉ ሁለት ሰዎች።
የዚያን ቀን ሲገናኙም የዓላማ ምግባራቸዉ ቅራኔ የማይታረቅነቱን በማወቅና መጪዉን እኩል ባለማሳወቅም አንድ ነበሩ።
የስለላዉ የበላይ አብዱላሕ ሴኑሲ ለብዙ ዘመን ብዙ ጊዜ ያደረጉትን መድገማቸዉን እንጂ የመሪያቸዉን ሞት የሥርዓታቸዉን ዉድቀት ማፅደቃቸዉ መሆኑን አላወቁም።
ከዚያ በፊት እንደሚያዉቁት የሚደርስባቸዉን ሥቃይ የሚገደሉበትን ዕለት መቼነት እያሰላሰሉ እስር ቤት ተወረወሩ።
አርብ የሊቢያ ሕዝባዊ አመፅ አንደኛ አመቱ ተከበረ የአመፁ አንደኛ አመት፥
ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ለባራክ ኦባማ ደግሞ እራሳቸዉ ኦባማ ያኔ እንዳሉት ከመሐመድ ጅብሪል፥
ካሁኑ የሊቢያ መሪ ከሙስጠፋ አብዱል ጀሊልም ደስታ አለፍ ያለ ዓይነት ነበር።
በዓለም አቀፉ አሸባሪ ድርጅት አል ቃኢዳ ላይ የተቀዳጁት ድል ማጠናከሪያ ነበር።
ከሁሉም በላይ ኦባማ እንደተናገሩት የቃዛፊ መገደል መስተዳድራቸዉ የኢራቅና አፍቃኒስታኑን ጦርነት በድል አድራጊነት የማጠናቀቁ ዋቢ አድርገዉት ወይም መስሏቸዉ ነበር።
ሁለት ሺሕ አስራ አንድ ዘመኑ በሙሉ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ከዋሽንግተን።
ይሕ የጋዛፊ መገደል የሆነዉ የአሜሪካ አመራር በመላዉ ዓለም በተጠናከረበት ወቅት ነዉ።
አሁን ደግሞ ሊቢያ ዉስጥ ከወዳጆቻችንና አጋሮቻችን ጋር ያከናወነዉ ምግባር በሃያ አንደኛዉ ምዕተ ዓመት የጋራ እርምጃ ሊያከናዉነዉ የሚችለዉን አሳይተናል።
ተወላጆች የፖለቲካዉን ሥልጣንም የደለበዉን ሐብትም የአምበሳ ድርሻ ተጋሪ የመሆናቸዉ መሠረት ነዉ።
ለአብዛኛዉ ሊቢያ ደግሞ ያኔ ኦባማ እንዳሉት ከረጅም ዘመን አምባገነናዊ አገዛዝ የመላቀቅ ምኞቱ ስኬት፥
ዕለቱ ቃዛፊ ያሰቃያቸዉ እና ያጠፋቸዉ ወገኖቻቸዉን የሚያስታውሱበት እና የአዲስ ዘመን ቃል የሚያማትሩበት ነዉ።
በርግጥም የሊቢያ ሕዝብ ከዚያ ቀን ለመድረስ ወዶም ሆነ ተገዶ፥
አዉቆም ሆነ ሳያዉቅ ስምንት ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በትንሽ ግምት ከሰላሳ ሺ በላይ ወገኖቹን ሕይወት ለቃዛፊ ጦር ታንክ፥
ከሐምሳ ሺሕ የሚበልጡ ወገኖችን አካል የሰወስቱ ወገኖች ቦምብ ሚሳዬል ጥይት አረር ማብረጃ ማድረግ ነበረበት።
ቁስለት የዳነዉ ሊቢያዊዉ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት የሐብታም ሐገሩ ሐብት ንብረት፥
ምጣኔ ሐብታዊ ሥርዓት አስመርሮት የተሻለ ኑሮ ነፃነት ፍለጋ የተሰደደ በሺ የሚቆጠር አፍሪቃዊ የባሕር ዉስጥ አዉሬ ሲሳይ መሆን ነበረበት።
የአርባ አንድ ዘመን ሥርዓታቸዉን ለገረሰሰዉ ጦርነት መለኮስ ሰበብ የሆነዉ የቤንጋዚ ሕዝብ ተቃዉሞ ነበር።
ተቃዉሞዉ የተጀመረበት አንደኛ አመት ባለፈዉ አርብ ሲከበር አንዲት የቤንጋዚ ወጣት ተማሪ እንዳለችዉ ቢያንስ ቤንጋዚ ብዙ ተቀይራለች።
ባለፈዉ አርብ ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ቢሮ የወጣዉ መግለጫም ፕሬዝዳንቱ ባለፈዉ ጥቅምት ካሉት ጋር አይጣጣምም።
በዓለም አቀፉ የሠብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል የሊቢያ ጉዳይ አጥኚ ካርስተን ዩርገንሰን እንዳሉት ደግሞ ሊቢያ ዛሬም ሥልጣን የያዘ፥
ካለፈዉ ጥር አጋማሽ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሊቢያ ነበርን።
እኛ ከመድረሳችን ከአንድ ሰዓት በፊት እንኳን የተገረፉ እንደነበሩ ነግረዉናል።
በድብደባና ግርፋት ብዛት በየእስር ቤቱ ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ የሞቱባቸዉን ሰዎች አነጋግረናል።
የእነዚሕ ሰዎች ቤተ ሰቦች እስር ቤት ዉስጥ እንደሚሰቃዩት ሁሉ ፍትሕን ይጠይቃሉ።
የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አጥኚ ሊቢያ እስር ቤቶች ሥላዩ ሥላጠኑት ከለንደን ሲናገሩ በቀደም አርብ፥
የሊቢያዉ የወጣቶች እና የስፖርት ሚንስትር ፈትሒ ተረቤል የአምና ይኼኔ ትዝታ፥
የሕግ ባለሙያዉ ከመያዛቸዉ ከሁለት ቀን በፊት የሊቢያ ሕዝብ የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊ አገዛዝን በመቃወም አደባባይ እንዲወጣ የሚጠይቅ ፅሁፍ በኢንተርኔት አሰራጭተዉ ነበር።
በተለይ በዚያ አመት ሐሙስ በሚዉለዉ የካቲት አስራ ሰባት ሕዝቡ የቁጣ ዕለት ብሎ ብሶቱን ባደባባይ እንዲገልፅ ተርቤል ይጠይቃሉ።
የካቲት አስራ ሰባት ለቤንጋዚዎች የቆየ በደል የተፈፀበት ዕለትም ነዉ።
የሚወነጅሉት ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊ ከዚያ ጊዜ ጥቂት ቀደም ብሎ ከነ ቡሽ፥
ከነ ቤርሎስኪኒ የጀመሩትን ወዳጅነት ለመጠበቅ ሲሉ ሰልፈኛዉ እንዲበተን ያዛሉ።
የቤንጋዚ ነዋሪ በተለይም ኢንተርኔት የሚያገኘዉ ወጣት የቱኒዚያ ግብፆችን አመፅ ጀግንነት ዉጤቱንም እየቀላወጠ፥
የካቲት አስራ ሰባት ሲጠብቅ ነዉ የሕግ ባለሙያዉን ፅሁፍ ያነበበዉ።
መልዕክቱ የቱኒዝ ካይሮ የዘመናት ፖለቲካዊ ሥርዓትን የገለባበጠዉን ሕዝባዊ አብዮት በጥሞና ለሚከታተሉት፥
አብዮቱ ድንበር ተሻግሮ ወደ ደቡብ ዝቅ ቢል የሚያከሽፉበትን ሥልት ለሚያብሰለስሉት ለትሪፖሊ ሹማምንት ልዩ ትርጉም ነበረዉ።
እና መልዕክቱ እንደበተነ ወደ ቤንጋዚ የገቡት የሰለላዉ ድርጅት የበላይ አብዱላሕ አል ሴኑሲ ፀሐፊዉ እንዲታሰሩ ወሰኑ።
የአዲሶቹ የሊቢያ መሪዎች አጋሮች የሴኑሲን የትዕዛዝ ወረቀት የያዙት ነጭ ለባሾች ተርቤልን ከመኪናቸዉ አዉርደዉ ቤንጋዚ ፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት ወረወሯቸዉ።
የዚያኑ ቀን ማታ ሴኑሲ ተርቤልን አስጠርተዉ ለሁለት ሰአታት ያሕል አነጋገሯቸዉ።
አንዳዴ ያስፈራራኝ ሌላ ጊዜ ደግሞ አድቤ እንድቀመጥ ይመክረኝ ነበር።
በዚያች ማታ ቤንጋዚ የተጀመረዉ ሕዝባዊ አመፅ የአርባ አንድ ዘመኑ ሥርዓት የፍፃሜ መጀመሪያ መሆኑ አላነጋገረም።
ሕዝባዊ አመፅ ግን እንደ ሊቢያ ጎረቤቶች በሕዝብ ፍላጎትና ጥያቄ ተጀመረ እንጂ በሕዝብ ሙሉ ተሳትፎ፥
ደም ባራጨ ዉጊያ ጦርነት አዝግሞ በብቀላ ቂም ቁርቁስ ነዉ ያበቃዉ።
የአምንስቲ ኢንተርናሽናሉ አጥኚ እንዳሉት ደግሞ የድሕረ ቃዛፊዉ ሥርዓተ አልበኝነት ከእስካሁኑም እንዳይብስ ነዉ ያሁኑ ሥጋት።
ችግሩ ደግሞ እነዚሕ ሰዎች እስረኞቹን የሚቆጣጠሩት ሚሊሺያዎች ከሕግ በላይ መሆናቸዉ ነዉ።
ያነጋገርናቸዉ ሕግ አስከባሪዎች በግልፅ እንደነገሩን ሚሊሺያዎቹ ማንም የሚቆጣጠራቸዉ የለም።
እና አሁን ያለዉ ሥጋት የሊቢያ ሁኔታ ከእስካሁኑም ይበላሻል የሚለዉ ነዉ።
የኤርትራ ስደተኞች ዳዳብ የሚገኙ ሶማሊያውያን የሄልሙት ሽሚድት ዜና ዕረፍትና የሃዘን መግለጫ መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የኩላሊት ተግባር መዳከም ምንነት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ብዙዎች ለኩላሊት ህመም ስለመዳረጋቸው በሰፊዉ ሲወራ ይሰማል።
ለህክምና ከመድረስ በፊት ኩላሊት ሥራው እንዲዳከም ወይም እንዲቆም የሚያደርገው ምን ይሆን
ደምን የማጣራት ብሎም በምግብ ሆነ በመድኃኒት ምክንያት የወደሰዉነት የገቡ መርዛማ ነገሮችን የማስወገድ ታላቅ ኃላፊነት ያለበት የሰውነት አካል ነው ኩላሊት።
ቢያንስ እስከአሁን ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ሕፃናት ሞተዋል ሌሎች ሁለት ሺህ የሚሆኑ ደግሞ አስቻኳዩ ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸው እናውቃለን።
በሺዎቹ ለሚቆጠሩት ሕፃናት ሊኖሩበት የሚችሉ ንፁሕ የተፈጥሮ አካባቢ የለም ለማለት ይቻላል ምክንያቱም የሚኖሩባቸው ቤቶች፡ ውሀው፡ በጠቅላላ አካባቢው በእርሳሱ ማዕድን ተበክለዋል።