input
stringlengths
1
130k
በተቃራኒዉ ከጋና በርካታ ወጣቶች ለትምህርትም ሆነ ለሙያዊ ሥልጠና ወደ ጀርመን እንዲመጡ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ እንፈልጋለን።
ሕገወጥ ስደተኝነትን መዋጋት ይኖርብናል ሆኖም በአንፃሩ ለወጣቶች ሕጋዊ ዕድሎች እንዲከፈቱ እንፈልጋለን።
ጀርመን ዉስጥ በአሁን ወቅት ወደጋና ሊመለሱ ይችላሉ የተባሉ አራት ሺህ ገደማ ተሰዳጆች ይኖራሉ።
የተመላሽ ስደተኞችን ሁኔታ ለማመቻቸትም አክራ ላይ በጀርመን ትብብር አንድ ማዕከል ተከፍቷል።
እንዲያም ሆኖ የጋናዉ ፕሬዝደንት ወደጋና ይመለሳሉ የተባሉት ማንነት አስቀድሞ እንዲጣራ ጠይቀዋል።
መዝናኛ፦ አዝማሪ ከያንያን ራድዮ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን።
የቱርክ ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ባለፈው እሁድ ቱርክ ያካሄደችው ህዝበ ውሳኔ የቱርክ ፕሬዝዳንት ጠይብ ሬቼፕ ኤርዶሃን የሚፈልጉትን ውጤት አስገኝቷል ።
ድምጽ ለመስጠት ከወጣው ህዝብ በመቶው በቱርክ ህገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደርግ ተስማምቷል።
ማሻሻያው የቱርክን አስተዳደር ከፓርላሜንታዊ ወደ ፕሬዝዳንታዊ የመንግሥት ስርዓት የሚቀይር ነው ።
ፕሬዝዳንቱ ቀድሞ ያልነበረውን ሚኒስትሮች የመሰየም በጀት የማዘጋጀት እና አብዛኛዎቹን ከፍተኛ ዳኞች የመሾም ሥልጣን ያገኛል።
በመቶ ድምፅ ሰጭዎች ማሻሻያው ፕሬዝዳንቱ ሥልጣኑን በሙሉ ጠቅለው እንዲይዙ ስለሚያደርግ ህገ መንግሥቱ እንዳለ ይቀጥል ሲሉ ነበር ድምጻቸውን የሰጡት ።
ከዚህ ሌላ ህዝቡ ስለ ህዝበ ውሳኔው ምንነት አስቀድሞ በቂ መረጃ እንዲያገኝ አልተደረገም ሲሉም ተችተዋል።
በህገ መንግሥታዊ ማሻሻያ ጥያቄ ላይ የተካሄደው የሚያዚያ ቱ ህዝበ ውሳኔ በተመጣጣኝ የመፎካከሪያ ሜዳ ላይ አልተካሄደም ።
ድምጽ ሰጭዎች ስለ ማሻሻያው ቁልፍ ጉዳዮች ገለልተኛ የሆነ መረጃ አልተሰጣቸውም።
በሐምሌ ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለዴሞክራሲያዊ ሂደት ወሳኝ የሆኑ መሠረታዊ ነጻነቶችን ገድቧል።
ቱርክን ከአውሮጳ ህብረት ጋር ካቃቃሯት ጉዳዮች አንዱ የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን ስታካሂድ የነበረው ድርድር መገታት ነው።
ህብረቱ ሀገሪቱ ማሟላት አለባት የሚላቸውን በሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮሩ መስፈርቶችን ለድርድሩ አለመቀጠል አንደ አንድ ምክንያት ይጠቀሳል።
የዶቼቬለ የኢስታንቡል ዘጋቢ ዶርያን ጆንስ እንዳለው የአውሮጳ ታዛቢዎች አስተያየት እና የኤርዶሀን ዛቻ በድርድሩ ተስፋ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም።
የአውሮጳ ምክር ቤት እና ኦ ኤስ ሲ ኢ ህዝበ ውሳኔው የተካሄደበትን መንገድ በጥብቅ አውግዘዋል።
እናም ቱርክ ኤርዶጋን በሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ የአውሮጳ ህብረት ህብረት አባል መሆን አትችልም የሚለው አስተሳሰብ በአውሮፓ እንዲሰፍን አድርጓል ።
እንደሚመስለኝ ከአውሮጳ ህብረት ጋር ስታካሂድ የቆየችው ድርድር ወደፊት የመራመዱ ተስፋ አናሳ ነው ።
የጀርመን ጥምር መንግሥት አካል የሆነው የክርስቲያን ሶሻል ህብረት ፓርቲ በምህፃሩ ሊቀመንበር ማንፍሬድ ቬበር ይህን ካሉት የጀርመን ፖለቲከኞች አንዱ ናቸው።
ቱርክ አሁን በአውሮጳ ህብረት እይታ የተሳሳተ መንገድ ለመከተል ከመረጠች ከቱርክ ጋር ያለንን ግንኙነት እንደገና መፈተሽ አለብን ።
ያ ማለት በቱርክ የአውሮጳ ህብረት አባልነት ማመልከቻ ላይ የምናካሂደው ድርድር በረዥሙ ጊዜ ሊቀጥል አይችልም።
ለንግግር መቅረብ ያለበት የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም የሚያስጠብቅ አጋርነት ነው።
ይህን መታዘቡን ያሳወቀው የጀርመን መንግሥት ክፍፍሉን ለማስወገድ በቱርክፖለቲካዊ ውይይት እንዲካሄድ ጠይቋል።
ይሁንና እና ፕሬዝዳንት ኤርዶሀን ከድሉ በኋላ ትናንት ባሰሙት ንግግር ማሳሰቢያዎቹን ከቁብ የቆጠሩት አይመስልም ።
ስለ ህዝበ ውሳኔው የሚደረገው ውይይትም ሆነ ውዝግቡ አብቅቷል ትችቱም መቆም አለበት ብለዋል ።
የህዝበ ውሳኔው ውጤት የተቃወሙትንም ተመልከቱ እንዴት ሽንፈታቸውን እንደሚያከበሩ ሲሉ አሹፈውባቸዋል።
ምንም እንኳን ከአንድ በመቶ በላይ በሆነ ድምጽ ቢያሸንፉም ትችቱ መቆም አለበት የሚል እምነት ነው ያላቸው።
እናም ፕሬዝዳንቱ በተቃዋሚዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ ይወስዳሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
ጋዜጠኛ ዲርያን እንደሚለው ኤርዶሀን ከሁለት ዓመት በኋላ ማለትም በጎርጎሮሳዊው በቱርክ ለሚካሄደው ምርጫ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ከአሁን መንገዱን እያመቻቹ ነው።
ፀረ አውሮጳ ንግግራቸውም ሆነ ዛቻቸው በህዝበ ውሳኔ ያጡትን ድምጽ ለማግኘት የሚጠቀሙበት ዘዴም ነው ይላል።
ከቱርክ ብሔረተኞች አብዛኛዎቹ በህዝበ ውሳኔው ልደገፏቸውም የሚል ግምት አለ ።
በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ በሚካሄደው ምርጫ ኤርዶሀን የብሔረተኞች ድምጽ ያስፈልጋቸዋል ።
እናም የሞት ቅጣት ተመልሶ ህጋዊ ይሁን አይሁን የሚለው ጉዳይ እና በአውሮጳ ህብረት ላይ የሚያነሱት ጥያቄ የብሔረተኞችን ቀልብ ለመሳብ ይጠቅማቸዋል ።
ግን ጥያቄው እነዚህ ጉዳዮች ለህዝበ ውሳኔ ይቀርባሉ ወይ ነው ።
ከአውሮፓ ምክር ቤትም ሆነ ከአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትጋር የሚኖራት ግንኙነትም ጥያቄ ውስጥ ይገባል።
ስደተኞች ወደ አውሮጳ እንዳይገቡ ለመከላከል ከህብረቱ ጋር የደረሰችበት ውል ሁለቱን ወገኖች ከሚያስተሳስሯቸው ጥቅሞች አንዱ ነው ።
ቱርክ የአውሮፓ ህብረት ዋነኛ የንግድ አጋር መሆንዋም ሌላው የጋራ ጥቅማቸው መገለጫ ነው።
የነዚህ ትስስሮች የወደፊት እጣ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አሁንም ማነጋገሩ እንደቀጠለ ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት የቀድሞውን የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት በአዲስ አበባ እንዳይተላለፉ ያገደው ባለፈው እሁድ ነበር፡፡
የስፖርት ዘገባ ዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሩስያን በተመለከተ ትናንት ያስተላለፈው ውሳኔ ብዙዎችን አስደምሟል።
የሩስያ መንግሥት አትሌቶቹ አበረታች ንጥረ ነገሮችን እንዲጠቀሙ ሁኔታዎችን ሲያመቻች በመክረሙ ቡድኑ ሙሉ ለሙሉ ከሪዮ ኦሎምፒክ ሊታገድ ይችላል ተብሎ ነበር።
የቱር ደ ፍሯንስ ብስክሌት ሽቅድምድም በብሪታንያዊው ክሪስ ፍሮም ድል ተጠናቋል።
በሜዳ ቴኒስ የሞንትሪያል ውድድር ሴሬና ዊሊያምስ ለሦስት ጊዜያት ያሸነፈችበት ውድድር ላይ አትካፈልም።
የአውስትራሊያ የኦሎምፒክ ቡድን ወደ ሪዮ የኦሎምፒክ መንደር እንደማይገባ አስታወቋል።
በፖላንዱ ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ፉክክር ኢትዮፕያ የሦስተኛ ደረጃን አገኘች።
ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሩስያ ሙሉ ለሙሉ ከሪዮ ኦሎምፒክ ትታገድ የሚለውን ሐሳብ ውድቅ አድርጓል።
ሐሳቡ የቀረበው በዓለም አቀፉ ጸረ አበረታች ንጥረ ነገር ተከታታይ ተቋም በእንግሊዝኛ ምኅጻሩ ነበር።
እያንዳንዱ አትሌት በውድድሩ ላይ መሳተፍ አለያም አለመሳተፉን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽኖች በተናጠል ሊወስኑ ይችላሉ ብሏል።
ብዙአየሁ ዋጋው የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበርን ጨምሮ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ መገናኛ አውታሮች ዘጋቢ ነው።
በሩስያ ጉዳይ ዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማቱ ወዲህ እና ወዲያ የማለታቸውን ምክንያት እንዲህ ያብራራል።
ይህን የተናገሩት የሩስያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ኃላፊ አሌክሳንደር ዙኮቭ መሆናቸውን አር ስፖርት የዜና ምንጭ ዘግቧል ሲል ሮይተርስ አክሎ ጠቅሷል።
በፖላንድ ቢድጎቺች ከተማ ለ ቀናት የተከናወነው የታዳጊዎች የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ትናንት ተጠናቋል።
ዕድሜያቸው ከ ዓመት በታች የሆኑ አትሌቶች በሚሳተፉበት ውድድር ኢትዮጵያ የወርቅ የብር እና የነሀስ በአጠቃላይ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ኬንያን ተከትላ ሦስተኛ ወጥታለች።
የወርቅ የብር እና የነሀስ በአጠቃላይ ሜዳሊያዎች ሰብስባ ዩናይትድ ስቴትስ አንደኛ ወጥታለች።
ስዋንሲ ሲቲ ደግሞ የ ዓመቱ ዊልፍሬድ ቦኒን ከማንቸስተር ሲቲ ሊያስፈርም እየተነጋገረ መሆኑን ሰንዴይ ኤክስፕረስ የተሰኘው ጋዜጣ አትቷል።
ቸልሲ በቅርቡ ያስፈረመው ንጎሎ ካንቴ በሚቀጥለው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የሚለብሰው ሰባት ቁጥር መለያ ሰጥቶታል።
የማርሴዩ የክንፍ ተጨዋች ጌኦርጌስ ኬቪን ንኮዱ ለቶትንሀም ለመፈረም ጫፍ ላይ መድረሱን ኢንዲፔንደት ዘግቧል።
ሊቨርፑል ለአውሮጳ ሊግ ከስፔኑ ሴቪያ ጋር በተጫወተበት ወቅት ደጋፊዎቹ ርችቶችን እየተኮሱ በመበጥበጣቸው ፓውንድ መቀጣቱ ተገልጧል።
የደጋፊዎች ብጥብጡ የተከሰተው ከሁለት ወራት በፊት የስዊዘርላንድ ባዝል ከተማ ውስጥ ነበር።
ብስክሌት ብሪታንያዊው ክሪስ ፍሮም በቱር ደ ፍሯንስ የብስክሌት ሽቅድምድም ኛ እና የመጨረሻ ዙር ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ።
ክሪስ ዘንድሮ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሲሆን ለሦስተኛ ጊዜ ነው።
አሜሪካዊው ላንስ አርምስትሮንግ ውጤቶቹን በመነጠቁ ክሪስ ፍሮም ከስፔናዊው ሚጉዌል ኢንዱራይን ቀጥሎ ውጤቱን በማስጠበቅ ሁለተኛ ነው።
ለ ተከታታይ ጊዜያት አሸናፊ የነበረው አሜሪካዊው ላንስ አርምስትሮንግ አጠቃላይ ውጤቶቹ የተሰረዙበት አበረታች ንጥረ ነገር መጠቀሙን በማመኑ ነበር።
ስፔናዊው ሚጉዌል ኢንዱራይንእንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ከ አንስቶ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት የቱር ደ ፍሯንስ የብስክሌት ሽቅድምድም አሸናፊ ጠንካራ ተወዳዳሪ ነው።
የዘንድሮውን ጨምሮ ለሦስት ዓመታት ባለድል የሆነው የብሪታንያው ክሪስ ፍሮሜሚጉዌል ላይ ለመድረስ እየገሰገሰ ነው።
ምናልባት ጥንካሬው በዚሁ ከቀጠለ እና በተከታታይ ካሸነፈ በ ዓመቱ ስፔናዊውን በመብለጥ ክብርወሰኑን ይሰብር ይሆናል።
ለ የተለያዩ ቀናት በተከናወነው የቱር ደ ፍሯንስ የብስክሌት ሽቅድምድም አጠቃላይ ውጤት ኢትዮጵያዊው ጽጋቡ ገብረማርያም ከ ተወዳዳሪዎች የ ኛ ደረጃን አግኝቷል።
ጽጋቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በቱር ደ ፍሯንስ ያስመዘገበው ውጤት እጅግ የሚበረታታ ነው።
የኤርትራው ናትናኤል ብርሃኔ ኛ ደረጃን ሲያገኝ ሌላኛው የኤርትራ ተወዳዳሪ ዳንኤል ተክለ ሃይማኖት ኛ በመውጣት ጠንካራ ብስክሌተኛነቱን አስመስክሯል።
ሴሬና ከውድድሩ የወጣችው ትከሻዋ ላይ በደረሰባት ጉዳት መሆኑን የውድድሩ አዘጋጆች ገልጠዋል።
በእሁዱ የሐንጋሪ ግራንድ ፕሪ ሽቅድምድም ሐሚልተን ሰአት ከ ደቂቃ ከ ሰከንድ በማጠናቀቅ መሪነቱን አስጠብቋል።
በፌራሪ ተሽከርካሪው የሚወዳደረው የፊንላንዱ አሽከርካሪ ኪም ሬይከነን በ ነጥቡ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አሜሪካዊቷ ሴሬና ዊሊያምስ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የስደተኞች ቡድን በኦሎምፒክ ይሳተፋል።
በስደተኞች ቡድን ከታቀፉት አትሌቶች መካከል የ ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ማራቶን ሯጭ ዮናስ ኪዳኔ ይገኝበታል።
ዮናስ ካለፉት አምስት ዓመታት አንስቶ ነዋሪነቱን በአውሮጳ ሉግዘምበርግ አድርጓል።
ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ጀርመን ውስጥ ያደረገውን ውድድርም ሰአት ከ ደቂቃ በማጠናቀቅ ብርቱ ተፎካካሪ መሆኑን አሳይቷል።
የአውስትራሊያ የኦሎምፒክ ቡድን የብራዚሏ ሪዮ የኦሎምፒክ መንደር የጥራት ደረጃውን የጠበቀ አይደለም በሚል አትሌቶቹ መንደሩ ውስጥ እንደማይቆዪ አስታወቀ።
ፍሳሽ በአግባቡ የማያስተላልፉ መጸዳጃ ቤቶች እና የሚያንጠባጥቡ ቧንቧዎች መገኘታቸው አውስትራሊያ ወደ ኦሎምፒክ መንደሩ ላለመሄድ ምክንያት እንደሆናት አስታውቃለች።
ከ ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የፍጻሜ እና የደረጃ ውድድሮች የፊታችን ቅዳሜ እንደሚከናወኑ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በኢሜል በላከው መልእክት ገልጧል።
የጀርመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቮልፍጋንግ ኒርስባኅ ከማንኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ለአንድ ዓመት ታገዱ።
ሆኖም አብዛኛዎቹ ጀርመን እንድትቀበላቸው የጠየቁ አመልካቾች የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ባለሞያዎች ይናገራሉ ።
ጀርመን ውስጥ ካለ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሰቀቀን ህይወት በመግፋት ላይ የሚገኙም ጥቂት አይደሉም ።
ለዚህም ድርጅቱ በዋነኛ ምክንያትነት ያቀረበው የሶሪያውን የርስ በርስ ጦርነት ነው ።
ከሶሪያና ከሌሎች ሃገራት ተሰደው በ በኢንዱስትሪ በበለፀጉት ሃገራት ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ያመለከቱ ስደተኞች ቁጥር ከ ሺህ በላይ ነው ።
በዓመቱ ጀርመን ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ያመለከቱ ስደተኞች ወደ ሺህ ይጠጋሉ ።
ዩናይትድ ስቴትስ ሁለተኛውን ደረጃ ስትይዝ የጥገኝነት ማመልከቻ ያስገቡት ቁጥር ሺህ ነው ።
የጀርመን የተገን አሰጣጥ ሂደት ቢያንስ አንድ ዓመት ወይም ደግሞ ከዚያ በላይ የሚወስድ በመሆኑ ከአመልካቾቹ ምን ያህሉ ጀርመን እንደሚቆዩ አይታወቅም ።
የአብዛኛው ተገን ጠያቂዎች ምርጫ ጀርመን የሆነበት ምክንያት እያነጋገረ ነው ።
አብዛኛዎቹ በሌላ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገር የተመዘገቡ ናቸው ።
እዚያም አብዛኛዎቹ ተገን ጠያቂዎች እስከመኖራቸው የተረሱ በአግባቡም ያልተያዙና የሃገራቱ ስደተኞች አቀባበል ስርዓት የተከተለ አይደለም ።
ከምክንያቶቹ አንደኛው በአውሮፓ ህብረት ህግ መሰረት አንድ ተገን ጠያቂ ጉዳዩ መታየት ያለበት መጀመሪያ በገባበት ሃገር መሆኑ ነው ።
የጀርመን የውጭ ዜጎችና የስደተኞች ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጀርመን እንድትቀበላቸው የሚያመለክቱ ተገን ጠያቂዎችን ወደ መጡበት ለመመለስ የተቻለውን ሁሉ ይሞክራል ።
በተለይ የተሻለ አያያዝ አላቸው ተብለው ከሚታሰቡት ሃገራት የሚመጡት ሰዎች ማመልከዎች ተቀባይነት ያለማግኘት እድላቸው ከፍተኛ ነው ።
በሜሶቪክ እምነት በ ጀርመን ከደረሷት ሺህ የተገን ጠያቂዎች ማመልከቻዎች አብዛኛዎቹ በቀደመው በ ዓም ጥያቄአቸው ውድቅ የተደረገባቸው ስደተኞች ማመልከቻዎችም ናቸው ።
ጥቂት የማይባሉም የፖለቲካ ጭቆና ወይም ኢሰብዓዊ ቅጣቶች አይፈፀሙባቸውም ለህይወት አስጊ አይደሉም ከሚባሉ የባልካን አገራት ነው የመጡት ።
የጀርመን መንግሥት ከነዚህ ሃገራት የሚሰደዱትን ሰዎች ማመልከቻቸውን በቀላሉ ውድቅ ለማድረግ የሚረዳውን ህግ እያረቀቀ ነው ።
አሁን የፌደራል ጀርመን መንግስት ከምዕራብ ባልካን ሃገራት የመጡ ስደተኞች ላስገቧቸው የጥገኝነት ማመልከቻዎች መልስ መስጠት የሚችልበትን ረቂቅ ህግ እያዘጋጀ ነው ።