input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
በሁለቱ ፖለቲከኞች እና የውሳኔ ሐሳቡን ያጸደቁትን የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፖለቲከኞች ያወገዙም አሉ።
|
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ውሳኔው ወቅቱን ያልጠበቀ እና ያልተገባ ነው ሲል ተችቷል።
|
አሁን ገና የሰላም አየር መተንፈስ መጀመራችንን እንደሰሙ አፀደቅን ምናምን እሚሉን
|
በውሳኔ ሐሳብ የተነሱትን ጥያቄዎች በተመለከተም ጽሑፉን ሲቀጥል፦ የአሁኑ ጠ ሚ እንደሚያደርጋቸው ባለሙሉ ተስፋ ነን።
|
በዘር ተከፋፍለን አንዱ በይ ሌላው ተመልካች የሚል አስተያየት አስፍሯል።
|
ጉራቻ ጉማባሱ የተባለ አስተያየት ሰጪ፦ ለወያኔዎቹ የመጨረሻዉ የራስ ምታትና ኮንትሮባንዳቸውን ዋጋ ያሳጣ ውሳኔ ስለሆነ ይወተውታሉ ግን ማምለጥ አይችሉም ብሏል።
|
የኢትዮጵያ ችግር በኢትዮጵያውያን እንጂ በአሜሪካውያን ሊፈታ አይችልም የወርቁ ዋንታላ አስተያት ነው።
|
ወያኔዎች ምንም አይነት በደል ካልሰሩ የተሰኘውን ሕግ ለምን እንደዚ አጥብቀው ጠሉት
|
ማይክ ሐረር፦ የኢትዮጵያ አለቃ አሜሪካ ሳትሆን ህዝቦቿ ናቸው ።
|
ሰብአዊ መብት ካወቁ በሶርያ ምንም በማያውቁት ህፃናት ላይ ቦምቦችን ለምን ያዘንባሉ ሲል ዮሴፍ ደሳለኝ፦ መግለጫ ብቻ ከሆነ ለምን እንዳይፀድቅ ጣሩ
|
ለማስፈፀም የምሯሯጡት ዲያስፖራዎች ፀባቸው ከኢህአዴግ ጋር ነዉ ወይስ ከኢትዮጲያ እስቲ ይንገሩን።
|
ዓላማዉ የኢትዮጲያን መንግስት ስልጣንና ተግባር በመድፈቅ ሙሉ በሙሉ በምዕራባዉያን ሕግ ለመተካት ያለመ ተግባር ነዉ ብሏል፡፡
|
ክሪስቶፈር መኮንን ደግሞ፦ ኤች አር ሕግ እንዲኾን ደግሞ እንግፋ የሚል አስተያየት ሰጥቷል።
|
ከጥንቷ የሮማ ገዢዎች ዘር የሚወርሰዉ ያ ወጣት የቅዱስ ሮማ ሥርወ መንግሥት ከተሰኘዉ ጎራ ተሠልፎ ሲዋጋ ቡድኑ ተሸንፎ ከተማይቱ በጣሎቶቹ ተማረከች።
|
የጳጳሱ ታማኞች ይባሉ የነበሩት አሸናፊዎቹ ዳንቴ አምስት ሺሕ ፍሎሪን የፍሎሬንሶች ገንዘብ እንዲከፍል አለያም በእሳት ተቃጥሎ እንዲገደል ፈረዱበት።
|
ይሕ የሥነፅሁፍ በረከቱ ዳንቴን በወገኖቹ ዘንድ ኢል ሶሞ ፖኤታ፥
|
ልዕለ ገጣሚ ሲያሰኘዉ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ፔትሬርክና ከቦካሺዮ ጋር ተደምሮ የኢጣሊያ ሥነፅፍ ዘዉዶች የሚል አክብሮት አስችሮታል።
|
ለዳንቴ ኢጣሊያ በተለይም ፍሎሬንስ ዉስጥ የተለያዩ መታሰቢያ ሐዉልቶች ቆመዉለታል።
|
እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር በ ዎቹ መጀመሪያ የተበየነበት ፍርድ የተነሳለት ግን ባለፈዉ አመት ሰኔ ነበር።
|
ዳንቴ በሕወቱ ኮሞዲያ ያለዉን መፅሐፉን የመጀሪያዉ የሕወት ታሪክ ፀሐፊዉ ቦካሺዮ ዲቪና ያከለበትን ቅኔ የሮማዉ ወኪላችን ተኽለ እግዚ ገብረየሱስ ባጭሩ ያወጋን።
|
ኮሚሽኑ ሲቋቋም ጀምሮ ድጋፍ እና ተቃውሞ ገጥሞታል ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
ቀጣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት እንዳሉት የሙቀት ልቀት መጠንን ለመቀነስ አምና የተደረሰበትን ሥምምነት ያፈርሳሉ።
|
ዩናይትድ ስቴትስ ጃፓንን ጨምሮ ከአስራ አንድ የፓሲፊክ አካባቢ ሐገራት ጋር ያደረገችዉን ዉል ን ይሰርዛሉ።
|
ዩናይትድ ስቴትስ ከኩባ ጋር የነበራትን የግማሽ ምዕተ ዓመት ጠብ ለማርገብ ያደረገችዉ ስምምነት ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳታመርት የሚያግደዉን ዉሉ ይሰርዛሉ።
|
በተገን ጠያቂዎች መኖሪያዎች ላይ የተባባሰው ጥቃት ጀርመን ለስደት አዲስ የምትባል ሃገር አይደለችም።
|
ጀርመናውያንም በተለያዩ ሃገራት ተሰደው የሚኖሩ ህዝቦች እንደመሆናቸው ስደትን አያውቁትም ማለት አይቻልም ።
|
ሆኖም ለስደተኞችም ሆነ ለስደት አዲስ ባልሆነችው በጀርመን በውጭ ዜጎች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ጥቃቶች ይፈፀማሉ ።
|
ከቅርብ ወራት ወዲህ ጀርመን ውስጥ በተገን ጠያቂዎች የመኖሪያ ህንፃዎች ላይ ተከታታይ ቃጠሎዎች ደርሰዋል።
|
ይህም በጎርጎሮሳውያኑ ዓመተ ምህረት ከተመዘገቡት ጥቃቶች በልጦ ነው የተገኘው ።
|
ጀርመን ውስጥ እነዚህን መሰል አደጋዎች ሲደርሱ ግን አዲስ አይደለም ።
|
በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ ዎቹ በተለይ በምሥራቅ ጀርመን በውጭ ዜጎች ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ደርሰዋል ።
|
ከዚያን ወዲህም በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚደርሱ እነዚህን የመሳሰሉ የዘረኞች ጥቃቶች ሰለባ የሆኑ የውጭ ዜጎች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ።
|
በዶክተር ሽፈራው አስተያየት ቀኝ አክራሪዎች ህብረተሰቡ ተገን ጠያቂዎች ጀርመን መግባታቸውን እንዲቃወም ልዩ ልዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ ።
|
ጀርመን የምትቀበላቸው ተገን ጠያቂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄድ እዚህ ሁሌም የሚያነጋግር ጉዳይ ነው ።
|
የስደተኞች ቁጥር ባደገ መጠን እነርሱን ለማስተናገድ የሚወጣው ገንዘብም ማከራከሩ አልቆመም ።
|
በጎርጎሮሳውያኑ ቱ የጀርመን ፌደራል ግዛቶች ለተገን ጠያቂዎች ጉዳይ የሚውል ተጨማሪ ቢሊዮን ዩሮ ያወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
|
ይህ ገንዘብም ሃገሪቱ በ ለዚሁ ለተገን ጠያቂዎች ከመደበችው በጀት በእጥፍ የሚበልጥ ነው ።
|
በዚህ ዓመት ጀርመን እንድትቀበላቸው ማመልከቻ ያስገቡ ተገን ጠያቂዎች ቁጥር ከ ሺህ ይበልጣል ።
|
የአመልካቾቹ ቁጥር በዚሁ ዓመት ከ ሺህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ።
|
ጀርመን ይህን ያህል መጠን ያላቸውን ተገን ጠያቂዎች መቀበሏን የሚቃወሙ ወገኖችና አንዳንድ ፖለቲከኞች ሃገሪቱ ጫናው በዝቶባታል ሲሉ ይከራከራሉ ።
|
ከጥቃቶች አብዛኛዎቹ ጀርመን ለጀርመናውያን ብቻ የሚል አስተሳሰብ በሚያራምዱ ቀኝ አክራሪዎች ና ደጋፊዎቻቸው የሚፈፀሙ መሆናቸው ይታመናል ።
|
ለምሳሌ ባለፉት ስድስት ወራት ከደረሱት አደጋዎች በመቶው በቀኝ አክራሪዎች የተፈፀሙ መሆናቸው ተነግሯል ።
|
አሁን አሁን ከነዚህ ወገኖች ጋር ግንኙነት የሌላቸው ጀርመናውያንም የቀኝ አክራሪዎቹን አመለካከት እንደያዙ ዶክተር መኮንን ያስረዳሉ ።
|
ሆኖም በንፅፅር የተሻለ ሲባል በቆየው በምዕራብ ጀርመንም በቀን አክራሪዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች እየተባባሱ መሆኑ ነው የተነገረው ።
|
በርሳቸው እምነት ይህን ለማስተካከል ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ብዙ ይቀረዋል ።
|
መጽሐፍትን በተንቀሳቃሽ ስልክ በስልክ ወይም በተመሳሳይ የኮምፒውተር መገልገያዎች ለንባብ የቀረቡ መፅሀፍት ኢትዮጵያ ውስጥ መሸጥ እስካሁን ብዙም የተለመደ አይደለም።
|
በአንድ በኩል ይህንን አገልግሎት የሚሰጥ አፕሊኬሽን አለመኖሩ ሲሆን በሌላ ወገን ደግሞ ክፍያው በኦንላይን መፈፀም ስላለበት ነው።
|
ቴክኖሎጂውም እያደገ ሲሄድ ሰዎች መፅሀፉን በ ይገዙና እና ያነቡ ጀመር።
|
የኢትዮጵያ መጽሀፎችን ለገበያ ያቀረበው ሎሚ ቡክስ ወይም ሎሚ መፅሀፍት ከነዚህ አንዱ ነው።
|
ሰዎች በቀላሉ ስልካቸውን ተጠቅመው መፅሀፍ ማንበብ እንዲችሉ ነው ይላል የሎሚ መፅሀፍት መስራች ብሩክ ኃይሉ።
|
ለጊዜው ግን የዚህ ተጠቃሚ የሚሆኑት የአንድሮይድ ተገልጋዮች ብቻ ናቸው።
|
የኢ ቡክ ወይም በዲጂታል መልክ የሚቀርብ መፅሀፍ ከሚታተመው መፅሀፍ ጋር ሲነፃፀር ዋጋው መለስተኛ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አማራጮችንም ይሰጣል።
|
አንባቢያን የማይችሉት ነገር ቢኖር አንዴ የገዙትን መፅፋት ለሌላ ሰው መላክ ወይም ማጋራት ነው።
|
ሎሚ ቡክስ በአሁኑ ሰዓት ከ መፅሀፎች ለገበያ እንዳቀረበ ይናገራል።
|
ከዚህም ሌላ ደራሲያኑ ምን ያህል መጽሀፋቸው እንደተሸጠ ራሳቸው ገብተው የሚቆጣጠሩበት መንገድ እንደተዘጋጀላቸው የሎሚ ቡክስ መስራች ይናገራል።
|
አንባብያኑም ከዚህ ቀደም በቀላሉ የማያገኙትን አገልግሎት ይዘን ብቅ ስላልን ጥሩ አስተያየት እየሰጡን ነው ይላል ብሩክ።
|
ደራሲ ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፋ መንገደኛ የሚለው መፅሀፉን በሎሚ መፅሀፍት አማካኝነት በኦንላይን ከሚሸጡ ደራስያን አንዱ ነው።
|
ደራሲው መፅሀፎቹን በአፕሊኬሽን መልክ የመሸጡ ጥያቄ ሲቀርብለት በደስታ ነው የተቀበለው።
|
ደራሲ አለማየሁ ገላጋይም ቢሆን ሎሚ መጽሀፍት ሶስት መፅሀፎቹን ኦንላይን ላይ እንዲሸጥ ፈቅዷል።
|
ፍቃድ ጠይቀውት መፅሀፉ በኦንላይን ሲሸጥ ይህ የመጀመሪያ ጊዜው ነው።
|
ከዚህ በፊት ግን ያለ ፍቃድ ስኬን እያደረጉ መፅሀፎቼን በኦንላይን አሰራጭተዋል ይላል።
|
የፖለቲካ ፍጥጫ ያስከተለው ስጋት እኛና እነሱ የፖለቲካ አሰላለፍ አገሪቱን ወደ አልሆነ አቅጣጫ እየወሰዳት እንደሆነ ምሁራን አሳሰቡ።
|
ከስልሳዎቹ አንስቶ የሚታየው የተቃራኒ ፖለቲካ አካሄድ ዛሬም ሐገሪቱን እያሰጋ መሆኑን አመልክተዋል።
|
የሃሳብ ልዩነት መኖሩ መጥፎ እንዳልሆነ የጠቆሙት ምሁራኑ መነጋገርና መመካከሩ ግን መፍትሄ ያመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።
|
ይህን ተከትሎም የውህደቱ ደጋፊዎችና የውህደቱ ተቃዋሚዎች በየፊናቸው እኛ እና እነሱ በሚል የፖለቲካ አሰላለፍ ገብተዋል።
|
ይህ የፖለቲካ አካሄድ አገሪቱን ወደ ባሰ ችግር ውስጥ እንደሚወስዳት ምሁራን ስጋታቸውን ገልፀዋል።
|
የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ተ ማርያምም የሁለቱን ምሁራን አስተያየት ይጋራሉ።
|
አገሪቱና ህዝቦቿ አሁን ከደረሱበት አጣብቂኝ ውስጥ ለማውጣት ፖለቲከኞች የሃሳብ ትግል አድርገው አሸናፊውን ሀሳብ መቀበል ተገቢ እንደሆነ ዶ ር ሲሳ ተናግረዋል።
|
ዶ ር ገብረ ኢየሱስ እንደሚሉት ደግሞ ወደግጭት ከሚመሩ ቃላትና ነገሮች መቆጠብና ከራስ ስልጣን ይልቅ የአገርን ጥቅም ማስቀድም ይገባል።
|
የተቃውሞ ሰልፉን የጀመረችው አውስትራሊያ ስትኾን እንደ ተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች ከኾነ ቢያንስ ሰው በተቃውሞው ተሳታፊ ኾኗል።
|
በታይላንድ ሕንድ እና ደቡብ ኮሪያም ተማሪዎች እንዲሁም የሰልፉ ደጋፊዎች ተሳታፊ ኾነዋል።
|
በርሊን ከተማ ውስጥ በተደረገው የከባቢ አየር ጥበቃ የተቃውሞ ሰልፍ ሰዎች መሳተፋቸው ተገልጧል።
|
ቦን የሚገኘው የዶይቸ ቬለ ሠራተኞችም ዶይቸ ቬለ ከሚገኝበት ሕንጻ አቅራቢያ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ተከናውኗል።
|
በመላው ዓለም ዙሪያ በዛሬው ዕለት ከ በላይ የተቃውሞ ሰልፎች መከናወናቸው ታውቋል።
|
የኢንተርኔት ጥሪ ቁለፋ መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
|
አፍሪቃ የካሜሩን ቀውስ እና ቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በካሜሩን የፊታችን መስከረም ዓም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ይካሄዳል።
|
የሀገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሰረትም የምርጫው ዘመቻ በዛሬው ዕለት በይፋ ዘመቻ ተጀምሯል።
|
የካሜሩን ምርጫ ካሜሩንን ካለፉት ዓመት ወዲህ በሚመሩት ፕሬዚደንት ፖል ቢያ አንፃር ስምንት እጩዎች በተወዳዳሪነት ቀርበዋል።
|
ይሁንና ውዝግብ በቀጠለበት እንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ በሆነው የሀገሪቱ አካባቢ ምርጫውን እና ዘመቻውን እንደታሰበው ማካሄድ መቻሉ አጠራጣሪ ሆኗል።
|
ይህንኑ አካባቢ ከተቀረው ካሜሩን ለመገንጠል የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች እነርሱ ሀገር በሚሉት በዚሁ አካባቢ የውጭ ምርጫ እንዲካሄድ እንደማይፈቅዱ ዝተዋል።
|
ከ ሚልዮኑ የካሜሩን ህዝብ መካከል ፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነው።
|
ይህን ተከትሎ ታድያ ብዙ ሕዝብ በአካባቢው ተደጋግሞ በመታየት ላይ ያለውን ግጭት መሸሹን መርጧል።
|
የግዛቱ ዋና አስተዳዳሪ ቤርናር ኦካሊያ ቢላይ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ነዋሪዎቹ ወደየመኖሪያቸው እንዲመለሱ ተማፅነዋል።
|
የጦር ኃይሉ በዚያ ያለው ህዝቡን እና ንብረቱን ከጥቃት ለመከላከል እና ጥቃቱን ለማስቆም ነው።
|
እንግሊዝኛ ተናጋሪዎቹ ዓማፅያን ናቸው የኃይል ተግባር እየፈጸሙ ያሉት በሚል ዋና አስተዳዳሪ ቤርናር ኦካሊያ ቢላይ ያካባቢውን ህዝብ ለማረጋጋት ሙከራቸውን ቀጥለዋል።
|
ነዋሪዎች ከለላ እንደሚደረግላቸው በማስታወቅ በየቤታቸው እንዲቆዩ የተማፀኑት ዋና አስተዳዳሪው ራሳቸው በሚከ ላከሏቸው ወታደሮች ታጅበው ነው የሚዘዋወሩት።
|
ባጠቃላይ ነዋሪዎቹ ውዝግቡ ባካባቢው እስካላበቃ ድረስ ነፃና ትክክለና ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ብለው አያምኑም።
|
በሰሜን ምዕራቡ እና በደቡብ ምዕራቡ ካሜሩን ግዛቶች ተዓማኒ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም።
|
እና በሁለቱ አካባቢዎች ነፃ እና ትክክለኛ ምርጫ ለማካሄድ ቢፈለግም ጊዜው በማለፉ በወቅቱ ምንም ሊደረግ አይችልም።
|
ብዙ እጩዎች ሰዎች ድምፃቸውን እንዲሰጡ ለማበረታትት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።
|
ይሁንና እስካሁን የተቃዋሚው የካሜሩን ብሔራዊ ዜግነት ንቅናቄ ፓርቲ እጩ አፋኑዊ ብቻ ናቸው ውዝግብ ወደሚታይበት አካባቢ የሄዱት።
|
የህዝቡን ጥያቄ እና ፍላጎት የማያዳምጥ መንግሥት ስላለን ብቻ በውዝግብ ላይ የምትገ።
|
ሌላው ፕሬዚደንታዊ እጩ ጆሹዋ ኦሲህ ለቀውሱ የተሻለ መፍትሔ እንዳላቸው ነው የገለጹት።
|
ችግሩ ወደ መገንጠል ጥያቄ ያመራው ህዝቡን የማግለሉ ድርጊት እና በህዝቡም ላይ እየተፈጸመ ያለው ኢፍትሓዊ አሰራር ነው።
|
ጉዳዩን የሚረዳ ፕሬዚደንት ካለ ችግሩን ለማስወገድ በመጀመሪያ ህዝብ ለሚገለልበት አሰራር መፍትሄ መስጠት ነው።
|
እኔ ፕሬዚደንት ሆኜ ብመረጥ የመጀመሪያው ውሳኔዬ የሚሆነው ጉዳዩ የፖለቲካ ችግር መሆኑን አምኖ መቀበል ነው።
|
የካሜሩን አስመራጭ ቦርድ ሊቀ መንበር ኤኖው አብራምስ ምርጫው በሁሉም አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
|
ለምርጫ የሚያስፈልገው ቁሳቁስ ከሞላ ጎደል ተዘጋጅቷል የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የመሳሰሉት ቁሳቁሶችም ወዳካባቢው በመላክ ላይ ነው።
|
በካሜሩን የአውሮጳ ህብረት ተጠሪ ሀንስ ፔተር ሻዴክ እንዳስታወቁት ህብረቱ በምርጫው በታዛቢነት ባይሰማራም የምርጫውን ሂደት መከታተሉ አይቀርም።
|
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ በጀርመን ቡንደስሊጋ ቦሩስያ ዶርትሙንድ አጀማመሩ የሰመረ ይመስላል።
|
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.