input
stringlengths
1
130k
በብሪታንያ የሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ካለፈው ሰኔ ወር በኋላ ጊዜ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተፈፅመዋል።
የፖላንድ እና የብሪታንያ ባለስልጣናት አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው ስለዚሁ ጉዳይ በተደጋጋሚ ተወያይተዋል።
የልዑካን ቡድን በብሪታንያ ያሉትን ዜጎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚቻልበትን መፍትሔ የማፈላለግ ዓላማ ይዞ ነው ወደ ለንደን የተጓዘው።
የሽብሩ እንዴትነት የፀረ ሽብሩ ዉጊያ እስከየትነት ያፍታ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ።
ከጋየዉ መኪና አጠገብ በካራ የታረደ የአንድ ሰዉ ጭንቅላትና በአረብኛ የተፃፉ ሐይማኖታዊ ጥቅሶች አገኙ።
የኬሚካሉን ፋብሪካ በኬሚካል ሊያጋይ ኬሜካል የተሞላበትን ጠርሙስ ለመክፈት ይታገላል።
የእሳት አደጋ ተከላካዮቹ እሳቱን ከምንጩ የሚያጠፉበትን ብልሐት ለማወቅ ማሰብ ማሰላሰል አላስፈለጋቸዉም።
ጀርመናዊቷ የፖለቲካ አጥኚ ክሌር ደመስማይ ከባድ ጥፋት ሊደርስ ይችል እንደነበር አልተከራከሩም።
የጀርመንና የፈረንሳይን ግንኙነት የሚያጠኑት ደመስሜይ ሙከራዉን ራሱን አስገራሚ ይሉታል።
በጣም ያስገረማቸዉ ግን ባለፈዉ ጥር ሻርሊ ኤብዶ ከተጠቃ በኋላ የፀጥታ አስከባሪዎች ክትትል ቁጥጥርና ጥንቃቄ ሳይላላ ሌላ ጥቃት መቃጣቱ ነዉ።
ፈረንሳይ ዉስጥ ዳግም ጥቃት መሠንዘሩን በማየቴ በጣም ነዉ የተገረምኩት።
በሐገሪቱ ያለዉን ዉጥረት ለተመለከተ ግን እጅግ በጣም የሚያስገርመዉ ጥቃት መሰንዘሩ አይደለም።
ፓሪስ ዉስጥ ብዙ ተቋማት በተለይ ምኩራቦች እና የአይሁድ ትምሕር ቤቶች በፖሊስ ሲጠበቁ ይታያሉ።
ጥበቃ ጥንቃቄዉ ግን ከሌላ ጥቃት ያዉም ከራስዋ ከፈረንሳይ በቀል አጥቂዎች ሊያድናት አለመቻሉ እንጂ ዚቁ።
የአሜሪካዉን የኬሚካል ፋብሪካ ለማጋየት የሞከረዉ ግለሰብ ከዚሕ ቀደም ከፅንፈኞች ጋር ግንኙነት እንደነበረዉ የፈረንሳይ ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል።
ይሁንና ሰዉዬዉ እራሱን የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት ወይም ደዓሽ ብሎ የሚጠራዉ ድርጅት አባል ሥለመሆን አለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም።
የፈረንሳዩ ጥቃት እንዴትነት የደረሰዉ ጥፋት እስከምንነት የአጥቂዉ ማንነት ገና በቅጡ ሳይተነትን ከቀድሞዋ የፈረንሳይ ቅኝ ተገዢ ከቱኒዚያ ሌላ የሽብር ጥቃት ተሰማ።
በዉቧ የመዝናኛ ከተማ ሶሴ ባሕር ዳር የተንጣለለዉ ዘመናይ የቅንጦት ሆቴል በጥይት ሩምታ ተደበላለቀ።
የቱኒዚያ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት የቤልጂግ የጀርመን የአየር ላንድና የፖርቱጋል አንዳድ ዜጎችም ተገድለዋል።
ሐገር ጎብኚዎቹን በጥይትና በእጅ ቦምብ የገደለዉ ወጣትም በፀጥታ አስከባሪዎች ተገድሏል።
የመቀጠር በግሉ የመሥራት በትምሕርቱ የመቀጠል ሠፊ እድል የነበረዉ አዲስ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ።
ፖሊስ እንዳለዉ የወጣቱ ተንቀሳቃሽ ስልክ ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ ተገኝቷል።
አሸባሪዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አይ ሲ ስ ሐላፊነቱን ወስዷል።
በዚሕ አራት አመት ዉጥስ ከሚተራመሱባት ታጣቂዎች ወይም አሸባሪዎች አንዱ እራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለዉ ቡድን ነዉ።
ቡድኑ በየሥፍራዉ የሚወጉትን መንግሥታት ዜጎች ወይም ተባባሪዎቻቸን ለመጥፋት ከሊቢያ ሻገር እያለ ቱኒዚያን ኢላማዉ ማድረግ ብዙም አልከበደዉም።
ቡድኑ ባለፈዉ መጋቢት እዚያዉ ቱኒዚያ ዉስጥ በሐገር ጎብኚዎች ላይ በጣለዉ ተመሳሳይ ጥቃት ሃያ አንድ ሰዎች ገድሎ ነበር።
የቱኒዚያ መንግሥት ከመጋቢቱ ጥቃት በኋላ የአክራሪዉ ቡድን አባላት ወይም ደጋፊዎች ብሎ የጠረጠራቸዉን በርካታ ሰዎች አስሯል።
የሶሴዉን ግድያ ካዩት አንዱ ሽብርን ለማስቆም አብነቱ መተባበርን ነዉ ይላሉ።
በአብዮቱ ወቅት የነበረንን በጋራ የመቆም ስሜት ዳግም ማሰብ አለብን።
ለነፃነታችንና ለሠብአዊ መብት መከበር በአንድነት በአደባባይ እንደታገልን ሁሉ በአንድነት ከቆምን አሸባሪነትን ድል ማድረግ እንችላለን።
የኩዌት ኤምሬት ባለሥልጣናት ኋላ እንዳስታወቁት ሳዑዲ አረቢያዊዉ ወጣት ከሳዑዲ አረቢያ በማናማ ባሕሬን አድርጎ ኩዌት ሲቲ የገባዉ የዚያን ቀን ማለዳ ነዉ።
የዓለም መገናኛ ዘዴዎች የፈረንሳዩንና የቱኒዚያዉን ጥቃት እየተቀባበሉ በሚያራግቡበት መሐል ወጣቱን ያሳፈረዉ መኪና ኢማም ሳዲቅ መስጊድ ቅጥር ግቢ ገባ።
የሃያ ሰወስት ዓመቱ ወጣት ቦምቡን እንዳሸረጠ ወደ መስጊዱ ዘለቀ።
እራሱን የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራዉ ቡድን ወጣቱን አጥፍቶ ጠፊ ማዝመቱን አረጋግጧል።
ቡድኑ መናፍቅ የሚላቸዉን ወገኖች በተለይም ሺዓዎችን በቅርብ ቀን እንደሚገድል ከጥቂት ቀናት በፊት ዝቶ ነበር።
እርግጥ ነዉ የሺዓዎች ሐራጥቃ ሐገር ተቆርቃሪም ተደርጋ የምትቆጠረዉ ኢራን ሶሪያና ኢራቅ ዉስጥ አክራሪዉን ቡድን ትወጋለች።
በቴሕራን የሚደገፉት የደማስቆና የባግዳድ መንግሥታትም አንድም ሺዓ አለያም ለሺዓ የሚቀርበዉ የአላዊት ሐራጥቃ ተከታዮች ናቸዉ።
ከአይሲስ ጋር የሚደረገዉን ዉጊያ ወይም ፀረ ሽብር የሚባለዉን ዘመቻ በግልፅ ቋንቋ መበየን አስቸጋሪ ነዉ።
ሳዑዲ አረቢያ ኩዌትን ጨምሮ የፋርስ ባሕረ ሠላጤ አካባቢ መንግሥታትን በበላይነት ትመራለች።
ከግብፅ መዳከም በኋላማ የሪያድ ነገስታት መላዉን ዓረብ ከሆነላቸዉም መላዉን ሙስሊም ዓለም ለመምራት እየተንጠራሩ ነዉ።
ዩናይትድ ስቴትስ የምዕራብም የምሥራቅም ወዳጆችዋና ተባባሪዎችዋ በነሳዑዲ አረቢያ ከሚመሩት አረቦች ጋር ሆነዉ ባንድ በኩል የሶሪያን መንግሥት የሚወጉ ሐይላትን ያስታጥቃሉ።
ኢራንና በኢራን የሚደገፈዉ የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቦላሕ የደማስቆ መንግሥትን ደግፈዉ በዩናይትድ ስቴትስ በሳዑዲ አረቢያና በተባባሪዎቻቸዉ የሚደገፉ አማፂያንን ይወጋሉ።
ኢራን ሶሪያ ኢራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ሳዑዲ አረቢያና ተባባሪዎቻዉ በቀጥታ ይዋጋሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ለምትመራዉና ለምታስተባበረዉ ዘመቻ ኢራቅና ሶሪያ ዉስጥ ብቻ እንዲት ዩናይትድ ስቴትስ ብቻ በቀን ወደ ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ትከሰክሳለች።
የሌሎቹ መንግሥታት ድምር ወጪ ከዩናይትድ ስቴትስ ቢበልጥ እንጂ አያንስም።
ዓመት ሊደፍን ጥቂት በቀረዉ ዉጊያ ከስልሳ ሺሕ በላይ ሰዉ ተገድሏል።
የኩዌቱ የምክር ቤት እንደራሴ አድናን አል ሙተዋ እንዳሉማ ሠላማዊዉ ሰዉ መሸሸጊያ ነዉ ያጣዉ።
ኢላማ ያደረጉት አንድ ሐራጥቃን ብቻ አይደለም መላዉን አረብና ሙስሊምን አንጂ።
የባሕረ ሠላጤዉ ትብብብር ሐገራትና መላዉ ሙስሊም ሐገራት አሸባሪነትን እንዲዋጉ እንጠይቃለን።
አል ቃኢዳ የተፈለፈለ የተመሠረተ የተሠራጨዉ በ እና ከመንግሥት አልባዋ አፍቃኒስታን ነበር።
የ የተመሠረተ የተጠናከረ የተሠራጨዉም ጠንካራ መንግሥት አልባዋ ኢራቅ ነዉ።
ፈጥኖ የተዛመዉ ወደምትወድመዉ ሶሪያ እና ወደ ፈራረሰችዉ ሊቢያ ነዉ።
አፍቃኒስታን ኢራቅ ሊቢያ የመን ለምን እና እንዴት መንግሥት አልባ ሆኑ።
ዓለም ያለነፃነት እና ክስ አምስት ዓመት ዊክሊክስ የተሰኘዉ አጋላጭ ድረገጽ መሥራች ጁሊያን አሳንዥ ክስ ሳይመሠረትበት ነፃነቱን እንዳጣ አምስተኛ ዓመቱን ያዘ።
በጎርጎሪዮሳዊዉ ዓ ም ልክ በትናንትናዉ ዕለት ነበር አሳንዥ ስዊድን ዉስጥ ክስ የቀረበበት።
ከሁለት ዓመታት በኋላም የለንደን ፖሊስ አሳልፎ ለስዊድን እንዳይሰጠዉ እዚያ በሚገኘዉ በኤኳዶር ኤምባሲ ዉስጥ ገብቶ ከለላ አገኘ።
ጁሊያን አሳንዥ ከዚያን ጊዜ አንስቶም ጉዳዩ እንደተንጠለጠ እሱም ከተደበቀበት ሳይወጣ ለዚህ ጊዜ ደረሰ።
ከጎርጎሪዮሳዊዉ የሰኔ ወር አንስቶ እያንዳንዷን ዕለት አሳንዥ ያሳለፈዉ በዚህ ኤምባሲ ሕንፃ ዉስጥ ነዉ።
ጉዳዩ ለስቶክሆልም አቃቤ ሕግ ይቀርብ እና ጉዳዩን የተመለከቱት አቃቢተ ሕግ ለጥርጣሬ የሚያደር በቂ ነገር በማጣታቸዉ ይጥሉታል።
ከዚያም ሌላ አቃቤ ሕግ ከጎንተንበርግ ከተማ ጉዳዩን ዳግም እንደአዲስ ያነሳሉ።
ስለጉዳዩ የሚነሳ ነገር ካለም ስዊድን በግለሰቡ ላይ ይፋ ያደረገችዉ የእስር ማዘዣ ብቻ ነዉ።
በዚያም ላይ ስዊድን አሳንዥን ለዩናይትድ ስቴትስ አሳልፋ እንደማትሰጥ ዋስትና ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነችም።
ይህ ያሰጋዉ አሳንዥ ጥገኝነት ባገኘበት የኤኳዶር ኤምባሲ መቀመጥ ግድ ሆኖበታል።
የአሜሪካን መንግሥት ቁጣና ትኩረትም በምሥጢር አጋላጩ ድረገጽ ላይ ብቻ ሳይሆን ገመናዉን ባቀበለዉ አካል ላይም ነዉ።
ደራሲ እና ጋዜጠኛ ቻርለስ ግላስ የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ መንግሥት ከቀድሞዎቹ በበለጠ በርካታ ጋዜጠኞች ላይ ክስ መመሥረቱን ያስረዳል።
የኦባማ አስተዳደር ያለፉት መንግሥታት ባጠቃላይ ካደረጉት ይበልጥ በርካታ ጋዜጠኞችን ከሷል።
የኦባማ አስተዳደር በመላዉ ዓለም የሚፈፅመዉ የቁም ስቅል ግድያ እንዲሁም ተጠርጣሪዎችን ከአንድ ሀገር ይዞ ወደሌላ መዉሰድ እንዲጋለጥ አይፈልግም።
የግላስን አስተያየት ለጋዜጠኞች የሚሟገተዉ የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የቦርድ አባል ማቲያስ ሽፒልካምፕም ይጋሩታል።
እዉነታዉን ስንመለከት ምሥጢር አጋላጮቹ ላይ የሚቀርበዉ ክስ ተጠናክሯል ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታም ጠንካራ ክትትል እየተደረገባቸዉ ነዉ።
ሽፒልካም አክለዉም ዩናይትድ ስቴትስ ዊክሊክስ ሌሎች አጋላጭ መረጃዎችን ይፋ እንዳያደርግ የተለያዩ የማደናቀፍ ሙከራዎች ማድረጓም የፕረስ ነፃነትን የሚገድብ ነዉ በማለት ይተቻሉ።
ዊኪሊክስ የሰዎችን ህይወት ለአደጋ አጋልጧል የሚለዉን የዋሽንግተንን ክስም ያጣጥላሉ።
ይህ ሁሉ ምናልባት በአሳንዥ የስዊድን የፍርድ ቤት ጉዳይ ላይ ተፅዕኖ ይኖረዉ ይሆን
የወንጀል ሕግ ምሁር የሆኑት ኒኮላዎስ ጋሴዝ የፍርድ ሂደቱ ሚዛናዊነት ጥያቄ ላይ ወድቋል ይላሉ።
አሳንዥን በተለመለከተ ግን አንዲት አስተያየት ሳይሰነዝር ለረዥም ዓመታት ዝም ማለቱ ያልተለመደ ነዉ።
እናም በዚህ ሁኔታ እንደምናዉቀዉ አንድ ይፋዊ ጉዳይ እንዲሁ እንዲተዉ አድርጓል።
አካሄዱም እሳቸዉ እንደሚሉት ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት ማድረስ የሚችል አቅም ያለዉ አቃቤ ሕግ ያለ እንዳይመስል አድርጎታል።
የጤና ድርጅቱ እንደሚለዉ አብዛኞቹ እናቶች ለልጃቸዉ እንዴት ጡት ማጥባት እንዳለባቸዉ ባለማወቃቸዉ አንዳንዶቹ ደግሞ በሚሰማቸዉ ህመም ምክንያት ማጥባትን ይተዋሉ።
አውሮፓ እና ጀርመን ጀርመናውያን ከሚያሳስቧቸው አበይት ጉዳዮች መካከል ወደ አገሪቱ የሚነጉዱ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ ስደተኞች እና ፍላጎቶቻቸው ይገኝበታል።
በጀርመን በተሰራ አንድ ጥናት መሠረት በርካታ ዜጎች አገሪቱ ከጎርጎሮሳዊው ዓ ም ወዲህ የበረታውን የስደት ቀውስ መቋቋም አትችልም የሚል ሥጋት ተጭኗቸዋል።
በዛሬው የአውሮፓ እና ጀርመን መሰናዶ ይልማ ኃይለሚካኤል ጀርመናውያኑን የሚያሳስቧቸውን ጉዳዮች ይዳስሳል።
ህልሟን እዉን ያደረገች ወጣት ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ሁለቱም አክቲቪስቶች እንደሚሉት ከሆነ የአዲስ አበባ ዉዝግብን በዉይይት ለመፍታት ዝግጁ ነን።
የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ የአስተዳደር ጉዳይ ከፍተኛ የሆነ ዉዝግብ ቀስቅሶአል።
ሁለቱም አክቲቪስቶች እንደሚሉት ከሆነ ዉዝግቡን በዉይይት ለመፍታት ዝግጁ ነን።
በቅድምያ ነጋሽ መሐመድ ከጃዋር ጋር ያደረገዉ ቃለ ምልልስ ይደመጣል።
በመለጠቅ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ እስክንድር ነጋም ዉዝግቡን ማስወገድ የሚቻለዉ በዉይይትና በድርድር እንደሆነ በሰጠዉ ቃለ ምልልስ አሳዉቋል።
በጎይተ ኢንስቲትዩት ውይይት ተካሂዷል ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ያልተሳኩት ቃል ኪዳኖችና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
ጤፍን መሰል አዝርዕትና እጽዋት በማይገባቸው ኩባንያዎች ስም ተመዝግበው ይገኛሉ አውዲዮውን ያዳምጡ።
ኢትዮጵያ የፍትህ ሥርዓቱ ሀገርኛ ሚና ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ክልሎች የሚቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም አልረገበም።
በአፋር እና ሶማሌ ብሄረሰቦች በጋሞ በኦሮሚያ በመስቃንና ማረቆ በስልጤ አካባቢ የተነሱት ግጭቶችን በባህላዊ ስርዓት ለመፍታት ጥረት መደረጉ ይታወቃል።
መንግስት በክልሎች በሚቀሰቀሱ ግጭቶች እልባት የመስጠቱ ጉዳይ እምብዛም ነው ሲባል ይደመጣል።
እነዚህ ግጭቶች ወዴት እያመሩ እንደሆነ በግልፅ የሚታወቅ ነገር የለም።
ይሁንና ከዚህ ቀደም የሀገር ሽማግሌዎች አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ግጭት በመፍታት ዘላቂ እርቀ ሠላም ለማውረድ ችለዋል።
የሀገር ሽማግሌዎቹ ለረጅም ዘመናት የዘለቀው ታሪካዊ ትስስር አንድነትና ወንድማማችነት በህዝቦች መሀል እንዲጠነክር የአስታራቂነት ድርሻቸውን እንደተወጡ የብዙዎች እምነት ነው፡፡
የፍትህ ስርዓት ግጭት አፈታት አንደኛው ነው ሁለተኛው ሀይማኖታዊ እንደዚሁም ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓቶች ናቸው።
የመንግሥት የፍትህ ስርዓት አሁን የተፈጠሩትን ግጭቶች የመፍታት አቅም አለው ብዬ አላምንም።
ተጨባጭ ነገር እያየን ያለነው የባህላዊና ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስርዓቶች በተለያየ ደረጃ ጣልቃ በመግባት ጉዳዩን በሚገርም ሁኔታ እየፈቱ እንዳሉ ነው።
ከመንግሥታዊ የፍትህ ስርዓት ባህላዊውና ሀይማኖታዊ የሆነው የሀገር ሽማግሌዎች ችግርን የመፍታቱ ሚና የተሻለ እንደሆነ ዶ ር ከይረዲን ያስረግጣሉ።
ሽማግሌዎች የገቡባቸው ዕርቅ ባህላዊ ህግጋት የተደገፉ ስለሆኑ ለችግሩ እልባት የመፍጠራቸው አቅም በየትኛውም ደረጃ ሲመዘን ከመንግሥታዊ ፍትህ ስርዓት የተሻሉ ናቸው።