input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
የጤናማ እናትነት ወር ግንዛቤ በድሬደዋ ከወሊድ ጋር በተገናኘ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር እንዲቀንስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ይነገራል።
|
በተመድ የምዕተአመቱ የልማት ግብ በተለይ በአፍሪቃ ሃገራት የእናቶችን ሞት በ በመቶ ለመቀነስ ታልሞ ኢትዮጵያም ያንን ለማሳካት እየሠራች መሆኑን ታመለክታለች።
|
ዛሬም ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ከወሊድ ጋር በተገናኘ በዓመት ሺህ እናቶች ሕይወታቸው እንደሚያልፍ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
|
ኢትዮጵያ ውስጥ ለእናቶች ሞት መንስኤ ከሆኑ ዋና ምክንያቶች ግንባር ቀደሙ ደም መፍሰስ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
|
ይህ ደግሞ በርካታ እናቶች በገጠርም ሆነ በከተማ በቤት ውስጥ በመውለዳቸው ምክንያት የሚያጋጥም መሆኑ ነው የሚገለፀው።
|
የድምጽ ቅንብሩ የጤናማ እናትነት ወርን አስመልክቶ በድሬደዋ ያለውን እንቅስቃሴ ያስቃኛል።
|
ተሰዳጆቹ እንደሚሉት ወደ አውሮጳ ለመሻገር ከ ሺህ እስከ ሺህ ብር ለሕገ ወጥ አሸጋጋሪዎች ከፍለዋል።
|
አላማቸው ሩቅ ነው ሰው መዋጥ የለመደበትን ሜዲትራኒያን ባህር በሆነ ተአምር ተሻግረው አውሮጳ መግባት።
|
ለዚህም በተደጋጋሚ ለሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለዋል።
|
እነሱ እንደሚሉትም ለረዥም ጊዜ በዚህ ስቃይ ውስጥ መቆየታቸው ሞትን እንዲጋፈጡ ገፋፍቷቸዋል።
|
ከዚያም የ ባልደረቦች መሆናቸውን የገለፁላቸው አካላት ወደ አንድ መጠለያ እንደወሰዷቸው እና ቢጫ ወረቀት እንደሰጧቸውም ገልጸዋል።
|
ከዛሬ ነገ ም ወደ ሌላ ስፍራ እንዛወራለን በሚል ተስፋ ለሦስት ወራት ተመልካች ማጣታቸውንም ያስረዳሉ።
|
ከሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎቹ እጅ መትረፋቸውን እንደ አንድ ጥሩ ነገር ቢቆጥሩትም አሁን ባሉበትም የሊቢያ ፖሊሶች ዱላ አልቀረላቸውም።
|
እነዚህ ተሰዳጆች የሊቢያ የባህር ጠረፎች እንደበፊቱ በቀላሉ እንደማይታለፉ ከፍተኛ ጥበቃ እንዳለባቸው ያውቃሉ ግን መንገድ አያጣም ባዮች ናቸው።
|
ዛሬ ዕለቱ ዓርብ በመሆኑ እና በሊቢያ የሥራ ቀን ባለመሆኑ ጉዳዩን ያውቃል የተባለውን የ ቢሮ በስልክ ለማነጋገር ያደርግነው ጥረት አልተሳካም።
|
ኢትዮጵያ የጀመረችዉን የፖለቲካና የኤኮኖሚ ለዉጥ ጎዳና አድንቀዋል ይዘት ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
ካትሪን የአፖሎ የጨረቃ ደርሶ መልስ ቀመር ያሰሉ የሂሳብ ሊቅ ናቸዉ
|
ይሁንና የኮሎኔል አለበል ደሞዝ በመቋረጡ መቸገራቸዉን የቤተሰባቸዉ አባላት ሲናገሩ የብርጌድየር ጀነራል ተፈራ ቤተሰብ ግን እስካሁን ደሞዝ እንደሚያገኝ አስታዉቀዋል።
|
የባሕርዳሩ ዘጋቢያችን ዓለምነዉ መኮንን እንደሚለዉ ስለጉዳዩ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽንን ለማነጋገር ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካለትም።
|
ኤኮኖሚ የጥሬ ሀብት ንግድ ማሽቆልቆል እና አፍሪቃ በአሁኑ ወቅት በዓለም ገበያ የጥሬ ሀብት ዋጋ እጅግ አሽቆልቁሎአል።
|
በጥሬ ሀብቱ ዋጋ መቀነስ የተጎዳዉ ደግሞ ደሃዉ የአፍሪቃ ኅብረተሰብ ነዉ።
|
ዛክ ሊሱኩ በናይጄርያ ሪቨርስ አዉራጃ ዉስጥ በሚገኘዉ አንድ የዘይት ኤንዱስትሪ ማዕከል በኃይል ምንጭ ዘርፍ ባለሞያነት ያገለግላሉ።
|
ዛክ ሊሱኩ ከወራቶች ጀምሮ በሀገራቸዉ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ማሽቆልቆል መጀመሩን እየታዘቡ ነዉ።
|
ባለፈዉ ሰኔ ወር አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ማለትም የ ሊትር የነዳጅ ዘይት ዶላር ያወጣ ነበር።
|
አሁን በያዝነዉ ጥቅምት ወር ማለቂያ ላይ ደግሞ የአንድ በርሜል ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ዶላር ገብቶአል።
|
የነዳጅ ዘይት ዋጋ በማሽቆልቆሉ ግን ምንም ሥጋት እንደሌላቸዉ ነዉ ዛክ ሊሱኩ የሚገልፁት።
|
በአፍሪቃ በነዳጅ ዘይት ንግድ ኤኮኖሚያቸዉ ካደገ ሃገሮች መካከል ናይጀርያ ትጠቀሳለች።
|
በሀገሬቱ የሚገኙ የዘርፉ ባለሞያዎች ግን እስከ ዛሬ መተንበይ አልቻሉም።
|
ባለፉት ዓመታት ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት ፈጣን የኤኮኖሚ እድገት ነዉ የታየዉ ።
|
በነዚህ ሃገራት በመቶ የሚሆነዉ ገቢ የተገኘዉም ጥሬ እቃን ለዉጭ ገበያ በማቅረብ ነዉ ።
|
ይህን ፈጣን የኤኮኖሚ እድገት እንደ ጥሬ እቃዉ ዋጋ ዉድቀት ሊገታ ሊቀንስ ይችላል።
|
ሲሉ በሀንቡርግ ጊጋ በተሰኘዉ የአፍሪቃ ጥናት ተቋም ፕሬዚዳንትና በአፍሪቃ ኤኮኖሚ ላይ ጥናት የሚያደርጉት ፕሮፊሰር ሮበርት ካፕል ተናግረዋል።
|
ካፕል እንደሚሉት በዓለም ገበያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ማሽቆልቆል የናይጄያን ኤኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የጎዳዉ የአፍሪቃ ሃገራት ኤኮኖሚንም አንቆ ይዞአል።
|
ተለዋጭ የኤኮኖሚ ገቢ ዘርፍ መጀመር የነበረበት ደግሞ የነዳጅ ዘይት ገብያቸዉ በሰመረበት ግዝያት እንደነበርም አመልክተዋል።
|
ለዚህም በምሳሌነት የባሕረ ሰላጤዉ አረብ ሀገሮች ተጠቃሽ ናቸዉ ።
|
ናይጀርያ ለዉጭ ገበያ ከምታቀርበዉ የነዳጅ ንግድ ተቀማጭ ሃብት የላትም ባገኘችዉ ገቢም ሌሎች የኤኮኖሚ ዘርፎችንም አላቋቋመችም።
|
በዚህም ይላሉ ፕሮፊሰር ሮበርት ካፕል ሀገሮች በነዳጅ ዘይት ዋጋ መዋዠቅ የሚገጥማቸዉ የገቢ ምንጭ ማነስ ችግር ማኅበረሰቡ ላይ ተፅኖ ያሳድራል።
|
ለምሳሌ በመንግሥት መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ የሚፈሰዉ መዋለ ንዋይ ሲቀንስ ተጎጅዉ ማኅበረሰቡ ነዉ።
|
አንጎላ ከሠራችዉ ትልቅ ቁም ነገር ገንዘብ አጠራቅማ ወደ ሰላሳ ቢሊዮን ዶላር ተቀማጭ እንዲኖራት ማድረጓ ነዉ።
|
መንግሥት ወደ ቢሊዮን ዶላር የሚሆነዉን የሀገሪቱን የነዳጅ ዘይት ገቢ የሚጠራቀምበትን ስልት ቀይሷል።
|
መዋለ ንዋይ የፈሰሰባቸዉ ግዙፍ ፕሮዤዎች ልክ እንደ ዱባይ ባለሃብትን ወደ ሃገራቸዉ ለመሳብ ታስቦ የተገነባ ቢሆንም አልተሳካላቸዉም።
|
የነዳጅ ዘይት ዋጋ ማሽቆልቆል ከቀጠለ የሠሯቸዉን መሠረተ ልማቶች በዘላቂነት ሊጠቀሙባቸዉ አይችሉም።
|
ጋና ዉስጥ በማሽቆልቆል ላይ ያለዉ የጥሬ ሃብት ዋጋ ተፅዕኖ በጣም ጉልህ በሆነ ሁኔታ ይታያል።
|
ይህች ምዕራባዊት የአፍሪቃ ሀገር ከሌላዉ ከጥቂት ዓመታት ጀምሮ ነዳጅ ዘይትን በማምረት ለዉጭ ገበያ ማቅረብ ጀምራለች።
|
ባለፉት ግዜያት በጋና ለማኅበረሰቡ የሥራ ቦታ ያስገኙ የነበሩ የወርቅ ማዕድን ማዉጫና የካካዎ ምርቶች ነበሩ።
|
እንደ ኤለርስ የነዚህ ሁለት ጥሬ ሃብቶች ዋጋ በዓለም ገበያ ላይ ከመጠን በላይ ዝቅ ብሏል።
|
የወርቅ ማዕድን መቆፈርያ ቦታዎች ትርፍ የማያስገኙ ከሆነ ቶሎ ይዘጋሉ።
|
በነዚህ የማዕድን ማዉጫ ቦታዎች ይሠሩ የነበሩ በርካታ ጋናዉያን ከሥራ ተባረዋል።
|
ችግሩ በጣም ጉልህ ሆኖ የሚታየዉ ትናንሽ የካካዎ ምርት አቅራቢዎች በካካዎ ዋጋ መዉደቅ የሚደርስባቸዉ ኪሳራ ነዉ።
|
በዓለም ገበያ የካካዎ ምርት በሚወድቅበት ጊዜ የነዚህ ሀገር መንግሥታት ከገበሬዉ የካካዎ ምርቱን የሚሸምቱት በድሮዉ ዋጋ ብቻ ነዉ።
|
እንደ ኤለርስ አብዛኞቹ የአፍሪቃ ሀገሮች በአብዛኛዉ የሥራ ቦታ ያለዉ እርሻ ላይ ነዉ።
|
ስለዚህም የጥሬ ሃብት ንግድ ማቆልቆል ቀዉስ በሚከሰትበት ወቅት አብዛኛዉ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ችግር ይደርስበታል።
|
እንደ ኤለርስ ገለፃ በነዳጅ ዘይት ዘርፍ በሚደርሰዉ የዋጋ ዉዥቀት ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችና ትላልቅ ባለሃብቶች ላይ የሚደረሰዉ ቀዉስ በጣም ከፍተኛ የሚባል አይደለም።
|
እነዚህ ባለሃብቶች ሥራ ላይ ያዋሉት ገንዘብ በቢሊዮን የሚቆጠር ቢሆንም ለ ዓመት ታስቦ የተደረገ ነዉ።
|
ስለዚህ ለረጅም ግዜ መዋለ ንዋይ የፈሰሰበት የልማት ዘርፍ በአጭር ጊዜዉ የዋጋ ዉዥቀት ጉዳት አይደርስበትም።
|
እንደ አብዛኞች ምሁራን አስተያየት የአፍሪቃ ኤኮኖሚ በቅርቡ ይንኮታኮታል የሚል እምነት የለም።
|
በጀርመን ባንክ ጥናት ላይ የሚገኙት ቻርተርጂ እንደሚሉት ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት በከፍተኛ ፍጥነት እድገት እየታየባቸዉ ነዉ።
|
በነዚህ ሃገራት በመጭዉ የጎርጎረሳዊ ዓ ም በመቶ እድገት ይታያል ተብሎ ይጠበቃል።
|
በሌላ በኩል የጥሪ ሃብት ዋጋ ማሽቆልቆል በአብዛኛዉ ነዋሪ ላይ ተፅኖ ያሳድራል ሲሉ ፕሮፊሰር ሮበርት ካፕል ይናገራሉ።
|
ይሁን እና ዳግም አገርሽቶ ሰዎች ሞተዋል ቆስለዋል በሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።
|
ስለ ስሞታው ዶቼቬለ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ቅነሳ ስራ አመራር ኮሚሽንን አነጋግሯል።
|
የሴት ልጅ ግርዛት በጀርመን እንደ ሰብዓዊ የመብቶች ተሟጋቹ ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል መዘርዝር አውሮፓ ውስጥ የሴት ልጅ ግርዛት ሰለባዎች ይኖራሉ።
|
የኦህዴድ ውሳኔዎች እና የተጨማሪ እስረኞች ፍቺ መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ አስራ አራት ሺህ ሰራተኞቹን ከዛሬ ጀምሮ በጊዚያዊነት ከስራ ማሰናበቱን አስታወቀ።
|
የኢትዮጵያዉያን ርዳታ ድርጅቱ ከአባላቱ ያሰባሰበዉን ገንዘብ ለእርዳታ ፈላጊዎቹ ያደርስለት ዘንድ ዎርልድ ቪዥን የተባለዉን የእርዳታ ድርጅት መምረጡን አስታዉቋል።
|
ድርጅቱ ሌሎች ኢትዮጵያዉያንም የፖለቲካም ሆነ የጎሳ ልዩነትን ወደጎን ብለዉ በድርቅ ለተጎዱት ወገኖች እንዲደርሱ ጥሪዉን አቅርቧል።
|
ለሐዋሳ ነዋሪዎች ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ክልላዊ መንግሥት ለማቆም ጥያቄ ስላቀረቡ ዞኖች የሰጡት ማብራሪያ ለአንዳንዶች ተገቢ ለሌሎች ኢ ምክንያታዊ ሆኖባቸዋል።
|
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሁለት እግሩ ሳይቆም ክልል የመፍጠር ጉዳይ ብንሞክር ፍላጎት ብቻ ነው የሚሆነው ሲሉም አስረድተዋል።
|
አሁን ደቡብ አካባቢ ያለውን ነገር መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ በክብር ተቀብሏል።
|
ደኢሕዴን የሚባለው ክልሉን የሚያስተዳድረው ድርጅትም ጥያቄውን ተቀብሎ በሕግ እየመረመረ ይገኛል።
|
ዐቢይ ከሕጋዊ መንገድ ውጪ ምንም አይነት ሙከራ ቢደረግ ሱማሌ እንደሆነው ደቡብም ይሆናል።
|
የሐዋሳው የዶይቼ ቬለ ወኪል ሸዋንግዛው ወጋየሁ በጉዳዩ ላይ የከተማዋን ነዋሪዎች ዘወር ዘወር ብሎ አነጋግሯል።
|
የጎርጎሪዮስን የቀን ቀመር የሚከተሉ በመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች በዛሬው ዕለት የክርስቶስ መወለድን በማክበር ላይ ይገኛሉ።
|
የገና በዓል ቫቲካን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የገና ቃለ ቡራኬያቸውን አስምተዋል።
|
ኤት ኡርቢ በማለት ለሦስተኛ ዓመትም ዛሬ በካቶሊክ ዋና መቀመጫ ቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ ሠገነት ላይ ሆነው አሰምተዋል።
|
በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰውን ምዕምን አውቶማቲክ ጠመንጃዎችን የታጠቁ ጸረ ሽብር የጸጥታ ኃይላት እየተዘዋወሩ ሲጠብቁም ተስተውሏል።
|
ወኪሎቻችን ከቫቲካን ከብራስልስ እና ከዩናይትድ ስቴትስ ያጠናቀሩትን ዘገባ ልከውልናል።
|
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲሰጠው መወሰኑ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
ከፈረሰ ዓመት ያለፈው ግንብ አሻራ በእነዚያ ገደማ አመታት ከ በላይ ሰዎች ከምሥራቅ ጀርመን ወደ ምዕራብ ጀርመን ለማምለጥ ሞክረው ያክሉ ተሳክቶላቸዋል።
|
ዓለም የሮሂንግያ ሙስሊሞች የደረሰባቸው በደል በሁለት ሳምንት ውስጥም ከ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
|
የሮሂንግያ ሙስሊሞች በምያንማር የሮሂንግያ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ በተከፈተው ግጭት ምክንያት ህዝቡ ለሞት እና ለስደት ተዳርጓል።
|
የአኝዋክ ስደተኞች በጎሮም መጠለያ ጣቢያ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
የእስራኤል ምክር ቤት ዉሳኔ የገጠመዉ ተቃዉሞ ወቅቱም ለአክራሪዎቹ አመቺ ነዉ።
|
ኢትዮጵያ የሕዝብ አስተያየት ስለ የኮሮና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ በተደነገገው የኮሮና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ተከልክለዋል።
|
አገር አቋራጭም ይሁን የከተማ ውስጥ ታክሲ በሙሉ አቅማቸው መጫን አይችሉም።
|
ለመሆኑ ይኸን ጠበቅ ያለ ገደብ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዴት አገኙት
|
እድር ደቦ እና እቁብን መሰል ማኅበራዊ ግንኙነቶች ከአራት ሰው በላይ ማሳተፍ አይችሉም።
|
ቤት ተከራዮችን ማስወጣት ኪራይ መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተከለከለ ነው።
|
በሰራተኛና አሰሪ አዋጅ የሚተዳደሩ የግል ተቋማት ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም አይችሉም።
|
ሳይንስ እና ኅብረተሰብ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብታዊ ዕድገት አካታች ካልሆነ ወደ ግጭት ሊመራ እንደሚችል ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ስጋት አላቸው።
|
የጌድኦ ተፈናቃዮች ሮሮ ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
ራድዮ ምናባዊ እውነታ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ተቀምጦ እንዴት ላሊበላን መጎብኘት ይቻላል
|
የጀርመን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ በዛሬዉ ዕለት ከአፍሪቃ ኅብረት ባለስልጣናት ጋር ተነጋገሩ።
|
መሰረታዊ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች ሹም ሽር ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን የፖለቲካ ቀውስ አይፈታም ሲሉ አዲሱን የሚኒስትሮች ሹመት አልተቀበሉትም፡፡
|
ህዝብ እየጠየቀ ያለው የፖሊሲ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች መለዋወጥ ለውጥ አያመጣም ብለዋል፡፡
|
ከአዲሶቹ ተሿሚዎች ውስጥ አራቱ በባለፈው ካቢኔ ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ሲመሩ የነበሩ እና ወደ አዲስ ቦታ የተዘዋወሩ ናቸው፡፡
|
ከዚህ ቀደም ሚኒስቴር የነበሩ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪነት ሲሰሩ የነበሩ አንድ ባለስልጣን ደግሞ ወደ ሚኒስትርነት ቦታ ተመልሰዋል፡፡
|
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራረሮች ግን ሹመቱ መሰረታዊውን የኢትዮጵያን ችግር እና የወቅቱን የፖለቲካ ቀውስ አይፈታም ባይ ናቸው፡፡
|
ሊቀመንበሩ ሹም ሽሩን ገዢው ፓርቲ ቀባብቶ በማለፍ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርገው ሲሉ ይተቹታል፡፡
|
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.