input
stringlengths
1
130k
ቤተሰቦቻቸውም በማዕድናቱ ውስጥ መሥራታቸውን በመቀጠላቸው መኖሪያ ቤቶቹ ብክለት ሊወገድ አልቻለም።
ይሁንና፡ ይላሉ፡ የሂውማን ራይትስ ዎች የጤና ተመራማሪ ወይዘሮ ጄን ኮኸን ይህ ተግባሩ ቀላል አይሆንም።
እና ያካባቢው መስተዳድር ችግሩን ውጤታማ እና አጠቃላይ በሆነ መንገድ ለመታገል ቁርጠኝነት እና ከፌዴራሉ መንግሥትም ድጋፍ ያስፈልገዋል።
ፌዴራሉ መንግሥት እስካሁን በዚሁ አኳያ ይህ ነው የሚባል ሚና አልተጫወተም።
እንዲያውም፡ የፌዴራሉ የማዕድን ሚንስትር ችግሩን ለመታገል በዛምፋራ ፌዴራዊ ክፍለ ሀገር ያሉ ማዕድናት ሁሉ እንዲዘጉ የሚያዝ መግለጫ ትናንት አውጥቶዋል።
ይህ ካሁን ቀደም ተሞክሮ ነበር ግን ችግሩን ይበልጡን ነበር ያባባሰው።
ይህ ሲሆን ያካባቢው ነዋሪዎች ቤተሰቦቻቸውን አደጋ ላይ ሳይጥሉ በማዕድኑ ሥራ መሥራታቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ።
ሦስተኛው፡ ያካባቢው ሕፃናት በእርሳስ ማዕድኑ ብናኝ ተመርዘው መሆን አለመሆናቸውን በምርመራ ማጣራትና ማከም ይሆናል።
የፖለቲከኞቹ ተሥፋ እና ሥጋት በአዲስ አመት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አዲሱን አመት ሲቀበሉ ተስፋ እና ምኞታቸው እጅጉን የተራራቀ ነው።
ጠቅላይ ሚኒሥትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዋዜማው ባደረጉት ንግግር በአዲሱ አመት መንግሥታቸው የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ እንዲጎለብት ጠንክሮ ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒሥትር ሐይለማርያም ደሳለኝ እና ኢሕአዴግ አብዝቶ የፈተናቸውን እስከ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድረስም ያንደረደራቸውን ዓ ም ተሰናበቱ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በዋዜማው ባዘጋጀው ድግስ ጠቅላይ ሚኒሥትሩ በእርግጥ የጸጥታ መደፍረስ በተጫነው ዓ ም የገጠሟቸውን ፈተናዎች አልጠቀሱም።
ጠቅላይ ሚኒሥትሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታደሙት እና በቀጥታ የቴሌቭዥን ሥርጭት በተላለፈው ንግግራቸው ስለ መቻቻል እና አንድነት ሰብከዋል።
ጠቅላይ ሚኒሥትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመንግሥታቸውን ውጥኖች ከግብ ለማድረስ የአገሪቱ ዜጎች ያልተቆጠበ ያሉትን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ሰላማችን እንዲረጋገጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የጀመርንውን የጸረ ሙስና ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን።
ዶ ር ያዕቆብ ሐይለማርያም ኢትዮጵያ አዲሱን አመት ስትቀበል እንደ ጠቅላይ ሚኒሥትሩ ተስፈኛ አይደሉም።
ብዙም የሚባል ነገር የለም የሚሉት የሕግ ባለሙያ በአሮጌው አመት የተከሰቱ ኩነቶችን እያስታወሱ ይብሰለሰላሉ።
የበርካታ ሰዎች ህይወት ያለፉባቸው አካል የጎደለባቸው የቆሼ እና የኢሬቻን የመሰሉ አደጋዎች ኃላፊነት ያለባቸው ወገኖች ተጠያቂ አለመሆናቸውን እያነሱ ይተቻሉ።
ጠቅላይ ሚኒሥትሩ የጠቀሱት የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲህ በቅርበት ለመምጣቱም እርግጠኛ አይደሉም።
ደግሞም እንዲህ እንዲያደርግ የሚገፋፋው ሌላ ፓርቲ እስከ ሌለ ድረስ ያ ፓርቲ በጀመረው መስመር ይቀጥላል።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው መልካም ምኞት መደርደር ከባድ አልነበረም ሲሉ ይናገራሉ።
አገሪቱ ገጥመዋታል የሚሉትን ውስብስብ ችግሮች እየጠቀሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ተጨባጭ መፍትሔ ለማበጀቱ ግን እርግጠኛ አይደሉም።
ስለ ፍቅር ስለ ሰላም ማውራት የሚቻለው ከአሁን በፊት በግፍ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት ፈቃደኝነት ቢገኝ ኖሮ ነበር ።
ስለዚህ መጪው ዓመት እግዚያብሔር ከፈቀደ እነዚህ ሁሉ የሚስተካከሉ እና ለሕዝባችን ሰላም ፍትኃዊ አንድነት ሁሉ እኛ እንመኛለን።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ እንደ አቶ ሙላቱ ሁሉ ያለፈው ዓመት ፈታኝ እንደነር ይስማማሉ።
እርሳቸው ያለፈው ዓመት ተቃውሞ የአገሪቱን የፖለቲካ ሥርዓት ለማሻሻል ሁነኛው መንገድ እንደሆነ ያምናሉ።
በሚመጣው አመት ቢሆን ጥሩ ነው ብዬ የማስበው ሕዝቡ በሰላማዊ ትግል ሥርዓቱን በካርድ ለመቀየር ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው ነው።
ይቺ አገር እንደ አገር እንድትቀጥል ዜጎቿ በዴሞክራሲ መስመር እንዲጓዙ እና ዴሞክራሲ በአገሪቱ እንዲሰፋ ንቁ ተሳትፎ ቢኖረው ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ።
አዲስ አበባን በተመለከተ አቋማችን ከጋዜጠኛ እና ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ጋር ተመሳሳይ ነው ለማለት ያህል ነው።
ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ በህጋዊ መንገድ ለመደራጀት የሚያደርገውን ጥረት እደግፋለሁ
አዲስ አበባ ይድነቃቸዉ መኮንን በፊስ ቡክ ያስቀመጡት አስተያየት ነዉ።
ሰሞኑን በተለይ መገናኛ ብዙኃን ሲቀባበለዉ የነበረዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ንግግር ነበር።
ግልጽ ደብዳቤለክቡር ጠ ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ ከምንገኝ ተቆርቋሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሲሉ ኢትዮጵያዉያን መልክት አስተላለፉ።
ይድረስ ለ ቱ ዳያስፖራ ኣቤቱታ እቅራቢዎች ግልፅ ደብዳቤ በሚል ርዕስ።
ይላል ነፃነት ኪዳኔ የተባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚ ባስቀመጡት አስተያየት ደግሞ እስክንድር ትናንት አባቶችህንም በብእሩ ነው ያስቀዘናቸው።
አሁንም በሀሳብ ልዕልና እንጂ ወጣቶችን ወደ አላስፈላጊ ረብሻ የሚነዳ መደዴ አይደለም።
ይፋታኤል አቤል የተባሉ ተጠቃሚ በበኩላቸዉ በአደባባይ ገጀራ ይዞ የወጣን ቄሮ ዝም ብሉ።
በስላማዊ መንገድ የሚታገለውን የአዲስ አበባ ህዝብን እና እስክንድርን ለማስፍራራት መሞከር ከአብይ አይጠበቅም።
ዶ ር አብይ ባላደራ የተባለው ባልደራስ ከመሰብሰብ ውጭ ምን ችግር ፈጥሮ ነው እንደዚህ አይነት ጨዋታ አንፈልግም የተባለዉ
የለገጣሮ ቤት ሲፈርስ ያልሰማ ሰው አንድ አዳራሽ ውስጥ የነበረን ተሰብሳቢ እንዴት ተማህ
ድንጋይ፡ ሜንጫና ሚስማር በሀገሪቱ መዲናና ከተሞች ይዞ የሚወጣውን ለማስንጠንቀቅ ለምን ዳር ዳር ተባለ፡፡
አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ ነው ወይስ አይጥ ለሞቷ የድመት አፋንጫ ታሸታለች ነው፡፡
ጃሳ ኖሚና የተባሉ ተከታታይ በበኩላቸዉ አብይ በየዕለቱ የሚወገዘው ፡ የሚሰደበው በእርግጥም እስከዛሬ ከነበሩት የተሻለ መሪ ሰለሆነ ነው፡፡
የመናገር የመፃፍ የመደራጀት ነፃነት በር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ስለከፈተ ነው፡፡
ዛሬ ያገኘነው ነፃነት እስከ ዛሬ ያላየነውና ያልለመድነው ሆኖ ነው አብይን ደካማ መሪ ያሰመሠለብን፡፡
አቶ ታከለ ይሄን የማሸጋገር ሂደት በሚመለከት በትክክል ያልሰራው ነገር አለ ከተባለ ሂስ ማቅረብ ጥሩ ነው።
ዋና ተግባራችን ለሚቀጥለው ምርጫ በአዲስ አበባ ዙሪያ ጥሩ አቋም እና የነዋሪዎቿን መብት ያስጠብቃል ያልነውን ፓርቲ ህዝቡ እንዲመርጠው ግፊት ማድረግ ነው።
ግድግዳ ጡፍ ወይም ግራፊቲ በሐዋሳ ከተማ በምዕራቡ ሀገራት የግድግዳ ጡፍ ወይም ግራፊቲ እንደ ተመልካቹ እና ማህበረሰቡ አተረጓጎም ይለያያል።
አንዳንዶች ግራፊቲን ከውንብድና ጋር ሲያገናኙ ሌሎች ስሜት የሚገለፅበት አንድ መንገድ እንደሆነ ይናገራሉ።
ሐዋሳ ከተማ የሚገኙ የተወሰኑ ወጣቶች የግድግዳ ጡፍን እንደ አንድ የስዕል ጥበብ ነድፈው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።
የጣሊያንኛው ቃል ግራፊቶ ለብዙዎች ግራፊቲ በድንጋይ ላይ ተጫጭሮ የሚቀረፅ ጹሁፍ ወይም ምስል እንደማለት ነው።
በሐዋሳ ከተማ ግራፊቲ ኢትዮጵያ የወጣቶች ማህበር ብለው አንድ ማህበር በመመስረት ላይ ያሉ ወጣቶች እንደዚህ አይነቱ አሳሳል ዛሬ በከተማዋ የሚታወቁበት ሆኗል።
በሐዋሳ ከተማ የ ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው በሁሉም ለስዕል የተለየ ፍቅር እንዳለው ይናገራል።
ምንም እንኳን በሁሉም እና ባልደረቦቹ የግራፊቲ ስልቱን ከምዕራቡ ሀገራት ቢወስዱም ስራቸውን ለመስራት ባለቤቱን ፍቃድ ጠይቀው ነው።
አብዛኞቹም የግድግዳ ጸሀፊዎች እንይያዙ ስለሚፈሩ የሚፅፉት ወይም የሚስሉት ሌሊት ነው ።
በሐዋሳ ከተማ የግድግዳን ጡፍ ወይም ግራፊቲን እንደ አንድ የአሳሳል ስልት ከሚያየው ሌላው ወጣት አንዱ የበሁሉም ጓደኛ በረከት ተሾመ ነው።
በረከት በቴክኒክ ሙያ ተመርቆ ኮምፒውተር እና ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ይጠግናል።
እሱም የግድግዳ ጡፍን የሚገልፀው እንደ በሁሉም ሀሳብን ለመግለፅ ነው።
በሁሉም እንደገለጸልን የ ግራፊቲ ኢትዮጵያ የወጣቶች ማህበር አባላት ራሳቸውን ለሌሎች የሚያስተዋውቁበት የመረጃ ገፅ በአሁኑ ሰዓት በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።
ወጣቶቹ ሙያቸውን ለማዳበር ፌስ ቡክ እና ዩ ቱይፕ ከመሳሰሉ የማህበራዊ መገናኛ ድረ ገፆች መረጃ ያፈላልጋሉ።
ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ወደእነሱም ብቅ ይሉ እና ሀሳብ ይለዋወጣሉ።
የትግራይ ተቃዋሚ አባላት አሁንም እንደታሰሩ ነዉ ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የቀድሞዉ የወታደራዊ ደሕንነት ከፍተኛ መኮንን የስቃይ ታሪክ አውዲዮውን ያዳምጡ።
ካሪቡኒ የሙዚቃ ቅንብሩ በአፍሪቃ የሚነገሩ ተረቶችን ምሳልያዊ አነጋገሮችን የአፍሪቃን ሁኔታ በታሪክ መልክ እያስረዳ ነዉ አስከትሎ ዜማዉን የሚያስደምጠዉ።
ለወባ ክትባት ምርምር በጎርጎሪዮሳዊዉ ዓ ም በዓለም ዙሪያ በወባ በሽታ ሺ ሰዎች ማለቃቸዉን የዓለም የጤና ድርጅት ያመለክታል።
ኑሮ እጅግ ከመጠን በላይ ከብዷል እናም አስቸኳይ መፍትሄ እና አንድ እልባት ሊበጅለት ይገባል ይላሉ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጭዎች።
አዲስ ወረርሽን በድሬደዋ ምሥራቅ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው በሽታ ብዙዎችን ማዳረሱ እየተነገረ ነው።
የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊ እስካሁን በአዲሱ በሽታ ከ ሺህ ሰዎች በላይ በመያዛቸው በከተማው ወረርሽኝ መከሰቱን ይፋ አድርገዋል።
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች እሮሮ የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሠራተኞች በአሠሪዎቻቸው የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚፈጸሙባቸው ገለጹ፡፡
ድንጋይ ይወረዉሩ እንደነበር የተገለጸዉን የቡድኑን ደጋፊዎች ለመበተንም ፖሊስ የሚያስለቅስ ጭስ ተጠቅሟል።
የግብፁ ሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበር አንጋፋና እድሜ ጠገብ ስብስብ መሆኑ ነዉ የሚገለጸዉ።
የሽግግር መንግስቱ ሙስሊም ወንድማማቾችን በአሸባሪነት የፈረጀዉ በአንድ የፖሊስ ሕንፃ ላይ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰዉ ጥቃት የ ሰዎች ህይወት ካለፈ በኋላ ነዉ።
ሌላ አንድ ጀሃዳዊ ቡድን ለድርጊቱ ኃላፊነቱን ቢወስድም በይፋ ተጠያቂ የሆነዉ የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበር ነዉ።
የግብፅ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆሳም ኤይሳ እንዲህ ነዉ ያሉት መንግስት እንደገና ወደኋላ መመለስ የማይችል መሆኑን በድጋሚ ማረጋገጥ ይሻል።
ስለሆነም መንግሥት በሕገ መንግሥት አንቀጽ የወንጀለኛ መቅጫ ደንብ መሠረት የሙስሊም ወንድማማችነት ማህበር አባላት አሸባሪዎች ድርጅቱም አሸባሪ ነው።
ስለሆነም እርሱን በጽሑፍም ሆነ በቃል የሚያበራታቱ ወይም በሌላ ዓይነት መንገድ የሚረዱና ተግባሩን በገንዘብ የሚደግፉ የወንጀል ተባባሪዎች ናቸው።
እንዲሁም በአንቀጽ የተገለጠው ቅጣት በማንም ተባባሪ ግለሰብም ሆነ ቡድን ላይ ተፋጻሚ ይሆናል ።
ሙስሊም ወንድማማቾች በአሸባሪነት መፈረጁን በማዉገዝ ሰላማዊ ተቃዉሞዉን እንደሚቀጥልበት አስታዉቋል።
መንግሥት ሙስሊም ወንድማማቾችን የወነጀለበትን ፍንዳታ ያደረሰዉ ሌላ ቡድን ነዉ።
ዋና ከተማ ካይሮ አንድ ጓዳ ሠራሽ ፈንጂ በህዝብ መጓጓዣ አቅራቢያ ፈንድቶ አምስት ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ ዉጥረት ነግሶባታል።
መንግስት ረቡዕ ዕለት ቡድኑን በአሸባሪነት ከመዘገበ በኋላ እሱን በመደገፍ አደባባይ የሚወጣ ሰልፈኛን እንደማይታገስ ፖሊስ ዝቷል።
ዛሬ ከካይሮ የወጡ ዘገባዎች አልአዝሃር ዩኒቨርሲቲ ጊቢ የተማሪዎች ማደሪያ ዉስጥ ጭስ ይታይ እንደነበር ያመለክታሉ።
የአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ፖሊሶች አስለቃሹን ጭስ ከተኮሱ በኋላ ሁኔታዉ መከተሰቱን ነዉ የገለፀዉ።
የሙስሊም ወንድማማቾች ማኅበር አባል የነበሩት የቀድሞዉ ፕሬዝደንት ሞሐመድ ሙርሲ እስር ላይ ናቸዉ።
ከእሳቸዉ ሌላም የቡድኑ አመራር አካላት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወህኒ ወርደዋል።
ሙርሲ ከስልጣን ከተነሱበት ካለፈዉ ሐምሌ ወር አንስቶም ሙስሊም ወንድማማቾች ባለማቋረጥ የተቃዉሞ ሰልፉን ቀጥሎበታል።
የግብፅ የፀጥታ ኃይሎች በመላ ሀገሪቱ ዛሬ ለሰልፍ ከወጡ ደጋፊዎች ጋ ተጋጭተዋል ከመቶ በላይ ሰዎችን አስረዋል።
ካይሮ ዉስጥ መሳሪያ የተጠመደባቸዉ ተሽከርካሪዎች የከተማዉን ዋና አደባባይ መንገድ ዘግተዋል።
ሙርሲ ከስልጣን ከወረዱ ወዲህ በየጊዜዉ ተመሳሳይ የተቃዉሞ ሰልፉ ቀጥሏል ሰልፉን ለመበተን በሚወሰድ ርምጃም በሺዎች የሚገመቱ ሰዎች ህይወት አልፏል።
በተለይ በከፍተኛ ስልጣን ላይ የነበሩት አባላቱ በየሰላማዊ ሰልፉ ለሞቱ በተጠያቂነት በሀገር ክህደት እንዲሁም በአሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸዋል።
በአዲስ አበባ ዙሪያ ጥሩ አቋም እና የነዋሪዎቿን መብት ያስጠብቃል ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ጤና እና አካባቢ አነጋጋሪዉ የሴቶች መብት ይዞታ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከትናንት በስተያ ታስቦ ዉሏል።
ዘንድሮ የሴቶች ቀን ሲታሰብም የተመረጠዉ መሪ ቃል እዉን አድርጉት የሚል ነዉ።
በዚህ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለሴቶች መብት ለሚደረገዉ ትግል የተደረሰዉን መሠረታዊ ስምምነት ኛ ዓመትም እናከብራለን።
ይህም ለፆታ እኩልነትና በተለያዩ ሙያዎችና ማኅበራዊ ዘርፎች ሴቶችና ልጃገረዶች ለአመራር ብቁ እንዲሆኑ ግልፅ አቅጣጫን አመላካች ነዉ።
በርካታ ልጃገረዶች በፊት ከነበረዉ በተሻለ መልኩ ትምህርት የማግኘት እድል አግኝተዋል በወሊድ ጊዜ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከነበረዉ በግማሽ ቀንሷል።
በርካታ ሴቶች በንግዱ ዓለም በመንግሥት አስተዳደርና በዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ዉስጥ የመሪነት ቦታ ይዘዋል።
አሁም ግን ሴቶች ሊደርሱባቸዉ የሚገባ በርካታ ግቦች አሉ እንደየቤት ዉስጥ ጥቃት ግርዛት እንዲሁም የተለያዩ የጥቃት ዓይነቶች።
አድሎ አሁንም ጣሪያ እንደነካ ነዉ ይህን ሁሉ ተባብረን ማስቀረት ይኖርብናል።
በማለት ነዉ ዕለቱን አስመልክተዉ የተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ጊ ሙን መልዕክታቸዉን ያስተላለፉት።