input
stringlengths
1
130k
ለምሳሌ፦ አባ ገዳዎች በቅርቡ በኦፒዲ አመራሮችና በኦነግ መካከል ያደረጉት የዕርቅ ሥነ ሥርዓት እስካሁን ድረስ ሲመረቅዝ አላየንም።
የበለጠ ተጠንተው የፍትህ ሥርዓት ውስጥ መካተት ቢችል ግጭት ከመፍታት አልፎ ሰላም በመፍጠር ወደፊትም የበለጠ ሚና ይኖራቸዋልም ብለዋል።
ግጭቶች በዚሁ ከቀጠሉ መቆጣጠር ከምንችለው በላይ ሊሆን እንደሚችልም ካሁኑም እልባት ሊበጅለት ይገባል ካልሆነ የሀገርን ሰላም ማምጣት አንችልም ብዙዎች ሲሉ ይደመጣል።
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ላይ ዶቼቬለ የፖለቲካ አቀንቃኞችንም አክቪስቶች ንም አስተያየት ጠይቋል።
ኢትዮጵያ የሲዳማዉ ጥፋት ፖሊስ ሥለሞቱት ሰዎች ቁጥር የሚያዉቀዉ ሆስፒታል ደርሰዉ ስለሞቱት ወይም አስከሬናቸዉ ሆስፒታል ስለደረሰ ሟቾች ብቻ ነዉ።
በየአካባቢዉ ተገድለዉ የተቀበሩ ሰዎች በፖሊስ ስሌት ዉስጥ አለመካተታቸዉን አዛዡ አስታዉቀዋል አውዲዮውን ያዳምጡ።
በየአካባቢዉ ተገድለዉ የተቀበሩ ሰዎች በፖሊስ ስሌት ዉስጥ አለመካተታቸዉን አዛዡ አስታዉቀዋል።
ከሟቾቹ በተጨማሪ ሰዎች መቁሰላቸዉን የፖሊስ አዛዡ አስታዉቀዉ በረብሻዉ የተጠረጠሩ ሰዎች መያዛቸዉን አረጋግጠዋል።
በረብሻዉ ፋብሪካዎች የሸቀጥ መደብሮች ሆቴሎች መኖሪያና መስሪያ ቤቶች መዉደማቸዉን ገሚሶቹ መዘረፋቸዉንም ፖሊስ አስታዉቋል።
የደቡብ ሱዳን ምሥቅልቅል ሁለቱ ጠበኞች እንደወዳጅ ተጨባብጠዉ የድሮ ስልጣናቸዉን በአዲስ መንግሥት ሥም በያዙ ማግሥት ሐምሌ መጀመሪያ ላይ እንደገና ተጠሉ።
የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚያስገኘው የፍጻሜ ውድድር ላይ ለመድረስ ጨዋታዎች መከናወን ይገባቸዋል።
የኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድር የሚከናወነው ልክ እንደ ዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ፍልሚያ በየአራት ዓመቱ ነው።
ቀጣዩ የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሩስያ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫን እያስተናገደች ስትገኝ ለውድድሩ ከመላው ዓለም ሃገራት ተካፋይ ናቸው።
ከስምንቱ የውድድሩ ተካፋዮች ስድስቱ በፊፋ የኮንፌዴሬሽን አሸናፊዎች አሸናፊ የአኅጉራት የዋንጫ ባለድሎች ናቸው።
አንዱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ሲሆን ሌላኛው ሃገር የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሀገር ነው።
በምድብ ሁለት ደግሞ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን ቺሊ አውስትራሊያ እና ካሜሩን ተካፋይ ናቸው።
በትናንትናው ግጥሚያ የእግር ኳስ ዳኞችን በውሳኔ አሰጣጥ ሊያግዝ ይችላል የተባለለት አዲስ ስነ ቴክኒክ ማለትም ዳኛ ደጋፊ ቪዲዮ ተግባራዊ ኾኗል።
ፖርቹጋል እና ሜክሲኮ አቻ በወጡበት ውድድር ዳኛ ደጋፊ ቪዲዮው ውጤታማ ሆኖ ታይቷል።
የቺሌው ኤድዋርዶ ቫርጋስ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ግብ ያስቆጥራል ዳኛውም ግቡን ያጸድቃሉ።
አፍታም ሳይቆዩ ግን በዳኛ ደጋፊ ቪዲዮው መረጃ መሠረት ግብ ያሉትን ውሳኔ ከጨዋታ ውጪ በሚል ይሽሩታል።
ብዙዎች ኤድዋርዶ ከጨዋታ ውጪ ነው የተባለበትን ቪዲዮ በመተቸት ትከሻው ብቻ ከመሥመር ማለፉ ከጨዋታ ውጪ ሊያስብል አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል።
የሚገርመው ነገር ግን ቺሌ ለ ባሸነፈችበት ጨዋታ አሌክሲስ ሳንቼዝ ግብ ያስቆጠረው ከጨዋታ ውጪ ሆኖ ነበር።
በዚህ ጊዜ ዳኛ ደጋፊ ቪዲዮ መረጃ ቺሌን የጠቀመ ይመስላል።
ትናንት ቺሌ ካሜሩንን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ጨዋታም ልቆ ታይቷል።
በትናንቱ ጨዋታ ለቺሌ አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ቪዳል ግብ አስቆጥረዋል።
በተለይ ቪዳል ከፍ ብሎ በመዝለል በጭንቅላት ያስቆጠራት ድንቅ ግብ ተብላ ተመዝግባለች።
የቺሌው አሰልጣኝ ኹዋን አንቶኒዮ ፒሲ ከጨዋታው በፊት አሌክሲስ ላይሰለፍ እንደሚችል ስጋታቸውን እንዲህ ገልጠው ነበር።
ግን ደግሞ እስዳስተዋልነው ከሆነ ትንሽ ኅመም ብጤ ስለሚሰማው በደንብ ሊሻለው ይገባል።
አሌክሲስ ሳንቼዝ ከጨዋታው በኋላ ከመልበሻ ክፍል ውስጥ ሆኖ ያበጠ የግራ እግሩ ቁርጭምጭሚትን የሚሳያይ ምስል በማኅበራዊ መገናኛ አውታር አሰራጭጭቷል።
ከትናንት በስትያ በመክፈቻው የመጀመሪያውን ጨዋታ ከአስተናጋጇ ሩስያ ጋር የተጋጠመችው ኒውዚላንድ የ ለ ሽንፈት ደርሶባታል።
የኮንፌዴሬሽን ካፕ የእግር ኳስ ግጥሚያ ፍጻሜን ብራዚል ለሦስት ጊዜያት በተከታታይ በአጠቃላይ ደግሞ ለ ጊዜያት አሸንፋለች።
ዋንጫው በተከታታይ ብራዚል እጅ ከመግባቱ አስቀድሞ ፈረንሳይ የዛሬ እና ዓመት ለሁለት ጊዜያት አሸናፊ ኾናለች።
ሜክሲኮ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ ብራዚልን ተከትላ ለአንድ ጊዜ የዋንጫ አሸናፊ መኾን ችላ ነበር።
አልሳድቅ ሁለተኛ የገባበት ሰአት ሦስት ደቂቃ ከ ነጥብ ሰከንድ ነው።
አማን ከአልሳዲቅ ከአንድ ሰከንድ ባነሰ ጊዜ ተበልጦ በሦስት ደቂቃ ከ ነጥብ ሰከንድ ማጠናቀቅ ችሏል።
የያኔው የአንደኛ ደረጃ ውጤት ሰአት ከ ነጥብ ሰከንድ ነበር።
በ ሜትር መሰናከል ሩጫ የትናንቱ የስቶኮልም ዲያመንድ ሊግ ውድድር ደግሞ ጫላ በዮ ደቂቃ ከ ነጥብ ሰከንድ በመግባት አራተኛ ሆኖ አጠናቋል።
በዚህ ውድድር የኤርትራው አትሌት የማነ ኃይለ ሥላሤ በሁለተኛነት ጨርሷል።
እስከዛሬ በተደረጉ ውድድሮች በተሰበሰበ ነጥብ ጽጋቡ ከ ብስክሌተኞች የ ኛ ደረጃ ይዟል።
በአጠቃላይ ድምር ውጤት ከ ተወዳዳሪዎች መካከል የኤርትራው መርሐዊ ቅዱስ ኛ ደረጃን በመያዝ ጠንካራ ብስክሌተኛነቱን አስመስክሯል።
የ ዓመቱ አንዲ ሙራይ ነገ በሚወዳደርበት ኲዊንስ ክለብ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ማሸነፍ ችሏል።
የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ዮኣሒም ጋውክ ሰኞ መጋቢት ቀን ዓም የቄስ ጉዲና ቱምሳ መቃብርን ጎብኝተው የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸው ተዘግቧል።
የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መሪ የነበሩት ቄስ ጉዲና በምን ይታወሳሉ
በደርግ ዘመነ መንግስት የመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መሪ ነበሩ ቄስ ጉዲና ቱምሳ።
የቄስ ጉዲና የመጨረሻ ልጅ የሆኑት ወሮ ሌንሳ ጉዲናም አባታቸው ለሁለተኛ ጊዜ ሲታሰሩ ለመጠየቅ በሄዱበት እስር ቤት ተይዘው ታስረው እንደነበር ገልፀዋል።
ከውጭ በነበረው ጫና ለሁለተኛው ጊዜ ከታሰሩበት እስር ቤት ተለቀው ነበር።
ከሶስተኛው እስር በኋላ ግን ዱካቸው ሳይገኝ ለ ዓመታት ቆይቷል።
ያኔ የ ዓመት ታዳጊ የነበሩት ወሮ ሌንሳ ጉዲና አባታቸው ቄስ ጉዲና የሚታወሱበትን ጉዳይ እንዲህ ይጠቅሳሉ።
ይህን በተመለከተ የቄስ ጉዲና ቱምሳ የመጨረሻ ልጅ ወ ሮ ሌንሳ ጉዲና መልስ አላቸው።
ወሮ ሌንሳ ጉዲና አያይዘውም ስለ ቄስ ጉዲና ማንነት ለመናገር አባታቸው ትተው ያለፏቸውን ጽሑፎች መመርመር ያስፈልጋል ብለዋል።
የአባታቸውን ጽሑፎች ለህትመት እያበቁ እንደሆነ በመጥቀስ በፅሁፎቹ ውስጥ ቄስ ጉዲና ስለተጨቆኑ ሰዎች ሁሉ አጥብቀው ይጠይቁ እንደነበር ጠቅሰዋል።
የሙቀት መጠኑ እጅግ ሲቀንስ ወይንም ቅዝቃዜው አይሎ ላ ኒኛ የተሰኘችው የአየር ጠባይ ስትከተል በዓለማችን ምን ይከሰታል
ላ ኒኛ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሄዷ የአየር ትንበያን አስቸጋሪ የሚያደርገውስ ለምን ይኾን
ኢትዮጵያን ጨምሮ በደቡባዊ እና ምሥራቃዊ አፍሪቃ የሚገኙ ሃገራት ለዐሥርተ ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ መመታታቸው ተዘግቧል።
የድርቁ ዋነኛ መዘዝ ደግሞ የኤል ኒኞ አየር ጠባይ ነው ተብሏል።
በተለይ ላለፉት ወራት በብርቱው ኤል ኒኞ የተነሳ የተከሰተው አደገኛ ድርቅ ላለፉት ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ እንደኾነ ተነግሮለታል።
በዓለማችን የትኛውም አቅጣጫ ውቅያኖስ ከተለመደው የአየር ጠባይ እጅግ ሲቀዘቅዝ አለያም ሲሞቅ በሌላኛው የዓለም ክፍል ብርቱ ክንዱን ያሳርፋል።
እናም ሞቅ ያለው የውቅያኖስ ውኃ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ይመለሳል።
በደቡብ አሜሪካ አህጉር የባሕር ወሽመጦች ላይ የሚገኘውን ቀዝቃዛ ውኃም ይቀንሰዋል።
ሒደቱን የከባቢ አየር ሳይንቲስቶች ኤልኒኞ ይሉታል በስጳኝ ቋንቋ አጠራሩ ትንሹ ልጅ እንደማለት ነው ትርጓሜው።
ኤል ኒኞ በሌላ ጊዜ ጠንከር ብሎ ወደ ምዕራብ ሲቀዝፍ የዓለማችን ምሥራቃዊ ክፍል የውቅያኖስ ውኃ ከተለመደው በላቀ እንዲቀዘቅዝ ያደርገዋል።
ካናዳ በሚገኘው የካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ አከባቢ ተጽዕኖ ቅነሳ ፋኩልቲ ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር የኾኑት ዶክተር ጌታቸው አሰፋ ይበልጥ ያብራሩታል።
በመደበኛ የውቅያኖስ ዑደት ላይ እነ ኢንዶኔዢያ አውስትራሊያ ያሉበት የምዕራቡ ክፍል ሙቅ ውኃው የሚሰበሰብበት ነው።
ብርቱው ኤል ኒኞ እንዳለፈ ዘንድሮ የተከሰተችው ላ ኒኛ በጥር ወር ሞዛምቢክ ውስጥ የጎርፍ መጥለቅለቅ በማስከተል ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሳለች።
ብርቱ ዝናም በማስከተልም በደቡባዊ አፍሪቃ የሚገኙ ሃገራት ነዋሪዎች ላይ መፈናቀል አስከትላለች።
ኤል ኒኞም ኾነ ላ ኒኛ በተለምዶ ከ እስከ ወራት ይቆያሉ።
ዘንድሮ ብርቱውን ኤል ኒኞ የተከተለችው ላ ኒኛ አቅመ ደካማ ቆይታዋ አጭር ነበር።
ይኽ ወደፊት በወቅታዊ እና የረዥም ጊዜ የአየር ትንበያ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይጠቀሳል።
የኤል ኒኞ እና የላ ኒኛ መደበኛ ዑደት ሲያጥር ሁለት እና ሦስት ዓመት ሲረዝም ደግሞ ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት ይቆያል።
ኢትዮጵያ ላ ኒኛን ከስድስት ዓመት ግድም በኋላ ያስከተለው ኤል ኒኞ የአየር ጠባይ ክስተት ብርቱ ጥፋት ከደረሰባቸው ሃገራት አንዷ ናት።
በውይይት መድረኩ በዶ ር አርከበ ዕቁባይ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከ ኩባንያዎች ጋር ተሳትፏል።
የለንደኗ ወኪላችን ሐና ደምሴ መድረኩን ተከታትላ የሚከተለውን ዘገባ አቀብላናለች።
በኢትዮጵያ የዜጎች መብት እና የሕግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ አውዲዮውን ያዳምጡ።
የህብረተሰቡን የህይወት ክንዋኔ ይገልጻል የባህል መገለጫም ሆኖ እንደሚያገለግል ያስረግጣሉ።
ተጽእኖ እንዳለ ሆኖ ሙሉ ለሙሉ ግን ባህሉ ላይ ተመስርቷል ማለት እንደማይቻል ይገልጻሉ።
ሥነ ቃሉ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም ክንዋኔ የሚገልጽ ነው።
የሚገልጸውም የህብረተሰቡን አስተሳሰብ አመለካከት እርስ በርሱ ያለውን ግንኙነት ይገልጻል።
ሥነ ቃል ለአንድ ማህበረሰብ ዛሬም ሀብት ሆኖ ያገለግላል ሲሉ አቶ መስፍን ይገልጻሉ።
ዛሬ ላይ ሥነ ቃል በከተማ በገጠርም እንዴት ይተላለፋል ብለን ስንመረምር ድሮ ከነበረው የተለወጠ ነገር ልናገኝ እንችላለን።
ሥነ ቃል በአንድ ወቅት የነበረው አገልግሎት አይቋረጥም ማለት አይደለም።
ልጆች ባህላቸው ባእድ የመሆኑ ችግር በገዘፈ ሁኔታ አለ የሚሉት ወ ሮ ሰተቴ ገ ሀና ናቸው።
የውጭ መረጃ ብዙውን ሲያውቁ ሀገር በቀል የሆኑ ባህሎቻቸውን ግን አያውቁም ሲሉም ችግሩ የጎላ እንደሆነ ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሁፍ የአማርኛ ቋንቋ ሥነ ዘዴ ላይ የማስተርስ ትምህርታቸውን ሰርተዋል።
በጊዜ በቦታ በምክንያት እንዲሁም በአቀራረብ ስልት ከዋኙም የሚቀያይረው ነገር ይኖራል።
አፍሪቃ የጁባላንድ ምርጫና የህገ መንግስቱ ተቃርኖ በሶማሊያ የጁባላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ምክር ቤት ባለፈው ቅዳሜ አህመድ ማዶቤ ኢስላንን በፕሬዝዳንትነት መርጧል።
የጌዶ መካከለኛውና ታችኛው ጁባ አካባቢዎችን በማጣመር የተመሰረተው የጁባላንድ ራስ ገዝ አስተዳደር ከማዕከላዊ ሶማሊያ ጋር ያለው ግንኙነት የሻከረ ነው።
የጌዶ መካከለኛውና ታችኛው ጁባ አካባቢዎችን በማጣመር የተመሰረተውን የጁባላንድ በጊዜያዊነት ሲያስተዳድሩ የቆዩት ማዶቤ ለምርጫ የቀረቡት ከሌሎች ሶስት ተፎካካሪዎች ጋር ነበር።
የቀድሞው የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች አጋር ተፎካካሪዎቻቸውን በከፍተኛ የድምጽ ብልጫ ማሸነፋቸውን በሞቅዲሹ የዶይቼ ቨሌ ተባባሪ ዘጋቢ የሆነው መሐመድ ኦማር ሁሴን ይናገራል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት አህመድ ማዶቤ ከሰባ አራቱ የፓርላማ አባላት መካከል የስልሳ ስምንቱን ድምጽ አግኝተዋል።
ከሶማሊያ መንግስት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩና ጥቂት የፓርላማ አባላት ምርጫውን ታዝበዋል።
ከመሐመድ ዚያድ ባሬ ውድቀት ጀምሮ በአገሪቱ የተፈጠሩ ታጣቂ ቡድኖች እርስ በርስ የሚጋጩባት የኪስማዩ ከተማና ወደብ በዚሁ ግዛት ይገኛል።
በከሰል ንግድና ቀረጥ ከፍተኛ ገቢ የምታስገኘው ኪስማዩ ከስድስት አመታት በላይ በአሸባብ ጠንካራ መዳፍ ስር ቆይታለች።
በሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስትና በጁባላንድ አስተዳደር መካከል ያለው ግንኙነትም የሻከረ ነው።
በቻተምሃውስየሶማሊያፖለቲካተንታኝአህመድሱሌይማን የጁባላንድ አመሰራረት ለሶማሊያ ፌዴራላዊ የመንግስት አወቃቀር ፈተና እንደሆነ ይናገራሉ።
በግዛቶች አመሰራረትም ህገ መንግስታዊ ህዝበ ውሳኔ ሊኖር ይገባ ነበር።
አስፈላጊ ከሆነም በግዛቶች አመሰራረትና አስተዳዳሪዎች ምርጫ ላይ ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ ማድረግ ይቻል ነበር።
መሐመድ ኦማር ሁሴን አሁን ፕሬዝዳንት የመረጠው የጁባላንድ ምክር ቤት በሶማሊያ መንግስት ዘንድ ያለው ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ መሆኑን ይናገራል።
ባለፉት ጥቂት ወራት በሶማሊያ መንግስትና በጁባላንድ አስተዳደር መካከል ያለው ግንኙነት በጥሩ ሁኔታ ውስጥ አልነበረም።
ቅርብ ጊዜ የሶማሊያ ምክር ቤት የጁባላንድ ምክር ቤት ህጋዊ አይደለም ሲል ድምጽ ሰጥቷል።
የምክር ቤቱ አባላት በጁባላንድ ነዋሪዎች የተመረጡ ባለመሆናቸው ህጋዊነትም ይሁን ተቀባይነት የላቸውም ብሏል።